﻿<?xml version="1.0" encoding="UTF-8"?>
<bible translation="Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))" status="Bible Society of Ethiopia" link="https://www.bible.com/bible/3200/GEN.13.አማ2000">
	<testament name="Old">
		<book number="1">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በመ​ጀ​መ​ሪያ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ፈጠረ።</verse>
				<verse number="2">ምድር ግን ባዶ ነበ​ረች፤ አት​ታ​ይ​ምም ነበር፤ የተ​ዘ​ጋ​ጀ​ችም አል​ነ​በ​ረ​ችም፤ ጨለ​ማም በው​ኃው ላይ ነበረ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በው​ኃው ላይ ይሰ​ፍፍ ነበር።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ብር​ሃን ይሁን” አለ፤ ብር​ሃ​ንም ሆነ።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብር​ሃኑ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በብ​ር​ሃ​ኑና በጨ​ለ​ማው መካ​ከል ለየ።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብር​ሃ​ኑን “ቀን፥” ጨለ​ማ​ው​ንም “ሌሊት” ብሎ ጠራው። ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ አን​ደኛ ቀንም ሆነ።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በው​ኃው መካ​ከል ጠፈር ይሁን፤ በው​ኃና በውኃ መካ​ከ​ልም ይለይ” አለ፤ እን​ዲ​ሁም ሆነ።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጠፈ​ርን አደ​ረገ፤ ከጠ​ፈር በላ​ይና ከጠ​ፈር በታች ያሉ​ት​ንም ውኆች ለየ።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያን ጠፈር “ሰማይ” ብሎ ጠራው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ ሁለ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሰ​ማይ በታች ያለው ውኃ በአ​ንድ ስፍራ ይሰ​ብ​ሰብ፥ የብ​ሱም ይገ​ለጥ አለ፤ እን​ዲ​ሁም ሆነ። ከሰ​ማይ በታች ያለው ውኃም በመ​ጠ​ራ​ቀ​ሚ​ያው ተሰ​በ​ሰበ፤ የብ​ሱም ተገ​ለጠ።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የብ​ሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፤ የውኃ መጠ​ራ​ቀ​ሚ​ያ​ው​ንም “ባሕር” ብሎ ጠራው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም “ምድር በየ​ዘሩ፥ በየ​ወ​ገ​ኑና በየ​መ​ልኩ ዘር የሚ​ሰጥ ቡቃ​ያን፥ በም​ድ​ርም ላይ በየ​ወ​ገኑ ዘሩ በው​ስጡ የሚ​ገ​ኘ​ው​ንና ፍሬ የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን ዛፍ ታብ​ቅል” አለ፤ እን​ዲ​ሁም ሆነ።</verse>
				<verse number="12">ምድ​ርም በየ​ዘሩ፥ በየ​ወ​ገ​ኑና በየ​መ​ልኩ የሚ​ዘራ ቡቃ​ያን፥ በም​ድር ላይ በየ​ወ​ገኑ ዘሩ በው​ስጡ የሚ​ገ​ኘ​ው​ንና ፍሬ የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን ዛፍ አበ​ቀ​ለች። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ።</verse>
				<verse number="13">ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ። ሦስ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “በም​ድር ላይ ያበሩ ዘንድ፥ በቀ​ንና በሌ​ሊ​ትም ይለዩ ዘንድ ብር​ሃ​ናት በሰ​ማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለም​ል​ክ​ቶች፥ ለዘ​መ​ናት፥ ለዕ​ለ​ታት፥ ለዓ​መ​ታ​ትም ይሁኑ።</verse>
				<verse number="15">በም​ድር ላይ ያበሩ ዘንድ፥ በሰ​ማይ ጠፈር ለማ​ብ​ራት ይሁኑ፤” እን​ዲ​ሁም ሆነ።</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሁለት ታላ​ላቅ ብር​ሃ​ና​ትን አደ​ረገ፤ ትልቁ ብር​ሃን ቀንን እን​ዲ​መ​ግብ፥ ትንሹ ብር​ሃ​ንም ከከ​ዋ​ክ​ብት ጋር ሌሊ​ትን እን​ዲ​መ​ግብ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰ​ማይ ጠፈር አኖ​ራ​ቸው፤</verse>
				<verse number="18">መዓ​ል​ት​ንና ሌሊ​ት​ንም እን​ዲ​መ​ግቡ፥ በመ​ዓ​ል​ትና በሌ​ሊ​ትም መካ​ከል እን​ዲ​ለዩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ።</verse>
				<verse number="19">ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ አራ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “ውኃ የሕ​ይ​ወት እስ​ት​ን​ፋስ ያላ​ቸ​ውን ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችና በም​ድር ላይ ከሰ​ማይ በታች የሚ​በ​ርሩ አዕ​ዋ​ፍን ታስ​ገኝ፥” እን​ዲ​ሁም ሆነ።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታላ​ላቅ አን​በ​ሪ​ዎ​ችን፥ ውኃ ያስ​ገ​ኘ​ውን ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ ሕያው ፍጥ​ረ​ትን ሁሉ በየ​ወ​ገኑ፥ የሚ​በ​ርሩ አዕ​ዋ​ፍ​ንም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ፈጠረ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ብሎ ባረ​ካ​ቸው፥ “ብዙ፤ ተባ​ዙም፤ የባ​ሕ​ር​ንም ውኃ ሙሉ​አት፤ ወፎ​ችም በም​ድር ላይ ይብዙ።”</verse>
				<verse number="23">ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ አም​ስ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።</verse>
				<verse number="24">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “ምድር ሕያ​ዋን ፍጥ​ረ​ታ​ትን እንደ ወገኑ፥ እን​ስ​ሳ​ት​ንና ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችን፥ የም​ድር አራ​ዊ​ት​ንም እን​ደ​የ​ወ​ገኑ ታውጣ፥” እን​ዲ​ሁም ሆነ።</verse>
				<verse number="25">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የም​ድር አራ​ዊ​ትን እን​ደ​የ​ወ​ገኑ፥ እን​ስ​ሳ​ት​ንም እን​ደ​የ​ወ​ገኑ፥ በም​ድር የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰ​ው​ንም ሁሉ እን​ደ​የ​ወ​ገኑ አደ​ረገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ።</verse>
				<verse number="26">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “ሰውን በአ​ር​ኣ​ያ​ች​ንና በአ​ም​ሳ​ላ​ችን እን​ፍ​ጠር፤ የባ​ሕር ዓሣ​ዎ​ች​ንና የም​ድር አራ​ዊ​ትን፥ የሰ​ማይ ወፎ​ችን፥ እን​ስ​ሳ​ት​ንና ምድ​ርን ሁሉ፥ በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ትን ሁሉ ይግዛ።”</verse>
				<verse number="27">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ሳል ፈጠ​ረው። ወን​ድና ሴት አድ​ርጎ ፈጠ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="28">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባረ​ካ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት፤ ግዙ​አ​ትም፤ የባ​ሕ​ርን ዓሣ​ዎ​ች​ንና የም​ድር አራ​ዊ​ትን፥ የሰ​ማይ ወፎ​ች​ንና እን​ስ​ሳ​ት​ንም ሁሉ፥ በም​ድር ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ት​ንም ሁሉ ግዙ​አ​ቸው።”</verse>
				<verse number="29">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “እነሆ፥ መብል ይሆ​ና​ችሁ ዘንድ በየ​ዘሩ የሚ​ዘ​ራ​ው​ንና የሚ​በ​ቅ​ለ​ውን፥ በም​ድር ሁሉ ላይ የም​ት​ዘ​ሩ​ትን የእ​ህል ፍሬ፥ ዘሩ በው​ስጡ ያለ​ውን ቡቃያ፥ በየ​ፍ​ሬ​ውም የሚ​ዘ​ራ​ውን ዛፍ ሁሉ ሰጠ​ኋ​ችሁ።</verse>
				<verse number="30">ለም​ድር አራ​ዊት ሁሉ፥ ለሰ​ማ​ይም ወፎች ሁሉ፥ ሕያው ነፍስ ላላ​ቸው ለም​ድር ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችም ሁሉ ሐመ​ል​ማሉ ሁሉ መብል ይሁ​ን​ላ​ችሁ።” እን​ዲ​ሁም ሆነ።</verse>
				<verse number="31">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የፈ​ጠ​ረ​ውን ሁሉ እጅግ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ ስድ​ስ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ሰማ​ይና ምድር ዓለ​ማ​ቸ​ውም ሁሉ ተፈ​ጸሙ።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሠ​ራ​ውን ሥራ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ቀን ፈጸመ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ከሠ​ራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰባ​ተ​ኛ​ዋን ቀን ባረ​ካት፤ ቀደ​ሳ​ትም፤ ሊፈ​ጥ​ረው ከጀ​መ​ረው ሥራ ሁሉ በእ​ር​ስዋ ዐር​ፎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በፈ​ጠ​ረ​በት ቀን፥ በተ​ፈ​ጠሩ ጊዜ የሰ​ማ​ይና የም​ድር ፍጥ​ረት ይህ ነው።</verse>
				<verse number="5">የሜዳ ቍጥ​ቋጦ ሁሉ በም​ድር ላይ ከመ​ኖሩ በፊት፥ የሜ​ዳ​ውም ቡቃያ ሁሉ ከመ​ብ​ቀሉ በፊት፥ አዳ​ምም ከመ​ፈ​ጠሩ በፊት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ በም​ድር ላይ አላ​ዘ​ነ​በም ነበር፤ ምድ​ር​ንም የሚ​ሠ​ራ​ባት ሰው አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="6">ነገር ግን የውኃ ምንጭ ከም​ድር ይወጣ ነበር፤ የም​ድ​ር​ንም ፊት ሁሉ ያጠጣ ነበር።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ሰውን ከም​ድር አፈር ፈጠ​ረው፤ በፊ​ቱም የሕ​ይ​ወት እስ​ት​ን​ፋ​ስን እፍ አለ​በት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም በኤ​ዶም በስ​ተ​ም​ሥ​ራቅ ገነ​ትን ተከለ፤ የፈ​ጠ​ረ​ው​ንም ሰው በዚያ አኖ​ረው።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ለማ​የት ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን፥ ለመ​ብ​ላ​ትም መል​ካም የሆ​ነ​ውን ዛፍ ሁሉ ደግሞ ከም​ድር አበ​ቀለ፤ በገ​ነ​ትም መካ​ከል የሕ​ይ​ወ​ትን ዛፍ፥ መል​ካ​ም​ንና ክፉን የሚ​ያ​ሳ​የ​ው​ንና የሚ​ያ​ስ​ታ​ው​ቀ​ው​ንም ዛፍ አበ​ቀለ።</verse>
				<verse number="10">ወን​ዝም ገነ​ትን ያጠጣ ዘንድ ከኤ​ዶም ይወጣ ነበር፤ ከዚ​ያም ለዐ​ራት መዓ​ዝን ይከ​ፈል ነበር።</verse>
				<verse number="11">የአ​ን​ደ​ኛው ወንዝ ስም ኤፌ​ሶን ነው፤ እር​ሱም ወርቅ የሚ​ገ​ኝ​በ​ትን የኤ​ው​ላጥ ምድ​ርን ይከ​ብ​ባል።</verse>
				<verse number="12">የዚ​ያ​ችም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው።</verse>
				<verse number="13">በዚ​ያም የሚ​ያ​በራ ዕን​ቍና የሚ​ያ​ብ​ረ​ቀ​ርቅ ዕንቍ አለ። የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እር​ሱም የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያን ምድር ሁሉ ይከ​ብ​ባል፤</verse>
				<verse number="14">የሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ወንዝ ስም ጤግ​ሮስ ነው፤ እር​ሱም በአ​ሶር ላይ የሚ​ሄድ ነው። አራ​ተ​ኛ​ውም ወንዝ ኤፍ​ራ​ጥስ ነው።</verse>
				<verse number="15">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ሰውን ወስዶ ያበ​ጃ​ትም፥ ይጠ​ብ​ቃ​ትም ዘንድ በኤ​ዶም ገነት አኖ​ረው።</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም አዳ​ምን እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “በገ​ነት ካለው ዛፍ ሁሉ ብላ፤</verse>
				<verse number="17">ነገር ግን መል​ካ​ም​ንና ክፉን ከሚ​ያ​ሳ​የ​ውና ከሚ​ያ​ስ​ታ​ው​ቀው ዛፍ አት​ብላ፤ ከእ​ርሱ በበ​ላህ ቀን ሞትን ትሞ​ታ​ለ​ህና።”</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም አለ፥ “ሰው ብቻ​ውን ይኖር ዘንድ መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ የሚ​ረ​ዳ​ውን ጓደኛ እን​ፍ​ጠ​ር​ለት እንጂ።”</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም የም​ድር አራ​ዊ​ት​ንና የሰ​ማይ ወፎ​ችን ሁሉ ደግሞ ከም​ድር ፈጠረ፤ በምን ስም እን​ደ​ሚ​ጠ​ራ​ቸ​ውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመ​ጣ​ቸው፤ አዳ​ምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እን​ደ​ጠ​ራው ስሙ ያው ሆነ።</verse>
				<verse number="20">አዳ​ምም ለእ​ን​ስ​ሳት ሁሉ፥ ለሰ​ማይ ወፎ​ችም ሁሉ፥ ለም​ድር አራ​ዊ​ትም ሁሉ ስም አወ​ጣ​ላ​ቸው። ነገር ግን ለአ​ዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አል​ተ​ገ​ኘ​ለ​ትም ነበር።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም በአ​ዳም ላይ እን​ቅ​ል​ፍን አመጣ፤ አን​ቀ​ላ​ፋም ፤ ከጎ​ኑም አጥ​ን​ቶች አንድ አጥ​ን​ትን ወስዶ ስፍ​ራ​ውን በሥጋ መላው።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ከአ​ዳም የወ​ሰ​ዳ​ትን አጥ​ንት ሴት አድ​ርጎ ሠራት፤ ወደ አዳ​ምም አመ​ጣት።</verse>
				<verse number="23">ያን ጊዜም አዳም አለ፥ “ይህች አጥ​ንት ከአ​ጥ​ንቴ ናት፤ ሥጋ​ዋም ከሥ​ጋዬ ናት፤ እር​ስዋ ከባ​ልዋ ተገ​ኝ​ታ​ለ​ችና ሚስት ትሁ​ነኝ።”</verse>
				<verse number="24">ስለ​ዚህ ሰው አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ይተ​ዋል፤ ሚስ​ቱ​ንም ይከ​ተ​ላል ፤ ሁለ​ቱም አንድ ሥጋ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="25">አዳ​ምና ሚስ​ቱም ዕራ​ቁ​ታ​ቸ​ውን ነበሩ፤ አይ​ተ​ፋ​ፈ​ሩም ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">እባ​ብም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ከፈ​ጠ​ራ​ቸው ከም​ድር አራ​ዊት ሁሉ ይልቅ ተን​ኰ​ለኛ ነበር። እባ​ብም ሴቲ​ቱን “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በገ​ነት ካለው ዛፍ ሁሉ አት​ብሉ ያላ​ችሁ ለም​ን​ድን ነው?” አላት።</verse>
				<verse number="2">ሴቲ​ቱም ለእ​ባቡ አለ​ችው፥ “በገ​ነት መካ​ከል ካለው ከሚ​ያ​ፈ​ራው ዛፍ ፍሬ እን​በ​ላ​ለን፤</verse>
				<verse number="3">ነገር ግን በገ​ነት መካ​ከል ካለው ከዛፉ ፍሬ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አለ፦ እን​ዳ​ት​ሞቱ ከእ​ርሱ አት​ብሉ፤ አት​ን​ኩ​ትም።”</verse>
				<verse number="4">እባ​ብም ለሴ​ቲቱ አላት፥ “ሞትን አት​ሞ​ቱም፤</verse>
				<verse number="5">ከእ​ር​ስዋ በበ​ላ​ችሁ ቀን፥ ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ እን​ዲ​ከ​ፈቱ፥ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ደ​ም​ት​ሆኑ፥ መል​ካ​ም​ንና ክፉን እን​ደ​ም​ታ​ውቁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ​ሚ​ያ​ውቅ ነው እንጂ።”</verse>
				<verse number="6">ሴቲ​ቱም ዛፉ ለመ​ብ​ላት ያማረ እን​ደ​ሆነ፥ ለዐ​ይ​ንም ለማ​የት እን​ደ​ሚ​ያ​ስ​ጐ​መጅ፥ መል​ካ​ም​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ሳ​ውቅ ባየች ጊዜ፥ ከፍ​ሬው ወሰ​ደ​ችና በላች፤ ለባ​ል​ዋም ደግሞ ሰጠ​ችው፤ እር​ሱም ከእ​ር​ስዋ ጋር በላ።</verse>
				<verse number="7">የሁ​ለ​ቱም ዐይ​ኖች ተከ​ፈቱ፤ እነ​ር​ሱም ዕራ​ቁ​ታ​ቸ​ውን እንደ ሆኑ ዐወቁ፤ አፈ​ሩም፤ የበ​ለ​ስ​ንም ቅጠ​ሎች ሰፍ​ተው ለእ​ነ​ርሱ ለራ​ሳ​ቸው ግል​ድም አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="8">እነ​ር​ሱም ቀኑ በመሸ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የአ​ም​ላ​ክን ድምፅ በገ​ነት ውስጥ ሲመ​ላ​ለስ ሰሙ፤ አዳ​ምና ሚስ​ቱም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ም​ላክ ፊት በገ​ነት ዛፎች መካ​ከል ተሸ​ሸጉ።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም አዳ​ምን ጠርቶ፥ “አዳም፥ ወዴት አለህ?” አለው።</verse>
				<verse number="10">አዳ​ምም አለ፥ “በገ​ነት ስት​መ​ላ​ለስ ድም​ፅ​ህን ሰማሁ፤ ዕራ​ቁ​ቴ​ንም ስለ​ሆ​ንሁ ፈራሁ፤ ተሸ​ሸ​ግ​ሁም።”</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “ዕራ​ቁ​ት​ህን እን​ደ​ሆ​ንህ ማን ነገ​ረህ? ከእ​ርሱ እን​ዳ​ት​በላ ካዘ​ዝ​ሁህ ዛፍ በውኑ በላ​ህን?”</verse>
				<verse number="12">አዳ​ምም አለ፥ “ከእኔ ጋር እን​ድ​ት​ሆን የሰ​ጠ​ኸኝ ሴት እር​ስዋ ከዛፉ ሰጠ​ች​ኝና በላሁ።”</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ሴቲ​ቱን፥ “ይህን ለምን አደ​ረ​ግሽ?” አላት። ሴቲ​ቱም አለች፥ “እባብ አሳ​ተ​ኝና በላሁ።”</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም እባ​ቡን አለው፥ “ይህን ስላ​ደ​ረ​ግህ ከእ​ን​ስ​ሳት ሁሉ፥ ከም​ድር አራ​ዊ​ትም ሁሉ ተለ​ይ​ተህ አንተ የተ​ረ​ገ​ምህ ሁን ፤ በደ​ረ​ት​ህና በሆ​ድ​ህም ትሄ​ዳ​ለህ፤ በሕ​ይ​ወ​ት​ህም ዘመን ሁሉ አፈ​ርን ትበ​ላ​ለህ።</verse>
				<verse number="15">በአ​ን​ተና በሴ​ቲቱ መካ​ከል፥ በዘ​ር​ህና በዘ​ር​ዋም መካ​ከል ጠላ​ት​ነ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እርሱ ራስ​ህን ይቀ​ጠ​ቅ​ጣል፤ አን​ተም ሰኰ​ና​ውን ትነ​ድ​ፋ​ለህ።”</verse>
				<verse number="16">ለሴ​ቲ​ቱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አላት፥ “ጭን​ቅ​ሽን እጅግ አበ​ዛ​ለሁ፤ በጭ​ንቅ ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ ከወ​ለ​ድ​ሽም በኋላ ፈቃ​ድሽ ወደ ባልሽ ይሆ​ናል፤ እር​ሱም ይገ​ዛ​ሻል።”</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አዳ​ምን አለው፥ “የሚ​ስ​ት​ህን ቃል ሰም​ተ​ሃ​ልና፥ ከእ​ርሱ እን​ዳ​ት​በላ ከአ​ዘ​ዝ​ሁህ ከዚያ ዛፍም በል​ተ​ሃ​ልና ምድር በሥ​ራህ የተ​ረ​ገ​መች ትሁን፤ በሕ​ይ​ወት ዘመ​ን​ህም ሁሉ በድ​ካም ከእ​ር​ስዋ ትበ​ላ​ለህ፤</verse>
				<verse number="18">እሾ​ህ​ንና አሜ​ከ​ላን ታበ​ቅ​ል​ብ​ሃ​ለች፤ የም​ድ​ር​ንም ቡቃያ ትበ​ላ​ለህ።</verse>
				<verse number="19">ወደ ወጣ​ህ​በት መሬት እስ​ክ​ት​መ​ለስ ድረስ በፊ​ትህ ወዝ እን​ጀ​ራ​ህን ትበ​ላ​ለህ፤ አፈር ነህና ወደ አፈ​ርም ትመ​ለ​ሳ​ለ​ህና።”</verse>
				<verse number="20">አዳ​ምም ለሚ​ስቱ “ሔዋን” ብሎ ስም አወጣ፤ የሕ​ያ​ዋን ሁሉ እናት ናትና።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ለአ​ዳ​ምና ለሚ​ስቱ የቁ​ር​በ​ትን ልብስ አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው፥ አለ​በ​ሳ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም አለ፥ “እነሆ፥ አዳም መል​ካ​ም​ንና ክፉን ለማ​ወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ አሁ​ንም እጁን እን​ዳ​ይ​ዘ​ረጋ፥ ደግ​ሞም ከሕ​ይ​ወት ዛፍ ወስዶ እን​ዳ​ይ​በላ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ሕያው ሆኖ እን​ዳ​ይ​ኖር፥”</verse>
				<verse number="23">ስለ​ዚህ የተ​ገ​ኘ​ባ​ትን መሬት ያርስ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ደስታ ከሚ​ገ​ኝ​ባት ገነት አስ​ወ​ጣው።</verse>
				<verse number="24">አዳ​ም​ንም አስ​ወ​ጣው፤ ደስታ በሚ​ገ​ኝ​ባት በገ​ነት አን​ጻ​ርም አኖ​ረው፤ ወደ ሕይ​ወት ዛፍ የሚ​ወ​ስ​ደ​ው​ንም መን​ገድ ለመ​ጠ​በቅ የም​ት​ገ​ለ​ባ​በጥ የነ​በ​ል​ባል ሰይ​ፍን በእ​ጃ​ቸው የያዙ ኪሩ​ቤ​ልን አዘ​ዛ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">አዳ​ምም ሚስ​ቱን ሔዋ​ንን ዐወ​ቃት፤ ፀነ​ሰ​ችም፤ ቃየ​ል​ንም ወለ​ደ​ችው።</verse>
				<verse number="2">እር​ስ​ዋም “ወንድ ልጅ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ኘሁ” አለች። ደግ​ሞም ወን​ድ​ሙን አቤ​ልን ወለ​ደ​ችው። አቤ​ልም በግ ጠባቂ ሆነ፤ ቃየ​ልም ምድ​ርን የሚ​ያ​ርስ ሆነ።</verse>
				<verse number="3">ከብዙ ቀን በኋ​ላም እን​ዲህ ሆነ፤ ቃየል ከም​ድር ፍሬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕ​ትን አቀ​ረበ፤</verse>
				<verse number="4">አቤ​ልም ደግሞ ከበ​ጎቹ መጀ​መ​ሪያ የተ​ወ​ለ​ደ​ው​ንና ከሰ​ቡት አቀ​ረበ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ አቤ​ልና ወደ መሥ​ዋ​ዕቱ ተመ​ለ​ከተ፤</verse>
				<verse number="5">ወደ ቃየ​ልና ወደ መሥ​ዋ​ዕቱ ግን አል​ተ​መ​ለ​ከ​ተም። ቃየ​ል​ንም እጅግ አሳ​ዘ​ነው፤ ፊቱም ጠቈረ።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ቃየ​ልን አለው፥ “ለምን ታዝ​ና​ለህ? ለም​ንስ ፊትህ ጠቈረ?</verse>
				<verse number="7">በእ​ው​ነት ያመ​ጣ​ህ​ልኝ አይ​ደ​ለም፤ አግ​ባ​ብስ በእ​ው​ነት ታመ​ጣ​ልኝ ዘንድ ነበር። በደ​ልህ፤ እን​ግ​ዲህ ዝም በል፤ የወ​ን​ድ​ምህ መመ​ለ​ሻው ወደ አንተ ነው፤ አን​ተም ትሰ​ለ​ጥ​ን​በ​ታ​ለህ።”</verse>
				<verse number="8">ቃየ​ልም ወን​ድ​ሙን አቤ​ልን፥ “ና ወደ ሜዳ እን​ሂድ” አለው። በሜ​ዳም ሳሉ ቃየል በወ​ን​ድሙ በአ​ቤል ላይ ተነ​ሣ​በት፤ ገደ​ለ​ውም።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃየ​ልን አለው፥ “ወን​ድ​ምህ አቤል ወዴት ነው?” ቃየ​ልም አለ፥ “አላ​ው​ቅም፤ በውኑ የወ​ን​ድሜ ጠባ​ቂው እኔ ነኝን?”</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “ቃየል! ምን አደ​ረ​ግህ? የወ​ን​ድ​ምህ የአ​ቤል የደሙ ድምፅ ከም​ድር ወደ እኔ ይጮ​ሃል።</verse>
				<verse number="11">አሁ​ንም የወ​ን​ድ​ም​ህን ደም ከእ​ጅህ ለመ​ቀ​በል አፍ​ዋን በከ​ፈ​ተች በም​ድር ላይ አንተ የተ​ረ​ገ​ምህ ነህ።</verse>
				<verse number="12">ምድ​ር​ንም ባረ​ስህ ጊዜ እን​ግ​ዲህ ኀይ​ል​ዋን አት​ሰ​ጥ​ህም፤ በም​ድር ላይ ኮብ​ላ​ይና ተቅ​በ​ዝ​ባዥ ትሆ​ና​ለህ።”</verse>
				<verse number="13">ቃየ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ኀጢ​አቴ ይቅር የማ​ት​ባል ታላቅ ናትን?</verse>
				<verse number="14">እነሆ፥ ዛሬ ከም​ድር ፊት ከአ​ሳ​ደ​ድ​ኸኝ፥ ከፊ​ትህ እሰ​ወ​ራ​ለሁ፤ በም​ድ​ርም ላይ ኮብ​ላ​ይና ተቅ​በ​ዝ​ባዥ እሆ​ና​ለሁ፤ የሚ​ያ​ገ​ኘ​ኝም ሁሉ ይገ​ድ​ለ​ኛል።”</verse>
				<verse number="15">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እን​ግ​ዲህ ቃየ​ልን የገ​ደለ ሁሉ ሰባት እጥፍ ይበ​ቀ​ል​በ​ታል።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃየ​ልን ያገ​ኘው ሁሉ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ለው ምል​ክት አደ​ረ​ገ​ለት።</verse>
				<verse number="16">ቃየ​ልም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወጣ፤ በኤ​ዶም አን​ጻር ባለ​ችው ኖድ በም​ት​ባ​ለው ምድ​ርም ኖረ።</verse>
				<verse number="17">ቃየ​ልም ሚስ​ቱን ዐወ​ቃት፤ ፀነ​ስ​ችም፤ ሄኖ​ሕ​ንም ወለ​ደች። ከተ​ማም ሠራ፤ የከ​ተ​ማ​ይ​ቱ​ንም ስም በልጁ ስም “ሄኖሕ” አላት።</verse>
				<verse number="18">ሄኖ​ሕም ጋይ​ዳ​ድን ወለደ፤ ጋይ​ዳ​ድም ሜኤ​ልን ወለደ፤ ሜኤ​ልም ማቱ​ሳ​ኤ​ልን ወለደ፤ ማቱ​ሳ​ኤ​ልም ላሜ​ሕን ወለደ።</verse>
				<verse number="19">ላሜ​ሕም ለራሱ ሁለት ሚስ​ቶ​ችን አገባ፤ የአ​ን​ዲቱ ስም ዓዳ፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ይቱ ስም ሴላ ነበር።</verse>
				<verse number="20">ዓዳም ዮቤ​ልን ወለ​ደች፤ እር​ሱም በድ​ን​ኳን የሚ​ቀ​መ​ጡት የዘ​ላ​ኖች አባት ነበረ።</verse>
				<verse number="21">የወ​ን​ድ​ሙም ስም ኢዮ​ቤል ነበር፤ እር​ሱም በገ​ና​ንና መሰ​ን​ቆን አስ​ተ​ማረ።</verse>
				<verse number="22">ሴላም ደግሞ ቶቤ​ልን ወለ​ደች። እር​ሱም ናስና ብረ​ትን የሚ​ሠራ ሆነ። የእ​ኅ​ቱም ስም ኖሄም ነበረ።</verse>
				<verse number="23">ላሜ​ሕም ለሚ​ስ​ቶቹ ለዓ​ዳና ለሴላ አላ​ቸው፥ “እና​ንት የላ​ሜሕ ሚስ​ቶች ቃሌን ስሙ፤ ነገ​ሬ​ንም አድ​ምጡ፤ እኔ ጐል​ማ​ሳ​ውን ስለ መቍ​ሰሌ፤ ብላ​ቴ​ና​ው​ንም ስለ መወ​ጋቴ ገድ​የ​ዋ​ለ​ሁና፤</verse>
				<verse number="24">ቃየ​ልን ሰባት እጥፍ ይበ​ቀ​ሉ​ታል፤ ላሜ​ሕን ግን ሰባ ጊዜ ሰባት።”</verse>
				<verse number="25">አዳ​ምም ዳግ​መኛ ሚስ​ቱን ዐወ​ቃት፤ ፀነ​ሰ​ችም፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች። ስሙ​ንም ቃየል በገ​ደ​ለው በአ​ቤል ፈንታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሌላ ዘር ተክ​ቶ​ል​ኛል ስትል ሴት አለ​ችው።</verse>
				<verse number="26">ሴትም ወንድ ልጅ ወለደ። ስሙ​ንም ሄኖስ አለው፤ እር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም መጥ​ራት የጀ​መረ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">የሰ​ዎች የት​ው​ልድ መጽ​ሐፍ ይህ ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዳ​ምን በፈ​ጠረ ቀን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሳሌ አደ​ረ​ገው፤</verse>
				<verse number="2">ወን​ድና ሴት አድ​ርጎ ፈጠ​ራ​ቸው፤ ባረ​ካ​ቸ​ውም። እነ​ር​ሱ​ንም በፈ​ጠ​ረ​በት ቀን ስሙን አዳም ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="3">አዳ​ምም ሁለት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ልጅ​ንም እንደ ምሳ​ሌው እንደ መልኩ ወለደ፤ ስሙ​ንም ሴት ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="4">አዳ​ምም ሴትን ከወ​ለደ በኋላ የኖ​ረው ሰባት መቶ ዓመት ሆነ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ።</verse>
				<verse number="5">አዳ​ምም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ፤ ሞተም።</verse>
				<verse number="6">ሴትም ሁለት መቶ አም​ስት ዓመት ኖረ፤ ሄኖ​ስ​ንም ወለደ፤</verse>
				<verse number="7">ሴትም ሄኖ​ስን ከወ​ለደ በኋላ ሰባት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ።</verse>
				<verse number="8">ሴትም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።</verse>
				<verse number="9">ሄኖ​ስም መቶ ዘጠና ዓመት ኖረ፤ ቃይ​ና​ን​ንም ወለደ፤</verse>
				<verse number="10">ሄኖ​ስም ቃይ​ና​ንን ከወ​ለደ በኋላ ሰባት መቶ ዐሥራ አም​ስት ዓመት ኖረ። ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ።</verse>
				<verse number="11">ሄኖ​ስም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አም​ስት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።</verse>
				<verse number="12">ቃይ​ና​ንም መቶ ሰባ ዓመት ኖረ፤ መላ​ል​ኤ​ል​ንም ወለደ፤</verse>
				<verse number="13">ቃይ​ና​ንም መላ​ል​ኤ​ልን ከወ​ለደ በኋላ ሰባት መቶ አርባ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ።</verse>
				<verse number="14">ቃይ​ና​ንም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ዐሥር ዓመት ሆነ፤ ሞተም።</verse>
				<verse number="15">መላ​ል​ኤ​ልም መቶ ስድሳ አም​ስት ዓመት ኖረ፤ ያሬ​ድ​ንም ወለደ፤</verse>
				<verse number="16">መላ​ል​ኤ​ልም ያሬ​ድን ከወ​ለደ በኋላ ሰባት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ።</verse>
				<verse number="17">መላ​ል​ኤ​ልም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ስም​ንት መቶ ዘጠና አም​ስት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።</verse>
				<verse number="18">ያሬ​ድም መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ኖረ፤ ሄኖ​ክ​ንም ወለደ፤</verse>
				<verse number="19">ያሬ​ድም ሄኖ​ክን ከወ​ለደ በኋላ ስም​ንት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ።</verse>
				<verse number="20">ያሬ​ድም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።</verse>
				<verse number="21">ሄኖ​ክም መቶ ስድሳ አም​ስት ዓመት ኖረ፤ ማቱ​ሳ​ላ​ንም ወለደ፤</verse>
				<verse number="22">ሄኖ​ክም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ አሰ​ኘው፤ ሄኖ​ክም ማቱ​ሳ​ላን ከወ​ለደ በኋላ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ።</verse>
				<verse number="23">ሄኖ​ክም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ሦስት መቶ ስድሳ አም​ስት ዓመት ሆነ።</verse>
				<verse number="24">ሄኖ​ክም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ ስላ​ሰ​ኘው አል​ተ​ገ​ኘም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው​ሮ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="25">ማቱ​ሳ​ላም መቶ ሰማ​ንያ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ላሜ​ሕ​ንም ወለደ፤</verse>
				<verse number="26">ማቱ​ሳ​ላም ላሜ​ሕን ከወ​ለደ በኋላ ሰባት መቶ ሰማ​ንያ ሁለት ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ።</verse>
				<verse number="27">ማቱ​ሳ​ላም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ዘጠኝ ዓመት ሆነ፤ ሞተም።</verse>
				<verse number="28">ላሜ​ሕም መቶ ሰማ​ንያ ሁለት ዓመት ኖረ፤ ልጅ​ንም ወለደ።</verse>
				<verse number="29">ስሙ​ንም ከሥ​ራዬ፥ ከእጄ ድካ​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከረ​ገ​ማት ምድር ይህ ያሳ​ር​ፈኝ ዘንድ አለው ሲል “ኖኅ” ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="30">ላሜ​ሕም ኖኅን ከወ​ለደ በኋላ አም​ስት መቶ ስድሳ አም​ስት ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም ወለደ።</verse>
				<verse number="31">ላሜ​ሕም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ሰባት መቶ አርባ ሰባት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።</verse>
				<verse number="32">ለኖ​ኅም አም​ስት መቶ ዓመት ሆነው፤ ኖህም ሦስት ልጆ​ችን ወለደ፤ እነ​ር​ሱም ሴም፥ ካምና ያፌት ናቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሰዎች በም​ድር ላይ መብ​ዛት በጀ​መሩ ጊዜ መልከ መል​ካ​ሞች ሴቶች ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ላ​ቸው፤</verse>
				<verse number="2">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆ​ችም የሰ​ውን ሴቶች ልጆች መል​ካ​ሞች እን​ደ​ሆኑ አዩ፤ ከመ​ረ​ጡ​አ​ቸ​ውም ሁሉ ሚስ​ቶ​ችን ለራ​ሳ​ቸው ወሰዱ።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “መን​ፈሴ በሰው ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ኖ​ርም፤ እነ​ርሱ ሥጋ ናቸ​ውና፤ ዘመ​ና​ቸ​ውም መቶ ሃያ ዓመት ይሆ​ናል” አለ።</verse>
				<verse number="4">በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት ረዓ​ይት በም​ድር ላይ ነበሩ። ከዚ​ያም በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ወደ ሰው ሴቶች ልጆች በገቡ ጊዜ ልጆ​ችን ወለ​ዱ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም በዱሮ ዘመን ስማ​ቸ​ውን ያስ​ጠሩ ኀያ​ላን ሰዎች ሆኑ።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሰ​ዎች ክፉ ሥራ በም​ድር ላይ እን​ደ​በዛ፥ የል​ባ​ቸው ዐሳብ ምኞ​ትም ሁል ጊዜ ፈጽሞ ክፉ እን​ደ​ሆነ አየ።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰውን በም​ድር ላይ በመ​ፍ​ጠሩ ተጸ​ጸተ፤ በል​ቡም አዘነ።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “የፈ​ጠ​ር​ሁ​ትን ሰው ከም​ድር ላይ አጠ​ፋ​ለሁ፤ ከሰው እስከ እን​ስ​ሳና አራ​ዊት፥ እስከ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሽም፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ፤ ስለ ፈጠ​ር​ኋ​ቸው ተጸ​ጽ​ቻ​ለ​ሁና” አለ።</verse>
				<verse number="8">ኖኅ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሞገ​ስን አገኘ።</verse>
				<verse number="9">የኖኅ ትው​ልድ እን​ዲህ ነው። ኖኅም በት​ው​ልዱ ጻድቅ፥ ፍጹ​ምም ሰው ነበረ፤ ኖኅም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ አሰ​ኘው።</verse>
				<verse number="10">ኖኅም ሦስት ልጆ​ችን ሴምን፥ ካምን ያፌ​ት​ንም ወለደ።</verse>
				<verse number="11">ምድ​ርም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተበ​ላ​ሸች፤ ምድ​ርም ግፍን ተመ​ላች።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምድ​ርን እንደ ተበ​ላ​ሸች፥ ሥጋን የለ​በሱ ሁሉም በም​ድር ላይ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን እንደ አበ​ላሹ አየ።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ኖኅን አለው፥ “የሰው ሁሉ ጊዜው በፊቴ ደር​ሶ​አል፤ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ነሣ ምድር በግፍ ተመ​ል​ታ​ለ​ችና፤ እኔም እነሆ፥ ከም​ድር ጋር አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">ባለ አራት መዓ​ዝን የዕ​ን​ጨት መር​ከ​ብን ለአ​ንተ ሥራ፤ በመ​ር​ከ​ቢ​ቱም ክፍ​ሎ​ችን አድ​ርግ፤ በው​ስ​ጥም፥ በው​ጭም በቅ​ጥ​ራን ለቅ​ል​ቃት።</verse>
				<verse number="15">መር​ከ​ብ​ዋ​ንም እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ታ​ለህ፤ የመ​ር​ከ​ቢቱ ርዝ​መት ሦስት መቶ ክንድ፥ ወር​ድዋ አምሳ ክንድ፥ ከፍ​ታዋ ሠላሳ ክንድ ይሁን።</verse>
				<verse number="16">ለመ​ር​ከ​ቢ​ቱም መስ​ኮ​ትን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ ከቁ​መ​ቷም ክንድ ሙሉ ትተህ ጨር​ሳት፤ የመ​ር​ከ​ቢ​ቱ​ንም በር በጎ​ንዋ አድ​ርግ፤ ታች​ኛ​ው​ንም፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም፥ ሦስ​ተ​ኛ​ው​ንም ደርብ ታደ​ር​ግ​ላ​ታ​ለህ።</verse>
				<verse number="17">እኔም እነሆ፥ ከሰ​ማይ በታች የሕ​ይ​ወት ነፍስ ያለ​ውን ሥጋ ሁሉ ለማ​ጥ​ፋት በም​ድር ላይ የጥ​ፋት ውኃን አመ​ጣ​ለሁ፤ በም​ድር ያለው ሁሉ ይጠ​ፋል።</verse>
				<verse number="18">ቃል ኪዳ​ኔ​ንም ከአ​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ፤ ወደ መር​ከ​ብም አንተ ልጆ​ች​ህ​ንና ሚስ​ት​ህን፥ የል​ጆ​ች​ህ​ንም ሚስ​ቶች ይዘህ ትገ​ባ​ለህ።</verse>
				<verse number="19">ከእ​ን​ስሳ ሁሉ፥ ከተ​ን​ቀ​ሳ​ቃሽ አራ​ዊ​ትም ሁሉ፥ ሥጋ ካለው ሁሉ ከአ​ንተ ጋር ትመ​ግ​ባ​ቸው ዘንድ ከሁ​ሉም ሁለት ሁለት ወደ መር​ከብ ታገ​ባ​ለህ፤ ተባ​ትና እን​ስት ይሁን።</verse>
				<verse number="20">ከወ​ፎች ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ ከእ​ን​ስ​ሳም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በም​ድር ላይ ከሚ​ሳቡ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ከአ​ንተ ጋር ይመ​ገቡ ዘንድ ከሁ​ሉም ሁለት ሁለት ወን​ድና ሴት እየ​ሆኑ ወደ አንተ ይግቡ።</verse>
				<verse number="21">ከሚ​በ​ላ​ውም የመ​ብል ዓይ​ነት ሁሉ ለአ​ንተ ውሰድ፤ ወደ አንተ ትሰ​በ​ስ​ባ​ለህ፤ እር​ሱም ለአ​ንተ፥ ለእ​ነ​ር​ሱም መብል ይሆ​ናል።”</verse>
				<verse number="22">ኖኅም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረገ፤ እን​ዲሁ አደ​ረገ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ኖኅን አለው፥ “አንተ ቤተ​ሰ​ቦ​ች​ህን ሁሉ ይዘህ ወደ መር​ከብ ግባ፤ በዚህ ትው​ልድ በፊቴ ጻድቅ ሆነህ አይ​ች​ሃ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="2">ከን​ጹሕ እን​ስሳ ሁሉ ሰባት ስባት ተባ​ትና እን​ስት፥ ንጹሕ ካል​ሆ​ነም እን​ስሳ ሁለት ሁለት ተባ​ትና እን​ስት፤</verse>
				<verse number="3">ከን​ጹሕ የሰ​ማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባ​ትና እን​ስት፥ ንጹሕ ካል​ሆነ የሰ​ማይ ወፍም ሁለት ሁለት ተባ​ትና እን​ስት እያ​ደ​ረ​ግህ በም​ድር ላይ ለም​ግ​ብና ለዘር ይቀር ዘንድ ለአ​ንተ ትወ​ስ​ዳ​ለህ።</verse>
				<verse number="4">ከሰ​ባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በም​ድር ላይ ዝናብ አዘ​ን​ባ​ለ​ሁና፤ የፈ​ጠ​ር​ሁ​ት​ንም ፍጥ​ረት ሁሉ ከም​ድር ሁሉ ላይ አጠ​ፋ​ለ​ሁና።”</verse>
				<verse number="5">ኖኅም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="6">ኖኅም የጥ​ፋት ውኃ በም​ድር ላይ በሆነ ጊዜ የስ​ድ​ስት መቶ ዓመት ዕድሜ ነበረ።</verse>
				<verse number="7">ኖኅም ስለ ጥፋት ውኃ ልጆ​ቹ​ንና ሚስ​ቱን፥ የል​ጆ​ቹ​ንም ሚስ​ቶች ይዞ ወደ መር​ከብ ገባ።</verse>
				<verse number="8">ከን​ጹ​ሓን ወፎ​ችና ንጹ​ሓን ካል​ሆኑ ወፎች፥ ከን​ጹሕ እን​ስሳ፥ ንጹ​ሕም ካል​ሆ​ነው እን​ስሳ፥ በም​ድር ላይ ከሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰው ሁሉ፥</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኖኅን እን​ዳ​ዘ​ዘው፥ ሁለት ሁለት ተባ​ትና እን​ስት እየ​ሆኑ ወደ ኖኅ ወደ መር​ከብ ውስጥ ገቡ።</verse>
				<verse number="10">ከሰ​ባት ቀን በኋ​ላም የጥ​ፋት ውኃ በም​ድር ላይ ሆነ።</verse>
				<verse number="11">በኖኅ ዕድሜ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው መቶ ዓመት በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ ሰባ​ተ​ኛው ዕለት፥ በዚ​ያው ቀን የታ​ላቁ ቀላይ ምን​ጮች ሁሉ ተነ​ደሉ፤ የሰ​ማይ መስ​ኮ​ቶ​ችም ተከ​ፈቱ፤</verse>
				<verse number="12">ዝና​ቡም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በም​ድር ላይ ሆነ።</verse>
				<verse number="13">በዚ​ያ​ውም ቀን ኖኅ ወደ መር​ከብ ገባ፤ የኖኅ ልጆ​ችም ሴም፥ ካም፥ ያፌ​ትና የኖኅ ሚስት፥ ሦስ​ቱም የል​ጆቹ ሚስ​ቶች ከእ​ርሱ ጋር ገቡ።</verse>
				<verse number="14">አራ​ዊ​ትም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ እን​ስ​ሳ​ትም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በም​ድር ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀሱ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ ወፎ​ችም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ የሚ​በሩ ወፎ​ችም ሁሉ፥</verse>
				<verse number="15">ሥጋ ያላ​ቸው ሕያ​ዋን ሁሉ ሁለት ሁለት እየ​ሆኑ ወደ ኖኅ መር​ከብ ውስጥ ገቡ።</verse>
				<verse number="16">ሥጋ ካለው ሁሉ የገ​ቡ​ትም ተባ​ትና እን​ስት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኖኅን እን​ዳ​ዘ​ዘው ገቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም መር​ከ​ብ​ዋን በስ​ተ​ውጭ ዘጋት።</verse>
				<verse number="17">የጥ​ፋት ውኃ በም​ድር ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ነበረ፤ ውኃ​ውም በዛ፤ መር​ከ​ቢ​ቱ​ንም አነሣ፤ ከም​ድ​ርም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለች።</verse>
				<verse number="18">ውኃ​ውም አሸ​ነፈ፤ በም​ድር ላይም እጅግ በዛ፤ መር​ከ​ቢ​ቱም በውኃ ላይ ተን​ሳ​ፈ​ፈች።</verse>
				<verse number="19">ውኃ​ውም በም​ድር ላይ እጅግ በጣም አሸ​ነፈ፤ ከሰ​ማይ በታች ያሉ ረዣ​ዥም ተራ​ሮ​ችን ሁሉ ሸፈነ።</verse>
				<verse number="20">ውኃው ወደ ላይ ዐሥራ አም​ስት ክንድ ከፍ ከፍ አለ፤ ረዣ​ዥም ተራ​ሮ​ች​ንም ሸፈነ።</verse>
				<verse number="21">በም​ድር ላይ ሥጋ ያለው የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰው ሁሉ ወፉም፥ እን​ስ​ሳ​ውም፥ አራ​ዊ​ቱም፥ በም​ድር ላይ የሚ​ር​መ​ሰ​መ​ሰው ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሹ​ም​ሁሉ፥ ሰውም ሁሉ ጠፋ።</verse>
				<verse number="22">የሕ​ይ​ወት እስ​ት​ን​ፋስ ያለው ሁሉ፥ በየ​ብ​ስም ያለው ሁሉ ሞተ።</verse>
				<verse number="23">በም​ድር ላይ የነ​በ​ረ​ውም ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ፥ እስ​ከ​ሚ​ር​መ​ሰ​መ​ሰ​ውም ሁሉ ድረስ፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ ተደ​መ​ሰሰ፤ ከም​ድ​ርም ተደ​መ​ሰሱ። ኖኅም አብ​ረ​ውት በመ​ር​ከብ ከነ​በ​ሩት ጋር ብቻ​ውን ቀረ።</verse>
				<verse number="24">ውኃ​ውም መቶ አምሳ ቀን በም​ድር ላይ ሞላ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኖኅን፥ በመ​ር​ከ​ብም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ረ​ውን አራ​ዊ​ቱን ሁሉ፥ እን​ስ​ሳ​ው​ንም ሁሉ፥ አዕ​ዋ​ፍ​ንም ሁሉ፥ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰ​ው​ንም ሁሉ ዐሰበ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድር ላይ ነፋ​ስን አመጣ፤ ውኃ​ውም ጐደለ፤</verse>
				<verse number="2">የቀ​ላ​ዩም ምን​ጮች፥ የሰ​ማ​ይም መስ​ኮ​ቶች ተደ​ፈኑ፤ ዝና​ብም ከሰ​ማይ ተከ​ለ​ከለ፤</verse>
				<verse number="3">ውኃ​ውም ከም​ድር ላይ እያ​ደር እየ​ቀ​ለለ ይሄድ ጀመረ፤ ከመቶ አምሳ ቀንም በኋላ ውኃው ጐደለ።</verse>
				<verse number="4">መር​ከ​ቢ​ቱም በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ቀን በአ​ራ​ራት ተራ​ሮች ላይ ተቀ​መ​ጠች።</verse>
				<verse number="5">ውኃ​ውም እስከ ዐሥ​ረ​ኛው ወር ድረስ ይጐ​ድል ነበር፤ በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የተ​ራ​ሮቹ ራሶች ተገ​ለጡ።</verse>
				<verse number="6">ከአ​ርባ ቀን በኋ​ላም ኖኅ የሠ​ራ​ውን የመ​ር​ከ​ቢ​ቱን መስ​ኮት ከፈተ፤</verse>
				<verse number="7">ከም​ድ​ርም ላይ ውኃዉ ጐድሎ እን​ደ​ሆነ ያይ ዘንድ ቁራ​ውን ላከው፤ እር​ሱም ሄደ፤ ነገር ግን ውኃው ከም​ድር ላይ እስ​ኪ​ደ​ርቅ ድረስ አል​ተ​መ​ለ​ሰም።</verse>
				<verse number="8">ርግ​ብ​ንም ውኃው ከም​ድር ፊት ጐድሎ እንደ ሆነ እን​ድ​ታይ ከእ​ርሱ በኋላ ላካት።</verse>
				<verse number="9">ነገር ግን ርግብ እግ​ር​ዋን የም​ታ​ሳ​ር​ፍ​በት ስፍራ አላ​ገ​ኘ​ችም፤ ወደ እር​ሱም ወደ መር​ከብ ተመ​ለ​ሰች፤ ውኃው በም​ድር ላይ ሁሉ ነበ​ረና፤ እጁን ዘረ​ጋና ተቀ​በ​ላት፤ ወደ እር​ሱም ወደ መር​ከብ ውስጥ አገ​ባት።</verse>
				<verse number="10">ከዚ​ያም በኋላ ደግሞ ሰባት ቀን ቆይቶ፥ ርግ​ብን እን​ደ​ገና ከመ​ር​ከብ ላካት።</verse>
				<verse number="11">ርግ​ብም በማታ ጊዜ ወደ እርሱ ተመ​ለ​ሰች፤ በአ​ፍ​ዋም እነሆ፥ የለ​መ​ለመ የወ​ይራ ቅጠል ይዛ ነበር። ኖኅም ከም​ድር ላይ ውኃው እንደ ጐደለ ዐወቀ።</verse>
				<verse number="12">ደግሞ ሰባት ቀን ቆይቶ፥ ርግ​ብን ላካት፤ ዳግ​መ​ኛም ወደ እርሱ አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም።</verse>
				<verse number="13">በኖኅ ዕድሜ በስ​ድ​ስት መቶ አንድ ዓመት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ውኃው ከም​ድር ላይ ደረቀ፤ ኖኅም የሠ​ራ​ትን የመ​ር​ከ​ቢ​ቱን ክዳን አነሣ፤ እነ​ሆም፥ ውኃው ከም​ድር ፊት እንደ ደረቀ አየ።</verse>
				<verse number="14">በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር ከወ​ሩም በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ቀን ምድር ደረ​ቀች።</verse>
				<verse number="15">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለኖኅ እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፤</verse>
				<verse number="16">“አንተ ሚስ​ት​ህ​ንና ልጆ​ች​ህን፥ የል​ጆ​ች​ህ​ንም ሚስ​ቶች ይዘህ ከመ​ር​ከብ ውጣ።</verse>
				<verse number="17">ከአ​ንተ ጋር ያሉ​ትን አራ​ዊት ሁሉ፥ ሥጋ ያላ​ቸ​ውን ሁሉ፥ ወፎ​ች​ንና እን​ስ​ሶ​ችን ሁሉ፥ በም​ድር ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ት​ንም ሁሉ ከአ​ንተ ጋር አው​ጣ​ቸው፤ በም​ድ​ርም ላይ ብዙ፤ ተባዙ። ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት።”</verse>
				<verse number="18">ኖኅም ሚስ​ቱን፥ ልጆ​ቹ​ንና የል​ጆ​ቹ​ንም ሚስ​ቶች ከእ​ርሱ ጋር ይዞ ወጣ፤</verse>
				<verse number="19">አራ​ዊት ሁሉ፥ እን​ስ​ሳም ሁሉ፥ ወፎ​ችም ሁሉ፥ በም​ድር ላይ የሚ​ር​መ​ሰ​መ​ሰው ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ከመ​ር​ከብ ወጡ።</verse>
				<verse number="20">ኖኅም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያ​ዉን ሠራ፥ ከን​ጹ​ሕም እን​ስሳ ሁሉ፥ ከን​ጹ​ሓን ወፎ​ችም ሁሉ ወሰደ፤ በመ​ሠ​ው​ያ​ውም ላይ መሥ​ዋ​ዕ​ትን አቀ​ረበ።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም መል​ካ​ሙን መዓዛ አሸ​ተተ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በልቡ አለ፥ “ምድ​ርን ዳግ​መኛ ስለ ሰዎች ሥራ አል​ረ​ግ​ምም፤ በሰው ልብ ከታ​ና​ሽ​ነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖ​ራል፤ ደግ​ሞም ከዚህ ቀደም እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ሁት ሕያ​ዋ​ንን ሁሉ እን​ደ​ገና አል​መ​ታም።</verse>
				<verse number="22">በም​ድር ዘመን ሁሉ መዝ​ራ​ትና ማጨድ፥ ብር​ድና ሙቀት፥ በጋና ክረ​ምት፥ ቀንና ሌሊት አያ​ቋ​ር​ጡም።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኖኅ​ንና ልጆ​ቹን ባረ​ካ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት፤ ግዙ​አ​ትም።</verse>
				<verse number="2">አስ​ፈ​ሪ​ነ​ታ​ች​ሁና አስ​ደ​ን​ጋ​ጭ​ነ​ታ​ችሁ በም​ድር አራ​ዊት፥ በሰ​ማይ ወፎች፥ በም​ድር ላይ በሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ትም፥ በባ​ሕር ዓሦ​ችም ሁሉ ላይ ይሁን፤ እነ​ር​ሱ​ንም በእ​ጃ​ችሁ ሰጠ​ኋ​ችሁ።</verse>
				<verse number="3">ሕይ​ወት ያለው ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ ሁሉ መብል ይሁ​ና​ችሁ፤ ሁሉ​ንም እንደ ለመ​ለመ ቡቃያ ሰጠ​ኋ​ችሁ።</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን ደመ ነፍስ ያለ​በ​ትን ሥጋ አት​ብሉ፤</verse>
				<verse number="5">ነፍ​ሳ​ችሁ ያለ​ች​በ​ትን ደማ​ች​ሁን ከአ​ራ​ዊት ሁሉ እጅ እሻ​ዋ​ለሁ፤ ከሰ​ውም እጅ፥ ከሰው ወን​ድም እጅ፥ የሰ​ውን ነፍስ እሻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="6">የሰ​ውን ደም የሚ​ያ​ፈ​ስስ ሁሉ ስለ​ዚያ ደም ፈንታ ደሙ ይፈ​ስ​ሳል፤ ሰውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መልክ ፈጥ​ሬ​ዋ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="7">እና​ን​ተም ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት፤ ግዙ​አ​ትም።”</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለኖኅ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ለል​ጆቹ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ፦</verse>
				<verse number="9">“እኔም እነሆ፥ ቃል ኪዳ​ኔን ከእ​ና​ንተ ጋር፥ ከእ​ና​ን​ተም በኋላ ከዘ​ራ​ችሁ ጋር አጸ​ና​ለሁ፤</verse>
				<verse number="10">ከእ​ና​ንተ ጋር ላሉ​ትም፥ ሕያው ነፍስ ላላ​ቸው ሁሉ፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ከመ​ር​ከብ ለወ​ጡት ለወ​ፎች፥ ለእ​ን​ስ​ሳ​ትም፥ ለም​ድር አራ​ዊ​ትም ሁሉ፥ ለማ​ን​ኛ​ውም ለም​ድር አራ​ዊት ሁሉ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="11">ቃል ኪዳ​ኔ​ንም ከእ​ና​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ፤ ሥጋ ያለ​ውም ሁሉ ዳግ​መኛ በጥ​ፋት ውኃ አይ​ጠ​ፋም፤ ምድ​ር​ንም ለማ​ጥ​ፋት ዳግ​መኛ የጥ​ፋት ውኃ አይ​ሆ​ንም።”</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ለኖኅ አለው፥ “በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል፥ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ባለው በሕ​ያው ነፍስ ሁሉ መካ​ከል፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ትው​ልድ የማ​ደ​ር​ገው የቃል ኪዳኔ ምል​ክት ይህ ነው፤</verse>
				<verse number="13">ቀስ​ቴን በደ​መና አኖ​ራ​ለሁ፤ የቃል ኪዳ​ኔም ምል​ክት በእ​ኔና በም​ድር መካ​ከል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="14">በም​ድር ላይ ደመ​ናን በጋ​ረ​ድሁ ጊዜ ቀስቴ በደ​መ​ናው ትታ​ያ​ለች፤</verse>
				<verse number="15">በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል፥ ሕያው ነፍስ ባለ​ውም ሥጋ ሁሉ መካ​ከል ያለ​ውን ቃል ኪዳ​ኔን አስ​ባ​ለሁ፤ ሥጋ ያለ​ው​ንም ሁሉ ያጠፋ ዘንድ ዳግ​መኛ የጥ​ፋት ውኃን አላ​መ​ጣም።</verse>
				<verse number="16">ቀስ​ቴም በደ​መና ትሆ​ና​ለች፤ በእ​ኔና በም​ድር መካ​ከል፥ በም​ድር ላይ በሚ​ኖር ሥጋ ባለው በሕ​ያው ነፍስ ሁሉ መካ​ከል ያለ​ውን የዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳን ለማ​ሰብ አያ​ታ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኖኅን፥ “በእ​ኔና በም​ድር ላይ በሚ​ኖር፥ ሥጋ ባለው ሁሉ መካ​ከል ያጸ​ና​ሁት የቃል ኪዳን ምል​ክት ይህ ነው” አለው።</verse>
				<verse number="18">ከመ​ር​ከብ የወ​ጡት የኖኅ ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ሴም፥ ካም፥ ያፌት፤ ካምም የከ​ነ​ዓን አባት ነው።</verse>
				<verse number="19">በም​ድር ሁሉ ላይ የተ​በ​ተኑ የኖኅ ልጆች እነ​ዚህ ሦስቱ ናቸው።</verse>
				<verse number="20">ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፤ ወይ​ንም ተከለ።</verse>
				<verse number="21">ከወ​ይን ጠጁም ጠጣና ሰከረ፤ በድ​ን​ኳ​ኑም ውስጥ ዕራ​ቁ​ቱን ሆነ።</verse>
				<verse number="22">የከ​ነ​ዓን አባት ካምም የአ​ባ​ቱን ዕራ​ቁ​ት​ነት አየ፤ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁ​ለቱ ወን​ድ​ሞቹ ነገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">ሴምና ያፌ​ትም ልብስ ወስ​ደው በጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ አደ​ረጉ፤ የኋ​ሊ​ትም ሄደው የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን ዕራ​ቁ​ት​ነት አለ​በሱ፤ ፊታ​ቸ​ውም ወደ ኋላ ነበር፤ የአ​ባ​ታ​ቸ​ው​ንም ዕራ​ቁ​ት​ነት አላ​ዩም።</verse>
				<verse number="24">ኖኅም ከወ​ይኑ ስካር በነቃ ጊዜ፥ ታናሹ ልጁ ያደ​ረ​ገ​በ​ትን ዐወቀ።</verse>
				<verse number="25">ኖኅም እን​ዲህ አለ፥ “ከነ​ዓን ርጉም ይሁን፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም የባ​ሪ​ያ​ዎች ባሪያ ይሁን።”</verse>
				<verse number="26">እን​ዲ​ህም አለ፥ “የሴም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ረክ፤ ከነ​ዓ​ንም ለእ​ርሱ ባሪያ ይሁን።</verse>
				<verse number="27">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የያ​ፌ​ትን ሀገር ያስፋ፤ በሴ​ምም ድን​ኳን ይደር፤ ከነ​ዓ​ንም ለእ​ርሱ ባሪያ ይሁን።”</verse>
				<verse number="28">ኖኅም ከጥ​ፋት ውኃ በኋላ ሦስት መቶ አምሳ ዓመት ኖረ።</verse>
				<verse number="29">ኖኅም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አምሳ ዓመት ሆነ፤ ሞተም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">የኖኅ ልጆች የሴም፥ የካ​ምና፥ የያ​ፌት ትው​ልድ ይህ ነው፤ ከጥ​ፋት ውኃም በኋላ ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">የያ​ፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ይህ​ያን፥ ይልሳ፥ ቶቤል፥ሞሳሕ፥ ቴራስ ናቸው።</verse>
				<verse number="3">የጋ​ሜ​ርም ልጆች አስ​ከ​ናዝ፥ ሪፋት፥ ቴር​ጋማ ናቸው።</verse>
				<verse number="4">የይ​ህ​ያ​ንም ልጆች ኤልሳ፥ ተር​ሴስ፥ ኬቲም፥ ሮድኢ ናቸው።</verse>
				<verse number="5">ከእ​ነ​ዚ​ህም የአ​ሕ​ዛብ ደሴ​ቶች ሁሉ በየ​ም​ድ​ራ​ቸው፥ በየ​ቋ​ን​ቋ​ቸው፥ በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው፥ በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸው ተከ​ፋ​ፈሉ።</verse>
				<verse number="6">የካ​ምም ልጆች ኩሽ፥ ምስ​ራ​ይም፥ ፉጥ፥ ከነ​ዓን ናቸው።</verse>
				<verse number="7">የኩ​ሽም ልጆች ሳባ፥ ኤው​ላጥ፥ ሰብታ፥ ሬጌም፥ ሰበ​ቅታ ናቸው። የሬ​ጌም ልጆ​ችም ሳባ፥ ዮድ​ዳን ናቸው።</verse>
				<verse number="8">ኩሽም ናም​ሩ​ድን ወለደ፤ እር​ሱም በም​ድር ላይ ኀያል መሆን ጀመረ።</verse>
				<verse number="9">እር​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ኀያል አዳኝ ነበረ፤ ስለ​ዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ኀያል አዳኝ እንደ ናም​ሩድ ተባለ።</verse>
				<verse number="10">የግ​ዛ​ቱም መጀ​መ​ሪያ በሰ​ና​ዖር ሀገር ባቢ​ሎን፥ ኦሬክ፥ አር​ካድ፥ ካሌ​ድን ናቸው።</verse>
				<verse number="11">አሦ​ርም ከዚ​ያች ሀገር ወጣ፤ ነነ​ዌን፥ ረሆ​ቦት የተ​ባ​ለ​ች​ውን ከተማ ካለ​ህን፥</verse>
				<verse number="12">በነ​ነ​ዌና በካ​ለህ መካ​ከ​ልም ዳስን ሠራ፤ እር​ስ​ዋም ታላ​ቂቱ ከተማ ናት።</verse>
				<verse number="13">ምስ​ራ​ይ​ምም ሉዲ​ምን፥ ኢኒ​ሜ​ቲ​ምን፥ ላህ​ቢ​ምን፥ ንፍ​ታ​ሌ​ምን፥ ጳጥ​ሮ​ሶ​ኒ​ምን፥</verse>
				<verse number="14">ከእ​ነ​ርሱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሰዎች የወ​ጡ​ባ​ቸ​ውን ከስ​ሎ​ሂ​ም​ንና ቀፍ​ቶ​ሪ​ም​ንም ወለደ።</verse>
				<verse number="15">ከነ​ዓ​ንም የበ​ኵር ልጁን ሲዶ​ንን፥ ኬጤ​ዎ​ንን፥</verse>
				<verse number="16">ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ንን፥ አሞ​ሬ​ዎ​ንን፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ንን፥</verse>
				<verse number="17">ኤዌ​ዎ​ንን፥ አሩ​ቄ​ዎ​ንን፥ ኤሴ​ኒ​ዎ​ንን፥</verse>
				<verse number="18">አራ​ዲ​ዎ​ንን፥ ሰማ​ር​ዮ​ንን፥ አማ​ቲ​ንን ወለደ። ከዚ​ህም በኋላ የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ነገድ ተበ​ተኑ።</verse>
				<verse number="19">የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ወሰን ከሲ​ዶን እስከ ጌራ​ራና ጋዛ ድረስ ነው፤ ወደ ሰዶ​ምና ወደ ገሞራ፥ ወደ አዳ​ማና ወደ ሴባ​ዮም እስከ ላሳ ይደ​ር​ሳል።</verse>
				<verse number="20">የካም ልጆች በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸ​ውና በየ​ቋ​ን​ቋ​ቸው፥ በየ​ም​ድ​ራ​ቸ​ውና በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="21">ለሴ​ምም ደግሞ ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ እር​ሱም የያ​ፌት ታላቅ ወን​ድ​ምና የዔ​ቦር ልጆች ሁሉ አባት የሆ​ነው ነው።</verse>
				<verse number="22">የሴ​ምም ልጆች ኤላም፥ አሦር፥ አር​ፋ​ክ​ስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ ቃይ​ናን።</verse>
				<verse number="23">የአ​ራ​ምም ልጆች ዑፅ፥ ሁል፥ ጋቴር፥ ሞሳሕ ናቸው።</verse>
				<verse number="24">አር​ፋ​ክ​ስ​ድም ቃይ​ና​ንን ወለደ፤ ቃይ​ና​ንም ሳላን፥ ሳላም ዔቦ​ርን ወለደ።</verse>
				<verse number="25">ለዔ​ቦ​ርም ሁለት ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ የአ​ን​ደ​ኛው ስሙ ፋሌቅ ነው፤ ምድር በዘ​መኑ ተከ​ፍ​ላ​ለ​ችና፤ የወ​ን​ድ​ሙም ስም ዮቅ​ጣን ነው።</verse>
				<verse number="26">ዮቅ​ጣ​ንም ኤል​ሞ​ዳ​ድን፥ ሳሌ​ፍ​ንም፥ ሐሰ​ረ​ሞ​ት​ንም፥ ያራ​ሕ​ንም፥</verse>
				<verse number="27">ሀዶ​ራ​ም​ንም፥ አዚ​ላ​ንም፥ ደቅ​ላ​ንም፥</verse>
				<verse number="28">ዖባ​ል​ንም፥ አቤ​ማ​ኤ​ል​ንም፥ ሳባ​ንም፥</verse>
				<verse number="29">አፌ​ር​ንም፥ ኤው​ላ​ጥ​ንም፥ ዮባ​ብ​ንም ወለደ፤ እነ​ዚህ ሁሉ የዮ​ቅ​ጣን ልጆች ናቸው።</verse>
				<verse number="30">ስፍ​ራ​ቸ​ውም ከማሲ አን​ስቶ ወደ ስፋር ሲል እስከ ምሥ​ራቅ ተራራ ድረስ ነው።</verse>
				<verse number="31">የሴም ልጆች በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸ​ውና በየ​ቋ​ን​ቋ​ቸው፥ በየ​ም​ድ​ራ​ቸ​ውና በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="32">የኖኅ የል​ጆቹ ነገ​ዶች እንደ ትው​ል​ዳ​ቸው በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው። ከእ​ነ​ዚ​ህም ከጥ​ፋት ውኃ በኋላ ሕዝ​ቦች በም​ድር ላይ ተዘሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">የዓ​ለም ሁሉ ቋንቋ አንድ፥ ንግ​ግ​ሩም አንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="2">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከም​ሥ​ራ​ቅም ተነ​ሥ​ተው በሄዱ ጊዜ በሰ​ና​ዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="3">እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ኑ ጡብ እን​ሥራ፤ በእ​ሳ​ትም እን​ተ​ኵ​ሰው” ተባ​ባሉ። ጡባ​ቸ​ውም እንደ ድን​ጋይ፥ ጭቃ​ቸ​ውም እንደ ዝፍት ሆነ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ኑ ለእኛ ከተ​ማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚ​ደ​ርስ ግንብ እን​ሥራ፤ በም​ድር ፊት ሁሉ ላይ ሳን​በ​ተን ስማ​ች​ንን እና​ስ​ጠ​ራው” ተባ​ባሉ።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሰ​ዎች ልጆች የሠ​ሩ​ትን ከተ​ማና ግንብ ለማ​የት ወረደ።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “እነሆ፥ እነ​ርሱ አንድ ወገን ናቸው፤ ለሁ​ሉም አንድ ቋንቋ አላ​ቸው፤ ይህ​ንም ለማ​ድ​ረግ ጀመሩ፤ አሁ​ንም ያሰ​ቡ​ትን ሁሉ መሥ​ራ​ትን አይ​ተ​ዉም።</verse>
				<verse number="7">ኑ እን​ው​ረድ፤ አንዱ የሌ​ላ​ውን ነገር እን​ዳ​ይ​ሰ​ማው ቋን​ቋ​ቸ​ውን በዚያ እን​ደ​ባ​ል​ቀው።”</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቋን​ቋ​ቸ​ውን ለያየ፤ ከዚ​ያም በም​ድር ፊት ሁሉ ላይ በተ​ና​ቸው፤ ከዚ​ያም በኋላ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንና ግን​ቡን መሥ​ራ​ትን ተዉ።</verse>
				<verse number="9">ስለ​ዚ​ህም ስምዋ ባቢ​ሎን ተባለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ የም​ድ​ርን ቋንቋ ሁሉ ደባ​ል​ቆ​አ​ልና፤ ከዚ​ያም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ሁሉ ፊት ላይ እነ​ር​ሱን በት​ኖ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="10">የሴም ትው​ልድ ይህ ነው። ሴም ከጥ​ፋት ውኃ በኋላ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት አር​ፋ​ክ​ስ​ድን በወ​ለደ ጊዜ የመቶ ዓመት ሰው ነበረ።</verse>
				<verse number="11">ሴምም አር​ፋ​ክ​ስ​ድን ከወ​ለደ በኋላ አም​ስት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም።</verse>
				<verse number="12">አር​ፋ​ክ​ስ​ድም መቶ ሠላሳ አም​ስት ዓመት ኖረ፤ ቃይ​ና​ን​ንም ወለደ፤</verse>
				<verse number="13">አር​ፋ​ክ​ስ​ድም ቃይ​ና​ንን ከወ​ለደ በኋላ አራት መቶ አርባ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም። ቃይ​ና​ንም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ሳላ​ንም ወለደ፤ ቃይ​ና​ንም ሳላን ከወ​ለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ልጆች ወለደ፤ ሞተም።</verse>
				<verse number="14">ሳላም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ዔቦ​ር​ንም ወለደ፤</verse>
				<verse number="15">ሳላም ዔቦ​ርን ከወ​ለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም።</verse>
				<verse number="16">ዔቦ​ርም መቶ ሠላሳ አራት ዓመት ኖረ፤ ፋሌ​ቅ​ንም ወለደ፤</verse>
				<verse number="17">ዔቦ​ርም ፋሌ​ቅን ከወ​ለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም።</verse>
				<verse number="18">ፋሌ​ቅም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ራግ​ው​ንም ወለደ፤</verse>
				<verse number="19">ፋሌ​ቅም ራግ​ውን ከወ​ለደ በኋላ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም።</verse>
				<verse number="20">ራግ​ውም መቶ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ፤ ሴሮ​ሕ​ንም ወለደ፤</verse>
				<verse number="21">ራግ​ውም ሴሮ​ሕን ከወ​ለደ በኋላ ሁለት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም።</verse>
				<verse number="22">ሴሮ​ሕም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ናኮ​ር​ንም ወለደ፤</verse>
				<verse number="23">ሴሮ​ሕም ናኮ​ርን ከወ​ለደ በኋላ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም።</verse>
				<verse number="24">ናኮ​ርም መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ ታራ​ንም ወለደ፤</verse>
				<verse number="25">ታራ​ንም ከወ​ለደ በኋላ ናኮር መቶ ሀያ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም።</verse>
				<verse number="26">ታራም መቶ ዓመት ኖረ፥ አብ​ራ​ም​ንና ናኮ​ርን፥ አራ​ን​ንም ወለደ።</verse>
				<verse number="27">አራ​ንም ሎጥን ወለደ።</verse>
				<verse number="28">አራ​ንም በተ​ወ​ለ​ደ​ባት ሀገር በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር በአ​ባቱ በታራ ፊት ሞተ።</verse>
				<verse number="29">አብ​ራ​ምና ናኮ​ርም ሚስ​ቶ​ችን አገቡ፤ የአ​ብ​ራም ሚስት ስምዋ ሦራ ነው፤ የና​ኮ​ርም ሚስት የአ​ራን ልጅ ሚልካ ናት፤ አራ​ንም የሚ​ል​ካና የዮ​ስካ አባት ነው።</verse>
				<verse number="30">ሦራም መካን ነበ​ረች፤ ልጆ​ችም አል​ነ​በ​ሩ​አ​ትም።</verse>
				<verse number="31">ታራም ልጁን አብ​ራ​ም​ንና የልጅ ልጁን የአ​ራ​ንን ልጅ ሎጥን፥ የል​ጁ​ንም የአ​ብ​ራ​ምን ሚስት ምራ​ቱን ሦራን ወሰደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ወደ ከነ​ዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር አወ​ጣ​ቸው። ወደ ካራ​ንም መጡ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="32">ታራም በካ​ራን ምድር የኖ​ረ​በት ዘመን ሁለት መቶ አም​ስት ዓመት ሆነ፤ ታራም በካ​ራን ሞተ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ራ​ምን አለው፥ “ከሀ​ገ​ርህ፥ ከዘ​መ​ዶ​ች​ህም፥ ከአ​ባ​ት​ህም ቤት ተለ​ይ​ተህ ውጣ፤ እኔ ወደ​ማ​ሳ​ይ​ህም ምድር ሂድ።</verse>
				<verse number="2">ታላቅ ሕዝ​ብም አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፤ ስም​ህ​ንም ከፍ ከፍ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ቡሩ​ክም ትሆ​ና​ለህ፤ የሚ​ባ​ር​ኩ​ህ​ንም እባ​ር​ካ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="3">የሚ​ረ​ግ​ሙ​ህ​ንም እረ​ግ​ማ​ለሁ፤ የም​ድር ነገ​ዶ​ችም ሁሉ በአ​ንተ ይባ​ረ​ካሉ።”</verse>
				<verse number="4">አብ​ራ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ረው ሄደ፤ ሎጥም ከእ​ርሱ ጋር ሄደ፤ አብ​ራ​ምም ከካ​ራን በወጣ ጊዜ ሰባ አም​ስት ዓመት ሆኖት ነበረ።</verse>
				<verse number="5">አብ​ራ​ምም ሚስ​ቱን ሦራ​ንና የወ​ን​ድ​ሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገ​ኙ​ትን ከብት ሁሉና በካ​ራን ያገ​ኙ​አ​ቸ​ውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነ​ዓን ምድር ለመ​ሄድ ወጣ፤ ወደ ከነ​ዓ​ንም ምድር ገቡ።</verse>
				<verse number="6">አብ​ራ​ምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ታላቁ ዛፍ ድረስ በዚ​ያች ምድር አለፈ፤ የከ​ነ​ዓን ሰዎ​ችም በዚ​ያን ጊዜ በዚ​ያች ምድር ነበሩ።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ብ​ራም ተገ​ለ​ጠ​ለ​ትና፥ “ይህ​ችን ምድር ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ” አለው። አብ​ራ​ምም ለእ​ርሱ ለተ​ገ​ለ​ጠ​ለት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ መሠ​ው​ያን ሠራ።</verse>
				<verse number="8">ከዚ​ያም በቤ​ቴል ምሥ​ራቅ ወዳ​ለው ተራራ ወጣ፤ በዚ​ያም ቤቴ​ልን ወደ ምዕ​ራብ፥ ጋይን ወደ ምሥ​ራቅ አድ​ርጎ ድን​ኳ​ኑን ተከለ፤ በዚ​ያም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያን ሠራ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ጠራ።</verse>
				<verse number="9">አብ​ራ​ምም ከዚያ ተነሣ፤ እየ​ተ​ጓ​ዘም ወደ አዜብ ሄደ፤ በዚ​ያም ኖረ።</verse>
				<verse number="10">በም​ድ​ርም ራብ ሆነ፤ አብ​ራ​ምም በዚያ በእ​ን​ግ​ድ​ነት ይቀ​መጥ ዘንድ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በም​ድር ራብ ጠንቶ ነበ​ረና።</verse>
				<verse number="11">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ አብ​ራም ወደ ግብፅ ለመ​ግ​ባት በቀ​ረበ ጊዜ ሚስ​ቱን ሦራን እን​ዲህ አላት፥ “አንቺ መልከ መል​ካም ሴት እንደ ሆንሽ እነሆ እኔ አው​ቃ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="12">የግ​ብፅ ሰዎች ያዩሽ እንደ ሆነ ሚስቱ ናት ይላሉ፤ እኔ​ንም ይገ​ድ​ሉ​ኛል፤ አን​ቺ​ንም በሕ​ይ​ወት ይተ​ዉ​ሻል።</verse>
				<verse number="13">እን​ግ​ዲህ በአ​ንቺ ምክ​ን​ያት መል​ካም ይሆ​ን​ልኝ ዘንድ፥ ስለ አን​ቺም ነፍሴ ትድን ዘንድ እኅቱ ነኝ በዪ።”</verse>
				<verse number="14">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ አብ​ራም ወደ ግብፅ በገባ ጊዜ የግ​ብፅ ሰዎች ሴቲ​ቱን እጅግ ውብ እንደ ሆነች አዩ፤</verse>
				<verse number="15">የፈ​ር​ዖ​ንም አለ​ቆች አዩ​አት፤ በፈ​ር​ዖ​ንም ፊት አደ​ነ​ቁ​አት፤ ወደ ፈር​ዖን ቤትም ወሰ​ዱ​አት።</verse>
				<verse number="16">ለአ​ብ​ራ​ምም ስለ እር​ስዋ መል​ካም አደ​ረ​ጉ​ለት፤ ለእ​ርሱ በጎ​ችም፥ በሬ​ዎ​ችም፥ አህ​ዮ​ችም፥ በቅ​ሎ​ዎ​ችም፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎ​ችም፥ ግመ​ሎ​ችም ነበ​ሩት።</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ብ​ራም ሚስት በሦራ ምክ​ን​ያት ፈር​ዖ​ን​ንና የቤ​ቱን ሰዎች በታ​ላቅ መቅ​ሠ​ፍት መታ።</verse>
				<verse number="18">ፈር​ዖ​ንም አብ​ራ​ምን ጠርቶ አለው፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብኝ ምን​ድን ነው? እር​ስዋ ሚስ​ትህ እንደ ሆነች ለምን አል​ገ​ለ​ጥ​ህ​ል​ኝም?</verse>
				<verse number="19">ለም​ንስ ‘እኅቴ ናት’ አልህ? ለእኔ ሚስት ትሆ​ነኝ ዘንድ ወስ​ጃት ነበር። አሁ​ንም እነ​ኋት፥ ሚስ​ትህ በፊ​ትህ ናት፤ ይዘ​ሃ​ትም ሂድ።”</verse>
				<verse number="20">ፈር​ዖ​ንም ሰዎ​ቹን ስለ አብ​ራም አዘዘ፤ እር​ሱ​ንም፥ ሚስ​ቱ​ንም፥ የነ​በ​ረ​ው​ንም ሁሉ ሸኙ​አ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">አብ​ራ​ምም ከግ​ብፅ ወጣ፤ እር​ሱና ሚስቱ፥ ለእ​ርሱ የነ​በ​ረ​ውም ሁሉ፥ ሎጥም ከእ​ርሱ ጋር ወደ አዜብ ወጡ።</verse>
				<verse number="2">አብ​ራ​ምም በከ​ብት፥ በብ​ርና በወ​ርቅ እጅግ በለ​ጸገ።</verse>
				<verse number="3">ከአ​ዜብ ባደ​ረ​ገው በጕ​ዞ​ውም ወደ ቤቴል ሄደ፤ ያም ስፍራ አስ​ቀ​ድሞ በቤ​ቴ​ልና በጋይ መካ​ከል ድን​ኳን ተክ​ሎ​በት የነ​በ​ረው ነው፤</verse>
				<verse number="4">ስፍ​ራ​ውም አስ​ቀ​ድሞ መሠ​ውያ የሠ​ራ​በት ነው፤ በዚ​ያም አብ​ራም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ጠራ።</verse>
				<verse number="5">ከአ​ብ​ራም ጋር የሄ​ደው ሎጥ ደግሞ የላ​ምና የበግ መንጋ ድን​ኳ​ኖ​ችም ነበ​ሩት።</verse>
				<verse number="6">በአ​ን​ድ​ነ​ትም ይቀ​መጡ ዘንድ ምድር አል​በ​ቃ​ቸ​ውም፤ ንብ​ረ​ታ​ቸው ብዙ ነበ​ርና፤ ስለ​ዚ​ህም ባን​ድ​ነት ይቀ​መጡ ዘንድ ምድር አል​በ​ቃ​ቻ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="7">በአ​ብ​ራ​ምና በሎጥ መን​ጎች ጠባ​ቆች መካ​ከ​ልም ጠብ ሆነ፤ በዚያ ዘመን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንና ፌር​ዛ​ው​ያን በዚ​ያች ምድር ተቀ​ም​ጠው ነበር።</verse>
				<verse number="8">አብ​ራ​ምም ሎጥን አለው፥ “እኛ ወን​ድ​ማ​ማች ነንና በእ​ኔና በአ​ንተ፥ በእ​ረ​ኞ​ቼና በእ​ረ​ኞ​ችህ መካ​ከል ጠብ አይ​ሁን።</verse>
				<verse number="9">እነሆ፥ ምድር ሁሉ በፊ​ትህ አይ​ደ​ለ​ች​ምን? ከእኔ ትለይ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ አንተ ወደ ግራው ብት​ሄድ እኔ ወደ ቀኝ እሄ​ዳ​ለሁ፤ አን​ተም ወደ ቀኙ ብት​ሄድ እኔ ወደ ግራ እሄ​ዳ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="10">ሎጥም ዓይ​ኖ​ቹን አነሣ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ዙሪያ ያለ​ው​ንም ሀገር ሁሉ ውኃ የሞ​ላ​በት መሆ​ኑን አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰዶ​ም​ንና ገሞ​ራን ከማ​ጥ​ፋቱ አስ​ቀ​ድሞ እስከ ሴጎር ድረስ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነ​ትና እንደ ግብፅ ምድር እንደ ነበረ አየ።</verse>
				<verse number="11">ሎጥም ለራሱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ዙሪያ ያለ​ውን ሀገር ሁሉ መረጠ፤ ሎጥም ወደ ምሥ​ራቅ ተጓዘ፤ አን​ዱም ከሌ​ላው እርስ በር​ሳ​ቸው ተለ​ያዩ።</verse>
				<verse number="12">አብ​ራም በከ​ነ​ዓን ምድር ተቀ​መጠ፤ ሎጥም በጎ​ረ​ቤት ሕዝ​ቦች ከተማ ተቀ​መጠ፤ ድን​ኳ​ኑ​ንም በሰ​ዶም ተከለ፤</verse>
				<verse number="13">የሰ​ዶም ሰዎች ግን ክፉ​ዎ​ችና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጅግ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ነበሩ።</verse>
				<verse number="14">ሎጥ ከተ​ለ​የው በኋ​ላም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ​ራ​ምን አለው፥ “ዐይ​ን​ህን አን​ሣና አንተ ካለ​ህ​በት ስፍራ ወደ መስ​ዕና ወደ አዜብ፥ ወደ ምሥ​ራ​ቅና ወደ ምዕ​ራብ እይ፤</verse>
				<verse number="15">የም​ታ​ያ​ትን ምድር ሁሉ ለአ​ን​ተና ለዘ​ርህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እሰ​ጣ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="16">ዘር​ህ​ንም እንደ ባሕር አሸዋ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የባ​ሕር አሸ​ዋን ይቈ​ጥር ዘንድ የሚ​ችል ሰው ቢኖር ዘርህ ደግሞ ይቈ​ጠ​ራል።</verse>
				<verse number="17">ተነሣ፤ በም​ድር በር​ዝ​መ​ቷም፥ በስ​ፋ​ቷም ዙር፤ እር​ስ​ዋን ለአ​ን​ተና ለዘ​ርህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እሰ​ጣ​ለ​ሁና።”</verse>
				<verse number="18">አብ​ራ​ምም ድን​ኳ​ኑን ነቀለ፤ መጥ​ቶም በኬ​ብ​ሮን ባለው የመ​ምሬ ዛፍ ተቀ​መጠ፤ በዚ​ያም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያን ሠራ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">በሰ​ና​ዖር ንጉሥ በአ​ሚ​ሮ​ፌል፥ በእ​ላ​ሳር ንጉሥ በአ​ር​ዮክ፥ በኤ​ላም ንጉሥ በኮ​ሎ​ዶ​ጎ​ሞር፥ በአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ በቴ​ሮ​ጋል ዘመን እን​ዲህ ሆነ፤</verse>
				<verse number="2">ከሰ​ዶም ንጉሥ ከባላ፥ ከገ​ሞራ ንጉሥ ከበ​ርሳ፥ ከአ​ዳማ ንጉሥ ከሰ​ና​አር፥ ከሲ​ባዮ ንጉሥ ከሲ​ም​ቦር፤ ሴጎር ከተ​ባ​ለች ከባላ ንጉ​ሥም ጋር ጦር​ነት አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="3">እነ​ዚህ ሁሉ በኤ​ሌ​ቄን ሸለቆ ተሰ​ብ​ስ​በው ተባ​በሩ፤ ይኸ​ውም የጨው ባሕር ነው።</verse>
				<verse number="4">ዐሥራ ሁለት ዓመት ለኮ​ሎ​ዶ​ጎ​ሞር ተገዙ፤ በዐ​ሥራ ሦስ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ዐመፁ።</verse>
				<verse number="5">በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ኮሎ​ዶ​ጎ​ሞ​ርና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ነገ​ሥ​ታት መጡ፤ ረዐ​ይ​ትን በአ​ስ​ጣ​ሮት ቃር​ና​ይም፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ጽኑ​ዓን ሰዎ​ች​ንና ኦሚ​ዎ​ስን በሴዊ ከተማ ገደ​ሉ​አ​ቸው፤</verse>
				<verse number="6">በሴ​ይር ተራ​ራ​ዎች ያሉ የኬ​ሬ​ዎስ ሰዎ​ች​ንም በበ​ረሃ አጠ​ገብ እስከ አለ​ችው እስከ ፋራን ዛፍ ድረስ መቱ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">ተመ​ል​ሰ​ውም ቃዴስ ወደ ተባ​ለች ወደ ፍርድ ምንጭ መጡ፤ የአ​ማ​ሌ​ቅን አለ​ቆች ሁሉና በአ​ሳ​ሶን ታማር የሚ​ኖሩ አሞ​ራ​ው​ያ​ን​ንም ገደ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">የሰ​ዶም ንጉ​ሥና የገ​ሞራ ንጉሥ፥ የአ​ዳማ ንጉ​ሥና የሲ​ባ​ዮን ንጉሥ፥ ሴጎር የተ​ባ​ለች የባ​ላቅ ንጉ​ሥም ወጡ፤ እነ​ዚህ ሁሉ በጨው ሸለቆ በእ​ነ​ርሱ ላይ ለሰ​ልፍ ወጡ፤</verse>
				<verse number="9">ከኤ​ላም ንጉሥ ከኮ​ሎ​ዶ​ጎ​ሞር፥ ከአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ ከቴ​ሮ​ጋል፥ ከሰ​ና​ዖር ንጉሥ ከአ​ሜ​ሮ​ፌል፥ ከእ​ላ​ሳር ንጉሥ ከአ​ር​ዮክ ጋር ተጋ​ጠሙ። እነ​ዚህ አራቱ ነገ​ሥ​ታት ከአ​ም​ስቱ ነገ​ሥ​ታት ጋር ተዋጉ።</verse>
				<verse number="10">ያም የጨው ሸለቆ የዝ​ፍት ጕድ​ጓ​ዶች ነበ​ሩ​በት። የሰ​ዶም ንጉ​ሥና የገ​ሞራ ንጉ​ሥም ሸሹና በዚያ ወደቁ፤ የቀ​ሩ​ትም ወደ ተራ​ራ​ማው ሀገር ሸሹ።</verse>
				<verse number="11">የሰ​ዶ​ም​ንና የገ​ሞ​ራን ፈረ​ሶች ሁሉ፥ ስን​ቃ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ይዘው ሄዱ።</verse>
				<verse number="12">እነ​ር​ሱም የአ​ብ​ራ​ምን የወ​ን​ድም ልጅ ሎጥ​ንና ገን​ዘ​ቡን ይዘው ሄዱ። እርሱ በሰ​ዶም ይኖር ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="13">ከአ​መ​ለ​ጡ​ትም አንድ ሰው መጣ፤ ለዕ​ብ​ራ​ዊው ለአ​ብ​ራ​ምም ነገ​ረው፤ እር​ሱም የኤ​ስ​ኮል ወን​ድ​ምና የአ​ው​ናን ወን​ድም በሆነ በአ​ሞ​ራ​ዊው የመ​ምሬ ዛፍ ይኖር ነበር፤ እነ​ዚ​ያም ከአ​ብ​ራም ጋር ቃል ኪዳን ገብ​ተው ነበር።</verse>
				<verse number="14">አብ​ራ​ምም የወ​ን​ድሙ ልጅ ሎጥ እንደ ተማ​ረከ በሰማ ጊዜ ወገ​ኖ​ቹ​ንና ቤተ​ሰ​ቦ​ቹን ሁሉ ቈጠ​ራ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ሦስት መቶ ዐሥራ ስም​ንት ሆኑ፤ እስከ ዳን ድረስ ተከ​ትሎ አሳ​ደ​ዳ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">እር​ሱም ከብ​ላ​ቴ​ኖቹ ጋር በሌ​ሊት ደረ​ሰ​ባ​ቸው፤ መታ​ቸ​ውም፤ በደ​ማ​ስቆ ግራ እስ​ካ​ለ​ች​ውም እስከ ሖባ ድረስ አሳ​ደ​ዳ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">የሰ​ዶ​ምን ፈረ​ሶች ሁሉ አስ​መ​ለሰ፤ ደግ​ሞም የወ​ን​ድ​ሙን ልጅ ሎጥ​ንና ንብ​ረ​ቱን፥ ሴቶ​ች​ንና ሕዝ​ቡ​ንም አስ​መ​ለሰ።</verse>
				<verse number="17">ኮሎ​ዶ​ጎ​ሞ​ር​ንና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ነገ​ሥ​ታት ወግቶ ከተ​መ​ለ​ሰም በኋላ የሰ​ዶም ንጉሥ የን​ጉሥ ሜዳ በሆነ በሴዊ ሸለቆ ሊቀ​በ​ለው ወጣ።</verse>
				<verse number="18">የሳ​ሌም ንጉሥ መልከ ጼዴ​ቅም እን​ጀ​ራ​ንና የወ​ይን ጠጅን አወጣ፤ እር​ሱም የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካህን ነበረ።</verse>
				<verse number="19">አብ​ራ​ም​ንም ባረ​ከው፤ “አብ​ራም ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ለፈ​ጠረ ለል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ረከ ነው፤</verse>
				<verse number="20">ጠላ​ቶ​ች​ህን በእ​ጅህ የጣ​ለ​ልህ ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቡሩክ ነው” አለው። አብ​ራ​ምም ከሁሉ ዐሥ​ራ​ትን ሰጠው።</verse>
				<verse number="21">የሰ​ዶም ንጉ​ሥም አብ​ራ​ምን፥ “ሰዎ​ቹን ስጠኝ፤ ፈረ​ሶ​ቹን ግን ለአ​ንተ ውሰድ” አለው።</verse>
				<verse number="22">አብ​ራ​ምም የሰ​ዶ​ምን ንጉሥ አለው፥ “ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ወደ ፈጠረ ወደ ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጄን ከፍ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="23">አንተ፦ አብ​ራ​ምን ባለ​ጠጋ አደ​ረ​ግ​ሁት እን​ዳ​ትል፥ ከአ​ንተ ገን​ዘብ ሁሉ ፈት​ልም ቢሆን፥ የጫማ ማዘ​ቢ​ያም ቢሆን እን​ዳ​ል​ወ​ስድ፥</verse>
				<verse number="24">ብላ​ቴ​ኖች ከበ​ሉት እህ​ልና ከእኔ ጋር ከመ​ጡት ድርሻ በቀር፥ አው​ናን፥ ኤስ​ኮ​ልም፥ መም​ሬም እነ​ርሱ ድር​ሻ​ቸ​ውን ይው​ሰዱ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">ከዚ​ህም ነገር በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በራ​እይ ወደ አብ​ራም መጣ፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አብ​ራም ሆይ፥ አት​ፍራ፤ እኔ ጋሻ እሆ​ን​ሃ​ለሁ፤ ዋጋ​ህም በእኔ ዘንድ እጅግ ብዙ ነው።”</verse>
				<verse number="2">አብ​ራ​ምም፥ “አቤቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ምን ትሰ​ጠ​ኛ​ለህ? እነሆ፥ ልጅ ሳል​ወ​ልድ እሞ​ታ​ለሁ፤ የቤ​ቴም ወራሽ ከዘ​መዴ ወገን የሚ​ሆን የደ​ማ​ስቆ ሰው የማ​ሴቅ ልጅ ይህ ኢያ​ው​ብር ነው” አለ።</verse>
				<verse number="3">አብ​ራ​ምም፥ “ለእኔ ዘር አል​ሰ​ጠ​ኸ​ኝም፤ የዘ​መዴ ልጅ እርሱ ይወ​ር​ሰ​ኛል” አለ።</verse>
				<verse number="4">ያን ጊዜም የአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ አብ​ራም እን​ዲህ ሲል መጣ፤ “እርሱ አይ​ወ​ር​ስ​ህም፤ ነገር ግን ከአ​ብ​ራ​ክህ የሚ​ወ​ጣው እርሱ ይወ​ር​ስ​ሃል።”</verse>
				<verse number="5">ወደ ሜዳም አወ​ጣ​ውና “ወደ ላይ ወደ ሰማይ ተመ​ል​ከት፤ ልት​ቈ​ጥ​ራ​ቸው ትችል እን​ደ​ሆነ ከዋ​ክ​ብ​ትን ቍጠ​ራ​ቸው። ዘር​ህም እን​ደ​ዚሁ ነው” አለው።</verse>
				<verse number="6">አብ​ራ​ምም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አመነ፤ ጽድ​ቅም ሆኖ ተቈ​ጠ​ረ​ለት።</verse>
				<verse number="7">“ይህ​ችን ምድር ትወ​ር​ሳት ዘንድ እን​ድ​ሰ​ጥህ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር ያወ​ጣ​ሁህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ” አለው።</verse>
				<verse number="8">“አቤቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ እን​ደ​ም​ወ​ር​ሳት በምን አው​ቃ​ለሁ?” አለው።</verse>
				<verse number="9">እር​ሱም አለው፥ “የሦ​ስት ዓመት ላም፥ የሦ​ስት ዓመት ፍየ​ልም፥ የሦ​ስት ዓመት በግም፥ ዋኖ​ስም፥ ርግ​ብም አምጣ፤ እኒ​ህ​ንም ሁሉ አም​ጥ​ተህ ከሁ​ለት ከሁ​ለት ቍረ​ጣ​ቸው፤ ወፎ​ችን ግን አት​ቍ​ረ​ጣ​ቸው።”</verse>
				<verse number="10">እን​ዲ​ሁም እነ​ዚ​ህን ሁሉ ወሰ​ደ​ለት፤ በየ​ሁ​ለ​ትም ከፈ​ላ​ቸው፤ የተ​ከ​ፈ​ሉ​ት​ንም በየ​ወ​ገኑ ትይዩ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ ወፎ​ችን ግን አል​ቈ​ረ​ጣ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="11">አሞ​ራ​ዎ​ችም በተ​ቈ​ረ​ጠው ሥጋ​ቸው ላይ ወረዱ፤ አብ​ራ​ምም በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ተቀ​ምጦ አባ​ረ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ በአ​ብ​ራም ድን​ጋጤ መጣ​በት፤ እነ​ሆም፥ የሚ​ያ​ስ​ፈራ ጽኑዕ ጨለማ መጣ​በት፤</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ራ​ምን አለው፥ “ዘርህ ለእ​ነ​ርሱ ባል​ሆ​ነች ምድር ስደ​ተ​ኞች እን​ዲ​ሆኑ በእ​ር​ግጥ ዕወቅ፤ አራት መቶ ዓመ​ታ​ትም ባሪ​ያ​ዎች አድ​ር​ገው ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ ያሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸ​ዋል፤ ያስ​ጨ​ን​ቋ​ቸ​ዋ​ልም።</verse>
				<verse number="14">ደግ​ሞም የሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸ​ውን እኔ እፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ። ከዚ​ህም በኋላ ከብዙ ገን​ዘብ ጋር ወደ​ዚህ ይወ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="15">አንተ ግን ወደ አባ​ቶ​ችህ በሰ​ላም ትሄ​ዳ​ለህ፤ በመ​ል​ካም ሽም​ግ​ል​ናም ትቀ​በ​ራ​ለህ።</verse>
				<verse number="16">በአ​ራ​ተ​ኛው ትው​ልድ ግን ወደ​ዚህ ይመ​ለ​ሳሉ፤ እስከ ዛሬ ድረስ የአ​ሞ​ራ​ው​ያን ኀጢ​አት አል​ተ​ፈ​ጸ​መ​ምና።”</verse>
				<verse number="17">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ ነበ​ል​ባል መጣ፤ የእ​ሳት መብ​ራ​ትና የሚ​ጤስ ምድ​ጃም መጣ፤ በዚ​ያም በተ​ከ​ፈ​ለው መካ​ከል አለፈ።</verse>
				<verse number="18">በዚ​ያ​ችም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ራም ተስፋ ያደ​ረ​ገ​ለ​ትን ቃል ኪዳን አጸና፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ከግ​ብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ ይህ​ችን ምድር ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="19">ቀኔ​ዎ​ሳ​ው​ያ​ንን፥ ቄኔ​ዜ​ዎ​ሳ​ው​ያ​ንን፥ ቄኔ​ሚ​ሎ​ሳ​ው​ያ​ንን፥</verse>
				<verse number="20">ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም፥ ፈራ​ዮ​ና​ው​ያ​ን​ንም፤</verse>
				<verse number="21">አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም፥ ከና​ኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">የአ​ብ​ራም ሚስት ሦራ ግን ልጅ አል​ወ​ለ​ደ​ች​ለ​ትም ነበር፤ ስምዋ አጋር የተ​ባለ ግብ​ፃ​ዊት አገ​ል​ጋ​ይም ነበ​ረ​ቻት።</verse>
				<verse number="2">ሦራም አብ​ራ​ምን፥ “እነሆ፥ እን​ዳ​ል​ወ​ልድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘጋኝ፤ ከእ​ር​ስዋ ትወ​ልድ ዘንድ ወደ አገ​ል​ጋዬ ሂድ” አለ​ችው። አብ​ራ​ምም የሚ​ስ​ቱን የሦ​ራን ቃል ሰማ።</verse>
				<verse number="3">አብ​ራ​ምም በከ​ነ​ዓን ምድር ዐሥር ዓመት ከተ​ቀ​መጠ በኋላ፥ የአ​ብ​ራም ሚስት ሦራ ግብ​ፃ​ዊት አገ​ል​ጋ​ይ​ዋን አጋ​ርን ወስዳ ለአ​ብ​ራም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠ​ችው።</verse>
				<verse number="4">አብ​ራ​ምም ወደ አጋር ገባ፤ ፀነ​ሰ​ችም፤ እንደ ፀነ​ሰ​ችም ባየች ጊዜ እመ​ቤ​ቷን ማክ​በ​ር​ዋን ተወች።</verse>
				<verse number="5">ሦራም አብ​ራ​ምን፥ “ከአ​ንተ የተ​ነሣ እገ​ፋ​ለሁ፤ እኔ አገ​ል​ጋ​ዬን በብ​ብ​ትህ ሰጠ​ሁህ፤ እንደ ፀነ​ሰ​ችም ባየች ጊዜ እኔን ማክ​በ​ርን ተወች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ይፍ​ረድ” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="6">አብ​ራ​ምም ሚስ​ቱን ሦራን፥ “እነሆ፥ አገ​ል​ጋ​ይሽ በእ​ጅሽ ናት፤ እንደ ወደ​ድሽ አድ​ር​ጊ​ባት” አላት። ሦራም አጋ​ርን አሠ​ቃ​የ​ቻት፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ኰበ​ለ​ለች።</verse>
				<verse number="7">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም በውኃ ምንጭ አጠ​ገብ በሱር በረሃ በመ​ን​ገድ አገ​ኛት።</verse>
				<verse number="8">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “የሦራ አገ​ል​ጋይ አጋር ሆይ፥ ከወ​ዴት መጣሽ? ወዴ​ትስ ትሄ​ጂ​ያ​ለሽ?” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “እኔ ከእ​መ​ቤቴ ከሦራ ፊት እኰ​በ​ል​ላ​ለሁ” አለች።</verse>
				<verse number="9">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም፥ “ወደ እመ​ቤ​ትሽ ተመ​ለሺ፤ ከእ​ጅ​ዋም በታች ራስ​ሽን ዝቅ አድ​ርጊ” አላት።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም “ከብ​ዛቱ የተ​ነሣ እስ​ከ​ማ​ይ​ቈ​ጠር ድረስ ዘር​ሽን እጅግ አበ​ዛ​ለሁ፥” አላት።</verse>
				<verse number="11">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም አላት፥ “እነሆ፥ አንቺ ፀን​ሰ​ሻል፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ ስሙ​ንም ይስ​ማ​ኤል ብለሽ ትጠ​ሪ​ዋ​ለሽ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥቃ​ይ​ሽን ሰም​ቶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="12">እር​ሱም የበ​ረሃ ሰው ይሆ​ናል፤ እጁ በሁሉ ላይ ይሆ​ናል፤ የሁ​ሉም እጅ ደግሞ በእ​ርሱ ላይ ይሆ​ናል፤ እር​ሱም በወ​ን​ድ​ሞቹ ሁሉ ፊት ይኖ​ራል።”</verse>
				<verse number="13">አጋ​ርም ይና​ገ​ራት የነ​በ​ረ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ጠራች፤ “አቤቱ የራ​ራ​ህ​ልኝ አንተ ነህ፤ የተ​ገ​ለ​ጠ​ል​ኝን በፊቴ አይ​ች​ዋ​ለ​ሁና።”</verse>
				<verse number="14">ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያን ጕድ​ጓድ ስም “በፊቴ የተ​ገ​ለ​ጠ​ልኝ የእ​ርሱ ጕድ​ጓድ” ብላ ጠራ​ችው፤ እር​ሱም በቃ​ዴ​ስና በባ​ሬድ መካ​ከል ነው። አጋ​ርም ተመ​ለ​ሰች።</verse>
				<verse number="15">ከዚ​ህም በኋላ አጋር ለአ​ብ​ራም ወንድ ልጅን ወለ​ደ​ች​ለት፤ አብ​ራ​ምም አጋር የወ​ለ​ደ​ች​ለ​ትን የሕ​ፃ​ኑን ስም ይስ​ማ​ኤል ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="16">አጋር ይስ​ማ​ኤ​ልን በወ​ለ​ደ​ች​ለት ጊዜ አብ​ራም የሰ​ማ​ንያ አም​ስት ዓመት ሰው ነበረ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ አብ​ራም የዘ​ጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ራም ተገ​ለ​ጠ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አለው “በፊ​ትህ የሄ​ድሁ ፈጣ​ሪህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ፤ በፊቴ መል​ካም አድ​ርግ፤ ንጹ​ሕም ሁን፤</verse>
				<verse number="2">ቃል ኪዳ​ኔ​ንም በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል አጸ​ና​ለሁ፤ እጅ​ግም አበ​ዛ​ሃ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="3">አብ​ራ​ምም በግ​ን​ባሩ ወደቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ራ​ምን እን​ዲህ አለው፦</verse>
				<verse number="4">“እነሆ፥ ቃል ኪዳ​ኔን በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል አጸ​ና​ለሁ፤ ለብዙ አሕ​ዛ​ብም አባት ትሆ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="5">እን​ግ​ዲህ ስምህ አብ​ራም አይ​ባ​ልም ‘አብ​ር​ሃም’ ይባ​ላል እንጂ፤ ለብዙ አሕ​ዛብ አባት አድ​ር​ጌ​ሃ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="6">እጅ​ግም በጣም አበ​ዛ​ሃ​ለሁ፤ ሕዝ​ብም፥ ነገ​ሥ​ታ​ትም ከአ​ንተ እን​ዲ​ወጡ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">ቃል ኪዳ​ኔ​ንም በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል፥ ከአ​ን​ተም በኋላ በዘ​ርህ መካ​ከል በት​ው​ል​ዳ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ኪዳን አቆ​ማ​ለሁ፤ ለአ​ን​ተና ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ርህ አም​ላክ እሆን ዘንድ።</verse>
				<verse number="8">በው​ስ​ጥዋ የም​ት​ኖ​ር​ባ​ትን ይህ​ችን ምድር፥ የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር ሁሉ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይገ​ዙ​አት ዘንድ ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ፤ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “አንተ ደግሞ ቃል ኪዳ​ኔን ትጠ​ብ​ቃ​ለህ፤ አንተ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ዘርህ በት​ው​ል​ዳ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል፥ ከአ​ን​ተም በኋላ በዘ​ርህ መካ​ከል የም​ት​ጠ​ብ​ቋት ቃል ኪዳኔ ይህች ናት፤ ከእ​ና​ንተ ወንድ ሁሉ ይገ​ረዝ።</verse>
				<verse number="11">የሰ​ው​ነ​ታ​ች​ሁን ቍል​ፈት ትገ​ረ​ዛ​ላ​ችሁ፤ በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ላለ​ውም ቃል ኪዳን ምል​ክት ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="12">ሕፃ​ኑ​ንም በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ትገ​ር​ዙ​ታ​ላ​ችሁ፤ በቤት የተ​ወ​ለደ ወይም ከዘ​ራ​ችሁ ያይ​ደለ፥ በብ​ርም ከእ​ን​ግዳ ሰው የተ​ገዛ ወንድ ሁሉ በት​ው​ል​ዳ​ችሁ ይገ​ረዝ።</verse>
				<verse number="13">በቤ​ት​ህም የተ​ወ​ለደ፥ በብ​ርም የተ​ገዛ ፈጽሞ ይገ​ረዝ። ቃል ኪዳ​ኔም በሥ​ጋ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳን ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="14">በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን የሥ​ጋ​ውን ቍል​ፈት ያል​ተ​ገ​ረዘ፥ ያች ነፍስ ከወ​ገ​ንዋ ተለ​ይታ ትጥፋ፤ ቃል ኪዳ​ኔን አፍ​ር​ሳ​ለ​ችና።”</verse>
				<verse number="15">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “ሚስ​ትህ ሦራ እን​ግ​ዲህ ሦራ ተብላ አት​ጠ​ራም፤ ስምዋ ‘ሣራ’ ይሆ​ናል እንጂ።</verse>
				<verse number="16">እባ​ር​ካ​ታ​ለ​ሁና፥ ከአ​ን​ተም ልጆ​ችን እሰ​ጣ​ታ​ለ​ሁና፤ አሕ​ዛ​ብና የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት ከእ​ር​ስዋ ይወ​ጣሉ።”</verse>
				<verse number="17">አብ​ር​ሃ​ምም በግ​ን​ባሩ ወደቀ፤ ሳቀም፤ በል​ቡም እን​ዲህ ብሎ አሰበ፥ “የመቶ ዓመት ሰው ስሆን በውኑ እኔ ልጅ እወ​ል​ዳ​ለ​ሁን? ዘጠና ዓመት የሆ​ና​ትም ሣራ ትወ​ል​ዳ​ለ​ችን?”</verse>
				<verse number="18">አብ​ር​ሃ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ይህ ይስ​ማ​ኤል ብቻ በፊ​ትህ ይኖ​ር​ልኝ ዘንድ አቤቱ፥ እማ​ል​ድ​ሃ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “እሺ እነሆ፥ ሚስ​ትህ ሣራ ወንድ ልጅን ትወ​ል​ድ​ል​ሃ​ለች፤ ስሙ​ንም ይስ​ሐቅ ብለህ ትጠ​ራ​ዋ​ለህ፤ ለእ​ር​ሱና ከእ​ርሱ በኋላ ለዘሩ አም​ላክ እሆን ዘንድ ቃል ኪዳ​ኔን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳን ከእ​ርሱ ጋር አቆ​ማ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">ስለ ይስ​ማ​ኤ​ልም እነሆ፥ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ፤ እባ​ር​ከ​ዋ​ለሁ፤ አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ እጅ​ግም አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ዐሥራ ሁለት አለ​ቆ​ች​ንም ይወ​ል​ዳል፤ ታላቅ ሕዝ​ብም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="21">ቃል ኪዳ​ኔን ግን በሚ​መ​ጣው ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከም​ት​ወ​ል​ድ​ልህ ከይ​ስ​ሐቅ ጋር አቆ​ማ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ንግ​ግ​ሩን ከእ​ርሱ ጋር በፈ​ጸመ ጊዜ ከአ​ብ​ር​ሃም ተለ​ይቶ ወጣ።</verse>
				<verse number="23">አብ​ር​ሃ​ምም ልጁን ይስ​ማ​ኤ​ልን፥ በቤ​ቱም የተ​ወ​ለ​ዱ​ትን ሁሉ፥ በወ​ር​ቅም የገ​ዛ​ውን ወንድ ሁሉ፥ ከቤተ ሰቡም ወን​ዶ​ቹን ሁሉ ወሰደ። የሥ​ጋ​ቸ​ው​ንም ቍል​ፈት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ለው በዚ​ያው ቀን ገረዘ።</verse>
				<verse number="24">አብ​ር​ሃ​ምም የሥ​ጋ​ውን ቍል​ፈት በተ​ገ​ረዘ ጊዜ ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሆኖት ነበረ፤</verse>
				<verse number="25">ልጁ ይስ​ማ​ኤ​ልም የሥ​ጋ​ውን ቍል​ፈት በተ​ገ​ረዘ ጊዜ ዐሥራ ሦስት ዓመት ሆኖት ነበረ።</verse>
				<verse number="26">በዚ​ያም ቀን አብ​ር​ሃም ተገ​ረዘ፤ ልጁ ይስ​ማ​ኤ​ልም።</verse>
				<verse number="27">በቤት የተ​ወ​ለ​ዱ​ትና በብር ከእ​ን​ግ​ዶች የተ​ገ​ዙት፥ የቤቱ ወን​ዶች ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ተገ​ረዙ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">በቀ​ት​ርም ጊዜ አብ​ር​ሃም በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ ተቀ​ምጦ ሳለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ምሬ ዛፍ ሥር ተገ​ለ​ጠ​ለት።</verse>
				<verse number="2">ዐይ​ኑ​ንም በአ​ነሣ ጊዜ እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያ​ቸ​ውም ጊዜ ሊቀ​በ​ላ​ቸው ከድ​ን​ኳኑ ደጃፍ ተነ​ሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድ​ርም ሰገደ፤</verse>
				<verse number="3">እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ በፊ​ት​ህስ ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ ባሪ​ያ​ህን አት​ለ​ፈው፤</verse>
				<verse number="4">ውኃ እና​ም​ጣ​ላ​ችሁ፤ እግ​ራ​ች​ሁ​ንም እን​ጠ​ባ​ችሁ።</verse>
				<verse number="5">ከዛ​ፉም ሥር ዕረፉ፤ እን​ጀ​ራም እና​ም​ጣ​ላ​ች​ሁና ብሉ፤ ከዚ​ያም በባ​ሪ​ያ​ችሁ ዘንድ ከአ​ረ​ፋ​ችሁ በኋላ፥ ወደ ዐሰ​ባ​ች​ሁት ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ።” እነ​ር​ሱም፥ “እን​ዳ​ልህ እን​ዲሁ አድ​ርግ” አሉት።</verse>
				<verse number="6">አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ድን​ኳን ወደ ሚስቱ ወደ ሣራ ፈጥኖ ገባና፥ “ሦስት መስ​ፈ​ሪያ የተ​ሰ​ለቀ ዱቄት ፈጥ​ነሽ ለውሺ፤ እን​ጎ​ቻም አድ​ርጊ” አላት።</verse>
				<verse number="7">አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ላሞቹ ሮጠ፤ እጅግ የሰ​ባም ታናሽ ጥጃ ያዘና ለብ​ላ​ቴ​ናው ሰጠው፤ ያዘ​ጋ​ጅም ዘንድ ተቻ​ኮለ።</verse>
				<verse number="8">እር​ጎና መዓር፥ ያን ያዘ​ጋ​ጀ​ው​ንም ጥጃ አመጣ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም አቀ​ረ​በው፤ እር​ሱም ከዛፉ በታች በፊ​ታ​ቸው ቆሞ ያሳ​ል​ፍ​ላ​ቸው ነበር፤ እነ​ር​ሱም በሉ።</verse>
				<verse number="9">እር​ሱም፥ “ሚስ​ትህ ሣራ ወዴት ናት?” አለው። እር​ሱም፥ “በድ​ን​ኳኑ ውስጥ ናት” አለው።</verse>
				<verse number="10">እር​ሱም፥ “የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ወደ አንተ ተመ​ልሼ እመ​ጣ​ለሁ፤ ሚስ​ትህ ሣራም ልጅን ታገ​ኛ​ለች” አለ።</verse>
				<verse number="11">ሣራም በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ በስ​ተ​ኋ​ላው ቆማ ሳለች ይህን ሰማች። አብ​ር​ሃ​ምና ሣራም በዕ​ድ​ሜ​ያ​ቸው ሸም​ግ​ለው ፈጽ​መው አር​ጅ​ተው ነበር፤ በሴ​ቶች የሚ​ሆ​ነ​ውም ልማድ ከሣራ ተቋ​ርጦ ነበር።</verse>
				<verse number="12">ሣራም ለብ​ቻዋ በል​ብዋ እን​ዲህ ስትል ሳቀች፥ “እስከ ዛሬ ገና ነኝን? ጌታ​ዬም ፈጽሞ ሽም​ግ​ሎ​አል።”</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “ሣራን ለብ​ቻዋ በል​ብዋ ምን አሳ​ቃት? እስከ ዛሬ ገና ነኝን? በእ​ው​ነ​ትስ እወ​ል​ዳ​ለ​ሁን? ጌታ​ዬም አር​ጅ​ት​ዋል እነሆ፥ እኔም አር​ጅ​ቻ​ለሁ ብላ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="14">በውኑ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሳ​ነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ ሣራም ልጅን ታገ​ኛ​ለች።”</verse>
				<verse number="15">ሣራም ስለ ፈራች “አል​ሳ​ቅ​ሁም” ብላ ካደች። እር​ሱም፥ “አይ​ደ​ለም፥ ሳቅሽ እንጂ” አላት።</verse>
				<verse number="16">እነ​ዚ​ያም ሰዎች ከዚያ ተነ​ሥ​ተው ወደ ሰዶ​ምና ወደ ገሞራ አቀኑ፤ አብ​ር​ሃ​ምም ሊሸ​ኛ​ቸው አብ​ሮ​አ​ቸው ሄደ፤ አብ​ር​ሃ​ምም ተመ​ልሶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆመ።</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “እኔ የማ​ደ​ር​ገ​ውን ከወ​ዳጄ አብ​ር​ሃም አል​ሰ​ው​ርም፤</verse>
				<verse number="18">አብ​ር​ሃም በእ​ው​ነት ታላ​ቅና ብርቱ ሕዝብ ይሆ​ና​ልና፤ የም​ድር ሕዝ​ቦ​ችም ሁሉ በእ​ርሱ ይባ​ረ​ካ​ሉና።</verse>
				<verse number="19">ጽድ​ቅ​ንና ፍር​ድን በማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ይጠ​ብቁ ዘንድ፥ ልጆ​ቹ​ንና ቤቱን ያዝ​ዛ​ቸው ዘንድ እን​ዳ​ለው አው​ቃ​ለ​ሁና፤ ይህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ር​ሃም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ያደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ ነው።”</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ብ​ር​ሃም አለው፥ “የሰ​ዶ​ምና የገ​ሞራ ጩኸት በእኔ ዘንድ በዛ፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም እጅግ ከበ​ደች፤</verse>
				<verse number="21">እን​ግ​ዲ​ህስ ወደ እኔ እንደ መጣች እንደ ጩኸቷ ይፈ​ጽ​ሙ​አት እንደ ሆነ አይ ዘንድ እወ​ር​ዳ​ለሁ፤ እን​ዲ​ሁም ባይ​ሆን አው​ቃ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="22">ሰዎ​ቹም ከዚያ በተ​መ​ለሱ ጊዜ ወደ ሰዶም መጡ፤ አብ​ር​ሃም ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር።</verse>
				<verse number="23">አብ​ር​ሃ​ምም ቀረበ፤ አለም፥ “አቤቱ፥ ጻድ​ቃ​ንን ከኃ​ጥ​ኣን ጋር አታ​ጥፋ፤ ጻድቁ እንደ ኃጥኡ አይ​ሁን።</verse>
				<verse number="24">አምሳ ጻድ​ቃን በከ​ተ​ማ​ዪቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠ​ፋ​ለ​ህን? ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንስ በእ​ር​ስዋ ስለ​ሚ​ገኙ አምሳ ጻድ​ቃን አት​ም​ር​ምን?</verse>
				<verse number="25">አቤቱ ይህ ለአ​ንተ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም፤ ይህን ነገር አታ​ድ​ርግ፤ ጻድ​ቃ​ንን ከኃ​ጥ​ኣን ጋር አታ​ጥፋ፤ ምድ​ርን ሁሉ የም​ት​ገዛ ይህን ፍርድ ታደ​ርግ ዘንድ ለአ​ንተ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም።”</verse>
				<verse number="26">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “በሰ​ዶም ከተማ ውስጥ አምሳ ጻድ​ቃን ባገኝ ከተ​ማ​ውን ሁሉ ስለ እነ​ርሱ አድ​ና​ለሁ።”</verse>
				<verse number="27">አብ​ር​ሃ​ምም መለሰ፤ አለም፥ “እኔ አፈ​ርና አመድ ስሆን ከጌ​ታዬ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር እና​ገር ዘንድ አሁን ጀመ​ርሁ፤</verse>
				<verse number="28">ከእ​ነ​ዚያ አምሳ ጻድ​ቃን አም​ስት ቢጐ​ድሉ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሁሉ በጐ​ደ​ሉት በአ​ም​ስቱ ምክ​ን​ያት ታጠ​ፋ​ለ​ህን?” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ከዚያ አርባ አም​ስት ባገኝ ስለ እነ​ርሱ አላ​ጠ​ፋ​ትም” አለው።</verse>
				<verse number="29">አብ​ር​ሃ​ምም አለው፥ “ከዚያ አርባ ቢገ​ኙሳ?” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ለአ​ር​ባው ስል አላ​ጠ​ፋ​ትም” አለው።</verse>
				<verse number="30">አብ​ር​ሃ​ምም እን​ደ​ገና ነገ​ሩን ደገመ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ከዚያ ሠላሳ ቢገ​ኙሳ?” እር​ሱም፥ “ስለ ሠላ​ሳው አላ​ጠ​ፋ​ትም” አለው።</verse>
				<verse number="31">ደግ​ሞም፥ “እነሆ፥ ከጌ​ታዬ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር እነ​ጋ​ገር ዘንድ ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን ካገ​ኘሁ ከዚያ ሃያ ቢገ​ኙሳ?” አለው። እር​ሱም፥ “ስለ ሃያው አላ​ጠ​ፋ​ትም” አለው።</verse>
				<verse number="32">አብ​ር​ሃ​ምም አለው፥ “አቤቱ እን​ደ​ገና እና​ገር ዘንድ ፍቀ​ድ​ልኝ፤ ከዚያ ዐሥር ቢገ​ኙሳ?” እር​ሱም፥ “ስለ ዐሥሩ አላ​ጠ​ፋ​ትም” አለው።</verse>
				<verse number="33">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ብ​ር​ሃም ጋር ንግ​ግ​ሩን በጨ​ረሰ ጊዜ ሄደ፤ አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ስፍ​ራው ተመ​ለሰ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">ሁለ​ቱም መላ​እ​ክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ደረሱ፤ ሎጥም በሰ​ዶም ከተማ በር ተቀ​ምጦ ነበር። ሎጥም ባያ​ቸው ጊዜ ሊቀ​በ​ላ​ቸው ተነሣ፤ ፊቱ​ንም ወደ ምድር ደፍቶ ሰገ​ደ​ላ​ቸው፤</verse>
				<verse number="2">አላ​ቸ​ውም፥ “ጌቶች ሆይ፥ ወደ ባሪ​ያ​ችሁ ቤት ገብ​ታ​ችሁ እደሩ፤ እግ​ራ​ች​ሁ​ንም ታጠቡ፤ ነገም ማል​ዳ​ችሁ መን​ገ​ዳ​ች​ሁን ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ።” እነ​ር​ሱም፥ “በአ​ደ​ባ​ባዩ እና​ድ​ራ​ለን እንጂ፥ አይ​ሆ​ንም” አሉት።</verse>
				<verse number="3">እር​ሱም ግድ አላ​ቸው፤ ወደ እር​ሱም አቀኑ፤ ወደ ቤቱም ገቡ፤ ቂጣ​ንም አስ​ጋ​ገ​ረ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም በሉ።</verse>
				<verse number="4">ገና ሳይ​ተ​ኙም የዚ​ያች ከተማ ሰዎች፥ ታና​ሹም፥ ታላ​ቁም ቤቱን በአ​ን​ድ​ነት ከበ​ቡት።</verse>
				<verse number="5">ሎጥ​ንም ጠር​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “በሌ​ሊት ወደ አንተ የገ​ቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እና​ው​ቃ​ቸው ዘንድ ወደ እኛ አው​ጣ​ቸው።”</verse>
				<verse number="6">ሎጥም ወደ እነ​ርሱ ወደ ደጅ ፊት ለፊት ወጣ፤ መዝ​ጊ​ያ​ው​ንም በስ​ተ​ኋ​ላው ዘጋው፤</verse>
				<verse number="7">እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ለእ​ና​ንተ አግ​ባ​ባ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ በእ​ነ​ዚህ ላይ ክፉ አታ​ድ​ርጉ፤</verse>
				<verse number="8">እነሆ፥ ወን​ድን ያላ​ወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነ​ር​ሱን ላው​ጣ​ላ​ችሁ፤ እንደ ወደ​ዳ​ች​ሁም አድ​ር​ጉ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ዚህ ሰዎች ብቻ ምንም በደል አታ​ድ​ርጉ፤ እነ​ርሱ በቤቴ ጥላ ሥር ገብ​ተ​ዋ​ልና።”</verse>
				<verse number="9">እነ​ር​ሱም፥ “ወዲያ ሂድ፤ ከእኛ ጋር ልት​ኖር መጣህ እንጂ ልት​ገ​ዛን አይ​ደ​ለም፤ አሁ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ይልቅ አን​ተን እና​ሠ​ቃ​ይ​ሃ​ለን” አሉት።</verse>
				<verse number="10">እጅ​ግም ተጋ​ፉት፤ የደ​ጁ​ንም መዝ​ጊያ ለመ​ስ​በር ቀረቡ። እነ​ዚ​ያም ሰዎች እጃ​ቸ​ውን ዘር​ግ​ተው ሎጥን ወደ እነ​ርሱ ዘንድ ወደ ቤት ስበው አገ​ቡት፤ መዝ​ጊ​ያ​ው​ንም ዘጉት።</verse>
				<verse number="11">በቤቱ ደጃፍ የነ​በ​ሩ​ት​ንም ሰዎች ከታ​ና​ሻ​ቸው ጀምሮ እስክ ታላ​ቃ​ቸው ድረስ ዐይ​ና​ቸ​ውን አሳ​ወ​ሩ​አ​ቸው፤ ደጃ​ፉ​ንም ሲፈ​ልጉ ደከሙ፤ አጡ​ትም።</verse>
				<verse number="12">እነ​ዚ​ያም መላ​እ​ክት ሎጥን አሉት፥ “ከዚህ ሌላ ማን አለህ? አማ​ችም ቢሆን፥ ወንድ ልጅም ቢሆን፥ ሴት ልጅም ብት​ሆን፥ በዚህ ከተማ የም​ታ​ው​ቀው ወዳጅ ቢኖ​ርህ ያለ​ህን ሁሉ ከዚህ ስፍራ አስ​ወ​ጣ​ቸው፤</verse>
				<verse number="13">እኛ ይህ​ችን ስፍራ እና​ጠ​ፋ​ታ​ለ​ንና፥ ጩኸ​ታ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትልቅ ሆኖ​አ​ልና፤ እና​ጠ​ፋ​ትም ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልኮ​ናል።”</verse>
				<verse number="14">ሎጥም ወጣ፤ ልጆ​ቹን ለሚ​ያ​ገ​ቡት ለአ​ማ​ቾ​ቹም አላ​ቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን ከተማ ያጠ​ፋ​ታ​ልና።” ለአ​ማ​ቾቹ ግን የሚ​ያ​ፌ​ዝ​ባ​ቸው መሰ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">ጎህም በቀ​ደደ ጊዜ መላ​እ​ክት ሎጥን፥ “ተነሣ፤ ሚስ​ት​ህ​ንና ከዚህ ያሉ​ትን ሁለ​ቱን ሴቶች ልጆ​ች​ህን ውሰድ፤ አን​ተም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ሰዎች ኀጢ​አት እን​ዳ​ት​ጠፋ” እያሉ ያስ​ቸ​ኩ​ሉት ነበር።</verse>
				<verse number="16">እር​ሱም በዘ​ገየ ጊዜ እነ​ዚያ መላ​እ​ክት የእ​ር​ሱን እጅ፥ የሚ​ስ​ቱ​ንም እጅ፥ የሁ​ለ​ቱን ሴቶች ልጆ​ቹ​ንም እጅ ይዘው አወ​ጡ​አ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራር​ቶ​ላ​ቸ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="17">ወደ ሜዳም በወጡ ጊዜ እን​ዲህ አሉት፥ “ራስ​ህን አድን፤ ወደ ኋላም አት​መ​ል​ከት፤ አን​ተ​ንም መከራ እን​ዳ​ታ​ገ​ኝህ በዚች ሀገር በዳ​ር​ቻ​ዋና በተ​ራ​ራዋ አት​ቁም።”</verse>
				<verse number="18">ሎጥም አላ​ቸው፥ “ጌቶች ሆይ፥ በጀ በሉኝ፤</verse>
				<verse number="19">እነሆ፥ ባሪ​ያህ በፊ​ትህ ምሕ​ረ​ትን አግ​ኝቼ እን​ደ​ሆነ፥ ሰው​ነ​ቴ​ንም ታድ​ናት ዘንድ፥ ቸር​ነ​ት​ህን አብ​ዝ​ተ​ህ​ልኝ እንደ ሆነ፥ መከራ አግ​ኝ​ቶኝ እን​ዳ​ል​ጠፋ ወደ ተራራ ሸሽቼ ራሴን ማዳን አል​ች​ልም።</verse>
				<verse number="20">እነሆ፥ ይህች ከተማ ወደ እር​ስዋ ሸሽቶ ለማ​ም​ለጥ ቅርብ ናት፤ እር​ስ​ዋም ትንሽ ናት፤ ነፍ​ሴን ለማ​ዳን ወደ እር​ስዋ ሸሽቼ ራሴን ላድን፤ ሰው​ነ​ቴም ከዳ​ነች ትንሽ አይ​ደ​ለ​ችም፤”</verse>
				<verse number="21">እር​ሱም አለው፥ “ስለ እር​ስዋ የነ​ገ​ር​ኸ​ኝን ያችን ከተማ እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋት እነሆ፥ እን​ዳ​ል​ኸው ልመ​ና​ህን ተቀ​ብ​ዬ​ሃ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="22">እን​ግ​ዲህ ፍጠ​ንና በዚያ ራስ​ህን አድን፤ ወደ​ዚያ እስ​ክ​ት​ደ​ርስ ድረስ ምንም አደ​ርግ ዘንድ አል​ች​ል​ምና።” ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያች ከተማ ስም ሴጎር ተባለ።</verse>
				<verse number="23">ፀሐይ በም​ድር ላይ ወጣች፤ ሎጥም ወደ ሴጎር ገባ።</verse>
				<verse number="24">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ዶ​ምና በገ​ሞራ ላይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ከሰ​ማይ እሳ​ትና ዲን አዘ​ነበ፤</verse>
				<verse number="25">እነ​ዚ​ያ​ንም ከተ​ሞች፥ በዙ​ሪ​ያ​ቸው ያለ​ው​ንም ሁሉ፥ በከ​ተ​ሞ​ችም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ፥ የም​ድ​ሩ​ንም ቡቃያ ሁሉ ገለ​በጠ።</verse>
				<verse number="26">የሎ​ጥም ሚስት ወደ ኋላዋ ተመ​ለ​ከ​ተች፤ የጨው ሐው​ል​ትም ሆነች።</verse>
				<verse number="27">አብ​ር​ሃ​ምም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆሞ ወደ ነበ​ረ​በት ስፍራ ለመ​ሄድ ማልዶ ተነሣ፤</verse>
				<verse number="28">ወደ ሰዶ​ምና ገሞራ፥ ወደ አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ዋም ሁሉ ተመ​ለ​ከተ፤ እነ​ሆም፥ ነበ​ል​ባል ከም​ድር እንደ ምድጃ ጢስ ሲወጣ አየ።</verse>
				<verse number="29">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እነ​ዚ​ያን ከተ​ሞ​ችና ሎጥ የሚ​ኖ​ር​ባ​ቸ​ውን አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ዋን ሁሉ ባጠፋ ጊዜ አብ​ር​ሃ​ምን ዐሰ​በው፤ ሎጥ​ንም ከጥ​ፋት መካ​ከል አወ​ጣው።</verse>
				<verse number="30">ሎጥም ከሴ​ጎር ወጣ፤ ከሁ​ለ​ቱም ሴቶች ልጆቹ ጋር በተ​ራራ ተቀ​መጠ፤ በሴ​ጎር መቀ​መ​ጥን ፈር​ቶ​አ​ልና እር​ሱና ሁለቱ ሴቶች ልጆቹ በዋሻ ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="31">ታላ​ቂ​ቱም ታና​ሺ​ቱን አለ​ቻት፥ “አባ​ታ​ችን ሽማ​ግሌ ነው፤ በም​ድ​ርም ሁሉ እን​ዳ​ለው ልማድ ሊገ​ና​ኘን የሚ​ችል ሰው በም​ድር ላይ የለም።</verse>
				<verse number="32">ነዪ፥ አባ​ታ​ች​ንን ወይን እና​ጠ​ጣ​ውና ከእ​ርሱ ጋር እን​ተኛ፤ ከአ​ባ​ታ​ች​ንም ዘር እና​ስ​ቀር።”</verse>
				<verse number="33">በዚ​ያ​ችም ሌሊት አባ​ታ​ቸ​ውን ወይን አጠ​ጡት፤ ታላ​ቂ​ቱም ገባች፤ በዚ​ያ​ችም ሌሊት ከአ​ባቷ ጋር ተኛች፤ እር​ሱም ስት​ተ​ኛም፥ ስት​ነ​ሣም አላ​ወ​ቀም።</verse>
				<verse number="34">በነ​ጋ​ውም ታላ​ቂቱ ታና​ሺ​ቱን አለ​ቻት፥ “እነሆ፥ ትና​ንት ከአ​ባቴ ጋር ተኛሁ፤ ዛሬ ሌሊት ደግሞ ወይን እና​ጠ​ጣው፤ አን​ቺም ግቢና ከእ​ርሱ ጋር ተኚ፤ ከአ​ባ​ታ​ች​ንም ዘር እና​ስ​ቀር።”</verse>
				<verse number="35">አባ​ታ​ቸ​ው​ንም በዚ​ያች ሌሊት ደግሞ ወይን አጠ​ጡት፤ ታና​ሺ​ቱም ገብታ ከአ​ባቷ ጋር ተኛች፤ እር​ሱም ስት​ተ​ኛም ስት​ነ​ሣም አላ​ወ​ቀም።</verse>
				<verse number="36">የሎ​ጥም ሁለቱ ሴቶች ልጆች ከአ​ባ​ታ​ቸው ፀነሱ።</verse>
				<verse number="37">ታላ​ቂ​ቱም ወንድ ልጅ ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ሞዓብ ብላ ጠራ​ችው፤ ይህም ከአ​ባቴ የወ​ለ​ድ​ሁት ማለት ነው። እር​ሱም እስከ ዛሬ የሞ​ዓ​ባ​ው​ያን አባት ነው።</verse>
				<verse number="38">ታና​ሺ​ቱም ደግሞ ወንድ ልጅ ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም የወ​ገኔ ልጅ ስትል አሞን ብላ ጠራ​ችው፤ እር​ሱም እስከ ዛሬ የአ​ሞ​ና​ው​ያን አባት ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">አብ​ር​ሃ​ምም ከዚያ ተነ​ሥቶ ወደ አዜብ ምድር አቅ​ጣጫ ሄደ፤ በቃ​ዴ​ስና በሱር መካ​ከ​ልም ኖረ፤ በጌ​ራ​ራም በእ​ን​ግ​ድ​ነት ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="2">አብ​ር​ሃ​ምም ሚስ​ቱን ሣራን “እኅቴ ናት” አላ​ቸው፤ የከ​ተ​ማ​ዪቱ ሰዎች ስለ እር​ስዋ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ሉት “ሚስቴ” ናት ማለ​ትን ፈር​ቶ​አ​ልና፤ የጌ​ራራ ንጉሥ አቤ​ሜ​ሌ​ክም ላከና ሣራን ወሰ​ዳት።</verse>
				<verse number="3">በዚ​ያች ሌሊ​ትም አቤ​ሜ​ሌክ ተኝቶ ሳለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ልም ወደ እርሱ መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ አንተ ስለ ወሰ​ድ​ሃት ሴት ትሞ​ታ​ለህ፤ እር​ስዋ ባለ ባል ናትና።”</verse>
				<verse number="4">አቤ​ሜ​ሌክ ግን አል​ቀ​ረ​ባ​ትም ነበር፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክም እን​ዲህ አለ፥ “አቤቱ ያላ​ወ​ቀ​ውን ሕዝብ በእ​ው​ነት ታጠ​ፋ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="5">እኅቴ ናት ያለኝ እርሱ አይ​ደ​ለ​ምን? እር​ስዋ ደግሞ ራስዋ ወን​ድሜ ነው አለች፤ በልቤ ቅን​ነ​ትና በእጄ ንጹ​ሕ​ነት ይህን አደ​ረ​ግ​ሁት።”</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ልም አለው፥ “ይህን በል​ብህ ቅን​ነት እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ እኔ ዐወ​ቅሁ፤ እኔም ደግሞ በፊቴ ኀጢ​አ​ትን እን​ዳ​ት​ሠራ ጠበ​ቅ​ሁህ፤ ስለ​ዚ​ህም ትቀ​ር​ባት ዘንድ አል​ተ​ው​ሁ​ህም።</verse>
				<verse number="7">አሁ​ንም የሰ​ው​የ​ውን ሚስት መልስ፤ ነቢይ ነውና፥ ስለ አን​ተም ይጸ​ል​ያል፤ ትድ​ና​ለ​ህም። ባት​መ​ል​ሳት ግን አንተ እን​ድ​ት​ሞት፥ ለአ​ንተ የሆ​ነ​ውም ሁሉ እን​ዲ​ሞት በር​ግጥ ዕወቅ።”</verse>
				<verse number="8">አቤ​ሜ​ሌ​ክም በጥ​ዋት ተነሣ፤ ብላ​ቴ​ኖ​ቹ​ንም ሁሉ ጠራ፤ ይህ​ንም ነገር ሁሉ በጆ​ሮ​አ​ቸው ተና​ገረ፤ ቤተ ሰዎ​ቹም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጅግ ፈሩ።</verse>
				<verse number="9">አቤ​ሜ​ሌ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን ጠርቶ አለው፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው? ምንስ ክፉ ሠራ​ሁ​ብህ? በእ​ኔና በመ​ን​ግ​ሥቴ ላይ ትልቅ ኀጢ​አት አው​ር​ደ​ሃ​ልና፤ ማንም የማ​ያ​ደ​ር​ገው የማ​ይ​ገባ ሥራ በእኔ ሠራ​ህ​ብኝ።”</verse>
				<verse number="10">አቤ​ሜ​ሌ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “ይህን ነገር ማድ​ረ​ግህ ምን አይ​ተህ ነው?”</verse>
				<verse number="11">አብ​ር​ሃ​ምም አለ፥ “ምን​አ​ል​ባት በዚህ ስፍራ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ስለ​ሌለ በሚ​ስቴ ምክ​ን​ያት ይገ​ድ​ሉ​ኛል ብዬ ነው።</verse>
				<verse number="12">እር​ስ​ዋም ደግሞ በእ​ናቴ ወገን አይ​ደ​ለ​ችም እንጂ በእ​ው​ነት በአ​ባቴ ወገን እኅቴ ናት፤ ለእ​ኔም ሚስት ሆነች።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ባቴ ቤት ባወ​ጣኝ ጊዜ አል​ኋት፥ ‘ይህን ጽድቅ አድ​ር​ጊ​ልኝ፤ በገ​ባ​ን​በት ሀገር ሁሉ ወን​ድሜ ነው በዪ።’ ”</verse>
				<verse number="14">አቤ​ሜ​ሌ​ክም አንድ ሺህ ምዝ​ምዝ ብርን በጎ​ች​ንና ላሞ​ችን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎ​ችን አመጣ፤ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምም ሰጠው፤ ሚስ​ቱን ሣራ​ንም መለ​ሰ​ለት።</verse>
				<verse number="15">አቤ​ሜ​ሌ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “እነሆ፥ ምድሬ በፊ​ትህ ናት፤ በወ​ደ​ድ​ኸው ተቀ​መጥ።”</verse>
				<verse number="16">ሣራ​ንም አላት “እነሆ፥ ለወ​ን​ድ​ምሽ አንድ ሺህ ምዝ​ምዝ ብር ሰጠ​ሁት፤ ይህም ለፊ​ትሽ ክብር ይሁ​ንሽ፤ በሁ​ሉም እው​ነ​ትን ተና​ገ​ራት።”</verse>
				<verse number="17">አብ​ር​ሃ​ምም ወደ እግ​ዚ​ዘ​ብ​ሔር ጸለየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አቤ​ሜ​ሌ​ክን፥ ሚስ​ቱ​ንም፥ ሴቶች ልጆ​ቹ​ንም፥ በቤቱ ውስጥ ያሉ ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ፈወ​ሳ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ወለዱ፤</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ብ​ር​ሃም ሚስት በሣራ ምክ​ን​ያት በአ​ቤ​ሜ​ሌክ ቤት ማኅ​ፀ​ኖ​ችን ሁሉ በፍ​ጹም ዘግቶ ነበ​ርና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው ሣራን ጐበ​ኛት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው ለሣራ አደ​ረ​ገ​ላት።</verse>
				<verse number="2">ሣራም ፀነ​ሰች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በተ​ና​ገ​ረው ወራት ለአ​ብ​ር​ሃም በእ​ር​ጅ​ናዋ ወንድ ልጅን ወለ​ደ​ች​ለት።</verse>
				<verse number="3">አብ​ር​ሃ​ምም ሣራ የወ​ለ​ደ​ች​ለ​ትን የል​ጁን ስም ይስ​ሐቅ ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="4">አብ​ር​ሃ​ምም ልጁን ይስ​ሐ​ቅን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ገረ​ዘው።</verse>
				<verse number="5">አብ​ር​ሃ​ምም ልጁ ይስ​ሕቅ በተ​ወ​ለ​ደ​ለት ጊዜ መቶ ዓመቱ ነበረ።</verse>
				<verse number="6">ሣራም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ አሰ​ኘኝ፤ ይህን የሚ​ሰማ ሁሉ በእኔ ምክ​ን​ያት ደስ ይሰ​ኛ​ልና” አለች።</verse>
				<verse number="7">ደግ​ሞም ሣራ “በእ​ር​ጅ​ናዋ የወ​ለ​ደ​ች​ውን ሕፃን እን​ድ​ታ​ጠባ ለአ​ብ​ር​ሃም ማን በነ​ገ​ረው?” አለች።</verse>
				<verse number="8">ሕፃ​ኑም አደገ፤ ጡት​ንም አስ​ጣ​ሉት፤ አብ​ር​ሃ​ምም ይስ​ሐ​ቅን ጡት ባስ​ጣ​ለ​በት ቀን ትልቅ ግብ​ዣን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="9">ሣራም ግብ​ፃ​ዊቱ አጋር ለአ​ብ​ር​ሃም የወ​ለ​ደ​ች​ለ​ትን ልጅ ይስ​ማ​ኤ​ልን ከል​ጅዋ ከይ​ስ​ሐቅ ጋር ሲጫ​ወት አየ​ችው።</verse>
				<verse number="10">ሣራም አብ​ር​ሃ​ምን አለ​ችው፥ “ይህ​ችን ባሪያ ከነ​ል​ጅዋ አባ​ር​ራት፤ የዚ​ህች ባሪያ ልጅ ከልጄ ከይ​ስ​ሐቅ ጋር አይ​ወ​ር​ስ​ምና።”</verse>
				<verse number="11">ይህም ነገር በአ​ብ​ር​ሃም ዘንድ ስለ ልጁ እጅግ ችግር ሆነ​በት።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “ስለ​ዚች አገ​ል​ጋ​ይ​ህና ስለ ሕፃኑ አት​ዘን፤ ሣራም የም​ት​ነ​ግ​ር​ህን ቃል ሁሉ ስማ፤ በይ​ስ​ሐቅ ዘር ይጠ​ራ​ል​ሃ​ልና።</verse>
				<verse number="13">የባ​ሪ​ያ​ዪ​ቱን ልጅ ደግሞ ታላቅ ሕዝብ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ዘርህ ነውና።”</verse>
				<verse number="14">አብ​ር​ሃ​ምም ማልዶ ተነሣ፤ እን​ጀ​ራ​ንም ወሰደ፤ የውኃ አቍ​ማ​ዳ​ንም ለአ​ጋር በት​ከ​ሻዋ አሸ​ከ​ማት፤ ሕፃ​ኑ​ንም ሰጥቶ አስ​ወ​ጣት፤ እር​ስ​ዋም ሄደች፤ በዐ​ዘ​ቅተ መሐ​ላም በኩል ባለው ምድረ በዳ ተቅ​በ​ዘ​በ​ዘች።</verse>
				<verse number="15">ውኃ​ውም ከአ​ቍ​ማ​ዳው አለቀ፤ ሕፃ​ኑ​ንም ከአ​ንድ ቍጥ​ቋጦ ሥር ጥላው ሄደች፤</verse>
				<verse number="16">ልጄ ሲሞት አላ​የ​ውም ብላ ቀስት ተወ​ር​ውሮ የሚ​ደ​ር​ስ​በ​ትን ያህል ርቃ በአ​ን​ጻሩ እየ​ተ​መ​ለ​ከ​ተች፥ ፊት ለፊት ተቀ​መ​ጠች፤ ቃል​ዋ​ንም አሰ​ምታ አለ​ቀ​ሰች።</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሕ​ፃ​ኑን ጩኸት ሰማ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ከሰ​ማይ አጋ​ርን እን​ዲህ ሲል ጠራት፥ “አጋር ሆይ፥ ምን ሆንሽ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የል​ጅ​ሽን ድምፅ ባለ​በት ስፍራ ሰም​ቶ​አ​ልና አት​ፍሪ።</verse>
				<verse number="18">ተነሺ፤ ልጅ​ሽ​ንም አንሺ፤ በእ​ጅ​ሽም አጽ​ኚው፤ ትልቅ ሕዝብ አደ​ር​ገ​ዋ​ለ​ሁና።”</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ጋር ዐይ​ን​ዋን ከፈ​ተ​ላት፤ የውኃ ጕድ​ጓ​ድ​ንም አየች፤ ሄዳም አቍ​ማ​ዳ​ውን በውኃ ሞላች፤ ልጅ​ዋ​ንም አጠ​ጣ​ችው።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከዚያ ሕፃን ጋር ነበረ፤ አደ​ገም፤ በም​ድረ በዳም ተቀ​መጠ፤ ቀስ​ተ​ኛም ሆነ።</verse>
				<verse number="21">በፋ​ራን ምድረ በዳም ተቀ​መጠ፤ እና​ቱም ከም​ድረ ግብፅ ሚስት ወሰ​ደ​ች​ለት።</verse>
				<verse number="22">በዚያ ዘመን አቤ​ሜ​ሌክ፥ ሚዜው አኮ​ዘ​ትና የሠ​ራ​ዊቱ አለቃ ፋኮል ወደ አብ​ር​ሃም ሄደው አሉት፥ “በም​ታ​ደ​ር​ገው ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው፤</verse>
				<verse number="23">አሁ​ንም በእ​ኔም፥ በል​ጄም፥ በወ​ገ​ኔም፥ ከእ​ኔም ጋር ባለ ክፉ እን​ዳ​ታ​ደ​ር​ግ​ብኝ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማል​ልኝ፤ ነገር ግን በእ​ን​ግ​ድ​ነት መጥ​ተህ ለአ​ንተ ቸር​ነት እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ አን​ተም ለእኔ፥ ለተ​ቀ​ም​ጥ​ህ​ባ​ትም ምድር ቸር​ነ​ትን ታደ​ር​ጋ​ለህ።”</verse>
				<verse number="24">አብ​ር​ሃ​ምም፥ “እሺ እኔ እም​ላ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="25">አብ​ር​ሃ​ምም አቤ​ሜ​ሌ​ክን ብላ​ቴ​ኖቹ በቀ​ሙት በውኃ ጕድ​ጓድ ምክ​ን​ያት ወቀ​ሰው።</verse>
				<verse number="26">አቤ​ሜ​ሌ​ክም አለ፥ “ይህን ነገር ማን እን​ዳ​ደ​ረ​ገው አላ​ወ​ቅ​ሁም፤ አን​ተም ደግሞ ምንም አል​ነ​ገ​ር​ኸ​ኝም፤ እኔም ከዛሬ በቀር አል​ሰ​ማ​ሁም።”</verse>
				<verse number="27">አብ​ር​ሃ​ምም በጎ​ች​ንና ላሞ​ችን አም​ጥቶ ለአ​ቤ​ሜ​ሌክ ሰጠው፤ ሁለ​ቱም ቃል ኪዳን አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="28">አብ​ር​ሃ​ምም ሰባ ቄቦች በጎ​ችን ለብ​ቻ​ቸው አቆመ።</verse>
				<verse number="29">አቤ​ሜ​ሌ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን፥ “ለብ​ቻ​ቸው ያቆ​ም​ሃ​ቸው እነ​ዚያ ሰባ ቄቦች በጎች ምን​ድን ናቸው?” አለው።</verse>
				<verse number="30">እር​ሱም፥ “እኔ ይህ​ችን የውኃ ጕድ​ጓድ እን​ደ​ቈ​ፈ​ርሁ ምስ​ክር ይሆ​ኑ​ልኝ ዘንድ እነ​ዚ​ህን ሰባ ቄቦች በጎች ከእጄ ትወ​ስ​ዳ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="31">ስለ​ዚ​ህም ያን ጕድ​ጓድ ዐዘ​ቅተ መሐላ ብሎ ጠራው፤ በዚያ እርስ በር​ሳ​ቸው ተማ​ም​ለ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="32">በዐ​ዘ​ቅተ መሐላ አጠ​ገ​ብም ቃል ኪዳ​ንን አደ​ረጉ። አቤ​ሜ​ሌ​ክና ሚዜው አኮ​ዞት፥ የሠ​ራ​ዊቱ አለቃ ፋኮ​ልም ተነ​ሥ​ተው ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ምድር ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="33">አብ​ር​ሃ​ምም በዐ​ዘ​ቅተ መሐላ አጠ​ገብ የተ​ምር ዛፍን ተከለ፤ በዚ​ያም የዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙን አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ጠራ።</verse>
				<verse number="34">አብ​ር​ሃ​ምም በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ምድር ብዙ ቀን እን​ግዳ ሆኖ ተቀ​መጠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">ከእ​ነ​ዚ​ህም ነገ​ሮች በኋላ እን​ዲህ ሆነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ​ር​ሃ​ምን ፈተ​ነው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “አብ​ር​ሃም! አብ​ር​ሃም ሆይ፥” እር​ሱም፥ “እነሆ፥ አለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="2">“የም​ት​ወ​ድ​ደ​ውን አንድ ልጅ​ህን ይስ​ሐ​ቅን ይዘህ ወደ ከፍ​ተ​ኛው ተራራ ሂድ፤ እኔም በም​ነ​ግ​ርህ በአ​ንድ ተራራ ላይ በዚያ መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገህ ሠዋው” አለው።</verse>
				<verse number="3">አብ​ር​ሃ​ምም በማ​ለዳ ተነ​ሥቶ አህ​ያ​ውን ጫነ፤ ሁለ​ቱ​ንም ሎሌ​ዎ​ቹ​ንና ልጁን ይስ​ሐ​ቅን ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ፤ ዕን​ጨ​ት​ንም ለመ​ሥ​ዋ​ዕት ሰነ​ጠቀ፤ ተነ​ሥ​ቶም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለው ቦታ ሄደ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ደረሰ።</verse>
				<verse number="4">አብ​ር​ሃ​ምም ዐይ​ኑን አነ​ሣና ቦታ​ውን ከሩቅ አየ።</verse>
				<verse number="5">አብ​ር​ሃ​ምም ሎሌ​ዎ​ቹን አላ​ቸው፥ “አህ​ያ​ውን ይዛ​ችሁ በዚህ ቈዩ፤ እኔና ልጄ ወደ​ዚያ ተራራ ሄደን እን​ሰ​ግ​ዳ​ለን፤ ሰግ​ደ​ንም ወደ እና​ንተ እን​መ​ለ​ሳ​ለን።”</verse>
				<verse number="6">አብ​ር​ሃ​ምም የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን ዕን​ጨት አን​ሥቶ ለልጁ ለይ​ስ​ሐቅ አሸ​ከ​መው፤ እር​ሱም እሳ​ቱ​ንና ቢላ​ዋ​ዉን በእጁ ያዘ፤ ሁለ​ቱም አብ​ረው ሄዱ።</verse>
				<verse number="7">ይስ​ሐ​ቅም አባ​ቱን አብ​ር​ሃ​ምን ተና​ገ​ረው፥ “አባቴ ሆይ፥” አለ፤ እር​ሱም፥ “ልጄ፥ ምን​ድን ነው?” አለው። “እሳ​ቱና ዕን​ጨቱ ይኸው አለ፤ የመ​ሥ​ዋ​ዕቱ በግ ግን ወዴት አለ?” አለው።</verse>
				<verse number="8">አብ​ር​ሃ​ምም፥ “ልጄ ሆይ፥ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን በግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ጋ​ጃል” አለው፤ ሁለ​ቱም አብ​ረው ሄዱ።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለ​ውም ወደ​ዚያ ቦታ ደረሱ፤ አብ​ር​ሃ​ምም በዚያ መሠ​ዊ​ያ​ዉን ሠራ፤ ዕን​ጨ​ት​ንም ረበ​ረበ፤ ልጁን ይስ​ሐ​ቅ​ንም አስሮ በመ​ሠ​ዊ​ያዉ በዕ​ን​ጨቱ ላይ በልቡ አስ​ተ​ኛው።</verse>
				<verse number="10">አብ​ር​ሃ​ምም እጁን ዘረጋ፤ ልጁ​ንም ያርድ ዘንድ ቢላዋ አነሣ።</verse>
				<verse number="11">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም ከሰ​ማይ ጠራና፥ “አብ​ር​ሃም! አብ​ር​ሃም” አለው፤ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ” አለ።</verse>
				<verse number="12">እር​ሱም፥ “በብ​ላ​ቴ​ናው ላይ እጅ​ህን አት​ዘ​ርጋ፤ አን​ዳ​ችም አታ​ድ​ር​ግ​በት፤ ለም​ት​ው​ድ​ደው ልጅህ ከእኔ አል​ራ​ራ​ህ​ለ​ት​ምና አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈራ እን​ደ​ሆ​ንህ አሁን ዐው​ቄ​አ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="13">አብ​ር​ሃ​ምም ዐይ​ኖ​ቹን አቅ​ንቶ በተ​መ​ለ​ከተ ጊዜ፥ በኋ​ላው እነሆ፥ አንድ በግ ቀን​ዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤ አብ​ር​ሃ​ምም ሄዶ በጉን ወሰ​ደው፤ በልጁ በይ​ስ​ሐቅ ፈን​ታም ሠዋው።</verse>
				<verse number="14">አብ​ር​ሃ​ምም ዛሬ በዚህ ተራራ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈጽሞ ታየኝ ሲል ያን ቦታ “ራእየ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="15">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን ከሰ​ማይ ሁለ​ተኛ ጊዜ ጠራው፤ እን​ዲ​ህም አለው፦</verse>
				<verse number="16">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በራሴ ማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ ለም​ት​ወ​ድ​ደው ልጅ​ህም ከእኔ አል​ራ​ራ​ህ​ምና መባ​ረ​ክን እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="17">ዘር​ህ​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብ​ትና በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ዘር​ህም የጠ​ላት ሀገ​ሮ​ችን ይወ​ር​ሳሉ፤</verse>
				<verse number="18">የም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉም በዘ​ርህ ይባ​ረ​ካሉ፤ ቃሌን ሰም​ተ​ሃ​ልና።”</verse>
				<verse number="19">አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ብላ​ቴ​ኖቹ ተመ​ለሰ፤ ተነ​ሥ​ተ​ውም ወደ ዐዘ​ቅተ መሐላ አብ​ረው ሄዱ፤ አብ​ር​ሃ​ምም በዐ​ዘ​ቅተ መሐላ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="20">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከዚህ ነገር በኋላ ለአ​ብ​ር​ሃም እን​ዲህ ተብሎ ተነ​ገረ፥ “እነሆ፥ ሚልካ ደግሞ ለወ​ን​ድ​ምህ ለና​ኮር ልጆ​ችን ወለ​ደች፤</verse>
				<verse number="21">እነ​ር​ሱም በኵሩ ዑፅ፥ ወን​ድሙ በዋ​ክሲ፤ የአ​ራም አባት ቀማ​ኤል፥</verse>
				<verse number="22">አኮ​ዛት፥ ኤዝ​ራው፥ ፌል​ዳስ፥ ዮፋ​ትና ባቱ​ኤል” ናቸው።</verse>
				<verse number="23">ባቱ​ኤ​ልም ርብ​ቃን ወለደ፤ ሚልካ ለአ​ብ​ር​ሃም ወን​ድም ለና​ኮር የወ​ለ​ደ​ች​ለት ስም​ንቱ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="24">ሬሕማ የሚ​ሉ​አት ዕቅ​ብቱ ደግሞ ጥባ​ህን፥ ቤካን፥ ጠኮ​ንና ሜካን ወለ​ደች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="23">
				<verse number="1">የሣ​ራም ዕድሜ መቶ ሃያ ሰባት ዓመት ሆነ።</verse>
				<verse number="2">ሣራም በቈላ ውስጥ ባለች አር​ባቅ በም​ት​ባል ከተማ ሞተች፤ እር​ስ​ዋም በከ​ነ​ዓን ምድር ያለች ኬብ​ሮን ናት፤ አብ​ር​ሃ​ምም ለሣራ ሊያ​ዝ​ን​ላ​ትና ሊያ​ለ​ቅ​ስ​ላት ተነሣ።</verse>
				<verse number="3">አብ​ር​ሃ​ምም ከሬ​ሳው አጠ​ገብ ተነሣ፤ ለኬጢ ልጆ​ችም እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፦</verse>
				<verse number="4">“እኔ በእ​ና​ንተ ዘንድ ስደ​ተ​ኛና መጻ​ተኛ ነኝ፤ በእ​ና​ንተ ዘንድ እን​ድ​ገዛ የመ​ቃ​ብር ርስት ስጡኝ፤ ሬሳ​ዬ​ንም እንደ እና​ንተ ልቅ​በር።”</verse>
				<verse number="5">የኬጢ ልጆ​ችም ለአ​ብ​ር​ሃም መለሱ፤ አሉ​ትም፦</verse>
				<verse number="6">“አይ​ሆ​ንም፥ ጌታ ሆይ፥ ስማን፤ አንተ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ለእኛ ንጉሥ ነህና ከመ​ቃ​ብር ስፍ​ራ​ችን በመ​ረ​ጥ​ኸው ቦታ ሬሳ​ህን ቅበር፤ ሬሳ​ህን በዚያ ትቀ​ብር ዘንድ ከእኛ መቃ​ብ​ሩን የሚ​ከ​ለ​ክ​ልህ የለም።”</verse>
				<verse number="7">አብ​ር​ሃ​ምም ተነሣ፤ በሀ​ገሩ ሕዝብ ፊትም ለኬጢ ልጆች ሰገደ።</verse>
				<verse number="8">እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ሬሳ​ዬን ከፊቴ አርቄ እን​ድ​ቀ​ብር ከወ​ደ​ዳ​ች​ሁስ ስሙኝ፤ ለሰ​ዓር ልጅ ለኤ​ፍ​ሮ​ንም ስለ እኔ ንገ​ሩት፤</verse>
				<verse number="9">በእ​ር​ሻው ዳር ያለ​ች​ውን ድርብ ክፍል ያላ​ትን ዋሻ​ውን ይስ​ጠኝ፤ መቃ​ብሩ የእኔ ርስት እን​ዲ​ሆን በሚ​ገ​ባው ዋጋ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ይስ​ጠኝ፤ ከእ​ር​ሱም እገ​ዛ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="10">ኤፍ​ሮ​ንም በኬጢ ልጆች መካ​ከል ተቀ​ምጦ ነበር፤ የኬጢ ሰው ኤፍ​ሮ​ንም የኬጢ ልጆ​ችና ወደ ከተማ የሚ​ገቡ ሁሉ ሲሰሙ ለአ​ብ​ር​ሃም እን​ዲህ ሲል መለ​ሰ​ለት፦</verse>
				<verse number="11">“አይ​ደ​ለም፥ ጌታዬ፥ ቀር​በህ ስማኝ፤ እር​ሻ​ውን፥ በው​ስ​ጡም ያለ​ውን ዋሻ​ውን ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ በወ​ገኔ ልጆች ፊት ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ሬሳ​ህን ቅበር።”</verse>
				<verse number="12">አብ​ር​ሃ​ምም በሀ​ገሩ ሕዝብ ሁሉ ፊት ሰገደ፤</verse>
				<verse number="13">የሀ​ገሩ ሕዝ​ብም ሲሰሙ ለኤ​ፍ​ሮን እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፥ “ከእኔ ቅርብ ነህና ስማኝ፤ የእ​ር​ሻ​ህ​ንም ዋጋ ከእኔ ውሰድ፤ ሬሳ​ዬ​ንም በዚያ እቀ​ብ​ራ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="14">ኤፍ​ሮ​ንም ለአ​ብ​ር​ሃም እን​ዲህ ሲል መለ​ሰ​ለት፥ “አይ​ሆ​ንም፤ ጌታዬ ሆይ፥ እኔን ስማኝ፤</verse>
				<verse number="15">የአ​ራት መቶ ምዝ​ምዝ ብር ዋጋ ምድር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ምን​ድን ነው? እን​ግ​ዲህ ሬሳ​ህን በዚያ ቅበር።”</verse>
				<verse number="16">አብ​ር​ሃ​ምም የኤ​ፍ​ሮ​ንን ነገር ሰማ፤ አብ​ር​ሃ​ምም በኬጢ ልጆች ፊት የነ​ገ​ረ​ው​ንና ተቀ​ባ​ይ​ነት ያለ​ውን ግብዝ ያይ​ደለ አራት መቶ ምዝ​ምዝ ብር መዝኖ ለኤ​ፍ​ሮን ሰጠው።</verse>
				<verse number="17">በመ​ምሬ ፊት ያለው ባለ ድርብ ክፍል የሆ​ነው የኤ​ፍ​ሮን እር​ሻም ለአ​ብ​ር​ሃም ጸና፤ እር​ሻው፥ በእ​ር​ሱም ያለ ዋሻው፥ በእ​ር​ሻ​ውም ውስጥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ያለው ዕን​ጨት ሁሉ፤</verse>
				<verse number="18">በኬጢ ልጆ​ችና በከ​ተ​ማ​ዪቱ በር በሚ​ገቡ ሁሉ ፊት ለአ​ብ​ር​ሃም ርስቱ ሆነ።</verse>
				<verse number="19">ከዚ​ህም በኋላ አብ​ር​ሃም ኬብ​ሮን በም​ት​ባል በመ​ምሬ ፊት በከ​ነ​ዓን ምድር ባለው እርሻ ባለ ድርብ ክፍል በሆ​ነው ዋሻ ውስጥ ሚስ​ቱን ሣራን ቀበረ።</verse>
				<verse number="20">እር​ሻ​ውና በእ​ርሱ ያለው ዋሻም በኬጢ ልጆች ዘንድ ለአ​ብ​ር​ሃም የመ​ቃ​ብር ርስት ሆኖ ጸና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="24">
				<verse number="1">አብ​ር​ሃ​ምም ሸመ​ገለ፤ ዘመ​ኑም አለፈ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን በሁሉ ባረ​ከው።</verse>
				<verse number="2">አብ​ር​ሃ​ምም ሎሌ​ውን፥ የቤ​ቱን ሽማ​ግሌ፥ የከ​ብ​ቱን ሁሉ አዛዥ አለው፦</verse>
				<verse number="3">“እጅ​ህን በእጄ ላይ አድ​ርግ፤ እኔም አብሬ ከም​ኖ​ራ​ቸው ከከ​ነ​ዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይ​ስ​ሐቅ ሚስት እን​ዳ​ት​ወ​ስ​ድ​ለት በሰ​ማ​ይና በም​ድር አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ል​ሃ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን ወደ ተወ​ለ​ድ​ሁ​በት ወደ ሀገ​ሬና ወደ ተወ​ላ​ጆች ሂድ፤ ለልጄ ለይ​ስ​ሐ​ቅም ከዚያ ሚስ​ትን አም​ጣ​ለት።”</verse>
				<verse number="5">ሎሌ​ውም፥ “ሴቲቱ ምና​ል​ባት ወደ​ዚህ ሀገር ከእኔ ጋር ለመ​ም​ጣት ባት​ወ​ድ​ድስ ልጅ​ህን ወደ መጣ​ህ​በት ሀገር ልመ​ል​ሰ​ውን?” አለው።</verse>
				<verse number="6">አብ​ር​ሃ​ምም አለው፥ “ልጄን ወደ​ዚያ እን​ዳ​ት​መ​ልስ ተጠ​ን​ቀቅ፤</verse>
				<verse number="7">ከአ​ባቴ ቤት፥ ከተ​ወ​ለ​ድ​ሁ​ባት ምድር ያወ​ጣኝ፦ ‘ይህ​ች​ንም ምድር ለአ​ን​ተና ለዘ​ርህ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ’ ብሎ የነ​ገ​ረ​ኝና የማ​ለ​ልኝ የሰ​ማ​ይና የም​ድር አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እርሱ መል​አ​ኩን በፊ​ትህ ይሰ​ድ​ዳል፤ ከዚ​ያም ለልጄ ሚስ​ትን ትወ​ስ​ዳ​ለህ።</verse>
				<verse number="8">ሴቲ​ቱም ከአ​ንተ ጋር ወደ​ዚች ምድር ለመ​ም​ጣት ባት​ፈ​ቅድ አንተ ከዚህ መሐላ ንጹሕ ነህ፤ ልጄን ግን ወደ​ዚያ እን​ዳ​ት​መ​ል​ሰው ተጠ​ን​ቀቅ።”</verse>
				<verse number="9">ሎሌ​ውም በጌ​ታው በአ​ብ​ር​ሃም እጅ ላይ እጁን አደ​ረገ፤ ስለ​ዚ​ሁም ነገር ማለ​ለት።</verse>
				<verse number="10">ሎሌ​ውም ከጌ​ታው ግመ​ሎች መካ​ከል ዐሥር ግመ​ሎ​ችን ወስዶ፥ ከጌ​ታ​ውም ዕቃ መል​ካም መል​ካ​ሙን ይዞ ተነሣ፤ ተነ​ሥ​ቶም ወደ ሦርያ ወን​ዞች መካ​ከል ወደ ናኮር ከተማ ሄደ።</verse>
				<verse number="11">ሲመ​ሽም ውኃ ቀጂ​ዎች ውኃ ሊቀዱ በሚ​መ​ጡ​በት ጊዜ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ውጪ በውኃ ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ግመ​ሎ​ቹን አሳ​ረፈ።</verse>
				<verse number="12">እን​ዲ​ህም አለ፥ “የጌ​ታዬ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ እማ​ል​ድ​ሃ​ለሁ፤ መን​ገ​ዴን ዛሬ በፊቴ አቅ​ና​ልኝ፤ ለጌ​ታ​ዬም ለአ​ብ​ር​ሃም ምሕ​ረ​ትን አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="13">እነሆ፥ በው​ኃው ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ቆሜ​አ​ለሁ፤ የከ​ተ​ማዋ ሰዎች ሴቶች ልጆ​ችም ውኃ​ውን ሊቀዱ ይወ​ጣሉ፤</verse>
				<verse number="14">እን​ስ​ራ​ሽን አዘ​ን​ብ​ለሽ ውኃ አጠ​ጭኝ የም​ላት እር​ስ​ዋም፦ ‘አንተ ጠጣ፥ ግመ​ሎ​ች​ህን ደግሞ እስ​ኪ​ረኩ አጠ​ጣ​ለሁ’ የም​ት​ለኝ ድን​ግል፥ እር​ስዋ ለባ​ሪ​ያህ ለይ​ስ​ሐቅ ያዘ​ጋ​ጀ​ሃት ትሁን፤ በዚ​ህም ለጌ​ታዬ ለአ​ብ​ር​ሃም ምሕ​ረ​ትን እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ አው​ቃ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="15">እን​ደ​ዚህ በልቡ ያሰ​በ​ውን መና​ገ​ሩን ሳይ​ፈ​ጽም እን​ዲህ ሆነ፦ የአ​ብ​ር​ሃም ወን​ድም የና​ኮር ሚስት የሚ​ልካ ልጅ የባ​ቱ​ኤል ሴት ልጅ ርብቃ እነሆ፥ መጣች፥ እን​ስ​ራ​ዋ​ንም በጫ​ን​ቃዋ ተሸ​ክማ ነበር።</verse>
				<verse number="16">ብላ​ቴ​ና​ይ​ቱም መል​ክዋ እጅግ ያማረ፥ ወንድ የማ​ታ​ውቅ ድን​ግል ነበ​ረች። ወደ ውኃው ጕድ​ጓ​ድም ወረ​ደች፤ ውኃም ቀዳች፤ እን​ስ​ራ​ዋ​ንም ሞልታ ወጣች።</verse>
				<verse number="17">ያም ሰው ሊገ​ና​ኛት ሮጠና፥ “ከእ​ን​ስ​ራሽ ጥቂት ውኃ አጠ​ጪኝ” አላት።</verse>
				<verse number="18">እር​ስ​ዋም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ጠጣ” አለ​ችው፤ ፈጥ​ናም እን​ስ​ራ​ዋን ከጫ​ን​ቃዋ በእ​ጅዋ አው​ርዳ እስ​ኪ​ረካ አጠ​ጣ​ችው።</verse>
				<verse number="19">እር​ሱ​ንም ከአ​ጠ​ጣች በኋላ፦ “ለግ​መ​ሎ​ችህ ደግሞ ሁሉም እስ​ኪ​ረኩ ድረስ ውኃ እቀ​ዳ​ለሁ” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="20">ፈጥ​ናም ውኃ​ውን ከእ​ን​ስ​ራዋ በማ​ጠ​ጫው ውስጥ ገለ​በ​ጠ​ችው፤ ደግ​ሞም ልት​ቀዳ ወደ ጕድ​ጓዱ ሮጠች፤ ለግ​መ​ሎ​ቹም ሁሉ ውኃ ቀዳች።</verse>
				<verse number="21">ሰው​የ​ውም ትክ ብሎ ይመ​ለ​ከ​ታት ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገ​ዱን አቅ​ን​ቶ​ለት እንደ ሆነ ወይም እን​ዳ​ል​ሆነ ለማ​ወ​ቅም ዝም አለ።</verse>
				<verse number="22">ግመ​ሎ​ቹም ከጠጡ በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ ሰው​ዬው አንድ አንድ ወቄት የሚ​መ​ዝን የወ​ርቅ ጉትቻ፥ ለእ​ጆ​ች​ዋም ዐሥር ወቄት የሚ​መ​ዝን ጥንድ የወ​ርቅ አም​ባር አወጣ፤</verse>
				<verse number="23">ጠር​ቶም እን​ዲህ አላት፥ “አንቺ የማን ልጅ ነሽ? በአ​ባ​ትሽ ቤት የም​ና​ድ​ር​በት ስፍራ እን​ዳለ እስኪ ንገ​ሪኝ፤”</verse>
				<verse number="24">አለ​ች​ውም፥ “እኔ ሚልካ ለና​ኮር የወ​ለ​ደ​ች​ለት የባ​ቱ​ኤል ልጅ ነኝ።</verse>
				<verse number="25">በእኛ ዘንድ ለግ​መ​ሎ​ችህ ሣርና ገለባ የሚ​በቃ ያህል አለ፤ ማደ​ሪ​ያም አለን።”</verse>
				<verse number="26">ሰው​የ​ውም ደስ አለው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰገደ።</verse>
				<verse number="27">እን​ዲ​ህም አለ፥ “ቸር​ነ​ቱ​ንና እው​ነ​ቱን ከጌ​ታዬ ያላ​ራቀ የጌ​ታዬ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ ለእ​ኔም ወደ ጌታዬ ወደ አብ​ር​ሃም ወን​ድም ቤት መን​ገ​ዴን አቀ​ና​ልኝ።”</verse>
				<verse number="28">ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም ሮጠች፥ ለእ​ና​ቷም ቤት ይህን ሁሉ ነገር ተና​ገ​ረች።</verse>
				<verse number="29">ለር​ብ​ቃም ስሙ ላባ የተ​ባለ ወን​ድም ነበ​ራት፤ ላባም ወደ ውጪ ወደ ውኃው ጕድ​ጓድ ወደ ሰው​ዬው ሮጠ።</verse>
				<verse number="30">ጉት​ቻ​ው​ንና አም​ባ​ሮ​ቹን በእ​ኅቱ እጅ ባየ ጊዜ፥ የእ​ኅ​ቱ​ንም የር​ብ​ቃን ነገር፦ ያ ሰው እን​ዲህ አለኝ ያለ​ች​ውን በሰማ ጊዜ፥ እርሱ ወደ​ዚያ ሰው መጣ፤ እነ​ሆም በው​ኃው ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ከግ​መ​ሎቹ ዘንድ ቆሞ ነበር።</verse>
				<verse number="31">እር​ሱም አለው፥ “አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ፥ ግባ ስለ​ምን አንተ በውጪ ቆመ​ሃል? እኛም ቤትን፥ ለግ​መ​ሎ​ች​ህም ማደ​ሪ​ያን አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ናል።”</verse>
				<verse number="32">ሰው​ዬ​ውም ወደ ቤት ገባ፤ ግመ​ሎ​ቹ​ንም አራ​ገፈ፤ ለግ​መ​ሎ​ቹም ሣርና ገለባ አቀ​ረ​ቡ​ላ​ቸው፤ እግ​ሩን ይታ​ጠብ ዘንድ ውኃ አመ​ጡ​ለት፤ ከእ​ርሱ ጋር ላሉ ሰዎ​ችም አመ​ጡ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="33">ይበ​ላም ዘንድ እን​ጀ​ራን አቀ​ረ​ቡ​ለት፤ እርሱ ግን “ነገ​ሬን እስ​ክ​ና​ገር ደረስ አል​በ​ላም” አለ። እነ​ር​ሱም “ተና​ገር” አሉት።</verse>
				<verse number="34">እር​ሱም አለ፥ “እኔ የአ​ብ​ር​ሃም ሎሌ ነኝ።</verse>
				<verse number="35">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌታ​ዬን እጅግ ባረ​ከው፤ አገ​ነ​ነ​ውም፤ ላሞ​ች​ንና በጎ​ችን፥ ወር​ቅ​ንና ብርን፥ ወን​ዶች ባሪ​ያ​ዎ​ች​ንና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎ​ችን፥ ግመ​ሎ​ች​ንና አህ​ዮ​ች​ንም ሰጠው።</verse>
				<verse number="36">የጌ​ታዬ የአ​ብ​ር​ሃም ሚስት ሣራም በእ​ር​ጅ​ናዋ ለጌ​ታዬ ወንድ ልጅን ወለ​ደች፤ የነ​በ​ረ​ው​ንም ሁሉ ሰጠው።”</verse>
				<verse number="37">ጌታዬ እን​ዲህ ሲል አማ​ለኝ፥ “እኔ ካለ​ሁ​በት ሀገር ከከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ሴቶች ልጆች ለልጄ ሚስ​ትን አት​ው​ሰድ፤</verse>
				<verse number="38">ነገር ግን ወደ አባቴ ቤት ወደ ወገ​ኔም ሂድ፤ ለል​ጄም ከዚያ ሚስ​ትን ውሰ​ድ​ለት።</verse>
				<verse number="39">ጌታ​ዬ​ንም ሴቲቱ ምና​ል​ባት ከእኔ ጋር መም​ጣ​ትን ባት​ፈ​ቅ​ድስ አል​ሁት።</verse>
				<verse number="40">እር​ሱም አለኝ፦ አካ​ሄ​ዴን በፊቱ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ለት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ኩን ከአ​ንተ ጋር ይል​ካል። መን​ገ​ድ​ህ​ንም ያቀ​ናል፤ ለል​ጄም ከወ​ገ​ኖች ከአ​ባ​ቴም ቤት ሚስ​ትን ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤</verse>
				<verse number="41">የዚ​ያን ጊዜ ከመ​ሐ​ላዬ ንጹሕ ትሆ​ና​ለህ፤ ወደ ዘመ​ዶች ሄደህ እነ​ርሱ ባይ​ሰ​ጡህ ካማ​ል​ሁህ መሐላ ንጹሕ ትሆ​ና​ለህ።”</verse>
				<verse number="42">ዛሬም ወደ ውኃው ጕድ​ጓድ መጣሁ፤ እን​ዲ​ህም አልሁ፥ “የጌ​ታዬ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ዛሬ የም​ሄ​ድ​በ​ትን መን​ገ​ዴን ብታ​ቀ​ና​ልኝ፥</verse>
				<verse number="43">እነሆ፥ እኔ በው​ኃው ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ቆሜ​አ​ለሁ፤ የከ​ተ​ማዋ ሰዎች ሴቶች ልጆ​ችም ውኃን ሊቀዱ ይወ​ጣሉ፤ ጥቂት ውኃ ከእ​ን​ስ​ራሽ አጠ​ጪኝ ስላት፥</verse>
				<verse number="44">እር​ስ​ዋም ፦ ‘አንተ ጠጣ፤ ደግ​ሞም ለግ​መ​ሎ​ችህ እቀ​ዳ​ለሁ’ የም​ት​ለኝ ድን​ግል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጌ​ታዬ ልጅ ለባ​ሪ​ያዉ ለይ​ስ​ሐቅ ያዘ​ጋ​ጃት ሚስት እር​ስዋ ትሁን። በዚ​ህም ለጌ​ታዬ ምሕ​ረ​ትን እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ አው​ቃ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="45">እኔም በልቤ ያሰ​ብ​ሁ​ትን ሳል​ፈ​ጽም እን​ዲህ ሆነ፤ ያን ጊዜ ርብቃ እን​ስ​ራ​ዋን በት​ከ​ሻዋ ተሸ​ክማ ወጣች፥ ወደ ምን​ጭም ወርዳ ውኃ ቀዳች፤ እኔም “እስቲ ውኃ አጠ​ጪኝ” አል​ኋት።</verse>
				<verse number="46">ፈጥ​ናም እን​ስ​ራ​ዋን ከት​ከ​ሻዋ አወ​ረ​ደ​ችና፥ “አንተ ጠጣ፤ ግመ​ሎ​ች​ህን ደግሞ አጠ​ጣ​ለሁ” አለ​ችኝ፤ እኔም ጠጣሁ፤ ግመ​ሎ​ች​ንም ደግሞ አጠ​ጣች።</verse>
				<verse number="47">እኔም “አንቺ የማን ልጅ ነሽ? ንገ​ሪኝ” ብዬ ጠየ​ቅ​ኋት። እር​ስ​ዋም፥ “ሚልካ የወ​ለ​ደ​ች​ለት የና​ኮር ልጅ የባ​ቱ​ኤል ልጅ ነኝ” አለ​ችኝ፤</verse>
				<verse number="48">ይህ​ንም ነገር ከአ​ን​ደ​በቷ በሰ​ማሁ ጊዜ እጅግ ደስ አሰ​ኘ​ችኝ። ለጆ​ሮ​ዎ​ች​ዋም ጉት​ቻ​ዎ​ችን ለእ​ጆ​ች​ዋም አም​ባ​ሮ​ችን አድ​ርጌ አስ​ጌ​ጥ​ኋት። ደስ ባሰ​ኘ​ች​ኝም ጊዜ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገ​ድሁ፤ የጌ​ታ​ዬን የወ​ን​ድ​ሙን ልጅ ለልጁ እወ​ስድ ዘንድ በቀና መን​ገድ የመ​ራ​ኝን የጌ​ታ​ዬን የአ​ብ​ር​ሃ​ምን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ንሁ።</verse>
				<verse number="49">አሁ​ንም ቸር​ነ​ት​ንና እው​ነ​ትን ለጌ​ታዬ ትሠሩ እንደ ሆነ ንገ​ሩኝ፤ ይህም ባይ​ሆን ንገ​ሩኝ፤ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ እመ​ለስ ዘንድ።</verse>
				<verse number="50">ባቱ​ኤ​ልና ላባም መለሱ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ነገሩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መጥ​ቶ​አል፤ ክፉ ወይም በጎ ልን​መ​ል​ስ​ልህ አን​ች​ልም።</verse>
				<verse number="51">ርብቃ እን​ኋት፤ በፊ​ትህ ናት፤ ይዘ​ሃት ሂድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ ለጌ​ታህ ልጅ ሚስት ትሁን።”</verse>
				<verse number="52">የአ​ብ​ር​ሃ​ምም ሎሌ ነገ​ራ​ቸ​ውን በሰማ ጊዜ ወደ ምድር ወድቆ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ።</verse>
				<verse number="53">ሎሌ​ውም የብ​ርና የወ​ርቅ ጌጥ፥ ልብ​ስም አወጣ፤ ለር​ብ​ቃም ሰጣት፤ ዳግ​መ​ኛም ለአ​ባ​ቷና ለእ​ናቷ እጅ መንሻ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="54">ከዚ​ህም ሁሉ በኋላ እርሱ፥ ከእ​ርሱ ጋር ያሉ​ትም በሉ፤ ጠጡም፤ በዚ​ያም አደሩ፤ በማ​ለ​ዳም ተነ​ሥቶ፥ “ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ቱኝ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="55">አባቷ እና​ቷና ወን​ድ​ምዋ፦ “ብላ​ቴ​ና​ዪቱ ዐሥር ቀን ያህል እንኳ በእኛ ዘንድ ትቀ​መጥ፤ ከዚ​ያም በኋላ ትሄ​ዳ​ለች” አሉ።</verse>
				<verse number="56">እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገ​ዴን አቅ​ን​ቶ​ልኝ ሳለ አታ​ዘ​ግ​ዩኝ፤ ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ቱኝ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="57">እነ​ር​ሱም፥ “ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱን እን​ጥ​ራና ከአ​ፍዋ እን​ጠ​ይቅ” አሉ።</verse>
				<verse number="58">ርብ​ቃ​ንም ጠር​ተው፥ “ከዚህ ሰው ጋር ትሄ​ጃ​ለ​ሽን?” አሉ​አት። እር​ስ​ዋም፥ “አዎን እሄ​ዳ​ለሁ” አለች።</verse>
				<verse number="59">እኅ​ታ​ቸ​ው​ንም ርብ​ቃን ሞግ​ዚ​ቷ​ንም ከገ​ን​ዘብ ጋር፥ የአ​ብ​ር​ሃ​ምን ሎሌና ሰዎ​ቹ​ንም አሰ​ና​በ​ቱ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="60">እኅ​ታ​ቸው ርብ​ቃ​ንም መረ​ቁ​አ​ትና፥ “አንቺ እኅ​ታ​ችን፥ እልፍ አእ​ላ​ፋት ሁኚ፤ ዘር​ሽም የጠ​ላት ሀገ​ሮ​ችን ይው​ረስ” አሉ​አት።</verse>
				<verse number="61">ርብ​ቃም ተነ​ሣች፤ ደን​ገ​ጥ​ሮ​ች​ዋም፥ በግ​መ​ሎ​ችዋ ላይ ተቀ​ም​ጠው ከሰ​ው​ዬው ጋር አብ​ረው ሄዱ፤ ሎሌ​ውም ርብ​ቃን ተቀ​ብሎ ሄደ።</verse>
				<verse number="62">ይስ​ሐ​ቅም በዐ​ዘ​ቅተ ራእይ በኩል ወደ ምድረ በዳ ይመ​ለ​ከት ነበር፤ በአ​ዜብ በኩል ባለው ምድር ተቀ​ምጦ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="63">ይስ​ሐ​ቅም በመሸ ጊዜ በልቡ እያ​ሰ​ላ​ሰለ ወደ ሜዳ ወጥቶ ነበር፤ ዓይ​ኖ​ቹ​ንም አቀና፤ እነ​ሆም ግመ​ሎች ሲመጡ አየ።</verse>
				<verse number="64">ርብ​ቃም ዓይ​ኖ​ች​ዋን አቀ​ናች፤ ይስ​ሐ​ቅ​ንም አየች፤ ከግ​መ​ልም ወረ​ደች።</verse>
				<verse number="65">ሎሌ​ው​ንም፥ “ሊቀ​በ​ለን በሜዳ የሚ​መጣ ይህ ሰው ማነው?” አለ​ችው። ሎሌ​ውም፥ “እርሱ ጌታዬ ነው” አላት፤ እር​ስ​ዋም ቀጸ​ላ​ዋን ወስዳ ተከ​ና​ነ​በች።</verse>
				<verse number="66">ሎሌ​ውም ያደ​ረ​ገ​ውን ነገር ሁሉ ለይ​ስ​ሐቅ ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="67">ይስ​ሐ​ቅም ወደ እናቱ ቤት ገባ፤ ርብ​ቃ​ንም ወሰ​ዳት፤ ሚስ​ትም ሆነ​ችው፤ ወደ​ዳት፤ ይስ​ሐ​ቅም ስለ እናቱ ስለ ሣራ ተጽ​ናና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="25">
				<verse number="1">አብ​ር​ሃ​ምም ደግሞ ስምዋ ኬጡራ የተ​ባ​ለች ሚስት አገባ።</verse>
				<verse number="2">እር​ስ​ዋም ዘን​በ​ሪን፥ ዮቃ​ጤ​ንን፥ ሜዳ​ንን፥ ዮብ​ቅን፥ ምድ​ያ​ም​ንና ሴሂን ወለ​ደ​ች​ለት።</verse>
				<verse number="3">ዮቃ​ጤ​ንም ሶቤ​ቅን፥ ቲማ​ን​ንና ድዳ​ንን ወለደ። የድ​ዳ​ንም ልጆች ራጉ​ኤል፥ ንበ​ከዝ፥ እስ​ራ​ኦ​ምና ሎአም ናቸው።</verse>
				<verse number="4">የም​ድ​ያ​ምም ልጆች ጌፌር፥ ዔፋር፥ ሄኖኅ፥ አቢ​ሮ​ንና ቲያ​ሮስ ናቸው። እነ​ዚ​ህም ሁሉ የኬ​ጡራ ልጆች ናቸው።</verse>
				<verse number="5">አብ​ር​ሃ​ምም በሕ​ይ​ወቱ ሳለ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ ለልጁ ለይ​ስ​ሐቅ ሰጠው፤</verse>
				<verse number="6">አብ​ር​ሃ​ምም ለቁ​ባ​ቶቹ ልጆች ሀብ​ትን ሰጣ​ቸው፤ እር​ሱም ገና በሕ​ይ​ወቱ ሳለ ከልጁ ከይ​ስ​ሐቅ ለይቶ ወደ ምሥ​ራቅ ሀገር ሰደ​ዳ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">አብ​ር​ሃ​ምም የኖ​ረ​በት የዕ​ድ​ሜው ዓመ​ታት እነ​ዚህ ናቸው፤ መቶ ሰባ አም​ስት ዓመት ኖረ።</verse>
				<verse number="8">አብ​ር​ሃ​ምም መል​ካም ሽም​ግ​ል​ናን ሸም​ግሎ፥ ዘመ​ኑ​ንም ፈጽሞ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ።</verse>
				<verse number="9">ልጆቹ ይስ​ሐ​ቅና ይስ​ማ​ኤ​ልም በመ​ምሬ ፊት ለፊት ባለው በኬ​ጢ​ያ​ዊው በሰ​ዓር ልጅ በኤ​ፍ​ሮን እርሻ ላይ ባለ ድርብ ክፍል በሆ​ነው ዋሻ ውስጥ ቀበ​ሩት።</verse>
				<verse number="10">ይህም አብ​ር​ሃም ከኬጢ ልጆች የገ​ዛው እርሻ ነው፤ አብ​ር​ሃ​ም​ንና ሚስ​ቱን ሣራን በዚያ ቀበ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">እን​ዲ​ህም ሆነ፥ አብ​ር​ሃ​ምም ከሞተ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን ይስ​ሐ​ቅን ባረ​ከው፤ ይስ​ሐ​ቅም ዐዘ​ቅተ ራእይ ተብሎ በሚ​ጠ​ራው ምንጭ አጠ​ገብ ኖረ።</verse>
				<verse number="12">የሣራ ባሪያ ግብ​ፃ​ዊቱ አጋር ለአ​ብ​ር​ሃም የወ​ለ​ደ​ች​ለት የአ​ብ​ር​ሃም ልጅ የይ​ስ​ማ​ኤል ትው​ልድ ይህ ነው፤</verse>
				<verse number="13">የይ​ስ​ማ​ኤ​ልም የል​ጆቹ ስም በየ​ስ​ማ​ቸ​ውና በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው እን​ዲህ ነው።</verse>
				<verse number="14">የይ​ስ​ማ​ኤል የበ​ኵር ልጁ ናቡ​አት፥ ቄዳር፥ ነብ​ዳ​ኤል፥ መብ​ሳን፥</verse>
				<verse number="15">ማሴሜ፥ ዱማ፥ ማሤን፥ ኩዳን፥ ቴማን፥ ኤያ​ጤር፥ ናፌስ፥ ቄድን።</verse>
				<verse number="16">የይ​ስ​ማ​ኤል ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ስማ​ቸ​ውም በየ​መ​ን​ደ​ራ​ቸ​ውና በየ​ሰ​ፈ​ራ​ቸው ይህ ነው፤ በየ​ወ​ገ​ና​ቸ​ውም ዐሥራ ሁለት አለ​ቆች ናቸው።</verse>
				<verse number="17">እር​ሱም ከኤ​ው​ላጥ አን​ሥቶ በግ​ብፅ ፊት ለፊት እስ​ከ​ም​ት​ገኝ እስከ ሴይር ባለው ሀገር ኖረ፤ ወደ አሦ​ር​ዮ​ንም ደረሰ፤ እን​ዲ​ህም ከወ​ን​ድ​ሞቹ ሁሉ ፊት ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="18">ይስ​ማ​ኤ​ልም የኖ​ረ​በት የዕ​ድ​ሜው ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው ፤ ሸም​ግሎ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ።</verse>
				<verse number="19">የአ​ብ​ር​ሃም ልጅ የይ​ስ​ሐቅ ትው​ል​ድም ይህ ነው፤ አብ​ር​ሃም ይስ​ሐ​ቅን ወለደ፥</verse>
				<verse number="20">ይስ​ሐ​ቅም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ የሶ​ር​ያ​ዊ​ውን የላ​ባን እኅት፥ የሶ​ር​ያ​ዊ​ውን የባ​ቱ​ኤ​ልን ልጅ ርብ​ቃን ከሁ​ለቱ ከሶ​ርያ ወን​ዞች መካ​ከል በወ​ሰ​ዳት ጊዜ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር።</verse>
				<verse number="21">ይስ​ሐ​ቅም ስለ ሚስቱ ርብቃ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመነ፤ መካን ነበ​ረ​ችና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማው፤ ሚስቱ ርብ​ቃም ፀነ​ሰች።</verse>
				<verse number="22">ልጆ​ች​ዋም በሆ​ድዋ ውስጥ ይን​ቀ​ሳ​ቀሱ ነበር ፤ እር​ስ​ዋም፥ “እን​ዲህ እሆን ዘንድ ካለኝ ይህ ለእኔ ምኔ ነው?” አለች። ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትለ​ምን ዘንድ ሄደች።</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አላት፥ “ሁለት ሕዝ​ቦች በማ​ኅ​ፀ​ንሽ አሉ፤ ሁለ​ቱም ሕዝብ ከሆ​ድሽ ይወ​ለ​ዳሉ፤ ሕዝ​ብም ከሕ​ዝብ ይበ​ረ​ታል፤ ታላ​ቁም ለታ​ናሹ ይገ​ዛል።”</verse>
				<verse number="24">የም​ት​ወ​ል​ድ​በ​ትም ወራት ተፈ​ጸመ፤ በማ​ኅ​ፀ​ን​ዋም መንታ ነበሩ።</verse>
				<verse number="25">የበ​ኵር ልጅ​ዋም ወጣ፤ እንደ ጽጌ​ረ​ዳም ቀይ ነበረ፤ ሁለ​ን​ተ​ና​ውም ጠጕ​ራም ነበር፤ ስሙ​ንም ዔሳው ብላ ጠራ​ችው።</verse>
				<verse number="26">ከዚ​ያም በኋላ ወን​ድሙ ወጣ፤ በእ​ጁም የዔ​ሳ​ውን ተረ​ከዝ ይዞ ነበር፤ ስሙ​ንም ያዕ​ቆብ ብላ ጠራ​ችው። ርብቃ ዔሳ​ው​ንና ያዕ​ቆ​ብን በወ​ለ​ደ​ቻ​ቸው ጊዜ ይስ​ሐቅ ስድሳ ዓመት ሆኖት ነበር።</verse>
				<verse number="27">ብላ​ቴ​ኖ​ቹም አደጉ፤ ጐለ​መ​ሱም፤ ዔሳ​ውም አደን የሚ​ያ​ውቅ የበ​ረሃ ሰው ሆነ፤ ያዕ​ቆብ ግን ጭምት ሰው ነበረ፤ በቤ​ትም ይቀ​መጥ ነበር።</verse>
				<verse number="28">ይስ​ሐ​ቅም ዔሳ​ውን ይወድ ነበር፤ እርሱ ከአ​ደ​ነው ይበላ ነበ​ርና። ርብቃ ግን ያዕ​ቆ​ብን ትወድ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="29">ለያ​ዕ​ቆ​ብም የም​ስር ንፍሮ ቀቀ​ለ​ች​ለት፤ ዔሳ​ውም ደክሞ ከበ​ረሃ ገባ፤</verse>
				<verse number="30">ዔሳ​ውም ያዕ​ቆ​ብን፥ “ከም​ስር ንፍ​ሮህ አብ​ላኝ፤ እኔ እጅግ ደክ​ሜ​አ​ለ​ሁና” አለው፤ ስለ​ዚ​ህም ስሙ ኤዶም ተባለ።</verse>
				<verse number="31">ያዕ​ቆ​ብም ዔሳ​ውን፥ “ዛሬ ብኵ​ር​ና​ህን ስጠኝ” አለው።</verse>
				<verse number="32">ዔሳ​ውም፥ “እነሆ፥ እኔ ልሞት ነኝ፤ ይህች ብኵ​ርና ለምኔ ናት?” አለ።</verse>
				<verse number="33">ያዕ​ቆ​ብም፥ “ብኵ​ር​ና​ህን ትሰ​ጠኝ ዘንድ እስኪ ዛሬ ማል​ልኝ” አለው። ዔሳ​ውም ማለ​ለት፤ ብኵ​ር​ና​ው​ንም ለያ​ዕ​ቆብ ሸጠ።</verse>
				<verse number="34">ያዕ​ቆ​ብም ለዔ​ሳው እን​ጀ​ራና የም​ስር ንፍሮ ሰጠው፤ በላ፥ ጠጣ፥ ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ ዔሳ​ውም ብኵ​ር​ና​ውን አቃ​ለ​ላት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="26">
				<verse number="1">በም​ድ​ርም ቀድሞ በአ​ብ​ር​ሃም ዘመን ከሆ​ነው ራብ ሌላ ራብ ሆነ፤ ይስ​ሐ​ቅም ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ንጉሥ ወደ አቤ​ሜ​ሌክ ወደ ጌራራ ሄደ።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተገ​ለ​ጠ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ወደ ግብፅ አት​ው​ረድ፤ እኔ በም​ልህ ምድር ተቀ​መጥ።</verse>
				<verse number="3">በዚ​ህች ምድር ተቀ​መጥ፤ ከአ​ንተ ጋርም እሆ​ና​ለሁ፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለ​ሁም፤ ይህ​ችን ምድር ሁሉ ለአ​ን​ተም፥ ለዘ​ር​ህም እሰ​ጣ​ለ​ሁና፥ ለአ​ባ​ት​ህም ለአ​ብ​ር​ሃም የማ​ል​ሁ​ለ​ትን መሐላ ከአ​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">ዘር​ህ​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ይህ​ች​ንም ምድር ሁሉ ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ፤ የም​ድ​ርም ሕዝ​ቦች ሁሉ በዘ​ርህ ይባ​ረ​ካሉ፤</verse>
				<verse number="5">አባ​ትህ አብ​ር​ሃም ቃሌን ሰም​ቶ​አ​ልና፤ ትእ​ዛ​ዜ​ንና ፍር​ዴን፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንና ሕጌ​ንም ጠብ​ቆ​አ​ልና።”</verse>
				<verse number="6">ይስ​ሐ​ቅም በጌ​ራራ ተቀ​መጠ። የዚ​ያም ስፍራ ሰዎች ስለ ሚስቱ ስለ ርብቃ ጠየ​ቁት፤ እር​ሱም፥ “እኅቴ ናት” አላ​ቸው፤</verse>
				<verse number="7">የዚህ ስፍራ ሰዎች ለር​ብቃ ሲሉ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ሉኝ ብሎ ሚስቴ ናት ማለ​ትን ፈር​ቶ​አ​ልና፤ እር​ስ​ዋም ውብ ነበ​ረ​ችና።</verse>
				<verse number="8">በዚ​ያም ብዙ ቀን ተቀ​መጠ። የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ንጉሥ አቤ​ሜ​ሌ​ክም በመ​ስ​ኮት ሆኖ በተ​መ​ለ​ከተ ጊዜ ይስ​ሐ​ቅን ከሚ​ስቱ ከር​ብቃ ጋር ሲጫ​ወት አየው።</verse>
				<verse number="9">አቤ​ሜ​ሌ​ክም ይስ​ሐ​ቅን ጠራ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ ሚስ​ትህ ናት፤ እን​ዴ​ትስ እር​ስ​ዋን፦ ‘እኅቴ ናት’ አልህ?” ይስ​ሐ​ቅም፥ “በእ​ር​ስዋ ምክ​ን​ያት እን​ዳ​ል​ሞት ብዬ ነው” አለው።</verse>
				<verse number="10">አቤ​ሜ​ሌ​ክም አለ፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው? ከሕ​ዝቡ አንዱ ባለ​ማ​ወቅ ከሚ​ስ​ትህ ጋር ሊተኛ ጥቂት በቀ​ረው ነበር፤ ኀጢ​አ​ት​ንም ልታ​መ​ጣ​ብን ነበር።”</verse>
				<verse number="11">አቤ​ሜ​ሌ​ክም ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ “ይህን ሰው፥ ሚስ​ቱ​ንም የሚ​ነካ ፍርዱ ክፉ ሞት ነው” ብሎ አዘዘ።</verse>
				<verse number="12">ይስ​ሐ​ቅም በዚ​ያች ምድር ዘርን ዘራ፤ በዚ​ያች ዓመ​ትም መቶ እጥፍ ገብስ አገኘ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባረ​ከው።</verse>
				<verse number="13">ከፍ ከፍም አለ፤ እጅ​ግም ታላቅ እስ​ኪ​ሆን ድረስ እየ​ጨ​መረ ይበዛ ነበር፤</verse>
				<verse number="14">ወን​ዶ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ችን፥ ብዙ በጎ​ች​ንና ላሞ​ችን፥ የእ​ርሻ መሬ​ት​ንም ገዛ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሰዎ​ችም ቀኑ​በት።</verse>
				<verse number="15">በአ​ባቱ በአ​ብ​ር​ሃም ዘመን የአ​ባቱ ሎሌ​ዎች የማ​ሱ​አ​ቸ​ውን ጕድ​ጓ​ዶች ሁሉ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሰዎች ደፈ​ኑ​አ​ቸው፤ አፈ​ር​ንም ሞሉ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">አቤ​ሜ​ሌ​ክም ይስ​ሐ​ቅን፥ “ከእኛ ተለ​ይ​ተህ ሂድ፤ ከእኛ ይልቅ እጅግ በር​ት​ተ​ሃ​ልና” አለው።</verse>
				<verse number="17">ይስ​ሐ​ቅም ከዚያ ሄደ፤ በጌ​ራ​ራም ሸለቆ ሰፈረ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="18">ይስ​ሐ​ቅም የአ​ባቱ የአ​ብ​ር​ሃም አገ​ል​ጋ​ዮች ቈፍ​ረ​ዋ​ቸው የነ​በ​ሩ​ትን የውኃ ጕድ​ጓ​ዶች ደግሞ አስ​ቈ​ፈረ፤ አባቱ አብ​ር​ሃም ከሞተ በኋላ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሰዎች ደፍ​ነ​ዋ​ቸው ነበ​ርና፤ አባ​ቱም አብ​ር​ሃም ይጠ​ራ​ቸው በነ​በ​ረው ስም ጠራ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">የይ​ስ​ሐቅ ሎሌ​ዎ​ችም በጌ​ራራ ሸለቆ ውስጥ ጕድ​ጓድ ቈፈሩ፤ በዚ​ያም ጣፋጭ የውኃ ምንጭ አገኙ።</verse>
				<verse number="20">የጌ​ራራ እረ​ኞች ከይ​ስ​ሐቅ እረ​ኞች ጋር፥ “ውኃው የእኛ ነው” ሲሉ ተጣሉ፤ የዚ​ያ​ች​ንም ጕድ​ጓድ ስም “ዐዘ​ቅተ ዐመፃ” ብሎ ጠራት፤ እነ​ርሱ በድ​ለ​ው​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="21">ይስ​ሐ​ቅም ከዚያ ሄደ በዚ​ያም ሌላ ጕድ​ጓድ ማሰ፥ ስለ እር​ስ​ዋም ደግሞ ተጣ​ሉት፤ ስም​ዋ​ንም “ጽልእ” ብሎ ጠራት።</verse>
				<verse number="22">ከዚ​ያም እልፍ ብሎ ሌላ ጕድ​ጓድ ቈፈረ፤ ስለ እር​ስ​ዋም አል​ተ​ጣ​ሉ​ትም፤ ስም​ዋ​ንም “መር​ኅብ” ብሎ ጠራት፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሰ​ፋ​ልን፤ በም​ድ​ርም አበ​ዛን።”</verse>
				<verse number="23">ከዚ​ያም ወደ ዐዘ​ቅተ መሐላ ሄደ።</verse>
				<verse number="24">በዚ​ያ​ችም ሌሊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገ​ለ​ጠ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እኔ የአ​ባ​ትህ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ ነኝ፤ አት​ፍራ፤ እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፤ ስለ አባ​ትህ ስለ አብ​ር​ሃም ዘር​ህን አበ​ዛ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="25">በዚ​ያም ለአ​ም​ላኩ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያን ሠራ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ጠራ፤ በዚ​ያም ድን​ኳን ተከለ፤ የይ​ስ​ሐ​ቅም ሎሌ​ዎች በዚያ ጕድ​ጓድ ማሱ።</verse>
				<verse number="26">አቤ​ሜ​ሌ​ክና ሚዜው አኮ​ዘት፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ ፋኮል ከጌ​ራራ ወደ እርሱ ሄዱ።</verse>
				<verse number="27">ይስ​ሐ​ቅም፥ “ለምን ወደ እኔ መጣ​ችሁ? እና​ንተ ጠል​ታ​ች​ሁ​ኛል፤ ከእ​ና​ን​ተም ለይ​ታ​ችሁ አሳ​ድ​ዳ​ች​ሁ​ኛ​ልና” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="28">እነ​ር​ሱም አሉት፥ “እኛ የጠ​ላ​ንህ አይ​ደ​ለም፤ በመ​ል​ካም አኑ​ረን፥ በመ​ል​ካም አሰ​ና​በ​ት​ንህ እንጂ፥ አሁ​ንም አንተ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ ነህ።</verse>
				<verse number="29">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ንተ ጋር እንደ አለ በአ​የን ጊዜ በአ​ን​ተና በእኛ መካ​ከል መሐላ ይሁን፤ አንተ በእኛ ላይ ክፉ እን​ዳ​ታ​ደ​ርግ፤ እኛም በአ​ንተ ላይ ክፉ እን​ዳ​ና​ደ​ርግ እን​ማ​ማ​ላ​ለን።”</verse>
				<verse number="30">ይስ​ሐ​ቅም ማዕድ አቀ​ረ​በ​ላ​ቸው፤ በሉም፤ ጠጡም።</verse>
				<verse number="31">ማል​ደ​ውም ተነሡ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተማ​ማሉ፤ ይስ​ሐ​ቅም አሰ​ና​በ​ታ​ቸው፤ ከእ​ር​ሱም በደ​ኅና ሄዱ።</verse>
				<verse number="32">በዚ​ያም ቀን የይ​ስ​ሐቅ ሎሌ​ዎች መጡ፤ ስለ ቈፈ​ሩ​አ​ትም ጕድ​ጓድ፥ ውኃ አገ​ኘን ብለው ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="33">ስም​ዋ​ንም “መሐላ” ብሎ ጠራት፤ ስለ​ዚ​ህም የከ​ተ​ማ​ዪቱ ስም እስከ ዛሬ ድረስ “ዐዘ​ቅተ መሐላ” ይባ​ላል።</verse>
				<verse number="34">ዔሳ​ውም አርባ ዓመት ሲሆ​ነው የኬ​ጢ​ያ​ዊው የብ​ኤ​ልን ልጅ ዮዲ​ትን፥ የኬ​ጢ​ያ​ዊው የኤ​ሎ​ንን ልጅ ቤሴ​ሞ​ት​ንም ሚስ​ቶች አድ​ርጎ አገባ፤</verse>
				<verse number="35">እነ​ር​ሱም ይስ​ሐ​ቅ​ንና ርብ​ቃን ያሳ​ዝኑ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="27">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፦ ይስ​ሐቅ ፈጽሞ ከአ​ረጀ በኋላ ዐይ​ኖቹ ፈዝ​ዘው አያ​ይም ነበር። ታላ​ቁን ልጁን ዔሳ​ው​ንም ጠርቶ፥ “ልጄ ሆይ፥” አለው፤ እር​ሱም፥ “እነሆ አለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="2">እር​ሱም አለው፥ “እነሆ እኔ አረ​ጀሁ፤ የም​ሞ​ት​በ​ትን ቀን አላ​ው​ቅም።</verse>
				<verse number="3">አሁ​ንም ማደ​ኛ​ህን የፍ​ላ​ጻ​ህን አፎ​ትና ቀስ​ት​ህን ውሰድ፤ ወደ ምድረ በዳም ውጣ፤ አደ​ንም አድ​ን​ልኝ፤</verse>
				<verse number="4">ሳል​ሞ​ትም ነፍሴ እን​ድ​ት​ባ​ር​ክህ እኔ እን​ደ​ም​ወ​ደው መብል አዘ​ጋ​ጅ​ተህ እበላ ዘንድ አም​ጣ​ልኝ።”</verse>
				<verse number="5">ርብ​ቃም ይስ​ሐቅ ለልጁ ለዔ​ሳው እን​ደ​ዚህ ሲነ​ግር ትሰማ ነበር። ዔሳ​ውም ለአ​ባቱ አደን ሊያ​ድን ወደ ምድረ በዳ ሄደ።</verse>
				<verse number="6">ርብ​ቃም ታናሹ ልጅ​ዋን ያዕ​ቆ​ብን እን​ዲህ አለ​ችው፦</verse>
				<verse number="7">“እነሆ፥ አባ​ትህ ለወ​ን​ድ​ምህ ለዔ​ሳው፦ እን​ዲህ ሲለው ሰማሁ፤ ‘ሂድና ከአ​ደ​ን​ኸው መብል አዘ​ጋ​ጅ​ተህ አም​ጣ​ልኝ፤ ሳል​ሞ​ትም በልች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ልባ​ር​ክህ።’</verse>
				<verse number="8">አሁ​ንም ልጄ ሆይ፥ እኔ እን​ደ​ማ​ዝ​ዝህ ስማኝ፤</verse>
				<verse number="9">ወደ በጎ​ቻ​ችን ሄደህ ሁለት መል​ካም ጠቦ​ቶች አም​ጣ​ልኝ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ለአ​ባ​ትህ እን​ደ​ሚ​ወ​ደው መብል አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="10">ለአ​ባ​ት​ህም ሳይ​ሞት እን​ዲ​ባ​ር​ክህ፥ ይበላ ዘንድ ትወ​ስ​ድ​ለ​ታ​ለህ።”</verse>
				<verse number="11">ያዕ​ቆ​ብም እና​ቱን ርብ​ቃን፥ “እነሆ ዔሳው ወን​ድሜ ጠጕ​ራም ሰው ነው፥ እኔ ግን ለስ​ላሳ ነኝ፤</verse>
				<verse number="12">ምና​ል​ባት አባቴ ቢዳ​ስ​ሰኝ በፊቱ እን​ደ​ም​ን​ቀው እሆ​ና​ለሁ፤ መር​ገ​ምን በላዬ አመ​ጣ​ለሁ፤ በረ​ከ​ት​ንም አይ​ደ​ለም።”</verse>
				<verse number="13">እና​ቱም አለ​ችው፥ “ልጄ ሆይ፥ መር​ገ​ምህ በእኔ ላይ ይሁን፥ ቃሌን ብቻ ስማኝ፤ ሂድና ያል​ሁ​ህን አም​ጣ​ልኝ።”</verse>
				<verse number="14">ሄዶም አመጣ፤ ለእ​ና​ቱም ሰጣት፤ እና​ቱም መብ​ልን አባቱ እን​ደ​ሚ​ወ​ድ​ደው አደ​ረ​ገች።</verse>
				<verse number="15">ርብ​ቃም ከእ​ር​ስዋ ዘንድ በቤት የነ​በ​ረ​ውን የታ​ላ​ቁን ልጅ​ዋን የዔ​ሳ​ውን መል​ካ​ሙን ልብስ አመ​ጣች፤ ለታ​ናሹ ልጅዋ ለያ​ዕ​ቆ​ብም አለ​በ​ሰ​ችው፤</verse>
				<verse number="16">የጠ​ቦ​ቶ​ች​ንም ለምድ በእ​ጆ​ቹና በለ​ስ​ላ​ሳው አን​ገቱ ላይ አደ​ረ​ገች፤</verse>
				<verse number="17">ያን የሠ​ራ​ች​ውን መብ​ልና እን​ጀ​ራ​ውን ለል​ጅዋ ለያ​ዕ​ቆብ በእጁ ሰጠ​ችው።</verse>
				<verse number="18">ወደ አባ​ቱም አግ​ብቶ፥ “አባቴ ሆይ፥” አለው፦ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ፤ ልጄ ሆይ፥ አንተ ማን ነህ?” አለ።</verse>
				<verse number="19">ያዕ​ቆ​ብም አባ​ቱን አለው፥ “የበ​ኵር ልጅህ እኔ ዔሳው ነኝ፤ እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኸኝ አደ​ረ​ግሁ፤ ነፍ​ስህ ትባ​ር​ከኝ ዘንድ ቀና ብለህ ተቀ​መጥ፤ ካደ​ን​ሁ​ትም ብላ።”</verse>
				<verse number="20">ይስ​ሐ​ቅም ልጁን፥ “ልጄ ሆይ፥ ፈጥ​ነህ ያገ​ኘ​ኸው ይህ ምን​ድን ነው?” አለው። እር​ሱም፥ “አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊቴ የሰ​ጠኝ ነው” አለ።</verse>
				<verse number="21">ይስ​ሐ​ቅም ያዕ​ቆ​ብን፥ “ልጄ ሆይ፥ አንተ ልጄ ዔሳው እንደ ሆንህ ወይም እን​ዳ​ል​ሆ​ንህ ቅረ​በ​ኝና ልዳ​ስ​ስህ” አለው።</verse>
				<verse number="22">ያዕ​ቆ​ብም ወደ አባቱ ወደ ይስ​ሐቅ ቀረበ፤ ዳሰ​ሰ​ውም፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ይህ ድምፅ የያ​ዕ​ቆብ ድምፅ ነው፥ እጆች ግን የዔ​ሳው እጆች ናቸው” አለው።</verse>
				<verse number="23">እር​ሱም አላ​ወ​ቀ​ውም ነበር፤ እጆቹ እንደ ወን​ድሙ እንደ ዔሳው እጆች ጠጕ​ራም ነበ​ሩና፤ ይስ​ሐ​ቅም ባረ​ከው ።</verse>
				<verse number="24">አለ​ውም፥ “አንተ ልጄ ዔሳው ነህን?” እር​ሱም፥ “እኔ ነኝ” አለ።</verse>
				<verse number="25">እር​ሱም፥ “ልጄ ሆይ፥ ከአ​ደ​ን​ኸው እን​ድ​በ​ላና ነፍሴ እን​ድ​ት​ባ​ር​ክህ አም​ጣ​ልኝ” አለው። አቀ​ረ​በ​ለ​ትም፤ በላም፤ ወይ​ንም አመ​ጣ​ለት፤ እር​ሱም ጠጣ።</verse>
				<verse number="26">አባቱ ይስ​ሐ​ቅም፥ “ልጄ ሆይ፥ ወደ እኔ ቅረብ፤ ሳመ​ኝም” አለው።</verse>
				<verse number="27">ወደ እር​ሱም ቀረበ፤ ሳመ​ውም፤ የል​ብ​ሱ​ንም ሽታ አሸ​ተተ፤ ባረ​ከ​ውም፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “የልጄ ሽታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ባረ​ከው የእ​ርሻ ሽታ ነው፤</verse>
				<verse number="28">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሰ​ማይ ጠል፥ ከም​ድ​ርም ስብ፥ የእ​ህ​ል​ንም፥ የወ​ይ​ን​ንም፥ የዘ​ይ​ት​ንም ብዛት ይስ​ጥህ፤</verse>
				<verse number="29">አሕ​ዛብ ይገ​ዙ​ልህ፤ አለ​ቆ​ችም ይስ​ገ​ዱ​ልህ፤ ለወ​ን​ድ​ምህ ጌታ ሁን፤ የአ​ባ​ት​ህም ልጆች ይስ​ገ​ዱ​ልህ፤ የሚ​ረ​ግ​ምህ እርሱ ርጉም ይሁን፤ የሚ​ባ​ር​ክ​ህም ቡሩክ ይሁን።”</verse>
				<verse number="30">ይስ​ሐ​ቅም ያዕ​ቆ​ብን ባርኮ ከፈ​ጸመ በኋላ፥ ያዕ​ቆብ ከአ​ባቱ ከይ​ስ​ሐቅ ፊት ወጣ፥ ወን​ድሙ ዔሳ​ውም ከአ​ደኑ መጣ፤</verse>
				<verse number="31">እር​ሱም ደግሞ መብል አዘ​ጋጀ፥ ለአ​ባ​ቱም አመጣ፤ አባ​ቱ​ንም፥ “አባቴ ተነሥ፤ ነፍ​ስ​ህም ትባ​ር​ከኝ ዘንድ ልጅህ ከአ​ደ​ነው ብላ” አለው።</verse>
				<verse number="32">አባቱ ይስ​ሐ​ቅም፥ “አንተ ማን ነህ?” አለው። እር​ሱም፥ “እኔ የበ​ኵር ልጅህ ዔሳው ነኝ” አለው።</verse>
				<verse number="33">ይስ​ሐ​ቅም እጅግ ደነ​ገጠ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ያደ​ነ​ውን አደን ወደ እኔ ያመ​ጣው ማን ነው? አንተ ሳት​መ​ጣም ከሁሉ በላሁ፤ ባረ​ክ​ሁ​ትም፤ እር​ሱም የተ​ባ​ረከ ነው።”</verse>
				<verse number="34">ዔሳ​ውም የአ​ባ​ቱን ቃል በሰማ ጊዜ ታላቅ፥ እጅ​ግም መራራ ጩኸት ጮኸ፤ አባ​ቱ​ንም፥ “አባቴ ሆይ፥ እኔ​ንም ደግሞ ባር​ከኝ” አለው።</verse>
				<verse number="35">ይስ​ሐ​ቅም ዔሳ​ውን አለው፥ “ወን​ድ​ምህ በተ​ን​ኰል መጥቶ በረ​ከ​ት​ህን ወሰ​ደ​ብህ።”</verse>
				<verse number="36">ዔሳ​ውም አለ፥ “በእ​ው​ነት ስሙ ያዕ​ቆብ ተባለ፤ ሁለት ጊዜ አሰ​ና​ክ​ሎ​ኛ​ልና፤ መጀ​መ​ሪያ ብኵ​ር​ና​ዬን ወሰደ፤ አሁ​ንም እነሆ በረ​ከ​ቴን ወሰደ።” ዔሳ​ውም አባ​ቱን አለው፥ “ደግ​ሞም አባቴ ሆይ፥ ለእኔ በረ​ከ​ትን አላ​ስ​ቀ​ረ​ህ​ል​ኝ​ምን?”</verse>
				<verse number="37">ይስ​ሐ​ቅም መለሰ ዔሳ​ው​ንም አለው፥ “እነሆ ጌታህ አደ​ረ​ግ​ሁት፤ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ሁሉ ለእ​ርሱ ተገ​ዦች አደ​ረ​ግ​ኋ​ቸው፤ እህ​ሉን፥ ወይ​ኑ​ንና ዘይ​ቱ​ንም አበ​ዛ​ሁ​ለት፤ ለአ​ንተ ግን፥ ልጄ ሆይ፥ ምን ላድ​ር​ግ​ልህ?”</verse>
				<verse number="38">ዔሳ​ውም አባ​ቱን ይስ​ሐ​ቅን አለው፥ “አባቴ ሆይ፥ በረ​ከ​ትህ አን​ዲት ብቻ ናትን? አባቴ ሆይ፥ እኔ​ንም ደግሞ ባር​ከኝ።” ዔሳ​ውም ጮሆ አለ​ቀሰ።</verse>
				<verse number="39">አባቱ ይስ​ሐ​ቅም መለሰ፤ አለ​ውም፥ “እነሆ መኖ​ሪ​ያህ ከላይ ከሰ​ማይ ጠል፥ ከም​ድ​ርም ስብ ይሁን፤</verse>
				<verse number="40">በሰ​ይ​ፍ​ህም ትኖ​ራ​ለህ፤ ለወ​ን​ድ​ም​ህም ትገ​ዛ​ለህ፤ ነገር ግን ቀን​በ​ሩን ከአ​ን​ገ​ትህ ልት​ጥል ብት​ወ​ድድ ከእ​ርሱ ጋር ተስ​ማማ።”</verse>
				<verse number="41">ዔሳ​ውም አባቱ ስለ ባረ​ከው በያ​ዕ​ቆብ ቂም ያዘ​በት፤ ዔሳ​ውም በልቡ አለ፥ “ለአ​ባቴ የል​ቅሶ ቀን ትቅ​ረብ፤ ወን​ድ​ሜን ያዕ​ቆ​ብን እገ​ድ​ለ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="42">ለር​ብ​ቃም ታላቁ ልጅዋ ዔሳው ያለው ተነ​ገ​ራት፤ ታና​ሹን ልጅ​ዋን ያዕ​ቆ​ብ​ንም ልካ ጠራ​ችው፤ አለ​ች​ውም፥ “እነሆ ወን​ድ​ምህ ዔሳው ያድ​ድ​ን​ሃል፤ ሊገ​ድ​ል​ህም ይፈ​ል​ጋል።</verse>
				<verse number="43">አሁ​ንም ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ስማ፤ ተነ​ሣና በሶ​ርያ ወን​ዞች መካ​ከል ወደ ካራን ምድር ወደ ወን​ድሜ ወደ ላባ ሂድ፤</verse>
				<verse number="44">በእ​ር​ሱም ዘንድ ጥቂት ቀን ተቀ​መጥ። የወ​ን​ድ​ምህ ቍጣ ከአ​ንተ እስ​ኪ​በ​ርድ ድረስ፥</verse>
				<verse number="45">ያደ​ረ​ግ​ህ​በ​ት​ንም እስ​ኪ​ረ​ሳው ድረስ፤ በአ​ንድ ቀን ሁለ​ታ​ች​ሁን እን​ዳ​ላጣ፥ ከዚ​ያም ልኬ አመ​ጣ​ሃ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="46">ርብ​ቃም ይስ​ሐ​ቅን አለ​ችው፥ “ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተ​ነሣ ሕይ​ወ​ቴን ጠላ​ሁት፤ ያዕ​ቆብ ከዚህ ሀገር ሴቶች ልጆች ሚስ​ትን የሚ​ያ​ገባ ከሆነ በሕ​ይ​ወት መኖር ለእኔ ምኔ ነው?”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="28">
				<verse number="1">ይስ​ሐ​ቅም ያዕ​ቆ​ብን ጠራው፤ ባረ​ከ​ውም፥ እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዘው፥ “ከከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ሴቶች ልጆች ሚስ​ትን አታ​ግባ፤</verse>
				<verse number="2">ተነ​ሣና ወደ እና​ትህ አባት ወደ ባቱ​ኤል ቤት ወደ ሁለቱ ወን​ዞች መካ​ከል ሂድ፤ ከዚ​ያም ከእ​ና​ትህ ከር​ብቃ ወን​ድም ከላባ ሴቶች ልጆች ሚስ​ትን አግባ።</verse>
				<verse number="3">አም​ላኬ ከአ​ንተ ጋር ይሂድ፤ ከፍ ከፍም ያድ​ር​ግህ፤ ይባ​ር​ክህ፤ ያብ​ዛህ፤ ብዙ ሕዝ​ብም ሁን ፤</verse>
				<verse number="4">ስደ​ተኛ ሆነህ የተ​ቀ​መ​ጥ​ህ​ባ​ትን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ር​ሃም የሰ​ጣ​ትን ምድር ትወ​ርስ ዘንድ የአ​ባ​ቴን የአ​ብ​ር​ሃ​ምን በረ​ከት ለአ​ንተ ይስ​ጥህ፤ ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ርህ።”</verse>
				<verse number="5">ይስ​ሐ​ቅም ልጁ ያዕ​ቆ​ብን ላከው፤ እር​ሱም የያ​ዕ​ቆ​ብና የዔ​ሳው እናት የር​ብቃ ወን​ድም የሚ​ሆን የሶ​ር​ያ​ዊው ባቱ​ኤል ልጅ ላባ ወዳ​ለ​በት ወደ ሁለቱ ወን​ዞች መካ​ከል ሄደ።</verse>
				<verse number="6">ዔሳ​ውም ይስ​ሐቅ ያዕ​ቆ​ብን እንደ ባረ​ከው በአየ ጊዜ ከዚ​ያም ሚስ​ትን ያገባ ዘንድ ወደ ሁለቱ የሶ​ርያ ወን​ዞች መካ​ከል እንደ ላከው፥ በባ​ረ​ከ​ውም ጊዜ፥ “ከከ​ነ​ዓን ሴቶች ልጆች ሚስ​ትን አታ​ግባ” ብሎ እን​ዳ​ዘ​ዘው፥</verse>
				<verse number="7">ያዕ​ቆ​ብም የአ​ባ​ቱ​ንና የእ​ና​ቱን ቃል ሰምቶ ወደ ሁለቱ ወን​ዞች መካ​ከል እንደ ሄደ፥</verse>
				<verse number="8">የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ሴቶች ልጆች በአ​ባቱ በይ​ስ​ሐቅ ፊት የተ​ጠሉ እንደ ሆኑ ዔሳው በአየ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="9">ዔሳው ወደ ይስ​ማ​ኤል ሄደ፤ ቤሴ​ሞ​ት​ንም በፊት ካሉ ሚስ​ቶቹ ጋር ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ወሰ​ዳት፤ እር​ስ​ዋም የና​ኮር ወን​ድም የአ​ብ​ር​ሃም ልጅ የሆ​ነው የይ​ስ​ማ​ኤል ልጅና የና​ቡ​ዓት እኅት ናት።</verse>
				<verse number="10">ያዕ​ቆ​ብም ከአ​ዘ​ቅተ መሐላ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ።</verse>
				<verse number="11">ወደ አንድ ስፍ​ራም ደረሰ፤ ፀሐ​ይም ጠልቃ ነበ​ርና በዚያ አደረ፤ ከዚ​ያም ስፍራ ድን​ጋ​ዮች አንድ ድን​ጋይ አነሣ፤ ከራ​ሱም በታች ተን​ተ​ርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ።</verse>
				<verse number="12">ሕል​ምም አለመ፤ እነ​ሆም መሰ​ላል በም​ድር ላይ ተተ​ክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነ​ሆም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ይወ​ጡ​በ​ትና ይወ​ር​ዱ​በት ነበር።</verse>
				<verse number="13">እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላዩ ቆሞ​በት ነበር፥ እን​ዲ​ህም አለ፥ “የአ​ባ​ትህ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ አት​ፍራ፥ ይህ​ችን አንተ የተ​ኛ​ህ​ባ​ትን ምድር ለአ​ን​ተም ለዘ​ር​ህም እሰ​ጣ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="14">ዘር​ህም እንደ ባሕር አሸዋ ይሆ​ናል፤ እስከ ባሕ​ርና እስከ አዜብ እስከ መስ​ዕና እስከ ምሥ​ራቅ ይበ​ዛል፤ ይሞ​ላ​ልም፤ የም​ድ​ርም ሕዝ​ቦች ሁሉ በአ​ንተ፥ በዘ​ር​ህም ይባ​ረ​ካሉ።</verse>
				<verse number="15">እነ​ሆም፥ እኔ ከአ​ንተ ጋር እሄ​ዳ​ለሁ፤ በም​ት​ሄ​ድ​በ​ትም መን​ገድ ሁሉ እጠ​ብ​ቅ​ሃ​ለሁ፤ ወደ​ዚ​ያ​ችም ምድር እመ​ል​ስ​ሃ​ለሁ፤ የነ​ገ​ር​ሁ​ህን ሁሉ እስ​ካ​ደ​ር​ግ​ልህ ድረስ አል​ተ​ው​ህ​ምና።”</verse>
				<verse number="16">ያዕ​ቆ​ብም ከእ​ን​ቅ​ልፉ ተነ​ሥቶ፥ “በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ስፍራ አለ፤ እኔ አላ​ወ​ቅ​ሁም ነበር” አለ።</verse>
				<verse number="17">ፈራ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህ ስፍራ እን​ዴት ያስ​ፈራ፤ ይህ ስፍራ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይ​ደ​ለም፤ ይህ​ችም የሰ​ማይ ደጅ ናት።”</verse>
				<verse number="18">ያዕ​ቆ​ብም ማልዶ ተነሣ፤ ተን​ተ​ር​ሷት የነ​በ​ረ​ች​ው​ንም ድን​ጋይ ወስዶ ሐው​ልት አድ​ርጎ አቆ​ማት፥ በላ​ይ​ዋም ዘይ​ትን አፈ​ሰ​ሰ​ባት።</verse>
				<verse number="19">ያዕ​ቆ​ብም ያን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው፤ አስ​ቀ​ድሞ ግን የዚያ ከተማ ስም ሎዛ ነበረ።</verse>
				<verse number="20">ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲህ ብሎ ስእ​ለት ተሳለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በም​ሄ​ድ​ባ​ትም በዚች መን​ገድ ቢጠ​ብ​ቀኝ፥ የም​በ​ላ​ው​ንም እን​ጀራ፥ የም​ለ​ብ​ሰ​ው​ንም ልብስ ቢሰ​ጠኝ፥</verse>
				<verse number="21">ወደ አባ​ቴም ቤት በጤና ቢመ​ል​ሰኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኬ ይሆ​ን​ል​ኛል፤</verse>
				<verse number="22">ለሐ​ው​ልት ያቆ​ም​ኋት ይህ​ችም ድን​ጋይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ትሆ​ን​ል​ኛ​ለች፤ ከሰ​ጠ​ኸ​ኝም ሁሉ ለአ​ንተ ከዐ​ሥር እጅ አን​ዱን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="29">
				<verse number="1">ያዕ​ቆ​ብም በማ​ለዳ ተነ​ሥቶ የያ​ዕ​ቆ​ብና የዔ​ሳው እናት የር​ብቃ ወን​ድም የሶ​ርያ ሰው የባ​ቱ​ኤል ልጅ ወደ​ሚ​ሆን ወደ ላባ ሄደ።</verse>
				<verse number="2">በተ​መ​ለ​ከ​ተም ጊዜ በሜ​ዳው እነሆ ጕድ​ጓ​ድን አየ፤ በዚ​ያም ሦስት የበ​ጎች መን​ጎች በላዩ ተመ​ስ​ገው ነበር፤ ከዚ​ያች ጕድ​ጓድ በጎ​ቹን ያጠጡ ነበ​ርና፤ በጕ​ድ​ጓ​ድ​ዋም አፍ ታላቅ ድን​ጋይ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="3">መን​ጎ​ችም ሁሉ ከዚያ በተ​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ እረ​ኞች ድን​ጋ​ይ​ዋን ከጕ​ድ​ጓዱ አፍ ገለል አድ​ር​ገው በጎ​ቹን ያጠጡ ነበር፤ ድን​ጋ​ይ​ዋ​ንም ወደ ስፍ​ራው መል​ሰው በጕ​ድ​ጓዱ አፍ እን​ደ​ገና ይገ​ጥ​ሙት ነበር።</verse>
				<verse number="4">ያዕ​ቆ​ብም፥ “ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እና​ንት ከወ​ዴት ናችሁ?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">እነ​ር​ሱም፥ “እኛ ከካ​ራን ነን” አሉት። “የና​ኮ​ርን ልጅ ላባን ታው​ቁ​ታ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “እና​ው​ቀ​ዋ​ለን” አሉት።</verse>
				<verse number="6">“እርሱ ደኅና ነውን?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “አዎ ደኅና ነው፤ አሁ​ንም ልጁ ራሔል የአ​ባ​ቷን በጎች ይዛ ትመ​ጣ​ለች” አሉት።</verse>
				<verse number="7">እር​ሱም፥ “ቀኑ ገና ቀትር ነው፥ ከብ​ቶቹ የሚ​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት ሰዓ​ቱም ገና አል​ደ​ረ​ሰም፤ አሁ​ንም በጎ​ቹን አጠ​ጡና ሄዳ​ችሁ አሰ​ማ​ሩ​አ​ቸው” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">እነ​ር​ሱም አሉ፥ “እረ​ኞች ሁሉ ካል​ተ​ሰ​በ​ሰ​ቡና ድን​ጋ​ዪ​ቱን ከጕ​ድ​ጓዱ አፍ ካላ​ነ​ሡ​አት በቀር አን​ች​ልም፤ ከዚ​ያም በኋላ በጎ​ቹን እና​ጠ​ጣ​ለን።”</verse>
				<verse number="9">እር​ሱም ገና ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሲነ​ጋ​ገር እነሆ፥ የላባ ልጅ ራሔል የአ​ባ​ት​ዋን በጎች ይዛ ደረ​ሰች፤ እር​ስዋ የአ​ባ​ቷን በጎች ትጠ​ብቅ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="10">ያዕ​ቆ​ብም የእ​ና​ቱን ወን​ድም የላ​ባን ልጅ ራሔ​ል​ንና የአ​ጎ​ቱን የላ​ባን በጎች በአየ ጊዜ ቀረበ፤ ከጕ​ድ​ጓ​ዱም አፍ ድን​ጋ​ዩን አነሣ፤ የአ​ጎ​ቱን የላ​ባን በጎ​ችም አጠጣ።</verse>
				<verse number="11">ያዕ​ቆ​ብም ራሔ​ልን ሳማት፤ ቃሉ​ንም ከፍ አድ​ርጎ አለ​ቀሰ።</verse>
				<verse number="12">ያዕ​ቆ​ብም የአ​ባቷ ዘመ​ድና የር​ብቃ ልጅ መሆ​ኑን ለራ​ሔል አስ​ታ​ወ​ቃት፤ እር​ስ​ዋም ሮጣ ሄዳ ለአ​ባቷ ይህን ነገር ነገ​ረ​ችው።</verse>
				<verse number="13">ላባም የእ​ኅ​ቱን የር​ብ​ቃን ልጅ የያ​ዕ​ቆ​ብን ስም በሰማ ጊዜ ሊቀ​በ​ለው ሮጠ፥ አቅ​ፎም ሳመው፥ ወደ ቤቱም አገ​ባው። ነገ​ሩ​ንም ሁሉ ለላባ ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="14">ላባም ያዕ​ቆ​ብን፥ “በእ​ው​ነት አንተ አጥ​ንቴ ሥጋ​ዬም ነህ፤ ከእኔ ጋር ተቀ​መጥ” አለው። አንድ ወር የሚ​ያ​ህ​ልም ከእ​ርሱ ጋር ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="15">ላባም ያዕ​ቆ​ብን፥ “ወን​ድሜ ስለ​ሆ​ንህ በከ​ንቱ አታ​ገ​ለ​ግ​ለ​ኝም ደመ​ወ​ዝህ ምን​ድን ነው? ንገ​ረኝ” አለው</verse>
				<verse number="16">ለላ​ባም ሁለት ሴቶች ልጆች ነበ​ሩት፤ የታ​ላ​ቂቱ ስም ልያ የታ​ና​ሺ​ቱም ስም ራሔል ነበረ።</verse>
				<verse number="17">ልያም ዓይነ ልም ነበ​ረች፤ ራሔል ግን መልከ መል​ካም ነበ​ረች፥ ፊቷም ውብ ነበረ።</verse>
				<verse number="18">ያዕ​ቆ​ብም ራሔ​ልን ወደ​ዳት፤ ያዕ​ቆ​ብም ላባን እን​ዲህ አለው፥ “ስለ ታና​ሺቱ ልጅህ ስለ ራሔል ሰባት ዓመት እገ​ዛ​ል​ሃ​ለሁ። ሚስት ትሆ​ነኝ ዘንድ እር​ስ​ዋን ስጠኝ” አለው።</verse>
				<verse number="19">ላባም፥ “ለሌላ ሰው ከም​ሰ​ጣት ይልቅ ለማ​ው​ቅህ ለዘ​መዴ ለአ​ንተ ብሰ​ጣት ይሻ​ላል፤ ከእኔ ጋር ተቀ​መጥ” አለው።</verse>
				<verse number="20">ያዕ​ቆ​ብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ይወ​ድ​ዳት ስለ​ነ​በረ በእ​ርሱ ዘንድ ጥቂት ቀን ሆነ​ለት።</verse>
				<verse number="21">ያዕ​ቆ​ብም ላባን፥ “እን​ግ​ዲህ ወደ እር​ስዋ እገባ ዘንድ ሚስ​ቴን ስጠኝ፥ ቀኔ ተፈ​ጽ​ሞ​አ​ልና አለው።”</verse>
				<verse number="22">ላባም የዚ​ያን ስፍራ ሰዎች ሁሉ ሰበ​ሰበ፥ ሰር​ግም አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="23">በመ​ሸም ጊዜ ልጁን ልያን ወስዶ ወደ ያዕ​ቆብ አስ​ገ​ባት፤ ያዕ​ቆ​ብም ወደ እር​ስዋ ገባ።</verse>
				<verse number="24">ላባም ለልጁ ልያ አገ​ል​ጋ​ዪ​ቱን ዘለ​ፋን አገ​ል​ጋይ ትሆ​ናት ዘንድ ሰጣት።</verse>
				<verse number="25">በነ​ጋም ጊዜ እነሆ ልያ ነበ​ረች፤ ያዕ​ቆ​ብም ላባን፥ “ምነው እን​ደ​ዚህ አደ​ረ​ግ​ህ​ብኝ? ያገ​ለ​ገ​ል​ሁህ ስለ ራሔል አል​ነ​በ​ረ​ምን? ለምን አታ​ለ​ል​ኸኝ?” አለው።</verse>
				<verse number="26">ላባም እን​ዲህ አለ፥ “በሀ​ገ​ራ​ችን ታላ​ቂቱ ሳለች፥ ታና​ሺ​ቱን እን​ሰጥ ዘንድ ወግ አይ​ደ​ለም፤</verse>
				<verse number="27">ለዚ​ችም ሰባት ዓመት ፈጽም፤ ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለ​ም​ታ​ገ​ለ​ግ​ለኝ አገ​ል​ግ​ሎት እር​ስ​ዋን ደግሞ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="28">ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲህ አደ​ረገ፤ ለዚ​ችም ሰባት ዓመት ፈጸመ፤ ልጁን ራሔ​ል​ንም ለእ​ርሱ ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠው።</verse>
				<verse number="29">ላባም ለልጁ ለራ​ሔል አገ​ል​ጋ​ዪ​ቱን ባላን አገ​ል​ጋይ ትሆ​ናት ዘንድ ሰጣት።</verse>
				<verse number="30">ያዕ​ቆ​ብም ወደ ራሔል ደግሞ ገባ። ራሔ​ል​ንም ከልያ ይልቅ ወደ​ዳት፤ ሌላ ሰባት ዓመ​ትም ተገ​ዛ​ለት።</verse>
				<verse number="31">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልያ የተ​ጠ​ላች መሆ​ን​ዋን በአየ ጊዜ ማኅ​ፀ​ን​ዋን ከፈ​ተ​ላት፤ ራሔል ግን መካን ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="32">ልያም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች፥ ስሙ​ንም ሮቤል ብላ ጠራ​ችው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዋ​ረ​ዴን አይ​ቶ​አ​ልና፥ እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ ባሌ ይወ​ድ​ደ​ኛል” ስትል።</verse>
				<verse number="33">ልያም ዳግ​መኛ ፀነ​ሰች፤ ሁለ​ተኛ ወንድ ልጅ​ንም ለያ​ዕ​ቆብ ወለ​ደ​ች​ለት፤ “እኔ እንደ ተጠ​ላሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ሰማ ይህን ጨመ​ረ​ልኝ” አለች፤ ስሙ​ንም ስም​ዖን ብላ ጠራ​ችው ።</verse>
				<verse number="34">ደግ​ሞም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች፤ “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ህስ ባሌ ወደ እኔ ይጠ​ጋል፤ ሦስት ወን​ዶች ልጆ​ችን ወል​ጄ​ለ​ታ​ለ​ሁና” አለች፤ ስለ​ዚ​ህም ስሙን ሌዊ ብላ ጠራ​ችው።</verse>
				<verse number="35">ደግ​ሞም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች፤ በዚ​ህም ጊዜ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ” አለች፤ ስለ​ዚ​ህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራ​ችው። መው​ለ​ድ​ንም አቆ​መች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="30">
				<verse number="1">ራሔ​ልም ለያ​ዕ​ቆብ ልጅ እን​ዳ​ል​ወ​ለ​ደች በአ​የች ጊዜ በእ​ኅቷ ላይ ቀና​ች​ባት፤ ያዕ​ቆ​ብ​ንም “ልጅ ስጠኝ፤ ይህስ ከአ​ል​ሆነ እሞ​ታ​ለሁ” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="2">ያዕ​ቆ​ብም፥ “የማ​ኅ​ፀ​ን​ሽን ፍሬ የም​ከ​ለ​ክ​ልሽ እኔ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝን?” ብሎ ራሔ​ልን ተቈ​ጣት።</verse>
				<verse number="3">እር​ስ​ዋም፥ “ባሪ​ያዬ ባላ እነሆ አለች፤ ወደ እር​ስዋ ግባ፤ በእ​ኔም ጭን ላይ ትው​ለድ፤ የእ​ር​ስ​ዋም ልጆች ለእኔ ደግሞ ይሁ​ኑ​ልኝ” አለች።</verse>
				<verse number="4">አገ​ል​ጋ​ይ​ዋን ባላ​ንም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ለእ​ርሱ ሰጠ​ችው፤ ያዕ​ቆ​ብም ወደ እር​ስዋ ገባ።</verse>
				<verse number="5">የራ​ሔል አገ​ል​ጋይ ባላም ፀነ​ስች፤ ወንድ ልጅ​ንም ለያ​ዕ​ቆብ ወለ​ደ​ች​ለት።</verse>
				<verse number="6">ራሔ​ልም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈረ​ደ​ልኝ፤ ቃሌ​ንም ደግሞ ሰማ፤ ወንድ ልጅ​ንም ሰጠኝ” አለች፤ ስለ​ዚህ ስሙን ዳን ብላ ጠራ​ችው።</verse>
				<verse number="7">የራ​ሔ​ልም አገ​ል​ጋይ ባላ ደግማ ፀነ​ስች፤ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ሁለ​ተኛ ወንድ ልጅን ወለ​ደች።</verse>
				<verse number="8">ራሔ​ልም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ከፍ አደ​ረ​ገኝ፤ ብርቱ ትግ​ል​ንም ከእ​ኅቴ ጋር ታገ​ልሁ፤ አሸ​ነ​ፍ​ሁም፤ እኅ​ቴ​ንም መሰ​ል​ኋት” አለች፤ ስሙ​ንም ንፍ​ታ​ሌም ብላ ጠራ​ችው።</verse>
				<verse number="9">ልያም መው​ለ​ድን እን​ዳ​ቆ​መች በአ​የች ጊዜ አገ​ል​ጋ​ይ​ዋን ዘለ​ፋን ወሰ​ደች፤ ሚስት ትሆ​ነ​ውም ዘንድ ለያ​ዕ​ቆብ ሰጠ​ችው፤ ያዕ​ቆ​ብም ወደ እር​ስዋ ገባ።</verse>
				<verse number="10">የልያ አገ​ል​ጋይ ዘለ​ፋም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅ​ንም ለያ​ዕ​ቆብ ወለ​ደች።</verse>
				<verse number="11">ልያም፥ “እኔም ራሴን ብፅ​ዕት አሰ​ኘሁ” ስትል ስሙን ጋድ ብላ ጠራ​ችው።</verse>
				<verse number="12">የልያ አገ​ል​ጋይ ዘለ​ፋም ዳግ​መኛ ለያ​ዕ​ቆብ ወንድ ልጅን ወለ​ደች።</verse>
				<verse number="13">ልያም፥ “እኔ ብፅ​ዕት ነኝ፤ ሴቶች ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ኛ​ልና” አለች፤ ስሙ​ንም አሴር ብላ ጠራ​ችው።</verse>
				<verse number="14">ሮቤል ስንዴ በሚ​ታ​ጨ​ድ​በት ወራት ወጣ፤ በእ​ር​ሻም እን​ኮይ አገኘ፥ ለእ​ናቱ ለል​ያም አመ​ጣ​ላት። ራሔ​ልም ልያን፥ “የል​ጅ​ሽን እን​ኮይ ስጪኝ” አለ​ቻት።</verse>
				<verse number="15">ልያም፥ “ባሌን መው​ሰ​ድሽ አይ​በ​ቃ​ሽ​ምን? አሁን ደግሞ የል​ጄን እን​ኮይ ልት​ወ​ስጂ ትፈ​ል​ጊ​ያ​ለ​ሽን?” አለ​ቻት። ራሔ​ልም “እን​ኪ​ያስ ስለ ልጅሽ እን​ኮይ በዚ​ህች ሌሊት ከአ​ንቺ ጋር ይደር” አለች፤ ሰጠ​ቻ​ትም።</verse>
				<verse number="16">ያዕ​ቆ​ብም ሲመሽ ከዱር ገባ፤ ልያም ልት​ቀ​በ​ለው ወጣች፤ እን​ዲ​ህም አለ​ችው፥ “እኔ ዘንድ ታድ​ራ​ለህ፤ በልጄ እን​ኮይ በእ​ር​ግጥ ተስ​ማ​ም​ቼ​ሃ​ለ​ሁና።”</verse>
				<verse number="17">በዚ​ያ​ችም ሌሊት ከእ​ር​ስዋ ጋር አደረ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የል​ያን ጸሎት ሰማ፤ ፀነ​ሰ​ችም፤ አም​ስ​ተኛ ወንድ ልጅ​ንም ለያ​ዕ​ቆብ ወለ​ደች።</verse>
				<verse number="18">ልያም፥ “የል​ጄን እን​ኮይ ስለ ሰጠሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዋጋ​ዬን ሰጠኝ” አለች፤ ስሙ​ንም ይሳ​ኮር ብላ ጠራ​ችው።</verse>
				<verse number="19">ልያም ደግማ ፀነ​ስች፤ ስድ​ስ​ተኛ ወንድ ልጅ​ንም ለያ​ዕ​ቆብ ወለ​ደች።</verse>
				<verse number="20">ልያም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካም ስጦ​ታን ሰጠኝ፤ እን​ግ​ዲ​ህስ ከዛሬ ጀምሮ ባሌ ይወ​ደ​ድ​ኛል ስድ​ስት ልጆ​ችን ወል​ጄ​ለ​ታ​ለ​ሁና” አለች፤ ስሙ​ንም ዛብ​ሎን ብላ ጠራ​ችው።</verse>
				<verse number="21">ከዚ​ያም በኋላ ሴት ልጅን ወለ​ደች፤ ስም​ዋ​ንም ዲና አለ​ቻት።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ራሔ​ልን አሰ​ባት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተለ​መ​ናት፤ ማኅ​ፀ​ን​ዋ​ንም ከፈ​ተ​ላት፤ ፀነ​ሰ​ችም፤</verse>
				<verse number="23">ወንድ ልጅ​ንም ለያ​ዕ​ቆብ ወለ​ደ​ችና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሽሙ​ጤን ከእኔ አስ​ወ​ገደ” አለች፤</verse>
				<verse number="24">ስሙ​ንም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁለ​ተኛ ወንድ ልጅን ይጨ​ም​ር​ልኝ” ስትል ዮሴፍ ብላ ጠራ​ችው።</verse>
				<verse number="25">ራሔ​ልም ዮሴ​ፍን ከወ​ለ​ደች በኋላ ያዕ​ቆብ ላባን እን​ዲህ አለው፥ “ወደ ስፍ​ራዬ፥ ወደ ሀገ​ሬም እመ​ለስ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ተኝ።</verse>
				<verse number="26">ስለ እነ​ርሱ የተ​ገ​ዛ​ሁ​ላ​ቸ​ውን ሚስ​ቶ​ቼ​ንና ልጆ​ችን ስጠ​ኝና ልሂድ፤ የተ​ገ​ዛ​ሁ​ል​ህን መገ​ዛት ታው​ቃ​ለ​ህና።”</verse>
				<verse number="27">ላባም፥ “በዐ​ይ​ንህ ፊት ሞገ​ስን የማ​ገኝ ብሆ​ንስ ከዚሁ ተቀ​መጥ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ንተ ምክ​ን​ያት እንደ ባረ​ከኝ ተመ​ል​ክ​ቼ​አ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="28">ደመ​ወ​ዝ​ህን ንገ​ረኝ፤ እር​ሱ​ንም እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="29">ያዕ​ቆ​ብም አለው፥ “እን​ዴት እን​ዳ​ገ​ለ​ገ​ል​ሁህ፥ በእኔ ዘንድ ያሉ ከብ​ቶ​ችህ ምን ያህል እንደ ሆኑ አታ​ው​ቅ​ምን? ጥቂት ሆነው አግ​ኝ​ቻ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፤</verse>
				<verse number="30">አሁን ግን ፈጽ​መው በዝ​ተ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእኔ መም​ጣት ባር​ኮ​አ​ቸ​ዋል፤ አሁን ደግሞ ለቤቴ የም​ሠ​ራው መቼ ነው?”</verse>
				<verse number="31">ላባም፥ “የም​ሰ​ጥህ ምን​ድን ነው?” አለው። ያዕ​ቆ​ብም አለው፥ “ምንም አት​ስ​ጠኝ፤ ይህ​ንም ነገር ብታ​ደ​ር​ግ​ልኝ እን​ደ​ገና በጎ​ች​ህን አሰ​ማ​ራ​ለሁ፤ እጠ​ብ​ቃ​ለ​ሁም።</verse>
				<verse number="32">ዛሬ በጎ​ችህ ሁሉ ይለፉ፤ በዚ​ያም ከበ​ጎ​ችህ መካ​ከል ዝን​ጕ​ር​ጕ​ርና ነቍጣ ያለ​በ​ትን ጥቁ​ሩ​ንም በግ ሁሉ፥ ከፍ​የ​ሎ​ቹም ነቍ​ጣና ዝን​ጕ​ር​ጕር ያለ​በ​ትን ለይ​ልኝ፤ እነ​ር​ሱም ደመ​ወዜ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="33">ስለ​ዚ​ህም በፊ​ትህ ያለ​ውን ደመ​ወ​ዜን ለመ​መ​ል​ከት በመ​ጣህ ጊዜ ወደ​ፊት ጻድ​ቅ​ነ​ቴን ይመ​ሰ​ክ​ር​ል​ኛል፤ ከፍ​የ​ሎች ዝን​ጕ​ር​ጕ​ርና ነቍጣ የሌ​ለ​በት፥ ከበግ ጠቦ​ቶ​ችም ጥቁር ያል​ሆኑ ሁሉ፥ እርሱ በእኔ ዘንድ ቢገኝ እንደ ተሰ​ረቀ ይቈ​ጠ​ር​ብኝ።”</verse>
				<verse number="34">ላባም፥ “እነሆ እንደ ቃልህ ይሁን” አለ።</verse>
				<verse number="35">በዚ​ያም ቀን ከተ​ባ​ቶቹ ፍየ​ሎች ሽመ​ል​መሌ መሳ​ይና ነቍጣ ያለ​ባ​ቸ​ውን፥ ከእ​ን​ስ​ቶቹ ፍየ​ሎች ዝን​ጕ​ር​ጕ​ርና ነቍጣ ያለ​ባ​ቸ​ውን፥ ነጭ ያለ​በ​ትን ማን​ኛ​ው​ንም ሁሉ፥ ከበ​ጎ​ቹም መካ​ከል ጥቁ​ሩን በግ ሁሉ ለይቶ ለል​ጆቹ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="36">በእ​ር​ሱና በያ​ዕ​ቆብ መካ​ከ​ልም የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ያህል አራ​ቃ​ቸው፤ ያዕ​ቆ​ብም የቀ​ሩ​ትን የላ​ባን በጎች ይጠ​ብቅ ነበር።</verse>
				<verse number="37">ያዕ​ቆ​ብም ልብን፥ ለውዝ፥ ኤር​ሞን ከሚ​ባሉ ዕን​ጨ​ቶች ርጥብ በት​ርን ወስዶ በበ​ት​ሮቹ ውስጥ ያለው ነጭ እን​ዲ​ታይ ነጭ ሽመ​ል​መሌ አድ​ርጎ ላጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="38">በጎ​ቹም ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ በት​ሮቹ በፊ​ታ​ቸው ይሆኑ ዘንድ የላ​ጣ​ቸ​ውን በት​ሮች በውኃ ማጠጫ ገን​ዳው ውስጥ አኖ​ራ​ቸው፤</verse>
				<verse number="39">በጎ​ቹም መጥ​ተው በጠጡ ጊዜ ሽመ​ል​መሌ መሳ​ይና ዝን​ጕ​ር​ጕር፥ ነቍ​ጣም ያለ​በ​ትን በበ​ት​ሮቹ አም​ሳል ፀነሱ።</verse>
				<verse number="40">ያዕ​ቆ​ብም ተባት በጎ​ች​ንና እን​ስት በጎ​ችን ለይቶ ነጭና ሐመደ ክቦ በሆኑ አው​ራ​ዎች ፊት አቆ​ማ​ቸው፤ መን​ጎ​ቹ​ንም ለብ​ቻ​ቸው አቆ​ማ​ቸው። ከላባ በጎች ጋርም አል​ጨ​መ​ራ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="41">እን​ዲ​ህም ሆነ፦ በጎቹ በሚ​ፀ​ን​ሱ​በት ወራት በበ​ት​ሮቹ አም​ሳል ይፀ​ንሱ ዘንድ ያዕ​ቆብ በት​ሮ​ቹን በበ​ጎቹ ፊት በውኃ ማጠጫ ገን​ዳው ውስጥ ያኖ​ራ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="42">በጎ​ችም ከወ​ለዱ በኋላ በፊ​ታ​ቸው በት​ሩን አያ​ደ​ር​ገ​ውም ነበር፤ ምል​ክት ያላ​ቸው ለያ​ዕ​ቆብ፥ ምል​ክት የሌ​ላ​ቸ​ውም ለላባ ሆኑ።</verse>
				<verse number="43">ያዕ​ቆ​ብም እጅግ ባለ​ጠጋ ሆነ፤ ሴቶ​ችም ወን​ዶ​ችም አገ​ል​ጋ​ዮች፥ ብዙ ከብ​ትም፤ ላሞ​ችም፥ በጎ​ችም፥ ግመ​ሎ​ችና አህ​ዮ​ችም ሆኑ​ለት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="31">
				<verse number="1">ያዕ​ቆ​ብም የላባ ልጆች ያሉ​ትን ነገር፥ “ያዕ​ቆብ ለአ​ባ​ታ​ችን የሆ​ነ​ውን ሁሉ ወሰደ፤ ይህ​ንም ሁሉ ክብር ከአ​ባ​ታ​ችን ከብት አገኘ” ሲሉ ሰማ።</verse>
				<verse number="2">ያዕ​ቆ​ብም የላ​ባን ፊት አየ፤ እነ​ሆም፥ ከእ​ርሱ ጋር እንደ ዱሮው አል​ሆ​ነም።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዕ​ቆ​ብን፥ “ወደ አባ​ት​ህና ወደ ዘመ​ዶ​ችህ ሀገር ተመ​ለስ፤ እኔም ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="4">ያዕ​ቆ​ብም ልኮ ራሔ​ል​ንና ልያን ወደ በጎቹ መሰ​ማ​ሪያ ወደ ሜዳ ጠራ​ቸው፤</verse>
				<verse number="5">እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እነሆ፥ የአ​ባ​ታ​ችሁ ፊት እንደ ዱሮ ከእኔ ጋር እን​ዳ​ል​ሆነ አያ​ለሁ፤ ነገር ግን የአ​ባቴ አም​ላክ ከእኔ ጋር ነው።</verse>
				<verse number="6">እኔ ባለኝ ጕል​በቴ ሁሉ አባ​ታ​ች​ሁን እን​ዳ​ገ​ለ​ገ​ልሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="7">አባ​ታ​ችሁ ግን አሳ​ዘ​ነኝ፥ ደመ​ወ​ዜ​ንም ዐሥር ጊዜ ለወጠ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ክፉን ያደ​ር​ግ​ብኝ ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="8">ደመ​ወ​ዝህ ዝን​ጕ​ር​ጕ​ሮቹ ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ዝን​ጕ​ር​ጕ​ሮ​ችን ወለዱ፤ ነጫ​ጮቹ ደመ​ወ​ዝህ ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ነጫ​ጮ​ችን ወለዱ።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የአ​ባ​ታ​ች​ሁን በጎች ሁሉ ነሥቶ ለእኔ ሰጠኝ።</verse>
				<verse number="10">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በጎቹ በሚ​ፀ​ንሱ ጊዜ ዐይ​ኔን አን​ሥቼ በሕ​ልም አየሁ፤ እነ​ሆም፥ በበ​ጎ​ችና በፍ​የ​ሎች ላይ የሚ​ን​ጠ​ላ​ጠ​ሉት የበ​ጎ​ችና የፍ​የ​ሎች አው​ራ​ዎች ነጭ፥ ዝን​ጕ​ር​ጕ​ሮ​ችና ሐመደ ክቦ ነበሩ።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ልም፦ ‘ያዕ​ቆብ ያዕ​ቆብ’ አለኝ፤ እኔም፦ ‘እነ​ሆኝ ምን​ድን ነው?’ አል​ሁት።</verse>
				<verse number="12">እን​ዲ​ህም አለኝ፦ ዐይ​ን​ህን አቅ​ን​ተህ እይ፤ በበ​ጎ​ችና በፍ​የ​ሎች ላይ የሚ​ን​ጠ​ላ​ጠ​ሉት የበ​ጎ​ችና የፍ​የ​ሎች አው​ራ​ዎች ነጭ፥ ሐመደ ክቦና ዝን​ጕ​ር​ጕ​ሮች ናቸው፤ ላባ በአ​ንተ ላይ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን አይ​ቻ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="13">ሐው​ል​ቱን ዘይት በቀ​ባ​ህ​ባት፥ በዚ​ያች ለእኔ ስእ​ለት በተ​ሳ​ል​ህ​ባት ሀገር የተ​ገ​ለ​ጥ​ሁ​ልህ ፈጣ​ሪህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ። አሁ​ንም ተነ​ሥ​ተህ ከዚህ ሀገር ውጣ፤ ወደ ተወ​ለ​ድ​ህ​ባ​ትም ምድር ተመ​ለስ፤ እኔም ከአ​ንተ ጋር እኖ​ራ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="14">ራሔ​ልና ልያም መል​ሰው እን​ዲህ አሉት፥ “በአ​ባ​ታ​ችን ቤት ለእኛ ድርሻ ወይም ርስት በውኑ አለን?</verse>
				<verse number="15">እኛ በእ​ርሱ ዘንድ እንደ ባዕድ የተ​ቈ​ጠ​ርን አይ​ደ​ለ​ምን? እርሱ እኛን ሽጦ ዋጋ​ች​ንን በል​ቶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="16">ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ባ​ታ​ችን የነ​ሣው ይህ ሁሉ ሀብ​ትና ክብር ለእ​ኛና ለል​ጆ​ቻ​ችን ነው፤ አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያለ​ህን ሁሉ አድ​ርግ።”</verse>
				<verse number="17">ያዕ​ቆ​ብም ተነሣ፤ ልጆ​ቹ​ንና ሚስ​ቶ​ቹ​ንም በግ​መ​ሎች ላይ አስ​ቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="18">መን​ጎ​ቹ​ንም ሁሉ፥ የቤ​ቱ​ንም ዕቃ ሁሉ፥ በሁ​ለቱ ወን​ዞች መካ​ከል ሳለ ያገ​ኛ​ቸ​ውን ከብ​ቶች ሁሉ ይዞ ወደ አባቱ ወደ ይስ​ሐቅ ወደ ከነ​ዓን ምድር ሄደ።</verse>
				<verse number="19">ላባ ግን በጎ​ቹን ለመ​ሸ​ለት ሄዶ ነበር፤ ራሔ​ልም የአ​ባ​ቷን ጣዖ​ቶች ሰረ​ቀች።</verse>
				<verse number="20">ያዕ​ቆ​ብም ነገ​ሩን ከሶ​ር​ያ​ዊው ከላባ ሰወረ፤ እን​ደ​ሚ​ሄ​ድም አል​ነ​ገ​ረ​ውም።</verse>
				<verse number="21">እር​ሱም ያለ​ውን ሁሉ ይዞ ኰበ​ለለ፤ ተነ​ሥ​ቶም ወን​ዙን ተሻ​ገረ፤ በገ​ለ​ዓድ ተራ​ራም አደረ።</verse>
				<verse number="22">ለሶ​ር​ያ​ዊው ላባም ያዕ​ቆብ እንደ ኰበ​ለለ ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="23">ላባም ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ ይዞ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ተከ​ተ​ላ​ቸው፤ በገ​ለ​ዓድ ተራ​ራም ላይ አገ​ኛ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ ሶር​ያ​ዊው ወደ ላባ በሌ​ሊት በሕ​ልም መጥቶ፥ “በባ​ሪ​ያዬ በያ​ዕ​ቆብ ላይ ክፉ ነገር እን​ዳ​ት​ና​ገር ተጠ​ን​ቀቅ” አለው።</verse>
				<verse number="25">ላባም ያዕ​ቆ​ብን አገ​ኘው፤ ያዕ​ቆ​ብም ድን​ኳ​ኑን በተ​ራ​ራው ላይ ተክሎ ነበር፤ ላባም ወን​ድ​ሞ​ቹን በገ​ለ​ዓድ ተራራ አስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">ላባም ያዕ​ቆ​ብን አለው፥ “ለምን እን​ዲህ አደ​ረ​ግህ? ከእኔ በስ​ውር የኰ​በ​ለ​ልህ? ልጆ​ች​ንስ ሰር​ቀህ በሰ​ይፍ እን​ደ​ማ​ረከ የወ​ሰ​ድ​ኻ​ቸው?</verse>
				<verse number="27">ብት​ነ​ግ​ረኝ ኑሮ በደ​ስ​ታና በሐ​ሴት፥ በዘ​ፈን፥ በከ​በ​ሮና በበ​ገና በሸ​ኘ​ሁህ ነበር።</verse>
				<verse number="28">ወይስ ወን​ዶ​ቹ​ንና ሴቶ​ቹን ልጆ​ችን እስም ዘንድ አይ​ገ​ባ​ኝ​ምን? አሁ​ንም ይህን እንደ አላ​ዋቂ አደ​ረ​ግህ።</verse>
				<verse number="29">አሁ​ንም በአ​ንተ ላይ ክፉ ማድ​ረግ በቻ​ልሁ ነበር፤ ነገር ግን የአ​ባ​ትህ አም​ላክ ትና​ንት፦ በያ​ዕ​ቆብ ላይ ክፉ እን​ዳ​ታ​ደ​ርግ ተጠ​ን​ቀቅ ብሎ ነገ​ረኝ።</verse>
				<verse number="30">አሁ​ንም የአ​ባ​ት​ህን ቤት ከና​ፈ​ቅህ ሂድ፤ ነገር ግን አም​ላ​ኮ​ቼን ለምን ሰረ​ቅህ?”</verse>
				<verse number="31">ያዕ​ቆ​ብም መለሰ፤ ላባ​ንም እን​ዲህ አለው፥ “ልጆ​ች​ህ​ንና ገን​ዘ​ቤን ሁሉ ከእኔ የም​ት​ቀ​ማኝ ስለ​መ​ሰ​ለ​ኝና ስለ​ፈ​ራሁ ይህን አደ​ረ​ግሁ።”</verse>
				<verse number="32">ያዕ​ቆ​ብም አለ፥ “አም​ላ​ኮ​ች​ህን የም​ታ​ገ​ኝ​በት ሰው ግን እርሱ ይሙት፤ ገን​ዘ​ብ​ህም በእኔ ዘንድ ካለ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ፊት እይ፤ ለአ​ን​ተም ውሰ​ደው” አለ። ያዕ​ቆብ ሚስቱ ራሔል እንደ ሰረ​ቀ​ቻ​ቸው አያ​ው​ቅም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="33">ላባም ወደ ያዕ​ቆብ ድን​ኳ​ንና ወደ ልያም ድን​ኳን ገባና በረ​በረ፤ አላ​ገ​ኘ​ምም፤ ከዚ​ያም ወጣና ወደ ሁለቱ ዕቁ​ባ​ቶቹ ድን​ኳን ገባ፤ ነገር ግን አላ​ገ​ኘም። ወደ ራሔ​ልም ድን​ኳን ገባ።</verse>
				<verse number="34">ራሔ​ልም የአ​ባ​ቷን ጣዖ​ቶች ወስዳ ከግ​መል ኮርቻ በታች ሸሸ​ገች፤ በላ​ዩም ተቀ​መ​ጠ​ች​በት። ላባም ድን​ኳ​ኑን ሁሉ ፈለገ፤ አን​ዳ​ችም አላ​ገ​ኘም።</verse>
				<verse number="35">እር​ስ​ዋም አባ​ቷን፥ “ጌታዬ በፊ​ትህ ለመ​ቆም ስላ​ል​ቻ​ልሁ የአ​ቀ​ለ​ል​ሁህ አይ​ም​ሰ​ልህ፤ በሴ​ቶች የሚ​ደ​ርስ ግዳጅ ደር​ሶ​ብ​ኛ​ልና” አለ​ችው። ላባም የራ​ሔ​ልን ድን​ኳን በረ​በረ፤ ነገር ግን ጣዖ​ቶ​ቹን አላ​ገ​ኘም።</verse>
				<verse number="36">ያዕ​ቆ​ብም ተቈጣ፤ ላባ​ንም ወቀ​ሰው፤ ያዕ​ቆ​ብም መለሰ፤ ላባ​ንም እን​ዲህ አለው፥ “የበ​ደ​ል​ሁህ በደል ምን​ድን ነው? ኀጢ​አ​ቴስ ምን​ድን ነው? ይህን ያህል ያሳ​ደ​ድ​ኸኝ?</verse>
				<verse number="37">አሁ​ንም ዕቃ​ዬን ሁሉ በረ​በ​ርህ፤ ከቤ​ት​ህስ ዕቃ ሁሉ ምን አገ​ኘህ? እነ​ርሱ በእኛ በሁ​ለ​ታ​ችን መካ​ከል ይፈ​ርዱ ዘንድ በወ​ን​ድ​ሞ​ችና በወ​ን​ድ​ሞ​ችህ ፊት አቅ​ር​በው።</verse>
				<verse number="38">ሃያ አንድ ዓመት በጎ​ች​ህ​ንና ፍየ​ሎ​ች​ህን ስጠ​ብቅ ኖርሁ፥ ከበ​ጎ​ች​ህም ጠቦ​ቶ​ችን አል​በ​ላ​ሁም፤</verse>
				<verse number="39">አውሬ የሰ​በ​ረ​ው​ንም አላ​መ​ጣ​ሁ​ል​ህም ነበር፤ በቀ​ንም ሆነ በሌ​ሊት የተ​ሰ​ረቀ ቢኖር ከእኔ እከ​ፍ​ልህ ነበር።</verse>
				<verse number="40">የቀን ሐሩር፥ የሌ​ሊት ቍር ይበ​ላኝ ነበር፤ ዕን​ቅ​ል​ፍም ከዐ​ይኔ ጠፋ።</verse>
				<verse number="41">ለአ​ንተ ቤት የተ​ገ​ዛ​ሁ​ልህ ዛሬ ሃያ አንድ ዓመት ነው፤ ዐሥራ አራት ዓመት ስለ ሁለቱ ሴቶች ልጆ​ችህ፥ ሰባት ዓመት ስለ በጎ​ችህ ተገ​ዛ​ሁ​ልህ፤ ደመ​ወ​ዜ​ንም ዐሥር ጊዜ ለዋ​ወ​ጥ​ኸው።</verse>
				<verse number="42">የአ​ባቴ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ የይ​ስ​ሐ​ቅም ፍር​ሀት ከእኔ ጋር ባይ​ሆ​ንስ ዛሬ ባዶ እጄን በሰ​ደ​ድ​ኸኝ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዋ​ረ​ዴ​ንና የእ​ጆ​ችን ድካም አየ፤ ትና​ን​ትም ገሠ​ጸህ።”</verse>
				<verse number="43">ላባም ለያ​ዕ​ቆብ እን​ዲህ ብሎ መለ​ሰ​ለት፥ “ሴቶቹ ልጆች ልጆች ናቸው፤ ወን​ዶ​ቹም ልጆች ልጆች ናቸው፤ መን​ጎ​ቹም ከብ​ቶች ናቸው፤ ይህ የም​ታ​የው ሁሉ የእኔ ነው፤ የል​ጆ​ችም ሀብት ነው፤ ዛሬም በእ​ነ​ዚህ በሴ​ቶች ልጆ​ችና በወ​ለ​ዱ​አ​ቸው ልጆ​ቻ​ቸው ላይ ምን አደ​ር​ጋ​ለሁ?</verse>
				<verse number="44">አሁ​ንም ና፤ አን​ተና እኔ ቃል ኪዳን እን​ጋባ፤ በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ምስ​ክር ይሁን።”</verse>
				<verse number="45">ያዕ​ቆ​ብም ድን​ጋይ ወስዶ ሐው​ልት አቆመ።</verse>
				<verse number="46">ያዕ​ቆ​ብም ወን​ድ​ሞ​ቹን፥ “ድን​ጋይ ሰብ​ስቡ” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ድን​ጋይ ሰብ​ስ​በው ከመሩ፤ በድ​ን​ጋ​ዩም ክምር ላይ በሉ።</verse>
				<verse number="47">ላባም፥ “ይህች የድ​ን​ጋይ ክምር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ምስ​ክር ትሁን” አለው። ላባም “ወግረ ስምዕ” ብሎ ጠራት፤ ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲሁ አላት።</verse>
				<verse number="48">ላባም፥ “ይህች ያቆ​ም​ኋት የድ​ን​ጋይ ክምር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ዛሬ ምስ​ክር ናት” አለ። ስለ​ዚ​ህም ስምዋ ወግረ ስምዕ ተባለ።</verse>
				<verse number="49">ላባም አለው፥ “እኛ አን​ዳ​ችን ከሌ​ላው እን​ለ​ያ​ያ​ለ​ንና ራእ​ይን የገ​ለ​ጠ​ልኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ሆኖ ይመ​ል​ከት።</verse>
				<verse number="50">ልጆ​ችን ብት​በ​ድ​ላ​ቸው ወይም በላ​ያ​ቸው ላይ ሚስ​ቶ​ችን ብታ​ገ​ባ​ባ​ቸው እነሆ፥ ከእኛ ጋር ያለ ሰው እን​ደ​ሌለ አስ​ተ​ውል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ምስ​ክር ነው።”</verse>
				<verse number="51">ላባም ያዕ​ቆ​ብን አለው፥ “እነሆ፥ ይህች የድ​ን​ጋይ ክም​ርና ይህ​ችም ሐው​ልት ምስ​ክ​ሮች ናቸው።</verse>
				<verse number="52">እኔ ወደ አንተ በክ​ፋት ባልፍ ይህች የድ​ን​ጋይ ክምር፥ ይህ​ችም ሐው​ልት በክፉ ነገር ትከ​ተ​ለኝ።</verse>
				<verse number="53">አን​ተም ወደ እኔ ብታ​ልፍ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ የና​ኮ​ርም አም​ላክ በእኛ መካ​ከል ይፍ​ረድ።” ያዕ​ቆ​ብም በአ​ባቱ በይ​ስ​ሐቅ አም​ላክ ማለ።</verse>
				<verse number="54">ያዕ​ቆ​ብም በተ​ራ​ራው ላይ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋ፤ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ጠራ፤ እነ​ር​ሱም በሉ፤ ጠጡም፤ በዚ​ያም በተ​ራ​ራው አደሩ።</verse>
				<verse number="55">ላባም ማልዶ ተነ​ሥቶ ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ችን ልጆ​ቹን ሳመ፤ ባረ​ካ​ቸ​ውም፤ ላባም ተመ​ልሶ ወደ ስፍ​ራው ሄደ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="32">
				<verse number="1">ያዕ​ቆ​ብም መን​ገ​ዱን ሄደ፤ በዐ​ይ​ኖ​ቹም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሠራ​ዊት ከት​መው አየ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክ​ትም ተገ​ና​ኙት።</verse>
				<verse number="2">ያዕ​ቆ​ብም በአ​ያ​ቸው ጊዜ፥ “እነ​ዚህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠራ​ዊት ናቸው” አለ፤ የዚ​ያ​ንም ስፍራ ስም “ተዓ​ይን” ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="3">ያዕ​ቆ​ብም ወደ ወን​ድሙ ወደ ዔሳው ወደ ሴይር ምድር ወደ ኤዶም ሀገር በፊቱ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤</verse>
				<verse number="4">እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “ለጌ​ታዬ ለዔ​ሳው፦ ባሪ​ያህ ያዕ​ቆብ እን​ዲህ አለ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦ በላባ ዘንድ በስ​ደት ተቀ​መ​ጥሁ፤ እስከ ዛሬ ድረስ ቈየሁ፤</verse>
				<verse number="5">ላሞ​ች​ንም፥ ግመ​ሎ​ች​ንም፥ አህ​ዮ​ች​ንም፥ በጎ​ች​ንም፥ ወን​ዶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ንም፥ ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ንም አገ​ኘሁ፤ አሁ​ንም በፊ​ትህ ሞገ​ስን አገኝ ዘንድ ለጌ​ታዬ ለዔ​ሳው ለመ​ን​ገር ላክሁ።”</verse>
				<verse number="6">የላ​ካ​ቸው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ወደ ያዕ​ቆብ ተመ​ል​ሰው እን​ዲህ አሉት፥ “ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እር​ሱም ደግሞ ሊቀ​በ​ልህ ይመ​ጣል፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ።”</verse>
				<verse number="7">ያዕ​ቆ​ብም እጅግ ፈራ፤ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ው​ንም አጣ። ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉ​ትን ሰዎች ላሞ​ች​ንም፥ ግመ​ሎ​ች​ንም፥ በጎ​ች​ንም ሁለት ወገን አድ​ርጎ ከፈ​ላ​ቸው፤</verse>
				<verse number="8">ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲህ አለ፥ “ዔሳው መጥቶ አን​ዱን ወገን የመታ እንደ ሆነ የቀ​ረው ወገን ይድ​ናል።”</verse>
				<verse number="9">ያዕ​ቆ​ብም አለ፥ “የአ​ባቴ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ ሆይ፥ የአ​ባቴ የይ​ስ​ሐቅ አም​ላክ ሆይ፥ ‘ወደ ምድ​ርህ ወደ ተወ​ለ​ድ​ህ​በ​ትም ስፍራ ተመ​ለስ፤ በጎ​ነ​ት​ንም አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ’ ያል​ኸኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥</verse>
				<verse number="10">ለባ​ሪ​ያህ በአ​ደ​ረ​ግ​ኸው በም​ሕ​ረ​ት​ህና በእ​ው​ነ​ት​ህም ሁሉ በጎ​ውን አድ​ር​ግ​ልኝ፤ በት​ሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግሬ ነበ​ርና፥ አሁን ግን የሁ​ለት ክፍል ሠራ​ዊት ሆንሁ።</verse>
				<verse number="11">አቤቱ ከወ​ን​ድሜ ከዔ​ሳው እጅ አድ​ነኝ፤ መጥቶ እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋኝ፥ እና​ትን ከል​ጆ​ችዋ ጋር እን​ዳ​ያ​ጠፋ እኔ እፈ​ራ​ዋ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="12">አን​ተም፦ ‘በር​ግጥ መል​ካም አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ፥ ዘር​ህ​ንም ከብ​ዛቱ የተ​ነሣ እን​ደ​ማ​ይ​ቈ​ጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደ​ር​ጋ​ለሁ ብለህ ነበር።’ ”</verse>
				<verse number="13">በዚ​ያ​ችም ሌሊት በዚ​ያው አደረ። ለወ​ን​ድሙ ለዔ​ሳ​ውም የሚ​ወ​ስ​ደ​ውን እጅ መንሻ አወጣ፤</verse>
				<verse number="14">ሁለት መቶ እን​ስት ፍየ​ሎ​ች​ንና ሃያ የፍ​የል አው​ራ​ዎ​ችን፥ ሁለት መቶ እን​ስት በጎ​ች​ንና ሃያ የበግ አው​ራ​ዎ​ችን፥</verse>
				<verse number="15">ሃምሳ የሚ​ያ​ጠቡ ግመ​ሎ​ችን ከግ​ል​ገ​ሎ​ቻ​ቸው ጋር፥ አርባ ላም፥ ዐሥር በሬ፥ ሃያ እን​ስት አህያ፥ ዐሥ​ርም የአ​ህያ ውር​ን​ጫ​ዎች፤</verse>
				<verse number="16">መን​ጎ​ቹ​ንም ለየ​ብቻ ከፍሎ ለብ​ላ​ቴ​ኖቹ ሰጣ​ቸው፤ ብላ​ቴ​ኖ​ቹ​ንም፥ “በፊቴ እለፉ፤ መን​ጋ​ውን ከመ​ን​ጋው አርቁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">የፊ​ተ​ኛ​ው​ንም እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “ወን​ድሜ ዔሳው ያገ​ኘህ እንደ ሆነ፦ ‘አንተ የማን ነህ? ወዴ​ትስ ትሄ​ዳ​ለሀ? በፊ​ትህ ያለው ይህስ መንጋ የማን ነው?’ ብሎ የጠ​የ​ቀ​ህም እን​ደ​ሆነ፥</verse>
				<verse number="18">በዚያ ጊዜ አንተ፦ ‘ለጌ​ታዬ ለዔ​ሳው እጅ መንሻ የላ​ከው የአ​ገ​ል​ጋ​ይህ የያ​ዕ​ቆብ ነው፤ እር​ሱም ደግሞ እነሆ ከኋ​ላ​ችን ተከ​ት​ሎ​ናል’ በለው።”</verse>
				<verse number="19">እን​ዲ​ሁም ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንና ሦስ​ተ​ኛ​ውን፥ በፊቱ የሚ​ሄ​ዱ​ት​ንና መን​ጋ​ውን የሚ​ነ​ዱ​ትን ሁሉ እን​ዲሁ ብሎ አዘዘ፦“ ወን​ድሜ ዔሳ​ውን ባገ​ኛ​ች​ሁት ጊዜ ይህ​ንኑ ነገር ንገ​ሩት፤</verse>
				<verse number="20">እን​ዲ​ህም በሉ፦ እነሆ አገ​ል​ጋ​ይህ ያዕ​ቆብ ከኋ​ላ​ችን ነው። በፊቴ በሚ​ሄ​ደው እጅ መንሻ እታ​ረ​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ምና​ል​ባት ይራ​ራ​ል​ኛል፤ ፊቱ​ንም አያ​ለሁ ብሎ​አ​ልና።”</verse>
				<verse number="21">እጅ መን​ሻ​ውን ከእ​ርሱ አስ​ቀ​ድሞ ላከ፤ እርሱ ግን በዚ​ያች ሌሊት በሰ​ፈር አደረ።</verse>
				<verse number="22">በዚ​ያ​ችም ሌሊት ተነሣ፥ ሁለ​ቱን ሚስ​ቶ​ቹ​ንና ሁለ​ቱን ዕቁ​ባ​ቶ​ቹን ዐሥራ አን​ዱ​ንም ልጆ​ቹን ይዞ የያ​ቦ​ቅን ወንዝ ተሻ​ገረ።</verse>
				<verse number="23">ወሰ​ዳ​ቸ​ውም፤ ወን​ዙ​ንም አሻ​ገ​ራ​ቸው፤ ገን​ዘ​ቡ​ንም ሁሉ አሻ​ገረ።</verse>
				<verse number="24">ያዕ​ቆብ ግን ለብ​ቻው ቀረ፤ አንድ ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ይታ​ገ​ለው ነበር።</verse>
				<verse number="25">እን​ዳ​ላ​ሸ​ነ​ፈ​ውም ባየ ጊዜ የጭ​ኑን ሹልዳ ያዘው፤ የያ​ዕ​ቆ​ብም የጭኑ ሹልዳ ሲታ​ገ​ለው ደነ​ዘዘ።</verse>
				<verse number="26">እን​ዲ​ህም አለው፥ “ሊነጋ ጎሕ ቀድ​ዶ​አ​ልና ልቀ​ቀኝ።” እር​ሱም “ከአ​ል​ባ​ረ​ክ​ኸኝ አል​ለ​ቅ​ህም” አለው።</verse>
				<verse number="27">እን​ዲ​ህም አለው፥ “ስምህ ማን ነው?” እር​ሱም፥ “ያዕ​ቆብ ነኝ” አለው።</verse>
				<verse number="28">አለ​ውም፥ “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ስምህ እስ​ራ​ኤል ይባል እንጂ ያዕ​ቆብ አይ​ባል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ከሰው ጋር ታግ​ለህ በር​ት​ተ​ሃ​ልና።”</verse>
				<verse number="29">ያዕ​ቆ​ብም፥ “ስም​ህን ንገ​ረኝ” ብሎ ጠየ​ቀው። እር​ሱም፥ “ስሜን ለምን ትጠ​ይ​ቃ​ለህ? ድንቅ ነውና” አለው።</verse>
				<verse number="30">በዚ​ያም ስፍራ ባረ​ከው። ያዕ​ቆ​ብም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፊት ለፊት አየሁ፤ ሰው​ነ​ቴም ዳነች” ሲል የዚ​ያን ቦታ ስም “ራእየ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="31">ራእየ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በተወ ጊዜ ፀሐይ ወጣ​ች​በት። እር​ሱም በጭኑ ምክ​ን​ያት ያነ​ክስ ነበር።</verse>
				<verse number="32">ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ የወ​ር​ችን ሹልዳ አይ​በ​ሉም፤ የያ​ዕ​ቆ​ብን ጭን ይዞ የወ​ር​ቹን ሹልዳ አደ​ን​ዝ​ዞ​አ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="33">
				<verse number="1">ያዕ​ቆ​ብም ዐይ​ኑን አነሣ፤ እነ​ሆም፥ ዔሳ​ውን ሲመጣ አየው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች ነበሩ፤ ልጆ​ቹ​ንም ከፍሎ ወደ ልያና ወደ ራሔል ወደ ሁለ​ቱም ዕቁ​ባ​ቶቹ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤</verse>
				<verse number="2">ዕቁ​ባ​ቶ​ቹ​ንና ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በፊት አደ​ረገ፤ ልያ​ንና ልጆ​ች​ዋን በኋላ፥ ራሔ​ል​ንና ዮሴ​ፍ​ንም ከሁሉ በኋላ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="3">እር​ሱም በፊ​ታ​ቸው አለፈ፤ ወደ ወን​ድሙ ወደ ዔሳ​ውም እስ​ኪ​ደ​ርስ ድረስ ወደ ምድር ሰባት ጊዜ ሰገደ።</verse>
				<verse number="4">ዔሳ​ውም ሊገ​ና​ኘው ሮጠ፤ አን​ገ​ቱ​ንም አቅፎ ሳመው፤ ሁለ​ቱም በአ​ን​ድ​ነት አለ​ቀሱ።</verse>
				<verse number="5">ዔሳ​ውም ዐይ​ኑን አነ​ሣና ሴቶ​ች​ንና ልጆ​ችን አየ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነ​ዚህ ምኖ​ችህ ናቸው?” እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእኔ ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ የሰ​ጠኝ ልጆች ናቸው” አለ።</verse>
				<verse number="6">ዕቁ​ባ​ቶ​ቹም ከል​ጆ​ቻ​ቸው ጋር ቀር​በው ሰገዱ፤</verse>
				<verse number="7">ደግ​ሞም ልያና ልጆ​ችዋ ቀር​በው ሰገ​ዱ​ለት፤ ከዚ​ያም በኋላ ዮሴ​ፍና ራሔል ቀር​በው ሰገዱ።</verse>
				<verse number="8">ዔሳ​ውም፥ “ያገ​ኘ​ሁት ይህ ሠራ​ዊት ሁሉ ምንህ ነው?” አለ። እር​ሱም፥ “በጌ​ታዬ ፊት ሞገ​ስን አገኝ ዘንድ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ልህ ነው” አለ።</verse>
				<verse number="9">ዔሳ​ውም፥ “ለእኔ ብዙ አለኝ፤ ወን​ድሜ ሆይ፥ የአ​ንተ ለአ​ንተ ይሁን” አለ።</verse>
				<verse number="10">ያዕ​ቆ​ብም አለ፥ “እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን በፊ​ትህ ሞገ​ስን አግ​ኝቼ እንደ ሆንሁ እጅ መን​ሻ​ዬን ከእጄ ተቀ​በ​ለኝ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፊት እን​ደ​ሚ​ያይ ፊት​ህን አይ​ቻ​ለ​ሁና፥ በቸ​ር​ነ​ትም ተቀ​ብ​ለ​ኸ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="11">ከወ​ደ​ድ​ኸ​ኝስ ይህ​ችን ያመ​ጣ​ሁ​ል​ህን በረ​ከ​ቴን ተቀ​በል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራር​ቶ​ል​ኛ​ልና፥ ለእ​ኔም ብዙ አለ​ኝና።” እስ​ኪ​ቀ​በ​ለ​ውም ድረስ ግድ አለው፤ ተቀ​በ​ለ​ውም።</verse>
				<verse number="12">እር​ሱም፥ “ተነ​ሣና ወደ ፊት እን​ሂድ” አለው።</verse>
				<verse number="13">እር​ሱም አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ልጆቹ ደካ​ሞች እንደ ሆኑ ታው​ቃ​ለህ፤ በጎ​ችና ላሞ​ችም ግል​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ያጠ​ባሉ፤ ሰዎ​ችም በአ​ንድ ወይም በሁ​ለት ቀን በች​ኮላ የነ​ዱ​አ​ቸው እንደ ሆነ ከብ​ቶቹ ሁሉ ይሞ​ታሉ።</verse>
				<verse number="14">ጌታዬ ከአ​ገ​ል​ጋዩ ፊት ቀድሞ ይለፍ፤ እኛም እንደ ቻልን እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በጎ​ዳ​ናም እን​ው​ላ​ለን፤ ወደ ጌታ​ችን ወደ ሴይር እስ​ክ​ን​ደ​ር​ስም በሕ​ፃ​ናቱ ርምጃ መጠን እን​ሄ​ዳ​ለን” አለው።</verse>
				<verse number="15">ዔሳ​ውም፥ “ከእኔ ጋር ካሉ ሰዎች ከፍዬ ልተ​ው​ል​ህን?” አለ። እር​ሱም፥ “ይህ ለም​ን​ድን ነው? በጌ​ታዬ ዘንድ ሞገ​ስን ማግ​ኘቴ ይበ​ቃ​ኛል” አለ።</verse>
				<verse number="16">ዔሳ​ውም በዚያ ቀን ወደ ሴይር ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="17">ያዕ​ቆብ ግን በሰ​ፈሩ አደረ፤ በዚ​ያም ለእ​ርሱ ቤትን ሠራ፤ ለከ​ብ​ቶ​ቹም ዳሶ​ችን አደ​ረገ፤ ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያን ቦታ ስም ማኅ​ደር ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="18">ያዕ​ቆ​ብም ከሁ​ለቱ ወን​ዞች መካ​ከል በተ​መ​ለሰ ጊዜ በከ​ነ​ዓን ምድር ወዳ​ለ​ችው ወደ ሰቂ​ሞን ከተማ ወደ ሴሎም መጣ፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ፊት ለፊት ሰፈረ።</verse>
				<verse number="19">ድን​ኳ​ኑን ተክ​ሎ​በት የነ​በ​ረ​ው​ንም የእ​ርሻ ክፍል ከሴ​ኬም አባት ከኤ​ሞር ልጆች በመቶ በጎች ገዛው።</verse>
				<verse number="20">በዚ​ያም መሠ​ው​ያ​ዉን አቆመ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ ጠራ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="34">
				<verse number="1">ለያ​ዕ​ቆብ የተ​ወ​ለ​ደች የልያ ልጅ ዲናም የዚ​ያን ሀገር ሴቶች ልጆ​ችን ለማ​የት ወጣች።</verse>
				<verse number="2">የሀ​ገሩ አለቃ የኤ​ዊ​ያ​ዊው ሰው የኤ​ሞር ልጅ ሴኬም አያት፤ ወሰ​ዳ​ትም፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ተኛ፤ አስ​ነ​ወ​ራ​ትም።</verse>
				<verse number="3">ልቡ​ና​ውም በያ​ዕ​ቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነ​ደፈ፤ ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱ​ንም ወደ​ዳት፤ ልብ​ዋ​ንም ደስ በሚ​ያ​ሰ​ኛት ነገር ተና​ገ​ራት።</verse>
				<verse number="4">ሴኬ​ምም አባ​ቱን ኤሞ​ርን፥ “ይህ​ችን ብላ​ቴና አጋ​ባኝ” ብሎ ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="5">ያዕ​ቆ​ብም ልጁን ዲናን የኤ​ሞር ልጅ እን​ዳ​ስ​ነ​ወ​ራት ሰማ፤ ልጆ​ቹም ከከ​ብ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር በም​ድረ በዳ ነበሩ፤ ያዕ​ቆ​ብም ልጆቹ እስ​ኪ​መጡ ድረስ ዝም አለ።</verse>
				<verse number="6">የሴ​ኬም አባት ኤሞ​ርም ይነ​ግ​ረው ዘንድ ወደ ያዕ​ቆብ መጣ።</verse>
				<verse number="7">የያ​ዕ​ቆ​ብም ልጆች ከም​ድረ በዳ መጡ፤ ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ ፈጽ​መው ደነ​ገጡ፤ የያ​ዕ​ቆ​ብን ልጅ በመ​ተ​ኛቱ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ኀፍ​ረ​ትን ስላ​ደ​ረገ አዘኑ፤ እጅ​ግም ተቈጡ፤ እን​ዲህ አይ​ደ​ረ​ግ​ምና።</verse>
				<verse number="8">ኤሞ​ርም እን​ዲህ ብሎ ነገ​ራ​ቸው፥ “ልጄ ሴኬም ልጃ​ች​ሁን ወዶ​አ​ታ​ልና ሚስት እን​ድ​ት​ሆ​ነው እር​ስ​ዋን ስጡት።</verse>
				<verse number="9">ጋብ​ቾ​ችም ሁኑን፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ስጡን፤ እና​ን​ተም የእ​ኛን ሴቶች ልጆች ለል​ጆ​ቻ​ችሁ ውሰዱ።</verse>
				<verse number="10">ከእ​ኛም ጋር ተቀ​መጡ፤ ምድ​ራ​ች​ንም በፊ​ታ​ችሁ ሰፊ ናት፤ ኑሩ​ባት፤ ነግ​ዱም፤ ግዙ​አ​ትም።”</verse>
				<verse number="11">ሴኬ​ምም አባ​ቷ​ንና ወን​ድ​ሞ​ች​ዋን እን​ዲህ አለ፥ “በፊ​ታ​ችሁ ሞገ​ስን በአ​ገኝ የም​ት​ሉ​ትን ሁሉ እሰ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">ብዙ ማጫ አምጣ በሉኝ፤ በም​ት​ጠ​ይ​ቁ​ኝም መጠን እሰ​ጣ​ለሁ፤ ይህ​ችን ብላ​ቴና ግን ሚስት ትሆ​ነኝ ዘንድ ስጡኝ።”</verse>
				<verse number="13">የያ​ዕ​ቆ​ብም ልጆች ለሴ​ኬ​ምና ለአ​ባቱ ለኤ​ሞር በተ​ን​ኰል መለሱ፤ እኅ​ታ​ቸ​ውን ዲናን አስ​ነ​ው​ሮ​አ​ታ​ልና፤</verse>
				<verse number="14">የዲና ወን​ድ​ሞች ስም​ዖ​ንና ሌዊም እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “እኅ​ታ​ች​ንን ላል​ተ​ገ​ረዘ ሰው ለመ​ስ​ጠት ይህን ነገር እና​ደ​ርግ ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ንም፤ ይህ ነውር ይሆ​ን​ብ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="15">እና​ን​ተም እንደ እኛ ወን​ዶ​ቻ​ች​ሁን ሁሉ ብት​ገ​ርዙ በዚህ ብቻ እን​መ​ስ​ላ​ች​ኋ​ለን፤ ከእ​ና​ን​ተም ጋር እን​ኖ​ራ​ለን፤</verse>
				<verse number="16">ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ን​ንም እን​ሰ​ጣ​ች​ኋ​ለን፤ የእ​ና​ን​ተ​ንም ሴቶች ልጆች ለሚ​ስ​ት​ነት እን​ወ​ስ​ዳ​ለን፤ አንድ ሕዝ​ብም ሆነን ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ኖ​ራ​ለን።</verse>
				<verse number="17">ትገ​ረዙ ዘንድ እኛን ባት​ሰሙ ግን ልጃ​ች​ንን ይዘን እን​ሄ​ዳ​ለን።”</verse>
				<verse number="18">ነገ​ራ​ቸ​ውም ኤሞ​ር​ንና የኤ​ሞ​ርን ልጅ ሴኬ​ምን ደስ አሰ​ኛ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">ብላ​ቴ​ና​ውም ይህን ነገር ያደ​ርግ ዘንድ አል​ዘ​ገ​የም፤ የያ​ዕ​ቆ​ብን ልጅ ወድ​ዶ​አ​ልና፤ እር​ሱም ከአ​ባቱ ቤተ ሰብእ ሁሉ የከ​በረ ነበረ።</verse>
				<verse number="20">ኤሞ​ርና ልጁ ሴኬ​ምም ሄዱና ወደ ከተ​ማ​ቸው በር ደረሱ፤ ለከ​ተ​ማ​ቸ​ውም ሰዎች ሁሉ እን​ዲህ ብለው ነገሩ፦</verse>
				<verse number="21">“እነ​ዚህ ሰዎች በእኛ ዘንድ የሰ​ላም ሰዎች ናቸው፤ በም​ድ​ራ​ችን ይቀ​መጡ፤ ይነ​ግ​ዱ​ባ​ትም፤ እነ​ሆም፥ ምድ​ሪቱ ሰፊ ናት፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለሚ​ስ​ት​ነት እን​ው​ሰድ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ንን እን​ስጥ።</verse>
				<verse number="22">እነ​ርሱ እንደ እኛ ይሆኑ ዘንድ በዚህ ብቻ እን​ም​ሰ​ላ​ቸው። አንድ ወገ​ንም እን​ሁን፤ እነ​ርሱ እን​ደ​ሚ​ገ​ርዙ ወን​ዶ​ቻ​ች​ንን ሁሉ እን​ገ​ር​ዛ​ለን።</verse>
				<verse number="23">መን​ጋ​ቸ​ውም፥ የጋማ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፥ ገን​ዘ​ባ​ቸ​ውም ሁሉ ለእኛ አይ​ደ​ሉ​ምን? ነገር ግን በዚህ ብቻ ከመ​ሰ​ል​ና​ቸው ከእኛ ጋር ይቀ​መ​ጣሉ።”</verse>
				<verse number="24">በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በር የሚ​ገቡ ሁሉ ኤሞ​ር​ንና ልጁን ሴኬ​ምን እሺ አሉ፤ ወን​ዶ​ችም ሁሉ የሰ​ው​ነ​ታ​ቸ​ውን ሸለ​ፈት ተገ​ረዙ።</verse>
				<verse number="25">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን እጅግ ቈስ​ለው ሳሉ ሁለቱ የያ​ዕ​ቆብ ልጆች የዲና ወን​ድ​ሞች ስም​ዖ​ንና ሌዊ እየ​ራ​ሳ​ቸው ሰይ​ፋ​ቸ​ውን ይዘው ተደ​ፋ​ፍ​ረው ወደ ከተማ ገቡ፤ ወን​ዱ​ንም ሁሉ ገደሉ፤</verse>
				<verse number="26">ኤሞ​ር​ንና ልጁን ሴኬ​ም​ንም በሰ​ይፍ ገደሉ፤ እኅ​ታ​ቸው ዲና​ንም ከሴ​ኬም ቤት ይዘው ወጡ።</verse>
				<verse number="27">የያ​ዕ​ቆብ ልጆ​ችም ወደ ሞቱት ገብ​ተው እኅ​ታ​ቸው ዲናን ያስ​ነ​ወ​ሩ​ባ​ትን ከተ​ማ​ዪ​ቱን ዘረፉ፤</verse>
				<verse number="28">ላሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ በጎ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ አህ​ዮ​ቻ​ቸ​ው​ንም በሜ​ዳም፥ በከ​ተ​ማም ያለ​ውን ወሰዱ ።</verse>
				<verse number="29">ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንና ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ የቤ​ታ​ቸ​ው​ንም ቈሳ​ቍስ ሁሉ ማረኩ፤ በቤ​ትና በከ​ተማ ያለ​ው​ንም ሁሉ ዘረፉ።</verse>
				<verse number="30">ያዕ​ቆ​ብም ስም​ዖ​ን​ንና ሌዊን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ክፉ አደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ብኝ፤ በዚች ሀገር በሚ​ኖሩ በከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንና በፌ​ር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያን ሰዎች ዘንድ አስ​ጠ​ላ​ች​ሁኝ። እኔ በቍ​ጥር ጥቂት ነኝ፤ እነ​ርሱ በእኔ ላይ ይሰ​በ​ሰ​ቡና ይወ​ጉ​ኛል፤ እኔና ቤቴም እን​ጠ​ፋ​ለን።”</verse>
				<verse number="31">እነ​ር​ሱም፥ “እኅ​ታ​ች​ንን እንደ አመ​ን​ዝራ አድ​ር​ገው ለምን አዋ​ረ​ዷት?” አሉት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="35">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዕ​ቆ​ብን አለው፥ “ተነ​ሥ​ተህ ወደ ቤቴል ውጣ፤ በዚ​ያም ኑር፤ ከወ​ን​ድ​ምህ ከዔ​ሳው ፊት በሸ​ሸህ ጊዜ ለተ​ገ​ለ​ጥ​ሁ​ልህ ለእኔ መሥ​ው​ያን ሥራ።”</verse>
				<verse number="2">ያዕ​ቆ​ብም ለቤተ ሰቡና ከእ​ርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “ከእ​ና​ንተ ጋር ያሉ እን​ግ​ዶች አማ​ል​ክ​ትን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አስ​ወ​ግዱ፤ ንጹ​ሓ​ንም ሁኑ፤ ልብ​ሳ​ች​ሁ​ንም እጠቡ፤</verse>
				<verse number="3">ተነ​ሡና ወደ ቤቴል እን​ውጣ፤ በዚ​ያም በመ​ከ​ራዬ ቀን ለሰ​ማኝ፥ በሄ​ድ​ሁ​በ​ትም መን​ገድ ከእኔ ጋር ለነ​በ​ረው፥ ከመ​ከ​ራም አድኖ ላሻ​ገ​ረኝ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያን እን​ሥራ።”</verse>
				<verse number="4">በእ​ጃ​ቸው ያሉ​ት​ንም እን​ግ​ዶች አማ​ል​ክት ሁሉ፥ በጆ​ሮ​አ​ቸ​ውም ያሉ​ትን ጉት​ቾች ለያ​ዕ​ቆብ ሰጡት፤ ያዕ​ቆ​ብም በሴ​ቄም አጠ​ገብ ካለ​ችው ዛፍ በታች ቀበ​ራ​ቸው። እስከ ዛሬም ድረስ አጠ​ፋ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">እስ​ራ​ኤ​ልም ከሴ​ቄም ሄደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መፍ​ራት በዙ​ሪ​ያ​ቸው ባሉት ከተ​ሞች ሁሉ ወደቀ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ለማ​ሳ​ደድ አል​ተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="6">ያዕ​ቆ​ብም እርሱ፥ ከእ​ርሱ ጋርም የነ​በ​ሩት ሰዎች ሁሉ በከ​ነ​ዓን ምድር ወዳ​ለ​ችው ወደ ሎዛ መጡ፤ እር​ስ​ዋም ቤቴል ናት።</verse>
				<verse number="7">በዚ​ያም መሠ​ው​ያ​ዉን ሠራ፤ የዚ​ያ​ንም ቦታ ስም ቤቴል ብሎ ጠራው፤ እርሱ ከወ​ን​ድሙ ከዔ​ሳው ፊት በሸ​ሸ​በት ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ ተገ​ል​ጦ​ለት ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="8">የር​ብቃ ሞግ​ዚት ዲቦ​ራም ሞተች፤ ከቤ​ቴል በታች ባላን በሚ​ባል ዛፍ ሥርም ተቀ​በ​ረች፤ ያዕ​ቆ​ብም ስሙን “የል​ቅሶ ዛፍ” ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለያ​ዕ​ቆብ ከሁ​ለት ወን​ዞች መካ​ከል ከሶ​ርያ ከተ​መ​ለሰ በኋላ እን​ደ​ገና በሎዛ ተገ​ለ​ጠ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባረ​ከው።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “ስምህ ያዕ​ቆብ አይ​ባል፤ ስምህ እስ​ራ​ኤል ይባል እንጂ” ስሙ​ንም እስ​ራ​ኤል ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “አም​ላ​ክህ እኔ ነኝ፤ ብዛ፤ ተባ​ዛም፤ ሕዝ​ብና የአ​ሕ​ዛብ ማኅ​በር ከአ​ንተ ይሆ​ናል፤ ነገ​ሥ​ታ​ትም ከጕ​ል​በ​ትህ ይወ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="12">ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐ​ቅም የሰ​ጠ​ኋ​ትን ምድር ለአ​ንተ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ከተ​ነ​ጋ​ገ​ረ​በት ስፍራ ወደ ላይ ወጣ።</verse>
				<verse number="14">ያዕ​ቆ​ብም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር በተ​ነ​ጋ​ገ​ረ​በት ቦታ የድ​ን​ጋይ ሐው​ልት ተከለ፤ የመ​ጠጥ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም በእ​ርሱ ላይ አፈ​ሰሰ፤ ዘይ​ት​ንም አፈ​ሰ​ሰ​በት።</verse>
				<verse number="15">ያዕ​ቆ​ብም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር የተ​ነ​ጋ​ገ​ረ​በ​ትን ያን ቦታ “ቤቴል” ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="16">ያዕ​ቆ​ብም ከቤ​ቴል ተጓዘ፤ በጋ​ዲር ግንብ አጠ​ገብ ድን​ኳን ተከለ፤ ወደ ኤፍ​ራ​ታም ለመ​ድ​ረስ በቀ​ረበ ጊዜ ራሔ​ልን ምጥ ያዛት፤ በም​ጡም ተጨ​ነ​ቀች።</verse>
				<verse number="17">በምጥ ሳለ​ችም አዋ​ላ​ጂቱ፥ “አት​ፍሪ ይህ​ኛው ደግሞ ወንድ ልጅ ይሆ​ን​ል​ሻ​ልና” አለ​ቻት።</verse>
				<verse number="18">ከዚ​ያም በኋላ ነፍ​ስዋ ልት​ወጣ ደረ​ሰች፤ ሞትዋ በእ​ርሱ ሆኖ​አ​ልና ስሙን የጭ​ን​ቀቴ ልጅ ብላ ጠራ​ችው ፤ አባቱ ግን ብን​ያም አለው።</verse>
				<verse number="19">ራሔ​ልም ሞተች፤ ወደ ኤፍ​ራ​ታም በም​ት​ወ​ስድ መን​ገድ ተቀ​በ​ረች፤ እር​ስ​ዋም ቤተ ልሔም ናት።</verse>
				<verse number="20">ያዕ​ቆ​ብም በመ​ቃ​ብ​ርዋ ላይ ሐው​ልት አቆመ፤ እር​ስ​ዋም እስከ ዛሬ የራ​ሔል የመ​ቃ​ብ​ርዋ ሐው​ልት ትባ​ላ​ለች።</verse>
				<verse number="21">ከዚ​ህም በኋላ እስ​ራ​ኤል በዚ​ያች ምድር ሳለ ሮቤል ሄደ፤ ከአ​ባቱ ከያ​ዕ​ቆብ ዕቅ​ብት ከባላ ጋርም ተኛ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሰማ። በፊ​ቱም ክፉ ነገር ሆነ።</verse>
				<verse number="22">የያ​ዕ​ቆ​ብም ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው፤</verse>
				<verse number="23">የልያ ልጆች፤ የያ​ዕ​ቆብ በኵር ልጅ ሮቤል፥ ስም​ዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳ​ኮር፥ ዛብ​ሎን፤</verse>
				<verse number="24">የራ​ሔል ልጆች፤ ዮሴፍ፥ ብን​ያም፤</verse>
				<verse number="25">የራ​ሔል አገ​ል​ጋይ የባላ ልጆ​ችም፤ ዳን፥ ንፍ​ታ​ሌም፤</verse>
				<verse number="26">የልያ አገ​ል​ጋይ የዘ​ለፋ ልጆ​ችም፤ ጋድ፥ አሴር፤ እነ​ዚህ በሁ​ለቱ ወን​ዞች መካ​ከል በሶ​ርያ የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት የያ​ዕ​ቆብ ልጆች ናቸው።</verse>
				<verse number="27">ያዕ​ቆ​ብም ወደ አባቱ ወደ ይስ​ሐቅ፥ አብ​ር​ሃ​ምና ይስ​ሐቅ እን​ግ​ዶች ሆነው ወደ ተቀ​መ​ጡ​ባት በአ​ር​ባቅ ከተማ ወደ​ም​ት​ገ​ኘው ወደ መምሬ እር​ስ​ዋም ኬብ​ሮን ወደ​ም​ት​ባ​ለው መጣ።</verse>
				<verse number="28">የይ​ስ​ሐ​ቅም ዕድሜ መቶ ሰማ​ንያ ዓመት ሆነ።</verse>
				<verse number="29">ይስ​ሐ​ቅም ሸም​ግሎ ዕድ​ሜ​ንም ጠግቦ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ፤ ልጆ​ቹም ዔሳ​ውና ያዕ​ቆብ ቀበ​ሩት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="36">
				<verse number="1">ኤዶም የተ​ባ​ለው የዔ​ሳው ትው​ልድ እን​ዲህ ነው።</verse>
				<verse number="2">ዔሳው ከከ​ነ​ዓን ልጆች ሚስ​ቶ​ችን አገባ፤ የኬ​ጤ​ያ​ዊ​ውን የዔ​ሎን ልጅ ሐዳ​ሶን፥ የኤ​ው​ያ​ዊው የሴ​ቤሶ ልጅ ሐና የወ​ለ​ዳ​ትን ኤሌ​ባ​ማን፥</verse>
				<verse number="3">የይ​ስ​ማ​ኤ​ልን ልጅ የና​ቡ​አት እኅት ቤሴ​ሞ​ትን።</verse>
				<verse number="4">ሐዳሶ ለእ​ርሱ ኤል​ፋ​ዝን ወለ​ደች፤ ቤሴ​ሞ​ትም ራጉ​ኤ​ልን ወለ​ደች፤</verse>
				<verse number="5">ኤሌ​ባ​ማም ዮሔ​ልን፥ ይጉ​ሜ​ልን፥ ቆሬ​ንም ወለ​ደች። በከ​ነ​ዓን ምድር የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት የዔ​ሳው ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="6">ዔሳ​ውም ሚስ​ቶ​ቹን፥ ወን​ዶች ልጆ​ቹ​ንና ሴቶች ልጆ​ቹን፥ ቤተ ሰቡ​ንም ሁሉ፥ እን​ስ​ሶ​ቹ​ንም ሁሉ፥ በከ​ነ​ዓ​ንም ሀገር ያገ​ኘ​ውን ገን​ዘ​ቡን ሁሉ ይዞ ከወ​ን​ድሙ ከያ​ዕ​ቆብ ፊት ከከ​ነ​ዓን ሀገር ሄደ።</verse>
				<verse number="7">ከብ​ታ​ቸው ስለ​በዛ በአ​ን​ድ​ነት ይቀ​መጡ ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ በእ​ን​ግ​ድ​ነት የተ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትም ምድር ከከ​ብ​ታ​ቸው ብዛት የተ​ነሣ ልት​በ​ቃ​ቸው አል​ቻ​ለ​ችም።</verse>
				<verse number="8">ዔሳ​ውም በሴ​ይር ተራራ ተቀ​መጠ፤ ዔሳ​ውም ኤዶም ነው።</verse>
				<verse number="9">በሴ​ይር ተራራ የሚ​ኖሩ የኤ​ዶ​ማ​ው​ያን አባት የዔ​ሳው ትው​ል​ድም እን​ዲህ ነው።</verse>
				<verse number="10">የዔ​ሳው ልጆች ስም ይህ ነው፤ የዔ​ሳው ሚስት የሐ​ዳሶ ልጅ ኤል​ፋዝ፤ የዔ​ሳው ሚስት የቤ​ሴ​ሞት ልጅ ራጉ​ኤል።</verse>
				<verse number="11">የዔ​ሳው ልጅ የኤ​ል​ፋዝ ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ቴማን፥ ኤሞር፥ ሳፍር፥ ጎቶን፥ ቄኔዝ።</verse>
				<verse number="12">ቴም​ና​ሕም ለዔ​ሳው ልጅ ለኤ​ል​ፋዝ ዕቅ​ብት ነበ​ረች፤ አማ​ሌ​ቅ​ንም ለኤ​ል​ፋዝ ወለ​ደ​ች​ለት፤ የዔ​ሳ​ውም ሚስት የሐ​ዳሶ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="13">የዔ​ሳው ልጅ የራ​ጉ​ኤል ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ናሖት፥ ዛራ፥ ሲም፥ ሞዛህ፤ እነ​ዚ​ህም የዔ​ሳው ሚስት የቤ​ሴ​ሞት ልጆች ናቸው።</verse>
				<verse number="14">የሴ​ቤ​ጎን ልጅ የሐና ልጅ የዔ​ሳው ሚስት የኤ​ሌ​ባማ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ለዔ​ሳ​ውም ዮሔ​ልን፥ ዩጉ​ሜ​ልን፥ ቆሬን ወለ​ደች።</verse>
				<verse number="15">የዔ​ሳው ልጆች መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው፤ የዔ​ሳው የበ​ኵር ልጅ የኤ​ል​ፋዝ ልጆች፤ ቴማን መስ​ፍን፥ ኦሜር መስ​ፍን፥ ሳፍር መስ​ፍን፥ ቄኔዝ መስ​ፍን፥</verse>
				<verse number="16">ቆሬ መስ​ፍን፥ ጎቶን መስ​ፍን፥ አማ​ሌቅ መስ​ፍን፤ በኤ​ዶም ምድር የኤ​ል​ፋዝ መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው፤ እነ​ዚህ የሓ​ዳሶ ልጆች ናቸው ።</verse>
				<verse number="17">የዔ​ሳው ልጅ የራ​ጉ​ኤል ልጆች መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው፤ ናሖት መስ​ፍን፥ ዛራ መስ​ፍን፥ ሲን መስ​ፍን፥ ሞዛህ መስ​ፍን፤ በኤ​ዶም ምድር የራ​ጉ​ኤል ልጆች መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው፤ እነ​ዚ​ህም የዔ​ሳው ሚስት የቤ​ሴ​ሞት ልጆች ናቸው።</verse>
				<verse number="18">የዔ​ሳው ሚስት የኤ​ሌ​ባማ ልጆች መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው፤ ዮሔል መስ​ፍን፥ ይጉ​ሜል መስ​ፍን፥ ቆሬ መስ​ፍን፤ የዔ​ሳው ሚስት የሐና ልጅ የኤ​ሌ​ባማ ልጆች መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="19">የዔ​ሳው ልጆ​ችና መስ​ፍ​ኖ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው፤ እነ​ር​ሱም የኤ​ዶም ልጆች ናቸው።</verse>
				<verse number="20">በዚ​ያች ሀገር የተ​ቀ​መጡ የሖ​ሪ​ያ​ዊው የሴ​ይር ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ሉጣን፥ ሦባን፥ ሳባቅ፥ አናም፥</verse>
				<verse number="21">ዲሶን፥ ኤሶር፥ ዲሳን፤ እነ​ዚህ በኤ​ዶም ምድር የሖ​ሪ​ያ​ዊው የሴ​ይር ልጆች መሳ​ፍ​ንት ናቸው።</verse>
				<verse number="22">የሉ​ጣን ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ሖሪ፥ ሃማን ናቸው፤ የሉ​ጣ​ንም እኅት ትም​ናዕ ናት።</verse>
				<verse number="23">የሦ​ባን ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ዓል​ዋን፥ ማኔ​ሐት፥ ኤቤል፥ ሳፋር፥ አው​ናም።</verse>
				<verse number="24">የሳ​ባቅ ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ኢኣ፥ ዓናን፤ ይህም ዓናን በም​ድረ በዳ የአ​ባ​ቱን የሳ​ባ​ቅን አህ​ዮች ሲጠ​ብቅ ፍል ውኃ​ዎ​ችን ያገኘ ነው።</verse>
				<verse number="25">የዓ​ናን ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ዲሶን፤ የዓ​ናን ሴት ልጅ ኤሌ​ባማ።</verse>
				<verse number="26">የዲ​ሶ​ንም ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ሕም​ዳን፥ አስ​ባን፥ ቤዖር፥ ይት​ራን፥ ክራን።</verse>
				<verse number="27">የኤ​ሶር ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ከል​ሐን፥ ዛኦን፥ ዓቃን።</verse>
				<verse number="28">የሪ​ሶን ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ዑሳ፥ አራን።</verse>
				<verse number="29">የሖሪ መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው፤ ሉጣን መስ​ፍን፥ ሦባን መስ​ፍን፥ ሳባቅ መስ​ፍን፥ ዓናን መስ​ፍን፥</verse>
				<verse number="30">ዲሶን መስ​ፍን፥ ኤሶር መስ​ፍን፥ ሪሶን መስ​ፍን፤ በሴ​ይር ምድር በየ​ሹ​መ​ታ​ቸው መሳ​ፍ​ንት የሆኑ የሖሪ መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="31">በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ንጉሥ ከመ​ን​ገሡ በፊት በኤ​ዶም ሀገር የነ​ገሡ ነገ​ሥ​ታት እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="32">በኤ​ዶ​ምም የቤ​ዖር ልጅ ባላቅ ነገሠ፤ የከ​ተ​ማ​ዋም ስም ዴናባ ናት።</verse>
				<verse number="33">ባላ​ቅም ሞተ፤ በእ​ርሱ ፈን​ታም የባ​ሶ​ራው የዛራ ልጅ ኢዮ​ባብ ነገሠ።</verse>
				<verse number="34">ኢዮ​ባ​ብም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፈንታ የቴ​ማ​ኒው ሀገር ሑሳም ነገሠ።</verse>
				<verse number="35">ሑሳ​ምም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፈንታ የም​ድ​ያ​ምን ሰዎች በሞ​ዓብ ሜዳ የገ​ደለ የቤ​ዳድ ልጅ አዳድ ነገሠ፤ የከ​ተ​ማ​ዋም ስም ዓዊት ተባለ።</verse>
				<verse number="36">ዓዳ​ድም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፈንታ የም​ስ​ሬ​ቃው ሠምላ ነገሠ።</verse>
				<verse number="37">ሠም​ላም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፈንታ በወ​ንዝ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከር​ኆ​ቦት ሳኦል ነገሠ።</verse>
				<verse number="38">ሳኦ​ልም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፈንታ የዓ​ክ​ቦር ልጅ በአ​ል​ሐ​ናን ነገሠ።</verse>
				<verse number="39">የአ​ክ​ቦር ልጅ በአ​ል​ሐ​ና​ንም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፈንታ አዳር ነገሠ፤ የከ​ተ​ማ​ውም ስም ፎጎር ነው፤ ሚስ​ቱም የሜ​ዛ​አብ ልጅ መጥ​ሬድ የወ​ለ​ደ​ቻት ምኤ​ጠ​ብ​ኤል ትባ​ላ​ለች።</verse>
				<verse number="40">የዔ​ሳ​ውም የመ​ሳ​ፍ​ንቱ ስም በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው፥ በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸው፥ በያ​ገ​ራ​ቸ​ውና በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸው ይህ ነው፤ ትም​ናዕ መስ​ፍን፥ ዓልዋ መስ​ፍን፥ ኤቴት መስ​ፍን፥</verse>
				<verse number="41">ኤሌ​ባማ መስ​ፍን፥ ኤላ መስ​ፍን፥ ፊኖን መስ​ፍን፥</verse>
				<verse number="42">ቄኔዝ መስ​ፍን፥ ቴማን መስ​ፍን፥ ሜብ​ሳር መስ​ፍን፥</verse>
				<verse number="43">መግ​ዴ​ኤል መስ​ፍን፥ ኤራም መስ​ፍን፤ እነ​ዚህ በግ​ዛ​ታ​ቸው ምድር በየ​መ​ኖ​ሪ​ያ​ቸው የኤ​ዶም መሳ​ፍ​ንት ናቸው። የኤ​ዶ​ማ​ው​ያ​ንም አባት ይህ ዔሳው ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="37">
				<verse number="1">ያዕ​ቆ​ብም አባቱ በስ​ደት በኖ​ረ​በት ሀገር በከ​ነ​ዓን ምድር ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="2">የያ​ዕ​ቆ​ብም ትው​ልድ እን​ዲህ ነው። ዮሴፍ ዐሥራ ሰባት ዓመት በሆ​ነው ጊዜ ከወ​ን​ድ​ሞቹ ጋር የአ​ባ​ቱን በጎች ይጠ​ብቅ ነበር፤ እር​ሱም ከአ​ባቱ ሚስ​ቶች ከባ​ላና ከዘ​ለፋ ልጆች ጋር ሳለ ብላ​ቴና ነበረ፤ ዮሴ​ፍም የክ​ፋ​ታ​ቸ​ውን ወሬ ወደ አባ​ታ​ቸው ወደ እስ​ራ​ኤል ያመጣ ነበር።</verse>
				<verse number="3">ያዕ​ቆ​ብም ዮሴ​ፍን ከል​ጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወ​ድ​ደው ነበር፤ እርሱ በሽ​ም​ግ​ል​ናው የወ​ለ​ደው ነበ​ርና። በብዙ ኅብር ያጌ​ጠ​ችም ቀሚስ አደ​ረ​ገ​ለት።</verse>
				<verse number="4">ወን​ድ​ሞ​ቹም አባ​ታ​ቸው ከል​ጆቹ ሁሉ ይልቅ እን​ደ​ሚ​ወ​ድ​ደው በአዩ ጊዜ ጠሉት፤ በሰ​ላም ይና​ገ​ሩ​ትም ዘንድ አል​ቻ​ሉም።</verse>
				<verse number="5">ዮሴ​ፍም ሕል​ምን አለመ፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም ነገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">እር​ሱም አላ​ቸው፥ “እኔ ያለ​ም​ሁ​ትን ሕልም ስሙ፤</verse>
				<verse number="7">እነሆ፥ እኛ በእ​ርሻ መካ​ከል ነዶ ስና​ስር ነበ​ርና፥ እነሆ፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእ​ና​ን​ተም ነዶ​ዎች በዙ​ርያ ከብ​በው እነሆ፥ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።”</verse>
				<verse number="8">ወን​ድ​ሞ​ቹም፥ “በእኛ ላይ ልት​ነ​ግ​ሥ​ብን ይሆን? ወይስ ገዢ ትሆ​ነን ይሆን?” አሉት። እን​ደ​ገ​ናም ስለ ሕል​ሙና ስለ ነገሩ የበ​ለጠ ጠሉት።</verse>
				<verse number="9">ደግ​ሞም ሌላ ሕል​ምን አየ፤ ለአ​ባ​ቱና ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም ነገ​ራ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነሆ፥ ደግሞ ሌላ ሕልም አለ​ምሁ፤ ሕል​ሙም እን​ዲህ ነው፦ ፀሐ​ይና ጨረቃ ዐሥራ አንድ ከዋ​ክ​ብ​ትም ይሰ​ግ​ዱ​ልኝ ነበር።”</verse>
				<verse number="10">አባ​ቱም ገሠ​ጸው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ይህ ያለ​ም​ኸው ሕልም ምን​ድን ነው? በውኑ እኔና እና​ትህ፥ ወን​ድ​ሞ​ች​ህም መጥ​ተን በም​ድር ላይ እን​ሰ​ግ​ድ​ልህ ይሆን?”</verse>
				<verse number="11">ወን​ድ​ሞ​ቹም ቀኑ​በት፤ አባቱ ግን ይህን ነገር በልቡ ይጠ​ብ​ቀው ነበር።</verse>
				<verse number="12">ወን​ድ​ሞ​ቹም በሴ​ኬም የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን በጎች ይጠ​ብቁ ዘንድ ሄዱ።</verse>
				<verse number="13">እስ​ራ​ኤ​ልም ዮሴ​ፍን፥ “ወን​ድ​ሞ​ችህ በሴ​ኬም በጎ​ችን የሚ​ጠ​ብቁ አይ​ደ​ሉ​ምን? ወደ እነ​ርሱ እል​ክህ ዘንድ ና” አለው። እር​ሱም፥ “እሺ” አለው።</verse>
				<verse number="14">እር​ሱም፥ “ሄደህ ወን​ድ​ሞ​ች​ህና በጎቹ ደኅና እንደ ሆኑ እይ፤ ወሬ​አ​ቸ​ው​ንም አም​ጣ​ልኝ” አለው። ወደ ኬብ​ሮ​ንም ቆላ ላከው፤ ወደ ሴኬ​ምም መጣ።</verse>
				<verse number="15">እነ​ሆም፥ በም​ድረ በዳ ሲቅ​በ​ዘ​በዝ ሳለ አንድ ሰው አገ​ኘው፤ ሰው​የ​ውም፥ “ምን ትፈ​ል​ጋ​ለህ?” ብሎ ጠየ​ቀው።</verse>
				<verse number="16">እር​ሱም፥ “ወን​ድ​ሞ​ችን እፈ​ል​ጋ​ለሁ፤ በጎ​ቹን የሚ​ጠ​ብ​ቁ​በት ወዴት እንደ ሆነ እባ​ክህ ንገ​ረኝ?” አለ።</verse>
				<verse number="17">ሰው​የ​ውም፥ “ከዚህ ተነ​ሥ​ተ​ዋል፤ ወደ ዶታ​ይን እን​ሂድ ሲሉም ሰም​ቼ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለው። ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን ተከ​ታ​ትሎ ሄደ፤ በዶ​ታ​ይ​ንም አገ​ኛ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">እነ​ር​ሱም ወደ እነ​ርሱ ሳይ​ቀ​ርብ ከሩቅ አስ​ቀ​ድ​መው አዩት፥ ይገ​ድ​ሉ​ትም ዘንድ በእ​ርሱ ላይ ተማ​ከሩ።</verse>
				<verse number="19">አን​ዱም ለአ​ንዱ እን​ዲህ አለው፥ “ያ ባለ ሕልም ይኸው መጣ።</verse>
				<verse number="20">ኑ፥ እን​ግ​ደ​ለ​ውና በአ​ንድ ጕድ​ጓድ ውስጥ እን​ጣ​ለው፤ ክፉ አው​ሬም በላው እን​ላ​ለን፤ ሕል​ሞ​ቹም ምን እን​ደ​ሚ​ሆኑ እና​ያ​ለን።”</verse>
				<verse number="21">ሮቤ​ልም ይህን ሰማ፤ ከእ​ጃ​ቸ​ውም አዳ​ነው፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ሕይ​ወ​ቱን አና​ጥፋ።”</verse>
				<verse number="22">ሮቤ​ልም፥ “ደም አታ​ፍ​ስሱ፤ በዚች ምድረ በዳ ባለ​ችው ጕድ​ጓድ ጣሉት፤ ነገር ግን እጃ​ች​ሁን አት​ጣ​ሉ​በት” አላ​ቸው። ሮቤ​ልም እን​ዲህ ማለቱ ከእ​ጃ​ቸው ሊያ​ድ​ነ​ውና ወደ አባቱ ሊመ​ል​ሰው ነው።</verse>
				<verse number="23">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዮሴፍ ወደ ወን​ድ​ሞቹ በቀ​ረበ ጊዜ የለ​በ​ሳ​ትን በብዙ ኅብር ያጌ​ጠ​ቺ​ውን ቀሚ​ሱን ገፈ​ፉት፤</verse>
				<verse number="24">ወስ​ደ​ውም ወደ ጕድ​ጓድ ጣሉት፤ ጕድ​ጓ​ዱም ውኃ የሌ​ለ​በት ባዶ ነበረ።</verse>
				<verse number="25">እን​ጀ​ራም ሊበሉ ተቀ​መጡ፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም በአ​ነሡ ጊዜ እነሆ፥ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ነጋ​ድ​ያን ከገ​ለ​ዓድ ሲመጡ አዩ፤ ግመ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም ሽቱና በለ​ሳን፥ ከር​ቤም ተጭ​ነው ነበር። ወደ ግብፅ ሀገ​ርም ሊያ​ራ​ግፉ ይሄዱ ነበር።</verse>
				<verse number="26">ይሁ​ዳም ወን​ድ​ሞ​ቹን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ወን​ድ​ማ​ች​ንን ገድ​ለን ደሙን ብን​ሸ​ሽግ ጥቅ​ማ​ችን ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="27">ኑ፥ ለእ​ነ​ዚህ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን እን​ሽ​ጠው፤ እጃ​ች​ንን ግን በእ​ርሱ ላይ አን​ጣል፤ ወን​ድ​ማ​ችን ሥጋ​ችን ነውና።” ወን​ድ​ሞ​ቹም የነ​ገ​ራ​ቸ​ውን ሰሙት።</verse>
				<verse number="28">እነ​ዚያ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ነጋ​ዴ​ዎ​ችም ሲያ​ልፉ ወን​ድ​ሞቹ ዮሴ​ፍን ከጕ​ድ​ጓድ ጐት​ተው አወ​ጡት፤ ለይ​ስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም ዮሴ​ፍን በሃያ ብር ሸጡት፤ እነ​ር​ሱም ዮሴ​ፍን ወደ ግብፅ ወሰ​ዱት።</verse>
				<verse number="29">ሮቤ​ልም ወደ ጕድ​ጓዱ ተመ​ለሰ፤ እነ​ሆም፥ ዮሴ​ፍን ከጕ​ድ​ጓድ በአ​ጣው ጊዜ ልብ​ሱን ቀደደ።</verse>
				<verse number="30">ሮቤ​ልም ወደ ወን​ድ​ሞቹ ተመ​ልሶ፥ “ብላ​ቴ​ናው በጕ​ድ​ጓድ የለም፤ እን​ግ​ዲህ እኔ ወዴት እሄ​ዳ​ለሁ?” አለ።</verse>
				<verse number="31">የዮ​ሴ​ፍ​ንም ቀሚስ ወሰዱ፤ የፍ​የ​ልም ጠቦት አር​ደው ቀሚ​ሱን በደም ነከ​ሩት።</verse>
				<verse number="32">ብዙ ኅብር ያለ​በ​ትን ቀሚ​ሱ​ንም ላኩ፤ ወደ አባ​ታ​ቸ​ውም አገ​ቡት፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “ይህን ልብስ አገ​ኘን፤ ይህ የል​ጅህ ልብስ እንደ ሆነ ወይም እን​ዳ​ል​ሆነ እስኪ እየው?”</verse>
				<verse number="33">እር​ሱም ዐውቆ፥ “የልጄ ቀሚስ ነው፤ ክፉ አውሬ በል​ቶ​ታል፤ ዮሴ​ፍን ቦጫ​ጭ​ቆ​ታል” አለ።</verse>
				<verse number="34">ያዕ​ቆ​ብም ልብ​ሱን ቀደደ፤ በወ​ገ​ቡም ማቅ ታጥቆ ለልጁ ብዙ ቀን አለ​ቀሰ።</verse>
				<verse number="35">ወን​ዶች ልጆ​ቹና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው መጡ። ኀዘ​ኑ​ንም ያስ​ተ​ዉት ዘንድ አባ​ታ​ቸ​ውን ማለ​ዱት። ኀዘ​ኑ​ንም መተ​ውን እንቢ አለ፥ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ወደ ልጄ ወደ መቃ​ብር እያ​ዘ​ንሁ እወ​ር​ዳ​ለሁ።” አባ​ቱም ስለ እርሱ አለ​ቀሰ።</verse>
				<verse number="36">እነ​ዚያ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ሰዎች ግን ዮሴ​ፍን በግ​ብፅ ለፈ​ር​ዖን ጃን​ደ​ረባ ለዘ​በ​ኞቹ አለቃ ለጲ​ጥ​ፋራ ሸጡት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="38">
				<verse number="1">በዚ​ያም ወራት እን​ዲህ ሆነ፤ ይሁዳ ከወ​ን​ድ​ሞቹ ተለ​ይቶ ወረደ፤ ስሙ ኤራስ በሚ​ባል በዓ​ዶ​ሎ​ማ​ዊ​ውም ሰው ዘንድ አደረ።</verse>
				<verse number="2">ከዚ​ያም ይሁዳ ያንድ ከነ​ዓ​ናዊ ሰው ሴት ልጅን አየ፤ ስም​ዋም ሴዋ ይባ​ላል። ወሰ​ዳ​ትም፤ ወደ እር​ስ​ዋም ገባ።</verse>
				<verse number="3">ፀነ​ሰ​ችም፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ዔር ብላ ጠራ​ችው።</verse>
				<verse number="4">ደግ​ሞም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም አው​ናን ብላ ጠራ​ችው።</verse>
				<verse number="5">እን​ደ​ገና ደግሞ ወንድ ልጅን ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ሴሎም ብላ ጠራ​ችው፤ እነ​ር​ሱ​ንም በወ​ለ​ደች ጊዜ ኬሴቢ በሚ​ባል ሀገር ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="6">ይሁ​ዳም ለበ​ኵር ልጁ ለዔር ትዕ​ማር የም​ት​ባል ሚስት አጋ​ባው።</verse>
				<verse number="7">የይ​ሁ​ዳም የበ​ኵር ልጅ ዔር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀሠ​ፈው።</verse>
				<verse number="8">ይሁ​ዳም አው​ና​ንን፥ “ወደ ወን​ድ​ምህ ሚስት ግባ፤ አግ​ባ​ትም፤ ለወ​ን​ድ​ም​ህም ዘርን አቁ​ም​ለት” አለው።</verse>
				<verse number="9">አው​ና​ንም ዘሩ ለእ​ርሱ እን​ዳ​ይ​ሆን ዐወቀ፤ ወደ ወን​ድሙ ሚስ​ትም በገባ ጊዜ ለወ​ን​ድሙ ዘር እን​ዳ​ይ​ተካ ዘሩን በም​ድር ያፈ​ስ​ሰው ነበር።</verse>
				<verse number="10">ይህም ሥራው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ክፉ ሆነ​በት፤ እን​ዲህ አድ​ር​ጎ​አ​ልና እር​ሱ​ንም ደግሞ ቀሠ​ፈው።</verse>
				<verse number="11">ይሁ​ዳም ምራ​ቱን ትዕ​ማ​ርን፥ “ልጄ ሴሎም እስ​ኪ​ያ​ድግ ድረስ በአ​ባ​ትሽ ቤት መበ​ለት ሆነሽ ተቀ​መጪ” አላት፤ እርሱ ደግሞ እንደ ወን​ድ​ሞቹ እን​ዳ​ይ​ሞ​ት​ብኝ ብሎ​አ​ልና። ትዕ​ማ​ርም ሄዳ በአ​ባቷ ቤት ተቀ​መ​ጠች።</verse>
				<verse number="12">ዘመ​ን​ዋም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ የይ​ሁዳ ሚስት ሴዋ ሞተች፤ ይሁ​ዳም ተጽ​ናና፤ የበ​ጎ​ቹን ጠጕር ወደ​ሚ​ሸ​ል​ቱት ሰዎ​ችም ወደ ተምና ወጣ፤ እር​ሱም ዓዶ​ሎ​ማ​ዊው በግ ጠባ​ቂው ኤራ​ስም።</verse>
				<verse number="13">ለም​ራቱ ትዕ​ማ​ርም፥ “እነሆ፥ አማ​ትሽ ይሁዳ የበ​ጎ​ቹን ጠጕር ይሸ​ልት ዘንድ ወደ ተምና ይወ​ጣል” ብለው ነገ​ሩ​አት።</verse>
				<verse number="14">እር​ስ​ዋም የመ​በ​ለ​ት​ነ​ቷን ልብስ አወ​ለ​ቀች፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ዋ​ንም ለበ​ሰች፤ ተሸ​ፈ​ነ​ችም፤ ወደ ተም​ናም በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ዳር በኤ​ና​ይም ደጅ ተቀ​መ​ጠች፤ ሴሎም እንደ አደገ፥ ሚስ​ትም ትሆ​ነው ዘንድ እር​ስ​ዋን ሊሰ​ጠው እን​ዳ​ል​ፈ​ለገ አይ​ታ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="15">ይሁ​ዳም በአ​ያት ጊዜ ዘማ መሰ​ለ​ችው፤ ፊቷን ተሸ​ፍና ነበ​ርና አላ​ወ​ቃ​ትም።</verse>
				<verse number="16">ወደ እር​ስ​ዋም አዘ​ነ​በለ፥ “እባ​ክሽ ወደ አንቺ ልግባ አላት፤” እር​ስዋ ምራቱ እንደ ሆነች አላ​ወ​ቀም ነበ​ርና። እር​ስ​ዋም፥ “ወደ እኔ ብት​ገባ ምን ትሰ​ጠ​ኛ​ለህ?” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="17">“የፍ​የል ጠቦት ከመ​ን​ጋዬ እል​ክ​ል​ሻ​ለሁ” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “እስ​ክ​ት​ል​ክ​ልኝ ድረስ መያዣ ስጠኝ” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="18">እር​ሱም፥ “ምን መያዣ ልስ​ጥሽ?” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “ቀለ​በ​ት​ህን፥ ኩፌ​ት​ህን፥ በእ​ጅህ ያለ​ውን በትር” አለች። እር​ሱም ሰጣ​ትና ከእ​ር​ስዋ ደረሰ፤ እር​ስ​ዋም ፀነ​ሰ​ች​ለት።</verse>
				<verse number="19">እር​ስ​ዋም ተነ​ሥታ ሄደች፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ዋ​ንም አው​ልቃ የመ​በ​ለ​ት​ነ​ቷን ልብስ ለበ​ሰች።</verse>
				<verse number="20">ይሁ​ዳም መያ​ዣ​ውን ከሴ​ቲቱ እጅ ይቀ​በል ዘንድ በበግ ጠባ​ቂው በዓ​ዶ​ሎ​ማ​ዊው እጅ የፍ​የ​ሉን ጠቦት ላከ​ላት፤ እር​ስ​ዋ​ንም አላ​ገ​ኛ​ትም።</verse>
				<verse number="21">እር​ሱም የሀ​ገ​ሩን ሰዎች፥ “በኤ​ና​ይም በመ​ን​ገድ ዳር ተቀ​ምጣ የነ​በ​ረች ዘማ ወዴት ናት?” ብሎ ጠየ​ቃ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “በዚህ ዘማ አል​ነ​በ​ረ​ችም” አሉት።</verse>
				<verse number="22">ወደ ይሁ​ዳም ተመ​ልሶ እን​ዲህ አለው፥ “አላ​ገ​ኘ​ኋ​ትም፤ የሀ​ገሩ ሰዎች ደግሞ፦ ከዚህ ዘማ የለ​ችም” አሉኝ።</verse>
				<verse number="23">ይሁ​ዳም፥ “እኛ መዘ​በቻ እን​ዳ​ን​ሆን ትው​ሰ​ደው፤ እነሆ፥ የፍ​የ​ሉን ጠቦት ላክ​ሁ​ላት፤ አን​ተም አላ​ገ​ኘ​ሃ​ትም” አለ።</verse>
				<verse number="24">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከሦ​ስት ወር በኋላ ለይ​ሁዳ፥ “ምራ​ትህ ትዕ​ማር ሴሰ​ነች፤ እነሆ፥ በዝ​ሙት ፀነ​ሰች” ብለው ነገ​ሩት። ይሁ​ዳም፥ “አው​ጡ​አ​ትና በእ​ሳት ትቃ​ጠል” አለ።</verse>
				<verse number="25">እር​ስ​ዋም ሲወ​ስ​ዱ​አት ወደ አማቷ እን​ዲህ ብላ ላከች፤ “ተመ​ል​ከት፦ ይህ ቀለ​በት፥ ይህ ኩፌት፥ ይህ በትር የማን ነው? ይህስ ፅንስ የማን ነው?”</verse>
				<verse number="26">ይሁ​ዳም አይቶ “ከእኔ ይልቅ ትዕ​ማር እው​ነ​ተኛ ሆነች፤ ልጄን ሴሎ​ምን አል​ሰ​ጠ​ኋ​ት​ምና” አለ። ትገ​ደል ማለ​ት​ንም ተወ፤ ደግ​ሞም አላ​ወ​ቃ​ትም።</verse>
				<verse number="27">መው​ለ​ጃ​ዋም በደ​ረሰ ጊዜ እነሆ፥ መንታ ልጆች በሆ​ድዋ ነበሩ።</verse>
				<verse number="28">ስት​ወ​ል​ድም አንዱ እጁን አወጣ፤ አዋ​ላ​ጂ​ቱም ቀይ ፈትል ወስዳ በእጁ አሰ​ረች፥ “ይህ መጀ​መ​ሪያ ይወ​ጣል” አለች።</verse>
				<verse number="29">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ እጁን በመ​ለሰ ጊዜ እነሆ፥ ወን​ድሙ ወጣ፤ እር​ስ​ዋም፥ “ለምን ጥሰህ ወጣህ? ስትል ስሙን ፋሬስ” ብላ ጠራ​ችው።</verse>
				<verse number="30">ከእ​ር​ሱም በኋላ ቀይ ፈትል በእጁ ያለ​በት ወን​ድሙ ወጣ፤ ስሙም ዛራ ተባለ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="39">
				<verse number="1">ዮሴፍ ግን ወደ ግብፅ ወረደ፤ የፈ​ር​ዖን ጃን​ደ​ረባ የመ​ጋ​ቢ​ዎ​ቹም አለቃ የሚ​ሆን የግ​ብፅ ሰው ጲጥ​ፋራ ወደ ግብፅ ከአ​ወ​ረ​ዱት ከይ​ስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን እጅ ገዛው።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከዮ​ሴፍ ጋር ነበር፤ ሥራ​ውም የተ​ከ​ና​ወ​ነ​ለት ሰው ሆነ፤ በግ​ብ​ፃ​ዊው ጌታ​ውም ቤት ተሾመ።</verse>
				<verse number="3">ጌታ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዮ​ሴፍ ጋር እን​ዳለ፥ እርሱ የሚ​ሠ​ራ​ው​ንም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ እን​ዲ​ያ​ከ​ና​ው​ን​ለት አየ።</verse>
				<verse number="4">ዮሴ​ፍም በጌ​ታው ፊት ሞገ​ስን አገኘ፤ እር​ሱ​ንም ደስ ያሰ​ኘው ነበር፤ በቤ​ቱም ላይ ሾመው፤ ያለ​ው​ንም ሁሉ በእጁ ሰጠው።</verse>
				<verse number="5">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በቤቱ ባለ​ውም ሁሉ ላይ ከሾ​መው በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የግ​ብ​ፃ​ዊ​ውን ቤት በዮ​ሴፍ ምክ​ን​ያት ባረ​ከው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በረ​ከት በቤ​ቱም፥ በእ​ር​ሻ​ውም ባለው ሁሉ ላይ ሆነ።</verse>
				<verse number="6">ያለ​ው​ንም ሁሉ ለዮ​ሴፍ በእጁ አስ​ረ​ከ​በው፤ ከሚ​በ​ላ​ውም እን​ጀራ በቀር ምንም የሚ​ያ​ው​ቀው አል​ነ​በ​ረም። ዮሴ​ፍም መልኩ ያማረ፥ ፊቱም እጅግ የተ​ዋበ ነበር።</verse>
				<verse number="7">ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ የጌ​ታው ሚስት በዮ​ሴፍ ላይ ዐይ​ን​ዋን ጣለ​ች​በት፤ “ከእ​ኔም ጋር ተኛ” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="8">እር​ሱም እንቢ አለ፤ ለጌ​ታ​ውም ሚስት እን​ዲህ አላት፥ “እነሆ፥ ጌታዬ በቤቱ ያለ​ውን ሁሉ ለእኔ በእጄ አስ​ረ​ክ​ቦ​ኛል፤ በቤቱ ያለ​ው​ንም ምንም የሚ​ያ​ው​ቀው የለም፤</verse>
				<verse number="9">በዚህ ቤት ከእኔ የሚ​በ​ልጥ ሰው የለም፤ ሚስቱ ስለ​ሆ​ንሽ ከአ​ንቺ በቀር ያል​ሰ​ጠኝ ነገር የለም፤ እን​ዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደ​ር​ጋ​ለሁ? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዴት ኀጢ​አ​ትን እሠ​ራ​ለሁ?”</verse>
				<verse number="10">ይህ​ንም ነገር በየ​ዕ​ለቱ ለዮ​ሴፍ ትነ​ግ​ረው ነበር፤ እር​ሱም ከእ​ር​ስዋ ጋር ይተኛ ዘንድ፥ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ይሆን ዘንድ አል​ሰ​ማ​ትም።</verse>
				<verse number="11">በአ​ን​ዲ​ትም ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ በዚያ ቀን ሥራ​ውን እን​ዲ​ሠራ ዮሴፍ ወደ ቤቱ ገባ፤ በቤ​ትም ውስጥ ከቤተ ሰዎች ማንም አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="12">ልብ​ሱን ይዛ፥ “ና ከእኔ ጋር ተኛ” አለ​ችው፤ እር​ሱም ልብ​ሱን በእ​ጅዋ ትቶ​ላት ሸሸ፤ ወደ ውጭም ወጣ።</verse>
				<verse number="13">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ልብ​ሱን ትቶ ወደ ውጭ እንደ ሸሸ በአ​የች ጊዜ፥</verse>
				<verse number="14">የቤ​ቷን ሰዎች ወደ እር​ስዋ ጠርታ እን​ዲህ ብላ ነገ​ረ​ቻ​ቸው፥ “እዩ፤ ይህ ዕብ​ራዊ ባርያ በእኛ እን​ዲ​ሣ​ለቅ አመ​ጣ​ብን፤ እርሱ ወደ እኔ ገብቶ ከእኔ ጋር ተኚ አለኝ፤ እኔም ድም​ፄን ከፍ አድ​ርጌ ጮኽሁ፤</verse>
				<verse number="15">ድም​ፄ​ንም ከፍ አድ​ርጌ እንደ ጮኽሁ ቢሰማ፥ ልብ​ሱን በእኔ ዘንድ ጥሎ ሸሸ፤ ወደ ውጭም ወጣ።”</verse>
				<verse number="16">ጌታው ወደ ቤቱ እስ​ኪ​ገባ ድረ​ስም ልብ​ሱን ከእ​ር​ስዋ ዘንድ አኖ​ረች።</verse>
				<verse number="17">ይህ​ንም ነገር እን​ዲህ ብላ ነገ​ረ​ችው፥ “ያመ​ጣ​ኸው ዕብ​ራ​ዊው ባሪያ ሊሣ​ለ​ቅ​ብኝ ወደ እኔ ገባ፤ ከአ​ን​ቺም ጋር ልተኛ አለኝ።</verse>
				<verse number="18">እኔም ድም​ፄን ከፍ አድ​ርጌ ስጮኽ ልብ​ሱን በእጄ ተወና ወደ ውጭ ሸሸ።”</verse>
				<verse number="19">ጌታ​ውም፥ “ባሪ​ያህ እን​ዲህ አደ​ረ​ገኝ” ብላ የነ​ገ​ረ​ች​ውን የሚ​ስ​ቱን ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ።</verse>
				<verse number="20">ዮሴ​ፍ​ንም ወሰ​ደው፤ የን​ጉሡ እስ​ረ​ኞች ወደ​ሚ​ታ​ሰ​ሩ​በት ስፍራ ወደ ግዞት ቤትም አገ​ባው፤ ከዚ​ያም በግ​ዞት ነበረ።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከዮ​ሴፍ ጋር ነበረ፤ ምሕ​ረ​ት​ንም አበ​ዛ​ለት፤ በግ​ዞት ቤቱም አለቃ ፊት ሞገ​ስን ሰጠው።</verse>
				<verse number="22">የግ​ዞት ቤቱም አለቃ በግ​ዞት ያሉ​ትን እስ​ረ​ኞች ሁሉ በዮ​ሴፍ እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ በዚ​ያም የሚ​ደ​ረ​ገው ነገር ሁሉ እርሱ የሚ​ያ​ደ​ር​ገው ነበረ።</verse>
				<verse number="23">የግ​ዞት ቤቱ ጠባ​ቂ​ዎች አለ​ቃም በግ​ዞት ቤት የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ምንም አያ​ው​ቅም ነበር፤ ሁሉን ለዮ​ሴፍ ትቶ​ለት ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነበ​ረና፤ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ው​ንም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ ያቀ​ና​ለት ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="40">
				<verse number="1">ከዚህ ነገር በኋ​ላም እን​ዲህ ሆነ፤ የግ​ብፅ ንጉሥ የጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎች አለ​ቃና የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎች አለቃ ጌታ​ቸ​ውን የግ​ብፅ ንጉ​ሥን በደሉ።</verse>
				<verse number="2">ፈር​ዖ​ንም በሁ​ለቱ ሹሞች በጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎቹ አለ​ቃና በእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎቹ አለቃ ላይ ተቈጣ፤</verse>
				<verse number="3">በእ​ስር ቤት ውስ​ጥም ዮሴፍ ታስሮ በነ​በ​ረ​በት የግ​ዞት ስፍራ አጋ​ዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">የእ​ስር ቤቱ ዘበ​ኞች አለ​ቃም ለዮ​ሴፍ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ እር​ሱም ያገ​ለ​ግ​ላ​ቸው ነበር፤ በግ​ዞት ቤትም አንድ ዓመት ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="5">ሁለ​ቱም በአ​ን​ዲት ሌሊት ሕል​ምን አለሙ። በግ​ዞት ቤት የነ​በ​ሩት የግ​ብፅ ንጉሥ ጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎች አለ​ቃና የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎች አለቃ ሁለ​ቱም እየ​ራ​ሳ​ቸው ሕል​ምን አለሙ።</verse>
				<verse number="6">ዮሴ​ፍም ማልዶ ወደ እነ​ርሱ ገባ፤ እነ​ሆም፥ አዝ​ነው አያ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">በጌ​ታው ቤት ከእ​ርሱ ጋር በግ​ዞት የነ​በ​ሩ​ት​ንም የፈ​ር​ዖን ሹሞች እን​ዲህ ብሎ ጠየ​ቃ​ቸው፥ “እና​ንት ዛሬ ስለ​ምን አዝ​ና​ች​ኋል?”</verse>
				<verse number="8">እነ​ር​ሱም፥ “ሕል​ምን አል​መን የሚ​ተ​ረ​ጕ​ም​ልን አጣን” አሉት። ዮሴ​ፍም አላ​ቸው፥ “ሕል​ምን የሚ​ተ​ረ​ጕም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠው አይ​ደ​ለ​ምን? እስቲ ንገ​ሩኝ፤ ሕል​ማ​ችሁ ምን​ድን ነው?”</verse>
				<verse number="9">የጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎች አለ​ቃም ለዮ​ሴፍ ሕል​ሙን እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “በሕ​ልሜ የወ​ይን ሐረግ በፊቴ ሆና አየሁ፥</verse>
				<verse number="10">በሐ​ረ​ጉም ሦስት ቅር​ን​ጫ​ፎች ወጡ፤ እር​ስ​ዋም ቅጠ​ልና አበባ አወ​ጣች፤ ዘለ​ላም አን​ጠ​ለ​ጠ​ለች፤ የዘ​ለ​ላ​ዋም ፍሬ በሰለ፤</verse>
				<verse number="11">የፈ​ር​ዖ​ንም ጽዋ በእጄ ነበር፤ ፍሬ​ው​ንም ወስጄ በፈ​ር​ዖን ጽዋ ጨመ​ቅ​ሁት፤ ጽዋ​ዉ​ንም ለፈ​ር​ዖን በእጁ ሰጠ​ሁት።”</verse>
				<verse number="12">ዮሴ​ፍም አለው፥ “የሕ​ል​ምህ ትር​ጓ​ሜው ይህ ነው፤ ሦስት ቅር​ን​ጫ​ፎች ሦስት ቀኖች ናቸው።</verse>
				<verse number="13">እስከ ሦስት ቀንም ድረስ ፈር​ዖን ሹመ​ት​ህን ያስ​ባል፤ ወደ ጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎች አለ​ቃ​ነ​ት​ህም ይመ​ል​ስ​ሃል፤ ጠጅ አሳ​ላፊ በነ​በ​ር​ህ​በት ጊዜ ስታ​ደ​ር​ገው እንደ ነበ​ረው እንደ ቀድ​ሞው ሹመ​ት​ህም የፈ​ር​ዖ​ንን ጽዋ በእጁ ትሰ​ጣ​ለህ።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን በጎ ነገር በተ​ደ​ረ​ገ​ልህ ጊዜ እኔን ዐስ​በኝ፤ ምሕ​ረ​ት​ንም አድ​ር​ግ​ልኝ፤ ስለ እኔም ለፈ​ር​ዖን አሳ​ስ​በህ ከዚህ እስር ቤት አው​ጣኝ፤</verse>
				<verse number="15">ሌቦች በስ​ውር ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ሀገር ሰር​ቀ​ው​ኛ​ልና፤ በዚ​ህም ደግሞ ምንም ያደ​ረ​ግ​ሁት ሳይ​ኖር በግ​ዞት ቤት አኑ​ረ​ው​ኛ​ልና።”</verse>
				<verse number="16">የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎቹ አለ​ቃም ሕል​ሙን በመ​ል​ካም እንደ ተረ​ጐ​መ​ለት በአየ ጊዜ ዮሴ​ፍን እን​ዲህ አለው፥ “እኔም ደግሞ ሕልም አይች ነበር፤ እነ​ሆም፥ ሦስት መሶብ ነጭ እን​ጀራ በራሴ ላይ ነበረ፤</verse>
				<verse number="17">በላ​ይ​ኛ​ውም መሶብ ፈር​ዖን የሚ​በ​ላው ጋጋ​ሪው በያ​ይ​ነቱ የሠ​ራው መብል ነበ​ረ​በት፤ ወፎ​ችም በራሴ ላይ ከመ​ሶቡ ይበሉ ነበር።”</verse>
				<verse number="18">ዮሴ​ፍም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “የሕ​ል​ምህ ትር​ጓ​ሜው ይህ ነው፤ ሦስቱ መሶብ ሦስት ቀን ነው፤</verse>
				<verse number="19">እስከ ሦስት ቀን ድረስ ፈር​ዖን ራስ​ህን ይቈ​ር​ጥ​ሃል፤ በዕ​ን​ጨ​ትም ላይ ይሰ​ቅ​ል​ሃል፤ የሰ​ማይ ወፎ​ችም ሥጋ​ህን ይበ​ሉ​ታል።”</verse>
				<verse number="20">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ፈር​ዖን የተ​ወ​ለ​ደ​በት ዕለት ነበር፤ ለሠ​ራ​ዊ​ቱም ሁሉ ግብር አደ​ረገ፤ የጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ቹን አለ​ቃና የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎ​ቹን አለቃ በአ​ሽ​ከ​ሮቹ መካ​ከል ዐሰበ።</verse>
				<verse number="21">የጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ቹ​ንም አለቃ ወደ ሹመቱ መለ​ሰው፤ ጽዋ​ው​ንም በፈ​ር​ዖን እጅ ሰጠ፤</verse>
				<verse number="22">የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎ​ቹ​ንም አለቃ በዕ​ን​ጨት ላይ ሰቀ​ለው፤ ዮሴፍ እንደ ተረ​ጐ​መ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">የጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎች አለቃ ግን ዮሴ​ፍን አላ​ሰ​በ​ውም፤ ረሳው እንጂ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="41">
				<verse number="1">ከሁ​ለት ዓመት በኋ​ላም ፈር​ዖን ሕል​ምን አየ፤ እነ​ሆም፥ በወ​ንዙ ዳር ቆሞ ነበር።</verse>
				<verse number="2">እነ​ሆም፥ መል​ካ​ቸው ያማረ፥ ሥጋ​ቸ​ውም የወ​ፈረ ሰባት ላሞች ከወ​ንዙ ወጡ፤ በወ​ን​ዙም ዳር በመ​ስኩ ይሰ​ማሩ ነበር።</verse>
				<verse number="3">ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ እነሆ፥ መል​ካ​ቸው የከፋ፥ ሥጋ​ቸ​ውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወ​ንዙ ወጡ፤ በእ​ነ​ዚ​ያም ላሞች አጠ​ገብ በወ​ንዙ ዳር ተሰ​ማ​ር​ተው ነበር።</verse>
				<verse number="4">መል​ካ​ቸው የከፋ፥ ሥጋ​ቸ​ውም የከሳ እነ​ዚያ ሰባት ላሞች መል​ካ​ቸው ያማ​ረ​ውን፥ ሥጋ​ቸ​ውም የወ​ፈ​ረ​ውን ሰባ​ቱን ላሞች ዋጡ​አ​ቸው። ፈር​ዖ​ንም ነቃ፤</verse>
				<verse number="5">ደግ​ሞም ተኛ፤ ሁለ​ተኛ ሕል​ም​ንም አየ፤ እነ​ሆም፥ በአ​ንድ አገዳ ላይ የነ​በሩ፥ ያማ​ሩና ምርጥ የሆኑ ሰባት እሸ​ቶች ወጡ፤</verse>
				<verse number="6">እነ​ሆም፥ ከእ​ነ​ርሱ በኋላ የሰ​ለ​ቱና በነ​ፋስ የተ​መቱ ሰባት እሸ​ቶች ወጡ፤</verse>
				<verse number="7">እነ​ዚ​ያም የሰ​ለ​ቱና ነፋስ የመ​ታ​ቸው እሸ​ቶች ሰባ​ቱን ያማ​ሩና የጐ​መሩ እሸ​ቶች ዋጡ​አ​ቸው። ፈር​ዖ​ንም ነቃ፤ እነ​ሆም ሕልም ነበር።</verse>
				<verse number="8">በነ​ጋም ጊዜ መን​ፈሱ ታወ​ከ​ች​በት፤ የግ​ብፅ ሕልም ተር​ጓ​ሚ​ዎ​ች​ንና ጠቢ​ባ​ንን ሁሉ ልኮ አስ​ጠ​ራ​ቸው፤ ፈር​ዖ​ንም ሕል​ሙን ነገ​ራ​ቸው፤ ነገር ግን ከእ​ነ​ርሱ ለፈ​ር​ዖን ሕል​ሙን የሚ​ተ​ረ​ጕ​ም​ለት አል​ተ​ገ​ኘም።</verse>
				<verse number="9">የዚ​ያን ጊዜ የጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎቹ አለቃ እን​ዲህ ብሎ ለፈ​ር​ዖን ተና​ገረ፥ “እኔ ኀጢ​አ​ቴን ዛሬ አስ​ባ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="10">ፈር​ዖን በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ላይ ተቈጣ፤ እኔ​ንም የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎ​ቹ​ንም አለቃ በግ​ዞት ቤት አኖ​ረን፤</verse>
				<verse number="11">እኛም በአ​ን​ዲት ሌሊት ሕል​ምን አለ​ምን፤ እኔና እርሱ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችን እንደ ሕል​ማ​ችን ትር​ጓሜ አለ​ምን።</verse>
				<verse number="12">በዚ​ያም የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎች አለቃ አገ​ል​ጋይ የሆነ አንድ ዕብ​ራዊ ጐል​ማሳ ከእኛ ጋር ነበር፤ ለእ​ር​ሱም ነገ​ር​ነው፤ ሕል​ማ​ች​ን​ንም ተረ​ጐ​መ​ልን።</verse>
				<verse number="13">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ እንደ ተረ​ጐ​መ​ልን እን​ደ​ዚ​ያው ሆነ፤ እኔ ወደ ሹመቴ ተመ​ለ​ስሁ፤ እር​ሱም ተሰ​ቀለ።”</verse>
				<verse number="14">ፈር​ዖ​ንም ልኮ ዮሴ​ፍን አስ​ጠ​ራው፤ ከግ​ዞት ቤትም አወ​ጡት፤ ራሱ​ንም ላጩት፤ ልብ​ሱ​ንም ለወጡ፤ ወደ ፈር​ዖ​ንም ገባ።</verse>
				<verse number="15">ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን አለው፥ “ሕል​ምን አየሁ፤ የሚ​ተ​ረ​ጕ​ም​ል​ኝም አጣሁ፤ ሕል​ምን እንደ ሰማህ፥ እንደ ተረ​ጐ​ም​ህም ስለ አንተ ሰማሁ።”</verse>
				<verse number="16">ዮሴ​ፍም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከገ​ለ​ጸ​ለት ሰው በቀር መተ​ር​ጐም የሚ​ችል የለም” ብሎ ለፈ​ር​ዖን መለ​ሰ​ለት።</verse>
				<verse number="17">ፈር​ዖ​ንም ለዮ​ሴፍ እን​ዲህ አለው፥ “እነሆ፥ በሕ​ልሜ በወ​ንዝ ዳር ቆሜ ነበር፤</verse>
				<verse number="18">እነ​ሆም፥ ሥጋ​ቸው የወ​ፈረ፥ መል​ካ​ቸ​ውም ያማረ ሰባት ላሞች ወጡ፤ በወ​ንዙ ዳር በመ​ስ​ኩም ይሰ​ማሩ ነበር፤</verse>
				<verse number="19">ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ እነሆ፥ የደ​ከሙ፥ መል​ካ​ቸ​ውም እጅግ የከፋ፥ ሥጋ​ቸ​ውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወ​ንዙ ወጡ፤ በግ​ብ​ፅም ምድር ሁሉ እንደ እነ​ርሱ መልከ ክፉ ከቶ አላ​የ​ሁም፤</verse>
				<verse number="20">እነ​ዚያ የከ​ሱ​ትና መልከ ክፉ​ዎቹ ላሞች እነ​ዚ​ያን የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዎ​ቹን ያማ​ሩና የወ​ፈሩ ሰባት ላሞች ዋጡ​አ​ቸው፤ በሆ​ዳ​ቸ​ውም ተዋጡ፤</verse>
				<verse number="21">በሆ​ዳ​ቸ​ውም ውስጥ የገባ እን​ደ​ሌለ ሆኑ፤ መል​ካ​ቸ​ውም በመ​ጀ​መ​ሪያ እንደ ነበ​ረው የከፋ ነበረ፤ ነቃ​ሁም። ዳግ​መ​ኛም ተኛሁ፤</verse>
				<verse number="22">በሕ​ል​ሜም እነሆ፥ የጐ​መ​ሩና መል​ካም የሆኑ ሰባት እሸ​ቶች ከአ​ንድ አገዳ ሲወጡ አየሁ፤</verse>
				<verse number="23">ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ እነሆ የሰ​ለ​ቱና በነ​ፋስ የተ​መቱ ሌሎች ሰባት እሸ​ቶች ወጡ፤</verse>
				<verse number="24">እነ​ዚያ የሰ​ለ​ቱ​ትና በነ​ፋስ የተ​መ​ቱት እሸ​ቶች እነ​ዚ​ያን ያማ​ሩ​ት​ንና የጐ​መ​ሩ​ትን ሰባ​ቱን እሸ​ቶች ዋጡ​አ​ቸው። ለሕ​ልም ተር​ጓ​ሚ​ዎ​ችም ሕል​ሜን ነገ​ርሁ፤ የተ​ረ​ጐ​መ​ል​ኝም የለም።”</verse>
				<verse number="25">ዮሴ​ፍም ፈር​ዖ​ንን አለው፥ “የፈ​ር​ዖን ሕልሙ አንድ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ደ​ር​ገው ያለ​ውን ለፈ​ር​ዖን አሳ​ይ​ቶ​ታል።</verse>
				<verse number="26">እነ​ዚያ ሰባቱ መል​ካ​ካ​ሞች ላሞች ሰባት ዓመ​ታት ናቸው፤ እነ​ዚ​ያም ሰባቱ መል​ካ​ካ​ሞች እሸ​ቶች ሰባት ዓመ​ታት ናቸው፤ የፈ​ር​ዖን ሕልሙ አንድ ነው።</verse>
				<verse number="27">ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ የወ​ጡት እነ​ዚያ የከ​ሱና መልከ ክፉ​ዎቹ ሰባት ላሞች ሰባት ዓመ​ታት ናቸው፤ እነ​ዚ​ያም የሰ​ለ​ቱ​ትና ነፋስ የመ​ታ​ቸው ሰባቱ እሸ​ቶች እነ​ርሱ ራብ የሚ​ሆ​ን​ባ​ቸው ሰባት ዓመ​ታት ናቸው።</verse>
				<verse number="28">ለፈ​ር​ዖን የነ​ገ​ር​ሁት ነገር ይህ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ደ​ር​ገው ያለ​ውን ለፈ​ር​ዖን አሳ​የው።</verse>
				<verse number="29">እነሆ፥ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ እጅግ ጥጋብ የሚ​ሆ​ን​ባ​ቸው ሰባት ዓመ​ታት ይመ​ጣሉ፤</verse>
				<verse number="30">ደግ​ሞም ከዚህ በኋላ ሰባት የራብ ዓመት ይመ​ጣል፤ በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ የነ​በ​ረ​ው​ንም ጥጋብ ሁሉ ይረ​ሱ​ታል፤ ራብም ምድ​ርን ሁሉ ያጠ​ፋል፤</verse>
				<verse number="31">በኋ​ላም ከሚ​ሆ​ነው ከዚያ ራብ የተ​ነሣ በም​ድር የሆ​ነው ጥጋብ አይ​ታ​ወ​ቅም፤ እጅግ ጽኑ ይሆ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="32">ሕል​ሙም ለፈ​ር​ዖን ደጋ​ግሞ መታ​የቱ ነገሩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ቈ​ረጠ ስለ​ሆነ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፈጥኖ ያደ​ር​ገ​ዋል።</verse>
				<verse number="33">አሁ​ንም ብል​ህና ዐዋቂ ሰውን ለአ​ንተ ፈልግ፤ በግ​ብፅ ምድር ላይም ሹመው።</verse>
				<verse number="34">ፈር​ዖን በግ​ብፅ ምድር ላይ ሹሞ​ችን ይሹም፤ በሰ​ባ​ቱም የጥ​ጋብ ዓመ​ታት ከሚ​ገ​ኘው ፍሬ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ከአ​ም​ስት እጅ አን​ደ​ኛ​ውን ይው​ሰድ።</verse>
				<verse number="35">የሚ​መ​ጡ​ትን የመ​ል​ካ​ሞ​ቹን ሰባት ዓመ​ታት እህ​ላ​ቸ​ውን ያከ​ማቹ፤ ስን​ዴ​ው​ንም ከፈ​ር​ዖን እጅ በታች ያኑሩ፤ እህ​ሎ​ችም በከ​ተ​ሞች ይጠ​በቁ።</verse>
				<verse number="36">በግ​ብፅ ምድር ስለ​ሚ​ሆ​ነው ስለ ሰባቱ ዓመ​ታት ራብ እህሉ ለሀ​ገሩ ሁሉ ተጠ​ብቆ ይኑር፥ ምድ​ሪ​ቱም በራብ አት​ጠ​ፋም።”</verse>
				<verse number="37">ነገ​ሩም ፈር​ዖ​ን​ንና ሰዎ​ቹን ሁሉ ደስ አሰ​ኛ​ቸው፤</verse>
				<verse number="38">ፈር​ዖ​ንም ሎሌ​ዎ​ቹን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በውኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ያለ​በ​ትን እን​ደ​ዚህ ያለ ሰውን እና​ገ​ኛ​ለን?”</verse>
				<verse number="39">ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ሁሉ ገል​ጦ​ል​ሃ​ልና ከአ​ንተ ይልቅ ብል​ህና ዐዋቂ ሰው የለም።</verse>
				<verse number="40">አንተ በቤቴ ላይ ተሾም፤ ሕዝ​ቤም ሁሉ ለቃ​ልህ ይታ​ዘዝ፤ እኔም ከዙ​ፋኔ በቀር ከአ​ንተ የም​በ​ል​ጥ​በት የለም።”</verse>
				<verse number="41">ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን፥ “በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾም​ሁህ” አለው።</verse>
				<verse number="42">ፈር​ዖን ቀለ​በ​ቱን ከእጁ አወ​ለቀ፤ በዮ​ሴ​ፍም እጅ አደ​ረ​ገው፤ የነጭ ሐር ልብ​ስ​ንም አለ​በ​ሰው፤ በአ​ን​ገ​ቱም የወ​ርቅ ዝር​ግ​ፍን አደ​ረ​ገ​ለት፤</verse>
				<verse number="43">የእ​ር​ሱም በም​ት​ሆን በሁ​ለ​ተ​ኛ​ይቱ ሰረ​ገላ አስ​ቀ​መ​ጠው፤ ስገዱ እያ​ለም በፊት በፊቱ አዋጅ ነጋሪ እን​ዲ​ሄድ አደ​ረገ፤ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ላይም ሾመው።</verse>
				<verse number="44">ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን አለው፥ “እኔ ራሴ ፈር​ዖን ነኝ፤ በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ ያለ አንተ ማንም እጁን አያ​ንሣ።”</verse>
				<verse number="45">ፈር​ዖ​ንም የዮ​ሴ​ፍን ስም “እስ​ፍ​ን​ቶ​ፎ​ኔህ” ብሎ ጠራው፤ የሄ​ል​ዮቱ ከተማ ካህን የጴ​ጤ​ፌራ ልጅ የም​ት​ሆን አስ​ኔ​ት​ንም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠው።</verse>
				<verse number="46">ዮሴ​ፍም በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድ​ሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴ​ፍም ከፈ​ር​ዖን ፊት ወጣ፤ የግ​ብፅ ምድ​ር​ንም ሁሉ ዞረ።</verse>
				<verse number="47">በሰ​ባ​ቱም የጥ​ጋብ ዓመ​ታት ግብፅ ያስ​ገ​ኘ​ችው እህል ሁሉ ክምር ሆነ።</verse>
				<verse number="48">በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ያለ​ውን የሰ​ባ​ቱን የጥ​ጋብ ዓመ​ታት እህል ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ እህ​ል​ንም በከ​ተ​ሞቹ አደ​ለበ፤ በየ​ከ​ተ​ማ​ይ​ቱም ዙሪያ ያለ​ውን የእ​ር​ሻ​ውን እህል ሁሉ በዚ​ያው ከተተ።</verse>
				<verse number="49">ዮሴ​ፍም እንደ ባሕር አሸዋ እጅግ ብዙ የሆነ ስን​ዴን አከ​ማቸ፤ መስ​ፈር እስ​ኪ​ሳ​ና​ቸው ድረስ፤ ሊሰ​ፈር አል​ተ​ቻ​ለ​ምና።</verse>
				<verse number="50">ለዮ​ሴ​ፍም የሄ​ል​ዮቱ ከተማ ካህን የጴ​ጤ​ፌራ ልጅ አስ​ኔት የወ​ለ​ደ​ች​ለት ሁለት ልጆች የራብ ዘመን ገና ሳይ​መጣ ተወ​ለ​ዱ​ለት።</verse>
				<verse number="51">ዮሴ​ፍም የበ​ኵር ልጁን ስም ምናሴ ብሎ ጠራው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መከ​ራ​ዬን ሁሉ የአ​ባ​ቴ​ንም ቤት እን​ድ​ረሳ አደ​ረ​ገኝ፤”</verse>
				<verse number="52">የሁ​ለ​ተ​ኛ​ው​ንም ስም ኤፍ​ሬም ብሎ ጠራው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ከ​ራዬ ሀገር አብ​ዝ​ቶ​ኛ​ልና።”</verse>
				<verse number="53">በግ​ብፅ ምድር የነ​በ​ረ​ውም ሰባቱ የጥ​ጋብ ዓመት አለፈ፤</verse>
				<verse number="54">ዮሴ​ፍም እንደ ተና​ገረ ሰባቱ የራብ ዓመት መም​ጣት ጀመረ። በየ​ሀ​ገ​ሩም ሁሉ ራብ ሆነ፤ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ግን እህል ነበረ።</verse>
				<verse number="55">የግ​ብፅ ምድ​ርም ሁሉ ተራበ፤ ሕዝ​ቡም ስለ እህል ወደ ፈር​ዖን ጮኸ፤ ፈር​ዖ​ንም የግ​ብፅ ሰዎ​ችን ሁሉ፥ “ወደ ዮሴፍ ሂዱ፤ እርሱ ያላ​ች​ሁ​ንም ሁሉ አድ​ርጉ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="56">በም​ድ​ርም ሁሉ ላይ ራብ ሆነ፤ ዮሴ​ፍም እህል ያለ​በ​ትን ጎተራ ሁሉ ከፍቶ ለግ​ብፅ ሰዎች ሁሉ ይሸጥ ነበር።</verse>
				<verse number="57">ሀገ​ሮ​ችም ሁሉ ከዮ​ሴፍ እህል ይገዙ ዘንድ ወደ ግብፅ ወጡ፤ በም​ድር ሁሉ ራብ እጅግ ጸንቶ ነበ​ርና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="42">
				<verse number="1">ያዕ​ቆ​ብም በግ​ብፅ የሚ​ሸ​መት እህል እን​ዳለ ሰማ፤ ልጆ​ቹ​ንም፥ “ለምን ትተ​ክ​ዛ​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነሆ፥ እህል በግ​ብፅ እን​ዳለ ሰም​ቼ​አ​ለሁ፤ ወደ​ዚያ ውረዱ፤ እን​ድ​ን​ድ​ንና በራብ እን​ዳ​ን​ሞ​ትም ከዚያ ሸም​ቱ​ልን።”</verse>
				<verse number="3">የዮ​ሴ​ፍም ዐሥሩ ወን​ድ​ሞቹ እህ​ልን ከግ​ብፅ ይሸ​ምቱ ዘንድ ወረዱ፤</verse>
				<verse number="4">የዮ​ሴ​ፍን ወን​ድም ብን​ያ​ምን ግን ያዕ​ቆብ ከወ​ን​ድ​ሞቹ ጋር አል​ሰ​ደ​ደ​ውም፥ “ምና​ል​ባት ክፉ እን​ዳ​ያ​ገ​ኘው” ብሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="5">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለእ​ህል ሸመታ ከመ​ጡት ጋር ገቡ፤ በከ​ነ​ዓን ሀገር ራብ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="6">ዮሴ​ፍም በግ​ብፅ ምድር ላይ ገዥ ነበረ፤ እር​ሱም ለም​ድር ሕዝብ ሁሉ እህል ይሸጥ ነበር፤ የዮ​ሴ​ፍም ወን​ድ​ሞች በመጡ ጊዜ በም​ድር ላይ በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ሰገ​ዱ​ለት።</verse>
				<verse number="7">ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን በአ​ያ​ቸው ጊዜ ዐወ​ቃ​ቸው፤ እን​ደ​ማ​ያ​ው​ቃ​ቸ​ውም ሆነ፤ ክፉ ቃል​ንም ተና​ገ​ራ​ቸው፥ “እና​ንተ ከወ​ዴት መጣ​ችሁ?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “ከከ​ነ​ዓን ምድር እህል ልን​ሸ​ምት የመ​ጣን ነን” አሉት።</verse>
				<verse number="8">ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን ዐወ​ቃ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን አላ​ወ​ቁ​ትም፤ ዮሴ​ፍም አይ​ቶት የነ​በ​ረ​ውን ሕልም ዐሰበ።</verse>
				<verse number="9">እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰላ​ዮች ናችሁ ፤ የሀ​ገ​ሩን ሁኔታ ልታዩ መጥ​ታ​ች​ኋል።”</verse>
				<verse number="10">እነ​ር​ሱም አሉት፥ “ጌታ ሆይ፥ አይ​ደ​ለም፤ ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህስ ስንዴ ሊገዙ መጥ​ተ​ዋል፤</verse>
				<verse number="11">እኛ ሁላ​ችን የአ​ንድ ሰው ልጆች ነን፤ እኛ የሰ​ላም ሰዎች ነን፤ ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህስ ሰላ​ዮች አይ​ደ​ሉም።”</verse>
				<verse number="12">እር​ሱም አላ​ቸው፥ “አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን እና​ንተ ሰላ​ዮች ናችሁ፤ የሀ​ገ​ሩ​ንም ሁኔታ ልታዩ መጥ​ታ​ች​ኋል።”</verse>
				<verse number="13">እነ​ር​ሱም አሉ፥ “ባሪ​ያ​ዎ​ችህ በከ​ነ​ዓን ምድር የም​ን​ኖር ዐሥራ ሁለት ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች ነን፤ ታና​ሹም እነሆ ዛሬ ከአ​ባ​ታ​ችን ጋር ነው፤ ሌላ​ውም ሞቶ​አል።”</verse>
				<verse number="14">ዮሴ​ፍም አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰላ​ዮች ናችሁ ብዬ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​አ​ች​ሁም ይህ ነው፤ በዚህ ትታ​ወ​ቃ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="15">ታናሽ ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ከአ​ላ​መ​ጣ​ችሁ በቀር ‘የፈ​ር​ዖ​ንን ሕይ​ወት!’ ከዚህ አት​ወ​ጡም።</verse>
				<verse number="16">ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ያመጣ ዘንድ ከእ​ና​ንተ አን​ዱን ላኩ፤ እና​ንተ ግን እው​ነ​ትን የም​ት​ና​ገሩ ከሆነ ወይም ከአ​ል​ሆነ ነገ​ራ​ችሁ እስ​ኪ​ታ​ወቅ ድረስ ከዚህ ተቀ​መጡ፤ ይህ ከአ​ል​ሆነ ‘የፈ​ር​ዖ​ንን ሕይ​ወት!’ ሰላ​ዮች ናችሁ።”</verse>
				<verse number="17">ሦስት ቀን ያህ​ልም በግ​ዞት ቤት ጨመ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ዮሴፍ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ትድኑ ዘንድ ይህን አድ​ርጉ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እፈ​ራ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="19">እና​ንተ ሰላ​ማ​ው​ያን ከሆ​ና​ችሁ ከእ​ና​ንተ አንዱ ወን​ድ​ማ​ችሁ በግ​ዞት ቤት ይታ​ሰር፤ እና​ንተ ግን ሂዱ፤ የሸ​መ​ታ​ች​ሁ​ትን እህ​ልም ውሰዱ፤</verse>
				<verse number="20">ታና​ሹ​ንም ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ወደ እኔ አምጡ፤ ነገ​ራ​ችሁ የታ​መነ ይሆ​ና​ልና፤ ይህ ከአ​ል​ሆነ ግን ትሞ​ታ​ላ​ችሁ።” እን​ዲ​ህም አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="21">እነ​ር​ሱም እርስ በር​ሳ​ቸው እን​ዲህ ተባ​ባሉ፥ “በእ​ው​ነት ወን​ድ​ማ​ች​ንን በድ​ለ​ናል፤ እኛን በመ​ማ​ጠን ነፍሱ ስት​ጨ​ነቅ አይ​ተን አል​ሰ​ማ​ነ​ው​ምና፤ ስለ​ዚህ ይህ መከራ መጣ​ብን።”</verse>
				<verse number="22">ሮቤ​ልም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ብላ​ቴ​ና​ውን አት​በ​ድሉ ብዬ​አ​ችሁ አል​ነ​በ​ረ​ምን? እኔ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም፤ ስለ​ዚህ እነሆ፥ አሁን ደሙ ይፈ​ላ​ለ​ጋ​ች​ኋል።”</verse>
				<verse number="23">እነ​ር​ሱም ዮሴፍ ነገ​ራ​ቸ​ውን እን​ደ​ሚ​ሰ​ማ​ባ​ቸው አላ​ወ​ቁም፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አስ​ተ​ር​ጓሚ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="24">ዮሴ​ፍም ከእ​ነ​ርሱ ዘወር ብሎ አለ​ቀሰ፤ ደግ​ሞም ወደ እነ​ርሱ ተመ​ልሶ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ስም​ዖ​ን​ንም ከእ​ነ​ርሱ ለይቶ ወስዶ በፊ​ታ​ቸው አሰ​ረው።</verse>
				<verse number="25">ዮሴ​ፍም ዓይ​በ​ታ​ቸ​ውን እህል ይሞ​ሉት ዘንድ አዘዘ፤ የየ​ራ​ሳ​ቸ​ው​ንም ብር በየ​ዓ​ይ​በ​ታ​ቸው ይመ​ል​ሱት ዘንድ፥ ደግ​ሞም የመ​ን​ገድ ስንቅ ይሰ​ጡ​አ​ቸው ዘንድ አዘዘ። እን​ዲ​ህም አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="26">እነ​ር​ሱም እህ​ሉን በአ​ህ​ዮ​ቻ​ቸው ላይ ጫኑ፤ ከዚ​ያም ተነ​ሥ​ተው ሄዱ።</verse>
				<verse number="27">ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ በአ​ደ​ሩ​በት ስፍራ ለአ​ህ​ዮቹ ገፈ​ራን ይሰጥ ዘንድ ዓይ​በ​ቱን ፈታ፤ ብሩ​ንም በዓ​ይ​በቱ አፍ ተቋ​ጥሮ አገኘ።</verse>
				<verse number="28">ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ “ብሬ ተመ​ለ​ሰ​ች​ልኝ፤ እር​ስ​ዋም በዓ​ይ​በቴ አፍ እነ​ኋት” አላ​ቸው። ልባ​ቸ​ውም ደነ​ገጠ፤ እየ​ታ​ወ​ኩም እርስ በር​ሳ​ቸው ተባ​ባሉ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ረ​ገ​ብን ይህ ምን​ድን ነው?”</verse>
				<verse number="29">ወደ አባ​ታ​ቸ​ውም ወደ ያዕ​ቆብ ወደ ከነ​ዓን ምድር መጡ፤ የደ​ረ​ሰ​ባ​ቸ​ው​ንም ነገር ሁሉ እን​ዲህ ብለው አወሩ፦</verse>
				<verse number="30">“የሀ​ገሩ ጌታ የሆ​ነው ሰው በክፉ ንግ​ግር ተና​ገ​ረን፤ የም​ድ​ሪ​ቱም ሰላ​ዮች እን​ደ​ሆን አድ​ርጎ ወደ እስር ቤት አስ​ገ​ባን።”</verse>
				<verse number="31">እኛም እን​ዲህ አል​ነው፥ “ሰላ​ማ​ው​ያን ሰዎች ነን እንጂ ሰላ​ዮች አይ​ደ​ለ​ንም፤</verse>
				<verse number="32">እኛ የአ​ባ​ታ​ችን ልጆች ዐሥራ ሁለት ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች ነን፤ አንዱ ሞቶ​አል፤ ታና​ሹም በከ​ነ​ዓን ምድር ዛሬ ከአ​ባ​ታ​ችን ጋር አለ።</verse>
				<verse number="33">የሀ​ገ​ሩም ጌታ ያ ሰው እን​ዲህ አለን፦ ‘ሰላ​ማ​ው​ያን ሰዎች ከሆ​ና​ችሁ በዚህ ዐው​ቃ​ለሁ፤ አን​ደ​ኛ​ውን ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ከእኔ ጋር ተዉት፤ ለቤ​ታ​ች​ሁም የሸ​መ​ታ​ች​ሁ​ትን እህል ይዛ​ችሁ ሂዱ፤</verse>
				<verse number="34">ታና​ሹ​ንም ወን​ድ​ማ​ች​ሁን አም​ጡ​ልኝ፤ ሰላ​ማ​ው​ያን እንጂ ሰላ​ዮች አለ​መ​ሆ​ና​ች​ሁ​ንም በዚህ ዐው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ወን​ድ​ማ​ች​ሁ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም በሀ​ገ​ራ​ችን ትነ​ግ​ዳ​ላ​ችሁ።’ ”</verse>
				<verse number="35">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዓይ​በ​ታ​ቸ​ውን በፈቱ ጊዜ እነሆ፥ ከእ​ነ​ርሱ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ብራ​ቸ​ውን በዓ​ይ​በ​ታ​ቸው ተቋ​ጥሮ አገ​ኙት፤ እነ​ር​ሱም አባ​ታ​ቸ​ውም የተ​ቋ​ጠረ ብራ​ቸ​ውን አይ​ተው ፈሩ።</verse>
				<verse number="36">አባ​ታ​ቸው ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ልጅ አልባ አስ​ቀ​ራ​ች​ሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስም​ዖ​ንም የለም፤ ብን​ያ​ም​ንም ትወ​ስ​ዱ​ብ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ይህ ሁሉ በእኔ ላይ ደረሰ።”</verse>
				<verse number="37">ሮቤ​ልም አባ​ቱን አለው፥ “ወደ አንተ መልሼ ያላ​መ​ጣ​ሁት እን​ደ​ሆነ ሁለ​ቱን ልጆ​ችን ግደል፤ ልጅ​ህን በእጄ ስጠኝ፤ እኔም ወደ አንተ እመ​ል​ሰ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="38">እር​ሱም አለ፥ “ልጄ ከእ​ና​ንተ ጋር አይ​ወ​ር​ድም፤ ወን​ድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀር​ቶ​አ​ልና፤ በም​ት​ሄ​ዱ​በት መን​ገድ ምና​ል​ባት ክፉ ነገር ቢያ​ገ​ኘው ሽም​ግ​ል​ና​ዬን በኀ​ዘን ወደ መቃ​ብር ታወ​ር​ዱ​ታ​ላ​ችሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="43">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ ራብ በሀ​ገር ላይ ጸና።</verse>
				<verse number="2">ከግ​ብ​ፅም ያመ​ጡ​ትን እህል በል​ተው ከፈ​ጸሙ በኋላ አባ​ታ​ቸው፥ “እን​ደ​ገና ሂዱ፤ ጥቂት እህል ሸም​ታ​ችሁ አም​ጡ​ልን” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ይሁ​ዳም እን​ዲህ አለው፥ “የሀ​ገሩ ጌታ ያ ሰው፦ ‘ወን​ድ​ማ​ችሁ ከእ​ና​ንተ ጋር ከአ​ል​መጣ ፊቴን አታ​ዩም’ ብሎ በም​ስ​ክር ፊት አዳ​ኝ​ቶ​ብ​ናል።</verse>
				<verse number="4">ወን​ድ​ማ​ች​ንን ከእኛ ጋር ብት​ል​ከው እን​ወ​ር​ዳ​ለን፤ እህ​ልም እን​ሸ​ም​ት​ል​ሃ​ልን፤</verse>
				<verse number="5">ወን​ድ​ማ​ች​ንን ከእኛ ጋር ባት​ል​ከው ግን አን​ሄ​ድም፤ ያ ሰው ‘ታናሽ ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ከእ​ና​ንተ ጋር ካላ​መ​ጣ​ችሁ ፊቴን አታ​ዩም’ ብሎ​ና​ልና።”</verse>
				<verse number="6">እስ​ራ​ኤ​ልም አላ​ቸው፥ “በእኔ ላይ ያደ​ረ​ጋ​ች​ኋት ይህች ክፋት ምን​ድን ናት? በዚ​ያ​ውስ ላይ ሌላ ወን​ድም አለን ብላ​ችሁ ለምን ነገ​ራ​ች​ሁት?”</verse>
				<verse number="7">እነ​ር​ሱም አሉ፥ “ያ ሰው ስለ እኛና ስለ ትው​ል​ዳ​ችን ፈጽሞ ጠየ​ቀን፤ እን​ዲ​ህም አለን፦ ‘ሽማ​ግ​ሌው አባ​ታ​ችሁ ገና በሕ​ይ​ወት ነው? ወን​ድ​ምስ አላ​ች​ሁን?’ እኛም እን​ደ​ዚሁ እንደ ጠየ​ቀን መለ​ስ​ን​ለት፤ በውኑ፦ ‘ወን​ድ​ማ​ች​ሁን አምጡ’ እን​ዲ​ለን እና​ውቅ ነበ​ርን?”</verse>
				<verse number="8">ይሁ​ዳም አባ​ቱን እስ​ራ​ኤ​ልን አለው፥ “እኛና አንተ ልጆ​ቻ​ች​ንም ደግሞ እን​ድ​ን​ድን፥ እን​ዳ​ን​ሞ​ትም ብላ​ቴ​ና​ውን ከእኔ ጋር ላከው፤ እኛም ተነ​ሥ​ተን እን​ሄ​ዳ​ለን።</verse>
				<verse number="9">እኔ እዋ​ሳ​ለሁ፤ ከእጄ ትሻ​ዋ​ለህ፤ ወደ አንተ ባላ​መ​ጣው፥ በፊ​ት​ህም ባላ​ቆ​መው፥ በዘ​መ​ናት ሁሉ አን​ተን የበ​ደ​ል​ሁህ ልሁን።</verse>
				<verse number="10">ባን​ዘ​ገ​ይስ ኖሮ አሁን ሁለ​ተኛ ጊዜ በተ​መ​ለ​ስን ነበር።”</verse>
				<verse number="11">አባ​ታ​ቸው እስ​ራ​ኤ​ልም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ነገሩ እን​ዲህ ከሆ​ነስ ይህን አድ​ርጉ ፤ ከም​ድሩ ፍሬ በዓ​ይ​በ​ታ​ችሁ ይዛ​ችሁ ሂዱ፤ ለዚ​ያም ሰው እጅ መንሻ፥ ጥቂት በለ​ሳን፥ ጥቂት ማር፥ ሽቱ፥ ዕጣን፥ ተምር፥ ለውዝ ውሰዱ።</verse>
				<verse number="12">ብሩን በአ​ጠ​ፌታ አድ​ር​ጋ​ችሁ በእ​ጃ​ችሁ ውሰዱ፤ በዓ​ይ​በ​ታ​ች​ሁም አፍ የተ​መ​ለ​ሰ​ውን ብር መል​ሳ​ችሁ ውሰዱ፤ ምና​ል​ባት ባለ​ማ​ወቅ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="13">ወን​ድ​ማ​ች​ሁ​ንም ከእ​ና​ንተ ጋር ውሰዱ፤ ተነ​ሥ​ታ​ች​ሁም ወደ​ዚያ ሰው ውረዱ።</verse>
				<verse number="14">አም​ላ​ኬም በዚያ ሰው ፊት ሞገ​ስን ይስ​ጣ​ችሁ፤ ያን ወን​ድ​ማ​ች​ሁ​ንና ብን​ያ​ም​ንም ይመ​ል​ስ​ላ​ችሁ፤ እኔም ልጆ​ችን እን​ዳ​ጣሁ አጣሁ።”</verse>
				<verse number="15">ሰዎ​ቹም በእ​ጃ​ቸው ያችን እጅ መን​ሻና ብራ​ቸ​ውን በእ​ጥፍ፥ ብን​ያ​ም​ንም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ወሰዱ፤ ተነ​ሥ​ተ​ውም ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዮ​ሴ​ፍም ፊት ቆሙ፤ ሰገ​ዱ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="16">ዮሴ​ፍም ብን​ያ​ምን ከእ​ነ​ርሱ ጋር በአ​የው ጊዜ የቤ​ቱን አዛዥ እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “እነ​ዚ​ያን ሰዎች ወደ ቤት አስ​ገ​ባ​ቸው፤ እር​ድም እረድ፤ አዘ​ጋ​ጅም፤ እነ​ዚያ ሰዎች በእ​ኩለ ቀን ከእኔ ጋር ይበ​ላ​ሉና።”</verse>
				<verse number="17">ያም ሰው ዮሴፍ እን​ዳ​ለው አደ​ረገ፤ ሰዎ​ቹ​ንም ወደ ዮሴፍ ቤት አስ​ገባ።</verse>
				<verse number="18">እነ​ዚ​ያም ሰዎች ወደ ዮሴፍ ቤት እንደ ገቡ በአዩ ጊዜ እን​ዲህ አሉ፥ “በዓ​ይ​በ​ታ​ችን ቀድሞ ስለ ተመ​ለ​ሰው ብር ሊተ​ነ​ኰ​ሉ​ብን፥ ሊወ​ድ​ቁ​ብ​ንም፥ እኛ​ንም በባ​ር​ነት ሊገ​ዙን፥ አህ​ዮ​ቻ​ች​ን​ንም ሊወ​ስዱ ወደ​ዚህ አስ​ገ​ቡን።”</verse>
				<verse number="19">ወደ ዮሴፍ ቤት አዛ​ዥም ቀረቡ፤ በቤ​ቱም ደጅ ተና​ገ​ሩት፤</verse>
				<verse number="20">እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ጌታ ሆይ፥ እን​ማ​ል​ድ​ሃ​ለን፤ ቀድሞ እህ​ልን ልን​ሸ​ምት ወር​ደን ነበር፤</verse>
				<verse number="21">እን​ዲ​ህም ሆነ፥ ወደ​ም​ና​ድ​ር​በ​ትም ስፍራ በደ​ረ​ስን ጊዜ ዓይ​በ​ታ​ች​ንን ከፈ​ትን፤ እነ​ሆም፥ የየ​አ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ብር በየ​ዓ​ይ​በቱ አፍ ነበር፤ አሁ​ንም ብራ​ች​ንን በእ​ጃ​ችን እንደ ሚዛኑ መለ​ስ​ነው።</verse>
				<verse number="22">እህል እን​ሸ​ም​ት​በት ዘንድ ሌላም ብር በእ​ጃ​ችን አመ​ጣን፤ ብራ​ች​ን​ንም በዓ​ይ​በ​ታ​ችን ማን እንደ ጨመ​ረው አና​ው​ቅም።”</verse>
				<verse number="23">እር​ሱም አላ​ቸው፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን፥ አት​ፍሩ፤ አም​ላ​ካ​ችሁ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ በዓ​ይ​በ​ታ​ችሁ የተ​ሰ​ወረ ገን​ዘብ ሰጣ​ችሁ፤ ብራ​ች​ሁ​ንስ መዝኜ ተቀ​ብ​ያ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="24">ስም​ዖ​ን​ንም ወደ እነ​ርሱ አወ​ጣ​ላ​ቸው። እግ​ራ​ቸ​ው​ንም ሊታ​ጠቡ ውኃ አመ​ጣ​ላ​ቸው፤ ለአ​ህ​ዮ​ቻ​ቸ​ውም ገፈራ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">ዮሴ​ፍም በእ​ኩለ ቀን እስ​ኪ​ገባ ድረስ እነ​ርሱ እጅ መን​ሻ​ቸ​ውን አዘ​ጋጁ፤ ከዚያ ምሳ እን​ደ​ሚ​በሉ ሰም​ተ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="26">ዮሴ​ፍም ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ በእ​ጃ​ቸው ያለ​ውን እጅ መንሻ በቤት ውስጥ አቀ​ረ​ቡ​ለት፤ ወደ ምድ​ርም በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወድ​ቀው ሰገ​ዱ​ለት።</verse>
				<verse number="27">እር​ሱም ደኅ​ን​ነ​ታ​ቸ​ውን ጠየ​ቃ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “የነ​ገ​ራ​ች​ሁኝ ሽማ​ግሌ አባ​ታ​ችሁ ደኅና ነውን? ገና በሕ​ይ​ወት አለን?”</verse>
				<verse number="28">እነ​ር​ሱም አሉት፥ “ባሪ​ያህ ሽማ​ግ​ሌው አባ​ታ​ችን ደኅና ነው፤ ገና በሕ​ይ​ወት አለ።” ዮሴ​ፍም አለ፥ “ሰው​የው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የባ​ረ​ከው ነው።” ራሳ​ቸ​ው​ንም ዝቅ አድ​ር​ገው ሰገ​ዱ​ለት።</verse>
				<verse number="29">ዮሴ​ፍም ዐይ​ኑን አን​ሥቶ የእ​ና​ቱን ልጅ ወን​ድሙ ብን​ያ​ምን አየው፤ እር​ሱም አለ፥ “ወደ አንተ እና​መ​ጣ​ዋ​ለን ብላ​ችሁ የነ​ገ​ራ​ች​ሁኝ ታናሽ ወን​ድ​ማ​ችሁ ይህ ነውን?” እነ​ር​ሱም፥ “አዎን” አሉት። እን​ዲ​ህም አለው፥ “ልጄ ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ይበ​ልህ።”</verse>
				<verse number="30">ዮሴ​ፍም ታወከ፤ አን​ጀቱ ወን​ድ​ሙን ናፍ​ቆ​ታ​ልና፤ ሊያ​ለ​ቅ​ስም ወደደ፤ ወደ እል​ፍ​ኙም ገብቶ በዚያ አለ​ቀሰ።</verse>
				<verse number="31">ፊቱ​ንም ታጥቦ ተጽ​ና​ን​ቶም ወጣ። “እን​ጀራ አቅ​ር​ቡ​ልን” አለ።</verse>
				<verse number="32">ለእ​ር​ሱም ለብ​ቻው አቀ​ረቡ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም ለብ​ቻ​ቸው፤ ከእ​ርሱ ጋር ለሚ​በ​ሉት ለግ​ብፅ ሰዎ​ችም ለብ​ቻ​ቸው፤ የግ​ብፅ ሰዎች ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ጋር መብ​ላት አይ​ች​ሉ​ምና፥ ይህ ለግ​ብፅ ሰዎች እንደ መር​ከስ ነውና።</verse>
				<verse number="33">በፊ​ቱም በኵሩ እንደ ታላ​ቅ​ነቱ፥ ታና​ሹም እንደ ታና​ሽ​ነቱ ተቀ​መጡ፤ እነ​ር​ሱም እርስ በር​ሳ​ቸው በመ​ደ​ነቅ ተያዩ።</verse>
				<verse number="34">በፊ​ቱም ከአ​ለው መብል ፈን​ታ​ቸ​ውን አቀ​ረ​በ​ላ​ቸው፤ የብ​ን​ያ​ምም ፈንታ ከሁሉ አም​ስት እጅ የሚ​በ​ልጥ ነበረ። እነ​ር​ሱም በሉ፤ ጠጡም፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ደስ አላ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="44">
				<verse number="1">ዮሴ​ፍም የቤ​ቱን አዛዥ እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “የእ​ነ​ዚህ ሰዎች ዓይ​በ​ቶ​ቻ​ቸው መያዝ የሚ​ች​ሉ​ትን ያህል እህል ሙላ​ላ​ቸው፤ የሁ​ሉ​ንም ብር በየ​ዓ​ይ​በ​ታ​ቸው አፍ ጨም​ረው፤</verse>
				<verse number="2">በታ​ና​ሹም ዓይ​በት አፍ የብ​ሩን ጽዋ​ዬ​ንና የእ​ህ​ሉን ዋጋ ጨም​ረው።” እር​ሱም ዮሴፍ እን​ዳ​ለው አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="3">ነግህ በሆነ ጊዜም ሰዎቹ አህ​ዮ​ቻ​ቸ​ውን ይዘው ይሄዱ ዘንድ አሰ​ና​በ​ታ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ወጥ​ተው ገና ሳይ​ርቁ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እን​ዲህ አለ፥ “ተነ​ሥ​ተህ ሰዎ​ቹን ተከ​ት​ለህ ያዛ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ በመ​ል​ካሙ ፈንታ ስለ​ምን ክፉን መለ​ሳ​ችሁ?</verse>
				<verse number="5">ጌታዬ የሚ​ጠ​ጣ​በ​ትን፥ ምስ​ጢ​ር​ንም የሚ​ያ​ው​ቅ​በ​ትን የብር ጽዋ ለምን ሰረ​ቃ​ችሁ? ባደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ነገር በደ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="6">እር​ሱም ሂዶ አገ​ኛ​ቸው፤ “ለምን እን​ዲህ አደ​ረ​ጋ​ችሁ? ስለ አደ​ረ​ግ​ሁ​ላ​ችሁ መል​ካም ነገር ለምን ክፉ ትከ​ፍ​ሉ​ኛ​ላ​ችሁ? የጌ​ታ​ዬ​ንስ የብር ጽዋ ለምን ሰረ​ቃ​ች​ሁኝ?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">እነ​ር​ሱም አሉት፥ “ጌታ​ችን እን​ደ​ዚህ ለምን ክፉ ትና​ገ​ራ​ለህ? ይህን ነገር ያደ​ር​ጉት ዘንድ ለባ​ሪ​ያ​ዎ​ችህ አግ​ባ​ባ​ቸው አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="8">በየ​ዓ​ይ​በ​ታ​ችን አፍ ያገ​ኘ​ነ​ውን ብር እን​ኳን ይዘን ከከ​ነ​ዓን ሀገር ወደ አንተ ተመ​ል​ሰ​ናል፤ ከጌ​ታ​ህስ ቤት ወርቅ ወይስ ብር እን​ዴት እን​ሰ​ር​ቃ​ለን?</verse>
				<verse number="9">አሁ​ንም ከባ​ሪ​ያ​ዎ​ችህ ጽዋው የተ​ገ​ኘ​በት እርሱ ይሙት፤ እኛም ደግሞ ለጌ​ታ​ችን አገ​ል​ጋ​ዮች እን​ሁን።”</verse>
				<verse number="10">እር​ሱም አለ፥ “አሁ​ንም እን​ዲሁ እንደ ነገ​ራ​ችሁ ይሁን፤ ጽዋው የተ​ገ​ኘ​በት እርሱ ለእኔ አገ​ል​ጋይ ይሁ​ነኝ፤ እና​ን​ተም ንጹ​ሓን ትሆ​ና​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="11">እየ​ራ​ሳ​ቸ​ውም ፈጥ​ነው ዓይ​በ​ታ​ቸ​ውን ወደ ምድር አወ​ረዱ፤ እየ​ራ​ሳ​ቸ​ውም ዓይ​በ​ታ​ቸ​ውን ፈቱ።</verse>
				<verse number="12">እር​ሱም ከታ​ላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ በረ​በ​ራ​ቸው፤ ጽዋ​ው​ንም በብ​ን​ያም ዓይ​በት ውስጥ አገ​ኘው።</verse>
				<verse number="13">ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ቀደዱ፤ ዓይ​በ​ታ​ቸ​ው​ንም በየ​አ​ህ​ዮ​ቻ​ቸው ጭነው ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="14">ይሁ​ዳም ከወ​ን​ድ​ሞቹ ጋር ወደ ዮሴፍ ገባ፤ እር​ሱም ገና ከዚ​ያው ነበረ፤ በፊ​ቱም በም​ድር ላይ ወደቁ።</verse>
				<verse number="15">ዮሴ​ፍም፥ “ይህ ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ነገር ምን​ድን ነው? እንደ እኔ ያለ ሰው ምሥ​ጢ​ርን እን​ዲ​ያ​ውቅ አታ​ው​ቁ​ምን?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">ይሁ​ዳም አለ፦ “ለጌ​ታ​ችን ምን እን​መ​ል​ሳ​ለን? ምንስ እን​ና​ገ​ራ​ለን? ወይስ በምን እን​ነ​ጻ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን ኀጢ​አት ገለጠ። እነሆ፥ እኛም ጽዋው ከእ​ርሱ ዘንድ የተ​ገ​ኘ​በ​ትም ደግሞ ለጌ​ታ​ችን አገ​ል​ጋ​ዮቹ ነን።”</verse>
				<verse number="17">ዮሴ​ፍም አላ​ቸው፥ “ይህን አደ​ርግ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ጽዋው የተ​ገ​ኘ​በት ሰው እርሱ አገ​ል​ጋይ ይሁ​ነኝ እንጂ፤ እና​ንተ ግን ወደ አባ​ታ​ችሁ በደ​ኅና ሂዱ።”</verse>
				<verse number="18">ይሁ​ዳም ወደ እርሱ ቀረበ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ በፊ​ትህ አን​ዲት ቃልን እን​ድ​ና​ገር እለ​ም​ና​ለሁ፤ እኔን አገ​ል​ጋ​ይ​ህን አት​ቈ​ጣኝ፤ አንተ ከፈ​ር​ዖን ቀጥ​ለህ ነህና።</verse>
				<verse number="19">ጌታዬ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን፦ አባት አላ​ች​ሁን? ወይስ ወን​ድም? ብለህ ጠየ​ቅ​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">እኛም ለጌ​ታዬ እን​ዲህ አልን፦ ሽማ​ግሌ አባት አለን፤ በሽ​ም​ግ​ል​ናው የወ​ለ​ደ​ውም ታናሽ ብላ​ቴና አለ፤ ወን​ድሙ ግን ሞተ፤ ለእ​ና​ቱም እርሱ ብቻ​ውን ቀረ፤ አባ​ቱም ይወ​ድ​ደ​ዋል።</verse>
				<verse number="21">አን​ተም ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ፦ ወደ እኔ አም​ጡት፤ እኔም እጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለሁ አልህ።</verse>
				<verse number="22">ጌታ​ዬ​ንም፦ ብላ​ቴ​ናው አባ​ቱን መተው አይ​ሆ​ን​ለ​ትም፤ የተ​ወው እንደ ሆነ አባቱ ይሞ​ታ​ልና አል​ንህ።</verse>
				<verse number="23">አንተ ጌታ​ች​ንም አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን፦ ታናሽ ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ከእ​ና​ንተ ጋር ከአ​ላ​መ​ጣ​ች​ሁት ዳግ​መኛ ፊቴን አታ​ዩም አል​ኸን።</verse>
				<verse number="24">ወደ ባሪ​ያህ ወደ አባ​ታ​ችን በተ​መ​ለ​ስን ጊዜም የጌ​ታ​ች​ንን ቃል ነገ​ር​ነው።</verse>
				<verse number="25">አባ​ታ​ች​ንም፦ ዳግ​መኛ ሄዳ​ችሁ ጥቂት እህል ሸም​ቱ​ልን አለን።</verse>
				<verse number="26">እኛም አል​ነው፦ ታናሹ ወን​ድ​ማ​ችን ከእኛ ጋር ካል​ሄደ መሄድ አን​ች​ልም፤ ታናሹ ወን​ድ​ማ​ችን ከእኛ ጋር ከሌለ የዚ​ያን ሰው ፊት ማየት አይ​ቻ​ለ​ን​ምና።</verse>
				<verse number="27">አገ​ል​ጋ​ይህ አባ​ታ​ች​ንም እን​ዲህ አለን፦ ሚስቴ ሁለት ወን​ዶች ልጆ​ችን እንደ ወለ​ደ​ች​ልኝ እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="28">አን​ዱም ከእኔ ወጣ፤ አውሬ በላው አላ​ች​ሁኝ፤ እስከ ዛሬም ገና አላ​የ​ሁ​ትም፤</verse>
				<verse number="29">ይህ​ንም ከእኔ ለይ​ታ​ችሁ ደግሞ ብት​ወ​ስ​ዱት በመ​ን​ገ​ድም ክፉ ቢያ​ገ​ኘው፥ እር​ጅ​ና​ዬን በኀ​ዘን ወደ መቃ​ብር ታወ​ር​ዱ​ታ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="30">አሁ​ንም እኛ ወደ አባ​ታ​ችን ወደ አገ​ል​ጋ​ይህ ብን​ሄድ፥ ብላ​ቴ​ና​ውም ከእኛ ጋር ከሌለ፥ ነፍሱ በብ​ላ​ቴ​ናው ነፍስ ታስ​ራ​ለ​ችና</verse>
				<verse number="31">ብላ​ቴ​ናው ከእኛ ጋር እን​ደ​ሌለ በአየ ጊዜ ይሞ​ታል፤ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህም የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን የአ​ባ​ታ​ች​ንን እር​ጅና በኀ​ዘን ወደ መቃ​ብር እና​ወ​ር​ዳ​ለን።</verse>
				<verse number="32">እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ በአ​ባቴ ዘንድ ስለ ብላ​ቴ​ናው እን​ዲህ ብዬ ተው​ሼ​አ​ለ​ሁና፦ እር​ሱ​ንስ ወደ አንተ መልሼ በፊ​ትህ ባላ​ቆ​መው በአ​ባቴ ዘንድ በዘ​መ​ናት ሁሉ ኀጢ​አ​ተኛ እሆ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="33">አሁ​ንም እኔ በብ​ላ​ቴ​ናው ፈንታ የጌ​ታዬ አገ​ል​ጋይ ሆኜ ልቀ​መጥ፤ ብላ​ቴ​ናው ግን ከወ​ን​ድ​ሞቹ ጋር ይሂድ።</verse>
				<verse number="34">አለ​ዚ​ያም ብላ​ቴ​ናው ከእኛ ጋር ከሌለ እኔ ወደ አባ​ታ​ችን እን​ዴት እሄ​ዳ​ለሁ? አባ​ታ​ች​ንን የሚ​ያ​ገ​ኘ​ውን መከራ እን​ዳ​ላይ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="45">
				<verse number="1">ዮሴ​ፍም በፊቱ ሰዎች ሁሉ ቆመው ሳሉ ሊታ​ገሥ አል​ተ​ቻ​ለ​ውም፥ “ሰዎ​ቹ​ንም ሁሉ ከፊቴ አስ​ወ​ጡ​ልኝ” ብሎ ተና​ገረ፤ ዮሴፍ ለወ​ን​ድ​ሞቹ ራሱን በገ​ለጠ ጊዜ በእ​ርሱ ዘንድ የቆመ ማንም አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="2">ቃሉ​ንም ከፍ አድ​ርጎ አለ​ቀሰ፤ የግ​ብፅ ሰዎ​ችም ሰሙ፤ በፈ​ር​ዖን ቤትም ተሰማ።</verse>
				<verse number="3">ዮሴ​ፍም ለወ​ን​ድ​ሞቹ፥ “እኔ ወን​ድ​ማ​ችሁ ዮሴፍ ነኝ፤ አባቴ እስከ አሁን በሕ​ይ​ወቱ ነውን?” አላ​ቸው። ወን​ድ​ሞ​ቹም ይመ​ል​ሱ​ለት ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ ደን​ግ​ጠው ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="4">ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን፥ “ወደ እኔ ቅረቡ” አላ​ቸው። ወደ እር​ሱም ቀረቡ። እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ወደ ግብፅ የሸ​ጣ​ች​ሁኝ እኔ ወን​ድ​ማ​ችሁ ዮሴፍ ነኝ።</verse>
				<verse number="5">አሁ​ንም ወደ​ዚህ ስለ​ሸ​ጣ​ች​ሁኝ አት​ፍሩ፤ አት​ቈ​ር​ቈ​ሩም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ይ​ወት ከእ​ና​ንተ በፊት ልኮ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="6">እነሆ፥ ይህ ሁለቱ ዓመት በም​ድር ላይ ራብ የሆ​ነ​በት ነውና፤ የማ​ይ​ታ​ረ​ስ​በ​ትና የማ​ይ​ታ​ጨ​ድ​በት አም​ስት ዓመት ገና አለ።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድር ላይ እን​ድ​ት​ድ​ኑና እን​ድ​ት​ተ​ርፉ እመ​ግ​ባ​ችሁ ዘንድ ከእ​ና​ንተ በፊት ላከኝ።</verse>
				<verse number="8">አሁ​ንም እና​ንተ ወደ​ዚህ የላ​ካ​ች​ሁኝ አይ​ደ​ላ​ች​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላከኝ እንጂ፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም እንደ አባት አደ​ረ​ገኝ፤ በቤ​ቱም ሁሉ ላይ ጌታ፥ በግ​ብፅ ምድ​ርም ሁሉ ላይ አለቃ አደ​ረ​ገኝ።</verse>
				<verse number="9">አሁ​ንም ፈጥ​ና​ችሁ ወደ አባቴ ሂዱ፤ እን​ዲ​ህም በሉት፦ ልጅህ ዮሴፍ የሚ​ለው ነገር ይህ ነው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ላይ ጌታ አደ​ረ​ገኝ፤ ወደ እኔ ና፤ በዚ​ያም አት​ዘ​ግይ፤</verse>
				<verse number="10">በዐ​ረብ በኩል በጌ​ሤም ምድ​ርም ትቀ​መ​ጣ​ለህ፤ ወደ እኔም ትቀ​ር​ባ​ለህ። አን​ተና ልጆ​ችህ የል​ጆ​ች​ህም ልጆች፥ በጎ​ች​ህና ላሞ​ችህ፥ የአ​ንተ የሆ​ነው ሁሉ፥</verse>
				<verse number="11">በዚ​ያም አን​ተና የቤ​ትህ ሰዎች የአ​ንተ የሆ​ነው ሁሉ እን​ዳ​ት​ቸ​ገሩ እመ​ግ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የራቡ ዘመን ገና አም​ስት ዓመት ቀር​ቶ​አ​ልና፤</verse>
				<verse number="12">እነ​ሆም፥ ለእ​ና​ንተ እኔ ራሴ በአፌ እንደ ተና​ገ​ር​ሁ​አ​ችሁ እና​ንተ በዐ​ይ​ኖ​ቻ​ችሁ አይ​ታ​ች​ኋል፤ ወን​ድሜ ብን​ያም በዐ​ዓ​ይ​ኖቹ አይ​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="13">ለአ​ባቴ በግ​ብፅ ምድር ያለ​ኝን ክብ​ሬን ሁሉ፥ በዐ​ይ​ኖ​ቻ​ችሁ ያያ​ች​ሁ​ት​ንም ሁሉ ንገ​ሩት፤ አባ​ቴ​ንም ወደ​ዚህ ፈጥ​ና​ችሁ አም​ጡት።”</verse>
				<verse number="14">የወ​ን​ድ​ሙን የብ​ን​ያ​ም​ንም አን​ገት አቅፎ አለ​ቀሰ፤ ብን​ያ​ምም በአ​ን​ገቱ ላይ አለ​ቀሰ።</verse>
				<verse number="15">ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ ሳማ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ አለ​ቀሰ፤ ከዚ​ያም በኋላ ወን​ድ​ሞቹ ከእ​ርሱ ጋር ተጨ​ዋ​ወቱ።</verse>
				<verse number="16">በፈ​ር​ዖ​ንም ቤት፥ “የዮ​ሴፍ ወን​ድ​ሞች መጡ” ተብሎ ወሬ ተሰማ፤ ፈር​ዖ​ንና ቤተ ሰቡም ሁሉ ደስ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን አለው፥ “ለወ​ን​ድ​ሞ​ችህ እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ይህን አድ​ርጉ፤ ዕቃ​ች​ሁን ጭና​ችሁ ወደ ከነ​ዓን ምድር ሂዱ፤</verse>
				<verse number="18">አባ​ታ​ች​ሁ​ንና ንብ​ረ​ታ​ች​ሁን ሁሉ ይዛ​ችሁ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም የግ​ብ​ፅን ምድር በረ​ከት ሁሉ እሰ​ጣ​ች​ሁ​አ​ለሁ፤ የም​ድ​ሪ​ቱ​ንም ድልብ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="19">አን​ተም ወን​ድ​ሞ​ች​ህን፦ እን​ዲህ አድ​ርጉ በላ​ቸው፤ ከግ​ብፅ ምድር ለሕ​ፃ​ኖ​ቻ​ችሁ፥ ለሴ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሰረ​ገ​ሎ​ችን ውሰዱ፤ አባ​ታ​ች​ሁ​ንም ይዛ​ችሁ ኑ፤</verse>
				<verse number="20">ለዕ​ቃ​ች​ሁም ዐይ​ና​ችሁ ለአ​የ​ውም ሁሉ አታ​ስቡ፤ የግ​ብፅ በረ​ከት ሁሉ ለእ​ና​ንተ ነውና።”</verse>
				<verse number="21">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም እንደ አዘ​ዛ​ቸው አደ​ረጉ፤ ዮሴ​ፍም የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን እንደ ነገ​ረው ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ለመ​ን​ገድ ስን​ቅን ሰጣ​ቸው፤</verse>
				<verse number="22">ለሁ​ሉም ሁለት ሁለት መለ​ወጫ ልብስ ሰጣ​ቸው፤ ለብ​ን​ያም ግን ሦስት መቶ ብርና አም​ስት መለ​ወጫ ልብስ ሰጠው።</verse>
				<verse number="23">ለአ​ባ​ቱም እን​ደ​ዚሁ ላከ፤ ከግ​ብፅ በረ​ከት ሁሉ የተ​ጫኑ ዐሥር አህ​ዮ​ችን፥ ደግ​ሞም በመ​ን​ገድ ለአ​ባቱ ስንቅ የተ​ጫኑ ዐሥር በቅ​ሎ​ዎ​ችን።</verse>
				<verse number="24">ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን አሰ​ና​በ​ታ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “በመ​ን​ገድ እርስ በር​ሳ​ችሁ አት​ጣሉ።”</verse>
				<verse number="25">እነ​ር​ሱም ከግ​ብፅ ሀገር ወጥ​ተው ሄዱ፤ ወደ ከነ​ዓ​ንም ምድር ወደ አባ​ታ​ቸው ወደ ያዕ​ቆብ ደረሱ።</verse>
				<verse number="26">እን​ዲ​ህም ብለው ነገ​ሩት፥ “ልጅህ ዮሴፍ በሕ​ይ​ወቱ ነው፤ እር​ሱም በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ላይ ገዥ ሆኖ​አል።” ያዕ​ቆ​ብም ልቡ ደነ​ገጠ፤ አላ​መ​ና​ቸ​ው​ምም፤</verse>
				<verse number="27">እነ​ር​ሱም ዮሴፍ ያላ​ቸ​ውን፥ የተ​ና​ገ​ራ​ቸ​ው​ንም ነገር ሁሉ ነገ​ሩት፤ ይወ​ስ​ዱት ዘንድ ዮሴፍ የላ​ካ​ቸ​ውን ሰረ​ገ​ሎች በአየ ጊዜ የአ​ባ​ታ​ቸው የያ​ዕ​ቆብ ልቡ፥ መን​ፈ​ሱም ታደሰ።</verse>
				<verse number="28">እስ​ራ​ኤ​ልም፥ “ልጄ ዮሴፍ ገና በሕ​ይ​ወት ከሆነ ይህ ለእኔ ታላቅ ነገር ነው፤ ሳል​ሞት እን​ዳ​የው እሄ​ዳ​ለሁ” አለ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="46">
				<verse number="1">እስ​ራ​ኤ​ልም ለእ​ርሱ ያለ​ውን ሁሉ ይዞ ተነሣ፤ ወደ ዐዘ​ቅተ መሐ​ላም መጣ፤ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም ለአ​ባቱ ለይ​ስ​ሐቅ አም​ላክ ሠዋ።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሌ​ሊት ራእይ፥ “ያዕ​ቆብ ያዕ​ቆብ” ብሎ ለእ​ስ​ራ​ኤል ተና​ገ​ረው። እር​ሱም “ምን​ድን ነው?” አለ።</verse>
				<verse number="3">አለ​ውም፥ “የአ​ባ​ቶ​ችህ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ፤ ወደ ግብፅ መው​ረ​ድን አት​ፍራ፤ በዚያ ትልቅ ሕዝብ አደ​ር​ግ​ሃ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="4">እኔ ወደ ግብፅ አብ​ሬህ እወ​ር​ዳ​ለሁ፤ ከዚ​ያም ደግሞ እኔ አወ​ጣ​ሃ​ለሁ፤ ልጅህ ዮሴ​ፍም እጁን በዐ​ይ​ንህ ላይ ያኖ​ራል።”</verse>
				<verse number="5">ያዕ​ቆ​ብም ከዐ​ዘ​ቅተ መሐላ ተነሣ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አባ​ታ​ቸ​ውን፥ ገን​ዘ​ባ​ቸ​ውን፥ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም እነ​ር​ሱን ያመ​ጡ​ባ​ቸው ዘንድ ዮሴፍ በላ​ካ​ቸው ሰረ​ገ​ሎች ጭነው ወሰዱ።</verse>
				<verse number="6">ጓዛ​ቸ​ውን፥ በከ​ነ​ዓን ሀገ​ርም ያገ​ኙ​ትን ጥሪ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ይዘው ያዕ​ቆ​ብና ዘሩ ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ወደ ግብፅ መጡ፤</verse>
				<verse number="7">ወን​ዶች ልጆ​ቹ​ንና የወ​ን​ዶች ልጆ​ቹን ወን​ዶች ልጆች፥ ሴቶች ልጆ​ቹ​ንና የሴ​ቶች ልጆ​ቹን ሴቶች ልጆች፥ ዘሩ​ንም ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ወደ ግብፅ አስ​ገ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">ከአ​ባ​ታ​ቸው ከያ​ዕ​ቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገ​ቡት የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ስም ይህ ነው፤ ያዕ​ቆ​ብና ልጆቹ፤ የያ​ዕ​ቆብ በኵር ሮቤል።</verse>
				<verse number="9">የሮ​ቤ​ልም ልጆች፤ ሄኖኅ፥ ፍሉስ፥ አስ​ሮን፥ ከርሜ።</verse>
				<verse number="10">የስ​ም​ዖን ልጆች፤ ይሙ​ኤል፥ ያሚን፥ አኡድ፥ ያኪን፥ ሱሐር፥ የከ​ነ​ዓ​ና​ዊት ልጅ ሳዑል።</verse>
				<verse number="11">የሌ​ዊም ልጆች፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።</verse>
				<verse number="12">የይ​ሁ​ዳም ልጆች፤ ዔር፥ አው​ናን፥ ሴሎም፥ ፋሬስ፥ ዛራ፤ ዔርና አው​ናን በከ​ነ​ዓን ምድር ሞቱ። የፋ​ሬ​ስም ልጆች እኒህ ናቸው፤ ኤስ​ሮም፥ ይሞ​ሔል፤</verse>
				<verse number="13">የይ​ሳ​ኮ​ርም ልጆች፤ ቶላዕ፥ ፎሓ፥ ያሱብ፥ ስምራ።</verse>
				<verse number="14">የዛ​ብ​ሎ​ንም ልጆች፤ ሳሬድ፥ አሎን፥ አሌል።</verse>
				<verse number="15">ልያ በመ​ስ​ጴ​ጦ​ምያ በሶ​ርያ ለያ​ዕ​ቆብ የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸው ልጆ​ችና ሴቲቱ ልጅዋ ዲና እነ​ዚህ ናቸው፤ ወን​ዶ​ችም ሴቶ​ችም ልጆ​ችዋ ሁሉ ሠላሳ አራት ነፍስ ናቸው።</verse>
				<verse number="16">የጋ​ድም ልጆች፤ ስፎን፥ ሐጊ፥ ሱኒ፥ አዜን፥ አድ፥ አሮ​ሐድ፥ አር​ሔል።</verse>
				<verse number="17">የአ​ሴ​ርም ልጆች፤ ኢያ​ምን፥ ኢያሱ፥ኢዩል፥ በሪዓ፥ እኅ​ታ​ቸው ሳራ፤ የበ​ሪዓ ልጆ​ችም፤ ኮቦር፥ መል​ኪ​ኤል።</verse>
				<verse number="18">ላባ ለልጁ ለልያ የሰ​ጣት የዘ​ለፋ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ እር​ስ​ዋም እነ​ዚ​ህን ዐሥራ ስድ​ስ​ቱን ነፍስ ለያ​ዕ​ቆብ ወለ​ደች።</verse>
				<verse number="19">የያ​ዕ​ቆብ ሚስት የራ​ሔል ልጆች ዮሴ​ፍና ብን​ያም ናቸው።</verse>
				<verse number="20">ለዮ​ሴ​ፍም በግ​ብፅ ምድር ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ እነ​ር​ሱም የሄ​ል​ዮቱ ከተማ ካህን የጴ​ጤ​ፌራ ልጅ አስ​ኔት የወ​ለ​ደ​ች​ለት ምና​ሴና ኤፍ​ሬም ናቸው። ሶር​ያ​ዊት ዕቅ​ብቱ የወ​ለ​ደ​ች​ለት የም​ና​ሴም ልጅ ማኪር ነው። ማኪ​ርም ገለ​ዓ​ድን ወለደ፤ የም​ና​ሴም ወን​ድም የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ሱታ​ላና ጠኀን ናቸው። የሱ​ታላ ልጅም ኤዴን ነው።</verse>
				<verse number="21">የብ​ን​ያ​ምም ልጆች፤ ቤላ፥ ቦኮር፥ አስ​ቤር፤ የቤላ ልጆ​ችም፤ ጌራ፥ ኖሔ​ማን፥ አሒ፥ ሮስ፥ ማን​ፌን፥ ሑፈም፤ ጌራም አራ​ድን ወለደ።</verse>
				<verse number="22">ለያ​ዕ​ቆብ የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት የራ​ሔል ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ሁሉም ዐሥራ አራት ነፍስ ናቸው።</verse>
				<verse number="23">የዳ​ንም ልጅ አሳ ነው።</verse>
				<verse number="24">የን​ፍ​ታ​ሌ​ምም ልጆች፤ አሴ​ሔል፥ ጎሂን፥ ዮሴር ሴሌም።</verse>
				<verse number="25">ላባ ለልጁ ለራ​ሔል የሰ​ጣት የባላ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ለያ​ዕ​ቆብ ወለ​ደ​ች​ለት፤ ባላ የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸው ሁሉም ሰባት ነፍስ ናቸው።</verse>
				<verse number="26">ከያ​ዕ​ቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገ​ቡት ሰዎች ሁሉ ከጕ​ል​በቱ የወ​ጡት፥ ከል​ጆቹ ሚስ​ቶች ሌላ፥ ሁላ​ቸው ስድሳ ሰባት ናቸው።</verse>
				<verse number="27">በግ​ብፅ ምድር የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት የዮ​ሴ​ፍም ልጆች ሁለት ናቸው፤ ወደ ግብፅ የገ​ቡት የያ​ዕ​ቆብ ቤተ ሰዎች ሁሉ ሰባ ናቸው።</verse>
				<verse number="28">ይሁ​ዳ​ንም ኤሮስ በም​ት​ባል በራ​ምሴ ከተማ እን​ዲ​ቀ​በ​ለው በፊቱ ወደ ዮሴፍ ላከው፤</verse>
				<verse number="29">ዮሴ​ፍም ሰረ​ገ​ላ​ውን አዘ​ጋጀ፤ አባ​ቱ​ንም እስ​ራ​ኤ​ልን ሊገ​ና​ኘው ወደ ኤሮስ ከተማ ወጣ፤ በአ​የ​ውም ጊዜ አን​ገ​ቱን አቀ​ፈው፤ ረዥም ጊዜም አለ​ቀሰ።</verse>
				<verse number="30">እስ​ራ​ኤ​ልም ዮሴ​ፍን፥ “አንተ ገና በሕ​ይ​ወት ሳለህ ፊት​ህን አይ​ች​አ​ለ​ሁና አሁን ልሙት” አለው።</verse>
				<verse number="31">ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ ሄጄ ለፈ​ር​ዖን እን​ዲህ ብዬ እነ​ግ​ረ​ዋ​ለሁ፦ በከ​ነ​ዓን ምድር የነ​በ​ሩት ወን​ድ​ሞ​ችና የአ​ባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥ​ተ​ዋል፤</verse>
				<verse number="32">እነ​ር​ሱም ከብት ጠባ​ቂ​ዎች፥ መንጋ አር​ቢ​ዎች ናቸው፤ በጎ​ቻ​ቸ​ው​ንና ላሞ​ቻ​ቸ​ውን፥ ያላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አመጡ።</verse>
				<verse number="33">ፈር​ዖ​ንም ቢጠ​ራ​ችሁ ተግ​ባ​ራ​ች​ሁስ ምን​ድን ነው? ቢላ​ችሁ፥</verse>
				<verse number="34">በግ ጠባቂ ሁሉ ለግ​ብፅ ሰዎች ርኩስ ነውና በዐ​ረብ በኩል በጌ​ሤም እን​ድ​ት​ቀ​መጡ እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ከብ​ላ​ቴ​ን​ነ​ታ​ችን ጀም​ረን እስከ አሁን ድረስ እኛም አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም እን​ስሳ አር​ቢ​ዎች ነን” በሉት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="47">
				<verse number="1">ዮሴ​ፍም ገባ፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “አባ​ቴና ወን​ድ​ሞች በጎ​ቻ​ቸ​ውም፥ ላሞ​ቻ​ቸ​ውም፥ ያላ​ቸ​ውም ሁሉ ከከ​ነ​ዓን ምድር መጡ፤ እነ​ር​ሱም እነሆ፥ ወደ ጌሤም ምድር ደረሱ።”</verse>
				<verse number="2">ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹም አም​ስት ሰዎ​ችን ወስዶ በፈ​ር​ዖን ፊት አቆ​ማ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ፈር​ዖ​ንም የዮ​ሴ​ፍን ወን​ድ​ሞች፥ “ሥራ​ችሁ ምን​ድን ነው?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም ፈር​ዖ​ንን፥ “እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ፥ አባ​ታ​ች​ንም ከብት ጠባ​ቂ​ዎች ነን” አሉት።</verse>
				<verse number="4">ፈር​ዖ​ን​ንም እን​ዲህ አሉት፥ “በም​ድር ልን​ቀ​መጥ በእ​ን​ግ​ድ​ነት መጣን፤ የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በጎች የሚ​ሰ​ማ​ሩ​በት ስፍራ የለ​ምና፤ ራብም በከ​ነ​ዓን ምድር እጅግ ጸን​ቶ​አ​ልና፤ አሁ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በጌ​ሤም ምድር እን​ቀ​መጥ።”</verse>
				<verse number="5">ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፥ “አባ​ት​ህና ወን​ድ​ሞ​ችህ መጥ​ተ​ው​ል​ሃል፤ እነሆ፥ የግ​ብፅ ምድር በፊ​ትህ ናት፤</verse>
				<verse number="6">በመ​ል​ካሙ ምድር አባ​ት​ህ​ንና ወን​ድ​ሞ​ች​ህን አኑ​ራ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ውስጥ ዕው​ቀት ያላ​ቸ​ውን ሰዎች ታውቅ እን​ደ​ሆነ በእ​ን​ስ​ሶች ጠባ​ቂ​ዎች ላይ አለ​ቆች አድ​ር​ጋ​ቸው።”</verse>
				<verse number="7">ዮሴ​ፍም ያዕ​ቆ​ብን አባ​ቱን አስ​ገ​ብቶ በፈ​ር​ዖን ፊት አቆ​መው፤ ያዕ​ቆ​ብም ፈር​ዖ​ንን ባረ​ከው።</verse>
				<verse number="8">ፈር​ዖ​ንም ያዕ​ቆ​ብን፥ “የኖ​ር​ኸው ዘመን ስንት ነው?” አለው።</verse>
				<verse number="9">ያዕ​ቆ​ብም ለፈ​ር​ዖን አለው፥ “በእ​ን​ግ​ድ​ነት የኖ​ር​ሁት የሕ​ይ​ወቴ ዘመ​ንስ መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፤ የሕ​ይ​ወ​ቴም ዘመ​ኖች ጥቂ​ትም ክፉም ሆኑ​ብኝ፤ አባ​ቶች በእ​ን​ግ​ድ​ነት የተ​ቀ​መ​ጡ​በ​ት​ንም ዘመን አያ​ህ​ሉም።”</verse>
				<verse number="10">ያዕ​ቆ​ብም ፈር​ዖ​ንን ባረ​ከው፤ ከፈ​ር​ዖ​ንም ፊት ወጣ።</verse>
				<verse number="11">ዮሴ​ፍም አባ​ቱ​ንና ወን​ድ​ሞ​ቹን አኖረ፤ ፈር​ዖን እን​ዳ​ዘ​ዘ​ላ​ቸ​ውም በግ​ብፅ ምድር በተ​ሻ​ለ​ችው በራ​ምሴ ምድር ርስ​ትን ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">ዮሴ​ፍም ለአ​ባ​ቱና ለወ​ን​ድ​ሞቹ፥ ለአ​ባ​ቱም ቤተ ሰዎች ሁሉ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው እየ​ሰ​ፈረ እህ​ልን ለም​ግብ ይሰ​ጣ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="13">በም​ድ​ርም ሁሉ እህል አል​ነ​በ​ረም፤ ራብ እጅግ ጸን​ቶ​አ​ልና፤ ከራ​ብም የተ​ነሣ የግ​ብፅ ምድ​ርና የከ​ነ​ዓን ምድር ተጐዳ።</verse>
				<verse number="14">ዮሴ​ፍም ከግ​ብፅ ምድ​ርና ከከ​ነ​ዓን ምድር በእ​ህል ሸመታ የተ​ገ​ኘ​ውን ብሩን ሁሉ አከ​ማቸ፤ ዮሴ​ፍም ብሩን ወደ ፈር​ዖን ቤት አስ​ገ​ባው።</verse>
				<verse number="15">ብሩም በግ​ብፅ ምድ​ርና በከ​ነ​ዓን ምድር አለቀ፤ የግ​ብፅ ሰዎ​ችም ሁሉ ወደ ዮሴፍ መጡ፤ እን​ዲህ ሲሉ፥ “በፊ​ትህ እን​ዳ​ን​ሞት እህል ስጠን፤ ብሩ አል​ቆ​ብ​ና​ልና።”</verse>
				<verse number="16">ዮሴ​ፍም፥ “ከብ​ቶ​ቻ​ች​ሁን አም​ጡ​ልኝ፤ ብር ከአ​ለ​ቀ​ባ​ችሁ በከ​ብ​ቶ​ቻ​ችሁ ፈንታ እህል እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="17">ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ወደ ዮሴፍ አመጡ፤ ዮሴ​ፍም በፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸው፥ በበ​ጎ​ቻ​ቸ​ውም፥ በላ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም፥ በአ​ህ​ዮ​ቻ​ቸ​ውም ፈንታ እህ​ልን ሰጣ​ቸው፤ በዚ​ያች ዓመ​ትም ስለ ከብ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ ፈንታ እህ​ልን መገ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">ያችም ዓመት ተፈ​ጸ​መች፤ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ዋም ዓመት ወደ እርሱ መጥ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “እኛ ለጌ​ታ​ችን ሞተን እን​ዳ​ና​ል​ቅ​በት እህል ስጠን፤ ብሩ በፍ​ጹም አለቀ፤ ንብ​ረ​ታ​ች​ንና ከብ​ታ​ች​ንም በጌ​ታ​ችን ዘንድ ነው፤ ከሰ​ው​ነ​ታ​ች​ንና ከም​ድ​ራ​ችን በቀር በጌ​ታ​ችን ፊት አን​ዳች የቀ​ረን የለም፤</verse>
				<verse number="19">እን​ግ​ዲህ እኛ በፊ​ትህ እን​ዳ​ን​ሞት፥ ምድ​ራ​ች​ንም እን​ዳ​ት​ጠፋ፥ እኛ​ንም፥ ምድ​ራ​ች​ን​ንም በእ​ህል ግዛን፤ እኛም ለፈ​ር​ዖን አገ​ል​ጋ​ዮች እን​ሁን፤ ምድ​ራ​ች​ንም ለእ​ርሱ ትሁን፤ እኛ እን​ድ​ን​ድን፥ እን​ዳ​ን​ሞ​ትም፥ ምድ​ራ​ች​ንም እን​ዳ​ት​ጠፋ እን​ዘራ ዘንድ ዘር ስጠን።”</verse>
				<verse number="20">ዮሴ​ፍም የግ​ብ​ፅን ምድር ሁሉ ለፈ​ር​ዖን ገዛ፤ የግ​ብፅ ሰዎች ሁሉ ራብ ስለ​ጸ​ና​ባ​ቸው ርስ​ታ​ቸ​ውን ሸጠ​ዋ​ልና፤ ምድ​ሪቱ ለፈ​ር​ዖን ሆነች።</verse>
				<verse number="21">ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ ከግ​ብፅ ዳርቻ አን​ሥቶ እስከ ሌላው ዳር​ቻዋ ድረስ አገ​ል​ጋ​ዮች አደ​ረ​ጋ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">ዮሴፍ የካ​ህ​ና​ትን ምድር ብቻ አል​ገ​ዛም፤ ፈር​ዖን ለካ​ህ​ናቱ ድርጎ ይሰ​ጣ​ቸው ነበ​ርና፥ ፈር​ዖ​ንም የሰ​ጣ​ቸ​ውን ድርጎ ይበሉ ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም ምድ​ራ​ቸ​ውን አል​ሸ​ጡም።</verse>
				<verse number="23">ዮሴ​ፍም የግ​ብ​ፅን ሰዎች ሁሉ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እነሆ ዛሬ እና​ን​ተ​ንና ምድ​ራ​ች​ሁን ለፈ​ር​ዖን ገዝ​ቻ​ች​ኋ​ለሁ፤ ለእ​ና​ንተ ዘር ውሰ​ዱና ምድ​ሪ​ቱን ዝሩ፤</verse>
				<verse number="24">በመ​ከ​ርም ጊዜ ፍሬ​ውን ከአ​ም​ስት እጅ አን​ዱን እጅ ለፈ​ር​ዖን ስጡ፤ አራ​ቱም እጅ ለእ​ና​ንተ ለራ​ሳ​ችሁ፥ ለእ​ር​ሻው ዘርና ለእ​ና​ንተ ምግብ፥ ለቤተ ሰባ​ች​ሁም ሁሉ ሲሳይ ይሁን።”</verse>
				<verse number="25">እነ​ር​ሱም፥ “አንተ አዳ​ን​ኸን፤ በጌ​ታ​ች​ንም ፊት ሞገ​ስን አገ​ኘን፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮች እን​ሆ​ና​ለን” አሉት።</verse>
				<verse number="26">ዮሴ​ፍም ለፈ​ር​ዖን ካል​ሆ​ነ​ችው ከካ​ህ​ናቱ ምድር በቀር አም​ስ​ተ​ኛው እጅ ለፈ​ር​ዖን እን​ዲ​ሆን በግ​ብፅ ምድር እስከ ዛሬ ሕግ አደ​ረ​ጋት።</verse>
				<verse number="27">እስ​ራ​ኤ​ልም በግ​ብፅ ምድር በጌ​ሤም ሀገር ተቀ​መጠ፤ እር​ስ​ዋም ርስ​ታ​ቸው ሆነች፤ በዙ፤ እጅ​ግም ተባዙ።</verse>
				<verse number="28">ያዕ​ቆ​ብም በግ​ብፅ ምድር ዐሥራ ሰባት ዓመት ተቀ​መጠ፤ የያ​ዕ​ቆ​ብም መላው የሕ​ይ​ወቱ ዘመን መቶ አርባ ሰባት ዓመት ሆነ።</verse>
				<verse number="29">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የሞቱ ቀን ቀረበ፤ ልጁን ዮሴ​ፍ​ንም ጠርቶ እን​ዲህ አለው፥ “በፊ​ትህ ሞገ​ስን አግ​ኝቼ እንደ ሆንሁ እጅ​ህን በጕ​ል​በቴ ላይ አድ​ርግ፤ በግ​ብፅ ምድ​ርም እን​ዳ​ት​ቀ​ብ​ረኝ ምሕ​ረ​ት​ንና እው​ነ​ትን አድ​ር​ግ​ልኝ፤</verse>
				<verse number="30">ከአ​ባ​ቶ​ችም ጋር በአ​ን​ቀ​ላ​ፋሁ ጊዜ ከግ​ብፅ ምድር አው​ጥ​ተህ ትወ​ስ​ደ​ኛ​ለህ፤ በአ​ባ​ቶ​ችም መቃ​ብር ትቀ​ብ​ረ​ኛ​ለህ።” እር​ሱም፥ “እንደ ቃልህ አደ​ር​ጋ​ለሁ” አለ። እር​ሱም፥ “ማል​ልኝ” አለው።</verse>
				<verse number="31">ዮሴ​ፍም ማለ​ለት፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በአ​ል​ጋው ራስ ላይ ሰገደ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="48">
				<verse number="1">ከዚ​ህም ነገር በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ “እነሆ፥ አባ​ታ​ችን ደከመ” ብለው ለዮ​ሴፍ ነገ​ሩት፤ እር​ሱም ሁለ​ቱን ልጆ​ቹን ምና​ሴ​ንና ኤፍ​ሬ​ምን ይዞ ሄደ።</verse>
				<verse number="2">ለያ​ዕ​ቆ​ብም፥ “እነሆ፥ ልጅህ ዮሴፍ መጥ​ቶ​ል​ሃል” ብለው ነገ​ሩት፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ተጠ​ነ​ካ​ከረ፤ በአ​ል​ጋ​ውም ላይ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="3">ያዕ​ቆብ ዮሴ​ፍን አለው፥ “አም​ላኬ በከ​ነ​ዓን ምድር በሎዛ ተገ​ለ​ጠ​ልኝ፤ ባረ​ከ​ኝም።</verse>
				<verse number="4">እን​ዲ​ህም አለኝ፦ እነሆ፥ አበ​ዛ​ሃ​ለሁ፤ አባ​ዛ​ሃ​ለ​ሁም፤ ለብ​ዙም ሕዝብ ጉባኤ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ ይህ​ች​ንም ምድር ለአ​ንተ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ርስት ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">አሁ​ንም እኔ ወደ አንተ ከመ​ም​ጣቴ በፊት በግ​ብፅ ምድር የተ​ወ​ለ​ዱ​ልህ ሁለቱ ልጆ​ችህ ለእኔ ይሁኑ፤ ኤፍ​ሬ​ምና ምናሴ ለእኔ እንደ ሮቤ​ልና እንደ ስም​ዖን ናቸው።</verse>
				<verse number="6">ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ የም​ት​ወ​ል​ዳ​ቸው ልጆች ለአ​ንተ ይሁኑ፤ በር​ስ​ታ​ቸው በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ስም ይጠሩ።</verse>
				<verse number="7">እኔም ከሶ​ርያ መስ​ጴ​ጦ​ምያ በመ​ጣሁ ጊዜ፥ ወደ ኤፍ​ራታ ለመ​ግ​ባት ጥቂት ቀር​ቶኝ በፈ​ረስ መጋ​ለ​ቢ​ያው መን​ገድ ሳለሁ፥ ራሔል በከ​ነ​ዓን ምድር ሞተ​ች​ብኝ፤ በዚ​ያም በኤ​ፍ​ራታ ወደ ፈረስ መጋ​ለ​ቢያ በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ላይ ቀበ​ር​ኋት፤ እር​ስ​ዋም ቤተ ልሔም ናት።”</verse>
				<verse number="8">እስ​ራ​ኤ​ልም የዮ​ሴ​ፍን ልጆች ለይቶ፥ “እነ​ዚህ ምኖ​ችህ ናቸው?” አለው።</verse>
				<verse number="9">ዮሴ​ፍም ለአ​ባቱ ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ የሰ​ጠኝ ልጆች ናቸው” አለው። ያዕ​ቆ​ብም፥ “እባ​ር​ካ​ቸው ዘንድ ወደ እኔ አቅ​ር​ብ​ልኝ” አለው።</verse>
				<verse number="10">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዐይ​ኖች ከሽ​ም​ግ​ልና የተ​ነሣ ከብ​ደው ነበር፤ ማየ​ትም አይ​ች​ልም ነበር፤ ወደ እር​ሱም አቀ​ረ​ባ​ቸው፤ ሳማ​ቸ​ውም፤ አቀ​ፋ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="11">እስ​ራ​ኤ​ልም ዮሴ​ፍን፥ “ከፊ​ትህ አል​ተ​ለ​የ​ሁም፤ እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘር​ህን ደግሞ አሳ​የኝ” አለው።</verse>
				<verse number="12">ዮሴ​ፍም ከጕ​ል​በቱ ፈቀቅ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ ወደ ምድ​ርም በግ​ን​ባሩ ሰገደ።</verse>
				<verse number="13">ዮሴ​ፍም ሁለ​ቱን ልጆ​ቹን ወሰደ፤ ኤፍ​ሬ​ም​ንም በቀኙ በእ​ስ​ራ​ኤል ግራ፥ ምና​ሴ​ንም በግ​ራው በእ​ስ​ራ​ኤል ቀኝ አቆ​ማ​ቸው፤ ወደ አባ​ቱም አቀ​ረ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">እስ​ራ​ኤ​ልም ቀኝ እጁን ዘር​ግቶ በኤ​ፍ​ሬም ራስ ላይ አኖ​ረው፤ እር​ሱም ታናሽ ነበረ፤ ግራ​ው​ንም በም​ናሴ ራስ ላይ አኖረ፤ እጆ​ቹ​ንም አስ​ተ​ላ​ለፈ።</verse>
				<verse number="15">ያዕ​ቆ​ብም ባረ​ካ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አባ​ቶች አብ​ር​ሃ​ምና ይስ​ሐቅ በፊቱ ደስ ያሰ​ኙት እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከታ​ና​ሽ​ነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመ​ገ​በኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥</verse>
				<verse number="16">ከከፉ ነገር ሁሉ የአ​ዳ​ነኝ መል​አክ እርሱ እነ​ዚ​ህን ብላ​ቴ​ኖች ይባ​ርክ፤ ስሜም፥ የአ​ባ​ቶች የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐ​ቅም ስም በእ​ነ​ርሱ ይጠራ፤ በም​ድር ላይ ይብዙ፤ የብዙ ብዙም ይሁኑ፤”</verse>
				<verse number="17">ዮሴ​ፍም አባቱ ቀኝ እጁን በኤ​ፍ​ሬም ራስ ላይ ጭኖ በአየ ጊዜ ከባድ ነገር ሆነ​በት፤ ዮሴ​ፍም የአ​ባ​ቱን እጅ በም​ናሴ ራስ ላይ ይጭ​ነው ዘንድ ከኤ​ፍ​ሬም ራስ ላይ አነ​ሣው።</verse>
				<verse number="18">ዮሴ​ፍም አባ​ቱን፥ “አባቴ ሆይ፥ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ በኵሩ ይህ ነውና ቀኝ​ህን በራሱ ላይ አድ​ርግ” አለው።</verse>
				<verse number="19">አባ​ቱም እንቢ አለ፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አው​ቃ​ለሁ ልጄ ሆይ፥ አው​ቃ​ለሁ፤ ይህም ደግሞ ሕዝብ ይሆ​ናል፤ ታላ​ቅም ይሆ​ናል፤ ነገር ግን ታናሽ ወን​ድሙ ከእ​ርሱ ይበ​ል​ጣል፤ ዘሩም ብዙ ሕዝብ ይሆ​ናል።”</verse>
				<verse number="20">በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ብሎ ባረ​ካ​ቸው፥ “በእ​ና​ንተ እስ​ራ​ኤል እን​ዲህ ተብሎ ይባ​ረ​ካል፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ኤፍ​ሬ​ምና እንደ ምናሴ ይባ​ር​ክህ።” ኤፍ​ሬ​ም​ንም ከም​ናሴ ፊት አደ​ረ​ገው።</verse>
				<verse number="21">እስ​ራ​ኤ​ልም ዮሴ​ፍን፥ “እነሆ፥ እኔ እሞ​ታ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ና​ንተ ጋር ይሆ​ናል፤ ወደ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ምድር ይመ​ል​ሳ​ች​ኋል፤</verse>
				<verse number="22">እኔም ከአ​ሞ​ራ​ው​ያን እጅ በሰ​ይ​ፌና በቀ​ስቴ የወ​ሰ​ድ​ሁ​ትን ምርኮ ለአ​ንተ ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ የተ​ሻ​ለ​ውን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="49">
				<verse number="1">ያዕ​ቆ​ብም ልጆ​ቹን ጠርቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በኋ​ለ​ኛው ዘመን የሚ​ያ​ገ​ኛ​ች​ሁን እን​ድ​ነ​ግ​ራ​ችሁ ተሰ​ብ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="2">እና​ንት የያ​ዕ​ቆብ ልጆች ኑ፥ ተሰ​ብ​ሰቡ፤ ስሙም፤ አባ​ታ​ችሁ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም አድ​ምጡ።</verse>
				<verse number="3">“ሮቤል እርሱ የበ​ኵር ልጄና ኀይሌ፥ የል​ጆ​ችም መጀ​መ​ሪያ ነው፤ ክፉ ሆነ፤ አን​ገ​ቱ​ንም አደ​ነ​ደነ። ጭንቅ ነገ​ር​ንም አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="4">እንደ ውኃ የሚ​ዋ​ልል ነው፤ ኀይል የለ​ውም፤ ወደ አባቱ መኝታ ወጥ​ቶ​አ​ልና፤ ያን ጊዜ የወ​ጣ​በ​ትን አልጋ አር​ክ​ሶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="5">“ስም​ዖ​ንና ሌዊ ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች ናቸው፤ በጭ​ቅ​ጭ​ቃ​ቸ​ውና በጦ​ራ​ቸው ዐመ​ፅን ፈጸ​ሙ​አት።</verse>
				<verse number="6">በም​ክ​ራ​ቸው ሰው​ነቴ አት​ገ​ና​ኛ​ቸው፤ ዐሳ​ቤም በአ​መ​ፃ​ቸው አት​ተ​ባ​በ​ርም፤ በቍ​ጣ​ቸው ሰውን ገድ​ለ​ዋ​ልና፤ በገዛ ፈቃ​ዳ​ቸ​ውም የሀ​ገ​ርን ሥር ቈር​ጠ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="7">ቍጣ​ቸው ርጉም ይሁን፤ ጽኑ ነበ​ርና፤ ኵር​ፍ​ታ​ቸ​ውም ብርቱ ነበ​ርና፤ በያ​ዕ​ቆብ እከ​ፋ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም እበ​ታ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">“ይሁዳ፥ ወን​ድ​ሞ​ችህ አን​ተን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፤ እጅህ በጠ​ላ​ቶ​ችህ ደን​ደስ ላይ ነው፤ የአ​ባ​ትህ ልጆች በፊ​ትህ ይሰ​ግ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="9">ይሁዳ የአ​ን​በሳ ደቦል ነው፤ ልጄ ሆይ፥ ከመ​ሰ​ማ​ሪ​ያህ ወጣህ፤ እንደ አን​በሳ ተኛህ፤ አን​ቀ​ላ​ፋ​ህም፤ እንደ አን​በ​ሳም ደቦል የሚ​ቀ​ሰ​ቅ​ስህ የለም።</verse>
				<verse number="10">መን​ግ​ሥት ከይ​ሁዳ አይ​ጠ​ፋም፤ ምስ​ፍ​ናም ከአ​ብ​ራኩ፥ ለእ​ርሱ የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውን እስ​ኪ​ያ​ገኝ ድረስ፤ የአ​ሕ​ዛብ ተስ​ፋ​ቸው እርሱ ነውና፤</verse>
				<verse number="11">አህ​ያ​ይ​ቱን በወ​ይን ግንድ ያስ​ራል፤ የአ​ህ​ያ​ይ​ቱ​ንም ግል​ገል በወ​ይን ሐረግ፤ ልብ​ሱን በወ​ይን ያጥ​ባል፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ው​ንም በዘ​ለ​ላው ደም።</verse>
				<verse number="12">ዐይ​ኖቹ ከወ​ይን ይልቅ ደስ ያሰ​ኛሉ፤ ጥር​ሱም ከወ​ተት ይልቅ ነጭ ነው።</verse>
				<verse number="13">“ዛብ​ሎን ጫማ​ውን አዝቦ ይኖ​ራል፤ እር​ሱም እንደ መር​ከ​ቦች ወደብ ይሆ​ናል፤ ዳር​ቻ​ውም እስከ ሲዶና ይሰ​ፋል።</verse>
				<verse number="14">“ይሳ​ኮር መል​ካም ነገ​ርን ወደደ፤ በተ​ወ​ራ​ራ​ሾ​ቹም መካ​ከል ያር​ፋል።</verse>
				<verse number="15">ዕረ​ፍ​ትም መል​ካም መሆ​ን​ዋን፥ ምድ​ሪ​ቱም የለ​ማች መሆ​ን​ዋን በአየ ጊዜ ምድ​ርን ያር​ሳት ዘንድ ትከ​ሻ​ውን ዝቅ አደ​ረገ፤ በሥ​ራም ገበሬ ሆነ።</verse>
				<verse number="16">“ዳን ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ እንደ አንዱ በወ​ገኑ ይፈ​ር​ዳል፤</verse>
				<verse number="17">ዳን በጎ​ዳና ላይ እን​ደ​ሚ​ያ​ደባ እባብ ይሆ​ናል፤ በመ​ን​ገ​ዱም የፈ​ረ​ሱን ሰኰና እን​ደ​ሚ​ና​ደፍ እንደ ቀን​ዳም እባብ ነው፤ ፈረ​ሰ​ኛ​ውም ወደ​ኋ​ላው ይወ​ድ​ቃል።</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያድ​ነው ዘንድ ይጠ​ብ​ቃል።</verse>
				<verse number="19">“ጋድን ሽፍ​ቶች ቀሙት፤ እር​ሱም ፍለ​ጋ​ቸ​ውን ተከ​ታ​ትሎ ቀማ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">“የአ​ሴር እን​ጀራ ወፍ​ራም ነው፤ እር​ሱም ለአ​ለ​ቆች ደስ የሚ​ያ​ሰኝ መብ​ልን ይሰ​ጣል።</verse>
				<verse number="21">“ንፍ​ታ​ሌም በፍ​ሬው ላይ ውበ​ትን የሚ​ሰጥ ሰፊ ዘን​ባባ ነው።</verse>
				<verse number="22">“ዮሴፍ የሚ​ያ​ድግ ልጅ ነው፤ ለእኔ በጣም የተ​ወ​ደደ የሚ​ቀ​ና​ል​ኝና የሚ​ያ​ድ​ግ​ልኝ ልጅ ነው፤ ወደ እኔ የሚ​መ​ለ​ስም ጐል​ማሳ ነው።</verse>
				<verse number="23">በም​ክ​ራ​ቸው የሰ​ደ​ቡት ጌቶች ሆኑ​በት፤ ቀስ​ተ​ኞ​ችም ወጉት፤</verse>
				<verse number="24">ነገር ግን ቀስ​ቶ​ቻ​ቸው በኀ​ይል ተቀ​ጠ​ቀጡ፤ የእ​ጆ​ቻ​ቸው ክንድ ሥርም በያ​ዕ​ቆብ ኀያል እጅ ዛለ፤ በዚ​ያም በአ​ባ​ትህ አም​ላክ ዘንድ እስ​ራ​ኤ​ልን አጸ​ናው።</verse>
				<verse number="25">“የእኔ አም​ላክ ረዳህ፤ ከላይ በሰ​ማይ በረ​ከት፥ ሁሉ በሚ​ገ​ኝ​ባት፥ በም​ድር በረ​ከት፥ በጡ​ትና በማ​ኅ​ፀን በረ​ከት ባረ​ከህ፤</verse>
				<verse number="26">የአ​ባ​ት​ህና የእ​ና​ትህ በረ​ከ​ቶች ጽኑ​ዓን ከሆኑ ከተ​ራ​ሮች በረ​ከ​ቶች ይልቅ ይበ​ል​ጣሉ፤ ዘለ​ዓ​ለ​ማ​ው​ያን ከሆኑ ከኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም በረ​ከ​ቶች ይልቅ ኀያ​ላን ናቸው፤ እነ​ር​ሱም በዮ​ሴፍ ራስ ላይ ይሆ​ናሉ፤ በወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል አለቃ በሆ​ነ​ውም ራስ አናት ላይ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="27">“ብን​ያም ነጣቂ ተኵላ ነው፤ በጥ​ዋት ይበ​ላል፤ የማ​ረ​ከ​ው​ንም ምግ​ቡን በማታ ለሕ​ዝብ ይሰ​ጣል።”</verse>
				<verse number="28">እነ​ዚ​ህም ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የያ​ዕ​ቆብ ልጆች ናቸው፤ አባ​ታ​ቸ​ውም ይህን ነገር ነገ​ራ​ቸው፤ ባረ​ካ​ቸ​ውም፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ው​ንም እንደ በረ​ከ​ታ​ቸው ባረ​ካ​ቸው።</verse>
				<verse number="29">እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “እኔ ወደ ወገ​ኖች እሰ​በ​ሰ​ባ​ለሁ፤ በኬ​ጢ​ያ​ዊው በኤ​ፍ​ሮን እርሻ ላይ ባለ​ችው ዋሻ ከአ​ባ​ቶች ጋር ቅበ​ሩኝ፤ እር​ስ​ዋም በከ​ነ​ዓን ምድር በመ​ምሬ ፊት ያለች፥</verse>
				<verse number="30">አብ​ር​ሃም ለመ​ቃ​ብር ርስት ከኬ​ጢ​ያ​ዊው ከኤ​ፍ​ሮን ከእ​ር​ሻው ጋር የገ​ዛት፥ ባለ ድርብ ክፍል ዋሻ ናት።</verse>
				<verse number="31">አብ​ር​ሃ​ም​ንና ሚስቱ ሣራ​ንም በዚያ ቀበ​ሩ​አ​ቸው፤ ይስ​ሐ​ቅ​ንና ሚስቱ ርብ​ቃ​ንም በዚያ ቀበ​ሩ​አ​ቸው፤ ከዚ​ያም እኔ ልያን ቀበ​ር​ኋት</verse>
				<verse number="32">እር​ሻ​ውና በእ​ር​ስዋ ላይ ያለ​ችው ዋሻ ከኬጢ ልጆች የተ​ገዙ ናቸው።”</verse>
				<verse number="33">ያዕ​ቆ​ብም ትእ​ዛ​ዙን ለል​ጆቹ ተና​ግሮ በፈ​ጸመ ጊዜ እግ​ሮ​ቹን በአ​ል​ጋው ላይ ዘር​ግቶ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="50">
				<verse number="1">ዮሴ​ፍም በአ​ባቱ ፊት ወደቀ፤ በእ​ር​ሱም ላይ አለ​ቀሰ፤ ሳመ​ውም።</verse>
				<verse number="2">ዮሴ​ፍም ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶች አገ​ል​ጋ​ዮቹ አባ​ቱን በሽቱ ያሹት ዘንድ አዘዘ፤ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶ​ችም እስ​ራ​ኤ​ልን በሽቱ አሹት።</verse>
				<verse number="3">አርባ ቀንም ፈጸ​ሙ​ለት፤ ሽቱ የሚ​ቀ​ቡ​በ​ትን ቀን እን​ዲሁ ይቈ​ጥ​ራ​ሉና፤ የግ​ብ​ፅም ሰዎች ሰባ ቀን አለ​ቀ​ሱ​ለት።</verse>
				<verse number="4">የል​ቅ​ሶ​ውም ወራት ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ ዮሴፍ ለፈ​ር​ዖን መኳ​ን​ንት እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ፥ “እኔ በፊ​ታ​ችሁ ሞገ​ስን አግ​ኝቼ እንደ ሆንሁ ለፈ​ር​ዖን እን​ዲህ ብላ​ችሁ ስለ እኔ ንገ​ሩት፦</verse>
				<verse number="5">አባቴ ሳይ​ሞት አም​ሎ​ኛል፤ እን​ዲህ ሲል፦ ‘እነሆ እኔ እሞ​ታ​ለሁ፤ በቈ​ፈ​ር​ሁት መቃ​ብር በከ​ነ​ዓን ምድር በዚያ ቅበ​ረኝ።’ አሁ​ንም ወጥቼ አባ​ቴን ልቅ​በ​ርና ልመ​ለስ።”</verse>
				<verse number="6">ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን አለው፥ “ውጣ፤ አባ​ት​ህ​ንም እን​ዳ​ማ​ለህ ቅበ​ረው።”</verse>
				<verse number="7">ዮሴ​ፍም አባ​ቱን ሊቀ​ብር ወጣ፤ የፈ​ር​ዖን ሎሌ​ዎ​ችም ሁሉ፥ የቤቱ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ሁሉ፥ የግ​ብፅ ምድር ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ወጡ፤</verse>
				<verse number="8">የዮ​ሴ​ፍም ቤተ ሰቦች ሁሉ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም፥ የአ​ባ​ቱም ቤተ ሰቦች ወጡ፤ ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና በጎ​ቻ​ቸ​ውን፥ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ብቻ በጌ​ሤም ተዉ።</verse>
				<verse number="9">ሰረ​ገ​ሎ​ችም፥ ፈረ​ሰ​ኞ​ችም ከእ​ርሱ ጋር ወጡ፤ ሠራ​ዊ​ቱም ብዙ ነበር።</verse>
				<verse number="10">በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወዳ​ለ​ችው ወደ አጣድ አው​ድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅ​ሶም አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ ለአ​ባ​ቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደ​ረ​ገ​ለት።</verse>
				<verse number="11">በዚ​ያች ምድር የሚ​ኖሩ የከ​ነ​ዓን ሰዎ​ችም በአ​ጣድ አው​ድማ የሆ​ነ​ውን ልቅሶ በአዩ ጊዜ፥ “የግ​ብፅ ልቅሶ እን​ዲህ ታላቅ ነውን?” አሉ፤ ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያን ቦታ ስም “ላሐ ግብፅ” ብለው ጠሩት፤ እር​ሱም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ነው።</verse>
				<verse number="12">ልጆ​ቹም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው እን​ደ​ዚ​ያው አደ​ረ​ጉ​ለት፤</verse>
				<verse number="13">ልጆ​ቹም ወደ ከነ​ዓን ምድር መለ​ሱት፤ ባለ ሁለት ክፍል በሆ​ነች ዋሻም ቀበ​ሩት፤ እር​ስ​ዋም በመ​ምሬ ፊት ያለች፥ አብ​ር​ሃም ለመ​ቃ​ብር ርስት ከኬ​ጢ​ያ​ዊው ከኤ​ፍ​ሮን ከእ​ር​ሻው ጋር የገ​ዛት ዋሻ ናት።</verse>
				<verse number="14">ዮሴ​ፍና ወን​ድ​ሞቹ፥ አባ​ቱ​ንም ሊቀ​ብሩ ከእ​ርሱ ጋር የወ​ጡት ሰዎች ሁሉ አባ​ቱን ከቀ​በረ በኋላ ወደ ግብፅ ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="15">የዮ​ሴ​ፍም ወን​ድ​ሞች አባ​ታ​ቸው እንደ ሞተ በአዩ ጊዜ እን​ዲህ አሉ፥ “ምና​ል​ባት ዮሴፍ ያደ​ረ​ግ​ን​በ​ትን ክፋት ያስ​ብ​ብን ይሆ​ናል፤ ባደ​ረ​ግ​ን​በ​ትም ክፋት ሁሉ ብድ​ራት ይመ​ል​ስ​ብን ይሆ​ናል።”</verse>
				<verse number="16">ወደ ዮሴ​ፍም መጡ፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “አባ​ትህ ገና ሳይ​ሞት እን​ዲህ ብሎ አዝ​ዟል፦</verse>
				<verse number="17">‘ዮሴ​ፍን እን​ዲህ በሉት፦ እባ​ክህ የወ​ን​ድ​ሞ​ች​ህን በደል ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይቅር በል፤ እነ​ርሱ በአ​ንተ ክፉ አድ​ር​ገ​ው​ብ​ሃ​ልና፤’ አሁ​ንም እባ​ክህ የአ​ባ​ትህ አም​ላክ ባሪ​ያ​ዎች የበ​ደ​ሉ​ህን ይቅር በል።”</verse>
				<verse number="18">ዮሴ​ፍም ይህን ሲሉት አለ​ቀሰ። ወን​ድ​ሞቹ ደግሞ መጡ፤ “እነሆ፥ እኛ ለአ​ንተ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ነን” አሉት።</verse>
				<verse number="19">ዮሴ​ፍም አላ​ቸው፥ “አት​ፍሩ፤ ይህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ሆኖ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="20">እና​ንተ በእኔ ላይ ክፉ መከ​ራ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እን​ዲ​መ​ገብ ለማ​ድ​ረግ ለእኔ መል​ካም መከረ።</verse>
				<verse number="21">አሁ​ንም አት​ፍሩ፤ እኔ እና​ን​ተ​ንና ቤተ ሰቦ​ቻ​ች​ሁን እመ​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።” አጽ​ና​ና​ቸ​ውም፤ በል​ባ​ቸው የሚ​ገባ ነገ​ርም ነገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">ዮሴ​ፍም በግ​ብፅ ሀገር ተቀ​መጠ፤ እር​ሱና ወን​ድ​ሞቹ የአ​ባ​ቱም ቤተ ሰብ፤ ዮሴ​ፍም መቶ ዐሥር ዓመት ኖረ።</verse>
				<verse number="23">ዮሴ​ፍም የኤ​ፍ​ሬ​ምን ልጆች እስከ ሦስት ትው​ልድ አየ። የም​ናሴ ልጅ የማ​ኪር ልጆ​ችም በዮ​ሴፍ ጭን ላይ ተወ​ለዱ።</verse>
				<verse number="24">ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን አላ​ቸው፥ “እኔ እሞ​ታ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መጐ​ብ​ኘ​ትን ይጐ​በ​ኛ​ች​ኋል፤ ከዚ​ህ​ችም ምድር ያወ​ጣ​ች​ኋል። ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ያገ​ባ​ች​ኋል።”</verse>
				<verse number="25">ዮሴ​ፍም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጐ​በ​ኛ​ችሁ ጊዜ አጥ​ን​ቴን ከዚህ አን​ሥ​ታ​ችሁ ከእ​ና​ንተ ጋር አውጡ” ብሎ አማ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">ዮሴ​ፍም በመቶ ዐሥር ዓመት ዕድ​ሜው ሞተ፤ በሽ​ቱም አሹት፤ በግ​ብፅ ምድ​ርም በሣ​ጥን ውስጥ አኖ​ሩት።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="2">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">ከአ​ባ​ታ​ቸው ከያ​ዕ​ቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገ​ቡት የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ስሞች እነ​ዚህ ናቸው፤ ሰው ሁሉ ከቤተ ሰቡ ጋር ገባ፤</verse>
				<verse number="2">ሮቤል፥ ስም​ዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥</verse>
				<verse number="3">ይሳ​ኮር፥ ዛብ​ሎን፥ ብን​ያም።</verse>
				<verse number="4">ዳን፥ ንፍ​ታ​ሌም፥ ጋድ፥ አሴር።</verse>
				<verse number="5">ዮሴ​ፍም አስ​ቀ​ድሞ በግ​ብፅ ነበረ። ከያ​ዕ​ቆብ ጕል​በት የወ​ጡት ሰዎች ሁሉ ሰባ ነፍ​ሶች ነበሩ፤</verse>
				<verse number="6">ዮሴ​ፍም ሞተ፤ ወን​ድ​ሞ​ቹም፥ ያም ትው​ልድ ሁሉ።</verse>
				<verse number="7">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በዙ፤ ተባ​ዙም፤ የተ​ጠ​ሉም ሆኑ። እጅ​ግም ጸኑ፤ ምድ​ሪ​ቱም በእ​ነ​ርሱ ሞላች።</verse>
				<verse number="8">በግ​ብፅ ዮሴ​ፍን ያላ​ወቀ ሌላ ንጉሥ ተነሣ።</verse>
				<verse number="9">እር​ሱም ሕዝ​ቡን፥ “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሕዝብ ታላ​ቅና ብዙ ሆነ​ዋል፤ ከእ​ኛም ይልቅ በር​ት​ተ​ዋል፤</verse>
				<verse number="10">ኑ፤ እን​ጠ​በ​ብ​ባ​ቸው፤ የበዙ እን​ደ​ሆነ ጦር​ነት በመ​ጣ​ብን ጊዜ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን ላይ ተደ​ር​በው በኋ​ላ​ችን ይወ​ጉ​ና​ልና፥ ከም​ድ​ራ​ች​ንም ያስ​ወ​ጡ​ና​ልና።”</verse>
				<verse number="11">በብ​ርቱ ሥራም ያስ​ጨ​ን​ቋ​ቸው ዘንድ የሠ​ራ​ተ​ኞች አለ​ቆ​ችን ሾመ​ባ​ቸው፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም ፌቶ​ምን፥ ራም​ሴ​ንና የፀ​ሐይ ከተማ የም​ት​ባል ዖንን ጽኑ ከተ​ሞች አድ​ር​ገው ሠሩ።</verse>
				<verse number="12">ነገር ግን እን​ዳ​ስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸው መጠን እን​ዲሁ በዙ፤ እጅ​ግም ጸኑ ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ይጸ​የ​ፉ​አ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="13">ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በግ​ፍዕ ገዙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">በጽኑ ሥራ፥ በጭቃ፥ በጡ​ብም፥ በእ​ር​ሻም ሥራ ሁሉ፥ በመ​ከ​ራም በሚ​ያ​ሠ​ሩ​አ​ቸው ሥራ ሁሉ፤ ሕይ​ወ​ታ​ቸ​ውን ያስ​መ​ር​ሩ​አ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="15">የግ​ብ​ፅም ንጉሥ አን​ዲቱ ሲፓራ፥ ሁለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ፎሓ የሚ​ባ​ሉ​ትን የዕ​ብ​ራ​ው​ያ​ትን አዋ​ላ​ጆች እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ፦</verse>
				<verse number="16">“እና​ንተ ዕብ​ራ​ው​ያ​ትን ሴቶች ስታ​ዋ​ልዱ ለመ​ው​ለድ እንደ ደረሱ በአ​ያ​ችሁ ጊዜ፥ ወንድ ቢሆን ግደ​ሉት፤ ሴት ብት​ሆን ግን አት​ግ​ደ​ሏት።”</verse>
				<verse number="17">አዋ​ላ​ጆች ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈሩ፤ የግ​ብፅ ንጉ​ሥም እንደ አዘ​ዛ​ቸው አላ​ደ​ረ​ጉም፤ ወን​ዶ​ቹን ሕፃ​ና​ት​ንም አዳ​ኑ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">የግ​ብ​ፅም ንጉሥ አዋ​ላ​ጆ​ችን ጠርቶ፥ “ለምን እን​ዲህ አደ​ረ​ጋ​ችሁ? ወን​ዶ​ቹን ሕፃ​ና​ት​ንስ ለምን አዳ​ና​ችሁ?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">አዋ​ላ​ጆ​ችም ፈር​ዖ​ንን፥ “የዕ​ብ​ራ​ው​ያን ሴቶች እንደ ግብፅ ሴቶች ስላ​ል​ሆኑ አዋ​ላ​ጆች ሳይ​ገቡ ይወ​ል​ዳሉ” አሉት።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ዋ​ላ​ጆች መል​ካም አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው፤ ሕዝ​ቡም በዙ፤ እጅ​ግም ጸኑ።</verse>
				<verse number="21">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ አዋ​ላ​ጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ​ፈሩ ቤቶ​ችን አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">ፈር​ዖ​ንም፥ “የሚ​ወ​ለ​ደ​ውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወደ ወንዝ ጣሉት፤ ሴትን ልጅ ሁሉ ግን በሕ​ይ​ወት አድ​ኑ​አት” ብሎ ሕዝ​ቡን ሁሉ አዘዘ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ከሌዊ ወገን እን​በ​ረም የሚ​ባል አንድ ሰው ነበረ፤ እር​ሱም ከሌዊ ሴቶች ልጆች ሚስ​ትን አገባ።</verse>
				<verse number="2">ሴቲ​ቱም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች፤ መል​ካ​ምም እን​ደ​ሆነ በአዩ ጊዜ ሦስት ወር ሸሸ​ጉት።</verse>
				<verse number="3">ደግ​ሞም ሊሸ​ሽ​ጉት በአ​ል​ቻሉ ጊዜ እናቱ የደ​ን​ገል ሣጥን ለእ​ርሱ ወስዳ ዝፍ​ትና ቅጥ​ራን ለቀ​ለ​ቀ​ችው፤ ሕፃ​ኑ​ንም አኖ​ረ​ች​በት፤ በወ​ን​ዝም ዳር ባለ በቄ​ጠማ ውስጥ አስ​ቀ​መ​ጠ​ችው።</verse>
				<verse number="4">እኅ​ቱም ምን እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ስ​በት ታውቅ ዘንድ በሩቅ ቆማ ትጐ​በ​ኘው ነበር።</verse>
				<verse number="5">የፈ​ር​ዖ​ንም ሴት ልጅ ልት​ታ​ጠብ ወደ ወንዝ ወረ​ደች፤ ደን​ገ​ጥ​ሮ​ች​ዋም በወ​ንዝ ዳር ይሄዱ ነበር፤ ሣጥ​ኑ​ንም በቄ​ጠማ ውስጥ አየች፤ ደን​ገ​ጥ​ር​ዋ​ንም ልካ አስ​መ​ጣ​ችው።</verse>
				<verse number="6">ሣጥ​ኑን በከ​ፈ​ተ​ችም ጊዜ ሕፃ​ኑን አየች፤ እነ​ሆም፥ ሕፃኑ በሣ​ጥኑ ውስጥ ያለ​ቅስ ነበር፤ የፈ​ር​ዖ​ንም ልጅ አዘ​ነ​ች​ለት፥ “ይህ ሕፃን ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ልጆች አንዱ ነው” አለች።</verse>
				<verse number="7">የዚ​ያም ሕፃን እኅት ለፈ​ር​ዖን ልጅ፥ “ሕፃ​ኑን ታጠ​ባ​ልሽ ዘንድ ሄጄ የም​ታ​ጠባ ሴት ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ሴቶች ልጥ​ራ​ል​ሽን?” አለ​ቻት።</verse>
				<verse number="8">የፈ​ር​ዖ​ንም ልጅ፥ “ሂጂና ጥሪ​ልኝ” አለ​ቻት፤ ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም ሄዳ የሕ​ፃ​ኑን እናት ጠራች።</verse>
				<verse number="9">የፈ​ር​ዖ​ንም ልጅ፥ “ይህን ሕፃን ተን​ከ​ባ​ክ​በሽ አጥ​ቢ​ልኝ፤ ዋጋ​ሽ​ንም እሰ​ጥ​ሻ​ለሁ” አለ​ቻት። ሴቲ​ቱም ሕፃ​ኑን ወስዳ አጠ​ባ​ችው።</verse>
				<verse number="10">ሕፃ​ኑም በአ​ደገ ጊዜ ወደ ፈር​ዖን ልጅ ወሰ​ደ​ችው፤ ለእ​ር​ስ​ዋም ልጅ ሆነ​ላት። እኔ ከውኃ አው​ጥ​ቼ​ዋ​ለ​ሁና ስት​ልም ስሙን ሙሴ ብላ ጠራ​ችው ።</verse>
				<verse number="11">ከብዙ ቀን በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ ሙሴ አደገ፤ ወደ ወን​ድ​ሞ​ቹም ወጣ፤ መከ​ራ​ቸ​ው​ንም ተመ​ለ​ከተ፤ የግ​ብ​ፅም ሰው ከወ​ን​ድ​ሞቹ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አን​ዱን ዕብ​ራዊ ሰው ሲመታ አየ።</verse>
				<verse number="12">ወዲ​ህና ወዲያ ተመ​ለ​ከተ፤ ማን​ንም አላ​የም፤ ግብ​ፃ​ዊ​ው​ንም ገደ​ለው፤ በአ​ሸዋ ውስ​ጥም ቀበ​ረው።</verse>
				<verse number="13">በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ወጣ፤ ሁለ​ቱም የዕ​ብ​ራ​ው​ያን ሰዎች ሲጣሉ አየ፤ ሙሴም በዳ​ዩን፥ “ለምን ባል​ን​ጀ​ራ​ህን ትመ​ታ​ዋ​ለህ?” አለው።</verse>
				<verse number="14">ወን​ድ​ሙን የሚ​በ​ድ​ለው ያም ሰው፥ “በእኛ ላይ አን​ተን አለቃ ወይስ ዳኛ ማን አደ​ረ​ገህ? ወይስ ግብ​ፃ​ዊ​ውን ትና​ንት እንደ ገደ​ል​ኸው ልት​ገ​ድ​ለኝ ትሻ​ለ​ህን?” አለው። ሙሴም፥ “በእ​ው​ነት ይህ ነገር ታው​ቆ​አ​ልን?” ብሎ ፈራ።</verse>
				<verse number="15">ፈር​ዖ​ንም ይህን ነገር ሰማ፤ ሙሴ​ንም ሊገ​ድ​ለው ፈለገ። ሙሴ ግን ከፈ​ር​ዖን ፊት ኰበ​ለለ፤ በም​ድ​ያ​ምም ምድር ተቀ​መጠ፤ ወደ ምድ​ያም ምድር በደ​ረሰ ጊዜም በው​ኃው ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ዐረፈ።</verse>
				<verse number="16">ለም​ድ​ያ​ምም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበ​ሩት፤ የአ​ባ​ታ​ቸ​ው​ንም የዮ​ቶ​ርን በጎች ይጠ​ብቁ ነበር፤ እነ​ር​ሱም መጥ​ተው ውኃ ቀዱ፤ የአ​ባ​ታ​ቸ​ው​ንም የዮ​ቶ​ርን በጎች ሊያ​ጠጡ የው​ኃ​ዉን ገንዳ ሞሉ።</verse>
				<verse number="17">እረ​ኞ​ችም መጥ​ተው ገፉ​አ​ቸው፤ ሙሴ ግን ተነ​ሥቶ አዳ​ና​ቸው፤ እየ​ቀ​ዳም በጎ​ቻ​ቸ​ዉን አጠ​ጣ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">ወደ አባ​ታ​ቸ​ውም ወደ ራጉ​ኤል መጡ እር​ሱም፥ “ዛሬስ እን​ዴት ፈጥ​ና​ችሁ መጣ​ችሁ?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">እነ​ር​ሱም፥ “አንድ የግ​ብፅ ሰው ከእ​ረ​ኞች እጅ አዳ​ነን፤ ደግ​ሞም ቀዳ​ልን፤ በጎ​ቻ​ች​ን​ንም አጠ​ጣ​ልን” አሉት።</verse>
				<verse number="20">ልጆ​ቹ​ንም፥ “ሰው​ዬው ወዴት ነው? ለም​ንስ ያን ሰው ተዋ​ች​ሁት? ጥሩት፤ እን​ጀ​ራም ይብላ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">ሙሴም ከዚያ ሰው ጋር ሊቀ​መጥ ወደደ፤ ልጁ​ንም ሲፓ​ራን ለሙሴ ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠው።</verse>
				<verse number="22">ያችም ሴት ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች፤ ሙሴም፥ “በሌላ ምድር መጻ​ተኛ ነኝ” ሲል ስሙን ጌር​ሳም ብሎ ጠራው። ዳግ​መ​ኛም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ኤል​ኤ​ዜር አለው፤ የአ​ባቴ ፈጣሪ ረዳቴ ነው ሲል።</verse>
				<verse number="23">ከዚ​ያም ከብዙ ቀን በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ የግ​ብፅ ንጉሥ ሞተ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከባ​ር​ነት የተ​ነሣ አለ​ቀሱ፤ ጮኹም፤ ስለ ባር​ነ​ታ​ቸ​ውም ጩኸ​ታ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወጣ።</verse>
				<verse number="24">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጩኸ​ታ​ቸ​ውን ሰማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ብ​ር​ሃ​ምና ከይ​ስ​ሐቅ፥ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ጋር ያደ​ረ​ገ​ውን ቃል ኪዳን ዐሰበ።</verse>
				<verse number="25">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ጐበ​ኛ​ቸው፤ ታወ​ቀ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ሙሴም የአ​ማ​ቱን የም​ድ​ያ​ምን ካህን የዮ​ቶ​ርን በጎች ይጠ​ብቅ ነበር፤ በጎ​ቹ​ንም ወደ ምድረ በዳ ዳርቻ ነዳ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ።</verse>
				<verse number="2">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ለሙሴ በእ​ሳት ነበ​ል​ባል በቍ​ጥ​ቋጦ መካ​ከል ታየው፤ እነ​ሆም፥ ቍጥ​ቋ​ጦው በእ​ሳት ሲነ​ድድ፥ ቍጥ​ቋ​ጦ​ውም ሳይ​ቃ​ጠል አየ።</verse>
				<verse number="3">ሙሴም፥ “ልሂ​ድና ቍጥ​ቋ​ጦው ስለ​ምን አል​ተ​ቃ​ጠ​ለም? ይህን ታላቅ ራእይ ልይ” አለ።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ ይመ​ለ​ከት ዘንድ እንደ መጣ በአየ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከቍ​ጥ​ቋ​ጦው ውስጥ እር​ሱን ጠርቶ፥ “ሙሴ! ሙሴ!” አለው እር​ሱም፥ “ይህ ምን​ድን ነው?” አለ።</verse>
				<verse number="5">“ወደ​ዚህ አት​ቅ​ረብ፤ አንተ የቆ​ም​ህ​ባት ስፍራ የተ​ቀ​ደ​ሰች መሬት ናትና፥ ጫማ​ህን ከእ​ግ​ርህ አውጣ” አለው።</verse>
				<verse number="6">ደግ​ሞም፥ “እኔ የአ​ባ​ቶ​ችህ አም​ላክ፥ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ ነኝ” አለው። ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያይ ዘንድ ፈር​ቶ​አ​ልና ፊቱን መለሰ።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “በግ​ብፅ ያለ​ውን የሕ​ዝ​ቤን መከራ በእ​ው​ነት አየሁ፦ ከአ​ሠ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ጩኸ​ታ​ቸ​ውን ሰማሁ፤ ሥቃ​ያ​ቸ​ው​ንም ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="8">ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም እጅ አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ ከዚ​ያ​ችም ሀገር ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ሀገር፥ ወደ ሰፊ​ዪ​ቱና ወደ መል​ካ​ሚቱ ሀገር፥ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ስፍራ አወ​ጣ​ቸው ዘንድ ወረ​ድሁ።</verse>
				<verse number="9">አሁ​ንም እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጩኸት ወደ እኔ ደረሰ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ባ​ቸ​ውን ግፍ ደግሞ አየሁ።</verse>
				<verse number="10">አሁ​ንም ና፤ ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ፈር​ዖን እል​ክ​ሃ​ለሁ። ሕዝ​ቤን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ታወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።”</verse>
				<verse number="11">ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ፈር​ዖን እሄድ ዘንድ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ከግ​ብፅ ምድር አወጣ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?” አለው።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ተና​ገ​ረው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “በእ​ው​ነት እኔ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ እኔም እንደ ላክ​ሁህ ይህ ለአ​ንተ ምል​ክት ይሆ​ን​ሃል፤ ሕዝ​ቡን ከግ​ብፅ በአ​ወ​ጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ል​ካ​ላ​ችሁ” አለው።</verse>
				<verse number="13">ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “እነሆ፥ እኔ ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች እሄ​ዳ​ለሁ፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ ወደ እና​ንተ ላከኝ እላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ‘ስሙስ ማን ነው?’ ብለው በጠ​የ​ቁኝ ጊዜ ምን እላ​ቸ​ዋ​ለሁ?” አለው።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙሴ ነገ​ረው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “ያለና የሚ​ኖር እኔ ነኝ፤ እን​ዲህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ‘ያለና የሚ​ኖር’ ወደ እና​ንተ ላከኝ ትላ​ቸ​ዋ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="15">ዳግ​መ​ኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን አለው፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ትላ​ለህ፦ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ፥ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ እና​ንተ ላከኝ፤ ይህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ስሜ ነው፤ እስከ ልጅ ልጅ ድረ​ስም መታ​ሰ​ቢ​ያዬ ይህ ነው።</verse>
				<verse number="16">ሂድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሰብ​ስብ፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ፥ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል ተገ​ለ​ጠ​ልኝ፦ መጐ​ብ​ኘ​ትን ጐበ​ኘ​ኋ​ችሁ፤ በግ​ብ​ፅም የሚ​ደ​ረ​ግ​ባ​ች​ሁን አየሁ፤</verse>
				<verse number="17">እን​ዲ​ህም አልሁ፦ ከግ​ብፅ መከራ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን፥ ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያን ሀገር፥ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስስ ሀገር አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="18">እነ​ር​ሱም ቃል​ህን ይሰ​ማሉ፤ አን​ተና የእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወደ ግብፅ ንጉሥ ትገ​ባ​ላ​ችሁ፦ የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠር​ቶ​ናል፤ አሁ​ንም ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ሠዋ ዘንድ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ወደ ምድረ በዳ እን​ሄ​ዳ​ለን ትሉ​ታ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="19">ነገር ግን በጽኑ እጅ ካል​ሆነ በቀር ትሄዱ ዘንድ የግ​ብፅ ንጉሥ እን​ደ​ማ​ይ​ፈ​ቅ​ድ​ላ​ችሁ እኔ አው​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">እኔም እጄን እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ በማ​ደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ውም ተአ​ም​ራቴ ሁሉ ግብ​ፅን እመ​ታ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ይለ​ቅ​ቋ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="21">በግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ፊት ለዚህ ሕዝብ ሞገ​ስን እሰ​ጣ​ለሁ፤ በም​ት​ሄ​ዱም ጊዜ ባዶ እጃ​ች​ሁን አት​ሄ​ዱም፤</verse>
				<verse number="22">ነገር ግን እያ​ን​ዳ​ን​ዲቱ ሴት ከጎ​ረ​ቤቷ፥ በቤ​ቷም ካለ​ችው ሴት የብር ዕቃ፥ የወ​ርቅ ዕቃ፥ ልብ​ስም ትዋ​ሳ​ለች፤ በወ​ን​ዶ​ችና በሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ችሁ ላይም ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ችሁ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም ትበ​ዘ​ብ​ዛ​ላ​ችሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ሙሴም መለሰ፥ “እነሆ፥ ባያ​ም​ኑኝ፥ ቃሌ​ንም ባይ​ሰሙ፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አል​ተ​ገ​ለ​ጠ​ል​ህም’ ቢሉኝ ምን እላ​ቸ​ዋ​ለሁ?” አለ።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይህ በእ​ጅህ ያለው ምን​ድን ነው?” አለው። እር​ሱም፥ “በትር ነው” አለ።</verse>
				<verse number="3">“ወደ መሬት ጣለው” አለው፤ እር​ሱም በመ​ሬት ጣለው፤ እባ​ብም ሆነ፤ ሙሴም ከእ​ርሱ ሸሸ።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “እጅ​ህን ዘር​ግ​ተህ ጅራ​ቱን ያዝ” አለው፤ ሙሴም እጁን ዘር​ግቶ፥ ጅራ​ቱን ይዞ፥ አነ​ሣው በእ​ጁም በትር ሆነ።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ፥ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እንደ ታየህ ያም​ኑ​ሃል” አለው።</verse>
				<verse number="6">ዳግ​መ​ኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “እጅ​ህን ወደ ብብ​ትህ አግባ አለው።” እጁ​ንም ወደ ብብቱ አገ​ባት፤ “እጅ​ህ​ንም ከብ​ብ​ትህ አውጣ” አለው፤ እጁ​ንም ከብ​ብቱ አወጣ፤ እጁም ለምጽ ሆነች።</verse>
				<verse number="7">ዳግ​መ​ኛም፥ “እጅ​ህን ወደ ብብ​ትህ መልስ” አለው። እጁ​ንም ወደ ብብቱ መለ​ሳት፤ “እጅ​ህን ከብ​ብ​ትህ አውጣ” አለው፤ እጁ​ንም ከብ​ብቱ አወጣ፤ ተመ​ል​ሳም ገላ​ውን መሰ​ለች።</verse>
				<verse number="8">ደግ​ሞም አለው፥ “እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ባያ​ም​ኑህ፥ በፊ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ምል​ክት ቃል​ህን ባይ​ሰሙ፥ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪቱ ምል​ክት ቃል​ህን ያም​ናሉ።</verse>
				<verse number="9">እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ እነ​ዚ​ህን ሁለት ምል​ክ​ቶች ባያ​ምኑ፥ ቃል​ህ​ንም ባይ​ሰሙ፥ ከወ​ንዙ ውኃን ውሰድ፤ በደ​ረ​ቁም መሬት ላይ አፍ​ስ​ሰው፤ ከወ​ን​ዙም የወ​ሰ​ድ​ኸው ውኃ በደ​ረቁ መሬት ላይ ደም ይሆ​ናል።”</verse>
				<verse number="10">ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ጌታ ሆይ፥ እማ​ል​ድ​ሃ​ለሁ፤ ትና​ንት፥ ከት​ና​ንት ወዲያ ባሪ​ያ​ህን ከተ​ና​ገ​ር​ኸኝ ጀምሮ አፈ ትብ ሰው አይ​ደ​ለ​ሁም። እኔ አፌ ኰል​ታፋ፥ ምላ​ሴም ተብ​ታባ የሆነ ሰው ነኝ።”</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ለሰው አፍን የሰጠ ማን ነው? ዲዳስ፥ ደን​ቆ​ሮስ፥ የሚ​ያ​ይስ፥ ዕው​ርስ የሚ​ያ​ደ​ርግ ማን ነው? እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን?</verse>
				<verse number="12">እን​ግ​ዲህ አሁን ሂድ፤ እኔም አን​ደ​በ​ት​ህን አረ​ታ​ለሁ፤ ትና​ገ​ረ​ውም ዘንድ ያለ​ህን አለ​ብ​ም​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="13">ሙሴም፥ “ጌታ ሆይ፥ እማ​ል​ድ​ሃ​ለሁ፤ መና​ገር የሚ​ችል የም​ት​ል​ከው ሌላ ሰው ፈልግ” አለው።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሙሴ ላይ እጅግ ተቈጣ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ሌዋ​ዊው ወን​ድ​ምህ አሮን አለ አይ​ደ​ለ​ምን? እርሱ እን​ደ​ሚ​ና​ገ​ር​ልህ አው​ቃ​ለሁ፤ እነ​ሆም፥ እርሱ ሊገ​ና​ኝህ ይመ​ጣል፤ በአ​የ​ህም ጊዜ በልቡ ደስ ይለ​ዋል።</verse>
				<verse number="15">አን​ተም ትና​ገ​ረ​ዋ​ለህ፤ ቃሌ​ንም በአፉ ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ፤ እኔ አን​ደ​በ​ት​ህ​ንና አን​ደ​በ​ቱን አረ​ታ​ለሁ፤ የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ት​ንም አለ​ብ​ማ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">እርሱ ስለ አንተ ከሕ​ዝቡ ጋር ይነ​ጋ​ገ​ራል፤ እርሱ አፍ ይሆ​ን​ል​ሃል፤ አን​ተም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ትሆ​ን​ለ​ታ​ለህ።</verse>
				<verse number="17">ይህ​ች​ንም ተአ​ም​ራት የም​ታ​ደ​ር​ግ​ባ​ትን በትር በእ​ጅህ ያዝ።”</verse>
				<verse number="18">ሙሴም ሄደ፤ ወደ አማቱ ወደ ዮቶ​ርም ተመ​ለሰ፥ “እስከ ዛሬ በሕ​ይ​ወት እንደ አሉ አይ ዘንድ ተመ​ልሼ ወደ ግብፅ ወደ ወን​ድ​ሞች እሄ​ዳ​ለሁ” አለው። ዮቶ​ርም ሙሴን፥ “በደ​ኅና ሂድ” አለው።</verse>
				<verse number="19">ከብዙ ዘመ​ንም በኋላ የግ​ብፅ ንጉሥ ሞተ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን በም​ድ​ያም፥ “ነፍ​ስ​ህን የሚ​ሹ​አት ሰዎች ሁሉ ሞተ​ዋ​ልና ተመ​ል​ሰህ ወደ ግብፅ ሂድ” አለው።</verse>
				<verse number="20">ሙሴም ሚስ​ቱ​ንና ልጆ​ቹን ወሰደ፤ በአ​ህ​ዮች ላይም አስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው፤ ወደ ግብ​ፅም ሀገር ተመ​ለሰ፤ ሙሴም ያችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በትር በእጁ ይዞ ሄደ።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ግብፅ ተመ​ል​ሰህ ስት​ሄድ በእ​ጅህ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ተአ​ም​ራ​ቴን ሁሉ በፈ​ር​ዖን ፊት ታደ​ር​ገው ዘንድ ተመ​ል​ከት፤ እኔ ግን ልቡን አጸ​ና​ዋ​ለሁ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አይ​ለ​ቅ​ቅም።</verse>
				<verse number="22">አንተ ግን ፈር​ዖ​ንን እን​ዲህ ትለ​ዋ​ለህ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እስ​ራ​ኤል የበ​ኵር ልጄ ነው፤</verse>
				<verse number="23">ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ አል​ሁህ፤ አን​ተም ልት​ለ​ቅ​ቃ​ቸው ባት​ፈ​ቅድ፤ እኔ የበ​ኵር ልጅ​ህን እን​ደ​ም​ገ​ድል ዕወቅ።”</verse>
				<verse number="24">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በመ​ን​ገድ ላይ በአ​ደ​ረ​በት ስፍራ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ተገ​ና​ኘው፤ ሊገ​ድ​ለ​ውም ፈለገ።</verse>
				<verse number="25">ሚስቱ ሲፓ​ራም ባል​ጩት ወሰ​ደች፤ የል​ጅ​ዋ​ንም ሸለ​ፈት ገረ​ዘች፤ “ይህ የልጄ የግ​ር​ዛቱ ደም ስለ እርሱ ፈንታ ይሁን” ብላ ከእ​ግሩ በታች ወደ​ቀች።</verse>
				<verse number="26">ከእ​ር​ሱም ሄደ፤ የዚያ ጊዜ፥ “ይህ የልጄ የግ​ር​ዛቱ ደም ስለ እርሱ ፈንታ ይሁን” ብላ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="27">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን አለው፥ “ሄደህ በም​ድረ በዳ ሙሴን ተገ​ና​ኘው፤” ሄዶም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ ተገ​ና​ኘው፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተሳ​ሳሙ።</verse>
				<verse number="28">ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የላ​ከ​ውን ቃል ሁሉ፥ የአ​ዘ​ዘ​ው​ንም ተአ​ም​ራት ሁሉ ለአ​ሮን ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="29">ሙሴና አሮ​ንም ሄዱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ሰበ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="30">አሮ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ የነ​ገ​ረ​ውን ቃል ሁሉ ተና​ገረ፤ ተአ​ም​ራ​ቱ​ንም በሕ​ዝቡ ፊት አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="31">ሕዝ​ቡም አመኑ፤ ደስም አላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ጐብ​ኝ​ቶ​አ​ልና፤ ጭን​ቀ​ታ​ቸ​ው​ንም አይ​ቶ​አ​ልና፤ ሕዝ​ቡም ራሳ​ቸ​ውን ዝቅ አድ​ር​ገው ሰገዱ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ፈር​ዖን ገብ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘በም​ድረ በዳ በዓል ያደ​ር​ግ​ልኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።’ ”</verse>
				<verse number="2">ፈር​ዖ​ንም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እለ​ቅቅ ዘንድ ቃሉን የም​ሰ​ማው እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማን ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ው​ቅም፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ደግሞ አል​ለ​ቅ​ቅም” አለ።</verse>
				<verse number="3">እነ​ር​ሱም፥ “ቸነ​ፈር ወይም ሰይፍ እን​ዳ​ይ​ጥ​ል​ብን የሦ​ስት ቀን መን​ገድ በም​ድረ በዳ እን​ድ​ን​ሄድ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ድ​ን​ሠዋ የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ ጠራን” አሉት።</verse>
				<verse number="4">የግ​ብፅ ንጉ​ሥም፥ “እና​ንተ ሙሴና አሮን፥ ሕዝ​ቡን ለምን ሥራ​ቸ​ዉን ታስ​ተ​ዋ​ላ​ችሁ? ወደ ተግ​ባ​ራ​ችሁ ሂዱ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">ፈር​ዖ​ንም ለሕ​ዝቡ አለ፥ “እነሆ፥ ሕዝቡ በም​ድር በጣም በዝ​ተ​ዋል፤ እና​ን​ተም ከሥ​ራ​ቸው አሳ​ር​ፋ​ች​ኋ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">ፈር​ዖ​ንም በዚያ ቀን የሕ​ዝ​ቡን አሠ​ሪ​ዎ​ችና ጸሓ​ፊ​ዎች እን​ዲህ ሲል አዘዘ፦</verse>
				<verse number="7">“እንደ ወት​ሮው ለጡብ ሥራ ደግሞ ገለባ ለሕ​ዝቡ አት​ስጡ፤ ነገር ግን እነ​ርሱ ሄደው ለራ​ሳ​ቸው ገለባ ይሰ​ብ​ስቡ።</verse>
				<verse number="8">ቀድሞ ያደ​ር​ጉት የነ​በ​ረ​ውን የጡብ ቍጥር እን​ዲሁ በየ​ቀኑ በእ​ነ​ርሱ ላይ አድ​ር​ጉት፤ ምንም ከእ​ርሱ አታ​ጕ​ድሉ፤ ሥራ ሰል​ች​ተ​ዋ​ልና ስለ​ዚህ፦ ‘ለአ​ም​ላ​ካ​ችን እን​ድ​ን​ሠዋ እን​ሂድ’ እያሉ ይጮ​ሃሉ።</verse>
				<verse number="9">በእ​ነ​ዚህ ሰዎች ላይ ሥራው ይክ​በ​ድ​ባ​ቸው፤ ይህን ብቻ ያስ​ባሉ፤ ከንቱ ቃልም አያ​ስ​ቡም።”</verse>
				<verse number="10">የሕ​ዝ​ቡም አሠ​ሪ​ዎ​ችና ጸሓ​ፊ​ዎች ወጡ፤ ሕዝ​ቡ​ንም፥ “ፈር​ዖን እን​ዲህ ይላል፦ እን​ግ​ዲህ ገለባ አይ​ሰ​ጣ​ች​ሁም፤</verse>
				<verse number="11">እና​ንተ ሂዱ፤ ከም​ታ​ገ​ኙ​በ​ትም ስፍራ ገለባ ሰብ​ስቡ፤ ከም​ት​ሠ​ሩት ጡብ ግን ምንም አይ​ጐ​ድ​ልም” አሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">ሕዝ​ቡም ሁሉ ስለ ገለባ እብቅ ሊሰ​በ​ስቡ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ተበ​ተኑ።</verse>
				<verse number="13">አሠ​ሪ​ዎ​ቹም፥ “ገለባ ትቀ​በ​ሉ​በት እን​ደ​ነ​በረ ጊዜ የቀን ሥራ​ች​ሁን ጨርሱ” እያሉ ያስ​ቸ​ኩ​ሉ​አ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="14">የፈ​ር​ዖ​ንም ሹሞች፥ “ቀድሞ ታደ​ር​ጉት እንደ ነበ​ራ​ችሁ እንደ ትና​ን​ት​ና​ውና እንደ ትና​ን​ትና በስ​ቲ​ያው የተ​ቈ​ጠ​ረ​ውን ጡብ ዛሬስ ስለ​ምን አት​ጨ​ር​ሱም?” እያሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን አለ​ቆች ይገ​ርፉ ነበር።</verse>
				<verse number="15">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አለ​ቆ​ችም ወደ ፈር​ዖን ገቡ፥ “ለምን በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ለህ? ገለባ አይ​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውም፤ ጡቡ​ንም ሥሩ ይሉ​አ​ቸ​ዋል፤</verse>
				<verse number="16">እነ​ሆም፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ይገ​ረ​ፋሉ፤ ይገ​ፋ​ሉም፤ ግፉም በአ​ንተ ሕዝብ ላይ ነው” ብለው ጮኹ።</verse>
				<verse number="17">እርሱ ግን፥ “እና​ንተ አር​ፋ​ች​ኋል፤ ቦዝ​ና​ች​ኋል፤ ስለ​ዚ​ህም፦ ‘እን​ሂድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ሠዋ’ ትላ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="18">አሁ​ንም ሂዱ፤ ሥሩ፤ ገለ​ባም አይ​ሰ​ጡ​አ​ች​ሁም፤ የጡ​ቡን ቍጥር ግን ታመ​ጣ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አለ​ቆች ዕለት ዕለት ከም​ት​ሠ​ሩት ከጡቡ ቍጥር ምንም አታ​ጕ​ድሉ ባሉ​አ​ቸው ጊዜ ነገሩ እንደ ከፋ​ባ​ቸው አዩ።</verse>
				<verse number="20">ከፈ​ር​ዖ​ንም ዘንድ ሲወጡ ሙሴ​ንና አሮ​ንን በፊ​ታ​ቸው ቆመው ተገ​ና​ኙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">እነ​ር​ሱም፥ “በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት ሽታ​ች​ንን አግ​ም​ታ​ች​ሁ​ታ​ልና፥ ይገ​ድ​ለ​ንም ዘንድ ሰይ​ፍን በእጁ ሰጥ​ታ​ች​ሁ​ታ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ል​ከ​ታ​ችሁ፤ ይፍ​ረ​ድ​ባ​ች​ሁም” አሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ለ​ሰና፥ “ጌታ ሆይ፥ ስለ​ምን ይህን ሕዝብ አስ​ከ​ፋህ? ስለ ምንስ ላክ​ኸኝ?</verse>
				<verse number="23">በስ​ምህ እና​ገር ዘንድ ወደ ፈር​ዖን ከገ​ባሁ ወዲህ፥ ይህን ሕዝብ አስ​ከ​ፍ​ቶ​ታ​ልና፤ አን​ተም ሕዝ​ብ​ህን ከቶ አላ​ዳ​ን​ኸ​ውም” አለ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “በጸ​ናች እጅ ይለ​ቅ​ቃ​ቸ​ዋ​ልና፥ በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ ከም​ድሩ አስ​ወ​ጥቶ ይሰ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ልና አሁን በፈ​ር​ዖን የማ​ደ​ር​ገ​ውን ታያ​ለህ።”</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ተና​ገ​ረው አለ​ውም፥ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።</verse>
				<verse number="3">ለአ​ብ​ር​ሃ​ምም፥ ለይ​ስ​ሐ​ቅም፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ሁሉን እን​ደ​ሚ​ችል አም​ላክ ተገ​ለ​ጥሁ፤ ነገር ግን ስሜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ታ​ወ​ቀ​ላ​ቸ​ውም ነበር።</verse>
				<verse number="4">የነ​በ​ሩ​ባ​ት​ንም የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳ​ኔን አቆ​ምሁ።</verse>
				<verse number="5">ደግሞ እኔ ግብ​ፃ​ው​ያን የገ​ዙ​አ​ቸ​ውን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ልቅሶ ሰማሁ፤ ቃል ኪዳ​ኔ​ንም አሰ​ብሁ።”</verse>
				<verse number="6">ስለ​ዚ​ህም ፈጥ​ነህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ በላ​ቸው፥ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ተገ​ዥ​ነት አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከባ​ር​ነ​ታ​ቸ​ውም አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ በተ​ዘ​ረጋ ክንድ፤ በታ​ላቅ ፍር​ድም እታ​ደ​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="7">ለእ​ኔም ሕዝብ እን​ድ​ት​ሆኑ እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን ባር​ነት ያወ​ጣ​ኋ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="8">ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም እሰ​ጣት ዘንድ እጄን ወደ ዘረ​ጋ​ሁ​ባት ምድር አገ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ርስት አድ​ርጌ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።”</verse>
				<verse number="9">ሙሴም ይህን ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተና​ገረ፤ እነ​ርሱ ግን ከሰ​ው​ነ​ታ​ቸው መጨ​ነቅ፥ ከሥ​ራ​ቸ​ውም ክብ​ደት የተ​ነሣ ቃሉን አል​ሰ​ሙ​ትም።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="11">“ግባ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከሀ​ገሩ ይለ​ቅቅ ዘንድ ለግ​ብፅ ንጉሥ ለፈ​ር​ዖን ንገ​ረው።”</verse>
				<verse number="12">ሙሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት፥ “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አል​ሰ​ሙ​ኝም፤ እን​ዴ​ትስ ፈር​ዖን ይሰ​ማ​ኛል? እኔም አን​ደ​በተ ርቱዕ አይ​ደ​ለ​ሁም” ብሎ ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ተና​ገ​ራ​ቸው፤ የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከግ​ብፅ እን​ዲ​ያ​ወ​ጣ​ቸው ይነ​ግ​ሩት ዘንድ አዘ​ዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤት አለ​ቆች እነ​ዚህ ናቸው። የእ​ስ​ራ​ኤል የበ​ኵር ልጅ የሮ​ቤል ልጆች ሄኖኅ፥ ፍሉስ፥ አስ​ሮን፥ ከርሚ፤ እነ​ዚህ የሮ​ቤል ትው​ልድ ናቸው።</verse>
				<verse number="15">የስ​ም​ዖ​ንም ልጆች፤ ይሙ​ኤል፥ ያሚን፥ አኡድ፥ ያኪን፥ ሱሐር፥ የፊ​ኒ​ቃ​ዊ​ቱም ልጅ ሳኡል፤ እነ​ዚህ የስ​ም​ዖን ትው​ልድ ናቸው።</verse>
				<verse number="16">እነ​ዚ​ህም እንደ ወገ​ኖ​ቻ​ቸው የሌዊ ልጆች ስሞች ናቸው፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ናቸው። የሌ​ዊም የሕ​ይ​ወት ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።</verse>
				<verse number="17">የጌ​ድ​ሶ​ንም ልጆች በየ​አ​ባ​ታ​ቸው ወገን ሎቤኒ፥ ሰሜኢ ናቸው።</verse>
				<verse number="18">የቀ​ዓ​ትም ልጆች እን​በ​ረም፥ ይስ​ዓር፥ ኬብ​ሮን፥ ዑዝ​ኤል ናቸው፤ የቀ​ዓ​ትም የሕ​ይ​ወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሦስት ዓመት ነው።</verse>
				<verse number="19">የሜ​ራሪ ልጆች ሞሖሊ፥ ሐሙሲ ናቸው። እነ​ዚ​ህም እንደ ትው​ል​ዳ​ቸው የሌዊ ትው​ልድ ናቸው።</verse>
				<verse number="20">እን​በ​ረ​ምም የአ​ባ​ቱን ወን​ድም ልጅ ዮካ​ብ​ድን አገባ፤ አሮ​ን​ንና ሙሴን፥ እኅ​ታ​ቸ​ው​ንም ማር​ያ​ምን ወለ​ደ​ች​ለት፤ የእ​ን​በ​ረ​ምም የሕ​ይ​ወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።</verse>
				<verse number="21">የይ​ስ​ዓ​ርም ልጆች ቆሬ፥ ናፌግ፥ ዝክሪ ናቸው።</verse>
				<verse number="22">የዑ​ዝ​ኤ​ልም ልጆች ሚሳ​ኤል፥ ኤል​ሳ​ፋን፥ ሴትሪ ናቸው።</verse>
				<verse number="23">አሮ​ንም የአ​ሚ​ና​ዳ​ብን ልጅ የነ​አ​ሶ​ንን እኅት ኤል​ሳ​ቤ​ጥን አገባ። እር​ስ​ዋም ናዳ​ብ​ንና አብ​ዩ​ድን፥ አል​ዓ​ዛ​ር​ንና ኢታ​ም​ርን ወለ​ደ​ች​ለት።</verse>
				<verse number="24">የቆሬ ልጆች አሴር፥ ሕል​ቃና፥ አብ​ያ​ሳፍ ናቸው፤ እነ​ዚህ የቆሬ ልጆች ትው​ልድ ናቸው።</verse>
				<verse number="25">የአ​ሮ​ንም ልጅ አል​ዓ​ዛር ከፋ​ት​ኤል ልጆች ሚስ​ትን አገባ፤ እር​ስ​ዋም ፊን​ሐ​ስን ወለ​ደ​ች​ለት። እነ​ዚ​ህም በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው የሌ​ዋ​ው​ያን አባ​ቶች አለ​ቆች ናቸው።</verse>
				<verse number="26">እነ​ዚህ አሮ​ንና ሙሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ከግ​ብፅ ምድር ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አውጡ” ያላ​ቸው ናቸው።</verse>
				<verse number="27">እነ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከግ​ብፅ ያወጡ ዘንድ ከግ​ብፅ ንጉሥ ከፈ​ር​ዖን ጋር የተ​ነ​ጋ​ገሩ ናቸው፤ እነ​ዚ​ህም ሙሴና አሮን ናቸው።</verse>
				<verse number="28">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በግ​ብፅ ሀገር ሙሴን በተ​ና​ገ​ረው ቀን እን​ዲህ ሆነ፤</verse>
				<verse number="29">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን፥ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ እኔ የም​ነ​ግ​ር​ህን ሁሉ ለግ​ብፅ ንጉሥ ለፈ​ር​ዖን ንገር” ብሎ ተና​ገ​ረው።</verse>
				<verse number="30">ሙሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት፥ “እነሆ፥ እኔ አን​ደ​በተ ርቱዕ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ እን​ዴ​ትስ ፈር​ዖን ይሰ​ማ​ኛል?” አለ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እነሆ፥ እኔ ለፈ​ር​ዖን አም​ላክ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ ወን​ድ​ም​ህም አሮን ነቢይ ይሆ​ን​ል​ሃል።</verse>
				<verse number="2">ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ነገር ሁሉ አንተ ትነ​ግ​ረ​ዋ​ለህ፤ ወን​ድ​ም​ህም አሮን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከሀ​ገሩ ይለ​ቅቅ ዘንድ ለፈ​ር​ዖን ይን​ገ​ረው።</verse>
				<verse number="3">እኔም የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸ​ና​ለሁ፤ በግ​ብፅ ምድ​ርም ድን​ቄ​ንና ተአ​ም​ራ​ቴን አበ​ዛ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">ፈር​ዖ​ንም አይ​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ እጄ​ንም በግ​ብፅ ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ሕዝ​ቤን በኀ​ይሌ በታ​ላቅ ፍርድ ከግ​ብፅ ሀገር አወ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም እጄን በግ​ብፅ ላይ በዘ​ረ​ጋሁ ጊዜ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው በአ​ወ​ጣሁ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”</verse>
				<verse number="6">ሙሴና አሮ​ንም እን​ዲህ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="7">ፈር​ዖ​ን​ንም በተ​ና​ገ​ሩት ጊዜ ሙሴ ሰማ​ንያ ዓመት ሆኖት ነበር፤ አሮ​ንም ሰማ​ንያ ሦስት ዓመት ሆኖት ነበረ።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ራ​ቸው፦</verse>
				<verse number="9">“ፈር​ዖን፦ ተአ​ም​ራ​ት​ንና ድን​ቅን አሳ​ዩኝ ሲላ​ችሁ፥ ወን​ድ​ምህ አሮ​ንን፦ ‘በት​ር​ህን ወስ​ደህ በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት ጣላት’ በለው፤ እባ​ብም ትሆ​ና​ለች።”</verse>
				<verse number="10">ሙሴና አሮ​ንም ወደ ፈር​ዖን ገቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ አሮ​ንም በት​ሩን በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት ጣለ፤ እባ​ብም ሆነች።</verse>
				<verse number="11">ፈር​ዖ​ንም ጠቢ​ባ​ን​ንና መተ​ተ​ኞ​ችን ጠራ፤ የግ​ብ​ፅም ጠን​ቋ​ዮች በአ​ስ​ማ​ታ​ቸው እን​ዲሁ ደግሞ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="12">እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም በት​ራ​ቸ​ውን ጣሉ፤ እባ​ቦ​ችም ሆኑ፤ የአ​ሮን በትር ግን በት​ራ​ቸ​ውን ዋጠች።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ፥ የፈ​ር​ዖን ልብ ጸና፤ መስ​ማ​ት​ንም እንቢ አለ።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ሕዝ​ቡን እን​ዳ​ይ​ለ​ቅቅ የፈ​ር​ዖን ልብ ደነ​ደነ።</verse>
				<verse number="15">ማል​ደህ ወደ ፈር​ዖን ሂድ፤ እነሆ፥ ወደ ውኃ ይወ​ጣል፤ ትገ​ና​ኘ​ውም ዘንድ አንተ በወ​ንዝ ዳር ትቆ​ማ​ለህ፤ እባ​ብም ሆና የተ​ለ​ወ​ጠ​ች​ዉን በትር በእ​ጅህ ትወ​ስ​ዳ​ለህ።</verse>
				<verse number="16">እን​ዲ​ህም ትለ​ዋ​ለህ፦ ‘የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በም​ድረ በዳ እን​ዲ​ያ​መ​ል​ኩኝ ሕዝ​ቤን ልቀቅ’ ብሎ ወደ አንተ ላከኝ፤ እነ​ሆም፥ እስከ ዛሬ አል​ሰ​ማ​ህም።</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታው​ቃ​ለህ፤ እነሆ፥ እኔ የወ​ን​ዙን ውኃ በእጄ ባለ​ችው በትር እመ​ታ​ለሁ፤ ውኃ​ውም ወደ ደም ይለ​ወ​ጣል።</verse>
				<verse number="18">በወ​ን​ዙም ያሉት ዓሦች ይሞ​ታሉ፤ ወን​ዙም ይገ​ማል፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም የወ​ን​ዙን ውኃ ለመ​ጠ​ጣት አይ​ች​ሉም።”</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወን​ድ​ምህ አሮ​ንን፦ ‘በት​ር​ህን ውሰድ፤ በግ​ብፅ ውኆች፥ በወ​ን​ዞ​ቻ​ቸው፥ በመ​ስ​ኖ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ በኩ​ሬ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ በውኃ ማከ​ማ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ላይ እጅ​ህን ዘርጋ’ በለው፤ ደምም ይሆ​ናል፤” በግ​ብ​ፅም ሀገር ሁሉ በዕ​ን​ጨት ዕቃና በድ​ን​ጋይ ዕቃ ሁሉ ደም ሆነ።</verse>
				<verse number="20">ሙሴና አሮ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ አሮ​ንም በት​ሩን አነሣ፤ በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት የወ​ን​ዙን ውኃ መታ፤ የወ​ን​ዙም ውኃ ሁሉ ተለ​ውጦ ደም ሆነ።</verse>
				<verse number="21">በወ​ን​ዙም የነ​በሩ ዓሦች ሞቱ፤ ወን​ዙም ገማ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ከወ​ንዙ ውኃ ይጠጡ ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ ደሙም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ ሆነ።</verse>
				<verse number="22">የግ​ብ​ፅም ጠን​ቋ​ዮች በአ​ስ​ማ​ታ​ቸው እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ የፈ​ር​ዖን ልብ ጸና፤ አል​ሰ​ማ​ቸ​ው​ምም።</verse>
				<verse number="23">ፈር​ዖ​ንም ተመ​ልሶ ወደ ቤቱ ገባ፤ በዚ​ህም ሁሉ ልቡ አል​ተ​መ​ለ​ሰም።</verse>
				<verse number="24">ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ሁሉ ከወ​ንዙ ውኃ ይጠጡ ዘንድ አል​ቻ​ሉ​ምና በወ​ንዙ ዳር ውኃ ሊጠጡ ቈፈሩ።</verse>
				<verse number="25">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወን​ዙን ከመታ በኋላ ሰባት ቀን ተፈ​ጸመ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ፈር​ዖን ግባ፤ እን​ዲ​ህም በለው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።</verse>
				<verse number="2">ለመ​ል​ቀቅ እንቢ ብትል ግን እነሆ፥ ሀገ​ር​ህን ሁሉ በጓ​ጕ​ን​ቸ​ሮች እመ​ታ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="3">ወን​ዙም ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ችን ያፈ​ላል፤ ወጥ​ተ​ውም ወደ ቤትህ፥ ወደ መኝታ ቤትህ፥ ወደ አል​ጋ​ህም፥ ወደ ሹሞ​ች​ህም ቤት፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም ላይ፥ ወደ ቡሃ​ቃ​ዎ​ች​ህም፥ ወደ ምድ​ጃ​ዎ​ች​ህም ይገ​ባሉ፤</verse>
				<verse number="4">ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ችም በአ​ንተ፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም፥ በሹ​ሞ​ች​ህም ሁሉ ላይ ይወ​ጣሉ።”</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወን​ድ​ም​ህን አሮ​ንን፦ ‘በት​ር​ህን ይዘህ በወ​ን​ዞ​ቹና በመ​ስ​ኖ​ዎቹ፥ በውኃ ማከ​ማ​ቻ​ዎ​ቹም ላይ እጅ​ህን ዘርጋ፤ ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ች​ንም አውጣ’ ” በለው።</verse>
				<verse number="6">አሮ​ንም በግ​ብፅ ውኆች ላይ እጁን ዘረጋ፤ ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹም ወጡ፤ የግ​ብ​ፅ​ንም ሀገር ሸፈኑ።</verse>
				<verse number="7">የግ​ብፅ ጠን​ቋ​ዮ​ችም በአ​ስ​ማ​ታ​ቸው እን​ዲህ አደ​ረጉ፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ላይ ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ችን አወጡ።</verse>
				<verse number="8">ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠርቶ፥ “ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹን ከእኔ፥ ከሕ​ዝ​ቤም እን​ዲ​ያ​ርቅ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ዩ​ልኝ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሠዋ ዘንድ ሕዝ​ቡን እለ​ቅ​ቃ​ለሁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ሙሴም ፈር​ዖ​ንን፥ “ጓጕ​ን​ቸ​ሮቹ ከአ​ንተ፥ ከሕ​ዝ​ብ​ህም፥ ከቤ​ቶ​ች​ህም እን​ዲ​ጠፉ፥ በወ​ን​ዙም ብቻ እን​ዲ​ቀሩ፥ ለአ​ንተ፥ ለሹ​ሞ​ች​ህም፥ ለሕ​ዝ​ብ​ህም መቼ እን​ድ​ጸ​ልይ ቅጠ​ረኝ” አለው። ፈር​ዖ​ንም፥ “ነገ” አለው።</verse>
				<verse number="10">ሙሴም፥ “ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ታውቅ ዘንድ እሺ እንደ አልህ ይሁን።</verse>
				<verse number="11">ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹም ከአ​ንተ፥ ከቤ​ቶ​ች​ህም፥ ከመ​ን​ደ​ሮ​ች​ህም፥ ከሹ​ሞ​ች​ህም፥ ከሕ​ዝ​ብ​ህም ይሄ​ዳሉ፤ በወ​ን​ዙም ብቻ ይቀ​ራሉ” አለው።</verse>
				<verse number="12">ሙሴና አሮ​ንም ከፈ​ር​ዖን ዘንድ ወጡ፤ ሙሴም ፈር​ዖን እንደ ቀጠ​ረው ሰለ ጓጕ​ን​ቸ​ሮቹ መራቅ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ እንደ አለ አደ​ረገ፤ ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹም ከቤት፥ ከመ​ን​ደ​ርም፥ ከሜ​ዳም ሞቱ።</verse>
				<verse number="14">እንደ ክም​ርም አድ​ር​ገው ሰበ​ሰ​ቡ​አ​ቸው፤ ምድ​ርም ገማች።</verse>
				<verse number="15">ፈር​ዖ​ንም ጸጥታ እንደ ሆነ በአየ ጊዜ ልቡ ደነ​ደነ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “አሮ​ንን፦ ‘በት​ር​ህን በእ​ጅህ ዘርጋ፤ የም​ድ​ሩ​ንም ትቢያ ምታ’ በለው፤ ቅማ​ልም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ በሰ​ውና በእ​ን​ስሳ ላይ ይወ​ጣል።”</verse>
				<verse number="17">አሮ​ንም እጁን ዘረጋ፤ በበ​ት​ሩም የም​ድ​ሩን ትቢያ መታው፤ በሰ​ውና በእ​ን​ስ​ሳም ላይ ቅማል ሆነ፤ በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ የም​ድር ትቢያ ሁሉ ቅማል ሆነ።</verse>
				<verse number="18">የግ​ብፅ ጠን​ቋ​ዮ​ችም በአ​ስ​ማ​ታ​ቸው ቅማል ያወጡ ዘንድ እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ ነገር ግን አል​ቻ​ሉም፤ ቅማ​ሉም በሰ​ውና በእ​ን​ስሳ ላይ ነበረ።</verse>
				<verse number="19">ጠን​ቋ​ዮ​ችም ፈር​ዖ​ንን፥ “ይህስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት ነው” አሉት፤ የፈ​ር​ዖን ልብ ግን ጸና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ማል​ደህ ተነሣ፤ በፈ​ር​ዖ​ንም ፊት ቁም፤ እነሆ፥ እርሱ ወደ ውኃ ይወ​ር​ዳል፤ እን​ዲ​ህም በለው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በም​ድረ በዳ እን​ዲ​ያ​መ​ል​ኩኝ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።</verse>
				<verse number="21">ሕዝ​ቤን ለመ​ል​ቀቅ እንቢ ብትል ግን እነሆ፥ በአ​ንተ፥ በሹ​ሞ​ች​ህም፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም፥ በቤ​ቶ​ች​ህም ላይ የውሻ ዝንብ እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የግ​ብ​ፃ​ው​ያን ቤቶች፥ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም ምድር ሁሉ በውሻ ዝንብ ይመ​ላሉ።</verse>
				<verse number="22">በዚ​ያም ቀን የም​ድር ሁሉ አም​ላክ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ፥ በዚያ የውሻ ዝንብ እን​ዳ​ይ​ሆን ሕዝቤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትን የጌ​ሤ​ምን ምድር እለ​ያ​ለሁ።</verse>
				<verse number="23">በሕ​ዝ​ቤና በሕ​ዝ​ብህ መካ​ከል እለ​ያ​ለሁ፤ ይህም ነገር ነገ በም​ድ​ሪቱ ላይ ይሆ​ናል።”</verse>
				<verse number="24">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አደ​ረገ፤ የው​ሻው ዝን​ብም በፈ​ር​ዖን ቤት፥ በሹ​ሞ​ቹም ቤቶች ውሰጥ፥ በግ​ብ​ፅም ሀገር ሁሉ መጣ፤ ምድ​ሪ​ቱም ከው​ሻው ዝንብ የተ​ነሣ ጠፋች።</verse>
				<verse number="25">ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠርቶ፥ “ሂዱ፤ በዚ​ያች ምድር ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ሠዉ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">ሙሴም፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ግብ​ፃ​ው​ያን እርም የሚ​ሉ​ትን እን​ሠ​ዋ​ለ​ንና እን​ዲሁ ይሆን ዘንድ አይ​ቻ​ልም፤ እነሆ፥ ግብ​ፃ​ው​ያን እርም የሚ​ሉ​ትን እኛ በፊ​ታ​ቸው ብን​ሠዋ በድ​ን​ጋይ ይወ​ግ​ሩ​ናል።</verse>
				<verse number="27">እኛስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላ​ካ​ችን እን​ሠዋ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘን የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ወደ ምድረ በዳ እን​ሄ​ዳ​ለን” አለ።</verse>
				<verse number="28">ፈር​ዖ​ንም፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በም​ድረ በዳ ትሠዉ ዘንድ እለ​ቅ​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ነገር ግን በጣም ርቃ​ችሁ አት​ሂዱ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸል​ዩ​ልኝ” አለ።</verse>
				<verse number="29">ሙሴም፥ “እነሆ፥ ከአ​ንተ ዘንድ እወ​ጣ​ለሁ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጸ​ል​ያ​ለሁ፤ የውሻ ዝን​ቡም ከአ​ንተ፥ ከሹ​ሞ​ች​ህና ከሕ​ዝ​ብህ ነገ ይር​ቃል፤ ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሠዉ ዘንድ ሕዝ​ቡን እን​ደ​ማ​ት​ለ​ቅቅ እን​ደ​ገና ማታ​ለ​ልን አት​ድ​ገም።”</verse>
				<verse number="30">ሙሴም ከፈ​ር​ዖን ዘንድ ወጣ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸለየ።</verse>
				<verse number="31">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ እንደ አለ አደ​ረገ፤ የው​ሻ​ው​ንም ዝንብ ከፈ​ር​ዖን፥ ከሹ​ሞ​ቹም፥ ከሕ​ዝ​ቡም አራቀ፤ አንድ ስንኳ አል​ቀ​ረም።</verse>
				<verse number="32">ፈር​ዖ​ንም በዚህ ጊዜ ደግሞ ልቡን አደ​ነ​ደነ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አል​ለ​ቀ​ቀም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ፈር​ዖን ገብ​ተህ እን​ዲህ በለው፦ የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።</verse>
				<verse number="2">ሕዝ​ቤን ልት​ለ​ቃ​ቸው እንቢ ብትል፥ ብት​ይ​ዛ​ቸ​ውም፥</verse>
				<verse number="3">እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በሜዳ ውስጥ በአ​ሉት በከ​ብ​ቶ​ችህ፥ በፈ​ረ​ሶ​ችም፥ በአ​ህ​ዮ​ችም፥ በግ​መ​ሎ​ችም፥ በበ​ሬ​ዎ​ችም፥ በበ​ጎ​ችም ላይ ትሆ​ና​ለች፤ ይኸ​ውም እጅግ ጽኑዕ ሞት ነው፤</verse>
				<verse number="4">በዚያ ጊዜም በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ከብ​ቶ​ችና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከብ​ቶች መካ​ከል ልዩ​ነት አደ​ር​ጋ​ለሁ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከብ​ቶች አን​ዳች አይ​ሞ​ትም።”</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ነገ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ነገር በም​ድር ላይ ያደ​ር​ጋል ብሎ ጊዜን ወሰነ።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያን ነገር በነ​ጋው አደ​ረገ፤</verse>
				<verse number="6">የግ​ብ​ፅም ከብት ሁሉ ሞተ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከብት ግን አንድ ስንኳ አል​ሞ​ተም።</verse>
				<verse number="7">ፈር​ዖ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከብት አንድ ስንኳ እን​ዳ​ል​ሞተ በአየ ጊዜ ልቡ ደነ​ደነ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አል​ለ​ቀ​ቀም።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን፥ “እጃ​ች​ሁን ሞል​ታ​ችሁ ከም​ድጃ አመድ ውሰዱ፤ ሙሴም በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት ወደ ሰማይ ይበ​ት​ነው።</verse>
				<verse number="9">እር​ሱም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ ትቢያ ይሆ​ናል፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ሁሉ በሰ​ውና በእ​ን​ስሳ ላይ ሻህኝ የሚ​ያ​መጣ ቍስል ይሆ​ናል” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">ሙሴም አመ​ዱን በፈ​ር​ዖን ፊት ወስዶ ወደ ሰማይ በተ​ነው፤ በሰ​ውና በእ​ን​ስ​ሳም ላይ ሻህኝ የሚ​ያ​ወጣ ቍስል ሆነ።</verse>
				<verse number="11">ጠን​ቋ​ዮ​ችም ቍስል ስለ ነበ​ረ​ባ​ቸው በሙሴ ፊት መቆም አል​ቻ​ሉም፤ ቍስል ጠን​ቋ​ዮ​ች​ንና ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን ሁሉ ይዞ​አ​ቸው ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙ​ሴና ለአ​ሮን እንደ ተና​ገ​ረው አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ማል​ደህ ተነሣ፤ በፈ​ር​ዖ​ንም ፊት ቆመህ እን​ዲህ በለው፦ የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እን​ዲ​ያ​መ​ል​ኩኝ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።</verse>
				<verse number="14">በም​ድር ሁሉ እንደ እኔ ያለ እን​ደ​ሌለ ታውቅ ዘንድ በሰ​ው​ነ​ትህ፥ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህም፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም ላይ መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ሁሉ በዚህ ጊዜ እል​ካ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">አሁን እጄን ዘር​ግቼ አን​ተን እመ​ታ​ሃ​ለሁ፤ ሕዝ​ብ​ህ​ንም እገ​ድ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ምድ​ራ​ች​ሁም ትመ​ታ​ለች።</verse>
				<verse number="16">ነገር ግን ኀይ​ሌን እገ​ል​ጥ​ብህ ዘንድ፥ ስሜም በም​ድር ሁሉ ላይ ይነ​ገር ዘንድ ስለ​ዚህ ጠበ​ቅ​ሁህ።</verse>
				<verse number="17">አንተ ግን እን​ዳ​ት​ለ​ቃ​ቸው ገና በሕ​ዝቤ ላይ ትታ​በ​ያ​ለህ፤</verse>
				<verse number="18">እነሆ፥ ከተ​መ​ሠ​ረ​ተች ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንደ እርሱ ያለ በግ​ብፅ ሆኖ የማ​ያ​ውቅ እጅግ ታላቅ በረዶ ነገ በዚህ ጊዜ አዘ​ን​ባ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">አሁን እን​ግ​ዲህ ፥ ከብ​ቶ​ች​ህ​ንም በሜ​ዳም ያለ​ህን ሁሉ ፈጥ​ነህ ሰብ​ስብ። በሜዳ የተ​ገኘ ወደ ቤት ያል​ገባ ሰውና እን​ስሳ ሁሉ በረዶ ወር​ዶ​በት ይሞ​ታ​ልና።”</verse>
				<verse number="20">ከፈ​ር​ዖን ሹሞች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል የፈራ ከብ​ቶ​ቹን ወደ ቤቶቹ ሰበ​ሰበ።</verse>
				<verse number="21">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በልቡ ያላ​ሰበ ግን ከብ​ቶ​ቹን በሜዳ ተወ።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እጅ​ህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ሁሉ በሰ​ውና በእ​ን​ስ​ሳም በም​ድ​ርም ቡቃያ ሁሉ ላይ በረዶ ይሆ​ናል።”</verse>
				<verse number="23">ሙሴም እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነጐ​ድ​ጓ​ድና በረዶ ላከ፤ እሳ​ትም ወደ ምድር ወረደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ ላይ በረዶ አዘ​ነበ።</verse>
				<verse number="24">በረ​ዶም ነበረ፤ በበ​ረ​ዶ​ውም መካ​ከል እሳት ይቃ​ጠል ነበር፤ በረ​ዶ​ውም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ ሕዝብ ከኖ​ረ​በት ጊዜ ጀምሮ እስ​ከ​ዚች ቀን እንደ እርሱ ያል​ሆነ እጅግ ብዙና ጠን​ካራ ነበረ።</verse>
				<verse number="25">በረ​ዶ​ውም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ በሜዳ ያለ​ውን ሁሉ ሰው​ንና እን​ስ​ሳን መታ፤ በረ​ዶ​ውም የእ​ር​ሻን ቡቃያ ሁሉ መታ። የጫ​ካ​ው​ንም ዛፍ ሁሉ ሰበረ።</verse>
				<verse number="26">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተቀ​ም​ጠው በነ​በ​ሩ​ባት በጌ​ሤም ሀገር ብቻ በረዶ አል​ወ​ረ​ደም።</verse>
				<verse number="27">ፈር​ዖ​ንም ልኮ ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠራ፤ “አሁ​ንም በደ​ልሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድቅ ነው፤ እኔና ሕዝቤ ግን ኀጢ​አ​ተ​ኞች ነን።</verse>
				<verse number="28">እን​ግ​ዲህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ዩ​ልኝ፤ የአ​ም​ላክ ነጐ​ድ​ጓድ፥ በረ​ዶ​ውም፥ እሳ​ቱም ጸጥ ይላል፤ እኔም እለ​ቅ​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ከዚህ አት​ቀ​መ​ጡም” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="29">ሙሴም፥ “ለፈ​ር​ዖን ከከ​ተማ በወ​ጣሁ ጊዜ እጄን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነች ታውቅ ዘንድ ነጐ​ድ​ጓዱ ጸጥ ይላል፤ በረ​ዶ​ውም፥ ዝና​ቡም ደግሞ አይ​ወ​ር​ድም።</verse>
				<verse number="30">ነገር ግን አን​ተና ሹሞ​ችህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክን ምን​ጊ​ዜም እን​ደ​ማ​ት​ፈሩ አው​ቃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="31">ተል​ባ​ውና ገብሱ ተመታ፤ ገብሱ አሽቶ፥ ተል​ባ​ውም አፍ​ርቶ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="32">ስን​ዴ​ውና አጃው ግን አል​ተ​መ​ቱም፤ ገና ቡቃያ ነበ​ሩና።</verse>
				<verse number="33">ሙሴም ከፈ​ር​ዖን ዘንድ ከከ​ተማ ወጣ፤ እጁ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘረጋ፤ ነጐ​ድ​ጓ​ዱም፥ በረ​ዶ​ውም ጸጥ አለ፤ ዝና​ቡም በም​ድር ላይ አላ​ካ​ፋም።</verse>
				<verse number="34">ፈር​ዖ​ንም ዝናቡ፥ በረ​ዶ​ውም፥ ነጐ​ድ​ጓ​ዱም ጸጥ እንደ አለ በአየ ጊዜ በደ​ልን ጨመረ፤ እር​ሱና ሹሞ​ቹም ልባ​ቸ​ውን አደ​ነ​ደኑ።</verse>
				<verse number="35">የፈ​ር​ዖ​ንም ልብ ጸና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሙሴ አፍ እንደ ተና​ገረ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አል​ለ​ቀ​ቀም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፥ “ወደ ፈር​ዖን ግባ፤ እኔ የፈ​ር​ዖ​ን​ንና የሹ​ሞ​ቹን ልብ አጽ​ን​ቼ​አ​ለ​ሁና፥ ተአ​ም​ራቴ በእ​ነ​ርሱ ላይ በት​ክ​ክል ይመጣ ዘንድ፤</verse>
				<verse number="2">በግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ላይ የተ​ዘ​ባ​በ​ት​ሁ​ትን ሁሉ፥ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ባ​ቸ​ው​ንም ተአ​ም​ራ​ቴን በል​ጆ​ቻ​ች​ሁና በልጅ ልጆ​ቻ​ችሁ ጆሮች ትነ​ግሩ ዘንድ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="3">ሙሴና አሮ​ንም ወደ ፈር​ዖን ገቡ፤ አሉ​ትም፥ “የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔን ማፈ​ርን እስከ መቼ እንቢ ትላ​ለህ? ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።</verse>
				<verse number="4">ሕዝ​ቤን ለመ​ል​ቀቅ እንቢ ብትል ግን፥ እነሆ፥ ነገ በዚህ ጊዜ በተ​ራ​ራ​ዎ​ችህ ሁሉ ላይ አን​በ​ጣን አመ​ጣ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="5">የም​ድ​ሩ​ንም ፊት ይሸ​ፍ​ናል፤ ምድ​ሩን ለማ​የት አይ​ቻ​ልም፤ ከበ​ረ​ዶ​ውም ተርፎ በም​ድር ላይ የቀ​ረ​ላ​ች​ሁን ትርፍ ሁሉ ይበ​ላል፤ ያደ​ገ​ላ​ች​ሁ​ንም የእ​ር​ሻ​ውን ዛፍ ሁሉ ይበ​ላል፤</verse>
				<verse number="6">ቤቶ​ች​ህም የሹ​ሞ​ች​ህም ሁሉ ቤቶች፥ የግ​ብ​ፃ​ው​ያን ሁሉ ቤቶች በእ​ርሱ ይሞ​ላሉ፤ አባ​ቶ​ችህ፥ የአ​ባ​ቶ​ች​ህም አባ​ቶች በም​ድር ላይ ከተ​ቀ​መ​ጡ​በት ቀን ጀምሮ እስ​ከ​ዚህ ቀን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያላ​ዩት ነው።” ሙሴም ተመ​ልሶ ከፈ​ር​ዖን ዘንድ ወጣ።</verse>
				<verse number="7">የፈ​ር​ዖ​ንም ሹሞች፥ “ይህ ሰው እስከ መቼ እን​ቅ​ፋት ይሆ​ን​ብ​ናል? አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ል​ኩት ዘንድ ሰዎ​ችን ልቀቅ፤ ግብ​ፅስ እንደ ጠፋች ገና አታ​ው​ቅ​ምን?” አሉት።</verse>
				<verse number="8">ሙሴ​ንና አሮ​ን​ንም ወደ ፈር​ዖን ጠሩ​አ​ቸው፤ ፈር​ዖ​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሂዱ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አም​ልኩ፤ ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ጋር የሚ​ሄ​ዱት እነ​ማን ናቸው?”</verse>
				<verse number="9">ሙሴም አለው፥ “እኛ ከታ​ና​ና​ሾ​ቻ​ች​ንና ከሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ችን፥ ከወ​ን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችን ጋር እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በጎ​ቻ​ች​ን​ንና ላሞ​ቻ​ች​ን​ንም እን​ወ​ስ​ዳ​ለን። የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል ነውና።”</verse>
				<verse number="10">ፈር​ዖ​ንም አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን፤ እነሆ፥ እና​ን​ተን ስለቅ ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም መል​ቀቅ አለ​ብ​ኝን? ክፉ ነገር እን​ደ​ሚ​ገ​ጥ​ማ​ችሁ ዕወቁ።</verse>
				<verse number="11">እን​ዲ​ህም አይ​ደ​ለም፤ እና​ንተ ወን​ዶቹ ሂዱ፤ ይህን ፈል​ጋ​ች​ኋ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አም​ልኩ” አላ​ቸው። ሙሴ​ንና አሮ​ን​ንም ከፈ​ር​ዖን ፊት አስ​ወ​ጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “በግ​ብፅ ሀገር ላይ እጅ​ህን ዘርጋ፤ አን​በ​ጣም በም​ድር ላይ ይወ​ጣል፤ ከበ​ረ​ዶ​ውም የተ​ረ​ፈ​ውን የም​ድር ቡቃያ ሁሉና የዛ​ፉን ፍሬ ሁሉ ይበ​ላል።”</verse>
				<verse number="13">ሙሴም በት​ሩን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የደ​ቡ​ብን ነፋስ ያን ቀን ሁሉ ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ አመጣ፤ ማለ​ዳም በሆነ ጊዜ የደ​ቡብ ነፋስ አን​በ​ጣን አመጣ።</verse>
				<verse number="14">አን​በ​ጣም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ ላይ ወጣ፤ በግ​ብ​ፅም ዳርቻ ሁሉ ላይ ተቀ​መጠ፤ እጅ​ግም ብዙና ጠን​ካራ ነበር፤ ይህ​ንም የሚ​ያ​ህል አን​በጣ በፊት አል​ነ​በ​ረም፤ ወደ​ፊ​ትም ደግሞ እንደ እርሱ አይ​ሆ​ንም።</verse>
				<verse number="15">የም​ድ​ሩ​ንም ፊት ፈጽሞ ሸፈ​ነው፤ ሀገ​ሪ​ቱም ጠፋች፤ የሀ​ገ​ሪ​ቱን ቡቃያ ሁሉ ከበ​ረ​ዶ​ውም የተ​ረ​ፈ​ውን፥ በዛፉ የነ​በ​ረ​ውን ፍሬ ሁሉ በላ፤ ለም​ለም ነገር በዛ​ፎች ላይ፥ በእ​ር​ሻ​ውም ቡቃያ ሁሉ ላይ በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ አል​ቀ​ረም።</verse>
				<verse number="16">ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን በፍ​ጥ​ነት ጠራ፥ “በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት፥ በእ​ና​ን​ተም ላይ በደ​ልሁ፤</verse>
				<verse number="17">አሁን እን​ግ​ዲህ እን​ደ​ገና በዚህ ጊዜ ብቻ ኀጢ​አ​ቴን ይቅር በሉኝ፤ ይህ​ንም ሞት ብቻ ከእኔ ያነ​ሣ​ልኝ ዘንድ ወደ አም​ላ​ካ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ዩ​ልኝ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">ሙሴም ከፈ​ር​ዖን ፊት ወጣ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸለየ።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከባ​ሕር ዐውሎ ነፋ​ሱን አስ​ወ​ገደ፤ አን​በ​ጣ​ዎ​ች​ንም ወስዶ በኤ​ር​ትራ ባሕር ውስጥ ጣላ​ቸው፤ አንድ አን​በ​ጣም እን​ኳን በግ​ብፅ ዳርቻ ሁሉ አል​ቀ​ረም።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸና የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች አል​ል​ቀ​ቀም።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “እጅ​ህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ላይ ጨለማ ይሁን፤ ጨለ​ማ​ውም የሚ​ዳ​ሰስ ነው” አለው።</verse>
				<verse number="22">ሙሴም እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ሁሉ ላይ ጽኑ ጨለ​ማና ጭጋግ ሦስት ቀን ሆነ፤</verse>
				<verse number="23">ማንም ወን​ድ​ሙን አላ​የም፤ ሦስት ቀን ሙሉም ከመ​ኝ​ታው ማንም አል​ተ​ነ​ሣም፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ግን በተ​ቀ​መ​ጡ​በት ስፍራ ሁሉ ብር​ሃን ነበ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠርቶ፥ “ሂዱ፤ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አም​ልኩ፤ ነገር ግን በጎ​ቻ​ች​ሁ​ንና ከብ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ብቻ ተዉ፤ ልጆ​ቻ​ች​ሁና ሴቶ​ቻ​ችሁ ግን ከእ​ና​ንተ ጋር ይሂዱ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">ሙሴም አለው፥ “አይ​ሆ​ንም! አንተ ደግሞ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ን​ሠ​ዋው መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትን ትሰ​ጠ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="26">ከብ​ቶ​ቻ​ችን ከእኛ ጋር ይሄ​ዳሉ፤ አንድ ሰኰ​ናም አይ​ቀ​ርም፤ አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​ም​ለክ ከእ​ነ​ርሱ እን​ወ​ስ​ዳ​ለ​ንና፤ አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ደ​ም​ና​መ​ል​ከው ከዚያ እስ​ክ​ን​ደ​ርስ አና​ው​ቅም።”</verse>
				<verse number="27">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸና፤ ሊለ​ቅ​ቃ​ቸ​ውም አል​ወ​ደ​ደም።</verse>
				<verse number="28">ፈር​ዖ​ንም ሙሴን፥ “ከእኔ ዘንድ ሂድ፤ በፊቴ በም​ት​ታ​ይ​በት ቀን ትሞ​ታ​ለ​ህና ዳግ​መኛ ፊቴን እን​ዳ​ታይ ተጠ​ን​ቀቅ” አለው።</verse>
				<verse number="29">ሙሴም፥ “እንደ ተና​ገ​ርህ ይሁን፤ ፊት​ህን እን​ደ​ገና አላ​ይም” አለ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “በፈ​ር​ዖ​ንና በግ​ብፅ ላይ ገና አን​ዲት መቅ​ሠ​ፍት አመ​ጣ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ከዚያ ይለ​ቅ​ቃ​ች​ኋል፤ ሲለ​ቅ​ቃ​ች​ሁም ከመ​ነሻ ገን​ዘብ ጋር ይሰ​ድ​ዳ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="2">ወንዱ ከወ​ዳጁ፥ ሴቲ​ቱም ከወ​ዳ​ጅዋ የብ​ርና የወ​ርቅ ዕቃ፥ ልብ​ስም ይዋሱ ዘንድ በሕ​ዝቡ ጆሮ በስ​ውር ተና​ገር።”</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ፊት ለሕ​ዝቡ ሞገ​ስን ሰጠ፤ አዋ​ሱ​አ​ቸ​ውም፤ ይህ ሙሴም በግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንና በፈ​ር​ዖን፥ በሹ​ሞ​ቹም ፊት እጅግ የከ​በረ ሰው ነበረ።</verse>
				<verse number="4">ሙሴም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ኩለ ሌሊት እኔ በግ​ብፅ መካ​ከል እገ​ባ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="5">በግ​ብ​ፅም ሀገር ያለ በኵር ሁሉ፥ በዙ​ፋኑ ከሚ​ቀ​መ​ጠው ከፈ​ር​ዖን በኵር ጀምሮ በወ​ፍጮ እግር እስ​ካ​ለ​ችው እስከ አገ​ል​ጋ​ዪቱ በኵር ድረስ፥ የከ​ብ​ቱም በኵር ሁሉ ይሞ​ታል።</verse>
				<verse number="6">በግ​ብ​ፅም ሀገር ሁሉ አስ​ቀ​ድሞ እንደ እርሱ ያል​ሆነ፥ ኋላም ደግሞ እንደ እርሱ የማ​ይ​ሆን ታላቅ ጩኸት ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንና በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ታላቅ ልዩ​ነ​ትን እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርግ እን​ድ​ታ​ውቁ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ ድረስ ውሻ ምላ​ሱን አያ​ን​ቀ​ሳ​ቅ​ስ​ባ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="8">እነ​ዚህ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ሁሉ፦ አንተ ውጣ፤ የሚ​ከ​ተ​ሉ​ህም ሕዝብ ሁሉ ከዚ​ያች ምድር ይውጡ እያሉ ወደ እኔ ይወ​ር​ዳሉ፤ ለእ​ኔም ይሰ​ግ​ዳሉ፤ ከዚ​ያም በኋላ እወ​ጣ​ለሁ።” ሙሴም በጽኑ ቍጣ ከፈ​ር​ዖን ዘንድ ወጣ።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ተአ​ም​ራ​ቴና ድንቄ በግ​ብፅ ሀገር ብዙ እን​ዲ​ሆን ፈር​ዖን አይ​ሰ​ማ​ች​ሁም።”</verse>
				<verse number="10">ሙሴና አሮ​ንም እነ​ዚ​ህን ተአ​ም​ራ​ቶ​ችና ድን​ቆች ሁሉ በፈ​ር​ዖን ፊት አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸና፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ለመ​ል​ቀቅ እንቢ አለ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በግ​ብፅ ሀገር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦</verse>
				<verse number="2">“ይህ ወር የወ​ሮች መጀ​መ​ሪያ ይሁ​ና​ችሁ፤ የዓ​መ​ቱም መጀ​መ​ሪያ ወር ይሁ​ና​ችሁ።</verse>
				<verse number="3">ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ተና​ገሩ፤ በሉ​አ​ቸ​ውም፦ በዚህ ወር በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን ሰው ሁሉ ለአ​ባቱ ቤተ ሰቦች ቤቶች አንድ አንድ ጠቦት፥ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰውም ለራሱ ቤተ ሰብእ አንድ ጠቦት ይው​ሰድ።</verse>
				<verse number="4">በቤት ያሉት ሰዎች ጥቂት ቢሆኑ፥ አንድ በግም የማ​ይ​ጨ​ርሱ ቢሆኑ በጉን ሊጨ​ርሱ በሚ​በቁ በሰ​ዎች ቍጥር እያ​ን​ዳ​ንዱ በአ​ጠ​ገቡ የሚ​ኖ​ረ​ውን ጎረ​ቤ​ቱን ይው​ሰድ።</verse>
				<verse number="5">ነውር የሌ​ለ​በት የአ​ንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለእ​ና​ንተ ይሁን፤ ከበ​ጎች ወይም ከፍ​የ​ሎች ውሰዱ።</verse>
				<verse number="6">በዚ​ህም ወር እስከ ዐሥራ አራ​ተኛ ቀን ድረስ ጠብ​ቁት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ሲመሽ ይረ​ዱት።</verse>
				<verse number="7">ከደ​ሙም ወስ​ደው በሚ​በ​ሉ​በት ቤት ሁለ​ቱን መቃ​ንና ጉበ​ኑን ይቅ​ቡት።</verse>
				<verse number="8">በእ​ሳ​ትም የተ​ጠ​በ​ሰ​ውን ሥጋ​ውን በዚ​ያች ሌሊት ይብሉ፤ ቂጣ​ውን እን​ጀ​ራም ከመ​ራራ ቅጠል ጋር ይብ​ሉት።</verse>
				<verse number="9">ጥሬ​ው​ንም፥ በው​ኃም የበ​ሰ​ለ​ውን አት​ብሉ፤ ነገር ግን በእ​ሳት የተ​ጠ​በ​ሰ​ውን ራሱን፥ እግ​ሩ​ንና ሆድ ዕቃ​ውን ብሉት።</verse>
				<verse number="10">ከእ​ር​ሱም እስከ ጥዋት አን​ዳች አታ​ስ​ቀሩ፤ አጥ​ን​ቱ​ንም ከእ​ርሱ አት​ስ​በሩ፤ ከእ​ር​ሱም እስከ ጥዋት የተ​ረፈ ቢኖር በእ​ሳት አቃ​ጥ​ሉት።</verse>
				<verse number="11">ወገ​ቦ​ቻ​ች​ሁን ታጥ​ቃ​ችሁ፥ ጫማ​ች​ሁን በእ​ግ​ራ​ችሁ ተጫ​ም​ታ​ችሁ፥ በት​ራ​ች​ሁ​ንም በእ​ጃ​ችሁ ይዛ​ችሁ እን​ዲህ ብሉት፦ እየ​ቸ​ኰ​ላ​ች​ሁም ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ፤ እርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲካ ነውና።</verse>
				<verse number="12">እኔም በዚ​ያች ሌሊት በግ​ብፅ ሀገር አል​ፋ​ለሁ፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ከሰው እስከ እን​ስሳ ድረስ በኵ​ርን ሁሉ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ በግ​ብ​ፅም አማ​ል​ክት ሁሉ ላይ በቀ​ልን አደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።</verse>
				<verse number="13">ደሙም ባላ​ች​ሁ​ባ​ቸው ቤቶች ምል​ክት ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፤ ደሙ​ንም አያ​ለሁ፤ እና​ን​ተ​ንም እሰ​ው​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም የግ​ብ​ፅን ሀገር በመ​ታሁ ጊዜ የጥ​ፋት መቅ​ሠ​ፍት አይ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="14">ይህም ቀን መታ​ሰ​ቢያ ይሁ​ና​ችሁ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዓል ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ችሁ፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም ሥር​ዐት ሆኖ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="15">“ሰባት ቀን ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያም ቀን እር​ሾ​ውን ከቤ​ታ​ችሁ ታወ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ቀን አን​ሥቶ እስከ ሰባ​ተ​ኛው ቀን እርሾ ያለ​በ​ትን እን​ጀራ የሚ​በላ ነፍስ ከእ​ስ​ራ​ኤል ተለ​ይቶ ይጥፋ።</verse>
				<verse number="16">የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዪቱ ቀን ቅድ​ስት ትባ​ላ​ላች፤ እን​ዲ​ሁም ሰባ​ተ​ኛዋ ቀን ቅድ​ስት ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ለነ​ፍስ ከሚ​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ በቀር ማና​ቸ​ው​ንም ሥራ ሁሉ አት​ሥሩ</verse>
				<verse number="17">በዚ​ህም ቀን ሠራ​ዊ​ታ​ች​ሁን ከግ​ብፅ ሀገር አወ​ጣ​ዋ​ለ​ሁና ይህን ትእ​ዛዝ ጠብ​ቁት፤ እን​ግ​ዲህ ይህን ቀን ለልጅ ልጃ​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት አድ​ር​ጋ​ችሁ ትጠ​ብ​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="18">ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን ሠርክ ጀም​ራ​ችሁ እስ​ከ​ዚሁ ወር ሃያ አን​ደኛ ቀን ሠርክ ድረስ ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="19">ሰባት ቀን በቤ​ታ​ችሁ እርሾ አይ​ገኝ፤ እርሾ ያለ​በ​ት​ንም እን​ጀራ የሚ​በላ ሁሉ ያ ሰው ከመ​ጻ​ተ​ኛው ጀምሮ እስከ ሀገር ልጁ ድረስ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ተለ​ይቶ ይጥፋ።</verse>
				<verse number="20">እርሾ ያለ​በ​ትን ምንም አት​ብሉ፤ በቤ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ ውስጥ ቂጣ ብሉ።”</verse>
				<verse number="21">ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጠርቶ አላ​ቸው፥ “ሂዱና በየ​ወ​ገ​ና​ችሁ ጠቦት ውሰዱ፤ ለፋ​ሲ​ካም እረ​ዱት።</verse>
				<verse number="22">ከሂ​ሶጵ ቅጠ​ልም ጭብጥ ውሰዱ፤ በዕቃ ውስጥ ባለ​ውም ደም ንከ​ሩት፤ በዕ​ቃ​ውም ውስጥ ከአ​ለው ደም ሁለ​ቱን መቃ​ኖ​ችና ጉበ​ኑን እርጩ፤ ከእ​ና​ን​ተም አንድ ሰው እስ​ኪ​ነጋ ድረስ ከቤቱ ደጅ አይ​ውጣ።</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን ይመታ ዘንድ ያል​ፋ​ልና፤ ደሙ​ንም በጉ​በ​ኑና በሁ​ለቱ መቃ​ኖች ላይ በአየ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሩን ያል​ፋል፤ አጥ​ፊ​ውም ይመ​ታ​ችሁ ዘንድ ወደ ቤታ​ችሁ እን​ዲ​ገባ አይ​ተ​ወ​ውም።</verse>
				<verse number="24">ለእ​ና​ንተ ለል​ጆ​ቻ​ች​ሁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይሆ​ና​ችሁ ዘንድ ይህን ሕግ ጠብቁ።</verse>
				<verse number="25">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ሀገር በገ​ባ​ችሁ ጊዜ ይህን አም​ልኮ ጠብ​ቁት።</verse>
				<verse number="26">ልጆ​ቻ​ችሁ፦ ‘ይህ ሥር​ዐት ለእ​ና​ንተ ምን​ድር ነው?’ ባሉ​አ​ችሁ ጊዜ እና​ንተ፦</verse>
				<verse number="27">‘ይህ በግ​ብፅ ሀገር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ቤቶች ሰውሮ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶ​ቻ​ች​ንን የአ​ዳነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፋ​ሲ​ካው መሥ​ዋ​ዕት ነው’ ትሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።” ሕዝ​ቡም ተጐ​ነ​በሱ፤ ሰገ​ዱም።</verse>
				<verse number="28">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሄዱ፤ እን​ዲ​ህም አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እንደ አዘ​ዛ​ቸው እን​ዲሁ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="29">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ እኩለ ሌሊት በሆነ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ፋን ከተ​ቀ​መ​ጠው ከፈ​ር​ዖን በኵር ጀምሮ እስከ ውኃ ቀጅዋ ምር​ኮኛ በኵር ድረስ፥ በግ​ብፅ ምድር በኵ​ሩን ሁሉ፥ የእ​ን​ስ​ሳ​ው​ንም በኵር ሁሉ መታ።</verse>
				<verse number="30">ፈር​ዖ​ንም፥ ሹሞ​ቹም ሁሉ፥ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ሁሉ በሌ​ሊት ተነሡ፤ የሞተ የሌ​ለ​በት ቤት አል​ነ​በ​ረ​ምና በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ታላቅ ልቅሶ ሆነ።</verse>
				<verse number="31">ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን በሌ​ሊት ጠርቶ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተነሡ፤ ከሕ​ዝቤ መካ​ከል ውጡ፤ ሂዱም፤ እን​ዳ​ላ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አም​ል​ኩት፤</verse>
				<verse number="32">በጎ​ቻ​ች​ሁ​ንም፥ ላሞ​ቻ​ች​ሁ​ንም ውሰዱ፤ ሂዱም፤ እኔ​ንም ደግሞ ባር​ኩኝ።”</verse>
				<verse number="33">ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ፈጥ​ነው ከም​ድሩ ይወጡ ዘንድ ሕዝ​ቡን ያስ​ቸ​ኩ​ሉ​አ​ቸው ነበር፥ “ሁላ​ች​ንም እን​ሞ​ታ​ለን” ብለ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="34">ሕዝ​ቡም ሊጡን ሳይ​ቦካ ተሸ​ከሙ፤ ቡሃ​ቃ​ው​ንም በል​ብ​ሳ​ቸው ጠቅ​ል​ለው በት​ከ​ሻ​ቸው ተሸ​ከ​ሙት።</verse>
				<verse number="35">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሙሴ እን​ዳ​ዘዘ አደ​ረጉ። ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም የብ​ር​ንና የወ​ር​ቅን ዕቃ፥ ልብ​ስ​ንም ተዋሱ።</verse>
				<verse number="36">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሕ​ዝቡ በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ፊት ሞገ​ስን ሰጠ፤ እነ​ር​ሱም አዋ​ሱ​አ​ቸው። እነ​ር​ሱም ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በዘ​በ​ዙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="37">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከራ​ምሴ ተነ​ሥ​ተው ወደ ሱኮት ሄዱ፤ ከጓዝ ጋር ካሉት ሌላ ስድ​ስት መቶ ሺህ ሰው የሚ​ያ​ህል እግ​ረኛ ነበረ።</verse>
				<verse number="38">ደግ​ሞም ሌላ ብዙ ድብ​ልቅ ሕዝብ፥ መን​ጎ​ችና ላሞ​ችም እጅግ ብዙም ከብ​ቶች ከእ​ነ​ርሱ ጋር ወጡ።</verse>
				<verse number="39">ከግ​ብ​ፅም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ያወ​ጡ​ትን ሊጥ ቂጣ እን​ጎቻ አድ​ር​ገው ጋገ​ሩት። አል​ቦ​ካም ነበ​ርና፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ስለ አስ​ወ​ጡ​አ​ቸው ይቈዩ ዘንድ አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና፤ ለመ​ን​ገ​ድም ስንቅ አላ​ሰ​ና​ዱም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="40">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በግ​ብፅ ምድ​ርና በከ​ነ​ዓን ምድር እነ​ር​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ቸው የተ​ቀ​መ​ጡት ዘመን አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ነው።</verse>
				<verse number="41">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠራ​ዊት ሁሉ በሌ​ሊት ከግ​ብፅ ምድር ወጣ።</verse>
				<verse number="42">ይህች ሌሊት ከግ​ብፅ ምድር ስላ​ወ​ጣ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ጠ​በ​ቀች ናት፤ ይህች ሌሊት በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ዘንድ እስከ ልጅ ልጃ​ቸው ድረስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ጠ​በ​ቀች ናት።</verse>
				<verse number="43">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን አላ​ቸው፥ “ይህ የፋ​ሲካ ሕግ ነው፤ ከእ​ርሱ ባዕድ ሰው አይ​ብላ።</verse>
				<verse number="44">አገ​ል​ጋይ ወይም በብር የተ​ገዛ ቢኖር ከተ​ገ​ረዘ በኋላ ያን ጊዜ ከእ​ርሱ ይብላ።</verse>
				<verse number="45">ጥገ​ኛና ሞያ​ተኛ ግን ከእ​ርሱ አይ​ብሉ።</verse>
				<verse number="46">በአ​ንድ ቤትም ይበላ፤ ከሥ​ጋ​ውም አን​ዳች ከቤት ወደ ሜዳ አታ​ውጡ፤ አጥ​ን​ቱ​ንም አት​ስ​በሩ።</verse>
				<verse number="47">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ማኅ​በር ሁሉ ያድ​ር​ጉት።</verse>
				<verse number="48">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፋሲካ ያደ​ርግ ዘንድ ወደ እና​ንተ የመጣ መጻ​ተኛ ቢኖር ወን​ዱን ሁሉ ትገ​ር​ዛ​ለህ፤ ያን ጊዜም ፋሲካ ያደ​ርግ ዘንድ ይገ​ባል፤ እንደ ሀገር ልጅም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፤ ያል​ተ​ገ​ረዘ ሁሉ ግን ከእ​ርሱ አይ​ብላ።</verse>
				<verse number="49">ለሀ​ገር ልጅ፥ በእ​ና​ንተ መካ​ከ​ልም ለሚ​ቀ​መጡ መጻ​ተ​ኞች አንድ ሥር​ዐት ይሆ​ናል።”</verse>
				<verse number="50">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እን​ዲህ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እንደ አዘዘ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="51">በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ጋር ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ከሰ​ውም፥ ከእ​ን​ስ​ሳም መጀ​መ​ሪያ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ማሕ​ፀ​ንን የሚ​ከ​ፍት በኵር ሁሉ ለእኔ ለይ​ልኝ፤ የእኔ ነው።”</verse>
				<verse number="3">ሙሴም ሕዝ​ቡን አለ፥ “ከባ​ር​ነት ቤት ከግ​ብፅ የወ​ጣ​ች​ሁ​ባ​ትን ይህ​ችን ቀን ዐስቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚህ ቦታ በበ​ረ​ታች እጅ አው​ጥ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና። ስለ​ዚህ የቦካ እን​ጀራ አት​ብሉ።</verse>
				<verse number="4">እና​ንተ በዚች ቀን በሚ​ያ​ዝያ ወር ወጥ​ታ​ች​ኋ​ልና።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእ​ና​ንተ ይሰ​ጣት ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ወደ​ማ​ለ​ላ​ቸው፥ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስስ ምድር፥ ወደ ከና​ኔ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ኬጢ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ምድር በአ​ገ​ባ​ችሁ ጊዜ ይህ​ችን ሥር​ዐት በዚህ ወር አድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="6">ስድ​ስት ቀን ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ሰባ​ተ​ኛ​ውም ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="7">ሰባት ቀንም ሙሉ ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በእ​ና​ን​ተም ዘንድ እርሾ ያለ​በት እን​ጀራ አይ​ታይ፤ በአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ቻ​ችሁ ሁሉ እርሾ አይ​ኑር።</verse>
				<verse number="8">በዚ​ያም ቀን፦ ‘ከግ​ብፅ በወ​ጣሁ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ስለ​አ​ደ​ረ​ገ​ልኝ ነው’ ስትል ለል​ጅህ ትነ​ግ​ረ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በበ​ረ​ታች እጅ ከግ​ብፅ አው​ጥ​ቶ​ሃ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ በአ​ፍህ ይሆን ዘንድ በእ​ጅህ እንደ ምል​ክት፥ በዐ​ይ​ኖ​ች​ህም መካ​ከል እንደ መታ​ሰ​ቢያ ይሁ​ን​ልህ።</verse>
				<verse number="10">ከቀን ወደ ቀን በየ​ጊ​ዜው ይህን ሕግ ጠብ​ቁት።</verse>
				<verse number="11">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ባ​ቶ​ችህ እን​ደ​ማለ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን ምድር በአ​ገ​ባህ ጊዜ፥ እር​ስ​ዋ​ንም ለአ​ንተ በሰ​ጠህ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="12">ማሕ​ፀ​ንን የሚ​ከ​ፍ​ተ​ውን ሁሉ ለይ፤ ከመ​ን​ጋ​ህና ከከ​ብ​ት​ህም መጀ​መ​ሪያ የሚ​ወ​ለ​ደው ተባት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="13">የአ​ህ​ያ​ውን በኵር በበግ ትለ​ው​ጠ​ዋ​ለህ፤ ባት​ለ​ው​ጠው ግን ትዋ​ጀ​ዋ​ለህ። የሰ​ው​ንም በኵር ሁሉ ከል​ጆ​ችህ መካ​ከል ትዋ​ጀ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="14">እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ከዚህ በኋላ ልጅህ፦ ‘ይህ ምን​ድን ነው?’ ብሎ በጠ​የ​ቀህ ጊዜ እን​ዲህ ትለ​ዋ​ለህ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በብ​ርቱ እጅ ከባ​ር​ነት ቤት ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣን፤</verse>
				<verse number="15">ፈር​ዖ​ንም እኛን ለመ​ል​ቀቅ እንቢ ባለ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰው በኵር ጀምሮ እስከ እን​ስሳ በኵር ድረስ በግ​ብፅ ምድር ያለ​ውን በኵር ሁሉ ገደለ፤ ስለ​ዚህ ወንድ ሆኖ ማሕ​ፀ​ንን የከ​ፈ​ተ​ውን ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሠ​ዋ​ለሁ፤ ነገር ግን የል​ጆ​ችን በኵር ሁሉ እዋ​ጃ​ለሁ።’</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በብ​ርቱ እጅ ከግ​ብፅ አው​ጥ​ቶ​ሃ​ልና በእ​ጅህ እንደ ምል​ክት ፥ ከዐ​ይ​ኖ​ች​ህም እን​ደ​ማ​ይ​ርቅ ነገር ይሁ​ን​ልህ።”</verse>
				<verse number="17">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ፈር​ዖን ሕዝ​ቡን በለ​ቀቀ ጊዜ፥ ምንም ቅርብ ቢሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ምድር መን​ገድ አል​መ​ራ​ቸ​ውም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ሕዝቡ ሰል​ፉን በአየ ጊዜ እን​ዳ​ይ​ጸ​ጽ​ተው፥ ወደ ግብ​ፅም እን​ዳ​ይ​መ​ለስ” ብሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="18">ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን በዙ​ሪያ መን​ገድ በኤ​ር​ትራ ባሕር ባለ​ችው ምድረ በዳ መራ​ቸው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ትው​ልድ ከግ​ብፅ ምድር ወጡ።</verse>
				<verse number="19">ሙሴም የዮ​ሴ​ፍን ዐጽም ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መጐ​ብ​ኘ​ትን በጐ​በ​ኛ​ችሁ ጊዜ ዐጽ​ሜን ውሰዱ፤ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ከዚህ አውጡ” ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አም​ሎ​አ​ቸው ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="20">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ከሱ​ኮት ተጓዙ፤ በም​ድረ በዳ​ውም ዳር በኦ​ቶም ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ገድ ሊያ​ሳ​ያ​ቸው ቀን በዐ​ምደ ደመና፥ ሌሊ​ትም በዐ​ምደ እሳት ይመ​ራ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="22">ዐምደ ደመ​ናው በቀን፥ ዐምደ እሳ​ቱም በሌ​ሊት ከሕ​ዝቡ ፊት ከቶ ፈቀቅ አላ​ለም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“ተመ​ል​ሰው በመ​ግ​ደ​ሎና በባ​ሕር መካ​ከል፥ በብ​ኤ​ል​ሴ​ፎን ፊት ለፊት ባለው ገላጣ መን​ደር አን​ጻር እን​ዲ​ሰ​ፍሩ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተና​ገር፤ ከእ​ር​ሱም አጠ​ገብ በባ​ሕር ዳር ትሰ​ፍ​ራ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="3">ፈር​ዖ​ንም ለሕ​ዝቡ ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆች፦ ‘በም​ድር ይቅ​በ​ዘ​በ​ዛሉ፤ ምድረ በዳም ዘጋ​ቻ​ቸው’ ይላል።</verse>
				<verse number="4">እኔም የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸ​ና​ለሁ፤ እር​ሱም ከኋ​ላ​ቸው ይከ​ተ​ላ​ቸ​ዋል፤ እኔም በፈ​ር​ዖ​ንና በሠ​ራ​ዊቱ ሁሉ ላይ እከ​ብ​ራ​ለሁ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ሁሉ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።” እነ​ር​ሱም እን​ዲሁ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="5">ሕዝ​ቡም እንደ ኰበ​ለሉ ለግ​ብፅ ንጉሥ ነገ​ሩት፤ የፈ​ር​ዖ​ንና የሹ​ሞ​ቹም ልብ በሕ​ዝቡ ላይ ተለ​ወ​ጠና፥ “እን​ዳ​ይ​ገ​ዙ​ልን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች የለ​ቀ​ቅ​ነው ምን ማድ​ረ​ጋ​ችን ነው?” አሉ።</verse>
				<verse number="6">ፈር​ዖ​ንም ሰረ​ገ​ላ​ውን አሰ​ናዳ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ከእ​ርሱ ጋር ሰበ​ሰበ።</verse>
				<verse number="7">ስድ​ስት መቶ የተ​መ​ረጡ ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንም፥ የግ​ብ​ፅ​ንም ፈረ​ሶች ሁሉ ወስዶ ሁሉ​ንም ከሦ​ስት ከፈ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የግ​ብ​ፅን ንጉሥ የፈ​ር​ዖ​ን​ንና የሹ​ሞ​ቹን ልብ አጸና፤ እር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አሳ​ደደ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከፍ ባለች እጅ ወጡ።</verse>
				<verse number="9">ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም፥ የፈ​ር​ዖን ፈረ​ሶች፥ ሰረ​ገ​ሎ​ቹም፥ ፈረ​ሰ​ኞ​ቹም፥ ሠራ​ዊ​ቱም ሁሉ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ በባ​ሕሩ ዳር በብ​ኤ​ል​ሴ​ፎን ፊት ለፊት ባለው ገላጣ መን​ደር አን​ጻ​ርም ሰፍ​ረው አገ​ኙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">ፈር​ዖ​ንም በቀ​ረበ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዐይ​ና​ቸ​ውን አነሡ፤ እነ​ሆም፥ ግብ​ፃ​ው​ያን ሲከ​ተ​ሉ​አ​ቸው አዩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እጅግ ፈሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ።</verse>
				<verse number="11">ሙሴ​ንም አሉት፥ “በግ​ብፅ መቃ​ብር ስላ​ል​ኖረ በም​ድረ በዳ እን​ሞት ዘንድ አወ​ጣ​ኸን? ከግ​ብፅ ታወ​ጣን ዘንድ ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="12">በም​ድረ በዳ ከም​ን​ሞት ብን​ገ​ዛ​ላ​ቸው ይሻ​ለ​ና​ልና፦ ‘ተወን፤ ለግ​ብ​ፃ​ው​ያን እን​ገዛ’ ብለን በግ​ብፅ ሳለን ያል​ንህ ቃል ይህ አይ​ደ​ለ​ምን?”</verse>
				<verse number="13">ሙሴም ለሕ​ዝቡ፥ “አት​ፍሩ፤ ዛሬ የም​ታ​ዩ​አ​ቸ​ውን ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አታ​ዩ​አ​ቸ​ው​ምና ቁሙ፤ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማዳን እዩ።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እና​ንተ ይዋ​ጋል፤ እና​ን​ተም ዝም ትላ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ለምን ትጮ​ኽ​ብ​ኛ​ለህ? ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን እን​ዲ​ነዱ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ንገር።</verse>
				<verse number="16">አን​ተም በት​ር​ህን አንሣ፤ እጅ​ህ​ንም በባ​ሕሩ ላይ ዘርጋ፤ ክፈ​ለ​ውም፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በባ​ሕሩ ውስጥ በየ​ብስ ያል​ፋሉ።</verse>
				<verse number="17">እነ​ሆም፥ እኔ የፈ​ር​ዖ​ን​ንና የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንን ልብ አጸ​ና​ለሁ፤ በኋ​ላ​ቸ​ውም ይገ​ባሉ፤ በፈ​ር​ዖ​ንና በሠ​ራ​ዊ​ቱም ሁሉ፥ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹም፥ በፈ​ረ​ሰ​ኞ​ቹም ላይ እከ​ብ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="18">ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም በፈ​ር​ዖ​ንና በሰ​ረ​ገ​ሎቹ፥ በፈ​ረ​ሰ​ኞ​ቹም ላይ ክብር በአ​ገ​ኘሁ ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”</verse>
				<verse number="19">በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሠራ​ዊት ፊት ይሄድ የነ​በ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ፈቀቅ ብሎ በኋ​ላ​ቸው ሄደ፤ የደ​መ​ና​ውም ዐምድ ከፊ​ታ​ቸው ፈቀቅ ብሎ በኋ​ላ​ቸው ቆመ፤</verse>
				<verse number="20">በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ሰፈ​ርና በእ​ስ​ራ​ኤል ሰፈር መካ​ከ​ልም ገባ፤ በዚ​ያም ጭጋ​ግና ጨለማ ነበረ፤ ሌሊ​ቱም አለፈ፤ ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ እርስ በእ​ር​ሳ​ቸው አል​ተ​ቃ​ረ​ቡም።</verse>
				<verse number="21">ሙሴም በባ​ሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሌሊ​ቱን ሁሉ ጽኑ የአ​ዜብ ነፋስ አም​ጥቶ ባሕ​ሩን አስ​ወ​ገ​ደው፤ ባሕ​ሩ​ንም አደ​ረ​ቀው፤ ውኃ​ውም ተከ​ፈለ።</verse>
				<verse number="22">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በባ​ሕሩ መካ​ከል በየ​ብስ ገቡ፤ ውኃ​ውም በቀ​ኛ​ቸ​ውና በግ​ራ​ቸው እንደ ግድ​ግዳ ሆነ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም፥ የፈ​ር​ዖን ፈረ​ሶ​ችና ሰረ​ገ​ሎች፥ ፈረ​ሰ​ኞ​ቹም ሁሉ እያ​ሳ​ደዱ በኋ​ላ​ቸው ወደ ባሕር መካ​ከል ገቡ።</verse>
				<verse number="24">ንጋ​ትም በሆነ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ሳ​ትና በደ​መና ዐምድ ሆኖ የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንን ሠራ​ዊት ተመ​ለ​ከተ፤ የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም ሠራ​ዊት አወከ።</verse>
				<verse number="25">የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም መን​ኰ​ራ​ኵር አሰረ፤ ወደ ጭን​ቅም አገ​ባ​ቸው፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እነ​ርሱ ይዋ​ጋ​ላ​ቸ​ዋ​ልና ከእ​ስ​ራ​ኤል ፊት እን​ሽሽ” አሉ።</verse>
				<verse number="26">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እጅ​ህን በባ​ሕሩ ላይ ዘርጋ፤ ውኃ​ውም በግ​ብ​ፃ​ው​ያን፥ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም፥ በፈ​ረ​ሰ​ኞ​ቻ​ቸ​ውም ላይ ይመ​ለስ፤ ይሸ​ፍ​ና​ቸ​ውም።”</verse>
				<verse number="27">ሙሴም እጁን በባ​ሕሩ ላይ ዘረጋ፤ ባሕ​ሩም ማለዳ ወደ መፍ​ሰሱ ተመ​ለሰ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ከእ​ርሱ ሸሹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በባ​ሕሩ መካ​ከል ጣላ​ቸው።</verse>
				<verse number="28">ውኃ​ውም ተመ​ልሶ በኋ​ላ​ቸው ወደ ባሕር የገ​ቡ​ትን ሰረ​ገ​ሎ​ችን፥ ፈረ​ሰ​ኞ​ች​ንም፥ የፈ​ር​ዖ​ን​ንም ሠራ​ዊት ሁሉ ከደነ፤ ከመ​ጡ​ትም ሁሉ አንድ ስንኳ የቀረ የለም።</verse>
				<verse number="29">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን በባ​ሕሩ ውስጥ በየ​ብስ ሄዱ፤ ውኃ​ውም በቀ​ኛ​ቸ​ውና በግ​ራ​ቸው እንደ ግድ​ግዳ ሆነ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="30">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚያ ቀን እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን እጅ አዳ​ና​ቸው፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ግብ​ፃ​ው​ያን እንደ ሞቱ በባ​ሕር ዳር አዩ።</verse>
				<verse number="31">እስ​ራ​ኤ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ያደ​ረ​ጋ​ትን ታላ​ቂ​ቱን እጅ አዩ፤ ሕዝ​ቡም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አመኑ፤ ባሪ​ያ​ው​ንም ሙሴን አከ​በሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">በዚያ ጊዜም ሙሴና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይህን መዝ​ሙር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘመሩ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ተና​ገሩ፦ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዘ​ም​ራ​ለን፤ በክ​ብር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፤ ፈረ​ሱ​ንና ፈረ​ሰ​ኛ​ውን በባ​ሕር ጣለ።</verse>
				<verse number="2">እኔን ለማ​ዳን ረዳ​ትና ሰዋሪ ሆነኝ፤ ይህ አም​ላኬ ነው፤ አመ​ሰ​ግ​ነ​ው​ማ​ለሁ፤ የአ​ባቴ አም​ላክ ነው፤ ከፍ ከፍም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጦር​ነ​ትን ያጠ​ፋል፤ ስሙም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤</verse>
				<verse number="4">የፈ​ር​ዖ​ንን ሰረ​ገ​ሎች፥ ሠራ​ዊ​ቱ​ንም በባ​ሕር ጣላ​ቸው። በሦ​ስት የተ​ከ​ፈሉ ፈረ​ሰ​ኞ​ችም በኤ​ር​ትራ ባሕር ሰጠሙ።</verse>
				<verse number="5">ማዕ​በ​ልም ከደ​ና​ቸው፤ ወደ ባሕር ጥል​ቀት እንደ ድን​ጋይ ሰጠሙ።</verse>
				<verse number="6">አቤቱ፥ ቀኝህ በኀ​ይል ከበረ፤ አቤቱ፥ ቀኝህ ጠላ​ቶ​ችን አደ​ቀቀ።</verse>
				<verse number="7">በክ​ብ​ር​ህም ብዛት ጠላ​ቶ​ች​ህን አጠ​ፋህ፤ ቍጣ​ህን ሰደ​ድህ፤ እንደ ገለ​ባም በላ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">በቍ​ጣህ እስ​ት​ን​ፋስ ውኃው ቆመ፤ ውኃ​ዎች እንደ ግደ​ግዳ ቆሙ፤ ሞገ​ዱም በባ​ሕር መካ​ከል ረጋ።</verse>
				<verse number="9">ጠላ​ትም፦ ‘አሳ​ድጄ እይ​ዛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ምር​ኮም እካ​ፈ​ላ​ለሁ፤ ነፍ​ሴ​ንም አጠ​ግ​ባ​ታ​ለሁ፤ በሰ​ይ​ፌም እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ በእ​ጄም እገ​ዛ​ለሁ’ አለ።</verse>
				<verse number="10">ነፋ​ስ​ህን ላክህ፤ ባሕ​ርም ከደ​ና​ቸው፤ በብዙ ውኆች ውስጥ እንደ አረር ሰጠሙ።</verse>
				<verse number="11">አቤቱ፦ በአ​ማ​ል​ክት መካ​ከል አን​ተን የሚ​መ​ስል ማን ነው? በቅ​ዱ​ሳ​ንም ዘንድ እንደ አንተ የከ​በረ ማን ነው? በም​ስ​ጋና የተ​ደ​ነ​ቅህ ነህ፤ ድን​ቅ​ንም የም​ታ​ደ​ርግ ነህ፤</verse>
				<verse number="12">ቀኝ​ህን ዘረ​ጋህ፤ ምድ​ርም ዋጠ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">በቸ​ር​ነ​ትህ የተ​ቤ​ዠ​ሃ​ቸ​ውን ሕዝ​ብ​ህን መራህ፤ በኀ​ይ​ልህ ወደ ቅዱስ ማደ​ሪ​ያህ ጠራ​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">አሕ​ዛብ ሰሙ፤ ተቈ​ጡም፤ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ምጥ ያዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">ያን ጊዜ የኤ​ዶም አለ​ቆች ሸሹ፤ የሞ​ዓ​ብ​ንም አለ​ቆች መን​ቀ​ጠ​ቀጥ ያዛ​ቸው፤ በከ​ነ​ዓን የሚ​ኖሩ ሁሉ ቀለጡ።</verse>
				<verse number="16">ፍር​ሀ​ትና ድን​ጋጤ ወደ​ቀ​ባ​ቸው፤ የክ​ን​ድህ ብር​ታ​ትም ከድ​ን​ጋይ ይልቅ ጸና፤ አቤቱ፥ ሕዝ​ብህ እስ​ኪ​ያ​ልፉ ድረስ፥ የተ​ቤ​ዠ​ሃ​ቸው እኒህ ሕዝ​ብህ እስ​ኪ​ያ​ልፉ ድረስ፤</verse>
				<verse number="17">አቤቱ፥ አንተ ታስ​ገ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በመ​መ​ስ​ገ​ኛህ ተራ​ራም ትተ​ክ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤ አቤቱ፥ ለማ​ደ​ሪ​ያህ ባደ​ረ​ግ​ኸው ስፍራ፥ አቤቱ፥ እጆ​ችህ ባዘ​ጋ​ጁት መቅ​ደስ፤</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለ​ምም ይነ​ግ​ሣል።</verse>
				<verse number="19">“የፈ​ር​ዖን ፈረ​ሶች ከሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹና ከፈ​ረ​ሰ​ኞቹ ጋር ወደ ባሕር ገቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የባ​ሕ​ሩን ውኆች መለ​ሰ​ባ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን በባ​ሕሩ መካ​ከል በየ​ብስ አለፉ፤ ውኃ​ውም ለእ​ነ​ርሱ በቀኝ እንደ ግድ​ግዳ፥ በግ​ራም እንደ ግድ​ግዳ ሆነ​ላ​ቸው።”</verse>
				<verse number="20">የአ​ሮን እኅት ነቢ​ይቱ ማር​ያ​ምም ከበሮ በእ​ጅዋ ወሰ​ደች፤ ሴቶ​ችም ሁሉ በከ​በ​ሮና በዝ​ማሬ በኋ​ላዋ ወጡ።</verse>
				<verse number="21">ማር​ያ​ምም አስ​ቀ​ድማ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዘ​ምር አለች፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዘ​ምር በክ​ብር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፤ ፈረ​ሱ​ንና ፈረ​ሰ​ኛ​ውን በባ​ሕር ጥሎ​አ​ልና።”</verse>
				<verse number="22">ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከኤ​ር​ትራ ባሕር አው​ጥቶ ወደ ሱር ምድረ በዳ ወሰ​ዳ​ቸው። በም​ድረ በዳም ሦስት ቀን ተጓዙ፤ ይጠ​ጡም ዘንድ ውኃ አላ​ገ​ኙም።</verse>
				<verse number="23">ወደ ማራም በመጡ ጊዜ ከማራ ውኃ ሊጠጡ አል​ቻ​ሉም፤ ውኃው መራራ ነበ​ርና፤ ስለ​ዚህ የዚያ ስፍራ ስም “መሪር” ተብሎ ተጠራ።</verse>
				<verse number="24">ሕዝ​ቡም፥ “ምን እን​ጠ​ጣ​ለን?” ብለው በሙሴ ላይ አን​ጐ​ራ​ጐሩ።</verse>
				<verse number="25">ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዕን​ጨ​ትን አሳ​የው፤ በው​ኃ​ውም ላይ ጣለው፤ ውኃ​ውም ጣፈጠ። በዚ​ያም ሥር​ዐ​ት​ንና ፍር​ድን አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው፤ በዚ​ያም ፈተ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="26">እር​ሱም፥ “አንተ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አጥ​ብ​ቀህ ብት​ሰማ፥ በፊ​ቱም መል​ካ​ምን ብታ​ደ​ርግ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ብታ​ደ​ምጥ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ሁሉ ብት​ጠ​ብቅ፥ በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ያመ​ጣ​ሁ​ትን በሽታ አላ​ደ​ር​ስ​ብ​ህም፤ እኔ ፈዋ​ሽህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና” አለ።</verse>
				<verse number="27">እነ​ር​ሱም ወደ ኤሎም መጡ፤ በዚ​ያም ዐሥራ ሁለት የውኃ ምን​ጮ​ችና ሰባ የዘ​ን​ባባ ዛፎች ነበ​ሩ​ባት፤ በዚ​ያም በው​ኃው አጠ​ገብ ሰፈሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ከኤ​ሎም ተጓዙ፤ ከግ​ብፅ ሀገር ከወጡ በኋላ በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን በኤ​ሎ​ምና በሲና መካ​ከል ወዳ​ለ​ችው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጡ።</verse>
				<verse number="2">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ አን​ጐ​ራ​ጐሩ።</verse>
				<verse number="3">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አሉ​አ​ቸው፥ “በሥ​ጋው ምን​ቸት አጠ​ገብ ተቀ​ም​ጠን እስ​ክ​ን​ጠ​ግብ ድረስ እን​ጀ​ራና ሥጋ በም​ን​በ​ላ​በት ጊዜ በግ​ብፅ ምድር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ምነው በሞ​ትን! ይህን ጉባኤ ሁሉ በራብ ልት​ገ​ድሉ እኛን ወደ​ዚች ምድረ በዳ አም​ጥ​ታ​ች​ኋ​ልና።”</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “በሕጌ ይሄዱ ወይም አይ​ሄዱ እንደ ሆነ እኔ እን​ድ​ፈ​ት​ና​ቸው፥ እነሆ፥ ከሰ​ማይ እን​ጀ​ራን አዘ​ን​ብ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሕዝ​ቡም ወጥ​ተው ለዕ​ለት ለዕ​ለት የሚ​በ​ቃ​ቸ​ውን ይሰ​ብ​ስቡ።</verse>
				<verse number="5">እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ቀን ያመ​ጡ​ትን ያዘ​ጋጁ፤ ዕለት ዕለ​ትም ከሚ​ለ​ቅ​ሙት ይልቅ ሁለት እጥፍ ይሁን” አለው።</verse>
				<verse number="6">ሙሴና አሮ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ ምድር እንደ አወ​ጣ​ችሁ ማታ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="7">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ክብር ጥዋት ታያ​ላ​ችሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ያን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁ​ትን ሰም​ቶ​አ​ልና፤ በእ​ኛም ላይ የም​ታ​ን​ጐ​ራ​ጕሩ እኛ ምን​ድን ነን?” አሉ።</verse>
				<verse number="8">ሙሴም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁ​በ​ትን ማን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁን ሰም​ቶ​አ​ልና በመሸ ጊዜ ትበሉ ዘንድ ሥጋን፥ በማ​ለ​ዳም ትጠ​ግቡ ዘንድ እን​ጀ​ራን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ እኛም ምን​ድን ነን? ማን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ነው እንጂ በእኛ ላይ አይ​ደ​ለም” አለ።</verse>
				<verse number="9">ሙሴም አሮ​ንን፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ፦ ‘ማን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁን ሰም​ቶ​አ​ልና ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅረቡ’ በል” አለው።</verse>
				<verse number="10">አሮ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በተ​ና​ገረ ጊዜ ወደ ምድረ በዳ ፊታ​ቸ​ውን አቀኑ፤ እነ​ሆም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር በደ​መ​ናው ታየ።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፦</verse>
				<verse number="12">“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማን​ጐ​ራ​ጐር ሰማሁ፦ ማታ ሥጋን ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ማለ​ዳም እን​ጀ​ራን ትጠ​ግ​ባ​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ በላ​ቸው።”</verse>
				<verse number="13">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በመሸ ጊዜ ድር​ጭ​ቶች መጡ፤ ሰፈ​ሩ​ንም ሸፈ​ኑት፤ በማ​ለ​ዳም በሰ​ፈሩ ዙሪያ ጠል ወድቆ ነበር።</verse>
				<verse number="14">የወ​ደ​ቀው ጠል በአ​ለፈ ጊዜ፥ እነሆ፥ በመ​ሬት ላይ እንደ ውርጭ ነጭ ሆኖ ድን​ብ​ላል የሚ​መ​ስል ደቃቅ ነገር በም​ድረ በዳ ታየ።</verse>
				<verse number="15">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በአ​ዩት ጊዜ እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ይህ ምን​ድን ነው?” ተባ​ባሉ። ያ ምን እን​ደ​ሆነ አላ​ወ​ቁ​ምና። ሙሴም አላ​ቸው፥ “ትበሉ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጣ​ችሁ እን​ጀራ ይህ ነው።</verse>
				<verse number="16">ታደ​ር​ጉት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘው ነገር ይህ ነው፦ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ለቤተ ሰቡ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አንድ ጎሞር ይሰ​ብ​ስብ፤ እንደ ቤተ ሰቡ ቍጥር ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ በድ​ን​ኳኑ አብ​ረ​ውት ከሚ​ኖ​ሩት ጋር ይሰ​ብ​ስብ።”</verse>
				<verse number="17">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ አንዱ አብ​ዝቶ፥ አን​ዱም አሳ​ንሶ ሰበ​ሰበ።</verse>
				<verse number="18">በጎ​ሞ​ርም በሰ​ፈ​ሩት ጊዜ እጅግ ለሰ​በ​ሰበ አል​ተ​ረ​ፈ​ውም፤ ጥቂ​ትም ለሰ​በ​ሰበ አል​ጐ​ደ​ለ​በ​ትም፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ለየ​ቤቱ ሰበ​ሰበ።</verse>
				<verse number="19">ሙሴም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማንም ከእ​ርሱ አን​ዳች ለነገ አያ​ስ​ቀር” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">ነገር ግን ሙሴን አል​ሰ​ሙ​ትም፤ አን​ዳ​ንድ ሰዎ​ችም ከእ​ርሱ ለነገ አስ​ቀሩ፤ እር​ሱም ተላ፤ ሸተ​ተም፤ ሙሴም ተቈ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">ሰውም ሁሉ ለየ​ራሱ ጥዋት ጥዋት ሰበ​ሰበ፤ ፀሐ​ይም በተ​ኰሰ ጊዜ ቀለጠ።</verse>
				<verse number="22">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ቀን ሁለት እጥፍ አድ​ር​ገው እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ሁለት ጎሞር እን​ጀራ ሰበ​ሰቡ፤ የማ​ኅ​በ​ሩም አለ​ቆች ሁሉ መጥ​ተው ለሙሴ ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="23">ሙሴም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረው ይህ ነው፦ ነገ ዕረ​ፍት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቀ​ደሰ ሰን​በት ነው፤ ነገ የም​ት​ጋ​ግ​ሩ​ትን ዛሬ ጋግሩ፤ የም​ት​ቀ​ቅ​ሉ​ት​ንም ቀቅሉ፤ የተ​ረ​ፈ​ው​ንም ሁሉ ለነገ እን​ዲ​ጠ​በቅ አኑሩ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">ሙሴም እንደ አዘዘ ለነገ አኖ​ሩት፤ አል​ሸ​ተ​ተም፤ ትልም አል​ሆ​ነ​በ​ትም።</verse>
				<verse number="25">ሙሴም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰን​በት ዛሬ ነውና ብሉት፤ ዛሬ በሜዳ አታ​ገ​ኙ​ትም።</verse>
				<verse number="26">ስድ​ስት ቀን ልቀ​ሙት፤ ሰባ​ተ​ኛው ቀን ግን ሰን​በት ነው፤ በእ​ርሱ አይ​ገ​ኝም” አለ።</verse>
				<verse number="27">በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ ከሕ​ዝቡ አን​ዳ​ንድ ሰዎች ሊለ​ቅሙ ወጡ፤ ግን ምንም አላ​ገ​ኙም።</verse>
				<verse number="28">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ትእ​ዛ​ዞ​ች​ንና ሕጎ​ችን ለመ​ስ​ማት እስከ መቼ እንቢ ትላ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="29">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰን​በ​ትን እንደ ሰጣ​ችሁ እዩ፤ ስለ​ዚህ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ቀን የሁ​ለት ቀን እን​ጀራ ሰጣ​ችሁ፤ ሰው ሁሉ በቤቱ ይቀ​መጥ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ማንም ከቤቱ አይ​ሂድ” አለው።</verse>
				<verse number="30">ሕዝ​ቡም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ዐረፈ።</verse>
				<verse number="31">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ስሙን መና ብለው ጠሩት፤ እር​ሱም እንደ ድን​ብ​ላል ዘር ነጭ ነው፤ ጣዕ​ሙም እንደ ማር እን​ጀራ ነው።</verse>
				<verse number="32">ሙሴም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘው ነገር ይህ ነው፦ ከግ​ብፅ ምድር በአ​ወ​ጣ​ኋ​ችሁ ጊዜ በም​ድረ በዳ ያበ​ላ​ኋ​ች​ሁን እን​ጀራ ያዩ ዘንድ ከእ​ርሱ አንድ ጎሞር ሙሉ ለልጅ ልጆ​ቻ​ችሁ ይጠ​በቅ” አለ።</verse>
				<verse number="33">ሙሴም አሮ​ንን፥ “አንድ የወ​ርቅ መሶብ ወስ​ደህ ጎሞር ሙሉ መና አግ​ባ​በት፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም ይጠ​በቅ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አኑ​ረው” አለው።</verse>
				<verse number="34">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ ይጠ​በቅ ዘንድ አሮን በም​ስ​ክሩ ፊት አኖ​ረው።</verse>
				<verse number="35">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ​ሚ​ኖ​ሩ​ባት ምድር እስ​ከ​ሚ​መጡ ድረስ አርባ ዓመት መና በሉ።</verse>
				<verse number="36">ወደ ፊኒ​ቆ​ንም ምድር እስ​ኪ​መጡ ድረስ መና በሉ። ጎሞ​ርም የሦ​ስት ላዳን መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ ክፍል ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘዘ ከሲን ምድረ በዳ ሊጓዙ ተነሡ፤ በራ​ፊ​ድም ሰፈሩ፤ በዚ​ያም ሕዝቡ የሚ​ጠ​ጡት ውኃ አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="2">ሕዝ​ቡም ሙሴን ተጣ​ሉት፥ “የም​ን​ጠ​ጣ​ውን ውኃ ስጠን” አሉ። ሙሴም፥ “ለምን ትጣ​ሉ​ኛ​ላ​ችሁ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንስ ለምን ትፈ​ታ​ተ​ና​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ሕዝ​ቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፥ “እኛ​ንና ልጆ​ቻ​ች​ንን፥ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ን​ንም በጥ​ማት ልት​ገ​ድል ለምን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ኸን?” ሲሉ በሙሴ ላይ አን​ጐ​ራ​ጐሩ።</verse>
				<verse number="4">ሙሴም፦ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ለዚህ ሕዝብ ምን ላድ​ርግ? በድ​ን​ጋይ ሊወ​ግ​ሩኝ ጥቂት ቀር​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና።”</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “በሕ​ዝቡ ፊት እለፍ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችን ከአ​ንተ ጋር ውሰድ፤ ወን​ዙ​ንም የመ​ታ​ህ​ባ​ትን በትር በእ​ጅህ ይዘ​ሃት ሂድ።</verse>
				<verse number="6">እነሆ፥ እኔ በዚያ በኮ​ሬብ በዓ​ለት ላይ በፊ​ትህ እቆ​ማ​ለሁ፤ ዓለ​ቱ​ንም ትመ​ታ​ለህ፤ ሕዝ​ቡም ይጠጣ ዘንድ ከእ​ርሱ ውኃ ይወ​ጣል” አለው። ሙሴም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ዲሁ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="7">ስለ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ክር​ክር፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችን ነውን? ወይስ አይ​ደ​ለም?” ሲሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ተፈ​ታ​ተ​ኑት የዚ​ያን ስፍራ ስም “መን​ሱት” ደግ​ሞም “ጋእዝ” ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="8">ዐማ​ሌ​ቅም መጥቶ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋራ በራ​ፊድ ተዋጋ።</verse>
				<verse number="9">ሙሴም ኢያ​ሱን፥ “ጐል​ማ​ሶ​ችን ለአ​ንተ ምረጥ፤ ሲነ​ጋም ወጥ​ተህ ከዐ​ማ​ሌቅ ጋር ተዋጋ፤ እኔም በተ​ራ​ራው ራስ ላይ እቆ​ማ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በትር በእጄ ናት” አለው።</verse>
				<verse number="10">ኢያ​ሱም ሙሴ እንደ አለው አደ​ረገ፤ ወጥ​ቶም ከዐ​ማ​ሌቅ ጋር ተዋጋ፤ ሙሴና አሮን፥ ሖርም ወደ ኮረ​ብ​ታው ራስ ወጡ።</verse>
				<verse number="11">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ እጁን በአ​ነሣ ጊዜ እስ​ራ​ኤል ድል ያደ​ርግ ነበር ፤ እጁ​ንም በአ​ወ​ረደ ጊዜ ዐማ​ሌቅ ድል ያደ​ርግ ነበር።</verse>
				<verse number="12">የሙሴ እጆች ግን ከብ​ደው ነበር፤ ድን​ጋ​ይም ወሰዱ፤ በበ​ታ​ቹም አኖሩ፤ እር​ሱም ተቀ​መ​ጠ​በት፤ አሮ​ንና ሖርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሆነው እጆ​ቹን ይደ​ግፉ ነበር፤ ፀሐ​ይም እስ​ክ​ት​ገባ ድረስ እጆቹ ተዘ​ር​ግ​ተው ነበር።</verse>
				<verse number="13">ኢያ​ሱም ዐማ​ሌ​ቅ​ንና ሕዝ​ቡን በሰ​ይፍ ስለት አሸ​ነፈ።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “የዐ​ማ​ሌ​ቅን ዝክር ከሰ​ማይ በታች ጨርሼ እደ​መ​ስ​ሳ​ለ​ሁና ይህን ለመ​ታ​ሰ​ቢያ በመ​ጽ​ሐፍ ጻፈው፤ በኢ​ያ​ሱም ጆሮ ተና​ገር” አለው።</verse>
				<verse number="15">ሙሴም መሠ​ዊያ ሠራ፤ ስሙ​ንም “ምም​ሕ​ፃን” ብሎ ጠራው፤</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ሰ​ወ​ረች እጅ ዐማ​ሌ​ቅን እስከ ልጅ ልጅ ይዋ​ጋ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">የም​ድ​ያም ካህን የሙሴ አማት ዮቶር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙ​ሴና ለሕ​ዝቡ ለእ​ስ​ራ​ኤል ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ እንደ አወጣ ሰማ።</verse>
				<verse number="2">በዚያ ጊዜ የሙሴ አማት ዮቶር ትቶ​አት የነ​በ​ረ​ውን የሙ​ሴን ሚስት ሲፓ​ራን፥ ሁለ​ቱ​ንም ልጆ​ች​ዋን ወሰደ።</verse>
				<verse number="3">የአ​ን​ደ​ኛው ስም ጌር​ሳም ነበረ፤ አባቱ “በሌላ ሀገር ስደ​ተኛ ነበ​ርሁ” ብሎ​አ​ልና፤</verse>
				<verse number="4">የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ስም አል​ዓ​ዛር ነበረ፤ “የአ​ባቴ አም​ላክ ረዳኝ፤ ከፈ​ር​ዖ​ንም እጅ አዳ​ነኝ” ብሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="5">የሙሴ አማት ዮቶ​ርም ከል​ጆ​ቹና ከሚ​ስቱ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ አጠ​ገብ በም​ድረ በዳ ወደ ሰፈረ ወደ ሙሴ መጣ።</verse>
				<verse number="6">ሙሴ​ንም፥ “እነሆ፥ አማ​ትህ ዮቶር፥ ሚስ​ት​ህም ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ሁለቱ ልጆ​ችህ መጥ​ተ​ው​ል​ሃል” አሉት።</verse>
				<verse number="7">ሙሴም አማ​ቱን ሊገ​ናኝ ወጣ፤ እጅ ነሣው፤ ሳመ​ውም፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ሰላ​ምታ ተሰ​ጣጡ፤ ወደ ድን​ኳ​ኑም ገቡ።</verse>
				<verse number="8">ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ር​ዖ​ንና በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ስለ እስ​ራ​ኤል ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፥ በመ​ን​ገ​ድም ያገ​ኛ​ቸ​ውን ድካም ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ አዳ​ና​ቸው ለአ​ማቱ ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="9">ዮቶ​ርም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ረ​ገ​ላ​ቸ​ውን ቸር​ነት ሁሉ፥ ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን እጅና ከፈ​ር​ዖን እጅ እንደ አዳ​ና​ቸው ሰምቶ በሁሉ አደ​ነቀ።</verse>
				<verse number="10">ዮቶ​ርም፥ “ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን እጅና ከፈ​ር​ዖን እጅ ሕዝ​ቡን የአ​ዳነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ ነው።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብ​ፃ​ው​ያን ከሚ​መ​ኩ​ባ​ቸ​ውና ከሚ​ገ​ዙ​ላ​ቸው አማ​ል​ክት ሁሉ እን​ዲ​በ​ልጥ አሁን ዐወ​ቅሁ” አለ።</verse>
				<verse number="12">የሙሴ አማት ዮቶ​ርም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና ሌላ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወሰደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ከሙሴ አማት ጋር እን​ጀራ ሊበሉ አሮ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ መጡ።</verse>
				<verse number="13">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በነ​ጋው ሙሴ በሕ​ዝቡ ሊፈ​ርድ ተቀ​መጠ፤ ሕዝ​ቡም በሙሴ ፊት ከጥ​ዋት እስከ ማታ ድረስ ቆመው ነበር።</verse>
				<verse number="14">ዮቶ​ርም ሙሴ በሕ​ዝቡ ላይ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ሁሉ አይቶ እን​ዲህ አለው፥ “ብቻ​ህን ተቀ​ም​ጠህ በሕ​ዝቡ የም​ታ​ደ​ር​ገው ይህ ምን​ድን ነው? ሕዝቡ ሁሉ ከጥ​ዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ በዙ​ሪ​ያህ ቆመ​ዋል።”</verse>
				<verse number="15">ሙሴም አማ​ቱን፥ “ሕዝቡ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ ለመ​ጠ​የቅ ወደ እኔ ይመ​ጣሉ፤</verse>
				<verse number="16">ነገ​ርም ቢኖ​ራ​ቸው ወደ እኔ ይመ​ጣሉ፤ በዚ​ህና በዚያ ሰውም መካ​ከል እፈ​ር​ዳ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥር​ዐ​ትና ሕግ አስ​ታ​ው​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="17">የሙ​ሴም አማት አለው፥ “አንተ የም​ታ​ደ​ር​ገው ይህ ነገር ትክ​ክል አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="18">አንተ፥ ከአ​ን​ተም ጋር ያለው ሕዝብ ትደ​ክ​ማ​ላ​ችሁ፤ ይህ ነገር ይከ​ብ​ድ​ብ​ሃል፤ አንተ ብቻ​ህን ልታ​ደ​ር​ገው አት​ች​ልም።</verse>
				<verse number="19">አሁ​ንም እመ​ክ​ር​ሃ​ለ​ሁና ስማኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ንተ ጋር ይሆ​ናል፤ አንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለሕ​ዝቡ ሁን፤ ነገ​ራ​ቸ​ው​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አድ​ርስ፤</verse>
				<verse number="20">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥር​ዐ​ቱ​ንና ሕጉን መስ​ክ​ር​ላ​ቸው፤ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መን​ገድ፥ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ት​ንም ሥራ ሁሉ አሳ​ያ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">አን​ተም ከሕ​ዝቡ ሁሉ ኀያ​ላን ሰዎ​ችን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ሩ​ትን እው​ነ​ተ​ኞች ሰዎ​ችን፥ ትዕ​ቢ​ት​ንም የሚ​ጠሉ ሰዎ​ችን ፈልግ። ከእ​ነ​ር​ሱም የሺህ አለ​ቆ​ችን፥ የመቶ አለ​ቆ​ችን፥ የአ​ምሳ አለ​ቆ​ችን፥ የዐ​ሥ​ርም አለ​ቆ​ችን ሹም​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">በሕ​ዝቡ ላይ ሁል ጊዜ ይፍ​ረዱ፤ የከ​በ​ዳ​ቸ​ውን ነገር ወደ አንተ ያም​ጡት፤ ቀላ​ሉን ነገር ሁሉ እነ​ርሱ ይፍ​ረዱ፤ ያቃ​ል​ሉ​ል​ሃል፤ ይረ​ዱ​ሃ​ልም።</verse>
				<verse number="23">ይህ​ንም ቃሌን ብታ​ደ​ርግ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያበ​ረ​ታ​ሃል፤ መፍ​ረ​ድም ትች​ላ​ለህ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በሰ​ላም ወደ ስፍ​ራው ይመ​ለ​ሳል።”</verse>
				<verse number="24">ሙሴም የአ​ማ​ቱን ቃል ሰማ፤ እንደ አለ​ውም አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="25">ሙሴም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ችሎታ ያላ​ቸ​ውን ሰዎች መረጠ፤ በሕ​ዝ​ቡም ላይ የሺህ አለ​ቆች፥ የመቶ አለ​ቆች፥ የአ​ም​ሳም አለ​ቆች፥ የዐ​ሥ​ርም አለ​ቆች አድ​ርጎ ሾማ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">በሕ​ዝ​ቡም ላይ ሁል​ጊዜ ፈረዱ፤ የከ​በ​ዳ​ቸ​ው​ንም ነገር ወደ ሙሴ አመጡ፤ ቀላ​ሉን ነገር ሁሉ ግን እነ​ርሱ ፈረዱ።</verse>
				<verse number="27">ሙሴም አማ​ቱን አሰ​ና​በ​ተው፤ እር​ሱም ወደ ሀገሩ ተመ​ለሰ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሦ​ስ​ተ​ኛው ወር በዚያ ቀን ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ።</verse>
				<verse number="2">ከራ​ፊ​ድም ተነ​ሥ​ተው ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ፤ በዚ​ያም እስ​ራ​ኤል በተ​ራ​ራው ፊት ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="3">ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከተ​ራ​ራው ጠርቶ አለው፥ “ለያ​ዕ​ቆብ ቤት እን​ዲህ በል፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ንገር፤</verse>
				<verse number="4">በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን፥ እንደ ንስር ክን​ፍም እንደ ተሸ​ከ​ም​ኋ​ችሁ፥ ወደ እኔም እን​ዳ​መ​ጣ​ኋ​ችሁ አይ​ታ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="5">አሁ​ንም ቃሌን በእ​ው​ነት ብት​ሰሙ፥ ኪዳ​ኔ​ንም ብት​ጠ​ብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ የተ​መ​ረጠ ርስት ትሆ​ኑ​ል​ኛ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="6">እና​ን​ተም የክ​ህ​ነት መን​ግ​ሥት፥ የተ​ቀ​ደ​ሰም ሕዝብ ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ይህ​ንም ቃል ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ንገ​ራ​ቸው።”</verse>
				<verse number="7">ሙሴም መጣ፤ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጠርቶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ይህን ቃል ሁሉ በፊ​ታ​ቸው ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="8">ሕዝ​ቡም ሁሉ አንድ ቃል ሆነው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያለ​ውን ሁሉ እን​ሰ​ማ​ለን፤ እና​ደ​ር​ጋ​ለ​ንም” ብለው መለሱ፤ ሙሴም የሕ​ዝ​ቡን ቃል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አደ​ረሰ።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን፥ “ከአ​ንተ ጋር ስነ​ጋ​ገር ሕዝቡ እን​ዲ​ሰሙ፥ ደግ​ሞም ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዲ​ያ​ም​ኑ​ብህ፥ እነሆ፥ በዐ​ምደ ደመና ወደ አንተ እመ​ጣ​ለሁ” አለው። ሙሴም የሕ​ዝ​ቡን ቃል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነገረ።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ውረድ፤ ዛሬና ነገ ራሳ​ቸ​ውን ያንጹ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ያጥቡ ዘንድ ሕዝ​ቡን እዘ​ዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሕዝቡ ሁሉ ሲያዩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሲና ተራራ ላይ ይወ​ር​ዳ​ልና ለሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ተዘ​ጋ​ጅ​ተው ይጠ​ብቁ።</verse>
				<verse number="12">ለሕ​ዝ​ቡም በዙ​ሪ​ያው ወሰን አድ​ር​ግ​ላ​ቸው፤ ወደ ተራ​ራው እን​ዳ​ት​ወጡ፥ ከእ​ርሱ ማን​ኛ​ው​ንም ክፍል እን​ዳ​ት​ነኩ ተጠ​ን​ቀቁ፤ ተራ​ራ​ው​ንም የነካ ፈጽሞ ይሞ​ታል” ብለህ ንገ​ራ​ቸው፤</verse>
				<verse number="13">የማ​ንም እጅ አይ​ንካ፤ የሚ​ነ​ካ​ውም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ይወ​ገ​ራል፤ ወይም በፍ​ላጻ ይወ​ጋል፤ እን​ስሳ ወይም ሰው ቢሆን የቀ​ረበ አይ​ድ​ንም። የመ​ለ​ከት ድም​ፅና ደመና በተ​ራ​ራው በዐ​ለፈ ጊዜ ወደ ተራ​ራው ይውጡ።</verse>
				<verse number="14">ሙሴም ከተ​ራ​ራው ወደ ሕዝቡ ወረደ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ቀደሰ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አጠቡ።</verse>
				<verse number="15">ሕዝ​ቡ​ንም፥ “ለሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ተዘ​ጋጁ፤ ወደ ሴቶ​ቻ​ች​ሁም አት​ቅ​ረቡ” አለ።</verse>
				<verse number="16">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን በማ​ለዳ ጊዜ ነጐ​ድ​ጓ​ድና መብ​ረቅ፥ ከባ​ድም ደመና፥ ጉምም በሲና ተራራ ላይ ሆነ፤ እጅ​ግም የበ​ረታ የቀ​ንደ መለ​ከት ድምፅ ተሰማ፤ በሰ​ፈ​ሩም የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ተን​ቀ​ጠ​ቀጡ።</verse>
				<verse number="17">ሙሴም ሕዝ​ቡን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ለማ​ገ​ና​ኘት ከሰ​ፈር አወ​ጣ​ቸው፤ በተ​ራ​ራ​ውም እግ​ርጌ ቆሙ።</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ሳት ስለ ወረ​ደ​በት የሲና ተራራ ሁሉ እንደ ምድጃ ጢስ ይጤስ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ተራ​ራ​ውም ሁሉ እጅግ ይና​ወጥ ነበር፤ ሕዝ​ቡም ፈጽ​መው ደነ​ገጡ።</verse>
				<verse number="19">የቀ​ንደ መለ​ከ​ቱም ድምፅ እጅግ እየ​ፈ​ጠነ በር​ትቶ ይሰማ ነበር። ሙሴም ተና​ገረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በድ​ምፅ መለ​ሰ​ለት።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሲና ተራራ ላይ ወደ ተራ​ራው ራስ ወረደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ወደ ተራ​ራው ራስ ጠራው፤ ሙሴም ወጣ።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ውረድ፤ ይህ​ንም ለመ​ረ​ዳት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ይ​ቀ​ርቡ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ብዙ እን​ዳ​ይ​ጠፉ ለሕ​ዝቡ አስ​ጠ​ን​ቅ​ቃ​ቸው፤</verse>
				<verse number="22">ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ቀ​ር​ቡት ካህ​ናት ደግሞ እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው ራሳ​ቸ​ውን ይቀ​ድሱ” አለው።</verse>
				<verse number="23">ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “ሕዝቡ ወደ ሲና ተራራ ይወጡ ዘንድ አይ​ች​ሉም፤ አንተ፦ በተ​ራ​ራው ዙሪያ ወሰን አድ​ርግ፤ ቀድ​ሰ​ውም ብለህ አስ​ጠ​ን​ቅ​ቀ​ኸ​ኛ​ልና” አለው።</verse>
				<verse number="24">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሂድ፤ ውረድ፤ አንተ አሮ​ንም ከአ​ንተ ጋር ትወ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ካህ​ና​ቱና ሕዝቡ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይወጡ ዘንድ አይ​ደ​ፋ​ፈሩ” አለው።</verse>
				<verse number="25">ሙሴም ወደ ሕዝቡ ወረደ፤ ይህ​ንም ነገ​ራ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይህን ቃል ሁሉ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ፦</verse>
				<verse number="2">“ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ሁህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እኔ ነኝ፤</verse>
				<verse number="3">“ከእኔ በቀር ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አታ​ም​ልክ።</verse>
				<verse number="4">“በላይ በሰ​ማይ ከአ​ለው፥ በታ​ችም በም​ድር ከአ​ለው፥ ከም​ድ​ርም በታች በውኃ ከአ​ለው ነገር የማ​ና​ቸ​ው​ንም ምስል ለአ​ንተ አም​ላክ አታ​ድ​ርግ።</verse>
				<verse number="5">አት​ስ​ገ​ድ​ላ​ቸው፤ አታ​ም​ል​ካ​ቸ​ውም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ቀና​ተኛ አም​ላክ ነኝና። በሚ​ጠ​ሉኝ እስከ ሦስ​ተ​ኛና አራ​ተኛ ትው​ልድ ድረስ የአ​ባ​ቶ​ችን ኀጢ​አት በል​ጆች ላይ የማ​መጣ፤</verse>
				<verse number="6">ለሚ​ወ​ድ​ዱኝ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ለሚ​ጠ​ብቁ እስከ ሺህ ትው​ልድ ድረስ ምሕ​ረ​ትን የማ​ደ​ርግ አም​ላክ ነኝና።</verse>
				<verse number="7">“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የአ​ም​ላ​ክ​ህን ስም በከ​ንቱ አት​ጥራ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙን በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ራ​ውን ከበ​ደል አያ​ነ​ጻ​ው​ምና።</verse>
				<verse number="8">“የሰ​ን​በ​ትን ቀን ትቀ​ድ​ሳት ዘንድ አስብ።</verse>
				<verse number="9">ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ሥራ፤ ተግ​ባ​ር​ህ​ንም ሁሉ አድ​ርግ፤</verse>
				<verse number="10">ሰባ​ተ​ኛዋ ቀን ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላ​ክህ ሰን​በት ናት፤ አንተ፥ ወንድ ልጅ​ህም፥ ሴት ልጅ​ህም፥ ሎሌ​ህም፥ ገረ​ድ​ህም፥ አህ​ያ​ህም፥ ከብ​ት​ህም፥ በደ​ጆ​ች​ህም ውስጥ ያለ እን​ግዳ በእ​ር​ስዋ ምንም ሥራ አት​ሥሩ፤</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በስ​ድ​ስት ቀን ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን፥ ባሕ​ር​ንም፥ በው​ስ​ጣ​ቸው ያለ​ው​ንም ሁሉ ፈጥሮ በሰ​ባ​ተ​ኛዋ ቀን ዐር​ፎ​አ​ልና፤ ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ን​በ​ትን ቀን ባር​ኮ​ታል፤ ቀድ​ሶ​ታ​ልም።</verse>
				<verse number="12">“አባ​ት​ህ​ንና እና​ት​ህን አክ​ብር፤ መል​ካም እን​ዲ​ሆ​ን​ልህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ በሚ​ሰ​ጥህ ምድ​ርም ዕድ​ሜህ እን​ዲ​ረ​ዝም።</verse>
				<verse number="13">“አት​ግ​ደል።</verse>
				<verse number="14">“አታ​መ​ን​ዝር።</verse>
				<verse number="15">“አት​ስ​ረቅ።</verse>
				<verse number="16">“በባ​ል​ን​ጀ​ራህ ላይ በሐ​ሰት አት​መ​ስ​ክር።</verse>
				<verse number="17">“የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህን ሚስት፥ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህን ቤት አት​መኝ፤ እር​ሻ​ው​ንም፥ ሎሌ​ው​ንም፥ ገረ​ዱ​ንም፥ በሬ​ው​ንም፥ አህ​ያ​ው​ንም፥ ከብ​ቱ​ንም ሁሉ ከባ​ል​ን​ጀ​ራህ ገን​ዘብ ሁሉ ማን​ኛ​ው​ንም አት​መኝ።”</verse>
				<verse number="18">ሕዝ​ቡም ሁሉ ነጐ​ድ​ጓ​ዱ​ንና መብ​ረ​ቁን፥ የቀ​ንደ መለ​ከ​ቱን ድምፅ፥ ተራ​ራ​ው​ንም ሲጤስ አዩ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ፈር​ተው ርቀው ቆሙ።</verse>
				<verse number="19">ሙሴ​ንም፥ “አንተ ከእኛ ጋር ተና​ገር፤ ነገር ግን እን​ዳ​ን​ሞት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር አይ​ና​ገር” አሉት።</verse>
				<verse number="20">ሙሴም ለሕ​ዝቡ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊፈ​ት​ና​ችሁ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም እን​ዳ​ት​ሠሩ እር​ሱን መፍ​ራት በእ​ና​ንተ ያድር ዘንድ መጥ​ቶ​አ​ልና አት​ፍሩ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">ሕዝ​ቡም ርቀው ቆሙ፤ ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለ​በት ወደ ጨለ​ማው ቀረበ።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን አለው፥ “ለያ​ዕ​ቆብ ቤት ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እን​ዲህ በል፦ እኔ ከሰ​ማይ እንደ ተና​ገ​ር​ኋ​ችሁ እና​ንተ አይ​ታ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="23">የብር አማ​ል​ክ​ትን አታ​ም​ልኩ፤ የወ​ርቅ አማ​ል​ክ​ት​ንም አታ​ም​ልኩ። የዕ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ አም​ላ​ክ​ንም አታ​ም​ልኩ፤ እን​ዲህ ያለ አም​ላ​ክን ለእ​ና​ንተ አታ​ድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="24">ከአ​ፈ​ርም መሠ​ዊያ ሥራ​ልኝ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን፥ በጎ​ች​ህ​ንም፥ በሬ​ዎ​ች​ህ​ንም ሠዋ​በት፤ ስሜን ባስ​ጠ​ራ​ሁ​በት ስፍራ ሁሉ ወደ አንተ መጥቼ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="25">የድ​ን​ጋ​ይም መሠ​ዊያ ብታ​ደ​ር​ግ​ልኝ ጠር​በህ አት​ሥ​ራው፤ በመ​ሣ​ሪያ ብት​ነ​ካው ታረ​ክ​ሰ​ዋ​ለ​ህና።</verse>
				<verse number="26">ኀፍ​ረተ ሥጋህ በእ​ርሱ እን​ዳ​ይ​ገ​ለጥ ወደ መሠ​ዊ​ያዬ በደ​ረጃ አት​ውጣ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">“በፊ​ታ​ቸው የም​ታ​ደ​ር​ገው ሥር​ዐት ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">ዕብ​ራዊ ባሪያ የገ​ዛህ እንደ ሆነ ስድ​ስት ዓመት ያገ​ል​ግ​ልህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ዓመት በነጻ አር​ነት ይውጣ።</verse>
				<verse number="3">ብቻ​ውን መጥቶ እንደ ሆነ ብቻ​ውን ይውጣ፤ ከሚ​ስ​ቱም ጋር መጥቶ እንደ ሆነ ሚስቱ ከእ​ርሱ ጋር ትውጣ።</verse>
				<verse number="4">ጌታው ሚስት አጋ​ብ​ቶት እንደ ሆነ ወን​ዶች ወይም ሴቶች ልጆች ብት​ወ​ል​ድ​ለት፥ ሚስ​ቱና ልጆቹ ለጌ​ታው ይገዙ፤ እር​ሱም ብቻ​ውን ነጻ ይውጣ።</verse>
				<verse number="5">ባሪ​ያ​ውም፦ ጌታ​ዬን፥ ሚስ​ቴን፥ ልጆ​ች​ንም እወ​ድ​ዳ​ለሁ፤ አር​ነ​ትም አል​ወ​ጣም ብሎ ቢና​ገር፥</verse>
				<verse number="6">ጌታው ወደ ቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራ​ጆች ይው​ሰ​ደው፤ ወደ ደጁም፥ ወደ መቃ​ኑም አቅ​ርቦ አፍ​ን​ጫ​ውን በወ​ስፌ ይብ​ሳው፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ባሪ​ያው ይሁ​ነው።</verse>
				<verse number="7">“ሴት ልጁን ለባ​ር​ነት አሳ​ልፎ የሰጠ ቢኖር ሴቶች ባሪ​ያ​ዎች አር​ነት እን​ደ​ሚ​ወጡ እር​ስዋ ትውጣ።</verse>
				<verse number="8">ለእ​ርሱ ከታ​ጨች በኋላ ጌታ​ዋን ደስ ባታ​ሰ​ኘው በዎጆ ይስ​ደ​ዳት፤ ነገር ግን ለሌላ ወገን ይሸ​ጣት ዘንድ አይ​ገ​ባ​ውም። እርሱ አር​ክ​ሶ​አ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="9">ለል​ጁም ሊድ​ራት ቢወ​ድድ፥ ለሴት ልጆች የሚ​ገ​ባ​ውን ያድ​ር​ግ​ላት፤</verse>
				<verse number="10">ከእ​ር​ስ​ዋም ሌላ ቢያ​ገባ፥ ቀለ​ብ​ዋን፥ ልብ​ስ​ዋ​ንም፥ ለጋ​ብ​ቻ​ዋም ተገ​ቢ​ውን ይስ​ጣት፤ እን​ዳ​ል​በ​ደ​ላ​ትም ምስ​ክር ያሰ​ማ​ባት።</verse>
				<verse number="11">ይህ​ንም ሦስት ነገር ባያ​ደ​ር​ግ​ላት ያለ ገን​ዘብ ነጻ ትውጣ።</verse>
				<verse number="12">“ሰው ሰውን ቢመታ፥ ቢሞ​ትም፥ የመ​ታው ፈጽሞ ይገ​ደል።</verse>
				<verse number="13">ሳይ​ፈ​ቅድ ቢመ​ታው፥ ባይ​ሸ​ም​ቅ​በ​ትም፥ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድን​ገት በእጁ ቢጥ​ለው፥ ገዳዩ የሚ​ሸ​ሽ​በ​ትን ስፍራ እኔ አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">ሰው ግን ቢሸ​ምቅ ጠላ​ቱ​ንም በተ​ን​ኰል ቢገ​ድ​ለ​ውና ቢማ​ፀን፥ እን​ዲ​ገ​ደል ከመ​ሠ​ዊ​ያዬ አው​ጥ​ተህ ውሰ​ደው።</verse>
				<verse number="15">“አባ​ቱን ወይም እና​ቱን የሚ​ማታ ይገ​ደል።</verse>
				<verse number="16">“አባ​ቱን ወይም እና​ቱን የሚ​ሰ​ድብ በሞት ይቀጣ።</verse>
				<verse number="17">“ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አን​ዱን የሰ​ረቀ ወይም ግፍ የፈ​ጸ​መ​በት፥ ወይም አሳ​ልፎ ቢሰ​ጠው፥ ወይም በእ​ርሱ ዘንድ ቢገኝ፥ እርሱ ይገ​ደል።</verse>
				<verse number="18">“ሁለት ሰዎ​ችም እርስ በር​ሳ​ቸው ቢጣሉ፥ አን​ዱም ሌላ​ውን በድ​ን​ጋይ ወይም በጡጫ ቢመታ፥ ያም ባይ​ሞት ነገር ግን በአ​ል​ጋው ላይ ቢተኛ፥</verse>
				<verse number="19">ተነ​ሥ​ቶም በም​ር​ኩዝ ወደ ሜዳ ቢወጣ፥ የመ​ታው ንጹሕ ነው፤ ነገር ግን ተግ​ባ​ሩን ስላ​ስ​ፈ​ታው ገን​ዘብ ይክ​ፈ​ለው፤ ለባለ መድ​ኀ​ኒ​ትም ይክ​ፈ​ል​ለት።</verse>
				<verse number="20">“ሰውም ወንድ ባሪ​ያ​ውን ወይም ሴት ባሪ​ያ​ውን በበ​ትር ቢመታ፥ በእጁ ቢሞ​ት​በ​ትም፥ ፈጽሞ ይቀጣ፤</verse>
				<verse number="21">የተ​መ​ታው ግን አንድ ወይም ሁለት ቀን ቢቈይ ገን​ዘቡ ነውና አይ​ቀጣ።</verse>
				<verse number="22">“ሁለት ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው ቢጣሉ፥ ያረ​ገ​ዘ​ች​ንም ሴት ቢያ​ቈ​ስሉ ተሥ​ዕ​ሎተ መል​ክእ ያል​ተ​ፈ​ጸ​መ​ለት ፅን​ስም ቢያ​ስ​ወ​ር​ዳት፥ የሴ​ቲቱ ባል የጣ​ለ​በ​ትን ያህል ካሳ ይክ​ፈል፤</verse>
				<verse number="23">ተሥ​ዕ​ሎተ መል​ክእ የተ​ፈ​ጸ​መ​ለት ፅንስ ቢያ​ስ​ወ​ር​ዳት ግን ሕይ​ወት በሕ​ይ​ወት፥</verse>
				<verse number="24">ዐይን በዐ​ይን፥ ጥርስ በጥ​ርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእ​ግር፥</verse>
				<verse number="25">መቃ​ጠል በመ​ቃ​ጠል፥ ቍስል በቍ​ስል፥ ግር​ፋት በግ​ር​ፋት ይክ​ፈል።</verse>
				<verse number="26">“ሰውም የባ​ሪ​ያ​ውን ዐይን ወይም የባ​ሪ​ያ​ዪ​ቱን ዐይን ቢመታ፥ ቢያ​ጠ​ፋ​ውም፥ ስለ ዐይ​ና​ቸው አር​ነት ያው​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="27">የባ​ሪ​ያ​ውን ጥርስ ወይም የባ​ሪ​ያ​ዪ​ቱን ጥርስ ቢሰ​ብር፥ ስለ ጥር​ሳ​ቸው አር​ነት ያው​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="28">“በሬም ወን​ድን ወይም ሴትን ቢወጋ ቢሞ​ቱም፥ በሬው በድ​ን​ጋይ ይወ​ገር፤ ሥጋ​ውም አይ​በላ፤ የበ​ሬው ባለ​ቤት ግን ንጹሕ ነው።</verse>
				<verse number="29">በሬው ግን ከት​ና​ን​ትና ከት​ና​ንት ወዲያ ተዋጊ ቢሆን፥ ሰዎ​ችም ለባ​ለ​ቤቱ ቢመ​ሰ​ክ​ሩ​ለት ባያ​ስ​ወ​ግ​ደ​ውም፥ ወን​ድን ወይም ሴትን ቢገ​ድል፥ በሬው ይወ​ገር፤ ባለ​ቤቱ ደግሞ ይገ​ደል።</verse>
				<verse number="30">ከእ​ርሱ ግን ካሳ ቢፈ​ልጉ፥ የሕ​ይ​ወ​ቱን ካሳ የጫ​ኑ​በ​ትን ያህል ይስጥ።</verse>
				<verse number="31">በሬው ወን​ድን ልጅ ቢወጋ፥ ሴት​ንም ልጅ ቢወጋ ይህ​ንኑ ፍርድ ያድ​ር​ጉ​በት።</verse>
				<verse number="32">በሬው ወንድ ባሪያ ወይም ሴት ባሪያ ቢወጋ፥ የበ​ሬው ባለ​ቤት ሠላሳ የብር ሰቅል ለጌ​ታ​ቸው ይስጥ፤ በሬ​ውም ይወ​ገር።</verse>
				<verse number="33">“ሰውም ጕድ​ጓድ ቢከ​ፍት ወይም ጕድ​ጓድ ቢቈ​ፍር ባይ​ከ​ድ​ነ​ውም፥ በሬም ወይም አህያ፤ ቢወ​ድ​ቅ​በት፥</verse>
				<verse number="34">የጕ​ድ​ጓዱ ባለ​ቤት ዋጋ​ቸ​ውን ለባ​ለ​ቤ​ታ​ቸው ይክ​ፈል፤ የሞ​ተ​ውም ለእ​ርሱ ይሁን።</verse>
				<verse number="35">“የሰው በሬ የሌ​ላ​ውን በሬ ቢወጋ፥ ቢሞ​ትም፥ ደኅ​ና​ውን በሬ ይሽጡ፤ ዋጋ​ው​ንም በት​ክ​ክል ይካ​ፈሉ፤ የሞ​ተ​ው​ንም ደግሞ በት​ክ​ክል ይካ​ፈሉ።</verse>
				<verse number="36">በሬ​ውም ትና​ን​ትና ከት​ና​ንት ወዲያ ተዋጊ መሆኑ ቢታ​ወቅ ለባ​ለ​ቤ​ቱም ቢመ​ሰ​ክ​ሩ​ለት፥ ባለ​ቤ​ቱም ባያ​ስ​ወ​ግ​ደው በሬ​ውን በበ​ሬው ፋንታ ይስጥ፤ የሞ​ተ​ውም ለእ​ርሱ ይሁ​ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">“ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰ​ርቅ፥ ቢያ​ር​ደው ወይም ቢሸ​ጠው፥ በአ​ንድ በሬ ፋንታ አም​ስት በሬ​ዎች፥ በአ​ንድ በግም ፋንታ አራት በጎች ይክ​ፈል።</verse>
				<verse number="2">ሌባ ቤት ሲምስ ቢገኝ፥ እር​ሱም ቢመታ፥ ቢሞ​ትም በመ​ታው ሰው ላይ የደም ዕዳ አይ​ሆ​ን​በ​ትም።</verse>
				<verse number="3">ፀሐይ ግን ከወ​ጣ​ች​በት የደም ዕዳ አለ​በት፤ የገ​ደ​ለው ይገ​ደል፤ ሌባው ቢያዝ የሚ​ከ​ፍ​ለ​ውም ቢያጣ ስለ ሰረ​ቀው ይሸጥ።</verse>
				<verse number="4">የሰ​ረ​ቀው ደኅና ሆኖ በእጁ ቢገኝ፥ በሬ ወይም በግ ቢሆን፥ የሰ​ረ​ቀ​ውን ያህል ሁለት እጥፍ ይክ​ፈል።</verse>
				<verse number="5">“የሰ​ውን አዝ​መራ ከብ​ቱን ያስ​በላ፥ የሌላ ሰው ወይ​ን​ንም ያስ​በላ ሰው ቢኖር ግም​ቱን ይክ​ፈል። የሰ​ውን አዝ​መራ ፈጽሞ ቢያ​ስ​በላ ግን በአ​ጠ​ገቡ ባለ አዝ​መራ ልክ ይክ​ፈል፤ ወይ​ንም ቢሆን በአ​ጠ​ገቡ ባለ ወይን ልክ ይክ​ፈል።</verse>
				<verse number="6">“እሳት ቢነሣ ጫካ​ው​ንም ቢይዝ፥ ዐው​ድ​ማ​ው​ንም፥ ክም​ሩ​ንም ወይም ያል​ታ​ጨ​ደ​ውን እህል ወይም እር​ሻ​ውን ቢያ​ቃ​ጥል እሳ​ቱን ያነ​ደ​ደው ይክ​ፈል።</verse>
				<verse number="7">“ሰው በባ​ል​ን​ጀ​ራው ዘንድ ብር ወይም ሌላ ዕቃ እን​ዲ​ጠ​ብ​ቅ​ለት አደራ ቢያ​ኖር ከቤ​ቱም ቢሰ​ረቅ፥ ሌባው ቢገኝ እጥፍ ይክ​ፈል።</verse>
				<verse number="8">ሌባው ባይ​ገኝ ባለ​ቤቱ ወደ ፈጣሪ ፊት ይቅ​ረብ፤ ባል​ን​ጀ​ራው አደራ በአ​ስ​ቀ​መ​ጠ​በት ገን​ዘ​ብም ላይ እን​ዳ​ል​ተ​ተ​ነ​ኰ​ለና ክፉ እን​ዳ​ላ​ሰበ ይማል።</verse>
				<verse number="9">ሰዎች ስለ በሬ ወይም ስለ አህያ ወይም ስለ በግ ወይም ስለ ልብስ ወይም ስለ​ሌላ ስለ ጠፋ ነገር ቢካ​ሰሱ፥ አን​ዱም፦ ‘ይህ የእኔ ነው’ ቢል፥ ክር​ክ​ራ​ቸው በፈ​ጣሪ ፊት ይቅ​ረብ፤ በፈ​ጣሪ ፊት የተ​ፈ​ረ​ደ​በት እርሱ ለባ​ል​ን​ጀ​ራው እጥፍ ይክ​ፈል።</verse>
				<verse number="10">“ሰው በባ​ል​ን​ጀ​ራው ዘንድ አህያ ወይም በሬ ወይም በግ ወይም ሌላ እን​ስሳ እን​ዲ​ጠ​ብ​ቅ​ለት አደራ ቢያ​ኖር፥ ማንም ሳያይ ቢሞት ወይም ቢጐዳ ወይም ቢማ​ረክ፥</verse>
				<verse number="11">በባ​ል​ን​ጀ​ራው ከብት ላይ እጁን እን​ዳ​ል​ዘ​ረጋ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሐላ በሁ​ለ​ታ​ቸው መካ​ከል ይሁን፤ የከ​ብ​ቱም ባለ​ቤት ይህን ከተ​ቀ​በለ፥ እርሱ ምንም አይ​ክ​ፈል።</verse>
				<verse number="12">ከእ​ር​ሱም ዘንድ ቢሰ​ረቅ ለባ​ለ​ቤቱ ይክ​ፈል።</verse>
				<verse number="13">በም​ድረ በዳም አውሬ ቢበ​ላው ውዳ​ቂ​ውን ያሳይ፤ አይ​ክ​ፈ​ልም።</verse>
				<verse number="14">ሰው ከባ​ል​ን​ጀ​ራው አን​ዳች ቢዋስ ባለ​ቤቱ ከእ​ርሱ ጋር ሳይ​ኖር ቢጎዳ፥ ወይም ቢሞት፥ ወይም ቢነ​ጠቅ ፈጽሞ ይክ​ፈ​ለው።</verse>
				<verse number="15">ባለ​ቤቱ ግን ከእ​ርሱ ጋር ቢኖር አይ​ክ​ፈል፤ ቢከ​ራ​የ​ውም ኪራ​ዩን ይክ​ፈል።</verse>
				<verse number="16">“ሰው ያል​ታ​ጨ​ች​ውን ድን​ግል ቢያ​ስ​ታት፥ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ቢተኛ ሚስት አድ​ርጎ ይው​ሰ​ዳት።</verse>
				<verse number="17">አባ​ቷም እር​ስ​ዋን እን​ዳ​ይ​ሰ​ጠው ፈጽሞ እንቢ ቢል እንደ ደና​ግል ማጫ ያህል ማጫ​ዋን ይስ​ጠው።</verse>
				<verse number="18">“ከመ​ተ​ተኛ ጋር አንድ አት​ሁኑ።</verse>
				<verse number="19">“ከእ​ን​ስሳ የሚ​ደ​ርስ ሁሉ ሞትን ይሙት።</verse>
				<verse number="20">“ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ በቀር ለአ​ማ​ል​ክት የሚ​ሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ።</verse>
				<verse number="21">እና​ንተ በግ​ብፅ ምድር ስደ​ተ​ኞች ነበ​ራ​ች​ሁና ስደ​ተ​ኛ​ውን አት​በ​ድ​ሉት፤ ግፍም አታ​ድ​ር​ጉ​በት።</verse>
				<verse number="22">መበ​ለ​ቲ​ቱ​ንና ድሀ-አደ​ጎ​ቹን አታ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">ብታ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ቸ​ውና ወደ እኔ ቢጮኹ እኔ ጩኸ​ታ​ቸ​ውን ፈጽሞ እሰ​ማ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="24">ቍጣ​ዬም ይጸ​ና​ባ​ች​ኋል፤ በሰ​ይ​ፍም አስ​ገ​ድ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁም መበ​ለ​ቶች፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁም ድሀ-አደ​ጎች ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="25">“ከአ​ንተ ጋር ለተ​ቀ​መ​ጠው ለድ​ሃው ወገ​ንህ ብር ብታ​በ​ድ​ረው፥ አታ​ስ​ጨ​ን​ቀው፤ አራ​ጣም አታ​ስ​ከ​ፍ​ለው።</verse>
				<verse number="26">የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህን ልብስ ለመ​ያዣ ብት​ወ​ስድ ፀሐይ ሳት​ገባ መል​ስ​ለት፤</verse>
				<verse number="27">ልብሱ ነውና፥ ዕር​ቃ​ኑ​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ን​በት ይህ ብቻ ነውና፤ የሚ​ተ​ኛ​በ​ትም ሌላ የለ​ው​ምና፤ ወደ እኔም ቢጮኽ ፈጥኜ እሰ​ማ​ዋ​ለሁ፤ መሓሪ ነኝና።</verse>
				<verse number="28">“ፈራ​ጆ​ችን አት​ስ​ደብ፥ የሕ​ዝ​ብ​ህ​ንም አለቃ ክፉ አት​ና​ገ​ረው።</verse>
				<verse number="29">የአ​ው​ድ​ማ​ህ​ንና የወ​ይ​ን​ህ​ንም መጀ​መ​ሪያ ለማ​ቅ​ረብ አት​ዘ​ግይ፤ የል​ጆ​ች​ህ​ንም በኵር ትሰ​ጠ​ኛ​ለህ።</verse>
				<verse number="30">እን​ዲ​ሁም በበ​ሬ​ዎ​ች​ህና በበ​ጎ​ችህ፥ በአ​ህ​ያ​ህም ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ፤ ሰባት ቀን ከእ​ናቱ ጋር ይቀ​መጥ፤ በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ለእኔ ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="31">ቅዱስ ወገን ትሆ​ኑ​ል​ኛ​ላ​ችሁ፤ ስለ​ዚህ አውሬ የገ​ደ​ለ​ውን ሥጋ ለውሻ ጣሉት እንጂ አት​ብ​ሉት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="23">
				<verse number="1">“ሐሰ​ተኛ ወሬ አት​ቀ​በል፤ የዐ​መፅ ምስ​ክ​ርም ትሆን ዘንድ ከዐ​መ​ፀኛ ጋር አት​ቀ​መጥ።</verse>
				<verse number="2">ለዐ​መፅ ከብዙ ሰው ጋር አንድ አት​ሁን፤ ፍር​ድ​ንም ለማ​ጣ​መም ከብዙ ሰው ጋር አት​ጨ​መር።</verse>
				<verse number="3">በፍ​ርድ ለድ​ሀው አት​ራራ።</verse>
				<verse number="4">“የጠ​ላ​ት​ህን በሬ ወይም አህ​ያ​ውን ጠፍቶ ብታ​ገ​ኘው ፈጽሞ መል​ስ​ለት።</verse>
				<verse number="5">የጠ​ላ​ት​ህን አህያ ከጭ​ነቱ በታች ወድቆ ብታ​ገ​ኘው አት​ለ​ፈው፤ ነገር ግን ከእ​ርሱ ጋር ለማ​ን​ሣት ርዳው።</verse>
				<verse number="6">“በፍ​ርድ የድ​ሀ​ውን ፍርድ አታ​ጣ​ምም።</verse>
				<verse number="7">ከዐ​መፅ ፍርድ ሁሉ ራቅ፤ በደል የሌ​ለ​በ​ት​ንና ጻድ​ቅን አት​ግ​ደል፤ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ው​ንም በመ​ማ​ለጃ አታ​ድን፤</verse>
				<verse number="8">መማ​ለ​ጃን አት​ቀ​በል፤ መማ​ለጃ የዐ​ይ​ና​ማ​ዎ​ችን ዐይን ያሳ​ው​ራ​ልና፥ እው​ነ​ተኛ ቃል​ንም ያጣ​ም​ማ​ልና።</verse>
				<verse number="9">በስ​ደ​ተ​ኛው ግፍ አታ​ድ​ርጉ፤ እና​ንተ በግ​ብፅ ምድር ስደ​ተ​ኞች ስለ ነበ​ራ​ችሁ የስ​ደ​ተኛ ነፍስ እን​ዴት እንደ ሆነች ዐው​ቃ​ች​ኋ​ልና።</verse>
				<verse number="10">“ስድ​ስት ዓመት ምድ​ር​ህን ዝራ፤ ፍሬ​ዋ​ንም አግባ፤</verse>
				<verse number="11">በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ግን ተዋት፤ አሳ​ር​ፋ​ትም፤ የሕ​ዝ​ብ​ህም ድሆች ይበ​ሉ​ታል፤ እነ​ርሱ ያስ​ቀ​ሩ​ት​ንም የሜዳ እን​ስሳ ይብ​ላው። እን​ዲ​ሁም በወ​ይ​ን​ህና በወ​ይ​ራህ አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="12">ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ሁሉ ሥራ፤ በሬ​ህና አህ​ያህ ያርፉ ዘንድ ለባ​ሪ​ያ​ህም ልጅ ለመ​ጻ​ተ​ኛ​ውም ዕረ​ፍት ይሆን ዘንድ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ዕረፍ።</verse>
				<verse number="13">ያል​ኋ​ች​ሁ​ንም ነገር ሁሉ ጠብቁ፤ የሌ​ሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት ስም አት​ጥሩ፤ ከአ​ፋ​ች​ሁም አይ​ሰማ።</verse>
				<verse number="14">“በዓ​መት ሦስት ጊዜ በዓል አድ​ር​ጉ​ልኝ።</verse>
				<verse number="15">የቂ​ጣ​ውን በዓል ጠብቁ፤ በአ​ዲስ ወር ከግ​ብፅ ምድር ወጥ​ታ​ች​ኋ​ልና በዚህ ወር እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኋ​ችሁ ሰባት ቀን ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="16">በፊቴ ባዶ እጅ​ህን አት​ታይ። በእ​ር​ሻም የም​ት​ዘ​ራ​ትን የፍ​ሬ​ህን በኵ​ራት የመ​ከር በዓል፥ ዓመ​ቱም ሲያ​ልቅ ፍሬ​ህን ከእ​ርሻ ባከ​ማ​ቸህ ጊዜ የመ​ክ​ተ​ቻ​ውን በዓል ጠብቅ።</verse>
				<verse number="17">በዓ​መት ሦስት ጊዜ በአ​ንተ ዘንድ ያለው ወንድ ሁሉ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይታይ።</verse>
				<verse number="18">“የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቴን ደም ከቦካ እን​ጀራ ጋር አት​ሠዋ፤ የበ​ዓ​ሌም ስብ እስ​ኪ​ነጋ አይ​ደር።</verse>
				<verse number="19">የም​ድ​ር​ህን ፍሬ በኵ​ራት ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አምጣ። ጠቦ​ትን በእ​ናቱ ወተት አት​ቀ​ቅል።</verse>
				<verse number="20">“በመ​ን​ገድ ይጠ​ብ​ቅህ ዘንድ፥ ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ል​ህም ስፍራ ያገ​ባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መል​አ​ኬን በፊ​ትህ እል​ካ​ለሁ።</verse>
				<verse number="21">ራስ​ህን ጠብቅ፤ ስማው፤ እን​ቢም አት​በ​ለው፤ ስሜ በእ​ርሱ ስለ ሆነ ይቅር አይ​ል​ምና።</verse>
				<verse number="22">አንተ ግን ቃሌን ብት​ሰማ፥ ያል​ሁ​ህ​ንም ሁሉ ብታ​ደ​ርግ፥ ጠላ​ቶ​ች​ህን እጥ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የሚ​ቃ​ወ​ሙ​ህ​ንም እቃ​ወ​ማ​ለሁ።</verse>
				<verse number="23">መል​አኬ በፊ​ትህ ይሄ​ዳ​ልና፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ያገ​ባ​ሃል፤ እኔም አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="24">ለአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸው አት​ስ​ገድ፤ አታ​ም​ል​ካ​ቸ​ውም፤ እንደ ሥራ​ቸ​ውም አት​ሥራ፤ ነገር ግን ፈጽ​መህ አፍ​ር​ሳ​ቸው፤ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሰባ​ብ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ል​ካ​ለህ፤ እኔ እህ​ል​ህ​ንና ወይ​ን​ህን፥ ውኃ​ህ​ንም እባ​ር​ካ​ለሁ፤ በሽ​ታ​ንም ከአ​ንተ አር​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="26">በም​ድ​ር​ህም መካን፥ ወይም የማ​ይ​ወ​ልድ አይ​ኖ​ርም፤ የዘ​መ​ን​ህ​ንም ቍጥር እሞ​ላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="27">በፊ​ትህ መፈ​ራ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የም​ት​ሄ​ድ​በ​ትን ሕዝብ ሁሉ አስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ጠላ​ቶ​ች​ህ​ንም ሁሉ እን​ዲ​ሸ​ሹ​ልህ አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="28">በፊ​ት​ህም ተርብ እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ አሞ​ራ​ዊ​ው​ንም፥ ኤዌ​ዎ​ያ​ዊ​ው​ንም፥ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ከፊ​ትህ ያባ​ር​ራ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="29">ምድር ባድማ እን​ዳ​ት​ሆን፥ የም​ድር አራ​ዊ​ትም እን​ዳ​ይ​በ​ዙ​ብህ፥ በአ​ንድ ዓመት አላ​ባ​ር​ራ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="30">ነገር ግን እስ​ክ​ት​በዛ፥ ምድ​ር​ንም እስ​ክ​ት​ወ​ርስ ድረስ ጥቂት በጥ​ቂት አባ​ር​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="31">ድን​በ​ር​ህ​ንም ከኤ​ር​ትራ ባሕር እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ባሕር፥ ከም​ድረ በዳም እስከ ታላቁ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ አሰ​ፋ​ለሁ፤ በም​ድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን በእ​ጅህ እጥ​ላ​ለ​ሁና፤ ከአ​ን​ተም አስ​ወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="32">ከእ​ነ​ር​ሱና ከአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ቃል ኪዳን አታ​ድ​ርግ።</verse>
				<verse number="33">እኔን እን​ድ​ት​በ​ድል እን​ዳ​ያ​ደ​ር​ጉህ በሀ​ገ​ርህ ላይ አይ​ቀ​መጡ፤ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ብታ​መ​ልክ ወጥ​መድ ይሆ​ኑ​ብ​ሃ​ልና።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="24">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “አንተ፥ አሮ​ንም፥ ናዳ​ብም፥ አብ​ዩ​ድም፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰባ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ውጡ፤ በሩ​ቁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስገዱ፤</verse>
				<verse number="2">ሙሴም ብቻ​ውን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ረብ፤ እነ​ርሱ ግን አይ​ቅ​ረቡ፤ ሕዝ​ቡም ከእ​ነ​ርሱ ጋር አይ​ውጡ።”</verse>
				<verse number="3">ሙሴም ገባ፤ ለሕ​ዝ​ቡም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃሎች ሁሉ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ሁሉ ነገረ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በአ​ንድ ድምፅ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ራ​ቸ​ውን ቃሎች ሁሉ እን​ሰ​ማ​ለን፤ እና​ደ​ር​ጋ​ለ​ንም” ብለው መለሱ።</verse>
				<verse number="4">ሙሴም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃሎች ጻፈ፤ ማለ​ዳም ተነሣ፤ ከተ​ራ​ራ​ውም በታች መሠ​ዊ​ያን ሠራ፤ ዐሥራ ሁለ​ትም ድን​ጋ​ዮ​ችን ለዐ​ሥራ ሁለቱ የእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ አቆመ።</verse>
				<verse number="5">የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ጐል​ማ​ሶች ላከ፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም አቀ​ረቡ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ደኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት በሬ​ዎ​ችን ሠዉ።</verse>
				<verse number="6">ሙሴም የደ​ሙን እኵ​ሌታ ወስዶ በቆሬ ውስጥ አደ​ረ​ገው፤ የደ​ሙ​ንም እኵ​ሌታ በመ​ሠ​ዊ​ያው ረጨው።</verse>
				<verse number="7">የቃል ኪዳ​ኑ​ንም መጽ​ሐፍ ወስዶ ለሕ​ዝቡ አነ​በ​በ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያለ​ውን ሁሉ እን​ሰ​ማ​ለን፤ እና​ደ​ር​ጋ​ለ​ንም” አሉ።</verse>
				<verse number="8">ሙሴም ደሙን ወስዶ በሕ​ዝቡ ላይ ረጨው፤ በዚህ ቃል ሁሉ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር ያደ​ረ​ገው የቃል ኪዳኑ ደም እነሆ” አለ።</verse>
				<verse number="9">ሙሴም፥ አሮ​ንም፥ ናዳ​ብም፥ አብ​ዩ​ድም፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰባ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወጡ፤</verse>
				<verse number="10">የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የቆ​መ​በ​ትን ቦታ አዩ፤ ከእ​ግ​ሩም በታች እንደ ሰማይ መልክ የሚ​ያ​በራ፥ እንደ ብሩህ ሰን​ፔር ድን​ጋይ የሚ​መ​ስል ወለል ነበረ።</verse>
				<verse number="11">የሚ​መ​ስ​ላ​ቸው የሌለ የእ​ስ​ራ​ኤል ምር​ጦ​ችም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቦታ ታዩ፤ በሉም፤ ጠጡም።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ወደ እኔ ወደ ተራ​ራው ውጣ፤ በዚ​ያም ሁን፤ እኔ የጻ​ፍ​ሁ​ትን ሕግና ትእ​ዛዝ፥ የድ​ን​ጋ​ይም ጽላት እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ ሕግ​ንም ትሠ​ራ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="13">ሙሴም ከኢ​ያሱ ጋር ተነሣ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራ​ራም ወጡ።</verse>
				<verse number="14">ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ች​ንም፥ “ወደ እና​ንተ እስ​ክ​ን​መ​ለስ ድረስ በዚህ ቈዩን፤ ግር​ግር አት​በሉ፤ አሮ​ንና ሆርም እነሆ፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ናቸው፤ ነገ​ረ​ተ​ኛም ቢኖር ወደ እነ​ርሱ ይሂድ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">ሙሴም ከኢ​ያሱ ጋር ወደ ተራራ ወጣ፤ ደመ​ና​ውም ተራ​ራ​ውን ሸፈ​ነው።</verse>
				<verse number="16">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር በሲና ተራራ ላይ ወረደ፤ ደመ​ና​ውም ስድ​ስት ቀን ሸፈ​ነው፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከደ​መ​ናው ውስጥ ሙሴን ጠራው።</verse>
				<verse number="17">በተ​ራ​ራ​ውም ራስ ላይ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር መታ​የት እን​ደ​ሚ​ያ​ቃ​ጥል እሳት ነበረ።</verse>
				<verse number="18">ሙሴም ወደ ደመ​ናው ውስጥ ገባ፤ ወደ ተራ​ራ​ውም ወጣ፤ ሙሴም በተ​ራ​ራው ላይ አርባ ቀን፥ አርባ ሌሊ​ትም ቈየ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="25">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በል​ባ​ችሁ ያሰ​ባ​ች​ሁ​ትን ከገ​ን​ዘ​ባ​ችሁ መባ አም​ጡ​ልኝ” በላ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ከእ​ነ​ር​ሱም የም​ት​ቀ​በ​ሉት መባ ይህ ነው፤ ወርቅ፥ ብር፥ ናስም፥</verse>
				<verse number="4">ሰማ​ያ​ዊና ሐም​ራዊ፥ ቀይም ድርብ ግምጃ፥ ጥሩ በፍ​ታም፥</verse>
				<verse number="5">የፍ​የ​ልም ጠጕር፥ ቀይ የተ​ለፋ የአ​ውራ በግ ቍር​በት፥ ሰማ​ያዊ ቀለም የገባ ቍር​በት፥ የማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት፥</verse>
				<verse number="6">የመ​ብ​ራ​ትም ዘይት፥ ለቅ​ብ​ዐት ዘይ​ትና ለጣ​ፋጭ ዕጣን ቅመም፥</verse>
				<verse number="7">መረ​ግ​ድም፥ ለል​ብሰ እን​ግ​ድ​ዓና ለደ​ረት ኪስ የሚ​ደ​ረግ ፈርጥ።</verse>
				<verse number="8">መቅ​ደስ ትሠ​ራ​ል​ኛ​ለህ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም አድ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">በተ​ራ​ራው እን​ዳ​ሳ​የ​ሁህ ሁሉ፥ እንደ ማደ​ሪ​ያው ምሳሌ፥ እንደ ዕቃ​ውም ሁሉ ምሳሌ ለእኔ ትሠ​ራ​ለህ፤ እን​ዲሁ ትሠ​ራ​ለህ።</verse>
				<verse number="10">“ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨ​ትም የም​ስ​ክ​ሩን ታቦት ሥራ፤ ርዝ​መቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመ​ቱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን።</verse>
				<verse number="11">በው​ስ​ጥና በው​ጭም በጥሩ ወርቅ ለብ​ጠው፤ በእ​ር​ሱም ላይ በዙ​ሪ​ያው የወ​ርቅ አክ​ሊል አድ​ር​ግ​ለት።</verse>
				<verse number="12">አራት የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶ​ችም አድ​ር​ግ​ለት፤ እነ​ር​ሱ​ንም በአ​ራቱ እግ​ሮቹ ላይ አኑር፤ በአ​ንድ ወገን ሁለት ቀለ​በ​ቶች፥ በሌላ ወገን ሁለት ቀለ​በ​ቶች ይሁኑ።</verse>
				<verse number="13">መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ንም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ሥራ፤ በወ​ር​ቅም ለብ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">ለታ​ቦቱ መሸ​ከ​ሚያ በታ​ቦቱ ጎን ባሉት አራት ቀለ​በ​ቶች መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹን አግባ።</verse>
				<verse number="15">መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹም በታ​ቦቱ ቀለ​በ​ቶች ውስጥ ተዋ​ድ​ደው ይኑሩ፤ ከቶም አይ​ውጡ።</verse>
				<verse number="16">በታ​ቦ​ቱም ውስጥ እኔ የም​ሰ​ጥ​ህን ምስ​ክር ታስ​ቀ​ም​ጣ​ለህ።</verse>
				<verse number="17">ከጥሩ ወር​ቅም ርዝ​መቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስ​ር​የት መክ​ደኛ ሥራ።</verse>
				<verse number="18">ሁለት ኪሩ​ቤል ከተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ወርቅ ሥራ፤ በስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ላይ በሁ​ለት ወገን ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="19">ከስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ጋር አን​ዱን ኪሩብ በአ​ንድ ወገን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ኪሩብ በሌ​ላው ወገን አድ​ር​ገህ በአ​ንድ ላይ ትሠ​ራ​ዋ​ለህ፤ ሁለ​ቱ​ንም ኪሩ​ቤል እን​ዲሁ በሁ​ለት ወገን ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="20">ኪሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ወደ ላይ ይዘ​ረ​ጋሉ፤ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው ይሸ​ፍ​ናሉ፤ ፊታ​ቸ​ውም እርስ በርሱ ይተ​ያ​ያል፤ የኪ​ሩ​ቤ​ልም ፊቶ​ቻ​ቸው ወደ ስር​የት መክ​ደ​ኛው ይሁን።</verse>
				<verse number="21">የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በታ​ቦቱ ላይ ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ፤ እኔም የም​ሰ​ጥ​ህን ምስ​ክር በታ​ቦቱ ውስጥ ታኖ​ረ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="22">በዚ​ያም እገ​ለ​ጥ​ል​ሃ​ለሁ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የማ​ዝ​ዝ​ህን ሁሉ፥ በም​ስ​ክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁ​ለት ኪሩ​ቤል መካ​ከል፥ በስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ላይ ሆኜ እነ​ጋ​ገ​ር​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="23">“ርዝ​መ​ቱም ሁለት ክንድ፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ፥ ቁመ​ቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ገበታ ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ሥራ።</verse>
				<verse number="24">በጥ​ሩም ወርቅ ትለ​ብ​ጠ​ዋ​ለህ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም የወ​ርቅ አክ​ሊል አድ​ር​ግ​ለት፤</verse>
				<verse number="25">በዙ​ሪ​ያ​ውም አንድ ጋት የሚ​ያ​ህል ክፈፍ አድ​ር​ግ​ለት፤ የወ​ር​ቅም አክ​ሊል በክ​ፈፉ ዙሪያ አድ​ር​ግ​ለት።</verse>
				<verse number="26">አራ​ትም የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች አድ​ር​ግ​ለት፤ ቀለ​በ​ቶ​ቹ​ንም አራት እግ​ሮቹ ባሉ​በት በአ​ራቱ ማዕ​ዘ​ኖች አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="27">ቀለ​በ​ቶ​ቹም ገበ​ታ​ውን ለመ​ሸ​ከም መሎ​ጊ​ያ​ዎቹ እን​ዲ​ሰ​ኩ​ባ​ቸው በክ​ፈፉ አቅ​ራ​ቢያ ይሁኑ።</verse>
				<verse number="28">መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ሥራ፤ በን​ጹሕ ወር​ቅም ለብ​ጣ​ቸው፤ ገበ​ታ​ውም በእ​ነ​ርሱ ይነሣ።</verse>
				<verse number="29">ለማ​ፍ​ሰ​ሻም ይሆኑ ዘንድ ወጭ​ቶ​ች​ዋን፥ ጭል​ፋ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ መቅ​ጃ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ ጽዋ​ዎ​ች​ዋ​ንም አድ​ርግ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ከጥሩ ወርቅ አድ​ር​ጋ​ቸው።</verse>
				<verse number="30">በገ​በ​ታም ላይ ኅብ​ስተ ገጹን ሁል​ጊዜ በፊቴ ታደ​ር​ጋ​ለህ።</verse>
				<verse number="31">“መቅ​ረ​ዝ​ንም ከጥሩ ወርቅ አድ​ርግ፤ የመ​ቅ​ረ​ዙም እግ​ሩና ቅር​ን​ጫ​ፎቹ የተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ሥራ ይሁን፤ ጽዋ​ዎ​ቹም፥ ጕብ​ጕ​ቦ​ቹም፥ አበ​ቦ​ቹም አን​ድ​ነት በእ​ርሱ ይደ​ረ​ጉ​በት።</verse>
				<verse number="32">በስ​ተ​ጐኑ ስድ​ስት ቅር​ን​ጫ​ፎች ይው​ጡ​ለት፤ ሦስት የመ​ቅ​ረዙ ቅር​ን​ጫ​ፎች በአ​ንድ ወገን፥ ሦስ​ትም የመ​ቅ​ረዙ ቅር​ን​ጫ​ፎች በሌላ ወገን ይውጡ።</verse>
				<verse number="33">በአ​ን​ደ​ኛ​ውም ቅር​ን​ጫፍ ጕብ​ጕ​ብና አበባ፥ ሦስ​ትም የለ​ውዝ አበባ የሚ​መ​ስ​ሉ​ትን ጽዋ​ዎች፤ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቅር​ን​ጫፍ ጕብ​ጕ​ብና አበባ፥ ሦስ​ትም የለ​ውዝ አበባ የሚ​መ​ስ​ሉ​ትን ጽዋ​ዎች፤ እን​ዲ​ሁም ከመ​ቅ​ረዙ ለሚ​ወጡ ለስ​ድ​ስት ቅር​ን​ጫ​ፎች አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="34">በመ​ቅ​ረ​ዙም ጕብ​ጕ​ቦ​ቹ​ንና አበ​ቦ​ቹን፥ አራ​ትም የለ​ውዝ አበባ የሚ​መ​ስ​ሉ​ትን ጽዋ​ዎች ከእ​ርሱ አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="35">ከመ​ቅ​ረዙ ለሚ​ወጡ ለስ​ድ​ስቱ ቅር​ን​ጫ​ፎች ከሁ​ለት ቅር​ን​ጫ​ፎች በታች አንድ ሆኖ የተ​ሠራ አንድ ጕብ​ጕብ፥ ከሁ​ለ​ቱም ቅር​ን​ጫ​ፎች በታች አንድ ሆኖ የተ​ሠራ አንድ ጕብ​ጕብ፥ ደግሞ ከሁ​ለት ቅር​ን​ጫ​ፎች በታች አንድ ሆኖ የተ​ሠራ አንድ ጕብ​ጕብ ይሁን።</verse>
				<verse number="36">ጕብ​ጕ​ቦ​ቹና ቅር​ን​ጫ​ፎቹ ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር አንድ ይሁኑ፤ ሁሉም አንድ ሆኖ ከተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ከጥሩ ወርቅ ይደ​ረግ።</verse>
				<verse number="37">ሰባ​ቱ​ንም መብ​ራ​ቶች ሥራ፤ በፊቱ ያበሩ ዘንድ መብ​ራ​ቶ​ቹን ያቀ​ጣ​ጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="38">መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋን፥ የኵ​ስ​ታሪ ማድ​ረ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም ከጥሩ ወርቅ አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="39">መቅ​ረ​ዙም፥ ዕቃ​ውም ሁሉ ከአ​ንድ መክ​ሊት ጥሩ ወርቅ ይሠሩ።</verse>
				<verse number="40">በተ​ራራ ላይ እን​ዳ​ሳ​የ​ሁህ ምሳሌ እን​ድ​ት​ሠራ ተጠ​ን​ቀቅ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="26">
				<verse number="1">“ለድ​ን​ኳ​ኑም ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ ዐሥር መጋ​ረ​ጆ​ችን ሥራ፤ ኪሩ​ቤ​ልም በእ​ነ​ርሱ ላይ ይሁኑ፤ እንደ ሽመና ሥራም በብ​ል​ሃት ትሠ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="2">የእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ መጋ​ረጃ ርዝ​መት ሃያ ስም​ንት ክንድ፥ ወር​ዱም አራት ክንድ ይሁን፤ የመ​ጋ​ረ​ጆ​ችም ሁሉ መጠን ትክ​ክል ይሁን።</verse>
				<verse number="3">አም​ስቱ መጋ​ረ​ጃ​ዎች እርስ በር​ሳ​ቸው የተ​ጋ​ጠሙ ይሁኑ፤ ሌሎ​ችም አም​ስት መጋ​ረ​ጃ​ዎች እን​ዲሁ እርስ በር​ሳ​ቸው የተ​ጋ​ጠሙ ይሁኑ።።</verse>
				<verse number="4">ከሚ​ጋ​ጠ​ሙት መጋ​ረ​ጆች በአ​ን​ደ​ኛው መጋ​ረጃ ዘርፍ ላይ የሰ​ማ​ያ​ዊ​ውን ግምጃ ቀለ​በ​ቶች አድ​ርግ፤ ደግሞ ከተ​ጋ​ጠ​ሙት ከሌ​ሎች በአ​ን​ደ​ኛው መጋ​ረጃ ዘርፍ ላይ በውጭ በኩል እን​ዲሁ አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="5">አምሳ ቀለ​በ​ቶ​ችን በአ​ንድ መጋ​ረጃ አድ​ርግ፤ አም​ሳ​ው​ንም ቀለ​በ​ቶች በሁ​ለ​ተ​ኛው መጋ​ረጃ ዘርፍ አድ​ርግ፤ ቀለ​በ​ቶቹ ሁሉ እርስ በር​ሳ​ቸው ፊት ለፊት ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="6">አምሳ የወ​ርቅ መያ​ዣ​ዎች ሥራ፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችን እርስ በር​ሳ​ቸው በመ​ያ​ዣ​ዎች አጋ​ጥ​ማ​ቸው፤ ድን​ኳ​ኑም አንድ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="7">“ከማ​ደ​ሪ​ያ​ውም በላይ ለድ​ን​ኳን የሚ​ሆኑ መጋ​ረ​ጃ​ዎች ከፍ​የል ጠጕር አድ​ርግ፤ ዐሥራ አንድ መጋ​ረ​ጃ​ዎች ታደ​ር​ጋ​ለህ።</verse>
				<verse number="8">እያ​ን​ዳ​ን​ዱም መጋ​ረጃ ርዝ​መቱ ሠላሳ ክንድ፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም መጋ​ረጃ ወርዱ አራት ክንድ ይሁን፤ የዐ​ሥራ አን​ዱም መጋ​ረ​ጃ​ዎች መጠ​ና​ቸው ትክ​ክል ይሁን።</verse>
				<verse number="9">አም​ስቱ መጋ​ረ​ጃ​ዎች እርስ በር​ሳ​ቸው አንድ ሆነው ይጋ​ጠሙ፤ ስድ​ስ​ቱም መጋ​ረ​ጃ​ዎች እርስ በር​ሳ​ቸው አንድ ሆነው ይጋ​ጠሙ፤ ስድ​ስ​ተ​ኛ​ውም መጋ​ረጃ በድ​ን​ኳኑ ፊት ይደ​ረብ።</verse>
				<verse number="10">በውጭ ከተ​ጋ​ጠ​ሙት መጋ​ረ​ጃ​ዎች በአ​ን​ደ​ኛው መጋ​ረጃ ዘርፍ ላይ አምሳ ቀለ​በ​ቶች አድ​ርግ፤ ደግሞ ከተ​ጋ​ጠ​ሙት ከሌ​ሎቹ በአ​ን​ደ​ኛው መጋ​ረጃ ዘርፍ ላይ እን​ዲሁ አምሳ ቀለ​በ​ቶች አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="11">አም​ሳም የናስ መያ​ዣ​ዎ​ችን ሥራ፤ መያ​ዣ​ዎ​ች​ንም ወደ ቀለ​በ​ቶች አግ​ባ​ቸው፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ች​ንም አጋ​ጥ​ማ​ቸው፤ አን​ድም ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="12">ከድ​ን​ኳኑ መጋ​ረ​ጃ​ዎች የቀረ ትርፍ ግማሽ መጋ​ረጃ በድ​ን​ኳኑ ጀርባ ይጋ​ረድ።</verse>
				<verse number="13">ድን​ኳ​ኑን እን​ዲ​ሸ​ፍን ከር​ዝ​መቱ በአ​ንድ ወገን አንድ ክንድ፤ በአ​ንድ ወገ​ንም አንድ ክንድ ከድ​ን​ኳኑ መጋ​ረ​ጆች የቀ​ረው ትርፍ በድ​ን​ኳኑ ውጭ በወ​ዲ​ህና በወ​ዲያ ይጋ​ረድ።</verse>
				<verse number="14">ለድ​ን​ኳ​ኑም መደ​ረ​ቢያ ከቀይ አውራ በግ ቍር​በት፥ ከዚ​ያም በላይ ሌላ መደ​ረ​ቢያ ከአ​ቆ​ስጣ ቍር​በት አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="15">“ለድ​ን​ኳ​ኑም ሳን​ቆ​ችን ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="16">የእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሳንቃ ርዝ​መቱ ዐሥር ክንድ፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን።</verse>
				<verse number="17">ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሳንቃ አን​ዱን በአ​ንዱ ላይ የሚ​ያ​ያ​ይዙ ሁለት ማጋ​ጠ​ሚ​ያ​ዎች ይሁ​ኑ​ለት፤ ለድ​ን​ኳኑ ሳን​ቆች ሁሉ እን​ዲሁ አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="18">ለድ​ን​ኳ​ኑም በደ​ቡብ በኩል ሃያ ሳን​ቆ​ችን አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="19">ከሃ​ያ​ውም ሳን​ቆች በታች አርባ የብር እግ​ሮ​ችን አድ​ርግ፤ ከእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ሳንቃ በታች ለሁ​ለት ማጋ​ጠ​ሚ​ያ​ዎች ሁለት እግ​ሮች ይሁኑ። ከሌ​ላ​ውም ሳንቃ በታች ለሁ​ለት ማጋ​ጠ​ሚ​ያ​ዎች ሁለት እግ​ሮች ይሁኑ።</verse>
				<verse number="20">ለድ​ን​ኳኑ ለሁ​ለ​ተ​ኛው ወገን በሰ​ሜን በኩል ሃያ ሳን​ቆች፥</verse>
				<verse number="21">ለእ​ነ​ር​ሱም አርባ የብር እግ​ሮች ይሁኑ፤ ከእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሳንቃ በታች ሁለት እግ​ሮች ይሁኑ።</verse>
				<verse number="22">ለድ​ን​ኳ​ኑም በም​ዕ​ራቡ በኩል በስ​ተ​ኋላ ስድ​ስት ሳን​ቆች አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="23">ለድ​ን​ኳ​ኑም ለሁ​ለቱ ማዕ​ዘን በስ​ተ​ኋላ ሁለት ሳን​ቆች አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="24">ከታ​ችም እኩል ይሁኑ፤ ከላይ እስከ አን​ደ​ኛው መጋ​ጠ​ሚያ ድረስ እንደ አን​ደኛ ክፍል እኩል ይሁኑ፤ እን​ዲ​ሁም ለሁ​ለቱ ማዕ​ዘን አድ​ርግ፤ እኩ​ልም ይሁኑ።</verse>
				<verse number="25">ስም​ንት ሳን​ቆ​ችና ዐሥራ ስድ​ስት የብር እግ​ሮ​ቻ​ቸው ይሁኑ፤ ከእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሳንቃ በታች በሁ​ለ​ቱም መጋ​ጠ​ሚ​ያ​ዎች ሁለት ሁለት እግ​ሮች ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="26">“ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችን ሥራ፤ በድ​ን​ኳኑ በአ​ን​ደ​ኛው ገጽ ላሉ ሳን​ቆች አም​ስት መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችን፥</verse>
				<verse number="27">በድ​ን​ኳኑ በሁ​ለ​ተኛ ወገን ላሉት ሳን​ቆች አም​ስት መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችን፥ በድ​ን​ኳ​ኑም በስ​ተ​ኋላ በም​ዕ​ራብ በኩል ላሉት ሳን​ቆች አም​ስት መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችን አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="28">መካ​ከ​ለ​ኛ​ውም መወ​ር​ወ​ሪያ በሳ​ን​ቆቹ መካ​ከል ከዳር እስከ ዳር ይለፍ።</verse>
				<verse number="29">ሳን​ቆ​ቹን በወ​ርቅ ለብ​ጣ​ቸው፤ ቀለ​በ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም የመ​ወ​ር​ወ​ሪያ ቤት እን​ዲ​ሆ​ኑ​ላ​ቸው ከወ​ርቅ ሥራ​ቸው፤ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ንም በወ​ርቅ ለብ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="30">ድን​ኳ​ኑ​ንም በተ​ራ​ራው ላይ በአ​ሳ​የ​ሁህ ምሳሌ ሥራ።</verse>
				<verse number="31">“መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍ​ታም አድ​ርግ፤ በሽ​መና ሥራም ኪሩ​ቤ​ልን ሥራ።</verse>
				<verse number="32">በወ​ርቅ በተ​ለ​በ​ጡት፥ ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨ​ትም በተ​ሠ​ሩት በአ​ራቱ ምሰ​ሶ​ዎች ላይ ስቀ​ለው፤ ኩላ​ቦ​ቻ​ቸ​ውም ከወ​ርቅ፥ አራ​ቱም እግ​ሮ​ቻ​ቸው ከብር የተ​ሠሩ ይሁኑ።</verse>
				<verse number="33">መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም በም​ሰ​ሶ​ዎች ላይ ስቀ​ለው፤ በመ​ጋ​ረ​ጃ​ውም ውስጥ የም​ስ​ክ​ሩን ታቦት አግ​ባው፤ መጋ​ረ​ጃ​ውም በቅ​ድ​ስ​ቱና በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ መካ​ከል መለያ ይሁ​ና​ችሁ።</verse>
				<verse number="34">መጋ​ረ​ጃ​ውም የም​ስ​ክ​ሩን ታቦት በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ውስጥ ይጋ​ርድ።</verse>
				<verse number="35">ገበ​ታ​ው​ንም በመ​ጋ​ረ​ጃው ውጭ፥ መቅ​ረ​ዙ​ንም በገ​በ​ታው ፊት ለፊት በድ​ን​ኳኑ በደ​ቡብ ወገን አድ​ርግ፤ ገበ​ታ​ው​ንም በድ​ን​ኳኑ በሰ​ሜን ወገን አድ​ር​ገው።</verse>
				<verse number="36">ለድ​ን​ኳኑ ደጃ​ፍም ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀይ ግም​ጃም ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍ​ም​ታም በጥ​ልፍ አሠ​ራር የተ​ሠራ መጋ​ረጃ አድ​ር​ግ​ለት።</verse>
				<verse number="37">ለመ​ጋ​ረ​ጃ​ውም አም​ስት ምሰ​ሶ​ዎች ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት አድ​ርግ፤ በወ​ር​ቅም ለብ​ጣ​ቸው፤ ኩላ​ቦ​ቻ​ቸ​ውም ከወ​ርቅ የተ​ሠሩ ይሁኑ፤ አም​ስ​ትም የናስ እግ​ሮች አድ​ር​ግ​ላ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="27">
				<verse number="1">“ርዝ​መቱ አም​ስት ክንድ፥ ወር​ዱም አም​ስት ክንድ መሠ​ዊ​ያን ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት አድ​ርግ፤ አራት ማዕ​ዘ​ንም ይሁን፤ ከፍ​ታ​ውም ሦስት ክንድ ይሁን።</verse>
				<verse number="2">በአ​ራ​ቱም ማዕ​ዘን ቀን​ዶ​ችን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ ቀን​ዶቹ ሥረ-ወጥ ይሁኑ፤ በና​ስም ለብ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ለመ​ሠ​ዊ​ያው ክዳን ሥራ​ለት፤ መሸ​ፈ​ኛ​ውን፥ ጽዋ​ዎ​ቹን፥ የሥጋ ሜን​ጦ​ዎ​ቹን፥ የእ​ሳት መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አድ​ርግ። ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ከናስ አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="4">ለመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም እንደ መረብ ሆኖ የተ​ሠራ የናስ መከታ አድ​ር​ግ​ለት፤ ለመ​ከ​ታ​ውም አራት የናስ ቀለ​በት በአ​ራት ማዕ​ዘኑ አድ​ር​ግ​ለት።</verse>
				<verse number="5">መከ​ታ​ውም እስከ መሠ​ዊ​ያው እኩ​ሌታ ይደ​ርስ ዘንድ ከመ​ሠ​ዊ​ያው እር​ከን በታች አኑ​ረው።</verse>
				<verse number="6">ለመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ችን ሠር​ተህ በናስ ለብ​ጣ​ቸው፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹም በቀ​ለ​በ​ቶች ውስጥ ይግቡ፤</verse>
				<verse number="7">መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ስት​ሸ​ከሙ መሎ​ጊ​ያ​ዎቹ በመ​ሠ​ዊ​ያው በሁ​ለት ወገን ይሁኑ።</verse>
				<verse number="8">ሰሌ​ዳ​ውም ፍል​ፍል ይሁን፤ በተ​ራ​ራው እን​ዳ​ሳ​የ​ሁህ ምሳሌ እን​ዲሁ አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="9">“ለድ​ን​ኳ​ኑም አደ​ባ​ባይ ሥራ፤ ከጥሩ በፍታ የተ​ሠሩ የአ​ደ​ባ​ባዩ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችም በደ​ቡብ በኩል ይሁኑ። የአ​ን​ዱም ወገን ርዝ​መት መቶ ክንድ ይሁን፤</verse>
				<verse number="10">ከናስ የተ​ሠሩ ሃያ ምሰ​ሶ​ዎ​ችና ሃያ እግ​ሮች ይሁ​ኑ​ለት፤ የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹም ኩላ​ቦ​ችና ዘን​ጎች የብር ይሁኑ።</verse>
				<verse number="11">እን​ዲ​ሁም በሰ​ሜን ወገን መቶ ክንድ ርዝ​መት ያላ​ቸው መጋ​ረ​ጃ​ዎች፥ ከናስ የተ​ሠሩ ሃያ ምሰ​ሶ​ዎች፥ ሃያም እግ​ሮች ይሁኑ፤ ለም​ሰ​ሶ​ዎ​ችም በብር የተ​ለ​በጡ ኩላ​ቦ​ችና ዘን​ጎች ይሁኑ።</verse>
				<verse number="12">በም​ዕ​ራ​ብም ወገን ለአ​ደ​ባ​ባዩ ስፋት አምሳ ክንድ ርዝ​መት ያላ​ቸው መጋ​ረ​ጃ​ዎች፥ ዐሥ​ርም ምሰ​ሶ​ዎች፥ ዐሥ​ርም እግ​ሮች ይሁ​ኑ​ለት።</verse>
				<verse number="13">በም​ሥ​ራ​ቅም ወገን የአ​ደ​ባ​ባዩ ስፋት አምሳ ክንድ ይሁን፤ ምሰ​ሶ​ዎ​ችም ዐሥር፥ እግ​ሮ​ቹም ዐሥር ይሁኑ።</verse>
				<verse number="14">በአ​ንድ ወገን የመ​ጋ​ረ​ጃ​ዎቹ ርዝ​መት ዐሥራ አም​ስት ክንድ ይሁን፤ ምሰ​ሶ​ዎ​ቹም ሦስት፥ እግ​ሮ​ቹም ሦስት ይሁኑ።</verse>
				<verse number="15">በሌ​ላ​ውም ወገን የመ​ጋ​ረ​ጃ​ዎቹ ርዝ​መት ዐሥራ አም​ስት ክንድ ይሆ​ናል፤ ምሰ​ሶ​ዎ​ቹም ሦስት፥ እግ​ሮ​ቹም ሦስት ይሁኑ።</verse>
				<verse number="16">ለአ​ደ​ባ​ባዩ ደጅም ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም ከቀ​ይም ግምጃ ከጥሩ በፍ​ታም በጥ​ልፍ አሠ​ራር የተ​ሠራ ሃያ ክንድ መጋ​ረጃ ይሆ​ናል፤ ምሰ​ሶ​ዎ​ቹም አራት፥ እግ​ሮ​ቹም አራት ይሁኑ።</verse>
				<verse number="17">በዙ​ሪ​ያ​ውም ያሉ የአ​ደ​ባ​ባዩ ምሰ​ሶ​ዎች ሁሉ በብር የተ​ለ​በጡ ይሁኑ፤ የብ​ርም ክባ​ሶች፥ የና​ስም እግ​ሮች ይሁ​ኑ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">የአ​ደ​ባ​ባዩ ርዝ​መት በየ​ገጹ መቶ ክንድ፥ ስፋ​ቱም በየ​ገጹ አምሳ ክንድ ይሁን፤ የመ​ጋ​ረ​ጃ​ውም ከፍታ አም​ስት ክንድ ይሁን፤ መጋ​ረ​ጃ​ውም ከጥሩ በፍታ፥ እግ​ሮ​ቹም ከናስ የተ​ሠሩ ይሁኑ።</verse>
				<verse number="19">ለማ​ገ​ል​ገል ሁሉ የድ​ን​ኳን ዕቃ ሁሉ፥ አው​ታ​ሮቹ ካስ​ማ​ዎ​ቹም ሁሉ፤ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩም ካስ​ማ​ዎች ሁሉ የናስ ይሁኑ።</verse>
				<verse number="20">“አን​ተም መብ​ራ​ቱን ሁል ጊዜ ያበ​ሩት ዘንድ ለመ​ብ​ራት ተወ​ቅጦ የተ​ጠ​ለለ ጥሩ የወ​ይራ ዘይት እን​ዲ​ያ​መ​ጡ​ልህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እዘ​ዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ካለው መጋ​ረጃ ውጭ አሮ​ንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያብ​ሩት፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃ​ቸው የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="28">
				<verse number="1">“አን​ተም ወን​ድ​ም​ህን አሮ​ንን ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆ​ቹን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለይ​ተህ በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ወደ አንተ አቅ​ርብ፤ አሮ​ንን የአ​ሮ​ን​ንም ልጆች፥ ናዳ​ብን፥ አብ​ዩ​ድ​ንም፥ አል​ዓ​ዛ​ር​ንም ኢታ​ም​ር​ንም አቅ​ርብ።</verse>
				<verse number="2">የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ልብስ ለክ​ብ​ርና ለመ​ለያ እን​ዲ​ሆን ለወ​ን​ድ​ምህ ለአ​ሮን ሥራ​ለት።</verse>
				<verse number="3">አን​ተም የጥ​በብ መን​ፈስ ለሞ​ላ​ሁ​ባ​ቸው፥ በል​ባ​ቸው ጥበ​በ​ኞች ለሆ​ኑት ሁሉ ተና​ገር። እነ​ር​ሱም ካህን ሆኖ እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለኝ ለአ​ሮን ለቤተ መቅ​ደስ የሚ​ሆን የተ​ለየ ልብስ ይሥሩ፤</verse>
				<verse number="4">የሚ​ሠ​ሩ​አ​ቸ​ውም ልብ​ሶች እነ​ዚህ ናቸው፤ ልብሰ እን​ግ​ድዓ፥ ልብሰ መት​ከፍ፥ ቀሚ​ስም፥ ዥን​ጕ​ር​ጕር እጀ ጠባብ፥ መጠ​ም​ጠ​ሚያ፥ መታ​ጠ​ቂ​ያም፤ እነ​ዚ​ህ​ንም በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ለወ​ን​ድ​ምህ ለአ​ሮን፥ ለል​ጆ​ቹም የተ​ቀ​ደሰ ልብስ ያድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="5">ወርቅ፥ ሰማ​ያ​ዊና ሐም​ራዊ፥ ቀይ ግምጃ፥ ጥሩ በፍ​ታም ይው​ሰዱ።</verse>
				<verse number="6">“ልብሰ መት​ከ​ፉ​ንም ከወ​ርቅ፥ ከሰ​ማ​ያ​ዊና ከሐ​ም​ራዊ፥ ከተ​ፈ​ተለ ከቀይ ግምጃ በግ​ብረ መርፌ የተ​ሠራ፥ የተ​ለየ የሽ​መና ሥራ ያድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="7">ሁለቱ ወገን አንድ እን​ዲ​ሆን በሁ​ለቱ ጫንቃ ላይ የሚ​ጋ​ጠም ጨርቅ ይሁን።</verse>
				<verse number="8">በላ​ዩም የተ​ጠ​ለ​ፈው የል​ብሰ መት​ከፍ ቋድ እንደ እርሱ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር አንድ ይሁን፤ ከወ​ርቅ፥ ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራዊ፥ ከቀይ ግም​ጃም ከተ​ፈ​ተለ፥ ከጥሩ በፍ​ታም የተ​ሠራ ይሁን።</verse>
				<verse number="9">ሁለ​ትም የመ​ረ​ግድ ድን​ጋይ ወስ​ደህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ስም ስማ​ቸ​ውን ቅረ​ጽ​ባ​ቸው፤</verse>
				<verse number="10">እንደ አወ​ላ​ለ​ዳ​ቸው ስድ​ስት ስሞ​ችን በአ​ንዱ ድን​ጋይ፥ የቀ​ሩ​ት​ንም ስድ​ስ​ቱን ስሞች በሌ​ላው ድን​ጋይ ቅረጽ።</verse>
				<verse number="11">በቅ​ርጽ ሠራ​ተኛ ሥራ እንደ ማኅ​ተም ቅርጽ አድ​ር​ገህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ስሞች በሁ​ለት ድን​ጋ​ዮች ቅረጽ፤ በወ​ር​ቅም ፈርጥ አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="12">ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም የመ​ታ​ሰ​ቢያ ድን​ጋ​ዮች ይሆኑ ዘንድ ሁለ​ቱን ዕን​ቍ​ዎች በል​ብሰ መት​ከፉ ጫን​ቃ​ዎች ላይ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ አሮ​ንም በሁ​ለቱ ጫን​ቃ​ዎች ላይ ለመ​ታ​ሰ​ቢያ ስማ​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይሸ​ከ​ማል።</verse>
				<verse number="13">ፈር​ጦ​ች​ንም ከጥሩ ወርቅ ሥራ፤</verse>
				<verse number="14">ሁለት ቋዶ​ች​ንም ከጥሩ ወርቅ እንደ ተጐ​ነ​ጐነ ገመድ አድ​ር​ገህ ሥራ፤ የተ​ጐ​ነ​ጐ​ኑ​ት​ንም ቋዶች በፈ​ር​ጦቹ ላይ አን​ጠ​ል​ጥል።</verse>
				<verse number="15">“ብልህ ሠራ​ተ​ኛም እን​ደ​ሚ​ሠራ የፍ​ር​ዱን ልብሰ እን​ግ​ድዓ ሥራው፤ እንደ ልብሰ መት​ከ​ፍም አሠ​ራር ሥራው፤ ከወ​ር​ቅና ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ፥ ከጥሩ በፍ​ታም ሥራው።</verse>
				<verse number="16">ርዝ​መቱ ስን​ዝር ስፋ​ቱም ስን​ዝር፥ ሆኖ አራት ማዕ​ዘን ድርብ ይሁን።</verse>
				<verse number="17">በአ​ራት ተራ የሆነ የዕ​ንቍ ፈርጥ አድ​ር​ግ​በት፤ የድ​ን​ጋ​ዮ​ቹም ተራ ሰር​ድ​ዮን፥ ጳዝ​ዮን፥ መረ​ግድ ነው፤ ይህም መጀ​መ​ሪ​ያው ተራ ነው፤</verse>
				<verse number="18">ሁለ​ተ​ኛ​ውም ተራ በሉር፥ ሰን​ፔር፥ ኢያ​ሰ​ጲድ፤</verse>
				<verse number="19">ሦስ​ተ​ኛ​ውም ተራ ለግ​ር​ዮን፥ አካ​ጥስ፥ አሜ​ቴ​ስ​ጢ​ኖስ፤</verse>
				<verse number="20">አራ​ተ​ኛ​ውም ተራ ወር​ቃማ ድን​ጋይ፥ ቢረሌ፥ ሶም በየ​ተ​ራ​ቸው በወ​ርቅ የተ​ለ​በ​ጡና የታ​ሠሩ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="21">የዕ​ን​ቍም ድን​ጋ​ዮች እንደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ስሞች ዐሥራ ሁለት ይሆ​ናሉ፤ በየ​ስ​ማ​ቸ​ውም ማኅ​ተም አቀ​ራ​ረጽ ይቀ​ረጹ፤ ስለ ዐሥራ ሁለቱ ነገ​ዶ​ችም ይሁኑ።</verse>
				<verse number="22">ለል​ብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውም የተ​ጐ​ነ​ጐ​ኑ​ትን ቋዶች እንደ ገመድ አድ​ር​ገህ ከጥሩ ወርቅ ሥራ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">ለል​ብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውም ሁለት የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች ሥራ፤ ሁለ​ቱ​ንም ቀለ​በ​ቶች በል​ብሰ እን​ግ​ድ​ዓው በሁ​ለቱ ወገን አድ​ር​ጋ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">የተ​ጐ​ነ​ጐ​ኑ​ት​ንም ሁለ​ቱን የወ​ርቅ ቋዶች በል​ብሰ እን​ግ​ድ​ዓው በሁ​ለት ወገ​ኖች ወዳ​ሉት ወደ ሁለት ቀለ​በ​ቶች ታገ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="25">የሁ​ለ​ቱ​ንም ቋዶች ጫፎች በሁ​ለቱ ፈር​ጦች ውስጥ አግ​ብ​ተህ በል​ብሰ መት​ከፉ ጫን​ቃ​ዎች ላይ በስ​ተ​ፊት በመ​ጋ​ጠ​ሚ​ያ​ቸው ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="26">ሁለት የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶ​ች​ንም ሥራ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ልብሰ መት​ከፉ በው​ስጥ በሚ​ያ​ል​ፍ​በት በከ​ን​ፈሩ በኩል በሁ​ለቱ የል​ብሰ እን​ግ​ድዓ ጫፎች ላይ ታኖ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="27">ደግ​ሞም ሁለት የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች ሥራ፤ በል​ብሰ መት​ከፉ ፊት ከጫ​ን​ቃ​ዎች በታች በብ​ል​ሃት ከተ​ጠ​ለፈ ከል​ብሰ መት​ከፉ ቋድ በላይ በመ​ጋ​ጠ​ሚ​ያው አጠ​ገብ ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="28">ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውም በብ​ል​ሃት ከተ​ጠ​ለፈ ከል​ብሰ መት​ክፉ ቋድ በላይ እን​ዲ​ሆን፥ ከል​ብሰ መት​ከ​ፉም እን​ዳ​ይ​ለይ፥ ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውን ከቀ​ለ​በ​ቶቹ ወደ ልብሰ መት​ከፉ ቀለ​በ​ቶች በሰ​ማ​ያዊ ፈትል ያያ​ይ​ዙ​ታል።</verse>
				<verse number="29">አሮ​ንም ወደ መቅ​ደስ በገባ ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለዘ​ለ​ዓ​ለም መታ​ሰ​ቢያ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ስሞች በፍ​ርዱ ልብሰ እን​ግ​ድዓ ውስጥ በልቡ ላይ ይሸ​ከም።</verse>
				<verse number="30">በፍ​ርዱ ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓም ውስጥ ኡሪ​ም​ንና ቱሚ​ምን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ወደ ቤተ መቅ​ደስ በገባ ጊዜ በአ​ሮን ልብ ላይ ይሆ​ናሉ፤ አሮ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሁል​ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ፍርድ በልቡ ላይ ይሸ​ከ​ማል።</verse>
				<verse number="31">“ቀሚ​ሱ​ንም ሁሉ ሰማ​ያዊ አድ​ር​ገው።</verse>
				<verse number="32">ከላ​ይም በመ​ካ​ከል አን​ገ​ትጌ ይሁ​ን​በት፤ እን​ዳ​ይ​ቀ​ደ​ድም በግ​ብረ መርፌ የተ​ሠራ ጥልፍ በአ​ን​ገ​ት​ጌው ዙሪያ ይሁ​ን​በት።</verse>
				<verse number="33">በታ​ች​ኛ​ውም ዘርፍ ዙሪያ ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራዊ፥ ከቀ​ይም ግምጃ ሮማ​ኖ​ችን አድ​ርግ፤ በእ​ነ​ዚ​ያም መካ​ከል በዙ​ሪ​ያው በተ​መ​ሳ​ሳይ ቅርጽ የወ​ርቅ ሮማ​ኖች ሻኵ​ራ​ዎ​ችን አድ​ርግ፤</verse>
				<verse number="34">የወ​ርቅ ሻኩራ ሮማ​ንም፥ ሌላም የወ​ርቅ ሻኩራ ሮማ​ንም በቀ​ሚሱ ዘርፍ ዙሪ​ያ​ውን ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="35">በማ​ገ​ል​ገል ጊዜም በአ​ሮን ላይ ይሆ​ናል፤ እር​ሱም እን​ዳ​ይ​ሞት ወደ መቅ​ደሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሲገ​ባና ሲወጣ ድምፁ ይሰ​ማል።</verse>
				<verse number="36">“ከጥሩ ወር​ቅም የወ​ርቅ ቅጠል ሥራ፤ በእ​ር​ሱም እንደ ማኅ​ተም ቅርጽ አድ​ር​ገህ፦ ቅድ​ስና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚል ትቀ​ር​ጽ​በ​ታ​ለህ።</verse>
				<verse number="37">በሰ​ማ​ያ​ዊም ፈትል በመ​ጠ​ም​ጠ​ሚ​ያው ላይ በስ​ተ​ፊቱ ታን​ጠ​ለ​ጥ​ለ​ዋ​ለህ ።</verse>
				<verse number="38">በአ​ሮ​ንም ግን​ባር ላይ ይሆ​ናል፤ አሮ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በሚ​ያ​ቀ​ር​ቡ​ትና በሚ​ቀ​ድ​ሱት በቅ​ዱሱ ስጦ​ታ​ቸው ሁሉ ላይ የሠ​ሩ​ትን ኀጢ​አት ይሸ​ከም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ተቀ​ባ​ይ​ነት ያለው እን​ዲ​ሆ​ን​ላ​ቸው ሁል​ጊዜ በግ​ን​ባሩ ላይ ይሁን።</verse>
				<verse number="39">ቀሚ​ሱ​ንም ከጥሩ በፍታ ዝን​ጕ​ር​ጕር አድ​ር​ገህ፥ አክ​ሊ​ልን ከበ​ፍታ ትሠ​ራ​ለህ፤ በጥ​ልፍ አሠ​ራ​ርም መታ​ጠ​ቂያ ትሠ​ራ​ለህ።</verse>
				<verse number="40">ለአ​ሮ​ንም ልጆች የበ​ፍታ ቀሚ​ሶ​ችን፥ መታ​ጠ​ቂ​ያ​ዎ​ች​ንም፥ ቆቦ​ች​ንም ለክ​ብ​ርና ለመ​ለያ ታደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="41">ይህ​ንም ሁሉ ወን​ድ​ም​ህን አሮ​ንን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆ​ቹን ታለ​ብ​ሳ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በክ​ህ​ነት እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉኝ ትቀ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ እጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ታነ​ጻ​ለህ፤ ትቀ​ድ​ሳ​ቸ​ው​ማ​ለህ።</verse>
				<verse number="42">ኀፍ​ረተ ሥጋ​ቸ​ው​ንም ይከ​ድ​ኑ​በት ዘንድ የተ​ልባ እግር ሱሪ ታደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ከወ​ገ​ባ​ቸ​ውም እስከ ጭና​ቸው ይደ​ር​ሳል፤</verse>
				<verse number="43">እን​ዲ​ሁም ኀጢ​አት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው፥ እን​ዳ​ይ​ሞ​ቱም፥ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ሲገቡ፥ በመ​ቅ​ደ​ሱም ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ወደ መሠ​ዊ​ያው ሲቀ​ርቡ በአ​ሮ​ንና በል​ጆቹ ላይ ይሆ​ናል፤ ለእ​ርሱ፥ ከእ​ር​ሱም በኋላ ለዘሩ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="29">
				<verse number="1">“እኔ​ንም በክ​ህ​ነት እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉኝ ትቀ​ድ​ሳ​ቸው ዘንድ የም​ታ​ደ​ር​ግ​ላ​ቸው ነገር ይህ ነው፤ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን አንድ ወይ​ፈ​ንና ሁለት አውራ በጎች ትወ​ስ​ዳ​ለህ።</verse>
				<verse number="2">ቂጣ እን​ጀራ፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ለ​ወሰ የቂጣ እን​ጎቻ፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ቀባ ስስ ቂጣ ከመ​ል​ካም ስንዴ ታደ​ር​ጋ​ለህ።</verse>
				<verse number="3">በአ​ንድ መሶ​ብም ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ከወ​ይ​ፈ​ኑና ከሁ​ለቱ አውራ በጎች ጋር በመ​ሶብ ታቀ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="4">አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ታቀ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በው​ኃም ታጥ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="5">ልብ​ሶ​ችን ወስ​ደህ ለወ​ን​ድ​ምህ ለአ​ሮን የነጭ ሐር እጀ ጠባብ ቀሚስ፥ ልብሰ መት​ከ​ፍና ልብሰ እን​ግ​ድዓ ታለ​ብ​ሰ​ዋ​ለህ፤ ለእ​ር​ሱም ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውን ከል​ብሰ መት​ከፉ ጋር አያ​ይ​ዝ​ለት።</verse>
				<verse number="6">አክ​ሊ​ል​ንም በራሱ ላይ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ የወ​ር​ቁ​ንም ቀጸላ በአ​ክ​ሊሉ ላይ ታኖ​ራ​ለህ።</verse>
				<verse number="7">የቅ​ብ​ዐ​ት​ንም ዘይት ወስ​ደህ በራሱ ላይ ታፈ​ስ​ሰ​ዋ​ለህ፤ ትቀ​ባ​ው​ማ​ለህ።</verse>
				<verse number="8">ልጆ​ቹ​ንም ታቀ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ቀሚ​ሶ​ች​ንም ታለ​ብ​ሳ​ቸ​ዋ​ለህ፤</verse>
				<verse number="9">በመ​ታ​ጠ​ቂ​ያም ታስ​ታ​ጥ​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ቆብ​ንም ታደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐ​ትም ክህ​ነት ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ እን​ዲ​ሁም የአ​ሮ​ን​ንና የል​ጆ​ቹን እጆች ትቀ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="10">“ወይ​ፈ​ኑ​ንም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን በር ታቀ​ር​በ​ዋ​ለህ፤ አሮ​ንና ልጆ​ቹም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን በር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጆ​ቻ​ቸ​ውን በወ​ይ​ፈኑ ራስ ላይ ይጭ​ናሉ።</verse>
				<verse number="11">ወይ​ፈ​ኑ​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን በር አጠ​ገብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ታር​ደ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="12">ከወ​ይ​ፈ​ኑም ደም ወስ​ደህ በመ​ሠ​ዊ​ያው ቀን​ዶች ላይ በጣ​ትህ ትረ​ጨ​ዋ​ለህ፤ የተ​ረ​ፈ​ው​ንም ደም ሁሉ ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች ታፈ​ስ​ሰ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="13">የሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ ሁሉ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ፥ ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በላ​ያ​ቸ​ውም ያለ​ውን ስብ ወስ​ደህ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ታስ​ቀ​ም​ጣ​ለህ።</verse>
				<verse number="14">የወ​ይ​ፈ​ኑን ሥጋ ግን፥ ቍር​በ​ቱ​ንም፥ ፈር​ሱ​ንም ከሰ​ፈር ውጭ በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ለ​ዋ​ለህ፤ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና።</verse>
				<verse number="15">“አን​ደ​ኛ​ው​ንም አውራ በግ ትወ​ስ​ደ​ዋ​ለህ፤ አሮ​ንና ልጆ​ቹም በአ​ው​ራው በግ ራስ ላይ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ይጭ​ናሉ።</verse>
				<verse number="16">አው​ራ​ው​ንም በግ ታር​ደ​ዋ​ለህ፤ ደሙ​ንም ወስ​ደህ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ትረ​ጨ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="17">አው​ራ​ው​ንም በግ በየ​ብ​ልቱ ትቈ​ር​ጠ​ዋ​ለህ፤ የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹ​ንም በውኃ ታጥ​ባ​ለህ፤ ከብ​ል​ቱና ከራ​ሱም ጋር ታኖ​ረ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="18">አው​ራ​ንም በግ በሞ​ላው በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ስለ ጣፋጭ ሽታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ረበ የእ​ሳት ቍር​ባን ነው።</verse>
				<verse number="19">“ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም አውራ በግ ትወ​ስ​ደ​ዋ​ለህ፤ አሮ​ንና ልጆ​ቹም እጆ​ቻ​ቸ​ውን በአ​ው​ራው በግ ራስ ላይ ይጭ​ናሉ።</verse>
				<verse number="20">አው​ራ​ው​ንም በግ ታር​ደ​ዋ​ለህ፤ ደሙ​ንም ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ የአ​ሮ​ን​ንም የቀኝ ጆሮ ጫፍ፥ የቀኝ እጁ​ንና የቀኝ እግ​ሩን አውራ ጣት ጫፍ፥ የል​ጆ​ቹ​ንም የቀኝ ጆሮ​አ​ቸ​ውን ጫፍ፥ የቀኝ እጃ​ቸ​ው​ንና የቀኝ እግ​ራ​ቸ​ውን አውራ ጣት ታስ​ነ​ካ​ለህ፤ ደሙ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ትረ​ጨ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="21">በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ ካለው ደም ከቅ​ብ​ዐት ዘይ​ትም ወስ​ደህ በአ​ሮ​ንና በል​ብሱ ላይ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ባሉት በል​ጆ​ቹና በል​ብ​ሶ​ቻ​ቸው ላይ ትረ​ጨ​ዋ​ለህ፤ እር​ሱም ልብ​ሶ​ቹም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆቹ፥ ልብ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ይቀ​ደ​ሳሉ።</verse>
				<verse number="22">የበ​ጉ​ንም ስብ፥ የሆድ ዕቃ​ውን የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ፥ ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በላ​ያ​ቸ​ውም ላይ ያለ​ውን ስብ፥ የቀ​ኙ​ንም ወርች ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ የሚ​ቀ​ደ​ሱ​በት ነውና።</verse>
				<verse number="23">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመ​ሶብ ካለው አንድ የዘ​ይት እን​ጀ​ራና አንድ የቂጣ እን​ጐቻ ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤</verse>
				<verse number="24">ሁሉ​ንም በአ​ሮን እጆ​ችና በል​ጆቹ እጆች ታኖ​ረ​ዋ​ለህ፤ ለሚ​ለይ ቍር​ባን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትለ​የ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="25">ከእ​ጃ​ቸ​ውም ትቀ​በ​ለ​ዋ​ለህ፤ በመ​ሥ​ዊ​ያ​ውም ላይ ከሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ታቃ​ጥ​ለ​ዋ​ለህ፤ እርሱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት ነው።</verse>
				<verse number="26">“ለአ​ሮ​ንም ክህ​ነት የታ​ረ​ደ​ውን የአ​ው​ራ​ውን በግ ፍር​ምባ ወስ​ደህ ለሚ​ለይ ቍር​ባን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትለ​የ​ዋ​ለህ፤ እር​ሱም የአ​ንተ ወግ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="27">ከሚ​ካ​ኑ​በ​ትም አውራ በግ የተ​ወ​ሰደ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ወግ የሚ​ሆን ለመ​ሥ​ዋ​ዕት የተ​ለ​የ​ውን ፍር​ም​ባና የተ​ነ​ሣ​ውን ወርች ትቀ​ድ​ሳ​ለህ።</verse>
				<verse number="28">ይህም የተ​ለየ ቍር​ባን ነውና ከእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ል​ጆች ዘንድ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የአ​ሮ​ንና የል​ጆቹ ሕግ ይሁን፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸው የተ​ለየ ቍር​ባን ይሆ​ናል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለየ ቍር​ባን ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="29">“የአ​ሮ​ንም የቅ​ድ​ስ​ናው ልብስ ይቀ​ቡ​በ​ትና እጆ​ቻ​ቸው ይቀ​ደ​ሱ​በት ዘንድ ከእ​ርሱ በኋላ ለል​ጆቹ ይሁን።</verse>
				<verse number="30">ከል​ጆ​ቹም በእ​ርሱ ፋንታ ካህን የሚ​ሆ​ነው በመ​ቅ​ደስ ለማ​ገ​ል​ገል ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ሲገባ ሰባት ቀን ይል​በ​ሰው።</verse>
				<verse number="31">“የቅ​ድ​ስ​ና​ው​ንም በግ ወስ​ደህ ሥጋ​ውን በተ​ቀ​ደሰ ስፍራ ትቀ​ቅ​ለ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="32">አሮ​ንና ልጆ​ቹም የአ​ው​ራ​ውን በግ ሥጋ፥ በመ​ሶ​ብም ያለ​ውን እን​ጀራ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን በር ይበ​ሉ​ታል።</verse>
				<verse number="33">ለመ​ክ​በ​ራ​ቸው እጆ​ቻ​ቸ​ውን ይቀ​ድሱ ዘንድ በተ​ቀ​ደ​ሱ​በት በዚያ ቦታ ይብ​ሉት፤ የባ​ዕድ ልጅ ግን አይ​ብ​ላው፤ የተ​ቀ​ደሰ ነውና።</verse>
				<verse number="34">ከቅ​ድ​ስ​ናው መሥ​ዋ​ዕት ሥጋ ወይም እን​ጀራ እስከ ነገ ቢተ​ርፍ፥ የቀ​ረ​ውን በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ለ​ዋ​ለህ፤ የተ​ቀ​ደሰ ነውና አይ​በ​ላም።</verse>
				<verse number="35">“እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁ​ህም ሁሉ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ እን​ዲህ አድ​ርግ፤ ሰባት ቀን እጆ​ቻ​ቸ​ውን ትቀ​ድ​ሳ​ለህ።</verse>
				<verse number="36">ዕለት ዕለ​ትም ስለ ማስ​ተ​ስ​ረይ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ኑን ታቀ​ር​ባ​ለህ፤ ማስ​ተ​ስ​ረ​ያም ባደ​ረ​ግህ ጊዜ መሠ​ዊ​ያ​ውን ታነ​ጻ​ዋ​ለህ፤ ቅዱ​ስም ይሆን ዘንድ ትቀ​ባ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="37">ሰባት ቀን መሠ​ዊ​ያ​ውን ታነ​ጻ​ዋ​ለህ፤ ትቀ​ድ​ሰ​ው​ማ​ለህ፤ መሠ​ዊ​ያ​ውም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ይሆ​ናል፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም የሚ​ነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="38">“በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ የም​ታ​ቀ​ር​በው ይህ ነው፤ በቀን በቀን ዘወ​ትር በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ሁለት ንጹ​ሓን የዓ​መት ጠቦ​ቶች ታቀ​ር​ባ​ለህ።</verse>
				<verse number="39">አን​ዱን ጠቦት በነ​ግህ፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ጠቦት በሠ​ርክ መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገህ ታቀ​ር​በ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="40">ከአ​ንዱ ጠቦ​ትም ጋር የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ በሆነ ተወ​ቅጦ በተ​ጠ​ለለ ዘይት የተ​ለ​ወሰ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ እጅ መል​ካም ዱቄት፥ ደግሞ ለመ​ጠጥ ቍር​ባን የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ የወ​ይን ጠጅ ታቀ​ር​ባ​ለህ።</verse>
				<verse number="41">ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ጠቦት በሠ​ርክ ታቀ​ር​በ​ዋ​ለህ፤ እንደ ነግ​ሁም የእ​ህ​ልና የመ​ጠጥ ቍር​ባን ታደ​ር​ግ​በ​ታ​ለህ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የእ​ሳት ቍር​ባን ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="42">በዚያ እና​ገ​ርህ ዘንድ ለአ​ንተ በም​ገ​ለ​ጥ​በት በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ወ​ትር መሥ​ዋ​ዕት ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="43">በዚ​ያም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አዝ​ዛ​ለሁ፤ በክ​ብ​ሬም እቀ​ደ​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="44">የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም እቀ​ድ​ሳ​ለሁ፤ በክ​ህ​ነ​ትም ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን እቀ​ድ​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="45">በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መካ​ከል እኖ​ራ​ለሁ፤ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="46">በእ​ነ​ርሱ እጠራ ዘንድ፥ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ቸው ዘንድ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኋ​ቸው አም​ላ​ካ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="30">
				<verse number="1">“የዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያ​ውን ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ሥራ።</verse>
				<verse number="2">ርዝ​መቱ አንድ ክንድ፥ ስፋ​ቱም አንድ ክንድ፥ አራት ማዕ​ዘን ይሁን፤ ቁመ​ቱም ሁለት ክንድ ይሆ​ናል፤ ቀን​ዶ​ቹም ከእ​ርሱ ይሠሩ።</verse>
				<verse number="3">ወለ​ሉ​ንና የግ​ድ​ግ​ዳ​ው​ንም ዙሪያ፥ ቀን​ዶ​ቹ​ንም በጥሩ ወርቅ ትለ​ብ​ጠ​ዋ​ለህ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም የጥሩ ወርቅ ክፈፍ ታደ​ር​ግ​ለ​ታ​ለህ።</verse>
				<verse number="4">ከክ​ፈ​ፉም በታች ሁለት የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች አድ​ር​ግ​ለት። በዚ​ህና በዚያ በሁ​ለቱ ጐን ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ፤ እር​ሱን ያነ​ሡ​ባ​ቸው ዘንድ የመ​ሎ​ጊ​ያ​ዎቹ መግ​ቢያ ይሁኑ።</verse>
				<verse number="5">መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት አድ​ርግ፤ በወ​ር​ቅም ለብ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">ለአ​ንተ በም​ገ​ለ​ጥ​በት በም​ስ​ክሩ ታቦት ላይ ባለው መጋ​ረጃ ፊት ታኖ​ረ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="7">አሮ​ንም በጎ መዓዛ ያለው የደ​ቀቀ ዕጣን በው​ስጡ በየ​ማ​ለ​ዳው ይጠ​ን​በት፤ መብ​ራ​ቶ​ቹን ሲያ​ዘ​ጋጅ ይጠ​ነው።</verse>
				<verse number="8">ይህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ወ​ትር ዕጣን ይሆን ዘንድ አሮን በማታ ጊዜ መብ​ራ​ቶ​ቹን ሲያ​በራ ያጥ​ነ​ዋል።</verse>
				<verse number="9">ሌላም ዕጣን፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን አታ​ቀ​ር​ብ​በ​ትም፤ የመ​ጠ​ጥም ቍር​ባን አታ​ፈ​ስ​ስ​በ​ትም።</verse>
				<verse number="10">አሮ​ንም በዓ​መት አንድ ጊዜ በቀ​ን​ዶቹ ላይ ማስ​ተ​ስ​ረያ ያደ​ር​ጋል፤ በዓ​መት አንድ ጊዜ ኀጢ​አ​ትን ከሚ​ያ​ነ​ጻው ደም ይወ​ስ​ዳል፤ የልጅ ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም እን​ዲ​ያ​ነጻ ያደ​ር​ጋል፤ ይህም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።”</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="12">“አንተ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ቍጥር የወ​ሰ​ድህ እንደ ሆነ በቈ​ጠ​ር​ሃ​ቸው ጊዜ መቅ​ሠ​ፍት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው፥ በቈ​ጠ​ር​ሃ​ቸው ጊዜ ከእ​ነ​ርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቍጥ​ራ​ቸው መጠን የነ​ፍ​ሱን ቤዛ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይስጥ።</verse>
				<verse number="13">ይቈ​ጠሩ ዘንድ የሚ​ያ​ል​ፉት ሁሉ የሚ​ሰ​ጡት ይህ ነው፤ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን የሰ​ቅል ግማሽ ይሰ​ጣል። ሰቅ​ሉም ሃያ አቦሊ ነው፤ የሰ​ቅ​ሉም ግማሽ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን ነው።</verse>
				<verse number="14">ይቈ​ጠር ዘንድ የሚ​ያ​ል​ፈው ሁሉ፥ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም ከፍ ያለ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስጦታ ይሰ​ጣል።</verse>
				<verse number="15">ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ቤዛ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስጦታ ስት​ሰጡ ባለ ጠጋው ከሰ​ቅል ግማሽ አይ​ጨ​ምር፤ ድሃ​ውም አያ​ጕ​ድል።</verse>
				<verse number="16">የማ​ስ​ተ​ስ​ረ​ያ​ው​ንም ገን​ዘብ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወስ​ደህ ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ማገ​ል​ገያ ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ቤዛ እን​ዲ​ሆን ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መታ​ሰ​ቢያ ይሁን።”</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="18">“የመ​ታ​ጠ​ቢያ ሰን ከናስ፥ መቀ​መ​ጫ​ው​ንም ከናስ ሥራ፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳ​ንና በመ​ሠ​ዊ​ያው መካ​ከል ታኖ​ረ​ዋ​ለህ፤ ውኃም ትጨ​ም​ር​በ​ታ​ለህ።</verse>
				<verse number="19">አሮ​ንና ልጆ​ቹም እጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ይታ​ጠ​ቡ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="20">ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን በገቡ ጊዜ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ሳት መሥ​ዋ​ዕት ያቃ​ጥሉ ዘንድ ወደ መሠ​ዊ​ያው ሊያ​ገ​ለ​ግሉ በቀ​ረቡ ጊዜ እን​ዳ​ይ​ሞቱ ይታ​ጠ​ቡ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="21">ወደ ምስ​ክ​ሩም ድን​ኳን በገቡ ጊዜ እን​ዳ​ይ​ሞቱ እጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ይታ​ጠቡ፤ ይህም ለእ​ነ​ርሱ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ለል​ጆ​ቻ​ቸው የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል።”</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="23">“አን​ተም ክቡ​ሩን ሽቱ ውሰድ፤ የተ​መ​ረጠ የከ​ርቤ አበባ አም​ስት መቶ ሰቅል፥ የዚ​ህም ግማሽ ጣፋጭ ቀረፋ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፤ ያማረ የጠጅ ሣርም እን​ዲሁ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፤</verse>
				<verse number="24">ብር​ጉ​ድም አም​ስት መቶ ሰቅል እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን፥ የወ​ይራ ዘይ​ትም አንድ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ትወ​ስ​ዳ​ለህ።</verse>
				<verse number="25">በቀ​ማ​ሚም ብል​ሃት እንደ ተሠራ ቅመም፥ የተ​ቀ​ደሰ የቅ​ብ​ዐት ዘይት ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ፤ የተ​ቀ​ደሰ የቅ​ብ​ዐት ዘይት ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="26">የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን፥ የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ታቦት፥</verse>
				<verse number="27">ገበ​ታ​ው​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ መቅ​ረ​ዙ​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም፥ የዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም፥</verse>
				<verse number="28">ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊ​ያና ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንና መቀ​መ​ጫ​ው​ንም ትቀ​ባ​በ​ታ​ለህ።</verse>
				<verse number="29">ሁሉ​ንም ትቀ​ድ​ሳ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ቅዱሰ ቅዱ​ሳ​ንም ይሆ​ናሉ፤ የሚ​ነ​ካ​ቸ​ውም ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="30">በክ​ህ​ነ​ትም ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን ቅባ​ቸው፤ ቀድ​ሳ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="31">አን​ተም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ተና​ገር፤ ይህ ለልጅ ልጃ​ችሁ የተ​ቀ​ደሰ የቅ​ብ​ዐት ዘይት ይሁን።</verse>
				<verse number="32">በሌላ ሰው ሥጋ ላይ አይ​ፍ​ሰስ፤ እንደ እር​ሱም የተ​ሠራ ሌላ ቅብ​ዐት አታ​ድ​ርጉ፤ ቅዱስ ነው፤ ለእ​ና​ን​ተም ቅዱስ ይሁን።</verse>
				<verse number="33">እንደ እርሱ ያለ​ውን የሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው፥ በሌ​ላም ሰው ላይ የሚ​ያ​ፈ​ስ​ሰው ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ።”</verse>
				<verse number="34">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ጣፋጭ ሽቱ ውሰድ፤ የሚ​ን​ጠ​ባ​ጠብ ሙጫ፥ በዛ​ጎል ውስጥ የሚ​ገኝ ሽቱ፥ የሚ​ሸ​ት​ትም ሙጫ፥ ጥሩም ዕጣን ውሰድ፤ የሁ​ሉም መጠን ትክ​ክል ይሁን።</verse>
				<verse number="35">በቀ​ማሚ ብል​ሃት እንደ ተሠራ፥ የተ​ቀ​መመ ንጹ​ሕና ቅዱስ ዕጣን አድ​ር​ገው።</verse>
				<verse number="36">ከእ​ር​ሱም ጥቂት ትወ​ቅ​ጣ​ለህ፤ ታል​መ​ው​ማ​ለህ፤ ከዚ​ያም ለአ​ንተ በም​ገ​ለ​ጥ​በት በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በም​ስ​ክሩ ፊት ታኖ​ረ​ዋ​ለህ። እር​ሱም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ይሁ​ን​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="37">በዚ​ህም አሠ​ራር የዚ​ህን ዕጣን ዐይ​ነት ለእ​ና​ንተ አታ​ድ​ርጉ፤ በእ​ና​ን​ተም ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ይሁን።</verse>
				<verse number="38">ሊያ​ሸ​ት​ተ​ውም እንደ እርሱ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="31">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“እይ! ከይ​ሁዳ ነገድ የሚ​ሆን የሆር የልጅ ልጅ የኡሪ ልጅ ባስ​ል​ኤ​ልን በስሙ ጠር​ቼ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">በሥራ ሁሉ ያስ​ተ​ውል ዘንድ በጥ​በ​ብም፥ በማ​ስ​ተ​ዋ​ልም፥ በዕ​ው​ቀ​ትም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ፈስ ሞላ​ሁ​በት፤</verse>
				<verse number="4">የአ​ና​ጺ​ዎች አለቃ ይሆን ዘንድ ወር​ቅ​ንና ብርን፥ ናስ​ንም፥ ብጫና ሰማ​ያዊ፥ እጥፍ ሆኖ የተ​ፈ​ተለ ነጭና ቀይ ሐርን ይሠራ ዘንድ፤</verse>
				<verse number="5">በሥ​ራ​ውም ሁሉ የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን የድ​ን​ጋይ ማለ​ዘ​ብን፥ ከዕ​ን​ጨ​ትም የሚ​ጠ​ረ​በ​ውን ይሠራ ዘንድ።</verse>
				<verse number="6">እኔም እነሆ፥ ከዳን ነገድ የሚ​ሆን የአ​ሂ​ሳ​ሚ​ክን ልጅ ኤል​ያ​ብን ሰጠሁ፤ ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ሁሉ ያደ​ርጉ ዘንድ በል​ባ​ቸው ጥበ​በ​ኞች ለሆ​ኑት ሁሉ ዕው​ቅ​ትን ሰጠሁ።</verse>
				<verse number="7">የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን፥ የቃል ኪዳ​ኑ​ንም ታቦት፥ በእ​ር​ሱም ላይ ያለ​ውን የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውን፥ የድ​ን​ኳ​ኑ​ንም ዕቃ ሁሉ፤</verse>
				<verse number="8">የዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያ​ውን፥ ገበ​ታ​ው​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም፥ ከዕ​ቃው ሁሉ የነ​ጻ​ውን መቅ​ረዝ፥</verse>
				<verse number="9">ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊያ፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንና መቀ​መ​ጫ​ው​ንም፥</verse>
				<verse number="10">በክ​ህ​ነት እኔን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ትን የካ​ህ​ኑን የአ​ሮ​ንን ልብሰ ተክ​ህ​ኖና የል​ጆ​ቹን ልብስ፥</verse>
				<verse number="11">የሚ​ቀ​ቡ​ትን የቅ​ብ​ዐ​ቱ​ንም ዘይት፥ ለመ​ቅ​ደሱ የሚ​ያ​ጥ​ኑ​ትን ዕጣን እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁህ ሁሉ ያድ​ርጉ።”</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="13">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ እኔ የም​ቀ​ድ​ሳ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእ​ኔና በእ​ና​ንተ ዘንድ ለልጅ ልጃ​ችሁ ምል​ክት ነውና ሰን​በ​ቴን ፈጽሞ ጠብቁ።</verse>
				<verse number="14">ለእ​ና​ንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ሰች ናትና ሰን​በ​ቴን ጠብቁ፤ የሚ​ያ​ረ​ክ​ሳ​ትም ሰው ሁሉ ፈጽሞ ይገ​ደል፤ ሥራ​ንም በእ​ር​ስዋ የሠራ ሰው ሁሉ ያች ነፍስ ከሕ​ዝ​ብዋ መካ​ከል ተለ​ይታ ትጥፋ።</verse>
				<verse number="15">ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ሥራ፤ ሰባ​ተ​ኛዋ ቀን ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ስች የዕ​ረ​ፍት ሰን​በት ናት፤ በሰ​ን​በት ቀን የሚ​ሠራ ሁሉ ፈጽሞ ይገ​ደል።</verse>
				<verse number="16">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለልጅ ልጃ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳን ዕረ​ፍት ያደ​ርጉ ዘንድ ሰን​በ​ትን ይጠ​ብቁ።</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በስ​ድ​ስት ቀን ስለ ፈጠረ፥ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሥራ​ውን ፈጽሞ ስላ​ረፈ፥ በእ​ኔና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ የዘ​ለ​ዓ​ለም ምል​ክት ነው።”</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር በሲና ተራራ የተ​ና​ገ​ረ​ውን በፈ​ጸመ ጊዜ ሁለ​ቱን የም​ስ​ክር ጽላት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት የተ​ጻ​ፈ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="32">
				<verse number="1">ሕዝ​ቡም ሙሴ ከተ​ራ​ራው ሳይ​ወ​ርድ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ፥ ወደ አሮን ተሰ​ብ​ስ​በው፥ “ይህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ሆነ አና​ው​ቅ​ምና ተነ​ሥ​ተህ በፊ​ታ​ችን የሚ​ሄዱ አማ​ል​ክት ሥራ​ልን” አሉት።</verse>
				<verse number="2">አሮ​ንም፥ “በሚ​ስ​ቶ​ቻ​ች​ሁና በሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ችሁ ጆሮ ያሉ​ትን የወ​ርቅ ጌጦች አም​ጡ​ልኝ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ሕዝ​ቡም ሁሉ በጆ​ሮ​ዎ​ቻ​ቸው ያሉ​ትን የወ​ርቅ ጌጦች ወደ አሮን አመ​ጡ​ለት።</verse>
				<verse number="4">ከእ​ጃ​ቸ​ውም ተቀ​ብሎ በመ​ቅ​ረጫ ቀረ​ጸው፤ ቀልጦ የተ​ሠራ ጥጃም አደ​ረ​ገው፤ እር​ሱም፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እነ​ዚህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጡህ አማ​ል​ክ​ትህ ናቸው” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">አሮ​ንም በአ​የው ጊዜ መሠ​ዊ​ያ​ውን በፊቱ ሠራ፤ አሮ​ንም፥ “ነገ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል ነው” ሲል አወጀ።</verse>
				<verse number="6">አሮ​ንም በነ​ጋው ማልዶ ተነሣ፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም ሠዋ፤ የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም አቀ​ረበ ሕዝ​ቡም ሊበ​ሉና ሊጠጡ ተቀ​መጡ፤ ሊዘ​ፍ​ኑም ተነሡ።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ተና​ገ​ረው እን​ዲ​ህም አለው፥ “ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኻ​ቸው ሕዝ​ብህ በድ​ለ​ዋ​ልና ሂድ፤ ፈጥ​ነህ ውረድ።</verse>
				<verse number="8">ካዘ​ዝ​ኋ​ቸው መን​ገድ ፈጥ​ነው ፈቀቅ አሉ፤ ቀልጦ የተ​ሠራ የጥጃ ምስል ለራ​ሳ​ቸው አደ​ረጉ፤ ሰገ​ዱ​ለ​ትም፤ ሠዉ​ለ​ትም፤</verse>
				<verse number="9">‘እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እነ​ዚህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጡህ አማ​ል​ክ​ትህ ናቸው’ አሉ።</verse>
				<verse number="10">አሁ​ንም ተቈ​ጥቼ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ተወኝ፤ አን​ተ​ንም ለታ​ላቅ ሕዝብ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="11">ሙሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ም​ላኩ ፊት ጸለየ፤ አለም፥ “አቤቱ፥ በታ​ላቅ ኀይ​ልና በጽኑ እጅ ከግ​ብፅ ምድር በአ​ወ​ጣ​ኸው በሕ​ዝ​ብህ ላይ ለምን ተቈ​ጣህ?</verse>
				<verse number="12">ግብ​ፃ​ው​ያ​ንስ፦ ‘በተ​ራራ መካ​ከል ሊገ​ድ​ላ​ቸው፥ ከም​ድ​ርም ፊት ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው ለክ​ፋት አወ​ጣ​ቸው’ ብለው ስለ ምን ይና​ገ​ራሉ? ከመ​ዓ​ትህ ተመ​ለስ፤ ለሕ​ዝ​ብ​ህም በክ​ፋ​ታ​ቸው ላይ ራራ።</verse>
				<verse number="13">ዘራ​ች​ሁን እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አበ​ዛ​ለሁ፤ ይህ​ች​ንም የተ​ና​ገ​ር​ኋ​ትን ምድር ሁሉ ለዘ​ራ​ችሁ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ይወ​ር​ሱ​አ​ታል ብለህ በራ​ስህ የማ​ል​ህ​ላ​ቸው ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህን አብ​ር​ሃ​ም​ንና ይስ​ሐ​ቅን ያዕ​ቆ​ብ​ንም ዐስብ።”</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ዝቡ ላይ ሊያ​ደ​ርግ ስላ​ሰ​በው ክፋት ይቅር አለ።</verse>
				<verse number="15">ሙሴም ተመ​ለሰ፤ ሁለ​ቱ​ንም የም​ስ​ክር ጽላት በእጁ ይዞ ከተ​ራ​ራው ወረደ፤ የድ​ን​ጋይ ጽላ​ቱም በዚ​ህና በዚያ በሁ​ለት ወገን ተጽ​ፎ​ባ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="16">ጽላቱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ነበሩ፤ ጽሕ​ፈ​ቱም በጽ​ላቱ ላይ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ባ​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽሕ​ፈት ነበረ።</verse>
				<verse number="17">ኢያ​ሱም ሲጮሁ የሕ​ዝ​ቡን ድምፅ ሰምቶ ሙሴን፥ “የሰ​ልፍ ድምፅ በሰ​ፈሩ ውስጥ አለ” አለው።</verse>
				<verse number="18">ሙሴም፥ “ይህ የድል ነሺ​ዎች ወይም የድል ተነ​ሺ​ዎች ድምፅ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን የወ​ይን ስካር ድምፅ እሰ​ማ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="19">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ወደ ሰፈሩ ሲቀ​ርብ ጥጃ​ው​ንም ዘፈ​ኑ​ንም አየ፤ የሙ​ሴም ቍጣ ተቃ​ጠለ፤ እነ​ዚ​ያ​ንም ሁለ​ቱን ጽላት ከእጁ ጥሎ ከተ​ራ​ራው በታች ሰበ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">የሠ​ሩ​ት​ንም ጥጃ ወስዶ በእ​ሳት አቀ​ለ​ጠው፤ ፈጨው፤ አደ​ቀ​ቀ​ውም፤ በው​ኃም ላይ በተ​ነው፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አጠ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">ሙሴም አሮ​ንን፥ “ይህን ታላቅ ኀጢ​አት ታመ​ጣ​በት ዘንድ ይህ ሕዝብ ምን አደ​ረ​ገህ?” አለው።</verse>
				<verse number="22">አሮ​ንም እን​ዲህ አለ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በእኔ ላይ አት​ቈጣ፤ የዚ​ህን ሕዝብ ጠባይ አንተ ታው​ቃ​ለህ።</verse>
				<verse number="23">እነ​ር​ሱም ይህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ሆነ አና​ው​ቅ​ምና በፊ​ታ​ችን የሚ​ሄዱ አማ​ል​ክት ሥራ​ልን አሉኝ።</verse>
				<verse number="24">እኔም ከእ​ና​ንተ ወርቅ ያለው ሰው ያም​ጣ​ልኝ አል​ኋ​ቸው፤ ሰጡ​ኝም፤ በእ​ሳ​ትም ላይ ጣል​ሁት፤ ይህም ጥጃ ወጣ።”</verse>
				<verse number="25">ሙሴም በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ፊት እን​ዲ​ነ​ወሩ አሮን ስድ ለቅ​ቆ​አ​ቸ​ዋ​ልና ሕዝቡ ስድ እንደ ተለ​ቀቀ በአየ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="26">ሙሴ በሰ​ፈሩ ደጅ ቆሞ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወገን የሆነ ወደ እኔ ይምጣ” አለ፤ የሌዊ ልጆች ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="27">እር​ሱም፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰይ​ፉን በወ​ገቡ ላይ ይታ​ጠቅ፤ ሂዱና በሰ​ፈሩ ውስጥ ከበር እስከ በር ተመ​ላ​ለሱ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወን​ድ​ሙን፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ጎረ​ቤ​ቱን፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም የቅ​ር​ቡን ይግ​ደል” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="28">የሌ​ዊም ልጆች ሙሴ እን​ዳለ አደ​ረጉ፤ በዚ​ያም ቀን ከሕ​ዝቡ ሦስት ሺህ ሰዎች ሞቱ።</verse>
				<verse number="29">ሙሴም፥ “ዛሬ በረ​ከ​ትን እን​ዲ​ያ​ወ​ር​ድ​ላ​ችሁ ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ ከል​ጁና፥ ከወ​ን​ድሙ የተ​ነሣ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በእ​ጃ​ችሁ ደስ አሰ​ኛ​ች​ሁት” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="30">በነ​ጋ​ውም ሙሴ ለሕ​ዝቡ፥ “እና​ንተ ታላቅ በደል ሠር​ታ​ች​ኋል፤ አሁ​ንም አስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ችሁ ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እወ​ጣ​ለሁ፤” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="31">ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ልሶ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ እኒህ ሕዝብ ታላቅ ኀጢ​አት ሠር​ተ​ዋል፤ ለራ​ሳ​ቸ​ውም የወ​ርቅ አማ​ል​ክት አድ​ር​ገ​ዋል፤</verse>
				<verse number="32">አሁ​ንም ይህን ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይቅር ትላ​ቸው እን​ደ​ሆነ ይቅር በላ​ቸው፤ ያለ​ዚያ ግን ከጻ​ፍ​ኸው መጽ​ሐፍ ደም​ስ​ሰኝ” አለ።</verse>
				<verse number="33">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “በፊቴ የበ​ደ​ለ​ውን እር​ሱን ከመ​ጽ​ሐፌ እደ​መ​ስ​ሰ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="34">አሁ​ንም ሂድ፤ ይህ​ንም ሕዝብ ወደ ነገ​ር​ሁህ ቦታ ምራ፤ እነሆ፥ መል​አኬ በፊ​ትህ ይሄ​ዳል፤ ነገር ግን በም​ጐ​በ​ኝ​በት ቀን ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="35">አሮን የሠ​ራ​ውን ጥጃ ስለ ሠሩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ቀሠፈ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="33">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፥ “ሂድ፤ አንተ ከግ​ብፅ ከአ​ወ​ጣ​ኸው ሕዝ​ብህ ጋር ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ለዘ​ራ​ችሁ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ ብዬ ወደ ማል​ሁ​ባት ምድር ውጣ።</verse>
				<verse number="2">መል​አ​ኬ​ንም ከአ​ንተ ጋር በፊ​ትህ እል​ካ​ለሁ፤ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ውን፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ያወ​ጣ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="3">ወተ​ትና ማርም ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ምድር አስ​ገ​ባ​ሃ​ለሁ፤ አን​ገተ ደን​ዳና ስለ​ሆኑ ሕዝ​ብህ በመ​ን​ገድ ላይ እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋህ እኔ ከአ​ንተ ጋር አል​ወ​ጣም።”</verse>
				<verse number="4">ሕዝ​ቡም ይህን ክፉ ወሬ ሰም​ተው ታላቅ ኀዘን አዘኑ፤</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እና​ንተ አን​ገተ ደን​ዳና ሕዝብ ናችሁ፤ ሌላ መቅ​ሠ​ፍት እን​ዳ​ላ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁና እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ፤ አሁ​ንም የክ​ብር ልብ​ሳ​ች​ሁ​ንና ጌጣ​ች​ሁን ከእ​ና​ንተ አውጡ፤ የማ​ደ​ር​ግ​ባ​ች​ሁ​ንም አሳ​ያ​ች​ኋ​ለሁ በላ​ቸው” አለው።</verse>
				<verse number="6">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከኮ​ሬብ ተራራ ጀም​ረው ልብ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ጌጦ​ቻ​ቸ​ውን አወጡ።</verse>
				<verse number="7">ሙሴም ድን​ኳ​ኑን ወስዶ ከሰ​ፈር ውጭ ይተ​ክ​ለው ነበር፤ ከሰ​ፈ​ሩም ራቅ ያደ​ር​ገው ነበር፤ “የም​ስ​ክ​ሩም ድን​ኳን” ብሎ ጠራው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የፈ​ለገ ሁሉ ከሰ​ፈር ውጭ ወደ​አ​ለው ወደ ድን​ኳኑ ይወጣ ነበር።</verse>
				<verse number="8">ሙሴም ከሰ​ፈር ውጭ ወደ​አ​ለው ድን​ኳን በሄደ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ እየ​ጠ​በቀ ይቆም ነበር፤ ሙሴም ወደ ድን​ኳኑ እስ​ኪ​ገባ ድረስ ይመ​ለ​ከ​ቱት ነበር።</verse>
				<verse number="9">ሙሴም ወደ ድን​ኳኑ በገባ ጊዜ ዐምደ ደመና ይወ​ርድ ነበር፤ በድ​ን​ኳ​ኑም ደጃፍ ይቆም ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ይና​ገ​ረው ነበር።</verse>
				<verse number="10">ሕዝ​ቡም ሁሉ ዐምደ ደመ​ናው በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ ሲቆም ያየው ነበር፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ተነ​ሥቶ እያ​ን​ዳ​ንዱ በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ ይሰ​ግድ ነበር።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ ሰው ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ጋር እን​ደ​ሚ​ነ​ጋ​ገር ፊት ለፊት ከሙሴ ጋር ይነ​ጋ​ገር ነበር። ሙሴም ወደ ሰፈሩ ይመ​ለስ ነበር፤ ነገር ግን አገ​ል​ጋዩ ብላ​ቴና የነዌ ልጅ ኢያሱ ከድ​ን​ኳኑ አይ​ወ​ጣም ነበር።</verse>
				<verse number="12">ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “እነሆ፥ አንተ፦ ይህን ሕዝብ አውጣ ትለ​ኛ​ለህ፤ ነገር ግን ከእኔ ጋር የም​ት​ል​ከ​ውን አላ​ስ​ታ​ወ​ቅ​ኸ​ኝም። አን​ተም ከሁሉ ይልቅ ዐወ​ቅ​ሁህ፥ ደግ​ሞም በእኔ ፊት ሞገ​ስን አገ​ኘህ አል​ኸኝ።</verse>
				<verse number="13">አሁ​ንም በፊ​ትህ ሞገ​ስን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ፥ ዐው​ቅህ ዘንድ በፊ​ት​ህም ሞገ​ስን አገኝ ዘንድ ይህም ትልቅ ሕዝብ ሕዝ​ብህ እንደ ሆነ ዐውቅ ዘንድ ተገ​ለ​ጥ​ልኝ” አለው።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “እኔ በፊ​ትህ እሄ​ዳ​ለሁ፥ አሳ​ር​ፍ​ህ​ማ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="15">እር​ሱም፥ “አንተ ከእኛ ጋር ካል​ወ​ጣ​ህስ፥ ከዚህ አታ​ው​ጣን።</verse>
				<verse number="16">በም​ድ​ርም ከአ​ለው ሕዝብ ሁሉ እኔና ሕዝ​ብህ ተለ​ይ​ተን እን​ከ​ብር ዘንድ አንተ ከእኛ ጋር ካል​ሄ​ድህ፥ እኔና ሕዝ​ብህ በአ​ንተ ዘንድ በእ​ው​ነት ሞገስ ማግ​ኘ​ታ​ችን በምን ይታ​ወ​ቃል?” አለው።</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ይህን ያል​ኸ​ኝን ነገር አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ፤ በፊቴ ሞገ​ስን አግ​ኝ​ተ​ሀ​ልና ከሁሉ ይልቅ ዐው​ቄ​ሃ​ለ​ሁና” አለው።</verse>
				<verse number="18">እር​ሱም፥ “ክብ​ር​ህን አሳ​የኝ” አለው።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “እኔ በክ​ብሬ በፊ​ትህ አል​ፋ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም በፊ​ትህ እጠ​ራ​ለሁ፤ ይቅ​ርም የም​ለ​ውን ይቅር እላ​ለሁ፤ የም​ም​ረ​ው​ንም እም​ራ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ሰው አይ​ቶኝ አይ​ድ​ን​ምና ፊቴን ማየት አይ​ቻ​ል​ህም” አለ።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “እነሆ፥ ስፍራ በእኔ ዘንድ አለ፥ በዐ​ለ​ቱም ላይ ትቆ​ማ​ለህ፤</verse>
				<verse number="22">ክብ​ሬም በአ​ለፈ ጊዜ በአ​ለቱ ስን​ጥቅ ውስጥ አኖ​ር​ሃ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="23">እስከ አል​ፍም ድረስ እጄን በላ​ይህ እጋ​ር​ዳ​ለሁ፤ እጄ​ንም ፈቀቅ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በዚያ ጊዜ ጀር​ባ​ዬን ታያ​ለህ፤ ፊቴ ግን ለአ​ንተ አይ​ታ​ይም።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="34">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ሁለት የድ​ን​ጋይ ጽላት እንደ ፊተ​ኞቹ አድ​ር​ገህ ቅረጽ፤ ወደ እኔም ወደ ተራራ ውጣ፤ በሰ​በ​ር​ሃ​ቸው በፊ​ተ​ኞቹ ጽላት የነ​በ​ሩ​ትን ቃላት እጽ​ፍ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">ለጥ​ዋ​ትም የተ​ዘ​ጋ​ጀህ ሁን፤ ወደ ሲና ተራራ ወጥ​ተህ በዚያ በተ​ራ​ራው ራስ ላይ በፊቴ ቁም።</verse>
				<verse number="3">ከአ​ን​ተም ጋር ማንም ሰው አይ​ውጣ፤ በተ​ራ​ራ​ውም ሁሉ ማንም አይ​ታይ፤ መን​ጎ​ችና ከብ​ቶ​ችም በዚያ ተራራ አጠ​ገብ አይ​ሰ​ማሩ።</verse>
				<verse number="4">ሙሴም እንደ ፊተ​ኞቹ አድ​ርጎ ሁለት የድ​ን​ጋይ ጽላት ቀረጸ፤ ሁለ​ቱ​ንም የድ​ን​ጋይ ጽላት በእጁ ወሰደ፤ በነ​ጋ​ውም ማልዶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው ወደ ሲና ተራራ ወጣ፤</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በደ​መ​ናው ውስጥ ወረደ፤ በዚ​ያም ከእ​ርሱ ጋር ቆመ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ጠራ።</verse>
				<verse number="6">ጌታም በፊቱ አለፈ፥ “ስሜም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ መሓሪ፥ ይቅር ባይ፥ ከመ​ዓት የራቀ ምሕ​ረቱ የበዛ ጻድቅ፥</verse>
				<verse number="7">ለብዙ ሺህ ጽድ​ቅን የሚ​ጠ​ብቅ፥ ቸር​ነ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ አበ​ሳ​ንና መተ​ላ​ለ​ፍን፥ ኀጢ​አ​ት​ንም ይቅር የሚል፥ በደ​ለ​ኛ​ው​ንም ከቶ የማ​ያ​ነጻ፥ የአ​ባ​ቶ​ች​ንም ኀጢ​አት በል​ጆች፥ እስከ ሦስ​ትና እስከ አራት ትው​ል​ድም በልጅ ልጆች የሚ​ያ​መጣ አም​ላክ ነው” ሲል አወጀ።</verse>
				<verse number="8">ሙሴም ፈጥኖ ወደ መሬት ተጎ​ነ​በ​ሰና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ፦</verse>
				<verse number="9">“አቤቱ በፊ​ት​ህስ ሞገ​ስን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ፥ ይህ ሕዝብ አን​ገተ ደን​ዳና ነውና ጌታዬ ከእኛ ጋር ይሂድ፤ ጠማ​ማ​ነ​ታ​ች​ንን፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ን​ንና በደ​ላ​ች​ንን ይቅር በለን፤ ለአ​ን​ተም እን​ሆ​ና​ለን” አለ።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እነሆ፥ እኔ በሕ​ዝ​ብህ ፊት ሁሉ ቃል ኪዳን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በም​ድር ሁሉ፥ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ዘንድ እንደ እርሱ ያለ ከቶ ያል​ተ​ደ​ረ​ገ​ውን ታላቅ ተአ​ም​ራ​ትን አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ፤ እኔም የማ​ደ​ር​ግ​ልህ ነገር ድንቅ ነውና አንተ በመ​ካ​ከሉ ያለ​ህ​በት ይህ ሕዝብ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ያያል።</verse>
				<verse number="11">በዚህ ቀን የማ​ዝ​ዝ​ህን ነገር ጠብቅ፤ እነሆ፥ እኔ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ከፊ​ትህ አወ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">በመ​ካ​ከ​ልህ ወጥ​መድ እን​ዳ​ይ​ሆ​ኑ​ብህ አንተ በም​ት​ገ​ባ​በት ምድር ከሚ​ኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እን​ዳ​ታ​ደ​ርግ ተጠ​ን​ቀቅ፤</verse>
				<verse number="13">ነገር ግን መሠ​ው​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውን ታፈ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤ ሐው​ል​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትሰ​ብ​ራ​ላ​ችሁ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ቻ​ቸ​ውን ትቈ​ር​ጣ​ላ​ችሁ፤ ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="14">ስሙ ቀና​ተኛ የሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅን​ዐት ያለው አም​ላክ ነውና ለሌላ አም​ላክ አት​ስ​ገድ።</verse>
				<verse number="15">በዚ​ያች ምድር ከሚ​ኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እን​ዳ​ታ​ደ​ርግ፥ እነ​ርሱ አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለው በአ​መ​ነ​ዘ​ሩና በሠ​ዉ​ላ​ቸው ጊዜ እን​ዳ​ይ​ጠ​ሩህ፥ ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውም እን​ዳ​ት​በላ፥</verse>
				<verse number="16">ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ም​ንም ከወ​ንድ ልጆ​ችህ፥ ሴቶች ልጆ​ች​ህ​ንም ከወ​ንድ ልጆ​ቻ​ቸው ጋር እን​ዳ​ታ​ጋባ፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለው ሲያ​መ​ነ​ዝሩ ከአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው በኋላ ሄደው አመ​ን​ዝ​ረ​ውም ልጆ​ች​ህን እን​ዳ​ያ​ስቱ ተጠ​ን​ቀቅ።</verse>
				<verse number="17">ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ትን አማ​ል​ክት ለአ​ንተ አታ​ድ​ርግ።</verse>
				<verse number="18">“የቂ​ጣ​ውን በዓል ትጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለህ። በሚ​ያ​ዝያ ወር ከግ​ብፅ ወጥ​ተ​ሃ​ልና በታ​ዘ​ዘው ዘመን በሚ​ያ​ዝያ ወር እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁህ ሰባት ቀን ቂጣ ብላ።</verse>
				<verse number="19">መጀ​መ​ሪያ የሚ​ወ​ለድ ተባት ሁሉ የእኔ ነው፤ የላ​ም​ህም በኵር፥ የበ​ግ​ህም በኵር፥ የበ​ሬ​ህም በኵር ሁሉ የእኔ ነው።</verse>
				<verse number="20">የአ​ህ​ያ​ው​ንም በኵር በበግ ትዋ​ጀ​ዋ​ለህ፤ ባት​ዋ​ጀው ግን ዋጋ​ውን ትሰ​ጣ​ለህ። የል​ጆ​ች​ህ​ንም በኵር ሁሉ ትዋ​ጃ​ለህ። በፊ​ቴም ባዶ እጅ​ህን አት​ታይ።</verse>
				<verse number="21">“ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ትሠ​ራ​ለህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ታር​ፋ​ለህ። በም​ት​ዘ​ራ​በ​ትና በም​ታ​ጭ​ድ​በት ዘመን ታር​ፋ​ለህ።</verse>
				<verse number="22">የሰ​ባ​ቱ​ንም ሱባዔ በዓል ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ እር​ሱም የስ​ንዴ መከር መጀ​መ​ሪያ ነው፤ በዓ​መ​ቱም መካ​ከል የመ​ክ​ተቻ በዓል ታደ​ር​ጋ​ለህ።</verse>
				<verse number="23">ወንድ ልጅህ ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዓ​መት ሦስት ጊዜ ይታይ።</verse>
				<verse number="24">አሕ​ዛ​ብን ከፊ​ትህ በአ​ወ​ጣሁ ጊዜ ሀገ​ር​ህን አሰ​ፋ​ለሁ፤ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊትም ለመ​ታ​የት በዓ​መት ሦስት ጊዜ ስት​ወጣ ማንም ምድ​ር​ህን አይ​መ​ኝም።</verse>
				<verse number="25">“የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቴን ደም ከቦካ እን​ጀራ ጋር አት​ሠዋ፤ የፋ​ሲ​ካ​ውም በዓል መሥ​ዋ​ዕት እስከ ነገ አይ​ደር።</verse>
				<verse number="26">የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውን የም​ድ​ር​ህን ፍሬ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ትወ​ስ​ዳ​ለህ። ጠቦ​ቱን በእ​ናቱ ወተት አት​ቀ​ቅል።”</verse>
				<verse number="27">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “በእ​ነ​ዚህ ቃሎች ከአ​ን​ተና ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ቃል ኪዳን አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና እነ​ዚ​ህን ቃሎች ጻፍ” አለው።</verse>
				<verse number="28">በዚ​ያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነበረ፤ እን​ጀ​ራም አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም። በጽ​ላ​ቱም ዐሥ​ሩን የቃል ኪዳን ቃሎች ጻፈ።</verse>
				<verse number="29">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ ከሲና ተራራ በወ​ረደ ጊዜ ሁለቱ ጽላት በሙሴ እጅ ነበሩ፤ ሙሴም ከተ​ራ​ራው በወ​ረደ ጊዜ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ሲነ​ጋ​ገር ፊቱ እን​ዳ​ን​ጸ​ባ​ረቀ አላ​ወ​ቀም ነበር።</verse>
				<verse number="30">አሮ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እነሆ፥ ፊቱ እን​ዳ​ን​ጸ​ባ​ረቀ ሙሴን በአዩ ጊዜ፥ ወደ እርሱ ለመ​ቅ​ረብ ፈሩ።</verse>
				<verse number="31">ሙሴም ጠራ​ቸው፤ አሮ​ንም የማ​ኅ​በ​ሩም አለ​ቆች ሁሉ ወደ እርሱ ተመ​ለሱ፤ ሙሴም ተና​ገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="32">ከዚ​ያም በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ወደ እርሱ ቀረቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሲና ተራራ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር ሁሉ አዘ​ዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="33">ሙሴም ለእ​ነ​ርሱ ተና​ግሮ ከጨ​ረሰ በኋላ በፊቱ መሸ​ፈኛ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="34">ሙሴም ከእ​ርሱ ጋር ይነ​ጋ​ገር ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በገባ ጊዜ እስ​ኪ​ወጣ ድረስ መሸ​ፈ​ኛ​ውን ከፊቱ ያነሣ ነበር፤ በወ​ጣም ጊዜ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የታ​ዘ​ዘ​ውን ነገር ይነ​ግ​ራ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="35">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የሙ​ሴን ፊት እን​ዳ​ን​ጸ​ባ​ረቀ ያዩ ነበር፤ እር​ሱም ከእ​ርሱ ጋር ሊነ​ጋ​ገር እስ​ኪ​ገባ ድረስ እንደ ገና በፊቱ መሸ​ፈኛ ያደ​ርግ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="35">
				<verse number="1">ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ሰብ​ስቦ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ታደ​ርጉ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያለው ነገር ይህ ነው፤</verse>
				<verse number="2">ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ትሠ​ራ​ለህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ታር​ፋ​ለህ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ የዕ​ረ​ፍት ሰን​በት ነው፤ የሚ​ሠ​ራ​በ​ትም ሁሉ ይሙት።</verse>
				<verse number="3">በማ​ደ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ችሁ ውስጥ በሰ​ን​በት ቀን እሳ​ትን አታ​ን​ድዱ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።”</verse>
				<verse number="4">ሙሴም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ያዘ​ዘው ነገር ይህ ነው፤</verse>
				<verse number="5">ከእ​ና​ንተ ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባ​ንን አቅ​ርቡ፤ የልብ ፈቃድ ያለው ከገ​ን​ዘቡ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያምጣ፤ ወር​ቅና ብር፥ ናስም፤</verse>
				<verse number="6">ሰማ​ያ​ዊም፥ ሐም​ራ​ዊም፥ ድርብ ቀይ ግም​ጃም፥ የተ​ፈ​ተለ በፍ​ታም፥ የፍ​የል ጠጕ​ርም፤</verse>
				<verse number="7">ቀይ ቀለ​ምም የገ​ባ​በት የአ​ውራ በግ ቍር​በት፥ የአ​ቆ​ስ​ጣም ቍር​በት፥ የማ​ይ​ነ​ቅ​ዝም ዕን​ጨት፤</verse>
				<verse number="8">ለመ​ብ​ራ​ትም ዘይት፥ ለቅ​ብ​ዐት ሽቱን፥ ለማ​ዕ​ጠ​ንት ዕጣ​ንን፤</verse>
				<verse number="9">የመ​ረ​ግድ ድን​ጋ​ይና የተ​ቀ​ረጸ ድን​ጋይ፥ ለል​ብሰ መት​ከ​ፍና ለል​ብሰ እን​ግ​ድዓ የሚ​ደ​ረግ ፈርጥ ያምጣ።</verse>
				<verse number="10">“በእ​ና​ንተ ዘንድ ያለ፥ በልቡ ጥበ​በኛ የሆነ ሁሉ መጥቶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ያድ​ርግ።</verse>
				<verse number="11">ድን​ኳ​ኑ​ንም፥ አደ​ባ​ባ​ዩ​ንም፥ መደ​ረ​ቢ​ያ​ው​ንም፥ መያ​ዣ​ዎ​ቹ​ንም፥ ሳን​ቆ​ቹ​ንም፥ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ንና እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን፤</verse>
				<verse number="12">የቃል ኪዳ​ኑን ታቦ​ትም፥ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም፥ መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም፤</verse>
				<verse number="13">ገበ​ታ​ው​ንና መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ ኅብ​ስተ ገጹ​ንም፤</verse>
				<verse number="14">መብ​ራት የሚ​ያ​በ​ሩ​በ​ትን መቅ​ረ​ዙን፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ ቀን​ዲ​ሉ​ንም፥ የመ​ብ​ራ​ቱ​ንም ዘይት፤</verse>
				<verse number="15">የዕ​ጣ​ኑ​ንም መሠ​ዊያ፥ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ የቅ​ብ​ዐ​ቱ​ንም ዘይት፥ ጣፋ​ጩ​ንም ዕጣን፥ ለማ​ደ​ሪ​ያ​ውም ደጃፍ የሚ​ሆን የደ​ጃ​ፉን መጋ​ረጃ፤</verse>
				<verse number="16">ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊ​ያ​ውን፥ የና​ሱ​ንም መከታ፥ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንም፥ መቀ​መ​ጫ​ው​ንም፤</verse>
				<verse number="17">የአ​ደ​ባ​ባ​ዩን መጋ​ረ​ጆች፥ ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ንም፥ እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ደጃፍ መጋ​ረጃ፤</verse>
				<verse number="18">የማ​ደ​ሪ​ያ​ውን ካስ​ማ​ዎች፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ካስ​ማ​ዎች፥ አው​ታ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም፤</verse>
				<verse number="19">በመ​ቅ​ደስ ውስጥ ለማ​ገ​ል​ገል በብ​ል​ሃት የተ​ሠ​ሩ​ትን ልብ​ሶች፥ በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግ​ሉ​በት ዘንድ የተ​ቀ​ደ​ሱ​ትን የካ​ህ​ኑን የአ​ሮ​ንን ልብ​ሶች፥ የል​ጆ​ቹ​ንም ልብ​ሶች።”</verse>
				<verse number="20">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ከሙሴ ዘንድ ወጡ።</verse>
				<verse number="21">ከእ​ነ​ር​ሱም ሰው ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ልቡ እን​ዳ​ነ​ሣ​ሣው፥ መን​ፈ​ሱም እሺ እን​ዳ​ሰ​ኘው ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥራ ለማ​ገ​ል​ገ​ያ​ውም ሁሉ ለመ​ቅ​ደስ ልብስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጦታ አመጡ።</verse>
				<verse number="22">ወን​ዶ​ችና ሴቶ​ችም ልባ​ቸው እንደ ፈቀደ ማር​ዳ​ዎ​ችን፥ ሎቲ​ዎ​ች​ንም፥ ቀለ​በ​ቶ​ች​ንም፥ ድሪ​ዎ​ች​ንም፥ የወ​ርቅ ጌጦ​ች​ንም ሁሉ አመጡ፤ ሰዎ​ችም ሁሉ የወ​ርቅ ስጦታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቀ​ረቡ።</verse>
				<verse number="23">ሰማ​ያ​ዊም፥ ሐም​ራ​ዊም፥ ቀይ ግም​ጃም፥ የተ​ፈ​ተለ በፍ​ታም፥ የፍ​የል ጠጕ​ርም፥ ቀይ የአ​ውራ በግ ቍር​በ​ትም፥ የአ​ቆ​ስጣ ቍር​በ​ትም ያላ​ቸው ሰዎች ሁሉ አመጡ።</verse>
				<verse number="24">ስዕ​ለት የተ​ሳለ ሁሉ፥ የብ​ር​ንም፥ የና​ስ​ንም ስጦታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን አቀ​ረበ፤ የማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ያለው ሁሉ ለድ​ን​ኳኑ ማገ​ል​ገያ ለሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገው ሥራ አመጣ።</verse>
				<verse number="25">በል​ባ​ቸው ጥበ​በ​ኞች የሆኑ ሴቶ​ችም በእ​ጃ​ቸው ፈተሉ፤ የፈ​ተ​ሉ​ት​ንም ሰማ​ያ​ዊ​ውን፥ ሐም​ራ​ዊ​ው​ንም፥ ቀዩ​ንም ግምጃ፥ ጥሩ​ው​ንም በፍታ አመጡ።</verse>
				<verse number="26">ልባ​ቸ​ውም በጥ​በብ ያስ​ነ​ሣ​ቸው ሴቶች ሁሉ የፍ​የ​ልን ጠጕር ፈተሉ።</verse>
				<verse number="27">አለ​ቆ​ችም የመ​ረ​ግድ ድን​ጋ​ይና የተ​ቀ​ረጸ ድን​ጋ​ይን ለል​ብሰ መት​ከ​ፍና ለል​ብሰ እን​ግ​ድዓ የሚ​ገ​ቡ​ት​ንም ፈር​ጦ​ችን፥</verse>
				<verse number="28">ለመ​ብ​ራ​ትም፥ ለቅ​ብ​ዐት ዘይ​ትም፥ ለጣ​ፋጭ ዕጣ​ንም ሽቱ​ንና ዘይ​ትን አመጡ።</verse>
				<verse number="29">ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ያመጡ ዘንድ ልባ​ቸው ያስ​ነ​ሣ​ቸው ወን​ዶ​ችና ሴቶች ሁሉ ሙሴ ይሠራ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላዘ​ዘው ሥራ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጦታ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው አመጡ።</verse>
				<verse number="30">ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አላ​ቸው፥ “እዩ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከይ​ሁዳ ነገድ የሆ​ነ​ውን የሆር የልጅ ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስ​ል​ኤ​ልን በስሙ ጠራው።</verse>
				<verse number="31">በሥራ ሁሉ ብል​ሃት፥ በጥ​በ​ብም፥ በማ​ስ​ተ​ዋ​ልም፥ በዕ​ው​ቀ​ትም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ፈስ ሞላ​በት፤</verse>
				<verse number="32">በአ​ና​ጺ​ዎች ላይ አለቃ ይሆን ዘንድ፥ የጥ​በ​ብ​ንም ሥራ ያስ​ተ​ውል ዘንድ፥ በወ​ር​ቅና በብር፥ በና​ስም ይሠራ ዘንድ፥</verse>
				<verse number="33">በፈ​ርጥ የሚ​ሆ​ነ​ውን የዕ​ንቍ ድን​ጋይ ይቀ​ርጽ ዘንድ፥ ዕን​ጨ​ቱ​ንም ይጠ​ርብ ዘንድ፥ የብ​ል​ሃት ሥራ​ው​ንም ሁሉ ይሠራ ዘንድ።</verse>
				<verse number="34">እር​ሱና የዳን ነገድ የሆ​ነው የአ​ሒ​ሳ​ሚክ ልጅ ኤል​ያብ ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ በል​ባ​ቸው አሳ​ደ​ረ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="35">በአ​ን​ጥ​ረኛ፥ በብ​ልህ ሠራ​ተ​ኛም፥ በሰ​ማ​ያ​ዊና በሐ​ም​ራዊ፥ በቀ​ይም ግምጃ፥ በጥሩ በፍ​ታም በሚ​ሠራ ጠላፊ፥ በሸ​ማ​ኔም ሥራ የሚ​ሠ​ራ​ውን፥ ማና​ቸ​ው​ንም ሥራና በብ​ል​ሃት የሚ​ሠ​ራ​ውን ሁሉ ያደ​ርጉ ዘንድ በእ​ነ​ርሱ ልብ ጥበ​ብን ሞላ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="36">
				<verse number="1">“ባስ​ል​ኤ​ልና ኤል​ያብ፥ ለመ​ቅ​ደ​ስም ማገ​ል​ገያ ሥራ ሁሉ ያደ​ርጉ ዘንድ እን​ዲ​ያ​ውቁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን የሰ​ጣ​ቸው በል​ባ​ቸ​ውም ጥበ​በ​ኞች የሆኑ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ነገር ሁሉ አደ​ረጉ።”</verse>
				<verse number="2">ሙሴም ባስ​ል​ኤ​ል​ንና ኤል​ያ​ብን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዕው​ቀ​ት​ንና ጥበ​ብን በል​ቡ​ና​ቸው ያሳ​ደ​ረ​ባ​ቸ​ው​ንና ጥበብ ያላ​ቸ​ውን፥ ሥራ​ው​ንም ለመ​ሥ​ራት ይቀ​ርብ ዘንድ ልቡ ያስ​ነ​ሣ​ውን ሁሉ ሥራ​ውን ሠር​ተው ይፈ​ጽሙ ዘንድ ጠራ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">እነ​ር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለመ​ቅ​ደስ ማገ​ል​ገያ ሥራ ያመ​ጡ​ትን ስጦታ ሁሉ ይሠሩ ዘንድ ከሙሴ ተቀ​በሉ። እነ​ዚ​ያም እንደ ፈቃ​ዳ​ቸው ማለዳ ማለዳ ስጦ​ታ​ውን ገና ወደ እርሱ ያመጡ ነበር።</verse>
				<verse number="4">እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በሚ​ሠ​ሩት የመ​ቅ​ደ​ሱን ሥራ የሚ​ሠሩ ጠቢ​ባን ሁሉ መጡ፤</verse>
				<verse number="5">እነ​ር​ሱም ለሙሴ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይደ​ረግ ዘንድ ላዘ​ዘው ሥራ ከሚ​በቃ በላይ እጅግ የሚ​በ​ልጥ ሕዝቡ አመጡ” ብለው ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="6">ሙሴም አዘ​ዘና፥ “ወንድ ወይም ሴት ለመ​ቅ​ደስ ስጦታ ከዚህ የበ​ለጠ የሚ​ያ​መጣ አይ​ኑር” ብሎ በሰ​ፈሩ ውስጥ አወጀ። ሕዝ​ቡም እን​ዳ​ያ​መጡ ተከ​ለ​ከሉ።</verse>
				<verse number="7">ያመ​ጡ​ትም ነገር ሥራን ሁሉ ለመ​ፈ​ጸም በቅቶ ገና ይተ​ርፍ ነበ​ረና።</verse>
				<verse number="8">በእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ ያሉት፥ ሥራ ሲሠሩ የነ​በ​ሩት በል​ባ​ቸው ጥበ​በ​ኞች ሁሉ ድን​ኳ​ኑን ከዐ​ሥር መጋ​ረ​ጃ​ዎች ሠሩ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰ​ማ​ያ​ዊም፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ ሠሩ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ በጥ​ልፍ ሥራ ኪሩ​ቤ​ልን አደ​ረ​ጉ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">የእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ መጋ​ረጃ ርዝ​መት ሃያ ስም​ንት ክንድ፥ ወር​ዱም አራት ክንድ ነበረ፤ የመ​ጋ​ረ​ጃ​ዎቹ ሁሉ ልክ ትክ​ክል ነበረ።</verse>
				<verse number="10">አም​ስ​ቱ​ንም መጋ​ረ​ጃ​ዎች እርስ በር​ሳ​ቸው አን​ዱን ከሌ​ላው ጋር አጋ​ጠሙ፤ አም​ስ​ቱ​ንም መጋ​ረ​ጃ​ዎች እርስ በር​ሳ​ቸው እን​ዲሁ አጋ​ጠሙ።</verse>
				<verse number="11">ከሚ​ጋ​ጠ​ሙ​ትም መጋ​ረ​ጃ​ዎች በአ​ን​ደ​ኛው መጋ​ረጃ ዘርፍ ላይ የሰ​ማ​ያ​ዊ​ውን ግምጃ ቀለ​በ​ቶች አደ​ረጉ፤ ደግሞ ከተ​ጋ​ጠ​ሙት ከሌ​ሎቹ በአ​ን​ደ​ኛው መጋ​ረጃ ዘርፍ ላይ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="12">አምሳ ቀለ​በ​ቶ​ችን በአ​ንድ መጋ​ረጃ አደ​ረጉ፤ አም​ሳ​ው​ንም ቀለ​በ​ቶች በሁ​ለ​ተ​ኛው መጋ​ረጃ ዘርፍ አደ​ረጉ፤ ቀለ​በ​ቶቹ እርስ በር​ሳ​ቸው ፊት ለፊት የሚ​ተ​ያዩ ነበሩ።</verse>
				<verse number="13">አም​ሳም የወ​ርቅ መያ​ዣ​ዎ​ችን ሠሩ፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ች​ንም አን​ዱን ከሌ​ላው በመ​ያ​ዣ​ዎች አጋ​ጠ​ሙ​አ​ቸው፤ አንድ ድን​ኳ​ንም ሆነ።</verse>
				<verse number="14">ከድ​ን​ኳ​ኑም በላይ የሚ​ሆኑ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችን ከፍ​የል ጠጕር አደ​ረጉ፤ ዐሥራ አንድ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ች​ንም አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="15">እያ​ን​ዳ​ን​ዱም መጋ​ረጃ ርዝ​መቱ ሠላሳ ክንድ፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም መጋ​ረጃ ወርዱ አራት ክንድ ነበረ፤ የእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም መጋ​ረጃ መጠኑ ትክ​ክል ነበረ።</verse>
				<verse number="16">አም​ስ​ቱ​ንም መጋ​ረ​ጃ​ዎች እርስ በር​ሳ​ቸው አንድ አደ​ረጉ፤ ስድ​ስ​ቱ​ንም መጋ​ረ​ጃ​ዎች አንድ አድ​ር​ገው አጋ​ጠ​ሙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">ከተ​ጋ​ጠ​ሙ​ትም መጋ​ረ​ጃ​ዎች በአ​ን​ደ​ኛው መጋ​ረጃ ጠርዝ ላይ አምሳ ቀለ​በ​ቶ​ችን አደ​ረጉ፤ እን​ዲ​ሁም በሁ​ለ​ተ​ኛው መጋ​ረጃ ጠርዝ በሚ​ጋ​ጠ​ሙ​በት በኩል አምሳ ቀለ​በ​ቶ​ችን አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="18">ድን​ኳ​ኑም አንድ እን​ዲ​ሆን ያጋ​ጥ​ሙት ዘንድ አምሳ የናስ መያ​ዣ​ዎ​ችን ሠሩ።</verse>
				<verse number="19">ለድ​ን​ኳ​ኑም መደ​ረ​ቢያ ከቀይ አውራ በግ የተ​ለፋ ቍር​በት፥ ከዚ​ያም በላይ ሌላ መደ​ረ​ቢያ ከአ​ቆ​ስጣ ቍር​በት አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="20">ለድ​ን​ኳ​ኑም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት የሚ​ቆ​ሙ​ትን ሳን​ቆች አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="21">የሳ​ን​ቃው ሁሉ ርዝ​መቱ ዐሥር ክንድ፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ ተኩል ነበረ።</verse>
				<verse number="22">ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሳንቃ አን​ዱን በአ​ንዱ ላይ የሚ​ያ​ያ​ይዙ ሁለት ማጋ​ጠ​ሚ​ያ​ዎች ነበሩ፤ ለድ​ን​ኳ​ኑም ሳን​ቆች ሁሉ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="23">ለድ​ን​ኳ​ኑም በደ​ቡብ ወገን ሃያ ሳን​ቆ​ችን አደ​ረጉ፤</verse>
				<verse number="24">ከሃ​ያ​ውም ሳን​ቆች በታች አርባ የብር እግ​ሮች አደ​ረጉ፤ ከእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሳንቃ በታች ለሁ​ለቱ ማጋ​ጠ​ሚ​ያ​ዎች ሁለት እግ​ሮች ነበሩ።</verse>
				<verse number="25">ለድ​ን​ኳ​ኑም ለሁ​ለ​ተ​ኛው ወገን በሰ​ሜን በኩል ሃያ ሳን​ቆች አደ​ረጉ፤</verse>
				<verse number="26">ለእ​ነ​ር​ሱም አርባ የብር እግ​ሮች፥ ከእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሳንቃ በታች ሁለት እግ​ሮች አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="27">ለድ​ን​ኳ​ኑም በም​ዕ​ራቡ ወገን በስ​ተ​ኋላ ስድ​ስት ሳን​ቆች አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="28">ለድ​ን​ኳ​ኑም ለሁ​ለቱ ማዕ​ዘን በስ​ተ​ኋላ ሁለት ሳን​ቆች አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="29">ከታ​ችም እስከ ላይ እስከ አን​ደ​ኛው ቀለ​በት ድረስ አንድ ሳንቃ ድርብ ነበረ፤ ለሁ​ለ​ቱም ማዕ​ዘን እን​ዲሁ ሁለት ነበሩ።</verse>
				<verse number="30">ስም​ንት ሳን​ቆ​ችና ዐሥራ ስድ​ስቱ የብር እግ​ሮ​ቻ​ቸው፥ ከእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሳንቃ በታች ሁለት ሁለት እግ​ሮች ነበሩ።</verse>
				<verse number="31">ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት በድ​ን​ኳኑ በአ​ን​ደ​ኛው ወገን ላሉት ሳን​ቆች አም​ስት መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችን፥</verse>
				<verse number="32">በድ​ን​ኳ​ኑም በሁ​ለ​ተ​ኛው ወገን ላሉት ሳን​ቆች አም​ስት መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችን፥ ከድ​ን​ኳ​ኑም በስ​ተ​ኋላ በም​ዕ​ራቡ ወገን ላሉት ሳን​ቆች አም​ስት መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችን አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="33">መካ​ከ​ለ​ኛ​ው​ንም መወ​ር​ወ​ሪያ በሳ​ን​ቆቹ መካ​ከል ከዳር እስከ ዳር እን​ዲ​ያ​ልፍ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="34">ሳን​ቆ​ቹ​ንም በወ​ርቅ ለበ​ጡ​አ​ቸው፤ ቀለ​በ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም የመ​ወ​ር​ወ​ሪያ ቤት እን​ዲ​ሆ​ኑ​ላ​ቸው ከወ​ርቅ አደ​ረጉ፤ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም በወ​ርቅ ለበ​ጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="35">መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም ከሰ​ማ​ያ​ዊና ከሐ​ም​ራዊ፥ ከቀ​ይም ግምጃ፥ ከተ​ፈ​ተ​ለም ከጥሩ በፍታ አደ​ረጉ፤ ኪሩ​ቤ​ል​ንም በጥ​ልፍ ሥራ በእ​ርሱ ላይ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="36">ከማ​ይ​ነ​ቅ​ዝም ዕን​ጨት አራት ምሰ​ሶ​ዎች አደ​ረ​ጉ​ለት፤በወ​ር​ቅም ለበ​ጡ​አ​ቸው፤ ኵላ​ቦ​ቻ​ቸ​ውም የወ​ርቅ ነበሩ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም አራት የብር እግ​ሮች አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="37">ለድ​ን​ኳ​ኑም ደጃፍ ከሰ​ማ​ያ​ዊና ከሐ​ም​ራዊ፥ ከቀ​ይም ግምጃ፥ ከተ​ፈ​ተ​ለም ከጥሩ በፍታ በጥ​ልፍ አሠ​ራር የተ​ሠራ መጋ​ረጃ አደ​ረጉ፤</verse>
				<verse number="38">አም​ስ​ቱ​ንም ምሰ​ሶ​ዎች፥ ኵላ​ቦ​ቻ​ቸ​ው​ንም አደ​ረጉ፤ ጉል​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ዘን​ጎ​ቻ​ቸ​ው​ንም በወ​ርቅ ለበ​ጡ​አ​ቸው፤ አም​ስ​ቱም እግ​ሮ​ቻ​ቸው የናስ ነበሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="37">
				<verse number="1">ባስ​ል​ኤ​ልም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ታቦ​ትን ሠራ፤ ርዝ​መቷ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወር​ድዋ አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመ​ቷም አንድ ክንድ ተኩል ነበረ።</verse>
				<verse number="2">በው​ስ​ጥ​ዋም፥ በው​ጭ​ዋም በጥሩ ወርቅ ለበ​ጣት፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም የወ​ርቅ አክ​ሊል አደ​ረ​ገ​ላት።</verse>
				<verse number="3">አራት የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶ​ችም አደ​ረ​ገ​ላት፤ እነ​ር​ሱ​ንም በአ​ራቱ እግ​ሮ​ችዋ ላይ አኖረ። በአ​ንድ ወገን ሁለት ቀለ​በ​ቶች፥ በሌ​ላ​ውም ወገን ሁለት ቀለ​በ​ቶች ሆኑ።</verse>
				<verse number="4">መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ሠራ፤ በወ​ር​ቅም ለበ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">ታቦ​ቷ​ንም ለመ​ሸ​ከም በታ​ቦቷ አጠ​ገብ ባሉት አራት ቀለ​በ​ቶች መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋን አገባ።</verse>
				<verse number="6">ከጥሩ ወር​ቅም ርዝ​መቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስ​ር​የት መክ​ደኛ ሠራ​ላት።</verse>
				<verse number="7">ሁለት ኪሩ​ቤ​ል​ንም ከተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ወርቅ ሠራ፤ በስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ላይ በሁ​ለት ወገን አደ​ረ​ጋ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">ከስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ጋር አን​ዱን ኪሩብ በአ​ንድ ወገን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ኪሩብ በሌላ ወገን በዚ​ህና በዚያ ሁለ​ቱን ኪሩ​ቤል ከስ​ር​የት መክ​ደ​ኛው በላይ ሠራ፤</verse>
				<verse number="9">ኪሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ወደ ላይ የዘ​ረጉ ሆኑ፥ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው ሸፈኑ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተያዩ፤ የኪ​ሩ​ቤ​ልም ፊቶ​ቻ​ቸው ወደ መክ​ደ​ኛው ተመ​ለ​ከቱ።</verse>
				<verse number="10">ርዝ​መቱ ሁለት ክንድ፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ፥ ቁመ​ቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆ​ነ​ውን ገበታ ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ሠራ።</verse>
				<verse number="11">በጥ​ሩም ወርቅ ለበ​ጠው፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም የወ​ርቅ አክ​ሊል አደ​ረ​ገ​ለት።</verse>
				<verse number="12">በዙ​ሪ​ያ​ውም አንድ ጋት የሚ​ያ​ህል ክፈፍ አደ​ረ​ገ​ለት፤ የወ​ር​ቅም አክ​ሊል በክ​ፈፉ ዙሪያ አደ​ረ​ገ​ለት።</verse>
				<verse number="13">አራ​ትም የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች አደ​ረ​ገ​ለት፤ ቀለ​በ​ቶ​ቹ​ንም አራቱ እግ​ሮቹ ባሉ​በት በአ​ራቱ ማዕ​ዘ​ኖች አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="14">ገበ​ታ​ው​ንም ለመ​ሸ​ከም መሎ​ጊ​ያ​ዎቹ እን​ዲ​ሰ​ኩ​ባ​ቸው ቀለ​በ​ቶች በክ​ፈፉ አቅ​ራ​ቢያ ነበሩ።</verse>
				<verse number="15">ገበ​ታ​ው​ንም ይሸ​ከ​ሙ​ባ​ቸው ዘንድ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹን ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ሠርቶ በወ​ርቅ ለበ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">ለማ​ፍ​ሰ​ሻም ይሆኑ ዘንድ በገ​በ​ታው ላይ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ዕቃ​ዎች፥ ወጭ​ቶ​ቹ​ንና ጭል​ፋ​ዎ​ቹን፥ ጽዋ​ዎ​ቹ​ንም፥ መቅ​ጃ​ዎ​ቹ​ንም ከጥሩ ወርቅ አደ​ረ​ጋ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">መቅ​ረ​ዝ​ዋ​ንም ከጥሩ ወርቅ አደ​ረገ፤ መቅ​ረ​ዝ​ዋ​ንም ከእ​ግ​ር​ዋና ከአ​ገ​ዳዋ ጋር በተ​ቀ​ረጸ ሥራ አደ​ረገ፤ ጽዋ​ዎ​ች​ዋን፥ ጕብ​ጕ​ቦ​ች​ዋን፥ አበ​ቦ​ች​ዋን ከዚ​ያው በአ​ን​ድ​ነት አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="18">በስ​ተ​ጎ​ንዋ ስድ​ስት ቅር​ን​ጫ​ፎች ወጡ​ላት፤ ሦስቱ የመ​ቅ​ረ​ዝዋ ቅር​ን​ጫ​ፎች በአ​ንድ ወገን፥ ሦስ​ቱም የመ​ቅ​ረ​ዝዋ ቅር​ን​ጫ​ፎች በሁ​ለ​ተ​ኛው ወገን ወጡ።</verse>
				<verse number="19">በአ​ን​ደ​ኛው ቅር​ን​ጫፍ ጕብ​ጕ​ቡ​ንና አበ​ባ​ውን፥ ሦስ​ትም የለ​ውዝ አበባ የሚ​መ​ስ​ሉ​ትን ጽዋ​ዎች፥ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቅር​ን​ጫፍ ጕብ​ጕ​ቡ​ንና አበ​ባ​ውን፥ ሦስ​ትም የለ​ውዝ አበባ የሚ​መ​ስ​ሉ​ትን ጽዋ​ዎች፥ እን​ዲ​ሁም ከመ​ቅ​ረ​ዝዋ ለወጡ ለስ​ድ​ስቱ ቅር​ን​ጫ​ፎች አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="20">በመ​ቅ​ረ​ዝ​ዋም ጕብ​ጕ​ቦ​ች​ዋ​ንና አበ​ቦ​ች​ዋን፥ አራ​ትም የለ​ውዝ አበባ የሚ​መ​ስ​ሉ​ትን ጽዋ​ዎች አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="21">ከመ​ቅ​ረ​ዝዋ ለወጡ ለስ​ድ​ስት ቅር​ን​ጫ​ፎች ከሁ​ለት ቅር​ን​ጫ​ፎች በታች አንድ ሆኖ የተ​ሠራ አንድ ጕብ​ጕብ፥ ከሁ​ለ​ትም ቅር​ን​ጫ​ፎች በታች አንድ ሆኖ የተ​ሠራ አንድ ጕብ​ጕብ፥ ደግሞ ከሁ​ለት ቅር​ን​ጫ​ፎች በታች አንድ ሆኖ የተ​ሠራ አንድ ጕብ​ጕብ ነበረ።</verse>
				<verse number="22">ጕብ​ጕ​ቦ​ች​ዋና ቅር​ን​ጫ​ፎ​ችዋ ከእ​ርሱ ጋር አንድ ነበሩ፤ ሁሉም አንድ ሆኖ ከተ​ቀ​ረጸ ከጥሩ ወርቅ ተሠ​ርቶ ነበር።</verse>
				<verse number="23">ሰባ​ቱ​ንም መብ​ራ​ቶ​ች​ዋን መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ የኵ​ስ​ታሪ ማድ​ረ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም ከጥሩ ወርቅ ሠራ።</verse>
				<verse number="24">መቅ​ረ​ዙ​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ከአ​ንድ መክ​ሊት ጥሩ ወርቅ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="25">የዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያ​ንም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ሠራ፤ ርዝ​መቱ አንድ ክንድ፥ ስፋቱ አንድ ክንድ፤ አራት ማዕ​ዘን ነበር፤ ከፍ​ታ​ውም ሁለት ክንድ ነበር፤ ቀን​ዶ​ቹም ከእ​ርሱ ጋር በአ​ን​ድ​ነት የተ​ሠሩ ነበሩ።</verse>
				<verse number="26">ላይ​ኛ​ው​ንና የግ​ድ​ግ​ዳ​ው​ንም ዙሪያ፥ ቀን​ዶ​ቹ​ንም በጥሩ ወርቅ ለበ​ጠው፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም የወ​ርቅ ክፈፍ አደ​ረ​ገ​በት።</verse>
				<verse number="27">ከክ​ፈ​ፉም በታች ሁለት የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች አደ​ረ​ገ​በት፤ በዚ​ህና በዚያ በሁ​ለ​ቱም ጎን አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ ለመ​ሸ​ከ​ምም የመ​ሎ​ጊ​ያ​ዎች መግ​ቢያ ነበሩ።</verse>
				<verse number="28">መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት አደ​ረገ፤ በወ​ር​ቅም ለበ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="29">የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም የቅ​ብ​ዐ​ቱን ዘይት፥ ጥሩ​ው​ንም የጣ​ፋጭ ሽቱ ዕጣን በቀ​ማሚ ብል​ሃት እንደ ተሠራ አደ​ረገ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="38">
				<verse number="1">ርዝ​መቱ አም​ስት ክንድ፥ ወር​ዱም አም​ስት ክንድ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆን መሠ​ዊ​ያን ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት አደ​ረገ፤ አራት ማዕ​ዘ​ንም ነበረ፤ ከፍ​ታ​ውም ሦስት ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="2">ቀን​ዶ​ቹ​ንም በአ​ራቱ ማዕ​ዘን አደ​ረ​ገ​በት፤ ቀን​ዶ​ቹም ከእ​ርሱ ጋር ሥረ-ወጥ ነበሩ፤ በና​ስም ለበ​ጠው።</verse>
				<verse number="3">የመ​ሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ዕቃ ሁሉ፥ ምን​ቸ​ቶ​ቹ​ንም፥ መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንም፥ ሜን​ጦ​ዎ​ቹ​ንም፥ የእ​ሳት ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረገ፤ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ከናስ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="4">እንደ መረብ ሆኖም የተ​ሠራ የናስ መከታ ለመ​ሠ​ዊ​ያው አደ​ረገ፤ መከ​ታ​ውም እስከ መሠ​ዊ​ያው እኩ​ሌታ ይደ​ርስ ዘንድ በመ​ሠ​ዊ​ያው በሚ​ዞ​ረው በደ​ረ​ጃው ታች አደ​ረ​ገው።</verse>
				<verse number="5">ለና​ሱም መከታ ለአ​ራቱ ማዕ​ዘን የመ​ሎ​ጊ​ያ​ዎች ስፍራ ይሆኑ ዘንድ አራት ቀለ​በ​ቶች አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="6">መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ሠራ፤ በና​ስም ለበ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">ይሸ​ከ​ሙ​ባ​ቸ​ውም ዘንድ በመ​ሠ​ዊ​ያው ጎን ባሉት ቀለ​በ​ቶች ውስጥ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹን አገባ፤ ከሳ​ን​ቃ​ዎ​ቹም ሠርቶ ክፍት አደ​ረ​ገው።</verse>
				<verse number="8">የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንና መቀ​መ​ጫ​ው​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ከሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ከሴ​ቶች መስ​ተ​ዋት ከናስ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="9">ለድ​ን​ኳ​ኑም በደ​ቡብ በኩል በስ​ተ​ቀኝ አደ​ባ​ባይ አደ​ረገ፤ የአ​ደ​ባ​ባዩ መጋ​ረ​ጃም ከተ​ፈ​ተለ ጥሩ በፍታ የተ​ሠራ ርዝ​መቱ መቶ ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="10">ሃያ​ው​ንም ምሰ​ሶ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንና ሃያ​ውን እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ከናስ አደ​ረገ፤ የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹ​ንም ኵላ​ቦ​ችና ዘን​ጎች ከብር አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="11">በሰ​ሜ​ኑም ወገን መቶ ክንድ ርዝ​መት ያላ​ቸ​ውን መጋ​ረ​ጃ​ዎች፥ ከና​ስም የተ​ሠሩ ሃያ ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ንና ሃያ እግ​ሮ​ችን፥ ለም​ሰ​ሶ​ዎ​ችም የብር ኵላ​ቦ​ች​ንና ዘን​ጎ​ችን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="12">በም​ዕ​ራ​ብም ወገን አምሳ ክንድ ርዝ​መት ያላ​ቸ​ውን መጋ​ረ​ጃ​ዎች፥ ዐሥ​ሩ​ንም ምሰ​ሶ​ዎች፥ ዐሥ​ሩ​ንም የናስ እግ​ሮች፥ ለም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹም የብር ኵላ​ቦ​ች​ንና ዘን​ጎ​ችን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="13">በም​ሥ​ራ​ቅም ወገን አምሳ ክንድ ርዝ​መት ያላ​ቸ​ውን መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="14">በአ​ዜብ በኩል የመ​ጋ​ረ​ጃ​ዎች ርዝ​መት ዐሥራ አም​ስት ክንድ፥ ምሰ​ሶ​ዎ​ቹም ሦስት፥ እግ​ሮ​ቹም ሦስት ነበሩ።</verse>
				<verse number="15">እን​ዲ​ሁም በሁ​ለ​ተ​ኛው ወገን በአ​ደ​ባ​ባዩ ደጅ በዚ​ህና በዚያ ዐሥራ አም​ስት ክንድ ርዝ​መት ያላ​ቸው መጋ​ረ​ጃ​ዎች፥ ሦስ​ትም ምሰ​ሶ​ዎች፥ ሦስ​ትም እግ​ሮች ነበሩ።</verse>
				<verse number="16">በአ​ደ​ባ​ባዩ ዙሪያ ያሉ መጋ​ረ​ጃ​ዎች ሁሉ ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍታ ተሠ​ር​ተው ነበር።</verse>
				<verse number="17">የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹም እግ​ሮች የናስ፥ የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹም ኵላ​ቦ​ችና ዘን​ጎች የብር ነበሩ፤ የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹም ጕል​ላ​ቶች በብር ተለ​ብ​ጠው ነበር፤ በአ​ደ​ባ​ባዩ ላሉ ምሰ​ሶ​ዎች ሁሉ የብር ዘን​ጎች ነበ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">የአ​ደ​ባ​ባ​ዩም ደጅ መጋ​ረጃ ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ ፥ ከጥ​ሩም በፍታ በጥ​ልፍ አሠ​ራር የተ​ሠራ ነበረ፤ ርዝ​መቱ ሃያ ክንድ ነበረ፤ ቁመ​ቱም እንደ አደ​ባ​ባዩ መጋ​ረ​ጃ​ዎች አም​ስት ክንድ ነበረ፤</verse>
				<verse number="19">ከናስ የተ​ሠሩ ምሰ​ሶ​ዎ​ቹም አራት፥ እግ​ሮ​ቹም አራት ነበሩ፤ ኵላ​ቦ​ቹም የብር ነበሩ፤ ጕል​ላ​ቶ​ቹና ዘን​ጎ​ቹም በብር ተለ​ብ​ጠው ነበር።</verse>
				<verse number="20">የድ​ን​ኳ​ኑም ካስ​ማ​ዎች፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ያሉ የአ​ደ​ባ​ባዩ ካስ​ማ​ዎች የናስ ነበሩ።</verse>
				<verse number="21">በካ​ህኑ በአ​ሮን ልጅ በይ​ታ​ምር እጅ የሌ​ዋ​ው​ያን ተል​እኮ ይሆን ዘንድ ሙሴ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ደ​ታ​ዘዘ የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥር​ዐት ይህ ነው።</verse>
				<verse number="22">ከይ​ሁዳ ነገ​ድም የሆነ የሆር የልጅ ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስ​ል​ኤል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="23">ከእ​ር​ሱም ጋር ከዳን ነገድ የሆነ የአ​ሒ​ሳ​ሚክ ልጅ ኤል​ያብ ነበረ፤ እር​ሱም በሰ​ማ​ያዊ፥ በሐ​ም​ራዊ፥ በቀ​ይም ግምጃ፥ በጥሩ በፍታ የሽ​መና ሥራ ይሠራ ዘንድ የቅ​ርጽ፥ የሽ​መ​ናና የጥ​ልፍ ሥራ አለቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="24">የተ​ሰ​ጠው ወርቅ ሁሉ፥ ለድ​ን​ኳኑ ሥራ ሁሉ የተ​ደ​ረ​ገው ወርቅ፥ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን ሃያ ዘጠኝ መክ​ሊት ሰባት መቶ ሠሳሳ ሰቅል ነበረ።</verse>
				<verse number="25">በማ​ኅ​በ​ሩም ከሚ​ቈ​ጠ​ሩት የተ​ገኘ ብር፥ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን፥ መቶ መክ​ሊ​ትና አንድ ሺህ ሰባት መቶ ከሰባ አም​ስት ሰቅል ነበረ።</verse>
				<verse number="26">እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሰው አንድ አንድ ዲድ​ር​ክም አዋጣ፤ አንድ ዲድ​ር​ክም እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን የሰ​ቅል ግማሽ ነው፤ ይህም የተ​ዋ​ጣው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ከተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ ስድ​ስት መቶ ሦስት ሺህ አም​ስት መቶ አምሳ ሰዎች ነበረ።</verse>
				<verse number="27">መቶ​ውም የብር መክ​ሊት ለድ​ን​ኳኑ ምሰ​ሶ​ዎች እግ​ሮ​ችና ለመ​ጋ​ረ​ጃው ምሰ​ሶ​ዎች እግ​ሮች ተደ​ረገ፤ መቶ​ውም መክ​ሊት ለመቶ እግ​ሮች፤ ለአ​ንድ እግ​ርም አንድ መክ​ሊት ሆነ።</verse>
				<verse number="28">ከሺህ ሰባት መቶ ሰባ አም​ስት ሰቅል የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹን ኵላ​ቦ​ችና ዘን​ጎች አደ​ረገ፤ የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹ​ንም ጕል​ላ​ቶች ለበጠ።</verse>
				<verse number="29">የተ​ሰ​ጠ​ውም ናስ አራት መቶ ሰባ መክ​ሊ​ትና ሁለት ሺህ አራት መቶ ሰቅል ነበረ።</verse>
				<verse number="30">ከእ​ር​ሱም የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ደጃፍ እግ​ሮች፥ የና​ሱ​ንም መሠ​ዊያ፥ ለእ​ር​ሱም የሆ​ነ​ውን የና​ሱን መከታ፥ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ዕቃ ሁሉ፥</verse>
				<verse number="31">በአ​ደ​ባ​ባዩ ዙሪያ ያሉ​ትን እግ​ሮች፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ደጃፍ እግ​ሮች፥ የድ​ን​ኳ​ኑ​ንም ካስ​ማ​ዎች ሁሉ፥ በአ​ደ​ባ​ባዩ ዙሪ​ያም ያሉ​ትን ካስ​ማ​ዎች ሁሉ አደ​ረገ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="39">
				<verse number="1">የቀ​ረ​ውም የመባ ወርቅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይሠ​ሩ​በት ዘንድ ንዋየ ቅድ​ሳት ሆኖ ተሠራ። ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም ከቀይ ግም​ጃም ለመ​ቅ​ደሱ አገ​ል​ግ​ሎት ልብ​ሶ​ችን ሠሩ፤ እን​ዲ​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ለአ​ሮን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ልብስ ሠሩ።</verse>
				<verse number="2">ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ው​ንም ከወ​ርቅ፥ ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀይ ግም​ጃም፥ ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍ​ታም ሠሩ።</verse>
				<verse number="3">ወር​ቁ​ንም ቀጥ​ቅ​ጠው እንደ ቅጠል ስስ አደ​ረ​ጉት፤ እንደ ፈት​ልም ቈረ​ጡት። ብልህ ሠራ​ተ​ኛም እን​ደ​ሚ​ሠራ ሰማ​ያዊ፥ ሐም​ራ​ዊም፥ ቀይ ግም​ጃም፥ የተ​ፈ​ተ​ለም ጥሩ በፍታ፥ ከእ​ርሱ ጠለፉ።</verse>
				<verse number="4">ሁለቱ ወገን እን​ዲ​ጋ​ጠሙ፥ በሁ​ለት ጫን​ቃ​ዎች ላይ የሚ​ጋ​ጠም ልብሰ መት​ከፍ ሠሩ።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው እር​ስ​ዋን ከወ​ርቅ፥ ከሰ​ማ​ያ​ዊና ከሐ​ም​ራዊ፥ ከቀይ ግም​ጃም፥ ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍ​ታም እንደ ሠሩ የል​ብሰ መት​ከ​ፉን ቋድ ሠሩ።</verse>
				<verse number="6">በወ​ርቅ ፈርጥ የተ​ያዙ የመ​ረ​ግድ ድን​ጋ​ዮች ሠር​ተው እንደ ማኅ​ተም ቅርጽ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ስም ቀረ​ጹ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የመ​ታ​ሰ​ቢያ ድን​ጋ​ዮች ይሆኑ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው፥ በል​ብሰ መት​ከፉ ጫን​ቃ​ዎች ላይ አደ​ረ​ጓ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውን ብልህ ሠራ​ተኛ እን​ደ​ሚ​ሠራ፥ እንደ ልብሰ መት​ከፉ አሠ​ራር ከወ​ር​ቅና ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ፥ ከተ​ፈ​ት​ለም ከጥሩ በፍታ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="9">አራት ማዕ​ዘ​ንም ነበረ፤ ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውም ድርብ ነበር፤ ርዝ​መቱ ስን​ዝር፥ ወር​ዱም ስን​ዝር፥ ድር​ብም ነበረ።</verse>
				<verse number="10">ዕን​ቍ​ዎ​ቹ​ንም በአ​ራት ተራ አደ​ረ​ጉ​በት፤ በፊ​ተ​ኛ​ውም ተራ ሰር​ድ​ዮን፥ ቶጳ​ዝ​ዮን፥ መረ​ግድ፤</verse>
				<verse number="11">በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ተራ በሉር፥ ሰን​ፔር፥ ኢያ​ሰ​ጲድ፤</verse>
				<verse number="12">በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ተራ ለግ​ር​ዮን፥አካ​ጥስ፥ አሜ​ቴ​ስ​ጢ​ኖስ፤</verse>
				<verse number="13">በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ተራ ወር​ቃማ ድን​ጋይ፥ ቢረሌ፥ ሶም፤ ዙሪ​ያ​ውም በወ​ርቅ ፈርጥ ተደ​ረገ።</verse>
				<verse number="14">የዕ​ን​ቍ​ዎ​ችም ድን​ጋ​ዮች እንደ ዐሥራ ሁለቱ እንደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ስሞች ነበሩ፤ በየ​ስ​ማ​ቸ​ውም ማተ​ሚያ እን​ደ​ሚ​ቀ​ረጽ ተቀ​ረጹ፤ ስለ ዐሥራ ሁለ​ቱም ነገ​ዶች ነበሩ።</verse>
				<verse number="15">ለል​ብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውም የተ​ጐ​ነ​ጐ​ኑ​ትን ድሪ​ዎች እንደ ገመድ አድ​ር​ገው ከጥሩ ወርቅ ሠሩ።</verse>
				<verse number="16">ሁለ​ትም የወ​ርቅ ፈር​ጦች፥ ሁለ​ትም የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች ሠሩ፤ ሁለ​ቱ​ንም የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች በል​ብሰ እን​ግ​ድ​ዓው በሁ​ለቱ ወገን አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="17">ሁለ​ቱ​ንም የተ​ጐ​ነ​ጐ​ኑ​ትን የወ​ርቅ ድሪ​ዎች በል​ብሰ እን​ግ​ድ​ዓው በሁ​ለቱ ወገ​ኖች ወዳ​ሉት ወደ ሁለቱ ቀለ​በ​ቶች አገቡ።</verse>
				<verse number="18">የሁ​ለ​ቱ​ንም ድሪ​ዎች ጫፎች በሁ​ለቱ ፈር​ጦች ውስጥ አግ​ብ​ተው በል​ብሰ መት​ከፉ ጫን​ቃ​ዎች ላይ ፊት ለፊት አደ​ረ​ጓ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">ሁለ​ቱ​ንም የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች ሠሩ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ከል​ብሰ መት​ከፉ ፊት ለፊት ባለው በል​ብሰ እን​ግ​ድ​ዓው በሁ​ለቱ ጫፎች ላይ አደ​ረ​ጓ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">ደግ​ሞም ሁለት የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች ሠሩ፤ በመ​ደ​ረ​ቢ​ያው ፊት፥ ከጫ​ን​ቃ​ዎች በታች፥ በብ​ል​ሃት ከተ​ጠ​ለፈ ከመ​ደ​ረ​ቢ​ያው ቋድ በላይ፥ በመ​ያ​ዣው አጠ​ገብ አደ​ረ​ጓ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓው በብ​ል​ሃት ከተ​ጠ​ለ​ፈው ከመ​ደ​ረ​ቢ​ያው ቋድ በላይ እን​ዲ​ሆን፥ ከመ​ደ​ረ​ቢ​ያው እን​ዳ​ይ​ለይ ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውን ከቀ​ለ​በ​ቶቹ ጋር ወደ መደ​ረ​ቢ​ያው ቀለ​በ​ቶች በሰ​ማ​ያዊ ፈትል አሰ​ሩት።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው፥ የመ​ደ​ረ​ቢ​ያ​ውን ቀሚስ ሞላ​ውን በሸ​ማኔ ሥራ ሰማ​ያዊ አድ​ርጎ ሠራው።</verse>
				<verse number="23">በቀ​ሚ​ሱም መካ​ከል አን​ገ​ትጌ ነበረ፤ እን​ዳ​ይ​ቀ​ደ​ድም በአ​ን​ገ​ት​ጌው ዙሪያ በአ​ን​ድ​ነት የተ​ያ​ያዘ ጥልፍ ነበረ።</verse>
				<verse number="24">በቀ​ሚ​ሱም ታችኛ ዘርፍ ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀይ ግም​ጃም፥ ከተ​ፈ​ተለ በፍ​ታም የአ​በቡ ሮማ​ኖ​ችን አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="25">ከጥሩ ወር​ቅም ሻኵ​ራ​ዎ​ችን ሠሩ፤ ሻኵ​ራ​ዎ​ቹ​ንም ከሮ​ማ​ኖች መካ​ከል በቀ​ሚሱ ዘርፍ ዙሪያ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="26">በቀ​ሚሱ ዘርፍ ዙሪያ ሻኵ​ራ​ንና ሮማ​ንን፥ ሻኩ​ራ​ንና ሮማ​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ለማ​ገ​ል​ገል አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="27">እንደ ሸማኔ ሥራ ከጥሩ በፍታ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ እጀ ጠባ​ቦ​ችን፥ ከጥሩ በፍ​ታም አክ​ሊ​ልን፥</verse>
				<verse number="28">ከጥሩ በፍ​ታም መል​ካ​ሞ​ቹን ቆቦች፥ ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍ​ታም የእ​ግር ሱሪ​ዎ​ችን፥</verse>
				<verse number="29">ከተ​ፈ​ተ​ለም ከጥሩ በፍታ፥ ከሰ​ማ​ያ​ዊም፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ በጥ​ልፍ አሠ​ራር የተ​ሠራ መታ​ጠ​ቂ​ያ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="30">ከጥሩ ወርቅ የተ​ለየ የወ​ርቅ ቅጠል ሠሩ፤ በእ​ር​ሱም እንደ ማኅ​ተም ቅርጽ አድ​ር​ገው፥ “ቅድ​ስና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” የሚል ጻፉ​በት።</verse>
				<verse number="31">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው፥ በአ​ክ​ሊሉ ላይ ያን​ጠ​ለ​ጥ​ሉት ዘንድ ሰማ​ያ​ዊ​ውን ፈትል አሰ​ሩ​በት።</verse>
				<verse number="32">እን​ዲ​ሁም የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥራ ሁሉ ተፈ​ጸመ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አደ​ረጉ፤ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="33">ድን​ኳ​ኑ​ንም፥ መደ​ረ​ቢ​ያ​ው​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ወደ ሙሴ አመጡ፤ መያ​ዣ​ዎ​ቹን፥ ሳን​ቆ​ቹን፥ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹን፥ ምሰ​ሶ​ዎ​ቹን፥ እግ​ሮ​ቹ​ንም፤</verse>
				<verse number="34">ከቀይ አውራ በግ ቍር​በ​ትም የተ​ሠራ መደ​ረ​ቢያ፥ ከአ​ቆ​ስጣ ቁር​በ​ትም የተ​ሠራ መደ​ረ​ቢያ፥ የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ው​ንም መጋ​ረጃ፥</verse>
				<verse number="35">የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ታቦት፥ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም፤</verse>
				<verse number="36">ገበ​ታ​ው​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ ኅብ​ስተ ገጹ​ንም፤</verse>
				<verse number="37">ጥሩ​ው​ንም መቅ​ረዝ፥ መብ​ራ​ቶ​ቹ​ንም፥ በተራ የሚ​ሆ​ኑ​ት​ንም ቀን​ዲ​ሎች፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ የመ​ብ​ራ​ቱ​ንም ዘይት፤</verse>
				<verse number="38">የወ​ር​ቁ​ንም መሠ​ዊያ፥ የቅ​ብ​ዐ​ቱ​ንም ዘይት፥ ጣፋ​ጩ​ንም ዕጣን፥ የድ​ን​ኳ​ኑ​ንም ደጃፍ መጋ​ረጃ፤</verse>
				<verse number="39">የና​ሱ​ንም መሠ​ዊያ፥ የና​ሱ​ንም መከታ፥ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንም፥ መቀ​መ​ጫ​ው​ንም፤</verse>
				<verse number="40">የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም መጋ​ረ​ጆች፥ ምሰ​ሶ​ዎ​ቹ​ንም፥ እግ​ሮ​ቹ​ንም፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ደጃፍ መጋ​ረጃ፥ አው​ታ​ሮ​ቹ​ንም፥ ካስ​ማ​ዎ​ቹ​ንም፥ ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ማገ​ል​ገያ የሚ​ሆ​ኑ​ትን ዕቃ​ዎች ሁሉ፤</verse>
				<verse number="41">በመ​ቅ​ደስ ውስጥ ለማ​ገ​ል​ገል በብ​ል​ሃት የተ​ሠ​ሩ​ትን ልብ​ሶች፥ በክ​ህ​ነ​ትም ያገ​ለ​ግ​ሉ​በት ዘንድ የተ​ቀ​ደ​ሱ​ትን የካ​ህ​ኑን የአ​ሮ​ንን ልብ​ሶች፥ የል​ጆ​ቹ​ንም ልብ​ሶች አመጡ።</verse>
				<verse number="42">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ ሁሉ እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሥራ​ውን ሁሉ ሠሩ።</verse>
				<verse number="43">ሙሴም ሥራ​ውን ሁሉ አየ፤ እነ​ሆም፥ አድ​ር​ገ​ውት ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ አድ​ር​ገ​ውት ነበር፤ ሙሴም ባረ​ካ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="40">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በፊ​ተ​ኛው ቀን የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ትተ​ክ​ላ​ለህ።</verse>
				<verse number="3">በእ​ር​ሱም ውስጥ የም​ስ​ክ​ሩን ታቦት ታኖ​ራ​ለህ፤ ታቦ​ቱ​ንም በመ​ጋ​ረጃ ትጋ​ር​ዳ​ለህ።</verse>
				<verse number="4">ገበ​ታ​ው​ንም ታገ​ባ​ለህ፤ በሥ​ር​ዐ​ቱም ታሰ​ና​ዳ​ዋ​ለህ፤ መቅ​ረ​ዙ​ንም አግ​ብ​ተህ ቀን​ዲ​ሎ​ቹን ትለ​ኵ​ሳ​ለህ።</verse>
				<verse number="5">የወ​ር​ቁ​ንም ማዕ​ጠ​ንት በም​ስ​ክሩ ታቦት ፊት ታኖ​ራ​ለህ፤ በድ​ን​ኳ​ኑም ደጃፍ ፊት መጋ​ረ​ጃ​ውን ትጋ​ር​ዳ​ለህ።</verse>
				<verse number="6">ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ው​ንም መሠ​ዊያ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ ፊት ታኖ​ረ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="7">የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳ​ንና በመ​ሠ​ዊ​ያው መካ​ከል ታኖ​ረ​ዋ​ለህ፤ በው​ስ​ጡም ውኃ ትጨ​ም​ር​በ​ታ​ለህ።</verse>
				<verse number="8">በዙ​ሪ​ያ​ውም አደ​ባ​ባ​ዩን ትሠ​ራ​ለህ፤ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ደጃፍ መጋ​ረጃ ትዘ​ረ​ጋ​ለህ።</verse>
				<verse number="9">የቅ​ብ​ዐ​ቱ​ንም ዘይት ወስ​ደህ ድን​ኳ​ኑን፥ በው​ስ​ጥ​ዋም ያለ​ውን ሁሉ ትቀ​ባ​ለህ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ዕቃ​ዋ​ንም ሁሉ ትቀ​ድ​ሳ​ለህ፤ ቅድ​ስ​ትም ትሆ​ና​ለች።</verse>
				<verse number="10">ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትም የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊያ፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ትቀ​ባ​ዋ​ለህ፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ትቀ​ድ​ሳ​ለህ፤ መሠ​ዊ​ያ​ውም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="11">የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንና መቀ​መ​ጫ​ው​ንም ቀብ​ተህ ትቀ​ድ​ሳ​ለህ።</verse>
				<verse number="12">አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹ​ንም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አቅ​ር​በህ በውኃ ታጥ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="13">ለአ​ሮ​ንም የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ልብስ ታለ​ብ​ሰ​ዋ​ለህ፤ ትቀ​ባ​ዋ​ለህ፤ ትቀ​ድ​ሰ​ው​ማ​ለህ፤ ካህ​ንም ይሆ​ነ​ኛል።</verse>
				<verse number="14">ልጆ​ቹ​ንም ታቀ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ቀሚ​ሳ​ቸ​ው​ንም ታለ​ብ​ሳ​ቸ​ዋ​ለህ፤</verse>
				<verse number="15">አባ​ታ​ቸ​ውን እንደ ቀባህ ትቀ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ካህ​ና​ትም ይሆ​ኑ​ኛል። ይህም ለልጅ ልጃ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም የክ​ህ​ነት ቅብ​ዐት ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል።”</verse>
				<verse number="16">ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረገ፤ እን​ዲ​ሁም አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="17">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት በፊ​ተ​ኛው ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ድን​ኳ​ንዋ ተተ​ከ​ለች።</verse>
				<verse number="18">ሙሴም ድን​ኳ​ን​ዋን ተከለ፤ እግ​ሮ​ች​ዋ​ንም አኖረ፤ ሳን​ቆ​ች​ዋ​ንም አቆመ፤ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም አደ​ረ​ገ​ባ​ቸው፤ ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ዋ​ንም አቆመ።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው መጋ​ረ​ጃ​ውን በድ​ን​ኳኑ ላይ ዘረ​ጋው፤ የድ​ን​ኳ​ኑ​ንም መደ​ረ​ቢያ በላዩ አደ​ረ​ገ​በት።</verse>
				<verse number="20">ሙሴም ጽላ​ቱን ወስዶ በታ​ቦቱ ውስጥ አኖ​ረው፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም በታ​ቦቱ ቀለ​በ​ቶች ውስጥ አደ​ረገ፤ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በታ​ቦቱ ላይ አኖ​ረው።</verse>
				<verse number="21">ታቦ​ቷ​ንም ወደ ድን​ኳኑ አገባ፥ የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ው​ንም መጋ​ረጃ አድ​ርጎ የም​ስ​ክ​ሩን ታቦት ሸፈነ።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ገበ​ታ​ውን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ፥ ከመ​ጋ​ረ​ጃው ውጭ በድ​ን​ኳኑ በመ​ስዕ በኩል አኖ​ረው፤</verse>
				<verse number="23">ኅብ​ስተ ገጹ​ንም በላዩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አሰ​ናዳ።</verse>
				<verse number="24">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው መቅ​ረ​ዙን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ፥ በገ​በ​ታ​ውም ፊት ለፊት፥ በድ​ን​ኳኑ በአ​ዜብ በኩል አኖረ፤</verse>
				<verse number="25">ቀን​ዲ​ሎ​ቹ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አበራ።</verse>
				<verse number="26">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው የወ​ር​ቁን ማዕ​ጠ​ንት በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በመ​ጋ​ረ​ጃው ፊት አኖረ።</verse>
				<verse number="27">የአ​ዘ​ጋ​ጀ​ው​ንም ዕጣን ዐጠ​ነ​በት።</verse>
				<verse number="28">ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አዘ​ዘው በድ​ን​ኳኑ ደጅ ፊት መጋ​ረ​ጃ​ውን ዘረጋ።</verse>
				<verse number="29">ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊ​ያም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ አኖረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው በላዩ መሥ​ዋ​ዕ​ቱ​ንና ቍር​ባ​ኑን አቀ​ረበ።</verse>
				<verse number="30">የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ው​ንም ሰን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳ​ንና በመ​ሠ​ዊ​ያው መካ​ከል አኖረ፤ ለመ​ታ​ጠ​ቢ​ያም ውኃን ጨመ​ረ​በት።</verse>
				<verse number="31">በእ​ር​ሱም ሙሴና አሮን፥ ልጆ​ቹም እጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ታጠቡ፤</verse>
				<verse number="32">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን በገቡ ጊዜ፥ ወደ መሠ​ዊ​ያ​ውም በቀ​ረቡ ጊዜ ይታ​ጠቡ ነበር።</verse>
				<verse number="33">በድ​ን​ኳ​ኑና በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ዙሪያ አደ​ባ​ባ​ዩን ሠራ፤ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ደጃፍ መጋ​ረጃ ዘረጋ። እን​ዲ​ሁም ሙሴ ሥራ​ውን ፈጸመ።</verse>
				<verse number="34">ደመ​ና​ውም የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ከደነ፤ ድን​ኳ​ን​ዋም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ተሞ​ላች።</verse>
				<verse number="35">ደመ​ና​ውም በላዩ ስለ​ነ​በር ድን​ኳ​ኑም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ስለ ተሞላ ሙሴ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ይገባ ዘንድ አል​ቻ​ለም።</verse>
				<verse number="36">ደመ​ና​ውም ከድ​ን​ኳኑ በተ​ነሣ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው ይጓዙ ነበር።</verse>
				<verse number="37">ደመ​ናው ካል​ተ​ነሣ ግን ደመ​ናው እስ​ከ​ሚ​ነ​ሣ​በት ቀን ድረስ አይ​ጓ​ዙም ነበር።</verse>
				<verse number="38">ደመና በቀን በድ​ን​ኳኑ ላይ ነበ​ርና፥ እሳ​ቱም በሚ​ጓ​ዙ​በት ሁሉ በሌ​ሊት በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት በእ​ር​ስዋ ላይ ነበ​ርና።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="3">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ሙሴን ጠርቶ እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ከእ​ና​ንተ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ የሚ​ያ​ቀ​ርብ ሰው ቢኖር መባ​ች​ሁን ከእ​ን​ስሳ ወገን ከላ​ሞች ወይም ከበ​ጎች ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="3">“መባ​ውም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ከላ​ሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባ​ቱን ያቀ​ር​ባል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተቀ​ባ​ይ​ነት እን​ዲ​ኖ​ረው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል።</verse>
				<verse number="4">ተቀ​ባ​ይ​ነት ይኖ​ረው ዘንድ ስለ እር​ሱም ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለት ዘንድ እጁን በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ራስ ላይ ይጭ​ናል።</verse>
				<verse number="5">በሬ​ው​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ደ​ዋል፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ ደሙን ያቀ​ር​ባሉ፤ ደሙ​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ፊት ባለው በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል።</verse>
				<verse number="6">የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ይገ​ፍ​ፈ​ዋል፤ በየ​ብ​ል​ቱም ይቈ​ር​ጠ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">የካ​ህ​ኑም የአ​ሮን ልጆች በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ እሳት ያነ​ድ​ዳሉ፤ በእ​ሳ​ቱም ላይ ዕን​ጨት ይረ​በ​ር​ባሉ፤</verse>
				<verse number="8">የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ የተ​ቈ​ረ​ጡ​ትን ብል​ቶች፥ ራሱ​ንም፥ ስቡ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በእ​ሳቱ ላይ ባለው በዕ​ን​ጨቱ ላይ ይረ​በ​ር​ቡ​ታል።</verse>
				<verse number="9">የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹን ግን በውኃ ያጥ​ባሉ፤ ካህ​ኑም ሁሉን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል።</verse>
				<verse number="10">“ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ር​በው መባ ከበ​ጎች ወይም ከፍ​የ​ሎች ቢሆን፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባ​ቱን፥ የፊት እግ​ሮ​ቹ​ንና ራሱን ጨምሮ ያቀ​ር​በ​ዋል።</verse>
				<verse number="11">በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም አጠ​ገብ በመ​ስዕ በኩል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ዱ​ታል፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ ደሙን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል።</verse>
				<verse number="12">በየ​ብ​ል​ቱም ራሱን፥ ስቡ​ንም ይቈ​ር​ጡ​ታል፤ ካህ​ና​ቱም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በእ​ሳቱ ላይ ባለው በዕ​ን​ጨቱ ላይ ይረ​በ​ር​ቡ​ታል፤</verse>
				<verse number="13">የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹን ግን በውኃ ያጥ​ቡ​ታል። ካህ​ኑም ሁሉን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ለቍ​ር​ባን ያቀ​ር​በ​ዋል፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጎ መዓዛ ያለው ቍር​ባን ነው።</verse>
				<verse number="14">“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ያ​ቀ​ር​በው ቍር​ባን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ከዎ​ፎች ቢሆን፥ ቍር​ባ​ኑን ከዋ​ኖስ ወይም ከር​ግብ ያቀ​ር​ባል።</verse>
				<verse number="15">ካህ​ኑም ወደ መሠ​ዊ​ያው ያቀ​ር​በ​ዋል፤ አን​ገ​ቱ​ንም ይቈ​ር​ጠ​ዋል፥ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ ያኖ​ረ​ዋል። ደሙ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ያን​ጠ​ፈ​ጥ​ፈ​ዋል፤</verse>
				<verse number="16">የሆድ ዕቃ​ው​ንም ከላ​ባ​ዎች ጋር ለይቶ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ በም​ሥ​ራቅ በኩል በአ​መዱ ስፍራ ይጥ​ለ​ዋል፤</verse>
				<verse number="17">ከክ​ን​ፎ​ቹም ይሰ​ብ​ረ​ዋል፤ ነገር ግን አይ​ለ​የ​ውም። ካህ​ኑም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በእ​ሳቱ ላይ ባለው በዕ​ን​ጨቱ ላይ ያኖ​ረ​ዋል፤ መሥ​ዋ​ዕቱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው ቍር​ባን ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">“ማና​ቸ​ውም ሰው ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት እን​ዲ​ሆን ቢያ​ቀ​ርብ፥ ቍር​ባኑ ከመ​ል​ካም ስንዴ ዱቄት ይሁን፤ ዘይ​ትም ያፈ​ስ​ስ​በ​ታል፤ ነጭ ዕጣ​ንም ይጨ​ም​ር​በ​ታል፤ ይህም መሥ​ዋ​ዕት ነው።</verse>
				<verse number="2">ወደ ካህኑ ወደ አሮን ልጆች ያመ​ጣ​ዋል፤ ከመ​ል​ካም ስንዴ ዱቄ​ቱና ከዘ​ይ​ቱም አንድ እፍኝ ሙሉና ነጩ​ንም ዕጣን ሁሉ ወስዶ ካህኑ የእ​ሳት ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ለመ​ታ​ሰ​ቢያ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቃ​ጥ​ለ​ዋል።</verse>
				<verse number="3">ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱም የተ​ረ​ፈው ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ይሆ​ናል፤ ይህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የተ​ረፈ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።</verse>
				<verse number="4">“በእ​ቶን የተ​ጋ​ገ​ረ​ውን ቍር​ባን ስታ​ቀ​ርብ፥ በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ የመ​ል​ካም ስንዴ ዱቄት፥ የቂጣ እን​ጎቻ ወይም በዘ​ይት የተ​ቀባ ስስ ቂጣ ይሁን።</verse>
				<verse number="5">ቍር​ባ​ን​ህም በም​ጣድ የተ​ጋ​ገረ ቍር​ባን ቢሆን፥ በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ የመ​ል​ካም ስንዴ ዱቄት ቂጣ ይሁን።</verse>
				<verse number="6">ቈር​ሰ​ህም ዘይት ታፈ​ስ​ስ​በ​ታ​ለህ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት ነው።</verse>
				<verse number="7">ቍር​ባ​ን​ህም በመ​ቀ​ቀያ የበ​ሰለ ቍር​ባን ቢሆን፥ ዘይት የገ​ባ​በት ከመ​ል​ካም ስንዴ ዱቄት የተ​ደ​ረገ ይሁን።</verse>
				<verse number="8">ከዚ​ህም ያደ​ረ​ግ​ኸ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመ​ጣ​ለህ፤ ወደ ካህ​ኑም ታቀ​ር​በ​ዋ​ለህ፤ ካህ​ኑም ወደ መሠ​ዊ​ያው ያቀ​ር​በ​ዋል።</verse>
				<verse number="9">ካህ​ኑም ከቍ​ር​ባኑ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ውን ይወ​ስ​ዳል፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው የሚ​ቃ​ጠል ቍር​ባን ነው።</verse>
				<verse number="10">ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱም የተ​ረ​ፈው ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ይሆ​ናል፤ ይህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የተ​ረፈ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።</verse>
				<verse number="11">“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ታ​ቀ​ር​ቡት የእ​ህል ቍር​ባን ሁሉ እርሾ አይ​ሁ​ን​በት፤ እርሾ ያለ​በት ነገር፥ ማርም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን ይሆን ዘንድ አታ​ቀ​ር​ቡ​ምና።</verse>
				<verse number="12">እነ​ዚ​ህ​ንም ዐሥ​ራት አድ​ር​ጋ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለበጎ መዓዛ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ አይ​ቀ​ር​ቡም።</verse>
				<verse number="13">የም​ታ​ቀ​ር​ቡት ቍር​ባን ሁሉ በጨው ይጣ​ፈ​ጣል፤ የአ​ም​ላ​ክ​ህም ቃል ኪዳን ጨው ከቍ​ር​ባ​ንህ አይ​ጕ​ደል፤ በቍ​ር​ባ​ና​ችሁ ሁሉ ላይ ጨው ትጨ​ም​ራ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="14">“ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው እህ​ልህ መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብታ​ቀ​ርብ በእ​ሳት የተ​ጠ​በ​ሰና የተ​ፈ​ተገ የእ​ህል እሸት ታቀ​ር​ባ​ለህ።</verse>
				<verse number="15">ዘይ​ትም ታፈ​ስ​ስ​በ​ታ​ለህ፤ ዕጣ​ንም ትጨ​ም​ር​በ​ታ​ለህ፤ የእ​ህል ቍር​ባን ነው።</verse>
				<verse number="16">ካህ​ኑም ከተ​ፈ​ተ​ገው እህል፥ ከዘ​ይ​ቱም ወስዶ ከዕ​ጣኑ ጋር መታ​ሰ​ቢ​ያ​ውን ያቀ​ር​ባል፤ ይህም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ር​በው ቍር​ባን የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ቢሆን፥ ከላ​ሞች መንጋ ተባት ወይም እን​ስት ቢያ​ቀ​ርብ፥ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቅ​ርብ።</verse>
				<verse number="2">እጁ​ንም ለቍ​ር​ባን በቀ​ረ​በው ራስ ላይ ይጭ​ናል፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አጠ​ገብ ያር​ደ​ዋል፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ ደሙን በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት፥ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል።</verse>
				<verse number="3">ከደ​ኅ​ን​ነ​ቱም መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳት ቍር​ባን አድ​ር​ገው ያቀ​ር​ባሉ፤ የሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ፥ በሆድ ዕቃ​ውም ላይ ያለ​ውን ስብ ሁሉ፥</verse>
				<verse number="4">ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በእ​ነ​ር​ሱም ላይና በጎ​ድኑ አጠ​ገብ ያለ​ውን ስብ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ ከኵ​ላ​ሊ​ቶቹ ጋር ያመ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="5">የአ​ሮ​ንም ልጆች ከሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ጋር በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በእ​ሳቱ ላይ ባለው በዕ​ን​ጨቱ ላይ ያቀ​ር​ቡ​ታል፤ የእ​ሳት ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ነው።</verse>
				<verse number="6">“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ር​በው ቍር​ባኑ ከበ​ጎች ተባት ወይም እን​ስት ቢሆን፥ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ያቀ​ር​ባል።</verse>
				<verse number="7">ለቍ​ር​ባኑ የበግ ጠቦ​ትን ቢያ​ቀ​ርብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል፤</verse>
				<verse number="8">እጁ​ንም ለቍ​ር​ባን በቀ​ረ​በው ራስ ላይ ይጭ​ናል በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ያር​ደ​ዋል፤ ካህ​ና​ቱም የአ​ሮን ልጆች ደሙን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል።</verse>
				<verse number="9">ከደ​ኅ​ን​ነ​ቱም መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አድ​ርጎ ያቀ​ር​ባል፤ ስቡን፥ እስከ ጀር​ባ​ውም ድረስ የተ​ቈ​ረጠ ሙሉ ላቱን፥ የሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ፥ በሆድ ዕቃ​ውም ላይ ያለ​ውን ስብ ሁሉ፥</verse>
				<verse number="10">ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በእ​ነ​ር​ሱም ላይና በጎ​ድ​ኑም አጠ​ገብ ያለ​ውን ስብ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ ከኵ​ላ​ሊ​ቶቹ ጋር ይወ​ስ​ዳል።</verse>
				<verse number="11">ካህ​ኑም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል፤ በጎ መዓዛ ያለው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው።</verse>
				<verse number="12">“ቍር​ባ​ኑም ፍየል ቢሆን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል፤</verse>
				<verse number="13">እጁ​ንም በራሱ ላይ ይጭ​ን​በ​ታል፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃ​ፍም ያር​ደ​ዋል፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ደሙን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል።</verse>
				<verse number="14">ከእ​ር​ሱም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳት ቍር​ባን አድ​ርጎ ያቀ​ር​በ​ዋል፤ ሆድ ዕቃ​ውን የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ፥ በሆድ ዕቃ​ውም ላይ ያለ​ውን ስብ ሁሉ፥</verse>
				<verse number="15">ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በእ​ነ​ር​ሱም ላይና በጎ​ድኑ አጠ​ገብ ያለ​ውን ስብ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ ከኵ​ላ​ሊ​ቶቹ ጋር ይወ​ስ​ዳል።</verse>
				<verse number="16">ካህ​ኑም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው። ስቡ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።</verse>
				<verse number="17">ስብና ደም እን​ዳ​ት​በሉ በም​ት​ኖ​ሩ​በት ሁሉ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ማና​ቸ​ውም ሰው ሳያ​ውቅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ኀጢ​አት ቢሠራ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አት​ሥሩ ካላ​ቸው ትእ​ዛ​ዛት አን​ዲ​ቱን ቢተ​ላ​ለፍ፥</verse>
				<verse number="3">የተ​ቀ​ባ​ውም ሊቀ ካህ​ናት በሕ​ዝቡ ላይ በደል እን​ዲ​ቈ​ጠ​ር​ባ​ቸው ኀጢ​አት ቢሠራ፥ ስለ ሠራው ስለ ኀጢ​አቱ ከመ​ን​ጋው ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ወይ​ፈን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​በ​ዋል።</verse>
				<verse number="4">ወይ​ፈ​ኑ​ንም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያመ​ጣ​ዋል፤ እጁ​ንም በወ​ይ​ፈኑ ራስ ላይ ይጭ​ነ​ዋል፤ ወይ​ፈ​ኑ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ደ​ዋል።</verse>
				<verse number="5">ተቀ​ብቶ የተ​ሾ​መው ካህን ከወ​ይ​ፈኑ ደም በእጁ ወስዶ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ያመ​ጣ​ዋል፤</verse>
				<verse number="6">ካህ​ኑም ጣቱን በደሙ ውስጥ ነክሮ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመ​ቅ​ደሱ መጋ​ረጃ ፊት ደሙን ሰባት ጊዜ ይረ​ጨ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">ካህ​ኑም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያለው ጣፋጭ ዕጣን በሚ​ታ​ጠ​ን​በት መሠ​ዊያ ቀን​ዶች ላይ ከደሙ ያደ​ር​ጋል፤ የወ​ይ​ፈ​ኑ​ንም ደም ሁሉ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ ባለው ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።</verse>
				<verse number="8">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከሚ​ታ​ረ​ደው ወይ​ፈን ስብን ሁሉ ይወ​ስ​ዳል፤ ሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ፥ በሆድ ዕቃ​ውም ላይ ያለ​ውን ስብ ሁሉ፥</verse>
				<verse number="9">ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በእ​ነ​ር​ሱም ላይና በጎ​ድኑ አጠ​ገብ ያለ​ውን ስብ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ ከኵ​ላ​ሊ​ቶች ጋር፥</verse>
				<verse number="10">ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ከታ​ረ​ደው ወይ​ፈን እንደ ተወ​ሰ​ደው ይወ​ስ​ዳል፤ ካህ​ኑም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል።</verse>
				<verse number="11">የወ​ይ​ፈ​ኑን ቍር​በት፥ ሥጋ​ው​ንም ሁሉ፥ ራሱ​ንም፥ እግ​ሮ​ቹ​ንም፥ ሆድ ዕቃ​ው​ንም፥ ፈር​ሱ​ንም፤</verse>
				<verse number="12">ወይ​ፈ​ኑን ሁሉ ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ አመድ ወደ​ሚ​ፈ​ስ​ስ​በት ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወ​ስ​ዱ​ታል፤ በዕ​ን​ጨ​ትም ላይ በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​ታል፤ አመድ በሚ​ፈ​ስ​ስ​በት ስፍራ ይቃ​ጠ​ላል።</verse>
				<verse number="13">“የእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ቢስቱ፥ ነገ​ሩም ከማ​ኅ​በሩ ዐይን ቢሸ​ሸግ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አት​ሥሩ ካላ​ቸው ትእ​ዛ​ዛት አን​ዲ​ቱን ቢተ​ላ​ለፉ፤</verse>
				<verse number="14">ከዚ​ህም በኋላ፥ የሠ​ሩት ኀጢ​አት ቢታ​ወ​ቃ​ቸ​ውና ንስሓ ቢገቡ ማኅ​በሩ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ንን ያቀ​ር​ባሉ፤ ወደ ምስ​ክ​ሩም ድን​ኳን ፊት ያመ​ጡ​ታል።</verse>
				<verse number="15">የማ​ኅ​በ​ሩም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች እጆ​ቻ​ቸ​ውን በወ​ይ​ፈኑ ራስ ላይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይጭ​ናሉ፤ ወይ​ፈ​ኑ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ዱ​ታል።</verse>
				<verse number="16">የተ​ቀ​ባ​ውም ካህን ከወ​ይ​ፈኑ ደም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ያመ​ጣል፤</verse>
				<verse number="17">ካህ​ኑም ጣቱን በደሙ ውስጥ ነክሮ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመ​ቅ​ደሱ መጋ​ረጃ ፊት ለፊት ሰባት ጊዜ ይረ​ጨ​ዋል።</verse>
				<verse number="18">በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ባለው በዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያው ቀን​ዶች ላይ ከደሙ ያደ​ር​ጋል፤ ደሙ​ንም ሁሉ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ ባለው ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።</verse>
				<verse number="19">ስቡ​ንም ሁሉ ከእ​ርሱ ወስዶ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል።</verse>
				<verse number="20">እን​ዲ​ህም በወ​ይ​ፈኑ ያደ​ር​ጋል፤ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት በታ​ረ​ደው ወይ​ፈን እንደ አደ​ረገ እን​ዲሁ በዚህ ያደ​ር​ጋል፤ ካህ​ኑም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ኀጢ​አ​ቸ​ውም ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="21">ወይ​ፈ​ኑ​ንም ሁሉ ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ ይወ​ስ​ዱ​ታል፤ የፊ​ተ​ኛ​ው​ንም ወይ​ፈን እን​ዳ​ቃ​ጠሉ ያቃ​ጥ​ሉ​ታል፤ የማ​ኅ​በሩ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና።</verse>
				<verse number="22">“መኰ​ን​ንም ኀጢ​አ​ትን ቢሠራ፥ ሳያ​ው​ቅም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኩ፦ አት​ሥራ ያለ​ውን ትእ​ዛዝ ቢተ​ላ​ለፍ፥ እን​ዲ​ህም ቢበ​ድል፥</verse>
				<verse number="23">የሠ​ራው ኀጢ​አት ቢታ​ወ​ቀ​ውና ንስሓ ቢገባ፥ ከፍ​የ​ሎች ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባት ፍየል ለቍ​ር​ባኑ ያቀ​ር​ባል፤</verse>
				<verse number="24">በፍ​የ​ሉም ራስ ላይ እጁን ይጭ​ናል፤ የሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ታ​ረ​ድ​በት ስፍራ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ደ​ዋል፤ እርሱ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና።</verse>
				<verse number="25">ካህ​ኑም ከኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ደም በጣቱ ወስዶ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ቀን​ዶች ላይ ያደ​ር​ገ​ዋል፤ ደሙ​ንም ሁሉ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ከሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።</verse>
				<verse number="26">ስቡ​ንም ሁሉ እንደ ደኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ስብ፥ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል። ካህ​ኑም ኀጢ​አ​ቱን ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="27">“ከሀ​ገ​ሩም ሕዝብ አንድ ሰው ኀጢ​አ​ትን ሳያ​ውቅ ቢሠራ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አት​ሥራ ያለ​ውን ትእ​ዛዝ ቢተ​ላ​ለፍ፥ ቢበ​ድ​ልም፥</verse>
				<verse number="28">ለእ​ር​ሱም የሠ​ራው ኀጢ​አት ቢታ​ወ​ቀ​ውና ንስሓ ቢገባ፥ ስለ ሠራው ኀጢ​አት ነውር የሌ​ለ​ባ​ትን እን​ስት ፍየል ለቍ​ር​ባኑ ያመ​ጣል።</verse>
				<verse number="29">እጁ​ንም በኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ራስ ላይ ይጭ​ናል፤ ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት እን​ስ​ሳ​ትን በሚ​ያ​ር​ዱ​በት ስፍራ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ፍየ​ል​ዋን ያር​ዳ​ታል።</verse>
				<verse number="30">ካህ​ኑም ከደ​ምዋ በጣቱ ወስዶ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ቀን​ዶች ላይ ያደ​ር​ገ​ዋል፤ ደሙ​ንም ሁሉ ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።</verse>
				<verse number="31">ስቡም ሁሉ ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ሰድ፥ ስብ​ዋን ሁሉ ይወ​ስ​ዳል፤ ካህ​ኑም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል፤ ካህ​ኑም ስለ እርሱ ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="32">“ስለ ኀጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት የበግ ጠቦት ቢያ​ቀ​ርብ፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ትን እን​ስት ያመ​ጣል።</verse>
				<verse number="33">እጁ​ንም በኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ራስ ላይ ይጭ​ናል፤ የሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ታ​ረ​ድ​በት ስፍራ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያር​ዳ​ታል።</verse>
				<verse number="34">ካህ​ኑም ከኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ደም በጣቱ ወስዶ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ቀን​ዶች ላይ ያደ​ር​ገ​ዋል፤ ደሙ​ንም ሁሉ ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።</verse>
				<verse number="35">ስቡ ሁሉ ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ከታ​ረ​ደው የበግ ጠቦት ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ሰድ ስብ​ዋን ሁሉ ይወ​ስ​ዳሉ፤ ካህ​ኑም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ሳት በተ​ቃ​ጠ​ለው ቍር​ባን ላይ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል። ካህ​ኑም ስለ ሠራው ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">“አንድ ሰው ቢበ​ድል፥ የሚ​ያ​ም​ለ​ው​ንም ቃል ቢሰማ፥ ምስ​ክ​ርም ሆኖ አንድ ነገር አይቶ እንደ ሆነ፥ ወይም ዐውቆ እንደ ሆነ ያነን ባይ​ና​ገር በደ​ሉን ይሸ​ከ​ማል፤</verse>
				<verse number="2">ርኩስ ነገ​ርን፥ የሞ​ተ​ውን፥ አውሬ የነ​ከ​ሰ​ውን፥ ወይም የበ​ከተ፥ ወይም የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ የእ​ን​ስ​ሳን በድን የነካ፥ ከእ​ር​ሱም ያነሣ ሰው ቢኖር፤</verse>
				<verse number="3">ወይም ርኩ​ስ​ነ​ቱን ሳያ​ውቅ ርኩ​ስን ሰው ቢነካ፥ በማ​ና​ቸ​ውም ርኵ​ሰት ቢረ​ክስ፥ ነገሩ በታ​ወቀ ጊዜ በደል ይሆ​ን​በ​ታል።</verse>
				<verse number="4">ሰው ሳያ​ስብ ክፉን ወይም መል​ካ​ምን ያደ​ርግ ዘንድ ሳያ​ስብ በከ​ን​ፈሩ ተና​ግሮ ቢምል፥ ሳያ​ስብ የማ​ለ​ውም ከዚህ ባንዱ ነገር ቢሆን፥ በታ​ወ​ቀው ጊዜ ከዚህ ነገር በአ​ንዱ በደ​ለኛ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="5">ከእ​ነ​ዚህ ነገ​ሮች በአ​ን​ዲቱ በደ​ለኛ ቢሆን፥ የሠ​ራ​ውን ኀጢ​አት ይና​ዘ​ዛል።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ መበ​ደ​ሉና ስለ ሠራው ኀጢ​አት ከበ​ጎቹ ነውር የሌ​ለ​ባ​ትን እን​ስት በግ ወይም ከፍ​የ​ሎች እን​ስት ፍየል ያመ​ጣል፤ ካህ​ኑም ስለ ኀጢ​አቱ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="7">“ስለ ሠራው ኀጢ​አት የበግ መግዣ ገን​ዘብ በእጁ ባይ​ኖ​ረው ግን፥ ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች፥ አን​ዱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ር​ባል። ወደ ካህ​ኑም ያመ​ጣ​ቸ​ዋል፤</verse>
				<verse number="8">ካህ​ኑም አስ​ቀ​ድሞ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሆ​ነ​ውን ያቀ​ር​ባል፤ ራሱ​ንም ከአ​ን​ገቱ ይቆ​ለ​ም​መ​ዋል፤ ነገር ግን አይ​ቈ​ር​ጠ​ውም።</verse>
				<verse number="9">ከኀ​ጢ​አ​ቱም መሥ​ዋ​ዕት ደም በመ​ሠ​ዊ​ያው ግድ​ግዳ ላይ ይረ​ጨ​ዋል፤ የተ​ረ​ፈ​ው​ንም ደም ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች ያን​ጠ​ፈ​ጥ​ፋል፤ እርሱ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና።</verse>
				<verse number="10">እንደ ሥር​ዐ​ቱም ሁለ​ተ​ኛ​ውን ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያዘ​ጋ​ጀ​ዋል። ካህ​ኑም ስለ ሠራው ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="11">“ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ለማ​ም​ጣት ገን​ዘብ በእጁ ባይ​ኖ​ረው፥ ስለ ሠራው ኀጢ​አት የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ ክፍል መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና ዘይት አያ​ፈ​ስ​ስ​በ​ትም፤ ዕጣ​ንም አይ​ጨ​ም​ር​በ​ትም።</verse>
				<verse number="12">ወደ ካህ​ኑም ያመ​ጣ​ዋል፤ ካህ​ኑም ስለ መታ​ሰ​ቢ​ያው ለእ​ርሱ እፍኝ ሙሉ ይዘ​ግ​ናል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ሳት በተ​ቃ​ጠ​ለው ቍር​ባን ላይ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል፤ እር​ሱም የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነው።</verse>
				<verse number="13">ካህ​ኑም ከእ​ነ​ዚያ በአ​ን​ዳ​ቸው ስለ ሠራው ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል። የተ​ረ​ፈ​ውም እንደ እህሉ ቍር​ባን ለካ​ህኑ ይሆ​ናል።”</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="15">“ሰው ቢዘ​ነጋ፥ ሳያ​ው​ቅም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ቀ​ደ​ሰው በማ​ና​ቸ​ውም ነገር ኀጢ​አ​ትን ቢሠራ፥ ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከመ​ን​ጋዉ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን በብር ሰቅል የተ​ገ​መ​ተ​ውን አውራ በግ ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል።</verse>
				<verse number="16">በተ​ቀ​ደሰ ነገር ላይ ስለ ሠራው ኀጢ​አት ዕዳ ይከ​ፍ​ላል፤ አም​ስ​ተ​ኛ​ው​ንም እጅ ይጨ​ም​ር​በ​ታል፤ ለካ​ህ​ኑም ይሰ​ጠ​ዋል። ካህ​ኑም በበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት አውራ በግ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="17">“ሰው ባለ​ማ​ወቅ ኀጢ​አት ቢሠራ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አት​ሥሩ ካላ​ቸው ትእ​ዛ​ዛት አን​ዲ​ቱን ቢተ​ላ​ለፍ፥ ቢታ​ወ​ቀው፥ ኀጢ​አት ስለ​ሆ​ነ​ች​በ​ትም ንስሓ ቢገባ፥</verse>
				<verse number="18">ነውር የሌ​ለ​በ​ትን በሰ​ቅል የተ​ገ​መ​ተ​ውን አውራ በግ ከመ​ን​ጋው ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ወደ ካህኑ ያመ​ጣ​ዋል፤ ካህ​ኑም ሳያ​ውቅ ስለ ሳተው ስሕ​ተት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="19">እርሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ንስሓ ገብ​ቶ​አ​ልና።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“ሰው ኀጢ​አ​ትን ቢሠራ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ትእ​ዛዝ ቸል ቢል፥ ያኖ​ረ​በ​ትን አደራ ወይም የኅ​ብ​ረ​ትን ገን​ዘብ ወስዶ ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ቢክድ፥ ወይም ቢቀማ፥ ወይም በባ​ል​ን​ጀ​ራው ላይ ግፍ ቢሠራ፥</verse>
				<verse number="3">ወይም የጠ​ፋ​ውን ነገር ቢያ​ገኝ፥ ስለ​ዚ​ህም ቢዋሽ፥ ሰው ኀጢ​አ​ትን ለመ​ሥ​ራት ከሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ቸው ከእ​ነ​ዚህ ነገ​ሮች ሁሉ በአ​ን​ዲቱ በሐ​ሰት ቢምል፥</verse>
				<verse number="4">እርሱ ቢበ​ድ​ልና ከዚህ በኋላ ንስሓ ቢገባ፥ በቅ​ድ​ሚያ የወ​ሰ​ደ​ውን፥ ወይም በዐ​መ​ፅና በግፍ የተ​ቀ​በ​ለ​ውን፥ ወይም የተ​ሰ​ጠ​ውን አደራ፥ ወይም ጠፍቶ ያገ​ኘ​ውን፥</verse>
				<verse number="5">ወይም በሐ​ሰት የማ​ለ​በ​ትን ነገር ቢመ​ልስ፥ በሙሉ ይመ​ልስ፤ ከዚ​ያም በላይ አም​ስ​ተ​ኛ​ውን ክፍል ጨምሮ የበ​ደ​ሉን መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ያ​ቀ​ር​ብ​በት ቀን ለባለ ገን​ዘቡ ይስ​ጠው።</verse>
				<verse number="6">ስለ በደል መሥ​ዋ​ዕ​ትም ከመ​ን​ጋው ነውር የሌ​ለ​በ​ትን፥ ዋጋው እንደ በደሉ የተ​ገ​መ​ተ​ውን አውራ በግ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያምጣ። ።</verse>
				<verse number="7">ካህ​ኑም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ስለ​ዚ​ያም ስለ አደ​ረ​ገው በደል ሁሉ ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል።”</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="9">“አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን እን​ዲህ ብለህ እዘ​ዛ​ቸው፦ የሚ​ቃ​ጠ​ለው የመ​ሥ​ዋ​ዕቱ ሕግ ይህ ነው፤ የመ​ሠ​ዊ​ያው እሳት በላዩ እየ​ነ​ደ​ደች እስ​ኪ​ነጋ ትተ​ዉ​ታ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="10">ካህ​ኑም የተ​ልባ እግር ቀሚ​ስና የተ​ልባ እግር ሱሪ በሰ​ው​ነቱ ላይ ይለ​ብ​ሳል፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት እሳቱ ከበ​ላው በኋላ አመ​ዱን አን​ሥቶ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።</verse>
				<verse number="11">ልብ​ሱ​ንም ያወ​ል​ቃል፤ ሌላም ልብስ ይለ​ብ​ሳል፤ አመ​ዱ​ንም ተሸ​ክሞ ከሰ​ፈሩ ንጹሕ ወደ ሆነ ስፍራ ወደ ውጭ ያወ​ጣ​ዋል።</verse>
				<verse number="12">እሳ​ቱም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ዘወ​ትር ይነ​ድ​ዳል፤ አይ​ጠ​ፋም፤ ካህ​ኑም ማለዳ ማለዳ ዕን​ጨት ያቃ​ጥ​ል​በ​ታል፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት በዚያ ላይ ይረ​በ​ር​ባል፤ በዚ​ያም የደ​ኅ​ን​ነ​ትን መሥ​ዋ​ዕት ስብ ያቃ​ጥ​ላል።</verse>
				<verse number="13">ዘወ​ትር በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ እሳት ይነ​ድ​ዳል፤ አይ​ጠ​ፋም።</verse>
				<verse number="14">“የአ​ሮን ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት ለፊት የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የመ​ሥ​ዋ​ዕት ሥር​ዐት ይህ ነው።</verse>
				<verse number="15">ካህ​ኑም ከእ​ህሉ ቍር​ባን መል​ካ​ሙን የስ​ንዴ ዱቄት ከዘ​ይት ጋር እፍኝ ሙሉ፥ ደግ​ሞም በእ​ህሉ ቍር​ባን ላይ ያለ​ውን ዕጣን ሁሉ ያነ​ሣል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ መዓዛ ያለው የመ​ታ​ሰ​ቢያ ቍር​ባን እን​ዲ​ሆን ለመ​ታ​ሰ​ቢያ ነውና በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል።</verse>
				<verse number="16">ከእ​ር​ሱም የተ​ረ​ፈ​ውን አሮ​ንና ልጆቹ ይበ​ሉ​ታል፤ ቂጣ ሆኖ በተ​ቀ​ደ​ሰው ስፍራ ይበ​ላል፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ ባለው አደ​ባ​ባይ ይበ​ሉ​ታል።</verse>
				<verse number="17">በእ​ርሾ ቦክቶ አይ​ጋ​ገ​ርም። ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የሰ​ጠ​ኋ​ቸው ዕድል ፈንታ ይህ ነው፤ እር​ሱም እንደ ኀጢ​አ​ትና እንደ በደል መሥ​ዋ​ዕት ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።</verse>
				<verse number="18">ከካ​ህ​ናት ወገን ወንድ ሁሉ ይበ​ላ​ዋል፤ በዘ​መ​ና​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ ነው። ከሚ​ቃ​ጠ​ለው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል።”</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="20">“እር​ሱን በቀ​ባ​ህ​በት ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የአ​ሮ​ንና የል​ጆቹ መባ ይህ ነው። የኢፍ መስ​ፈ​ርያ ዐሥ​ረኛ ክፍል መል​ካ​ሙን ዱቄት እኩ​ሌ​ታ​ውን በጥ​ዋት፥ እኩ​ሌ​ታ​ው​ንም በማታ ለዘ​ወ​ትር መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባሉ።</verse>
				<verse number="21">ከዘ​ይት ጋር በም​ጣድ ላይ ያደ​ር​ጉ​ታል፤ ለው​ሰ​ውም ያገ​ቡ​ታል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ፈ​ተት መሥ​ዋ​ዕት ነው።</verse>
				<verse number="22">ከል​ጆ​ቹም በእ​ርሱ ፋንታ የተ​ቀ​ባው ካህን ያቀ​ር​በ​ዋል። ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው፤ ሁል​ጊ​ዜም ይደ​ረ​ጋል።</verse>
				<verse number="23">ካህ​ና​ትም የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የእ​ህል ቍር​ባን ሁሉ ፈጽሞ ይቃ​ጠ​ላል፤ ከእ​ር​ሱም አን​ዳች አይ​በ​ላም።”</verse>
				<verse number="24">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="25">“አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ታ​ረ​ድ​በት ስፍራ የኀ​ጢ​አቱ መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይታ​ረ​ዳል፤ እር​ሱም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።</verse>
				<verse number="26">የሚ​ሠ​ዋው ካህን ይበ​ላ​ዋል፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ በአ​ለው አደ​ባ​ባይ በተ​ቀ​ደሰ ስፍራ ይበ​ሉ​ታል።</verse>
				<verse number="27">ሥጋ​ውን የሚ​ነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል፤ ማና​ቸ​ውም ልብስ ደም ቢረ​ጭ​በት የተ​ረ​ጨ​በ​ትን በተ​ቀ​ደሰ ስፍራ ያጥ​ቡ​ታል።</verse>
				<verse number="28">የሚ​ቀ​ቀ​ል​በ​ትን ሸክላ ይሰ​ብ​ሩ​ታል፤ በና​ስም ዕቃ ቢቀ​ቀል ይፈ​ገ​ፍ​ጉ​ታል፤ በው​ኃም ያጥ​ቡ​ታል።</verse>
				<verse number="29">ከካ​ህ​ናት ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ከእ​ርሱ ይበ​ላል፤ እር​ሱም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።</verse>
				<verse number="30">ነገር ግን በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ለማ​ስ​ተ​ስ​ረያ ይሆን ዘንድ ከደሙ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን የሚ​ገ​ባው የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁሉ አይ​በ​ላም፤ በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">“የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው፤ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።</verse>
				<verse number="2">የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ያ​ር​ዱ​በት ስፍራ የበ​ደ​ሉን መሥ​ዋ​ዕት በግ በዚያ ያር​ዱ​ታል፤ ደሙ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል።</verse>
				<verse number="3">ስቡ​ንም ሁሉ፥ ላቱ​ንም፥ የሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ ሁሉ፥ በአ​ን​ጀ​ቱም ላይ ያለ​ውን ስብ፤</verse>
				<verse number="4">ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በእ​ነ​ር​ሱም ላይና በጎ​ድኑ አጠ​ገብ ያለ​ውን ስብ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ ከኵ​ላ​ሊ​ቶቹ ጋር ካህኑ ይለ​ያል።</verse>
				<verse number="5">ካህ​ኑም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳት ቍር​ባን እን​ዲ​ሆን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል፤ እር​ሱም የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ነው።</verse>
				<verse number="6">ከካ​ህ​ናት ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ይበ​ላ​ዋል፤ በተ​ቀ​ደሰ ስፍ​ራም ይበ​ሉ​ታል፤ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።</verse>
				<verse number="7">የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት እንደ ሆነ እን​ዲሁ የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ነው፤ ለሁ​ለቱ አንድ ሕግ ነው፤ በእ​ነ​ርሱ የሚ​ያ​ስ​ተ​ሰ​ርይ ካህን ይወ​ስ​ደ​ዋል።</verse>
				<verse number="8">የሰ​ውን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ርብ ካህን ያቀ​ረ​በው የሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ቍር​በት ለዚ​ያው ካህን ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="9">በእ​ቶን የተ​ጋ​ገ​ረው የእ​ህል ቍር​ባን ሁሉ፥ በመ​ቀ​ቀ​ያም ወይም በም​ጣድ የበ​ሰ​ለው ሁሉ ለሚ​ያ​ቀ​ር​በው ካህን ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="10">በዘ​ይ​ትም የተ​ለ​ወ​ሰው ወይም የደ​ረ​ቀው የእ​ህል ቍር​ባን ሁሉ ለአ​ሮን ልጆች ሁሉ ይሆ​ናል፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም እኩል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="11">“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው።</verse>
				<verse number="12">ለም​ስ​ጋና ቢያ​ቀ​ር​በው፥ ከም​ስ​ጋ​ናው መሥ​ዋ​ዕት ጋር በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ የቂጣ እን​ጎቻ፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ቀባ ስስ ቂጣ፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ለ​ወሰ መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት ያቀ​ር​ባል።</verse>
				<verse number="13">ለም​ስ​ጋና የሚ​ሆ​ነ​ውን የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት በአ​ቀ​ረበ ጊዜ እርሾ ያለ​በ​ትን ኅብ​ስት ያቀ​ር​ባል።</verse>
				<verse number="14">ከቍ​ር​ባ​ኑም ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድርሻ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዱን ያነ​ሣል። እር​ሱም የደ​ኅ​ን​ነ​ትን መሥ​ዋ​ዕት ደም ለሚ​ረ​ጨው ካህን ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="15">“ለም​ስ​ጋና የሚ​ሆ​ነው የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሥጋም ለእ​ርሱ ነው፤ በሚ​ቀ​ር​ብ​በ​ትም ቀን ይበ​ሉ​ታል፤ ከእ​ርሱ እስከ ነገ ምንም አያ​ተ​ር​ፉም።</verse>
				<verse number="16">የቍ​ር​ባ​ኑም መሥ​ዋ​ዕት የስ​እ​ለት ወይም የፈ​ቃድ ቢሆን፥ መሥ​ዋ​ዕቱ በሚ​ቀ​ር​ብ​በት ቀን ይብ​ሉት፤ ከእ​ር​ሱም የቀ​ረ​ውን በነ​ጋው ይብ​ሉት፤</verse>
				<verse number="17">ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱም ሥጋ እስከ ሦስ​ተ​ኛው ቀን የሚ​ቈ​የ​ውን በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​ታል።</verse>
				<verse number="18">በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሥጋ ቢበላ፥ አይ​ሠ​ም​ርም፤ ላቀ​ረ​በው ሰው የተ​ጠላ ይሆ​ን​በ​ታል እንጂ ቍር​ባን ሆኖ አይ​ቈ​ጠ​ር​ለ​ትም፤ ከእ​ር​ሱም የበላ ሰው ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል።</verse>
				<verse number="19">“ርኩስ ነገር የሚ​ነ​ካ​ውን ሥጋ አይ​ብ​ሉት፤ በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉት እንጂ። ንጹሕ የሆነ ሰው ሁሉ ግን ከሥ​ጋው ይብላ።</verse>
				<verse number="20">ኀጢ​አት ሳለ​ባት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆ​ነው ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሥጋ የበ​ላች ሰው​ነት፥ ያች ሰው​ነት ከሕ​ዝ​ብዋ ተለ​ይታ ትጥፋ።</verse>
				<verse number="21">ከር​ኩስ ሁሉ፥ ወይም ከረ​ከ​ሰው ሰው፥ ወይም ንጹሕ ካል​ሆ​ነው እን​ስሳ የነ​ካች ሰው​ነት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆ​ነው ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሥጋ ብት​በላ፥ ያች ሰው​ነት ከሕ​ዝ​ብዋ ተለ​ይታ ትጥፋ።”</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="23">“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ የበሬ ወይም የበግ ወይም የፍ​የል ስብ ከቶ አት​ብሉ።</verse>
				<verse number="24">የሞ​ተ​ውን ስብ፥ አውሬ የሰ​በ​ረ​ው​ንም ስብ ለሌላ ተግ​ባር አድ​ር​ጉት፤ እና​ንተ ግን አት​ብ​ሉት፤</verse>
				<verse number="25">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ሳት ከሚ​ቀ​ር​በው ከእ​ን​ስሳ ስብ የሚ​በላ ሁሉ ያች የበ​ላች ሰው​ነት ከሕ​ዝ​ብዋ ተለ​ይታ ትጥፋ።</verse>
				<verse number="26">በመ​ኖ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ችሁ ሁሉ የወፍ ወይም የእ​ን​ስሳ ደም ቢሆን አት​ብሉ።</verse>
				<verse number="27">ደም የም​ት​በላ ሰው​ነት ሁሉ ያች ሰው​ነት ከሕ​ዝ​ብዋ ተለ​ይታ ትጥፋ።”</verse>
				<verse number="28">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="29">“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ርብ ሰው ቍር​ባ​ኑን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከደ​ኅ​ን​ነቱ መሥ​ዋ​ዕት ያመ​ጣል።</verse>
				<verse number="30">የእ​ርሱ እጆች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳ​ቱን ቍር​ባን ያመ​ጣሉ፤ ፍር​ም​ባ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቍር​ባን ያቀ​ርብ ዘንድ በጉ​በቱ ላይ ያለ​ውን መረ​ብና የፍ​ር​ም​ባ​ውን ስብ ያመ​ጣል።</verse>
				<verse number="31">ካህ​ኑም ስቡን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረው፤ ፍር​ም​ባ​ውም ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ይሁን።</verse>
				<verse number="32">ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችሁ ቀኝ ወር​ቹን ለማ​ን​ሣት ቍር​ባን እን​ዲ​ሆን ለካ​ህኑ ትሰ​ጡ​ታ​ላ​ቸሁ።</verse>
				<verse number="33">ከአ​ሮ​ንም ልጆች የደ​ኅ​ን​ነ​ትን መሥ​ዋ​ዕት ደሙ​ንና ስቡን ለሚ​ያ​ቀ​ርብ ለእ​ርሱ ቀኝ ወርቹ እድል ፈን​ታው ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="34">ፍር​ም​ባ​ው​ንና የቀኝ ወር​ቹን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸው ወስ​ጄ​አ​ለሁ፤ ለካ​ህኑ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆ​ቹም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ እን​ዲ​ሆን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ሰጥ​ቼ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="35">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ በተ​ቀ​ቡ​በት ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆነ ከእ​ሳት ቍር​ባን የአ​ሮ​ንና የል​ጆቹ ሕግ ይህ ነው።</verse>
				<verse number="36">ለልጅ ልጃ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ እን​ዲ​ሆን በቀ​ባ​ቸው ቀን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይሰ​ጡ​አ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘው ይህ ነው።</verse>
				<verse number="37">የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህል ቍር​ባን፥ የኀ​ጢ​አ​ትና የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት፥ የቅ​ድ​ስ​ናና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው።</verse>
				<verse number="38">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሲና ምድረ በዳ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ርቡ ዘንድ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ባዘዘ ጊዜ በሲና ተራራ ለሙሴ ያዘ​ዘው ይህ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“አሮ​ንን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆ​ቹን፥ ልብ​ሱ​ንም፥ የቅ​ብ​ዐ​ቱ​ንም ዘይት፥ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕ​ትም የሆ​ነ​ውን ወይ​ፈን፥ ሁለ​ቱ​ንም አውራ በጎች፥ የቂ​ጣ​ው​ንም እን​ጀራ መሶብ ውሰድ፤</verse>
				<verse number="3">ማኅ​በ​ሩ​ንም ሁሉ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ሰብ​ስ​ባ​ቸው።”</verse>
				<verse number="4">ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረገ፤ ማኅ​በ​ሩ​ንም ሁሉ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ሰበ​ሰበ።</verse>
				<verse number="5">ሙሴም ማኅ​በ​ሩን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታደ​ርጉ ዘንድ ያዘ​ዘው ነገር ይህ ነው” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">ሙሴም አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን አቀ​ረበ፤ በው​ኃም አጠ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">እጀ ጠባ​ብም አለ​በ​ሰው፤ በመ​ታ​ጠ​ቂ​ያም አስ​ታ​ጠ​ቀው፤ የበ​ፍታ ቀሚ​ስም አለ​በ​ሰው፤ ልብሰ መት​ከ​ፍም ደረ​በ​ለት፤ በል​ብሰ መት​ከ​ፉም አሠ​ራር ላይ በብ​ል​ሃት በተ​ጠ​ለፈ ቋድ አስ​ታ​ጠ​ቀ​ውና በእ​ርሱ ላይ አሰ​ረው።</verse>
				<verse number="8">ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ው​ንም በእ​ርሱ ላይ አደ​ረገ፤ በል​ብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውም ላይ የም​ል​ክ​ትና የእ​ው​ነት መገ​ለ​ጫ​ዎ​ችን አኖ​ረ​በት።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው በራሱ ላይ አክ​ሊል አደ​ረ​ገ​ለት፤ በአ​ክ​ሊ​ሉም ላይ በፊቱ በኩል የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን የወ​ርቅ መር​ገፍ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="10">ሙሴም የቅ​ብ​ዐ​ቱን ዘይት ወሰደ፤ ከእ​ር​ሱም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ሰባት ጊዜ ረጨ፤</verse>
				<verse number="11">ይቀ​ድ​ሳ​ቸ​ውም ዘንድ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንና ዕቃ​ውን ሁሉ፥ የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንና መቀ​መ​ጫ​ውን ቀባ፤ ድን​ኳ​ኒ​ቱ​ንና ዕቃ​ዋን ሁሉ ቀብቶ ቀደ​ሳ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">ከቅ​ብ​ዐ​ቱም ዘይት በአ​ሮን ራስ ላይ አፈ​ሰሰ፤ ቀባው፤ ቀደ​ሰ​ውም።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሙሴ የአ​ሮ​ንን ልጆች አቀ​ረበ፤ የበ​ፍታ ቀሚ​ሶ​ች​ንም አለ​በ​ሳ​ቸው፤ በመ​ታ​ጠ​ቂ​ያም አስ​ታ​ጠ​ቃ​ቸው፤ አክ​ሊ​ልም ደፋ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">የኀ​ጢ​አ​ት​ንም መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈን አቀ​ረበ፤ አሮ​ንና ልጆ​ቹም በኀ​ጢ​አቱ መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈን ራስ ላይ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ጫኑ።</verse>
				<verse number="15">አረ​ዱ​ትም፤ ሙሴም ደሙን ወስዶ በጣቱ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ቀን​ዶች ዙሪያ ቀባ፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም አነ​ጻው፤ ደሙ​ንም ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች አፈ​ሰ​ሰው፤ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ትም ዘንድ ቀደ​ሰው።</verse>
				<verse number="16">ሙሴም በሆድ ዕቃው ላይ ያለ​ውን ስብ ሁሉ፥ የጉ​በ​ቱ​ንም መረብ፥ ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ ስባ​ቸ​ው​ንም ወሰደ፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ ጨመ​ረው።</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ወይ​ፈ​ኑን፥ ቍር​በ​ቱ​ንም፥ ሥጋ​ው​ንም፥ ፈር​ሱ​ንም ከሰ​ፈሩ ውጭ በእ​ሳት አቃ​ጠለ።</verse>
				<verse number="18">ሙሴም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆን አውራ በግ አቀ​ረበ፤ አሮ​ንና ልጆ​ቹም በአ​ው​ራው በግ ራስ ላይ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ጫኑ።</verse>
				<verse number="19">ሙሴም ያን በግ አረ​ደው፤ ደሙ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ዙሪያ ረጨው።</verse>
				<verse number="20">አው​ራ​ው​ንም በግ በየ​ብ​ልቱ ቈረጠ፤ ሙሴም ጭን​ቅ​ላ​ቱን፥ ብል​ቶ​ቹ​ንም፥ ስቡ​ንም ጨመረ።</verse>
				<verse number="21">የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹ​ንም በውኃ አጠበ፤ ሙሴም አው​ራ​ውን በግ ሁሉ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመረ፤ ይህ በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳት ቍር​ባን ነበረ።</verse>
				<verse number="22">ሙሴም ለቅ​ድ​ስና የሚ​ሆ​ነ​ውን ሁለ​ተ​ኛ​ውን አውራ በግ አቀ​ረበ፤ አሮ​ንና ልጆ​ቹም በአ​ው​ራው በግ ራስ ላይ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ጫኑ፤</verse>
				<verse number="23">አረ​ዱ​ትም። ሙሴም ከደሙ ወስዶ የአ​ሮ​ንን የቀኝ ጆሮ​ውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁ​ንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግ​ሩ​ንም አውራ ጣት ቀባው።</verse>
				<verse number="24">የአ​ሮ​ን​ንም ልጆች አቀ​ረበ፤ ሙሴም የቀኝ ጆሮ​አ​ቸ​ውን ጫፍ፥ የቀኝ እጃ​ቸ​ው​ንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግ​ራ​ቸ​ው​ንም አውራ ጣት ከደሙ ቀባ፤ ሙሴም ደሙን በመ​ሠ​ዊ​ያው ዙሪያ ረጨ።</verse>
				<verse number="25">ስቡ​ንና ላቱን፥ በሆድ ዕቃ​ውም ላይ ያለ​ውን ስብ ሁሉ፥ የጉ​በ​ቱ​ንም መረብ፥ ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ ስባ​ቸ​ው​ንም፥ ቀኝ ወር​ቹ​ንም ወሰደ፤</verse>
				<verse number="26">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ካለው የቅ​ድ​ስና መሶብ አንድ የቂጣ እን​ጎቻ፥ አን​ድም የዘ​ይት እን​ጀራ፥ አን​ድም ስስ ቂጣ ወስዶ በስ​ቡና በቀኝ ወርቹ ላይ አኖ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="27">ሁሉ​ንም በአ​ሮ​ንና በል​ጆቹ እጆች ላይ አደ​ረገ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቍር​ባ​ንን አቀ​ረበ፤</verse>
				<verse number="28">ሙሴም ከእ​ጃ​ቸው ተቀ​ብሎ በመ​ሠ​ዊ​ያው በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ላይ አኖ​ረው። በጎ መዓዛ የቅ​ድ​ስና መሥ​ዋ​ዕት ነበረ። እር​ሱም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳት ቍር​ባን ነበረ።</verse>
				<verse number="29">ሙሴም ከቅ​ድ​ስ​ናው አውራ በግ ፍር​ም​ባ​ውን ወስዶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​በው ዘንድ ቈራ​ረጠ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ይህ ለቅ​ድ​ስና ከታ​ረ​ደው አውራ በግ የሙሴ እድል ፈንታ ሆነ።</verse>
				<verse number="30">ሙሴም ከቅ​ብ​ዐቱ ዘይ​ትና በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ከአ​ለው ከደሙ ወስዶ በአ​ሮ​ንና በል​ብሱ ላይ ፥ በል​ጆ​ቹና በል​ጆቹ ልብስ ላይ ረጨው፤ አሮ​ን​ንና ልብ​ሱ​ንም፥ ልጆ​ቹ​ንም፥ የል​ጆ​ቹ​ንም ልብስ ቀደሰ።</verse>
				<verse number="31">ሙሴም አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን አላ​ቸው፥ “ሥጋ​ውን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ በተ​ቀ​ደ​ሰው ቦታ ቀቅሉ፤ አሮ​ንና ልጆቹ ይብ​ሉት ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘኝ በዚያ እር​ሱ​ንና በቅ​ድ​ስ​ናው መሶብ ያለ​ውን እን​ጀራ ብሉ።</verse>
				<verse number="32">ከሥ​ጋ​ውና ከእ​ን​ጀ​ራ​ውም የተ​ረ​ፈ​ውን በእ​ሳት አቃ​ጥ​ሉት።</verse>
				<verse number="33">ሰባት ቀን ይክ​ና​ች​ኋ​ልና የክ​ህ​ነ​ታ​ችሁ ቀን እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ ሰባት ቀን ከማ​ኅ​በሩ ድን​ኳን ደጃፍ አት​ውጡ።</verse>
				<verse number="34">በዚህ ቀን እንደ ተደ​ረገ ለእ​ና​ንተ ለማ​ስ​ተ​ስ​ረያ ይደ​ረግ ዘንድ እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዘዘ።</verse>
				<verse number="35">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ አዝ​ዞ​ኛ​ልና እን​ዳ​ት​ሞቱ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ሌሊ​ቱ​ንና ቀኑን ሰባት ቀን ተቀ​መጡ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥር​ዐት ጠብቁ፤”</verse>
				<verse number="36">አሮ​ንና ልጆ​ቹም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረጉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ ሙሴ አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጠራ።</verse>
				<verse number="2">ሙሴም አሮ​ንን አለው፥ “ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ከመ​ን​ጋው እን​ቦ​ሳ​ውን፥ ስለ​ሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አው​ራ​ውን በግ ወስ​ደህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቅ​ር​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች፦ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት አውራ ፍየ​ልን፥ ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን አንድ ዓመት የሆ​ና​ቸ​ውን ጥጃና ጠቦ​ትን፥</verse>
				<verse number="4">ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት በሬ​ንና አውራ በግን፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ለ​ወሰ የእ​ህ​ልን ቍር​ባን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይሠዉ ዘንድ ውሰዱ፤ ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገ​ለ​ጥ​ላ​ች​ኋ​ልና ብለህ ንገ​ራ​ቸው።”</verse>
				<verse number="5">ሙሴም ያዘ​ዛ​ቸ​ውን ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አመጡ፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ ቀር​በው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆሙ።</verse>
				<verse number="6">ሙሴም፥ “ታደ​ር​ጉት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዛ​ችሁ ቃል ይህ ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ይገ​ለ​ጥ​ላ​ች​ኋል” አለ።</verse>
				<verse number="7">ሙሴም አሮ​ንን፥ “ወደ መሠ​ዊ​ያው ቀር​በህ የኀ​ጢ​አ​ት​ህን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን ሠዋ፤ ለራ​ስ​ህና ለወ​ገ​ንህ አስ​ተ​ስ​ርይ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘዘ የሕ​ዝ​ቡን ቍር​ባን አቅ​ርብ፤ አስ​ተ​ስ​ር​ይ​ላ​ቸ​ውም” አለው።</verse>
				<verse number="8">አሮ​ንም ወደ መሠ​ዊ​ያው ቀርቦ ስለ ራሱ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሆ​ነ​ውን ጥጃ አረደ።</verse>
				<verse number="9">የአ​ሮ​ንም ልጆች ደሙን አቀ​ረ​ቡ​ለት፤ ጣቱ​ንም በደሙ ውስጥ ነክሮ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ቀን​ዶች ቀባ፤ ደሙ​ንም ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች አፈ​ሰ​ሰው።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ከኀ​ጢ​አቱ መሥ​ዋ​ዕት ስቡ​ንና ኵላ​ሊ​ቶ​ቹን፥ የጉ​በ​ቱ​ንም መረብ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመረ።</verse>
				<verse number="11">ሥጋ​ው​ንና ቍር​በ​ቱ​ንም ከሰ​ፈሩ ውጭ በእ​ሳት አቃ​ጠሉ።</verse>
				<verse number="12">የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አረደ፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ደሙን አመ​ጡ​ለት፤ እር​ሱም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ረጨው።</verse>
				<verse number="13">የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት በየ​ብ​ልቱ፥ ራሱ​ንም አመ​ጡ​ለት፤ እር​ሱም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመ​ረው።</verse>
				<verse number="14">የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹ​ንም በውኃ አጠበ፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ላይ ጨመ​ረው።</verse>
				<verse number="15">ከዚ​ህም በኋላ የሕ​ዝ​ቡን ቍር​ባን አቀ​ረበ፤ ስለ ሕዝቡ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሆ​ነ​ውን ፍየል ወስዶ አረ​ደው፤ አነ​ጻ​ውም፤ እንደ ፊተ​ኛ​ውም ለየው።</verse>
				<verse number="16">የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ እንደ ሥር​ዐ​ቱም አደ​ረ​ገው።</verse>
				<verse number="17">የስ​ን​ዴ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ ከእ​ር​ሱም እፍኝ ሙሉ ወስዶ በጥ​ዋት ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ሌላ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመ​ረው።</verse>
				<verse number="18">ስለ ሕዝቡ የሆ​ነ​ውን የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት፥ በሬ​ው​ንና አው​ራ​ውን በግ አረደ፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ደሙን አመ​ጡ​ለት፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ዙሪያ ረጨው፤</verse>
				<verse number="19">የበ​ሬ​ው​ንና የአ​ው​ራ​ው​ንም በግ ስብ፥ ላቱ​ንም፥ የሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ፥ ሁለ​ቱን ኵላ​ሊ​ቶ​ቹ​ንም፥ በላ​ያ​ቸ​ውም ያለ​ውን ስብ፥ የጉ​በ​ቱ​ንም መረብ አመ​ጡ​ለት።</verse>
				<verse number="20">ስቡ​ንም በፍ​ር​ም​ባ​ዎቹ ላይ አኖረ፤ ስቡ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመረ፤</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አሮን ፍር​ም​ባ​ዎ​ቹ​ንና ቀኝ ወር​ቹን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለየ።</verse>
				<verse number="22">አሮ​ንም እጆ​ቹን ወደ ሕዝቡ ዘረጋ፤ ባረ​ካ​ቸ​ውም፤ የኀ​ጢ​አ​ቱን፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም፥ የደ​ኅ​ን​ነ​ቱ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ከሠዋ በኋላ ወረደ።</verse>
				<verse number="23">ሙሴና አሮ​ንም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ገቡ፤ ወጡም፤ ሕዝ​ቡ​ንም ባረኩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ለሕ​ዝቡ ሁሉ ተገ​ለጠ።</verse>
				<verse number="24">እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጣ፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ ስቡ​ንም በላ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አይ​ተው ተደ​ነቁ፤ በግ​ም​ባ​ራ​ቸ​ውም ወደቁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">የአ​ሮ​ንም ልጆች ናዳ​ብና አብ​ዩድ በየ​ራ​ሳ​ቸው ጥና​ውን ወስ​ደው እሳት አደ​ረ​ጉ​በት፤ በላ​ዩም ዕጣን ጨመ​ሩ​በት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያላ​ዘ​ዛ​ቸ​ውን ሌላ እሳት አቀ​ረቡ።</verse>
				<verse number="2">እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጥቶ በላ​ቸው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ሞቱ።</verse>
				<verse number="3">ሙሴም አሮ​ንን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ እኔ በሚ​ቀ​ርቡ እመ​ሰ​ገ​ና​ለሁ፤ በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት እከ​ብ​ራ​ለሁ ብሎ የተ​ና​ገ​ረው ይህ ነው” አለው፤ አሮ​ንም ደነ​ገጠ።</verse>
				<verse number="4">ሙሴም የአ​ሮ​ንን አጎት የአ​ዚ​ሔ​ልን ልጆች ሚሳ​ዴ​ንና ኤል​ሳ​ፍ​ንን ጠርቶ፥ “ሂዱ፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ሁን ከመ​ቅ​ደሱ ፊት አን​ሥ​ታ​ችሁ ከሰ​ፈር ወደ ውጭ ውሰ​ዱ​አ​ቸው” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">እነ​ር​ሱም ገብ​ተው አነ​ሡ​አ​ቸው፤ ሙሴም እን​ዳለ በል​ብ​ሳ​ቸው ከሰ​ፈር ወደ ውጭ ወሰ​ዱ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">ሙሴም አሮ​ንን፥ ልጆ​ቹ​ንም አል​ዓ​ዛ​ር​ንና ኢታ​ም​ርን፥ “እን​ዳ​ት​ሞቱ፥ በማ​ኅ​በ​ሩም ላይ ሁሉ ቍጣ እን​ዳ​ይ​ወ​ርድ ራሳ​ች​ሁን አት​ንጩ፤ ልብ​ሳ​ች​ሁ​ንም አት​ቅ​ደዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስላ​ቃ​ጠ​ላ​ቸው ማቃ​ጠል ግን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ያል​ቅሱ።</verse>
				<verse number="7">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቅ​ብ​ዐት ዘይት በላ​ያ​ችሁ ነውና እን​ዳ​ት​ሞቱ ከም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አት​ውጡ” አላ​ቸው። ሙሴም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="9">“እን​ዳ​ት​ሞቱ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ስት​ገቡ ወይም ወደ መሠ​ዊ​ያው ስት​ቀ​ርቡ አን​ተና ልጆ​ችህ የወ​ይን ጠጅና የሚ​ያ​ሰ​ክ​ርን ነገር ሁሉ አት​ጠጡ፤ ይህም ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤</verse>
				<verse number="10">በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውና በአ​ል​ተ​ቀ​ደ​ሰው፥ በር​ኩ​ሱና በን​ጹ​ሑም መካ​ከል ትለ​ያ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሙሴ እጅ የነ​ገ​ራ​ቸ​ውን ሥር​ዐት ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ታስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ዋ​ለህ።”</verse>
				<verse number="12">ሙሴም አሮ​ንን፥ የተ​ረ​ፉ​ለ​ትን ልጆ​ቹን አል​ዓ​ዛ​ር​ንና ኢታ​ም​ርን አላ​ቸው፥ “ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነውና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆ​ነው ከእ​ሳት ቍር​ባን የቀ​ረ​ውን የስ​ን​ዴ​ውን ቍር​ባን ውሰዱ፤ ቂጣም አድ​ር​ጋ​ችሁ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ብሉት፤</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አዝ​ዞ​ኛ​ልና፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆ​ነው ከእ​ሳት ቍር​ባን ለአ​ን​ተም፥ ለል​ጆ​ች​ህም የተ​ሰጠ ሥር​ዐት ነውና በቅ​ዱስ ስፍራ ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="14">እነ​ዚ​ህም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ቶች ለአ​ን​ተና ለል​ጆ​ችህ ሥር​ዐት እን​ዲ​ሆኑ ስለ ተሰጡ፥ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን ፍር​ም​ባና ወርች አንተ፥ ከአ​ንተ ጋርም ልጆ​ችህ፥ ቤተ​ሰ​ብ​ህም ተለ​ይቶ በን​ጹሕ ስፍራ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="15">የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን ወር​ችና ፍር​ምባ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከሚ​ቀ​ር​በው መሥ​ዋ​ዕት የእ​ሳት ቍር​ባን ከሆ​ነው ስብ ጋር ያመ​ጣሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘዘ ለአ​ንተ፥ ከአ​ንተ ጋርም ለወ​ን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ችህ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል።”</verse>
				<verse number="16">ሙሴም የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ፍየል እጅግ ፈለ​ገው፤ በፈ​ለ​ገ​ውም ጊዜ እነሆ ተቃ​ጥሎ ነበር፤ ሙሴም የቀ​ሩ​ትን የአ​ሮ​ንን ልጆች አል​ዓ​ዛ​ር​ንና ኢታ​ም​ርን ተቈ​ጣ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፦</verse>
				<verse number="17">“ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነውና፥ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ኀጢ​አት እን​ድ​ት​ሸ​ከሙ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት እን​ድ​ታ​ስ​ተ​ሰ​ር​ዩ​ላ​ቸው ይህን ትበሉ ዘንድ ለእ​ና​ንተ ሰጥ​ቶ​ታ​ልና ስለ ምን የኀ​ጢ​አ​ትን መሥ​ዋ​ዕት በቅ​ዱሱ ስፍራ አል​በ​ላ​ች​ሁም?</verse>
				<verse number="18">እነሆ፥ ደሙን ወደ መቅ​ደስ ውስጥ አላ​ገ​ባ​ች​ሁ​ትም፤ እኔ እን​ደ​ታ​ዘ​ዝሁ በቅ​ዱስ ስፍራ ውስጥ ትበ​ሉት ዘንድ ይገ​ባ​ችሁ ነበር።”</verse>
				<verse number="19">አሮ​ንም ሙሴን ተና​ገ​ረው እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ ዛሬ የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በለዩ ጊዜ፥ ይህች አገ​ኘ​ችኝ፤ ዛሬም የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት እበላ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካም አይ​ደ​ለም።”</verse>
				<verse number="20">ሙሴም ሰማ፤ ደስም አለው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦</verse>
				<verse number="2">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩ​አ​ቸው፦ በም​ድር ካሉት እን​ስ​ሳት ሁሉ የም​ት​በ​ሉ​አ​ቸው እን​ስ​ሳት እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="3">የተ​ሰ​ነ​ጠቀ ሰኰና ያለ​ው​ንና የሚ​ያ​መ​ሰ​ኳ​ውን እን​ስሳ ሁሉ ብሉ።</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን ከሚ​ያ​መ​ሰ​ኩት ፥ ሰኰ​ና​ቸ​ውም ስን​ጥቅ ከሆ​ነው ከእ​ነ​ዚህ አት​በ​ሉም፤ ግመል ያመ​ሰ​ኳል፤ ነገር ግን ሰኰ​ናው ስላ​ል​ተ​ሰ​ነ​ጠቀ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="5">ጥን​ቸል ያመ​ሰ​ኳል፤ ነገር ግን ሰኰ​ናው ስላ​ል​ተ​ሰ​ነ​ጠቀ ይህ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="6">ሽኮኮ ያመ​ሰ​ኳል፤ ነገር ግን ሰኰ​ናው ስላ​ል​ተ​ሰ​ነ​ጠቀ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="7">እር​ያም ሰኰ​ናው ተሰ​ን​ጥ​ቆ​አል፤ ነገር ግን ስለ​ማ​ያ​መ​ሰኳ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="8">የእ​ነ​ዚ​ህን ሥጋ አት​በ​ሉም፤ በድ​ና​ቸ​ው​ንም አት​ነ​ኩም፤ ለእ​ና​ንተ ርኩ​ሳን ናቸው።</verse>
				<verse number="9">“በውኃ ውስጥ ከሚ​ኖ​ሩት ሁሉ እነ​ዚ​ህን ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በው​ኆች፥ በባ​ሕ​ሮ​ችም፥ በወ​ን​ዞ​ችም ውስጥ ከሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ክን​ፍና ቅር​ፊት ያላ​ቸ​ውን ትበ​ላ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="10">በው​ኆች ውስጥ ከሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀሱ፥ በው​ኆች ውስጥ የሕ​ይ​ወት ነፍስ ከአ​ላ​ቸው ሁሉ፥ በባ​ሕ​ሮ​ችና በወ​ን​ዞች ውስጥ ክን​ፍና ቅር​ፊት የሌ​ላ​ቸው ሁሉ በእ​ና​ንተ ዘንድ የተ​ጸ​የፉ ናቸው።</verse>
				<verse number="11">በእ​ና​ን​ተም ዘንድ የተ​ጸ​የፉ ይሆ​ናሉ። ሥጋ​ቸ​ው​ንም አት​በ​ሉም፤ በድ​ና​ቸ​ው​ንም ትጸ​የ​ፋ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="12">ክን​ፍና ቅር​ፊ​ትም የሌ​ላ​ቸው በውኃ ውስጥ የሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ለእ​ና​ንተ ርኩ​ሳን ናቸው።</verse>
				<verse number="13">“ከወ​ፎ​ችም ወገን የም​ት​ጸ​የ​ፉ​አ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው፤ አይ​በ​ሉም፤ የተ​ጸ​የፉ ናቸው፤ ንስር፥ ገዴ አሞራ፥ ዓሣ አውጭ፥</verse>
				<verse number="14">ጭላት፥ ጭል​ፊት፥ አንጭ አሞራ በየ​ወ​ገኑ፤</verse>
				<verse number="15">ቁራ ሁሉ በየ​ወ​ገኑ፤</verse>
				<verse number="16">ሰጎን በየ​ወ​ገኑ፤ ጠለቋ፥ ዝዪ፥ በቋል በየ​ወ​ገኑ፤</verse>
				<verse number="17">ጉጉት፥ እር​ኩም፥ ጋጋኖ፥</verse>
				<verse number="18">የውኃ ዶሮ፥ ይብራ፥ ጥምብ አንሣ አሞራ፥</verse>
				<verse number="19">ሸመላ፥ ሳቢሳ በየ​ወ​ገኑ፤ ጅን​ጅ​ላቴ ወፍ፥ የሌ​ሊት ወፍ።</verse>
				<verse number="20">“የሚ​በ​ር​ርም፥ በአ​ራት እግ​ሮ​ችም የሚ​ሄድ ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ ሁሉ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="21">ነገር ግን ከሚ​በ​ር​ሩት፥ አራ​ትም እግ​ሮች ካሉ​አ​ቸው፥ ከእ​ግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም በላይ በም​ድር ላይ የሚ​ዘ​ል​ሉ​ባ​ቸው ጭኖች ካሉ​አ​ቸው ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች እነ​ዚ​ህን ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="22">ከእ​ነ​ር​ሱም እነ​ዚ​ህን አት​በ​ሉም፤ ኩብ​ኩባ የሚ​መ​ስ​ለ​ውም፥ ፌንጣ የሚ​መ​ስ​ለ​ውም፥ አሸን የሚ​መ​ስ​ለ​ውም፥ አን​በጣ የሚ​መ​ስ​ለ​ውም።</verse>
				<verse number="23">የሚ​በ​ርር፥ አራ​ትም እግ​ሮች ያሉት ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ ሁሉ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="24">“በእ​ነ​ዚ​ህም ርኩስ ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ የእ​ነ​ር​ሱ​ንም በድን የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="25">ከእ​ነ​ር​ሱም በድን የሚ​ያ​ነሣ ሁሉ ልብ​ሱን ይጠብ፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="26">ሰኰ​ናም ያለው፥ ነገር ግን ሰኰ​ናው ያል​ተ​ሰ​ነ​ጠቀ፥ የማ​ያ​መ​ሰ​ኳም እን​ስሳ ሁሉ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው፤ እር​ሱን የሚ​ነካ ሁሉ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="27">በአ​ራት እግ​ሮቹ ከሚ​ሄድ እን​ስሳ ሁሉ በመ​ዳ​ፎቹ ላይ የሚ​ሄድ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው፤ የእ​ር​ሱን በድን የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="28">በድ​ና​ቸ​ው​ንም የሚ​ያ​ነሣ ልብ​ሱን ይጠብ፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው። እነ​ር​ሱም በእ​ና​ንተ ዘንድ ርኩ​ሳን ናቸው።</verse>
				<verse number="29">“በም​ድር ላይም ከሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ እነ​ዚህ ለእ​ና​ንተ ርኩ​ሳን ናቸው፤ ሙጭ​ል​ጭላ፥ አይጥ፥ እን​ሽ​ላ​ሊት በየ​ወ​ገኑ፥</verse>
				<verse number="30">ኤሊ፥ አዞ፥ ገበሎ፥ አር​ጃኖ፥ እስ​ስት።</verse>
				<verse number="31">ከሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱት ሁሉ በእ​ና​ንተ ዘንድ ርኩ​ሳን የሚ​ሆኑ እነ​ዚህ ናቸው። ከእ​ነ​ር​ሱም በድ​ና​ቸ​ውን የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="32">ከእ​ነ​ር​ሱም በድ​ና​ቸው በም​ንም ላይ ቢወ​ድቅ እርሱ ርኩስ ነው፤ የዕ​ን​ጨት ዕቃ ወይም ልብስ ወይም ቍር​በት ወይም ከረ​ጢት ቢሆን የሚ​ሠ​ራ​በት ዕቃ ሁሉ እር​ሱን በውኃ ውስጥ ይን​ከ​ሩት፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው፤ ከዚ​ያም በኋላ ንጹሕ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="33">ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዳች በው​ስጡ የወ​ደ​ቀ​በ​ትን የሸ​ክ​ላ​ውን ዕቃ ሁሉ ስበ​ሩት፤ በው​ስ​ጡም ያለው ሁሉ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="34">በእ​ርሱ ውስጥ ያለው፤ ውኃም የሚ​ፈ​ስ​ስ​በት፥ የሚ​በላ መብል ሁሉ ርኩስ ነው፤ በዚ​ህም ዕቃ ሁሉ ያለው የሚ​ጠጣ መጠጥ ሁሉ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="35">ከእ​ነ​ዚ​ህም በድን የሚ​ወ​ድ​ቅ​በት ሁሉ ርኩስ ነው፤ እቶን ወይም ምድጃ ቢሆን ይሰ​ባ​በ​ራል፤ ርኩ​ሳን ናቸ​ውና፤ ለእ​ና​ንተ ርኩ​ሳን ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="36">ነገር ግን ምንጩ፥ ጉድ​ጓ​ዱም፥ የው​ኃ​ውም ኵሬ ንጹ​ሓን ናቸው፤ በድ​ና​ቸ​ውን ግን የሚ​ነካ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="37">ከበ​ድ​ና​ቸ​ውም በሚ​ዘራ ዘር ላይ አን​ዳች ቢው​ድቅ እርሱ ንጹሕ ነው።</verse>
				<verse number="38">ነገር ግን በዘሩ ላይ ውኃ ቢፈ​ስ​ስ​በት፥ ከዚህ በኋላ ከበ​ድ​ና​ቸው አን​ዳች ቢወ​ድ​ቅ​በት፥ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="39">“ለመ​ብል ከሚ​ሆ​ኑ​ላ​ችሁ እን​ስ​ሳት የሞተ ቢኖር፥ በድ​ኑን የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="40">ከበ​ድ​ኑም የሚ​በላ ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሆ​ናል፤ በድ​ኑ​ንም የሚ​ያ​ነሣ፤ ልብ​ሱን ይጠብ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="41">“በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ አውሬ ሁሉ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው፤ አት​ብ​ሉ​ትም።</verse>
				<verse number="42">በሆዱ የሚ​ሳብ፥ በአ​ራ​ትም እግ​ሮች የሚ​ሳብ፥ ብዙ እግ​ሮ​ችም ያሉት፥ በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀሱ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ሁሉ ርኩ​ሳን ናቸ​ውና አት​ብ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="43">በም​ድር ላይ በሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀሱ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ሁሉ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን አታ​ር​ክሱ፤ በእ​ነ​ር​ሱም እን​ዳ​ት​ረ​ክሱ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን አታ​ር​ክ​ሱ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="44">እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ቀድሱ፤ ቅዱ​ሳ​ንም ሁኑ፤ እኔ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ነኝና፤</verse>
				<verse number="45">በም​ድ​ርም ላይ በሚ​ሳብ ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ ሁሉ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን አታ​ሳ​ድፉ። እኔ አም​ላ​ካ​ችሁ እሆን ዘንድ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኋ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ እን​ግ​ዲህ እኔ ቅዱስ ነኝና እና​ን​ተም ቅዱ​ሳን ሁኑ።</verse>
				<verse number="46">“የእ​ን​ስ​ሳና የወፍ፥ በው​ኃ​ውም ውስጥ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ የፍ​ጥ​ረት ሁሉ፥ በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ የፍ​ጥ​ረት ሁሉ ሕግ ይህ ነው።</verse>
				<verse number="47">በር​ኩ​ስና በን​ጹሕ መካ​ከል፥ የሕ​ይ​ወት ነፍስ ካላ​ቸ​ውም በም​ት​በ​ሉ​ትና በማ​ት​በ​ሉት መካ​ከል እን​ድ​ት​ለዩ ነው።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ ሴት ብታ​ረ​ግዝ ወንድ ልጅም ብት​ወ​ልድ፥ ሰባት ቀን ያህል የረ​ከ​ሰች ናት፤</verse>
				<verse number="3">እንደ ግዳ​ጅዋ ወራት ትረ​ክ​ሳ​ለች። በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ልጁ ከሥ​ጋው ሸለ​ፈት ይገ​ረዝ።</verse>
				<verse number="4">ከደ​ም​ዋም እስ​ክ​ት​ነጻ ሠላሳ ሦስት ቀን ትቈይ፤ የመ​ን​ጻቷ ቀንም እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ የተ​ቀ​ደ​ሰን ነገር አት​ንካ፤ ወደ መቅ​ደ​ስም አት​ግባ።</verse>
				<verse number="5">ሴት ልጅም ብት​ወ​ልድ እንደ ግዳ​ጅዋ ወራት ሁለት ሳም​ንት ያህል የረ​ከ​ሰች ናት፤ ከደ​ም​ዋም እስ​ክ​ት​ነጻ ድረስ ስድሳ ስድ​ስት ቀን ትቈይ።</verse>
				<verse number="6">“የመ​ን​ጻቷ ወራ​ትም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥ ለወ​ንድ ልጅ ወይም ለሴት ልጅ፥ የአ​ንድ ዓመት ጠቦት ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ የር​ግ​ብም ግል​ገል ወይም ዋኖስ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ታመ​ጣ​ለች።</verse>
				<verse number="7">ካህ​ኑም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል፤ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ት​ማል፤ ከደ​ም​ዋም ፈሳሽ ትነ​ጻ​ለች። ወንድ ወይም ሴት ለም​ት​ወ​ልድ ሴት ሕጉ ይህ ነው።</verse>
				<verse number="8">ጠቦት ለማ​ም​ጣት የሚ​በቃ ገን​ዘብ በእ​ጅዋ ባይ​ኖ​ራት ሁለት ዋኖ​ሶች፥ ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች፥ አን​ዱን ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ሌላ​ው​ንም ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ለች፤ ካህ​ኑም ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ታል፤ እር​ስ​ዋም ትነ​ጻ​ለች።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦</verse>
				<verse number="2">“ሰው በሥ​ጋው ቆዳ ላይ እባጭ ብት​ወ​ጣ​በት፥ ብት​ነ​ጣም፥ በሥ​ጋ​ውም ቆዳ እንደ ለምጽ ደዌ ብት​መ​ስል፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ከካ​ህ​ናቱ ልጆች ወደ አንዱ ያም​ጡት።</verse>
				<verse number="3">ካህ​ኑም በሥ​ጋው ቆዳ ያለ​ች​ውን ያችን ደዌ ይያት፤ ጠጕ​ሯም ተለ​ውጣ ብት​ነጣ በሥ​ጋው ቆዳ ያለች የዚ​ያች ደዌ መልክ ቢከፋ፥ ደዌ​ውም ወደ ሥጋው ቆዳ ቢጠ​ልቅ፥ እር​ስዋ የለ​ምጽ ደዌ ናት፤ ካህ​ኑም አይቶ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይበ​ለው።</verse>
				<verse number="4">ቋቍ​ቻ​ውም በሥ​ጋው ቆዳ ላይ ቢነጣ፥ ከቆ​ዳ​ውም የጠ​ለቀ ባይ​መ​ስል፥ ጠጕ​ሩም ባይ​ነጣ፥ ካህኑ የታ​መ​መ​ውን ሰው ሰባት ቀን ይዘ​ጋ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="5">በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ካህኑ ያችን ደዌ ይያት፤ እነ​ሆም፥ ያች ደዌ በፊት እንደ ነበ​ረች ብት​ሆን፥ በቆ​ዳ​ውም ላይ ባት​ሰፋ፥ ካህኑ ሰባት ቀን ደግሞ ይለ​የ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">ደግሞ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ካህኑ ያየ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ ያች ደዌ ብት​ከ​ስም፥ በቆ​ዳ​ውም ላይ ባት​ሰፋ፥ ካህኑ፦ ‘ንጹሕ ነው’ ይለ​ዋል፤ ምል​ክት ነውና፥ ልብ​ሱ​ንም አጥቦ ንጹሕ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="7">ስለ መን​ጻቱ በካ​ህኑ ዘንድ ከታየ በኋላ ምል​ክቱ በቆ​ዳው ላይ ቢሰፋ፥ እን​ደ​ገና ሊታይ ወደ ካህኑ ይቀ​ር​ባል።</verse>
				<verse number="8">ካህ​ኑም ያያል፤ እነ​ሆም፥ ምል​ክቱ በቆ​ዳው ላይ ቢሰፋ ካህኑ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ ለምጽ ነውና።</verse>
				<verse number="9">“የለ​ምጽ ደዌ በሰው ላይ ቢወጣ እርሱ ወደ ካህኑ ይሄ​ዳል።</verse>
				<verse number="10">ካህ​ኑም ያየ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ በቆ​ዳው ላይ ነጭ እባጭ ቢሆን፥ ጠጕ​ሩም ተለ​ውጦ ቢነጣ፥ ሥጋ​ውም በእ​ባጩ ውስጥ ቢያዥ፥</verse>
				<verse number="11">እርሱ በሥ​ጋው ቆዳ ላይ አሮጌ ለምጽ ነው፤ ካህ​ኑም፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ እርሱ ርኩስ ነውና ይለ​የ​ዋል።</verse>
				<verse number="12">ለም​ጹም በቆ​ዳው ላይ ሰፍቶ ቢወጣ፥ ለም​ጹም የታ​መ​መ​ውን ሰው ቆዳ​ውን ሁሉ ከራሱ እስከ እግ​ሮቹ ድረስ እንደ ከደ​ነው ለካ​ህኑ ቢመ​ስ​ለው፤</verse>
				<verse number="13">ካህኑ ያየ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ ለምጹ ቆዳ​ውን ሁሉ ቢከ​ድን የታ​መ​መ​ውን ሰው፦ ካህኑ ‘ንጹሕ ነህ’ ይለ​ዋል፤ ሁለ​መ​ናው ተለ​ውጦ ነጭ ሆኖ​አ​ልና ንጹሕ ነው።</verse>
				<verse number="14">ደዌው በታ​የ​በት ቀን ጤነ​ኛው ቆዳ ርኩስ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="15">ካህ​ኑም ጤነ​ኛ​ውን ቆዳ አይቶ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ ስለ​ዚህ ለምጽ ነውና ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="16">ጤነ​ኛው ቆዳ ተመ​ልሶ ቢነጣ እን​ደ​ገና ወደ ካህኑ ይመ​ጣል።</verse>
				<verse number="17">ካህ​ኑም ያየ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ ደዌው ቢነጣ ካህኑ የታ​መ​መ​ውን፦ ‘ንጹሕ ነው’ ይለ​ዋል፤ ንጹሕ ነውና።</verse>
				<verse number="18">“በሥ​ጋ​ውም ቆዳ ላይ ቍስል ቢሆ​ንና ቢሽር፥</verse>
				<verse number="19">በቍ​ስ​ሉም ስፍራ ነጭ እባጭ ወይም ቀላ ያለ ቋቍቻ ቢወጣ፥ በካ​ህኑ ዘንድ ይታ​ያል።</verse>
				<verse number="20">ካህ​ኑም ያያል፤ እነ​ሆም፥ ወደ ቆዳው ውስጥ ጠልቆ ቢታይ፥ ጠጕ​ሩም ተለ​ውጦ ቢነጣ፥ ካህኑ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ የለ​ምጽ ደዌ ነው፤ ከቍ​ስሉ ውስጥ ወጥ​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="21">ካህ​ኑም ቢያ​የው፥ ነጭም ጠጕር ባይ​ኖ​ር​በት፥ ወደ ቆዳ​ውም ውስጥ ባይ​ጠ​ልቅ ነገር ግን ቢከ​ስም፥ ካህኑ ሰባት ቀን ይለ​የ​ዋል።</verse>
				<verse number="22">በቆ​ዳ​ውም ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ የለ​ምጽ ደዌ ነው፤ በእ​ት​ራቱ ላይ ወጥ​ቶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="23">ያች ደዌ ግን በስ​ፍ​ራዋ ብት​ቆም፥ ባት​ሰ​ፋም፥ የቍ​ስል እት​ራት ናት፤ ካህ​ኑም፦ ‘ንጹሕ ነው’ ይለ​ዋል።</verse>
				<verse number="24">“በሥ​ጋ​ውም ቆዳ የእ​ሳት ትኩ​ሳት ቢኖ​ር​በት፥ በተ​ቃ​ጠ​ለ​ውም ስፍራ ነጭ፥ ወይም ቀላ ያለ ቋቍቻ ቢታይ፥</verse>
				<verse number="25">ካህኑ ያየ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ በቋ​ቁ​ቻው ጠጕሩ ተለ​ውጦ ቢነጣ፥ ወደ ቆዳ​ውም ውስጥ ቢጠ​ልቅ፥ ለምጽ ነው፤ ከተ​ቃ​ጠ​ለ​ውም ስፍራ ወጥ​ቶ​አል፤ ካህ​ኑም፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ የለ​ምጽ ደዌ ነውና።</verse>
				<verse number="26">ካህ​ኑም ቢያ​የው፥ በቋ​ቍ​ቻ​ውም ነጭ ጠጕር ባይ​ኖር፥ ወደ ቆዳ​ውም ባይ​ጠ​ልቅ፥ ነገር ግን ቢከ​ስም፥ ካህኑ ሰባት ቀን ይለ​የ​ዋል።</verse>
				<verse number="27">ካህ​ኑም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ያየ​ዋል፤ በቆ​ዳ​ውም ላይ ቢሰፋ ካህኑ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ የለ​ምጽ ደዌ ነውና በእ​ት​ራቱ ላይ ወጥ​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="28">ቋቍ​ቻ​ውም በስ​ፍ​ራው ላይ ቢቆም፥ በቆ​ዳ​ውም ላይ ባይ​ሰፋ፥ ነገር ግን ቢከ​ስም፥ የት​ኩ​ሳት እባጭ ነው፤ የት​ኩ​ሳ​ትም ጠባሳ ነውና ካህኑ፦ ‘ንጹሕ ነው’ ይለ​ዋል።</verse>
				<verse number="29">“ማና​ቸ​ውም ወንድ ወይም ሴት በራሱ ወይም በአ​ገጩ የለ​ምጽ ደዌ ቢኖ​ር​በት፥ ካህኑ የለ​ም​ጹን ደዌ ያያል፤</verse>
				<verse number="30">እነ​ሆም፥ ወደ ቆዳው ቢጠ​ልቅ፥ በው​ስ​ጡም ቀጭን ብጫ ጠጕር ቢኖ​ር​በት፥ ካህኑ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ ቈረ​ቈር ነው፤ የራስ ወይም የአ​ገጭ ለምጽ ነው።</verse>
				<verse number="31">ካህ​ኑም የቈ​ረ​ቈ​ሩን ደዌ ቢያይ፥ ወደ ቆዳ​ውም ባይ​ጠ​ልቅ፥ ጥቁ​ርም ጠጕር ባይ​ኖ​ር​በት፥ ካህኑ የቈ​ረ​ቈር ደዌ ያለ​በ​ትን ሰው ሰባት ቀን ይለ​የ​ዋል።</verse>
				<verse number="32">ካህ​ኑም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ደዌ​ውን ያያል፤ እነ​ሆም፥ ቈረ​ቈሩ ባይ​ሰፋ፥ በው​ስ​ጡም ብጫ ጠጕር ባይ​ኖር፥ የቈ​ረ​ቈ​ሩም መልክ ወደ ቆዳው ባይ​ጠ​ልቅ፤ ይላ​ጫል፤</verse>
				<verse number="33">ቈረ​ቈሩ ግን አይ​ላ​ጭም፤ ካህ​ኑም ቈር​ቈር ያለ​በ​ትን ሰው ሰባት ቀን ደግሞ ይለ​የ​ዋል።</verse>
				<verse number="34">ካህ​ኑም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ቈረ​ቈ​ሩን ያያል፤ እነ​ሆም፥ ከተ​ላጨ በኋላ ቈረ​ቈሩ በቆ​ዳው ላይ ባይ​ሰፋ፥ መል​ኩም ወደ ቆዳው ባይ​ጠ​ልቅ፥ ካህኑ፦ ‘ንጹሕ ነው’ ይለ​ዋል፤ ልብ​ሱን አጥቦ ንጹሕ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="35">ከነጻ በኋላ ግን ቈረ​ቈሩ በቆ​ዳው ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ ያየ​ዋል፤</verse>
				<verse number="36">እነ​ሆም፥ ቈረ​ቈሩ በቆ​ዳው ላይ ቢሰፋ ካህኑ ብጫ​ውን ጠጕር አይ​ፈ​ል​ግም፤ ርኩስ ነውና።</verse>
				<verse number="37">ቈረ​ቈሩ ግን ፊት እንደ ነበረ በቦ​ታው ቢኖር፥ ጥቁ​ርም ጠጕር ቢበ​ቅ​ል​በት፥ ቈረ​ቈሩ ሽሮ​አል፤ እር​ሱም ንጹሕ ነው፤ ካህ​ኑም፦ ‘ንጹሕ ነው’ ይለ​ዋል።</verse>
				<verse number="38">“ማና​ቸ​ውም ወንድ ወይም ሴት በሥ​ጋው ቆዳ ላይ ነጭ ቋቍቻ ቢኖ​ር​በት፥</verse>
				<verse number="39">ካህኑ ያያል፤ እነ​ሆም፥ በሥ​ጋ​ቸው ቆዳ ላይ ያለው ቋቍቻ ፈገግ ቢል አጓ​ጐት ነው፤ ከቆ​ዳው ውስጥ ወጥ​ቶ​አል፤ ንጹሕ ነው።</verse>
				<verse number="40">“የሰ​ውም ጠጕር ከራሱ ቢመ​ለጥ እርሱ በራ ነው፤ ነገር ግን ንጹሕ ነው።</verse>
				<verse number="41">ጠጕሩ ከግ​ን​ባሩ ቢመ​ለጥ እርሱ ራሰ በራ ነው፤ ነገር ግን ንጹሕ ነው።</verse>
				<verse number="42">በቡ​ሀ​ነቱ ወይም በራሰ በራ​ነቱ ነጭ፥ ወይም ቀላ ያለ ደዌ ቢኖ​ር​በት፥ እርሱ ከቡ​ሀ​ነቱ ወይም ከራሰ በራ​ነቱ የወጣ ለምጽ ነው።</verse>
				<verse number="43">ካህ​ኑም ያየ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ የደ​ዌው እብ​ጠት በሥ​ጋው ቆዳ ላይ የሆነ ለምጽ መስሎ፥ በቡ​ሀ​ነቱ ወይም በራሰ በራ​ነቱ ነጭ ወይም ቀላ ያለ ቢሆን፥</verse>
				<verse number="44">ለም​ጻም ሰው ነው፤ ርኩስ ነው፤ ካህኑ፦ በር​ግጥ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ ደዌው በራሱ ነው።</verse>
				<verse number="45">“የለ​ምጽ ደዌ ያለ​በት ሰው ልብሱ የተ​ቀ​ደደ ይሁን፤ ራሱም የተ​ገ​ለጠ ይሁን፤ ከን​ፈ​ሩ​ንም ይሸ​ፍን፤ ርኩስ ይባ​ላል።</verse>
				<verse number="46">ደዌው ባለ​በት ዘመን ሁሉ ርኩስ ይሆ​ናል፤ እርሱ ርኩስ ነው፤ ብቻ​ውን ይቀ​መ​ጣል፤ መኖ​ሪ​ያ​ውም ከሰ​ፈር በውጭ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="47">“የለ​ም​ጽም ደዌ በል​ብስ ላይ ቢሆን፥ ልብ​ሱም የበግ ጠጕር ወይም የተ​ልባ እግር ቢሆን፥</verse>
				<verse number="48">በድሩ ወይም በማጉ ላይ ቢሆን፥ የበግ ጠጕር ወይም የተ​ልባ እግር ቢሆን፥ ቆዳ ወይም ከቆዳ የሚ​ደ​ረግ ነገር ቢሆን፥</verse>
				<verse number="49">ደዌው በል​ብሱ ወይም በቆ​ዳው ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከቆዳ በሚ​ደ​ረ​ገው ነገር አረ​ን​ጓዴ ወይም ቀይ ቢሆን፥ የለ​ምጽ ደዌ ነው፤ ለካ​ህኑ ያሳ​ያል።</verse>
				<verse number="50">ካህ​ኑም ደዌ​ውን አይቶ ደዌው ያለ​በ​ትን ነገር ሰባት ቀን ይለ​የ​ዋል።</verse>
				<verse number="51">በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ደዌ​ውን ያያል፤ ደዌ​ውም በል​ብስ ላይ ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም በቆ​ዳው ወይም ከቆ​ዳው በሚ​ደ​ረግ ነገር ቢሰፋ፥ ደዌው እየ​ፋገ የሚ​ሄድ ለምጽ ነው፤ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="52">ልብ​ሱን ያቃ​ጥ​ላል፤ ድሩ ወይም ማጉ የበግ ጠጕር ወይም የተ​ልባ እግር ቢሆን ወይም ከቆዳ የተ​ደ​ረገ ቢሆን፥ ደዌ ያለ​በት ሁሉ እየ​ፋገ የሚ​ሄድ ለምጽ ነውና በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላል።</verse>
				<verse number="53">“ካህኑ ቢያይ፥ እነ​ሆም፥ ደዌው በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከቆዳ በተ​ደ​ረገ ነገር ቢሆን በል​ብሱ ላይ ባይ​ሰፋ፥</verse>
				<verse number="54">ካህኑ ደዌ ያለ​በቱ ነገር እን​ዲ​ታ​ጠብ ያዝ​ዛል፤ ሌላም ሰባት ቀን ይለ​የ​ዋል።</verse>
				<verse number="55">ደዌ​ውም ከታ​ጠበ በኋላ ካህኑ ያየ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ ደዌው መል​ኩን ባይ​ለ​ውጥ፥ ባይ​ሰ​ፋም፥ ርኩስ ነው፤ በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​ታል፤ በል​ብ​ሱም ውስጥ በማ​ጉም፥ በድ​ሩም ወጥ​ቶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="56">“ካህ​ኑም ቢያይ፥ እነሆ፥ ደዌው ከታ​ጠበ በኋላ ቢከ​ስም፥ ከል​ብሱ ወይም ከድሩ ወይም ከማጉ ወይም ከቆ​ዳው ይቅ​ደ​ደው።</verse>
				<verse number="57">በል​ብ​ሱም ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከቆዳ በተ​ደ​ረገ ነገር ላይ ደግሞ ቢታይ፥ የወጣ ለምጽ ነው፤ ደዌው ያለ​በ​ትን ነገር ያቃ​ጥ​ሉት።</verse>
				<verse number="58">ልብሱ ወይም ድሩ ወይም ማጉ ወይም ከቆዳ የተ​ደ​ረ​ገው ነገር ከታ​ጠበ በኋላ ደዌው ቢለ​ቅ​ቀው ሁለ​ተኛ ጊዜ ይታ​ጠ​ባል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="59">“በበግ ጠጕር ልብስ፥ ወይም በተ​ልባ እግር ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከቆዳ በተ​ደ​ረገ ነገር ላይ ቢሆን፥ ንጹሕ ወይም ርኩስ ያሰኝ ዘንድ የለ​ምጽ ደዌ ሕግ ይህ ነው።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“ለምጽ ለያ​ዘው ሰው ሕጉ ይህ ነው፤ ከለ​ምጽ በነ​ጻ​በት ቀን ወደ ካህኑ ይወ​ስ​ዱ​ታል።</verse>
				<verse number="3">ካህ​ኑም ከሰ​ፈር ወደ ውጭ ይወ​ጣል፤ ካህ​ኑም ያየ​ዋል፤</verse>
				<verse number="4">እነ​ሆም፥ የለ​ምጹ ደዌ ከለ​ም​ጻሙ ላይ ቢጠፋ፥ ካህኑ ስለ​ሚ​ነ​ጻው ሰው ሁለት ንጹ​ሓን ዶሮ​ዎች በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው፥ የዝ​ግ​ባም ዕን​ጨት፥ ቀይ ግም​ጃም፥ ሂሶ​ጵም ያመጣ ዘንድ ያዝ​ዛል።</verse>
				<verse number="5">ካህ​ኑም ከሁ​ለቱ ዶሮ​ዎች አን​ደ​ኛ​ዋን በሸ​ክላ ዕቃ ውስጥ በም​ንጭ ውኃ ላይ ያርድ ዘንድ ያዝ​ዛል።</verse>
				<verse number="6">ያል​ታ​ረ​ደ​ች​ው​ንም ዶሮ፥ ዝግ​ባ​ው​ንም ዕን​ጨት፥ ቀዩ​ንም ግምጃ፥ ሂሶ​ጱ​ንም ወስዶ በም​ንጭ ውኃ ላይ በታ​ረ​ደ​ችው ዶሮ ደም ውስጥ ይነ​ክ​ራ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">ከለ​ም​ጹም በሚ​ነ​ጻው ሰው ላይ ሰባት ጊዜ ይረ​ጫል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል፤ ያል​ታ​ረ​ደ​ች​ውን ዶሮ ወደ ሜዳ ይለ​ቅ​ቃ​ታል።</verse>
				<verse number="8">የነ​ጻ​ውም ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ጠጕ​ሩ​ንም ሁሉ ይላ​ጫል፤ በው​ኃም ይታ​ጠ​ባል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል። ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገ​ባል፤ ነገር ግን ከቤቱ በውጭ ሆኖ ሰባት ቀን ይቀ​መ​ጣል።</verse>
				<verse number="9">በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ጠጕ​ሩን ሁሉ ይላ​ጫል፤ ራሱ​ንም፥ ጢሙ​ንም፥ ቅን​ድ​ቡ​ንም፥ የገ​ላ​ው​ንም ጠጕር ሁሉ ይላ​ጫል፤ ልብ​ሱ​ንም፥ ገላ​ው​ንም በውኃ ያጥ​ባል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="10">“በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን፥ ዓመት የሞ​ላ​ቸ​ውን ሁለት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ት​ንም አን​ዲት የዓ​መት እን​ስት የበግ ጠቦት፥ ስለ እህ​ልም ቍር​ባን ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ የሆነ፥ በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት፥ አንድ ማሰሮ ዘይ​ትም ይወ​ስ​ዳል።</verse>
				<verse number="11">የሚ​ያ​ነ​ጻ​ውም ካህን እነ​ዚ​ህን ነገ​ሮች፥ የሚ​ነ​ጻ​ው​ንም ሰው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አጠ​ገብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="12">ካህ​ኑም አን​ዱን ጠቦት ወስዶ ስለ በደል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ያንም አንድ ማሰሮ ዘይት ስለ ልዩ ቍር​ባን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይለ​የ​ዋል።</verse>
				<verse number="13">የኀ​ጢ​አ​ትን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ያ​ር​ዱ​በት በተ​ቀ​ደ​ሰው ስፍራ ጠቦ​ቱን ያር​ዱ​ታል፤ የበ​ደሉ መሥ​ዋ​ዕት ለካ​ህኑ እን​ደ​ሚ​ሆን፥ እን​ዲሁ የኀ​ጢ​አቱ መሥ​ዋ​ዕት ነውና፤ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።</verse>
				<verse number="14">ካህ​ኑም ከበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ደም ወስዶ የሚ​ነ​ጻ​ውን ሰው የቀኝ ጆሮ​ውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁ​ንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግ​ሩ​ንም አውራ ጣት ይቀ​ባ​ዋል።</verse>
				<verse number="15">ካህ​ኑም ከማ​ሰ​ሮው ዘይት ወስዶ በግራ እጁ ውስጥ ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።</verse>
				<verse number="16">ካህ​ኑም በግራ እጁ ውስጥ ባለው ዘይት ቀኝ ጣቱን ነክሮ ከዘ​ይቱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሰባት ጊዜ በጣቱ ይረ​ጫል።</verse>
				<verse number="17">ካህ​ኑም በእጁ ውስጥ ከቀ​ረው ዘይት የሚ​ነ​ጻ​ውን ሰው የቀኝ ጆሮ​ውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁ​ንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግ​ሩ​ንም አውራ ጣት የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ደም ባረ​ፈ​በት ላይ ይቀ​ባ​ዋል።</verse>
				<verse number="18">በካ​ህ​ኑም እጅ ውስጥ የቀ​ረ​ውን ዘይት ካህኑ በሚ​ነ​ጻው ሰው ራስ ላይ ያደ​ር​ግ​በ​ታል፤ ካህ​ኑም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="19">ካህ​ኑም የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ካህ​ኑም ከኀ​ጢ​አቱ ለማ​ን​ጻት ለሚ​ነ​ጻው ሰው ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ከዚ​ህም በኋላ ካህኑ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያር​ዳል።</verse>
				<verse number="20">ካህ​ኑም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​ባል፤ ካህ​ኑም ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ እር​ሱም ንጹሕ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="21">“ድሃም ቢሆን፥ በእ​ጁም ገን​ዘብ ባይ​ኖ​ረው፥ ማስ​ተ​ስ​ረያ ይሆ​ን​ለት ዘንድ አንድ ጠቦት ስለ በደል የመ​ለ​የት መሥ​ዋ​ዕት፥ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያ​ውም ከዐ​ሥር እጅ አንድ እጅ የሆነ በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ የስ​ንዴ ዱቄት ለቍ​ር​ባን፥ አንድ ማሰሮ ዘይ​ትም ያመ​ጣል።</verse>
				<verse number="22">ሁለት ዋኖ​ሶች፥ ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች በእጁ እን​ዳ​ገኘ አን​ዲ​ቱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ አን​ዲ​ቱ​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ይወ​ስ​ዳል።</verse>
				<verse number="23">በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ያነ​ጹት ዘንድ ወደ ካህኑ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያመ​ጣ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="24">ካህ​ኑም የበ​ደ​ሉን መሥ​ዋ​ዕት የበግ ጠቦት የማ​ሰ​ሮ​ው​ንም ዘይት ይወ​ስ​ዳል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ለቍ​ር​ባን ያቀ​ር​በ​ዋል።</verse>
				<verse number="25">የበ​ደ​ሉ​ንም መሥ​ዋ​ዕት የበግ ጠቦት ያር​ዳል፤ ካህ​ኑም ከበ​ደሉ መሥ​ዋ​ዕት ደም ወስዶ የሚ​ነ​ጻ​ውን ሰው የቀኝ ጆሮ​ውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁ​ንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግ​ሩ​ንም አውራ ጣት ይቀ​ባ​ዋል።</verse>
				<verse number="26">ካህ​ኑም ከዘ​ይቱ በግራ እጁ ውስጥ ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።</verse>
				<verse number="27">ካህ​ኑም በግራ እጁ ውስጥ ከአ​ለው ዘይት በቀኝ ጣቱ ሰባት ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይረ​ጨ​ዋል።</verse>
				<verse number="28">ካህ​ኑም በእጁ ውስጥ ከአ​ለው ዘይት የሚ​ነ​ጻ​ውን ሰው የቀኝ ጆሮ​ውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁ​ንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግ​ሩ​ንም አውራ ጣት የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ደም ባረ​ፈ​በት ላይ ይቀ​ባ​ዋል።</verse>
				<verse number="29">በካ​ህኑ እጅ ውስጥ የቀ​ረ​ውን ዘይት በሚ​ነ​ጻው ሰው ራስ ላይ ያደ​ር​ገ​ዋል፤ ካህ​ኑም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="30">በእጁ ከአ​ለው ከዋ​ኖ​ሶች ወይም ከር​ግብ ግል​ገ​ሎች አን​ዱን ያቀ​ር​ባል።</verse>
				<verse number="31">አን​ዲ​ቱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ ሌላ​ዪ​ቱ​ንም ከእ​ህል ቍር​ባን ጋር ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ካህ​ኑም ለሚ​ነ​ጻው ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="32">ለመ​ን​ጻቱ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ውን ነገር ለማ​ያ​ገኝ የለ​ምጽ ደዌ ላለ​በት ሰው ሕጉ ይህ ነው።”</verse>
				<verse number="33">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦</verse>
				<verse number="34">“ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ እኔ ወደ​ም​ሰ​ጣ​ችሁ ርስት ወደ ከነ​ዓን ምድር በገ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ እኔም የለ​ምጽ ደዌ ምል​ክት በር​ስ​ታ​ችሁ ምድር ቤቶች ባደ​ረ​ግሁ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="35">ባለ​ቤቱ መጥቶ ካህ​ኑን፦ ‘ደዌ በቤቴ ውስጥ እን​ዳለ አይ​ቻ​ለሁ’ ብሎ ይን​ገ​ረው።</verse>
				<verse number="36">ካህ​ኑም በቤቱ ውስጥ ያለው ዕቃ ሁሉ እን​ዳ​ይ​ረ​ክስ፥ እርሱ የለ​ም​ጹን ምል​ክት ለማ​የት ወደ ቤት ሳይ​ገባ፥ ቤቱን ባዶ እን​ዲ​ያ​ደ​ር​ጉት ያዝ​ዛል፤ በኋ​ላም ካህኑ ቤቱን ለማ​የት ይገ​ባል።</verse>
				<verse number="37">የለ​ም​ጹ​ንም ምል​ክት ያያል፤ እነ​ሆም፥ የለ​ምጹ ምል​ክት በግ​ንቡ ላይ በአ​ረ​ን​ጓ​ዴና በቀይ ቢዥ​ጐ​ረ​ጐር፥ መል​ኩም ወደ ግንቡ ውስጥ ቢጠ​ልቅ፥</verse>
				<verse number="38">ካህኑ ከቤቱ ውስጥ ወደ ቤቱ በር ወጥቶ ሰባት ቀን ቤቱን ይዘ​ጋ​ዋል።</verse>
				<verse number="39">ካህ​ኑም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ተመ​ልሶ ቤቱን ያያል፤</verse>
				<verse number="40">እነ​ሆም፥ ደዌው በቤቱ ግንብ ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ ደዌ ያለ​ባ​ቸ​ውን ድን​ጋ​ዮች እን​ዲ​ያ​ወጡ፥ ከከ​ተ​ማ​ውም ወደ ውጭ ወደ ረከ​ሰው ስፍራ እን​ዲ​ጥ​ሉ​አ​ቸው ያዝ​ዛል።</verse>
				<verse number="41">ቤቱ​ንም በው​ስጡ በዙ​ሪ​ያው ያስ​ፍ​ቀ​ዋል፤ የፋ​ቁ​ት​ንም የም​ር​ጊ​ቱን አፈር ከከ​ተ​ማው ወደ ውጭ ወደ ረከሰ ስፍራ ያፈ​ስ​ሱ​ታል።</verse>
				<verse number="42">በእ​ነ​ዚ​ያም ድን​ጋ​ዮች ስፍራ ሌሎች ድን​ጋ​ዮ​ችን ያገ​ባሉ፤ ሌላም ጭቃ ወስ​ደው ቤቱን ይመ​ር​ጉ​ታል።</verse>
				<verse number="43">“ደዌ​ውም ዳግም ቢመ​ለስ፥ ድን​ጋ​ዮ​ቹም ከወጡ፥ ቤቱም ከተ​ፋ​ቀና ከተ​መ​ረገ በኋላ በቤቱ ውስጥ ቢሰፋ፥</verse>
				<verse number="44">ካህኑ ገብቶ ያያል፤ እነ​ሆም፥ ደዌው በቤቱ ውስጥ ቢሰፋ፥ በቤቱ ውስጥ ያለው እየ​ፋገ የሚ​ሄድ ለምጽ ነው፤ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="45">ቤቱ​ንም፥ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም፥ ዕን​ጨ​ቱ​ንም፥ የቤ​ቱ​ንም ምር​ጊት ሁሉ ያፈ​ር​ሳል፤ እነ​ር​ሱ​ንም ከከ​ተ​ማው ወደ ውጭ ወደ ርኩስ ስፍራ ያወ​ጣል።</verse>
				<verse number="46">በተ​ዘ​ጋ​በ​ትም ጊዜ ሁሉ ወደ ቤቱ የሚ​ገባ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="47">በቤ​ቱም የሚ​ተኛ ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው፤ በቤ​ቱም የሚ​በላ ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="48">“ካህ​ኑም ገብቶ ቢያ​የው፥ እነ​ሆም፥ ቤቱ ከተ​መ​ረገ በኋላ ደዌው በቤቱ ውስጥ ባይ​ሰፋ፥ ደዌው ስለ ሻረ ካህኑ ቤቱን፦ ንጹሕ ነው ይለ​ዋል።</verse>
				<verse number="49">ካህ​ኑም ቤቱን ለማ​ን​ጻት ሁለት ዶሮ​ዎች፥ የዝ​ግባ ዕን​ጨት፥ ቀይ ግምጃ፥ ሂሶ​ጵም ይወ​ስ​ዳል።</verse>
				<verse number="50">አን​ደ​ኛ​ዪ​ቱ​ንም ዶሮ በሸ​ክላ ዕቃ ውስጥ ከም​ንጩ ውኃ በላይ ያር​ዳል።</verse>
				<verse number="51">የዝ​ግ​ባ​ውን ዕን​ጨት፥ ሂሶ​ጱ​ንም፥ ቀዩ​ንም ግምጃ፥ ደኅ​ነ​ኛ​ዪ​ቱ​ንም ዶሮ ወስዶ በታ​ረ​ደ​ችው ዶሮ ደምና በም​ንጩ ውኃ ውስጥ ይነ​ክ​ራ​ቸ​ዋል፥ ቤቱ​ንም ሰባት ጊዜ ይረ​ጨ​ዋል።</verse>
				<verse number="52">ቤቱ​ንም በዶ​ሮ​ዪቱ ደም በም​ን​ጩም ውኃ፥ በደ​ኅ​ነ​ኛ​ዪ​ቱም ዶሮ፥ በዝ​ግ​ባ​ውም ዕን​ጨት፥ በሂ​ሶ​ጱም፥ በቀ​ዩም ግምጃ ያነ​ጻ​ዋል።</verse>
				<verse number="53">ደኅ​ነ​ኛ​ዪ​ቱ​ንም ዶሮ ከከ​ተማ ወደ ሜዳ ይሰ​ድ​ዳ​ታል፤ ለቤ​ቱም ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="54">“ይህም ሕግ ነው፤ ለሁሉ ዓይ​ነት ለም​ጽና የቈ​ረ​ቈር ደዌ ሕጉ ይህ ነው፤</verse>
				<verse number="55">በል​ብ​ስና በቤ​ትም ላለ ለምጽ፥</verse>
				<verse number="56">ለዕ​ባ​ጭም፥ ለብ​ጕ​ርም፥ ለቋ​ቍ​ቻም፤</verse>
				<verse number="57">በሚ​ረ​ክ​ስና በሚ​ነጻ ጊዜ እን​ዲ​ያ​ስ​ታ​ውቅ ይህ የለ​ምጽ ሕግ ነው።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፥</verse>
				<verse number="2">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩ​አ​ቸው፦ ከሰ​ው​ነቱ ዘር የሚ​ፈ​ስ​ሰው ሰው ቢኖር ስለ​ሚ​ፈ​ስ​ሰው ነገር ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="3">ከሰ​ው​ነቱ ፈሳሽ ለሚ​ፈ​ስ​ሰው ሰው የር​ኵ​ሰቱ ሕግ ይህ ነው፤ ፈሳሽ የሚ​ፈ​ስ​ሰው ሰው ፈሳሹ እየ​ፈ​ሰ​ሰው በሚ​ኖ​ር​በት ጊዜ ሁሉ ርኩስ ነው፤ ፈሳሹ ያረ​ክ​ሰ​ዋል።</verse>
				<verse number="4">ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ሰው የሚ​ተ​ኛ​በት መኝታ ሁሉ ርኩስ ነው፤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​በ​ትም ነገር ሁሉ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="5">መኝ​ታ​ው​ንም የሚ​ነካ ሰው ሁሉ ልብ​ሱን ይጠብ፤ በው​ኃም ሰው​ነ​ቱን ይታ​ጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="6">ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ሰው በተ​ቀ​መ​ጠ​በት ነገር ላይ የሚ​ቀ​መ​ጥ​በት ሰው ልብ​ሱን ይጠብ፤ በው​ኃም ይታ​ጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="7">ፈሳሽ ነገር ያለ​በ​ትን የሰ​ውን ሥጋ የሚ​ነካ ልብ​ሱን ይጠብ፤ በው​ኃም ይታ​ጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="8">ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ሰው በን​ጹሕ ሰው ላይ ቢተፋ ልብ​ሱን ይጠብ፤ በው​ኃም ይታ​ጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="9">ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ሰው የተ​ቀ​መ​ጠ​በት ኮርቻ ሁሉ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="10">ከበ​ታ​ቹም ያለ​ውን ነገር የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ነገ​ሮች የሚ​ያ​ነሣ ሁሉ ልብ​ሱን ይጠብ፤ በው​ኃም ይታ​ጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="11">ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ሰው እጁን በውኃ ሳይ​ታ​ጠብ የሚ​ነ​ካው ሁሉ ልብ​ሶ​ቹን ይጠብ፤ በው​ኃም ይታ​ጠብ፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="12">ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ሰው የሚ​ነ​ካ​ውን የሸ​ክላ ዕቃ ይስ​በ​ሩት፤ የዕ​ን​ጨ​ቱ​ንም ዕቃ ሁሉ በውኃ ይጠ​ቡት፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="13">“ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ሰው ከፈ​ሳሹ ነገር ሲነጻ ስለ መን​ጻቱ ሰባት ቀን ይቈ​ጥ​ራል፤ ልብ​ሶ​ቹ​ንም ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በም​ንጭ ውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="14">በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ይዞ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያመ​ጣል፤ ለካ​ህ​ኑም ይሰ​ጠ​ዋል።</verse>
				<verse number="15">ካህ​ኑም አን​ዲ​ቱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ አን​ዲ​ቱ​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ካህ​ኑም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስለ ፈሳሹ ነገር ሁሉ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="16">“ማንም ሰው ዘር ከእ​ርሱ ቢወጣ፥ ገላ​ውን ሁሉ በውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="17">ዘር የነ​ካው ልብስ ሁሉ፥ ቍር​በ​ትም ሁሉ በውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="18">ሴት ፈሳሽ ከአ​ለ​በት ወንድ ጋር ብት​ገ​ናኝ ሁለ​ቱም በውኃ ይታ​ጠ​ባሉ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩ​ሳን ናቸው።</verse>
				<verse number="19">“ሴት ፈሳሽ ነገር ቢኖ​ር​ባት፥ በሥ​ጋ​ዋም ያለው ፈሳሽ ነገር ደም ቢሆን፥ በግ​ዳ​ጅዋ ሰባት ቀን ትቀ​መ​ጣ​ለች፤ የሚ​ነ​ካ​ትም ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="20">በግ​ዳ​ጅም ሳለች የም​ት​ተ​ኛ​በት ነገር ሁሉ ርኩስ ነው፤ የም​ት​ቀ​መ​ጥ​በ​ትም ነገር ሁሉ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="21">መኝ​ታ​ዋ​ንም የሚ​ነካ ሁሉ ልብ​ሶ​ቹን ያጥ​ባል፤ በው​ኃም ሰው​ነ​ቱን ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="22">የም​ት​ቀ​መ​ጥ​በ​ት​ንም ነገር ሁሉ የሚ​ነካ ሁሉ ልብ​ሶ​ቹን ያጥ​ባል፤ በው​ኃም ሰው​ነ​ቱን ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="23">በመ​ኝ​ታ​ዋም ላይ ወይም በም​ት​ቀ​መ​ጥ​በት ነገር ላይ ቢሆን ሲነ​ካው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="24">ማንም ከእ​ር​ስዋ ጋር ቢተኛ፥ ግዳ​ጅ​ዋም ቢነ​ካው፥ ሰባት ቀን ርኩስ ነው፤ የሚ​ተ​ኛ​በ​ትም መኝታ ሁሉ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="25">“ሴትም ከግ​ዳ​ጅዋ ቀን ሌላ ደምዋ ብዙ ቀን ቢፈ​ስስ፥ ወይም ደምዋ ከግ​ዳ​ጅዋ ወራት በኋላ ቢፈ​ስስ፥ በግ​ዳ​ጅዋ ወራት እንደ ሆነች እን​ዲሁ በፈ​ሳ​ሽዋ ርኩ​ስ​ነት ወራት ትሆ​ና​ለች፤ ርኵ​ስት ናት።</verse>
				<verse number="26">ደም​ዋም በሚ​ፈ​ስ​ስ​በት ወራት ሁሉ የም​ት​ተ​ኛ​በት መኝታ ሁሉ በግ​ዳ​ጅዋ ጊዜ እንደ ነበ​ረው መኝታ ያለ ይሆ​ን​ባ​ታል፤ የም​ት​ቀ​መ​ጥ​በት ነገር ሁሉ እንደ ግዳ​ጅዋ ርኩ​ስ​ነት ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="27">እነ​ዚ​ህ​ንም ነገ​ሮች የሚ​ነካ ሁሉ ርኩስ ነው፤ ልብ​ሱ​ንም ያጥ​ባል፤ በው​ኃም ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="28">ከፈ​ሳ​ሽ​ዋም ብት​ነጻ ሰባት ቀን ትቈ​ጥ​ራ​ለች፤ ከዚ​ያም በኋላ ንጽ​ሕት ትሆ​ና​ለች።</verse>
				<verse number="29">በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ይዛ ወደ ካህኑ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ታመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለች።</verse>
				<verse number="30">ካህ​ኑም አን​ዲ​ቱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ አን​ዲ​ቱ​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ካህ​ኑም ስለ ፈሳ​ሽዋ ርኩ​ስ​ነት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ታል።</verse>
				<verse number="31">“እን​ዲ​ሁም በእ​ነ​ርሱ መካ​ከል ያለ​ች​ውን ድን​ኳ​ኔን ባረ​ከሱ ጊዜ፥ በር​ኩ​ስ​ነ​ታ​ቸው እን​ዳ​ይ​ሞቱ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከር​ኩ​ስ​ነ​ታ​ቸው አን​ጹ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="32">“ፈሳሽ ነገር ላለ​በት ሰው፥ ይረ​ክ​ስም ዘንድ ዘሩ ለሚ​ወ​ጣ​በት ሰው፥</verse>
				<verse number="33">በግ​ዳ​ጅ​ዋም ደም ለሚ​ፈ​ስ​ሳት፥ ፈሳ​ሽም ነገር ላለ​ባ​ቸው ለወ​ን​ድም ለሴ​ትም፥ ከረ​ከ​ሰ​ችም ሴት ጋር ለሚ​ተኛ ሰው ሕጉ ይህ ነው።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሌላ እሳ​ትን ስላ​መጡ የሞቱ ሁለቱ የአ​ሮን ልጆች ከሞቱ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን ተና​ገ​ረው።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እኔ በስ​ር​የቱ መክ​ደኛ ላይ በደ​መ​ናው ውስጥ እታ​ያ​ለ​ሁና እን​ዳ​ይ​ሞት በመ​ጋ​ረ​ጃው ውስጥ በም​ስ​ክሩ ታቦት ላይ ወዳ​ለው ወደ ስር​የቱ መክ​ደኛ ወደ ተቀ​ደ​ሰው ስፍራ ሁል​ጊዜ እን​ዳ​ይ​ገባ ለወ​ን​ድ​ምህ ለአ​ሮን ንገ​ረው።</verse>
				<verse number="3">እን​ዲሁ አሮን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ከላ​ሞች ወይ​ፈን፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትም አውራ በግ ይዞ ወደ ተቀ​ደ​ሰው ስፍራ ይግባ።</verse>
				<verse number="4">የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም የተ​ልባ እግር ቀሚስ ይል​በስ፤ የተ​ልባ እግ​ርም ሱሪ በገ​ላው ላይ ይሁን፤ የተ​ልባ እግር መታ​ጠ​ቂያ ይታ​ጠቅ፤ የተ​ልባ እግር አክ​ሊ​ልም በራሱ ላይ ያድ​ርግ፤ እነ​ዚህ የተ​ቀ​ደሱ ልብ​ሶች ናቸው፤ ገላ​ው​ንም በውኃ ታጥቦ ይል​በ​ሳ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁለት የፍ​የል ጠቦ​ቶች፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ በግ ይው​ሰድ።</verse>
				<verse number="6">“አሮ​ንም የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈን ያቀ​ር​ባል፤ ለራ​ሱም፥ ለቤ​ተ​ሰ​ቡም ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል።</verse>
				<verse number="7">ሁለ​ቱ​ንም የፍ​የል ጠቦ​ቶች ወስዶ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አጠ​ገብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቆ​ማ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="8">አሮ​ንም በሁ​ለቱ የፍ​የል ጠቦ​ቶች ላይ ዕጣ ይጥ​ል​ባ​ቸ​ዋል፤ አን​ዱን ዕጣ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ሌላ​ው​ንም ዕጣ ለሚ​ለ​ቀቅ።</verse>
				<verse number="9">አሮ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ባ​ሔር ዕጣ የሆ​ነ​በ​ትን ፍየል ያቀ​ር​ባል፤ ስለ ኀጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ያደ​ር​ገ​ዋል።</verse>
				<verse number="10">የመ​ለ​ቀ​ቅም ዕጣ የሆ​ነ​በ​ትን ፍየል ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​በት ዘንድ፥ ለመ​ለ​ቀ​ቅም ወደ ምድረ በዳ ይሰ​ድ​ደው ዘንድ በሕ​ይ​ወቱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቆ​መ​ዋል።</verse>
				<verse number="11">“አሮ​ንም ስለ ራሱ ኀጢ​አት የሚ​ሠ​ዋ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ኑን ያቀ​ር​ባል፤ ለራ​ሱም ለቤ​ተ​ሰ​ቡም ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ስለ ኀጢ​አቱ የእ​ር​ሱን መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ኑን ያር​ዳል።</verse>
				<verse number="12">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ከአ​ለው መሠ​ዊያ ላይ የእ​ሳት ፍም አም​ጥቶ ጥና​ውን ይሞ​ላል፤ ከተ​ወ​ቀ​ጠ​ውም ልቅ​ምና ደቃቅ ዕጣን እጁን ሙሉ ይወ​ስ​ዳል፤ ወደ መጋ​ረ​ጃ​ውም ውስጥ ያመ​ጣ​ዋል።</verse>
				<verse number="13">እን​ዳ​ይ​ሞ​ትም የጢሱ ደመና በም​ስ​ክሩ ታቦት ላይ ያለ​ውን መክ​ደኛ ይሸ​ፍን ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዕጣ​ኑን በእ​ሳቱ ላይ ያደ​ር​ጋል።</verse>
				<verse number="14">ከወ​ይ​ፈ​ኑም ደም ወስዶ በስ​ር​የቱ መክ​ደኛ ላይ ወደ ምሥ​ራቅ በጣቱ ይረ​ጨ​ዋል፤ ከደ​ሙም በመ​ክ​ደ​ኛው ፊት በጣቱ ሰባት ጊዜ ይረ​ጫል።</verse>
				<verse number="15">“ስለ ሕዝ​ቡም ኀጢ​አት የሚ​ሠ​ዋ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ፍየል ያር​ዳል፤ ደሙ​ንም ወደ መጋ​ረ​ጃው ውስጥ ያመ​ጣ​ዋል፤ በወ​ይ​ፈ​ኑም ደም እን​ዳ​ደ​ረገ በፍ​የሉ ደም ያደ​ር​ጋል፤ በመ​ክ​ደ​ኛው ላይና በመ​ክ​ደ​ኛው ፊት ይረ​ጨ​ዋል።</verse>
				<verse number="16">ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርኩ​ስ​ነት፥ ከመ​ተ​ላ​ለ​ፋ​ቸ​ውም፥ ከኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ለመ​ቅ​ደሱ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ እን​ዲ​ሁም በር​ኩ​ስ​ነ​ታ​ቸው መካ​ከል ከእ​ነ​ርሱ ጋር ለኖ​ረች ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ያደ​ር​ጋል።</verse>
				<verse number="17">እርሱ ለማ​ስ​ተ​ስ​ረይ ወደ መቅ​ደሱ በገባ ጊዜ ለራሱ፥ ለቤ​ተ​ሰ​ቡም፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ አስ​ተ​ስ​ርዮ እስ​ኪ​ወጣ ድረስ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ማንም አይ​ኖ​ርም።</verse>
				<verse number="18">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ወዳ​ለው ወደ መሠ​ዊ​ያው ወጥቶ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ከወ​ይ​ፈ​ኑም ደም፥ ከፍ​የ​ሉም ደም ወስዶ በመ​ሠ​ዊ​ያው ዙሪያ ያሉ​ትን ቀን​ዶች ያስ​ነ​ካል።</verse>
				<verse number="19">ከደ​ሙም በእ​ርሱ ላይ ሰባት ጊዜ በጣቱ ይረ​ጫል፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ርኩ​ስ​ነት ያነ​ጻ​ዋል፤ ይቀ​ድ​ሰ​ው​ማል።</verse>
				<verse number="20">“ስለ​መ​ቅ​ደሱ፥ስለ ምስ​ክ​ሩም ድን​ኳን፥ ስለ መሠ​ዊ​ያ​ውም ማስ​ተ​ስ​ረ​ያና ስለ ካህ​ና​ትም ማን​ጻት ከፈ​ጸመ በኋላ ደኅ​ነ​ኛ​ውን ፍየል ያቀ​ር​ባል።</verse>
				<verse number="21">አሮ​ንም ሁለ​ቱን እጆ​ቹን በደ​ኅ​ነ​ኛው ፍየል ራስ ላይ ይጭ​ናል፤ በላ​ዩም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በደል ሁሉ፥ መተ​ላ​ለ​ፋ​ቸ​ውን ሁሉ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ በፍ​የ​ሉም ራስ ላይ ያሸ​ክ​መ​ዋል፤ በተ​ዘ​ጋ​ጀው ሰውም እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰ​ድ​ደ​ዋል።</verse>
				<verse number="22">ፍየ​ሉም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ወደ በረሃ ይሸ​ከ​ማል፤ ፍየ​ሉ​ንም ዛፍ በሌ​ለ​በት በም​ድረ በዳ ውስጥ ይለ​ቅ​ቀ​ዋል።</verse>
				<verse number="23">“አሮ​ንም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ይገ​ባል፤ ወደ መቅ​ደ​ሱም በገባ ጊዜ የለ​በ​ሰ​ውን የተ​ልባ እግር ልብስ ያወ​ል​ቃል፤ በዚ​ያም ይተ​ወ​ዋል።</verse>
				<verse number="24">በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ስፍራ ገላ​ውን በውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ ሌላ​ው​ንም ልብስ ለብሶ ይወ​ጣል፤ የእ​ር​ሱ​ንም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ለካ​ህ​ናቱ እን​ዳ​ስ​ተ​ሰ​ረየ ለራ​ሱም፥ ለሕ​ዝ​ቡም ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል።</verse>
				<verse number="25">የኀ​ጢ​አ​ቱ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ስብ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቃ​ጥ​ለ​ዋል።</verse>
				<verse number="26">ለመ​ለ​ቀቅ የሚ​ሆ​ነ​ውን ፍየል የወ​ሰደ ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገ​ባል።</verse>
				<verse number="27">ለማ​ስ​ተ​ስ​ረ​ያም እን​ዲ​ሆን ደማ​ቸው ወደ መቅ​ደስ የገ​ባ​ውን የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ንና የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ፍየል ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ ያወ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ ቍር​በ​ታ​ቸ​ው​ንም፥ ሥጋ​ቸ​ው​ንም፥ ፈር​ሳ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላሉ።</verse>
				<verse number="28">ያቃ​ጠ​ላ​ቸ​ውም ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገ​ባል።</verse>
				<verse number="29">“ይህም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁ​ን​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="30">በዚህ ቀን ትነጹ ዘንድ ማስ​ተ​ስ​ረያ ይሆ​ን​ላ​ች​ኋ​ልና በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን ራሳ​ች​ሁን አስ​ጨ​ን​ቋት፤ የሀ​ገር ልጅም፥ በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል የተ​ቀ​መጠ እን​ግዳ ሥራን ሁሉ አት​ሥ​ሩ​በት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ሁሉ ትነ​ጻ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="31">ታላቅ ሰን​በት ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፤ ራሳ​ች​ሁ​ንም ታዋ​ር​ዳ​ላ​ችሁ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው።</verse>
				<verse number="32">የሚ​ቀ​ባ​ውም፥ በአ​ባ​ቱም ፋንታ ካህን ሊሆን የሚ​ካ​ነው ካህን ያስ​ተ​ስ​ርይ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም የተ​ልባ እግር ልብስ ይል​በስ።</verse>
				<verse number="33">ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ንም ያስ​ተ​ስ​ርይ፤ ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን፥ ለመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ያስ​ተ​ስ​ርይ፤ ለካ​ህ​ና​ቱም፥ ለጉ​ባ​ኤ​ውም ሕዝብ ሁሉ ያስ​ተ​ስ​ርይ።</verse>
				<verse number="34">ይህም አንድ ጊዜ በዓ​መት ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው ሁሉ ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁ​ን​ላ​ችሁ።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ አደ​ረገ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው-</verse>
				<verse number="2">“ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እን​ዲህ ብለህ ንገር፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘው ይህ ነው፤ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="3">ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ከሚ​ኖሩ እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው በሬ፥ ወይም በግ፥ ወይም ፍየል ቢያ​ርድ፥ በሰ​ፈሩ ውስጥ ወይም ከሰ​ፈሩ ውጭ ቢያ​ር​ደው፥</verse>
				<verse number="4">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው የተ​መ​ረጠ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም የድ​ኅ​ነት መሥ​ዋ​ዕት ያደ​ር​ገው ዘንድ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ባያ​መ​ጣው፥ በሌ​ላም ቦታ ቢያ​ር​ደው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪያ ፊት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን ያቀ​ርብ ዘንድ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ባያ​መ​ጣው፥ ደሙ በዚያ ሰው ላይ ይቈ​ጠ​ር​በ​ታል፤ ደም አፍ​ስ​ሶ​አ​ልና፤ ያም ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ።</verse>
				<verse number="5">ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በሜዳ የሚ​ያ​ር​ዱ​ትን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ያመ​ጡ​ታል፤ ወደ ካህ​ኑም አም​ጥ​ተው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለድ​ኅ​ነት መሥ​ዋ​ዕት ይሠ​ዉ​ታል።</verse>
				<verse number="6">ካህ​ኑም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ባለው በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደሙን ይረ​ጨ​ዋል፤ ስቡ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ያቃ​ጥ​ለ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ው​ንም ደግሞ ተከ​ት​ለው ላመ​ነ​ዘ​ሩ​ባ​ቸው ለሰ​ይ​ጣ​ናት አይ​ሠዉ። ይህ ለእ​ነ​ርሱ ለልጅ ልጃ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁን።”</verse>
				<verse number="8">ለእ​ነ​ርሱ እን​ዲህ በላ​ቸው፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ከሚ​ኖሩ እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ወይም ሌላ መሥ​ዋ​ዕት ቢያ​ቀ​ርብ፥</verse>
				<verse number="9">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሠዋ ዘንድ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ባያ​መ​ጣው፥ ያ ሰው ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ።</verse>
				<verse number="10">“ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ ወይም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ከሚ​ኖሩ እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው ደም ቢበላ፥ ደም በሚ​በ​ላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከ​ብ​ድ​በ​ታ​ለሁ፤ ያንም ሰው ከሕ​ዝቡ ለይች አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">የሥጋ ሁሉ ሕይ​ወት ደሙ ነው፤ ደሙም ከሕ​ይ​ወቱ የተ​ነሣ ያስ​ተ​ሰ​ር​ያ​ልና በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ማስ​ተ​ስ​ረያ ይሆን ዘንድ እኔ ለእ​ና​ንተ ሰጠ​ሁት።</verse>
				<verse number="12">ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች፦ ‘ከእ​ና​ንተ ማንም ደምን አይ​በ​ላም፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ች​ሁም ከሚ​ኖሩ እን​ግ​ዶች ማንም ደምን አይ​በ​ላም’ አልሁ።</verse>
				<verse number="13">“ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ ወይም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ከሚ​ኖሩ እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው የሚ​በላ እን​ስሳ ወይም ወፍ እያ​ደነ ቢይዝ፥ ደሙን ያፈ​ስ​ሳል፤ በአ​ፈ​ርም ይከ​ድ​ነ​ዋል።</verse>
				<verse number="14">የሥጋ ሁሉ ሕይ​ወት ደሙ ነውና፤ ስለ​ዚህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፦ የሥጋ ሁሉ ሕይ​ወት ደሙ ነውና የሥ​ጋ​ውን ሁሉ ደም አት​ብሉ፤ የሚ​በ​ላ​ውም ሁሉ ተለ​ይቶ ይጥፋ አል​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">የሞ​ተ​ውን ወይም አውሬ የሰ​በ​ረ​ውን የሚ​በላ ሰው ሁሉ፥ የሀ​ገር ልጅ ወይም እን​ግዳ ቢሆን፥ ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ በው​ኃም ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሆ​ናል፤ ከዚ​ያም በኋላ ንጹሕ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="16">ልብ​ሱ​ንና ገላ​ውን ባያ​ጥብ ግን ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።</verse>
				<verse number="3">እንደ ተቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​ባት እንደ ግብፅ ምድር ሥራ አት​ሥሩ፤ እኔም ወደ እር​ስዋ እን​ደ​ማ​ገ​ባ​ችሁ እንደ ከነ​ዓን ምድር ሥራ አት​ሥሩ፤ በሥ​ር​ዐ​ታ​ቸ​ውም አት​ሂዱ።</verse>
				<verse number="4">ፍር​ዴን አድ​ርጉ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ትሄዱ ዘንድ ሥር​ዐ​ቴን ጠብቁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።</verse>
				<verse number="5">የሚ​ሠ​ራ​ቸው ሰው በእ​ነ​ርሱ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራ​ልና ሥር​ዐ​ቴ​ንና ፍር​ዴን ጠብቁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።</verse>
				<verse number="6">“ከእ​ና​ን​ተም ማንም ሰው ኀፍ​ረተ ሥጋ​ውን ይገ​ልጥ ዘንድ ወደ ሥጋ ዘመዱ ሁሉ አይ​ቅ​ረብ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።</verse>
				<verse number="7">የአ​ባ​ት​ህን ኀፍ​ረተ ሥጋና የእ​ና​ት​ህን ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ እና​ትህ ናትና ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን አት​ግ​ለጥ።</verse>
				<verse number="8">የአ​ባ​ት​ህን ሚስት ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ የአ​ባ​ትህ ኀፍ​ረተ ሥጋ ነው።</verse>
				<verse number="9">የእ​ኅ​ት​ህን ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ የአ​ባ​ትህ ልጅ ወይም የእ​ና​ትህ ልጅ በቤት ወይም በውጭ የተ​ወ​ለ​ደች ብት​ሆን፥ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን አት​ግ​ለጥ።</verse>
				<verse number="10">የወ​ንድ ልጅ​ህን ሴት ልጅ ኀፍ​ረተ ሥጋ ወይም የሴት ልጅ​ህን ሴት ልጅ ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ የአ​ንተ ኀፍ​ረተ ሥጋ ነውና።</verse>
				<verse number="11">ከአ​ባ​ትህ የተ​ወ​ለ​ደ​ች​ውን የአ​ባ​ት​ህን ሚስት ልጅ ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ ከአ​ባ​ትህ የተ​ወ​ለ​ደች እኅ​ትህ ናት፤ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን አት​ግ​ለጥ።</verse>
				<verse number="12">የአ​ባ​ት​ህን እኅት ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ የአ​ባ​ትህ ዘመድ ናትና።</verse>
				<verse number="13">የእ​ና​ት​ህን እኅት ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ የእ​ና​ትህ ዘመድ ናትና።</verse>
				<verse number="14">የአ​ባ​ት​ህን ወን​ድም ሚስት ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ ዘመ​ድህ ናትና።</verse>
				<verse number="15">የም​ራ​ት​ህን ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ የል​ጅህ ሚስት ናት፤ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን አት​ግ​ለጥ።</verse>
				<verse number="16">የወ​ን​ድ​ም​ህን ሚስት ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ የወ​ን​ድ​ምህ ኀፍ​ረተ ሥጋ ነውና።</verse>
				<verse number="17">የሴ​ት​ንና የሴት ልጅ​ዋን ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ የወ​ንድ ልጅ​ዋን ሴት ልጅ ወይም የሴት ልጅ​ዋን ሴት ልጅ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን ትገ​ልጥ ዘንድ አታ​ግባ፤ ዘመ​ዶች ናቸው፤ ኀጢ​አት ነውና።</verse>
				<verse number="18">በእ​ኅቷ ላይ እን​ዳ​ት​ቀና ሚስ​ትህ በሕ​ይ​ወት ሳለች የእ​ኅ​ቷን ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ።</verse>
				<verse number="19">“እር​ስ​ዋም በግ​ዳ​ጅዋ ርኵ​ሰት ሳለች ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን ትገ​ልጥ ዘንድ ሳት​ነጻ በግ​ዳ​ጅዋ ወደ አለች ሴት አት​ቅ​ረብ።</verse>
				<verse number="20">ከባ​ል​ን​ጀ​ራህ ሚስት ጋር አት​ተኛ፤ ዘር​ህ​ንም አት​ዝ​ራ​ባት።</verse>
				<verse number="21">ከዘ​ር​ህም ለሞ​ሎክ አት​ስጥ የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም ስም አታ​ር​ክስ፤ እኔ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።</verse>
				<verse number="22">ከሴ​ትም ጋር እን​ደ​ም​ት​ተኛ ከወ​ንድ ጋር አት​ተኛ፤ ጸያፍ ነገር ነውና።</verse>
				<verse number="23">ዘር​ህን በእ​ር​ስዋ ላይ እን​ዳ​ት​ዘ​ራና እን​ዳ​ት​ረ​ክ​ስ​ባት ወደ እን​ስሳ አት​ሂድ፤ ሴት ከእ​ርሱ ጋር ትተኛ ዘንድ በእ​ን​ስሳ ፊት አት​ቁም፤ የተ​ጠላ ነገር ነውና።</verse>
				<verse number="24">“ከፊ​ታ​ችሁ የማ​ሳ​ድ​ዳ​ቸው አሕ​ዛብ በእ​ነ​ዚህ ሁሉ ረክ​ሰ​ዋ​ልና በእ​ነ​ዚህ ነገ​ሮች ሁሉ አት​ር​ከሱ።</verse>
				<verse number="25">ምድ​ሪ​ቱም ረከ​ሰች፤ ስለ​ዚህ ኀጢ​አ​ቷን በእ​ር​ስዋ ላይ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱም የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትን ሰዎች ትተ​ፋ​ለች።</verse>
				<verse number="26">ሥር​ዐ​ቴ​ንና ፍር​ዴን ጠብቁ፤ እና​ን​ተም የሀ​ገሩ ልጆች፥ በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል የሚ​ኖ​ሩት እን​ግ​ዶች ከዚህ ርኵ​ሰት ምንም አት​ሥሩ፤</verse>
				<verse number="27">ከእ​ና​ንተ በፊት የነ​በ​ሩት የሀ​ገሩ ልጆች ይህን ርኵ​ሰት ሁሉ ሠር​ተ​ዋ​ልና፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አር​ክ​ሰ​ዋ​ታ​ልና፤</verse>
				<verse number="28">ምድ​ሪ​ቱም ከእ​ና​ንተ በፊት የነ​በ​ረ​ውን ሕዝብ እንደ ተፋች ባረ​ከ​ሳ​ች​ኋት ጊዜ እና​ን​ተ​ንም እን​ዳ​ት​ተ​ፋ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ።</verse>
				<verse number="29">ከዚህ ርኵ​ሰት ሁሉ ማና​ቸ​ውን የሚ​ያ​ደ​ርግ ያ ሰው ከሕ​ዝቡ መካ​ከል ተለ​ይቶ ይጠ​ፋ​ልና።</verse>
				<verse number="30">ስለ​ዚህ ከእ​ና​ንተ በፊት የነ​በሩ ሰዎች የሠ​ሩ​ትን ጸያፍ የሆ​ነ​ውን ወግ ሁሉ እን​ዳ​ት​ሠሩ፥ በእ​ር​ሱም እን​ዳ​ት​ረ​ክሱ ሥር​ዐ​ቴን ጠብቁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ እን​ዲህ በላ​ቸው፦ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ቅዱስ ነኝና እና​ንተ ቅዱ​ሳን ሁኑ።</verse>
				<verse number="3">ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ይፍራ፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ጠብቁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።</verse>
				<verse number="4">ጣዖ​ታ​ት​ንም አት​ከ​ተሉ፤ ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም የአ​ማ​ል​ክት ምስ​ሎች ለእ​ና​ንተ አታ​ድ​ርጉ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።</verse>
				<verse number="5">“የድ​ኅ​ነ​ትን መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስት​ሠዉ ንጹሕ አድ​ር​ጋ​ችሁ ሠዉት።</verse>
				<verse number="6">በም​ት​ሠ​ዉ​በት ቀንና በነ​ጋው ይበ​ላል፤ እስከ ሦስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ድረስ ቢተ​ርፍ በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላል።</verse>
				<verse number="7">በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ቢበላ ጸያፍ ነው፤ ተቀ​ባ​ይ​ነት የለ​ውም፤</verse>
				<verse number="8">የበ​ላ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ነገር አር​ክ​ሶ​አ​ልና ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል፤ ያም ሰው ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ።</verse>
				<verse number="9">“የም​ድ​ራ​ች​ሁ​ንም መከር በሰ​በ​ሰ​ባ​ችሁ ጊዜ የእ​ር​ሻ​ች​ሁን አጨዳ አታ​ጥሩ፤ ስታ​ጭ​ዱም የወ​ደ​ቀ​ውን ቃር​ሚያ አት​ል​ቀሙ።</verse>
				<verse number="10">የወ​ይ​ን​ህን ቃር​ሚያ አጥ​ር​ተህ አት​ቃ​ርም፤ የወ​ደ​ቀ​ው​ንም የወ​ይ​ን​ህን ፍሬ አት​ሰ​ብ​ስብ፤ ለድ​ሆ​ችና ለእ​ን​ግ​ዶች ተወው፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።</verse>
				<verse number="11">“አት​ስ​ረቁ፤ አት​ዋ​ሹም፤ ባል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም የሚ​ቀማ አይ​ኑር።</verse>
				<verse number="12">በስ​ሜም በሐ​ሰት አት​ማሉ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን ቅዱስ ስም አታ​ር​ክሱ፤ እኔ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።</verse>
				<verse number="13">“በባ​ል​ን​ጀ​ራህ ግፍ አታ​ድ​ርግ፤ አት​ቀ​ማ​ውም። የሞ​ያ​ተ​ኛው ዋጋ እስከ ነገ ድረስ በአ​ንተ ዘንድ አይ​ደ​ር​ብህ።</verse>
				<verse number="14">ደን​ቆ​ሮ​ውን አት​ስ​ደብ፤ በዕ​ው​ርም ፊት ዕን​ቅ​ፋት አታ​ድ​ርግ፤ ነገር ግን አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ፤ እኔ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።</verse>
				<verse number="15">“በፍ​ርድ ዐመፃ አታ​ድ​ርጉ፤ ለድሃ አታ​ድላ፤ ባለ​ጠ​ጋ​ው​ንም አታ​ክ​ብር፤ ነገር ግን ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ በእ​ው​ነት ፍረድ።</verse>
				<verse number="16">በሕ​ዝ​ብህ መካ​ከል በሸ​ን​ጋ​ይ​ነት አት​ዙር፤ በባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህም ደም ላይ አት​ቁም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝ።</verse>
				<verse number="17">“ወን​ድ​ም​ህን አት​በ​ድ​ለው፤ በል​ብ​ህም አት​ጥ​ላው፤ በእ​ርሱ ምክ​ን​ያት ኀጢ​አት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ብህ ባል​ን​ጀ​ራ​ህን የም​ት​ነ​ቅ​ፍ​በ​ትን ንገ​ረው፤ ገሥ​ጸ​ውም።</verse>
				<verse number="18">አት​በ​ቀል፤ በሕ​ዝ​ብ​ህም ልጆች ቂም አት​ያዝ፤ ነገር ግን ባል​ን​ጀ​ራ​ህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝና።</verse>
				<verse number="19">“ሥር​ዐ​ቴን ጠብቁ፤ በበ​ሬህ በባ​ዕድ ቀን​በር አት​ረስ፤ በወ​ይን ቦታህ የተ​ለ​ያየ ዘር አት​ዝራ፤ ከሁ​ለት ዐይ​ነት ነገር የተ​ሠራ ልብስ ኀፍ​ረት ነውና አት​ል​በስ።</verse>
				<verse number="20">“ማና​ቸ​ውም ሰው ከሴት ባሪያ ጋር ቢተኛ፥ እር​ስ​ዋም ለባል የተ​ሰ​ጠች፥ ዋጋ​ዋም ያል​ተ​ከ​ፈለ፥ አር​ነት ያል​ወ​ጣች ብት​ሆን፥ ቅጣት አለ​ባ​ቸው፤ አር​ነት አል​ወ​ጣ​ች​ምና አይ​ገ​ደ​ሉም።</verse>
				<verse number="21">እር​ሱም የበ​ደ​ሉን መሥ​ዋ​ዕት አውራ በግ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ያመ​ጣል።</verse>
				<verse number="22">ካህ​ኑም ስለ ሠራው ኀጢ​አት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት በግ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ የሠ​ራ​ውም ኀጢ​አት ይቀ​ር​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="23">“አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር በገ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ የሚ​በላ የፍሬ ዛፍ ሁሉ በተ​ከ​ላ​ች​ሁም ጊዜ ከር​ኵ​ሰቱ ሁሉ ታጠ​ሩ​ታ​ላ​ችሁ፤ የሦ​ስቱ ዓመት ፍሬም ርኩስ ነው፤ አይ​በ​ላም።</verse>
				<verse number="24">በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ፍሬ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ቅዱስ ይሁን።</verse>
				<verse number="25">በአ​ም​ስ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ፍሬ​ውን ብሉ፤ ፍሬ​ውም ይበ​ዛ​ላ​ች​ኋል፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።</verse>
				<verse number="26">“በተ​ራራ ላይ አት​ብሉ፤ አት​ር​ከሱ፥ በወ​ፍም አታ​ሟ​ርቱ።</verse>
				<verse number="27">የራስ ጠጕ​ራ​ች​ሁ​ንም ዙሪ​ያ​ውን አት​ከ​ር​ክ​ሙት፤ ጢማ​ች​ሁ​ንም አት​ላጩ።</verse>
				<verse number="28">ሰው ቢሞት ምላጭ ወደ ሥጋ​ችሁ አታ​ቅ​ርቡ፤ ገላ​ች​ሁ​ንም አት​ን​ቀ​ሱት፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።</verse>
				<verse number="29">“ምድ​ሪቱ ከግ​ል​ሙ​ትና፥ ከር​ኵ​ሰ​ትም እን​ዳ​ት​ሞላ ሴት ልጅ​ህን ታመ​ነ​ዝር ዘንድ አታ​ር​ክ​ሳት።</verse>
				<verse number="30">ሰን​በ​ታ​ቴን ጠብቁ፤ መቅ​ደ​ሴ​ንም አክ​ብሩ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።</verse>
				<verse number="31">“ወደ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ችና ወደ ጠን​ቋ​ዮች አት​ሂዱ፤ እን​ዳ​ት​ረ​ክ​ሱ​ባ​ቸ​ውም አት​ፈ​ል​ጉ​አ​ቸው፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።</verse>
				<verse number="32">“በሽ​በ​ታሙ ፊት ተነሣ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ው​ንም አክ​ብር፤ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ፍራ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።</verse>
				<verse number="33">“በሀ​ገ​ራ​ችሁ ውስጥ እን​ግዳ ከእ​ና​ንተ ጋር ቢቀ​መጥ ግፍ አታ​ድ​ር​ጉ​በት።</verse>
				<verse number="34">እና​ንተ በግ​ብፅ ምድር እን​ግ​ዶች ነበ​ራ​ች​ሁና፤ ወደ እና​ንተ የመጣ እን​ግዳ እንደ ሀገር ልጅ ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ እር​ሱን እንደ ራሳ​ችሁ ውደ​ዱት፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።</verse>
				<verse number="35">“በፍ​ርድ፥ በመ​ለ​ካ​ትም፥ በመ​መ​ዘ​ንም፥ በመ​ስ​ፈ​ርም ዐመፃ አታ​ድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="36">የእ​ው​ነ​ትም ሚዛን፥ የእ​ው​ነ​ትም መመ​ዘኛ፥ የእ​ው​ነ​ትም የፈ​ሳሽ መስ​ፈ​ሪያ ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኋ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እኔ ነኝ።</verse>
				<verse number="37">ሕጌን ሁሉ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ሁሉ ጠብቁ፤ አድ​ር​ጉ​ትም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“ደግሞ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወይም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ከሚ​ቀ​መጡ እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው ዘሩን ለሞ​ሎክ አገ​ል​ግ​ሎት ቢሰጥ ፈጽሞ ይገ​ደል፤ የሀ​ገሩ ሕዝብ በድ​ን​ጋይ ይው​ገ​ሩት።</verse>
				<verse number="3">መቅ​ደ​ሴን ያረ​ክስ ዘንድ፥ የቅ​ዱ​ሳ​ኔ​ንም ስም ያጐ​ስ​ቍል ዘንድ ዘሩን ለሞ​ሎክ አገ​ል​ግ​ሎት ሰጥ​ቶ​አ​ልና እኔ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከ​ብ​ዳ​ለሁ፤ ከሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ለይች አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">ዘሩ​ንም ለሞ​ሎክ ሲሰጥ፥ የሀ​ገሩ ሕዝብ ያን ሰው ቸል ቢሉት፥ አይ​ተው እን​ዳ​ላዩ ቢሆኑ፥ ባይ​ገ​ድ​ሉ​ትም፥ እኔ በዚያ ሰውና በቤተ ሰቡ ላይ ፊቴን አከ​ብ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">እር​ሱ​ንና ከሞ​ሎክ ጋር ያመ​ነ​ዝሩ ዘንድ የሚ​ከ​ተ​ሉ​ትን ሁሉ ከሕ​ዝ​ባ​ቸው መካ​ከል ለይች አጠ​ፋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="6">“እነ​ር​ሱን ተከ​ትሎ ያመ​ነ​ዝር ዘንድ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን የሚ​ከ​ተል ሰው ቢኖር፥ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከ​ብ​ዳ​ለሁ፤ ከሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ለይች አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">እን​ግ​ዲህ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ቅዱስ ነኝና ቅዱ​ሳን ሁኑ።</verse>
				<verse number="8">ሕጌ​ንና ትእ​ዛ​ዜን ጠብቁ፤ አድ​ር​ጉ​ትም፤ እኔ የም​ቀ​ድ​ሳ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።</verse>
				<verse number="9">ማና​ቸ​ውም ሰው አባ​ቱን ወይም እና​ቱን ቢሰ​ድብ ፈጽሞ ይገ​ደል፤ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ሰድ​ቦ​አ​ልና በደ​ለኛ ነው።</verse>
				<verse number="10">“ማና​ቸ​ውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ወይም ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ሚስት ጋር ቢያ​መ​ነ​ዝር አመ​ን​ዝ​ራ​ውና አመ​ን​ዝ​ራ​ዪቱ ፈጽ​መው ይገ​ደሉ።</verse>
				<verse number="11">ማና​ቸ​ውም ሰው ከአ​ባቱ ሚስት ጋር ቢተኛ የአ​ባ​ቱን ኀፍ​ረተ ሥጋ ገል​ጦ​አል፤ ሁለ​ቱም ፈጽ​መው ይገ​ደሉ፤ በደ​ለ​ኞች ናቸው።</verse>
				<verse number="12">ማና​ቸ​ውም ሰው ከም​ራቱ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ፈጽ​መው ይገ​ደሉ፤ ጸያፍ ነገር አድ​ር​ገ​ዋል፤ በደ​ለ​ኞች ናቸው።</verse>
				<verse number="13">ማና​ቸ​ውም ሰው ከሴት ጋር እን​ደ​ሚ​ተኛ ከወ​ንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድ​ር​ገ​ዋል፤ ፈጽ​መው ይገ​ደሉ፤ በደ​ለ​ኞች ናቸው።</verse>
				<verse number="14">ማና​ቸ​ውም ሰው እና​ቲ​ቱ​ንና ልጂ​ቱን ቢያ​ገባ ኀጢ​አት ነው፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ኀጢ​አት እን​ዳ​ይ​ሆን እር​ሱ​ንና እነ​ር​ሱን በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">ማና​ቸ​ውም ሰው ከእ​ን​ስሳ ጋር ቢገ​ናኝ ፈጽሞ ይገ​ደል፤ እን​ስ​ሳ​ዪ​ቱ​ንም ግደ​ሉ​አት።</verse>
				<verse number="16">ማን​ኛ​ዪ​ቱም ሴት ወደ እን​ስሳ ብት​ቀ​ርብ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ብት​ገ​ናኝ፥ ሴቲ​ቱ​ንና እን​ስ​ሳ​ውን ግደሉ፤ ፈጽ​መው ይገ​ደሉ፤ በደ​ለ​ኞች ናቸው።</verse>
				<verse number="17">“ማና​ቸ​ውም ሰው የአ​ባ​ቱን ልጅ ወይም የእ​ና​ቱን ልጅ እኅ​ቱን ቢያ​ገባ፥ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋ​ንም ቢያይ፥ እር​ስ​ዋም ኀፍ​ረተ ሥጋ​ውን ብታይ፥ ይህ ጸያፍ ነገር ነው፤ በሕ​ዝ​ባ​ቸ​ውም ልጆች ፊት ይገ​ደሉ፤ የእ​ኅ​ቱን ኀፍ​ረተ ሥጋ ገል​ጦ​አ​ልና ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል።</verse>
				<verse number="18">ማና​ቸ​ውም ሰው ከባለ ግዳጅ ሴት ጋር ቢተኛ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋ​ንም ቢገ​ልጥ፥ ፈሳ​ሽ​ዋን ገል​ጦ​አ​ልና፥ እር​ስ​ዋም የደ​ም​ዋን ፈሳሽ ገል​ጣ​ለ​ችና ሁለቱ ከሕ​ዝ​ባ​ቸው መካ​ከል ተለ​ይ​ተው ይጥፉ።</verse>
				<verse number="19">የአ​ባ​ት​ህን ወይም የእ​ና​ት​ህን እኅት ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ የዘ​መ​ድን ኀፍ​ረተ ሥጋ ገል​ጦ​አል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይሸ​ከ​ማሉ።</verse>
				<verse number="20">ሰውም ከቅ​ርብ ዘመዱ ሚስት ጋር ቢተኛ የቅ​ርብ ዘመ​ዱን ኀፍ​ረተ ሥጋ ገል​ጦ​አል፤ ያለ ልጅ ይሞ​ታሉ።</verse>
				<verse number="21">ሰውም የወ​ን​ድ​ሙን ሚስት ቢያ​ገባ ርኵ​ሰት ነው፤ የወ​ን​ድ​ሙን ኀፍ​ረተ ሥጋ ገል​ጦ​አል፤ ያለ ልጅም ይሙቱ።</verse>
				<verse number="22">“እን​ግ​ዲህ ትቀ​መ​ጡ​ባት ዘንድ የማ​ገ​ባ​ችሁ ምድር እን​ዳ​ት​ተ​ፋ​ችሁ ትእ​ዛ​ዜን ሁሉ፥ ፍር​ዴ​ንም ሁሉ ጠብቁ፤ አድ​ር​ጉ​ትም።</verse>
				<verse number="23">ከፊ​ታ​ችሁ በማ​ወ​ጣ​ቸው ሕዝብ ሕግ አት​ሂዱ፤ ይህን ሁሉ አድ​ር​ገ​ዋ​ልና ተጸ​የ​ፍ​ኋ​ቸው</verse>
				<verse number="24">ነገር ግን እና​ንተ፦ ምድ​ራ​ቸ​ውን ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤ ትወ​ር​ሱ​አ​ትም ዘንድ ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ አል​ኋ​ችሁ፤ እኔ ከአ​ሕ​ዛብ የለ​የ​ኋ​ችሁ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።</verse>
				<verse number="25">እን​ግ​ዲህ በን​ጹ​ሕና በር​ኩስ እን​ስሳ መካ​ከል፥ በን​ጹ​ሕና በር​ኩ​ስም ወፍ መካ​ከል ለየ​ሁ​ላ​ችሁ፤ ርኩ​ሳን ናቸው ብዬ በለ​የ​ኋ​ቸው በእ​ን​ስ​ሳና በወፍ፥ በም​ድ​ርም ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ ሁሉ ነፍ​ሳ​ች​ሁን አታ​ር​ክሱ።</verse>
				<verse number="26">እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ነኝና፥ ለእ​ኔም ትሆኑ ዘንድ ከአ​ሕ​ዛብ ለይ​ቻ​ች​ኋ​ለ​ሁና ቅዱ​ሳን ትሆ​ኑ​ል​ኛ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="27">“ወንድ ወይም ሴት መና​ፍ​ስ​ትን ቢጠሩ፥ ወይም ጠን​ቋ​ዮች ቢሆኑ ፈጽ​መው ይገ​ደሉ፤ በድ​ን​ጋ​ይም ይው​ገ​ሩ​አ​ቸው፤ በደ​ለ​ኞች ናቸ​ውና።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፥ “ከወ​ገ​ና​ቸው በሞተ ሰው ራሳ​ቸ​ውን እን​ዳ​ያ​ረ​ክሱ ለካ​ህ​ናቱ ለአ​ሮን ልጆች ንገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">ከቅ​ርብ ዘመ​ዶ​ቻ​ቸው፥ ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው፥ ወይም ከእ​ና​ቶ​ቻ​ቸው፥ ወይም ከወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸው፥ ወይም ከሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ቸው፥ ወይም ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው፥</verse>
				<verse number="3">ወይም ከቀ​ረ​በች ያላ​ገ​ባች ድን​ግል እኅት በቀር ራሳ​ቸ​ውን አያ​ር​ክሱ።</verse>
				<verse number="4">ራሱን ያጐ​ሰ​ቍል ዘንድ ከሕ​ዝቡ በማ​ንም አይ​ር​ከስ።</verse>
				<verse number="5">ስለ ሞተው ሰው ራሳ​ቸ​ውን አይ​ላጩ፤ ጢማ​ቸ​ው​ንም አይ​ላጩ፤ ሥጋ​ቸ​ው​ንም አይ​ንጩ።</verse>
				<verse number="6">ለአ​ም​ላ​ካ​ቸው ቅዱ​ሳን ይሁኑ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም ስም አያ​ር​ክሱ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን መባ ያቀ​ር​ባ​ሉና ቅዱ​ሳን ይሁኑ።</verse>
				<verse number="7">ለአ​ም​ላኩ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ነውና ጋለ​ሞ​ታን ሴት ወይም የረ​ከ​ሰ​ች​ውን አያ​ግባ፤ ወይም ከባ​ልዋ የተ​ፋ​ታ​ች​ውን አያ​ግባ።</verse>
				<verse number="8">የአ​ም​ላ​ክ​ህን መባ ያቀ​ር​ባ​ልና ስለ​ዚህ ትቀ​ድ​ሰ​ዋ​ለህ፤ እኔም የም​ቀ​ድ​ሳ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ነኝና እርሱ ቅዱስ ይሁ​ን​ልህ።</verse>
				<verse number="9">የካ​ህ​ንም ሰው ልጅ በግ​ል​ሙ​ትና ራስ​ዋን ብታ​ረ​ክስ በግ​ል​ሙ​ትና አባ​ቷን ታረ​ክ​ሰ​ዋ​ለች፤ በእ​ሳት ትቃ​ጠል።</verse>
				<verse number="10">“በራ​ሱም ላይ የቅ​ባት ዘይት የፈ​ሰ​ሰ​በት፥ የክ​ህ​ነ​ትም ልብስ ይለ​ብስ ዘንድ የተ​ቀ​ደሰ፥ ከወ​ን​ድ​ሞቹ የተ​ለ​የው ካህን ራሱን አይ​ላጭ፤ ልብ​ሱ​ንም አይ​ቅ​ደድ።</verse>
				<verse number="11">ወደ ሞተ ሰው ሁሉ አይ​ግባ፤ በአ​ባ​ቱም ወይም በእ​ናቱ አይ​ር​ከስ።</verse>
				<verse number="12">የአ​ም​ላ​ኩም ቅባት ዘይት ቅዱ​ስ​ነት በላዩ ነውና ከመ​ቅ​ደስ አይ​ውጣ፤ የአ​ም​ላ​ኩ​ንም ቅዱስ ስም አያ​ር​ክስ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።</verse>
				<verse number="13">እር​ሱም ከወ​ገኑ ድን​ግል ሴትን ያግባ።</verse>
				<verse number="14">ባልዋ የሞ​ተ​ባ​ትን፥ ወይም የተ​ፋ​ታ​ች​ውን፥ የተ​ጠ​ላ​ች​ውን ወይም ጋለ​ሞ​ታ​ዪ​ቱን አያ​ግባ፤ ነገር ግን ከወ​ገኑ ድን​ግ​ሊ​ቱን ያግባ፤</verse>
				<verse number="15">እኔም የም​ቀ​ድ​ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና በሕ​ዝቡ መካ​ከል ዘሩን አያ​ጐ​ስ​ቍል።”</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="17">“ለአ​ሮን እን​ዲህ ብለህ ንገ​ረው፦ ከወ​ገ​ንህ በት​ው​ል​ዳ​ቸው ነውር ያለ​በት ሰው ሁሉ የአ​ም​ላ​ኩን መባ ያቀ​ርብ ዘንድ አይ​ቅ​ረብ።</verse>
				<verse number="18">ንጹሕ ያል​ሆነ ሰው ሁሉ አይ​ቅ​ረብ፤ ዕውር፥ ወይም አን​ካሳ፥ ወይም አፍ​ንጫ ደፍ​ጣጣ፥ ወይም ጆሮ ቈራጣ፥</verse>
				<verse number="19">ወይም እጀ ሰባራ፥ ወይም እግረ ሰባራ፥</verse>
				<verse number="20">ወይም ጎባጣ፥ ወይም ድንክ፥ ወይም ዐይነ መጭ​ማጫ፥ ወይም ቅን​ድበ መላጣ፥ ወይም እከ​ካም፥ ወይም ቋቍ​ቻም፥ ወይም የአ​ባ​ለ​ዘሩ ፍሬ አንድ የሆነ ነው​ረኛ ሁሉ አይ​ቅ​ረብ።</verse>
				<verse number="21">ከካ​ህኑ ከአ​ሮን ዘር ነውር ያለ​በት ሰው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርብ ዘንድ አይ​ቅ​ረብ፤ ነው​ረኛ ነው፤ የአ​ም​ላ​ኩን መባ ያቀ​ርብ ዘንድ አይ​ቅ​ረብ።</verse>
				<verse number="22">የቅ​ዱ​ሱ​ንና የቅ​ዱሰ ቅዱ​ሳ​ኑን የአ​ም​ላ​ኩን መባ ይብላ፤</verse>
				<verse number="23">ነገር ግን ነው​ረኛ ነውና መቅ​ደ​ሶ​ችን እን​ዳ​ያ​ረ​ክስ ወደ መጋ​ረ​ጃው አይ​ግባ፤ ወደ መሠ​ዊ​ያ​ውም አይ​ቅ​ረብ፤ የም​ቀ​ድ​ሳ​ቸው እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።”</verse>
				<verse number="24">ሙሴም ይህን ለአ​ሮን፥ ለል​ጆ​ቹም፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ነገ​ራ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለእኔ ከሚ​ቀ​ድ​ሱ​አ​ቸው ከቅ​ዱ​ሳን ነገ​ሮች ራሳ​ቸ​ውን እን​ዲ​ለዩ፥ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ስሜን እን​ዳ​ያ​ረ​ክሱ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ንገ​ራ​ቸው፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።</verse>
				<verse number="3">እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ማና​ቸ​ውም ሰው ከዘ​ራ​ችሁ በት​ው​ል​ዳ​ችሁ ርኵ​ሰት እያ​ለ​በት የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ቀ​ድ​ሱት ወደ ቅዱስ ነገር ቢቀ​ርብ፥ ያ ሰው ከፊቴ ተለ​ይቶ ይጥፋ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።</verse>
				<verse number="4">ከአ​ሮን ዘር ለምጽ ወይም ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ሁሉ ንጹሕ እስ​ኪ​ሆን ድረስ ከተ​ቀ​ደ​ሰው አይ​ብላ። ከበ​ድ​ንም የተ​ነሣ ርኩስ የሆ​ነ​ውን፥ ወይም ዘሩ ከእ​ርሱ የሚ​ፈ​ስ​ስ​በ​ትን የሚ​ነካ፥</verse>
				<verse number="5">ወይም የሚ​ያ​ረ​ክ​ሰ​ውን ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ፥ ወይም በሁሉ ዐይ​ነት የረ​ከ​ሰ​ውን ሰው የሚ​ነካ፥</verse>
				<verse number="6">እነ​ዚ​ህን ሁሉ የሚ​ነካ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል፤ ገላ​ውን በውኃ ካል​ታ​ጠበ ከተ​ቀ​ደ​ሰው አይ​ብላ።</verse>
				<verse number="7">ፀሐ​ይም በገ​ባች ጊዜ ንጹሕ ይሆ​ናል፤ ከዚ​ያም በኋላ ምግቡ ነውና ከተ​ቀ​ደ​ሰው ይብላ።</verse>
				<verse number="8">በእ​ር​ሱም እን​ዳ​ይ​ረ​ክስ፥ የሞ​ተ​ውን፥ አው​ሬም የሰ​በ​ረ​ውን አይ​ብላ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።</verse>
				<verse number="9">ቢያ​ረ​ክ​ሱ​አት እን​ዳ​ይ​ሞቱ፥ ስለ እር​ስ​ዋም ኀጢ​አ​ትን እን​ዳ​ይ​ሸ​ከሙ፥ ሕግን ይጠ​ብቁ፤ የም​ቀ​ድ​ሳ​ቸው እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።</verse>
				<verse number="10">“ከባ​ዕድ ወገን የሆነ ሰው ከተ​ቀ​ደ​ሰው አይ​ብላ፤ የካ​ህ​ኑም እን​ግዳ፥ ደመ​ወ​ዘ​ኛ​ውም ከተ​ቀ​ደ​ሰው አይ​ብላ።</verse>
				<verse number="11">ካህኑ ግን በገ​ን​ዘቡ አገ​ል​ጋይ ቢገዛ እርሱ ከም​ግቡ ይብላ፤ በቤ​ቱም የተ​ወ​ለ​ዱት ከእ​ን​ጀ​ራው ይብሉ።</verse>
				<verse number="12">የካ​ህ​ንም ልጅ ከሌላ ወገን ጋር ብት​ጋባ፥ እር​ስዋ ከተ​ቀ​ደ​ሰው ዐሥ​ራት አት​ብላ።</verse>
				<verse number="13">የካ​ህን ልጅ ግን ባልዋ ቢሞት፥ ወይም ብት​ፋታ፥ ልጅም ባይ​ኖ​ራት፥ በብ​ላ​ቴ​ን​ነቷ እንደ ነበ​ረች ወደ አባቷ ቤት ብት​መ​ለስ፥ ከአ​ባቷ እን​ጀራ ትብላ፤ ከሌላ ወገን የሆነ ባዕድ ሰው ግን ከእ​ርሱ አይ​ብላ።</verse>
				<verse number="14">ማና​ቸ​ውም ሰው ሳያ​ውቅ ከተ​ቀ​ደ​ሰው ቢበላ አም​ስ​ተኛ እጅ ጨምሮ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ለካ​ህኑ ይስጥ።</verse>
				<verse number="15">ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡ​ትን፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ነገር አያ​ር​ክሱ።</verse>
				<verse number="16">በኀ​ጢ​አት ሳሉ ከተ​ቀ​ደ​ሰው መሥ​ዋ​ዕት ከበሉ ግን ኀጢ​አ​ትና በደል ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል፤ የማ​ነ​ጻ​ቸው እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።”</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="18">“ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ወይም ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ከሚ​ቀ​መ​ጡት እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው ስእ​ለ​ቱን ሁሉ፥ በፈ​ቃ​ዱም የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን ሁሉ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን ቍር​ባን ቢያ​ቀ​ርብ፥</verse>
				<verse number="19">ይሠ​ም​ር​ላ​ችሁ ዘንድ ከበሬ፥ ወይም ከበግ፥ ወይም ከፍ​የል ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባ​ቱን አቅ​ርቡ።</verse>
				<verse number="20">ነገር ግን አይ​ሠ​ም​ር​ላ​ች​ሁ​ምና ነውር ያለ​በ​ትን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አታ​ቅ​ርቡ።</verse>
				<verse number="21">ማና​ቸ​ውም ሰው ስእ​ለ​ቱን ለመ​ፈ​ጸም ወይም በፈ​ቃዱ ለማ​ቅ​ረብ የደ​ኅ​ን​ነ​ትን መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም በሬን፥ ወይም በግን፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢያ​ቀ​ርብ፥ ይሰ​ም​ር​ለት ዘንድ ፍጹም ይሁን፤ ነው​ርም አይ​ሁ​ን​በት።</verse>
				<verse number="22">ዕውር፥ ወይም ሰባራ፥ ወይም ምላሱ የተ​ቈ​ረጠ፥ ወይም የሚ​መ​ግል ቍስል ያለ​በት፥ ወይም እከ​ካም፥ ወይም ቋቍ​ቻም ቢሆን፥ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አታ​ቅ​ርቡ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ለእ​ሳት ቍር​ባን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ሔር አታ​ሳ​ርጉ።</verse>
				<verse number="23">በሬው፥ ወይም በጉ ጆሮው፥ ወይም ጅራቱ የተ​ቈ​ረጠ ቢሆን፥ ቈጥ​ረህ የራ​ስህ ገን​ዘብ አድ​ር​ገው እንጂ ለስ​እ​ለት አይ​ቀ​በ​ል​ህም።</verse>
				<verse number="24">የተ​ቀ​ጠ​ቀ​ጠ​ውን፥ ወይም የተ​ሰ​በ​ረ​ውን፥ ወይም የተ​ቈ​ረ​ጠ​ውን ወይም የተ​ሰ​ነ​ጋ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አታ​ቅ​ርቡ፤ በም​ድ​ራ​ች​ሁም እነ​ዚ​ህን አት​ሠዉ።</verse>
				<verse number="25">ከእ​ነ​ዚ​ህም ከባ​ዕድ ወገን ከሆነ ሰው እጅ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ መባ አታ​ቅ​ርቡ፤ ርኵ​ሰ​ትም፥ ነው​ርም አለ​ባ​ቸ​ውና አይ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁም።”</verse>
				<verse number="26">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="27">“ላም፥ ወይም በግ፥ ወይም ፍየል ሲወ​ለድ ሰባት ቀን ከእ​ናቱ ጋር ይቀ​መጥ፤ በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን፥ ከዚ​ያም በላይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳት ቍር​ባን የሠ​መረ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="28">ላም፥ ወይም በግ፥ ወይም ፍየል ብት​ሆን እር​ስ​ዋ​ንና ልጅ​ዋን በአ​ንድ ቀን አት​ረዱ።</verse>
				<verse number="29">የም​ስ​ጋ​ና​ንም መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስት​ሠዉ እን​ዲ​ቀ​በ​ላ​ችሁ ሠዉ​ለት።</verse>
				<verse number="30">በዚ​ያው ቀን ይብ​ሉት፤ ከእ​ርሱ እስከ ነገ ምንም አት​ተዉ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።</verse>
				<verse number="31">ትእ​ዛ​ዛ​ቴን ጠብቁ፤ አድ​ር​ጉ​ትም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።</verse>
				<verse number="32">የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ስሜን አታ​ር​ክሱ፤ እኔ ግን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል እቀ​ደ​ሳ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="33">የም​ቀ​ድ​ሳ​ችሁ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና። አም​ላ​ካ​ች​ሁም እሆን ዘንድ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኋ​ችሁ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="23">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ቅዱ​ሳት ጉባ​ኤ​ያት ብላ​ችሁ የም​ት​ጠ​ሩ​አ​ቸው በዓ​ላቴ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ላት እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="3">ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ትሠ​ራ​ለህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ግን የዕ​ረ​ፍት ሰን​በት ነው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ጉባኤ ይሆ​ን​በ​ታል፤ ምንም ሥራ አት​ሠ​ሩም፤ በም​ት​ኖ​ሩ​በት ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰን​በት ነው።</verse>
				<verse number="4">እነ​ዚህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ላት፥ በየ​ዘ​መ​ና​ቸው የም​ታ​ው​ጁ​አ​ቸው፥ የተ​ቀ​ደሱ ጉባ​ኤ​ያት ናቸው።</verse>
				<verse number="5">“በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን ሲመሽ የእ​ግ​ዚ​እ​ብ​ሔር ፋሲካ ነው።</verse>
				<verse number="6">በዚ​ህም ወር በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቂጣ በዓል ነው፤ ሰባት ቀን ቂጣ ብሉ።</verse>
				<verse number="7">መጀ​መ​ሪ​ያ​ይቱ ቀን ቅድ​ስት ጉባኤ ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ የተ​ግ​ባር ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​ባት።</verse>
				<verse number="8">ሰባት ቀንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርቡ፤ ሰባ​ተ​ኛዋ ቀን ቅድ​ስት ጉባኤ ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ የተ​ግ​ባር ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​ባት።”</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="10">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ወደ​ም​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር በገ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ መከ​ሩ​ንም ባጨ​ዳ​ችሁ ጊዜ፥ የእ​ና​ን​ተን መከር በኵ​ራት ነዶ ወደ ካህኑ አምጡ፤</verse>
				<verse number="11">እር​ሱም ነዶ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዲ​ሠ​ም​ር​ላ​ችሁ ያቀ​ር​በ​ዋል፤ በማ​ግ​ስቱ ከሰ​ን​በት በኋላ ካህኑ ያቅ​ር​በው፤</verse>
				<verse number="12">ነዶ​ው​ንም ባቀ​ረ​ባ​ች​ሁ​በት ቀን ነውር የሌ​ለ​በ​ትን የአ​ንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ርቡ።</verse>
				<verse number="13">የስ​ን​ዴም ቍር​ባን ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ የሆነ በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው ቍር​ባን ይሁን፤ የመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን የወ​ይን ጠጅ የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ ይሁን።</verse>
				<verse number="14">እን​ጀ​ራ​ው​ንም፥ የተ​ጠ​በ​ሰ​ው​ንም እሸት፥ ለም​ለ​ሙ​ንም እሸት የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን ቍር​ባን እስ​ከ​ም​ታ​ቀ​ር​ቡ​በት እስ​ከ​ዚህ ቀን ድረስ አት​ብሉ። ይህ በም​ት​ቀ​መ​ጡ​በት ሀገር ሁሉ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው።</verse>
				<verse number="15">“ያቀ​ረ​ባ​ች​ሁ​ትን ነዶ ከም​ታ​መ​ጡ​በት ቀን በኋላ ከሰ​ን​በት ማግ​ስት ፍጹም ሰባት ሱባዔ ቍጠሩ፤</verse>
				<verse number="16">እስከ መጨ​ረ​ሻዋ ሰባ​ተኛ ሰን​በት ማግ​ስት ድረስ አምሳ ቀን ቍጠሩ፤ አዲ​ሱ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ርቡ።</verse>
				<verse number="17">ከየ​ማ​ደ​ሪ​ያ​ችሁ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ ከሆነ መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት የተ​ሠራ ሁለት የቍ​ር​ባን እን​ጀራ ታመ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ከእ​ህ​ላ​ችሁ ቀዳ​ም​ያት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ርሾ ይጋ​ገ​ራል።</verse>
				<verse number="18">ከኅ​ብ​ስ​ቱም ጋር ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን የአ​ንድ ዓመት ሰባት ጠቦ​ቶች፥ ከመ​ን​ጋ​ውም አንድ ወይ​ፈን፥ ሁለ​ትም ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸው አውራ በጎች ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው መሥ​ዋ​ዕት እን​ዲ​ሆን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውና ቍር​ባ​ና​ቸው፥ ወይ​ና​ቸ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁን።</verse>
				<verse number="19">አን​ድም አውራ ፍየል ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ ሁለ​ትም የአ​ንድ ዓመት ተባት ጠቦ​ቶች ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው የእ​ህል ቍር​ባን ጋር ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርቡ።</verse>
				<verse number="20">ካህ​ኑም ከበ​ኵ​ራቱ ኅብ​ስት፥ ከሁ​ለ​ቱም ጠቦ​ቶች ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለቍ​ር​ባን ያቅ​ር​በው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ፈንታ ነው፤ ላቀ​ረ​በው ለካ​ህኑ ይሁን።</verse>
				<verse number="21">ያች​ንም ቀን ቅድ​ስት ጉባኤ ብላ​ችሁ ታው​ጃ​ላ​ችሁ፤ የተ​ግ​ባር ሥራ ሁሉ አታ​ድ​ር​ጉ​ባት፤ በም​ት​ቀ​መ​ጡ​በት ሀገር ሁሉ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው።</verse>
				<verse number="22">“የም​ድ​ራ​ች​ሁን መከር በሰ​በ​ሰ​ባ​ችሁ ጊዜ በእ​ር​ሻ​ችሁ የቀ​ረ​ውን አጥ​ር​ታ​ችሁ አት​ጨዱ፤ የመ​ከ​ሩ​ንም ቃር​ሚያ አት​ል​ቀሙ፤ ለድ​ሆ​ችና ለእ​ን​ግ​ዶች ተዉት፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።”</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="24">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ዕረ​ፍት፥ በመ​ለ​ከት ድምፅ መታ​ሰ​ቢያ፥ የተ​ቀ​ደ​ሰች ጉባኤ ትሁ​ን​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="25">የተ​ግ​ባር ሥራ ሁሉ አታ​ድ​ር​ጉ​ባት፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርቡ።”</verse>
				<verse number="26">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="27">“በዚህ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ዐሥ​ረ​ኛዋ ቀን የማ​ስ​ተ​ስ​ረያ ቀን ናት፤ ቅድ​ስት ጉባኤ ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን አስ​ጨ​ን​ቋት፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርቡ።</verse>
				<verse number="28">በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስለ እና​ንተ ማስ​ተ​ስ​ረያ ትሆ​ን​ላ​ችሁ ዘንድ የማ​ስ​ተ​ስ​ረያ ቀን ናትና በዚ​ያች ቀን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​ባት።</verse>
				<verse number="29">በዚ​ያ​ችም ቀን ራሱን የማ​ያ​ዋ​ርድ ሰው ሁሉ ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ።</verse>
				<verse number="30">በዚ​ያ​ችም ቀን ሥራ የሚ​ሠራ ሰው ከሕ​ዝቡ መካ​ከል ተለ​ይቶ ይጠ​ፋል።</verse>
				<verse number="31">ሥራ ሁሉ አታ​ድ​ር​ጉ​ባት፤ በም​ት​ቀ​መ​ጡ​በት ሀገር ሁሉ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ ነው።</verse>
				<verse number="32">የዕ​ረ​ፍት ሰን​በት ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም አዋ​ርዱ፤ በወሩ በዘ​ጠ​ነ​ኛው ቀን ከማታ ጀም​ራ​ችሁ እስከ ዐሥ​ረ​ኛው ቀን ማታ ድረስ፥ ሰን​በ​ታ​ች​ሁን አድ​ርጉ።”</verse>
				<verse number="33">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="34">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ በዚህ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ከዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን ጀምሮ ሰባት ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዳስ በዓል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="35">የመ​ጀ​መ​ሪ​ያዋ ቀን ቅድ​ስት ጉባኤ ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ የተ​ግ​ባር ሥራ ሁሉ አታ​ድ​ር​ጉ​ባት።</verse>
				<verse number="36">ሰባት ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርቡ፤ ስም​ን​ተ​ኛ​ዋም ቀን የተ​ቀ​ደ​ሰች ጉባኤ ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርቡ፤ የመ​ሰ​ና​በቻ በዓል ነውና፤ የተ​ግ​ባር ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​በት።</verse>
				<verse number="37">“የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን፥ መሥ​ዋ​ዕ​ቱ​ንም፥ የመ​ጠ​ጡ​ንም ቍር​ባን፥ በየ​ቀኑ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቀ​ር​ቡ​ባ​ቸው ዘንድ የተ​ቀ​ደሱ በዓ​ላት እን​ዲ​ሆኑ የም​ታ​ው​ጁ​አ​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ላት እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="38">እነ​ዚ​ህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰን​በ​ታት ሌላ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከም​ት​ሰ​ጡት ከስ​ጦ​ታ​ችሁ ሌላ፥ ከስ​እ​ለ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ ሌላ፥ በፈ​ቃ​ዳ​ች​ሁም ከም​ታ​ቀ​ር​ቡ​አ​ቸው ሁሉ ሌላ ናቸው።</verse>
				<verse number="39">ከሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን የም​ድ​ሩን ፍሬ ካከ​ማ​ቻ​ችሁ በኋላ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በዓል ሰባት ቀን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ፤ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያዋ ቀን ዕረ​ፍት ትሁን፤ ስም​ን​ተ​ኛ​ዋም ቀን ዕረ​ፍት ትሁን።</verse>
				<verse number="40">በመ​ጀ​መ​ሪ​ያዋ ቀን የመ​ል​ካም ዛፍ ፍሬ፥ የዘ​ን​ባ​ባ​ው​ንም ቅር​ን​ጫፍ፥ የለ​መ​ለ​መ​ው​ንም ዛፍ ቅር​ን​ጫፍ፥ የወ​ን​ዝም አኻያ ዛፍ ውሰዱ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በየ​ዓ​መቱ ሰባት ቀን ደስ ይበ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="41">በየ​ዓ​መቱ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ይህን በዓል ታደ​ርጉ ዘንድ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ ይሁ​ን​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="42">ሰባት ቀን በዳ​ሶች ውስጥ ትቀ​መ​ጣ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="43">ከግ​ብፅ ምድር ባወ​ጣ​ኋ​ቸው ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በዳስ ውስጥ እን​ዳ​ስ​ቀ​መ​ጥ​ኋ​ቸው የልጅ ልጆ​ቻ​ችሁ ያውቁ ዘንድ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ያሉት የሀ​ገር ልጆች ሁሉ በዳስ ውስጥ ይቀ​መጡ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።”</verse>
				<verse number="44">ሙሴም የጌ​ታን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በዓ​ላት ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተና​ገረ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="24">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“መብ​ራ​ቱን ሁል ጊዜ እን​ድ​ታ​በ​ራ​በት ለመ​ብ​ራት ጥሩ ተወ​ቅጦ የተ​ጠ​ለለ የወ​ይራ ዘይት ያመ​ጡ​ልህ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እዘ​ዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ከመ​ጋ​ረ​ጃው ውጭ አሮ​ንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሁል ጊዜ ያበ​ሩ​ታል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ለልጅ ልጃ​ችሁ ሥር​ዐት ይሁን።</verse>
				<verse number="4">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በጥሩ መቅ​ረዝ ላይ መብ​ራ​ቶ​ቹን ሁል ጊዜ እስ​ኪ​ነጋ አብ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">“የስ​ንዴ ዱቄት ወስ​ደህ ዐሥራ ሁለት ኅብ​ስት ጋግር፤ በእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ኅብ​ስት ውስጥ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ ይሁን።</verse>
				<verse number="6">እነ​ዚ​ህ​ንም ስድ​ስት ስድ​ስ​ቱን በሁ​ለት ተርታ አድ​ር​ገህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በን​ጹሕ ገበታ ላይ አኑ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">በሁ​ለ​ቱም ተራ ንጹሕ ዕጣ​ንና ጨው ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ እነ​ዚ​ህም ነገ​ሮች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለመ​ታ​ሰ​ቢያ ለተ​ዘ​ጋ​ጁት ኅብ​ስ​ቶች ይሁኑ።</verse>
				<verse number="8">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሁል ጊዜ በሰ​ን​በት ቀን ሁሉ ያድ​ር​ጉት፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ የዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳን ነው።</verse>
				<verse number="9">ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆ​ቹም ይሁን፤ በእ​ሳት ከተ​ደ​ረ​ገው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ለእ​ርሱ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነውና በተ​ቀ​ደሰ ስፍራ ይብ​ሉት።”</verse>
				<verse number="10">አባቱ ግብ​ፃዊ የነ​በረ የእ​ስ​ራ​ኤ​ላ​ዊት ሴት ልጅ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ወጣ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ላ​ዊቱ ሴት ልጅና አንድ እስ​ራ​ኤ​ላዊ ሰው በሰ​ፈር ውስጥ ተጣሉ፤</verse>
				<verse number="11">የእ​ስ​ራ​ኤ​ላ​ዊ​ቱም ሴት ልጅ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ጠርቶ ሰደበ፤ ወደ ሙሴም አመ​ጡት። እና​ቱም ከዳን ነገድ የዳ​ቤር ልጅ ነበ​ረች፤ ስም​ዋም ሰሎ​ሚት ነበረ።</verse>
				<verse number="12">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ እስ​ኪ​ፈ​ር​ዱ​በት ድረስ በግ​ዞት አኖ​ሩት።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="14">“ተሳ​ዳ​ቢ​ውን ከሰ​ፈር ወደ ውጭ አው​ጣው፤ የሰ​ሙ​ትም ሁሉ እጃ​ቸ​ውን በራሱ ላይ ይጫ​ኑ​በት፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ይው​ገ​ሩት።”</verse>
				<verse number="15">ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ትነ​ግ​ራ​ለህ፥ “ማና​ቸ​ውም ሰው አም​ላ​ኩን ቢሰ​ድብ ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል።</verse>
				<verse number="16">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ጠርቶ የሚ​ሰ​ድብ ሁሉ ፈጽሞ ይገ​ደል፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ይው​ገ​ሩት፤ መጻ​ተኛ ወይም የሀ​ገር ልጅ ቢሆን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ጠርቶ ቢሳ​ደብ ይገ​ደል።</verse>
				<verse number="17">ሰውን የገ​ደለ ሰው ሁሉ ፈጽሞ ይገ​ደል።</verse>
				<verse number="18">እን​ስ​ሳ​ንም ቢገ​ድል በነ​ፍስ ፋንታ ነፍስ ይክ​ፈል።</verse>
				<verse number="19">ሰውም ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ቢጎዳ፥ እርሱ እን​ዳ​ደ​ረገ እን​ዲሁ ይደ​ረ​ግ​በት።</verse>
				<verse number="20">ስብ​ራት በስ​ብ​ራት ፋንታ፥ ዐይን በዐ​ይን ፋንታ፥ ጥርስ በጥ​ርስ ፋንታ፥ ሰውን እንደ ጎዳ እን​ዲሁ ይደ​ረ​ግ​በት።</verse>
				<verse number="21">ሰው​ንም የመ​ታና የገ​ደለ ፈጽሞ ይገ​ደል።</verse>
				<verse number="22">እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና ለመ​ጻ​ተ​ኛና ለሀ​ገር ልጅ አንድ ዐይ​ነት ሕግ ይሁ​ን​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="23">ሙሴም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ተሳ​ዳ​ቢ​ው​ንም ከሰ​ፈር ወደ ውጭ አወ​ጡት፤ በድ​ን​ጋ​ይም ወገ​ሩት። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረጉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="25">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን በሲና ተራራ ላይ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ እኔ ወደ​ም​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር በገ​ባ​ችሁ ጊዜ እኔ የም​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ታር​ፋ​ለች፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰን​በት ታደ​ር​ጋ​ለች።</verse>
				<verse number="3">ስድ​ስት ዓመት እር​ሻ​ህን ትዘ​ራ​ለህ፤ ስድ​ስት ዓመ​ትም ወይ​ን​ህን ትቈ​ር​ጣ​ለህ፤ ፍሬ​ዋ​ንም ትሰ​በ​ስ​ባ​ለህ።</verse>
				<verse number="4">በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ግን ሰን​በት ነው፤ የም​ድር ዕረ​ፍት ነው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰን​በት ነው፤ እር​ሻ​ህን አት​ዝራ፤ ወይ​ን​ህ​ንም አት​ቍ​ረጥ።</verse>
				<verse number="5">የም​ድ​ራ​ች​ሁን ገቦ አት​ጨ​ደው፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም የወ​ይ​ን​ህን ፍሬ አታ​ከ​ማች፤ ለም​ድ​ሪቱ የዕ​ረ​ፍት ዓመት ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="6">የም​ድ​ርም ሰን​በት ለአ​ንተ፥ ለወ​ንድ ባሪ​ያ​ህም፥ ለሴት ባሪ​ያ​ህም፥ ለም​ን​ደ​ኛም፥ ከአ​ንተ ጋር ለሚ​ኖር ለመ​ጻ​ተ​ኛም ምግብ ይሁን።</verse>
				<verse number="7">ለእ​ን​ስ​ሶ​ች​ህም፥ በም​ድ​ር​ህም ላሉት አራ​ዊት ፍሬዋ ሁሉ ምግብ ይሁን።</verse>
				<verse number="8">“የዓ​መ​ታ​ትን ሰባት ሰን​በ​ቶች ሰባት ጊዜ ሰባት ለራ​ስህ ትቈ​ጥ​ራ​ለህ፤ እነ​ዚ​ህም ሰባት የዓ​መ​ታት ሱባ​ዔ​ያት አርባ ዘጠኝ ዓመ​ታት ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="9">ከዚ​ያም በኋላ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ከወሩ በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን በም​ድ​ራ​ችሁ ሁሉ በቀ​ንደ መለ​ከት ታው​ጃ​ለህ፤ በማ​ስ​ተ​ስ​ረያ ቀን በም​ድ​ራ​ችሁ ሁሉ በቀ​ንደ መለ​ከት ታው​ጃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="10">አም​ሳ​ኛ​ው​ንም ዓመት ትቀ​ድ​ሳ​ላ​ችሁ፤ በም​ድ​ሪ​ቱም ለሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ነጻ​ነ​ትን ታው​ጃ​ላ​ችሁ፤ እርሱ ለእ​ና​ንተ ኢዮ​ቤ​ልዩ ነው፤ ሰው ሁሉ ወደ ርስ​ቱና ወደ ወገኑ ይመ​ለስ።</verse>
				<verse number="11">ያ አም​ሳ​ኛው ዓመት ለእ​ና​ንተ ኢዮ​ቤ​ልዩ ይሆ​ናል፤ በእ​ር​ሱም አት​ዝሩ፤ የገ​ቦ​ው​ንም አት​ጨዱ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም በእ​ርሱ አት​ል​ቀሙ።</verse>
				<verse number="12">ኢዮ​ቤ​ልዩ ነውና የተ​ቀ​ደሰ ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ በሜዳ ላይ የበ​ቀ​ለ​ውን ብሉ።</verse>
				<verse number="13">“በዚች ኢዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ሰው ሁሉ ወደ ርስቱ ይመ​ለ​ሳል።</verse>
				<verse number="14">ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህም አን​ዳች ብት​ሸ​ጥ​ለት፥ ወይም ከባ​ል​ን​ጀ​ራህ እጅ ብት​ገዛ፥ ሰው ባል​ን​ጀ​ራ​ውን አያ​ስ​ጨ​ን​ቀው።</verse>
				<verse number="15">ከኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመት በኋላ እንደ ዓመ​ታቱ ቍጥር ከባ​ል​ን​ጀ​ራህ ትገ​ዛ​ለህ፤ እር​ሱም እንደ መከሩ ዓመ​ታት ቍጥር ይከ​ፍ​ል​ሃል።</verse>
				<verse number="16">እንደ ዓመ​ታቱ ብዛት ዋጋ​ውን ያበ​ዛል፤ እንደ ዓመ​ታ​ቱም ማነስ ዋጋ​ውን ያሳ​ን​ሳል፤ እንደ መከሩ ቍጥር ይሸ​ጥ​ል​ሃል።</verse>
				<verse number="17">እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና ሰው ባል​ን​ጀ​ራ​ውን አያ​ስ​ጨ​ንቅ፤ ነገር ግን አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ።</verse>
				<verse number="18">“ሥር​ዐ​ቴ​ንም አድ​ርጉ፤ ፍር​ዴ​ንም ጠብቁ፤ አድ​ር​ጉ​ትም፤ በም​ድ​ሪ​ቱም ውስጥ ተዘ​ል​ላ​ችሁ ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="19">ምድ​ሪ​ቱም ፍሬ​ዋን ትሰ​ጣ​ለች፤ እስ​ክ​ት​ጠ​ግ​ቡም ድረስ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ውስጥ ተዘ​ል​ላ​ችሁ ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="20">እና​ን​ተም፦ ‘ካል​ዘ​ራን፥ እህ​ላ​ች​ን​ንም ካላ​ከ​ማ​ቸን በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ምን እን​በ​ላ​ለን?’ ብትሉ፥</verse>
				<verse number="21">እኔ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ዓመት በረ​ከ​ቴን በላ​ያ​ችሁ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱም የሦ​ስት ዓመት ፍሬ ታፈ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="22">በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ዓመት ትዘ​ራ​ላ​ችሁ፤ ከከ​ረ​መ​ውም እህል ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ፍሬዋ እስ​ኪ​ገባ፥ እስከ ዘጠ​ነ​ኛው ዓመት ድረስ፥ ከከ​ረ​መው እህል ትበ​ላ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="23">“ምድ​ርም ለእኔ ናትና፥ እና​ን​ተም በእኔ ፊት እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች ናች​ሁና ምድ​ርን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አት​ሽጡ።</verse>
				<verse number="24">በር​ስ​ታ​ች​ሁም ምድር ሁሉ መቤ​ዠ​ትን ለም​ድ​ሪቱ አድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="25">ወን​ድ​ም​ህም ቢደ​ኸይ፥ ከር​ስ​ቱም ቢሸጥ፥ ለእ​ርሱ የቀ​ረበ ዘመዱ መጥቶ ወን​ድሙ የሸ​ጠ​ውን ይቤ​ዠ​ዋል።</verse>
				<verse number="26">የሚ​ቤ​ዠ​ውም ሰው ቢያጣ፥ እር​ሱም እጁ ቢረ​ጥብ፥ ለመ​ቤ​ዠ​ትም የሚ​በቃ ቢያ​ገኝ፥</verse>
				<verse number="27">የሽ​ያ​ጩን ዘመን ቈጥሮ የቀ​ረ​ውን ወደ ገዛው ሰው ይመ​ልስ፤ እር​ሱም ወደ ርስቱ ይመ​ለስ።</verse>
				<verse number="28">ለራ​ሱም ዕዳ​ውን መክ​ፈል ባይ​ችል፥ ሽያጩ በገ​ዛው ሰው እጅ እስከ ኢዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ድረስ ይቀ​መጥ፤ በኢ​ዮ​ቤ​ል​ዩም ዓመት ይውጣ፤ እር​ሱም ወደ ርስቱ ይመ​ለስ።</verse>
				<verse number="29">“ሰውም ቅጥር ባለ​በት ከተማ መኖ​ርያ ቤትን ቢሸጥ፥ ከተ​ሸጠ በኋላ አንድ ዓመት እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ ለመ​ቤ​ዠት ይች​ላል፤ ለአ​ንድ ሙሉ ዓመት መቤ​ዠት ይች​ላል።</verse>
				<verse number="30">አንድ ዓመት እስ​ኪ​ጨ​ረስ ባይ​ቤ​ዠው ቤቱ ለገዡ ይሆ​ናል፤ ቅጥር ባለ​በት ከተማ ያለ​ውን ያን ቤት ይመ​ረ​ም​ሩ​ለ​ታል፤ ለገ​ዛው ሰው ለልጅ ልጁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጸ​ና​ለ​ታል፤ በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመ​ትም አይ​ወ​ስ​ዱ​በ​ትም።</verse>
				<verse number="31">ቅጥር በሌ​ለ​በት መን​ደር ያሉ ቤቶች ግን እንደ እርሻ ይቈ​ጠ​ራሉ፤ ይቤ​ዣሉ፤ በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመ​ትም ይመ​ለ​ሳሉ።</verse>
				<verse number="32">የሌ​ዋ​ው​ያ​ንን ከተ​ሞች፥ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ያሉ ቤቶ​ቻ​ቸ​ውን ሌዋ​ው​ያን ለዘ​ለ​ዓ​ለም መቤ​ዠት ይች​ላሉ።</verse>
				<verse number="33">ማና​ቸ​ውም ሰው ከሌ​ዋ​ው​ያን ቢገዛ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል የሌ​ዋ​ው​ያን ከተ​ሞች ቤቶች ርስ​ቶ​ቻ​ቸው ናቸ​ውና በር​ስቱ ከተማ ያለ የተ​ሸ​ጠው ቤት በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ይመ​ለ​ሳል።</verse>
				<verse number="34">በከ​ተ​ማ​ዎ​ቻ​ቸው ዙሪያ ያሉ እር​ሻ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም የዘ​ለ​ዓ​ለም ርስ​ቶ​ቻ​ቸው ናቸ​ውና አይ​ሸ​ጡም።</verse>
				<verse number="35">“ከአ​ንተ ጋር ያለው ወን​ድ​ምህ ቢደ​ኸይ፥ እጁም በአ​ንተ ዘንድ ቢደ​ክም እንደ እን​ግ​ዳና እንደ መጻ​ተኛ ትረ​ዳ​ዋ​ለህ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ይኑር።</verse>
				<verse number="36">ወን​ድ​ምህ ከአ​ንተ ጋር ይኖር ዘንድ ከእ​ርሱ ምንም ወለድ ወይም ትርፍ አት​ው​ሰድ፤ ነገር ግን አም​ላ​ክ​ህን ፍራ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።</verse>
				<verse number="37">ብር​ህን በወ​ለድ አታ​በ​ድ​ረው፤ እህ​ል​ህ​ንም በት​ርፍ አት​ስ​ጠው።</verse>
				<verse number="38">የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር እሰ​ጥህ ዘንድ፥ አም​ላ​ክም እሆ​ንህ ዘንድ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ሁህ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝና።</verse>
				<verse number="39">“ወን​ድ​ምህ ቢቸ​ገር፥ ራሱ​ንም ለአ​ንተ ቢሸጥ፥ እንደ ባሪያ አድ​ር​ገህ አት​ግ​ዛው።</verse>
				<verse number="40">እንደ ምን​ደ​ኛና እንደ ስደ​ተኛ ከአ​ንተ ጋር ይሁን፤ እስከ ኢዮ​ቤ​ልዩ ዓመ​ትም ያገ​ል​ግ​ልህ።</verse>
				<verse number="41">በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመ​ትም እርሱ ከል​ጆቹ ጋር ከአ​ንተ ይወ​ጣል፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም፥ ወደ አባ​ቱም ርስት ይመ​ለ​ሳል።</verse>
				<verse number="42">ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኋ​ቸው ባሪ​ያ​ዎች ናቸ​ውና ባሪያ እን​ደ​ሚ​ሸጥ አይ​ሸጡ።</verse>
				<verse number="43">በሥራ አታ​ስ​ጨ​ን​ቀው፤ ነገር ግን አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ።</verse>
				<verse number="44">ምን ያህል ወንድ ባሪ​ያና ሴት ባሪያ እን​ዲ​ኖ​ሩህ ብት​ፈ​ልግ ግን በዙ​ሪ​ያ​ችሁ ካሉት ከእ​ነ​ርሱ ከአ​ሕ​ዛብ ወን​ድና ሴት ባያ​ሪ​ያ​ዎ​ችን ግዙ።</verse>
				<verse number="45">በእ​ና​ንተ መካ​ከል ከሚ​ቀ​መ​ጡት ስደ​ተ​ኞች ልጆች ለራ​ሳ​ችሁ ትገ​ዛ​ላ​ችሁ፤ ከዘ​መ​ዶ​ቻ​ቸ​ውም በም​ድ​ራ​ችሁ የሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ለር​ስ​ታ​ችሁ ይሁ​ኑ​አ​ችሁ።</verse>
				<verse number="46">ከእ​ና​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ቻ​ችሁ ታወ​ር​ሱ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ እነ​ር​ሱም ለእ​ና​ንተ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ውርስ ይሆ​ናሉ፤ ነገር ግን ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማና​ቸ​ውም ሰው ወን​ድ​ሙን በሥራ አያ​ስ​ጨ​ን​ቀው።</verse>
				<verse number="47">“በአ​ን​ተም ዘንድ የሚ​ኖር መጻ​ተኛ ወይም እን​ግዳ ሀብ​ታም ቢሆን፥ ወን​ድ​ም​ህም በእ​ርሱ አጠ​ገብ ቢደ​ኸይ፥ ራሱ​ንም ለመ​ጻ​ተ​ኛው፥ ወይም ለእ​ን​ግ​ዳው ወይም ለወ​ገ​ኖቹ ዘር ቢሸጥ፥</verse>
				<verse number="48">ከተ​ሸጠ በኋላ መቤ​ዠት ይች​ላል፤ ከወ​ን​ድ​ሞቹ አንዱ ይቤ​ዠው፤</verse>
				<verse number="49">ወይም አጎቱ ወይም የአ​ጎቱ ልጅ ይቤ​ዠው፤ ወይም ከወ​ገኑ ለእ​ርሱ የቀ​ረበ ዘመድ ይቤ​ዠው፤ ወይም እርሱ እጁ ቢረ​ጥብ ራሱን ይቤ​ዠው።</verse>
				<verse number="50">ከገ​ዛ​ውም ሰው ጋር ከገ​ዛ​በት ዓመት ጀምሮ እስከ ኢዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ድረስ ይቍ​ጠር፤ የሽ​ያ​ጩም ብር እንደ ዓመ​ታቱ ቍጥር ይሁን፤ እንደ ምን​ደ​ኛ​ውም ዘመን ከእ​ርሱ ጋር ይሁን።</verse>
				<verse number="51">ብዙ ዓመ​ታ​ትም ቢቀሩ እንደ እነ​ርሱ ቍጥር ከሽ​ያጩ ብር የመ​ቤ​ዠ​ቱን ዋጋ ይመ​ልስ።</verse>
				<verse number="52">እስከ ኢዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ድረስ ጥቂት ዓመ​ታት ቢቀሩ እንደ ዓመቱ ይቍ​ጠ​ሩ​ለት፤ እንደ ኣመ​ታ​ቱም መጠን የመ​ቤ​ዠ​ቱን ዋጋ ይመ​ልስ።</verse>
				<verse number="53">በየ​ዓ​መቱ እንደ ምን​ደኛ ከእ​ርሱ ጋር ይኑር፤ በፊ​ትህ እንደ ቀደ​መው አያ​ስ​ጨ​ን​ቀው።</verse>
				<verse number="54">በዚህ ዘመን ሁሉ ግን ባይ​ቤዥ በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመት እርሱ ከል​ጆቹ ጋር ይውጣ።</verse>
				<verse number="55">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለእኔ ባሪ​ያ​ዎች ናቸ​ውና፤ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኋ​ቸው ባሪ​ያ​ዎች ናቸው፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="26">
				<verse number="1">“ለእ​ና​ንተ በእጅ የተ​ሠራ ጣዖት አታ​ድ​ርጉ፤ የተ​ቀ​ረ​ጸም ምስል ወይም ሐው​ልት አታ​ቁሙ፤ ትሰ​ግ​ዱ​ለ​ትም ዘንድ በም​ድ​ራ​ችሁ ላይ የተ​ቀ​ረጸ ድን​ጋይ አታ​ኑሩ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።</verse>
				<verse number="2">ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ጠብቁ፤ የቀ​ደ​ስ​ኋ​ቸ​ው​ንም ፍሩ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።</verse>
				<verse number="3">“በሥ​ር​ዐቴ ብት​ሄዱ፥ ትእ​ዛ​ዛ​ቴ​ንም ብት​ጠ​ብቁ፥ ብታ​ደ​ር​ጉ​ትም፥</verse>
				<verse number="4">ዝና​ሙን በወ​ቅቱ አዘ​ን​ማ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱም እህ​ል​ዋን ትሰ​ጣ​ለች፤ የሜ​ዳው ዛፎ​ችም ፍሬ​ያ​ቸ​ውን ይሰ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="5">የእ​ህ​ሉም ማበ​ራ​የት በእ​ና​ንተ ዘንድ እስከ ወይኑ መቈ​ረጥ ይደ​ር​ሳል፤ የወ​ይ​ኑም መቈ​ረጥ እስከ እህሉ መዝ​ራት ይደ​ር​ሳል፤ እስ​ክ​ት​ጠ​ግ​ቡም ድረስ እን​ጀ​ራ​ች​ሁን ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በም​ድ​ራ​ች​ሁም ላይ ተዘ​ል​ላ​ችሁ ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="6">በም​ድ​ራ​ች​ሁም ላይ ሰላ​ምን እሰ​ጣ​ለሁ፤ ትተ​ኛ​ላ​ችሁ፤ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ች​ሁም የለም፤ ክፉ​ዎ​ች​ንም አራ​ዊት ከም​ድ​ራ​ችሁ አጠ​ፋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ታሳ​ድ​ዳ​ላ​ችሁ፤ በፊ​ታ​ች​ሁም በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="8">ከእ​ና​ን​ተም አም​ስቱ መቶ​ውን ያሳ​ድ​ዳሉ፤ መቶ​ውም ዐሥ​ሩን ሺህ ያሳ​ድ​ዳሉ፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በፊ​ታ​ችሁ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="9">ወደ እና​ን​ተም እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ፤ አባ​ዛ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከፍ ከፍም አደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤ ቃል ኪዳ​ኔ​ንም ከእ​ና​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">ብዙ ጊዜ የተ​ቀ​መ​ጠ​ውን፥ የከ​ረ​መ​ው​ንም እህል ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ አዲ​ሱ​ንም ታስ​ገቡ ዘንድ የከ​ረ​መ​ውን ታወ​ጣ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="11">ማደ​ሪ​ያ​ዬ​ንም በእ​ና​ንተ መካ​ከል አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ነፍ​ሴም አት​ጸ​የ​ፋ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="12">በመ​ካ​ከ​ላ​ች​ሁም እመ​ላ​ለ​ሳ​ለሁ፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ሕዝብ ትሆ​ኑ​ል​ኛ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="13">ባሪ​ያ​ዎች ከነ​በ​ራ​ች​ሁ​በት ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኋ​ችሁ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ፤ የባ​ር​ነ​ታ​ች​ሁን ቀን​በር ሰብ​ሬ​አ​ለሁ፤ በግ​ል​ጽም አወ​ጣ​ኋ​ችሁ።</verse>
				<verse number="14">“ነገር ግን ባት​ሰ​ሙኝ፥ እነ​ዚ​ህ​ንም ትእ​ዛ​ዛት ሁሉ ባታ​ደ​ርጉ፥</verse>
				<verse number="15">ሥር​ዐ​ቴ​ንም ብት​ንቁ፥ ትእ​ዛ​ዛ​ቴ​ንም ሁሉ እን​ዳ​ታ​ደ​ርጉ፥ ቃል ኪዳ​ኔ​ንም እን​ድ​ታ​ፈ​ርሱ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ፍር​ዴን ብት​ሰ​ለች፥</verse>
				<verse number="16">እኔም እን​ዲህ አደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ፍር​ሀ​ትን፥ ክሳ​ት​ንም፥ ዐይ​ና​ች​ሁ​ንም የሚ​ያ​ፈ​ዝዝ፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም የሚ​ያ​ጠፋ ትኩ​ሳት አወ​ር​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ዘራ​ች​ሁ​ንም በከ​ንቱ ትዘ​ራ​ላ​ችሁ፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ችሁ ይበ​ሉ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="17">ፊቴ​ንም አከ​ብ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ፊት ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ የሚ​ጠ​ሏ​ች​ሁም ያሸ​ን​ፉ​አ​ች​ኋል። ማንም ሳያ​ሳ​ድ​ዳ​ችሁ ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="18">እስ​ከ​ዚ​ህም ድረስ ባት​ሰ​ሙኝ፥ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ በቅ​ጣ​ታ​ችሁ ላይ ሰባት እጥፍ መቅ​ሠ​ፍ​ትን እጨ​ም​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">የት​ዕ​ቢ​ታ​ች​ሁን ስድብ አጠ​ፋ​ለሁ፤ ሰማ​ያ​ች​ሁ​ንም እንደ ብረት፥ ምድ​ራ​ች​ሁ​ንም እንደ ናስ አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">ጕል​በ​ታ​ች​ሁም በከ​ንቱ ያል​ቃል፤ ምድ​ራ​ች​ሁም እህ​ል​ዋን አት​ሰ​ጥም፤ የዱር ዛፎ​ችም ፍሬ​ያ​ቸ​ውን አይ​ሰ​ጡም።</verse>
				<verse number="21">“ከዚ​ያም በኋላ በእ​ን​ቢ​ተ​ኝ​ነት ብት​ሄ​ዱ​ብኝ፥ ልት​ሰ​ሙ​ኝም ባት​ፈ​ቅዱ እንደ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ መጠን በመ​ቅ​ሠ​ፍት ላይ ሰባት እጥፍ እጨ​ም​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="22">በእ​ና​ንተ ላይ ክፉ​ዎች የም​ድ​ርን አራ​ዊት እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ይበ​ሉ​አ​ች​ኋል፤ እን​ስ​ሶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ያጠ​ፋሉ፤ እና​ን​ተ​ንም ያሳ​ን​ሳሉ፤ መን​ገ​ዶ​ቻ​ች​ሁም በረሃ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="23">“እስ​ከ​ዚ​ህም ድረስ ባት​ቀጡ፥ አግ​ድ​ማ​ች​ሁም ብት​ሄዱ፥</verse>
				<verse number="24">እኔ ደግሞ አግ​ድሜ በቍጣ እሄ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም ሰባት እጥፍ እበ​ቀ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="25">የቃል ኪዳ​ኔ​ንም በቀል ይበ​ቀ​ል​ባ​ችሁ ዘንድ ሰይፍ አመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወደ ከተ​ማ​ች​ሁም ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ፤ ቸነ​ፈ​ር​ንም እሰ​ድ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ። በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም እጅ ተላ​ል​ፋ​ችሁ ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="26">በእ​ህል ረሃብ ባስ​ጨ​ነ​ክ​ኋ​ችሁ ጊዜ ዐሥር ሴቶች እን​ጀራ በአ​ንድ ምጣድ ይጋ​ግ​ራሉ፤ በሚ​ዛ​ንም መዝ​ነው እን​ጀ​ራ​ች​ሁን ይመ​ል​ሱ​ላ​ች​ኋል፤ በበ​ላ​ች​ሁም ጊዜ አት​ጠ​ግ​ቡም።</verse>
				<verse number="27">እስ​ከ​ዚ​ህም ድረስ ባት​ሰ​ሙኝ፥ አግ​ድ​ማ​ች​ሁም ብት​ሄ​ዱ​ብኝ፥</verse>
				<verse number="28">እኔ ደግሞ አግ​ድሜ በቍጣ እሄ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እንደ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም ሰባት እጥፍ እቀ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="29">የወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም ሥጋ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ የሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም ሥጋ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="30">የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቻ​ች​ሁን አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ በእጅ የተ​ሠሩ የዕ​ን​ጨት ምስ​ሎ​ቻ​ች​ሁ​ንም አጠ​ፋ​ለሁ፤ ሬሳ​ች​ሁ​ንም በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ችሁ ሬሳ​ዎች ላይ እጥ​ላ​ለሁ፤ ነፍ​ሴም ትጸ​የ​ፋ​ች​ኋ​ለች።</verse>
				<verse number="31">ከተ​ሞ​ቻ​ች​ሁ​ንም ባድማ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ መቅ​ደ​ሶ​ቻ​ች​ሁ​ንም አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁ​ንም መዓዛ አላ​ሸ​ት​ትም።</verse>
				<verse number="32">ምድ​ሪ​ቱ​ንም የተ​ፈ​ታች አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባት ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ከእ​ር​ስዋ የተ​ነሣ ይደ​ነ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="33">እና​ን​ተ​ንም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እበ​ት​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ በሄ​ዳ​ች​ሁ​በ​ትም ሁሉ ሰይፍ ታጠ​ፋ​ች​ኋ​ለች፤ ምድ​ራ​ች​ሁም የተ​ፈ​ታች ትሆ​ና​ለች፤ ከተ​ሞ​ቻ​ች​ሁም ባድማ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="34">“በዚ​ያም በተ​ፈ​ታ​ች​በት ዘመን ሁሉ እና​ን​ተም በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ምድር ሳላ​ችሁ፥ ምድ​ሪቱ ሰን​በት በማ​ድ​ረ​ግዋ ደስ ይላ​ታል፤ በዚ​ያም ጊዜ ምድ​ሪቱ ታር​ፋ​ለች፤ ስን​በ​ት​ንም በማ​ድ​ረ​ግዋ ደስ ይላ​ታል።</verse>
				<verse number="35">እና​ንተ ተቀ​ም​ጣ​ች​ሁ​ባት በነ​በረ ጊዜ በሰ​ን​በ​ቶ​ቻ​ችሁ አላ​ረ​ፈ​ችም ነበ​ርና በተ​ፈ​ታ​ች​በት ዘመን ሁሉ ታር​ፋ​ለች።</verse>
				<verse number="36">በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ምድ​ሮች ሳሉ ከእ​ና​ንተ ተለ​ይ​ተው በቀ​ሩት ላይ በል​ባ​ቸው ድን​ጋ​ጤን እሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በነ​ፋ​ስም የም​ት​ን​ቀ​ሳ​ቀስ የቅ​ጠል ድምፅ ታሸ​ብ​ራ​ቸ​ዋ​ለች፤ ከሰ​ይፍ እን​ደ​ሚ​ሸሹ ይሸ​ሻሉ ፤</verse>
				<verse number="37">ማንም ሳያ​ሳ​ድ​ዳ​ቸው ከሰ​ይፍ እን​ዲ​ሸሹ እርስ በር​ሳ​ቸው ይሰ​ነ​ካ​ከ​ላሉ፤ እና​ን​ተም በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ፊት መቆም አት​ች​ሉም።</verse>
				<verse number="38">በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ፤ የጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ምድር ትው​ጣ​ች​ኋ​ለች።</verse>
				<verse number="39">ከእ​ና​ን​ተም ተለ​ይ​ተው የቀ​ሩት ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው ይጠ​ፋሉ፤ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ኀጢ​አት ደግሞ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ምድር ይቀ​ል​ጣሉ።</verse>
				<verse number="40">“እንደ ከዱኝ፥ ቸልም እን​ዳ​ሉኝ፥ በፊ​ቴም አግ​ድ​መው እንደ ሄዱ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንና፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ኀጢ​አት ይና​ዘ​ዛሉ።</verse>
				<verse number="41">እኔም ደግሞ አግ​ድሜ ከእ​ነ​ርሱ ጋር በቍጣ ሄድሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ምድር አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ። ነገር ግን በዚ​ያን ጊዜ ያል​ተ​ገ​ረ​ዘው ልባ​ቸው ያፍ​ራል፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ይና​ዘ​ዛሉ፤</verse>
				<verse number="42">ያን ጊዜ እኔ ከያ​ዕ​ቆብ ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን አስ​ባ​ለሁ፤ ደግ​ሞም ከይ​ስ​ሐቅ ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን፥ ከአ​ብ​ር​ሃ​ምም ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን አስ​ባ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አስ​ባ​ለሁ።</verse>
				<verse number="43">ምድ​ርም ከእ​ነ​ርሱ መጥ​ፋት የተ​ነሣ ባዶ ትቀ​ራ​ለች፤ እነ​ር​ሱም ሳይ​ኖሩ በተ​ፈ​ታ​ች​በት ዘመን ዕረ​ፍት ታደ​ር​ጋ​ለች፤ ፍር​ዴ​ንም ስለ ናቁ፥ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም ሥር​ዐ​ቴን ስለ ተጸ​የ​ፈች የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ቅጣት ይሸ​ከ​ማሉ።</verse>
				<verse number="44">ነገር ግን እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው ነኝና እነ​ርሱ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ምድር ሳሉ፥ እስ​ካ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ያለ​ኝን ቃል ኪዳን እስ​ካ​ፈ​ርስ ድረስ አል​ጥ​ላ​ቸ​ውም፤ አል​ጸ​የ​ፋ​ቸ​ው​ምም።</verse>
				<verse number="45">እኔ አም​ላ​ካ​ቸው እሆን ዘንድ አሕ​ዛብ እያዩ ከግ​ብፅ ምድር ከግ​ዞት ቤት እን​ዳ​ወ​ጣ​ኋ​ቸው የቀ​ድሞ ቃል ኪዳ​ና​ቸ​ውን ስለ እነ​ርሱ አስ​ባ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።”</verse>
				<verse number="46">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ር​ሱና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል በሲና ተራራ ላይ በሙሴ እጅ የሰ​ጣ​ቸው ሥር​ዐ​ቶ​ችና ፍር​ዶች፥ ሕግ​ጋ​ትም እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="27">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ማና​ቸ​ውም ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለት ቢሳል አንተ እን​ደ​ም​ት​ገ​ም​ተው መጠን ስለ ሰው​ነቱ ዋጋ​ውን ይስጥ።</verse>
				<verse number="3">ለወ​ንድ ከሃያ ዓመት ጀምሮ እስከ ስድሳ ዓመት ድረስ እንደ መቅ​ደሱ ሚዛን ግምቱ አምሳ የብር ዲድ​ር​ክም ይሁን።</verse>
				<verse number="4">ሴትም ብት​ሆን ግምቷ ሠላሳ የብር ዲድ​ር​ክም ይሁን።</verse>
				<verse number="5">ከአ​ም​ስት ዓመ​ትም ጀምሮ እስከ ሃያ ዓመት ድረስ ግምቱ ለወ​ንድ ሃያ የብር ዲድ​ር​ክም፥ ለሴ​ትም ዐሥር የብር ዲድ​ር​ክም ይሁን።</verse>
				<verse number="6">ከአ​ንድ ወርም እስከ አም​ስት ዓመት ድረስ ለወ​ንድ ግምቱ አም​ስት የብር ዲድ​ር​ክም፥ ለሴ​ትም ግምቷ ሦስት የብር ዲድ​ር​ክም ይሁን።</verse>
				<verse number="7">ከስ​ድሳ ዓመ​ትም ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ወንድ ቢሆን ግምቱ ዐሥራ አም​ስት ዲድ​ር​ክም፥ ለሴ​ትም ዐሥር ዲድ​ር​ክም ይሁን።</verse>
				<verse number="8">ለግ​ምቱ የሚ​ከ​ፍ​ለ​ውን ቢያጣ ግን በካ​ህኑ ፊት ይቁም፤ ካህ​ኑም የተ​ሳ​ለ​ውን ሰው ከእጁ ባለው ገን​ዘብ መጠን ይገ​ም​ት​ለት፤ ካህ​ኑም የተ​ሳ​ለው ሰው እን​ደ​ሚ​ችል መጠን ይገ​ም​ት​ለት።</verse>
				<verse number="9">“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሥ​ዋ​ዕት አድ​ርጎ የሚ​ያ​ቀ​ር​በው እን​ስሳ ቢሆን፥ ሰው ከእ​ነ​ዚህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጠው ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="10">መል​ካ​ሙን በክፉ፥ ክፉ​ው​ንም በመ​ል​ካም አይ​ለ​ውጥ፤ እን​ስ​ሳ​ንም በእ​ን​ስሳ ቢለ​ውጥ እር​ሱና ልዋጩ የተ​ቀ​ደሱ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="11">እን​ስ​ሳው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት መሆን የማ​ይ​ገ​ባው ርኩስ ቢሆን፥ እን​ስ​ሳ​ውን በካ​ህኑ ፊት ያቁ​መው።</verse>
				<verse number="12">መል​ካ​ምም ቢሆን ክፉም ቢሆን ካህኑ ይገ​ም​ተው፤ ካህ​ኑም እን​ደ​ሚ​ገ​ም​ተው መጠን እን​ዲሁ ይሁን።</verse>
				<verse number="13">ይቤ​ዠው ዘንድ ቢወ​ድድ ግን ከግ​ምቱ በላይ አም​ስ​ተኛ እጅ ይጨ​ምር።</verse>
				<verse number="14">“ሰውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ይሆን ዘንድ ቤቱን ቢቀ​ድስ፥ ካህኑ መል​ካም ወይም ክፉ እንደ ሆነ ይገ​ም​ተ​ዋል፤ ካህ​ኑም እን​ደ​ሚ​ገ​ም​ተው መጠን እን​ዲሁ ይቆ​ማል።</verse>
				<verse number="15">የተ​ሳ​ለ​ውም ሰው ቤቱን ይቤ​ዠው ዘንድ ቢወ​ድድ ከግ​ምቱ ገን​ዘብ በላይ አም​ስ​ተኛ እጅ ይጨ​ምር፤ ቤቱም ለእ​ርሱ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="16">“ሰውም ከር​ስቱ እርሻ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢሳል፥ እንደ መዘ​ራቱ መጠን ይገ​መት፤ አንድ የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ገብስ የሚ​ዘ​ራ​በት እርሻ አምሳ ወቄት ብር ይገ​መ​ታል።</verse>
				<verse number="17">እር​ሻ​ው​ንም ከኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ጀምሮ ቢሳል፥ እንደ ግምቱ መጠን ይቆ​ማል።</verse>
				<verse number="18">እር​ሻ​ው​ንም ከኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመት በኋላ ቢሳል፥ ካህኑ እስከ ኢዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ድረስ እንደ ቀሩት ዓመ​ታት ገን​ዘ​ቡን ይቈ​ጥ​ር​ለ​ታል፤ ከግ​ም​ቱም ይጐ​ድ​ላል።</verse>
				<verse number="19">እር​ሻ​ው​ንም የተ​ሳለ ሰው ይቤ​ዠው ዘንድ ቢወ​ድድ፥ ከግ​ምቱ ገን​ዘብ በላይ አም​ስ​ተኛ እጅ ይጨ​ምር፤ ለእ​ር​ሱም ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="20">እር​ሻ​ው​ንም ባይ​ቤ​ዠው፥ ወይም ለሌላ ሰው ቢሸጥ እንደ ገና ይቤ​ዠው ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ውም።</verse>
				<verse number="21">እር​ሻው ግን በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ሲወጣ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ እርሻ ይሆ​ናል፤ ርስ​ቱም ለካ​ህኑ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="22">ከር​ስቱ እርሻ ያል​ሆ​ነ​ውን የገ​ዛ​ውን እርሻ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢሳል፥</verse>
				<verse number="23">ካህኑ እስከ ኢዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ድረስ የግ​ም​ቱን ዋጋ ይቈ​ጥ​ር​ለ​ታል፤ በዚ​ያም ቀን ግም​ቱን እንደ ተቀ​ደሰ ነገር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ጣል።</verse>
				<verse number="24">በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመት እር​ሻው የም​ድ​ሪቱ ባለ ርስት ወደ ነበ​ረው ወደ ሸጠው ሰው ይመ​ለ​ሳል፤ የራሱ ወሰን ምድር ነውና።</verse>
				<verse number="25">ግም​ቱም ሁሉ እንደ መቅ​ደሱ ሚዛን ይሆ​ናል፤ አንዱ ዲድ​ር​ክም ሃያ አቦሊ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="26">“ከእ​ን​ስ​ሳህ የሚ​ወ​ለድ በኵር ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ማንም ይለ​ው​ጠው ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ውም፤ በሬ ቢሆን ወይም በግ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።</verse>
				<verse number="27">የረ​ከ​ሰም እን​ስሳ ቢሆን እንደ ግምቱ ይቤ​ዠው፤ በእ​ር​ሱም የዋ​ጋ​ውን አም​ስ​ተኛ እጅ ይጨ​ም​ር​በ​ታል፤ ባይ​ቤ​ዥም እንደ ግምቱ ይሸ​ጣል።</verse>
				<verse number="28">“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ለየ እርም የሆነ ነገር ሁሉ፥ ሰው ቢሆን ወይም እን​ስሳ ወይም የር​ስቱ እርሻ ቢሆን፥ አይ​ሸ​ጥም፤ አይ​ቤ​ዥም፤ እርም የሆነ ነገር ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።</verse>
				<verse number="29">ከሰ​ዎ​ችም መባ ሆኖ የቀ​ረበ ሁሉ እስ​ኪ​ሞት ድረስ አይ​ቤ​ዥም።</verse>
				<verse number="30">“የም​ድ​ርም ዐሥ​ራት፥ ወይም የም​ድር ዘር፥ ወይም የዛፍ ፍሬ ቢሆን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ነው።</verse>
				<verse number="31">ሰውም ዐሥ​ራ​ቱን ሊቤዥ ቢወ​ድድ፥ አም​ስ​ተኛ እጅ ይጨ​መ​ር​በ​ታል።</verse>
				<verse number="32">ከበ​ሬም ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ፥ ከበ​ግም ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ፥ ከእ​ረ​ኛ​ውም በትር በታች ከሚ​ያ​ልፍ ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="33">መል​ካ​ሙን በክፉ፥ ክፉ​ው​ንም በመ​ል​ካም አይ​ለ​ውጥ፤ ቢለ​ው​ጠ​ውም እር​ሱና ልዋጩ የተ​ቀ​ደሱ ይሆ​ናሉ፤ አይ​ቤ​ዠ​ውም።”</verse>
				<verse number="34">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሲና ተራራ ላይ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ዘንድ ሙሴን ያዘ​ዘው ትእ​ዛ​ዛት እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="4">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን በሲና ምድረ በዳ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ፥ በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን፥ ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ድምር፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ በየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር፥ ወን​ዱን ሁሉ እያ​ን​ዳ​ን​ዱን ቍጠሩ።</verse>
				<verse number="3">ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡ​ትን ሁሉ፥ አን​ተና አሮን በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ቍጠ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">እንደ እየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ከየ​ነ​ገዱ አለ​ቆች አንድ አንድ ሰው ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን።</verse>
				<verse number="5">ከእ​ና​ን​ተም ጋር የሚ​ቆ​ሙት ሰዎች ስሞ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው፤ ከሮ​ቤል የሰ​ዲ​ዮር ልጅ ኤሊ​ሱር፥</verse>
				<verse number="6">ከስ​ም​ዖን የሴ​ሩ​ሳዴ ልጅ ሰላ​ም​ያል፥</verse>
				<verse number="7">ከይ​ሁዳ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነአ​ሶን፥</verse>
				<verse number="8">ከይ​ሳ​ኮር የሰ​ገር ልጅ ናት​ና​ኤል፥</verse>
				<verse number="9">ከዛ​ብ​ሎን የኬ​ሎን ልጅ ኤል​ያብ፥</verse>
				<verse number="10">ከዮ​ሴፍ ልጆች ከኤ​ፍ​ሬም የኤ​ም​ዩድ ልጅ ኤሊ​ሳማ፥ ከም​ናሴ የፈ​ዳ​ሱር ልጅ ገማ​ል​ያል፥</verse>
				<verse number="11">ከብ​ን​ያም የጋ​ዲ​ዮን ልጅ አቢ​ዳን፥</verse>
				<verse number="12">ከዳን የአ​ሚ​ሳዲ ልጅ አክ​ያ​ዚር፥</verse>
				<verse number="13">ከአ​ሴር የኤ​ክ​ራን ልጅ ፋጋ​ኤል፥</verse>
				<verse number="14">ከጋድ የራ​ጉ​ኤል ልጅ ኤል​ሳፍ፥</verse>
				<verse number="15">ከን​ፍ​ታ​ሌም የዔ​ናን ልጅ አኪሬ።</verse>
				<verse number="16">ከማ​ኅ​በሩ የተ​መ​ረጡ የእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ አለ​ቆ​ችና መሳ​ፍ​ንት በየ​ወ​ገ​ና​ቸው እነ​ዚህ ናቸው።”</verse>
				<verse number="17">ሙሴና አሮ​ንም እነ​ዚ​ህን በየ​ስ​ማ​ቸው የተ​ጠ​ሩ​ትን ሰዎች ወሰ​ዱ​አ​ቸው፤</verse>
				<verse number="18">በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ማኅ​በ​ሩን ሁሉ ሰበ​ሰ​ቡ​አ​ቸው፤ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን ወንድ ሁሉ በየ​ራሱ፥ በየ​ወ​ገ​ኑም፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች፥ በየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር ትው​ል​ዳ​ቸ​ውን ተና​ገሩ።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ እን​ዲሁ በሲና ምድረ በዳ ቈጠ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">የእ​ስ​ራ​ኤል በኵር የሮ​ቤል ልጆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች እንደ እየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር፥ በየ​ራ​ሳ​ቸው፥ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥</verse>
				<verse number="21">ከሮ​ቤል ነገድ የተ​ቈ​ጠ​ሩት አርባ ስድ​ስት ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="22">የስ​ም​ዖን ልጆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች የተ​ቈ​ጠሩ፥ እንደ እየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር፥ በየ​ራ​ሳ​ቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥</verse>
				<verse number="23">ከስ​ም​ዖን ነገድ የተ​ቈ​ጠ​ሩት አምሳ ዘጠኝ ሺህ ሦስት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="24">የይ​ሁዳ ልጆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ እንደ እየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር፥ በየ​ራ​ሳ​ቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥</verse>
				<verse number="25">ከይ​ሁዳ ነገድ የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሰባ አራት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="26">የይ​ሳ​ኮር ልጆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ እንደ እየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር፥ በየ​ራ​ሳ​ቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥</verse>
				<verse number="27">ከይ​ሳ​ኮር ነገድ የተ​ቈ​ጠ​ሩት አምሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="28">የዛ​ብ​ሎን ልጆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ እንደ እየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር፥ በየ​ራ​ሳ​ቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥</verse>
				<verse number="29">ከዛ​ብ​ሎን ነገድ የተ​ቈ​ጠ​ሩት አምሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="30">ከዮ​ሴፍ ልጆች፥ የኤ​ፍ​ሬም ልጆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ እንደ እየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር፥ በየ​ራ​ሳ​ቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥</verse>
				<verse number="31">ከኤ​ፍ​ሬም ነገድ የተ​ቈ​ጠ​ሩት አርባ ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="32">የም​ናሴ ልጆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች- እንደ እየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር፥ በየ​ራ​ሳ​ቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥</verse>
				<verse number="33">ከም​ናሴ ነገድ የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሠላሳ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="34">የብ​ን​ያም ልጆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ እንደ እየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር፥ በየ​ራ​ሳ​ቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥</verse>
				<verse number="35">ከብ​ን​ያም ነገድ የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሠላሳ አም​ስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="36">የጋድ ልጆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው- በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ እንደ እየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር፥ በየ​ራ​ሳ​ቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥</verse>
				<verse number="37">ከጋድ ነገድ የተ​ቈ​ጠ​ሩት አርባ አም​ስት ሺህ ስድ​ስት መቶ አምሳ ነበሩ።</verse>
				<verse number="38">የዳን ልጆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ እን​ደ​እየ ስማ​ቸው ቍጥር፥ በየ​ራ​ሳ​ቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥</verse>
				<verse number="39">ከዳን ነገድ የተ​ቈ​ጠ​ሩት ስድሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="40">የአ​ሴር ልጆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ እንደ እየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር፥ በየ​ራ​ሳ​ቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥</verse>
				<verse number="41">ከአ​ሴር ነገድ የተ​ቈ​ጠ​ሩት አርባ አንድ ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="42">የን​ፍ​ታ​ሌም ልጆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ እንደ እየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር፥ በየ​ራ​ሳ​ቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥</verse>
				<verse number="43">ከን​ፍ​ታ​ሌም ነገድ የተ​ቈ​ጠ​ሩት አምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="44">ሙሴና አሮን ዐሥራ ሁለ​ቱም የእ​ስ​ራ​ኤል አለ​ቆች እነ​ር​ሱን የቈ​ጠ​ሩ​በት ቍጥር ይህ ነው።</verse>
				<verse number="45">ከእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ነገድ ከየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አንድ አንድ አለቃ ነበረ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሁሉ፥ በየ​ሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው፥ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉት፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥</verse>
				<verse number="46">የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሁሉ ስድ​ስት መቶ ሦስት ሺህ አም​ስት መቶ አምሳ ነበሩ።</verse>
				<verse number="47">ሌዋ​ው​ያን ግን በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ነገድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር አል​ተ​ቈ​ጠ​ሩም።</verse>
				<verse number="48">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="49">“የሌ​ዊን ነገድ እን​ዳ​ት​ቈ​ጥ​ራ​ቸው፥ ቍጥ​ራ​ቸ​ው​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር እን​ዳ​ት​ቀ​በል ዕወቅ፤</verse>
				<verse number="50">ነገር ግን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳ​ንና በዕ​ቃ​ዎ​ችዋ ሁሉ፥ በው​ስ​ጥ​ዋም ባለው ነገር ሁሉ ላይ ሌዋ​ው​ያ​ንን አቁ​ማ​ቸው። ድን​ኳ​ን​ዋ​ንና ዕቃ​ዎ​ች​ዋን ሁሉ ይሸ​ከሙ፤ ያገ​ል​ግ​ሉ​አ​ትም፤ በድ​ን​ኳ​ን​ዋም ዙሪያ ይስ​ፈሩ።</verse>
				<verse number="51">ድን​ኳ​ን​ዋም ስት​ነሣ ሌዋ​ው​ያን ይን​ቀ​ሉ​አት፤ ድን​ኳ​ን​ዋም ስታ​ርፍ ሌዋ​ው​ያን ይት​ከ​ሉ​አት፤ ሌላ ሰው ግን ለመ​ን​ካት ቢቀ​ርብ ይገ​ደል።</verse>
				<verse number="52">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው በየ​ሰ​ፈሩ፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሰው በየ​አ​ለ​ቃው፥ በየ​ጭ​ፍ​ራ​ውም ይሰ​ፍ​ራሉ።</verse>
				<verse number="53">ነገር ግን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ዕዳ እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው ሌዋ​ው​ያን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ ፊት ለፊት ይስ​ፈሩ፤ ሌዋ​ው​ያን የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሕግ ይጠ​ብቁ።”</verse>
				<verse number="54">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙ​ሴና ለአ​ሮን ያዘ​ዛ​ቸ​ውን ሁሉ አደ​ረጉ፤ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙ​ሴና ለአ​ሮን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ፦</verse>
				<verse number="2">“የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እያ​ን​ዳ​ንዱ በየ​ሥ​ር​ዐቱ፥ በየ​ዓ​ላ​ማው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ አን​ጻር ይስ​ፈሩ።</verse>
				<verse number="3">በመ​ጀ​መ​ሪያ በም​ሥ​ራቅ በኩል የሚ​ሰ​ፍ​ሩት ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር የይ​ሁዳ ሰፈር ሰዎች ይሆ​ናሉ፤ የይ​ሁዳ ልጆ​ችም አለቃ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነአ​ሶን ነበረ።</verse>
				<verse number="4">የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም ሰባ አራት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="5">በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የሚ​ሰ​ፍሩ የይ​ሳ​ኮር ነገድ ይሆ​ናሉ፤ የይ​ሳ​ኮ​ርም ልጆች አለቃ የሰ​ገር ልጅ ናት​ና​ኤል ነበረ።</verse>
				<verse number="6">የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አምሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="7">በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የዛ​ብ​ሎን ነገድ ነበረ፤ የዛ​ብ​ሎ​ንም ልጆች አለቃ የኬ​ሎን ልጅ ኤል​ያብ ነበረ።</verse>
				<verse number="8">የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አምሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="9">ከይ​ሁዳ ሰፈር የተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው መቶ ሰማ​ንያ ስድ​ስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። እነ​ዚ​ህም አስ​ቀ​ድ​መው ይጓ​ዛሉ።</verse>
				<verse number="10">“በአ​ዜብ በኩል በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው የሮ​ቤል ሰፈር ዓላማ ይሆ​ናል፤ የሮ​ቤ​ልም ልጆች አለቃ የሴ​ድ​ዮር ልጅ ኤሊ​ሱር ነበረ።</verse>
				<verse number="11">የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አርባ ስድ​ስት ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="12">በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የሚ​ሰ​ፍሩ የስ​ም​ዖን ነገድ ናቸው፤ የስ​ም​ዖ​ንም ልጆች አለቃ የሲ​ሩ​ሳዴ ልጅ ሰላ​ም​ያል ነበረ።</verse>
				<verse number="13">የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አምሳ ዘጠኝ ሺህ ሦስት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="14">በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የጋድ ነገድ ነበረ፤ የጋ​ድም ልጆች አለቃ የራ​ጉ​ኤል ልጅ ኤል​ሳፍ ነበረ።</verse>
				<verse number="15">የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አርባ አም​ስት ሺህ ስድ​ስት መቶ አምሳ ነበሩ።</verse>
				<verse number="16">ከሮ​ቤል ሰፈር የተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው መቶ አምሳ አንድ ሺህ አራት መቶ አምሳ ነበሩ። እነ​ር​ሱም ቀጥ​ለው ይጓ​ዛሉ።</verse>
				<verse number="17">“ከዚ​ያም በኋላ የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን፥ በሰ​ፈ​ሮ​ቹም መካ​ከል የሌ​ዋ​ው​ያን ወገን ይጓ​ዛል፤ እንደ አሰ​ፋ​ፈ​ራ​ቸው ሰው ሁሉ በየ​ስ​ፍ​ራው፥ በየ​ዓ​ላ​ማ​ውም ይጓ​ዛሉ።</verse>
				<verse number="18">“በባ​ሕር በኩል እንደ ሠራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው የኤ​ፍ​ሬም ሰፈር ዓላማ ይሆ​ናል፤ የኤ​ፍ​ሬም ልጆች አለቃ የኤ​ሜ​ሁድ ልጅ ኤሌ​ሳማ ነበረ።</verse>
				<verse number="19">የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አርባ ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="20">በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የም​ናሴ ነገድ ይሆ​ናል፤ የም​ና​ሴም ልጆች አለቃ የፈ​ዳ​ሱር ልጅ ገማ​ል​ያል ነበረ።</verse>
				<verse number="21">የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም ሠላሳ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="22">በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የብ​ን​ያም ነገድ ይሆ​ናል፤ የብ​ን​ያ​ምም ልጆች አለቃ የጋ​ዴ​ዮን ልጅ አቢ​ዳን ነበረ።</verse>
				<verse number="23">የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም፥ ሠላሳ አም​ስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="24">ከኤ​ፍ​ሬም ሰፈር የተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው መቶ ስም​ንት ሺህ አንድ መቶ ነበሩ። እነ​ር​ሱም ሦስ​ተኛ ሆነው ይጓ​ዛሉ።</verse>
				<verse number="25">“በመ​ስዕ በኩል እንደ ሠራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው የዳን ሰፈር ዓላማ ይሆ​ናል፤ የዳ​ንም ልጆች አለቃ የአ​ሚ​ሳዲ ልጅ አክ​ያ​ዜር ነበረ።</verse>
				<verse number="26">የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም ስድሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="27">በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የሚ​ሰ​ፍሩ የአ​ሴር ነገድ ይሆ​ናሉ፤ የአ​ሴ​ርም ልጆች አለቃ የኤ​ክ​ራን ልጅ ፋጋ​ኤል ነበረ።</verse>
				<verse number="28">የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አርባ አንድ ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="29">በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የን​ፍ​ታ​ሌም ነገድ ይሆ​ናል፤ የን​ፍ​ታ​ሌ​ምም ልጆች አለቃ የዔ​ናን ልጅ አኪሬ ነበረ።</verse>
				<verse number="30">የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="31">ከዳን ሰፈር የተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ መቶ አምሳ ሰባት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበሩ። እነ​ር​ሱም በየ​ዓ​ላ​ማ​ቸው በመ​ጨ​ረሻ ይጓ​ዛሉ።”</verse>
				<verse number="32">ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች የተ​ቈ​ጠሩ እነ​ዚህ ናቸው፤ ከየ​ሰ​ፈሩ በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው የተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ ስድ​ስት መቶ ሦስት ሺህ አም​ስት መቶ አምሳ ነበሩ።</verse>
				<verse number="33">ሌዋ​ው​ያን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር አል​ተ​ቈ​ጠ​ሩም።</verse>
				<verse number="34">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ እን​ዲሁ በየ​ዓ​ላ​ማ​ዎ​ቻ​ቸው ሰፈሩ፤ እን​ዲ​ሁም በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ተጓዙ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሲና ተራራ ላይ ሙሴን በተ​ና​ገ​ረ​በት ቀን የአ​ሮ​ንና የሙሴ ትው​ልድ ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="2">የአ​ሮን ልጆች ስም ይህ ነው፤ በኵሩ ናዳብ፥ አብ​ዩድ፥ አል​ዓ​ዛር፥ ኢታ​ምር።</verse>
				<verse number="3">በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ የተ​ቀ​ቡና እጆ​ቻ​ቸ​ውን የተ​ቀ​ደሱ የአ​ሮን ልጆች ስም ይህ ነው።</verse>
				<verse number="4">ናዳ​ብና አብ​ዩድ በሲና ምድረ በዳ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከሌላ እሳት ጭረው አም​ጥ​ተ​ዋ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሞቱ፤ ልጆ​ችም አል​ነ​በ​ሩ​አ​ቸ​ውም። አል​ዓ​ዛ​ርና ኢታ​ምር ከአ​ባ​ታ​ቸው ከአ​ሮን ጋር በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግሉ ነበር።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="6">“የሌ​ዊን ነገድ አቅ​ር​በህ ያገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ በካ​ህኑ በአ​ሮን ፊት አቁ​ማ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">የድ​ን​ኳ​ኑን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ሕጉ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሕግ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት ይጠ​ብቁ።</verse>
				<verse number="8">እንደ ድን​ኳኑ ሥራ​ዎች ሁሉ የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ዕቃና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሕግ ይጠ​ብቁ።</verse>
				<verse number="9">ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ አሮ​ንና ወደ ልጆቹ ወደ ካህ​ናቱ ታገ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ። ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተለ​ይ​ተው ለእኔ ሀብት ሆነው ተሰ​ጥ​ተ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="10">አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት አቁ​ማ​ቸው፤ ክህ​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም፥ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውና በመ​ጋ​ረ​ጃው ውስጥ ያለ​ው​ንም ሁሉ ይጠ​ብቁ፤ ከሌላ ወገን የዳ​ሰሰ ቢኖር ይገ​ደል።”</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="12">“እነሆ፥ እኔ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ መጀ​መ​ሪያ በሚ​ወ​ለ​ደው በበ​ኵር ሁሉ ፋንታ ሌዋ​ው​ያ​ንን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለይች ወስ​ጃ​ለሁ፤ በእ​ነ​ርሱ ፋንታ ሌዋ​ው​ያን ለእኔ ይሁኑ፤</verse>
				<verse number="13">በኵር ሁሉ ለእኔ ነውና፤ በግ​ብፅ ምድር በኵ​ርን ሁሉ በመ​ታሁ ቀን ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ በኵ​ርን ሁሉ፥ ሰው​ንና እን​ስ​ሳን፥ ለእኔ ለይ​ች​አ​ለሁ፤ ለእኔ ይሁኑ። እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።”</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን በሲና ምድረ በዳ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="15">“የሌ​ዊን ልጆች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸ​ውም ቍጠር፤ ወን​ዱን ሁሉ ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን ቍጠ​ራ​ቸው።”</verse>
				<verse number="16">ሙሴና አሮ​ንም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አዘ​ዛ​ቸው ቈጠ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">የሌዊ ልጆች በየ​ስ​ማ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።</verse>
				<verse number="18">የጌ​ድ​ሶ​ንም ልጆች ስሞች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው እነ​ዚህ ናቸው፤ ሎቤን፥ ሰሜይ።</verse>
				<verse number="19">የቀ​ዓ​ትም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው እን​በ​ረም፥ ይሳ​ዓር፥ ኬብ​ሮን፥ አዛ​ሄል።</verse>
				<verse number="20">የሜ​ራ​ሪም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ሞሐሊ፥ ሙሲ። የሌ​ዋ​ው​ያን ወገ​ኖች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="21">ለጌ​ድ​ሶን የሎ​ቤን ወገን፥ የሰ​ሜ​ይም ወገን ነበ​ሩት፤ የጌ​ድ​ሶን ወገ​ኖች እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="22">ከእ​ነ​ርሱ የተ​ቈ​ጠ​ሩት የወ​ን​ዶች ሁሉ ቍጥር ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሰባት ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="23">የጌ​ድ​ሶን ልጆች ከድ​ን​ኳን በኋላ በባ​ሕር በኩል ይሰ​ፍ​ራሉ።</verse>
				<verse number="24">የጌ​ድ​ሶን አባ​ቶች ቤት አለቃ የዳ​ሔል ልጅ ኤሊ​ሳፍ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="25">የጌ​ድ​ሶን ልጆች በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን የሚ​ጠ​ብ​ቁት ማደ​ሪ​ያ​ውና ድን​ኳኑ፥ መደ​ረ​ቢ​ያ​ውም፥ የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ መጋ​ረጃ፥</verse>
				<verse number="26">የአ​ደ​ባ​ባዩ መጋ​ረጃ፥ በድ​ን​ኳኑ አደ​ባ​ባይ በር ያለው መጋ​ረ​ጃና የቀ​ረ​ውም ሥራዋ ሁሉ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="27">ለቀ​ዓ​ትም የእ​ን​በ​ረም ወገን፥ የይ​ስ​ዓር ወገን፥ የኬ​ብ​ሮ​ንም ወገን፥ የአ​ዛ​ሔ​ልም ወገን ነበሩ፤ የቀ​ዓት ወገ​ኖች እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="28">ወን​ዶች ሁሉ እንደ ቍጥ​ራ​ቸው ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ስም​ንት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበሩ፤ መቅ​ደ​ሱ​ንም ይጠ​ብቁ ነበር።</verse>
				<verse number="29">የቀ​ዓት ልጆች ወገ​ኖች በድ​ን​ኳኑ አጠ​ገብ በአ​ዜብ በኩል ይሰ​ፍ​ራሉ።</verse>
				<verse number="30">የቀ​ዓት ወገ​ኖች አባ​ቶች ቤት አለቃ የአ​ዛ​ሔል ልጅ ኤሊ​ሳፋ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="31">ታቦ​ቱ​ንም፥ ገበ​ታ​ው​ንም፥ መቅ​ረ​ዙ​ንም፥ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ት​ንም የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ፥ መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም፥ ማገ​ል​ገ​ያ​ው​ንም ሁሉ ይጠ​ብ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="32">የሌ​ዋ​ው​ያ​ንም አለ​ቆች አለቃ የተ​ቀ​ደሱ ነገ​ሮ​ችን ይጠ​ብቅ ዘንድ የተ​ሾ​መው የካ​ህኑ የአ​ሮን ልጅ አል​ዓ​ዛር ነው።</verse>
				<verse number="33">ለሜ​ራሪ የሞ​ሖሊ ወገን የሙሲ ወገን ነበሩ፤ የሜ​ራሪ ወገ​ኖች እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="34">ከእ​ነ​ር​ሱም ወን​ዶች ሁሉ እንደ ቍጥ​ራ​ቸው ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ የተ​ቈ​ጠ​ሩት ስድ​ስት ሽህ አምሳ ነበሩ።</verse>
				<verse number="35">የሜ​ራ​ሪም ወገ​ኖች አባ​ቶች ቤት አለቃ የአ​ቢ​ኪያ ልጅ ሱራ​ሔል ነበረ፤ በድ​ን​ኳኑ አጠ​ገብ በሰ​ሜን በኩል ይሰ​ፍ​ራሉ።</verse>
				<verse number="36">የሜ​ራ​ሪም ልጆች የሚ​ጠ​ብ​ቁት የድ​ን​ኳኑ ምሰ​ሶ​ዎች፥ ኩላ​ቦች፥ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችም፥ ተራ​ዳ​ዎ​ችም፥ እግ​ሮ​ቹም፥</verse>
				<verse number="37">ዕቃ​ውም ሁሉ፥ ማገ​ል​ገ​ያ​ውም ሁሉ፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም የሚ​ቆሙ የአ​ደ​ባ​ባይ ምሰ​ሶ​ዎች፥ እግ​ሮ​ቹም፥ ካስ​ማ​ዎ​ቹም፥ አው​ታ​ሮ​ቹም ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="38">በም​ሥ​ራቅ በኩል በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት የሚ​ሰ​ፍ​ሩት ሙሴና አሮን ልጆ​ቹም ይሆ​ናሉ፥ እንደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ሕግም የመ​ቅ​ደ​ሱን ሕግ ይጠ​ብ​ቃሉ፥ ከሌላ ወገን የዳ​ሰሰ ቢኖር ይገ​ደል።</verse>
				<verse number="39">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ሙሴና አሮን የቈ​ጠ​ሩ​አ​ቸው፥ ከሌ​ዋ​ው​ያን ወን​ዶች ሁሉ ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሁሉ ሃያ ሁለት ሺህ ነበሩ።</verse>
				<verse number="40">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ወን​ዱን በኵር ሁሉ ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉ​ትን ቍጠር፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ው​ንም በየ​ስ​ማ​ቸው ውሰድ፤</verse>
				<verse number="41">ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በኵር ሁሉ ፋንታ፥ የሌ​ዋ​ው​ያ​ን​ንም እን​ስ​ሶች በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ስ​ሶች በኵር ሁሉ ፋንታ ለእኔ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አድ​ር​ጋ​ቸው” አለው።</verse>
				<verse number="42">ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በኵር ሁሉ ቈጠረ።</verse>
				<verse number="43">ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠሩ ወን​ዶች በኵ​ሮች ሁሉ በየ​ስ​ማ​ቸው ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ሃያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ነበሩ።</verse>
				<verse number="44">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="45">“ሌዋ​ው​ያ​ንን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በኵር ሁሉ ፋንታ፥ የሌ​ዋ​ው​ያ​ን​ንም እን​ስ​ሶች በእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ቸው ፋንታ ውሰድ፤ ሌዋ​ው​ያ​ንም ለእኔ ይሁኑ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።</verse>
				<verse number="46">በሌ​ዋ​ው​ያን ላይ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በኵር ስለ ተረ​ፉት ስለ ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ቤዛ፥</verse>
				<verse number="47">በየ​ራሱ አም​ስት ዲድ​ር​ክም ውሰድ፤ እንደ መቅ​ደሱ ዲድ​ር​ክም ብዛት ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ ዲድ​ር​ክም ሃያ አቦሊ ነው።</verse>
				<verse number="48">ስለ ተረ​ፉ​ትም የመ​ቤ​ዣ​ውን ገን​ዘብ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።”</verse>
				<verse number="49">ሙሴም በሌ​ዋ​ው​ያን ከተ​ቤ​ዡት በላይ ከተ​ረ​ፉት ዘንድ የመ​ቤ​ዣ​ውን ገን​ዘብ ወሰደ።</verse>
				<verse number="50">ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በኵ​ሮች ገን​ዘ​ቡን ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ አም​ስት ዲድ​ር​ክም እንደ መቅ​ደሱ ዲድ​ር​ክም ሚዛን ወሰደ።</verse>
				<verse number="51">እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሙሴ የመ​ቤ​ዣ​ውን ገን​ዘብ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ሰጠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦</verse>
				<verse number="2">“ከሌዊ ልጆች መካ​ከል በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች የቀ​ዓ​ትን ልጆች ለዩ​አ​ቸው፤</verse>
				<verse number="3">ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ገ​ቡ​በ​ትን ሁሉ ትለ​ያ​ለህ።</verse>
				<verse number="4">በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ዘንድ የቀ​ዓት ልጆች ሥራ ይህ ነው፤</verse>
				<verse number="5">ሰፈሩ በተ​ነሣ ጊዜ አሮ​ንና ልጆቹ ገብ​ተው የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን መጋ​ረጃ ያወ​ር​ዳሉ፤ የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ታቦት ይጠ​ቀ​ል​ሉ​በ​ታል፤</verse>
				<verse number="6">በላ​ዩም የአ​ቆ​ስ​ጣ​ውን ቍር​በት መሸ​ፈኛ ያድ​ር​ጉ​በት፤ ከእ​ር​ሱም በላይ ሁለ​ን​ተ​ናው ሰማ​ያዊ የሆነ መጐ​ና​ጸ​ፊያ ያግ​ቡ​በት፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ያግ​ቡ​በት።</verse>
				<verse number="7">በኅ​ብ​ስተ ገጹ ገበታ ላይም ሰማ​ያ​ዊ​ውን መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይዘ​ር​ጉ​በት፤ በእ​ር​ሱም ላይ ወጭ​ቶ​ቹን፥ ጭል​ፋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ጽዋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ለማ​ፍ​ሰ​ስም መቅ​ጃ​ዎ​ቹን ያድ​ር​ጉ​በት፤ ሁል​ጊ​ዜም የሚ​ኖር ኅብ​ስት በእ​ርሱ ላይ ይሁን።</verse>
				<verse number="8">በእ​ነ​ር​ሱም ላይ ቀይ መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይዘ​ርጉ፤ በአ​ቆ​ስ​ጣ​ውም ቍር​በት መሸ​ፈኛ ይሸ​ፍ​ኑት። መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ያግቡ።</verse>
				<verse number="9">ሰማ​ያ​ዊ​ው​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይው​ሰዱ፤ የሚ​ያ​በ​ሩ​ባ​ት​ንም መቅ​ረዝ፥ ቀን​ዲ​ሎ​ች​ዋ​ንም፥ መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ የኵ​ስ​ታሪ ማድ​ረ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ እር​ስ​ዋ​ንም ለማ​ገ​ል​ገል የዘ​ይ​ቱን ማሰ​ሮ​ዎች ሁሉ ይሸ​ፍኑ፤</verse>
				<verse number="10">እር​ስ​ዋ​ንና ዕቃ​ዎ​ች​ዋን ሁሉ በአ​ቆ​ስጣ ቍር​በት መሸ​ፈኛ ውስጥ ያድ​ርጉ፤ በመ​ሸ​ከ​ሚ​ያ​ውም ላይ ያድ​ር​ጉት።</verse>
				<verse number="11">በወ​ር​ቁም መሠ​ዊያ ላይ ሰማ​ያ​ዊ​ውን መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይዘ​ር​ጉ​በት፤ በአ​ቆ​ስ​ጣም ቍር​በት መሸ​ፈኛ ይሸ​ፍ​ኑት፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ያግቡ።</verse>
				<verse number="12">በመ​ቅ​ደ​ስም ውስጥ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ትን የማ​ገ​ል​ገ​ያ​ውን ዕቃ ሁሉ ይው​ሰዱ፤ በሰ​ማ​ያ​ዊ​ዉም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ውስጥ ያስ​ቀ​ም​ጡት፤ በአ​ቆ​ስ​ጣም ቍር​በት መሸ​ፈኛ ይሸ​ፍ​ኑት፤ በመ​ሸ​ከ​ሚ​ያ​ውም ላይ ያድ​ር​ጉት።</verse>
				<verse number="13">አመ​ዱ​ንም ያስ​ወ​ግዱ፤ መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያድ​ርጉ፤ ሐም​ራ​ዊ​ዉ​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይዘ​ር​ጉ​በት፤</verse>
				<verse number="14">የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ትን ዕቃ​ውን ሁሉ፥ ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹን፥ ሜን​ጦ​ዎ​ቹ​ንም፥ ጽዋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንም፥ መክ​ደ​ኛ​ዎ​ቹ​ንም፥ ያመድ ማፍ​ሰ​ሻ​ዎ​ቹን፥ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ዕቃ ሁሉ ያስ​ቀ​ም​ጡ​በት፤ በእ​ር​ሱም የአ​ቆ​ስ​ጣን ቍር​በት መሸ​ፈኛ ይዘ​ርጉ፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ያግቡ። ሐም​ራ​ዊ​ዉ​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ወስ​ደው ማስ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ው​ንና ማስ​ቀ​መ​ጫ​ውን ይሸ​ፍ​ኑት፤ በአ​ቆ​ስ​ጣው ቍር​በት መሸ​ፈኛ ውስ​ጥም አድ​ር​ገው በመ​ሸ​ከ​ሚ​ያ​ዎቹ ላይ ያኑ​ሩት፤</verse>
				<verse number="15">አሮ​ንና ልጆቹ መቅ​ደ​ሱ​ንና የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ ሁሉ ሸፍ​ነው ከጨ​ረሱ በኋላ ሰፈሩ ሲነሣ የቀ​ዓት ልጆች ሊሸ​ከ​ሙት ይገ​ባሉ። እን​ዳ​ይ​ሞቱ ግን ንዋየ ቅድ​ሳ​ቱን አይ​ንኩ። በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ የቀ​ዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው።</verse>
				<verse number="16">የካ​ህ​ኑም የአ​ሮን ልጅ አል​ዓ​ዛር በመ​ብ​ራቱ ዘይት በጣ​ፋ​ጩም ዕጣን ላይ ፥ ሁል​ጊ​ዜም በሚ​ቀ​ር​በው በእ​ህሉ ቍር​ባ​ንና በቅ​ባቱ ዘይት ላይ ሹም ነው፤ ድን​ኳ​ኑን ሁሉ፥ በእ​ር​ሱም ውስጥ ያለ​ውን ሁሉ፥ መቅ​ደ​ሱ​ንና ዕቃ​ውን ይጠ​ብ​ቃል።”</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦</verse>
				<verse number="18">“የቀ​ዓ​ትን ወገ​ኖች ነገድ ከሌ​ዋ​ው​ያን መካ​ከል አታ​ጥ​ፉ​አ​ቸው፤</verse>
				<verse number="19">ነገር ግን ወደ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ በቀ​ረቡ ጊዜ በሕ​ይ​ወት ይኖሩ ዘንድ እንጂ እን​ዳ​ይ​ሞቱ እን​ዲሁ አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ አሮ​ንና ልጆቹ ይግቡ፤</verse>
				<verse number="20">ከእ​ነ​ርሱ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ሥራ​ው​ንና ሸክ​ሙን ያዘ​ጋጁ፤ ነገር ግን እን​ዳ​ይ​ሞቱ ንዋየ ቅዱ​ሳ​ቱን ለድ​ን​ገት እን​ኳን ለማ​የት አይ​ግቡ።”</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="22">“የጌ​ድ​ሶ​ንን ልጆች ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ጀም​ረህ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ቍጠ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ገ​ቡ​ትን ሁሉ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ቍጠ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">የጌ​ድ​ሶን ወገ​ኖች ሥራ በማ​ገ​ል​ገ​ልና በመ​ሸ​ከም ይህ ነው፤</verse>
				<verse number="25">የድ​ን​ኳ​ኑን መጋ​ረ​ጃ​ዎች፥ የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን፥ መደ​ረ​ቢ​ያ​ውን፥ በላ​ዩም ያለ​ውን የአ​ቆ​ስ​ጣ​ውን ቍር​በት መደ​ረ​ቢያ፥ የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን ደጃፍ መጋ​ረጃ፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም መጋ​ረጃ፥</verse>
				<verse number="26">በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ ያለ​ውን የአ​ደ​ባ​ባ​ዩን ደጃፍ መጋ​ረጃ፥ ለማ​ገ​ል​ገ​ልም የሚ​ሠ​ሩ​በ​ትን ዕቃ ሁሉ ይሸ​ከሙ፤ በዚ​ህም ያገ​ል​ግሉ።</verse>
				<verse number="27">የጌ​ድ​ሶን ልጆች አገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ፥ በተ​ራ​ቸ​ውም ሁሉ፥ በሥ​ራ​ቸ​ውም ሁሉ በአ​ሮ​ንና በል​ጆቹ ትእ​ዛዝ ይሁን፤ በስ​ማ​ቸ​ውና በተ​ራ​ቸ​ውም ትቈ​ጥ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="28">የጌ​ድ​ሶን ልጆች አገ​ል​ግ​ሎት በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ ይህ ነው፤ ከካ​ህኑ ከአ​ሮን ልጅ ከኢ​ታ​ምር እጅ በታች ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="29">“የሜ​ራ​ሪ​ንም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች ቍጠ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="30">የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ገ​ቡ​ትን ሁሉ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ቍጠ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="31">በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ ባለው አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ሁሉ፥ የድ​ን​ኳኑ ሳን​ቆች፥ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹም፥ ተራ​ዳ​ዎ​ቹም፥ እግ​ሮ​ቹም፥ መሸ​ፈ​ኛ​ዎ​ቹም፥ መቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹም፥ የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ መጋ​ረጃ፥</verse>
				<verse number="32">በዙ​ሪ​ያ​ውም የሚ​ቆ​ሙት የአ​ደ​ባ​ባዩ ምሰ​ሶ​ዎች፥ እግ​ሮ​ቹም፥ የአ​ደ​ባ​ባዩ ደጃፍ መጋ​ረጃ ምሰ​ሶ​ዎች፥ እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም፥ ካስ​ማ​ዎ​ቹም፥ አው​ታ​ሮ​ቹም፥ ዕቃ​ዎ​ቹና ማገ​ል​ገ​ያ​ዎቹ ሸክ​ማ​ቸው ነው፤ የሚ​ጠ​ብ​ቁ​ት​ንም የሸ​ክ​ማ​ቸ​ውን ዕቃ ሁሉ በየ​ስ​ማ​ቸው ቍጠሩ።</verse>
				<verse number="33">በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ ባለው ሥራ​ቸው ሁሉ የሜ​ራሪ ልጆች ወገ​ኖች አገ​ል​ግ​ሎት ይህ ነው፤ እነ​ር​ሱም ከካ​ህኑ ከአ​ሮን ልጅ ከኢ​ታ​ምር እጅ በታች ይሆ​ናሉ።”</verse>
				<verse number="34">ሙሴና አሮ​ንም፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አለ​ቆች የቀ​ዓ​ትን ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች ቈጠ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="35">በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ወደ አገ​ል​ግ​ሎት የገ​ቡ​ትን ሁሉ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉ​ትን ቈጠ​ሩ​አ​ቸው፤</verse>
				<verse number="36">በየ​ወ​ገ​ና​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሁለት ሺህ ሰባት መቶ አምሳ ነበሩ።</verse>
				<verse number="37">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ እን​ዳ​ዘዘ፥ ሙሴና አሮን እንደ ቈጠ​ሩ​አ​ቸው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ የሚ​ገ​ቡት ሁሉ፥ የቀ​ዓት ልጆች ቍጥር ይህ ነው።</verse>
				<verse number="38">የጌ​ድ​ሶ​ን​ንም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች፥</verse>
				<verse number="39">በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የገ​ቡት ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉ​ትን ቈጠ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="40">ቍጥ​ራ​ቸ​ውም በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች ሁለት ሺህ ስድ​ስት መቶ አምሳ ነበር።</verse>
				<verse number="41">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ እን​ዳ​ዘዘ፥ ሙሴና አሮን የቈ​ጠ​ሩ​አ​ቸው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ያገ​ለ​ገ​ሉት ሁሉ የጌ​ድ​ሶን ልጆች ቍጥር ይህ ነው።</verse>
				<verse number="42">የሜ​ራ​ሪ​ንም ልጆች ወገ​ኖች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች፥</verse>
				<verse number="43">በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ወደ አገ​ል​ግ​ሎት የገ​ቡት ሁሉ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉ​ትን ቈጠ​ሯ​ቸው።</verse>
				<verse number="44">ቍጥ​ራ​ቸ​ውም በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች ሦስት ሺህ ሁለት መቶ ነበረ።</verse>
				<verse number="45">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሙሴ እጅ እን​ዳ​ዘዘ ሙሴና አሮን የቈ​ጠ​ሩ​አ​ቸው የሜ​ራሪ ልጆች ወገ​ኖች ቍጥር ይህ ነው።</verse>
				<verse number="46">በየ​ወ​ገ​ና​ቸ​ውና በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ከሌ​ዋ​ው​ያን የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሁሉ፥ ሙሴና አሮን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አለ​ቆች የቈ​ጠ​ሩ​አ​ቸው፥</verse>
				<verse number="47">በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ሥራ​ውን ለመ​ሥ​ራ​ትና ዕቃ​ውን ለመ​ሸ​ከም የገ​ቡት ሁሉ፥ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉት፥</verse>
				<verse number="48">ከእ​ነ​ርሱ የተ​ቈ​ጠ​ሩት ስም​ንት ሺህ አም​ስት መቶ ሰማ​ንያ ነበሩ።</verse>
				<verse number="49">እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውና በየ​ሸ​ክ​ማ​ቸው በሙሴ እጅ ተቈ​ጠሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ እን​ዲሁ በእ​ርሱ ተቈ​ጠሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለም​ጻ​ሙን ሁሉ ፈሳሽ ነገ​ርም ያለ​በ​ትን ሁሉ በሰ​ው​ነቱ የረ​ከ​ሰ​ውን ሁሉ ከሰ​ፈሩ እን​ዲ​ያ​ወጡ እዘ​ዛ​ቸው፤</verse>
				<verse number="3">እኔ በመ​ካ​ከሉ የማ​ድ​ር​በ​ትን ሰፈ​ራ​ቸ​ውን እን​ዳ​ያ​ረ​ክሱ ከወ​ንድ እስከ ሴት ከሰ​ፈሩ አው​ጡ​አ​ቸው።”</verse>
				<verse number="4">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ ከሰ​ፈሩ አወ​ጡ​አ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እንደ ተና​ገ​ረው፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲሁ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="6">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ወንድ ወይም ሴት ቸል ብለው ወይም ባለ​ማ​ወቅ ሰው ከሚ​ሠ​ራው ኀጢ​አት ሁሉ የሠ​ሩት ቢኖር፥</verse>
				<verse number="7">ያች ሰው​ነት ብት​ና​ዘዝ፥ ያደ​ረ​ገ​ች​ው​ንም ኀጢ​አት ሁሉ ብት​ና​ገር የወ​ሰ​ደ​ውን ዓይ​ነ​ቱን ሁሉ ይመ​ልስ። አም​ስ​ተኛ እጅም ለባለ ገን​ዘቡ ይጨ​ምር።</verse>
				<verse number="8">ነገር ግን ይመ​ል​ስ​ለት ዘንድ ሰው​ዬው ዘመድ ባይ​ኖ​ረው፥ ስለ በደል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​መ​ል​ሰው ነገር ለካ​ህኑ ይሁን፤ ይህም ስለ እርሱ ማስ​ተ​ስ​ረያ ከሚ​ደ​ረ​ግ​በት አውራ በግ ላይ ይጨ​መር።</verse>
				<verse number="9">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡ​አ​ቸው የተ​ቀ​ደሱ ነገ​ሮች ሁሉ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ለካ​ህኑ ነው።</verse>
				<verse number="10">የተ​ቀ​ደሰ የሰው ነገር ሁሉ፥ ሰውም ለካ​ህኑ የሚ​ሰ​ጠው ሁሉ ለእ​ርሱ ይሁን።”</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="12">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ የማ​ን​ኛ​ውም ሰው ሚስት ከእ​ርሱ ፈቀቅ ብትል፥ በእ​ር​ሱም ላይ ብት​በ​ድል፥</verse>
				<verse number="13">ሌላም ሰው ከእ​ር​ስዋ ጋር ቢተኛ፥ ብታ​መ​ነ​ዝር፥ ከባ​ል​ዋም ዐይን ቢሸ​ሸግ፥ እር​ስ​ዋም ተሰ​ውራ ብት​ረ​ክስ፥</verse>
				<verse number="14">ምስ​ክ​ርም ባይ​ኖ​ር​ባት፥ በም​ን​ዝ​ርም ባት​ያዝ፥ በባ​ል​ዋም ላይ የቅ​ን​ዐት መን​ፈስ ቢመ​ጣ​በት፥ እር​ስ​ዋም ስት​ረ​ክስ ስለ ሚስቱ ቢቀና ወይም እር​ስዋ ሳት​ረ​ክስ የቅ​ን​ዐቱ መን​ፈስ ቢመ​ጣ​በት፥ ስለ ሚስ​ቱም ቢቀና፥</verse>
				<verse number="15">ያ ሰው ሚስ​ቱን ወደ ካህኑ ያም​ጣት፤ የኢፍ መስ​ፈ​ሪ​ያም ዐሥ​ረኛ እጅ ገብስ ዱቄት ቍር​ባን ስለ እር​ስዋ ያምጣ፤ የቅ​ን​ዐት ቍር​ባን ነውና፥ ኀጢ​አ​ት​ንም የሚ​ያ​ሳ​ስብ የመ​ታ​ሰ​ቢያ ቍር​ባን ነውና ዘይት አያ​ፍ​ስ​ስ​በት፤ ዕጣ​ንም አይ​ጨ​ም​ር​በት።</verse>
				<verse number="16">“ካህ​ኑም ያቀ​ር​ባ​ታል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ያቆ​ማ​ታል፤</verse>
				<verse number="17">ካህ​ኑም የተ​ቀ​ደሰ ውኃ በሸ​ክላ ማሰሮ ይወ​ስ​ዳል፤ ካህ​ኑም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ካለው ትቢያ ወስዶ በውኃ ላይ ይረ​ጨ​ዋል፤</verse>
				<verse number="18">ካህ​ኑም ሴቲ​ቱን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቆ​ማ​ታል፤ የሴ​ቲ​ቱ​ንም ራስ ይገ​ል​ጣል፤ በእ​ጅ​ዋም ለመ​ታ​ሰ​ቢያ የሚ​ሆ​ነ​ውን የእ​ህል ቍር​ባን፥ የቅ​ን​ዐት ቍር​ባን ያኖ​ራል፤ በካ​ህ​ኑም እጅ ርግ​ማ​ንን የሚ​ያ​መ​ጣው መራራ ውኃ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="19">ካህ​ኑም ያም​ላ​ታል፤ ሴቲ​ቱ​ንም እን​ዲህ ይላ​ታል፦ ሌላ ወንድ አል​ተ​ኛሽ፥ ባል​ሽ​ንም አል​ተ​ውሽ፥ ራስ​ሽ​ንም አላ​ረ​ከ​ስሽ እንደ ሆነ፥ ርግ​ማ​ንን ከሚ​ያ​መጣ ከዚህ መራራ ውኃ ንጹሕ ሁኚ፤</verse>
				<verse number="20">ነገር ግን ባል​ሽን ትተሽ ረክ​ሰሽ እንደ ሆነ፥ ከባ​ል​ሽም ሌላ ወንድ ከአ​ንቺ ጋር ተኝቶ እንደ ሆነ፤</verse>
				<verse number="21">ካህ​ኑም ሴቲ​ቱን በመ​ር​ገም መሐላ ያም​ላ​ታል፤ ካህ​ኑም ሴቲ​ቱን እን​ዲህ ይበ​ላት፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ረ​ገ​ምሽ ያድ​ር​ግሽ ጎን​ሽን ያረ​ግ​ፈው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሕ​ዝ​ብሽ መካ​ከል ለይቶ ያጥ​ፋሽ፤ ሆድ​ሽን ይሰ​ን​ጥ​ቀው፤</verse>
				<verse number="22">ርግ​ማ​ን​ንም የሚ​ያ​መጣ ይህ ውኃ ወደ ሆድሽ ይግባ፥ ማኅ​ፀ​ን​ሽ​ንም ይሰ​ን​ጥ​ቀው፤ ጎን​ሽም ይር​ገፍ። ሴቲ​ቱም፦ ይሁን ይሁን ትላ​ለች።</verse>
				<verse number="23">“ካህ​ኑም እነ​ዚ​ህን መር​ገ​ሞች በሰ​ሌዳ ላይ ይጽ​ፋ​ቸ​ዋል፤ በመ​ር​ገ​ሙም መራራ ውኃ ይደ​መ​ስ​ሳ​ቸ​ዋል፤</verse>
				<verse number="24">የመ​ር​ገ​ሙን መራራ ውኃ ለሴ​ቲቱ ያጠ​ጣ​ታል፤ የር​ግ​ማ​ኑም ውኃ ወደ ሆድዋ ይገ​ባል።</verse>
				<verse number="25">ካህ​ኑም የቅ​ን​ዐ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ከሴ​ቲቱ እጅ ይወ​ስ​ዳል፤ ያንም መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል፥ ወደ መሠ​ዊ​ያ​ውም ያመ​ጣ​ዋል፤</verse>
				<verse number="26">ካህ​ኑም ከእ​ህሉ ቍር​ባን አንድ እፍኝ ሙሉ ለመ​ታ​ሰ​ቢ​ያው ወስዶ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል። ከዚ​ያም በኋላ ለሴ​ቲቱ ያን ውኃ ያጠ​ጣ​ታል።</verse>
				<verse number="27">ውኃ​ውን ካጠ​ጣት በኋላ እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ራስ​ዋን አር​ክ​ሳና ባል​ዋን ቸል ብላው ከሆነ፤ የመ​ር​ገሙ መራራ ውኃ ወደ ሆድዋ ይገ​ባል፤ ሆድ​ዋ​ንም ይሰ​ነ​ጥ​ቀ​ዋል፤ ጎኗም ይረ​ግ​ፋል፤ ሴቲ​ቱም በሕ​ዝ​ብዋ መካ​ከል ለመ​ር​ገም ትሆ​ና​ለች።</verse>
				<verse number="28">ራስ​ዋን ያላ​ረ​ከ​ሰች እንደ ሆነች፥ ያለ ነው​ርም እንደ ሆነች፥ ያነ​ጻ​ታል፤ ልጆ​ች​ንም ትወ​ል​ዳ​ለች።</verse>
				<verse number="29">“በባ​ልዋ ላይ ለበ​ደ​ለ​ችና ራስ​ዋን ላረ​ከ​ሰች ሴት የቅ​ን​ዐት ሕግ ይህ ነው፤</verse>
				<verse number="30">በሰው ላይ የቅ​ን​ዐት መን​ፈስ ቢመጣ፥ ስለ ሚስ​ቱም ቢቀና፤ ሴቲ​ቱን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቆ​ማ​ታል፤</verse>
				<verse number="31">ካህ​ኑም ይህን ሕግ ሁሉ ያደ​ር​ግ​ባ​ታል። ሰው​የ​ውም ከኀ​ጢ​አት ንጹሕ ይሆ​ናል፤ ሴቲ​ቱም ኀጢ​አ​ቷን ትሸ​ከ​ማ​ለች።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፤ ወንድ ወይም ሴት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሱን የተ​ለየ ያደ​ርግ ዘንድ ልዩ ስእ​ለት ቢሳል፥</verse>
				<verse number="3">ከወ​ይን ጠጅና ከሚ​ያ​ሰ​ክር መጠጥ ራሱን የተ​ለየ ያድ​ርግ፤ ከወ​ይን ወይም ከሌላ ከሚ​ያ​ሰ​ክር ነገር የሚ​ገ​ኘ​ውን ሆም​ጣጤ አይ​ጠጣ፤ የወ​ይ​ንም ጭማቂ አይ​ጠጣ፤ የወ​ይ​ንም እሸት ወይም ዘቢብ አይ​ብላ።</verse>
				<verse number="4">ራሱን የተ​ለየ ባደ​ረ​ገ​በት ወራት ሁሉ ከወ​ይን የሆ​ነ​ውን ነገር ሁሉ ከው​ስጡ ፍሬ ጀምሮ እስከ ደረ​ቀው ዘቢብ ድረስ አይ​ብላ።</verse>
				<verse number="5">“ራሱን ለመ​ለ​የት ስእ​ለት ባደ​ረ​ገ​በት ወራት ሁሉ ራሱን አይ​ላጭ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለ​የ​በት ወራት እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ ቅዱስ ይሆ​ናል፤ የራ​ሱ​ንም ጠጕር ያሳ​ድ​ጋል።</verse>
				<verse number="6">“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሱን የተ​ለየ ባደ​ረ​ገ​በት ወራት ሁሉ ወደ ሬሳ አይ​ቅ​ረብ።</verse>
				<verse number="7">ለአ​ም​ላኩ ያደ​ረ​ገው ብፅ​ዐት በራሱ ላይ ነውና አባቱ፥ ወይም እናቱ፥ ወይም ወን​ድሙ፥ ወይም እኅቱ ሲሞቱ ሰው​ነ​ቱን አያ​ር​ክ​ስ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">በብ​ፅ​ዐቱ ወራት ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ነውና።</verse>
				<verse number="9">“ሰውም በአ​ጠ​ገቡ ድን​ገት ቢሞት የራሱ ብፅ​ዐት ይረ​ክ​ሳል፤ እርሱ በሚ​ነ​ጻ​በት ቀን ራሱን ይላጭ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ይላ​ጨው።</verse>
				<verse number="10">በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ያምጣ፤</verse>
				<verse number="11">ካህ​ኑም አን​ዲ​ቱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱ​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ በሬ​ሳም የተ​ነሣ ኀጢ​አት ሠር​ቶ​አ​ልና ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ በዚ​ያም ቀን ራሱን ይቀ​ድ​ሰ​ዋል።</verse>
				<verse number="12">በስ​እ​ለቱ ወራ​ትም ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቀ​ደ​ሳል፤ የአ​ንድ ዓመ​ትም ተባት ጠቦት ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ያምጣ፤ ስእ​ለቱ ግን ረክ​ሶ​አ​ልና ያለ​ፈው ወራት ሁሉ አይ​ቈ​ጠ​ር​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="13">“የተ​ሳ​ለው ሰው ሕግ ይህ ነው፤ የስ​እ​ለቱ ወራት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ ራሱ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ይቅ​ረብ፤ ቍር​ባ​ኑ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቅ​ርብ።</verse>
				<verse number="14">ነውር የሌ​ለ​በት የአ​ንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ነው​ርም የሌ​ለ​ባ​ትን የአ​ንድ ዓመት እን​ስት ጠቦት ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን አውራ በግ ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት፥</verse>
				<verse number="15">አንድ ሌማ​ትም በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ የስ​ንዴ ቂጣ እን​ጀራ፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ቀባ ስስ ቂጣ፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን፥ የመ​ጠ​ጡ​ንም ቍር​ባን ያቅ​ርብ።</verse>
				<verse number="16">ካህ​ኑም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቅ​ር​በው። የኀ​ጢ​አ​ቱ​ንም መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ያሳ​ር​ግ​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="17">አው​ራ​ው​ንም በግ ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ከሌ​ማቱ ቂጣ እን​ጀራ ጋር ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ር​ባል፤ ካህ​ኑም ደግሞ የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ንና የመ​ጠ​ጡን ቍር​ባን ያቀ​ር​ባል።</verse>
				<verse number="18">የተ​ሳ​ለ​ውም የተ​ሳ​ለ​ውን የራስ ጠጕር በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን አጠ​ገብ ይላ​ጫል፤ የስ​እ​ለ​ቱ​ንም ራስ ጠጕር ወስዶ ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት በታች ወዳ​ለው እሳት ይጥ​ለ​ዋል።</verse>
				<verse number="19">ካህ​ኑም የተ​ቀ​ቀ​ለ​ውን የአ​ው​ራ​ውን በግ ወርች፥ ከሌ​ማ​ቱም አንድ ቂጣ እን​ጎቻ፥ አን​ድም ስስ ቂጣ ይወ​ስ​ዳል፤ የተ​ሳ​ለ​ው​ንም የራስ ጠጕር ከተ​ላጨ በኋላ በባ​ለ​ስ​እ​ለቱ እጆች ላይ ያኖ​ራ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="20">ካህ​ኑም እነ​ዚ​ህን ሁሉ ቍር​ባን አድ​ርጎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​ባል፤ ይህም የቍ​ር​ባን ፍር​ም​ባና የመ​ባው ወርች ለካ​ህኑ የተ​ቀ​ደሰ ነው፤ ከዚ​ያም በኋላ ባለ​ስ​እ​ለቱ ወይን ይጠ​ጣል።</verse>
				<verse number="21">“ስእ​ለ​ቱን የተ​ሳ​ለው የባ​ለ​ስ​እ​ለቱ፥ እጁም ከሚ​ያ​ገ​ኘው ሌላ ስለ ስእ​ለቱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​በው የቍ​ር​ባኑ ሕግ ይህ ነው፤ ስእ​ለ​ቱን እንደ ተሳለ እንደ ስእ​ለቱ ሕግ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋል።”</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="23">“ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ንገ​ራ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ስት​ባ​ር​ኩ​አ​ቸው እን​ዲህ በሉ​አ​ቸው፦</verse>
				<verse number="24">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ር​ክህ፥ ይጠ​ብ​ቅ​ህም፤</verse>
				<verse number="25">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊቱን ያብ​ራ​ልህ፥ ይራ​ራ​ል​ህም።</verse>
				<verse number="26">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ፥ ሰላ​ም​ንም ይስ​ጥህ።</verse>
				<verse number="27">እን​ዲሁ ስሜን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ይጠ​ራሉ፤ እኔም እባ​ር​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ ድን​ኳ​ኑን ፈጽሞ በተ​ከ​ለ​ባት፥ እር​ስ​ዋ​ንና ዕቃ​ዋን ሁሉ በቀ​ባና በቀ​ደ​ሰ​ባት፥ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንና ዕቃ​ው​ንም ሁሉ በቀ​ባና በቀ​ደ​ሰ​ባት ቀን፥</verse>
				<verse number="2">ዐሥራ ሁለቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አለ​ቆች፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች፥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን አቀ​ረቡ፤ እነ​ዚ​ህም ከተ​ቈ​ጠ​ሩት በላይ የተ​ሾሙ የነ​ገ​ዶች አለ​ቆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="3">መባ​ቸ​ው​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቀ​ረቡ፤ የተ​ከ​ደኑ ስድ​ስት ሰረ​ገ​ሎች ዐሥራ ሁለ​ትም በሬ​ዎች፤ በየ​ሁ​ለ​ቱም አለ​ቆች አንድ ሰረ​ገላ አቀ​ረቡ፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ አንድ በሬ በድ​ን​ኳኑ ፊት አቀ​ረቡ።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="5">“ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥራ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግል ይሆን ዘንድ፥ ከእ​ነ​ርሱ ተቀ​ብ​ለህ ለሌ​ዋ​ው​ያን ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ እንደ አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ስጣ​ቸው።”</verse>
				<verse number="6">ሙሴም ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና በሬ​ዎ​ችን ተቀ​ብሎ ለሌ​ዋ​ው​ያን ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">ለጌ​ድ​ሶን ልጆች እንደ አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ሁለት ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና አራት በሬ​ዎ​ችን ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">ከካ​ህ​ኑም ከአ​ሮን ልጅ ከኢ​ታ​ምር እጅ በታች ላሉት ለሜ​ራሪ ልጆች እንደ አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው መጠን አራት ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ስም​ንት በሬ​ዎ​ችን ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ለቀ​ዓት ልጆች ግን መቅ​ደ​ሱን ማገ​ል​ገል የእ​ነ​ርሱ ነውና፥ በት​ከ​ሻ​ቸ​ውም ይሸ​ከ​ሙት ነበ​ርና ምንም አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="10">መሠ​ዊ​ያ​ውም በተ​ቀባ ቀን አለ​ቆቹ መሠ​ዊ​ያ​ውን ለመ​ቀ​ደስ ቍር​ባ​ንን አቀ​ረቡ፤ አለ​ቆ​ችም መባ​ቸ​ውን በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት አቀ​ረቡ።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “እያ​ን​ዳ​ንዱ አለቃ በየ​ቀኑ መሠ​ዊ​ያ​ውን ለመ​ቀ​ደስ እያ​ን​ዳ​ንዱ አለቃ መባ​ውን በቀን በቀኑ ያቅ​ርብ” አለው።</verse>
				<verse number="12">በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ቀን መባ​ውን ያቀ​ረበ ከይ​ሁዳ ነገድ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነአ​ሶን ነበረ።</verse>
				<verse number="13">መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤</verse>
				<verse number="14">ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤</verse>
				<verse number="15">ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት ከመ​ን​ጋ​ዎች አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤</verse>
				<verse number="16">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤</verse>
				<verse number="17">ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ የነ​አ​ሶን መባ ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="18">በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን የይ​ሳ​ኮር አለቃ የሰ​ገር ልጅ ናት​ና​ኤል አቀ​ረበ።</verse>
				<verse number="19">ለመ​ባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞ​ሉ​ትን፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆ​ነ​ውን አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆ​ነ​ውን አንድ የብር ድስት፤</verse>
				<verse number="20">ዕጣ​ንም የተ​ሞ​ላ​ውን ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆ​ነ​ውን አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤</verse>
				<verse number="21">ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤</verse>
				<verse number="22">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤</verse>
				<verse number="23">ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች አቀ​ረበ፤ የሰ​ገር ልጅ የና​ት​ና​ኤል መባ ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="24">በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን የዛ​ብ​ሎን ልጆች አለቃ የኬ​ሎን ልጅ ኤል​ያብ መባ​ውን አቀ​ረበ።</verse>
				<verse number="25">መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤</verse>
				<verse number="26">ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤</verse>
				<verse number="27">ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤</verse>
				<verse number="28">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤</verse>
				<verse number="29">ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የኬ​ሎን ልጅ የኤ​ል​ያብ መባ ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="30">በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ቀን የሮ​ቤል ልጆች አለቃ የሴ​ድ​ዮር ልጅ ኤሊ​ሱር መባ​ውን አቀ​ረበ፤</verse>
				<verse number="31">መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ስቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤</verse>
				<verse number="32">ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤</verse>
				<verse number="33">ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤</verse>
				<verse number="34">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤</verse>
				<verse number="35">ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የሴ​ድ​ዮር ልጅ የኤ​ሊ​ሱር መባ ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="36">በአ​ም​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን የስ​ም​ዖን ልጆች አለቃ የሲ​ሩ​ሳዴ ልጅ ሰላ​ም​ያል መባ​ውን አቀ​ረበ፤</verse>
				<verse number="37">መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤</verse>
				<verse number="38">ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤</verse>
				<verse number="39">ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤</verse>
				<verse number="40">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤</verse>
				<verse number="41">ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የሲ​ሩ​ሳዴ ልጅ የሰ​ላ​ም​ያል መባ ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="42">በስ​ድ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን የጋድ ልጆች አለቃ የራ​ጉ​ኤል ልጅ ኤሊ​ሳፍ መባ​ውን አቀ​ረበ፤</verse>
				<verse number="43">መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤</verse>
				<verse number="44">ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤</verse>
				<verse number="45">ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት ጠቦት፤</verse>
				<verse number="46">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤</verse>
				<verse number="47">ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የራ​ጉ​ኤል ልጅ የኤ​ሊ​ሳፍ መባ ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="48">በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን የኤ​ፍ​ሬም ልጆች አለቃ የኤ​ሚ​ሁድ ልጅ ኤሊ​ሳማ መባ​ውን አቀ​ረበ፤</verse>
				<verse number="49">መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑ ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤</verse>
				<verse number="50">ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤</verse>
				<verse number="51">ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤</verse>
				<verse number="52">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤</verse>
				<verse number="53">ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የኤ​ሚ​ሁድ ልጅ የኤ​ሊ​ሳማ መባ ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="54">በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን የም​ናሴ ልጆች አለቃ የፈ​ዳ​ሱር ልጅ ገማ​ል​ያል መባ​ውን አቀ​ረበ፤</verse>
				<verse number="55">መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑ ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤</verse>
				<verse number="56">ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤</verse>
				<verse number="57">ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤</verse>
				<verse number="58">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤</verse>
				<verse number="59">ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የፈ​ዳ​ሱር ልጅ የገ​ማ​ል​ያል መባ ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="60">በዘ​ጠ​ነ​ኛ​ውም ቀን የብ​ን​ያም ልጆች አለቃ የጋ​ዴ​ዮን ልጅ አቢ​ዳን መባ​ውን አቀ​ረበ፤</verse>
				<verse number="61">መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤</verse>
				<verse number="62">ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤</verse>
				<verse number="63">ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤</verse>
				<verse number="64">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤</verse>
				<verse number="65">ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የጋ​ዴ​ዮን ልጅ የአ​ቢ​ዳን መባ ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="66">በዐ​ሥ​ረ​ኛ​ውም ቀን የዳን ልጆች አለቃ የአ​ሚ​ሳዲ ልጅ አኪ​ያ​ዜር መባ​ውን አቀ​ረበ፤</verse>
				<verse number="67">መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤</verse>
				<verse number="68">ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤</verse>
				<verse number="69">ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤</verse>
				<verse number="70">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤</verse>
				<verse number="71">ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የአ​ሚ​ሳዲ ልጅ የአ​ኪ​ያ​ዜር መባ ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="72">በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛ​ውም ቀን የአ​ሴር ልጆች አለቃ የኤ​ክ​ራን ልጅ ፋግ​ኤል መባ​ውን አቀ​ረበ፤</verse>
				<verse number="73">መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤</verse>
				<verse number="74">ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤</verse>
				<verse number="75">ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤</verse>
				<verse number="76">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤</verse>
				<verse number="77">ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የኤ​ክ​ራን ልጅ የፋ​ግ​ኤል መባ ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="78">በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ቀን የን​ፍ​ታ​ሌም ልጆች አለቃ የዔ​ናን ልጅ አኪሬ መባ​ውን አቀ​ረበ፤</verse>
				<verse number="79">መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤</verse>
				<verse number="80">ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤</verse>
				<verse number="81">ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤</verse>
				<verse number="82">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤</verse>
				<verse number="83">ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የዔ​ናን ልጅ የአ​ኪሬ መባ ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="84">መሠ​ዊ​ያው በተ​ቀባ ቀን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አለ​ቆች ለመ​ሠ​ዊ​ያው መቀ​ደሻ ያቀ​ረ​ቡት መባ ይህ ነበረ፤ ዐሥራ ሁለት የብር ወጭ​ቶች፥ ዐሥራ ሁለት የብር ድስ​ቶች፥ ዐሥራ ሁለት የወ​ርቅ ጭል​ፋ​ዎች፤</verse>
				<verse number="85">እያ​ን​ዳ​ን​ዱም የብር ወጭት መቶ ሠላሳ ሰቅል፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ድስት ሰባ ሰቅል ነበረ፤ የዚ​ህም ዕቃ ሁሉ ብር በመ​ቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን ሁለት ሺህ አራት መቶ ሰቅል ነበረ።</verse>
				<verse number="86">ዕጣ​ንም የተ​ሞሉ ዐሥራ ሁለት የወ​ርቅ ጭል​ፋ​ዎች፥ እያ​ን​ዳ​ንዱ በመ​ቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን ዐሥር ዐሥር ሰቅል ነበረ፤ የጭ​ል​ፋ​ዎቹ ወርቅ ሁሉ መቶ ሃያ ሰቅል ነበረ።</verse>
				<verse number="87">የሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ከብት ሁሉ ከእ​ህሉ ቍር​ባን ጋር ዐሥራ ሁለት ወይ​ፈ​ኖች፥ ዐሥራ ሁለ​ትም አውራ በጎች፥ ዐሥራ ሁለ​ትም የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ነበሩ፤ የኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አውራ ፍየ​ሎች ዐሥራ ሁለት ነበሩ።</verse>
				<verse number="88">የደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከብት ሁሉ፥ ሃያ አራት ጊደ​ሮች፥ ስድ​ሳም አውራ በጎች፥ ስድ​ሳም አውራ ፍየ​ሎች፥ ስድ​ሳም ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸው የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበሩ። መሠ​ዊ​ያው ከተ​ቀባ በኋላ ለመ​ቀ​ደ​ሻው የቀ​ረበ ቍር​ባን ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="89">ሙሴም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን እር​ሱን ለመ​ነ​ጋ​ገር በገባ ጊዜ በቃል ኪዳኑ ታቦት ላይ ካለው ከስ​ር​የት መክ​ደ​ኛው በላይ ከኪ​ሩ​ቤ​ልም መካ​ከል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድምፅ ይሰማ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ይና​ገር ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“መብ​ራ​ቶ​ቹን ስታ​በራ ሰባቱ መብ​ራ​ቶች በመ​ቅ​ረዙ ፊት ያበ​ራሉ ብለህ ለአ​ሮን ንገ​ረው።”</verse>
				<verse number="3">አሮ​ንም እን​ዲሁ አደ​ረገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ በመ​ቅ​ረዙ ፊት መብ​ራ​ቶ​ቹን አበራ።</verse>
				<verse number="4">የመ​ቅ​ረ​ዝ​ዋም ሥራዋ እን​ዲህ ነበረ። ሁለ​ን​ተ​ና​ቸው ወርቅ የሆነ አፅ​ቆ​ችዋ ሥረ-ወጥ ነበሩ፤ አበ​ቦ​ች​ዋም ሁለ​ን​ተ​ና​ቸው ሥረ-ወጥ ነበሩ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ሳ​የው ምሳሌ መቅ​ረ​ዝ​ዋን እን​ዲሁ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="6">“ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ሌዋ​ው​ያ​ንን ወስ​ደህ አን​ጻ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">ታነ​ጻ​ቸው ዘንድ እን​ዲህ ታደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በማ​ን​ጻት ውኃ ትረ​ጫ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ይላጩ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ይጠቡ፤ ንጹ​ሓ​ንም ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="8">ከላ​ሞች አንድ ወይ​ፈን፥ ለእ​ህ​ሉም ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄ​ትን ይው​ሰዱ፤ ሌላ​ው​ንም የአ​ንድ ዓመት ወይ​ፈን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ይው​ሰዱ።</verse>
				<verse number="9">ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት አቅ​ርብ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ሰብ​ስብ።</verse>
				<verse number="10">ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቅ​ር​ባ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በሌ​ዋ​ው​ያን ላይ እጃ​ቸ​ውን ይጫ​ኑ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">አሮ​ንም ሌዋ​ው​ያን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ስጦታ አድ​ርጎ፥ ሌዋ​ው​ያ​ንን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይለ​ያ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="12">ሌዋ​ው​ያ​ኑም በወ​ይ​ፈ​ኖቹ ራሶች ላይ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ይጫኑ፤ ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ስለ ማስ​ተ​ስ​ረያ አን​ዱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ርብ።</verse>
				<verse number="13">ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም በአ​ሮ​ንና በል​ጆቹ ፊት አቁ​ማ​ቸው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ስጦታ አድ​ር​ገህ አቅ​ር​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">እን​ዲሁ ሌዋ​ው​ያ​ንን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለይ፤ እነ​ር​ሱም ለእኔ ይሁኑ።</verse>
				<verse number="15">“ከዚ​ያም በኋላ ሌዋ​ው​ያን የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ይገ​ባሉ፤ ታነ​ጻ​ቸ​ው​ማ​ለህ፤ ስጦ​ታም አድ​ር​ገህ በፊቴ ታቀ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="16">እነ​ር​ሱም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ፈጽሞ ለእኔ ተሰ​ጥ​ተ​ዋ​ልና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በኵ​ራት ሁሉ፥ መጀ​መ​ሪያ በሚ​ወ​ለድ ሁሉ ፋንታ ለእኔ ወስ​ጄ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="17">በግ​ብፅ ምድር ያለ​ውን በኵር ሁሉ በገ​ደ​ል​ሁ​በት ቀን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በኵ​ራት ሁሉ፥ ሰው ወይም እን​ስሳ፥ ለእኔ ቀድ​ሼ​አ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና የእኔ ናቸው።</verse>
				<verse number="18">በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በኵር ሁሉ ፋንታ ሌዋ​ው​ያ​ንን ወስ​ጄ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም ስጦታ አድ​ርጌ አገ​ባ​ኋ​ቸው፤ ልዩ በሆ​ነች ድን​ኳን ውስጥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሥራ ይሠሩ ዘንድ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ኀጢ​አት ያቃ​ልሉ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ተሰጡ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ መቅ​ደስ የሚ​ቀ​ርብ አይ​ኑር።”</verse>
				<verse number="20">ሙሴና አሮን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ እን​ዲሁ በሌ​ዋ​ው​ያን ላይ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን ስለ ሌዋ​ው​ያን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አደ​ረ​ጉ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">ሌዋ​ው​ያ​ንም ከኀ​ጢ​አት ራሳ​ቸ​ውን አነጹ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አጠቡ፤ አሮ​ንም ስጦታ አድ​ርጎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቀ​ረ​ባ​ቸው፤ አሮ​ንም ያነ​ጻ​ቸው ዘንድ አስ​ተ​ሰ​ረ​የ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">ከዚ​ያም በኋላ ሌዋ​ው​ያን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በአ​ሮ​ንና በል​ጆቹ ፊት አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውን ይፈ​ጽሙ ዘንድ ገቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን ስለ ሌዋ​ው​ያን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ አደ​ረ​ጉ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="24">“የሌ​ዋ​ው​ያን ሕግ ይህ ነው፤ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉት እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥራ ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ይገ​ባሉ።</verse>
				<verse number="25">ከአ​ምሳ ዓመት በኋላ ከሥ​ራው ይሰ​ና​በት። ከዚ​ያም ወዲያ እርሱ አያ​ገ​ል​ግል።</verse>
				<verse number="26">ወን​ድ​ሙ​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ያገ​ል​ግል፤ ሰሞ​ና​ቸ​ው​ንም ይጠ​ብቅ። ነገር ግን አገ​ል​ግ​ሎ​ቱን ይተው። እን​ዲሁ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ታደ​ር​ጋ​ለህ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር በወጡ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በሲና ምድረ በዳ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በጊ​ዜው ፋሲ​ካ​ውን ያድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="3">በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን በመሸ ጊዜ በጊ​ዜው አድ​ር​ጉት፤ እንደ ሥር​ዐቱ ሁሉ እንደ ፍር​ዱም ሁሉ አድ​ር​ጉት።”</verse>
				<verse number="4">ሙሴም ፋሲ​ካን ያደ​ርጉ ዘንድ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ነገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን በሲና ምድረ በዳ ፋሲ​ካን አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="6">በሰ​ው​ነ​ታ​ቸው ርኵ​ሰት የነ​በ​ረ​ባ​ቸው ሰዎች መጡ፤ ስለ​ዚ​ህም በዚያ ቀን ፋሲ​ካን ያደ​ርጉ ዘንድ አል​ቻ​ሉም።</verse>
				<verse number="7">በዚ​ያም ቀን ወደ ሙሴና ወደ አሮን ቀረቡ። እነ​ዚ​ያም ሰዎች “እኛ በሰ​ው​ነ​ታ​ችን ርኵ​ሰት ያለ​ብን ሰዎች ነን፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል በጊ​ዜው ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ና​ቀ​ርብ ስለ ምን እን​ከ​ለ​ከ​ላ​ለን?” አሉት።</verse>
				<verse number="8">ሙሴም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እና​ንተ የሚ​ያ​ዝ​ዘ​ውን እስ​ክ​ሰማ ቈዩ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="10">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ከእ​ና​ንተ ወይም ከት​ው​ል​ዶ​ቻ​ችሁ ዘንድ ማን​ኛ​ውም ሰው በሰ​ው​ነቱ ቢረ​ክስ፥ ወይም ሩቅ መን​ገድ ቢሄድ፥ ወይም በተ​ወ​ለ​ዳ​ች​ሁ​በት ሀገር ያለም ቢሆን እርሱ ደግሞ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲ​ካን ያድ​ርግ።</verse>
				<verse number="11">በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን በመሸ ጊዜ ያድ​ር​ጉት፤ ከቂጣ እን​ጀ​ራና ከመ​ራራ ቅጠል ጋር ይብ​ሉት።</verse>
				<verse number="12">ከእ​ር​ሱም እስከ ነገ ምንም አያ​ስ​ቀሩ፤ ከእ​ር​ሱም አጥ​ን​ትን አይ​ስ​በሩ፤ እንደ ፋሲካ ሥር​ዐት ሁሉ ያድ​ር​ጉት።</verse>
				<verse number="13">ነገር ግን ንጹሕ የሆነ ሰው በመ​ን​ገ​ድም ላይ ያል​ሆነ ፋሲ​ካን ባያ​ደ​ርግ፥ ያ ሰው ከሕ​ዝቡ ዘንድ ተለ​ይቶ ይጠ​ፋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቍር​ባን በጊ​ዜው አላ​ቀ​ረ​በ​ምና ያ ሰው ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል።</verse>
				<verse number="14">ወደ አገ​ራ​ችሁ መጻ​ተኛ ቢመጣ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፋሲካ እንደ ፋሲ​ካው ሕግ እንደ ትእ​ዛ​ዙም ያድ​ርግ፤ ለመ​ጻ​ተ​ኛና ለሀ​ገር ልጅ አንድ ሥር​ዐት ይሁ​ን​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="15">ድን​ኳ​ን​ዋን በተ​ከ​ሉ​በት ቀን ደመ​ናው የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሸፈ​ናት፤ ከማ​ታም ጀምሮ እስከ ጥዋት ድረስ በድ​ን​ኳኑ ላይ እንደ እሳት ይመ​ስል ነበር።</verse>
				<verse number="16">እን​ዲሁ ሁል​ጊዜ ነበረ፤ በቀን ደመና፥ በሌ​ሊ​ትም የእ​ሳት አም​ሳል ይሸ​ፍ​ናት ነበር።</verse>
				<verse number="17">ደመ​ና​ውም ከድ​ን​ኳኑ ላይ በተ​ነሣ ጊዜ በዚ​ያን ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይጓዙ ነበር፤ ደመ​ና​ውም በቆ​መ​በት ስፍራ በዚያ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይሰ​ፍሩ ነበር።</verse>
				<verse number="18">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይጓዙ ነበር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ይሰ​ፍሩ ነበር፤ ደመ​ናው በድ​ን​ኳኑ ላይ በተ​ቀ​መ​ጠ​በት ዘመን ሁሉ በሰ​ፈ​ራ​ቸው ይቀ​መጡ ነበር።</verse>
				<verse number="19">ደመ​ና​ውም በድ​ን​ኳኑ ላይ ብዙ ቀን በተ​ቀ​መጠ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ይጠ​ብቁ ነበር፤ አይ​ጓ​ዙ​ምም ነበር።</verse>
				<verse number="20">ደመ​ናው ድን​ኳ​ኑን በጋ​ረ​ደ​በት ቀን ቍጥር ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይሰ​ፍሩ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ይጓዙ ነበር።</verse>
				<verse number="21">አን​ዳ​ንድ ጊዜም ደመ​ናው ከማታ ጀምሮ እስከ ጥዋት ድረስ ይቀ​መጥ ነበር፤ በጥ​ዋ​ትም ደመ​ናው በተ​ነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር። በቀ​ንም በሌ​ሊ​ትም ቢሆን ደመ​ናው በተ​ነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር</verse>
				<verse number="22">ደመ​ና​ውም እስከ ወር ቈይቶ በድ​ን​ኳኑ ላይ ቢቀ​መጥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በሰ​ፈ​ራ​ቸው ይቀ​መጡ ነበር፤ አይ​ጓ​ዙ​ምም ነበር፤ ነገር ግን በተ​ነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር።</verse>
				<verse number="23">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ይሰ​ፍሩ ነበር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ይጓዙ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ ቃል እንደ አዘዘ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ይጠ​ብቁ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“ሁለት የብር መለ​ከ​ቶች አስ​ጠ​ፍ​ጥ​ፈህ ለአ​ንተ አድ​ርግ፤ ማኅ​በ​ሩን ለመ​ጥ​ራት ከሰ​ፈ​ራ​ቸ​ውም ለማ​ስ​ጓዝ ይሁ​ኑ​ልህ።</verse>
				<verse number="3">ሁለ​ቱም መለ​ከ​ቶች በተ​ነፉ ጊዜ ማኅ​በሩ ሁሉ ወደ አንተ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ይሰ​ብ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="4">አንድ መለ​ከት ሲነፋ ታላ​ላ​ቆቹ የእ​ስ​ራ​ኤል አእ​ላፍ አለ​ቆች ወደ አንተ ይሰ​ብ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="5">መለ​ከ​ቱ​ንም በም​ል​ክት ስት​ነፉ በም​ሥ​ራቅ በኩል የሰ​ፈ​ሩት ይጓዙ።</verse>
				<verse number="6">ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም በም​ል​ክቱ ስት​ነፉ በአ​ዜብ በኩል የሰ​ፈ​ሩት ይጓዙ፤ ሦስ​ተ​ኛ​ው​ንም በም​ል​ክቱ በነ​ፋ​ችሁ ጊዜ በባ​ሕር በኩል የሰ​ፈ​ሩት ይጓዙ፤ አራ​ተ​ኛ​ው​ንም በም​ል​ክቱ በነ​ፋ​ችሁ ጊዜ በመ​ስዕ በኩል የሰ​ፈ​ሩት ሠራ​ዊት ይጓዙ፤ ለማ​ስ​ጓዝ በም​ል​ክት ትነ​ፉ​ታ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="7">ጉባ​ኤ​ውም በሚ​ሰ​በ​ሰ​ብ​በት ጊዜ ያለ ምል​ክት ትነ​ፉ​ታ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="8">የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ መለ​ከ​ቱን ይንፉ፤ ይህም ለልጅ ልጃ​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁ​ን​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="9">በሚ​ገ​ፋ​ች​ሁም ጠላት ላይ በም​ድ​ራ​ችሁ ወደ ሰልፍ ስት​ወጡ በም​ል​ክት መለ​ከ​ቶ​ችን ንፉ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ፊት ትታ​ሰ​ባ​ላ​ችሁ፤ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ትድ​ና​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="10">ደግሞ በደ​ስ​ታ​ችሁ ቀን፥ በበ​ዓ​ላ​ታ​ች​ሁም ዘመን፥ በወ​ርም መባቻ፥ በሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁና በደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችሁ ላይ መለ​ከ​ቶ​ችን ንፉ፤ እነ​ር​ሱም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ፊት ለመ​ታ​ሰ​ቢያ ይሆ​ኑ​ላ​ች​ኋል፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።”</verse>
				<verse number="11">በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ዓመት በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሃ​ያ​ኛው ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ ደመ​ናው ከም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ላይ ተነሣ።</verse>
				<verse number="12">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከሲና ምድረ በዳ በየ​ጉ​ዞ​አ​ቸው ተጓዙ፤ ደመ​ና​ውም በፋ​ራን ምድረ በዳ ቆመ።</verse>
				<verse number="13">በመ​ጀ​መ​ሪ​ያም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ ቃል እን​ዳ​ዘዘ ተጓዙ።</verse>
				<verse number="14">በመ​ጀ​መ​ሪ​ያም የይ​ሁዳ ልጆች ሰፈር በሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ከየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠ​ራ​ዊ​ቱም ላይ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነአ​ሶን አለቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="15">በይ​ሳ​ኮ​ርም ልጆች ነገድ ሠራ​ዊት ላይ የሰ​ገር ልጅ ናት​ና​ኤል አለቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="16">በዛ​ብ​ሎ​ንም ልጆች ነገድ ሠራ​ዊት ላይ የኬ​ሎን ልጅ ኤል​ያብ አለቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="17">ድን​ኳ​ኑም ተነ​ቀለ፤ ድን​ኳ​ኑ​ንም የተ​ሸ​ከሙ የጌ​ድ​ሶን ልጆ​ችና የሜ​ራሪ ልጆች ተጓዙ።</verse>
				<verse number="18">የሮ​ቤ​ልም ሰፈር በሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ከየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠ​ራ​ዊ​ቱም ላይ የሰ​ዲ​ዮር ልጅ ኤሊ​ሱር አለቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="19">በስ​ም​ዖ​ንም ልጆች ነገድ ሠራ​ዊት ላይ የሲ​ሩ​ሳዴ ልጅ ሰላ​ም​ያል አለቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="20">በጋ​ድም ልጆች ነገድ ሠራ​ዊት ላይ የራ​ጉ​ኤል ልጅ ኤሊ​ሳፍ አለቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="21">የቀ​ዓ​ትም ልጆች ንዋየ ቅድ​ሳ​ቱን ተሸ​ክ​መው ተጓዙ፤ እነ​ዚ​ህም እስ​ኪ​መጡ ድረስ እነ​ዚያ ድን​ኳ​ኑን ተከሉ።</verse>
				<verse number="22">የኤ​ፍ​ሬ​ምም ልጆች ሰፈር በሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ከየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠ​ራ​ዊ​ቱም ላይ የኣ​ሚ​ሁድ ልጅ ኤሊ​ሳማ አለቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="23">በም​ና​ሴም ልጆች ነገድ ሠራ​ዊት ላይ የፈ​ዳ​ሱር ልጅ ገማ​ል​ያል አለቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="24">በብ​ን​ያ​ምም ልጆች ነገድ ሠራ​ዊት ላይ የጋ​ዲ​ዮን ልጅ አቢ​ዳን አለቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="25">ከሠ​ራ​ዊቱ ሁሉ በኋላ የዳን ልጆች ሰፈር በሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ከየ​ሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠ​ራ​ዊ​ቱም ላይ የአ​ሚ​ሳዲ ልጅ አኪ​ያ​ዜር አለቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="26">በአ​ሴ​ርም ልጆች ነገድ ሠራ​ዊት ላይ የኤ​ክ​ራን ልጅ ፋግ​ኤል አለቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="27">በን​ፍ​ታ​ሌ​ምም ልጆች ነገድ ሠራ​ዊት ላይ የዔ​ናን ልጅ አኪሬ አለቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="28">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጉዞ እን​ደ​ዚህ ነበር፤ ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ጋር ተጓዙ።</verse>
				<verse number="29">ሙሴም የሚ​ስ​ቱን አባት የም​ድ​ያ​ማ​ዊ​ውን የራ​ጉ​ኤ​ልን ልጅ ኦባ​ብን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ለእ​ና​ንተ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ ወዳ​ለው ስፍራ እን​ሄ​ዳ​ለን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እስ​ራ​ኤል መል​ካ​ምን ነገር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና አንተ ከእኛ ጋር ና፥ መል​ካ​ምን እና​ደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለን” አለው።</verse>
				<verse number="30">እር​ሱም፥ “አል​ሄ​ድም፥ ነገር ግን ወደ ሀገ​ሬና ወደ ዘመ​ዶች እመ​ለ​ሳ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="31">እር​ሱም፥ “እባ​ክህ፥ በም​ድረ በዳ ከእኛ ጋር ኑረ​ሃ​ልና በእ​ኛም ዘንድ አር​ጅ​ተ​ሃ​ልና አት​ተ​ወን፤</verse>
				<verse number="32">ከእ​ኛም ጋር ብት​ሄድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ልን መል​ካም ነገር ሁሉ እኛ ለአ​ንተ እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አለው።</verse>
				<verse number="33">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተራራ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ያህል ተጓዙ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የኪ​ዳኑ ታቦት የሚ​ያ​ድ​ሩ​በ​ትን ቦታ ታገ​ኝ​ላ​ቸው ዘንድ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ትቀ​ድ​ማ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="34">ሙሴም ታቦቷ በተ​ጓ​ዘች ጊዜ፥ “አቤቱ፥ ተነሣ፤ ጠላ​ቶ​ችህ ይበ​ተኑ፤ የሚ​ጠ​ሉ​ህም ከፊ​ትህ ይሽሹ” ይል ነበር።</verse>
				<verse number="35">ባረ​ፈም ጊዜ፥ “አቤቱ፥ ወደ እስ​ራ​ኤል እልፍ አእ​ላ​ፋት ተመ​ለስ” ይል ነበር።</verse>
				<verse number="36">ከሰ​ፈ​ራ​ቸ​ውም በተ​ጓዙ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደመና ቀን ቀን በላ​ያ​ቸው ላይ ነበረ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">ሕዝ​ቡም በክ​ፋት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አጕ​ረ​መ​ረሙ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰምቶ ተቈጣ፤ እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በእ​ነ​ርሱ ላይ ነደ​ደች፤ ከሰ​ፈ​ሩም አን​ዱን ወገን በላች።</verse>
				<verse number="2">ሕዝ​ቡም ወደ ሙሴ ጮኹ፤ ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለየ፤ እሳ​ቲ​ቱም ጠፋች።</verse>
				<verse number="3">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ በእ​ነ​ርሱ ላይ እሳት ስለ ነደ​ደች የዚያ ስፍራ ስም “መካነ ውዕ​የት” ተብሎ ተጠራ።</verse>
				<verse number="4">ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የተ​ቀ​ላ​ቀሉ ሕዝብ እጅግ ጐመጁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተቀ​ም​ጠው እን​ዲህ እያሉ አለ​ቀሱ፥ “ሥጋ ማን ያበ​ላ​ናል?</verse>
				<verse number="5">በግ​ብፅ ያለ ዋጋ እን​በ​ላው የነ​በ​ረ​ውን ዓሣ፥ ዳቦ​ው​ንም፥ በጢ​ኹ​ንም፥ ኩራ​ቱ​ንም፥ ቀዩ​ንም ሽን​ኩ​ርት፥ ነጩ​ንም ሽን​ኩ​ርት ቍንዶ በር​በ​ሬ​ው​ንም እና​ስ​ባ​ለን።</verse>
				<verse number="6">አሁን ግን ሰው​ነ​ታ​ችን ደረ​ቀች፤ ዐይ​ና​ች​ንም ከዚህ መና በቀር ምንም አታ​ይም” አሉ።</verse>
				<verse number="7">መና​ውም እንደ ድን​ብ​ላል ዘር ነበረ፤ መል​ኩም እንደ በረድ ነጭ ነበር።</verse>
				<verse number="8">ሕዝ​ቡም እየ​ዞሩ ይለ​ቅሙ ነበር፤ በወ​ፍ​ጮም ይፈ​ጩት፥ ወይም በሙ​ቀጫ ይወ​ቅ​ጡት፥ በም​ን​ቸ​ትም ይቀ​ቅ​ሉት ነበር፤ እን​ጎ​ቻም ያደ​ር​ጉት ነበር፤ ጣዕ​ሙም በዘ​ይት እንደ ተለ​ወሰ እን​ጎቻ ነበረ።</verse>
				<verse number="9">ሌሊ​ትም ጠል በሰ​ፈሩ ላይ በወ​ረደ ጊዜ መናው በላዩ ይወ​ርድ ነበር።</verse>
				<verse number="10">ሙሴም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በየ​ወ​ገ​ና​ቸው በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ፥ ሲያ​ለ​ቅሱ ሰማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅግ ተቈጣ፤ ነገ​ሩም በሙሴ ፊት ክፉ ሆነ።</verse>
				<verse number="11">ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ለምን በአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ላይ ክፉ አደ​ረ​ግህ? ለም​ንስ በፊ​ትህ ሞገ​ስን አላ​ገ​ኘ​ሁም? ለም​ንስ የዚ​ህን ሁሉ ሕዝብ ሸክም በእኔ ላይ አደ​ረ​ግህ?</verse>
				<verse number="12">አንተ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ወደ ማል​ህ​ላ​ቸው ምድር አደ​ር​ሳ​ቸው ዘንድ፦ ሞግ​ዚት የሚ​ጠ​ባ​ውን ልጅ እን​ድ​ታ​ቅፍ በብ​ትህ እቀ​ፋ​ቸው የም​ት​ለኝ፥ በውኑ ይህን ሕዝብ ሁሉ እኔ ፀነ​ስ​ሁ​ትን? ወይስ ወለ​ድ​ሁ​ትን?</verse>
				<verse number="13">በፊቴ ያለ​ቅ​ሳ​ሉና፦ የም​ን​በ​ላ​ውን ሥጋ ስጠን ይላ​ሉና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ የም​ሰ​ጠው ሥጋ ከየት አለኝ?</verse>
				<verse number="14">እጅግ ከብ​ዶ​ኛ​ልና ይህን ሁሉ ሕዝብ ብቻ​ዬን ልሸ​ከም አል​ች​ልም።</verse>
				<verse number="15">እን​ዲ​ህስ ከም​ታ​ደ​ር​ግ​ብኝ፥ በፊ​ትህ ይቅ​ር​ታን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ፥ በእኔ ላይ የሚ​ሆ​ነ​ውን መከራ እን​ዳ​ላይ፥ እባ​ክህ፥ ፈጽሞ ግደ​ለኝ።”</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ ለሕ​ዝቡ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ጸሐ​ፍት ይሆኑ ዘንድ የም​ታ​ው​ቃ​ቸ​ውን፥ ሰባ ሰዎች ሰብ​ስ​ብ​ልኝ፤ ወደ ምስ​ክ​ሩም ድን​ኳን አም​ጣ​ቸው፤ በዚ​ያም ከአ​ንተ ጋር አቁ​ማ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">እኔም እወ​ር​ዳ​ለሁ፤ በዚ​ያም አነ​ጋ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤ በአ​ንተ ካለ​ውም መን​ፈስ ወስጄ በእ​ነ​ርሱ ላይ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ አን​ተም ብቻ እን​ዳ​ት​ሸ​ከም የሕ​ዝ​ቡን ሸክም ከአ​ንተ ጋር ይሸ​ከ​ማሉ።</verse>
				<verse number="18">ሕዝ​ቡ​ንም በላ​ቸው፦ ሥጋ ማን ያበ​ላ​ናል? በግ​ብፅ ደኅና ነበ​ረ​ልን እያ​ላ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አል​ቅ​ሳ​ች​ኋ​ልና ለነገ ተቀ​ደሱ፤ ሥጋ​ንም ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሥጋን ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ ትበ​ሉ​ማ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="19">አንድ ቀን፥ ወይም ሁለት ቀን፥ ወይም አም​ስት ቀን፥ ወይም ዐሥር ቀን ወይም ሃያ ቀን አት​በ​ሉም፤</verse>
				<verse number="20">ነገር ግን በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ያለ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ንቃ​ች​ኋ​ልና፥ በፊ​ቱም፦ ለምን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ኸን? ብላ​ችሁ አል​ቅ​ሳ​ች​ኋ​ልና በአ​ፍ​ን​ጫ​ችሁ እስ​ኪ​ወጣ መር​ዝም እስ​ኪ​ሆ​ን​ባ​ችሁ ድረስ ወር ሙሉ ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="21">ሙሴም፥ “እኔ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ያለሁ ሕዝብ ስድ​ስት መቶ ሺህ እግ​ረኛ ናቸው፤ አን​ተም፦ ሥጋን እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ወር ሙሉም ይበ​ሉ​ታል አልህ።</verse>
				<verse number="22">የበ​ሬና የበግ መንጋ ቢታ​ረድ፥ የባ​ሕር ዓሣ ሁሉ ቢሰ​በ​ሰብ ይበ​ቃ​ቸ​ዋ​ልን?” አለ።</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “በውኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ አት​ች​ል​ምን? አሁን ቃሌ ይፈ​ጸም ወይም አይ​ፈ​ጸም እንደ ሆነ እነሆ፥ አንተ ታያ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="24">ሙሴም ወጣ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃሎች ለሕ​ዝቡ ነገረ፤ ከሕ​ዝቡ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ሰባ​ውን ሰዎች ሰብ​ስቦ በድ​ን​ኳኑ ዙሪያ አቆ​ማ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በደ​መ​ናው ወረደ፤ ተና​ገ​ረ​ውም፤ በእ​ር​ሱም ላይ ከነ​በ​ረው መን​ፈስ ወስዶ በሰ​ባው ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ላይ አደ​ረገ፤ መን​ፈ​ሱም በላ​ያ​ቸው ባደረ ጊዜ ትን​ቢት ተና​ገሩ፤ ከዚያ በኋላ ግን አል​ተ​ጨ​መ​ረ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="26">ከእ​ነ​ር​ሱም ሁለት ሰዎች በሰ​ፈር ቀር​ተው ነበር፤ የአ​ን​ዱም ስም ኤል​ዳድ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ሞዳድ ነበረ፤ መን​ፈ​ስም ዐረ​ፈ​ባ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ከተ​ጻ​ፉት ጋር ነበሩ፤ ወደ ድን​ኳኑ ግን አል​ወ​ጡም ነበር፤ በሰ​ፈ​ሩም ውስጥ ትን​ቢት ተና​ገሩ።</verse>
				<verse number="27">አንድ ጐል​ማሳ ሰው እየ​ሮጠ መጥቶ፥ “ኤል​ዳ​ድና ሞዳድ በሰ​ፈር ትን​ቢት ይና​ገ​ራሉ” ብሎ ለሙሴ ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="28">የሙሴ ምርጥ ባለ​ሟል የነ​በ​ረው የነዌ ልጅ ኢያሱ፥ “ጌታዬ ሙሴ ሆይ ፥ ከል​ክ​ላ​ቸው” አለው።</verse>
				<verse number="29">ሙሴም “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ሁሉ ነቢ​ያት ቢሆኑ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ነ​ርሱ ላይ መን​ፈ​ሱን ቢያ​ሳ​ድር አንተ ስለ እኔ ትቀ​ና​ለ​ህን?” አለው።</verse>
				<verse number="30">ሙሴም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጋር ወደ ሰፈር ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="31">ነፋ​ስም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጣ፤ ከባ​ሕ​ርም ድር​ጭ​ቶ​ችን አወጣ፤ የአ​ንድ ቀንም መን​ገድ ያህል በዚህ፥ የአ​ንድ ቀንም መን​ገድ ያህል በዚያ በሰ​ፈሩ ላይ በተ​ና​ቸው፤ በዚ​ያም በሰ​ፈሩ ዙሪያ ከፍ​ታው ከም​ድር ወደ ላይ ሁለት ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="32">በዚ​ያም ቀን ሁሉ፥ በሌ​ሊ​ትም ሁሉ፥ በነ​ጋ​ውም ሁሉ ሕዝቡ ተነ​ሥ​ተው ድር​ጭ​ትን ሰበ​ሰቡ፤ ከሁሉ ጥቂት የሰ​በ​ሰበ ዐሥር የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ያህል ሰበ​ሰበ፤ በሰ​ፈ​ሩም ዙሪያ ሁሉ አስ​ጥ​ተው አደ​ረ​ቁት።</verse>
				<verse number="33">ሥጋ​ውም ገና በጥ​ር​ሳ​ቸው መካ​ከል ሳለ ሳያ​ኝ​ኩ​ትም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን እጅግ ታላቅ በሆነ መቅ​ሠ​ፍት አጠ​ፋ​ቸው።</verse>
				<verse number="34">የጐ​መጁ ሕዝብ በዚያ ተቀ​ብ​ረ​ዋ​ልና የዚያ ስፍራ ስም “መቃ​ብረ ፍት​ወት” ተብሎ ተጠራ።</verse>
				<verse number="35">ሕዝ​ቡም ከመ​ቃ​ብረ ፍት​ወት ወደ አሴ​ሮት ተጓዙ፤ በአ​ሴ​ሮ​ትም ተቀ​መጡ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">ሙሴም ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ዊ​ቱን ሴት አግ​ብ​ቶ​አ​ልና ባገ​ባት በኢ​ት​ዮ​ጵ​ያ​ዊቱ ሴት ምክ​ን​ያት ማር​ያ​ምና አሮን አሙት።</verse>
				<verse number="2">እነ​ር​ሱም፥ “በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ ብቻ ተና​ግ​ሮ​አ​ልን? በእ​ኛስ ደግሞ የተ​ና​ገረ አይ​ደ​ለ​ምን?” አሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማ።</verse>
				<verse number="3">ሙሴም በም​ድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ የዋህ ሰው ነበረ።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወዲ​ያው ሙሴ​ንና አሮ​ንን ማር​ያ​ም​ንም፥ “ሦስ​ታ​ችሁ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ኑ ብሎ ተና​ገረ፤ ሦስ​ቱም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ወጡ።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በደ​መና ዐምድ ወረደ፤ በም​ስ​ክ​ሩም ድን​ኳን ደጃፍ ቆመ፤ አሮ​ን​ንና ማር​ያ​ም​ንም ጠራ​ቸው፤ ሁለ​ቱም ወጡ።</verse>
				<verse number="6">እር​ሱም፥ “ቃሌን ስሙ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ የሆነ ቢኖር በራ​እይ እገ​ለ​ጥ​ለ​ታ​ለሁ፤ ወይም በሕ​ልም እና​ገ​ረ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">አገ​ል​ጋዬ ሙሴ ግን እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እርሱ በቤቴ ሁሉ የታ​መነ ነው።</verse>
				<verse number="8">እኔ አፍ ለአፍ በግ​ልጥ እና​ገ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በስ​ው​ርም አይ​ደ​ለም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ክብር ያያል፤ አገ​ል​ጋዬ ሙሴን ማማ​ትን ስለ ምን አል​ፈ​ራ​ች​ሁም?” አለ።</verse>
				<verse number="9">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ በእ​ነ​ርሱ ላይ ወረደ፤ እር​ሱም ሄደ።</verse>
				<verse number="10">ደመ​ና​ውም ከድ​ን​ኳኑ ተነሣ፤ እነ​ሆም፥ ማር​ያም ለም​ጻም ሆነች፤ እንደ በረ​ዶም ነጭ ሆነች፤ አሮ​ንም ማር​ያ​ምን ተመ​ለ​ከተ፤ እነ​ሆም፥ ለም​ጻም ሆና ነበር።</verse>
				<verse number="11">አሮ​ንም ሙሴን፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ስን​ፍና አድ​ር​ገ​ና​ልና፥ በድ​ለ​ን​ማ​ልና እባ​ክህ፥ ኀጢ​አት አታ​ድ​ር​ግ​ብን።</verse>
				<verse number="12">ከእ​ናቱ ማኅ​ፀን ሞቶ እንደ ተወ​ለደ፥ ከተ​በላ ግማሽ ሥጋዋ ጋር ለሞት አት​ተ​ዋት።”</verse>
				<verse number="13">ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እየ​ጮኸ፥ “አቤቱ፥ እባ​ክህ፥ አድ​ናት” አለው።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “አባቷ ምራ​ቁን በፊቷ ቢተ​ፋ​ባት ስንኳ ሰባት ቀን ታፍር ዘንድ ይገ​ባት ነበር፤ ሰባት ቀን ከሰ​ፈር ውጭ ተዘ​ግታ ትቀ​መጥ፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈር ትመ​ለስ” አለው።</verse>
				<verse number="15">ማር​ያ​ምም ከሰ​ፈር ውጭ ሰባት ቀን ተለ​ይታ ተቀ​መ​ጠች፤ ማር​ያ​ምም እስ​ክ​ት​ነጻ ድረስ ሕዝቡ አል​ተ​ጓ​ዙም።</verse>
				<verse number="16">ከዚ​ያም በኋላ ሕዝቡ ከአ​ሴ​ሮት ተጓዙ፤ በፋ​ራ​ንም ምድረ በዳ ሰፈሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“ይገ​ዙ​አት ዘንድ እኔ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የም​ሰ​ጣ​ትን የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር የሚ​ሰ​ልሉ ሰዎ​ችን ላክ፤ ከአ​ባ​ቶች ቤት ከእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ነገድ ሁሉ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አለቃ የሆነ አንድ አንድ ሰው ትል​ካ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="3">ሙሴም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ከፋ​ራን ምድረ በዳ ላካ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አለ​ቆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="4">ስማ​ቸ​ውም ይህ ነበረ፤ ከሮ​ቤል ነገድ የዝ​ኩር ልጅ ሰሙ​ኤል፤</verse>
				<verse number="5">ከስ​ም​ዖን ነገድ የሱሬ ልጅ ሰፈጥ ፤</verse>
				<verse number="6">ከይ​ሁዳ ነገድ የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ፤</verse>
				<verse number="7">ከይ​ሳ​ኮር ነገድ የዮ​ሴፍ ልጅ ኢጋል፤</verse>
				<verse number="8">ከኤ​ፍ​ሬም ነገድ የነዌ ልጅ አውሴ፤</verse>
				<verse number="9">ከብ​ን​ያም ነገድ የራፋ ልጅ ፈልጢ፤</verse>
				<verse number="10">ከዛ​ብ​ሎን ነገድ የሶዲ ልጅ ጉዲ​ኤል፤</verse>
				<verse number="11">ከዮ​ሴፍ ነገድ ከም​ናሴ ልጆች የሱሲ ልጅ ጋዲ፤</verse>
				<verse number="12">ከዳን ነገድ የገ​ማሊ ልጅ ዓሚ​ሄል፤</verse>
				<verse number="13">ከአ​ሴር ነገድ የሚ​ካ​ኤል ልጅ ሳቱር፤</verse>
				<verse number="14">ከን​ፍ​ታ​ሌም ነገድ የያቢ ልጅ ናቢ፤</verse>
				<verse number="15">ከጋድ ነገድ የማኪ ልጅ ጉዲ​ኤል።</verse>
				<verse number="16">ምድ​ሪ​ቱን ይሰ​ልሉ ዘንድ ሙሴ የላ​ካ​ቸው ሰዎች ስሞች እነ​ዚህ ናቸው። ሙሴም የነ​ዌን ልጅ አው​ሴን ኢያሱ ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="17">ሙሴም የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር ይሰ​ልሉ ዘንድ ላካ​ቸው፤ አላ​ቸ​ውም፥ “ከዚህ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ፥ ወደ ተራ​ሮ​ችም ውጡ።</verse>
				<verse number="18">ምድ​ሪ​ቱ​ንም እን​ዴት እንደ ሆነች፥ በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖሩ ሰዎች ብር​ቱ​ዎች ወይም ደካ​ሞች፥ ጥቂ​ቶች ወይም ብዙ​ዎች እንደ ሆኑ፥</verse>
				<verse number="19">የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም ምድር መል​ካም ወይም ክፉ፥ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸ​ውም ከተ​ሞች ቅጥር ያላ​ቸው ወይም የሌ​ላ​ቸው እንደ ሆኑ፥</verse>
				<verse number="20">ምድ​ሪ​ቱም ለም ወይም ጠፍ፥ ዛፍ ያለ​ባት ወይም የሌ​ለ​ባት እንደ ሆነች አይ​ታ​ችሁ፥ ከም​ድ​ሪቱ ፍሬ አምጡ፤” ወራ​ቱም ወይኑ አስ​ቀ​ድሞ ፍሬ የሚ​ያ​ፈ​ራ​በት ነበረ።</verse>
				<verse number="21">ወጡም፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ከጺን ምድረ በዳ በኤ​ማት ዳር እስ​ካ​ለ​ችው እስከ ረአብ ድረስ ሰለሉ።</verse>
				<verse number="22">ወደ ምድረ በዳም ወጡ፤ ወደ ኬብ​ሮ​ንም ደረሱ፤ በዚ​ያም የዔ​ናቅ ዘሮች አኪ​ማን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብ​ሮ​ንም በግ​ብፅ ካለ​ችው ከጣ​ኔ​ዎስ ከተማ በፊት ሰባት ዓመ​ታት ተሠ​ርታ ነበር።</verse>
				<verse number="23">ወደ ወይን ዘለላ ሸለ​ቆም መጡ፤ አዩ​ኣ​ትም፤ ከዚ​ያም ከወ​ይኑ አንድ ዘለላ የነ​በ​ረ​በ​ትን አረግ ቈረጡ፤ በመ​ሎ​ጊ​ያም ተሸ​ከ​ሙት፤ ደግ​ሞም ከሮ​ማኑ ከበ​ለ​ሱም አመጡ።</verse>
				<verse number="24">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከዚያ ስለ ቈረ​ጡት ዘለላ የዚ​ያን ስፍራ ስም የወ​ይን ዘለላ ሸለቆ ብለው ጠሩት።</verse>
				<verse number="25">ምድ​ሪ​ቱ​ንም ሰል​ለው ከአ​ርባ ቀን በኋላ ከዚያ ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="26">ገሥ​ግ​ሠ​ውም በቃ​ዴስ ፋራን ምድረ በዳ ወዳ​ሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ደረሱ፤ ወሬ​ው​ንም ለእ​ነ​ር​ሱና ለማ​ኅ​በሩ ሁሉ ነገ​ሩ​አ​ቸው፤ የም​ድ​ሪ​ቱ​ንም ፍሬ አሳ​ዩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="27">እን​ዲ​ህም ብለው ነገ​ሩት፥ “ወደ ላክ​ኸን ምድር ደረ​ስን፤ እር​ስ​ዋም ወተ​ትና ማር ታፈ​ስ​ሳ​ለች፤ ፍሬ​ዋም ይህ ነው።</verse>
				<verse number="28">ነገር ግን በም​ድ​ሪቱ የሚ​ኖሩ ሰዎች ኀያ​ላን ናቸው፤ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም የተ​መ​ሸጉ፥ እጅ​ግም የጸኑ ታላ​ላቅ ናቸው።</verse>
				<verse number="29">ደግ​ሞም በዚያ የዔ​ና​ቅን ዘሮች አየን፤ በአ​ዜብ በኩል ዐማ​ሌቅ ተቀ​ም​ጦ​አል፤ በተ​ራ​ሮ​ች​ዋም ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ውና ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ውም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊው፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ውም ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ውም በባ​ሕር ዳርና በዮ​ር​ዳ​ኖስ ወንዝ አጠ​ገብ ተቀ​ም​ጦ​አል።”</verse>
				<verse number="30">ካሌ​ብም ሕዝ​ቡን በሙሴ ፊት ዝም አሰ​ኘና፥ “አይ​ደ​ለም! ማሸ​ነ​ፍን እን​ች​ላ​ለ​ንና እን​ውጣ፤ እን​ው​ረ​ሳት” አለ።</verse>
				<verse number="31">ከእ​ርሱ ጋር የወጡ ሰዎች ግን ፥ “በኀ​ይል ከእኛ ይበ​ረ​ታ​ሉና በዚህ ሕዝብ ላይ መው​ጣት አን​ች​ልም” አሉ።</verse>
				<verse number="32">ስለ ሰለ​ሉ​አ​ትም ምድር ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እያ​ወሩ፥ “እኛ ዞረን የሰ​ለ​ል​ናት ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትን ሰዎች የም​ት​በላ ምድር ናት፤ በእ​ር​ስ​ዋም ዘንድ ያየ​ና​ቸው ሰዎች ሁሉ ረጃ​ጅም ሰዎች ናቸው፤</verse>
				<verse number="33">በዚ​ያም ግዙ​ፋን የሆ​ኑ​ትን አየን፤ እኛም በእ​ነ​ርሱ ፊት እንደ አን​በ​ጣ​ዎች ሆን፤ እን​ዲ​ሁም በፊ​ታ​ቸው ነበ​ርን፤” እያሉ የሰ​ለ​ሉ​አ​ትን ምድር ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አስ​ፈሪ አደ​ረ​ጓት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">ማኅ​በ​ሩም ሁሉ ድም​ፃ​ቸ​ውን አን​ስ​ተው ጮኹ፤ ሕዝ​ቡም ሌሊ​ቱን ሁሉ አለ​ቀሱ።</verse>
				<verse number="2">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ አጕ​ረ​መ​ረሙ፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ፥ “በዚህ ምድረ በዳ ከም​ን​ሞት በግ​ብፅ ምድር ሳለን ብን​ሞት በተ​ሻ​ለን ነበር።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጦ​ር​ነት እን​ሞት ዘንድ ወደ​ዚች ምድር ለምን ያገ​ባ​ናል? ሴቶ​ቻ​ች​ንና ልጆ​ቻ​ችን ለን​ጥ​ቂያ ይሆ​ናሉ፤ አሁ​ንም ወደ ግብፅ መመ​ለስ አይ​ሻ​ለ​ን​ምን?” አሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ኑ፥ አለቃ ሾመን ወደ ግብፅ እን​መ​ለስ” ተባ​ባሉ።</verse>
				<verse number="5">ሙሴና አሮ​ንም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጉባኤ ፊት በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወደቁ።</verse>
				<verse number="6">ምድ​ሪ​ቱን ከሰ​ለ​ሉት ጋር የነ​በ​ሩት የነዌ ልጅ ኢያ​ሱና የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀደዱ፤</verse>
				<verse number="7">ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ “የሰ​ለ​ል​ናት ምድር እጅግ በጣም መል​ካም ናት።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ከመ​ረ​ጠን ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ወደ​ዚች ምድር ያገ​ባ​ናል፤ እር​ስ​ዋ​ንም ይሰ​ጠ​ናል።</verse>
				<verse number="9">ነገር ግን እና​ንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ አታ​ምፁ፤ እኛ እና​ጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለ​ንና የም​ድ​ሪ​ቱን ሰዎች አት​ፍሩ፤ ጊዜ​አ​ቸው አል​ፎ​ባ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእኛ ጋር ነው፤ አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው” ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">ማኅ​በሩ ሁሉ ግን “በድ​ን​ጋይ እን​ው​ገ​ራ​ቸው” አሉ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ተገ​ለጠ።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “እኒህ ሕዝብ እስከ መቼ ያስ​ቈ​ጡ​ኛል? በፊ​ታ​ቸ​ውስ ባደ​ረ​ግ​ሁት ተአ​ም​ራት ሁሉ እስከ መቼ አያ​ም​ኑ​ብ​ኝም?</verse>
				<verse number="12">በሞት እቀ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም፤ አን​ተ​ንና የአ​ባ​ት​ህን ቤት ግን ለታ​ላ​ቅና ከዚህ ለሚ​በዛ ሕዝብ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="13">ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ግብ​ፃ​ው​ያን ይሰ​ማሉ፤ እኒ​ህን ሕዝብ ከእ​ነ​ርሱ በኀ​ይ​ልህ አው​ጥ​ተ​ኻ​ቸ​ዋ​ልና፤</verse>
				<verse number="14">የዚ​ያች ምድር ሰዎች፥ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ሕዝ​ብህ መካ​ከል እንደ ሆንህ ሰም​ተ​ዋል፤ አን​ተም፥ አቤቱ፥ ዐይን በዐ​ይን እን​ደ​ሚ​ተ​ያይ ተገ​ል​ጠ​ህ​ላ​ቸ​ዋል። ደመ​ና​ህም በላ​ያ​ቸው ቆመች። በቀ​ንም በደ​መና ዐምድ ፥ በሌ​ሊ​ትም በእ​ሳት ዐምድ በፊ​ታ​ቸው ትሄ​ዳ​ለህ።</verse>
				<verse number="15">እኒ​ህን ሕዝብ እንደ አንድ ሰው ብት​ገ​ድል ስም​ህን የሰሙ አሕ​ዛብ፦</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ‘እነ​ዚ​ህን ሕዝብ ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ያገ​ባ​ቸው ዘንድ አል​ቻ​ለ​ምና በም​ድረ በዳ ገደ​ላ​ቸው’ ብለው ይና​ገ​ራሉ።</verse>
				<verse number="17">አሁ​ንም አቤቱ፥ ኀይ​ልህ ይገ​ለጥ፤ እን​ዲህ ብለህ እንደ ተና​ገ​ርህ፦</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓቱ የራቀ ምሕ​ረቱ የበዛ ጻድቅ፥ አበ​ሳን፥ መተ​ላ​ለ​ፍ​ንና ኀጢ​አ​ትን ይቅር የሚል፥ ኀጢ​አ​ተ​ኞ​ች​ንም ከቶ የማ​ያ​ነጻ፥ የአ​ባ​ቶ​ችን ኀጢ​አት እስከ ሦስ​ትና አራት ትው​ልድ ድረስ በል​ጆች ላይ የሚ​ያ​መጣ ነው።</verse>
				<verse number="19">እነ​ዚ​ህን ሕዝብ ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ይቅር እን​ዳ​ል​ሃ​ቸው፥ እንደ ምሕ​ረ​ትህ ብዛት የእ​ነ​ዚ​ህን ሕዝብ ኀጢ​አት ይቅር በል።”</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እንደ ቃልህ ይቅር አልሁ፤</verse>
				<verse number="21">ነገር ግን እኔ ሕያው ነኝ፤ ስሜም ሕያው ነው፤ በእ​ው​ነት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ምድ​ርን ሁሉ ይሞ​ላል።</verse>
				<verse number="22">በግ​ብፅ ምድ​ርና በም​ድረ በዳ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ተአ​ም​ራ​ቴ​ንና ክብ​ሬን ያዩ እነ​ዚህ ሰዎች ሁሉ ዐሥር ጊዜ ስለ ተፈ​ታ​ተ​ኑኝ፥ ቃሌ​ንም ስላ​ል​ሰሙ፥</verse>
				<verse number="23">በእ​ው​ነት ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው የማ​ል​ሁ​ላ​ቸ​ውን ምድር አያ​ዩም፤ ከእኔ ጋር በዚህ ላሉ መል​ካ​ም​ንና ክፉን ለይ​ተው ለማ​ያ​ውቁ ልጆ​ቻ​ቸው፥ የሚ​ያ​ው​ቀው ለሌለ ለታ​ናሹ ሁሉ ያችን ሀገር እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ለጥ​ፋት ያነ​ሳ​ሱኝ ሁሉ አያ​ዩ​አ​ትም።</verse>
				<verse number="24">ወዳጄ ካሌብ ግን ሌላ መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ ስለ ሆነና ስለ ተከ​ተ​ለኝ እርሱ ወደ ገባ​ባት ምድር አገ​ባ​ዋ​ለሁ፤ ዘሩም ይወ​ር​ሳ​ታል።</verse>
				<verse number="25">ዐማ​ሌ​ቅና ከነ​ዓ​ና​ዊ​ውም በሸ​ለቆ ውስጥ ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ እና​ንተ ግን ነገ ተመ​ል​ሳ​ችሁ በኤ​ር​ትራ ባሕር መን​ገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።”</verse>
				<verse number="26">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦</verse>
				<verse number="27">“የሚ​ያ​ጕ​ረ​መ​ር​ሙ​ብ​ኝን እኒ​ህን ክፉ ማኅ​በር እስከ መቼ እታ​ገ​ሣ​ቸ​ዋ​ለሁ? ስለ እና​ንተ በእኔ ላይ የሚ​ያ​ጕ​ረ​መ​ር​ሙ​ትን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማጕ​ረ​ም​ረ​ምን ሰማሁ።</verse>
				<verse number="28">እን​ዲህ በላ​ቸው፦ እኔ ሕያው ነኝና በጆ​ሮዬ እንደ ተና​ገ​ራ​ች​ሁት እን​ዲሁ በእ​ው​ነት አደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="29">በድ​ኖ​ቻ​ችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወ​ድ​ቃሉ፤ የተ​ቈ​ጠ​ራ​ችሁ ሁሉ፥ እንደ ቍጥ​ራ​ችሁ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ የሆነ ሁሉ፥ እና​ንተ ያጕ​ረ​መ​ረ​ማ​ች​ሁ​ብኝ፥</verse>
				<verse number="30">ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌ​ብና ከነዌ ልጅ ከኢ​ያሱ በቀር በእ​ር​ስዋ አስ​ቀ​ም​ጣ​ችሁ ዘንድ እጄን ዘር​ግቼ ወደ ማል​ሁ​ላ​ችሁ ምድር በእ​ው​ነት እና​ንተ አት​ገ​ቡም።</verse>
				<verse number="31">ንጥ​ቂያ ይሆ​ናሉ ያላ​ች​ኋ​ቸ​ውን ልጆ​ቻ​ች​ሁን እነ​ር​ሱን አገ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም የና​ቃ​ች​ኋ​ትን ምድር ይወ​ር​ሷ​ታል።</verse>
				<verse number="32">የእ​ና​ንተ ግን በድ​ኖ​ቻ​ችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወ​ድ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="33">ልጆ​ቻ​ች​ሁም በም​ድረ በዳ አርባ ዓመት ይቅ​በ​ዘ​በ​ዛሉ፤ በድ​ኖ​ቻ​ች​ሁም በም​ድረ በዳ እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ ግል​ሙ​ት​ና​ች​ሁን ይሸ​ከ​ማሉ።</verse>
				<verse number="34">ምድ​ሪ​ቱን እንደ ሰለ​ሉ​ባ​ቸው እንደ እነ​ዚያ አርባ ቀኖች ቍጥር ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ ሁሉ አር​ባው ቀን አርባ ዓመት፥ አንዱ ቀንም አንድ ዓመት ይሁ​ን​ባ​ችሁ፤ እን​ግ​ዲህ የቍ​ጣ​ዬን መቅ​ሠ​ፍት ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="35">እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በእኔ ላይ በተ​ሰ​በ​ሰበ በዚህ ክፉ ማኅ​በር ሁሉ ላይ እን​ዲህ አደ​ር​ጋ​ለሁ ብዬ ተና​ገ​ርሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ ያል​ቃሉ፤ በዚ​ያም ይሞ​ታሉ።”</verse>
				<verse number="36">ምድ​ሪ​ቱ​ንም ሊሰ​ልሉ ሙሴ ልኮ​አ​ቸው የተ​መ​ለ​ሱት ሰዎች ስለ እር​ስዋ በማ​ኅ​በሩ ሁሉ ፊት አጕ​ረ​መ​ረሙ።</verse>
				<verse number="37">ስለ​ዚ​ያ​ችም ምድር ክፉን ነገር ተና​ገሩ፤ ስለ​ዚ​ያ​ችም ምድር ክፉ የተ​ና​ገሩ እነ​ዚያ ሰዎች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመ​ቅ​ሠ​ፍት ሞቱ፤ ምድ​ሪቱ ግን መል​ካም ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="38">ነገር ግን ምድ​ሪ​ቱን ሊሰ​ልሉ ከሄዱ ሰዎች የነዌ ልጅ ኢያ​ሱና የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ በሕ​ይ​ወት ኖሩ።</verse>
				<verse number="39">ሙሴም ይህን ነገር ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ነገረ። ሕዝ​ቡም እጅግ አዘኑ፤</verse>
				<verse number="40">በነ​ጋ​ውም ማል​ደው ተነሡ፤ ወደ ተራ​ራ​ውም ራስ ወጥ​ተው፥ “እነሆ፥ እኛ ከዚህ አለን፤ በድ​ለ​ና​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለው ስፍራ እን​ወ​ጣ​ለን” አሉ።</verse>
				<verse number="41">ሙሴም አለ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ለምን ትተ​ላ​ለ​ፋ​ላ​ችሁ? ይህ ለእ​ና​ንተ መል​ካም አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="42">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር አይ​ደ​ለ​ምና በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ፊት እን​ዳ​ት​ወ​ድቁ አት​ውጡ።</verse>
				<verse number="43">ዐማ​ሌ​ቃ​ዊና ከነ​ዓ​ናዊ በፊ​ታ​ችሁ ናቸ​ውና በሰ​ይፍ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ከ​ተል ተመ​ል​ሳ​ች​ኋ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር አይ​ሆ​ንም።”</verse>
				<verse number="44">እነ​ርሱ ግን ተደ​ፋ​ፍ​ረው ወደ ተራ​ራው ራስ ወጡ፤ ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦ​ትና ሙሴ ከሰ​ፈሩ አል​ተ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱም።</verse>
				<verse number="45">በዚ​ያም ተራራ ላይ የተ​ቀ​መጡ ዐማ​ሌ​ቃ​ዊና ከነ​ዓ​ናዊ ወረዱ፤ መት​ተ​ዋ​ቸ​ውም እስከ ኤርማ ድረስ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው። ወደ ከተ​ማም ተመ​ለሱ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ወደ​ም​ሰ​ጣ​ችሁ ወደ መኖ​ሪ​ያ​ችሁ ምድር በገ​ባ​ችሁ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="3">በፈ​ቃ​ዳ​ች​ሁም ቢሆን በበ​ዓ​ላ​ች​ሁም ቢሆን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ይሆን ዘንድ ስእ​ለ​ቱን አብ​ዝ​ታ​ችሁ በአ​መ​ጣ​ችሁ ጊዜ ከላም ወይም ከበግ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ወይም መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆን የእ​ሳት ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ርቡ።</verse>
				<verse number="4">ቍር​ባ​ኑን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ርብ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ በሆነ ዘይት የተ​ለ​ወሰ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ እጅ የሆነ የመ​ል​ካም ዱቄት መሥ​ዋ​ዕት ያመ​ጣል።</verse>
				<verse number="5">ለመ​ጠጥ ቍር​ባ​ንም የኢን መስ​ፈ​ሪያ የሆነ መል​ካም ዱቄት አራ​ተኛ እጅ በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ወይም በእ​ህሉ ቍር​ባን ላይ ያደ​ር​ጋል፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ጠቦት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው መሥ​ዋ​ዕት ይሆን ዘንድ ይህን ያህል ያድ​ርግ።</verse>
				<verse number="6">ለአ​ን​ዱም አውራ በግ የሚ​ቃ​ጠል ቍር​ባን ወይም መሥ​ዋ​ዕት ባደ​ረ​ጋ​ችሁ ጊዜ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ሢሶ በሆነ ዘይት የተ​ለ​ወሰ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ መል​ካም ዱቄት ለእ​ህል ቍር​ባን ታዘ​ጋ​ጃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="7">ለመ​ጠጥ ቍር​ባ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የኢን መስ​ፈ​ሪያ ሦስ​ተኛ እጅ ወይን ታቀ​ር​ባ​ለህ።</verse>
				<verse number="8">ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም ለሌላ መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም ስእ​ለ​ትን ለመ​ፈ​ጸም፥ ወይም ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ከላም ወገን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብታ​ዘ​ጋጅ፥</verse>
				<verse number="9">በላሙ ላይ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ግማሽ በሆነ ዘይት የተ​ለ​ወሰ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ መል​ካም ዱቄት ለእ​ህል ቍር​ባን ታቀ​ር​ባ​ለህ።</verse>
				<verse number="10">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በእ​ሳት ለተ​ደ​ረገ ቍር​ባን፥ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ግማሽ ወይን ለመ​ጠጥ ቍር​ባን ታቀ​ር​ባ​ለህ።</verse>
				<verse number="11">“እን​ዲሁ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ወይ​ፈን፥ ወይም ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አውራ በግ፥ ወይም ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ተባት የበግ ወይም የፍ​የል ጠቦት ይደ​ረ​ጋል።</verse>
				<verse number="12">እን​ዳ​ዘ​ጋ​ጃ​ች​ሁት ቍጥር፥ እን​ዲሁ እንደ ቍጥ​ራ​ቸው ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="13">የሀ​ገር ልጅ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ቍር​ባን ባቀ​ረበ ጊዜ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋል።</verse>
				<verse number="14">መጻ​ተ​ኛም ከእ​ና​ንተ ጋር ቢቀ​መጥ፥ ወይም በት​ው​ል​ዳ​ችሁ መካ​ከል ማንም ሰው ቢኖር፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ቍር​ባን በእ​ሳት ቢያ​ቀ​ርብ እና​ንተ የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን እርሱ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋል።</verse>
				<verse number="15">ለእ​ና​ንተ፥ በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል ለሚ​ኖሩ መጻ​ተ​ኞች አንድ ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤ እና​ንተ እንደ ሆና​ችሁ እን​ዲሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መጻ​ተኛ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="16">ለእ​ና​ን​ተና ከእ​ና​ንተ ጋር ለሚ​ኖር መጻ​ተኛ አንድ ሕግና አንድ ፍርድ ይሆ​ናል።”</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ፤ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="18">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፤</verse>
				<verse number="19">ወደ​ማ​መ​ጣ​ችሁ ምድር በገ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ እና​ንተ የም​ድ​ሪ​ቱን እን​ጀራ በበ​ላ​ችሁ ጊዜ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለየ ቍር​ባን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="20">መጀ​መ​ሪያ ከም​ታ​ደ​ር​ጉት ሊጥ አንድ እን​ጎቻ ለይ​ታ​ችሁ ቍር​ባን ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ከአ​ው​ድ​ማ​ውም እን​ደ​ም​ት​ለ​ዩት ቍር​ባን እን​ዲሁ ትለ​ያ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="21">መጀ​መ​ሪ​ያም ከም​ታ​ደ​ር​ጉት ሊጥ የተ​ለየ ቍር​ባን እስከ ልጅ ልጃ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="22">“ብት​በ​ድ​ሉም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ ያዘ​ዛ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ህን ትእ​ዛ​ዛት ሁሉ ባታ​ደ​ርጉ፥</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካዘ​ዘ​በት ከፊ​ተ​ኛው ቀን ጀምሮ ወደ ፊትም እስከ ልጅ ልጃ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ እንደ አዘ​ዛ​ችሁ ባታ​ደ​ርጉ፥</verse>
				<verse number="24">በማ​ኅ​በ​ሩም ፊት ያል​ታ​ወቀ ኀጢ​አት ቢኖር፥ ማኅ​በሩ ሁሉ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ከመ​ን​ጋ​ዎች አንድ ንጹሕ ወይ​ፈን ያቀ​ር​ባሉ። የእ​ህሉ ቍር​ባ​ንና የመ​ጠጡ ቍር​ባ​ንም እንደ ሕጉ ነው፤ ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል ያቀ​ር​ባሉ።</verse>
				<verse number="25">ካህ​ኑም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ቸ​ዋል፤ ባለ​ማ​ወቅ ነበ​ርና ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ዋል፤ እነ​ር​ሱም ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውና ስላ​ለ​ማ​ወ​ቃ​ቸው ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንና መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ር​ባሉ።</verse>
				<verse number="26">በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ዘንድ ያለ ዕው​ቀት ተደ​ር​ጎ​አ​ልና ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ወደ እና​ን​ተም ለሚ​መጣ መጻ​ተኛ ስር​የት ይደ​ረ​ግ​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="27">“አንድ ሰው ሳያ​ውቅ ኀጢ​አት ቢሠራ፥ ስለ ኀጢ​አት አን​ዲት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት ፍየል ያቀ​ር​ባል።</verse>
				<verse number="28">ካህ​ኑም ባለ​ማ​ወቅ ስለ በደ​ለው ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ባለ​ማ​ወ​ቅም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ኀጢ​አት ስለ ሠራው ሰው ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="29">ትው​ልዱ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ቢሆን፥ ወይም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው የሚ​ኖር መጻ​ተኛ ቢሆን፥ ሳያ​ውቅ ኀጢ​አ​ትን ለሚ​ሠራ ሁሉ ሕጉ አንድ ይሆ​ን​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="30">የሀ​ገር ልጅ ቢሆ​ንም ወይም መጻ​ተኛ ቢሆን፥ በእጁ ትዕ​ቢ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰድ​ቦ​አል፤ ያም ሰው ከሕ​ዝቡ መካ​ከል ተለ​ይቶ ይጠ​ፋል።</verse>
				<verse number="31">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስለ​ናቀ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ስለ ሰበረ፥ ያ ሰው ፈጽሞ ይጥፋ፤ ኀጢ​አቱ በራሱ ላይ ነው።”</verse>
				<verse number="32">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በም​ድረ በዳ ነበሩ፤ አንድ ሰውም በሰ​ን​በት ቀን ዕን​ጨት ሲለ​ቅም አገኙ።</verse>
				<verse number="33">በሰ​ን​በት ቀን ዕን​ጨት ሲለ​ቅም ያገ​ኙ​ትም ሰዎች ወደ ሙሴና ወደ አሮን፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ አመ​ጡት።</verse>
				<verse number="34">እን​ዴት እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጉት አል​ፈ​ረ​ዱ​ምና በግ​ዞት ቤት አዋ​ሉት።</verse>
				<verse number="35">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “ሰው​ዬው ይገ​ደል፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ይው​ገ​ሩት” አለው።</verse>
				<verse number="36">ማኅ​በ​ሩም ሁሉ ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ አወ​ጡት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው በድ​ን​ጋይ ወገ​ሩት።</verse>
				<verse number="37">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="38">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ በላ​ቸው፦ እነ​ር​ሱም በት​ው​ል​ዳ​ቸው ሁሉ በል​ብ​ሳ​ቸው ጫፍ ዘርፍ ያደ​ርጉ ዘንድ፥ በዘ​ር​ፉም ሁሉ ላይ ሰማ​ያዊ ፈትል ያደ​ርጉ ዘንድ እዘ​ዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="39">እር​ሱም በዘ​ርፉ ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ትመ​ለ​ከ​ቱ​ታ​ላ​ች​ሁም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ትእ​ዛ​ዛት ታስ​ባ​ላ​ችሁ፤ ታደ​ር​ጉ​አ​ቸ​ው​ማ​ላ​ችሁ፤ እነ​ር​ሱን በመ​ከ​ተል ያመ​ነ​ዘ​ራ​ች​ሁ​ባ​ትን የሕ​ሊ​ና​ች​ሁ​ንና የዐ​ይ​ኖ​ቻ​ች​ሁን ፈቃድ አት​ከ​ተሉ።</verse>
				<verse number="40">ትእ​ዛ​ዙን ታስ​ቡና ታደ​ርጉ ዘንድ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም ቅዱ​ሳን ትሆኑ ዘንድ፤</verse>
				<verse number="41">እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ፤ አም​ላክ እሆ​ና​ችሁ ዘንድ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኋ​ችሁ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">የሌ​ዊም ልጅ የቀ​ዓት ልጅ የይ​ስ​ዓር ልጅ ቆሬ ከኤ​ል​ያብ ልጆች ከዳ​ታ​ንና ከአ​ቤ​ሮን፥ ከሮ​ቤ​ልም ልጅ ከፋ​ሌት ልጅ ከአ​ው​ናን ጋር ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="2">በሙ​ሴም ላይ ተነሡ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በም​ክር የተ​መ​ረጡ፥ ዝና​ቸ​ውም የተ​ሰማ ሁለት መቶ አምሳ የማ​ኅ​በሩ አለ​ቆች ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበሩ።</verse>
				<verse number="3">በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ ተነሡ፤ “ለእ​ና​ንተ ይበ​ቃ​ች​ኋል፤ ማኅ​በሩ ሁሉ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ቅዱ​ሳን ናቸ​ውና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ነውና፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ጉባኤ ላይ ለምን ትታ​በ​ያ​ላ​ችሁ?” አሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ሙሴም በሰማ ጊዜ በግ​ን​ባሩ ወደቀ።</verse>
				<verse number="5">ለቆ​ሬም ለማ​ኅ​በ​ሩም ሁሉ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ነገ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ርሱ የሚ​ሆ​ኑ​ትን፥ ቅዱ​ሳ​ንም የሆ​ኑ​ትን ያያል፥ ያው​ቃ​ልም፤ የመ​ረ​ጣ​ቸ​ው​ንም ሰዎች ወደ እርሱ ያቀ​ር​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">እን​ዲሁ አድ​ርጉ፤ ቆሬና ማኅ​በሩ ሁሉ፥ ጥና​ዎ​ቹን ውሰዱ፤</verse>
				<verse number="7">ነገም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እሳት አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ ዕጣ​ንም ጨም​ሩ​ባ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​መ​ር​ጠው ይህ ሰው ለሌዊ ልጆች ቅዱስ ይሁ​ን​ላ​ቸው።”</verse>
				<verse number="8">ሙሴም ቆሬን አለው፥ “እና​ንተ የሌዊ ልጆች፥ ስሙኝ፤</verse>
				<verse number="9">የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ከእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ለይቶ የመ​ረ​ጣ​ች​ሁን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ትሠሩ ዘንድ፥ እን​ድ​ታ​ገ​ለ​ግ​ሉ​አ​ቸ​ውም በማ​ኅ​በሩ ፊት ትቆሙ ዘንድ ወደ እርሱ ያቀ​ረ​ባ​ች​ሁን ታሳ​ን​ሱ​ታ​ላ​ች​ሁን?</verse>
				<verse number="10">አን​ተን ከአ​ን​ተም ጋር የሌ​ዊን ልጆች ወን​ድ​ሞ​ች​ህን ሁሉ ወደ እርሱ አቅ​ር​ቦ​አል፤ ካህ​ና​ትም ትሆኑ ዘንድ ትፈ​ል​ጋ​ላ​ች​ሁን?</verse>
				<verse number="11">ስለ​ዚ​ህም አን​ተና ማኅ​በ​ርህ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ተሰ​ብ​ስ​ባ​ች​ኋል፤ በእ​ር​ሱም ላይ ታጕ​ረ​መ​ርሙ ዘንድ አሮን ማን​ነው?”</verse>
				<verse number="12">ሙሴም የኤ​ል​ያ​ብን ልጆች ዳታ​ን​ንና አቤ​ሮ​ንን እን​ዲ​ጠ​ሩ​አ​ቸው ላከ፤ እነ​ር​ሱም፥ “አን​መ​ጣም፤</verse>
				<verse number="13">በም​ድረ በዳ ትገ​ድ​ለን ዘንድ፥ በእ​ኛም ላይ አለ​ቃ​ችን ትሆን ዘንድ ወተ​ትና ማር ከም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ምድር ያወ​ጣ​ኸን አነ​ሰ​ህን?</verse>
				<verse number="14">አንተ አለቃ ነህን? ደግ​ሞስ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስስ ምድር አገ​ባ​ኸ​ንን? እር​ሻ​ንና የወ​ይን ቦታ​ንስ አወ​ረ​ስ​ኸ​ንን? የእ​ነ​ዚ​ህ​ንስ ሰዎች ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ታወ​ጣ​ለ​ህን? አን​መ​ጣም” አሉ።</verse>
				<verse number="15">ሙሴም እጅግ አዘነ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አለው፥ “ወደ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸው አት​መ​ል​ከት፤ እኔ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዳ​ችም ተመ​ኝቼ አል​ወ​ሰ​ድ​ሁም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ሰው አል​በ​ደ​ል​ሁም።”</verse>
				<verse number="16">ሙሴም ቆሬን አለው፥ “ማኅ​በ​ር​ህን ለይ፤ ነገ አንተ፥ ማኅ​በ​ር​ህም ሁሉ፥ አሮ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዝግ​ጁ​ዎች ሁኑ።</verse>
				<verse number="17">ሁላ​ች​ሁም ጥና​ዎ​ቻ​ች​ሁን ውሰዱ፤ ዕጣ​ንም አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም ሁለት መቶ አምሳ ጥና​ዎ​ቻ​ች​ሁን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አምጡ፤ አንተ ደግሞ አሮ​ንም ጥና​ዎ​ቻ​ች​ሁን አምጡ” አለው።</verse>
				<verse number="18">እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ጥና​ውን ወሰደ፤ እሳ​ትም አደ​ረ​ገ​በት፤ ዕጣ​ንም ጨመ​ረ​በት፤ ሙሴና አሮ​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ቆሙ።</verse>
				<verse number="19">ቆሬም ማኅ​በ​ሩን ሁሉ ወደ ምስ​ክሩ ደጃፍ በእ​ነ​ርሱ ላይ ሰበ​ሰበ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ለማ​ኅ​በሩ ሁሉ ተገ​ለጠ።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦</verse>
				<verse number="21">“ሁሉን በቅ​ጽ​በት አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ከዚህ ማኅ​በር መካ​ከል ፈቀቅ በሉ።”</verse>
				<verse number="22">እነ​ር​ሱም በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወድ​ቀው፥ “የነ​ፍ​ስና የሥጋ ሁሉ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ አንድ ሰው ኀጢ​አት ቢሠራ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በማ​ኅ​በሩ ላይ ይሆ​ና​ልን?” አሉ።</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="24">“ለማ​ኅ​በሩ፦ ከቆሬ ማኅ​በር ዙሪያ ፈቀቅ በሉ ብለህ ንገ​ራ​ቸው።”</verse>
				<verse number="25">ሙሴም ተነ​ሥቶ ወደ ዳታ​ንና ወደ አቤ​ሮን ሄደ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ሄዱ።</verse>
				<verse number="26">ማኅ​በ​ሩ​ንም፥ “ከእ​ነ​ዚህ ክፉ​ዎች ሰዎች ድን​ኳን ፈቀቅ በሉ፤ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ እን​ዳ​ት​ጠፉ ለእ​ነ​ርሱ የሆ​ነ​ውን ሁሉ አት​ንኩ” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="27">ከቆሬ ድን​ኳን ዙሪ​ያም ሁሉ ፈቀቅ አሉ፤ ዳታ​ንና አቤ​ሮ​ንም ከሴ​ቶ​ቻ​ቸው፥ ከል​ጆ​ቻ​ቸ​ውና ከጓ​ዛ​ቸው ጋር ወጥ​ተው በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸው ደጃፍ ቆሙ።</verse>
				<verse number="28">ሙሴም አለ፥ “ይህን ሥራ ሁሉ አደ​ርግ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ላከኝ እንጂ ከልቤ እን​ዳ​ይ​ደለ በዚህ ታው​ቃ​ላ​ቸሁ።</verse>
				<verse number="29">እነ​ዚህ ሰዎች ሰው እን​ደ​ሚ​ሞት ቢሞቱ፥ ወይም መቅ​ሠ​ፍ​ታ​ቸው እንደ ሰው ሁሉ መቅ​ሠ​ፍት ቢሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ላ​ከ​ኝም።</verse>
				<verse number="30">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን አዲስ ነገር ቢፈ​ጥር፥ ምድ​ርም አፍ​ዋን ከፍታ እነ​ር​ሱን፥ ቤታ​ቸ​ውን፥ ድን​ኳ​ና​ቸ​ውን፥ ለእ​ነ​ር​ሱም ያለ​ውን ሁሉ ብት​ው​ጣ​ቸው፥ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸ​ውም ወደ ሲኦል ቢወ​ርዱ፥ ያን​ጊዜ እነ​ዚህ ሰዎች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ አስ​ቈጡ ታው​ቃ​ላ​ቸሁ።”</verse>
				<verse number="31">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ይህን ቃል ሁሉ መና​ገር በፈ​ጸመ ጊዜ ከበ​ታ​ቻ​ቸው ያለ​ችው መሬት ተሰ​ነ​ጠ​ቀች፤</verse>
				<verse number="32">ምድ​ሪ​ቱም አፍ​ዋን ከፍታ እነ​ር​ሱን፥ ቤተ ሰቦ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ለቆ​ሬም የነ​በ​ሩ​ትን ሰዎች ሁሉ፥ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ዋጠ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="33">እነ​ር​ሱም፥ ለእ​ነ​ር​ሱም የነ​በሩ ሁሉ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው ወደ ሲኦል ወረዱ፤ ምድ​ሪ​ቱም ተዘ​ጋ​ች​ባ​ቸው፤ ከማ​ኅ​በ​ሩም መካ​ከል ጠፉ።</verse>
				<verse number="34">በዙ​ሪ​ያ​ቸው የነ​በሩ የእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ከጩ​ኸ​ታ​ቸው የተ​ነሣ፥ “ምድ​ሪቱ እን​ዳ​ት​ው​ጠን” ብለው ሸሹ።</verse>
				<verse number="35">እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጥታ ያጥኑ የነ​በ​ሩ​ትን ሁለት መቶ አምሳ ሰዎች በላች።</verse>
				<verse number="36">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው።</verse>
				<verse number="37">ለካ​ህኑ ለአ​ሮን ልጅ ለአ​ል​ዓ​ዛር እን​ዲህ ብለህ ንገ​ረው፥ “ከተ​ቃ​ጠ​ሉት ሰዎች መካ​ከል የናስ የሚ​ሆኑ ጥና​ዎ​ችን አውጣ፤ ከሌላ ያመ​ጡ​ትን ያንም እሳት ወዲያ ጣል፤</verse>
				<verse number="38">የእ​ነ​ዚህ ኃጥ​ኣን ጥና​ዎ​ቻ​ቸው በሰ​ው​ነ​ታ​ቸው ጥፋት ተቀ​ድ​ሰ​ዋ​ልና፤ የተ​ጠ​ፈ​ጠፈ ሰሌዳ አድ​ር​ጋ​ቸው፤ ለመ​ሠ​ዊያ መለ​በ​ጫም ይሁኑ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቅ​ር​በ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና የተ​ቀ​ደሱ ናቸው፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ምል​ክት ይሆ​ናሉ።”</verse>
				<verse number="39">የካ​ህ​ኑም የአ​ሮን ልጅ አል​ዓ​ዛር የተ​ቃ​ጠ​ሉት ሰዎች ያቀ​ረ​ቡ​አ​ቸ​ውን የናስ ጥና​ዎች ወስዶ ጠፍ​ጥ​ፎም ለመ​ሠ​ዊያ መለ​በጫ አደ​ረ​ጋ​ቸው።</verse>
				<verse number="40">እንደ ቆሬና ከእ​ር​ሱም ጋር እንደ ተቃ​ወ​ሙት ሰዎች እን​ዳ​ይ​ሆን፥ ከአ​ሮን ልጆች ያል​ሆነ ሌላ ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዕጣን ያጥን ዘንድ እን​ዳ​ይ​ቀ​ርብ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ ቃል እንደ ተና​ገ​ረው፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መታ​ሰ​ቢያ አደ​ረ​ጋ​ቸው።</verse>
				<verse number="41">በነ​ጋ​ውም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ፥ “እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕዝብ ገድ​ላ​ች​ኋል” ብለው በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ አጕ​ረ​መ​ረሙ።</verse>
				<verse number="42">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ማኅ​በሩ በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ በተ​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ከበ​ቡ​አ​ቸው፤ እነ​ሆም፥ ደመ​ናው ሸፈ​ናት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ተገ​ለጠ።</verse>
				<verse number="43">ሙሴና አሮ​ንም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት ገቡ።</verse>
				<verse number="44">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦</verse>
				<verse number="45">“ከዚህ ማኅ​በር መካ​ከል ፈቀቅ በሉ፥ እኔም በቅ​ጽ​በት አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።” በግ​ን​ባ​ራ​ቸ​ውም ወደቁ።</verse>
				<verse number="46">ሙሴም አሮ​ንን፥ “ጥና​ህን ውሰድ፤ ከመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ እሳት አድ​ር​ግ​በት፤ ዕጣ​ንም ጨም​ር​በት፤ ወደ ማኅ​በ​ሩም ፈጥ​ነህ ውሰ​ደው፤ አስ​ተ​ስ​ር​ይ​ላ​ቸ​ውም፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቍጣ ወጥ​ቶ​አ​ልና፥ ሕዝ​ቡ​ንም ያጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ጀም​ሮ​አል” አለው።</verse>
				<verse number="47">አሮ​ንም ሙሴ እንደ ተና​ገ​ረው ጥና​ውን ወስዶ ወደ ማኅ​በሩ መካ​ከል ፈጥኖ ሮጠ፤ እነ​ሆም፥ መቅ​ሠ​ፍቱ በሕ​ዝቡ መካ​ከል ጀምሮ ነበር፤ ዕጣ​ንም ጨመረ፤ ለሕ​ዝ​ቡም አስ​ተ​ሰ​ረ​የ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="48">በሙ​ታ​ንና በሕ​ያ​ዋን መካ​ከል ቆመ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ቱም ተከ​ለ​ከለ።</verse>
				<verse number="49">በቆ​ሬም ምክ​ን​ያት ከሞ​ቱት ሌላ በመ​ቅ​ሠ​ፍቱ የሞ​ቱት ዐሥራ አራት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="50">አሮ​ንም ወደ ሙሴ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ተመ​ለሰ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ቱም ፀጥ አለ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ንገ​ራ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ከእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ከየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት አንድ አንድ በትር፥ ከአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም ከየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ዐሥራ ሁለት በት​ሮች ውሰድ፤ የእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱ​ንም ስም በየ​በ​ትሩ ላይ ጻፍ።</verse>
				<verse number="3">ለየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ወገን አንድ በትር ይሰ​ጣ​ሉና በሌዊ በትር ላይ የአ​ሮ​ንን ስም ጻፍ።</verse>
				<verse number="4">እኔ ለእ​ና​ንተ በም​ገ​ለ​ጥ​በት በዚያ በመ​ገ​ና​ኛው ድን​ኳን ውስጥ በም​ስ​ክሩ ፊት አኑ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ የመ​ረ​ጥ​ሁት ሰው በትር ትለ​መ​ል​ማ​ለች፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ የሚ​ያ​ጕ​ረ​መ​ር​ሙ​ባ​ችሁ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማጕ​ረ​ም​ረም ከእኔ ዘንድ አጠ​ፋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="6">ሙሴም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ነገ​ራ​ቸው፤ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ አንድ አንድ በትር ሰጡት፤ ለአ​ንድ አለቃ አንድ በትር፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ዐሥራ ሁለት በት​ሮች፤ የአ​ሮ​ንም በትር በበ​ት​ሮ​ቻ​ቸው መካ​ከል ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="7">ሙሴም በት​ሮ​ቹን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ አኖ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በነ​ጋው ሙሴና አሮን ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ገቡ፤ እነ​ሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆ​ነች የአ​ሮን በትር አቈ​ጠ​ቈ​ጠች፤ ለመ​ለ​መ​ችም፤ አበ​ባም አወ​ጣች፤ የበ​ሰለ ለው​ዝም አፈ​ራች።</verse>
				<verse number="9">ሙሴም በት​ሮ​ቹን ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ አወ​ጣ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም አዩ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም በት​ሩን ወሰደ።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “ማጕ​ረ​ም​ረ​ማ​ቸው ከእኔ ዘንድ እን​ዲ​ጠፋ፥ እነ​ር​ሱም እን​ዳ​ይ​ሞቱ ለማ​ይ​ሰሙ ልጆች ምል​ክት ሆና ትጠ​በቅ ዘንድ የአ​ሮ​ንን በትር በም​ስ​ክሩ ፊት አኑር።”</verse>
				<verse number="11">ሙሴና አሮ​ንም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረጉ፤ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="12">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሙሴን አሉት፥ “እነሆ፥ እን​ሞ​ታ​ለን፤ እን​ጠ​ፋ​ለን፤ ሁላ​ች​ንም እና​ል​ቃ​ለን።</verse>
				<verse number="13">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድን​ኳን የሚ​ነካ ሁሉ ይሞ​ታል። በውኑ ሁላ​ችን ፈጽ​መን እን​ሞ​ታ​ለን?”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “አንተ ከአ​ን​ተም ጋር ልጆ​ች​ህና የአ​ባ​ቶ​ችህ ወገ​ኖች፥ የክ​ህ​ነ​ታ​ች​ሁን ኀጢ​አት ትሸ​ከ​ማ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="2">ደግ​ሞም የአ​ባ​ት​ህን የሌ​ዊን ነገድ ወን​ድ​ሞ​ች​ህን ወደ አንተ ሰብ​ስብ፤ ከአ​ን​ተም ጋር በአ​ን​ድ​ነት ይሁኑ፤ ያገ​ል​ግ​ሉ​ህም፤ አንተ ከአ​ን​ተም ጋር ልጆ​ችህ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት ትሆ​ና​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="3">እነ​ር​ሱም ትእ​ዛ​ዝ​ህን የድ​ን​ኳ​ኑ​ንም ሕግ ይጠ​ብቁ፤ ነገር ግን እን​ዳ​ይ​ሞቱ፥ እና​ን​ተም ደግሞ ከእ​ነ​ርሱ ጋር እን​ዳ​ት​ሞቱ፥ እነ​ርሱ ወደ መቅ​ደሱ ዕቃና ወደ መሠ​ዊ​ያው አይ​ቅ​ረቡ።</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ጋር በአ​ን​ድ​ነት ይሁኑ፤ ለድ​ን​ኳ​ኑም አገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሕግ ይጠ​ብቁ፤ ከባ​ዕድ ወገን የሆነ ሰው ወደ አንተ አይ​ቅ​ረብ።</verse>
				<verse number="5">እንደ ገና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ቍጣ እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው እና​ንተ የመ​ቅ​ደ​ሱ​ንና የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ሕግ ጠብቁ።</verse>
				<verse number="6">እኔም፦ እነሆ፥ ሌዋ​ው​ያ​ንን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ወስ​ጄ​አ​ለሁ፤ የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ያደ​ርጉ ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሰጡ ስጦ​ታ​ዎች ናቸው።</verse>
				<verse number="7">አን​ተም ከአ​ን​ተም ጋር ልጆ​ችህ እንደ መሠ​ዊ​ያ​ውና፥ በመ​ጋ​ረ​ጃ​ውም ውስጥ እን​ዳ​ለው ሥር​ዐት ሁሉ ክህ​ነ​ታ​ች​ሁን ጠብቁ፤ የሀ​ብተ ክህ​ነት አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ች​ሁ​ንም አድ​ርጉ፤ ከሌ​ላም ወገን የሆነ ሰው ቢቀ​ርብ ይገ​ደል።”</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን ተና​ገ​ረው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለእኔ የለ​ዩ​ትን የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውን ቍር​ባ​ኔን ሁሉ ትጠ​ብቁ ዘንድ ለአ​ንተ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ለአ​ንተ እስ​ክ​ታ​ረጅ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ችህ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ እን​ዲ​ሆን ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">በእ​ሳት ከሚ​ቀ​ር​በው ከተ​ቀ​ደ​ሰው ይህ ለአ​ንተ ይሆ​ናል፤ ለእኔ የሚ​ያ​መ​ጡት መባ​ቸው ሁሉ፥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም ሁሉ፥ የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም መሥ​ዋ​ዕት ሁሉ፥ የበ​ደ​ላ​ቸ​ውም መሥ​ዋ​ዕት ሁሉ፥ ከተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ሁሉ ለአ​ንተ ለል​ጆ​ች​ህም ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="10">በቅ​ዱሰ ቅዱ​ሳን ብሉት፤ ወን​ዶች ሁሉ ይብ​ሉት፤ አን​ተም ልጆ​ች​ህም ብሉት፤ ለአ​ንተ የተ​ቀ​ደሰ ነውና።</verse>
				<verse number="11">ይህም ለእ​ና​ንተ ነው፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለስ​ጦታ ያቀ​ረ​ቡ​ትን የመ​ጀ​መ​ሪያ ቍር​ባን ሁሉ ለአ​ንተ ከአ​ን​ተም ጋር ለወ​ን​ዶ​ችና ለሴ​ቶች ልጆ​ችህ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ እን​ዲ​ሆን ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ በቤ​ትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብ​ላው።</verse>
				<verse number="12">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ሰ​ጡት የፍሬ መጀ​መ​ሪያ ከዘ​ይ​ትና ከወ​ይን ከስ​ን​ዴም የተ​መ​ረ​ጠ​ውን ሁሉ ለአ​ንተ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="13">ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​መ​ጡት በም​ድ​ራ​ቸው ያለው የፍሬ መጀ​መ​ሪያ ሁሉ ለአ​ንተ ይሆ​ናል፤ በቤ​ትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብ​ላው፤</verse>
				<verse number="14">በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ የተ​ከ​ለ​ከ​ለው ሁሉ ለአ​ንተ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="15">ከሰው እስከ እን​ስሳ ቢሆን፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ሥጋ ሁሉ፥ መጀ​መ​ሪያ የሚ​ወ​ለድ ሁሉ ለአ​ንተ ይሆ​ናል፤ ነገር ግን የሰ​ውን በኵ​ራት ፈጽሞ ትቤ​ዠ​ዋ​ለህ፤ ያል​ነ​ጹ​ት​ንም እን​ስ​ሳት በኵ​ራት ትቤ​ዣ​ለህ።</verse>
				<verse number="16">አንድ ወር የሆ​ነው ልጅ ዋጋው በቤተ መቅ​ደስ ሚዛን አም​ስት ሰቅል ነው። ይኸ​ውም ሃያ አቦሊ ነው።</verse>
				<verse number="17">ነገር ግን የላ​ሞ​ቹን በኵ​ራት፥ ወይም የበ​ጎ​ቹን በኵ​ራት፥ የፍ​የ​ሎ​ች​ንም በኵ​ራት አት​ቤ​ዥም፤ ቅዱ​ሳን ናቸ​ውና፤ ደማ​ቸ​ውን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ትረ​ጨ​ዋ​ለህ፤ ስባ​ቸ​ው​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን መሥ​ዋ​ዕት ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="18">ሥጋ​ውም ለአ​ንተ ይሆ​ናል፤ እን​ደ​ሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ፍር​ምባ እንደ ቀኙም ወርች ለአ​ንተ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="19">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ለ​ዩ​ትን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን መባ ሁሉ ለአ​ንተ ከአ​ን​ተም ጋር ለወ​ን​ዶ​ችና ለሴ​ቶች ልጆ​ችህ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ይህም ለአ​ንተ ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ርህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግና የሁ​ል​ጊዜ ቃል ኪዳን ነው።”</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን አለው፥ “በም​ድ​ራ​ቸው ርስት አት​ወ​ር​ስም፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ድርሻ አይ​ሆ​ን​ል​ህም፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ድር​ሻ​ህና ርስ​ትህ እኔ ነኝ።</verse>
				<verse number="21">“ለሌ​ዊም ልጆች እነሆ፥ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ስለ​ሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ዐሥ​ራት ርስት አድ​ርጌ ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="22">ከዚ​ህም በኋላ ለሞት የሚ​ያ​በቃ በደል እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን አይ​ግቡ።</verse>
				<verse number="23">ሌዋ​ው​ያን ግን የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ይሥሩ፤ እነ​ር​ሱም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይሸ​ከ​ማሉ፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መካ​ከል ርስት አይ​ወ​ር​ሱም።</verse>
				<verse number="24">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አድ​ር​ገው የሚ​ለ​ዩ​ትን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ዐሥ​ራት ለሌ​ዋ​ው​ያን ርስት አድ​ርጌ ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ርስት አት​ወ​ር​ሱም አል​ኋ​ቸው።”</verse>
				<verse number="25">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="26">“ለሌ​ዋ​ው​ያን እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከእ​ና​ንተ ርስት አድ​ርጌ የሰ​ጠ​ኋ​ች​ሁን ዐሥ​ራት በተ​ቀ​በ​ላ​ችሁ ጊዜ፥ እና​ን​ተ​ም​ከ​እ​ርሱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አድ​ር​ጋ​ችሁ የዐ​ሥ​ራት ዐሥ​ራት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="27">መባ​ች​ሁም እንደ እህል ዐው​ድ​ማው ስን​ዴና እንደ ወይን መጭ​መ​ቂ​ያው ፍሬ ይቈ​ጠ​ር​ላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="28">እን​ዲሁ እና​ንተ ደግሞ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከም​ት​ቀ​በ​ሉት ዐሥ​ራት ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አድ​ር​ጋ​ችሁ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መባ ለይ​ታ​ችሁ ለካ​ህኑ ለአ​ሮን ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="29">ከም​ት​ቀ​በ​ሉት ስጦታ ሁሉ፥ ከተ​መ​ረ​ጠው ከተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ድርሻ ሁሉ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የመ​ጀ​መ​ሪያ መባ ሁሉ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="30">ስለ​ዚህ ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፦ ከእ​ርሱ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው በለ​ያ​ችሁ ጊዜ እንደ አው​ድ​ማው እህ​ልና እንደ ወይን መጭ​መ​ቂ​ያው ፍሬ ለሌ​ዋ​ው​ያን ይቈ​ጠ​ር​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="31">እና​ን​ተም ቤተ ሰቦ​ቻ​ች​ሁም፥ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ የማ​ገ​ል​ገ​ላ​ችሁ ዋጋ ነውና በሁሉ ስፍራ ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="32">የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ው​ንም ከእ​ርሱ ባነ​ሣ​ችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኀጢ​አት አይ​ሆ​ን​ባ​ች​ሁም፤ እን​ዳ​ት​ሞ​ቱም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የቀ​ደ​ሱ​ትን አታ​ር​ክሱ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦</verse>
				<verse number="2">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘው የሕጉ ትእ​ዛዝ ይህ ነው፤ መል​ካ​ሚ​ቱን፥ ነው​ርም የሌ​ለ​ባ​ትን፥ ቀን​በ​ርም ያል​ተ​ጫ​ነ​ባ​ትን ቀይ ጊደር ያመ​ጡ​ልህ ዘንድ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ንገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">እር​ስ​ዋ​ንም ለካ​ህኑ ለአ​ል​ዓ​ዛር ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ፤ ከሰ​ፈር ወደ ውጭ ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወ​ስ​ዷ​ታል፤ በፊ​ቱም ያር​ዷ​ታል።</verse>
				<verse number="4">አል​ዓ​ዛ​ርም ከደ​ምዋ በጣቱ ይወ​ስ​ዳል፤ ከደ​ም​ዋም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት ሰባት ጊዜ ይረ​ጫል።</verse>
				<verse number="5">ጊደ​ሪ​ቱ​ንም በፊቱ ያቃ​ጥ​ሏ​ታል፤ ቍር​በ​ቷ​ንም፥ ሥጋ​ዋ​ንም፥ ደም​ዋ​ንም፥ ፈር​ስ​ዋ​ንም ያቃ​ጥ​ሉት።</verse>
				<verse number="6">ካህ​ኑም የዝ​ግባ ዕን​ጨት ሂሶ​ጵም፥ ቀይ ግም​ጃም ወስዶ ጊደ​ሪቱ በም​ት​ቃ​ጠ​ል​በት እሳት መካ​ከል ይጥ​ለ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">ካህ​ኑም ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በውሃ ይታ​ጠ​ባል፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገ​ባል፤ ካህ​ኑም እስከ ማታ ርኩስ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="8">ያቃ​ጠ​ላ​ትም ሰው ልብ​ሱን በውሃ ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="9">ንጹ​ሕም ሰው የጊ​ደ​ሪ​ቱን አመድ ያከ​ማ​ቻል፤ ከሰ​ፈ​ሩም ውጭ በን​ጹሕ ስፍራ ያኖ​ረ​ዋል፤ ርኵ​ሰት ለሚ​ያ​ነጻ ውኃ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ይጠ​በ​ቃል፤ ይነ​ጹ​በ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="10">የጊ​ደ​ሪ​ቱ​ንም አመድ ያከ​ማ​ቸው ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል፤ ይህም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ለሚ​ኖር መጻ​ተኛ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="11">“የሞ​ተ​ውን ሰው በድን የሚ​ነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="12">እን​ደ​ዚሁ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ሁለ​መ​ና​ውን ያነ​ጻል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል፤ ነገር ግን በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ሁለ​መ​ና​ውን ባያ​ነጻ ንጹሕ አይ​ሆ​ንም።</verse>
				<verse number="13">የሞ​ተ​ውን ሰው በድን የነካ ሁለ​መ​ና​ውን ባያ​ነጻ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድን​ኳን ያረ​ክ​ሳል፤ ያ ሰው ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ተለ​ይቶ ይጠ​ፋል፤ በእ​ር​ሱም ላይ የሚ​ያ​ነጻ ውኃ አል​ተ​ረ​ጨ​ምና ርኩስ ይሆ​ናል፤ ርኵ​ሰቱ ገና በእ​ርሱ ላይ ነው።</verse>
				<verse number="14">“ሰው በቤት ውስጥ ቢሞት ሕጉ ይህ ነው፤ ወደ ቤት የሚ​ገባ ሁሉ በቤ​ቱም ውስጥ ያለው ሁሉ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="15">መክ​ደ​ኛው ያል​ታ​ሰረ የተ​ከ​ፈተ ዕቃ ሁሉ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="16">በሜ​ዳም የተ​ገ​ደ​ለ​ውን ወይም የሞ​ተ​ውን በድን፥ ወይም የሰ​ውን አጥ​ንት፥ ወይም መቃ​ብር የሚ​ነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="17">ለአ​ን​ጽሖ እን​ድ​ት​ሆን ከተ​ቃ​ጠ​ለ​ችው ጊደር አመድ ለር​ኩሱ ይወ​ስ​ዱ​ለ​ታል፤ በዕ​ቃ​ውም ውስጥ የም​ንጭ ውኃ ይቀ​ላ​ቅ​ሉ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="18">ንጹ​ሕም ሰው ሂሶ​ጱን ወስዶ በው​ኃው ውስጥ ያጠ​ል​ቀ​ዋል፤ በቤ​ቱም፥ በዕ​ቃ​ውም ሁሉ፥ በዚ​ያም ባሉ ሰዎች ላይ፥ አጥ​ን​ቱ​ንም ወይም የተ​ገ​ደ​ለ​ውን፥ ወይም የሞ​ተ​ውን፥ ወይም መቃ​ብ​ሩን በነ​ካው ላይ ይረ​ጨ​ዋል።</verse>
				<verse number="19">ንጹ​ሑም በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀንና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን በር​ኩሱ ላይ ይረ​ጨ​ዋል፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ይነ​ጻል፤ እር​ሱም ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በውኃ ይታ​ጠ​ባል፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="20">“ሰውም ርኩስ ቢሆን ሁለ​መ​ና​ው​ንም ባያ​ነጻ፥ ያ ሰው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መቅ​ደስ አር​ክ​ሶ​አ​ልና ከማ​ኅ​በሩ መካ​ከል ተለ​ይቶ ይጠ​ፋል፤ በሚ​ያ​ነጻ ውኃ አል​ተ​ረ​ጨ​ምና ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="21">ይህ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፤ የሚ​ያ​ነ​ጻ​ውን ውኃ የሚ​ረጭ ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ የሚ​ያ​ነ​ጻ​ው​ንም ውኃ የሚ​ነካ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="22">ርኩ​ሱም የሚ​ነ​ካው ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆ​ናል፤ የሚ​ነ​ካ​ውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ፤ ሕዝ​ቡም በቃ​ዴስ ተቀ​መጡ፤ ማር​ያ​ምም በዚያ ሞተች፤ ተቀ​በ​ረ​ችም።</verse>
				<verse number="2">ለማ​ኅ​በ​ሩም ውኃ አል​ነ​በ​ረም፤ ሕዝ​ቡም በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="3">ሙሴ​ንም ተጣ​ሉት፤ እን​ዲ​ህም ብለው ተና​ገ​ሩት፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ምነው በሞ​ትን ኖሮ፤</verse>
				<verse number="4">እኛ፥ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ንም በዚያ እን​ሞት ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማኅ​በር ወደ​ዚህ ምድረ በዳ ለምን አወ​ጣ​ችሁ?</verse>
				<verse number="5">ዘር ወደ​ማ​ይ​ዘ​ራ​በት፥ በለ​ስና ወይ​ንም፥ ሮማ​ንም፥ የሚ​ጠ​ጣም ውኃ ወደ​ሌ​ለ​በት ወደ​ዚህ ክፉ ስፍራ ታመ​ጡን ዘንድ ከግ​ብፅ ለምን አወ​ጣ​ች​ሁን?”</verse>
				<verse number="6">ሙሴና አሮ​ንም ከማ​ኅ​በሩ ፊት ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ዳጃፍ ሄደው በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወደቁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ተገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="8">“ይህ​ችን በት​ር​ህን ውሰድ፤ አን​ተና ወን​ድ​ምህ አሮ​ንም ማኅ​በ​ሩን ሰብ​ስቡ፤ ዐለ​ቷ​ንም በፊ​ታ​ቸው እዘ​ዟት፤ ውኃ ትሰ​ጣ​ለች፤ ከድ​ን​ጋ​ይ​ዋም ውኃ ታወ​ጡ​ላ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ እን​ዲ​ሁም ማኅ​በ​ሩን፥ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ታጠ​ጡ​ላ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="9">ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አዘ​ዘው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የነ​በ​ረ​ች​ውን በት​ሩን ወሰደ።</verse>
				<verse number="10">ሙሴና አሮ​ንም ማኅ​በ​ሩን በዐ​ለቷ ፊት ሰብ​ስ​በው፥ “እና​ንተ ዓመ​ፀ​ኞች፥ እን​ግ​ዲህ ስሙ፤ በውኑ ከዚ​ህች ዐለት ውኃን እና​ወ​ጣ​ላ​ችሁ ነበር?” አሏ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ሙሴም እጁን ዘር​ግቶ ዐለ​ቷን ሁለት ጊዜ በበ​ትሩ መታት፤ ብዙም ውኃ ወጣ፤ ማኅ​በ​ሩም፥ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ጠጡ።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ትቀ​ድ​ሱኝ ዘንድ በእኔ አላ​መ​ና​ች​ሁ​ምና ስለ​ዚህ ወደ ሰጠ​ኋ​ችሁ ምድር ይህን ማኅ​በር ይዛ​ችሁ አት​ገ​ቡም” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተከ​ራ​ክ​ረ​ው​በ​ታ​ልና ይህ ውኃ የክ​ር​ክር ውኃ ተባለ። እር​ሱም ቅዱስ መሆኑ የተ​ገ​ለ​ጠ​በት ይህ የክ​ር​ክር ውኃ ነው።</verse>
				<verse number="14">ሙሴም ከቃ​ዴስ ወደ ኤዶ​ም​ያስ ንጉሥ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን እን​ዲህ ብሎ ላከ፥ “ወን​ድ​ምህ እስ​ራ​ኤል እን​ዲህ ይላል፦ ያገ​ኘ​ንን መከራ ሁሉ አንተ ታው​ቃ​ለህ፤</verse>
				<verse number="15">አባ​ቶ​ቻ​ችን ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በግ​ብ​ፅም እጅግ ዘመን ተቀ​መ​ጥን፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም እኛ​ንና አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን በደሉ።</verse>
				<verse number="16">ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጮኽን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ድም​ፃ​ች​ንን ሰማ፤ መል​አ​ክ​ንም ልኮ ከግ​ብፅ አወ​ጣን፤ እነ​ሆም፥ በም​ድ​ርህ ዳርቻ ባለ​ችው ከተማ በቃ​ዴስ ተቀ​ም​ጠ​ናል።</verse>
				<verse number="17">እባ​ክህ፥ በም​ድ​ርህ ላይ እን​ለፍ፤ ወደ እር​ሻም ወደ ወይ​ንም አን​ገ​ባም፤ ከጕ​ድ​ጓ​ዶ​ችም ውኃን አን​ጠ​ጣም፤ በን​ጉሡ ጎዳና እን​ሄ​ዳ​ለን፤ ዳር​ቻ​ህ​ንም እስ​ክ​ና​ልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አን​ልም።”</verse>
				<verse number="18">የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ “በእኔ በኩል አታ​ል​ፍም፤ ይህ ካል​ሆነ ግን እን​ዋ​ጋ​ለን፤ በጦ​ርም እቀ​በ​ልህ ዘንድ እወ​ጣ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="19">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ “በተ​ራ​ራው በኩል እና​ል​ፋ​ለን፤ እኛም ከብ​ቶ​ቻ​ች​ንም ከው​ኃህ ብን​ጠጣ ዋጋ​ውን እን​ከ​ፍ​ላ​ለን፤ ይህ ምንም አይ​ደ​ለም፤ በተ​ራ​ራው እን​ለፍ” አሉት።</verse>
				<verse number="20">እር​ሱም፥ “በእኔ በኩል አታ​ል​ፍም” አለ። የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ በብዙ ሠራ​ዊት በጽኑ እጅ ሊገ​ጥ​መው ወጣ።</verse>
				<verse number="21">የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ እስ​ራ​ኤል በዳ​ር​ቻው እን​ዲ​ያ​ልፍ አል​ፈ​ቀ​ደም፤ ስለ​ዚህ እስ​ራ​ኤል ከእ​ርሱ ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="22">ከቃ​ዴ​ስም ተጓዙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በሖር ተራራ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድር ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦</verse>
				<verse number="24">“አሮን ወደ ወገኑ ይጨ​መር፤ በክ​ር​ክር ውኃ ዘንድ ስለ አሳ​ዘ​ና​ች​ሁኝ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ ሰጠ​ኋት ምድር አት​ገ​ቡም።</verse>
				<verse number="25">አሮ​ን​ንና ልጁን አል​ዓ​ዛ​ርን ይዘህ በማ​ኅ​በሩ ሁሉ ፊት ወደ ሖር ተራራ ላይ አም​ጣ​ቸው፤</verse>
				<verse number="26">ከአ​ሮ​ንም ልብ​ሱን አውጣ፤ ልጁ​ንም አል​ዓ​ዛ​ርን አል​ብ​ሰው፤ አሮ​ንም ወደ ወገኑ ይጨ​መር፤ በዚ​ያም ይሙት።”</verse>
				<verse number="27">ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘዘ አደ​ረገ፤ በማ​ኅ​በ​ሩም ሁሉ ፊት እያዩ ወደ ሖር ተራራ አወ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="28">ሙሴም የአ​ሮ​ንን ልብስ አወጣ፤ ልጁ​ንም አል​ዓ​ዛ​ርን አለ​በ​ሰው፤ አሮ​ንም በዚያ በተ​ራ​ራው ራስ ላይ ሞተ፤ ሙሴና አል​ዓ​ዛ​ርም ከተ​ራ​ራው ራስ ላይ ወረዱ።</verse>
				<verse number="29">ማኅ​በ​ሩም ሁሉ አሮን እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ለአ​ሮን ሠላሳ ቀን አለ​ቀሱ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">በአ​ዜብ በኩል ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረው ከነ​ዓ​ና​ዊው የአ​ራድ ንጉሥ በአ​ታ​ሪን መን​ገድ እስ​ራ​ኤል እንደ መጡ ሰማ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጋር ሰልፍ አደ​ረገ ከእ​ነ​ር​ሱም ምርኮ ማረከ።</verse>
				<verse number="2">እስ​ራ​ኤ​ልም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ይህን ሕዝብ አሳ​ል​ፈህ በእ​ጃ​ችን ብት​ሰ​ጠን እር​ሱ​ንና ከተ​ሞ​ቹን ሕርም ብለን እና​ጠ​ፋ​ዋ​ለን” ብለው ስእ​ለት ተሳሉ።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ድምፅ ሰማ፤ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም አሳ​ልፎ በእ​ጃ​ቸው ሰጣ​ቸው፤ እነ​ር​ሱ​ንም፥ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሕርም ብለው አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ የዚ​ያን ስፍራ ስም “ሕርም” ብለው ጠሩት።</verse>
				<verse number="4">ከሖ​ርም ተራራ በኤ​ር​ትራ ባሕር መን​ገድ ተጓዙ፤ የኤ​ዶ​ም​ንም ምድር ዞሩ​አት፤ ሕዝ​ቡም በመ​ን​ገድ ተበ​ሳጩ።</verse>
				<verse number="5">ሕዝ​ቡም፥ “በም​ድረ በዳ እን​ሞት ዘንድ ከግ​ብፅ ለምን አወ​ጣ​ኸን?” ብለው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ሙሴ​ንም አሙ። “እን​ጀራ የለም፤ ውኃም የለ​ምና፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ንም ይህን ጥቅም የሌ​ለው እን​ጀራ ተጸ​የ​ፈች” ብለው ተና​ገሩ።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ዝቡ ላይ የሚ​ገ​ድሉ እባ​ቦ​ችን ሰደደ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ነደፉ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ብዙ ሰዎች ሞቱ።</verse>
				<verse number="7">ሕዝ​ቡም ወደ ሙሴ መጥ​ተው፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በአ​ንተ ስለ ተና​ገ​ርን በድ​ለ​ናል፤ እባ​ቦ​ችን ከእኛ ያር​ቅ​ልን ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ይ​ልን” አሉት። ሙሴም ስለ ሕዝቡ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለየ።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “የናስ እባ​ብን ሠር​ተህ በዓ​ላማ ላይ ስቀል፤ እባ​ቡም ሰውን ቢነ​ድፍ የተ​ነ​ደ​ፈው ሁሉ ይመ​ል​ከ​ተው፤ ይድ​ና​ልም” አለው።</verse>
				<verse number="9">ሙሴም የና​ሱን እባብ ሠርቶ በዓ​ላማ ላይ ሰቀለ፤ እባ​ብም የነ​ደ​ፈ​ችው ሁሉ የና​ሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ።</verse>
				<verse number="10">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተጓዙ፤ በኦ​ቦ​ትም ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="11">ከኦ​ቦ​ትም ተጕ​ዘው በሞ​ዓብ ፊት ለፊት ባለ​ችው ምድረ በዳ፥ በፀ​ሐይ መውጫ በኩል በጌ​ል​ጋይ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="12">ከዚ​ያም ተጕ​ዘው በዘ​ሬድ ሸለቆ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="13">ከዚ​ያም ተጕ​ዘው ከአ​ሞ​ራ​ው​ያን ዳርቻ በሚ​ወ​ጣው ምድረ በዳ ውስጥ በአ​ር​ኖን ማዶ ሰፈሩ፤ አር​ኖን በሞ​ዓ​ብና በአ​ሞ​ራ​ው​ያን መካ​ከል ያለ የሞ​ዓብ ዳርቻ ነውና።</verse>
				<verse number="14">ስለ​ዚህ በመ​ጽ​ሐፍ ተባለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጦር​ነት ዞኦ​ብ​ንና የአ​ር​ኖን ሸለ​ቆ​ዎ​ችን አቃ​ጠለ።</verse>
				<verse number="15">ወደ ዒር ማደ​ሪያ የሚ​ወ​ርድ፥ በሞ​ዓብ ዳር​ቻም የሚ​ጠጋ የሸ​ለ​ቆ​ዎች ፈሳ​ሾ​ች​ንም አቆመ።</verse>
				<verse number="16">ከዚ​ያም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን፥ “ሕዝ​ቡን ሰብ​ስብ፤ የሚ​ጠ​ጡት ውኃ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ” ብሎ ወደ ተና​ገ​ረ​ላት ጕድ​ጓድ ሄዱ።</verse>
				<verse number="17">በዚ​ያም ጊዜ እስ​ራ​ኤል በዚያ ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ይህን መዝ​ሙር ስለ ጕድ​ጓዱ መዘ​መር ጀመሩ፦</verse>
				<verse number="18">“አለ​ቆች ቈፈ​ሩ​አት፥ በበ​ትረ መን​ግ​ሥት፥ በበ​ት​ራ​ቸ​ውም፥ የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት በመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቸ​ውና በግ​ዛ​ታ​ቸው አጐ​ደ​ጐ​ዱ​አት።”</verse>
				<verse number="19">ከዚ​ያ​ችም ምንጭ ወደ መን​ተ​ና​ይን ተጓዙ፤ ከመ​ን​ተ​ና​ይ​ንም ወደ ነሃ​ል​ያል፥ ከነ​ሃ​ል​ያ​ልም ወደ ባሞት፥</verse>
				<verse number="20">ከባ​ሞ​ትም ምድረ በዳ​ውን ከላይ ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው ወደ ፈስጋ ተራራ ራስ በሞ​ዓብ በረሃ ወዳ​ለው ወደ ያኒን ሸለቆ ተጓዙ።</verse>
				<verse number="21">እስ​ራ​ኤ​ልም ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ንጉሥ ወደ ሴዎን በሰ​ላም ቃል እን​ዲህ ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤</verse>
				<verse number="22">“በም​ድ​ርህ ላይ እን​ለፍ፤ በመ​ን​ገ​ዱም እን​ሄ​ዳ​ለን፤ ወደ እር​ሻና ወደ ወይን ቦታ አን​ገ​ባም፤ ከጕ​ድ​ጓ​ድ​ህም ውኃን አን​ጠ​ጣም፤ እስ​ክ​ን​ወጣ ድረስ በን​ጉሥ ጎዳና እን​ሄ​ዳ​ለን።”</verse>
				<verse number="23">ሴዎ​ንም እስ​ራ​ኤል በወ​ሰኑ ላይ ያልፉ ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደም፤ ሴዎ​ንም ሕዝ​ቡን ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ለመ​ው​ጋት ወደ ምድረ በዳ ወጣ፤ ወደ ኢያ​ሶ​ንም መጣ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ተዋ​ጋ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">እስ​ራ​ኤ​ልም በሰ​ይፍ መታው፤ ምድ​ሩ​ንም ከአ​ር​ኖን ጀምሮ እስከ አሞን ልጆች እስከ ያቦቅ ድረስ ወረሰ፤ የአ​ሞ​ንም ልጆች ዳርቻ ኢያ​ዜር ነበረ።</verse>
				<verse number="25">እስ​ራ​ኤ​ልም እነ​ዚ​ህን ከተ​ሞች ሁሉ ወሰደ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በአ​ሞ​ራ​ው​ያን ከተ​ሞች ሁሉ፥ በሐ​ሴ​ቦ​ንና በመ​ን​ደ​ሮቹ ሁሉ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="26">ሐሴ​ቦ​ንም የአ​ሞ​ራ​ው​ያን ንጉሥ የሴ​ዎን ከተማ ነበረ፤ እር​ሱም የፊ​ተ​ኛ​ውን የሞ​ዓ​ብን ንጉሥ ወግቶ ከአ​ሮ​ኤር እስከ አር​ኖን ድረስ ምድ​ሩን ሁሉ ወስዶ ነበር።</verse>
				<verse number="27">ስለ​ዚህ የም​ሳሌ ሰዎች እን​ዲህ ብለው ይና​ገ​ራሉ፦ “ወደ ሐሴ​ቦን ኑ፤ የሴ​ዎን ከተማ ይመ​ሥ​ረት፤ ይገ​ንባ፤</verse>
				<verse number="28">እሳት ከሐ​ሴ​ቦን፥ ነበ​ል​ባ​ልም ከሴ​ዎን ከተማ ወጣ፤ እስከ ሞዓብ ድረስ በላ፤ የአ​ር​ኖን ሐው​ል​ቶ​ች​ንም ዋጠ፤</verse>
				<verse number="29">ሞዓብ ሆይ፥ ወዮ​ልህ! የካ​ሞስ ሕዝብ ሆይ፥ ጠፋህ፤ ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለማ​ደን፥ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለም​ርኮ፤ ለአ​ሞ​ራ​ው​ያን ንጉሥ ለሴ​ዎን ሰጠ።</verse>
				<verse number="30">ዘራ​ቸ​ውም ከሐ​ሴ​ቦን እስከ ዴቦን ድረስ ጠፋ፤ ሴቶ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ በሞ​ዓብ ላይ እሳ​ትን አነ​ደዱ።”</verse>
				<verse number="31">እስ​ራ​ኤ​ልም በአ​ሞ​ራ​ው​ያን ከተ​ሞች ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="32">ሙሴም ሰላ​ዮ​ቹን ወደ ኢያ​ዜር ላከ፤ እር​ስ​ዋ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋ​ንም ያዙ፤ በዚ​ያም የነ​በ​ሩ​ትን አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አባ​ረሩ።</verse>
				<verse number="33">ተመ​ል​ሰ​ውም በባ​ሳን መን​ገድ ወጡ፤ የባ​ሳ​ንም ንጉሥ ዐግ ከሕ​ዝቡ ሁሉ ጋር በኤ​ድ​ራ​ይን ይወ​ጋ​ቸው ዘንድ ወጣ።</verse>
				<verse number="34">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “እር​ሱ​ንና ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አሳ​ልፌ በእ​ጅህ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለ​ሁና አት​ፍ​ራው፤ በሐ​ሴ​ቦ​ንም በተ​ቀ​መ​ጠው በአ​ሞ​ሬ​ዎን ንጉሥ በሴ​ዎን እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ እን​ዲሁ ታደ​ር​ግ​በ​ታ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="35">እር​ሱ​ንና ልጆ​ቹን፥ ሕዝ​ቡን ሁሉ አንድ ሰው ሳያ​መ​ልጥ መቱ፤ ምድ​ሩ​ንም ወረሱ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተጓዙ፤ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በሞ​ዓብ ምዕ​ራ​ብም ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="2">የሴ​ፎር ልጅ ባላቅ እስ​ራ​ኤል በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ላይ ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ አየ።</verse>
				<verse number="3">ብዙም ነበ​ረና ሞዓብ ከሕ​ዝቡ እጅግ ፈራ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የተ​ነሣ ሞዓብ ደነ​ገጠ።</verse>
				<verse number="4">ሞዓ​ብም የም​ድ​ያ​ምን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ “በሬ የለ​መ​ለ​መ​ውን ሣር እን​ደ​ሚ​ጨ​ርስ ይህ ሠራ​ዊት በዙ​ሪ​ያ​ችን ያለ​ውን ሁሉ ይጨ​ር​ሳል” አላ​ቸው። በዚ​ያን ጊዜ የሶ​ፎር ልጅ ባላቅ የሞ​ዓብ ንጉሥ ነበረ።</verse>
				<verse number="5">በወ​ን​ዙም አጠ​ገብ ባለ​ችው በሕ​ዝቡ ልጆች ምድር በፋ​ቱራ ወደ ተቀ​መ​ጠው ወደ ቢዖር ልጅ ወደ በለ​ዓም፥ “እነሆ፥ ከግ​ብፅ የወጣ ሕዝብ አለ፤</verse>
				<verse number="6">እነ​ሆም፥ የም​ድ​ሩን ሁሉ ፊት ሸፈነ፤ በአ​ቅ​ራ​ቢ​ያ​ች​ንም ተቀ​ም​ጦ​አል፤ አሁ​ንም ይህ ሕዝብ ከእኔ ይበ​ል​ጣ​ልና ልወ​ጋ​ቸ​ውና ከም​ድ​ሪቱ ላሳ​ድ​ዳ​ቸው እችል እንደ ሆነ፥ ና ርገ​ም​ልኝ፤ አንተ የመ​ረ​ቅ​ኸው ምሩቅ፥ የረ​ገ​ም​ኸ​ውም ርጉም እንደ ሆነ አው​ቃ​ለ​ሁና” ብሎ ይጠ​ሩት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ።</verse>
				<verse number="7">የሞ​ዓብ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና የም​ድ​ያም ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም የም​ዋ​ር​ቱን ዋጋ በእ​ጃ​ቸው ይዘው ሄዱ፤ ወደ በለ​ዓ​ምም መጡ፤ የባ​ላ​ቅ​ንም ቃል ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="8">እር​ሱም፥ “ዛሬ ሌሊት በዚህ እደሩ፤ እግ​ዚ​እ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ነ​ግ​ረ​ኝን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ” አላ​ቸው፤ የሞ​ዓብ አለ​ቆ​ችም በበ​ለ​ዓም ዘንድ አደሩ።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ በለ​ዓም መጥቶ፥ “እነ​ዚህ በአ​ንተ ዘንድ ያሉ ሰዎች እነ​ማን ናቸው?” አለው።</verse>
				<verse number="10">በለ​ዓ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲህ አለው፥ “የሞ​ዓብ ንጉሥ የሶ​ፎር ልጅ ባላቅ፦ እን​ዲህ ሲል ወደ እኔ ልኮ​አ​ቸ​ዋል፤</verse>
				<verse number="11">እነሆ፥ ከግ​ብፅ የወጣ ሕዝብ የም​ድ​ርን ፊት ሸፈነ፤ በአ​ቅ​ራ​ቢ​ያ​ዬም ተቀ​ም​ጦ​አል፤ ምና​ል​ባት እወ​ጋው፥ አሳ​ድ​ደ​ውም ዘንድ እችል እንደ ሆነ አሁ​ንም ና እር​ሱን ርገ​ም​ልኝ።”</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በለ​ዓ​ምን፥ “ከእ​ነ​ርሱ ጋር አት​ሂድ፤ የተ​ባ​ረከ ነውና ሕዝ​ቡን አት​ር​ገም” አለው።</verse>
				<verse number="13">በለ​ዓ​ምም ሲነጋ ተነ​ሥቶ የባ​ላ​ቅን አለ​ቆች፥ “ከእ​ና​ንተ ጋር እሄድ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ፈ​ቀ​ደ​ል​ኝ​ምና ወደ ጌታ​ችሁ ሂዱ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">የሞ​ዓብ አለ​ቆ​ችም ተነሡ፤ ወደ ባላ​ቅም መጥ​ተው፥ “በለ​ዓም ከእኛ ጋር ይመጣ ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደም” አሉት።</verse>
				<verse number="15">ባላ​ቅም ደግሞ ከእ​ነ​ዚያ የበ​ዙና የከ​በሩ ሌሎ​ችን አለ​ቆች ሰደደ።</verse>
				<verse number="16">ወደ በለ​ዓ​ምም መጥ​ተው፥ “የሶ​ፎር ልጅ ባላቅ፦ እባ​ክህ ወደ እኔ መም​ጣ​ትን ቸል አት​በል፤</verse>
				<verse number="17">ክብ​ር​ህን እጅግ ታላቅ አደ​ር​ገ​ዋ​ለ​ሁና፥ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ው​ንም ሁሉ አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለ​ሁና ና፥ ይህን ሕዝብ ርገ​ም​ልኝ ብሏል” አሉት።</verse>
				<verse number="18">በለ​ዓ​ምም መልሶ የባ​ላ​ቅን አለ​ቆች፥ “ባላቅ በቤቱ የሞ​ላ​ውን ወር​ቅና ብር ቢሰ​ጠኝ፥ በት​ንሹ ወይም በት​ልቁ ቢሆን የአ​ም​ላ​ኬን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እተ​ላ​ለፍ ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ኝም፤</verse>
				<verse number="19">አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደግሞ የሚ​ነ​ግ​ረ​ኝን አውቅ ዘንድ ዛሬ ሌሊት ደግሞ በዚህ እደሩ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ በለ​ዓም በሌ​ሊት መጥቶ፥ “ሰዎቹ ይጠ​ሩህ ዘንድ መጥ​ተው እንደ ሆነ፥ ተነሣ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የም​ነ​ግ​ር​ህን ቃል ታደ​ር​ጋ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="21">በለ​ዓ​ምም ሲነጋ ተነሣ፤ አህ​ያ​ዪ​ቱ​ንም ጭኖ ከሞ​ዓብ አለ​ቆች ጋር ሄደ።</verse>
				<verse number="22">እር​ሱም ስለ ሄደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቈጣ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ሊያ​ሰ​ና​ክ​ለው ተነሣ።</verse>
				<verse number="23">እር​ሱም በአ​ህ​ያ​ዪቱ ላይ ተቀ​ምጦ ነበር፤ ሁለ​ቱም ብላ​ቴ​ና​ዎቹ ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ። አህ​ያ​ዪ​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ በመ​ን​ገድ ላይ ቆሞ የተ​መ​ዘ​ዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየች፤ ከመ​ን​ገ​ዱም ላይ ፈቀቅ ብላ ወደ ሜዳ ውስጥ ገባች፤ በለ​ዓ​ምም ወደ መን​ገድ ይመ​ል​ሳት ዘንድ አህ​ያ​ዪ​ቱን መታት።</verse>
				<verse number="24">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ከወ​ይኑ ቦታ​ዎች መካ​ከል በወ​ዲ​ያና በወ​ዲህ ወገን ግንብ በነ​በ​ረ​በት ቆመ።</verse>
				<verse number="25">አህ​ያ​ዪ​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ አይታ ወደ ቅጥሩ ተጠ​ጋች፤ የበ​ለ​ዓ​ም​ንም እግ​ሩን ላጠ​ችው፤ እር​ሱም ደግሞ መታት።</verse>
				<verse number="26">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ወደ ፊት ሄደ፤ በቀ​ኝና በግራ መተ​ላ​ለ​ፊያ በሌ​ለ​በት በጠ​ባብ ስፍራ ቆመ።</verse>
				<verse number="27">አህ​ያ​ዪ​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ አየች፤ ከበ​ለ​ዓ​ምም በታች ተኛች፤ በለ​ዓ​ምም ተቈጣ፤ አህ​ያ​ዪ​ቱ​ንም በበ​ትሩ ደበ​ደ​ባት።</verse>
				<verse number="28">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የአ​ህ​ያ​ዪ​ቱን አፍ ከፈተ፤ በለ​ዓ​ም​ንም፥ “ሦስት ጊዜ የመ​ታ​ኸኝ ምን አድ​ር​ጌ​ብህ ነው?” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="29">በለ​ዓ​ምም አህ​ያ​ዪ​ቱን፥ “ስለ​ዘ​በ​ት​ሽ​ብኝ ነው፤ በእ​ጄስ ሰይፍ ቢኖር አሁን በገ​ደ​ል​ሁሽ ነበር” አላት።</verse>
				<verse number="30">አህ​ያ​ዪ​ቱም በለ​ዓ​ምን፥ “ከወ​ጣ​ት​ነ​ትህ ጀምሮ እስከ ዛሬ የም​ት​ቀ​መ​ጥ​ብኝ አህ​ያህ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? በውኑ አን​ተን ቸል ያል​ሁ​በት፥ በአ​ን​ተም እን​ዲህ ያደ​ረ​ግ​ሁ​በት ጊዜ ነበ​ርን?” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ግ​ሽ​ብ​ኝም” አላት።</verse>
				<verse number="31">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የበ​ለ​ዓ​ምን ዐይ​ኖች ከፈተ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መል​አክ በመ​ን​ገድ ላይ ቆሞ፥ የተ​መ​ዘ​ዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ፤ በግ​ን​ባ​ሩም ወድቆ ሰገ​ደ​ለት።</verse>
				<verse number="32">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “አህ​ያ​ህን ሦስት ጊዜ ለምን መታህ? እነሆ፥ መን​ገ​ድህ በፊቴ ቀና አል​ነ​በ​ረ​ምና ላሰ​ና​ክ​ልህ ወጥ​ቼ​አ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="33">አህ​ያ​ዪ​ቱም አይ​ታኝ ከፊቴ ፈቀቅ አለች፤ ይህም ሦስ​ተኛ ጊዜ ነው፤ ከፊ​ቴስ ፈቀቅ ባላ​ለች በእ​ው​ነት አሁን አን​ተን በገ​ደ​ል​ሁህ፤ እር​ሷ​ንም ባዳ​ን​ኋት ነበር” አለው።</verse>
				<verse number="34">በለ​ዓ​ምም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ፥ “በድ​ያ​ለሁ፤ አንተ በመ​ን​ገድ ላይ በፊቴ እንደ ቆም​ህ​ብኝ አላ​ወ​ቅ​ሁም፤ እን​ግ​ዲህ አሁን አት​ወ​ድድ እን​ደ​ሆነ እመ​ለ​ሳ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="35">የእ​ግ​ዚ​እ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በለ​ዓ​ምን፥ “ከሰ​ዎቹ ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የም​ና​ገ​ር​ህን ቃል ብቻ ለመ​ና​ገር ተጠ​ን​ቀቅ” አለው። በለ​ዓ​ምም ከባ​ላቅ አለ​ቆች ጋር ሄደ።</verse>
				<verse number="36">“ባላ​ቅም በለ​ዓም እንደ መጣ በሰማ ጊዜ ከዳ​ር​ቻ​ዎች በአ​ን​ደኛ ክፍል በአ​ለ​ችው በአ​ር​ኖን ዳርቻ ወደ አለ​ችው ወደ ሞዓብ ከተማ ሊገ​ና​ኘው ወጣ።</verse>
				<verse number="37">ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን፥ “አን​ተን ለመ​ጥ​ራት የላ​ክ​ሁ​ብህ አይ​ደ​ለ​ምን? ለም​ንስ ወደ እኔ አል​መ​ጣ​ህም? አን​ተን ለማ​ክ​በር እኔ አል​ች​ል​ምን?” አለው።</verse>
				<verse number="38">በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን፥ “እነሆ፥ ወደ አንተ መጥ​ቼ​አ​ለሁ፤ አሁን አን​ዳ​ችን ነገር ለመ​ና​ገር እች​ላ​ለ​ሁን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአፌ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ቃል እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="39">በለ​ዓ​ምም ከባ​ላቅ ጋር ሄደ፤ ወደ ቅጽር ግቢ​ውም ገቡ።</verse>
				<verse number="40">ባላ​ቅም በሬ​ዎ​ች​ንና በጎ​ችን አርዶ ወደ በለ​ዓም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ወዳ​ሉት አለ​ቆች ላከ።</verse>
				<verse number="41">በነ​ጋ​ውም ባላቅ በለ​ዓ​ምን ይዞ ወደ በአል ኮረ​ብታ አወ​ጣው፤ በዚ​ያም ሆኖ የሕ​ዝ​ቡን አንድ ወገን አሳ​የው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="23">
				<verse number="1">በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን፥ “ሰባት መሠ​ዊያ በዚህ ሥራ​ልኝ፤ ሰባ​ትም ወይ​ፈን፥ ሰባ​ትም አውራ በግ በዚህ አዘ​ጋ​ጅ​ልኝ” አለው።</verse>
				<verse number="2">ባላ​ቅም በለ​ዓም እንደ ተና​ገረ አደ​ረገ፤ በየ​መ​ሠ​ዊ​ያው ላይ አንድ ወይ​ፈ​ንና አንድ አውራ በግ አሳ​ረገ።</verse>
				<verse number="3">በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን፥ “በመ​ሥ​ዋ​ዕ​ትህ ዘንድ ቈይ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢገ​ለ​ጥ​ልኝ፥ ቢገ​ና​ኘ​ኝም እሄ​ዳ​ለሁ፤ የሚ​ገ​ል​ጥ​ል​ኝ​ንም ቃል እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ” አለው። ባላ​ቅም በመ​ሠ​ዊ​ያው ዘንድ ቆመ፤ በለ​ዓም ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይጠ​ይቅ ዘንድ አቅ​ንቶ ሄደ።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለበ​ለ​ዓም ታየው፤ በለ​ዓ​ምም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “እነሆ፥ ሰባት መሠ​ዊ​ያ​ዎች አዘ​ጋ​ጀሁ፤ በየ​መ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ አንድ ወይ​ፈ​ንና አንድ አውራ በግ አሳ​ረ​ግሁ” አለው።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በበ​ለ​ዓም አፍ ቃልን አኖረ፤ “ወደ ባላቅ ተመ​ለስ፤ እን​ዲ​ህም በል” አለው።</verse>
				<verse number="6">ወደ እር​ሱም ተመ​ለሰ፤ እነ​ሆም፥ እር​ሱና የሞ​ዓብ አለ​ቆች ሁሉ በመ​ሥ​ዋ​ዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ ወደ እርሱ መጣ፤</verse>
				<verse number="7">በም​ሳ​ሌም ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ “የሞ​ዓብ ንጉሥ ባላቅ ከም​ሥ​ራቅ ተራ​ሮች፤ ከሜ​ስ​ጴ​ጦ​ምያ ጠርቶ አመ​ጣኝ፤ ና፥ ያዕ​ቆ​ብን ርገ​ም​ልኝ፤ ና፥ እስ​ራ​ኤ​ልን ተጣ​ላ​ልኝ” ብሎ።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያል​ረ​ገ​መ​ውን እን​ዴት እረ​ግ​ማ​ለሁ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ያል​ተ​ጣ​ላ​ውን እን​ዴት እጣ​ላ​ለሁ?</verse>
				<verse number="9">በተ​ራ​ሮች ራስ ላይ ሆኜ አየ​ዋ​ለሁ፤ በኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም ላይ ሆኜ እመ​ለ​ከ​ተ​ዋ​ለሁ፤ እነሆ፥ ብቻ​ውን የሚ​ቀ​መጥ ሕዝብ ነው፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል አይ​ቈ​ጠ​ርም።</verse>
				<verse number="10">የያ​ዕ​ቆ​ብን ዘር ማን ያው​ቀ​ዋል? የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንስ ሕዝብ ማን ይቈ​ጥ​ረ​ዋል? ሰው​ነ​ቴም ከጻ​ድ​ቃን ሰው​ነት ጋር ትሙት፤ ዘሬም እንደ እነ​ርሱ ዘር ትሁን።”</verse>
				<verse number="11">ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን፥ “ያደ​ረ​ግ​ኽ​ብኝ ምን​ድን ነው? ጠላ​ቶ​ችን ትረ​ግ​ም​ልኝ ዘንድ ጠራ​ሁህ፤ እነ​ሆም፥ መባ​ረ​ክን ባረ​ክ​ሃ​ቸው” አለው።</verse>
				<verse number="12">በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን መልሶ፥ “በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአፌ ያደ​ረ​ገ​ውን እና​ገር ዘንድ የም​ጠ​ነ​ቀቅ አይ​ደ​ለ​ምን?”</verse>
				<verse number="13">ባላ​ቅም፥ “በዚያ እነ​ር​ሱን ወደ​ማ​ታ​ይ​በት ወደ ሌላ ቦታ እባ​ክህ፥ ከእኔ ጋር ና፤ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዱን ወገን ብቻ ታያ​ለህ፤ ሁሉን ግን አታ​ይም፤ በዚ​ያም እነ​ር​ሱን ርገ​ም​ልኝ” አለው።</verse>
				<verse number="14">በሜዳ ወደ ተገ​ነባ ግንብ ራስ ላይም ወሰ​ደው፤ አዞ​ረ​ውም፤ ሰባ​ትም መሠ​ዊ​ያ​ዎች ሠራ፤ በየ​መ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ አንድ ወይ​ፈን፥ አን​ድም አውራ በግ አሳ​ረገ።</verse>
				<verse number="15">በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን አለው፥ “በዚህ በመ​ሥ​ዋ​ዕ​ትህ ዘንድ ቈይ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጠ​ይቅ ዘንድ እሄ​ዳ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በለ​ዓ​ምን ተገ​ና​ኘው፤ ቃል​ንም በአፉ አኖረ፥ “ወደ ባላቅ ተመ​ለስ፤ እን​ዲ​ህም በለው።”</verse>
				<verse number="17">ወደ እር​ሱም መጣ፤ እነሆ፥ እርሱ ከእ​ር​ሱም ጋር የሞ​ዓብ አለ​ቆች በመ​ሥ​ዋ​ዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር፤ ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን አለ?”</verse>
				<verse number="18">በም​ሳ​ሌም ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ “ባላቅ ሆይ፥ ተነሣ፤ ስማ፤ የሶ​ፎር ልጅ ሆይ፥ ምስ​ክር ሁነህ አድ​ምጥ፤</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰው የሚ​ታ​ለል አይ​ደ​ለም። እንደ ሰው ልጅም የሚ​ዛ​ት​በት አይ​ደ​ለም፤ እርሱ ያለ​ውን አያ​ደ​ር​ገ​ው​ምን? አይ​ና​ገ​ረ​ው​ምን? አይ​ፈ​ጽ​መ​ው​ምን?</verse>
				<verse number="20">እነሆ፥ መጥ​ቻ​ለሁ፤ እባ​ር​ካ​ለሁ፤ አል​መ​ለ​ስ​ምም፤</verse>
				<verse number="21">በያ​ዕ​ቆብ ላይ ድካም የለም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕማም አይ​ታ​ይም፤ አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነው፤ የአ​ለ​ቆ​ችም ክብር ለእ​ርሱ ነው።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ ያወ​ጣው እርሱ ጕል​በቱ አንድ ቀንድ እን​ዳ​ለው ክብር ነው።</verse>
				<verse number="23">በያ​ዕ​ቆብ ላይ ጥን​ቆላ የለም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ምዋ​ርት የለም፤ በየ​ጊ​ዜው ስለ ያዕ​ቆ​ብና ስለ እስ​ራ​ኤል፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን አደ​ረገ? ይባ​ላል።</verse>
				<verse number="24">እነሆ፥ ሕዝቡ እንደ አን​በሳ ደቦል ያገ​ሣል፤ እንደ አን​በ​ሳም ይነ​ሣል፤ ያደ​ነ​ውን እስ​ኪ​በላ፥ የገ​ደ​ለ​ው​ንም ደሙን እስ​ኪ​ጠጣ አይ​ተ​ኛም።”</verse>
				<verse number="25">ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን አለው፥ “ከቶ አት​ር​ገ​ማ​ቸው፤ ከቶም አት​ባ​ር​ካ​ቸው።”</verse>
				<verse number="26">በለ​ዓ​ምም መልሶ ባላ​ቅን አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ኝን ቃል ሁሉ አደ​ር​ጋ​ለሁ ብዬ አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁ​ህ​ምን?”</verse>
				<verse number="27">ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን አለው፥ “ና፥ ወደ ሌላ ስፍራ እወ​ስ​ድ​ሃ​ለሁ፤ ምና​ል​ባት በዚህ ሆነህ እነ​ር​ሱን ትረ​ግ​ም​ልኝ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይወ​ድድ ይሆ​ናል።”</verse>
				<verse number="28">ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን በም​ድረ በዳ ወደ ተከ​በ​በው ወደ ፌጎር ተራራ ወሰ​ደው።</verse>
				<verse number="29">በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን፥ “በዚህ ሰባት መሠ​ዊ​ያ​ዎች ሥራ​ልኝ፤ በዚ​ህም ሰባት ወይ​ፈን፥ ሰባ​ትም አውራ በግ አዘ​ጋ​ጅ​ልኝ” አለው።</verse>
				<verse number="30">ባላ​ቅም በለ​ዓም እን​ዳ​ለው አደ​ረገ፤ በየ​መ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ አንድ ወይ​ፈ​ንና አንድ አውራ በግ አሳ​ረገ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="24">
				<verse number="1">በለ​ዓ​ምም እስ​ራ​ኤ​ልን መባ​ረክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካም እንደ ሆነ ባየ ጊዜ፥ እንደ ልማዱ ለማ​ሟ​ረት ወደ ፊት አል​ሄ​ደም፤ ነገር ግን ወደ ምድረ በዳ ፊቱን መለሰ።</verse>
				<verse number="2">በለ​ዓ​ምም ዐይ​ኑን አን​ሥቶ እስ​ራ​ኤል በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው ሲጓዙ አየ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በላዩ መጣ።</verse>
				<verse number="3">በም​ሳ​ሌም ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “የቢ​ዖር ልጅ በለ​ዓም እን​ዲህ ይላል፥ በት​ክ​ክል የሚ​ያይ ሰው እን​ዲህ ይላል፤</verse>
				<verse number="4">“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል የሚ​ሰማ፥ ሁሉን የሚ​ችል የአ​ም​ላ​ክን ራእይ የሚ​ያይ፥ ተኝቶ ዐይ​ኖቹ የተ​ከ​ፈ​ቱ​ለት እን​ዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="5">ያዕ​ቆብ ሆይ፥ ቤቶ​ችህ፥ እስ​ራ​ኤል ሆይ ድን​ኳ​ኖ​ችህ ምንኛ ያም​ራሉ!</verse>
				<verse number="6">እን​ደ​ሚ​ጋ​ርዱ ዛፎች፥ በወ​ንዝ ዳር እን​ዳሉ የተ​ክል ቦታ​ዎች፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተከ​ላ​ቸው ድን​ኳ​ኖች በው​ኃም ዳር እን​ዳሉ ዝግ​ባ​ዎች ናቸው።</verse>
				<verse number="7">ከዘሩ ሰው ይወ​ጣል፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንም ይገ​ዛል፥ መን​ግ​ሥ​ቱም ከአ​ጋግ ይልቅ ከፍ ከፍ ትላ​ለች፥ መን​ግ​ሥ​ቱም ትሰ​ፋ​ለች።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ መርቶ አው​ጥ​ቶ​ታል፤ አንድ ቀንድ እን​ዳ​ለው ክብር አለው፤ ጠላ​ቶ​ቹን አሕ​ዛ​ብን ይበ​ላል፤ አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይሰ​ባ​ብ​ራል፤ በፍ​ላ​ጾ​ቹም ጠላ​ቱን ይወ​ጋ​ዋል።</verse>
				<verse number="9">አር​ፎ​አል፥ እንደ አን​በ​ሳና እንደ አን​በሳ ደቦል ተጋ​ድ​ሞ​አል፤ ማን ያስ​ነ​ሣ​ዋል? የሚ​መ​ር​ቁህ ሁሉ የተ​መ​ረቁ ይሁኑ፤ የሚ​ረ​ግ​ሙ​ህም ሁሉ የተ​ረ​ገሙ ይሁኑ።”</verse>
				<verse number="10">ባላ​ቅም በበ​ለ​ዓም ላይ ተቈጣ፤ እጆ​ቹ​ንም አጨ​በ​ጨበ፤ ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን አለው፦ ጠላ​ቶ​ችን ትረ​ግም ዘንድ ጠራ​ሁህ፥</verse>
				<verse number="11">እነ​ሆም፥ ፈጽ​መህ መረ​ቅ​ሃ​ቸው፤ ይህ ሦስ​ተ​ኛህ ነው፤ አሁ​ንም እን​ግ​ዲህ ወደ ስፍ​ራህ ሂድ፤ እኔ አከ​ብ​ር​ሃ​ለሁ ብዬ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እነሆ፥ ክብ​ር​ህን ከለ​ከለ።”</verse>
				<verse number="12">በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን አለው፦</verse>
				<verse number="13">ባላቅ በቤቱ የሞ​ላ​ውን ብርና ወርቅ ቢሰ​ጠኝ፥ መል​ካ​ሙን ወይም ክፉ​ውን ከልቤ ለማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እተ​ላ​ለፍ ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ኝም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ ብዬ ወደ እኔ ለላ​ክ​ሃ​ቸው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችህ አል​ተ​ና​ገ​ር​ኋ​ቸ​ው​ምን?</verse>
				<verse number="14">አሁ​ንም፥ እነሆ፥ ወደ ሕዝቤ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ና፥ ይህ ሕዝብ በኋ​ለ​ኛው ዘመን በሕ​ዝ​ብህ ላይ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="15">በም​ሳ​ሌም ይና​ገር ጀመር፥ እን​ዲ​ህም አለ፦ “የቢ​ዖር ልጅ በለ​ዓም እን​ዲህ ይላል፥ በት​ክ​ክል የሚ​ያይ ሰው እን​ዲህ ይላል፤</verse>
				<verse number="16">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል የሚ​ሰማ፥ የል​ዑ​ል​ንም ዕው​ቀት የሚ​ያ​ውቅ፥ ሁሉን የሚ​ችል የአ​ም​ላ​ክን ራእይ የሚ​ያይ፥ ተኝቶ ዐይ​ኖቹ የተ​ከ​ፈ​ቱ​ለት እን​ዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="17">አየ​ዋ​ለሁ፥ አሁን ግን አይ​ደ​ለም፤ እባ​ር​ከ​ዋ​ለሁ፥ በቅ​ርብ ግን አይ​ደ​ለም፤ ከያ​ዕ​ቆብ ኮከብ ይወ​ጣል፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰው ይነ​ሣል፥ የሞ​ዓ​ብ​ንም አለ​ቆች ይመ​ታል፤ የሤ​ት​ንም ልጆች ሁሉ ይማ​ር​ካል።</verse>
				<verse number="18">ኤዶ​ም​ያ​ስም ርስቱ ይሆ​ናል፤ ጠላቱ ኤሳው ደግሞ ርስቱ ይሆ​ናል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በኀ​ይል ያደ​ር​ጋል።</verse>
				<verse number="19">ከያ​ዕ​ቆ​ብም ኀያል ሰው ይወ​ጣል፤ ከከ​ተ​ማ​ውም የቀ​ሩ​ትን ያጠ​ፋል።”</verse>
				<verse number="20">ዐማ​ሌ​ቅ​ንም አይቶ በም​ሳሌ ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ “ዐማ​ሌቅ የአ​ሕ​ዝብ አለቃ ነበረ፤ ዘራ​ቸ​ውም ይጠ​ፋል።”</verse>
				<verse number="21">ቄኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም አይቶ በም​ሳሌ ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ “ማደ​ሪ​ያህ የጸ​ናች ናት፤ ጎጆ​ህም በአ​ንባ ላይ ተሠ​ር​ቶ​አል፤</verse>
				<verse number="22">ቢዖር የጥ​ፋት ጎጆ ቢሆ​ንም አሦር ይማ​ር​ክ​ሃል።”</verse>
				<verse number="23">አግ​ንም ባየው ጊዜ በም​ሳሌ ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ሲያ​ደ​ርግ አወይ ማን በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል?</verse>
				<verse number="24">ከቄ​ጤ​ዎ​ንም እጅ የሚ​ወ​ጣው አሦ​ር​ንና ዕብ​ራ​ው​ያ​ንን ያስ​ጨ​ን​ቃል፤ እነ​ር​ሱም በአ​ን​ድ​ነት ይጠ​ፋሉ።”</verse>
				<verse number="25">በለ​ዓ​ምም ተነሣ፤ ተመ​ል​ሶም ወደ ስፍ​ራው ሄደ፤ ባላ​ቅም ደግሞ ወደ ቤቱ ገባ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="25">
				<verse number="1">እስ​ራ​ኤ​ልም በሰ​ጢን አደሩ፤ ሕዝ​ቡም ከሞ​ዓብ ልጆች ጋር አመ​ነ​ዘሩ፤ ረከ​ሱም።</verse>
				<verse number="2">ሕዝ​ቡ​ንም ወደ አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው መሥ​ዋ​ዕት ጠሩ፤ ሕዝ​ቡም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን በሉ፤ ለአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውም ሰገዱ።</verse>
				<verse number="3">እስ​ራ​ኤ​ልም ለብ​ዔል ፌጎር ራሳ​ቸ​ውን ለዩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ስላ​ፈ​ረሱ የሕ​ዝ​ቡን አለ​ቆች ሁሉ ወስ​ደህ በፀ​ሐይ ፊት ቅጣ​ቸው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ ከእ​ስ​ራ​ኤል ይር​ቃል።”</verse>
				<verse number="5">ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሕዝ​ቦች፥ “እና​ንተ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ብዔል ፌጎ​ርን የተ​ከ​ተ​ሉ​ትን ሰዎ​ቻ​ች​ሁን ግደሉ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">እነ​ሆም፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አንዱ መጥቶ በሙ​ሴና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ፊት ወን​ድ​ሙን ወደ ምድ​ያ​ማ​ዊት ሴት ወሰ​ደው፤ እነ​ር​ሱም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዳጃፍ ያለ​ቅሱ ነበር።</verse>
				<verse number="7">የካ​ህ​ኑም የአ​ሮን ልጅ የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ ባየው ጊዜ ከማ​ኅ​በሩ መካ​ከል ተነ​ሥቶ በእጁ ጦር አነሣ።</verse>
				<verse number="8">ያንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰው ተከ​ትሎ ወደ ድን​ኳኑ ገባ። ሁለ​ቱ​ንም እስ​ራ​ኤ​ላ​ዊ​ውን ሰውና ምድ​ያ​ማ​ዊ​ቱን ሴት ሆዳ​ቸ​ውን ወጋ​ቸው፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መቅ​ሠ​ፍቱ ተወ​ገደ።</verse>
				<verse number="9">በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ቱም የሞ​ቱት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="11">“የካ​ህኑ የአ​ሮን ልጅ የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ በቅ​ን​ዓቴ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቀን​ቶ​አ​ልና ቍጣ​ዬን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መለሰ፤ እኔም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በቅ​ን​ዓቴ አላ​ጠ​ፋ​ሁም።</verse>
				<verse number="12">ስለ​ዚህ አልሁ፦ እነሆ፥ የሰ​ላ​ሜን ቃል ኪዳን እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">ለአ​ም​ላኩ ቀን​ቶ​አ​ልና፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አስ​ተ​ስ​ር​ዮ​አ​ልና፥ ለእ​ርሱ ከእ​ር​ሱም በኋላ ለዘሩ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የክ​ህ​ነት ቃል ኪዳን ይሆ​ን​ለ​ታል።”</verse>
				<verse number="14">ከም​ድ​ያ​ማ​ዊ​ቱም ጋር የተ​ገ​ደ​ለው የእ​ስ​ራ​ኤ​ላ​ዊው ሰው ስም ዘን​በሪ ነበረ፤ የአ​ባቱ ቤት አለቃ የስ​ም​ዖ​ና​ው​ያን የሆነ የሰሉ ልጅ ነበረ።</verse>
				<verse number="15">የተ​ገ​ደ​ለ​ች​ውም ምድ​ያ​ማ​ዊት ስምዋ ከስቢ ነበረ፤ እር​ስ​ዋም የሱር ልጅ ነበ​ረች፤ እር​ሱም የም​ድ​ያም አባ​ቶች ወገን የሚ​ሆን የሳ​ሞት ወገን አለቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦</verse>
				<verse number="17">ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንን አስ​ጨ​ን​ቋ​ቸው፤ ግደ​ሉ​አ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="18">ስለ ምድ​ያም አለቃ ልጅ ስለ እኅ​ታ​ቸው ስለ ከስቢ በፌ​ጎር ምክ​ን​ያት በሸ​ነ​ገ​ሉ​አ​ችሁ ሽን​ገላ አስ​ጨ​ን​ቀ​ዋ​ች​ኋ​ልና።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="26">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፦ መቅ​ሠ​ፍቱ ከሆነ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴ​ንና ካህ​ኑን አል​ዓ​ዛ​ርን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦</verse>
				<verse number="2">“ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጣ​ውን ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ቍጠሩ።”</verse>
				<verse number="3">ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት በሞ​ዓብ ሜዳ ላይ እን​ዲህ ብለው ነገ​ሩ​አ​ቸው፦</verse>
				<verse number="4">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ከሃያ ዓመት ጀምሮ፥ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን ሕዝብ ቍጠሩ።” ከግ​ብፅ ምድር የወጡ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="5">የእ​ስ​ራ​ኤል በኵር ሮቤል፤ የሮ​ቤል ልጆች፤ ከሄ​ኖኅ የሄ​ኖ​ኃ​ው​ያን ወገን፤ ከፈ​ሉስ የፈ​ሉ​ሳ​ው​ያን ወገን።</verse>
				<verse number="6">ከአ​ስ​ሮን የአ​ስ​ሮ​ና​ው​ያን ወገን፤ ከከ​ርሚ የከ​ር​ማ​ው​ያን ወገን።</verse>
				<verse number="7">እነ​ዚህ የሮ​ቤ​ላ​ው​ያን ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት አርባ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ።</verse>
				<verse number="8">የፈ​ሉ​ስም ልጆች፤ ኤል​ያብ።</verse>
				<verse number="9">የኤ​ል​ያ​ብም ልጆች፥ ናሙ​ኤል፥ ዳታን፥ አቤ​ሮን፤ እነ​ዚ​ህም ከማ​ኅ​በሩ የተ​መ​ረጡ ነበሩ፤ ከቆሬ ወገን ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ባመፁ ጊዜ ሙሴ​ንና አሮ​ንን ተጣሉ፤</verse>
				<verse number="10">ማኅ​በ​ሩም በሞቱ ጊዜ ምድ​ሪቱ አፍ​ዋን ከፍታ ከቆሬ ጋር ዋጠ​ቻ​ቸው፤ በዚ​ያም ጊዜ እሳ​ቲቱ ሁለት መቶ አም​ሳ​ውን ሰዎች አቃ​ጠ​ለ​ቻ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ለም​ል​ክት ሆኑ።</verse>
				<verse number="11">የቆሬ ልጆች ግን አል​ሞ​ቱም።</verse>
				<verse number="12">የስ​ም​ዖ​ንም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከና​ሙ​ሄል የና​ሙ​ሄ​ላ​ው​ያን ወገን፥ ከኢ​ያ​ሚን የኢ​ያ​ሚ​ና​ው​ያን ልጆች ወገን፥ ከያ​ክን የያ​ክ​ና​ው​ያን ልጆች ወገን፥</verse>
				<verse number="13">ከዛራ የዛ​ራ​ው​ያን ልጆች ወገን፥ ከሳ​ው​ኡል የሳ​ው​ኡ​ላ​ው​ያን ወገን።</verse>
				<verse number="14">እነ​ዚህ የስ​ም​ዖ​ና​ው​ያን ወገ​ኖች ናቸው፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም ሃያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="15">የይ​ሁዳ ልጆች ኤርና አው​ናን፥ ሴሎ​ምና ፋሬስ ዛራም፤ ዔርና አው​ና​ንም በከ​ነ​ዓን ምድር ሞቱ።</verse>
				<verse number="16">የይ​ሁ​ዳም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከሴ​ሎም የሴ​ሎ​ማ​ው​ያን ወገን፥ ከፋ​ሬስ የፋ​ሬ​ሳ​ው​ያን ወገን፥ ከዛራ የዛ​ራ​ው​ያን ወገን።</verse>
				<verse number="17">የፋ​ሬ​ስም ልጆች፤ ከኤ​ስ​ሮም የኤ​ስ​ሮ​ማ​ው​ያን ወገን፥ ከያ​ሙ​ሔል የያ​ሙ​ሔ​ላ​ው​ያን ወገን።</verse>
				<verse number="18">እነ​ዚህ የይ​ሁዳ ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሰባ ስድ​ስት ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="19">የይ​ሳ​ኮር ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከቶላ የቶ​ላ​ው​ያን ወገን፥ ከፉሓ የፉ​ሓ​ው​ያን ወገን፤</verse>
				<verse number="20">ከያ​ሱብ የያ​ሱ​ባ​ው​ያን ወገን፥ ከሥ​ምራ የሥ​ም​ራ​ው​ያን ወገን።</verse>
				<verse number="21">እነ​ዚህ የይ​ሳ​ኮር ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት ስድሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="22">የዛ​ብ​ሎን ወገ​ኖች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ ከሳ​ሬድ የሳ​ሬ​ዳ​ው​ያን ወገን፥ ከኤ​ሎኒ የኤ​ሎ​ኒ​ያ​ው​ያን ወገን፥ ከያ​ሕ​ል​ኤል የያ​ሕ​ል​ኤ​ላ​ው​ያን ወገን።</verse>
				<verse number="23">እነ​ዚህ የዛ​ብ​ሎን ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት ስድሳ ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="24">የጋድ ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከሳ​ፎን የሳ​ፎ​ና​ው​ያን ወገን፥ ከሐጊ የሐ​ጋ​ው​ያን ወገን፥ ከሱኒ የሱ​ኒ​ያ​ው​ያን ወገን፤</verse>
				<verse number="25">ከኤ​ዜን የኤ​ዜ​ና​ው​ያን ወገን፥ ከሳ​ድፍ የሳ​ዳ​ፋ​ው​ያን ወገን፤</verse>
				<verse number="26">ከአ​ሮ​ሐድ የአ​ሮ​ሐ​ዳ​ው​ያን ወገን፥ ከአ​ሩ​ሔል የአ​ሩ​ሔ​ላ​ው​ያን ወገን።</verse>
				<verse number="27">እነ​ዚህ የጋድ ልጆች ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት አርባ አራት ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="28">የአ​ሴር ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከኢ​ያ​ምን የኢ​ያ​ም​ና​ው​ያን ወገን፥ ከኢ​ያሱ የኢ​ያ​ሱ​ያ​ው​ያን ወገን፥ ከበ​ርያ የበ​ር​ያ​ው​ያን ወገን።</verse>
				<verse number="29">ከኮ​ቤር ልጆች፤ ከከ​ቤር የከ​ቤ​ራ​ው​ያን ወገን፥ ከሜ​ል​ክ​ያል የሜ​ል​ክ​ያ​ላ​ው​ያን ወገን።</verse>
				<verse number="30">የአ​ሴ​ርም የሴት ልጁ ስም ሳራ ነበረ።</verse>
				<verse number="31">እነ​ዚህ የአ​ሴር ልጆች ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት አርባ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="32">የዮ​ሴፍ ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ምና​ሴና ኤፍ​ሬም።</verse>
				<verse number="33">የም​ናሴ ልጆች፤ ከማ​ኪር የማ​ኪ​ራ​ው​ያን ወገን፤ ማኪ​ርም ገለ​ዓ​ድን ወለደ፤ ከገ​ለ​ዓድ የገ​ለ​ዓ​ዳ​ው​ያን ወገን።</verse>
				<verse number="34">የገ​ለ​ዓድ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ከአ​ክ​ያ​ዝር የአ​ክ​ያ​ዝ​ራ​ው​ያን ወገን፥ ከኬ​ሌግ የኬ​ሌ​ጋ​ው​ያን ወገን፥</verse>
				<verse number="35">ከኢ​ሳ​ር​ያል የኢ​ሳ​ር​ያ​ላ​ው​ያን ወገን፥ ከሴ​ኬም የሴ​ኬ​ማ​ው​ያን ወገን፥</verse>
				<verse number="36">ከሲ​ማ​ኤር የሲ​ማ​ኤ​ራ​ው​ያን ወገን፥ ከኦ​ፌር የኦ​ፌ​ራ​ው​ያን ወገን።</verse>
				<verse number="37">የኦ​ፌ​ርም ልጅ ሰለ​ጰ​ዓድ ሴቶች ልጆች እንጂ ወን​ዶች ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​ትም፤ የሰ​ለ​ጰ​ዓ​ድም የሴ​ቶች ልጆቹ ስም መሐላ፥ ኑኃ፥ ሄግላ፥ ሚልካ፥ ቴርሳ ነበረ።</verse>
				<verse number="38">እነ​ዚ​ህም የም​ናሴ ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት አምሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="39">በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የኤ​ፍ​ሬም ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ከሱ​ቱላ የሱ​ቱ​ላ​ው​ያን ወገን ከጣ​ናህ የጣ​ና​ሃ​ው​ያን ወገን።</verse>
				<verse number="40">እነ​ዚህ የሱ​ቱላ ልጆች ናቸው፤ ከዔ​ዴን የዔ​ዴ​ና​ው​ያን ወገን።</verse>
				<verse number="41">እነ​ዚህ የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሠላሳ ሁለት ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ። በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የዮ​ሴፍ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="42">የብ​ን​ያም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከበ​ዓሌ የበ​ዓ​ላ​ው​ያን ወገን፥ ከአ​ሲ​ቤር የአ​ሲ​ቤ​ራ​ው​ያን ወገን፥ ከአ​ኪ​ራን የአ​ኪ​ራ​ና​ው​ያን ወገን፥</verse>
				<verse number="43">ከሶ​ፋን የሶ​ፋ​ና​ው​ያን ወገን፥</verse>
				<verse number="44">የበ​ዓ​ሌም ልጆች አዴ​ርና ኖሐ​ማን፤ ከአ​ዴር የአ​ዴ​ራ​ው​ያን ወገን፥ ከኖ​ሐ​ማን የኖ​ሐ​ማ​ና​ው​ያን ወገን።</verse>
				<verse number="45">በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የብ​ን​ያም ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት አርባ አም​ስት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="46">በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የዳን ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ከሰ​ምዒ፥ የሰ​ም​ዒ​ያ​ው​ያን ወገን፤ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የዳን ወገ​ኖች እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="47">የሰ​ም​ዒ​ያ​ው​ያን ወገ​ኖች ሁሉ ቍጥ​ራ​ቸው ስድሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="48">የን​ፍ​ታ​ሌም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከአ​ሴ​ሔል የአ​ሴ​ሔ​ላ​ው​ያን ወገን፥ ከጎ​ሄኒ የጎ​ሄ​ና​ው​ያን ወገን፥</verse>
				<verse number="49">ከየ​ሴር የየ​ሴ​ራ​ው​ያን ወገን፥ ከሴ​ሌም የሴ​ሌ​ማ​ው​ያን ወገን።</verse>
				<verse number="50">በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የን​ፍ​ታ​ሌም ወገ​ኖች እነ​ዚህ ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት አርባ አም​ስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="51">ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የተ​ቈ​ጠ​ሩት እነ​ዚህ ናቸው፤ ስድ​ስት መቶ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ።</verse>
				<verse number="52">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="53">“ለእ​ነ​ዚህ በየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር ምድ​ሪቱ ርስት ሆና ትከ​ፈ​ላ​ለች።</verse>
				<verse number="54">ለብ​ዙ​ዎቹ ብዙ ርስ​ትን ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ለጥ​ቂ​ቶ​ችም ጥቂት ርስ​ትን ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ። ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው እንደ ቍጥ​ራ​ቸው መጠን ርስ​ታ​ቸ​ውን ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="55">ነገር ግን ምድ​ሪቱ በየ​ስ​ማ​ቸው በዕጣ ትከ​ፋ​ፈ​ላ​ለች፤ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ነገድ ይወ​ር​ሳሉ።</verse>
				<verse number="56">በብ​ዙ​ዎ​ችና በጥ​ቂ​ቶች መካ​ከል ርስ​ታ​ቸ​ውን በዕጣ ትከ​ፍ​ላ​ለህ።</verse>
				<verse number="57">የሌዊ ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የተ​ቈ​ጠ​ሩት እነ​ዚህ ናቸው፤ ከጌ​ድ​ሶን የጌ​ድ​ሶ​ና​ው​ያን ወገን፥ ከቀ​ዓት የቀ​ዓ​ታ​ው​ያን ወገን፥ ከሜ​ራሪ የሜ​ራ​ራ​ው​ያን ወገን።</verse>
				<verse number="58">እነ​ዚህ የሌዊ ልጆች ወገ​ኖች ናቸው፤ የሎ​ቢኒ ወገን፥ የኬ​ብ​ሮን ወገን፥ የሞ​ሓሊ ወገን፥ የሐ​ሙሲ ወገን፥</verse>
				<verse number="59">የቆሬ ወገን፥ የቀ​ዓት ወገን። ቀዓ​ትም እን​በ​ረ​ምን ወለደ። በግ​ብፅ ሀገር እነ​ዚ​ህን ሌዋ​ው​ያ​ንን የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸው የሌዊ ልጅ የእ​ን​በ​ረም ሚስት ስም ዮካ​ብድ ነበረ። ለእ​ን​በ​ረ​ምም አሮ​ን​ንና ሙሴን እኅ​ታ​ቸ​ው​ንም ማር​ያ​ምን ወለ​ደ​ች​ለት።</verse>
				<verse number="60">ለአ​ሮ​ንም ናዳብ፥ አብ​ዩድ፥ አል​ዓ​ዛ​ርና ኢታ​ምር ተወ​ለ​ዱ​ለት።</verse>
				<verse number="61">በሲና በረሃ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከሌላ እሳት ባቀ​ረቡ ጊዜ ናዳ​ብና አብ​ዩድ ሞቱ።</verse>
				<verse number="62">ከአ​ንድ ወርም ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉ ወን​ዶች ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ቈ​ጠሩ ሃያ ሦስት ሺህ ነበሩ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መካ​ከል ርስት አል​ተ​ሰ​ጣ​ቸ​ው​ምና ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር አል​ተ​ቈ​ጠ​ሩም።</verse>
				<verse number="63">በሞ​ዓብ ሜዳ ላይ በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት ሲቈ​ጥሩ፥ ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛር የቈ​ጠ​ሩ​አ​ቸው የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="64">ነገር ግን ሙሴና ካህኑ አሮን በሲና ምድረ በዳ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በቈ​ጠ​ሩ​አ​ቸው ጊዜ ከነ​በ​ሩት ከእ​ነ​ዚያ መካ​ከል አን​ድም ሰው አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="65">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እነ​ርሱ፥ “በእ​ው​ነት በም​ድረ በዳ ይሞ​ታሉ” ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና። ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌብ፥ ከነ​ዌም ልጅ ከኢ​ያሱ በቀር ከእ​ነ​ርሱ አንድ ሰው ስንኳ አል​ቀ​ረም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="27">
				<verse number="1">ከዮ​ሴፍ ልጅ ከም​ናሴ ወገን ፥ የም​ናሴ ልጅ፥ የማ​ኪር ልጅ፥ የገ​ለ​አድ ልጅ፥ የኦ​ፌር ልጅ፥ የሰ​ለ​ጰ​ዓድ ሴቶች ልጆች መጡ፤ የእ​ነ​ዚ​ህም ሴቶች ልጆች ስሞች መሐላ፥ ኑኃ፥ ሄግላ፥ ሚልካ፥ ቴርሳ ነበሩ።</verse>
				<verse number="2">በም​ስ​ክ​ሩም ድን​ኳን ደጃፍ አጠ​ገብ በሙ​ሴና በካ​ህኑ በአ​ል​ዓ​ዛር፥ በአ​ለ​ቆ​ቹም፥ በማ​ኅ​በ​ሩም ሁሉ ፊት ቆመው እን​ዲህ አሉ፦</verse>
				<verse number="3">“አባ​ታ​ችን በም​ድረ በዳ ሞተ፤ በራሱ ኀጢ​አት ሞተ እንጂ ከቆሬ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ በተ​ሰ​በ​ሰቡ ወገን መካ​ከል አል​ነ​በ​ረም፤ ወን​ዶ​ችም ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​ትም።</verse>
				<verse number="4">ወንድ ልጅስ ባይ​ኖ​ረው የአ​ባ​ታ​ችን ስም ከወ​ገኑ መካ​ከል ለምን ይጠ​ፋል?</verse>
				<verse number="5">በአ​ባ​ታ​ችን ወን​ድ​ሞች መካ​ከል ርስ​ትን ስጠን።” ሙሴም ነገ​ራ​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቀ​ረበ።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="7">“የሰ​ለ​ጰ​ዓድ ልጆች እው​ነት ተና​ግ​ረ​ዋል፤ በአ​ባ​ታ​ቸው ወን​ድ​ሞች መካ​ከል የር​ስት ድርሻ ስጣ​ቸው፤ የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን ርስት ለእ​ነ​ርሱ ስጥ።</verse>
				<verse number="8">ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ሰው ቢሞት፥ ወንድ ልጅም ባይ​ኖ​ረው፥ ርስ​ቱን ለሴ​ቶች ልጆቹ ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="9">ሴት ልጅም ባት​ኖ​ረው፥ ርስ​ቱን ለወ​ን​ድ​ሞቹ ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="10">ወን​ድ​ሞ​ችም ባይ​ኖ​ሩት፥ ርስ​ቱን ለአ​ባቱ ወን​ድ​ሞች ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="11">የአ​ባ​ቱም ወን​ድ​ሞች ባይ​ኖ​ሩት ከወ​ገኑ ለቀ​ረበ ዘመድ ርስ​ቱን ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤ እር​ሱም ይው​ረ​ሰው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ይሁን።”</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ​ዚህ በና​ባው አሻ​ገር ወዳ​ለው ተራራ ውጣ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ይገ​ዙ​አት ዘንድ እኔ የም​ሰ​ጣ​ቸ​ውን የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር እያት፤</verse>
				<verse number="13">ባየ​ሃ​ትም ጊዜ ወን​ድ​ምህ አሮን በሖር ተራራ እንደ ተጨ​መረ አንተ ደግሞ ወደ ወገ​ንህ ትጨ​መ​ራ​ለህ።</verse>
				<verse number="14">እና​ንተ በጺን ምድረ በዳ በማ​ኅ​በሩ ጠብ በቃሌ ላይ ዐም​ፃ​ች​ኋ​ልና፥ በእ​ነ​ር​ሱም ፊት በው​ኃው ዘንድ አላ​ከ​በ​ራ​ች​ሁ​ኝ​ምና። ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃ​ዴስ ያለው የክ​ር​ክር ውኃ ነው።”</verse>
				<verse number="15">ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="16">“የሥ​ጋና የነ​ፍስ ሁሉ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ሕዝብ ላይ የሚ​ሆ​ነ​ውን ሰው ይሹም፤</verse>
				<verse number="17">በፊ​ታ​ቸው የሚ​ወ​ጣ​ው​ንና የሚ​ገ​ባ​ውን፥ የሚ​ያ​ስ​ወ​ጣ​ቸ​ው​ንና፥ የሚ​ያ​ስ​ገ​ባ​ቸ​ው​ንም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማኅ​በር እረኛ እን​ደ​ሌ​ለው መንጋ እን​ዳ​ይ​ሆን።”</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “መን​ፈስ ቅዱስ ያለ​በ​ትን ሰው የነ​ዌን ልጅ ኢያ​ሱን ወስ​ደህ እጅ​ህን በላዩ ጫን​በት፤</verse>
				<verse number="19">በካ​ህ​ኑም በአ​ል​ዓ​ዛር ፊት አቁ​መው፤ በማ​ኅ​በ​ሩም ፊት እዘ​ዘው፤ ስለ እር​ሱም በፊ​ታ​ቸው እዘዝ።</verse>
				<verse number="20">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እን​ዲ​ታ​ዘ​ዙት ከክ​ብ​ርህ ስጠው።</verse>
				<verse number="21">በካ​ህ​ኑም በአ​ል​ዓ​ዛር ፊት ይቁም፤ እር​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ፍርድ ይጠ​ይ​ቅ​ለት፤ እርሱ ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፤ በቃ​ሉም ይግቡ።”</verse>
				<verse number="22">ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረገ፤ ኢያ​ሱ​ንም ወስዶ በካ​ህኑ በአ​ል​ዓ​ዛ​ርና በማ​ኅ​በሩ ሁሉ ፊት አቆ​መው፤</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እንደ አዘ​ዘው፥ እጁን በላዩ ጫነ​በ​ትና፥ ሾመው፤ አዘ​ዘ​ውም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="28">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ ብለህ እዘ​ዛ​ቸው፦ ቍር​ባ​ኔን፥ መባ​ዬ​ንና የበጎ መዓዛ መሥ​ዋ​ዕ​ቴን በበ​ዓ​ላት ቀኖች ታቀ​ር​ቡ​ልኝ ዘንድ ጠብቁ።</verse>
				<verse number="3">እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ በእ​ሳት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ታ​ቀ​ር​ቡት ቍር​ባን ይህ ነው፤ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሁለት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ዕለት ዕለት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="4">አን​ዱን ጠቦት በማ​ለዳ፥ ሌላ​ው​ንም ጠቦት በማታ አቅ​ርቡ፤</verse>
				<verse number="5">ለእ​ህ​ልም ቍር​ባን የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ በሆነ፥ ተወ​ቅጦ በተ​ጠ​ለለ ዘይት የተ​ለ​ወሰ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ እጅ መል​ካም ዱቄት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="6">በእ​ሳት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የቀ​ረበ፥ በሲና ተራራ የተ​ሠራ ለዘ​ወ​ትር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው።</verse>
				<verse number="7">የመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ለአ​ንድ ጠቦት የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተ​ኛው እጅ ነው፤ በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ጠጥ ቍር​ባን መጠጥ ታፈ​ስ​ሳ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="8">ሌላ​ው​ንም ጠቦት በማታ ጊዜ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ንና የመ​ጠ​ጡን ቍር​ባን በማ​ለዳ እን​ዳ​ቀ​ረ​ባ​ችሁ በእ​ሳት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ታቀ​ር​ቡ​ታ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="9">“በሰ​ን​በ​ትም ቀን ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሁለት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥ ለእ​ህ​ልም ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ መል​ካም ዱቄት፥ የመ​ጠ​ጡ​ንም ቍር​ባን ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="10">በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ሌላ፥ ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ፥ በየ​ሰ​ን​በቱ ሁሉ የም​ታ​ቀ​ር​ቡት የሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ይህ ነው።</verse>
				<verse number="11">“በወ​ሩም መባቻ ለእ​ግ​ዚ​አ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ከላ​ሞች ሁለት፥ አንድ አውራ በግ፥ ነው​ርም የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥</verse>
				<verse number="12">ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወይ​ፈን ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ መል​ካም ዱቄት፥ ለአ​ው​ራው በግ ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ፥ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ መል​ካም ዱቄት፥</verse>
				<verse number="13">ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ጠቦት ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ፥ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ዐሥ​ረኛ እጅ ሁለት እጅ መል​ካም ዱቄት፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በእ​ሳት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="14">የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም ለአ​ንድ ወይ​ፈን የኢን ግማሽ፥ ለአ​ው​ራው በግም የኢን ሲሦ፥ ለአ​ን​ዱም ጠቦት የኢን አራ​ተኛ እጅ የወ​ይን ጠጅ ይሆ​ናል፤ ይህ ለዓ​መቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው።</verse>
				<verse number="15">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ​ኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከመ​ጠጡ ቍር​ባን ሌላ ይቀ​ር​ባል።</verse>
				<verse number="16">“በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲካ ነው።</verse>
				<verse number="17">በዚ​ህም ወር በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን በዓል ይሆ​ናል፤ ሰባት ቀን ቂጣ እን​ጀራ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="18">የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የተ​ቀ​ደሰ ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ በእ​ር​ሱም የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​በት።</verse>
				<verse number="19">በእ​ሳ​ትም የተ​ደ​ረ​ገ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ከላ​ሞች ሁለት በሬ​ዎች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸው ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="20">የእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንም በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት፥ ለአ​ንድ ወይ​ፈን ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአ​ው​ራ​ውም በግ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ፥</verse>
				<verse number="21">ለሰ​ባ​ቱም ጠቦ​ቶች ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ጠቦት ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ዐሥ​ረኛ እጅ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="22">ማስ​ተ​ስ​ረያ የሚ​ሆ​ን​ላ​ች​ሁን ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="23">ማልዶ ከሚ​ቀ​ር​በው በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ሌላ እነ​ዚ​ህን ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="24">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በእ​ሳት የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ቍር​ባ​ንና መሥ​ዋ​ዕት ሰባት ቀን በየ​ዕ​ለቱ እን​ዲሁ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከመ​ጠጡ ቍር​ባን ሌላ ይቀ​ር​ባል።</verse>
				<verse number="25">ሰባ​ተ​ኛ​ውም ቀን የተ​ቀ​ደሰ ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​በት።</verse>
				<verse number="26">“በበ​ዓለ ሠዊት ቀን በሰ​ን​በ​ታት በዓ​ላ​ችሁ አዲ​ሱን የእ​ህል ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባቀ​ረ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ የተ​ቀ​ደሰ ቀን ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፤ የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​በት።</verse>
				<verse number="27">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ከላ​ሞች ሁለት በሬ​ዎች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥</verse>
				<verse number="28">ለእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸው በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት፥ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ወይ​ፈን ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአ​ን​ዱም አውራ በግ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ፥</verse>
				<verse number="29">ለሰ​ባ​ቱም ጠቦ​ቶች ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ጠቦት ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ዐሥ​ረኛ እጅ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="30">ማስ​ተ​ስ​ረያ የሚ​ሆ​ን​ላ​ች​ሁን ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="31">በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን ሌላ እነ​ር​ሱ​ንና የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ነው​ርም የሌ​ለ​ባ​ቸው ይሁኑ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="29">
				<verse number="1">“በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ከወሩ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያዋ ቀን ለእ​ና​ንተ ይህች ዕለት የተ​ቀ​ደ​ሰች ናት፤ የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​ባት፤ ምል​ክት ያለ​ባት ቀን ትሁ​ን​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="2">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ ከላ​ሞች አንድ በሬ፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት፥ የበግ ጠቦ​ቶች፥</verse>
				<verse number="3">ለእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸው በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት፥ ለበ​ሬው ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአ​ው​ራው በግ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ፥</verse>
				<verse number="4">ለሰ​ባቱ ጠቦ​ቶች ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ዐሥ​ረኛ እጅ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="5">ማስ​ተ​ስ​ረ​ያም የሚ​ሆ​ን​ላ​ች​ሁን ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="6">በወሩ መባቻ ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ሌላ ከእ​ህሉ ቍር​ባን፥ ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን እንደ ሕጋ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በእ​ሳት የሚ​ቀ​ርቡ ናቸው።</verse>
				<verse number="7">“የዚ​ህም ወር ዐሥ​ረ​ኛዋ ቀን ለእ​ና​ንተ የተ​ቀ​ደ​ሰች ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን አስ​ጨ​ን​ቁ​አት፤ ከሥራ ሁሉ ምንም አታ​ድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="8">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ፥ ከላ​ሞች አንድ በሬ፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውም ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="9">ለእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት፥ ለበ​ሬው ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአ​ው​ራው በግ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ፥</verse>
				<verse number="10">ለሰ​ባቱ ጠቦ​ቶች ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ዐሥ​ረኛ እጅ፥</verse>
				<verse number="11">ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል አቅ​ርቡ። ከሚ​ያ​ስ​ተ​ሰ​ር​የው ከኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ በዘ​ወ​ት​ርም ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን፥ ከመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም ሌላ አቅ​ር​ቡት።</verse>
				<verse number="12">“በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ዐሥራ አም​ስ​ተ​ኛዋ ቀን ለእ​ና​ንተ የተ​ቀ​ደ​ሰች ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​ባት፤ ሰባት ቀንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል አድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="13">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ ዐሥራ ሦስት በሬ​ዎች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ዐሥራ አራት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች አቅ​ርቡ፤ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውም ይሁኑ።</verse>
				<verse number="14">ለእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት፥ ለዐ​ሥራ ሦስት በሬ​ዎች ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለሁ​ለቱ አውራ በጎች ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ፥</verse>
				<verse number="15">ለዐ​ሥራ አራቱ ጠቦ​ቶች ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ዐሥ​ረኛ እጅ፥</verse>
				<verse number="16">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ የሚ​ቀ​ርቡ ናቸው።</verse>
				<verse number="17">“በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ዐሥራ ሁለት በሬ​ዎ​ችን፥ ሁለት አውራ በጎ​ችን፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ዐሥራ አራት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶ​ችን፥</verse>
				<verse number="18">ለበ​ሬ​ዎ​ቹና ለአ​ውራ በጎቹ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም የእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንና የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን እንደ ቍጥ​ራ​ችው መጠን እንደ ሕጉ፥</verse>
				<verse number="19">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየ​ልን ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን፥ ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባ​ና​ቸው ሌላ የሚ​ቀ​ርቡ ናቸው።</verse>
				<verse number="20">“በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ዐሥራ አንድ በሬ​ዎች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ዐሥራ አራት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥</verse>
				<verse number="21">ለበ​ሬ​ዎ​ቹና ለአ​ውራ በጎቹ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም የእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንና የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን እንደ ቍጥ​ራ​ቸው መጠን እንደ ሕጋ​ቸው፥</verse>
				<verse number="22">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል፥ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን፥ ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="23">“በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ቀን ዐሥር በሬ​ዎች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸው ዐሥራ አራት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥</verse>
				<verse number="24">ለበ​ሬ​ዎ​ቹና ለአ​ውራ በጎቹ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም የእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንና የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን እንደ ቍጥ​ራ​ችው መጠን እንደ ሕጋ​ቸው፥</verse>
				<verse number="25">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል፥ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን፥ ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="26">“በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ቀን ዘጠኝ በሬ​ዎች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸው ዐሥራ አራት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥</verse>
				<verse number="27">ለበ​ሬ​ዎ​ቹና ለአ​ውራ በጎቹ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም የእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንና የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን እንደ ቍጥ​ራ​ቸው መጠን እንደ ሕጋ​ቸው፥</verse>
				<verse number="28">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል፥ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን፥ ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="29">“በስ​ድ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ስም​ንት በሬ​ዎች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ዐሥራ አራት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥</verse>
				<verse number="30">ለበ​ሬ​ዎ​ችና ለአ​ውራ በጎቹ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም የእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንና የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን እንደ ቍጥ​ራ​ቸው መጠን እንደ ሕጋ​ቸው፥</verse>
				<verse number="31">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል፥ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="32">“በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሰባት በሬ​ዎች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ዐሥራ አራት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥</verse>
				<verse number="33">ለበ​ሬ​ዎቹ፥ ለአ​ውራ በጎቹ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም የእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንና የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን እንደ ቍጥ​ራ​ቸው መጠን እንደ ሕጋ​ቸው፥</verse>
				<verse number="34">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል፥ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="35">“ስም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን የተ​ቀ​ደሰ በዓል ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​በት።</verse>
				<verse number="36">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በእ​ሳት የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ አንድ በሬ፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="37">የእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ውና የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸው ለበ​ሬው፥ ለአ​ው​ራ​ውም በግ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም እንደ ቍጥ​ራ​ቸው መጠን እንደ ሕጋ​ቸው ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="38">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ የሚ​ቀ​ርቡ ናቸው።</verse>
				<verse number="39">“እነ​ዚ​ህ​ንም፥ ከስ​እ​ለ​ታ​ች​ሁና በፈ​ቃ​ዳ​ችሁ ከም​ታ​መ​ጡት ሌላ፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ለእ​ህ​ልም፥ ለመ​ጠ​ጥም ቍር​ባን፥ ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችሁ በበ​ዓ​ላ​ችሁ ጊዜ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ርቡ።”</verse>
				<verse number="40">ሙሴም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ነገ​ራ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="30">
				<verse number="1">ሙሴም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ነገ​ዶች አለ​ቆች እን​ዲህ ብሎ ነገ​ራ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘው ነገር ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">ሰው ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለት ቢሳል፥ ወይም መሐ​ላን ቢምል፤ ራሱ​ንም ቢለይ፥ ቃሉን አያ​ር​ክስ፤ ከአፉ እንደ ወጣው ሁሉ ያድ​ርግ።</verse>
				<verse number="3">ሴትም ደግሞ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለት ብት​ሳል፥ እር​ስ​ዋም በአ​ባቷ ቤት ሳለች በብ​ላ​ቴ​ን​ነቷ ጊዜ ራስ​ዋን ብት​ለይ፥</verse>
				<verse number="4">አባ​ቷም ስእ​ለ​ቷ​ንና ራስ​ዋን የለ​የ​ች​በ​ትን ቢሰማ፥ አባ​ቷም ዝም ቢላት፥ ስእ​ለቷ ሁሉ ይጸ​ናል፤ ራስ​ዋ​ንም ያሰ​ረ​ች​በት መሐላ ሁሉ ይጸ​ናል።</verse>
				<verse number="5">አባቷ ግን በሰ​ማ​በት ቀን ቢከ​ለ​ክ​ላት፥ ስእ​ለቷ፥ ራስ​ዋ​ንም ያሰ​ረ​ች​በት መሐ​ላዋ አይ​ጸ​ኑም፤ አባቷ ከል​ክ​ሎ​አ​ታ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ይላ​ታል።</verse>
				<verse number="6">“ባል ያገ​ባች ብት​ሆን፥ በአ​ን​ደ​በ​ቷም እንደ ተና​ገ​ረች ስለ ራስዋ የተ​ሳ​ለ​ችው ስእ​ለት በራ​ስዋ ላይ ቢሆን፥</verse>
				<verse number="7">ባል​ዋም ቢሰማ፥ በሰ​ማ​በ​ትም ቀን ዝም ቢላት፥ ስእ​ለቷ፥ ራስ​ዋ​ንም ያሰ​ረ​ች​በት መሐላ ይጸ​ናሉ።</verse>
				<verse number="8">ባልዋ ግን በሰ​ማ​በት ቀን ቢከ​ለ​ክ​ላት፥ ስእ​ለ​ቷና ራስ​ዋን ያሰ​ረ​ች​በት መሐላ አይ​ጸ​ኑም፤ ባልዋ ከል​ክ​ሎ​አ​ታ​ልና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይቅር ይላ​ታል።</verse>
				<verse number="9">“ባልዋ የሞ​ተ​ባት ወይም የተ​ፋ​ታች ግን ስእ​ለ​ቷና ራስ​ዋን ያሰ​ረ​ች​በት መሐላ ይጸ​ኑ​ባ​ታል።</verse>
				<verse number="10">ሴትም በባ​ልዋ ቤት ሳለች ብት​ሳል፥ ወይም ራስ​ዋን በመ​ሐላ ብታ​ስር፥</verse>
				<verse number="11">ባል​ዋም ሰምቶ ዝም ቢላት፥ ባይ​ከ​ለ​ክ​ላ​ትም፥ ስእ​ለቷ ሁሉ ራስ​ዋ​ንም ያሰ​ረ​ች​በት መሐላ ሁሉ ይጸ​ናል።</verse>
				<verse number="12">ባልዋ ግን በሰ​ማ​በት ቀን ስእ​ለ​ቷን ቢከ​ለ​ክ​ላት፥ ስለ ስእ​ለቷ ወይም ራስ​ዋን ስላ​ሰ​ረ​ች​በት መሐላ ከአ​ፍዋ የወ​ጣው ነገር አይ​ጸ​ናም፤ ባልዋ ከል​ክ​ሏ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያነ​ጻ​ታል።</verse>
				<verse number="13">“ስእ​ለ​ቷን ሁሉ፥ ነፍ​ስ​ዋ​ንም የሚ​ያ​ዋ​ር​ደ​ውን የመ​ሐላ ማሰ​ሪያ ሁሉ ባልዋ ያጸ​ና​ዋል፤ ወይም ባልዋ ይከ​ለ​ክ​ለ​ዋል።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን በየ​ዕ​ለቱ ዝም ቢላት፥ ስእ​ለ​ቷን ሁሉ፥ በእ​ር​ስ​ዋም ላይ ያለ​ውን መሐላ ሁሉ ያጸ​ና​ዋል፤ በሰ​ማ​በት ቀን ዝም ብሎ​አ​ታ​ልና አጽ​ን​ቶ​ታል።</verse>
				<verse number="15">ከሰ​ማው በኋላ ግን ቢከ​ለ​ክ​ላት ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል።”</verse>
				<verse number="16">እር​ስዋ በብ​ላ​ቴ​ን​ነቷ ጊዜ በአ​ባቷ ቤት ሳለች በአ​ባ​ትና በል​ጂቱ መካ​ከል፥ ወይም በባ​ልና በሚ​ስት መካ​ከል ይሆን ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን ያዘ​ዘው ሥር​ዐት ይህ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="31">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በቀል ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንን ተበ​ቀል፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ወገ​ኖ​ችህ ትጨ​መ​ራ​ለህ።”</verse>
				<verse number="3">ሙሴም ለሕ​ዝቡ እን​ዲህ ብሎ ነገ​ራ​ቸው፥ “ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ሰዎ​ችን አስ​ታ​ጥቁ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ምድ​ያ​ምን ይበ​ቀሉ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከም​ድ​ያም ጋር ይሰ​ለፉ።</verse>
				<verse number="4">ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ሁሉ ከየ​ነ​ገዱ አንድ አንድ ሺህ ሰው ወደ ጦር​ነት ስደዱ፤”</verse>
				<verse number="5">ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አእ​ላ​ፋት፥ ከየ​ነ​ገዱ አንድ አንድ ሺህ ቈጠሩ፤ ለጦ​ር​ነት የተ​ሰ​ለ​ፉ​ትም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሆኑ።</verse>
				<verse number="6">ሙሴም ከየ​ነ​ገዱ አንድ ሺህ ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸ​ውና ከካ​ህኑ ከአ​ሮን ልጅ ከአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ከፊ​ን​ሐስ ጋር ሰደደ፤ ንዋ​ያተ ቅድ​ሳ​ቱና ምል​ክት መስጫ መለ​ከ​ቶ​ችም በእ​ጆ​ቻ​ቸው ነበሩ።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ ከም​ድ​ያም ጋር ተዋጉ፤ ወን​ዶ​ች​ንም ሁሉ ገደሉ።</verse>
				<verse number="8">የም​ድ​ያ​ም​ንም ነገ​ሥ​ታት በዚ​ያው ጦር​ነት በአ​ን​ድ​ነት ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ አም​ስ​ቱም የም​ድ​ያም ነገ​ሥ​ታት ኤዊ፥ ሮቆም፥ ሱር፥ ሑር፥ ሮባቅ ነበሩ፤ የቢ​ዖ​ር​ንም ልጅ በለ​ዓ​ምን ደግሞ በዚ​ያው ጦር​ነት በሰ​ይፍ ገደ​ሉት።</verse>
				<verse number="9">የም​ድ​ያ​ም​ንም ሴቶ​ችና ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ማረኩ፤ እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ዕቃ​ቸ​ውን፥ ንብ​ረ​ታ​ቸ​ው​ንና ኀይ​ላ​ቸ​ውን በዘ​በዙ።</verse>
				<verse number="10">የተ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ውን ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ፥ ሰፈ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ በእ​ሳት አቃ​ጠሉ።</verse>
				<verse number="11">ከሰው እስከ እን​ስሳ ምር​ኮ​አ​ቸ​ው​ንና ብዝ​በ​ዛ​ቸ​ውን ሁሉ ወሰዱ።</verse>
				<verse number="12">የማ​ረ​ኩ​ትን ምር​ኮ​ው​ንና የዘ​ረ​ፉ​ትን ወደ ሙሴና ወደ ካህኑ ወደ አል​ዓ​ዛር፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት በሞ​ዓብ ሜዳ ወዳ​ለው ሰፈር አመጡ።</verse>
				<verse number="13">ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም፥ የማ​ኅ​በ​ሩም አለ​ቆች ሁሉ ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ ሊገ​ና​ኙ​አ​ቸው ወጡ።</verse>
				<verse number="14">ሙሴም ከዘ​መቻ በተ​መ​ለ​ሱት በጭ​ፍራ አለ​ቆች፥ በሻ​ለ​ቆ​ችና በመቶ አለ​ቆች ላይ ተቈጣ።</verse>
				<verse number="15">ሙሴም አላ​ቸው፥ “ሴቶ​ችን ሁሉ ለምን አዳ​ና​ች​ኋ​ቸው?</verse>
				<verse number="16">እነ​ርሱ በበ​ለ​ዓም ምክር በፌ​ጎር ምክ​ን​ያት የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች የሚ​ያ​ስቱ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል እን​ዲ​ስቱ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ዕን​ቅ​ፋ​ቶች ናቸ​ውና፤ ስለ​ዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማኅ​በር ላይ መቅ​ሠ​ፍት ሆኖ​አል፤</verse>
				<verse number="17">አሁ​ንም እን​ግ​ዲህ ወን​ዱን ሁሉ በአ​ለ​በት ግደሉ፥ ወን​ድ​ንም የም​ታ​ው​ቀ​ውን ሴት ሁሉ ግደሉ።</verse>
				<verse number="18">ወን​ድን የማ​ያ​ው​ቁ​ትን ሴቶች ልጆ​ችን ሁሉ ግን አድ​ኑ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">እና​ን​ተም ከሰ​ፈሩ ውጭ ሰባት ቀን ስፈሩ፤ ሰውን የገ​ደለ ሁሉ፥ የተ​ገ​ደ​ለ​ው​ንም የዳ​ሰሰ ሁሉ፥ እና​ን​ተና የማ​ረ​ካ​ች​ኋ​ቸ​ውም በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ንጹሕ አድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="20">ልብ​ስ​ንም፥ ከቁ​ር​በ​ትም የተ​ዘ​ጋ​ጀ​ውን ሁሉ፥ ከፍ​የ​ልም ጠጕር፥ ከዕ​ን​ጨ​ትም የተ​ሠ​ራ​ውን ሁሉ ንጹሕ አድ​ርጉ።”</verse>
				<verse number="21">ካህ​ኑም አል​ዓ​ዛር ከሰ​ልፍ የመ​ጡ​ትን ሰዎች አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን ያዘ​ዘው የሕጉ ሥር​ዐት ይህ ነው፤</verse>
				<verse number="22">ወር​ቁና ብሩ፥ ናሱም፥ ብረ​ቱም፥ ቆር​ቆ​ሮ​ውም፥ እር​ሳ​ሱም፥</verse>
				<verse number="23">በእ​ሳት ለማ​ለፍ የሚ​ች​ለው ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ ይሆ​ናል፤ ነገር ግን በማ​ን​ጻት ውኃ ደግሞ ይጠ​ራል። በእ​ሳ​ትም ለማ​ለፍ የማ​ይ​ች​ለ​ውን በውኃ ታሳ​ል​ፉ​ታ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="24">በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ልብ​ሳ​ች​ሁን እጠቡ፤ ንጹ​ሓ​ንም ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ትቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="25">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="26">“አን​ተና ካህኑ አል​ዓ​ዛር፥ የማ​ኅ​በ​ሩም አባ​ቶች አለ​ቆች የተ​ማ​ረ​ኩ​ትን ሰውና እን​ስሳ ቍጠሩ።</verse>
				<verse number="27">ምር​ኮ​ው​ንም በተ​ዋ​ጉ​ትና ወደ ሰልፍ በወ​ጡት፥ በማ​ኅ​በ​ሩም ሁሉ መካ​ከል ትከ​ፍ​ላ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="28">ከእ​ነ​ዚ​ያም ከተ​ዋ​ጉት፥ ወደ ሰል​ፍም ከወ​ጡት ሰል​ፈ​ኞች ዘንድ ከሰ​ዎ​ችም፥ ከበ​ሬ​ዎ​ችም፥ ከበ​ጎ​ችም፥ ከአ​ህ​ዮ​ችም፥ ከአ​ም​ስት መቶ አንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግብር ታወ​ጣ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="29">ከድ​ር​ሻ​ቸው እኩ​ሌታ ወስ​ደህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቀዳ​ም​ያት ለካ​ህኑ ለአ​ል​ዓ​ዛር ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="30">ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ድርሻ እኩ​ሌታ፥ ከሰ​ዎ​ችም፥ ከበ​ሬ​ዎ​ችም፥ ከበ​ጎ​ችም፥ ከአ​ህ​ዮ​ችም፥ ከእ​ን​ስ​ሶ​ችም ሁሉ ከአ​ምሳ አንድ ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ድን​ኳን ሥር​ዐት ለሚ​ጠ​ብቁ ለሌ​ዋ​ው​ያን ትሰ​ጣ​ለህ።”</verse>
				<verse number="31">ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="32">ወደ ሰልፍ የወጡ ሰዎ​ችም ከወ​ሰ​ዱት ብዝ​በዛ የቀ​ረው ምርኮ እን​ዲህ ሆነ፤ ስድ​ስት መቶ ሰባ አም​ስት ሺህ በጎች፤</verse>
				<verse number="33">ሰባ ሁለት ሺህ በሬ​ዎች፥</verse>
				<verse number="34">ስድሳ አንድ ሺህ አህ​ዮች፥</verse>
				<verse number="35">ወንድ ከማ​ያ​ውቁ ሴቶ​ችም ሠላሳ ሁለት ሺህ ነፍስ።</verse>
				<verse number="36">በዘ​መ​ቻም ለነ​በሩ ሰዎች ድርሻ የሆነ እኩ​ሌታ ከበግ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ሺህ አም​ስት መቶ በጎች ነበሩ፤</verse>
				<verse number="37">ከበ​ጎ​ችም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግብር ስድ​ስት መቶ ሰባ አም​ስት ነበረ።</verse>
				<verse number="38">በሬ​ዎ​ችም ሠላሳ ስድ​ስት ሺህ ነበሩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብር ሰባ ሁለት ነበረ።</verse>
				<verse number="39">አህ​ዮ​ቹም ሠላሳ ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብር ስድሳ አንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="40">ሰዎ​ቹም ዐሥራ ስድ​ስት ሺህ ነበሩ ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብር ሠላሳ ሁለት ነበረ።</verse>
				<verse number="41">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሙሴ፦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የለ​ዩ​ትን ግብር ለካ​ህኑ ለአ​ል​ዓ​ዛር ሰጠው።</verse>
				<verse number="42">ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እኩ​ሌ​ታም፥ ወደ ሰልፍ ከወ​ጡት ወን​ዶች ላይ ሙሴ የለ​የው፥</verse>
				<verse number="43">የማ​ኅ​በሩ ድርሻ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ሺህ አም​ስት መቶ በጎች፥</verse>
				<verse number="44">ሠላሳ ስድ​ስት ሺህ በሬ​ዎች፤</verse>
				<verse number="45">ሠላሳ ሺህ አም​ስት መቶ አህ​ዮች፥</verse>
				<verse number="46">ዐሥራ ስድ​ስት ሺህ ሰዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="47">ሙሴ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ድርሻ ከሰ​ውና ከእ​ን​ስሳ ከሃ​ምሳ አንድ ወሰደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድን​ኳን ሥር​ዐት ለሚ​ጠ​ብቁ ሌዋ​ው​ያን ሰጠ።</verse>
				<verse number="48">በሠ​ራ​ዊት አእ​ላ​ፋት ላይ የተ​ሾ​ሙት አለ​ቆች፥ ሻለ​ቆ​ችና የመቶ አለ​ቆች ወደ ሙሴ ቀረቡ፤ ሙሴ​ንም እን​ዲህ አሉት፦</verse>
				<verse number="49">“ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ወደ ሰልፍ የወ​ጡ​ትን ከእ​ጃ​ችን በታች ያሉ​ትን ቈጠሩ፤ ከእ​ኛም አንድ አል​ጐ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="50">ሰውም ሁሉ ከአ​ገ​ኘው ከወ​ርቅ ዕቃ፥ ከእ​ግር አል​ቦም፥ ከአ​ም​ባ​ርም፥ ከቀ​ለ​በ​ትም ከጕ​ት​ቻም፥ ከድ​ሪ​ውም ስለ እኛ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ታስ​ተ​ሰ​ር​ዩ​ልን ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አም​ጥ​ተ​ናል” አሉት።</verse>
				<verse number="51">ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም ወር​ቁ​ንና በልዩ ልዩ የተ​ሠ​ራ​ውን ዕቃ ሁሉ ከእ​ጃ​ቸው ተቀ​በሉ።</verse>
				<verse number="52">ከሻ​ለ​ቆ​ችና ከመቶ አለ​ቆች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የለ​ዩ​ትና ያቀ​ረ​ቡት ወርቅ ሁሉ ዐሥራ ስድ​ስት ሺህ ሰባት መቶ አምሳ ሰቅል ነበረ።</verse>
				<verse number="53">ወደ ሰልፍ የወጡ ሰዎች ሁሉ የማ​ረ​ኩ​ትን ለየ​ራ​ሳ​ቸው ወሰዱ።</verse>
				<verse number="54">ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም ወር​ቁን ከሻ​ለ​ቆ​ችና ከመቶ አለ​ቆች ወሰዱ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መታ​ሰ​ቢያ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን አገ​ቡት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="32">
				<verse number="1">ለሮ​ቤል ልጆ​ችና ለጋድ ልጆች እጅግ ብዙ እን​ስ​ሶች ነበ​ሩ​አ​ቸው፤ እነ​ሆም፥ የኢ​ያ​ዜር ምድ​ርና የገ​ለ​ዓድ ምድር የከ​ብት ሀገር እንደ ነበረ አዩ።</verse>
				<verse number="2">የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆ​ችም መጥ​ተው ሙሴ​ንና ካህ​ኑን አል​ዓ​ዛ​ርን፥ የማ​ኅ​በ​ሩ​ንም አለ​ቆች እን​ዲህ ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው፦</verse>
				<verse number="3">“አጣ​ሮት፥ ዲቦን፥ ያዜር፥ ነምራ፥ ሐሴ​ቦን፥ ኤል​ያሌ፥ ሲባማ፥ ናባው፥ ቤያን፤</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት የሰ​ጣት ምድር የከ​ብት መሰ​ማ​ሪያ ሀገር ናት፤ ለእ​ኛም ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ብዙ እን​ስ​ሳት አሉን።</verse>
				<verse number="5">እኛስ በአ​ንተ ዘንድ ሞገ​ስን አግ​ኝ​ተን እንደ ሆነ ይህን ምድር ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ርስት አድ​ር​ገህ ስጠን፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስን አታ​ሻ​ግ​ረን።”</verse>
				<verse number="6">ሙሴም ለሮ​ቤል ልጆ​ችና ለጋድ ልጆች አላ​ቸው፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ወደ ጦር​ነት ሲሄዱ እና​ንተ በዚህ ትቀ​መ​ጣ​ላ​ች​ሁን?</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ቸው ምድር እን​ዳ​ይ​ሻ​ገሩ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ልብ ለምን ታጣ​ም​ማ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="8">ምድ​ሪ​ቱን ይሰ​ልሉ ዘንድ ከቃ​ዴስ በርኔ በላ​ክ​ኋ​ቸው ጊዜ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ እን​ዲህ አድ​ር​ገው አል​ነ​በ​ረ​ምን?</verse>
				<verse number="9">ወደ ወይን ዘለላ ሸለቆ መጡ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አዩ​አት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ ሰጣ​ቸው ምድር እን​ዳ​ይ​ገቡ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ልብ መለሱ።</verse>
				<verse number="10">በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቈጣ፤ እን​ዲ​ህም ብሎ ማለ፦</verse>
				<verse number="11">ከግ​ብፅ የወ​ጡት ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉት መል​ካ​ም​ንና ክፉን የሚ​ያ​ውቁ ሰዎች እኔን ፈጽ​መው አል​ተ​ከ​ተ​ሉ​ምና ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም እሰጥ ዘንድ የማ​ል​ሁ​ባ​ትን ምድር አያ​ዩም፤</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተከ​ት​ለ​ዋ​ልና ከእ​ነ​ዚህ፥ ልዩ ከሆነ ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌ​ብና ከነዌ ልጅ ከኢ​ያሱ በቀር፤</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በጠና ተቈጣ። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ያደ​ረገ ትው​ልድ ሁሉ እስ​ኪ​ጠፋ ድረስ አርባ ዓመት በም​ድረ በዳ ውስጥ አን​ከ​ራ​ተ​ታ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">እነ​ሆም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መዓት በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አብ​ዝ​ታ​ችሁ ትጨ​ምሩ ዘንድ እና​ንተ በኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ሰዎች በደል በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ፋንታ ተነ​ሥ​ታ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="15">እር​ሱን ትታ​ች​ሁ​ታ​ልና ዳግ​መ​ኛም በም​ድረ በዳ ትታ​ች​ሁ​ታል፤ በዚ​ችም ማኅ​በር ሁሉ ላይ ትበ​ድ​ላ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="16">ወደ እር​ሱም ቀር​በው አሉት፥ “በዚህ ለእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ችን በረ​ቶ​ችን፥ ለል​ጆ​ቻ​ች​ንም ከተ​ሞ​ችን እን​ሠ​ራ​ለን፤</verse>
				<verse number="17">እኛ ግን ለጦ​ር​ነት ታጥ​ቀን ወደ ስፍ​ራ​ቸው እስ​ክ​ና​ገ​ባ​ቸው ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በዚ​ህም ምድር ስላሉ ሰዎች ልጆ​ቻ​ችን በተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞች ይቀ​መ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="18">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ርስ​ታ​ቸ​ውን እስ​ኪ​ወ​ርሱ ድረስ ወደ ቤታ​ችን አን​መ​ለ​ስም፤</verse>
				<verse number="19">ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ወዲህ ወደ ምሥ​ራቅ ርስ​ታ​ችን ደር​ሶ​ና​ልና እኛ ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ​ዚያ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ርስት አን​ወ​ር​ስም።”</verse>
				<verse number="20">ሙሴም አላ​ቸው፥ “ይህ​ንስ እን​ዳ​ላ​ች​ሁት ብታ​ደ​ርጉ፥ ታጥ​ቃ​ች​ሁም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ ጦር​ነት ብት​ሄዱ፥</verse>
				<verse number="21">እር​ሱም ጠላቱ ከፊቱ እስ​ኪ​ጠፋ ድረስ ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው የጦር መሣ​ሪ​ያ​ውን ይዞ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዮር​ዳ​ኖ​ስን ቢሻ​ገር፥</verse>
				<verse number="22">ምድ​ሪ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ድል እስ​ክ​ት​ሆን ድረስ ከዚ​ያም በኋላ ትመ​ለ​ሳ​ላ​ችሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ንጹ​ሓን ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ ይህች ምድ​ርም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ርስት ትሆ​ና​ች​ኋ​ለች።</verse>
				<verse number="23">እን​ዲህ ባታ​ደ​ርጉ ግን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትበ​ድ​ላ​ላ​ችሁ፤ ክፉ ነገር ባገ​ኛ​ችሁ ጊዜ በደ​ላ​ች​ሁን ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="24">ለል​ጆ​ቻ​ችሁ ከተ​ሞ​ችን፥ ለበ​ጎ​ቻ​ች​ሁም በረ​ቶ​ችን ሥሩ፤ ከአ​ፋ​ች​ሁም የወ​ጣ​ውን ነገር አድ​ርጉ።”</verse>
				<verse number="25">የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆ​ችም ሙሴን እን​ዲህ ብለው ተና​ገ​ሩት፥ “እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ጌታ​ችን እን​ዳ​ዘዘ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።</verse>
				<verse number="26">ልጆ​ቻ​ችን ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ እን​ሰ​ሶ​ቻ​ች​ንም ሁሉ በዚያ በገ​ለ​ዓድ ከተ​ሞች ይሆ​ናሉ፤</verse>
				<verse number="27">እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ግን ሁላ​ችን የጦር መሣ​ሪ​ያ​ች​ንን ይዘን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጌታ​ችን እንደ ተና​ገረ ወደ ጦር​ነት እን​ሄ​ዳ​ለን።”</verse>
				<verse number="28">ሙሴም ካህ​ኑን አል​ዓ​ዛ​ርን፥ የነ​ዌ​ንም ልጅ ኢያ​ሱን፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ነገድ አባ​ቶች አለ​ቆች አዘ​ዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="29">ሙሴም፥ “የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች ሁላ​ቸው የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይዘው ከእ​ና​ንተ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለጦ​ር​ነት ዮር​ዳ​ኖ​ስን ቢሻ​ገሩ፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ድል ብት​ነሡ ፥ የገ​ለ​ዓ​ድን ምድር ርስት አድ​ር​ጋ​ችሁ ትሰ​ጡ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="30">የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይዘው ከእ​ና​ንተ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ ጦር​ነት ባይ​ሻ​ገሩ ግን ልጆ​ቻ​ቸ​ውን፥ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በፊ​ታ​ችሁ ወደ ከነ​ዓን ምድር ንዱ​አ​ቸው፤ በከ​ነ​ዓን ምድር በእ​ና​ንተ መካ​ከል ርስ​ታ​ቸ​ውን ይወ​ር​ሳሉ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="31">የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆ​ችም መል​ሰው፥ “ጌታ​ችን ለእኛ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እንደ ተና​ገረ እን​ዲሁ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።</verse>
				<verse number="32">የጦር መሣ​ሪ​ያ​ች​ንን ይዘን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ ከነ​ዓን ምድር እን​ሻ​ገ​ራ​ለን፤ ከዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ የወ​ረ​ስ​ነው ርስት ይሆ​ን​ል​ናል” አሉት።</verse>
				<verse number="33">ሙሴም ለጋድ ልጆ​ችና ለሮ​ቤል ልጆች፥ ለዮ​ሴ​ፍም ልጅ ለም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ፥ የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ንጉሥ የሴ​ዎ​ንን መን​ግ​ሥት፥ የባ​ሳ​ን​ንም ንጉሥ የዐ​ግን መን​ግ​ሥት፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም፥ ከተ​ራ​ሮ​ችም ጋር ከተ​ሞ​ችን፥ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ያሉ​ትን የም​ድ​ሪ​ቱን ከተ​ሞች ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="34">የጋድ ልጆች ዲቦ​ንን፥ አጣ​ሮ​ትን፥ አሮ​ዔ​ርን፤</verse>
				<verse number="35">ሶፋ​ንን፥ ኢያ​ዜ​ርን፥</verse>
				<verse number="36">ናም​ራን፥ ቤታ​ራ​ንን ሰባት የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞች አድ​ር​ገው ሠሩ፤ አስ​ረ​ዘ​ሙ​አ​ቸ​ውም፤ የበ​ጎች በረ​ቶ​ች​ንም ሠሩ።</verse>
				<verse number="37">የሮ​ቤ​ልም ልጆች ሐሴ​ቦ​ንን፥ ኤል​ያ​ሌ​ንን፥ ቂር​ያ​ታ​ይ​ምን፤ በቅ​ጥር የተ​ከ​በቡ በኤ​ል​ሜ​ዎ​ን​ንና፥ ሴባ​ማን ሠሩ፤</verse>
				<verse number="38">እነ​ዚ​ህ​ንም የሠ​ሩ​አ​ቸ​ውን ከተ​ሞች በየ​ስ​ማ​ቸው ጠሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="39">የም​ና​ሴም ልጅ የማ​ኪር ልጅ ወደ ገለ​ዓድ ሄዶ ገለ​ዓ​ድን ያዘ፤ በእ​ር​ስ​ዋም የነ​በ​ሩ​ትን አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አጠፋ።</verse>
				<verse number="40">ሙሴም ለም​ናሴ ልጅ ለማ​ኪር ገለ​ዓ​ድን ሰጠው፤ በእ​ር​ስ​ዋም ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="41">የም​ና​ሴም ልጅ ኢያ​ዕር ሄዶ መን​ደ​ሮ​ች​ዋን ወሰደ፤ የኢ​ያ​ዕ​ርም መን​ደ​ሮች ብሎ ጠራ​ቸው።</verse>
				<verse number="42">ናባ​ውም ሄዶ ቄና​ት​ንም፥ መን​ደ​ሮ​ች​ዋ​ንም ወሰደ፤ በስ​ሙም ናቦት ብሎ ጠራ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="33">
				<verse number="1">በሙ​ሴና በአ​ሮን እጅ ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የሰ​ፈ​ሩ​በት ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">ሙሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ እንደ ተጓዙ የሰ​ፈ​ሩ​በ​ትን ጻፈ፥ እየ​ተ​ጓዙ ያደ​ሩ​በት ይህ ነው።</verse>
				<verse number="3">በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን ከራ​ምሴ ተጓዙ፤ ከፋ​ሲካ በኋላ በነ​ጋው የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን ሁሉ ፊት ከፍ ባለች እጅ ወጡ።</verse>
				<verse number="4">በዚ​ያም ጊዜ ግብ​ፃ​ው​ያን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የገ​ደ​ላ​ቸ​ውን በኵ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ይቀ​ብሩ ነበር፤ በአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈረ​ደ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከራ​ምሴ ተጕ​ዘው በሱ​ኮት ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="6">ከሱ​ኮ​ትም ተጕ​ዘው በም​ድረ በዳ ዳርቻ ባለች በኤ​ታም ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="7">ከኤ​ታ​ምም ተጕ​ዘው በኤ​ል​ሴ​ፎን ፊት ወደ ነበ​ረች በኤ​ሮት በር፤ በመ​ግ​ደሎ ፊት ለፊት ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="8">ከኤ​ሮ​ትም ፊት ለፊት ተጕ​ዘው በባ​ሕሩ መካ​ከል ወደ ምድረ በዳ ተሻ​ገሩ፤ በኤ​ታ​ምም በረሃ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ሄደው በም​ረት ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="9">ከም​ረ​ትም ተጕ​ዘው ወደ ኤሊም መጡ፤ በኤ​ሊ​ምም ዐሥራ ሁለት የውኃ ምን​ጮች፥ ሰባ ዘን​ባ​ቦ​ችም ነበሩ፤ በዚ​ያም በውኃ አጠ​ገብ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="10">ከኤ​ሊ​ምም ተጕ​ዘው በኤ​ር​ትራ ባሕር ዳር ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="11">ከኤ​ር​ት​ራም ባሕር ተጕ​ዘው በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="12">ከሲና ምድረ በዳም ተጕ​ዘው በራ​ፋቃ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="13">ከራ​ፋ​ቃም ተጕ​ዘው በኤ​ሉስ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="14">ከኤ​ሉ​ስም ተጕ​ዘው በራ​ፊ​ድን ሰፈሩ፤ በዚ​ያም ሕዝቡ የሚ​ጠ​ጡት ውኃ አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="15">ከራ​ፊ​ድ​ንም ተጕ​ዘው በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="16">ከሲና ምድረ በዳም ተጕ​ዘው በም​ኞት መቃ​ብር ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="17">ከም​ኞት መቃ​ብ​ርም ተጕ​ዘው በአ​ቤ​ሮት ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="18">ከአ​ቤ​ሮ​ትም ተጕ​ዘው በራ​ታማ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="19">ከራ​ታ​ማም ተጕ​ዘው በሬ​ሞት ዘፋ​ሬስ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="20">ከሬ​ሞት ዘፋ​ሬ​ስም ተጕ​ዘው በል​ብና ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="21">ከል​ብ​ናም ተጕ​ዘው በሪሳ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="22">ከሪ​ሳም ተጕ​ዘው በመ​ቄ​ላት ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="23">ከመ​ቄ​ላ​ትም ተጕ​ዘው በሳ​ፋር ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="24">ከሳ​ፋ​ርም ተጕ​ዘው በካ​ሬ​ደት ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="25">ከካ​ሬ​ደ​ትም ተጕ​ዘው በመ​ቄ​ሎት ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="26">ከመ​ቄ​ሎ​ትም ተጕ​ዘው በቀ​ጠ​አት ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="27">ከቀ​ጠ​አ​ትም ተጕ​ዘው በተ​ሪት ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="28">ከተ​ሪ​ትም ተጕ​ዘው በሚ​ትቃ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="29">ከሚ​ት​ቃም ተጕ​ዘው በኤ​ሴ​ምና ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="30">ከኤ​ሴ​ም​ናም ተጕ​ዘው በመ​ሱ​ሩት ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="31">ከመ​ሱ​ሩ​ትም ተጕ​ዘው በብ​ን​ያ​ቅን ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="32">ከብ​ን​ያ​ቅ​ንም ተጕ​ዘው በገ​ድ​ገድ ተራራ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="33">ከገ​ድ​ገ​ድም ተጕ​ዘው በአ​ጤ​ቤት ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="34">ከአ​ጤ​ቤ​ትም ተጕ​ዘው በኤ​ብ​ሮና ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="35">ከኤ​ብ​ሮ​ናም ተጕ​ዘው በጋ​ስ​ዮ​ን​ጋ​ቤር ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="36">ከጋ​ስ​ዮ​ን​ጋ​ቤ​ርም ተጕ​ዘው በጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ። ከጺን ምድረ በዳም ተጕ​ዘው በፋ​ራን ምድረ በዳ ሰፈሩ። ይህ​ችም ቃዴስ ናት።</verse>
				<verse number="37">ከቃ​ዴ​ስም ተጕ​ዘው በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድር ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="38">ካህ​ኑም አሮን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፤ በዚ​ያም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በአ​ር​ባ​ኛው ዓመት፥ በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር፥ ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ሞተ።</verse>
				<verse number="39">አሮ​ንም በሖር ተራራ ላይ በሞተ ጊዜ ዕድ​ሜው መቶ ሃያ ሦስት ዓመት ነበረ።</verse>
				<verse number="40">በከ​ነ​ዓን ምድ​ርም ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረው ከነ​ዓ​ና​ዊው የዓ​ራድ ንጉሥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እንደ መጡ ሰማ።</verse>
				<verse number="41">እነ​ር​ሱም ከሖር ተራራ ተጕ​ዘው በሴ​ል​ሞና ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="42">ከሴ​ል​ሞ​ናም ተጕ​ዘው በፌኖ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="43">ከፌ​ኖም ተጕ​ዘው በአ​ቦት ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="44">ከአ​ቦ​ትም ተጕ​ዘው በሞ​ዓብ ዳርቻ ባለው በጋይ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="45">ከጋ​ይም ተጕ​ዘው በዲ​ቦ​ን​ጋድ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="46">ከዲ​ቦ​ን​ጋ​ድም ተጕ​ዘው በጌ​ል​ሞ​ን​ዲ​ብ​ላ​ታ​ይም ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="47">ከጌ​ል​ሞ​ን​ዲ​ብ​ላ​ታ​ይ​ምም ተጕ​ዘው በና​ባው ፊት ባሉት በአ​ባ​ሪም ተራ​ሮች ላይ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="48">በና​ባው ፊት ካሉት ከአ​ባ​ሪም ተራ​ሮ​ችም ተጕ​ዘው በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል ባለው በሞ​ዓብ ምዕ​ራብ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="49">በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም አጠ​ገብ በሞ​ዓብ ምዕ​ራብ ከአ​ሲ​ሞት መካ​ከል እስከ አቤ​ል​ሰ​ጢም ድረስ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="50">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል በሞ​ዓብ ምዕ​ራብ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው።</verse>
				<verse number="51">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ወደ ከነ​ዓን ምድር ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="52">በዚ​ያ​ችም ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ከፊ​ታ​ችሁ አጥ​ፉ​አ​ቸው፤ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ት​ንም ድን​ጋ​ዮ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ ታጠ​ፋ​ላ​ችሁ፤ ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ ታጠ​ፋ​ላ​ችሁ፤ በኮ​ረ​ብታ ላይ ያሉ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ታፈ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="53">በዚ​ያች ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም አጥ​ፍ​ታ​ችሁ በው​ስ​ጥዋ ኑሩ። ምድ​ሪ​ቱን ለእ​ና​ንተ ርስት አድ​ርጌ ሰጥ​ቼ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="54">ምድ​ሪ​ቱ​ንም ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ች​ሁም ትከ​ፋ​ፈ​ሏ​ታ​ላ​ችሁ፤ ለብ​ዙ​ዎች ድር​ሻ​ቸ​ውን አብ​ዙ​ላ​ቸው፤ ለጥ​ቂ​ቶ​ችም ድር​ሻ​ቸ​ውን ጥቂት አድ​ርጉ፤ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሁሉ ዕጣ እንደ ወደ​ቀ​ለት በዚያ ርስቱ ይሆ​ናል፤ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ነገ​ዶች ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="55">የሀ​ገ​ሩ​ንም ስዎች ከፊ​ታ​ችሁ ባታ​ሳ​ድዱ፥ ያስ​ቀ​ራ​ች​ኋ​ቸው ለዐ​ይ​ና​ችሁ እንደ እሾህ፥ ለጐ​ና​ች​ሁም እንደ አሜ​ከላ ይሆ​ኑ​ባ​ች​ኋል፤ በም​ት​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትም ምድር ያስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="56">እኔም በእ​ነ​ርሱ አደ​ር​ገው ዘንድ ያሰ​ብ​ሁ​ትን በእ​ና​ንተ አደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="34">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ ብለህ እዘ​ዛ​ቸው፦ እነሆ እና​ንተ ወደ ከነ​ዓን ምድር ትገ​ባ​ላ​ችሁ፤ የከ​ነ​ዓ​ንም ምድር ከአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ችዋ ጋር ለእ​ና​ንተ ርስት ትሆ​ና​ለች።</verse>
				<verse number="3">የአ​ዜቡ ወገን ከጺን ምድረ በዳ በኤ​ዶ​ም​ያስ መያ​ያዣ ይሆ​ናል፤ የአ​ዜ​ብም ዳርቻ ከጨው ባሕር ዳር በም​ሥ​ራቅ በኩል ይጀ​ም​ራል፤</verse>
				<verse number="4">ዳር​ቻ​ች​ሁም በአ​ቅ​ራ​ቦን ዐቀ​በት በአ​ዜብ በኩል ይዞ​ራል፤ እስከ ኤና​ቅም ይደ​ር​ሳል፤ መው​ጫ​ውም በቃ​ዴስ በርኔ በአ​ዜብ በኩል ይሆ​ናል፤ ወደ አራድ ሀገ​ሮ​ችም ይደ​ር​ሳል፤ ወደ አሴ​ሞ​ናም ያል​ፋል፤</verse>
				<verse number="5">ዳር​ቻ​ውም ከአ​ሴ​ሞና ወደ ግብፅ ወንዝ ይዞ​ራል፤ ወሰኑ ባሕሩ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="6">“ለባ​ሕ​ርም ዳርቻ ታላቁ ባሕር ዳር​ቻ​ችሁ ይሆ​ናል፤ ይህ የባ​ሕር ዳር​ቻ​ችሁ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="7">“በመ​ስ​ዕም በኩል ወሰ​ና​ችሁ ከታ​ላቁ ባሕር በተ​ራ​ራው በኩል ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="8">ከተ​ራ​ራው እስከ ተራ​ራው ድረስ ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፤ እስከ ኤማ​ትም ይደ​ር​ሳል፤ የዳ​ር​ቻ​ውም መውጫ በሰ​ረ​ደክ ይሆ​ናል፤</verse>
				<verse number="9">ዳር​ቻ​ውም ወደ ዲፍ​ሮና ያል​ፋል፤ መው​ጫ​ውም አር​ሴ​ና​ይን ይሆ​ናል፤ በመ​ስዕ በኩል ያለው ወሰ​ና​ች​ሁም በዚህ ይሁ​ና​ችሁ።</verse>
				<verse number="10">“በም​ሥ​ራቅ በኩል ያለው ወሰ​ና​ች​ሁም ከሴ​ፋማ አር​ሴ​ና​ይን ጀምሮ ነው።</verse>
				<verse number="11">ዳር​ቻ​ውም ከሴ​ፋማ በዐ​ይን ምሥ​ራቅ ወዳ​ለው ወደ አር​ቤላ ይወ​ር​ዳል፤ እስከ ኬኔ​ሬት የባ​ሕር ወሽ​መጥ በም​ሥ​ራቅ በኩል ይደ​ር​ሳል፤</verse>
				<verse number="12">ዳር​ቻ​ውም ወደ ዮር​ዳ​ኖስ ይወ​ር​ዳል፤ መው​ጫ​ውም በጨው ባሕር ይሆ​ናል። ምድ​ራ​ችሁ እንደ ዳር​ቻዋ በዙ​ሪ​ያዋ ይህች ናት።”</verse>
				<verse number="13">ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ጠኙ ነገ​ድና ለም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ይሰ​ጡ​አ​ቸው ዘንድ እንደ አዘዘ በዕጣ የም​ት​ወ​ር​ሱ​አት ምድር ይህች ናት፤</verse>
				<verse number="14">የሮ​ቤ​ልም ልጆች ነገድ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት፥ የጋ​ድም ልጆች ነገድ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ርስ​ታ​ቸ​ውን ወር​ሰ​ዋል።</verse>
				<verse number="15">እነ​ዚህ ሁለቱ ነገ​ድና የአ​ንዱ ነገድ እኩ​ሌታ ርስ​ታ​ቸ​ውን በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በም​ሥ​ራቅ በኩል ወረሱ።”</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ፤ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="17">“ምድ​ሪ​ቱን ርስት አድ​ር​ገው የሚ​ከ​ፍ​ሉ​ላ​ችሁ ሰዎች ስማ​ቸው ይህ ነው፤ ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርና የነዌ ልጅ ኢያሱ።</verse>
				<verse number="18">ምድ​ሪ​ቱ​ንም ርስት አድ​ር​ገው የሚ​ያ​ካ​ፍ​ሏ​ቸው ከየ​ነ​ገዱ አንድ አንድ አለቃ ይወ​ስ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="19">የሰ​ዎ​ቹም ስም ይህ ነው፤ ከይ​ሁዳ ነገድ የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ፥</verse>
				<verse number="20">ከስ​ም​ዖን ልጆች ነገድ የዓ​ሚ​ሁድ ልጅ ሰላ​ም​ያል፥</verse>
				<verse number="21">ከብ​ን​ያም ነገድ የኪ​ስ​ሎን ልጅ ኤል​ዳድ፥</verse>
				<verse number="22">ከዳን ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የዮ​ቅሊ ልጅ ባቂ፥</verse>
				<verse number="23">ከዮ​ሴ​ፍም ልጆች ከም​ናሴ ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የሱ​ፊድ ልጅ አን​ሄል፥</verse>
				<verse number="24">ከኤ​ፍ​ሬም ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የሳ​ፍ​ጣን ልጅ ቃሙ​ሔል፥</verse>
				<verse number="25">ከዛ​ብ​ሎን ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የበ​ር​ናክ ልጅ ኤሊ​ሳ​ፈን፥</verse>
				<verse number="26">ከይ​ሳ​ኮር ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የሖዛ ልጅ ፈል​ጥ​ሔል፥</verse>
				<verse number="27">ከአ​ሴር ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የሴ​ሌሚ ልጅ አኪ​ሖር፥</verse>
				<verse number="28">ከን​ፍ​ታ​ሌም ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የአ​ሚ​ሁድ ልጅ ፈዳ​ሄል።</verse>
				<verse number="29">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በከ​ነ​ዓን ምድር ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርስ​ታ​ቸ​ውን ይከ​ፍሉ ዘንድ ያዘ​ዛ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="35">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በሞ​ዓብ ምዕ​ራብ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“ሌዋ​ው​ያን የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ውን ከተ​ሞች ከሚ​ካ​ፈ​ሉት ርስ​ታ​ቸው ይሰጡ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እዘ​ዛ​ቸው፤ በከ​ተ​ሞ​ቹም ዙሪያ ያሉ​ትን መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎች ለሌ​ዋ​ው​ያን ይስ​ጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ከተ​ሞ​ቹም ለእ​ነ​ርሱ መኖ​ሪያ ይሆ​ናሉ፤ መሰ​ማ​ር​ያ​ቸ​ውም ለከ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ለእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ቸው ይሁን።</verse>
				<verse number="4">ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም የም​ት​ሰ​ጡት የከ​ተማ መሰ​ማ​ርያ በከ​ተ​ማው ዙሪያ ከቅ​ጥሩ ወደ ውጭ አንድ ሺህ ክንድ ይሁን።</verse>
				<verse number="5">ከከ​ተ​ማው ውጭ በም​ሥ​ራቅ በኩል ሁለት ሺህ ክንድ፥ በደ​ቡብ በኩል ሁለት ሺህ ክንድ፥ በም​ዕ​ራብ በኩል ሁለት ሺህ ክንድ፥ በሰ​ሜ​ንም በኩል ሁለት ሺህ ክንድ ትከ​ነ​ዳ​ላ​ችሁ፤ ከተ​ማ​ውም በመ​ካ​ከል ይሆ​ናል፤ ይህም የከ​ተ​ሞቹ መሰ​ማ​ርያ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ከተ​ሞ​ችን ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ከም​ት​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውም ከተ​ሞች ስድ​ስቱ ነፍሰ ገዳይ የሚ​ሸ​ሽ​ባ​ቸው የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞች ናቸው፤ ከእ​ነ​ዚህ ሌላ አርባ ሁለት ከተ​ሞ​ችን ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="7">ለሌ​ዋ​ው​ያን የም​ት​ሰ​ጡ​አ​ቸው ከተ​ሞች ሁሉ አርባ ስም​ንት ከተ​ሞች ይሆ​ናሉ፤ እነ​ዚ​ህም ከመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ጋር ናቸው።</verse>
				<verse number="8">ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርስት ለሌ​ዋ​ው​ያን የም​ት​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውን ከተ​ሞች እን​ዲህ ስጡ፤ ከብ​ዙ​ዎቹ ብዙ፥ ከጥ​ቂ​ቶቹ ጥቂት ትወ​ስ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እያ​ን​ዳ​ንዱ እንደ ወረ​ሱት እንደ ርስ​ታ​ቸው መጠን ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ይሰ​ጣሉ።”</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="10">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦</verse>
				<verse number="11">እነሆ፥ ወደ ከነ​ዓን ምድር ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤ ባላ​ማ​ወቅ ነፍስ የገ​ደለ ወደ​ዚያ ይሸሽ ዘንድ የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞች እን​ዲ​ሆ​ኑ​ላ​ችሁ ከተ​ሞ​ችን ለእ​ና​ንተ ለዩ።</verse>
				<verse number="12">ነፍሰ ገዳዩ በማ​ኅ​በሩ ፊት ለፍ​ርድ እስ​ከ​ሚ​ቆም ድረስ እን​ዳ​ይ​ሞት፥ ከተ​ሞቹ ከደም ተበ​ቃይ የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞች ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="13">የም​ት​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውም ስድ​ስቱ ከተ​ሞች የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞች ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="14">በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ሦስት ከተ​ሞ​ችን ትለ​ያ​ላ​ችሁ፤ በከ​ነ​ዓ​ንም ምድር ሦስት ከተ​ሞ​ችን ትለ​ያ​ላ​ችሁ፤ የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞ​ችም ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="15">ባለ​ማ​ወቅ ነፍስ የገ​ደለ ሁሉ ይሸ​ሽ​ባ​ቸው ዘንድ እነ​ዚህ ስድ​ስት ከተ​ሞች ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ለሚ​ቀ​መጡ እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች መማ​ፀኛ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="16">“በብ​ረት መሣ​ሪያ ቢመ​ታው፥ ቢሞ​ትም ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳ​ዩም ፈጽሞ ይገ​ደል።</verse>
				<verse number="17">ሰውም በሚ​ሞ​ት​በት በእጁ ባለው ድን​ጋይ ቢመ​ታው፥ የተ​መ​ታ​ውም ቢሞት፥ እርሱ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳ​ዩም ፈጽሞ ይገ​ደል።</verse>
				<verse number="18">ሰውም በሚ​ሞ​ት​በት በእጁ ባለው በእ​ን​ጨት መሣ​ሪያ ቢመ​ታው፥ የተ​መ​ታ​ውም ቢሞት፥ እርሱ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳ​ዩም ፈጽሞ ይገ​ደል።</verse>
				<verse number="19">ደም ተበ​ቃዩ ራሱ ነፍሰ ገዳ​ዩን ይግ​ደል፤ ባገ​ኘው ጊዜ ይግ​ደ​ለው።</verse>
				<verse number="20">ጥል ቢጣ​ላው፥ ወይም ሸምቆ አን​ዳች ነገር ቢጥ​ል​በት፥ ቢሞ​ትም፥</verse>
				<verse number="21">ወይም በጥ​ላቻ እስ​ኪ​ሞት ድረስ በእጁ ቢመ​ታው፥ የመ​ታው ፈጽሞ ይገ​ደል፤ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ባለ ደሙ ወይም ተበ​ቃዩ ባገ​ኘው ጊዜ ነፍሰ ገዳ​ዩን ይግ​ደ​ለው።</verse>
				<verse number="22">“ነገር ግን ያለ ጥላቻ ድን​ገት ቢደ​ፋው፥ ሳይ​ሸ​ም​ቅም አን​ዳች ነገር ቢጥ​ል​በት፥</verse>
				<verse number="23">ወይም ሳያ​የው እስ​ኪ​ሞት ድረስ ሰው የሚ​ሞ​ት​በ​ትን ድን​ጋይ ቢጥ​ል​በት፥</verse>
				<verse number="24">ጠላ​ቱም ባይ​ሆን፥ ክፉም ያደ​ር​ግ​በት ዘንድ ባይሻ፥ ማኅ​በሩ በመ​ቺ​ውና በባለ ደሙ መካ​ከል ፍር​ድን እን​ደ​ዚህ ይፍ​ረዱ፤</verse>
				<verse number="25">ማኅ​በ​ሩም ነፍሰ ገዳ​ዩን ከባለ ደሙ እጅ ያድ​ኑ​ታል፤ ማኅ​በ​ሩም ወደ ሸሸ​በት ወደ መማ​ፀ​ኛው ከተማ ይመ​ል​ሱ​ታል፤ በቅ​ዱስ ዘይ​ትም የተ​ቀ​ባው ታላቁ ካህን እስ​ኪ​ሞት ድረስ በዚያ ይቀ​መ​ጣል።</verse>
				<verse number="26">ነፍሰ ገዳዩ ግን ከሸ​ሸ​በት ከመ​ማ​ፀ​ኛው ከተማ ዳርቻ ቢወጣ፥ ባለ ደሙም ከመ​ማ​ፀ​ኛው ከተማ ዳርቻ ውጭ ቢያ​ገ​ኘው፥</verse>
				<verse number="27">ባለ ደሙም ነፍሰ ገዳ​ዩን ቢገ​ድ​ለው፥ በደል የለ​በ​ትም፤</verse>
				<verse number="28">ታላቁ ካህን እስ​ኪ​ሞት ድረስ በመ​ማ​ፀ​ኛው ከተማ ውስጥ መቀ​መጥ ይገ​ባው ነበ​ርና። ታላቁ ካህን ከሞተ በኋላ ግን ነፍሰ ገዳዩ ወደ ርስቱ ምድር ይመ​ለ​ሳል።</verse>
				<verse number="29">“እነ​ዚ​ህም ነገ​ሮች ለልጅ ልጃ​ችሁ በማ​ደ​ሪ​ያ​ችሁ ሁሉ ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="30">ነፍሰ ገዳይ ሁሉ በም​ስ​ክ​ሮች ቃል ይገ​ደ​ላል፤ በአ​ንድ ምስ​ክር ግን ማና​ቸ​ው​ንም ሰው መግ​ደል አይ​ገ​ባም።</verse>
				<verse number="31">ሞት የተ​ፈ​ረ​ደ​በ​ትን ነፍሰ ገዳ​ዩ​ንም ለማ​ዳን የነ​ፍስ ዋጋ አት​ቀ​በሉ፤ እርሱ ፈጽሞ ይገ​ደል።</verse>
				<verse number="32">ታላቁ ካህን እስ​ኪ​ሞት ወደ ምድሩ ትመ​ል​ሱት ዘንድ ወደ መማ​ፀ​ኛው ከተማ ከሸ​ሸው ዋጋ አት​ቀ​በሉ።</verse>
				<verse number="33">ምድ​ርን የሚ​ያ​ረ​ክ​ሳት ደም ነውና የም​ት​ኖ​ሩ​ባ​ትን ምድር በነ​ፍስ ግድያ አታ​ር​ክ​ሷት። ምድ​ሪ​ቱም በደም አፍ​ሳሹ ደም ካል​ሆነ በቀር ከፈ​ሰ​ሰ​ባት ደም አት​ነ​ጻም።</verse>
				<verse number="34">እና​ንተ በው​ስ​ጥዋ የም​ት​ኖ​ሩ​ባ​ትን፥ እኔም ከእ​ና​ንተ ጋር የማ​ድ​ር​ባ​ትን ምድር አታ​ር​ክ​ሱ​ኣት፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል የማ​ድር እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="36">
				<verse number="1">ከዮ​ሴፍ ልጆች ወገ​ኖች የም​ናሴ ልጅ የማ​ኪር ልጅ የገ​ለ​ዓድ ልጆች ወገን አለ​ቆች መጡ፤ በሙ​ሴና በካ​ህኑ በአ​ል​ዓ​ዛር፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አባ​ቶች አለ​ቆች ፊት ተና​ገሩ፤ አሉም፦</verse>
				<verse number="2">“ምድ​ሪ​ቱን ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርስት አድ​ርጎ በዕጣ ከፍሎ ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጌታ​ች​ንን አዘ​ዘው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የወ​ን​ድ​ማ​ች​ንን የሰ​ለ​ጰ​ዓ​ድን ርስት ለሴ​ቶች ልጆቹ ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ጌታ​ች​ንን አዘ​ዘው።</verse>
				<verse number="3">ከሌ​ላም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ነገድ ባል ቢያ​ገቡ፥ ርስ​ታ​ቸው ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ርስት ይነ​ቀ​ላል፤ እነ​ር​ሱም ለሚ​ገ​ቡ​በት ለሌ​ላው ነገድ ርስት ይጨ​መ​ራል፤ እን​ደ​ዚ​ህም የር​ስ​ታ​ችን ዕጣ ይጐ​ድ​ላል።</verse>
				<verse number="4">ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ኢዮ​ቤ​ልዩ በሆነ ጊዜ ርስ​ታ​ቸው ሴቶቹ ወደ አገ​ቡ​በት ወደ ሌላ ነገድ ርስት ይጨ​መ​ራል፤ እነሆ፥ ርስ​ታ​ቸው ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ነገድ ርስት ይጐ​ድ​ላል።”</verse>
				<verse number="5">ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “የዮ​ሴፍ ልጆች ነገድ በእ​ው​ነት ተና​ገሩ።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ሰለ​ጰ​ዓድ ሴቶች ልጆች ያዘ​ዘው ነገር ይህ ነው፤ የወ​ደ​ዱ​ትን ያግቡ፤ ነገር ግን ከአ​ባ​ታ​ቸው ነገድ ብቻ ያግቡ።</verse>
				<verse number="7">እን​ደ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርስት ከነ​ገድ ወደ ነገድ ምንም አይ​ተ​ላ​ለፍ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ አባ​ቶቹ ነገድ ርስት ይጠጋ።</verse>
				<verse number="8">ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው የአ​ባ​ቶ​ቹን ርስት ይወ​ርስ ዘንድ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ነገድ ሁሉ፥ ርስት ያላት ሴት ልጅ ሁሉ ከአ​ባቷ ነገድ ባል ታግባ።</verse>
				<verse number="9">እን​ደ​ዚ​ህም ከአ​ንድ ነገድ ወደ ሌላ ነገድ ምንም ርስት አይ​ተ​ላ​ለፍ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ነገድ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ርስቱ ይጠጋ።”</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ የሰ​ለ​ጰ​ዓድ ሴቶች ልጆች አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="11">የሰ​ለ​ጰ​ዓድ ሴቶች ልጆች መሐላ፥ ቴርሳ፥ ሄግላ፥ ሚልካ፥ ኑኃ ከአ​ባ​ታ​ቸው ወን​ድ​ሞች ልጆች ጋር ተጋቡ።</verse>
				<verse number="12">ከዮ​ሴፍ ልጅ ከም​ናሴ ልጆች ወገ​ኖች ባሎ​ቻ​ቸ​ውን አገቡ፥ ርስ​ታ​ቸ​ውም በአ​ባ​ታ​ቸው ነገድ ጸና።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በሞ​ዓብ ምዕ​ራብ ያዘ​ዛ​ቸው ትእ​ዛዝ፥ ሥር​ዐ​ትና ፍርድ እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="5">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በም​ድረ በዳ፥ በም​ዕ​ራብ በኩል በኤ​ር​ትራ ባሕር አጠ​ገብ በፋ​ራ​ንና በጦ​ፌል፥ በላ​ባ​ንና በአ​ው​ሎን፥ በካ​ታ​ኪ​ሪ​ሲ​ያም መካ​ከል፥ ሙሴ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ የነ​ገ​ራ​ቸው ቃላት እኒህ ናቸው።</verse>
				<verse number="2">በሴ​ይር ተራራ መን​ገድ ከኮ​ሬብ እስከ ቃዴስ በርኔ ድረስ የዐ​ሥራ አንድ ቀን ጕዞ ነው።</verse>
				<verse number="3">በአ​ር​ባ​ኛው ዓመት በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን፥ ሙሴ እን​ዲ​ነ​ግ​ራ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እነ​ርሱ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ነገ​ራ​ቸው፤</verse>
				<verse number="4">በሐ​ሴ​ቦን ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረ​ውን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ንጉሥ ሴዎ​ንን፥ በአ​ስ​ጣ​ሮ​ትና በኤ​ድ​ራ​ይን ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረ​ው​ንም የባ​ሳ​ንን ንጉሥ ዐግን ከገ​ደ​ሉት በኋላ፥</verse>
				<verse number="5">በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሞ​ዓብ ምድር ሙሴ እን​ዲህ ብሎ ይህን ሕግ ይገ​ልጥ ጀመር፦</verse>
				<verse number="6">“አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኮ​ሬብ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረን፦ በዚህ ተራራ መቀ​መ​ጣ​ችሁ በቃ፤</verse>
				<verse number="7">ተመ​ል​ሳ​ችሁ ተጓዙ፤ ወደ አሞ​ራ​ው​ያን ተራራ፥ ወደ አረ​ባም ሀገ​ሮች ሁሉ፥ በተ​ራ​ራ​ውም፥ በሜ​ዳ​ውም፥ በሊ​ባም፥ በባ​ሕ​ርም ዳር ወዳሉ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን ምድር፥ ወደ ሊባ​ኖ​ስም ፊት ለፊት እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ድረስ ሂዱ።</verse>
				<verse number="8">እነሆ፥ ምድ​ሪ​ቱን ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ ግቡ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ነ​ርሱ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ለዘ​ራ​ቸው ይሰ​ጣት ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ምድር ውረሱ።</verse>
				<verse number="9">“በዚ​ያም ዘመን እን​ዲህ ብዬ ተና​ገ​ር​ኋ​ችሁ፦ እኔ ብቻ​ዬን ልሸ​ከ​ማ​ችሁ አል​ች​ልም፤</verse>
				<verse number="10">አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ​ዝ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና፥ እነ​ሆም፥ እና​ንተ ዛሬ እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት ብዙ​ዎች ናችሁ።</verse>
				<verse number="11">የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ቍጥር ላይ እልፍ አእ​ላ​ፋት ይጨ​ምር፤ እንደ ተና​ገ​ራ​ች​ሁም ይባ​ር​ካ​ችሁ።</verse>
				<verse number="12">እኔ ብቻ​ዬን ድካ​ማ​ች​ሁን፥ ሸክ​ማ​ች​ሁ​ንም፥ ክር​ክ​ራ​ች​ሁ​ንም እሸ​ከም ዘንድ እን​ዴት እች​ላ​ለሁ?</verse>
				<verse number="13">ከእ​ና​ንተ ከየ​ነ​ገ​ዳ​ችሁ ጥበ​በ​ኞች፥ አስ​ተ​ዋ​ዮ​ችም፥ ዐዋ​ቂ​ዎ​ችም የሆ​ኑ​ትን ሰዎች አምጡ፤ እኔም በላ​ያ​ችሁ አለ​ቆች አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">እና​ን​ተም፦ ‘እና​ደ​ር​ገው ዘንድ የተ​ና​ገ​ር​ኸው ይህ ነገር መል​ካም ነው’ ብላ​ችሁ መል​ሳ​ችሁ ነገ​ራ​ች​ሁኝ።</verse>
				<verse number="15">ከእ​ና​ን​ተም ጥበ​በ​ኞ​ችና ዐዋ​ቂ​ዎች፥ አስ​ተ​ዋ​ዮ​ችም የሆ​ኑ​ትን ሰዎች ወሰ​ድሁ፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ አለ​ቆች፥ የሻ​ለ​ቆ​ችም፥ የመቶ አለ​ቆ​ችም፥ የአ​ምሳ አለ​ቆ​ችም፥ የዐ​ሥር አለ​ቆ​ችም፥ ለፈ​ራ​ጆ​ቻ​ች​ሁም ጻፎች አድ​ርጌ ሰየ​ም​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">በዚ​ያን ጊዜ ፈራ​ጆ​ቻ​ች​ሁን አዘ​ዝ​ኋ​ቸው። አል​ኋ​ቸ​ውም፦ የወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ነገር ስሙ፤ በሰ​ውና በወ​ን​ድሙ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ባለው መጻ​ተኛ መካ​ከል በጽ​ድቅ ፍረዱ።</verse>
				<verse number="17">በፍ​ር​ድም ፊት አትዩ፤ ለት​ል​ቁም፥ ለት​ን​ሹም በእ​ው​ነት ፍረዱ፤ ለሰው ፊት አታ​ድሉ፤ ፍርድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና። አንድ ነገር ቢከ​ብ​ዳ​ችሁ እር​ሱን ወደ እኔ አም​ጡት፤ እኔም እሰ​ማ​ዋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="18">በዚ​ያን ጊዜም ልታ​ደ​ር​ጉት የሚ​ገ​ባ​ች​ሁን ነገር ሁሉ አዘ​ዝ​ኋ​ችሁ።</verse>
				<verse number="19">“ከኮ​ሬ​ብም ተጓ​ዝን፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘን በታ​ላቁ፥ እጅ​ግም በሚ​ያ​ስ​ፈራ በዚያ ባያ​ች​ሁት ምድረ በዳ ሁሉ በኩል በአ​ሞ​ሬ​ዎን ተራራ መን​ገድ ሄድን፤ ወደ ቃዴስ በር​ኔም መጣን።</verse>
				<verse number="20">እኔም አል​ኋ​ችሁ፦ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስከ ሰጣ​ችሁ እስከ አሞ​ሬ​ዎን ተራራ ኑ፤</verse>
				<verse number="21">እነሆ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ሪ​ቱን በፊ​ታ​ችሁ እንደ ሰጣ​ችሁ እዩ፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ላ​ችሁ ውጡ፤ ውረ​ሷት፤ አት​ፍሩ፤ አት​ደ​ን​ግ​ጡም።</verse>
				<verse number="22">እና​ን​ተም ሁላ​ችሁ ወደ እኔ ቀር​ባ​ችሁ፦ ምድ​ሪ​ቱን እን​ዲ​ሰ​ል​ሉ​ል​ንና እን​ወ​ጣ​ባት ዘንድ የሚ​ገ​ባ​ንን የመ​ን​ገ​ዱ​ንና የም​ን​ገ​ባ​ባ​ቸ​ውን የእ​ነ​ዚ​ያን ከተ​ሞች ወሬ ተመ​ል​ሰው እን​ዲ​ነ​ግ​ሩን በፊ​ታ​ችን ሰዎች እን​ላክ አላ​ች​ሁኝ።</verse>
				<verse number="23">ያም ነገር ደስ አሰ​ኘኝ፤ ከእ​ና​ን​ተም ዐሥራ ሁለት ሰው ወሰ​ድሁ፤ ከየ​ነ​ገዱ ሁሉ አንድ አንድ ሰው ነበረ።</verse>
				<verse number="24">ሄዱም፤ ወደ ተራ​ራ​ውም ወጡ፤ ወደ ወይን ዘለላ ሸለቆ መጥ​ተው ሰለ​ሉ​አት።</verse>
				<verse number="25">ከም​ድ​ሪ​ቱም ፍሬ በእ​ጃ​ቸው ወሰዱ፤ ወደ እኛም ይዘ​ውት መጡ፦ ‘አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጠን ምድር መል​ካም ናት አሉን፤’</verse>
				<verse number="26">“ወደ እር​ስዋ መው​ጣ​ት​ንም እንቢ አላ​ችሁ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ላይም ዐመ​ፃ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="27">በድ​ን​ኳ​ና​ች​ሁም ውስጥ እን​ዲህ እያ​ላ​ችሁ አጕ​ረ​መ​ረ​ማ​ችሁ፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ጠላን እን​ዲ​ያ​ጠ​ፋን በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጠን ዘንድ ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣን።</verse>
				<verse number="28">ወዴት እን​ወ​ጣ​ለን? ሕዝቡ ታላ​ቅና ብዙ ነው፤ ከእ​ኛም ይጠ​ነ​ክ​ራሉ፤ ከተ​ሞ​ቹም ታላ​ላ​ቆች፥ የተ​መ​ሸ​ጉም፥ እስከ ሰማ​ይም የደ​ረሱ ናቸው፤ የረ​ዐ​ይ​ት​ንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየ​ና​ቸው ብለው ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ልባ​ች​ንን አስ​ፈ​ሩት።’</verse>
				<verse number="29">እኔም አል​ኋ​ችሁ፦ አት​ደ​ን​ግጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አት​ፍሩ፤</verse>
				<verse number="30">በፊ​ታ​ችሁ የሚ​ሄ​ደው አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ በግ​ብፅ ምድር እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ላ​ችሁ ሁሉ፥ ስለ እና​ንተ አብ​ሮ​አ​ችሁ ይዋ​ጋል፤</verse>
				<verse number="31">ወደ​ዚ​ህም ስፍራ እስ​ክ​ት​መጡ ድረስ በሄ​ዳ​ች​ሁ​በት መን​ገድ ሁሉ፥ ሰው ልጁን እን​ዲ​መ​ግብ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድረ በዳ እን​ደ​መ​ገ​ባ​ችሁ እና​ንተ አይ​ታ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="32">ዳሩ ግን በዚህ ነገር አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​መ​ና​ች​ሁ​ትም።</verse>
				<verse number="33">እር​ሱም ስፍ​ራን እን​ዲ​መ​ር​ጥ​ላ​ችሁ፥ ትሄ​ዱ​በ​ትም ዘንድ የሚ​ገ​ባ​ውን መን​ገድ እን​ዲ​ያ​ሳ​ያ​ችሁ ሌሊት በእ​ሳት፥ ቀን በደ​መና በፊ​ታ​ችሁ በመ​ን​ገድ ሲሄድ የነ​በ​ረ​ውን አላ​መ​ና​ች​ሁ​ትም።</verse>
				<verse number="34">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የቃ​ላ​ች​ሁን ድምፅ ሰምቶ ተቈጣ፤ እን​ዲ​ህም ብሎ ማለ፦</verse>
				<verse number="35">ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ እሰ​ጣት ዘንድ የማ​ል​ሁ​ላ​ቸ​ውን መል​ካ​ሚ​ቱን ምድር ከእ​ነ​ዚህ ሰዎች ማንም አያ​ይም፥</verse>
				<verse number="36">ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌብ በስ​ተ​ቀር፥ እርሱ ግን ያያ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሞ ተከ​ት​ሎ​አ​ልና የረ​ገ​ጣ​ትን ምድር ለእ​ርሱ፥ ለል​ጆ​ቹም እሰ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="37">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት በእኔ ተቈጣ፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ አንተ ደግሞ ወደ​ዚያ አት​ገ​ባም፤</verse>
				<verse number="38">በፊ​ትህ የሚ​ቆም የነዌ ልጅ ኢያሱ እርሱ ወደ​ዚያ ይገ​ባል፤ እር​ሱን አበ​ር​ታው፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ምድ​ሪ​ቱን ያወ​ር​ሳ​ልና።</verse>
				<verse number="39">ደግሞ፦ ይማ​ረ​ካሉ ያላ​ች​ኋ​ቸው ልጆ​ቻ​ችሁ፥ ዛሬም መል​ካ​ሙን ከክፉ መለ​የት የማ​ይ​ችሉ ሕፃ​ኖ​ቻ​ችሁ እነ​ርሱ ወደ​ዚያ ይገ​ባሉ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ለእ​ነ​ርሱ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ይወ​ር​ሱ​አ​ታ​ልም።</verse>
				<verse number="40">እና​ንተ ግን ተመ​ል​ሳ​ችሁ በኤ​ር​ትራ ባሕር መን​ገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።</verse>
				<verse number="41">“እና​ን​ተም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በድ​ለ​ናል፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘን ሁሉ እን​ወ​ጣ​ለን፤ እን​ዋ​ጋ​ማ​ለን ብላ​ችሁ መለ​ሳ​ች​ሁ​ልኝ። ከእ​ና​ን​ተም ሰው ሁሉ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ውን ያዘ፤ ወደ ተራ​ራም ወጣ​ችሁ።</verse>
				<verse number="42">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ እኔ ከእ​ና​ንተ ጋር አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ፊት እን​ዳ​ት​ወ​ድቁ አት​ውጡ፤ አት​ዋ​ጉም በላ​ቸው አለኝ።</verse>
				<verse number="43">እኔም ተና​ገ​ር​ኋ​ችሁ፤ እና​ንተ ግን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ተላ​ለ​ፋ​ችሁ፤ በኀ​ይ​ላ​ች​ሁም ወደ ተራ​ራ​ማው አገር ወጣ​ችሁ።</verse>
				<verse number="44">በዚ​ያም ተራ​ራማ አገር ይኖሩ የነ​በሩ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ወጥ​ተው ተጋ​ጠ​ሙ​አ​ችሁ፤ ንብ እን​ደ​ም​ት​ነ​ድ​ፍም ነደ​ፉ​አ​ችሁ፤ አሳ​ደ​ዱ​አ​ች​ሁም፤ ከሴ​ይር እስከ ሔር​ማም ድረስ መቱ​አ​ችሁ።</verse>
				<verse number="45">ተቀ​ም​ጣ​ች​ሁም በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አለ​ቀ​ሳ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ድም​ፃ​ች​ሁን አል​ሰ​ማም፤ ወደ እና​ን​ተም አል​ተ​መ​ለ​ከ​ተም።</verse>
				<verse number="46">ቀድሞ እንደ ተቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​በ​ትም ዘመን መጠን በቃ​ዴስ ብዙ ቀን ተቀ​መ​ጣ​ችሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ለኝ ተመ​ል​ሰን በኤ​ር​ትራ ባሕር መን​ገድ ወደ ምድረ በዳ ሄድን፤ የሴ​ይ​ር​ንም ተራራ ብዙ ቀን ዞርን።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረኝ፦</verse>
				<verse number="3">‘ይህን ተራራ መዞር ይበ​ቃ​ች​ኋል፤ ተመ​ል​ሳ​ችሁ ወደ መስዕ ሂዱ።’</verse>
				<verse number="4">ሕዝ​ቡ​ንም እን​ዲህ ብለህ እዘ​ዛ​ቸው፦ በሴ​ይር ላይ በተ​ቀ​መ​ጡት በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ በዔ​ሳው ልጆች ሀገር ታል​ፋ​ላ​ችሁ፤ እነ​ርሱ ይፈ​ሩ​አ​ች​ኋል፤ እን​ግ​ዲህ እጅግ ተጠ​ን​ቀቁ።</verse>
				<verse number="5">የሴ​ይ​ርን ተራራ ለዔ​ሳው ልጆች ርስት አድ​ርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከም​ድ​ራ​ቸው የጫማ መር​ገጫ ታህል እን​ኳን አል​ሰ​ጣ​ች​ሁ​ምና አት​ጣ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">ከእ​ነ​ርሱ በገ​ን​ዘብ ምግብ ገዝ​ታ​ችሁ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ውኃም ደግሞ በገ​ን​ዘብ በመ​ለ​ኪያ ገዝ​ታ​ችሁ ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="7">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ጅ​ህን ሥራ ሁሉ ባር​ኮ​ል​ሃ​ልና፤ ይህን ታላ​ቅና የሚ​ያ​ስ​ፈራ ምድረ በዳ እን​ዴት እንደ ዞር​ኸው ዕወቅ፤ በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነበረ፤ ከተ​ና​ገ​ር​ኸው ሁሉ አን​ዳ​ችም አላ​ሳ​ጣ​ህም።</verse>
				<verse number="8">በሴ​ይ​ርም ከተ​ቀ​መ​ጡት ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከዔ​ሳው ልጆች በዓ​ረባ መን​ገድ ከኤ​ሎ​ንና ከጋ​ስ​ዮን-ጋብር አለ​ፍን። ተመ​ል​ሰ​ንም በሞ​ዓብ ምድረ በዳ መን​ገድ አለ​ፍን።</verse>
				<verse number="9">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ እኔ አሮ​ኤ​ርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድ​ርጌ ስለ ሰጠሁ ከም​ድሩ ርስት አል​ሰ​ጣ​ች​ሁ​ምና ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን አት​ጣላ፤ በሰ​ል​ፍም አት​ው​ጋ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">እንደ ዔና​ቃ​ው​ያን ታላ​ቅና ብዙ ሕዝብ ኀያ​ላ​ንም የሆኑ ኦሚ​ና​ው​ያን አስ​ቀ​ድሞ በዚያ ይቀ​መጡ ነበር።</verse>
				<verse number="11">እነ​ር​ሱም ደግሞ እንደ ዔና​ቃ​ው​ያን ራፋ​ይም ተብ​ለው ይታ​ወቁ ነበር፤ ሞዓ​ባ​ው​ያን ግን “ኦሚን” ብለው ይጠ​ሩ​አ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="12">ሖራ​ው​ያ​ንም ደግሞ አስ​ቀ​ድሞ በሴ​ይር ላይ ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ የዔ​ሳው ልጆች ግን መቱ​አ​ቸው፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ጠው በር​ስቱ ምድር እስ​ራ​ኤል እን​ዳ​ደ​ረገ፥ በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="13">አሁ​ንም ‘ተነ​ሡና ተጓዙ፤ የዛ​ሬ​ድ​ንም ፈፋ ተሻ​ገሩ፤’ የዛ​ሬ​ድ​ንም ፈፋ ተሻ​ገ​ርን።</verse>
				<verse number="14">የዛ​ሬ​ድ​ንም ፈፋ እስከ ተሻ​ገ​ር​ን​በት ድረስ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ማለ​ባ​ቸው ተዋ​ጊ​ዎች የሆኑ የዚ​ያች ትው​ልድ ሰዎች ከሰ​ፈሩ መካ​ከል እስከ ጠፉ ድረስ፥ ከቃ​ዴስ በርኔ የተ​ጓ​ዝ​ን​በት ዘመን ሠላሳ ስም​ንት ዓመት ሆነ።</verse>
				<verse number="15">ከሰ​ፈ​ርም መካ​ከል ተለ​ይ​ተው እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በላ​ያ​ቸው ነበረ።</verse>
				<verse number="16">“እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ተዋ​ጊ​ዎቹ ከጠፉ፥ ከሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ከሞቱ በኋላ፥</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረኝ፦</verse>
				<verse number="18">‘አንተ ዛሬ የሞ​ዓ​ብን ዳርቻ አሮ​ኤ​ርን ታል​ፋ​ለህ፤</verse>
				<verse number="19">ለሎ​ጥም ልጆች ርስት አድ​ርጌ ስለ ሰጠሁ ከአ​ሞን ልጆች ምድር ርስት አል​ሰ​ጥ​ህ​ምና በአ​ሞን ልጆች አቅ​ራ​ቢያ ስት​ደ​ርስ አት​ጣ​ላ​ቸው፤ አት​ው​ጋ​ቸ​ውም።’</verse>
				<verse number="20">ያም ደግሞ የራ​ፋ​ይም ምድር ተብሎ ተቈ​ጠረ፤ ራፋ​ይ​ምም አስ​ቀ​ድሞ በዚያ ተቀ​ም​ጠው ነበረ፤ አሞ​ና​ው​ያን ግን “ዘም​ዞ​ማ​ው​ያን” ብለው ይጠ​ሩ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="21">እነ​ር​ሱም እንደ ዔና​ቃ​ው​ያን ታላ​ቅና ብዙ፥ ጽኑ​ዓ​ንም ሕዝብ ነበሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፊ​ታ​ቸው አጠ​ፋ​ቸው፤ እነ​ር​ሱ​ንም አሳ​ድ​ደው በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="22">ሖራ​ው​ያ​ንን ከፊ​ታ​ቸው አጥ​ፍቶ በሴ​ይር ለተ​ቀ​መ​ጡት ለዔ​ሳው ልጆች እን​ዳ​ደ​ረገ እነ​ርሱ ወረ​ሱ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ፋንታ እስከ ዛሬ ድረስ ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="23">እስከ ጋዛም ድረስ በአ​ሴ​ሮት ተቀ​ም​ጠው የነ​በ​ሩ​ትን ኤዋ​ው​ያ​ን​ንና ከቀ​ጰ​ዶ​ቅያ የወጡ ቀጰ​ዶ​ቃ​ው​ያ​ንን አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ፋንታ ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="24">ደግ​ሞም አለ፦ ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ሂዱ፤ የአ​ር​ኖ​ን​ንም ሸለቆ ተሻ​ገሩ፤ እነሆ፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ውን የሐ​ሴ​ቦ​ንን ንጉሥ ሴዎ​ንን፥ ምድ​ሩ​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋን ግዛት፤ ውረ​ሳት፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ተዋጋ።</verse>
				<verse number="25">ከሰ​ማይ በታች ባሉ አሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ማስ​ደ​ን​ገ​ጥ​ህ​ንና ማስ​ፈ​ራ​ት​ህን እሰ​ድድ ዘንድ ዛሬ እጀ​ም​ራ​ለሁ፤ ስም​ህን በሰሙ ጊዜ በፊ​ትህ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ድን​ጋ​ጤም ይይ​ዛ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="26">“ከቄ​ድ​ሞ​ትም ምድረ በዳ የሰ​ላ​ምን ቃል ይነ​ግ​ሩት ዘንድ ወደ ሐሴ​ቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን እን​ዲህ ብዬ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላክሁ፦</verse>
				<verse number="27">‘በሀ​ገ​ርህ ላይ ልለፍ፤ በአ​ውራ ጎዳና እሄ​ዳ​ለሁ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አል​ተ​ላ​ለ​ፍም።</verse>
				<verse number="28">የም​በ​ላ​ውን ምግብ በገ​ን​ዘብ ሽጥ​ልኝ፤ የም​ጠ​ጣ​ው​ንም ውኃ በገ​ን​ዘብ ስጠኝ፤ በእ​ግሬ ብቻ ልለፍ፤</verse>
				<verse number="29">በሴ​ይር የተ​ቀ​መጡ የዔ​ሳው ልጆች፥ በአ​ሮ​ዔ​ርም የተ​ቀ​መጡ ሞዓ​ባ​ው​ያን እን​ዳ​ደ​ረ​ጉ​ልኝ፥ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጠን ምድር ዮር​ዳ​ኖ​ስን እስ​ክ​ሻ​ገር ድረስ በእ​ግሬ ልለፍ።</verse>
				<verse number="30">የሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳ​ል​ፈን ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ይሰ​ጠው ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ሱን አደ​ን​ድ​ኖ​ታ​ልና፥ ልቡ​ንም አጽ​ን​ቶ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="31">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ‘የሐ​ሴ​ቦ​ንን ንጉሥ አሞ​ራ​ዊ​ውን ሴዎ​ን​ንና ምድ​ሩን በፊ​ትህ በእ​ጅህ አሳ​ልፌ መስ​ጠት እነሆ፥ ጀመ​ርሁ፤ ምድ​ሩን ትገዛ ዘንድ መው​ረስ ጀምር’ አለኝ።</verse>
				<verse number="32">ሴዎ​ንም ሕዝ​ቡም ሁሉ ሊዋ​ጉን ወደ ኢያሳ ወጡ።</verse>
				<verse number="33">አም​ላ​ካ​ች​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እር​ሱን አሳ​ልፎ በእ​ጃ​ችን ሰጠን፤ እር​ሱ​ንም፥ ልጆ​ቹ​ንም፥ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ መታን።</verse>
				<verse number="34">በዚ​ያን ጊዜም ከተ​ሞ​ቹን ሁሉ ወሰ​ድን፤ ከተ​ማ​ው​ንም ሁሉ፥ ሴቶ​ች​ንም፥ ሕፃ​ኖ​ች​ንም አጠ​ፋን፤ አን​ዳ​ችም የሸሸ በሕ​ይ​ወት አላ​ስ​ቀ​ረ​ንም፥</verse>
				<verse number="35">ለእኛ ከማ​ረ​ክ​ና​ቸው ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ከወ​ሰ​ድ​ነው ምርኮ በቀር።</verse>
				<verse number="36">በአ​ር​ኖን ሸለቆ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔ​ርና በሸ​ለ​ቆ​ውም ውስጥ ካለ​ችው ከተማ ጀም​ረን እስከ ገለ​ዓድ ተራራ ድረስ ማን​ኛ​ዪ​ቱም ከተማ አላ​መ​ለ​ጠ​ች​ንም፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁሉን አሳ​ልፎ በእ​ጃ​ችን ሰጠን።</verse>
				<verse number="37">ዳሩ ግን አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘን ወደ አሞን ልጆች ምድር፥ በያ​ቦ​ቅም ወንዝ አጠ​ገብ ወደ አለው ስፍራ ሁሉ፥ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም ሀገር ወደ አሉ ከተ​ሞች አል​ደ​ረ​ስ​ንም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">“ተመ​ል​ሰ​ንም በባ​ሳን መን​ገድ ወጣን፤ የባ​ሳን ንጉሥ ዐግም፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ በኤ​ድ​ራ​ይን ሊዋ​ጉን ወጡ።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ እር​ሱ​ንና ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ ምድ​ሩ​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​አ​ለ​ሁና አት​ፍ​ራው፤ በሐ​ሴ​ቦን ይኖር በነ​በ​ረው በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ንጉሥ በሴ​ዎን ላይ እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ በእ​ር​ሱም ታደ​ር​ግ​በ​ታ​ለህ አለኝ።</verse>
				<verse number="3">አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ የባ​ሳ​ንን ንጉሥ ዐግን ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጠን፤ እኛም አጠ​ፋ​ነው፤ አንድ ሰው እን​ኳን ለዘር አል​ቀ​ረ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="4">በዚ​ያን ጊዜም ከተ​ሞ​ቹን ሁሉ ወሰ​ድን፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ያል​ወ​ሰ​ድ​ነው ሀገር የለም፤ በባ​ሳን ያለ​ውን የዐ​ግን መን​ግ​ሥት፥ የአ​ር​ጎ​ብን አው​ራ​ጃ​ዎች ሁሉ፥ ስድሳ ከተ​ሞ​ችን ወሰ​ድን።</verse>
				<verse number="5">እጅግ ብዙ ከሆ​ኑት ከፌ​ር​ዜ​ዎን ከተ​ሞች ሌላ፥ እነ​ዚህ ከተ​ሞች ሁሉ ቁመቱ ረዥም በሆነ ቅጥር በመ​ዝ​ጊ​ያና በመ​ወ​ር​ወ​ሪ​ያም የተ​መ​ሸጉ ነበሩ።</verse>
				<verse number="6">በሐ​ሴ​ቦ​ንም ንጉሥ በሴ​ዎን እን​ዳ​ደ​ረ​ግን ፈጽሞ አጠ​ፋ​ና​ቸው፤ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት፥ የሚ​ሸሽ ሳና​ስ​ቀር ሴቶ​ች​ንም፥ ሕፃ​ና​ቱ​ንም ፈጽሞ አጠ​ፋ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="7">ከብ​ቶ​ቹን ሁሉ የከ​ተ​ሞ​ቹ​ንም ምርኮ ለእኛ ወሰ​ድን።</verse>
				<verse number="8">“በዚ​ያም ዘመን ከአ​ር​ኖን ሸለቆ ጀምሮ እስከ ኤር​ሞን ድረስ ምድ​ሪ​ቱን በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ከነ​በሩ ከሁ​ለቱ ከአ​ሞ​ሬ​ዎን ነገ​ሥ​ታት እጅ ወሰ​ድን፤</verse>
				<verse number="9">ፊኒ​ቃ​ው​ያን ኤር​ሞ​ንን “ሳኒ​ዮር” ብለው ይጠ​ሩ​ታል፤ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ሳኔር ብለው ይጠ​ሩ​ታል።</verse>
				<verse number="10">የሚ​ሶ​ር​ንም ከተ​ሞች ሁሉ፥ የገ​ለ​ዓ​ድ​ንም ሁሉ፥ የባ​ሳ​ን​ንም ሁሉ እስከ ኤል​ከ​ድና እስከ ኤድ​ራ​ይን ድረስ በባ​ሳን የሚ​ኖር የዐ​ግን መን​ግ​ሥት ከተ​ሞች ሁሉ ወሰ​ድን።</verse>
				<verse number="11">ከራ​ፋ​ይ​ንም ወገን የባ​ሳን ንጉሥ ዐግ ብቻ​ውን ቀርቶ ነበር፤ እነሆ፥ አል​ጋው የብ​ረት አልጋ ነበረ፤ እርሱ በአ​ሞን ልጆች ሀገር ዳርቻ አለ፤ ርዝ​መቱ ዘጠኝ ክንድ ወር​ዱም አራት ክንድ በሰው ክንድ ልክ ነበረ።</verse>
				<verse number="12">“ይህ​ች​ንም ምድር በዚ​ያን ዘመን ወረ​ስን፤ በአ​ር​ኖ​ንም ሸለቆ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ የገ​ለ​ዓ​ድን ተራ​ራማ ሀገር እኩ​ሌታ፥ ከተ​ሞ​ቹ​ንም ለሮ​ቤ​ልና ለጋድ ነገድ ሰጠ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">ከገ​ለ​ዐ​ድም የቀ​ረ​ውን የዐ​ግን መን​ግ​ሥት ባሳ​ንን ሁሉ፥ የአ​ር​ጎ​ብ​ንም ምድር ሁሉ ለም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ሰጠሁ፤ ያችም ባሳን ሁሉ የራ​ፋ​ይም ሀገር ተብላ ተቈ​ጠ​ረች።</verse>
				<verse number="14">የም​ናሴ ልጅ ኢያ​ዕር እስከ ጌር​ጋ​ሴና እስከ መካቲ ዳርቻ ድረስ የአ​ር​ጎ​ብን አው​ራጃ ሁሉ ወሰደ፤ ይህ​ች​ንም የባ​ሳ​ንን ምድር እስ​ከ​ዚች ቀን ድረስ በስሙ አው​ታይ ኢያ​ዕር ብሎ ጠራ።</verse>
				<verse number="15">ለማ​ኪ​ርም ገለ​ዓ​ድን ሰጠ​ሁት።</verse>
				<verse number="16">ለሮ​ቤ​ልና ለጋ​ድም ከገ​ለ​ዓድ ምድር ጀምሮ እስከ አር​ኖን ሸለቆ ድረስ የሸ​ለ​ቆ​ውን እኩ​ሌታ ዳር​ቻ​ው​ንም፥ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ እስከ ኢያ​ቦቅ ወንዝ ድረስ፥</verse>
				<verse number="17">ከመ​ካ​ናራ ወሰን ከፈ​ስጋ ተራራ በታች ወደ ምሥ​ራቅ እስከ ዓረባ ባሕር እር​ሱም የጨው ባሕር ድረስ ዓረ​ባን፥ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ሰጠ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">“በዚ​ያም ዘመን እን​ዲህ ብዬ አዘ​ዝ​ኋ​ችሁ፦ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን ምድር ርስት አድ​ርጎ ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ መሣ​ሪ​ያ​ች​ሁን ይዛ​ችሁ እና​ንተ አር​በ​ኞች ሁሉ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="19">ነገር ግን እጅግ ከብ​ቶች እን​ዳ​ሉ​አ​ችሁ አው​ቃ​ለ​ሁና ሴቶ​ቻ​ች​ሁና ልጆ​ቻ​ችሁ፥ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በሰ​ጠ​ኋ​ችሁ ከተ​ሞች ይቀ​መ​ጣሉ፤</verse>
				<verse number="20">ይኸ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ እና​ንተ፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን እስ​ኪ​ያ​ሳ​ርፍ ድረስ፥ እነ​ር​ሱም ደግሞ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ምድር እስ​ኪ​ወ​ርሱ ድረስ ነው። ከዚ​ያም በኋላ ሁላ​ችሁ ወደ ሰጠ​ኋ​ችሁ ርስት ትመ​ለ​ሳ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="21">በዚ​ያም ጊዜ ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብዬ አዘ​ዝ​ሁት፦ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ነ​ዚህ በሁ​ለቱ ነገ​ሥት ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ዐይ​ኖ​ችህ አይ​ተ​ዋል፤ እን​ዲሁ በም​ታ​ል​ፍ​ባ​ቸው መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ር​ጋል።</verse>
				<verse number="22">አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ ስለ እና​ንተ ይዋ​ጋ​ልና ከእ​ነ​ርሱ የተ​ነሣ አት​ፍሩ።</verse>
				<verse number="23">“በዚ​ያም ዘመን እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲህ ብዬ ለመ​ን​ሁት፦</verse>
				<verse number="24">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! ታላ​ቅ​ነ​ት​ህ​ንና ኀይ​ል​ህን፥ የጸ​ናች እጅ​ህ​ንና የተ​ዘ​ረ​ጋች ክን​ድ​ህን ለእኔ ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ማሳ​የት ጀም​ረ​ሃል፤ በሰ​ማ​ይና በም​ድ​ርም እንደ ሥራህ፥ እንደ ኀይ​ል​ህም ይሠራ ዘንድ የሚ​ችል አም​ላክ ማን ነው?</verse>
				<verse number="25">እኔ እን​ድ​ሻ​ገ​ርና፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ ያለ​ች​ውን መል​ካ​ሚ​ቱን ምድር፥ ያንም መል​ካ​ሙን ተራ​ራ​ማ​ውን ሀገር አንጢ ሊባ​ኖ​ስ​ንም እን​ዳይ ፍቀ​ድ​ልኝ።</verse>
				<verse number="26">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት ተቈ​ጣኝ፤ አል​ሰ​ማ​ኝ​ምም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ ‘ይበ​ቃ​ሃል፤ በዚህ ነገር ደግ​መህ አት​ና​ገ​ረኝ።’</verse>
				<verse number="27">ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን አት​ሻ​ገ​ር​ምና ወደ ተራ​ራው ራስ ውጣ፤ ዐይ​ን​ህ​ንም ወደ ባሕር ወደ መስ​ዕም፥ ወደ አዜ​ብም ወደ ምሥ​ራ​ቅም አን​ሥ​ተህ በዐ​ይ​ንህ ተመ​ል​ከት።</verse>
				<verse number="28">ኢያሱ በዚህ ሕዝብ ፊት ይሻ​ገ​ራ​ልና፥ አን​ተም የም​ታ​ያ​ትን ምድር እርሱ ያወ​ር​ሳ​ቸ​ዋ​ልና ኢያ​ሱን እዘ​ዘው፤ አደ​ፋ​ፍ​ረ​ውም፥ አጽ​ና​ውም።</verse>
				<verse number="29">በቤተ ፌጎ​ርም ፊት ለፊት በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ተቀ​መ​ጥን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">“አሁ​ንም እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እን​ድ​ታ​ደ​ር​ጉ​አ​ቸው፥ በሕ​ይ​ወ​ትም እን​ድ​ት​ኖሩ፥ እን​ድ​ት​በ​ዙም፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ገብ​ታ​ችሁ እን​ድ​ት​ወ​ርሱ፥ ዛሬ የማ​ስ​ተ​ም​ራ​ች​ሁን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ስሙ።</verse>
				<verse number="2">ዛሬ እኔ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁን የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ትጠ​ብ​ቃ​ላ​ችሁ እንጂ ባዘ​ዝ​ኋ​ችሁ ቃል ላይ አት​ጨ​ም​ሩም፤ ከእ​ር​ሱም አታ​ጐ​ድ​ሉም።</verse>
				<verse number="3">ብዔ​ል​ፌ​ጎ​ርን የተ​ከ​ተ​ለ​ውን ሰው ሁሉ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ለይቶ አጥ​ፍ​ቶ​ታ​ልና አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በብ​ዔ​ል​ፌ​ጎር ያደ​ረ​ገ​ውን ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ አይ​ተ​ዋል።</verse>
				<verse number="4">እና​ንተ ግን አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የተ​ከ​ተ​ላ​ችሁ እስከ ዛሬ ድረስ ሁላ​ችሁ በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="5">እነሆ፥ እና​ንተ ገብ​ታ​ችሁ በም​ት​ወ​ር​ሱ​አት ምድር ውስጥ እን​ዲህ ታደ​ርጉ ዘንድ አም​ላኬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘኝ ሥር​ዐ​ትና ፍር​ድን አሳ​የ​ኋ​ችሁ።</verse>
				<verse number="6">ጠብ​ቁት፤ አድ​ር​ጉ​ትም፤ ይህን ሥር​ዐት ሁሉ ሰም​ተው፦ እነሆ፥ ‘ይህ ታላቅ ሕዝብ ጠቢ​ብና አስ​ተ​ዋይ ሕዝብ ነው’ በሚሉ በአ​ሕ​ዛብ ፊት ጥበ​ባ​ች​ሁና ማስ​ተ​ዋ​ላ​ችሁ ይህ ነውና፤</verse>
				<verse number="7">አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ን​ጠ​ራው ጊዜ ሁሉ እን​ደ​ሚ​ቀ​ር​በን፥ አም​ላኩ ወደ እርሱ የቀ​ረ​በው ታላቅ ሕዝብ ማን ነው?</verse>
				<verse number="8">ዛሬ በፊ​ታ​ችሁ እን​ደ​ማ​ኖ​ራት እን​ደ​ዚ​ህች ሕግ ሁሉ ጽድቅ የሆ​ነች ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ያለው ታላቅ ሕዝብ ማን ነው?</verse>
				<verse number="9">“ለራ​ስህ ዕወቅ፤ ሰው​ነ​ት​ህን ፈጽ​መህ ጠብቅ፤ ዐይ​ኖ​ችህ ያዩ​ትን ይህን ሁሉ ነገር አት​ርሳ፤ በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ ከል​ቡ​ናህ አይ​ውጣ፤ ለል​ጆ​ች​ህና ለልጅ ልጆ​ች​ህም አስ​ተ​ም​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ወደ እኔ ሰብ​ስ​ባ​ቸው፤ እነ​ርሱ በም​ድር ላይ በሕ​ይ​ወት በሚ​ኖ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ እኔን መፍ​ራት ይማ​ሩና ለል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ ቃሌን ይስሙ ብሎ​ኛ​ልና በኮ​ሬብ በተ​ሰ​በ​ሰ​ባ​ችሁ ጊዜ በፈ​ጣ​ሪ​ያ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ቆማ​ችሁ ንገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">እና​ን​ተም ቀር​ባ​ችሁ ከተ​ራ​ራው በታች ቆማ​ችሁ ነበር፤ ተራ​ራ​ውም እስከ ሰማይ ድረስ በእ​ሳት ይነ​ድድ ነበር፤ ጨለ​ማና አውሎ ነፋስ፥ ድቅ​ድቅ ጨለ​ማም ነበረ።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ሳት መካ​ከል ሆኖ ተና​ገ​ራ​ችሁ፤ የቃ​ልን ድምፅ ሰማ​ችሁ፤ ከድ​ምፅ በቀር መል​ክን ግን አላ​ያ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="13">ታደ​ር​ጉ​ትም ዘንድ ያዘ​ዛ​ች​ሁን ቃል ኪዳን ዐሥ​ሩን ቃላት ነገ​ራ​ችሁ፤ በሁ​ለ​ቱም የድ​ን​ጋይ ጽላት ላይ ጻፋ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ ተሻ​ግ​ራ​ችሁ በም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር የም​ታ​ደ​ር​ጉ​አ​ትን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ አስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚ​ያን ጊዜ አዘ​ዘኝ።</verse>
				<verse number="15">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኮ​ሬብ ተራራ በእ​ሳት መካ​ከል ሆኖ በተ​ና​ገ​ራ​ችሁ ቀን መል​ኩን ከቶ አላ​ያ​ች​ሁ​ምና ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን እጅግ ጠብቁ፤</verse>
				<verse number="16">እን​ዳ​ት​በ​ድሉ፥ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል፥ የማ​ና​ቸ​ው​ንም ነገር ምሳሌ፥ በወ​ንድ ወይም በሴት መልክ የተ​ሠ​ራ​ውን፥ በም​ድር ላይ ያለ​ውን፥</verse>
				<verse number="17">የእ​ን​ስ​ሳን ሁሉ ምሳሌ ፥ ከሰ​ማ​ይም በታች የሚ​በ​ር​ረ​ውን የወ​ፍን ሁሉ ምሳሌ፥</verse>
				<verse number="18">በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ሽ​ከ​ረ​ከ​ረ​ውን ሁሉ ምሳሌ፥ ከም​ድ​ርም በታች በውኃ ውስጥ የሚ​ኖ​ረ​ውን የዓ​ሣን ሁሉ ምሳሌ አታ​ድ​ርጉ፤</verse>
				<verse number="19">ወደ ሰማይ አት​መ​ል​ከት፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ሁሉ በታች ላሉት አሕ​ዛብ ሁሉ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ፀሐ​ይ​ንና ጨረ​ቃን፥ ከዋ​ክ​ብ​ት​ንና የሰ​ማ​ይን ሠራ​ዊት ሁሉ አይ​ተህ፥ ሰግ​ደ​ህ​ላ​ቸው፥ አም​ል​ከ​ሃ​ቸ​ውም እን​ዳ​ት​ስት ተጠ​ን​ቀቅ።</verse>
				<verse number="20">እና​ን​ተን ግን እንደ ዛሬው ሁሉ የር​ስቱ ሕዝብ ትሆ​ኑ​ለት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወስዶ ከብ​ረት እቶን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ችሁ።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እና​ንተ በተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁት ምክ​ን​ያት ተቈ​ጣኝ፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም እን​ዳ​ል​ሻ​ገር፥ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ወደ መል​ካ​ሚቱ ምድር እን​ዳ​ል​ገባ ማለ።</verse>
				<verse number="22">እኔ ግን በዚ​ህች ምድር እሞ​ታ​ለሁ። ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም አል​ሻ​ገ​ርም፤ እና​ንተ ግን ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤ ያች​ንም መል​ካ​ሚ​ቱን ምድር ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="23">ከእ​ና​ንተ ጋር የተ​ማ​ማ​ለ​ውን የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን እን​ዳ​ት​ረሱ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የከ​ለ​ከ​ለ​ውን፥ በማ​ና​ቸ​ውም ቅርጽ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል እን​ዳ​ታ​ደ​ርጉ እን​ግ​ዲህ ተጠ​ን​ቀቁ።</verse>
				<verse number="24">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​በላ እሳት፥ ቀና​ተ​ኛም አም​ላክ ነውና።</verse>
				<verse number="25">“ልጆ​ችን፥ የልጅ ልጆ​ች​ንም በወ​ለ​ዳ​ችሁ ጊዜ፥ በም​ድ​ሪ​ቱም ረዥም ዘመን በተ​ቀ​መ​ጣ​ችሁ ጊዜ፥ በበ​ደ​ላ​ች​ሁም ጊዜ፥ በማ​ና​ቸ​ውም ቅርጽ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል ባደ​ረ​ጋ​ችሁ ጊዜ፥ ታስ​ቈ​ጡ​ትም ዘንድ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ የሆ​ነ​ውን ነገር በሠ​ራ​ችሁ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="26">ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ራ​ችሁ ከም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር ፈጥ​ና​ችሁ እን​ድ​ት​ጠፉ እኔ ዛሬ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በእ​ና​ንተ አስ​መ​ሰ​ክ​ራ​ለሁ፤ ፈጽ​ሞም ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ እንጂ ረዥም ዘመን አት​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትም።</verse>
				<verse number="27">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይበ​ት​ና​ች​ኋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በው​ስ​ጣ​ቸው በሚ​ያ​ኖ​ራ​ችሁ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከ​ልም በቍ​ጥር ጥቂ​ቶች ሆና​ችሁ ትቀ​ራ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="28">በዚ​ያም የማ​ያ​ዩ​ትን፥ የማ​ይ​ሰ​ሙ​ት​ንም፥ የማ​ይ​በ​ሉ​ት​ንም፥ የማ​ያ​ሸ​ቱ​ት​ንም፥ በሰው እጅ ከእ​ን​ጨ​ትና ከድ​ን​ጋይ የተ​ሠ​ሩ​ትን ሌሎች አማ​ል​ክት ታመ​ል​ካ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="29">ነገር ግን ከዚያ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትሻ​ላ​ችሁ፤ በመ​ከ​ራ​ህም ጊዜ በል​ብ​ህም ሁሉ፥ በነ​ፍ​ስ​ህም ሁሉ​የ​ፈ​ለ​ግ​ኸው እንደ ሆነ ታገ​ኘ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="30">ይህም ሁሉ ነገር በመ​ጨ​ረ​ሻው ዘመን ይደ​ር​ስ​ብ​ሃል፤ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትመ​ለ​ሳ​ለህ፤ ቃሉ​ንም ትሰ​ማ​ለህ።</verse>
				<verse number="31">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓሪ አም​ላክ ነውና አይ​ተ​ው​ህም፤ አያ​ጠ​ፋ​ህ​ምም፤ ለአ​ባ​ቶ​ች​ህም የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ቃል ኪዳ​ኑን አይ​ረ​ሳም።</verse>
				<verse number="32">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰውን በም​ድር ላይ ከፈ​ጠ​ረው ጀምሮ፥ ከሰ​ማይ ዳር እስከ ሰማይ ዳርቻ ድረስ ከቶ እን​ዲህ ያለ ታላቅ ነገር ሆኖ፥ ወይም እንደ እርሱ ያለ ተሰ​ምቶ እንደ ሆነ ከአ​ንተ በፊት የነ​በ​ረ​ውን የቀ​ደ​መ​ውን ዘመን ጠይቅ።</verse>
				<verse number="33">አንተ ከእ​ሳት መካ​ከል ሆኖ ሲና​ገር የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድምፅ እንደ ሰማ​ህና በሕ​ይ​ወት እን​ዳ​ለህ ሌላ ሕዝብ ሰምቶ እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="34">አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት በግ​ብፅ ለእ​ና​ንተ እንደ ሠራው ሁሉ ፥ በፈ​ተ​ናና በተ​አ​ም​ራት፥ በድ​ን​ቅና በሰ​ልፍ፥ በጸ​ናች እጅና በተ​ዘ​ረጋ ክንድ፥ በታ​ላ​ቅም ማስ​ፈ​ራ​ራት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሌላ ሕዝብ መካ​ከል ገብቶ ለእ​ርሱ ሕዝ​ብን ይወ​ስድ ዘንድ ሞክሮ እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="35">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አም​ላክ እንደ ሆነና ከእ​ር​ሱም ሌላ አም​ላክ እንደ ሌለ እን​ድ​ታ​ውቅ፥</verse>
				<verse number="36">ያስ​ተ​ም​ርህ ዘንድ ከሰ​ማይ ድም​ፁን አሰ​ማህ፤ በም​ድ​ርም ላይ ታላ​ቁን እሳት አሳ​የህ፤ ከእ​ሳ​ቱም መካ​ከል ቃሉን ሰማህ።</verse>
				<verse number="37">አባ​ቶ​ች​ህን ወድ​ዶ​አ​ልና ከእ​ነ​ርሱ በኋላ ዘራ​ቸ​ውን መረጠ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ሆኖ በታ​ላቅ ኀይሉ ከግ​ብፅ አወ​ጣህ፤</verse>
				<verse number="38">ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከግ​ብፅ ከአ​ንተ የጸ​ኑ​ትን ታላ​ላ​ቆ​ቹን አሕ​ዛብ በፊ​ትህ እን​ዲ​ያ​ወጣ፥ አን​ተ​ንም እን​ዲ​ያ​ገ​ባህ፥ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም ርስት አድ​ርጎ እን​ዲ​ሰ​ጥህ፥</verse>
				<verse number="39">እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላይ በሰ​ማይ በታ​ችም በም​ድር አም​ላክ እንደ ሆነ፥ ሌላም እንደ ሌለ ዛሬ ዕወቅ፤ በል​ብ​ህም ያዝ።</verse>
				<verse number="40">ለእ​ና​ንተ፥ ከእ​ና​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ቻ​ችሁ መል​ካም ይሆን ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም በሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ዕድ​ሜ​አ​ችሁ ይረ​ዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዙን ጠብቁ።”</verse>
				<verse number="41">በዚ​ያን ጊዜ ሙሴ በም​ሥ​ራቅ በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ሦስት ከተ​ሞ​ችን ለየ።</verse>
				<verse number="42">ትና​ንት፥ ከት​ናት በስ​ቲ​ያም ጠላቱ ያል​ሆ​ነ​ውን ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ሳያ​ውቅ የገ​ደለ ገዳዩ ይማ​ፀ​ን​ባ​ቸው ዘንድ፥ ከእ​ነ​ዚ​ህም ከተ​ሞች በአ​ን​ዲቱ ተማ​ፅኖ በሕ​ይ​ወት ይኖር ዘንድ፤</verse>
				<verse number="43">ለሮ​ቤል ነገድ በም​ድረ በዳ በደ​ል​ዳላ ስፍራ ያለ ባሶር፥ ለጋ​ድም ነገድ በገ​ለ​ዓድ ያለ ራሞት፥ ለም​ና​ሴም ነገድ በባ​ሳን ያለ ጎላን ነበሩ።</verse>
				<verse number="44">ሙሴም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ያኖ​ራት ሕግ ይህች ናት፤</verse>
				<verse number="45">ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ ሙሴ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የተ​ና​ገ​ረው ምስ​ክ​ርና ሥር​ዐት፤ ፍር​ድም ይህ ነው።</verse>
				<verse number="46">ሙሴና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ በመ​ቱት፥ በሐ​ሴ​ቦን ተቀ​ምጦ በነ​በ​ረው በአ​ሞ​ሬ​ዎን ንጉሥ በሴ​ዎን ምድር፥ በቤተ ፌጎር አቅ​ራ​ቢያ ባለው ሸለቆ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ፤</verse>
				<verse number="47">የእ​ር​ሱ​ንና የባ​ሳ​ንን ንጉሥ፥ የዐ​ግን ምድር፥ በም​ሥ​ራቅ በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ የነ​በ​ሩ​ትን የሁ​ለ​ቱን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ንን ነገ​ሥ​ታት ምድር ወሰዱ።</verse>
				<verse number="48">በአ​ር​ኖን ወንዝ ዳር ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ እስከ ሴዎን ተራራ እስከ ኤር​ሞን ድረስ፥</verse>
				<verse number="49">በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ መሿ​ለ​ኪያ ካለው ከአ​ሴ​ዶን ተራራ በታች ያለ​ውን ዓረባ ሁሉ ወሰዱ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">ሙሴም እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ጠርቶ አላ​ቸው፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ እን​ድ​ት​ማ​ሩ​አ​ትም፥ በማ​ድ​ረ​ግም እን​ድ​ት​ጠ​ብ​ቁ​አት ዛሬ በጆ​ሮ​አ​ችሁ የም​ና​ገ​ራ​ትን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ስሙ።</verse>
				<verse number="2">አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኮ​ሬብ ከእ​ና​ንተ ጋር ቃል ኪዳ​ኑን አጸና።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ በዚህ በሕ​ይ​ወት ካላ​ች​ሁት ከእ​ና​ንተ ከሁ​ላ​ችሁ ጋር እንጂ ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ጋር ይህ​ችን ቃል ኪዳን አላ​ጸ​ናም።</verse>
				<verse number="4">በተ​ራ​ራው ላይ በእ​ሳት መካ​ከል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለፊት ተና​ገ​ራ​ችሁ።</verse>
				<verse number="5">እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እነ​ግ​ራ​ችሁ ዘንድ በዚ​ያን ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ቆሜ ነበር፤ እና​ንተ ከእ​ሳቱ ፊት ፈር​ታ​ች​ኋ​ልና፥ ወደ ተራ​ራው አል​ወ​ጣ​ች​ሁ​ምና። እር​ሱም አለ፦</verse>
				<verse number="6">“ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ሁህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እኔ ነኝ።</verse>
				<verse number="7">“ከእኔ በቀር ሌሎች አማ​ል​ክት አይ​ሁ​ኑ​ልህ።</verse>
				<verse number="8">“በላይ በሰ​ማይ ካለው፥ በታ​ችም በም​ድር ካለው፥ ከም​ድ​ርም በታች በውኃ ካለው ነገር ማን​ኛ​ው​ንም ምሳሌ፥ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ው​ንም ምስል ለአ​ንተ አታ​ድ​ርግ፤</verse>
				<verse number="9">አት​ስ​ገ​ድ​ላ​ቸው፤ አታ​ም​ል​ካ​ቸ​ውም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ቀና​ተኛ አም​ላክ ነኝና፤ በሚ​ጠ​ሉኝ እስከ ሦስ​ተ​ኛና እስከ አራ​ተኛ ትው​ልድ ድረስ የአ​ባ​ቶ​ችን ኀጢ​አት በል​ጆች ላይ የማ​መጣ፤</verse>
				<verse number="10">ለሚ​ወ​ድ​ዱኝ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ለሚ​ጠ​ብቁ እስከ ሺህ ትው​ልድ ድረስ ምሕ​ረ​ትን የማ​ደ​ርግ።</verse>
				<verse number="11">“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የአ​ም​ላ​ክ​ህን ስም በሐ​ሰት አት​ጥራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙን በሐ​ሰት የሚ​ጠ​ራ​ውን ከበ​ደል አያ​ነ​ጻ​ው​ምና።</verse>
				<verse number="12">“ዕለተ ሰን​በ​ትን ጠብቅ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እን​ዳ​ዘ​ዘ​ህም ቀድ​ሳት።</verse>
				<verse number="13">ስድ​ስት ቀን ሥራ፤ ተግ​ባ​ር​ህ​ንም ሁሉ አድ​ርግ፥</verse>
				<verse number="14">ሰባ​ተ​ኛው ቀን ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላ​ክህ ሰን​በት ነው፤ አንተ እን​ደ​ም​ታ​ርፍ ሎሌ​ህና ገረ​ድህ ያርፉ ዘንድ፥ አንተ፥ ወንድ ልጅ​ህም፥ ሴት ልጅ​ህም፥ ሎሌ​ህም፥ ገረ​ድ​ህም፥ በሬ​ህም፥ አህ​ያ​ህም፥ ከብ​ት​ህም ሁሉ፥ በደ​ጆ​ች​ህም ውስጥ ያለ መጻ​ተኛ በእ​ርሱ ምንም ሥራ አት​ሥሩ።</verse>
				<verse number="15">አን​ተም በግ​ብፅ ባሪያ እንደ ነበ​ርህ አስብ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ በጸ​ናች እጅና በተ​ዘ​ረጋ ክንድ ከዚያ አወ​ጣህ፤ ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ዕለተ ሰን​በ​ትን ትጠ​ብ​ቃ​ትና ትቀ​ድ​ሳት ዘንድ አዘ​ዘህ።</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እን​ዳ​ዘ​ዘህ አባ​ት​ህ​ንና እና​ት​ህን አክ​ብር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር ላይ ዕድ​ሜህ እን​ዲ​ረ​ዝም፥ መል​ካ​ምም እን​ዲ​ሆ​ን​ልህ።</verse>
				<verse number="17">“አታ​መ​ን​ዝር።</verse>
				<verse number="18">“ነፍስ አት​ግ​ደል።</verse>
				<verse number="19">“አት​ስ​ረቅ።</verse>
				<verse number="20">“በባ​ል​ን​ጀ​ራህ ላይ በሐ​ሰት አት​መ​ስ​ክር፤ ምስ​ክ​ር​ንም አታ​ሳ​ብል።</verse>
				<verse number="21">“የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህን ሚስት አት​መኝ፤ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህ​ንም ቤት፥ እር​ሻ​ው​ንም፥ ሎሌ​ው​ንም፥ ገረ​ዱ​ንም፥ በሬ​ው​ንም፥ አህ​ያ​ው​ንም፥ ከባ​ል​ን​ጀ​ራህ ገን​ዘብ ሁሉ ማና​ቸ​ው​ንም አት​መኝ።</verse>
				<verse number="22">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ራ​ራው ላይ፤ በእ​ሳ​ትና በጨ​ለማ፥ በጭ​ጋ​ግና በዓ​ውሎ ነፋስ መካ​ከል ሆኖ በታ​ላቅ ድምፅ እነ​ዚ​ህን ቃሎች ለጉ​ባ​ኤ​ያ​ችሁ ሁሉ ተና​ገረ፤ ምንም አል​ጨ​መ​ረም። በሁ​ለ​ቱም የድ​ን​ጋይ ጽላት ላይ ጻፋ​ቸው፤ ለእ​ኔም ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">“እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በእ​ሳት መካ​ከል ድም​ፁን በሰ​ማ​ችሁ ጊዜ፥ ተራ​ራ​ውም በእ​ሳት ሲነ​ድድ እና​ንተ፥ የነ​ገ​ዶ​ቻ​ችሁ አለ​ቆች፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁም፥ ወደ እኔ ቀረ​ባ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="24">አላ​ች​ሁም፦ እነሆ፥ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ሩ​ንና ታላ​ቅ​ነ​ቱን አሳ​ይ​ቶ​ናል፤ ከእ​ሳ​ቱም መካ​ከል ድም​ፁን ሰም​ተ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሰው ጋር ሲነ​ጋ​ገር፥ ሰው​ዬው በሕ​ይ​ወት ሲኖር ዛሬ አይ​ተ​ናል።</verse>
				<verse number="25">አሁ​ንም አን​ሙት፤ ይህ​ችም ታላቅ እሳት አታ​ጥ​ፋን፤ እኛ የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድምፅ ዳግ​መኛ ብን​ሰማ እን​ሞ​ታ​ለን።</verse>
				<verse number="26">ከሥጋ ለባሽ ሁሉ እኛ እንደ ሰማን በእ​ሳት መካ​ከል ሆኖ ሲና​ገር የሕ​ያው አም​ላ​ክን ድምፅ ሰምቶ በሕ​ይ​ወት የኖረ ማን ነው?</verse>
				<verse number="27">አንተ ቅረብ፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ለ​ውን ሁሉ ስማ፤ እም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ንተ የሚ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ለእኛ ንገ​ረን፤ እኛም ሰም​ተን እና​ደ​ር​ገ​ዋ​ለን።</verse>
				<verse number="28">“በተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁ​ኝም ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ና​ን​ተን ቃል ድምፅ ሰማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ ይህ ሕዝብ የተ​ና​ገ​ሩ​ህን ቃል ድምፅ ሰም​ቼ​አ​ለሁ፤ የተ​ና​ገ​ሩህ ሁሉ ትክ​ክል ነው።</verse>
				<verse number="29">ለእ​ነ​ርሱ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ለል​ጆ​ቻ​ቸው መል​ካም ይሆ​ን​ላ​ቸው ዘንድ፥ እን​ዲ​ፈ​ሩኝ፥ ሁል​ጊ​ዜም ትእ​ዛ​ዜን ሁሉ እን​ዲ​ጠ​ብቁ እን​ዲህ ያለ ልብ ማን በሰ​ጣ​ቸው፥</verse>
				<verse number="30">ሄደህ፦ ወደ ቤቶ​ቻ​ችሁ ተመ​ለሱ በላ​ቸው።</verse>
				<verse number="31">አንተ ግን በዚህ በእኔ ዘንድ ቁም፤ ርስት አድ​ርጌ በም​ሰ​ጣ​ቸው ምድር ላይ ያደ​ር​ጉ​አት ዘንድ የም​ታ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ውን ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሥር​ዐ​ቴን፥ ፍር​ዴ​ንም ሁሉ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="32">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አም​ላ​ካ​ችሁ እን​ዳ​ዘ​ዛ​ችሁ ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ፤ ከእ​ር​ሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አት​በሉ።</verse>
				<verse number="33">በሕ​ይ​ወት እን​ድ​ት​ኖሩ፥ መል​ካ​ምም እን​ዲ​ሆ​ን​ላ​ችሁ፥ በም​ት​ወ​ር​ሱ​አ​ትም ምድር ዕድ​ሜ​አ​ችሁ እን​ዲ​ረ​ዝም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ባዘ​ዛ​ችሁ መን​ገድ ሁሉ ሂዱ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">“ልት​ወ​ር​ሱ​አት በም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር ታደ​ር​ጉት ዘንድ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ያዘ​ዘው ትእ​ዛ​ዝና ሥር​ዐት፥ ፍር​ድም ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">እና​ንተ፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁም፥ የልጅ ልጆ​ቻ​ች​ሁም በዕ​ድ​ሜ​አ​ችሁ ሁሉ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈር​ታ​ችሁ እኔ ለእ​ና​ንተ ያዘ​ዝ​ሁ​ትን ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዙን ሁሉ ትጠ​ብቁ ዘንድ፥ ዕድ​ሜ​አ​ች​ሁም ይረ​ዝም ዘንድ፤</verse>
				<verse number="3">እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ፦ ማርና ወተት የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ይሰ​ጥህ ዘንድ የአ​ባ​ቶ​ችህ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ እጅግ እን​ድ​ት​በዛ፥ መል​ካ​ምም እን​ዲ​ሆ​ን​ልህ ታደ​ር​ጋት ዘንድ ጠብቅ።” ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ በኋላ ሙሴ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በም​ድረ በዳ ያዘ​ዛ​ቸው ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ሁሉ ይህ ነው።</verse>
				<verse number="4">“እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤</verse>
				<verse number="5">አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ፥ በፍ​ጹ​ምም ኀይ​ልህ ውደድ።</verse>
				<verse number="6">እኔም ዛሬ አን​ተን የማ​ዝ​ዘ​ውን ይህን ቃል በል​ብህ፥ በነ​ፍ​ስ​ህም ያዝ።</verse>
				<verse number="7">ለል​ጆ​ች​ህም አስ​ተ​ም​ረው፤ በቤ​ት​ህም ስት​ቀ​መጥ፥ በመ​ን​ገ​ድም ስት​ሄድ፥ ስት​ተ​ኛም፥ ስት​ነ​ሣም አስ​ተ​ም​ረው።</verse>
				<verse number="8">በእ​ጅ​ህም እንደ ምል​ክት አድ​ር​ገው፤ በዐ​ይ​ኖ​ች​ህም መካ​ከል እን​ደ​ማ​ይ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ ይሁ​ን​ልህ።</verse>
				<verse number="9">በቤ​ት​ህም መቃ​ኖች፥ በደ​ጃ​ፍ​ህም በሮች ላይ ጻፈው።</verse>
				<verse number="10">“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ንተ ሊሰ​ጣት ለአ​ባ​ቶ​ችህ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ባገ​ባህ ጊዜ፤ ያል​ሠ​ራ​ሃ​ቸ​ው​ንም ታላ​ቅና መል​ካም ከተ​ሞች፥</verse>
				<verse number="11">ያል​ሞ​ላ​ሃ​ቸ​ው​ንም ሀብ​ትን የሞሉ ቤቶች፥ ያል​ማ​ስ​ሃ​ቸ​ው​ንም የተ​ማሱ ጕድ​ጓ​ዶች፥ ያል​ተ​ከ​ል​ሃ​ቸ​ው​ንም ወይ​ንና ወይራ በሰ​ጠህ ጊዜ፥ በበ​ላ​ህና በጠ​ገ​ብ​ህም ጊዜ፤</verse>
				<verse number="12">ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ት​ረሳ ተጠ​ን​ቀቅ።</verse>
				<verse number="13">አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ፤ እር​ሱ​ንም ብቻ አም​ልክ፤ እር​ሱ​ንም ተከ​ተል በስ​ሙም ማል።</verse>
				<verse number="14">በዙ​ሪ​ያ​ችሁ ያሉት አሕ​ዛብ የሚ​ያ​መ​ል​ኩ​አ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት አት​ከ​ተሉ።</verse>
				<verse number="15">በመ​ካ​ከ​ልህ ያለው አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀና​ተኛ አም​ላክ ነውና የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቁጣ እን​ዳ​ይ​ነ​ድ​ድ​ብህ፥ ከም​ድ​ርም ፊት እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋህ ተጠ​ን​ቀቅ።</verse>
				<verse number="16">“በፈ​ተና ቀን እንደ ፈተ​ን​ኸው አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አት​ፈ​ታ​ተ​ነው።</verse>
				<verse number="17">ለአ​ንተ ያዘ​ዘ​ውን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ፥ ምስ​ክ​ሩ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም አጥ​ብ​ቀህ ጠብቅ።</verse>
				<verse number="18">መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ልህ ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ባ​ቶ​ችህ ወደ ማለ​ላ​ቸው ወደ መል​ካ​ሚቱ ምድር ገብ​ተህ እር​ስ​ዋን ትወ​ርስ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅኑ​ንና መል​ካ​ሙን አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ ጠላ​ቶ​ች​ህን ሁሉ ከፊ​ትህ ያሳ​ድ​ድ​ልህ ዘንድ።</verse>
				<verse number="20">“ነገ ልጅህ፦ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዛ​ችሁ ምስ​ክ​ርና ሥር​ዐት፥ ፍር​ድስ ምን​ድን ነው? ብሎ በጠ​የ​ቀህ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="21">አንተ ልጅ​ህን በለው፦ በግ​ብፅ የፈ​ር​ዖን ባሪ​ያ​ዎች ነበ​ርን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጽኑ እጅ፥ በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ ከዚያ አወ​ጣን፤</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በግ​ብ​ፅና በፈ​ር​ዖን በቤ​ቱም ሁሉ ላይ በፊ​ታ​ችን ታላ​ቅና ክፉ ምል​ክት፥ ተአ​ም​ራ​ትም አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="23">ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ያገ​ባ​ንና እር​ስ​ዋን ይሰ​ጠን ዘንድ እኛን ከዚያ አወ​ጣን።</verse>
				<verse number="24">እንደ ዛሬም በሕ​ይ​ወት እን​ዲ​ያ​ኖ​ረን፥ ሁል​ጊ​ዜም መል​ካም እን​ዲ​ሆ​ን​ልን፥ አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ፈራ ዘንድ፥ ይህ​ች​ንም ሥር​ዐት ሁሉ እና​ደ​ርግ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዘ​ዘን።</verse>
				<verse number="25">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘን በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እና​ደ​ር​ጋት ዘንድ ይህ​ችን ትእ​ዛዝ ሁሉ ብን​ጠ​ብቅ ለእኛ ምሕ​ረት ይሆ​ን​ል​ናል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልት​ወ​ር​ሳት ወደ​ም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር ባመ​ጣህ ጊዜ፥ ከፊ​ት​ህም ብዙና ታላ​ላቅ አሕ​ዛ​ብን፥ ከአ​ንተ የበ​ለ​ጡ​ትን፥ የበ​ረ​ቱ​ት​ንም ሰባ​ቱን አሕ​ዛብ፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ባወጣ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="2">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ጅህ አሳ​ልፎ በሰ​ጣ​ቸ​ውና በመ​ታ​ሃ​ቸው ጊዜ፥ ፈጽ​መህ አጥ​ፋ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ቃል ኪዳን አታ​ድ​ርግ፤ አት​ማ​ራ​ቸ​ውም፤</verse>
				<verse number="3">ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር አት​ጋባ፤ ሴት ልጅ​ህን ለወ​ንድ ልጁ አት​ስጥ፥ ሴት ልጁ​ንም ለወ​ንድ ልጅህ አት​ው​ሰድ።</verse>
				<verse number="4">ልጅ​ህን ከእኔ ያር​ቀ​ዋ​ልና፤ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክ​ትም ያመ​ል​ካ​ልና። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ ይነ​ድ​ድ​ባ​ች​ኋል፤ ፈጥ​ኖም ያጠ​ፋ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="5">ነገር ግን እን​ዲህ አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ መሠ​ዊ​ያ​ቸ​ውን አፍ​ርሱ፤ ሐው​ል​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሰባ​ብሩ፥ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቍረጡ፥ የአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ምስል በእ​ሳት አቃ​ጥሉ።</verse>
				<verse number="6">“ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፤ በም​ድር ፊት ከሚ​ኖሩ አሕ​ዛብ ሁሉ ይልቅ ለእ​ርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆ​ን​ለት ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መር​ጦ​ሃ​ልና።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የወ​ደ​ዳ​ች​ሁና የመ​ረ​ጣ​ችሁ፥ ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ስለ በዛ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ እና​ንት ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ጥቂ​ቶች ነበ​ራ​ች​ሁና፤</verse>
				<verse number="8">ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ወደ​ዳ​ችሁ፥ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን መሐላ ስለ ጠበቀ፥ ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽኑ እጅ፥ በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ አወ​ጣ​ችሁ፤ ከባ​ር​ነ​ትም ቤት ከግ​ብፅ ንጉሥ ከፈ​ር​ዖን እጅ አዳ​ና​ችሁ።</verse>
				<verse number="9">አን​ተም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላክ እንደ ሆነ፥ ለሚ​ወ​ድ​ዱ​ትም፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ለሚ​ጠ​ብቁ ቃል ኪዳ​ኑ​ንና ምሕ​ረ​ቱን እስከ ሺህ ትው​ልድ ድረስ የሚ​ጠ​ብቅ የታ​መነ አም​ላክ እንደ ሆነ ዕወቅ፤</verse>
				<verse number="10">የሚ​ጠ​ሉ​ትን ለማ​ጥ​ፋት በፊ​ታ​ቸው ብድ​ራት ይመ​ል​ስ​ባ​ቸ​ዋል፤ ለሚ​ጠ​ላው አይ​ዘ​ገ​ይም፤ ነገር ግን በፊቱ ብድ​ራ​ትን ይመ​ል​ስ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="11">እን​ግ​ዲህ ታደ​ር​ጓት ዘንድ እኔ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዛ​ትን ትእ​ዛ​ዝና ሥር​ዐት፥ ፍር​ድ​ንም ጠብቁ።</verse>
				<verse number="12">“እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ይህ​ችን ፍርድ ሰም​ታ​ችሁ ብት​ጠ​ብ​ቋት፥ ብታ​ደ​ር​ጓ​ትም፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ የማ​ለ​ውን ቃል ኪዳ​ንና ምሕ​ረት ለእ​ና​ንተ ይጠ​ብ​ቅ​ላ​ች​ኋል፤</verse>
				<verse number="13">ይወ​ድ​ድ​ህ​ማል፤ ይባ​ር​ክ​ህ​ማል፤ ያባ​ዛ​ህ​ማል፤ ይሰ​ጥ​ህም ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ችህ በማ​ለ​ላ​ቸው ምድር የሆ​ድ​ህን ፍሬ፥ የመ​ሬ​ት​ህ​ንም ፍሬ፥ እህ​ል​ህን፥ ወይ​ን​ህ​ንም፥ ዘይ​ት​ህ​ንም፥ የከ​ብ​ት​ህ​ንም ብዛት፥ የበ​ግ​ህ​ንም መንጋ ይባ​ር​ክ​ል​ሃል።</verse>
				<verse number="14">ከአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ይልቅ የተ​ባ​ረ​ክህ ትሆ​ና​ለህ፤ ከሴ​ቶ​ችህ መካን አት​ኖ​ርም፤ ልጆች የሌ​ሏት አገ​ል​ጋ​ይም አት​ኖ​ርም፤ ከከ​ብ​ት​ህም መካን አይ​ኖ​ርም።</verse>
				<verse number="15">በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ሲመጣ ያየ​ኸ​ውን ክፉ ሕማ​ምና ደዌ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ያር​ቅ​ል​ሃል፤ ያየ​ኸ​ው​ንም መከራ ሁሉ ወደ አንተ አያ​መ​ጣ​ውም፤ ከአ​ን​ተም በሚ​ጠ​ሉህ ሁሉ ላይ ይመ​ል​ሰ​ዋል።</verse>
				<verse number="16">አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጥ​ህን የአ​ሕ​ዛብ ምርኮ ትበ​ላ​ለህ፤ ዐይ​ን​ህም አታ​ዝ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ ያም ለአ​ንተ ክፉ ይሆ​ን​ብ​ሃ​ልና አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አታ​ም​ል​ካ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">“በል​ብ​ህም፦ እነ​ዚህ አሕ​ዛብ ከእኔ ይልቅ ይበ​ዛ​ሉና አወ​ጣ​ቸው ዘንድ እን​ዴት እች​ላ​ለሁ? ብለህ፥ አት​ፍ​ራ​ቸው፤</verse>
				<verse number="18">ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ር​ዖ​ንና በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ሁሉ ያደ​ረ​ገ​ውን ፈጽ​መህ አስብ፤</verse>
				<verse number="19">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዓይ​ንህ እያ​የች፥ ታላቅ መቅ​ሠ​ፍ​ትን፥ ምል​ክ​ት​ንም፥ ተአ​ም​ራ​ት​ንም፥ የጸ​ና​ች​ው​ንም እጅ፥ የተ​ዘ​ረ​ጋ​ው​ንም ክንድ አድ​ርጎ እን​ዳ​ወ​ጣህ፤ እን​ዲሁ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ በም​ት​ፈ​ራ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ያደ​ር​ጋል።</verse>
				<verse number="20">ደግ​ሞም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ሩት፥ ከፊ​ት​ህም የተ​ሸ​ሸ​ጉት እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ መቅ​ሠ​ፍ​ትን ይል​ክ​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="21">ከፊ​ታ​ቸው አት​ደ​ን​ግጥ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከአ​ንተ ጋር ነውና፥ እር​ሱም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላ​ቅና ጽኑዕ ነውና።</verse>
				<verse number="22">አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ በጥ​ቂት በጥ​ቂቱ ከፊ​ትህ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፤ ምድ​ርም ምድረ በዳ እን​ዳ​ት​ሆን የም​ድረ በዳ አራ​ዊ​ትም እን​ዳ​ይ​በ​ዙ​ብህ ፈጥኜ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ አት​በል።</verse>
				<verse number="23">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እነ​ር​ሱን በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል፥ እስ​ኪ​ጠ​ፉም ድረስ በታ​ላቅ ውር​ደት ይደ​መ​ስ​ሳ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="24">ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል፤ ስማ​ቸ​ው​ንም ከዚያ ቦታ ያጠ​ፋል፤ እስ​ክ​ታ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ ማንም ከፊ​ትህ ይቆም ዘንድ አይ​ች​ልም።</verse>
				<verse number="25">የአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን ምስል በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ሠ​ራ​ባ​ቸ​ውን ብር​ንና ወር​ቅን፥ አት​መኝ፤ በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እን​ዳ​ት​በ​ድ​ል​በት ከእ​ርሱ ምንም አት​ው​ሰድ።</verse>
				<verse number="26">ርኩ​ስን ነገር ወደ ቤትህ አታ​ግባ፤ እንደ እር​ሱም ርጉም ትሆ​ና​ለህ፤ ርጉም ነውና መጸ​የ​ፍን ተጸ​የ​ፈው፤ መጥ​ላ​ት​ንም ጥላው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">“በሕ​ይ​ወት እን​ድ​ት​ኖሩ፥ እን​ድ​ት​በ​ዙም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ገብ​ታ​ችሁ እን​ድ​ት​ወ​ር​ሱ​አት፥ ዛሬ ለአ​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛዝ ሁሉ ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ።</verse>
				<verse number="2">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ት​ንህ ዘንድ፥ በል​ብ​ህም ያለ​ውን ትእ​ዛ​ዙን ትጠ​ብቅ ወይም አት​ጠ​ብቅ እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ፥ ሊያ​ስ​ጨ​ን​ቅህ በም​ድረ በዳ የመ​ራ​ህን መን​ገድ ሁሉ አስብ።</verse>
				<verse number="3">ሰውም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ በሚ​ወጣ ነገር ሁሉ በሕ​ይ​ወት እን​ዲ​ኖር እንጂ ሰው በእ​ን​ጀራ ብቻ በሕ​ይ​ወት እን​ዳ​ይ​ኖር ያስ​ታ​ው​ቅህ ዘንድ አስ​ጨ​ነ​ቀህ፥ አስ​ራ​በ​ህም፤ አን​ተም ያላ​ወ​ቅ​ኸ​ውን፥ አባ​ቶ​ች​ህም ያላ​ወ​ቁ​ትን መና መገ​በህ።</verse>
				<verse number="4">የለ​በ​ስ​ኸው ልብስ አላ​ረ​ጀም፤ እግ​ር​ህም አል​ነ​ቃም፤ እነሆ፥ አርባ ዓመት ሆነ።</verse>
				<verse number="5">ሰውም ልጁን እን​ደ​ሚ​ገ​ሥጽ እን​ዲሁ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አን​ተን እን​ዲ​ገ​ሥጽ በል​ብህ ዕወቅ።</verse>
				<verse number="6">በመ​ን​ገ​ዱም እን​ድ​ት​ሄድ፥ እር​ሱ​ንም እን​ድ​ት​ፈራ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ጠብቅ።</verse>
				<verse number="7">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መል​ካ​ምና ሰፊ ምድር፥ ከሜ​ዳና ከተ​ራ​ሮች የሚ​መ​ነጩ የውኃ ጅረ​ቶ​ችና ፈሳ​ሾ​ችም ወዳ​ሉ​ባት ምድር፥</verse>
				<verse number="8">ስንዴ፥ ገብ​ስም፥ ወይ​ንም፥ በለ​ስም፥ ሮማ​ንም ወደ ሞሉ​ባት፥ ወይ​ራም፥ ቅቤም፥ ማርም ወደ ሞሉ​ባት ምድር፥</verse>
				<verse number="9">ሳይ​ጐ​ድ​ልህ እን​ጀ​ራን ወደ​ም​ት​በ​ላ​ባት፥ አን​ዳ​ችም ወደ​ማ​ታ​ጣ​ባት ምድር፥ ድን​ጋ​ይዋ ብረት ወደ ሆነ፥ ከተ​ራ​ራ​ዋም መዳብ ወደ​ሚ​ማ​ስ​ባት ምድር ያገ​ባ​ሃል።</verse>
				<verse number="10">ትበ​ላ​ማ​ለህ፤ ትጠ​ግ​ብ​ማ​ለህ፤ ስለ ሰጠ​ህም ስለ መል​ካ​ሚቱ ምድር አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="11">“ዛሬ እኔ አን​ተን የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛ​ዙ​ንና ፍር​ዱን፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ባለ​መ​ጠ​በቅ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ት​ረሳ ተጠ​ን​ቀቅ፤</verse>
				<verse number="12">ከበ​ላ​ህና ከጠ​ገ​ብህ በኋላ፥ መል​ካ​ምም ቤት ሠር​ተህ ከተ​ቀ​መ​ጥ​ህ​ባት በኋላ፤</verse>
				<verse number="13">የላ​ምና የበግ መንጋ ከበ​ዛ​ልህ በኋላ፥ ብር​ህና ወር​ቅ​ህም፥ ያለ​ህም ሁሉ ከበ​ዛ​ልህ በኋላ፥ ልብህ እን​ዳ​ይ​ታ​በይ፤</verse>
				<verse number="14">ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ህን፥</verse>
				<verse number="15">የሚ​ና​ደፍ እባ​ብና ጊንጥ፥ ጥማ​ትም ባለ​ባት፥ ውኃም በሌ​ለ​ባት፥ በታ​ላ​ቂ​ቱና በም​ታ​ስ​ፈ​ራው ምድረ በዳ የመ​ራ​ህን፥ ከጭ​ንጫ ድን​ጋ​ይም ጣፋጭ ውኃን ያወ​ጣ​ል​ህን፥</verse>
				<verse number="16">በመ​ጨ​ረ​ሻም ዘመን መል​ካም ያደ​ር​ግ​ልህ ዘንድ ሊፈ​ት​ንህ፥ ሊያ​ዋ​ር​ድ​ህም አባ​ቶ​ችህ ያላ​ወ​ቁ​ትን መና በም​ድረ በዳ የመ​ገ​በ​ህን አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ት​ረሳ፥</verse>
				<verse number="17">በል​ብ​ህም፦ በጕ​ል​በቴ፥ በእ​ጄም ብር​ታት ይህን ሁሉ ታላቅ ኀይል አደ​ረ​ግሁ እን​ዳ​ትል።</verse>
				<verse number="18">ነገር ግን ዛሬ እንደ ሆነ ለአ​ባ​ቶ​ችህ የማ​ለ​ውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ እርሱ ኀይ​ልን ስለ​ሚ​ሰ​ጥህ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አስ​በው።</verse>
				<verse number="19">አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሞ ብት​ረሳ፥ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት ብት​ከ​ተል፥ ብታ​መ​ል​ካ​ቸ​ውም፥ ብት​ሰ​ግ​ድ​ላ​ቸ​ውም፥ ፈጽሞ እን​ደ​ም​ት​ጠፋ እኔ ዛሬ​ውኑ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን አስ​መ​ሰ​ክ​ር​ብ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስለ አል​ሰ​ማ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊ​ታ​ችሁ እን​ደ​ሚ​አ​ጠ​ፋ​ቸው እንደ አሕ​ዛብ ሁሉ እና​ን​ተም እን​ዲሁ ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">“እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ፤ ከአ​ንተ የበ​ለ​ጡ​ት​ንና የበ​ረ​ቱ​ትን አሕ​ዛብ፥ የቅ​ጽ​ራ​ቸው ግንብ እስከ ሰማይ የሚ​ደ​ርስ ታላ​ላ​ቆች ከተ​ሞ​ችን ለመ​ው​ረስ ትገቡ ዘንድ ዛሬ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ረ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="2">አን​ተም የም​ታ​ው​ቃ​ቸው፥ ስለ እነ​ር​ሱም፦ በዔ​ናቅ ልጆች ፊት መቆም ማን ይች​ላል? ሲባል የሰ​ማ​ኸው ታላቅ፥ ብዙና ረዥም ሕዝብ የዔ​ናቅ ልጆች ናቸው።</verse>
				<verse number="3">አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ትህ እን​ዲ​ያ​ልፍ ዛሬ ዕወቅ፤ እርሱ የሚ​በላ እሳት ነው፤ እርሱ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፤ በፊ​ት​ህም ያዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ነገ​ረህ ከፊ​ትህ ያር​ቃ​ቸ​ዋል፥ ፈጥ​ኖም ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="4">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ያን አሕ​ዛብ ከፊ​ትህ ባወ​ጣ​ቸው ጊዜ፦ ስለ ጽድቄ እወ​ር​ሳት ዘንድ ወደ​ዚች መል​ካም ምድር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ባኝ ብለህ በል​ብህ አት​ና​ገር፤</verse>
				<verse number="5">ምድ​ራ​ቸ​ውን ትወ​ር​ሳት ዘንድ የም​ት​ገ​ባው ስለ ጽድ​ቅ​ህና ስለ ልብህ ቅን​ነት አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊ​ትህ በሚ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው በእ​ነ​ዚያ አሕ​ዛብ ኀጢ​አት ምክ​ን​ያ​ትና ለአ​ባ​ቶ​ችህ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ቃል ያጸና ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="6">እን​ግ​ዲህ አንተ አን​ገተ ደን​ዳና ሕዝብ ነህና አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን መል​ካም ምድር ርስት አድ​ርጎ የሰ​ጠህ ስለ ጽድ​ቅህ እን​ዳ​ይ​ደለ ዛሬ ዕወቅ።</verse>
				<verse number="7">“አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በም​ድረ በዳ ምን ያህል እን​ዳ​ሳ​ዘ​ን​ኸው፥ ከግ​ብፅ ሀገር ከወ​ጣ​ህ​በት ቀን ጀምሮ ወደ​ዚህ ስፍራ እስከ መጣ​ችሁ ድረስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ እን​ዳ​መ​ፃ​ችሁ አስብ፤ አት​ር​ሳም።</verse>
				<verse number="8">በኮ​ሬብ ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አሳ​ዘ​ና​ች​ሁት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሊያ​ጠ​ፋ​ችሁ በእ​ና​ንተ ላይ ተቈጣ።</verse>
				<verse number="9">ሁለ​ቱን የድ​ን​ጋይ ጽላት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር የተ​ማ​ማ​ለ​ባ​ቸ​ውን የቃል ኪዳን ጽላት እቀ​በል ዘንድ ወደ ተራራ በወ​ጣሁ ጊዜ፥ በተ​ራ​ራው አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ተቀ​ምጬ ነበር፤ እን​ጀራ አል​በ​ላ​ሁም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣ​ሁም።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት የተ​ጻ​ፉ​ትን ሁለት የድ​ን​ጋይ ጽላት ሰጠኝ፤ በተ​ሰ​በ​ሰ​ባ​ችሁ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ራ​ራው ላይ የነ​ገ​ረኝ ቃል ሁሉ ተጽ​ፎ​ባ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="11">ከአ​ርባ ቀንና ከአ​ርባ ሌሊ​ትም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁለ​ቱን የድ​ን​ጋይ ጽላት፥ የቃል ኪዳ​ኑን ጽላት ሰጠኝ።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ ተነ​ሥ​ተህ ከዚህ ፈጥ​ነህ ውረድ፤ ከግ​ብፅ ያወ​ጣ​ሃ​ቸው ሕዝ​ብህ በድ​ለ​ዋ​ልና፤ ፈጥ​ነው ካዘ​ዝ​ኋ​ቸው መን​ገድ ፈቀቅ ብለ​ዋ​ልና፥ ቀልጦ የተ​ሠራ ምስ​ልም ለራ​ሳ​ቸው አድ​ር​ገ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ ‘አንድ ጊዜም ሁለት ጊዜም እን​ዲህ ብዬ ነገ​ር​ሁህ፤ ይህ ሕዝብ አን​ገተ ደን​ዳና ሕዝብ እንደ ሆነ አይ​ች​አ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="14">አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ፥ ስማ​ቸ​ው​ንም ከሰ​ማይ በታች እደ​መ​ስስ ዘንድ ተወኝ፤ አን​ተ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ለሚ​በ​ረ​ታና እጅግ ለሚ​በዛ ሕዝብ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።’</verse>
				<verse number="15">እኔም ተመ​ልሼ ከተ​ራ​ራው ወረ​ድሁ፤ ተራ​ራ​ውም በእ​ሳት ይነ​ድድ ነበር፤ ሁለ​ቱም የቃል ኪዳን ጽላት በሁ​ለቱ እጆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="16">እነሆ፥ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ በደ​ላ​ችሁ፥ ለእ​ና​ን​ተም ቀልጦ የተ​ሠራ ምስል ሠር​ታ​ችሁ ልት​ጠ​ብ​ቁት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካዘ​ዛ​ችሁ መን​ገድ ፈጥ​ና​ችሁ ፈቀቅ እን​ዳ​ላ​ችሁ ባየሁ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="17">ሁለ​ቱ​ንም ጽላት ያዝሁ፤ ከሁ​ለ​ቱም እጆች ጣል​ኋ​ቸው፤ በእ​ና​ን​ተም ፊት ሰበ​ር​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">ስለ ሠራ​ች​ሁት ኀጢ​አት ሁሉ፥ እር​ሱ​ንም ለማ​ስ​ቈ​ጣት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ የሆ​ነ​ውን ነገር ስላ​ደ​ረ​ጋ​ችሁ፥ እንደ ፊተ​ኛው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ዳግ​መኛ ለመ​ንሁ፤ እን​ጀራ አል​በ​ላ​ሁም፥ ውኃም አል​ጠ​ጣ​ሁም።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሊያ​ጠ​ፋ​ችሁ ከተ​ቈ​ጣ​ባ​ችሁ ከቍ​ጣ​ውና ከመ​ዓቱ የተ​ነሣ ፈራሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚ​ያን ጊዜ ደግሞ ሰማኝ።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን ሊያ​ጠ​ፋው እጅግ ተቈ​ጣው፤ ስለ አሮ​ንም ደግሞ በዚ​ያን ጊዜ ጸለ​ይሁ።</verse>
				<verse number="21">ስለ አደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ትም ኀጢ​አት የጥ​ጃ​ውን ምስል ወሰ​ድሁ፤ በእ​ሳ​ትም አቃ​ጠ​ል​ሁት፤ አደ​ቀ​ቅ​ሁ​ትም፤ እንደ ትቢ​ያም እስ​ኪ​ሆን ድረስ ፈጨ​ሁት፤ እንደ ትቢ​ያም ሆነ፤ ትቢ​ያ​ው​ንም ከተ​ራ​ራው በሚ​ወ​ርድ ወንዝ ጨመ​ር​ሁት።</verse>
				<verse number="22">“በው​ዕ​የት፥ በፈ​ተ​ናም በም​ኞት መቃ​ብ​ርም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አስ​ቈ​ጣ​ች​ሁት።</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ውጡ፤ የሰ​ጠ​ኋ​ች​ሁ​ንም ምድር ውረሱ ብሎ ከቃ​ዴስ በርኔ በላ​ካ​ችሁ ጊዜ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ዐመ​ፃ​ችሁ፤ በእ​ር​ሱም አላ​መ​ና​ች​ሁም፤ ቃሉ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="24">ለእ​ና​ንተ ከታ​ወ​ቀ​በት ቀን ጀምሮ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐመ​ፀ​ኞች ነበ​ራ​ችሁ።</verse>
				<verse number="25">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ያጠ​ፋ​ችሁ ዘንድ ስለ ተና​ገረ ቀድሞ እንደ ለመ​ንሁ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለመ​ንሁ።</verse>
				<verse number="26">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት እን​ዲህ ብዬ ጸለ​ይሁ፦ የአ​ማ​ል​ክት ንጉሥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ በታ​ላቅ ኀይ​ልህ የተ​ቤ​ዠ​ሃ​ቸ​ውን፥ በጠ​ነ​ከ​ረ​ች​ውም እጅ​ህና በተ​ዘ​ረ​ጋች ክን​ድህ ከግ​ብፅ ያወ​ጣ​ሃ​ቸ​ውን ሕዝ​ብ​ህ​ንና ርስ​ት​ህን አታ​ጥፋ።</verse>
				<verse number="27">በራ​ስህ የማ​ል​ህ​ላ​ቸ​ውን አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን አብ​ር​ሃ​ም​ንና ይስ​ሐ​ቅን፥ ያዕ​ቆ​ብ​ንም አስብ፤ የዚ​ህን ሕዝብ ልበ ደን​ዳ​ና​ነት፥ ክፋ​ቱ​ንም፥ ኀጢ​አ​ቱ​ንም አት​መ​ል​ከት፤</verse>
				<verse number="28">ከእ​ር​ስዋ እኛን ያወ​ጣ​ህ​ባት ምድር ሰዎች፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተስፋ ወደ ሰጣ​ቸው ምድር ያገ​ባ​ቸው ዘንድ አል​ቻ​ለ​ምና፥ ጠል​ቶ​አ​ቸ​ው​ማ​ልና ስለ​ዚህ በም​ድረ በዳ ሊገ​ድ​ላ​ቸው አወ​ጣ​ቸው እን​ዳ​ይሉ።</verse>
				<verse number="29">እነ​ር​ሱም በታ​ላቅ ኀይ​ልህ፥ በጸ​ና​ውና በተ​ዘ​ረ​ጋ​ውም ክን​ድህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ሃ​ቸው ሕዝ​ብ​ህና ርስ​ትህ ናቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">“በዚ​ያን ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ፊተ​ኞች ያሉ​ትን ሁለት የድ​ን​ጋይ ጽላት ለአ​ንተ ቀር​ፀህ ወደ እኔ ወደ ተራ​ራው ውጣ፤ ለአ​ን​ተም የእ​ን​ጨት ታቦት ሥራ፤</verse>
				<verse number="2">በሰ​በ​ር​ሃ​ቸው በፊ​ተ​ኞቹ ጽላት የነ​በ​ሩ​ትን ቃሎች ሁሉ በእ​ነ​ዚህ ጽላት እጽ​ፋ​ለሁ፤ በታ​ቦ​ቱም ውስጥ ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ አለኝ።</verse>
				<verse number="3">ከማ​ይ​ነ​ቅዝ እን​ጨ​ትም ታቦ​ቱን ሠራሁ፤ እንደ ፊተ​ኞ​ችም ሁለት የድ​ን​ጋይ ጽላት ቀረ​ፅሁ፤ ወደ ተራ​ራ​ውም ወጣሁ፤ ሁለ​ቱም ጽላት በእጄ ነበሩ፤</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በተ​ራ​ራው ላይ በእ​ሳት መካ​ከል የተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁን ዐሠ​ር​ቱን ቃላት ቀድሞ ተጽ​ፈው እንደ ነበረ በጽ​ላቱ ላይ ጻፈ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እነ​ር​ሱን ለእኔ ሰጠኝ።</verse>
				<verse number="5">ተመ​ል​ሼም ከተ​ራ​ራው ወረ​ድሁ፤ ጽላ​ቱ​ንም በሠ​ራ​ሁት ታቦት ውስጥ አደ​ረ​ግ​ኋ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘኝ በዚያ ኖሩ።</verse>
				<verse number="6">“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የማ​ስቢ ወገን ከሚ​ሆን ከኢ​ያ​ቅም ልጆች ቦታ ከቤ​ሮስ ተጓዙ። በዚ​ያም አሮን ሞተ፤ ተቀ​በ​ረም፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ልጁ አል​ዓ​ዛር ካህን ሆነ።</verse>
				<verse number="7">ከዚ​ያም ወደ ገድ​ገድ ተጓዙ፤ ከገ​ድ​ገ​ድም ወደ ውኃ ፈሳ​ሾች ምድር ወደ ኤጤ​ባታ ተጓዙ።</verse>
				<verse number="8">በዚ​ያን ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት ይሸ​ከም ዘንድ፥ እር​ሱ​ንም ለማ​ገ​ል​ገል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይቆም ዘንድ፥ በስ​ሙም ይባ​ርክ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስከ ዛሬ ድረስ የሌ​ዊን ነገድ ለየ።</verse>
				<verse number="9">ስለ​ዚህ ለሌ​ዋ​ው​ያን ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር ክፍ​ልና ርስት የላ​ቸ​ውም፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ራ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስ​ታ​ቸው ነውና።</verse>
				<verse number="10">“እኔም እንደ ፊተ​ኛው ጊዜ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በተ​ራ​ራው ላይ ቆምሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚህ ጊዜ ደግሞ ሰማኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሊያ​ጠ​ፋ​ችሁ አል​ወ​ደ​ደም።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ‘ተነ​ሥ​ተህ በሕ​ዝቡ ፊት ተጓዝ፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ልሰ​ጣ​ቸው ወደ ማል​ሁ​ላ​ቸው ምድር ይግቡ፤ ይው​ረ​ሱ​አ​ትም’ አለኝ።</verse>
				<verse number="12">“እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ አሁ​ንስ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ የሚ​ፈ​ል​ገው ምን​ድን ነው? አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትፈራ ዘንድ፥ በመ​ን​ገ​ዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድድ ዘንድ፥ በፍ​ጹ​ምም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ ታመ​ል​ከው ዘንድ ነው እንጂ፥</verse>
				<verse number="13">መል​ካ​ምም እን​ዲ​ሆ​ን​ልህ ዛሬ ለአ​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛ​ዝና ሥር​ዐት ትጠ​ብቅ ዘንድ ነው እንጂ፤</verse>
				<verse number="14">እነሆ፥ ሰማይ፥ ሰማየ ሰማ​ያ​ትም፥ ምድ​ርም፥ በእ​ር​ስ​ዋም ያለው ሁሉ የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።</verse>
				<verse number="15">ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን መረ​ጣ​ቸው፤ ወደ​ዳ​ቸ​ውም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ እና​ን​ተን ዘራ​ቸ​ውን እንደ ዛሬው ሁሉ ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ መረጠ።</verse>
				<verse number="16">እና​ንተ የል​ባ​ች​ሁን ክፋት ግዘሩ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አን​ገ​ታ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ።</verse>
				<verse number="17">አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ፥ የጌ​ቶች ጌታ፥ ታላቅ አም​ላክ፥ ኀያ​ልም፥ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራም፥ በፍ​ር​ድም የማ​ያ​ደላ፥ መማ​ለ​ጃም የማ​ይ​ቀ​በል ነውና።</verse>
				<verse number="18">ለመ​ጻ​ተኛ፥ ለድሃ አደ​ጉና ለመ​በ​ለ​ቲቱ ይፈ​ር​ዳል፤ መብ​ልና ልብ​ስም ይሰ​ጠው ዘንድ ስደ​ተ​ኛ​ውን ይወ​ድ​ዳል።</verse>
				<verse number="19">እና​ንተ በግ​ብፅ ሀገር ስደ​ተ​ኞች ነበ​ራ​ች​ሁና ስለ​ዚህ ስደ​ተ​ኛ​ውን ውደዱ።</verse>
				<verse number="20">አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ፤ እር​ሱ​ንም አም​ልክ፤ እር​ሱ​ንም ተከ​ተል፤ በስ​ሙም ማል።</verse>
				<verse number="21">ዐይ​ኖ​ችህ ያዩ​አ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ህን ታላ​ላ​ቆች የከ​በ​ሩ​ትን ነገ​ሮች ያደ​ረ​ገ​ልህ እርሱ መመ​ኪ​ያ​ችሁ ነው፤ እር​ሱም አም​ላ​ክህ ነው።</verse>
				<verse number="22">አባ​ቶ​ችህ ሰባ ነፍስ ሆነው ወደ ግብፅ ወረዱ፤ አሁን ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብዛ​ት​ህን እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አደ​ረገ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">“አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ውደድ፤ ሕጉ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም፥ ፍር​ዱ​ንም በዘ​መ​ንህ ሁሉ ጠብቅ።</verse>
				<verse number="2">ዛሬ ልጆ​ቻ​ችሁ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተግ​ሣጽ፥ ታላ​ቅ​ነ​ቱ​ንም፥ የጸ​ና​ችም እጁን፥ የተ​ዘ​ረ​ጋ​ው​ንም ክን​ዱን፥ ያዩና ያወቁ እን​ዳ​ይ​ደሉ ዕወቁ።</verse>
				<verse number="3">በግ​ብ​ፅም መካ​ከል በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖ​ንና በሀ​ገሩ ሁሉ ላይ ያደ​ረ​ጋ​ትን ተአ​ም​ራ​ቱ​ንና ድንቅ ሥራ​ዉን፥</verse>
				<verse number="4">በተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ች​ሁም ጊዜ በኤ​ር​ትራ ባሕር ውኃ እን​ዳ​ሰ​ጠ​ማ​ቸው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስከ ዛሬ ድረስ እን​ዳ​ጠ​ፋ​ቸው፥ በግ​ብፅ ጭፍራ በፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም፥ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም ያደ​ረ​ገ​ውን፥</verse>
				<verse number="5">ወደ​ዚህ ስፍራ እስ​ክ​ት​መጡ ድረስ በም​ድረ በዳ ያደ​ረ​ገ​ላ​ች​ሁን ሁሉ፥</verse>
				<verse number="6">በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ መካ​ከል ምድር አፍ​ዋን ከፍታ እነ​ር​ሱ​ንና ቤተ ሰቦ​ቻ​ቸ​ውን፥ ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ለእ​ነ​ር​ሱም የነ​በ​ራ​ቸ​ውን ሁሉ በዋ​ጠ​ቻ​ቸው በሮ​ቤል ልጅ በኤ​ል​ያብ ልጆች በዳ​ታ​ንና በአ​ቤ​ሮን ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፤</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ረ​ጋ​ቸ​ውን ታላ​ላቅ ሥራ​ዎች ሁሉ ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ አይ​ተ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="8">“በሕ​ይ​ወት ትኖሩ ዘንድ፥ ትበ​ዙም ዘንድ፥ ትወ​ር​ሱ​አ​ትም ዘንድ ዮር​ዳ​ኖ​ስን የም​ት​ሻ​ገ​ሩ​ላ​ትን ምድር እን​ድ​ት​ወ​ር​ሷት ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛዝ ሁሉ ጠብቁ፤</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ነ​ር​ሱና ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ለዘ​ራ​ቸው ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ በማ​ለ​ላ​ቸው ምድር ላይ ዕድ​ሜ​ያ​ችሁ እን​ዲ​ረ​ዝም።</verse>
				<verse number="10">ትወ​ር​ሳት ዘንድ የም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር፥ በአ​ት​ክ​ልት ስፍራ እን​ደ​ሚ​ዘሩ ዘር​ህን እንደ ዘራ​ህ​ባት፥ በእ​ግ​ር​ህም እን​ዳ​ጠ​ጣ​ሃት፥ እንደ ወጣ​ህ​ባት እንደ ግብፅ ምድር አይ​ደ​ለ​ችም።</verse>
				<verse number="11">ነገር ግን ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ ተሻ​ግ​ራ​ችሁ የም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር ተራ​ሮ​ችና ሜዳ​ዎች ያሉ​ባት ሀገር ናት፤ በሰ​ማይ ዝናብ ውኃ ትረ​ካ​ለች።</verse>
				<verse number="12">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ጐ​በ​ኛት ሀገር ናት፤ ከዓ​መቱ መጀ​መ​ሪያ እስከ ዓመቱ መጨ​ረሻ ድረስ የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይን ሁል ጊዜ በእ​ር​ስዋ ላይ ነው።</verse>
				<verse number="13">“እና​ንተ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድዱ ዘንድ፥ በፍ​ጹም ልባ​ችሁ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ሳ​ችሁ ታመ​ል​ኩት ዘንድ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛ​ዜን ፈጽ​ማ​ችሁ ብት​ሰሙ፥</verse>
				<verse number="14">እህ​ል​ህን፥ ወይ​ን​ህ​ንም፥ ዘይ​ት​ህ​ንም ትሰ​በ​ስብ ዘንድ በየ​ጊ​ዜው የበ​ል​ጉን ዝና​ብና የክ​ረ​ም​ቱን ዝናብ ለም​ድ​ርህ ይሰ​ጣል።</verse>
				<verse number="15">በሜ​ዳህ ለእ​ን​ስ​ሶ​ችህ ሣርን ይሰ​ጣል፤ ትበ​ላ​ማ​ለህ፤ ትጠ​ግ​ብ​ማ​ለህ።</verse>
				<verse number="16">ልባ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ስት፥ ፈቀቅ እን​ዳ​ትሉ፥ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት እን​ዳ​ታ​መ​ልኩ፥ እን​ዳ​ት​ሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም ተጠ​ን​ቀቁ።</verse>
				<verse number="17">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ እን​ዳ​ይ​ነ​ድ​ድ​ባ​ችሁ፥ ዝና​ብም እን​ዳ​ይ​ዘ​ንብ፥ ምድ​ሪ​ቱም ፍሬ​ዋን እን​ዳ​ት​ሰጥ ሰማ​ይን እን​ዳ​ይ​ዘ​ጋ​ባ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር ፈጥ​ና​ችሁ እን​ዳ​ት​ጠፉ ተጠ​ን​ቀቁ።</verse>
				<verse number="18">“እን​ግ​ዲህ እነ​ዚ​ህን ቃሎች በል​ባ​ች​ሁና በነ​ፍ​ሳ​ችሁ አኑሩ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ለም​ል​ክት በእ​ጃ​ችሁ ላይ እሰ​ሩ​አ​ቸው፤ በዐ​ይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም መካ​ከል እን​ደ​ማ​ይ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ ይሁኑ።</verse>
				<verse number="19">ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው፤ በቤ​ትም ሲቀ​መጡ፥ በመ​ን​ገ​ድም ሲሄዱ፥ ሲተ​ኙም፥ ሲነ​ሡም እን​ዲ​ነ​ጋ​ገ​ሩ​በት፤</verse>
				<verse number="20">በቤ​ትህ መቃ​ኖ​ችና በደ​ጃ​ፍ​ህም በሮች ላይ ጻፈው።</verse>
				<verse number="21">በም​ድር ላይ የሰ​ማ​ይን ዘመን ያህል ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ በማ​ለ​ላ​ቸው ምድር ዘመ​ና​ችሁ የል​ጆ​ቻ​ች​ሁም ዘመን ይረ​ዝም ዘንድ፤</verse>
				<verse number="22">አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድዱ ዘንድ፥ በመ​ን​ገ​ዱም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ እር​ሱ​ንም ትከ​ተሉ ዘንድ፥ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛዝ ሁሉ ብት​ጠ​ብቁ ብታ​ደ​ር​ጉ​አ​ትም፥</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ ሁሉ ከፊ​ታ​ችሁ ያወ​ጣል፤ ከእ​ና​ን​ተም የሚ​በ​ል​ጡ​ትን፥ የሚ​በ​ረ​ቱ​ት​ንም አሕ​ዛብ ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="24">የእ​ግ​ራ​ችሁ ጫማ የም​ት​ረ​ግ​ጣት ስፍራ ሁሉ ለእ​ና​ንተ ትሆ​ና​ለች፤ ከም​ድረ በዳም፥ ከአ​ን​ጢ​ሊ​ባ​ኖ​ስም፥ ከታ​ላ​ቁም ከኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ባሕር ድረስ ዳር​ቻ​ችሁ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="25">በእ​ና​ን​ተም ፊት ማንም መቆም አይ​ች​ልም፤ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ እንደ ተና​ገ​ራ​ችሁ፥ ማስ​ፈ​ራ​ታ​ች​ሁን፥ ማስ​ደ​ን​ገ​ጣ​ች​ሁ​ንም በም​ት​ረ​ግ​ጡ​አት ምድር ሁሉ ላይ ያኖ​ራል።</verse>
				<verse number="26">“እነሆ፥ እኔ ዛሬ በፊ​ታ​ችሁ በረ​ከ​ት​ንና መር​ገ​ምን አኖ​ራ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="27">በረ​ከ​ትም፥ እኔ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ብት​ሰሙ ነው፤</verse>
				<verse number="28">መር​ገ​ምም፥ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ባት​ሰሙ፥ ዛሬ ካዘ​ዝ​ኋ​ችሁ መን​ገድ ፈቀቅ ብትሉ፥ ሌሎ​ች​ንም የማ​ታ​ው​ቁ​አ​ቸ​ውን አማ​ል​ክት ብት​ከ​ተሉ፥ ብታ​መ​ል​ኳ​ቸ​ውም ነው።</verse>
				<verse number="29">አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ አን​ተን ወደ​ም​ት​ሄ​ድ​ባት ምድር ባገ​ባህ ጊዜ፥ በረ​ከ​ቱን በገ​ሪ​ዛን ተራራ፥ መር​ገ​ሙ​ንም በጌ​ባል ተራራ ታኖ​ራ​ለህ።</verse>
				<verse number="30">እነ​ር​ሱም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ፥ ከፀ​ሐይ መግ​ቢያ ካለ​ችው መን​ገድ በኋላ በዓ​ረባ በተ​ቀ​መ​ጡት በከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ምድር፥ በጌ​ል​ጌላ ፊት ለፊት በረ​ዥሙ ዛፍ አጠ​ገብ ናቸው።</verse>
				<verse number="31">አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዕ​ጣ​ችሁ ለሁ​ል​ጊዜ የሚ​ሰ​ጣ​ች​ሁን ምድር ትገ​ቡና ትወ​ርሱ ዘንድ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤ ትወ​ር​ሱ​አ​ታ​ላ​ች​ሁም፤ ትቀ​መ​ጡ​ባ​ታ​ላ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="32">እኔም ዛሬ በፊ​ታ​ችሁ የማ​ኖ​ራ​ትን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ሁሉ ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">“በም​ድር ላይ በም​ት​ኖ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሷት ዘንድ በሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ሀገር ታደ​ር​ጉት ዘንድ የም​ት​ጠ​ብ​ቁት ሥር​ዐት፥ ፍር​ድም ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">እና​ንተ የም​ት​ወ​ር​ሱ​አ​ቸው አሕ​ዛብ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ያመ​ለ​ኩ​ባ​ቸ​ውን፥ በረ​ዥም ተራ​ሮች፥ በኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም ላይ ከለ​ም​ለ​ምም ዛፍ በታች ያለ​ውን ስፍራ ሁሉ ፈጽ​ማ​ችሁ አጥ​ፉት፤</verse>
				<verse number="3">መሠ​ዊ​ያ​ቸ​ው​ንም አፍ​ርሱ፤ ሐው​ል​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሰባ​ብሩ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐጸ​ዶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቁረጡ፤ የአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ምስ​ሎች በእ​ሳት አቃ​ጥሉ፤ ከዚ​ያም ስፍራ ስማ​ቸ​ውን አጥፉ።</verse>
				<verse number="4">ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ያለ ሥራ በዚያ አት​ሥሩ።</verse>
				<verse number="5">ነገር ግን አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ችሁ ሁሉ በአ​ንዱ ስሙ ይጠራ ዘንድ የመ​ረ​ጠ​ውን ስፍራ ትሻ​ላ​ችሁ፤ ወደ​ዚ​ያም ትመ​ጣ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="6">ወደ​ዚ​ያም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ ቍር​ባ​ና​ች​ሁ​ንም፥ ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ ቀዳ​ም​ያ​ታ​ች​ሁን፥ ስዕ​ለ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ በፈ​ቃ​ዳ​ችሁ የም​ታ​ቀ​ር​ቡ​ትን፥ የላ​ማ​ች​ሁ​ንና የበ​ጋ​ች​ሁ​ንም በኵ​ራት ውሰዱ።</verse>
				<verse number="7">በዚ​ያም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ብሉ፤ እጃ​ች​ሁ​ንም በም​ት​ዘ​ረ​ጉ​በት፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በባ​ረ​ካ​ችሁ ነገር ሁሉ፥ እና​ን​ተና ቤተ​ሰ​ባ​ችሁ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="8">ሰው ሁሉ በፊቱ መል​ካም መስሎ የታ​የ​ውን፥ እኛ በዚህ ዛሬ የም​ና​ደ​ር​ገ​ውን ሁሉ አታ​ድ​ርጉ፤</verse>
				<verse number="9">አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ማረ​ፊ​ያና ርስት እስከ ዛሬ ድረስ አል​ደ​ረ​ሳ​ች​ሁ​ምና።</verse>
				<verse number="10">ዮር​ዳ​ኖ​ስን ግን በተ​ሻ​ገ​ራ​ችሁ ጊዜ፥ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ያ​ወ​ር​ሳ​ችሁ ምድር በተ​ቀ​መ​ጣ​ችሁ ጊዜ፥ ያለ ፍር​ሀ​ትም እን​ድ​ት​ኖሩ ከከ​በ​ቡ​አ​ችሁ ጠላ​ቶች ሁሉ ዕረ​ፍት በሰ​ጣ​ችሁ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="11">በዚ​ያን ጊዜ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ ወደ​ዚያ ወደ መረ​ጠው ስፍራ፥ እኔ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሁሉ፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ ቍር​ባ​ና​ች​ሁ​ንም፥ ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ ከእ​ጃ​ችሁ ሥራ ቀዳ​ም​ያ​ቱን የተ​መ​ረ​ጠ​ው​ንም መባ​ች​ሁን ሁሉ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም የተ​ሳ​ላ​ች​ሁ​ትን ሁሉ ውሰዱ።</verse>
				<verse number="12">እና​ን​ተም፥ ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ች​ሁና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ቻ​ች​ሁም፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ክፍ​ልና ርስት ስለ​ሌ​ለው በደ​ጆ​ቻ​ችሁ ውስጥ የተ​ቀ​መ​ጠው ሌዋ​ዊም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደስ ይበ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="13">የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን በሚ​ታ​ይህ ስፍራ ሁሉ እን​ዳ​ታ​ቀ​ርብ ተጠ​ን​ቀቅ።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከነ​ገ​ዶ​ችህ ከአ​ንዱ ዘንድ በመ​ረ​ጠው ስፍራ በዚያ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን አቅ​ርብ፤ በዚ​ያም ዛሬ እኔ የማ​ዝ​ዝ​ህን ሁሉ አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="15">“ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰጠህ በረ​ከት፥ እንደ ፈቀ​ድህ፥ በሀ​ገ​ርህ ሁሉ ውስጥ አር​ደህ ሥጋን ብላ፤ ከአ​ንተ ንጹሕ ሰው፥ ንጹ​ሕም ያል​ሆነ ሰው እንደ ሚዳ​ቋና እንደ ዋላ ያለ​ውን ይብ​ላው።</verse>
				<verse number="16">ደሙን ግን እንደ ውኃ በም​ድር ላይ አፍ​ስ​ሱት እንጂ አት​ብ​ሉት።</verse>
				<verse number="17">የእ​ህ​ል​ህን፥ የወ​ይን ጠጅ​ህን፥ የዘ​ይ​ት​ህ​ንም ዐሥ​ራት፥ የላ​ም​ህ​ንና የበ​ግ​ህ​ንም በኵ​ራት፥ የተ​ሳ​ል​ኸ​ው​ንም ስእ​ለት ሁሉ፥ በፈ​ቃ​ድህ ያቀ​ረ​ብ​ኸ​ውን፥ የእ​ጅ​ህ​ንም ቀዳ​ም​ያት በከ​ተ​ሞ​ችህ ሁሉ ውስጥ መብ​ላት አት​ች​ልም።</verse>
				<verse number="18">ነገር ግን አንተ፥ ወን​ድና ሴት ልጅ​ህም፥ ወን​ድና ሴት አገ​ል​ጋ​ይ​ህም፥ በሀ​ገ​ር​ህም ውስጥ ያለው መጻ​ተኛ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ረ​ጠው ስፍራ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ብሉት፤ እጅ​ህ​ንም በም​ት​ዘ​ረ​ጋ​በት ነገር ሁሉ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደስ ይበ​ልህ።</verse>
				<verse number="19">በም​ድ​ርህ ላይ በም​ት​ኖ​ር​በት ዘመን ሁሉ ሌዋ​ዊ​ዉን ቸል እን​ዳ​ትል ተጠ​ን​ቀቅ።</verse>
				<verse number="20">“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ረህ ድን​በ​ር​ህን ባሰ​ፋ​ልህ ጊዜ፥ ሰው​ነ​ት​ህም ሥጋ መብ​ላት ስለ ወደ​ደች፦ ሥጋ ልብላ ስትል፥ ሰው​ነ​ትህ ከወ​ደ​ደ​ችው ሁሉ ብላ።</verse>
				<verse number="21">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ ስሙ ይጠራ ዘንድ የመ​ረ​ጠው ስፍራ ከአ​ንተ ሩቅ ቢሆ​ንም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ጠህ ከላ​ምና ከበግ መን​ጋህ እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁህ እረድ፤ ሰው​ነ​ት​ህም የወ​ደ​ደ​ች​ውን በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ብላው።</verse>
				<verse number="22">ሚዳ​ቋና ዋላ እን​ደ​ሚ​በሉ እን​ዲሁ ብላው፤ ከአ​ንተ ንጹሕ ሰው፥ ንጹ​ሕም ያል​ሆነ ይብ​ላው።</verse>
				<verse number="23">ደምን እን​ዳ​ት​በላ ተጠ​ን​ቀቅ፤ ደሙ ነፍሱ ነውና፥ ነፍ​ስም ከሥጋ ጋር አይ​በ​ላ​ምና።</verse>
				<verse number="24">በም​ድር ላይ እንደ ውኃ አፍ​ስ​ሰው እንጂ አት​ብ​ላው።</verse>
				<verse number="25">በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካ​ምና ጥሩ የሆ​ነ​ውን ነገር ስታ​ደ​ርግ ለአ​ንተ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ችህ መል​ካም እን​ዲ​ሆ​ን​ላ​ችሁ፥ አት​ብ​ላው።</verse>
				<verse number="26">ነገር ግን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ነገ​ር​ህን፥ ስእ​ለ​ት​ህ​ንም ይዘህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ በዚያ እን​ዲ​ጠራ ወደ መረ​ጠው ስፍራ ሂድ።</verse>
				<verse number="27">ሥጋ​ውን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገህ፥ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ላይ አቅ​ርብ፤ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ት​ህም ደም በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ላይ ይፍ​ሰስ፥ ሥጋ​ው​ንም ብላው።</verse>
				<verse number="28">በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካ​ምና ጥሩ የሆ​ነ​ውን ነገር ስታ​ደ​ርግ ለአ​ንተ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ችህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም መል​ካም ይሆ​ን​ላ​ችሁ ዘንድ እኔ የማ​ዝ​ዝ​ህን እነ​ዚ​ህን ቃሎች ሁሉ ሰም​ተህ ጠብቅ።</verse>
				<verse number="29">“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳ​ቸው ዘንድ የም​ት​ሄ​ድ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛብ በፊ​ትህ ባጠፋ ጊዜ፥ አን​ተም በወ​ረ​ስ​ሃ​ቸው ጊዜ፥ በም​ድ​ራ​ቸ​ውም በተ​ቀ​መ​ጥህ ጊዜ፥ ከፊ​ትህ ከጠፉ በኋላ እነ​ር​ሱን ለመ​ከ​ተል እን​ዳ​ትሻ፥</verse>
				<verse number="30">አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ው​ንም እን​ዳ​ትሻ፥ አሕ​ዛ​ብም ለአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርጉ እኔም አደ​ር​ጋ​ለሁ እን​ዳ​ትል ራስ​ህን ጠብቅ።</verse>
				<verse number="31">ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ አታ​ድ​ርግ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው በእ​ሳት ስለ​ሚ​ያ​ቃ​ጥሉ አሕ​ዛብ ለአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ርኩስ ነገር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ላ​ልና።</verse>
				<verse number="32">“እኔ ዛሬ የማ​ዝ​ዝ​ህን ነገር ሁሉ ታደ​ር​ገው ዘንድ ጠብቅ፤ ምንም በእ​ርሱ ላይ አት​ጨ​ምር፤ ከእ​ር​ሱም ምንም አታ​ጕ​ድል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">“ከአ​ን​ተም ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቢነሣ፥ ምል​ክ​ትም፥ ተአ​ም​ራ​ትም ቢሰ​ጥህ፥</verse>
				<verse number="2">እር​ሱም፦ ሄደን የማ​ታ​ው​ቃ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት እን​ከ​ተል እና​ም​ል​ካ​ቸ​ውም ብሎ የተ​ና​ገ​ረህ ምል​ክቱ ወይም ተአ​ም​ራቱ ቢፈ​ጸም፥</verse>
				<verse number="3">አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በፍ​ጹም ልባ​ችሁ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ሳ​ችሁ ትወ​ድ​ዱት እን​ደ​ሆን ያውቅ ዘንድ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊፈ​ት​ና​ችሁ ነውና የዚ​ያን ነቢይ ቃል ወይም ያን ሕልም አላሚ አት​ስሙ።</verse>
				<verse number="4">አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተከ​ተሉ፤ እር​ሱ​ንም ፍሩ፤ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ጠብቁ፤ ቃሉ​ንም ስሙ፥ እር​ሱ​ንም ተማ​ጠ​ኑት።</verse>
				<verse number="5">ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ችሁ፥ ከባ​ር​ነ​ትም ቤት ካዳ​ና​ችሁ ከአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ስ​ታ​ችሁ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትሄ​ድ​ባት ዘንድ ካዘ​ዘህ መን​ገድ ሊያ​ወ​ጣህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገ​ደል፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከአ​ንተ አርቅ።</verse>
				<verse number="6">“የአ​ባ​ትህ ወይም የእ​ና​ትህ ልጅ ወን​ድ​ምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም አብ​ራህ የም​ት​ተኛ ሚስ​ትህ ወይም እንደ ነፍ​ስህ ያለ ወዳ​ጅህ በስ​ውር፦ ና፥ ሄደን አን​ተም አባ​ቶ​ች​ህም የማ​ታ​ው​ቋ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት እና​ም​ልክ ብሎ ቢያ​ስ​ትህ፥</verse>
				<verse number="7">ከም​ድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ወደ አንተ የቀ​ረ​ቡት ከአ​ን​ተም የራ​ቁት አን​ተን ከብ​በ​ውህ ያሉ አሕ​ዛብ ከሚ​ያ​መ​ል​ኩ​አ​ቸው አማ​ል​ክት፥</verse>
				<verse number="8">ከእ​ርሱ ጋር አት​ተ​ባ​በር፤ አት​ስ​ማ​ውም፤ ዐይ​ን​ህም አይ​ራ​ራ​ለት፤ አት​ማ​ረ​ውም፤ አት​ሸ​ሽ​ገ​ውም፤</verse>
				<verse number="9">ነገር ግን ፈጽ​መህ ተና​ገር፤ እር​ሱን ለመ​ግ​ደል በፊት ያንተ እጅ፥ ከዚ​ያም በኋላ የሕ​ዝቡ ሁሉ እጅ በላዩ ትሁን።</verse>
				<verse number="10">ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ካወ​ጣህ ከአ​ም​ላ​ክህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ር​ቅህ ወድ​ዶ​አ​ልና በድ​ን​ጋይ ይው​ገ​ሩት፤ ይግ​ደ​ሉ​ትም።</verse>
				<verse number="11">እስ​ራ​ኤል ሁሉ ሰም​ተው ይፍሩ፤ እን​ዲህ ያለ ክፉ ሥራም እን​ደ​ገና በእ​ና​ንተ መካ​ከል አይ​ደ​ገም።</verse>
				<verse number="12">“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልት​ኖ​ር​ባት ከሰ​ጠህ ከተ​ሞች በአ​ን​ዲቱ ከተ​ማህ፦</verse>
				<verse number="13">ክፋ​ተ​ኞች ሰዎች ከእ​ና​ንተ ዘንድ ወጥ​ተው፦ ሄደን የማ​ታ​ው​ቋ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት እና​ም​ልክ ብለው የከ​ተ​ማ​ቸ​ውን ሰዎች አሳቱ ሲሉ ወሬ ብት​ሰማ፥</verse>
				<verse number="14">ትፈ​ል​ጋ​ለህ ትመ​ረ​ም​ራ​ለ​ህም፤ ትጠ​ይ​ቃ​ለ​ህም፤ እነ​ሆም፥ እው​ነት ቢሆን፥ ይህም ክፉ ነገር በመ​ካ​ከ​ልህ እንደ ተደ​ረገ ርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥</verse>
				<verse number="15">የዚ​ያ​ችን ሀገር ሰዎች በሰ​ይፍ ስለት ፈጽሞ ትመ​ታ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ሀገ​ሪ​ቱን፥ በው​ስ​ጥ​ዋም ያለ​ውን ሁሉ ትረ​ግ​ማ​ለህ።</verse>
				<verse number="16">ዕቃ​ዋ​ንም ሁሉ ወደ አደ​ባ​ባ​ይዋ ትሰ​በ​ስ​ባ​ለህ፤ ከተ​ማ​ይ​ቱ​ንም፥ ዕቃ​ዋ​ንም ሁሉ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በእ​ሳት ፈጽ​መህ ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ወና ትሆ​ና​ለች፤ ደግ​ሞም አት​ሠ​ራም።</verse>
				<verse number="17">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ቅ​ሠ​ፍቱ ቍጣ ይመ​ለስ ዘንድ፥ ለአ​ባ​ቶ​ች​ህም እንደ ማለ​ላ​ቸው ይም​ርህ ዘንድ፥ ይራ​ራ​ል​ህም ዘንድ፥ ያበ​ዛ​ህም ዘንድ፥ ርጉም ከሆ​ነው አን​ዳች ነገር በእ​ጅህ አት​ንካ።</verse>
				<verse number="18">ዛሬም እኔ የማ​ዝ​ዝ​ህን ትእ​ዛዝ ሁሉ ብት​ጠ​ብቅ፥ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካ​ምና ጥሩ የሆ​ነ​ውን ብታ​ደ​ርግ፥ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ብት​ሰማ ለእ​ርሱ ልጅ ትሆ​ና​ለህ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">“ለሞተ ሰውም በዐ​ይ​ና​ችሁ መካ​ከል ፊታ​ች​ሁን አት​ንጩ፤ ራሳ​ች​ሁ​ንም አት​ላጩ፤</verse>
				<verse number="2">ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፥ በም​ድ​ርም ላይ ከሚ​ኖሩ አሕ​ዛብ ሁሉ ይልቅ ለእ​ርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆ​ን​ለት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አን​ተን መር​ጦ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="3">“ርኩ​ስን ነገር ሁሉ አት​ብሉ።</verse>
				<verse number="4">የም​ት​በ​ሉ​አ​ቸው እን​ስ​ሶች እነ​ዚህ ናቸው፤ በሬ፥ በግ፥ ፍየል፥</verse>
				<verse number="5">ዋልያ፥ ሚዳቋ፥ የበ​ረሃ ፍየል፥ ጎሽ፥ ብሖር፥ ሳላ፥ ድኵላ።</verse>
				<verse number="6">ከእ​ን​ስ​ሶች ሰኰ​ናው የተ​ሰ​ነ​ጠ​ቀ​ውን፥ ጥፍ​ሩም ከሁ​ለት የተ​ከ​ፈ​ለ​ውን፥ የሚ​ያ​መ​ሰ​ኳ​ው​ንም እን​ስሳ ሁሉ ትበ​ላ​ለህ።</verse>
				<verse number="7">ነገር ግን ከሚ​ያ​መ​ሰኩ ወይም ሰኰ​ና​ቸው ከተ​ሰ​ነ​ጠቀ እነ​ዚ​ህን አት​በ​ሉም፤ ግመ​ልን፥ ሽኮ​ኮን፥ ጥን​ቸ​ልን አት​በ​ሉም፤ ያመ​ሰ​ኳ​ሉና፥ ነገር ግን ሰኰ​ና​ቸው አል​ተ​ሰ​ነ​ጠ​ቀ​ምና እነ​ዚህ ለእ​ና​ንተ ርኩ​ሳን ናቸው።</verse>
				<verse number="8">እር​ያም፥ ሰኰ​ናው ስለ​ተ​ሰ​ነ​ጠቀ፥ ጥፍ​ሩም ከሁ​ለት ስለ​ተ​ከ​ፈለ፥ ነገር ግን ሰለ​ማ​ያ​መ​ሰኳ፥ እርሱ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው፤ ሥጋ​ዉን አት​ብሉ፤ በድ​ኑ​ንም አት​ንኩ።</verse>
				<verse number="9">“በው​ኆች ውስጥ ከሚ​ኖ​ሩት ሁሉ የም​ት​በ​ሉ​አ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው፤ ክን​ፍና ቅር​ፊ​ትም ያላ​ቸ​ውን ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="10">ክን​ፍና ቅር​ፊ​ትም የሌ​ላ​ቸ​ውን አት​በ​ሉም፤ ለእ​ና​ንተ ርኩ​ሳን ናቸው።</verse>
				<verse number="11">“ንጹ​ሓን የሆ​ኑ​ትን ወፎች ሁሉ ብሉ።</verse>
				<verse number="12">ሊበሉ የማ​ይ​ገ​ባ​ቸው ግን እነ​ዚህ ናቸው፤ ንስር፥ ገዴ፥ ዓሣ አውጭ።</verse>
				<verse number="13">ጭል​ፊት፥ ጭላ​ትና መሰ​ሎ​ቻ​ቸው፥</verse>
				<verse number="14">ቍራና መሰ​ሎቹ፤</verse>
				<verse number="15">ሰጎን፥ አራት ራስ አሞራ፥ ዝዪ፥ በቋል በየ​ወ​ገኑ።</verse>
				<verse number="16">ጉጉት፥ ጋጋኖ፥ የውኃ ዶሮ።</verse>
				<verse number="17">ይብራ፥ ጥምብ አንሣ አሞ​ራና መሰ​ሎ​ቻ​ቸው፥</verse>
				<verse number="18">ዕር​ኩም፥ ሽመላ፥ ሳቢ​ሳና መሰ​ሎቹ፥ ጅን​ጅ​ላቴ ወፍ፥ የሌ​ሊት ወፍ።</verse>
				<verse number="19">የሚ​በ​ር​ሩም አዕ​ዋፍ ሁሉ ለእ​ና​ንተ ንጹ​ሓን አይ​ደ​ሉ​ምና ከእ​ነ​ርሱ አት​ብሉ፤</verse>
				<verse number="20">ነገር ግን ንጹ​ሓን የሆ​ኑ​ትን ወፎች ሁሉ ብሉ።</verse>
				<verse number="21">የበ​ከ​ተ​ዉን ሁሉ አት​ብሉ፤ ይበ​ላው ዘንድ በሀ​ገ​ርህ ደጅ ለተ​ቀ​መጠ መጻ​ተኛ ወይም ለባ​ዕድ ስጠው፤ አንተ ለአ​ም​ላ​ካህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ሕዝብ ነህና፥ የፍ​የ​ሉን ጠቦት በእ​ናቱ ወተት አት​ቀ​ቅል።</verse>
				<verse number="22">“ከእ​ር​ሻህ ዘር​ተህ በየ​ዓ​መቱ ከም​ታ​ገ​ኘው እህ​ልህ ሁሉ ዐሥ​ራት ታወ​ጣ​ለህ።</verse>
				<verse number="23">በዘ​መ​ን​ህም ሁሉ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራ​ትን ትማር ዘንድ፥ ስሙ እን​ዲ​ጠ​ራ​በት በመ​ረ​ጠው ስፍራ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የእ​ህ​ል​ህን፥ የወ​ይ​ን​ህን፥ የዘ​ይ​ት​ህ​ንም ዐሥ​ራት፥ የላ​ም​ህ​ንና የበ​ግ​ህ​ንም በኵ​ራት ብላ።</verse>
				<verse number="24">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባር​ኮ​ሃ​ልና፥ መን​ገዱ ሩቅ ቢሆን፥ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙን ያኖ​ር​በት ዘንድ የመ​ረ​ጠው ስፍራ ቢር​ቅ​ብህ፥ ይህን ወደ​ዚያ ለመ​ሸ​ከም ባት​ችል፥</verse>
				<verse number="25">በብር ትሸ​ጠ​ዋ​ለህ፤ ብሩ​ንም በእ​ጅህ ይዘህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መረ​ጠው ስፍራ ትሄ​ዳ​ለህ።</verse>
				<verse number="26">በዚ​ያም በብሩ ሰው​ነ​ትህ የፈ​ለ​ገ​ውን፥ በሬ ወይም በግ፥ ወይም የወ​ይን ጠጅ፥ ወይም ብርቱ መጠጥ፥ ሰው​ነ​ትህ የሚ​ሻ​ውን ሁሉ ትገ​ዛ​ለህ፤ በዚ​ያም በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትበ​ላ​ዋ​ለህ፤ አን​ተና ቤተ ሰብ​ህም ደስ ይላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="27">ድር​ሻና ርስት ከአ​ንተ ጋር ስለ​ሌ​ለው በከ​ተ​ማህ ውስጥ ያለ​ውን ሌዋዊ ቸል አት​በል።</verse>
				<verse number="28">“በየ​ሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት መጨ​ረሻ በዚያ ዓመት የፍ​ሬ​ህን ዐሥ​ራት ሁሉ አም​ጥ​ተህ በከ​ተ​ማ​ዎ​ችህ ውስጥ ታኖ​ረ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="29">ሌዋ​ዊ​ዉም፥ ከአ​ንተ ጋር ክፍ​ልና ርስት የለ​ው​ምና፥ በከ​ተ​ማህ ውስጥ ያለ መጻ​ተኛ፥ ድሃ-አደ​ግም፥ መበ​ለ​ትም መጥ​ተው ይበ​ላሉ፤ ይጠ​ግ​ባ​ሉም፤ ይኸ​ውም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ታ​ደ​ር​ገው በእ​ጅህ ሥራ ሁሉ ይባ​ር​ክህ ዘንድ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">“በየ​ሰ​ባቱ ዓመት የዕዳ ምሕ​ረ​ትን ታደ​ር​ጋ​ለህ።</verse>
				<verse number="2">ለም​ሕ​ረ​ቱም የሚ​ገባ ትእ​ዛዝ ይህ ነው፤ ባል​ን​ጀ​ራህ ወይም ወን​ድ​ምህ የሚ​ከ​ፍ​ል​ህን ገን​ዘብ ሁሉ አት​ከ​ፈል፤ የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሕ​ረት ተብ​ላ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="3">ከባ​ዕድ ግን በእ​ርሱ ዘንድ ያለ​ህን ሁሉ መቀ​በል ትች​ላ​ለህ፤ በወ​ን​ድ​ምህ ላይ ያለ​ውን ሁሉ ግን ተው​ለት።</verse>
				<verse number="4">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ ርስት አድ​ርጎ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር ላይ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈጽሞ ይባ​ር​ክ​ሃ​ልና በመ​ካ​ከ​ልህ ድሃ አይ​ኖ​ርም፤</verse>
				<verse number="5">አንተ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ፈጽ​መህ ብት​ሰማ፥ ታደ​ር​ጋ​ትም ዘንድ ዛሬ የማ​ዝ​ዝ​ህን ይህ​ችን ትእ​ዛዝ ሁሉ ብት​ጠ​ብቅ፥</verse>
				<verse number="6">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ረህ ይባ​ር​ክ​ሃል፤ ለብዙ አሕ​ዛ​ብም ብዙ ታበ​ድ​ራ​ለህ፤ አንተ ግን አት​በ​ደ​ርም፤ ብዙ አሕ​ዛ​ብ​ንም ትገ​ዛ​ለህ፤ አን​ተን ግን አይ​ገ​ዙ​ህም።</verse>
				<verse number="7">“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ጠህ ምድር ካሉ ከተ​ሞች በአ​ን​ዲ​ትዋ ውስጥ ከሚ​ኖሩ ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ አንዱ ቢቸ​ገር ልብ​ህን አታ​ጽና፤ ለወ​ን​ድ​ምህ ከመ​ስ​ጠት እጅ​ህን አት​መ​ልስ።</verse>
				<verse number="8">ነገር ግን እጅ​ህን ለእ​ርሱ ዘርጋ፤ የለ​መ​ነ​ህ​ንም ሁሉ ስጠው።</verse>
				<verse number="9">ሰባ​ተ​ኛው ዓመት የም​ሕ​ረት ዓመት ቅርብ ነው፤ አል​ሰ​ጠ​ው​ምም ብለህ ክፉ ዐሳብ በል​ብህ እን​ዳ​ታ​ስብ ለራ​ስህ ዕወቅ። ወን​ድ​ም​ህም ዐይ​ኑን በአ​ንተ ላይ ያከ​ፋል፤ እር​ሱም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ንተ ላይ ይጮ​ሃል፤ ኀጢ​አ​ትም ይሆ​ን​ብ​ሃል።</verse>
				<verse number="10">እጅ​ህን በም​ት​ጥ​ል​በት ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ​ዚህ በሥ​ራህ ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃ​ልና ፈጽ​መህ ስጠው፤ የለ​መ​ነ​ህ​ንም ያህል አበ​ድ​ረው፤ በሰ​ጠ​ኸ​ውም ጊዜ በል​ብህ አት​ጸ​ጸት።</verse>
				<verse number="11">ድሃ ከም​ድ​ርህ ላይ አይ​ታ​ጣ​ምና ስለ​ዚህ እኔ፦ በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ላለው ድሃ፥ ለሚ​ለ​ም​ን​ህም ወን​ድ​ምህ እጅ​ህን ዘርጋ ብዬ አዝ​ዝ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">“አን​ተም ወን​ድ​ም​ህን ዕብ​ራ​ዊ​ዉን ወይም ዕብ​ራ​ዊ​ቱን ብት​ገዛ ስድ​ስት ዓመት ያገ​ል​ግ​ሉህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ከአ​ንተ ዘንድ አር​ነት አው​ጥ​ተህ ልቀ​ቀው።</verse>
				<verse number="13">ከአ​ን​ተም ዘንድ አር​ነት አው​ጥ​ተህ በለ​ቀ​ቅ​ኸው ጊዜ ባዶ​ውን አት​ል​ቀ​ቀው።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን ከበ​ጎ​ችህ፥ ከእ​ህ​ል​ህም፥ ከወ​ይ​ን​ህም መጭ​መ​ቂያ ስንቅ ትሰ​ን​ቅ​ለ​ታ​ለህ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ባረ​ከህ መጠን ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="15">አን​ተም በግ​ብፅ ምድር ባሪያ እንደ ነበ​ርህ፥ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚያ እን​ዳ​ዳ​ነህ ዐስብ፤ ስለ​ዚህ እኔ ዛሬ ይህን ነገር አዝ​ዝ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">እርሱ ግን አን​ተ​ንና ቤት​ህን ስለ ወደደ፥ በአ​ን​ተም ዘንድ መኖር መል​ካም ስለ​ሆ​ነ​ለት፦ ‘አል​ወ​ጣም’ ቢል፥</verse>
				<verse number="17">አንተ ወስፌ ወስ​ደህ በቤ​ትህ በር ላይ ጆሮ​ውን ትበ​ሳ​ዋ​ለህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ባሪያ ይሆ​ን​ል​ሃል። በሴት ባሪ​ያ​ህም ደግሞ እን​ዲሁ ታደ​ር​ጋ​ለህ።</verse>
				<verse number="18">እር​ሱ​ንም አር​ነት ባወ​ጣ​ኸው ጊዜ የም​ን​ደ​ኝ​ነ​ቱን ሥራ ሁለት ዕጥፍ አድ​ርጎ ስድ​ስት ዓመት አገ​ል​ግ​ሎ​ሃ​ልና አያ​ስ​ጨ​ን​ቅህ፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ት​ሠ​ራው ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃል።</verse>
				<verse number="19">“ላም​ህና በግህ የወ​ለ​ዱ​ትን ተባት የሆ​ነ​ውን በኵ​ራት ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቀ​ድ​ሳ​ለህ፤ በበ​ሬህ በኵ​ራት አት​ሥ​ራ​በት፤ የበ​ግ​ህ​ንም በኵ​ራት አት​ሸ​ልት።</verse>
				<verse number="20">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ረ​ጠው ስፍራ አን​ተና ቤተ ሰብህ በየ​ዓ​መቱ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ብላው።</verse>
				<verse number="21">ነው​ረኛ ወይም አን​ካሳ ወይም ዕውር ቢሆን፥ ወይም አን​ዳች ክፉ ነውር ቢኖ​ረው፥ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አት​ሠ​ዋው።</verse>
				<verse number="22">በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ትበ​ላ​ዋ​ለህ፤ ንጹሕ ሰው፥ ንጹ​ሕም ያል​ሆነ፥ ሚዳ​ቋ​ንና ዋሊ​ያን እን​ደ​ሚ​በሉ ይበ​ሉ​ታል።</verse>
				<verse number="23">ነገር ግን ደሙን በም​ድር ላይ እንደ ውኃ አፍ​ስ​ሰው እንጂ አት​ብ​ላው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">“በሚ​ያ​ዝያ ወር ከግ​ብፅ ሀገር በሌ​ሊት ወጥ​ተ​ሃ​ልና የሚ​ያ​ዝ​ያን ወር ጠብ​ቀህ፥ የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፋሲካ አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="2">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ በመ​ረ​ጠው ስፍራ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲካ ከበ​ግና ከላም መንጋ ሠዋ።</verse>
				<verse number="3">የቦ​ካ​ውን እን​ጀራ ከእ​ርሱ ጋር አት​ብላ፤ ከግ​ብፅ ሀገር በች​ኮላ ስለ ወጣህ ከግ​ብፅ ሀገር የወ​ጣ​ህ​በ​ትን ቀን በዕ​ድ​ሜህ ሁሉ ታስብ ዘንድ የመ​ከ​ራን እን​ጀራ፥ ቂጣ እን​ጀራ ሰባት ቀን ከእ​ርሱ ጋር ብላ።</verse>
				<verse number="4">ሰባት ቀንም በሀ​ገ​ርህ ሁሉ የቦካ አይ​ታ​ይም፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ማታ ከሠ​ዋ​ኸው ሥጋ እስከ ነገ ድረስ ምንም አይ​ደር።</verse>
				<verse number="5">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ጠህ ከተ​ሞች በማ​ን​ኛ​ዪ​ቱም ፋሲ​ካን ትሠዋ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ህም።</verse>
				<verse number="6">ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ በመ​ረ​ጠው በዚያ ስፍራ ከግ​ብፅ በወ​ጣ​ህ​በት ወራት፥ ፀሐይ ሲገባ፥ ማታ ፋሲ​ካን ትሠ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="7">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ረ​ጠው ስፍራ ትጠ​ብ​ሰ​ዋ​ለህ፤ ታበ​ስ​ለ​ዋ​ለ​ህም፤ ትበ​ላ​ው​ማ​ለህ፤ በነ​ጋ​ውም ተመ​ል​ሰህ ወደ ቤትህ ትሄ​ዳ​ለህ።</verse>
				<verse number="8">ስድ​ስት ቀን ቂጣ እን​ጀራ ብላ፤ ሰባ​ተ​ኛው ቀን ግን መው​ጫው ስለ​ሆነ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል ይሁን፤ ለነ​ፍ​ስም ከሚ​ሠ​ራው በቀር ሥራን ሁሉ አታ​ድ​ር​ግ​በት።</verse>
				<verse number="9">“ሰባት ሳም​ን​ትም ትቈ​ጥ​ራ​ለህ፤ መከ​ሩን ማጨድ ከም​ት​ጀ​ም​ር​በት ቀን ጀምሮ ሰባት ሳም​ንት መቍ​ጠር ትጀ​ም​ራ​ለህ።</verse>
				<verse number="10">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የባ​ረ​ከ​ህን ያህል እጅህ መስ​ጠት በም​ት​ች​ለው መጠን ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ባ​ቱን ሱባዔ በዓል ታደ​ር​ጋ​ለህ።</verse>
				<verse number="11">አንተ፥ ወንድ ልጅ​ህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባሪ​ያ​ህና ሴት ባሪ​ያህ፥ በሀ​ገ​ር​ህም ውስጥ ያለው ሌዋዊ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ህም ያሉ መጻ​ተ​ኛና ድሃ-አደግ፥ መበ​ለ​ትም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ በሚ​መ​ር​ጠው ስፍራ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደስ ይበ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="12">አን​ተም በግ​ብፅ ባሪያ እንደ ነበ​ርህ ዐስብ፤ ይህ​ንም ሥር​ዐት ጠብቅ፤ አድ​ር​ገ​ውም።</verse>
				<verse number="13">“ከአ​ው​ድ​ማ​ህና ከወ​ይን መጭ​መ​ቂ​ያህ ፍሬ​ህን በሰ​በ​ሰ​ብህ ጊዜ ሰባት ቀን የዳስ በዓል አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="14">አን​ተም፥ ወንድ ልጅ​ህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባሪ​ያ​ህና ሴት ባሪ​ያህ፥ በሀ​ገ​ር​ህም ውስጥ ያለ ሌዋ​ዊና መጻ​ተኛ፥ ድሃ-አደ​ግና መበ​ለ​ትም በበ​ዓ​ልህ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="15">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለራሱ በመ​ረ​ጠው ስፍራ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰባት ቀን በዓል ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፍ​ሬህ ሁሉ፥ በእ​ጅ​ህም ሥራ ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃ​ልና። አን​ተም ፈጽሞ ደስ ይል​ሃ​ልና።</verse>
				<verse number="16">በዓ​መት ሦስት ጊዜ በቂጣ በዓል፥ በሰ​ባቱ ሱባ​ዔም በዓል፥ በዳ​ስም በዓል ወንድ ልጅህ ሁሉ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ረ​ጠው ስፍራ ይታይ፤</verse>
				<verse number="17">በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ባዶ እጅ​ህን አት​ታይ። አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ጣ​ችሁ በረ​ከት መጠን እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ እንደ ችሎ​ታ​ችሁ ታመ​ጣ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="18">“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ሰ​ጥህ በሀ​ገ​ርህ ደጅ ሁሉ በየ​ነ​ገ​ዶ​ችህ ፈራ​ጆ​ች​ንና መባ​ውን የሚ​ጽ​ፉ​ትን ሹሙ፤ ለሕ​ዝ​ቡም ቅን ፍር​ድን ይፍ​ረዱ።</verse>
				<verse number="19">ፍር​ድን አታ​ጣ​ምም፤ ፊት አይ​ተ​ህም አታ​ድላ፤ ጉቦን አት​ቀ​በል፥ ጉቦ የጥ​በ​በ​ኞ​ችን ዐይን ያሳ​ው​ራ​ልና፥ የእ​ው​ነ​ት​ንም ቃል ያጣ​ም​ማ​ልና ጉቦ አት​ቀ​በል።</verse>
				<verse number="20">በሕ​ይ​ወት ትኖር ዘንድ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ሰ​ጥ​ህን ምድር ትወ​ርስ ዘንድ እው​ነ​ተ​ኛ​ውን ፍርድ ተከ​ተል።</verse>
				<verse number="21">“ለአ​ንተ በም​ት​ሠ​ራው በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ አጠ​ገብ ከማ​ና​ቸ​ውም ዛፍ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐጸድ አድ​ር​ገህ አት​ት​ከል።</verse>
				<verse number="22">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ጠ​ላ​ውን ሐው​ልት ለአ​ንተ አታ​ቁም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">“በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ጠላ ነውና ነውር ወይም ክፉ ነገር ያለ​በ​ትን በሬ ወይም በግ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አት​ሠዋ።</verse>
				<verse number="2">“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ጠህ ሀገ​ሮች በአ​ን​ዲ​ትዋ ውስጥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን ቃል ኪዳ​ኑን በማ​ፍ​ረስ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፋት የሠራ ቢገኝ፥</verse>
				<verse number="3">ሄዶም ሌሎች አማ​ል​ክ​ትን ያመ​ለከ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላላ​ዘ​ዘህ ለፀ​ሐ​ይና ለጨ​ረቃ ወይም ለሰ​ማይ ከዋ​ክ​ብት የሰ​ገደ ቢገኝ፥</verse>
				<verse number="4">ቢያ​ወ​ሩ​ል​ህም ብት​ሰ​ማም፥ ያን ፈጽ​መህ መር​ምር፤ እነ​ሆም፥ እው​ነት ቢሆን፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መካ​ከል እን​ዲህ ያለ ርኵ​ሰት እንደ ተሠራ ርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥</verse>
				<verse number="5">ይህን ክፉ ነገር የሠ​ሩ​ትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ታወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ፥ እስ​ኪ​ሞ​ቱም ድረስ በድ​ን​ጋይ ትመ​ት​ዋ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="6">በሁ​ለት ወይም በሦ​ስት ምስ​ክ​ሮች ሞት የሚ​ገ​ባ​ቸው ይገ​ደሉ፤ በአ​ንድ ምስ​ክር ግን አይ​ገ​ደሉ።</verse>
				<verse number="7">እር​ሱን ለመ​ግ​ደል በመ​ጀ​መ​ሪያ የም​ስ​ክ​ሮች እጅ በኋ​ላም የሕ​ዝቡ ሁሉ እጅ ትሁ​ን​በት፤ እን​ዲሁ ክፉ​ውን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አስ​ወ​ግዱ።</verse>
				<verse number="8">“በደ​ምና በደም መካ​ከል፥ በፍ​ር​ድና በፍ​ርድ መካ​ከል፥ በመ​ቍ​ሰ​ልና በመ​ቍ​ሰል መካ​ከል፥ በክ​ር​ክ​ርና በክ​ር​ክር መካ​ከል በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ሰዎች ስለ​ሚ​ከ​ራ​ከ​ሩ​በት ክር​ክር የሚ​ሳ​ንህ የፍ​ርድ ነገር ቢኖር፥ አንተ ተነ​ሥ​ተህ ስሙ በዚያ ይጠራ ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መረ​ጠው ስፍራ ትወ​ጣ​ለህ፤</verse>
				<verse number="9">ወደ ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት በዚ​ያም ዘመን ወደ አሉ ፈራ​ጆች መጥ​ተህ ትጠ​ይ​ቃ​ለህ፤ እነ​ር​ሱም የፍ​ር​ዱን ነገር ይነ​ግ​ሩ​ሃል።</verse>
				<verse number="10">ስሙ በዚያ ይጠራ ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ረ​ጠው ስፍራ እንደ ነገ​ሩህ ቃል ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ ያስ​ተ​ማ​ሩ​ህ​ንም ሕጉን ታደ​ርግ ዘንድ ጠብቅ።</verse>
				<verse number="11">እን​ዳ​ስ​ተ​ማ​ሩ​ህም ሕግ፥ እንደ ነገ​ሩ​ህም ፍርድ አድ​ርግ፤ ከነ​ገ​ሩህ ፍርድ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አት​በል።</verse>
				<verse number="12">ማና​ቸ​ውም ሰው ቢኰራ፥ በአ​ም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ለማ​ገ​ል​ገል የሚ​ቆ​መ​ውን ካህ​ኑን ወይም በዚያ ወራት ያለ​ውን ፈራ​ጁን ባይ​ሰማ ያ ሰው ይሙት፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ክፉ​ውን አስ​ወ​ግዱ፤</verse>
				<verse number="13">ሕዝ​ቡም ሁሉ ሰምቶ ይፈ​ራል፤ ከዚ​ያም ወዲያ ደግሞ አይ​በ​ድ​ልም።</verse>
				<verse number="14">“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ምድር በገ​ባህ፥ በወ​ረ​ስ​ሃ​ትም ጊዜ፥ በተ​ቀ​መ​ጥ​ህ​ባ​ትም ጊዜ፦ በዙ​ሪ​ያዬ እን​ዳ​ሉት አሕ​ዛብ ሁሉ በላዬ አለቃ እሾ​ማ​ለሁ ብትል፥</verse>
				<verse number="15">ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ መካ​ከል አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ረ​ጠ​ውን ለአ​ንተ አለቃ ትሾ​ማ​ለህ፤ ወን​ድ​ምህ ያል​ሆ​ነ​ውን ሌላ ሰው በአ​ንተ ላይ መሾም አት​ች​ልም።</verse>
				<verse number="16">ለእ​ርሱ ፈረ​ሶ​ችን እን​ዳ​ያ​በዛ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ወደ ግብፅ እን​ዳ​ይ​መ​ልስ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በዚ​ያች መን​ገድ መመ​ለ​ስን አት​ድ​ገም ብሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="17">ልቡም እን​ዳ​ይ​ስት ሚስ​ቶ​ችን ለእ​ርሱ አያ​ብዛ፤ ወር​ቅና ብርም ለእ​ርሱ እጅግ አያ​ብዛ።</verse>
				<verse number="18">“በግ​ዛ​ቱም በተ​ቀ​መጠ ጊዜ ከሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ወስዶ ይህን ሁለ​ተኛ ሕግ ለራሱ በመ​ጽ​ሐፍ ይጻፍ።</verse>
				<verse number="19">መጽ​ሐፉ ከእ​ርሱ ጋር ይኑር፤ ዕድ​ሜ​ው​ንም ሁሉ ያን​ብ​በው። አም​ላ​ኩን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ይማር ዘንድ፥ የዚ​ህን ሕግ ቃል ሁሉ፥ ይህ​ች​ንም ሥር​ዐት ጠብቆ ያደ​ርግ ዘንድ፥</verse>
				<verse number="20">ልቡ በወ​ን​ድ​ሞቹ ላይ እን​ዳ​ይ​ኰራ፥ የአ​ም​ላኩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ እን​ዳ​ይ​ተው፥ ቀኝና ግራም እን​ዳ​ይል፥ እር​ሱም ልጆ​ቹም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ረዥም ዘመን ይገዙ ዘንድ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">“ለሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት፥ ለሌ​ዊም ነገድ ሁሉ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ድር​ሻና ርስት አይ​ኑ​ራ​ቸው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ር​በው መሥ​ዋ​ዕት ድር​ሻ​ቸው ነው፤ እር​ሱን ይመ​ገ​ባሉ።</verse>
				<verse number="2">በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም መካ​ከል ርስት አይ​ኖ​ራ​ቸ​ውም፤ እርሱ እንደ ተና​ገ​ራ​ቸው ርስ​ታ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና።</verse>
				<verse number="3">በሬ ወይም በግ ለመ​ሥ​ዋ​ዕት ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ሕዝብ የካ​ህ​ናቱ ወግ ይህ ይሆ​ናል፤ ወር​ቹ​ንና ሁለ​ቱን ጕን​ጮ​ቹን፥ ጨጓ​ራ​ው​ንም ለካ​ህኑ ይሰ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="4">የእ​ህ​ል​ህን፥ የወ​ይ​ን​ህን፥ የዘ​ይ​ት​ህ​ንም ቀዳ​ም​ያት፥ አስ​ቀ​ድ​ሞም የተ​ሸ​ለ​ተ​ውን የበ​ግ​ህን ጠጕር ለእ​ርሱ ትሰ​ጣ​ለህ።</verse>
				<verse number="5">እርሱ ከል​ጆቹ ጋር በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቁሞ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያገ​ለ​ግል ዘንድ፥ በስ​ሙም ይባ​ርክ ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከነ​ገ​ዶ​ችህ ሁሉ መር​ጦ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="6">“አንድ ሌዋዊ ሰው ከሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዘንድ ካሉት ከተ​ሞች ከአ​ን​ዲቱ፥ በፍ​ጹም ልብም ሊያ​ገ​ለ​ግል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መረ​ጠው ስፍራ ቢመጣ፥</verse>
				<verse number="7">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ደ​ሚ​ቆ​ሙት እንደ ወን​ድ​ሞቹ እንደ ሌዋ​ው​ያን ሁሉ በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ያገ​ለ​ግ​ላል።</verse>
				<verse number="8">ከአ​ባ​ቶቹ ከብት ዋጋ ሌላ እንደ ባል​ን​ጀ​ሮቹ ከመ​ብል ድር​ሻ​ውን ይወ​ስ​ዳል።</verse>
				<verse number="9">“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ምድር በገ​ባህ ጊዜ እነ​ዚያ አሕ​ዛብ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ርኵ​ሰት ታደ​ርግ ዘንድ አት​ማር።</verse>
				<verse number="10">ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን በእ​ሳት የሚ​ሠዋ፥ ምዋ​ር​ተ​ኛም፥ ሞራ ገላ​ጭም፥ አስ​ማ​ተ​ኛም፥ መተ​ተ​ኛም፥</verse>
				<verse number="11">በድ​ግ​ምት የሚ​ጠ​ነ​ቍ​ልም፥ መና​ፍ​ስ​ት​ንም የሚ​ጠራ፥ ጠን​ቋ​ይም፥ ሙታን ሳቢም፥ በወ​ፍም የሚ​ያ​ሟ​ርት በአ​ንተ ዘንድ አይ​ገኝ።</verse>
				<verse number="12">ይህ​ንም የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ጠላ ነው፤ ስለ​ዚ​ህም ርኵ​ሰት አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊ​ትህ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="13">አንተ ግን በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ፍጹም ሁን።</verse>
				<verse number="14">አንተ የም​ት​ወ​ር​ሳ​ቸው እነ​ዚህ አሕ​ዛብ ሞራ ገላ​ጮ​ች​ንና ምዋ​ር​ተ​ኞ​ችን ያዳ​ም​ጣሉ፤ ለአ​ንተ ግን እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ፈ​ቀ​ደ​ምና።</verse>
				<verse number="15">“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስ​ነ​ሣ​ል​ሃል፤ እር​ሱ​ንም ስሙት።</verse>
				<verse number="16">አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በኮ​ሬብ በተ​ሰ​በ​ሰ​ባ​ች​ሁ​በት ቀን፦ ‘እን​ዳ​ን​ሞት የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድምፅ ደግሞ አን​ስማ፤ ይህ​ችን ታላቅ እሳት ደግሞ አንይ’ ብላ​ችሁ እንደ ለመ​ና​ች​ሁት ሁሉ።</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ ለአ​ንተ የተ​ና​ገ​ሩት ሁሉ ልክ ነው።</verse>
				<verse number="18">ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቃሌ​ንም በአፉ አኖ​ራ​ለሁ፤ እንደ አዘ​ዝ​ሁ​ትም ይነ​ግ​ራ​ቸ​ዋል፤</verse>
				<verse number="19">በስ​ሜም በሚ​ና​ገ​ረው ሁሉ ያን ነቢይ የማ​ይ​ሰ​ማ​ውን ሰው እኔ እበ​ቀ​ለ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">ነገር ግን ይና​ገር ዘንድ ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ትን ቃል በስሜ የሚ​ና​ገር ነቢይ፥ በሌላ አማ​ል​ክት ስም የሚ​ና​ገር ነቢ​ይም፥ እርሱ ይገ​ደል።</verse>
				<verse number="21">በል​ብ​ህም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያል​ተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል እን​ዴት አው​ቃ​ለሁ ብትል፥</verse>
				<verse number="22">ያ ነቢይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ከተ​ና​ገ​ረው ሁሉ ቃሉ ባይ​ደ​ርስ፤ እንደ ተና​ገ​ረ​ውም ባይ​ሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያን ቃል አል​ተ​ና​ገ​ረ​ውም፤ ነቢዩ በሐ​ሰት ተና​ግ​ሮ​ታ​ልና አት​ስ​ማው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ራ​ቸ​ውን የሚ​ሰ​ጥ​ህን አሕ​ዛብ ባጠ​ፋ​ቸው ጊዜ፥ በወ​ረ​ስ​ሃ​ቸ​ውም ጊዜ፥ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውና በቤ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም በተ​ቀ​መ​ጥህ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="2">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ሰ​ጥህ በም​ድ​ርህ መካ​ከል ሦስት ከተ​ሞ​ችን ለራ​ስህ ትለ​ያ​ለህ።</verse>
				<verse number="3">ለአ​ን​ተም መን​ገ​ድ​ህን ታዘ​ጋ​ጃ​ለህ፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ወ​ር​ስ​ህን ምድር ከሦ​ስት አድ​ር​ገህ ትከ​ፍ​ላ​ለህ፤ ለነ​ፍሰ ገዳ​ይም ሁሉ መማ​ጸኛ ይሁን።</verse>
				<verse number="4">“የነ​ፍሰ ገዳይ ሕግ ይህ ነው፤ ቀድሞ ጠላቱ ሳይ​ሆን ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ሳያ​ውቅ የገ​ደለ ወደ​ዚያ ሸሽቶ በሕ​ይ​ወት ይኑር።</verse>
				<verse number="5">ሰው ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ጋር እን​ጨት ሊለ​ቅም ወደ ዱር ቢሄድ፥ ዛፉ​ንም ሲቈ​ርጥ ምሳሩ ከእጁ ቢወ​ድቅ፥ ብረ​ቱም ከእ​ጄ​ታው ቢወ​ልቅ፥ በባ​ል​ን​ጀ​ራ​ውም ላይ ቢወ​ድ​ቅና ቢገ​ድ​ለው፥ ከእ​ነ​ዚህ ከተ​ሞች በአ​ን​ዲቱ ተማ​ጥኖ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፤</verse>
				<verse number="6">ባለ ደሙ ነፍሰ ገዳ​ዩን በልቡ ተና​ድዶ እን​ዳ​ያ​ሳ​ድ​ደው መን​ገ​ዱም ሩቅ ስለ​ሆነ አግ​ኝቶ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ለው፥ አስ​ቀ​ድሞ ጠላቱ አል​ነ​በ​ረ​ምና ሞት አይ​ገ​ባ​ውም።</verse>
				<verse number="7">ስለ​ዚህ እኔ፦ ለአ​ንተ ሦስት ከተ​ሞ​ችን ለይ ብዬ አዝ​ዤ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ችህ እንደ ማለ​ላ​ቸው ዳር​ቻ​ህን ቢያ​ሰፋ፥ ለአ​ባ​ቶ​ችህ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ ብሎ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ምድር ሁሉ ቢሰ​ጥህ፥</verse>
				<verse number="9">አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድድ ዘንድ፥ ሁል​ጊ​ዜም በመ​ን​ገዱ ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ ዛሬ የማ​ዝ​ዝ​ህን ይህ​ችን ትእ​ዛዝ ሁሉ ታደ​ር​ጋት ዘንድ ብት​ሰማ፥ በእ​ነ​ዚህ በሦ​ስት ከተ​ሞች ላይ ሌሎች ሦስት ከተ​ሞ​ችን ትጨ​ም​ራ​ለህ።</verse>
				<verse number="10">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር ውስጥ ንጹሕ ደም እን​ዳ​ይ​ፈ​ስስ፥ በው​ስ​ጥ​ህም የደም ወን​ጀ​ለኛ እን​ዳ​ይ​ኖር።</verse>
				<verse number="11">“ሰው ግን ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ቢጠላ፥ ቢሸ​ም​ቅ​በ​ትም፥ በእ​ር​ሱም ላይ ቢነሣ፥ ቢገ​ድ​ለ​ውም፥ ከእ​ነ​ዚህ ከተ​ሞች በአ​ን​ዲቱ ቢማ​ጠን፥</verse>
				<verse number="12">የከ​ተ​ማው ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ይል​ካሉ፤ ከዚ​ያም ይይ​ዙ​ታል። በባ​ለ​ደ​ሙም እጅ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ታል፤ ይሞ​ታ​ልም።</verse>
				<verse number="13">ዐይ​ን​ህም አት​ራ​ራ​ለት፤ ነገር ግን ንጹ​ሑን ደም ከእ​ስ​ራ​ኤል ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ፤ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ል​ሃል።</verse>
				<verse number="14">“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር፤ በም​ት​ካ​ፈ​ላት ርስ​ትህ አባ​ቶ​ችህ የተ​ከ​ሉ​ትን የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህን የድ​ን​በር ምል​ክት አት​ን​ቀል።</verse>
				<verse number="15">“ስለ በደል ሁሉ፥ ክፉ በማ​ድ​ረ​ግም ስለ​ሚ​ሠ​ራት ኀጢ​አት ሁሉ በማ​ንም ላይ አንድ ምስ​ክር አይ​ሁን፤ በሁ​ለት ምስ​ክ​ሮች ወይም በሦ​ስት ምስ​ክ​ሮች ቃል ነገር ሁሉ ይጸ​ናል።</verse>
				<verse number="16">በዐ​መፃ ይከ​ስ​ሰው ዘንድ በሰው ላይ ሐሰ​ተኛ ምስ​ክር ቢቆም፥</verse>
				<verse number="17">ሁለቱ ጠበ​ኞች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በካ​ህ​ና​ቱና በዚያ ዘመን በሚ​ፈ​ርዱ ፈራ​ጆች ፊት ይቆ​ማሉ፤</verse>
				<verse number="18">ፈራ​ጆ​ቹም አጥ​ብ​ቀው ይመ​ረ​ም​ራሉ፤ ያም ምስ​ክር ሐሰ​ተኛ ምስ​ክር ሆኖ በወ​ን​ድሙ ላይ በሐ​ሰት ተና​ግሮ ቢገኝ፥</verse>
				<verse number="19">በወ​ን​ድሙ ላይ ክፋ​ትን ያደ​ርግ ዘንድ እንደ ወደደ በእ​ርሱ ላይ ታደ​ር​ጉ​በ​ታ​ላ​ችሁ፤ እን​ዲ​ሁም ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ክፉ​ውን ታስ​ወ​ግ​ዳ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="20">ሌላ​ውም ሰምቶ ይፈ​ራል፤ እን​ደ​ዚህ ያለ​ው​ንም ክፋት በመ​ካ​ከ​ልህ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ደግሞ አያ​ደ​ር​ግም።</verse>
				<verse number="21">ዐይ​ን​ህም አት​ራ​ራ​ለት፤ ነፍስ በነ​ፍስ፥ ዐይን በዐ​ይን፥ ጥርስ በጥ​ርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእ​ግር ይመ​ለ​ሳል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">“ጠላ​ቶ​ች​ህን ለመ​ው​ጋት በወ​ጣህ ጊዜ፥ ፈረ​ሶ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ሕዝ​ቡ​ንም ከአ​ንተ ይልቅ በዝ​ተው ባየህ ጊዜ፥ ከግ​ብፅ ሀገር ያወ​ጣህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና አት​ፍ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">ወደ ጦር​ነ​ትም በቀ​ረ​ባ​ችሁ ጊዜ ካህኑ ይቅ​ረብ፤ ለሕ​ዝ​ቡም እን​ዲህ ብሎ ይን​ገ​ራ​ቸው፦</verse>
				<verse number="3">እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ፤ ዛሬ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ለመ​ው​ጋት ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ፤ ልባ​ችሁ አይ​ታ​ወክ፤ አት​ፍሩ፤ አት​ሸ​በሩ፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም ፈቀቅ አት​በሉ፤</verse>
				<verse number="4">ከእ​ና​ንተ ጋር የሚ​ሄድ፥ ያድ​ና​ች​ሁም ዘንድ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ስለ እና​ንተ የሚ​ወጋ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና።</verse>
				<verse number="5">ጸሐ​ፍ​ትም ለሕ​ዝቡ እን​ዲህ ብለው ይና​ገሩ፦ አዲስ ቤት ሠርቶ ያላ​ስ​መ​ረቀ ሰው ቢኖር በጦ​ር​ነት እን​ዳ​ይ​ሞት ሌላም ሰው እን​ዳ​ያ​ስ​መ​ር​ቀው ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ።</verse>
				<verse number="6">ወይ​ንም ተክሎ ደስ ያል​ተ​ሰ​ኘ​በት ሰው ቢኖር በጦ​ር​ነት እን​ዳ​ይ​ሞት ሌላም ሰው ደስ እን​ዳ​ይ​ሰ​ኝ​በት ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ።</verse>
				<verse number="7">ሚስ​ትም አጭቶ ያላ​ገ​ባት ሰው ቢኖር በጦ​ር​ነት እን​ዳ​ይ​ሞት ሌላም ሰው እን​ዳ​ያ​ገ​ባት ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ።</verse>
				<verse number="8">ጸሐ​ፍ​ቱም ደግሞ ጨም​ረው፦ ማንም ፈሪና ልበ ድን​ጉጥ ሰው ቢሆን የወ​ን​ድ​ሞ​ቹን ልብ እንደ እርሱ እን​ዳ​ያ​ስ​ፈራ ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ ብለው ለሕ​ዝቡ ይና​ገሩ።</verse>
				<verse number="9">ጸሐ​ፍ​ቱም ለሕ​ዝቡ ነግ​ረው በጨ​ረሱ ጊዜ ከታ​ላ​ላቁ ሕዝብ መካ​ከል የሠ​ራ​ዊት አለ​ቆ​ችን ይሹሙ።</verse>
				<verse number="10">“ለመ​ዋ​ጋት ወደ አን​ዲት ከተማ በደ​ረ​ስህ ጊዜ አስ​ቀ​ድ​መህ በሰ​ላም ቃል ጥራ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">የሰ​ላም ቃልም ቢመ​ል​ሱ​ልህ ደጅም ቢከ​ፍ​ቱ​ልህ፥ በከ​ተ​ማው ያለው ሕዝብ ሁሉ ይገ​ብ​ሩ​ልህ፤ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ይሁ​ኑህ።</verse>
				<verse number="12">የሰ​ላም ቃልም ባይ​መ​ል​ሱ​ልህ ከአ​ን​ተም ጋር መዋ​ጋት ቢወ​ድዱ፥ አንተ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ትከ​ብ​ባ​ለህ፤</verse>
				<verse number="13">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጅህ አሳ​ልፎ በሰ​ጣት ጊዜ፥ በእ​ር​ስዋ ያሉ​ትን ወን​ዶች ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት ትገ​ድ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤</verse>
				<verse number="14">ከሴ​ቶ​ቹና ከጓዙ በቀር እን​ስ​ሶ​ቹን፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ያለ​ውን ምርኮ ሁሉ ዘር​ፈህ ለአ​ንተ ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጥ​ህን የጠ​ላ​ቶ​ች​ህን ምርኮ ትበ​ላ​ለህ።</verse>
				<verse number="15">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ርስ ዘንድ ምድ​ራ​ቸ​ውን ከሚ​ሰ​ጥህ ከእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ከተ​ሞች ባይ​ደ​ሉት ከአ​ንተ እጅግ በራ​ቁት ከተ​ሞች ሁሉ እን​ዲሁ ታደ​ር​ጋ​ለህ።</verse>
				<verse number="16">ከእ​ነ​ር​ሱም ምንም ነፍስ አታ​ድ​ንም።</verse>
				<verse number="17">ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘህ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ዉን፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ዉን፥ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ዉ​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ዉ​ንም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ዉ​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ዉ​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ዉ​ንም ፈጽ​መህ ትረ​ግ​ማ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="18">ለአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸው ያደ​ረ​ጉ​ትን ርኵ​ሰት ሁሉ ታደ​ርጉ ዘንድ እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩ​አ​ችሁ፥ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኀጢ​አት እን​ዳ​ት​ሠሩ ትረ​ግ​ማ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="19">“ከተ​ማ​ዪ​ቱን ለመ​ው​ጋ​ትና ለመ​ው​ሰድ ብዙ ቀን ብት​ከ​ብ​ባት፥ ምሳ​ር​ህን አን​ሥ​ተህ ዛፎ​ች​ዋን አት​ቍ​ረጥ፤ ከእ​ነ​ርሱ ትበ​ላ​ለ​ህና አት​ቍ​ረ​ጣ​ቸው፤ ወደ አንተ ይመ​ጣና ወደ ቅጥ​ር​ህም ይገባ ዘንድ የም​ድር ዛፍ ሰው መሆኑ ነውን?</verse>
				<verse number="20">ለመ​ብል የማ​ይ​ሆ​ኑ​ትን የም​ታ​ው​ቃ​ቸ​ውን ዛፎች ታጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ትቈ​ር​ጣ​ቸ​ው​ማ​ለህ፤ እስ​ክ​ታ​ሸ​ን​ፋ​ትም ድረስ በም​ት​ዋ​ጋህ ከተማ ላይ ምሽግ ትመ​ሽ​ጋ​ለህ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር የተ​ገ​ደለ ሰው በሜዳ ወድቆ ቢገኝ፥ ገዳ​ዩም ባይ​ታ​ወቅ፥</verse>
				<verse number="2">ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ች​ህና ፈራ​ጆ​ችህ ወጥ​ተው በተ​ገ​ደ​ለው ሰው ዙሪያ እስ​ካ​ሉት ከተ​ሞች ድረስ በስ​ፍር ይለኩ፤</verse>
				<verse number="3">ለተ​ገ​ደ​ለ​ውም ሰው አቅ​ራ​ቢያ የሆ​ነች የከ​ተ​ማ​ዪቱ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ከላ​ሞች ለሥራ ያል​ደ​ረ​ሰ​ች​ውን፥ ቀን​በ​ርም ያል​ተ​ጫ​ነ​ባ​ትን ጊደር ይው​ሰዱ፤</verse>
				<verse number="4">የዚ​ያ​ችም ከተማ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጊደ​ሪ​ቱን ይዘው ፈሳሽ ውኃ ወዳ​ለ​በት ወዳ​ል​ታ​ረ​ሰና ዘርም ወዳ​ል​ተ​ዘ​ራ​በት ሽለቆ ይሄ​ዳሉ፤ በዚ​ያም በሸ​ለ​ቆው ውስጥ የጊ​ደ​ሪ​ቱን ቋን​ጃ​ዋን ይቈ​ር​ጣሉ።</verse>
				<verse number="5">የሌዊ ልጆች ካህ​ና​ትም ይቀ​ር​ባሉ፤ በፊቱ እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግሉ፥ በስ​ሙም እን​ዲ​ባ​ርኩ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መር​ጦ​አ​ቸ​ዋ​ልና፤ በእ​ነ​ር​ሱም ቃል ክር​ክር ሁሉ ጕዳ​ትም ሁሉ ይቆ​ማ​ልና፤</verse>
				<verse number="6">ወደ ተገ​ደ​ለው ሰው አቅ​ራ​ቢያ የሆ​ነ​ችው የከ​ተ​ማ​ዪቱ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ቋን​ጃዋ በተ​ቈ​ረ​ጠው ጊደር ራስ ላይ እጃ​ቸ​ውን ይታ​ጠቡ፦</verse>
				<verse number="7">‘እጆ​ቻ​ችን ይህን ደም አላ​ፈ​ሰ​ሱም፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ንም አላ​ዩም፤</verse>
				<verse number="8">አቤቱ፥ ከግ​ብፅ ምድር የተ​ቤ​ዠ​ኸ​ውን ሕዝ​ብ​ህን እስ​ራ​ኤ​ልን ይቅር በል፤ በሕ​ዝ​ብ​ህም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ የን​ጹ​ሑን ደም በደል አት​ቍ​ጠር’ ብለው ይና​ገሩ፤ ስለ ደሙም ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="9">አን​ተም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካ​ምና ጥሩ የሆ​ነ​ውን ባደ​ረ​ግህ ጊዜ የን​ጹ​ሑን ደም በደል ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ታር​ቃ​ለህ።</verse>
				<verse number="10">“ጠላ​ቶ​ች​ህን ልት​ወጋ በወ​ጣህ ጊዜ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጅህ አሳ​ልፎ በሰ​ጣ​ቸ​ውና በማ​ረ​ክ​ሃ​ቸው ጊዜ፥</verse>
				<verse number="11">በም​ር​ኮው ውስጥ የተ​ዋ​በች ሴት ብታይ፥ ብት​መ​ኛ​ትም፥ ሚስ​ትም ልታ​ደ​ር​ጋት ብት​ወ​ድድ፥</verse>
				<verse number="12">ወደ ቤትህ ታመ​ጣ​ታ​ለህ፤ ራስ​ዋ​ንም ትላ​ጫ​ታ​ለህ፤ ጥፍ​ር​ዋ​ንም ትቈ​ር​ጥ​ላ​ታ​ለህ፤</verse>
				<verse number="13">የተ​ማ​ረ​ከ​ች​በ​ት​ንም ልብስ ታወ​ል​ቅ​ላ​ታ​ለህ፤ በቤ​ት​ህም ታስ​ቀ​ም​ጣ​ታ​ለህ፤ ስለ አባ​ቷና ስለ እናቷ አንድ ወር ሙሉ ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ ከዚ​ያም በኋላ ትደ​ር​ስ​ባ​ታ​ለህ፤ ባልም ትሆ​ና​ታ​ለህ፤ እር​ስ​ዋም ሚስት ትሆ​ን​ል​ሃ​ለች።</verse>
				<verse number="14">ከዚ​ያም በኋላ በእ​ር​ስዋ ደስ ባይ​ልህ አር​ነት አው​ጥ​ተህ ትለ​ቅ​ቃ​ታ​ለህ፤ በዋጋ ግን አት​ሸ​ጣ​ትም፤ አግ​ብ​ተ​ሃ​ታ​ልና እን​ደ​ባ​ሪያ አት​ቍ​ጠ​ራት።</verse>
				<verse number="15">“ለአ​ንድ ሰው አን​ዲቱ የተ​ወ​ደ​ደች፥ አን​ዲ​ቱም የተ​ጠ​ላች ሁለት ሚስ​ቶች ቢኖ​ሩት፥ ለእ​ር​ሱም የተ​ወ​ደ​ደ​ችው፥ ደግ​ሞም የተ​ጠ​ላ​ችው ልጆ​ችን ቢወ​ልዱ፥ በኵ​ሩም ከተ​ጠ​ላ​ችው ሚስት የተ​ወ​ለ​ደው ልጅ ቢሆን፥</verse>
				<verse number="16">ለል​ጆቹ ከብ​ቱን በሚ​ያ​ወ​ር​ስ​በት ቀን ከተ​ጠ​ላ​ችው ሚስት በተ​ወ​ለ​ደው በበ​ኵሩ ፊት ከተ​ወ​ደ​ደ​ችው ሚስት የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ልጅ በኵር ያደ​ር​ገው ዘንድ አይ​ገ​ባ​ውም፤</verse>
				<verse number="17">ነገር ግን ከከ​ብቱ ሁለት እጥፍ ለእ​ርሱ በመ​ስ​ጠት ከተ​ጠ​ላ​ችው ሚስት የተ​ወ​ለ​ደው ልጅ በኵር እንደ ሆነ ያስ​ታ​ውቅ። የኀ​ይሉ መጀ​መ​ሪያ ነውና በኵ​ር​ነቱ የእ​ርሱ ነው።</verse>
				<verse number="18">“ማንም ሰው ለአ​ባቱ ቃልና ለእ​ናቱ ቃል የማ​ይ​ታ​ዘዝ፥ ቢገ​ሥ​ጹ​ትም የማ​ይ​ሰ​ማ​ቸው ትዕ​ቢ​ተ​ኛና ዐመ​ፀኛ ልጅ ቢኖ​ረው፥</verse>
				<verse number="19">አባ​ቱና እናቱ ይዘው ወደ ከተ​ማዉ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ ወደ​ሚ​ኖ​ር​በ​ትም ስፍራ በር ይው​ሰ​ዱት፤</verse>
				<verse number="20">የከ​ተ​ማ​ዉ​ንም ሰዎች፦ ‘ይህ ልጃ​ችን ትዕ​ቢ​ተ​ኛና ዐመ​ፀኛ ነው፥ ቃላ​ች​ን​ንም አይ​ሰ​ማም፤ ስስ​ታ​ምና ሰካ​ራም ነው’ ይበ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">የከ​ተ​ማ​ዉም ሰዎች ሁሉ በድ​ን​ጋይ ደብ​ድ​በው ይግ​ደ​ሉት፤ እን​ዲ​ህም ክፉ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ልህ ታር​ቃ​ለህ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ሰም​ተው ይፈ​ራሉ።</verse>
				<verse number="22">“ማንም ሰው ለሞት የሚ​ያ​በ​ቃ​ውን ኀጢ​አት ቢሠራ፥ እን​ዲ​ሞ​ትም ቢፈ​ረ​ድ​በት፥ በእ​ን​ጨ​ትም ላይ ብት​ሰ​ቅ​ለው፥</verse>
				<verse number="23">በእ​ን​ጨት ላይ የተ​ሰ​ቀለ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ረ​ገመ ነውና ሥጋው በእ​ን​ጨት ላይ አይ​ደር፤ ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ የሰ​ጠ​ህን ምድር እን​ዳ​ታ​ረ​ክስ በእ​ር​ግጥ በዚ​ያው ቀን ቅበ​ረው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">“የወ​ን​ድ​ምህ በሬ ወይም በግ በመ​ን​ገድ ጠፍቶ ብታይ ቸል አት​በል፤ እነ​ር​ሱን መል​ሰህ ለወ​ን​ድ​ምህ ስጥ።</verse>
				<verse number="2">ወን​ድ​ም​ህም በአ​ቅ​ራ​ቢ​ያህ ባይ​ሆን ወይም ባታ​ው​ቀው ይዘ​ሃ​ቸው ወደ ቤትህ ትገ​ባ​ለህ፤ ወን​ድ​ምህ እስ​ኪ​ሻ​ቸው ድረስ በአ​ንተ ዘንድ ይቀ​መ​ጣሉ፤ ለእ​ር​ሱም ትመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለህ።</verse>
				<verse number="3">አህ​ያ​ውም ቢሆን፥ በሬ​ውም ቢሆን፥ ወይም ልብሱ ቢሆን እን​ዲሁ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ እን​ዲ​ሁም በወ​ን​ድ​ምህ በጠ​ፋ​በት ነገር ሁሉ ባገ​ኘ​ኸው ጊዜ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ ቸል ልት​ለው አይ​ገ​ባ​ህም።</verse>
				<verse number="4">የወ​ን​ድ​ምህ አህ​ያው ወይም በሬው በመ​ን​ገድ ወድቆ ብታይ ቸል አት​በ​ላ​ቸው፤ ነገር ግን ከእ​ርሱ ጋር ሆነህ አነ​ሣ​ሣው።</verse>
				<verse number="5">“ሴት የወ​ንድ ልብስ አት​ል​በስ፤ ወን​ድም የሴት ልብስ አይ​ል​በስ፤ ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ጠላ ነውና።</verse>
				<verse number="6">“በመ​ን​ገድ በማ​ና​ቸ​ውም ዛፍ ላይ ወይም በመ​ሬት ላይ ከጫ​ጭ​ቶ​ችና ከእ​ን​ቍ​ላል ጋር እና​ቲቱ በእ​ነ​ዚህ ላይ ተቀ​ምጣ የወፍ ጎጆ ብታ​ገኝ እና​ቲ​ቱን ከጫ​ጭ​ቶ​ችዋ ጋር አት​ው​ሰድ።</verse>
				<verse number="7">ነገር ግን መል​ካም ይሆ​ን​ልህ ዘንድ፥ ዕድ​ሜ​ህም ይረ​ዝም ዘንድ እና​ቲ​ቱን ልቀቅ፤ ጫጭ​ቶ​ች​ንም ለአ​ንተ ውሰድ።</verse>
				<verse number="8">“አዲስ ቤት በሠ​ራህ ጊዜ ማንም ከእ​ርሱ ወድቆ በቤ​ትህ ግድያ እን​ዳ​ታ​ደ​ርግ ለሰ​ገ​ነ​ትህ መከታ አድ​ር​ግ​ለት።</verse>
				<verse number="9">“ፍሬ​ው​ንና የዘ​ራ​ኸ​ውን ዘር ከወ​ይ​ንህ ፍሬ ጋር እን​ዳ​ት​ለ​ቅም በወ​ይ​ንህ ቦታ ላይ የተ​ለ​ያየ ዓይ​ነት ተክል አት​ት​ከል።</verse>
				<verse number="10">በአ​ህ​ያ​ህና በበ​ሬህ በአ​ን​ድ​ነት አት​ረስ።</verse>
				<verse number="11">ከተ​ልባ እግ​ርና ከበግ ጠጕር በአ​ን​ድ​ነት የተ​ሠራ ልብስ አት​ል​በስ።</verse>
				<verse number="12">“በም​ት​ለ​ብ​ሰው በል​ብ​ስህ በአ​ራቱ ማዕ​ዘን ዘርፍ አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="13">“ማና​ቸ​ውም ሰው ሚስት ቢያ​ገባ፥ አብ​ሮ​አ​ትም ከኖረ በኋላ ቢጠ​ላት፥</verse>
				<verse number="14">የነ​ውር ነገ​ርም ቢያ​መ​ጣ​ባት፥ እኔ ይህ​ችን ሴት ሚስቴ አድ​ርጌ አገ​ባ​ኋት፤ በደ​ረ​ስ​ሁ​ባ​ትም ጊዜ ድን​ግ​ል​ና​ዋን አላ​ገ​ኘ​ሁ​ባ​ትም ብሎ ክፉ ስም ቢያ​ወ​ጣ​ባት፥</verse>
				<verse number="15">የብ​ላ​ቴ​ና​ዪቱ አባ​ትና እናት የል​ጃ​ቸ​ውን የድ​ን​ግ​ል​ና​ዋን ልብስ ወስ​ደው በበሩ አደ​ባ​ባይ ወደ ተቀ​መጡ ወደ ከተማ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ያም​ጡት፤</verse>
				<verse number="16">የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹን፦ እኔ ለዚህ ሰው ልጄን ዳር​ሁ​ለት፤ እር​ሱም ጠላት፤</verse>
				<verse number="17">እነ​ሆም፦ በል​ጅህ ድን​ግ​ልና አላ​ገ​ኘ​ሁ​ባ​ትም ብሎ የነ​ውር ነገር አወ​ራ​ባት፤ የል​ጄም የድ​ን​ግ​ል​ናዋ ልብስ ይኸው ይላ​ቸ​ዋል። በከ​ተ​ማም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ፊት ልብ​ሱን ይዘ​ረ​ጋሉ።</verse>
				<verse number="18">የዚ​ያች ከተማ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ያን ሰው ወስ​ደው ይገ​ሥ​ጹት፤</verse>
				<verse number="19">በእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ላይ ክፉ ስም አም​ጥ​ቶ​አ​ልና መቶ የብር ሰቅል ያስ​ከ​ፍ​ሉት፤ ለብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት ይስ​ጡት፤ እር​ስ​ዋም ሚስት ትሁ​ነው፤ በዕ​ድ​ሜ​ውም ዘመን ሁሉ ሊፈ​ታት አይ​ገ​ባ​ውም።</verse>
				<verse number="20">“ነገሩ ግን እው​ነት ቢሆን፥ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም ድን​ግ​ል​ናዋ ባይ​ገኝ፥</verse>
				<verse number="21">ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱን ወደ አባቷ ቤት ደጅ ያው​ጡ​አት፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ስን​ፍ​ናን አድ​ር​ጋ​ለ​ችና፥ የአ​ባ​ቷ​ንም ቤት አስ​ነ​ው​ራ​ለ​ችና የከ​ተ​ማው ሰዎች በድ​ን​ጋይ ወግ​ረው ይግ​ደ​ሉ​አት፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ልህ ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ።</verse>
				<verse number="22">“ማና​ቸ​ውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ፥ አመ​ን​ዝ​ራ​ውና አመ​ን​ዝ​ራ​ዪቱ ሁለ​ታ​ቸው ይገ​ደሉ፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከእ​ስ​ራ​ኤል ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ።</verse>
				<verse number="23">“ለወ​ንድ የታ​ጨች ድን​ግል ልጅ ብት​ኖር፥ ሌላ ሰውም በከ​ተማ ውስጥ አግ​ኝቶ ከእ​ር​ስዋ ጋር ቢተኛ፥ ሁለ​ቱን ወደ​ዚ​ያች ከተማ በር አው​ጡ​አ​ቸው፤</verse>
				<verse number="24">ብላ​ቴ​ና​ዪቱ በከ​ተማ ውስጥ ሳለች አል​ጮ​ኸ​ች​ምና፥ ሰው​የ​ውም የባ​ል​ጀ​ራ​ውን ሚስት አስ​ነ​ው​ሮ​አ​ልና በድ​ን​ጋይ ወግ​ረው ይግ​ደ​ሉ​አ​ቸው፤ እን​ዲሁ ክፉ​ውን ነገር ከው​ስ​ጥህ ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ።</verse>
				<verse number="25">“ነገር ግን ሰው የታ​ጨ​ች​ውን ልጃ​ገ​ረድ በሜዳ ቢያ​ገ​ኛት፥ በግድ አሸ​ን​ፎም ቢደ​ር​ስ​ባት፥ ያ የደ​ረ​ሰ​ባት ሰው ብቻ​ውን ይገ​ደል።</verse>
				<verse number="26">በብ​ላ​ቴ​ና​ዪቱ ላይ ግን ምንም አታ​ድ​ርጉ፤ በብ​ላ​ቴ​ና​ዪቱ ላይ ለሞት የሚ​ያ​በቃ ኀጢ​አት የለ​ባ​ትም፤ ሰው በባ​ል​ን​ጀ​ራው ላይ ተነ​ሥቶ እን​ደ​ሚ​ገ​ድ​ለው ይህ ነገር ደግሞ እን​ደ​ዚሁ ነውና፤</verse>
				<verse number="27">በሜዳ ባገ​ኛት ጊዜ የታ​ጨ​ችው ልጃ​ገ​ረድ ጮኻ​ለ​ችና፥ የሚ​ታ​ደ​ጋ​ትም አል​ነ​በ​ረ​ምና።</verse>
				<verse number="28">ማና​ቸ​ውም ሰው ድን​ግ​ልና ያላ​ትን ያል​ታ​ጨች ልጃ​ገ​ረድ ቢያ​ገኝ፥ በግድ አሸ​ንፎ ቢደ​ፍ​ራት፥ ቢያ​ገ​ኙ​ትም፥</verse>
				<verse number="29">ያ የደ​ፈ​ራት ሰው አምሳ የብር ሰቅል ለብ​ላ​ቴ​ና​ዪቱ አባት ይስጥ፤ አስ​ነ​ው​ሮ​አ​ታ​ልና ሚስት ትሁ​ነው፤ በዕ​ድ​ሜ​ውም ዘመን ሁሉ ሊፈ​ታት አይ​ገ​ባ​ውም።</verse>
				<verse number="30">“ማና​ቸ​ውም ሰው የእ​ን​ጀራ እና​ቱን አይ​ው​ሰድ፤ የአ​ባ​ቱ​ንም ኀፍ​ረት አይ​ግ​ለጥ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="23">
				<verse number="1">“ፍሬ ዘሩ የተ​ቀ​ጠ​ቀጠ፥ አባለ ዘሩም የተ​ቈ​ረጠ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ።</verse>
				<verse number="2">ዲቃላ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ፤</verse>
				<verse number="3">“አሞ​ናዊ ወይም ሞዓ​ባዊ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ፤ እስከ ዐሥር ትው​ልድ ድረስ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ።</verse>
				<verse number="4">ከግ​ብፅ በወ​ጣ​ችሁ ጊዜ እን​ጀ​ራና ውኃ ይዘው በመ​ን​ገድ ላይ አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​አ​ች​ሁ​ምና፥ ከመ​ስ​ጴ​ጦ​ምያ የቢ​ዖ​ርን ልጅ በለ​ዓ​ምን ዋጋ ሰጥ​ተው ይረ​ግ​ማ​ችሁ ዘንድ ተዋ​ው​ለ​ው​ባ​ች​ኋ​ልና።</verse>
				<verse number="5">ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በለ​ዓ​ምን ይሰማ ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወድ​ዶ​ሃ​ልና ርግ​ማ​ኑን ወደ በረ​ከት ለወ​ጠ​ልህ።</verse>
				<verse number="6">በዘ​መ​ንህ ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሰላም እን​ደ​ሚ​ገ​ባ​ቸው አታ​ና​ግ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">“ኤዶ​ማ​ዊዉ ወን​ድ​ምህ ነውና አት​ጸ​የ​ፈው፤ ግብ​ፃ​ዊ​ዉ​ንም በሀ​ገሩ ስደ​ተኛ ነበ​ር​ህና አት​ጸ​የ​ፈው።</verse>
				<verse number="8">ከእ​ነ​ር​ሱም በሦ​ስ​ተ​ኛው ትው​ልድ የሚ​ወ​ለዱ ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ይግቡ።</verse>
				<verse number="9">“ጠላ​ቶ​ች​ህን ልት​ወጋ በወ​ጣህ ጊዜ ከክፉ ነገር ሁሉ ሰው​ነ​ት​ህን ጠብቅ።</verse>
				<verse number="10">በእ​ና​ንተ ውስጥ ሌሊት በሚ​ሆ​ነው ርኵ​ሰት የረ​ከሰ ሰው ቢኖር፥ ከሰ​ፈር ወደ ውጭ ይውጣ፤ ወደ ሰፈ​ርም አይ​ግባ።</verse>
				<verse number="11">በመ​ሸም ጊዜ ሰው​ነ​ቱን በውኃ ይታ​ጠብ፤ ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ ወደ ሰፈር ይመ​ለስ።</verse>
				<verse number="12">ወደ ሜዳም ትወ​ጣ​ባት ዘንድ ከሰ​ፈር ውጭ ቦታ ይኑ​ርህ።</verse>
				<verse number="13">ከመ​ሣ​ር​ያ​ህም ጋር መቈ​ፈ​ሪያ ያዝ፤ ሜዳም በተ​ቀ​መ​ጥህ ጊዜ ትም​ስ​በ​ታ​ለህ፤ ዞረ​ህም ከአ​ንተ የወ​ጣ​ውን በአ​ፈር ትከ​ድ​ነ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="14">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ድ​ንህ፥ ጠላ​ቶ​ች​ህ​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ሊሰ​ጥህ በሰ​ፈ​ርህ ውስጥ ይሄ​ዳ​ልና ስለ​ዚህ ነው​ረኛ ነገር እን​ዳ​ያ​ይ​ብህ፥ ፊቱ​ንም ከአ​ንተ እን​ዳ​ይ​መ​ልስ ሰፈ​ርህ የተ​ቀ​ደሰ ይሁን።</verse>
				<verse number="15">“ከጌ​ታዉ ኰብ​ልሎ ወደ አንተ የተ​ጠ​ጋ​ውን ባሪያ ለጌ​ታው አሳ​ል​ፈህ አት​ስጥ።</verse>
				<verse number="16">ከአ​ንተ ጋር ይኑር፤ በመ​ካ​ከ​ል​ህም በሚ​ወ​ድ​ዳት በአ​ን​ዲቱ ስፍራ ይቀ​መጥ፤ አን​ተም አታ​ስ​ጨ​ን​ቀው።</verse>
				<verse number="17">“ከእ​ስ​ራ​ኤል ሴቶች ልጆች ሴት አመ​ን​ዝራ አት​ገኝ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወን​ዶች ልጆች ወንድ አመ​ን​ዝራ አይ​ገኝ።</verse>
				<verse number="18">ስለ ተሳ​ል​ኸው ስእ​ለት ሁሉ የአ​መ​ን​ዝ​ራ​ዪ​ቱን ዋጋና የው​ሻ​ውን ዋጋ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አታ​ቅ​ርብ፤ ሁለ​ቱም በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሚ​ያ​ጸ​ይፉ ናቸ​ውና።</verse>
				<verse number="19">“ለወ​ን​ድ​ምህ በወ​ለድ አታ​በ​ድር፤ የብር ወይም የእ​ህል፥ ወይም የማ​ና​ቸ​ው​ንም ነገር ሁሉ ወለድ አት​ው​ሰድ።</verse>
				<verse number="20">ለእ​ን​ግ​ዳው በወ​ለድ አበ​ድር፤ ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልት​ወ​ር​ሳት በም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር በሥ​ራህ ሁሉ ይባ​ር​ክህ ዘንድ ለወ​ን​ድ​ምህ በወ​ለድ አታ​በ​ድር።</verse>
				<verse number="21">“ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለት በተ​ሳ​ልህ ጊዜ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ፈጽሞ ይሻ​ዋ​ልና፥ ኀጢ​አ​ትም ይሆ​ን​ብ​ሃ​ልና መክ​ፈ​ሉን አታ​ዘ​ግይ።</verse>
				<verse number="22">ባት​ሳል ግን ኀጢ​አት የለ​ብ​ህም።</verse>
				<verse number="23">በአ​ፍህ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃ​ድህ ተስ​ለ​ሃ​ልና ከከ​ን​ፈ​ርህ የወ​ጣ​ውን ታደ​ርግ ዘንድ ጠብቅ።</verse>
				<verse number="24">“ወደ ባል​ን​ጀ​ራህ እርሻ በገ​ባህ ጊዜ እሸ​ቱን በእ​ጅህ ቀጥ​ፈህ ብላ፤ ወዳ​ል​ታ​ጨ​ደው ወደ ባል​ን​ጀ​ራህ እህል ግን ማጭድ አታ​ግባ።</verse>
				<verse number="25">ወደ ባል​ን​ጀ​ራህ የወ​ይን ቦታ በገ​ባህ ጊዜ እስ​ክ​ት​ጠ​ግብ ድረስ ከወ​ይኑ ብላ፤ ወደ ዕቃህ ግን ከእ​ርሱ ምንም አታ​ግባ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="24">
				<verse number="1">“አንድ ሰው ሴትን ወስዶ ቢያ​ገባ፥ የእ​ፍ​ረት ነገር ስላ​ገ​ኘ​ባት በእ​ርሱ ዘንድ ሞገስ ባታ​ገኝ፥ የፍ​ች​ዋን ጽሕ​ፈት ጽፎ በእ​ጅዋ ይስ​ጣት፤ ከቤ​ቱም ይስ​ደ​ዳት።</verse>
				<verse number="2">ከቤ​ቱም ከወ​ጣች በኋላ ሌላ ወንድ ብታ​ገባ፥</verse>
				<verse number="3">ሁለ​ተ​ኛ​ውም ባል ቢጠ​ላት፥ የፍ​ች​ዋ​ንም ጽሕ​ፈት ጽፎ በእ​ጅዋ ቢሰ​ጣት ፥ ከቤ​ቱም ቢሰ​ድ​ዳት፥ ወይም ሚስት አድ​ርጎ ያገ​ባት ሁለ​ተ​ኛው ባልዋ ቢሞት፥</verse>
				<verse number="4">የሰ​ደ​ዳት የቀ​ድሞ ባልዋ ከረ​ከ​ሰች በኋላ ደግሞ ያገ​ባት ዘንድ አይ​ገ​ባ​ውም፤ ያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ጠላ ነውና፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ የሰ​ጠ​ህን ምድር አታ​ር​ክስ።</verse>
				<verse number="5">“አዲስ ሚስ​ትም ያገባ ሰው ወደ ጦር​ነት አይ​ሂድ፤ ምንም ነገር አይ​ጫ​ኑ​በት፤ ነገር ግን አንድ ዓመት በቤቱ በፈ​ቃዱ ይቀ​መጥ፤ የወ​ሰ​ዳ​ት​ንም ሚስ​ቱን ደስ ያሰ​ኛት።</verse>
				<verse number="6">“የሰ​ውን ነፍስ እንደ መው​ሰድ ነውና ወፍጮ ወይም መጅ ስለ መያዣ ማንም አይ​ው​ሰድ።</verse>
				<verse number="7">“ማንም ሰው ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከወ​ን​ድ​ሞቹ ሰውን አፍኖ ሲሰ​ር​ቅና ሲሸጥ ቢገኝ ያን የሰ​ረ​ቀ​ውን ሰው ይግ​ደ​ሉት፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አርቁ።</verse>
				<verse number="8">“ስለ ለምጽ ደዌ ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት ያስ​ተ​ማ​ሩ​ህን ሁሉ ፈጽ​መህ እን​ድ​ት​ጠ​ብቅ እን​ድ​ታ​ደ​ር​ግም ተጠ​ን​ቀቅ፤ እኔ ያዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ውን እን​ዲሁ ታደ​ርግ ዘንድ ጠብቅ።</verse>
				<verse number="9">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ ባወ​ጣ​ችሁ ጊዜ በመ​ን​ገድ ሳላ​ችሁ በማ​ር​ያም ላይ ያደ​ረ​ገ​ውን ዐስብ።</verse>
				<verse number="10">“ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ ባበ​ደ​ር​ኸው ጊዜ መያ​ዣ​ውን ልት​ወ​ስድ ወደ ቤቱ አት​ግባ።</verse>
				<verse number="11">አንተ ግን በውጭ ቁም፤ ያበ​ደ​ር​ኸ​ውም ሰው መያ​ዣ​ውን ወደ ውጭ ያው​ጣ​ልህ።</verse>
				<verse number="12">ያም ሰው ድሃ ቢሆን መያ​ዣ​ውን በአ​ንተ ዘንድ አታ​ሳ​ድር።</verse>
				<verse number="13">ለብ​ሶት እን​ዲ​ተኛ እን​ዲ​ባ​ር​ክ​ህም ፀሐይ ሳይ​ገባ መያ​ዣ​ውን ፈጽ​መህ መል​ስ​ለት፤ በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ምጽ​ዋት ይሆ​ን​ል​ሃል።</verse>
				<verse number="14">“ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ ወይም በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ከአ​ሉት መጻ​ተ​ኞች ድሃና ችግ​ረኛ የሆ​ነ​ውን ምን​ደኛ ደመ​ወ​ዙን አት​ከ​ል​ክ​ለው፤</verse>
				<verse number="15">ድሃ ነውና፥ ተስ​ፋ​ውም እርሱ ነውና ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ይ​ጮ​ኽ​ብህ፥ ኀጢ​አ​ትም እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ብህ ደመ​ወ​ዙን ፀሐይ ሳይ​ገባ በቀኑ ስጠው።</verse>
				<verse number="16">“አባ​ቶች ስለ ልጆ​ቻ​ቸው አይ​ገ​ደሉ፤ ልጆ​ችም ስለ አባ​ቶ​ቻ​ቸው አይ​ገ​ደሉ፤ ነገር ግን ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ በኀ​ጢ​አቱ ይገ​ደል።</verse>
				<verse number="17">“የመ​ጻ​ተ​ኛ​ው​ንና የድሃ-አደ​ጉን፥ የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም ፍርድ አታ​ጣ​ም​ም​ባ​ቸው፤ የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም ልብስ ለመ​ያዣ አት​ው​ሰ​ድ​ባት።</verse>
				<verse number="18">አን​ተም በግ​ብፅ ባሪያ እንደ ነበ​ርህ፥ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚያ እን​ዳ​ዳ​ነህ ዐስብ፤ ስለ​ዚህ ይህን ነገር ታደ​ርግ ዘንድ አዝ​ዤ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">“የእ​ር​ሻ​ህን መከር ባጨ​ድህ ጊዜ ነዶም ረስ​ተህ በእ​ር​ሻህ ብታ​ስ​ቀር፥ ትወ​ስ​ደው ዘንድ አት​መ​ለስ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጅህ ሥራ ሁሉ እን​ዲ​ባ​ር​ክህ፥ ለመ​ጻ​ተ​ኛና ለድሃ-አደግ፥ ለመ​በ​ለ​ትም ተወው።</verse>
				<verse number="20">የወ​ይ​ራ​ህን ፍሬ በለ​ቀ​ምህ ጊዜ ከቅ​ር​ን​ጫ​ፎቹ ላይ አጥ​ር​ተህ ለመ​ል​ቀም ዳግ​መኛ አት​መ​ለስ፤ ለመ​ጻ​ተ​ኛና ለድሃ-አደግ፥ ለመ​በ​ለ​ትም ይሁን።</verse>
				<verse number="21">የወ​ይ​ን​ህን ፍሬ በቈ​ረ​ጥህ ጊዜ ቃር​ሚ​ያ​ውን አት​ል​ቀ​መው፤ ለመ​ጻ​ተ​ኛና ለድሃ-አደግ፥ ለመ​በ​ለ​ትም ይሁን።</verse>
				<verse number="22">አን​ተም በግ​ብፅ ሀገር መጻ​ተኛ እንደ ነበ​ርህ ዐስብ፤ ስለ​ዚህ ይህን ነገር ታደ​ርግ ዘንድ አዝ​ዤ​ሃ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="25">
				<verse number="1">“በሰ​ዎች መካ​ከል ጠብ ቢሆን፥ ወደ ፍር​ድም ቢመጡ፥ ቢፋ​ረ​ዱም ለጻ​ድቁ ይፈ​ረ​ድ​ለት፤ በበ​ደ​ለ​ኛ​ውም ይፈ​ረ​ድ​በት።</verse>
				<verse number="2">በደ​ለ​ኛ​ውም መገ​ረፍ ቢገ​ባው እን​ዲ​ገ​ረፍ ፈራጁ በፊቱ በም​ድር ላይ ያጋ​ድ​መው፤ የግ​ር​ፋ​ቱም ቍጥር እንደ ኀጢ​አቱ መጠን ይሁን።</verse>
				<verse number="3">ግር​ፋ​ቱም አርባ ይሁን፤ ከዚህ በላይ ጨምሮ ብዙ ግር​ፋት ቢገ​ር​ፈው ወን​ድ​ምህ በፊ​ትህ ነው​ረኛ ይሆ​ና​ልና ከዚህ በላይ አይ​ጨ​መ​ር​በት።</verse>
				<verse number="4">“እህ​ል​ህን በም​ታ​በ​ራይ ጊዜ በሬ​ዉን አፉን አት​ሰ​ረው።</verse>
				<verse number="5">“ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች በአ​ን​ድ​ነት ቢቀ​መጡ፥ አን​ዱም ልጅ ሳይ​ኖ​ረው ቢሞት፥ የሞ​ተው ሰው ሚስት ሌላ ሰው ታገባ ዘንድ ወደ ውጭ አት​ሂድ፤ ነገር ግን የባ​ልዋ ወን​ድም ወደ እር​ስዋ ገብቶ እር​ስ​ዋን ያግባ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ይኑር።</verse>
				<verse number="6">የም​ዋቹ ስም ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ እን​ዳ​ይ​ጠፋ ከእ​ር​ስዋ የሚ​ወ​ለ​ደው ልጅ በሞ​ተው በወ​ን​ድሙ ስም ይጠራ።</verse>
				<verse number="7">ያም ሰው የወ​ን​ድ​ሙን ሚስት ማግ​ባት ባይ​ወ​ድድ፥ ዋር​ሳ​ዪቱ በበሩ አደ​ባ​ባይ ወደ​ሚ​ቀ​መጡ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሄዳ፦ ‘ዋር​ሳዬ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ለወ​ን​ድሙ ስም ማቆም እንቢ አለ፤ ከእ​ኔም ጋር ሊኖር አል​ወ​ደ​ደም’ ትበ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">የከ​ተ​ማ​ውም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጠር​ተው ይጠ​ይ​ቁት፤ እር​ሱም በዚያ ቆሞ፦ ‘አገ​ባት ዘንድ አል​ወ​ድ​ድም’ ቢል፥</verse>
				<verse number="9">ዋር​ሳ​ዪቱ በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎቹ ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፦ ‘የወ​ን​ድ​ሙን ቤት በማ​ይ​ሠራ ሰው ላይ እን​ዲህ ይደ​ረ​ግ​በ​ታል’ ስትል የአ​ንድ እግ​ሩን ጫማ ታውጣ፤ በፊ​ቱም እን​ትፍ ትበ​ል​በት።</verse>
				<verse number="10">በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ስሙ ‘የጫማ ፈቱ ቤት’ ተብሎ ይጠራ።</verse>
				<verse number="11">“ሁለት ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው ቢጣሉ፥ የአ​ን​ደ​ኛ​ውም ሰው ሚስት ባል​ዋን ከሚ​መ​ታው ሰው እጅ ታድ​ነው ዘንድ ብት​ቀ​ርብ፥ እጅ​ዋ​ንም ዘር​ግታ ሁለ​ቱን የብ​ል​ቱን ፍሬ​ዎች ብት​ይዝ፥</verse>
				<verse number="12">እጅ​ዋን ቍረጥ፤ ዐይ​ን​ህም አት​ራ​ራ​ላት።</verse>
				<verse number="13">“በከ​ረ​ጢ​ትህ ውስጥ ታላ​ቅና ታናሽ ሚዛን አይ​ኑ​ር​ልህ።</verse>
				<verse number="14">በቤ​ትህ ውስጥ ታላ​ቅና ታናሽ መስ​ፈ​ሪያ አይ​ኑ​ር​ልህ።</verse>
				<verse number="15">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር ላይ ዕድ​ሜህ ይረ​ዝም ዘንድ እው​ነ​ተ​ኛና ፍጹም ሚዛን ይሁ​ን​ልህ፤ እው​ነ​ተ​ኛና ፍጹም መስ​ፈ​ሪ​ያም ይሁ​ን​ልህ።</verse>
				<verse number="16">ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ፥ ክፋ​ት​ንም የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ጠላ ነውና።</verse>
				<verse number="17">“ከግ​ብፅ በወ​ጣህ ጊዜ ዐማ​ሌቅ በመ​ን​ገድ ላይ ያደ​ረ​ገ​ብ​ህን ዐስብ፤</verse>
				<verse number="18">በመ​ን​ገድ ላይ እንደ ተቃ​ወ​መህ፥ አን​ተም ተር​በ​ህና ደክ​መህ ሳለህ ጓዝ​ህ​ንና ከአ​ንተ በኋላ ደክ​መው የነ​በ​ሩ​ትን ሁሉ እንደ መታ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ፈ​ራ​ውም።</verse>
				<verse number="19">ስለ​ዚህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር ከሚ​ከ​ብ​ቡህ ጠላ​ቶ​ችህ ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሳ​ረ​ፈህ ጊዜ፥ የዐ​ማ​ሌ​ቅን ዝክረ ስሙን ከሰ​ማይ በታች አጥ​ፋው፤ ይህ​ንም አት​ርሳ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="26">
				<verse number="1">“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ምድር በገ​ባህ ጊዜ፥ በወ​ረ​ስ​ሃ​ትም፥ በኖ​ር​ህ​ባ​ትም ጊዜ፥</verse>
				<verse number="2">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ሰ​ጥህ ምድር ከም​ት​ሰ​በ​ስ​በው ፍሬ ሁሉ ቀዳ​ም​ያት ውሰድ፤ በዕ​ን​ቅ​ብም አድ​ር​ገው፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ ወደ መረ​ጠው ስፍራ ይዘህ ሂድ።</verse>
				<verse number="3">በዚ​ያም ወራት ወደ​ሚ​ሆ​ነው ካህን መጥ​ተህ፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ጠን ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር እንደ ገባሁ ዛሬ በአ​ም​ላኬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አስ​ታ​ው​ቃ​ለሁ’ በለው።</verse>
				<verse number="4">ካህ​ኑም ዕን​ቅ​ቡን ከእ​ጅህ ወስዶ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ፊት ያኑ​ረው፤</verse>
				<verse number="5">በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዲህ ብለህ ተና​ገር፦ አባቴ ከሶ​ርያ ወጥቶ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚ​ያም በቍ​ጥር ጥቂት ሆኖ ኖረ፤ በዚ​ያም ታላ​ቅና የበ​ረታ፥ ብዙም ሕዝብ ሆነ።</verse>
				<verse number="6">ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ክፉ ነገር አደ​ረ​ጉ​ብን፤ አስ​ጨ​ነ​ቁ​ንም፤ በላ​ያ​ች​ንም ከባድ ሥራን ጫኑ​ብን፤</verse>
				<verse number="7">ወደ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም አም​ላክ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኽን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃላ​ች​ንን ሰማ፤ ጭን​ቀ​ታ​ች​ን​ንም፥ ድካ​ማ​ች​ን​ንም፥ ግፋ​ች​ን​ንም አየ፤</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጸ​ናች እጅና በተ​ዘ​ረጋ ክንድ፥ በታ​ላ​ቅም ግርማ፥ በታ​ላቅ ተአ​ም​ራ​ትም፥ በድ​ን​ቅም ከግ​ብፅ አወ​ጣን፤</verse>
				<verse number="9">ወደ​ዚ​ህም ስፍራ አገ​ባን፤ ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ው​ንም ይህ​ችን ምድር ሰጠን።</verse>
				<verse number="10">አሁ​ንም እነሆ፥ አቤቱ፥ አንተ የሰ​ጠ​ኸ​ኝን ማርና ወተት የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን የም​ድ​ሪ​ቱን ፍሬ ቀዳ​ም​ያት አቅ​ር​ቤ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">አን​ተም በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አኑ​ረው፥ በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስገድ። አን​ተም፥ በመ​ካ​ከ​ል​ህም ያለ ሌዋ​ዊና መጻ​ተኛ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ን​ተና ለቤ​ትህ በሰ​ጠው ቸር​ነት ሁሉ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="12">“ዐሥ​ራት በም​ታ​ወ​ጣ​በት በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት የም​ድ​ር​ህን ፍሬ ሁሉ ዐሥ​ራት አው​ጥ​ተህ በፈ​ጸ​ምህ ጊዜ፥ ሁለ​ተኛ ዐሥ​ራት አው​ጥ​ተህ በከ​ተ​ሞ​ችህ ውስጥ ይበሉ ዘንድ፥ ይጠ​ግ​ቡም ዘንድ ለሌ​ዋ​ዊው፥ ለመ​ጻ​ተ​ኛ​ውም፥ ለድሃ-አደ​ጉም፥ ለመ​በ​ለ​ቲ​ቱም ስጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዲህ በል፦ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ነገር ከቤቴ ለይች ለሌ​ዋ​ዊው፥ ለመ​ጻ​ተ​ኛ​ውም፥ ለድሀ-አደ​ጉም፥ ለመ​በ​ለ​ቲ​ቱም እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኸኝ ትእ​ዛዝ ሁሉ ሰጥ​ቼ​አ​ለሁ፤ ትእ​ዛ​ዝ​ህን ምንም አላ​ፈ​ረ​ስ​ሁም፤ አል​ረ​ሳ​ሁ​ምም፤</verse>
				<verse number="14">በኀ​ዘ​ኔም ጊዜ እኔ ከእ​ርሱ አል​በ​ላ​ሁም፤ ለር​ኩ​ስም ነገር ከእ​ርሱ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት አል​ሠ​ዋ​ሁም፤ ከእ​ር​ሱም አን​ዳች ለሞተ ሰው አል​ሰ​ጠ​ሁም፤ የአ​ም​ላ​ኬ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰም​ቼ​አ​ለሁ፤ ያዘ​ዝ​ኸ​ኝ​ንም ሁሉ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">ከቅ​ዱስ ማደ​ር​ያህ ከሰ​ማይ ጐብኝ፤ ሕዝ​ብ​ህ​ንም እስ​ራ​ኤ​ልን፥ ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ትሰ​ጠን ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን እንደ ማል​ህ​ላ​ቸው የሰ​ጠ​ሃ​ቸ​ው​ንም ምድር ባርክ።</verse>
				<verse number="16">“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ታደ​ርግ ዘንድ ዛሬ አዝ​ዞ​ሃል፤ አን​ተም በፍ​ጹም ልብ​ህና በፍ​ጹም ነፍ​ስህ ጠብ​ቀው፤ አድ​ር​ገ​ውም።</verse>
				<verse number="17">አን​ተም በመ​ን​ገዱ ትሄድ ዘንድ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዙን፥ ፍር​ዱ​ንም ትጠ​ብቅ ዘንድ፥ ቃሉ​ንም ትሰማ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላ​ክህ እን​ዲ​ሆን ዛሬ መር​ጠ​ሃል።</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ ርስ​ቱና ሕዝቡ ትሆን ዘንድ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ሁሉ ትጠ​ብቅ ዘንድ፥ ዛሬ መር​ጦ​ሃ​ልና፤</verse>
				<verse number="19">ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ በላይ ትሆን ዘንድ፥ እር​ሱም እንደ ተና​ገረ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ሕዝብ ትሆን ዘንድ ታላቅ ስምን፥ ምስ​ጋ​ናና ክብ​ር​ንም አደ​ረ​ገ​ልህ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="27">
				<verse number="1">ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “ዛሬ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁን ትእ​ዛዝ ታደ​ርጉ ዘንድ ዕወቁ፤</verse>
				<verse number="2">አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ዮር​ዳ​ኖ​ስን በተ​ሻ​ገ​ራ​ችሁ ጊዜ ታላ​ላቅ ድን​ጋ​ዮ​ችን ለእ​ና​ንተ አቁሙ፤ በኖ​ራም ምረ​ጓ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ራ​ችሁ፥ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስስ ምድር፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ትገቡ ዘንድ በተ​ሻ​ገ​ራ​ችሁ ጊዜ፥ የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ሁሉ በድ​ን​ጋ​ዮች ላይ ጻፉ።</verse>
				<verse number="4">ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም በተ​ሻ​ገ​ራ​ችሁ ጊዜ፥ ዛሬ እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኋ​ችሁ፥ እነ​ዚ​ህን ድን​ጋ​ዮች በጌ​ባል ተራራ አቁሙ፤ በኖ​ራም ምረ​ጓ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">በዚ​ያም ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሥራ፤ መሠ​ዊ​ያ​ውም ብረት ካል​ነ​ካው ድን​ጋይ ይሁን።</verse>
				<verse number="6">ካል​ተ​ጠ​ረ​በም ድን​ጋይ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሥራ፤ ለአ​ም​ላ​ክ​ህም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን አቅ​ር​ብ​በት፤</verse>
				<verse number="7">ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሠዋ​በት፤ በዚ​ያም ብላ፤ ጥገ​ብም፤ በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደስ ይበ​ልህ።</verse>
				<verse number="8">የዚ​ህ​ንም ሕግ ቃሎች ሁሉ የተ​ገ​ለጠ አድ​ር​ገህ በድ​ን​ጋ​ዮቹ ላይ ጻፍ።”</verse>
				<verse number="9">ሙሴና ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ እን​ዲህ ብለው ተና​ገሩ፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ዝም ብለህ አድ​ምጥ፤ ዛሬ የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ሆነ​ሃል።</verse>
				<verse number="10">የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ ዛሬም የማ​ዝ​ዝ​ህን ትእ​ዛ​ዙ​ንና ሥር​ዐ​ቱን አድ​ርግ።”</verse>
				<verse number="11">ሙሴም በዚያ ቀን እን​ዲህ ብሎ ሕዝ​ቡን አዘዘ፦</verse>
				<verse number="12">“ዮር​ዳ​ኖ​ስን በተ​ሻ​ገ​ራ​ችሁ ጊዜ ሕዝ​ቡን ይባ​ርኩ ዘንድ በገ​ሪ​ዛን ተራራ ላይ የሚ​ቆሙ እነ​ዚህ ናቸው፤ ስም​ዖ​ንና ሌዊ፥ ይሁ​ዳና ይሳ​ኮር፥ ዮሴ​ፍና ብን​ያም።</verse>
				<verse number="13">ይረ​ግ​ሙም ዘንድ በጌ​ባል ተራራ ላይ የሚ​ቆሙ እነ​ዚህ ናቸው፤ ሮቤ​ልና ጋድ፥ አሴ​ርና ዛብ​ሎን፥ ዳንና ንፍ​ታ​ሌም።</verse>
				<verse number="14">ሌዋ​ው​ያ​ንም ከፍ ባለች ድምፅ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ እን​ዲህ ብለው ይና​ገሩ።</verse>
				<verse number="15">“በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ጠላ የሠ​ራ​ተኛ እጅ ሥራን፥ የተ​ቀ​ረፀ ወይም ቀልጦ የተ​ሠራ ምስ​ልን የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በስ​ው​ርም የሚ​ያ​ቆ​መው ሰው ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ መል​ሰው አሜን ይላሉ።</verse>
				<verse number="16">“አባ​ቱን ወይም እና​ቱን የሚ​ያ​ቃ​ልል ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።</verse>
				<verse number="17">“የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ውን የድ​ን​በር ምል​ክት የሚ​ገፋ ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።</verse>
				<verse number="18">“ዕው​ሩን ከመ​ን​ገድ ፈቀቅ የሚ​ያ​ደ​ርግ ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።</verse>
				<verse number="19">“በመ​ጻ​ተኛ፥ በድሃ-አደ​ጉም፥ በመ​በ​ለ​ቲ​ቱም ላይ ፍር​ድን የሚ​ያ​ጣ​ምም ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።</verse>
				<verse number="20">“ከእ​ን​ጀራ እናቱ ጋር የሚ​ተኛ የአ​ባ​ቱን ኀፍ​ረት ገል​ጦ​አ​ልና ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።</verse>
				<verse number="21">“ከእ​ን​ስሳ ሁሉ የሚ​ደ​ርስ ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።</verse>
				<verse number="22">“ከአ​ባቱ ወይም ከእ​ናቱ ልጅ ከእ​ኅቱ ጋር የሚ​ተኛ ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።</verse>
				<verse number="23">“ከአ​ማቱ ጋር የሚ​ተኛ ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ። ከዋ​ር​ሳው ጋር የሚ​ተኛ ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይሁን ይላሉ።</verse>
				<verse number="24">“ባል​ን​ጀ​ራ​ውን በተ​ን​ኰል የሚ​መታ ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።</verse>
				<verse number="25">“የን​ጹ​ሑን ሰው ነፍስ ለመ​ግ​ደል ጉቦ የሚ​ቀ​በል ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።</verse>
				<verse number="26">“የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ያደ​ርግ ዘንድ የማ​ያ​ጸና ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="28">
				<verse number="1">“እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ፈጽ​መህ ብት​ሰማ፥ ዛሬም ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ትእ​ዛ​ዙን ሁሉ ብታ​ደ​ርግ፥ ብት​ጠ​ብ​ቅም፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ግ​ሃል።</verse>
				<verse number="2">የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ብት​ሰማ እነ​ዚህ በረ​ከ​ቶች ሁሉ ይመ​ጡ​ል​ሃል፤ ያገ​ኙ​ህ​ማል።</verse>
				<verse number="3">አንተ በከ​ተማ ቡሩክ ትሆ​ና​ለህ፤ በእ​ር​ሻም ቡሩክ ትሆ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="4">የሆ​ድህ ፍሬ፥ የም​ድ​ር​ህም ፍሬ፥ የከ​ብ​ት​ህም ፍሬ፥ የላ​ም​ህም መንጋ፥ የበ​ግ​ህም መንጋ ቡሩክ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="5">መዛ​ግ​ብ​ት​ህና የቀ​ረ​ውም ሁሉ ቡሩክ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="6">አን​ተም በመ​ግ​ባ​ትህ ቡሩክ ትሆ​ና​ለህ፥ በመ​ው​ጣ​ት​ህም ቡሩክ ትሆ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="7">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ግ​ርህ በታች ይወ​ድቁ ዘንድ የሚ​ቃ​ወ​ሙ​ህን ጠላ​ቶ​ች​ህን በእ​ጅህ ይጥ​ላ​ቸ​ዋል፤ በአ​ንድ መን​ገድ ይመ​ጡ​ብ​ሃል፤ በሰ​ባ​ትም መን​ገድ ከፊ​ትህ ይሸ​ሻሉ።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በረ​ከ​ቱን በአ​ንተ ላይ፥ በጎ​ተ​ራህ፥ በእ​ህ​ል​ህም ሥራ ሁሉ እን​ዲ​ወ​ርድ ይል​ካል፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ሰ​ጥ​ህም ምድር ይባ​ር​ክ​ሃል።</verse>
				<verse number="9">የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ብት​ሰማ፥ በመ​ን​ገ​ዱም ብት​ሄድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ችህ እንደ ማለ ለእ​ርሱ የተ​ቀ​ደሰ ሕዝብ አድ​ርጎ ያቆ​ም​ሃል።</verse>
				<verse number="10">የም​ድር አሕ​ዛ​ብም ሁሉ የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም በአ​ንተ ላይ እንደ ተጠራ አይ​ተው ይፈ​ሩ​ሃል።</verse>
				<verse number="11">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እር​ስ​ዋን ይሰ​ጥህ ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ችህ በማ​ለ​ላ​ቸው በም​ድ​ርህ ላይ፥ በሆ​ድህ ፍሬ፥ በእ​ር​ሻ​ህም ፍሬ፥ ከብ​ቶ​ች​ህን በማ​ብ​ዛት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ​ነ​ቱን ያበ​ዛ​ል​ሃል።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለም​ድ​ርህ በወ​ራቱ ዝና​ብን ይሰጥ ዘንድ፥ የእ​ጅ​ህ​ንም ሥራ ሁሉ ይባ​ርክ ዘንድ መል​ካ​ሙን መዝ​ገብ ሰማ​ዩን ይከ​ፍ​ት​ል​ሃል፤ ለብዙ አሕ​ዛ​ብም ታበ​ድ​ራ​ለህ፥ አንተ ግን ከማ​ንም አት​በ​ደ​ርም፤ ብዙ አሕ​ዛ​ብን ትገ​ዛ​ለህ፥ አን​ተን ግን እነ​ርሱ አይ​ገ​ዙ​ህም።</verse>
				<verse number="13">ዛሬም ያዘ​ዝ​ሁ​ህን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ሰም​ተህ ብት​ጠ​ብ​ቃት፥ ብታ​ደ​ር​ጋ​ትም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራስ ያደ​ር​ግ​ሃል እንጂ ጅራት አያ​ደ​ር​ግ​ህም፤ ሁል​ጊ​ዜም በላይ እንጂ በታች አት​ሆ​ንም።</verse>
				<verse number="14">ዛሬም ካዘ​ዝ​ሁህ ከእ​ነ​ዚህ ቃሎች ወደ ቀኝ፥ ወደ ግራም ፈቀቅ ባትል፥ ታመ​ል​ካ​ቸ​ውም ዘንድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ባት​ከ​ተል።</verse>
				<verse number="15">“ነገር ግን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ባት​ሰማ፥ ዛሬም ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዙን ሁሉ ባት​ጠ​ብቅ፥ ባታ​ደ​ር​ግም፥ እነ​ዚህ መር​ገ​ሞች ሁሉ ይመ​ጡ​ብ​ሃል፤ ያገ​ኙ​ህ​ማል።</verse>
				<verse number="16">በከ​ተማ ርጉም ትሆ​ና​ለህ፤ በእ​ር​ሻም ርጉም ትሆ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="17">መዛ​ግ​ብ​ት​ህና የቀ​ረ​ውም ርጉ​ማን ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="18">የሆ​ድህ ፍሬ፥ የም​ድ​ር​ህም ፍሬ፥ የላ​ም​ህም መንጋ፥ የበ​ግ​ህም መንጋ ርጉ​ማን ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="19">አንተ በመ​ግ​ባ​ት​ህና በመ​ው​ጣ​ት​ህም ርጉም ትሆ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="20">እኔን ስለ​ተ​ው​ኸኝ፥ ስለ ሥራህ ክፋት፥ እስ​ክ​ት​ጠፋ፥ ፈጥ​ነ​ህም እስ​ክ​ታ​ልቅ ድረስ በም​ት​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ችግ​ርን፥ ረኃ​ብን፦ ቸነ​ፈ​ር​ንም ይል​ክ​ብ​ሃል።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ ከም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋህ ድረስ ሞትን ያመ​ጣ​ብ​ሃል።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በክ​ሳት፥ በን​ዳ​ድም፥ በጥ​ብ​ሳ​ትም፥ በት​ኵ​ሳ​ትም፥ በድ​ር​ቅም፥ በዋ​ግም፥ በአ​ረ​ማ​ሞም ይመ​ታ​ሃል፤ እስ​ክ​ት​ጠ​ፋም ድረስ ያሳ​ድ​ዱ​ሃል።</verse>
				<verse number="23">በራ​ስ​ህም ላይ ሰማይ ናስ ይሆ​ን​ብ​ሃል፤ ከእ​ግ​ር​ህም በታች ምድ​ሪቱ ብረት ትሆ​ን​ብ​ሃ​ለች።</verse>
				<verse number="24">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ር​ህን ዝናብ ጭጋግ ያደ​ር​ጋል፤ እስ​ክ​ት​ጠ​ፋም ድረስ ከሰ​ማይ አፈር ይወ​ር​ድ​ብ​ሃል።</verse>
				<verse number="25">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጠ​ላ​ቶ​ችህ ፊት የተ​መ​ታህ ያደ​ር​ግ​ሃል፤ በአ​ንድ መን​ገድ ትወ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በሰ​ባት መን​ገ​ድም ከእ​ነ​ርሱ ትሸ​ሻ​ለህ፤ በም​ድ​ርም መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ የተ​በ​ተ​ንህ ትሆ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="26">ሬሳህ ለሰ​ማይ ወፎች ሁሉ፥ ለም​ድ​ርም አራ​ዊት መብል ይሆ​ናል፤ የሚ​ቀ​ብ​ር​ህም አታ​ገ​ኝም።</verse>
				<verse number="27">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈውስ በሌ​ለው በግ​ብፅ ቍስል፥ በእ​ባ​ጭም፥ በቋ​ቁ​ቻም፥ በች​ፌም ይመ​ታ​ሃል።</verse>
				<verse number="28">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዕ​ብ​ደት፥ በዕ​ው​ር​ነት፥ በልብ ድን​ጋ​ጤም ይመ​ታ​ሃል።</verse>
				<verse number="29">ዕውር በጨ​ለማ እን​ደ​ሚ​ዳ​ብስ በቀ​ትር ጊዜ ትዳ​ብ​ሳ​ለህ፤ መን​ገ​ድ​ህም የቀና አይ​ሆ​ንም፤ በዘ​መ​ን​ህም ሁሉ የተ​ገ​ፋህ፥ የተ​ዘ​ረ​ፍ​ህም ትሆ​ና​ለህ፤ የሚ​ረ​ዳ​ህም የለም።</verse>
				<verse number="30">ሚስት ታገ​ባ​ለህ፤ ሌላም ሰው ይነ​ጥ​ቅ​ሃል፤ ቤት ትሠ​ራ​ለህ፤ በእ​ር​ሱም አት​ቀ​መ​ጥ​በ​ትም፤ ወይን ትተ​ክ​ላ​ለህ፤ ከእ​ር​ሱም አት​ለ​ቅ​ምም።</verse>
				<verse number="31">በሬህ በፊ​ትህ ይታ​ረ​ዳል፤ ከእ​ር​ሱም አት​በ​ላም። አህ​ያህ ከእ​ጅህ በግድ ይወ​ሰ​ዳል፤ ወደ አን​ተም አይ​መ​ለ​ስም፤ በጎ​ችህ ለጠ​ላ​ቶ​ችህ ይሰ​ጣሉ፤ የሚ​ረ​ዳ​ህም አታ​ገ​ኝም።</verse>
				<verse number="32">ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ችህ ለሌላ ሕዝብ ይሰ​ጣሉ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ሲመ​ቱ​አ​ቸው በዐ​ይ​ኖ​ችህ ታያ​ለህ፤ ልታ​ደ​ር​ገ​ውም የም​ት​ች​ለው የለም።</verse>
				<verse number="33">የም​ድ​ር​ህን ፍሬ፥ ድካ​ም​ህ​ንም ሁሉ የማ​ታ​ው​ቀው ሕዝብ ይበ​ላ​ዋል፤ አን​ተም ሁል​ጊዜ የተ​ጨ​ነ​ቅህ፥ የተ​ገ​ፋ​ህም ትሆ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="34">ዐይ​ኖ​ች​ህም ከሚ​ያ​ዩት የተ​ነሣ ዕብድ ትሆ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="35">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልት​ድን በማ​ት​ች​ል​በት በክፉ ቍስል ጕል​በ​ት​ህ​ንና ጭን​ህን ከእ​ግ​ርህ ጫማ እስከ አና​ትህ ድረስ ይመ​ታ​ሃል።</verse>
				<verse number="36">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​ተን፥ በአ​ን​ተም ላይ የም​ት​ሾ​ማ​ቸ​ውን አለ​ቆ​ች​ህን አን​ተና አባ​ቶ​ችህ ወዳ​ላ​ወ​ቃ​ች​ኋ​ቸው ሕዝብ ይወ​ስ​ድ​ሃል፤ በዚ​ያም ሌሎ​ችን የእ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ አማ​ል​ክ​ትን ታመ​ል​ካ​ለህ።</verse>
				<verse number="37">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ እነ​ርሱ በሚ​ወ​ስ​ድህ አሕ​ዛብ መካ​ከል ሁሉ የደ​ነ​ገ​ጥህ፥ ለም​ሳ​ሌና ለተ​ረ​ትም ትሆ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="38">ብዙ ዘርም ወደ እርሻ ታወ​ጣ​ለህ፤ አን​በ​ጣም ይበ​ላ​ዋ​ልና ጥቂት ትሰ​በ​ስ​ባ​ለህ።</verse>
				<verse number="39">ወይን ትተ​ክ​ላ​ለህ፤ ታበ​ጀ​ው​ማ​ለህ፤ ከወ​ይ​ኑም አት​ጠ​ጣም፤ ክፉ ትልም ይበ​ላ​ዋ​ልና በእ​ርሱ ደስ አይ​ል​ህም።</verse>
				<verse number="40">የወ​ይራ ዛፍ በሀ​ገ​ርህ ሁሉ ይሆ​ን​ል​ሃል፤ ፍሬ​ውም ይረ​ግ​ፋ​ልና ዘይ​ቱን አት​ቀ​ባም።</verse>
				<verse number="41">ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ችን ትወ​ል​ዳ​ለህ፤ ማር​ከው ይወ​ስ​ዷ​ቸ​ዋ​ልና አይ​ቀ​ሩ​ል​ህም።</verse>
				<verse number="42">ዛፍ​ህን ሁሉ፤ የም​ድ​ር​ህ​ንም ፍሬ ሁሉ ኩብ​ኩባ ያጠ​ፋ​ዋል።</verse>
				<verse number="43">በአ​ንተ መካ​ከል ያለ መጻ​ተኛ በአ​ንተ ላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ አንተ ግን ዝቅ ዝቅ ትላ​ለህ።</verse>
				<verse number="44">እርሱ ያበ​ድ​ር​ሃል፤ አንተ ግን አታ​በ​ድ​ረ​ውም፤ እርሱ ራስ ይሆ​ናል፤ አን​ተም ጅራት ትሆ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="45">የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስላ​ል​ሰ​ማህ፥ ያዘ​ዘ​ህ​ንም ትእ​ዛ​ዙ​ንና ሥር​ዐ​ቱን ስላ​ል​ጠ​በ​ቅህ፥ እስ​ክ​ት​ጠፋ ድረስ እነ​ዚህ መር​ገ​ሞች ሁሉ ይወ​ር​ዱ​ብ​ሃል፤ ያሳ​ድ​ዱ​ህ​ማል፤ ያገ​ኙ​ህ​ማል።</verse>
				<verse number="46">በአ​ን​ተም በልጅ ልጅ​ህም ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ለም​ል​ክ​ትና ለድ​ንቅ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="47">“ሁሉን አብ​ዝቶ ስለ ሰጠህ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በፍ​ሥ​ሓና በቀና ልብ አላ​መ​ለ​ክ​ኸ​ው​ምና፥</verse>
				<verse number="48">በራ​ብና በጥ​ማት፥ በዕ​ራ​ቁ​ት​ነ​ትም፥ ሁሉ​ንም በማ​ጣት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ል​ክ​ብህ ለጠ​ላ​ቶ​ችህ ትገ​ዛ​ለህ፤ እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋ​ህም ድረስ በአ​ን​ገ​ትህ ላይ የብ​ረት ቀን​በር ይጭ​ናል።</verse>
				<verse number="49">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ንስር እን​ደ​ሚ​በ​ርር ከሩቅ ሀገር፥ ከም​ድር ዳር ቋን​ቋ​ቸ​ውን የማ​ት​ሰ​ማ​ውን ሕዝብ፥</verse>
				<verse number="50">ፊቱ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ውን፥ የሽ​ማ​ግ​ሌ​ው​ንም ፊት የማ​ያ​ፍ​ረ​ውን፥ ሕፃ​ኑ​ንም የማ​ይ​ም​ረ​ውን ሕዝብ ያመ​ጣ​ብ​ሃል።</verse>
				<verse number="51">እስ​ክ​ት​ጠ​ፋም ድረስ የከ​ብ​ት​ህን ፍሬ፥ የም​ድ​ር​ህ​ንም ፍሬ ይበ​ላል፤ እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋ​ህም ድረስ እህ​ል​ህን፥ ወይ​ን​ህ​ንም፥ ዘይ​ት​ህ​ንም፥ የላ​ም​ህ​ንና የበ​ግ​ህ​ንም መንጋ አይ​ተ​ው​ል​ህም።</verse>
				<verse number="52">በሀ​ገ​ርህ ሁሉ ያሉ፥ ትታ​መ​ን​ባ​ቸው የነ​በሩ፥ የረ​ዘሙ፥ የጸ​ኑም ቅጥ​ሮች እስ​ኪ​ፈ​ርሱ ድረስ፥ በከ​ተ​ሞ​ችህ ሁሉ ያጠ​ፋ​ሃል፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ጠህ ምድር ሁሉ፥ በደ​ጆች ሁሉ ያስ​ጨ​ን​ቅ​ሃል።</verse>
				<verse number="53">ጠላ​ቶ​ች​ህም በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ከብ​በው ባስ​ጨ​ነ​ቁ​ህና መከራ ባሳ​ዩህ ጊዜ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጥ​ህን የሆ​ድ​ህን ፍሬ፥ የወ​ን​ዶ​ችና የሴ​ቶች ልጆ​ች​ህን ሥጋ ትበ​ላ​ለህ።</verse>
				<verse number="54">በአ​ንተ ዘንድ የተ​ደ​ላ​ደ​ለና የተ​ቀ​ማ​ጠለ ሰው በወ​ን​ድሙ፥ አብ​ራ​ውም በም​ት​ተኛ በሚ​ስቱ፥ በቀ​ሩ​ትም ልጆቹ ይቀ​ናል፤</verse>
				<verse number="55">በከ​ተ​ሞ​ችህ ሁሉ ውስጥ ጠላ​ቶ​ችህ ከብ​በው ባስ​ጨ​ነ​ቁ​ህና መከራ ባሳ​ዩህ ጊዜ ሌላ ነገር የቀ​ረው የለ​ምና ከሚ​በ​ላው ከል​ጆቹ ሥጋ ለአ​ንዱ አይ​ሰ​ጥም።</verse>
				<verse number="56">በአ​ንተ ዘንድ የተ​ለ​ሳ​ለ​ሰ​ችና የተ​ቀ​ማ​ጠ​ለች፥ ከል​ስ​ላ​ሴና ከቅ​ም​ጥ​ል​ነት የተ​ነሣ የእ​ግር ጫማ​ዋን በም​ድር ላይ ያላ​ደ​ረ​ገ​ችው ሴት፥ አቅፋ በተ​ኛ​ችው ባልዋ፥ በወ​ን​ድና በሴት ልጅ​ዋም ትቀ​ና​ለች፥</verse>
				<verse number="57">ከአ​ካ​ልዋ የሚ​ወ​ጣ​ውን የእ​ን​ግዴ ልጅ፥ የም​ት​ወ​ል​ዳ​ቸ​ው​ንም ልጆች፤ በደ​ጆ​ችህ ውስጥ ጠላ​ቶ​ችህ፤ ከብ​በው ባስ​ጨ​ነ​ቁ​ህና መከራ ባሳ​ዩህ ጊዜ ሁሉን ስላ​ጣች በስ​ውር ትበ​ላ​ቸ​ዋ​ለች።</verse>
				<verse number="58">“በዚህ መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፉ​ትን የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ታደ​ርግ ዘንድ፥ ይህ​ንም ክቡ​ርና ምስ​ጉን ስም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክ​ህን ትፈራ ዘንድ ባት​ሰማ፥</verse>
				<verse number="59">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ሠ​ፍ​ት​ህን፥ የዘ​ር​ህ​ንም መቅ​ሠ​ፍት፥ ታላ​ቅና የሚ​ያ​ስ​ፈራ መቅ​ሠ​ፍ​ትን፥ ለብዙ ጊዜ የሚ​ኖር ክፉ ደዌና ሕማ​ምን ሁሉ ያመ​ጣ​ብ​ሃል።</verse>
				<verse number="60">የፈ​ራ​ኸ​ው​ንም የግ​ብፅ ደዌ ሁሉ እን​ደ​ገና ያመ​ጣ​ብ​ሃል፤ ያጣ​ብ​ቅ​ብ​ህ​ማል።</verse>
				<verse number="61">ደግ​ሞም ይህ ሕግ ባለ​በት መጽ​ሐፍ ውስጥ ያል​ተ​ጻ​ፈ​ውን ደዌ ሁሉ፥ መቅ​ሠ​ፍ​ት​ንም ሁሉ እስ​ክ​ት​ጠፋ ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያመ​ጣ​ብ​ሃል።</verse>
				<verse number="62">የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምና ከብ​ዛ​ታ​ችሁ የተ​ነሣ እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት የነ​በ​ረው ቍጥ​ራ​ችሁ ጥቂት ሆኖ ይቀ​ራል።</verse>
				<verse number="63">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ ያደ​ር​ግ​ልህ ዘንድ፥ ያበ​ዛ​ህም ዘንድ ደስ ይለው እንደ ነበረ፥ እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሲያ​ጠ​ፋህ፥ ሲያ​ፈ​ር​ስ​ህም ደስ ይለ​ዋል፤ ትወ​ር​ሳ​ትም ዘንድ ከም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር ትነ​ቀ​ላ​ለህ ።</verse>
				<verse number="64">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከም​ድር ዳር እስከ ዳር​ቻዋ ድረስ ወደ አሉ አሕ​ዛብ ሁሉ ይበ​ት​ን​ሃል፤ በዚ​ያም አን​ተና አባ​ቶ​ችህ ያላ​ወ​ቃ​ች​ኋ​ቸ​ውን ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት፥ እን​ጨ​ት​ንና ድን​ጋ​ይን ታመ​ል​ካ​ለህ።</verse>
				<verse number="65">በእ​ነ​ዚ​ያም አሕ​ዛብ መካ​ከል ዕረ​ፍት አታ​ገ​ኝም፤ ለእ​ግ​ር​ህም ጫማ ማረ​ፊያ አይ​ሆ​ንም፤ በዚ​ያም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተን​ቀ​ጥ​ቃጭ ልብ ፥ ፈዛዛ ዐይን፥ ደካ​ማም ነፍስ ያመ​ጣ​ብ​ሃል።</verse>
				<verse number="66">ሕይ​ወ​ትህ በዐ​ይ​ኖ​ችህ ፊት የተ​ሰ​ቀ​ለች ትሆ​ና​ለች፤ ሌሊ​ትና ቀንም ትደ​ነ​ግ​ጣ​ለህ፤ በሕ​ይ​ወ​ት​ህም አት​ታ​መ​ንም፤</verse>
				<verse number="67">ከፈ​ራ​ህ​በት ከል​ብህ ፍር​ሀት የተ​ነሣ፥ በዐ​ይ​ን​ህም ካየ​ኸው የተ​ነሣ፥ ሲነጋ እን​ዴት ይመሽ ይሆን? ትላ​ለህ፤ ሲመ​ሽም እን​ዴት ይነጋ ይሆን? ትላ​ለህ።</verse>
				<verse number="68">ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ተመ​ል​ሰህ አታ​ያ​ትም ባል​ሁህ መን​ገ​ድም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ር​ከብ ወደ ግብፅ ይመ​ል​ስ​ሃል፤ በዚ​ያም ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ወን​ዶ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮች ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ የሚ​ራ​ራ​ላ​ች​ሁም አይ​ኖ​ርም።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="29">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኮ​ሬብ ካደ​ረ​ገው ቃል ኪዳን ሌላ በሞ​ዓብ ምድር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር ያደ​ር​ገው ዘንድ ሙሴን ያዘ​ዘው የቃል ኪዳኑ ቃሎች እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="2">ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሁሉ ጠርቶ አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ታ​ችሁ በግ​ብፅ ምድር፥ በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ሁሉ፥ በም​ድ​ሩም ሁሉ ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፥</verse>
				<verse number="3">ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም ያዩ​አ​ቸ​ውን ታላ​ላ​ቆች ፈተ​ና​ዎ​ችን፥ ታላ​ላ​ቆች ተአ​ም​ራ​ት​ንና ድን​ቆ​ችን አይ​ታ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ታስ​ተ​ውሉ ዘንድ ልብን፥ ታዩም ዘንድ ዐይ​ንን፥ ትሰ​ሙም ዘንድ ጆሮ​ዎ​ችን እስከ ዛሬ ድረስ አል​ሰ​ጣ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="5">አርባ ዓመት በም​ድረ በዳ መራ​ችሁ፤ ልብ​ሳ​ች​ሁም አላ​ረ​ጀ​ባ​ች​ሁም፤ ጫማ​ች​ሁም በእ​ግ​ራ​ችሁ ላይ አል​ተ​ቀ​ደ​ደም።</verse>
				<verse number="6">አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ እዚህ ቦታ እስ​ክ​ት​ደ​ርሱ ድረስ እን​ጀራ አል​በ​ላ​ች​ሁም፤ የወ​ይን ጠጅና የሚ​ያ​ሰ​ክ​ረ​ውን መጠ​ጥም አል​ጠ​ጣ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="7">የሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ ሴዎን፥ የባ​ሳ​ንም ንጉሥ ዐግ ሊወ​ጉን ወጡ​ብን፤ እኛም መታ​ና​ቸው፤</verse>
				<verse number="8">ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም ወስ​ደን ለሮ​ቤ​ልና ለጋድ፥ ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ርስት አድ​ር​ገን ሰጠ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="9">የም​ታ​ደ​ር​ጉት ሁሉ ይከ​ና​ወ​ን​ላ​ችሁ ዘንድ የዚ​ህን ቃል ኪዳን ቃሎች ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ።</verse>
				<verse number="10">ሁላ​ችሁ፥ የነ​ገ​ዶ​ቻ​ችሁ አለ​ቆች ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁም፥ ሹሞ​ቻ​ች​ሁም፥ ጻፎ​ቻ​ች​ሁም፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ወንድ ሁሉ ዛሬ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆማ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="11">ሴቶ​ቻ​ች​ሁም፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁም ከእ​ን​ጨት ለቃ​ሚ​ያ​ችሁ እስከ ውኃ ቀጃ​ችሁ በሰ​ፈ​ራ​ችሁ ያለ መጻ​ተኛ፤</verse>
				<verse number="12">ይኸ​ውም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ዛሬ በሚ​ያ​ደ​ር​ገው ቃል ኪዳ​ንና አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር በተ​ማ​ማ​ለው መሐላ ትገባ ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="13">ዛሬ ለእ​ርሱ ሕዝብ ያደ​ር​ግህ ዘንድ፥ እር​ሱም ለአ​ንተ እንደ ተና​ገረ ለአ​ባ​ቶ​ች​ህም ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም እንደ ማለ አም​ላክ ይሆ​ን​ልህ ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="14">“እኔም ይህን ቃል ኪዳ​ንና ይህን መሐላ የማ​ደ​ር​ገው ከእ​ና​ንተ ጋር ብቻ አይ​ደ​ለም፤</verse>
				<verse number="15">ነገር ግን ዛሬ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከእኛ ጋር በዚህ ከሚ​ቆም ሰው ጋር፥ ዛሬም ከእኛ ጋር በዚህ ከሌለ ሰው ጋር ነው እንጂ፤</verse>
				<verse number="16">ነገር ግን እኛ በግ​ብፅ ምድር እንደ ተቀ​መ​ጥን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ባለ​ፋ​ች​ሁ​ባ​ቸው አሕ​ዛብ መካ​ከል እን​ዳ​ለ​ፍን ዐው​ቃ​ች​ኋ​ልና፥</verse>
				<verse number="17">ርኩ​ስ​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም፥ በእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ የነ​በ​ሩ​ትን የእ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ፥ የብ​ርና የወ​ር​ቅም ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አይ​ታ​ች​ኋ​ልና፥</verse>
				<verse number="18">ሄዶ የእ​ነ​ዚ​ያን አሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ያመ​ልክ ዘንድ ከአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡን ዛሬ የሚ​ያ​ስት ወንድ ወይም ሴት ወይም ወገን ወይም ነገድ አይ​ኑ​ር​ባ​ችሁ፤ ሐሞ​ትና እሬ​ትም የሚ​ያ​በ​ቅል ሥር አይ​ሁ​ን​ባ​ችሁ።</verse>
				<verse number="19">“የዚ​ህ​ንም ርግ​ማን ቃሎች በሰ​ማ​ችሁ ጊዜ በልቡ ‘ይህን በልቤ ስን​ፍና በማ​ድ​ረግ ሄጃ​ለ​ሁና ይቅር ይለ​ኛል’ የሚል ቢኖር የበ​ደ​ለኛ ፍዳ ካል​በ​ደለ ጋር እን​ዳ​ይ​ተ​ካ​ከል፥</verse>
				<verse number="20">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ፥ ቅን​አ​ቱም በዚያ ሰው ላይ ይነ​ድ​ዳል እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ርታ አያ​ደ​ር​ግ​ለ​ትም፤ በዚ​ህም መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈው ርግ​ማን ሁሉ በላዩ ይኖ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስሙን ከሰ​ማይ በታች ይደ​መ​ስ​ሰ​ዋል።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚህ ሕግ መጽ​ሐፍ እንደ ተጻ​ፈው እንደ ቃል ኪዳኑ ርግ​ማን ሁሉ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ሁሉ ለጥ​ፋት ይለ​የ​ዋል።</verse>
				<verse number="22">“ከዚ​ያም በኋላ የሚ​ነሣ ትው​ልድ፥ ከእ​ና​ን​ተም በኋላ የሚ​ሆኑ ልጆ​ቻ​ችሁ ከሩቅ ሀገ​ርም የሚ​መጣ እን​ግዳ፥ የዚ​ችን ሀገር መቅ​ሠ​ፍት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በላ​ይዋ የላ​ከ​ውን ሥቃ​ይ​ዋን፥</verse>
				<verse number="23">ምድ​ርም በሁ​ለ​ን​ተ​ናዋ ዲንና ጨው፥ መቃ​ጠ​ልም እንደ ሆነ​ባት፥ እን​ዳ​ይ​ዘ​ራ​ባ​ትም፥ እን​ዳ​ታ​በ​ቅ​ልም፥ ማና​ቸ​ውም ሣርና ልም​ላ​ሜም እን​ዳ​ይ​ወ​ጣ​ባት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣ​ውና በመ​ዓቱ እንደ ገለ​በ​ጣ​ቸው እንደ ሰዶ​ምና ገሞራ፥ እንደ አዳ​ማና እንደ ሲባዮ እንደ ሆነች ባዩ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="24">አሕ​ዛብ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚ​ህች ምድር ስለ ምን እን​ደ​ዚህ አደ​ረገ? ይህስ የቍ​ጣው ታላቅ መቅ​ሠ​ፍት ምን​ድን ነው? ይላሉ።</verse>
				<verse number="25">ሰዎ​ችም እን​ዲህ ይላሉ፦ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ ምድር ባወ​ጣ​ቸው ጊዜ ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ያደ​ረ​ገ​ውን ቃል ኪዳን ስለ​ተዉ፥</verse>
				<verse number="26">ሄደ​ውም የማ​ያ​ው​ቋ​ቸ​ው​ንና የማ​ይ​ጠ​ቅ​ሟ​ቸ​ውን ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ስላ​መ​ለ​ኩና ስለ ሰገ​ዱ​ላ​ቸው፥</verse>
				<verse number="27">ስለ​ዚህ በዚህ የሕግ መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን መር​ገም ሁሉ ያመ​ጣ​ባት ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በዚ​ህች ምድር ነደደ፤</verse>
				<verse number="28">ዛሬም እን​ዳሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣና በመ​ቅ​ሠ​ፍት፥ በታ​ላ​ቅም መዓት ከም​ድ​ራ​ቸው ነቀ​ላ​ቸው፤ ወደ ሌላም ምድር ጣላ​ቸው።</verse>
				<verse number="29">“ምስ​ጢሩ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ የተ​ገ​ለ​ጠው ግን የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እና​ደ​ርግ ዘንድ ለእ​ኛና ለል​ጆ​ቻ​ችን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="30">
				<verse number="1">“እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ እኔ በፊ​ትህ ያኖ​ር​ሁት ይህ ነገር ሁሉ፥ በረ​ከ​ቱና መር​ገሙ በወ​ረ​ደ​ብህ ጊዜ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​በ​ት​ንህ በዚያ በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል ሆነህ በል​ብህ ዐስ​በው፤</verse>
				<verse number="2">ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተመ​ለስ፤ እኔም ዛሬ እን​ደ​ማ​ዝ​ዝህ ሁሉ አን​ተና ልጆ​ችህ በፍ​ጹም ልብና በፍ​ጹም ነፍስ ቃሉን ስማ፤</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀጢ​አ​ት​ህን ይቅር ይል​ሃል ይራ​ራ​ል​ህ​ማል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​ተን ከበ​ተ​ነ​በት ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል መልሶ ይሰ​በ​ስ​ብ​ሃል።</verse>
				<verse number="4">መበ​ተ​ን​ህም እስከ ሰማይ ዳርቻ ቢሆን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚያ ይሰ​በ​ስ​ብ​ሃል፤ ከዚ​ያም ያመ​ጣ​ሃል።</verse>
				<verse number="5">አባ​ቶ​ች​ህም ወደ ወረ​ሱ​አት ምድር አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይወ​ስ​ድ​ሃል፤ ትወ​ር​ሳ​ት​ማ​ለህ፤ መል​ካ​ምም ነገር ያደ​ር​ግ​ል​ሃል፤ ከአ​ባ​ቶ​ች​ህም ይልቅ ያበ​ዛ​ሃል።</verse>
				<verse number="6">በሕ​ይ​ወ​ትም እን​ድ​ት​ኖር፥ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ እን​ድ​ት​ወ​ድድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብ​ህን፥ የዘ​ር​ህ​ንም ልብ ያጠ​ራ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን መር​ገም ሁሉ በጠ​ላ​ቶ​ች​ህና በሚ​ጠ​ሉህ በሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​ህም ላይ ያመ​ጣ​ታል።</verse>
				<verse number="8">አን​ተም ተመ​ል​ሰህ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ትሰ​ማ​ለህ፤ ዛሬም እኔ የማ​ዝ​ዝ​ህን ትእ​ዛ​ዙን ሁሉ ታደ​ር​ጋ​ለህ።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ባ​ቶ​ችህ ደስ እን​ዳ​ለው በመ​ል​ካሙ ነገር ሁሉ እንደ ገና በአ​ንተ ደስ ይለ​ዋ​ልና አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጅህ ሥራ ሁሉ፥ በሆ​ድ​ህም ፍሬ፥ በእ​ር​ሻ​ህም ፍሬ፥ በከ​ብ​ት​ህም ብዛት እጅግ ይባ​ር​ክ​ሃል።</verse>
				<verse number="10">በዚህ የሕግ መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፉ​ትን ትእ​ዛ​ዙን፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንና ፍር​ዱን ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ብት​ሰማ፥ በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብት​መ​ለስ ይባ​ር​ክ​ሃል።</verse>
				<verse number="11">“እኔ ዛሬ የማ​ዝ​ዝህ ይህች ትእ​ዛዝ ከባድ አይ​ደ​ለ​ችም፤ ከአ​ን​ተም የራ​ቀች አይ​ደ​ለ​ችም።</verse>
				<verse number="12">ሰም​ተን እና​ደ​ር​ጋት ዘንድ ስለ እኛ ወደ ሰማይ ወጥቶ እር​ስ​ዋን የሚ​ያ​መ​ጣ​ልን ማን​ነው? እን​ዳ​ትል በሰ​ማይ አይ​ደ​ለ​ችም።</verse>
				<verse number="13">ሰም​ተን እና​ደ​ር​ጋት ዘንድ ስለ እኛ ባሕ​ሩን ተሻ​ግሮ እር​ስ​ዋን የሚ​ያ​መ​ጣ​ልን ማን ነው? እን​ዳ​ትል ከባ​ሕሩ ማዶ አይ​ደ​ለ​ችም።</verse>
				<verse number="14">ታደ​ር​ገው ዘንድ ቃሉ በአ​ፍ​ህና በል​ብህ፥ በእ​ጅ​ህም ውስጥ ለአ​ንተ እጅግ ቅርብ ነው።</verse>
				<verse number="15">“እነሆ፥ ዛሬ በፊ​ትህ ሕይ​ወ​ት​ንና ሞትን፥ መል​ካ​ም​ነ​ት​ንና ክፉ​ነ​ትን አኑ​ሬ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">ዛሬ እኔ የማ​ዝ​ዝ​ህን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛ​ዛት ብት​ሰማ፥ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ብት​ወ​ድድ፥ በመ​ን​ገ​ዶ​ቹም ሁሉ ብት​ሄድ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንና ፍር​ዱ​ንም ብት​ጠ​ብቅ በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ለህ፤ በቍ​ጥ​ርም ትበ​ዛ​ለህ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልት​ወ​ር​ሳት በም​ት​ሄ​ድ​ባት በም​ድ​ሪቱ ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃል።</verse>
				<verse number="17">ልብህ ግን ቢስት፥ አን​ተም ባት​ሰማ፥ ብት​ታ​ለ​ልም፥ ለሌ​ሎች አማ​ል​ክ​ትም ብት​ሰ​ግድ፥ ብታ​መ​ል​ካ​ቸ​ውም፥</verse>
				<verse number="18">ፈጽ​መህ እን​ደ​ም​ት​ጠፋ እኔ ዛሬ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ረህ ትወ​ር​ሳት ዘንድ በም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር ዘመ​ንህ አይ​ረ​ዝ​ምም።</verse>
				<verse number="19">በፊ​ትህ ሕይ​ወ​ት​ንና ሞትን፥ በረ​ከ​ት​ንና መር​ገ​ምን እን​ዳ​ስ​ቀ​መ​ጥሁ እኔ ዛሬ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በአ​ንተ ላይ አስ​መ​ሰ​ክ​ራ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲህ አን​ተና ዘርህ በሕ​ይ​ወት ትኖሩ ዘንድ ሕይ​ወ​ትን ምረጥ፤</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ባ​ቶ​ችህ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም እን​ዲ​ሰ​ጣ​ቸው በማ​ለ​ላ​ቸው በም​ድ​ሪቱ ትቀ​መጥ ዘንድ፥ እርሱ ሕይ​ወ​ትህ፥ የዘ​መ​ን​ህም ርዝ​መት ነውና አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ውደ​ደው፤ ቃሉን ስማው፤ አጥ​ና​ውም።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="31">
				<verse number="1">ሙሴም ይህን ቃል ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ተና​ግሮ ጨረሰ።</verse>
				<verse number="2">አላ​ቸ​ውም፥ “እኔ ዛሬ መቶ ሃያ ዓመት ሆኖ​ኛል፤ ከዚህ በኋላ እወ​ጣና እገባ ዘንድ አል​ች​ልም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ‘ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን አት​ሻ​ገ​ርም’ ብሎ​ኛል።</verse>
				<verse number="3">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ በፊ​ትህ ያል​ፋል፤ እርሱ እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ ከፊ​ትህ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፤ ትወ​ር​ሳ​ቸ​ው​ማ​ለህ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ ኢያሱ በፊ​ትህ ይሄ​ዳል።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ባጠ​ፋ​ቸው በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሚ​ኖሩ በሁ​ለቱ በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ነገ​ሥ​ታት በሴ​ዎ​ንና በዐግ፥ በም​ድ​ራ​ቸ​ውም እን​ዳ​ደ​ረገ እን​ዲሁ ያደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፊ​ታ​ችሁ አሳ​ልፎ ይጥ​ላ​ቸ​ዋል፤ እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁም ሁሉ ታደ​ር​ጉ​ባ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="6">ጽና፤ በርታ፤ አት​ፍራ፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም አት​ደ​ን​ግጥ፤ አት​ድ​ከም፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ ከአ​ንተ ጋር ይሄ​ዳል፤ አይ​ጥ​ል​ህም፤ አይ​ተ​ው​ህ​ምም።</verse>
				<verse number="7">ሙሴም ኢያ​ሱን ጠርቶ በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት፦ ‘አንተ ከዚህ ሕዝብ ጋር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው እን​ዲ​ሰጥ ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ትገ​ባ​ለ​ህና፥ እር​ስ​ዋ​ንም ለእ​ነ​ርሱ ታወ​ር​ሳ​ለ​ህና ጽና፤ በርታ።</verse>
				<verse number="8">በፊ​ት​ህም የሚ​ሄድ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ከአ​ንተ ጋር ይሆ​ናል፤ አይ​ጥ​ል​ህም፤ አይ​ተ​ው​ህም፤ አት​ፍራ፤ አት​ደ​ን​ግጥ’ ” አለው።</verse>
				<verse number="9">ሙሴም ይህ​ችን ሕግ ጻፈ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ይሸ​ከሙ ለነ​በ​ሩት ለሌዊ ልጆች ለካ​ህ​ናቱ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ሰጣት።</verse>
				<verse number="10">ሙሴም በዚ​ያች ቀን እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት መጨ​ረሻ በም​ሕ​ረት ዓመት በዳስ በዓል፥</verse>
				<verse number="11">እስ​ራ​ኤል ሁሉ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይታይ ዘንድ እርሱ በመ​ረ​ጠው ቦታ በአ​ን​ድ​ነት በሚ​ሄ​ድ​በት ጊዜ፥ ይህን ሕግ በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት በጆ​ሮው አን​ብ​በው።</verse>
				<verse number="12">ይሰ​ሙና ይማሩ ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈሩ ዘንድ፥ የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ሰም​ተው ያደ​ርጉ ዘንድ ሕዝ​ቡን ወን​ዶ​ችና ሴቶ​ችን፥ ሕፃ​ኖ​ቻ​ች​ሁ​ንም፥ በሀ​ገ​ራ​ችሁ ደጅ ያለ​ው​ንም መጻ​ተኛ ሰብ​ስብ።</verse>
				<verse number="13">የማ​ያ​ውቁ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ራ​ችሁ ልት​ወ​ር​ሱ​አት በም​ት​ሄ​ዱ​ባት ምድር በም​ት​ኖ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ ይስሙ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መፍ​ራት ይማሩ።”</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “የም​ት​ሞ​ት​በት ቀን እነሆ ቀረበ፤ ኢያ​ሱን ጠር​ተህ እር​ሱን አዝ​ዘው ዘንድ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ከእ​ርሱ ጋር ቁም” አለው። ሙሴና ኢያ​ሱም ሄደው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ቆሙ።</verse>
				<verse number="15">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በደ​መና ዐምድ ወረደ፤ የደ​መ​ና​ውም ዐምድ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ላይ ቆመ።</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እነሆ፥ ከአ​ባ​ቶ​ችህ ጋር ታን​ቀ​ላ​ፋ​ለህ፤ ይህም ሕዝብ ይነ​ሣል፤ ይቀ​መ​ጥ​ባ​ትም ዘንድ በሚ​ሄ​ድ​ባት ምድር መካ​ከል ያሉ​ትን ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ተከ​ትሎ ያመ​ነ​ዝ​ራል፤ እኔ​ንም ይተ​ወ​ኛል፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን ያፈ​ር​ሳሉ።</verse>
				<verse number="17">በዚ​ያም ቀን ቍጣዬ ይነ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ እተ​ዋ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ ፊቴ​ንም ከእ​ነ​ርሱ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም መብል ይሆ​ናሉ፤ በዚ​ያም ቀን፦ በእ​ው​ነት አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቶ​ና​ልና፥ በእ​ኛም መካ​ከል የለ​ምና ይህ ክፉ ነገር ሁሉ አገ​ኘን እስ​ኪሉ ድረስ ብዙ ክፉ ነገ​ርና ጭን​ቀት ይደ​ር​ስ​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="18">ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ተከ​ት​ለ​ዋ​ልና ስላ​ደ​ረ​ጉት ክፋት ሁሉ እኔ በዚያ ቀን ፈጽሜ ፊቴን እሰ​ው​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">አሁ​ንም ይህ​ችን መዝ​ሙር ለእ​ና​ንተ ጻፉ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው፤ ይህ​ችም መዝ​ሙር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ምስ​ክር ትሆ​ን​ልኝ ዘንድ በአ​ፋ​ቸው አድ​ር​ጓት።</verse>
				<verse number="20">ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ወደ ማል​ሁ​ላ​ቸው፥ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ምድር ካገ​ባ​ኋ​ቸው በኋላ፥ ከበ​ሉም፥ ከጠ​ገ​ቡም በኋላ ይስ​ታሉ፤ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክ​ትም ወደ ማም​ለክ ይመ​ለ​ሳሉ፤ እኔ​ንም ያስ​ቈ​ጡ​ኛል፤ ቃል ኪዳ​ኔ​ንም ያፈ​ር​ሳሉ።</verse>
				<verse number="21">ዛሬ ወደ ማል​ሁ​ላ​ቸው ምድር ገና ሳላ​ገ​ባ​ቸው ክፋ​ታ​ቸ​ውን አው​ቃ​ለ​ሁና፥ ከአ​ፋ​ቸ​ውና ከል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም አፍ አት​ረ​ሳ​ምና ብዙ ክፉ ነገ​ርና ጭን​ቀት በደ​ረ​ሰ​ባ​ቸው ጊዜ ይህች መዝ​ሙር ምስ​ክር ሆና በፊ​ታ​ቸው ትቆ​ማ​ለች።”</verse>
				<verse number="22">ሙሴም በዚያ ቀን ይህ​ችን መዝ​ሙር ጻፈ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አስ​ተ​ማ​ራት።</verse>
				<verse number="23">የነ​ዌ​ንም ልጅ ኢያ​ሱን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ታገ​ባ​ለ​ህና ጽና፤ በርታ፤ እር​ሱም ከአ​ንተ ጋር ይሆ​ናል” ብሎ አዘ​ዘው።</verse>
				<verse number="24">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ የዚ​ህን ሕግ ቃሎች እስከ መጨ​ረሻ በመ​ጽ​ሐፍ ጽፎ ከፈ​ጸመ በኋላ፥</verse>
				<verse number="25">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት የሚ​ሸ​ከ​ሙ​ትን ሌዋ​ው​ያ​ንን እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፦</verse>
				<verse number="26">“ይህን የሕግ መጽ​ሐፍ ውሰዱ፤ በዚ​ያም በእ​ና​ንተ ላይ ምስ​ክር እን​ዲ​ሆን በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት አጠ​ገብ አኑ​ሩት።</verse>
				<verse number="27">እኔ ዐመ​ፃ​ች​ሁ​ንና የአ​ን​ገ​ታ​ች​ሁን ድን​ዳኔ አው​ቃ​ለ​ሁና፤ እኔም ዛሬ ከእ​ና​ንተ ጋር ገና በሕ​ይ​ወት ሳለሁ እና​ንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐም​ፃ​ች​ኋል፤ ይል​ቁ​ንስ ከሞ​ትሁ በኋላ እን​ዴት ይሆ​ናል?</verse>
				<verse number="28">ይህን ቃል በጆ​ሮ​አ​ቸው እነ​ግር ዘንድ፥ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ር​ንም አስ​መ​ሰ​ክ​ር​ባ​ቸው ዘንድ የነ​ገ​ዶ​ቻ​ች​ሁን አለ​ቆች፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁን ሁሉ፥ ሹሞ​ቻ​ች​ሁ​ንም፥ ጻፎ​ቻ​ች​ሁ​ንም ሰብ​ስ​ቡ​ልኝ፤</verse>
				<verse number="29">ከሞ​ትሁ በኋላ ፈጽ​ማ​ችሁ እን​ድ​ት​ረ​ክሱ፥ ካዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁም መን​ገድ ፈቀቅ እን​ድ​ትሉ አው​ቃ​ለ​ሁና። በእ​ጃ​ች​ሁም ሥራ ታስ​ቈ​ጡት ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ስላ​ደ​ረ​ጋ​ችሁ፥ በኋ​ለ​ኛው ዘመን ክፉ ነገር ያገ​ኛ​ች​ኋል።”</verse>
				<verse number="30">ሙሴም በእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ ጆሮ የዚ​ህ​ችን መዝ​ሙር ቃሎች እስከ መጨ​ረ​ሻው ድረስ ተና​ገረ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="32">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም አለ፦ “ሰማይ ሆይ፥ አድ​ምጥ፥ ልን​ገ​ርህ፤ ምድ​ርም የአ​ፌን ቃሎች ትስማ።</verse>
				<verse number="2">ትም​ህ​ር​ቴ​ንም እንደ ዝናም ተስፋ ታድ​ር​ገው፤ ነገሬ እንደ ጠል ይው​ረድ፤ በእ​ር​ሻም ላይ እንደ ዝናም፥ በሣ​ርም ላይ እንደ ጤዛ።</verse>
				<verse number="3">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም እጠ​ራ​ለ​ሁና፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ታላ​ቅ​ነ​ትን ስጡ።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሥ​ራው እው​ነ​ተኛ ነው፤ መን​ገ​ዱም ሁሉ የቀና ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መነ ነው፤ ክፋ​ትም የለ​በ​ትም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድ​ቅና ቸር ነው።</verse>
				<verse number="5">እነ​ርሱ በደሉ፤ ልጆ​ቹም አይ​ደ​ሉም፤ ነው​ርም አለ​ባ​ቸው፤ ጠማ​ማና ገል​በ​ጥ​ባጣ ትው​ልድ ናቸው።</verse>
				<verse number="6">ደን​ቆሮ፥ ብል​ሃ​ተ​ኛም ያል​ሆ​ንህ ሕዝብ ሆይ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ትመ​ል​ሳ​ለ​ህን? የፈ​ጠ​ረህ አባ​ትህ አይ​ደ​ለ​ምን? የፈ​ጠ​ረ​ህና ያጸ​ናህ እርሱ ነው።</verse>
				<verse number="7">የዱ​ሮ​ውን ዘመን አስብ፤ የልጅ ልጅ​ንም ዓመ​ታት አስ​ተ​ውል፤ አባ​ት​ህን ጠይቅ፥ ይነ​ግ​ር​ህ​ማል፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ች​ህን ጠይቅ፤ ይተ​ር​ኩ​ል​ህ​ማል።</verse>
				<verse number="8">ልዑል አሕ​ዛ​ብን በከ​ፈ​ላ​ቸው ጊዜ፥ የአ​ዳ​ም​ንም ልጆች በለ​ያ​ቸው ጊዜ፥ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ቍጥር፥ አሕ​ዛ​ብን በየ​ድ​ን​በ​ራ​ቸው አቆ​ማ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ሕዝቡ ያዕ​ቆ​ብም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዕድል ፋንታ ሆነ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም የር​ስቱ ገመድ ነው።</verse>
				<verse number="10">በም​ድረ በዳ አጠ​ገ​ባ​ቸው፤ በጥ​ማ​ትና በድ​ካም ቦታ፥ በው​ድማ ከበ​ባ​ቸው፤ መገ​ባ​ቸው፤ መራ​ቸ​ውም፤ እንደ ዐይን ብሌ​ንም ጠበ​ቃ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ንስር ጫጩ​ቶ​ቹን በክ​ን​ፎቹ በታች እን​ደ​ሚ​ሰ​በ​ስብ፥ በጎ​ኑም እን​ደ​ሚ​ያ​ቅፍ፥ በክ​ን​ፎቹ አዘ​ላ​ቸው፤ በደ​ረ​ቱም ተሸ​ከ​ማ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ​ውን መራ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሌላ አም​ላክ አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="13">በም​ድር ኀይል ላይ አወ​ጣ​ቸው፤ የእ​ር​ሻ​ው​ንም ፍሬ መገ​ባ​ቸው፤ ከዓ​ለ​ትም ድን​ጋይ በሚ​ገኝ ማር፥ ከጭ​ን​ጫ​ውም ድን​ጋይ በሚ​ገኝ ዘይት አሳ​ደ​ጋ​ቸው፤</verse>
				<verse number="14">በላሙ ቅቤ፥ በበ​ጉም ወተት፥ ከፍ​የል ጠቦ​ትና ከላም፥ ከጊ​ደ​ሮ​ችና ከበ​ጎች ስብ ጋር፥ ከፍ​ትግ ስንዴ ጋር መገ​ባ​ቸው፤ የዘ​ለ​ላ​ው​ንም ደም የወ​ይን ጠጅ አድ​ር​ገው ጠጡ።</verse>
				<verse number="15">ያዕ​ቆብ በላ፤ ጠገ​በም፤ የተ​ወ​ደ​ደ​ውን ጥጋብ አቀ​ና​ጣው፤ ሰባ፥ ወፈረ፥ ሰፋ፤ የፈ​ጠ​ረ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ሔ​ርን ተወ፤ ከሕ​ይ​ወቱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ራቀ።</verse>
				<verse number="16">በዚህ በልዩ ጣዖት አነ​ሣ​ሡኝ፤ በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውም አስ​መ​ረ​ሩኝ።</verse>
				<verse number="17">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያይ​ደለ ለአ​ጋ​ን​ንት፥ ለማ​ያ​ው​ቋ​ቸ​ውም አማ​ል​ክት፥ ድን​ገት ለተ​ገኙ ለማ​ይ​ሠ​ሩና ለማ​ይ​ጠ​ቅሙ አማ​ል​ክት፥ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ለማ​ያ​ው​ቋ​ቸው አማ​ል​ክት ሠዉ።</verse>
				<verse number="18">የወ​ለ​ደ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተውህ፤ ያሳ​ደ​ገ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ረሳ​ኸው።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አይቶ ቀና፤ በወ​ን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ችም ፈጽሞ ተቈጣ።</verse>
				<verse number="20">እር​ሱም አለ፦ ፊቴን ከእ​ነ​ርሱ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ በመ​ጨ​ረ​ሻው ዘመን ምን እንደ ሆነ አያ​ለሁ፤ ጠማማ ትው​ልድ፥ እም​ነት የሌ​ላ​ቸው ልጆች ናቸ​ውና።</verse>
				<verse number="21">አም​ላክ ባል​ሆ​ነው አስ​ቀ​ኑኝ፤ በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አስ​ቈ​ጡኝ፤ እኔም ሕዝብ ባል​ሆ​ነው አስ​ቀ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በማ​ያ​ስ​ተ​ውል ሕዝ​ብም አስ​ቈ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="22">እሳት ከቍ​ጣዬ ትነ​ድ​ዳ​ለ​ችና፥ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃ​ጥ​ላ​ለች፤ ምድ​ር​ንም ከፍ​ሬዋ፤ ጋር ትበ​ላ​ለች፤ የተ​ራ​ሮ​ችን መሠ​ረት ታነ​ድ​ዳ​ለች።</verse>
				<verse number="23">ለመ​ከራ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ፍላ​ጻ​ዎ​ች​ንም እጨ​ር​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="24">በራብ ያል​ቃሉ፤ ለሰ​ማይ ወፎ​ችም መብል ይሆ​ናሉ፤ ኀይ​ላ​ቸ​ውም ይደ​ክ​ማል፥ ከም​ድር ይጠፉ ዘንድ የም​ድር አራ​ዊ​ትን ጥርስ፥ ከመ​ርዝ ጋር እል​ክ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="25">ጐል​ማ​ሳ​ውን ከድ​ን​ግል፥ ሕፃ​ኑ​ንም ከሽ​ማ​ግሌ ጋር፥ በሜዳ ሰይፍ፥ በቤ​ትም ውስጥ ድን​ጋጤ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="26">እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ፤ ከሰ​ዎ​ችም መካ​ከል መታ​ሰ​ቢ​ያ​ቸ​ውን አጠ​ፋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="27">ነገር ግን ጠላ​ቶ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ይ​ታ​በዩ፦ እጃ​ችን ከፍ ከፍ አለች እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ሁሉ አላ​ደ​ረ​ገም እን​ዳ​ይሉ፥ በቍጣ ጠላት ሆኑኝ።</verse>
				<verse number="28">ምክር ያጡ ሕዝብ ናቸው፤ ምግ​ባ​ርና ሃይ​ማ​ኖት የላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="29">ይህ​ንም ያው​ቁት ዘንድ አላ​ሰ​ቡ​ትም፤ በሚ​መ​ጣ​ውም ዘመን አያ​ው​ቁ​ትም።</verse>
				<verse number="30">አንዱ ሽሁን እን​ዴት ያሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋል? ሁለ​ቱስ ዐሥ​ሩን ሽህ እን​ዴት ያባ​ር​ሩ​አ​ቸ​ዋል? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍዳ​ውን አም​ጥ​ቶ​ባ​ቸ​ዋ​ልና። አም​ላ​ካ​ች​ንም አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="31">አም​ላ​ካ​ችን እንደ አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው አይ​ደ​ለ​ምና፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሰነ​ፎች ናቸው።</verse>
				<verse number="32">ወይ​ና​ቸው ከሰ​ዶም ወይን፥ ሐረ​ጋ​ቸ​ውም ከገ​ሞራ ነው፤ ፍሬ​አ​ቸ​ውም ሐሞት ነው፤ ዘለ​ላ​ቸ​ውም መራራ ነው።</verse>
				<verse number="33">የወ​ይን ጠጃ​ቸው የእ​ባብ መርዝ፥ የሚ​ገ​ድ​ልም የእ​ፉ​ኝት መርዝ ነው።</verse>
				<verse number="34">በእኔ ዘንድ ያለው ትእ​ዛዝ ይህ አይ​ደ​ለ​ምን? በመ​ዝ​ገ​ቤስ የታ​ተመ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="35">በፍ​ርድ ቀን እበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እግ​ራ​ቸው በሚ​ሰ​ና​ከ​ል​በት ጊዜ፥ የጥ​ፋ​ታ​ቸው ቀን ቀር​ቦ​አ​ልና፥ የተ​ዘ​ጋ​ጀ​ላ​ች​ሁም ፈጥኖ ይደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋ​ልና።</verse>
				<verse number="36">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ ይፈ​ር​ዳል፤ ስለ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ይራ​ራል፤ በያ​ሉ​በት መሳ​ለ​ቂያ ሆነው እንደ ኖሩ፥ ኀይ​ላ​ቸ​ውም እንደ ደከመ፥ በጠ​ላ​ትም እጅ እንደ ወደቁ አይ​ቶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="37">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፦ ትታ​መ​ኑ​ባ​ቸው የነ​በ​ሩት አማ​ል​ክት የት አሉ?</verse>
				<verse number="38">የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ስብ የም​ት​በ​ሉ​ላ​ቸው፥ የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ች​ው​ንም ወይን የም​ት​ጠ​ጡ​ላ​ቸው፥ እነ​ርሱ ይነሡ፤ ይር​ዱ​አ​ች​ሁም፤ የሚ​ያ​ድ​ኑ​አ​ች​ሁም ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="39">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእ​ኔም በቀር አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ዕወቁ፤ ዕወቁ። እኔ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ አድ​ን​ማ​ለሁ፤ እኔ እገ​ር​ፋ​ለሁ፤ ይቅ​ርም እላ​ለሁ፤ ከእ​ጄም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም።</verse>
				<verse number="40">እጄን ወደ ሰማይ እዘ​ረ​ጋ​ለ​ሁና፥ በቀኜ እም​ላ​ለሁ፦ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም እኔ ሕያው ነኝ እላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="41">ሰይ​ፌን እንደ መብ​ረቅ እስ​ላ​ታ​ለሁ፤ እጄም ፍር​ድን ትይ​ዛ​ለች፤ ለሚ​ጠ​ሉ​ኝም ፍዳ​ቸ​ውን እከ​ፍ​ላ​ለሁ፤ ጠላ​ቶ​ች​ንም እበ​ቀ​ላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="42">ከተ​ወ​ጉት፥ ከተ​ማ​ረ​ኩ​ትም ደም፥ ፍላ​ጻ​ዎ​ቼን በደም አሰ​ክ​ራ​ለሁ፤ ከጠ​ላት አለ​ቆ​ችም ራስ ሰይፌ ሥጋን ትበ​ላ​ለች።</verse>
				<verse number="43">ሰማ​ያት ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መላ​እ​ክት ሁሉ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል። አሕ​ዛ​ብም ከሕ​ዝቡ ጋር ደስ ይላ​ቸ​ዋል። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ሁሉ እርሱ ጽኑዕ ነው ይላሉ፤ የል​ጆ​ቹን ደም ይበ​ቀ​ላ​ልና፥ ጠላ​ቶ​ቹ​ንም ይበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ልና፥ ለሚ​ጠ​ላ​ቸ​ውም ፍዳ​ቸ​ውን ይከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሕ​ዝ​ቡን ምድር ያነ​ጻል።”</verse>
				<verse number="44">ሙሴም በዚ​ያች ቀን ይህ​ችን መዝ​ሙር ጻፋት፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አስ​ተ​ማ​ራት፤ ሙሴም ገባ እር​ሱና የነዌ ልጅ ኢያ​ሱም የዚ​ህ​ችን ሕግ ቃሎች ሁሉ በሕ​ዝቡ ጆሮ ተና​ገሩ።</verse>
				<verse number="45">ሙሴም ይህን ቃል ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ተና​ግሮ ፈጸመ።</verse>
				<verse number="46">እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ይጠ​ብ​ቁና ያደ​ርጉ ዘንድ ልጆ​ቻ​ች​ሁን እን​ድ​ታ​ዝ​ዙ​በት ዛሬ የም​መ​ሰ​ክ​ር​ላ​ች​ሁን ቃል ሁሉ በል​ባ​ችሁ አኑ​ሩት።</verse>
				<verse number="47">ይህ ነገር ሕይ​ወ​ታ​ችሁ ነው እንጂ ለእ​ና​ንተ ከንቱ አይ​ደ​ለ​ምና፤ በዚ​ህም ነገር ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ራ​ችሁ በም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር ዘመ​ና​ችሁ ይረ​ዝ​ማል።”</verse>
				<verse number="48">በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="49">“በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በሞ​ዓብ ምድር በዓ​ባ​ሪም ተራራ ውስጥ ወዳ​ለው ወደ ናባው ተራራ ውጣ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ርስት አድ​ርጌ የም​ሰ​ጣ​ቸ​ውን የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር እያት፤</verse>
				<verse number="50">ወን​ድ​ምህ አሮን በሖር ተራራ እንደ ሞተ፥ ወደ ወገ​ኖ​ቹም እንደ ተጨ​መረ፥ በወ​ጣ​ህ​በት ተራራ ሙት፤ ወደ ወገ​ኖ​ች​ህም ተጨ​መር፤</verse>
				<verse number="51">በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል በጺን ምድረ በዳ በቃ​ዴስ ባለው በክ​ር​ክር ውኃ ለቃሌ አል​ታ​ዘ​ዛ​ች​ሁ​ምና፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መካ​ከል አል​ቀ​ደ​ሳ​ች​ሁ​ኝ​ምና፥</verse>
				<verse number="52">ምድ​ሪ​ቱን ፊት ለፊት ታያ​ለህ እንጂ ወደ​ዚ​ያች ምድር አት​ገ​ባም።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="33">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሙሴ ሳይ​ሞት የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች የባ​ረ​ከ​ባት በረ​ከት ይህች ናት።</verse>
				<verse number="2">እን​ዲ​ህም አለ፦ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሲና መጣ፤ በሴ​ይ​ርም ተገ​ለ​ጠ​ልን፤ ከፋ​ራን ተራራ፥ ከቃ​ዴስ አእ​ላ​ፋት ጋር ፈጥኖ መጣ፤ መላ​እ​ክ​ቱም ከእ​ርሱ ጋር በቀኙ ነበሩ።</verse>
				<verse number="3">ለሕ​ዝ​ቡም ራራ​ላ​ቸው፤ ቅዱ​ሳን ሁሉ ከእ​ጅህ በታች ናቸው፤ እነ​ር​ሱም የአ​ንተ ናቸው። ቃሎ​ች​ህ​ንም ይቀ​በ​ላሉ።</verse>
				<verse number="4">ሙሴም ለያ​ዕ​ቆብ ማኅ​በር ርስት የሆ​ነ​ውን ሕግ አዘ​ዘን።</verse>
				<verse number="5">የሕ​ዝቡ አለ​ቆች ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ሁሉ ጋር በተ​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ፥ አለቃ በተ​ወ​ዳጁ ዘንድ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="6">ሮቤ​ልን እፈ​ል​ገ​ዋ​ለሁ፤ አይ​ሙ​ት​ብኝ፤ ቍጥ​ሩም ብዙ ይሁን።</verse>
				<verse number="7">የይ​ሁ​ዳም በረ​ከት ይህች ናት፤ አቤቱ የይ​ሁ​ዳን ቃል ስማ፤ ወደ ሕዝ​ቡም ይግባ፤ እጆ​ቹም ይግዙ፤ በጠ​ላ​ቶቹ ላይ ረዳት ትሆ​ነ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="8">ስለ ሌዊም እን​ዲህ አለ፥ ለሌዊ ቃሉን፥ በመ​ከ​ራም ለፈ​ተ​ኑት፥ በክ​ር​ክር ውኃም ለሰ​ደ​ቡት፥ ለእ​ው​ነ​ተ​ኛው ሰው ጽድ​ቁን መልስ።</verse>
				<verse number="9">እና​ቱ​ንና አባ​ቱን አላ​የ​ኋ​ች​ሁም ላለ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ላላ​ወቀ፥ ልጆ​ቹ​ንም ላላ​ስ​ተ​ዋለ፤ ቃል​ህን ለጠ​በቀ፥ በቃል ኪዳ​ን​ህም ለተ​ማ​ጠነ።</verse>
				<verse number="10">ፍር​ድ​ህን ለያ​ዕ​ቆብ፥ ሕግ​ህ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ያስ​ተ​ም​ራሉ፤ በማ​ዕ​ጠ​ን​ትህ ዕጣ​ንን፥ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ህም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሁል​ጊዜ ያቀ​ር​ባሉ።</verse>
				<verse number="11">አቤቱ ኀይ​ሉን ባርክ፤ የእ​ጁ​ንም ሥራ ተቀ​በል፤ በሚ​ቃ​ወ​ሙት ጠላ​ቶቹ ላይ መከ​ራን አው​ርድ፤ የሚ​ጠ​ሉ​ትም አይ​ነሡ።</verse>
				<verse number="12">ስለ ብን​ያ​ምም እን​ዲህ አለ፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ወ​ደደ በእ​ርሱ ዘንድ ተማ​ምኖ ይኖ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዘ​መኑ ሁሉ ይጋ​ር​ደ​ዋል፤ በት​ከ​ሻ​ውም መካ​ከል ያድ​ራል።</verse>
				<verse number="13">ስለ ዮሴ​ፍም እን​ዲህ አለ፦ ምድሩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በረ​ከት፥ ከሰ​ማይ ዝና​ምና ጠል፥ ከታ​ችም ከጥ​ልቁ ምንጭ ናት።</verse>
				<verse number="14">ከፀ​ሐይ መው​ጣት ከሚ​ገ​ኘው ፍሬ፥ በወ​ራት ቍጥር ከሚ​ገ​ኘው ምርት፥</verse>
				<verse number="15">ከቀ​ደ​ሙ​ትም ተራ​ሮች ከፍ​ተ​ኛ​ነት፥ ከዘ​ለ​ዓ​ለሙ ኮረ​ብ​ቶች ራሶች፥</verse>
				<verse number="16">በየ​ወ​ቅ​ቱም ከም​ድ​ሪቱ ምላት፥ በቍ​ጥ​ቋ​ጦው ውስጥ ከነ​በ​ረው በረ​ከት፥ በዮ​ሴፍ ራስ ላይ፥ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹም በከ​በ​ረው በእ​ርሱ ራስ ላይ ይው​ረድ።</verse>
				<verse number="17">ውበቱ እንደ ላም በኵር ነው፤ ቀን​ዶቹ አንድ ቀንድ እን​ዳ​ለው ናቸው፤ በእ​ነ​ርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉ​ትን አሕ​ዛብ ሁሉ ይወ​ጋል፤ የኤ​ፍ​ሬም እልፍ አእ​ላ​ፋት፥ የም​ና​ሴም አእ​ላ​ፋት እነ​ርሱ ናቸው።</verse>
				<verse number="18">ስለ ዛብ​ሎ​ንም እን​ዲህ አለ፦ ዛብ​ሎን ሆይ፥ በመ​ው​ጣ​ትህ፥ ይሳ​ኮር ሆይ፥ በድ​ን​ኳ​ንህ ውስጥ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="19">አሕ​ዛ​ብን ያጠ​ፉ​አ​ቸ​ዋል፤ በዚ​ያም ይጠ​ሩ​አ​ቸ​ዋል፤ የጽ​ድቅ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም ይሠ​ዋሉ፤ የባ​ሕ​ሩም ሀብት፥ በባ​ሕሩ ዳር የሚ​ኖሩ ሰዎ​ችም ገን​ዘብ ይመ​ግ​ብ​ሃ​ልና፥</verse>
				<verse number="20">ስለ ጋድም እን​ዲህ አለ፦ ጋድን ሰፊ ያደ​ረገ ቡሩክ ይሁን፤ እንደ አን​በሳ ያለ​ቆ​ችን ክንድ ቀጥ​ቅጦ ያር​ፋል።</verse>
				<verse number="21">በዚያ ከሕ​ዝቡ ገዦች ጋር የተ​ሰ​በ​ሰቡ የአ​ለ​ቆች ምድር እንደ ተከ​ፈ​ለች፥ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውን ፍሬ አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጽድ​ቁን፥ ፍር​ዱ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="22">ስለ ዳንም እን​ዲህ አለ፦ ዳን የአ​ን​በሳ ደቦል ነው፤ ከባ​ሳን ይበ​ር​ራል።</verse>
				<verse number="23">ስለ ንፍ​ታ​ሌ​ምም እን​ዲህ አለ፦ ንፍ​ታ​ሌም ከበጎ ነገር ጠግ​ቦ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በረ​ከት ተሞ​ል​ቶ​አል፤ ባሕ​ር​ንና ሊባን ይወ​ር​ሳል።</verse>
				<verse number="24">ስለ አሴ​ርም እን​ዲህ አለ፦ አሴር ከል​ጆች የተ​ነሣ የተ​ባ​ረከ ይሁን፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም የተ​መ​ረጠ ይሁን፤ እግ​ሩ​ንም በዘ​ይት ያጥ​ባል።</verse>
				<verse number="25">ጫማህ ብረ​ትና ናስ ይሆ​ናል፤ እንደ ዕድ​ሜህ እን​ዲሁ ኀይ​ልህ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="26">እንደ ፍቁሩ አም​ላክ ማንም የለም፤ በሰ​ማይ የሚ​ኖ​ረው፥ በጠ​ፈ​ርም በታ​ላ​ቅ​ነት ያለው እርሱ ረዳ​ትህ ነው።</verse>
				<verse number="27">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ለፊት፥ በዘ​ለ​ዓ​ለም ክን​ዶች ኀይል ይጋ​ር​ድ​ሃል፤ ጠላ​ት​ህን ከፊ​ትህ አው​ጥቶ፦ አጥ​ፋው ይላል።</verse>
				<verse number="28">እስ​ራ​ኤ​ልም ተማ​ምኖ፥ በያ​ዕ​ቆብ ምድር ብቻ​ውን፥ በስ​ን​ዴና በወ​ይን ምድር ይኖ​ራል፤ ሰማይ ከደ​መ​ናና ከጠል ጋር ለአ​ንተ ነው።</verse>
				<verse number="29">እስ​ራ​ኤል ሆይ ብፁዕ ነህ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን​ነው? እርሱ ያጸ​ን​ሃል፤ ይረ​ዳ​ሃ​ልም፤ ትም​ክ​ሕ​ትህ በሰ​ይ​ፍህ ነው፤ ጠላ​ቶ​ችህ ውሸ​ታ​ሞች ናቸው፤ አን​ተም በአ​ን​ገ​ታ​ቸው ላይ ትጫ​ና​ለህ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="34">
				<verse number="1">ሙሴም ከሞ​ዓብ ሜዳ በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት ወዳ​ለው ወደ ናባው ተራራ ወደ ፈስጋ ራስ ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስከ ዳን ድረስ ያለ​ውን የገ​ለ​ዓ​ድን ምድር አሳ​የው፤</verse>
				<verse number="2">የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ምድር ሁሉ፥ የም​ና​ሴ​ንም ምድር ሁሉ፥ እስከ ምዕ​ራ​ብም ባሕር ድረስ ያለ​ውን የይ​ሁ​ዳን ምድር ሁሉ፤</verse>
				<verse number="3">ምድረ በዳ​ውን፥ የኢ​ያ​ሪ​ኮን ዙሪያ፥ እስከ ሴይር ዙሪያ ያለ​ው​ንም የፊ​ን​ቆ​ንን ከተማ አሳ​የው፤</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ ብዬ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም የማ​ል​ሁ​ላ​ቸው ምድር ይህች ናት፤ እነ​ሆም፥ በዐ​ይ​ንህ እን​ድ​ታ​ያት አደ​ረ​ግ​ሁህ፤ ነገር ግን ወደ​ዚ​ያች አት​ገ​ባም” አለው።</verse>
				<verse number="5">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በዚያ በሞ​ዓብ ምድር ሞተ።</verse>
				<verse number="6">በቤተ ፌጎ​ርም አቅ​ራ​ቢያ በና​ባው ምድር ቀበ​ሩት፤ እስከ ዛሬም ድረስ መቃ​ብ​ሩን ማንም የሚ​ያ​ውቅ የለም።</verse>
				<verse number="7">ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድ​ሜዉ መቶ ሃያ ዓመት ነበረ፤ ዐይ​ኖ​ቹም አል​ፈ​ዘ​ዙም፤ ጕል​በ​ቱም አል​ደ​ከ​መም ነበር።</verse>
				<verse number="8">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በዮ​ር​ዳ​ኖስ በኢ​ያ​ሪኮ አቅ​ራ​ቢያ በሞ​ዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን ለሙሴ አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ ለሙ​ሴም ያለ​ቀ​ሱ​ለት የል​ቅ​ሶው ወራት ተፈ​ጸመ።</verse>
				<verse number="9">ሙሴም እጆ​ቹን ስለ ጫነ​በት የነዌ ልጅ ኢያሱ የጥ​በ​ብን መን​ፈስ ተሞላ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ታዘ​ዙ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለፊት እንደ ተና​ገ​ረው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አል​ተ​ነ​ሣም፤</verse>
				<verse number="11">በግ​ብፅ ምድር በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ሁሉ ላይ፥ በም​ድ​ሪ​ቱም ሁሉ ላይ ምል​ክ​ት​ንና ድን​ቅን ያደ​ርግ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ላከው ያለ፥</verse>
				<verse number="12">በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት በታ​ላቅ ተአ​ምር ሁሉና በጸ​ናች እጅ፥ በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ ሁሉ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ አል​ተ​ነ​ሣም።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="6">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሙ​ሴን አገ​ል​ጋይ የነ​ዌን ልጅ ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“አገ​ል​ጋዬ ሙሴ ሞቶ​አል፤ አሁ​ንም አን​ተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ​ም​ሰ​ጣ​ቸው ምድር ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ።</verse>
				<verse number="3">ለሙሴ እንደ ነገ​ር​ሁት የእ​ግ​ራ​ችሁ ጫማ የሚ​ረ​ግ​ጠ​ውን ቦታ ሁሉ ለእ​ና​ንተ ሰጥ​ቼ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">ከሊ​ባ​ኖስ ፊት ለፊት ምድረ በዳ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ድረስ የኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያን ምድር ሁሉ እስከ ፀሐይ መግ​ቢያ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ወሰ​ና​ችሁ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="5">በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ የሚ​ቋ​ቋ​ምህ የለም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ነበ​ርሁ እን​ዲሁ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ አል​ጥ​ል​ህም፥ ቸልም አል​ል​ህም።</verse>
				<verse number="6">ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ የማ​ል​ሁ​ላ​ቸ​ውን ምድር ለዚህ ሕዝብ ታወ​ር​ሳ​ለ​ህና ጽና፥ በርታ።</verse>
				<verse number="7">አገ​ል​ጋዬ ሙሴ እንደ አዘ​ዘህ ሕግን ሁሉ ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ ጽና፤ እጅ​ግም በርታ፤ ሁሉን እን​ዴት እን​ደ​ም​ት​ሠራ ታውቅ ዘንድ ከእ​ርሱ ወደ ቀኝ ወደ ግራም አት​በል።</verse>
				<verse number="8">የዚህ ሕግ መጽ​ሐፍ ከአ​ፍህ አይ​ለይ፤ ነገር ግን የተ​ጻ​ፈ​በ​ትን ሁሉ ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ በቀ​ንም በሌ​ሊ​ትም አን​ብ​በው፤ የዚ​ያን ጊዜም መን​ገ​ድህ ይቀ​ና​ል​ሃል፤ አስ​ተ​ዋ​ይም ትሆ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="9">እነሆ አዝ​ዝ​ሃ​ለሁ፤ በም​ት​ሄ​ድ​በት ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና ጽና፥ በርታ፤ አት​ፍራ፥ አት​ደ​ን​ግ​ጥም።”</verse>
				<verse number="10">ኢያ​ሱም የሕ​ዝ​ቡን ጻፎች እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፦</verse>
				<verse number="11">“በሰ​ፈሩ መካ​ከል ዕለፉ፥ ሕዝ​ቡ​ንም፦ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር እስከ ሦስት ቀን ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ራ​ችሁ ልት​ወ​ር​ሱ​አት ትገ​ቡ​ባ​ታ​ላ​ች​ሁና ስን​ቃ​ች​ሁን አዘ​ጋጁ ብላ​ችሁ እዘ​ዙ​አ​ቸው።”</verse>
				<verse number="12">ኢያ​ሱም ሮቤ​ል​ንና ጋድን የም​ና​ሴ​ንም ነገድ እኩ​ሌታ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦</verse>
				<verse number="13">“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ እን​ዲህ ብሎ ያዘ​ዛ​ች​ሁን ቃል አስቡ፦ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሳ​ር​ፋ​ች​ኋል፤ ይህ​ች​ንም ምድር ይሰ​ጣ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="14">ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁና ልጆ​ቻ​ችሁ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሙሴ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሰ​ጣ​ችሁ በዚች ምድር ይቀ​መጡ፤ እና​ንተ፥ ጽኑ​ዓን ሁሉ ግን ታጥ​ቃ​ችሁ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ፊት ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም ተዋ​ጉ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ እና​ንተ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን እስ​ኪ​ያ​ሳ​ርፍ ድረስ፥ እነ​ር​ሱም ደግሞ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ምድር እስ​ኪ​ወ​ርሱ ድረስ፤ ከዚ​ያም በኋላ ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ በፀ​ሐይ መውጫ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ሰጣ​ችሁ ወደ ርስ​ታ​ችሁ ምድር ትገ​ባ​ላ​ችሁ፤ ትወ​ር​ሱ​አ​ት​ማ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="16">እነ​ር​ሱም ለኢ​ያሱ እን​ዲህ ብለው መለ​ሱ​ለት፥ “ያዘ​ዝ​ኸ​ንን ነገር ሁሉ እና​ደ​ር​ጋ​ለን ወደ​ም​ት​ል​ከ​ንም ስፍራ እን​ሄ​ዳ​ለን።</verse>
				<verse number="17">በሁ​ሉም ለሙሴ እንደ ታዘ​ዝን እን​ዲሁ ለአ​ንተ ደግሞ እን​ታ​ዘ​ዛ​ለን፤ ብቻ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ ከአ​ንተ ጋር ይሁን።</verse>
				<verse number="18">ለአ​ንተ የማ​ይ​ታ​ዘዝ፥ የም​ታ​ዝ​ዘ​ው​ንም ቃል የማ​ይ​ሰማ ሁሉ፥ እርሱ ይገ​ደል፤ አሁ​ንም ጽና፥ በርታ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">የነ​ዌም ልጅ ኢያሱ፥ “ውጡና ምድ​ሪ​ቱን ኢያ​ሪ​ኮን እዩ” ብሎ ከሰ​ጢም ሁለት ጐል​ማ​ሶች ሰላ​ዮ​ችን በስ​ውር ላከ። እነ​ዚ​ያም ሁለት ጐል​ማ​ሶች ሄዱ፤ ወደ ኢያ​ሪ​ኮም ደረሱ፤ ረዓብ ወደ​ሚ​ሉ​አ​ትም ዘማ ቤት ገቡ፤ በዚ​ያም ዐደሩ።</verse>
				<verse number="2">ለኢ​ያ​ሪ​ኮም ንጉሥ፥ “እነሆ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሰላ​ዮች ሀገ​ራ​ች​ንን ሊሰ​ልሉ ወደ​ዚህ በሌ​ሊት ገቡ” ብለው ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="3">የኢ​ያ​ሪ​ኮም ንጉሥ፥ “ሀገ​ራ​ች​ንን ሁሉ ሊሰ​ልሉ መጥ​ተ​ዋ​ልና ወደ አንቺ የመ​ጡ​ትን በዚ​ችም ሌሊት ወደ ቤትሽ የገ​ቡ​ትን ሰዎች አውጪ በሉ​አት” ብሎ ወደ ረዓብ ላከ።</verse>
				<verse number="4">ሴቲ​ቱም ሁለ​ቱን ሰዎች ወስዳ ሸሸ​ገ​ቻ​ቸው፤ እር​ስ​ዋም፥ “አዎን፥ ሰዎቹ ወደ እኔ መጡ፤ ከወ​ዴት እንደ ሆኑ ግን አላ​ወ​ቅ​ሁም፤</verse>
				<verse number="5">በሩም ሲዘጋ፥ ሲጨ​ል​ምም ሰዎቹ ወጡ፤ ወዴት እንደ ሄዱ አላ​ው​ቅም፤ ፈጥ​ና​ችሁ ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው፤ ምን​አ​ል​ባት ታገ​ኙ​አ​ቸው ይሆ​ናል” አለ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">እር​ስዋ ግን ወደ ሰገ​ነቱ አው​ጥታ በተ​ከ​መረ እን​ጨት መካ​ከል በቀ​ር​ከሃ ጠቅ​ልላ ደብ​ቃ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="7">ሰዎ​ቹም ወደ ዮር​ዳ​ኖስ መሻ​ገ​ሪያ በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው፤ በሩም ተቈ​ለፈ።</verse>
				<verse number="8">እነ​ዚ​ህም ሳይ​ተኙ ሴቲቱ ወደ እነ​ርሱ ወደ ሰገ​ነቱ ወጣች።</verse>
				<verse number="9">ሰዎ​ቹ​ንም እን​ዲህ አለ​ቻ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ሪ​ቱን አሳ​ልፎ እንደ ሰጣ​ችሁ ዐወ​ቅሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እና​ን​ተን መፍ​ራ​ት​ን በ​ላ​ያ​ችን አም​ጥ​ት​ዋ​ልና፥ በም​ድ​ሪ​ቱም የሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ከፊ​ታ​ችሁ የተ​ነሣ ቀል​ጠ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="10">ከግ​ብፅ ምድር በወ​ጣ​ችሁ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኤ​ር​ት​ራን ባሕር በፊ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ደ​ረቀ፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ በነ​በ​ሩት፥ እና​ን​ተም ፈጽ​ማ​ችሁ ባጠ​ፋ​ች​ኋ​ቸው በሁ​ለቱ በአ​ሞ​ራ​ው​ያን ነገ​ሥ​ታት፥ በሴ​ዎ​ንና በዐግ ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ትን ሰም​ተ​ናል።</verse>
				<verse number="11">ይህ​ንም ነገር ሰም​ተን በል​ባ​ችን ደነ​ገ​ጥን፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላይ በሰ​ማይ፥ በታ​ችም በም​ድር እርሱ አም​ላክ ነውና ከእ​ና​ንተ የተ​ነሣ ከእኛ የአ​ን​ዱም እን​ኳን ነፍስ አል​ቀ​ረም።</verse>
				<verse number="12">አሁ​ንም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማሉ​ልኝ፤ እኔ ለእ​ና​ንተ ቸር​ነት እንደ አደ​ረ​ግሁ እና​ንተ ደግሞ ለአ​ባቴ ቤት ቸር​ነት እን​ድ​ታ​ደ​ርጉ፥ በእ​ው​ነት ምል​ክት ስጡኝ።</verse>
				<verse number="13">የአ​ባ​ቴን ቤት፥ እና​ቴ​ንም፥ ወን​ድ​ሞ​ቼ​ንና ቤቴ​ንም ሁሉ፥ ያላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አድኑ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ን​ንም ከሞት አድኑ።”</verse>
				<verse number="14">ሰዎ​ቹም፥ “ሕይ​ወ​ታ​ች​ንን ስለ እና​ንተ አሳ​ል​ፈን ለሞት እን​ሰ​ጣ​ለን” አሉ፤ እር​ስ​ዋም አለች፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ሪ​ቱን በሰ​ጣ​ችሁ ጊዜ ቸር​ነ​ት​ንና ጽድ​ቅን ታደ​ር​ጉ​ል​ና​ላ​ችሁ።” ሰዎ​ቹም፥ “ይህን ነገ​ራ​ች​ንን ባት​ገ​ልጪ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሀገ​ራ​ች​ሁን በእ​ው​ነት አሳ​ልፎ ከሰ​ጠን ከአ​ንቺ ጋር ቸር​ነ​ትን እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አሏት።</verse>
				<verse number="15">ቤቷም በከ​ተማ ቅጥር የተ​ጠጋ ነበ​ረና፥ እር​ስ​ዋም በቅ​ጥሩ ላይ ተቀ​ምጣ ነበ​ርና በመ​ስ​ኮቱ በገ​መድ አወ​ረ​ደ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">እር​ስ​ዋም፥ “የሚ​ከ​ተ​ሉ​አ​ችሁ እን​ዳ​ያ​ገ​ኙ​አ​ችሁ ወደ ተራ​ራው ሂዱ፤ የሚ​ከ​ተ​ሉ​አ​ች​ሁም እስ​ከ​ሚ​መ​ለሱ ድረስ በዚያ ሦስት ቀን ተሰ​ው​ራ​ችሁ ተቀ​መጡ፤ በኋ​ላም መን​ገ​ዳ​ች​ሁን ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ” አለ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">ሰዎ​ቹም አሉ​አት፥ “እኛ ከዚህ ካማ​ል​ሽን መሐላ ንጹ​ሓን እን​ሆ​ና​ለን።</verse>
				<verse number="18">እነሆ፥ እኛ ወደ ሀገሩ በገ​ባን ጊዜ ይህን ቀይ ፈትል እኛን ባወ​ረ​ድ​ሽ​በት መስ​ኮት በኩል እሰ​ሪው፤ አባ​ት​ሽ​ንም፥ እና​ት​ሽ​ንም፥ ወን​ድ​ሞ​ች​ሽ​ንም፥ የአ​ባ​ት​ሽ​ንም ቤተ ሰብ ሁሉ ወደ አንቺ ወደ ቤትሽ ሰብ​ስቢ።</verse>
				<verse number="19">ከቤ​ት​ሽም ደጅ ወደ ሜዳ የሚ​ወጣ ሁሉ ደሙ በራሱ ላይ ይሆ​ናል፤ እኛም ከዚህ ካማ​ል​ሽን መሐላ ንጹ​ሓን እን​ሆ​ና​ለን፤ ነገር ግን ከአ​ንቺ ጋር በቤ​ትሽ ውስጥ ያለ ቢሞት ደሙ በእኛ ላይ ነው።</verse>
				<verse number="20">ነገር ግን ይህን ነገ​ራ​ች​ንን ብት​ገ​ልጪ ከዚህ ካማ​ል​ሽን መሐላ ንጹ​ሓን እን​ሆ​ና​ለን።”</verse>
				<verse number="21">እር​ስ​ዋም፥ “እንደ ቃላ​ችሁ ይሁን” አለች፤ አሰ​ና​በ​ተ​ቻ​ቸ​ውም፤ እነ​ር​ሱም ሄዱ፤ ቀዩ​ንም ፈትል በመ​ስ​ኮቱ በኩል አን​ጠ​ለ​ጠ​ለ​ችው።</verse>
				<verse number="22">እነ​ር​ሱም ወጥ​ተው ወደ ተራ​ራው ሄዱ፤ የሚ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውና የሚ​ፈ​ል​ጉ​አ​ቸ​ውም እስ​ኪ​መ​ለሱ ሦስት ቀን በዚያ ተቀ​መጡ፤ በመ​ን​ገ​ዱም አላ​ገ​ኙ​አ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="23">ሁለ​ቱም ጐል​ማ​ሶች ተመ​ለሱ፤ ከተ​ራ​ራ​ውም ወር​ደው ተሻ​ገሩ፤ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ መጡ፤ የደ​ረ​ሰ​ባ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አወ​ሩ​ለት።</verse>
				<verse number="24">ኢያ​ሱ​ንም፥ “በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሀገ​ሩን ሁሉ በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አል፤ በዚ​ያች ምድር የሚ​ኖሩ አሕ​ዛብ ሁሉ ከእኛ የተ​ነሣ ደነ​ገጡ” አሉት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ኢያ​ሱም ማልዶ ተነሣ፤ እር​ሱና እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ከሰ​ጢም ተጕ​ዘው ወደ ዮር​ዳ​ኖስ መጡ፤ ሳይ​ሻ​ገ​ሩም በዚያ አደሩ።</verse>
				<verse number="2">ከሦ​ስት ቀንም በኋላ ጸሓ​ፊ​ዎች በሰ​ፈሩ መካ​ከል ገቡ።</verse>
				<verse number="3">ለሕ​ዝ​ቡም እን​ዲህ ብለው ዐወጁ፥ “የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ሌዋ​ው​ያ​ንና ካህ​ናት ተሸ​ክ​መ​ውት ባያ​ችሁ ጊዜ፥ ከሰ​ፈ​ራ​ችሁ ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ተከ​ተ​ሉት።</verse>
				<verse number="4">በእ​ና​ን​ተና በታ​ቦቱ መካ​ከል ያለው ርቀት በስ​ፍር ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ይሁን፤ በዚህ መን​ገድ በፊት አል​ሄ​ዳ​ች​ሁ​በ​ት​ምና የም​ት​ሄ​ዱ​በ​ትን መን​ገድ እን​ድ​ታ​ውቁ ወደ ታቦቱ አት​ቅ​ረቡ።”</verse>
				<verse number="5">ኢያ​ሱም ሕዝ​ቡን፥ “ነገ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ድንቅ ነገር ያደ​ር​ጋ​ልና ራሳ​ች​ሁን አንጹ” አለ።</verse>
				<verse number="6">ኢያ​ሱም ካህ​ና​ቱን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ክ​ማ​ችሁ በሕ​ዝቡ ፊት ሂዱ” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ክ​መው በሕ​ዝቡ ፊት ሄዱ።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እን​ዲሁ ከአ​ንተ ጋር መሆ​ኔን ያውቁ ዘንድ በዚህ ቀን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደ​ር​ግህ ዘንድ እጀ​ም​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">አሁ​ንም አንተ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የሚ​ሸ​ከ​ሙ​ትን ካህ​ናት በዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ዳር ስት​ደ​ርሱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ውስጥ ቁሙ ብለህ እዘዝ” አለው።</verse>
				<verse number="9">ኢያ​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ “ወደ​ዚህ ቀር​ባ​ችሁ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ” አለ።</verse>
				<verse number="10">ኢያ​ሱም አለ፥ “ሕያው አም​ላክ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እንደ ሆነ፥ እር​ሱም ከፊ​ታ​ችሁ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ውን፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ፈጽሞ እን​ዲ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው በዚህ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="11">እነሆ፥ የም​ድር ሁሉ ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት በፊ​ታ​ችሁ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="12">አሁ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ዐሥራ ሁለት ሰዎ​ችን ምረጡ፤ ከየ​ነ​ገዱ አንድ አንድ ሰው ይሁን።</verse>
				<verse number="13">እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ የም​ድ​ርን ሁሉ ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት እግር ጫማ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ውስጥ ሲቆም፥ የዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ይደ​ር​ቃል፤ ከላይ የሚ​ወ​ር​ደ​ውም ውኃ ይቆ​ማል።”</verse>
				<verse number="14">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሕዝቡ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ሊሻ​ገሩ ከየ​ድ​ን​ኳ​ና​ቸው በወጡ ጊዜ፥ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት በሕ​ዝቡ ፊት ይሄዱ ነበር።</verse>
				<verse number="15">እንደ ክረ​ም​ትና እንደ መከር ወራት ሁሉ ዮር​ዳ​ኖስ እስከ ወሰኑ ሞልቶ ነበ​ርና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸ​ካ​ሚ​ዎቹ ወደ ዮር​ዳ​ኖስ በገቡ ጊዜ፥ ታቦ​ቱን የተ​ሸ​ከ​ሙት የካ​ህ​ናቱ እግ​ሮች በው​ኃዉ ዳር ሲጠ​ልቁ፥</verse>
				<verse number="16">ከላይ የሚ​ወ​ር​ደው ውኃ ቆመ፤ እስከ ቀር​ያ​ት​ያ​ርም አው​ራጃ እጅግ ርቆ እንደ ግድ​ግዳ ቆመ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚ​ወ​ር​ደው ውኃም ፈጽሞ ደረቀ፤ ሕዝ​ቡም በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት ቆሙ።</verse>
				<verse number="17">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል በደ​ረቅ መሬት ጸን​ተው ቆመው ነበር፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ፈጽ​መው እስ​ኪ​ሻ​ገሩ ድረስ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ በደ​ረቅ መሬት ተሻ​ገሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሕዝቡ ሁሉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ፈጽ​መው በተ​ሻ​ገሩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“ከሕ​ዝቡ ከየ​ነ​ገዱ አንድ አንድ ሰው፥ ዐሥራ ሁለት ሰዎ​ችን ውሰድ፦</verse>
				<verse number="3">በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል የካ​ህ​ናት እግር ከቆ​መ​በት ስፍራ ዐሥራ ሁለት ቀላል ድን​ጋ​ዮ​ችን እን​ዲ​ያ​ነሡ እዘ​ዛ​ቸው፤ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ውሰ​ዱ​አ​ቸው፤ ከዚ​ያም ሌሊት በም​ታ​ድ​ሩ​በት ቦታ በየ​ነ​ገ​ዳ​ችሁ ጠብ​ቋ​ቸው።”</verse>
				<verse number="4">ኢያ​ሱም ከየ​ነ​ገዱ አንድ አንድ ሰው፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የታ​ወ​ቁ​ትን ዐሥራ ሁለት ሰዎች ጠራ።</verse>
				<verse number="5">ኢያ​ሱም አላ​ቸው፥ “በእ​ኔና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ ዮር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ዕለፉ፤ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው በዐ​ሥራ ሁለቱ ነገደ እስ​ራ​ኤል ቍጥር በት​ከ​ሻው ላይ አንድ አንድ ድን​ጋይ ከዚያ ይሸ​ከም።</verse>
				<verse number="6">እነ​ዚ​ህም ምል​ክት ይሆ​ኑ​ላ​ች​ኋል፤ ልጅህ ነገ፦ ‘እነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮች ምን​ድን ናቸው?’ ብሎ በጠ​የ​ቀህ ጊዜ፥ ልጅ​ህን እን​ዲህ ትለ​ዋ​ለህ፦</verse>
				<verse number="7">አንተ በም​ድር ሁሉ ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ስን​ሻ​ገር የዮ​ር​ዳ​ኖስ ወንዝ ስለ ደረቀ ነው፤ እነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮ​ችም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለዘ​ለ​ዓ​ለም መታ​ሰ​ቢያ ይሆ​ናሉ።”</verse>
				<verse number="8">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ኢያሱ እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዮር​ዳ​ኖ​ስን አካ​ት​ተው በተ​ሻ​ገሩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን እንደ አዘ​ዘው በእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ቍጥር ከዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ዐሥራ ሁለት ድን​ጋ​ዮች አን​ሥ​ተው ወደ ሰፈ​ራ​ቸው ወሰዱ፤ በዚ​ያም አኖ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ኢያ​ሱም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት እግ​ሮች በቆ​ሙ​በት ስፍራ በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ሌሎች ዐሥራ ሁለት ድን​ጋ​ዮ​ችን አቆመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።</verse>
				<verse number="10">ኢያ​ሱም ለሕ​ዝቡ እን​ዲ​ነ​ግር፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ እስ​ኪ​ፈ​ጽም ድረስ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ቆመው ነበር፤ ሕዝ​ቡም ፈጥ​ነው ተሻ​ገሩ።</verse>
				<verse number="11">ሕዝ​ቡም ሁሉ አካ​ት​ተው በተ​ሻ​ገሩ ጊዜ ታቦተ ሕጉ ተሻ​ገ​ረች፤ እነ​ዚ​ያም ድን​ጋ​ዮች በፊ​ታ​ቸው ተሻ​ገሩ።</verse>
				<verse number="12">ሙሴም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው የሮ​ቤል ልጆች፥ የጋ​ድም ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ታጥ​ቀው በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ተሻ​ገሩ።</verse>
				<verse number="13">አርባ ሺህ ያህል ለጦ​ር​ነት የታ​ጠቁ ሰዎች የኢ​ያ​ሪ​ኮን ሀገር ይወጉ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተሻ​ገሩ።</verse>
				<verse number="14">በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ፊት ከፍ አደ​ረ​ገው፤ ሙሴ​ንም እንደ ፈሩ በዕ​ድ​ሜው ሁሉ ፈሩት።</verse>
				<verse number="15">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="16">“የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የሚ​ሸ​ከ​ሙ​ትን ካህ​ናት ከዮ​ር​ዳ​ኖስ እን​ዲ​ወጡ እዘ​ዛ​ቸው።”</verse>
				<verse number="17">ኢያ​ሱም ካህ​ና​ቱን፥ “ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ውጡ” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የቃል ኪዳን ታቦተ ሕግ የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት ከዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል በወጡ ጊዜ፥ በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም የብስ በረ​ገጡ ጊዜ፥ የዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ተወ​ር​ውሮ ወደ ስፍ​ራው ተመ​ለሰ፤ ቀድ​ሞም እንደ ነበረ ሂዶ ዳር እስከ ዳር ሞላ።</verse>
				<verse number="19">ሕዝ​ቡም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ወጡ፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም በም​ሥ​ራቅ በኩል በጌ​ል​ገላ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="20">ኢያ​ሱም ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ውስጥ የወ​ሰ​ዱ​አ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ያን ዐሥራ ሁለ​ቱን ድን​ጋ​ዮች በጌ​ል​ገላ አቆ​ማ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">ኢያ​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፥ “ልጆ​ቻ​ችሁ፦ ‘እነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮች ምን​ድን ናቸው?’ ብለው በሚ​ጠ​ይ​ቋ​ችሁ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="22">ለል​ጆ​ቻ​ችሁ እን​ዲህ ብላ​ችሁ ትነ​ግ​ሯ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፦ ‘እስ​ራ​ኤል ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን በደ​ረቅ ተሻ​ገረ፤’</verse>
				<verse number="23">እስ​ክ​ና​ልፍ ድረስ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኤ​ር​ት​ራን ባሕር ከፊ​ታ​ችን እን​ዳ​ደ​ረቀ እን​ዲሁ እስ​ክ​ን​ሻ​ገር ድረስ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስን ውኃ ከፊ​ታ​ችን አደ​ረቀ።</verse>
				<verse number="24">ይኸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ጠን​ካራ እንደ ሆነች የም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ እን​ዲ​ያ​ውቁ፥ አም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በሥ​ራው ሁሉ እን​ድ​ት​ፈሩ ነው።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በባ​ሕር በኩል የነ​በ​ሩት የአ​ሞ​ራ​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ፥ በባ​ሕ​ሩም አጠ​ገብ የነ​በሩ የፊ​ኒ​ቃ​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስን ውኃ እስ​ኪ​ሻ​ገሩ ድረስ እን​ዳ​ደ​ረቀ በሰሙ ጊዜ፥ ልባ​ቸው ቀለጠ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የተ​ነሣ አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን ሳቱ።</verse>
				<verse number="2">በዚ​ያን ጊዜም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን፥ “ከሻፎ ድን​ጋይ የባ​ል​ጩት መቍ​ረጫ ሠር​ተህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ዳግ​መኛ ግረ​ዛ​ቸው” አለው።</verse>
				<verse number="3">ኢያ​ሱም የባ​ል​ጩት መቍ​ረጫ ሠርቶ የግ​ር​ዛት ኮረ​ብታ በተ​ባለ ስፍራ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ገረዘ።</verse>
				<verse number="4">ኢያሱ ሕዝ​ቡን ሁሉ የገ​ረ​ዘ​በት ምክ​ን​ያት ይህ ነው፤ ከግ​ብፅ የወጡ ወን​ዶች ተዋ​ጊ​ዎች ሁሉ ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ በመ​ን​ገድ ላይ በም​ድረ በዳ ሞቱ፤ የወ​ጡ​ትም ወን​ዶች ሁሉ ተገ​ር​ዘው ነበር።</verse>
				<verse number="5">ነገር ግን ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ በመ​ን​ገድ፥ በም​ድረ በዳ የተ​ወ​ለዱ ሕዝብ ሁሉ አል​ተ​ገ​ረ​ዙም ነበ​ርና፥ ኢያሱ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ገረ​ዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ለእኛ ይሰ​ጠን ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ምድር እን​ደ​ማ​ያ​ሳ​ያ​ቸው የማ​ለ​ባ​ቸ​ውን፥ ከግ​ብፅ የወጡ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ያል​ሰሙ፥ እነ​ዚያ ተዋ​ጊ​ዎች ሁሉ እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አርባ ዓመት በመ​ድ​በራ ምድረ በዳ ይዞሩ ነበር።</verse>
				<verse number="7">ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ነ​ርሱ ፋንታ አስ​ነሣ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ኢያሱ ገረ​ዛ​ቸው፤ በመ​ን​ገድ ስለ​ተ​ወ​ለዱ አል​ተ​ገ​ረ​ዙም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="8">በተ​ገ​ረ​ዙም ጊዜ እስ​ኪ​ድኑ ድረስ በሰ​ፈር ውስጥ ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “ዛሬ የግ​ብ​ፅን ተግ​ዳ​ሮት ከእ​ና​ንተ ላይ አስ​ወ​ግ​ጃ​ለሁ” አለው፤ ስለ​ዚህ የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌል​ገላ ተብሎ ተጠራ።</verse>
				<verse number="10">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በጌ​ል​ገላ ሰፈሩ፤ ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን በመሸ ጊዜ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በኢ​ያ​ሪኮ ምዕ​ራብ ፋሲ​ካን አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="11">ከም​ድ​ሪ​ቱም ፍሬ ቂጣና አዲስ እህል በዚ​ያው ቀን በሉ።</verse>
				<verse number="12">በነ​ጋ​ውም ከም​ድ​ሪቱ ፍሬ ከበሉ በኋላ መናው ቀረ፤ ከዚ​ያም በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዳግ​መኛ መና አላ​ገ​ኙም፤ በዚ​ያው ዓመት የፊ​ኒ​ቆ​ንን ምድር ፍሬ ሰበ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="13">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ኢያሱ በኢ​ያ​ሪኮ አጠ​ገብ ሳለ ዐይ​ኑን አን​ሥቶ ተመ​ለ​ከተ፤ እነ​ሆም፥ የተ​መ​ዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያ​ሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን ወገን ነህ?” አለው።</verse>
				<verse number="14">እር​ሱም፥ “እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠራ​ዊት አለቃ ነኝ፤ አሁ​ንም ወደ አንተ መጥ​ቼ​አ​ለሁ” አለ። ኢያ​ሱም ወደ ምድር በግ​ም​ባሩ ተደ​ፍቶ ሰገ​ደና፥ “በባ​ሪ​ያህ ዘንድ ምን አቁ​ሞ​ሃል?” አለው።</verse>
				<verse number="15">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሠራ​ዊት አለቃ ኢያ​ሱን፥ “አንተ የቆ​ም​ህ​በት ስፍራ የተ​ቀ​ደሰ ነውና ጫማ​ህን ከእ​ግ​ርህ አው​ልቅ” አለው። ኢያ​ሱም እን​ዲሁ አደ​ረገ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">ኢያ​ሪ​ኮም በግ​ንብ ታጥራ ተዘ​ግታ ነበር፤ ወደ እር​ስዋ የሚ​ገባ፥ ከእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ወጣ አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን አለው፥ “እነሆ፥ ኢያ​ሪ​ኮ​ንና ንጉ​ሥ​ዋን ጽኑ​ዓን፥ ኀያ​ላ​ን​ዋ​ንም በእ​ጅህ ሰጥ​ቼ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">አን​ተም ተዋ​ጊ​ዎ​ችን ሁሉ በዙ​ሪ​ያው አሰ​ል​ፋ​ቸው። ተዋ​ጊ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዙሪያ አንድ ጊዜ ይዙሩ፤ እን​ዲ​ሁም ስድ​ስት ቀን አድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="4">ሰባ​ትም ካህ​ናት ሰባት ቀንደ መለ​ከት በታ​ቦቱ ፊት ይያዙ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ፤ ካህ​ና​ቱም ቀንደ መለ​ከ​ቱን ይንፉ።</verse>
				<verse number="5">ቀንደ መለ​ከ​ቱም ባለ​ማ​ቋ​ረጥ ሲነፋ፥ የመ​ለ​ከ​ቱን ድምፅ ስት​ሰሙ፥ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኹ፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ቅጥር ይወ​ድ​ቃል፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ፊት ለፊት እየ​ሮጠ ይገ​ባ​ባ​ታል።”</verse>
				<verse number="6">የነ​ዌም ልጅ ኢያሱ ካህ​ና​ቱን ጠርቶ፥ “የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ከሙ፤ ሰባ​ትም ካህ​ናት ሰባት ቀንደ መለ​ከት ወስ​ደው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት ይሂዱ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">ሕዝ​ቡ​ንም፥ “ሂዱ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ዙሩ፤ ተዋ​ጊ​ዎ​ችም ከጦር መሣ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት ይሂዱ ብላ​ችሁ እዘ​ዙ​አ​ቸው” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ይሄዱ ዘንድ ኢያሱ እንደ ነገ​ራ​ቸው ሰባቱ ካህ​ናት የተ​ቀ​ደሱ ሰባ​ቱን ቀንደ መለ​ከት ይዘው ሄዱ፤ በሄ​ዱም ጊዜ አሰ​ም​ተው በም​ል​ክት ነፉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሕጉ ታቦት ትከ​ተ​ላ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="9">ሰል​ፈ​ኞ​ችም ፊት ፊት ይሄዱ ነበር፤ ካህ​ና​ቱም ነጋ​ሪት ይመቱ ነበር፤ ከታ​ቦቱ በኋላ ይከ​ተሉ የነ​በ​ሩ​ትም ቀንደ መለ​ከ​ቱን እየ​ነፉ ይሄዱ ነበር።</verse>
				<verse number="10">ኢያ​ሱም ሕዝ​ቡን፦ እን​ዳ​ይ​ጮኹ ማንም ድም​ፃ​ቸ​ውን እን​ዳ​ይ​ሰማ፥ እን​ዲ​ጮኹ እስ​ኪ​ያ​ዛ​ቸ​ውም ድረስ ከአ​ፋ​ቸው ቃል እን​ዳ​ይ​ወጣ አዘ​ዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የቃል ኪዳኑ ታቦት ሄደች፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ዞረች፤ ወደ ሰፈ​ርም ተመ​ልሳ በዚያ አደ​ረች።</verse>
				<verse number="12">ኢያ​ሱም በማ​ግ​ሥቱ ማለዳ ተነሣ፤ ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሕ​ጉን ታቦት ተሸ​ከሙ።</verse>
				<verse number="13">ሰባ​ቱም ካህ​ናት ሰባ​ቱን ቀንደ መለ​ከት ይዘው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት ይሄዱ ነበር፤ ቀንደ መለ​ከ​ቱ​ንም ይነፉ ነበር፤ ተዋ​ጊ​ዎ​ችም በፊ​ታ​ቸው ይሄዱ ነበር፤ የቀ​ሩ​ትም ሕዝብ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳን ታቦት በኋላ ይሄዱ ነበር፤ ካህ​ና​ቱም ቀንደ መለ​ከ​ቱን ይነፉ ነበር።</verse>
				<verse number="14">በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን የቀ​ረው ሕዝብ ሁሉ ከተ​ማ​ዪ​ቱን አንድ ጊዜ ዞረው ወደ ሰፈር ተመ​ለሱ፤ ስድ​ስት ቀንም እን​ዲህ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="15">በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን በነጋ ጊዜ ማል​ደው ተነሡ፤ እን​ደ​ዚ​ህም ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰባት ጊዜ ዞሩ፤ በዚ​ያም ቀን ብቻ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰባት ጊዜ ዞሩ።</verse>
				<verse number="16">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰባት ጊዜ በዞ​ሩና ካህ​ናቱ ቀንደ መለ​ከ​ቱን በነፉ ጊዜ፤ ኢያሱ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና ጩኹ።</verse>
				<verse number="17">ከተ​ማ​ዪ​ቱም በእ​ር​ስ​ዋም ያለው ሁሉ ለሠ​ራ​ዊት ጌታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርም ይሆ​ናሉ፤ የላ​ክ​ና​ቸ​ውን መል​እ​ክ​ተ​ኞች ስለ ሸሸ​ገች ዘማ​ዊቱ ረዓብ፥ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር በቤቷ ውስጥ ያሉ ሁሉ ብቻ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራሉ።</verse>
				<verse number="18">እና​ንተ ግን እርም ብለን ከተ​ው​ነው እን​ዳ​ት​ወ​ስዱ ተጠ​ን​ቀቁ፤ ከእ​ር​ሱም ተመ​ኝ​ታ​ችሁ አት​ው​ሰዱ፤ ብት​ወ​ስዱ ግን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰፈር የተ​ረ​ገ​መች ታደ​ር​ጓ​ታ​ላ​ችሁ፤ እኛ​ንም ታጠ​ፉ​ና​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="19">ነገር ግን ብርና ወርቅ ሁሉ፥ የና​ስና የብ​ረ​ትም ዕቃ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ይሁን፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግምጃ ቤት ይግባ።”</verse>
				<verse number="20">ሕዝ​ቡም ጮኹ፥ ካህ​ና​ቱም ቀንደ መለ​ከ​ቱን ነፉ፤ ሕዝ​ቡም የቀ​ንደ መለ​ከ​ቱን ድምፅ በሰሙ ጊዜ ታላቅ ጩኸት ጮኹ፤ ቅጥ​ሩም ወደቀ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ገቡ፤ ሁሉም ወደ ፊታ​ቸው ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ሮጡ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም እጅ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="21">ኢያ​ሱም ከተ​ማ​ዋን፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ውስጥ የነ​በ​ሩ​ትን ሁሉ፥ ከወ​ንድ እስከ ሴት፥ ከሕ​ፃን እስከ ሽማ​ግሌ፥ ከበሬ እስከ በግና እስከ አህያ በሰ​ይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋ።</verse>
				<verse number="22">ኢያ​ሱም ምድ​ሪ​ቱን የሰ​ለሉ ሁለ​ቱን ሰዎች፥ “ወደ ዘማ​ዪቱ ቤት ግቡ፤ ከዚ​ያም ሴቲ​ቱ​ንና ያላ​ትን ሁሉ እን​ደ​ማ​ላ​ች​ሁ​ላት አውጡ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">እነ​ዚ​ያም ከተ​ማ​ዪ​ቱን የሰ​ለሉ ሁለቱ ጐል​ማ​ሶች ወደ ዘማ​ዪቱ ረዓብ ቤት ገብ​ተው ረዓ​ብን፥ አባ​ቷ​ንና እና​ቷን፥ ወን​ድ​ሞ​ች​ዋ​ንም፥ ያላ​ት​ንም ሁሉ፥ ቤተ ዘመ​ዶ​ች​ዋ​ንም ሁሉ አወ​ጡ​አ​ቸው፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰፈር በውጭ አስ​ቀ​መ​ጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም፥ በእ​ር​ስ​ዋም የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ በእ​ሳት አቃ​ጠሉ፤ ነገር ግን ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ የና​ሱ​ንና የብ​ረ​ቱ​ንም ዕቃ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግምጃ ቤት ውስጥ አገቡ።</verse>
				<verse number="25">ኢያ​ሪ​ኮን ሊሰ​ልሉ ኢያሱ የላ​ካ​ቸ​ው​ንም መል​እ​ክ​ተ​ኞች ስለ ሸሸ​ገች ዘማ​ዊ​ቱን ረዓ​ብን፥ የአ​ባ​ቷ​ንም ቤተ ሰብ፥ ያላ​ት​ንም ሁሉ ኢያሱ አዳ​ና​ቸው፤ እር​ስ​ዋም በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል እስከ ዛሬ ድረስ ተቀ​ም​ጣ​ለች።</verse>
				<verse number="26">በዚ​ያ​ችም ቀን ኢያሱ፥ “ይህ​ችን ከተማ ኢያ​ሪ​ኮን ለመ​ሥ​ራት የሚ​ነሣ ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ርጉም ይሁን፤ መሠ​ረ​ቷን በበ​ኵር ልጁ የሚ​ጥል፥ በሮ​ች​ዋ​ንም በታ​ናሹ ልጁ የሚ​ያ​ቆም ርጉም ይሁን” ብሎ ማለ።</verse>
				<verse number="27">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከኢ​ያሱ ጋር ነበረ፤ ስሙም በም​ድር ሁሉ ላይ ደረሰ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን እርም በሆ​ነው ነገር ታላቅ በደል በደሉ፤ ከይ​ሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እር​ሱም የከ​ርሚ ልጅ፥ የዘ​ን​በሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ እርም ከሆ​ነው ነገር ወሰደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ተቈጣ።</verse>
				<verse number="2">ኢያ​ሱም ከቤ​ቴል በም​ሥ​ራቅ በኩል በቤ​ት​አ​ዊን አጠ​ገብ ወዳ​ለ​ችው ወደ ጋይ ሰዎ​ችን ከኢ​ያ​ሪኮ ልኮ፥ “ውጡ፤ ጋይ​ንም ሰልሉ” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ሰዎ​ቹም ወጡ፤ ጋይ​ንም ሰለሉ።</verse>
				<verse number="3">ወደ ኢያ​ሱም ተመ​ል​ሰው፥ “ሁለት ወይም ሦስት ሺህ ያህል ሰው ወጥ​ተው ጋይን ይምቱ እንጂ ሕዝቡ ሁሉ አይ​ውጣ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕዝብ ሁሉ ግን ወደ​ዚያ አት​ው​ሰድ፤ ጥቂ​ቶች ናቸ​ውና” አሉት።</verse>
				<verse number="4">ሦስት ሺህ ያህል ሰዎ​ችም ወደ​ዚያ ወጡ፤ የጋ​ይም ሰዎች አባ​ረ​ሩ​አ​ቸው፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም ሸሹ።</verse>
				<verse number="5">የጋይ ሰዎ​ችም ከእ​ነ​ርሱ ሠላሳ ስድ​ስት ሰዎ​ችን ገደሉ፤ ከበሩ ጀም​ረው እስከ አጠ​ፉ​አ​ቸው ድረስ አባ​ረ​ሩ​አ​ቸው፤ በቍ​ል​ቍ​ለ​ቱም ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ የሕ​ዝ​ቡም ልብ ደነ​ገጠ፤ እንደ ውኃም ሆነ።</verse>
				<verse number="6">ኢያ​ሱም ልብ​ሱን ቀደደ፤ እር​ሱና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደፉ፤ በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ ትቢያ ነሰ​ነሱ።</verse>
				<verse number="7">ኢያ​ሱም አለ፥ “ወዮ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን እጅ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጠን፥ ታጠ​ፋ​ንም ዘንድ አገ​ል​ጋ​ይህ ይህን ሕዝብ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ለምን አሻ​ገረ? በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ተቀ​ም​ጠን በኖ​ርን ነበር እኮ!</verse>
				<verse number="8">ጌታ ሆይ! እስ​ራ​ኤል ጀር​ባ​ውን ወደ ጠላ​ቶቹ ከመ​ለሰ እን​ግ​ዲህ ምን እላ​ለሁ?</verse>
				<verse number="9">ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም፥ በም​ድ​ሪ​ቱም የሚ​ኖሩ ሁሉ ሰም​ተው ይከ​ብ​ቡ​ናል፤ ከም​ድ​ርም ያጠ​ፉ​ናል፤ ለታ​ላቁ ስም​ህም የም​ታ​ደ​ር​ገው ምን​ድር ነው?”</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን አለው፥ “ለምን በግ​ን​ባ​ርህ ተደ​ፍ​ተ​ሃል? ተነሥ!</verse>
				<verse number="11">ሕዝቡ በድ​ለ​ዋል፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን አፍ​ር​ሰ​ዋል፤ እርም ከሆ​ነ​ውም ነገር ሰር​ቀው ወሰዱ፤ በዕ​ቃ​ቸ​ውም ውስጥ ሸሸ​ጉት።</verse>
				<verse number="12">ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ፊት መቆም አይ​ች​ሉም፤ የተ​ረ​ገሙ ስለ​ሆኑ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ፊት ይሸ​ሻሉ፤ እርም የሆ​ነ​ው​ንም ነገር ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ካላ​ጠ​ፋ​ችሁ ከዚህ በኋላ ከእ​ና​ንተ ጋር አል​ሆ​ንም።</verse>
				<verse number="13">ተነ​ሣና ሕዝ​ቡን ቀድስ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ‘እስ​ራ​ኤል ሆይ! እርም የሆነ ነገር በመ​ካ​ከ​ልህ አለ፤ እር​ምም የሆ​ነ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እስ​ክ​ታ​ጠፉ ድረስ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ፊት መቆም አት​ች​ሉም’ ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና እስከ ነገ ራሳ​ች​ሁን አንጹ።</verse>
				<verse number="14">ነገም በየ​ነ​ገ​ዳ​ችሁ ትቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ለ​የው ነገድ በየ​ወ​ገ​ኖቹ ይቀ​ር​ባል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ለ​የው ወገን በየ​ቤተ ሰቦቹ ይቀ​ር​ባል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ለ​የው ቤተ ሰብ በየ​ሰዉ ይቀ​ር​ባል።</verse>
				<verse number="15">ምል​ክት የታ​የ​በት ሰው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን አፍ​ር​ሶ​አ​ልና፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ በደል አድ​ር​ጎ​አ​ልና፥ እር​ሱና ያለው ሁሉ በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላሉ።”</verse>
				<verse number="16">ኢያ​ሱም ማልዶ ተነሣ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም በየ​ነ​ገ​ዶ​ቻ​ቸው ሰበ​ሰ​ባ​ቸው፤ በይ​ሁ​ዳም ነገድ ላይ ምል​ክት ታየ፤</verse>
				<verse number="17">የይ​ሁ​ዳም ወገ​ኖች ተለዩ፤ በዛ​ራም ወገን ምል​ክት ታየ፤ የዛ​ራም ወገን በየ​ቤተ ሰቡ ተለየ፤</verse>
				<verse number="18">በዘ​ን​በ​ሪም ወገን ምል​ክት ታየ፤ የዘ​ን​በ​ሪም ቤተ ሰብ እያ​ን​ዳ​ንዱ ተለየ፤ ከይ​ሁ​ዳም ወገን በሆነ በከ​ርሚ ልጅ በዘ​ን​በሪ ልጅ በዛራ ልጅ በአ​ካን ላይ ምል​ክት ታየ።</verse>
				<verse number="19">ኢያ​ሱም አካ​ንን፥ “ልጄ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ስጥ፤ ለእ​ር​ሱም ተና​ዘዝ፤ ያደ​ረ​ግ​ኸ​ው​ንም ንገ​ረኝ፤ አት​ሸ​ሽ​ገ​ኝም” አለው።</verse>
				<verse number="20">አካ​ንም መልሶ ኢያ​ሱን፥ “በእ​ው​ነት በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በድ​ያ​ለሁ፤ እን​ዲ​ህና እን​ዲ​ህም አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="21">በዘ​ረፋ መካ​ከል አንድ ያማረ ካባ፥ ሁለት መቶ ሰቅል ብር፥ ሚዛ​ኑም አምሳ ሰቅል የሆነ ወርቅ አይቼ ተመ​ኘ​ኋ​ቸው፤ ወሰ​ድ​ኋ​ቸ​ውም፤ እነ​ሆም በድ​ን​ኳኔ ውስጥ በመ​ሬት ተሸ​ሽ​ገ​ዋል፤ ብሩም ከሁሉ በታች ነው” አለው።</verse>
				<verse number="22">ኢያ​ሱም መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ ወደ ሰፈ​ርም ወደ ድን​ኳኑ ሮጡ፤ እነ​ሆም እርሱ በድ​ን​ኳኑ ውስጥ ተደ​ብቆ፥ ብሩም በበ​ታቹ ነበረ።</verse>
				<verse number="23">ከድ​ን​ኳ​ኑም ውስጥ አው​ጥ​ተው ወደ ኢያ​ሱና ወደ እስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ አመ​ጡት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ም​ፊት አኖ​ሩት።</verse>
				<verse number="24">ኢያ​ሱም የዛ​ራን ልጅ አካ​ንን፥ ብሩ​ንም፥ ልብ​ሱ​ንም፥ ልሳነ ወር​ቁ​ንም ወደ አኮር ሸለቆ ወሰ​ዳ​ቸው፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቹ​ንም፥ በሬ​ዎ​ቹ​ንም፥ አህ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ በጎ​ቹ​ንም፥ ድን​ኳ​ኑ​ንም፥ ንብ​ረ​ቱ​ንም ሁሉ ወደ ዔሜ​ቃ​ኮር ወሰደ።</verse>
				<verse number="25">ኢያ​ሱም፥ “ለምን አጠ​ፋ​ኸን? ዛሬ እን​ዳ​ጠ​ፋ​ኸን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ያጥ​ፋህ” አለው፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ወገ​ሩት፤ በእ​ሳ​ትም አቃ​ጠ​ሉት፤ በድ​ን​ጋ​ይም ወገ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">በላ​ዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ተመ​ለሰ። ስለ​ዚ​ህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ዔሜ​ቃ​ኮር ተብሎ ተጠራ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “አት​ፍራ፤ አት​ደ​ን​ግጥ፤ ተዋ​ጊ​ዎ​ችን ሁሉ ከአ​ንተ ጋር ውሰድ፤ ተነ​ሥ​ተ​ህም ወደ ጋይ ውጣ፤ እነሆ፥ የጋ​ይ​ንም ንጉሥ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ከተ​ማ​ው​ንም ምድ​ሩ​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">በኢ​ያ​ሪ​ኮና በን​ጉ​ሥ​ዋም እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ እን​ዲሁ በጋ​ይና በን​ጉ​ሥዋ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ የከ​ብ​ቱን ምርኮ ግን ለራ​ሳ​ችሁ ትዘ​ር​ፋ​ላ​ችሁ፤ ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በስ​ተ​ኋላ ይከ​ብ​ቧት ዘንድ ጦር ላክ” አለው።</verse>
				<verse number="3">ኢያ​ሱም፥ ተዋ​ጊ​ዎ​ቹም ሕዝብ ሁሉ ተነ​ሥ​ተው ወደ ጋይ ወጡ፤ ኢያ​ሱም ጽኑ​ዓን፥ ተዋ​ጊ​ዎ​ችና ኀያ​ላን የሆ​ኑ​ትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች መረጠ፤ በሌ​ሊ​ትም ላካ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “እነሆ፥ ሂዱና ከከ​ተ​ማ​ዪቱ በስ​ተ​ኋላ ተደ​በቁ፤ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ አት​ራቁ፤ ሁላ​ች​ሁም ተዘ​ጋ​ጅ​ታ​ችሁ ተቀ​መጡ፤</verse>
				<verse number="5">እኔ፥ ከእ​ኔም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ወደ ከተ​ማ​ዪቱ እን​ቀ​ር​ባ​ለን፤ የጋ​ይም ሰዎች እኛን ሊገ​ናኙ እንደ ፊተ​ኛው በወጡ ጊዜ ከፊ​ታ​ቸው እን​ሸ​ሻ​ለን፤</verse>
				<verse number="6">ወጥ​ተ​ውም በተ​ከ​ተ​ሉን ጊዜ ከከ​ተማ እና​ር​ቃ​ቸ​ዋ​ለን፤ እነ​ር​ሱም እንደ በፊቱ ከፊ​ታ​ችን ሸሹ ይላሉ፤ እኛም ከፊ​ታ​ቸው እን​ሸ​ሻ​ለን።</verse>
				<verse number="7">እን​ግ​ዲህ እና​ን​ተም ከተ​ደ​በ​ቃ​ች​ሁ​በት ስፍራ ተነሡ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እር​ስ​ዋን በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ልና ከተ​ማ​ዪ​ቱን ያዙ።</verse>
				<verse number="8">በያ​ዛ​ች​ኋ​ትም ጊዜ ከተ​ማ​ዪ​ቱን በእ​ሳት አቃ​ጥ​ሉ​አት፤ እንደ አል​ኋ​ችሁ አድ​ርጉ፤ እነሆ፥ አዝ​ዣ​ች​ኋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="9">ኢያ​ሱም ላካ​ቸው፤ ወደ​ሚ​ደ​በ​ቁ​በ​ትም ስፍራ ሄዱ፤ በጋ​ይና በቤ​ቴል መካ​ከ​ልም በጋይ በባ​ሕር በኩል ተቀ​መጡ፤ ኢያሱ ግን በዚ​ያች ሌሊት በሕ​ዝቡ መካ​ከል አደረ።</verse>
				<verse number="10">ኢያ​ሱም ማልዶ ተነሣ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አያ​ቸው፤ እር​ሱም፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ከሕ​ዝቡ በፊት ወደ ጋይ ወጡ።</verse>
				<verse number="11">ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ተዋ​ጊ​ዎች ሕዝብ ሁሉ ወጥ​ተው ቀረቡ፤ ወደ ከተ​ማ​ዪ​ቱም ፊት ደረሱ፤ በጋ​ይም በም​ሥ​ራቅ በኩል ሰፈሩ፤ በእ​ነ​ር​ሱና በጋ​ይም መካ​ከል ሸለቆ ነበረ።</verse>
				<verse number="12">ኢያ​ሱም አም​ስት ሺህ ሰዎ​ችን ወስዶ በቤ​ቴ​ልና በጋይ መካ​ከል በጋይ ባሕር በኩል ይከ​ብቡ ዘንድ አስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">ሕዝ​ቡም ሁሉ ሠራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን በከ​ተ​ማው መስዕ በኩል አኖሩ፤ ዳር​ቻ​ውም እስከ ከተ​ማው ባሕር ድረስ ነው፤ ኢያ​ሱም በዚ​ያች ሌሊት ወደ ሸለ​ቆው መካ​ከል ሄደ።</verse>
				<verse number="14">የጋ​ይም ንጉሥ በሰማ ጊዜ ፈጥኖ ሄደ። የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ሰዎች ወጡ፤ እር​ሱና ሕዝ​ቡም ሁሉ በተ​ወ​ሰ​ነው ጊዜ በዓ​ረባ ፊት ባለው አንድ ስፍራ እስ​ራ​ኤ​ልን በጦ​ር​ነት ተቀ​በ​ሉ​አ​ቸው፤ እርሱ ግን ከከ​ተ​ማ​ዪቱ በስ​ተ​ኋላ እንደ ተደ​በቁ አያ​ው​ቅም ነበር።</verse>
				<verse number="15">በደ​ረ​ሱ​ባ​ቸ​ውም ጊዜ ኢያ​ሱና እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከፊ​ታ​ቸው አፈ​ገ​ፈጉ፤ በም​ድረ በዳው መን​ገ​ድም ሸሹ።</verse>
				<verse number="16">የሀ​ገ​ሪ​ቱም ሰዎች ሁሉ ተጠሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ተከ​ት​ለው አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም እን​ዲ​ርቁ አደ​ረ​ጓ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">በጋ​ይና በቤ​ቴ​ልም ውስጥ እስ​ራ​ኤ​ልን ለማ​ሳ​ደድ ያል​ወጣ ሰው አል​ነ​በ​ረም፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ከፍ​ተው ተዉ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም አሳ​ደ​ዱት።</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “ጋይን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጥ​ሃ​ለ​ሁና በእ​ጅህ ያለ​ውን ጦር በላ​ይዋ ዘርጋ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም የከ​በ​ቡ​አት ፈጥ​ነው ከስ​ፍ​ራ​ቸው ይነ​ሣሉ” አለው፤ ኢያ​ሱም በከ​ተ​ማዋ ላይ በእጁ ያለ​ውን ጦር ዘረጋ።</verse>
				<verse number="19">የተ​ደ​በ​ቁ​ትም ፈጥ​ነው ከስ​ፍ​ራ​ቸው ተነሡ፤ ኢያ​ሱም እጁን በዘ​ረጋ ጊዜ ወጡ፤ ወደ ከተ​ማ​ዋም ገብ​ተው ያዙ​አት፤ ፈጥ​ነ​ውም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ሉ​አት።</verse>
				<verse number="20">የጋ​ይም ሰዎች ወደ ኋላ​ቸው ዞረው በተ​መ​ለ​ከቱ ጊዜ የከ​ተ​ማ​ዪቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወዲ​ህና ወዲያ መሸሽ አል​ቻ​ሉም፤ ወደ ምድረ በዳም የሸሹ ሕዝብ በሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ቸው ላይ ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="21">ኢያሱ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ተደ​ብ​ቀው የነ​በ​ሩት ከተ​ማ​ዪ​ቱን እንደ ያዙ፥ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ ባዩ ጊዜ ወደ​ኋላ ተመ​ል​ሰው የጋ​ይን ሰዎች ገደ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">እነ​ዚ​ያም ከከ​ተማ ወጥ​ተው ተቀ​በ​ሉ​አ​ቸው፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሠራ​ዊት መካ​ከ​ልም አገ​ቡ​አ​ቸው፤ እኒያ ከወ​ዲያ፥ እኒ​ህም ከወ​ዲህ ሆነው አንድ እን​ኳን ሳይ​ቀ​ርና ሳያ​መ​ልጥ ገደ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">የጋ​ይ​ንም ንጉሥ ሳይ​ሞት ይዘው ወደ ኢያሱ አመ​ጡት።</verse>
				<verse number="24">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተከ​ት​ለ​ዋ​ቸው በነ​በ​ረ​በት በተ​ራ​ራው ቍል​ቍ​ለ​ትና በም​ድረ በዳ የጋ​ይን ሰዎች መግ​ደ​ልን ከጨ​ረሱ፥ ሁሉ​ንም በጦር ወግ​ተው ከአ​ጠ​ፉ​አ​ቸው በኋላ ኢያሱ ወዲ​ያ​ውኑ ወደ ጋይ ተመ​ልሶ፥ በሰ​ይፍ አጠ​ፋት።</verse>
				<verse number="25">በዚ​ያም ቀን የወ​ደ​ቁት ሁሉ ወን​ድም፥ ሴትም፥ የጋይ ሰዎች ሁሉ ዐሥራ ሁለት ሺህ ነፍስ ነበሩ።</verse>
				<verse number="26">ኢያ​ሱም የጋ​ይን ሰዎች እስ​ኪ​ያ​ጠፋ ድረስ ጦር የዘ​ረ​ጋ​በ​ትን እጁን አላ​ጠ​ፈም።</verse>
				<verse number="27">ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን እን​ዳ​ዘ​ዘው የዚ​ያ​ችን ከተማ ከብ​ትና ምርኮ ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለራ​ሳ​ቸው ዘረፉ፤</verse>
				<verse number="28">ኢያ​ሱም ከተ​ማ​ዋን በእ​ሳት አቃ​ጠ​ላት፤ ዐመ​ድም ሆነች፤ እስከ ዛሬም ድረስ ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ የሚ​ኖ​ር​ባት እን​ዳ​ይ​ኖር አደ​ረ​ጋት።</verse>
				<verse number="29">የጋ​ይ​ንም ንጉሥ በዝ​ግባ ዛፍ ላይ ሰቀ​ለው፤ እስከ ማታም ድረስ በዛፉ ላይ ቈየ። ፀሐ​ይም በገ​ባች ጊዜ ኢያሱ ያወ​ር​ዱት ዘንድ አዘዘ፤ ከዛ​ፉም አወ​ረ​ዱት፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በር አደ​ባ​ባይ ጣሉት፤ በላ​ዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ​ውን ታላቅ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመ​ሩ​በት።</verse>
				<verse number="30">የዚያ ጊዜም ኢያሱ በጌ​ባል ተራራ ላይ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊ​ያን ሠራ።</verse>
				<verse number="31">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዳ​ዘዘ፥ በሙ​ሴም ሕግ መጽ​ሐፍ እንደ ተጻ​ፈው፥ መሠ​ዊ​ያው ካል​ተ​ወ​ቀ​ረና ብረት ካል​ነ​ካው ድን​ጋይ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ላይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ የደ​ኅ​ን​ነ​ት​ንም መሥ​ዋ​ዕት ሠዋ።</verse>
				<verse number="32">ኢያ​ሱም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ፊት በድ​ን​ጋ​ዮቹ ላይ ሙሴ የጻ​ፈ​ውን ይህን ሁለ​ተ​ኛ​ውን ሕግ በድ​ን​ጋ​ዮች ላይ ጻፈ።</verse>
				<verse number="33">የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሕዝብ አስ​ቀ​ድሞ ይባ​ር​ኩ​አ​ቸው ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪያ ሙሴ እን​ዳ​ዘዘ፥ እስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ ጸሓ​ፊ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ ፈራ​ጆ​ቻ​ቸ​ውም፥ የሀ​ገሩ ልጆ​ችም፥ መጻ​ተ​ኞ​ችም እኩ​ሌ​ቶቹ በገ​ሪ​ዛን ተራራ አጠ​ገብ፥ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም በጌ​ባል ተራራ አጠ​ገብ ሆነው፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦተ ሕግ በተ​ሸ​ከ​ሙት በሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ፊት ለፊት፥ በታ​ቦ​ቱም ፊት በግ​ራና በቀኝ ቆመው ነበር።</verse>
				<verse number="34">ከዚ​ህም በኋላ ኢያሱ በሙሴ ሕግ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ፥ የሕ​ጉን ቃሎች ሁሉ በረ​ከ​ቱ​ንና ርግ​ማ​ኑን አነ​በበ።</verse>
				<verse number="35">ኢያ​ሱም በእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ፥ በወ​ን​ዶ​ቹም፥ በሴ​ቶ​ቹም፥ በሕ​ፃ​ና​ቱም፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም በሚ​ኖ​ሩት መጻ​ተ​ኞች ፊት ሙሴ ካዘ​ዘው ያላ​ነ​በ​በ​ውና ያላ​ሰ​ማው ቃል የለም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በተ​ራ​ራ​ማው በሜ​ዳ​ውም በታ​ላቁ ባሕር ዳር በሊ​ባ​ኖ​ስም ፊት ለፊት የነ​በሩ ነገ​ሥት ሁሉ፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊዉ፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ዉም፥ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ዉም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ዉም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ዉም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ዉም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ዉም ይህን በሰሙ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="2">ኢያ​ሱ​ንና እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="3">በገ​ባ​ዖን የሚ​ኖሩ ሰዎች ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​ያ​ሪ​ኮና በጋይ ያደ​ረ​ገ​ውን በሰሙ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="4">እነ​ርሱ ደግሞ ተን​ኰል አድ​ር​ገው መጡ፤ ለራ​ሳ​ቸ​ውም ስንቅ ያዙ፤ በት​ከ​ሻ​ቸ​ውም ላይ አሮጌ ዓይ​በ​ትና ያረ​ጀና የተ​ቀ​ደደ የተ​ጠ​ቀ​መም የጠጅ ረዋት ተሸ​ከሙ።</verse>
				<verse number="5">በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም ያደ​ረ​ጉት ጫማ ያረ​ጀና ማዘ​ቢ​ያው የተ​በ​ጣ​ጠሰ፥ ልብ​ሳ​ቸ​ውም በላ​ያ​ቸው ያረጀ ነበረ፤ ለስ​ን​ቅም የያ​ዙት እን​ጀራ ሁሉ የደ​ረቀ፥ የሻ​ገ​ተና የተ​በ​ላሸ ነበረ።</verse>
				<verse number="6">ወደ ኢያ​ሱና ወደ እስ​ራ​ኤል ጉባኤ ወደ ጌል​ገላ መጥ​ተው ለኢ​ያ​ሱና ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ “ከሩቅ ሀገር መጥ​ተ​ናል፤ አሁ​ንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድ​ርጉ” አሉ።</verse>
				<verse number="7">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን፥ “ምና​ል​ባት በመ​ካ​ከ​ላ​ችን የም​ት​ቀ​መጡ እንደ ሆነ እን​ዴ​ትስ ከእ​ና​ንተ ጋር ቃል ኪዳን እና​ደ​ር​ጋ​ለን?” አሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">ኢያ​ሱ​ንም፥ “እኛ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ነን፤ ከሩቅ ሀገ​ርም ነን” አሉት። ኢያ​ሱም፥ “እና​ንተ እነ​ማን ናችሁ? ከወ​ዴ​ትስ መጣ​ችሁ?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">እነ​ር​ሱም አሉት፥ “በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም እጅግ ከራቀ ሀገር ባሪ​ያ​ዎ​ችህ መጥ​ተ​ናል፤ ዝና​ው​ንም፥ በግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፥</verse>
				<verse number="10">በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶም በነ​በ​ሩት በሁ​ለቱ በአ​ሞ​ሬ​ዎን ነገ​ሥት በሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ በሴ​ዎን፥ በአ​ስ​ታ​ሮ​ትና በኤ​ድ​ራ​ይን በነ​በ​ረው በባ​ሳን ንጉሥ በዐግ ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ሰም​ተ​ናል።</verse>
				<verse number="11">ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ንና የሀ​ገ​ራ​ችን ሰዎች ሁሉ፦ ለመ​ን​ገድ ስንቅ ያዙ፤ ልት​ገ​ና​ኙ​አ​ቸ​ውም ሂዱ፦ እኛ ባሪ​ያ​ዎ​ቻ​ችሁ ነን፤ አሁ​ንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድ​ርጉ በሉ​አ​ቸው አሉን።</verse>
				<verse number="12">ወደ እና​ንተ ለመ​ም​ጣት በተ​ነ​ሣ​ን​በት ቀን ይህን እን​ጀራ ትኩ​ሱን ለስ​ንቅ ከቤ​ታ​ችን ያዝ​ነው፤ አሁ​ንም እነሆ፥ ደር​ቆ​አል፤ ሻግ​ቶ​አ​ልም።</verse>
				<verse number="13">እነ​ዚ​ህም የጠጅ ረዋ​ቶች አዲ​ሶች ሳሉ ሞላ​ን​ባ​ቸው፤ እነ​ሆም፥ አር​ጅ​ተው ተቀ​ድ​ደ​ዋል፤ መን​ገ​ዳ​ች​ንም እጅግ ስለ ራቀ​ብን እነ​ዚህ ልብ​ሶ​ቻ​ች​ንና ጫማ​ዎ​ቻ​ችን አር​ጅ​ተ​ዋል።”</verse>
				<verse number="14">አለ​ቆ​ችም ከስ​ን​ቃ​ቸው ወሰዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ጠ​የ​ቁም።</verse>
				<verse number="15">ኢያ​ሱም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሰላም አደ​ረገ፤ በሕ​ይ​ወት እን​ዲ​ተ​ዋ​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ የማ​ኅ​በ​ሩም አለ​ቆች ማሉ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ቃል ኪዳን ካደ​ረጉ ከሦ​ስት ቀን በኋላ ከቅ​ርብ እን​ደ​ሆ​ኑና በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸው እን​ደ​ሚ​ኖሩ ሰሙ።</verse>
				<verse number="17">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተጕ​ዘው በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ወደ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው ደረሱ፤ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ገባ​ዖን፥ ከፊራ፥ ብኤ​ሮ​ትና ኢያ​ሪም ነበሩ።</verse>
				<verse number="18">የማ​ኅ​በ​ሩም አለ​ቆች በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ማሉ​ላ​ቸው የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አል​ገ​ደ​ሉ​አ​ቸ​ውም። ማኅ​በ​ሩም ሁሉ በአ​ለ​ቆቹ ላይ አጕ​ረ​መ​ረሙ።</verse>
				<verse number="19">አለ​ቆ​ቹም ሁሉ ለማ​ኅ​በሩ ሁሉ፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምለ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ ስለ​ዚ​ህም እን​ነ​ካ​ቸው ዘንድ ምንም አን​ች​ልም።</verse>
				<verse number="20">ስለ​ማ​ል​ን​ላ​ቸው መሐላ ጥፋት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ብን ይህን አና​ድ​ር​ግ​ባ​ቸው፤ በሕ​ይ​ወ​ትም እን​ተ​ዋ​ቸው፤ እን​ግ​ዛ​ቸ​ውም” አሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">አለ​ቆ​ቹም “አዳ​ን​ና​ችሁ፤ ለማ​ኅ​በ​ሩም እን​ጨት ትቈ​ር​ጡና ውኃ ትቀዱ ዘንድ መደ​ብ​ና​ችሁ” አሉ​አ​ቸው። አለ​ቆ​ቹም እን​ዲሁ አዘ​ዙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">ኢያ​ሱም ጠርቶ፥ “እና​ንተ በመ​ካ​ከ​ላ​ችን የም​ት​ኖሩ ስት​ሆኑ፦ ‘ከእ​ና​ንተ እጅግ የራ​ቅን ነን’ ብላ​ችሁ ለምን አታ​ለ​ላ​ች​ሁን?</verse>
				<verse number="23">አሁ​ንም የተ​ረ​ገ​ማ​ችሁ ሁኑ፤ ለእ​ኔም፥ ለአ​ም​ላ​ኬም እን​ጨት ቈራጭ፥ ውኃም ቀጂ የሆነ ባሪያ ከእ​ና​ንተ አይ​ጠ​ፋም” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">መል​ሰ​ውም ኢያ​ሱን፥ “እኛ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ምድ​ሪ​ቱን ሁሉ ይሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ፥ በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ከፊ​ታ​ችሁ ያጠፋ ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪ​ያ​ውን ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ በእ​ው​ነት ሰም​ተ​ናል፤ ስለ​ዚ​ህም ከእ​ና​ንተ የተ​ነሣ ስለ ነፍ​ሳ​ችን እጅግ ፈራን፤ ይህ​ንም ነገር አድ​ር​ገ​ናል፤</verse>
				<verse number="25">አሁ​ንም እነሆ፥ በእ​ጃ​ችሁ ውስጥ ነን፤ እንደ ወደ​ዳ​ች​ሁና ደስ እን​ደ​ሚ​ላ​ችሁ አድ​ር​ጉ​ብን” አሉት፤</verse>
				<verse number="26">ኢያ​ሱም እን​ዲሁ አደ​ረ​ገ​ባ​ቸው፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እጅ አዳ​ና​ቸው፤ አል​ገ​ደ​ሉ​አ​ቸ​ው​ምም።</verse>
				<verse number="27">በዚ​ያም ቀን ኢያሱ እነ​ር​ሱን ለማ​ኅ​በ​ሩና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ እን​ጨት ቈራ​ጮ​ችና ውኃ ቀጂ​ዎች አደ​ረ​ጋ​ቸው። ስለ​ዚ​ህም የገ​ባ​ዖን ሰዎች ለማ​ኅ​በ​ሩና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለመ​ረ​ጠው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ጨት ቈራ​ጮች፥ ውኃም ቀጂ​ዎች ሆኑ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ንጉሥ አዶ​ኒ​ቤ​ዜቅ ኢያሱ ጋይን እንደ ያዘ፥ ፈጽ​ሞም እን​ዳ​ጠ​ፋት፥ በኢ​ያ​ሪ​ኮና በን​ጉ​ሥ​ዋም ያደ​ረ​ገ​ውን እን​ዲሁ በጋ​ይና በን​ጉ​ሥ​ዋም እን​ዳ​ደ​ረገ፥ የገ​ባ​ዖ​ንም ሰዎች ከኢ​ያ​ሱና ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ሰላም እን​ዳ​ደ​ረጉ፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም እንደ ሆኑ በሰማ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="2">ገባ​ዖን ከመ​ን​ግ​ሥ​ታት ከተ​ሞች እንደ አን​ዲቱ ታላቅ ከተማ ስለ​ሆ​ነች፥ ከጋ​ይም ስለ በለ​ጠች፥ ሰዎ​ች​ዋም ሁሉ ኀያ​ላን ስለ ነበሩ እጅግ ፈራ።</verse>
				<verse number="3">ስለ​ዚ​ህም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ንጉሥ አዶ​ኒ​ቤ​ዜቅ ወደ ኬብ​ሮን ንጉሥ ወደ ኤላም፥ ወደ የር​ሙት ንጉ​ሥም ወደ ፊዶን፥ ወደ ለኪስ ንጉ​ሥም ወደ ኤፍታ፥ ወደ አዶ​ላም ንጉ​ሥም ወደ ዳቤር ልኮ፥</verse>
				<verse number="4">“ወደ እኔ ኑ፤ ከኢ​ያ​ሱና ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ጋር ሰላም አድ​ር​ገ​ዋ​ልና ገባ​ዖ​ንን ለመ​ው​ጋት አግ​ዙኝ” አለ።</verse>
				<verse number="5">አም​ስ​ቱም የኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎን ነገ​ሥት፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ንጉሥ የኬ​ብ​ሮን ንጉሥ፥ የየ​ር​ሙት ንጉሥ፥ የላ​ኪስ ንጉሥ፥ የአ​ዶ​ላም ንጉሥ፥ ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ ጋር ተሰ​ብ​ስ​በው ወጡ፤ ከገ​ባ​ዖ​ንም ጋር ሊጋ​ጠሙ ከበ​ቡ​አት።</verse>
				<verse number="6">የገ​ባ​ዖ​ንም ሰዎች ኢያሱ ወደ ሰፈ​ረ​በት ወደ ጌል​ገላ ልከው፥ “ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህን ለመ​ር​ዳት እጅ​ህን አት​መ​ልስ፤ በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር የሚ​ኖሩ የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በ​ው​ብ​ና​ልና ፈጥ​ነህ ወደ እኛ ውጣ፤ አድ​ነ​ንም፤ ርዳ​ንም፤” አሉት።</verse>
				<verse number="7">ኢያ​ሱም ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ተዋ​ጊ​ዎች ሁሉ፥ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላ​ኑም ሁሉ ከጌ​ል​ጌላ ወጡ።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​አ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና አት​ፍ​ራ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ሰው በፊ​ትህ የሚ​ተ​ርፍ የለም፤” አለው።</verse>
				<verse number="9">ኢያ​ሱም ከጌ​ል​ገላ ሌሊ​ቱን ሁሉ ገሥ​ግሦ በድ​ን​ገት ደረ​ሰ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት አስ​ደ​ነ​ገ​ጣ​ቸው፤ በገ​ባ​ዖ​ንም ታላቅ መም​ታት መታ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ፊት እየ​ሸሹ በቤ​ት​ሖ​ሮን ቍል​ቍ​ለት ሲወ​ርዱ፥ ወደ ዓዜ​ቃና ወደ መቄዳ እስ​ኪ​ደ​ርሱ ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ታላ​ላቅ የበ​ረዶ ድን​ጋይ አወ​ረ​ደ​ባ​ቸ​ውና ሞቱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በሰ​ይፍ ከገ​ደ​ሉ​አ​ቸው ይልቅ በበ​ረዶ ድን​ጋይ የሞ​ቱት በለጡ።</verse>
				<verse number="12">ያን ጊዜም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እጅ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አሳ​ልፎ ሰጠ፤ እርሱ በገ​ባ​ዖን እነ​ር​ሱን ባጠ​ፋ​በት፥ እነ​ር​ሱም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት በጠ​ፉ​በት ቀን ኢያሱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ተነ​ጋ​ገረ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “በገ​ባ​ዖን ላይ ፀሐይ ትቁም፤ በኢ​ሎ​ንም ሸለቆ ጨረቃ፤”</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን እስ​ኪ​ያ​ጠፋ ድረስ ፀሐ​ይና ጨረቃ በየ​ቦ​ታ​ቸው ቆሙ። ይህም እነሆ በዚህ መጽ​ሐፍ በጊ​ዜው ተጻፈ። ፀሐ​ይም በሰ​ማይ መካ​ከል ቆመች፤ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል አል​ጠ​ለ​ቀ​ችም።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ይዋጋ ነበ​ርና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ውን ቃል የሰ​ማ​በት እን​ደ​ዚያ ያለ ቀን ከዚ​ያም በፊት ከዚ​ያም በኋላ አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="15">ኢያ​ሱም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ወደ ሰፈ​ራ​ቸው ወደ ጌል​ገላ ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="16">እነ​ዚ​ህም አም​ስት ነገ​ሥት ሸሽ​ተው በመ​ቄዳ ዋሻ ተሸ​ሸጉ።</verse>
				<verse number="17">ለኢ​ያ​ሱም “አም​ስቱ ነገ​ሥት በመ​ቄዳ ዋሻ ተሸ​ሽ​ገው ተገኙ፤” ብለው ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="18">ኢያ​ሱም እን​ዲህ አለ፥ “ወደ ዋሻው አፍ ታላ​ላቅ ድን​ጋይ አን​ከ​ባ​ል​ላ​ችሁ፥ ይጠ​ብ​ቋ​ቸው ዘንድ ሰዎ​ችን በዚያ አኑሩ፤</verse>
				<verse number="19">እና​ንተ ግን አት​ዘ​ግዩ፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም እስከ መጨ​ረ​ሻው ተከ​ታ​ት​ላ​ችሁ ያዙ​አ​ቸው፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና ወደ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ይ​ገቡ ከል​ክ​ሉ​አ​ቸው፤” አለ።</verse>
				<verse number="20">እስ​ኪ​ጠ​ፉም ድረስ ኢያ​ሱና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በታ​ላቅ መም​ታት መም​ታ​ታ​ቸ​ውን በፈ​ጸሙ ጊዜ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ያመ​ለ​ጡት ወደ ተመ​ሸገ ከተማ በገቡ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="21">ሕዝቡ ሁሉ ኢያሱ ወደ ሰፈ​ረ​በት ወደ መቄዳ በደ​ኅና ተመ​ለሱ፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ምላ​ሱን ማን​ቀ​ሳ​ቀስ የደ​ፈረ ማንም ሰው የለም።</verse>
				<verse number="22">ኢያ​ሱም፥ “የዋ​ሻ​ውን አፍ ክፈቱ፤ እነ​ዚ​ያ​ንም አም​ስት ነገ​ሥት ከዋ​ሻው ወደ እኔ አው​ጡ​አ​ቸው” አለ።</verse>
				<verse number="23">እን​ዲ​ህም አደ​ረጉ፤ አም​ስ​ቱ​ንም ነገ​ሥት፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ንጉሥ፥ የኬ​ብ​ሮ​ን​ንም ንጉሥ፥ የየ​ር​ሙ​ት​ንም ንጉሥ፥ የላ​ኪ​ስ​ንም ንጉሥ፥ የአ​ዶ​ላ​ም​ንም ንጉሥ ከዋ​ሻው ወደ እርሱ አወ​ጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">እነ​ዚ​ያ​ንም ነገ​ሥት ወደ ኢያሱ ባመ​ጡ​አ​ቸው ጊዜ ኢያሱ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰዎች ሁሉ ጠራ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የሄ​ዱ​ትን የተ​ዋ​ጊ​ዎ​ችን አለ​ቆች “ቅረቡ፤ በእ​ነ​ዚ​ህም ነገ​ሥት አን​ገት ላይ እግ​ራ​ች​ሁን አኑሩ” አላ​ቸው። ቀረ​ቡም በአ​ን​ገ​ታ​ቸ​ውም ላይ እግ​ራ​ቸ​ውን አኖሩ።</verse>
				<verse number="25">ኢያ​ሱም፥ “በም​ት​ወ​ጉ​አ​ቸው በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ሁሉ ላይ እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ር​ጋ​ልና አት​ፍሩ፤ አት​ደ​ን​ግጡ፤ ጽኑ፤ አይ​ዞ​አ​ችሁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">ከዚ​ህም በኋላ መት​ተው ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ በአ​ም​ስ​ቱም ዛፎች ላይ ሰቀ​ሉ​አ​ቸው፤ እስከ ማታም ደረስ በዛ​ፎቹ ላይ ተሰ​ቅ​ለው ቈዩ።</verse>
				<verse number="27">ፀሐ​ይም ልት​ገባ በቀ​ረ​በች ጊዜ ኢያሱ አዘዘ፤ ከዛ​ፎ​ችም አወ​ረ​ዱ​አ​ቸው፤ ተሸ​ሽ​ገ​ውም በነ​በ​ሩ​በት ዋሻ ጣሉ​አ​ቸው፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዋ​ሻው አፍ ታላ​ላቅ ድን​ጋይ ተደ​ር​ጎ​አል።</verse>
				<verse number="28">በዚ​ያም ቀን መቄ​ዳን ያዟት፤ እር​ስ​ዋ​ንና ንጉ​ሥ​ዋ​ንም በሰ​ይፍ ስለት ገደሉ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ ፈጽ​መው አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዱን ስንኳ አላ​ስ​ቀ​ሩም፤ የዳ​ነም፥ ያመ​ለ​ጠም የለም፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም ንጉሥ እን​ዳ​ደ​ረጉ በመ​ቄዳ ንጉሥ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="29">ኢያ​ሱም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከመ​ቄዳ ወደ ልብና አለፉ፤ ልብ​ና​ንም ወጉ።</verse>
				<verse number="30">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እር​ስ​ዋ​ንና ንጉ​ሥ​ዋን በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጠ፤ እር​ስ​ዋ​ንም በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት መታ፤ በእ​ር​ስ​ዋም አን​ዱን ስንኳ አላ​ስ​ቀ​ረም፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም ንጉሥ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው በል​ብና ንጉሥ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="31">ኢያ​ሱም ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከል​ብና ወደ ላኪስ አለፉ፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ሰፈሩ፤ ከበ​ቡ​አ​ትም።</verse>
				<verse number="32">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ላኪ​ስን በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጣት፤ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ያዙ​አት፤ በል​ብ​ናም እን​ዳ​ደ​ረ​ጉት ሁሉ፥ እር​ስ​ዋን፥ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት መቱ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="33">በዚያ ጊዜም የጋ​ዜር ንጉሥ ኤላም ላኪ​ስን ለመ​ር​ዳት ወጣ፤ ኢያ​ሱም አንድ ስንኳ ሳይ​ቀር በሰ​ይፍ ስለት እር​ሱ​ንና ሕዝ​ቡን መታ፤ የዳ​ነም፥ ያመ​ለ​ጠም የለም።</verse>
				<verse number="34">ኢያ​ሱም ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከላ​ኪስ ወደ አዶ​ላም አለፉ፤ ከበ​ቡ​አ​ትም፤ ወጉ​አ​ትም፤</verse>
				<verse number="35">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ር​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጣት፤ በዚ​ያም ቀን ያዙ​አት፤ በሰ​ይ​ፍም ስለት መቱ​አት፤ በላ​ኪ​ስም እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ፥ በእ​ር​ስዋ ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።</verse>
				<verse number="36">ኢያ​ሱም ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከአ​ዶ​ላም ወደ ኬብ​ሮን ወጡ፤ ወጉ​አ​ትም፤ ያዙ​አ​ትም፤</verse>
				<verse number="37">እር​ስ​ዋ​ንም፥ ንጉ​ሥ​ዋ​ንም፥ ከተ​ሞ​ች​ዋ​ንም ሁሉ፥ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት መቱ፤ በአ​ዶ​ላም እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም ፤ እር​ስ​ዋ​ንም፥ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።</verse>
				<verse number="38">ኢያ​ሱም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ወደ ዳቤር ተመ​ለሱ፤ ወጉ​አ​ትም፤</verse>
				<verse number="39">እር​ስ​ዋ​ንም፥ ንጉ​ሥ​ዋ​ንም፥ ከተ​ሞ​ች​ዋ​ንም ያዙ፤ በሰ​ይ​ፍም ስለት መቱ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ውስጥ ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ ፈጽ​መው አጠፉ፤ ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም፤ በኬ​ብ​ሮ​ንና በን​ጉ​ሥ​ዋም እን​ዳ​ደ​ረ​ገው እን​ዲሁ በዳ​ቤ​ርና በን​ጉ​ሥዋ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="40">እን​ዲ​ሁም ኢያሱ ምድ​ሪ​ቱን ሁሉ፥ ተራ​ራ​ማ​ውን ሀገር፥ ደቡ​ቡ​ንም፥ ቆላ​ው​ንም፥ ቍል​ቍ​ለ​ቱ​ንም፥ ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ መታ፤ ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘ​ውም ነፍስ ያለ​በ​ትን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።</verse>
				<verse number="41">ኢያ​ሱም ከቃ​ዴስ በርኔ እስከ ጋዛ ድረስ፥ የጎ​ሶ​ም​ንም ምድር ሁሉ እስከ ገባ​ዖን ድረስ መታ።</verse>
				<verse number="42">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ስለ ተዋ​ጋ​ላ​ቸው ኢያሱ እነ​ዚ​ህን ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም በአ​ንድ ጊዜ ያዘ።</verse>
				<verse number="43">ኢያ​ሱም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ወደ ሰፈሩ ወደ ጌል​ገላ ተመ​ለሱ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የአ​ሶር ንጉሥ ኢያ​ቢስ ይህን በሰማ ጊዜ ወደ ማሮን ንጉሥ ወደ ዮባብ፥ ወደ ስሚ​ዖን ንጉሥ፥ ወደ አዚ​ፍም ንጉሥ፥</verse>
				<verse number="2">በመ​ስ​ዕም በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ፥ በከ​ነ​ሬ​ትም ዐዜብ በዓ​ረባ፥ በቆ​ላ​ውም ባለ በፊ​ና​ዶር ሸለቆ ወደ ነበሩ ነገ​ሥ​ታት፥</verse>
				<verse number="3">በም​ሥ​ራ​ቃዊ ባሕር ዳርቻ ወዳ​ለው ወደ ከነ​ዓ​ና​ዊው፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ውም፥ ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ውም፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ውም፥ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም ሀገር ወዳ​ለው ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊው፥ በቆ​ላ​ማ​ውና በመ​ሴፋ ወዳ​ለው ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ዉም ላከ።</verse>
				<verse number="4">እነ​ርሱ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሠራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ ብዛ​ታ​ቸው እንደ ባሕር አሸዋ ሆነው ወጡ፤ ፈረ​ሶ​ችና ሰረ​ገ​ሎ​ችም እጅግ ብዙ​ዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="5">እነ​ዚ​ህም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው መጡ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም በማ​ሮን ውኃ አጠ​ገብ አንድ ሆነው ተያ​ያ​ዙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ይሞቱ ዘንድ ነገ በዚህ ጊዜ ሁሉን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና አት​ፍ​ራ​ቸው፤ የፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን ቋንጃ ትቈ​ር​ጣ​ለህ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="7">ኢያ​ሱና ተዋ​ጊ​ዎች ሕዝ​ብም ሁሉ በድ​ን​ገት ወደ ማሮን ውኃ መጡ​ባ​ቸው፤ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም ቦታ ወደ​ቁ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ መቱ​አ​ቸ​ውም፤ ወደ ታላ​ቂ​ቱም ሲዶና፥ ወደ ማሴ​ሮ​ንም፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ወዳ​ለው ወደ ሞሳሕ ሸለቆ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ ማን​ንም ሳያ​ስ​ቀሩ መቱ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ኢያ​ሱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረ​ገ​ባ​ቸው፤ የፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቋንጃ ቈረጠ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠለ።</verse>
				<verse number="10">በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት ኢያሱ ተመ​ልሶ አሶ​ርን ያዘ፤ ንጉ​ሥ​ዋ​ንም በሰ​ይፍ ገደለ፤ አሶ​ርም አስ​ቀ​ድሞ የእ​ነ​ዚህ መን​ግ​ሥ​ታት ዋና ከተማ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="11">በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ሰዎች ሁሉ በሰ​ይፍ ገደሉ፤ እስ​ት​ን​ፋስ ያላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ሳያ​ስ​ቀሩ ሁሉ​ንም አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ አሶ​ር​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ላት፤</verse>
				<verse number="12">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋይ ሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው፥ ኢያሱ የእ​ነ​ዚ​ህን መን​ግ​ሥ​ታት ከተ​ሞች ሁሉ፥ ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ያዘ፤ በሰ​ይ​ፍም መታ​ቸው፤ ፈጽ​ሞም አጠ​ፋ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">ከአ​ቃ​ጠ​ሏት ከአ​ሶር ብቻ በቀር እስ​ራ​ኤል በየ​አ​ው​ራ​ጃ​ቸው የነ​በ​ሩ​ትን ሌሎች ከተ​ሞች ሁሉ አላ​ቃ​ጠ​ሉም።</verse>
				<verse number="14">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የእ​ነ​ዚ​ህን ከተ​ሞች ምርኮ ሁሉ፥ ከብ​ቶ​ቹ​ንም ለራ​ሳ​ቸው ዘረፉ፤ ሰዎ​ቹን ሁሉ ግን እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በሰ​ይፍ ስለት መቱ​አ​ቸው፤ እስ​ት​ን​ፋስ ያለ​ው​ንም ሁሉ አን​ድም አላ​ስ​ቀ​ሩም።</verse>
				<verse number="15">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋ​ዩን ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ እን​ዲሁ ሙሴ ኢያ​ሱን አዝ​ዞት ነበር፤ ኢያ​ሱም እን​ዲሁ አደ​ረገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ካዘ​ዘው ሁሉ ምንም አላ​ስ​ቀ​ረም።</verse>
				<verse number="16">ኢያ​ሱም ያን ምድር ሁሉ፥ ተራ​ራ​ማ​ውን፥ ደቡ​ቡ​ንም ሁሉ፥ የጎ​ሶ​ም​ንም ምድር ሁሉ ፥ ሜዳ​ው​ንም፥ በም​ዕ​ራብ በኩል ያለ​ው​ንም፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ተራ​ራ​ማ​ው​ንና ቆላ​ውን ያዘ፤</verse>
				<verse number="17">እስከ ሴይ​ርም ከሚ​ያ​ወ​ጣው ከኤ​ኬል ተራራ ጀምሮ ከአ​ር​ሞ​ን​ዔም ተራራ በታች እስከ ሊባ​ኖስ ሜዳና እስከ በላ​ጋድ ድረስ፤ ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ ይዞ መታ​ቸው፤ ገደ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="18">ኢያ​ሱም ብዙ ዘመን ከእ​ነ​ዚሁ ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር።</verse>
				<verse number="19">በገ​ባ​ዖን ከሚ​ኖሩ ከኤ​ዎ​ና​ው​ያን በቀር፤ እስ​ራ​ኤል ያል​ያ​ዙት ከተማ አል​ነ​በ​ረም፥ ሁሉን በጦ​ር​ነት ያዙ።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ፥ ያጠ​ፉ​አ​ቸው ዘንድ እን​ዳ​ይ​ራ​ሩ​ላ​ቸው ፈጽ​መው እን​ዲ​ያ​ጠ​ፉ​አ​ቸው፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ይጋ​ጠሙ ዘንድ ልባ​ቸ​ውን እን​ዲ​ያ​ደ​ነ​ድኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልባ​ቸ​ውን አጸና።</verse>
				<verse number="21">በዚያ ጊዜም ኢያሱ ሄደ፤ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም ሀገር የሚ​ኖሩ ኤና​ቃ​ው​ያ​ንን ከኬ​ብ​ሮ​ንና ከዳ​ቤር፥ ከአ​ና​ቦ​ትም፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተራራ ሁሉ፥ ከይ​ሁ​ዳም ተራራ ሁሉ አጠ​ፋ​ቸው፤ ኢያ​ሱም ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር ፈጽሞ አጠ​ፋ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">በጋዛ፥ በጌ​ትም፥ በአ​ዛ​ጦ​ንም ከቀ​ሩት በቀር በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ከኤ​ና​ቃ​ው​ያን ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም።</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ ኢያሱ ምድ​ሪ​ቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያ​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል እንደ ክፍ​ላ​ቸው በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው ርስት አድ​ርጎ ምድ​ሪ​ቱን ሰጣ​ቸው፤ ምድ​ሪ​ቱም ከጦ​ር​ነት ዐረ​ፈች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የመ​ቱ​አ​ቸው፥ ከአ​ር​ኖ​ንም ሸለቆ ጀምሮ እስከ አር​ሞ​ን​ዔም ተራራ ድረስ በም​ሥ​ራቅ በኩል ያለ​ውን ዓረባ ሁሉ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ በፀ​ሐይ መውጫ ያለ​ውን ሀገ​ራ​ቸ​ውን የወ​ረ​ሱ​አ​ቸው የም​ድር ነገ​ሥት እነ​ዚህ ናቸው፤</verse>
				<verse number="2">በሐ​ሴ​ቦን የተ​ቀ​መ​ጠው፥ በአ​ር​ኖ​ንም ሸለቆ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር፥ ከሸ​ለ​ቆ​ውም መካ​ከል ጀምሮ የገ​ለ​ዓ​ድን እኩ​ሌታ እስከ ኢያ​ቦቅ ወንዝ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ፤</verse>
				<verse number="3">በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ያለ​ውን ዓረባ እስከ ኬኔ​ሬት ባሕር ድረስ፥ በአ​ሴ​ሞት መን​ገድ አጠ​ገብ እስ​ካ​ለው እስከ ዓረባ ባሕር እስከ ጨው ባሕር ድረስ፥ በደ​ቡ​ብም በኩል ከፋ​ስጋ ተራራ አፋፍ በታች ያለ​ውን ምድር የገ​ዛው የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ንጉሥ ሴዎን፤</verse>
				<verse number="4">ከረ​ዓ​ይት ወገን የቀረ፥ በአ​ስ​ጣ​ሮ​ትና በኤ​ን​ድ​ራ​ይን የተ​ቀ​መ​ጠው፥</verse>
				<verse number="5">የአ​ር​ሞ​ን​ኤ​ምን ተራራ፥ ካሴ​ኪን፥ ባሳ​ን​ንም ሁሉ እስከ ጌር​ጌ​ሲና እስከ መከጢ ዳርቻ፥ የገ​ለ​ዓ​ድ​ንም እኩ​ሌታ እስከ ሐሴ​ቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ዳርቻ ድረስ የገ​ዛው የባ​ሳን ንጉሥ ዐግ፤</verse>
				<verse number="6">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋይ ሙሴ ርስት አድ​ርጎ ለሮ​ቤል ልጆች፥ ለጋ​ድም ልጆች፥ ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ምድ​ሪ​ቱን ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና ኢያሱ በሊ​ባ​ኖስ ቆላ፥ በበ​ላ​ጋድ ባሕር፥ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ሴይር በሚ​ደ​ርስ በኬ​ልኪ ተራራ የገ​ደ​ሉ​አ​ቸው የከ​ነ​ዓን ነገ​ሥት እነ​ዚህ ናቸው። ኢያ​ሱም ያችን ምድር ለእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">በተ​ራ​ራና በሜዳ በዓ​ረባ፥ በአ​ሴ​ዶት በቆ​ላው፥ በና​ጌብ፥ በኬ​ጤ​ዎ​ንና በአ​ሞ​ሬ​ዎን፥ በከ​ና​ኔ​ዎ​ንና በፌ​ር​ዜ​ዎን፥ በኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎ​ንና በኤ​ዌ​ዎን ያለ ርስ​ታ​ቸ​ውን አወ​ረ​ሳ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">የኢ​ያ​ሪኮ ንጉሥ፥ በቤ​ቴል አጠ​ገብ ያለ​ችው የጋይ ንጉሥ፥</verse>
				<verse number="10">የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ንጉሥ፥ የኬ​ብ​ሮን ንጉሥ፥</verse>
				<verse number="11">የኢ​ያ​ሪ​ሙት ንጉሥ፥ የለ​ኪስ ንጉሥ፥</verse>
				<verse number="12">የኤ​ላም ንጉሥ፥ የጋ​ዜር ንጉሥ፥</verse>
				<verse number="13">የዳ​ቤር ንጉሥ፥ የጋሴ ንጉሥ፥</verse>
				<verse number="14">የኤ​ር​ሞት ንጉሥ፥ የዓ​ራድ ንጉሥ፥</verse>
				<verse number="15">የል​ብና ንጉሥ፥ የዓ​ዶ​ላም ንጉሥ፥</verse>
				<verse number="16">የመ​ቄዳ ንጉሥ፥</verse>
				<verse number="17">የኤ​ጣ​ፋድ ንጉሥ፥</verse>
				<verse number="18">የኦ​ፌር ንጉሥ፥</verse>
				<verse number="19">የአ​ፌ​ጠ​ቀ​ሰ​ሩት ንጉሥ፥ የአ​ሶር ንጉሥ፥</verse>
				<verse number="20">የስ​ሚ​ዖን ንጉሥ፥ የመ​ም​ሮት ንጉሥ፥</verse>
				<verse number="21">የአ​ዚፍ ንጉሥ፥ የቃ​ዴስ ንጉሥ፥</verse>
				<verse number="22">የዘ​ቃክ ንጉሥ፥ የማ​ር​ዶት ንጉሥ፥ በቀ​ር​ሜ​ሎስ የነ​በረ የዴ​ቆም ንጉሥ፥</verse>
				<verse number="23">በፌ​ና​ድር ክፍል የም​ት​ሆን የኤ​ዶር ንጉሥ፥ በጋ​ልያ ክፍል የም​ት​ሆን የሐጌ ንጉሥ፥ የቲ​ርሣ ንጉሥ፥</verse>
				<verse number="24">እነ​ዚህ ነገ​ሥት ሁሉ ሃያ ዘጠኝ ናቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">ኢያ​ሱም ሸመ​ገለ፤ ዘመ​ኑም አለፈ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን አለው፥ “እነሆ ዘመ​ንህ አለፈ፤ ያል​ተ​ወ​ረ​ሰች እጅግ ብዙ ምድር ገና ቀር​ታ​ለች፤</verse>
				<verse number="2">የቀ​ረ​ች​ውም ምድር ይህች ናት፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን፥ የጌ​ሴ​ር​ያ​ው​ያ​ንና የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ሀገር ሁሉ፥</verse>
				<verse number="3">በግ​ብፅ ፊት ካለው ምድረ በዳ ጀምሮ ለአ​ም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ግዛ​ቶች ለጋዛ፥ ለአ​ዛ​ጦን፥ ለአ​ስ​ቀ​ሎና፥ ለጌት፥ ለአ​ቃ​ሮን፥ እን​ዲ​ሁም ለኤ​ዌ​ዎ​ና​ው​ያን በተ​ቈ​ጠ​ረ​ችው በከ​ነ​ዓን ግራ በኩል እስ​ካ​ለ​ችው እስከ አቃ​ሮን ዳርቻ ድረስ ነው፤</verse>
				<verse number="4">ከደ​ቡብ ጀምሮ በጋ​ዛና በሲ​ዶና ፊት ያለ​ውን የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ምድር ሁሉ እስከ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ዳርቻ እስከ አፌቅ ድረስ፥</verse>
				<verse number="5">በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ያለው የጌ​ባ​ላ​ው​ያን ምድር ሁሉ፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ከአ​ር​ሞ​ን​ዔም ተራራ በታች ካለ​ችው ጌል​ገላ ጀምሮ እስከ ኤማት መግ​ቢያ ድረስ ያለ​ችው ሊባ​ኖስ ሁሉ፥</verse>
				<verse number="6">በተ​ራ​ራ​ማ​ውም ሀገር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ከሊ​ባ​ኖስ ጀምሮ እስከ ማሴ​ሬ​ት​ሜ​ም​ፎ​ማ​ይም መያ​ያዣ ድረስ ሲዶ​ና​ው​ያን ሁሉ፤ እነ​ዚ​ህን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁ​ህም ምድ​ራ​ቸ​ውን ለእ​ስ​ራ​ኤል ርስት አድ​ር​ገህ አካ​ፍ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">አሁ​ንም ይህን ምድር ለዘ​ጠኙ ነገድ፥ ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ርስት አድ​ር​ገህ ክፈ​ለው። ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ጀምሮ በም​ዕ​ራብ እስ​ካ​ለው ታላቁ ባሕር ድረስ ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ታላቁ ባሕር ይሆ​ናል።”</verse>
				<verse number="8">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴም እንደ ሰጣ​ቸው ከእ​ርሱ ከም​ናሴ ጋር የሮ​ቤ​ልና የጋድ ልጆች፥ በም​ሥ​ራቅ በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ሙሴ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ርስ​ታ​ቸ​ውን ተቀ​በሉ።</verse>
				<verse number="9">በአ​ር​ኖን ሸለቆ ዳር ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር፥ በሸ​ለ​ቆ​ውም መካ​ከል ካለ​ችው ከተማ ጀምሮ የሚ​ሶር ሜዳ ሁሉ እስከ ዲቦን ድረስ፥</verse>
				<verse number="10">በሐ​ሴ​ቦ​ንም የነ​ገሠ የአ​ሞ​ሬ​ዎን ንጉሥ የሴ​ዎን ከተ​ሞ​ችን ሁሉ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ፥</verse>
				<verse number="11">ገለ​ዓ​ድ​ንም፥ የጌ​ሴ​ሪ​ያ​ው​ያ​ን​ንና የመ​ከ​ጢ​ያ​ው​ያ​ንን ዳርቻ ሁሉ፥ የአ​ር​ሞ​ን​ዔ​ም​ንም ተራራ ሁሉ፥ ባሳ​ን​ንም ሁሉ፥ እስከ ሰልካ ድረስ፥</verse>
				<verse number="12">በባ​ሳን የነ​በ​ረ​ውን፥ በአ​ስ​ታ​ሮ​ትና በኤ​ን​ድ​ራ​ይን የነ​ገ​ሠ​ውን የዐ​ግን መን​ግ​ሥት ሁሉ፤ እር​ሱም ከረ​ዓ​ይት የቀረ ነበረ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ሙሴ አወ​ጣ​ቸው፤ ገደ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="13">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን ጌሴ​ሪ​ያ​ው​ያ​ንን፥ መከ​ጢ​ያ​ው​ያ​ን​ንና ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን አላ​ጠ​ፉ​አ​ቸ​ውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ጌሴ​ሪና መከጢ በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ይኖ​ራሉ።</verse>
				<verse number="14">ለሌዊ ነገድ ግን ርስት አል​ተ​ሰ​ጠም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ራ​ቸው የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስ​ታ​ቸው ነውና፥ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሞ​ዓብ ሜዳ ሙሴ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዳ​ካ​ፈ​ላ​ቸው እን​ዲሁ ተካ​ፈሉ።</verse>
				<verse number="15">ሙሴም ለሮ​ቤል ነገድ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ርስ​ትን ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">ድን​በ​ራ​ቸ​ውም በአ​ር​ኖን ሸለቆ ዳር ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ በሸ​ለ​ቆው መካ​ከል ያለ​ችው ከተማ፥ ሜሶ​ርም ሁሉ፥</verse>
				<verse number="17">ሐሴ​ቦን፥ በሜ​ሶ​ርም ያሉት ከተ​ሞች ሁሉ፥ ዲቦን፥ ባሞ​ት​በ​ዐል፥ ቤት​በ​አ​ል​ም​ዖን፥</verse>
				<verse number="18">ባሳን፥ ቀዲ​ሞት፥ ሜፍዓ፥</verse>
				<verse number="19">ቂር​ያ​ታ​ይም፥ ሴባማ፥ ሲራ​ዳት፥ በሸ​ለ​ቆ​ውም ተራራ ያለ​ችው ሲዮን፥</verse>
				<verse number="20">ቤተ ፌጎር፥ ከፈ​ስጋ ተራራ በታች ያለው ምድር፥ ቤት​ሲ​ሞት፥</verse>
				<verse number="21">የሚ​ሶር ከተ​ሞች ሁሉ፥ በሐ​ሴ​ቦ​ንም የነ​ገ​ሠው የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ንጉሥ የሴ​ዎን መን​ግ​ሥት ሁሉ ነበረ፤ ሙሴም እር​ሱ​ንና በም​ድ​ሪቱ የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን የሴ​ዎ​ንን መሳ​ፍ​ንት፥ የም​ድ​ያ​ምን አለ​ቆች ኤዊን፥ ሮቦ​ቅን፥ ሱርን፥ ኡርን፥ ሮቤን በሲ​ዮን የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም ገደ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">ሟር​ተ​ኛ​ውን የቢ​ዖ​ርን ልጅ በለ​ዓ​ም​ንም በአ​ን​ድ​ነት በሰ​ይፍ ገደ​ሉት።</verse>
				<verse number="23">የሮ​ቤ​ልም ልጆች ድን​በር የዮ​ር​ዳ​ኖስ ወን​ዝና ዳር​ቻው ነበረ። የሮ​ቤል ልጆች ርስት ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="24">ሙሴም ለጋድ ነገድ ለጋ​ድም ልጆች በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ርስት አድ​ርጎ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ኢያ​ዜ​ርና የገ​ለ​ዓድ ከተ​ሞች ሁሉ፥ የአ​ሞ​ንም ልጆች ምድር እኩ​ሌታ በራ​ባት ፊት እስ​ካ​ለ​ችው እስከ አሮ​ዔር ድረስ፥</verse>
				<verse number="26">ከሐ​ሴ​ቦን ጀምሮ እስከ አራ​ቦት መሴፋ፥ እስከ ቦጣ​ኒም ድረስ፥ ከማ​ኦን ጀምሮ እስከ ዴቦን ዳርቻ ድረስ፥</verse>
				<verse number="27">በሸ​ለ​ቆ​ውም ቤት​ሀ​ራም፥ ቤት​ን​ምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ የሴ​ዎን መን​ግ​ሥት ቅሬታ ነበረ። ድን​በ​ሩም ዮር​ዳ​ኖ​ስና በም​ሥ​ራቅ በኩል ባለው በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ የኬ​ኔ​ሬት ባሕር ወዲ​ያ​ኛው ዳርቻ ነበረ።</verse>
				<verse number="28">የጋድ ልጆች ርስት ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም፥ መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ። በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ፊት ጀር​ባ​ቸ​ውን መል​ሰው ሸሹ፤ መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውና ከተ​ሞ​ቻ​ቸው በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ሆነ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="29">ሙሴም ለም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ርስት ሰጣ​ቸው፤</verse>
				<verse number="30">ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ከመ​ሐ​ና​ይም ጀምሮ የባ​ሳን ንጉሥ የዐግ መን​ግ​ሥት፥ ባሳን ሁሉ፥ በባ​ሳ​ንም ያሉት የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች ሁሉ ስድ​ሳው ከተ​ሞች፥ የገ​ለ​ዓ​ድም እኩ​ሌታ፥</verse>
				<verse number="31">በባ​ሳ​ንም ያሉት የዐግ መን​ግ​ሥት ከተ​ሞች፥ አስ​ጣ​ሮ​ትና ኤድ​ራ​ይን ነበረ። እነ​ዚ​ህም ለም​ናሴ ልጅ ለማ​ኪር ልጆች ሆኑ፤ ለም​ናሴ ልጅ ለማ​ኪር ልጆች እኩ​ሌ​ታም በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="32">ሙሴ በም​ሥ​ራቅ በኩል በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሞ​ዓብ ሜዳ ሳለ ርስት ያካ​ፈ​ላ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በከ​ነ​ዓን ምድር የወ​ረ​ሱት ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርና የነዌ ልጅ ኢያሱ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ነገድ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አለ​ቆች ያወ​ረ​ሱ​አ​ቸው ርስት ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ እን​ዳ​ዘዘ ለዘ​ጠኙ ነገ​ድና ለእ​ኩ​ሌ​ታው በየ​ር​ስ​ታ​ቸው በዕጣ አከ​ፋ​ፈ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ለሁ​ለቱ ነገ​ድና ለእ​ኩ​ሌ​ታው ነገድ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ሙሴ ርስት ሰጥቶ ነበር፤ ነገር ግን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ርስት አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="4">የዮ​ሴፍ ልጆች ምና​ሴና ኤፍ​ሬም ሁለት ነገ​ዶች ነበሩ፤ ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ከሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸው ከተ​ሞች ለእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ቸው ከሚ​ሆን ማሰ​ማ​ሪ​ያ​ቸ​ውና ከእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም በቀር በም​ድሩ ውስጥ ድርሻ አል​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አደ​ረጉ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ተካ​ፈሉ።</verse>
				<verse number="6">የይ​ሁ​ዳም ልጆች በጌ​ል​ገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ቄኔ​ዛ​ዊ​ውም የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ አለው፥ “ለአ​ም​ላክ ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቃ​ዴስ በርኔ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ታው​ቃ​ለህ።</verse>
				<verse number="7">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ ምድ​ርን እሰ​ልል ዘንድ ከቃ​ዴስ በርኔ በላ​ከኝ ጊዜ እኔ የአ​ርባ ዓመት ሰው ነበ​ርሁ፤ እኔም በልቡ የነ​በ​ረ​ውን ቃል መለ​ስ​ሁ​ለት።</verse>
				<verse number="8">ከእኔ ጋር የወጡ ወን​ድ​ሞች ግን የሕ​ዝ​ቡን ልብ አስ​ካዱ፤ እኔ ግን አም​ላ​ኬን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሜ እከ​ተ​ለው ዘንድ ተመ​ለ​ስሁ።</verse>
				<verse number="9">ሙሴም በዚያ ቀን፦ ‘አም​ላ​ኬን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽ​መህ ተከ​ት​ለ​ሃ​ልና እግ​ርህ የረ​ገ​ጠው ምድር ለአ​ን​ተና ለል​ጆ​ችህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በር​ግጥ ርስት ይሆ​ናል’ ብሎ ማለ።</verse>
				<verse number="10">አሁ​ንም፥ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ ይህን ቃል ከተ​ና​ገረ በኋላ፥ እስ​ራ​ኤል በም​ድረ በዳ ሲዞሩ፥ እርሱ እንደ ተና​ገ​ረኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አርባ አም​ስት ዓመ​ታት በሕ​ይ​ወት አኖ​ረኝ፤ አሁ​ንም፥ እነሆ፥ ለእኔ ዛሬ ሰማ​ንያ አም​ስት ዓመት ሆነኝ።</verse>
				<verse number="11">ሙሴም በላ​ከኝ ጊዜ ጽኑዕ እንደ ነበ​ርሁ፥ ዛሬም ገና እን​ዲሁ ለመ​ዋ​ጋት ለመ​ው​ጣ​ትም ለመ​ግ​ባ​ትም ጽኑዕ ነኝ።</verse>
				<verse number="12">አሁን እን​ግ​ዲህ በዚያ ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን ይህን ተራ​ራማ ሀገር ስጠኝ፤ አንተ በዚያ ቀን ዔና​ቃ​ው​ያን፥ ታላ​ላ​ቆ​ችና የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞ​ችም በዚያ እን​ዳሉ ሰም​ተህ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ጋር ቢሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ረኝ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="13">ኢያ​ሱም የቄ​ኔዝ ልጅ፥ የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌ​ብን ባረ​ከው፤ ኬብ​ሮ​ን​ንም ርስት አድ​ርጎ ሰጠው።</verse>
				<verse number="14">ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሞ ስለ ተከ​ተለ ኬብ​ሮን እስከ ዛሬ ለቄ​ኔ​ዛ​ዊው ለዮ​ፎኒ ልጅ ለካ​ሌብ ርስት ሆነች።</verse>
				<verse number="15">የኬ​ብ​ሮ​ንም ስም አስ​ቀ​ድሞ የአ​ር​ቦቅ ከተማ ትባል ነበር፤ እር​ስ​ዋም የዔ​ና​ቃ​ው​ያን ዋና ከተማ ነበ​ረች። ምድ​ሪ​ቱም ከው​ጊያ ዐረ​ፈች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">የይ​ሁ​ዳም ነገድ ድን​በር በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ከኤ​ዶ​ም​ያስ ዳርቻ፥ ከጺን ምድረ በዳ ጀምሮ በዐ​ዜብ በኩል እስከ ቃዴስ ድረስ ነው።</verse>
				<verse number="2">በደ​ቡ​ብም በኩል ያለው ድን​በ​ራ​ቸው እስከ ጨው ባሕር ዳርቻ ወደ ሊባ እስ​ከ​ሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ነበረ።</verse>
				<verse number="3">ከዚ​ያም በአ​ቅ​ረ​ቢን ዐቀ​በት ፊት ይሄ​ዳል፤ ወደ ጺንም ይወ​ጣል፤ በቃ​ዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ይወ​ጣል፤ በአ​ስ​ሮ​ንም በኩል ያል​ፋል፤ ወደ ሰራ​ዳም ይወ​ጣል፥ ወደ ቃዴስ ምዕ​ራ​ብም ይዞ​ራል።</verse>
				<verse number="4">ወደ አጽ​ሞ​ንም ያል​ፋል፤ በግ​ብ​ፅም ሸለቆ በኩል ይወ​ጣል፤ የድ​ን​በ​ሩም መውጫ በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ፤ በደ​ቡብ በኩል ያለው ድን​በ​ራ​ቸው ይህ ነው።</verse>
				<verse number="5">በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ያለው ድን​በ​ራ​ቸው እስከ ጨው ባሕር እስከ ዮር​ዳ​ኖ​ስም ነበረ። በሰ​ሜ​ንም በኩል ያለው ድን​በር በዮ​ር​ዳ​ኖስ መጨ​ረሻ እስ​ካ​ለው እስከ ባሕሩ ልሳን ድረስ ነበረ፤</verse>
				<verse number="6">ከዚ​ያም ድን​በ​ራ​ቸው ወደ ቤተ ገለ​ዓም ይወ​ጣል፤ በቤ​ት​ዓ​ረባ በሰ​ሜን በኩል ያል​ፋል፤ ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ወደ ሮቤል ልጅ ወደ ሊቶን ቢዮን ይወ​ጣል፤</verse>
				<verse number="7">ድን​በ​ሩም በአ​ኮር ሸለቆ አራ​ተኛ ክፍል ላይ ይወ​ጣል፤ በአ​ዱ​ሚን ዐቀ​በት ፊት ለፊት፥ በደ​ቡብ በኩል ወዳ​ለ​ችው ወደ ጌል​ገላ ይወ​ር​ዳል፤ ድን​በ​ሩም ወደ ፀሐይ ምንጭ ውኃ ያል​ፋል፤ መው​ጫ​ውም በሮ​ጌል ምንጭ አጠ​ገብ ነበረ፤</verse>
				<verse number="8">ድን​በ​ሩም በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ አጠ​ገብ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ​ም​ት​ባ​ለው ወደ ኢያ​ቡስ ወደ ደቡብ ወገን ይወ​ጣል፤ ድን​በ​ሩም በሰ​ሜን በኩል በራ​ፋ​ይም ሸለቆ ዳር ባለው በሄ​ኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በባ​ሕር በኩል ወዳ​ለው ተራራ ራስ ላይ ይወ​ጣል፤</verse>
				<verse number="9">ድን​በ​ሩም ከተ​ራ​ራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ይሄ​ዳል፤ ወደ ዔፍ​ሮ​ንም ተራራ ይደ​ር​ሳል፤ ወደ ኢያ​ሪም ከተማ ወደ በኣላ ይደ​ር​ሳል።</verse>
				<verse number="10">ድን​በ​ሩም ከበ​ኣላ በባ​ሕር በኩል ያል​ፋል፤ ከዚ​ያም በኢ​ያ​ሪም ከተማ ደቡብ በኩ​ልና በኪ​ስ​ሎን ሰሜን በኩል ወደ አሥ​ራ​ቱስ ድን​በር ያል​ፋል፤ በፀ​ሐይ ከተ​ማም ላይ ይወ​ር​ዳል፤ በሊ​ባም በኩል ያል​ፋል።</verse>
				<verse number="11">ድን​በ​ሩም ወደ አቃ​ሮን ደቡብ ይወ​ጣል፤ ወደ ሰሜን ወገን ይመ​ለ​ሳል፤ ድን​በሩ ወደ ሰቆት ይወ​ጣል፤ ወደ ደቡ​ብም ያል​ፋል፤ በሌ​ብና በኩ​ልም ይወ​ጣል፤ የድ​ን​በ​ሩም መውጫ በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ።</verse>
				<verse number="12">በባ​ሕር በኩል ያለው ድን​በ​ራ​ቸ​ውም እስከ ታላቁ ባሕ​ርና እስከ ዳር​ቻው ድረስ ነበረ። ለይ​ሁዳ ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው በዙ​ሪ​ያው ያለ ድን​በ​ራ​ቸው ይህ ነው።</verse>
				<verse number="13">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ለዮ​ፎኒ ልጅ ለካ​ሌብ በይ​ሁዳ ልጆች መካ​ከል ድር​ሻ​ውን ሰጠው፤ ኢያ​ሱም የዔ​ናቅ ዋና ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን የአ​ር​ቦ​ቅን ከተማ ሰጠው። እር​ስ​ዋም ኬብ​ሮን ናት።</verse>
				<verse number="14">የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌ​ብም ሦስ​ቱን የዔ​ና​ቅን ልጆች ሱሲን፥ ተለ​ሚ​ንና አካ​ሚን ከዚያ አጠ​ፋ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">ከዚ​ያም ካሌብ በዳ​ቤር ሰዎች ላይ ዘመተ፤ የዳ​ቤ​ርም ስም አስ​ቀ​ድሞ “ሀገረ መጻ​ሕ​ፍት” ነበረ።</verse>
				<verse number="16">ካሌ​ብም፥ “ሀገረ መጻ​ሕ​ፍ​ትን ለሚ​መታ፥ ለሚ​ይ​ዛ​ትም ልጄን አክ​ሳን ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="17">የካ​ሌብ ወን​ድም የቄ​ኔዝ ልጅ ጎቶ​ን​ያል ያዛት፤ ልጁን አክ​ሳ​ንም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠው።</verse>
				<verse number="18">እር​ስ​ዋም ወደ እርሱ በመ​ጣች ጊዜ “አባ​ቴን እርሻ ልለ​ም​ነው” ብላ አማ​ከ​ረ​ችው፤ እር​ስ​ዋም በአ​ህ​ያዋ ላይ ሆና ጮኸች፤ ካሌ​ብም፥ “ምን ሆንሽ?” አላት።</verse>
				<verse number="19">እር​ስ​ዋም፥ “በረ​ከ​ትን ስጠኝ፤ በደ​ቡብ በኩል ያለ​ውን ምድር ሰጥ​ተ​ኸ​ኛ​ልና አሁን ደግሞ የው​ኃ​ውን ምን​ጭ ስ​ጠኝ” አለ​ችው። እር​ሱም የላ​ይ​ኛ​ው​ንና የታ​ች​ኛ​ውን ምንጭ ሰጣት።</verse>
				<verse number="20">በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም የይ​ሁዳ ልጆች ነገድ ርስት ይህ ነው።</verse>
				<verse number="21">በደ​ቡ​ብም በኩል በም​ድ​ራ​ቸው ዳርቻ እስከ ኤዶ​ም​ያስ ድን​በር ያሉት የይ​ሁዳ ልጆች ነገድ ከተ​ሞች እነ​ዚህ ነበሩ፤ ቤሴ​ሌ​ኤል፥ አራ፥ አሦር፤</verse>
				<verse number="22">ኤቃም፥ ሬግማ፥ አሩ​ሔል፤</verse>
				<verse number="23">ቃዴስ፥ አሶ​ር​ዮ​ስም፤ ሚናን፤</verse>
				<verse number="24">በል​ማ​ንና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም፤</verse>
				<verse number="25">የአ​ሴ​ሮም ከተ​ሞች እር​ስ​ዋም አሶር ናት።</verse>
				<verse number="26">ሲን፥ ሰላ​ማዓ፥ ሞላዳ፤</verse>
				<verse number="27">ሴሪ፥ ቤፋ​ላድ፤</verse>
				<verse number="28">ኮላ​ሴ​ዎል፥ ቤር​ሳ​ቤ​ሕና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="29">ባላ፥ ባቆ​ብና አሶም፤</verse>
				<verse number="30">ኤለ​ቦ​ሂ​ዳድ፥ ቤቴ​ልና ኤር​ማም፤</verse>
				<verse number="31">ሴቄ​ላቅ፥ ማኬ​ሪ​ምር፥ ሴቱ​ናቅ፤</verse>
				<verse number="32">ላቦስ ሳሌ፥ ኤር​ሞ​ትም ሃያ ዘጠኝ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="33">በቆ​ላው፥ አስ​ጣል፥ ሳራዓ፥ አሳ፤</verse>
				<verse number="34">ራሜ፥ ጣኖ፥ ኢዱ​ቶት፥ መሐ​ንስ፤</verse>
				<verse number="35">ኤር​ሙት፥ ኤዶ​ላም፥ ሜም​ብራ፥ ሰአክ፥ አዚቃ፤</verse>
				<verse number="36">ሴቃ​ርም፥ ጋዴ​ርና ሰፈ​ሮ​ችዋ፥ ዐሥራ አራት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="37">ሴና፥ አዳ​ሶን፥ ማጋ​ዳ​ል​ጋድ፤</verse>
				<verse number="38">አዶ​ላል፥ መሴፋ፥ ይቃ​ሩል፥ ለኪስ፤</verse>
				<verse number="39">በሴ​ዶት ይዴሃ፥ ደል​ያም፤</verse>
				<verse number="40">ኮብራ፥ ማኬስ፥ መሐ​ኮ​ስም፤</verse>
				<verse number="41">ጌዶር፥ በጋ​ድ​ያል፥ ኖማን፥ መቄ​ዶም፥ ዐሥራ ስድ​ስት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="42">ሌምና፥ ኤተቅ፥ አኖክ፥</verse>
				<verse number="43">ኢድና ናሲ​ብም፤</verse>
				<verse number="44">ኤላም፥ አቁ​ዛም፥ ኬዜብ ቴርሳ፥ ኤሎ​ምም፥ ዐሥር ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="45">አቃ​ሮን ከመ​ን​ደ​ሮ​ች​ዋና ከመ​ሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ችዋ ጋር።</verse>
				<verse number="46">ከአ​ቃ​ሮ​ንና ከጌ​ምና ጀምሮ በአ​ሴ​ዶት አቅ​ራ​ቢያ ያሉ ሁሉና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው፤</verse>
				<verse number="47">አሴ​ያ​ዶት መን​ደ​ሮ​ች​ዋና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም፥ ጋዛም መን​ደ​ሮ​ች​ዋና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ፥ ታላቁ ባሕ​ርም ወሰኑ ነው።</verse>
				<verse number="48">የሳ​ምር ተራ​ራ​ዎች ፥ ኢዩ​ቴር፥ ሦካ፤</verse>
				<verse number="49">ሬና፥ የመ​ጽ​ሐፍ ሀገር የሆ​ነች ዳቤር፤</verse>
				<verse number="50">አኖን፥ ሴቄማ፥ ኤሳ​ማም፤</verse>
				<verse number="51">ጎሶም ከሉም፥ ከናም፥ ዐሥራ አንድ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="52">ኤሬም፥ ሬምና፥ ሶማ፤</verse>
				<verse number="53">ኢያ​ማ​ይን፥ ቤታ​ቁም፥ ፋቁሕ፤</verse>
				<verse number="54">ኤውማ፥ የአ​ር​ቦቅ ከተማ እር​ስ​ዋም ኬብ​ሮን ናት፥ ሶሬት፥ ዘጠኝ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="55">ማሖር፥ ኬር​ሜል፥ አዚብ፥ ኢጣን፤</verse>
				<verse number="56">ኢያ​ሬ​ዬል፥ ኢያ​ሪ​ቅም፥ ዘቃ​ይ​ንም፤</verse>
				<verse number="57">ጋባ፥ ተምና፥ ዘጠኝ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="58">አሌዋ፥ ቤተ​ሱር፥ ጌዶር፤</verse>
				<verse number="59">ማዕ​ራት፥ ቤት​አ​ኖት፥ ኤል​ት​ቆን፥ ስድ​ስት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="60">ቴቆ፥ ኤፍ​ራታ፥ ይኽ​ች​ውም ቤተ ልሔም ናት፤ ፋጎ​ርም፥ ኤጣ​ንም፥ ቁሎን፥ ጠጦ​ንም፥ ሶብ​ሄም፥ ቃሬም፥ ጌሌም፥ ኤቴር፥ መነ​ኮም፥ ዐሥራ አንድ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው፥ ቅር​ያ​ት​በ​ኣል፥ ይኽ​ች​ውም የኢ​ያ​ርም ከተማ ናት፤ ሶቤታ፥ ሁለቱ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="61">ባዳ​ር​ጊስ፥ ተራ​ብ​ዐ​ምም፥ ኤኖን፤ ሴኬ​ዎ​ዛን፥</verse>
				<verse number="62">ናፍ​ላ​ዛ​ንና ከተ​ሞ​ቻ​ቸው፥ ሳዶን፥ አቃ​ዴስ፥ ሰባት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="63">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ግን የይ​ሁዳ ልጆች ሊያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ቸው አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ውም፤ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም እስከ ዛሬ ድረስ በይ​ሁዳ ልጆች መካ​ከል በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ ተቀ​ም​ጠ​ዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">የዮ​ሴ​ፍም ልጆች ድን​በ​ራ​ቸው በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በም​ሥ​ራቅ በኩል ካለው ከዮ​ር​ዳ​ኖስ አን​ሥቶ በም​ድረ በዳ​ውና በተ​ራ​ራ​ማው በኩል ከኢ​ያ​ሪኮ ሎዛ ትባል ወደ ነበ​ረ​ችው ቤቴል ይደ​ር​ሳል፤</verse>
				<verse number="2">ከቤ​ቴል ሎዛም በከ​ሮ​ንቲ ዳርቻ በኩል ወደ አጣ​ሮት አው​ራጃ ይደ​ር​ሳል፤</verse>
				<verse number="3">ወደ ምዕ​ራ​ብም እስከ የፍ​ሌ​ጣ​ው​ያን ዳርቻ እስከ ታች​ኛው ቤቶ​ሮን ዳርቻ ድረስ ይወ​ር​ዳል፤ መው​ጫ​ውም በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ።</verse>
				<verse number="4">የዮ​ሴ​ፍም ልጆች ምና​ሴና ኤፍ​ሬም ርስ​ታ​ቸ​ውን ወረሱ።</verse>
				<verse number="5">የኤ​ፍ​ሬ​ምም ልጆች ድን​በር በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እን​ደ​ዚህ ነበረ፤ የር​ስ​ታ​ቸው ድን​በር ከአ​ጣ​ሮ​ትና፥ ከኤ​ሮሕ ምሥ​ራቅ ከጋ​ዛራ እስከ ላይ​ኛው ቤቶ​ሮን ድረስ ነበረ፤</verse>
				<verse number="6">ድን​በ​ሩም ወደ ምዕ​ራብ ወደ አካ​ስ​ሞን በቴ​ርማ ሰሜን ያል​ፋል፤ ወደ ምሥ​ራ​ቅም ወደ ቲና​ስና ሴላስ ይዞ​ራል፥ ከም​ሥ​ራ​ቅም ወደ ኢያ​ኖክ ያል​ፋል።</verse>
				<verse number="7">ከኢ​ያ​ኖ​ክም ወደ መአ​ኮና፥ ወደ አጣ​ሮ​ትም፥ ወደ መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ያል​ፋል፤ ወደ ኢያ​ሪ​ኮም ይገ​ባል፥ ወደ ዮር​ዳ​ኖ​ስም ይወ​ጣል።</verse>
				<verse number="8">ድን​በ​ሩም ከጣፉ ወደ ባሕር እስከ ኬል​ቃን ወንዝ ድረስ ያል​ፋል፥ መው​ጫ​ውም በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ። የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ነገድ ርስት በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="9">ይኸ​ውም በም​ናሴ ልጆች ርስት መካ​ከል ለኤ​ፍ​ሬም ልጆች ከተ​ለዩ ከተ​ሞች ጋር፥ ከተ​ሞች ሁሉ ከመ​ን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ጋር ነው።</verse>
				<verse number="10">በጋ​ዜ​ርም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን ኤፍ​ሬም አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በኤ​ፍ​ሬም መካ​ከል ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ገባ​ርም ሆኑ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">የም​ናሴ ልጆች ነገድ ድን​በር ይህ ነው፤ የዮ​ሴፍ በኵር እርሱ ነውና። የም​ና​ሴም በኵር የገ​ለ​ዓድ አባት ማኪር ብርቱ ተዋጊ ስለ ነበረ ገለ​ዓ​ድ​ንና ባሳ​ንን ወረሰ።</verse>
				<verse number="2">ዕጣ​ውም ለቀ​ሩት ለም​ናሴ ልጆች በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው፥ ለኢ​ያ​ዜር ልጆች፥ ለቄ​ሌዝ ልጆች፥ ለኢ​የ​ዚ​ኤል ልጆች፥ ለሴ​ኬም ልጆች፥ ለሱ​ማ​ሪም ልጆች፥ ለኦ​ፌር ልጆች ሆነ፤ ወን​ዶቹ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="3">ለኦ​ፌር ልጅ፥ ለሰ​ለ​ጰ​ዓድ ግን ሴቶች ልጆች እንጂ ወን​ዶች ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​ትም፤ የሰ​ለ​ጰ​ዐ​ድም የሴ​ቶች ልጆቹ ስሞች፦ መሐላ፥ ኑዓ፥ ሔግላ፥ ሚልካ፥ ቴርሳ ነበሩ።</verse>
				<verse number="4">እነ​ር​ሱም ወደ ካህኑ ወደ አል​ዓ​ዛ​ርና ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱ ወደ አለ​ቆ​ችም ቀር​በው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን መካ​ከል ርስት እን​ዲ​ሰ​ጠን በሙሴ እጅ አዘዘ” አሉ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ከአ​ባ​ታ​ቸው ወን​ድ​ሞች ጋር ርስት ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">ዕጣ​ቸ​ውም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ከአ​ለው ከገ​ለ​ዓ​ድና ከባ​ሳን ሀገር በቀር ለም​ናሴ ዐሥር ዕጣ ሆነ፤</verse>
				<verse number="6">የም​ናሴ ሴቶች ልጆች በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው መካ​ከል ርስት ተቀ​ብ​ለ​ዋ​ልና፤ የገ​ለ​ዓ​ድም ምድር ለቀ​ሩት ለም​ናሴ ልጆች ሆኖ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="7">የም​ና​ሴም ልጆች ድን​በር በሐ​ነት ልጆች ፊት ያለው ዴላ​ናታ ነው። በኢ​ያ​ሚ​ንና በኢ​ያ​ሲብ ድን​በር በተ​ፍ​ቶት ምንጭ ላይ ያል​ፋል።</verse>
				<verse number="8">የጣ​ፌት ምድር ለም​ናሴ ነበረ፤ ጣፌት ግን በኤ​ፍ​ሬም ልጆ​ችና በም​ናሴ ልጆች አው​ራጃ ያለ ነው።</verse>
				<verse number="9">ድን​በ​ራ​ቸ​ውም በደ​ቡብ በኩል ወዳ​ለው ወደ ቃራና ሸለ​ቆና ወደ ኢያ​ሪ​ያል ሸለቆ ይወ​ር​ዳል፤ የኤ​ፍ​ሬም ዕጣ የሆ​ነው ጤሬ​ሜ​ን​ቶስ የሚ​ባ​ለው ዛፍም በም​ናሴ ከተ​ሞች መካ​ከል አለ፤ የም​ና​ሴም ድን​በር በሰ​ሜን በኩል ወደ ወንዙ ይወ​ር​ዳል፤ መው​ጫ​ውም በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ።</verse>
				<verse number="10">በደ​ቡብ በኩል ያለው ለኤ​ፍ​ሬም ነበረ፤ በሰ​ሜን በኩል ያለ​ውም ለም​ናሴ ነበረ፤ ድን​በ​ሩም ባሕር ነበረ፤ በሰ​ሜን በኩል ወደ አሴር፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ወደ ይሳ​ኮር ይደ​ር​ሳል።</verse>
				<verse number="11">በይ​ሳ​ኮ​ርና በአ​ሴር መካ​ከል ቤት​ሳ​ንና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ ዶርና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ መጌ​ዶና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ የመ​ፌታ ሦስ​ተኛ እጅና መን​ደ​ሮ​ችዋ ለም​ናሴ ነበሩ።</verse>
				<verse number="12">የም​ናሴ ልጆ​ችም የእ​ነ​ዚ​ህን ከተ​ሞች ሰዎች ማጥ​ፋት ተሳ​ና​ቸው፤ ነገር ግን ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በዚ​ያች ሀገር ለመ​ቀ​መጥ መጡ።</verse>
				<verse number="13">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በረ​ቱ​ባ​ቸው፤ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም ገዙ​አ​ቸው፤ ነገር ግን ፈጽ​መው አላ​ጠ​ፉ​አ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="14">የዮ​ሴ​ፍም ልጆች ኢያ​ሱን፥ “እኛ ብዙ ሕዝብ ስን​ሆን እስከ አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ባረ​ከን ለምን አንድ ክፍል፥ አን​ድም ዕጣ ብቻ ርስት አድ​ር​ገህ ሰጠ​ኸን?” ብለው ወቀ​ሱት።</verse>
				<verse number="15">ኢያ​ሱም፥ “ብዙ ሕዝብ ከሆ​ና​ችሁ፥ ተራ​ራ​ማው የኤ​ፍ​ሬም ሀገ​ርም ከጠ​በ​ባ​ችሁ ወደ ዱር ወጥ​ታ​ችሁ መን​ጥ​ራ​ችሁ አቅ​ኑ​አት” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">እነ​ር​ሱም፥ “ተራ​ራ​ማው የኤ​ፍ​ሬም ሀገር አይ​በ​ቃ​ንም፤ በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ለሚ​ኖ​ሩት፥ በቤ​ት​ሳ​ንና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ልም ሸለቆ ለሚ​ኖ​ሩት ከነ​ዓ​ና​ው​ያን የተ​መ​ረጡ ፈረ​ሶ​ችና ሰይፍ አሏ​ቸው” አሉት።</verse>
				<verse number="17">ኢያ​ሱም ለዮ​ሴፍ ልጆች፥ “እና​ንተ ብዙ ሕዝብ ከሆ​ና​ችሁ፥ ጽኑ ኀይ​ልም ከአ​ላ​ችሁ አንድ ዕጣ ብቻ አይ​ሆ​ን​ላ​ች​ሁም፤</verse>
				<verse number="18">ነገር ግን ተራ​ራ​ማው ሀገር ለእ​ና​ንተ ይሆ​ናል፤ ዱር እንኳ ቢሆ​ንም ትመ​ነ​ጥ​ሩ​ታ​ላ​ችሁ፤ ለእ​ና​ን​ተም ይሆ​ናል፤ ለከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም የተ​መ​ረጡ ፈረ​ሶ​ችና የብ​ረት ሰረ​ገ​ሎች ቢሆ​ኑ​ላ​ቸው፥ የበ​ረቱ ቢሆ​ኑም እና​ንተ እስ​ክ​ታ​ጠ​ፉ​አ​ቸው ድረስ ትበ​ረ​ቱ​ባ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በሴሎ ተሰ​በ​ሰቡ፤ በዚ​ያም የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ተከሉ፤ ምድ​ሩም ጸጥ ብሎ ተገ​ዛ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ርስት ያል​ተ​ካ​ፈሉ ሰባት ነገድ ቀር​ተው ነበር።</verse>
				<verse number="3">ኢያ​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አላ​ቸው፥ “የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጣ​ች​ሁን ምድር እን​ዳ​ት​ወ​ር​ሱ​አት እስከ መቼ ድረስ ታቈ​ዩ​አ​ታ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="4">ከየ​ነ​ገ​ዳ​ችሁ ሁሉ ሦስት ሦስት ሰዎ​ችን አምጡ፥ ተነ​ሥ​ተ​ውም ሀገ​ሪ​ቱን ይዙ​ሩ​አት፤ ለመ​ክ​ፈ​ልም እን​ዲ​ያ​መች ገል​ጠው ይጻ​ፉ​አት፤ ወደ እኔም ይመ​ለ​ሳሉ።</verse>
				<verse number="5">በሰ​ባ​ትም ክፍል ይከ​ፍ​ሉ​ታል፤ ይሁዳ በደ​ቡብ በኩል በዳ​ር​ቻው ውስጥ ይቀ​መ​ጣል፤ የዮ​ሴ​ፍም ልጆች በሰ​ሜን በኩል በዳ​ር​ቻው ውስጥ ይቀ​መ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="6">እና​ን​ተም ምድ​ሪ​ቱን በሰ​ባት ክፍል ክፈ​ሏት፤ ወደ እኔም ወዲህ አም​ጡ​ልኝ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዚህ ዕጣ አጣ​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክህ​ነት ርስ​ታ​ቸው ነውና ለሌዊ ልጆች በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እድል ፋንታ የላ​ቸ​ውም፤ ጋድም፥ ሮቤ​ልም፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በም​ሥ​ራቅ በኩል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ርስ​ታ​ቸ​ውን ተቀ​ብ​ለ​ዋል።”</verse>
				<verse number="8">ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው ሄዱ፤ ኢያ​ሱም ምድ​ሩን ሊጽፉ የሄ​ዱ​ትን፥ “ሂዱ፤ ምድ​ሩ​ንም ዞራ​ችሁ ጻፉት፤ ወደ እኔም ተመ​ለሱ፤ በዚ​ህም በሴሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዕጣ አጣ​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ሰዎ​ቹም ሄደው ምድ​ሩን ዞሩ፥ አዩ​ትም፤ እንደ ከተ​ሞ​ችም በሰ​ባት ክፍል ከፈ​ሉት፤ በመ​ጽ​ሐ​ፍም ጻፉት፤ ወደ ኢያ​ሱም አመጡ።</verse>
				<verse number="10">ኢያ​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሴሎ ዕጣ አጣ​ጣ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">የብ​ን​ያ​ምም ነገድ ዕጣ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው በቅ​ድ​ሚያ ወጣ፤ የዕ​ጣ​ቸ​ውም ዳርቻ በይ​ሁዳ ልጆ​ችና በዮ​ሴፍ ልጆች መካ​ከል ወጣ።</verse>
				<verse number="12">በሰ​ሜን በኩል ድን​በ​ራ​ቸው ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ጀመረ፤ ድን​በ​ሩም ከኢ​ያ​ሪኮ አዜብ ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፥ ከዚ​ያም በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ወደ ባሕር ወጣ፤ መው​ጫ​ውም የቤ​ቶን ምድ​ብ​ራ​ይ​ጣስ ነበረ።</verse>
				<verse number="13">ድን​በ​ሩም ከዚያ በደ​ቡብ በኩል ቤቴል ወደ​ም​ት​ባል ወደ ሎዛ ዐለፈ፤ ድን​በ​ሩም በታ​ች​ኛው ቤቶ​ሮን ደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ ማአ​ጣ​ሮ​ቶ​ሬክ ወረደ።</verse>
				<verse number="14">ድን​በ​ሩም ወደ ባሕር ሄደ፤ በቤ​ቶ​ሮ​ንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ አዜብ ዞረ፤ መው​ጫ​ውም ቂር​ያ​ታ​ርም በም​ት​ባል በይ​ሁዳ ልጆች ከተማ በቂ​ር​ያ​ት​በ​ኣል ነበረ፤ ይህ በባ​ሕር በኩል ነበረ።</verse>
				<verse number="15">የደ​ቡ​ብም ዳርቻ ከቅ​ር​ያ​ታ​ርም መጨ​ረሻ ነበረ፤ ድን​በ​ሩም በጋ​ሲን ላይ ወደ ነፍቶ ውኃ ምንጭ ወጣ።</verse>
				<verse number="16">ድን​በ​ሩም በሄ​ኖም ሸለቆ ፊት ለፊት ወዳ​ለው ተራራ መጨ​ረሻ ወረደ፤ እር​ሱም በራ​ፋ​ይም ሸለቆ በሰ​ሜን በኩል ነው፤ ወደ ሄኖም ሸለቆ ወደ ኢያ​ቡስ ዳር በደ​ቡብ በኩል ወረደ፥ ወደ ሮጌል ምን​ጭም ወረደ።</verse>
				<verse number="17">ወደ ቤተ​ሳ​ሚ​ስም ምንጭ ያል​ፋል፤ በኢ​ታ​ሚም አቀ​በት ፊት ለፊት ወዳ​ለው ወደ ኬል​ዩት ይገ​ባል፤ ወደ ሮቤ​ልም ልጅ ወደ ቤዎን ድን​ጋይ ይወ​ር​ዳል፤</verse>
				<verse number="18">በሰ​ሜ​ንም በኩል ወደ ቤተ ራባ ጀርባ ያል​ፋል። በመ​ስ​ዕም ወደ ባሕር መን​ገድ ይወ​ር​ዳል፤</verse>
				<verse number="19">የድ​ን​በ​ራ​ቸ​ውም ፍጻሜ በሰ​ሜን በኩል ወደ ጨው ባሕር ልሳን ይደ​ር​ሳል፤ በደ​ቡ​ብም በኩል ድን​በ​ራ​ቸው ዮር​ዳ​ኖስ ነው። ይህም በደ​ቡብ በኩል ያለው ድን​በር ነው።</verse>
				<verse number="20">በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ድን​በሩ ዮር​ዳ​ኖስ ነበረ። ይህ በዙ​ሪ​ያ​ቸው ዳርቻ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው የብ​ን​ያም ልጆች ርስት ነበረ።</verse>
				<verse number="21">የብ​ን​ያ​ምም ልጆች ነገድ ከተ​ሞች በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ነበሩ፤ ኢያ​ሪኮ፥ ቤት​ሖ​ግሊ፥ ዐመ​ቀ​ስስ፤</verse>
				<verse number="22">ቤተ ባራ፥ ሰራ፥ ቤስና፤</verse>
				<verse number="23">አኢን፥ ፋራ፥ ኤፍ​ራ​ታም፥</verse>
				<verse number="24">ቃራፋ፥ ቄፍራ፥ ሞኒ፥ ጋባህ፤ ዐሥራ ሁለቱ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">ገባ​ዖን፥ ራማ፥ ብኤ​ሮት፤</verse>
				<verse number="26">ማሴማ፥ ቤሮን፥ አሞቂ፥</verse>
				<verse number="27">ቤራ፥ ቃፋን፥ ናቃና፥ ሴሌ​ቃን፥ ታራ​ኤላ፤</verse>
				<verse number="28">ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ት​ባል የኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎን ከተ​ማና የኢ​ያ​ሪ​ሞን ከተማ ገባ​ዖን፤ ዐሥራ ሦስት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው። የብ​ን​ያም ልጆች ርስት በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለስ​ም​ዖን ልጆች ነገድ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ወጣ፤ ርስ​ታ​ቸ​ውም በይ​ሁዳ ልጆች ርስት መካ​ከል ነበረ።</verse>
				<verse number="2">ዕጣ​ቸ​ውም እነ​ዚህ ነበሩ፤ ቤር​ሳ​ቤህ፥ ሰማህ፥ ቆሎ​ዶን፤</verse>
				<verse number="3">አር​ሳላ፥ ባላ፥ ኢያ​ሶ​ንም፤</verse>
				<verse number="4">ኤር​ቱላ፥ ቡላ፥ ሔር​ማም፤</verse>
				<verse number="5">ሴቄ​ላቅ፥ ቤተ​ማ​ኮ​ሬብ፥ ሰር​ሱ​ሲን፤</verse>
				<verse number="6">ቦታ​ሩ​ትና ሜዳ​ዎ​ቻ​ቸው፥ ዐሥራ ሦስት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው፤</verse>
				<verse number="7">ሬሞን፥ ቴልካ፥ ኢያ​ቴር፥ አሳ​ንም፥ አራት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው፤</verse>
				<verse number="8">እስከ ባሌቅ ድረስ በእ​ነ​ዚህ ከተ​ሞች ዙሪያ ያሉ መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ሁሉ ናቸው። ይህም በባ​ሜት ላይ ወደ ደቡብ ያል​ፋል። የስ​ም​ዖን ልጆች ነገድ ርስት በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="9">ከይ​ሁዳ ልጆች ክፍል የስ​ም​ዖን ልጆች ርስት ሆነ፤ የይ​ሁ​ዳም ልጆች ዕድል ፋንታ ስለ በዛ​ባ​ቸው የስ​ም​ዖን ልጆች በር​ስ​ታ​ቸው መካ​ከል ወረሱ።</verse>
				<verse number="10">ሦስ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለዛ​ብ​ሎን ልጆች በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ወጣ፤ የር​ስ​ታ​ቸ​ውም ድን​በር እስከ ኤሴ​ዴቅ ጎላ ነበረ፤</verse>
				<verse number="11">ድን​በ​ራ​ቸ​ውም በም​ዕ​ራብ በኩል ወደ ማራ​ጌላ ይወ​ጣል፤ እስከ ቤተ ራባም ይደ​ር​ሳል፤ በኢ​ያ​ቃ​ንም ፊት ለፊት ወዳ​ለው ሸለ​ቆም ይደ​ር​ሳል፤</verse>
				<verse number="12">ከሴ​ዱ​ቅም ወደ ቤተ ሳሚስ ምሥ​ራቅ ወደ ካሲ​ሎ​ቴት ዳርቻ ይዞ​ራል፤ ወደ ዳቤ​ሮ​ትም ይወ​ጣል፤ ወደ ፋን​ጊም ይደ​ር​ሳል፤</verse>
				<verse number="13">ከዚ​ያም ወደ ጌቤሮ ምሥ​ራቅ ወደ ከታ​ሤም ከተማ ያል​ፋል፤ ወደ ሪና​ሞን ወደ ማታ​ር​ዮዛ ይወ​ጣል።</verse>
				<verse number="14">ድን​በ​ሩም በሰ​ሜን በኩል ወደ አሞት ይዞ​ራል፥ መው​ጫ​ውም በሐ​ናት በኩል በጌ​ፋ​ሄል ሸለቆ ነበረ።</verse>
				<verse number="15">ቃጠ​ናት፥ ናባ​ሐል፥ ሲም​ዖን፥ ኢያ​ሪሆ፥ ቤቴ​ሜ​ንም፤ ዐሥራ ሁለት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">የዛ​ብ​ሎን ልጆች ነገድ ርስት በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ናቸው።</verse>
				<verse number="17">አራ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለይ​ሳ​ኮር ልጆች ወጣ።</verse>
				<verse number="18">ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ኢይ​ዝ​ራ​ኤል፥ ከል​ሰ​ሉት፥ ሱሳን፤</verse>
				<verse number="19">አጊን፥ ሴዎ​ንና፥ ርሄቱ፥</verse>
				<verse number="20">አን​ከ​ሬት፥ ዳቤ​ሮት፥ ቂሶን፥ ሮቤስ፤</verse>
				<verse number="21">ሬማስ፥ ያዖን፥ ቶማን፥ ኤሜ​ሬቅ፥ ቤር​ሳ​ፌስ ነበረ።</verse>
				<verse number="22">ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ወደ ታቦ​ርና ወደ ሰሌም፥ በም​ዕ​ራብ በኩል ወደ ቤተ​ሳ​ሚስ ይደ​ር​ሳል፤ የድ​ን​በ​ራ​ቸው መው​ጫም ዮር​ዳ​ኖስ ነበረ፤ ዐሥራ ስድ​ስት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="23">የይ​ሳ​ኮር ልጆች ነገድ ርስት በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ናቸው።</verse>
				<verse number="24">አም​ስ​ተ​ኛው ዕጣ ለአ​ሴር ልጆች ነገድ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ወጣ።</verse>
				<verse number="25">ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ኤል​ኬት፥ ኤሌፍ፥ ቤቶቅ፥ ቂያፍ፤</verse>
				<verse number="26">አሊ​ሜ​ሌክ፥ አሜ​ሕል፥ ማሕሳ ነበር፤ በባ​ሕ​ርም በኩል ወደ ቀር​ሜ​ሎስ፥ ወደ ሴዎ​ንና ሊበ​ናት ይደ​ር​ሳል፤</verse>
				<verse number="27">ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ቤቴ​ጌ​ነት ይዞ​ራል፤ በመ​ስ​ዕም በኩል ከዛ​ብ​ሎ​ንና ከጋይ ከይ​ፍ​ታ​ሕ​ኤል ይያ​ያ​ዛል ወደ ሳፍቱ ቤታ​ሜ​ሕና ወደ ኢን​ሂል ይደ​ር​ሳል፤ ወደ ኮባ ማሾ​ሜ​ልም ያል​ፋል፤</verse>
				<verse number="28">ከዚ​ያም ወደ ኤብ​ሮን፥ ወደ ረዓብ፥ ወደ አሜ​ማ​ህን፥ ወደ ቀን​ታን እስከ ታላቁ ሲዶና ይደ​ር​ሳል።</verse>
				<verse number="29">ድን​በ​ሩም ወደ ራማ፥ ወደ መስ​ፋጥ ምንጭ ወደ ጢሮስ ይዞ​ራል፤ ድን​በ​ሩም ወደ ኢያ​ሴፍ ይዞ​ራል፤ መው​ጫ​ውም በሌ​ብና በኮ​ዛብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ፤</verse>
				<verse number="30">አር​ኮብ፥ አፌቅ፥ ረአ​ውም ደግሞ ነበሩ፤ ሃያ ሁለት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="31">የአ​ሴር ልጆች ነገድ ርስት በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ናቸው።</verse>
				<verse number="32">ስድ​ስ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለን​ፍ​ታ​ሌም ልጆች ነገድ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ወጣ።</verse>
				<verse number="33">ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ከመ​ሐ​ላም፥ ከሞ​ላም፥ ከቤ​ሴ​ሜ​ይን፥ ከአ​ርሜ፥ ከና​ቦ​ቅና፥ ከኢ​ያ​ፍ​ታ​ሜን እስከ ይዳም ድረስ ነበረ፤ መው​ጫ​ውም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ነበረ።</verse>
				<verse number="34">ድን​በ​ሩም ወደ ምዕ​ራብ ወደ አዝ​ኖ​ት​ታ​ቦር ይዞ​ራል፤ ከዚ​ያም ወደ ያቃና ይወ​ጣል፤ ከዚ​ያም በደ​ቡብ በኩል ወደ ዛብ​ሎን፤ በም​ዕ​ራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም በፀ​ሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ይደ​ር​ሳል።</verse>
				<verse number="35">የተ​መ​ሸ​ጉ​ትም የሲ​ዶና ከተ​ሞች እነ​ዚህ ነበሩ፤ ጤሮስ፥ አማ​ታ​ዳ​ቄት፥ ቄሬት፥</verse>
				<verse number="36">አር​ሜት፥ አራ​ሂን፥ አሦር፥</verse>
				<verse number="37">ቃዴስ፥ አስ​ራ​ይስ፥ የአ​ሦር ምንጭ፥</verse>
				<verse number="38">ቄሮህ፥ ሚጋ​ላ​ህ​ሪም፥ ቤታ​ሚና፥ ቴስ​ሚስ፤ ዐሥራ ዘጠኝ መን​ደ​ሮ​ችና ከተ​ሞ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="39">የን​ፍ​ታ​ሌም ልጆች ነገድ ርስት እነ​ዚህ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ናቸው።</verse>
				<verse number="40">ሰባ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለዳን ልጆች ወጣ።</verse>
				<verse number="41">የር​ስ​ታ​ቸ​ውም ዳርቻ ይህ ነበረ፤ ሠራ​ሕት፥ አሳ፥ የሰ​መ​ውስ ከተማ፥</verse>
				<verse number="42">ሰሊ​ባን፥ አሞን፥ ሴላታ፥</verse>
				<verse number="43">ኤሎን፥ ቴም​ናታ፥ አቃ​ሮን፥</verse>
				<verse number="44">አል​ቃታ፥ ቤጌ​ቶን፥ ጌቤ​ላን፥</verse>
				<verse number="45">አዞር፥ ቤኔ​ቤ​ቃት፥ ጌት​ሬ​ሞን፤</verse>
				<verse number="46">በባ​ሕር በኩል በኢ​ዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ኢያ​ራ​ቆን።</verse>
				<verse number="47">የዳን ልጆች ነገድ ርስት በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ናቸው። የዳን ልጆ​ችም በተ​ራ​ራው ላይ የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቋ​ቸው አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አላ​ስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸ​ውም። አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ወደ ሸለ​ቆ​ዎች ይወ​ርዱ ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ዱ​ላ​ቸ​ውም። ከእ​ነ​ር​ሱም ከር​ስ​ታ​ቸው ዳርቻ አንድ ክፍ​ልን ወሰዱ።</verse>
				<verse number="48">የዳን ልጆ​ችም ሄደው ለኪ​ስን መቱ​አት፤ ከተ​ማ​ቸ​ው​ንም ያዟት፤ በሰ​ይ​ፍም መቱ​አት። በው​ስ​ጥ​ዋም ተቀ​መጡ። ስሟ​ንም በአ​ባ​ታ​ቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩ​አት። አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም በኤ​ዶ​ምና በሰ​ላ​ሚን ለመ​ኖር ቀጠሉ። የኤ​ፍ​ሬ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ በእ​ነ​ርሱ ላይ በረ​ታች። ገባ​ሪ​ዎ​ችም ሆኑ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="49">ምድ​ሩ​ንም ሁሉ በየ​ድ​ን​በሩ ርስት እን​ዲ​ሆን ከፍ​ለው ከጨ​ረሱ በኋላ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለነዌ ልጅ ለኢ​ያሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ርስት ሰጡት።</verse>
				<verse number="50">በኤ​ፍ​ሬም ተራ​ራማ ሀገር ያለ​ች​ውን ተም​ና​ሴራ የም​ት​ባ​ለ​ውን የፈ​ለ​ጋ​ትን ከተማ ሰጡት፤ ከተ​ማም ሠርቶ ተቀ​መ​ጠ​ባት።</verse>
				<verse number="51">ካህኑ አል​ዓ​ዛር፥ የነ​ዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ነገ​ዶች የአ​ባ​ቶች አለ​ቆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሴሎ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አጠ​ገብ በዕጣ የተ​ካ​ፈ​ሉት ርስት ይህ ነው። ምድ​ሪ​ቱ​ንም መካ​ፈል ፈጸሙ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="2">“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ በሙሴ ቃል የነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁን የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞ​ችን ስጡ።</verse>
				<verse number="3">ባለ​ማ​ወቅ ሳይ​ወ​ድድ ሰውን የገ​ደለ በዚያ ይማ​ፀን ዘንድ፥ ለእ​ና​ንተ የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞ​ችን ሥሩ፤ ነፍስ የገ​ደለ ሰውም በአ​ደ​ባ​ባይ ለፍ​ርድ እስ​ኪ​ቀ​ርብ ድረስ በደም ተበ​ቃዩ አይ​ገ​ደል።</verse>
				<verse number="4">ከእ​ነ​ዚ​ህም ከተ​ሞች በአ​ን​ዲቱ ይማ​ፀ​ናል፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በር አደ​ባ​ባይ ቆሞ ለከ​ተ​ማ​ዪቱ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ነገ​ሩን ይና​ገ​ራል፤ እነ​ር​ሱም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ያገ​ቡ​ታል። የሚ​ቀ​መ​ጥ​በ​ትም ስፍራ ይሰ​ጡ​ታል።</verse>
				<verse number="5">ባለ ደሙ ቢያ​ሳ​ድ​ደው፥ አስ​ቀ​ድሞ ሳይ​ጠ​ላው ባል​ን​ጀ​ራ​ውን በስ​ሕ​ተት ስለ ገደ​ለው ነፍሰ ገዳ​ዩን በእጁ አሳ​ል​ፈው አይ​ስ​ጡት።</verse>
				<verse number="6">በማ​ኅ​በሩ ፊት ለፍ​ርድ እስ​ኪ​ቆም ድረስ ፥ በዚ​ያም ወራት ያለው ታላቁ ካህን እስ​ኪ​ሞት ድረስ በዚ​ያች ከተማ ይቀ​መጥ፤ ከዚ​ያም ወዲያ ነፍሰ ገዳዩ ይመ​ለ​ሳል፤ ወደ ከተ​ማ​ውም፥ ወደ ቤቱም ሸሽቶ ወደ ወጣ​በ​ትም ከተማ ይገ​ባል።”</verse>
				<verse number="7">በን​ፍ​ታ​ሌም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር በገ​ሊላ ቃዴ​ስን፥ በኤ​ፍ​ሬ​ምም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ሴኬ​ምን፥ በይ​ሁ​ዳም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ኬብ​ሮን የም​ት​ባ​ለ​ውን የአ​ር​ቦ​ቅን ከተማ ለዩ።</verse>
				<verse number="8">በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ ከኢ​ያ​ሪኮ ወደ ምሥ​ራቅ ከሮ​ቤል ነገድ በም​ድረ በዳው በደ​ል​ዳ​ላው ስፍራ ቦሶ​ርን፥ ከጋ​ድም ነገድ በገ​ለ​ዓድ ኤር​ሞ​ትን፥ ከም​ና​ሴም ነገድ በባ​ሳን ጎላ​ንን ለዩ።</verse>
				<verse number="9">በማ​ኅ​በሩ ፊት እስ​ኪ​ቆ​ምና እስ​ኪ​መ​ረ​መር ድረስ ባለ​ደሙ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ለው ሳያ​ውቅ ሰውን የገ​ደለ ወደ​ዚያ እን​ዲ​ማ​ፀን፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ፥ በመ​ካ​ካ​ላ​ቸ​ውም ለሚ​ቀ​መጥ መጻ​ተኛ የተ​መ​ረጡ ከተ​ሞች እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">የሌዊ ልጆች አለ​ቆች ወደ ካህኑ ወደ አል​ዓ​ዛር፥ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ሕዝብ አባ​ቶች ነገ​ዶች አለ​ቆች መጡ፤</verse>
				<verse number="2">በከ​ነ​ዓን ምድር ባለ​ችው በሴሎ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ የም​ን​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸ​ውን ከተ​ሞች፥ ለከ​ብ​ቶ​ቻ​ች​ንም መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎች ትሰ​ጡን ዘንድ አዝ​ዞ​አል” ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ከር​ስ​ታ​ቸው እነ​ዚ​ህን ከተ​ሞ​ችና መሰ​ማ​ር​ያ​ቸ​ውን ለሌ​ዋ​ው​ያን ሰጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ለቀ​ዓ​ትም ወገ​ኖች ልጆች ዕጣ ወጣ፤ ሌዋ​ው​ያ​ንም ለነ​በሩ ለካ​ህኑ ለአ​ሮን ልጆች ከይ​ሁዳ ነገድ፥ ከስ​ም​ዖ​ንም ነገድ፥ ከብ​ን​ያ​ምም ነገድ ዐሥራ ሦስት ከተ​ሞች በዕጣ ተሰ​ጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">ለቀ​ሩ​ትም ለቀ​ዓት ልጆች ከኤ​ፍ​ሬም ነገድ፥ ከዳ​ንም ነገድ፥ ከም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ዐሥር ከተ​ሞች በዕጣ ተሰ​ጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">ለጌ​ድ​ሶ​ንም ልጆች ከይ​ሳ​ኮር ነገድ፥ ከአ​ሴ​ርም ነገድ፥ ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምም ነገድ፥ በባ​ሳ​ንም ካለው ከም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ዐሥራ ሦስት ከተ​ሞች በዕጣ ተሰ​ጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">ለሜ​ራ​ሪም ልጆች በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ከሮ​ቤል ነገድ፥ ከጋ​ድም ነገድ፥ ከዛ​ብ​ሎ​ንም ነገድ ዐሥራ ሁለት ከተ​ሞች ተሰ​ጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እነ​ዚ​ህን ከተ​ሞ​ችና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ለሌ​ዋ​ው​ያን በዕጣ ሰጡ።</verse>
				<verse number="9">የይ​ሁ​ዳም ልጆች ነገድ፥ የስ​ም​ዖ​ንም ልጆች ነገድ፥ የብ​ን​ያ​ምም ልጆች ነገድ በስ​ማ​ቸው የተ​ጠ​ሩ​ትን እነ​ዚ​ህን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">የፊ​ተ​ኛው ዕጣ ለእ​ነ​ርሱ ስለ​ወጣ የሌዊ ልጆች የቀ​ዓት ወገን ለሆኑ ለአ​ሮን ልጆች ሆኑ።</verse>
				<verse number="11">የኤ​ናቅ ልጆች ከተማ ቅር​ያ​ት​ያ​ር​ቦ​ቅ​ንና በዙ​ሪ​ያዋ ያሉ መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ችን ሰጡ​አ​ቸው፤ ይህ​ች​ውም በይ​ሁዳ ተራራ ያለች ኬብ​ሮን ናት።</verse>
				<verse number="12">ኢያ​ሱም የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱን እርሻ መን​ደ​ሮ​ች​ዋ​ንም ለዮ​ፎኒ ልጅ ለካ​ሌብ ልጆች ርስት አድ​ርጎ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">ለካ​ህ​ኑም ለአ​ሮን ልጆች እነ​ዚ​ህን ሰጡ፤ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን ኬብ​ሮ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ሌም​ና​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥</verse>
				<verse number="14">ኤቴ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኤታ​ም​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤</verse>
				<verse number="15">ሄሎ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ዳቤ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥</verse>
				<verse number="16">አሳ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ዮጣ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቤት​ሳ​ሚ​ስ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ከእ​ነ​ዚህ ከሁ​ለቱ ነገ​ዶች ዘጠኝ ከተ​ሞ​ችን ሰጡ።</verse>
				<verse number="17">ከብ​ን​ያ​ምም ነገድ ገባ​ዖ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ጋቲ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤</verse>
				<verse number="18">ዓና​ቶ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ አል​ሞ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራት ከተ​ሞ​ችን ሰጡ።</verse>
				<verse number="19">የካ​ህ​ናቱ የአ​ሮን ልጆች ከተ​ሞች ከመ​ሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ጋር ዐሥራ ሦስት ናቸው፤</verse>
				<verse number="20">ለቀ​ሩ​ትም ለሌ​ዋ​ው​ያኑ ለቀ​ዓት ልጆች የዕ​ጣ​ቸው ከተ​ሞች ከኤ​ፍ​ሬም ነገድ ደረ​ሱ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን ሴኬ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ጌዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤</verse>
				<verse number="22">ቄብ​ጻ​ይ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቤቶ​ሮ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">ከዳ​ንም ነገድ ኤል​ቆ​ታ​ይ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ገባ​ቶ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤</verse>
				<verse number="24">ኤሎ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ጌቴ​ራ​ሞ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">ከም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ጠና​ሕ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ዬባ​ታ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ሁለ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">የቀ​ሩት የቀ​ዓት ልጆች ወገ​ኖች ከተ​ሞች ሁሉ ከመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ቸው ጋር ዐሥር ናቸው።</verse>
				<verse number="27">ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ወገ​ኖች ለጌ​ድ​ሶን ልጆች ከም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ በባ​ሳን ውስጥ የሆ​ነ​ች​ውን ጎላ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቦሶ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ሁለ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="28">ከይ​ሳ​ኮ​ርም ነገድ ቂሶ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ዳብ​ራ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤</verse>
				<verse number="29">ሬማ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ዓይ​ን​ጋ​ኒ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="30">ከአ​ሴ​ርም ነገድ መሴ​ላ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ አቤ​ዶ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥</verse>
				<verse number="31">ሔል​ቃ​ት​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ረዓ​ብ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱ​ንም ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="32">ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምም ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን በገ​ሊላ ውስጥ ቃዴ​ስ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኤማ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቃር​ቴ​ን​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፤ ሦስ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="33">የጌ​ድ​ሶን ልጆች ከተ​ሞች ሁሉ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ዐሥራ ሦስት ከተ​ሞች ከመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ቸው ጋር ናቸው።</verse>
				<verse number="34">ከሌ​ዋ​ው​ያን ለቀ​ሩት ለሜ​ራሪ ልጆች ወገን ከዛ​ብ​ሎን ነገድ ዮቅ​ና​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቃዴ​ስ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥</verse>
				<verse number="35">ዲም​ና​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ሴላ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ።</verse>
				<verse number="36">በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል ከሮ​ቤል ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ በሚ​ሶን ምድረ በዳ ቦሶ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኢያ​ዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤</verse>
				<verse number="37">ቄዴ​ሞ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ሜፍ​ዐ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ።</verse>
				<verse number="38">ከጋ​ድም ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን በገ​ለ​ዓድ ውስጥ ራሞ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቃሚ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤</verse>
				<verse number="39">ሐሴ​ቦ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኢያ​ዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ።</verse>
				<verse number="40">ከሌዊ ወገ​ኖች የቀ​ሩት የሜ​ራሪ ልጆች ከተ​ሞች ሁሉ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ነበሩ፤ ዕጣ​ቸ​ውም ዐሥራ ሁለት ከተማ ነበረ።</verse>
				<verse number="41">በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርስት መካ​ከል የነ​በ​ሩት የሌ​ዋ​ው​ያን ከተ​ሞች ሁሉ በእ​ነ​ዚህ ከተ​ሞች ዙሪያ ካሉ ከመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ጋር አርባ ስም​ንት ከተ​ሞች ነበሩ።</verse>
				<verse number="42">እነ​ዚ​ህም ከተ​ሞች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ቸው ጋር ነበሩ፤ እነ​ዚ​ህም ከተ​ሞች ሁሉ እን​ዲሁ ነበሩ። [ኢያ​ሱም በየ​ድ​ን​በ​ሮ​ቻ​ቸው ምድ​ርን ማካ​ፈ​ልን ጨረሰ። የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ለኢ​ያሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ድር​ሻ​ውን ሰጡት፤ እርሱ የሚ​ፈ​ል​ጋ​ትን ከተማ በኤ​ፍ​ሬም ተራራ የም​ት​ገ​ኘ​ውን ቴም​ና​ሴ​ራን ሰጡት፤ ከተ​ማም ሠራ​ባት፤ በው​ስ​ጧም ተቀ​መጠ። ኢያ​ሱም በም​ደረ በዳ በመ​ን​ገድ የተ​ወ​ለ​ዱ​ትን የገ​ረ​ዘ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ባል​ጩ​ቶች ወስዶ በቴ​ም​ና​ሴራ አኖ​ራ​ቸው።]</verse>
				<verse number="43">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ምድር ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሰጠ፤ ወረ​ሱ​አ​ትም፥ ተቀ​መ​ጡ​ባ​ትም።</verse>
				<verse number="44">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው እንደ ማለ​ላ​ቸው በዙ​ሪ​ያ​ቸው ካሉት አሳ​ረ​ፋ​ቸው፤ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ይቋ​ቋ​ማ​ቸው ዘንድ ማንም ሰው አል​ቻ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ በእ​ጃ​ቸው አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="45">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ከተ​ና​ገ​ረው መል​ካም ነገር ሁሉ ተፈ​ጸመ እንጂ ምንም አል​ቀ​ረም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">በዚ​ያን ጊዜም ኢያሱ የሮ​ቤ​ልን ልጆ​ችና የጋ​ድን ልጆች የም​ና​ሴ​ንም ነገድ እኩ​ሌታ ጠርቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፦</verse>
				<verse number="2">“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ ያዘ​ዛ​ች​ሁን ሁሉ ሰም​ታ​ች​ኋል፤ እኔም ላዘ​ዝ​ኋ​ችሁ ነገር ሁሉ ታዝ​ዛ​ች​ኋል፤</verse>
				<verse number="3">ይህ​ንም ያህል ብዙ ጊዜ እስከ ዛሬ ድረስ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን አል​ተ​ዋ​ች​ሁም፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ጠብ​ቃ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="4">አሁ​ንም አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ራ​ቸው ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን አሳ​ር​ፎ​አ​ቸ​ዋል፤ አሁን እን​ግ​ዲህ ተመ​ለሱ፤ ወደ ቤታ​ች​ሁና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ሰጣ​ችሁ ወደ ርስ​ታ​ችሁ ምድር ሂዱ።</verse>
				<verse number="5">ብቻ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ ያዘ​ዛ​ች​ሁን ትእ​ዛ​ዙ​ንና ሕጉን ታደ​ርጉ ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ትወ​ድዱ ዘንድ፥ መን​ገ​ዱ​ንም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ትጠ​ብቁ ዘንድ፥ እር​ሱ​ንም ትከ​ተሉ ዘንድ፥ በፍ​ጹ​ምም ልባ​ችሁ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ሳ​ችሁ ታመ​ል​ኩት ዘንድ እጅግ ተጠ​ን​ቀቁ።”</verse>
				<verse number="6">ኢያ​ሱም መረ​ቃ​ቸው፤ አሰ​ና​በ​ታ​ቸ​ውም፤ ወደ ቤታ​ቸ​ውም ሄዱ።</verse>
				<verse number="7">ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ሙሴ በባ​ሳን ውስጥ ርስት ሰጥ​ቶ​አ​ቸው ነበር፤ ለቀ​ረው ለእ​ኩ​ሌ​ታው ግን ኢያሱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በባ​ሕር በኩል በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው መካ​ከል ርስት ሰጣ​ቸው። ኢያ​ሱም ወደ ቤታ​ቸው በአ​ሰ​ና​በ​ታ​ቸው ጊዜ እን​ዲህ ብሎ መረ​ቃ​ቸው፦</verse>
				<verse number="8">“በብዙ ብል​ጥ​ግና፥ በእ​ጅ​ግም ብዙ ከብት፥ በብ​ርም፥ በወ​ር​ቅም፥ በና​ስም፥ በብ​ረ​ትም፥ በእ​ጅ​ግም ብዙ ልብስ ወደ ቤታ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ የጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ምርኮ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ጋር ተካ​ፈሉ።”</verse>
				<verse number="9">የሮ​ቤ​ልም ልጆች የጋ​ድም ልጆች የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ሄዱ፤ በሙ​ሴም እጅ በተ​ሰጠ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ወደ ተቀ​በ​ሉት ወደ ርስ​ታ​ቸው ወደ ገለ​ዓድ ምድር ይገቡ ዘንድ በከ​ነ​ዓን ምድር ካለ​ችው ከሴሎ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="10">በከ​ነ​ዓን ምድር ወዳ​ለው ወደ ዮር​ዳ​ኖስ አቅ​ራ​ቢ​ያም ወደ ገለ​ዓድ በመጡ ጊዜ የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ በዚያ በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ የሚ​ታይ ታላቅ መሠ​ዊያ ሠሩ።</verse>
				<verse number="11">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በከ​ነ​ዓን ምድር ዳርቻ በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ ባለው በገ​ለ​ዓድ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ባሉ​በት ወገን፥ የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ መሠ​ዊያ እንደ ሠሩ ሰሙ።</verse>
				<verse number="12">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ይህን በሰሙ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ወጥ​ተው እነ​ር​ሱን ሊዋጉ በሴሎ ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="13">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በገ​ለ​ዓድ ምድር ወዳ​ሉት ወደ ሮቤል ልጆ​ችና ወደ ጋድ ልጆች ወደ ምና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ የካ​ህኑ የአ​ሮ​ንን ልጅ የአ​ል​ዓ​ዛ​ርን ልጅ ፊን​ሐ​ስን ላኩ።</verse>
				<verse number="14">ዐሥር አለ​ቆ​ችም ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ አንድ አንድ የእ​የ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት አለቃ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም በእ​ስ​ራ​ኤል አእ​ላ​ፋት መካ​ከል የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት አለቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="15">በገ​ለ​ዓ​ድም ምድር ወዳ​ሉት ወደ ሮቤል ልጆ​ችና ወደ ጋድ ልጆች፥ ወደ ምና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ደረሱ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ነገ​ሩ​አ​ቸው</verse>
				<verse number="16">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማኅ​በር ሁሉ የሚ​ለው ይህ ነው፥ “ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መከ​ተ​ልን ትተዉ ዘንድ፥ መሠ​ዊ​ያም ትሠሩ ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ዛሬ ትክ​ዱት ዘንድ ይህ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ፊት ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ኀጢ​አት ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="17">እኛ እስከ ዛሬ ድረስ ከእ​ርሱ ያል​ነ​ጻ​ን​በት የፌ​ጎር ኀጢ​አት ጥቂት ነውን? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማኅ​በር ላይ መቅ​ሠ​ፍት ወረደ።</verse>
				<verse number="18">እና​ንተ ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መከ​ተ​ልን ትታ​ች​ኋል፤ ዛሬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ብታ​ምፁ ነገ በእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ላይ መቅ​ሠ​ፍት ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="19">ነገር ግን የር​ስ​ታ​ችሁ ምድር ቢያ​ን​ሳ​ችሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪያ ወደ​ሚ​ቀ​መ​ጥ​በት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት ምድር አል​ፋ​ችሁ ከእኛ ጋር ውረሱ፤ ከአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ውጭ ለእ​ና​ንተ መሠ​ዊያ ሠር​ታ​ች​ኋ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አት​ካዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አት​ተ​ዉት።</verse>
				<verse number="20">የዛራ ልጅ አካን እርም ነገር በመ​ው​ሰድ ኀጢ​አ​ትን ስለ ሠራ በእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ላይ ቍጣ አል​ወ​ረ​ደ​ምን? እር​ሱም ብቻ​ውን ቢበ​ድል በኀ​ጢ​አቱ ብቻ​ውን ሞተን?”</verse>
				<verse number="21">የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ለእ​ስ​ራ​ኤል አእ​ላ​ፋት አለ​ቆች እን​ዲህ ብለው መለ​ሱ​ላ​ቸው፦</verse>
				<verse number="22">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነው፤ ጌታም ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ ነው፤ እርሱ ያው​ቃል። እስ​ራ​ኤ​ልም ያው​ቀ​ዋል። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያደ​ረ​ግ​ነው ለበ​ደ​ልና ለመ​ካድ ከሆነ ዛሬ አያ​ድ​ነን፤</verse>
				<verse number="23">አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ድ​ን​ክ​ደው፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ልን ቍር​ባን እን​ድ​ና​ሳ​ር​ግ​በት፥ የደ​ኅ​ን​ነ​ት​ንም መሥ​ዋ​ዕት እን​ድ​ና​ቀ​ር​ብ​በት መሠ​ዊያ ሠር​ተን እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ ራሱ ይመ​ራ​መ​ረን፤</verse>
				<verse number="24">ይል​ቁ​ንም ከል​ባ​ችን ፍር​ሀት የተ​ነሣ፦ ነገ ልጆ​ቻ​ችሁ ልጆ​ቻ​ች​ንን፦ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አም​ላክ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ምን አላ​ችሁ? እን​ዳ​ይ​ሉ​አ​ቸው ስለ​ፈ​ራን ይህን የሠ​ራ​ነው ካል​ሆነ፥ እና​ንተ የሮ​ቤ​ልና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ፥</verse>
				<verse number="25">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ኛና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ዮር​ዳ​ኖ​ስን ድን​በር አድ​ር​ጎ​አ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ዕድል ፋንታ የላ​ች​ሁም ይሉ​አ​ቸ​ዋል፤ በዚ​ሁም ልጆ​ቻ​ችሁ ልጆ​ቻ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከማ​ም​ለክ እን​ዳ​ያ​ወ​ጡ​አ​ቸው ብለን ይህን አደ​ረ​ግን።</verse>
				<verse number="26">ስለ​ዚ​ህም መሠ​ዊያ እን​ሥራ አልን፤ ነገር ግን ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ወይም ለቍ​ር​ባን አይ​ደ​ለም፤</verse>
				<verse number="27">ነገር ግን በእ​ኛና በእ​ና​ንተ መካ​ከል፥ ከእ​ኛም በኋላ በት​ው​ል​ዳ​ች​ንና በት​ው​ል​ዳ​ችሁ መካ​ከል በሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና በቍ​ር​ባን፥ በደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ልክ ዘንድ፥ ነገ ልጆ​ቻ​ችሁ ልጆ​ቻ​ች​ንን፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ዕድል ፋንታ የላ​ች​ሁም እን​ዳ​ይሉ ምስ​ክር ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="28">ኋላ ይህ በተ​ደ​ረገ ጊዜ ነገ ለእኛ ወይም ለት​ው​ል​ዳ​ችን ይህን ሲሉ፥ እኛ፦ እነሆ፥ አባ​ቶ​ቻ​ችን ያደ​ረ​ጉ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መሠ​ዊያ ምሳሌ እዩ፤ በእ​ኛና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ምስ​ክር ነው እንጂ ስለ​ሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና ስለ ቍር​ባን አይ​ደ​ለም እን​ላ​ለን።</verse>
				<verse number="29">በድ​ን​ኳኑ ፊት ካለው ከአ​ም​ላ​ካ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሌላ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና ለሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕት፥ ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ትም የሚ​ሆን መሠ​ዊ​ያን የሠ​ራ​ነው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ በማ​መፅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ዛሬ መከ​ተ​ልን ለመ​ተው በማ​ለት እንደ ሆነ ይህ ከእኛ ይራቅ።”</verse>
				<verse number="30">ካህኑ ፊን​ሐ​ስና የማ​ኅ​በሩ አለ​ቆች፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት የእ​ስ​ራ​ኤል መሳ​ፍ​ንት ሁሉ ፥ የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ የተ​ና​ገ​ሩ​ትን ቃል በሰሙ ጊዜ ዝም አሉ፤ ደስም አሰ​ኛ​ቸው።</verse>
				<verse number="31">የካ​ህ​ኑም የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ ለሮ​ቤል ልጆ​ችና ለጋድ ልጆች ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ፥ “ይህን መተ​ላ​ለፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ አላ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችን እን​ዳለ ዛሬ እና​ው​ቃ​ለን፤ አሁን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ አድ​ና​ች​ኋል” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="32">የካ​ህ​ኑም የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ ከእ​ር​ሱም ጋር የማ​ኅ​በሩ አለ​ቆች ከሮ​ቤል ልጆ​ችና ከጋድ ልጆች፥ ከም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ዘንድ ከገ​ለ​ዓድ ሀገር ወደ ከነ​ዓን ሀገር ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ተመ​ለሱ፤ ወሬም አመ​ጡ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="33">ነገ​ሩም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ደስ አሰኘ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በነ​ገ​ሩ​አ​ቸው ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ፤ ከዚ​ያም ወዲያ የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ የተ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትን ምድር ያጠፉ ዘንድ ለመ​ው​ጋት አን​ወ​ጣም ተባ​ባሉ።</verse>
				<verse number="34">ኢያ​ሱም መሠ​ዊ​ያ​ውን “የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ምስ​ክር” ብሎ ጠራው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው እንደ ሆነ ይህ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ምስ​ክር ነውና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="23">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከብዙ ዘመን በኋላ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስ​ራ​ኤ​ልን በዙ​ሪ​ያ​ቸው ካሉት ጠላ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ ካሳ​ረፈ በኋላ፥ ኢያሱ ሸመ​ገለ፤ ዘመ​ኑም ዐለፈ፤</verse>
				<verse number="2">ኢያሱ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሁሉ፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ፈራ​ጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ሹሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ጠርቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ እነሆ ሸም​ግ​ያ​ለሁ፤ ዘመ​ኔም አል​ፎ​አል፤</verse>
				<verse number="3">እና​ን​ተም አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ታ​ችሁ ባሉ በእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ሁሉ ስለ እና​ንተ ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ አይ​ታ​ች​ኋል፤ ስለ እና​ንተ የተ​ዋጋ እርሱ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።</verse>
				<verse number="4">እነሆ እኔ ካጠ​ፋ​ኋ​ቸው አሕ​ዛብ ሁሉ ጋር ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ጀምሮ በፀ​ሐይ መግ​ቢያ እስ​ካ​ለው እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ለነ​ገ​ዶ​ቻ​ችሁ ርስት እን​ዲ​ሆኑ የቀ​ሩ​ትን እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ በዕጣ ከፈ​ል​ሁ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="5">አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ ከፊ​ታ​ችሁ እስ​ኪ​ደ​መ​ሰሱ ድረስ ያጠ​ፋ​ላ​ች​ኋል፤ ከፊ​ታ​ች​ሁም እነ​ር​ሱ​ንና ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ውን እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ የዱር አራ​ዊ​ትን ይሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ ምድ​ራ​ቸ​ውን ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="6">በሙሴ ሕግ መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ ትጠ​ብ​ቁና ታደ​ርጉ ዘንድ በጣም በርቱ፥ ከእ​ር​ሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አት​በሉ።</verse>
				<verse number="7">በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል ወደ ቀሩት ወደ እነ​ዚህ አሕ​ዛብ አት​ግቡ፤ የአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ስሞች በእ​ና​ንተ መካ​ከል አይ​ጠሩ፤ አት​ማ​ሉ​ባ​ቸ​ውም፤ አታ​ም​ል​ኳ​ቸ​ውም፤ አት​ስ​ገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፤</verse>
				<verse number="8">ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ እን​ዳ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁት አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተከ​ተሉ።</verse>
				<verse number="9">እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላ​ላ​ቆ​ች​ንና ኀይ​ለ​ኞ​ችን አሕ​ዛብ ከፊ​ታ​ችሁ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፤ እስከ ዛሬም ድረስ የተ​ቋ​ቋ​ማ​ችሁ በፊ​ታ​ችሁ ማንም የለም።</verse>
				<verse number="10">አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ረን ስለ እና​ንተ የሚ​ዋጋ እርሱ ነውና ከእ​ና​ንተ አንዱ ሰው ሺህ ሰውን ያሳ​ድ​ዳል።</verse>
				<verse number="11">አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድ​ዱት ዘንድ ለራ​ሳ​ችሁ እጅግ ተጠ​ን​ቀቁ።</verse>
				<verse number="12">እና​ንተ ግን ተመ​ል​ሳ​ችሁ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ወደ ቀሩት ወደ እነ​ዚህ አሕ​ዛብ ብት​ጠጉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ብት​ጋቡ፥ እና​ን​ተም ወደ እነ​ርሱ፥ እነ​ር​ሱም ወደ እና​ንተ ብት​ደ​ራ​ረሱ፥</verse>
				<verse number="13">አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ጣ​ችሁ ከዚ​ህች ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር እስ​ክ​ት​ጠፉ ድረስ መው​ደ​ቂ​ያና ወጥ​መድ፥ በእ​ግ​ራ​ች​ሁም ችን​ካር፥ በዐ​ይ​ና​ች​ሁም እሾህ ይሆ​ኑ​ባ​ች​ኋል እንጂ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ ከፊ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው ራሳ​ችሁ ዕወቁ።</verse>
				<verse number="14">“እኔም በም​ድር እን​ዳ​ሉት ሰዎች ሁሉ ዛሬ ወደ መን​ገድ እሄ​ዳ​ለሁ፤ እና​ን​ተም አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እኛ ከተ​ና​ገ​ረው ከመ​ል​ካም ነገር ሁሉ አንድ ነገር እን​ዳ​ል​ቀረ በል​ባ​ችሁ ሁሉ፥ በነ​ፍ​ሳ​ች​ሁም ሁሉ ዕወቁ፤ ሁሉ ደር​ሶ​ናል፤ ከእ​ር​ሱም ያላ​ገ​ኘ​ነው የለም።</verse>
				<verse number="15">አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረው መል​ካም ነገር ሁሉ እንደ ደረ​ሰ​ላ​ችሁ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ጣ​ችሁ ከዚ​ህች ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር እና​ን​ተን እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋ​ችሁ ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ ክፉን ነገር ሁሉ ያመ​ጣ​ባ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="16">አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዛ​ች​ሁን ቃል ኪዳን ብታ​ፈ​ርሱ፥ ሄዳ​ች​ሁም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ብታ​መ​ልኩ፥ ብት​ሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፥ በዚያ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ይነ​ድ​ድ​ባ​ች​ኋል፥ ከሰ​ጣ​ች​ሁም ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር ፈጥ​ና​ችሁ ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="24">
				<verse number="1">ኢያ​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴሎ ሰበ​ሰበ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ጸሓ​ፊ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ፈራ​ጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ጠራ​ቸው። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት አቆ​ማ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">ኢያ​ሱም ለሕ​ዝቡ ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘አባ​ቶ​ቻ​ችሁ፥ የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የና​ኮር አባት ታራ፥ አስ​ቀ​ድ​መው በወ​ንዝ ማዶ ተቀ​መጡ፤ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት አመ​ለኩ።</verse>
				<verse number="3">አባ​ታ​ች​ሁ​ንም አብ​ር​ሃ​ምን ከወ​ንዝ ማዶ ወስጄ በከ​ነ​ዓን ምድር ሁሉ መራ​ሁት፤ ዘሩ​ንም አበ​ዛሁ፤ ይስ​ሐ​ቅ​ንም ሰጠ​ሁት።</verse>
				<verse number="4">ለይ​ስ​ሐ​ቅም ያዕ​ቆ​ብ​ንና ዔሳ​ውን ሰጠ​ሁት፤ ለዔ​ሳ​ውም የሴ​ይ​ርን ተራራ ርስት አድ​ርጌ ሰጠ​ሁት፤ የያ​ዕ​ቆ​ብም ልጆች ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዚ​ያም ታላቅ ሕዝብ ሆኑ፤ በዙም፤ በረ​ቱም፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም መከራ አጸ​ኑ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">ሙሴ​ንና አሮ​ን​ንም ላክሁ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ ስላ​ደ​ረ​ጉት ነገር ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን ቀሠ​ፍ​ኋ​ቸው፤</verse>
				<verse number="6">ከዚ​ያም በኋላ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ኋ​ቸው፤ ወደ ባሕ​ሩም ገባ​ችሁ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችና በፈ​ረ​ሶች እስከ ኤር​ትራ ባሕር ድረስ ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጮ​ሃ​ችሁ ጊዜ በእ​ና​ን​ተና በግ​ብ​ፃ​ው​ያን መካ​ከል ደመ​ና​ንና ጭጋ​ግን አደ​ረ​ግሁ፤ ባሕ​ሩ​ንም መለ​ስ​ሁ​ባ​ቸው፤ አሰ​ጠ​ማ​ቸ​ውም፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም በግ​ብፅ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን አዩ፤ በም​ድረ በዳም ብዙ ጊዜ ተቀ​መ​ጣ​ችሁ።</verse>
				<verse number="8">በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ተቀ​መ​ጡት ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ምድ​ርም ወሰ​ድ​ኋ​ችሁ፤ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ተዋጉ፤ ሙሴም ተዋ​ጋ​ቸው፤ አሳ​ል​ፌም በእ​ጃ​ችሁ ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም ወረ​ሳ​ችሁ፤ ከፊ​ታ​ች​ሁም አጠ​ፋ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">የሞ​ዓ​ብም ንጉሥ የሴ​ፎር ልጅ ባላቅ ተነ​ሥቶ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ተዋጋ፤ እን​ዲ​ረ​ግ​ማ​ች​ሁም የቢ​ዖ​ርን ልጅ በለ​ዓ​ምን ልኮ አስ​ጠ​ራው።</verse>
				<verse number="10">እኔ ግን ላጠ​ፋ​ችሁ አል​ወ​ደ​ድ​ሁም፤ መባ​ረ​ክ​ንም ባረ​ክ​ኋ​ችሁ፤ ከእ​ጁም አዳ​ን​ኋ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="11">ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ገ​ራ​ችሁ፤ ወደ ኢያ​ሪ​ኮም መጣ​ችሁ፤ የኢ​ያ​ሪ​ኮም ሰዎች፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊው፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊው፥ ከነ​ዓ​ና​ዊው፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊው፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊው፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊው፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊው ተዋ​ጉ​አ​ችሁ፥ አሳ​ል​ፌም በእ​ጃ​ችሁ ሰጠ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">በፊ​ታ​ች​ሁም ተርብ ሰደ​ድሁ፤ በሰ​ይ​ፍ​ህም፥ በቀ​ስ​ት​ህም ሳይ​ሆን ዐሥራ ሁለ​ቱን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ነገ​ሥ​ታት ከፊ​ታ​ችሁ አሳ​ደ​ድ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">ያል​ደ​ከ​ማ​ች​ሁ​በ​ት​ንም ምድር፥ ያል​ሠ​ራ​ች​ኋ​ቸ​ው​ንም ከተ​ሞች ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ ተቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​ባ​ቸ​ውም፤ ካል​ተ​ከ​ላ​ች​ኋ​ቸ​ውም ከወ​ይ​ንና ከወ​ይራ በላ​ችሁ።’</verse>
				<verse number="14">“አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍሩት፤ በእ​ው​ነ​ትና በቅ​ን​ነ​ትም አም​ል​ኩት፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በወ​ንዝ ማዶ፥ በግ​ብ​ፅም ውስጥ ያመ​ለ​ኩ​አ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት ከእ​ና​ንተ አርቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አም​ልኩ።</verse>
				<verse number="15">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ልኩ ዘንድ ባት​ወ​ድዱ ግን፥ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ በወ​ንዝ ማዶ ሳሉ ያመ​ለ​ኩ​አ​ቸ​ውን አማ​ል​ክት፥ ወይም በም​ድ​ራ​ቸው ያላ​ች​ሁ​ባ​ቸ​ውን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አማ​ል​ክት ታመ​ልኩ እንደ ሆነ፥ የም​ታ​መ​ል​ኩ​ትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ካ​ለን፤ እርሱ ቅዱስ ነውና።”</verse>
				<verse number="16">ሕዝ​ቡም መል​ሰው እን​ዲህ አሉ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተን ሌሎች አማ​ል​ክ​ትን ማም​ለክ ከእኛ ይራቅ፤</verse>
				<verse number="17">እኛ​ንና አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን ከባ​ር​ነት ቤት ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣን፥ በዐ​ይ​ና​ች​ንም ፊት እነ​ዚ​ያን ታላ​ላቅ ተአ​ም​ራት ያደ​ረገ፥ በሄ​ድ​ን​ባ​ትም መን​ገድ ሁሉ፥ ባለ​ፍ​ን​ባ​ቸ​ውም አሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል የጠ​በ​ቀን፥ እርሱ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና።</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሕ​ዛ​ብን ሁሉ፥ በም​ድ​ሪ​ቱም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ከፊ​ታ​ችን አሳ​ደደ፤ ስለ​ዚህ እርሱ አም​ላ​ካ​ችን ነውና እኛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ካ​ለን።”</verse>
				<verse number="19">ኢያ​ሱም ሕዝ​ቡን፥ “እርሱ ቅዱስ አም​ላክ ነውና፥ እር​ሱም ቀና​ተኛ አም​ላክ ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማም​ለክ አት​ች​ሉም፤ ብታ​ስ​ቀ​ኑት መተ​ላ​ለ​ፋ​ች​ሁ​ንና ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁን ይቅር አይ​ልም።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትታ​ችሁ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ብታ​መ​ልኩ፥ መል​ካ​ምን ባደ​ረ​ገ​ላ​ችሁ ፋንታ ተመ​ልሶ ክፉ ነገር ያደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋል፤ ያጠ​ፋ​ች​ሁ​ማል” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">ሕዝ​ቡም ኢያ​ሱን፥ “እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ካ​ለን” አሉት።</verse>
				<verse number="22">ኢያ​ሱም ሕዝ​ቡን፥ “እን​ድ​ታ​መ​ል​ኩት እና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ መረ​ጣ​ችሁ በራ​ሳ​ችሁ ላይ ምስ​ክ​ሮች ናችሁ” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “ምስ​ክ​ሮች ነን” አሉ።</verse>
				<verse number="23">እር​ሱም፥ “አሁን እን​ግ​ዲህ በእ​ና​ንተ ዘንድ ያሉ​ትን ሌሎች አማ​ል​ክት አርቁ፤ ልባ​ች​ሁ​ንም ወደ እስ​ራ​ኤል አም​ላክ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅኑ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">ሕዝ​ቡም ኢያ​ሱን፥ “አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ካ​ለን፤ ቃሉ​ንም እን​ሰ​ማ​ለን” አሉት።</verse>
				<verse number="25">በዚ​ያም ቀን ኢያሱ ከሕ​ዝቡ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ በሴ​ሎም በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ድን​ኳን ፊት ሕግ​ንና ፍር​ድን ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">ኢያ​ሱም ይህን ቃል ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ መጽ​ሐፍ ጻፈው፤ ኢያ​ሱም ታላ​ቁን ድን​ጋይ ወስዶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በነ​በ​ረ​ችው በአ​ሆማ ዛፍ በታች አቆ​ማት።</verse>
				<verse number="27">ኢያ​ሱም ለሕ​ዝቡ ሁሉ፥ “ይህች ድን​ጋይ በእ​ና​ንተ ላይ ምስ​ክር ናት፤ እር​ስዋ፥ ዛሬ እንደ ነገ​ራ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ባ​ለ​ውን ሁሉ ሰም​ታ​ለ​ችና በኋላ ዘመን አም​ላ​ኬን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ብት​ክ​ዱት ይህች ድን​ጋይ ምስ​ክር ትሆ​ን​ባ​ች​ኋ​ለች” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="28">ኢያ​ሱም ሕዝ​ቡን አሰ​ና​በተ፤ ሁሉም ወደ​የ​ቦ​ታ​ቸው ገቡ።</verse>
				<verse number="29">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከዚህ ነገር በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ ዕድ​ሜው መቶ ዐሥር ዓመት ሲሆ​ነው ሞተ።</verse>
				<verse number="30">በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር በገ​ዓስ ተራራ በሰ​ሜን ባለ​ችው በር​ስቱ ዳርቻ በተ​ም​ና​ሴራ ቀበ​ሩት። በዚ​ያም ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በገ​ል​ገላ የገ​ረ​ዘ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ባል​ጩ​ቶ​ችን እር​ሱን በቀ​በ​ሩ​በት መቃ​ብር ከእ​ርሱ ጋር ቀበሩ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።</verse>
				<verse number="31">ኢያሱ ባለ​በት ዘመን ሁሉ፥ ከኢ​ያ​ሱም በኋላ በነ​በ​ሩት ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ያደ​ረ​ገ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ሁሉ ባወ​ቁት በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች ዘመን ሁሉ፥ እስ​ራ​ኤል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ለኩ።</verse>
				<verse number="32">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከግ​ብፅ ያወ​ጡ​ትን የዮ​ሴ​ፍን አፅም ያዕ​ቆብ በሰ​ቂማ ከሚ​ኖሩ ከአ​ሞ​ራ​ው​ያን በመቶ በጎች በገ​ዛው ለዮ​ሴፍ ድርሻ አድ​ርጎ በሰ​ጠው እርሻ በአ​ንዱ ክፍል በሰ​ቂማ ቀበ​ሩት።</verse>
				<verse number="33">የአ​ሮ​ንም ልጅ ሊቀ ካህ​ናቱ አል​ዓ​ዛር ሞተ፤ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ለልጁ ለፊ​ን​ሐስ በተ​ሰ​ጠ​ችው በጊ​ብ​ዓት መሬት ቀበ​ሩት።</verse>
				<verse number="34">የዚ​ያን ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይዘ​ዋት ሄዱ። ፊን​ሐ​ስም እስከ ሞተና በቦ​ታ​ቸው በጊ​ብ​ዓት እስከ ቀበ​ሩት ድረስ በአ​ባቱ በአ​ል​ዓ​ዛር ፋንታ ሊቀ ካህ​ናት ሆነ።</verse>
				<verse number="35">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ወደ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውና ወደ ቤታ​ቸው ገቡ። ከዚህ በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አስ​ጠ​ራ​ጢ​ን​ንና አስ​ጣ​ሮ​ትን፥ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም የነ​በ​ሩ​ትን የአ​ሕ​ዛ​ብን አማ​ል​ክት አመ​ለኩ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሞ​ዓብ ንጉሥ በኤ​ግ​ሎም እጅ ጣላ​ቸው፤ ዐሥራ ስም​ንት ዓመ​ትም ገዛ​ቸው።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="7">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ኢያሱ ከሞተ በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ “ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን የሚ​ወ​ጋ​ልን ማን አለቃ ይወ​ጣ​ል​ናል?” ብለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠየቁ።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይሁዳ ይውጣ፤ እነሆ፥ ምድ​ሪ​ቱን በእጁ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​አ​ታ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="3">ይሁ​ዳም ወን​ድ​ሙን ስም​ዖ​ንን፥ “ከእኔ ጋር ወደ ዕጣዬ ውጣ፤ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም እን​ው​ጋ​ቸው፤ እኔም ደግሞ ከአ​ንተ ጋር ወደ ዕጣህ እሄ​ዳ​ለሁ” አለው። ስም​ዖ​ንም ከእ​ርሱ ጋር ሄደ።</verse>
				<verse number="4">ይሁ​ዳም ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንና ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን በእጁ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በቤ​ዜቅ ውስጥ ዐሥር ሺህ ሰዎ​ችን ገደ​ለ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">አዶ​ኒ​ቤ​ዜ​ቅ​ንም በቤ​ዜቅ አገ​ኙ​ትና ተዋ​ጉት፤ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንና ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም ገደ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">አዶ​ኒ​ቤ​ዜ​ቅም ሸሸ፤ ተከ​ታ​ት​ለ​ውም ያዙት፤ የእ​ጁ​ንና የእ​ግ​ሩ​ንም አውራ ጣቶች ቈረጡ።</verse>
				<verse number="7">አዶ​ኒ​ቤ​ዜ​ቅም፥ “የእ​ጆ​ቻ​ቸ​ውና የእ​ግ​ሮ​ቻ​ቸው አውራ ጣቶች የተ​ቈ​ረጡ ሰባ ነገ​ሥ​ታት ከገ​በ​ታዬ በታች ፍር​ፋሪ ይለ​ቅሙ ነበሩ፤ እኔ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ መለ​ሰ​ልኝ” አለ። ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወሰ​ዱት፥ በዚ​ያም ሞተ።</verse>
				<verse number="8">የይ​ሁ​ዳም ልጆች ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ተዋ​ግ​ተው ያዙ​አት፤ በሰ​ይፍ ስለ​ትም መቱ​አት፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ሉ​አት።</verse>
				<verse number="9">ከዚ​ያም በኋላ የይ​ሁዳ ልጆች በተ​ራ​ራ​ማው ሀገ​ርና በደ​ቡብ በኩል በቈ​ላው ውስጥ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን ሊወጉ ወረዱ።</verse>
				<verse number="10">ይሁ​ዳም በኬ​ብ​ሮን ወደ​ሚ​ኖሩ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን ሄደ። የኬ​ብ​ሮ​ንም ሰዎች ወጥ​ተው ተቀ​በ​ሉት፤ የኬ​ብ​ሮ​ንም ስም አስ​ቀ​ድሞ ቂር​ያ​ታ​ር​ቦ​ቅ​ሴ​ፌር ነበረ። የኤ​ና​ቅ​ንም ትው​ልድ ሴሲ​ንና አኪ​ማ​ምን፥ ተለ​ሜ​ን​ንም ገደ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ከዚ​ያም ወደ ዳቤር ሰዎች ሄዱ፤ አስ​ቀ​ድ​ሞም የዳ​ቤር ስም ሀገረ መጻ​ሕ​ፍት ነበረ።</verse>
				<verse number="12">ካሌ​ብም፥ “ሀገረ መጻ​ሕ​ፍ​ትን ለሚ​መ​ታና ለሚ​ይዝ ልጄን ዓስ​ካን ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="13">የካ​ሌ​ብም ትንሽ ወን​ድም የቄ​ኔዝ ልጅ ጎቶ​ን​ያል ያዛት፤ ሚስ​ትም ትሆ​ነው ዘንድ ልጁን ዓስ​ካን ሰጠው።</verse>
				<verse number="14">እር​ስ​ዋም ወደ እርሱ በመ​ጣች ጊዜ የእ​ርሻ ቦታ ይሰ​ጣት ዘንድ አባ​ቷን እን​ድ​ት​ለ​ም​ነው ጎቶ​ን​ያል መከ​ራት። እር​ስ​ዋም በአ​ህ​ያዋ ላይ ሆና አን​ጐ​ራ​ጐ​ረች፤ “ወደ ደቡብ ሰድ​ደ​ኸ​ኛል” ብላም ጮኸች። ካሌ​ብም፥ “ምን ሆነ​ሻል?” አላት።</verse>
				<verse number="15">ዓስ​ካም፥ “በረ​ከ​ትን ስጠኝ፤ ወደ ደቡብ በረሃ ሰድ​ደ​ኸ​ኛ​ልና ውኃ የማ​ጣ​ቴን ዋጋ ደግሞ ስጠኝ” አለ​ችው። ካሌ​ብም በል​ብዋ እንደ ተመ​ኘ​ችው የመ​ከ​ራ​ዋ​ንና የኀ​ዘ​ኗን ዋጋ ሰጣት።</verse>
				<verse number="16">የቄ​ና​ዊው የሙሴ አማት የዮ​ባብ ልጆ​ችም ከዘ​ን​ባባ ከተማ ተነ​ሥ​ተው ከዓ​ራድ በአ​ዜብ በኩል ወዳ​ለው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ወደ ይሁዳ ልጆች ሄደው ከሕ​ዝቡ ጋር ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="17">ይሁ​ዳም ከወ​ን​ድሙ ከስ​ም​ዖን ጋር ሄደ፤ በሴ​ፌት የተ​ቀ​መ​ጡ​ት​ንም ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን መቱ፤ ፈጽ​መ​ውም አጠ​ፉ​አት፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ስም ሕርም ብለው ጠሩ​አት።</verse>
				<verse number="18">ይሁ​ዳም ጋዛ​ንና አው​ራ​ጃ​ዋን፥ አስ​ቀ​ሎ​ና​ንና አው​ራ​ጃ​ዋን፥ አቃ​ሮ​ን​ንና አው​ራ​ጃ​ዋን፥ አዛ​ጦ​ን​ንና አው​ራ​ጃ​ዋን አል​ወ​ረ​ሳ​ትም።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከይ​ሁዳ ጋር ነበረ፤ ይሁ​ዳም ተራ​ራ​ማ​ውን ሀገር ወረሰ፤ በሸ​ለ​ቆው የሚ​ኖ​ሩ​ትን ግን የብ​ረት ሰረ​ገ​ሎች ነበ​ሩ​አ​ቸ​ውና ሊወ​ር​ሳ​ቸው አል​ቻ​ለም።</verse>
				<verse number="20">ሙሴም እንደ ተና​ገረ ለካ​ሌብ ኬብ​ሮ​ንን ሰጡት፤ ከዚ​ያም ሠላሳ ከተ​ሞ​ችን ወረሰ፤ ከዚ​ያም ሦስ​ቱን የዔ​ናቅ ልጆች አስ​ወ​ገ​ዳ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">ነገር ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን የብ​ን​ያም ልጆች አላ​ወ​ጡ​አ​ቸ​ውም፤ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ከብ​ን​ያም ልጆች ጋር እስከ ዛሬ ድረስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​ም​ጠ​ዋል።</verse>
				<verse number="22">የዮ​ሴ​ፍም ልጆች ደግሞ ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበረ።</verse>
				<verse number="23">እነ​ር​ሱም ሰፍ​ረው ቤቴ​ልን ሰለ​ሉ​አት። አስ​ቀ​ድ​ሞም የዚ​ያች ከተማ ስም ሎዛ ይባል ነበር።</verse>
				<verse number="24">ጠባ​ቂ​ዎ​ቹም አንድ ሰው ከከ​ተማ ሲወጣ አይ​ተው ያዙ​ትና፥ “የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱን መግ​ቢያ አሳ​የን፤ እኛም ምሕ​ረት እና​ደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለን” አሉት።</verse>
				<verse number="25">የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም መግ​ቢያ አሳ​ያ​ቸው፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም በሰ​ይፍ ስለት መቱ​አት፤ ያን ሰውና ዘመ​ዶ​ቹን ግን ለቀ​ቁ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">ሰው​የ​ውም ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያን ምድር ሄደ፤ በዚ​ያም ከተ​ማን ሠራ፤ ስም​ዋ​ንም ሎዛ ብሎ ጠራት። እስከ ዛሬም ድረስ ስምዋ ያው ነው።</verse>
				<verse number="27">ምና​ሴም የሰ​ቂ​ቶን ከተማ ቤት​ሶ​ን​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ ኢቀ​ጸ​አ​ድ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ የዶ​ርን ነዋ​ሪ​ዎ​ችና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ የዮ​በ​ለ​ዓ​ምን ነዋ​ሪ​ዎች፥ መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ የመ​ጊ​ዶን ነዋ​ሪ​ዎች መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን አል​ወ​ረ​ሳ​ቸ​ውም፤ ነገር ግን ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በዚ​ያች ሀገር ይቀ​መጡ ዘንድ ጸኑ።</verse>
				<verse number="28">እስ​ራ​ኤ​ልም በበ​ረቱ ጊዜ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን ገባ​ሮች አደ​ረ​ጉ​አ​ቸው፤ ነገር ግን ፈጽ​መው አላ​ጠ​ፏ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="29">ኤፍ​ሬ​ምም በጋ​ዜር የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ ነገር ግን ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው በጋ​ዜር ተቀ​መጡ፤ ገባ​ሮ​ችም ሆኑ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="30">ዛብ​ሎ​ንም በቄ​ድ​ሮ​ንና በአ​ማን የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሰዎች አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ ነገር ግን ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ተቀ​መጡ፤ ግብ​ርም የሚ​ገ​ብ​ሩ​ላ​ቸው ሆኑ።</verse>
				<verse number="31">አሴ​ርም የዓኮ ነዋ​ሪ​ዎ​ችን አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ ነገር ግን ገባ​ሮች ሆኑ​ላ​ቸው፤ የዶር ነዋ​ሪ​ዎ​ች​ንና የሲ​ዶን ነዋ​ሪ​ዎ​ችን፥ የደ​ላ​ፍ​ንም ነዋ​ሪ​ዎች፥ የአ​ክ​ሶ​ዚ​ብ​ንና የሄ​ል​ባን፥ የአ​ፌ​ቅ​ንና የረ​ዓ​ብ​ንም ሰዎች አላ​ጠ​ፉ​አ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="32">አሴ​ርም በዚ​ያች ምድር በተ​ቀ​መ​ጡት ከነ​ዓ​ና​ው​ያን መካ​ከል ተቀ​መጠ፤ ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው አል​ቻ​ለ​ምና።</verse>
				<verse number="33">ንፍ​ታ​ሌ​ምም የቤ​ት​ሳ​ሚ​ስ​ንና የቤ​ቴ​ኔ​ስን ሰዎች አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ በም​ድ​ሩም በተ​ቀ​መ​ጡት በከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን መካ​ከል ተቀ​መጡ፤ ነገር ግን በቤ​ት​ሳ​ሚ​ስና በቤ​ቴ​ኔስ የሚ​ኖሩ ሰዎች ገባ​ሮች ሁኑ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="34">አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም የዳ​ንን ልጆች በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር አስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸው፤ ወደ ሸለ​ቆው እን​ዲ​ወ​ርዱ አይ​ፈ​ቅ​ዱ​ላ​ቸ​ውም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="35">አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ድብና ቀበ​ሮ​ዎች በሚ​ኖ​ሩ​በት በመ​ር​ስ​ኖ​ኖስ ተራራ መቀ​መጥ ጀመሩ፤ ነገር ግን የዮ​ሴፍ ወገን እጅ በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ላይ ጸናች፤ ገባ​ርም አደ​ረ​ጉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="36">የአ​ሞ​ና​ው​ያ​ንም ድን​በር ከአ​ቅ​ራ​ቢም ዐቀ​በት ከጭ​ን​ጫው ጀምሮ እስከ ላይ​ኛው ድረስ ነበረ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ከገ​ል​ገላ ወደ ቀላ​ው​ት​ም​ኖስ ወደ ቤቴል ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት ወጥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ከግ​ብፅ አው​ጥ​ቼ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ እሰ​ጣ​ች​ሁም ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ወደ ማል​ሁ​ላ​ቸው ምድር አግ​ብ​ቻ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም፦ ከእ​ና​ንተ ጋር ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አላ​ፈ​ር​ስም፤</verse>
				<verse number="2">እና​ን​ተም በዚች ምድር ከሚ​ኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን አታ​ድ​ርጉ፤ ለአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አት​ስ​ገ​ዱ​ላ​ቸው፤ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ስበሩ፤ መሠ​ዊ​ያ​ቸ​ው​ንም አፍ​ርሱ አልሁ። እና​ንተ ግን ቃሌን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ ይህ​ንስ ለምን አደ​ረ​ጋ​ችሁ?</verse>
				<verse number="3">ስለ​ዚ​ህም እኔ አሕ​ዛ​ብን ከፊ​ታ​ችሁ አላ​ወ​ጣ​ቸ​ውም፤ ነገር ግን ያስ​ጨ​ን​ቋ​ች​ኋል፤ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወጥ​መድ ይሆ​ኑ​ባ​ች​ኋል” አልሁ።</verse>
				<verse number="4">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ይህን ቃል ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ በተ​ና​ገረ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ድም​ፃ​ቸ​ውን አን​ሥ​ተው አለ​ቀሱ።</verse>
				<verse number="5">የዚ​ያም ስፍራ ስም “መካነ ብካይ” ተብሎ ተጠራ፤ በዚ​ያም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠዉ።</verse>
				<verse number="6">ኢያ​ሱም ሕዝ​ቡን ባሰ​ና​በተ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ምድ​ሪ​ቱን ሊወ​ርሱ ወደ​የ​ር​ስ​ታ​ቸው ገቡ።</verse>
				<verse number="7">ኢያ​ሱም በነ​በ​ረ​በት ዘመን ሁሉ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ያደ​ረ​ገ​ውን ታላ​ቁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ሁሉ ባወ​ቁት፥ ከኢ​ያሱ በኋላ በነ​በሩ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ዘመን ሁሉ ሕዝቡ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዙ።</verse>
				<verse number="8">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ ዕድ​ሜው መቶ ዐሥር ዓመት ሲሆ​ነው ሞተ።</verse>
				<verse number="9">በተ​ራ​ራ​ማዉ በኤ​ፍ​ሬም ሀገር በገ​ዓስ ተራራ በሰ​ሜን ባለ​ችው በር​ስቱ ዳርቻ በተ​ም​ና​ሴራ ቀበ​ሩት።</verse>
				<verse number="10">ትው​ልድ ሁሉ ደግሞ ወደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ተጨ​መሩ፤ ከእ​ነ​ዚ​ያም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ያደ​ረ​ገ​ውን ሥራ ያላ​ወቀ ሌላ ትው​ልድ ተነሣ።</verse>
				<verse number="11">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረጉ፤ በዓ​ሊ​ም​ንም አመ​ለኩ።</verse>
				<verse number="12">ከግ​ብፅ ምድ​ርም ያወ​ጣ​ቸ​ውን የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተዉ፤ ሌሎ​ች​ንም በዙ​ሪ​ያ​ቸው ያሉ የአ​ሕ​ዛ​ብን አማ​ል​ክት ተከ​ተሉ፤ ሰገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አስ​ቈ​ጡት።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ትተው በዓ​ል​ንና አስ​ታ​ሮ​ትን አመ​ለኩ።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ተቈጣ፤ ወደ ማረ​ኳ​ቸ​ውም ማራ​ኪ​ዎች እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ ማረ​ኩ​አ​ቸ​ውም፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ባሉት በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ ከዚ​ያም ወዲያ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሊቋ​ቋሙ አል​ቻ​ሉም።</verse>
				<verse number="15">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ነ​ርሱ ላይ እንደ ማለ፥ ወደ ወጡ​በት ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ትከ​ፋ​ባ​ቸው ነበ​ረች፤ እጅ​ግም ተጨ​ነቁ።</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሳ​ፍ​ን​ትን አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው፤ ከሚ​ማ​ር​ኳ​ቸ​ውም እጅ አዳ​ኗ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">ሌሎች አማ​ል​ክ​ትን ተከ​ት​ለው አመ​ነ​ዘሩ፤ ሰገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም እንጂ፥ መሳ​ፍ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አል​ሰ​ሙም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አስ​ቈ​ጡት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል እን​ዳ​ይ​ሰሙ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ይሄ​ዱ​ባት የነ​በ​ረ​ች​ውን መን​ገድ ፈጥ​ነው ተዉ​አት፤ እን​ዲ​ሁም አላ​ደ​ረ​ጉም።</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሳ​ፍ​ን​ትን ባስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከመ​ስ​ፍኑ ጋር ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሚ​ዋ​ጉ​አ​ቸው ሰዎች ፊት ከመ​ከ​ራ​ቸው የተ​ነሣ ይቅር ብሏ​ቸ​ዋ​ልና በመ​ስ​ፍኑ ዘመን ሁሉ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ አዳ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="19">መስ​ፍኑ ግን ከሞተ በኋላ ዳግ​መኛ ተመ​ል​ሰው ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ይልቅ እጅግ ይበ​ድሉ፤ ነበር፤ ሂደ​ውም ሌሎች አማ​ል​ክ​ትን ተከ​ት​ለው ያመ​ል​ኳ​ቸው ነበር፤ ይሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም ነበር፤ ክፋ​ታ​ቸ​ው​ንም አይ​ተ​ዉም ነበር፤ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም አይ​መ​ለ​ሱም ነበር።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህ ሕዝብ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ያዘ​ዝ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን ስለ ተላ​ለፉ፥ ቃሌ​ንም ስላ​ል​ሰሙ፥</verse>
				<verse number="21">እኔም የነዌ ልጅ ኢያሱ ትቶ​አ​ቸው ከአ​ለፈ አሕ​ዛብ አን​ዱን ሰው እን​ኳን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ከፊ​ታ​ቸው አላ​ወ​ጣም።</verse>
				<verse number="22">አባ​ቶ​ቻ​ቸው እንደ ጠበቁ፥ ይሄ​ዱ​ባት ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ይጠ​ብቁ ወይም አይ​ጠ​ብቁ እንደ ሆነ እስ​ራ​ኤ​ልን እፈ​ት​ን​ባ​ቸው ዘንድ፤”</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ አስ​ቀረ፤ ፈጥ​ኖም አላ​ወ​ጣ​ቸ​ውም፤ በኢ​ያ​ሱም እጅ አሳ​ልፎ አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም ጦር​ነት ሁሉ ያላ​ወ​ቁ​ትን እስ​ራ​ኤ​ልን በእ​ነ​ርሱ ይፈ​ት​ና​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ ተዋ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">ይህም ጦር​ነ​ትን ያስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው ዘንድ ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆች ትው​ልድ ብቻ ነው፤ ነገር ግን ከእ​ነ​ርሱ በፊት የነ​በ​ሩት እነ​ዚ​ህን አላ​ወ​ቋ​ቸ​ውም ነበር፤</verse>
				<verse number="3">እነ​ር​ሱም አም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መኳ​ን​ንት፥ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ሁሉ ፥ ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም፥ ከበ​ዓ​ል​ሄ​ር​ሞን ተራራ ጀምሮ እስከ ኤማት መግ​ቢያ ድረስ በሊ​ባ​ኖስ ተራራ የሚ​ኖ​ሩ​ትም ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፤</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ያዘ​ዘ​ውን ትእ​ዛዝ መስ​ማ​ታ​ቸው እን​ዲ​ታ​ወቅ እስ​ራ​ኤል ይፈ​ተ​ኑ​ባ​ቸው ዘንድ እነ​ዚህ ቀሩ።</verse>
				<verse number="5">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን፥ በኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያን፥ በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን፥ በፌ​ር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያን፥ በኤ​ዌ​ዎ​ና​ው​ያን፥ በኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም መካ​ከል ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="6">ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም አገ​ቡ​አ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸው ሰጡ፤ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አመ​ለኩ።</verse>
				<verse number="7">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረጉ፤ አም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረስ​ተው በዓ​ሊ​ም​ንና አስ​ታ​ሮ​ትን አመ​ለኩ።</verse>
				<verse number="8">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ፤ በወ​ን​ዞ​ችም መካ​ከል ባለች በሶ​ርያ ንጉሥ በኩ​ሳ​ር​ሳ​ቴም እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለኩ​ሳ​ር​ሳ​ቴም ስም​ንት ዓመት ተገ​ዙ​ለት።</verse>
				<verse number="9">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእ​ስ​ራ​ኤል መድ​ኀ​ኒ​ትን አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው። የካ​ሌብ የታ​ናሽ ወን​ድሙ የቄ​ኔዝ ልጅ ጎቶ​ን​ያ​ልም አዳ​ና​ቸው፤ ለእ​ር​ሱም ታዘ​ዙ​ለት።</verse>
				<verse number="10">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ አደረ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ይፈ​ርድ ነበር፤ ለጦ​ር​ነ​ትም ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በወ​ን​ዞች መካ​ከል ያለች የሶ​ርያ ንጉሥ ኩሳ​ር​ሳ​ቴ​ምን በእጁ አሳ​ልፎ ሰጠው፤ እጁም በኩ​ሳ​ር​ሳ​ቴም ላይ በረ​ታች።</verse>
				<verse number="11">ምድ​ሪ​ቱም አርባ ዓመት ዐረ​ፈች፤ የቄ​ኔ​ዝም ልጅ ጎቶ​ን​ያል ሞተ።</verse>
				<verse number="12">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ስለ ሠሩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሞ​ዓ​ብን ንጉሥ ዔግ​ሎ​ምን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አበ​ረ​ታ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">የአ​ሞ​ንን ልጆ​ችና አማ​ሌ​ቅን ወደ እርሱ ሰበ​ሰበ፤ ሄዶም እስ​ራ​ኤ​ልን መታ፤ ዘን​ባባ ያለ​ባ​ት​ንም ከተማ ያዘ።</verse>
				<verse number="14">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለሞ​ዓብ ንጉሥ ለዔ​ግ​ሎም ዐሥራ ስም​ንት ዓመት ተገዙ።</verse>
				<verse number="15">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብን​ያ​ማ​ዊ​ውን የጌ​ራን ልጅ ናዖ​ድን ሁለቱ እጆቹ ቀኝ የሆ​ኑ​ለ​ትን ሰው አዳኝ አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ርሱ እጅ ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ ዔግ​ሎም እጅ መንሻ ላኩ።</verse>
				<verse number="16">ናዖ​ድም ሁለት አፍ ያላት ርዝ​መቷ አንድ ስን​ዝር የሆ​ነች ሰይፍ አበጀ፤ ከል​ብ​ሱም በታች በቀኝ በኩል በወ​ገቡ ታጠ​ቃት።</verse>
				<verse number="17">ለሞ​ዓ​ብም ንጉሥ ለዔ​ግ​ሎም እጅ መን​ሻ​ውን አቀ​ረበ፤ ዔግ​ሎ​ምም እጅግ ወፍ​ራም ሰው ነበረ።</verse>
				<verse number="18">እጅ መን​ሻ​ው​ንም ማቅ​ረብ በጨ​ረሰ ጊዜ፥ እጅ መንሻ የተ​ሸ​ከ​ሙ​ትን ሰዎች አሰ​ና​በ​ታ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">ዔግ​ሎ​ምም ከገ​ል​ገል ከጣ​ዖ​ታቱ ቤት ተመ​ለሰ። ናዖ​ድም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ ለብ​ቻህ የም​ነ​ግ​ርህ የም​ሥ​ጢር ነገር አለኝ” አለ፤ ዔግ​ሎ​ምም ሁሉ ከእ​ርሱ ዘንድ እን​ዲ​ወጣ አዘዘ፤ በእ​ር​ሱም ዘንድ የቆ​ሙት ሁሉ ወጡ ።</verse>
				<verse number="20">ናዖ​ድም ወደ እርሱ ገባ፤ እር​ሱም በበጋ ቤቱ ሰገ​ነት ለብ​ቻው ተቀ​ምጦ ነበር። ናዖ​ድም፥ “ንጉሥ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​እ​ክት ለአ​ንተ አለኝ” አለው። ዔግ​ሎ​ምም ከዙ​ፋኑ ተነሣ፥ ቀረ​በ​ውም።</verse>
				<verse number="21">ናዖ​ድም በተ​ነሣ ጊዜ ግራ እጁን ዘር​ግቶ ከቀኝ ጎኑ ሰይ​ፉን መዘዘ፤ ዔግ​ሎ​ም​ንም ሆዱን ወጋው፤</verse>
				<verse number="22">እስከ ውላ​ጋ​ዋም አስ​ገ​ባት፤ እስከ ጀር​ባ​ውም በረ​በ​ረው፥ ሰይ​ፉ​ንም ከሆዱ መልሶ አላ​ወ​ጣ​ትም።</verse>
				<verse number="23">ናዖ​ድም የእ​ል​ፍ​ኙን ደጅ ዘግ​ቶና ቈልፎ ወደ ውጭ ወጣ።</verse>
				<verse number="24">ናዖ​ድም ከሄደ በኋላ አገ​ል​ጋ​ዮቹ መጡ፤ የሰ​ገ​ነ​ቱም ደጅ ተቈ​ልፎ ባዩ ጊዜ፥ “ምና​ል​ባት በበጋ ሰገ​ነቱ ውስጥ ወገ​ቡን ይሞ​ክር ይሆ​ናል” አሉ።</verse>
				<verse number="25">እስ​ኪ​ያ​ፍ​ሩም ድረስ ቈዩ፤ የሰ​ገ​ነ​ቱ​ንም ደጅ እን​ዳ​ል​ከ​ፈተ ባዩ ጊዜ መክ​ፈ​ቻ​ውን ወስ​ደው ከፈቱ፤ እነ​ሆም፥ ጌታ​ቸው በም​ድር ላይ ወድቆ ሞቶም አገ​ኙት።</verse>
				<verse number="26">እስ​ከ​ሚ​ታ​ወ​ኩም ድረስ ናዖድ አመ​ለጠ፤ ያወ​ቀ​ውም የለም፤ ከጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አልፎ ወደ ሴይ​ሮታ አመ​ለጠ።</verse>
				<verse number="27">ከዚ​ህም በኋላ ወደ እስ​ራ​ኤል ምድር በደ​ረሰ ጊዜ በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ራም ሀገር ቀንደ መለ​ከት ነፋ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከእ​ርሱ ጋር ከተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ወረዱ፤ እር​ሱም በፊ​ታ​ቸው ሄደ።</verse>
				<verse number="28">እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንን ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ና​ልና ተከ​ተ​ሉኝ” አላ​ቸው። ተከ​ት​ለ​ው​ትም ወረዱ፤ ወደ ሞዓ​ብም የሚ​ያ​ሻ​ግ​ረ​ውን የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስን መሻ​ገ​ርያ ያዙ፤ ማንም ሰው እን​ዲ​ያ​ልፍ አል​ፈ​ቀ​ዱም።</verse>
				<verse number="29">በዚ​ያም ወራት ከሞ​ዓብ ዐሥር ሺህ የሚ​ያ​ህ​ሉ​ትን፥ ጐል​ማ​ሶ​ችና ጽኑ​ዓን ሁሉ ገደሉ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ሰው እንኳ አላ​መ​ለ​ጠም።</verse>
				<verse number="30">በዚ​ያም ወራት ሞዓ​ባ​ው​ያን በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ ገቡ፤ ምድ​ሪ​ቱም ሰማ​ንያ ዓመት ዐረ​ፈች። ናዖ​ድም እስ​ኪ​ሞት ድረስ ገዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="31">ከእ​ር​ሱም በኋላ የሐ​ናት ልጅ ሴሜ​ጋር ተነሣ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ስድ​ስት መቶ ሰው በበሬ መው​ጊያ ገደለ፤ እር​ሱም ደግሞ እስ​ራ​ኤ​ልን አዳነ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ ናዖድ ግን ሞቶ ነበር።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሦር በነ​ገ​ሠው በከ​ነ​ዓን ንጉሥ በኢ​ያ​ቢን እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ ሲሣራ ነበረ፤ እር​ሱም በአ​ሕ​ዛብ አሪ​ሶት ይቀ​መጥ ነበረ።</verse>
				<verse number="3">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ ዘጠኝ መቶ የብ​ረት ሰረ​ገ​ሎች ነበ​ሩ​ትና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ሃያ ዓመት እጅግ ያስ​ጨ​ን​ቃ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="4">በዚ​ያም ወራት ነቢ​ይቱ የለ​ፊ​ዶት ሚስት ዲቦራ እስ​ራ​ኤ​ልን ትገ​ዛ​ቸው ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="5">እር​ስ​ዋም በኤ​ፍ​ሬም ተራራ በቤ​ቴ​ልና በኢ​ያማ መካ​ከል “የዲ​ቦራ ዘን​ባባ” ተብሎ በሚ​ጠ​ራው ዛፍ ሥር ተቀ​ምጣ ነበር፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እር​ስዋ ለፍ​ርድ ይወጡ ነበር።</verse>
				<verse number="6">ዲቦ​ራም ልካ ከቃ​ዴስ ንፍ​ታ​ሌም የአ​ቢኒ​ሔ​ምን ልጅ ባር​ቅን ጠርታ እን​ዲህ አለ​ችው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ያዘ​ዘህ አይ​ደ​ለ​ምን? ሄደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምና ከዛ​ብ​ሎን ልጆች ዐሥር ሺህ ሰዎች ውሰድ፤</verse>
				<verse number="7">እኔም የኢ​ያ​ቢ​ንን ሠራ​ዊት አለቃ ሲሣ​ራን፥ ሰረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም፥ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ ወደ አንተ ወደ ቂሶን ወንዝ እስ​ባ​ለሁ፤ በእ​ጅ​ህም አሳ​ልፌ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="8">ባር​ቅም፥ “አንቺ ከእኔ ጋር ብት​ሄጂ እኔ እሄ​ዳ​ለሁ፤ አንቺ ግን ከእኔ ጋር ባት​ሄጂ እኔ አል​ሄ​ድም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ኩን ከእኔ ጋር የሚ​ል​ክ​በ​ትን ዕለት አላ​ው​ቃ​ት​ምና” አላት።</verse>
				<verse number="9">ዲቦ​ራም፥ “በእ​ው​ነት ከአ​ንተ ጋር እሄ​ዳ​ለሁ፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሲሣ​ራን በሴት እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ልና በዚህ በም​ት​ሄ​ድ​በት መን​ገድ ለአ​ንተ ክብር አይ​ሆ​ንም” አለ​ችው። ዲቦ​ራም ተነ​ሥታ ከባ​ርቅ ጋር ወደ ቃዴስ ሄደች።</verse>
				<verse number="10">ባር​ቅም ዛብ​ሎ​ን​ንና ንፍ​ታ​ሌ​ምን ወደ ቃዴስ ጠራ​ቸው፤ ዐሥር ሺህም ሰዎች ተከ​ት​ለ​ውት ወጡ፤ ዲቦ​ራም ከእ​ርሱ ጋር ወጣች።</verse>
				<verse number="11">ቄና​ዊ​ውም ሔቤር ከሙሴ አማት ከኢ​ዮ​ባብ ልጆች ከቄ​ና​ው​ያን ተለ​ይቶ ድን​ኳ​ኑን በቃ​ዴስ አጠ​ገብ እስከ ነበ​ረው ታላቅ ዛፍ ድረስ ተከለ።</verse>
				<verse number="12">የአ​ቢ​ኒ​ሔ​ምም ልጅ ባርቅ ወደ ታቦር ተራራ እንደ ወጣ ለሲ​ሣራ ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="13">ሲሣ​ራም ሰረ​ገ​ሎ​ቹን ሁሉ፥ ዘጠኝ መቶ የብ​ረት ሰረ​ገ​ሎች፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝ​ቡን ሁሉ ከአ​ሕ​ዛብ አሪ​ሶት ወደ ቂሶን ወንዝ ሰበ​ሰ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">ዲቦ​ራም ባር​ቅን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሲሣ​ራን በእ​ጅህ አሳ​ልፎ የሚ​ሰ​ጥ​በት ቀን ዛሬ ነውና ተነሣ፤ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ትህ ይሄ​ዳል” አለ​ችው። ባር​ቅም ዐሥር ሺህ ሰዎች ተከ​ት​ለ​ውት ከታ​ቦር ተራራ ወረደ።</verse>
				<verse number="15">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሲሣ​ራን፥ ሰረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ሠራ​ዊ​ቱ​ንም ሁሉ ከባ​ርቅ ፊት በሰ​ይፍ ስለት አስ​ደ​ነ​ገ​ጣ​ቸው፤ ሲሣ​ራም ከሰ​ረ​ገ​ላው ወርዶ በእ​ግሩ ሸሸ።</verse>
				<verse number="16">ባር​ቅም ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ሠራ​ዊ​ቱን እስከ አሕ​ዛብ አሪ​ሶት ድረስ አባ​ረረ፤ የሲ​ሣ​ራም ሠራ​ዊት ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት ወደቀ፤ አንድ እንኳ አል​ቀ​ረም።</verse>
				<verse number="17">ሲሣ​ራም ወደ ጓደ​ኛው ወደ ቄና​ዊው ወደ ሔቤር ሚስት ወደ ኢያ​ዔል ድን​ኳን በእ​ግሩ ሸሸ፤ በአ​ሶር ንጉሥ በኢ​ያ​ቢ​ንና በቄ​ና​ዊው በሔ​ቤር ቤት መካ​ከል ሰላም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="18">ኢያ​ዔ​ልም ሲሣ​ራን ለመ​ቀ​በል ወጥታ፥ “ግባ፥ ጌታዬ ሆይ፥ ወደ እኔ ግባ፤ አት​ፍ​ራም” አለ​ችው። ወደ እር​ስ​ዋም ወደ ድን​ኳ​ንዋ ገባ፤ በም​ን​ጣ​ፍም ሸፈ​ነ​ችው።</verse>
				<verse number="19">ሲሣ​ራም፥ “ጠም​ቶ​ኛ​ልና እባ​ክሽ የም​ጠ​ጣው ጥቂት ውኃ ስጪኝ” አላት፤ እር​ስ​ዋም የወ​ተ​ቱን ዕቃ ፈትታ አጠ​ጣ​ችው፤ ፊቱ​ንም ሸፈ​ነ​ችው።</verse>
				<verse number="20">እር​ሱም፥ “ከድ​ን​ኳኑ ደጃፍ ቁሚ፤ ሰውም መጥቶ፦ ‘በዚህ ሰው አለን?’ ብሎ ቢጠ​ይ​ቅሽ አንቺ፦ ‘የለም’ ትዪ​ዋ​ለሽ” አላት።</verse>
				<verse number="21">የሔ​ቤ​ርም ሚስት ኢያ​ዔል የድ​ን​ኳ​ኑን ካስማ ወሰ​ደች፤ በሁ​ለ​ተኛ እጅ​ዋም መዶሻ ያዘች፤ ቀስ ብላም ወደ እርሱ ቀረ​በች፤ በጆሮ ግን​ዱም ካስ​ማ​ውን ቸነ​ከ​ረ​ች​በት፤ እር​ሱም ደክሞ አን​ቀ​ላ​ፍቶ ነበ​ርና ካስ​ማው ወደ መሬት ጠለቀ፤ እር​ሱም ከእ​ግ​ርዋ በታች ተን​ፈ​ራ​ፈረ፤ ተዘ​ር​ሮም ሞተ።</verse>
				<verse number="22">እነ​ሆም፥ ባርቅ ሲሣ​ራን ሲያ​ባ​ርር ኢያ​ዔል ልት​ገ​ና​ኘው ወጥታ፥ “ና፤ የም​ት​ሻ​ውን ሰው አሳ​ይ​ሃ​ለሁ” አለ​ችው። ወደ እር​ስ​ዋም ገባ፤ እነ​ሆም፥ ሲሣ​ራን ወድቆ፥ ሞቶም አገ​ኘው፤ ካስ​ማ​ውም በጆሮ ግንዱ ውስጥ ነበረ።</verse>
				<verse number="23">በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የከ​ነ​ዓ​ንን ንጉሥ ኢያ​ቢ​ንን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት አዋ​ረ​ደው።</verse>
				<verse number="24">የከ​ነ​ዓ​ንን ንጉሥ ኢያ​ቢ​ን​ንም እስ​ኪ​ያ​ጠፉ ድረስ በከ​ነ​ዓን ንጉሥ በኢ​ያ​ቢን ላይ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እጅ እየ​በ​ረ​ታች ሄደች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">በዚ​ያ​ችም ቀን ዲቦ​ራና የአ​ቢኒ​ሔም ልጅ ባርቅ እን​ዲህ ብለው ዘመሩ፦</verse>
				<verse number="2">በእ​ስ​ራ​ኤል ውስጥ መሳ​ፍ​ንት ስለ መሩ ሕዝ​ቡም ስለ ፈቀዱ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት።</verse>
				<verse number="3">ነገ​ሥ​ታት ሆይ፥ ስሙ፤ ጽኑ​ዓን መኳ​ን​ን​ትም ሆይ፥ አድ​ምጡ፤ እኔ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እቀ​ኛ​ለሁ፤ እኔ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እዘ​ም​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">አቤቱ! ከሴ​ይር በወ​ጣህ ጊዜ፥ ከኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ሜዳ በተ​ራ​መ​ድህ ጊዜ፥ ምድ​ሪቱ ተና​ወ​ጠች፤ ሰማ​ያ​ትም ጠልን አን​ጠ​ባ​ጠቡ፤ ደመ​ና​ትም ደግሞ ውኃን አን​ጠ​ባ​ጠቡ።</verse>
				<verse number="5">ተራ​ሮች ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ነሣ ተነ​ዋ​ወጡ፤ ያም ሲና ከእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ነሣ፤</verse>
				<verse number="6">በሐ​ናት ልጅ በሰ​ሜ​ጋር ዘመን፥ በኢ​ያ​ዔል ዘመን ነገ​ሥት መን​ገ​ዶ​ችን ተዉ፤ በስ​ርጥ መን​ገ​ድም ይሄዱ ነበር፤ በጠ​ማማ መን​ገ​ድም ሄዱ።</verse>
				<verse number="7">መተ​ር​ጕ​ማን ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አለቁ፥ ዲቦራ እስ​ክ​ት​ነሣ ድረስ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም እናት ሆና እስ​ክ​ት​ነሣ ድረስ አለቁ።</verse>
				<verse number="8">አዲ​ሶች አማ​ል​ክ​ትን መረጡ፤ በዚያ ጊዜ ሰልፍ በበ​ሮች ሆነ፤ በአ​ርባ ሺህ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ጦርና ጋሻ አል​ታ​ዩም።</verse>
				<verse number="9">ልቤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ወደ ታዘ​ዘው ትእ​ዛዝ ነው፤ እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ኀያ​ላን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት።</verse>
				<verse number="10">በነ​ጫጭ አህ​ዮች ላይ የም​ት​ጫኑ፥ በፍ​ርድ ወን​በር ላይ​የ​ም​ት​ቀ​መጡ፥ በመ​ን​ገ​ድም የም​ት​ሄዱ በቃ​ላ​ችሁ ተና​ገሩ።</verse>
				<verse number="11">በብ​ዙ​ዎች ደስ​ተ​ኞች መካ​ከል መሰ​ን​ቆን ምቱ፤ በዚያ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ድቅ ሥራን፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ውስጥ ጽድ​ቅ​ንና ኀይ​ልን ያቀ​ር​ባሉ። ያን​ጊ​ዜም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ወደ ከተ​ማ​ዎቹ ወረዱ።</verse>
				<verse number="12">ተነሺ፥ ዲቦራ ሆይ፦ ተነሺ፤ አእ​ላ​ፍን ከሕ​ዝብ ጋር አስ​ነሺ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ቅኔ​ው​ንም ተቀኚ፤ ባርቅ ሆይ! በኀ​ይል ተነሣ፤ ዲቦ​ራም ባር​ቅን አጽ​ኚው፥ የአ​ቢ​ኒ​ሔም ልጅ ባር​ቅም ሆይ! ምር​ኮ​ህን ማርክ።</verse>
				<verse number="13">በዚያ ጊዜ የቀ​ሩት ወደ ኀያ​ላ​ኑና ወደ ሕዝቡ ወረዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ እኔ በኀ​ያ​ላን ላይ ወረደ።</verse>
				<verse number="14">በአ​ማ​ሌቅ ዘንድ ሥር የነ​በ​ራ​ቸው እነ​ርሱ ከኤ​ፍ​ሬም፥ ብን​ያም ሆይ! በሕ​ዝብ መካ​ከል ከአ​ንተ በኋላ ወረዱ፤ አለ​ቆች ከማ​ኪር፥ የን​ጉ​ሥ​ንም ዘንግ የሚ​ይዙ ከዛ​ብ​ሎን ወረዱ።</verse>
				<verse number="15">የይ​ሳ​ኮ​ርም አለ​ቆች ከዲ​ቦራ ጋር ነበሩ፤ ይሳ​ኮ​ርም እንደ ባርቅ ነበረ፤ ከእ​ግሩ በኋላ ወደ ሸለ​ቆው ቸኮሉ፤ በሮ​ቤል ፈሳ​ሾች አጠ​ገብ ብዙ የልብ ማመ​ን​ታት ነበረ።</verse>
				<verse number="16">መን​ጎች ሲያ​ፍ​ዋጩ ለመ​ስ​ማት፥ በበ​ጎች ጉረኖ መካ​ከል ለምን ተቀ​መ​ጥህ? በሮ​ቤል ፈሳ​ሾች አጠ​ገብ ታላቅ የልብ ምር​ምር ነበረ።</verse>
				<verse number="17">ገለ​ዓድ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ተቀ​መጠ፤ ዳንም ለምን በመ​ር​ከብ ውስጥ ቀረ? አሴ​ርም በባ​ሕሩ ዳር ተቀ​መጠ፥ በወ​ን​ዞ​ቹም ዳርቻ ዐረፈ።</verse>
				<verse number="18">ዛብ​ሎን ነፍ​ሱን ወደ ሞት ያሳ​ለፈ ሕዝብ ነው፤ ንፍ​ታ​ሌ​ምም በሀ​ገሩ ኮረ​ብታ ላይ ነው።</verse>
				<verse number="19">ነገ​ሥ​ታት መጡ፤ ተዋ​ጉም፤ በዚያ ጊዜ በመ​ጌዶ ውኆች አጠ​ገብ በቶ​ናሕ የከ​ነ​ዓን ነገ​ሥ​ታት ተዋጉ፤ በቅ​ሚ​ያም ብርን አል​ወ​ሰ​ዱም።</verse>
				<verse number="20">ከዋ​ክ​ብት በሰ​ማይ ተዋጉ፤ በሰ​ል​ፋ​ቸ​ውም ከሲ​ሣራ ጋር ተዋጉ።</verse>
				<verse number="21">ከዱሮ ጀምሮ የታ​ወቀ ያ የቂ​ሶን ወንዝ፥ የቂ​ሶን ወንዝ ጠርጎ ወሰ​ዳ​ቸው። ነፍሴ ሆይ፥ በርቺ።</verse>
				<verse number="22">ያን ጊዜ ከኀ​ያ​ላን ግል​ቢያ ብር​ታት የተ​ነሣ፥ የፈ​ረ​ሶች ጥፍ​ሮች ተቀ​ጠ​ቀጡ።</verse>
				<verse number="23">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ አለ፥ “ሜሮ​ዝን ርገሙ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርዳታ አል​መ​ጡ​ምና፥ በኀ​ያ​ላን መካ​ከል ወደ እርሱ ርዳታ አል​መ​ጡ​ምና፥ በቤ​ቶ​ችዋ ያሉ​ትን ሰዎች ፈጽ​ማ​ችሁ ርገሙ።”</verse>
				<verse number="24">የቄ​ና​ዊው የሔ​ቤር ሚስት ኢያ​ዔል፥ ከሴ​ቶች ይልቅ የተ​ባ​ረ​ከች ትሁን፤ በድ​ን​ኳን ውስጥ ከሚ​ኖሩ ሴቶች ይልቅ የተ​ባ​ረ​ከች ትሁን።</verse>
				<verse number="25">ውኃ ለመነ፤ ወተ​ትም ሰጠ​ችው፤ በተ​ከ​በረ ዳካ እርጎ አቀ​ረ​በ​ች​ለት።</verse>
				<verse number="26">ግራ እጅ​ዋን ወደ ካስማ፤ ቀኝ እጅ​ዋ​ንም ወደ ሠራ​ተኛ መዶሻ አደ​ረ​ገች፤ በመ​ዶ​ሻ​ውም ሲሣ​ራን መታ​ችው፤ ራሱ​ንም ቸነ​ከ​ረች፤ ጆሮ ግን​ዱ​ንም በሳች፤ ጐዳ​ች​ውም።</verse>
				<verse number="27">በእ​ግ​ሮ​ችዋ አጠ​ገብ ተደፋ፤ ወደቀ፤ ተኛ፤ በእ​ግ​ሮ​ችዋ አጠ​ገብ ተፈ​ራ​ገጠ፤ በተ​ፈ​ራ​ገ​ጠ​በ​ትም በዚያ ተጐ​ሳ​ቍሎ ሞተ።</verse>
				<verse number="28">የሲ​ሣራ እናት በመ​ስ​ኮት ሆና ተመ​ለ​ከ​ተች፤ በሰ​ቅ​ሰ​ቅም ዘልቃ፦ ከሲ​ሣራ የተ​መ​ለሰ እን​ዳለ አየች፤ ስለ​ምን ለመ​ም​ጣት ሰረ​ገ​ላው ዘገየ? ስለ​ም​ንስ የሰ​ረ​ገ​ላው መን​ኰ​ራ​ኵር ቈየ? ብላ ጮኸች።</verse>
				<verse number="29">ብል​ሃ​ተ​ኞች ሴቶ​ችዋ መለ​ሱ​ላት፤ እር​ስዋ ደግሞ ለራ​ስዋ እን​ዲህ ብላ መለ​ሰች፦</verse>
				<verse number="30">ምር​ኮ​ውን ሲካ​ፈል፥ በኀ​ያ​ላ​ኑም ቸብ​ቸቦ ላይ ወዳ​ጆ​ችን ሲወ​ዳጅ ያገ​ኙት አይ​ደ​ለ​ምን? የሲ​ሣራ ምርኮ በየ​ኅ​ብሩ ነበረ፤ የኅ​ብ​ሩም ቀለም የተ​ለ​ያየ ነበረ፤ የማ​ረ​ከ​ውም ወርቀ ዘቦ ግምጃ በአ​ን​ገቱ ላይ ነበረ።</verse>
				<verse number="31">አቤቱ ጠላ​ቶ​ችህ ሁሉ እን​ዲሁ ይጥፉ፤ ወዳ​ጆ​ችህ ግን ፀሐይ በኀ​ይሉ በወጣ ጊዜ እን​ደ​ሚ​ሆን፤ እን​ዲሁ ይሁኑ። ምድ​ሪ​ቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረ​ፈች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድ​ያም እጅ ሰባት ዓመት አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">የም​ድ​ያ​ምም እጅ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ጠነ​ከ​ረች፤ ከም​ድ​ያ​ምም ፊት የተ​ነሣ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በተ​ራ​ሮ​ችና በገ​ደ​ሎች ላይ ጕድ​ጓ​ድና ዋሻ፥ ምሽ​ግም አበጁ።</verse>
				<verse number="3">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዘር በዘሩ ጊዜ ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንና አማ​ሌ​ቃ​ው​ያን ይዘ​ም​ቱ​ባ​ቸው ነበር፥ በም​ሥ​ራ​ቅም የሚ​ኖሩ ልጆች አብ​ረው ይዘ​ም​ቱ​ባ​ቸው ነበር፤</verse>
				<verse number="4">በእ​ነ​ር​ሱም ላይ ይሰ​ፍሩ ነበር፤ ወደ ጋዛም እስ​ከ​ሚ​ደ​ርሱ የእ​ር​ሻ​ቸ​ውን ፍሬ ያጠፉ ነበር፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ምድር ለሕ​ይ​ወት የሚ​ሆን ምንም አይ​ተ​ዉም ነበር፤ ከመ​ን​ጋ​ዎ​ችም በሬ ወይም አህያ ቢሆን አይ​ተ​ዉም ነበር።</verse>
				<verse number="5">እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ይዘው በብ​ዛት እንደ አን​በጣ ሆነው ይመ​ጡ​ባ​ቸው ነበር፤ ለእ​ነ​ር​ሱና ለግ​መ​ሎ​ቻ​ቸው ቍጥር አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ያጠ​ፏት ዘንድ ይመጡ ነበር።</verse>
				<verse number="6">ከም​ድ​ያ​ምም ፊት የተ​ነሣ እስ​ራ​ኤል እጅግ ተቸ​ገሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ።</verse>
				<verse number="7">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በም​ድ​ያም ምክ​ን​ያት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጮኹ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ነቢይ ላከ፤ እር​ሱም አለ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣ​ኋ​ችሁ፤ ከባ​ር​ነ​ትም ቤት አስ​ለ​ቀ​ቅ​ኋ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="9">ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም እጅ ከሚ​ጋ​ፉ​አ​ች​ሁም ሁሉ እጅ አዳ​ን​ኋ​ችሁ፤ ከፊ​ታ​ች​ሁም አሳ​ደ​ድ​ኋ​ቸው፤ ሀገ​ራ​ቸ​ው​ንም ሰጠ​ኋ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="10">እና​ን​ተ​ንም፦ እኔ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ በም​ድ​ራ​ቸው የተ​ቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​ባ​ቸ​ውን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አማ​ል​ክት አት​ፍሩ አል​ኋ​ችሁ። እና​ንተ ግን ቃሌን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም።”</verse>
				<verse number="11">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ መጥቶ በኤ​ፍ​ራታ ባለ​ችው ለኤ​ዝሪ አባት ለኢ​ዮ​አስ በነ​በ​ረ​ችው ዛፍ በታች ተቀ​መጠ፤ ልጁም ጌዴ​ዎን ከም​ድ​ያ​ማ​ው​ያን ለማ​ሸሽ በወ​ይን መጭ​መ​ቂ​ያው ውስጥ ስንዴ ይወቃ ነበር።</verse>
				<verse number="12">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ለእ​ርሱ ተገ​ልጦ፥ “አንተ ጽኑዕ ኀያል ሰው! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው” አለው።</verse>
				<verse number="13">ጌዴ​ዎ​ንም፥ “ጌታዬ ሆይ! እሺ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረ​ሰ​ብን? አባ​ቶ​ቻ​ች​ንስ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ አው​ጥ​ቶ​ናል ብለው ይነ​ግ​ሩን የነ​በረ ተአ​ም​ራት ወዴት አለ? አሁን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቶ​ናል፤ በም​ድ​ያም እጅም አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ናል” አለው።</verse>
				<verse number="14">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ወደ እርሱ ተመ​ለ​ከ​ተና፥ “በዚህ በጕ​ል​በ​ትህ ሂድ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ከም​ድ​ያም እጅ ታድ​ና​ቸ​ዋ​ለህ፤ እነሆ፥ ልኬ​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="15">እር​ሱም፥ “ጌታ ሆይ! እሺ፥ እስ​ራ​ኤ​ልን በምን አድ​ና​ለሁ? ወገኔ በም​ናሴ ነገድ ዘንድ ጥቂ​ቶች ናቸው፤ እኔም በአ​ባቴ ቤት የሁሉ ታናሽ ነኝ” አለው።</verse>
				<verse number="16">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው፤ ምድ​ያ​ም​ንም እንደ አንድ ሰው አድ​ር​ገህ ታጠ​ፋ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="17">ጌዴ​ዎ​ንም፥ “በፊ​ትህ ሞገ​ስን ካገ​ኘሁ፥ የም​ት​ና​ገ​ረ​ኝም አንተ እንደ ሆንህ ምል​ክት አድ​ር​ግ​ልኝ፤</verse>
				<verse number="18">ወደ አን​ተም እስ​ክ​መ​ለስ ድረስ፥ መሥ​ዋ​ዕ​ቴ​ንም አም​ጥቼ እስ​ካ​ቀ​ር​ብ​ልህ ድረስ፥ እባ​ክህ፥ ከዚህ አት​ሂድ” አለው። እር​ሱም፥ “እስ​ክ​ት​መ​ለስ ድረስ እቈ​ያ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="19">ጌዴ​ዎ​ንም ሄደ፤ የፍ​የ​ሉ​ንም ጠቦት፥ የኢፍ መስ​ፈ​ሪ​ያም ዱቄት የቂጣ እን​ጎቻ አዘ​ጋጀ፤ ሥጋ​ው​ንም በሌ​ማት አኖረ፤ መረ​ቁ​ንም በም​ን​ቸት ውስጥ አደ​ረገ፤ ሁሉ​ንም ይዞ በዛፍ በታች አቀ​ረ​በ​ለት። ሰገ​ደ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="20">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “ሥጋ​ው​ንና የቂ​ጣ​ውን እን​ጎቻ ወስ​ደህ በዚህ ድን​ጋይ ላይ አኑር፤ መረ​ቁ​ንም አፍ​ስስ” አለው። እን​ዲ​ሁም አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="21">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በእጁ ያለ​ውን በት​ሩን ዘር​ግቶ ሥጋ​ዉ​ንና የቂ​ጣ​ዉን እን​ጎቻ አስ​ነካ፤ እሳ​ትም ከድ​ን​ጋዩ ውስጥ ወጥታ ሥጋ​ዉ​ንና የቂ​ጣ​ዉን እን​ጎቻ በላች። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ከዐ​ይ​ኖቹ ተሰ​ወረ።</verse>
				<verse number="22">ጌዴ​ዎ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ እንደ ሆነ ዐወቀ። ጌዴ​ዎ​ንም፥ “አቤቱ! አም​ላኬ ሆይ! ወዮ​ልኝ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ ፊት ለፊት አይ​ቻ​ለ​ሁና” አለ።</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሰላም ለአ​ንተ ይሁን፤ አት​ፍራ፤ አት​ሞ​ትም” አለው።</verse>
				<verse number="24">ጌዴ​ዎ​ንም በዚያ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሠራ፤ ስሙ​ንም እስከ ዛሬ ድረስ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰላም” ብሎ ጠራው። እር​ሱም እስከ ዛሬ ድረስ ለኤ​ዝሪ አባት በሆ​ነ​ችው በኤ​ፍ​ራታ አለ።</verse>
				<verse number="25">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዚ​ያች ሌሊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “የአ​ባ​ት​ህን በሬ፥ ሰባት ዓመት የሆ​ነ​ውን ሁለ​ተ​ኛ​ውን በሬ ውሰድ፤ የአ​ባ​ትህ የሆ​ነ​ው​ንም የበ​ዓል መሠ​ዊያ አፍ​ርስ፤ በእ​ር​ሱም ዙሪያ ያለ​ውን የማ​ም​ለ​ኪያ ዐጸድ ቍረጥ፤</verse>
				<verse number="26">በዚ​ያም ተራራ አናት ላይ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ አሳ​ም​ረህ ሥራ፤ ሁለ​ተ​ኛ​ዉ​ንም በሬ ውሰድ፤ በዚ​ያም በቈ​ረ​ጥ​ኸው በማ​ም​ለ​ኪያ ዐጸዱ እን​ጨት ላይ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርብ” አለው።</verse>
				<verse number="27">ጌዴ​ዎ​ንም ከባ​ሪ​ያ​ዎቹ ዐሥራ ሦስት ሰዎ​ችን ወስዶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ለው አደ​ረገ፤ የአ​ባ​ቱ​ንም ቤተ ሰቦች፥ የከ​ተ​ማ​ዉ​ንም ሰዎች ስለ​ፈራ ይህን በቀን ለማ​ድ​ረግ አል​ቻ​ለም፤ ነገር ግን በሌ​ሊት አደ​ረ​ገው።</verse>
				<verse number="28">የከ​ተ​ማ​ውም ሰዎች ማል​ደው ተነሡ፤ እነ​ሆም፥ የበ​ዓል መሠ​ዊያ ፈርሶ፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ያለው የማ​ም​ለ​ኪያ ዐጸድ ተቈ​ርጦ፥ በተ​ሠ​ራ​ውም መሠ​ዊያ ላይ ሁለ​ተ​ኛው በሬ ተሠ​ውቶ አገ​ኙት።</verse>
				<verse number="29">እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ይህን ነገር ያደ​ረገ ማን ነው?” ተባ​ባሉ። በጠ​የ​ቁና በመ​ረ​መ​ሩም ጊዜ፥ “ይህን ነገር ያደ​ረገ የኢ​ዮ​አስ ልጅ ጌዴ​ዎን ነው” አሉ።</verse>
				<verse number="30">የከ​ተ​ማ​ዉም ሰዎች ኢዮ​አ​ስን፥ “የበ​ዓ​ልን መሠ​ዊያ አፍ​ር​ሶ​አ​ልና፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ያለ​ውን የማ​ም​ለ​ኪያ ዐጸድ ቈር​ጦ​አ​ልና ይገ​ደል ዘንድ ልጅ​ህን አምጣ” አሉት።</verse>
				<verse number="31">ኢዮ​አ​ስም በእ​ርሱ ላይ የተ​ነ​ሡ​በ​ትን ሁሉ፥ “ለበ​ዓል እና​ንተ ዛሬ ትበ​ቀ​ሉ​ለ​ታ​ላ​ች​ሁን? ወይስ የበ​ደ​ለ​ውን ትገ​ድ​ሉ​ለት ዘንድ የም​ታ​ድ​ኑት እና​ንተ ናች​ሁን? እርሱ አም​ላክ ከሆ​ነስ የበ​ደ​ለው እስከ ነገ ድረስ ይሙት። መሠ​ዊ​ያ​ዉ​ንም ያፈ​ረ​ሰ​ውን እርሱ ይበ​ቀ​ለው” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="32">በዚ​ያች ቀንም መሠ​ዊ​ያ​ዉን አፍ​ር​ሶ​አ​ልና በዓል ከእ​ርሱ ጋር ይሟ​ገት ሲል ጌዴ​ዎ​ንን ይሩ​በ​ኣል ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="33">ምድ​ያ​ምና አማ​ሌ​ቅም ሁሉ፥ የም​ሥ​ራ​ቅም ልጆች አንድ ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ፤ ተሻ​ግ​ረ​ውም በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ሸለቆ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="34">ጌዴ​ዎ​ን​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ አጸ​ናው፤ እር​ሱም ቀንደ መለ​ከ​ቱን ነፋ፤ አብ​ዔ​ዜ​ርም በኋ​ላው ጮኸ።</verse>
				<verse number="35">ወደ ምና​ሴም ነገድ ሁሉ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እር​ሱም ከኋ​ላው ሆኖ ጮኸ፤ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ች​ንም ወደ አሴ​ርና ወደ ዛብ​ሎን ወደ ንፍ​ታ​ሌ​ምም ላከ፤ እነ​ር​ሱም ሊቀ​በ​ሉ​አ​ቸው ወጡ።</verse>
				<verse number="36">ጌዴ​ዎ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “እንደ ተና​ገ​ርህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በእኔ እጅ ታድን እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="37">እነሆ! በዐ​ው​ድ​ማዉ ላይ የተ​ባ​ዘተ የበግ ጠጕር አኖ​ራ​ለሁ፤ በጠ​ጕሩ ብቻ ላይ ጠል ቢሆን በም​ድ​ሩም ሁሉ ደረቅ ቢሆን፥ እንደ ተና​ገ​ርህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በእኔ እጅ እን​ደ​ም​ታ​ድ​ና​ቸው አው​ቃ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="38">እን​ዲ​ሁም ሆነ፤ በነ​ጋው ማልዶ ተነሣ፤ ጠጕ​ሩ​ንም ጨመ​ቀው፤ ከጠ​ጕ​ሩም የተ​ጨ​መ​ቀው ጠል አንድ መን​ቀል ሙሉ ውኃ ሆነ።</verse>
				<verse number="39">ጌዴ​ዎ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “በቍ​ጣህ አት​ቈ​ጣኝ፤ ደግሞ አን​ዲት ነገር ልና​ገር፤ ጠጕሩ ብቻ​ውን ደረቅ ይሁን፤ በም​ድ​ሩም ላይ ጠል ይው​ረድ።”</verse>
				<verse number="40">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚ​ያች ሌሊት እን​ዲሁ አደ​ረገ፤ ጠጕሩ ብቻ ደረቅ ሆነ፥ በም​ድ​ሩም ሁሉ ላይ ጠል ወረደ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">ጌዴ​ዎን የተ​ባ​ለ​ውም ይሩ​በ​ኣል ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሕዝብ ሁሉ ማል​ደው ተነሡ፤ በአ​ሮ​ኤድ ምንጭ አጠ​ገብ ሰፈሩ፤ የም​ድ​ያ​ምም ሰፈር ከእ​ነ​ርሱ ወደ ሰሜን በኩል በሞሬ ኮረ​ብታ አጠ​ገብ በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ነበረ።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌዴ​ዎ​ንን፥ “ከአ​ንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝ​ቶ​አል፤ ስለ​ዚህ እስ​ራ​ኤል፦ እጄ አዳ​ነኝ ብሎ እን​ዳ​ይ​ታ​በ​ይ​ብኝ እኔ ምድ​ያ​ምን በእ​ጃ​ቸው አሳ​ልፌ አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም።”</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሁን እን​ግ​ዲህ፥ “የፈራ፥ የደ​ነ​ገ​ጠም ከገ​ለ​ዓድ ተራራ ተነ​ሥቶ ይመ​ለስ ብለህ በሕ​ዝቡ ጆሮ አውጅ” አለው። ከሕ​ዝ​ቡም ሃያ ሁለት ሺህ ተመ​ለሱ፤ ዐሥ​ርም ሺህ ቀሩ።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌዴ​ዎ​ንን፥ “ሕዝቡ ገና ብዙ ነው፤ ወደ ውኃ አው​ር​ዳ​ቸው፤ በዚ​ያም እፈ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔም፦ ይህ ከአ​ንተ ጋር ይሂድ የም​ለው እርሱ ከአ​ንተ ጋር ይሄ​ዳል፤ እኔም፦ ይህ ከአ​ንተ ጋር አይ​ሂድ የም​ለው እርሱ አይ​ሄ​ድም” አለው።</verse>
				<verse number="5">ሕዝ​ቡ​ንም ወደ ውኃ አወ​ረደ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌዴ​ዎ​ንን፥ “ውሻ እን​ደ​ሚ​ጠጣ ውኃ በም​ላሱ የሚ​ጠ​ጣ​ውን ሁሉ፥ እር​ሱን ለብ​ቻው አድ​ር​ገው፤ እን​ዲ​ሁም ሊጠጣ በጕ​ል​በቱ የሚ​ን​በ​ረ​ከ​ከ​ውን ሁሉ ለብ​ቻው አድ​ር​ገው” አለው።</verse>
				<verse number="6">በእ​ጃ​ቸ​ውም ውኃ ወደ አፋ​ቸው አድ​ር​ገው የጠ​ጡት ቍጥር ሦስት መቶ ሆነ፤ የቀ​ሩት ሕዝብ ግን ውኃ ሊጠጡ በጕ​ል​በ​ታ​ቸው ተን​በ​ረ​ከኩ።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌዴ​ዎ​ንን፥ “በእ​ጃ​ቸው ውኃ በጠ​ጡት በሦ​ስት መቶ ሰዎች አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ ምድ​ያ​ም​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ የቀ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ግን ወደ ስፍ​ራ​ቸው ይመ​ለሱ” አለው።</verse>
				<verse number="8">የሕ​ዝ​ቡ​ንም ስን​ቅና ቀንደ መለ​ከት በእ​ጃ​ቸው ወሰዱ፤ የቀ​ሩ​ት​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ድን​ኳ​ና​ቸው ሰደ​ዳ​ቸው፤ ሦስ​ቱን መቶ ሰዎች ግን በእ​ርሱ ዘንድ ጠበ​ቃ​ቸው፤ የም​ድ​ያ​ምም ሰፈር ከእ​ርሱ በታች በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ነበረ።</verse>
				<verse number="9">በዚ​ያ​ችም ሌሊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ተነ​ሥ​ተህ ወደ ሰፈር ውረድ።</verse>
				<verse number="10">ብቻ​ህ​ንም ለመ​ው​ረድ ብት​ፈራ አንተ ከሎ​ሌህ ፋራን ጋር ወደ ሰፈሩ ውረድ፤</verse>
				<verse number="11">የሚ​ና​ገ​ሩ​ት​ንም አድ​ም​ጣ​ቸው፤ ከዚ​ያም በኋላ እጆ​ችህ ይበ​ረ​ታሉ፤ ወደ ሰፈ​ርም ትወ​ር​ዳ​ለህ” አለው። እር​ሱም ከሎ​ሌው ፋራን ጋር ከሰ​ፈሩ በአ​ንድ ወገን የአ​ምሳ አለቃ ጦር ወደ ሰፈ​ረ​በት ወረደ።</verse>
				<verse number="12">ብዛ​ታ​ቸ​ውም እንደ አን​በጣ የሆነ ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንና አማ​ሌ​ቃ​ው​ያን የም​ሥ​ራ​ቅም ልጆች ሁሉ በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ሰፍ​ረው ነበር፤ የግ​መ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም ብዛት ቍጥር እን​ደ​ሌ​ለው በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ ነበረ።</verse>
				<verse number="13">ጌዴ​ዎ​ንም በደ​ረሰ ጊዜ አንድ ሰው ሕል​ምን ለባ​ል​ን​ጀ​ራው ሲያ​ጫ​ውት፥ “እነሆ፥ ሕልም አለ​ምሁ፤ እነ​ሆም፥ አን​ዲት የገ​ብስ እን​ጎቻ ወደ ምድ​ያም ሰፈር ተን​ከ​ባ​ልላ ወረ​ደች፤ ወደ ድን​ኳ​ኑም ደርሳ እስ​ኪ​ወ​ድቅ ድረስ መታ​ችው፤ ገለ​በ​ጠ​ች​ውም፤ ድን​ኳ​ኑም ወደቀ” ይል ነበር።</verse>
				<verse number="14">ባል​ን​ጀ​ራ​ውም መልሶ፥ “ይህ ነገር ከእ​ስ​ራ​ኤል ሰው ከኢ​ዮ​አስ ልጅ ከጌ​ዴ​ዎን ሰይፍ በቀር ሌላ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ያ​ም​ንና ሠራ​ዊ​ቱን ሁሉ በእጁ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አል” አለው።</verse>
				<verse number="15">ጌዴ​ዎ​ንም ሕል​ሙ​ንና ትር​ጓ​ሜ​ዉን በሰማ ጊዜ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ሰፈር ተመ​ልሶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ያ​ምን ሠራ​ዊት በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና ተነሡ” አለ።</verse>
				<verse number="16">ሦስ​ቱ​ንም መቶ ሰዎች በሦ​ስት ወገን ከፈ​ላ​ቸው፤ በሁ​ሉም እጅ ቀንደ መለ​ከ​ትና ባዶ ማሰሮ፥ በማ​ሰ​ሮ​ዉም ውስጥ ችቦ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">እር​ሱም፥ “እኔን ተመ​ል​ከቱ፤ እን​ዲ​ሁም አድ​ርጉ፤ እነ​ሆም፥ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ በደ​ረ​ስሁ ጊዜ እኔ እን​ደ​ማ​ደ​ርግ እን​ዲሁ እና​ንተ አድ​ርጉ፤</verse>
				<verse number="18">እኔ ከእ​ኔም ጋር ያሉት ሁሉ ቀንደ መለ​ከት ስን​ነፋ፥ እና​ንተ ደግሞ በሰ​ፈሩ ዙሪያ ሁሉ ቀንደ መለ​ከ​ታ​ች​ሁን ንፉ፦ ኀይል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ሰይፍ የጌ​ዴ​ዎን በሉ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">ጌዴ​ዎ​ንም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት መቶ ሰዎች በመ​ካ​ከ​ለ​ኛው ትጋት መጀ​መ​ሪያ ዘብ ጠባ​ቂ​ዎች ሳይ​ነቁ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፤ ቀንደ መለ​ከ​ቶ​ች​ንም ነፉ፤ በእ​ጃ​ቸ​ውም የነ​በ​ሩ​ትን ማሰ​ሮ​ዎች ሰባ​በሩ፤</verse>
				<verse number="20">ሦስ​ቱም ወገ​ኖች ቀንደ መለ​ከ​ቶ​ችን ነፉ፤ ማሰ​ሮ​ዎ​ች​ንም ሰበሩ፤ በግራ እጃ​ቸ​ውም ችቦ​ዎ​ችን፥ በቀኝ እጃ​ቸ​ውም ቀንደ መለ​ከ​ቶ​ችን ይዘው እየ​ነፉ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና የጌ​ዴ​ዎን ሰይፍ” ብለው ጮኹ።</verse>
				<verse number="21">ሁሉም በየ​ቦ​ታው፥ በሰ​ፈሩ ዙሪያ ቆመ፤ ሠራ​ዊ​ቱም ሁሉ ደን​ግ​ጠው ሸሹ።</verse>
				<verse number="22">ሦስ​ቱ​ንም መቶ ቀንደ መለ​ከ​ቶ​ችን ነፉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሰ​ውን ሁሉ ሰይፍ በባ​ል​ን​ጀ​ራ​ዉና በሠ​ራ​ዊቱ ሁሉ ላይ አደ​ረገ፤ ሠራ​ዊ​ቱም በጽ​ሬራ በኩል እስከ ቤት​ሲጣ ጋራ​ጋታ ድረስ በጣ​ባት አጠ​ገብ እስ​ካ​ለው እስከ አቤ​ል​ሜ​ሁላ ዳርቻ ድረስ ሸሸ።</verse>
				<verse number="23">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምና ከአ​ሴር፥ ከም​ና​ሴም ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው ምድ​ያ​ምን አሳ​ደዱ።</verse>
				<verse number="24">ጌዴ​ዎ​ንም፥ “ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንን ለመ​ግ​ጠም ውረዱ፥ እስከ ቤት​ባ​ራም ድረስ ያለ​ውን ውኃ፥ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም፥ ያዙ​ባ​ቸው” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን በኤ​ፍ​ሬም ወዳ​ለው ተራ​ራማ ሀገር ሁሉ ላከ። የኤ​ፍ​ሬ​ምም ሰዎች ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው እስከ ቤት​ባራ ድረስ ውኃ​ውን፥ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ቀድ​መው ያዙ።</verse>
				<verse number="25">የም​ድ​ያ​ምን ሁለ​ቱን አለ​ቆች ሔሬ​ብ​ንና ዜብን ያዙ፤ ሔሬ​ብ​ንም በሱ​ር​ኤ​ራብ ገደ​ሉት፥ ዜብ​ንም በኢ​ያ​ፌቅ ገደ​ሉት፤ የም​ድ​ያ​ም​ንም ሰዎች አሳ​ደዱ፤ የሔ​ሬ​ብ​ንና የዜ​ብ​ንም ራስ ይዘው ወደ ዮር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ጌዴ​ዎን አመጡ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">የኤ​ፍ​ሬም ሰዎ​ችም፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው? ምድ​ያ​ምን ለመ​ዋ​ጋት በወ​ጣህ ጊዜ ለምን አል​ጠ​ራ​ኸ​ንም?” አሉት። ጽኑ ጥልም ተጣ​ሉት።</verse>
				<verse number="2">እር​ሱም፥ “እኔ ዛሬ እና​ንተ እን​ዳ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ምን አደ​ረ​ግሁ? የኤ​ፍ​ሬም ወይን ቃር​ሚያ ከአ​ቢ​ዔ​ዜር ወይን መከር አይ​ሻ​ል​ምን?</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ያ​ምን አለ​ቆች ሔሬ​ብ​ንና ዜብን በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋል እና​ንተ ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ትን የሚ​መ​ስል እኔ ምን ማድ​ረግ እችል ኖር​አል?” አላ​ቸው። ከዚህ በኋላ ተዉት፤ ይህን ቃል በተ​ና​ገ​ራ​ቸ​ውም ጊዜ መን​ፈ​ሳ​ቸው ዐረ​ፈች።</verse>
				<verse number="4">ጌዴ​ዎ​ንም ወደ ዮር​ዳ​ኖስ መጥቶ ተሻ​ገረ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉት ሦስት መቶ ሰዎች ተሻ​ገሩ፤ ምንም እንኳ ቢራ​ቡም ያሳ​ድዱ ነበር።</verse>
				<verse number="5">የሱ​ኮ​ት​ንም ሰዎች፥ “ተር​በ​ዋ​ልና እኔን ለተ​ከ​ተሉ ሰዎች እባ​ካ​ችሁ እህል ስጡ​አ​ቸው፤ እኔም የም​ድ​ያ​ምን ነገ​ሥ​ታት ዛብ​ሄ​ል​ንና ስል​ማ​ናን አሳ​ድ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">የሱ​ኮ​ትም አለ​ቆች፥ “እኛ ለሠ​ራ​ዊ​ትህ እህል እን​ድ​ን​ሰጥ የዛ​ብ​ሄ​ልና የስ​ል​ማና እጅ አሁን በእ​ጅህ ነውን?” አሉ።</verse>
				<verse number="7">ጌዴ​ዎ​ንም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛብ​ሄ​ል​ንና ስል​ማ​ናን በእጄ አሳ​ልፎ ቢሰ​ጠኝ እኔ በም​ድረ በዳ እሾ​ህና በኩ​ር​ን​ችት ሥጋ​ች​ሁን እገ​ር​ፋ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="8">ከዚ​ያም ወደ ፋኑ​ሄል ወጣ፤ ለፋ​ኑ​ሄ​ልም ሰዎች እን​ዲሁ አላ​ቸው፤ የፋ​ኑ​ሄ​ልም ሰዎች የሱ​ኮት ሰዎች እንደ መለሱ መለ​ሱ​ለት።</verse>
				<verse number="9">እር​ሱም የፋ​ኑ​ሄ​ልን ሰዎች፥ “በደ​ኅና በተ​መ​ለ​ስሁ ጊዜ ይህን ግንብ አፈ​ር​ሰ​ዋ​ለሁ” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">ዛብ​ሄ​ልና ስል​ማ​ናም ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር በቀ​ር​ቀር ነበሩ፤ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ መቶ ሃያ ሺህ ሰዎች ወድ​ቀው ነበ​ርና ከም​ሥ​ራቅ ሰዎች ሠራ​ዊት ሁሉ የቀሩ ዐሥራ አም​ስት ሺህ ያህል ሰዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="11">ጌዴ​ዎ​ንም በድ​ን​ኳን የሚ​ኖሩ ሰዎች ባሉ​በት መን​ገድ በኖ​ቤ​ትና በዮ​ግ​ቤል በም​ሥ​ራቅ በኩል ወጣ፤ ሠራ​ዊ​ቱም ተዘ​ልሎ ሳለ አጠ​ፋ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">ዛብ​ሄ​ልና ስል​ማ​ናም ሸሹ፤ እር​ሱም አሳ​ደ​ዳ​ቸው፤ ሁለ​ቱ​ንም የም​ድ​ያም ነገ​ሥ​ታት ዛብ​ሄ​ል​ንና ስል​ማ​ናን ያዘ፤ ጌዴ​ዎ​ንም ሠራ​ዊ​ቱን ሁሉ አጠፋ።</verse>
				<verse number="13">የኢ​ዮ​አስ ልጅ ጌዴ​ዎ​ንም ከአ​ሬስ ዳገት ከጦ​ር​ነት ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="14">ከሱ​ኮ​ትም ሰዎች አንድ ብላ​ቴና ይዞ መረ​መ​ረው፤ እር​ሱም ሰባ ሰባ​ቱን የሱ​ኮ​ትን አለ​ቆ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችን አስ​ቈ​ጠ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">ጌዴ​ዎ​ንም ወደ ሱኮት አለ​ቆች መጥቶ፥ “ለደ​ከ​ሙት ሰዎ​ችህ እህል እን​ሰጥ ዘንድ የዛ​ብ​ሄ​ልና የስ​ል​ማና እጅ አሁን በእ​ጅህ ነውን? ብላ​ችሁ የተ​ላ​ገ​ዳ​ች​ሁ​ብኝ፥ ዛብ​ሄ​ልና ስል​ማና እነሆ፥” አለ።</verse>
				<verse number="16">የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና አለ​ቆች ያዘ፥ የም​ድረ በዳ​ንም እሾ​ህና ኩር​ን​ችት ወስዶ የሱ​ኮ​ትን ሰዎች ገረ​ፋ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">የፋ​ኑ​ሄ​ል​ንም ግንብ አፈ​ረሰ፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ሰዎች ገደ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">ዛብ​ሄ​ል​ንና ስል​ማ​ናን፥ “በታ​ቦር የገ​ደ​ላ​ች​ኋ​ቸው ሰዎች እን​ዴት ያሉ ነበሩ?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “እን​ዳ​ንተ ያሉ ነበሩ፤ አን​ተ​ንም ይመ​ስሉ ነበር፤ መል​ካ​ቸ​ውም እንደ ነገ​ሥት ልጆች መልክ ነበረ” ብለው መለ​ሱ​ለት።</verse>
				<verse number="19">ጌዴ​ዎ​ንም፥ “የእ​ናቴ ልጆች ወን​ድ​ሞቼ ነበሩ፤ አድ​ና​ች​ኋ​ቸው ቢሆን ኖሮ፥ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እኔ አል​ገ​ድ​ላ​ች​ሁም ነበር” አለ።</verse>
				<verse number="20">በኵ​ሩ​ንም ዮቶ​ርን፥ “ተነ​ሥ​ተህ ግደ​ላ​ቸው” አለው፤ ብላ​ቴ​ናው ግን ገና ትንሽ ነበ​ረና ስለ ፈራ ሰይ​ፉን አል​መ​ዘ​ዘም።</verse>
				<verse number="21">ዛብ​ሄ​ልና ስል​ማ​ናም፥ “ኀይ​ልህ እንደ ጐል​ማሳ ኀይል ነውና አንተ ተነ​ሥ​ተህ ውደ​ቅ​ብን” አሉት። ጌዴ​ዎ​ንም ተነ​ሥቶ ዛብ​ሄ​ል​ንና ስል​ማ​ናን ገደለ፤ በግ​መ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም አን​ገት የነ​በ​ሩ​ትን ሥሉ​ሴ​ዎች ማረከ።</verse>
				<verse number="22">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ጌዴ​ዎ​ንን፥ “ከም​ድ​ያም እጅ አድ​ነ​ኸ​ና​ልና አንተ፥ ልጅ​ህም፥ የልጅ ልጅ​ህም ደግሞ ግዙን” አሉት።</verse>
				<verse number="23">ጌዴ​ዎ​ንም፥ “እኔ አል​ገ​ዛ​ች​ሁም፤ ልጄም አይ​ገ​ዛ​ች​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገ​ዛ​ች​ኋል እንጂ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">እስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም ስለ ነበሩ የወ​ርቅ ጕትቻ ነበ​ራ​ቸ​ውና ጌዴ​ዎን፥ “ሁላ​ች​ሁም ከም​ር​ኮ​አ​ችሁ ጕት​ቻ​ች​ሁን እን​ድ​ት​ሰ​ጡኝ እለ​ም​ና​ች​ኋ​ለሁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">እነ​ር​ሱም፥ “መስ​ጠ​ትን ፈቅ​ደን እን​ሰ​ጥ​ሃ​ለን” ብለው መለ​ሱ​ለት። መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያም አነ​ጠፉ፤ ሰውም ሁሉ የም​ር​ኮ​ውን ጕትቻ በዚያ ላይ ጣለ።</verse>
				<verse number="26">የለ​መ​ነ​ውም የወ​ርቅ ጕትቻ ሚዛኑ ከአ​ም​ባሩ፥ ከድ​ሪ​ውም፥ የም​ድ​ያ​ምም ነገ​ሥ​ታት ከለ​በ​ሱት ከቀዩ ቀሚስ፥ በግ​መ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም አን​ገት ከነ​በ​ሩት ሥሉ​ሴ​ዎች ሌላ ሺህ ሰባት መቶ ሰቅለ ወርቅ ነበረ።</verse>
				<verse number="27">ጌዴ​ዎ​ንም ምስል አድ​ርጎ ሠራው፤ በከ​ተ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ራታ አኖ​ረው፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ተከ​ትሎ አመ​ነ​ዘ​ረ​በት፤ ለጌ​ዴ​ዎ​ንና ለቤ​ቱም ወጥ​መድ ሆነ።</verse>
				<verse number="28">ምድ​ያ​ምም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተዋ​ረዱ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ዳግ​መኛ አላ​ነ​ሡም፤ በጌ​ዴ​ዎ​ንም ዕድሜ ምድ​ሪቱ አርባ ዓመት ዐረ​ፈች።</verse>
				<verse number="29">የኢ​ዮ​አ​ስም ልጅ ይሩ​በ​ኣል ሄዶ በቤቱ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="30">ለጌ​ዴ​ዎ​ንም ብዙ ሚስ​ቶች ነበ​ሩ​ትና ከአ​ብ​ራኩ የወጡ ሰባ ልጆች ነበ​ሩት።</verse>
				<verse number="31">በሴ​ኬ​ምም የነ​በ​ረ​ችው ዕቅ​ብቱ ወንድ ልጅ ወለ​ደ​ች​ለት፤ ስሙ​ንም አቤ​ሜ​ሌክ ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="32">የኢ​ዮ​አ​ስም ልጅ ጌዴ​ዎን በመ​ል​ካም ሽም​ግ​ልና ሞተ፤ በአ​ብ​ያ​ዜ​ራ​ው​ያ​ንም ከተማ በኤ​ፍ​ራታ በነ​በ​ረ​ችው በአ​ባቱ በኢ​ዮ​አስ መቃ​ብር ተቀ​በረ።</verse>
				<verse number="33">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ጌዴ​ዎን ከሞተ በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተመ​ለሱ፤ በዓ​ሊ​ም​ንም ተከ​ት​ለው አመ​ነ​ዘሩ፤ በዓ​ሊ​ምም አም​ላክ ይሆ​ና​ቸው ዘንድ ከእ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገቡ።</verse>
				<verse number="34">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በዙ​ሪ​ያ​ቸው ከነ​በ​ሩት ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ እጅ ያዳ​ና​ቸ​ውን አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ሰ​ቡ​ትም፤</verse>
				<verse number="35">እር​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል በጎ ነገ​ርን ሁሉ እን​ዳ​ደ​ረገ መጠን፥ እነ​ርሱ ይሩ​በ​ኣል ለተ​ባ​ለው ለጌ​ዴ​ዎን ቤት ወረታ አላ​ደ​ረ​ጉም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">የይ​ሩ​በ​ኣል ልጅ አቤ​ሜ​ሌ​ክም ወደ ሰቂማ ወደ እናቱ ወን​ድ​ሞች ሄደ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም፥ ለእ​ናቱ አባት ቤተ ሰቦ​ችም ሁሉ እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፦</verse>
				<verse number="2">“ለሰ​ቂማ ሰዎች ሁሉ፦ ሰባ የሆ​ኑት የይ​ሩ​በ​ኣል ልጆች ሁሉ ቢገ​ዙ​አ​ችሁ ወይስ አንድ ሰው ቢገ​ዛ​ችሁ ምን ይሻ​ላ​ች​ኋል? ብላ​ችሁ ንገ​ሩ​አ​ቸው፤ ደግ​ሞም እኔ የአ​ጥ​ን​ታ​ችሁ ፍላጭ፥ የሥ​ጋ​ችሁ ቍራጭ እንደ ሆንሁ አስቡ።”</verse>
				<verse number="3">የእ​ና​ቱም ወን​ድ​ሞች ይህን ቃል ሁሉ ስለ እርሱ በሰ​ቂማ ሰዎች ሁሉ ጆሮ ተና​ገሩ፤ እነ​ር​ሱም፥ “እርሱ ወን​ድ​ማ​ችን ነው” ብለው ልባ​ቸ​ውን ወደ አቤ​ሜ​ሌክ መለ​ሱት።</verse>
				<verse number="4">ከበ​ዓ​ልም ቤት ሰባ ብር ሰጡት፤ በዚ​ያም አቤ​ሜ​ሌክ ወን​በ​ዴ​ዎ​ች​ንና አስ​ደ​ን​ጋ​ጮ​ችን ቀጠ​ረ​በት፤ እነ​ር​ሱም ተከ​ት​ለ​ውት ሄዱ።</verse>
				<verse number="5">ወደ አባ​ቱም ቤት ወደ ኤፍ​ራታ ገባ፤ ሰባ የሆ​ኑ​ትን የይ​ሩ​በ​ኣ​ልን ልጆች ወን​ድ​ሞ​ቹን በአ​ንድ ድን​ጋይ ላይ ገደ​ላ​ቸው፤ ትንሹ የይ​ሩ​በ​ኣል ልጅ ኢዮ​አ​ታም ግን ተሸ​ሽጎ ነበ​ርና ተረፈ።</verse>
				<verse number="6">የሰ​ቂ​ማም ሰዎች ሁሉ፥ የመ​ሐ​ሎ​ንም ቤት ሁሉ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሄደ​ውም በሰ​ቂማ በዐ​ምዱ አጠ​ገብ ባለው የወ​ይራ ዛፍ በታች አቤ​ሜ​ሌ​ክን አነ​ገሡ።</verse>
				<verse number="7">ይህ​ንም ነገር ለኢ​ዮ​አ​ታም በነ​ገ​ሩት ጊዜ፥ ሄዶ በገ​ሪ​ዛን ተራራ ራስ ላይ ቆመ፤ ድም​ፁ​ንም አን​ሥቶ አለ​ቀሰ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “የሰ​ቂማ ሰዎች ሆይ! ስሙኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይስ​ማ​ችሁ።</verse>
				<verse number="8">አንድ ጊዜ ዛፎች በላ​ያ​ቸው ንጉሥ ሊያ​ነ​ግሡ ሄዱ፤ ወይ​ራ​ንም፦ በእኛ ላይ ንገ​ሺ​ልን አሉ​አት።</verse>
				<verse number="9">ወይ​ራዋ ግን፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰዎ​ችን የሚ​ያ​ከ​ብ​ር​በ​ትን ቅባ​ቴን ትቼ በዛ​ፎች ላይ ለመ​ን​ገሥ ልሂ​ድን? አለ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">ዛፎ​ችም በለ​ሲ​ቱን፦ መጥ​ተሽ በላ​ያ​ችን ንገ​ሺ​ልን አሉ​አት።</verse>
				<verse number="11">በለሷ ግን፦ ጣፋ​ጭ​ነ​ቴ​ንና መል​ካ​ሙን ፍሬ​ዬን ትቼ በዛ​ፎች ላይ እነ​ግሥ ዘንድ ልሂ​ድን? አለ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">ዛፎ​ችም ሁሉ ወይ​ኑን፦ መጥ​ተህ በላ​ያ​ችን ንገሥ አሉት።</verse>
				<verse number="13">ወይ​ኑም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ሰውን ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን የወ​ይን ጠጅ​ነ​ቴን ትቼ በዛ​ፎች ላይ እነ​ግሥ ዘንድ ልሂ​ድን? አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">ዛፎ​ችም ዶግን፦ መጥ​ተሽ በላ​ያ​ችን ንገሺ አሉ​አት፤</verse>
				<verse number="15">ዶግም ዛፎ​ቹን፦ በእ​ው​ነት እኔን በእ​ና​ንተ ላይ ካነ​ገ​ሣ​ች​ሁኝ እሳት ከዶግ ወጥቶ የሊ​ባ​ኖ​ስን ዝግባ ካል​በ​ላው ከጥ​ላዬ በታች ታርፉ ዘንድ ኑ አለ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">አሁን እን​ግ​ዲህ አቤ​ሜ​ሌ​ክን በማ​ን​ገ​ሣ​ችሁ እው​ነ​ት​ንና ቅን​ነ​ትን አድ​ር​ጋ​ችሁ እንደ ሆነ፥ ለይ​ሩ​በ​ኣ​ልም፥ ለቤ​ቱም በጎ አድ​ር​ጋ​ችሁ እን​ደ​ሆ​ነና እንደ እጁም ዋጋ መጠን ለእ​ርሱ የተ​ገ​ባ​ውን አድ​ር​ጋ​ችሁ እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="17">አባ​ቴስ ለእ​ና​ንተ እንደ ተጋ​ደለ፥ በፊ​ታ​ች​ሁም ሰው​ነ​ቱን ለሞት አሳ​ልፎ እንደ ሰጠ፥ ከም​ድ​ያ​ምም እጅ እንደ አዳ​ና​ችሁ፥</verse>
				<verse number="18">እና​ን​ተም ዛሬ በአ​ባቴ ቤት ተነ​ሥ​ታ​ች​ኋል፤ ሰባ የሆ​ኑ​ትን ልጆ​ቹ​ንም በአ​ንድ ድን​ጋይ ላይ ገድ​ላ​ች​ኋል፤ ወን​ድ​ማ​ች​ሁም ስለ​ሆነ የዕ​ቅ​ብ​ቱን ልጅ አቤ​ሜ​ሌ​ክን በሰ​ቂማ ሰዎች ላይ አን​ግ​ሣ​ች​ኋል፥</verse>
				<verse number="19">ለይ​ሩ​በ​ኣ​ልና ለቤቱ እው​ነ​ት​ንና ቅን​ነ​ትን ዛሬ አድ​ር​ጋ​ችሁ እንደ ሆነ የተ​ባ​ረ​ካ​ችሁ ሁኑ፤ በአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክም ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ እር​ሱም ደግሞ በእ​ና​ንተ ደስ ይበ​ለው፤</verse>
				<verse number="20">እን​ዲህ ባይ​ሆን ግን ከአ​ቤ​ሜ​ሌክ እሳት ትውጣ፤ የሰ​ቂ​ማ​ንም ሰዎች፥ የመ​ሐ​ሎ​ን​ንም ቤት ትብላ፤ ያም ባይ​ሆን ከሰ​ቂማ ሰዎች ከመ​ሐ​ሎ​ንም ቤት እሳት ትውጣ፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንም ትብ​ላው።”</verse>
				<verse number="21">ኢዮ​አ​ታ​ምም ሸሽቶ አመ​ለጠ፤ ወን​ድ​ሙን አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንም ፈርቶ ወደ ብኤር ሄደ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="22">አቤ​ሜ​ሌ​ክም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ሦስት ዓመት ገዥ ሆነ።</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክና በሰ​ቂማ ሰዎች መካ​ከል ክፉን መን​ፈስ ሰደደ፤ የሰ​ቂ​ማም ሰዎች የአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክን ቤት ከዱት።</verse>
				<verse number="24">ይህም የሆ​ነው፥ በሰ​ባው የይ​ሩ​በ​ኣል ልጆች ላይ የተ​ደ​ረ​ገው ዐመፅ እን​ዲ​መጣ፥ ደማ​ቸ​ውም በገ​ደ​ላ​ቸው በወ​ን​ድ​ማ​ቸው በአ​ቤ​ሜ​ሌክ ላይ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንም እን​ዲ​ገ​ድል እጆ​ቹን ባጸ​ኑ​አ​ቸው በሰ​ቂማ ሰዎች ላይ እን​ዲ​ሆን ነው።</verse>
				<verse number="25">የሰ​ቂ​ማም ሰዎች በተ​ራ​ሮች ራስ ላይ ድብቅ ጦር አደ​ረጉ፤ መን​ገድ ተላ​ላ​ፊ​ዎ​ች​ንም ሁሉ ይዘ​ርፉ ነበር፤ ለአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክም ይህን አወ​ሩ​ለት።</verse>
				<verse number="26">የአ​ቤ​ድም ልጅ ገዓል ከወ​ን​ድ​ሞቹ ጋር መጣ፤ የሰ​ቂማ ሰዎ​ችም ከእ​ርሱ ጋር ተባ​በሩ።</verse>
				<verse number="27">ወደ እር​ሻ​ውም ወጡ፤ ወይ​ና​ቸ​ው​ንም ለቀሙ፤ ጠመ​ቁ​ትም፤ የደ​ስ​ታም በዓል አደ​ረጉ፤ ወደ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም ቤት ገቡ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንም ረገ​ሙት።</verse>
				<verse number="28">የአ​ቤ​ድም ልጅ ገዓል፥ “አቤ​ሜ​ሌክ ማን ነው? እን​ገ​ዛ​ለ​ትስ ዘንድ የሴ​ኬም ልጅ ማን ነው? እርሱ የይ​ሩ​በ​ኣል ልጅ አይ​ደ​ለ​ምን? ዜቡ​ልስ የእ​ርሱ ጠባቂ አይ​ደ​ለ​ምን? ከሴ​ኬም አባት ከኤ​ሞር ሰዎች ጋርስ አገ​ል​ጋዩ አይ​ደ​ለ​ምን? ስለ​ም​ንስ ለዚህ እን​ገ​ዛ​ለን?</verse>
				<verse number="29">ይህ ሕዝብ ከእጄ በታች ቢሆን ኖሮ አቤ​ሜ​ሌ​ክን አሳ​ድ​ደው ነበር” አለ። አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንም፥ “ሠራ​ዊ​ት​ህን አብ​ዝ​ተህ ና፤ ውጣ” አለው።</verse>
				<verse number="30">የከ​ተ​ማ​ዪቱ ገዥ ዜቡ​ልም የአ​ቤ​ድን ልጅ የገ​ዓ​ልን ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ።</verse>
				<verse number="31">እን​ዲ​ህም ብሎ ወደ አቤ​ሜ​ሌክ ከእጅ መንሻ ጋር መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፥ “እነሆ፥ የአ​ቤድ ልጅ ገዓ​ልና ወን​ድ​ሞቹ ወደ ሰቂማ መጥ​ተ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ በአ​ንተ ምክ​ን​ያት ከተ​ማ​ዪ​ቱን ይወ​ጓ​ታል።</verse>
				<verse number="32">አሁ​ንም አን​ተና ከአ​ንተ ጋር ያሉት ሕዝብ በሌ​ሊት ተነሡ፤ በሜ​ዳም ሸምቁ፤</verse>
				<verse number="33">ነገም ፀሐይ በወ​ጣች ጊዜ ማል​ደህ ተነሣ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ክበ​ባት፤ እነ​ሆም፥ እር​ሱና ከእ​ርሱ ጋር ያሉት ሕዝብ በአ​ንተ ላይ በወጡ ጊዜ እጅህ እን​ዳ​ገ​ኘች አድ​ር​ግ​በት።”</verse>
				<verse number="34">አቤ​ሜ​ሌ​ክና ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉት ሕዝብ ሁሉ በሌ​ሊት መጡ። ሰቂ​ማ​ንም በአ​ራት ወገን ከበ​ቡ​አት።</verse>
				<verse number="35">በነ​ጋም ጊዜ የአ​ቤድ ልጅ ገዓል ወጥቶ በከ​ተ​ማ​ዪቱ መግ​ቢያ በር ቆመ፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክና ከእ​ርሱ ጋር ያሉት ሕዝ​ብም ከሸ​መ​ቁ​በት ስፍራ ተነሡ።</verse>
				<verse number="36">የአ​ቤድ ልጅ ገዓ​ልም ሕዝ​ቡን ባየ ጊዜ ዜቡ​ልን፥ “እነሆ፥ ከተ​ራ​ሮች ራስ ሕዝብ ይወ​ር​ዳል” አለው። ዜቡ​ልም፥ “ሰዎ​ችን የሚ​መ​ስ​ለ​ውን የተ​ራ​ሮ​ችን ጥላ ታያ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="37">ገዓ​ልም ደግሞ፥ “እነሆ፥ ሕዝብ በባ​ሕር በኩል ወደ ምድር መካ​ከል ይወ​ር​ዳል፤ የአ​ን​ድም አለቃ ሠራ​ዊት በአ​ድ​ባሩ ዛፍ መን​ገድ አን​ጻር ይመ​ጣል” ብሎ ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="38">ዜቡ​ልም፥ “እን​ገ​ዛ​ለት ዘንድ አቤ​ሜ​ሌክ ማን ነው? ያል​ህ​በት አፍህ አሁን የት አለ? ይህ የና​ቅ​ኸው ሕዝብ አይ​ደ​ለ​ምን? አሁ​ንም ወጥ​ተህ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ተዋጋ” አለው።</verse>
				<verse number="39">ገዓ​ልም በሰ​ቂማ ሰዎች ፊት ወጣ፤ ከአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክም ጋር ተዋጋ።</verse>
				<verse number="40">አቤ​ሜ​ሌ​ክም አሳ​ደ​ደው፤ በፊ​ቱም ሸሸ፤ እስከ ከተ​ማው በርም አደ​ባ​ባይ ድረስ ብዙ​ዎች ተጐ​ድ​ተው ወደቁ።</verse>
				<verse number="41">አቤ​ሜ​ሌ​ክም በአ​ሪማ ተቀ​መጠ፤ ዜቡ​ልም ገዓ​ል​ንና ወን​ድ​ሞ​ቹን በሰ​ቂማ እን​ዳ​ይ​ኖሩ ከለ​ከ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="42">በነ​ጋ​ውም ሕዝቡ ወደ እርሻ ወጡ፤ ለአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክም ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="43">ሕዝ​ቡ​ንም ወስዶ በሦ​ስት ወገን ከፈ​ላ​ቸው፤ በሜ​ዳም ሸመቀ፤ ተመ​ለ​ከ​ተም፤ እነ​ሆም፥ ሕዝቡ ከከ​ተማ ወጡ፤ ተነ​ሣ​ባ​ቸ​ውም፤ ገደ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="44">አቤ​ሜ​ሌ​ክም ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉት ሠራ​ዊት በከ​ተ​ማ​ዪቱ መግ​ቢያ በር ሸም​ቀው ቆሙ። እነ​ዚያ ሁለቱ ሠራ​ዊት ግን ወደ ጫካው ተበ​ት​ነው አጠ​ፉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="45">አቤ​ሜ​ሌ​ክም በዚያ ቀን ሁሉ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ጋር ተዋጋ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ይዞ በእ​ር​ስዋ የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ገደለ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም አፈ​ረሰ፤ ጨውም ዘራ​ባት።</verse>
				<verse number="46">በሰ​ቂ​ማም ግንብ ውስጥ የነ​በሩ ሰዎች ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ በዓል ቤት ወደ ምሽጉ ውስጥ ገቡ።</verse>
				<verse number="47">ለአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክም በሰ​ቂማ ግንብ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ አንድ ሆነው እንደ ተሰ​በ​ሰቡ ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="48">አቤ​ሜ​ሌ​ክና ከእ​ርሱ ጋር ያሉ​ትም ሕዝብ ሁሉ ወደ ሄር​ሞን ተራራ ወጡ፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክም በእጁ መጥ​ረ​ቢያ ወስዶ የዛ​ፉን ቅር​ን​ጫፍ ቈረጠ፤ አን​ሥ​ቶም በጫ​ን​ቃው ላይ ተሸ​ከ​መው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ለነ​በ​ሩት ሕዝብ፥ “እኔ ሳደ​ርግ ያያ​ች​ሁ​ትን፥ እና​ን​ተም ፈጥ​ና​ችሁ እኔ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ አድ​ርጉ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="49">ሕዝ​ቡም ሁሉ እን​ዲሁ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው የዛ​ፉን ቅር​ን​ጫ​ፎች ቈረጡ፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንም ተከ​ት​ለው በም​ሽጉ ዙሪያ አኖ​ሩ​አ​ቸው፤ ምሽ​ጉ​ንም በላ​ያ​ቸው በእ​ሳት አቃ​ጠ​ሉት፤ የሰ​ቂ​ማም ግንብ ሰዎች ሁሉ ደግሞ አንድ ሺህ የሚ​ያ​ህሉ ወን​ድና ሴት ሞቱ።</verse>
				<verse number="50">አቤ​ሜ​ሌ​ክም ወደ ቴቤስ መጣ።</verse>
				<verse number="51">በእ​ር​ስ​ዋም ተቀ​መጠ፤ እጅም አደ​ረ​ጋት። በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ውስጥ ብርቱ ግንብ ነበረ፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ሰዎች ሁሉ፥ ወን​ዱና ሴቱ ሁሉ፥ ወደ​ዚያ ሸሹ፤ ደጁ​ንም በኋ​ላ​ቸው ዘጉ፤ ወደ ግን​ቡም ሰገ​ነት ላይ ወጡ።</verse>
				<verse number="52">አቤ​ሜ​ሌ​ክም ወደ ግንቡ ሄደ። እነ​ር​ሱም ተዋ​ጉት። አቤ​ሜ​ሌ​ክም በእ​ሳት ሊያ​ቃ​ጥ​ለው ወደ ግንቡ ደጅ ቀረበ።</verse>
				<verse number="53">አን​ዲ​ትም ሴት በአ​ቤ​ሜ​ሌክ ራስ ላይ የወ​ፍጮ መጅ ጣለ​ች​በት፤ አና​ቱ​ንም ሰበ​ረ​ችው።</verse>
				<verse number="54">እር​ሱም ፈጥኖ ጋሻ ዣግ​ሬ​ውን ጠርቶ፥ “ሴት ገደ​ለ​ችው እን​ዳ​ይሉ ሰይ​ፍ​ህን መዝ​ዘህ ግደ​ለኝ” አለው፤ ጐል​ማ​ሳ​ውም ወጋው፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክም ሞተ።</verse>
				<verse number="55">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች አቤ​ሜ​ሌክ እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ስፍ​ራው ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="56">እን​ዲሁ ሰባ ወን​ድ​ሞ​ቹን በመ​ግ​ደል አቤ​ሜ​ሌክ በአ​ባቱ ቤት ላይ ያደ​ረ​ገ​ውን ክፋት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መለ​ሰ​በት።</verse>
				<verse number="57">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሰ​ቂ​ማን ሰዎች ክፋት ሁሉ በራ​ሳ​ቸው ላይ መለ​ሰ​ባ​ቸው፤ የይ​ሩ​በ​ኣል ልጅ የኢ​ዮ​አ​ታ​ምም ርግ​ማን ደረ​ሰ​ባ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">ከአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክም በኋላ ከይ​ሳ​ኮር ነገድ የሆነ የአ​ባቱ ወን​ድም ልጅ የፎሓ ልጅ ቶላ እስ​ራ​ኤ​ልን ለማ​ዳን ተነሣ፤ እር​ሱም በኤ​ፍ​ሬም ተራራ በሳ​ምር ተቀ​ምጦ ነበር።</verse>
				<verse number="2">እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሃያ ሦስት ዓመት ገዛ፤ ሞተም፤ በሳ​ም​ርም ተቀ​በረ።</verse>
				<verse number="3">ከእ​ር​ሱም በኋላ ገለ​ዓ​ዳ​ዊዉ ኢያ​ዕር ተነሣ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሃያ ሁለት ዓመት ገዛ።</verse>
				<verse number="4">በሠ​ላሳ ሁለት የአ​ህያ ግል​ገ​ሎች ይቀ​መጡ የነ​በሩ ሠላሳ ሁለት ልጆ​ችም ነበ​ሩት፤ ለእ​ነ​ር​ሱም እስከ ዛሬ ድረስ የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች የተ​ባሉ በገ​ለ​ዓድ ምድር ያሉ ሠላሳ ሁለት ከተ​ሞች ነበ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">ኢያ​ዕ​ርም ሞተ፤ በራ​ሞ​ንም ተቀ​በረ።</verse>
				<verse number="6">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ በዓ​ሊ​ም​ንና አስ​ታ​ሮ​ትን፥ የሶ​ር​ያ​ንም አማ​ል​ክት፥ የሲ​ዶ​ና​ንም አማ​ል​ክት፥ የሞ​ዓ​ብ​ንም አማ​ል​ክት፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች አማ​ል​ክት፥ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም አማ​ል​ክት አመ​ለኩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ተዉ፤ አላ​መ​ለ​ኩ​ት​ምም።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ፤ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅና በአ​ሞን ልጆች እጅም አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">በዚ​ያም ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሥቃይ አበ​ዙ​ባ​ቸው፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ሀገር በገ​ለ​ዓድ ውስጥ ያሉ​ትን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሁሉ ዐሥራ ስም​ንት ዓመት አስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">የአ​ሞ​ንም ልጆች ከይ​ሁዳ፥ ከብ​ን​ያ​ምና ከኤ​ፍ​ሬም ቤት ጋር ደግሞ ሊዋጉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም እጅግ ተጨ​ነቁ።</verse>
				<verse number="10">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ “አን​ተን አም​ላ​ካ​ች​ንን ትተን በዓ​ሊ​ምን አም​ል​ከ​ና​ልና ኀጢ​አት ሠር​ተ​ናል” ብለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አላ​ቸው፥ “ግብ​ፃ​ው​ያን፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ የአ​ሞ​ንና የሞ​አ​ብም ልጆች፥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥</verse>
				<verse number="12">ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም፥ ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንም፥ አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንም አላ​ስ​ጨ​ነ​ቋ​ች​ሁ​ምን? ወደ እኔም ጮኻ​ችሁ፤ እኔም ከእ​ጃ​ቸው አዳ​ን​ኋ​ችሁ።</verse>
				<verse number="13">እና​ንተ ግን ተዋ​ች​ሁኝ፤ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት አመ​ለ​ካ​ችሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ደግሞ አላ​ድ​ና​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="14">ሄዳ​ችሁ ወደ መረ​ጣ​ች​ኋ​ቸው አማ​ል​ክት ጩኹ፤ እነ​ር​ሱም በመ​ከ​ራ​ችሁ ጊዜ ያድ​ኑ​አ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="15">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “እኛ ኀጢ​አ​ትን ሠር​ተ​ናል፤ አንተ በፊ​ትህ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን አድ​ር​ግ​ብን፤ ዛሬ ግን እባ​ክህ አድ​ነን” አሉት።</verse>
				<verse number="16">ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አስ​ወ​ገዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ብቻ አመ​ለኩ፤ ደስም አሰ​ኙት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከሥ​ቃይ የተ​ነሣ አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን አጥ​ተው ነበር።</verse>
				<verse number="17">የአ​ሞ​ንም ልጆች ወጥ​ተው በገ​ለ​ዓድ ሰፈሩ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተሰ​ብ​ስ​በው በመ​ሴፋ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="18">የገ​ለ​ዓድ ሕዝብ አለ​ቆ​ችም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ከአ​ሞን ልጆች ጋር መዋ​ጋ​ትን የሚ​ጀ​ምር ማን ነው? እርሱ በገ​ለ​ዓድ ሰዎች ሁሉ ላይ አለቃ ይሆ​ናል” አሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">ገለ​ዓ​ዳ​ዊ​ዉም ዮፍ​ታሔ ጽኑዕ ኀያል ሰው የጋ​ለ​ሞታ ሴትም ልጅ ነበረ። ለገ​ለ​ዓ​ድም ዮፍ​ታ​ሔን ወለ​ደ​ች​ለት።</verse>
				<verse number="2">የገ​ለ​ዓ​ድም ሚስት ወን​ዶች ልጆ​ችን ወለ​ደ​ች​ለት፤ ልጆ​ች​ዋም ባደጉ ጊዜ ዮፍ​ታ​ሔን፥ “የሌላ ሴት ልጅ ነህና በአ​ባ​ታ​ችን ቤት አት​ወ​ር​ስም” ብለው አስ​ወ​ጡት።</verse>
				<verse number="3">ዮፍ​ታ​ሔም ከወ​ን​ድ​ሞቹ ፊት ሸሽቶ በጦብ ምድር ተቀ​መጠ፤ ድሆች ሰዎ​ችም ተሰ​ብ​ስ​በው ዮፍ​ታ​ሔን ተከ​ተ​ሉት።</verse>
				<verse number="4">ከዚ​ያም ወራት በኋላ የአ​ሞን ልጆች እስ​ራ​ኤ​ልን ተዋ​ጉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">የገ​ለ​ዓድ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ዮፍ​ታ​ሔን ከጦብ ምድር ለማ​ም​ጣት ሄዱ።</verse>
				<verse number="6">ዮፍ​ታ​ሔ​ንም፥ “ና፥ ከአ​ሞን ልጆች ጋር እን​ድ​ን​ዋጋ መስ​ፍን ሁነን” አሉት።</verse>
				<verse number="7">ዮፍ​ታ​ሔም የገ​ለ​ዓ​ድን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ “የጠ​ላ​ች​ሁኝ፥ ከአ​ባ​ቴም ቤት ያስ​ወ​ጣ​ች​ሁኝ እና​ንተ አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን? አሁን በተ​ጨ​ነ​ቃ​ችሁ ጊዜ ለምን ወደ እኔ መጣ​ችሁ?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">የገ​ለ​ዓ​ድም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ዮፍ​ታ​ሔን፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ ከእኛ ጋር እን​ድ​ት​ወጣ፥ ከአ​ሞ​ንም ልጆች ጋር እን​ድ​ቷጋ፥ ስለ​ዚህ አሁን ወደ አንተ ተመ​ል​ሰን መጣን፤ በገ​ለ​ዓ​ድም ሰዎች ሁሉ ላይ አለ​ቃ​ችን ትሆ​ና​ለህ” አሉት።</verse>
				<verse number="9">ዮፍ​ታ​ሔም የገ​ለ​ዓ​ድን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ “ከአ​ሞን ልጆች ጋር ለመ​ዋ​ጋት ብት​ወ​ስ​ዱኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእጄ አሳ​ልፎ ቢሰ​ጣ​ቸው፥ እኔ አለ​ቃ​ችሁ እሆ​ና​ለ​ሁን?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">የገ​ለ​ዓ​ድም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ዮፍ​ታ​ሔን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችን ምስ​ክር ይሁን፤ በር​ግጥ እንደ ቃልህ እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አሉት።</verse>
				<verse number="11">ዮፍ​ታ​ሔም ከገ​ለ​ዓድ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጋር ሄደ፤ ሕዝ​ቡም መስ​ፍን ይሆ​ና​ቸው ዘንድ በላ​ያ​ቸው አለቃ አድ​ር​ገው ሾሙት፤ ዮፍ​ታ​ሔም ቃሉን ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመ​ሴፋ ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="12">ዮፍ​ታ​ሔም ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ፥ “ሀገ​ሬን ለመ​ው​ጋት ወደ እኔ የም​ት​መጣ አንተ ከእኔ ጋር ምን አለህ?” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ።</verse>
				<verse number="13">የአ​ሞ​ንም ልጆች ንጉሥ የዮ​ፍ​ታ​ሔን መል​እ​ክ​ተ​ኞች፥ “እስ​ራ​ኤል ከግ​ብፅ በወጣ ጊዜ ከአ​ር​ኖን ጀምሮ እስከ ያቦ​ቅና እስከ ዮር​ዳ​ኖስ ድረስ ምድ​ሬን ስለ ወሰደ ነው፤ አሁ​ንም በሰ​ላም መል​ሱ​ልኝ” ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">ዮፍ​ታ​ሔም የላ​ካ​ቸው ወደ ዮፍ​ታሔ ተመ​ለሱ፤ ዮፍ​ታ​ሔም ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን እንደ ገና ላከ፤ እን​ዲ​ህም አለው፦</verse>
				<verse number="15">ዮፍ​ታሔ እን​ዲህ ይላል፥ “እስ​ራ​ኤል ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ የሞ​ዓ​ብን ምድር፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች ምድር አል​ወ​ሰ​ዱም፤</verse>
				<verse number="16">ነገር ግን እስ​ራ​ኤል በም​ድረ በዳ እስከ ኤር​ትራ ባሕር ሄዱ፤ ወደ ቃዴ​ስም ደረሱ፤</verse>
				<verse number="17">እስ​ራ​ኤል ወደ ኤዶ​ም​ያስ ንጉሥ፦ ‘በም​ድ​ርህ እን​ዳ​ልፍ፥ እባ​ክህ፥ ፍቀ​ድ​ልኝ’ ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ እንቢ አለ። እን​ዲ​ሁም ወደ ሞዓብ ንጉሥ ላከ፤ እር​ሱም እንቢ አለ።</verse>
				<verse number="18">እስ​ራ​ኤ​ልም በቃ​ዴስ ተቀ​መጠ። በም​ድረ በዳም በኩል አለፈ፤ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስ​ንና የሞ​ዓ​ብ​ንም ምድር ዞሩ፤ ከሞ​ዓብ ምድ​ርም በም​ሥ​ራቅ በኩል መጡ፤ በአ​ር​ኖ​ንም ማዶ ሰፈሩ፤ አር​ኖ​ንም የሞ​ዓብ ድን​በር ነበ​ረና ወደ ሞዓብ ድን​በር አል​ገ​ቡም።</verse>
				<verse number="19">እስ​ራ​ኤ​ልም ወደ አሞ​ራ​ዊው ወደ ሐሴ​ቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም፦ ‘በም​ድ​ርህ በኩል ወደ ስፍ​ራ​ችን፥ እባ​ክህ፥ አሳ​ል​ፈን’ አለው።</verse>
				<verse number="20">ሴዎ​ንም እስ​ራ​ኤል በድ​ን​በሩ እን​ዲ​ያ​ልፍ እንቢ አለ፤ ነገር ግን ሴዎን ሕዝ​ቡን ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ በኢ​ያ​ሴ​ርም ሰፈረ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጋር ተዋጋ።</verse>
				<verse number="21">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሴዎ​ን​ንና ሕዝ​ቡን ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጠ፤ ገደ​ሉ​አ​ቸ​ውም፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በዚያ ምድር ተቀ​ም​ጠው የነ​በ​ሩ​ትን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ምድር ሁሉ ወረሱ።</verse>
				<verse number="22">ከአ​ር​ኖ​ንም እስከ ያቦቅ ድረስ፥ ከም​ድረ በዳ​ውም እስከ ዮር​ዳ​ኖስ ድረስ የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አው​ራጃ ሁሉ ወረሱ።</verse>
				<verse number="23">አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሕ​ዝቡ ከእ​ስ​ራ​ኤል ፊት አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አስ​ወ​ገደ፤ አን​ተም በተ​ራህ ትወ​ር​ሳ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="24">አም​ላ​ክህ ኮሞስ የሚ​ሰ​ጥ​ህን የም​ት​ወ​ርስ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? እኛም አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊ​ታ​ችን ያስ​ወ​ጣ​ቸ​ውን የእ​ነ​ር​ሱን ምድር የም​ን​ወ​ርስ አይ​ደ​ለ​ን​ምን?</verse>
				<verse number="25">ወይስ ዛሬ ከሞ​ዓብ ንጉሥ ከሴ​ፎር ልጅ ከባ​ላቅ አንተ ትሻ​ላ​ለ​ህን? ወይስ እርሱ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ተጣ​ላን? ወይስ ተዋ​ጋ​ውን?</verse>
				<verse number="26">እስ​ራ​ኤ​ልም በሐ​ሴ​ቦ​ንና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በአ​ሮ​ዔ​ርና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በአ​ር​ኖ​ንም አቅ​ራ​ቢያ ባሉት ከተ​ሞች ሁሉ ሦስት መቶ ዓመት ተቀ​ምጦ በነ​በረ ጊዜ፥ በዚያ ዘመን ስለ ምን አላ​ዳ​ን​ሃ​ቸ​ውም ነበር?</verse>
				<verse number="27">እኔ አል​በ​ደ​ል​ሁ​ህም፤ አንተ ግን ከእኔ ጋር ትዋጋ ዘንድ ክፉ አታ​ድ​ር​ግ​ብኝ፤ ፈራጁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና በአ​ሞን ልጆች መካ​ከል ዛሬ ይፍ​ረድ።”</verse>
				<verse number="28">ነገር ግን ዮፍ​ታሔ የላ​ከ​በ​ትን ቃል የአ​ሞን ልጆች ንጉሥ አል​ሰ​ማም፤ እን​ቢም አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="29">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በዮ​ፍ​ታሔ ላይ መጣ፤ እር​ሱም የም​ናሴ ዕጣ ከም​ት​ሆን ከገ​ለ​ዓድ ምድ​ርና ከገ​ለ​ዓድ መሴፋ፥ ወደ አሞን ልጆች ማዶ ተሻ​ገረ።</verse>
				<verse number="30">ዮፍ​ታ​ሔም፥ “በእ​ው​ነት የአ​ሞ​ንን ልጆች በእጄ አሳ​ል​ፈህ ብት​ሰ​ጠኝ፥</verse>
				<verse number="31">ከአ​ሞን ልጆች ዘንድ በደ​ኅና በተ​መ​ለ​ስሁ ጊዜ፥ ከቤቴ ደጅ ወጥቶ የሚ​ቀ​በ​ለ​ኝን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ” ብሎ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለት ተሳለ።</verse>
				<verse number="32">ዮፍ​ታ​ሔም ሊዋ​ጋ​ቸው ወደ አሞን ልጆች ተሻ​ገረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእጁ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="33">ከአ​ሮ​ዔ​ርም እስከ ሚኒ​ትና እስከ አቤ​ል​ክ​ራ​ሚም ድረስ ሃያ ከተ​ሞ​ችን በታ​ላቅ ሰልፍ አጠ​ፋ​ቸው። የአ​ሞ​ንም ልጆች በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ተዋ​ረዱ።</verse>
				<verse number="34">ዮፍ​ታ​ሔም ወደ መሴፋ ወደ ቤቱ ተመ​ለሰ፤ እነ​ሆም፥ ልጁ ከበሮ ይዛ እየ​ዘ​ፈ​ነች ልት​ቀ​በ​ለው ወጣች፤ ለእ​ር​ሱም የሚ​ወ​ድ​ዳት አን​ዲት ብቻ ነበ​ረች። ከእ​ር​ስ​ዋም በቀር ወንድ ወይም ሴት ሌላ ልጅ አል​ነ​በ​ረ​ውም።</verse>
				<verse number="35">እር​ስ​ዋ​ንም ባየ ጊዜ ልብ​ሱን ቀድዶ፥ “ወዮ​ልኝ ልጄ ሆይ! ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፌን ከፍ​ቻ​ለ​ሁና፥ ከዚ​ያ​ውም እመ​ለስ ዘንድ አል​ች​ል​ምና አሰ​ና​ከ​ል​ሽኝ፤ አስ​ጨ​ነ​ቅ​ሽ​ኝም” አላት።</verse>
				<verse number="36">እር​ስ​ዋም፥ “አባቴ ሆይ፥ አፍ​ህን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከከ​ፈ​ትህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጠ​ላ​ቶ​ችህ በአ​ሞን ልጆች ላይ ተበ​ቅ​ሎ​ል​ሃ​ልና በአ​ፍህ እንደ ተና​ገ​ርህ አድ​ር​ግ​ብኝ” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="37">አባ​ቷ​ንም፥ “ይህ ነገር ይደ​ረ​ግ​ልኝ፤ ከዚህ ሄጄ በተ​ራ​ሮች ላይ እን​ድ​ወ​ጣና እን​ድ​ወ​ርድ፥ ከባ​ል​ን​ጀ​ሮቼም ጋር ለድ​ን​ግ​ል​ናዬ እን​ዳ​ለ​ቅስ ሁለት ወር አሰ​ና​ብ​ተኝ” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="38">እር​ሱም፥ “ሂጂ” አለ። ሁለት ወርም አሰ​ና​በ​ታት፤ ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ች​ዋም ጋር ሄደች፤ በተ​ራ​ሮ​ችም ላይ ለድ​ን​ግ​ል​ናዋ አለ​ቀ​ሰች።</verse>
				<verse number="39">ሁለት ወርም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ ወደ አባቷ ተመ​ለ​ሰች፤ ዮፍ​ታ​ሔም የተ​ሳ​ለ​ውን ስእ​ለት አደ​ረገ፤ እር​ስ​ዋም ወንድ አላ​ወ​ቀ​ችም ነበር።</verse>
				<verse number="40">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሴቶች ልጆች ለገ​ለ​ዓ​ዳ​ዊዉ ለዮ​ፍ​ታሔ ልጅ በዓ​መት አራት ቀን ያለ​ቅ​ሱ​ላት ዘንድ በዓ​መት በዓ​መት ይሄዱ ነበር። ይህ​ችም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ሥር​ዐት ሆነች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">የኤ​ፍ​ሬ​ምም ሰዎች ተሰ​በ​ሰቡ፤ ወደ ጻፎ​ንም ተሻ​ግ​ረው ዮፍ​ታ​ሔን፥ “ከአ​ሞን ልጆች ጋር ለመ​ዋ​ጋት ስታ​ልፍ ከአ​ንተ ጋር እን​ድ​ን​ሄድ ስለ​ምን አል​ጠ​ራ​ኸ​ንም? ቤት​ህን በአ​ንተ ላይ በእ​ሳት እና​ቃ​ጥ​ለ​ዋ​ለን” አሉት።</verse>
				<verse number="2">ዮፍ​ታ​ሔም፥ “እኔና ሕዝቤ የተ​ገ​ፋን ነን፤ የአ​ሞን ልጆ​ችም በጽ​ኑዕ አሠ​ቃ​ዩን፤ በጠ​ራ​ና​ች​ሁም ጊዜ ከእ​ጃ​ቸው አላ​ዳ​ና​ች​ሁ​ንም።</verse>
				<verse number="3">የሚ​ያ​ድን እን​ደ​ሌ​ለም ባየሁ ጊዜ ሰው​ነ​ቴን በእጄ አሳ​ልፌ ለሞት በመ​ስ​ጠት ወደ አሞን ልጆች ተሻ​ገ​ርሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፊቴ ጣላ​ቸው፤ ለም​ንስ ዛሬ ልት​ወ​ጉኝ ወደ እኔ መጣ​ችሁ?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ዮፍ​ታ​ሔም የገ​ለ​ዓ​ድን ሰዎች ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ ከኤ​ፍ​ሬ​ምም ጋር ተዋጋ፤ ኤፍ​ሬ​ምም፥ “ገለ​ዓ​ዳ​ው​ያን ሆይ! እና​ንተ በኤ​ፍ​ሬ​ምና በም​ናሴ መካ​ከል የተ​ቀ​መ​ጣ​ችሁ ከኤ​ፍ​ሬም ሸሽ​ታ​ችሁ ነው” ስላሉ የገ​ለ​ዓድ ሰዎች ኤፍ​ሬ​ምን መቱ።</verse>
				<verse number="5">የገ​ለ​ዓድ ሰዎ​ችም ኤፍ​ሬም በሚ​ያ​ል​ፍ​በት በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ደረ​ሱ​ባ​ቸው። ከዚህ በኋላ ከኤ​ፍ​ሬም ያመ​ለ​ጡት እን​ሻ​ገር ባሉ ጊዜ የገ​ለ​ዓድ ሰዎች፥ “በውኑ እና​ንተ ከኤ​ፍ​ሬም ወገን ናች​ሁን?” ቢሉ​አ​ቸው “አይ​ደ​ለ​ንም” አሉ።</verse>
				<verse number="6">እነ​ር​ሱም፥ “አሁን ሺቦ​ሌት በሉ” አሉ​አ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም አጥ​ር​ተው መና​ገር አል​ቻ​ሉ​ምና፥ “ሲቦ​ሌት” አሉ፤ ይዘ​ውም በዮ​ር​ዳ​ኖስ መሸ​ጋ​ገ​ርያ አረ​ዱ​አ​ቸው፤ በዚ​ያም ጊዜ ከኤ​ፍ​ሬም አርባ ሁለት ሺህ ሰዎች ወደቁ።</verse>
				<verse number="7">ዮፍ​ታ​ሔም እስ​ራ​ኤ​ልን ስድ​ስት ዓመት ገዛ። ገለ​ዓ​ዳ​ዊው ዮፍ​ታ​ሔም ሞተ፤ በሀ​ገሩ በገ​ለ​ዓ​ድም ተቀ​በረ።</verse>
				<verse number="8">ከእ​ር​ሱም በኋላ የቤተ ልሔሙ ሐሴ​ቦን እስ​ራ​ኤ​ልን ገዛ።</verse>
				<verse number="9">ሠላሳ ወን​ዶች ልጆ​ችና ሠላሳ ሴቶች ልጆ​ች​ንም ወለደ፤ ሠላሳ ሴቶች ልጆ​ቹ​ንም ወደ ውጭ ሀገር ዳረ፤ ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቹም ከውጭ ሀገር ሠላሳ ሴቶች ልጆ​ችን አመጣ። እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሰባት ዓመት ገዛ።</verse>
				<verse number="10">ሐሴ​ቦ​ንም ሞተ፤ በቤተ ልሔ​ምም ተቀ​በረ።</verse>
				<verse number="11">ከእ​ር​ሱም በኋላ ዛብ​ሎ​ና​ዊው ኤሎን እስ​ራ​ኤ​ልን ዐሥር ዓመት ገዛ።</verse>
				<verse number="12">ዛብ​ሎ​ና​ዊው ኤሎ​ንም ሞተ፤ በዛ​ብ​ሎ​ንም ምድር በኤ​ሎም ተቀ​በረ።</verse>
				<verse number="13">ከእ​ር​ሱም በኋላ የኤ​ፍ​ራ​ታ​ዊው የኤ​ሎን ልጅ ለቦን እስ​ራ​ኤ​ልን ገዛ።</verse>
				<verse number="14">አር​ባም ልጆች፥ ሠላ​ሳም የልጅ ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ በሰ​ባም የአ​ህያ ግል​ገ​ሎች ላይ ይቀ​መጡ ነበር። እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ስም​ንት ዓመት ገዛ።</verse>
				<verse number="15">የኤ​ፍ​ራ​ታ​ዊው የኤ​ሎን ልጅ ለቦ​ንም ሞተ፤ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን ምድር በኤ​ፍ​ሬም ባለ​ችው በኤ​ፍ​ራታ ተቀ​በረ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ አርባ ዓመት አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">ከዳን ወገን የሆነ ማኑሄ የሚ​ባል አንድ የሶ​ራሕ ሰው ነበረ፤ ሚስ​ቱም መካን ነበ​ረች፤ ልጅም አል​ወ​ለ​ደ​ችም ነበር።</verse>
				<verse number="3">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ለሴ​ቲቱ ተገ​ልጦ እን​ዲህ አላት፥ “እነሆ፥ አንቺ መካን ነሽ፤ ልጅም አል​ወ​ለ​ድ​ሽም፤ ነገር ግን ትፀ​ን​ሻ​ለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወ​ል​ጃ​ለሽ።</verse>
				<verse number="4">አሁ​ንም ተጠ​ን​ቀቂ፤ የወ​ይን ጠጅ​ንና የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥ​ንም አት​ጠጪ፤ ርኩ​ስም ነገር አት​ብዪ።</verse>
				<verse number="5">እነሆ፥ ትፀ​ን​ሻ​ለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ ልጁም ከእ​ናቱ ማኅ​ፀን ጀምሮ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለየ ናዝ​ራዊ ይሆ​ና​ልና በራሱ ላይ ምላጭ አይ​ድ​ረ​ስ​በት፤ እር​ሱም እስ​ራ​ኤ​ልን ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ማዳን ይጀ​ም​ራል።”</verse>
				<verse number="6">ሴቲ​ቱም ወደ ባልዋ መጥታ፥ “አንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፤ መል​ኩም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ እጅግ የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግጥ ነበረ፤ ከወ​ዴ​ትም እንደ መጣ ጠየ​ቅ​ሁት፥ እር​ሱም ስሙን አል​ነ​ገ​ረ​ኝም።</verse>
				<verse number="7">እር​ሱም፦ እነሆ፥ ትፀ​ን​ሻ​ለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ እን​ግ​ዲህ የወ​ይን ጠጅ​ንና የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥን አት​ጠጪ፥ ርኩስ ነገ​ር​ንም አት​ብዪ፤ ልጁ ከእ​ናቱ ማኅ​ፀን ጀምሮ እስ​ኪ​ሞት ድረስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለየ ናዝ​ራዊ ይሆ​ና​ልና አለኝ” ብላ ተና​ገ​ረች።</verse>
				<verse number="8">ማኑ​ሄም፥ “ጌታ ሆይ፥ ወደ እኛ የላ​ክ​ኸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው፥ እባ​ክህ እን​ደ​ገና ወደ እኛ ይምጣ፤ ለሚ​ወ​ለ​ደ​ውም ልጅ ምን እን​ደ​ም​ና​ደ​ርግ ያስ​ገ​ን​ዝ​በን” ብሎ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመነ።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የማ​ኑ​ሄን ቃል ሰማ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ እንደ ገና በእ​ርሻ ውስጥ ተቀ​ምጣ ሳለች ወደ ሴቲቱ መጣ፤ ባልዋ ማኑሄ ግን ከእ​ር​ስዋ ጋር አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="10">ሴቲ​ቱም ፈጥና ሮጠች ለባ​ል​ዋም፥ “እነሆ፥ አስ​ቀ​ድሞ ወደ እኔ የመ​ጣው ያ ሰው ደግሞ ተገ​ለ​ጠ​ልኝ” ብላ ነገ​ረ​ችው።</verse>
				<verse number="11">ማኑ​ሄም ተነ​ሥቶ ሚስ​ቱን ተከ​ተለ፤ ወደ ሰው​ዬ​ዉም መጥቶ፥ “ከሚ​ስቴ ጋር የተ​ነ​ጋ​ገ​ርህ አንተ ነህን?” አለው። መል​አ​ኩም፥ “እኔ ነኝ” አለ።</verse>
				<verse number="12">ማኑ​ሄም፥ “እነሆ፥ ቃልህ በደ​ረሰ ጊዜ የልጁ ነገሩ፥ ግብ​ሩስ ምን​ድን ነው?” አለው።</verse>
				<verse number="13">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ማኑ​ሄን፥ “ለሚ​ስ​ትህ ከነ​ገ​ር​ኋት ሁሉ ተጠ​በቁ።</verse>
				<verse number="14">ከወ​ይ​ንም ከሚ​ወ​ጣው ሁሉ አት​ብላ፤ የወ​ይን ጠጅ​ንና የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥ​ንም አት​ጠጣ፤ ርኩ​ስ​ንም ነገር ሁሉ አት​ብላ፤ ያዘ​ዝ​ኋ​ትን ሁሉ ጠብቁ” አለው።</verse>
				<verse number="15">ማኑ​ሄም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ፥ “የፍ​የል ጠቦት እና​ዘ​ጋ​ጅ​ልህ ዘንድ ግድ እን​ል​ሃ​ለን” አለው።</verse>
				<verse number="16">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ማኑ​ሄን፥ “አንተ የግድ ብት​ለኝ እህ​ል​ህን አል​በ​ላም፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ብታ​ደ​ርግ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ር​በው” አለው። ማኑ​ሄም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ መሆ​ኑን አላ​ወ​ቀም ነበር።</verse>
				<verse number="17">ማኑ​ሄም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ፥ “ነገ​ርህ በደ​ረሰ ጊዜ እን​ድ​ና​ከ​ብ​ርህ ስምህ ማን ነው” አለው።</verse>
				<verse number="18">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠ​ይ​ቃ​ለህ?” አለው።</verse>
				<verse number="19">ማኑ​ሄም የፍ​የ​ሉን ጠቦ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን ወስዶ በድ​ን​ጋይ ላይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቀ​ረ​በው። መል​አ​ኩም ተአ​ም​ራት አደ​ረገ፤ ማኑ​ሄና ሚስ​ቱም ይመ​ለ​ከቱ ነበር።</verse>
				<verse number="20">ነበ​ል​ባ​ሉም ከመ​ሠ​ዊ​ያዉ ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ በመ​ሠ​ዊ​ያዉ ነበ​ል​ባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ማኑ​ሄና ሚስ​ቱም ተመ​ለ​ከቱ፤ በም​ድ​ርም በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወደቁ።</verse>
				<verse number="21">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ዳግ​መኛ ለማ​ኑ​ሄና ለሚ​ስቱ አል​ተ​ገ​ለ​ጠም፤ ያን ጊዜም ማኑሄ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ መሆ​ኑን ዐወቀ።</verse>
				<verse number="22">ማኑ​ሄም ሚስ​ቱን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አይ​ተ​ና​ልና ሞትን እን​ሞ​ታ​ለን” አላት።</verse>
				<verse number="23">ሚስ​ቱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ሊገ​ድ​ለን ቢወ​ድድ ኖሮ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን ከእ​ጃ​ችን ባል​ተ​ቀ​በ​ለን፥ ይህ​ንም ነገር ሁሉ ባላ​ሳ​የን፥ እን​ዲህ ያለ ነገ​ርም በዚህ ጊዜ ባላ​ሰ​ማን ነበር” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="24">ሴቲ​ቱም ወንድ ልጅ ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ሶም​ሶን ብላ ጠራ​ችው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባረ​ከው፤ ልጁም አደገ።</verse>
				<verse number="25">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በሶ​ራ​ሕና በእ​ስ​ታ​ሔል መካ​ከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ከእ​ርሱ ጋር ይሄድ ጀመረ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">ሶም​ሶ​ንም ወደ ቴም​ናታ ወረደ፤ በቴ​ም​ና​ታም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ልጆች አን​ዲት ሴት አየ፤ እር​ስ​ዋም በፊቱ ደስ አለ​ችው።</verse>
				<verse number="2">ወጥ​ቶም ለአ​ባ​ቱና ለእ​ናቱ፥ “በቴ​ም​ናታ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ልጆች አን​ዲት ሴት አይ​ቻ​ለሁ፤ አሁ​ንም እር​ስ​ዋን አጋ​ቡኝ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">አባ​ቱና እና​ቱም፥ “ካል​ተ​ገ​ረ​ዙት ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሚስት ለማ​ግ​ባት ትሄድ ዘንድ ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ ሴቶች ልጆች፥ ከሕ​ዝ​ቤም ሁሉ መካ​ከል ሴት የለ​ች​ምን?” አሉት። ሶም​ሶ​ንም አባ​ቱን፥ “ለዐ​ይኔ እጅግ ደስ አሰ​ኝ​ታ​ኛ​ለ​ችና እር​ስ​ዋን አጋ​ባኝ” አለው።</verse>
				<verse number="4">አባ​ቱና እና​ቱም ነገሩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነ አላ​ወ​ቁም፤ እርሱ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን በቀ​ልን ይመ​ልስ ዘንድ ይፈ​ልግ ነበ​ርና። በዚ​ያም ወራት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እስ​ራ​ኤ​ልን ይገዙ ነበር።</verse>
				<verse number="5">ሶም​ሶ​ንም፥ አባ​ቱና እና​ቱም ወደ ቴም​ናታ ወረዱ፤ በቴ​ም​ና​ታም ወዳ​ለው ወደ ወይኑ ስፍራ ፈቀቅ አለ፤ እነ​ሆም፥ የአ​ን​በሳ ደቦል እያ​ገሣ መጣ​በት።</verse>
				<verse number="6">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ አደረ፤ የፍ​የል ጠቦ​ትን እን​ደ​ሚ​ጥ​ልም ጣለው፤ በእ​ጁም እንደ ኢም​ንት ሆነ፤ ያደ​ረ​ገ​ው​ንም ለአ​ባ​ቱና ለእ​ናቱ አል​ተ​ና​ገ​ረም።</verse>
				<verse number="7">ሂደ​ውም ከሴ​ቲቱ ጋር ተነ​ጋ​ገሩ፤ ሶም​ሶ​ን​ንም በፊቱ ደስ አሰ​ኘ​ችው።</verse>
				<verse number="8">ከጥ​ቂት ቀኖ​ችም በኋላ ሊያ​ገ​ባት ተመ​ለሰ፤ የአ​ን​በ​ሳ​ው​ንም ሬሳ ያይ ዘንድ ከመ​ን​ገድ ፈቀቅ አለ፤ እነ​ሆም፥ በአ​ን​በ​ሳው አፍ ውስጥ ንብ ሰፍ​ሮ​በት ነበር፤ ማርም ነበ​ረ​በት።</verse>
				<verse number="9">ወስ​ዶም በላ፤ እየ​በ​ላም ሄደ፤ ወደ አባ​ቱና ወደ እና​ቱም ደረሰ፤ ሰጣ​ቸ​ውም፤ እነ​ር​ሱም በሉ፤ ማሩ​ንም ከአ​ን​በ​ሳው አፍ ውስጥ እን​ዳ​ወ​ጣው አል​ነ​ገ​ራ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="10">አባ​ቱም ወደ ሴቲቱ ወረደ፤ ጐበ​ዞ​ችም እን​ዲሁ ያደ​ርጉ ነበ​ርና ሶም​ሶን በዚያ ሰባት ቀን በዓል አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="11">ከዚ​ህም በኋላ ፈር​ተው ሠላሳ ሰዎ​ችን በእ​ርሱ ላይ ሾሙ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="12">ሶም​ሶ​ንም አላ​ቸው፥ “እን​ቆ​ቅ​ልሽ ልስ​ጣ​ችሁ፤ በሰ​ባ​ቱም በበ​ዓሉ ቀኖች ውስጥ ፈት​ታ​ችሁ ብት​ነ​ግ​ሩኝ፥ ሠላሳ የበ​ፍታ ቀሚ​ስና ሠላሳ ልውጥ ልብስ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="13">መፍ​ታት ባት​ችሉ ግን እና​ንተ ለእኔ ሠላሳ የበ​ፍታ ቀሚ​ስና ሠላሳ ልውጥ ልብስ ትሰ​ጡ​ኛ​ላ​ችሁ።” እነ​ር​ሱም፥ “ምሳ​ሌ​ህን መስ​ልና እን​ስ​ማህ” አሉት።</verse>
				<verse number="14">እር​ሱም፥ “ከበ​ላ​ተኛ መብል ወጣ፤ ከብ​ር​ቱም ጣፋጭ ወጣ” አላ​ቸው። እስከ ሦስት ቀንም እን​ቆ​ቅ​ል​ሹን መፍ​ታት አል​ቻ​ሉም።</verse>
				<verse number="15">ከዚህ በኋላ በአ​ራ​ተ​ኛው ቀን የሶ​ም​ሶ​ንን ሚስት፥ “እን​ቆ​ቅ​ል​ሹን እን​ዲ​ነ​ግ​ርሽ ባል​ሽን አባ​ብ​ይው፤ አለ​ዚ​ያም አን​ቺ​ንና የአ​ባ​ት​ሽን ቤት በእ​ሳት እና​ቃ​ጥ​ላ​ለን፤ ወይስ ወደ​ዚህ የጠ​ራ​ች​ሁን ልታ​ደ​ኸ​ዩን ነውን?” አሉ​አት።</verse>
				<verse number="16">የሶ​ም​ሶ​ንም ሚስት በፊቱ እያ​ለ​ቀ​ሰ​ች​በት፥ “ጠል​ተ​ኸ​ኛል፤ ከቶም አት​ወ​ድ​ደ​ኝም፤ ለሕ​ዝቤ ልጆች የነ​ገ​ር​ኸ​ውን እን​ቆ​ቅ​ል​ሽ​ህን አል​ነ​ገ​ር​ኸ​ኝ​ምና” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “እነሆ፥ ለአ​ባ​ቴና ለእ​ናቴ አል​ነ​ገ​ር​ኋ​ቸ​ውም፤ ለአ​ንቺ እነ​ግ​ር​ሻ​ለ​ሁን?” አላት።</verse>
				<verse number="17">ሰባ​ቱ​ንም የበ​ዓል ቀን አለ​ቀ​ሰ​ች​በት፤ እር​ስ​ዋም ነዝ​ን​ዛ​ዋ​ለ​ችና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ነገ​ራት። ለሕ​ዝ​ብ​ዋም ልጆች ነገ​ረ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">በሰ​ባ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ቀን ፀሐይ ሳት​ገባ የከ​ተ​ማ​ዪቱ ሰዎች፥ “ከማር የሚ​ጣ​ፍጥ ምን​ድን ነው? ከአ​ን​በ​ሳስ የሚ​በ​ረታ ማን ነው?” አሉት። ሶም​ሶ​ንም፥ “በጥ​ጃዬ ባላ​ረ​ሳ​ችሁ ኑሮ የእ​ን​ቆ​ቅ​ል​ሼን ትር​ጓሜ ባላ​ወ​ቃ​ች​ሁም ነበር” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በላዩ ወረደ፤ ወደ አስ​ቀ​ሎ​ናም ወረደ፤ ከዚ​ያም ሠላሳ ሰዎ​ችን ገደለ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ገፍፎ እን​ቆ​ቅ​ል​ሹን ለነ​ገ​ሩት ሰዎች ሰጠ። ሶም​ሶ​ንም ተቈጣ፤ ወደ አባ​ቱም ቤት ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="20">የሶ​ም​ሶ​ንም ሚስት ከስር ሚዜው ጋር ተቀ​መ​ጠች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">ከጊ​ዜም በኋላ በስ​ንዴ መከር ጊዜ ሶም​ሶን የፍ​የል ጠቦት ይዞ ሚስ​ቱን ሊጠ​ይቅ ሄደና፥ “ወደ ጫጕላ ቤት ወደ ሚስቴ ልግባ” አለ፤ አባቷ ግን እን​ዳ​ይ​ገባ ከለ​ከ​ለው።</verse>
				<verse number="2">አባ​ቷም፥ “ፈጽ​መህ ጠላ​ህ​ዋት ያልህ መስ​ሎኝ ለሚ​ዜህ አጋ​ባ​ኋት፤ ታናሽ እኅቷ ከእ​ር​ስዋ ይልቅ የተ​ዋ​በች አይ​ደ​ለ​ች​ምን? እባ​ክህ በእ​ር​ስዋ ፋንታ አግ​ባት” አለው።</verse>
				<verse number="3">ሶም​ሶ​ንም፥ “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ላይ ክፉ ባደ​ርግ እኔ ንጹሕ ነኝ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ሶም​ሶ​ንም ሄዶ ሦስት መቶ ቀበ​ሮ​ችን ያዘ፤ ችቦም ወስዶ ሁለት ሁለ​ቱን ቀበ​ሮ​ዎች በጅ​ራ​ታ​ቸው አሰረ፤ በሁ​ለ​ቱም ጅራ​ቶች መካ​ከል አንድ ችቦ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="5">ችቦ​ው​ንም አን​ድዶ በቆ​መው በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እህል መካ​ከል ሰደ​ዳ​ቸው፤ ነዶ​ው​ንም፥ ክም​ሩ​ንም፥ የቆ​መ​ዉ​ንም እህል፥ ወይ​ኑ​ንም፥ ወይ​ራ​ዉ​ንም አቃ​ጠለ።</verse>
				<verse number="6">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥ “ይህን ያደ​ረገ ማን ነው?” አሉ። እነ​ር​ሱም፥ “ሚስ​ቱን ወስዶ ለሚ​ዜው አጋ​ብ​ቶ​በ​ታ​ልና የቴ​ም​ና​ታ​ዊዉ አማች ሶም​ሶን ነው” አሉ​አ​ቸው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ወጥ​ተው የአ​ባ​ቷን ቤትና እር​ስ​ዋን አባ​ቷ​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠሉ።</verse>
				<verse number="7">ሶም​ሶ​ንም አላ​ቸው- “ይህን ብታ​ደ​ር​ጉም ደስ አይ​ለ​ኝም፤ በቀሌ ከአ​ንድ ሰው ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ሁላ​ች​ሁ​ንም እበ​ቀ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ አር​ፋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="8">ሶም​ሶ​ንም ጭን ጭና​ቸ​ውን ብሎ በታ​ላቅ አገ​ዳ​ደል መታ​ቸው፤ ወር​ዶም ኢጣም በም​ት​ባል ዋሻ በወ​ንዝ ዳር ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="9">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ወጡ፤ በይ​ሁ​ዳም ሰፈሩ፤ የአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ንት በተ​ባለ ቦታም ተበ​ታ​ት​ነው ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="10">የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ሁሉ፥ “በእኛ ላይ የወ​ጣ​ች​ሁት ለም​ን​ድን ነው?” አሉ። እነ​ር​ሱም፥ “ሶም​ሶ​ንን ልና​ስር፥ እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ብ​ንም ልና​ደ​ር​ግ​በት መጥ​ተ​ናል” አሏ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ከይ​ሁ​ዳም ሰዎች ሦስት ሺህ የሚ​ያ​ህሉ በኢ​ጣም ዓለት ወዳ​ለው ዋሻ ወር​ደው ሶም​ሶ​ንን፥ “ገዢ​ዎ​ቻ​ችን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እን​ደ​ሆኑ አታ​ው​ቅ​ምን? ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ይህ ምን​ድን ነው?” አሉት። ሶም​ሶ​ንም፥ “እን​ዳ​ደ​ረ​ጉ​ባ​ችሁ እን​ዲሁ አደ​ረ​ግ​ሁ​ባ​ቸው” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">እነ​ር​ሱም፥ “አስ​ረን በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ አሳ​ል​ፈን ልን​ሰ​ጥህ መጥ​ተ​ናል” አሉት። ሶም​ሶ​ንም፥ “እና​ንተ እን​ዳ​ት​ገ​ድ​ሉኝ ማሉ​ልኝ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም አሳ​ል​ፋ​ችሁ ስጡኝ፤ እና​ንተ ግን ከእኔ ጋር አትዋጉ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">እነ​ር​ሱም፥ “በገ​መድ አስ​ረን በእ​ጃ​ቸው አሳ​ል​ፈን እን​ሰ​ጥ​ሃ​ለን እንጂ አን​ገ​ድ​ል​ህም” ብለው ማሉ​ለት። በሁ​ለ​ትም አዲስ ገመድ አስ​ረው ከዓ​ለቱ ውስጥ አወ​ጡት።</verse>
				<verse number="14">የአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ንት ወደ ተባለ ቦታም ደረሰ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ደን​ፍ​ተው ተቀ​በ​ሉት፤ ወደ እር​ሱም ሮጡ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ አደረ፤ በክ​ን​ዱም ያሉ እነ​ዚያ ገመ​ዶች በእ​ሳት ላይ እንደ ተጣለ ገለባ ሆኑ፤ ማሰ​ሪ​ያ​ውም ከክ​ንዱ ተፈታ፤</verse>
				<verse number="15">የወ​ደቀ የአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ን​ት​ንም በመ​ን​ገድ አገኘ። እጁ​ንም ዘር​ግቶ ወሰ​ደው፤ በእ​ር​ሱም አንድ ሺህ ሰው ገደለ።</verse>
				<verse number="16">ሶም​ሶ​ንም፥ “በአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ንት ክምር በክ​ምር ላይ አድ​ር​ጌ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ንት አንድ ሺህ ሰው ገድ​ያ​ለ​ሁና” አለ።</verse>
				<verse number="17">መና​ገ​ሩ​ንም በፈ​ጸመ ጊዜ መን​ጋ​ጋ​ውን ከእጁ ጣለ፤ የዚ​ያ​ንም ስፍራ ስም “ቀትለ አጽመ መን​ሰክ” ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="18">እር​ሱም እጅግ ተጠ​ምቶ ነበ​ርና፥ “አንተ ይህ​ችን ታላቅ ማዳን በባ​ሪ​ያህ እጅ ሰጥ​ተ​ሃል፤ አሁ​ንም በጥም እሞ​ታ​ለሁ፤ ባል​ተ​ገ​ረ​ዙ​ትም እጅ እወ​ድ​ቃ​ለሁ” ብሎ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የዚ​ያ​ችን የአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ንት ስን​ጥ​ቃት ከፈተ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ውኃ ወጣ፤ እር​ሱም ጠጣ፤ ነፍ​ሱም ተመ​ለ​ሰች፤ ከውኃ ጥሙም ዐረፈ። ስለ​ዚ​ህም የዚያ ቦታ ስም እስከ ዛሬ ድረስ “ነቅዐ አጽመ መን​ሰክ” ተብሎ ተጠራ።</verse>
				<verse number="20">በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ዘመን እስ​ራ​ኤ​ልን ሃያ ዓመት ገዛ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">ሶም​ሶ​ንም ወደ ጋዛ ሄደ፥ በዚ​ያም ጋለ​ሞታ ሴት አይቶ ወደ እር​ስዋ ገባ።</verse>
				<verse number="2">ለጋዛ ሰዎ​ችም፥ “ሶም​ሶን ወደ​ዚህ መጥ​ቶ​አል” ብለው ነገ​ሩ​አ​ቸው፤ ከበ​ቡ​ትም። ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ በከ​ተ​ማ​ዪቱ በር ሸመ​ቁ​በት፥ “ማለዳ እን​ገ​ድ​ለ​ዋ​ለን” ብለ​ውም ሌሊ​ቱን ሁሉ በዝ​ምታ ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="3">ሶም​ሶ​ንም እስከ እኩለ ሌሊት ተኛ፤ በእ​ኩለ ሌሊ​ትም ተነ​ሥቶ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱን በር መዝ​ጊያ ያዘ፤ ከሁ​ለቱ መቃ​ኖ​ችና ከመ​ወ​ር​ወ​ሪ​ያው ጋር ነቀ​ለው፤ በት​ከ​ሻ​ውም ላይ አደ​ረገ፤ በኬ​ብ​ሮ​ንም ፊት ወዳ​ለው ተራራ ራስ ላይ ተሸ​ክ​ሞት ወጣ፤ በዚ​ያም ጣለው።</verse>
				<verse number="4">ከዚህ በኋላ በሶ​ሬሕ ሸለቆ የነ​በ​ረች ደሊላ የተ​ባ​ለች አን​ዲት ሴትን ወደደ።</verse>
				<verse number="5">የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መሳ​ፍ​ን​ትም ወደ እር​ስዋ ወጥ​ተው፥ “እር​ሱን አባ​ብ​ለሽ በእ​ርሱ ያለ ታላቅ ኀይል በምን እንደ ሆነ፥ እኛም እር​ሱን ለማ​ዋ​ረድ እና​ስ​ረው ዘንድ የም​ና​ሸ​ን​ፈው በምን እንደ ሆነ ዕወቂ፤ እኛም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችን ሺህ አንድ መቶ ብር እን​ሰ​ጥ​ሻ​ለን” አሉ​አት።</verse>
				<verse number="6">ደሊ​ላም ሶም​ሶ​ንን፥ “ታላቅ ኀይ​ልህ በምን እንደ ሆነ፥ በም​ንስ ብት​ታ​ሰር እን​ደ​ምትዋ​ረድ እባ​ክህ ንገ​ረኝ” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="7">ሶም​ሶ​ንም፥ “በሰ​ባት ባል​ደ​ረቀ በር​ጥብ ጠፍር ቢያ​ስ​ሩኝ፥ እደ​ክ​ማ​ለሁ፤ እንደ ሌላም ሰው እሆ​ና​ለሁ” አላት ።</verse>
				<verse number="8">የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መሳ​ፍ​ን​ትም ሰባት ያል​ደ​ረቀ ርጥብ ጠፍር አመ​ጡ​ላት፤ በእ​ነ​ር​ሱም አሰ​ረ​ችው።</verse>
				<verse number="9">የሚ​ያ​ደ​ቡ​ትም ሰዎች በጓ​ዳዋ ውስጥ ተደ​ብ​ቀው ነበር። እር​ስ​ዋም፥ “ሶም​ሶን ሆይ! ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መጡ​ብህ” አለ​ችው። እር​ሱም ፈትል እሳት በሸ​ተ​ተው ጊዜ እን​ዲ​በ​ጠስ ጠፍ​ሩን በጣ​ጠ​ሰው፤ ኀይ​ሉም በምን እንደ ሆነ አል​ታ​ወ​ቀም።</verse>
				<verse number="10">ደሊ​ላም ሶም​ሶ​ንን፥ “እነሆ፥ አታ​ለ​ል​ኸኝ፤ የነ​ገ​ር​ኸ​ኝም ሐሰት ነው፤ አሁ​ንም የም​ት​ታ​ሰ​ር​በት ምን እን​ደ​ሆነ፥ እባ​ክህ ንገ​ረኝ” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="11">እር​ሱም፥ “ሥራ ባል​ተ​ሠ​ራ​ባ​ቸው ሰባት አዳ​ዲስ ገመ​ዶች ቢያ​ስ​ሩኝ፥ እደ​ክ​ማ​ለሁ፤ እንደ ሌላ​ውም ሰው እሆ​ና​ለሁ” አላት።</verse>
				<verse number="12">ደሊ​ላም ሰባት አዳ​ዲስ ገመ​ዶች ወስዳ በእ​ነ​ርሱ አሰ​ረ​ችው፤ የሚ​ያ​ደ​ቡ​ትም ሰዎች በጓ​ዳዋ ውስጥ ተቀ​ም​ጠው ነበር። እር​ስ​ዋም፥ “ሶም​ሶን ሆይ! ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መጡ​ብህ” አለ​ችው። ገመ​ዶ​ች​ንም ከክ​ንዱ እንደ ፈትል በጣ​ጠ​ሳ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">ደሊ​ላም ሶም​ሶ​ንን፥ “እስከ አሁን ድረስ አታ​ለ​ል​ኸኝ፤ የነ​ገ​ር​ኸ​ኝም ሐሰት ነው፤ የም​ት​ታ​ሰ​ር​በት ምን እን​ደ​ሆነ ንገ​ረኝ” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “የራ​ሴን ጠጕር ሰባ​ቱን ጕን​ጕን ከድር ጋር ብት​ጐ​ነ​ጕ​ኚው፥ በግ​ድ​ግ​ዳም ላይ በች​ካል ብት​ቸ​ክ​ዪው፥ ከሰ​ዎች እንደ አንዱ እደ​ክ​ማ​ለሁ፥” አላት።</verse>
				<verse number="14">ደሊ​ላም አስ​ተ​ኛ​ችው፤ የራ​ሱ​ንም ጠጕር ሰባ​ቱን ጕን​ጕን ከድር ጋር ጐነ​ጐ​ነ​ችው፤ በግ​ድ​ግ​ዳም ላይ በች​ካል ቸከ​ለ​ቻ​ቸው፥ “ሶም​ሶን ሆይ! ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መጡ​ብህ” አለ​ችው። ከእ​ን​ቅ​ል​ፉም ነቃ፥ ችካ​ሉ​ንም ከነ​ቈ​ን​ዳ​ላው ከግ​ድ​ግ​ዳው ነቀለ፤ ኀይ​ሉም አል​ታ​ወ​ቀም።</verse>
				<verse number="15">ደሊ​ላም፥ “ ‘አንተ እወ​ድ​ድ​ሻ​ለሁ’ እን​ዴት ትለ​ኛ​ለህ? ልብህ ከእኔ ጋር አይ​ደ​ለም፤ ስታ​ታ​ል​ለኝ ይህ ሦስ​ተኛ ጊዜህ ነው፥ ታላቅ ኀይ​ል​ህም በምን እንደ ሆነ አል​ነ​ገ​ር​ኸ​ኝም” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="16">ከዚ​ህም በኋላ ሌሊ​ቱን ሁሉ በነ​ገር በዘ​በ​ዘ​በ​ች​ውና በአ​ደ​ከ​መ​ችው ጊዜ፥ ልሙት እስ​ኪል ድረስ ተበ​ሳጨ።</verse>
				<verse number="17">እር​ሱም፥ “ከእ​ናቴ ማኅ​ፀን ጀምሬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናዝ​ራዊ ነኝና ራሴን ምላጭ አል​ነ​ካ​ኝም፤ የራ​ሴ​ንም ጠጕር ብላጭ ኀይሌ ከእኔ ይነ​ሣል፤ እደ​ክ​ማ​ለ​ሁም፤ እንደ ሌላም ሰው ሁሉ እሆ​ና​ለሁ” ብሎ የል​ቡን ሁሉ ነገ​ራት።</verse>
				<verse number="18">ደሊ​ላም የል​ቡን ሁሉ እንደ ነገ​ራት ባወ​ቀች ጊዜ፥ “የል​ቡን ሁሉ ነግ​ሮ​ኛ​ልና ይህን ጊዜ ደግሞ ኑ” ብላ ላከ​ችና የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መሳ​ፍ​ንት ጠራች። የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም መሳ​ፍ​ንት ብሩን በእ​ጃ​ቸው ይዘው ወደ እር​ስዋ መጡ።</verse>
				<verse number="19">እር​ስ​ዋም በጕ​ል​በቷ ላይ አስ​ተ​ኛ​ችው፤ ጠጕር ቈራ​ጭም ጠራች፤ እር​ሱም ሰባ​ቱን የራ​ሱን ጕን​ጕን ላጨው። ይደ​ክ​ምም ጀመረ፤ ኀይ​ሉም ከእ​ርሱ ሄደ።</verse>
				<verse number="20">ደሊ​ላም፥ “ሶም​ሶን ሆይ! ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መጡ​ብህ” አለ​ችው። ከእ​ን​ቅ​ል​ፉም ነቅቶ፥ “እወ​ጣ​ለሁ፤ እንደ ወት​ሮ​ውም ጊዜ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም” አለ። ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ እንደ ተለ​የው አላ​ወ​ቀም።</verse>
				<verse number="21">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ይዘው ዐይ​ኖ​ቹን አወ​ጡት፤ ወደ ጋዛም አው​ር​ደው በእ​ግር ብረት አሰ​ሩት፤ በግ​ዞ​ትም ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር።</verse>
				<verse number="22">የራ​ሱም ጠጕር ከላ​ጩት በኋላ ያድግ ጀመር።</verse>
				<verse number="23">የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም መሳ​ፍ​ን​ትም፥ “አም​ላ​ካ​ችን ጠላ​ታ​ች​ንን ሶም​ሶ​ንን በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጠን” እያሉ ለአ​ም​ላ​ካ​ቸው ለዳ​ጎን ታላቅ መሥ​ዋ​ዕት ይሠዉ ዘንድ፥ ደስም ይላ​ቸው ዘንድ ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="24">ሕዝ​ቡም ሁሉ ባዩት ጊዜ፥ “ምድ​ራ​ች​ንን ያጠ​ፋ​ውን፥ ከእ​ኛም ብዙ ሰው የገ​ደ​ለ​ውን ጠላ​ታ​ች​ንን አም​ላ​ካ​ችን በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጠን እያሉ አም​ላ​ካ​ቸ​ውን አመ​ሰ​ገኑ።</verse>
				<verse number="25">ከዚ​ህም በኋላ ልባ​ቸ​ውን ደስ ባለው ጊዜ፥ “በፊ​ታ​ችን እን​ዲ​ጫ​ወት ሶም​ሶ​ንን ከእ​ስር ቤት ጥሩት” አሉ። ሶም​ሶ​ን​ንም ከእ​ስር ቤት ጠሩት፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ተጫ​ወተ፤ ተዘ​ባ​በ​ቱ​በ​ትም፤ በም​ሰ​ሶና በም​ሰ​ሶም መካ​ከል አቆ​ሙት።</verse>
				<verse number="26">ሶም​ሶ​ንም የሚ​መ​ራ​ውን ብላ​ቴና፥ “ቤቱን የደ​ገ​ፉ​ትን ምሰ​ሶ​ዎች እደ​ገ​ፍ​ባ​ቸው ዘንድ እባ​ክህ አስ​ይ​ዘኝ” አለው፥ ብላ​ቴ​ና​ውም እን​ዳ​ለው አደ​ረ​ገ​ለት።</verse>
				<verse number="27">በቤ​ትም ውስጥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ሞል​ተ​ው​በት ነበር፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም መሳ​ፍ​ን​ትም ሁሉ በዚያ ነበሩ፤ በቤ​ቱም ሰገ​ነት ላይ ሶም​ሶን ሲጫ​ወት የሚ​ያዩ ሦስት ሺህ የሚ​ያ​ህሉ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ነበሩ።</verse>
				<verse number="28">ሶም​ሶ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፥ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ ጌታዬ ሆይ! አስ​በኝ፤ ጌታዬ ሆይ! አንድ ጊዜ አበ​ር​ታኝ፤ እን​ግ​ዲህ ስለ ሁለቱ ዐይ​ኖቼ ፋንታ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አን​ዲት በቀ​ልን እበ​ቀ​ላ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="29">ሶም​ሶ​ንም ቤቱ ተደ​ግ​ፎ​ባ​ቸው የነ​በ​ሩ​ትን ሁለ​ቱን መካ​ከ​ለ​ኞች ምሰ​ሶ​ዎች ያዘ፤ አን​ዱን በቀኝ እጁ፥ አን​ዱ​ንም በግራ እጁ ይዞ ገፋ​ቸው።</verse>
				<verse number="30">ሶም​ሶ​ንም፥ “ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ነፍሴ ትውጣ” አለ፤ ተጎ​ን​ብ​ሶም ምሰ​ሶ​ዎ​ቹን በሙሉ ኀይሉ ገፋ​ቸው፤ ቤቱም በው​ስጡ በነ​በ​ሩት በመ​ሳ​ፍ​ንቱ፥ በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ላይ ወደቀ፤ በሞ​ቱም የገ​ደ​ላ​ቸው ሙታን በሕ​ይ​ወቱ ሳለ ከገ​ደ​ላ​ቸው በዙ።</verse>
				<verse number="31">ወን​ድ​ሞ​ቹም፥ የአ​ባቱ ቤተ ሰቦ​ችም ሁሉ ወረዱ፤ ይዘ​ውም አመ​ጡት፤ በሶ​ሬ​ሕና በኢ​ስ​ታ​ሔል መካ​ከል ባለው በአ​ባቱ በማ​ኑሄ መቃ​ብር ቀበ​ሩት። እር​ሱም እስ​ራ​ኤ​ልን ሃያ ዓመት ገዛ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ሚካ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ።</verse>
				<verse number="2">እና​ቱ​ንም፥ “ከአ​ንቺ ዘንድ የተ​ሰ​ረ​ቀው፥ የረ​ገ​ም​ሽ​በ​ትም፥ በጆ​ሮ​ዬም የተ​ና​ገ​ር​ሽ​በት አንድ ሺህ አንድ መቶ ብር እነሆ፥ በእኔ ዘንድ አለ፤ እኔም ወስ​ጄው ነበር” አላት። እና​ቱም፥ “ልጄ ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ር​ክህ” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="3">አን​ዱን ሺህ አንድ መቶ ብርም ለእ​ናቱ መለ​ሰ​ላት፤ እና​ቱም፥ “ይህን ብር የተ​ቀ​ረፀ ምስ​ልና ቀልጦ የተ​ሠራ ምስል አድ​ርጌ ከእጄ ስለ ልጄ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እቀ​ድ​ሰ​ዋ​ለሁ፤ አሁ​ንም ለአ​ንተ እመ​ል​ሰ​ዋ​ለሁ” አለች።</verse>
				<verse number="4">ለእ​ና​ቱም ገን​ዘ​ቡን መለ​ሰ​ላት እና​ቱም ብሩን ወስዳ ከእ​ርሱ ሁለ​ቱን መቶ ብር ለአ​ን​ጥ​ረኛ ሰጠ​ችው፤ እር​ሱም የተ​ቀ​ረፀ ምስ​ልና ቀልጦ የተ​ሠራ ምስል አደ​ረ​ገው። በሚ​ካም ቤት አስ​ቀ​መ​ጡት።</verse>
				<verse number="5">ሰው​ዬ​ውም ሚካ የአ​ማ​ል​ክት ቤት ነበ​ረው፤ ኤፉ​ድና ተራ​ፊም አደ​ረገ፤ ከል​ጆ​ቹም አን​ዱን ቀደ​ሰው፤ ካህ​ንም ሆነ​ለት።</verse>
				<verse number="6">በዚ​ያም ዘመን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም፤ ሰውም ሁሉ በፊቱ መል​ካም መስሎ የታ​የ​ውን ያደ​ርግ ነበር።</verse>
				<verse number="7">በይ​ሁዳ ቤተ ልሔ​ምም ከይ​ሁዳ ወገን የሆነ አንድ ጐል​ማሳ ነበረ፤ እር​ሱም ሌዋዊ ነበረ፤ በዚ​ያም ይቀ​መጥ ነበር።</verse>
				<verse number="8">ይህም ሰው በአ​ገ​ኘው ስፍራ ይኖር ዘንድ ከይ​ሁዳ ከተማ ከቤተ ልሔም ሄደ፤ በዚ​ያም ያድር ዘንድ ወደ ተራ​ራ​ማው ወደ ኤፍ​ሬም ሀገር ወደ ሚካ ቤት ደረሰ።</verse>
				<verse number="9">ሚካም፥ “ከወ​ዴት መጣህ?” አለው። እር​ሱም፥ “ከይ​ሁዳ ቤተ ልሔም የሆ​ንሁ ሌዋዊ ነኝ፤ የም​ቀ​መ​ጥ​በ​ት​ንም ስፍራ ለመ​ሻት እሄ​ዳ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="10">ሚካም፥ “በእኔ ዘንድ ተቀ​መጥ፤ አባ​ትና ካህ​ንም ሁነኝ፤ እኔም ልብ​ሶ​ች​ንና ምግ​ብ​ህን፥ በየ​ዓ​መ​ቱም ዐሥር ብር እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="11">ሌዋ​ዊ​ዉም ሄደ። ከዚ​ያም ሰው ጋር ይኖር ዘንድ ጀመረ፤ ጐል​ማ​ሳ​ውም ከል​ጆቹ እንደ አንዱ ሆነ​ለት።</verse>
				<verse number="12">ሚካም ሌዋ​ዊ​ዉን እጁን ቀባው፤ ጐል​ማ​ሳ​ውም ካህን ሆነ​ለት፤ በሚ​ካም ቤት ኖረ።</verse>
				<verse number="13">ሚካም፥ “ሌዋዊ ካህን ስለ ሆነ​ልኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካም እን​ዲ​ሠ​ራ​ልኝ አሁን አው​ቃ​ለሁ” አለ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">በዚ​ያም ዘመን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም። እስ​ከ​ዚ​ያም ቀን ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች መካ​ከል ርስት አል​ደ​ረ​ሳ​ቸ​ውም ነበ​ርና በዚያ ዘመን የዳን ነገድ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባት ርስት ይሹ ነበር።</verse>
				<verse number="2">የዳ​ንም ልጆች ከወ​ገ​ና​ቸው አም​ስት ጽኑ​ዓን ሰዎች ምድ​ሪ​ቱን እን​ዲ​ሰ​ል​ሉና እን​ዲ​መ​ረ​ምሩ፥ “ሂዱ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ሰልሉ” ብለው ከሶ​ራ​ሕና ከኢ​ስ​ታ​ሔል ላኩ። እነ​ዚ​ያም ወደ ተራ​ራ​ማዉ ወደ ኤፍ​ሬም ሀገር ወደ ሚካ ቤት መጥ​ተው በዚያ አደሩ።</verse>
				<verse number="3">በሚካ ቤትም በነ​በሩ ጊዜ የሌ​ዋ​ዊ​ዉን የጐ​ል​ማ​ሳ​ውን ድምፅ ዐወቁ፤ ወደ እር​ሱም ቀር​በው፥ “ወደ​ዚህ ማን አመ​ጣህ? በዚ​ህስ የም​ታ​ደ​ር​ገው ምን​ድን ነው? በዚ​ህስ ምን አለህ?” አሉት።</verse>
				<verse number="4">እር​ሱም፥ “ሚካ እን​ዲህ እን​ዲህ አደ​ረ​ገ​ልኝ፤ ቀጠ​ረ​ኝም፤ እኔም ካህን ሆን​ሁ​ለት” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">እነ​ር​ሱም፥ “የም​ን​ሄ​ድ​በት መን​ገድ የቀና መሆ​ኑን እና​ውቅ ዘንድ፥ እባ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠይ​ቅ​ልን” አሉት።</verse>
				<verse number="6">ያም ካህን፥ “የም​ት​ሄ​ዱ​በት መን​ገድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነውና በሰ​ላም ሂዱ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">አም​ስ​ቱም ሰዎች ሄዱ፤ ወደ ሌሳም ደረሱ፤ በው​ስ​ጡም የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ተዘ​ል​ለው አዩ​አ​ቸው፤ እንደ ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም ልማድ ጸጥ ብለው፥ ዐር​ፈው፥ ተዘ​ል​ለ​ውም ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ በተ​መ​ዘ​ገ​በች የር​ስ​ታ​ቸው ምድ​ርም ቃልን መና​ገር አል​ቻ​ሉም፤ ከሲ​ዶ​ና​ው​ያ​ንም ርቀው ይኖሩ ነበር። ከሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንም ጋር ግን​ኙ​ነት አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="8">እነ​ዚ​ያም አም​ስቱ ሰዎች ወደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ወደ ሶራ​ሕና ወደ እስ​ታ​ሔል ተመ​ለሱ፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ “ምን አስ​ቀ​ም​ጦ​አ​ች​ኋል?” አሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">እነ​ር​ሱም፥ “ምድ​ሪቱ እጅግ መል​ካም እንደ ሆነች አይ​ተ​ናል፤ ተነሡ፤ በእ​ነ​ርሱ ላይ እን​ውጣ፤ እና​ንተ ዝም ትላ​ላ​ች​ሁን? ትሄዱ ዘንድ፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ለመ​ው​ረስ ትገቡ ዘንድ ቸል አት​በሉ።</verse>
				<verse number="10">በሄ​ዳ​ች​ሁም ጊዜ ተዘ​ል​ለው ወደ ተቀ​መጡ ሕዝብ ትደ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤ ምድ​ሪ​ቱም ሰፊ ናት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድር ካለው ነገር ሁሉ አን​ዳች የማ​ይ​ጐ​ድ​ል​ባ​ትን ስፍራ በእ​ጃ​ችሁ ሰጥ​ቶ​አል” አሉ።</verse>
				<verse number="11">ከዳን ወገ​ንም የጦር ዕቃ የታ​ጠቁ ስድ​ስት መቶ ሰዎች ከዚያ ከሶ​ራ​ሕና ከእ​ስ​ታ​ሔል ተነ​ሥ​ተው ሄዱ።</verse>
				<verse number="12">ወጥ​ተ​ውም በይ​ሁዳ ቂር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ሰፈሩ፤ ስለ​ዚ​ህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የዳን ሰፈር ተብሎ ተጠራ፤ እነ​ሆም፥ ቦታዉ ከቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም በስ​ተ​ኋላ ነው።</verse>
				<verse number="13">ከዚ​ያም ወደ ተራ​ራ​ማው ወደ ኤፍ​ሬም አገር አለፉ እስከ ሚካም ቤት ደረሱ።</verse>
				<verse number="14">የሌ​ሳን ምድር ሊሰ​ልሉ ሄደው የነ​በ​ሩት አም​ስቱ ሰዎ​ችም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን፥ “በእ​ነ​ዚህ ቤቶች ውስጥ ኢፉ​ድና ተራ​ፊም፥ የተ​ቀ​ረፀ ምስ​ልና ቀልጦ የተ​ሠራ ምስ​ልም እን​ዳሉ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁን?፤ አሁ​ንም የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን ዕወቁ” ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">ከመ​ን​ገ​ዱም ፈቀቅ ብለው ወደ ጐል​ማ​ሳው ሌዋዊ ቤት ወደ ሚካ ቤት መጡ፤ ሰላ​ም​ታም ሰጡት።</verse>
				<verse number="16">የጦር ዕቃ የታ​ጠ​ቁት፥ ከዳን ልጆ​ችም የሆ​ኑት ስድ​ስቱ መቶ ሰዎች በደ​ጃፉ አጠ​ገብ ቆመው ነበር።</verse>
				<verse number="17">ምድ​ሪ​ቱ​ንም ሊሰ​ልሉ ሄደው የነ​በ​ሩት አም​ስቱ ሰዎች መጥ​ተው ወደ​ዚያ ገቡ፤ የተ​ቀ​ረ​ፀ​ው​ንም ምስል ኤፉ​ዱ​ንም፥ ተራ​ፊ​ሙ​ንም ቀልጦ የተ​ሠ​ራ​ውን ምስ​ልም ወሰዱ፤ ካህ​ኑም የጦር ዕቃ ከታ​ጠ​ቁት ከስ​ድ​ስት መቶ ሰዎች ጋር በደ​ጃፉ አጠ​ገብ ቆሞ ነበር።</verse>
				<verse number="18">እነ​ዚ​ህም ሰዎች ወደ ሚካ ቤት ገብ​ተው የተ​ቀ​ረ​ፀ​ውን ምስል፥ ኤፉ​ዱ​ንም፥ ተራ​ፊ​ሙ​ንም፥ ቀልጦ የተ​ሠ​ራ​ውን ምስ​ልም ወሰዱ፤ ካህ​ኑም፥ “ምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">እነ​ር​ሱም፥ “ዝም በል፤ እጅ​ህ​ንም በአ​ፍህ ላይ ጫን፤ ከእ​ኛም ጋር ና፥ አባ​ትና ካህ​ንም ሁን​ልን፤ ለአ​ንድ ሰው ቤት ካህን መሆን ወይስ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ለነ​ገ​ድና ለወ​ገን ካህን መሆን ማና​ቸው ይሻ​ል​ሃል?” አሉት።</verse>
				<verse number="20">ካህ​ኑም በልቡ ደስ አለው፤ ኤፉ​ዱ​ንም፥ ተራ​ፊ​ሙ​ንም፥ የተ​ቀ​ረ​ፀ​ው​ንም ምስል፥ ቀልጦ የተ​ሠ​ራ​ው​ንም ምስል ወሰደ፤ በሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ገባ።</verse>
				<verse number="21">እነ​ር​ሱም ተመ​ል​ሰው ሄዱ፤ ቤተ ሰቡን፥ ገን​ዘ​ቡ​ንና ሀብ​ቱ​ንም ሁሉ፥ በፊ​ታ​ቸው አድ​ር​ገው ወሰዱ።</verse>
				<verse number="22">ከሚ​ካም ቤት ሳይ​ርቁ ሚካና የሚካ ጎረ​ቤ​ቶች ጮኹ፤ የዳ​ን​ንም ልጆች ተከ​ት​ለው ደረ​ሱ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">ወደ ዳንም ልጆች ጮኹ፤ የዳ​ንም ልጆች ፊታ​ቸ​ውን መል​ሰው ሚካን፥ “የም​ት​ጮ​ኸው ምን ሆነህ ነው?” አሉት።</verse>
				<verse number="24">እር​ሱም፥ “የሠ​ራ​ኋ​ቸ​ውን አማ​ል​ክ​ቴን፥ ካህ​ኑ​ንም ይዛ​ችሁ ሄዳ​ች​ኋል፤ ለእኔ ምን ተዋ​ች​ሁ​ልኝ? እና​ን​ተስ፦ ለምን ትጮ​ኻ​ለህ እን​ዴት ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ?” አለ።</verse>
				<verse number="25">የዳ​ንም ልጆች እን​ዲህ አሉት፥ “የተ​ቈጡ ሰዎች እን​ዳ​ያ​ገ​ኙ​ህና ነፍ​ስ​ህም፥ የቤተ ሰቦ​ች​ህም ነፍስ እን​ዳ​ይ​ጠ​ፋ​ብህ፥ ድም​ፅህ በእኛ መካ​ከል አይ​ሰማ።”</verse>
				<verse number="26">የዳ​ንም ልጆች መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ሄዱ፤ ሚካም ከእ​ርሱ እንደ በረቱ ባየ ጊዜ ተመ​ልሶ ወደ ቤቱ ሄደ።።</verse>
				<verse number="27">እነ​ር​ሱም ሚካ የሠ​ራ​ውን ጣዖ​ትና ለእ​ርሱ የነ​በ​ረ​ውን ካህን ይዘው ወደ ሌሳ፥ ጸጥ ብሎ ተዘ​ል​ሎም ወደ ተቀ​መ​ጠው ሕዝብ መጡ፤ በሰ​ይ​ፍም ስለት መቱ​አ​ቸው፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ሉ​አት።</verse>
				<verse number="28">የሚ​ታ​ደ​ግም አል​ነ​በ​ረም፤ ከሲ​ዶና ርቀው ነበ​ርና፥ እነ​ር​ሱም ከሌ​ሎች ሰዎች ጋር ግን​ኙ​ነት አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ው​ምና። እር​ስ​ዋም በቤ​ት​ሮ​አብ አጠ​ገብ ባለች ሸለቆ ውስጥ ነበ​ረች፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ሠር​ተው ተቀ​መ​ጡ​ባት።</verse>
				<verse number="29">ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል በተ​ወ​ለ​ደው በአ​ባ​ታ​ቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩ​አት፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ስም አስ​ቀ​ድሞ ሌሳ ነበረ።</verse>
				<verse number="30">የዳ​ንም ልጆች የተ​ቀ​ረ​ፀ​ውን የሚ​ካን ምስል ለራ​ሳ​ቸው አቆሙ፤ የሙ​ሴም ልጅ የጌ​ር​ሳም ልጅ ዮና​ታን፥ እር​ሱና ልጆቹ እስከ ሀገ​ራ​ቸው ምርኮ ድረስ ለዳን ነገድ ካህ​ናት ነበሩ።</verse>
				<verse number="31">ሚካም ያደ​ረ​ገ​ውን የተ​ቀ​ረፀ ምስል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሴሎ ባለ​በት ዘመን ሁሉ አቆሙ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">በዚ​ያም ዘመን ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም። በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ማዶ የተ​ቀ​መጠ አንድ ሌዋዊ ሰው ነበረ፤ ከይ​ሁዳ ቤተ ልሔ​ምም ዕቅ​ብት አገባ።</verse>
				<verse number="2">ዕቅ​ብ​ቱም ተጣ​ላ​ችው፤ ትታ​ውም ወደ አባቷ ቤት ወደ ይሁዳ ቤተ ልሔም ሄደች፤ በዚ​ያም አራት ወር ተቀ​መ​ጠች።</verse>
				<verse number="3">ባል​ዋም ተነሣ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ዕርቅ ሽቶ ወደ እርሱ ሊመ​ል​ሳት ፍለ​ጋ​ዋን ተከ​ትሎ ሄደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አንድ ብላ​ቴና፥ ሁለ​ትም አህ​ዮች ነበሩ። እር​ሱም ወደ አባቷ ቤት ሄደ፤ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት ባየው ጊዜ ደስ ብሎት ተቀ​በ​ለው።</verse>
				<verse number="4">የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት አማቱ ወደ ቤቱ አገ​ባው፤ በቤ​ቱም ሦስት ቀን ተቀ​መጠ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ በዚ​ያም አደሩ።</verse>
				<verse number="5">በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ቀን ማል​ደው ተነሡ፤ እር​ሱም ለመ​ሄድ ተነሣ፤ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት አማ​ቹን፥ “ሰው​ነ​ት​ህን በቁ​ራሽ እን​ጀራ አበ​ርታ፤ ከዚ​ያም በኋላ ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ” አለው።</verse>
				<verse number="6">ሁለ​ቱም በአ​ንድ ላይ ተቀ​መጡ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት ሰው​ዬ​ውን፥ “ዛሬ ደግሞ ከዚህ እደር ልብ​ህ​ንም ደስ ይበ​ለው” አለው።</verse>
				<verse number="7">ሰው​ዬ​ውም ሊሄድ ተነሣ፤ አማቱ ግን ግድ አለው፤ ዳግ​መ​ኛም በዚያ አደረ።</verse>
				<verse number="8">በአ​ም​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ለመ​ሄድ ማልዶ ተነሣ፤ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት፥ “እህል ብላ፤ ከዚ​ህም በኋላ ፀሐይ ሲበ​ርድ ትሄ​ዳ​ለህ” አለው። ሁለ​ቱም በሉ፤ ጠጡም።</verse>
				<verse number="9">ሰው​ዬ​ውም ከዕ​ቅ​ብ​ቱና ከብ​ላ​ቴ​ናው ጋር ለመ​ሄድ ተነሣ፤ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪቱ አባት አማ​ቱም፥ “እነሆ፥ መሽ​ት​ዋል፤ ፀሐ​ዩም ሊጠ​ልቅ ደር​ሷል፤ ዛሬም እዚህ እደር፤ በዚ​ህም ተቀ​መጥ፤ ልብ​ህም ደስ ይበ​ለው፤ በጥ​ዋ​ትም መን​ገ​ዳ​ች​ሁን ትገ​ሠ​ግ​ሣ​ላ​ችሁ፤ ወደ ቤት​ህም ትገ​ባ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="10">ሰው​ዬው ግን በዚያ ሌሊት ለማ​ደር አል​ፈ​ቀ​ደም፤ ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወደ ተባ​ለ​ችው ወደ ኢያ​ቡስ ፊት ለፊት ደረሰ። ከእ​ር​ሱም ጋር ሁለት የተ​ጫኑ አህ​ዮች ነበሩ፤ ዕቅ​ብ​ቱም ከእ​ርሱ ጋር ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="11">በኢ​ያ​ቡ​ስም አን​ጻር ገና ሳሉ ፀሐ​ይዋ ተቈ​ለ​ቈ​ለች፤ ብላ​ቴ​ና​ውም ጌታ​ውን፥ “ና፤ ወደ​ዚ​ህች ወደ ኢያ​ቡ​ሳ​ው​ያን ከተማ፥ እባ​ክህ እና​ቅና፤ በእ​ር​ስ​ዋም እን​ደር” አለው።</verse>
				<verse number="12">ጌታ​ውም፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወዳ​ል​ሆ​ነች ወደ እን​ግዳ ከተማ አን​ገ​ባም፤ እኛ ወደ ገባ​ዖን እን​ለፍ” አለው።</verse>
				<verse number="13">ብላ​ቴ​ና​ው​ንም፥ “ና፤ ከእ​ነ​ዚህ ስፍራ ወደ አንዱ እን​ቅ​ረብ፤ በገ​ባ​ዖን ወይም በራማ እን​ደር” አለው።</verse>
				<verse number="14">አል​ፈ​ውም ሄዱ፤ የብ​ን​ያ​ምም ነገድ በም​ት​ሆ​ነው በገ​ባ​ዖን አጠ​ገብ ሳሉ ፀሐይ ገባ​ች​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">በገ​ባ​ዖ​ንም ገብ​ተው ያድሩ ዘንድ ወደ​ዚያ አቀኑ። ገብ​ተ​ውም በከ​ተ​ማው አደ​ባ​ባይ በተ​ቀ​መጡ ጊዜ ወደ ቤቱ የሚ​ያ​ስ​ገ​ባ​ቸ​ውና የሚ​ያ​ሳ​ድ​ራ​ቸው አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="16">እነ​ሆም አንድ ሽማ​ግሌ ከእ​ር​ሻው ሥራ ወደ ማታ መጣ፤ ይህም ሰው ከተ​ራ​ራ​ማው ከኤ​ፍ​ሬም ሀገር ነበረ፤ በገ​ባ​ዖ​ንም በእ​ን​ግ​ድ​ነት ተቀ​ምጦ ነበር፤ የዚያ ሀገር ሰዎች ግን የብ​ን​ያም ልጆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="17">ዐይ​ኑ​ንም አን​ሥቶ መን​ገ​ደ​ኛ​ውን በከ​ተ​ማው አደ​ባ​ባይ አየ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ውም፥ “ወዴት ትሄ​ዳ​ለህ? ከወ​ዴ​ትስ መጣህ?” አለው።</verse>
				<verse number="18">እር​ሱም፥ “እኛ ከይ​ሁዳ ቤተ ልሔም ወደ ተራ​ራ​ማው ወደ ኤፍ​ሬም ሀገር ማዶ እና​ል​ፋ​ለን፤ እኔ ከዚያ ነኝ፤ ወደ ይሁዳ ቤተ ልሔ​ምም ሄጄ ነበር፥ አሁ​ንም ወደ ቤቴ እሄ​ዳ​ለሁ፤ በቤ​ቱም የሚ​ያ​ሳ​ድ​ረኝ አጣሁ፤</verse>
				<verse number="19">ለአ​ህ​ዮ​ቻ​ችን ገለ​ባና ገፈራ አለን፤ ለእ​ኔና ለገ​ረ​ድህ ከባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህም ጋር ላለው ብላ​ቴና እን​ጀ​ራና የወ​ይን ጠጅ አለን፤ ከሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገን ሁሉ አን​ዳ​ችም አላ​ጣ​ንም” አለው።</verse>
				<verse number="20">ሽማ​ግ​ሌ​ውም ሰው፥ “ሰላም ከአ​ንተ ጋር ይሁን፤ የም​ት​ሻ​ው​ንም ሁሉ እኔ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ በአ​ደ​ባ​ባይ ግን አት​ደር” አለው።</verse>
				<verse number="21">ወደ ቤቱም አስ​ገ​ባው፤ ለአ​ህ​ዮ​ቹም ገፈራ ጣለ​ላ​ቸው፤ እግ​ራ​ቸ​ው​ንም ታጠቡ፤ በሉም፤ ጠጡም።</verse>
				<verse number="22">ሰው​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ደስ ባሰኙ ጊዜ የኃ​ጥ​ኣን ልጆች የሆኑ የከ​ተ​ማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ፤ በሩ​ንም ይደ​በ​ድቡ ነበር፤ ባለ​ቤ​ቱ​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ውን ሰው፥ “ወደ ቤትህ የገ​ባ​ውን ሰው እን​ድ​ን​ደ​ር​ስ​በት አው​ጣ​ልን” አሉት።</verse>
				<verse number="23">ባለ​ቤ​ቱም ሽማ​ግ​ሌው ወደ እነ​ርሱ ወጥቶ፥ “ወን​ድ​ሞቼ ሆይ! ይህን ክፉ ነገር ታደ​ርጉ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ች​ሁም፤ ይህ ሰው ወደ ቤቴ ከገባ በኋላ እን​ደ​ዚህ ያለ ስን​ፍና አት​ሥሩ።</verse>
				<verse number="24">ድን​ግል ልጄና የእ​ር​ሱም ዕቅ​ብት እነሆ፥ አሉ፤ አሁ​ንም አወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አዋ​ር​ዱ​አ​ቸው፤ በዐ​ይ​ና​ች​ሁም ፊት ደስ የሚ​ላ​ች​ሁን አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ ነገር ግን በዚህ ሰው ላይ እን​ደ​ዚህ ያለ የስ​ን​ፍና ሥራ አታ​ድ​ርጉ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">ሰዎቹ ግን ሊሰ​ሙት አል​ፈ​ቀ​ዱም፤ ሰው​የ​ውም ዕቅ​ብ​ቱን ይዞ ወደ እነ​ርሱ አወ​ጣ​ላ​ቸው፤ አዋ​ረ​ድ​ዋ​ትም፤ ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ እስ​ኪ​ነጋ ድረስ አመ​ነ​ዘ​ሩ​ባት፤ ጎህም በቀ​ደደ ጊዜ ለቀ​ቁ​አት።</verse>
				<verse number="26">ሴቲ​ቱም ማለዳ መጣች፤ ጌታ​ዋም ባለ​በት በሰ​ው​ዬው ቤት ደጅ ወድቃ እስ​ኪ​ነጋ ድረስ በዚያ ቀረች።</verse>
				<verse number="27">ጌታ​ዋም ማለዳ ተነሣ፤ የቤ​ቱ​ንም ደጅ ከፈተ፤ መን​ገ​ዱ​ንም ለመ​ሄድ ወጣ፤ እነ​ሆም፥ ዕቅ​ብቱ ሴት በቤቱ ደጃፍ ላይ ወድቃ፥ እጆ​ች​ዋም በመ​ድ​ረኩ ላይ ወድ​ቀው አገ​ኛት።</verse>
				<verse number="28">እር​ሱም፥ “ተነሺ እን​ሂድ” አላት፤ እር​ስዋ ግን ሞታ ነበ​ርና አል​መ​ለ​ሰ​ችም፤ በዚያ ጊዜም በአ​ህ​ያው ላይ ጫናት፤ ተነ​ሥ​ቶም ወደ ስፍ​ራው ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="29">ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ ካራ አነሣ፤ ዕቅ​ብ​ቱ​ንም ይዞ ከአ​ጥ​ን​ቶ​ችዋ መለ​ያያ ላይ ለዐ​ሥራ ሁለት ቈራ​ርጦ ወደ እስ​ራ​ኤል ሀገር ሁሉ ሰደደ።</verse>
				<verse number="30">ከዚ​ያም በኋላ ያያት ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “እስ​ራ​ኤል ከግ​ብፅ ከወጡ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ዲህ ያለ ነገር የሆ​ነ​በት ጊዜ የለም፤ የታ​የ​በ​ትም ጊዜ የለም፤” ያም ሰው እነ​ዚ​ያን የላ​ካ​ቸ​ውን ሰዎች እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰዎች እን​ዲህ በሏ​ቸው፦ እስ​ራ​ኤል ከግ​ብፅ ከወጡ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ እን​ዲህ የሆ​ነ​በት ጊዜ አለን? እና​ንተ ተመ​ካ​ከ​ሩ​በት፤ የሚ​በ​ጀ​ው​ንም ተነ​ጋ​ገሩ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ወጡ፤ ማኅ​በ​ሩም ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ፥ ከገ​ለ​ዓ​ድም ሰዎች ጋር፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="2">ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገድ ሁሉ የሕ​ዝቡ ሁሉ አለ​ቆች ሰይፍ በሚ​መ​ዝዙ፥ በቍ​ጥ​ርም አራት መቶ ሺህ እግ​ረ​ኞች በሆኑ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ጉባኤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆሙ።</verse>
				<verse number="3">የብ​ን​ያ​ምም ልጆች የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ መሴፋ እንደ ወጡ ሰሙ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ “ይህ ክፉ ነገር እን​ደ​ምን እንደ ተደ​ረገ ንገ​ሩን” አሉ።</verse>
				<verse number="4">የተ​ገ​ደ​ለ​ች​ውም ሴት ባል ሌዋ​ዊዉ እን​ዲህ ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው፥ “እኔና ዕቅ​ብቴ በዚያ ለማ​ደር ወደ ብን​ያም ሀገር ወደ ገባ​ዖን መጣን።</verse>
				<verse number="5">የገ​ባ​ዖ​ንም ሰዎች ተነ​ሡ​ብን፤ ቤቱ​ንም በሌ​ሊት በእኛ ላይ ከበ​ቡት፤ ሊገ​ድ​ሉ​ኝም ወደዱ፤ ዕቅ​ብ​ቴ​ንም አዋ​ረ​ድ​ዋት፤ አመ​ነ​ዘ​ሩ​ባ​ትም፤ እር​ስ​ዋም ሞተች።</verse>
				<verse number="6">እኔም ዕቅ​ብ​ቴን ይዤ በመ​ለ​ያ​ያዋ ቈራ​ረ​ጥ​ኋት፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ እን​ደ​ዚህ ያለ ስን​ፍና ስለ ሠሩ ወደ እስ​ራ​ኤል ርስት አው​ራጃ ሁሉ ሰደ​ድሁ።</verse>
				<verse number="7">እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ፥ ሁላ​ችሁ፥ ምክ​ራ​ች​ሁ​ንና እዝ​ና​ታ​ች​ሁን በዚህ ስጡ።”</verse>
				<verse number="8">ሕዝ​ቡም ሁሉ እንደ አንድ ሰው ተነ​ሥ​ተው እን​ዲህ አሉ፥ “ከእኛ ዘንድ ማንም ወደ ሀገሩ አይ​ሄ​ድም፤ ወደ ቤቱም አይ​መ​ለ​ስም።</verse>
				<verse number="9">አሁ​ንም በገ​ባ​ዖን ላይ እን​ዲህ አድ​ርጉ፤ በየ​ዕ​ጣ​ችን እን​ዘ​ም​ት​ባ​ቸ​ዋ​ለን።</verse>
				<verse number="10">በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ስላ​ደ​ረ​ጉት ስን​ፍና ሁሉ የብ​ን​ያም ገባ​ዖ​ንን ይወጉ ዘንድ ለሚ​ሄዱ ሕዝብ በመ​ን​ገድ ስንቅ የሚ​ይዙ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ከመ​ቶው ዐሥር ሰው፥ ከሺ​ሁም መቶ ሰው፥ ከዐ​ሥ​ሩም ሺህ አንድ ሺህ ሰው እን​ወ​ስ​ዳ​ለን።”</verse>
				<verse number="11">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው በከ​ተ​ማ​ዪቱ ላይ ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="12">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ዶች፥ “በእ​ና​ንተ መካ​ከል የተ​ደ​ረገ ይህ ክፉ ነገር ምን​ድን ነው?” ብለው ወደ ብን​ያም ነገድ ሁሉ ሰዎ​ችን ላኩ።</verse>
				<verse number="13">“አሁ​ንም በገ​ባ​ዖን ውስጥ የበ​ደሉ የዐ​መፅ ሰዎ​ችን እን​ድ​ን​ገ​ድ​ላ​ቸው አው​ጥ​ታ​ችሁ ስጡን፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ክፋ​ትን እና​ር​ቃ​ለን።” የብ​ን​ያም ልጆች ግን የወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ቃል ሊሰሙ አል​ወ​ደ​ዱም።</verse>
				<verse number="14">የብ​ን​ያ​ምም ልጆች ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር ሊዋጉ ከየ​ከ​ተ​ማ​ዎ​ቻ​ቸው ወደ ገባ​ዖን ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="15">በዚ​ያም ቀን ከየ​ከ​ተ​ማው የመጡ የብ​ን​ያም ልጆች ተቈ​ጠሩ፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም ከገ​ባ​ዖን ሰዎች ሌላ ሃያ አም​ስት ሺህ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከገ​ባ​ዖ​ንም ሰባት መቶ የተ​መ​ረጡ ሰዎች ተቈ​ጠሩ፤</verse>
				<verse number="16">ከእ​ነ​ዚ​ያም ሕዝብ ሁሉ ሰባት መቶ የተ​መ​ረጡ፥ ሁለ​ቱም እጆ​ቻ​ቸው ቀኝ የሆ​ኑ​ላ​ቸው ሰዎች ነበሩ፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ድን​ጋይ ይወ​ነ​ጭፉ ነበር፤ አን​ዲት ጠጕ​ርስ እንኳ አይ​ስ​ቱም ነበር።</verse>
				<verse number="17">ከብ​ን​ያ​ምም ልጆች ሌላ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች አራት መቶ ሺህ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ሰዎች ተቈ​ጠሩ፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ሰል​ፈ​ኞች ነበሩ።</verse>
				<verse number="18">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተነ​ሥ​ተው ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፥ “የብ​ን​ያ​ምን ልጆች ለመ​ው​ጋት መሪ ሆኖ ማን ይው​ጣ​ልን?” ብለው ጠየ​ቁት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይሁዳ መሪ ይሁን” አለ፤</verse>
				<verse number="19">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በማ​ለዳ ተነ​ሥ​ተው በገ​ባ​ዖን ፊት ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="20">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ከብ​ን​ያም ጋር ሊዋጉ ወጡ፤ በገ​ባ​ዖ​ንም ገጠ​ሙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">የብ​ን​ያ​ምም ልጆች ከገ​ባ​ዖን ወጡ፤ በዚ​ያም ቀን ከእ​ስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን በም​ድር ላይ ገደሉ።</verse>
				<verse number="22">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ተበ​ራቱ፤ በፊ​ተ​ኛ​ውም ቀን በተ​ሰ​ለ​ፉ​በት ስፍራ ደግ​መው ተሰ​ለፉ።</verse>
				<verse number="23">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወጥ​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለ​ቀሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፥ “ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከብ​ን​ያም ልጆች ጋር ለመ​ዋ​ጋት ዳግ​መኛ እን​ቀ​ር​ባ​ለን?” ብለው ጠየቁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም “በእ​ነ​ርሱ ላይ ውጡ” አለ።</verse>
				<verse number="24">በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከብ​ን​ያም ልጆች ጋር ሊዋጉ ቀረቡ።</verse>
				<verse number="25">በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን የብ​ን​ያም ልጆች ሊገ​ጥ​ሙ​አ​ቸው ከገ​ባ​ዖን ወጡ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ደግሞ ዐሥራ ስም​ንት ሺህ ሰዎ​ችን በም​ድር ላይ ገደሉ፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ነበሩ።</verse>
				<verse number="26">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወጥ​ተው ወደ ቤቴል መጡ፤ አለ​ቀ​ሱም፤ በዚ​ያም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተቀ​መጡ፤ በዚ​ያም ቀን እስከ ማታ ድረስ ጾሙ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ትን አቀ​ረቡ።</verse>
				<verse number="27">በዚ​ያም ዘመን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት በዚያ ነበ​ረ​ችና፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቁ፤</verse>
				<verse number="28">በዚ​ያም ዘመን የአ​ሮን ልጅ የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ በፊቷ ይቆም ነበ​ርና። “ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከብ​ን​ያም ልጆች ጋር ለመ​ዋ​ጋት ዳግ​መኛ እን​ው​ጣን? ወይስ እን​ቅር?” አሉ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ነገ በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ውጡ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="29">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ገባ​ዖ​ንን የሚ​ከ​ብ​ቡ​አት ሰዎ​ችን በዙ​ሪ​ያዋ አኖ​ሩ​ባት።</verse>
				<verse number="30">በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ ብን​ያም ልጆች ወጡ፤ በገ​ባ​ዖ​ንም ፊት እንደ ቀድ​ሞው ጊዜ ተዋ​ጉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="31">የብ​ን​ያ​ምም ልጆች በሕ​ዝቡ ላይ ወጡ፤ ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ሸሹ፤ እንደ ቀድ​ሞ​ውም ጊዜ፥ በአ​ው​ራ​ዎቹ መን​ገ​ዶች፥ አን​ደ​ኛው ወደ ቤቴል፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ወደ ገባ​ዖን ሜዳ በሚ​ወ​ስ​ዱት መን​ገ​ዶች ላይ ሕዝ​ቡን ይመቱ፥ ይገ​ድ​ሉም ጀመር፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሠላሳ የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="32">የብ​ን​ያ​ምም ልጆች፥ “እንደ ቀድ​ሞው በፊ​ታ​ችን ይሞ​ታሉ” አሉ። የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን፥ “እን​ሽሽ፤ ከከ​ተ​ማም ወደ መን​ገድ እና​ር​ቃ​ቸው” አሉ።</verse>
				<verse number="33">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ከስ​ፍ​ራ​ቸው ተነ​ሥ​ተው በበ​ዓ​ል​ታ​ምር ተዋጉ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አድ​ፍ​ጠው የነ​በ​ሩት ከስ​ፍ​ራ​ቸው ከገ​ባ​ዖን ምዕ​ራብ ወጡ።</verse>
				<verse number="34">ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ የተ​መ​ረጡ ዐሥር ሺህ ሰዎች ወደ ገባ​ዖን አን​ጻር መጡ፤ ውጊ​ያ​ውም በር​ትቶ ነበር፤ መከ​ራም እን​ዲ​ያ​ገ​ኛ​ቸው አላ​ወ​ቁም ነበር።</verse>
				<verse number="35">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብን​ያ​ምን በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ጣላ​ቸው፤ በዚ​ያም ቀን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከብ​ን​ያም ሃያ አም​ስት ሺህ አንድ መቶ ሰዎ​ችን ገደሉ፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ነበሩ።</verse>
				<verse number="36">የብ​ን​ያም ልጆ​ችም እንደ ተመቱ አዩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን በገ​ባ​ዖን ላይ ባኖ​ሩት ድብቅ ጦር ታም​ነ​ዋ​ልና ለብ​ን​ያም ስፍራ ለቀ​ቁ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="37">ተደ​ብ​ቀው የነ​በ​ሩ​ትም ፈጥ​ነው ወደ ገባ​ዖን ሮጡ፤ ተደ​ብ​ቀው የነ​በ​ሩ​ትም መጥ​ተው ከተ​ማ​ውን ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት መቱ።</verse>
				<verse number="38">የተ​ደ​በ​ቁ​ትም ሰዎች ከከ​ተ​ማው ብዙ ጢስ እንደ ደመና እን​ዲ​ያ​ስ​ነሡ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና በተ​ደ​በ​ቁት ሰዎች መካ​ከል ምል​ክት ተደ​ርጎ ነበር።</verse>
				<verse number="39">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አር​በ​ኞች ከሰ​ልፉ ተመ​ለሱ፤ ብን​ያ​ማ​ው​ያ​ንም እንደ ቀድ​ሞው ሰልፍ በፊ​ታ​ችን ተመ​ት​ተ​ዋል እያሉ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሠላሳ የሚ​ያ​ህሉ ሰዎ​ችን መም​ታ​ትና መግ​ደል ጀመሩ።</verse>
				<verse number="40">ምል​ክ​ቱም በጢሱ ዐምድ ከከ​ተ​ማው ሊወጣ በጀ​መረ ጊዜ ብን​ያ​ማ​ው​ያን ወደ​ኋ​ላ​ቸው ተመ​ለ​ከቱ፤ እነ​ሆም፥ የሞላ ከተ​ማው ጥፋት ወደ ሰማይ ወጣ።</verse>
				<verse number="41">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተመ​ለሱ፤ የብ​ን​ያ​ምም ሰዎች ተሸ​በሩ፤ ክፉ ነገር እንደ ደረ​ሰ​ባ​ቸ​ውም አዩ።</verse>
				<verse number="42">ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ፊት ወደ ምድረ በዳ መን​ገድ ሸሹ፤ ሰል​ፉም ደረ​ሰ​ባ​ቸው፤ ከየ​ከ​ተ​ማ​ውም የወ​ጡት በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ገደ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="43">ብን​ያ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ወግ​ተው አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ በም​ሥ​ራቅ በኩል ባለው በገ​ባ​ዖ​ንም ፈጽ​መው ደመ​ሰ​ሱ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="44">ከብ​ን​ያ​ምም ዐሥራ ስም​ንት ሺህ ሰው ሞተ፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ጽኑ​ዓን ሰዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="45">ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ረ​ፉት ተመ​ል​ሰው ወደ ምድረ በዳ ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በየ​መ​ን​ገዱ ላይ አም​ስት ሺህ ሰውን ለቀሙ፤ ወደ ጊድ​ዓ​ምም አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን ገደሉ።</verse>
				<verse number="46">እን​ዲ​ሁም በዚያ ቀን ከብ​ን​ያም የሞ​ቱት ሃያ አም​ስት ሺህ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ሰዎች ነበሩ፤ እነ​ዚህ ሁሉ ጽኑ​ዓን ሰዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="47">ስድ​ስ​ቱም መቶ ሰዎች ተመ​ል​ሰው ወደ ምድረ በዳ ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፤ በሬ​ሞ​ንም ዓለት አራት ወር ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="48">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች በብ​ን​ያም ልጆች ላይ ዳግ​መኛ ተመ​ለሱ፤ ሞላ​ውን ከተማ፥ ከብ​ቱ​ንም፥ ያገ​ኙ​ት​ንም ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት አጠፉ፤ ያገ​ኙ​ት​ንም ከተማ ሁሉ በእ​ሳት አቃ​ጠሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች፥ “ከእኛ ማንም ሰው ሴት ልጁን ለብ​ን​ያም ልጆች በጋ​ብቻ አይ​ስጥ” ብለው በመ​ሴፋ ተማ​ማሉ።</verse>
				<verse number="2">ሕዝ​ቡም ወደ ቤቴል መጥ​ተው በዚያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ ተቀ​መጡ፤ ድም​ፃ​ቸ​ው​ንም ከፍ አድ​ር​ገው ጽኑዕ ልቅሶ አለ​ቀሱ።</verse>
				<verse number="3">እነ​ር​ሱም፥ “አቤቱ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ዛሬ ከእ​ስ​ራ​ኤል አንድ ነገድ መታ​ጣቱ፥ ስለ​ምን ይህ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ሆነ?” አሉ።</verse>
				<verse number="4">በነ​ጋ​ውም ሕዝቡ ማል​ደው ተነሡ፤ በዚ​ያም መሠ​ዊያ ሠሩ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ልና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም አቀ​ረቡ።</verse>
				<verse number="5">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ ስላ​ል​ወጣ ሰው፥ “እርሱ ፈጽሞ ይገ​ደል” ብለው ታላቅ መሐላ ምለው ነበ​ርና፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ወደ ጉባኤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያል​ወጣ ማን ነው?” አሉ።</verse>
				<verse number="6">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ስለ ወን​ድ​ማ​ቸው ስለ ብን​ያም ልጆች አዝ​ነው እን​ዲህ አሉ፥ “ዛሬ ከእ​ስ​ራ​ኤል አንድ ነገድ ጠፍ​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="7">እኛ ልጆ​ቻ​ች​ንን እን​ዳ​ን​ድ​ር​ላ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምለ​ና​ልና የተ​ረ​ፉት ሚስ​ቶ​ችን እን​ዲ​ያ​ገኙ ምን እን​ድ​ርግ?”</verse>
				<verse number="8">እነ​ር​ሱም፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ ያል​ወጣ ማን ነው?” አሉ። እነ​ሆም፥ ከኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓድ ወደ ሰፈሩ ወደ ጉባ​ኤው ማንም አል​ወ​ጣም ነበር።</verse>
				<verse number="9">ሕዝ​ቡም በተ​ቈ​ጠሩ ጊዜ፥ እነሆ፥ ከኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓድ ነዋ​ሪ​ዎች ሰው አል​ተ​ገ​ኘም።</verse>
				<verse number="10">ማኅ​በ​ሩም ወደ​ዚያ ዐሥራ ሁለት ሺህ ኀያ​ላን ሰዎ​ችን ልከው፥ “ሂዱ በኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓ​ድም ያሉ​ትን ሰዎች ሴቶ​ች​ንም ሕዝ​ቡ​ንም በሰ​ይፍ ስለት ግደሉ።</verse>
				<verse number="11">የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትም ይህ ነው፤ ወን​ዱን ሁሉ፥ ወንድ የሚ​ያ​ው​ቁ​ት​ንም ሴቶች ሁሉ ፈጽ​ማ​ችሁ አጥፉ፤ ደና​ግ​ሉን ግን አት​ግ​ደ​ሉ​አ​ቸው፤” ብለው አዘ​ዙ​አ​ቸው፤ እን​ዲ​ሁም አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="12">በኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓድ በሚ​ኖሩ መካ​ከ​ልም ወንድ ያላ​ወቁ አራት መቶ ቆነ​ጃ​ጅት ደና​ግ​ልን አገኙ፤ በከ​ነ​ዓ​ንም ሀገር ወዳ​ለ​ችው ወደ ሴሎ ወደ ሰፈሩ አመ​ጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">ማኅ​በ​ሩም ሁሉ በሬ​ሞን ዐለት ወዳ​ሉት ወደ ብን​ያም ልጆች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላኩ፤ በሰ​ላ​ምም ጠሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">በዚ​ያም ጊዜ የብ​ን​ያም ልጆች ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ተመ​ለሱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓድ ሴቶች ያዳ​ኑ​አ​ቸ​ውን ሴቶች ሰጡ​አ​ቸው። በዚ​ህም ተስ​ማሙ።</verse>
				<verse number="15">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ውስጥ ስብ​ራት ስላ​ደ​ረገ ሕዝቡ ስለ ብን​ያም አዘኑ።</verse>
				<verse number="16">የማ​ኅ​በሩ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም፥ “ከብ​ን​ያም ሴቶች ጠፍ​ተ​ዋ​ልና የቀ​ሩት ስዎች ሚስት እን​ዲ​ያ​ገኙ ምን እና​ደ​ር​ጋ​ለን?” አሉ።</verse>
				<verse number="17">ደግ​ሞም፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል አንድ ነገድ እን​ዳ​ይ​ደ​መ​ሰስ ከብ​ን​ያም ላመ​ለ​ጡት ርስት ይኑር።</verse>
				<verse number="18">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ “ልጁን ለብ​ን​ያም የሚ​ሰጥ ርጉም ይሁን ብለው ምለ​ዋ​ልና እኛ ከል​ጆ​ቻ​ችን ሚስ​ቶ​ችን ለእ​ነ​ርሱ መስ​ጠት አን​ች​ልም” አሉ።</verse>
				<verse number="19">እነ​ር​ሱም፥ “እነሆ፥ በቤ​ቴል በመ​ስዕ በኩል፥ ከቤ​ቴ​ልም ወደ ሰቂማ በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ በም​ሥ​ራቅ በኩል በሌ​ብና በዐ​ዜብ በኩል ባለ​ችው በሴሎ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል በየ​ዓ​መቱ አለ” አሉ።</verse>
				<verse number="20">የብ​ን​ያ​ም​ንም ልጆች እን​ዲህ ብለው አዘ​ዙ​አ​ቸው፥ “ሂዱ በወ​ይ​ኑም ስፍራ ተደ​በቁ፤</verse>
				<verse number="21">ተመ​ል​ከ​ቱም፤ እነሆ፥ የሴሎ ሴቶች ልጆች አታሞ ይዘው ለዘ​ፈን ሲወጡ ከወ​ይኑ ስፍራ ውጡ፤ ከሴሎ ሴቶች ልጆ​ችም ለየ​ራ​ሳ​ችሁ ሚስ​ትን ንጠቁ፤ ወደ ብን​ያም ምድ​ርም ሂዱ።</verse>
				<verse number="22">አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ሊጣ​ሉ​አ​ችሁ ወደ እኛ በመጡ ጊዜ፦ ስለ እኛ ማሩ​አ​ቸው፥ እኛ ሚስት ለያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በሰ​ልፍ አል​ወ​ሰ​ድ​ን​ላ​ቸ​ው​ምና፥ እና​ን​ተም በደል ይሆ​ን​ባ​ችሁ ስለ ነበር አላ​ጋ​ባ​ች​ኋ​ቸ​ው​ምና፥” እን​ላ​ቸ​ዋ​ለን።</verse>
				<verse number="23">የብ​ን​ያ​ምም ልጆች እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ በቍ​ጥ​ራ​ቸ​ውም መጠን ከተ​ነ​ጠ​ቁት ዘፋ​ኞች ሚስ​ትን ወሰዱ፤ ወደ ርስ​ታ​ቸ​ውም ተመ​ል​ሰው ሄዱ፤ ከተ​ሞ​ች​ንም ሠር​ተው ተቀ​መ​ጡ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">በዚያ ጊዜም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከዚያ ተነሡ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ ወገ​ኑና ወደ ነገዱ ሄደ፤ ሰውም ሁሉ ከዚያ ወደ ርስቱ ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="25">በዚ​ያም ዘመን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም፤ ሰው ሁሉ በፊቱ መል​ካም መስሎ የታ​የ​ውን ያደ​ርግ ነበር።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="8">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">እንዲህም ሆነ፥ መሳፍንት ይፈርዱ በነበረ ጊዜ በአገሩ ላይ ራብ ሆነ። አንድ ሰውም ከሚስቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋር በሞዓብ ምድር ሊቀመጥ ከቤተ ልሔም ይሁዳ ተነሥቶ ሄደ።</verse>
				<verse number="2">የሰውዮውም ስም አቤሜሌክ፥ የሚስቱም ስም ኑኃሚን፥ የሁለቱም ልጆች ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበረ፥ የቤተ ልሔም ይሁዳም የኤፍራታ ሰዎች ነበሩ። ወደ ሞዓብም ምድር መጡ በዚያም ተቀመጡ።</verse>
				<verse number="3">የኑኃሚንም ባል አቤሜሌክ ሞተ፣ እርስዋና ሁለቱ ልጆችዋ ቀሩ።</verse>
				<verse number="4">እነርሱም ከሞዓባውያን ሴቶች ሚስት አገቡ፣ የአንዲቱ ስም ዖርፋ የሁለተኛይቱም ስም ሩት ነበረ። በዚያም አሥር ዓመት ያህል ተቀመጡ።</verse>
				<verse number="5">መሐሎንና ኬሌዎንም ሁለቱ ሞቱ፣ ሴቲቱም ከሁለቱ ልጆችዋና ከባልዋ ተለይታ ቀረች።</verse>
				<verse number="6">እርስዋም በሞዓብ ምድር ሳለች እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ ጐበኘ እንጀራም እንደ ሰጣቸው ስለ ሰማች፥ ከሞዓብ ምድር ልትመለስ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ተነሣች።</verse>
				<verse number="7">እርስዋም ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ከተቀመጠችበት ስፍራ ወጣች፣ ወደ ይሁዳም ምድር ሊመለሱ በመንገድ ሄዱ።</verse>
				<verse number="8">ኑኃሚንም ምራቶችዋን፦ ሂዱ፥ ወደ እናቶቻችሁም ቤት ተመለሱ፣ በእኔና በሞቱት እንዳደረጋችሁ፥ እግዚአብሔር ቸርነት ያድርግላችሁ።</verse>
				<verse number="9">እግዚአብሔር በየባላችሁ ቤት ዕረፍት ይስጣችሁ አለቻቸው። ሳመቻቸውም፣ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው አለቀሱ።</verse>
				<verse number="10">እነርሱም፦ ከአንቺ ጋር ወደ ሕዝብሽ እንመለሳለን አሉአት።</verse>
				<verse number="11">ኑኃሚንም አለች፦ ልጆቼ ሆይ፥ ተመለሱ፣ ለምን ከእኔ ጋር ትሄዳላችሁ? ባሎቻችሁ የሚሆኑ ልጆች በሆዴ አሉኝን?</verse>
				<verse number="12">ልጆቼ ሆይ፥ ተመለሱ፣ ባል ለማግባት አርጅቻለሁና ሂዱ፣ ተስፋ አለኝ ብል፥ ዛሬ ሌሊትስ እንኳ ባል ባገባ፥ ወንዶች ልጆችም ብወልድ፥</verse>
				<verse number="13">እነርሱ እስኪያድጉ ድረስ ትቆያላችሁን? ስለ እነርሱስ ባል ማግባት ትተዋላችሁን? ልጆቼ ሆይ፥ እንዲህ አይደለም፣ የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ወጥቶአልና ከእናንተ የተነሣ እጅግ ተመርሬአለሁ።</verse>
				<verse number="14">ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው እንደ ገና አለቀሱ፣ ዖርፋም አማትዋን ሳመች፣ ሩት ግን ተጠጋቻት።</verse>
				<verse number="15">ኑኃሚንም፦ እነሆ፥ ባልንጀራሽ ወደ ሕዝብዋና ወደ አማልክትዋ ተመልሳለች፣ አንቺም ደግሞ ከባልንጀራሽ ጋር ተመለሽ አለቻት።</verse>
				<verse number="16">ሩትም፦ ወደምትሄጅበት እሄዳለሁና፥ በምታድሪበትም አድራለሁና እንድተውሽ ከአንቺም ዘንድ እንድመለስ አታስቸግሪኝ፣ ሕዝብሽ ሕዝቤ፥ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል፣</verse>
				<verse number="17">በምትሞችበትም ስፍራ እሞታለሁ፥ በዚያም እቀበራለሁ፣ ከሞት በቀር አንቺንና እኔን አንዳች ቢለየን እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ እንዲሁም ይጨምርብኝ አለች።</verse>
				<verse number="18">ኑኃሚንም ከእርስዋ ጋር ለመሄድ እንደ ቈረጠች ባየች ጊዜ እርስዋን ከመናገር ዝም አለች።</verse>
				<verse number="19">ሁለቱም እስከ ቤተ ልሔም ድረስ ሄዱ። ወደ ቤተ ልሔምም በደረሱ ጊዜ የከተማይቱ ሰዎች ሁሉ ስለ እነርሱ፦ ይህች ኑኃሚን ናትን? እያሉ ተንጫጩ።</verse>
				<verse number="20">እርስዋም፦ ሁሉን የሚችል አምላክ አስመርሮኛልና ማራ በሉኝ እንጂ ኑኃሚን አትበሉኝ።</verse>
				<verse number="21">በሙላት ወጣሁ፥ እግዚአብሔርም ወደ ቤቴ ባዶዬን መለሰኝ፣ እግዚአብሔር አዋርዶኛልና፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ አስጨንቆኛልና ኑኃሚን ለምን ትሉኛላችሁ? አለቻቸው።</verse>
				<verse number="22">ኑኃሚንም ከእርስዋም ጋር ከሞዓብ ምድር የተመለሰችው ሞዓባዊቱ ምራትዋ ሩት ተመለሱ። የገብስም መከር በተጀመረ ጊዜ ወደ ቤተልሔም መጡ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ለኑኃሚንም ባል የሚዛመደው ከአቤሜሌክ ወገን የሆነ ኃያል ሰው ስሙ ቦዔዝ የተባለ ሰው ነበረ።</verse>
				<verse number="2">ሞዓባዊቱም ሩት ኑኃሚንን፦ በፊቱ ሞገስ የማገኘውን ተከትዬ እህል እንድቃርም ወደ እርሻ ልሂድ አለቻት። እርስዋም፦ ልጄ ሆይ፥ ሂጂ አለቻት።</verse>
				<verse number="3">ሄደችም፥ ከአጫጆችም በኋላ በእርሻ ውስጥ ቃረመች፣ እንደ አጋጣሚውም የአቤሜሌክ ወገን ወደ ነበረው ወደ ቦዔዝ እርሻ ደረሰች።</verse>
				<verse number="4">እነሆም፥ ቦዔዝ ከቤተ ልሔም መጣ፥ አጫጆችንም፦ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን አላቸው። እነርሱም፦ እግዚአብሔር ይባርክህ ብለው መለሱለት።</verse>
				<verse number="5">ቦዔዝም በአጫጆች ላይ አዛዥ የነበረውን ሎሌውን፦ ይህች ቆንጆ የማን ናት? አለው።</verse>
				<verse number="6">የአጫጆቹም አዛዥ፦ ይህችማ ከሞዓብ ምድር ከኑኃሚን ጋር የመጣች ሞዓባዊቱ ቆንጆ ናት፣</verse>
				<verse number="7">እርስዋም፦ ከአጫጆቹ በኋላ በነዶው መካከል እንድቃርምና እንድለቅም፥ እባክህ፥ ፍቀድልኝ አለች፣ መጣችም፥ ከማለዳም ጀምራ እስከ አሁን ድረስ ቆይታለች፣ በቤትም ጥቂት ጊዜ እንኳ አላረፈችም አለው።</verse>
				<verse number="8">ቦዔዝም ሩትን፦ ልጄ ሆይ፥ ትሰሚያለሽን? ቃርሚያ ለመቃረም ወደ ሌላ እርሻ አትሂጂ፥ ከዚህም አትላወሺ፥ ነገር ግን ገረዶቼን ተጠጊ።</verse>
				<verse number="9">ወደሚያጭዱበትም ስፍራ ተመልከቺ፥ ተከተያቸውም፣ እንዳያስቸግሩሽም ጐበዛዝቱን አዝዣለሁ፣ በተጠማሽም ጊዜ ወደ ማድጋው ሄደሽ ጐበዛዝቱ ከቀዱት ውኃ ጠጪ አላት።</verse>
				<verse number="10">በግምባርዋም ተደፍታ በምድር ላይ ሰገደችለት፦ እኔንስ ለመቀበል በምን ነገር በፊትህ ሞገስ አገኘሁ? እኔ እንግዳ አይደለሁምን? አለችው።</verse>
				<verse number="11">ቦዔዝም፦ ባልሽ ከሞተ በኋላ አባትሽንና እናትሽን የተወለድሽባትንም ምድር ትተሽ ቀድሞ ወደማታውቂው ሕዝብ እንደ መጣሽ፥ ለአማትሽ ያደረግሽውን ነገር ሁሉ ፈጽሞ ሰምቻለሁ።</verse>
				<verse number="12">እግዚአብሔር እንደ ሥራሽ ይስጥሽ፣ ከክንፉም በታች መጠጊያ እንድታገኚ በመጣሽበት በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ዘንድ ደመወዝሽ ፍጹም ይሁን አላት።</verse>
				<verse number="13">እርስዋም፦ ጌታዬ ሆይ፥ ከባሪያዎችህ እንደ አንዲቱ ሳልሆን አጽናንተኽኛልና፥ የባሪያህንም ልብ ደስ አሰኝተሃልና በዓይንህ ሞገስ ላግኝ አለችው።</verse>
				<verse number="14">በምሳም ጊዜ ቦዔዝ፦ ወደዚህ ቅረቢ፣ ምሳ ብዪ፥ እንጀራሽንም በሆምጣጤው አጥቅሽ አላት። በአጫጆቹም አጠገብ ተቀመጠች የተጠበሰም እሸት ሰጣት፥ በልታም ጠገበች፥ አተረፈችም።</verse>
				<verse number="15">ደግሞም ልትቃርም በተነሣች ጊዜ ቦዔዝ ጐበዛዝቱን፦ በነዶው መካከል ትቃርም፥ እናንተም አታሳፍሩአት፣</verse>
				<verse number="16">ደግሞ ከነዶው አስቀርታችሁ ተዉላት፣ እርስዋም ትቃርም፥ አትውቀሱአትም ብሎ አዘዛቸው።</verse>
				<verse number="17">በእርሻውም ውስጥ እስከ ማታ ድረስ ቃረመች፣ የቃረመችውንም ወቃችው፣ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ያህልም ገብስ ሆነ።</verse>
				<verse number="18">ተሸክማውም ወደ ከተማ ገባች፥ አማትዋም የቃረመችውን አየች፣ ከጠገበችም በኋላ የተረፋትን አውጥታ ሰጠቻት።</verse>
				<verse number="19">አማትዋም፦ ዛሬ ወዴት ቃረምሽ? ወዴትስ ሠራሽ? የተቀበለሽ የተባረከ ይሁን አለቻት። እርስዋም፦ ዛሬ የሠራሁበት ሰው ስም ቦዔዝ ይባላል ብላ በማን ዘንድ እንደ ሠራች ለአማትዋ ነገረቻት።</verse>
				<verse number="20">ኑኃሚንም ምራትዋን፦ ቸርነቱን በሕያዋንና በሙታን ላይ አልተወምና በእግዚአብሔር የተባረከ ይሁን አለቻት። ኑኃሚንም ደግሞ፦ ይህ ሰው የቅርብ ዘመዳችን ነው፥ እርሱም ሊቤዡን ከሚችሉት አንዱ ነው አለቻት።</verse>
				<verse number="21">ሞዓባዊቱ ሩትም፦ ደግሞ፦ መከሬን እስኪጨርሱ ድረስ ጐበዛዝቴን ተጠጊ አለኝ አለቻት።</verse>
				<verse number="22">ኑኃሚንም ምራትዋን ሩትን፦ ልጄ ሆይ፥ ከገረዶቹ ጋር ብትወጪ፥ በሌላም እርሻ ባያገኙሽ መልካም ነው አለቻት።</verse>
				<verse number="23">ሩትም የገብሱና የስንዴው መከር እስኪጨረስ ድረስ ልትቃርም የቦዔዝን ገረዶች ተጠጋች፣ በአማትዋም ዘንድ ትቀመጥ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">አማትዋም ኑኃሚን አለቻት፦ ልጄ ሆይ፥ መልካም እንዲሆንልሽ ዕረፍት አልፈልግልሽምን?</verse>
				<verse number="2">አሁንም ከገረዶቹ ጋር የነበርሽበት ቦዔዝ ዘመዳችን አይደለምን? እነሆ፥ እርሱ በዛሬ ሌሊት በአውድማው ላይ ገብሱን በመንሽ ይበትናል።</verse>
				<verse number="3">እንግዲህ ታጠቢ፥ ተቀቢ፥ ልብስሽን ተላበሺ፥ ወደ አውድማውም ውረጂ፣ ነገር ግን መብሉንና መጠጡን እስኪጨርስ ድረስ ለሰውዮው አትታዪው።</verse>
				<verse number="4">በተኛም ጊዜ የሚተኛበትን ስፍራ ተመልከቺ፥ ገብተሽም እግሩን ግለጪ፥ ተጋደሚም፣ የምታደርጊውንም እርሱ ይነግርሻል።</verse>
				<verse number="5">ሩትም፦ የተናገርሽኝን ሁሉ አደርጋለሁ አለቻት።</verse>
				<verse number="6">ወደ አውድማውም ወረደች፥ አማትዋም ያዘዘቻትን ሁሉ አደረገች።</verse>
				<verse number="7">ቦዔዝም ከበላና ከጠጣ ሰውነቱንም ደስ ካሰኘ በኋላ፥ በእህሉ ክምር አጠገብ ሊተኛ ሄደ፣ ሩትም በቀስታ መጣች፥ እግሩንም ገልጣ ተኛች።</verse>
				<verse number="8">መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ሰውዮው ደነገጠ፥ ዘወርም አለ፣ እነሆም፥ አንዲት ሴት በእግርጌው ተኝታ ነበረች።</verse>
				<verse number="9">እርሱም፦ ማን ነሽ? አለ። እርስዋም፦ እኔ ባሪያህ ሩት ነኝ፣ ዋርሳዬ ነህና ልብስህን በባሪያህ ላይ ዘርጋ አለችው።</verse>
				<verse number="10">ቦዔዝም አላት፦ ልጄ ሆይ፥ በእግዚአብሔር የተባረክሽ ሁኚ፣ ባለጠጋም ድሀም ብለሽ ጐበዛዝትን አልተከተልሽምና ከፊተኛው ይልቅ በመጨረሻው ጊዜ ቸርነት አድርገሻል።</verse>
				<verse number="11">አሁንም፥ ልጄ ሆይ፥ አትፍሪ፣ በአገሬ ያሉ ሕዝብ ሁሉ ምግባረ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ ያውቃሉና ያልሽውን ነገር ሁሉ አደርግልሻለሁ።</verse>
				<verse number="12">የቅርብ ዘመድ መሆኔ እውነት ነው፣ ነገር ግን ከእኔ የቀረበ ዘመድ አለ።</verse>
				<verse number="13">ዛሬ ሌሊት እደሪ፣ ነገም እርሱ ዋርሳ መሆን ቢወድድ መልካም ነው፥ ዋርሳ ይሁን፣ ዋርሳ ሊሆን ባይወድድ ግን፥ ሕያው እግዚአብሔርን እኔ ዋርሳ እሆንሻለሁ፣ እስኪነጋ ድረስ ተኚ።</verse>
				<verse number="14">እስኪነጋም በእግርጌው ተኛች፣ ቦዔዝም፦ ሴት ወደ አውድማው እንደ መጣች ማንም እንዳያውቅ ብሎ ነበርና ገና ሰውና ሰው ሳይተያይ ተነሣች።</verse>
				<verse number="15">እርሱም፦ የለበስሽውን ኩታ አምጥተሽ ያዢው አላት፣ በያዘችም ጊዜ ስድስት መስፈሪያ ገብስ ሰፈረላት አሸከማትም።</verse>
				<verse number="16">እርሱም ወደ ከተማይቱ ሄደ። ወደ አማትዋም መጣች፥ አማትዋም፦ ልጄ ሆይ እንዴት ነሽ? አለቻት፣ እርስዋም ሰውዮው ያደረገላትን ሁሉ ነገረቻት።</verse>
				<verse number="17">ወደ አማትሽ ባዶ እጅሽን አትሂጂ ብሎ ይህን ስድስት መስፈሪያ ገብስ ሰጠኝ አለቻት።</verse>
				<verse number="18">እርስዋም፦ ልጄ ሆይ፥ ሰውዮው ይህን ነገር ዛሬ እስኪጨርስ ድረስ አያርፍምና ፍጻሜው እስኪታወቅ ድረስ ዝም በዪ አለች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ቦዓዝም ወደ ከተማይቱ በር አደባባይ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ። እነሆም፥ ቦዔዝ ስለ እርሱ ይናገር የነበረው የቅርብ ዘመድ ሲያልፍ ቦዔዝ፦ አንተ ቀርበህ በዚህ ተቀመጥ አለው። እርሱም ቀረብ ብሎ ተቀመጠ።</verse>
				<verse number="2">ቦዔዝም ከከተማይቱ ሽማግሌዎች አሥር ሰዎች ጠርቶ፦ በዚህ ተቀመጡ አላቸው። እነርሱም ተቀመጡ።</verse>
				<verse number="3">ቦዔዝም የቅርብ ዘመዱን፦ ከሞዓብ ምድር የተመለሰችው ኑኃሚን የወንድማችንን የአቤሜሌክን ጢንጦ ትሸጣለች።</verse>
				<verse number="4">እኔም በዚህ በተቀመጡት በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊት እንድትገዛው አስታውቅህ ዘንድ አሰብሁ። መቤዠት ብትወድድ ተቤዥው፣ መቤዥት ባትወድድ ግን ከአንተ በቀር ሌላ ወራሽ የለምና፥ እኔም ከእንተ በኋላ ነኝና እንዳውቀው ንገረኝ አለው። እርሱም፦ እቤዥዋለሁ አለው።</verse>
				<verse number="5">ቦዔዝም፦ እርሻውን ከኑኃሚን እጅ በምትገዛበት ቀን፥ ለሞተው በርስቱ ስሙን እንድታስነሣለት ከምዋቹ ሚስት ከሞዓባዊቱ ከሩት ደግሞ ትገዛለህ አለ።</verse>
				<verse number="6">የቅርብ ዘመዱም፦ የራሴን ርስት እንዳላበላሽ መቤዠት አልችልም፣ እኔ መቤዠቱን አልችልምና አንተ ከእኔ መቤዠቱን ውሰደው አለ።</verse>
				<verse number="7">በጥንት ጊዜም፥ ማንም ቢሸጥ ቢለውጥም፥ ነገሩን ለማጽናት ሰው ጫማውን እንዲያወልቅ ለባልንጀራውም እንዲሰጠው በእስራኤል ዘንድ ልማድ ነበረ። ይህም በእስራኤል ምስክር ነበረ።</verse>
				<verse number="8">የቅርብ ዘመዱም ቦዔዝን፦ አንተ ግዛው አለው፣ ጫማውንም አወለቀ።</verse>
				<verse number="9">ቦዔዝም ሽማግሌዎችንና ሕዝቡን ሁሉ፦ ለአቤሜሌክና ለኬሌዎን ለመሐሎንም የነበረውን ሁሉ ከኑኃሚን እጅ እንደ ገዛሁ እናንተ ዛሬ ምስክሮች ናችሁ።</verse>
				<verse number="10">ደግሞም የምዋቹ ስም ከወንድሞቹ መካከል ከአገሩም ደጅ እንዳይጠፋ፥ የምዋቹን ስም በርስቱ ላይ እንዳስነሣ የመሐሎንን ሚስት ሞዓባዊቱን ሩትን ሚስት ትሆነኝ ዘንድ ወሰድሁአት፣ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ አላቸው።</verse>
				<verse number="11">በከተማይቱ በር አደባባይም የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ሽማግሌዎቹም፦ እኛ ምስክሮች ነን፣ እግዚአብሔር ይህችን ወደ ቤትህ የምትገባውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ሠሩ እንደ ሁለቱ እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርጋት፣ አንተም በኤፍራታ ባለ ጠጋ ሁን፥ ስምህም በቤተ ልሔም ይጠራ።</verse>
				<verse number="12">ቤትህም እግዚአብሔር ከዚህች ቈንጆ ከሚስጥህ ዘር ትዕማር ለይሁዳ እንደ ወለደች እንደ ፋሬስ ቤት ይሁን አሉት።</verse>
				<verse number="13">ቦዔዝም ሩትን ወሰደ፥ ሚስትም ሆነችው፣ ደረሰባትም፥ እግዚአብሔርም ፅንስ ለጣት፥ ወንድ ልጅም ወለደች።</verse>
				<verse number="14">ሴቶችም ኑኃሚንን፦ ዛሬ ዋርሳ ያላሳጣሽ እግዚአብሔር ይባረክ፣ ስሙም በእስራኤል ይጠራ።</verse>
				<verse number="15">ከሰባትም ወንዶች ልጆች ይልቅ ለአንቺ ከምትሻል ከምትወድድሽ ምራት ተወልዶአልና ሰውነትሽን ያሳድሰዋል፥ በእርጅናሽም ይመግብሻል አሉአት።</verse>
				<verse number="16">ኑኃሚንም ሕፃኑን ወሰደች አቀፈችውም፥ ሞግዚትም ሆነችው።</verse>
				<verse number="17">ሴቶችም ጎረቤቶችዋ፥ ለኑኃሚን ወንድ ልጅ ተወለደላት እያሉ ስም አወጡለት፣ ስሙንም ኢዮቤድ ብለው ጠሩት። እርሱም የዳዊት አባት የእሴይ አባት ነው።</verse>
				<verse number="18">የፋሬስም ትውልድ ይህ ነው፣ ፋሬስ ኤስሮምን ወለደ፥</verse>
				<verse number="19">ኤስሮምም አራምን ወለደ፥ አራምም አሚናዳብን ወለደ፥</verse>
				<verse number="20">አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፥ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፥</verse>
				<verse number="21">ሰልሞንም ቦዔዝን ወለደ፥</verse>
				<verse number="22">ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፥ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፥ እሴይም ዳዊትን ወለደ።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="9">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ከአ​ር​ማ​ቴም መሴፋ የሆነ አንድ ሰው ነበረ። ስሙም፥ የና​ሲብ ልጅ የቴቆ ልጅ፥ የኤ​ልዩ ልጅ ፥ የኢ​ያ​ር​ም​ያል ልጅ፥ ኤፍ​ራ​ታ​ዊው ሕል​ቃና ነበረ።</verse>
				<verse number="2">ሁለ​ትም ሚስ​ቶች ነበ​ሩት፤ የአ​ን​ዲቱ ስም ሐና፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ስም ፍናና ነበረ፤ ለፍ​ና​ናም ልጆች ነበ​ሩ​አት፤ ለሐና ግን ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​አ​ትም።</verse>
				<verse number="3">ያም ሰው በሴሎ ይሰ​ግድ ዘንድ፥ ለሠ​ራ​ዊት ጌታም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሠዋ ዘንድ ከከ​ተ​ማው ከአ​ር​ማ​ቴም በየ​ዓ​መቱ ይወጣ ነበር። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ካህ​ናት ሁለቱ የዔሊ ልጆች አፍ​ኒ​ንና ፊን​ሐስ በዚያ ነበሩ።</verse>
				<verse number="4">ሕል​ቃ​ናም የሚ​ሠ​ዋ​በት ቀን በደ​ረሰ ጊዜ ለሚ​ስቱ ለፍ​ና​ናና ለል​ጆ​ችዋ ሁሉ ዕድል ፋን​ታ​ቸ​ውን ሰጣ​ቸዉ።</verse>
				<verse number="5">ለሐ​ናም ልጅ ስላ​ል​ነ​በ​ራት አንድ ዕድል ፋንታ ሰጣት፤ ሕል​ቃ​ናም ከዚ​ያ​ች​ኛ​ይቱ ይልቅ ሐናን ይወ​ድድ ነበር። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ማኅ​ፀ​ን​ዋን ዘግቶ ነበር።</verse>
				<verse number="6">እንደ መከ​ራ​ዋና እንደ ኀዘ​ን​ዋም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ አል​ሰ​ጣ​ትም ነበር። ስለ​ዚ​ህም ታዝን ነበር። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማኅ​ፀ​ን​ዋን ዘግ​ት​ዋ​ልና፥ ልጆ​ች​ንም አል​ሰ​ጣ​ት​ምና።</verse>
				<verse number="7">በየ​ዓ​መ​ቱም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሚ​ወ​ጣ​በት ጊዜ እን​ዲህ ያደ​ርግ ነበር፤ እር​ስ​ዋም ትበ​ሳ​ጭና ታለ​ቅስ ነበር። እህ​ልም አት​በ​ላም ነበር።</verse>
				<verse number="8">ባልዋ ሕል​ቃ​ናም፥ “ሐና ሆይ!” አላት እር​ስ​ዋም፥ “ጌታዬ እነ​ሆኝ” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “ለምን ታለ​ቅ​ሻ​ለሽ? ለም​ንስ አት​በ​ዪም? ለም​ንስ ልብሽ ያዝ​ን​ብ​ሻል? እኔስ ከዐ​ሥር ልጆች አል​ሻ​ል​ሽ​ምን?” አላት።</verse>
				<verse number="9">በሴ​ሎም ከበሉ በኋላ ሐና ተነ​ሣች። በሴ​ሎም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆመች። ካህ​ኑም ዔሊ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ መቃን አጠ​ገብ በወ​ን​በሩ ላይ ተቀ​ምጦ ነበር።</verse>
				<verse number="10">እር​ስ​ዋም በል​ብዋ አዝና አለ​ቀ​ሰች፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸለ​የች።</verse>
				<verse number="11">እር​ስ​ዋም፥ “አዶ​ናይ፥ የሠ​ራ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! የባ​ር​ያ​ህን መዋ​ረድ ተመ​ል​ክ​ተህ ብታ​ስ​በኝ፥ ለባ​ር​ያ​ህም ወንድ ልጅ ብት​ሰጥ ዕድ​ሜ​ውን ሁሉ ለአ​ንተ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ የወ​ይን ጠጅና የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥም አይ​ጠ​ጣም። ምላ​ጭም በራሱ ላይ አይ​ደ​ር​ስም” ብላ ስእ​ለት ተሳ​ለች።</verse>
				<verse number="12">ጸሎ​ቷ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ባበ​ዛች ጊዜ፥ ካህኑ ዔሊ አፍ​ዋን ይመ​ለ​ከት ነበር።</verse>
				<verse number="13">ሐናም በል​ብዋ ትና​ገር ነበር፤ ድም​ፅ​ዋም ሳይ​ሰማ ከን​ፈ​ር​ዋን ታን​ቀ​ሳ​ቅስ ነበር፤ ዔሊም እንደ ሰከ​ረች ቈጠ​ራት።</verse>
				<verse number="14">የዔ​ሊም አገ​ል​ጋይ፦ “ስካ​ርሽ እስከ መቼ ነው? የወ​ይን ጠጅ​ሽን ከአ​ንቺ አር​ቂው፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ውጪ” አላት።</verse>
				<verse number="15">ሐናም መልሳ እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አይ​ደ​ለም፤ እኔስ ወራት የባ​ሳት ሴት ነኝ፤ ጠጅና ሌላ የሚ​ያ​ሰ​ክር ነገር አል​ጠ​ጣ​ሁም፤ ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነፍ​ሴን አፈ​ሰ​ስሁ፤</verse>
				<verse number="16">ኀዘ​ኔና ጭን​ቀቴ ስለ በዛ እስከ አሁን ድረስ እደ​ክ​ማ​ለ​ሁና ባር​ያ​ህን እንደ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ሴቶች ልጆች አት​ቍ​ጠ​ራት።”</verse>
				<verse number="17">ዔሊም፥ “በሰ​ላም ሂጂ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ከአ​ንቺ ጋር ይሁን የለ​መ​ን​ሽ​ው​ንም ልመና ሁሉ ይስ​ጥሽ” ብሎ መለ​ሰ​ላት።</verse>
				<verse number="18">እር​ስ​ዋም፥ “ባር​ያህ በፊ​ትህ ሞገ​ስን አገ​ኘች” አለ​ችው። ሴቲ​ቱም መን​ገ​ድ​ዋን ሄደች፤ ወደ ቤት​ዋም ገባች፤ ከባ​ሏም ጋር በላች፤ ጠጣ​ችም ፤ ፊቷም ከዚያ በኋላ አዘ​ን​ተኛ መስሎ አል​ታ​የም።</verse>
				<verse number="19">ማል​ደ​ውም ተነ​ሥ​ተው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰግ​ደው ሄዱ፤ ወደ ቤታ​ቸ​ውም ወደ አር​ማ​ቴም ደረሱ፤ ሕል​ቃ​ናም ሚስ​ቱን ሐናን ዐወ​ቃት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሰ​ባት፤ ፀነ​ሰ​ችም።</verse>
				<verse number="20">የመ​ው​ለ​ጃ​ዋም ወራት በደ​ረሰ ጊዜ ሐና ወንድ ልጅ ወለ​ደች፤ እር​ስ​ዋም፥ “ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለም​ኜ​ዋ​ለሁ” ስትል ስሙን “ሳሙ​ኤል” ብላ ጠራ​ችው።</verse>
				<verse number="21">ሰው​ዬ​ውም ሕል​ቃና ከቤተ ሰቡ ሁሉ ጋር የዓ​መ​ቱን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ስእ​ለ​ቱን፥ የም​ድ​ሩ​ንም ዐሥ​ራት ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ርብ ዘንድ ወጣ።</verse>
				<verse number="22">ሐና ግን ከእ​ርሱ ጋር አል​ወ​ጣ​ችም። ለባ​ል​ዋም፥ “ሕፃ​ኑን ጡት እስከ አስ​ጥ​ለው፥ ከእ​ኔም ጋር እስ​ኪ​ወ​ጣና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እስ​ኪ​ታይ ድረስ አል​ወ​ጣም፤ በዚ​ያም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል” ብላ​ዋ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="23">ባል​ዋም ሕል​ቃና፥ “በዐ​ይ​ንሽ ደስ ያሰ​ኘ​ሽን አድ​ርጊ፤ ጡትም እስ​ኪ​ተው ድረስ ተቀ​መጪ፤ ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ፍሽ የወ​ጣ​ውን ያጽና” አላት። ሴቲ​ቱም ልጅ​ዋን እያ​ጠ​ባች ጡት እስ​ኪ​ተው ድረስ ተቀ​መ​ጠች።</verse>
				<verse number="24">እር​ስ​ዋም ከእ​ርሱ ጋር አንድ የሦ​ስት ዓመት ወይ​ፈን፥ እን​ጀራ፥ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዱቄት፥ አንድ አቁ​ማዳ የወ​ይን ጠጅ ይዛ ወደ ሴሎ ወጣች። በሴ​ሎም ወዳ​ለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ገባች። ልጃ​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበረ።</verse>
				<verse number="25">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት አቀ​ረ​ቡት ፤ አባ​ቱም በየ​ዓ​መቱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሠ​ዋ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ሠዋ። ሕፃ​ኑ​ንም አቀ​ረ​በው፤ ወይ​ፈ​ኑ​ንም አረደ፤ እና​ቱም ሐና ሕፃ​ኑን ወደ ዔሊ አገ​ባ​ችው።</verse>
				<verse number="26">እር​ስ​ዋም አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ጸ​ለይ በዚህ በፊ​ትህ ቆማ የነ​በ​ረች ሴት እኔ ነኝ።</verse>
				<verse number="27">ስለ​ዚህ ልጅ ተሳ​ልሁ፤ ጸለ​ይ​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የለ​መ​ን​ሁ​ትን ልመ​ና​ዬን ሰጥ​ቶ​ኛል፤</verse>
				<verse number="28">እኔም ደግሞ ዕድ​ሜ​ውን ሙሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያገ​ለ​ግል ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰጥ​ቼ​ዋ​ለሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ሐናም ጸለ​የች፤ እን​ዲ​ህም አለች፦ “ልቤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸና፤ ቀን​ዴም በአ​ም​ላኬ በመ​ድ​ኀ​ኒቴ ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠ​ላ​ቶቼ ላይ ተከ​ፈተ፤ በማ​ዳ​ን​ህም ደስ ብሎ​ኛል።</verse>
				<verse number="2">እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ የለ​ምና፥ እንደ አም​ላ​ካ​ች​ንም ጻድቅ የለ​ምና፤ አቤቱ፥ ከአ​ን​ተም በቀር ቅዱስ የለም።</verse>
				<verse number="3">አት​መኩ፤ የኵ​ራት ነገ​ሮ​ች​ንም አት​ና​ገሩ፤ ፅኑዕ ነገ​ርም ከአ​ፋ​ችሁ አይ​ውጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ዐዋቂ ነውና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዙፋ​ኑን ያዘ​ጋ​ጃል።</verse>
				<verse number="4">የኀ​ያ​ላ​ንን ቀስት ሰብ​ሮ​አል፤ ደካ​ሞ​ች​ንም ኀይ​ልን አስ​ታ​ጥ​ቋ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="5">እን​ጀራ ጠግ​በው የነ​በሩ ተራቡ፤ ተር​በ​ውም የነ​በሩ ጠገቡ፤ መካ​ኒቱ ሰባት ወል​ዳ​ለ​ችና፥ ብዙም የወ​ለ​ደ​ችው መው​ለድ አል​ቻ​ለ​ችም።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገ​ድ​ላል፤ ያድ​ና​ልም፤ ወደ ሲኦል ያወ​ር​ዳል፤ ያወ​ጣ​ልም።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድሀ ያደ​ር​ጋል፤ ባለ​ጠ​ጋም ያደ​ር​ጋል፤ ያዋ​ር​ዳል፤ ደግ​ሞም ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋል።</verse>
				<verse number="8">ችግ​ረ​ኛ​ውን ከመ​ሬት ያነ​ሣ​ዋል፤ ምስ​ኪ​ኑ​ንም ከጕ​ድፍ ያነ​ሣ​ዋል፤ ከሕ​ዝቡ መኳ​ን​ንት ጋር ያስ​ቀ​ም​ጠው ዘንድ፥ የክ​ብ​ር​ንም ዙፋን ያወ​ር​ሰው ዘንድ።</verse>
				<verse number="9">ለሚ​ጸ​ልይ ጸሎ​ቱን ይሰ​ጠ​ዋል፤ የጻ​ድ​ቃ​ንን ዘመን ይባ​ር​ካል፤ የሰው ኀይል ጽኑዕ አይ​ደ​ለ​ምና።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶ​ቹን ያደ​ክ​ማ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ ቅዱስ ነው፤ ጥበ​በኛ በጥ​በቡ አይ​መካ፤ ኀይ​ለ​ኛም በኀ​ይሉ አይ​መካ፤ ሀብ​ታ​ምም በሀ​ብቱ አይ​መካ፤ የሚ​መካ ግን በዚህ ይመካ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በማ​ወ​ቅና በማ​ስ​ተ​ዋል፤ በም​ድ​ርም መካ​ከል ፍር​ድ​ንና እው​ነ​ትን በማ​ድ​ረግ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ሰማይ ወጣ፤ አን​ጐ​ደ​ጐ​ደም። ጻድቅ እርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈ​ር​ዳል፤ ለን​ጉ​ሦ​ቻ​ች​ንም ኀይ​ልን ይሰ​ጣል፤ የመ​ሲ​ሑ​ንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋል።”</verse>
				<verse number="11">በዚ​ያም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተዉት። እነ​ር​ሱም ወደ አር​ማ​ቴም ወደ ቤታ​ቸው ገቡ፤ ልጁም በካ​ህኑ በዔሊ ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያገ​ለ​ግል ነበር።</verse>
				<verse number="12">የካ​ህ​ኑም የዔሊ ልጆች ክፉ​ዎች ነበሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አያ​ው​ቁም ነበር።</verse>
				<verse number="13">መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሠዉ በሕ​ዝቡ ሁሉ ዘንድ የነ​በረ የካ​ህ​ኑ​ንም ሕግ አያ​ው​ቁም ነበረ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ መሥ​ዋ​ዕት በሠዉ ጊዜ የካ​ህኑ ብላ​ቴና ይመጣ ነበር፤ በእ​ጁም ሦስት ጣት ያለው ሜንጦ ነበር፤</verse>
				<verse number="14">ወደ ድስ​ቱም ወይም ወደ ምን​ቸቱ ወይም ወደ አፍ​ላሉ ወይም ወደ ቶፋው ይሰ​ድ​ደው ነበር። ሜን​ጦ​ውም ያወ​ጣ​ውን ሁሉ ካህኑ ለእ​ርሱ ይወ​ስ​ደው ነበር፤ በሴ​ሎም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊሠዉ በሚ​ወጡ በእ​ስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ሁሉ ላይ እን​ዲህ ያደ​ርጉ ነበር።</verse>
				<verse number="15">ደግ​ሞም ስቡ ሳይ​ጤስ የካ​ህኑ ልጅ መጥቶ የሚ​ሠ​ዋ​ውን ሰው፥ “ጥሬ​ውን እንጂ የተ​ቀ​ቀ​ለ​ውን ሥጋ ከአ​ንተ አይ​ወ​ስ​ድ​ምና እጠ​ብ​ስ​ለት ዘንድ ለካ​ህኑ ሥጋ ስጠኝ” ይለው ነበር።</verse>
				<verse number="16">የሚ​ሠ​ዋ​ውም ሰው፥ “አስ​ቀ​ድሞ እንደ ሕጉ ስቡ ይጢስ፤ ኋላም ሰው​ነ​ት​ህን ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኛ​ትን ትወ​ስ​ዳ​ለህ” ቢለው፥ እርሱ፥ “አይ​ሆ​ንም፥ ነገር ግን አሁን ስጠኝ፤ ካል​ሆ​ነም በግድ አወ​ስ​ደ​ዋ​ለሁ” ይለው ነበር።</verse>
				<verse number="17">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቍር​ባን ይንቁ ነበ​ርና የዔሊ ልጆች ኀጢ​አት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጅግ ታላቅ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="18">ሳሙ​ኤል ግን ገና ብላ​ቴና ሳለ የበ​ፍታ ኤፉድ ታጥቆ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያገ​ለ​ግል ነበር።</verse>
				<verse number="19">እና​ቱም ታናሽ መደ​ረ​ቢያ ሠራ​ች​ለት፤ በየዓ​መ​ቱም መሥ​ዋ​ዕት ለመ​ሠ​ዋት ከባ​ልዋ ጋር ስት​ወጣ ትወ​ስ​ድ​ለት ነበር።</verse>
				<verse number="20">ዔሊም ሕል​ቃ​ና​ንና ሚስ​ቱን ባረ​ካ​ቸው፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አገ​ባ​ኸው ስጦታ ፈንታ ከዚ​ህች ሴት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘር ይስ​ጥህ” አለው፤ እነ​ር​ሱም ወደ ቤታ​ቸው ገቡ።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሐናን ጐበኘ፤ ዳግ​መ​ኛም ፀነ​ሰች፥ ሦስት ወን​ዶ​ችና ሁለት ሴቶች ልጆ​ችን ወለ​ደች። ብላ​ቴ​ናው ሳሙ​ኤ​ልም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አደገ።</verse>
				<verse number="22">ዔሊም እጅግ አረጀ፤ ልጆ​ቹም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ያደ​ረ​ጓ​ቸ​ውን፥ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ከሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉት ሴቶ​ችም ጋር እን​ደ​ሚ​ተኙ ሰማ።</verse>
				<verse number="23">እር​ሱም አላ​ቸው፥ “ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ሁሉ አፍ የም​ሰ​ማ​ውን ይህን ነገር ለምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="24">ልጆቼ ሆይ፥ ይህ አይ​ሆ​ንም፤ እኔ የም​ሰ​ማው ይህ ነገር መል​ካም አይ​ደ​ለ​ምና እን​ዲህ አታ​ድ​ርጉ። ሕዝ​ቡ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከማ​ገ​ል​ገል አት​ከ​ል​ክ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">ሰውስ ሰውን ቢበ​ድል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ል​ዩ​ለ​ታል፤ ሰው ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቢበ​ድል ስለ እርሱ ወደ ማን ይጸ​ል​ዩ​ለ​ታል?” እነ​ርሱ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው ወድ​ዶ​አ​ልና የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን ቃል አል​ሰ​ሙም።</verse>
				<verse number="26">ብላ​ቴ​ናው ሳሙ​ኤ​ልም አደገ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ውም ፊት ሞገስ እያ​ገኘ ሄደ።</verse>
				<verse number="27">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ እን​ዲህ አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በግ​ብፅ በፈ​ር​ዖን ቤት ባሪ​ያ​ዎች ሳሉ ለአ​ባ​ትህ ቤት ተገ​ለ​ጥሁ፤</verse>
				<verse number="28">ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገድ ሁሉ ካህን ይሆ​ነኝ ዘንድ፥ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዬም ላይ ይሠዋ ዘንድ፥ ዕጣ​ን​ንም ያጥን ዘንድ፥ ኤፉ​ድ​ንም በፊቴ ይለ​ብስ ዘንድ፥ የአ​ባ​ት​ህን ቤት ለእኔ መረ​ጥ​ሁት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች የእ​ሳት ቍር​ባን ሁሉ ስለ ምግብ ለአ​ባ​ትህ ቤት ሰጠሁ።</verse>
				<verse number="29">በመ​ሥ​ዋ​ዕቴ ላይና በዕ​ጣኔ ላይ ስለ ምን በክፉ ዐይን ተመ​ለ​ከ​ትህ? የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በፊቴ ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት መሥ​ዋ​ዕት ሁሉ በቀ​ዳ​ም​ያቱ ስለ አከ​በ​ር​ሁህ ከእኔ ይልቅ ልጆ​ች​ህን ለምን መረ​ጥህ?</verse>
				<verse number="30">ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ው​ነት ቤትህ፥ የአ​ባ​ት​ህም ቤት፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በፊቴ እን​ዲ​ኖር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አሁን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያከ​በ​ሩ​ኝን አከ​ብ​ራ​ለ​ሁና፥ የና​ቁ​ኝም ይና​ቃ​ሉና ይህ አይ​ሆ​ን​ል​ኝም።</verse>
				<verse number="31">እነሆ፥ ዘር​ህ​ንም፥ የአ​ባ​ት​ህ​ንም ቤት ዘር የማ​ጠ​ፋ​በት ዘመን ይመ​ጣል፤</verse>
				<verse number="32">በቤ​ት​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሽማ​ግሌ አይ​ገ​ኝም።</verse>
				<verse number="33">በዐ​ይ​ኖቹ የሚ​ፈ​ጽም በነ​ፍ​ሱም የሚ​ተጋ ሰውን ከመ​ሠ​ዊ​ያዬ አላ​ጠ​ፋም። ከቤ​ትህ የሚ​ቀ​ሩት ሰዎች ሁሉ ግን በጐ​ል​ማ​ሶች ሰይፍ ይሞ​ታሉ።</verse>
				<verse number="34">ይህ በሁ​ለቱ ልጆ​ችህ በአ​ፍ​ኒ​ንና በፊ​ን​ሐስ ላይ የሚ​መጣ ለአ​ንተ ምል​ክት ነው፤ ሁለቱ በአ​ንድ ቀን በጦር ይሞ​ታሉ።</verse>
				<verse number="35">የታ​መነ ካህን ለእኔ አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ በል​ቤም፥ በነ​ፍ​ሴም እን​ዳለ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋል፤ እኔም የታ​መነ ቤት እሠ​ራ​ለ​ታ​ለሁ፤ ዘመ​ኑን ሁሉ እኔ በቀ​ባ​ሁት ሰው ፊት ይሄ​ዳል።</verse>
				<verse number="36">ከቤ​ት​ህም የቀ​ረው ሁሉ ይመ​ጣል፤ ከካ​ህ​ና​ትም ወደ አን​ዲቱ ዕጣ፥ እን​ጀራ ወደ​ም​በ​ላ​በት እባ​ክህ ላከኝ ብሎ ለአ​ንድ ብር መሐ​ልቅ ለቍ​ራሽ እን​ጀራ በፊቱ ይሰ​ግ​ዳል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ብላ​ቴ​ናው ሳሙ​ኤ​ልም በዔሊ ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያገ​ለ​ግል ነበር፤ በዚ​ያም ዘመን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ክቡር ነበረ፤ ራእ​ይም አይ​ገ​ለ​ጥም ነበር።</verse>
				<verse number="2">በዚ​ያም ዘመን እን​ዲህ ሆነ፤ ዔሊም በስ​ፍ​ራው ተኝቶ ሳለ፥ ዐይ​ኖቹ መፍ​ዘዝ ጀም​ረው ነበር። ማየ​ትም አይ​ች​ልም ነበር።</verse>
				<verse number="3">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መብ​ራት ገና አል​ጠ​ፋም ነበር፤ ሳሙ​ኤ​ልም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ባለ​በት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ ተኝቶ ነበር፤</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ሳሙ​ኤል! ሳሙ​ኤል” ብሎ ጠራው፤ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ” አለ።</verse>
				<verse number="5">ወደ ዔሊም ሮጠ፥ “እነ​ሆኝ ስለ ጠራ​ኸኝ መጣሁ” አለው። እር​ሱም፥ “አል​ጠ​ራ​ሁ​ህም፤ ተመ​ል​ሰህ ተኛ” አለው። ሄዶም ተኛ።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ፥ “ሳሙ​ኤል! ሳሙ​ኤል” ብሎ ጠራው። ሳሙ​ኤ​ልም ተነ​ሥቶ ዳግ​መኛ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “እነ​ሆኝ ስለ ጠራ​ኸኝ መጣሁ” አለ። እር​ሱም፥ “አል​ጠ​ራ​ሁ​ህም ተመ​ል​ሰህ ተኛ” አለው።</verse>
				<verse number="7">ሳሙ​ኤል ግን ከዚህ በፊት ገና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ወ​ቀም ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ገና አል​ተ​ገ​ለ​ጠ​ለ​ትም ነበር።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን እንደ ገና ሦስ​ተኛ ጊዜ ጠራው። እር​ሱም ተነ​ሥቶ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “እነ​ሆኝ ስለ ጠራ​ኸኝ መጣሁ” አለ። ዔሊም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን እንደ ጠራው አስ​ተ​ዋለ።</verse>
				<verse number="9">ዔሊም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ልጄ፥ ሄደህ ተኛ፤ ቢጠ​ራ​ህም፦ አቤቱ፥ ባሪ​ያህ ይሰ​ማ​ልና ተና​ገር በለው፥” አለው። ሳሙ​ኤ​ልም ሄዶ በስ​ፍ​ራው ተኛ።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መጥቶ ቆመ፤ እንደ ቀድ​ሞ​ውም ጠራው። ሳሙ​ኤ​ልም፥ “ባሪ​ያህ ይሰ​ማ​ልና ተና​ገር” አለ።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን አለው፥ “እነሆ የሰ​ማ​ውን ሁሉ ሁለ​ቱን ጆሮ​ዎ​ቹን ጭው የሚ​ያ​ደ​ርግ ነገ​ሬን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">በዚ​ያም ቀን በቤቱ ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ሁሉ በዔሊ ላይ አጸ​ና​ለሁ፤ እኔም ጀምሬ እፈ​ጽ​ም​በ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">ልጆቹ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ክፉ እን​ዳ​ደ​ረጉ ዐውቆ አል​ገ​ሠ​ጻ​ቸ​ው​ምና ስለ ልጆቹ ኀጢ​አት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቤቱን እን​ደ​ም​በ​ቀል አስ​ታ​ው​ቄ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">ስለ​ዚ​ህም የዔሊ ቤት ኀጢ​አት በዕ​ጣ​ንና በመ​ሥ​ዋ​ዕት ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዳ​ይ​ሰ​ረ​ይ​ለት ለዔሊ ቤት ምያ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="15">ሳሙ​ኤ​ልም እስ​ኪ​ነጋ ተኛ፥ ማል​ዶም ተነ​ሥቶ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ደጅ ከፈተ። ሳሙ​ኤ​ልም ራእ​ዩን ለዔሊ መን​ገር ፈራ።</verse>
				<verse number="16">ዔሊም ሳሙ​ኤ​ልን ጠርቶ፥ “ልጄ ሳሙ​ኤል ሆይ፥” አለ፤ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ” አለ።</verse>
				<verse number="17">እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የነ​ገ​ረህ ነገር ምን​ድን ነው? ከእኔ አት​ሸ​ሽግ፤ ከነ​ገ​ረ​ህና ከሰ​ማ​ኸው ነገር ሁሉ የሸ​ሸ​ግ​ኸኝ እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ያድ​ር​ግ​ብህ፤ እን​ዲ​ህም ይጨ​ም​ር​ብህ” አለው።</verse>
				<verse number="18">ሳሙ​ኤ​ልም ነገ​ሩን ሁሉ ነገ​ረው፤ አን​ዳ​ችም አል​ሸ​ሸ​ገ​ውም። ዔሊም፥ “እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ደስ ያሰ​ኘ​ውን ያድ​ርግ” አለ።</verse>
				<verse number="19">ሳሙ​ኤ​ልም አደገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ከቃ​ሉም አን​ዳች በም​ድር ላይ አይ​ወ​ድ​ቅም ነበር።</verse>
				<verse number="20">እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ ሳሙ​ኤል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ ይሆን ዘንድ የታ​መነ እንደ ሆነ ዐወቀ።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ በሴሎ ተገ​ለጠ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሳ​ሙ​ኤል ይገ​ለ​ጥ​ለት ነበ​ርና። ሳሙ​ኤ​ልም ከም​ድር ዳርቻ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ እንደ ሆነ ታመነ። ዔሊም እጅግ አረጀ፥ ልጆቹ ግን በክ​ፋት ጸን​ተው ኖሩ፤ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት እን​ዲህ ሆነ። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ለጦ​ር​ነት በእ​ስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ላይ ተሰ​በ​ሰቡ። እስ​ራ​ኤ​ልም ሊዋ​ጉ​አ​ቸው ወጡ፤ በአ​ቤ​ኔ​ዜር አጠ​ገ​ብም ሰፈሩ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም በአ​ፌቅ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="2">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እስ​ራ​ኤ​ልን ለመ​ው​ጋት ተሰ​ለፉ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሸሹ፤ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ፊት ድል ሆኑ፤ ጦር​ነት በተ​ደ​ረ​ገ​በ​ትም ስፍራ ከእ​ስ​ራ​ኤል አራት ሺህ ሰዎች ተገ​ደሉ።</verse>
				<verse number="3">ሕዝ​ቡም ወደ ሰፈር በተ​መ​ለሱ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ “ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ስለ​ምን ጣለን? በፊ​ታ​ችን እን​ድ​ት​ሄድ፥ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ንም እጅ እን​ድ​ታ​ድ​ነን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ከሴሎ እና​ምጣ” አሉ።</verse>
				<verse number="4">ሕዝ​ቡም ወደ ሴሎ ላኩ፤ በኪ​ሩ​ቤ​ልም ላይ የሚ​ቀ​መ​ጠ​ውን የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ከዚያ አመጡ፤ ሁለ​ቱም የዔሊ ልጆች አፍ​ኒ​ንና ፊን​ሐስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት ጋር በዚያ ነበሩ።</verse>
				<verse number="5">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ሰፈር በገ​ባች ጊዜ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ታላቅ እል​ልታ አደ​ረጉ፤ ምድ​ሪ​ቱም አስ​ተ​ጋ​ባች።</verse>
				<verse number="6">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የእ​ል​ል​ታ​ውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ “በዕ​ብ​ራ​ው​ያን ሰፈር ያለው ይህ ታላቅ የእ​ል​ልታ ድምፅ ምን​ድን ነው?” አሉ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ወደ ሰፈሩ እንደ ደረ​ሰች አስ​ተ​ዋሉ።</verse>
				<verse number="7">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ፈር​ተው፥ “አማ​ል​ክት ወደ እነ​ርሱ ወደ ሰፈር መጥ​ተ​ዋል” አሉ። ደግ​ሞም እን​ዲህ አሉ፥ “ወዮ​ልን! አቤቱ፥ ዛሬ አድ​ነን፤ ከዚህ አስ​ቀ​ድሞ እን​ዲህ ያለ ነገር አል​ሆ​ነ​ምና።</verse>
				<verse number="8">ወዮ​ልን! ከእ​ነ​ዚህ ኀያ​ላን አማ​ል​ክት እጅ ማን ያድ​ነ​ናል? እነ​ዚህ አማ​ል​ክት ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በም​ድረ በዳ በልዩ ልዩ መቅ​ሠ​ፍት የመቱ ናቸው።</verse>
				<verse number="9">እና​ንተ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሆይ! በርቱ፤ ጐብዙ፤ እና​ንተ ባሪ​ያ​ዎች እን​ዳ​ደ​ረ​ጋ​ች​ኋ​ቸው ዕብ​ራ​ው​ያን ባሪ​ያ​ዎች እን​ዳ​ያ​ደ​ር​ጓ​ችሁ በርቱ፤ ተዋጉ።”</verse>
				<verse number="10">ከዚ​ህም በኋላ ተዋ​ጉ​አ​ቸው፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ወደቁ፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ወደ ድን​ኳ​ና​ቸው ሸሹ፤ እጅ​ግም ታላቅ ግድያ ሆነ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሠላሳ ሺህ እግ​ረ​ኞች ወደቁ።</verse>
				<verse number="11">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ተማ​ረ​ከች፤ ሁለ​ቱም የዔሊ ልጆች አፍ​ኒ​ንና ፊን​ሐስ ሞቱ።</verse>
				<verse number="12">በዚ​ያም ቀን አንድ የብ​ን​ያም ሰው ከሰ​ልፍ እየ​በ​ረረ ወደ ሴሎ መጣ፤ ልብ​ሱም ተቀ​ድዶ ነበር፤ በራ​ሱም ላይ ትቢያ ነስ​ንሶ ነበር።</verse>
				<verse number="13">በመ​ጣም ጊዜ ዔሊ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ልቡ ተና​ውጦ ነበ​ርና በመ​ን​ገድ ዳር በወ​ን​በሩ ላይ ተቀ​ምጦ ይጠ​ባ​በቅ ነበር፤ ሰው​ዬ​ውም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ገብቶ ባወራ ጊዜ ከተ​ማ​ዪቱ ሁሉ ተጭ​ዋ​ጭ​ዋ​ኸች።</verse>
				<verse number="14">ዔሊም የጩ​ኸ​ቱን ድምፅ በሰማ ጊዜ፥ “ይህ ጩኸት ምን​ድን ነው?” አለ። ሰው​ዬ​ውም ፈጥኖ መጣና ለዔሊ ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="15">ዔሊም የዘ​ጠና ስም​ንት ዓመት ሽማ​ግሌ ነበረ፤ ዐይ​ኖ​ቹም ፈዝ​ዘው አያ​ይም ነበር።</verse>
				<verse number="16">ሰው​ዬ​ው​ንም፥ “አንተ ከወ​ዴት ነህ?” አለው። እር​ሱም፥ “ጦር​ነቱ ከአ​ለ​በት ስፍራ የመ​ጣሁ እኔ ነኝ፥ ዛሬም ከሰ​ልፍ ሸሸሁ” አለ። እር​ሱም፥ “ልጄ ሆይ! ነገ​ሩስ እን​ዴት ሆነ?” አለው።</verse>
				<verse number="17">ያም ሰው መልሶ፥ “እስ​ራ​ኤል ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ሸሹ፤ ደግ​ሞም በሕ​ዝቡ ዘንድ ታላቅ ግድያ ሆኖ​አል፥ ሁለ​ቱም ልጆ​ችህ አፍ​ኒ​ንና ፊን​ሐስ ሞተ​ዋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ተማ​ር​ካ​ለች” አለው።</verse>
				<verse number="18">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ባሰ​ባት ጊዜ በበሩ አጠ​ገብ ካለው ከወ​ን​በሩ ወደቀ፤ እርሱ ሸም​ግሎ፥ ደን​ግ​ዞም ነበ​ርና ጀር​ባው ተሰ​ብሮ ሞተ። እር​ሱም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አርባ ዓመት ፈራጅ ነበረ።</verse>
				<verse number="19">ምራ​ቱም የፊ​ን​ሐስ ሚስት አር​ግዛ ልት​ወ​ልድ ተቃ​ርባ ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት እንደ ተማ​ረ​ከች፥ አማ​ቷና ባል​ዋም እንደ ሞቱ በሰ​ማች ጊዜ አለ​ቀ​ሰች፤ ከዚ​ያም በኋላ ወለ​ደች። ሕማ​ም​ዋም ተመ​ለ​ሰ​ባት።</verse>
				<verse number="20">ወደ ሞትም በቀ​ረ​በች ጊዜ በዙ​ሪ​ያዋ ያሉት ሴቶች “ወንድ ልጅ ወል​ደ​ሻ​ልና አት​ፍሪ” አሉ​አት። እር​ስዋ ግን አል​መ​ለ​ሰ​ች​ላ​ቸ​ውም፤ ልብ​ዋም አያ​ስ​ታ​ው​ስም ነበር።</verse>
				<verse number="21">እር​ስ​ዋም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ስለ ተማ​ረ​ከች፥ ስለ አማ​ቷና ስለ ባል​ዋም፦ የሕ​ፃ​ኑን ስም ዊቦ​ር​ኮ​ኢ​ቦት ብላ ጠራ​ችው።</verse>
				<verse number="22">እነ​ር​ሱም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ተማ​ር​ካ​ለ​ችና ክብር ከእ​ስ​ራ​ኤል ለቀቀ” አሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወሰ​ዱ​አት፤ ከአ​ቤ​ኔ​ዜ​ርም ወደ አዛ​ጦን ይዘ​ዋት መጡ።</verse>
				<verse number="2">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወስ​ደው ወደ ዳጎን ቤት አገ​ቡ​አት፤ በዳ​ጎ​ንም አጠ​ገብ አኖ​ሩ​አት።</verse>
				<verse number="3">በነ​ጋ​ውም የአ​ዛ​ጦን ሰዎች ማለዱ፤ ወደ ዳጎ​ንም ቤት ገቡ፤ እነ​ሆም፥ ዳጎን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ወድቆ አገ​ኙት፤ ዳጎ​ን​ንም አን​ሥ​ተው በስ​ፍ​ራው አቆ​ሙት።</verse>
				<verse number="4">በነ​ጋ​ውም ማለዱ፤ እነ​ሆም፥ ዳጎን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳን ታቦት ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ወድቆ ነበር፤ የዳ​ጎ​ንም ራስ፥ ሁለቱ እጆ​ቹም ተቈ​ር​ጠው እየ​ራ​ሳ​ቸው በመ​ድ​ረኩ ላይ ወድ​ቀው ነበር፤ ሁለቱ መሀል እጆ​ቹም በወ​ለሉ ላይ ወድ​ቀው ነበር። የዳ​ጎ​ንም ደረት ብቻ​ውን ቀርቶ ነበር።</verse>
				<verse number="5">ስለ​ዚ​ህም የዳ​ጎን ካህ​ናት፥ ወደ ዳጎን ቤት የሚ​ገ​ቡ​ትም ሁሉ በአ​ዛ​ጦን ያለ​ውን የዳ​ጎ​ንን መድ​ረክ እስከ ዛሬ ድረስ አይ​ረ​ግ​ጡም፤ ይራ​መ​ዱት ነበር እንጂ።</verse>
				<verse number="6">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በአ​ዛ​ጦን ሰዎች ላይ ከበ​ደች፤ ክፉም ነገር አመ​ጣ​ች​ባ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ በመ​ር​ከ​ቦች ውስጥ ወጣ፤ የአ​ዛ​ጦ​ን​ንና የአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ዋ​ንም ሰዎች የው​ስጥ አካ​ላ​ቸ​ውን በዕ​ባጭ መታ፤ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም መካ​ከል አይ​ጦች ወጡ፤ በከ​ተ​ማ​ውም ታላቅ መቅ​ሠ​ፍት ሆነ።</verse>
				<verse number="7">የአ​ዛ​ጦ​ንም ሰዎች እን​ዲህ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ፥ “እጁ በእ​ኛና በአ​ም​ላ​ካ​ችን በዳ​ጎን ላይ ጠን​ክ​ራ​ለ​ችና የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ታቦት ከእኛ ዘንድ አት​ቀ​መጥ” አሉ።</verse>
				<verse number="8">ልከ​ውም የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን አለ​ቆች ወደ እነ​ርሱ ሰበ​ሰ​ቡና፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ታቦት ምን እና​ድ​ርግ?” አሉ፤ የጌት ሰዎ​ችም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ታቦት ወደ እኛ ትዙር” ብለው መለሱ። የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ታቦ​ትም ወደ ጌት ሄደች።</verse>
				<verse number="9">ከሄ​ደ​ችም በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በከ​ተ​ማ​ዪቱ ላይ መጣች፤ ታላቅ ሁከ​ትም ሆነ፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ሰዎች ታላ​ቁ​ንም ታና​ሹ​ንም መታ፤ የው​ስጥ አካ​ላ​ቸ​ው​ንም በእ​ባጭ መታ​ቸው፤ የጌት ሰዎ​ችም የው​ስጥ አካ​ላ​ቸ​ውን ምስል ሠሩ፥</verse>
				<verse number="10">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ወደ አስ​ቀ​ሎና ላኩ​አት። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ወደ አስ​ቀ​ሎና በመ​ጣች ጊዜ አስ​ቀ​ሎ​ና​ው​ያን፥ “እኛ​ንና ሕዝ​ባ​ች​ንን ልታ​ስ​ገ​ድ​ሉን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ታቦት ለምን አመ​ጣ​ች​ሁ​ብን?” ብለው ጮኹ።</verse>
				<verse number="11">ልከ​ውም የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን አለ​ቆች ሁሉ ሰብ​ስ​በው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ታቦት ስደ​ዱ​አት፤ እኛ​ንና ሕዝ​ባ​ች​ንን እን​ዳ​ት​ገ​ድል በስ​ፍ​ራዋ ትቀ​መጥ” አሉ።</verse>
				<verse number="12">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ወደ​ዚያ በገ​ባች ጊዜ በከ​ተ​ማው ሁሉ ታላቅ ሁከት ሆኖ​አ​ልና። በሕ​ይ​ወ​ትም ያሉ፥ ያል​ሞ​ቱ​ትም ሰዎች በእ​ባጭ ተመቱ፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ዋይታ እስከ ሰማይ ወጣ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገር ሰባት ወር ተቀ​መ​ጠች። ምድ​ራ​ቸ​ውም አይ​ጦ​ችን አወ​ጣች።</verse>
				<verse number="2">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ካህ​ና​ት​ንና ምዋ​ር​ተ​ኞ​ችን ጠን​ቋ​ዮ​ች​ንም ጠር​ተው፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ላይ ምን እና​ድ​ርግ? ወደ ስፍ​ራ​ዋስ በምን እን​ስ​ደ​ዳት? አስ​ታ​ው​ቁን” አሉ።</verse>
				<verse number="3">እነ​ር​ሱም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ብት​ሰ​ድ​ዱ​አት ስለ አሳ​ዘ​ና​ች​ሁ​አት የበ​ደል መባእ ስጡ እንጂ ባዶ​ዋን አት​ስ​ደ​ዱ​አት፤ የዚ​ያን ጊዜም ትፈ​ወ​ሳ​ላ​ችሁ፤ ስር​የ​ትም ይደ​ረ​ግ​ላ​ች​ኋል፤ አለ​ዚያ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ከእ​ና​ንተ አይ​ር​ቅም” አሉ።</verse>
				<verse number="4">እነ​ር​ሱም፥ “ስለ መቅ​ሠ​ፍቱ የም​ን​ሰ​ጠው የበ​ደል መባእ ምን​ድን ነው?” አሉ። እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉ፥ “እና​ን​ተ​ንና አለ​ቆ​ቻ​ች​ሁን፥ ሕዝ​ባ​ች​ሁ​ንም ያገ​ኘች መቅ​ሠ​ፍት አን​ዲት ናትና እንደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች ቍጥር አም​ስት የወ​ርቅ እባ​ጮች፥ አም​ስ​ትም የወ​ርቅ አይ​ጦች አቅ​ርቡ።</verse>
				<verse number="5">እጁ ከእ​ና​ን​ተና ከአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ችሁ፥ ከም​ድ​ራ​ች​ሁም ይቀ​ልል ዘንድ፥ የእ​ባ​ጫ​ች​ሁን ምሳሌ፥ ምድ​ራ​ች​ሁ​ንም የሚ​ያ​ጠ​ፉ​ትን የአ​ይ​ጦ​ችን ምሳሌ አድ​ር​ጋ​ችሁ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ክብ​ርን ስጡ።</verse>
				<verse number="6">ግብ​ጻ​ው​ያ​ንና ፈር​ዖ​ንም ልባ​ቸ​ውን እን​ዳ​ጸኑ ልባ​ች​ሁን ለምን ታጸ​ና​ላ​ችሁ? በተ​ዘ​ባ​በ​ቱ​ባ​ቸው ጊዜ ያወ​ጡ​አ​ቸው አይ​ደ​ሉ​ምን? እነ​ር​ሱም አል​ሄ​ዱ​ምን?</verse>
				<verse number="7">አሁ​ንም ወስ​ዳ​ችሁ አን​ዲት አዲስ ሰረ​ገላ ሥሩ፤ የሚ​ያ​ጠ​ቡም፥ ቀን​በር ያል​ተ​ጫ​ነ​ባ​ቸ​ውን ሁለት ላሞች በሰ​ረ​ገላ ጥመ​ዱ​አ​ቸው፤ እን​ቦ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለይ​ታ​ችሁ ወደ ቤት መል​ሱ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ወስ​ዳ​ችሁ በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ አኑ​ሩ​አት፤ ስለ​በ​ደል መባእ ካሳ አድ​ር​ጋ​ችሁ ያቀ​ረ​ባ​ች​ሁ​ትን የወ​ር​ቁ​ንም ዕቃ በሣ​ጥን ውስጥ አድ​ር​ጋ​ችሁ በታ​ቦቷ አጠ​ገብ አኑ​ሩት፤ ትሄ​ድም ዘንድ ስደ​ዱ​አት።</verse>
				<verse number="9">ወደ​ም​ት​ሄ​ድ​በ​ትም ተመ​ል​ከቱ፤ በድ​ን​በ​ሩም መን​ገድ ላይ ወደ ቤት​ሳ​ሚስ ብት​ወጣ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ያደ​ረ​ገ​ብን እርሱ ነው፤ አለ​ዚ​ያም እን​ዲ​ያው መጥ​ቶ​ብ​ናል እንጂ የመ​ታን የእ​ርሱ እጅ እን​ዳ​ል​ሆነ እና​ው​ቃ​ለን።”</verse>
				<verse number="10">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ የሚ​ያ​ጠ​ቡ​ትን ሁለ​ቱን ላሞች ወሰዱ፤ በሰ​ረ​ገ​ላ​ውም ጠመ​ዱ​አ​ቸው፤ እን​ቦ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በቤት ዘጉ​ባ​ቸው፤</verse>
				<verse number="11">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት፥ የወ​ርቁ አይ​ጦ​ችና የአ​ካ​ላ​ቸው እባ​ጮች ምሳሌ ያሉ​በ​ት​ንም ሣጥን በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ጫኑ።</verse>
				<verse number="12">ላሞ​ችም ወደ ቤት​ሳ​ሚስ ወደ​ሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ አቅ​ን​ተው “እምቧ” እያሉ በጎ​ዳ​ናው ላይ ሄዱ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላ​ሉም፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆ​ችም እስከ ቤት​ሳ​ሚስ ዳርቻ ድረስ በኋላ በኋላ ይሄዱ ነበር።</verse>
				<verse number="13">የቤ​ት​ሳ​ሚስ ሰዎ​ችም በእ​ርሻ ውስጥ ስንዴ ያጭዱ ነበር፤ ዐይ​ና​ቸ​ው​ንም ከፍ አድ​ር​ገው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት አዩ፤ ደስ ብሎ​አ​ቸ​ውም ተቀ​በ​ሉ​አት።</verse>
				<verse number="14">ሰረ​ገ​ላ​ውም ወደ ቤት​ሳ​ሚ​ሳ​ዊው ወደ ኦሴዕ እርሻ መጣ፤ ታላ​ቅም ድን​ጋይ በነ​በ​ረ​በት በዚያ ቆመ፤ የሰ​ረ​ገ​ላ​ው​ንም ዕን​ጨት ፈል​ጠው ላሞ​ቹን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ።</verse>
				<verse number="15">ሌዋ​ው​ያ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት፥ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር የነ​በ​ረ​ውን የወ​ርቅ ዕቃ ያለ​በ​ትን ሣጥን አወ​ረዱ፤ በታ​ላ​ቁም ድን​ጋይ ላይ አኖ​ሩት፤ በዚ​ያም ቀን የቤ​ት​ሳ​ሚስ ሰዎች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን አቀ​ረቡ።</verse>
				<verse number="16">እነ​ዚ​ያም የፍ​ልስጥኤ​ማ​ው​ያን አም​ስቱ አለ​ቆች አይ​ተው በዚ​ያው ቀን ወደ አስ​ቀ​ሎና ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="17">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ስለ በደል መባእ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ረ​ቡ​አ​ቸው የሰ​ው​ነ​ታ​ቸው ምሳሌ የወ​ርቅ እባ​ጮች እነ​ዚህ ናቸው፦ አን​ዲቱ ለአ​ዛ​ጦን፥ አን​ዲ​ቱም ለጋዛ፥ አን​ዲ​ቱም ለአ​ስ​ቀ​ሎና፥ አን​ዲ​ቱም ለጌት፥ አን​ዲ​ቱም ለአ​ቃ​ሮን።</verse>
				<verse number="18">የወ​ር​ቁም አይ​ጦች ቍጥር ለአ​ም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች እንደ ነበ​ሩት ከተ​ሞች ሁሉ ቍጥር እን​ዲሁ ነበረ፤ እነ​ር​ሱም እስከ ታላቁ ድን​ጋይ የሚ​ደ​ርሱ ቅጥር ያላ​ቸው ከተ​ሞ​ችና የፌ​ር​ዜ​ዎን መን​ደ​ሮች ናቸው። በዚ​ህም ድን​ጋይ ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት አስ​ቀ​መጡ፤ ድን​ጋ​ዩም እስከ ዛሬ ድረስ በቤ​ት​ሳ​ሚ​ሳ​ዊው በኦ​ሴዕ እርሻ አለ።</verse>
				<verse number="19">የኢ​ያ​ኮ​ንዩ ልጆ​ችም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት ተመ​ል​ክ​ተው ከቤ​ት​ሳ​ሚስ ሰዎች ጋር አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​አ​ትም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሕ​ዝቡ አም​ስት ሺህ ሰባ ሰዎ​ችን መታ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕዝ​ቡን በታ​ላቅ ግዳይ ስለ መታ ሕዝቡ አለ​ቀሱ።</verse>
				<verse number="20">የቤ​ት​ሳ​ሚ​ስም ሰዎች፥ “በዚህ በቅ​ዱሱ አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ማለፍ ማን ይች​ላል? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ከእኛ ወጥታ ወደ ማን ትሄ​ዳ​ለች?” አሉ።</verse>
				<verse number="21">በቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪ​ምም ወደ ተቀ​መ​ጡት ሰዎች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ልከው፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት መል​ሰ​ዋል፤ ወር​ዳ​ች​ሁም ወደ እና​ንተ ውሰ​ዱ​አት” አሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">የቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ሰዎ​ችም መጥ​ተው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት አወጡ፤ በኮ​ረ​ብ​ታ​ውም ላይ ወዳ​ለው ወደ አሚ​ና​ዳብ ቤት አገ​ቡ​አት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት እን​ዲ​ጠ​ብቅ ልጁን አል​ዓ​ዛ​ርን ቀደ​ሱት።</verse>
				<verse number="2">ታቦ​ቲ​ቱም በቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ከተ​ቀ​መ​ጠ​ች​በት ቀን ጀምሮ ወራቱ ረዘመ፤ ሃያ ዓመ​ትም ሆነ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ አዝኖ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተከ​ተለ።</verse>
				<verse number="3">ሳሙ​ኤ​ልም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ሁሉ፥ “በሙሉ ልባ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተ​መ​ለ​ሳ​ችሁ እን​ግ​ዶ​ችን አማ​ል​ክ​ትና ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አርቁ፤ ልባ​ች​ሁ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅኑ፤ እር​ሱ​ንም ብቻ አም​ልኩ፤ እር​ሱም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ያድ​ና​ች​ኋል” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የበ​ዓ​ሊ​ምን አማ​ል​ክ​ትና የአ​ስ​ጣ​ሮ​ትን ምስ​ሎች አራቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ብቻ አመ​ለኩ።</verse>
				<verse number="5">ሳሙ​ኤ​ልም፥ “እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ወደ መሴፋ ሰብ​ስቡ፤ ስለ እና​ን​ተም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጸ​ል​ያ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="6">እነ​ር​ሱም ወደ መሴፋ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ውኃም ቀድ​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በም​ድር ላይ አፈ​ሰሱ፤ በዚ​ያም ቀን ጾሙ፤ በዚ​ያም፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በድ​ለ​ናል” አሉ። ሳሙ​ኤ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ በመ​ሴፋ ፈረደ።</verse>
				<verse number="7">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ መሴፋ እንደ ተሰ​በ​ሰቡ በሰሙ ጊዜ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ዘመቱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሰም​ተው ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ፈሩ።</verse>
				<verse number="8">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እኛ ከመ​ጮኽ ዝም አት​በል። እር​ሱም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ያድ​ነ​ናል” አሉት።</verse>
				<verse number="9">ሳሙ​ኤ​ልም አንድ የበግ ጠቦት ወስዶ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈጽሞ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አድ​ርጎ ከሕ​ዝቡ ጋር አቀ​ረ​በው፤ ሳሙ​ኤ​ልም ስለ እስ​ራ​ኤል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማው።</verse>
				<verse number="10">ሳሙ​ኤ​ልም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ሲያ​ሣ​ርግ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ሊዋጉ ቀረቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚ​ያች ቀን በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ላይ ታላቅ የነ​ጐ​ድ​ጓድ ድምፅ አን​ጐ​ደ​ጐደ፤ ደነ​ገ​ጡም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ፊት ድል ተመቱ።</verse>
				<verse number="11">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ከመ​ሴፋ ወጡ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም አሳ​ደዱ፤ በቤ​ኮር ታችም እስ​ኪ​ደ​ርሱ ድረስ መቱ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">ሳሙ​ኤ​ልም አንድ ድን​ጋይ ወስዶ በመ​ሴ​ፋና በአ​ሮ​ጌው ከተማ መካ​ከል አኖ​ረው፤ ስሙ​ንም፥ “እስከ አሁን ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረድ​ቶ​ናል” ሲል “አቤ​ን​ኤ​ዜር” ብሎ ጠራው። እብነ ረድ​ኤት ማለት ነው።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን አዋ​ረ​ዳ​ቸው፤ ዳግ​መ​ኛም ከዚያ ወዲያ ወደ እስ​ራ​ኤል ድን​በር አል​ወ​ጡም፤ በሳ​ሙ​ኤ​ልም ዘመን ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ላይ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="14">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ከአ​ስ​ቀ​ሎና ጀምሮ እስከ፤ ጌት ድረስ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የወ​ሰ​ዱ​አ​ቸው ከተ​ሞች ለእ​ስ​ራ​ኤል ተመ​ለሱ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ድን​በ​ሩን ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ወሰዱ። በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በአ​ሞ​ራ​ው​ያን መካ​ከ​ልም ሰላም ሆነ።</verse>
				<verse number="15">ሳሙ​ኤ​ልም በዘ​መኑ ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ይፈ​ርድ ነበር።</verse>
				<verse number="16">በየ​ዓ​መ​ቱም ወደ ቤቴል፥ ወደ ጌል​ጌ​ላና ወደ መሴፋ ይዞር ነበር፤ በእ​ነ​ዚ​ያም በተ​ቀ​ደሱ ስፍ​ራ​ዎች ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ይፈ​ርድ ነበር።</verse>
				<verse number="17">ቤቱም በዚያ ነበ​ረና ወደ አር​ማ​ቴም ይመ​ለስ ነበር፤ በዚ​ያም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ይፈ​ርድ ነበር፤ በዚ​ያም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሠራ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሳሙ​ኤል በሸ​መ​ገለ ጊዜ ልጆ​ቹን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈራ​ጆች አድ​ርጎ ሾማ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">የል​ጆ​ቹም ስሞች እነ​ዚህ ነበሩ። የበ​ኵር ልጁ ስም ኢዩ​ኤል፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ስም አብያ ነበረ። እነ​ር​ሱም በቤ​ር​ሳ​ቤህ ፈራ​ጆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="3">ልጆ​ቹም በመ​ን​ገዱ አል​ሄ​ዱም፤ ነገር ግን ረብ ለማ​ግ​ኘት ፈቀቅ አሉ፤ መማ​ለጃ በሉ፤ ፍርድ አደሉ።</verse>
				<verse number="4">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​ብ​ስ​በው ወደ ሳሙ​ኤል ወደ አር​ማ​ቴም መጡ፤</verse>
				<verse number="5">እን​ዲ​ህም አሉት፥ “እነሆ፥ አንተ ሸም​ግ​ለ​ሃል፤ ልጆ​ች​ህም በመ​ን​ገ​ድህ አይ​ሄ​ዱም፤ አሁ​ንም እንደ ሌሎች አሕ​ዛብ ሁሉ የሚ​ፈ​ር​ድ​ልን ንጉሥ አን​ግ​ሥ​ልን።”</verse>
				<verse number="6">“የሚ​ፈ​ር​ድ​ልን ንጉሥ ስጠን” ባሉት ጊዜም ነገሩ ሳሙ​ኤ​ልን አስ​ከ​ፋው፤ ሳሙ​ኤ​ልም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለየ።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን አለው፥ “በእ​ነ​ርሱ ላይ እን​ዳ​ል​ነ​ግሥ እኔን ናቁ እንጂ አን​ተን አል​ና​ቁ​ምና በሚ​ሉህ ነገር ሁሉ የሕ​ዝ​ቡን ቃል ስማ።</verse>
				<verse number="8">ከግ​ብፅ ካወ​ጣ​ኋ​ቸው ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን ትተው እን​ግ​ዶች አማ​ል​ክ​ትን በማ​ም​ለ​ካ​ቸው እንደ ሠሩት ሥራ ሁሉ እን​ዲሁ በአ​ንተ ደግሞ ያደ​ር​ጉ​ብ​ሃል።</verse>
				<verse number="9">አሁ​ንም ቃላ​ቸ​ውን ስማ፤ ነገር ግን ጽኑ ምስ​ክር መስ​ክ​ር​ባ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ የሚ​ነ​ግ​ሠ​ውን የን​ጉ​ሡን ሥር​ዐት ንገ​ራ​ቸው።”</verse>
				<verse number="10">ሳሙ​ኤ​ልም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሁሉ ንጉ​ሥን ለፈ​ለጉ ሕዝብ ነገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">እን​ዲ​ህም አለ፥ “በእ​ና​ንተ ላይ የሚ​ነ​ግ​ሠው የን​ጉሡ ሥር​ዐት ይህ ነው፤ ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ወስዶ ሰረ​ገላ ነጂ​ዎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም ፊት ይሮ​ጣሉ፤</verse>
				<verse number="12">ለራ​ሱም የሻ​ለ​ቆ​ችና የመቶ አለ​ቆች የአ​ምሳ አለ​ቆ​ችም ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ እር​ሻ​ው​ንም የሚ​ያ​ርሱ፥ እህ​ሉ​ንም የሚ​ያ​ጭዱ፥ ፍሬ​ው​ንም የሚ​ለ​ቅሙ፥ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ው​ንና የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም ዕቃ የሚ​ሠሩ ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="13">ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም ወስዶ ሽቱ ቀማ​ሚ​ዎ​ችና ወጥ ቤቶች፥ አበ​ዛ​ዎ​ችም ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="14">እር​ሻ​ች​ሁ​ንና ወይ​ና​ች​ሁ​ንም፥ መል​ካም መል​ካ​ሙ​ንም የዘ​ይት ቦታ​ች​ሁን ወስዶ ለሎ​ሌ​ዎቹ ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="15">ከዘ​ራ​ች​ሁና ከወ​ይ​ና​ች​ሁም ዐሥ​ራት ወስዶ ለጃ​ን​ደ​ረ​ቦ​ቹና ለሎ​ሌ​ዎቹ ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="16">ሎሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁ​ንና ገረ​ዶ​ቻ​ች​ሁን፥ ከከ​ብ​ቶ​ቻ​ች​ሁና ከአ​ህ​ዮ​ቻ​ች​ሁም መል​ካም መል​ካ​ሙን ወስዶ ያሠ​ራ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="17">ከላ​ሞ​ቻ​ችሁ፥ ከበ​ጎ​ቻ​ች​ሁና ከፍ​የ​ሎ​ች​ቻ​ች​ሁም ዐሥ​ራት ይወ​ስ​ዳል፤ እና​ን​ተም ባሪ​ያ​ዎች ትሆ​ኑ​ታ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="18">በዚ​ያም ቀን ለእ​ና​ንተ ከመ​ረ​ጣ​ች​ሁት ከን​ጉ​ሣ​ችሁ የተ​ነሣ ትጮ​ኻ​ላ​ችሁ፤ በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ሰ​ማ​ች​ሁም። ለራ​ሳ​ችሁ ንጉሥ መር​ጣ​ች​ኋ​ልና።”</verse>
				<verse number="19">ሕዝቡ ግን የሳ​ሙ​ኤ​ልን ነገር ይሰሙ ዘንድ እንቢ አሉ፥ “እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አን​ግ​ሥ​ልን፤</verse>
				<verse number="20">እኛም ደግሞ እንደ አሕ​ዛብ ሁሉ እን​ሆ​ና​ለን፤ ንጉ​ሣ​ች​ንም ይፈ​ር​ድ​ል​ናል፤ በፊ​ታ​ች​ንም ወጥቶ ስለ እኛ ጠላ​ታ​ች​ንን ይዋ​ጋል” አሉት።</verse>
				<verse number="21">ሳሙ​ኤ​ልም የሕ​ዝ​ቡን ቃል ሁሉ ሰማ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ቃላ​ቸ​ውን ስማ፤ ንጉ​ሥም አን​ግ​ሥ​ላ​ቸው” አለው። ሳሙ​ኤ​ልም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰዎች፥ “እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ወደ ከተ​ማ​ችሁ ሂዱ” አላ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">ከብ​ን​ያም ልጆች ስሙ ቂስ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ፥ እር​ሱም የአ​ብ​ሔል ልጅ፥ የያ​ሬድ ልጅ፥ የባ​ሔር ልጅ፥ የብ​ን​ያም ሰው፥ የአ​ፌቅ ልጅ፥ ጽኑዕ ኀያል ሰው ነበረ።</verse>
				<verse number="2">ለእ​ር​ሱም ሳኦል የሚ​ባል የተ​መ​ረጠ መል​ካም ልጅ ነበ​ረው፤ በም​ድር ሁሉ ላይ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከእ​ርሱ ይልቅ መል​ካም የሆነ ሰው አል​ነ​በ​ረም፤ ከሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ይልቅ ከት​ከ​ሻ​ውና ከዚ​ያም በላይ ቁመቱ ዘለግ ያለ ነበረ።</verse>
				<verse number="3">የሳ​ኦ​ልም አባት የቂስ አህ​ዮች ጠፍ​ተው ነበር፤ ቂስም ልጁን ሳኦ​ልን፥ “ከብ​ላ​ቴ​ኖቹ አን​ዱን ወስ​ደህ ተነ​ሡና ሄዳ​ችሁ አህ​ዮ​ችን ፈልጉ” አለው።</verse>
				<verse number="4">ወደ ተራ​ራ​ማ​ውም ወደ ኤፍ​ሬም ሀገር ሄዱ፤ በሲ​ልካ ምድ​ርም አለፉ፤ አላ​ገ​ኙ​አ​ቸ​ው​ምም፤ በፋ​ስ​ቂም ምድር አለፉ፤ በዚ​ያም አል​ነ​በ​ሩም፤ በኢ​ያ​ሚ​ንም ምድር አለፉ፤ አላ​ገ​ኙ​አ​ቸ​ው​ምም።</verse>
				<verse number="5">ወደ መሴፋ ምድ​ርም በደ​ረሱ ጊዜ ሳኦል ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ረ​ውን ብላ​ቴና፥ “አባቴ ስለ አህ​ዮች ማሰ​ብን ትቶ ስለ እኛ እን​ዳ​ይ​ጨ​ነቅ፥ ና፤ እን​መ​ለስ” አለው።</verse>
				<verse number="6">ብላ​ቴ​ና​ውም፥ “እነሆ፥ አንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በዚ​ህች ከተማ አለ፤ እር​ሱም የተ​ከ​በረ ሰው ነው፤ የሚ​ና​ገ​ረው ሁሉ በእ​ው​ነት ይፈ​ጸ​ማል፤ አሁ​ንም ወደ​ዚያ እን​ሂድ፤ ምና​ል​ባት የም​ን​ሄ​ድ​በ​ትን መን​ገድ ይነ​ግ​ረ​ና​ልና” አለው።</verse>
				<verse number="7">ሳኦ​ልም አብ​ሮት ያለ​ውን ብላ​ቴና፥ “እነሆ! እን​ሄ​ዳ​ለን፤ ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ምን እን​ወ​ስ​ድ​ለ​ታ​ለን? እን​ጀራ ከከ​ረ​ጢ​ታ​ችን አል​ቆ​አ​ልና፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው የም​ን​ወ​ስ​ድ​ለት ምንም የለ​ንም” አለው።</verse>
				<verse number="8">ብላ​ቴ​ናው ደግሞ ለሳ​ኦል መልሶ፥ “እነሆ፥ በእጄ የብር ሰቅል ሩብ አለኝ፤ እር​ሱ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ፤ የም​ን​ሄ​ድ​በ​ትን መን​ገ​ድም ይነ​ግ​ረ​ናል።</verse>
				<verse number="9">ቀድሞ ነቢ​ዩን ባለ ራእይ ይሉት ነበ​ርና አስ​ቀ​ድሞ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመ​ጠ​የቅ ሲሄድ፦ ኑ፤ ወደ ባለ ራእይ እን​ሂድ ይል ነበር።”</verse>
				<verse number="10">ሳኦ​ልም ብላ​ቴ​ና​ውን፥ “የተ​ና​ገ​ር​ኸው ነገር መል​ካም ነው፤ ና፤ እን​ሂድ” አለ​ውና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወዳ​ለ​በት ከተማ ሄዱ።</verse>
				<verse number="11">በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ዳገት በወጡ ጊዜ ቈነ​ጃ​ጅት ውኃ ሊቀዱ ሲወጡ አገ​ኙና፥ “ባለ ራእይ በዚህ አለ ወይ?” አሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">ቈነ​ጃ​ጅ​ቱም፥ “አዎን እነሆ፥ በፊ​ታ​ችሁ ነው። ዛሬ ወደ ከተ​ማ​ዪቱ መጥ​ቶ​አ​ልና፥ ዛሬም ሕዝቡ በባማ ኮረ​ብታ ላይ መሥ​ዋ​ዕት ማቅ​ረብ አለ​ባ​ቸ​ውና።</verse>
				<verse number="13">ወደ ከተ​ማ​ዪ​ቱም በገ​ባ​ችሁ ጊዜ ለመ​ብ​ላት ወደ ባማ ኮረ​ብታ ሳይ​ወጣ በከ​ተ​ማው ውስጥ ታገ​ኙ​ታ​ላ​ችሁ፤ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን እርሱ የሚ​ባ​ርክ ስለ​ሆነ እርሱ ሳይ​ወጣ ሕዝቡ ምንም አይ​ቀ​ም​ሱ​ምና፥ ከዚ​ያም በኋላ እን​ግ​ዶች ይበ​ላ​ሉና፤ በዚ​ህም ጊዜ ታገ​ኙ​ታ​ላ​ች​ሁና አሁን ውጡ” አሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">ወደ ከተ​ማ​ዪ​ቱም ወጡ፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም መካ​ከል በገቡ ጊዜ እነሆ፥ ሳሙ​ኤል ወደ ባማ ኮረ​ብታ ለመ​ው​ጣት ወደ እነ​ርሱ መጣ።</verse>
				<verse number="15">ገናም ሳኦል ሳይ​መጣ ከአ​ንድ ቀን በፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሳ​ሙ​ኤል ጆሮ​ውን ከፈ​ተ​ለት፥</verse>
				<verse number="16">እን​ዲ​ህም አለው፥ “ነገ በዚ​ህች ሰዓት ከብ​ን​ያም ሀገር አንድ ሰው እል​ክ​ል​ሃ​ለሁ፤ ልቅ​ሶ​አ​ቸው ወደ እኔ ስለ ደረሰ የሕ​ዝ​ቤን ሥቃ​ያ​ቸ​ውን ተመ​ል​ክ​ች​አ​ለ​ሁና ለሕ​ዝቤ ለእ​ስ​ራ​ኤል አለቃ ይሆን ዘንድ ትቀ​ባ​ዋ​ለህ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ ሕዝ​ቤን ያድ​ናል።”</verse>
				<verse number="17">ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን ባየ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ያ የነ​ገ​ር​ሁህ ሰው እነሆ፤ እር​ሱም በሕ​ዝቤ ላይ ይነ​ግ​ሣል” አለው።</verse>
				<verse number="18">ሳኦ​ልም በበሩ ወደ ሳሙ​ኤል ቀርቦ፥ “የባለ ራእዩ ቤት ወዴት እንደ ሆነ፥ እባ​ክህ፥ ንገ​ረኝ” አለው።</verse>
				<verse number="19">ሳሙ​ኤ​ልም መልሶ ሳኦ​ልን፥ “ባለ ራእዩ እኔ ነኝ፤ ዛሬም ከእኔ ጋር ወደ ባማ ኮረ​ብታ በፊቴ ውጣና ምሳ ብላ፤ ነገም በጥ​ዋት አሰ​ና​ብ​ት​ሃ​ለሁ፤ በል​ብ​ህም ያለ​ውን ነገር ሁሉ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="20">ከሦ​ስት ቀንም በፊት የጠፉ አህ​ዮ​ችህ ተገ​ኝ​ተ​ዋ​ልና ልብ​ህን አታ​ስ​ጨ​ን​ቀው። የእ​ስ​ራ​ኤል መል​ካም ምኞት ለማን ነው? ለአ​ን​ተና ለአ​ባ​ትህ ቤት አይ​ደ​ለ​ምን?” አለው።</verse>
				<verse number="21">ሳኦ​ልም መልሶ፥ “እኔ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ከሚ​ያ​ንስ ወገን የሆ​ንሁ ብን​ያ​ማዊ ሰው አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ወገ​ኔስ ከብ​ን​ያም ነገድ ወገ​ኖች ሁሉ የሚ​ያ​ንስ አይ​ደ​ለ​ምን? እን​ዲ​ህስ ያለ​ውን ነገር ለምን ነገ​ር​ኸኝ?” አለ።</verse>
				<verse number="22">ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ል​ንና ብላ​ቴ​ና​ውን ወስዶ ወደ አዳ​ራሽ አገ​ባ​ቸው፥ ሰባ ሰዎ​ችም ምሳ በሚ​በ​ሉ​በት በም​ር​ፋቁ ራስ አስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው፤</verse>
				<verse number="23">ሳሙ​ኤ​ልም ወጥ ቤቱን፥ “በአ​ንተ ዘንድ አኑ​ረው ብዬ የሰ​ጠ​ሁ​ህን እድል ፋንታ አምጣ” አለው።</verse>
				<verse number="24">ወጥ​ቤ​ቱም ወር​ቹን አም​ጥቶ በሳ​ኦል ፊት አኖ​ረው። ሳሙ​ኤ​ልም፥ “ሳኦ​ልን ለም​ስ​ክር ከባ​ል​ን​ጀ​ራህ ተለ​ይቶ ቀር​ቦ​ል​ሃ​ልና እነሆ፥ በል​ተህ የተ​ረ​ፈ​ህን በፊ​ትህ አኑር” አለው። በዚ​ያም ቀን ሳኦል ከሳ​ሙ​ኤል ጋር በላ።</verse>
				<verse number="25">ከባማ ኮረ​ብ​ታም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ወረዱ፤ ሳሙ​ኤ​ልም ለሳ​ኦል በሰ​ገ​ነቱ ላይ መኝታ አዘ​ጋ​ጀ​ለት፤ እር​ሱም ተኛ።</verse>
				<verse number="26">ማል​ደ​ውም ተነሡ፤ በነ​ጋም ጊዜ ሳሙ​ኤል ሳኦ​ልን፥ “ከሰ​ገ​ነቱ ላይ ጠርቶ፦ ተነ​ሣና ላሰ​ና​ብ​ትህ” አለው። ሳኦ​ልም ተነሣ፤ እር​ሱና ሳሙ​ኤ​ልም ሁለቱ ወደ ሜዳ ወጡ።</verse>
				<verse number="27">እነ​ር​ሱም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዳር ሲወ​ርዱ ሳሙ​ኤል ሳኦ​ልን፥ “ብላ​ቴ​ናው ወደ ፊታ​ችን እን​ዲ​ያ​ልፍ እዘ​ዘው፤ አንተ ግን ከእኔ ጋር ከዚህ ቁምና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ” አለው። ብላ​ቴ​ና​ውም አለፈ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">ሳሙ​ኤ​ልም የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ወስዶ በራሱ ላይ አፈ​ሰ​ሰው፤ ሳመ​ውም፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “በሕ​ዝቡ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ትነ​ግሥ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀብ​ቶ​ሃል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሕዝብ ትገ​ዛ​ለህ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ካሉ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ ታድ​ና​ቸ​ዋ​ለህ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በር​ስቱ ላይ ትነ​ግሥ ዘንድ እንደ ቀባህ ምል​ክቱ ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">ዛሬ ከእኔ በተ​ለ​የህ ጊዜ በብ​ን​ያም ግዛት በቤ​ቴል አው​ራጃ በራ​ሔል መቃ​ብር አጠ​ገብ ሁለት ሰዎች እየ​ቸ​ኰሉ ሲሄዱ ታገ​ኛ​ለህ፤ እነ​ር​ሱም፦ ልት​ፈ​ል​ጉ​አ​ቸው ሂዳ​ችሁ የነ​በ​ራ​ች​ሁ​ላ​ቸው አህ​ዮች ተገ​ኝ​ተ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ አባ​ትህ ስለ አህ​ዮቹ ማሰብ ትቶ፦ የል​ጄን ነገር እን​ዴት አደ​ር​ጋ​ለሁ? እያለ ስለ እና​ንተ ይጨ​ነ​ቃል ይሉ​ሃል።</verse>
				<verse number="3">ከዚ​ያም ደግሞ አል​ፈህ፥ ወደ ትልቁ የታ​ቦር ዛፍ ትደ​ር​ሳ​ለህ፤ በዚ​ያም ሦስት ሰዎች፥ አንዱ ሦስት የፍ​የል ጠቦ​ቶች ሲነዳ፥ ሁለ​ተ​ኛው ሦስት የዳቦ ስልቻ፥ ሦስ​ተ​ኛ​ውም የወ​ይን ጠጅ አቁ​ማዳ ይዘው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ታገ​ኛ​ለህ፤</verse>
				<verse number="4">ሰላ​ም​ታም ይሰ​ጡ​ሃል፤ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዎ​ቹን ሁለት ዳቦ​ዎ​ችም ይሰ​ጡ​ሃል፤ ከእ​ጃ​ቸ​ውም ትቀ​በ​ላ​ለህ።</verse>
				<verse number="5">ከዚ​ያም በኋላ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጭፍራ ወዳ​ለ​በት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኮረ​ብታ ትመ​ጣ​ለህ፤ በዚ​ያም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው ናሴብ አለ፤ ወደ​ዚ​ያም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ በደ​ረ​ስህ ጊዜ በገ​ናና ከበሮ፥ እም​ቢ​ል​ታና መሰ​ንቆ ይዘው ትን​ቢት እየ​ተ​ና​ገሩ ከኰ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ የሚ​ወ​ርዱ የነ​ቢ​ያ​ትን ጉባኤ ታገ​ኛ​ለህ።</verse>
				<verse number="6">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በአ​ንተ ይወ​ር​ዳል፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ትን​ቢት ትና​ገ​ራ​ለህ፤ እንደ ሌላም ሰው ሆነህ ትለ​ወ​ጣ​ለህ።</verse>
				<verse number="7">እነ​ዚ​ህም ምል​ክ​ቶች በደ​ረ​ሱህ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና እጅህ የም​ት​ች​ለ​ውን ሁሉ አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="8">በፊ​ቴም ወደ ጌል​ገላ ትወ​ር​ዳ​ለህ፤ እኔም እነሆ፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ርብ ዘንድ፥ የደ​ኅ​ን​ነ​ት​ንም መሥ​ዋ​ዕት እሠዋ ዘንድ ወደ አንተ እወ​ር​ዳ​ለሁ፤ እኔ ወደ አንተ እስ​ክ​መ​ጣና የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን እስ​ከ​ም​ነ​ግ​ርህ ድረስ ሰባት ቀን ትቈ​ያ​ለህ።”</verse>
				<verse number="9">ከሳ​ሙ​ኤ​ልም ዘንድ ለመ​ሄድ ፊቱን በመ​ለሰ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሌላ ልብ ለወ​ጠ​ለት፤ በዚ​ያም ቀን እነ​ዚህ ምል​ክ​ቶች ሁሉ ደረ​ሱ​ለት።</verse>
				<verse number="10">ወደ​ዚ​ያም ኮረ​ብታ በደ​ረሰ ጊዜ፥ እነሆ፥ የነ​ቢ​ያት ጉባኤ አገ​ኙት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ ወረደ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ትን​ቢት ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="11">ቀድ​ሞም የሚ​ያ​ው​ቁት ሁሉ በነ​ቢ​ያት መካ​ከል ባዩት ጊዜ ሕዝቡ እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “በቂስ ልጅ ላይ የሆ​ነው ምን​ድን ነው? በውኑ ሳኦል ከነ​ቢ​ያት ወገን ነውን?” ተባ​ባሉ።</verse>
				<verse number="12">ከዚ​ያም ስፍራ ያለ አንድ ሰው፥ “አባ​ቱስ ማን ነው?” ብሎ መለሰ። ስለ​ዚ​ህም “ሳኦል ደግሞ ከነ​ቢ​ያት ወገን ነውን?” የሚል ምሳሌ ሆነ።</verse>
				<verse number="13">ትን​ቢት መና​ገ​ሩ​ንም በፈ​ጸመ ጊዜ ወደ ኮረ​ብ​ታው ወጣ።</verse>
				<verse number="14">ከቤተ ሰቡም አንዱ እር​ሱ​ንና ብላ​ቴ​ና​ውን፥ “ወዴት ሄዳ​ችሁ ኖሮ​አል?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “አህ​ዮ​ችን ልን​ፈ​ልግ ሄደን ነበር፤ ባጣ​ና​ቸ​ውም ጊዜ ወደ ሳሙ​ኤል መጣን” አሉት።</verse>
				<verse number="15">ያም ቤተ ሰብ፥ “ሳሙ​ኤል ምን አለ? እባ​ክህ! ንገ​ረኝ” አለው፤</verse>
				<verse number="16">ሳኦ​ልም ለቤተ ሰቡ፥ “አህ​ዮች እንደ ተገኙ ገለ​ጠ​ልን” አለው፤ ነገር ግን የመ​ን​ግ​ሥ​ትን ነገር አላ​ወ​ራ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="17">ሳሙ​ኤ​ልም ሕዝ​ቡን ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ እን​ዲ​ሄዱ አዘ​ዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ አወ​ጣሁ፤ ከግ​ብፅ ንጉሥ ከፈ​ር​ዖ​ንም እጅ፥ ከሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ች​ሁም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ እጅ አዳ​ን​ኋ​ችሁ’ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">ዛሬ ግን ከመ​ከ​ራ​ች​ሁና ከጭ​ን​ቃ​ችሁ ሁሉ ያዳ​ና​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ንቃ​ችሁ፦ ‘እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አን​ግ​ሥ​ልን’ አላ​ች​ሁት። አሁ​ንም በየ​ነ​ገ​ዳ​ች​ሁና በየ​ወ​ገ​ና​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቁሙ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">ሳሙ​ኤ​ልም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ነገ​ዶች ሁሉ አቀ​ረበ፤ ዕጣ​ውም በብ​ን​ያም ወገን ላይ ወደቀ።</verse>
				<verse number="21">የብ​ን​ያ​ም​ንም ነገድ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው አቀ​ረበ፤ ዕጣ​ውም በማ​ጥር ወገን ላይ ወደቀ፤ የማ​ጥ​ር​ንም ወገን በየ​ሰዉ አቀ​ረበ፤ ዕጣ​ውም በቂስ ልጅ በሳ​ኦል ላይ ወደቀ፤ ፈለ​ገ​ውም፤ አላ​ገ​ኘ​ው​ምም።</verse>
				<verse number="22">ሳሙ​ኤ​ልም፦ ያ ሰው እዚህ ይመጣ እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “እነሆ፥ በዕቃ መካ​ከል ተሸ​ሽ​ጎ​አል” ብሎ መለሰ።</verse>
				<verse number="23">እር​ሱም ሮጦ ከዚያ አመ​ጣው፤ እር​ሱም በሕ​ዝቡ መካ​ከል አቆ​መው፤ ከሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ይልቅ ረዥም ነበረ፤ ሕዝ​ቡም ከት​ከ​ሻው በታች ሆኑ።</verse>
				<verse number="24">ሳሙ​ኤ​ልም ለሕ​ዝቡ ሁሉ፥ “ከሕ​ዝቡ ሁሉ እር​ሱን የሚ​መ​ስል እንደ ሌለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ረ​ጠ​ውን ታያ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “ንጉሥ ሕያው ይሁን” እያሉ እል​ልታ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="25">ሳሙ​ኤ​ልም የን​ጉ​ሡን ሥር​ዐት ነገ​ራ​ቸው፤ በመ​ጽ​ሐ​ፍም ጻፈው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት አኖ​ረው። ሳሙ​ኤ​ልም ሕዝ​ቡን ሁሉ ወደ እየ​ቤ​ታ​ቸው አሰ​ና​በ​ታ​ቸው። ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ እየ​ቤ​ታ​ቸው ሄዱ።</verse>
				<verse number="26">ሳኦ​ልም ወደ ቤቱ ወደ ገባ​ዖን ሄደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልባ​ቸ​ውን የነ​ካው ኀያ​ላ​ንም ከሳ​ኦል ጋር ሄዱ።</verse>
				<verse number="27">ክፉ​ዎች ሰዎች ግን፥ “ያድ​ነን ዘንድ ይህ ሰው ማን ነው?” ብለው ናቁት፤ እጅ መን​ሻም አላ​መ​ጡ​ለ​ትም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከአ​ንድ ወር በኋላ አሞ​ና​ዊው ናዖስ መጣ፤ በኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓ​ድም ሰፈረ፤ የኢ​ያ​ቢ​ስም ሰዎች ሁሉ፥ “አሞ​ና​ዊ​ውን ናዖ​ስን ቃል ኪዳን አድ​ር​ግ​ልን፤ እኛም እን​ገ​ዛ​ል​ሃ​ለን” አሉት።</verse>
				<verse number="2">አሞ​ና​ዊው ናዖ​ስም፦“ ቀኝ ዐይ​ና​ች​ሁን ብታ​ወጡ ከእ​ና​ንተ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ላይ ስድ​ብን አደ​ር​ጋ​ለሁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">የኢ​ያ​ቢ​ስም ሰዎች፥ “ወደ እስ​ራ​ኤል ሀገር ሁሉ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን እን​ድ​ን​ልክ ሰባት ቀን ቈይ​ልን፤ ከዚ​ያም በኋላ የሚ​ያ​ድ​ነን ባይ​ኖር ወደ አንተ እን​መ​ጣ​ለን” አሉት።</verse>
				<verse number="4">መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹም ሳኦል ወዳ​ለ​በት ወደ ገባ​ዖን መጥ​ተው ይህን ነገር በሕ​ዝቡ ጆሮ ተና​ገሩ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ድም​ፃ​ቸ​ውን ከፍ አድ​ር​ገው አለ​ቀሱ።</verse>
				<verse number="5">እነ​ሆም፥ ሳኦል ከእ​ር​ሻው አር​ፍዶ መጣ፤ ሳኦ​ልም፥ “ሕዝቡ የሚ​ያ​ለ​ቅስ ምን ሆኖ ነው?” አለ። የኢ​ያ​ቢ​ስ​ንም ሰዎች ነገር ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="6">ይህ​ንም ነገር በሰማ ጊዜ በሳ​ኦል ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ መጣ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ ተቈጣ።</verse>
				<verse number="7">ጥም​ዱ​ንም በሬ​ዎች ወስዶ በየ​ብ​ል​ታ​ቸው ቈራ​ረ​ጣ​ቸው፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ዳርቻ ሁሉ በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞቹ እጅ ላከና፥ “ሳኦ​ል​ንና ሳሙ​ኤ​ልን ተከ​ትሎ የማ​ይ​ወጣ ሁሉ፥ በበ​ሬ​ዎቹ እን​ዲሁ ይደ​ረ​ግ​በ​ታል” አለ። ድን​ጋ​ጤም በሕ​ዝቡ ላይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደቀ፤ እንደ አንድ ሰውም ሆነው ጮኹ።</verse>
				<verse number="8">በባማ ባለው በቤ​ዜ​ቅም ቈጠ​ራ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሦስት መቶ ሺህ፥ የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ሠላሳ ሺህ ነበሩ።</verse>
				<verse number="9">የመ​ጡ​ት​ንም መል​እ​ክ​ተ​ኞች፥ “የኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓ​ድን ሰዎች፦ ነገ ፀሐይ በተ​ኰሰ ጊዜ ድኅ​ነት ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል በሉ​አ​ቸው” አሉ​አ​ቸው። መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ መጥ​ተው ለኢ​ያ​ቢስ ሰዎች ነገሩ፤ ደስም አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">የኢ​ያ​ቢ​ስም ሰዎች፦ ለአ​ሞ​ና​ዊው ናዖስ “ነገ እን​ወ​ጣ​ላ​ች​ኋ​ለን፤ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኛ​ች​ሁ​ንም አድ​ር​ጉ​ብን” አሉት።</verse>
				<verse number="11">በነ​ጋ​ውም ሳኦል ሕዝ​ቡን በሦ​ስት ወገን አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ወገ​ግም ባለ ጊዜ ወደ ሰፈሩ መካ​ከል ገቡ፤ ቀት​ርም እስ​ኪ​ሆን ድረስ አሞ​ና​ው​ያ​ንን መቱ፤ የቀ​ሩ​ትም ተበ​ተኑ፤ ከው​ስ​ጣ​ቸ​ውም ሁለት በአ​ንድ ላይ ሆነው አል​ተ​ገ​ኙም።</verse>
				<verse number="12">ሕዝ​ቡም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ሳኦል አይ​ን​ገ​ሥ​ብን ያሉ እነ​ማን ናቸው? እነ​ዚ​ያን ሰዎች አው​ጡ​አ​ቸ​ውና እን​ግ​ደ​ላ​ቸው” አሉት።</verse>
				<verse number="13">ሳኦ​ልም፦“በዚ​ያች ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ድኅ​ነ​ትን አድ​ር​ጎ​አ​ልና ዛሬ አንድ ሰው አይ​ሞ​ትም” አለ።</verse>
				<verse number="14">ሳሙ​ኤ​ልም ሕዝ​ቡን፥ “ኑ፤ ወደ ጌል​ገላ እን​ሂድ፤ በዚ​ያም መን​ግ​ሥ​ቱን እና​ጽና” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ጌል​ገላ ሄዱ፤ ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን ቀብቶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በጌ​ል​ጌላ አነ​ገ​ሠው፤ በዚ​ያም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የእ​ህል ቍር​ባ​ንና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ በዚ​ያም ሳኦ​ልና የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ ታላቅ ደስታ አደ​ረጉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">ሳሙ​ኤ​ልም ለእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ሁሉ አለ፥ “የነ​ገ​ራ​ች​ሁ​ኝን ሁሉ ሰምቼ ንጉሥ አን​ግ​ሼ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">አሁ​ንም እነሆ፥ ንጉሡ በፊ​ታ​ችሁ ይሄ​ዳል፤ እኔም አር​ጅ​ቻ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲ​ህም አር​ፋ​ለሁ፤ እነ​ሆም፥ ልጆቼ ከእ​ና​ንተ ጋር ናቸው፤ እኔም ከሕ​ፃ​ን​ነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በፊ​ታ​ችሁ ሄድሁ።</verse>
				<verse number="3">እነ​ሆኝ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና እርሱ በቀ​ባው ፊት መስ​ክ​ሩ​ብኝ፤ የማ​ንን በሬ ወሰ​ድሁ? የማ​ን​ንስ አህያ ወሰ​ድሁ? ማን​ንስ ሸነ​ገ​ልሁ? በማ​ንስ ላይ ግፍ አደ​ረ​ግሁ? ነጠላ ጫማ እን​ኳን ቢሆን ከማን እጅ መማ​ለጃ ተቀ​በ​ልሁ? መስ​ክ​ሩ​ብኝ፤ እኔ እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="4">እነ​ር​ሱም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ግፍም አላ​ደ​ረ​ግ​ህ​ብ​ንም፤ የቀ​ማ​ኸን የለም፤ አላ​ሠ​ቃ​የ​ኸ​ንም፤ ከእ​ኛም ከማ​ንም እጅ ምንም አል​ወ​ሰ​ድ​ህም” አሉት።</verse>
				<verse number="5">ሳሙ​ኤ​ልም፥ “በእጄ ምንም እን​ዳ​ላ​ገ​ኛ​ችሁ ዛሬ በዚ​ህች ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክር ነው፤ እርሱ የቀ​ባ​ውም ምስ​ክር ነው” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “አዎ ምስ​ክር ነው” አሉ።</verse>
				<verse number="6">ሳሙ​ኤ​ልም ሕዝ​ቡን አለ፥ “ሙሴ​ንና አሮ​ንን ያላቀ፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ከግ​ብጽ ምድር ያወጣ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክር ነው።</verse>
				<verse number="7">አሁ​ንም ቁሙ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት እፋ​ረ​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፤ ለእ​ና​ን​ተና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ያደ​ረ​ገ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጽድቅ ሁሉ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">ያዕ​ቆ​ብና ልጆቹ ወደ ግብጽ በገቡ ጊዜ ግብ​ጻ​ው​ያን አስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸው፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ላከ፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ከግ​ብጽ አው​ጥ​ተው በዚህ ቦታ አኖ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">አም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረሱ፤ ለአ​ሶር ሠራ​ዊ​ትም አለቃ ለሲ​ሣራ እጅ፥ ለፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ፥ ለሞ​ዓ​ብም ንጉሥ እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ወጉ​አ​ቸው፤</verse>
				<verse number="10">እነ​ር​ሱም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተን በዓ​ሊ​ም​ንና ምስ​ሎ​ቹን በማ​ም​ለ​ካ​ችን በድ​ለ​ናል፤ አሁ​ንም ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን እጅ አድ​ነን፤ እና​መ​ል​ክ​ሃ​ለ​ንም” ብለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ ።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሩ​በ​ኣ​ልን፥ ባር​ቅ​ንም፥ ዮፍ​ታ​ሔ​ንም፥ ሳሙ​ኤ​ል​ንም ላከ፤ በዙ​ሪ​ያ​ች​ሁም ካሉት ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ እጅ አዳ​ኑ​አ​ችሁ፤ ተዘ​ል​ላ​ች​ሁም ተቀ​መ​ጣ​ችሁ።</verse>
				<verse number="12">የአ​ሞ​ንም ልጆች ንጉሥ ናዖስ እንደ መጣ​ባ​ችሁ ባያ​ችሁ ጊዜ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጉ​ሣ​ችሁ ሳለ፦ እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አን​ግ​ሥ​ልን አላ​ች​ሁኝ።</verse>
				<verse number="13">አሁ​ንም የመ​ረ​ጣ​ች​ሁ​ትን ንጉሥ እዩ፤ እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጉሥ ሰጣ​ችሁ።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ብት​ፈሩ፥ ብታ​መ​ል​ኩ​ትም፥ ቃሉ​ንም ብት​ሰሙ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ላይ ባታ​ምፁ፥ እና​ን​ተና በእ​ና​ንተ ላይ የነ​ገ​ሠው ንጉሥ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ብት​ከ​ተሉ፥ መል​ካም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="15">ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ባት​ሰሙ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ላይ ብታ​ምፁ፥ በእ​ና​ን​ተና በን​ጉ​ሣ​ችሁ ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ትመ​ጣ​ለች።</verse>
				<verse number="16">አሁ​ንም ቁሙ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ይህን ታላቅ ነገር ተመ​ል​ከቱ።</verse>
				<verse number="17">የስ​ንዴ መከር ዛሬ አይ​ደ​ለ​ምን? ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጮ​ኻ​ለሁ፤ እር​ሱም ነጐ​ድ​ጓ​ድ​ንና ዝና​ብን ይል​ካል፤ እና​ን​ተም ንጉሥ በመ​ለ​መ​ና​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ክፋት ታላቅ እንደ ሆነ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ታያ​ላ​ች​ሁም።”</verse>
				<verse number="18">ሳሙ​ኤ​ልም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚያ ቀን ነጐ​ድ​ጓ​ድ​ንና ዝና​ብን ላከ፤ ያን​ጊ​ዜም ሕዝቡ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ሳሙ​ኤ​ልን እጅግ ፈሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">ሕዝ​ቡም ሁሉ ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ንጉሥ በመ​ለ​መ​ና​ችን በኀ​ጢ​አ​ታ​ችን ሁሉ ላይ ይህን ክፋት ጨም​ረ​ና​ልና እን​ዳ​ን​ሞት ስለ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ይ​ልን” አሉት።</verse>
				<verse number="20">ሳሙ​ኤ​ልም ሕዝ​ቡን ሁሉ አላ​ቸው፥ “አት​ፍሩ፤ በእ​ው​ነት ይህን ክፋት ሁሉ አደ​ረ​ጋ​ችሁ፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በፍ​ጹም ልባ​ችሁ አም​ል​ኩት እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ከ​ተል ፈቀቅ አት​በሉ።</verse>
				<verse number="21">ምንም አይ​ደ​ሉ​ምና የማ​ይ​ረ​ቡ​ት​ንና የማ​ያ​ድ​ኑ​አ​ች​ሁን ለመ​ከ​ተል ከእ​ርሱ ፈቀቅ አት​በሉ።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ርሱ ሕዝብ ያደ​ር​ጋ​ችሁ ዘንድ ተቀ​ብ​ሎ​አ​ች​ኋ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ታላቅ ስሙ ሕዝ​ቡን አይ​ተ​ውም።</verse>
				<verse number="23">ደግሞ መል​ካ​ሙ​ንና ቅኑን መን​ገድ አሳ​ያ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ ስለ እና​ንተ መጸ​ለ​ይ​ንና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማገ​ል​ገ​ልን በመ​ተው እር​ሱን እበ​ድል ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን አያ​ድ​ር​ግ​ብኝ።</verse>
				<verse number="24">ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍሩ፤ ያደ​ረ​ገ​ላ​ች​ሁ​ንም ታላቅ ነገር አይ​ታ​ች​ኋ​ልና በፍ​ጹም ልባ​ችሁ በእ​ው​ነት አም​ል​ኩት፤</verse>
				<verse number="25">ነገር ግን ክፉ ብት​ሠሩ እና​ን​ተም፥ ንጉ​ሣ​ች​ሁም ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">ሳኦ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ከነ​ገሠ ሁለት ዓመት ሆነው፥</verse>
				<verse number="2">ያን​ጊ​ዜም ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎ​ችን ከእ​ስ​ራ​ኤል መረጠ፤ ሁለ​ቱም ሺህ በማ​ኪ​ማ​ስና በቤ​ቴል ተራራ ከሳ​ኦል ጋር ነበሩ፤ አን​ዱም ሺህ በብ​ን​ያም ገባ​ዖን ከልጁ ከዮ​ና​ታን ጋር ነበሩ፤ የቀ​ረ​ው​ንም ሕዝብ እያ​ን​ዳ​ን​ዱን ወደ ድን​ኳኑ አሰ​ና​በተ።</verse>
				<verse number="3">ዮና​ታ​ንም በኮ​ረ​ብ​ታው የነ​በ​ሩ​ትን የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ጭፍራ መታ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ያን ሰሙ፤ ሳኦ​ልም፦ እስ​ራ​ኤል ይስሙ ብሎ በሀ​ገሩ ሁሉ ቀንደ መለ​ከት ነፋ።</verse>
				<verse number="4">እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ሳኦል የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ጭፍራ እንደ መታ፥ ደግ​ሞም እስ​ራ​ኤል በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ዘንድ እንደ በረቱ ሰሙ፤ ሕዝ​ቡም ደን​ፍ​ተው ሳኦ​ልን ለመ​ከ​ተል ወደ ጌል​ጌላ ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="5">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ለመ​ዋ​ጋት ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሠላሳ ሺህ ሰረ​ገ​ሎች፥ ስድ​ስት ሺህም ፈረ​ሰ​ኞች፥ በባ​ሕ​ርም ዳር እን​ዳለ አሸዋ ብዙ ሕዝብ ነበሩ፤ ወጥ​ተ​ውም ከቤ​ቶ​ሮን በአ​ዜብ በኩል በማ​ኪ​ማስ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="6">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ወደ እነ​ርሱ መሄድ እን​ደ​ሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ በዋ​ሻና በግ​ንብ፥ በገ​ደ​ልና በቋ​ጥኝ፥ በጕ​ድ​ጓ​ድም ውስጥ ተሸ​ሸጉ።</verse>
				<verse number="7">ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ግ​ረው ወደ ጋድና ወደ ገለ​ዓድ ምድር የሄዱ አሉ፤ ሳኦል ግን ገና በጌ​ል​ጌላ ነበረ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ፈር​ተው እር​ሱን መከ​ተ​ልን ትተው ተበ​ተኑ።</verse>
				<verse number="8">ሳኦ​ልም ሳሙ​ኤል እንደ ቀጠ​ረው ጊዜ ሰባት ቀን ቈየ፤ ሳሙ​ኤል ግን ወደ ጌል​ጌላ አል​መ​ጣም፤ ሕዝ​ቡም ከእ​ርሱ ተለ​ይ​ተው ተበ​ታ​ተኑ።</verse>
				<verse number="9">ሳኦ​ልም፥ “የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት አም​ጡ​ልኝ” አለ። የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አሳ​ረገ።</verse>
				<verse number="10">የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ማሳ​ረግ በፈ​ጸመ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሳሙ​ኤል መጣ፤ ሳኦ​ልም እን​ዲ​ባ​ር​ከው ሊገ​ና​ኘው ወጣ።</verse>
				<verse number="11">ሳሙ​ኤ​ልም፥ “ያደ​ረ​ግ​ኸው ምን​ድን ነው?” አለ። ሳኦ​ልም፥ “ሕዝቡ ከእኔ ተለ​ይ​ተው እንደ ተበ​ታ​ተኑ፥ አን​ተም በነ​ገ​ር​ኸኝ መሠ​ረት በቀ​ጠ​ሮው ቀን እን​ዳ​ል​መ​ጣህ፥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ወደ ማኪ​ማስ እንደ ተሰ​በ​ሰቡ አየሁ፤</verse>
				<verse number="12">ስለ​ዚህ፦ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አሁን ወደ እኔ ወደ ጌል​ጌላ ይወ​ር​ዱ​ብ​ኛል፤ እኔም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፊት አል​ለ​መ​ን​ሁም አልሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ደፍሬ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትን አሳ​ረ​ግሁ” አለ።</verse>
				<verse number="13">ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን፥ “በድ​ለ​ኻል፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ህን ትእ​ዛ​ዙን አል​ጠ​በ​ቅ​ህ​ምና፤ ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥ​ት​ህን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጽ​ን​ቶ​ልህ ነበር።</verse>
				<verse number="14">ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ግን መን​ግ​ሥ​ትህ አይ​ጸ​ናም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ልቡ የሆነ ሰው መር​ጦ​አል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዘ​ዘ​ህን አል​ጠ​በ​ቅ​ህ​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ላይ ንጉ​ሥን ያነ​ግ​ሣል” አለው።</verse>
				<verse number="15">ሳሙ​ኤ​ልም ከጌ​ል​ጌላ ተነ​ሥቶ መን​ገ​ዱን ሄደ፤ የቀ​ሩ​ትም ሕዝብ ሳኦ​ልን ተከ​ት​ለው ሰል​ፈ​ኞ​ቹን ሊገ​ናኙ ሄዱ። ከጌ​ል​ጌ​ላም ተነ​ሥ​ተው ወደ ብን​ያም ገባ​ዖን መጡ፤ ሳኦ​ልም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ቈጠረ፤ ስድ​ስት መቶም የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="16">ሳኦ​ልና ልጁ ዮና​ታ​ንም፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሕዝብ በብ​ን​ያም ገባ​ዖን ተቀ​ም​ጠው አለ​ቀሱ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም በማ​ኪ​ማስ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="17">ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሰፈር ማራ​ኪ​ዎች በሦ​ስት ክፍል ሆነው ወጡ፤ አን​ዱም ክፍል በጎ​ፌር መን​ገድ ወደ ሦጋክ ምድር ሄደ።</verse>
				<verse number="18">ሁለ​ተ​ኛው ክፍል ወደ ቤቶ​ሮን መን​ገድ ዞረ፤ ሦስ​ተ​ኛ​ውም ክፍል በገ​ባ​ዖን መን​ገድ ባለው ወደ ሴቤ​ሮም ሸለቆ በሚ​መ​ለ​ከ​ተው በዳ​ር​ቻው መን​ገድ ዞረ።</verse>
				<verse number="19">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥ “ዕብ​ራ​ው​ያን ሰይ​ፍና ጦር እን​ዳ​ይ​ሠሩ” ብለው ነበ​ርና በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር ሁሉ ብረት ሠሪ አል​ተ​ገ​ኘም።</verse>
				<verse number="20">እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ማረ​ሻ​ው​ንና ማጭ​ዱን፥ መጥ​ረ​ቢ​ያ​ው​ንና መቈ​ፈ​ሪ​ያ​ውን ይስሉ ዘንድ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ይወ​ርዱ ነበር።</verse>
				<verse number="21">አዝ​መ​ራ​ውም ለአ​ጨዳ ደርሶ ነበር። ለማ​ረ​ሻ​ውና ለመ​ቈ​ፈ​ሪ​ያው ዋጋው ሦስት ሰቅል ነበር። መጥ​ረ​ቢ​ያ​ው​ንም ለማ​ሳል፥ መው​ጊ​ያ​ው​ንም ለማ​በ​ጀት ዋጋው ተመ​ሳ​ሳይ ነበር።</verse>
				<verse number="22">ስለ​ዚ​ህም በማ​ኪ​ማስ ጦር​ነት ጊዜ ሰይ​ፍና ጦር ከሳ​ኦ​ልና ከዮ​ና​ታን ጋር በነ​በሩ ሕዝብ ሁሉ እጅ አል​ተ​ገ​ኘም፤ ብቻ በሳ​ኦ​ልና በልጁ በዮ​ና​ታን ዘንድ ተገኘ።</verse>
				<verse number="23">ከዚ​ያም ጥቂ​ቶች ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሰፈር ወደ ማኪ​ማስ መተ​ላ​ለ​ፊያ ወጡ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">በነ​ጋም ጊዜ፥ የሳ​ኦል ልጅ ዮና​ታን ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን፥ “ና፤ በዚያ በኩል ወዳ​ለው ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሰፈር እን​ለፍ” አለው፤ ለአ​ባ​ቱም አል​ነ​ገ​ረ​ውም።</verse>
				<verse number="2">ሳኦ​ልም በመ​ጌ​ዶን ባለው በሮ​ማኑ ዛፍ በታች በኮ​ረ​ብ​ታው ላይ ተቀ​ምጦ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ረው ሕዝብ ስድ​ስት መቶ የሚ​ያ​ህል ሰው ነበረ።</verse>
				<verse number="3">የዔሊ ልጅ፥ የፊ​ን​ሐስ ልጅ፥ የዮ​ካ​ብድ ወን​ድም፥ የአ​ኪ​ጦብ ልጅ በሴሎ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካህን የሆነ፥ ኤፉ​ድም የለ​በሰ አኪያ አብሮ ነበር፤ ሕዝ​ቡም ዮና​ታን እንደ ሄደ አላ​ወ​ቁም ነበር።</verse>
				<verse number="4">ዮና​ታ​ንም ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሰፈር ሊሻ​ገ​ር​በት በወ​ደ​ደው መተ​ላ​ለ​ፊያ መካ​ከል በወ​ዲህ አንድ ሾጣጣ፥ በወ​ዲ​ህም አንድ ሾጣጣ ድን​ጋ​ዮች ነበሩ፤ የአ​ን​ዱም ስም ባዚስ፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ስም ሴና ነበረ።</verse>
				<verse number="5">አን​ደ​ኛዋ መን​ገድ በማ​ኪ​ማስ አን​ጻር በመ​ስዕ በኩል የም​ት​መጣ ናት፤ ሁለ​ተ​ኛ​ዋም መን​ገድ በገ​ባ​ዖን አን​ጻር በአ​ዜብ በኩል የም​ት​መጣ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="6">ዮና​ታ​ንም ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን፥ “ና፥ ወደ እነ​ዚህ ቈላ​ፋን ሰፈር እን​ለፍ፤ በብዙ ወይም በጥ​ቂት ማዳን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አያ​ስ​ቸ​ግ​ረ​ው​ምና ምና​ል​ባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይረ​ዳን ይሆ​ናል” አለው።</verse>
				<verse number="7">ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም፥ “ልብህ ያሰ​ኘ​ህን ሁሉ አድ​ርግ እነሆ፥ ከአ​ንተ ጋር ነኝ፤ እንደ አንተ ልብ የእ​ኔም ልብ እን​ዲሁ ነው” አለው።</verse>
				<verse number="8">ዮና​ታ​ንም አለው፥ “እነሆ፥ ወደ ሰዎቹ እና​ል​ፋ​ለን፤ ወደ እነ​ር​ሱም እን​ቀ​ር​ባ​ለን፤</verse>
				<verse number="9">እነ​ር​ሱም፦ እስ​ክ​ን​ነ​ግ​ራ​ችሁ ድረስ ርቃ​ችሁ ቈዩ ቢሉን ርቀን እን​ቆ​ማ​ለን፤ ወደ እነ​ር​ሱም አን​ወ​ጣም።</verse>
				<verse number="10">ነገር ግን ወደ እኛ ውጡ ቢሉን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና እን​ወ​ጣ​ለን፤ ምል​ክ​ታ​ች​ንም ይህ ይሆ​ናል።”</verse>
				<verse number="11">ሁለ​ታ​ቸ​ውም ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሰፈር ገቡ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም “እነሆ፥ ዕብ​ራ​ው​ያን ከተ​ሸ​ሸ​ጉ​በት ጕድ​ጓድ ይወ​ጣሉ” አሉ።</verse>
				<verse number="12">የሰ​ፈ​ሩም ሰዎች፦ ዮና​ታ​ን​ንና ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን “ወደ እኛ ውጡ፤ አንድ ነገ​ር​ንም እን​ነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለን” አሉ። ዮና​ታ​ንም ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና ተከ​ተ​ለኝ” አለው።</verse>
				<verse number="13">ዮና​ታ​ንም በእ​ጁና በእ​ግሩ ወጣ፤ ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ዮና​ታ​ንም ፊቱን መልሶ ገደ​ላ​ቸው፤ ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም ተከ​ትሎ ገደ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">የዮ​ና​ታ​ንና የጋሻ ጃግ​ሬ​ውም በወ​ን​ጭ​ፍና በዱላ የመ​ጀ​መ​ሪያ ግድ​ያ​ቸው በአ​ንድ ትልም እርሻ መካ​ከል ሃያ ያህል ሰው ነበረ።</verse>
				<verse number="15">በሰ​ፈ​ሩና በእ​ር​ሻ​ውም ድን​ጋጤ ሆነ፤ በሰ​ፈሩ የተ​ቀ​መጡ ሕዝ​ብና የሚ​ዋ​ጉ​ትም ሁሉ ተሸ​በሩ፤ መዋ​ጋ​ትም አል​ቻ​ሉም፤ ምድ​ሪ​ቱም ተና​ወ​ጠች፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ ታላቅ ድን​ጋጤ መጣ።</verse>
				<verse number="16">በብ​ን​ያም ገባ​ዖን ያሉ የሳ​ኦል ዘበ​ኞ​ችም ተመ​ለ​ከቱ፤ እነ​ሆም፥ ሠራ​ዊቱ ወዲ​ህና ወዲያ እየ​ተ​ራ​ወጡ ተበ​ታ​ተኑ።</verse>
				<verse number="17">ሳኦ​ልም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ፥ “እስኪ ተቋ​ጠሩ፤ ከእኛ ዘንድ የሄደ ማን እንደ ሆነ ተመ​ል​ከቱ” አላ​ቸው። በተ​ቋ​ጠ​ሩም ጊዜ እነሆ፥ ዮና​ታ​ንና ጋሻ ጃግ​ሬው በዚያ አል​ተ​ገ​ኙም።</verse>
				<verse number="18">በዚ​ያም ቀን አኪያ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ኤፉድ ይለ​ብስ ነበ​ርና ሳኦል፥ “ኤፉ​ድን አምጣ” አለው።</verse>
				<verse number="19">ሳኦ​ልም ከካ​ህኑ ጋር ሲነ​ጋ​ገር በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መን​ደር ግር​ግ​ርታ እየ​በዛ ሄደ፤ ሳኦ​ልም ካህ​ኑን፥ “እጅ​ህን መልስ” አለው።</verse>
				<verse number="20">ሳኦ​ልና ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው ወደ ውጊ​ያው መጡ፤ እነ​ሆም፥ የእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ሰይፍ በባ​ል​ን​ጀ​ራው ላይ ነበረ፤ እጅ​ግም ታላቅ ሽብር ሆነ።</verse>
				<verse number="21">ቀድሞ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር የነ​በ​ሩና ወደ ሠራ​ዊቱ የወጡ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ከሳ​ኦ​ልና ከዮ​ና​ታን ጋር ወደ ነበሩ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ለመ​ሆን ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="22">በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር የተ​ሸ​ሸ​ጉት እስ​ራ​ኤል ሁሉ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እንደ ሸሹ በሰሙ ጊዜ እነ​ርሱ ደግሞ ሊዋ​ጉ​አ​ቸው ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚያ ቀን እስ​ራ​ኤ​ልን አዳነ፤ ውጊ​ያ​ውም በባ​ሞት በኩል አለፈ። ከሳ​ኦ​ልም ጋር የነ​በሩ ሕዝብ ሁሉ ዐሥር ሺህ የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ፤ ውጊ​ያ​ውም በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ሬም ከተማ ሁሉ ተበ​ታ​ትኖ ነበር።</verse>
				<verse number="24">ሳኦ​ልም በዚያ ቀን ትልቅ በደል ፈጸመ፤ “ጠላ​ቶቼን እስ​ክ​በ​ቀል እስከ ማታ ድረስ መብል የሚ​በላ ሰው ርጉም ይሁን” ብሎ ሕዝ​ቡን አም​ሎ​አ​ቸው ነበ​ርና። ሕዝ​ቡም ሁሉ እህል አል​ቀ​መ​ሱም። ሀገ​ሩም ሁሉ ምሳ አል​በ​ላም።</verse>
				<verse number="25">ብዙ ንብ ያለ​በት የማር ቀፎም በዱሩ ይታይ ነበር።</verse>
				<verse number="26">ሕዝ​ቡም ማር ወደ አለ​በት ቀፎ ሄዱ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ይነ​ጋ​ገሩ ነበር። እነ​ሆም፥ ሕዝቡ መሐ​ላ​ውን ፈርቶ ነበ​ርና ማንም እጁን አን​ሥቶ ወደ አፉ አላ​ደ​ረ​ገም።</verse>
				<verse number="27">ዮና​ታን ግን አባቱ ሕዝ​ቡን ባማለ ጊዜ አል​ሰ​ማም ነበር፤ እር​ሱም በእጁ ያለ​ች​ውን በትር አን​ሥቶ ጫፍ​ዋን ወደ ወለ​ላው ነከረ፤ እጁ​ንም ወደ አፉ አደ​ረገ፤ ዐይ​ኑም በራ።</verse>
				<verse number="28">ከሕ​ዝ​ቡም አንድ ሰው መልሶ፥ “አባ​ትህ፦ ዛሬ መብል የሚ​በላ ሰው ርጉም ይሁን ብሎ ሕዝ​ቡን መሐላ አም​ሎ​አ​ቸ​ዋል” አለው፤ ሕዝ​ቡም ደከሙ።</verse>
				<verse number="29">ዮና​ታ​ንም “አባቴ ምድ​ሪ​ቱን አስ​ቸ​ገረ፤ ከዚህ ማር ጥቂት ብቀ​ምስ ዐይኔ እንደ በራ እዩ፤</verse>
				<verse number="30">ይል​ቅስ ሕዝቡ ካገ​ኙት ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ምርኮ በል​ተው ቢሆን ኑሮ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መመ​ታት ይበ​ልጥ አል​ነ​በ​ረ​ምን?” አለ።</verse>
				<verse number="31">በዚ​ያም ቀን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በማ​ኪ​ማስ መቱ​አ​ቸው፤ ሕዝ​ቡም እጅግ ደከሙ።</verse>
				<verse number="32">ሕዝ​ቡም ወደ ምርኮ ሄዱ፤ በጎ​ችን፥ በሬ​ዎ​ች​ንም፥ ጥጆ​ች​ንም ወስ​ደው እን​ዳ​ገኙ በም​ድር ላይ አረዱ፤ ሕዝ​ቡም ከደሙ ጋር በሉ።</verse>
				<verse number="33">ለሳ​ኦ​ልም፥ “እነሆ፥ ሕዝቡ ከደሙ ጋር በመ​ብ​ላ​ታ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በደሉ” ብለው ነገ​ሩት። ሳኦ​ልም በጌ​ቴም “ትልቅ ድን​ጋይ አን​ከ​ባ​ል​ላ​ችሁ አቅ​ር​ቡ​ልኝ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="34">ሳኦ​ልም፥ “በሕ​ዝቡ መካ​ከል እየ​ዞ​ራ​ችሁ፦ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው በሬ​ው​ንና በጉን ወደ እኔ ያቅ​ርብ፥ በዚ​ህም እረ​ዱና ብሉ፤ ከደ​ሙም ጋር በመ​ብ​ላ​ታ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አት​በ​ድሉ” በሉ​አ​ቸው አለ። እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሰው ሁሉ በእጁ ያለ​ውን በዚ​ያች ሌሊት አቀ​ረበ፤ በዚ​ያም አረ​ደው።</verse>
				<verse number="35">ሳኦ​ልም በዚያ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊ​ያን ሠራ፤ ይኸ​ውም ሳኦል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሠ​ራው የመ​ጀ​መ​ሪያ መሠ​ዊያ ነው።</verse>
				<verse number="36">ሳኦ​ልም፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በሌ​ሊት ተከ​ት​ለን እን​ው​ረድ፤ እስ​ኪ​ነ​ጋም ድረስ እን​በ​ዝ​ብ​ዛ​ቸው፤ አንድ ሰው እንኳ አና​ስ​ቀ​ር​ላ​ቸው” አለ። እነ​ር​ሱም፥ “ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን ሁሉ አድ​ርግ” አሉት። ካህ​ኑም፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ቅ​ረብ” አለ።</verse>
				<verse number="37">ሳኦ​ልም፥ “ልው​ረ​ድና ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ልከ​ተ​ልን? በእ​ስ​ራ​ኤ​ልስ እጅ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ህን?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየ​ቀው። በዚያ ቀን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​መ​ለ​ሰ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="38">ሳኦ​ልም፥ “እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል አለ​ቆ​ችን ሁሉ ወደ​ዚህ አቅ​ርቡ፤ ዛሬ ይህ ኀጢ​ኣት በማን እንደ ሆነ ዕወቁ፤ ተመ​ል​ከ​ቱም፤</verse>
				<verse number="39">እስ​ራ​ኤ​ልን የሚ​ያ​ድን ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ኀጢ​ኣቱ በልጄ በዮ​ና​ታን ቢሆን ፈጽሞ ይሞ​ታል” አለ። ከሕ​ዝ​ቡም ሁሉ አንድ የመ​ለ​ሰ​ለት ሰው አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="40">እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሁሉ፥ “እና​ንተ አንድ ወገን ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ እኔና ልጄ ዮና​ታ​ንም አንድ ወገን እን​ሆ​ና​ለን” አለ። ሕዝ​ቡም ሳኦ​ልን፥ “ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን አድ​ርግ” አሉት።</verse>
				<verse number="41">ሳኦ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ለእኔ ለባ​ሪ​ያህ ዛሬ ያል​መ​ለ​ስ​ህ​ልኝ ስለ ምን​ድን ነው? ይህች በደል በእኔ፥ በልጄ በዮ​ና​ታ​ንም እንደ ሆነች አቤቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ተና​ገር። ዕጣው ይህን የሚ​ገ​ልጥ ከሆነ ለሕ​ዝ​ብህ ለእ​ስ​ራ​ኤል እው​ነ​ትን ግለጥ፥” አለ። ዕጣም በዮ​ና​ታ​ንና በሳ​ኦል ላይ ወጣ፤ ሕዝ​ቡም ነፃ ወጣ።</verse>
				<verse number="42">ሳኦ​ልም፥ “በእ​ኔና በዮ​ና​ታን መካ​ከል ዕጣ አጣ​ጥ​ሉን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዕጣ ያወ​ጣ​በ​ትም ይሞ​ታል” አላ​ቸው። ሕዝ​ቡም ሳኦ​ልን፥ “እን​ዲህ ያለ ነገር አይ​ሆ​ንም” አሉት፤ ሳኦ​ልም ሕዝ​ቡን እንቢ አላ​ቸው። በእ​ር​ሱና በልጁ በዮ​ና​ታን መካ​ከ​ልም ዕጣ አጣ​ጣሉ። ዕጣ​ውም በልጁ በዮ​ና​ታን ላይ ወጣ።</verse>
				<verse number="43">ሳኦ​ልም ዮና​ታ​ንን፥ “ያደ​ረ​ግ​ኸ​ውን ንገ​ረኝ” አለው፤ ዮና​ታ​ንም፥ “በእጄ ባለው በበ​ትሬ ጫፍ ጥቂት ማር በር​ግጥ ቀም​ሻ​ለሁ፤ እነ​ሆኝ፥ እሞ​ታ​ለሁ” ብሎ ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="44">ሳኦ​ልም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ያድ​ር​ግ​ብኝ፤ እን​ዲ​ህም ይጨ​ም​ር​ብኝ፤ ዛሬ ፈጽ​መህ ትሞ​ታ​ለህ” አለ።</verse>
				<verse number="45">ሕዝ​ቡም ሳኦ​ልን፥ “በውኑ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ታላቅ መድ​ኀ​ኒት ያደ​ረገ ዮና​ታን ዛሬ ይሞ​ታ​ልን? ይህ አይ​ሁን፤ ዛሬ ለሕ​ዝቡ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አድ​ር​ጎ​አ​ልና ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ከራሱ ጠጕር አን​ዲት በም​ድር ላይ አት​ወ​ድ​ቅም” አሉት። ሕዝ​ቡም ያን ጊዜ ስለ ዮና​ታን ጸለዩ፤ እር​ሱም አል​ተ​ገ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="46">ሳኦ​ልም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ከመ​ከ​ተል ተመ​ለሰ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ወደ ስፍ​ራ​ቸው ሄዱ።</verse>
				<verse number="47">ሳኦ​ልም መን​ግ​ሥ​ቱን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አጸና፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ካሉት ከጠ​ላ​ቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞ​ዓ​ብም፥ ከአ​ሞ​ንም ልጆች፥ ከኤ​ዶ​ም​ያ​ስም፥ ከቢ​ዖ​ርም፥ ከሱ​ባም ነገ​ሥ​ታት፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር፤ በየ​ሄ​ደ​በ​ትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።</verse>
				<verse number="48">እር​ሱም ጀግና ነበረ፤ አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ን​ንም መታ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ከዘ​ራ​ፊ​ዎቹ እጅ አዳነ።</verse>
				<verse number="49">የሳ​ኦ​ልም ወን​ዶች ልጆች ዮና​ታን፥ የሱዊ፥ ሚል​ኪሳ ነበሩ፤ የሁ​ለ​ቱም ሴቶች ልጆቹ ስም ይህ ነበረ፤ የታ​ላ​ቂቱ ስም ሜሮብ፥ የታ​ና​ሺ​ቱም ስም ሜል​ኮል ነበረ።</verse>
				<verse number="50">የሳ​ኦ​ልም ሚስት ስም የአ​ኪ​ማ​ኦስ ልጅ አኪ​ና​ሆም ነበ​ረች፤ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ ስም የሳ​ኦል አጎት የኔር ልጅ አቤ​ኔር ነበረ።</verse>
				<verse number="51">የሳ​ኦ​ልም አባት ቂስ ነበረ፤ የአ​ቤ​ኔ​ርም አባት የአ​ብ​ኤል ልጅ የያ​ሚን ልጅ ኔር ነበረ።</verse>
				<verse number="52">በሳ​ኦ​ልም ዘመን ሁሉ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ጽኑ ውጊያ ነበረ፤ ሳኦ​ልም ጽኑ ወይም ኀያል ሰው ባየ ጊዜ ወደ እርሱ ይሰ​በ​ስብ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን አለው፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ እን​ድ​ት​ሆን እቀ​ባህ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላከኝ፤ አሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ።</verse>
				<verse number="2">የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እስ​ራ​ኤል ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ በመ​ን​ገድ እንደ ተዋጉ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ክፉ ያደ​ረ​ጉ​ትን አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ዛሬ እበ​ቀ​ላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">አሁ​ንም ሄደህ አማ​ሌ​ቅ​ንና ኢያ​ሬ​ምን ምታ፤ ያላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ፈጽ​መህ አጥፋ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የም​ታ​ድ​ነው የለም። አጥ​ፋ​ቸው፤ መከ​ራም አጽ​ና​ባ​ቸው፤ የእ​ነ​ርሱ የሆ​ነ​ውን ሁሉ አጥፋ፤ ለያ​ቸ​ውም፤ አት​ማ​ራ​ቸ​ውም፤ ወን​ዱ​ንና ሴቱን፥ ብላ​ቴ​ና​ው​ንና ሕፃ​ኑን፥ በሬ​ው​ንና በጉን፥ ግመ​ሉ​ንና አህ​ያ​ውን ግደል።”</verse>
				<verse number="4">ሳኦ​ልም ሕዝ​ቡን ጠርቶ በጌ​ል​ጌላ ቈጠ​ራ​ቸው፤ አራት መቶ ሺህ እግ​ረ​ኞች፥ ከይ​ሁ​ዳም ሠላሳ ሺህ ሰዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="5">ሳኦ​ልም ወደ አማ​ሌቅ ከተማ ወጣ፤ በሸ​ለ​ቆ​ውም ውስጥ ተደ​በቀ።</verse>
				<verse number="6">ሳኦ​ልም ቄኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን፥ “ከእ​ነ​ርሱ ጋር እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋ​ችሁ ከአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን መካ​ከል ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ሂዱ፤ ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ቸር​ነት አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና” አላ​ቸው። ቄኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ከአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን መካ​ከል ወጡ።</verse>
				<verse number="7">ሳኦ​ልም አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ከኤ​ው​ላጥ ጀምሮ በግ​ብፅ ፊት እስ​ካ​ለ​ችው እስከ ሱር ድረስ መታ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">የአ​ማ​ሌ​ቅ​ንም ንጉሥ አጋ​ግን በሕ​ይ​ወቱ ማረ​ከው፤ የኢ​ያ​ሬ​ም​ንም ሕዝብ ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት ፈጽሞ አጠ​ፋ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ነገር ግን ሳኦ​ልና ሕዝቡ ሁሉ አጋ​ግን፥ ከከ​ብ​ቱና ከበጉ መንጋ መል​ካም መል​ካ​ሙን፥ እህ​ሉ​ንም፥ ወይ​ኑ​ንም፥ መል​ካም የሆ​ነ​ውን ሁሉ አዳኑ። ፈጽ​መው ሊያ​ጠ​ፉ​አ​ቸ​ውም አል​ወ​ደ​ዱም፤ ነገር ግን የተ​ና​ቀ​ውን ሁሉ ፈጽ​መው አጠ​ፉት።</verse>
				<verse number="10">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ሳሙ​ኤል መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፦</verse>
				<verse number="11">“ሳኦል እኔን ከመ​ከ​ተል ተመ​ል​ሶ​አ​ልና፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም አል​ፈ​ጸ​መ​ምና ስላ​ነ​ገ​ሥ​ሁት ተጸ​ጸ​ትሁ።” ሳሙ​ኤ​ልም አዘነ። ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ።</verse>
				<verse number="12">ሳሙ​ኤ​ልም እስ​ራ​ኤ​ልን ለመ​ገ​ና​ኘት በጥ​ዋት ገሥ​ግሦ ሄደ። ለሳ​ሙ​ኤ​ልም፥ “ሳኦል ወደ ቀር​ሜ​ሎስ መጣ፤ እነ​ሆም፥ ለራሱ የመ​ታ​ሰ​ቢያ ዐምድ አቆመ” ብለው ነገ​ሩት። ሳሙ​ኤ​ልም ሰረ​ገ​ላ​ውን መልሶ ወደ ጌል​ጌላ ወደ ሳኦል ወረደ፤ ከአ​ማ​ሌቅ ዘንድ ከአ​መ​ጣ​ውም ከአ​ማ​ረው ከም​ር​ኮው መንጋ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ሲሠዋ አገ​ኘው፤</verse>
				<verse number="13">ሳሙ​ኤ​ልም ወደ ሳኦል መጣ፤ ሳኦ​ልም፥ “አንተ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ረ​ክህ ሁን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ፈጽ​ሜ​አ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="14">ሳሙ​ኤ​ልም፥ “ይህ በጆ​ሮዬ የም​ሰ​ማው የበ​ጎች ጩኸ​ትና የበ​ሬ​ዎች ግሣት ምን​ድር ነው?” አለ።</verse>
				<verse number="15">ሳኦ​ልም፦“ሕዝቡ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሠ​ዉ​አ​ቸው ዘንድ ከበ​ጎ​ችና ከላ​ሞች መን​ጋ​ዎች መል​ካም መል​ካ​ሙን አድ​ነ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና ከአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን አመ​ጣን፤ የቀ​ሩ​ት​ንም ፈጽሜ አጠ​ፋሁ” አለው።</verse>
				<verse number="16">ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን፥ “ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ሌሊት የነ​ገ​ረ​ኝን ልን​ገ​ርህ” አለው፤ እር​ሱም፥ “ተና​ገር” አለው።</verse>
				<verse number="17">ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን አለው፥ “በፊቱ ምንም ታናሽ ብት​ሆን ለእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች አለቃ አል​ሆ​ን​ህ​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባህ።</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ሄደህ ኀጢ​ኣ​ተ​ኞ​ቹን አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ፈጽ​መህ አጥ​ፋ​ቸው፤ እስ​ኪ​ጠ​ፉም ድረስ ውጋ​ቸው ብሎ በመ​ን​ገድ ላከህ።</verse>
				<verse number="19">ለም​ርኮ ሳስ​ተህ ለምን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ህም? ለም​ንስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረ​ግህ?”</verse>
				<verse number="20">ሳኦ​ልም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስለ​ሰ​ማሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላ​ከኝ መን​ገድ ሄጃ​ለሁ፤ የአ​ማ​ሌ​ቅን ንጉሥ አጋ​ግ​ንም አም​ጥ​ቻ​ለሁ፤ አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ን​ንም ፈጽሜ አጥ​ፍ​ቻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="21">ሕዝቡ ግን ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጌ​ል​ጌላ ይሠዉ ዘንድ ከእ​ርሙ የተ​መ​ረ​ጡ​ትን በጎ​ችና በሬ​ዎች ከም​ር​ኮው ወሰዱ” አለው።</verse>
				<verse number="22">ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን፥ “በውኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በመ​ስ​ማት ደስ እን​ደ​ሚ​ለው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ቃ​ጠ​ልና በሚ​ታ​ረድ መሥ​ዋ​ዕት ደስ ይለ​ዋ​ልን? እነሆ፥ መታ​ዘዝ ከመ​ሥ​ዋ​ዕት፥ ማዳ​መ​ጥም የአ​ውራ በግ ስብ ከማ​ቅ​ረብ ይበ​ል​ጣል።</verse>
				<verse number="23">ኀጢ​ኣት እንደ ምዋ​ር​ተ​ኝ​ነት ናትና አም​ል​ኮተ ጣዖ​ትም ደዌ​ንና ኀዘ​ንን ያመ​ጣል። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ንቀ​ሃ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጉሥ እን​ዳ​ት​ሆን ናቀህ” አለው።</verse>
				<verse number="24">ሳኦ​ልም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ሕዝ​ቡን ስለ ፈራሁ፥ ቃላ​ቸ​ው​ንም ስለ ሰማሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛ​ዝና የአ​ን​ተን ቃል በመ​ተ​ላ​ለፍ በድ​ያ​ለሁ።</verse>
				<verse number="25">አሁ​ንም እባ​ክህ ኀጢ​ኣ​ቴን ይቅር በለኝ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እሰ​ግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተመ​ለስ” አለው።</verse>
				<verse number="26">ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ንቀ​ሃ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ እን​ዳ​ት​ሆን ንቆ​ሃ​ልና ከአ​ንተ ጋር አል​መ​ለ​ስም” አለው።</verse>
				<verse number="27">ሳሙ​ኤ​ልም ሊሄድ ዘወር ባለ ጊዜ ሳኦል የል​ብ​ሱን ጫፍ ያዘ፤ ተቀ​ደ​ደም።</verse>
				<verse number="28">ሳሙ​ኤ​ልም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል መን​ግ​ሥ​ት​ህን ዛሬ ከእ​ጅህ ቀደ​ዳት፤ ከአ​ን​ተም ለሚ​ሻል ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ አሳ​ልፎ ሰጣት፤</verse>
				<verse number="29">እስ​ራ​ኤል ለሁ​ለት ይከ​ፈ​ላል፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም አይ​ሰ​በ​ሰ​ብም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ሰው የሚ​ጸ​ጸት አይ​ደ​ለ​ምና አይ​ጸ​ጸ​ትም” አለው።</verse>
				<verse number="30">ሳኦ​ልም፥ “በድ​ያ​ለሁ፤ አሁ​ንም በሕ​ዝቤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ፊትና በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት እባ​ክህ አክ​ብ​ረኝ፤ ለአ​ም​ላ​ክ​ህም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሰ​ግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተመ​ለስ” አለው።</verse>
				<verse number="31">ሳሙ​ኤ​ልም ከሳ​ኦል በኋላ ተመ​ለሰ፤ ሳኦ​ልም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ።</verse>
				<verse number="32">ሳሙ​ኤ​ልም፥ “የአ​ማ​ሌ​ቅን ንጉሥ አጋ​ግን አም​ጡ​ልኝ” አለ። አጋ​ግም እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጠ ወደ እርሱ መጣ። አጋ​ግም፥ “በውኑ ሞት እን​ደ​ዚህ መራራ ነውን?” አለ።</verse>
				<verse number="33">ሳሙ​ኤ​ልም አጋ​ግን፥ “ሰይ​ፍህ ሴቶ​ችን ልጆች አልባ እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ቻ​ቸው እን​ዲሁ እና​ትህ በሴ​ቶች መካ​ከል ልጅ አልባ ትሆ​ና​ለች” አለ፥ ሳሙ​ኤ​ልም አጋ​ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በጌ​ል​ጌላ ወጋው።</verse>
				<verse number="34">ሳሙ​ኤ​ልም ወደ አር​ማ​ቴም ሄደ፤ ሳኦ​ልም ወደ ቤቱ ወደ ገባ​ዖን ወጣ።</verse>
				<verse number="35">ሳሙ​ኤ​ልም እስከ ሞተ​በት ቀን ድረስ ሳኦ​ልን ለማ​የት ዳግ​መኛ አል​ሄ​ደም፤ ሳሙ​ኤ​ልም ለሳ​ኦል አለ​ቀሰ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ሳኦ​ልን ስላ​ነ​ገሠ ተጸ​ጸተ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ እን​ዳ​ይ​ነ​ግሥ ለና​ቅ​ሁት ለሳ​ኦል የም​ታ​ለ​ቅ​ስ​ለት እስከ መቼ ነው? የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ሞል​ተህ ና፤ በል​ጆቹ መካ​ከል ለእኔ ንጉሥ አዘ​ጋ​ጅ​ቼ​አ​ለ​ሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እል​ክ​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="2">ሳሙ​ኤ​ልም፥ “እን​ዴት እሄ​ዳ​ለሁ? ሳኦል ቢሰማ ይገ​ድ​ለ​ኛል” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አን​ዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፦ ‘ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሠዋ ዘንድ መጣሁ’ በል።</verse>
				<verse number="3">እሴ​ይ​ንም ወደ መሥ​ዋ​ዕቱ ጥራው፥ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ው​ንም አስ​ታ​ው​ቅ​ሃ​ለሁ፤ የም​ነ​ግ​ር​ህ​ንም ቅባው” አለው።</verse>
				<verse number="4">ሳሙ​ኤ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን አደ​ረገ፤ ወደ ቤተ ልሔ​ምም መጣ። የከ​ተ​ማ​ውም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች በተ​ገ​ና​ኙት ጊዜ ደነ​ገጡ፥ “ነቢይ! የመ​ጣ​ኸው ለሰ​ላም ነውን?” አሉት።</verse>
				<verse number="5">እር​ሱም፥ “ለሰ​ላም ነው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሠዋ ዘንድ መጣሁ፤ ቅዱ​ሳን ሁኑ፤ ከእ​ኔም ጋር ዛሬ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ከእ​ኔም ጋር ወደ መሥ​ዋ​ዕቱ ኑ” አለ። እሴ​ይ​ንና ልጆ​ቹ​ንም ቀደ​ሳ​ቸው፤ ወደ መሥ​ዋ​ዕ​ቱም ጠራ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በመጡ ጊዜ ወደ ኤል​ያብ ተመ​ል​ክቶ፥ “በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ባው በፊቱ ነው” አለ።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ፊቱን፥ የቁ​መ​ቱ​ንም ዘለ​ግታ አትይ፤ ሰው እን​ደ​ሚ​ያይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አያ​ይ​ምና ናቅ​ሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ልብን ያያል” አለው።</verse>
				<verse number="8">እሴ​ይም አሚ​ና​ዳ​ብን ጠርቶ በሳ​ሙ​ኤል ፊት አሳ​ለ​ፈው፤ እር​ሱም፥ “ይህን ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​መ​ረ​ጠ​ውም” አለ።</verse>
				<verse number="9">እሴ​ይም ሣማ​ዕን አሳ​ለ​ፈው፤ እር​ሱም፥ “ይህን ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​መ​ረ​ጠ​ውም” አለ።</verse>
				<verse number="10">እሴ​ይም ከል​ጆቹ ሰባ​ቱን በሳ​ሙ​ኤል ፊት አሳ​ለ​ፋ​ቸው። ሳሙ​ኤ​ልም እሴ​ይን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አል​መ​ረ​ጠም” አለው።</verse>
				<verse number="11">ሳሙ​ኤ​ልም እሴ​ይን፥ “ልጆ​ችህ እኒህ ብቻ ናቸው?” አለው። እር​ሱም፥ “ታናሹ ገና ቀር​ቶ​አል፤ እነ​ሆም፥ በጎ​ችን ይጠ​ብ​ቃል” አለ። ሳሙ​ኤ​ልም እሴ​ይን፥ “እርሱ እስ​ኪ​መጣ ድረስ ለማ​ዕድ አን​ቀ​መ​ጥ​ምና ልከህ አስ​መ​ጣው” አለው።</verse>
				<verse number="12">ልኮም አስ​መ​ጣው፤ እር​ሱም ቀይ፥ ዐይ​ኑም የተ​ዋበ፥ መል​ኩም ያማረ ነበረ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ይህ መል​ካም ነውና ተነ​ሥ​ተህ ዳዊ​ትን ቅባው” አለው።</verse>
				<verse number="13">ሳሙ​ኤ​ልም የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ወስዶ በወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል ቀባው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳ​ዊት ላይ መጣ። ሳሙ​ኤ​ልም ተነ​ሥቶ ወደ አር​ማ​ቴም ሄደ።</verse>
				<verse number="14">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ ከሳ​ኦል ራቀ፤ ክፉም መን​ፈስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ አስ​ጨ​ነ​ቀው።</verse>
				<verse number="15">የሳ​ኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖች፥ “እነሆ፥ ክፉ መን​ፈስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ያስ​ጨ​ን​ቅ​ሃል፤</verse>
				<verse number="16">አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በፊ​ትህ ይና​ገሩ፤ በበ​ገና የሚ​ዘ​ምር ሰውም ለጌ​ታ​ቸው ይፈ​ል​ጉ​ለት፤ ክፉ መን​ፈ​ስም በመ​ጣ​ብህ ጊዜ በገ​ና​ውን ሲመታ አንተ ደኅና ትሆ​ና​ለህ፤ እር​ሱም ያሳ​ር​ፍ​ሃል” አሉት።</verse>
				<verse number="17">ሳኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “መል​ካም አድ​ርጎ በገና መም​ታት የሚ​ችል ሰው ፈል​ጋ​ችሁ አም​ጡ​ልኝ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አንዱ መልሶ፥ “እነሆ፥ መል​ካም አድ​ርጎ በገና ሲመታ የቤተ ልሔ​ሙን የእ​ሴ​ይን ልጅ አይ​ቻ​ለሁ፤ ሰው​የ​ውም ጠቢብ፥ ተዋ​ጊም ነው፤ በነ​ገ​ርም ብልህ፥ መል​ኩም ያማረ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነው” አለ።</verse>
				<verse number="19">ሳኦ​ልም ወደ እሴይ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ልኮ፥ “ከመ​ን​ጋ​ዎ​ችህ ጋር ያለ​ውን ልጅ​ህን ዳዊ​ትን ላክ​ልኝ” አለ።</verse>
				<verse number="20">እሴ​ይም እን​ጀ​ራና የወ​ይን ጠጅ አቁ​ማዳ የተ​ጫነ አህያ፥ አን​ድም የፍ​የል ጠቦት ወስዶ በልጁ በዳ​ዊት እጅ ወደ ሳኦል ላከ።</verse>
				<verse number="21">ዳዊ​ትም ወደ ሳኦል መጣ፤ በፊ​ቱም ቆመ፤ እጅ​ግም ወደ​ደው፤ ለእ​ር​ሱም ጋሻ ጃግ​ሬው ሆነ።</verse>
				<verse number="22">ሳኦ​ልም ወደ እሴይ፥ “በዐ​ይኔ ሞገስ አግ​ኝ​ቶ​አ​ልና ዳዊት በፊቴ እባ​ክህ ይቁም፥” ብሎ ላከ።</verse>
				<verse number="23">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ያ ክፉ መን​ፈስ በሳ​ኦል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞ በእጁ ይመታ ነበር፤ ሳኦ​ል​ንም ደስ ያሰ​ኘው፥ ያሳ​ር​ፈ​ውም ነበር፥ ክፉው መን​ፈ​ስም ከእ​ርሱ ይርቅ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ለጦ​ር​ነት ሰበ​ሰቡ፤ ራሳ​ቸ​ውም በይ​ሁዳ በሰ​ኮት ተሰ​በ​ሰቡ፤ በሰ​ኮ​ትና በዓ​ዜቃ መካ​ከል በኤ​ፌ​ር​ሜም ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="2">ሳኦ​ልና የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎ​ችም ተሰ​በ​ሰቡ፤ በኤላ ሸለ​ቆም ሰፈሩ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጋር ሊዋጉ ተሰ​ለፉ።</verse>
				<verse number="3">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም በአ​ንድ ወገን በተ​ራራ ላይ ቆመው ነበር፥ እስ​ራ​ኤ​ልም በሌ​ላው ወገን በተ​ራራ ላይ ቆመው ነበር፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ሸለቆ ነበረ።</verse>
				<verse number="4">ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሰፈር የጌት ሰው ጎል​ያድ፥ ቁመ​ቱም ስድ​ስት ክንድ ከስ​ን​ዝር የሆነ፥ ኀይ​ለኛ ሰው መጣ።</verse>
				<verse number="5">በራ​ሱም የናስ ቍር ደፍቶ ነበር፤ ጥሩ​ርም ለብሶ ነበር፤ የጥ​ሩ​ሩም ሚዛን አም​ስት ሺህ ሰቅል ናስና ብረት ነበረ።</verse>
				<verse number="6">በእ​ግ​ሮ​ቹም ላይ የናስ ገም​ባሌ ነበረ፤ የና​ስም ጭሬ በት​ከ​ሻው ላይ ነበረ።</verse>
				<verse number="7">የጦ​ሩም የቦ እንደ ሸማኔ መጠ​ቅ​ለያ ነበረ፤ የጦ​ሩም ሚዛን ስድ​ስት መቶ ሰቅል ብረት ነበረ፤ ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም በፊቱ ይሄድ ነበር።</verse>
				<verse number="8">እር​ሱም ቆሞ ወደ እስ​ራ​ኤል ጭፍ​ሮች ጮኸ፥ “ከእኛ ጋር ትዋጉ ዘንድ ለምን ወጣ​ችሁ? እኔ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? እና​ን​ተስ የሳ​ኦል አገ​ል​ጋ​ዮች ዕብ​ራ​ው​ያን አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን? ከእ​ና​ንተ አንድ ሰው ምረጡ፤ ወደ እኔም ይው​ረድ፤</verse>
				<verse number="9">ከእ​ኔም ጋር ሊዋጋ ቢችል ቢገ​ድ​ለ​ኝም፥ ባሪ​ያ​ዎች እን​ሆ​ና​ች​ኋ​ለን፤ እኔ ግን ባሸ​ን​ፈው፥ ብገ​ድ​ለ​ውም፥ እና​ንተ ባሪ​ያ​ዎች ትሆ​ኑ​ና​ላ​ችሁ፤ ለእ​ኛም ትገ​ዛ​ላ​ችሁ” አለ።</verse>
				<verse number="10">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም፥ “ዛሬ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጭፍ​ሮች ተገ​ዳ​ደ​ር​ኋ​ቸው፤ አንድ ሰው ስጡኝ ሁለ​ታ​ች​ንም ለብ​ቻ​ችን እን​ዋጋ አል​ኋ​ቸው” አለ።</verse>
				<verse number="11">ሳኦ​ልና እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ይህን የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን ቃል በሰሙ ጊዜ እጅግ ፈሩ፤ ደነ​ገ​ጡም።</verse>
				<verse number="12">ዳዊ​ትም የዚያ የኤ​ፍ​ራ​ታ​ዊው ሰው ልጅ ነበረ፤ ያም ሰው ከቤተ ልሔም ይሁዳ ስሙም እሴይ ነበረ፤ ስም​ንት ልጆ​ችም ነበ​ሩት፤ እሴ​ይም በሳ​ኦል ዘመን በዕ​ድሜ አር​ጅቶ ሸም​ግ​ሎም ነበር።</verse>
				<verse number="13">የእ​ሴ​ይም ሦስቱ ታላ​ላ​ቆች ልጆቹ ሳኦ​ልን ተከ​ት​ለው ወደ ሰልፉ ሄደው ነበር፤ ወደ ሰል​ፉም የሄ​ዱት የሦ​ስቱ ልጆች ስም ይህ ነበረ፤ ታላቁ ኤል​ያብ፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም አሚ​ና​ዳብ፥ ሦስ​ተ​ኛ​ውም ሣማዕ ነበረ።</verse>
				<verse number="14">ዳዊ​ትም የሁሉ ታናሽ ነበረ፤ ሦስ​ቱም ታላ​ላ​ቆቹ ሳኦ​ልን ተከ​ት​ለው ነበር።</verse>
				<verse number="15">ዳዊ​ትም የአ​ባ​ቱን በጎች ለመ​ጠ​በቅ ከሳ​ኦል ዘንድ ወደ ቤተ ልሔም ይመ​ላ​ለስ ነበር።</verse>
				<verse number="16">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ጥዋ​ትና ማታ እየ​መጣ አርባ ቀን ይቆም ነበር።</verse>
				<verse number="17">እሴ​ይም ልጁን ዳዊ​ትን እን​ዲህ አለው፥ “ከዚህ በሶ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ እነ​ዚ​ህ​ንም ዐሥር እን​ጀ​ራ​ዎች ለወ​ን​ድ​ሞ​ችህ ውሰድ፤ ወደ ሰፈ​ሩም ፈጥ​ነህ ሂድና ለወ​ን​ድ​ሞ​ችህ ስጣ​ቸው፤</verse>
				<verse number="18">ይህ​ንም ዐሥ​ሩን አይብ ወደ ሻለ​ቃው ውሰ​ደው፤ የወ​ን​ድ​ሞ​ች​ህ​ንም ደኅ​ን​ነት ጠይቅ፤ ወሬ​አ​ቸ​ው​ንም አም​ጣ​ልኝ።”</verse>
				<verse number="19">ሳኦ​ልና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር እየ​ተ​ዋጉ በኤላ ሸለቆ ነበሩ።</verse>
				<verse number="20">ዳዊ​ትም ማልዶ ተነሣ፤ በጎ​ቹ​ንም ለጠ​ባቂ ተወ፤ እሴ​ይም ያዘ​ዘ​ውን ይዞ ሄደ፤ ጭፍ​ራ​ውም ተሰ​ልፎ ሲወጣ፥ ለሰ​ል​ፍም ሲጮኽ በሰ​ረ​ገ​ሎች ወደ ተከ​በ​በው ሰፈር መጣ።</verse>
				<verse number="21">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልና የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሠራ​ዊ​ትም ፊት ለፊት ተሰ​ላ​ል​ፈው ነበር።</verse>
				<verse number="22">ዳዊ​ትም ዕቃ​ውን በዕቃ ጠባ​ቂው እጅ አኖ​ረው፤ ወደ​ሚ​ዋ​ጉ​በ​ትም ሮጦ ሄደ፤ የወ​ን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ደኅ​ን​ነት ጠየቀ።</verse>
				<verse number="23">እር​ሱም ሲነ​ጋ​ገ​ራ​ቸው፥ እነሆ፥ ጎል​ያድ የተ​ባለ ያ አር​በኛ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ የጌት ሰው ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጭፍራ መካ​ከል ወጣ፤ ቀድሞ የተ​ና​ገ​ረ​ው​ንም ቃል ተና​ገረ፤ ዳዊ​ትም ሰማ።</verse>
				<verse number="24">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ሰው​ዬ​ውን ባዩ ጊዜ እጅግ ፈር​ተው ከፊቱ ሸሹ።</verse>
				<verse number="25">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች፥ “ይህን የወ​ጣ​ውን ሰው አያ​ች​ሁ​ትን? በእ​ው​ነት እስ​ራ​ኤ​ልን ሊገ​ዳ​ደር ወጣ፤ የሚ​ገ​ድ​ለ​ው​ንም ሰው ንጉሡ እጅግ ባለ​ጠጋ ያደ​ር​ገ​ዋል፤ ልጁ​ንም ይድ​ር​ለ​ታል፤ ያባ​ቱ​ንም ቤተ ሰብ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ከግ​ብር ነጻ ያወ​ጣ​ቸ​ዋል” አሉ።</verse>
				<verse number="26">ዳዊ​ትም በአ​ጠ​ገቡ ለቆ​ሙት ሰዎች፦ ይህን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ለሚ​ገ​ድል፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተግ​ዳ​ሮ​ትን ለሚ​ያ​ርቅ ሰው በውኑ ይህ ይደ​ረ​ግ​ለ​ታል? የሕ​ያው አም​ላ​ክን ጭፍ​ሮች የሚ​ገ​ዳ​ደር ይህ ያል​ተ​ገ​ረዘ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ማን ነው?” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="27">ሕዝ​ቡም፥ “ለሚ​ገ​ድ​ለው ሰው እን​ዲህ ይደ​ረ​ግ​ለ​ታል” ብለው እንደ ቀድ​ሞው መለ​ሱ​ለት።</verse>
				<verse number="28">ታላቅ ወን​ድ​ሙም ኤል​ያብ ከሰ​ዎች ጋር ሲነ​ጋ​ገር ሰማ፤ ኤል​ያ​ብም በዳ​ዊት ላይ እጅግ ተቈጣ፥ “ለምን ወደ​ዚህ ወረ​ድህ? እነ​ዚ​ያ​ንስ ጥቂ​ቶች በጎች በም​ድረ በዳ ለማን ተው​ሃ​ቸው? እኔ ኵራ​ት​ህ​ንና የል​ብ​ህን ክፋት አው​ቃ​ለ​ሁና ሰል​ፉን ለማ​የት መጥ​ተ​ሃል” አለው።</verse>
				<verse number="29">ዳዊ​ትም፥ “እኔ ምን አደ​ረ​ግሁ? ይህ ታላቅ ነገር አይ​ደ​ለ​ምን?” አለ።</verse>
				<verse number="30">ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ ወደ ሌላ ሰው ዘወር አለ፤ እን​ደ​ዚ​ህም ያለ ነገር ተና​ገረ፤ ሕዝ​ቡም እንደ ቀድ​ሞው ያለ ነገር መለ​ሱ​ለት።</verse>
				<verse number="31">ዳዊ​ትም የተ​ና​ገ​ረው ቃል ተሰማ፤ ለሳ​ኦ​ልም ነገ​ሩት፤ ወደ እር​ሱም ወሰ​ደው።</verse>
				<verse number="32">ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን፥ “ስለ እርሱ የማ​ንም ልብ አይ​ው​ደቅ፤ እኔ ባሪ​ያህ ሄጄ ያን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ እወ​ጋ​ዋ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="33">ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “አንተ ገና ብላ​ቴና ነህና፥ እር​ሱም ከብ​ላ​ቴ​ን​ነቱ ጀምሮ ጦረኛ ነውና ይህን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ለመ​ው​ጋት ትሄድ ዘንድ አት​ች​ልም” አለው።</verse>
				<verse number="34">ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን አለው፥ “እኔ ባሪ​ያህ የአ​ባ​ቴን በጎች ስጠ​ብቅ አን​በሳ ወይም ድብ ይመጣ ነበር፤ ከመ​ን​ጋ​ውም ጠቦት ይወ​ስድ ነበር።</verse>
				<verse number="35">በኋ​ላ​ውም እከ​ተ​ለ​ውና እመ​ታው ነበር። ከአ​ፉም አስ​ጥ​ለው ነበር፤ በተ​ነ​ሣ​ብ​ኝም ጊዜ ጕሮ​ሮ​ውን አንቄ እመ​ታ​ውና እገ​ድ​ለው ነበር።</verse>
				<verse number="36">እኔ ባሪ​ያህ አን​በ​ሳና ድብ ገደ​ልሁ፤ ይህም ያል​ተ​ገ​ረ​ዘው ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ከእ​ነ​ርሱ እንደ አንዱ ይሆ​ናል። እን​ግ​ዲህ እገ​ድ​ለው ዘንድ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተግ​ዳ​ሮ​ትን አስ​ወ​ግድ ዘንድ ዛሬ አል​ሄ​ድ​ምን? የሕ​ያው አም​ላክ ጭፍ​ሮ​ችን ይገ​ዳ​ደር ዘንድ ይህ ቈላፍ ምን​ድን ነው?”</verse>
				<verse number="37">ዳዊ​ትም፥ “ከአ​ን​በ​ሳና ከድብ እጅ ያስ​ጣ​ለኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚህ ያል​ተ​ገ​ረዘ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ እጅ ያስ​ጥ​ለ​ኛል” አለ። ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “ሂድ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ንተ ጋር ይሁን” አለው።</verse>
				<verse number="38">ሳኦ​ልም ለዳ​ዊት ጥሩር አለ​በ​ሰው፤ በራ​ሱም ላይ የናስ ቍር ደፋ​ለት።</verse>
				<verse number="39">ዳዊ​ት​ንም ሰይ​ፉን በል​ብሱ ላይ አስ​ታ​ጠ​ቀው፤ ዳዊ​ትም አን​ድና ሁለት ጊዜ ሲራ​መድ ደከመ። ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን፥ “አለ​መ​ድ​ሁ​ምና በዚህ መሄድ አል​ች​ልም” አለው። ከላ​ዩም አወ​ለ​ቁ​ለት።</verse>
				<verse number="40">ዳዊ​ትም በት​ሩን በእጁ ያዘ፤ ከወ​ን​ዝም አም​ስት ድብ​ል​ብል ድን​ጋ​ዮ​ችን መረጠ፤ በእ​ረኛ ኮሮ​ጆ​ውም በኪሱ ከተ​ታ​ቸው፤ ወን​ጭ​ፍም በእጁ ነበረ፤ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ቀረበ።</verse>
				<verse number="41">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም መጥቶ ወደ ዳዊት ቀረበ፤ ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም በፊቱ ይሄድ ነበር።</verse>
				<verse number="42">ጎል​ያ​ድም ዳዊ​ትን ትኩር ብሎ አየው፤ ቀይ ብላ​ቴና፥ መል​ኩም ያማረ ነበ​ረና ናቀው።</verse>
				<verse number="43">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን፥ “በት​ርና ድን​ጋይ ይዘህ የም​ት​መ​ጣ​ብኝ እኔ ውሻ ነኝን?” አለው። ዳዊ​ትም፥ “የለም ከውሻ ትከ​ፋ​ለህ” አለው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን በአ​ም​ላ​ኮቹ ረገ​መው።</verse>
				<verse number="44">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን፥ “ወደ እኔ ና፤ ሥጋ​ህ​ንም ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="45">ዳዊ​ትም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ዉን አለው፥ “አንተ ሰይ​ፍና ጦር፥ ጋሻም ይዘህ ትመ​ጣ​ብ​ኛ​ለህ፤ እኔ ግን ዛሬ በተ​ገ​ዳ​ደ​ር​ኸው በእ​ስ​ራ​ኤል ጭፍ​ሮች አም​ላክ ስም በሰ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም እመ​ጣ​ብ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="46">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ አን​ተን በእጄ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል፤ እመ​ታ​ህ​ማ​ለሁ፤ ራስ​ህ​ንም ከአ​ንተ እቈ​ር​ጠ​ዋ​ለሁ፤ ሬሳ​ህ​ንና የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ሠራ​ዊት ሬሶች ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት ዛሬ እሰ​ጣ​ለሁ። ምድር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር እን​ዳለ ያው​ቃሉ፤</verse>
				<verse number="47">ይህም ጉባኤ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ይ​ፍና በጦር የሚ​ያ​ድን እን​ዳ​ይ​ደለ ያው​ቃል። ሰልፉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እና​ን​ተን በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል።”</verse>
				<verse number="48">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ተነ​ሥቶ ዳዊ​ትን ሊገ​ና​ኘው በቀ​ረበ ጊዜ ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ዉን ሊገ​ና​ኘው ወደ ሰልፉ ሮጠ።</verse>
				<verse number="49">ዳዊ​ትም እጁን ወደ ኮሮ​ጆው አግ​ብቶ አንድ ድን​ጋይ ወሰደ፤ ወነ​ጨ​ፈ​ውም፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም ግን​ባ​ሩን መታው፤ ድን​ጋ​ዩም ጥሩ​ሩን ዘልቆ በግ​ን​ባሩ ተቀ​ረ​ቀረ፤ እር​ሱም በም​ድር ላይ በፊቱ ተደፋ።</verse>
				<verse number="50">ዳዊ​ትም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን በወ​ን​ጭ​ፍና በድ​ን​ጋይ አሸ​ነ​ፈው፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም መትቶ ገደለ ፤ በዳ​ዊ​ትም እጅ ሰይፍ አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="51">ዳዊ​ትም ሮጦ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው ላይ ቆመ፤ ሰይ​ፉ​ንም ይዞ ከሰ​ገ​ባው መዘ​ዘው፤ ገደ​ለ​ውም፤ ራሱ​ንም ቈረ​ጠው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ዋና​ቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ሸሹ።</verse>
				<verse number="52">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልና የይ​ሁዳ ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው እልል አሉ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም እስከ ጌትና እስከ አስ​ቀ​ሎና በር ድረስ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው። የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም በድ​ኖ​ቻ​ቸው እስከ ጌትና እስከ አቃ​ሮን በሮች ድረስ በመ​ን​ገድ ላይ ወደቁ።</verse>
				<verse number="53">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ከማ​ሳ​ደድ ተመ​ል​ሰው ሰፈ​ራ​ቸ​ውን በዘ​በዙ።</verse>
				<verse number="54">ዳዊ​ትም የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን ራስ ይዞ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመ​ጣው፤ ጋሻና ጦሩን ግን በድ​ን​ኳኑ ውስጥ አኖ​ረው።</verse>
				<verse number="55">ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን ሊዋጋ ሲወጣ ባየ ጊዜ ለሠ​ራ​ዊቱ አለቃ ለአ​ቤ​ኔር፥ “አቤ​ኔር ሆይ፥ ይህ ብላ​ቴና የማን ልጅ ነው?” አለው። አቤ​ኔ​ርም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ አላ​ው​ቅም” አለ።</verse>
				<verse number="56">ንጉ​ሡም፥ “ይህ ብላ​ቴና የማን ልጅ እንደ ሆነ አንተ ጠይ​ቅና ዕወቅ” አለው።</verse>
				<verse number="57">ዳዊ​ትም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን ገድሎ በተ​መ​ለሰ ጊዜ አቤ​ኔር ወሰ​ደው፤ ወደ ሳኦ​ልም ፊት አመ​ጣው፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም ራስ በእጁ ይዞ ነበር።</verse>
				<verse number="58">ሳኦ​ልም፥ “አንተ ብላ​ቴና የማን ልጅ ነህ?” አለው ዳዊ​ትም፥ “እኔ የቤተ ልሔሙ የባ​ሪ​ያህ የእ​ሴይ ልጅ ነኝ” ብሎ መለሰ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት ለሳ​ኦል መን​ገ​ሩን በፈ​ጸመ ጊዜ የዮ​ና​ታን ነፍስ በዳ​ዊት ነፍስ ታሰ​ረች፤ ዮና​ታ​ንም እንደ ነፍሱ ወደ​ደው።</verse>
				<verse number="2">በዚ​ያም ቀን ሳኦል ወሰ​ደው፤ ወደ አባ​ቱም ቤት ይመ​ል​ሰው ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="3">ዮና​ታ​ንም እንደ ነፍሱ ስለ ወደ​ደው ዮና​ታ​ንና ዳዊት ቃል ኪዳን አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="4">ዮና​ታ​ንም የለ​በ​ሰ​ውን ካባ አው​ልቆ እር​ሱ​ንና ልብ​ሱን፥ ሰይ​ፉ​ንም፥ ቀስ​ቱ​ንም፥ ዝና​ሩ​ንም ለዳ​ዊት ሸለ​መው።</verse>
				<verse number="5">ዳዊ​ትም ሳኦል ወደ ላከው ሁሉ ይሄድ ነበር፤ አስ​ተ​ው​ሎም ያደ​ርግ ነበር፤ ሳኦ​ልም በጦ​ረ​ኞች ላይ ሾመው፤ ይህም በሕ​ዝብ ሁሉ ዐይ​ንና በሳ​ኦል ባሪ​ያ​ዎች ዐይን መል​ካም ነበረ።</verse>
				<verse number="6">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን ገድሎ በተ​መ​ለሰ ጊዜ፥ እየ​ዘ​መ​ሩና እየ​ዘ​ፈኑ፥ እል​ልም እያሉ ከበ​ሮና አታሞ ይዘው ዳዊ​ትን ሊቀ​በሉ ሴቶች ከእ​ስ​ራ​ኤል ከተ​ሞች ሁሉ ወጡ።</verse>
				<verse number="7">ሴቶ​ችም፥ “ሳኦል ሺህ ገደለ፤ ዳዊ​ትም ዐሥር ሺህ ገደለ” እያሉ እየ​ተ​ቀ​ባ​በሉ ይዘ​ፍኑ ነበር።</verse>
				<verse number="8">ሳኦ​ልም እጅግ ተቈጣ፤ ይህም ነገር ሳኦ​ልን አስ​ከ​ፋው፤ እር​ሱም፥ “ለዳ​ዊት ዐሥር ሺህ ሰጡት፤ ለእኔ ግን ሺህ ብቻ ሰጡኝ፤ ከመ​ን​ግ​ሥት በቀር ምን ቀረ​በት?” አለ።</verse>
				<verse number="9">ከዚ​ያም ቀን ጀምሮ ሳኦል ዳዊ​ትን ሁል​ጊዜ ይጠ​ባ​በ​ቀው ነበር።</verse>
				<verse number="10">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በነ​ጋው ሳኦ​ልን ክፉ መን​ፈስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ያዘው፤ በቤ​ቱም ውስጥ ትን​ቢት ተና​ገረ። ዳዊ​ትም በየ​ቀኑ ያደ​ርግ እንደ ነበረ በእጁ በገና ይመታ ነበር። ሳኦ​ልም ጦሩን በእጁ ይዞ ነበር።</verse>
				<verse number="11">ሳኦ​ልም፥ “ዳዊ​ትን ከግ​ንቡ ጋር አጣ​ብቄ እመ​ታ​ዋ​ለሁ” ብሎ ጦሩን ወረ​ወረ። ዳዊ​ትም ሁለት ጊዜ ከፊቱ ዘወር አለ።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ስለ ነበረ፥ ከሳ​ኦ​ልም ስለ ተለየ ሳኦል ከዳ​ዊት ፊት የተ​ነሣ ፈራ።</verse>
				<verse number="13">ስለ​ዚ​ህም ሳኦል ከእ​ርሱ አራ​ቀው፤ የሺህ አለ​ቃም አድ​ርጎ ሾመው፤ በሕ​ዝ​ቡም ፊት ይወ​ጣና ይገባ ነበር።</verse>
				<verse number="14">ዳዊ​ትም በአ​ካ​ሄዱ ሁሉ ብል​ህና ዐዋቂ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነበረ።</verse>
				<verse number="15">ሳኦ​ልም እጅግ ብልህ እንደ ሆነ አይቶ እጅግ ፈራው።</verse>
				<verse number="16">ነገር ግን በፊ​ታ​ቸው ይወ​ጣና ይገባ ስለ​ነ​በረ እስ​ራ​ኤ​ልና ይሁዳ ሁሉ ዳዊ​ትን ወደዱ።</verse>
				<verse number="17">ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “ታላ​ቂቱ ልጄ ሜሮብ እነ​ኋት፤ እር​ስ​ዋን እድ​ር​ል​ሃ​ለሁ፤ ብቻ ጀግና ልጅ ሁን​ልኝ፤ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጦር​ነት ተጋ​ደል” አለው። ሳኦ​ልም፥ “የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ በእ​ርሱ ላይ ትሁን እንጂ የእኔ እጅ በእ​ርሱ ላይ አት​ሁን” ይል ነበር።</verse>
				<verse number="18">ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን፥ “ለን​ጉሥ አማች እሆን ዘንድ እኔ ማን ነኝ? ሰው​ነ​ቴስ ምን​ድን ናት? የአ​ባ​ቴስ ወገን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ምን​ድን ነው?” አለው።</verse>
				<verse number="19">ነገር ግን የሳ​ኦል ልጅ ሜሮብ ዳዊ​ትን የም​ታ​ገ​ባ​በት ጊዜ ሲደ​ርስ ለሚ​ሆ​ላ​ዊው ለአ​ድ​ር​ኤል ተዳ​ረች።</verse>
				<verse number="20">የሳ​ኦ​ልም ልጅ ሜል​ኮል ዳዊ​ትን ወደ​ደች፤ ይህም ወሬ ለሳ​ኦል ደረ​ሰ​ለት፤ ነገ​ሩም ደስ አሰ​ኘው።</verse>
				<verse number="21">ሳኦ​ልም፥ “እር​ስ​ዋን እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋም እን​ቅ​ፋት ትሆ​ን​በ​ታ​ለች” አለ። እነ​ሆም፥ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ በሳ​ኦል ላይ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="22">ሳኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “እነሆ፥ ንጉሥ እጅግ ወድ​ዶ​ሃል፤ ቤተ ሰቡም ሁሉ ወድ​ደ​ው​ሃል፤ አሁ​ንም ለን​ጉሥ አማች ሁን ብላ​ችሁ በስ​ውር ለዳ​ዊት ንገ​ሩት” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">የሳ​ኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖች ይህን ቃል በዳ​ዊት ጆሮ ተና​ገሩ፤ ዳዊ​ትም፥ “እኔ የተ​ዋ​ረ​ድ​ሁና ክብር የሌ​ለኝ ሰው ስሆን ለን​ጉሥ አማች እሆን ዘንድ ለእ​ና​ንተ ትንሽ ነገር ይመ​ስ​ላ​ች​ኋ​ልን?” አለ።</verse>
				<verse number="24">የሳ​ኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖች፦ ዳዊት እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ ብለው ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="25">ሳኦ​ልም አላ​ቸው፥ “የን​ጉ​ሥን ጠላ​ቶች ይበ​ቀል ዘንድ ከመቶ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሸለ​ፈት በቀር ንጉሥ ማጫ አይ​ሻም ብላ​ችሁ ለዳ​ዊት ንገ​ሩት” አላ​ቸው። ሳኦል ግን ይህን ማለቱ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ይጥ​ለው ዘንድ አስቦ ነው።</verse>
				<verse number="26">የሳ​ኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖች ይህን ቃል ለዳ​ዊት ነገ​ሩት፤ ለን​ጉ​ሥም አማች ይሆን ዘንድ ዳዊ​ትን ደስ አሰ​ኘው።</verse>
				<verse number="27">ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ተነ​ሥ​ተው ሄዱ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሁለት መቶ ሰዎ​ችን ገደሉ፤ ዳዊ​ትም ለን​ጉሥ አማች ይሆን ዘንድ ሰለ​ባ​ቸ​ውን አም​ጥቶ በቍ​ጥ​ራ​ቸው ልክ ለን​ጉሡ ሰጠ። ሳኦ​ልም ልጁን ሜል​ኮ​ልን ዳረ​ለት።</verse>
				<verse number="28">ሳኦ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዳ​ዊት ጋር እንደ ሆነ አየ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ወደ​ዱት።</verse>
				<verse number="29">ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን አጥ​ብቆ ፈራው፤ ሳኦ​ልም ዕድ​ሜ​ውን ሁሉ ለዳ​ዊት ጠላት ሆነ።</verse>
				<verse number="30">የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም አለ​ቆች ይወጡ ነበር፤ በወ​ጡም ጊዜ ሁሉ ከሳ​ኦል አገ​ል​ጋ​ዮች ሁሉ ይልቅ ዳዊት አስ​ተ​ውሎ ያደ​ርግ ነበ​ርና ስሙ እጅግ ተጠ​ርቶ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">ሳኦ​ልም ለልጁ ለዮ​ና​ታ​ንና ለብ​ላ​ቴ​ኖቹ ሁሉ ዳዊ​ትን ይገ​ድሉ ዘንድ ነገ​ራ​ቸው። የሳ​ኦል ልጅ ዮና​ታን ግን ዳዊ​ትን እጅግ ይወ​ድ​ደው ነበር።</verse>
				<verse number="2">ዮና​ታ​ንም፥ “አባቴ ሳኦል ሊገ​ድ​ልህ ፈል​ጎ​አል፤ አሁን እን​ግ​ዲህ ለነ​ገው ተጠ​ን​ቅ​ቀህ ተሸ​ሸግ፤ በስ​ው​ርም ተቀ​መጥ።</verse>
				<verse number="3">እኔም እወ​ጣ​ለሁ፤ አን​ተም ባለ​ህ​በት እርሻ በአ​ባቴ አጠ​ገብ እቆ​ማ​ለሁ፤ ስለ አን​ተም ለአ​ባቴ እነ​ግ​ረ​ዋ​ለሁ፤ የሆ​ነ​ው​ንም አይቼ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ” ብሎ ለዳ​ዊት ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="4">ዮና​ታ​ንም ለአ​ባቱ ለሳ​ኦል ስለ ዳዊት መል​ካም ተና​ገረ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እርሱ አል​በ​ደ​ለ​ህ​ምና፥ ሥራ​ውም ለአ​ንተ እጅግ መል​ካም ሆኖ​አ​ልና ንጉሡ ባሪ​ያ​ውን ዳዊ​ትን አይ​በ​ድ​ለው፤</verse>
				<verse number="5">ነፍ​ሱ​ንም በእጁ ጥሎ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ዉን ገደለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ርሱ ታላቅ መድ​ኀ​ኒት አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አይ​ተው ደስ አላ​ቸው፤ በከ​ንቱ ዳዊ​ትን ትገ​ድ​ለው ዘንድ ስለ​ምን በን​ጹሕ ደም ላይ ትበ​ድ​ላ​ለህ?”</verse>
				<verse number="6">ሳኦ​ልም የዮ​ና​ታ​ንን ቃል ሰማ፤ ሳኦ​ልም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ዳዊት አይ​ገ​ደ​ልም” ብሎ ማለ።</verse>
				<verse number="7">ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን ጠርቶ ይህን ነገር ሁሉ ነገ​ረው፤ ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን ወደ ሳኦል አመ​ጣው፤ እንደ ቀድ​ሞ​ውም በፊቱ ነበረ።</verse>
				<verse number="8">ደግ​ሞም ጦር​ነት ሆነ፤ ዳዊ​ትም ወጥቶ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ተዋጋ፤ ታላቅ ግዳ​ይም ገደ​ላ​ቸው፤ ከፊ​ቱም ሸሹ።</verse>
				<verse number="9">ሳኦ​ልም ጦሩን ይዞ በቤቱ ተቀ​ምጦ ሳለ ክፉ መን​ፈስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ያዘው። ዳዊ​ትም በእጁ በገና ይመታ ነበር።</verse>
				<verse number="10">ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ከግ​ንብ ጋር ያጣ​ብ​ቀው ዘንድ ጦሩን ወረ​ወረ፤ ዳዊ​ትም ከሳ​ኦል ፊት ዘወር አለ፤ ጦሩም በግ​ንቡ ውስጥ ተተ​ከለ፤ በዚ​ያም ሌሊት ዳዊት ሸሸቶ አመ​ለጠ።</verse>
				<verse number="11">ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ጠበ​ቀው፤ በነ​ጋው እን​ዲ​ገ​ድ​ሉት መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹን ወደ ዳዊት ቤት ላከ፤ ሚስ​ቱም ሜል​ኮል፥ “በዚ​ህች ሌሊት ነፍ​ስ​ህን ካላ​ዳ​ንህ ነገ ትገ​ደ​ላ​ለህ” ብላ ነገ​ረ​ችው።</verse>
				<verse number="12">ሜል​ኮ​ልም ዳዊ​ትን በመ​ስ​ኮት አወ​ረ​ደ​ችው፤ ሄደም፤ ሸሽ​ቶም አመ​ለጠ።</verse>
				<verse number="13">ሜል​ኮ​ልም ተራ​ፊ​ምን ወስዳ በአ​ልጋ ላይ አኖ​ረ​ችው፤ በራ​ስ​ጌ​ውም ጕን​ጕን የፍ​የል ጠጕር አደ​ረ​ገች፤ በል​ብ​ስም ከደ​ነ​ችው።</verse>
				<verse number="14">ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ይዘው እን​ዲ​ያ​መ​ጡት መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እር​ስ​ዋም ታሞ​አል አለ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">ሳኦ​ልም፥ “እገ​ድ​ለው ዘንድ ዳዊ​ትን ከነ​አ​ል​ጋው” አም​ጡ​ልኝ ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹን ወደ ዳዊት ላከ።</verse>
				<verse number="16">መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹም በገቡ ጊዜ እነሆ፥ ተራ​ፊ​ሙን በአ​ል​ጋው ላይ አገኙ፤ በራ​ስ​ጌ​ውም ጕን​ጕን የፍ​የል ጠጕር ነበረ።</verse>
				<verse number="17">ሳኦ​ልም ሜል​ኮ​ልን አላት፥ “ስለ​ምን እን​ዲህ አታ​ለ​ል​ሽኝ? ጠላ​ቴን አስ​ኰ​በ​ለ​ልሽ፤ እን​ዲ​ያ​መ​ል​ጥም አደ​ረ​ግ​ሽው?” ሜል​ኮ​ልም ለሳ​ኦል፥ “እርሱ፦ አው​ጥ​ተሽ ስደ​ጂኝ፤ አለ​ዚያ እገ​ድ​ል​ሻ​ለሁ አለኝ” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="18">ዳዊ​ትም ሸሽቶ አመ​ለጠ፤ ወደ አር​ማ​ቴ​ምም ወደ ሳሙ​ኤል መጣ፤ ሳኦ​ልም ያደ​ረ​ገ​በ​ትን ሁሉ ነገ​ረው፤ እር​ሱና ሳሙ​ኤ​ልም ሄዱ፤ በአ​ው​ቴ​ዘ​ራ​ማም ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="19">ለሳ​ኦ​ልም፥ “ዳዊት እነሆ፥ በአ​ው​ቴ​ዘ​ራማ ተቀ​ም​ጦ​አል” ብለው ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="20">ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ያመ​ጡት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ የነ​ቢ​ያ​ት​ንም ጉባኤ አገኙ፤ ሳሙ​ኤ​ልም አለ​ቃ​ቸው ሆኖ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቆሞ ነበረ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በሳ​ኦል መል​እ​ክ​ተ​ኞች ላይ ወረደ፤ እነ​ር​ሱም ትን​ቢት ይና​ገሩ ጀመር።</verse>
				<verse number="21">ለሳ​ኦ​ልም ይህን በነ​ገ​ሩት ጊዜ ሌሎች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እነ​ር​ሱም ደግሞ ትን​ቢት ተና​ገሩ። ሳኦ​ልም እንደ ገና ሦስ​ተኛ ጊዜ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እነ​ር​ሱም ደግሞ ትን​ቢት ተና​ገሩ።</verse>
				<verse number="22">ሳኦ​ልም እጅግ ተቈጣ፤ እር​ሱም ደግሞ ወደ አር​ማ​ቴም መጣ፤ በመ​ሴ​ፋም አው​ድማ ወዳ​ለው ወደ ታላቁ የውኃ ጕድ​ጓድ ደረሰ። “ሳሙ​ኤ​ልና ዳዊት የት ናቸው?” ብሎ ጠየቀ፤ “እነሆ፥ በአ​ው​ቴ​ዘ​ራማ ናቸው” አሉት።</verse>
				<verse number="23">ወደ አው​ቴ​ዘ​ራ​ማም ሄደ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ደግሞ ወረደ፤ እር​ሱም ሄደ፤ ወደ አው​ቴ​ዘ​ራ​ማም እስ​ኪ​መጣ ድረስ ትን​ቢት ይና​ገር ነበር።</verse>
				<verse number="24">ልብ​ሱ​ንም አወ​ለቀ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ትን​ቢት ተና​ገረ፤ ራቁ​ቱ​ንም ወድቆ በዚያ ቀን ሁሉ በዚ​ያም ሌሊት ሁሉ ተጋ​ደመ። ስለ​ዚህ፥ “ሳኦል ደግሞ ከነ​ቢ​ያት መካ​ከል ነውን?” ይባ​ባሉ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">ዳዊ​ትም ከአ​ው​ቴ​ዘ​ራማ ሸሸ፤ ወደ ዮና​ታ​ንም መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ምን አደ​ረ​ግሁ? ምንስ በደ​ልሁ? ነፍ​ሴ​ንም ይሻት ዘንድ በአ​ባ​ትህ ፊት ጥፋ​ቴና ኀጢ​አቴ ምን​ድን ነው?”</verse>
				<verse number="2">ዮና​ታ​ንም፥ “ይህ​ንስ ያር​ቀው፤ አት​ሞ​ትም፤ እነሆ፥ አባቴ አስ​ቀ​ድሞ ለእኔ ሳይ​ገ​ልጥ ትል​ቅም ሆነ ትንሽ ነገር ቢሆን አያ​ደ​ር​ግም፤ አባ​ቴስ ይህን ነገር ለምን ይሰ​ው​ረ​ኛል? እን​ዲህ አይ​ደ​ለም” አለው።</verse>
				<verse number="3">ዳዊ​ትም፥ “እኔ በፊ​ትህ ሞገ​ስን እን​ዳ​ገ​ኘሁ አባ​ትህ በእ​ው​ነት ያው​ቃል፤ እር​ሱም፦ ዮና​ታን እን​ዳ​ይ​ቃ​ወም አይ​ወቅ ይላል፤ ነገር ግን ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በሕ​ያው ነፍ​ስ​ህም እም​ላ​ለሁ፤ እኔ እን​ዳ​ል​ሁት በእ​ኔና በሞት መካ​ከል አንድ ርምጃ ያህል ቀር​ቶ​አል” ብሎ ማለ።</verse>
				<verse number="4">ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን፥ “ነፍ​ስህ ምን ትፈ​ል​ጋ​ለች? እኔስ ምን ላድ​ር​ግ​ልህ?” አለው።</verse>
				<verse number="5">ዳዊ​ትም ዮና​ታ​ንን አለው፥ “እነሆ ነገ መባቻ ነው፤ በን​ጉ​ሥም አጠ​ገብ ለምሳ አል​ቀ​መ​ጥም፤ እስከ ማታ ድረስ በውጭ በሜዳ እን​ድ​ሸ​ሸግ አሰ​ና​ብ​ተኝ ።</verse>
				<verse number="6">አባ​ት​ህም ቢፈ​ል​ገኝ፦ ለዘ​መ​ዶቹ ሁሉ በዚያ በቤተ ልሔም የዓ​መት መሥ​ዋ​ዕት አላ​ቸ​ውና ዳዊት ወደ ከተ​ማው ፈጥኖ ይሄድ ዘንድ አጽ​ንቶ ለም​ኖ​ኛል በለው።</verse>
				<verse number="7">እር​ሱም፦ መል​ካም ነው ቢል ለእኔ ለባ​ሪ​ያህ ሰላም ይሆ​ናል፤ ቢቈጣ ግን ክፋት ከእ​ርሱ ዘንድ በእኔ ላይ እንደ ተቈ​ረ​ጠች ዕወቅ።</verse>
				<verse number="8">እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ከባ​ሪ​ያህ ጋር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ለባ​ሪ​ያህ ቸር​ነ​ትን አድ​ርግ፤ በደል ግን ቢገ​ኝ​ብኝ አንተ ግደ​ለኝ፤ ለምን ወደ አባ​ትህ ታደ​ር​ሰ​ኛ​ለህ?”</verse>
				<verse number="9">ዮና​ታ​ንም፥ “ይህ ከአ​ንተ ይራቅ፤ ከአ​ባቴ ዘንድ ክፋት በላ​ይህ እንደ ተቈ​ረ​ጠች ያወ​ቅሁ እንደ ሆነ በከ​ተማ ባት​ኖ​ርም እን​ኳን ወደ አንተ መጥቼ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="10">ዳዊ​ትም ዮና​ታ​ንን፥ “አባ​ትህ ስለ እኔ ክፉ ነገር የነ​ገ​ረህ እንደ ሆነ ማን ይነ​ግ​ረ​ኛል?” አለው።</verse>
				<verse number="11">ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን፥ “ና፤ ወደ ሜዳ እን​ውጣ” አለው። ሁለ​ቱም ወደ ሜዳ ወጡ።</verse>
				<verse number="12">ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን አለው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያው​ቃል፤ እስከ ሦስት ቀን ድረስ በዚህ ጊዜ አባ​ቴን መር​ምሬ እነሆ፥ በዳ​ዊት ላይ መል​ካም ቢያ​ስብ፥ እነሆ፥ ወደ ሜዳ ወደ አንተ አል​ል​ክም፤ ይህም ምል​ክት ይሁ​ንህ፤</verse>
				<verse number="13">አባ​ቴም በአ​ንተ ላይ ክፋት ማድ​ረግ ቢወ​ድድ፥ እኔም ባላ​ስ​ታ​ው​ቅህ፥ በሰ​ላ​ምም ትሄድ ዘንድ ባላ​ሰ​ና​ብ​ትህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዮ​ና​ታን ይህን ያድ​ርግ፤ ይህ​ንም ይጨ​ምር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ባቴ ጋር እንደ ነበረ ከአ​ንተ ጋር ይሁን።</verse>
				<verse number="14">እኔም በሕ​ይ​ወት ሳለሁ ቸር​ነ​ትን ታደ​ር​ግ​ል​ኛ​ለህ፤</verse>
				<verse number="15">ብሞ​ትም ቸር​ነ​ት​ህን እስከ ዘለ​ዓ​ለም ከቤቴ አት​ተው፤ ደግ​ሞም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዳ​ዊ​ትን ጠላ​ቶች ሁሉ እያ​ን​ዳ​ን​ዱን ከም​ድር ፊት ባጠ​ፋ​ቸው ጊዜ የዮ​ና​ታን ስም በዳ​ዊት ቤት ይገ​ኛል።”</verse>
				<verse number="16">ዮና​ታ​ንም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዳ​ዊት ጠላ​ቶች እጅ ይፈ​ል​ገው” ብሎ ከዳ​ዊት ቤት ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="17">ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን እንደ ነፍሱ ይወ​ድድ ነበ​ርና እንደ ገና ማለ​ለት።</verse>
				<verse number="18">ዮና​ታ​ንም አለው፥ “ነገ መባቻ ነው፤ መቀ​መ​ጫ​ህም ባዶ ሆኖ ይገ​ኛ​ልና ትታ​ሰ​ባ​ለህ።</verse>
				<verse number="19">ሦስት ቀንም ያህል ቈይ፤ ከዚ​ህም በኋላ በፈ​ለ​ገህ ጊዜ ትመ​ጣና ነገሩ በተ​ደ​ረ​ገ​በት ቀን በተ​ሸ​ሸ​ግ​ህ​በት ስፍራ ትቀ​መ​ጣ​ለህ፤ በኤ​ር​ገብ ድን​ጋ​ይም አጠ​ገብ ቈይ።</verse>
				<verse number="20">እኔም በዓ​ላማ ላይ እወ​ረ​ው​ራ​ለሁ ብዬ ሦስት ፍላ​ጻ​ዎ​ችን ወደ ዓላ​ማው እወ​ረ​ው​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="21">እነ​ሆም፦ ሂድ ፍላ​ጻ​ዎ​ቹን ፈልግ ብዬ ብላ​ቴ​ና​ውን እል​ካ​ለሁ፤ ብላ​ቴ​ና​ው​ንም፦ እነሆ፥ ፍላ​ጻው ከአ​ንተ ወደ​ዚህ ነው፤ ይዘ​ኸው ወደ እኔ ና ያል​ሁት እንደ ሆነ፥ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ለአ​ንተ ሰላም ነውና ምንም ክፉ ነገር የለ​ብ​ህም።</verse>
				<verse number="22">ብላ​ቴ​ና​ውን ግን፦ እነሆ፥ ፍላ​ጻው ከአ​ንተ ወዲያ ነው ያል​ሁት እንደ ሆነ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሰ​ና​ብ​ቶ​ሃ​ልና መን​ገ​ድ​ህን ሂድ።</verse>
				<verse number="23">አን​ተና እኔም ስለ ተነ​ጋ​ገ​ር​ነው፥ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም በመ​ካ​ከ​ላ​ችን ምስ​ክር ነው።”</verse>
				<verse number="24">ዳዊ​ትም በሜ​ዳው ተሸ​ሸገ፤ መባ​ቻም በሆነ ጊዜ ንጉሡ ግብር ለመ​ብ​ላት ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="25">ንጉ​ሡም እንደ ቀድ​ሞው በግ​ንቡ አጠ​ገብ በዙ​ፋኑ ላይ ተቀ​መጠ፤ ዮና​ታ​ንም ቆመ፤ አቤ​ኔ​ርም በሳ​ኦል አጠ​ገብ ተቀ​መጠ፤ የዳ​ዊ​ትም ስፍራ ባዶ​ውን ነበረ።</verse>
				<verse number="26">ሳኦ​ልም፥ “አንድ ነገር ሆኖ ይሆ​ናል፤ ምን​አ​ል​ባ​ትም ንጹሕ አይ​ደ​ለም ይሆ​ናል፤ በእ​ው​ነ​ትም ንጹሕ አይ​ደ​ለም” ብሎ አስ​ቦ​አ​ልና በዚያ ቀን ምንም አል​ተ​ና​ገ​ረም።</verse>
				<verse number="27">ከመ​ባ​ቻም በኋላ በማ​ግ​ሥቱ በሁ​ለ​ተ​ኛው ቀን የዳ​ዊት ስፍራ ባዶ​ውን ነበረ፤ ሳኦ​ልም ልጁን ዮና​ታ​ንን፥ “የእ​ሴይ ልጅ ትና​ትና ዛሬ ወደ ግብር ያል​መጣ ስለ​ምን ነው?” አለው።</verse>
				<verse number="28">ዮና​ታ​ንም ለሳ​ኦል፥ “ዳዊት ወደ ከተ​ማው ወደ ቤተ ልሔም ይሄድ ዘንድ ነግ​ሮኝ ተሰ​ና​ብ​ቶ​ኛል።</verse>
				<verse number="29">እር​ሱም፥ “ዘመ​ዶቼ በከ​ተማ ውስጥ መሥ​ዋ​ዕት አላ​ቸ​ውና፥ ወን​ድ​ሞቼም ጠር​ተ​ው​ኛ​ልና እባ​ክህ! አሰ​ና​ብ​ተኝ፤ አሁ​ንም በዐ​ይ​ኖ​ችህ ሞገስ አግ​ኝቼ እንደ ሆነ ልሂ​ድና ወን​ድ​ሞ​ቼን ልይ አለ፤ ስለ​ዚህ ወደ ንጉሥ ማዕድ አል​መ​ጣም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።</verse>
				<verse number="30">ሳኦ​ልም በዮ​ና​ታን ላይ እጅግ ተቈጣ፥ “አንተ የከ​ዳ​ተ​ኞች ሴቶች ልጅ! የእ​ሴ​ይን ልጅ ለአ​ንተ ማፈ​ርያ፥ ለእ​ና​ት​ህም ኀፍ​ረተ ሥጋ ማፈ​ርያ እንደ መረ​ጥህ እኔ አላ​ው​ቅ​ምን?</verse>
				<verse number="31">የእ​ሴይ ልጅ በም​ድር ላይ በሕ​ይ​ወት በሚ​ኖ​ር​በት ዘመን ሁሉ መን​ግ​ሥ​ትህ አት​ጸ​ናም፤ አሁ​ንም ሞት የሚ​ገ​ባው ነውና ያን ብላ​ቴና ያመ​ጡት ዘንድ ላክ” አለው።</verse>
				<verse number="32">ዮና​ታ​ንም ለአ​ባቱ ለሳ​ኦል፥ “ስለ ምን ይሞ​ታል? ምንስ አደ​ረገ?” ብሎ መለ​ሰ​ለት።</verse>
				<verse number="33">ሳኦ​ልም ሊገ​ድ​ለው በዮ​ና​ታን ላይ ጦሩን አነሣ፤ ዮና​ታ​ንም አባቱ ዳዊ​ትን ይገ​ድ​ለው ዘንድ ያች ክፉ ነገር እንደ ተቈ​ረ​ጠች ዐወቀ።</verse>
				<verse number="34">አባቱ በእ​ርሱ ላይ ክፉ ነገ​ርን ሊያ​ደ​ርግ ስለ ቈረጠ ዮና​ታን ስለ ዳዊት አዝ​ኖ​አ​ልና እጅግ ተቈ​ጥቶ ከማ​ዕዱ ተነሣ፤ በመ​ባ​ቻ​ውም በሁ​ለ​ተ​ኛው ቀን ግብር አል​በ​ላም።</verse>
				<verse number="35">እን​ዲ​ህም ሆነ በነ​ጋው ዮና​ታን ከዳ​ዊት ጋር ምል​ክት ለማ​ድ​ረግ ወደ ተቃ​ጠ​ረ​በት ቦታ ወደ ሜዳ ወጣ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ታናሽ ብላ​ቴና ነበረ።</verse>
				<verse number="36">ብላ​ቴ​ና​ው​ንም፥ “ሮጠህ የም​ወ​ረ​ው​ራ​ቸ​ውን ፍላ​ጻ​ዎች ፈል​ግ​ልኝ” አለው። ብላ​ቴ​ና​ውም በሮጠ ጊዜ ዮና​ታን ፍላ​ጻ​ውን ወደ ማዶ አሳ​ልፎ ወረ​ወ​ረው።</verse>
				<verse number="37">ብላ​ቴ​ና​ውም ዮና​ታን ፍላ​ጻ​ውን ወደ ወረ​ወ​ረ​በት ስፍራ በመጣ ጊዜ ዮና​ታን፥ “ፍላ​ጻው ከአ​ንተ ወዲያ ነው” ብሎ ወደ ብላ​ቴ​ናው ጮኸ።</verse>
				<verse number="38">ዮና​ታ​ንም ደግሞ፥ “ቶሎ ፍጠን፤ አት​ቈይ” ብሎ ወደ ብላ​ቴ​ናው ጮኸ፤ የዮ​ና​ታ​ንም ብላ​ቴና ፍላ​ጻ​ዎ​ቹን ሰብ​ስቦ ወደ ጌታው መጣ።</verse>
				<verse number="39">ዮና​ታ​ንና ዳዊት ብቻ ነገ​ሩን ያውቁ ነበር እንጂ ብላ​ቴ​ናው ምንም አያ​ው​ቅም ነበር።</verse>
				<verse number="40">ዮና​ታ​ንም መሣ​ሪ​ያ​ውን ለብ​ላ​ቴ​ናው ሰጥቶ፥ “ሂድ ወደ ከተማ ግባ” አለው።</verse>
				<verse number="41">ብላ​ቴ​ና​ውም በሄደ ጊዜ ዳዊት ከኤ​ር​ገብ ተነሣ፤ በም​ድ​ርም ላይ በግ​ን​ባሩ ተደፋ፤ ሦስት ጊዜም ሰገደ፤ እርስ በእ​ር​ሳ​ቸ​ውም ተሳ​ሳሙ፤ ለረ​ዥም ሰዓ​ትም ተላ​ቀሱ።</verse>
				<verse number="42">ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን፥ “በሰ​ላም ሂድ፤ እነሆ፥ እኛ ሁለ​ታ​ችን በእ​ኔና በአ​ንተ፥ በዘ​ሬና በዘ​ርህ መካ​ከል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ምስ​ክር ይሁን ብለን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ተማ​ም​ለ​ናል” አለው። ዳዊ​ትም ተነ​ሥቶ ሄደ፤ ዮና​ታ​ንም ወደ ከተማ ገባ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">ዳዊ​ትም ወደ ካህኑ ወደ አቤ​ሜ​ሌክ ወደ ኖብ መጣ፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክም እር​ሱን በተ​ገ​ና​ኘው ጊዜ ደነ​ገጠ፥ “ስለ​ምን አንተ ብቻ​ህን ነህ? ከአ​ን​ተስ ጋር ስለ​ምን ማንም የለም?” አለው።</verse>
				<verse number="2">ዳዊ​ትም ካህ​ኑን አቤ​ሜ​ሌ​ክን፥ “የተ​ላ​ክ​ህ​በ​ትን ነገ​ርና የሰ​ጠ​ሁ​ህን ትእ​ዛዝ ማንም አይ​ወቅ ብሎ ንጉሡ አንድ ነገር አዝ​ዞ​ኛል፤ ስለ​ዚ​ህም ‘ብላ​ቴ​ኖቼን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​መን’ በሚ​ባ​ለው እን​ዲህ ባለው ስፍራ እን​ዲ​ሆኑ አዝ​ዣ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">አሁ​ንም አም​ስት እን​ጀራ በእ​ጅህ ካለ፥ ወይም በእ​ጅህ ያለ​ውን ስጠኝ” አለው።</verse>
				<verse number="4">ካህ​ኑም ለዳ​ዊት መልሶ፥ “ሁሉ የሚ​በ​ላው እን​ጀራ የለ​ኝም፤ ነገር ግን የተ​ቀ​ደሰ እን​ጀራ አለ፤ ብላ​ቴ​ኖቹ ከሴ​ቶች ንጹ​ሓን እንደ ሆኑ መብ​ላት ይች​ላሉ” አለው።</verse>
				<verse number="5">ዳዊ​ትም ለካ​ህኑ መልሶ፥ “ከሴ​ቶች ተለ​ይ​ተን ወደ መን​ገድ ከወ​ጣን ዛሬ ሦስ​ተኛ ቀና​ችን ነው። እኔም ብላ​ቴ​ኖ​ቼም ንጹ​ሓን ነን። ነገር ግን ዛሬ ሰው​ነቴ ንጽ​ሕት ስለ ሆነች ነው እንጂ ይህች መን​ገድ የነ​ጻች አይ​ደ​ለ​ችም” አለው።</verse>
				<verse number="6">ካህኑ አቤ​ሜ​ሌ​ክም በእ​ርሱ ፋንታ ትኩስ እን​ጀራ ይደ​ረግ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከአ​ለው ኅብ​ስት በቀር ሌላ እን​ጀራ አል​ነ​በ​ረ​ምና የቍ​ር​ባ​ኑን ኅብ​ስት ሰጠው።</verse>
				<verse number="7">በዚ​ያም ቀን ከሳ​ኦል አገ​ል​ጋ​ዮች አንድ ሰው በኔ​ሴራ አቅ​ራ​ቢያ በዚያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነበር፤ ስሙም ሶር​ያ​ዊው ዶይቅ ነበረ፤ የሳ​ኦ​ልም በቅ​ሎ​ዎች ጠባቂ ነበረ።</verse>
				<verse number="8">ዳዊ​ትም አቤ​ሜ​ሌ​ክን፥ “የን​ጉሥ ጉዳይ ስላ​ስ​ቸ​ኰ​ለኝ ሰይ​ፌ​ንና መሣ​ሪ​ያ​ዬን አላ​መ​ጣ​ሁ​ምና በአ​ንተ ዘንድ ጦር ወይም ሰይፍ እን​ዳለ እይ​ልኝ” አለው።</verse>
				<verse number="9">ካህ​ኑም፥ “በኤላ ሸለቆ የገ​ደ​ል​ኸው የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው የጎ​ል​ያድ ሰይፍ እነሆ፥ በመ​ጐ​ና​ጸ​ፊያ ተጠ​ቅ​ልላ አለች፤ የም​ት​ወ​ስ​ዳት ከሆነ ውሰ​ዳት፤ ከእ​ር​ስዋ በቀር ሌላ ከዚህ የለ​ምና” አለው። ዳዊ​ትም፥ “ከእ​ር​ስዋ በቀር ሌላ ከሌለ እር​ስ​ዋን ስጠኝ” አለው። እር​ሱም ሰጠው።</verse>
				<verse number="10">ዳዊ​ትም ተነሣ በዚ​ያም ቀን ከሳ​ኦል ፊት ሸሸ፤ ወደ ጌትም ንጉሥ ወደ አን​ኩስ መጣ።</verse>
				<verse number="11">የአ​ን​ኩስ ብላ​ቴ​ኖ​ችም፥ “ይህ ዳዊት የሀ​ገሩ ንጉሥ አይ​ደ​ለ​ምን? ሳኦል ሺህ፥ ዳዊ​ትም ዐሥር ሺህ ገደለ ብለው ሴቶች በዘ​ፈን የዘ​መ​ሩ​ለት እርሱ አይ​ደ​ለ​ምን?” አሉት።</verse>
				<verse number="12">ዳዊ​ትም ይህን ቃል በልቡ አኖረ፤ የጌ​ት​ንም ንጉሥ አን​ኩ​ስን እጅግ ፈራ።</verse>
				<verse number="13">በፊ​ቱም መል​ኩን ለወጠ፤ በዚ​ያ​ችም ቀን አመ​ለጠ። በከ​ተ​ማ​ውም በር ከበሮ ይዞ በእጁ መታ፤ በበ​ሩም መድ​ረክ ላይ ተን​ፈ​ራ​ፈረ፤ ልጋ​ጉም በጢሙ ላይ ይወ​ርድ ነበር።</verse>
				<verse number="14">አን​ኩ​ስም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “እነሆ፥ ይህ ሰው እብድ እንደ ሆነ አይ​ታ​ች​ኋል፤ ለምን ወደ እኔ አመ​ጣ​ች​ሁት?</verse>
				<verse number="15">በፊቴ ያብድ ዘንድ ይህን ያመ​ጣ​ች​ሁት እኔ የእ​ብ​ዶች አለቃ ነኝን? እን​ዲህ ያለ​ውስ ወደ ቤቴ ይገ​ባ​ልን?” አላ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">ዳዊ​ትም ከዚያ ተነ​ሥቶ አመ​ለጠ፤ ወደ ዔዶ​ላም ዋሻም መጣ፤ ወን​ድ​ሞ​ቹና የአ​ባቱ ቤተ ሰብ ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ እርሱ ወደ​ዚያ ወረዱ።</verse>
				<verse number="2">የተ​ጨ​ነ​ቀም ሁሉ፥ ዕዳም ያለ​በት ሁሉ፥ የተ​ከ​ፋም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​ባ​ሰበ፤ እር​ሱም በላ​ያ​ቸው አለቃ ሆነ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="3">ዳዊ​ትም ከዚያ በሞ​ዓብ ምድር ወዳ​ለ​ችው ወደ መሴፋ ሄደ፤ የሞ​ዓ​ብ​ንም ንጉሥ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ል​ኝን እስ​ካ​ውቅ ድረስ አባ​ቴና እናቴ ከአ​ንተ ጋር ይቀ​መጡ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="4">የሞ​ዓ​ብ​ንም ንጉሥ ማለ​ደው፤ ዳዊ​ትም በአ​ንባ ውስጥ በነ​በ​ረ​በት ወራት ሁሉ በእ​ርሱ ዘንድ ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="5">ነቢዩ ጋድም ዳዊ​ትን፥ “ተነ​ሥ​ተህ ወደ ይሁዳ ምድር ሂድ እንጂ በአ​ን​ባው ውስጥ አት​ቀ​መጥ” አለው፤ ዳዊ​ትም ሄደ፤ ወደ ሳሬቅ ከተ​ማም መጥቶ ተቀ​መጠ፤</verse>
				<verse number="6">ሳኦ​ልም ዳዊ​ትና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ሰዎች ያሉ​በት ቦታ እንደ ታወቀ ሰማ። ሳኦ​ልም በራማ በሚ​ገ​ኘው በመ​ሰ​ማ​ር​ያው ቦታ በኮ​ረ​ብ​ታው ላይ ተቀ​ምጦ በእ​ጁም ጦር ይዞ ነበር፤ ብላ​ቴ​ኖ​ቹም ሁሉ በአ​ጠ​ገቡ ቆመው ነበር።</verse>
				<verse number="7">ሳኦ​ልም በአ​ጠ​ገቡ የቆ​ሙ​ትን ብላ​ቴ​ኖች፥ “ብን​ያ​ማ​ው​ያን ሆይ! እን​ግ​ዲህ ስሙ በእ​ው​ነት የእ​ሴይ ልጅ እር​ሻና የወ​ይን ቦታ ለሁ​ላ​ችሁ ይሰ​ጣ​ች​ኋ​ልን? ሁላ​ች​ሁ​ንስ መቶ አለ​ቆ​ችና ሻለ​ቆች ያደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልን?</verse>
				<verse number="8">ሁላ​ችሁ በላዬ ዶል​ታ​ችሁ ተነ​ሣ​ች​ሁ​ብኝ፤ ልጄ ከእ​ሴይ ልጅ ጋር ሲማ​ማል ማንም አል​ገ​ለ​ጠ​ል​ኝም፤ ከእ​ና​ን​ተም አንድ ለእኔ የሚ​ያ​ዝን የለም፤ ዛሬም እንደ ሆነው ሁሉ ልጄ አገ​ል​ጋ​ዬን እን​ዲ​ዶ​ልት ሲያ​ስ​ነ​ሣ​ብኝ ማንም አላ​ስ​ታ​ወ​ቀ​ኝም” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">የሳ​ኦ​ልም በቅ​ሎ​ዎች ጠባቂ ሶር​ያ​ዊው ዶይቅ መልሶ፥ “የእ​ሴይ ልጅ ወደ ኖብ ወደ አኪ​ጦብ ልጅ ወደ ካህኑ አቤ​ሜ​ሌክ ሲመጣ አይቼ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ጠየ​ቀ​ለት፤ ስን​ቅ​ንም ሰጠው፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም የጎ​ል​ያ​ድን ሰይፍ ሰጠው” አለው።</verse>
				<verse number="11">ንጉ​ሡም የአ​ኪ​ጦ​ብን ልጅ ካህ​ኑን አቤ​ሜ​ሌ​ክን፥ በኖ​ብም ያሉ​ትን ካህ​ናት፥ የአ​ባ​ቱን ልጆች ሁሉ ልኮ አስ​ጠ​ራ​ቸው፤ ሁላ​ቸ​ውም ወደ ንጉሡ መጡ።</verse>
				<verse number="12">ሳኦ​ልም፥ “የአ​ኪ​ጦብ ልጅ ሆይ! እን​ግ​ዲህ ስማ” አለ፤ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ ጌታዬ ሆይ” ብሎ መለሰ።</verse>
				<verse number="13">ሳኦ​ልም፥ “አንተ ከእ​ሴይ ልጅ ጋር ለምን ዶለ​ት​ህ​ብኝ? እን​ጀ​ራና ሰይፍ ሰጠ​ኸው፤ ዛሬም እንደ ተደ​ረ​ገው ጠላት ሆኖ ይነ​ሣ​ብኝ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ እርሱ ጠየ​ቅ​ህ​ለት” አለው።</verse>
				<verse number="14">አቤ​ሜ​ሌ​ክም መልሶ ንጉ​ሡን፥ “ከባ​ሪ​ያ​ዎቹ ሁሉ የታ​መነ፥ ለን​ጉ​ሥም አማች የሆነ፥ የት​እ​ዛ​ዝህ ሁሉ አለቃ፥ በቤ​ት​ህም የከ​በረ እንደ ዳዊት ያለ ማን ነው?</verse>
				<verse number="15">በውኑ ስለ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጠ​ይቅ ዘንድ ዛሬ ጀመ​ር​ሁን? ይህ ከእኔ ይራቅ፤ እኔ ባሪ​ያህ ይህን ሁሉ ትልቅ ወይም ጥቂት ቢሆን አላ​ው​ቅ​ምና ንጉሡ እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ነገር በእኔ በባ​ሪ​ያ​ውና በአ​ባቴ ቤት ሁሉ ላይ አያ​ኑር” አለ።</verse>
				<verse number="16">ንጉ​ሡም፥ “አቤ​ሜ​ሌክ ሆይ! አን​ተና የአ​ባ​ትህ ቤት ሁሉ ፈጽ​ማ​ችሁ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ” አለ።</verse>
				<verse number="17">ንጉ​ሡም በዙ​ሪ​ያው የቆ​ሙ​ትን እግ​ረ​ኞች፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካህ​ናት እጅ ከዳ​ዊት ጋር ነውና፥ ኵብ​ለ​ላ​ው​ንም ሲያ​ውቁ አል​ነ​ገ​ሩ​ኝ​ምና፥ ዞራ​ችሁ ግደ​ሉ​አ​ቸው” አላ​ቸው። የን​ጉሡ አገ​ል​ጋ​ዮች ግን እጃ​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካህ​ናት ላይ ይዘ​ረጉ ዘንድ እንቢ አሉ።</verse>
				<verse number="18">ንጉ​ሡም ዶይ​ቅን፥ “አንተ ዞረህ ካህ​ና​ቱን ግደ​ላ​ቸው” አለው። ሶር​ያ​ዊው ዶይ​ቅም ዞሮ ካህ​ና​ቱን ገደ​ላ​ቸው፤ በዚ​ያም ቀን የበ​ፍታ ኤፉድ የለ​በ​ሱ​ትን ሦስት መቶ ሰማ​ንያ አም​ስት ሰዎ​ችን ገደለ።</verse>
				<verse number="19">የካ​ህ​ና​ቱ​ንም ከተማ ኖብን በሰ​ይፍ ስለት መታ፤ ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ች​ንም፥ ብላ​ቴ​ኖ​ች​ንና ጡት የሚ​ጠ​ቡ​ትን፥ በሬ​ዎ​ች​ንና አህ​ዮ​ች​ንም፥ በጎ​ች​ንም በሰ​ይፍ ስለት ገደለ።</verse>
				<verse number="20">ከአ​ኪ​ጦ​ብም ልጅ ከአ​ቤ​ሜ​ሌክ ልጆች ስሙ አብ​ያ​ታር የሚ​ባል አንዱ ልጅ አም​ልጦ ሸሸ፤ ዳዊ​ት​ንም ተከ​ተለ።</verse>
				<verse number="21">አብ​ያ​ታ​ርም ሳኦል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ካህ​ናት እንደ ፈጀ ለዳ​ዊት ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="22">ዳዊት አብ​ያ​ታ​ርን፦ ሶር​ያ​ዊው ዶይቅ በዚያ መኖ​ሩን ባየሁ ጊዜ፥ “ለሳ​ኦል በር​ግጥ ይነ​ግ​ራል ብዬ በዚያ ቀን አው​ቄ​ዋ​ለሁ፤ ለአ​ባ​ትህ ቤት ነፍስ ሁሉ ጥፋት በደ​ለ​ኛው እኔ ነኝ።</verse>
				<verse number="23">እን​ግ​ዲህ ወዲህ ከእኔ ጋር ተቀ​መጥ፤ አት​ፍራ፤ ለእኔ ነፍስ የደ​ኅ​ን​ነት ቦታን እን​ደ​ም​ፈ​ልግ ለአ​ን​ተም ነፍስ የደ​ኅ​ን​ነት ቦታን እፈ​ል​ጋ​ለ​ሁና፥ ከእ​ኔም ጋር ተጠ​ብ​ቀህ ትኖ​ራ​ለህ” አለው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="23">
				<verse number="1">ለዳ​ዊ​ትም፥ “እነሆ፥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ቂአ​ላን ይወ​ጋሉ፤ አው​ድ​ማ​ው​ንም ይዘ​ር​ፋሉ” ብለው ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="2">ዳዊ​ትም፥ “ልሂ​ድን? እነ​ዚ​ህ​ንስ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ልም​ታን?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሂድ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ምታ፤ ቂአ​ላ​ንም አድን” አለው።</verse>
				<verse number="3">የዳ​ዊ​ትም ሰዎች፥ “እነሆ፥ በዚህ በይ​ሁዳ መቀ​መጥ እን​ፈ​ራ​ለን፤ ይል​ቁ​ንስ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ለመ​ዝ​ረፍ ወደ ቂአላ ብን​ሄድ እን​ዴት እን​ሆ​ና​ለን?” አሉት።</verse>
				<verse number="4">ዳዊ​ትም ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መልሶ፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለ​ሁና ተነ​ሥ​ተህ ወደ ቂአላ ውረድ” አለው።</verse>
				<verse number="5">ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ወደ ቂአላ ሄዱ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጋር ተዋጉ፤ እነ​ር​ሱም ከፊቱ ሸሹ፤ እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ማረኩ፤ በታ​ላ​ቅም አገ​ዳ​ደል ገደ​ሉ​አ​ቸው። ዳዊ​ትም በቂ​አላ የሚ​ኖ​ሩ​ትን አዳነ።</verse>
				<verse number="6">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የአ​ቤ​ሜ​ሌክ ልጅ አብ​ያ​ታር ወደ ዳዊት ወደ ቂአላ በኰ​በ​ለለ ጊዜ ኤፉ​ዱን ይዞ ወርዶ ነበር።</verse>
				<verse number="7">ለሳ​ኦ​ልም ዳዊት ወደ ቂአላ እንደ መጣ ተነ​ገ​ረው፤ ሳኦ​ልም፥ “መዝ​ጊ​ያና መወ​ር​ወ​ሪያ ወዳ​ለ​ባት ከተማ ገብቶ ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጄ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ታል” አለ።</verse>
				<verse number="8">ሳኦ​ልም ወደ ቂአላ ወር​ደው ይዋጉ ዘንድ፥ ዳዊ​ት​ንና ሰዎ​ቹ​ንም ይከ​ብቡ ዘንድ ሕዝ​ቡን ሁሉ አዘዘ።</verse>
				<verse number="9">ዳዊ​ትም ሳኦል በእ​ርሱ ለክ​ፋት ዝም እን​ደ​ማ​ይል ዐወቀ፤ ዳዊ​ትም ካህ​ኑን አብ​ያ​ታ​ርን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ኤፉድ ወደ​ዚህ አምጣ” አለው።</verse>
				<verse number="10">ዳዊ​ትም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ! በእኔ ምክ​ን​ያት ከተ​ማ​ዪ​ቱን ያጠፋ ዘንድ ሳኦል ወደ ቂአላ ሊመጣ እን​ደ​ሚ​ፈ​ልግ እኔ ባሪ​ያህ ፈጽሜ ሰም​ቻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">የቂ​አላ ሰዎ​ችስ ይከ​በ​ባ​ሉን? ባሪ​ያ​ህስ እንደ ሰማ ሳኦል በውኑ ይወ​ር​ዳ​ልን? የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ! ለባ​ር​ያህ ንገ​ረው” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይወ​ር​ዳል” አለ።</verse>
				<verse number="12">ዳዊ​ትም፥ “የቂ​አላ ሰዎች እኔ​ንና ሰዎ​ቼን በሳ​ኦል እጅ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ና​ልን?” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​አ​ች​ኋል” ብሎ ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="13">ዳዊ​ትና ስድ​ስት መቶ የሚ​ሆኑ ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው ከቂ​አላ ወጡ፤ ወደ​ሚ​ሄ​ድ​በ​ትም ይከ​ተ​ሉት ነበር። ሳኦ​ልም ዳዊት ከቂ​አላ እንደ ሸሸ ሰማ፤ ስለ​ዚ​ህም ከመ​ው​ጣት ቀረ።</verse>
				<verse number="14">ዳዊ​ትም በም​ድረ በዳ በጠ​ባቡ በማ​ሴ​ሬም ይኖር ነበር፥ በአ​ው​ክ​ሞ​ዲስ ውስ​ጥም በዚፍ ተራራ ምድረ በዳ ተቀ​መጠ፤ ሳኦ​ልም ሁል​ጊዜ ይፈ​ል​ገው ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በእጁ አሳ​ልፎ አል​ሰ​ጠ​ውም።</verse>
				<verse number="15">ዳዊ​ትም ሳኦል ሊፈ​ል​ገው እንደ ወጣ አየ፤ ዳዊ​ትም በቄኒ ዚፍ ምድረ በዳ በአ​ው​ክ​ሞ​ዲስ ውስጥ ይኖር ነበር።</verse>
				<verse number="16">የሳ​ኦ​ልም ልጅ ዮና​ታን ተነ​ሥቶ ወደ ዳዊት ወደ ቄኒ ሄደ። እጁ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አጸና።</verse>
				<verse number="17">ለእ​ር​ሱም “የአ​ባቴ የሳ​ኦል እጅ አታ​ገ​ኝ​ህ​ምና አት​ፍራ፤ አን​ተም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ትሆ​ና​ለህ፤ እኔም ከአ​ንተ በታች እሆ​ና​ለሁ፤ ይህን ደግሞ አባቴ ሳኦል ያው​ቃል” አለው።</verse>
				<verse number="18">ሁለ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቃል ኪዳን አደ​ረጉ፤ ዳዊ​ትም በቄኒ ውስጥ ተቀ​መጠ፤ ዮና​ታ​ንም ወደ ቤቱ ሄደ።</verse>
				<verse number="19">የዚፍ ሰዎ​ችም ከአ​ው​ክ​ሞ​ዲስ ወደ ሳኦል ወደ ኮረ​ብ​ታው ወጥ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “እነሆ፥ ዳዊት በየ​ሴ​ሞን ቀኝ በጠ​ባቡ በኩል በኤ​ኬላ ኮረ​ብታ ላይ በቄኒ ውስጥ በማ​ሴ​ሬት በእኛ ዘንድ ተሸ​ሽጎ የለ​ምን?</verse>
				<verse number="20">አሁ​ንም፦ ንጉሥ ሆይ! ለመ​ው​ረድ ፈቃ​ድህ ከሆነ ወደ እኛ ውረድ፤ በን​ጉሡ እጅ ጥሎ​ታ​ልና።”</verse>
				<verse number="21">ሳኦ​ልም አለ፥ “እና​ንተ ስለ እኔ አዝ​ና​ች​ኋ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ባ​ረ​ካ​ችሁ ሁኑ፤</verse>
				<verse number="22">አሁ​ንም ደግሞ ሂዱና አዘ​ጋጁ፤ የተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁ​ት​ንም፥ ያለ​በ​ት​ንም ቦታ ሁሉ እን​ዳ​ያ​ታ​ል​ላ​ችሁ ፈጥ​ና​ችሁ ዕወቁ።</verse>
				<verse number="23">እን​ግ​ዲህ ዕወቁ፤ ከአ​ያ​ችሁ በኋላ ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በዚ​ያ​ችም ምድር ካለ በይ​ሁዳ አእ​ላፍ ሁሉ እፈ​ት​ሻ​ታ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="24">የዚፍ ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው ከሳ​ኦል በፊት ሄዱ፤ ዳዊ​ትና ሰዎቹ ግን በየ​ሴ​ሞን ቀኝ በኩል በዓ​ረባ በማ​ዖን ምድረ በዳ ነበሩ።</verse>
				<verse number="25">ሳኦ​ልና ሰዎ​ቹም ሊፈ​ል​ጉት ሄዱ፤ ለዳ​ዊ​ትም ነገ​ሩት፤ እር​ሱም በማ​ዖን ምድረ በዳ ወዳ​ለው ዓለት ወረደ፤ ሳኦ​ልም ያን በሰማ ጊዜ ዳዊ​ትን በማ​ዖን ምድረ በዳ ተከ​ትሎ አሳ​ደ​ደው።</verse>
				<verse number="26">ሳኦ​ልና ሰዎ​ቹም በተ​ራ​ራው በአ​ንድ ወገን ሄዱ፤ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም በተ​ራ​ራው በሌ​ላው ወገን ሄዱ። ዳዊ​ትም ከሳ​ኦል ፊት ያመ​ልጥ ዘንድ ተሰ​ውሮ ነበር። ሳኦ​ልና ሰዎቹ ዳዊ​ት​ንና ሰዎ​ቹን ለመ​ያዝ ከብ​በ​ዋ​ቸው ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="27">ወደ ሳኦ​ልም መል​እ​ክ​ተኛ መጥቶ፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገ​ሩን ወር​ረ​ው​ታ​ልና ፈጥ​ነህ ና” አለው።</verse>
				<verse number="28">ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ማሳ​ደ​ድን ትቶ ተመ​ለሰ። ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጋር ሊዋጋ ሄደ። ስለ​ዚህ የዚያ ስፍራ ስም የመ​ለ​ያ​የት ዓለት ተባለ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="24">
				<verse number="1">ዳዊ​ትም ከዚያ መጥቶ በዓ​ይን ጋዲ በጠ​ባብ ቦታ ተቀ​መጠ፤</verse>
				<verse number="2">ሳኦ​ልም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ከማ​ሳ​ደድ ከተ​መ​ለሰ በኋላ፥ “እነሆ! ዳዊት በዓ​ይን ጋዲ ምድረ በዳ አለ” ብለው ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="3">ሳኦ​ልም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ የተ​መ​ረ​ጡ​ትን ሦስት ሺህ ሰዎች ወሰደ፤ ዳዊ​ት​ንና ሰዎ​ቹ​ንም ለመ​ፈ​ለግ ዋሊ​ያ​ዎች ወደ​ሚ​ታ​ደ​ኑ​ባ​ቸው ዓለ​ቶች ሄደ።</verse>
				<verse number="4">በመ​ን​ገ​ድም አጠ​ገብ ወዳ​ሉት የበ​ጎች ማደ​ሪ​ያ​ዎች ወጣ፤ በዚ​ያም ዋሻ ነበረ፤ ሳኦ​ልም ወገ​ቡን ይሞ​ክር ዘንድ ወደ​ዚያ ዋሻ ገባ፤ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ከዋ​ሻው በው​ስ​ጠ​ኛው ቦታ ተቀ​ም​ጠው ነበር።</verse>
				<verse number="5">የዳ​ዊ​ትም ሰዎች፥ “እነሆ፥ ጠላ​ት​ህን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ በዐ​ይ​ን​ህም ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን ታደ​ር​ግ​በ​ታ​ለህ ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የነ​ገ​ረህ ቀን እነሆ ዛሬ ነው” አሉት። ዳዊ​ትም ተነ​ሥቶ የሳ​ኦ​ልን መጐ​ና​ጸ​ፊያ ዘርፍ በቀ​ስታ ቈረጠ።</verse>
				<verse number="6">ከዚ​ያም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ የሳ​ኦ​ልን የል​ብ​ሱን ዘርፍ ስለ ቈረጠ የዳ​ዊት ልብ በኀ​ዘን ተመታ።</verse>
				<verse number="7">ዳዊ​ትም ሰዎ​ቹን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ባው ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ባው በጌ​ታዬ ላይ እን​ዲህ ያለ​ውን ነገር አደ​ርግ ዘንድ፥ እጄ​ንም እጥ​ል​በት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ያር​ቀው” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">ዳዊ​ትም በዚህ ቃል ሰዎ​ቹን ከለ​ከ​ላ​ቸው። በሳ​ኦ​ልም ላይ ተነ​ሥ​ተው ይገድ​ሉት ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደ​ላ​ቸ​ውም፤ ሳኦ​ልም ከዋ​ሻው ተነ​ሥቶ መን​ገ​ዱን ሄደ።</verse>
				<verse number="9">ከእ​ር​ሱም በኋላ ዳዊት ደግሞ ተነሣ፤ ከዋ​ሻ​ውም ወጣ፤ ከሳ​ኦ​ልም በኋላ፦“ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ!” ብሎ ጮኸ፤ ሳኦ​ልም ወደ ኋላው ተመ​ለ​ከተ፤ ዳዊ​ትም ወደ ምድር ተጐ​ን​ብሶ እጅ ነሣ።</verse>
				<verse number="10">ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን አለው፥ “እነሆ፥ ዳዊት ክፉ ነገር ይሻ​ብ​ሃል የሚ​ሉ​ህን ሰዎች ቃል ለምን ትሰ​ማ​ለህ?</verse>
				<verse number="11">እነሆ፥ ዛሬ በዋ​ሻው ውስጥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጄ አሳ​ልፎ እንደ ሰጠህ ዐይ​ንህ አይ​ታ​ለች፤ አን​ተ​ንም እን​ድ​ገ​ድ​ልህ ሰዎች ተና​ገ​ሩኝ፤ እኔ ግን፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀባ ነውና እጄን በጌ​ታዬ ላይ አል​ዘ​ረ​ጋም ብዬ ራራ​ሁ​ልህ።</verse>
				<verse number="12">እነሆ፥ የል​ብ​ስህ ዘርፍ በእጄ እን​ዳለ ተመ​ል​ክ​ተህ ዕወቅ፤ የል​ብ​ስ​ህ​ንም ዘርፍ በቈ​ረ​ጥሁ ጊዜ አል​ገ​ደ​ል​ሁ​ህም፤ ስለ​ዚ​ህም በእጄ ክፋት፥ በደ​ልና ክዳት እን​ደ​ሌለ፥ አን​ተ​ንም እን​ዳ​ል​በ​ደ​ል​ሁህ ዕወቅ፤ አንተ ግን ነፍ​ሴን ልታ​ጠፋ ታጠ​ም​ዳ​ለህ።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​እ​ብ​ሔር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ይፍ​ረድ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​ተን ይበ​ቀ​ል​ልኝ፤ እጄ ግን በአ​ንተ ላይ አት​ሆ​ንም።</verse>
				<verse number="14">የጥ​ንት ምሳሌ፦ ‘ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ኀጢ​አት ይወ​ጣል’ እን​ደ​ሚል፥ እጄ ግን በአ​ንተ ላይ አት​ሆ​ንም።</verse>
				<verse number="15">አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ማንን ለማ​ሳ​ደድ ወጥ​ተ​ሀል? አን​ተስ ማንን ታሳ​ድ​ዳ​ለህ? የሞተ ውሻን ታሳ​ድ​ዳ​ለ​ህን? ወይስ ቍን​ጫን ታሳ​ድ​ዳ​ለህ?</verse>
				<verse number="16">እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዳኛ ይሁን፤ በእ​ኔና በአ​ን​ተም መካ​ከል ይፍ​ረድ፤ አይ​ቶም ለእኔ ይፍ​ረድ፤ ከእ​ጅ​ህም ያድ​ነኝ።”</verse>
				<verse number="17">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት ይህን ቃል ለሳ​ኦል መን​ገር በፈ​ጸመ ጊዜ፥ ሳኦል፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ይህ ድም​ፅህ ነውን?” አለ፤ ሳኦ​ልም ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ አለ​ቀሰ።</verse>
				<verse number="18">ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን አለው፥ “እኔ ክፉ በመ​ለ​ስ​ሁ​ልህ ፋንታ በጎ መል​ሰ​ህ​ል​ኛ​ልና አንተ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ነህ።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዛሬ በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶኝ ሳለ አል​ገ​ደ​ል​ኸ​ኝ​ምና ለእኔ መል​ካም እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ኽ​ልኝ ለእኔ ነገ​ር​ኸኝ።</verse>
				<verse number="20">ጠላ​ቱን ተቸ​ግሮ አግ​ኝቶ በመ​ል​ካም መን​ገድ ሸኝቶ የሚ​ሰ​ድድ ማን ነው? ስለ​ዚህ ለእኔ ስላ​ደ​ረ​ግ​ኸው ቸር​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካ​ሙን ይመ​ል​ስ​ልህ።</verse>
				<verse number="21">አሁ​ንም እነሆ፥ አንተ በር​ግጥ ንጉሥ እን​ድ​ት​ሆን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መን​ግ​ሥት በእ​ጅህ እን​ድ​ት​ጸና እኔ አው​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="22">አሁን እን​ግ​ዲህ ከእኔ በኋላ ዘሬን እን​ዳ​ት​ነ​ቅል ከአ​ባ​ቴም ቤት ስሜን እን​ዳ​ታ​ጠ​ፋው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማል​ልኝ።”</verse>
				<verse number="23">ዳዊ​ትም ለሳ​ኦል ማለ​ለት፤ ሳኦ​ልም ወደ ቤቱ ሄደ፤ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ወደ ጠባቡ ወደ ሜሴራ ወጡ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="25">
				<verse number="1">ሳሙ​ኤ​ልም ሞተ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ በአ​ር​ማ​ቴ​ምም በቤቱ ቀበ​ሩት። ዳዊ​ትም ተነ​ሥቶ ወደ ማዖን ምድረ በዳ ወረደ።</verse>
				<verse number="2">በማ​ዖ​ንም የተ​ቀ​መጠ አንድ ሰው ነበረ፤ ከብ​ቱም በቀ​ር​ሜ​ሎስ ነበረ፤ እጅ​ግም ታላቅ ሰው ነበረ፤ ለእ​ር​ሱም ሦስት ሺህ በጎ​ችና አንድ ሺህ ፍየ​ሎች ነበ​ሩት፤ በቀ​ር​ሜ​ሎ​ስም በጎ​ቹን ሊሸ​ልት ሄደ።</verse>
				<verse number="3">የሰ​ው​ዬ​ውም ስም ናባል፥ የሚ​ስ​ቱም ስም አቤ​ግያ ነበረ፤ ሴቲ​ቱም ደግና ብልህ፥ መል​ክ​ዋም እጅግ የተ​ዋበ ነበረ፤ ሰው​ዬው ግን ጨካ​ኝና ንፉግ ነበረ፤ ግብ​ሩም ክፉ ነበረ።</verse>
				<verse number="4">ዳዊ​ትም በም​ድረ በዳ ሳለ፥ “ናባል በቀ​ር​ሜ​ሎስ በጎ​ቹን ይሸ​ል​ታል” የሚል ወሬ ሰማ።</verse>
				<verse number="5">ዳዊ​ትም ዐሥር ብላ​ቴ​ኖ​ችን ላከ፤ ለብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አለ፥ “ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ወጥ​ታ​ችሁ ወደ ናባል ሂዱ፤ በስ​ሜም ሰላም በሉት፤</verse>
				<verse number="6">እን​ዲ​ህም በሉት፥ “ደኅ​ን​ነ​ትና ሰላም ለአ​ን​ተና ለቤ​ትህ፥ ለአ​ን​ተም ለሆ​ኑት ሁሉ ይሁን።</verse>
				<verse number="7">አሁ​ንም በጎ​ችህ እን​ደ​ሚ​ሸ​ለቱ ከእኛ ጋር በም​ድረ በዳ ያሉ ሰዎች ነገ​ሩን፤ እኛም አል​ከ​ለ​ከ​ል​ና​ቸ​ውም፤ በቀ​ር​ሜ​ሎ​ስም በነ​በ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ ከመ​ን​ጋ​ቸው ይሰ​ጡን ዘንድ አላ​ዘ​ዝ​ና​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="8">ብላ​ቴ​ኖ​ች​ህን ጠይ​ቃ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ይነ​ግ​ሩ​ሃል፤ አሁ​ንም እን​ግ​ዲህ በመ​ል​ካም ቀን መጥ​ተ​ና​ልና ብላ​ቴ​ኖች በፊ​ትህ ሞገስ ያግኙ፤ በእ​ጅ​ህም ከተ​ገ​ኘው ለል​ጅህ ለዳ​ዊት እባ​ክህ፥ ላክ።”</verse>
				<verse number="9">የዳ​ዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖች መጡ፤ ይህ​ንም የላ​ካ​ቸ​ውን ቃል ሁሉ በዳ​ዊት ስም ለና​ባል ነገ​ሩት፤</verse>
				<verse number="10">ናባ​ልም ተነ​ሥቶ ለዳ​ዊት ብላ​ቴ​ኖች መለ​ሰ​ላ​ቸው እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ዳዊት ማን ነው? የእ​ሴ​ይስ ልጅ ማን ነው? እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከጌ​ቶ​ቻ​ቸው የኰ​በ​ለሉ አገ​ል​ጋ​ዮች ዛሬ ብዙ ናቸው።</verse>
				<verse number="11">እን​ጀ​ራ​ዬ​ንና የወ​ይን ጠጄን፥ ለሸ​ላ​ቾ​ቼም ያረ​ድ​ሁ​ትን ሥጋ ወስጄ ከወ​ዴት እንደ ሆኑ ለማ​ላ​ው​ቃ​ቸው ሰዎች እሰ​ጣ​ለ​ሁን?”</verse>
				<verse number="12">የዳ​ዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖች ዞረው በመ​ጡ​በት መን​ገድ ተመ​ለሱ፤ መጥ​ተ​ውም ይህን ነገር ሁሉ ለዳ​ዊት ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="13">ዳዊ​ትም ሰዎ​ቹን፥ “ሁላ​ችሁ ሰይ​ፋ​ች​ሁን ታጠቁ” አላ​ቸው። ሁሉም ሰይ​ፋ​ቸ​ውን ታጠቁ፤ ዳዊ​ትም ሰይ​ፉን ታጠቀ፤ አራት መቶ ሰዎ​ችም ዳዊ​ትን ተከ​ት​ለው ወጡ፤ ሁለት መቶ​ውም በጓ​ዛ​ቸው ዘንድ ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="14">ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አንዱ ለና​ባል ሚስት ለአ​ቤ​ግያ እን​ዲህ ብሎ ነገ​ራት፥ “እነሆ፥ ዳዊት በም​ድረ በዳ ሳለ ጌታ​ች​ንን ሰላም ሊሉት መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እርሱ ግን ፊቱን አዞ​ረ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">እነ​ዚህ ሰዎች ግን በእኛ ዘንድ እጅግ ደጎች ነበሩ፤ የከ​ለ​ከ​ሉ​ንም የለም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር በኖ​ር​ን​በት ዘመን ሁሉ በም​ድረ በዳ ሳለን ከመ​ን​ጋው እን​ሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ያዘ​ዙን አን​ዳች ነገር የለም።</verse>
				<verse number="16">ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሆነን መን​ጋ​ውን በጠ​በ​ቅ​ን​በት ዘመን ሁሉ በም​ድረ በዳ ሌሊ​ትና ቀን አጥር ሆነ​ውን ነበር።</verse>
				<verse number="17">ስለ​ዚ​ህም በጌ​ታ​ች​ንና በቤቱ ሁላ ክፉ ነገር እን​ዲ​መጣ ተቈ​ር​ጦ​አ​ልና፥ እርሱ ክፉ ሰው ስለ ሆነ ማንም ሊና​ገ​ረው አይ​ች​ል​ምና የም​ታ​ደ​ር​ጊ​ውን ተመ​ል​ከ​ቺና ዕወቂ።”</verse>
				<verse number="18">አቤ​ግ​ያም ፈጥና፦ ሁለት መቶ እን​ጀራ፥ ሁለት አቁ​ማዳ የወ​ይን ጠጅ፥ አም​ስት የተ​ዘ​ጋጁ በጎች፥ አም​ስ​ትም መስ​ፈ​ሪያ በሶ፥ አንድ ጎሞር ዘቢብ፥ ሁለት መቶም የበ​ለስ ጥፍ​ጥፍ ወሰ​ደች፥ በአ​ህ​ዮ​ችም ላይ አስ​ጫ​ነች።</verse>
				<verse number="19">ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ዋም፥ “አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ በፊቴ ሂዱ፤ እነ​ሆም እከ​ተ​ላ​ች​ኋ​ለሁ” አለች። ይህ​ንም ለባ​ልዋ ለና​ባል አል​ነ​ገ​ረ​ች​ውም።</verse>
				<verse number="20">እር​ስ​ዋም በአ​ህ​ያዋ ላይ ተቀ​ምጣ በተ​ራ​ራው ላይ በተ​ሰ​ወረ ስፍራ በወ​ረ​ደች ጊዜ፥ እነሆ፥ ዳዊ​ትና ሰዎቹ ወደ እር​ስዋ ወር​ደው ተቀ​በ​ሏት፤ እር​ስ​ዋም ተገ​ና​ኘ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">ዳዊ​ትም አለ፥ “ለዚህ ሰው ከሆ​ነው ሁሉ አንድ ነገር እን​ዳ​ይ​ጠ​ፋ​በት በእ​ው​ነት ከብ​ቱን ሁሉ በም​ድረ በዳ በከ​ንቱ ጠበ​ቅሁ፤ ከገ​ን​ዘቡ ሁሉ አን​ዳች ይወ​ስ​ዱ​በት ዘንድ ያዘ​ዝ​ነው የለም፤ እር​ሱም በበጎ ፋንታ ክፉ መለ​ሰ​ልኝ።</verse>
				<verse number="22">ለና​ባ​ልም ከሆ​ነው ሁሉ እስከ ነገ ጥዋት ድረስ አጥር ተጠ​ግቶ የሚ​ሸን አንድ ስንኳ ብን​ተው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዳ​ዊት ላይ እን​ዲህ ያድ​ርግ፤ እን​ዲ​ህም ይጨ​ምር” ብሎ ነበር።</verse>
				<verse number="23">አቤ​ግ​ያም ዳዊ​ትን ባየች ጊዜ ከአ​ህ​ያዋ ላይ ፈጥና ወረ​ደች፤ በዳ​ዊ​ትም ፊት በግ​ን​ባ​ርዋ ወደ​ቀች፤ ምድ​ርም ነክታ ሰገ​ደ​ች​ለት።</verse>
				<verse number="24">በእ​ግ​ሩም ላይ ወደ​ቀች፤ እን​ዲ​ህም አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! ይህ ኀጢ​ኣት በእኔ ላይ ይሁን፤ እኔ ባሪ​ያህ በጆ​ሮህ ልና​ገር፥ የባ​ሪ​ያ​ህ​ንም ቃል አድ​ምጥ።</verse>
				<verse number="25">በዚህ ክፉ ሰው በና​ባል ላይ ጌታዬ ልቡን እን​ዳ​ይ​ጥል እለ​ም​ና​ለሁ፤ እንደ ስሙ እን​ዲሁ እርሱ ነው፤ ስሙ ናባል ነው፤ ስን​ፍ​ናም አድ​ሮ​በ​ታል፤ እኔ ባሪ​ያህ ግን አንተ የላ​ክ​ሃ​ቸ​ውን ብላ​ቴ​ኖ​ች​ህን አላ​የ​ሁም።</verse>
				<verse number="26">አሁ​ንም ጌታዬ ሆይ! ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ! ወደ ንጹሕ ደም እን​ዳ​ት​ገ​ባና፥ እጅ​ህን እን​ድ​ታ​ድን የከ​ለ​ከ​ለህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ አሁ​ንም ጠላ​ቶ​ች​ህና በጌ​ታዬ ላይ ክፉ የሚሹ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ።</verse>
				<verse number="27">አሁ​ንም ባሪ​ያህ ወደ ጌታዬ ያመ​ጣ​ች​ውን ይህን መተ​ያያ ተቀ​በል፤ በጌ​ታ​ዬም ዘንድ ለሚ​ቆሙ ሰዎች ስጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="28">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጌ​ታዬ የታ​መነ ቤትን ይሠ​ራ​ለ​ታ​ልና፥ የጌ​ታ​ዬ​ንም ጦር​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይዋ​ጋ​ለ​ታ​ልና የእ​ኔን የባ​ሪ​ያ​ህን ኀጢ​ኣት፥ እባ​ክህ፥ ይቅር በል፤ በዘ​መ​ን​ህም ሁሉ ክፋት አይ​ገ​ኝ​ብ​ህም።</verse>
				<verse number="29">የሚ​ያ​ሳ​ድ​ድ​ህና ነፍ​ስ​ህን የሚሻ ሰው ቢነሣ፥ የጌ​ታዬ ነፍስ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በሕ​ይ​ወት ማሰ​ሪያ የታ​ሰ​ረች ትሆ​ና​ለች፤ የጠ​ላ​ቶ​ችህ ነፍስ ግን በወ​ን​ጭፍ እን​ደ​ሚ​ወ​ነ​ጨፍ ትሁን።</verse>
				<verse number="30">እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጌ​ታዬ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቸር​ነት ሁሉ ያደ​ር​ግ​ል​ሃል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ አለቃ አድ​ርጎ ይሾ​ም​ሃል፤</verse>
				<verse number="31">ይህ ርኵ​ሰ​ትና የልብ በደል፥ በከ​ንቱ ንጹሕ ደም ማፍ​ሰ​ስም ለጌ​ታዬ አይ​ሁ​ኑ​በት፤ የጌ​ታ​ዬም እጁ ትዳን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለጌ​ታዬ በጎ ያድ​ር​ግ​ለት፤ በጎም ታደ​ር​ግ​ላት ዘንድ ባሪ​ያ​ህን አስብ።”</verse>
				<verse number="32">ዳዊ​ትም አቤ​ግ​ያን አላት፥ “ዛሬ እኔን ለመ​ገ​ና​ኘት አን​ቺን የላከ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።</verse>
				<verse number="33">ጠባ​ይሽ የተ​ባ​ረከ ነው። ወደ ደም እን​ዳ​ል​ገባ፥ እጄ​ንም እን​ዳ​ድን ዛሬ የከ​ለ​ከ​ል​ሽኝ አን​ቺም የተ​ባ​ረ​ክሽ ነሽ።</verse>
				<verse number="34">ነገር ግን ክፉ እን​ዳ​ላ​ደ​ር​ግ​ብሽ የከ​ለ​ከ​ለኝ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እኔን ለመ​ገ​ና​ኘት ፈጥ​ነሽ ባል​መ​ጣሽ ኖሮ፥ እስ​ኪ​ነጋ ድረስ ለና​ባል አጥር ተጠ​ግቶ የሚ​ሸን አንድ ስንኳ ባል​ቀ​ረ​ውም ብዬ ነበር።”</verse>
				<verse number="35">ዳዊ​ትም ያመ​ጣ​ች​ውን ከእ​ጅዋ ተቀ​ብሎ፥ “በሰ​ላም ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ እነሆ፥ ቃል​ሽን እንደ ሰማሁ፥ ፊት​ሽ​ንም እን​ዳ​ከ​በ​ርሁ ተመ​ል​ከቺ” አላት።</verse>
				<verse number="36">አቤ​ግ​ያም ወደ ናባል መጣች፤ እነ​ሆም፥ በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ ያደ​ርግ ነበር፤ ናባ​ልም እጅግ ሰክሮ ነበ​ርና ልቡ ደስ ብሎት ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም እስ​ኪ​ነጋ ድረስ ታናሽ ነገር ወይም ታላቅ ነገር አል​ነ​ገ​ረ​ች​ውም ነበር።</verse>
				<verse number="37">በነ​ጋ​ውም የወ​ይኑ ስካር ከና​ባል ባለፈ ጊዜ ሚስቱ ይህን ነገር ነገ​ረ​ችው፤ ልቡም በው​ስጡ ሞተ፤ እንደ ድን​ጋ​ይም ሆነ፤</verse>
				<verse number="38">ከዐ​ሥር ቀንም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናባ​ልን ቀሠ​ፈው፤ እር​ሱም ሞተ።</verse>
				<verse number="39">ዳዊ​ትም ናባል እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ፥ “ከና​ባል እጅ የስ​ድ​ቤን ፍርድ የፈ​ረ​ደ​ልኝ፥ ባሪ​ያ​ው​ንም ከክ​ፉ​ዎች እጅ የጠ​በቀ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የና​ባ​ልን ክፋት በራሱ ላይ መለሰ” አለ። ዳዊ​ትም ያገ​ባት ዘንድ አቤ​ግ​ያን እን​ዲ​ያ​ነ​ጋ​ግ​ሩ​ለት ላከ።</verse>
				<verse number="40">የዳ​ዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖች ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ወደ አቤ​ግያ መጡ፥ “ዳዊ​ትም ሚስት ትሆ​ኚው ዘንድ ወደ አንቺ ልኮ​ናል” ብለው ነገ​ሩ​አት።</verse>
				<verse number="41">ተነ​ሥ​ታም በግ​ን​ባ​ርዋ በም​ድር ወድቃ ሰገ​ደ​ችና፥ “እነሆ፥ እኔ ገረ​ድህ የጌ​ታ​ዬን ሎሌ​ዎች እግር አጥብ ዘንድ አገ​ል​ጋይ ነኝ” አለች።</verse>
				<verse number="42">አቤ​ግ​ያም ፈጥና ተነ​ሣች፤ በአ​ህ​ያም ላይ ተቀ​መ​ጠች፤ አም​ስ​ቱም ገረ​ዶ​ችዋ ተከ​ተ​ሉ​አት፤ የዳ​ዊ​ት​ንም መል​እ​ክ​ተ​ኞች ተከ​ትላ ሄደች፤ ሚስ​ትም ሆነ​ችው።</verse>
				<verse number="43">ዳዊ​ትም ደግሞ ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል አኪ​ና​ሆ​ምን ወሰደ፤ ሁለ​ቱም ሚስ​ቶቹ ሆኑ​ለት።</verse>
				<verse number="44">ሳኦል ግን የዳ​ዊ​ትን ሚስት ልጁን ሜል​ኮ​ልን ሀገሩ ሮማ ለነ​በ​ረው ለያ​ሚስ ልጅ ለፈ​ልጢ ሰጣት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="26">
				<verse number="1">የዚፍ ሰዎ​ችም ከአ​ው​ክ​ሞ​ዲስ ወደ ኮረ​ብ​ታው ወደ ሳኦል መጥ​ተው፥ “እነሆ፥ ዳዊት በየ​ሴ​ሞን ፊት ለፊት ባለው በኤ​ኬላ ኮረ​ብታ ላይ ከእኛ ጋር ተሸ​ሽጎ አለ” አሉት።</verse>
				<verse number="2">ሳኦ​ልም ተነ​ሥቶ ዳዊ​ትን በዚፍ ምድረ በዳ ይሻ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል የተ​መ​ረጡ ሦስት ሺህ ሰዎ​ችን ይዞ ወደ ዚፍ ምድረ በዳ ወረደ።</verse>
				<verse number="3">ሳኦ​ልም በየ​ሴ​ሞን ፊት ለፊት ባለው በኤ​ኬላ ኮረ​ብታ ላይ በመ​ን​ገዱ አጠ​ገብ ሰፈረ። ዳዊ​ትም በም​ድረ በዳ ውስጥ ተቀ​ምጦ ነበር፥ ዳዊ​ትም ሳኦል ሊፈ​ል​ገው ወደ ምድረ በዳ እንደ መጣ ዐወቀ።</verse>
				<verse number="4">ዳዊ​ትም ሰላ​ዮ​ችን ላከ፤ ሳኦ​ልም ተዘ​ጋ​ጅቶ ወደ ቂአላ እንደ መጣ በር​ግጥ ዐወቀ።</verse>
				<verse number="5">ዳዊ​ትም በቀ​ስታ ተነ​ሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈ​ረ​በት ቦታ መጣ፤ ሳኦ​ልና የሠ​ራ​ዊቱ አለቃ የኔር ልጅ አቤ​ኔ​ርም የተ​ኙ​በ​ትን ስፍራ አየ፤ ሳኦ​ልም በድ​ን​ኳን ውስጥ ተኝቶ ነበር፤ ሕዝ​ቡም በዙ​ሪ​ያው ሰፍሮ ነበር።</verse>
				<verse number="6">ዳዊ​ትም ኬጤ​ያ​ዊ​ዉን አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንና የሶ​ር​ህ​ያን ልጅ የኢ​ዮ​አ​ብን ወን​ድም አቢ​ሳን፥ “ወደ ሳኦል ወደ ሰፈሩ ከእኔ ጋር የሚ​ገባ ማን ነው?” ብሎ ጠየ​ቃ​ቸው፤ አቢ​ሳም፥ “እኔ ከአ​ንተ ጋር እገ​ባ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="7">ዳዊ​ትና አቢ​ሳም ወደ ሕዝቡ በሌ​ሊት መጡ፤ እነ​ሆም፥ ሳኦል በድ​ን​ኳን ውስጥ ተኝቶ ነበር፤ ጦሩም በራ​ስ​ጌው አጠ​ገብ በም​ድር ተተ​ክሎ ነበር፤ አቤ​ኔ​ርና ሕዝ​ቡም በዙ​ሪ​ያው ተኝ​ተው ነበር።</verse>
				<verse number="8">አቢ​ሳም ዳዊ​ትን፥ “ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ት​ህን በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ታል፤ አሁ​ንም እኔ በጦር አንድ ጊዜ ከም​ድር ጋር ላጣ​ብ​ቀው፤ ሁለ​ተ​ኛም አል​ደ​ግ​መ​ውም” አለው።</verse>
				<verse number="9">ዳዊ​ትም አቢ​ሳን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ባው ላይ እጁን የሚ​ዘ​ረጋ ንጹሕ አይ​ሆ​ን​ምና አት​ግ​ደ​ለው” አለው።</verse>
				<verse number="10">ደግ​ሞም ዳዊት አለው፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካል​ገ​ደ​ለው፥ ወይም ቀኑ ደርሶ ካል​ሞተ፥ ወይም ወደ ጦር​ነት ወርዶ ካል​ሞተ እኔ አል​ገ​ድ​ለ​ውም።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀ​ባው ላይ እጄን እዘ​ረጋ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ያር​ቀው፤ አሁ​ንም በራሱ አጠ​ገብ ያለ​ውን ጦርና የው​ኃ​ውን መን​ቀል ይዘህ እን​ሂድ፤” አለው።</verse>
				<verse number="12">ዳዊ​ትም በሳ​ኦል ራስጌ የነ​በ​ረ​ውን ጦርና የው​ኃ​ውን መን​ቀል ወሰደ፤ ወደ ቤታ​ቸ​ውም ተመ​ለሱ። ማንም ያየ አል​ነ​በ​ረም፤ ያወ​ቃ​ቸ​ውም ማንም አል​ነ​በ​ረም፤ የነ​ቃም ማንም አል​ነ​በ​ረም፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ከባድ እን​ቅ​ልፍ ወድ​ቆ​ባ​ቸው ነበ​ርና ሁሉ ተኝ​ተው ነበር።</verse>
				<verse number="13">ዳዊ​ትም ወደ ማዶ ተሻ​ገረ፤ በተ​ራ​ራ​ውም ራስ ላይ ርቆ ቆመ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ሰፊ ርቀት ነበረ።</verse>
				<verse number="14">ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡ​ንና የኔር ልጅ አቤ​ኔ​ርን ጠራ​ቸው፥ “አቤ​ኔር ሆይ፥ አት​መ​ል​ስ​ምን?” አለው። አቤ​ኔ​ርም መልሶ፥ “አንተ የም​ት​ጠ​ራኝ ማን ነህ?” አለ።</verse>
				<verse number="15">ዳዊ​ትም አቤ​ኔ​ርን፥ “አንተ ጐል​ማሳ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አን​ተን የሚ​መ​ስል ማን ነው? ጌታ​ህን ንጉ​ሡን ለመ​ግ​ደል አንድ ሰው ገብቶ ነበ​ርና ጌታ​ህን ንጉ​ሡን የማ​ት​ጠ​ብቅ ስለ​ምን ነው?</verse>
				<verse number="16">ይህ ያደ​ረ​ግ​ኸው ነገር መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ባ​ውን ጌታ​ች​ሁን አል​ጠ​በ​ቃ​ች​ሁ​ምና ሞት ይገ​ባ​ች​ኋል፤ አሁ​ንም የን​ጉሡ ጦርና በራሱ አጠ​ገብ የነ​በ​ረው የውኃ መን​ቀል የት እንደ ሆነ ተመ​ል​ከት” አለው።</verse>
				<verse number="17">ሳኦ​ልም የዳ​ዊት ድምፅ እንደ ሆነ ዐውቆ፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ይህ ድም​ፅህ ነውን?” አለው። ዳዊ​ትም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! አዎ እኔ ባሪ​ያህ ነኝ” አለው።</verse>
				<verse number="18">ደግ​ሞም አለ፥ “ጌታዬ አገ​ል​ጋ​ዩን ስለ​ምን ያሳ​ድ​ዳል? ምን አደ​ረ​ግሁ? ምንስ ክፋት በእጄ ላይ ተገ​ኘ​ብኝ?</verse>
				<verse number="19">አሁ​ንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! የእ​ኔን የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ቃል ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኔ ላይ አስ​ነ​ሥ​ቶህ እን​ደ​ሆነ፥ ቍር​ባ​ን​ህን ይቀ​በል፤ የሰው ልጆች ግን ቢሆኑ፦ ሂድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አም​ልክ ብለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት ላይ እን​ዳ​ል​ቀ​መጥ ዛሬ ጥለ​ው​ኛ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ርጉ​ማን ይሁኑ።</verse>
				<verse number="20">አሁ​ንም በተ​ራ​ራው ላይ ሰው ቆቅን እን​ደ​ሚሻ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ነፍ​ሴን ለመ​ሻት ወጥ​ቶ​አ​ልና ደሜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በም​ድር ላይ አይ​ፍ​ሰስ።”</verse>
				<verse number="21">ሳኦ​ልም፥ “በድ​ያ​ለሁ፤ ልጄ ዳዊት ሆይ! ተመ​ለስ፤ ዛሬ ነፍሴ በዐ​ይ​ንህ ፊት ከብ​ራ​ለ​ችና ከዚህ በኋላ ክፉ አላ​ደ​ር​ግ​ብ​ህም፤ እነሆ፥ ስን​ፍና እንደ አደ​ረ​ግ​ሁና፥ እጅግ ብዙም እንደ ሳትሁ ዐወ​ቅሁ” አለ።</verse>
				<verse number="22">ዳዊ​ትም መልሶ አለ፥ “የን​ጉሥ ጦር እነሆ፤ ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ችም አንድ ይም​ጣና ይው​ሰ​ዳት።</verse>
				<verse number="23">ዛሬም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጄ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶህ ሳለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ባው ላይ እጄን እዘ​ረጋ ዘንድ አል​ወ​ደ​ድ​ሁ​ምና ለሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ጽድ​ቁና እንደ እም​ነቱ ፍዳ​ውን ይክ​ፈ​ለው።</verse>
				<verse number="24">ነፍ​ስ​ህም ዛሬ በዐ​ይኔ ፊት እንደ ከበ​ረች እን​ዲሁ ነፍሴ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትክ​በር፤ ከመ​ከ​ራም ሁሉ ይሰ​ው​ረኝ፤ ያድ​ነ​ኝም።”</verse>
				<verse number="25">ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ቡሩክ ሁን፤ ማድ​ረ​ግን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ መቻ​ል​ንም ትች​ላ​ለህ” አለው። ዳዊ​ትም መን​ገ​ዱን ሄደ፤ ሳኦ​ልም ወደ ስፍ​ራው ተመ​ለሰ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="27">
				<verse number="1">ዳዊ​ትም በልቡ፥ “አንድ ቀን በሳ​ኦል እጅ እሞ​ታ​ለሁ፤ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ምድር ከመ​ሸሸ በቀር የሚ​ሻ​ለኝ የለም፤ ሳኦ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል አው​ራጃ ሁሉ እኔን መሻት ይተ​ዋል፤ እን​ዲ​ሁም ከእጁ እድ​ና​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="2">ዳዊ​ትም ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ስድ​ስቱ መቶ ሰዎች ተነ​ሥ​ተው ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አሜህ ልጅ ወደ አን​ኩስ አለፉ።</verse>
				<verse number="3">ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከነ​ቤ​ተ​ሰቡ ከአ​ን​ኩስ ጋር በጌት ተቀ​መጡ፤ ከዳ​ዊ​ትም ጋር ኢይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊቱ አኪ​ና​ሆ​ምና የቀ​ር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊው የና​ባል ሚስት አቤ​ግያ ሁለቱ ሚስ​ቶቹ ነበሩ።</verse>
				<verse number="4">ለሳ​ኦ​ልም ዳዊት ወደ ጌት እንደ ኰበ​ለለ ነገ​ሩት፤ ከዚ​ያም በኋላ ደግሞ አል​ፈ​ለ​ገ​ውም።</verse>
				<verse number="5">ዳዊ​ትም አን​ኩ​ስን፥ “አገ​ል​ጋ​ይህ በዐ​ይ​ንህ ፊት ሞገስ አግ​ኝቼ እንደ ሆነ በዚህ ሀገር ከከ​ተ​ሞ​ችህ በአ​ን​ዲቱ የም​ቀ​መ​ጥ​በት ስፍራ ስጠኝ፤ ስለ ምን እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ከአ​ንተ ጋር በን​ጉሥ ከተማ እቀ​መ​ጣ​ለሁ?” አለው።።</verse>
				<verse number="6">በዚ​ያም ቀን አን​ኩስ ሴቄ​ላ​ቅን ሰጠው፤ ስለ​ዚ​ህም ሴቄ​ላቅ እስከ ዛሬ ድረስ ለይ​ሁዳ ንጉሥ ሆነች።</verse>
				<verse number="7">ዳዊ​ትም በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገር የተ​ቀ​መ​ጠ​በት የዘ​መን ቍጥር አራት ወር ነበረ።</verse>
				<verse number="8">ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ወጥ​ተው በጌ​ሴ​ራ​ው​ያ​ንና በአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን ላይ አደጋ ጣሉ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ቅጽር ባላ​ቸው በጌ​ላ​ም​ሱ​ርና በአ​ኔ​ቆ​ን​ጦን እስከ ግብፅ ምድር ድረስ ተቀ​ም​ጠው አገ​ኙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ዳዊ​ትም ሀገ​ሪ​ቱን መታ፤ ወን​ድም ሆነ፥ ሴትም ሆነ፥ ማን​ንም በሕ​ይ​ወት አል​ተ​ወም፤ በጎ​ች​ንና ላሞ​ችን፥ አህ​ያ​ዎ​ች​ንና ግመ​ሎ​ችን፥ ልብ​ስ​ንም ማረከ፤ ተመ​ል​ሶም ወደ አን​ኩስ መጣ።</verse>
				<verse number="10">አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመ​ታ​ችሁ?” አለው፤ ዳዊ​ትም፥ “በይ​ሁዳ ደቡብ፥ በያ​ሴ​ሜጋ ደቡብ፥ በቄ​ኔ​ዛ​ው​ያን ደቡብ ላይ ዘመ​ትን” አለው።</verse>
				<verse number="11">ዳዊት እን​ዲህ አደ​ረገ፤ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሀገር በሚ​ቀ​መ​ጥ​በት ዘመን ሁሉ ልማዱ ይህ ነበረ ብለው እን​ዳ​ይ​ና​ገ​ሩ​ብን ብሎ ዳዊት ወደ ጌት ያመ​ጣ​ቸው ዘንድ ወን​ድም ሆነ ሴትም ሆነ ማን​ንም በሕ​ይ​ወት አል​ተ​ወም።</verse>
				<verse number="12">አን​ኩ​ስም፥ “በሕ​ዝቡ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ እጅግ የተ​ጠላ ሆኖ​አል፤ ስለ​ዚ​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባሪያ ይሆ​ነ​ኛል” ብሎ ዳዊ​ትን አመ​ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="28">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዚያ ወራት ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ይዋጉ ዘንድ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጭፍ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ለሰ​ልፍ ሰበ​ሰቡ፤ አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን፥ “አን​ተና ሰዎ​ችህ ከእኔ ጋር ወደ ሰልፍ እን​ድ​ት​ወጡ በር​ግጥ ዕወቅ” አለው።</verse>
				<verse number="2">ዳዊ​ትም አን​ኩ​ስን፥ “አሁን አገ​ል​ጋ​ይህ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ንገ​ረው” አለው። አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን፥ “እን​ግ​ዲህ በዘ​መኑ ሁሉ ራሴን ጠባቂ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="3">ሳሙ​ኤል ግን ሞቶ ነበር፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አል​ቅ​ሰ​ው​ለት ነበር፤ በከ​ተ​ማ​ውም በአ​ር​ማ​ቴም ቀብ​ረ​ውት ነበር። ሳኦ​ልም መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን ከም​ድር አጥ​ፍቶ ነበር።</verse>
				<verse number="4">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ተሰ​ብ​ስ​በው መጡ፤ በሱ​ነ​ምም ሰፈሩ፤ ሳኦ​ልም እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ በጌ​ላ​ቡ​ሄም ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="5">ሳኦ​ልም የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ጭፍራ ባየ ጊዜ ፈራ፤ ልቡም እጅግ ተን​ቀ​ጠ​ቀጠ።</verse>
				<verse number="6">ሳኦ​ልም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ልም አላ​ሚ​ዎች፥ ወይም በነ​ጋ​ሪ​ዎች፥ ወይም በነ​ቢ​ያት አል​መ​ለ​ሰ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="7">ሳኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “ወደ እር​ስዋ ሄጄ እጠ​ይቅ ዘንድ መና​ፍ​ስ​ትን የም​ት​ጠራ ሴት ፈል​ጉ​ልኝ” አላ​ቸው፤ ብላ​ቴ​ኖ​ቹም፥ “እነሆ፥ መና​ፍ​ስ​ትን የም​ት​ጠራ አን​ዲት ሴት በዓ​ይ​ን​ዶር አለች” አሉት።</verse>
				<verse number="8">ሳኦ​ልም መል​ኩን ለውጦ፥ ሌላ ልብ​ስም ለብሶ ሄደ፤ ሁለ​ትም ሰዎች ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ፤ በሌ​ሊ​ትም ወደ ሴቲቱ መጡ። ሳኦ​ልም፥ “እባ​ክሽ በመ​ና​ፍ​ስት አም​ዋ​ር​ቺ​ልኝ፤ የም​ል​ሽ​ንም አስ​ነ​ሽ​ልኝ” አላት።</verse>
				<verse number="9">ሴቲ​ቱም፥ “እነሆ፥ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን ከም​ድር እን​ዳ​ጠፋ ሳኦል ያደ​ረ​ገ​ውን ታው​ቃ​ለህ፤ ስለ​ምን እኔን ለማ​ስ​ገ​ደል ለነ​ፍሴ ወጥ​መድ ታደ​ር​ጋ​ለህ?” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="10">ሳኦ​ልም ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በዚህ ነገር ክፉ አያ​ገ​ኝ​ሽም ብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማለ​ላት።</verse>
				<verse number="11">ሴቲ​ቱም፥ “ማንን ላስ​ነ​ሣ​ልህ?” አለ​ችው፤ እር​ሱም፥ “ሳሙ​ኤ​ልን አስ​ነ​ሽ​ልኝ” አላት።</verse>
				<verse number="12">ሴቲ​ቱም ሳሙ​ኤ​ልን ባየች ጊዜ በታ​ላቅ ድምፅ ጮኸች፤ ሴቲ​ቱም ሳኦ​ልን፥ “አንተ ሳኦል ስት​ሆን ለምን አታ​ለ​ል​ኸኝ?” ብላ ተና​ገ​ረ​ችው።</verse>
				<verse number="13">ንጉ​ሡም፥ “አት​ፍሪ ፤ ንገ​ሪኝ፤ ማንን አየሽ?” አላት። ሴቲ​ቱም፥ “አማ​ል​ክት ከም​ድር ሲወጡ አየሁ” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="14">እር​ሱም፥ “ምን አየሽ?” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “ቀጥ ያለ ሽማ​ግሌ ሰው ከም​ድር ወጣ፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያም ተጐ​ና​ጽ​ፎ​አል” አለች። ሳኦ​ልም ሳሙ​ኤል እንደ ሆነ ዐወቀ፤ በፊ​ቱም ወደ ምድር ጐን​በስ ብሎ ሰገ​ደ​ለት።</verse>
				<verse number="15">ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን፥ “ለምን አወ​ክ​ኸኝ? ለም​ንስ አስ​ነ​ሣ​ኸኝ?” አለው። ሳኦ​ልም መልሶ፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ይወ​ጉ​ኛ​ልና እጅግ ተጨ​ን​ቄ​አ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእኔ ርቆ​አል፤ በነ​ቢ​ያት ወይም በሕ​ልም አላ​ሚ​ዎች አል​መ​ለ​ሰ​ል​ኝም፤ ስለ​ዚ​ህም የማ​ደ​ር​ገ​ውን ታስ​ታ​ው​ቀኝ ዘንድ ጠራ​ሁህ” አለው።</verse>
				<verse number="16">ሳሙ​ኤ​ልም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከራ​ቀህ፥ ወደ ባል​ን​ጀ​ራ​ህም ከተ​መ​ለሰ ለምን ትጠ​ይ​ቀ​ኛ​ለህ?</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቃሌ እንደ ተና​ገረ አድ​ር​ጎ​አል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥ​ት​ህን ከእ​ጅህ ነጥቆ ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ ለዳ​ዊት ሰጥ​ቶ​ታል።</verse>
				<verse number="18">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ህ​ምና፥ በአ​ማ​ሌ​ቅም ላይ ታላቅ የሆነ ቍጣ​ውን አላ​ደ​ረ​ግ​ህ​ምና ስለ​ዚህ ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ነገር አድ​ር​ጎ​ብ​ሃል።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስ​ራ​ኤ​ልን ከአ​ንተ ጋር በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል፤ ነገም አን​ተና ከአ​ንተ ጋር ያሉ ልጆ​ችህ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጭፍራ ደግሞ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል።</verse>
				<verse number="20">ሳኦ​ልም በዚያ ጊዜ በቁ​መቱ ሙሉ በም​ድር ላይ ወደቀ፤ ከሳ​ሙ​ኤ​ልም ቃል የተ​ነሣ እጅግ ፈራ። በዚ​ያም ቀን ሁሉ፥ በዚ​ያም ሌሊት ሁሉ እን​ጀራ አል​በ​ላ​ምና ኀይል አል​ቀ​ረ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="21">ሴቲ​ቱም ወደ ሳኦል መጣች፤ እጅ​ግም ደን​ግጦ እንደ ነበር አይታ፥ “እነሆ፥ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ቃል​ህን ሰማሁ፤ ነፍ​ሴ​ንም በእጄ ጣልሁ፤ የነ​ገ​ር​ኸ​ኝ​ንም ቃል ሰማሁ።</verse>
				<verse number="22">አሁን እን​ግ​ዲህ አንተ ደግሞ የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ቃል እን​ድ​ት​ሰማ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ በፊ​ት​ህም ቁራሽ እን​ጀራ ላኑ​ር​ልህ፤ መን​ገ​ድም ትሄ​ዳ​ለ​ህና ትበ​ረታ ዘንድ ብላ” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="23">እርሱ ግን፥ “አል​በ​ላም” ብሎ እንቢ አለ፤ ነገር ግን ብላ​ቴ​ኖ​ቹና ሴቲቱ አስ​ገ​ደ​ዱት፤ ቃላ​ቸ​ው​ንም ሰማ፤ ከም​ድ​ርም ተነ​ሥቶ በአ​ልጋ ላይ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="24">ለሴ​ቲ​ቱም የሰባ ጥጃ በቤት ነበ​ራት፤ ፈጥና አረ​ደ​ችው፤ ዱቄ​ቱ​ንም ወስዳ ለወ​ሰ​ችው፤ ቂጣም እን​ጀራ አድ​ርጋ ጋገ​ረ​ችው።</verse>
				<verse number="25">በሳ​ኦ​ልና በብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም ፊት አቀ​ረ​በ​ችው፤ በል​ተ​ውም ተነሡ፤ በዚ​ያም ሌሊት ሄዱ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="29">
				<verse number="1">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ ወደ አፌቅ ሰበ​ሰቡ፤ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ባለው ውኃ ምንጭ አጠ​ገብ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="2">የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም አለ​ቆች በመቶ በመቶ፥ በሺህ በሺህ እየ​ሆኑ ያልፉ ነበር፤ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ከአ​ን​ኩስ ጋር በኋ​ለ​ኛው ጭፍራ በኩል ያልፉ ነበር።</verse>
				<verse number="3">የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች፥ “እነ​ዚህ በኋላ የሚ​ሄ​ዱት እነ​ማን ናቸው?” አሉ፤ አን​ኩ​ስም የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን አለ​ቆች፥ “ይህ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የሳ​ኦል አገ​ል​ጋይ ዳዊት ነው፤ እርሱ በእ​ነ​ዚህ ሁለት ዓመ​ታት ከእኛ ጋር ነበረ፤ ወደ እኔም ከተ​ጠ​ጋ​በት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ምንም አላ​ገ​ኘ​ሁ​በ​ትም” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች ግን በእ​ርሱ ላይ ተቈ​ጥ​ተው፥ “ይህን ሰው ወደ አመ​ጣ​ህ​በት ቦታ መል​ሰው፤ በሰ​ል​ፉም ውስጥ ጠላት እን​ዳ​ይ​ሆ​ነን ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይ​ው​ረድ፤ ከጌ​ታው ጋር በምን ይታ​ረ​ቃል? የእ​ነ​ዚ​ህን ሰዎች ራስ በመ​ቍ​ረጥ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="5">ወይስ ሴቶች፦ ‘ሳኦል ሺህ ገደለ፥ ዳዊት ዐሥር ሺህ ገደለ’ ብለው በዘ​ፈን የዘ​መ​ሩ​ለት ይህ ዳዊት አይ​ደ​ለ​ምን?” አሉት።</verse>
				<verse number="6">አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን ጠርቶ፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! አንተ በፊቴ ጻድ​ቅና ደግ ነህ፤ ከእ​ኔም ጋር በጭ​ፍ​ራው በኩል መው​ጣ​ት​ህና መግ​ባ​ትህ በፊቴ መል​ካም ነው፤ ወደ እኔ ከመ​ጣህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ አን​ዳች ክፋት አላ​ገ​ኘ​ሁ​ብ​ህም፤ ነገር ግን በአ​ለ​ቆች ዘንድ አል​ተ​ወ​ደ​ድ​ህም።</verse>
				<verse number="7">አሁ​ንም ተመ​ል​ሰህ በሰ​ላም ሂድ፤ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም አለ​ቆች ዐይን ክፋት አታ​ድ​ርግ” አለው።</verse>
				<verse number="8">ዳዊ​ትም አን​ኩ​ስን፥ “ምን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ? ሄጄስ ከጌ​ታዬ ከን​ጉሡ ጠላ​ቶች ጋር እን​ዳ​ል​ዋጋ፥ በፊ​ትህ ከተ​ቀ​መ​ጥሁ ጀምሬ እስከ ዛሬ ድረስ በእኔ በአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ምን በደል አግ​ኝ​ተ​ህ​ብ​ኛል?” አለው።</verse>
				<verse number="9">አን​ኩ​ስም መልሶ ዳዊ​ትን፥ “በዐ​ይኔ ፊት ጻድቅ እንደ ሆንህ አው​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች፦ ‘ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይ​ወ​ጣም’ አሉ።</verse>
				<verse number="10">አሁ​ንም አንተ ከአ​ን​ተም ጋር የመጡ የጌ​ታህ ብላ​ቴ​ኖች ማል​ዳ​ችሁ ተነሡ፤ ሲነ​ጋም ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ወደ መጣ​ች​ሁ​በት ሂዱ። ክፉ ነገ​ር​ንም በል​ብህ አታ​ኑር፤ በዐ​ይኔ ፊት ጻድቅ ነህና፥ በነ​ጋም ጊዜ ገሥ​ግ​ሣ​ችሁ መን​ገ​ዳ​ች​ሁን ሂዱ” አለው። እነ​ር​ሱም ሄዱ።</verse>
				<verse number="11">ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ማል​ደው ይሄዱ ዘንድ፥ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሀገር ይመ​ለሱ ዘንድ ተነሡ። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሊዋጉ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ወጡ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="30">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊ​ትና ሰዎቹ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ወደ ሴቄ​ላቅ በገቡ ጊዜ፥ አማ​ሌ​ቃ​ው​ያን በአ​ዜብ በሰ​ቄ​ላ​ቅም ላይ ዘም​ተው ነበር፤ ሴቄ​ላ​ቅ​ንም መት​ተው በእ​ሳት አቃ​ጥ​ለ​ዋት ነበር፥</verse>
				<verse number="2">ሴቶ​ቹ​ንና በው​ስ​ጥ​ዋም የነ​በ​ሩ​ትን ሁሉ ከታ​ናሽ እስከ ታላቅ ድረስ ማር​ከው ነበር፤ ሁሉ​ንም ወስ​ደው መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ሄዱ እንጂ ሴቶ​ች​ንም ሆነ ወን​ዶ​ችን አል​ገ​ደ​ሉም።</verse>
				<verse number="3">ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ወደ ከተማ በመጡ ጊዜ፥ እነሆ፥ በእ​ሳት ተቃ​ጥላ፥ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ተማ​ር​ከው አገኙ።</verse>
				<verse number="4">ዳዊ​ትና ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሕዝብ ድም​ፃ​ቸ​ውን ከፍ አድ​ር​ገው ለማ​ል​ቀስ ኀይል እስ​ኪ​ያጡ ድረስ አለ​ቀሱ።</verse>
				<verse number="5">የዳ​ዊ​ትም ሁለቱ ሚስ​ቶቹ ኢይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊቱ አኪ​ና​ሆ​ምና የቀ​ር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊው የና​ባል ሚስት የነ​በ​ረ​ችው አቤ​ግያ ተማ​ር​ከው ነበር።</verse>
				<verse number="6">ስለ ወን​ዶ​ችና ስለ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም የሕ​ዝቡ ሁሉ ልብ አዝኖ ነበ​ርና ሕዝቡ ሊወ​ግ​ሩት ስለ ተና​ገሩ ዳዊት እጅግ ተጨ​ነቀ፤ ዳዊት ግን በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሱን አጽ​ናና።</verse>
				<verse number="7">ዳዊ​ትም የአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክን ልጅ ካህ​ኑን አብ​ያ​ታ​ርን፥ “ኤፉ​ዱን አቅ​ር​ብ​ልኝ” አለው፤ አብ​ያ​ታ​ርም ኤፉ​ዱን ለዳ​ዊት አቀ​ረ​በ​ለት።</verse>
				<verse number="8">ዳዊ​ትም፥ “የእ​ነ​ዚ​ህን ሠራ​ዊት ፍለጋ ልከ​ተ​ልን? አገ​ኛ​ቸ​ዋ​ለ​ሁን?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እር​ሱም፥ “ታገ​ኛ​ቸ​ዋ​ለ​ህና፥ ፈጽ​መ​ህም ምር​ኮ​ኞ​ቹን ታድ​ና​ለ​ህና ፍለ​ጋ​ቸ​ውን ተከ​ተል” ብሎ መለ​ሰ​ለት።</verse>
				<verse number="9">ዳዊ​ትም ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ስድ​ስት መቶ ሰዎች ሄዱ፤ እስከ ቦሦር ወንዝ ድረ​ስም መጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የቀ​ሩት በዚያ ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="10">ዳዊ​ትም ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉት አራት መቶ ሰዎች አሳ​ደዱ፤ ሁለቱ መቶ ሰዎች ግን የቦ​ሦር ወን​ዝን መሻ​ገር ደክ​መ​ዋ​ልና በኋላ ቀሩ።</verse>
				<verse number="11">በበ​ረ​ሃ​ውም ውስጥ አንድ ግብ​ፃዊ አግ​ኝ​ተው ወደ ዳዊት ይዘ​ውት መጡ፤ እን​ጀ​ራም ሰጡ​ትና በላ፤ ውኃም አጠ​ጡት።</verse>
				<verse number="12">ከበ​ለ​ሱም ጥፍ​ጥፍ ቍራጭ ሰጡ​ትና በላ፤ ነፍ​ሱም ወደ እርሱ ተመ​ለ​ሰች፤ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እን​ጀራ አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="13">ዳዊ​ትም፥ “አንተ የማን ነህ? ከወ​ዴት መጣህ?” አለው። ያም ግብ​ፃዊ ብላ​ቴና፥ “እኔ የአ​ማ​ሌ​ቃዊ ባሪያ ነኝ፤ ከሦ​ስት ቀንም በፊት ታምሜ ነበ​ርና ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ።</verse>
				<verse number="14">እኛም በከ​ሊ​ታ​ው​ያን አዜብ፥ በይ​ሁ​ዳም በኩል፥ በካ​ሌ​ብም አዜብ ላይ ዘመ​ትን፥ ሴቄ​ላ​ቅ​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ል​ናት” አለው።</verse>
				<verse number="15">ዳዊ​ትም፥ “ወደ እነ​ዚያ ሠራ​ዊት ልት​መ​ራኝ ትወ​ድ​ዳ​ለ​ህን?” አለው፥ እር​ሱም፥ “እን​ዳ​ት​ገ​ድ​ለኝ፥ ለጌ​ታ​ዬም እጅ አሳ​ል​ፈህ እን​ዳ​ት​ሰ​ጠኝ በአ​ም​ላክ ማል​ልኝ፤ እኔም ወደ እነ​ዚያ ሠራ​ዊት እመ​ራ​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="16">ወደ እዚ​ያም ባደ​ረ​ሰው ጊዜ፥ እነሆ፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንና ከይ​ሁዳ ምድር ከወ​ሰ​ዱት ከብዙ ምርኮ ሁሉ የተ​ነሣ በል​ተው፥ ጠጥ​ተው፥ የበ​ዓ​ልም ቀን አድ​ር​ገው፥ በም​ድር ሁሉ ላይ ተበ​ት​ነው አገ​ኛ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">ዳዊ​ትም ሄዶ የአ​ጥ​ቢያ ኮከብ ከሚ​ወ​ጣ​በት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ዳግ​መ​ኛም በማ​ግ​ሥቱ መታ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በግ​መል ተቀ​ም​ጠው ከሸ​ሹት አራት መቶ ጐል​ማ​ሶች በቀር አን​ድም ያመ​ለጠ የለም።</verse>
				<verse number="18">ዳዊ​ትም አማ​ሌ​ቃ​ው​ያን የወ​ሰ​ዱ​ትን ሁሉ አስ​ጣ​ላ​ቸው፤ ሁለ​ቱ​ንም ሚስ​ቶ​ቹን አዳነ።</verse>
				<verse number="19">ከወ​ን​ዶ​ችና ከሴ​ቶች ልጆች፥ ከወ​ሰ​ዱት ምርኮ ሁሉ፥ ታላ​ቅም ሆነ፥ ታና​ሽም ሆነ፥ ምንም የተ​ወ​ላ​ቸው የለም፤ ዳዊ​ትም ሁሉን አስ​ጣለ።</verse>
				<verse number="20">ዳዊ​ትም የበ​ጉ​ንና የላ​ሙን መንጋ ሁሉ ወሰደ፤ ምር​ኮ​ው​ንም በፊቱ ነዱ፤ ያንም ምርኮ “የዳ​ዊት ምርኮ” አሉት።</verse>
				<verse number="21">ዳዊ​ትም ደክ​መው ዳዊ​ትን ይከ​ተ​ሉት ዘንድ ወዳ​ል​ቻሉ፥ በቦ​ሦር ወንዝ ወዳ​ስ​ቀ​ራ​ቸው ወደ ሁለቱ መቶ ሰዎች መጣ፤ እነ​ር​ሱም ዳዊ​ትን ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ሊቀ​በሉ ወጡ፤ ዳዊ​ትም ወደ ሕዝቡ በቀ​ረበ ጊዜ ደኅ​ን​ነ​ቱን ጠየ​ቁት።</verse>
				<verse number="22">ከዳ​ዊ​ትም ጋር ከሄዱ ሰዎች ክፉ​ዎ​ቹና ዐመ​ፀ​ኞቹ ሁሉ፥ “እነ​ዚህ ከእኛ ጋር አል​መ​ጡ​ምና እየ​ራ​ሳ​ቸው ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ይዘው ይሂዱ እንጂ ካስ​ጣ​ል​ነው ምርኮ ምንም አን​ሰ​ጣ​ቸ​ውም” አሉ።</verse>
				<verse number="23">ዳዊ​ትም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​ልፎ ከሰ​ጠን በኋላ እን​ዲህ አታ​ድ​ርጉ፤ እርሱ ጠብ​ቆ​ናል፤ በእ​ኛም ላይ የመ​ጡ​ትን ሠራ​ዊት በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ናል፤</verse>
				<verse number="24">ይህ​ንስ ነገር ማን ይሰ​ማ​ች​ኋል? እና​ንተ ከእ​ነ​ርሱ አት​በ​ል​ጡ​ምና ወደ ጦር​ነት በሄ​ዱት ድርሻ ልክ ጓዝ የጠ​በቁ ሰዎች ድርሻ እን​ዲሁ ነው።”</verse>
				<verse number="25">ከዚ​ያም ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ይህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሥር​ዐ​ትና ሕግ ሆነ።</verse>
				<verse number="26">ዳዊ​ትም ወደ ሴቄ​ላቅ በመጣ ጊዜ ለይ​ሁዳ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ለወ​ዳ​ጆቹ፥ “እነሆ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶች ምርኮ በረ​ከ​ትን ተቀ​በሉ” ብሎ ከም​ር​ኮው ላከ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="27">በቤ​ት​ሶር ለነ​በሩ፥ በራማ አዜ​ብም ለነ​በሩ፥ በጌ​ትም ለነ​በሩ፥</verse>
				<verse number="28">በቄ​ኔት ለነ​በሩ፥ በሳ​ፌቅ ለነ​በሩ፥ በቴ​ማት ለነ​በሩ፥</verse>
				<verse number="29">በቀ​ር​ሜ​ሎስ ለነ​በሩ፥ በይ​ረ​ሕ​ም​ኤ​ላ​ው​ያ​ንና በቄ​ኔ​ዛ​ው​ያን ከተ​ሞ​ችም ለነ​በሩ፥</verse>
				<verse number="30">በኢ​ያ​ሬ​ሞት በቤ​ር​ሳ​ቤህ ለነ​በሩ፥ በኖ​ባማ ለነ​በሩ፥</verse>
				<verse number="31">በኬ​ብ​ሮን ለነ​በሩ፥ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም በተ​መ​ላ​ለ​ሱ​በት ስፍራ ለነ​በሩ ሰዎች ሁሉ ላከ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="31">
				<verse number="1">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ተዋጉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ሸሹ፤ ተዋ​ግ​ተ​ውም በጌ​ላ​ቡሄ ተራራ ላይ ወደቁ።</verse>
				<verse number="2">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሳኦ​ል​ንና ልጆ​ቹን ተከ​ት​ለው አገ​ኙ​አ​ቸው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የሳ​ኦ​ልን ልጆች ዮና​ታ​ን​ንና አሚ​ና​ዳ​ብን፥ ሜል​ኪ​ሳ​ንም ገደ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ሰል​ፍም በሳ​ኦል ላይ ጠነ​ከረ፤ ቀስ​ተ​ኞ​ችም አገ​ኙት፤ ታፋ​ው​ንም ወጉት።</verse>
				<verse number="4">ሳኦ​ልም ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን፥ “እነ​ዚህ ቈላ​ፋን መጥ​ተው እን​ዳ​ይ​ወ​ጉ​ኝና እን​ዳ​ይ​ሳ​ለ​ቁ​ብኝ ሰይ​ፍ​ህን መዝ​ዘህ ውጋኝ” አለ። ጋሻ ጃግ​ሬው ግን እጅግ ፈርቶ ነበ​ርና እንቢ አለ። ሳኦ​ልም ሰይ​ፉን ወስዶ በላዩ ወደቀ።</verse>
				<verse number="5">ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም ሳኦል እንደ ሞተ ባየ ጊዜ እርሱ ደግሞ በሰ​ይፉ ላይ ወደቀ። ከእ​ር​ሱም ጋር ሞተ።</verse>
				<verse number="6">በዚ​ያም ቀን ሳኦል ሦስ​ቱም ልጆቹ ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም በአ​ንድ ላይ ሞቱ።</verse>
				<verse number="7">በሸ​ለ​ቆ​ውም ማዶና በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ የነ​በሩ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች እንደ ሸሹ፥ ሳኦ​ልና ልጆ​ቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተ​ሞ​ቹን ለቅ​ቀው ሸሹ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም መጥ​ተው ተቀ​መ​ጡ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">በማ​ግ​ሥ​ቱም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን የሞ​ቱ​ትን ለመ​ግ​ፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦ​ልና ሦስቱ ልጆቹ በጌ​ላ​ቡሄ ተራራ ላይ ወድ​ቀው አገ​ኙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">አገ​ላ​ብ​ጠ​ውም የጦር መሣ​ሪ​ያ​ዎ​ችን ገፈፉ፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ላሉ ለጣ​ዖ​ታ​ቱና ለሕ​ዝቡ የም​ሥ​ራች ይነ​ግሩ ዘንድ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገር ሁሉ ላኩ።</verse>
				<verse number="10">የጦር መሣ​ሪ​ያ​ው​ንም በአ​ስ​ታ​ሮት መቅ​ደስ ውስጥ አኖ​ሩት። ሬሳ​ው​ንም በቤ​ት​ሶም ቅጥር ላይ አን​ጠ​ለ​ጠ​ሉት።</verse>
				<verse number="11">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም በሳ​ኦል ላይ ያደ​ረ​ጉ​ትን የኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓድ ሰዎች በሰሙ ጊዜ፥ ጀግ​ኖች ሰዎች ሁሉ ተነ​ሥ​ተው ሌሊ​ቱን ሁሉ ሄዱ፥</verse>
				<verse number="12">የሳ​ኦ​ል​ንም ሬሳ፥ የልጁ የዮ​ና​ታ​ን​ንም ሬሳ ከቤ​ት​ሶም ቅጥር ላይ አወ​ረዱ፤ ወደ ኢያ​ቢ​ስም አመ​ጡ​አ​ቸው፤ በዚ​ያም አቃ​ጠ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ወሰዱ፤ በኢ​ያ​ቢ​ስም ባለው የእ​ርሻ ቦታ ቀበ​ሩ​አ​ቸው፤ ሰባት ቀንም ጾሙ።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="10">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሳኦል ከሞተ በኋላ ዳዊት አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ከመ​ግ​ደል ተመ​ለሰ፤ ዳዊ​ትም በሴ​ቄ​ላቅ ሁለት ቀን ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="2">በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን፥ እነሆ፥ ከሰ​ፈር ከሳ​ኦል ወገን አንድ ሰው ልብ​ሱን ቀድዶ፥ በራ​ሱም ላይ ትቢያ ነስ​ንሶ መጣ፤ ወደ ዳዊ​ትም በመጣ ጊዜ በም​ድር ላይ ወድቆ ሰገ​ደ​ለት።</verse>
				<verse number="3">ዳዊ​ትም፥ “ከወ​ዴት መጣህ?” አለው፤ እር​ሱም፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ሰፈር አም​ልጬ መጣሁ” አለው።</verse>
				<verse number="4">ዳዊ​ትም፥ “ነገሩ ምን​ድን ነው? እስኪ ንገ​ረኝ” አለው። እር​ሱም መልሶ፥ “ሕዝቡ ከሰ​ልፉ ሸሽ​ቶ​አል፤ ከሕ​ዝ​ቡም ብዙው ወደቁ፤ ሞቱም፤ ሳኦ​ልና ልጁ ዮና​ታ​ንም ደግሞ ሞተ​ዋል” አለው።</verse>
				<verse number="5">ዳዊ​ትም ወሬ​ውን ያመ​ጣ​ለ​ትን ጐል​ማሳ፥ “ሳኦ​ልና ልጁ ዮና​ታን እንደ ሞቱ እን​ዴት ዐወ​ቅህ?” አለው።</verse>
				<verse number="6">ወሬ​ውን ያመ​ጣ​ለት ጎል​ማ​ሳም አለ፥ “በጌ​ላ​ቡሄ ተራራ ተዋ​ግ​ተው ወደቁ፤ እነ​ሆም፥ ሳኦል በጦሩ ላይ ተኝቶ ነበር፤ ሰረ​ገ​ሎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞ​ችም ተከ​ት​ለው ደረ​ሱ​በት።</verse>
				<verse number="7">ወደ ኋላ​ውም ዘወር አለና እኔን አይቶ ጠራኝ፤ እኔም፦ እነ​ሆኝ አልሁ።</verse>
				<verse number="8">እር​ሱም፦ አንተ ማን ነህ? አለኝ፤ እኔም አማ​ሌ​ቃዊ ነኝ ብዬ መለ​ስ​ሁ​ለት።</verse>
				<verse number="9">እር​ሱም፦ ክፉ ጨለማ ይዞ​ኛ​ልና ደግሞ እስ​ካ​ሁን ድረስ ነፍሴ ገና ፈጽማ ሕያ​ውት ናትና በላዬ ቆመህ ግደ​ለኝ አለኝ።</verse>
				<verse number="10">እኔም ከወ​ደቀ በኋላ አለ​መ​ዳ​ኑን አይቼ በላዩ ቆሜ ገደ​ል​ሁት፤ በራ​ሱም ላይ የነ​በ​ረ​ውን ዘውድ፥ በክ​ን​ዱም የነ​በ​ረ​ውን ቢተዋ ወሰ​ድሁ፤ ወደ​ዚ​ህም ወደ ጌታዬ አመ​ጣ​ሁት።”</verse>
				<verse number="11">ዳዊ​ትም ልብ​ሱን ቀደደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሰዎች ሁሉ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀደዱ።</verse>
				<verse number="12">በጦር ወድ​ቀ​ዋ​ልና ለሳ​ኦ​ልና ለልጁ ለዮ​ና​ታን፥ ለይ​ሁ​ዳም ሕዝብ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወገን እንባ እያ​ፈ​ሰሱ አለ​ቀሱ፤ እስከ ማታም ድረስ ጾሙ።</verse>
				<verse number="13">ዳዊ​ትም ወሬ​ውን ያመ​ጣ​ለ​ትን ጐል​ማሳ፥ “አንተ ከወ​ዴት ነህ?” አለው፤ እር​ሱም፥ “እኔ የመ​ጻ​ተ​ኛው የአ​ማ​ሌ​ቃ​ዊው ልጅ ነኝ” ብሎ መለ​ሰ​ለት።</verse>
				<verse number="14">ዳዊ​ትም፥ “ትገ​ድ​ለው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ባው ላይ እጅ​ህን ስት​ዘ​ረጋ እን​ዴት አል​ፈ​ራ​ህም?” አለው።</verse>
				<verse number="15">ዳዊ​ትም ከብ​ላ​ቴ​ኖቹ አን​ዱን ጠርቶ፥ “ሂድና ግደ​ለው” አለው፤ ገደ​ለ​ውም።</verse>
				<verse number="16">ዳዊ​ትም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ባ​ውን እኔ ገድ​ያ​ለሁ ብሎ አፍህ በላ​ይህ መስ​ክ​ሮ​አ​ልና ደምህ በራ​ስህ ላይ ይሁን” አለው።</verse>
				<verse number="17">ዳዊ​ትም ስለ ሳኦ​ልና ስለ ልጁ ዮና​ታን ይህን የኀ​ዘን ቅኔ ተቀኘ፤</verse>
				<verse number="18">የይ​ሁ​ዳ​ንም ልጆች ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ አዘዘ። እነሆ ይህ በጻ​ድ​ቃን መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።</verse>
				<verse number="19">“እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ለሞ​ቱ​ትና ለተ​ገ​ደ​ሉት ሐው​ልት ትከል፤ ኀያ​ላን እን​ዴት ወደቁ!</verse>
				<verse number="20">የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሴቶች ልጆች ደስ እን​ዳ​ይ​ላ​ቸው፥ የቈ​ላ​ፋ​ንም ሴቶች ልጆች እልል እን​ዳ​ይሉ፥ በጌት ውስጥ አታ​ውሩ፤ በአ​ስ​ቀ​ሎ​ናም አደ​ባ​ባይ የም​ስ​ራች አት​በሉ።</verse>
				<verse number="21">እና​ንተ የጌ​ላ​ቡሄ ተራ​ሮች ሆይ፥ ዝና​ብና ጠል አይ​ው​ረ​ድ​ባ​ችሁ፤ ቍር​ባ​ን​ንም የሚ​ያ​በ​ቅል እርሻ አይ​ሁ​ን​ባ​ችሁ። የኀ​ያ​ላን ጋሻ በዚያ ወድ​ቆ​አ​ልና፤ የሳ​ኦ​ልም ጋሻ ዘይት አል​ተ​ቀ​ባ​ምና።</verse>
				<verse number="22">ከሞ​ቱት ደምና ከኀ​ያ​ላን ስብ፥ የዮ​ና​ታን ቀስት ባዶ​ዋን አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ የሳ​ኦ​ልም ሰይፍ ባዶ​ዋን አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም።</verse>
				<verse number="23">ሳኦ​ልና ዮና​ታን የተ​ወ​ደ​ዱና ያማሩ ነበሩ፤ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸ​ውና በሞ​ታ​ቸው አል​ተ​ለ​ያ​ዩም፤ ከን​ስር ይልቅ ፈጣ​ኖች ነበሩ፤ ከአ​ን​በ​ሳም ይልቅ ብር​ቱ​ዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="24">የእ​ስ​ራ​ኤል ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ቀይ ሐርና ጥሩ ግምጃ ያለ​ብ​ሳ​ችሁ ለነ​በረ፥ በወ​ር​ቀ​ዘ​ቦም ያስ​ጌ​ጣ​ችሁ ለነ​በረ ለሳ​ኦል አል​ቅ​ሱ​ለት።</verse>
				<verse number="25">ኀያ​ላን በሰ​ልፍ ውስጥ እን​ዴት ወደቁ! ዮና​ታን ሆይ፥ ሌሎ​ችም የተ​መ​ቱት በኮ​ረ​ብ​ቶ​ችህ ላይ ወደቁ።</verse>
				<verse number="26">ወን​ድሜ ዮና​ታን ሆይ፥ እኔ ስለ አንተ እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ አንተ በእኔ ዘንድ እጅግ የተ​ወ​ደ​ድህ ነበ​ርህ፤ ከሴት ፍቅር ይልቅ ፍቅ​ርህ ለእኔ ድንቅ ነበረ።</verse>
				<verse number="27">ኀያ​ላን እን​ዴት ወደቁ! የሰ​ል​ፍም ዕቃ​ዎች እን​ዴት ጠፉ!”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ከዚ​ያም በኋላ ዳዊት፥ “ከይ​ሁዳ ከተ​ሞች ወደ አን​ዲቱ ልው​ጣን?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ውጣ” አለው። ዳዊ​ትም፥ “ወዴት ልውጣ?” አለ። እር​ሱም፥ “ወደ ኬብ​ሮን ውጣ” አለው።</verse>
				<verse number="2">ዳዊ​ትም ከሁ​ለቱ ሚስ​ቶቹ ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊቱ ከአ​ኪ​ና​ሆ​ምና የቀ​ር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊው የና​ባል ሚስት ከነ​በ​ረ​ችው ከአ​ቤ​ግያ ጋር ወደ​ዚያ ወደ ኬብ​ሮን ወጣ።</verse>
				<verse number="3">ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ሰዎች ሁሉ ከቤተ ሰባ​ቸው ጋር ወጡ፤ በኬ​ብ​ሮ​ንም ከተ​ሞች ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="4">የይ​ሁ​ዳም ሰዎች መጥ​ተው በይ​ሁዳ ቤት ይነ​ግሥ ዘንድ ዳዊ​ትን በዚያ ቀቡት። ሳኦ​ልን የቀ​በ​ሩት የኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓድ ሰዎች ናቸው ብለው ለዳ​ዊት ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="5">ዳዊ​ትም ወደ ኢያ​ቢስ ገለ​ዓድ ገዦች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ ዳዊ​ትም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለቀ​ባው ለጌ​ታ​ችሁ ለሳ​ኦል ይህን ቸር​ነት አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና፥ እር​ሱ​ንና ልጁን ዮና​ታ​ን​ንም ቀብ​ራ​ች​ኋ​ቸ​ዋ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ረ​ካ​ችሁ ሁኑ።</verse>
				<verse number="6">አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሕ​ረ​ት​ንና ጽድ​ቅን ያድ​ር​ግ​ላ​ችሁ፤ ይህ​ንም ነገር አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና እኔ ደግሞ ይህን በጎ​ነት እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">አሁ​ንም ጌታ​ችሁ ሳኦል ሞቶ​አ​ልና እጃ​ችሁ ትጽና፤ እና​ን​ተም በርቱ፤ የይ​ሁ​ዳም ቤት በእ​ነ​ርሱ ላይ ንጉሥ እሆን ዘንድ ቀብ​ተ​ው​ኛል።”</verse>
				<verse number="8">የሳ​ኦ​ልም ጭፍራ አለቃ የኔር ልጅ አበ​ኔር የሳ​ኦ​ልን ልጅ ኢያ​ቡ​ስ​ቴን ወስዶ ከሰ​ፈር ወደ መሃ​ና​ይም አወ​ጣው፤</verse>
				<verse number="9">በገ​ለ​ዓ​ድና በታ​ሲሪ፥ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ልም፥ በኤ​ፍ​ሬ​ምም፥ በብ​ን​ያ​ምም፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ላይ አነ​ገ​ሠው።</verse>
				<verse number="10">የሳ​ኦል ልጅ ኢያ​ቡ​ስ​ቴም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በነ​ገሠ ጊዜ አርባ ዓመት ሆኖት ነበረ፤ ዳዊ​ትን ከተ​ከ​ተ​ሉት ከይ​ሁዳ ወገ​ኖች ብቻ በቀር ሁለት ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="11">ዳዊ​ትም በይ​ሁዳ ቤት በኬ​ብ​ሮን የነ​ገ​ሠ​በት ዘመን ሰባት ዓመት ከስ​ድ​ስት ወር ነበረ።</verse>
				<verse number="12">የኔር ልጅ አበ​ኔ​ርና የሳ​ኦል ልጅ የኢ​ያ​ቡ​ስቴ ብላ​ቴ​ኖች ከመ​ሃ​ና​ይም ወደ ገባ​ዖን ወጡ።</verse>
				<verse number="13">የሶ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አ​ብና የዳ​ዊት ብላ​ቴ​ኖች ከኬ​ብ​ሮን ወጥ​ተው በገ​ባ​ዖን ውኃ መቆ​ሚያ አጠ​ገብ ተገ​ና​ኙ​አ​ቸው፤ በው​ኃ​ውም መቆ​ሚያ በአ​ንዱ ወገን እነ​ዚህ፥ በሌ​ላ​ውም ወገን እነ​ዚያ ሆነው ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="14">አበ​ኔ​ርም ኢዮ​አ​ብን፥ “ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ችን ይነሡ፤ በፊ​ታ​ች​ንም ይቈ​ራ​ቈሱ” አለው፤ ኢዮ​አ​ብም፥ “ይነሡ” አለ።</verse>
				<verse number="15">ለሳ​ኦል ልጅ ለኢ​ያ​ቡ​ስቴ ከብ​ን​ያም ልጆች ዐሥራ ሁለት፥ ከዳ​ዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖች ዐሥራ ሁለት ተቈ​ጥ​ረው ተነሡ።</verse>
				<verse number="16">ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ የወ​ደ​ረ​ኛ​ውን ራስ በእጁ ያዘ፤ ሰይ​ፉ​ንም በወ​ደ​ረ​ኛው ጐን ሻጠ፤ ተያ​ይ​ዘ​ውም ወደቁ። የዚ​ያም ስፍራ ስም “በገ​ባ​ዖን የሸ​መቁ ሰዎች ድርሻ” ተብሎ ተጠራ፤</verse>
				<verse number="17">በዚ​ያም ቀን እጅግ ጽኑ ሰልፍ ሆነ፤ በዳ​ዊ​ትም ሰዎች ፊት አበ​ኔ​ርና የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ተሸ​ነፉ።</verse>
				<verse number="18">በዚ​ያም ሦስቱ የሦ​ር​ህያ ልጆች ኢዮ​አ​ብና አቢሳ፥ አሣ​ሄ​ልም ነበሩ፤ የአ​ሣ​ሄ​ልም እግ​ሮቹ ፈጣ​ኖች ነበሩ፤ እንደ ዱር ሚዳ​ቋም ሯጭ ነበረ።</verse>
				<verse number="19">አሣ​ሄ​ልም የአ​በ​ኔ​ርን ፍለጋ ተከ​ታ​ተለ፤ አበ​ኔ​ር​ንም ከማ​ሳ​ደድ ቀኝና ግራ አላ​ለም።</verse>
				<verse number="20">አበ​ኔ​ርም ወደ ኋላው ተመ​ልሶ፥ “አንተ አሣ​ሄል ነህን?” አለው። እር​ሱም፥ “አዎ፥ እኔ ነኝ” አለው።</verse>
				<verse number="21">አበ​ኔ​ርም፥ “ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ፈቀቅ በል፤ ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አንድ ጐል​ማሳ ያዝ፤ መሣ​ሪ​ያ​ው​ንም ለራ​ስህ ውሰድ” አለው። አሣ​ሄል ግን እር​ሱን ከማ​ሳ​ደድ ፈቀቅ ይል ዘንድ እንቢ አለ።</verse>
				<verse number="22">አበ​ኔ​ርም አሣ​ሄ​ልን፥ “ከም​ድር ጋር እን​ዳ​ላ​ጣ​ብ​ቅህ እኔን ከማ​ሳ​ደድ ፈቀቅ በል፤ ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ ኢዮ​አብ ፊቴን አቅ​ንቼ አይ ዘንድ እን​ዴት ይቻ​ለ​ኛል? እን​ደ​ዚህ አይ​ሆ​ን​ምና ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ ኢዮ​አብ ተመ​ለስ” አለው።</verse>
				<verse number="23">ነገር ግን ከእ​ርሱ ፈቀቅ ይል ዘንድ እንቢ አለ። አበ​ኔ​ርም በጦሩ ጫፍ ወገ​ቡን ወጋው፤ ጦሩም በኋ​ላው ወጣ፤ በዚ​ያም ስፍራ ወድቆ በበ​ታቹ ሞተ። አሣ​ሄ​ልም ወድቆ በሞ​ተ​በት ስፍራ የሚ​ያ​ልፍ ሁሉ ይቆም ነበር።</verse>
				<verse number="24">ኢዮ​አ​ብና አቢ​ሳም አበ​ኔ​ርን አሳ​ደዱ፤ ፀሐ​ይም ጠለ​ቀች፤ እነ​ር​ሱም በገ​ባ​ዖን ምድረ በዳ መን​ገድ በጋይ ፊት ለፊት እስ​ካ​ለው እስከ አማን ኮረ​ብታ ድረስ መጡ።</verse>
				<verse number="25">በአ​በ​ኔር ኋላ የነ​በሩ የብ​ን​ያ​ምም ልጆች ተሰ​በ​ሰቡ፥ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ሆኑ፤ በአ​ንድ ኮረ​ብ​ታም ራስ ላይ ቆሙ።</verse>
				<verse number="26">አበ​ኔ​ርም ኢዮ​አ​ብን ጠርቶ እን​ዲህ አለው፥ “ሰይፍ ለድል የም​ታ​ጠፋ አይ​ደ​ለ​ምን? ፍጻ​ሜ​ዋስ መራራ እንደ ሆነ አታ​ው​ቅ​ምን? ሕዝቡ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ከማ​ሳ​ደድ ይመ​ለሱ ዘንድ ሕዝ​ቡን የማ​ት​ና​ገር እስከ መቼ ነው?”</verse>
				<verse number="27">ኢዮ​አ​ብም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ባት​ና​ገር ኖሮ ሕዝቡ ሁሉ በጥ​ዋት በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ላይ በወጡ ነበር” አለ።</verse>
				<verse number="28">ኢዮ​አ​ብም ቀንደ መለ​ከት ነፋ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ተመ​ለሰ፤ ከዚ​ያም በኋላ እስ​ራ​ኤ​ልን አላ​ሳ​ደ​ዱ​አ​ቸ​ውም፤ ደግ​መ​ውም አል​ተ​ዋ​ጉም።</verse>
				<verse number="29">አበ​ኔ​ርና ሰዎ​ቹም ሌሊ​ቱን ሁሉ ወደ ምዕ​ራብ ሄዱ፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ገሩ፤ ያን ቀጥ​ተኛ መን​ገድ ካለፉ በኋ​ላም ወደ ሰፈር መጡ።</verse>
				<verse number="30">ኢዮ​አ​ብም አበ​ኔ​ርን ከማ​ሳ​ደድ ተመ​ለሰ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ የዳ​ዊ​ት​ንም ብላ​ቴ​ኖች አስ​ቈ​ጠ​ራ​ቸው፤ የሞ​ቱ​ትም ሰዎች ከአ​ሣ​ሄል ሌላ ዐሥራ ዘጠኝ ሰዎች ናቸው።</verse>
				<verse number="31">የዳ​ዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖች ከብ​ን​ያም እና ከአ​በ​ኔር ሰዎች ሦስት መቶ ስድሳ ሰዎ​ችን ገደሉ።</verse>
				<verse number="32">አሣ​ሄ​ል​ንም አን​ሥ​ተው በቤተ ልሔም በአ​ባቱ መቃ​ብር ቀበ​ሩት፤ ኢዮ​አ​ብና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በሩ ሰዎ​ቹም ሌሊ​ቱን ሁሉ፤ ሄዱ፥ በኬ​ብ​ሮ​ንም አነጉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">በሳ​ኦል ቤትና በዳ​ዊት ቤት መካ​ከል ለብዙ ጊዜ ጦር​ነት ሆነ፤ የዳ​ዊት ቤት እየ​በ​ረታ፥ የሳ​ኦል ቤት ግን እየ​ደ​ከመ የሚ​ሄድ ሆነ።</verse>
				<verse number="2">ለዳ​ዊ​ትም ወን​ዶች ልጆች በኬ​ብ​ሮን ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ በኵ​ሩም ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊቱ ከአ​ኪ​ና​ሆም የተ​ወ​ለ​ደው አም​ኖን ነበረ።</verse>
				<verse number="3">ሁለ​ተ​ኛ​ውም ከቀ​ር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊቱ ከአ​ቤ​ግያ የተ​ወ​ለ​ደው ዶሎ​ሕያ ነበረ። ሦስ​ተ​ኛ​ውም ከጌ​ድ​ሶር ንጉሥ ከቶ​ል​ሜ​ልም ልጅ ከመ​ዓክ የተ​ወ​ለ​ደው አቤ​ሴ​ሎም ነበረ።</verse>
				<verse number="4">አራ​ተ​ኛ​ውም የአ​ጊት ልጅ አዶ​ን​ያስ፥ አም​ስ​ተ​ኛ​ውም የአ​ቢ​ጣል ልጅ ሰፋ​ጥያ ነበረ።</verse>
				<verse number="5">ስድ​ስ​ተ​ኛ​ውም የዳ​ዊት ሚስት የዒ​ገል ልጅ ይት​ረ​ኃም ነበረ። ለዳ​ዊት በኬ​ብ​ሮን የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት እነ​ዚህ ነበሩ።</verse>
				<verse number="6">በሳ​ኦል ቤትና በዳ​ዊት ቤት መካ​ከል ጦር​ነት ሆኖ ሳለ አበ​ኔር የሳ​ኦ​ልን ቤት ያበ​ረታ ነበር።</verse>
				<verse number="7">ለሳ​ኦ​ልም የኢ​ዮ​ሄል ልጅ ሩጻፋ የተ​ባ​ለች ዕቅ​ብት ነበ​ረ​ችው፤ ኢያ​ቡ​ስ​ቴም አበ​ኔ​ርን፥ “ወደ አባቴ ዕቅ​ብት ለምን ገባህ?” አለው።</verse>
				<verse number="8">አበ​ኔ​ርም ኢያ​ቡ​ስቴ እን​ዲህ ስላ​ለው እጅግ ተቈጣ፤ አበ​ኔ​ርም እን​ዲህ አለው፥ “በውኑ እኔ የውሻ ራስ ነኝን? እኔ ለአ​ባ​ትህ ለሳ​ኦል ቤት ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዘ​መ​ዶ​ቹም ቸር​ነት አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ አን​ተ​ንም ለዳ​ዊት እጅ አሳ​ልፌ አል​ሰ​ጠ​ሁ​ህም፤ አን​ተም ዛሬ ከዚ​ህች ሴት ጋር ስለ ሠራ​ሁት ኀጢ​አት ትከ​ስ​ሰ​ኛ​ለህ።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዳ​ዊት እንደ ማለ​ለት እን​ዲሁ ከእ​ርሱ ጋር ዛሬ ባላ​ደ​ርግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​በ​ኔር ይህን ያድ​ር​ግ​በት፤ ይህ​ንም ይጨ​ም​ር​በት።</verse>
				<verse number="10">የዳ​ዊ​ት​ንም ዙፋን በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ ከፍ ያደ​ርግ ዘንድ መን​ግ​ሥ​ትን ከሳ​ኦል ቤት ወሰ​ዳት።”</verse>
				<verse number="11">ኢያ​ቡ​ስ​ቴም አበ​ኔ​ርን ይፈ​ራው ነበ​ርና ቃልን ይመ​ል​ስ​ለት ዘንድ አል​ቻ​ለም።</verse>
				<verse number="12">አበ​ኔ​ርም ለዳ​ዊት፥ “ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን አድ​ርግ፤ እጄም ከአ​ንተ ጋር ትሆ​ና​ለች፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሁሉ ወደ አንተ እመ​ል​ሰ​ዋ​ለሁ” ብለው በስሙ ይነ​ግ​ሩት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ወዲ​ያ​ውኑ ላከ​ለት።</verse>
				<verse number="13">ዳዊ​ትም፥ “ይሁን፤ በመ​ል​ካም ፈቃ​ደ​ኛ​ነት ከአ​ንተ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር ከአ​ንተ እሻ​ለሁ፤ ፊቴን ለማ​የት በመ​ጣህ ጊዜ፥ የሳ​ኦ​ልን ልጅ ሜል​ኮ​ልን ካላ​መ​ጣ​ህ​ልኝ ፊቴን አታ​ይም” አለው።</verse>
				<verse number="14">ዳዊ​ትም ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያ​ቡ​ስቴ፥ “በመቶ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሸለ​ፈት ያጨ​ኋ​ትን ሚስ​ቴን ሜል​ኮ​ልን መል​ስ​ልኝ” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ።</verse>
				<verse number="15">ኢያ​ቡ​ስ​ቴም ልኮ ከሴ​ሊስ ልጅ ከባ​ልዋ ከፈ​ላ​ጥ​ያል ወሰ​ዳት።</verse>
				<verse number="16">ባል​ዋም እያ​ለ​ቀሰ ከእ​ር​ስዋ ጋር ሄደ፤ እስከ ብራ​ቂም ድረስ ተከ​ተ​ላት። አበ​ኔ​ርም፥ “ሂድ፤ ተመ​ለስ” አለው፤ እር​ሱም ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="17">አበ​ኔ​ርም ለእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ “አስ​ቀ​ድሞ ዳዊት በእ​ና​ንተ ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ ፈል​ጋ​ችሁ ነበር።</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ዳዊት፦ በባ​ሪ​ያዬ በዳ​ዊት እጅ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን ክፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅና ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ እጅ አድ​ና​ለሁ ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና እን​ግ​ዲህ አሁን አድ​ርጉ´ ብሎ ነገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">አበ​ኔ​ርም ደግሞ በብ​ን​ያም ልጆች ጆሮ ተና​ገረ፤ አበ​ኔ​ርም ደግሞ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በብ​ን​ያም ቤት ሁሉ መል​ካም የነ​በ​ረ​ውን ለዳ​ዊት ሊነ​ግ​ረው ወደ ኬብ​ሮን ሄደ።</verse>
				<verse number="20">አበ​ኔ​ርም ከሃያ ሰዎች ጋር ወደ ዳዊት ወደ ኬብ​ሮን መጣ፤ ዳዊ​ትም ለአ​በ​ኔ​ርና ከእ​ርሱ ጋር ለነ​በ​ሩት ሰዎች ግብዣ አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">አበ​ኔ​ርም ዳዊ​ትን፥ “ተነ​ሥቼ ልሂድ፤ ካንተ ጋርም ቃል ኪዳን እን​ዲ​ያ​ደ​ርጉ፥ ነፍ​ስ​ህም እንደ ወደ​ደች ሁሉን እን​ድ​ት​ገዛ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ለጌ​ታዬ ለን​ጉሥ ልሰ​ብ​ስብ” አለው። ዳዊ​ትም አበ​ኔ​ርን አሰ​ና​በ​ተው፤ በሰ​ላ​ምም ሄደ።</verse>
				<verse number="22">በዚያ ጊዜም የዳ​ዊት ብላ​ቴ​ኖ​ችና ኢዮ​አብ ከዘ​መቻ ታላቅ ምርኮ ይዘው መጡ። አበ​ኔር ግን ዳዊት አሰ​ና​ብ​ቶት በደ​ኅና ሄዶ ነበር እንጂ በኬ​ብ​ሮን አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="23">ኢዮ​አ​ብና ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በረ ጭፍራ ሁሉ በመጡ ጊዜ፥ “የኔር ልጅ አበ​ኔር ወደ ንጉሥ መጣ፤ አሰ​ና​በ​ተ​ውም፤ በሰ​ላ​ምም ሄደ” ብለው ሰዎች ለኢ​ዮ​አብ ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="24">ኢዮ​አ​ብም ወደ ንጉሥ ገብቶ፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ኸው ነገር ምን​ድን ነው? እነሆ፥ አበ​ኔር መጥ​ቶ​ልህ ነበር፤ በደ​ኅና እን​ዲ​ሄድ ስለ​ምን አሰ​ና​በ​ት​ኸው?</verse>
				<verse number="25">የኔር ልጅ አበ​ኔር ያታ​ል​ልህ ዘንድ፥ መው​ጫ​ህ​ንና መግ​ቢ​ያ​ህ​ንም ያውቅ ዘንድ ፥ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ው​ንም ነገር ሁሉ ያስ​ተ​ውል ዘንድ እንደ መጣ አታ​ው​ቅ​ምን?” አለው።</verse>
				<verse number="26">ኢዮ​አ​ብም ከዳ​ዊት በወጣ ጊዜ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ከአ​በ​ኔር በኋላ ላከ፤ ከሴ​ይ​ርም ጕድ​ጓድ መለ​ሱት። ዳዊት ግን ይህን አላ​ወ​ቀም።</verse>
				<verse number="27">አበ​ኔ​ርም ወደ ኬብ​ሮን በተ​መ​ለሰ ጊዜ ኢዮ​አብ በበር ውስጥ በቈ​ይታ ይና​ገ​ረው ዘንድ ወደ አጠ​ገቡ ወሰ​ደው፤ በዚ​ያም ለወ​ን​ድሙ ለአ​ሣ​ሄል ደም ተበ​ቅሎ ወገ​ቡን መታው፤ ሞተም።</verse>
				<verse number="28">ከዚ​ህም በኋላ ዳዊት ሰማ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ከኔር ልጅ ከአ​በ​ኔር ደም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እኔ ንጹሕ ነኝ፤ መን​ግ​ሥ​ቴም ንጹሕ ነው፤</verse>
				<verse number="29">በኢ​ዮ​አብ ራስ ላይና በአ​ባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይም​ጣ​በት፤ በኢ​ዮ​አ​ብም ቤት ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ወይም ለም​ጻም ወይም አን​ካሳ ወይም በሰ​ይፍ የሚ​ወ​ድቅ ወይም እን​ጀራ የሌ​ለው ሰው አይ​ታጣ።”</verse>
				<verse number="30">ኢዮ​አ​ብና ወን​ድሙ አቢ​ሳም በሰ​ልፍ በገ​ባ​ዖን ወን​ድ​ማ​ቸ​ውን አሣ​ሄ​ልን ገድሎ ነበ​ርና አበ​ኔ​ርን ይገ​ድ​ሉት ዘንድ ይጠ​ባ​በቁ ነበር።</verse>
				<verse number="31">ዳዊ​ትም ኢዮ​አ​ብ​ንና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ሁሉ፥ “ልብ​ሳ​ች​ሁን ቅደዱ፤ ማቅም ልበሱ፤ በአ​በ​ኔ​ርም ፊት አል​ቅሱ” አላ​ቸው። ንጉ​ሡም ዳዊት ከቃ​ሬ​ዛው በኋላ ሄደ።</verse>
				<verse number="32">አበ​ኔ​ር​ንም በኬ​ብ​ሮን ቀበ​ሩት፤ ንጉ​ሡም ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ በመ​ቃ​ብሩ አጠ​ገብ አለ​ቀሰ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ለአ​በ​ኔር አለ​ቀ​ሱ​ለት።</verse>
				<verse number="33">ንጉ​ሡም ለአ​በ​ኔር አለ​ቀ​ሰ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ “አበ​ኔር ሰነፍ እን​ደ​ሚ​ሞት ይሞ​ታ​ልን?</verse>
				<verse number="34">እጆ​ችህ አል​ታ​ሰ​ሩም፤ እግ​ሮ​ች​ህም በሰ​ን​ሰ​ለት አል​ተ​ያ​ዙም፤ ማንም እንደ ሰነፍ አል​ወ​ሰ​ደ​ህም፤ በዐ​መፃ ልጆ​ችም ፊት ወደ​ቅህ።” ሕዝ​ቡም ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው አለ​ቀ​ሱ​ለት።</verse>
				<verse number="35">ሕዝ​ቡም ሁሉ ገና ሳይ​መሽ ዳዊ​ትን እን​ጀራ ይበላ ዘንድ ሊጋ​ብ​ዙት መጡ፤ ዳዊት ግን፥ “ፀሐይ ሳት​ጠ​ልቅ እን​ጀራ ወይም ሌላ ነገር ብቀ​ምስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ያድ​ር​ግ​ብኝ፥ ይህ​ንም ይጨ​ም​ር​ብኝ” ብሎ ማለ።</verse>
				<verse number="36">ሕዝ​ቡም ሁሉ ይህን ዐወቁ፤ በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት ንጉሥ ያደ​ረ​ገው ሁሉ ደስ አሰ​ኛ​ቸው።</verse>
				<verse number="37">በዚ​ያም ቀን ሕዝቡ ሁሉ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ የኔር ልጅ አበ​ኔ​ርን እን​ዲ​ገ​ድ​ሉት ንጉሡ እን​ዳ​ላ​ዘዘ ዐወቁ።</verse>
				<verse number="38">ንጉ​ሡም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “ዛሬ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ታላቅ መኰ​ንን እንደ ወደቀ አታ​ው​ቁ​ምን?</verse>
				<verse number="39">እኔም ዛሬ ዘመዱ እንደ ሆንሁ፥ እር​ሱም በን​ጉሡ ዘንድ የተ​ሾመ እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? እነ​ዚ​ህም ሰዎች የሦ​ር​ህያ ልጆች በር​ት​ተ​ው​ብ​ኛል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመ​ል​ስ​በት” አላ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">የሳ​ኦ​ልም ልጅ ኢያ​ቡ​ስቴ አበ​ኔር በኬ​ብ​ሮን እንደ ሞተ ሰማ፤ እጆ​ቹም ደከሙ፤ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም ሁሉ ደነ​ገጡ።</verse>
				<verse number="2">ለሳ​ኦ​ልም ልጅ ለኢ​ያ​ቡ​ስቴ የጭ​ፍራ አለ​ቆች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበ​ሩት፤ የአ​ን​ደ​ኛው ስም በዓና፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ስም ሬካብ ነበረ፤ ከብ​ን​ያ​ምም ልጆች የቤ​ሮ​ታ​ዊው የሬ​ሞን ልጆች ነበሩ፤ ቤሮ​ትም ለብ​ን​ያም ተቈ​ጥራ ነበር።</verse>
				<verse number="3">ቤሮ​ታ​ው​ያ​ንም ወደ ጌቴም ሸሽ​ተው ነበር፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ተጠ​ግ​ተው ነበር።</verse>
				<verse number="4">ለሳ​ኦ​ልም ልጅ ለዮ​ና​ታን አንድ ሽባ የሆነ ልጅ ነበ​ረው። የሳ​ኦ​ልና የዮ​ና​ታን ወሬ ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል በመጣ ጊዜ የአ​ም​ስት ዓመት ልጅ ነበረ፤ ሞግ​ዚ​ቱም አዝ​ላው ሸሸች፤ ልት​ሸ​ሽም ስት​ሮጥ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ነበረ።</verse>
				<verse number="5">የቤ​ሮ​ታ​ዊ​ውም የሬ​ሞን ልጆች ሬካ​ብና በዓና ቀኑ ሲሞቅ ወደ ኢያ​ቡ​ስቴ ቤት መጡ፤ እር​ሱም በቀ​ትር ጊዜ በአ​ል​ጋው ላይ ተኝቶ ነበር።</verse>
				<verse number="6">በረ​ኛ​ዪ​ቱም ስንዴ ታበ​ጥር ነበር፤ አን​ቀ​ላ​ፍ​ታም ተኝታ ነበር፤ ወን​ድ​ማ​ማ​ቾቹ ሬካ​ብና በዓ​ናም በቀ​ስታ ወደ ቤት ገቡ።</verse>
				<verse number="7">ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ኢያ​ቡ​ስቴ በእ​ል​ፍኙ በም​ን​ጣፉ ላይ ተኝቶ ሳለ መቱት፥ ገደ​ሉ​ትም፤ ራሱ​ንም ቈር​ጠው ወሰ​ዱት፥ በዓ​ረ​ባም መን​ገድ ሌሊ​ቱን ሁሉ ሄዱ።</verse>
				<verse number="8">የኢ​ያ​ቡ​ስ​ቴ​ንም ራስ ይዘው ወደ ዳዊት ወደ ኬብ​ሮን መጡ፤ ንጉ​ሡ​ንም፥ “ነፍ​ስ​ህን ይሻ የነ​በ​ረው የጠ​ላ​ትህ የሳ​ኦል ልጅ የኢ​ያ​ቡ​ስቴ ራስ እነሆ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዛሬ ከጠ​ላ​ትህ ከሳ​ኦ​ልና ከዘሩ ለጌ​ታ​ችን ለን​ጉሥ በቀ​ሉን መለ​ሰ​ለት” አሉት።</verse>
				<verse number="9">ዳዊ​ትም ለቤ​ሮ​ታ​ዊው ለሬ​ሞን ልጆች ለሬ​ካ​ብና ለወ​ን​ድሙ ለበ​ዓና እን​ዲህ ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው፥ “ነፍ​ሴን ከመ​ከራ ሁሉ ያዳነ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን!</verse>
				<verse number="10">መል​ካም ወሬ የያዘ መስ​ሎት እነሆ፥ ሳኦል ሞተ ብሎ የነ​ገ​ረ​ኝን የም​ስ​ራቹ ዋጋ እን​ዲ​ሆን ይዤ በሴ​ቄ​ላቅ ገደ​ል​ሁት።</verse>
				<verse number="11">አሁ​ንም እና​ንተ ክፉ​ዎች ሰዎች በቤቱ ውስጥ በአ​ል​ጋው ላይ ጻድ​ቁን ሰው ገደ​ላ​ች​ሁት፤ እነሆ፥ ደሙን ከእ​ጃ​ችሁ እሻ​ለሁ፤ ከም​ድ​ርም አጠ​ፋ​ች​ኋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="12">ዳዊ​ትም ጐል​ማ​ሶ​ቹን አዘዘ፤ ገደ​ሉ​አ​ቸ​ውም፤ እጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ቈር​ጠው በኬ​ብ​ሮን በውኃ መቆ​ሚያ አጠ​ገብ አን​ጠ​ለ​ጠ​ሉ​አ​ቸው። የኢ​ያ​ቡ​ስ​ቴን ራስ ግን ወስ​ደው በአ​በ​ኔር መቃ​ብር በኬ​ብ​ሮን ቀበ​ሩት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገድ ሁሉ ወደ ኬብ​ሮን ወደ ዳዊት መጥ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “እኛ የአ​ጥ​ን​ትህ ፍላጭ የሥ​ጋህ ቍራጭ ነን።</verse>
				<verse number="2">አስ​ቀ​ድሞ ሳኦል በእኛ ላይ ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስ​ራ​ኤ​ልን የም​ታ​ወ​ጣና የም​ታ​ገባ አንተ ነበ​ርህ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አንተ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን ትጠ​ብ​ቃ​ለህ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ አለቃ ትሆ​ና​ለህ ብሎህ” ነበር።</verse>
				<verse number="3">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ወደ ኬብ​ሮን መጡ፤ ንጉሡ ዳዊ​ትም በኬ​ብ​ሮን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ይሆን ዘንድ ዳዊ​ትን ቀቡት።</verse>
				<verse number="4">ዳዊ​ትም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሠ​ላሳ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ አርባ ዓመ​ትም ነገሠ፤</verse>
				<verse number="5">በኬ​ብ​ሮን በይ​ሁዳ ላይ ሰባት ዓመት ከስ​ድ​ስት ወር ነገሠ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉና በይ​ሁዳ ላይ ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="6">ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም በሀ​ገሩ ውስጥ ወደ​ሚ​ኖ​ሩት ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሄዱ፤ እነ​ር​ሱም ዳዊ​ትን፥ “ወደ​ዚህ አት​ገ​ባም” አሉት። ዕው​ሮ​ችና አን​ካ​ሶ​ችም ወደ​ዚህ አት​ገ​ባም ብለው ተቃ​ወ​ሙት።</verse>
				<verse number="7">ነገር ግን ዳዊት አን​ባ​ዪ​ቱን ጽዮ​ንን ያዘ፤ እር​ስ​ዋም የዳ​ዊት ከተማ ናት።</verse>
				<verse number="8">በዚ​ያም ቀን ዳዊት፥ “ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን የሚ​መታ ሁሉ፥ ዕው​ሮ​ች​ንና አን​ካ​ሶ​ችን፥ የዳ​ዊ​ት​ንም ነፍስ የሚ​ጠ​ሉ​ትን ሁሉ በሳ​ንጃ ይው​ጋ​ቸው” አለ። ስለ​ዚ​ህም፥ “ዕው​ርና አን​ካሳ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግቡ” ተባለ።</verse>
				<verse number="9">ዳዊ​ትም በአ​ን​ባ​ዪቱ ውስጥ ተቀ​መጠ፤ እር​ስ​ዋም የዳ​ዊት ከተማ ተባ​ለች። ከተ​ማ​ዋ​ንም ዙሪ​ያ​ዋን እስከ ዳር​ቻዋ ድረስ ቀጠ​ራት፤ ቤቱ​ንም ሠራ።</verse>
				<verse number="10">ዳዊ​ትም እየ​በ​ረታ፥ ከፍ እያ​ለም ሄደ፤ ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነበረ።</verse>
				<verse number="11">የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራም ወደ ዳዊት መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን፥ የዝ​ግባ እን​ጨ​ት​ንም፥ አና​ጢ​ዎ​ች​ንም፥ ድን​ጋይ ጠራ​ቢ​ዎ​ች​ንም ላከ፤ ለዳ​ዊ​ትም ቤት ሠሩ​ለት።</verse>
				<verse number="12">ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ አድ​ርጎ እን​ዳ​ዘ​ጋ​ጀው፥ ስለ ሕዝቡ ስለ እስ​ራ​ኤ​ልም መን​ግ​ሥ​ቱን ከፍ እን​ዳ​ደ​ረገ ዐወቀ።</verse>
				<verse number="13">ዳዊ​ትም ከኬ​ብ​ሮን ከመጣ በኋላ እንደ ገና ቁባ​ቶ​ቹ​ንና ሚስ​ቶ​ቹን ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወሰደ፤ ለዳ​ዊ​ትም ደግሞ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት።</verse>
				<verse number="14">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት ስማ​ቸው ይህ ነው፤ ሳሚስ፥ ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎ​ሞን፥</verse>
				<verse number="15">ኢያ​ቢ​ሖር፥ ኤሊ​ሱስ፥ ናፌቅ፥ ያፍያ፥</verse>
				<verse number="16">ኤሊ​ሳማ፥ ኤሊ​ዳሂ፥ ኤሊ​ፋ​ላት፥ ሶሜኤ፥ ኢያ​ሴ​ቦት፥ ናታን፥ ጋላ​ማ​ሄን፥ የበ​አር፥ ትሄ​ሱስ፥ ኤል​ፋ​ላት፥ ናጌድ፥ ናሬት፥ ያናታ፥ ሊሳ​ሚስ፥ በአ​ሊ​ማት፥ ኤል​ፋ​ላድ።</verse>
				<verse number="17">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ዳዊት በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ እንደ ተቀባ ሰሙ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ዳዊ​ትን ሊፈ​ልጉ ወጡ፤ ዳዊ​ትም በሰማ ጊዜ ወደ ምሽጉ ወረደ።</verse>
				<verse number="18">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም መጥ​ተው በረ​ዓ​ይት ሸለቆ ተበ​ት​ነው ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="19">ዳዊ​ትም፥ “ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ልው​ጣን? በእ​ጄስ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ህን?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በር​ግጥ በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ውጣ” አለው።</verse>
				<verse number="20">ዳዊ​ትም ከላ​ይ​ኛው መጋ​ደያ መጣ፤ በዚ​ያም መታ​ቸ​ውና፥ “ውኃ እን​ደ​ሚ​ያ​ጠፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶቼን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በፊቴ አጠ​ፋ​ቸው” አለ። ስለ​ዚ​ህም የዚያ ስፍራ ስም “የላ​ይ​ኛው መጋ​ደያ” ተብሎ ተጠራ።</verse>
				<verse number="21">ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በዚያ ተዉ፤ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ወሰ​ዱ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ደግሞ መጡ፤ ወደ ረዓ​ይ​ትም ሸለቆ ወረዱ።</verse>
				<verse number="23">ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በኋ​ላ​ቸው ዞረህ በሾ​ላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠ​ማ​ቸው እንጂ አት​ውጣ።</verse>
				<verse number="24">በሾ​ላ​ውም ዛፍ ራስ ውስጥ የሽ​ው​ሽ​ውታ ድምፅ ስት​ሰማ፥ በዚያ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ጭፍራ ለመ​ም​ታት በፊ​ትህ ወጥቶ ይሆ​ና​ልና በዚያ ጊዜ ፍጠን” አለው።</verse>
				<verse number="25">ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረገ፤ ከገ​ባ​ዖ​ንም እስከ ጌሴራ ድረስ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">ዳዊ​ትም ደግሞ ከእ​ስ​ራ​ኤል የተ​መ​ረ​ጡ​ትን ሰባ ሺህ ያህል ሰው ሰበ​ሰበ።</verse>
				<verse number="2">ዳዊ​ትና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ከይ​ሁዳ አለ​ቆች ጋር ተነ​ሥ​ተው በኪ​ሩ​ቤል ላይ የተ​ቀ​መጠ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የተ​ጠ​ራ​ባ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ከዚያ ያመጡ ዘንድ ሄዱ።</verse>
				<verse number="3">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት በአ​ዲስ ሰረ​ገላ ላይ ጫኑ​አት፥ በኮ​ረ​ብ​ታ​ውም ላይ ከነ​በ​ረው ከአ​ሚ​ና​ዳብ ቤት አመ​ጡ​አት፤ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጆ​ችም ዖዛና ወን​ድ​ሞቹ ታቦቷ ያለ​ች​በ​ትን ሰረ​ገላ ይነዱ ነበር።</verse>
				<verse number="4">ወን​ድ​ሞ​ቹም በታ​ቦቷ ፊት ይሄዱ ነበር።</verse>
				<verse number="5">ዳዊ​ትና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ በዜማ መሣ​ሪ​ያ​ዎች በበ​ገ​ናና በመ​ሰ​ንቆ፥ በከ​በ​ሮና በነ​ጋ​ሪት፥ በጸ​ና​ጽ​ልና በዕ​ን​ዚራ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሙሉ ኀይ​ላ​ቸው ይጫ​ወቱ ነበር።</verse>
				<verse number="6">ወደ ናኮ​ንም አው​ድማ ደረሱ፤ ዖዛም በሬ​ዎቹ አነ​ቃ​ን​ቀ​ዋት ነበ​ርና ይይ​ዛት ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት እጁን ዘረጋ፤ አስ​ተ​ካ​ከ​ላ​ትም። ሲይ​ዛ​ትም በሬው ወጋው።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዖዛ ላይ ተቈጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚ​ያው ቀሠ​ፈው። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት አጠ​ገብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዚ​ያው ሞተ።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዖዛን ስለ ገደ​ለው ዳዊት አዘነ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የዚያ ስፍራ ስም “ዖዛ የሞ​ተ​በት” ተባለ።</verse>
				<verse number="9">በዚ​ያም ቀን ዳዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈራና፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ወደ እኔ እን​ዴት ትገ​ባ​ለች?” አለ።</verse>
				<verse number="10">ዳዊ​ትም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦተ ሕግ ወደ እርሱ ወደ ዳዊት ከተማ ያመ​ጣት ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም፤ ዳዊ​ትም በጌት ሰው በአ​ቢ​ዳራ ቤት አገ​ባት።</verse>
				<verse number="11">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት በጌት ሰው በአ​ቢ​ዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀ​መ​ጠች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አቢ​ዳ​ራ​ንና ቤቱን ሁሉ ባረከ።</verse>
				<verse number="12">ለን​ጉሡ ዳዊ​ትም “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ቢ​ዳ​ራን ቤትና የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ባረከ” ብለው ነገ​ሩት። ዳዊ​ትም ሄዶ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ከአ​ቢ​ዳራ ቤት ወደ ዳዊት ከተማ በደ​ስታ አመ​ጣት።</verse>
				<verse number="13">ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ሰባት መሰ​ንቆ የሚ​መቱ ክፍ​ሎች ነበሩ። በሬ​ዎ​ች​ንና በጎ​ችን ይሠዉ ነበር።</verse>
				<verse number="14">ዳዊ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በገና ይደ​ረ​ድር ነበር፤ ዳዊ​ትም ለዐ​ይን የሚ​ያ​ን​ጸ​ባ​ርቅ የሐር ቀሚስ ለብሶ ነበር።</verse>
				<verse number="15">ዳዊ​ትና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ በእ​ል​ልታ ቀንደ መለ​ከት እየ​ነፉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት አመ​ጡ​አት።</verse>
				<verse number="16">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደ​ረ​ሰች ጊዜ የሳ​ኦል ልጅ ሜል​ኮል በመ​ስ​ኮት ሆና ተመ​ለ​ከ​ተች፤ ንጉ​ሡም ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሲዘ​ል​ልና ሲዘ​ምር አየ​ችው፥ በል​ብ​ዋም ናቀ​ችው።</verse>
				<verse number="17">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት አም​ጥ​ተው ዳዊት በተ​ከ​ለ​ላት ድን​ኳን ውስጥ በስ​ፍ​ራዋ አኖ​ሩ​አት፤ ዳዊ​ትም የሚ​ቃ​ጠ​ልና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕ​ትን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አሳ​ረገ።</verse>
				<verse number="18">ዳዊ​ትም የሚ​ቃ​ጠ​ልና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕት ማሳ​ረ​ግን ከፈ​ጸመ በኋላ ሕዝ​ቡን በሰ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም መረቀ።</verse>
				<verse number="19">ለሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ወገን ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ለወ​ን​ዱም፥ ለሴ​ቱም ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አን​ዳ​ንድ እን​ጀራ፥ አን​ዳ​ን​ድም የሥጋ ቍራጭ፥ አን​ዳ​ን​ድም ጽዋዕ ወይን አከ​ፋ​ፈለ። ሕዝ​ቡም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ቤቱ ሄደ።</verse>
				<verse number="20">ዳዊ​ትም ቤተ ሰቡን ሊመ​ርቅ ተመ​ለሰ። የሳ​ኦል ልጅ ሜል​ኮ​ልም ዳዊ​ትን ለመ​ቀ​በል ወጣ​ችና ሰላ​ምታ ሰጠ​ችው፥ “ከሚ​ዘ​ፍ​ኑት አንዱ እን​ደ​ሚ​ገ​ለጥ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ሚስ​ቶች ፊት በመ​ገ​ለጡ ምንኛ የተ​ከ​በረ ነው!” አለች።</verse>
				<verse number="21">ዳዊ​ትም ሜል​ኮ​ልን፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዘም​ሬ​አ​ለሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ከአ​ባ​ት​ሽና ከቤቱ ሁሉ ይልቅ የመ​ረ​ጠኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ይሁን፤ ስለ​ዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጫ​ወ​ታ​ለሁ፤ እዘ​ም​ራ​ለ​ሁም፤</verse>
				<verse number="22">አሁ​ንም እገ​ለ​ጣ​ለሁ፤ በዐ​ይ​ንሽ ፊትና እን​ዴት ከበ​ርህ ባል​ሽ​ባ​ቸው ሴቶች ልጆች ፊት የተ​ና​ቅሁ እሆ​ና​ለሁ” አላት።</verse>
				<verse number="23">የሳ​ኦ​ልም ልጅ ሜል​ኮል እስከ ሞተ​ች​በት ቀን ድረስ ልጅ አል​ወ​ለ​ደ​ችም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ንጉሡ በቤቱ በተ​ቀ​መጠ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዙ​ሪ​ያው ያሉ ጠላ​ቶ​ቹን ሁሉ ባወ​ረ​ሰው ጊዜ፥</verse>
				<verse number="2">ንጉሡ ነቢዩ ናታ​ንን፥ “እኔ ከዝ​ግባ በተ​ሠራ ቤት ተቀ​ም​ጬ​አ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ግን በድ​ን​ኳን ውስጥ ተቀ​ም​ጣ​ለች” አለው።</verse>
				<verse number="3">ናታ​ንም ንጉ​ሡን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና፥ ሂድና በል​ብህ ያሰ​ብ​ኸ​ውን ሁሉ አድ​ርግ” አለው።</verse>
				<verse number="4">በዚ​ያም ሌሊት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ናታን መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፦</verse>
				<verse number="5">“ሂድ ለባ​ሪ​ያዬ ለዳ​ዊት ንገ​ረው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አንተ የም​ኖ​ር​በ​ትን ቤት አት​ሠ​ራ​ል​ኝም።</verse>
				<verse number="6">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ሁ​በት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በድ​ን​ኳ​ንና በማ​ደ​ሪያ እሄ​ድና እመ​ላ​ለስ ነበር እንጂ በቤት አል​ተ​ቀ​መ​ጥ​ሁ​ምና፥</verse>
				<verse number="7">ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ጋር ባለ​ፍ​ሁ​በት ስፍራ ሁሉ፦ ስለ​ምን ቤትን ከዝ​ግባ እን​ጨት አል​ሠ​ራ​ች​ሁ​ል​ኝም? ብዬ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን ይጠ​ብቅ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ላዘ​ዝ​ሁት ለአ​ንዱ በውኑ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁን?</verse>
				<verse number="8">አሁ​ንም ዳዊ​ትን ባሪ​ያ​ዬን እን​ዲህ በለው፦ ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ ወሰ​ድ​ሁህ፤</verse>
				<verse number="9">በሄ​ድ​ህ​በ​ትም ሁሉ ከአ​ንተ ጋር ነበ​ርሁ፤ ጠላ​ቶ​ች​ህ​ንም ሁሉ ከፊ​ትህ አጠ​ፋሁ፤ በም​ድ​ርም ላይ እን​ዳሉ እንደ ታላ​ላ​ቆቹ ስም ስም​ህን ታላቅ አደ​ረ​ግሁ።</verse>
				<verse number="10">ለሕ​ዝ​ቤም ለእ​ስ​ራ​ኤል ስፍራ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እተ​ክ​ላ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ ብቻ​ቸ​ውን ይቀ​መ​ጣሉ፤ ከዚ​ያም በኋላ የሚ​ጠ​ራ​ጠ​ሩት የለም፤ እንደ ቀድ​ሞው ዘመን የኀ​ጢ​አት ልጅ መከራ አያ​ጸ​ና​ባ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="11">በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈራ​ጆ​ችን በሾ​ምሁ ጊዜ ከጠ​ላ​ቶ​ችህ ሁሉ አሳ​ር​ፍ​ሃ​ለሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ፦ ቤት እን​ደ​ም​ት​ሠ​ራ​ለት ይነ​ግ​ር​ሃል፤ እሠ​ራ​ለ​ታ​ለሁ ብለ​ሃ​ልና።</verse>
				<verse number="12">ዕድ​ሜ​ህም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፤ ከአ​ባ​ቶ​ች​ህም ጋር ባን​ቀ​ላ​ፋህ ጊዜ፥ ከወ​ገ​ብህ የሚ​ወ​ጣ​ውን ዘር​ህን ከአ​ንተ በኋላ አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ መን​ግ​ሥ​ቱ​ንም አዘ​ጋ​ጃ​ለሁ ።</verse>
				<verse number="13">እርሱ ለስሜ ቤት ይሠ​ራል፤ ዙፋ​ኑን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጸ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">እኔም አባት እሆ​ነ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ልጅ ይሆ​ነ​ኛል፤ ክፉ ነገ​ርም ቢያ​ደ​ርግ፥ በሰ​ዎች በት​ርና በሰው ልጆች አለ​ንጋ እገ​ሥ​ጸ​ዋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="15">ከፊ​ቴም ከጣ​ል​ሁት ከሳ​ኦል ቤት እን​ዳ​ራ​ቅሁ ምሕ​ረ​ቴን ከእ​ርሱ አላ​ር​ቅም።</verse>
				<verse number="16">ቤቱ የታ​መነ ይሆ​ናል፤ መን​ግ​ሥ​ቱም በፊቴ ለዘ​ለ​ዓ​ለም፥ ዙፋ​ኑም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጸ​ናል።”</verse>
				<verse number="17">እን​ደ​ዚህ ቃል ሁሉ፥ እን​ደ​ዚ​ህም ራእይ ሁሉ ናታን ለዳ​ዊት እን​ዲሁ ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="18">ንጉሡ ዳዊ​ትም ገባ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ተቀ​ምጦ እን​ዲህ አለ፥ “ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ይህን ያህል የወ​ደ​ድ​ኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="19">ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ እኔ በፊ​ትህ እጅግ ታናሽ ስሆን ስለ ባሪ​ያህ ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተና​ገ​ርህ፤ ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ይህ የሰው ሕግ ነው።</verse>
				<verse number="20">ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ አንተ ባሪ​ያ​ህን ታው​ቃ​ለ​ህና ዳዊ​ትስ ይና​ገ​ርህ ዘንድ የሚ​ጨ​ም​ረው ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="21">ለባ​ሪ​ያ​ህም ታስ​ታ​ው​ቀው ዘንድ ስለ ቃልህ ምክ​ን​ያ​ትና እንደ ልብህ አሳብ ይህን ታላቅ ነገር ሁሉ አደ​ረ​ግህ።</verse>
				<verse number="22">ስለ​ዚ​ህም አቤቱ አም​ላኬ ሆይ፥ እን​ዳ​ንተ ያለ የለ​ምና፥ በጆ​ሮ​አ​ች​ንም እንደ ሰማን ሁሉ ከአ​ንተ በቀር አም​ላክ የለ​ምና አንተ ታላቅ ነህ።</verse>
				<verse number="23">ለእ​ርሱ ለራሱ እን​ዲ​ሆን ሕዝ​ብን ይቤዥ ዘንድ ለእ​ርሱ ለራ​ሱም ታላቅ ስምን ያደ​ርግ ዘንድ አሕ​ዛ​ብ​ንና ሰፈ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን በመ​በ​ተን ከግ​ብፅ በተ​ቤ​ዠ​ኸው ሕዝ​ብህ ፊት ታም​ራ​ት​ንና ድን​ቅን ያደ​ርግ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ መራው እንደ ሕዝ​ብህ እንደ እስ​ራ​ኤል ያለ በም​ድር ላይ ምን ሕዝብ አለ?</verse>
				<verse number="24">ሕዝ​ብ​ህ​ንም እስ​ራ​ኤ​ልን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕዝብ አድ​ር​ገህ አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ኸ​ዋል፤ አን​ተም፥ አቤቱ፥ አም​ላክ ሆነ​ሃ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="25">አቤቱ ሁሉን የም​ት​ገዛ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ አሁ​ንም ለባ​ሪ​ያ​ህና ለቤቱ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጽ​ናው፤ አሁ​ንም እንደ ተና​ገ​ርህ አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="26">ስምህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታላቅ ይሁን።</verse>
				<verse number="27">አቤቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሰ​ራ​ዊት ጌታ ሆይ፥ የባ​ሪ​ያ​ህን ጆሮ ከፈ​ትህ። አንተ፦ እኔ ቤት እሠ​ራ​ል​ሃ​ለሁ አልህ፤ ስለ​ዚ​ህም ባሪ​ያህ ይህ​ችን ጸሎት ወደ አንተ ይጸ​ልይ ዘንድ በልቡ አሰበ።</verse>
				<verse number="28">ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ አሁ​ንም አንተ አም​ላክ ነህ፤ ቃል​ህም እው​ነት ነው፤ ይህ​ንም መል​ካም ነገር ለባ​ሪ​ያህ ተና​ግ​ረ​ሃል።</verse>
				<verse number="29">ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ አንተ ተና​ግ​ረ​ሃ​ልና አሁን እን​ግ​ዲህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በፊ​ትህ ይሆን ዘንድ የባ​ሪ​ያ​ህን ቤት እባ​ክህ ባርክ፤ በበ​ረ​ከ​ት​ህም የባ​ሪ​ያህ ቤት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይባ​ረክ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ፤ አዋ​ረ​ዳ​ቸ​ውም፤ ዳዊ​ትም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ምር​ኮን ወሰደ።</verse>
				<verse number="2">ዳዊ​ትም ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን መታ፤ በም​ድ​ርም ጥሎ በገ​መድ ሰፈ​ራ​ቸው፤ በሁ​ለ​ትም ገመድ ለሞት፥ በአ​ን​ድም ገመድ ለሕ​ይ​ወት ሰፈ​ራ​ቸው፤ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት።</verse>
				<verse number="3">ዳዊ​ትም ደግሞ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ግዛት ለማ​ስ​ፋ​ፋት በሄደ ጊዜ የሱ​ባን ንጉሥ የረ​አ​ብን ልጅ አድ​ር​አ​ዛ​ርን መታ።</verse>
				<verse number="4">ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ ሺህ ሰረ​ገ​ላ​ዎ​ችን፥ ሰባት ሺህ ፈረ​ሰ​ኞ​ችን፥ ሃያ ሺህም እግ​ረ​ኞ​ችን ያዘ፤ ዳዊ​ትም የሰ​ረ​ገ​ለ​ኛ​ውን ፈረስ ሁሉ ቋንጃ ቈረጠ፤ ለራ​ሱም መቶ ሰረ​ገ​ላ​ዎ​ችን ብቻ አስ​ቀረ።</verse>
				<verse number="5">ከደ​ማ​ስ​ቆም ሶር​ያ​ው​ያን የሱ​ባን ንጉሥ አድ​ር​አ​ዛ​ርን ሊረዱ መጡ፤ ዳዊ​ትም ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን ገደለ።</verse>
				<verse number="6">ዳዊ​ትም በደ​ማ​ስቆ ሶርያ ጭፍ​ሮች አኖረ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሄ​ደ​በት ሁሉ ጠበ​ቀው።</verse>
				<verse number="7">ዳዊ​ትም ለሱ​ባን ንጉሥ ለአ​ድ​ር​አ​ዛር አገ​ል​ጋ​ዮች የነ​በ​ሩ​ትን ጋሻ አግ​ሬ​ዎች ወሰደ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አመ​ጣ​ቸው። እነ​ዚ​ህ​ንም የግ​ብፅ ንጉሥ ሱስ​ቀም በሰ​ሎ​ሞን ልጅ በሮ​ብ​ዓም ዘመን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በወጣ ጊዜ ወሰ​ዳ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">ንጉ​ሡም ዳዊት ከሶ​ቤ​ቅና ከተ​መ​ረ​ጡት ከአ​ድ​ር​አ​ዛር ከተ​ሞች እጅግ ብዙ ናስን ወሰደ። በእ​ር​ሱም ሰሎ​ሞን የብ​ረት ባሕ​ርና ምሰ​ሶ​ዎ​ችን፥ ሰኖ​ች​ንና ሌሎች ዕቃ​ዎ​ችን ሠራ።</verse>
				<verse number="9">የሓ​ማ​ትም ንጉሥ ታይ ዳዊት የአ​ድ​ር​አ​ዛ​ርን ጭፍራ ሁሉ እንደ መታ ሰማ።</verse>
				<verse number="10">ታይም የአ​ድ​ር​አ​ዛር ጠላት ነበ​ርና ዳዊት አድ​ር​አ​ዛ​ርን ስለ ተዋ​ጋ​ውና ስለ ገደ​ለው፥ ታይ ልጁን ኢያ​ዱ​ራን ደኅ​ን​ነ​ቱን ይጠ​ይቅ ዘንድ፥ ይመ​ር​ቀ​ውም ዘንድ ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ እር​ሱም የብ​ርና የወ​ርቅ የና​ስም ዕቃ ይዞ መጣ፤</verse>
				<verse number="11">እር​ሱ​ንም ንጉሥ ዳዊት ከሀ​ገ​ሮች ሁሉ አም​ጥቶ ከቀ​ደ​ሰው ከወ​ር​ቁና ከብሩ ጋር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀደሰ፤</verse>
				<verse number="12">ይኸ​ውም ከሶ​ርያ ከሞ​ዓ​ብና ከአ​ሞን ልጆች፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥ ከአ​ማ​ሌ​ቅም፥ ከረ​አ​ብም ልጅ ከሱባ ንጉሥ ከአ​ድ​ር​አ​ዛር ምርኮ ያመ​ጣው ነው።</verse>
				<verse number="13">ዳዊ​ትም በተ​መ​ለሰ ጊዜ ከኤ​ዶ​ም​ያስ ዐሥራ ስም​ንት ሺህ ሰዎች በጨው ሸለቆ ውስጥ በመ​ም​ታቱ ስሙ ተጠራ።</verse>
				<verse number="14">መላ​ዋን ኤዶ​ም​ያ​ስን ይጠ​ብቁ ዘንድ በኤ​ዶ​ም​ያስ ሁሉ ጭፍ​ሮ​ችን አኖረ፤ ኤዶ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ለን​ጉሥ ዳዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሚ​ሄ​ድ​በት ቦታ ሁሉ ጠበ​ቀው።</verse>
				<verse number="15">ዳዊ​ትም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤ ዳዊ​ትም ለሕ​ዝቡ ሁሉ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">የሦ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አ​ብም የሠ​ራ​ዊት አለቃ ነበረ፤ የአ​ሒ​ሎ​ድም ልጅ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ታሪክ ጸሓፊ ነበረ፤</verse>
				<verse number="17">የአ​ኪ​ጦ​ብም ልጅ ሳዶቅ፥ የአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክም ልጅ አብ​ያ​ታር ካህ​ናት ነበሩ። አሳም ጸሓፊ ነበረ፤</verse>
				<verse number="18">የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያ​ስም አማ​ካሪ ነበረ፤ ከሊ​ታ​ው​ያ​ንና፥ ፊሊ​ታ​ው​ያን፥ የዳ​ዊ​ትም ልጆች የፍ​ርድ ቤት አለ​ቆች ነበሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">ዳዊ​ትም፥ “ስለ ዮና​ታን ቸር​ነት አደ​ር​ግ​ለት ዘንድ ከሳ​ኦል ቤት የቀረ አንድ ሰው አለን?” አለ።</verse>
				<verse number="2">ከሳ​ኦ​ልም ቤት አንድ ብላ​ቴና ነበረ፤ ስሙም ሲባ ነበረ፤ ወደ ዳዊ​ትም ጠሩት፤ ንጉ​ሡም፥ “አንተ ሲባ ነህን?” አለው። እር​ሱም፥ “እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ነኝ” አለ።</verse>
				<verse number="3">ንጉ​ሡም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቸር​ነት አደ​ር​ግ​ለት ዘንድ ከሳ​ኦል ቤት የቀረ ሰው አለን?” አለ። ሲባም ንጉ​ሡን፥ “እግ​ሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ የዮ​ና​ታን ልጅ አለ” አለው።</verse>
				<verse number="4">ንጉ​ሡም፥ “ወዴት ነው?” አለው፤ ሲባም ለን​ጉሡ፥ “እነሆ እርሱ በሎ​ዶ​ባር በአ​ብ​ያል ልጅ በማ​ኪር ቤት አለ” አለው።</verse>
				<verse number="5">ንጉ​ሡም ዳዊት ልኮ ከሎ​ዶ​ባር ከአ​ብ​ያል ልጅ ከማ​ኪር ቤት አስ​መ​ጣው።</verse>
				<verse number="6">የሳ​ኦ​ልም ልጅ የዮ​ና​ታን ልጅ ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ወደ ዳዊት መጣ፤ በግ​ን​ባ​ሩም ወድቆ ሰገ​ደ​ለት፤ ንጉሥ ዳዊ​ትም፥ “ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ሆይ፥” አለ፤ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ አገ​ል​ጋ​ይህ” አለ።</verse>
				<verse number="7">ዳዊ​ትም፥ “ስለ አባ​ትህ ስለ ዮና​ታን ቸር​ነት ፈጽሜ አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለ​ሁና አት​ፍራ፤ የአ​ባ​ት​ህን አባት የሳ​ኦ​ልን መሬት ሁሉ እመ​ል​ስ​ል​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም ሁል ጊዜ ከገ​በ​ታዬ እን​ጀ​ራን ትበ​ላ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="8">እር​ሱም፥ “የሞተ ውሻ ወደ​ም​መ​ስል ወደ እኔ ትመ​ለ​ከት ዘንድ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ምን​ድን ነኝ?” ብሎ ሰገደ።</verse>
				<verse number="9">ንጉ​ሡም የሳ​ኦ​ልን አገ​ል​ጋይ ሲባን ጠርቶ፥ “ለሳ​ኦ​ልና ለቤቱ ሁሉ የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ለጌ​ታህ ልጅ ሰጥ​ቻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">አን​ተና ልጆ​ችህ፥ ሎሌ​ዎ​ች​ህም ምድ​ሩን እረ​ሱ​ለት፤ ለጌ​ታ​ህም ልጅ እን​ጀራ ይሆ​ነው ዘንድ ፍሬ​ውን አግቡ፤ እና​ን​ተም ትመ​ግ​ቡ​ታ​ላ​ችሁ፤ የጌ​ታህ ልጅ ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ግን ሁል​ጊዜ ከገ​በ​ታዬ ይበ​ላል” አለው። ለሲ​ባም ዐሥራ አም​ስት ልጆ​ችና ሃያ አገ​ል​ጋ​ዮች ነበ​ሩት።</verse>
				<verse number="11">ሲባም ንጉ​ሡን፥ “ጌታዬ ንጉሡ አገ​ል​ጋ​ዩን እን​ዳ​ዘዘ እን​ዲሁ አገ​ል​ጋ​ይህ ያደ​ር​ጋል” አለው። ሜም​ፌ​ቡ​ስ​ቴም ከን​ጉሡ ልጆች እንደ አንዱ ከዳ​ዊት ገበታ ይበላ ነበር።</verse>
				<verse number="12">ለሜ​ም​ፌ​ቡ​ስ​ቴም ሚካ የተ​ባለ ታናሽ ልጅ ነበ​ረው፤ በሲ​ባም ቤት ያሉ ሁሉ ለሜ​ም​ፌ​ቡ​ስቴ ያገ​ለ​ግሉ ነበር።</verse>
				<verse number="13">ሜም​ፌ​ቡ​ስ​ቴም ከን​ጉሥ ገበታ ሁል​ጊዜ እየ​በላ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ኖረ፤ ሁለት እግ​ሮ​ቹም ሽባ ነበሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">ከዚህ በኋላ የአ​ሞን ልጆች ንጉሥ ሞተ፤ ልጁም ሐኖን በፋ​ን​ታው ነገሠ።</verse>
				<verse number="2">ዳዊ​ትም፥ “አባቱ ቸር​ነ​ትን እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ልኝ እኔ ለና​ዖስ ልጅ ለሐ​ኖን ቸር​ነት አደ​ር​ጋ​ለሁ” አለ። ዳዊ​ትም ስለ አባቱ ያጽ​ና​ኑት ዘንድ ብላ​ቴ​ኖ​ቹን ላከ፤ የዳ​ዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖች ወደ አሞን ልጆች ሀገር መጡ።</verse>
				<verse number="3">የአ​ሞ​ንም ልጆች አለ​ቆች ጌታ​ቸ​ውን ሐኖ​ንን፥ “ዳዊት አባ​ት​ህን በፊ​ትህ ለማ​ክ​በር አጽ​ና​ኞ​ችን ወደ አንተ የላከ ይመ​ስ​ል​ሃ​ልን? ዳዊ​ትስ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ለመ​መ​ር​መ​ርና ለመ​ሰ​ለል፥ ለመ​ፈ​ተ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን የላከ አይ​ደ​ለ​ምን?” አሉት።</verse>
				<verse number="4">ሐኖ​ንም የዳ​ዊ​ትን አገ​ል​ጋ​ዮች ወስዶ የጢ​ማ​ቸ​ውን ገሚስ ላጨ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም እስከ ወገ​ባ​ቸው ድረስ ከሁ​ለት ቀድዶ ሰደ​ዳ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">ለዳ​ዊ​ትም ስለ ሰዎቹ ነገ​ሩት፤ ሰዎቹ እጅግ አፍ​ረው ነበ​ሩና ተቀ​ባ​ዮ​ችን ላከ። ንጉ​ሡም፥ “ጢማ​ችሁ እስ​ኪ​ያ​ድግ ድረስ በኢ​ያ​ሪኮ ተቀ​መጡ፤ ከዚ​ያም በኋላ ተመ​ለሱ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">የአ​ሞ​ንም ልጆች የዳ​ዊት ወገ​ኖች እንደ አፈሩ ባዩ ጊዜ፥ የአ​ሞን ልጆች ልከው ከቤ​ት​ሮ​ዖብ ሶር​ያ​ው​ያ​ንና ከሱባ ሶር​ያ​ው​ያን ሃያ ሺህ እግ​ረ​ኞ​ችን፥ ከአ​ማ​ሌቅ ንጉ​ሥም አንድ ሺህ ሰዎ​ችን፥ ከአ​ስ​ጦ​ብም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን ቀጠሩ።</verse>
				<verse number="7">ዳዊ​ትም በሰማ ጊዜ ኢዮ​አ​ብ​ንና የኀ​ያ​ላ​ኑን ሰራ​ዊት ሁሉ ላከ።</verse>
				<verse number="8">የአ​ሞ​ንም ልጆች ወጥ​ተው በበሩ መግ​ቢያ ፊት ለፊት ይዋጉ ጀመሩ፤ የሱ​ባና የሮ​ዖብ ሶር​ያ​ው​ያን፥ የአ​ስ​ጦ​ብና የአ​ማ​ሌ​ቅም ሰዎች ለብ​ቻ​ቸው በሰፊ ሜዳ ላይ ነበሩ።</verse>
				<verse number="9">ኢዮ​አ​ብም በፊ​ትና በኋላ ሰልፍ እንደ ከበ​በው ባየ ጊዜ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጐል​ማ​ሶ​ችን ሁሉ መረጠ፤ በሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንም ፊት አሰ​ለ​ፋ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">የቀ​ረ​ው​ንም ሕዝብ ከወ​ን​ድሙ ከአ​ቢሳ ጋር ላከ፤ በአ​ሞን ልጆች ፊትም አሰ​ለ​ፋ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">እር​ሱም አለው፥ “ሶር​ያ​ው​ያን ቢበ​ረ​ቱ​ብኝ ትረ​ዳ​ኛ​ለህ፤ የአ​ሞን ልጆ​ችም ቢበ​ረ​ቱ​ብህ እኔ መጥቼ እረ​ዳ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">በርታ፤ ስለ ሕዝ​ባ​ች​ንና ስለ አም​ላ​ካ​ች​ንም ከተ​ሞች እን​ጽና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዐ​ይኑ ፊት ደስ ያሰ​ኘ​ውን መል​ካ​ሙን ያድ​ርግ።”</verse>
				<verse number="13">ኢዮ​አ​ብና ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ረው ሕዝብ ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ጋር ሊዋጉ ቀረቡ፤ እነ​ር​ሱም ከፊቱ ሸሹ።</verse>
				<verse number="14">የአ​ሞን ልጆ​ችም ሶር​ያ​ው​ያን እንደ ሸሹ ባዩ ጊዜ እነ​ርሱ ደግሞ ከአ​ቢሳ ፊት ሸሹ፤ ወደ ከተ​ማ​ዪ​ቱም ገቡ፤ ኢዮ​አ​ብም ከአ​ሞን ልጆች ዘንድ ተመ​ልሶ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ገባ።</verse>
				<verse number="15">ሶር​ያ​ው​ያ​ንም በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት እንደ ተሸ​ነፉ ባዩ ጊዜ በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="16">አድ​ር​አ​ዛ​ርም ልኮ በካ​ላ​ማቅ ወንዝ ማዶ የነ​በ​ሩ​ትን ሶር​ያ​ው​ያን ሰበ​ሰ​ባ​ቸው፤ ወደ ኤላ​ምም መጡ፤ የአ​ድ​ር​አ​ዛ​ርም ሠራ​ዊት አለቃ ሶቤቅ በፊ​ታ​ቸው ነበረ።</verse>
				<verse number="17">ለዳ​ዊ​ትም ነገ​ሩት፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ግሮ ወደ ኤላም መጣ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም በዳ​ዊት ፊት ተሰ​ል​ፈው ከእ​ርሱ ጋር ተዋጉ።</verse>
				<verse number="18">ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊ​ትም ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ሰባት መቶ ሰረ​ገ​ለ​ኞ​ችን፥ አርባ ሺህም ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ገደለ፤ የሠ​ራ​ዊ​ቱ​ንም አለቃ ሶቤ​ቅን መታ፤ እር​ሱም በዚያ ሞተ።</verse>
				<verse number="19">ለአ​ድ​ር​አ​ዛ​ርም የሚ​ገ​ብሩ ነገ​ሥ​ታት ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት እንደ ተሸ​ነፉ ባዩ ጊዜ ለእ​ስ​ራ​ኤል ተገዙ፤ ገበ​ሩ​ላ​ቸ​ውም። ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ከዚያ ወዲያ የአ​ሞ​ንን ልጆች ይረዱ ዘንድ ፈሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዓ​መቱ መጨ​ረሻ ነገ​ሥ​ታት ወደ ሰልፍ በሚ​ወ​ጡ​በት ጊዜ፥ ዳዊት ኢዮ​አ​ብን ከእ​ር​ሱም ጋር አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሁሉ ሰደደ። የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች አጠፉ፤ አራ​ቦ​ት​ንም ከበቡ፤ ዳዊት ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቀርቶ ነበር።</verse>
				<verse number="2">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ወደ ማታ ጊዜ ዳዊት ከም​ን​ጣፉ ተነሣ፤ በን​ጉ​ሥም ቤት በሰ​ገ​ነት ላይ ተመ​ላ​ለሰ፤ በሰ​ገ​ነ​ቱም ሳለ አን​ዲት ሴት ስት​ታ​ጠብ አየ፤ ሴቲ​ቱም እጅግ የተ​ዋ​በች መልከ መል​ካም ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="3">ዳዊ​ትም ልኮ ስለ ሴቲቱ ጠየቀ፤ አንድ ሰውም፥ “የኤ​ል​ያብ ልጅ የኬ​ጤ​ያ​ዊው የኦ​ርዮ ሚስት ቤር​ሳ​ቤህ አይ​ደ​ለ​ች​ምን?” አለው።</verse>
				<verse number="4">ዳዊ​ትም መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ልኮ አስ​መ​ጣት፤ ወደ እር​ሱም ገባች፤ ከር​ኵ​ሰ​ቷም ነጽታ ነበ​ርና ከእ​ር​ስዋ ጋር ተኛ፤ ወደ ቤቷም ተመ​ለ​ሰች።</verse>
				<verse number="5">ሴቲ​ቱም አረ​ገ​ዘች፤ ወደ ዳዊ​ትም “አር​ግ​ዤ​አ​ለሁ” ብላ ላከ​ች​በት።</verse>
				<verse number="6">ዳዊ​ትም ወደ ኢዮ​አብ፦ ኬጤ​ያ​ዊ​ውን ኦር​ዮን ወዲህ ላከው ብሎ ላከ። ኢዮ​አ​ብም ኦር​ዮን ወደ ዳዊት ላከው።</verse>
				<verse number="7">ኦር​ዮም ደርሶ ወደ እርሱ በገባ ጊዜ ዳዊት የኢ​ዮ​አ​ብ​ንና የሕ​ዝ​ቡን ደኅ​ን​ነት፥ ሰል​ፉም እን​ዴት እንደ ሆነ ጠየ​ቀው።</verse>
				<verse number="8">ዳዊ​ትም ኦር​ዮን፥ “ወደ ቤትህ ሂድ፤ እግ​ር​ህ​ንም ታጠብ” አለው። ኦር​ዮም ከን​ጉሡ ቤት ሲወጣ አንድ የን​ጉሥ መል​እ​ክ​ተኛ ተከ​ተ​ለው።</verse>
				<verse number="9">ኦርዮ ግን ከጌ​ታው አገ​ል​ጋ​ዮች ሁሉ ጋር በን​ጉሥ ቤት ደጅ ተኛ፤ ወደ ቤቱም አል​ወ​ረ​ደም።</verse>
				<verse number="10">“ኦርዮ ወደ ቤቱ አል​ሄ​ደም” ብለው ለዳ​ዊት ነገ​ሩት፤ ዳዊ​ትም ኦር​ዮን፥ “አንተ ከመ​ን​ገድ የመ​ጣህ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? ስለ​ምን ወደ ቤትህ አል​ወ​ረ​ድ​ህም?” አለው።</verse>
				<verse number="11">ኦር​ዮም ለዳ​ዊት፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦ​ትና እስ​ራ​ኤል፥ ይሁ​ዳም በድ​ን​ኳን ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ጌታዬ ኢዮ​አ​ብና የጌ​ታ​ዬም አገ​ል​ጋ​ዮች በሰፊ ሜዳ ሰፍ​ረ​ዋል፤ እኔ ልበ​ላና ልጠጣ ወይስ ከሚ​ስቴ ጋር ልተኛ ወደ ቤቴ እሄ​ዳ​ለ​ሁን? በሕ​ይ​ወ​ት​ህና በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ! ይህን ነገር አላ​ደ​ር​ገ​ውም” አለው።</verse>
				<verse number="12">ዳዊ​ትም ኦር​ዮን፥ “ዛሬ ደግሞ በዚህ ተቀ​መጥ፤ ነገም አሰ​ና​ብ​ት​ሃ​ለሁ” አለው። ኦር​ዮም በዚያ ቀንና በነ​ጋው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="13">ዳዊ​ትም ጠራው፤ በፊ​ቱም በላና ጠጣ፤ አሰ​ከ​ረ​ውም፤ ነገር ግን በመሸ ጊዜ ወጥቶ ከጌ​ታው አገ​ል​ጋ​ዮች ጋር በም​ን​ጣፉ ላይ ተኛ፤ ወደ ቤቱም አል​ወ​ረ​ደም።</verse>
				<verse number="14">በነ​ጋም ጊዜ ዳዊት ለኢ​ዮ​አብ ደብ​ዳቤ ጻፈ፤ በኦ​ር​ዮም እጅ ላከው።</verse>
				<verse number="15">በደ​ብ​ዳ​ቤ​ውም፥ “ኦር​ዮን ጽኑ ሰልፍ ባለ​በት በፊ​ተ​ኛው ስፍራ አቁ​ሙት፤ ተወ​ግ​ቶም ይሞት ዘንድ ከኋላ ሽሹ” ብሎ ጻፈ።</verse>
				<verse number="16">ኢዮ​አ​ብም ከተ​ማ​ዪ​ቱን በከ​በበ ጊዜ ጀግ​ኖች እን​ዳ​ሉ​በት በሚ​ያ​ው​ቀው ስፍራ ኦር​ዮን አቆ​መው።</verse>
				<verse number="17">የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ሰዎች ወጥ​ተው ከኢ​ዮ​አብ ጋር ተዋጉ፤ ከዳ​ዊ​ትም አገ​ል​ጋ​ዮች ከሕ​ዝቡ አን​ዳ​ንዱ ወደቁ፤ ኬጤ​ያ​ዊው ኦር​ዮም ደግሞ ሞተ።</verse>
				<verse number="18">ኢዮ​አ​ብም የጦ​ር​ነ​ቱን ዜና ሁሉ ለዳ​ዊት ይነ​ግ​ሩት ዘንድ ላከ፤</verse>
				<verse number="19">ለመ​ል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውም እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “የጦ​ር​ነ​ቱን ነገር ሁሉ ለን​ጉሡ ነግ​ረህ በፈ​ጸ​ምህ ጊዜ፤</verse>
				<verse number="20">ንጉሡ ቢቈጣ፥ እን​ዲ​ህም ቢል፦ ልትዋጉ ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ለምን ቀረ​ባ​ችሁ? ከቅ​ጥሩ በላይ ፍላጻ እን​ዲ​ወ​ረ​ወር አታ​ው​ቁ​ምን?</verse>
				<verse number="21">የኔር ልጅ የይ​ሩ​በ​ዓ​ልን ልጅ አቤ​ሜ​ሌ​ክን ማን ገደ​ለው? አን​ዲት ሴት ከቅ​ጥር ላይ የወ​ፍጮ መጅ ጥላ​በት የሞተ አይ​ደ​ለ​ምን? ስለ​ምን ወደ ቅጥሩ እን​ደ​ዚህ ቀረ​ባ​ችሁ? አን​ተም፦ ባሪ​ያህ ኬጤ​ያ​ዊው ኦርዮ ደግሞ ሞተ በለው።”</verse>
				<verse number="22">የኢ​ዮ​አ​ብም መል​እ​ክ​ተኛ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ንጉሡ ሄደ። ደር​ሶም ኢዮ​አብ የነ​ገ​ረ​ውን የጦ​ር​ነ​ቱን ዜና ሁሉ ለዳ​ዊት ነገ​ረው። ዳዊ​ትም በኢ​ዮ​አብ ላይ ተቈጣ። ያንም መል​እ​ክ​ተኛ፥ “ትዋጉ ዘንድ ወደ ከተ​ማዋ ቅጥር ለምን ቀረ​ባ​ችሁ? በቅ​ጥ​ሩም እን​ደ​ም​ት​ቈ​ስሉ አታ​ው​ቁ​ምን? የይ​ሩ​በ​ዓል ልጅ አቤ​ሜ​ሌ​ክን ማን ገደ​ለው? አን​ዲት ሴት ከቅ​ጥር ላይ የወ​ፍጮ መጅ ጥላ​በት በቴ​ቤስ የሞተ አይ​ደ​ለ​ምን? ስለ​ምን ወደ ቅጥሩ ቀረ​ባ​ችሁ?” አለው።</verse>
				<verse number="23">መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውም ዳዊ​ትን፥ “ሰዎቹ በረ​ቱ​ብን፤ ወደ ሜዳም ወጡ​ብን፤ እኛም እስከ በሩ መግ​ቢያ ድረስ አሳ​ደ​ድ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="24">ፍላ​ጻም የሚ​ወ​ረ​ውሩ በቅ​ጥሩ ላይ ሆነው በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ላይ ወረ​ወሩ፤ ከን​ጉ​ሡም ብላ​ቴ​ኖች አን​ዳ​ንድ ሞቱ፤ አገ​ል​ጋ​ይህ ኬጤ​ያ​ዊው ኦርዮ ደግሞ ሞተ” አለው።</verse>
				<verse number="25">ዳዊ​ትም መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውን፥ “ሰይፍ አንድ ጊዜ ይህን፥ አንድ ጊዜም ያን ይበ​ላ​ልና ይህ ነገር በዐ​ይ​ንህ አይ​ክፋ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱን የሚ​ወ​ጉ​ትን አበ​ርታ፤ አፍ​ር​ሳ​ትም ብለህ ለኢ​ዮ​አብ ንገ​ረው፤ አን​ተም አጽ​ናው” አለው።</verse>
				<verse number="26">የኦ​ር​ዮም ሚስት ባልዋ ኦርዮ እንደ ሞተ በሰ​ማች ጊዜ ለባ​ልዋ አለ​ቀ​ሰች።</verse>
				<verse number="27">የል​ቅ​ሶ​ዋም ወራት ሲፈ​ጸም ዳዊት ልኮ ወደ ቤቱ አስ​መ​ጣት፤ ሚስ​ትም ሆነ​ችው፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደ​ች​ለት፤ ነገር ግን ዳዊት ያደ​ረ​ገው ነገር ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ሆነ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነቢዩ ናታ​ንን ወደ ዳዊት ላከ፤ ወደ እር​ሱም መጥቶ አለው፥ “በአ​ንድ ከተማ አንዱ ባለ​ጠጋ፥ አን​ዱም ድሃ የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="2">ባለ​ጠ​ጋ​ውም እጅግ ብዙ የበ​ግና የላም መንጋ ነበ​ረው።</verse>
				<verse number="3">ለድ​ሃው ግን ከገ​ዛት አን​ዲት ታናሽ በግ በቀር አን​ዳች አል​ነ​በ​ረ​ውም፤ አሳ​ደ​ጋ​ትም፤ ተን​ከ​ባ​ከ​ባ​ትም፤ ከእ​ር​ሱና ከል​ጆቹ ጋር አደ​ገች፤ ከእ​ን​ጀ​ራ​ውም ትበላ፥ ከዋ​ን​ጫ​ውም ትጠጣ፥ በብ​ብ​ቱም ትተኛ ነበረ፤ እንደ ልጁም ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="4">ወደ ባለ​ጠ​ጋ​ውም እን​ግዳ በመጣ ጊዜ ከበ​ጉና ከላሙ ወስዶ ለዚያ ወደ እርሱ ለመ​ጣው እን​ግዳ ያዘ​ጋ​ጅ​ለት ዘንድ ሳሳ፤ የዚ​ያ​ንም የድ​ሃ​ውን ሰው በግ ወስዶ ለዚያ ለመ​ጣው ሰው አዘ​ጋጀ።</verse>
				<verse number="5">ዳዊ​ትም በዚያ ሰው ላይ ተቈጣ፤ ዳዊ​ትም ናታ​ንን፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ይህን ያደ​ረገ ሰው ሞት የሚ​ገ​ባው ነው።</verse>
				<verse number="6">ይህን አድ​ር​ጎ​አ​ልና፥ አላ​ዘ​ነ​ምና ስለ አን​ዲቱ በግ አራት አድ​ርጎ ይመ​ልስ” አለው።</verse>
				<verse number="7">ናታ​ንም ዳዊ​ትን አለው፥ “ይህን ያደ​ረገ ያ ሰው አንተ ነህ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ልት​ሆን ቀባ​ሁህ፤ ከሳ​ኦ​ልም እጅ አዳ​ን​ሁህ፤</verse>
				<verse number="8">የጌ​ታ​ህ​ንም ቤት ሰጠ​ሁህ፤ የጌ​ታ​ህ​ንም ሚስ​ቶች በብ​ብ​ትህ ጣል​ሁ​ልህ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንና የይ​ሁ​ዳን ቤት ሰጠ​ሁህ፤ ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበ​ለጠ እጨ​ም​ር​ልህ ነበር።</verse>
				<verse number="9">አሁ​ንስ በፊቱ ክፉ ትሠራ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ነገር ለምን አቃ​ለ​ልህ? ኬጤ​ያ​ዊ​ውን ኦር​ዮን በሰ​ይፍ መት​ተ​ሃል፤ ሚስ​ቱ​ንም ለአ​ንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስ​ደ​ሃል፤ እር​ሱ​ንም በአ​ሞን ልጆች ሰይፍ ገድ​ለ​ሃል።</verse>
				<verse number="10">ስለ​ዚ​ህም አቃ​ል​ለ​ኸ​ኛ​ልና፥ የኬ​ጤ​ያ​ዊ​ው​ንም የኦ​ር​ዮን ሚስት ለአ​ንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስ​ደ​ሃ​ልና ለዘ​ለ​ዓ​ለም ከቤ​ትህ ሰይፍ አይ​ር​ቅም።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ከቤ​ትህ ክፉ ነገ​ርን አስ​ነ​ሣ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ሚስ​ቶ​ች​ህ​ንም በዐ​ይ​ኖ​ችህ እያ​የህ እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ለዘ​መ​ድ​ህም እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በዚ​ችም ፀሐይ ፊት ከሚ​ስ​ቶ​ችህ ጋር ይተ​ኛል።</verse>
				<verse number="12">አንተ ይህን በስ​ውር አድ​ር​ገ​ኸ​ዋል፤ እኔ ግን ይህን በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊትና በፀ​ሐይ ፊት አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="13">ዳዊ​ትም ናታ​ንን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በድ​ያ​ለሁ” አለው። ናታ​ንም ዳዊ​ትን አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደግሞ ኀጢ​አ​ት​ህን አር​ቆ​ል​ሃል፤ አት​ሞ​ት​ምም።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን በዚህ ነገር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶች መነ​ሣ​ሣት ምክ​ን​ያት አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ስለ​ዚህ ደግሞ የተ​ወ​ለ​ደ​ልህ ልጅ ፈጽሞ ይሞ​ታል” አለው።</verse>
				<verse number="15">ናታ​ንም ወደ ቤቱ ተመ​ለሰ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የኦ​ርዮ ሚስት ለዳ​ዊት የወ​ለ​ደ​ች​ውን ሕፃን ቀሠ​ፈው፤ እጅ​ግም ታምሞ ነበር።</verse>
				<verse number="16">ዳዊ​ትም ስለ ሕፃኑ እግ​ዚ​አ​ሔ​ርን ለመነ፤ ዳዊ​ትም ጾመ፤ ገብ​ቶም በመ​ሬት ላይ ተኛ።</verse>
				<verse number="17">የቤ​ቱም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ተነ​ሥ​ተው ከም​ድር ያነ​ሡት ዘንድ በአ​ጠ​ገቡ ቆሙ፤ እርሱ ግን እንቢ አለ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር እን​ጀራ አል​በ​ላም።</verse>
				<verse number="18">በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሕፃኑ ሞተ። የዳ​ዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖች፥ “ሕፃኑ በሕ​ይ​ወት ሳለ ብን​ነ​ግ​ረው አል​ሰ​ማ​ንም፤ ይል​ቁ​ንስ ሕፃኑ እንደ ሞተ ብን​ነ​ግ​ረው እን​ዴት ይሆን? በራሱ ላይ ክፉ ያደ​ር​ጋል” ብለው ሕፃኑ እንደ ሞተ ይነ​ግ​ሩት ዘንድ ፈሩ።</verse>
				<verse number="19">ዳዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖቹ በሹ​ክ​ሹ​ክታ ሲነ​ጋ​ገሩ ባየ ጊዜ ዳዊት ሕፃኑ እንደ ሞተ ዐወቀ፤ ዳዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “ሕፃኑ ሞቶ​አል?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “ሞቶ​አል” አሉት።</verse>
				<verse number="20">ዳዊ​ትም ከም​ድር ተነ​ሥቶ ታጠበ፤ ተቀ​ባም፤ ልብ​ሱ​ንም ለወጠ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ገብቶ ሰገደ። ወደ ቤቱም መጣ፦ እን​ጀ​ራም አም​ጡ​ልኝ አለ፤ በፊ​ቱም እን​ጀራ አቀ​ረ​ቡ​ለት፤ በላም።</verse>
				<verse number="21">ብላ​ቴ​ኖ​ቹም፥ “ይህ ስለ ሕፃኑ ያደ​ረ​ግ​ኸው ነገር ምን​ድን ነው? እርሱ በሕ​ይ​ወት ሳለ ጾም​ህና አለ​ቀ​ስህ፤ እን​ቅ​ል​ፍም አጣህ፤ ሕፃኑ ከሞተ በኋላ ግን ተነ​ሥ​ተህ እን​ጀራ በላህ፤ ጠጣ​ህም” አሉት።</verse>
				<verse number="22">ዳዊ​ትም፥ “ሕፃኑ ሕያው ሳለ፤ ምና​ል​ባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይም​ረኝ፥ ሕፃ​ኑም በሕ​ይ​ወት ይኖር እንደ ሆነ ማን ያው​ቃል? ብዬ ጾምሁ፤ አለ​ቀ​ስ​ሁም።</verse>
				<verse number="23">አሁን ግን ሞቶ​አል፤ የም​ጾ​መው ስለ ምን​ድን ነው? በውኑ እን​ግ​ዲህ እመ​ል​ሰው ዘንድ ይቻ​ለ​ኛ​ልን? እኔ ወደ እርሱ እሄ​ዳ​ለሁ እንጂ እርሱ ወደ እኔ አይ​መ​ለ​ስም” አለ።</verse>
				<verse number="24">ዳዊ​ትም ሚስ​ቱን ቤር​ሳ​ቤ​ህን አጽ​ና​ናት፤ ወደ እር​ስ​ዋም ገባ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ተኛ፤ ፀነ​ሰ​ችም፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ሰሎ​ሞን ብሎ ጠራው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ​ደው።</verse>
				<verse number="25">ደግ​ሞም በነ​ቢዩ በና​ታን እጅ ልኮ ስሙን ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍቁረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="26">ኢዮ​አ​ብም የአ​ሞ​ንን ልጆች ከተማ ራባ​ትን ወጋ፤ የመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቸ​ው​ንም ከተማ ያዘ።</verse>
				<verse number="27">ኢዮ​አ​ብም ወደ ዳዊት እን​ዲህ ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፥ “ራባ​ትን ወግ​ቻ​ለሁ፤ የው​ኃ​ው​ንም ከተማ ይዤ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="28">አሁ​ንም ከተ​ማ​ዪ​ቱን እኔ ቀድሜ እን​ዳ​ል​ይዝ፥ በስ​ሜም እን​ዳ​ት​ጠራ፥ የቀ​ረ​ውን ሕዝብ ሰብ​ስብ፥ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ከብ​በህ ቀድ​መህ ያዛት።”</verse>
				<verse number="29">ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡን ሁሉ ሰብ​ስቦ ወደ ራባት ሄደ፤ ወግ​ቶም ያዛት።</verse>
				<verse number="30">የን​ጉ​ሣ​ቸ​ው​ንም የሜ​ል​ኮ​ምን ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ። ክብ​ደ​ቱም አንድ መክ​ሊት ወርቅ ያህል ነበር፤ ክቡር ዕን​ቍም ነበ​ረ​በት፤ ዳዊ​ትም በራሱ ላይ አደ​ረ​ገው። ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም እጅግ ብዙ ምርኮ አወጣ።</verse>
				<verse number="31">በው​ስ​ጥ​ዋም የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ አው​ጥቶ በመ​ጋ​ዝና በብ​ረት መቈ​ፈ​ሪያ በብ​ረት መጥ​ረ​ቢ​ያም ሥር አኖ​ራ​ቸው፤ በሸ​ክላ ጡብ እቶ​ንም አሳ​ለ​ፋ​ቸው። በአ​ሞን ልጆች ከተ​ሞች ሁሉ እን​ዲሁ አደ​ረገ። ዳዊ​ትም፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ ለዳ​ዊት ልጅ ለአ​ቤ​ሴ​ሎም አን​ዲት የተ​ዋ​በች እኅት ነበ​ረ​ችው፤ ስም​ዋም ትዕ​ማር ነበረ፤ የዳ​ዊ​ትም ልጅ አም​ኖን ወደ​ዳት።</verse>
				<verse number="2">አም​ኖ​ንም ከእ​ኅቱ ከት​ዕ​ማር የተ​ነሣ እስ​ከ​ሚ​ታ​መም ድረስ እጅግ ተከዘ፤ ድን​ግ​ልም ነበ​ረ​ችና አን​ዳች ነገር ያደ​ር​ግ​ባት ዘንድ በዐ​ይኑ ፊት ጭንቅ ሆኖ​በት ነበር።</verse>
				<verse number="3">ለአ​ም​ኖ​ንም የዳ​ዊት ወን​ድም የሳ​ምዓ ልጅ ኢዮ​ና​ዳብ የሚ​ባል ወዳጅ ነበ​ረው፤ ኢዮ​ና​ዳ​ብም እጅግ ብልህ ሰው ነበረ።</verse>
				<verse number="4">እር​ሱም፥ “የን​ጉሥ ልጅ ሆይ፥ ስለ​ምን በየ​ቀኑ እን​ዲህ ከሳህ? አት​ነ​ግ​ረ​ኝ​ምን?” አለው። አም​ኖ​ንም፥ “የወ​ን​ድ​ሜን የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምን እኅት ትዕ​ማ​ርን እወ​ድ​ዳ​ታ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="5">ኢዮ​ና​ዳ​ብም አለው፦“ ታም​ሜ​አ​ለሁ ብለህ በአ​ል​ጋህ ላይ ተኛ፤ አባ​ት​ህም ሊያ​ይህ ይመ​ጣል፦ እኅቴ ትዕ​ማር እን​ድ​ት​መ​ጣና እኔ የም​በ​ላ​ውን እን​ጀራ እን​ድ​ት​ሰ​ጠኝ፥ መብ​ሉ​ንም እኔ እያ​የሁ እን​ድ​ታ​በ​ስ​ል​ልኝ፥ ከእ​ጅ​ዋም እን​ድ​በ​ላው እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ በለው።”</verse>
				<verse number="6">እን​ዲ​ሁም አም​ኖን፥ ታም​ሜ​አ​ለሁ ብሎ ተኛ፤ ንጉ​ሡም ሊያ​የው መጣ፤ አም​ኖ​ንም ንጉ​ሡን፥ “እኅቴ ትዕ​ማር እን​ድ​ት​መ​ጣና እኔ እያ​የሁ ሁለት እን​ጎቻ እን​ድ​ታ​በ​ስ​ል​ልኝ፥ ከእ​ጅ​ዋም እን​ድ​በላ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="7">ዳዊ​ትም፥ “ወደ ወን​ድ​ምሽ ወደ አም​ኖን ቤት ሂጂ፤ መብ​ል​ንም አዘ​ጋ​ጂ​ለት” ብሎ ወደ ትዕ​ማር ቤት ላከ።</verse>
				<verse number="8">ትዕ​ማ​ርም ወደ ወን​ድ​ምዋ ወደ አም​ኖን ቤት ሄደች፤ ተኝ​ቶም ነበር፤ ዱቄ​ትም ወስዳ ለወ​ሰች፤ በፊ​ቱም እን​ጎቻ አደ​ረ​ገች፤ ጋገ​ረ​ችም።</verse>
				<verse number="9">ምጣ​ዱ​ንም ወስዳ በፊቱ ገለ​በ​ጠች፤ እርሱ ግን ይበላ ዘንድ እንቢ አለ። አም​ኖ​ንም፥ “ሰውን ሁሉ ከእኔ ዘንድ አስ​ወጡ” አለ፤ ሰውም ሁሉ ከእ​ርሱ ዘንድ ወጣ።</verse>
				<verse number="10">አም​ኖ​ንም ትዕ​ማ​ርን፥ “በእ​ጅሽ እበላ ዘንድ መብ​ሉን ወደ እል​ፍኙ አግ​ቢው” አላት፤ ትዕ​ማ​ርም የሠ​ራ​ች​ውን እን​ጎቻ ወስዳ ወን​ድ​ምዋ አም​ኖን ወዳ​ለ​በት እል​ፍኝ አገ​ባ​ችው።</verse>
				<verse number="11">ይበ​ላም ዘንድ መብ​ሉን አቀ​ረ​በ​ች​ለት። እር​ሱም ያዛ​ትና፥ “እኅቴ ሆይ፥ ነዪ ከእኔ ጋር ተኚ” አላት።</verse>
				<verse number="12">እር​ስ​ዋም አለ​ችው፥ “ወን​ድሜ ሆይ፥ አታ​ዋ​ር​ደኝ፤ እን​ዲህ ያለ ነገር በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አይ​ገ​ባ​ምና ይህን ነው​ረኛ ሥራ አታ​ድ​ርግ።</verse>
				<verse number="13">እኔም ነው​ሬን ወዴት እጥ​ላ​ታ​ለሁ? አን​ተም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ከሰ​ነ​ፎች እንደ አንዱ ትሆ​ና​ለህ፤ እን​ግ​ዲ​ያስ ለን​ጉሡ ንገ​ረው፥ እኔ​ንም አይ​ነ​ሣ​ህም” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="14">አም​ኖ​ንም ቃል​ዋን አል​ሰ​ማም፤ ይዞም አደ​ከ​ማት፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ተኛ።</verse>
				<verse number="15">ከዚ​ያም በኋላ አም​ኖን ፈጽሞ ጠላት፤ አስ​ቀ​ድሞ ከአ​ፈ​ቀ​ራት ፍቅር ይልቅ በኋላ የጠ​ላት ጥል በለጠ። አም​ኖ​ንም፥ “ተነ​ሥ​ተሽ ሂጂ” አላት።</verse>
				<verse number="16">ትዕ​ማ​ርም፥ “ቀድሞ ከሠ​ራ​ኸው ክፋት ይልቅ እኔን በማ​ው​ጣ​ትህ የበ​ለጠ ክፋት ትሠ​ራ​ለህ” አለ​ችው፤ አም​ኖን ግን ቃል​ዋን አል​ሰ​ማ​ትም።</verse>
				<verse number="17">በበር ቁሞ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለ​ው​ንም ብላ​ቴና ጠርቶ፥ “ይህ​ችን ሴት ከፊቴ አስ​ወ​ጥ​ተህ በሩን ዝጋ​ባት” አለው።</verse>
				<verse number="18">ብዙ ኅብር ያለ​ው​ንም ልብስ ለብሳ ነበር፤ የን​ጉሡ ልጆች ደና​ግሉ እን​ዲህ ያለ​ውን ልብስ ይለ​ብሱ ነበ​ርና፤ አገ​ል​ጋ​ዩም አስ​ወ​ጥቶ በሩን ዘጋ​ባት።</verse>
				<verse number="19">ትዕ​ማ​ርም አመድ ወስዳ በራ​ስዋ ላይ ነሰ​ነ​ሰች፤ በላ​ይዋ የነ​በ​ረ​ው​ንም ብዙ ኅብር ያለ​ውን ልብ​ስ​ዋን ቀደ​ደ​ችው፤ እጅ​ዋ​ንም በራ​ስዋ ላይ ጭና እየ​ጮ​ኸች ሄደች።</verse>
				<verse number="20">ወን​ድ​ም​ዋም አቤ​ሴ​ሎም፥ “ወን​ድ​ምሽ አም​ኖን ከአ​ንቺ ጋር ነበ​ርን? እኅቴ ሆይ፥ አሁን ግን ዝም በዪ፤ ወን​ድ​ምሽ ነውና፤ ይህን ነገር ትና​ገሪ ዘንድ በል​ብሽ አታ​ስቢ” አላት። ትዕ​ማ​ርም በወ​ን​ድ​ምዋ በአ​ቤ​ሴ​ሎም ቤት መበ​ለት ሆና ተቀ​መ​ጠች።</verse>
				<verse number="21">ንጉ​ሡም ዳዊት ይህን ነገር ሁሉ ሰማ፤ እጅ​ግም ተቈጣ፥ ነገር ግን የበ​ኵር ልጁ ነበ​ረና ስለ ወደ​ደው የል​ጁን የአ​ም​ኖ​ንን ነፍስ አላ​ሳ​ዘ​ነም።</verse>
				<verse number="22">አቤ​ሴ​ሎ​ምም አም​ኖ​ንን ክፉም ሆነ መል​ካም አል​ተ​ና​ገ​ረ​ውም። እኅ​ቱን ትዕ​ማ​ርን ስላ​ስ​ነ​ወ​ራት አቤ​ሴ​ሎም አም​ኖ​ንን ጠል​ቶ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="23">ከሁ​ለት ዓመ​ትም በኋላ አቤ​ሴ​ሎም በኤ​ፍ​ሬም አቅ​ራ​ቢያ ባለ​ችው በቤ​ላ​ሶር በጎ​ቹን በሚ​ያ​ሸ​ል​ት​በት ጊዜ አቤ​ሴ​ሎም የን​ጉ​ሡን ልጆች ሁሉ ጠራ።</verse>
				<verse number="24">አቤ​ሴ​ሎ​ምም ወደ ንጉሡ መጥቶ፥ “እነሆ፥ አገ​ል​ጋ​ይህ በጎ​ቹን ያሸ​ል​ታል፤ ንጉሡ ከአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ጋር ይሂድ፤ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ይሂዱ” አለው።</verse>
				<verse number="25">ንጉ​ሡም አቤ​ሴ​ሎ​ምን፥ “ልጄ ሆይ፥ አይ​ሆ​ንም፤ እን​ከ​ብ​ድ​ብ​ሃ​ለ​ንና ሁላ​ችን አን​ሄ​ድም” አለው። የግ​ድም አለው፤ እርሱ ግን መረ​ቀው እንጂ ለመ​ሄድ እንቢ አለ።</verse>
				<verse number="26">አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ “አንተ እንቢ ካልህ ወን​ድሜ አም​ኖን ከእኛ ጋር እን​ዲ​ሄድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለ። ንጉ​ሡም፥ “ከአ​ንተ ጋር ለምን ይሄ​ዳል?” አለው።</verse>
				<verse number="27">አቤ​ሴ​ሎ​ምም የግድ አለው፤ አም​ኖ​ን​ንና የን​ጉ​ሡ​ንም ልጆች ከእ​ርሱ ጋር ላከ።</verse>
				<verse number="28">አቤ​ሴ​ሎ​ምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደ​ረገ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ “አም​ኖን የወ​ይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አም​ኖ​ንን ግደሉ ባል​ኋ​ችሁ ጊዜ ግደ​ሉት። አት​ፍ​ሩም፤ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁም እኔ ነኝና በርቱ፤ ጽኑም” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="29">የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም አገ​ል​ጋ​ዮች አቤ​ሴ​ሎም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው በአ​ም​ኖን ላይ አደ​ረ​ጉ​በት። የን​ጉ​ሡም ልጆች ሁሉ ተነ​ሥ​ተው በየ​በ​ቅ​ሎ​ዎ​ቻ​ቸው ተቀ​ም​ጠው ሸሹ።</verse>
				<verse number="30">ገናም በመ​ን​ገድ ሲሄዱ ለዳ​ዊት፥ “አቤ​ሴ​ሎም የን​ጉ​ሡን ልጆች ሁሉ ገደ​ላ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ አል​ቀ​ረም” የሚል ወሬ መጣ።</verse>
				<verse number="31">ንጉ​ሡም ተነ​ሥቶ ልብ​ሱን ቀደደ፤ በም​ድር ላይም ወደቀ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ቁመው የነ​በሩ ብላ​ቴ​ኖቹ ሁሉ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀደዱ።</verse>
				<verse number="32">የዳ​ዊ​ትም ወን​ድም የሳ​ምዓ ልጅ ኢዮ​ና​ዳብ መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “ጌታዬ ጐል​ማ​ሶቹ የን​ጉሡ ልጆች ሁሉ እንደ ሞቱ አያ​ስብ፤ እኅ​ቱን ትዕ​ማ​ርን በግድ ካስ​ነ​ወ​ራት ጀምሮ በአ​ቤ​ሴ​ሎም ዘንድ የተ​ቈ​ረጠ ነገር ነበ​ረና የሞተ አም​ኖን ብቻ ነው።</verse>
				<verse number="33">አሁ​ንም የሞተ አም​ኖን ብቻ ነው እንጂ የን​ጉሥ ልጆች ሁሉ ሞቱ ብሎ ጌታዬ ንጉሡ ይህን ነገር በልቡ አያ​ስብ።”</verse>
				<verse number="34">አቤ​ሴ​ሎ​ምም ኰበ​ለለ። ጕበ​ኛ​ውም ጐል​ማሳ ዐይ​ኑን ከፍ አደ​ረገ፤ እነ​ሆም፥ ብዙ ሰዎች በኋ​ላው በተ​ራ​ራው አጠ​ገብ በመ​ን​ገድ ሲመጡ አየ። ጕበ​ኛ​ውም መጥቶ ለን​ጉሡ እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “ብዙ ሰዎች በተ​ራ​ራው ጎን ባለው በአ​ር​ኖን መን​ገድ ሲመጡ አየሁ።”</verse>
				<verse number="35">ኢዮ​ና​ዳ​ብም ንጉ​ሡን፥ “እነሆ፥ የን​ጉሡ ልጆች መጥ​ተ​ዋል፤ አገ​ል​ጋ​ይህ እን​ዳ​ለው እን​ዲሁ ሆኖ​አል” አለው።</verse>
				<verse number="36">ተና​ግ​ሮም በጨ​ረሰ ጊዜ እነሆ፥ ወዲ​ያው የን​ጉሥ ልጆች ገቡ፤ ድም​ፃ​ቸ​ው​ንም ከፍ አድ​ር​ገው አለ​ቀሱ፤ ደግ​ሞም ንጉ​ሡና ብላ​ቴ​ኖቹ ሁሉ እጅግ ታላቅ ልቅሶ አለ​ቀሱ።</verse>
				<verse number="37">አቤ​ሴ​ሎም ግን ኰብ​ልሎ ወደ መአክ ሀገር ወደ ጌድ​ሶር ንጉሥ ወደ አሚ​ሁድ ልጅ ወደ ቶል​ማ​ይዮ ሄደ። ዳዊ​ትም ሁል ጊዜ ለልጁ ያለ​ቅስ ነበር።</verse>
				<verse number="38">አቤ​ሴ​ሎ​ምም ኰብ​ልሎ ወደ ጌድ​ሶር ሄደ፤ በዚ​ያም ሦስት ዓመት ያህል ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="39">ንጉ​ሡም ዳዊት አቤ​ሴ​ሎ​ምን መከ​ታ​ተ​ልን ተወ፤ ስለ ሞተው ልጁ ስለ አም​ኖን ተጽ​ና​ንቶ ነበ​ርና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">የሶ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አ​ብም የን​ጉሡ ልብ ወደ አቤ​ሴ​ሎም እን​ዳ​ዘ​ነ​በለ ዐወቀ።</verse>
				<verse number="2">ኢዮ​አ​ብም ወደ ቴቁሔ ልኮ ከዚያ ብል​ሃ​ተኛ ሴት አስ​መ​ጣና፥ “አል​ቅሺ፤ የኀ​ዘ​ንም ልብስ ልበሺ፤ ዘይ​ትም አት​ቀቢ፤ ስለ ሞተ ሰውም ብዙ ዘመን እን​ደ​ም​ታ​ለ​ቅስ ሴት ሁኚ፤</verse>
				<verse number="3">ወደ ንጉ​ሡም ገብ​ተሽ እን​ዲህ ያለ​ውን ቃል ንገ​ሪው” አላት፤ ኢዮ​አ​ብም ቃሉን በእ​ር​ስዋ አፍ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="4">እን​ዲ​ሁም የቴ​ቁ​ሔ​ዪቱ ሴት ወደ ንጉሥ ገብታ በግ​ን​ባ​ርዋ በም​ድር ላይ ወደ​ቀች፤ ሰግ​ዳም “ንጉሥ ሆይ፥ አድ​ነኝ፤ አድ​ነኝ” አለች።</verse>
				<verse number="5">ንጉ​ሡም፥ “ምን ሆነ​ሻል?” አላት። እር​ስ​ዋም አለች፥ “በእ​ው​ነት እኔ ባሌ የሞ​ተ​ብኝ ባል​ቴት ሴት ነኝ።</verse>
				<verse number="6">ለእ​ኔም ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ሁለት ወን​ዶች ልጆች ነበ​ሩኝ፤ በሜ​ዳም ተጣሉ፤ የሚ​ገ​ላ​ግ​ላ​ቸ​ውም አል​ነ​በ​ረም፤ አን​ዱም ሌላ​ውን መትቶ ገደ​ለው።</verse>
				<verse number="7">እነ​ሆም፥ ዘመ​ዶች ሁሉ በባ​ሪ​ያህ ላይ ተነሡ፤ ስለ ገደ​ለው ስለ ወን​ድሙ ነፍስ እን​ገ​ድ​ለው ዘንድ ወን​ድ​ሙን የገ​ደ​ለ​ውን አውጪ አሉኝ፤ እን​ዲ​ሁም ደግሞ ለባሌ ስምና ዘር በም​ድር ላይ እን​ዳ​ይ​ቀር ወራ​ሹን የቀ​ረ​ውን መብ​ራ​ቴን ያጠ​ፋሉ፤”</verse>
				<verse number="8">ንጉ​ሡም ሴቲ​ቱን፥ “ወደ ቤትሽ በሰ​ላም ሂጂ፤ እኔም ስለ አንቺ አዝ​ዛ​ለሁ” አላት።</verse>
				<verse number="9">የቴ​ቁ​ሔ​ዪ​ቱም ሴት ንጉ​ሡን፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ኀጢ​አቱ በእ​ኔና በአ​ባቴ ቤት ላይ ይሁን፤ ንጉ​ሡና ዙፋኑ ንጹሕ ይሁን” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="10">ንጉ​ሡም፥ “የሚ​ና​ገ​ርሽ ማን ነው? አም​ጪ​ልኝ፤ ከዚ​ያም በኋላ ደግሞ አይ​ነ​ካ​ሽም” አለ።</verse>
				<verse number="11">ያችም ሴት፥ “ለመ​ግ​ደል ባለ ደሞች እን​ዳ​ይ​በዙ፤ ልጄ​ንም እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ሉ​ብኝ ንጉሥ ፈጣ​ሪው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያስብ” አለች። እር​ሱም፥ “የል​ጅ​ሽስ አን​ዲት የራሱ ጠጕር በም​ድር ላይ እን​ዳ​ት​ወ​ድቅ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን” አላት።</verse>
				<verse number="12">ሴቲ​ቱም፥ “እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ለጌ​ታዬ ለን​ጉሥ አንድ ቃል ልና​ገር” አለች፤ እር​ሱም፥ “ተና​ገሪ” አላት።</verse>
				<verse number="13">ሴቲ​ቱም አለች፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ላይ እን​ዲህ ያለ ነገር ስለ​ምን አሰ​ብህ? ወይስ ንጉሥ ያሳ​ደ​ደ​ውን ስላ​ላ​ስ​መ​ለሰ እንደ በደል ከን​ጉሥ አፍ ይህ ቃል ወጥ​ቶ​አ​ልን?</verse>
				<verse number="14">ሞትን እን​ሞ​ታ​ለ​ንና፥ በም​ድ​ርም ላይ እንደ ፈሰ​ሰና እን​ደ​ማ​ይ​መ​ለስ ውኃ እን​ሆ​ና​ለ​ንና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነፍ​ስን ይወ​ስ​ዳል። የተ​ጣ​ለ​ው​ንም ከእ​ርሱ ያርቅ ዘንድ ያስ​ባል።</verse>
				<verse number="15">አሁ​ንም ሕዝቡ ስለ​ሚ​ያ​ዩኝ ይህን ነገር ለጌ​ታዬ ለን​ጉሥ እነ​ግ​ረው ዘንድ መጥ​ቻ​ለሁ፤ እኔም አገ​ል​ጋ​ይህ፦ የእ​ኔን የአ​ገ​ል​ጋ​ዩን ልመና ንጉሡ ያደ​ር​ግ​ልኝ እንደ ሆነ ለጌ​ታዬ ለን​ጉሥ ልና​ገር፤</verse>
				<verse number="16">እኔ​ንና ልጄን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት ያር​ቀን ዘንድ ከሚሻ ሰው እጅ ያድን ዘንድ ንጉሡ አገ​ል​ጋ​ዩን ይሰ​ማል አልሁ።”</verse>
				<verse number="17">ያችም ሴት አለች፥ “መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ውን ነገር ለመ​ስ​ማት ንጉሡ ጌታዬ እንደ መሥ​ዋ​ዕ​ትና እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ነውና የጌ​ታዬ የን​ጉሡ ቃል እን​ደ​ዚሁ ነው፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ይሁን።”</verse>
				<verse number="18">ንጉ​ሡም ለሴ​ቲቱ መልሶ፥ “የም​ጠ​ይ​ቅ​ሽን ነገር አት​ሰ​ው​ሪኝ” አላት። ሴቲ​ቱም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ይና​ገር” አለች።</verse>
				<verse number="19">ንጉ​ሡም፥ “በዚህ ሁሉ ነገር የኢ​ዮ​አብ እጅ ከአ​ንቺ ጋር አለን?” አላት። ሴቲ​ቱም ንጉ​ሡን አለ​ችው፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ! ጌታዬ ንጉሥ ከተ​ና​ገ​ረው ነገር ሁሉ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ሊል የሚ​ችል የለም፤ አገ​ል​ጋ​ይህ ኢዮ​አብ አዝ​ዞ​ኛል፤ ይህ​ንም ቃል ሁሉ በአ​ገ​ል​ጋ​ይህ አፍ አደ​ረ​ገው።</verse>
				<verse number="20">ይህን ነገር እና​ገር ዘንድ እን​ድ​መጣ ይህን ምክር ያደ​ረገ አገ​ል​ጋ​ይህ ኢዮ​አብ ነው። ጌታዬ ግን በዚህ ዓለም የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ታውቅ ዘንድ እንደ መል​አከ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ ጥበ​በኛ ነህ፤”</verse>
				<verse number="21">ንጉ​ሡም ኢዮ​አ​ብን፥ “እነሆ፥ ይህን ነገር አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ ሂድና ብላ​ቴ​ና​ውን አቤ​ሴ​ሎ​ምን መል​ሰው” አለው።</verse>
				<verse number="22">ኢዮ​አ​ብም በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ወድቆ ሰገ​ደ​ለት፤ ንጉ​ሡ​ንም አመ​ሰ​ገነ፤ ኢዮ​አ​ብም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ነገር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና በዐ​ይ​ንህ ፊት ሞገ​ስን እን​ዳ​ገኘ አገ​ል​ጋ​ይህ ዛሬ ዐወቀ” አለ።</verse>
				<verse number="23">ኢዮ​አ​ብም ተነ​ሥቶ ወደ ጌድ​ሶር ሄደ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ም​ንም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመ​ጣው።</verse>
				<verse number="24">ንጉ​ሡም፥ “ወደ ቤቱ ይሂድ እንጂ ፊቴን እን​ዳ​ያይ” አለ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም ወደ ቤቱ ተመ​ለሰ፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ፊት አላ​የም።</verse>
				<verse number="25">በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዘንድ እንደ አቤ​ሴ​ሎም በው​በቱ ያማረ ሰው አል​ነ​በ​ረም፤ ከእ​ግሩ እስከ ራሱ ድረስ ነውር አል​ነ​በ​ረ​በ​ትም።</verse>
				<verse number="26">ቀድሞ በመ​ጀ​መ​ሪያ ዘመን ጠጕሩ ይከ​ብ​ደው ነበ​ርና በዓ​መት አንድ ጊዜ ይቈ​ረ​ጠው ነበር፤ ሲቈ​ረ​ጥም የራሱ ጠጕር በን​ጉሥ ሚዛን ሁለት መቶ ሰቅል ያህል ይመ​ዝን ነበር።</verse>
				<verse number="27">ለአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም ሦስት ወን​ዶች ልጆ​ችና አን​ዲት ሴት ልጅ ተወ​ለ​ዱ​ለት። የሴ​ቲቱ ልጅም ስም ትዕ​ማር ይባ​ላል። ያች​ውም ሴት መልከ መል​ካም ነበ​ረች፤ እር​ሷም የሰ​ሎ​ሞን ልጅ የሮ​ብ​አም ሚስት ሆና አቢ​ያን ወለ​ደ​ች​ለት።</verse>
				<verse number="28">አቤ​ሴ​ሎ​ምም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሁለት ዓመት ሙሉ ተቀ​መጠ፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ፊት አላ​የም።</verse>
				<verse number="29">አቤ​ሴ​ሎ​ምም ወደ ንጉሡ ይል​ከው ዘንድ ወደ ኢዮ​አብ ላከ፤ ወደ እር​ሱም ሊመጣ አል​ወ​ደ​ደም፤ ሁለ​ተ​ኛም ላከ​በት፤ ሊመጣ ግን አል​ወ​ደ​ደም።</verse>
				<verse number="30">አቤ​ሴ​ሎ​ምም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “በእ​ር​ሻዬ አጠ​ገብ ያለ​ች​ውን የኢ​ዮ​አ​ብን እርሻ እዩ፤ በዚ​ያም ገብስ አለው፤ ሄዳ​ችሁ በእ​ሳት አቃ​ጥ​ሉት” አላ​ቸው። የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም ብላ​ቴ​ኖች እር​ሻ​ውን አቃ​ጠ​ሉት። የኢ​ዮ​አ​ብም አሽ​ከ​ሮች ልብ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን ቀድ​ደው ተመ​ል​ሰው፥ “የአ​ቤ​ሴ​ሎም አሽ​ከ​ሮች እር​ሻ​ህን በእ​ሳት አቃ​ጠ​ሉት” ብለው ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="31">ኢዮ​አ​ብም ተነ​ሥቶ ወደ አቤ​ሴ​ሎም ወደ ቤቱ መጣና፥ “ብላ​ቴ​ኖ​ችህ እር​ሻ​ዬን ስለ​ምን አቃ​ጠ​ሉት?” አለው።</verse>
				<verse number="32">አቤ​ሴ​ሎ​ምም ኢዮ​አ​ብን፥ “ከጌ​ድ​ሶር ለምን መጣሁ? በዚ​ያም ተቀ​ምጬ ቢሆን ይሻ​ለኝ ነበር ብለህ እን​ድ​ት​ነ​ግ​ረው ወደ ንጉሥ እል​ክህ ዘንድ ወደ እኔ ና ብዬ ወደ አንተ ላክሁ፤ አሁ​ንም የን​ጉ​ሡን ፊት አላ​የ​ሁም፤ ኀጢ​አት ቢኖ​ር​ብኝ ይግ​ደ​ለኝ” አለው።</verse>
				<verse number="33">ኢዮ​አ​ብም ወደ ንጉሥ መጥቶ ነገ​ረው፤ አቤ​ሴ​ሎ​ም​ንም ጠራው፥ ወደ ንጉ​ሡም ገብቶ ሰገ​ደ​ለት፤ በን​ጉ​ሡም ፊት ወደ ምድር በግ​ን​ባሩ ወደቀ፤ ንጉ​ሡም አቤ​ሴ​ሎ​ምን ሳመው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ አቤ​ሴ​ሎም ሰረ​ገ​ላና ፈረ​ሶች፥ በፊ​ቱም የሚ​ሮጡ አምሳ ሰዎች አዘ​ጋጀ።</verse>
				<verse number="2">አቤ​ሴ​ሎ​ምም በማ​ለዳ ተነ​ሥቶ በበሩ ጎዳና ይቆም ነበር፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም ከን​ጉሥ ለማ​ስ​ፈ​ረድ ጉዳይ የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ወደ እርሱ እየ​ጠራ፥ “አንተ ከወ​ዴት ከተማ ነህ?” ብሎ ይጠ​ይቅ ነበር። እር​ሱም፥ “እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ከእ​ስ​ራ​ኤል ወገን ከአ​ን​ዲቱ ነኝ” ይለው ነበር።</verse>
				<verse number="3">አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ “ነገ​ርህ መል​ካም ነው፤ ቀላ​ልም ነው፤ ነገር ግን ከን​ጉሥ ዘንድ የሚ​ሰ​ማህ የለም” ይለው ነበር።</verse>
				<verse number="4">አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ “ነገ​ርና ክር​ክር ያለው ሁሉ ወደ እኔ ይመጣ ዘንድ፥ ቅንም ፍርድ እፈ​ር​ድ​ለት ዘንድ በሀ​ገር ላይ ፈራጅ አድ​ርጎ ማን በሾ​መኝ?” ይል ነበር።</verse>
				<verse number="5">ሰውም እጅ ለመ​ን​ሣት ወደ እርሱ በቀ​ረበ ጊዜ እጁን ዘር​ግቶ አቅፎ ይስ​መው ነበር።</verse>
				<verse number="6">በን​ጉሡ ዘንድ ሊፋ​ረዱ ለሚ​መጡ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ አቤ​ሴ​ሎም እን​ዲህ ያደ​ርግ ነበር፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰዎች ልብ ማረከ።</verse>
				<verse number="7">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከአ​ራት ዓመት በኋላ አቤ​ሴ​ሎም አባ​ቱን፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሳ​ል​ሁ​ትን ስእ​ለት በኬ​ብ​ሮን አደ​ርግ ዘንድ ልሂድ።</verse>
				<verse number="8">እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ በሶ​ርያ ጌድ​ሶር ሳለሁ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ቢመ​ል​ሰኝ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ር​ባ​ለሁ ብዬ ስእ​ለት ተስዬ ነበ​ርና” አለው።</verse>
				<verse number="9">ንጉ​ሡም፥ “በሰ​ላም ሂድ” አለው፤ ተነ​ሥ​ቶም ወደ ኬብ​ሮን ሄደ።</verse>
				<verse number="10">አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ “የመ​ለ​ከት ድምፅ በሰ​ማ​ችሁ ጊዜ፥ አቤ​ሴ​ሎም በኬ​ብ​ሮን ነገሠ” በሉ የሚሉ ጕበ​ኞ​ችን ወደ እስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ላከ።</verse>
				<verse number="11">የተ​ጠ​ሩ​ትም ሁለት መቶ ሰዎች ከአ​ቤ​ሴ​ሎም ጋር ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሄዱ፤ እነ​ር​ሱም በየ​ዋ​ህ​ነት ሄዱ፤ ነገ​ሩ​ንም ሁሉ ከቶ አያ​ው​ቁም ነበር።</verse>
				<verse number="12">አቤ​ሴ​ሎ​ምም መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሠ​ዋ​በት ጊዜ የዳ​ዊት አማ​ካሪ ወደ ነበ​ረው ጌሎ​ና​ዊው አኪ​ጦ​ፌል ወደ ከተ​ማው ጊሎ ላከ። ሴራ​ውም ጽኑ ሆነ፤ ከአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም ጋር ያለው ሕዝብ እጅግ በዛ።</verse>
				<verse number="13">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ልብ ወደ አቤ​ሴ​ሎም ተመ​ል​ሶ​አል የሚል መል​እ​ክ​ተኛ ወደ ዳዊት ሄደ።</verse>
				<verse number="14">ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያሉ​ትን አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ሁሉ፥ “ተነሡ እን​ሽሽ፤ ከአ​ቤ​ሴ​ሎም እጅ የም​ን​ድ​ን​በት የለ​ን​ምና፤ ፈጥኖ እን​ዳ​ይ​ዘን፥ ክፉም እን​ዳ​ያ​መ​ጣ​ብን፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም በሰ​ልፍ ስለት እን​ዳ​ይ​መታ ፈጥ​ና​ችሁ እን​ሂድ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">የን​ጉ​ሡም ብላ​ቴ​ኖች ንጉ​ሡን፥ “እነሆ፥ ጌታ​ችን ንጉሥ የመ​ረ​ጠ​ውን ሁሉ እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አሉት።</verse>
				<verse number="16">ንጉ​ሡና ከእ​ር​ሱም በኋላ ቤተ ሰቡ ሁሉ በእ​ግ​ራ​ቸው ወጡ፤ ንጉ​ሡም ቁባ​ቶቹ የነ​በሩ ዐሥ​ሩን ሴቶች ቤቱን ይጠ​ብቁ ዘንድ ተወ።</verse>
				<verse number="17">ንጉ​ሡና ሕዝቡ ሁሉ በእ​ግር ወጡ፤ በሩ​ቅም ቦታ ቆሙ።</verse>
				<verse number="18">ብላ​ቴ​ኖ​ቹም ሁሉ ተከ​ተ​ሉት፤ ኬል​ቲ​ያ​ው​ያ​ንና ፌል​ታ​ው​ያ​ንም ሁሉ በም​ድረ በዳ በወ​ይራ ሥር ቆሙ። ሕዝ​ቡም ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ይሄዱ ነበር። ከእ​ርሱ ጋር ያሉ ሰዎ​ችም ሁሉ ስድ​ስት መቶ ነበሩ። ከእ​ርሱ ጋር ፌል​ታ​ው​ያ​ንና ኬል​ቲ​ያ​ው​ያን፥ በእ​ግ​ራ​ቸው ከጌት የመጡ ስድ​ስት መቶ ጌታ​ው​ያ​ንም ነበሩ። በን​ጉ​ሡም ፊት ይሄዱ ነበር።</verse>
				<verse number="19">ንጉ​ሡም ጌታ​ዊ​ውን ኤቲን፥ “ከእኛ ጋር ለምን መጣህ? አንተ ከስ​ፍ​ራህ የመ​ጣህ ስደ​ተ​ኛና እን​ግዳ ነህና ተመ​ለስ፤ ከን​ጉ​ሡም ጋር ተቀ​መጥ፤</verse>
				<verse number="20">የመ​ጣ​ኸው ትና​ንት ነው፤ ዛሬ ከእኛ ጋር ላዙ​ር​ህን? እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በት እሄ​ዳ​ለሁ፤ አንተ ግን ተመ​ለስ፤ ወን​ድ​ሞ​ች​ህ​ንም ከአ​ንተ ጋር መል​ሳ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምሕ​ረ​ቱ​ንና እው​ነ​ቱን ያድ​ር​ግ​ልህ” አለው።</verse>
				<verse number="21">ኤቲም ለን​ጉሡ መልሶ፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በጌ​ታ​ዬም በን​ጉሡ ሕይ​ወት እም​ላ​ለሁ! ጌታዬ ባለ​በት ስፍራ ሁሉ፥ በሞ​ትም ቢሆን በሕ​ይ​ወ​ትም፥ በዚያ ደግሞ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ እሆ​ና​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="22">ንጉ​ሡም ኤቲን፥ “ና ከእኔ ጋር ተሻ​ገር” አለው፤ ጌታ​ዊው ኤቲና ንጉ​ሡም፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ሕዝቡ ሁሉ ተሻ​ገሩ።</verse>
				<verse number="23">ሀገ​ሪ​ቱም ሁላ በታ​ላቅ ድምፅ አለ​ቀ​ሰች። ሕዝ​ቡም ሁሉ በቄ​ድ​ሮን ወንዝ ተሻ​ገሩ፤ ንጉ​ሡም ደግሞ የቄ​ድ​ሮ​ንን ወንዝ ተሻ​ገረ፤ ንጉ​ሡና ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ምድረ በዳ በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ተሻ​ገሩ።</verse>
				<verse number="24">እነ​ሆም፥ ደግሞ፥ ሳዶ​ቅና ከእ​ር​ሱም ጋር ሌዋ​ው​ያን ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት አመጡ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት አስ​ቀ​መጡ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ፈጽሞ እስ​ኪ​ያ​ልፉ ድረስ አብ​ያ​ታር ወጣ።</verse>
				<verse number="25">ንጉ​ሡም ሳዶ​ቅን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወደ ከተማ መልስ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይን ሞገስ አግ​ኝቼ እንደ ሆንሁ፥ መልሶ እር​ሷ​ንና ክብ​ሯን ያሳ​የ​ኛል፤</verse>
				<verse number="26">ነገር ግን አል​ወ​ድ​ድ​ህም ቢለኝ፥ እነ​ሆኝ በፊቱ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን ያድ​ር​ግ​ብኝ” አለው።</verse>
				<verse number="27">ንጉ​ሡም ደግሞ ካህ​ኑን ሳዶ​ቅን፥ “እነሆ፥ አን​ተና ልጅህ አኪ​ማ​ኦስ፥ የአ​ብ​ያ​ታ​ርም ልጅ ዮና​ታን፥ ሁለቱ ልጆ​ቻ​ችሁ ከእ​ና​ንተ ጋር በሰ​ላም ወደ ከተማ ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="28">እዩ፤ እኔም እነሆ፥ ከእ​ና​ንተ ዘንድ ወሬ እስ​ኪ​መ​ጣ​ልኝ ድረስ በም​ድረ በዳው ውስጥ በሜ​ዳው እቈ​ያ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="29">ሳዶ​ቅና አብ​ያ​ታ​ርም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መለ​ሷት፤ በዚ​ያም ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="30">ዳዊ​ትም ወደ ደብረ ዘይት ዐቀ​በት ወጣ፤ ሲወ​ጣም ያለ​ቅስ ነበር፤ ራሱ​ንም ተከ​ና​ንቦ ነበር፤ ያለ​ጫ​ማም ይሄድ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ተከ​ና​ን​በው ነበር፤ እያ​ለ​ቀ​ሱም ይወጡ ነበር።</verse>
				<verse number="31">አኪ​ጦ​ፌል ከአ​ቤ​ሴ​ሎም ጋር በሴራ አንድ ነው ብለው ለዳ​ዊት ነገ​ሩት፤ ዳዊ​ትም፥ “አቤቱ የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልን ምክር ለውጥ” አለ።</verse>
				<verse number="32">ዳዊ​ትም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ሰገ​ደ​በት ወደ ተራ​ራው ራስ መጣ፤ ወዳጁ ኵሲም ልብ​ሱን ቀደደ፤ በራ​ሱም ላይ ትቢያ ነስ​ንሶ ሊገ​ና​ኘው መጣ።</verse>
				<verse number="33">ዳዊ​ትም አለው፥ “ከእኔ ጋር ብት​ሻ​ገር ሸክም ትሆ​ን​ብ​ኛ​ለህ፤</verse>
				<verse number="34">ወደ ከተማ ግን ተመ​ል​ሰህ ለአ​ቤ​ሴ​ሎም፦ ወን​ድ​ሞ​ችህ፥ ንጉ​ሡም መጡ። እነሆ፥ በኋ​ላዬ ናቸው። ንጉሥ ሆይ፥ አገ​ል​ጋ​ይህ ነኝ፤ አስ​ቀ​ድሞ ለአ​ባ​ትህ አገ​ል​ጋይ ነበ​ርሁ፥ እን​ዲሁ አሁ​ንም ለአ​ንተ አገ​ል​ጋይ ነኝ፥ ተወኝ ልኑር ብት​ለው የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልን ምክር ትለ​ው​ጥ​ል​ኛ​ለህ።</verse>
				<verse number="35">እነሆ፥ ካህ​ናቱ ሳዶ​ቅና አብ​ያ​ታ​ርም በዚያ ከአ​ንተ ጋር ናቸው። ከን​ጉሡ ቤትም የም​ት​ሰ​ማ​ውን ነገር ሁሉ ለካ​ህ​ናቱ ለሳ​ዶ​ቅና ለአ​ብ​ያ​ታር ንገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="36">እነሆ፥ የሳ​ዶቅ ልጅ አኪ​ማ​ኦ​ስና የአ​ብ​ያ​ታር ልጅ ዮና​ታን፥ ልጆ​ቻ​ቸው በዚያ ከእ​ነ​ርሱ ጋር አሉ፤ የም​ት​ሰ​ሙ​ትን ሁሉ በእ​ነ​ርሱ እጅ ላኩ​ልኝ።”</verse>
				<verse number="37">የዳ​ዊ​ትም ወዳጅ ኩሲ ወደ ከተማ መጣ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም ደግሞ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ገባ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">ዳዊ​ትም ከተ​ራ​ራው ራስ ጥቂት እልፍ አለ። እነ​ሆም፥ የሜ​ም​ፌ​ቡ​ስቴ አገ​ል​ጋይ ሲባ ሁለት መቶ እን​ጀራ፥ አንድ መቶም ዘለላ ዘቢብ፥ አንድ መቶም ተምር፥ አንድ አቁ​ማ​ዳም ወይን ጠጅ የተ​ጫኑ ሁለት አህ​ዮች እየ​ነዳ ተገ​ና​ኘው።</verse>
				<verse number="2">ንጉ​ሡም ሲባን፥ “ይህ ለአ​ንተ ምን​ድን ነው?” አለው። ሲባም፥ “አህ​ዮቹ የን​ጉሥ ቤተ ሰቦች ይቀ​መ​ጡ​ባ​ቸው ዘንድ፥ እን​ጀ​ራ​ውና ተም​ሩም ብላ​ቴ​ኖቹ ይበ​ሉት ዘንድ፥ የወ​ይን ጠጁም በበ​ረሃ የሚ​ደ​ክ​ሙት ይጠ​ጡት ዘንድ ነው” አለ።</verse>
				<verse number="3">ንጉ​ሡም፥ “የጌ​ታህ ልጅ ወዴት ነው?” አለ። ሲባም ንጉ​ሡን፥ “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ዛሬ የአ​ባ​ቴን መን​ግ​ሥት ይመ​ል​ስ​ል​ኛል ብሎ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​ም​ጦ​አል” አለው።</verse>
				<verse number="4">ንጉ​ሡም ሲባን፥ “እነሆ፥ ለሜ​ም​ፌ​ቡ​ስቴ የነ​በ​ረው ሁሉ ለአ​ንተ ይሁን” አለው። ሲባም ሰግዶ፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በፊ​ትህ ሞገ​ስን ላግኝ” አለ።</verse>
				<verse number="5">ንጉሡ ዳዊ​ትም ወደ በው​ሪም መጣ፤ እነ​ሆም፥ ሳሚ የሚ​ባል የጌራ ልጅ ከሳ​ኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ከዚያ ወጣ፤ እየ​ሄ​ደም ይረ​ግ​መው ነበር።</verse>
				<verse number="6">ወደ ዳዊ​ትና ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ድን​ጋይ ይወ​ረ​ውር ነበር፤ በን​ጉ​ሡም ቀኝና ግራ ሕዝቡ ሁሉና ኀያ​ላኑ ሁሉ ነበሩ።</verse>
				<verse number="7">ሳሚም ሲረ​ግ​መው እን​ዲህ ይል ነበር፥ “ውጣ! አንተ የደም ሰውና ዐመ​ፀኛ ሰው ሂድ! ሂድ!</verse>
				<verse number="8">በፋ​ን​ታው ነግ​ሠ​ሃ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሳ​ኦ​ልን ቤት ደም ሁሉ መለ​ሰ​ብህ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥ​ት​ህን ለል​ጅህ ለአ​ቤ​ሴ​ሎም እጅ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ታል፤ እነ​ሆም፥ አንተ የደም ሰው ነህና በመ​ከራ ተይ​ዘ​ሃል።”</verse>
				<verse number="9">የሶ​ር​ህያ ልጅ አቢ​ሳም ንጉ​ሡን አለው፥ “ይህ የሞተ ውሻ ጌታ​ዬን ንጉ​ሡን ስለ​ምን ይረ​ግ​ማል? ልሻ​ገ​ርና ራሱን ልቍ​ረ​ጠው፤”</verse>
				<verse number="10">ንጉ​ሡም፥ “እና​ንተ የሶ​ር​ህያ ልጆች! በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ምን አለኝ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዳዊ​ትን ርገ​መው ብሎ አዝ​ዞ​ታ​ልና ይር​ገ​መኝ፤ ለም​ንስ እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ለህ? የሚ​ለው ማን ነው?” አለ።</verse>
				<verse number="11">ዳዊ​ትም አቢ​ሳ​ንና አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ሁሉ፥ “እነሆ፥ ከወ​ገቤ የወ​ጣው ልጄ ነፍ​ሴን ይሻል፤ ይል​ቁ​ንስ ይህ የኢ​ያ​ሚን ልጅ እን​ዴት ነዋ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዝ​ዞ​ታ​ልና ተዉት፥ ይር​ገ​መኝ።</verse>
				<verse number="12">ምና​ል​ባት መከ​ራ​ዬን አይቶ ስለ ርግ​ማኑ በዚህ ቀን መል​ካም ይመ​ል​ስ​ል​ኛል” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም በመ​ን​ገድ ይሄዱ ነበር፤ ሳሚም በተ​ራ​ራው አጠ​ገብ በአ​ቅ​ራ​ቢ​ያው ይሄድ ነበር፤ ሲሄ​ድም ይረ​ግ​መው፥ ድን​ጋ​ይም ይወ​ረ​ው​ር​በት ነበር፤ ትቢ​ያም ይበ​ት​ን​በት ነበር።</verse>
				<verse number="14">ንጉ​ሡና ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ረው ሕዝብ ሁሉ ደረሱ፤ ደክ​መ​ውም ነበር፤ በዚ​ያም ዐረፉ።</verse>
				<verse number="15">አቤ​ሴ​ሎ​ምና የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ሁሉ፥ አኪ​ጦ​ፌ​ልም ከእ​ርሱ ጋር ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጡ።</verse>
				<verse number="16">የዳ​ዊ​ትም ወዳጅ ኩሲ ወደ አቤ​ሴ​ሎም በመጣ ጊዜ ኩሲ አቤ​ሴ​ሎ​ምን፥ “ንጉሥ ሆይ! ሽህ ዓመት ያን​ግ​ሥህ” አለው።</verse>
				<verse number="17">አቤ​ሴ​ሎ​ምም ኩሲን፥ “ስለ ወዳ​ጅህ ያደ​ረ​ግ​ኸው ቸር​ነት ይህ ነውን? ከወ​ዳ​ጅህ ጋር ያል​ሄ​ድህ ስለ ምን​ድን ነው?” አለው።</verse>
				<verse number="18">ኩሲም አቤ​ሴ​ሎ​ምን፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ይህም ሕዝብ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ለመ​ረ​ጡት ለእ​ርሱ እሆ​ና​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር እኖ​ራ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="19">“ዳግ​ምም የማ​ገ​ለ​ግል ለማን ነው? በን​ጉሥ ልጅ ፊት አይ​ደ​ለ​ምን? በአ​ባ​ትህ ፊት እን​ዳ​ገ​ለ​ገ​ልሁ እን​ዲሁ በአ​ንተ ፊት እሆ​ና​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="20">አቤ​ሴ​ሎ​ምም አኪ​ጦ​ፌ​ልን፦ ምን እን​ደ​ም​ና​ደ​ርግ ምከሩ አለው።</verse>
				<verse number="21">አኪ​ጦ​ፌ​ልም አቤ​ሴ​ሎ​ምን፥ “ቤት ሊጠ​ብቁ ወደ ተዋ​ቸው ወደ አባ​ትህ ቁባ​ቶች ግባ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አባ​ት​ህን እን​ዳ​ሳ​ፈ​ር​ኸው ይሰ​ማሉ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ያሉት ሁሉ እጃ​ቸው ይበ​ረ​ታል” አለው።</verse>
				<verse number="22">ለአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም በሰ​ገ​ነት ላይ ድን​ኳን ተከ​ሉ​ለት፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት ወደ አባቱ ቁባ​ቶች ገባ።</verse>
				<verse number="23">በእ​ነ​ዚያ በመ​ጀ​መ​ሪያ ወራት የመ​ከ​ራት የአ​ኪ​ጦ​ፌል ምክር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እንደ መጠ​የቅ ነበ​ረች፤ የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልም ምክር ሁሉ ከዳ​ዊ​ትና ከአ​ቤ​ሴ​ሎም ጋር እን​ዲሁ ነበ​ረች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">አኪ​ጦ​ፌ​ልም አቤ​ሴ​ሎ​ምን አለው፥ “ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎች ልም​ረ​ጥና በዚ​ህች ሌሊት ተነ​ሥቼ ዳዊ​ትን ላሳ​ድድ።</verse>
				<verse number="2">ደክ​ሞና እጁ ዝሎ ሳለ እወ​ድ​ቅ​በ​ታ​ለሁ፤ አስ​ፈ​ራ​ው​ማ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ይሸ​ሻል፤ ንጉ​ሡ​ንም ብቻ​ውን እገ​ድ​ለ​ዋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="3">ሙሽራ ወደ ባልዋ እን​ደ​ም​ት​መ​ለስ ሕዝ​ቡን ሁሉ ወደ አንተ እመ​ል​ሰ​ዋ​ለሁ፤ የአ​ንድ ሰው ሰው​ነ​ትን ብቻ ትሻ​ለ​ህና፤ ለሕ​ዝቡ ሁሉ ግን ሰላም ይሆ​ናል፤”</verse>
				<verse number="4">ነገ​ሩም በአ​ቤ​ሴ​ሎም ፊትና በእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ፊት ደስ አሰኘ።</verse>
				<verse number="5">አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ “አር​ካ​ዊ​ውን ኩሲን ጥሩት፤ ደግ​ሞም እርሱ የሚ​ለ​ውን እን​ስማ” አለ።</verse>
				<verse number="6">ኩሲም ወደ አቤ​ሴ​ሎም በመጣ ጊዜ አቤ​ሴ​ሎም፥ “አኪ​ጦ​ፌል ያለው ይህ ነው፤ ነገ​ሩን እና​ደ​ር​ገው ዘንድ ይገ​ባ​ልን? ባይ​ሆን ግን አንተ ንገ​ረን” ብሎ ተና​ገ​ረው።</verse>
				<verse number="7">ኩሲም አቤ​ሴ​ሎ​ምን አለው፥ “አኪ​ጦ​ፌል በዚህ ጊዜ የመ​ከ​ራት ምክር መል​ካም አይ​ደ​ለ​ችም። ይች​ውም አን​ዲት ናት።”</verse>
				<verse number="8">ኩሲ ደግሞ አለ፥ “በሜዳ እን​ዳ​ለች አራስ ድብና እንደ ተኳር የዱር እሪያ በል​ባ​ቸው መራ​ሮ​ችና ኀያ​ላን መሆ​ና​ቸ​ውን አባ​ት​ህ​ንና ሰዎ​ቹን ታው​ቃ​ለህ፤ አባ​ትህ አር​በኛ ነው፤ ሕዝ​ቡ​ንም አያ​ሰ​ና​ብ​ትም።</verse>
				<verse number="9">በተ​ራ​ራው ላይ፥ ያም ባይ​ሆን በአ​ንድ ቦታ ተሰ​ው​ሮ​አ​ልና ከእ​ነ​ርሱ ፊተ​ኞቹ ቢወ​ድቁ የሚ​ሰ​ማው ሁሉ አቤ​ሴ​ሎ​ምን የተ​ከ​ተለ ሕዝብ ተመታ ይላል።</verse>
				<verse number="10">እርሱ ኀይ​ለኛ ሰው ነውና፥ ልቡም እንደ አን​በሳ ልብ ፈጽሞ ይና​ደ​ዳ​ልና፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አባ​ትህ ጽኑዕ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉት ስዎች ኀያ​ላን እንደ ሆኑ ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="11">እኔ እን​ዲህ እመ​ክ​ር​ሃ​ለሁ፤ ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ያሉ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ብዛ​ታ​ቸው እንደ ባሕር አሸዋ ሆኖ ወደ አንተ ይሰ​ብ​ሰቡ፤ አን​ተም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ትሄ​ዳ​ለህ።</verse>
				<verse number="12">እር​ሱ​ንም ወደ​ም​ና​ገ​ኝ​በት ወደ አንድ ስፍራ እን​ደ​ር​ስ​በ​ታ​ለን፤ ጠልም በም​ድር ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ድቅ እን​ወ​ር​ድ​በ​ታ​ለን፤ እር​ሱ​ንና ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉ ሰዎ​ችን ሁሉ አንድ ስንኳ አና​ስ​ቀ​ርም።</verse>
				<verse number="13">ወደ ከተ​ማም ቢገባ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ወደ​ዚ​ያች ከተማ ገመድ ይወ​ስ​ዳሉ፤ እኛም አንድ ድን​ጋይ እን​ኳን እስ​ከ​ማ​ይ​ገ​ኝ​ባት ድረስ ወደ ወንዙ ውስጥ እን​ስ​ባ​ታ​ለን።”</verse>
				<verse number="14">አቤ​ሴ​ሎ​ምና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ “የአ​ር​ካ​ዊው የኩሲ ምክር ከአ​ኪ​ጢ​ፌል ምክር ይሻ​ላል” አሉ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ቤ​ሴ​ሎም ላይ ክፉ ያመጣ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካ​ሚ​ቱን የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልን ምክር እን​ዲ​በ​ትን አዘዘ።</verse>
				<verse number="15">አር​ካ​ዊው ኩሲም ለካ​ህ​ናቱ ለሳ​ዶ​ቅና ለአ​ብ​ያ​ታር፥ “አኪ​ጦ​ፌል ለአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምና ለእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች እን​ዲ​ህና እን​ዲህ መክ​ሮ​አል፤ እኔ ግን እን​ዲ​ህና እን​ዲያ መክ​ሬ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">አሁን እን​ግ​ዲህ ንጉ​ሡና ከእ​ርሱ ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ እን​ዳ​ይ​ዋጡ፥ ሳት​ዘ​ገይ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገር እንጂ በዚ​ህች ሌሊት በም​ድረ በዳ ውስጥ በሜ​ዳው አት​ደር ብለው ለዳ​ዊት ይነ​ግ​ሩት ዘንድ ፈጥ​ና​ችሁ ላኩ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">ዮና​ታ​ንና አኪ​ማ​ሆ​ስም በሮ​ጌል ምንጭ አጠ​ገብ ቆመው ሳለ አን​ዲት ብላ​ቴና ሄዳ ነገ​ረ​ቻ​ቸው፤ ወደ ከተማ መግ​ባት አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ውም ነበ​ርና፤ እነ​ር​ሱም ሄደው ለን​ጉሡ ለዳ​ዊት ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="18">አንድ ብላ​ቴ​ናም አይቶ ለአ​ቤ​ሴ​ሎም ነገ​ረው፤ እነ​ርሱ ግን ፈጥ​ነው ሄዱ፤ ወደ ባው​ሪ​ምም ወደ አንድ ሰው ቤት መጡ፤ በግ​ቢ​ውም ውስጥ ጕድ​ጓድ ነበ​ረው፤ ወደ​ዚ​ያም ውስጥ ወረዱ፤</verse>
				<verse number="19">ሴቲ​ቱም ዳውጃ ወስዳ በጕ​ድ​ጓዱ አፍ ላይ ዘረ​ጋ​ች​በት፤ የተ​ፈ​ተገ እህ​ልም በላዩ አሰ​ጣ​ች​በት፤ ያወ​ቃ​ቸ​ውም የለም።</verse>
				<verse number="20">የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም አገ​ል​ጋ​ዮች ወደ ሴቲቱ ወደ ቤት መጥ​ተው፥ “አኪ​ማ​ሆ​ስና ዮና​ታን የት አሉ?” አሉ፤ ሴቲ​ቱም፥ “ፈፋ​ውን ተሻ​ግ​ረው ሄዱ፤ ጥቂ​ትም ቀደ​ሙ​አ​ችሁ” አለ​ቻ​ቸው። እነ​ር​ሱም ፈል​ገው አጡ​አ​ቸው፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="21">ከሄ​ዱም በኋላ እነ​ርሱ ከጕ​ድ​ጓዱ ወጥ​ተው ሄዱ፤ ለን​ጉ​ሡም ለዳ​ዊት ነገ​ሩት፤ ዳዊ​ት​ንም፥ “አኪ​ጦ​ፌል በእ​ና​ንተ ላይ እን​ዲህ መክ​ሮ​አ​ልና ተነሡ፤ ፈጥ​ና​ች​ሁም ውኃ​ውን ተሻ​ገሩ” አሉት።</verse>
				<verse number="22">ዳዊ​ትና ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ሁሉ ተነ​ሥ​ተው ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ፤ እስ​ኪ​ነ​ጋም ድረስ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ሳይ​ሻ​ገር አንድ ሰው እን​ኳን አል​ቀ​ረም።</verse>
				<verse number="23">አኪ​ጦ​ፌ​ልም ምክሩ እን​ዳ​ል​ሠራ ባየ ጊዜ አህ​ያ​ውን ጫነ፤ ተነ​ሥ​ቶም ወደ ቤቱ ወደ ከተ​ማው ሄደ፤ ቤቱ​ንም አደ​ራ​ጅቶ በገዛ እጁ ታንቆ ሞተ፤ በአ​ባ​ቱም መቃ​ብር ተቀ​በረ።</verse>
				<verse number="24">ዳዊ​ትም ወደ ምና​ሄም መጣ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ ከእ​ርሱ ጋር የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ።</verse>
				<verse number="25">አቤ​ሴ​ሎ​ምም በሠ​ራ​ዊቱ ላይ በኢ​ዮ​አብ ስፍራ አሜ​ሳ​ይን ሾመ፤ አሜ​ሳ​ይም የኢ​ዮ​አ​ብን እናት የሶ​ር​ህ​ያን እኅት የነ​ዓ​ሶ​ንን ልጅ አቢ​ግ​ያን የአ​ገ​ባው የኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው የዮ​ቶር ልጅ ነበር።</verse>
				<verse number="26">እስ​ራ​ኤ​ልና አቤ​ሴ​ሎ​ምም በገ​ለ​ዓድ ምድር ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="27">ዳዊ​ትም ወደ ምና​ሄም በመጣ ጊዜ በአ​ሞን ልጆች ሀገር በአ​ራ​ቦት የነ​በረ የነ​ዓ​ሶን ልጅ ኡኤ​ሴብ፥ የሎ​ዶ​ባ​ርም ሰው የአ​ሜ​ሄል ልጅ ማኪር፥ የሮ​ጌ​ሌ​ምም ሰው ገለ​ዓ​ዳ​ዊው ቤር​ዜሊ፥</verse>
				<verse number="28">ዐሥር አል​ጋ​ዎ​ችና ምን​ጣ​ፎች፥ ዐሥ​ርም ጋኖ​ችና ፊቀ​ኖች፥ የስ​ን​ዴና የገ​ብስ ዱቄት፥ ስልቅ አተ​ርና ምስር፥</verse>
				<verse number="29">ማርና ቅቤ፥ በግና ላም ይበሉ ዘንድ ለዳ​ዊ​ትና ከእ​ርሱ ጋር ላሉ ሰዎች አመጡ። ሕዝቡ በም​ድረ በዳ ተር​በ​ውና ተጠ​ም​ተው ደክ​መው ነበ​ርና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ቈጠረ፤ የሻ​ለ​ቆ​ች​ንና የመቶ አለ​ቆ​ች​ንም በላ​ያ​ቸው ሾመ።</verse>
				<verse number="2">ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡን ከኢ​ዮ​አብ እጅ በታች ሢሶ​ውን፥ ከኢ​ዮ​አ​ብም ወን​ድም ከሶ​ር​ህያ ልጅ ከአ​ቢሳ እጅ በታች ሢሶ​ውን፥ ከጌት ሰውም ከኤቲ እጅ በታች ሢሶ​ውን ላከ። ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡን፥ “እኔ ደግሞ ከእ​ና​ንተ ጋር እወ​ጣ​ለሁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">እነ​ርሱ ግን “አንተ ከእኛ ከሁ​ላ​ችን ይልቅ እንደ ዐሥር ሽህ ሠራ​ዊት ስለ​ሆ​ንህ ብን​ሸሽ ልባ​ቸው አይ​ከ​ተ​ለ​ን​ምና፥ እኩ​ሌ​ታ​ች​ንም ብን​ሞት ልባ​ቸው አይ​ከ​ተ​ለ​ን​ምና አት​ውጣ፤ አሁ​ንም መር​ዳ​ትን ትረ​ዳን ዘንድ በከ​ተማ ብት​ኖ​ር​ልን ይሻ​ለ​ናል” አሉት።</verse>
				<verse number="4">ንጉ​ሡም፥ “በፊ​ታ​ችሁ መል​ካም የሚ​መ​ስ​ላ​ች​ሁን አደ​ር​ጋ​ለሁ” አላ​ቸው። ንጉ​ሡም በበሩ አጠ​ገብ ቆመ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ መቶ በመቶ፥ ሺህ በሺህ እየ​ሆኑ ወጡ።</verse>
				<verse number="5">ንጉ​ሡም ኢዮ​አ​ብ​ንና አቢ​ሳን ኤቲ​ንም፥ “ለብ​ላ​ቴ​ናው ለአ​ቤ​ሴ​ሎም ስለ እኔ ራሩ​ለት” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው። ንጉ​ሡም ስለ አቤ​ሴ​ሎም አለ​ቆ​ቹን ሁሉ ሲያ​ዝዝ ሕዝቡ ሁሉ ሰሙ።</verse>
				<verse number="6">ሕዝ​ቡም ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ወደ በረሓ ወጡ፤ በኤ​ፍ​ሬ​ምም በረሓ ተዋ​ጓ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">በዚ​ያም የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ በዳ​ዊት አገ​ል​ጋ​ዮች ፊት ወደቁ፤ በዚ​ያም ቀን ታላቅ ውጊያ በዚያ ሆነ፤ ሃያ ሺህ ሰዎ​ችም ሞቱ።</verse>
				<verse number="8">ከዚ​ያም ጦሩ በሀ​ገሩ ሁሉ ፊት ተበ​ተነ፤ በዚ​ያም ቀን በሰ​ይፍ ከተ​ገ​ደ​ሉት ሕዝብ ይልቅ በበ​ረሓ የሞቱ ይበ​ዛሉ።</verse>
				<verse number="9">አቤ​ሴ​ሎ​ምም ከዳ​ዊት አገ​ል​ጋ​ዮች ጋር ተገ​ናኘ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም በበ​ቅሎ ተቀ​ምጦ ነበር፤ በቅ​ሎ​ውም ብዙ ቅር​ን​ጫፍ ባለው በታ​ላቅ ዛፍ በታች ገባ፤ ራሱም በዛፉ ተያዘ፤ በሰ​ማ​ይና በም​ድ​ርም መካ​ከል ተን​ጠ​ለ​ጠለ፤ ተቀ​ም​ጦ​በ​ትም የነ​በ​ረው በቅሎ በበ​ታቹ አለፈ።</verse>
				<verse number="10">አንድ ሰውም አይቶ፥ “እነሆ፥ አቤ​ሴ​ሎም በዛፍ ላይ ተን​ጠ​ል​ጥሎ አየሁ” ብሎ ለኢ​ዮ​አብ ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="11">ኢዮ​አ​ብም ለነ​ገ​ረው ሰው፥ “እነሆ፥ ካየ​ኸው ለምን በም​ድር ላይ አል​ገ​ደ​ል​ኸ​ውም? ዐሥር ብርና አንድ ድግ እሰ​ጥህ ነበር” አለው።</verse>
				<verse number="12">ሰው​የ​ውም ኢዮ​አ​ብን፥ “ንጉሡ አን​ተ​ንና አቢ​ሳን፥ ኤቲ​ንም፦ ብላ​ቴ​ና​ውን አቤ​ሴ​ሎ​ምን ጠብቁ ብሎ ሲያዝ እኛ በጆ​ሮ​አ​ችን ሰም​ተ​ና​ልና ሺህ ሰቅል ብር በእጄ ላይ ብት​መ​ዝን እጄን በን​ጉሡ ልጅ ላይ አል​ዘ​ረ​ጋም ነበር።</verse>
				<verse number="13">እኔም በሰ​ው​ነቱ ላይ ክፉ ነገር ባደ​ርግ ነገሩ በን​ጉሡ ዘንድ ባል​ተ​ሰ​ወ​ረም ነበር፤ አን​ተም በተ​ነ​ሣ​ህ​ብኝ ነበር” አለው።</verse>
				<verse number="14">ኢዮ​አ​ብም፥ “እኔ ከአ​ንተ ጋር እን​ዲህ እዘ​ገይ ዘንድ አል​ች​ልም” ብሎ ሦስት ጦሮች በእጁ ወሰደ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም ገና በዛፍ ላይ ተን​ጠ​ል​ጥሎ ሕያው ሳለ በልቡ ላይ ተከ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">ዐሥ​ሩም የኢ​ዮ​አብ ጋሻ ጃግ​ሬ​ዎች ከበ​ቡት፤ አቤ​ሴ​ሎ​ም​ንም መት​ተው ገደ​ሉት።</verse>
				<verse number="16">ኢዮ​አ​ብም ሕዝ​ቡን ስለ ራራ​ላ​ቸው መለ​ከት አስ​ነፋ፤ ሕዝ​ቡም እስ​ራ​ኤ​ልን ተከ​ት​ለው እን​ዳ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ቸው መለ​ሳ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">አቤ​ሴ​ሎ​ም​ንም ወስዶ በበ​ረሓ ባለ በታ​ላቅ ገደል ውስጥ ጣለው፤ እጅ​ግም ታላቅ የሆነ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመ​ረ​በት፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ሸሽ​ተው ወደ ድን​ኳ​ና​ቸው ገቡ።</verse>
				<verse number="18">አቤ​ሴ​ሎ​ምም በሕ​ይ​ወቱ ሳለ፥ “ለስሜ መታ​ሰ​ቢያ የሚ​ሆን ልጅ የለ​ኝም” ብሎ ሐው​ልት ወስዶ በን​ጉሥ ሸለቆ ውስጥ ለራሱ በስሙ አቁሞ ነበር፤ ያችም ሐው​ልት እስከ ዛሬ ድረስ “እደ አቤ​ሴ​ሎም” ተብላ ትጠ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="19">የሳ​ዶቅ ልጅ አኪ​ማ​ሖስ ግን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጠ​ላ​ቶቹ እጅ እንደ ፈረ​ደ​ለት ፈጥኜ ሄጄ ለን​ጉሥ የም​ሥ​ራች ልን​ገ​ርን?” አለ።</verse>
				<verse number="20">ኢዮ​አ​ብም፥ “አንተ በዚች ቀን የም​ሥ​ራች የም​ት​ና​ገር ሰው አይ​ደ​ለ​ህም፤ ወሬ​ውን በሌላ ቀን ትና​ገ​ራ​ለህ፤ በዚች ቀን ግን የን​ጉሡ ልጅ እንደ ሞተ ወሬ አት​ና​ገ​ርም” አለው።</verse>
				<verse number="21">ኢዮ​አ​ብም ኩሲን፥ “ሂድ፤ ያየ​ኸ​ው​ንም ሁሉ ለን​ጉሥ ንገር” አለው። ኩሲም ለኢ​ዮ​አብ ሰግዶ ወጣ።</verse>
				<verse number="22">ዳግ​መ​ኛም የሳ​ዶቅ ልጅ አኪ​ማ​ሖስ ኢዮ​አ​ብን፥ “የሆነ ሆኖ ኩሲን ተከ​ትዬ፥ እባ​ክህ ልሩጥ” አለው። ኢዮ​አ​ብም፥ “ልጄ ሆይ፥ ለምን ትሮ​ጣ​ለህ? ተመ​ለስ፤ ብት​ሄድ ይች ወሬ ለጥ​ቅም አት​ሆ​ን​ህ​ምና” አለ።</verse>
				<verse number="23">እር​ሱም፥ “እኔ ብሮጥ ምን ይገ​ድ​ዳል?” አለ። እር​ሱም፥ “ሩጥ” አለው። አኪ​ማ​ሖ​ስም በሰ​ርጥ ጎዳና በኩል ሮጠ፤ ኩሲ​ንም ቀደ​መው።</verse>
				<verse number="24">ዳዊ​ትም በሁ​ለት በር መካ​ከል ተቀ​ምጦ ነበር፤ ዘበ​ኛ​ውም በቅ​ጥሩ ላይ ወዳ​ለው ወደ በሩ ሰገ​ነት ወጣ፤ ዐይ​ኑ​ንም አቅ​ንቶ ብቻ​ውን የሚ​ሮጥ ሰው አየ።</verse>
				<verse number="25">ዘበ​ኛ​ውም ለን​ጉሡ ሊነ​ግ​ረው ጮኸ። ንጉ​ሡም፥ “ብቻ​ውን እንደ ሆነ በአፉ ወሬ ይኖ​ራል” አለ። እር​ሱም ፈጥኖ ቀረበ።</verse>
				<verse number="26">ዘበ​ኛ​ውም ሌላ ሰው ሲሮጥ አየ፤ ዘበ​ኛ​ውም ለደጅ ጠባ​ቂው ጮኾ፥ “እነሆ፥ ብቻ​ውን የሚ​ሮጥ ሌላ ሰው አየሁ” አለ። ንጉ​ሡም፥ “እርሱ ደግሞ ወሬ ይዞ ይሆ​ናል” አለ።</verse>
				<verse number="27">ዘበ​ኛ​ውም፥ “የፊ​ተ​ኛው ሩጫ እንደ ሳዶቅ ልጅ እንደ አኪ​ማ​ሖስ ሩጫ ይመ​ስ​ላል” አለ፤ “ንጉ​ሡም፦ እርሱ መል​ካም ሰው ነው፤ መል​ካ​ምም ወሬ ያመ​ጣል” አለ።</verse>
				<verse number="28">አኪ​ማ​ሖ​ስም ጮኾ ንጉ​ሡን፥ “ሰላም ለአ​ንተ ይሁን!” አለው። በን​ጉ​ሡም ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ሰግዶ፥ “በን​ጉሡ በጌ​ታዬ ላይ እጃ​ቸ​ውን ያነ​ሡ​ትን ሰዎች አሳ​ልፎ የሰጠ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን” አለ።</verse>
				<verse number="29">ንጉ​ሡም፥ “ብላ​ቴ​ናው አቤ​ሴ​ሎም ደኅና ነውን?” አለ። አኪ​ማ​ሖ​ስም፥ “ኢዮ​አብ እኔን ባሪ​ያ​ህ​ንና የን​ጉ​ሡን ባሪያ በላከ ጊዜ ብዙ ሰዎ​ችን አይ​ቻ​ለሁ፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላ​ወ​ቅ​ሁም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።</verse>
				<verse number="30">ንጉ​ሡም፥ “ፈቀቅ ብለህ ቁም” አለ፤ እር​ሱም ፈቀቅ ብሎ ቆመ።</verse>
				<verse number="31">እነ​ሆም፥ ኩሲ መጣ፤ ኩሲም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላ​ይህ የተ​ነ​ሡ​ትን ሁሉ ዛሬ እንደ ተበ​ቀ​ለ​ልህ ለጌ​ታዬ ለን​ጉሡ ወሬ አም​ጥ​ቻ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="32">ንጉ​ሡም ኩሲን፥ “ብላ​ቴ​ናው አቤ​ሴ​ሎም ደኅና ነውን?” አለው። ኩሲም፥ “የጌ​ታዬ የን​ጉሡ ጠላ​ቶች፥ በክ​ፉም የተ​ነ​ሡ​ብህ ሁሉ እን​ደ​ዚያ ብላ​ቴና ይሁኑ” ብሎ መለ​ሰ​ለት።</verse>
				<verse number="33">ንጉ​ሡም እጅግ ደነ​ገጠ፤ በበ​ሩም ላይ ወዳ​ለ​ችው ሰገ​ነት ወጥቶ አለ​ቀሰ፤ ሲሄ​ድም፥ “ልጄ አቤ​ሴ​ሎም ሆይ፥ ልጄ፥ ልጄ አቤ​ሴ​ሎም ሆይ፥ በአ​ንተ ፋንታ እኔ እን​ድ​ሞት ቤዛ​ህም እን​ድ​ሆን ማን ባደ​ረ​ገኝ፥ ልጄ አቤ​ሴ​ሎም፥ ልጄ ሆይ፥” ይል ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">ለኢ​ዮ​አብ፥ “ንጉሡ ስለ አቤ​ሴ​ሎም ያዝ​ናል፤ ያለ​ቅ​ሳ​ልም” ብለው ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="2">በዚ​ያም ቀን፥ “ንጉሡ ስለ ልጁ አዘነ” ሲባል ሕዝቡ ሰም​ቶ​አ​ልና በዚ​ያው ቀን ሕይ​ወት በሕ​ዝቡ ሁሉ ዘንድ ወደ ኀዘን ተለ​ወጠ።</verse>
				<verse number="3">ከሰ​ልፍ በሸሸ ጊዜ ያፈረ ሕዝብ ተሰ​ርቆ እን​ደ​ሚ​ገባ በዚያ ቀን ሕዝቡ ተሰ​ር​ቀው ወደ ከተማ ገቡ።</verse>
				<verse number="4">ንጉ​ሡም ፊቱን ሸፈነ፤ ንጉ​ሡም በታ​ላቅ ድምፅ፥ “ልጄ አቤ​ሴ​ሎም፥ አቤ​ሴ​ሎም፥ ልጄ” እያለ ይጮህ ነበር።</verse>
				<verse number="5">ኢዮ​አ​ብም ወደ ንጉሡ ወደ ቤት ገብቶ እን​ዲህ አለ፥ “ዛሬ ነፍ​ስ​ህ​ንና የወ​ን​ዶ​ች​ንና የሴ​ቶች ልጆ​ች​ህን ነፍስ፥ የሚ​ስ​ቶ​ች​ህ​ንና የቁ​ባ​ቶ​ች​ህን ነፍስ ያዳ​ኑ​ትን የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን ሁሉ ፊት በዚች ቀን አሳ​ፍ​ረ​ሃል።</verse>
				<verse number="6">አንተ የሚ​ጠ​ሉ​ህን ትወ​ድ​ዳ​ለህ፤ የሚ​ወ​ድ​ዱ​ህ​ንም ትጠ​ላ​ለህ፤ አለ​ቆ​ች​ህና አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እን​ደ​ማ​ይ​ጠ​ቅ​ሙህ እን​ደ​ም​ታ​ስብ ዛሬ ገል​ጠ​ሃ​ልና፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም ድኖ ቢሆን ዛሬ እኛ ሁላ​ችን እን​ሞት እንደ ነበር አው​ቃ​ለሁ። ይህ በፊ​ትህ ላንተ ቀና ነበ​ረና።</verse>
				<verse number="7">አሁ​ንም ተነ​ሥ​ተህ ወጥ​ተህ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በል​ባ​ቸው የሚ​ገባ ነገር ንገ​ራ​ቸው። ዛሬ ወደ እነ​ርሱ ካል​ወ​ጣህ በዚች ሌሊት አንድ ሰው ስንኳ ከአ​ንተ ጋር የሚ​ያ​ድር እን​ዳ​ይ​ኖር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እም​ላ​ለሁ፤ ከሕ​ፃ​ን​ነ​ትህ ጀምሮ እስ​ከ​ዚች ቀን ድረስ ካገ​ኘህ መከራ ሁሉ ዛሬ የም​ታ​ገ​ኝህ መከራ እን​ድ​ት​ከ​ፋ​ብህ እን​ግ​ዲህ አንተ ለራ​ስህ ዕወቅ” አለው።</verse>
				<verse number="8">ንጉ​ሡም ተነ​ሥቶ በበሩ ተቀ​መጠ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ንጉሡ በበሩ ተቀ​ም​ጧል ብለው ተና​ገሩ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በበሩ ወደ ንጉሡ ፊት ወጡ። እስ​ራ​ኤ​ልም እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ድን​ኳኑ ሸሽቶ ገብቶ ነበር።</verse>
				<verse number="9">ከመ​ላው ነገደ እስ​ራ​ኤል የተ​ሰ​በ​ሰቡ ሕዝብ፥ “ንጉሡ ዳዊት ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን እጅ ታድ​ጎ​ናል፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ አድ​ኖ​ናል፤ አሁ​ንም ስለ አቤ​ሴ​ሎም ከሀ​ገ​ሩና ከመ​ን​ግ​ሥቱ ሸሸ።</verse>
				<verse number="10">በላ​ያ​ችን ላይ የቀ​ባ​ነው አቤ​ሴ​ሎ​ምም በጦ​ር​ነት ሞቶ​አል፤ አሁ​ንም ንጉ​ሡን ለመ​መ​ለስ ስለ​ምን ዝም ትላ​ላ​ችሁ?” አሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቃል ወደ ንጉሥ ደረሰ።</verse>
				<verse number="11">ንጉሡ ዳዊ​ትም ለካ​ህ​ናቱ ለሳ​ዶ​ቅና ለአ​ብ​ያ​ታር ልኮ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ለይ​ሁዳ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች እን​ዲህ ብላ​ችሁ ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው፦ የእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ነገር ወደ ንጉሡ ደር​ሶ​አ​ልና ንጉ​ሡን ወደ ቤቱ ከመ​መ​ለስ ስለ​ምን ዘገ​ያ​ችሁ?</verse>
				<verse number="12">እና​ንተ ወን​ድ​ሞች፥ የአ​ጥ​ንቴ ፍላ​ጭና የሥ​ጋዬ ቍራጭ ናችሁ፤ እና​ንተ ንጉ​ሡን ወደ ቤቱ ከመ​መ​ለስ ስለ​ምን ዘገ​ያ​ችሁ?</verse>
				<verse number="13">ለአ​ሚ​ሳ​ይም፦ አንተ የአ​ጥ​ንቴ ፍላ​ጭና የሥ​ጋዬ ቍራጭ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? በዘ​መ​ን​ህም ሁሉ በኢ​ዮ​አብ ፋንታ በፊቴ የሠ​ራ​ዊት አለቃ ሳት​ሆን ብት​ቀር ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ያድ​ር​ግ​ብኝ፤ ይህ​ንም ይጨ​ም​ር​ብኝ በሉት።”</verse>
				<verse number="14">የይ​ሁ​ዳ​ንም ሰዎች ሁሉ ልብ እንደ አንድ ሰው ልብ አድ​ርጎ አዘ​ነ​በለ፤ ወደ ንጉ​ሡም፥ “አን​ተና ብላ​ቴ​ኖ​ችህ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህም ሁሉ ተመ​ለሱ” ብለው ላኩ​በት።</verse>
				<verse number="15">ንጉ​ሡም ተመ​ልሶ እስከ ዮር​ዳ​ኖስ ድረስ መጣ። የይ​ሁዳ ሰዎ​ችም ንጉ​ሡን ሊቀ​በሉ፥ ንጉ​ሡ​ንም ዮር​ዳ​ኖ​ስን ሊያ​ሻ​ግሩ ወደ ጌል​ገላ መጡ።</verse>
				<verse number="16">ከባ​ው​ሪም ሀገር የነ​በ​ረው የኢ​ያ​ሚን ልጅ የጌራ ልጅ ሳሚም ከይ​ሁዳ ሰዎች ጋር ንጉሥ ዳዊ​ትን ሊቀ​በል ፈጥኖ ወረደ።</verse>
				<verse number="17">ከእ​ር​ሱም ጋራ ከብ​ን​ያም ወገን የሆኑ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤ የሳ​ኦ​ልም ቤት አገ​ል​ጋይ ሲባ ከእ​ር​ሱም ጋር ዐሥራ አም​ስቱ ልጆ​ቹና ሃያው አገ​ል​ጋ​ዮቹ ነበሩ፤ በን​ጉ​ሡም ፊት በቀ​ጥታ ወደ ዮር​ዳ​ኖስ ሄዱ።</verse>
				<verse number="18">ንጉ​ሡ​ንም የማ​ሻ​ገር ሥራ ሠሩ። የን​ጉ​ሡ​ንም ቤተ ሰብእ ያነሡ ዘንድ፥ በፊ​ቱም የቀና ሥራን ይሠሩ ዘንድ ወደ ማዶ ተሻ​ገሩ። ንጉ​ሡም ዮር​ዳ​ኖ​ስን ከተ​ሻ​ገረ በኋላ የጌራ ልጅ ሳሚ በን​ጉሡ ፊት፦ በግ​ን​ባሩ ወደቀ።</verse>
				<verse number="19">እር​ሱም ንጉ​ሡን አለው፥ “ጌታዬ! ኀጢ​አ​ቴን አት​ቍ​ጠ​ር​ብኝ፤ ጌታዬ ንጉሡ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በወ​ጣህ ቀን ባሪ​ያህ የበ​ደ​ል​ሁ​ህን አታ​ስ​ብ​ብኝ፤ ጌታዬ ንጉ​ሡም በል​ብህ አታ​ኑ​ር​ብኝ።</verse>
				<verse number="20">እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ በደ​ለኛ እንደ ሆንሁ አው​ቄ​አ​ለ​ሁና እነሆ፥ ከዮ​ሴፍ ቤት ሁሉ አስ​ቀ​ድሜ ዛሬ መጣሁ፤ ጌታ​ዬ​ንም ንጉ​ሡን ልቀ​በል ወረ​ድሁ።”</verse>
				<verse number="21">የሶ​ር​ህያ ልጅ አቢሳ ግን፥ “ሳሚ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ባ​ውን ሰድ​ቦ​አ​ልና እን​ግ​ዲህ ሞት የተ​ገ​ባው አይ​ደ​ለ​ምን?” ብሎ መለሰ።</verse>
				<verse number="22">ዳዊ​ትም፥ “እና​ንተ የሶ​ር​ህያ ልጆች! ዛሬ ታስ​ቱኝ ዘንድ በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ምን አለኝ? ዛሬስ ከእ​ስ​ራ​ኤል የሚ​ሞት አንድ ሰው የለም። ዛሬስ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ እንደ ነገ​ሥሁ አላ​ው​ቅ​ምን?”</verse>
				<verse number="23">ንጉ​ሡም ሳሚን፥ “አት​ሞ​ትም” አለው። ንጉ​ሡም ማለ​ለት።</verse>
				<verse number="24">የሳ​ኦ​ልም የልጅ ልጅ ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ንጉ​ሡን ሊቀ​በል ወረደ፤ ንጉ​ሡም ከሄ​ደ​በት ቀን ጀምሮ በሰ​ላም እስከ ተመ​ለ​ሰ​በት ቀን ድረስ እግ​ሩን አላ​ነ​ጻም፤ ጥፍ​ሩ​ንም አል​ቈ​ረ​ጠም፤ ጢሙ​ንም አል​ላ​ጨም፤ ልብ​ሱ​ንም አላ​ጠ​በም ነበር።</verse>
				<verse number="25">ከዚ​ህም በኋላ ንጉ​ሡን ሊቀ​በ​ለው ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፥ “ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ፥ ከእኔ ጋር ስለ​ምን አል​ወ​ጣ​ህም?” አለው።</verse>
				<verse number="26">ሜም​ፌ​ቡ​ስ​ቴም አለ፥ “ጌታዬ፥ ንጉሥ፥ አገ​ል​ጋዬ አታ​ለ​ለኝ፥ እኔ ባሪ​ያህ አን​ካሳ ነኝና፦ ከን​ጉሡ ጋር እሄድ ዘንድ አህ​ያ​ዬን ጫን​ልኝ፤ እኔም እቀ​መ​ጥ​በ​ታ​ለሁ አል​ሁት።</verse>
				<verse number="27">እር​ሱም በእኔ በባ​ሪ​ያህ ላይ ክፉ አደ​ረገ፤ አንተ ጌታዬ ንጉሥ ግን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ነህ፤ በፊ​ት​ህም ደስ ያሰ​ኘ​ህን አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="28">የአ​ባቴ ቤት ሁሉ በጌ​ታዬ በን​ጉሥ ዘንድ ሞት የሚ​ገ​ባ​ቸው ነበሩ፤ አንተ ግን እኔን ባሪ​ያ​ህን በገ​በ​ታህ በሚ​በሉ መካ​ከል አስ​ቀ​መ​ጥ​ኸኝ፤ ለን​ጉሥ ደግሞ ለመ​ና​ገር ምን መብት አለኝ?”</verse>
				<verse number="29">ንጉ​ሡም፥ “ነገ​ር​ህን ለምን ታበ​ዛ​ለህ? አን​ተና ሲባ የሳ​ኦ​ልን እር​ሻ​ውን ትካ​ፈሉ ዘንድ ብያ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="30">ሜም​ፌ​ቡ​ስ​ቴም ንጉ​ሡን፥ “ጌታዬ ንጉሡ በደ​ኅና ወደ ቤቱ ከተ​መ​ለሰ እርሱ ሁሉን ይው​ሰ​ደው” አለው።</verse>
				<verse number="31">ገለ​ዓ​ዳ​ዊ​ውም ቤር​ዜሊ ከሮ​ግ​ሊም ወረደ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ሊሸ​ኘው ከን​ጉሡ ጋር ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገረ።</verse>
				<verse number="32">ቤር​ዜ​ሊም እጅግ ያረጀ የሰ​ማ​ንያ ዓመት ሽማ​ግሌ ነበረ፤ እጅ​ግም ትልቅ ሰው ነበ​ረና ንጉሡ በመ​ና​ሄም ሳለ ይቀ​ል​በው ነበር።</verse>
				<verse number="33">ንጉ​ሡም ቤር​ዜ​ሊን፥ “አንተ ከእኔ ጋር ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ራ​ለህ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ያረጀ ሰው​ነ​ት​ህን ከእኔ ጋር እጦ​ረ​ዋ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="34">ቤር​ዜ​ሊም ንጉ​ሡን አለው፥ “ከን​ጉሡ ጋር ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እወጣ ዘንድ ከሕ​ይ​ወቴ ዘመን ምን ያህል ቀረኝ?</verse>
				<verse number="35">ዛሬ የሰ​ማ​ንያ ዓመት ሽማ​ግሌ ነኝ፥ መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ውን መለ​የት እች​ላ​ለ​ሁን? እኔ ባሪ​ያህ የም​በ​ላ​ው​ንና የም​ጠ​ጣ​ውን ጣዕ​ሙን መለ​የት እች​ላ​ለ​ሁን? የወ​ን​ዱ​ንና የሴ​ቲ​ቱን ዘፈን ድምፅ መስ​ማ​ትስ እች​ላ​ለ​ሁን? እኔ ባሪ​ያህ በጌ​ታዬ በን​ጉሡ ላይ ለምን እከ​ብ​ድ​ብ​ሃ​ለሁ?</verse>
				<verse number="36">እኔ ባሪ​ያህ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግሬ ከን​ጉሡ ጋር ጥቂት ልሄድ ነበር፤ ንጉሡ እን​ዲህ ያለ ወረታ ለምን ይመ​ል​ስ​ል​ኛል?</verse>
				<verse number="37">እኔ ባሪ​ያህ ተመ​ልሼ በከ​ተ​ማዬ በአ​ባ​ቴና በእ​ናቴ መቃ​ብር አጠ​ገብ እባ​ክህ! ልሙት፤ ነገር ግን ባሪ​ያህ ከመ​ዓም ከጌ​ታዬ ከን​ጉሡ ጋር ይሻ​ገር፤ በዐ​ይ​ኖ​ችህ ፊት ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህ​ንም ለእ​ርሱ አድ​ርግ።”</verse>
				<verse number="38">ንጉ​ሡም፥ “ከመ​ዓም ከእኔ ጋር ይሻ​ገር፤ በፊቴ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ኝ​ንም አደ​ር​ግ​ለ​ታ​ለሁ፤ አን​ተም ከእኔ የም​ት​ሻ​ውን ነገር ሁሉ አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="39">ሕዝ​ቡም ሁሉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ፤ ንጉ​ሡም ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገረ፤ ንጉ​ሡም ቤር​ዜ​ሊን አቅፎ ሳመው፤ መረ​ቀ​ውም፤ ወደ ስፍ​ራ​ውም ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="40">ንጉ​ሡም ወደ ጌል​ገላ ተሻ​ገረ፤ ከመ​ዓ​ምም ከእ​ርሱ ጋር ተሻ​ገረ፤ የይ​ሁ​ዳም ሕዝብ ሁሉ፥ ደግ​ሞም የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ እኩ​ሌታ ከን​ጉሡ ጋር ተሻ​ገሩ።</verse>
				<verse number="41">እነ​ሆም፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ መጡ፤ ንጉ​ሡ​ንም፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን የይ​ሁዳ ሰዎች ለምን ሰረ​ቁህ? ንጉ​ሡ​ንም ቤተ ሰቡ​ንም ዮር​ዳ​ኖ​ስን አሻ​ገሩ። የዳ​ዊ​ትም ሰዎች ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ” አሉት።</verse>
				<verse number="42">የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች መል​ሰው፥ “ንጉሡ ለእኛ ቅር​ባ​ችን ነው፤ ስለ​ምን በዚህ ነገር ትቈ​ጣ​ላ​ችሁ? በውኑ ከን​ጉሡ አን​ዳች በል​ተ​ና​ልን? ወይስ እርሱ በረ​ከት ሰጥ​ቶ​ና​ልን? ወይስ ጭፍራ አድ​ርጎ ሾመ​ንን?” አሉ።</verse>
				<verse number="43">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ለይ​ሁዳ ሰዎች መል​ሰው፥ “በን​ጉሡ ዘንድ ለእኛ ዐሥር ክፍል አለን፤ ከእ​ና​ን​ተም እኛ እን​ቀ​ድ​ማ​ለን፤ እኛም በኵር ነን፤ ለዳ​ዊ​ትም ከእ​ና​ንተ እኛ እን​ቀ​ር​ባ​ለን፤ ስለ​ምን ናቃ​ች​ሁን? ንጉ​ሡ​ንስ እን​መ​ል​ሰው ዘንድ ከእ​ና​ንተ የእኛ ቃል አይ​ቀ​ድ​ም​ምን?” አሏ​ቸው። የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ቃል ከእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ቃል ይልቅ ጠነ​ከረ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">በዚ​ያም አንድ ብን​ያ​ማዊ የቢ​ኮሪ ልጅ ስሙ ሳቡሄ የሚ​ባል የዐ​መፅ ልጅ የሆነ ሰው ነበረ፤ እር​ሱም፥ “ከዳ​ዊት ዘንድ እድል ፋንታ የለ​ንም፦ ከእ​ሴ​ይም ልጅ ዘንድ ርስት የለ​ንም፤ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እያ​ን​ዳ​ን​ድህ ወደ ድን​ኳ​ንህ ተመ​ለስ” ብሎ መለ​ከት ነፋ።</verse>
				<verse number="2">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ከዳ​ዊት ተለ​ይ​ተው የቢ​ኮሪ ልጅ ሳቡ​ሄን ተከ​ት​ለው ሄዱ፤ የይ​ሁዳ ሰዎች ግን ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ጀም​ረው ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እስ​ኪ​ደ​ርሱ ንጉ​ሣ​ቸ​ውን ተከ​ተሉ።</verse>
				<verse number="3">ዳዊ​ትም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ቤቱ መጣ፤ ንጉ​ሡም ቤቱን ሊጠ​ብቁ የተ​ዋ​ቸ​ውን ዐሥ​ሩን ቁባ​ቶች ወስዶ ለጠ​ባቂ ሰጣ​ቸው፤ ቀለ​ብም ሰጣ​ቸው፤ ነገር ግን ወደ እነ​ርሱ አል​ገ​ባም፤ በቤ​ትም ተዘ​ግ​ተው እስ​ኪ​ሞቱ ድረስ መበ​ለ​ቶች ሆነው ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="4">ንጉ​ሡም አሜ​ሳ​ይን፥ “የይ​ሁ​ዳን ሰዎች ሁሉ በሦ​ስት ቀን ውስጥ ጥራ​ልኝ፤ አን​ተም አብ​ረህ በዚህ ሁን” አለው።</verse>
				<verse number="5">አሜ​ሳ​ይም የይ​ሁ​ዳን ሰዎች ሁሉ ይጠራ ዘንድ ሄደ፤ ነገር ግን ዳዊት የቀ​ጠ​ረ​ውን ቀን አሳ​ልፎ ዘገየ።</verse>
				<verse number="6">ዳዊ​ትም አቢ​ሳን፥ “አሁን አቤ​ሴ​ሎም ከአ​ደ​ረ​ገ​ብን ይልቅ የከፋ የሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ብን የቢ​ኮሪ ልጅ ሳቡሄ ነው፤ እርሱ የተ​መ​ሸ​ጉ​ትን ከተ​ሞች አግ​ኝቶ ከዐ​ይ​ና​ችን እን​ዳ​ይ​ሰ​ወር፥ አንተ የጌ​ታ​ህን ብላ​ቴ​ኖች ወስ​ደህ አሳ​ድ​ደው” አለው።</verse>
				<verse number="7">አቢ​ሳና የኢ​ዮ​አብ ሰዎች ከሊ​ታ​ው​ያ​ንም፥ ፈሊ​ታ​ው​ያ​ንም፥ ኀያ​ላ​ኑም ሁሉ ወጥ​ተው ተከ​ተ​ሉት፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወጥ​ተው የቢ​ኮሪ ልጅ ሳቡ​ሄን አሳ​ደ​ዱት።</verse>
				<verse number="8">በገ​ባ​ዖ​ንም ወዳ​ለው ወደ ታላቁ ድን​ጋይ በደ​ረሱ ጊዜ አሜ​ሳይ በፊ​ታ​ቸው መጣ፤ ኢዮ​አ​ብም የሰ​ልፍ ልብስ ለብሶ ነበር፤ በላ​ዩም መታ​ጠ​ቂያ ነበረ፤ በወ​ገ​ቡም ላይ ሰገባ ያለው ሰይፍ ታጥቆ ነበር፤ እር​ሱም ሲራ​መድ ሰይፉ ወደቀ።</verse>
				<verse number="9">ኢዮ​አ​ብም አሜ​ሳ​ይን፥ “ወን​ድሜ ሆይ፥ ደኅና ነህን?” አለው፤ ኢዮ​አ​ብም አሜ​ሳ​ይን የሚ​ስም መስሎ በቀኝ እጁ ጢሙን ያዘው።</verse>
				<verse number="10">አሜ​ሳይ ግን በኢ​ዮ​አብ እጅ ከነ​በ​ረው ሰይፍ አል​ተ​ጠ​ነ​ቀ​ቀም ነበር፤ ኢዮ​አ​ብም ሆዱን ወጋው፤ አን​ጀ​ቱ​ንም በም​ድር ላይ ዘረ​ገ​ፈው፤ ሁለ​ተ​ኛም አል​ወ​ጋ​ውም፤ ሞተም። ኢዮ​አ​ብና ወን​ድሙ አቢ​ሳም የቢ​ኮ​ሪን ልጅ ሳቡ​ሄን አሳ​ደዱ።</verse>
				<verse number="11">ከኢ​ዮ​አ​ብም ብላ​ቴ​ኖች አንዱ በአ​ሜ​ሳይ ሬሳ አጠ​ገብ ቆሞ፥ “ኢዮ​አብ የሚ​ፈ​ል​ገው ምን​ድን ነው? የዳ​ዊ​ትም የሆኑ ኢዮ​አ​ብን የሚ​ከ​ተሉ እነ​ማን ናቸው?” አለ።</verse>
				<verse number="12">አሜ​ሳ​ይም በደም ተነ​ክሮ በመ​ን​ገድ መካ​ከል ወድቆ ነበር፤ ያም ሰው ወደ እርሱ የሚ​መጣ ሁሉ ሲቆም አይ​ቶ​አ​ልና ሕዝቡ ሁሉ እንደ ቆመ ባየ ጊዜ አሜ​ሳ​ይን ከመ​ን​ገድ ላይ ወደ እርሻ ውስጥ ፈቀቅ አደ​ረ​ገው፤ በል​ብ​ስም ከደ​ነው።</verse>
				<verse number="13">ከመ​ን​ገ​ድም ፈጥኖ ራቅ ባለ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰው ሁሉ የቢ​ኮ​ሪን ልጅ ሳቡ​ሄን ለማ​ሳ​ደድ ኢዮ​አ​ብን ተከ​ትሎ ያልፍ ነበር።</verse>
				<verse number="14">እርሱ ግን ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ወደ አቤል፥ ወደ ቤተ​ማ​ካም ሁሉ አለፈ፤ በካሪ ያሉ ሰዎ​ችም ሁሉ ደግሞ ተሰ​ብ​ስ​በው ተከ​ተ​ሉት።</verse>
				<verse number="15">በቤተ ማካና በአ​ቤ​ልም መጥ​ተው ከበ​ቡት፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ላይ እስከ ቅጥ​ርዋ ድረስ የአ​ፈ​ርን ድል​ድል ደለ​ደሉ፤ እነ​ር​ሱም ከአ​ጥሩ ቀጥሎ ቆሙ፤ ቅጥ​ሩ​ንም ያፈ​ርሱ ዘንድ ከኢ​ዮ​አብ ጋር የነ​በሩ ሕዝብ ሁሉ ተስ​ማሙ።</verse>
				<verse number="16">ከቅ​ጥ​ሩም አን​ዲት ብል​ሃ​ተኛ ሴት፥ “ስሙ፥ ስሙ፥ ኢዮ​አ​ብ​ንም፦ እነ​ግ​ርህ ዘንድ ወደ​ዚህ ቅረብ በሉት” ስትል ጮኸች። ወደ እር​ስ​ዋም ቀረበ፤</verse>
				<verse number="17">ሴቲ​ቱም፥ “ኢዮ​አብ አንተ ነህን?” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “እኔ ነኝ” ብሎ መለ​ሰ​ላት። እር​ስ​ዋም፥ “የባ​ሪ​ያ​ህን ቃል ስማ” አለ​ችው። ኢዮ​አ​ብም፥ “እሰ​ማ​ለሁ” አላት።</verse>
				<verse number="18">እር​ስ​ዋም እን​ዲህ አለች፥ “የቀ​ደሙ ሰዎች በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አማ​ኞች በሚ​ያ​ስ​ቡት ነገር ተሳ​ስ​ተው እንደ ሆነ በአ​ቤ​ልና በዳን በእ​ው​ነት ይጠ​ይቁ ይባል ነበር፤ በር​ግ​ጥም በዚህ ዐይ​ነት ነገር ከተ​ሳ​ሳቱ በአ​ቤል ይጠ​ይቁ ነበር።</verse>
				<verse number="19">በእ​ስ​ራ​ኤል ኀያ​ላን ዘንድ ሰላ​ምን ከሚ​ወ​ድ​ዱት አን​ድዋ ነኝ፤ አንተ ግን በእ​ስ​ራ​ኤል ያለ​ች​ውን ከተ​ማና እናት ከተ​ማን ለማ​ፍ​ረስ ትሻ​ለህ፤ ስለ​ም​ንስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ርስት ታጠ​ፋ​ለህ?”</verse>
				<verse number="20">ኢዮ​አ​ብም መልሶ፥ “ይህ ማፍ​ረ​ስና ማጥ​ፋት ከእኔ ይራቅ፤</verse>
				<verse number="21">ነገሩ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ ከተ​ራ​ራ​ማው ከኤ​ፍ​ሬም ሀገር የሚ​ሆን የቢ​ኮሪ ልጅ ሳቡሄ የሚ​ባል አንድ ሰው ግን በን​ጉሡ በዳ​ዊት ላይ እጁን አነሣ፤ እር​ሱን ብቻ​ውን ስጡኝ፤ እኔም ከከ​ተ​ማ​ዪቱ እር​ቃ​ለሁ” አላት። ሴቲ​ቱም ኢዮ​አ​ብን፥ “እነሆ፥ ራሱ ከቅ​ጥር ላይ ይጣ​ል​ል​ሃል” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="22">ያቺም ሴት ወደ ሕዝቡ ሁሉ ገብታ ለከ​ተ​ማው ሕዝብ ሁሉ በብ​ል​ሀት ነገ​ረ​ቻ​ቸው፤ የቢ​ኮ​ሪን ልጅ የሳ​ቡ​ሄን ራስ ቈር​ጠው ሰጡ​አት፤ ወደ ኢዮ​አ​ብም ጣለ​ችው። ኢዮ​አ​ብም መለ​ከ​ቱን ነፋ፤ ሰውም ሁሉ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ርቆ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ድን​ኳኑ ሄደ። ኢዮ​አ​ብም ወደ ንጉሡ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="23">ኢዮ​አ​ብም በእ​ስ​ራ​ኤል ሠራ​ዊት ሁሉ ላይ አለቃ ነበረ፤ የዮ​ዳ​ሄም ልጅ በና​ያስ በከ​ሊ​ታ​ው​ያ​ንና በፈ​ሊ​ታ​ው​ያን ላይ አለቃ ነበረ፤</verse>
				<verse number="24">አዶ​ኔ​ራ​ምም ግብር አስ​ገ​ባሪ ነበረ፤ የአ​ኪ​ሎ​ትም ልጅ ኢዮ​ሳ​ፍጥ ታሪክ ጸሓፊ ነበረ፤</verse>
				<verse number="25">ሱሳም ጸሓፊ ነበረ፤ ሳዶ​ቅና አብ​ያ​ታ​ርም ካህ​ናት ነበሩ፤</verse>
				<verse number="26">የኢ​ያ​ዕር ሰው ኢራ​ስም ለዳ​ዊት ካህን ነበረ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">በዳ​ዊ​ትም ዘመን ሦስት ዓመት ያህል በተ​ከ​ታ​ታይ ራብ ሆነ፤ ዳዊ​ትም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ጠየቀ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “የገ​ባ​ዖ​ንን ሰዎች ስለ ገደለ በሳ​ኦ​ልና በቤቱ ላይ ደም አለ​በት፥”</verse>
				<verse number="2">ንጉሡ ዳዊ​ትም የገ​ባ​ዖ​ንን ሰዎች ጠራ፤ የገ​ባ​ዖን ሰዎ​ችም ከአ​ሞ​ራ​ው​ያን የተ​ረፉ ነበሩ እንጂ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወገን አል​ነ​በ​ሩም፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ምለ​ው​ላ​ቸው ነበር፤ ሳኦል ግን ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና ለይ​ሁዳ ስለ ቀና ሊገ​ድ​ላ​ቸው ወድዶ ነበር።</verse>
				<verse number="3">ዳዊ​ትም የገ​ባ​ዖ​ንን ሰዎች፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ርስት ትባ​ርኩ ዘንድ ምን ላድ​ር​ግ​ላ​ችሁ? ማስ​ተ​ስ​ረ​ያ​ውስ ምን​ድን ነው?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">የገ​ባ​ዖን ሰዎ​ችም፥ “ከሳ​ኦ​ልና ከቤቱ ወርቅ ወይም ብር አን​ፈ​ል​ግም፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወገን እኛ የም​ን​ገ​ድ​ለው የለም” አሉት።</verse>
				<verse number="5">እር​ሱም፥ “ምን ትላ​ላ​ችሁ? ተና​ገሩ፤ እኔም አደ​ር​ግ​ላ​ች​ኋ​ለሁ” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ለን​ጉሡ አሉት፥ “በእኛ ላይ ክፉ ያደ​ረ​ገ​ውን፥ ያሳ​ደ​ደ​ን​ንና ሊያ​ጠ​ፋን ያሰ​በ​ውን ሰው እና​ጥ​ፋው፤ እር​ሱም በእ​ስ​ራ​ኤል ዳርቻ እን​ዳ​ይ​ቆም እና​ደ​ር​ገ​ዋ​ለን።</verse>
				<verse number="6">ከል​ጆቹ ሰባት ሰዎች ስጠ​ንና ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​መ​ረ​ጠው በሳ​ኦል ሀገር በገ​ባ​ዖን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ሠ​ቅ​ላ​ቸ​ዋ​ለን።” ንጉ​ሡም፥ “እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="7">ንጉ​ሡም በእ​ነ​ርሱ መካ​ከል፥ በዳ​ዊ​ትና በሳ​ኦል ልጅ በዮ​ና​ታን መካ​ከል ስለ ነበ​ረው ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሐላ የሳ​ኦ​ልን ልጅ የዮ​ና​ታ​ንን ልጅ ሜም​ፌ​ቡ​ስ​ቴን ራራ​ለት።</verse>
				<verse number="8">ንጉ​ሡም ለሳ​ኦል የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸ​ውን የኢ​ዮ​ሄ​ልን ልጅ የሩ​ጻ​ፋን ሁለ​ቱን ልጆች ሄር​ሞ​ን​ስ​ቴ​ንና ሜም​ፌ​ቡ​ስ​ቴን፥ ለመ​ሓ​ላ​ታ​ዊ​ውም ለቤ​ር​ዜሊ ልጅ ለኤ​ስ​ድራ የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸ​ውን የሳ​ኦ​ልን ልጅ የሜ​ሮ​ብን አም​ስ​ቱን ልጆች ወሰደ፤</verse>
				<verse number="9">በገ​ባ​ዖ​ንም ሰዎች እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት በተ​ራ​ራው ላይ ሰቀ​ሏ​ቸው። ሰባ​ቱም በአ​ን​ድ​ነት ወደቁ፤ እህል በሚ​ታ​ጨ​ድ​በ​ትም ወራት በገ​ብሱ መከር መጀ​መ​ሪያ ተገ​ደሉ።</verse>
				<verse number="10">የኢ​ዮ​ሔል ልጅ ሩጻ​ፋም ማቅ ወስዳ ከመ​ከር ወራት ጀምሮ ዝናብ ከሰ​ማይ እስ​ኪ​ዘ​ንብ ድረስ በድ​ን​ጋይ ላይ ዘረ​ጋ​ችው፤ በቀ​ንም የሰ​ማይ ወፎች፥ በሌ​ሊ​ትም የዱር አራ​ዊት ያር​ፉ​ባ​ቸው ዘንድ አል​ተ​ወ​ችም።</verse>
				<verse number="11">የሳ​ኦ​ልም ዕቅ​ብት የኢ​ዮ​ሔል ልጅ ሩጻፋ ያደ​ረ​ገ​ች​ውን ለዳ​ዊት ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="12">ዳዊ​ትም ሄደ፤ ሳአ​ል​ንም በጌ​ላ​ቡሄ በገ​ደ​ሉት ጊዜ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ከሰ​ቀ​ሉ​አ​ቸው ስፍራ ከቤ​ት​ሳን አደ​ባ​ባይ ከሰ​ረ​ቁት ከኢ​ያ​ቤስ ገለ​ዓድ ሰዎች የሳ​ኦ​ልን አጥ​ን​ትና የል​ጁን የዮ​ና​ታ​ንን አጥ​ንት ወሰደ።</verse>
				<verse number="13">ከዚ​ያም የሳ​ኦ​ልን አጥ​ን​ትና የል​ጁን የዮ​ና​ታ​ንን አጥ​ንት አመጣ፤ የተ​ሰ​ቀ​ሉ​ት​ንም ሰዎች አጥ​ንት ሰበ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="14">የሳ​ኦ​ልን አጥ​ን​ትና የል​ጁን የዮ​ና​ታ​ንን አጥ​ንት፥ የተ​ሰ​ቀ​ሉ​ት​ንም ሰዎች አጥ​ንት በብ​ን​ያም በአ​ባቱ በቂስ መቃ​ብር አጠ​ገብ ቀበ​ሩ​አ​ቸው፤ ንጉ​ሡም ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረጉ። ከዚ​ያም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ርን ሰማት።</verse>
				<verse number="15">በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንና በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መካ​ከል ደግሞ ጦር​ነት ሆነ፤ ዳዊ​ትም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር አገ​ል​ጋ​ዮቹ ወረዱ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጋር ተዋጉ፤ ዳዊ​ትም ደከመ።</verse>
				<verse number="16">ከራ​ፋ​ይም ወገን የነ​በ​ረው ኤስቢ መጣ፤ የጦ​ሩም ሚዛን ክብ​ደት ሦስት መቶ ሰቅል ናስ ነበር። አዲስ የጦር መሣ​ሪ​ያም ታጥቆ ነበር፤ ዳዊ​ት​ንም ሊገ​ድ​ለው ፈለገ።</verse>
				<verse number="17">የሶ​ር​ህ​ያም ልጅ አቢሳ አዳ​ነው፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም ወግቶ ገደ​ለው። ያን​ጊ​ዜም የዳ​ዊት ሰዎች፥ “አንተ የእ​ስ​ራ​ኤል መብ​ራት እን​ዳ​ት​ጠፋ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ከእኛ ጋር ለሰ​ልፍ አት​ወ​ጣም” ብለው ማሉ​ለት።</verse>
				<verse number="18">ከዚ​ህም በኋላ እንደ ገና በጎብ ላይ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ጦር​ነት ሆነ፤ ያን ጊዜም አስ​ጣ​ጦ​ታ​ዊው ሴቤ​ኮይ ከራ​ፋ​ይም ወገን የሆ​ነ​ውን ሳፍን ገደ​ለው።</verse>
				<verse number="19">ደግ​ሞም በሮም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ጦር​ነት ሆነ፤ የቤ​ተ​ል​ሔ​ማ​ዊ​ውም የዓ​ሬ​ኦ​ር​ጌም ልጅ ኤል​ያ​ናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠ​ቅ​ለያ የነ​በ​ረ​ውን የጌት ሰው ጎዶ​ል​ያን ገደ​ለው።</verse>
				<verse number="20">ደግ​ሞም በጌት ላይ ጦር​ነት ሆነ፤ በዚ​ያም በእ​ጁና በእ​ግሩ ስድ​ስት ስድ​ስ​ት​ሁ​ላ​ሁሉ ሃያ አራት ጣቶች የነ​በ​ሩት አንድ ረዥም ሰው ነበረ፤ እርሱ ደግሞ ከራ​ፋ​ይም የተ​ወ​ለደ ነበረ።</verse>
				<verse number="21">እስ​ራ​ኤ​ል​ንም በተ​ገ​ዳ​ደረ ጊዜ የዳ​ዊት ወን​ድም የሴ​ማይ ልጅ ዮና​ታን ገደ​ለው።</verse>
				<verse number="22">እነ​ዚ​ያም አራቱ በጌት ውስጥ ከረ​ዐ​ይት የተ​ወ​ለዱ የራ​ፋ​ይም ወገ​ኖች ነበሩ፤ በዳ​ዊ​ትም እጅ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም እጅ ወደቁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሳ​ኦል እጅና ከጠ​ላ​ቶቹ ሁሉ እጅ ባዳ​ነው ቀን የዚ​ህን መዝ​ሙር ቃል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="2">እን​ዲ​ህም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዓለቴ፥ አም​ባ​ዬም፥ መድ​ኀ​ኒ​ቴም ነው፤</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠባ​ቂዬ ነው፤ በእ​ር​ሱም እታ​መ​ና​ለሁ፤ ጋሻ​ዬና የመ​ድ​ኀ​ኒቴ ቀንድ፥ ረዳቴ፥ መጠ​ጊ​ያ​ዬና መሸ​ሸ​ጊ​ያዬ፥ መድ​ኀ​ኒቴ ሆይ፥ ከግ​ፈኛ ታድ​ነ​ኛ​ለህ።</verse>
				<verse number="4">ምስ​ጋና የሚ​ገ​ባ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጠ​ራ​ለሁ፤ ከጠ​ላ​ቶቼም እድ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">የሞት ጭንቅ ያዘኝ፤ የዐ​መፅ ጎር​ፍም አስ​ፈ​ራኝ፤</verse>
				<verse number="6">የሞት ጣር ከበ​በኝ፤ የሞት ወጥ​መ​ድም ደረ​ሰ​ብኝ።</verse>
				<verse number="7">በጨ​ነ​ቀኝ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠራ​ሁት፤ እን​ዲ​ረ​ዳ​ኝም ወደ አም​ላኬ ጮኽሁ፤ ከመ​ቅ​ደ​ሱም ቃሌን ሰማኝ፤ ጩኸ​ቴም በፊቱ ወደ ጆሮ​ዎቹ ገባ።</verse>
				<verse number="8">ምድ​ርም ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠች፤ ተና​ወ​ጠ​ችም፤ የሰ​ማይ መሠ​ረ​ቶ​ችም ተነ​ቃ​ነቁ፤ ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጡም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቈ​ጥ​ቶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="9">ከቍ​ጣው ጢስ ወጣ፤ ከአ​ፉም የሚ​በላ እሳት ነደደ፤ ፍምም ከእ​ርሱ ተቃ​ጠለ።</verse>
				<verse number="10">ሰማ​ዮ​ችን አዘ​ነ​በለ፤ ወረ​ደም፤ ጭጋ​ግም ከእ​ግሩ በታች ነበረ።</verse>
				<verse number="11">በኪ​ሩ​ቤ​ልም ላይ ተቀ​ምጦ በረረ፤ በነ​ፋ​ስም ክን​ፎች ሆኖ ታየ፤</verse>
				<verse number="12">መሰ​ወ​ር​ያ​ውን ጨለማ አደ​ረገ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም የነ​በ​ረ​ውን ድን​ኳን የውኃ ጨለማ አደ​ረገ፤ በደ​መ​ናም አገ​ዘ​ፈው።</verse>
				<verse number="13">በፊ​ቱም ካለው ብር​ሃን የተ​ነሣ ፍም ተቃ​ጠለ።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሰ​ማይ አን​ጐ​ደ​ጐደ፤ ልዑ​ልም ቃሉን ሰጠ።</verse>
				<verse number="15">ፍላ​ጻ​ውን ላከ፤ በተ​ና​ቸ​ውም፤ መብ​ረ​ቅ​ንም አሰ​ምቶ አስ​ደ​ነ​ገ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተግ​ሣፅ የተ​ነሣ፥ ከመ​ዓ​ቱም መን​ፈስ እስ​ት​ን​ፋስ የተ​ነሣ፥ የባ​ሕር ፈሳ​ሾች ታዩ፤ የዓ​ለም መሠ​ረ​ቶ​ችም ተገ​ለጡ።</verse>
				<verse number="17">ከላይ ላከ፤ ወሰ​ደ​ኝም፤ ከብዙ ውኆ​ችም አወ​ጣኝ።</verse>
				<verse number="18">ከብ​ር​ቱ​ዎች ጠላ​ቶቼ፥ ከሚ​ጠ​ሉ​ኝም አዳ​ነኝ፤ በር​ት​ተ​ው​ብኝ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="19">በመ​ከ​ራዬ ቀን ደረ​ሱ​ብኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ደጋ​ፊዬ ሆነ።</verse>
				<verse number="20">ወደ ሰፊ ስፍ​ራም አወ​ጣኝ፤ ወድ​ዶ​ኛ​ልና አዳ​ነኝ።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ጽድቄ ይከ​ፍ​ለ​ኛል፤ እንደ እጄ ንጽ​ሕ​ናም ይመ​ል​ስ​ል​ኛል፤</verse>
				<verse number="22">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ጠብ​ቄ​አ​ለ​ሁና፥ በአ​ም​ላ​ኬም አላ​መ​ፅ​ሁ​ምና።</verse>
				<verse number="23">ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነበ​ርና፤ ጽድ​ቁም ከእኔ አል​ራ​ቀ​ምና።</verse>
				<verse number="24">በእ​ርሱ ዘንድ ንጹሕ እሆ​ና​ለሁ፤ ከዐ​መ​ፃ​ዬም ራሴን እጠ​ብ​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="25">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ጽድቄ፥ እንደ እጄም ንጽ​ሕና በዐ​ይ​ኖቹ ፊት መለ​ሰ​ልኝ።</verse>
				<verse number="26">ከጻ​ድቅ ጋር ጻድቅ ትሆ​ና​ለህ፤ ከን​ጹሕ ሰውም ጋር ንጹሕ ትሆ​ና​ለህ፤</verse>
				<verse number="27">ከተ​መ​ረ​ጠም ጋር የተ​መ​ረጠ ትሆ​ና​ለህ፤ ከጠ​ማማ ጋርም ጠማማ ትሆ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="28">አንተ የተ​ዋ​ረ​ደ​ውን ሕዝብ ታድ​ና​ለ​ህና፤ የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችን ዐይ​ኖች ግን ታዋ​ር​ዳ​ለህ።</verse>
				<verse number="29">አቤቱ! አንተ መብ​ራቴ ነህና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጨለ​ማ​ዬን ያበ​ራ​ል​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="30">በአ​ንተ ብቻ​ዬን እሮ​ጣ​ለ​ሁና፤ በአ​ም​ላ​ኬም ቅጥ​ሩን እዘ​ል​ላ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="31">የኀ​ያል አም​ላክ መን​ገድ ንጹሕ ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ጽኑዕ ነው፤ በእ​ሳ​ትም የጋለ ነው፤ በእ​ር​ሱም ለሚ​ታ​መ​ኑት ጠባ​ቂ​ያ​ቸው ነው።</verse>
				<verse number="32">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀር ጽኑዕ ማን ነው? ከአ​ም​ላ​ካ​ች​ንስ በቀር ፈጣሪ ማን ነው?</verse>
				<verse number="33">በኀ​ይል የሚ​ያ​ጸ​ናኝ ኀያል እርሱ ነው፤ መን​ገ​ዴ​ንም ንጹሕ አድ​ርጎ አዘ​ጋጀ፤</verse>
				<verse number="34">እግ​ሮቼን እንደ ዋልያ እግ​ሮች አጸና፤ በኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም አቆ​መኝ።</verse>
				<verse number="35">ለእ​ጆቼ ጦር​ነ​ትን ያስ​ተ​ም​ራል፤ ለክ​ን​ዴም የናስ ቀስት አዘዘ።</verse>
				<verse number="36">የመ​ድ​ኀ​ኒ​ቴ​ንም ጋሻ ሰጠ​ኸኝ፤ መል​ስ​ህም አበ​ዛ​ችኝ፤</verse>
				<verse number="37">በሜ​ዳም አረ​ማ​መ​ዴን በበ​ታቼ አሰ​ፋህ፤ እግ​ሮቼም አል​ተ​ን​ሸ​ራ​ተ​ቱም።</verse>
				<verse number="38">ጠላ​ቶ​ቼን አሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አጠ​ፋ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ እስ​ካ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም ድረስ አል​መ​ለ​ስም።</verse>
				<verse number="39">እቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ መቆ​ምም አይ​ች​ሉም፤ ከእ​ግ​ሬም በታች ይወ​ድ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="40">በጦ​ር​ነ​ትም ጊዜ በኀ​ይል ታጸ​ና​ኛ​ለህ፤ በላዬ የቆ​ሙ​ት​ንም በበ​ታቼ ታስ​ገ​ዛ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="41">የጠ​ላ​ቶ​ቼን ጀርባ ሰጠ​ኸኝ፤ የሚ​ጠ​ሉ​ኝ​ንም አጠ​ፋ​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="42">ጮኹ፤ የሚ​ረ​ዳ​ቸ​ውም አል​ነ​በ​ረም፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ አል​ሰ​ማ​ቸ​ው​ምም።</verse>
				<verse number="43">በነ​ፋስ ፊት እን​ዳለ እንደ ምድር ትቢያ ፈጨ​ኋ​ቸው፤ እንደ ጎዳ​ናም ጭቃ ረገ​ጥ​ኋ​ቸው፤ ደቀ​ደ​ቅ​ኋ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="44">ከአ​ሕ​ዛብ ጠብ አድ​ነኝ፤ የአ​ሕ​ዛ​ብም ራስ አድ​ር​ገህ ትሾ​መ​ኛ​ለህ፤ የማ​ላ​ው​ቀው ሕዝብ ተገ​ዛ​ልኝ።</verse>
				<verse number="45">የባ​ዕድ ልጆች ዋሹኝ፤ በጆሮ ሰም​ተው መለ​ሱ​ልኝ።</verse>
				<verse number="46">የባ​ዕድ ልጆች አረጁ፤ ከማ​ን​ከ​ሳ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ተሰ​ና​ከሉ።</verse>
				<verse number="47">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕያው ነው፤ ጠባ​ቂ​ዬም ቡሩክ ነው፤ የሕ​ይ​ወቴ ጠባቂ አም​ላኬ ከፍ ከፍ ይበል፤</verse>
				<verse number="48">በቀ​ሌን የሚ​መ​ል​ስ​ልኝ አም​ላክ ጽኑዕ ነው። አሕ​ዛ​ብን በበ​ታቼ ያስ​ገ​ዛ​ል​ኛል፤</verse>
				<verse number="49">ከጠ​ላ​ቶቼ የሚ​ያ​ወ​ጣኝ እርሱ ነው፤ በእ​ኔም ላይ ከቆሙ ከፍ ከፍ ታደ​ር​ገ​ኛ​ለህ፤ ከግ​ፈ​ኛም ሰው ታድ​ነ​ኛ​ለህ።</verse>
				<verse number="50">አቤቱ፥ ስለ​ዚህ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥ ለስ​ም​ህም እዘ​ም​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="51">የን​ጉ​ሡን መድ​ኀ​ኒት ታላቅ ያደ​ር​ጋል፤ ቸር​ነ​ቱ​ንም ለቀ​ባው ለዳ​ዊ​ትና ለዘሩ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያደ​ር​ጋል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="23">
				<verse number="1">የዳ​ዊ​ትም የመ​ጨ​ረሻ ቃሉ ይህ ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ከፍ ያደ​ረ​ገው፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ የቀ​ባው፥ የታ​ማኙ ሰው፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ መል​ካም ባለ​መ​ዝ​ሙር የሆ​ነው፥ የታ​ማኙ የእ​ሴይ ልጅ የዳ​ዊት ንግ​ግር ይህ ነው፤</verse>
				<verse number="2">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በእኔ ተና​ገረ፤ ቃሉም በአ​ን​ደ​በቴ ላይ ነበረ።</verse>
				<verse number="3">የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ተና​ገረ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጠባቂ በም​ሳሌ እን​ዲህ አለኝ፦ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ታጸኑ ዘንድ፥ በሰ​ዎች መካ​ከል ተና​ገ​ርሁ፥”</verse>
				<verse number="4">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብር​ሃን በጥ​ዋት፥ በማ​ለ​ዳም ፀሐይ ይወ​ጣል፤ ብር​ሃ​ኑም በነ​ግህ ይመ​ጣል፤ ከዝ​ና​ምም የተ​ነሣ በም​ድር ሐመ​ል​ማል ይለ​መ​ል​ማል።</verse>
				<verse number="5">በውኑ ቤቴ በኀ​ያሉ ዘንድ እን​ዲሁ አይ​ደ​ለ​ምን? ከእ​ኔም ጋር በዘ​መኑ ሁሉ የተ​ዘ​ጋ​ጀና የተ​ጠ​በቀ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳን አድ​ር​ጎ​አል፤ መድ​ኀ​ኒ​ቴም ፈቃ​ዴም ሁሉ ይህ ነውና። ዐመ​ፀ​ኛም አይ​በ​ቅ​ል​ምና።</verse>
				<verse number="6">እነ​ዚህ ሁሉ ግን ሰው በእጁ እን​ደ​ማ​ይ​ዘው፥ እንደ ተጣለ እሾህ ናቸው።</verse>
				<verse number="7">በእ​ሳት ከሚ​ቃ​ጠ​ሉና በው​ር​ደ​ታ​ቸው ከሚ​ነ​ድዱ በቀር በብ​ረት ብዛ​ትም ሆነ፥ በጦር ዘንግ ብዛት ሰው የሚ​ደ​ክ​ም​ባ​ቸው አይ​ደ​ሉም።</verse>
				<verse number="8">የዳ​ዊት ኀያ​ላን ስም ይህ ነው። የሦ​ስ​ተ​ኛው ክፍል አለቃ የሆነ ከነ​ዓ​ና​ዊው ኢያ​ቡ​ስቴ ነበረ፤ ጎራ​ዴ​ውን መዝዞ ስም​ንት መቶ ያህል ጭፍ​ሮ​ችን በአ​ንድ ጊዜ የገ​ደለ አሶ​ና​ዊው አዲ​ኖን ነበረ።</verse>
				<verse number="9">ከእ​ር​ሱም በኋላ የዳ​ዊት የአ​ጎቱ ልጅ የዱዲ ልጅ ኤል​ያ​ናን ነበረ፤ ለሰ​ልፍ የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡ​ትን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በተ​ገ​ዳ​ደሩ ጊዜ ከዳ​ዊት ጋር ከነ​በሩ ከሦ​ስቱ ኀያ​ላን አንዱ እርሱ ነበረ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="10">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች በጮኹ ጊዜ እርሱ ተነ​ሥቶ እጁ እስ​ከ​ሚ​ደ​ክ​ምና ከሰ​ይፉ ጋር እስ​ኪ​ጣ​በቅ ድረስ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ፤ በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ መድ​ኀ​ኒት አደ​ረገ፤ ሕዝ​ቡም ከእ​ርሱ በኋላ የሞ​ቱ​ትን ለመ​ግ​ፈፍ ብቻ ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="11">ከእ​ር​ሱም በኋላ የአ​ሮ​ዳ​ዊው የአጌ ልጅ ሴሜይ ነበረ። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም በቴ​ሪያ ተሰ​በ​ሰቡ። በዚ​ያም ምስር የሞ​ላ​በት የእ​ርሻ ክፍል ነበር፤ ሕዝ​ቡም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ሸሹ።</verse>
				<verse number="12">እርሱ ግን በእ​ር​ሻው መካ​ከል ቆሞ ጠበቀ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ገደለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታላቅ መድ​ኀ​ኒት አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="13">ከሠ​ላ​ሳ​ውም አለ​ቆች ሦስቱ ወር​ደው ወደ ቃሶን ወደ ዳዊት ወደ አዶ​ላም ዋሻ መጡ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍራ በራ​ፋ​ይም ሸለቆ ሰፍሮ ነበር።</verse>
				<verse number="14">በዚያ ጊዜም ዳዊት በም​ሽጉ ውስጥ ነበረ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍራ በዚያ ጊዜ በቤተ ልሔም ነበረ።</verse>
				<verse number="15">ዳዊ​ትም፥ “በበሩ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ማን ባጠ​ጣኝ?” ብሎ ተመኘ። ያን​ጊ​ዜም የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ኀይል በቤተ ልሔም ነበረ።</verse>
				<verse number="16">ሦስ​ቱም ኀያ​ላን የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ሠራ​ዊት ሰን​ጥ​ቀው ሄዱ፤ በበ​ሩም አጠ​ገብ ካለ​ችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ቀዱ፤ ይዘ​ውም ለዳ​ዊት አመ​ጡ​ለት፤ እርሱ ግን ሊጠጣ አል​ወ​ደ​ደም፤ ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፈ​ሰ​ሰው።</verse>
				<verse number="17">“አቤቱ፥ ይህን አደ​ርግ ዘንድ ከእኔ ይራቅ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውን ሰጥ​ተው የሄዱ ሰዎች ደም አይ​ደ​ለ​ምን?” ብሎ ይጠጣ ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም። ሦስቱ ኀያ​ላ​ንም ያደ​ረ​ጉት ይህ ነው።</verse>
				<verse number="18">የሶ​ር​ህ​ያም ልጅ የኢ​ዮ​አብ ወን​ድም አቢሳ የሦ​ስቱ አለቃ ነበር። እር​ሱም ጦሩን በሦ​ስቱ መቶ ላይ አን​ሥቶ ገደ​ላ​ቸው፤ ስሙም በሦ​ስቱ ዘንድ ተጠ​ርቶ ነበር።</verse>
				<verse number="19">እር​ሱም ከሦ​ስቱ ይልቅ የከ​በረ ነበር፤ አለ​ቃ​ቸ​ውም ሆነ፤ ነገር ግን ወደ ሦስቱ አል​ደ​ረ​ሰም።</verse>
				<verse number="20">በቀ​በ​ስ​ሄል የነ​በ​ረው ታላቅ ሥራ ያደ​ረ​ገው የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ የሞ​ዓ​ባ​ዊ​ውን የአ​ር​ኤ​ልን ሁለት ልጆች ገደለ፤ በአ​መ​ዳ​ዩም ወራት ወርዶ በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ አን​በሳ ገደለ።</verse>
				<verse number="21">እር​ሱም ልዩ የሆ​ነ​ውን ግብ​ፃዊ ሰው ገደለ፤ ግብ​ፃ​ዊ​ውም በእጁ ዛቢ​ያው እንደ ድል​ድይ ዕን​ጨት የሆነ ጦር ነበ​ረው፤ በና​ያስ ግን በትር ይዞ ወደ እርሱ ወረደ፤ ከግ​ብ​ፃ​ዊ​ውም እጅ ጦሩን ነጥቆ በገዛ ጦሩ ገደ​ለው።</verse>
				<verse number="22">የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ ያደ​ረ​ገው ይህ ነው፤ ስሙም በሦ​ስቱ ኀያ​ላን ተጠ​ርቶ ነበር።</verse>
				<verse number="23">ከሦ​ስ​ቱም ይልቅ የከ​በረ ነበረ፤ ነገር ግን ወደ ሦስቱ አል​ደ​ረ​ሰም። ዳዊ​ትም ትእ​ዛዝ አስ​ከ​ባሪ አድ​ርጎ ሾመው።</verse>
				<verse number="24">የዳ​ዊት ኀያ​ላ​ንም ስማ​ቸው ይህ ነው። የኢ​ዮ​አብ ወን​ድም አሣ​ሄል በሠ​ላ​ሳው መካ​ከል ነበረ፤ የቤተ ልሔም ሰው የአ​ጎቱ የዱዲ ልጅ ኤል​ያ​ናን፥</verse>
				<verse number="25">አሮ​ዳ​ዊው ሴሜይ፥ ሔሮ​ዳ​ዊው አል​ያቃ፥</verse>
				<verse number="26">ፈል​ጣ​ዊው ሴሌ፥ የቴ​ቁ​ሓ​ዊው የኤ​ስካ ልጅ ዔራስ፥</verse>
				<verse number="27">ከአ​ስ​ቲጡ ልጆች ወገን የሚ​ሆን አና​ቶ​ታ​ዊው አብ​ዔ​ዜር፥</verse>
				<verse number="28">የኤ​ሎ​ንያ ሰው ኤላን፥ የፋጤ ሰው ናኤ​ሬት፥</verse>
				<verse number="29">የአ​ን​ጢፋ ሰው የቦ​አና ልጅ ሔሌብ፥ ከብ​ን​ያም ወገን ከጌ​ብዓ የረ​ባይ ልጅ ኢታይ፥</verse>
				<verse number="30">ኤፍ​ራ​ታ​ዊው በና​ያስ፥ የአ​ብ​ሪስ ሰው አሶም፥</verse>
				<verse number="31">ዓረ​ባ​ዊው አቤ​ዔ​ል​ቦን፥ አል​ሞ​ና​ዊው ኤማ​ሱ​ኖስ፥</verse>
				<verse number="32">አሴ​ሌ​ቦ​ና​ዊው ኤል​ያ​ሕባ፥ የአ​ሶን ልጅ ዮና​ታን፥</verse>
				<verse number="33">አሮ​ዳ​ዊው ሳም​ናን፥ የሓ​ተ​ራ​ዊው የሶሬ ልጅ አም​ናን፥</verse>
				<verse number="34">የመ​ካኪ ልጅ የአ​ሶብ ልጅ ኤላ​ፍ​ላት፥ የጊ​ሎ​ና​ዊው የአ​ኪ​ጦ​ፌል ልጅ ኤል​ያብ፥</verse>
				<verse number="35">ቀር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊው አሰሬ፥ አረ​ባ​ዊው ኤፌዎ፥</verse>
				<verse number="36">የና​ታን ልጅ ኤአኪ፥ ከገ​ዓድ ልጆች ወገን ማሶባ፥</verse>
				<verse number="37">አሞ​ና​ዊው ኤልዩ፥ የሶ​ር​ህያ ልጅ የኢ​ዮ​አብ ጋሻ ጃግሬ ቤሮ​ታ​ዊው ጌሎሬ፥</verse>
				<verse number="38">ኤተ​ራ​ዊው ዒራስ፥ ኢታ​ና​ዊው ጋሬብ፥</verse>
				<verse number="39">ኬጤ​ያ​ዊው ኦርዮ፤ ሁሉም በሁሉ ሠላሳ ሰባት ናቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="24">
				<verse number="1">ደግ​ሞም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ነደደ፤ ዳዊ​ት​ንም፥ “ሂድ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንና ይሁ​ዳን ቍጠር” ብሎ በላ​ያ​ቸው አስ​ነ​ሣው።</verse>
				<verse number="2">ንጉ​ሡም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ረ​ውን የሠ​ራ​ዊት አለቃ ኢዮ​አ​ብን፥ “የሕ​ዝ​ቡን ድምር አውቅ ዘንድ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ ሂድ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ቍጠ​ራ​ቸው” አለው።</verse>
				<verse number="3">ኢዮ​አ​ብም ንጉ​ሡን፥ “የጌ​ታዬ የን​ጉሡ ዐይን እያየ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ካለው ሕዝብ መጠን በላይ መቶ እጥፍ ይጨ​ም​ር​በት፤ ጌታዬ ንጉሡ ግን ይህን ነገር ለምን ይፈ​ል​ጋል?” አለው።</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን የን​ጉሡ ቃል በኢ​ዮ​አ​ብና በሠ​ራ​ዊቱ አለ​ቆች ላይ አሸ​ነፈ። ኢዮ​አ​ብና የሠ​ራ​ዊቱ አለ​ቆ​ችም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሕዝብ ይቈ​ጥሩ ዘንድ ከን​ጉሥ ዘንድ ወጡ።</verse>
				<verse number="5">ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ገሩ፤ በጋድ ሸለቆ መካ​ከል ባለ​ች​ውም በኢ​ያ​ዜር ከተማ ቀኝ በኩል በአ​ሮ​ዔር ላይ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="6">ወደ ገለ​ዓ​ድም አዳ​ሳይ ወደ​ም​ት​ባል ወደ ተባ​ሶን ሀገ​ርም መጡ፤ ወደ ዳኒ​ዳ​ንና ወደ ኡዳ​ንም ደረሱ፤ ወደ ሲዶ​ናም ዞሩ፤</verse>
				<verse number="7">ወደ ጤሮ​ስም ምሽግ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ከተ​ሞች ሁሉ መጡ፤ በይ​ሁ​ዳም ደቡብ በኩል በቤ​ር​ሳ​ቤህ ወጡ።</verse>
				<verse number="8">በሀ​ገ​ሪ​ቱም ሁሉ ላይ ተመ​ላ​ል​ሰው ከዘ​ጠኝ ወርና ከሃያ ቀን በኋላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="9">ኢዮ​አ​ብም የሕ​ዝ​ቡን ቍጥር ድምር ለን​ጉሡ ሰጠ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ስም​ንት መቶ ሺህ ጽኑ​ዓን ሰዎች ነበሩ፤ የይ​ሁ​ዳም ተዋ​ጊ​ዎች ሰዎች አም​ስት መቶ ሺህ ነበሩ።</verse>
				<verse number="10">ሕዝ​ቡ​ንም ከቈ​ጠረ በኋላ ዳዊ​ትን ልቡ መታው፤ ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “ባደ​ረ​ግ​ሁት ነገር እጅግ በድ​ያ​ለሁ፤ አሁን ግን አቤቱ! ታላቅ ስን​ፍና አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና የባ​ሪ​ያ​ህን ኀጢ​አት ታርቅ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="11">ዳዊ​ትም ማልዶ በተ​ነሣ ጊዜ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ዳዊት ባለ ራእይ ወደ ነቢዩ ወደ ጋድ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="12">“ሂድና ለዳ​ዊት እን​ዲህ ብለህ ንገ​ረው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሦስት ነገ​ሮ​ችን በፊ​ትህ አኖ​ራ​ለሁ፤ አደ​ር​ግ​ብህ ዘንድ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዱን ምረጥ።”</verse>
				<verse number="13">ጋድም ወደ ዳዊት መጥቶ፥ “የሦ​ስት ዓመት ራብ በሀ​ገ​ርህ ላይ ይም​ጣ​ብ​ህን? ወይስ ጠላ​ቶ​ችህ እያ​ሳ​ደ​ዱህ ሦስት ወር ከእ​ነ​ርሱ ትሸ​ሽን? ወይስ የሦ​ስት ቀን ቸነ​ፈር በሀ​ገ​ርህ ላይ ይሁን? የሚ​ሻ​ል​ህን ምረጥ። አሁ​ንም ለላ​ከኝ ምን መልስ እን​ደ​ም​ሰጥ አስ​ብና መር​ምር” ብሎ ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="14">ዳዊ​ትም ጋድን፥ “በሁ​ሉም እጅግ ተጨ​ን​ቄ​አ​ለሁ፤ በሰው እጅ ከም​ወ​ድቅ ይልቅ ምሕ​ረቱ ብዙ ነውና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ መው​ደቅ ይሻ​ለ​ኛል” አለው።</verse>
				<verse number="15">ዳዊ​ትም ቸነ​ፈ​ሩን መረጠ፤ የስ​ን​ዴም መከር ወራት በሆነ ጊዜ ጌታ ከጥ​ዋት እስከ ቀትር ቸነ​ፈ​ርን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ላከ። ቸነ​ፈ​ሩም በሕ​ዝቡ መካ​ከል ጀመረ፤ ከሕ​ዝ​ቡም ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ሰባ ሺህ ሰው ሞተ።</verse>
				<verse number="16">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ያጠ​ፋት ዘንድ እጁን ዘረጋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከክ​ፉው ነገር ይቅር አላት፤ ሕዝ​ቡ​ንም የሚ​ያ​ጠ​ፋ​ውን መል​አክ፥ “እን​ግ​ዲህ በቃህ፤ እጅ​ህን መልስ” አለው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በኢ​ያ​ቡ​ሳ​ዊው በኦ​ርና አው​ድማ አጠ​ገብ ቆሞ ነበረ።</verse>
				<verse number="17">ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡን የሚ​መ​ታ​ውን መል​አክ ባየ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “እነሆ፥ እኔ በድ​ያ​ለሁ፤ ክፉም ሥራ እኔ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ እነ​ዚህ በጎች ግን ምን አደ​ረጉ? እጅህ በእ​ኔና በአ​ባቴ ቤት ላይ ትሆን ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” ብሎ ተና​ገ​ረው።</verse>
				<verse number="18">በዚ​ያም ቀን ጋድ ወደ ዳዊት መጥቶ፥ “ውጣ፤ በኢ​ያ​ቡ​ሳ​ዊው በኦ​ርና አው​ድማ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሥራ” አለው።</verse>
				<verse number="19">ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው እንደ ጋድ ነገር ወጣ።</verse>
				<verse number="20">ኦር​ናም ሲመ​ለ​ከት ንጉ​ሡና ብላ​ቴ​ና​ዎቹ ወደ እርሱ ሲመጡ አየ፤ ኦር​ናም ወጥቶ በን​ጉሡ ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ሰገደ።</verse>
				<verse number="21">ኦር​ናም፥ “ጌታ​ዬን ንጉ​ሡን ወደ አገ​ል​ጋዩ ያመ​ጣው ምክ​ን​ያት ምን​ድን ነው?” አለ። ዳዊ​ትም፥ “መቅ​ሠ​ፍቱ ከሕ​ዝቡ ላይ ይከ​ለ​ከል ዘንድ አው​ድ​ማ​ውን ከአ​ንተ ገዝቼ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ልሠራ ነው” አለው።</verse>
				<verse number="22">ኦር​ናም ዳዊ​ትን፥ “ጌታዬ ንጉሡ በፊቱ ደስ ያሰ​ኘ​ውን ወስዶ ያቅ​ርብ፤ እነ​ሆም፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሬ​ዎች፥ ለሚ​ቃ​ጠ​ልም እን​ጨት የአ​ው​ድማ ዕቃና የበሬ ዕቃ አለ።</verse>
				<verse number="23">ንጉሥ ሆይ፥ ኦርና ይህን ሁሉ ለን​ጉሡ ይሰ​ጣል” አለው፤ ኦር​ናም ንጉ​ሡን፥ “አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ር​ክህ” አለው።</verse>
				<verse number="24">ንጉ​ሡም ኦር​ናን፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን በዋጋ ከአ​ንተ እገ​ዛ​ለሁ፤ ለአ​ም​ላ​ኬም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያለ ዋጋ አላ​ቀ​ር​ብም” አለው። ዳዊ​ትም አው​ድ​ማ​ው​ንና በሬ​ዎ​ቹን በአ​ምሳ ሰቅል ብር ገዛ።</verse>
				<verse number="25">በዚ​ያም ዳዊት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሠራ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ልና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም አቀ​ረበ። ሰሎ​ሞ​ንም በኋላ ዘመን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመረ፤ ያን​ጊዜ አነ​ስ​ተኛ ነበ​ርና። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ሀገ​ሪቱ የተ​ለ​መ​ነ​ውን ሰማ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ቱም ከእ​ስ​ራ​ኤል ተከ​ለ​ከለ።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="11">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">ንጉሡ ዳዊ​ትም አረጀ፤ ዘመ​ኑም አለፈ፤ ልብ​ስም ይደ​ር​ቡ​ለት ነበር፤ ነገር ግን አይ​ሞ​ቀ​ውም ነበር።</verse>
				<verse number="2">የዳ​ዊት አሽ​ከ​ሮ​ችም፥ “ለጌ​ታ​ችን ለን​ጉሡ ድን​ግል ልጅ ትፈ​ለ​ግ​ለት፤ በን​ጉ​ሡም ፊት ቆማ ታገ​ል​ግ​ለው፥ በጌ​ታ​ች​ንም በን​ጉሡ ብብት ተኝታ ትቀ​ፈው፤ ታሙ​ቀ​ውም” አሉ።</verse>
				<verse number="3">በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሀገር ሁሉ የተ​ዋ​በች ቆንጆ ፈለጉ፤ ሱነ​ማ​ዪ​ቱን አቢ​ሳ​ንም አገኙ፤ ወደ ንጉ​ሡም ወሰ​ዱ​አት።</verse>
				<verse number="4">ቆን​ጆ​ዪ​ቱም እጅግ ውብ ነበ​ረች፤ ንጉ​ሡ​ንም ታቅ​ፈ​ውና ታገ​ለ​ግ​ለው ነበር፤ ንጉሡ ግን አያ​ው​ቃ​ትም ነበር።</verse>
				<verse number="5">የአ​ጊ​ትም ልጅ አዶ​ን​ያስ፥ “ንጉሥ እሆ​ና​ለሁ” ብሎ ተነሣ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን በፊ​ቱም የሚ​ሮጡ አምሳ ሰዎ​ችን አዘ​ጋጀ።</verse>
				<verse number="6">አባ​ቱም፥ “ከቶ ለምን እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ለህ?” ብሎ አል​ከ​ለ​ከ​ለ​ውም ነበር፤ እር​ሱም ደግሞ መልኩ እጅግ ያማረ ሰው ነበረ፤ እር​ሱ​ንም ከአ​ቤ​ሴ​ሎም በኋላ ወል​ዶት ነበር።</verse>
				<verse number="7">ሴራ​ውም ከሶ​ር​ህያ ልጅ ከኢ​ዮ​አ​ብና ከካ​ህኑ ከአ​ብ​ያ​ታር ጋር ነበረ፤ እነ​ር​ሱም አዶ​ን​ያ​ስን ተከ​ት​ለው ይረ​ዱት ነበር።</verse>
				<verse number="8">ነገር ግን ካህኑ ሳዶ​ቅና የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ ነቢ​ዩም ናታን፥ ሳሚም፥ ሬሲም፥ የዳ​ዊ​ትም ኀያ​ላን አዶ​ን​ያ​ስን አል​ተ​ከ​ተ​ሉም ነበር።</verse>
				<verse number="9">አዶ​ን​ያ​ስም በጎ​ች​ንና በሬ​ዎ​ችን፥ ጠቦ​ቶ​ች​ንም በሮ​ጌል ምንጭ አጠ​ገብ ባለ​ችው በዞ​ሔ​ሌት ድን​ጋይ ዘንድ ሠዋ፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ልጆች ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ፥ የን​ጉ​ሡ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮች፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ኀያ​ላን ሁሉ ጠራ።</verse>
				<verse number="10">ነገር ግን ነቢ​ዩን ናታ​ንን፥ በና​ያ​ስ​ንም፥ ኀያ​ላ​ኑ​ንም፥ ወን​ድ​ሙ​ንም ሰሎ​ሞ​ንን አል​ጠ​ራም።</verse>
				<verse number="11">ናታ​ንም የሰ​ሎ​ሞ​ንን እናት ቤር​ሳ​ቤ​ህን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራት፥ “ጌታ​ችን ዳዊት ሳያ​ውቅ የአ​ጊት ልጅ አዶ​ን​ያስ እንደ ነገሠ አል​ሰ​ማ​ሽ​ምን?</verse>
				<verse number="12">አሁ​ንም ነዪ፤ የል​ጅ​ሽን የሰ​ሎ​ሞ​ንን ነፍ​ስና የአ​ን​ቺን ነፍስ እን​ድ​ታ​ድኚ እመ​ክ​ር​ሻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">ሄደሽ ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት ግቢና፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ለእኔ ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ፦ ልጅሽ ሰሎ​ሞን ከእኔ በኋላ ይነ​ግ​ሣል፤ በዙ​ፋ​ኔም ይቀ​መ​ጣል ብለህ አል​ማ​ል​ህ​ል​ኝ​ምን? ስለ​ም​ንስ አዶ​ን​ያስ ይነ​ግ​ሣል? በዪው።</verse>
				<verse number="14">እነሆ፥ አንቺ በዚያ ለን​ጉሥ ስት​ነ​ግሪ እኔ ከአ​ንቺ በኋላ እገ​ባ​ለሁ፤ ቃል​ሽ​ንም አጸ​ና​ለሁ።”</verse>
				<verse number="15">ቤር​ሳ​ቤ​ህም ወደ ንጉሡ ወደ እል​ፍኝ ገባች፤ ንጉ​ሡም እጅግ ሸም​ግሎ ነበር፤ ሱነ​ማ​ዪ​ቱም አቢሳ ንጉ​ሡን ታገ​ለ​ግ​ለው ነበር።</verse>
				<verse number="16">ቤር​ሳ​ቤ​ህም አጎ​ን​ብሳ ለን​ጉሡ ሰገ​ደች፤ ንጉ​ሡም፥ “ምን ሆንሽ?” አላት።</verse>
				<verse number="17">እር​ስ​ዋም አለ​ችው፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ አንተ ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ፦ ልጅሽ ሰሎ​ሞን ከእኔ በኋላ ይነ​ግ​ሣል፤ በዙ​ፋ​ኔም ይቀ​መ​ጣል ብለህ በአ​ም​ላ​ክህ ምለ​ህ​ልኝ አል​ነ​በ​ረ​ምን?</verse>
				<verse number="18">አሁ​ንም፥ እነሆ፥ አዶ​ን​ያስ መን​ገሡ ነው፤ አን​ተም ጌታዬ ንጉሥ ይህን አታ​ው​ቅም፤</verse>
				<verse number="19">እር​ሱም ብዙ በሬ​ዎ​ች​ንና ጠቦ​ቶ​ችን፥ በጎ​ች​ንም ሠው​ቶ​አል፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ልጆች ሁሉ፥ ካህ​ኑ​ንም አብ​ያ​ታ​ርን፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱ​ንም አለቃ ኢዮ​አ​ብን ጠር​ቶ​አል፤ ባሪ​ያ​ህን ሰሎ​ሞ​ንን ግን አል​ጠ​ራ​ውም።</verse>
				<verse number="20">አሁ​ንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ከአ​ንተ በኋላ በጌ​ታዬ በን​ጉሥ ዙፋን ላይ የሚ​ቀ​መ​ጠ​ውን ትነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዐይን ይመ​ለ​ከ​ት​ሃል።</verse>
				<verse number="21">ይህ ባይ​ሆን፥ ጌታዬ ንጉሥ ከአ​ባ​ቶ​ችህ ጋር ባን​ቀ​ላ​ፋህ ጊዜ እኔና ልጄ ሰሎ​ሞን እንደ ኀጢ​አ​ተ​ኞች እን​ቈ​ጠ​ራ​ለን።”</verse>
				<verse number="22">እነ​ሆም፥ እር​ስዋ ከን​ጉሡ ጋር ስት​ነ​ጋ​ገር ነቢዩ ናታን መጣ፤</verse>
				<verse number="23">ለን​ጉ​ሡም፥ “እነሆ፥ ነቢዩ ናታን መጥ​ቶ​አል” ብለው ነገ​ሩት፤ እር​ሱም ወደ ንጉሡ ፊት በገባ ጊዜ በግ​ን​ባሩ በም​ድር ላይ ተደ​ፍቶ ለን​ጉሡ እጅ ነሣ።</verse>
				<verse number="24">ነቢዩ ናታ​ንም አለ፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፦ አንተ ከእኔ በኋላ አዶ​ን​ያስ ይነ​ግ​ሣል፥ በዙ​ፋኔ ላይም ይቀ​መ​ጣል ብለ​ሃ​ልን?</verse>
				<verse number="25">እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬ​ዎ​ች​ንና ጠቦ​ቶ​ችን፥ በጎ​ች​ንም ሠው​ቶ​አል፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ልጆች ሁሉ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱን አለቃ ኢዮ​አ​ብን፥ ካህ​ኑ​ንም አብ​ያ​ታ​ርን ጠር​ቶ​አል፤ እነ​ሆም፥ በፊቱ እየ​በ​ሉና እየ​ጠጡ፦ አዶ​ን​ያስ ሺህ ዓመት ይን​ገሥ ይላሉ።</verse>
				<verse number="26">ነገር ግን እኔን አገ​ል​ጋ​ይ​ህን፥ ካህ​ኑ​ንም ሳዶ​ቅን፥ የዮ​ዳ​ሄ​ንም ልጅ በና​ያ​ስን፥ አገ​ል​ጋ​ይ​ህ​ንም ሰሎ​ሞ​ንን አል​ጠ​ራም።</verse>
				<verse number="27">በውኑ ይህ ነገር ከጌ​ታዬ ከን​ጉሡ የተ​ደ​ረገ ነገር ነውን? ለአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህም ከአ​ንተ በኋላ በጌ​ታዬ በን​ጉሡ ዙፋን ላይ የሚ​ቀ​መ​ጠ​ውን ለምን አል​ነ​ገ​ር​ኸ​ውም?”</verse>
				<verse number="28">ንጉ​ሡም ዳዊት፥ “ቤር​ሳ​ቤ​ህን ጥሩ​ልኝ” ብሎ መለሰ። ወደ ንጉ​ሡም ገባች፤ በን​ጉ​ሡም ፊት ቆመች።</verse>
				<verse number="29">ንጉ​ሡም እን​ዲህ ብሎ ማለ፥ “ነፍ​ሴን ከመ​ከራ ሁሉ ያዳ​ነኝ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን!</verse>
				<verse number="30">በእ​ው​ነት፦ ልጅሽ ሰሎ​ሞን ከእኔ በኋላ ይነ​ግ​ሣል፤ በእ​ኔም ፋንታ በዙ​ፋኔ ላይ ይቀ​መ​ጣል ብዬ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ማል​ሁ​ልሽ፥ እን​ዲሁ ዛሬ በእ​ው​ነት አደ​ር​ጋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="31">ቤር​ሳ​ቤ​ህም በግ​ን​ባ​ርዋ በም​ድር ላይ ተደ​ፍታ ለን​ጉሡ ሰገ​ደ​ችና፥ “ጌታዬ ንጉሥ ዳዊት ለዘ​ለ​ዓ​ለም በሕ​ይ​ወት ይኑር” አለች።</verse>
				<verse number="32">ንጉ​ሡም ዳዊት፥ “ካህ​ኑን ሳዶ​ቅ​ንና ነቢዩ ናታ​ንን የዮ​ዳ​ሄ​ንም ልጅ በና​ያ​ስን ጥሩ​ልኝ” አለ።</verse>
				<verse number="33">ወደ ንጉ​ሡም ገቡ። ንጉ​ሡም አላ​ቸው፥ “የጌ​ታ​ች​ሁን አገ​ል​ጋ​ዮች ይዛ​ችሁ ሂዱ፥ ልጄ​ንም ሰሎ​ሞ​ንን በበ​ቅ​ሎዬ ላይ አስ​ቀ​ም​ጡት፥ ወደ ግዮ​ንም አው​ር​ዱት፤</verse>
				<verse number="34">በዚ​ያም ካህኑ ሳዶ​ቅና ነቢዩ ናታን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ቀብ​ተው ያን​ግ​ሡት፤ መለ​ከ​ትም ነፍ​ታ​ችሁ፦ ሰሎ​ሞን ሺህ ዓመት ይን​ገሥ በሉ።</verse>
				<verse number="35">በኋ​ላ​ውም ተከ​ት​ላ​ችሁ ውጡ፤ እር​ሱም መጥቶ በዙ​ፋኔ ላይ ይቀ​መጥ፤ በእ​ኔም ፋንታ ይን​ገሥ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁ​ዳም ላይ ይነ​ግሥ ዘንድ አዝ​ዣ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="36">የዮ​ዳ​ሄም ልጅ በና​ያስ መልሶ ለን​ጉሡ አለ፥ “እን​ዲሁ ይሁን፤ የጌ​ታ​ዬም የን​ጉሥ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ያጽና።</verse>
				<verse number="37">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጌ​ታዬ ከን​ጉሥ ጋር እንደ ነበረ እን​ዲሁ ከሰ​ሎ​ሞን ጋር ይሁን፤ ዙፋ​ኑ​ንም ከጌ​ታዬ ከን​ጉሡ ከዳ​ዊት ዙፋን የበ​ለጠ ያድ​ርግ።”</verse>
				<verse number="38">ካህ​ኑም ሳዶ​ቅና ነቢዩ ናታን የዮ​ዳ​ሄም ልጅ በና​ያስ ከሊ​ታ​ው​ያ​ንና ፈሊ​ታ​ው​ያ​ንም ወረዱ፤ ሰሎ​ሞ​ን​ንም በን​ጉሡ በዳ​ዊት በቅሎ ላይ አስ​ቀ​ም​ጠው ወደ ግዮን ወሰ​ዱት።</verse>
				<verse number="39">ካህ​ኑም ሳዶቅ ከድ​ን​ኳኑ የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ወስዶ ሰሎ​ሞ​ንን ቀባ፤ መለ​ከ​ትም ነፋ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “ሰሎ​ሞን ሺህ ዓመት ይን​ገሥ” አሉ።</verse>
				<verse number="40">ሕዝ​ቡም ሁሉ እር​ሱን ተከ​ት​ለው ወጡ፤ ከበ​ሮ​ንና መሰ​ን​ቆ​ንም መቱ፥ በታ​ላ​ቅም ደስታ ደስ አላ​ቸው፤ ከጩ​ኸ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ምድር ተና​ወ​ጠች።</verse>
				<verse number="41">አዶ​ን​ያ​ስና እር​ሱም የጠ​ራ​ቸው ሁሉ መብ​ሉና መጠጡ ተፈ​ጽሞ ሳለ ሰሙ፤ ኢዮ​አ​ብም የመ​ለ​ከት ድምፅ በሰማ ጊዜ፥ “ይህ በከ​ተማ የም​ሰ​ማው ድምፅ ምን​ድን ነው?” አለ።</verse>
				<verse number="42">እር​ሱም ይህን ሲና​ገር የካ​ህኑ የአ​ብ​ያ​ታር ልጅ ዮና​ታን መጣ፤ አዶ​ን​ያ​ስም፥ “አንተ ኀያል ሰው ነህና፥ መል​ካ​ምም ታወ​ራ​ል​ና​ለ​ህና ግባ” አለው።</verse>
				<verse number="43">ዮና​ታ​ንም ለአ​ዶ​ን​ያስ እን​ዲህ ብሎ መለሰ፥ “በእ​ው​ነት ጌታ​ችን ንጉሥ ዳዊት ሰሎ​ሞ​ንን አነ​ገ​ሠው።</verse>
				<verse number="44">ንጉ​ሡም ከእ​ርሱ ጋር ካህ​ኑን ሳዶ​ቅ​ንና ነቢ​ዩን ናታ​ንን፥ የዮ​ዳ​ሄ​ንም ልጅ በና​ያ​ስን፥ ከሊ​ታ​ው​ያ​ን​ንና ፈሊ​ታ​ው​ያ​ን​ንም ላከ፤ በን​ጉ​ሡም በቅሎ ላይ አስ​ቀ​መ​ጡት።</verse>
				<verse number="45">ካህ​ኑም ሳዶ​ቅና ነቢዩ ናታን ቀብ​ተው በግ​ዮን አነ​ገ​ሡት፤ ከዚ​ያም ደስ ብሎ​አ​ቸው ወጡ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱም አስ​ተ​ጋ​ባች፤ የሰ​ማ​ች​ሁ​ትም ድምፅ ይህ ነው።</verse>
				<verse number="46">ሰሎ​ሞ​ንም በመ​ን​ግ​ሥቱ ዙፋን ላይ ተቀ​ም​ጦ​አል።</verse>
				<verse number="47">የን​ጉ​ሡም አገ​ል​ጋ​ዮች ገብ​ተው፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ሎ​ሞ​ንን ስም ከስ​ምህ ይልቅ መል​ካም ያድ​ርግ፤ ዙፋ​ኑ​ንም ከዙ​ፋ​ንህ የበ​ለጠ ያድ​ርግ’ ብለው ጌታ​ቸ​ውን ንጉሡ ዳዊ​ትን መረቁ፤” ንጉ​ሡም በአ​ል​ጋው ላይ ሆኖ ሰገደ።</verse>
				<verse number="48">ንጉ​ሡም፥ “ዐይኔ እያየ ዛሬ በዙ​ፋኔ ላይ የሚ​ቀ​መ​ጠ​ውን ዘር የሰ​ጠኝ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን” አለ።</verse>
				<verse number="49">አዶ​ን​ያ​ስም የጠ​ራ​ቸው ሁሉ ፈሩ፤ ተነ​ሥ​ተ​ውም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በየ​መ​ን​ገ​ዳ​ቸው ሄዱ።</verse>
				<verse number="50">አዶ​ን​ያ​ስም ከሰ​ሎ​ሞን ፊት የተ​ነሣ ፈራ፤ ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ቀንድ ያዘ።</verse>
				<verse number="51">ለሰ​ሎ​ሞ​ንም፥ “እነሆ፥ አዶ​ን​ያስ ንጉ​ሡን ሰሎ​ሞ​ንን ፈርቶ፦ ንጉሡ ሰሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዩን በሰ​ይፍ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ለኝ ዛሬ ይማ​ል​ልኝ ብሎ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ቀንድ ይዞ​አል” አሉት።</verse>
				<verse number="52">ሰሎ​ሞ​ንም፥ “እርሱ አካ​ሄ​ዱን ያሳ​መረ እንደ ሆነ ከእ​ርሱ አን​ዲት ጠጕር እንኳ በም​ድር ላይ አት​ወ​ድ​ቅም፤ ነገር ግን ክፋት የተ​ገ​ኘ​በት እንደ ሆነ ይሞ​ታል” አለ።</verse>
				<verse number="53">ንጉሡ ሰሎ​ሞ​ንም ላከ፤ ከመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም አወ​ረ​ዱት፤ መጥ​ቶም ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን ሰገደ፤ ሰሎ​ሞ​ንም፥ “ወደ ቤትህ ሂድ” አለው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ዳዊ​ትም የሚ​ሞ​ት​በት ወራት ደረሰ፤ ልጁ​ንም ሰሎ​ሞ​ንን እን​ዲህ ሲል አዘ​ዘው፦</verse>
				<verse number="2">“እኔ የም​ድ​ሩን መን​ገድ ሁሉ እሄ​ዳ​ለሁ፤ በርታ ሰውም ሁን፤</verse>
				<verse number="3">እን​ደ​ማ​ዝ​ዝህ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ሁሉ ታውቅ ዘንድ፥ በሙሴ ሕግ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዛ​ቱን፥ ፍር​ዱ​ንና ምስ​ክ​ሩ​ንም ትጠ​ብቅ ዘንድ በመ​ን​ገ​ዱም ትሄድ ዘንድ፥ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ጠብቅ።</verse>
				<verse number="4">ይኸ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እኔ፦ ‘ልጆ​ችህ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ቢጠ​ብቁ፥ በፊ​ቴም በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውና በፍ​ጹም ነፍ​ሳ​ቸው በእ​ው​ነት ቢሄዱ ከእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን ሰው አይ​ጠ​ፋም’ ብሎ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ያጸና ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="5">አን​ተም ደግሞ የሶ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አብ፥ ሁለ​ቱን የእ​ስ​ራ​ኤል ሠራ​ዊት አለ​ቆች የኔር ልጅ አበ​ኔ​ርን የኢ​ያ​ቴ​ር​ንም ልጅ አሜ​ሳ​ይን ገድሎ፥ በእኔ ላይ ያደ​ረ​ገ​ውን ታው​ቃ​ለህ፤ የጦ​ር​ነ​ት​ንም ደም በሰ​ላም አፈ​ሰሰ፤ በወ​ገ​ቡም ባለው ድግና በእ​ግ​ሩም ባለው ጫማ ንጹሕ ደም አኖረ።</verse>
				<verse number="6">አን​ተም እንደ ጥበ​ብህ አድ​ርግ፤ ሽበ​ቱ​ንም በሰ​ላም ወደ መቃ​ብር አታ​ው​ር​ደው።</verse>
				<verse number="7">ከወ​ን​ድ​ምህ ከአ​ቤ​ሴ​ሎም ፊት በሸ​ሸሁ ጊዜ ቀር​በ​ው​ኛ​ልና ለገ​ለ​ዓ​ዳ​ዊው ለቤ​ር​ዜሊ ልጆች ቸር​ነ​ትን አድ​ር​ግ​ላ​ቸው። በማ​ዕ​ድ​ህም ከሚ​በ​ሉት መካ​ከል ይሁኑ።</verse>
				<verse number="8">የባ​ው​ሬም ሀገር ሰው የብ​ን​ያ​ማ​ዊው የጌራ ልጅ ሳሚ እነሆ! በአ​ንተ ዘንድ ነው፤ እኔም ወደ መሃ​ና​ይም በሄ​ድሁ ጊዜ ብርቱ ርግ​ማን ረገ​መኝ፤ ከዚ​ያም በኋላ ዮር​ዳ​ኖ​ስን በተ​ሻ​ገ​ርሁ ጊዜ ሊቀ​በ​ለኝ ወረደ፤ እኔም፦ ‘በሰ​ይፍ አል​ገ​ድ​ል​ህም’ ብዬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምየ​ለ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">አንተ ግን ጥበ​በኛ ሰው ነህና ንጹሕ አታ​ድ​ር​ገው፤ የም​ታ​ደ​ር​ግ​በ​ት​ንም አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ ሽበ​ቱ​ንም በደም ወደ መቃ​ብር አው​ር​ደው” አለው።</verse>
				<verse number="10">ዳዊ​ትም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ተቀ​በረ።</verse>
				<verse number="11">ዳዊ​ትም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ የነ​ገ​ሠ​በት ዘመን አርባ ዓመት ነበረ። በኬ​ብ​ሮን ሰባት ዓመት፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="12">ሰሎ​ሞ​ንም በአ​ባቱ በዳ​ዊት ዙፋን ተቀ​መጠ፤ መን​ግ​ሥ​ቱም እጅግ ጸና።</verse>
				<verse number="13">የአ​ጊት ልጅ አዶ​ን​ያ​ስም ወደ ሰሎ​ሞን እናት ወደ ቤር​ሳ​ቤህ መጣ፤ ሰገ​ደ​ላ​ትም፤ እር​ስ​ዋም፥ “ወደ እኔ መም​ጣ​ትህ በሰ​ላም ነውን?” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “በሰ​ላም ነው” አለ።</verse>
				<verse number="14">ደግ​ሞም፥ “ከአ​ንቺ ጋር ጉዳይ አለኝ” አለ፤ እር​ስ​ዋም፥ “ተና​ገር” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="15">እር​ሱም፥ “መን​ግ​ሥቱ ለእኔ እንደ ነበረ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ንጉሥ እሆን ዘንድ ፊታ​ቸ​ውን ወደ እኔ አድ​ር​ገው እንደ ነበረ አንቺ ታው​ቂ​ያ​ለሽ፤ ነገር ግን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ሆኖ​ለ​ታ​ልና መን​ግ​ሥት ተመ​ልሳ ለወ​ን​ድሜ ሆና​ለች።</verse>
				<verse number="16">አሁ​ንም አን​ዲት ልመና እለ​ም​ን​ሻ​ለሁ ፤ ፊት​ሽ​ንም አት​መ​ል​ሺ​ብኝ” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “ተና​ገር” አለ​ችው፤</verse>
				<verse number="17">እር​ሱም፥ “ፊቱን አይ​መ​ል​ስ​ብ​ሽ​ምና፥ ሱነ​ማ​ዪ​ቱን አቢ​ሳን ይድ​ር​ልኝ ዘንድ ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን እን​ድ​ት​ነ​ግ​ሪው እለ​ም​ን​ሻ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="18">ቤር​ሳ​ቤ​ህም፥ “መል​ካም ነው፤ ስለ አንተ ለን​ጉሡ እነ​ግ​ረ​ዋ​ለሁ” አለች።</verse>
				<verse number="19">ቤር​ሳ​ቤ​ህም የአ​ዶ​ን​ያ​ስን ነገር ትነ​ግ​ረው ዘንድ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎ​ሞን ገባች፤ ንጉ​ሡም ሊቀ​በ​ላት ተነሣ፤ ሳማ​ትም፤ በዙ​ፋ​ኑም ተቀ​መጠ፤ ለን​ጉ​ሡም እናት ወን​በር አስ​መ​ጣ​ላት፤ በቀ​ኙም ተቀ​መ​ጠች።</verse>
				<verse number="20">እር​ስ​ዋም፥ “አን​ዲት ትንሽ ልመና እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ ፊት​ህን አት​መ​ል​ስ​ብኝ” አለች። ንጉ​ሡም፥ “እናቴ ሆይ! ፊቴን አል​መ​ል​ስ​ብ​ሽ​ምና ለምኚ” አላት።</verse>
				<verse number="21">እር​ስ​ዋም፥ “ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ለወ​ን​ድ​ምህ ለአ​ዶ​ን​ያስ ሱነ​ማ​ዪቱ አቢ​ሳን ይስ​ጡት” አለች።</verse>
				<verse number="22">ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ለእ​ናቱ መልሶ፥ “ሱነ​ማ​ዪ​ቱን አቢ​ሳን ለአ​ዶ​ን​ያስ ለምን ትለ​ም​ኚ​ለ​ታ​ለሽ? ታላቅ ወን​ድሜ ነውና መን​ግ​ሥ​ትን ደግሞ ለም​ኚ​ለት፤ ካህ​ኑም አብ​ያ​ታ​ርና የሶ​ር​ህያ ልጅ የጭ​ፍ​ሮች አለቃ ኢዮ​አብ ደግሞ ከእ​ርሱ ጋር ናቸው” አላት።</verse>
				<verse number="23">ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን፦ እን​ዲህ ሲል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማለ። “አዶ​ን​ያስ ይህን ቃል በሕ​ይ​ወቱ ላይ እንደ ተና​ገረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ያድ​ር​ግ​ብኝ፤ ይህ​ንም ይጨ​ም​ር​ብኝ።</verse>
				<verse number="24">አሁ​ንም ያጸ​ናኝ፥ በአ​ባ​ቴም በዳ​ዊት ዙፋን ላይ ያስ​ቀ​መ​ጠኝ፥ እንደ ተና​ገ​ረ​ውም ቤትን የሠ​ራ​ልኝ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ዛሬ አዶ​ን​ያስ ፈጽሞ ይገ​ደ​ላል።</verse>
				<verse number="25">ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን የዮ​ዳ​ሄን ልጅ በና​ያ​ስን ላከ፤ እር​ሱም አረ​ደው፤ ያን​ጊ​ዜም አዶ​ን​ያስ ሞተ።</verse>
				<verse number="26">ንጉ​ሡም ካህ​ኑን አብ​ያ​ታ​ርን፥ “አንተ ዛሬ የሞት ሰው ነበ​ርህ፤ ነገር ግን የአ​ም​ላ​ክን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት በአ​ባቴ በዳ​ዊት ፊት ስለ ተሸ​ከ​ምህ፥ አባ​ቴም የተ​ቀ​በ​ለ​ውን መከራ ሁሉ አንተ ስለ ተቀ​በ​ልህ አል​ገ​ድ​ል​ህ​ምና በዓ​ና​ቶት ወዳ​ለው ወደ እር​ሻህ ፈጥ​ነህ ሂድ” አለው።</verse>
				<verse number="27">በሴ​ሎም በዔሊ ቤት ላይ የተ​ና​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ሰሎ​ሞን አብ​ያ​ታ​ርን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክህ​ነት አወ​ጣው።</verse>
				<verse number="28">ለሶ​ር​ህያ ልጅ ለኢ​ዮ​አ​ብም ወሬ ደረ​ሰ​ለት፤ ኢዮ​አብ ከአ​ዶ​ን​ያስ ጋር ተባ​ብሮ ተከ​ተ​ለው እንጂ ከሰ​ሎ​ሞን ጋር አል​ተ​ባ​በ​ረም፤ አል​ተ​ከ​ተ​ለ​ው​ምም ነበ​ርና። ኢዮ​አ​ብም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድን​ኳን ሸሽቶ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ቀንድ ያዘ።</verse>
				<verse number="29">ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ኢዮ​አብ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድን​ኳን ሸሽቶ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ቀንድ እንደ ያዘ ሰማ፤ ንጉሥ ሰሎ​ሞ​ንም ወደ ኢዮ​አብ እን​ዲህ ሲል ላከ፤ “በመ​ሠ​ዊ​ያው ቀንድ የተ​ማ​ጠ​ንህ ምን ሆነህ ነው?” ኢዮ​አ​ብም፥ “ፈር​ቼ​ሃ​ለ​ሁና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተማ​ጠ​ንሁ” አለ። ሰሎ​ሞ​ንም የዮ​ዳ​ሄን ልጅ በን​ያ​ስን ልኮ፥ “ሂድ ግደ​ልና ቅበ​ረው” ብሎ አዘ​ዘው።</verse>
				<verse number="30">የዮ​ዳሄ ልጅ በን​ያ​ስም ወደ ኢዮ​አብ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድን​ኳን መጥቶ፥ “ንጉሡ፦ ውጣ ይል​ሃል” አለው፤ ኢዮ​አ​ብም፥ “በዚህ እሞ​ታ​ለሁ እንጂ አል​ወ​ጣም” አለ። የዮ​ዳሄ ልጅ በን​ያ​ስም፦ ተመ​ልሶ “ኢዮ​አብ የተ​ና​ገ​ረው ቃል፥ የመ​ለ​ሰ​ል​ኝም እን​ዲህ ነው” ብሎ ለን​ጉሡ ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="31">ንጉ​ሡም አለው፥ “ሂድና እንደ ነገ​ረህ አድ​ርግ፤ ገድ​ለ​ህም ቅበ​ረው፤ ኢዮ​አ​ብም በከ​ንቱ ያፈ​ሰ​ሰ​ውን ደም ከእ​ኔና ከአ​ባቴ ቤት ታር​ቃ​ለህ።</verse>
				<verse number="32">አባቴ ዳዊት ሳያ​ውቅ ከእ​ርሱ የሚ​ሻ​ሉ​ትን ሁለ​ቱን ጻድ​ቃን ሰዎች፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሠራ​ዊት አለቃ የኔ​ርን ልጅ አበ​ኔ​ርን፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ሠራ​ዊት አለቃ የኢ​ያ​ቴ​ርን ልጅ አሜ​ሳ​ይን በሰ​ይፍ ገድ​ሎ​አ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዐ​መፅ ደሙን በራሱ ላይ መለሰ።</verse>
				<verse number="33">ደማ​ቸ​ውም በኢ​ዮ​አብ ራስና በዘሩ ራስ ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይመ​ለስ፤ ለዳ​ዊት ግን ለዘ​ሩና ለቤቱ፥ ለዙ​ፋ​ኑም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰላም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይሁን።”</verse>
				<verse number="34">የዮ​ዳ​ሄም ልጅ በን​ያስ ወጥቶ ያዘው፤ ገደ​ለ​ውም፤ በም​ድረ በዳም ባለው በራሱ ቤት ቀበ​ረው።</verse>
				<verse number="35">ንጉ​ሡም በእ​ርሱ ፋንታ የዮ​ዳ​ሄን ልጅ በን​ያ​ስን የሠ​ራ​ዊቱ አለቃ አድ​ርጎ ሾመ፤ መን​ግ​ሥ​ቱም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጸናች። በአ​ብ​ያ​ታ​ርም ፋንታ ካህ​ኑን ሳዶ​ቅን ሾመ።</verse>
				<verse number="36">ንጉ​ሡም ልኮ ሳሚን አስ​ጠ​ራ​ውና እን​ዲህ አለው፥ “በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቤት ሠር​ተህ ተቀ​መጥ፤ ወዲ​ህና ወዲ​ያም አት​ውጣ።</verse>
				<verse number="37">በም​ት​ወ​ጣ​በ​ትና የቄ​ድ​ሮ​ን​ንም ፈፋ በም​ት​ሻ​ገ​ር​በት ቀን ፈጽ​መህ እን​ደ​ም​ት​ሞት ዕወቅ፤ ደም​ህም በራ​ስህ ላይ ይሆ​ናል።” ያን​ጊ​ዜም ንጉሡ አማ​ለው።</verse>
				<verse number="38">ሳሚም ንጉ​ሡን፥ “ጌታዬ ንጉሥ የተ​ና​ገ​ር​ኸው ቃል መል​ካም ነው፤ አገ​ል​ጋ​ይ​ህም እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋል” አለው፤ ሳሚም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሦስት ዓመት ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="39">ከሦ​ስት ዓመ​ትም በኋላ ከሳሚ አገ​ል​ጋ​ዮች ሁለቱ ወደ ጌት ንጉሥ ወደ መዓካ ልጅ ወደ አን​ኩስ ኰበ​ለሉ፤ ለሳ​ሚም፥ “እነሆ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በጌት ናቸው” ብለው ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="40">ሳሚም ተነሣ፤ አህ​ያ​ው​ንም ጭኖ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ይሻ ዘንድ ወደ ጌት ወደ አን​ኩስ ዘንድ ሄደ፤ ሳሚም ሄዶ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ከጌት አመጣ።</verse>
				<verse number="41">ሰሎ​ሞ​ንም ሳሚ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ጌት ሄዶ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን እን​ዳ​መጣ ሰማ።</verse>
				<verse number="42">ንጉ​ሡም ልኮ ሳሚን አስ​ጠ​ራና፥ “ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ለመ​ሄድ በም​ት​ወ​ጣ​በት ቀን ፈጽ​መህ እን​ድ​ት​ሞት ዕወቅ ብዬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አላ​ስ​ማ​ል​ሁ​ህ​ምን? ወይስ አላ​ስ​መ​ሰ​ከ​ር​ሁ​ብ​ህ​ምን?</verse>
				<verse number="43">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መሐላ፥ እኔም ያዘ​ዝ​ሁ​ትን ትእ​ዛዝ ስለ​ምን አል​ጠ​በ​ቅ​ህም?” አለው።</verse>
				<verse number="44">ንጉ​ሡም ደግሞ ሳሚን፥ “አንተ በአ​ባቴ በዳ​ዊት ላይ የሠ​ራ​ኸ​ውን፥ ልብ​ህም ያሰ​በ​ውን ክፋት ሁሉ ታው​ቃ​ለህ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክፋ​ት​ህን በራ​ስህ ላይ ይመ​ል​ሳል።</verse>
				<verse number="45">ንጉሡ ሰሎ​ሞን ግን የተ​ባ​ረከ ይሆ​ናል፤ የዳ​ዊ​ትም ዙፋን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጸ​ናል” አለው።</verse>
				<verse number="46">ሰሎ​ሞ​ንም የዮ​ዳ​ሄን ልጅ በን​ያ​ስን አዘ​ዘው፤ ወጥ​ቶም ገደ​ለው። የሰ​ሎ​ሞ​ንም መን​ግ​ሥት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጸና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ሰሎ​ሞ​ንም ለግ​ብፅ ንጉሥ ለፈ​ር​ዖን አማች ሆነ፤ የፈ​ር​ዖ​ን​ንም ልጅ አገባ፤ ቤቱ​ንና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዙሪያ ያለ​ውን ቅጥር ሠርቶ እስ​ኪ​ፈ​ጽም ድረስ ወደ ዳዊት ከተማ አም​ጥቶ አስ​ገ​ባት።</verse>
				<verse number="2">እስ​ከ​ዚ​ያም ቀን ድረስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አል​ተ​ሠ​ራም ነበ​ርና ሕዝቡ በኮ​ረ​ብታ ላይ ይሠ​ዉና ያጥኑ ነበር።</verse>
				<verse number="3">ሰሎ​ሞ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይወ​ድድ ነበር፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ሥር​ዐት ይሄድ ነበር፤ ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ታው ላይ ይሠ​ዋና ያጥን ነበር።</verse>
				<verse number="4">ገባ​ዖን ፈጽማ ትሰፋ ነበ​ርና በዚያ መሥ​ዋ​ዕት ይሠዋ ዘንድ ተነ​ሥቶ ሄደ፤ ሰሎ​ሞ​ንም በዚያ መሠ​ዊያ ላይ በገ​ባ​ዖን አንድ ሺህ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ሠዋ።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በገ​ባ​ዖን ለሰ​ሎ​ሞን በሌ​ሊት በሕ​ልም ተገ​ለ​ጠ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰሎ​ሞ​ንን፥ “እን​ድ​ሰ​ጥህ የም​ት​ፈ​ል​ገ​ውን ለምን” አለው።</verse>
				<verse number="6">ሰሎ​ሞ​ንም አለ፥ “እርሱ በፊ​ትህ በእ​ው​ነ​ትና በጽ​ድቅ፥ በል​ብም ቅን​ነት ከአ​ንተ ጋር እንደ ሄደ፥ ከአ​ባቴ ከባ​ሪ​ያህ ከዳ​ዊት ጋር ታላቅ ቸር​ነት አድ​ር​ገ​ሃል፤ ዛሬ እንደ ሆነም በዙ​ፋኑ ላይ የሚ​ቀ​መጥ ልጅ ሰጥ​ተህ ታላ​ቁን ቸር​ነ​ት​ህን አቈ​ይ​ተ​ህ​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="7">አሁ​ንም አቤቱ አም​ላኬ ሆይ፥ እኔን ባሪ​ያ​ህን በአ​ባቴ በዳ​ዊት ፋንታ አን​ግ​ሠ​ኸ​ኛል፤ እኔም መው​ጫ​ዬ​ንና መግ​ቢ​ያ​ዬን የማ​ላ​ውቅ ታናሽ ብላ​ቴና ነኝ።</verse>
				<verse number="8">ባሪ​ያ​ህም ያለው አንተ በመ​ረ​ጥ​ኸው ሕዝ​ብህ፥ ስለ ብዛ​ቱም ይቈ​ጠር ዘንድ በማ​ይ​ቻል በታ​ላቅ ሕዝብ መካ​ከል ነው።</verse>
				<verse number="9">ስለ​ዚ​ህም ሰምቶ በሕ​ዝ​ብህ ላይ መፍ​ረድ ይችል ዘንድ፥ መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ው​ንም ይለይ ዘንድ ለባ​ሪ​ያህ አስ​ተ​ዋይ ልቡና ስጠው፤ አለ​ዚ​ያማ በዚህ በታ​ላቅ ሕዝብ ላይ ይፈ​ርድ ዘንድ ማን ይች​ላል?”</verse>
				<verse number="10">ሰሎ​ሞ​ንም ይህን ነገር ስለ ለመነ፥ ነገሩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ አሰ​ኘው።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “ፍር​ድን ትለይ ዘንድ ለራ​ስህ ማስ​ተ​ዋ​ልን ለመ​ንህ እንጂ ለራ​ስህ ብዙ ዘመ​ና​ትን፥ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ት​ንም፥ የጠ​ላ​ቶ​ች​ህ​ንም ነፍስ ሳት​ለ​ምን ይህን ነገር ለም​ነ​ሃ​ልና፥</verse>
				<verse number="12">እነሆ፥ እኔ እንደ ቃልህ አድ​ር​ጌ​ል​ሃ​ለሁ፤ እነ​ሆም፥ ማንም የሚ​መ​ስ​ልህ ከአ​ንተ በፊት እን​ደ​ሌለ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ እን​ዳ​ይ​ነሣ አድ​ርጌ ጥበ​በ​ኛና አስ​ተ​ዋይ ልቡና ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">ደግ​ሞም ከነ​ገ​ሥ​ታት የሚ​መ​ስ​ልህ ማንም እን​ዳ​ይ​ኖር ያል​ለ​መ​ን​ኸ​ውን ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትና ክብር ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">አባ​ት​ህም ዳዊት እንደ ሄደ፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንና ትእ​ዛ​ዜን ትጠ​ብቅ ዘንድ በመ​ን​ገዴ የሄ​ድህ እንደ ሆነ፥ ዘመ​ን​ህን አበ​ዛ​ል​ሀ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="15">ሰሎ​ሞ​ንም ነቃ፤ እነ​ሆም፥ ሕልም ነበረ፤ ተነ​ሥ​ቶም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሄደ፤ በጽ​ዮ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ቆመ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አሳ​ረገ፤ የደ​ኅ​ን​ነ​ት​ንም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ሁሉ ታላቅ ግብዣ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="16">በዚያ ጊዜም ሁለት ጋለ​ሞ​ታ​ዎች ሴቶች ወደ ንጉሡ መጥ​ተው ቆሙ።</verse>
				<verse number="17">አን​ደ​ኛ​ዪ​ቱም ሴት አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! ስማኝ፥ እኔና ይህች ሴት በአ​ንድ ቤት እን​ኖ​ራ​ለን፤ በአ​ንድ ቤትም ወለ​ድን።</verse>
				<verse number="18">እኔም በወ​ለ​ድሁ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ይህች ሴት ወለ​ደች፤ እኛ በቤት ውስጥ አብ​ረን ነበ​ርን፤ ከሁ​ለ​ታ​ች​ንም በቀር ማንም በቤት ውስጥ አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="19">እር​ስ​ዋም በላዩ ስለ ተኛ​ች​በት የዚ​ህች ሴት ልጅ በሌ​ሊት ሞተ።</verse>
				<verse number="20">እር​ስ​ዋም በእ​ኩለ ሌሊት ተነ​ሥታ፥ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ተኝቼ ሳለሁ፥ ልጄን ከብ​ብቴ ወሰ​ደች፤ በብ​ብ​ቷም አስ​ተ​ኛ​ችው፤ የሞ​ተ​ው​ንም ልጅ​ዋን በእኔ ብብት አስ​ተ​ኛ​ችው።</verse>
				<verse number="21">ልጄ​ንም አጠባ ዘንድ በማ​ለዳ ብነሣ፥ ያን የሞ​ተ​ውን ልጅ አገ​ኘሁ፤ ነገር ግን ብር​ሃን በሆነ ጊዜ ተመ​ለ​ከ​ት​ሁት፤ እነ​ሆም፥ የወ​ለ​ድ​ሁት ልጄ አል​ነ​በ​ረም።”</verse>
				<verse number="22">ሁለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ሴት፥ “አይ​ደ​ለም ደኅ​ነ​ኛው የእኔ ልጅ ነው፤ የሞ​ተው የአ​ንቺ ልጅ ነው እንጂ አለች።” እን​ዲ​ሁም በን​ጉሡ ፊት ይነ​ጋ​ገሩ ነበር።</verse>
				<verse number="23">በዚያ ጊዜም ንጉሡ፥ “አንቺ፦ ደኅ​ነ​ኛው የእኔ ልጅ ነው፤ የሞ​ተ​ውም የአ​ንቺ ልጅ ነው ትያ​ለሽ፤ አን​ቺም፦ አይ​ደ​ለም የሞ​ተው የአ​ንቺ ልጅ ነው፤ ደኅ​ነ​ኛ​ውም የእኔ ልጅ ነው ትያ​ለሽ”። አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">ንጉ​ሡም፥ “ሰይፍ አም​ጡ​ልኝ” አለ፤ እነ​ር​ሱም ወደ ንጉሡ ሰይፍ አመጡ።</verse>
				<verse number="25">ንጉ​ሡም፥ “ደኅ​ነ​ኛ​ውን ሕፃን ለሁ​ለት ቈር​ጣ​ችሁ ለአ​ን​ዲቱ አን​ዱን ክፍል፥ ለሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ሁለ​ተ​ኛ​ውን ክፍል ስጡ” አለ።</verse>
				<verse number="26">ደኅ​ነ​ኛ​ውም ሕፃን የነ​በ​ራት ሴት አን​ጀ​ትዋ ስለ ልጅዋ ታው​ኳ​ልና፥ “ጌታዬ ሆይ! አይ​ደ​ለም፤ ደኅ​ነ​ኛ​ውን ለእ​ር​ስዋ ስጣት እንጂ መግ​ደ​ልስ አት​ግ​ደ​ሉት” ብላ ለን​ጉሡ ተና​ገ​ረች። ያች​ኛ​ዪቱ ግን፥ “አካ​ፍ​ሉን እንጂ ለእ​ኔም ለእ​ር​ስ​ዋም አይ​ሁን” አለች።</verse>
				<verse number="27">ንጉ​ሡም መልሶ እን​ዲህ አለ፥ “ለእ​ር​ስዋ ስጧት እንጂ መግ​ደ​ልስ አት​ግ​ደ​ሉት ላለ​ችው ሴት ስጡ​አት፤ እናቱ እር​ስዋ ናትና።”</verse>
				<verse number="28">ንጉ​ሡም የፈ​ረ​ደ​ውን ፍርድ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ሰሙ፤ ፍር​ድን ለማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ በእ​ርሱ ላይ እንደ ነበረ አይ​ተ​ዋ​ልና ከን​ጉሡ ፊት የተ​ነሣ ፈሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር።</verse>
				<verse number="2">የነ​በ​ሩ​ትም አለ​ቆች እነ​ዚህ ናቸው፥ የሳ​ዶቅ ልጅ ካህኑ ዓዛ​ር​ያስ፤</verse>
				<verse number="3">ጸሓ​ፊ​ዎ​ቹም የሱባ ልጆች ኤል​ያ​ብና አኪያ፥ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሒ​ሉድ ልጅ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ነበረ።</verse>
				<verse number="4">የዮ​ዳ​ሄም ልጅ በን​ያስ የሠ​ራ​ዊት አለቃ ነበረ፤ ሳዶ​ቅና አብ​ያ​ታ​ርም ካህ​ናት ነበሩ፤</verse>
				<verse number="5">የና​ታ​ንም ልጅ ኦርኒያ የሹ​ሞች አለቃ ነበረ፤ የና​ታ​ንም ልጅ ዘባት የን​ጉሡ አማ​ካ​ሪና ወዳጅ ነበረ፤</verse>
				<verse number="6">አኪ​ያ​ልም የቤት አዛዥ፥ ኤል​ያ​ቅም የቤት አዛ​ዦች አለቃ ነበረ፥ የሳ​ፋን ልጅ ኤል​ያ​ፍም የቤተ ሰብ ሐላፊ፥ የአ​ዶን ልጅ አዶኒ​ራ​ምም ግብር አስ​ገ​ባሪ ነበረ።</verse>
				<verse number="7">ሰሎ​ሞ​ንም ለን​ጉ​ሡና ለቤ​ተ​ሰቡ ቀለብ የሚ​ሰጡ በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ ዐሥራ ሁለት ሹሞ​ችን ሾመ። ከዓ​መቱ ውስጥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱን ወር እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ይቀ​ልቡ ነበር።</verse>
				<verse number="8">ስማ​ቸ​ውም ይህ ነበረ፤ በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር በኤ​ፍ​ሬም የሖር ልጅ ቢዖር፥</verse>
				<verse number="9">በማ​ኪ​ስና በሰ​አ​ል​ቢን፥ በቤት ሳሚ​ስና በኤ​ሎ​ን​ቤ​ት​ሐ​ናን የዴ​ቀር ልጅ፥</verse>
				<verse number="10">በአ​ራ​ቦት፥ በሶ​ኮ​ትና በኦ​ፌር ሀገር ሁሉ የሔ​ሴድ ልጅ ነበረ፤</verse>
				<verse number="11">በዶር ሀገር ዳርቻ ሁሉ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነበረ፤ ለእ​ር​ሱም የሰ​ሎ​ሞን ልጅ ጣፈ​ትም ሚስቱ ነበ​ረች፤</verse>
				<verse number="12">ከቤ​ት​ሳን ጀምሮ እስከ አቤ​ል​ም​ሖ​ላና እስከ ዮቅ​ም​ዓም ማዶ ድረስ በታ​ዕ​ና​ክና በመ​ጊዶ በጸ​ር​ታ​ንም አጠ​ገብ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል በታች ባለው በቤ​ት​ሳን ሁሉ የአ​ሒ​ሉድ ልጅ በዓና ነበረ፤</verse>
				<verse number="13">በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ የጌ​ቤር ልጅ ነበረ፤ ለእ​ር​ሱም በገ​ለ​ዓድ ያሉት የም​ናሴ ልጅ የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች ነበሩ፤ ለእ​ር​ሱም ደግሞ በባ​ሳን፥ በአ​ር​ጎብ ዳርቻ ያሉት ቅጥ​ርና የናስ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎች የነ​በ​ረ​ባ​ቸው ስድሳ ታላ​ላቅ ከተ​ሞች ነበ​ሩ​በት፤</verse>
				<verse number="14">በማ​ሃ​ና​ይም የሳዶ ልጅ አሒ​ና​ዳብ ነበረ፤</verse>
				<verse number="15">በን​ፍ​ታ​ሌ​ምም አኪ​ማ​ኦስ ነበረ፤ እር​ሱም የሰ​ሎ​ሞ​ንን ልጅ ባሴ​ማ​ትን አግ​ብቶ ነበር፤</verse>
				<verse number="16">በአ​ሴ​ርና በበ​ዓ​ሎት የኩሲ ልጅ በዓና ነበረ፤</verse>
				<verse number="17">በይ​ሳ​ኮ​ርም የፋ​ሩዋ ልጅ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ነበረ፤</verse>
				<verse number="18">በብ​ን​ያም የኤላ ልጅ ሳሚ ነበረ፤</verse>
				<verse number="19">በአ​ሞ​ራ​ው​ያን ንጉሥ በሴ​ዎ​ንና በባ​ሳን ንጉሥ በዐግ ሀገር፥ በጋድ ሀገር፥ የአዴ ልጅ ጌቤር ነበረ፤ በይ​ሁ​ዳም ምድር ላይ እርሱ ብቻ​ውን ሹም ነበረ።</verse>
				<verse number="20">ይሁ​ዳና እስ​ራ​ኤ​ልም እንደ ባሕር አሸዋ ብዛት ብዙ ነበሩ፤ ይበ​ሉና ይጠ​ጡም፥ ደስም ይላ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="21">ሰሎ​ሞ​ንም ከወ​ንዙ ጀምሮ እስከ ግብፅ ምድር ዳርቻ እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገር ድረስ በመ​ን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር፤ ግብ​ርም ያመ​ጡ​ለት ነበር፤ በዕ​ድ​ሜ​ውም ሙሉ ለሰ​ሎ​ሞን ይገዙ ነበር።</verse>
				<verse number="22">ለሰ​ሎ​ሞ​ንም ለቀን ለቀኑ ቀለብ የሚ​ሆን ሠላሳ ቆሮስ መል​ካም ዱቄ​ትና ስድሳ ቆሮስ መናኛ ዱቄት፤</verse>
				<verse number="23">ከዋ​ሊ​ያና ከሚ​ዳቋ፥ ከበ​ረሃ ፍየ​ልና ከሰቡ ወፎች በቀር ዐሥር ፍሪ​ዳ​ዎች፥ ሃያም የተ​ሰ​ማሩ በሬ​ዎች፥ አንድ መቶም በጎች ነበረ።</verse>
				<verse number="24">ከወ​ንዙ ወዲህ ባሉት ነገ​ሥ​ታት ሁሉ፥ ከወ​ን​ዙም ወዲህ ባለው ሀገር ሁሉ ላይ ከቲ​ላሳ ጀምሮ እስከ ጋዛ ድረስ ነግሦ ነበር፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ባለው በሁሉ ወገን ሰላም ሆኖ​ለት ነበር።</verse>
				<verse number="25">በሰ​ሎ​ሞ​ንም ዘመን ሁሉ ይሁ​ዳና እስ​ራ​ኤል ከዳን ጀምሮ እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከወ​ይ​ኑና ከበ​ለሱ በታች ተዘ​ል​ለው ይቀ​መጡ ነበር።</verse>
				<verse number="26">ለሰ​ሎ​ሞ​ንም ሰረ​ገላ የሚ​ስቡ አርባ ሺህ ፈረ​ሶች፥ ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረ​ሰ​ኞች ነበ​ሩት።</verse>
				<verse number="27">እነ​ዚ​ያም ሹሞች እያ​ን​ዳ​ንዱ በየ​ወሩ ንጉ​ሡን ሰሎ​ሞ​ን​ንና ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎ​ሞን ማዕድ የሚ​ቀ​ር​ቡ​ትን ሁሉ ይቀ​ልቡ ነበር፤ ምንም አያ​ጐ​ድ​ሉም ነበር።</verse>
				<verse number="28">እያ​ን​ዳ​ን​ዱም እንደ ደንቡ የን​ጉ​ሡን ሰረ​ገ​ላ​ዎች ለሚ​ስቡ ለፈ​ረ​ሶ​ችና ለሰ​ጋር በቅ​ሎ​ዎች ገብ​ስና ገለባ፥ እን​ዲ​ሁም ዕቃ​ዎ​ችን ወደ ስፍ​ራ​ቸው ያመጡ ነበር።</verse>
				<verse number="29">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሰ​ሎ​ሞን እጅግ ብዙ ጥበ​ብ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን፥ በባ​ሕ​ርም ዳር እን​ዳለ አሸዋ የልብ ስፋ​ትን ሰጠው።</verse>
				<verse number="30">የሰ​ሎ​ሞ​ንም ጥበብ ከቀ​ደሙ ሰዎች ሁሉ ጥበ​ብና ከግ​ብፅ ጥበብ ሁሉ በዛ።</verse>
				<verse number="31">ከሰ​ዎ​ችም ሁሉ ይልቅ ብልህ ነበረ፤ ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው ከኤ​ታ​ንና ከማ​ሖል ልጆች ከአ​ው​ና​ንና ከከ​ል​ቀድ፥ ከደ​ራ​ልም ይልቅ ጥበ​በኛ ነበረ። በዙ​ሪ​ያ​ውም ባሉ አሕ​ዛብ ሁሉ ዝናው ወጣ።</verse>
				<verse number="32">ሰሎ​ሞ​ንም ሦስት ሺህ ምሳ​ሌ​ዎ​ችን ተና​ገረ፤ መሐ​ል​ዩም አንድ ሺህ አም​ስት ነበረ።</verse>
				<verse number="33">ስለ ዛፍም ከሊ​ባ​ኖስ ዝግባ ጀምሮ በቅ​ጥር ግንብ ላይ እስ​ከ​ሚ​በ​ቅ​ለው እስከ አሽ​ክት ድረስ ይና​ገር ነበር፤ ደግ​ሞም ስለ አው​ሬ​ዎ​ችና ስለ ወፎች ስለ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችና ስለ ዓሣ​ዎች ይና​ገር ነበር።</verse>
				<verse number="34">ከአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ፥ ጥበ​ቡን ሰም​ተው ከነ​በሩ ከም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ የሰ​ሎ​ሞ​ንን ጥበብ ለመ​ስ​ማት ሰዎች ይመጡ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራም ለአ​ባቱ ለዳ​ዊት በዘ​መኑ ሁሉ ወዳጁ ስለ ነበረ፥ ሰሎ​ሞን በአ​ባቱ ፋንታ ንጉሥ ለመ​ሆን እንደ ተቀባ ሰምቶ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ወደ ሰሎ​ሞን ላከ።</verse>
				<verse number="2">ሰሎ​ሞ​ንም ወደ ኪራም እን​ዲህ ብሎ ላከ፦</verse>
				<verse number="3">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ግሩ በታች እስ​ኪ​ጥ​ል​ለት ድረስ በዙ​ሪ​ያው ስለ ነበረ ጦር​ነት አባቴ ዳዊት ለአ​ም​ላኩ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት መሥ​ራት እን​ዳ​ል​ቻለ አንተ ታው​ቃ​ለህ።</verse>
				<verse number="4">አሁ​ንም አም​ላኬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ሪ​ያዬ ካሉት ዕረ​ፍት ሰጥ​ቶ​ኛል፤ ክፉም ነገር የሚ​ያ​ደ​ርግ ጠላት የለ​ብ​ኝም።</verse>
				<verse number="5">እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት፦ በአ​ንተ ፋንታ በዙ​ፋ​ንህ ላይ የማ​ስ​ቀ​ም​ጠው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤት ይሠ​ራል ብሎ እንደ ነገ​ረው፥ ለአ​ም​ላኬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት እሠራ ዘንድ አስ​ባ​ለሁ።</verse>
				<verse number="6">አሁ​ንም ከወ​ገኔ እንደ ሲዶ​ና​ው​ያን እን​ጨት መቍ​ረጥ የሚ​ያ​ውቅ እን​ደ​ሌለ ታው​ቃ​ለ​ህና የዝ​ግባ ዛፍ ከሊ​ባ​ኖስ ይቈ​ር​ጡ​ልኝ ዘንድ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን እዘዝ፤ አገ​ል​ጋ​ዮቼም ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ጋር ይሁኑ፤ የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህ​ንም ዋጋ እንደ ተና​ገ​ር​ኸው ሁሉ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="7">ኪራ​ምም የሰ​ሎ​ሞ​ንን ቃል ሰምቶ እጅግ ደስ አለ​ውና፥ “በዚህ ታላቅ ሕዝብ ላይ ጥበ​በኛ ልጅ ለዳ​ዊት የሰጠ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ይመ​ስ​ገን” አለ።</verse>
				<verse number="8">ኪራ​ምም እን​ዲህ ሲል ወደ ሰሎ​ሞን ላከ፥ “የላ​ክ​ህ​ብ​ኝን ሁሉ ሰማሁ፤ ስለ ዝግ​ባ​ውና ስለ ጥዱ እን​ጨት ፈቃ​ድ​ህን ሁሉ አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">አገ​ል​ጋ​ዮቼ ከሊ​ባ​ኖስ ወደ ባሕር ያወ​ር​ዱ​ል​ሃል፤ እኔም በመ​ር​ከብ አድ​ርጌ በባ​ሕር ላይ እያ​ን​ሳ​ፈ​ፍሁ አንተ እስከ ወሰ​ን​ኸው ስፍራ ድረስ አደ​ር​ስ​ል​ሃ​ለሁ፤ በዚ​ያም እፈ​ታ​ዋ​ለሁ፤ አን​ተም ከዚያ ታስ​ወ​ስ​ደ​ዋ​ለህ፤ አን​ተም ፈቃ​ዴን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ ለቤተ ሰቦ​ቼም ቀለብ የሚ​ሆ​ነ​ውን ትሰ​ጠ​ኛ​ለህ።”</verse>
				<verse number="10">እን​ዲ​ሁም ኪራም የዝ​ግ​ባ​ው​ንና የጥ​ዱን እን​ጨት፥ የሚ​ሻ​ው​ንም ሁሉ ለሰ​ሎ​ሞን ሰጠው።</verse>
				<verse number="11">ሰሎ​ሞ​ንም ለኪ​ራም ስለ ቤቱ ቀለብ ሃያ ሺህ የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ስንዴ፥ ሃያ ሺህም በቤት መስ​ፈ​ሪያ ጥሩ ዘይት ይሰ​ጠው ነበር፤ ሰሎ​ሞ​ንም ለኪ​ራም በየ​ዓ​መቱ ይህን ይሰጥ ነበር።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ነገ​ረው ለሰ​ሎ​ሞን ጥበ​ብን ሰጠው፤ በኪ​ራ​ምና በሰ​ሎ​ሞ​ንም መካ​ከል ሰላም ነበረ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ቃል ኪዳን አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="13">ሰሎ​ሞ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ገባ​ሮ​ቹን መርጦ አወጣ፤ የገ​ባ​ሮ​ቹም ቍጥር ሠላሳ ሺህ ሰዎች ነበረ።</verse>
				<verse number="14">በየ​ወ​ሩም እያ​ፈ​ራ​ረቀ ወደ ሊባ​ኖስ ዐሥር ዐሥር ሺህ ይልክ ነበር፤ አንድ ወርም በሊ​ባ​ኖስ፥ ሁለት ወርም በቤ​ታ​ቸው ይቀ​መጡ ነበር። አዶ​ኒ​ራ​ምም የገ​ባ​ሪ​ዎች አለቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="15">ለሰ​ሎ​ሞ​ንም ሰባ ሺህ ተሸ​ካ​ሚ​ዎች፥ ሰማ​ንያ ሺህም በተ​ራ​ራው ላይ ድን​ጋይ የሚ​ጠ​ርቡ ጠራ​ቢ​ዎች ነበ​ሩት።</verse>
				<verse number="16">ይኸ​ውም በሰ​ሎ​ሞን ሥራ ላይ ከተ​ሾ​ሙት ከሦ​ስት ሺህ ስድ​ስት መቶ የሠ​ራ​ተ​ኞች አለ​ቆች ሌላ ነው።</verse>
				<verse number="17">ንጉ​ሡም የለ​ዘቡ ታላ​ላቅ ድን​ጋ​ዮ​ች​ንና ለቤ​ቱም መሠ​ረት ያል​ተ​ጠ​ረ​በ​ውን ድን​ጋይ ያመጡ ዘንድ አዘዘ።</verse>
				<verse number="18">የሰ​ሎ​ሞ​ንና የኪ​ራም አና​ጢ​ዎች፥ ጌባ​ላ​ው​ያ​ንም ወቀ​ሩ​አ​ቸው፤ ለመ​ሠ​ረ​ትም አኖ​ሩ​አ​ቸው፤ ቤቱ​ንም ለመ​ሥ​ራት እን​ጨ​ቱ​ንና ድን​ጋ​ዮ​ቹን ሦስት ዓመት አዘ​ጋጁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ አራት መቶ ሰማ​ንያ አራት ዓመት በሆነ ጊዜ፥ ሰሎ​ሞን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በነ​ገሠ በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት፥ ዚፍ በሚ​ባ​ለው በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መሥ​ራት ጀመረ።</verse>
				<verse number="2">ንጉሡ ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሠ​ራው ቤት ርዝ​መቱ ስድሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ክንድ፥ ቁመ​ቱም ሠላሳ ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="3">በመ​ቅ​ደ​ሱም ፊት ወለል ነበረ፤ ርዝ​መ​ቱም እንደ መቅ​ደሱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ወር​ዱም ከቤቱ ወደ ፊት ዐሥር ክንድ ነበረ፤ ቤቱ​ንም ሠርቶ ጨረሰ።</verse>
				<verse number="4">ለቤ​ቱም በዐ​ይነ ርግብ የተ​ዘጉ መስ​ኮ​ቶ​ችን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="5">በቤ​ቱም ግንብ ዙሪያ፥ በመ​ቅ​ደ​ሱና በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ግንብ ዙሪያ ደርብ ሠራ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ጓዳ​ዎች አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="6">የታ​ች​ኛ​ውም ደርብ ወርዱ አም​ስት ክንድ፥ የመ​ካ​ከ​ለ​ኛ​ውም ደርብ ወርዱ ስድ​ስት ክንድ፥ የሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ደርብ ወርዱ ሰባት ክንድ ነበረ። ሰረ​ገ​ሎቹ በቤቱ ግንብ ውስጥ እን​ዳ​ይ​ገቡ ከቤቱ ግንብ ውጭ አረ​ፍ​ቶ​ችን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="7">ቤቱም በተ​ሠራ ጊዜ ፈጽ​መው በተ​ወ​ቀሩ ድን​ጋ​ዮች ተሠራ፤ ሲሠ​ሩ​ትም መራ​ጃና መጥ​ረ​ቢያ፥ የብ​ረ​ትም ዕቃ ሁሉ በቤቱ ውስጥ አል​ተ​ሰ​ማም።</verse>
				<verse number="8">የታ​ች​ኛ​ውም ደርብ ጓዳ​ዎች በር በቤቱ ቀኝ አጠ​ገብ ነበረ። ከዚ​ያም ወደ መካ​ከ​ለ​ኛው ደርብ፥ ከመ​ካ​ከ​ለ​ኛ​ውም ወደ ሦስ​ተ​ኛው ደርብ የሚ​ወ​ጡ​በት መውጫ ነበ​ረው።</verse>
				<verse number="9">ቤቱ​ንም ሠርቶ ፈጸ​መው፤ የቤ​ቱ​ንም ጠፈር በዝ​ግባ ሳን​ቃ​ዎች አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="10">በቤ​ቱም ዙሪያ ሁሉ ቁመ​ታ​ቸው አም​ስት አም​ስት ክንድ የሆኑ ደር​ቦ​ችን ሠራ፤ ከቤ​ቱም ጋር በዝ​ግባ እን​ጨት አጋ​ጠ​ማ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ሰሎ​ሞን እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="12">“ስለ​ዚህ ስለ​ም​ት​ሠ​ራ​ልኝ ቤት በሥ​ር​ዐቴ ብት​ሄድ፥ ፍር​ዴ​ንም ብታ​ደ​ርግ፥ ትመ​ላ​ለ​ስ​ባ​ቸ​ውም ዘንድ ትእ​ዛ​ዞቼን ሁሉ ብት​ጠ​ብቅ፥ ለአ​ባ​ትህ ለዳ​ዊት የነ​ገ​ር​ሁ​ትን ቃል ከአ​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መካ​ከል እኖ​ራ​ለሁ፤ ሕዝ​ቤ​ንም እስ​ራ​ኤ​ልን አል​ጥ​ልም።”</verse>
				<verse number="14">ሰሎ​ሞ​ንም ቤቱን ሠራው፤ ፈጸ​መ​ውም።</verse>
				<verse number="15">የቤ​ቱ​ንም ግንብ ውስ​ጡን በዝ​ግባ ሳንቃ ለበጠ፤ ከቤ​ቱም መሠ​ረት ጀምሮ እስከ ጣራው ድረስ የው​ስ​ጡን ግንብ በእ​ን​ጨት ለበ​ጠው፤ ደግ​ሞም የቤ​ቱን ወለል በጥድ እን​ጨት አነ​ጠ​ፈው።</verse>
				<verse number="16">ከቤተ መቅ​ደሱ አያ​ይዞ ከመ​ሠ​ረቱ ጀምሮ እስከ ጣራው ድረስ ሃያ​ውን ክንድ በዝ​ግባ ጠርብ ሠራ፤ ከመ​ቅ​ደ​ሱም ከፍሎ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="17">በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ፊት ያለ​ውም መቅ​ደስ ርዝ​መቱ አርባ ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="18">የቤ​ቱ​ንም ውስጥ በተ​ጐ​በ​ጐ​በና በፈ​ነዳ አበባ፥ በተ​ቀ​ረጸ ዝግባ ለበ​ጠው፤ ሁሉም ዝግባ ነበረ፤ ድን​ጋ​ዩም አል​ታ​የም ነበር።</verse>
				<verse number="19">በዚ​ያም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት ያኖር ዘንድ በቤቱ ውስጥ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑን አበጀ።</verse>
				<verse number="20">የቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑም ርዝ​መት ሃያ ክንድ፥ ስፋ​ቱም ሃያ ክንድ፥ ቁመ​ቱም ሃያ ክንድ ነበረ፤ በጥ​ሩም ወርቅ ለበ​ጠው።</verse>
				<verse number="21">በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑም ፊት ከዝ​ግባ መሠ​ዊ​ያን ሠራ፤ በጥሩ ወር​ቅም ለበ​ጠው።</verse>
				<verse number="22">የሠ​ራው ቤት ሁሉ እስከ ተፈ​ጸመ ድረስ ቤቱን ሁሉ በወ​ርቅ ለበ​ጠው፤ በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑም ፊት የነ​በ​ረ​ውን መሠ​ዊያ ሁሉ በወ​ርቅ ለበ​ጠው።</verse>
				<verse number="23">በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑም ውስጥ ቁመ​ታ​ቸው ዐሥር ክንድ የሆነ ከወ​ይራ እን​ጨት ሁለት ኪሩ​ቤ​ልን ሠራ።</verse>
				<verse number="24">የኪ​ሩ​ብም አን​ደ​ኛው ክንፍ አም​ስት ክንድ፥ የኪ​ሩ​ብም ሁለ​ተ​ኛው ክንፍ አም​ስት ክንድ ነበረ፤ ከአ​ን​ደ​ኛው ክንፍ ጫፍ ጀምሮ እስከ ሁለ​ተ​ኛው ክንፍ ጫፍ ድረስ ዐሥር ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="25">እን​ደ​ዚ​ሁም ሁለ​ተ​ኛው ኪሩብ ዐሥር ክንድ ነበረ፤ ሁለ​ቱም ኪሩ​ቤል አንድ ልክና አንድ መልክ ነበሩ።</verse>
				<verse number="26">የአ​ንዱ ኪሩብ ቁመት ዐሥር ክንድ ነበረ፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ኪሩብ እን​ዲሁ ነበረ።</verse>
				<verse number="27">ሁለ​ቱም ኪሩ​ቤል በው​ስ​ጠ​ኛው ቤት መካ​ከል ነበሩ። የኪ​ሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸው ተዘ​ር​ግ​ተው ነበር፤ የአ​ን​ዱም ኪሩብ ክንፍ አን​ደ​ኛ​ውን ግንብ ይነካ ነበር፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ኪሩብ ክንፍ ሁለ​ተ​ኛ​ውን ግንብ ይነካ ነበር፤ የሁ​ለ​ቱም ክን​ፎች በቤቱ መካ​ከል እርስ በር​ሳ​ቸው ይነ​ካኩ ነበር።</verse>
				<verse number="28">ኪሩ​ቤ​ል​ንም በወ​ርቅ ለበ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="29">በቤ​ቱም ግንብ ሁሉ ዙሪያ በው​ስ​ጥና በውጭ የኪ​ሩ​ቤ​ልና የዘ​ን​ባባ ዛፍ፥ የፈ​ነ​ዳም አበባ ሥዕል ቀረጸ።</verse>
				<verse number="30">የቤ​ቱ​ንም ወለል በው​ስ​ጥና በውጭ በወ​ርቅ ለበጠ።</verse>
				<verse number="31">ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑም መግ​ቢያ ከወ​ይራ እን​ጨት ሳን​ቃ​ዎ​ችን ሠራ፤ መድ​ረ​ኩ​ንና መቃ​ኖ​ቹን፥ ደፉ​ንም አም​ስት ማዕ​ዘን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="32">ሁለ​ቱ​ንም ሣን​ቃ​ዎች ከወ​ይራ እን​ጨት ሠራ፤ የኪ​ሩ​ቤ​ል​ንና የዘ​ን​ባባ ዛፍ፥ የፈ​ነ​ዳም አበባ ሥዕል ቀረ​ጸ​ባ​ቸው፤ በወ​ር​ቅም ለበ​ጣ​ቸው፤ ኪሩ​ቤ​ል​ንና የዘ​ን​ባ​ባ​ውን ዛፍ በወ​ርቅ ለበጠ።</verse>
				<verse number="33">እን​ዲ​ሁም ለመ​ቅ​ደሱ መግ​ቢያ ከወ​ይራ እን​ጨት አራት ማዕ​ዘን መቃን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="34">ሁለ​ቱ​ንም ደጆች ከጥድ እን​ጨት ሠራ፤ አንዱ ደጅ በማ​ጠ​ፊያ ከተ​ያ​ያዙ ከሁ​ለት ሣን​ቃ​ዎች ተሠራ፤ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ደጅ በማ​ጠ​ፊያ ከተ​ያ​ያዙ ከሁ​ለት ሣን​ቃ​ዎች ተሠራ።</verse>
				<verse number="35">የኪ​ሩ​ቤ​ል​ንና የዘ​ን​ባባ ዛፍ፥ የፈ​ነ​ዳም አበባ ሥዕል ቀረ​ጸ​ባ​ቸው፤ በተ​ቀ​ረ​ጸ​ውም ሥራ ላይ በወ​ርቅ ለበ​ጣ​ቸው፤ እስከ መድ​ረ​ካ​ቸ​ውም የተ​ያ​ያዙ ነበሩ።</verse>
				<verse number="36">የው​ስ​ጠ​ኛ​ው​ንም አደ​ባ​ባይ ቅጥር ሦስ​ቱን ተራ በተ​ጠ​ረበ ድን​ጋይ፥ አን​ዱ​ንም ተራ በዝ​ግባ ሣንቃ ሠራው፤ በመ​ቅ​ደሱ ፊት ለፊት ላለው ቤት ወለ​ልም መጋ​ረጃ ሠራ።</verse>
				<verse number="37">በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት ከሚ​ያ​ዝያ በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መሠ​ረተ።</verse>
				<verse number="38">በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛ​ውም ዓመት ቡል በሚ​ባል በስ​ም​ን​ተ​ኛው ወር ቤቱ እንደ ክፍ​ሎ​ቹና እንደ ሥር​ዐቱ ሁሉ ተጨ​ረሰ። በሰ​ባት ዓመ​ትም ሠራው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">ሰሎ​ሞ​ንም የራ​ሱን ቤት በዐ​ሥራ ሦስት ዓመት ሠራ፤ የቤ​ቱ​ንም ሥራ ሁሉ ጨረሰ።</verse>
				<verse number="2">የሊ​ባ​ኖስ ዱር ቤት የሚ​ባል ቤት​ንም ሠራ፤ ርዝ​መ​ቱ​ንም መቶ ክንድ፥ ስፋ​ቱ​ንም አምሳ ክንድ፥ ቁመ​ቱ​ንም ሠላሳ ክንድ አደ​ረገ፤ የዋ​ን​ዛም እን​ጨት በሦ​ስት ወገን በተ​ሠሩ አዕ​ማድ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአ​ዕ​ማ​ዱም ላይ የዋ​ንዛ እን​ጨት አግ​ዳሚ ሰረ​ገ​ሎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="3">በአ​ዕ​ማ​ዱም ላይ በነ​በሩ አግ​ዳ​ሚ​ዎች ቤቱ በዋ​ንዛ ሳንቃ ተሸ​ፍኖ ነበር፤ አዕ​ማ​ዱም በአ​ንዱ ወገን ዐሥራ አም​ስት፥ በአ​ንዱ ወገን ዐሥራ አም​ስት የሆኑ አርባ አም​ስት ነበሩ።</verse>
				<verse number="4">መስ​ኮ​ቶ​ቹም በሦ​ስት ወገን ነበሩ፤ መስ​ኮ​ቶ​ቹም በሦ​ስት ወገን ፊት ለፊት ይተ​ያዩ ነበር።</verse>
				<verse number="5">ደጆቹ፥ መቃ​ኖ​ቹና የታ​ች​ኛ​ውና የላ​ይ​ኛው መድ​ረ​ኮች ሁሉ አራት ማዕ​ዘን ነበሩ፤ መስ​ኮ​ቶ​ቹም በሦ​ስት ወገን ሆነው ፊት ለፊት ይተ​ያዩ ነበር።</verse>
				<verse number="6">አዕ​ማ​ዱም ያሉ​በ​ትን ቤት ሠራ፤ ርዝ​መ​ቱም አምሳ ክንድ፥ ስፋ​ቱም ሠላሳ ክንድ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ፊት ደግሞ ታላቅ አዕ​ማ​ድና መድ​ረክ ያሉ​በት ወለል ነበረ።</verse>
				<verse number="7">የሚ​ፈ​ር​ድ​በ​ትም የቤቱ ዙፋን በዚያ አለ። ለመ​ፍ​ረ​ጃ​ውም ቤትን ሠራ፤ ከላይ እስከ ታችም በዋ​ንዛ እን​ጨት አያ​ያ​ዘው።</verse>
				<verse number="8">ከፍ​ርድ ሰቀላ ወደ ውስጥ፥ በሌ​ላ​ውም አደ​ባ​ባይ ውስጥ የነ​በ​ረ​ውን የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ቤት እን​ዲሁ ሠራ፤ እን​ደ​ዚ​ህም ቤት ያለ ቤትን ሰሎ​ሞን ላገ​ባት ለፈ​ር​ዖን ልጅ ሠራ።</verse>
				<verse number="9">ይህም ሁሉ ከመ​ሠ​ረቱ ጀምሮ እስከ ጕል​ላቱ ድረስ በከ​በ​ረና በተ​ጠ​ረበ በው​ስ​ጥና በውጭ በልክ በተ​ከ​ረ​ከመ ድን​ጋይ ተሠ​ርቶ ነበር፤ በው​ጭ​ውም እስከ ታላቁ አደ​ባ​ባይ ድረስ እን​ዲሁ ነበረ።</verse>
				<verse number="10">መሠ​ረ​ቱም ዐሥር ዐሥር ክን​ድና ስም​ንት ስም​ንት ክንድ በሆኑ በከ​በሩ በታ​ላ​ላቅ ድን​ጋ​ዮች ተሠ​ርቶ ነበር።</verse>
				<verse number="11">በላ​ዩም ልክ ሆኖ የተ​ከ​ረ​ከመ ጥሩ ድን​ጋ​ይና የዝ​ግባ ሣንቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="12">በታ​ላ​ቁም አደ​ባ​ባይ ዙሪያ የነ​በ​ረው ቅጥር እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እንደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ ቅጥ​ርና እንደ ቤቱ ወለል ሦስቱ ወገን በተ​ጠ​ረበ ድን​ጋይ አን​ዱም ወገን በዝ​ግባ ሳንቃ ተሠ​ርቶ ነበር።</verse>
				<verse number="13">ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ልኮ ኪራ​ምን ከጢ​ሮስ አስ​መጣ።</verse>
				<verse number="14">እር​ሱም ከን​ፍ​ታ​ሌም ወገን የነ​በ​ረች የባል አልባ ሴት ልጅ ነበረ፤ አባ​ቱም የጢ​ሮስ ሰው ናስ ሠራ​ተኛ ነበረ፤ የና​ስ​ንም ሥራ ሁሉ ይሠራ ዘንድ በጥ​በ​ብና በማ​ስ​ተ​ዋል፥ በብ​ል​ሃ​ትም ተሞ​ልቶ ነበር። ወደ ንጉ​ሡም ወደ ሰሎ​ሞን መጥቶ ሥራ​ውን ሁሉ ሠራ።</verse>
				<verse number="15">በቤቱ ውስጥ ላለው ወለል ሁለ​ቱን የናስ አዕ​ማድ ሠራ፤ የአ​ን​ዱም ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስም​ንት ክንድ ነበረ፤ የዙ​ሪ​ያ​ውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ የዓ​ም​ዱም ውፍ​ረት አንድ ጋት ነበረ፤ ውስጠ ክፍ​ትም ነበረ። ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዓምድ እን​ዲሁ ነበረ።</verse>
				<verse number="16">በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ራስ ላይ እን​ዲ​ቀ​መጡ ከፈ​ሰሰ ናስ ሁለት ጕል​ላ​ትን ሠራ፤ የአ​ን​ዱም ጕል​ላት ቁመት አም​ስት ክንድ፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ጕል​ላት ቁመት አም​ስት ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="17">በአ​ዕ​ማ​ዱም ራስ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን ጕል​ላ​ቶች ይሸ​ፍኑ ዘንድ ሁለት እንደ መር​በብ ሥራ አደ​ረገ፤ አን​ዱም መር​በብ ለአ​ንዱ ጕል​ላት፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም መር​በብ ለሁ​ለ​ተ​ኛው ጕል​ላት ነበረ።</verse>
				<verse number="18">ሮማ​ኖ​ች​ንም ሠራ፤ በአ​ንድ ጕል​ላት ዙሪያ በሁ​ለት ተራ፥ በአ​ን​ድም መር​በብ ላይ ሁለት ተራ ነበረ፤ እን​ዲ​ሁም ለሁ​ለ​ተ​ኛው ጕል​ላት አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="19">በወ​ለ​ሉም አዕ​ማድ በነ​በ​ሩት ጕል​ላ​ቶች ላይ የሱፍ አበባ የሚ​መ​ስል ሥራ አራት ክንድ አድ​ርጎ ቀረጸ።</verse>
				<verse number="20">በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ በነ​በ​ሩት ጕል​ላ​ቶች ላይ በመ​ር​በቡ ሥራ አጠ​ገብ ሮማ​ኖ​ቹን አደ​ረገ። ሮማ​ኖ​ቹም በአ​ንዱ ወገን ሁለት መቶ ነበሩ። የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ጕል​ላት እን​ዲሁ ነበረ።</verse>
				<verse number="21">አዕ​ማ​ዱ​ንም በመ​ቅ​ደሱ ወለል አጠ​ገብ አቆ​ማ​ቸው፤ የቀ​ኙ​ንም ዓምድ አቁሞ ያቁም ብሎ ጠራው፤ የግ​ራ​ው​ንም ዓምድ አቁሞ በለዝ ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="22">በአ​ዕ​ማ​ዱም ራስ ላይ የሱፍ አበባ የሚ​መ​ስል ሥራ አደ​ረገ። እን​ዲ​ሁም የአ​ዕ​ማዱ ሥራ ተጨ​ረሰ።</verse>
				<verse number="23">ከፈ​ሰ​ሰም ናስ ከዳር እስከ ዳር ዐሥር ክንድ፥ ቁመ​ቱም አም​ስት ክንድ፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ሠላሳ ክንድ የሆነ ክብ ኩሬ ሠራ።</verse>
				<verse number="24">ከከ​ን​ፈ​ሩም በታች ለአ​ንድ ክንድ ዐሥር፥ ለአ​ንድ ክን​ድም ዐሥር ጕብ​ጕ​ቦች አዞ​ረ​በት፤ ከን​ፈ​ሮ​ቹም እንደ ጽዋ ከን​ፈር ነበሩ። በው​ስ​ጡም አበ​ቦች በቅ​ለ​ው​በት ነበር። ውፍ​ረ​ቱም ስን​ዝር ነበር።</verse>
				<verse number="25">ኩሬ​ውም በዐ​ሥራ ሁለት በሬ​ዎች ምስል ላይ ተቀ​ምጦ ነበር፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስ​ቱም ወደ ምዕ​ራብ፥ ሦስ​ቱም ወደ ደቡብ፥ ሦስ​ቱም ወደ ምሥ​ራቅ ይመ​ለ​ከቱ ነበር። ኩሬ​ውም በላ​ያ​ቸው ነበረ፤ የሁ​ሉም ጀር​ባ​ቸው በስ​ተ​ው​ስጥ ነበረ።</verse>
				<verse number="26">ውፍ​ረ​ቱም አንድ ጋት ነበረ። ከን​ፈ​ሩም እንደ ጽዋ ከን​ፈር ተሠ​ርቶ ነበር፤ እንደ ሱፍ አበ​ባ​ዎች ሆኖ ተከ​ር​ክሞ ነበር። ሁለት ሺህም የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ ይይዝ ነበር።</verse>
				<verse number="27">ዐሥ​ርም የናስ መቀ​መ​ጫ​ዎ​ችን ሠራ፤ የአ​ን​ዱም መቀ​መጫ ርዝ​መት አራት ክንድ፥ ወር​ዱም አራት ክንድ፥ ቁመ​ቱም ሦስት ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="28">መቀ​መ​ጫ​ዎ​ች​ንም እን​ዲሁ ሠራ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም አያ​ይዞ ሰን​በር ባለው ክፈፍ ሠራ​ቸው።</verse>
				<verse number="29">በክ​ፈ​ፎ​ቹም መካ​ከል በነ​በሩ ሰን​በ​ሮች ላይ አን​በ​ሳ​ዎ​ችና በሬ​ዎች፥ ኪሩ​ቤ​ልም ነበሩ፤ እን​ዲ​ሁም በክ​ፈ​ፎቹ ላይ ነበረ፤ ከአ​ን​በ​ሳ​ዎ​ቹና ከበ​ሬ​ዎቹ በታች ሻኩራ የሚ​መ​ስል ተን​ጠ​ል​ጥሎ ነበር።</verse>
				<verse number="30">በየ​መ​ቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹም ሁሉ አራት የናስ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮች ነበ​ሩ​ባ​ቸው፤ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ቹም የሚ​ዞ​ሩ​በ​ትን የናስ ወስ​ከ​ምት ሠራ፤ ከመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውም ሰን በታች በአ​ራቱ ማዕ​ዘን በኩል አራት በም​ስል የፈ​ሰሱ እግ​ሮች ነበሩ።</verse>
				<verse number="31">በክ​ፈ​ፉም ውስጥ የነ​በረ አን​ገት አንድ ክንድ ነበረ፤ አን​ገ​ቱም ድቡ​ል​ቡል ነበረ፤ ቁመ​ቱም ክንድ ተኩል ነበረ። በአ​ን​ገ​ቱም ላይ ቅርጽ ነበ​ረ​በት፤ ክፈፉ ግን አራት ማዕ​ዘን ነበረ እንጂ ድቡ​ል​ቡል አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="32">አራ​ቱም መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮች ከሰ​ን​በ​ሮቹ በታች ነበሩ፤ የመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ቹም ወስ​ከ​ምት በመ​ቀ​መ​ጫው ውስጥ ነበረ፤ የመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሩም ቁመት ክንድ ተኩል ነበረ።</verse>
				<verse number="33">የመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ቹም ሥራ እንደ ሰረ​ገላ መን​ኰ​ራ​ኵር ሥራ ነበረ፤ ወስ​ከ​ም​ቶ​ቹና የመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮቹ ክፈፍ፥ ቅት​ር​ቶ​ቹም፥ ወስ​ከ​ምቱ የሚ​ገ​ባ​በት ቧምቧ ሁሉ በም​ስል የፈ​ሰሰ ነበር።</verse>
				<verse number="34">በየ​አ​ን​ዳ​ን​ዱም መቀ​መጫ በአ​ራቱ ማዕ​ዘን በኩል አራት ደገ​ፋ​ዎች ነበሩ፤ ደገ​ፋ​ዎ​ቹም ከመ​ቀ​መ​ጫው ጋር ተጋ​ጥ​መው ነበር።</verse>
				<verse number="35">በመ​ቀ​መ​ጫ​ውም ራስ ላይ ስን​ዝር የሚ​ሆን ድቡ​ል​ቡል ነገር ነበረ፤ በመ​ቀ​መ​ጫ​ውም ላይ የነ​በሩ መያ​ዣ​ዎ​ችና ሰን​በ​ሮች ከእ​ርሱ ጋር ይጋ​ጠሙ ነበረ፤ ከላ​ይም ክፍት ነበረ፤</verse>
				<verse number="36">በክ​ፈ​ፎ​ቻ​ቸ​ውም ኪሩ​ቤ​ልና አን​በ​ሶች የዘ​ን​ባባ ዛፎ​ችም ነበሩ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ፊት ለፊት በስ​ተ​ው​ስ​ጥና በዙ​ሪ​ያው ተያ​ይዞ ነበር።</verse>
				<verse number="37">እን​ዲ​ሁም ዐሥ​ሩን መቀ​መ​ጫ​ዎች ሠራ፤ ሁሉም በመ​ጠን፥ በን​ድ​ፍም ትክ​ክ​ሎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="38">ዐሥ​ሩ​ንም የናስ መታ​ጠ​ቢያ ሰን ሠራ፤ አንዱ መታ​ጠ​ቢያ ሰን አርባ የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ ያነሣ ነበር፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም መታ​ጠ​ቢያ ሰን አራት ክንድ ነበረ፤ በዐ​ሥ​ሩም መቀ​መ​ጫ​ዎች ላይ በእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አንድ አንድ መታ​ጠ​ቢያ ሰን ይቀ​መጥ ነበር።</verse>
				<verse number="39">አም​ስ​ቱ​ንም መቀ​መ​ጫ​ዎች በቤቱ ቀኝ፥ አም​ስ​ቱ​ንም በቤቱ ግራ አኖ​ራ​ቸው፤ ኩሬ​ው​ንም በቤቱ ቀኝ በአ​ዜብ ፊት ለፊት በስ​ተ​ም​ሥ​ራቅ አኖ​ረው።</verse>
				<verse number="40">ኪራ​ምም ምን​ቸ​ቶ​ች​ንና መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ችን፥ ድስ​ቶ​ች​ንም ሠራ፤ ኪራ​ምም ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ ጨረሰ።</verse>
				<verse number="41">ሁለ​ቱ​ንም አዕ​ማድ፥ በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ራስ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን ኩብ የሚ​መ​ስ​ሉ​ትን ጕል​ላ​ቶች፥ በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን ሁለ​ቱን ጕል​ላ​ቶች የሚ​ሸ​ፍ​ኑ​ትን ሁለ​ቱን መር​በ​ቦች፥</verse>
				<verse number="42">በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን ሁለ​ቱን ጕል​ላ​ቶች ይሸ​ፍኑ ዘንድ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ መር​በብ በሁ​ለት በሁ​ለት ተራ አድ​ርጎ ለሁ​ለቱ መር​በ​ቦች አራት መቶ ሮማ​ኖ​ችን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="43">ዐሥ​ሩ​ንም መቀ​መ​ጫ​ዎች፥ በመ​ቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹም ላይ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን ዐሥ​ሩን መታ​ጠ​ቢያ ሰን፥</verse>
				<verse number="44">አን​ዱ​ንም ኩሬ፥ ከኩ​ሬ​ውም በታች የሚ​ሆ​ኑ​ትን ዐሥራ ሁለ​ቱን በሬ​ዎች፥</verse>
				<verse number="45">ምን​ቸ​ቶ​ቹ​ንም፥ መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንም፥ ዕቃ​ዎ​ቹ​ንም ሁሉ ኪራም ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሠራ። በን​ጉሡ ቤትና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትም አርባ ስም​ንት አዕ​ማድ ነበሩ። ኪራ​ምም ለን​ጉሡ የሠ​ራ​ቸው ዕቃ​ዎች ሁሉ ከጥሩ ናስ ነበር።</verse>
				<verse number="46">በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ሜዳ በሱ​ኮ​ትና በተ​ር​ታን መካ​ከል ባለው በወ​ፍ​ራሙ መሬት ውስጥ አስ​ፈ​ሰ​ሰው።</verse>
				<verse number="47">ይህ ሁሉ ሥራ ለተ​ሠ​ራ​በት ናስ ሚዛን አል​ነ​በ​ረ​ውም፤ የና​ሱም ሚዛን ብዙ ነበ​ርና አይ​ቈ​ጠ​ርም ነበር።</verse>
				<verse number="48">ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ዕቃን ሁሉ አሠራ፤ የወ​ር​ቁን መሠ​ዊያ፥ የገ​ጹም ኅብ​ስት የነ​በ​ረ​በ​ትን የወ​ርቅ ገበታ፥</verse>
				<verse number="49">በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ፊት አም​ስቱ በቀኝ፥ አም​ስ​ቱም በግራ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከጥሩ ወርቅ የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም መቅ​ረ​ዞች፥ የወ​ር​ቁ​ንም አበ​ባ​ዎ​ችና ቀን​ዲ​ሎች፥ መኮ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ንም፥</verse>
				<verse number="50">ከጥሩ ወር​ቅም የተ​ሠ​ሩ​ትን ጽዋ​ዎ​ችና ጕጠ​ቶች፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንና ጭል​ፋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹ​ንም፥ ጽን​ሐ​ሖ​ችን፥ ለው​ስ​ጠ​ኛ​ውም ቤት ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ደጆች፥ ለቤተ መቅ​ደ​ሱም ደጆች የሚ​ሆ​ኑ​ትን የወ​ርቅ ማጠ​ፊ​ያ​ዎች አሠራ።</verse>
				<verse number="51">እን​ዲ​ሁም ንጉሡ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የአ​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ ተፈ​ጸመ። አባ​ቱም ዳዊት የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ ራሱም የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ የብ​ርና የወ​ርቅ ዕቃ ሰሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በነ​በሩ ግምጃ ቤቶች አገባ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">ሰሎ​ሞ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የራ​ሱን ቤተ መን​ግ​ሥት ሠርቶ ከፈ​ጸመ ከሃያ ዓመት በኋላ ያን​ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳ​ዊት ከተማ ከጽ​ዮን ያወጡ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና የነ​ገድ አለ​ቆ​ችን ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ቤቶች መሳ​ፍ​ንት ንጉሡ ሰሎ​ሞን በጽ​ዮን ሰበ​ሰ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">ይኸ​ውም አታ​ሚን በሚ​ባል በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ነበር።</verse>
				<verse number="3">ካህ​ና​ቱም ታቦ​ቷን አነሡ፤</verse>
				<verse number="4">የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን፥ በድ​ን​ኳ​ኑም ውስጥ የነ​በ​ረ​ውን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ዕቃ ሁሉ አመጡ።</verse>
				<verse number="5">ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ከእ​ርሱ ጋር የተ​ሰ​በ​ሰቡ የእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር በታ​ቦቷ ፊት ሆነው፥ ከብ​ዛ​ታ​ቸው የተ​ነሣ የማ​ይ​ቈ​ጠ​ሩ​ት​ንና የማ​ይ​መ​ጠ​ኑ​ትን በጎ​ችና በሬ​ዎች ይሠዉ ነበር።</verse>
				<verse number="6">ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት በቤቱ በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ውስጥ ከኪ​ሩ​ቤል ክንፍ በታች ወደ ነበ​ረው ወደ ስፍ​ራዋ አገቧት።</verse>
				<verse number="7">ኪሩ​ቤ​ልም በታ​ቦቷ ስፍራ ላይ ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ዘር​ግ​ተው ነበር፤ ኪሩ​ቤ​ልም ታቦቷ​ንና የተ​ቀ​ደሱ ዕቃ​ዎ​ችን በስ​ተ​ላይ በኩል ሸፍ​ነው ነበር።</verse>
				<verse number="8">መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹም ረጃ​ጅ​ሞች ነበሩ፤ በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ፊት ከመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ጫፎ​ቻ​ቸው ይታዩ ነበር፤ በውጭ ግን አይ​ታ​ዩም ነበር፤</verse>
				<verse number="9">በታ​ቦ​ቷም ውስጥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር በወጡ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደ​ረገ ጊዜ ሙሴ በኮ​ሬብ ካስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው የቃል ኪዳን ጽላት ከሚ​ባ​ሉት ከሁ​ለቱ የድ​ን​ጋይ ጽላት በቀር ምንም አል​ነ​በ​ረ​ባ​ትም።</verse>
				<verse number="10">ካህ​ና​ቱም ከመ​ቅ​ደሱ በወጡ ጊዜ ደመ​ናው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሞላው።</verse>
				<verse number="11">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ቤቱን ሞል​ቶት ነበ​ርና ካህ​ናቱ ከደ​መ​ናው የተ​ነሣ ለማ​ገ​ል​ገል ይቆሙ ዘንድ አል​ቻ​ሉም።</verse>
				<verse number="12">ያን​ጊ​ዜም ሰሎ​ሞን እን​ዲህ አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በደ​መ​ናው ውስጥ እኖ​ራ​ለሁ ብሎ​አል፤</verse>
				<verse number="13">እኔም ለዘ​ለ​ዓ​ለም የም​ት​ኖ​ር​በ​ትን ማደ​ሪያ ቤት በእ​ው​ነት ሠራ​ሁ​ልህ።”</verse>
				<verse number="14">ንጉ​ሡም ፊቱን ዘወር አድ​ርጎ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጉባኤ ሁሉ መረ​ቃ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጉባኤ ሁሉ ቆመው ነበር።</verse>
				<verse number="15">እር​ሱም አለ፥ “ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት በአፉ የተ​ና​ገረ፥ በእ​ጁም የፈ​ጸመ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።</verse>
				<verse number="16">ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ ካወ​ጣ​ሁ​በት ቀን ጀምሮ ስሜ በዚያ ይሆን ዘንድ በእ​ር​ስ​ዋም ቤት ይሠ​ራ​ልኝ ዘንድ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ከተ​ማን አል​መ​ረ​ጥ​ሁም፤ አሁን ግን ስሜ በዚያ ይሆን ዘንድ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን መር​ጫ​ለሁ፤ በሕ​ዝ​ቤም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ ዳዊ​ትን መር​ጫ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="17">አባ​ቴም ዳዊት ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት ይሠራ ዘንድ በልቡ አሰበ።</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አባ​ቴን ዳዊ​ትን፥ “ለስሜ ቤት ትሠራ ዘንድ በል​ብህ አስ​በ​ሃ​ልና ይህን በል​ብህ ማሰ​ብህ መል​ካም አደ​ረ​ግህ።</verse>
				<verse number="19">ነገር ግን ከወ​ገ​ብህ የሚ​ወ​ጣው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤት ይሠ​ራል እንጂ ቤት የም​ት​ሠ​ራ​ልኝ አንተ አይ​ደ​ለ​ህም” አለው።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አጸና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተስፋ እንደ ሰጠ በአ​ባቴ በዳ​ዊት ፋንታ ተነ​ሣሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዙፋን ላይ ተቀ​መ​ጥሁ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት ሠራሁ።</verse>
				<verse number="21">ከግ​ብ​ፅም ምድር ባወ​ጣ​ቸው ጊዜ ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ጋር ያደ​ረ​ገው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ላለ​ባት ታቦት ስፍ​ራን በዚያ አደ​ር​ግ​ሁ​ላት።</verse>
				<verse number="22">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጉባኤ ሁሉ እያዩ ሰሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ፊት ቆሞ እጆ​ቹን ወደ ሰማይ ዘረጋ።</verse>
				<verse number="23">እን​ዲ​ህም አለ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ! በላይ በሰ​ማይ፥ በታ​ችም በም​ድር አን​ተን የሚ​መ​ስል አም​ላክ የለም፤ በፍ​ጹም ልቡ በፊ​ትህ ለሚ​ሄድ ባሪ​ያህ ቃል ኪዳ​ን​ንና ምሕ​ረ​ትን የም​ት​ጠ​ብቅ፥</verse>
				<verse number="24">ለባ​ሪ​ያህ ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት የሰ​ጠ​ኸ​ውን ተስፋ የጠ​በ​ቅህ፥ በአ​ፍህ ተና​ግ​ረህ፥ እንደ ዛሬ ቀንም በእ​ጅህ ፈጸ​ም​ኸው።</verse>
				<verse number="25">አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ፦ አንተ በፊቴ እንደ ሄድህ ልጆ​ችህ በፊቴ ይሄዱ ዘንድ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ቢጠ​ብቁ፥ በፊቴ በእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን የሚ​ቀ​መጥ ሰው ከአ​ንተ አይ​ጠ​ፋም ብለህ ለአ​ባ​ቴ ለ​ዳ​ዊት ተስፋ የሰ​ጠ​ኽ​ውን ጠብቅ።</verse>
				<verse number="26">አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ! ለባ​ሪ​ያህ ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት የተ​ና​ገ​ር​ኸው ቃል እባ​ክህ እው​ነት ይሁን።</verse>
				<verse number="27">“በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰው ጋር በም​ድር ላይ ይኖ​ራ​ልን? እነሆ ሰማይ ከሰ​ማ​ያ​ትም በላይ ያለው ሰማይ ይይ​ዝህ ዘንድ አይ​ች​ልም፤ ይል​ቁ​ንስ እኔ ለስ​ምህ የሠ​ራ​ሁት ቤት እን​ዴት ያንስ!</verse>
				<verse number="28">አቤቱ አም​ላኬ ሆይ! ወደ ባሪ​ያህ ጸሎ​ትና ልመና ተመ​ል​ከት፤ ዛሬም ባሪ​ያህ በፊ​ትህ የሚ​ጸ​ል​የ​ውን ጸሎት ስማ፤</verse>
				<verse number="29">ባሪ​ያህ ወደ​ዚህ ስፍራ የሚ​ጸ​ል​የ​ውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፦ በዚያ ስሜ ይሆ​ናል ወዳ​ል​ኸው ስፍራ ወደ​ዚህ ቤት ዐይ​ኖ​ችህ ሌሊ​ትና ቀን የተ​ገ​ለጡ ይሁኑ።</verse>
				<verse number="30">ባሪ​ያ​ህና ሕዝ​ብህ እስ​ራ​ኤል ወደ​ዚህ ስፍራ የሚ​ጸ​ል​ዩ​ትን ልመና ስማ፤ በማ​ደ​ሪ​ያህ በሰ​ማይ ስማ፤ ሰም​ተ​ህም ይቅር በል።</verse>
				<verse number="31">“ሰው ባል​ጀ​ራ​ውን ቢበ​ድል፥ ይም​ልም ዘንድ በላዩ መሐላ ቢጫ​ን​በት፥ እር​ሱም መጥቶ በዚህ ቤት በመ​ሠ​ዊ​ያህ ፊት ቢና​ዘዝ፥</verse>
				<verse number="32">በሰ​ማይ ስማ፤ አድ​ር​ግም፤ በባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ዳኛ ሁን፤ በበ​ደ​ለ​ኛ​ውም ላይ ፍረድ፤ መን​ገ​ዱ​ንም በራሱ ላይ መል​ስ​በት፤ ጻድ​ቁን አጽ​ድ​ቀው፤ እንደ ጽድ​ቁም ክፈ​ለው።</verse>
				<verse number="33">“ሕዝ​ብህ እስ​ራ​ኤል አን​ተን ስለ በደሉ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ፊት ድል ቢሆኑ፥ ወደ አን​ተም ቢመ​ለሱ፥ ለስ​ም​ህም ቢና​ዘዙ፥</verse>
				<verse number="34">በዚ​ህም ቤት ቢጸ​ል​ዩና ቢለ​ም​ኑህ፥ አንተ በሰ​ማይ ስማ፤ የሕ​ዝ​ብ​ህ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ኀጢ​አት ይቅር በል፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ሰጠ​ሃት ምድር መል​ሳ​ቸው።</verse>
				<verse number="35">“አን​ተን ስለ በደሉ ሰማይ ቢዘጋ፥ ዝና​ብም ባይ​ዘ​ንብ፥ በዚ​ህም ስፍራ ቢጸ​ልዩ፥ ለስ​ም​ህም ቢና​ዘዙ፥ ባስ​ጨ​ነ​ቅ​ሃ​ቸ​ውም ጊዜ ከኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ቢመ​ለሱ፥</verse>
				<verse number="36">አንተ በሰ​ማይ ስማ፤ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መል​ካም መን​ገድ በማ​ሳ​የት የባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህ​ንና የሕ​ዝ​ብ​ህን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ኀጢ​አት ይቅር በል፤ ለሕ​ዝ​ብ​ህም ርስት አድ​ር​ገህ ለሰ​ጠ​ሃት ምድር ዝና​ብን ስጥ።</verse>
				<verse number="37">“በም​ድር ላይም ራብ፥ ወይም ቸነ​ፈር፥ ወይም ዋግ፥ ወይም አረ​ማሞ ቢሆን፥ አን​በጣ፥ ወይም ኩብ​ኩባ ቢመጣ፥ የሕ​ዝ​ብ​ህም ጠላት ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው በአ​ን​ዲቱ ከብቦ ቢያ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ቸው፥ መቅ​ሠ​ፍ​ትና ደዌ ሁሉ ቢሆን፥</verse>
				<verse number="38">ማና​ቸ​ውም ሰው የል​ቡን ሕመም ዐውቆ ጸሎ​ትና ምህላ ቢያ​ደ​ርግ፥ እጆ​ቹ​ንም ወደ​ዚህ ቤት ቢዘ​ረጋ፥</verse>
				<verse number="39">በማ​ደ​ሪ​ያህ በሰ​ማይ ስማ፤ ይቅ​ርም በል፤ አንተ ብቻ የሰ​ውን ልጆች ሁሉ ልብ ታው​ቃ​ለ​ህና ልቡን ለም​ታ​ው​ቀው ሰው ሁሉ እንደ መን​ገዱ ሁሉ መጠን ክፈ​ለ​ውና ስጠው።</verse>
				<verse number="40">ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን በሰ​ጠ​ሃት ምድር ላይ በሚ​ኖ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ ይፈ​ሩህ ዘንድ።</verse>
				<verse number="41">“ከሕ​ዝ​ብ​ህም ከእ​ስ​ራ​ኤል ወገን ያል​ሆነ እን​ግዳ ስለ ስምህ ከሩቅ ሀገር ቢመጣ፥</verse>
				<verse number="42">ታላ​ቁን ስም​ህን፥ ብር​ቱ​ይ​ቱ​ንም እጅ​ህን፥ የተ​ዘ​ረ​ጋ​ች​ው​ንም ክን​ድ​ህን ሰም​ተው ቢመ​ጡና በዚህ ቤት ቢጸ​ልዩ፥</verse>
				<verse number="43">አንተ በማ​ደ​ሪ​ያህ በሰ​ማይ ስማ፤ የም​ድ​ርም አሕ​ዝብ ሁሉ ስም​ህን ያውቁ ዘንድ፥ እንደ ሕዝ​ብህ እንደ እስ​ራ​ኤል ይፈ​ሩህ ዘንድ፥ በዚ​ህም በሠ​ራ​ሁት ቤት ስምህ እንደ ተጠራ ያውቁ ዘንድ፥ እን​ግ​ዳው የሚ​ለ​ም​ን​ህን ሁሉ አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="44">“ሕዝ​ብ​ህም ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ለመ​ው​ጋት አንተ በም​ት​መ​ል​ሳ​ቸው መን​ገድ ቢወጡ፥ አን​ተም ወደ መረ​ጥ​ሃት ከተማ፥ እኔም ለስ​ምህ ወደ ሠራ​ሁት ቤት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቢጸ​ልዩ፥</verse>
				<verse number="45">ጸሎ​ታ​ቸ​ው​ንና ልመ​ና​ቸ​ውን በሰ​ማይ ስማ፤ ፍር​ድ​ንም አድ​ር​ግ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="46">“የማ​ይ​በ​ድ​ልም ሰው የለ​ምና አን​ተን ቢበ​ድሉ፥ ተቈ​ጥ​ተ​ህም ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው አሳ​ል​ፈህ ብት​ሰ​ጣ​ቸው፥ ሩቅ ወይም ቅርብ ወደ ሆነ ወደ ጠላ​ቶች ሀገር ቢማ​ረ​ኩም፥</verse>
				<verse number="47">በተ​ማ​ረ​ኩ​በ​ትም ሀገር ሆነው በል​ባ​ቸው ንስሓ ቢገቡ፥ በተ​ማ​ረ​ኩ​በ​ትም ሀገር ሳሉ ተመ​ል​ሰው፦ ኀጢ​አት ሠር​ተ​ናል፥ በድ​ለ​ን​ማል፥ ክፉ​ንም አድ​ር​ገ​ናል ብለው ቢለ​ም​ኑህ፥</verse>
				<verse number="48">በማ​ረ​ኩ​አ​ቸው በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ሀገር ሳሉ በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውና በፍ​ጹም ነፍ​ሳ​ቸው ወደ አንተ ቢመ​ለሱ፥ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ወደ ሰጠ​ሃት ወደ ምድ​ራ​ቸው ወደ መረ​ጥ​ሃ​ትም ከተማ ለስ​ም​ህም ወደ ሠራ​ሁት ቤት ቢጸ​ልዩ፥</verse>
				<verse number="49">ጸሎ​ታ​ቸ​ው​ንና ልመ​ና​ቸ​ውን በማ​ደ​ሪ​ያህ በሰ​ማይ ስማ፤</verse>
				<verse number="50">አን​ተ​ንም የበ​ደ​ሉ​ህን ሕዝ​ብ​ህን ፥ በአ​ን​ተም ላይ ያደ​ረ​ጉ​ትን በደ​ላ​ቸ​ውን ሁሉ ይቅር በል፤ ይራ​ሩ​ላ​ቸ​ውም ዘንድ በማ​ረ​ኩ​አ​ቸው ፊት ምሕ​ረ​ትን ስጣ​ቸው፤</verse>
				<verse number="51">ከግ​ብጽ ምድር ከብ​ረት እቶን ውስጥ ያወ​ጣ​ሃ​ቸው ሕዝ​ብ​ህና ርስ​ትህ ናቸ​ውና።</verse>
				<verse number="52">በጠ​ሩህ ጊዜ ሁሉ ትሰ​ማ​ቸው ዘንድ ለባ​ሪ​ያ​ህና ለሕ​ዝ​ብህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልመና ዐይ​ኖ​ችህ የተ​ገ​ለጡ፥ ጆሮ​ዎ​ችህ የተ​ከ​ፈቱ ይሁኑ።</verse>
				<verse number="53">ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን ከግ​ብፅ ባወ​ጣህ ጊዜ በባ​ሪ​ያህ በሙሴ እጅ እንደ ተና​ገ​ርህ ርስት ይሆ​ኑህ ዘንድ ከም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ ለይ​ተ​ሃ​ቸ​ዋ​ልና።” ያን​ጊ​ዜም ሰሎ​ሞን ሥራ​ውን በጨ​ረሰ ጊዜ ስለ​ዚያ ቤት እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ። “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማይ ፀሐ​ይን አሳየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጨ​ለማ ውስጥ እን​ደ​ሚ​ኖር ተና​ገረ፤ ቤቴን ሥራ፤ በመ​ታ​ደ​ስም ለመ​ኖር ለራ​ስህ ጥሩ ቤትን ሥራ፤” ይህ​ችስ በመ​ሐ​ልይ መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈች አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="54">ሰሎ​ሞ​ንም ይህ​ችን ጸሎ​ትና ልመና ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸልዮ በፈ​ጸመ ጊዜ፥ በጕ​ል​በቱ ተን​በ​ር​ክኮ፥ እጁ​ንም ወደ ሰማይ ዘር​ግቶ ነበ​ርና ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ፊት ከሰ​ገ​ደ​በት ተነሣ።</verse>
				<verse number="55">ቆሞም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጉባኤ ሁሉ በታ​ላቅ ድምፅ ሲመ​ርቅ እን​ዲህ አለ፦</verse>
				<verse number="56">“እንደ ተና​ገ​ረው ተስፋ ሁሉ ለሕ​ዝቡ ለእ​ስ​ራ​ኤል ዕረ​ፍ​ትን የሰጠ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፥ በባ​ሪ​ያው በሙሴ ቃል ከተ​ና​ገ​ረው ከመ​ል​ካም ቃል ሁሉ ያጐ​ደ​ለው አን​ድም ቃል የለም።</verse>
				<verse number="57">አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ጋር እንደ ነበረ ከእ​ኛም ጋር ይሁን፤ አይ​ተ​ወን፤ አይ​ጣ​ለ​ንም፤</verse>
				<verse number="58">በመ​ን​ገ​ዱም ሁሉ እን​ሄድ ዘንድ፥ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ያዘ​ዛ​ትን ትእ​ዛ​ዙ​ንና ሥር​ዐ​ቱን እን​ጠ​ብቅ ዘንድ፥ ልባ​ች​ንን ወደ እርሱ ይመ​ልስ።</verse>
				<verse number="59">ለባ​ሪ​ያ​ውና ለሕ​ዝቡ እስ​ራ​ኤል በየ​ዕ​ለቱ ፍር​ድን ያደ​ርግ ዘንድ ይህች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የለ​መ​ን​ኋት ቃል በቀ​ንና በሌ​ሊት ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ረ​በች ትሁን፤</verse>
				<verse number="60">የም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላክ እንደ ሆነ፥ ከእ​ር​ሱም በቀር ሌላ እንደ ሌለ ያውቁ ዘንድ፥</verse>
				<verse number="61">እንደ ዛሬው ቀን በሥ​ር​ዐቱ እን​ሄድ ዘንድ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም እን​ጠ​ብቅ ዘንድ፥ ከአ​ም​ላ​ካ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ልባ​ችን ፍጹም ይሁን።”</verse>
				<verse number="62">ንጉ​ሡም ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መሥ​ዋ​ዕት ሠዉ።</verse>
				<verse number="63">ንጉሡ ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ሰላም መሥ​ዋ​ዕት ሃያ ሁለት ሺህ በሬ​ዎ​ች​ንና መቶ ሃያ ሺህ በጎ​ችን አቀ​ረበ። ንጉ​ሡና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ እን​ዲሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ቀደሱ፤ አከ​በ​ሩም።</verse>
				<verse number="64">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያለው የናሱ መሠ​ዊያ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን የሰ​ላ​ሙ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ስብ ይይዝ ዘንድ ታናሽ ስለ ነበረ፥ በዚያ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የሰ​ላ​ሙ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ስብ አሳ​ር​ጎ​አ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት የነ​በ​ረ​ውን የአ​ደ​ባ​ባ​ዩን መካ​ከል ንጉሡ በዚያ ቀን ቀደሰ።</verse>
				<verse number="65">በዚ​ያም ዘመን ሰሎ​ሞን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከኤ​ማት መግ​ቢያ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ያለው ታላቅ ጉባኤ፥ እርሱ በሠ​ራው ቤት ውስጥ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እየ​በ​ሉና እየ​ጠጡ፥ ደስ​ታም እያ​ደ​ረጉ ሰባት ቀን በዓ​ሉን አከ​በሩ።</verse>
				<verse number="66">በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ሕዝ​ቡን አሰ​ና​በተ፤ እነ​ር​ሱም ንጉ​ሡን መረቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለባ​ሪ​ያው ለዳ​ዊ​ትና ለሕ​ዝቡ ለእ​ስ​ራ​ኤል ስላ​ደ​ረ​ገው ቸር​ነት ሁሉ በል​ባ​ቸው ደስ ብሏ​ቸው፥ ሐሴ​ትም አድ​ር​ገው ወደ እየ​ቤ​ታ​ቸው ሄዱ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት፥ የን​ጉ​ሡን ቤትና ሰሎ​ሞን ያደ​ር​ገው ዘንድ የወ​ደ​ደ​ውን ሁሉ ሠርቶ በፈ​ጸመ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በገ​ባ​ዖን ለሰ​ሎ​ሞን እንደ ተገ​ለ​ጠ​ለት ዳግ​መኛ ተገ​ለ​ጠ​ለት።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “በፊቴ የጸ​ለ​ይ​ኸ​ውን ጸሎ​ት​ህ​ንና ልመ​ና​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፤ እንደ ጸሎ​ት​ህም ሁሉ አደ​ረ​ግ​ሁ​ልህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠ​ራ​ኸ​ውን ቤት ቀድ​ሻ​ለሁ፤ ዐይ​ኖ​ችና ልቤም በዘ​መኑ ሁሉ በዚያ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="4">ዳዊ​ትም አባ​ትህ በጽ​ድቅ፥ በን​ጹሕ ልብና በቅ​ን​ነት እንደ ሄደ አንተ ደግሞ በፊቴ ብት​ሄድ፥ ያዘ​ዝ​ሁ​ህ​ንም ሁሉ ብታ​ደ​ርግ፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንም ሕጌ​ንም ብት​ጠ​ብቅ፥</verse>
				<verse number="5">እኔ፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ የሚ​ገዛ ሰውን ከአ​ንተ አላ​ጠ​ፋም ብዬ ለአ​ባ​ትህ ለዳ​ዊት እንደ ተና​ገ​ርሁ፥ የመ​ን​ግ​ሥ​ት​ህን ዙፋን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጸ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="6">ነገር ግን እና​ን​ተና ልጆ​ቻ​ችሁ እኔን ትታ​ችሁ ወደ ኋላ ብት​መ​ለሱ ለሙሴ በፊ​ታ​ችሁ የሰ​ጠ​ሁ​ትን ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሥር​ዐ​ቴን ባት​ጠ​ብቁ፥ ሄዳ​ች​ሁም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ብታ​መ​ልኩ፥ ብት​ሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፥</verse>
				<verse number="7">እስ​ራ​ኤ​ልን ከሰ​ጠ​ኋ​ቸው ምድር አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ለስ​ሜም የቀ​ደ​ስ​ሁ​ትን ይህን ቤት ከፊቴ እጥ​ለ​ዋ​ለሁ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል ለጥ​ፋ​ትና ለተ​ረት ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="8">ከፍ ከፍ ብሎ የነ​በ​ረ​ውም ይህ ቤት ባድማ ይሆ​ናል፤ በዚ​ያም የሚ​ያ​ልፍ ሁሉ እያ​ፍ​ዋጨ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ሀገ​ርና በዚህ ቤት ስለ ምን እን​ዲህ አደ​ረገ? ብሎ ይደ​ነ​ቃል።</verse>
				<verse number="9">መል​ሰ​ውም፦ ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ያወ​ጣ​ውን አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተው ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ስለ ተከ​ተሉ፥ ስለ ሰገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፥ ስለ አመ​ለ​ኩ​አ​ቸ​ውም፥ ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመ​ጣ​ባ​ቸው ይላሉ።” ያን​ጊ​ዜም ሰሎ​ሞን የፈ​ር​ዖ​ንን ልጅ ከዳ​ዊት ከተማ አው​ጥቶ በዚያ ወራት ለራሱ በሠ​ራው ቤት አስ​ገ​ባት።</verse>
				<verse number="10">ሰሎ​ሞ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የን​ጉ​ሡን ቤት ሁለ​ቱን ቤቶች በሠ​ራ​በት በሃያ ዓመት ውስጥ፥</verse>
				<verse number="11">የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራም በዝ​ግ​ባና በጥድ እን​ጨት፥ በወ​ር​ቅና በሚ​ሻ​ውም ሁሉ ሰሎ​ሞ​ንን ረድ​ቶት ነበር። ያን​ጊ​ዜም ንጉሡ ሰሎ​ሞን በገ​ሊላ ምድር ያሉ​ትን ሃያ ከተ​ሞች ለኪ​ራም ሰጠው።</verse>
				<verse number="12">ኪራ​ምም ሰሎ​ሞን የሰ​ጠ​ውን ከተ​ሞች ያይ ዘንድ ከጢ​ሮስ ወጣ፤ ወደ ገሊ​ላም ሄደ፤ ደስም አላ​ሰ​ኙ​ትም።</verse>
				<verse number="13">እር​ሱም አለው፥ “ወን​ድሜ ሆይ! የሰ​ጠ​ኸኝ እነ​ዚህ ከተ​ሞች ምን​ድን ናቸው?” እስከ ዛሬም ድረስ ወሰን ብሎ ጠራ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">ኪራ​ምም መቶ ሃያ መክ​ሊት ወርቅ ለሰ​ሎ​ሞን አመጣ።</verse>
				<verse number="15">ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና ቤተ መን​ግ​ሥ​ቱን፥ ሜሎ​ን​ንም፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቅጥር፥ አሶ​ር​ንም፥ መጊ​ዶ​ንም፥ ጋዜ​ር​ንም ይሠራ ዘንድ ሠራ​ተ​ኞ​ችን መል​ምሎ ነበር።</verse>
				<verse number="16">የግ​ብ​ፅም ንጉሥ ፈር​ዖን ወጥቶ ጋዜ​ርን ያዘ፤ በእ​ሳ​ትም አቃ​ጠ​ላት፤ በሜ​ር​ጎብ ይኖሩ የነ​በ​ሩ​ትን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም ገደ​ላ​ቸው፤ ለል​ጁም ለሰ​ሎ​ሞን ሚስት እነ​ዚ​ያን አገ​ሮች ትሎት አድ​ርጎ ሰጥ​ቶ​አት ነበር።</verse>
				<verse number="17">ሰሎ​ሞ​ንም ጋዜ​ር​ንና የታ​ች​ኛ​ውን ቤቶ​ሮ​ንን፥ ባዕ​ላ​ት​ንም ሠራ፤</verse>
				<verse number="18">በም​ድረ በዳ ሀገር ያለ​ች​ውን ኤያ​ቴ​ር​ሞ​ትን ሠራ፤</verse>
				<verse number="19">ለሰ​ሎ​ሞ​ንም የነ​በ​ሩ​ትን የዕቃ ቤት ከተ​ሞች ሁሉ፤ የሰ​ረ​ገ​ላ​ው​ንም ከተ​ሞች፥ የፈ​ረ​ሰ​ኞ​ች​ንም ከተ​ሞች፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም፥ በሊ​ባ​ኖ​ስም፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ቱም ምድር ሁሉ ሰሎ​ሞን ይሠራ ዘንድ የወ​ደ​ደ​ውን ሁሉ ሠራ።</verse>
				<verse number="20">ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዘንድ ያል​ነ​በ​ሩ​ትን ከአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንና ከኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ከከ​ና​ኔ​ዎን፥ ከፌ​ር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ከኤ​ዌ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ከኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንና ከጌ​ር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያን፥ የቀ​ሩ​ትን አሕ​ዛብ ሁሉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ በም​ድ​ሪቱ የቀ​ሩ​ትን፥</verse>
				<verse number="21">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ያጠ​ፉ​አ​ቸው ዘንድ ያል​ቻ​ሉ​ትን፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ሰሎ​ሞን እሰከ ዛሬ ድረስ ገባ​ሮች አድ​ርጎ መለ​መ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">ሰሎ​ሞ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማን​ንም ገባር አላ​ደ​ረ​ገም፤ እነ​ርሱ ግን ተዋ​ጊ​ዎች፥ ሎሌ​ዎ​ችም፥ መሳ​ፍ​ን​ትም፥ አለ​ቆ​ችም፥ የሰ​ረ​ገ​ሎ​ችና የፈ​ረ​ሶች ባል​ደ​ራ​ሶች ነበሩ።</verse>
				<verse number="23">ሰሎ​ሞ​ንም በሚ​ሠ​ራው ሥራ ላይ ሠራ​ተ​ኛ​ውን ሕዝብ የሚ​ያ​ዝዙ አለ​ቆች አም​ስት መቶ አምሳ ነበሩ።</verse>
				<verse number="24">የፈ​ር​ዖ​ን​ንም ልጅ ከዳ​ዊት ከተማ ሰሎ​ሞን ወደ ሠራ​ላት ወደ ቤቷ አመ​ጣት፤ በዚያ ጊዜም ሚሎ​ንን ሠራት።</verse>
				<verse number="25">ሰሎ​ሞ​ንም በየ​ዓ​መቱ ሦስት ጊዜ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንና የሰ​ላ​ሙን መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሠ​ራው መሠ​ዊያ ላይ ያሳ​ርግ ነበር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ባለው መሠ​ዊያ ላይ ዕጣን ያሳ​ርግ ነበር፤ ቤቱ​ንም ጨረሰ።</verse>
				<verse number="26">ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድር በኤ​ር​ትራ ባሕር ዳር በኤ​ላት አጠ​ገብ ባለ​ችው በጋ​ሴ​ዎ​ን​ጋ​ቤር መር​ከ​ቦ​ችን ሠራ።</verse>
				<verse number="27">ኪራ​ምም በእ​ነ​ዚያ መር​ከ​ቦች ከሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ጋር ባሕ​ሩን መቅ​ዘፍ የሚ​ያ​ውቁ መር​ከ​በ​ኞች አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ላከ።</verse>
				<verse number="28">ወደ አፌ​ርም ደረሱ፤ ከዚ​ያም አራት መቶ ሃያ መክ​ሊት ወርቅ ወሰዱ፤ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎ​ሞ​ንም ይዘው አገቡ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">የሳ​ባም ንግ​ሥት የሰ​ሎ​ሞ​ንን ስም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም በሰ​ማች ጊዜ ሰሎ​ሞ​ንን በእ​ን​ቆ​ቅ​ልሽ ትፈ​ት​ነው ዘንድ መጣች።</verse>
				<verse number="2">በግ​መ​ሎ​ችም ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ የከ​በ​ረም ዕንቍ አስ​ጭና ከታ​ላቅ ጓዝ ጋር ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ገባች፤ ወደ ሰሎ​ሞ​ንም በመ​ጣች ጊዜ በል​ብዋ ያለ​ውን ሁሉ ነገ​ረ​ችው።</verse>
				<verse number="3">ሰሎ​ሞ​ንም የጠ​የ​ቀ​ች​ውን ሁሉ ፈታ​ላት፤ ያል​ተ​ረ​ጐ​መ​ላ​ትና ከን​ጉሡ የተ​ሰ​ወረ ነገር አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="4">የሳ​ባም ንግ​ሥት የሰ​ሎ​ሞ​ንን ጥበብ ሁሉ፥ ሠር​ቶ​ትም የነ​በ​ረ​ውን ቤት፥</verse>
				<verse number="5">የሰ​ሎ​ሞ​ን​ንም የማ​ዕ​ዱን መብል፥ የብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹ​ንም አቀ​ማ​መጥ፥ የሎ​ሌ​ዎ​ቹ​ንም ሥር​ዐት፥ አለ​ባ​በ​ሳ​ቸ​ው​ንም፥ ጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ቹ​ንም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ባየች ጊዜ ተደ​ነ​ቀች።</verse>
				<verse number="6">ንጉ​ሡን ሰሎ​ሞ​ን​ንም አለ​ችው፥ “ስለ ነገ​ር​ህና ስለ ጥበ​ብህ በሀ​ገሬ ሳለሁ የሰ​ማ​ሁት ዝና እው​ነት ነው።</verse>
				<verse number="7">እኔም መጥቼ በዐ​ይኔ እስ​ካይ ድረስ የነ​ገ​ሩ​ኝን አላ​መ​ን​ሁም ነበር ፤ እነ​ሆም፥ እኩ​ሌ​ታ​ውን አል​ነ​ገ​ሩ​ኝም ነበር፤ በሀ​ገሬ ሳለሁ ከነ​ገ​ሩኝ ይልቅ የበ​ለጠ መል​ካም ተጨ​ማሪ አየሁ።</verse>
				<verse number="8">ሚስ​ቶ​ችህ የተ​መ​ሰ​ገኑ ናቸው፤ በፊ​ትህ ሁል​ጊዜ የሚ​ቆሙ፥ ጥበ​ብ​ህን የሚ​ሰሙ እነ​ዚህ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህም ምስ​ጉ​ኖች ናቸው።</verse>
				<verse number="9">አን​ተን በእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን ያስ​ቀ​ም​ጥህ ዘንድ የወ​ደደ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ይሁን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ራ​ኤ​ልን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያጸ​ናው ዘንድ ወድ​ዶ​ታ​ልና ስለ​ዚህ በየ​ነ​ገ​ራ​ቸው ጽድ​ቅና ፍርድ ታደ​ርግ ዘንድ በላ​ያ​ቸው አነ​ገ​ሠህ።”</verse>
				<verse number="10">ለን​ጉ​ሡም መቶ ሃያ መክ​ሊት ወርቅ እጅ​ግም ብዙ ሽቶ፥ የከ​በ​ረም ዕንቍ ሰጠ​ችው፤ የሳባ ንግ​ሥት ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን እንደ ሰጠ​ችው ያለ የሽቶ ብዛት ከዚያ ወዲያ አል​መ​ጣም ነበር።</verse>
				<verse number="11">ከኦ​ፌ​ርም ወርቅ ያመ​ጣች የኪ​ራም መር​ከብ እጅግ ብዙ የተ​ጠ​ረበ እን​ጨ​ትና የከ​በረ ዕንቍ አመ​ጣች።</verse>
				<verse number="12">ንጉ​ሡም ከተ​ጠ​ረ​በው እን​ጨት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና ለን​ጉሡ ቤት መከታ፥ ለመ​ዘ​ም​ራ​ኑም መሰ​ን​ቆና በገና አደ​ረገ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በም​ድር ላይ እን​ደ​ዚያ ያለ የተ​ጠ​ረበ እን​ጨት ከቶ አል​መ​ጣም፤ በየ​ትም ቦታ አል​ታ​የም።</verse>
				<verse number="13">ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን በእጁ ከሰ​ጣት ሌላ፥ የወ​ደ​ደ​ች​ውን ሁሉ፥ ከእ​ር​ሱም የጠ​የ​ቀ​ች​ውን ሁሉ ለሳባ ንግ​ሥት ሰጣት፤ የከ​ለ​ከ​ላ​ትም የለም፤ እር​ስ​ዋም ተመ​ልሳ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችዋ ጋር ወደ ሀገ​ርዋ ሄደች።</verse>
				<verse number="14">በየ​ዓ​መቱ ለሰ​ሎ​ሞን የሚ​መ​ጣ​ለት የወ​ርቅ ሚዛን ስድ​ስት መቶ ስድሳ ስድ​ስት መክ​ሊት ወርቅ ነበረ።</verse>
				<verse number="15">ይኽ​ንም፥ ግብር የሚ​ያ​ስ​ገ​ብሩ ሰዎች፥ ነጋ​ዴ​ዎ​ችም፥ በዙ​ሪ​ያው ያሉ ነገ​ሥ​ታ​ትም ሁሉ፥ የም​ድ​ርም ሹሞች ከሚ​ያ​ወ​ጡት ሌላ ነው።</verse>
				<verse number="16">ንጉሡ ሰሎ​ሞ​ንም ከጥ​ፍ​ጥፍ ወርቅ ሁለት መቶ አላ​ባሽ አግሬ ጋሻ አሠራ፤ በአ​ን​ዱም አላ​ባሽ አግሬ ጋሻ ውስጥ የገ​ባው ወርቅ ሦስት መቶ ሰቅል ነበረ።</verse>
				<verse number="17">ከጥ​ፍ​ጥ​ፍም ወርቅ ሦስት መቶ ጋሻ አሠራ፤ በአ​ን​ዱም ጋሻ የገ​ባው ወርቅ ሦስት ምናን ነው፤ ንጉ​ሡም የሊ​ባ​ኖስ ዱር በተ​ባ​ለው ቤት ውስጥ አኖ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">ንጉ​ሡም ደግሞ ከዝ​ሆን ጥርስ ታላቅ ዙፋን አሠራ፤ በጥ​ሩም ወርቅ ለበ​ጠው።</verse>
				<verse number="19">ወደ ዙፋ​ንም የሚ​ያ​ስ​ኬዱ ስድ​ስት እር​ከ​ኖች ነበሩ፤ በስ​ተ​ኋ​ላ​ውም ያለው የዙ​ፋኑ ራስ ክብ ነበረ፤ በላም ምስል የተ​ቀ​ረጸ በወ​ዲ​ህና በወ​ዲ​ያም መደ​ገ​ፊያ ነበ​ረው፤ በመ​ደ​ገ​ፊ​ያ​ዎ​ቹም አጠ​ገብ ሁለት አን​በ​ሶች ቆመው ነበር፤</verse>
				<verse number="20">በስ​ድ​ስ​ቱም እር​ከ​ኖች ላይ በዚ​ህና በዚያ ዐሥራ ሁለት አን​በ​ሶች ቆመው ነበር፤ በመ​ን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ እን​ዲህ ያለ ሥራ አል​ተ​ሠ​ራም።</verse>
				<verse number="21">ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ያሠ​ራው የመ​ጠጫ ዕቃ ሁሉ ወርቅ ነበረ፤ ኵስ​ኵ​ስ​ቱም የወ​ርቅ ነበረ፤ የሊ​ባ​ኖስ ዱር የተ​ባ​ለ​ውን የዚ​ያን ቤት ዕቃ ሁሉ በወ​ርቅ አስ​ለ​በ​ጠው። የብ​ርም ዕቃ አል​ነ​በ​ረም፤ በሰ​ሎ​ሞን ዘመን የብር ዋጋ ዝቅ​ተኛ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="22">ለን​ጉ​ሡም ከኪ​ራም መር​ከ​ቦች ጋር በባ​ሕር ውስጥ የተ​ር​ሴስ መር​ከ​ቦች ነበ​ሩት፤ በየ​ሦ​ስት ዓመ​ትም አንድ መር​ከብ ከተ​ር​ሴስ ወር​ቅና ብር፥ የተ​ቀ​ረ​ጸና የተ​ደ​ረ​ደረ ዕንቍ ይዞ ይመጣ ነበር።</verse>
				<verse number="23">ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን በብ​ል​ጥ​ግ​ናና በጥ​በብ ከም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ እጅግ በልጦ ነበር።</verse>
				<verse number="24">የም​ድ​ርም ነገ​ሥት ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በልቡ ያኖ​ረ​ለ​ትን ጥበ​ቡን ይሰሙ ዘንድ የሰ​ሎ​ሞ​ንን ፊት ለማ​የት ይሹ ነበር።</verse>
				<verse number="25">እነ​ር​ሱም ሁሉ በዓ​መት በዓ​መቱ ገጸ በረ​ከ​ቱን፥ የብ​ርና የወ​ርቅ ዕቃ፥ ልብ​ስና የጦር መሣ​ሪያ፥ ሽቱም፥ ፈረ​ሶ​ችና በቅ​ሎ​ዎች እየ​ያዙ ይመጡ ነበር።</verse>
				<verse number="26">ሰሎ​ሞ​ንም ለሰ​ረ​ገ​ሎቹ ዐራት ሺህ እን​ስት ፈረ​ሶች ነበ​ሩት፤ ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረ​ሰ​ኞ​ችም ነበ​ሩት፤ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም ከተ​ሞች ከን​ጉሡ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አኖ​ራ​ቸው። ሰሎ​ሞ​ንም ከወ​ንዙ ጀምሮ እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ምድ​ርና እስከ ግብፅ ድን​በር ድረስ በነ​ገ​ሥ​ታቱ ሁሉ ላይ ንጉሥ ነበር።</verse>
				<verse number="27">ንጉ​ሡም ብሩ​ንና ወር​ቁን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ ድን​ጋይ እን​ዲ​በዛ አደ​ረ​ገው፤ የዝ​ግ​ባም እን​ጨት ብዛት በቆላ እን​ደ​ሚ​በ​ቅል ሾላ ሆነ።</verse>
				<verse number="28">ሰሎ​ሞ​ንም ፈረ​ሶ​ችን ከግ​ብ​ፅና ከቴ​ቁሄ ሀገር አስ​መጣ፤ የን​ጉ​ሡም ነጋ​ዴ​ዎች በገ​ን​ዘብ እየ​ገዙ ከቴ​ቁሄ ያመ​ጡ​አ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="29">አን​ዱም ሰረ​ገላ በስ​ድ​ስት መቶ፥ አን​ዱም ፈረስ በመቶ ኀምሳ ብር ከግ​ብፅ ይወጣ ነበር። እን​ዲ​ሁም ለኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያን ነገ​ሥ​ታ​ትና ለሶ​ርያ ነገ​ሥ​ታት ሁሉ በባ​ሕሩ በኩል ያወ​ጡ​ላ​ቸው ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ሴቶ​ችን ይወድ ነበር፥ ከባ​ዕ​ዳን ሕዝ​ብም የፈ​ር​ዖ​ንን ልጅ፥ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ት​ንና አሞ​ና​ው​ያ​ትን፥ ሶር​ያ​ው​ያ​ት​ንና ሲዶ​ና​ው​ያ​ትን፥ ኤዶ​ማ​ው​ያ​ት​ንና አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ት​ንም፥ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ት​ንም፦ ሚስ​ቶ​ችን አገባ።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች፥ “አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን ትከ​ተሉ ዘንድ ልባ​ች​ሁን እን​ዳ​ይ​መ​ልሱ ወደ እነ​ርሱ አት​ግቡ፥ እነ​ር​ሱም ወደ እና​ንተ አይ​ግቡ” ካላ​ቸው ከአ​ሕ​ዝብ አገባ፤ ሰሎ​ሞን ግን እነ​ር​ሱን ተከ​ተለ፤ ወደ​ዳ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="3">ለእ​ር​ሱም ሰባት መቶ ሚስ​ቶ​ችና ሦስት መቶ ቁባ​ቶች ነበ​ሩት።</verse>
				<verse number="4">ከዚህ በኋላ ሰሎ​ሞን በሸ​መ​ገለ ጊዜ ልቡ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ ከአ​ም​ላኩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አል​ነ​በ​ረም። ከባ​ዕድ ያገ​ባ​ቸው ሚስ​ቶ​ቹም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ይከ​ተል ዘንድ ልቡን መለ​ሱት።</verse>
				<verse number="5">ሰሎ​ሞ​ንም የሲ​ዶ​ና​ው​ያ​ንን አም​ላክ አስ​ጠ​ራ​ጢ​ስን የአ​ሞ​ና​ው​ያ​ን​ንም ርኵ​ሰት ኮሞ​ስን ተከ​ተለ።</verse>
				<verse number="6">ሰሎ​ሞ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ፤ እንደ አባ​ቱም እንደ ዳዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ተ​ከ​ተ​ለ​ውም።</verse>
				<verse number="7">ያን​ጊ​ዜም ሰሎ​ሞን ለሞ​አብ ርኵ​ሰት ለኮ​ሞስ፥ ለአ​ሞን ልጆች ርኵ​ሰት ለሞ​ሎክ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አን​ጻር በአ​ለው ተራራ ላይ መስ​ገ​ጃን ሠራ።</verse>
				<verse number="8">ሰሎ​ሞ​ንም ልዩ ከሆኑ ከአ​ሕ​ዝብ ለአ​ገ​ባ​ቸው ሚስ​ቶቹ ሁሉ እን​ዲህ አደ​ረገ፤ ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋ፤ ዕጣ​ንም አጠነ።</verse>
				<verse number="9">ሁለት ጊዜም ከተ​ገ​ለ​ጠ​ለት ከእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡ​ና​ውን መል​ሶ​አ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ሎ​ሞን ላይ ቍጣን ተቈጣ።</verse>
				<verse number="10">ስለ​ዚ​ህም ነገር ወደ ባዕድ አም​ል​ኮት እን​ዳ​ይ​ሄድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ይጠ​ብ​ቅና ያደ​ርግ ዘንድ አዘ​ዘው፤ ልቡ​ናው ግን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ፍጹም አል​ሆ​ነም።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰሎ​ሞ​ንን አለው፥ “ይህን ሠር​ተ​ሃ​ልና፥ ያዘ​ዝ​ሁ​ህ​ንም ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሕጌን አል​ጠ​ብ​ቅ​ህ​ምና መን​ግ​ሥ​ት​ህን ከአ​ንተ ከፍዬ ለባ​ሪ​ያህ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">ነገር ግን ከል​ጅህ እጅ እከ​ፍ​ለ​ዋ​ለሁ እንጂ ስለ አባ​ትህ ስለ ዳዊት ይህን በዘ​መ​ንህ አላ​ደ​ር​ግም።</verse>
				<verse number="13">ነገር ግን ስለ ባሪ​ያዬ ስለ ዳዊ​ትና ስለ መረ​ጥ​ኋት ሀገሬ ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለል​ጅህ አንድ ነገድ እሰ​ጣ​ለሁ እንጂ መን​ግ​ሥ​ቱን ሁሉ አል​ከ​ፍ​ልም።”</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኤዶ​ማ​ዊው አዴ​ርን ከረ​ም​ማ​ቴር ወገን የኤ​ል​ያ​ዳሔ ልጅ ኤስ​ሮ​ምን የሲባ ንጉሥ ጌታ​ውን አድ​ረ​ዓ​ዛ​ርን ጠላት አድ​ርጎ በሰ​ሎ​ሞን ላይ አስ​ነሣ። ሰዎ​ችም ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ። የዓ​መ​ፁም አበ​ጋዝ እርሱ ነበር። ደማ​ስ​ቆ​ንም እጅ አደ​ረ​ጋት። በሰ​ሎ​ሞ​ንም ዘመን ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ጠላት ሆነ። ኤዶ​ማ​ዊው አዴ​ርም ከኤ​ዶ​ም​ያስ ነገ​ሥ​ታት ዘር ነበር።</verse>
				<verse number="15">ዳዊ​ትም ኤዶ​ም​ያ​ስን ባጠፋ ጊዜ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ ኢዮ​አብ ተወ​ግ​ተው የሞ​ቱ​ትን ሊቀ​ብር በወጣ ጊዜ፥ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስ​ንም ወንድ ሁሉ በገ​ደለ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="16">ኢዮ​አ​ብና እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስን ወንድ ሁሉ እስ​ኪ​ገ​ድሉ ድረስ ስድ​ስት ወር በዚያ ተቀ​ም​ጠው ነበር።</verse>
				<verse number="17">አዴር፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ከኤ​ዶ​ም​ያስ ሰዎች የሆኑ የአ​ባቱ አገ​ል​ጋ​ዮች ሁሉ ኰበ​ለሉ፤ ወደ ግብ​ፅም ገቡ። አዴር ግን ገና ሕፃን ነበር።</verse>
				<verse number="18">ከም​ድ​ያ​ምም ተነ​ሥ​ተው ወደ ፋራን ሄዱ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ከፋ​ራን ሰዎ​ችን ወሰዱ፤ ወደ ግብ​ፅም መጡ፤ ወደ ግብ​ፅም ንጉሥ ወደ ፈር​ዖን ሄዱ፤ አዴ​ርም ወደ ፈር​ዖን ገባ። እር​ሱም ቤት ሰጥቶ ቀለብ ዳረ​ገው።</verse>
				<verse number="19">አዴ​ርም በፈ​ር​ዖን ፊት እጅግ ባለ​ም​ዋል ሆነ። የሚ​ስ​ቱ​ንም የቴ​ቄ​ም​ና​ስን ታላቅ እኅት ሚስት አጋ​ባው።</verse>
				<verse number="20">የቴ​ቄ​ም​ናስ እኅት ወንድ ልጅ ጌን​ባ​ትን ለአ​ዴር ወለ​ደ​ች​ለት፤ ቴቄ​ም​ና​ስም በፈ​ር​ዖን ልጆች መካ​ከል አሳ​ደ​ገ​ችው፤ ጌን​ባ​ትም በፈ​ር​ዖን ልጆች መካ​ከል ነበረ።</verse>
				<verse number="21">አዴ​ርም በግ​ብፅ ሳለ ዳዊት እንደ አባ​ቶቹ እን​ዳ​ን​ቀ​ላፋ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ ኢዮ​አብ እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ አዴር ፈር​ዖ​ንን፥ “ወደ ሀገሬ እሄድ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ተኝ” አለው።</verse>
				<verse number="22">ፈር​ዖ​ንም፥ “እነሆ፥ ከእኔ ዘንድ ወደ ሀገ​ርህ መሄድ የፈ​ለ​ግህ ምን አጥ​ተህ ነው?” አለው። አዴ​ርም፥ “አን​ዳች አላ​ጣ​ሁም፤ ነገር ግን ልሂድ” ብሎ መለሰ። አዴ​ርም ወደ ሀገሩ ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ ከጌ​ታው ከሱባ ንጉሥ ከአ​ድ​ር​አ​ዛር የኰ​በ​ለ​ለ​ውን የኤ​ል​ያ​ዳን ልጅ ሬዞ​ንን ጠላት አድ​ርጎ አስ​ነ​ሣ​በት።</verse>
				<verse number="24">ዳዊ​ትም የሲ​ባን ሰዎች በገ​ደለ ጊዜ ሬዞን ሰዎ​ችን ሰብ​ስቦ የጭ​ፍራ አለቃ ሆነ፤ ወደ ደማ​ስ​ቆም ሄዱ፥ በዚ​ያም ተቀ​መጡ፤ በደ​ማ​ስ​ቆም ላይ አነ​ገ​ሡት።</verse>
				<verse number="25">በሰ​ሎ​ሞ​ንም ዘመን ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ጠላት ነበረ። አዴ​ርም ያደ​ረ​ጋት ክፋት ይህች ናት፤ እስ​ራ​ኤ​ልን አስ​ጨ​ነቀ በኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ነገሠ።</verse>
				<verse number="26">ከሳ​ሪራ ሀገር የሆነ የኤ​ፍ​ሬ​ማ​ዊው የና​ባ​ጥና ሳሩሃ የተ​ባ​ለች የመ​በ​ለት ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋይ ነበረ።</verse>
				<verse number="27">እር​ሱም ያደ​ረ​ገው ይህ ነው በን​ጉሡ በሰ​ሎ​ሞን ላይ እጁን አነሣ፤ ሰሎ​ሞ​ንም በዳ​ርቻ ያለ ቅጥ​ር​ንና የአ​ባ​ቱን የዳ​ዊ​ትን ከተማ ቅጥር ሠርቶ ጨረሰ።</verse>
				<verse number="28">ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ጽኑዕ ኀያል ሰው ነበረ፤ ሰሎ​ሞ​ንም ጐል​ማ​ሳው ኢዮ​ር​ብ​ዓም በሥራ የጸና መሆ​ኑን ባየ ጊዜ በዮ​ሴፍ ነገድ ሥራ ሁሉ ላይ ሾመው።</verse>
				<verse number="29">ከዚህ በኋ​ላም ኢዮ​ር​ብ​ዓም ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በወጣ ጊዜ ሴሎ​ና​ዊው ነቢዩ አኪያ በመ​ን​ገድ ላይ ተገ​ና​ኘው፤ ከመ​ን​ገ​ድም ገለል አደ​ረ​ገው፤ አኪ​ያም አዲስ ልብስ ለብሶ ነበር። ሁለ​ቱም በሜዳ ነበሩ።</verse>
				<verse number="30">አኪ​ያም የለ​በ​ሰ​ውን አዲስ ልብስ ይዞ ከዐ​ሥራ ሁለት ቀደ​ደው።</verse>
				<verse number="31">ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ም​ንም አለው፥ “ዐሥር ቅዳጅ ውሰድ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ እነሆ፥ ከሰ​ሎ​ሞን እጅ መን​ግ​ሥ​ቱን እለ​ያ​ታ​ለሁ፤ ዐሥ​ሩ​ንም ነገ​ዶች እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="32">ስለ ባሪ​ያዬ ስለ ዳዊት ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሀገ​ሮች ሁሉ ስለ መረ​ጥ​ኋት ከተማ ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ግን ሁለት ነገድ ይቀ​ሩ​ለ​ታል፤</verse>
				<verse number="33">ትቶ​ኛ​ልና፥ ለሲ​ዶ​ና​ው​ያ​ንም ርኵ​ሰት ለአ​ስ​ጠ​ራ​ጢስ፥ ለሞ​አ​ብም አም​ላክ ለኮ​ሞስ፥ ለአ​ሞ​ንም ልጆች አም​ላክ ለሞ​ሎክ ሰግ​ዶ​አ​ልና፥ አባ​ቱም ዳዊት እን​ዳ​ደ​ረገ በፊቴ ቅን ነገ​ርን ያደ​ርግ ዘንድ በመ​ን​ገ​ዶቼ አል​ሄ​ደ​ምና።</verse>
				<verse number="34">መን​ግ​ሥ​ቱ​ንም ሁሉ ከእጁ አል​ወ​ስ​ድም፤ ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሥር​ዐ​ቴን ስለ ጠበ​ቀው ስለ መረ​ጥ​ሁት ስለ ባሪ​ያዬ ስለ ዳዊት ግን በዕ​ድ​ሜው ሁሉ አለቃ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="35">መን​ግ​ሥ​ቱ​ንም ከልጁ እጅ እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ለአ​ን​ተም ዐሥ​ሩን ነገድ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="36">ስሜ​ንም ባኖ​ር​ሁ​ባት በዚ​ያች በመ​ረ​ጥ​ኋት ከተማ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለባ​ሪ​ያዬ ለዳ​ዊት በፊቴ ሁል​ጊዜ መብ​ራት ይሆ​ን​ለት ዘንድ ለልጁ ሁለት ነገ​ድን እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="37">አን​ተ​ንም እወ​ስ​ድ​ሃ​ለሁ፤ ነፍ​ስ​ህም በወ​ደ​ደ​ችው ሁሉ ላይ አነ​ግ​ሥ​ሃ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ንጉሥ ትሆ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="38">ባሪ​ያ​ዬም ዳዊት እን​ዳ​ደ​ረገ፥ ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ሁሉ ብት​ሰማ፥ በመ​ን​ገ​ዴም ብት​ሄድ፥ በፊ​ቴም የቀ​ና​ውን ብታ​ደ​ርግ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሥር​ዐ​ቴን ብት​ጠ​ብቅ፥ ከአ​ንተ ጋር እኖ​ራ​ለሁ፤ ለዳ​ዊ​ትም እንደ ሠራ​ሁ​ለት የታ​መነ ቤትን እሠ​ራ​ል​ሃ​ለሁ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ለአ​ንተ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="39">ስለ​ዚ​ህም የዳ​ዊ​ትን ዘር አስ​ጨ​ን​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን በዘ​መን ሁሉ አይ​ደ​ለም።”</verse>
				<verse number="40">ሰሎ​ሞ​ንም ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምን ሊገ​ድ​ለው ወደደ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ተነ​ሥቶ ወደ ግብፅ ሀገር፥ ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ሱስ​ቀም ኰብ​ልሎ ሄደ፥ ሰሎ​ሞ​ንም እስ​ኪ​ሞት ድረስ በግ​ብፅ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="41">የቀ​ረ​ውም የሰ​ሎ​ሞን ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ ጥበ​ቡም ሁሉ፥ እነሆ፥ በሰ​ሎ​ሞን የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።</verse>
				<verse number="42">ሰሎ​ሞ​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ የነ​ገ​ሠ​በት ዘመን አርባ ዓመት ነበረ።</verse>
				<verse number="43">ሰሎ​ሞ​ንም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ፥ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ተቀ​በረ፤ ልጁም ሮብ​ዓም በፋ​ን​ታው ነገሠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ያነ​ግ​ሡት ዘንድ ወደ ሰቂማ መጥ​ተው ነበ​ርና ሮብ​ዓም ወደ ሰቂማ ሄደ።</verse>
				<verse number="2">እን​ዲ​ህም ሆነ፥ የና​ባጥ ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ገና በግ​ብፅ ሳለ ይህን በሰማ ጊዜ፥ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ከን​ጉሡ ከሰ​ሎ​ሞን ፊት ኰብ​ልሎ በግ​ብፅ ተቀ​ምጦ ነበረ፤</verse>
				<verse number="3">በግ​ብ​ፅም ሳለ ልከው ጠሩት፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምና የእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ መጥ​ተው ሮብ​ዓ​ምን እን​ዲህ ብለው አነ​ጋ​ገ​ሩት፦</verse>
				<verse number="4">“አባ​ትህ ቀን​በር አክ​ብ​ዶ​ብን ነበር፤ አሁ​ንም አንተ ጽኑ​ውን የአ​ባ​ት​ህን አገ​ዛዝ፥ በላ​ያ​ች​ንም የጫ​ነ​ውን የከ​በ​ደ​ውን ቀን​በር አቃ​ል​ል​ልን፤ እኛም እን​ገ​ዛ​ል​ሃ​ለን።”</verse>
				<verse number="5">እር​ሱም፥ “ሂዱ፥ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ወደ እኔ ተመ​ለሱ” አላ​ቸው። ሕዝ​ቡም ሄዱ።</verse>
				<verse number="6">ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም፥ “ለዚህ ሕዝብ እመ​ል​ስ​ለት ዘንድ የም​ት​መ​ክ​ሩኝ ምን​ድን ነው?” ብሎ አባቱ ሰሎ​ሞን በሕ​ይ​ወቱ ሳለ በፊቱ ይቆሙ ከነ​በ​ሩት ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጋር ተማ​ከረ።</verse>
				<verse number="7">እነ​ር​ሱም፥ “ለዚህ ሕዝብ አሁን አገ​ል​ጋይ ብት​ሆን፥ ብት​ገ​ዛ​ላ​ቸ​ውም፥ መል​ሰ​ህም በገ​ር​ነት ብት​ነ​ግ​ራ​ቸው፥ በዘ​መኑ ሁሉ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ይሆ​ኑ​ል​ሃል” ብለው ተና​ገ​ሩት።</verse>
				<verse number="8">እርሱ ግን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች የመ​ከ​ሩ​ትን ምክር ትቶ ከእ​ርሱ ጋር ካደ​ጉ​ትና በፊቱ ይቆሙ ከነ​በ​ሩት ብላ​ቴ​ኖች ጋር ተማ​ከረ።</verse>
				<verse number="9">እር​ሱም፥ “አባ​ትህ የጫ​ነ​ብ​ንን ቀን​በር አቃ​ል​ል​ልን ለሚ​ሉኝ ሕዝብ እመ​ል​ስ​ላ​ቸው ዘንድ የም​ት​መ​ክ​ሩኝ ምን​ድን ነው?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">ከእ​ር​ሱም ጋር ያደ​ጉት፥ በፊቱ የሚ​ቆ​ሙት ብላ​ቴ​ኖች እን​ዲህ አሉት፥ “አባ​ትህ ቀን​በር አክ​ብ​ዶ​ብ​ናል፥ አንተ ግን ዛሬ አቃ​ል​ል​ልን ለሚ​ሉህ ሕዝብ፦ ታና​ሺቱ ጣቴ ከአ​ባቴ ወገብ ትወ​ፍ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="11">አሁ​ንም አባቴ ከባድ ቀን​በር ጭኖ​ባ​ች​ኋል፥ እኔ ግን በቀ​ን​በ​ራ​ችሁ ላይ እጨ​ም​ራ​ለሁ፤ አባቴ በአ​ለ​ንጋ ገር​ፎ​አ​ች​ኋል፥ እኔ ግን በጊ​ንጥ እገ​ር​ፋ​ች​ኋ​ለሁ በላ​ቸው።” ይህም ቃል ሮብ​ዓ​ምን ደስ አሰ​ኘው።</verse>
				<verse number="12">ንጉ​ሡም፥ “በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ወደ እኔ ተመ​ለሱ” ብሎ እንደ ተና​ገረ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምና ሕዝቡ ሁሉ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ወደ ሮብ​ዓም መጡ።</verse>
				<verse number="13">ንጉ​ሡም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች የመ​ከ​ሩ​ትን ምክር ትቶ ለሕ​ዝቡ ጽኑ ምላሽ መለ​ሰ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">እንደ ብላ​ቴ​ኖ​ችም ምክር፥ “አባቴ ቀን​በር አክ​ብ​ዶ​ባ​ችሁ ነበር፥ እኔ ግን በቀ​ን​በ​ራ​ችሁ ላይ እጨ​ም​ራ​ለሁ፤ አባቴ በአ​ለ​ንጋ ገር​ፎ​አ​ችሁ ነበር፥ እኔ ግን በጊ​ንጥ እገ​ር​ፋ​ች​ኋ​ለሁ” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሴ​ሎ​ና​ዊው በአ​ኪያ አፍ ለና​ባጥ ልጅ ለኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር እን​ዲ​ያ​ጸና ለውጡ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበ​ርና ንጉሡ ሕዝ​ቡን አል​ሰ​ማም።</verse>
				<verse number="16">እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ንጉሡ እን​ዳ​ል​ሰ​ማ​ቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ ለን​ጉሡ፥ “በዳ​ዊት ዘንድ ምን ክፍል አለን? በእ​ሴ​ይም ልጅ ዘንድ ርስት የለ​ንም። እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ወደ ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ ዳዊት ሆይ፥ አሁን የራ​ስ​ህን ቤት ተመ​ል​ከት” ብለው መለ​ሱ​ለት። እስ​ራ​ኤ​ልም ወደ​የ​ቤ​ታ​ቸው ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="17">በይ​ሁዳ ከተ​ሞች በተ​ቀ​መ​ጡት በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ግን ሮብ​ዓም ነገሠ።</verse>
				<verse number="18">ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም አስ​ገ​ባ​ሪ​ውን አዶኒ​ራ​ምን ላከ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ደበ​ደ​ቡት፥ ሞተም። ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም ፈጥኖ ወደ ሰረ​ገ​ላው ወጣ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሸሸ።</verse>
				<verse number="19">እስ​ራ​ኤ​ልም እስከ ዛሬ ድረስ የዳ​ዊ​ትን ቤት ከዱት።</verse>
				<verse number="20">ከዚ​ህም በኋላ እስ​ራ​ኤል በሙሉ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ከግ​ብፅ እንደ ተመ​ለሰ በሰሙ ጊዜ ልከው ወደ ሸን​ጎ​አ​ቸው ጠሩት፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ላይ አነ​ገ​ሡት። ከብ​ቻው ከይ​ሁ​ዳና ከብ​ን​ያም ነገድ በቀር የዳ​ዊ​ትን ቤት የተ​ከ​ተለ ማንም አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="21">ሮብ​ዓም ግን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቤት ወግ​ተው መን​ግ​ሥ​ቱን ወደ ሰሎ​ሞን ልጅ ወደ ሮብ​ዓም ይመ​ልሱ ዘንድ ከይ​ሁዳ ቤት ሁሉና ከብ​ን​ያም ነገድ የተ​መ​ረ​ጡ​ትን አንድ መቶ ሃያ ሺህ ተዋ​ጊ​ዎች ሰዎ​ችን ሰበ​ሰበ።</verse>
				<verse number="22">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ ሳማያ እን​ዲህ ሲል መጣ።</verse>
				<verse number="23">ለይ​ሁዳ ንጉሥ ለሰ​ሎ​ሞን ልጅ ለሮ​ብ​ዓ​ምና ለይ​ሁዳ፥ ለብ​ን​ያ​ምም ቤት ሁሉ፥ ለቀ​ረ​ውም ሕዝብ ሁሉ፦ እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህ ነገር ከእኔ ዘንድ ነውና አት​ውጡ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን አት​ውጉ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ ቤቱ ይመ​ለስ።” እነ​ር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰሙ፤ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ተመ​ል​ሰው ሄዱ።</verse>
				<verse number="25">ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ሰቂ​ማን ሠርቶ በዚያ ተቀ​መጠ፤ ደግ​ሞም ከዚያ ወጥቶ ፋኑ​ኤ​ልን ሠራ።</verse>
				<verse number="26">ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም በልቡ አለ፥ “እነሆ፥ ዛሬ መን​ግ​ሥት ወደ ዳዊት ቤት ይመ​ለ​ሳል።</verse>
				<verse number="27">ይህ ሕዝብ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ያቀ​ርብ ዘንድ ቢወጣ፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ወደ ጌታ​ቸው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብ​ዓም ይመ​ለ​ሳል፥ እኔ​ንም ይወ​ጉ​ኛል።”</verse>
				<verse number="28">ንጉ​ሡም ተማ​ከረ፤ ሁለ​ትም የወ​ርቅ ጥጆች ሠርቶ፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መው​ጣት ይበ​ቃ​ች​ኋል፤ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጡ​አ​ችሁ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ችሁ እነሆ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="29">አን​ዱን በቤ​ቴል ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም በዳን አኖረ።</verse>
				<verse number="30">ይህም ኀጢ​አት ሆነ፥ ሕዝቡ በዳን ወዳ​ለች ወደ አን​ዲቱ ጣዖት ይሄዱ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="31">በኮ​ረ​ብ​ቶ​ቹም ላይ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን ሠራ፤ ከሌዊ ልጆች ካይ​ደሉ ከማ​ን​ኛ​ውም ሕዝብ ሁሉ የጣ​ዖት ካህ​ና​ትን ሾመ።</verse>
				<verse number="32">ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም በስ​ም​ን​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን በይ​ሁዳ እን​ደ​ሚ​ደ​ረግ በዓል ያለ በዓል አደ​ረገ፤ ለሠ​ራ​ቸ​ውም ጥጆች ይሠዋ ዘንድ በቤ​ቴል ወደ ሠራው መሠ​ዊያ ወጣ፤ ለኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችም የመ​ረ​ጣ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ያን ካህ​ናት በቤ​ቴል አኖ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="33">በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ወር በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን በልቡ ባሰ​በው ቀን ወደ ሠራው መሠ​ዊያ ወጣ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በዓል አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው፤ ወደ መሠ​ዊ​ያ​ውም ሊሠዋ ወጣ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">እነ​ሆም፥ አንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ከይ​ሁዳ ወደ ቤቴል መጣ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም መሥ​ዋ​ዕት ይሠዋ ዘንድ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ቆሞ ነበር።</verse>
				<verse number="2">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ፥ “መሠ​ዊያ ሆይ፥ መሠ​ዊያ ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ስሙ ኢዮ​ስ​ያስ የሚ​ባል ልጅ ለዳ​ዊት ቤት ይወ​ለ​ዳል፤ ዕጣ​ንም የሚ​ያ​ጥ​ኑ​ብ​ህን የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቹን ካህ​ናት ይሠ​ዋ​ብ​ሃል፤ የሰ​ዎ​ቹ​ንም አጥ​ንት ያቃ​ጥ​ል​ብ​ሃል” ብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ጠራ።</verse>
				<verse number="3">በዚ​ያም ቀን፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው፤ “እነሆ፥ መሠ​ዊ​ያው ይሰ​ነ​ጠ​ቃል፤ በው​ስ​ጡም ያለው ስብ ይፈ​ስ​ሳል” ብሎ ምል​ክት ሰጠ።</verse>
				<verse number="4">ከዚ​ህም በኋላ ንጉሡ ኢዮ​ር​ብ​ዓም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በቤ​ቴል ባለው መሠ​ዊያ ላይ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር በሰማ ጊዜ፥ ንጉሡ፥ “ያዙት” ብሎ እጁን ከመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ አነሣ። ከዚ​ህም በኋላ በእ​ርሱ ላይ የዘ​ረ​ጋት እጁ ደረ​ቀች፤ ወደ እር​ሱም ይመ​ል​ሳት ዘንድ አል​ተ​ቻ​ለ​ውም።</verse>
				<verse number="5">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ሰጠው ምል​ክት መሠ​ዊ​ያው ተሰ​ነ​ጠቀ፤ በው​ስ​ጡም ያለው ስብ ፈሰሰ።</verse>
				<verse number="6">ንጉ​ሡም ኢዮ​ር​ብ​ዓም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው፥ “አሁን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፊት ለምን፤ እጄም ወደ እኔ ትመ​ለስ ዘንድ ስለ እኔ ጸልይ” አለው፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመነ፤ የን​ጉ​ሡም እጅ ወደ እርሱ ተመ​ለ​ሰች። እንደ ቀድ​ሞም ሆነች።</verse>
				<verse number="7">ንጉ​ሡም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው፥ “ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ና፥ ምሳም ብላ፥ ስጦ​ታም እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="8">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው ንጉ​ሡን፥ “የቤ​ት​ህን እኩ​ሌታ እን​ኳን ብት​ሰ​ጠኝ ከአ​ንተ ጋር አል​ገ​ባም፤ በዚ​ህም ስፍራ እን​ጀ​ራን አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም፤</verse>
				<verse number="9">እን​ጀ​ራም አት​ብላ፤ ውኃም አት​ጠጣ፤ በመ​ጣ​ህ​በት መን​ገ​ድም አት​መ​ለስ ሲል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቃሉ አዝ​ዞ​ኛ​ልና” አለው።</verse>
				<verse number="10">በሌ​ላም መን​ገድ ሄደ፤ ወደ ቤቴ​ልም በመ​ጣ​በት መን​ገድ አል​ተ​መ​ለ​ሰም።</verse>
				<verse number="11">በቤ​ቴ​ልም አንድ ሽማ​ግሌ ነቢይ ይኖር ነበር፤ ልጆ​ቹም ወደ እርሱ መጥ​ተው በዚ​ያች ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በቤ​ቴል ያደ​ረ​ገ​ውን ሥራ ሁሉ ነገ​ሩት፤ ደግ​ሞም ለን​ጉሡ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ሁሉ ለአ​ባ​ታ​ቸው ነገ​ሩት፤ አባ​ታ​ቸ​ውም ተቈ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">አባ​ታ​ቸ​ውም፥ “በየ​ት​ኛው መን​ገድ ሄደ?” አላ​ቸው። ልጆ​ቹም ከይ​ሁዳ የመ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው የሄ​ደ​በ​ትን መን​ገድ አመ​ለ​ከ​ቱት።</verse>
				<verse number="13">ልጆ​ቹ​ንም፥ “አህ​ያ​ዬን ጫኑ​ልኝ” አላ​ቸው፥ አህ​ያ​ው​ንም ጫኑ​ለት ተቀ​መ​ጠ​በ​ትም።</verse>
				<verse number="14">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሰው ተከ​ት​ሎት ሄደ፤ ከዛፍ በታ​ችም ተቀ​ምጦ አገ​ኘ​ውና፥ “ከይ​ሁዳ የመ​ጣህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው አንተ ነህን?” አለው። እር​ሱም፥ “አዎ፥ እኔ ነኝ” አለ።</verse>
				<verse number="15">እር​ሱም፥ “ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ና፥ እን​ጀ​ራም ብላ” አለው።</verse>
				<verse number="16">እር​ሱም፥ “ከአ​ንተ ጋር እመ​ለ​ስና እገባ ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ኝም፤ በዚ​ህም ስፍራ ከአ​ንተ ጋር እን​ጀራ አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም፤</verse>
				<verse number="17">በዚያ እን​ጀራ አት​ብላ፥ ውኃም አት​ጠጣ፤ በመ​ጣ​ህ​በት መን​ገ​ድም አት​መ​ለስ ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቃሉ አዝ​ዞ​ኛ​ልና” አለው።</verse>
				<verse number="18">እር​ሱም፥ “እኔ ደግሞ እን​ዳ​ንተ ነቢይ ነኝ፤ መል​አ​ክም፦ እን​ጀራ ይበላ ዘንድ ውኃም ይጠጣ ዘንድ ከአ​ንተ ጋር ወደ ቤትህ መል​ሰው ብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ተና​ገ​ረኝ” አለው። ዋሽ​ቶም ተና​ገ​ረው።</verse>
				<verse number="19">መለ​ሰ​ውም፥ በቤ​ቱም እን​ጀራ በላ፤ ውኃም ጠጣ።</verse>
				<verse number="20">በማ​ዕ​ድም ተቀ​ም​ጠው ሳሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ መለ​ሰው ነቢይ መጣ፤</verse>
				<verse number="21">ከይ​ሁ​ዳም የመ​ጣ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው እን​ዲህ አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ላይ አም​ፀ​ሃ​ልና፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዘ​ዘ​ህን ትእ​ዛዝ አል​ጠ​በ​ቅ​ህ​ምና፥</verse>
				<verse number="22">ተመ​ል​ሰ​ህም፦ እን​ጀራ አት​ብላ፥ ውኃም አት​ጠጣ ባለህ ስፍራ እን​ጀራ በል​ተ​ሃ​ልና፥ ውኃም ጠጥ​ተ​ሃ​ልና ሬሳህ ወደ አባ​ቶ​ችህ መቃ​ብር አይ​ገ​ባም።”</verse>
				<verse number="23">እን​ጀ​ራም ከበላ፥ ውኃም ከጠጣ በኋላ ለተ​መ​ለ​ሰው ነቢይ አህ​ያ​ውን ጫኑ​ለት።</verse>
				<verse number="24">ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ በመ​ን​ገ​ዱም ላይ አን​በሳ አግ​ኝቶ ገደ​ለው፤ ሬሳ​ውም በመ​ን​ገድ ላይ ተጋ​ድሞ ነበር፤ አህ​ያ​ውም በእ​ርሱ አጠ​ገብ ቆሞ ነበር፤ አን​በ​ሳ​ውም ደግሞ በሬ​ሳው አጠ​ገብ ቆሞ ነበር።</verse>
				<verse number="25">እነ​ሆም፥ መን​ገድ አላፊ ሰዎች ሬሳ​ውን በመ​ን​ገዱ ወድቆ፥ አን​በ​ሳ​ውም በሬ​ሳው አጠ​ገብ ቆሞ አዩ፤ ገብ​ተ​ውም ሽማ​ግ​ሌው ነቢይ ይኖ​ር​በት በነ​በ​ረው ከተማ አወሩ።</verse>
				<verse number="26">ያም ከመ​ን​ገድ የመ​ለ​ሰው ነቢይ ያን ሰምቶ፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ላይ ያመፀ ያ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ነው” አለ።</verse>
				<verse number="27">ልጆ​ቹ​ንም፥ “አህ​ያ​ዬን ጫኑ​ልኝ” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ጫኑ​ለት።</verse>
				<verse number="28">ሄዶም፥ ሬሳው በመ​ን​ገድ ወድቆ፥ በሬ​ሳ​ውም አጠ​ገብ አህ​ያ​ውና አን​በ​ሳው ቆመው፥ አን​በ​ሳ​ውም ሬሳ​ውን ሳይ​በ​ላው፥ አህ​ያ​ው​ንም ሳይ​ሰ​ብ​ረው አገኘ።</verse>
				<verse number="29">ነቢ​ዩም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው ሬሳ አነሣ፤ በአ​ህ​ያ​ውም ላይ ጫነው፤ ነቢ​ዩም በራሱ መቃ​ብር ይቀ​ብ​ረው ዘንድ ወደ ገዛ ከተ​ማው አመ​ጣው፤</verse>
				<verse number="30">ዋይ ዋይ፥ ወን​ድሜ ሆይ፥ እያ​ሉም አለ​ቀ​ሱ​ለት።</verse>
				<verse number="31">ከቀ​በ​ሩ​ትም በኋላ ልጆ​ቹን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፥ “በሞ​ትሁ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በተ​ቀ​በ​ረ​በት መቃ​ብር ቅበ​ሩኝ፤ አጥ​ን​ቶቼ ከአ​ጥ​ን​ቶቹ ጋር ይድኑ ዘንድ አጥ​ን​ቶቼን በአ​ጥ​ን​ቶቹ አጠ​ገብ አኑሩ፤</verse>
				<verse number="32">በቤ​ቴል ባለው መሠ​ዊያ ላይ፥ በሰ​ማ​ር​ያም ከተ​ሞች ውስጥ ባሉት በኮ​ረ​ብ​ታ​ዎቹ መስ​ገ​ጃ​ዎች ላይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል የተ​ና​ገ​ረው ነገር በእ​ው​ነት ይደ​ር​ሳ​ልና።”</verse>
				<verse number="33">ከዚ​ህም በኋላ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ከክ​ፋቱ አል​ተ​መ​ለ​ሰም፤ ነገር ግን ለኮ​ረ​ብ​ታ​ዎቹ መስ​ገ​ጃ​ዎች አብ​ልጦ ከሕ​ዝብ ሁሉ የጣ​ዖት ካህ​ና​ትን ሾመ፤ የሚ​ወ​ድ​ደ​ው​ንም ሁሉ ይቀ​ድስ ነበር፤ እር​ሱም ለኮ​ረ​ብ​ቶቹ መስ​ገ​ጃ​ዎች ካህን ይሆን ነበር።</verse>
				<verse number="34">ይህም ነገር ከገጸ ምድር ለመ​ፍ​ረ​ስና ለመ​ጥ​ፋት በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት ላይ ኀጢ​አት ሆነ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">በዚ​ያም ወራት የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ልጅ አብያ እጅግ ታመመ።</verse>
				<verse number="2">ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስቱ ሐኖ​ንን፥ “ተነሺ፥ ራስ​ሽን ለውጪ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስት እንደ ሆንሽ ማንም አይ​ወቅ፤ ወደ ሴሎም ሂጂ፤ ስለ​ዚ​ህም ሕፃን ከደ​ዌው ይድን እን​ደ​ሆነ ጠይቂ፤ እነሆ፥ በዚህ ሕዝብ ላይ እን​ደ​ም​ነ​ግሥ የነ​ገ​ረኝ ነቢዩ አኪያ በዚያ አለ።</verse>
				<verse number="3">በእ​ጅ​ሽም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ዐሥር እን​ጀ​ራና የወ​ይን እሸት አን​ድም ማሠሮ ማር ይዘሽ ወደ እርሱ ሂጂ፤ በል​ጁም የሚ​ሆ​ነ​ውን ይነ​ግ​ር​ሻል” አላት።</verse>
				<verse number="4">የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስት እን​ዲሁ አደ​ረ​ገች፤ ተነ​ሥ​ታም እን​ጀራ፥ የወ​ይን ዘለ​ላና አንድ ማሠሮ ማር በመ​ያዝ ወደ ሴሎ ሄደች፤ ወደ አኪ​ያም ቤት ገባች። አኪያ ግን ስለ መሸ​ም​ገሉ ዐይ​ኖቹ ፈዝ​ዘው ነበ​ርና ማየት አል​ቻ​ለም።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አኪ​ያን፥ “እነሆ፥ ስለ ታመ​መው ልጅዋ ትጠ​ይ​ቅህ ዘንድ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ሚስት ትመ​ጣ​ለች፤ ራስ​ዋ​ንም ለውጣ ወደ አንተ በገ​ባች ጊዜ እን​ዲ​ህና እን​ዲህ በላት” አለው።</verse>
				<verse number="6">እር​ስ​ዋም በደጅ ስት​ገባ አኪያ የእ​ግ​ር​ዋን ኮቴ ሰማ፤ እን​ዲ​ህም አላት፥ “የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ሚስት ሆይ፥ ግቢ! ስለ​ም​ንስ ራስ​ሽን ለወ​ጥሽ? እኔም የሚ​ያ​ስ​ጨ​ንቅ ወሬ ይዤ ወደ አንቺ ተል​ኬ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">ሂጂ ለኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም እን​ዲህ በዪው፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከሕ​ዝብ መካ​ከል ለይቼ ከፍ አድ​ር​ጌህ ነበር፤ በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይም ንጉሥ አድ​ር​ጌህ ነበር።</verse>
				<verse number="8">ከዳ​ዊ​ትም ቤት፤ መን​ግ​ሥ​ቱን ከፍዬ ሰጥ​ቼህ ነበር፤ ነገር ግን በፍ​ጹም ልቡ እንደ ተከ​ተ​ለኝ፥ በፊ​ቴም ቅን ነገር ብቻ እን​ዳ​ደ​ረገ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም እንደ ጠበቀ እንደ ባሪ​ያዬ እንደ ዳዊት አል​ሆ​ን​ህም።</verse>
				<verse number="9">ከአ​ን​ተም አስ​ቀ​ድ​መው ከነ​በ​ሩት ሁሉ ይልቅ ክፉ ሠራህ፤ ታስ​ቈ​ጣ​ኝም ዘንድ ሄደህ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክ​ትና ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ትን ምስ​ሎች አደ​ረ​ግህ፤ ወደ ኋላ​ህም ተው​ኸኝ።</verse>
				<verse number="10">ስለ​ዚህ እነሆ፥ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት ላይ መከ​ራን አመ​ጣ​ለሁ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ም​ንም አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ፤ አጥር ተጠ​ግቶ እስ​ከ​ሚ​ሸን ወንድ ድረስ አላ​ስ​ቀ​ር​ለ​ትም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ይነ​ግሥ ዘንድ አል​ተ​ወ​ውም፤ ሰው ገለባ እስ​ኪ​ያ​ልቅ ድረስ እን​ደ​ሚ​ያ​ነ​ድድ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት ላይ እሳ​ትን አነ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ወገን በከ​ተ​ማ​ዪቱ ውስጥ የሞ​ተ​ውን ውሾች ይበ​ሉ​ታል፤ በሜ​ዳ​ውም የሞ​ተ​ውን የሰ​ማይ ወፎች ይበ​ሉ​ታል።</verse>
				<verse number="12">እን​ግ​ዲህ ተነ​ሥ​ተሽ ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ እግ​ር​ሽም ወደ ከተማ በገባ ጊዜ ልጅሽ ይሞ​ታል።</verse>
				<verse number="13">ደን​ገ​ጡ​ሮ​ች​ሽም ሊቀ​በ​ሉሽ ይወ​ጣሉ፤ ልጅ​ሽም ሞተ ይሉ​ሻል፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ያለ​ቅ​ሱ​ለ​ታል፤ ይቀ​ብ​ሩ​ት​ማል፤ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት በዚህ ልጅ መል​ካም ነገር ተገ​ኝ​ቶ​በ​ታ​ልና ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም እርሱ ብቻ ይቀ​በ​ራል።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደግሞ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምን ቤት የሚ​ያ​ጠፋ ንጉሥ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ያነ​ግ​ሣል፤ እር​ሱም ዛሬ ይደ​ረ​ጋል፤ እን​ግ​ዲህ ወዲህ ምን እና​ገ​ራ​ለሁ?</verse>
				<verse number="15">በዚያ ጊዜም ሸም​በቆ በውኃ ውስጥ እን​ደ​ሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ እስ​ራ​ኤ​ልን ይመ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያስ​ቈጡ ዘንድ የማ​ም​ለ​ኪያ አፀድ ተክ​ለ​ዋ​ልና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ከሰ​ጣ​ቸው ከዚች ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር እስ​ራ​ኤ​ልን ይነ​ቅ​ላል፤ በወ​ን​ዙም ማዶ ይበ​ት​ና​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="16">ስለ በደ​ለ​ውና እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ስላ​ሳ​ተ​በት ስለ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት እስ​ራ​ኤ​ልን ይጥ​ላል።”</verse>
				<verse number="17">የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስት ተነ​ሥታ ሄደች፤ ወደ ቴር​ሳም መጣች፤ ወደ ቤቱም መድ​ረክ በገ​ባች ጊዜ ልጁ ሞተ።</verse>
				<verse number="18">በባ​ሪ​ያ​ውም በነ​ቢዩ በአ​ኪያ እንደ ተነ​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እስ​ራ​ኤል ሁሉ ቀበ​ሩት፥ አለ​ቀ​ሱ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="19">የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ነገር፥ እን​ዴት እንደ ተዋጋ፥ እን​ዴ​ትም እንደ ነገሠ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።</verse>
				<verse number="20">ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም የነ​ገ​ሠ​በት ዘመን ሃያ አራት ዓመት ነበረ፥ ከአ​ባ​ቶ​ቹም ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ ልጁም ናባጥ በፋ​ን​ታው ነገሠ።</verse>
				<verse number="21">የሰ​ሎ​ሞ​ንም ልጅ ሮብ​ዓም በይ​ሁዳ ነገሠ፤ ሮብ​ዓ​ምም ንጉሥ በሆነ ጊዜ የአ​ርባ አንድ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስሙን ያኖ​ር​ባት ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ በመ​ረ​ጣት ከተማ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዐሥራ ሰባት ዓመት ነገሠ፤ የእ​ና​ቱም ስም ናዕማ ነበረ፥ እር​ስ​ዋም አሞ​ና​ዊት ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="22">ሮብ​ዓ​ምም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ሠራ፤ አባ​ቶቹ በሠ​ሩት ኀጢ​አ​ትና በደል ሁሉ እንደ አስ​ቀ​ኑት በሠ​ራው ኀጢ​አት አስ​ቀ​ናው።</verse>
				<verse number="23">እነ​ር​ሱም ደግሞ ከፍ ባለው ኮረ​ብታ ሁሉ ላይ፥ ቅጠ​ሉም ከለ​መ​ለመ ዛፍ ሁሉ በታች መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን ሠሩ፤ ሐው​ል​ቶ​ች​ንና የማ​ም​ለ​ኪያ አፀ​ዶ​ች​ንም ለራ​ሳ​ቸው አቆሙ።</verse>
				<verse number="24">በም​ድ​ርም ሁሉ ዐመፅ ነበረ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሳ​ደ​ዳ​ቸው የአ​ሕ​ዛ​ብን ርኵ​ሰት ሁሉ ያደ​ርጉ ነበር።</verse>
				<verse number="25">ሮብ​ዓ​ምም በነ​ገሠ በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ዓመት የግ​ብፅ ንጉሥ ሱስ​ቀም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ዘመተ።</verse>
				<verse number="26">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ መዛ​ግ​ብ​ትና የን​ጉ​ሡን ቤተ መዛ​ግ​ብት ሁሉ ወሰደ፤ ዳዊ​ትም ከሱባ ንጉሥ ከአ​ድ​ር​ዓ​ዛር ልጆች እጅ ወስዶ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ጣ​ቸ​ውን የወ​ርቅ ጦሮ​ችና ሰሎ​ሞን የሠ​ራ​ቸ​ውን የወ​ር​ቁን ጋሻና ጦር ሁሉ ወደ ግብፅ ወሰደ።</verse>
				<verse number="27">ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም በፋ​ን​ታው የናስ ጋሾ​ችን ሠራ፤ በፊ​ቱም ለሚ​ሮ​ጡና የን​ጉ​ሥን ቤት ደጅ ለሚ​ጠ​ብቁ የዘ​በ​ኞች አለ​ቆች ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="28">ከዚህ በኋላ ንጉሡ ዘወ​ትር ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሲገባ ዘበ​ኞች ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸው ነበር፤ መል​ሰ​ውም በዘ​በ​ኞች ቤት ውስጥ ያኖ​ሩ​አ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="29">የቀ​ረ​ውም የሮ​ብ​ዓም ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ታሪክ መጽ​ሐፍ እነሆ፥ ተጽ​ፎ​አል።</verse>
				<verse number="30">በዘ​መ​ኑም ሁሉ በሮ​ብ​ዓ​ምና በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም መካ​ከል ጦር​ነት ነበረ።</verse>
				<verse number="31">ሮብ​ዓ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ። ልጁም አብያ በፋ​ን​ታው ነገሠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">የና​ባጥ ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም በነ​ገሠ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመት የሮ​ብ​ዓም ልጅ አብያ በይ​ሁዳ ላይ ንጉሥ ሆነ።</verse>
				<verse number="2">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሦስት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም መዓካ የተ​ባ​ለች የአ​ቤ​ሴ​ሎም ልጅ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="3">ከእ​ር​ሱም አስ​ቀ​ድሞ ባደ​ረ​ገው በአ​ባቱ ኀጢ​አት ሁሉ ሄደ፤ ልቡም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ ከአ​ም​ላኩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ፍጹም አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን ልጁን ከእ​ርሱ በኋላ ያስ​ነሣ ዘንድ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ያጸና ዘንድ አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ዳዊት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መብ​ራ​ትን አደ​ረ​ገ​ለት፤</verse>
				<verse number="5">ከኬ​ጥ​ያ​ዊው ከኦ​ርዮ ነገር በቀር ዳዊት በዘ​መኑ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አድ​ርጎ ነበ​ርና፥ ካዘ​ዘ​ውም ነገር ሁሉ ፈቀቅ አላ​ለም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="6">በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምና በሮ​ብ​ዓም መካ​ከል በዘ​መ​ና​ቸው ሁሉ ጠብ ነበረ።</verse>
				<verse number="7">የቀ​ረ​ውም የአ​ብያ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ታሪክ መጽ​ሐፍ እነሆ፥ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን? በአ​ብ​ያና በኢ​ዮ​ር​ብ​አም መካ​ከል ሰልፍ ነበረ።</verse>
				<verse number="8">ኢዮ​ር​ብ​ዓም በነ​ገሠ በሃያ አራ​ተኛ ዓመቱ አብያ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት። ልጁም አሳ በፋ​ን​ታው ነገሠ።</verse>
				<verse number="9">በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም በሃያ አራ​ተ​ኛው ዓመት አሳ በይ​ሁዳ ላይ ነገሠ።</verse>
				<verse number="10">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አርባ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ሐና የተ​ባ​ለች የአ​ቤ​ሴ​ሎም ልጅ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="11">አሳም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="12">ከሀ​ገ​ሩም የጣ​ዖ​ታ​ትን ምስል ሁሉ አስ​ወ​ገደ፥ አባ​ቶ​ቹም የሠ​ሩ​አ​ቸ​ውን ጣዖ​ታ​ትን ሁሉ አጠፋ።</verse>
				<verse number="13">የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ ጣዖ​ታ​ትን ስለ ሠራች እና​ቱን ሐናን እቴጌ እን​ዳ​ት​ሆን ሻራት፤ አሳም የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዱን አስ​ቈ​ረ​ጠው፥ በቄ​ድ​ሮ​ንም ፈፋ አጠ​ገብ በእ​ሳት አቃ​ጠ​ለው።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ቶች ላይ ያሉ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎች አላ​ራ​ቀም፤ የአሳ ልብ ግን በዘ​መኑ ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ፍጹም ነበረ።</verse>
				<verse number="15">አባቱ የቀ​ደ​ሰ​ው​ንና እር​ሱም የቀ​ደ​ሰ​ውን ወር​ቅና ብር፥ ዕቃ​ው​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አገ​ባው።</verse>
				<verse number="16">አሳና የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ባኦስ በዘ​መ​ና​ቸው ሁሉ ሲዋጉ ኖሩ።</verse>
				<verse number="17">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ባኦስ በይ​ሁዳ ላይ ወጣ፤ ከይ​ሁዳ ንጉሥ ከአሳ ዘንድ ማንም እን​ዳ​ይ​ወጣ ወደ እር​ሱም ማንም እን​ዳ​ይ​ገባ አድ​ርጎ ራማን ሠራት።</verse>
				<verse number="18">አሳም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና በን​ጉሥ ቤተ መዛ​ግ​ብት የተ​ገ​ኘ​ውን ብርና ወርቅ ሁሉ ወስዶ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ሰጣ​ቸው፤ ንጉ​ሡም አሳ በደ​ማ​ስቆ ለተ​ቀ​መ​ጠው ለአ​ዚን ልጅ ለጤ​ቤ​ር​ማን ልጅ ለሶ​ርያ ንጉሥ ለወ​ልደ አዴር፥</verse>
				<verse number="19">“በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል በአ​ባ​ቴና በአ​ባ​ትህ መካ​ከል ቃል ኪዳን ጸን​ቶ​አል፤ እነሆ፥ ብርና ወርቅ ገጸ በረ​ከት ልኬ​ል​ሃ​ለሁ፤ እርሱ ከእኔ ዘንድ እን​ዲ​ርቅ ሄደህ ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ከባ​ኦስ ጋር ያለ​ህን ቃል ኪዳን አፍ​ርስ” ብሎ ላከ።</verse>
				<verse number="20">ወልደ አዴ​ርም ለን​ጉሡ ለአሳ እሺ አለው፤ የሠ​ራ​ዊ​ቱ​ንም አለ​ቆች በእ​ስ​ራ​ኤል ከተ​ሞች ላይ ሰድዶ ኢና​ን​ንና ዳንን፥ አቤ​ል​ቤ​ት​መ​ዓ​ካ​ንና ኬኔሬ​ትን ሁሉ የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ሀገር ሁሉ መታ።</verse>
				<verse number="21">ባኦ​ስም ያን በሰማ ጊዜ ራማን መሥ​ራት ትቶ ወደ ቴርሳ ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="22">ንጉ​ሡም አሳ በይ​ሁዳ ሁሉ ላይ አዋጅ ነገረ፤ ማንም ነጻ አል​ነ​በ​ረም፥ ንጉሡ ባኦ​ስም የሠ​ራ​በ​ትን የራ​ማን ድን​ጋ​ይና እን​ጨት ወሰደ፤ የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ አሳ የብ​ን​ያ​ም​ንና የመ​ሴ​ፋን ኮረ​ብታ ሠራ​በት።</verse>
				<verse number="23">የቀ​ረ​ውም የአሳ ነገር ሁሉ ብርቱ ሥራ​ዎ​ቹም ሁሉ፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥት ታሪክ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን? ነገር ግን በሸ​መ​ገለ ጊዜ እግ​ሮቹ ታመሙ።</verse>
				<verse number="24">አሳም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ። ልጁም ኢዮ​ሣ​ፍጥ በፋ​ን​ታው ነገሠ።</verse>
				<verse number="25">በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በአሳ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ልጅ ናባጥ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ነገሠ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ሁለት ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="26">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ፤ በአ​ባ​ቱም መን​ገድ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ባሳ​ተ​በት ኀጢ​አት ሄደ።</verse>
				<verse number="27">ከበ​ለ​ዓን ቤት የሆነ የአ​ኪያ ልጅ ባኦስ ዐመ​ፀ​በት፤ ናባ​ጥና እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ገባ​ቶ​ንን ከብ​በው ነበ​ርና ባኦስ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ልም ሀገር ባለው በገ​ባ​ቶን ገደ​ለው።</verse>
				<verse number="28">በይ​ሁዳ ንጉሥ በአሳ በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት ባኦስ ናባ​ጥን ገደ​ለው፥ በፋ​ን​ታ​ውም ነገሠ።</verse>
				<verse number="29">ከነ​ገ​ሠም በኋላ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምን ወገን ሁሉ አጠፋ፥ በባ​ሪ​ያው በሴ​ሎ​ና​ዊው በአ​ኪያ እጅ እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋው ድረስ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ወገን ሕይ​ወት ያለ​ውን አላ​ስ​ቀ​ረም።</verse>
				<verse number="30">ይኸ​ውም ኢዮ​ር​ብ​ዓም ስለ ሠራው ኀጢ​አት፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ስላ​ሳ​ተ​በት፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስላ​ስ​ቈ​ጣ​በት ማስ​ቈ​ጣት ነው።</verse>
				<verse number="31">የቀ​ረ​ውም የና​ባጥ ነገ​ርና ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="32">በአ​ሳና በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በባ​ኦስ መካ​ከል በዘ​መ​ና​ቸው ሁሉ ጦር​ነት ነበረ።</verse>
				<verse number="33">በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በአሳ በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት የአ​ኪያ ልጅ ባኦስ በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ በቴ​ርሣ ንጉሥ ሆኖ ሃያ አራት ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="34">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ፥ በና​ባ​ጥም ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም መን​ገድ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ባሳ​ተ​በት ኀጢ​አት ሄደ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ስለ ባኦስ እን​ዲህ ብሎ ወደ አናኒ ልጅ ወደ ኢዩ መጣ።</verse>
				<verse number="2">“እኔ ከመ​ሬት አን​ሥቼ በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ አንተ ግን በከ​ንቱ ጣዖ​ታ​ቸው ያስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን በአ​ሳ​ታ​ቸው በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም መን​ገድ ሄድህ፤</verse>
				<verse number="3">ስለ​ዚ​ህም፥ እነሆ፥ ባኦ​ስ​ንና ቤቱን ፈጽሜ አጠ​ፋ​ለሁ፤ ቤት​ህ​ንም እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ቤት አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">ከባ​ኦ​ስም ወገን በከ​ተ​ማ​ዪቱ ውስጥ የሚ​ሞ​ተ​ውን ውሾች ይበ​ሉ​ታል፤ በሜ​ዳ​ውም የሚ​ሞ​ተ​ውን የሰ​ማይ ወፎች ይበ​ሉ​ታል።”</verse>
				<verse number="5">የቀ​ረ​ውም የባ​ኦስ ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሁሉ፥ ኀይ​ሉም ሁሉ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ ነው።</verse>
				<verse number="6">ባኦ​ስም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በቴ​ር​ሳም ተቀ​በረ፤ ልጁም ኤላ በአሳ በሃያ ስድ​ስ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በፋ​ን​ታው ነገሠ።</verse>
				<verse number="7">በእ​ጁም ሥራ ያስ​ቈ​ጣው ዘንድ፥ እንደ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ቤት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስላ​ደ​ረ​ገው ክፋት ሁሉ እር​ሱ​ንም ስለ ገደ​ለው፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በባ​ኦ​ስና በቤቱ ላይ ወደ አናኒ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢዩ መጣ።</verse>
				<verse number="8">የባ​ኦ​ስም ልጅ ኤላ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በቴ​ርሳ ሁለት ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="9">የእ​ኩ​ሌ​ቶቹ ፈረ​ሶች አለቃ ዘም​ሪም አሽ​ከ​ሮ​ቹን ሁሉ ሰብ​ስቦ ዐመፀ፤ ኤላም በቴ​ርሳ ነበረ፤ በቴ​ር​ሳም በነ​በ​ረው በመ​ጋ​ቢው በአሳ ቤት ይሰ​ክር ነበር።</verse>
				<verse number="10">በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በአሳ በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት ዘምሪ ገብቶ ወጋና ገደ​ለው፤ በፋ​ን​ታ​ውም ነገሠ።</verse>
				<verse number="11">ከነ​ገ​ሠና በዙ​ፋ​ኑም ከተ​ቀ​መጠ በኋላ፥ የባ​ኦ​ስን ቤት ሁሉ አጠፋ፤ አንድ ወንድ እንኳ አላ​ስ​ቀ​ረ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="12">በነ​ቢዩ በኢዩ አፍ በባ​ኦስ ቤት ላይ እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥</verse>
				<verse number="13">ባኦ​ስና ልጁ ኤላ ስለ ሠሩት ኀጢ​አት ሁሉ፥ በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸው የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያስ​ቈ​ጡት ዘንድ እስ​ራ​ኤ​ልን ስለ አሳ​ቱ​በት ኀጢ​አት፥ ዘምሪ የባ​ኦ​ስን ቤት ሁሉ እን​ዲሁ አጠፋ።</verse>
				<verse number="14">የቀ​ረ​ውም የኤላ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ ነው።</verse>
				<verse number="15">በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በአሳ በሃያ ዘጠ​ነ​ኛው ዓመት ዘምሪ በቴ​ርሳ ሰባት ቀን ነገሠ። የእ​ስ​ራ​ኤል ሠራ​ዊት ግን በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሀገር በገ​ባ​ቶን ሰፍ​ረው ነበር።</verse>
				<verse number="16">በሰ​ፈር ያሉ ሕዝ​ቡም “ዘምሪ ከድቶ ኤላን ገደ​ለው፥ በፋ​ን​ታ​ውም ነገሠ” ሲሉ ሰሙ። እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በዚያ ቀን በሰ​ፈሩ ውስጥ የሠ​ራ​ዊ​ቱን አለቃ ዘን​በ​ሪን አነ​ገሡ።</verse>
				<verse number="17">ዘን​በ​ሪም ከእ​ርሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከገ​ባ​ቶን ወጥ​ተው ቴር​ሳን ከበቡ። በእ​ር​ስ​ዋም ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="18">ዘም​ሪም ከተ​ማ​ዪቱ እንደ ተያ​ዘች ባየ ጊዜ ወደ ንጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ገባ፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤት በራሱ ላይ በእ​ሳት አቃ​ጠለ፤ ሞተም።</verse>
				<verse number="19">ስላ​ደ​ረ​ገ​ውም ኀጢ​አት፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ስላ​ሳ​ተ​በት ኀጢ​አት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አድ​ር​ጎ​አ​ልና፥ በና​ባጥ ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም መን​ገድ ሄዶ​አ​ልና ሞተ።</verse>
				<verse number="20">የቀ​ረ​ውም የዘ​ምሪ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ዐመፅ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ ነው።</verse>
				<verse number="21">በዚ​ያም ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ በሁ​ለት ተከ​ፈለ፤ የሕ​ዝ​ቡም እኩ​ሌታ የጎ​ና​ትን ልጅ ታም​ኒን ያነ​ግ​ሡት ዘንድ ተከ​ተ​ሉት፤ እኩ​ሌ​ቶ​ችም ዘን​በ​ሪን ተከ​ተሉ።</verse>
				<verse number="22">ዘን​በ​ሪ​ንም የተ​ከ​ተሉ ሕዝብ የጎ​ናት ልጅ ታምኒን የተ​ከ​ተ​ሉ​ትን ሕዝብ ድል አደ​ረ​ጉ​አ​ቸው፤ ታም​ኒም ሞተ፤ ወን​ድ​ሙም ኢዮ​ራም በዚ​ያው ዘመን ሞተ፤ ከታ​ምኒ በኋላ ዘን​በሪ ነገሠ።</verse>
				<verse number="23">በይ​ሁዳ ንጉሥ በአሳ በሠ​ላሳ አን​ደ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት ዘን​በሪ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ዐሥራ ሁለት ዓመት ነገሠ። በቴ​ር​ሳም ስድ​ስት ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="24">ዘን​በ​ሪም ከዚ​ያች ተራራ ባለ​ቤት ከሴ​ሜር በሁ​ለት መክ​ሊት ብር የሳ​ም​ሮ​ንን ተራራ ገዛ፤ በተ​ራ​ራ​ውም ላይ ከተማ ሠራ፤ የሠ​ራ​ት​ንም ከተማ በተ​ራ​ራው ባለ​ቤት በሳ​ምር ስም ሰማ​ርያ ብሎ ጠራት።</verse>
				<verse number="25">ዘን​በ​ሪም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ፤ ከእ​ር​ሱም አስ​ቀ​ድሞ ከነ​በ​ሩት ይልቅ እጅግ ከፋ።</verse>
				<verse number="26">በና​ባ​ጥም ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም መን​ገድ ሁሉ በር​ኩ​ስ​ነ​ታ​ቸው የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያስ​ቈ​ጡት ዘንድ እስ​ራ​ኤ​ልን ባሳ​ተ​በት ኀጢ​አት ሄደ።</verse>
				<verse number="27">የቀ​ረ​ውም ዘን​በሪ ያደ​ረ​ገው ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ጭከና፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ ነው።</verse>
				<verse number="28">ዘን​በ​ሪም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በሰ​ማ​ር​ያም ቀበ​ሩት፤ ልጁም አክ​አብ በፋ​ን​ታው ነገሠ። ‘ሀ’ ዘን​በ​ሪም ዐሥራ አንድ ዓመት ሲሆ​ነው የአሳ ልጅ ኢዮ​ሳ​ፍጥ ነገሠ። በነ​ገ​ሠም ጊዜ ሠላሳ አም​ስት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሃያ አም​ስት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ጋዙባ የም​ት​ባል የሴ​ላህ ልጅ ነበ​ረች። ‘ለ’ በአ​ባ​ቱም በአሳ መን​ገድ ሄደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ጽድ​ቅን ያደ​ርግ ዘንድ ከእ​ር​ስዋ ፈቀቅ አላ​ለም። በተ​ራ​ሮች የነ​በ​ሩ​ት​ንም አማ​ል​ክት አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ ሕዝ​ቡም በተ​ራ​ሮቹ ይሠ​ዉ​ላ​ቸ​ውና ያጥ​ኑ​ላ​ቸው ነበረ። ‘ሐ’ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ጋር የሠ​ራው፥ የተ​ዋ​ጋ​ውና ያደ​ረ​ገው ኀይል ሁሉ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ ነው። ‘መ’ በአ​ባ​ቱም በአሳ ዘመን የነ​በ​ረ​ውን ርኵ​ሰት ሁሉ ከም​ድር አስ​ወ​ገደ። በኤ​ዶ​ምም ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም። ‘ሠ’ ንጉሥ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም ወር​ቅና ብርን ሊያ​መ​ጡ​ለት ወደ አፌር ይልክ ዘንድ በተ​ር​ሴስ መር​ከብ አሠራ፤ በጋ​ስ​ዮንጋቤር የነ​በ​ረ​ችው መር​ከብ ተሰ​ብ​ራ​ለ​ችና አል​ሄ​ደ​ችም። ‘ረ’ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አካ​ዝ​ያስ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥን፥ “አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህ​ንና አገ​ል​ጋ​ዮቼን በመ​ር​ከብ እን​ላክ” አለው። ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም እንቢ አለ። ‘ሰ’ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ። በዳ​ዊ​ትም ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ። በእ​ር​ሱም ፋንታ ልጁ ኢዮ​ራም ነገሠ።</verse>
				<verse number="29">በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት የዘ​ን​በሪ ልጅ አክ​ዓብ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ ሃያ ሁለት ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="30">አክ​ዓ​ብም ከእ​ርሱ በፊት ከነ​በ​ሩት ሁሉ ይልቅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="31">በና​ባ​ጥም ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት መሄድ አል​በ​ቃ​ውም፤ የሲ​ዶ​ና​ው​ያ​ን​ንም ንጉሥ የኤ​ያ​ት​ባ​ሔ​ልን ልጅ ኤል​ዛ​ቤ​ልን አገባ፤ ሄዶም በዓ​ልን አመ​ለከ ሰገ​ደ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="32">በሰ​ማ​ር​ያም በሠ​ራው በበ​ዓል ቤት ውስጥ ለበ​ዓል መሠ​ዊ​ያን ሠራ።</verse>
				<verse number="33">አክ​ዓ​ብም የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ድን አሠራ፤ አክ​ዓ​ብም ሰው​ነቱ እን​ድ​ት​ጠፋ ከእ​ርሱ በፊት ከነ​በ​ሩት ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ይልቅ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​ስ​ቈ​ጣ​ውን ነገር አበዛ።</verse>
				<verse number="34">በእ​ር​ሱም ዘመን የቤ​ቴል ሰው አኪ​ያል ኢያ​ሪ​ኮን ሠራ፤ በነ​ዌም ልጅ በኢ​ያሱ ቃል እንደ ተነ​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ በበ​ኵር ልጁ በአ​ቢ​ሮን መሠ​ረ​ቷን አደ​ረገ፥ በታ​ናሹ ልጁም በዜ​ጉብ በሮ​ች​ዋን አቆመ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">በገ​ለ​ዓድ ቴስ​ባን የነ​በ​ረው ቴስ​ብ​ያ​ዊው ነቢዩ ኤል​ያስ አክ​ዓ​ብን፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት የኀ​ያ​ላን አም​ላክ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ከአፌ ቃል በቀር በእ​ነ​ዚህ ዓመ​ታት ዝና​ብም ጠልም አይ​ወ​ር​ድም” አለው።</verse>
				<verse number="2">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ኤል​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="3">“ከዚህ ተነ​ሥ​ተህ ወደ ምሥ​ራቅ ሂድ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ትይዩ ባለው በኮ​ራት ፈፋ ውስጥ ተሸ​ሸግ።</verse>
				<verse number="4">ከፈ​ፋው ትጠ​ጣ​ለህ፤ ቁራ​ዎ​ችም በዚያ ይመ​ግ​ቡህ ዘንድ አዝ​ዣ​ለሁ።” ሄደም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="5">ሄዶም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ትይዩ ባለው በኮ​ራት ፈፋ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="6">ቁራ​ዎ​ችም በየ​ጥ​ዋ​ቱና በየ​ማ​ታው እን​ጀ​ራና ሥጋ ያመ​ጡ​ለት ነበር፤ ከፈ​ፋ​ውም ይጠጣ ነበር።</verse>
				<verse number="7">ከብዙ ቀንም በኋላ በም​ድር ላይ ዝናብ አል​ነ​በ​ረ​ምና ፈፋው ደረቀ።</verse>
				<verse number="8">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ኤል​ያስ መጣ እን​ዲ​ህም አለው፦</verse>
				<verse number="9">“ተነ​ሥ​ተህ በሲ​ዶና አጠ​ገብ ወዳ​ለ​ችው ወደ ሰራ​ፕታ ሂድ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጥ፤ እነ​ሆም፥ ትመ​ግ​ብህ ዘንድ አን​ዲት መበ​ለት አዝ​ዣ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="10">ተነ​ሥ​ቶም ወደ ሰራ​ፕታ ሄደ፤ ወደ ከተ​ማ​ዪ​ቱም በር በደ​ረሰ ጊዜ አን​ዲት መበ​ለት በዚያ እን​ጨት ትለ​ቅም ነበር፤ ኤል​ያ​ስም ጠርቶ፥ “የም​ጠ​ጣው ጥቂት ውኃ በጽዋ ታመ​ጭ​ልኝ ዘንድ እለ​ም​ን​ሻ​ለሁ” አላት።</verse>
				<verse number="11">ውኃም ልታ​መ​ጣ​ለት በሄ​ደች ጊዜ ወደ እር​ስዋ ጠርቶ፥ “እግረ መን​ገ​ድ​ሽን ቍራሽ እን​ጀራ በእ​ጅሽ አም​ጭ​ልኝ” አላት።</verse>
				<verse number="12">ሴት​የ​ዋም፥ “አም​ላ​ክህ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በማ​ድጋ ካለው ከእ​ፍኝ ዱቄት በማ​ሰ​ሮም ካለው ከጥ​ቂት ዘይት በቀር እን​ጀራ የለ​ኝም፤ እነ​ሆም፥ ጥቂት እን​ጨት እሰ​በ​ስ​ባ​ለሁ፤ ሄጄም ለእ​ኔና ለልጄ እጋ​ግ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በል​ተ​ነ​ውም እን​ሞ​ታ​ለን” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="13">ኤል​ያ​ስም አላት፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እመኚ፤ አት​ፍሪ፤ ሄደ​ሽም እን​ዳ​ል​ሽው አድ​ርጊ፤ አስ​ቀ​ድ​መሽ ግን ከዱ​ቄቱ ለእኔ ታናሽ እን​ጎቻ አድ​ር​ገሽ አም​ጭ​ልኝ፥ ከዚ​ያም በኋላ ለአ​ን​ቺና ለል​ጅሽ አድ​ርጊ፤</verse>
				<verse number="14">የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ በም​ድር ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዝናብ እስ​ከ​ሚ​ሰ​ጥ​በት ቀን ድረስ፥ ዱቄቱ ከማ​ድ​ጋው አይ​ጨ​ረ​ስም፥ ዘይ​ቱም ከማ​ሰ​ሮው አይ​ጐ​ድ​ልም።”</verse>
				<verse number="15">እር​ስ​ዋም ሄዳ እን​ዲሁ አደ​ረ​ገች፤ እር​ስ​ዋና እርሱ ልጆ​ች​ዋም በሉ።</verse>
				<verse number="16">በአ​ገ​ል​ጋዩ በኤ​ል​ያ​ስም ቃል እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ዱቄቱ ከማ​ድ​ጋው አል​ተ​ጨ​ረ​ሰም፤ ዘይ​ቱም ከማ​ሰ​ሮው አል​ጐ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="17">ከዚ​ያም በኋላ የባ​ለ​ቤ​ቲቱ የዚ​ያች ሴት ልጅ ታመመ፤ ትን​ፋ​ሹም እስ​ኪ​ታጣ ድረስ ደዌው እጅግ ከባድ ነበረ።</verse>
				<verse number="18">እር​ስ​ዋም ኤል​ያ​ስን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ፥ እኔ ከአ​ንተ ጋር ምን አለኝ? አን​ተስ ከእኔ ጋር ምን አለህ? ኀጢ​አ​ቴ​ንስ ታሳ​ስብ ዘንድ፥ ልጄ​ንስ ትገ​ድል ዘንድ ወደ እኔ መጥ​ተ​ሃ​ልን?” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="19">ኤል​ያ​ስም፥ “ልጅ​ሽን ስጪኝ” አላት፥ ከብ​ብ​ቷም ወስዶ ተቀ​ም​ጦ​በት ወደ ነበ​ረው ሰገ​ነት አወ​ጣው፤ በአ​ል​ጋ​ውም ላይ አስ​ተ​ኛው።</verse>
				<verse number="20">ኤል​ያ​ስም፥ “እኔ በቤቷ ያደ​ርሁ የዚች መበ​ለት ምስ​ክ​ርዋ ጌታዬ ሆይ፥ ልጅ​ዋን በመ​ግ​ደ​ልህ ክፉ አድ​ር​ገ​ህ​ባ​ታ​ልና ወዮ​ልኝ!” ብሎ ጮኸ።</verse>
				<verse number="21">በብ​ላ​ቴ​ና​ውም ላይ ሦስት ጊዜ እፍ አለ​በት፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አቤቱ አም​ላኬ ሆይ፥ የዚህ ብላ​ቴና ነፍስ ወደ እርሱ ትመ​ለስ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠራው።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የኤ​ል​ያ​ስን ቃል ሰማ፤ የሕ​ፃ​ኑም ነፍስ ተመ​ለ​ሰች፥ ዳነም፤</verse>
				<verse number="23">ኤል​ያ​ስም ብላ​ቴ​ና​ውን ይዞ ከሰ​ገ​ነቱ ወደ ቤት አወ​ረ​ደው፥ ለእ​ና​ቱም ሰጣት፥ “እነሆ፥ ተመ​ል​ከች ልጅሽ ድኖ​አል” አለ።</verse>
				<verse number="24">ሴቲ​ቱም ኤል​ያ​ስን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ሆንህ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል በአ​ፍህ እው​ነት እንደ ሆነ አሁን ዐወ​ቅሁ” አለ​ችው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">ከብዙ ቀንም በኋላ በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት፥ “ሂድ ለአ​ክ​ዓብ ተገ​ለጥ፤ በም​ድር ላይም ዝናም እሰ​ጣ​ለሁ” የሚል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤል​ያስ መጣ።</verse>
				<verse number="2">ኤል​ያ​ስም ለአ​ክ​ዓብ ይገ​ለጥ ዘንድ ሄደ፤ በሰ​ማ​ር​ያም ራብ ጸንቶ ነበር።</verse>
				<verse number="3">አክ​ዓ​ብም የቤ​ቱን አዛዢ አብ​ድ​ዩን ጠራ፤ አብ​ድ​ዩም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጅግ ይፈራ ነበር።</verse>
				<verse number="4">ኤል​ዛ​ቤ​ልም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ነቢ​ያት ባስ​ገ​ደ​ለች ጊዜ አብ​ድዩ መቶ​ውን ነቢ​ያት ወስዶ አምሳ አም​ሳ​ውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እን​ጀ​ራና ውኃ ይመ​ግ​ባ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="5">አክ​ዓ​ብም አብ​ድ​ዩን፥ “በሀ​ገሩ መካ​ከል ወደ ውኃ ምንጭ ሁሉና ወደ ፈፋ ሁሉ ና እን​ሂድ፤ እን​ስ​ሶ​ችም ሁሉ እን​ዳ​ይ​ጠፉ ፈረ​ሶ​ች​ንና በቅ​ሎ​ችን የም​ና​ድ​ን​በት ሣር ምና​ል​ባት እና​ገኝ እንደ ሆነ” አለው።</verse>
				<verse number="6">በመ​ን​ገ​ድም ተለ​ያ​ይ​ተው ሄዱ፤ አክ​ዓ​ብም ለብ​ቻው በአ​ንድ መን​ገድ፥ አብ​ድ​ዩም ለብ​ቻው በሌላ መን​ገድ ሄዱ።</verse>
				<verse number="7">አብ​ድ​ዩም በመ​ን​ገድ ብቻ​ውን ሳለ እነሆ፥ ኤል​ያስ ሊገ​ና​ኘው ብቻ​ውን መጣ፤ አብ​ድ​ዩም ሮጠና፥ በግ​ን​ባሩ ወድቆ ሰገ​ደ​ለት፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ኤል​ያስ አንተ ነህን?” አለው።</verse>
				<verse number="8">ኤል​ያ​ስም፥ “አዎ እኔ ነኝ ሄደህ ለጌ​ታህ፦ እነሆ፥ ኤል​ያስ በዚህ አለ በል” አለው።</verse>
				<verse number="9">አብ​ድ​ዩም አለ፥ “እኔን አገ​ል​ጋ​ይ​ህን እን​ዲ​ገ​ድ​ለኝ በአ​ክ​ዓብ እጅ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጠኝ ዘንድ ምን በደ​ልሁ?</verse>
				<verse number="10">አም​ላ​ክህ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ጌታዬ፥ ይፈ​ል​ግህ ዘንድ ያል​ላ​ከ​በት ሕዝብ ወይም መን​ግ​ሥት የለም፤ ሁሉም፦ በዚህ የለም ባሉ ጊዜ አን​ተን እን​ዳ​ላ​ገኙ መን​ግ​ሥ​ቱ​ንና ሕዝ​ቡን አም​ሎ​አ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="11">አሁ​ንም፥ እነሆ፦ ሂድ፥ ኤል​ያስ አለ ብለህ ለጌ​ታህ ንገር ትለ​ኛ​ለህ።</verse>
				<verse number="12">እኔም ከአ​ንተ ጥቂት ራቅ ስል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ አን​ሥቶ ወደ​ማ​ላ​ው​ቀው ስፍራ ይወ​ስ​ድ​ሃል፤ እኔም ገብቼ ለአ​ክ​ዓብ ስና​ገር፥ ባያ​ገ​ኝህ ይገ​ድ​ለ​ኛል፤ እኔም ባሪ​ያህ ከት​ን​ሽ​ነቴ ጀምሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እፈራ ነበር።</verse>
				<verse number="13">ኤል​ዛ​ቤል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ነቢ​ያት ባስ​ገ​ደ​ለች ጊዜ፥ መቶ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢ​ያት ወስጄ፥ አምሳ አም​ሳ​ውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጌ፥ እን​ጀ​ራና ውኃ የመ​ገ​ብ​ኋ​ቸ​ውን፥ ይህን ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ነገር በውኑ አንተ ጌታዬ አል​ሰ​ማ​ህ​ምን?</verse>
				<verse number="14">አሁ​ንም፦ ሄደህ ኤል​ያስ አለ ብለህ ለጌ​ታህ ንገር ትላ​ለህ፤ እር​ሱም ይገ​ድ​ለ​ኛል።”</verse>
				<verse number="15">ኤል​ያ​ስም፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት የሠ​ራ​ዊት ጌታ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እኔ ዛሬ ለእ​ርሱ እገ​ለ​ጣ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="16">አብ​ድ​ዩም ሄዶ አክ​ዓ​ብን ተገ​ና​ኘው፤ ነገ​ረ​ውም፤ አክ​ዓ​ብም ሮጦ ሄዶ ኤል​ያ​ስን ተገ​ና​ኘው።</verse>
				<verse number="17">አክ​ዓ​ብም ኤል​ያ​ስን ባየው ጊዜ፥ አክ​ዓብ ኤል​ያ​ስን፥ “እስ​ራ​ኤ​ልን የም​ት​ገ​ለ​ባ​ብጥ አንተ ነህን?” አለው።</verse>
				<verse number="18">ኤል​ያ​ስም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትታ​ችሁ በዓ​ሊ​ምን የተ​ከ​ተ​ላ​ችሁ፥ አን​ተና የአ​ባ​ትህ ቤት ናችሁ እንጂ እኔስ እስ​ራ​ኤ​ልን አል​ገ​ለ​ባ​ብ​ጥም።</verse>
				<verse number="19">አሁ​ንም ወደ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ልከህ፥ አራት መቶ ሃምሳ ነቢ​ያተ ሐሰ​ትን፥ አራት መቶ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ ነቢ​ያ​ትን ወደ እኔ ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ተራራ ሰብ​ስብ” አለው።</verse>
				<verse number="20">አክ​ዓ​ብም ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ልኮ ነቢ​ያ​ቱን ሁሉ ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ተራራ ሰበ​ሰ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">ኤል​ያ​ስም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ፥ “እስከ መቼ በሁ​ለት አሳብ ታነ​ክ​ሳ​ላ​ችሁ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ቢሆን እር​ሱን ተከ​ተሉ፤ በዓ​ልም አም​ላክ ቢሆን እር​ሱን ተከ​ተሉ” አለ። ሕዝ​ቡም አን​ዲት ቃል አል​መ​ለ​ሱ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="22">ኤል​ያ​ስም ሕዝ​ቡን አለ፥ “ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢ​ያት አንድ እኔ ብቻ ቀር​ቻ​ለሁ፤ የበ​ዓል ነቢ​ያት ግን አራት መቶ ሃምሳ ሰዎች ናቸው። የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ ነቢ​ያ​ትም አራት መቶ ናቸው።</verse>
				<verse number="23">ሁለት ወይ​ፈ​ኖች ይሰ​ጡን፤ እነ​ር​ሱም አንድ ወይ​ፈን ይም​ረጡ፤ እየ​ብ​ል​ቱም ይቍ​ረ​ጡት፤ በእ​ን​ጨ​ትም ላይ ያኑ​ሩት፤ በበ​ታ​ቹም እሳት አይ​ጨ​ምሩ፤ እኔም ሁለ​ተ​ኛ​ውን ወይ​ፈን አዘ​ጋ​ጃ​ለሁ፤ በእ​ን​ጨ​ቱም ላይ አኖ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በበ​ታ​ቹም እሳት አል​ጨ​ም​ርም።</verse>
				<verse number="24">እና​ን​ተም የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን ስም ጥሩ፤ እኔም የፈ​ጣ​ሪ​ዬን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም እጠ​ራ​ለሁ፤ ሰም​ቶም በእ​ሳት የሚ​መ​ልስ አም​ላክ፥ እርሱ አም​ላክ ይሁን።” ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “ይህ ነገር መል​ካም ነው” ብለው መለሱ።</verse>
				<verse number="25">ኤል​ያ​ስም የበ​ዓ​ልን ነቢ​ያት፥ “እና​ንተ ብዙ​ዎች ናች​ሁና አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ አንድ ወይ​ፈን ምረ​ጡና አዘ​ጋጁ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም ስም ጥሩ፤ በበ​ታ​ቹም እሳት አት​ጨ​ምሩ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ወይ​ፈ​ንም ወስ​ደው አዘ​ጋጁ፤ ከጥ​ዋ​ትም እስከ ቀትር ድረስ፥ “በዓል ሆይ፥ ስማን፥” እያሉ የበ​ዓ​ልን ስም ጠሩ። ድም​ፅም አል​ነ​በ​ረም፤ የሚ​መ​ል​ስም አል​ነ​በ​ረም፤ የሠ​ሩ​ት​ንም መሠ​ዊያ እያ​ነ​ከሱ ይዞሩ ነበር።</verse>
				<verse number="27">በቀ​ት​ርም ጊዜ ቴስ​ብ​ያ​ዊው ኤል​ያስ፥ “አም​ላክ ነውና በታ​ላቅ ቃል ጩኹ፤ ምና​ል​ባት ይጫ​ወት ይሆ​ናል፥ ወይም አሳብ ይዞት ይሆ​ናል፥ ወይም ተኝቶ እንደ ሆነ መቀ​ስ​ቀስ ያስ​ፈ​ል​ገ​ዋል” እያለ ይዘ​ባ​በ​ት​ባ​ቸው ጀመር።</verse>
				<verse number="28">በታ​ላ​ቅም ቃል ይጮኹ ጀመር፤ እንደ ልማ​ዳ​ቸ​ውም ደማ​ቸው እስ​ኪ​ፈ​ስስ ድረስ ገላ​ቸ​ውን በጦ​ርና በሰ​ይፍ ይብ​ዋ​ጭሩ ነበር።</verse>
				<verse number="29">እስከ ሠር​ክም ድረስ ትን​ቢት ይና​ገሩ ነበር፤ ድም​ፅም አል​ነ​በ​ረም፤ የሚ​መ​ል​ስና የሚ​ያ​ደ​ም​ጥም አል​ነ​በ​ረም። ከዚ​ህም በኋላ መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ያ​ር​ግ​በት ጊዜ ኤል​ያስ ነቢ​ያተ ሐሰ​ትን፥ “እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲያ በቃ​ችሁ፤ ወግዱ፤ ሂዱም፥ እኔም መሥ​ዋ​ዕ​ቴን እሠ​ዋ​ለሁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="30">ኤል​ያ​ስም ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ “ወደ እኔ ቅረቡ” አላ​ቸው። ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ እርሱ ቀረቡ።</verse>
				<verse number="31">ኤል​ያ​ስም፦ ስምህ እስ​ራ​ኤል ይሆ​ናል የሚል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ደረ​ሰ​ለት እንደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ነገድ ቍጥር ዐሥራ ሁለት ድን​ጋ​ዮ​ችን ወሰደ።</verse>
				<verse number="32">ድን​ጋ​ዮ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም መሠ​ዊያ አድ​ርጎ ሠራ​ቸው፤ የፈ​ረ​ሰ​ው​ንም መሠ​ዊያ አደሰ፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ዙሪያ ሁለት መስ​ፈ​ሪያ እህል የሚ​ይዝ ጕድ​ጓድ ቈፈረ።</verse>
				<verse number="33">በሠ​ራ​ውም መሠ​ዊያ ላይ እን​ጨ​ቱን ደረ​ደረ፤ ወይ​ፈ​ኑ​ንም በብ​ልት በብ​ልቱ ቈረጠ፤ በእ​ን​ጨ​ቱም ላይ አኖረ፤</verse>
				<verse number="34">“አራት ጋን ውኃ አም​ጡ​ልኝ፤ በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና በእ​ን​ጨቱ ላይም አፍ​ስሱ” አለ፤ እነ​ር​ሱም እን​ዲሁ አደ​ረጉ። ደግ​ሞም፥ “ድገሙ” አለ፤ እነ​ር​ሱም ደገሙ። እር​ሱም፥ “ሦስ​ተኛ አድ​ርጉ” አለ፤ ሦስ​ተ​ኛም አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="35">ውኃ​ውም በመ​ሠ​ዊ​ያው ዙሪያ ፈሰሰ። ደግ​ሞም ጕድ​ጓ​ዱን በውኃ ሞላው።</verse>
				<verse number="36">ነቢዩ ኤል​ያ​ስም ወደ ሰማይ አቅ​ንቶ ጮኸ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ፥ የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐቅ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ሆይ፥ ስማኝ፤ ጌታዬ ሆይ፥ ዛሬ በእ​ሳት ስማኝ፤ አንተ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አም​ላክ እንደ ሆንህ፥ እኔም ባሪ​ያህ እንደ ሆንሁ፤ ይህ​ንም ሥራ ስለ አንተ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እነ​ዚህ ሕዝ​ቦች ይወቁ።</verse>
				<verse number="37">አንተ፥ አቤቱ፥ አም​ላክ እንደ ሆንህ፥ ልባ​ቸ​ው​ንም ደግሞ እንደ መለ​ስህ፤ ይህ ሕዝብ ያውቅ ዘንድ ስማኝ፤ አቤቱ፥ ስማኝ” አለ።</verse>
				<verse number="38">እሳ​ትም ከሰ​ማይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወረ​ደች፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ እን​ጨ​ቱ​ንም፥ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም በላች፤ በጕ​ድ​ጓ​ዱም ውስጥ ያለ​ውን ውኃ፥ አፈ​ሩ​ንም ላሰች።</verse>
				<verse number="39">ሕዝ​ቡም ሁሉ ያን ባዩ ጊዜ በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደ​ፍ​ተው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ው​ነት እርሱ አም​ላክ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላክ ነው” አሉ።</verse>
				<verse number="40">ኤል​ያ​ስም ሕዝ​ቡን፥ “የበ​ዓ​ልን ነቢ​ያት ያዙ፤ ከእ​ነ​ርሱ አንድ ሰው እን​ኳን የሚ​ያ​መ​ልጥ አይ​ኑር፤” አላ​ቸው። ያዙ​አ​ቸ​ውም፤ ኤል​ያ​ስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ፥ በዚያ እየ​ወጋ ጣላ​ቸው።</verse>
				<verse number="41">ኤል​ያ​ስም አክ​ዓ​ብን፥ “የዝ​ናቡ ውሽ​ን​ፍር እጅግ ነውና ተነ​ሥ​ተህ ውጣ፤ ብላም፤ ጠጣም” አለው።</verse>
				<verse number="42">አክ​ዓ​ብም ሊበ​ላና ሊጠጣ ወጣ። ኤል​ያ​ስም ወደ ቀር​ሜ​ሎስ አናት ወጣ፤ ፊቱ​ንም በጕ​ል​በቱ መካ​ከል አቀ​ር​ቅሮ በግ​ን​ባሩ ወደ ምድር ተደፋ።</verse>
				<verse number="43">ብላ​ቴ​ና​ው​ንም፥ “ወጥ​ተህ ወደ ባሕሩ ተመ​ል​ከት” አለው። ብላ​ቴ​ና​ውም ተመ​ል​ክቶ፥ “ምንም የለም” አለ። ኤል​ያ​ስም፥ “ሰባት ጊዜ ተመ​ላ​ለስ” አለው። ብላ​ቴ​ና​ውም ሰባት ጊዜ ተመ​ላ​ለሰ።</verse>
				<verse number="44">በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ጊዜ፥ “እነሆ፥ የሰው ጫማ የም​ታ​ህል ትንሽ ደመና ከባ​ሕር ውኃ ቋጥራ ስት​ወጣ አየሁ” አለ። እር​ሱም፥ “ወጥ​ተህ አክ​ዓ​ብን፦ ዝናብ እን​ዳ​ይ​ዝህ ሰረ​ገ​ላ​ህን ጭነህ ውረድ በለው” አለ።</verse>
				<verse number="45">ወዲያ ወዲ​ህም እስ​ኪ​መ​ላ​ለስ ድረስ ሰማዩ በደ​መ​ናና በነ​ፋስ ጨለመ፤ ትል​ቅም ዝናብ ዘነበ፤ አክ​ዓ​ብም በሰ​ረ​ገላ ተቀ​ምጦ እያ​ለ​ቀሰ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ሄደ።</verse>
				<verse number="46">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በኤ​ል​ያስ ላይ ነበ​ረች፤ ወገ​ቡ​ንም ታጥቆ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል እስ​ኪ​ገባ ድረስ በአ​ክ​ዓብ ፊት ይሮጥ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">አክ​ዓ​ብም ኤል​ያስ ያደ​ረ​ገ​ውን፥ የሐ​ሰት ነቢ​ያ​ት​ንም ሁሉ በሰ​ይፍ እንደ ገደ​ላ​ቸው ለሚ​ስቱ ለኤ​ል​ዛ​ቤል ነገ​ራት።</verse>
				<verse number="2">ኤል​ዛ​ቤ​ልም፥ “አንተ ኤል​ያስ ከሆ​ንህ እኔም ኤል​ዛ​ቤል ከሆ​ንሁ ነገ በዚህ ጊዜ ሰው​ነ​ት​ህን ከእ​ነ​ዚህ እንደ አንዱ ሰው​ነት ባላ​ደ​ር​ጋት፥ አማ​ል​ክት እን​ዲህ ያድ​ር​ጉ​ብኝ፤ እን​ዲ​ህም ይግ​ደ​ሉኝ” ብላ ወደ ኤል​ያስ ላከች።</verse>
				<verse number="3">ኤል​ያ​ስም ፈርቶ ተነሣ፤ ነፍ​ሱ​ንም ሊያ​ድን ሄደ፤ በይ​ሁ​ዳም ወዳ​ለው ወደ ቤር​ሳ​ቤህ መጥቶ ብላ​ቴ​ና​ውን በዚያ ተወ።</verse>
				<verse number="4">እር​ሱም አንድ ቀን የሚ​ያ​ህል መን​ገድ በም​ድረ በዳ ሄደ፤ መጥ​ቶም ከደ​ድሆ ዛፍ በታች ተቀ​መ​ጠና፦ ይበ​ቃ​ኛል፤ አሁ​ንም አቤቱ! እኔ ከአ​ባ​ቶቼ አል​በ​ል​ጥ​ምና ነፍ​ሴን ውሰድ” ብሎ እን​ዲ​ሞት ለመነ።</verse>
				<verse number="5">በደ​ድ​ሆ​ውም ዛፍ በታች ተኛ፤ እን​ቅ​ል​ፍም አን​ቀ​ላፋ፤ እነ​ሆም፥ መል​አክ ዳሰ​ሰ​ውና፥ “ተነ​ሥ​ተህ ብላ” አለው።</verse>
				<verse number="6">ከዚህ በኋላ ኤል​ያስ ተነ​ሥቶ፥ እነሆ፥ በራሱ አጠ​ገብ የተ​ጋ​ገረ እን​ጎ​ቻና በማ​ሰሮ ውኃ አገኘ። በላም፤ ጠጣም፤ ተመ​ል​ሶም ተኛ።</verse>
				<verse number="7">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ደግሞ ሁለ​ተኛ ጊዜ መጥቶ ዳሰ​ሰ​ውና፥ “የም​ት​ሄ​ድ​በት መን​ገድ ሩቅ ነውና ተነ​ሥ​ተህ ብላ” አለው።</verse>
				<verse number="8">ተነ​ሥ​ቶም በላ፤ ጠጣም፤ በዚ​ያም በበ​ላው የም​ግብ ኀይል እስከ ኮሬብ ድረስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሄደ።</verse>
				<verse number="9">እዚ​ያም ወዳለ ዋሻ ገባ፤ በዚ​ያም አደረ፤ እነ​ሆም፥ “ኤል​ያስ ሆይ! ምን አመ​ጣህ?” የሚል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ።</verse>
				<verse number="10">ኤል​ያ​ስም፥ “ሁሉን ለሚ​ገዛ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅግ ቀን​ቻ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ቃል ኪዳ​ን​ህን ትተ​ዋ​ልና፥ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ች​ህ​ንም አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና፥ ነቢ​ያ​ት​ህ​ንም በሰ​ይፍ ገድ​ለ​ዋ​ልና፤ እኔም ብቻ​ዬን ቀር​ቻ​ለሁ ነፍ​ሴ​ንም ሊወ​ስ​ዱ​አት ይሻሉ” አለ።</verse>
				<verse number="11">እር​ሱም አለ፥ “ነገ ውጣ፤ በተ​ራ​ራ​ውም ላይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቁም። እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ አለፈ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ትል​ቅና ብርቱ ነፋስ ተራ​ሮ​ቹን ሰነ​ጠቀ፤ ዓለ​ቶ​ቹ​ንም ሰባ​በረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በነ​ፋሱ ውስጥ አል​ነ​በ​ረም። ከነ​ፋ​ሱም በኋላ የም​ድር መና​ወጥ ሆነ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በም​ድር መና​ወጥ ውስጥ አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="12">ከም​ድር መና​ወጥ በኋላ እሳት ሆነ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ሳቱ ውስጥ አል​ነ​በ​ረም። ከእ​ሳ​ቱም በኋላ እንደ ፉጨት ያለ ቀጭን ድምፅ ሆነ፤ በዚ​ያም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነበረ።</verse>
				<verse number="13">ኤል​ያ​ስም ያን በሰማ ጊዜ ፊቱን በመ​ጐ​ና​ጸ​ፊ​ያው ሸፈነ፤ ወጥ​ቶም በዋ​ሻው ደጃፍ ቆመ። እነ​ሆም፥ “ኤል​ያስ ሆይ፥ ወደ​ዚህ ለምን መጣህ?” የሚል ቃል ወደ እርሱ መጣ።</verse>
				<verse number="14">እር​ሱም፥ “ሁሉን ለሚ​ገዛ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅግ ቀን​ቻ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ቃል ኪዳ​ን​ህን ትተ​ዋ​ልና፥ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ች​ህ​ንም አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና፥ ነቢ​ያ​ት​ህ​ንም በሰ​ይፍ ገድ​ለ​ዋ​ልና፤ እኔም ብቻ​ዬን ቀር​ቻ​ለሁ፤ ነፍ​ሴ​ንም ሊወ​ስ​ዱ​አት ይሻሉ” አለ።</verse>
				<verse number="15">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “ሂድ፤ በመ​ጣ​ህ​በ​ትም መን​ገድ በም​ድረ በዳ ወደ ደማ​ስቆ ተመ​ለስ፤ ከዚ​ያም በደ​ረ​ስህ ጊዜ በሶ​ርያ ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ አዛ​ሄ​ልን ቅባው፤</verse>
				<verse number="16">በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ የና​ሚ​ሶን ልጅ ኢዩን ቅባው፤ በፋ​ን​ታ​ህም ነቢይ ይሆን ዘንድ የአ​ቤ​ል​መ​ሁ​ላን ሰው የሣ​ፋ​ጥን ልጅ ኤል​ሳ​ዕን ቅባው፤</verse>
				<verse number="17">ከአ​ዛ​ሄ​ልም ሰይፍ የሚ​ያ​መ​ል​ጠ​ውን ሁሉ ኢዩ ይገ​ድ​ለ​ዋል፤ ከኢ​ዩም ሰይፍ የሚ​ያ​መ​ል​ጠ​ውን ሁሉ ኤል​ሳዕ ይገ​ድ​ለ​ዋል።</verse>
				<verse number="18">እኔም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጕል​በ​ታ​ቸ​ውን ለበ​ዓል ያላ​ን​በ​ረ​ከ​ኩ​ትን ሁሉ፥ በአ​ፋ​ቸ​ውም ያል​ሳ​ሙ​ትን ሁሉ፥ ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስ​ቀ​ራ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="19">ከዚ​ያም ሄደ፤ የሣ​ፋ​ጥ​ንም ልጅ ኤል​ሳ​ዕን በዐ​ሥራ ሁለት ጥማድ በሬ​ዎች ሲያ​ርስ፥ እር​ሱም ከዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ጋር ሆኖ አገ​ኘው። ኤል​ያ​ስም ወደ እርሱ አልፎ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ውን ጣለ​በት።</verse>
				<verse number="20">ኤል​ሳ​ዕም በሬ​ዎ​ቹን ተወ፤ ኤል​ያ​ስ​ንም ተከ​ትሎ ሄደ፥ “አባ​ቴ​ንና እና​ቴን እስ​ማ​ቸው ዘንድ፥ እባ​ክህ ተወኝ፤ ከዚ​ያም በኋላ እከ​ተ​ል​ሃ​ለሁ” አለው። እር​ሱም“ሂድና ተመ​ለስ፤ ምን አድ​ር​ጌ​ል​ሃ​ለሁ?” አለው።</verse>
				<verse number="21">ከእ​ር​ሱም ዘንድ ተመ​ልሶ ሁለ​ቱን በሬ​ዎች ወስዶ አረ​ዳ​ቸው፤ ሥጋ​ቸ​ው​ንም በበ​ሬ​ዎቹ ዕቃ ቀቀ​ለው፤ ለሕ​ዝ​ቡም ሰጣ​ቸው፤ በሉም፤ እር​ሱም ተነ​ሥቶ ኤል​ያ​ስን ተከ​ትሎ ሄደ፤ ያገ​ለ​ግ​ለ​ውም ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">ለኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው ለና​ቡቴ በሰ​ማ​ርያ ንጉሥ በአ​ክ​ዓብ ቤት አጠ​ገብ የወ​ይን ቦታ ነበ​ረው።</verse>
				<verse number="2">አክ​ዓ​ብም ናቡ​ቴን፥ “በቤቴ አቅ​ራ​ቢያ ነውና የአ​ት​ክ​ልት ቦታ አደ​ር​ገው ዘንድ የወ​ይን ቦታ​ህን ስጠኝ፤ ስለ እር​ሱም ከእ​ርሱ የተ​ሻለ የወ​ይን ቦታ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ ወይም ብት​ወ​ድድ ዋጋ​ውን ወርቅ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” ብሎ ተና​ገ​ረው።</verse>
				<verse number="3">ናቡ​ቴም አክ​ዓ​ብን፥ “የአ​ባ​ቶቼን ርስት እሰ​ጥህ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አያ​ም​ጣ​ብኝ” አለው።</verse>
				<verse number="4">አክ​ዓ​ብም አዝኖ ሄደ፤ በአ​ል​ጋ​ውም ላይ ተኝቶ ፊቱን ተሸ​ፋ​ፈነ፤ እን​ጀ​ራ​ንም አል​በ​ላም።</verse>
				<verse number="5">ሚስ​ቱም ኤል​ዛ​ቤል ወደ እርሱ ገብታ፥ “ምን ያሳ​ዝ​ን​ሃል? እን​ጀ​ራስ የማ​ት​በላ ምን ሆነ​ሃል?” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="6">እር​ሱም፥ “ኢይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊ​ውን ናቡ​ቴን፦ የወ​ይ​ን​ህን ቦታ በገ​ን​ዘብ ስጠኝ፤ ወይም ብት​ወ​ድድ በፋ​ን​ታው ሌላ የወ​ይን ቦታ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ ብዬ ተና​ገ​ር​ሁት፤ እርሱ ግን የአ​ባ​ቶ​ቼን ርስት አል​ሰ​ጥ​ህም ስለ አለኝ ነው” አላት።</verse>
				<verse number="7">ሚስቱ ኤል​ዛ​ቤ​ልም፥ “አሁ​ንም አንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሆነህ እን​ደ​ዚህ ታደ​ር​ጋ​ለ​ህን? ተነሣ፤ እን​ጀ​ራ​ንም ብላ፤ ራስ​ህ​ንም አጽና፤ ልብ​ህም ደስ ይበ​ላት፤ የኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊ​ው​ንም የና​ቡ​ቴን የወ​ይን ቦታ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="8">በአ​ክ​ዓ​ብም ስም ደብ​ዳቤ ጻፈች፤ በማ​ኅ​ተ​ሙም አተ​መ​ችው፤ በከ​ተ​ማው ወደ ነበ​ሩ​ትና ከና​ቡ​ቴም ጋር ወደ ተቀ​መ​ጡት ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና አለ​ቆች ደብ​ዳ​ቤ​ውን ላከች።</verse>
				<verse number="9">የዚ​ያች ደብ​ዳ​ቤም ቃል እን​ዲህ ይላል፥ “ጾምን ጹሙ፤ ናቡ​ቴ​ንም በሕ​ዝቡ መካ​ከል በከ​ፍ​ተኛ ቦታ አስ​ቀ​ም​ጡት፤</verse>
				<verse number="10">ሁለት የሐ​ሰት ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም በፊቱ አስ​ቀ​ም​ጡና፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ንጉ​ሡን ሰድ​ቦ​አል ብለው ይመ​ስ​ክ​ሩ​በት፤ አው​ጥ​ታ​ች​ሁም እስ​ኪ​ሞት ድረስ በድ​ን​ጋይ መት​ታ​ችሁ ግደ​ሉት።”</verse>
				<verse number="11">በከ​ተ​ማ​ውም የተ​ቀ​መ​ጡት የከ​ተ​ማው ሰዎ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ አለ​ቆ​ችም ኤል​ዛ​ቤል እን​ዳ​ዘ​ዘ​ቻ​ቸ​ውና ወደ እነ​ርሱ በተ​ላ​ከው ደብ​ዳቤ እንደ ተጻ​ፈው እን​ዲሁ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="12">የጾም አዋ​ጅም ነገሩ፤ ናቡ​ቴ​ንም በሕ​ዝቡ ፊት በከ​ፍ​ተኛ ቦታ አስ​ቀ​መ​ጡት።</verse>
				<verse number="13">ሁለ​ቱም የዐ​መፅ ልጆች የሆኑ ሰዎች ገብ​ተው በፊቱ ቆሙ፤ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ንጉ​ሡን ሰድ​በ​ሃል” ብለው መሰ​ከ​ሩ​በት። የዚያ ጊዜም ከከ​ተማ አው​ጥ​ተው በድ​ን​ጋይ ደብ​ድ​በው ገደ​ሉት።</verse>
				<verse number="14">ወደ ኤል​ዛ​ቤ​ልም፥ “ናቡቴ በድ​ን​ጋይ ተደ​ብ​ድቦ ሞተ” ብለው ላኩ።</verse>
				<verse number="15">ኤል​ዛ​ቤ​ልም በሰ​ማች ጊዜ አክ​ዓ​ብን፥ “ናቡቴ ሞቶ​አል እንጂ በሕ​ይ​ወት አይ​ደ​ለ​ምና በገ​ን​ዘብ ይሰ​ጥህ ዘንድ እንቢ ያለ​ውን የኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊ​ውን የና​ቡ​ቴን የወ​ይን ቦታ ተነ​ሥ​ተህ ውረስ” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="16">አክ​ዓ​ብም ኢይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው ናቡቴ እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው ወደ ናቡቴ ወይን ቦታ ሊወ​ር​ሰው ተነ​ሥቶ ወረደ።</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቴስ​ብ​ያ​ዊው ኤል​ያ​ስን እን​ዲህ አለው፦</verse>
				<verse number="18">“ተነ​ሥ​ተህ በሰ​ማ​ርያ የሚ​ኖ​ረ​ውን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ አክ​ዓ​ብን ትገ​ናኝ ዘንድ ውረድ፤ እነሆ፥ ይወ​ር​ሰው ዘንድ በወ​ረ​ደ​በት በና​ቡቴ የወ​ይን ቦታ ውስጥ አለ።</verse>
				<verse number="19">እን​ዲ​ህም ብለህ ንገ​ረው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ናቡ​ቴን ገድ​ለህ ወረ​ስ​ኸው፤ ስለ​ዚ​ህም ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጅቦ​ችና ውሾች የና​ቡ​ቴን ደም በላ​ሱ​በት ስፍራ የአ​ን​ተን ደም ደግሞ ውሾች ይል​ሱ​ታል፤ አመ​ን​ዝ​ራ​ዎ​ችም በደ​ምህ ይታ​ጠ​ባሉ” ብለህ ንገ​ረው።</verse>
				<verse number="20">አክ​ዓ​ብም ኤል​ያ​ስን፥ “ጠላቴ ሆይ! አገ​ኘ​ኸ​ኝን?” አለው። እር​ሱም እን​ዲህ ብሎ መለ​ሰ​ለት፥ “አግ​ኝ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ታስ​ቈ​ጣው ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="21">እነሆ፥ ክፉ ነገር አመ​ጣ​ብ​ሃ​ለሁ፤ እሳ​ትን ከኋ​ላህ አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ዐጥር ተጠ​ግቶ እስ​ከ​ሚ​ሸን ድረስ የአ​ክ​ዓ​ብን ዘር አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ውስጥ ያሉ​ት​ንም፥ የሌ​ሉ​ት​ንም እነ​ቅ​ላ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="22">በሥ​ራ​ህም አስ​ቈ​ጥ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም አስ​ተ​ሃ​ልና ቤት​ህን እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ቤት እንደ አኪ​ያም ልጅ እንደ ባኦስ ቤት አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ፥ “በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ቅጥር አጠ​ገብ ኤል​ዛ​ቤ​ልን ውሾች ይበ​ሉ​አ​ታል፥</verse>
				<verse number="24">ከአ​ክ​ዓ​ብም ወገን በከ​ተ​ማ​ዪቱ ውስጥ የሞ​ተ​ውን ውሾች ይበ​ሉ​ታል፤ በሜ​ዳ​ውም የሞ​ተ​ውን የሰ​ማይ ወፎች ይበ​ሉ​ታል።”</verse>
				<verse number="25">ነገር ግን አክ​ዓብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉን ያደ​ርግ ዘንድ ራሱን ሸጠ፤ ሚስቱ ኤል​ዛ​ቤል አስ​ታ​ዋ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="26">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ያጠ​ፋ​ቸው አሞ​ራ​ው​ያን እንደ ሠሩት ሁሉ፥ ጣዖ​ትን በመ​ከ​ተል እጅግ ርኩስ ነገ​ርን ሠራ።</verse>
				<verse number="27">አክ​ዓ​ብም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ነሣ ደነ​ገጠ፤ ልብ​ሱ​ንም ቀደደ፤ እያ​ለ​ቀ​ሰም ሄደ፤ በሰ​ው​ነ​ቱም ላይ ማቅ ለበሰ፤ ጾመም፤ ኢይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው ናቡ​ቴ​ንም በገ​ደ​ለ​በት ቀን ደግሞ ማቅ ለብሶ ነበር።</verse>
				<verse number="28">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ስለ አክዓብ ወደ ባሪ​ያው ወደ ኤል​ያስ መጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፦</verse>
				<verse number="29">“አክ​ዓብ በፊቴ እንደ ደነ​ገጠ አየ​ህን? በፊቴ በልጁ ዘመን በቤቱ ላይ ክፉ ነገር አመ​ጣ​ለሁ እንጂ በእ​ርሱ ዘመን ክፉ ነገር አላ​መ​ጣም።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">የሶ​ር​ያም ንጉሥ ወልደ አዴር ሠራ​ዊ​ቱን ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ ወጥ​ቶም ሰማ​ር​ያን ከበ​ባት፤ እየ​ጠ​በ​ቃ​ቸ​ውም ተቀ​መጠ። ከእ​ር​ሱም ጋር ሠላሳ ሁለት ነገ​ሥ​ታት ነበሩ፤ ፈረ​ሶ​ችና ሰረ​ገ​ሎ​ችም ነበሩ፤ ወጥ​ተ​ውም ሰማ​ር​ያን ከበ​ቧት፥ ወጓ​ትም።</verse>
				<verse number="2">ወደ ከተ​ማው ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ወደ አክ​ዓብ እን​ዲህ ብሎ ላከ፦</verse>
				<verse number="3">“ወልደ አዴር እን​ዲህ ይላል፦ ብር​ህና ወር​ቅህ የእኔ ነው፤ ሚስ​ቶ​ች​ህና ልጆ​ች​ህም የእኔ ናቸው።”</verse>
				<verse number="4">ንጉሡ አክ​ዓ​ብም መልሶ፥ “ጌታዬ ሆይ! አንተ እን​ዳ​ልህ፤ እኔ የአ​ንተ ነኝ፤ ለእ​ኔም የሆ​ነው ሁሉ የአ​ንተ ነው” አለ።</verse>
				<verse number="5">ደግ​ሞም መል​እ​ክ​ተ​ኞች ተመ​ል​ሰው መጥ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “ወልደ አዴር እን​ዲህ ይላል፦ ቀድ​መህ ብር​ህ​ንና ወር​ቅ​ህን፥ ሚስ​ቶ​ች​ህ​ንና ልጆ​ች​ህ​ንም ላክ​ልኝ ብዬ ልኬ​ብህ ነበር፤</verse>
				<verse number="6">ይህ ካል​ሆነ ነገ በዚህ ጊዜ አገ​ል​ጋ​ዮቼን እል​ክ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ቤት​ህ​ንም፥ የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህ​ንም ቤቶች ይበ​ረ​ብ​ራሉ፤ ለዐ​ይ​ና​ቸው ደስ ያሰ​ኛ​ቸ​ውን ሁሉና በእ​ጃ​ቸው የዳ​ሰ​ሱ​ት​ንም ሁሉ ይወ​ስ​ዳሉ።”</verse>
				<verse number="7">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ የሀ​ገ​ሩን አለ​ቆች ሁሉ ጠርቶ፥ “ተመ​ል​ከቱ፤ ይህም ሰው ክፉ እን​ዲሻ እዩ፤ ስለ ሚስ​ቶቼ ስለ ወን​ዶች ልጆ​ቼና ሴቶች ልጆቼ ላከ​ብኝ፤ ብሬ​ንና ወር​ቄን ግን አል​ከ​ለ​ከ​ል​ሁ​ትም” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">አለ​ቆ​ችና ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “እንቢ በለው፤ እሺም አት​በ​ለው” አሉት።</verse>
				<verse number="9">ለወ​ልደ አዴር መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም፥ “ለጌ​ታ​ችሁ፦ ለእኔ አገ​ል​ጋ​ይህ በመ​ጀ​መ​ሪያ የላ​ክ​ህ​ብ​ኝን ሁሉ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ይህን ነገር ግን አደ​ር​ገው ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ኝም” በሉት አላ​ቸው። መል​ክ​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ተመ​ል​ሰው ይህን ነገር ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="10">ዳግ​መ​ኛም ወልደ አዴር እን​ዲህ ብሎ ወደ እርሱ ላከ፥ “ሕዝ​ቤና ሠራ​ዊቴ ሁሉ ሀገ​ር​ህን ሰማ​ር​ያን ባያ​ጠ​ፉት፥ የቀ​በ​ሮም ማደ​ሪያ ባያ​ደ​ር​ጉት አማ​ል​ክት እን​ዲህ ያድ​ር​ጉ​ብኝ፤ እን​ዲ​ህም ይግ​ደ​ሉኝ።”</verse>
				<verse number="11">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ መልሶ፥ “ይሁን፤ ይህ ጐባጣ እንደ ቀና አይ​መካ” ብሎ መለሰ።</verse>
				<verse number="12">ከዚ​ህም በኋላ ይህን ነገር በሰማ ጊዜ አብ​ረ​ውት ካሉት ከነ​ገ​ሥ​ታቱ ሁሉ ጋር በድ​ን​ኳኑ ውስጥ ይጠጣ ነበር፤ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም፥ “ከተ​ማ​ውን እጠ​ሩት” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ትይዩ ተሰ​ለፉ።</verse>
				<verse number="13">እነ​ሆም፥ አንድ ነቢይ ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ወደ አክ​ዓብ መጥቶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህን ብዙ ሕዝብ ሁሉ ታያ​ለ​ህን? እነሆ፥ ዛሬ በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲህ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="14">አክ​ዓ​ብም፥ “በምን አው​ቃ​ለሁ?” አለ፤ እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በአ​ው​ራ​ጃ​ዎቹ አለ​ቆች ጐል​ማ​ሶች” አለ፤ አክ​ዓ​ብም፥ “ውጊ​ያ​ውን ማን ይጀ​ም​ራል?” አለ፤ እር​ሱም፥ “አንተ” አለው።</verse>
				<verse number="15">አክ​ዓ​ብም የአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ቹን አለ​ቆች ጐል​ማ​ሶች ቈጠረ፤ ሁለት መቶ ሠላሳ ሁለ​ትም ሆኑ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ የእ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሁሉ ቈጠረ፤ ሰባት ሺህም ሆኑ።</verse>
				<verse number="16">ቀት​ርም በሆነ ጊዜ ወጡ፤ ወልደ አዴ​ርም በማቅ ድን​ኳን ውስጥ ጠጥቶ ሰክሮ ነበረ፤ የሚ​ረ​ዱት ሠላሳ ሁለት ነገ​ሥ​ታ​ትም አብ​ረ​ውት ነበሩ።</verse>
				<verse number="17">የአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ቹም አለ​ቆች ጐል​ማ​ሶች አስ​ቀ​ድ​መው መጥ​ተው ለሶ​ርያ ንጉሥ ለወ​ልደ አዴር፥ “እነሆ፥ ሰዎች ከሰ​ማ​ርያ መጡ” ብለው ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="18">እር​ሱም፥ “ለሰ​ላም መጥ​ተው እንደ ሆነ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው ያዙ​አ​ቸው፤ ለው​ጊያ መጥ​ተው እንደ ሆነ ግን ተዋ​ጓ​ቸው” አለ።</verse>
				<verse number="19">እነ​ዚ​ህም የአ​ው​ራ​ጃ​ዎች አለ​ቆች ጐል​ማ​ሶች ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ወጡ፤ ሠራ​ዊ​ትም ተከ​ተ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ በፊቱ የነ​በ​ረ​ውን ሰው ገደለ፤ ደጋ​ግ​መ​ውም ገደሉ። ከዚ​ህም በኋላ ሶር​ያ​ው​ያን ሸሹ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ የሶ​ርያ ንጉሥ ወልደ አዴ​ርም በፈ​ጣን ፈረስ አመ​ለጠ።</verse>
				<verse number="21">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ወጥቶ ፈረ​ሶ​ቹ​ንና ሰረ​ገ​ሎ​ቹን ያዘ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ን​ንም በታ​ላቅ አገ​ዳ​ደል ገደ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">አንድ ነቢ​ይም ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ መጥቶ፥ “የሶ​ርያ ንጉሥ ወልደ አዴር በሚ​መ​ጣው ዓመት ይመ​ጣ​ብ​ሃ​ልና፥ በርታ፤ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ው​ንም ዕወቅ” አለው።</verse>
				<verse number="23">የሶ​ር​ያም ንጉሥ አገ​ል​ጋ​ዮች እን​ዲህ አሉት፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የተ​ራ​ሮች አም​ላክ ነው እንጂ የሸ​ለቆ አም​ላክ አይ​ደ​ለም፤ ስለ​ዚህ በር​ት​ተ​ው​ብን ነበር፤ ነገር ግን በሜዳ ብን​ዋ​ጋ​ቸው ድል እና​ደ​ር​ጋ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="24">ይህ​ንም የም​ነ​ግ​ር​ህን ነገር አድ​ርግ፤ ወደ ቤታ​ቸው ይመ​ለሱ ዘንድ እኒ​ህን ነገ​ሥ​ታት አሰ​ና​ብ​ታ​ቸው፤ በፋ​ን​ታ​ቸ​ውም አለ​ቆ​ችን ሹም።</verse>
				<verse number="25">ሌሎች ሠራ​ዊ​ትን እና​መ​ጣ​ል​ሃ​ለን፤ አን​ተም ቀድሞ በሞ​ቱ​ብህ ሠራ​ዊት ምትክ ሹም፤ ፈረ​ሱን በፈ​ረስ ፋንታ፥ ሰረ​ገ​ላ​ውን በሰ​ረ​ገላ ፋንታ ለውጥ፤ በሜ​ዳ​ውም እን​ዋ​ጋ​ቸ​ዋ​ለን፤ ድልም እና​ደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለን።” እር​ሱም ምክ​ራ​ቸ​ውን ሰማ፤ እን​ዲ​ሁም አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="26">ከዚ​ህም በኋላ በዓ​መቱ ወልደ አዴር ሶር​ያ​ው​ያ​ንን ቈጠ​ራ​ቸው፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጋር ይዋጋ ዘንድ ወደ አፌቅ ወጣ።</verse>
				<verse number="27">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተቈ​ጠሩ፤ ሊገ​ጥ​ሙ​አ​ቸ​ውም ወጡ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እንደ ሁለት ትና​ንሽ የፍ​የል መን​ጋ​ዎች ሆነው በፊ​ታ​ቸው ሰፈሩ፤ ሶር​ያ​ው​ያን ግን ምድ​ርን ሞል​ተ​ዋት ነበር።</verse>
				<verse number="28">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው መጥቶ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሶር​ያ​ው​ያን፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ራ​ሮች አም​ላክ ነው እንጂ የሸ​ለቆ አም​ላክ አይ​ደ​ለም ብለ​ዋ​ልና ይህን ታላቅ ሠራ​ዊት ሁሉ በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="29">እነ​ዚ​ህም በእ​ነ​ዚያ ትይዩ ሰባት ቀን ያህል ሰፈሩ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ተጋ​ጠሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከሶ​ር​ያ​ው​ያን በአ​ንድ ቀን መቶ ሺህ እግ​ረኛ ገደሉ።</verse>
				<verse number="30">የቀ​ሩ​ትም ወደ አፌቅ ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ውስጥ ሸሹ፤ ቅጥ​ሩም በቀ​ሩት በሃያ ሰባት ሺህ ሰዎች ላይ ወደቀ። ወልደ አዴ​ርም ሸሽቶ ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ወደ እል​ፍኙ ውስጥ ገባ።</verse>
				<verse number="31">እር​ሱም ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ፥ “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መሓ​ሪ​ዎች ነገ​ሥ​ታት እንደ ሆኑ አው​ቃ​ለሁ፤ በወ​ገ​ባ​ችን ማቅ እን​ታ​ጠቅ፤ በራ​ሳ​ች​ንም ገመድ እን​ጠ​ም​ጥም፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ እን​ሂድ፤ ምና​ል​ባት ሰው​ነ​ታ​ች​ንን ያድ​ናት ይሆ​ናል” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="32">ወገ​ባ​ቸ​ው​ንም በማቅ ታጠቁ፤ በራ​ሳ​ቸ​ውም ገመድ ጠመ​ጠሙ፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ገብ​ተው፥ “ባሪ​ያህ ወልደ አዴር፦ ሰው​ነ​ታ​ች​ንን አድ​ነን አለህ” አሉት። እር​ሱም፥ “ገና በሕ​ይ​ወት አለን? ወን​ድሜ ነው” አለ።</verse>
				<verse number="33">ሰዎ​ቹም የደግ ምል​ክት አደ​ረ​ጉ​ትና ቃሉን ከአፉ ተቀ​ብ​ለው፥ “ወን​ድ​ምህ ወልደ አዴር አለ” አሉት። እር​ሱም፥ “ሂዱና አም​ጡት” አለ። ወልደ አዴ​ርም ወደ እርሱ መጣ፤ በሰ​ረ​ገ​ላ​ውም ላይ አስ​ቀ​መ​ጠው።</verse>
				<verse number="34">ወልደ አዴ​ርም፥ “አባቴ ከአ​ባ​ትህ የወ​ሰ​ዳ​ቸ​ውን ከተ​ሞች እመ​ል​ስ​ል​ሃ​ለሁ፤ አባቴ በሰ​ማ​ርያ እን​ዳ​ደ​ረገ አን​ተም በደ​ማ​ስቆ መን​ገድ ታደ​ር​ጋ​ለህ” አለው። አክ​ዓ​ብም፥ “እኔም በዚህ ቃል ኪዳን እሰ​ድ​ድ​ሃ​ለሁ” አለ። ከእ​ር​ሱም ጋር ቃል ኪዳን አድ​ርጎ ሰደ​ደው።</verse>
				<verse number="35">ከነ​ቢ​ያ​ትም ልጆች አንድ ሰው መጥቶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ባል​ን​ጀ​ራ​ውን፥ “ግደ​ለኝ” አለው። ሰው​ዬ​ውም ይገ​ድ​ለው ዘንድ እንቢ አለ።</verse>
				<verse number="36">እር​ሱም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል መስ​ማት እንቢ ብለ​ሃ​ልና እነሆ፥ ከእኔ ተለ​ይ​ተህ በሄ​ድህ ጊዜ አን​በሳ ይገ​ድ​ል​ሃል” አለው። ከእ​ር​ሱም ተለ​ይቶ በሄደ ጊዜ አን​በሳ አግ​ኝቶ ገደ​ለው።</verse>
				<verse number="37">ደግ​ሞም ሌላ ሰው አግ​ኝቶ፥ “ግደ​ለኝ” አለው። ሰው​ዬ​ውም መታው በመ​ም​ታ​ቱም አቈ​ሰ​ለው።</verse>
				<verse number="38">ነቢ​ዩም ሄዶ በመ​ን​ገድ አጠ​ገብ ንጉ​ሡን ጠበ​ቀው፤ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም በቀ​ጸ​ላው ሸፈነ።</verse>
				<verse number="39">ንጉ​ሡም ባለፈ ጊዜ ወደ እርሱ ጮኸ፥ “ባሪ​ያህ ወደ ሰልፍ መካ​ከል ወጣ፤ እነ​ሆም፥ አንድ ሰው ፈቀቅ ብሎ ወደ እኔ መጣ፤ አንድ ሰውም አመ​ጣና፦ ይህን ሰው ጠብቅ፤ ቢኰ​በ​ል​ልም ነፍ​ስህ በነ​ፍሱ ፋንታ ትሆ​ና​ለች፤ ወይም አንድ መክ​ሊት ብር ትከ​ፍ​ላ​ለህ አለኝ።</verse>
				<verse number="40">ከዚ​ህም በኋላ አገ​ል​ጋ​ይህ ወዲ​ህና ወዲያ ሲመ​ለ​ከት ጠፋ” አለው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ፥ “ፍር​ድህ እን​ዲሁ ይሆ​ናል፤ አንተ ፈር​ደ​ኸ​ዋል” አለው።</verse>
				<verse number="41">ፈጥ​ኖም ቀጸ​ላ​ውን ከዐ​ይኑ አነሣ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ከነ​ቢ​ያት ወገን እንደ ሆነ ዐወ​ቀው።</verse>
				<verse number="42">ያም ነቢይ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ እርም ያል​ሁ​ትን፥ ሞትም የሚ​ገ​ባ​ውን ሰው ከእ​ጅህ አው​ጥ​ተ​ሃ​ልና፥ ነፍ​ስህ በነ​ፍሱ ፋንታ፥ ሕዝ​ብ​ህም በሕ​ዝቡ ፋንታ ይሆ​ናሉ” አለው።</verse>
				<verse number="43">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አዝ​ኖና ተክዞ ወደ ሰማ​ርያ ሄደ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">በሰ​ማ​ር​ያም ሦስት ዓመት ተቀ​መጠ፤ በሶ​ር​ያና በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መካ​ከል ጦር​ነት አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="2">ከዚ​ህም በኋላ በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ወረደ።</verse>
				<verse number="3">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ “ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ የእኛ እንደ ሆነች፥ እኛም ከሶ​ርያ ንጉሥ እጅ ሳን​ወ​ስ​ዳት ዝም እን​ዳ​ልን ታው​ቃ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥም ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ እን​ዋጋ ዘንድ ከእኔ ጋር ትዘ​ም​ታ​ለ​ህን?” አለው። ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ለእ​ስ​ራ​እል ንጉሥ፥ “እኔ እንደ አንተ፥ ሕዝ​ቤም እንደ ሕዝ​ብህ፥ ፈረ​ሶቼም እንደ ፈረ​ሶ​ችህ ናቸው” አለው።</verse>
				<verse number="5">የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ጠይ​ቁ​ልን” አለው።</verse>
				<verse number="6">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ነቢ​ያ​ቱን አራት መቶ የሚ​ያ​ህ​ሉ​ትን ሰዎች ሰበ​ሰበ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥም፥ “ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ለሰ​ልፍ ልሂ​ድን? ወይስ ልቅር?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በን​ጉሥ እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ታ​ልና ውጣ” አሉት።</verse>
				<verse number="7">ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እን​ጠ​ይ​ቀው ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ በዚህ አይ​ገ​ኝ​ምን?” አለው።</verse>
				<verse number="8">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ን​ጠ​ይ​ቅ​በት የይ​ምላ ልጅ ሚክ​ያስ የሚ​ባል አንድ ሰው አለ፤ ነገር ግን ክፉ እንጂ መል​ካም አይ​ና​ገ​ር​ል​ኝ​ምና እጠ​ላ​ዋ​ለሁ” አለው። የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም፥ “ንጉሥ እን​ዲህ አይ​በል” አለ።</verse>
				<verse number="9">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አን​ዱን ጃን​ደ​ረባ ጠርቶ፥ “የይ​ም​ላን ልጅ ሚክ​ያ​ስን ፈጥ​ነህ ጥራው” አለው።</verse>
				<verse number="10">የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ አክ​ዓ​ብና የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ከጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸው ጋር በሰ​ማ​ርያ በር መግ​ቢያ አጠ​ገብ በአ​ደ​ባ​ባይ በዙ​ፋ​ኖ​ቻ​ቸው ላይ ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ ነቢ​ያ​ቱም ሁሉ በፊ​ታ​ቸው ትን​ቢት ተና​ገሩ።</verse>
				<verse number="11">የከ​ሓና ልጅ ሴዴ​ቅ​ያ​ስም የብ​ረት ቀን​ዶች ሠርቶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በእ​ነ​ዚህ ቀን​ዶች ሶር​ያ​ው​ያ​ንን ትወ​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ” አለ።</verse>
				<verse number="12">ነቢ​ያ​ትም ሁሉ እን​ዲህ ብለው ትን​ቢት ተና​ገሩ፥ “ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ዝመት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይረ​ዳ​ሃል። ሶር​ያ​ው​ያ​ን​ንና ንጉ​ሣ​ቸ​ው​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል።”</verse>
				<verse number="13">ሚክ​ያ​ስ​ንም ሊጠራ የሄደ መል​እ​ክ​ተኛ፥ “እነሆ፥ ነቢ​ያት ሁሉ በአ​ንድ አፍ ሆነው ለን​ጉሡ መል​ካ​ምን ይና​ገ​ራሉ፤ ቃል​ህም እንደ ቃላ​ቸው እን​ዲ​ሆን መል​ካም እን​ድ​ት​ና​ገር እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="14">ሚክ​ያ​ስም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ነ​ግ​ረ​ኝን እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="15">ወደ ንጉ​ሡም ደረሰ። ንጉ​ሡም፥ “ሚክ​ያስ ሆይ! ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ለሰ​ልፍ እን​ሂ​ድን? ወይስ እን​ቅር?” አለው። እር​ሱም፥ “ውጣና ተከ​ና​ወን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በን​ጉሡ እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ታል” ብሎ መለ​ሰ​ለት።</verse>
				<verse number="16">ንጉ​ሡም፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም እው​ነት ትነ​ግ​ረኝ ዘንድ ስንት ጊዜ አም​ል​ሃ​ለሁ?” አለው።</verse>
				<verse number="17">እር​ሱም አለ፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ጠባቂ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው በጎች በተ​ራ​ሮች ላይ ተበ​ት​ነው አየሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ነ​ዚህ አም​ላክ አይ​ደ​ለ​ምን? እያ​ን​ዳ​ንዱ በሰ​ላም ወደ ቤቱ ይመ​ለስ።”</verse>
				<verse number="18">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥን፥ “ክፉ እንጂ መል​ካም እን​ደ​ማ​ይ​ና​ገ​ር​ልኝ አላ​ል​ሁ​ምን?” አለው።</verse>
				<verse number="19">ሚክ​ያ​ስም አለ፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል የሰ​ማ​ሁት እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ፋኑ ተቀ​ምጦ፥ የሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ በቀ​ኙና በግ​ራው ቆመው አየሁ።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ወጥቶ በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ ይወ​ድቅ ዘንድ አክ​ዓ​ብን የሚ​ያ​ሳ​ስት ማን ነው? አለ። አን​ዱም እን​ዲህ ያለ ነገር፥ ሌላ​ውም እን​ዲያ ያለ ነገር ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="21">መን​ፈ​ስም ወጣ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቆሞ፦ እኔ አስ​ተ​ዋ​ለሁ አለ።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ በምን ታስ​ተ​ዋ​ለህ? አለው፤ እር​ሱም ወጥቼ በነ​ቢ​ያቱ ሁሉ አፍ ሐሰ​ተኛ መን​ፈስ እሆ​ና​ለሁ አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ማሳ​ሳ​ትስ ታሳ​ስ​ተ​ዋ​ለህ፤ ይሆ​ን​ል​ሃ​ልም፤ ውጣ፤ እን​ዲ​ሁም አድ​ርግ አለ።</verse>
				<verse number="23">አሁ​ንም፥ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ነ​ዚህ በነ​ቢ​ያ​ትህ ሁሉ አፍ ሐሰ​ተኛ መን​ፈስ አድ​ር​ጎ​አል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በላ​ይህ ክፉ ተና​ግ​ሮ​ብ​ሃል።”</verse>
				<verse number="24">የከ​ሓ​ናም ልጅ ሴዴ​ቅ​ያስ ቀረበ፤ ሚክ​ያ​ስ​ንም ጕን​ጩን በጥፊ መታ​ውና፥ “ምን ዓይ​ነት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነው የተ​ና​ገ​ረህ?” አለው።</verse>
				<verse number="25">ሚክ​ያ​ስም፥ “እነሆ፥ በዚያ ቀን ልት​ሸ​ሸግ ወደ ውስ​ጠ​ኛው እል​ፍ​ኝህ በሄ​ድህ ጊዜ ታያ​ለህ” አለ።</verse>
				<verse number="26">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ፥ “ሚክ​ያ​ስን ውሰዱ፤ ወደ ከተ​ማ​ዪ​ቱም ሹም ወደ አሞን ወደ ንጉ​ሡም ልጅ ወደ ኢዮ​አስ መል​ሳ​ችሁ፦</verse>
				<verse number="27">ንጉሡ እን​ዲህ ይላል፦ በደ​ኅና እስ​ክ​መ​ለስ ድረስ ይህን ሰው በግ​ዞት አኑ​ሩት፤ የመ​ከ​ራም እን​ጀራ መግ​ቡት፤ የመ​ከ​ራም ውኃ አጠ​ጡት በሉ​አ​ቸው” አለ።</verse>
				<verse number="28">ሚክ​ያ​ስም፥ “በሰ​ላም ብት​መ​ለስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኔ የተ​ና​ገረ አይ​ደ​ለም” አለ። ደግ​ሞም አሕ​ዛብ ሁሉ ሆይ! ስሙኝ” አለ።</verse>
				<verse number="29">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉ​ሥና የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ዘመቱ።</verse>
				<verse number="30">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ልብ​ሴን ለውጬ ወደ ሰልፍ እገ​ባ​ለሁ፤ አንተ ግን የእ​ኔን ልብስ ልበስ” አለው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ልብ​ሱን ለውጦ ወደ ሰልፍ ገባ።</verse>
				<verse number="31">የሶ​ር​ያም ንጉሥ ሠላሳ ሁለ​ቱን የሰ​ረ​ገ​ሎች አለ​ቆች፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በቀር፥ ታናሽ ቢሆን ወይም ታላቅ ከማ​ና​ቸ​ውም ጋር አትዋጉ” ብሎ አዝዞ ነበር።</verse>
				<verse number="32">የሰ​ረ​ገ​ሎች አለ​ቆ​ችም የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን ባዩ ጊዜ፥ “በእ​ው​ነት የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ ይመ​ስ​ላል፤” አሉ ይዋ​ጉ​ትም ዘንድ ከበ​ቡት፤ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ጮኸ።</verse>
				<verse number="33">የሰ​ረ​ገ​ሎች አለ​ቆ​ችም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እን​ዳ​ል​ሆነ ባዩ ጊዜ እር​ሱን ከማ​ሳ​ደድ ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="34">አንድ ሰውም ቀስ​ቱን ድን​ገት ገትሮ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ በሳ​ን​ባ​ውና በደ​ረቱ መካ​ከል ወጋው፤ ሰረ​ገ​ለ​ኛ​ው​ንም፥ “መል​ሰህ ንዳ፤ ተወ​ግ​ቻ​ለ​ሁና ከሰ​ልፍ ውስጥ አው​ጣኝ” አለው።</verse>
				<verse number="35">በዚ​ያም ቀን ሰልፍ በረታ፤ ንጉ​ሡም ከጥ​ዋት እስከ ማታ በሶ​ር​ያ​ው​ያን ፊት በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ተደ​ግፎ ነበር፤ የቍ​ስ​ሉም ደም በሰ​ረ​ገ​ላው ውስጥ ፈሰሰ፤ ማታም ሞተ።</verse>
				<verse number="36">ፀሐ​ይም በገ​ባች ጊዜ አዋጅ ነጋ​ሪው ወጥቶ፥ “ንጉሡ ሞቶ​አ​ልና እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ከተ​ማው፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ ሀገሩ ይሂድ” ብሎ አዋጅ ነገረ።</verse>
				<verse number="37">ወደ ሰማ​ር​ያም መጡ፤ ንጉ​ሡ​ንም በሰ​ማ​ርያ ቀበ​ሩት፤</verse>
				<verse number="38">ሰረ​ገ​ላ​ው​ንም በሰ​ማ​ርያ ምንጭ አጠ​ቡት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በነ​ቢዩ አድሮ እንደ ተና​ገረ ውሾ​ችና ጅቦች ደሙን ላሱት። አመ​ን​ዝ​ሮች ሴቶ​ችም በደሙ ታጠ​ቡ​በት።</verse>
				<verse number="39">የቀ​ረ​ውም የአ​ክ​ዓብ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ነገር ሁሉ፥ ከዝ​ሆን ጥር​ስም የሠ​ራው ቤት፥ የሠ​ራ​ቸ​ውም ከተ​ሞች ሁሉ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።</verse>
				<verse number="40">አክ​ዓ​ብም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ልጁ አካ​ዝ​ያስ ነገሠ።</verse>
				<verse number="41">የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ አክ​ዓ​ብም በነ​ገሠ በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት የአሳ ልጅ ኢዮ​ሣ​ፍጥ በይ​ሁዳ ላይ ነገሠ።</verse>
				<verse number="42">ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሠ​ላሳ አም​ስት ዓመት ጎበዝ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሃያ አም​ስት ዓመት ነገሠ። እና​ቱም ዓዙባ የተ​ባ​ለች የሴ​ሜይ ልጅ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="43">በአ​ባ​ቱም በአሳ መን​ገድ ሁሉ ሄደ፤ ከእ​ር​ሱም ፈቀቅ አላ​ለም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን አደ​ረገ፤ ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ያሉ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን አላ​ራ​ቀም፤ ሕዝ​ቡም ገና በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ባሉት መስ​ገ​ጃ​ዎች ይሠ​ዋና ያጥን ነበር።</verse>
				<verse number="44">ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ጋር ታረቀ።</verse>
				<verse number="45">የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ነገር፥ ኀይ​ሉም፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።</verse>
				<verse number="46">ከአ​ባ​ቱም ከአሳ ዘመን የቀ​ረ​ውን ርኩስ ሥራ ከም​ድር አጠፋ።</verse>
				<verse number="47">በኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም፤ ሹሙም እንደ ንጉሥ ነበረ።</verse>
				<verse number="48">ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ወደ ኦፌር ሄደው ወርቅ ያመጡ ዘንድ በተ​ር​ሴስ መር​ከ​ብን ሠራ፤ ነገር ግን መር​ከ​ቢቱ በጋ​ሴ​ዎ​ን​ጋ​ቤር ተሰ​ብ​ራ​ለ​ችና አል​ሄ​ደ​ችም።</verse>
				<verse number="49">የአ​ክ​ዓ​ብም ልጅ አካ​ዝ​ያስ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮቼ ጋር በመ​ር​ከብ ይሂዱ” አለው፤ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ግን አል​ወ​ደ​ደም።</verse>
				<verse number="50">ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ልጁ ኢዮ​ራም ነገሠ።</verse>
				<verse number="51">በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ በዐ​ሥራ ሰባ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የአ​ክ​ዓብ ልጅ አካ​ዝ​ያስ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ መን​ገሥ ጀመረ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ሁለት ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="52">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ፤ በአ​ባቱ በአ​ክ​ዓብ፥ በእ​ና​ቱም በኤ​ል​ዛ​ቤል መን​ገድ፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ባሳ​ተው በና​ባጥ ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም መን​ገድ ሄደ።</verse>
				<verse number="53">በዓ​ሊ​ም​ንም አመ​ለከ፤ ሰገ​ደ​ላ​ቸ​ውም፤ ከእ​ር​ሱም አስ​ቀ​ድሞ አባ​ቶቹ እን​ዳ​ደ​ረ​ጉት ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አስ​ቈ​ጣው።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="12">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">አክ​ዓ​ብም ከሞተ በኋላ ሞዓብ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ዐመፀ።</verse>
				<verse number="2">አካ​ዝ​ያ​ስም በሰ​ማ​ርያ በሰ​ገ​ነቱ ላይ ሳለ በዐ​ይነ ርግቡ ወድቆ ታመመ፤ እር​ሱም፥ “ሂዱ፥ ከዚህ ደዌ እድን እንደ ሆነ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ጠይቁ” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እነ​ር​ሱም ሊጠ​ይ​ቁ​ለት ሄዱ።</verse>
				<verse number="3">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ቴስ​ብ​ያ​ዊ​ውን ኤል​ያ​ስን ጠርቶ፥ “ተነሣ፤ የሰ​ማ​ር​ያን ንጉሥ መል​እ​ክ​ተ​ኞች ለመ​ገ​ና​ኘት ሂድና፦ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ትጠ​ይቁ ዘንድ የም​ት​ሄ​ዱት በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አም​ላክ ስለ​ሌለ ነውን?</verse>
				<verse number="4">ነገሩ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ ከወ​ጣ​ህ​በት አልጋ አት​ወ​ር​ድም በላ​ቸው” አለው። ኤል​ያ​ስም ሄደ፤ እን​ዲ​ሁም ነገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹም ወደ አካ​ዝ​ያስ ተመ​ለሱ፤ እር​ሱም፥ “ለምን ተመ​ለ​ሳ​ችሁ?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">እነ​ር​ሱም፥ “አንድ ሰው ሊገ​ና​ኘን መጣና፦ ሂዱ፤ ወደ ላካ​ችሁ ንጉሥ ተመ​ል​ሳ​ችሁ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ትጠ​ይቅ ዘንድ የላ​ክህ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አም​ላክ ስለ​ሌለ ነውን? ስለ​ዚህ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ ከወ​ጣ​ህ​በት አልጋ አት​ወ​ር​ድም በሉት አለን” አሉት።</verse>
				<verse number="7">እር​ሱም፥ “ሊገ​ና​ኛ​ችሁ የወ​ጣው፦ ይህ​ንስ ቃል የነ​ገ​ራ​ችሁ ሰው መልኩ ምን ይመ​ስ​ላል?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">እነ​ር​ሱም፥ “ሰው​ዬው ጠጕ​ራም ነው፤ በወ​ገ​ቡም ጠፍር ታጥቆ ነበር” አሉት። እር​ሱም፥ “ቴስ​ብ​ያ​ዊው ኤል​ያስ ነው” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ንጉ​ሡም ይጠ​ሩት ዘንድ የአ​ምሳ አለ​ቃ​ውን ከአ​ምሳ ሰዎች ጋር ወደ እርሱ ላከ፤ ወደ እር​ሱም ሄዱ፤ እነ​ሆም፥ በተ​ራራ ራስ ላይ ተቀ​ምጦ አገ​ኙት። የአ​ምሳ አለ​ቃ​ውም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ! ንጉሡ ይጠ​ራ​ሃል ፈጥ​ነህ ና፤ ውረድ” አለው።</verse>
				<verse number="10">ኤል​ያ​ስም መልሶ የአ​ምሳ አለ​ቃ​ውን፥ “እኔስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ሆንሁ እሳት ከሰ​ማይ ትው​ረድ፤ አን​ተ​ንም፥ አም​ሳ​ው​ንም ሰዎ​ች​ህን ትብላ” አለው። እሳ​ትም ከሰ​ማይ ወርዳ እር​ሱ​ንና አም​ሳ​ውን ሰዎች በላች።</verse>
				<verse number="11">ደግ​ሞም ሌላ የአ​ምሳ አለቃ ከአ​ምሳ ሰዎች ጋር ላከ​በት፤ የአ​ምሳ አለ​ቃ​ውም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ! ንጉሡ፦ ና፤ ፈጥ​ነህ ውረድ ይላል” ብሎ ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="12">ኤል​ያ​ስም፥ “እኔስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ሆንሁ እሳት ከሰ​ማይ ትው​ረድ፤ አን​ተ​ንም፥ አም​ሳ​ው​ንም ሰዎ​ች​ህን ትብላ” አለው። እሳ​ትም ከሰ​ማይ ወርዳ እር​ሱ​ንና አም​ሳ​ውን ሰዎች በላች።</verse>
				<verse number="13">ንጉ​ሡም ደግሞ ሦስ​ተኛ የአ​ምሳ አለቃ ከአ​ምሳ ሰዎች ጋር ላከ፤ ሦስ​ተ​ኛ​ውም የአ​ምሳ አለቃ ወጥቶ በኤ​ል​ያስ ፊት በጕ​ል​በቱ ተን​በ​ረ​ከ​ከና ለመ​ነው እን​ዲ​ህም አለው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ! ሰው​ነ​ቴና የእ​ነ​ዚህ የአ​ም​ሳው ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ሰው​ነት በፊ​ትህ የከ​በ​ረች ትሁን።</verse>
				<verse number="14">እነሆ፥ እሳት ከሰ​ማይ ወርዳ የፊ​ተ​ኞ​ቹን ሁለ​ቱን የአ​ምሳ አለ​ቆ​ችና አምሳ አም​ሳ​ውን ሰዎ​ቻ​ቸ​ውን በላች፤ አሁን ግን ነፍሴ በፊ​ትህ የከ​በ​ረች ትሁን።”</verse>
				<verse number="15">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ኤል​ያ​ስን፥ “ከእ​ርሱ ጋር ውረድ፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ አት​ፍራ” ብሎ ነገ​ረው። ኤል​ያ​ስም ተነ​ሥቶ ከእ​ርሱ ጋር ወደ ንጉሡ ወረደ።</verse>
				<verse number="16">ኤል​ያ​ስም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ትጠ​ይቅ ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ለምን ላክህ? በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አም​ላክ ስለ​ሌለ ነውን? እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ ከወ​ጣ​ህ​በት አልጋ አት​ወ​ር​ድም” አለው።</verse>
				<verse number="17">ኤል​ያ​ስም እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሞተ።</verse>
				<verse number="18">አካ​ዝ​ያስ ያደ​ረ​ገው የቀ​ረ​ውም ነገር እነሆ፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል። በእ​ር​ሱም ፋንታ የአ​ክ​ዓብ ልጅ ወን​ድሙ ኢዮ​ራም ነገሠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኤል​ያ​ስን በዐ​ውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ በሚ​ያ​ወ​ጣው ጊዜ ኤል​ያ​ስና ኤል​ሳዕ ከጌ​ል​ጌላ ተነ​ሥ​ተው ሄዱ።</verse>
				<verse number="2">ኤል​ያ​ስም ኤል​ሳ​ዕን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ቤቴል ልኮ​ኛ​ልና በዚሁ ቈይ” አለው። ኤል​ሳ​ዕም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ሕያው ነፍ​ስ​ህ​ንም አል​ለ​ይ​ህም” አለው። ወደ ቤቴ​ልም ደረሱ።</verse>
				<verse number="3">በቤ​ቴ​ልም የነ​በሩ የነ​ቢ​ያት ልጆች ወደ ኤል​ሳዕ መጥ​ተው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጌታ​ህን ከአ​ንተ ለይቶ ዛሬ እን​ደ​ሚ​ወ​ስ​ደው ዐው​ቀ​ሃ​ልን?” አሉት። እር​ሱም፥ “አዎን፥ ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤ ዝም በሉ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ኤል​ያ​ስም ኤል​ሳ​ዕን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ኢያ​ሪኮ ልኮ​ኛ​ልና፥ በዚህ ቈይ” አለው። ኤል​ሳ​ዕም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ሕያው ነፍ​ስ​ህ​ንም አል​ለ​ይ​ህም” አለው።</verse>
				<verse number="5">ወደ ኢያ​ሪ​ኮም ደረሱ፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም የነ​በሩ የነ​ቢ​ያት ልጆች ወደ ኤል​ሳዕ ቀር​በው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጌታ​ህን ከራ​ስህ ላይ ዛሬ እን​ዲ​ወ​ስ​ደው ዐው​ቀ​ሃ​ልን?” አሉት። እር​ሱም፥ “አዎን፥ ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤ ዝም በሉ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">ኤል​ያ​ስም ኤል​ሳ​ዕን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ዮር​ዳ​ኖስ ልኮ​ኛ​ልና እባ​ክህ፥ በዚህ ቈይ” አለው። ኤል​ሳ​ዕም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ሕያው ነፍ​ስ​ህ​ንም አል​ለ​ይ​ህም” አለው፤ ሁለ​ቱም ሄዱ።</verse>
				<verse number="7">ከነ​ቢ​ያ​ትም ልጆች አምሳ ሰዎች ሄዱ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ርቀው ቆሙ፤ እነ​ዚ​ህም ሁለቱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ዳር ቆመው ነበር።</verse>
				<verse number="8">ኤል​ያ​ስም መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያ​ውን ወስዶ ጠቀ​ለ​ለው፤ የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ውኃ መታ​በት፤ ውኃ​ውም ወዲ​ህና ወዲያ ተከ​ፈለ፤ ሁለ​ቱም በደ​ረቅ ተሻ​ገሩ። ወጥ​ተ​ውም በም​ድረ በዳው ቆሙ።</verse>
				<verse number="9">ከተ​ሻ​ገ​ሩም በኋላ ኤል​ያስ ኤል​ሳ​ዕን፥ “ከአ​ንተ ሳል​ወ​ሰድ አደ​ር​ግ​ልህ ዘንድ የም​ት​ሻ​ውን ለምን” አለው፤ ኤል​ሳ​ዕም፥ “መን​ፈ​ስህ በእኔ ላይ ሁለት እጥፍ ይሆን ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="10">ኤል​ያ​ስም፥ “አስ​ቸ​ጋሪ ነገር ለም​ነ​ሃል፤ ነገር ግን ከአ​ንተ ዘንድ በተ​ወ​ሰ​ድሁ ጊዜ ብታ​የኝ ይሆ​ን​ል​ሃል፤ አለ​ዚያ ግን አይ​ሆ​ን​ል​ህም” አለው።</verse>
				<verse number="11">ሁለ​ቱም እየ​ተ​ነ​ጋ​ገሩ ሲሄዱ፥ እነሆ፥ የእ​ሳት ሰረ​ገ​ላና የእ​ሳት ፈረ​ሶች በሁ​ለቱ መካ​ከል ገብ​ተው ከፈ​ሉ​አ​ቸው፤ ኤል​ያ​ስም በዐ​ውሎ ነፋስ ንው​ጽ​ው​ጽታ ወደ ሰማይ ወጣ።</verse>
				<verse number="12">ኤል​ሳ​ዕም አይቶ፥ “አባቴ! አባቴ ሆይ! የእ​ስ​ራ​ኤል ኀይ​ላ​ቸ​ውና ጽን​ዓ​ቸው፥” ብሎ ጮኸ። ከዚ​ያም ወዲያ ዳግ​መኛ አላ​የ​ውም፤ ልብ​ሱ​ንም ይዞ ከሁ​ለት ቀደ​ደው።</verse>
				<verse number="13">ኤል​ያ​ስም መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያ​ውን ለኤ​ል​ሳዕ ጣለ​ለት፤ በኤ​ል​ሳ​ዕም ራስ ላይ ዐረፈ። ኤል​ሳ​ዕም ተመ​ልሶ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ዳር ቆመ።</verse>
				<verse number="14">በራሱ ላይ ያረ​ፈ​ች​ውን የኤ​ል​ያ​ስን መጠ​ም​ጠ​ሚያ ወስዶ ውኃ​ውን መታ​ባት፦ ውኃው ግን አል​ተ​ከ​ፈ​ለም፤ እር​ሱም፥ “የኤ​ል​ያስ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዴት ነው? እን​ዴ​ትስ ነው?” አለ። ከዚ​ህም በኋላ ውኃ​ውን በመታ ጊዜ ወዲ​ህና ወዲያ ተከ​ፈለ፤ ኤል​ሳ​ዕም ተሻ​ገረ።</verse>
				<verse number="15">በኢ​ያ​ሪ​ኮም የነ​በ​ሩት የነ​ቢ​ያት ልጆች ኤል​ሳዕ ወደ እነ​ርሱ ሲመጣ ባዩት ጊዜ፥ “የኤ​ል​ያስ መን​ፈስ በኤ​ል​ሳዕ ላይ ዐር​ፎ​አል” አሉ። ሊገ​ና​ኙ​ትም መጥ​ተው በፊቱ በም​ድር ላይ ሰገ​ዱ​ለት።</verse>
				<verse number="16">እነ​ር​ሱም፥ “እነሆ፥ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ጋር አምሳ ኀ`ያላን ሰዎች አሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ወደ ዮር​ዳ​ኖስ ወይም ወደ አንድ ተራራ ወይም ወደ አንድ ኮረ​ብታ ጥሎት እንደ ሆነ፥ ሄደው ጌታ​ህን ይፈ​ል​ጉት” አሉት። ኤል​ሳ​ዕም፥ “አት​ላኩ፤” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">እስ​ኪ​ያ​ፍ​ራ​ቸ​ውም ድረስ ግድ ባሉት ጊዜ፥ “ላኩ” አለ፤ አም​ሳም ሰዎች ላኩ፤ ሦስት ቀንም ፈል​ገው አላ​ገ​ኙ​ትም።</verse>
				<verse number="18">በኢ​ያ​ሪ​ኮም ተቀ​ምጦ ሳለ ወደ እርሱ ተመ​ለሱ፤ እር​ሱም፥ “አት​ላኩ፥ አት​ሂ​ዱም አላ​ል​ኋ​ች​ሁ​ምን?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ሰዎች ኤል​ሳ​ዕን፥ “እነሆ፥ ጌታ​ችን እን​ደ​ም​ታይ የዚች ከተማ ኑሮ መል​ካም ነው፤ ውኃው ግን ክፉ ነው፤ ሴቶ​ችም ሲጠ​ጡት ይመ​ክ​ናሉ፥” አሉት።</verse>
				<verse number="20">እር​ሱም፥ “አዲስ ማሰሮ አም​ጡ​ልኝ፤ ጨውም ጨም​ሩ​በት” አለ፤ ያንም አመ​ጡ​ለት።</verse>
				<verse number="21">ውኃው ወዳ​ለ​በ​ትም ምንጭ ወጥቶ ጨው ጣለ​በ​ትና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህን ውኃ ፈው​ሼ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ህም በኋላ የሚ​ሞት፥ የሚ​መ​ክ​ንም አይ​ኖ​ርም” አለ።</verse>
				<verse number="22">ኤል​ሳ​ዕም እንደ ተና​ገ​ረው ነገር ውኃው ከዚያ ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ተፈ​ው​ሶ​አል።</verse>
				<verse number="23">ከዚ​ያም ወደ ቤቴል ወጣ፤ በመ​ን​ገ​ድም ሲወጣ ልጆች ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ወጥ​ተው፥ “አንተ ራሰ በራ! ውጣ! አንተ ራሰ በራ! ውጣ” ብለው አፌ​ዙ​በት።</verse>
				<verse number="24">ዘወ​ርም ብሎ አያ​ቸው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም ረገ​ማ​ቸው፤ ወዲ​ያ​ውም ከዱር ሁለት ድቦች ወጥ​ተው ከእ​ነ​ርሱ አርባ ሁለ​ቱን ሰባ​በ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">ከዚ​ያም ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ተራራ ሄደ፤ ከዚ​ያም ወደ ሰማ​ርያ ተመ​ለሰ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የአ​ክ​ዓብ ልጅ ኢዮ​ራም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ መን​ገሥ ጀመረ፤ ዐሥራ ሁለ​ትም ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="2">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ፤ ነገር ግን እንደ አባ​ቱና እንደ እናቱ አል​ነ​በ​ረም፤ አባ​ቱም ያሠ​ራ​ውን የበ​ዓ​ልን ምስል አጠፋ።</verse>
				<verse number="3">ነገር ግን እስ​ራ​ኤ​ልን ያሳ​ታ​ቸ​ውን የና​ባ​ጥን ልጅ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምን ኀጢ​አት ተከ​ተለ፤ እር​ሱ​ንም አል​ተ​ወም።</verse>
				<verse number="4">የሞ​ዓ​ብም ንጉሥ ሞሳ ባለ በጎች ነበር፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ መቶ ሺህ የጠ​ጕር አውራ በጎ​ች​ንና መቶ ሺህ ጠቦ​ቶ​ችን ይገ​ብ​ር​ለት ነበር።</verse>
				<verse number="5">አክ​ዓ​ብም ከሞተ በኋላ የሞ​ዓብ ንጉሥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ ከዳው።</verse>
				<verse number="6">በዚ​ያም ጊዜ ንጉሡ ኢዮ​ራም ከሰ​ማ​ርያ ወጥቶ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ቈጠ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">ወደ ይሁ​ዳም ንጉሥ ወደ ኢዮ​ሣ​ፍጥ፥ “የሞ​ዓብ ንጉሥ ከዳኝ፤ ከእኔ ጋር በሞ​ዓብ ላይ ለሰ​ልፍ ትሄ​ዳ​ለ​ህን?” ብሎ፤ ላከ። እር​ሱም፥ “እወ​ጣ​ለሁ፤ እኔ እንደ አንተ፥ አን​ተም እንደ እኔ፥ ሕዝ​ቤም እንደ ሕዝ​ብህ፥ ፈረ​ሶ​ቼም እንደ ፈረ​ሶ​ችህ ናቸው” አለ።</verse>
				<verse number="8">ደግ​ሞም፥ “በየ​ት​ኛው መን​ገድ እን​ሄ​ዳ​ለን?” አለ፤ እር​ሱም፥ “በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድረ በዳ መን​ገድ” አለው።</verse>
				<verse number="9">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉ​ሥና የይ​ሁዳ ንጉሥ፥ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ ሄዱ፤ የሰ​ባ​ትም ቀን መን​ገድ ዞሩ፤ ለሠ​ራ​ዊ​ቱና ለሚ​ጫኑ እን​ስ​ሶች ውኃ አጡ።</verse>
				<verse number="10">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሞ​ዓብ እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ እነ​ዚ​ህን ሦስ​ቱን ነገ​ሥ​ታት ጠር​ቶ​አ​ልና ወዮ!” አለ።</verse>
				<verse number="11">ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም፥ “በእ​ርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ን​ጠ​ይ​ቅ​በት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ በዚህ አይ​ገ​ኝ​ምን?” አለ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አገ​ል​ጋ​ዮች አንዱ፥ “ኤል​ያ​ስን እጁን ያስ​ታ​ጥብ የነ​በ​ረው የሣ​ፋጥ ልጅ ኤል​ሳዕ እዚህ አለ” ብሎ መለሰ።</verse>
				<verse number="12">ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በእ​ርሱ ዘንድ ይገ​ኛል” አለ። የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥና የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ ወደ እርሱ ወረዱ።</verse>
				<verse number="13">ኤል​ሳ​ዕም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ፥ “እኔ ከአ​ንተ ጋር ምን አለኝ? ወደ አባ​ትህ ነቢ​ያ​ትና ወደ እና​ትህ ነቢ​ያት ሂድ፥” አለው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ፥ “አይ​ደ​ለም፤ በሞ​ዓብ እጅ ይጥ​ላ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን ሦስት ነገ​ሥ​ታት ጠር​ቶ​አ​ልን?” አለው።</verse>
				<verse number="14">ኤል​ሳ​ዕም፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት የሠ​ራ​ዊት ጌታ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን ያፈ​ርሁ ባል​ሆን ኖሮ አን​ተን ባል​ተ​መ​ለ​ከ​ት​ሁና ባላ​የሁ ነበር።</verse>
				<verse number="15">አሁ​ንም ባለ በገና አም​ጡ​ልኝ” አለ። ባለ በገ​ና​ውም በደ​ረ​ደረ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ርሱ ላይ መጣ።</verse>
				<verse number="16">እን​ዲ​ህም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዚህ ሸለቆ ሁሉ ጕድ​ጓድ ቈፍሩ።</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላል፦ ነፋስ አታ​ዩም፤ ዝና​ብም አታ​ዩም፤ ይህ ሸለቆ ግን ውኃ ይሞ​ላል፤ እና​ን​ተም፥ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ሁም፥ እን​ስ​ሶ​ቻ​ች​ሁም፥ ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="18">ይህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይን ቀላል ነገር ነውና፤ ደግ​ሞም ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል።</verse>
				<verse number="19">የተ​መ​ሸ​ጉ​ት​ንም ከተ​ሞች ሁሉ ትመ​ታ​ላ​ችሁ፤ የሚ​ያ​ም​ሩ​ት​ንም ዛፎች ሁሉ ትቈ​ር​ጣ​ላ​ችሁ፤ የው​ኃ​ው​ንም ምን​ጮች ሁሉ ትደ​ፍ​ና​ላ​ችሁ፤ መል​ካ​ሞ​ቹ​ንም እር​ሻ​ዎች ሁሉ በድ​ን​ጋይ ታበ​ላ​ሻ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="20">በነ​ጋ​ውም መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ቀ​ር​ብ​በት ጊዜ፥ እነሆ፥ ውኃ በኤ​ዶ​ም​ያስ መን​ገድ መጣ፤ ምድ​ሪ​ቱም ውኃ ሞላች።</verse>
				<verse number="21">ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም ሁሉ እነ​ዚያ ነገ​ሥ​ታት ሊወ​ጉ​አ​ቸው እንደ መጡ በሰሙ ጊዜ፥ “ሁላ​ችሁ መሣ​ሪ​ያ​ዎ​ችን ይዛ​ችሁ ርዱን” ብለው በሀ​ገ​ራ​ቸው ሁሉ ጮኹ። ተሰ​በ​ሰ​ቡም፤ ወጥ​ተ​ውም በተ​ራ​ራው ራስ ላይ ቆሙ።</verse>
				<verse number="22">ማል​ደ​ውም ተነሡ፤ ፀሐ​ይም በው​ኃው ላይ አን​ጸ​ባ​ረቀ፤ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም በፊ​ታ​ቸው ውኃው እንደ ደም ቀልቶ አዩና፦</verse>
				<verse number="23">“ይህ የጦር ደም ነው፤ እነ​ዚያ ነገ​ሥ​ታት እርስ በር​ሳ​ቸው ተጋ​ደሉ፤ ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም ገደሉ፤ አሁ​ንም ሞዓብ ሆይ! እን​ግ​ዲህ ወደ ምር​ኮህ ሂድ” አሉ።</verse>
				<verse number="24">ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ሰፈር በመጡ ጊዜ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ተነ​ሥ​ተው ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን መቱ፤ እነ​ር​ሱም ከፊ​ታ​ቸው ሸሹ፤ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ን​ንም እየ​መቱ ወደ ሀገሩ ውስጥ ገቡ።</verse>
				<verse number="25">ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም አፈ​ረሱ፤ በመ​ል​ካ​ሞ​ቹም እር​ሻ​ዎ​ቻ​ቸው ሁሉ ላይ እስ​ኪ​ሞሉ ድረስ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው አንድ አንድ ድን​ጋይ ይጥል ነበር፤ የው​ኃ​ው​ንም ምን​ጮች ሁሉ ደፈኑ፤ የከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቅጥር አፈ​ረሱ፤ የሚ​ያ​ም​ሩ​ትን ዛፎች ሁሉ ቈረጡ፤ ባለ ወን​ጭ​ፎ​ችም ከብ​በው መቱ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">የሞ​ዓ​ብም ንጉሥ እንደ ገደ​ሉ​አ​ቸ​ውና ድል እን​ደ​ነ​ሡ​አ​ቸው ባየ ጊዜ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ሰባት መቶ ሰዎ​ችን ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ፤ ወደ ኤዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ ያልፉ ዘንድ ሞከሩ፤ አል​ቻ​ሉ​ምም።</verse>
				<verse number="27">ከዚህ በኋላ በእ​ርሱ ፋንታ ንጉሥ የሚ​ሆ​ነ​ውን የበ​ኵር ልጁን ወስዶ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በቅ​ጥሩ ላይ አቀ​ረ​በው። እስ​ራ​ኤ​ልም ታላቅ ጸጸት ተጸ​ጸቱ፤ ከዚ​ያም ርቀው ወደ ምድ​ራ​ቸው ተመ​ለሱ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ከነ​ቢ​ያ​ትም ልጆች የአ​ንዱ ሚስት የሆ​ነች አን​ዲት ሴት፥ “ባሌ ባሪ​ያህ ሞቶ​አል፤ ባሪ​ያ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው እንደ ነበረ አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ ባለ ዕዳም ሁለቱ ልጆ​ቼን ባሪ​ያ​ዎች አድ​ርጎ ሊወ​ስ​ዳ​ቸው መጥ​ቶ​አል” ብላ ወደ ኤል​ሳዕ ጮኸች።</verse>
				<verse number="2">ኤል​ሳ​ዕም፥ “አደ​ር​ግ​ልሽ ዘንድ ምን ትሻ​ለሽ? በቤ​ት​ሽም ያለ​ውን ንገ​ሪኝ” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “ለእኔ ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ከዘ​ይት ማሰሮ በቀር በቤቴ አን​ዳች የለ​ኝም” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="3">እር​ሱም፥ “ሂጂና ከጎ​ረ​ቤ​ቶ​ችሽ ሁሉ ከውጭ ባዶ ማድ​ጋ​ዎ​ችን ተዋሺ፤ አታ​ሳ​ን​ሻ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="4">ወደ ቤት​ሽም ገብ​ተሽ ከአ​ን​ቺና ከል​ጆ​ችሽ በኋላ በሩን ዝጊ፤ ወደ እነ​ዚ​ህም ማድ​ጋ​ዎች ሁሉ ዘይ​ቱን ገል​ብጪ፤ የሞ​ላ​ው​ንም ፈቀቅ አድ​ርጊ” አላት።</verse>
				<verse number="5">እን​ዲ​ሁም ከእ​ርሱ ሄዳ፥ በሩን ከእ​ር​ስ​ዋና ከል​ጆ​ችዋ በኋላ ዘጋች፤ እነ​ር​ሱም ማድ​ጋ​ዎ​ቹን ወደ እር​ስዋ ያቀ​ር​ቡ​ላት ነበር፤ እር​ስ​ዋም ትገ​ለ​ብጥ ነበር።</verse>
				<verse number="6">ከዚ​ህም በኋላ ልጆ​ች​ዋን፥ “ደግሞ ማድጋ አም​ጡ​ልኝ” አለ​ቻ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “ሌላ ማድጋ የለም” አሏት፤ ዘይ​ቱም ቆመ።</verse>
				<verse number="7">መጥ​ታም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ነገ​ረ​ችው፤ እር​ሱም፥ “ሄደሽ ዘይ​ቱን ሽጭ ዕዳ​ሽ​ንም ክፈዪ፤ በተ​ረ​ፈ​ውም ዘይት የአ​ን​ቺ​ንና የል​ጆ​ች​ሽን ሰው​ነት አድኚ” አላት።</verse>
				<verse number="8">ከዚ​ህም በኋላ አንድ ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ ኤል​ሳዕ ወደ ሱማን አለፈ፤ በዚ​ያም ታላቅ ሴት ነበ​ረች፤ እን​ጀ​ራም ይበላ ዘንድ አቆ​መ​ችው፤ በዚ​ያም ባለፈ ቍጥር እን​ጀራ ሊበላ ወደ​ዚያ ይገባ ነበር።</verse>
				<verse number="9">ሴት​ዮ​ዋም ለባ​ልዋ፥ “ይህ በእኛ ዘንድ ሁል​ጊዜ የሚ​ያ​ል​ፈው ቅዱስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ሆነ አው​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">ትንሽ ቤት በሰ​ገ​ነቱ ላይ እን​ሥራ፤ በዚ​ያም አል​ጋና ጠረ​ጴዛ፥ ወን​በ​ርና መቅ​ረዝ እና​ኑ​ር​ለት፤ ወደ እኛም ሲመጣ ወደ​ዚያ ይግባ” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="11">አንድ ቀንም ወደ​ዚያ በመጣ ጊዜ ወደ ቤቱ ገብቶ በዚያ ተኛ።</verse>
				<verse number="12">ሎሌ​ው​ንም ግያ​ዝን፥ “ይህ​ችን ሱማ​ና​ዊት ጥራ” አለው። በጠ​ራ​ትም ጊዜ በፊቱ ቆመች።</verse>
				<verse number="13">እር​ሱም፥ “እነሆ፥ ይህን ሁሉ ክብር አከ​በ​ር​ሽኝ ምን ላድ​ር​ግ​ልሽ? ለን​ጉሥ ወይስ ለሠ​ራ​ዊት አለቃ የም​ነ​ግ​ር​ልሽ ጉዳይ እን​ዳ​ለሽ በላት” አለው፤ እር​ስ​ዋም፥ “እኔ በወ​ገኔ መካ​ከል እኖ​ራ​ለሁ” ብላ መለ​ሰች።</verse>
				<verse number="14">እር​ሱም ግያ​ዝን፥ “እን​ግ​ዲህ ምን እና​ድ​ር​ግ​ላት?” አለው። ሎሌው ግያ​ዝም፤ “ልጅ የላ​ትም፥ ባል​ዋም ሸም​ግ​ሎ​አል” ብሎ መለሰ።</verse>
				<verse number="15">እር​ሱም፥ “ጥራት” አለው። ጠራ​ትም በደ​ጃ​ፉም ቆመች።</verse>
				<verse number="16">ኤል​ሳ​ዕም፥ “በሚ​መ​ጣው ዓመት በዚህ ወራት ወንድ ልጅ ትታ​ቀ​ፊ​ያ​ለሽ” አላት፤ እር​ስ​ዋም፥ “አይ​ደ​ለም ጌታዬ ሆይ፥ አገ​ል​ጋ​ይ​ህን አትዋ​ሻት” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="17">ከዚ​ያም በኋላ ሴቲቱ ፀነ​ሰች፥ በዓ​መ​ቱም ኤል​ሳዕ በነ​ገ​ራት ወራት ወንድ ልጅ ወለ​ደች።</verse>
				<verse number="18">ሕፃ​ኑም አደገ፤ እህል አጫ​ጆ​ችም ወዳ​ሉ​በት ወደ አባቱ መጣ። አባ​ቱ​ንም፥ “ራሴን ራሴን” አለው፤</verse>
				<verse number="19">አባ​ቱም ሎሌ​ውን፥ “ተሸ​ክ​መህ ወደ እናቱ ውስ​ደው” አለው።</verse>
				<verse number="20">አን​ሥ​ቶም ወደ እናቱ ወሰ​ደው፤ በጕ​ል​በ​ቷም ላይ እስከ ቀትር ድረስ አስ​ተ​ኛ​ችው፤ ሞተም።</verse>
				<verse number="21">አው​ጥ​ታም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው አልጋ ላይ አጋ​ደ​መ​ችው፤ በሩ​ንም ዘግ​ታ​በት ወጣች።</verse>
				<verse number="22">ባል​ዋ​ንም ጠርታ፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ዘንድ በፍ​ጥ​ነት እሄ​ዳ​ለ​ሁና አንድ ሎሌና አንድ አህያ ላክ​ልኝ” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="23">እር​ሱም፥ “መባቻ ወይም ሰን​በት ያይ​ደለ ዛሬ ለምን ትሄ​ጃ​ለሽ?” አለ። እር​ስ​ዋም፥ “ደኅና ነው” አለች።</verse>
				<verse number="24">አህ​ያ​ው​ንም አስ​ጭና ሎሌ​ዋን፥ “ንዳ፥ ሂድ፤ እኔ ሳላ​ዝ​ዝህ አታ​ዘ​ግ​የኝ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ ቄር​ሜ​ሎስ ተራራ እን​ሂድ” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="25">እን​ዲ​ሁም ሄደች፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ተራራ ወጣች። ኤል​ሳ​ዕም ያችን ሴት ወደ እርሱ ስት​መጣ ባያት ጊዜ ሎሌ​ውን ግያ​ዝን፥ “እነ​ኋት፥ ሱማ​ና​ዊት መጣች፤</verse>
				<verse number="26">አሁ​ንም ሩጥና ተቀ​በ​ላት፤ በደ​ኅ​ናሽ ነውን? ባልሽ ደኅና ነውን? ልጅ​ሽስ ደኅና ነውን? በላት” አለው። እር​ስ​ዋም፥ “ደኅና ነው” አለች።</verse>
				<verse number="27">ወደ ተራ​ራ​ውም ወደ ኤል​ሳዕ ደርሳ እግ​ሮ​ቹን ጨበ​ጠች፤ ግያ​ዝም ሊያ​ር​ቃት መጣ፤ ኤል​ሳ​ዕም፥ “ነፍ​ስዋ አዝ​ና​ለ​ችና ተዋት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያን ከእኔ ሰው​ሮ​ታል፤ አል​ነ​ገ​ረ​ኝ​ምም” አለ።</verse>
				<verse number="28">እር​ስ​ዋም፥ “በውኑ ከጌ​ታዬ ልጅን ለመ​ን​ሁን? እኔም አታ​ታ​ል​ለኝ አላ​ል​ሁ​ህ​ምን?” አለች።</verse>
				<verse number="29">ኤል​ሳ​ዕም ግያ​ዝን፥ “ወገ​ብ​ህን ታጠቅ፤ በት​ሬ​ንም በእ​ጅህ ይዘህ ሂድ፤ ሰውም ብታ​ገኝ ሰላም አት​በል፤ እር​ሱም ሰላም ቢልህ አት​መ​ል​ስ​ለት፤ በት​ሬ​ንም በሕ​ፃኑ ፊት ላይ አኑር” አለው።</verse>
				<verse number="30">የሕ​ፃ​ኑም እናት፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ሕያው ነፍ​ስ​ህ​ንም! አል​ተ​ው​ህም” አለች፤ ኤል​ሳ​ዕም ተነ​ሥቶ ተከ​ተ​ላት።</verse>
				<verse number="31">ግያ​ዝም በፊ​ታ​ቸው ይሄድ ነበር፤ ግያ​ዝም ቀድ​ሞ​አ​ቸው ደረሰ፤ በት​ሩ​ንም በሕ​ፃኑ ፊት ላይ አኖ​ረው፤ ነገር ግን ድምፅ ወይም መስ​ማት አል​ነ​በ​ረም፤ እር​ሱ​ንም ሊገ​ና​ኘው ተመ​ልሶ፥ “ሕፃኑ አል​ተ​ነ​ሣም” ብሎ ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="32">ኤል​ሳ​ዕም ወደ ቤት በገባ ጊዜ እነሆ፥ ሕፃኑ ሞቶ በአ​ል​ጋው ላይ ተጋ​ድሞ ነበር።</verse>
				<verse number="33">ኤል​ሳ​ዕም ወደ ቤት ገብቶ በሩን በሁ​ለቱ ላይ ዘጋ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸለየ።</verse>
				<verse number="34">መጥ​ቶም በሕ​ፃኑ ላይ ተኛ፤ አፉ​ንም በአፉ፥ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም በዐ​ይ​ኖቹ፥ እጆ​ቹ​ንም በእ​ጆቹ ላይ አድ​ርጎ ተጋ​ደ​መ​በት፤ የሕ​ፃ​ኑም ሰው​ነት ሞቀ።</verse>
				<verse number="35">ተመ​ል​ሶም በቤቱ ውስጥ አንድ ጊዜ ወዲ​ህና ወዲያ ተመ​ላ​ለሰ፤ ደግ​ሞም ወጥቶ ሰባት ጊዜ በሕ​ፃኑ ላይ ተጋ​ደመ፤ ከዚ​ያም በኋላ ሕፃኑ ዐይ​ኖ​ቹን ከፈተ።</verse>
				<verse number="36">ግያ​ዝ​ንም ጠርቶ፥ “ይህ​ችን ሱማ​ና​ዊት ጥራ” አለው። ጠራ​ትም፤ ወደ እር​ሱም በገ​ባች ጊዜ፥ “ልጅ​ሽን አን​ሥ​ተሽ ውሰጂ” አላት።</verse>
				<verse number="37">ሴት​ዮ​ዋም ገብታ በእ​ግሩ አጠ​ገብ ወደ​ቀች በም​ድ​ርም ላይ ሰገ​ደች፤ ልጅ​ዋ​ንም አን​ሥታ ወጣች።</verse>
				<verse number="38">ኤል​ሳ​ዕም ዳግ​መኛ ወደ ጌል​ጌላ ተመ​ለሰ፤ በም​ድ​ርም ላይ ራብ ነበረ፤ የነ​ቢ​ያ​ትም ልጆች በፊቱ ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ ኤል​ሳ​ዕም ሎሌ​ውን፥ “ታላ​ቁን ምን​ቸት ጣድ፤ ለነ​ቢ​ያ​ትም ልጆች ቅጠላ ቅጠል አብ​ስ​ል​ላ​ቸው” አለው።</verse>
				<verse number="39">አን​ዱም ቅጠላ ቅጠል ያመጣ ዘንድ ወደ ሜዳ ወጣ፤ በም​ድረ በዳ​ውም የወ​ይን ቦታ አገኘ፤ ከዚ​ያም የም​ድር ቅጠላ ቅጠል ሰብ​ሰበ፤ ልብ​ሱ​ንም ሞላ፤ መት​ሮም በወጡ ምን​ቸት ውስጥ ጨመ​ረው፤ አበ​ሰ​ለ​ውም፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላ​ወ​ቁም።</verse>
				<verse number="40">ከዚ​ህም በኋላ ሰዎቹ ይበሉ ዘንድ አቀ​ረ​በ​ላ​ቸው፤ የበ​ሰ​ለ​ው​ንም ቅጠል በሚ​በ​ሉ​በት ጊዜ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ፥ በም​ን​ቸቱ ውስጥ መርዝ አለ” ብለው ጮኹ፤ ይበ​ሉም ዘንድ አል​ቻ​ሉም።</verse>
				<verse number="41">ኤል​ሳ​ዕም፥ “ዶቄት አም​ጣና በም​ን​ቸቱ ውስጥ ጨም​ረው” አለው፥ ኤል​ሳ​ዕም ግያ​ዝን፥ “ለሕ​ዝቡ መል​ስ​ላ​ቸው ይብሉ” አለው። ከዚ​ህም በኋላ በም​ን​ቸቱ ውስጥ ክፉ ነገር አል​ተ​ገ​ኘም።</verse>
				<verse number="42">አንድ ሰውም ከቤ​ት​ሣ​ሪሳ ከእ​ህሉ ቀዳ​ም​ያት፥ ሃያ የገ​ብስ እን​ጀራ፥ የእ​ህ​ልም እሸት በአ​ቁ​ማዳ ይዞ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው መጣ፤ ኤል​ሳ​ዕም አገ​ል​ጋ​ዩን፥ “ይበሉ ዘንድ ለሕ​ዝቡ ስጣ​ቸው” አለ።</verse>
				<verse number="43">ሎሌ​ውም፥ “ይህን እን​ዴት አድ​ርጌ ለመቶ ሰው አቀ​ር​ባ​ለሁ?” አለ። እር​ሱም፥ “ይበ​ላሉ፥ ያተ​ር​ፋ​ሉም ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና ይበሉ ዘንድ ለሕ​ዝቡ ስጣ​ቸው” አለው።</verse>
				<verse number="44">እር​ሱም አቀ​ረ​በ​ላ​ቸው፤ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል በሉ፤ አተ​ረ​ፉም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">የሶ​ርያ ንጉሥ ሠራ​ዊት አለቃ ንዕ​ማ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ርሱ እጅ ለሶ​ርያ ደኅ​ን​ነ​ትን ስለ ሰጠ፥ በጌ​ታው ዘንድ ታላ​ቅና ክቡር ሰው ነበረ፤ ሰው​ዬ​ውም ጽኑዕ፥ ኀያል ነበረ፤ ነገር ግን ለም​ጻም ነበረ።</verse>
				<verse number="2">ከሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንም ጋር ወደ ሰልፍ በወጣ ጊዜ ከእ​ስ​ራ​ኤል ምድር ታናሽ ብላ​ቴና ሴት ማረከ፤ ለሚ​ስ​ቱም አገ​ል​ጋይ አደ​ረ​ጋት።</verse>
				<verse number="3">እመ​ቤ​ቷ​ንም፥ “ጌታዬ በሰ​ማ​ርያ ወደ​ሚ​ኖ​ረው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ ነቢዩ ይሄድ ዘንድ በተ​ገ​ባው ነበር፤ ከለ​ም​ጹም በፈ​ወ​ሰው ነበር” አለ​ቻት።</verse>
				<verse number="4">ሚስ​ቱም ወደ እርሱ ገብታ፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ሀገር የመ​ጣች ይች ብላ​ቴና እን​ደ​ዚ​ህና እን​ደ​ዚህ አለች” ብላ ነገ​ረ​ችው።</verse>
				<verse number="5">የሶ​ር​ያም ንጉሥ ንዕ​ማ​ንን፥ “ሂድ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ደብ​ዳቤ እል​ካ​ለሁ” አለው። እር​ሱም ሄደ፤ ዐሥ​ርም መክ​ሊት ብር፥ ስድ​ስት ሺህም ወቄት ወርቅ፥ ዐሥ​ርም መለ​ወጫ ልብስ በእጁ ወሰደ።</verse>
				<verse number="6">ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ፦ ደብ​ዳ​ቤ​ውን አደ​ረሰ። ደብ​ዳ​ቤ​ውም እን​ዲህ ይላል፥ “ደብ​ዳ​ቤው ካንተ ዘንድ በደ​ረሰ ጊዜ ባለ​ሟ​ሌን ንዕ​ማ​ንን ወደ አንተ ልኬ​ዋ​ለ​ሁና ከለ​ምጹ ፈው​ሰው።”</verse>
				<verse number="7">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ደብ​ዳ​ቤ​ውን ባነ​በበ ጊዜ ልብ​ሱን ቀድዶ፥ “ሰውን ከለ​ምጹ እፈ​ውስ ዘንድ ይህ ሰው ወደ እኔ መስ​ደዱ እኔ በውኑ ለመ​ግ​ደ​ልና ለማ​ዳን የም​ችል አም​ላክ ነኝን? ተመ​ል​ከቱ፥ የጠብ ምክ​ን​ያት እን​ደ​ሚ​ፈ​ል​ግ​ብኝ ተመ​ል​ከቱ” አለ።</verse>
				<verse number="8">ኤል​ሳ​ዕም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ልብ​ሱን እንደ ቀደደ በሰማ ጊዜ፥ “ልብ​ስ​ህን ለምን ቀደ​ድህ? ንዕ​ማን ወደ እኔ ይምጣ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ነቢይ እን​ዳለ ያው​ቃል” ብሎ ወደ ንጉሡ ላከ።</verse>
				<verse number="9">ንዕ​ማ​ንም በፈ​ረ​ሱና በሰ​ረ​ገ​ላው መጣ፤ በኤ​ል​ሳ​ዕም ቤት ደጃፍ ውጭ ቆመ።</verse>
				<verse number="10">ኤል​ሳ​ዕም፥ “ሂድ፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ሰባት ጊዜ ተጠ​መቅ፤ ሰው​ነ​ት​ህም ይፈ​ወ​ሳል፤ አን​ተም ንጹሕ ትሆ​ና​ለህ” ብሎ ወደ እርሱ መል​እ​ክ​ተኛ ላከ።</verse>
				<verse number="11">ንዕ​ማን ግን ተቈ​ጥቶ ሄደ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነሆ፥ ወደ እኔ የሚ​መጣ፥ ቆሞም የአ​ም​ላ​ኩን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም የሚ​ጠራ፥ የለ​ም​ጹ​ንም ስፍራ በእጁ ዳስሶ የሚ​ፈ​ው​ሰኝ መስ​ሎኝ ነበር።</verse>
				<verse number="12">የደ​ማ​ስቆ ወን​ዞች ባብ​ናና ፋርፋ ከእ​ስ​ራ​ኤል ውኆች ሁሉ አይ​ሻ​ሉ​ምን? ሄጄስ በእ​ነ​ርሱ ውስጥ መጠ​መ​ቅና መን​ጻት አይ​ቻ​ለ​ኝም ኖሮ​አ​ልን?” ብሎ በቍጣ ተመ​ልሶ ሄደ።</verse>
				<verse number="13">አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ወደ እርሱ መጥ​ተው፥ “ነቢዩ ታላቅ ነገር ቢነ​ግ​ርህ ባደ​ረ​ግ​ኸው ነበር፤ ይል​ቁ​ንስ፦ ተጠ​መ​ቅና ንጹሕ ሁን ቢልህ እን​ዴት ነዋ!” ብለው ተና​ገ​ሩት።</verse>
				<verse number="14">ንዕ​ማ​ንም ወረደ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው ኤል​ሳዕ እንደ ተና​ገ​ረው በዮ​ር​ዳ​ኖስ ሰባት ጊዜ ተጠ​መቀ፤ ሰው​ነ​ቱም እንደ ገና እንደ ትንሽ ብላ​ቴና ሰው​ነት ሆኖ ተመ​ለሰ፤ ንጹ​ሕም ሆነ።</verse>
				<verse number="15">እር​ሱም ከጭ​ፍ​ራው ሁሉ ጋር ወደ ኤል​ሳዕ ተመ​ለሰ፤ ወደ እር​ሱም ደርሶ በፊቱ ቆመና፥ “እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነው እንጂ በም​ድር ሁሉ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ዐወ​ቅሁ፤ አሁ​ንም ከአ​ገ​ል​ጋ​ይህ በረ​ከት ተቀ​በል” አለው።</verse>
				<verse number="16">ኤል​ሳ​ዕም፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! አል​ቀ​በ​ልም” አለ። ይቀ​በ​ለ​ውም ዘንድ ግድ አለው፤ እርሱ ግን እንቢ አለ።</verse>
				<verse number="17">ንዕ​ማ​ንም፥ “እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀር ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ወይም ሌላ መሥ​ዋ​ዕት አላ​ቀ​ር​ብ​ምና ሁለት የበ​ቅሎ ጭነት አፈር ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ይስ​ጡት።</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ኔን የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ኀጢ​አት በዚህ ነገር ብቻ ይቅር ይበ​ለኝ፤ ጌታዬ በዚያ ይሰ​ግድ ዘንድ እጄን ተደ​ግፎ ወደ ሬማን ቤት በገ​ባና በሰ​ገደ ጊዜ፥ እኔም በሬ​ማን ቤት በሰ​ገ​ድሁ ጊዜ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ነገር እኔን አገ​ል​ጋ​ይ​ህን ይቅር ይለ​ኛል” አለ።</verse>
				<verse number="19">ኤል​ሳ​ዕም ንዕ​ማ​ንን፥ “በሰ​ላም ሂድ” አለው። ጥቂት መን​ገ​ድም ከእ​ርሱ ራቀ።</verse>
				<verse number="20">የኤ​ል​ሳ​ዕም ሎሌ ግያዝ፥ “ጌታዬ ሶር​ያ​ዊ​ውን ይህን ንዕ​ማ​ንን ማረው፤ ካመ​ጣ​ለ​ትም ነገር ምንም አል​ተ​ቀ​በ​ለም፤ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በስ​ተ​ኋ​ላው እሮ​ጣ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም አን​ዳች እወ​ስ​ዳ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="21">ግያ​ዝም ንዕ​ማ​ንን ተከ​ተ​ለው፤ ንዕ​ማ​ንም ዘወር ብሎ ወደ እርሱ ሲሮጥ ባየው ጊዜ ሊገ​ና​ኘው ከሰ​ረ​ገ​ላው ወርዶ፥ “ሁሉ ደኅና ነውን?” አለው።</verse>
				<verse number="22">እር​ሱም፥ “ሁሉ ደኅና ነው፦ አሁን ከነ​ቢ​ያት ወገን የሆኑ ሁለት ጐል​ማ​ሶች ከተ​ራ​ራ​ማው ከኤ​ፍ​ሬም ሀገር ወደ እኔ መጥ​ተ​ዋ​ልና፤ አንድ መክ​ሊት ብርና ሁለት መለ​ወጫ ልብስ ትሰ​ጣ​ቸው ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ ብሎ ጌታዬ ላከኝ” አለው።</verse>
				<verse number="23">ንዕ​ማ​ንም፥ “ሁለት የብር መክ​ሊት ውሰድ” አለው፤ ሁለ​ቱ​ንም መክ​ሊት ብር ተቀ​ብሎ በሁ​ለት ከረ​ጢት ውስጥ ጨመ​ረና ከሁ​ለት መለ​ወጫ ልብስ ጋር ለሁ​ለት ሎሌ​ዎቹ አስ​ያዘ፤ እነ​ር​ሱም ተሸ​ክ​መው በፊቱ ሄዱ።</verse>
				<verse number="24">ወደ ስውር ቦታም በደ​ረሱ ጊዜ ከእ​ጃ​ቸው ወስዶ በቤቱ ውስጥ አኖ​ራ​ቸው፤ ሰዎ​ቹ​ንም አሰ​ና​በተ።</verse>
				<verse number="25">ከዚ​ህም በኋላ ገብቶ፥ በጌ​ታው ፊት ቆመ፤ ኤል​ሳ​ዕም፥ “ግያዝ ሆይ፥ ከወ​ዴት መጣህ?” አለው። እር​ሱም፥ “እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ወዴ​ትም አል​ሄ​ድ​ሁም” አለ።</verse>
				<verse number="26">እር​ሱም፥ “ያ ሰው ከሰ​ረ​ገ​ላው ወርዶ ሊቀ​በ​ልህ በተ​መ​ለሰ ጊዜ ልቤ ከአ​ንተ ጋር አል​ሄ​ደ​ምን? አሁ​ንም ወር​ቁ​ንና ልብ​ሱን፥ ተቀ​ብ​ለ​ሃል፤ ለወ​ይን ቦታ፥ ለመ​ሰ​ማ​ርያ ቦታና ለዘ​ይት ቦታ፥ ለላ​ሞ​ችና ለበ​ጎች፥ ለወ​ን​ዶ​ችና ለሴ​ቶች ባሮች ይሁ​ንህ።</verse>
				<verse number="27">ነገር ግን የን​ዕ​ማን ለምጽ በአ​ን​ተና በዘ​ርህ ላይ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይመ​ለስ” አለው። እንደ በረ​ዶም ለም​ጻም ሆኖ ከእ​ርሱ ዘንድ ወጣ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">የነ​ቢ​ያ​ትም ልጆች ኤል​ሳ​ዕን፥ “እነሆ፥ በፊ​ትህ የም​ና​ድ​ር​በት ቤት ጠብ​ቦ​ናል።</verse>
				<verse number="2">ወደ ዮር​ዳ​ኖ​ስም እን​ሂድ፤ ከእ​ኛም እያ​ን​ዳ​ንዱ ከዚያ ምሰሶ ያምጣ፥ የም​ና​ድ​ር​በ​ትም ቤት እን​ሥራ፥” አሉት፤ እር​ሱም፥ “ሂዱ” አለ።</verse>
				<verse number="3">ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ፥ “አንተ ደግሞ ከእኛ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ጋር ለመ​ሄድ ና” አለ። ኤል​ሳ​ዕም፥ “እሽ እኔም እመ​ጣ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="4">ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሄደ፤ ወደ ዮር​ዳ​ኖ​ስም በደ​ረሱ ጊዜ እን​ጨት ቈረጡ።</verse>
				<verse number="5">ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ ዛፉን ሲቈ​ርጥ የም​ሳሩ ብረት ወልቆ ወደ ውኃው ውስጥ ወደቀ፤ እር​ሱም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ወየው! ወየው! የተ​ዋ​ስ​ሁት ነበር” ብሎ ጮኸ።</verse>
				<verse number="6">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው፥ “የወ​ደ​ቀው ወዴት ነው?” አለ፤ ስፍ​ራ​ው​ንም አሳ​የው፤ ከእ​ን​ጨ​ትም ቅር​ፊት ቀርፎ በዚያ ጣለው፤ ብረ​ቱም ተን​ሳ​ፈፈ።</verse>
				<verse number="7">እር​ሱም፥ “እነሆ፥ ምሳ​ርህ ውሰ​ደው” አለ፤ እጁ​ንም ዘር​ግቶ ወሰ​ደው።</verse>
				<verse number="8">የሶ​ር​ያም ንጉሥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ይዋጋ ነበር፤ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ጋር ተማ​ክሮ፥ “በዚህ ስውር ቦታ ተደ​ብ​ቀን እና​ድ​ራ​ለን።” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ኤል​ሳ​ዕም፥ “ሶር​ያ​ው​ያን በዚያ ተደ​ብ​ቀ​ዋ​ልና በዚያ ስፍራ እን​ዳ​ታ​ልፍ ተጠ​ን​ቀቅ” ብሎ ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ላከ።</verse>
				<verse number="10">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኤል​ሳዕ ወደ ነገ​ረው ስፍራ ላከ፤ አንድ ጊዜም ሳይ​ሆን፥ ሁለት ጊዜም ሳይ​ሆን በዚያ ራሱን አዳነ።</verse>
				<verse number="11">የሶ​ር​ያም ንጉሥ መን​ፈስ ስለ​ዚህ እጅግ ተበ​ሳ​ጨች፤ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ጠርቶ፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ማን እን​ደ​ሚ​ነ​ግ​ረው አት​ነ​ግ​ሩ​ኝ​ምን?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም አንዱ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ሀገር ነቢዩ ኤል​ሳዕ ያለ አይ​ደ​ለ​ምን? በእ​ል​ፍ​ኝህ ውስጥ ሆነህ የም​ት​ና​ገ​ረ​ው​ንና ቃል​ህን ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እርሱ ይነ​ግ​ረ​ዋል፤” አለ።</verse>
				<verse number="13">እር​ሱም፥ “ልኬ አስ​ይ​ዘው ዘንድ ሄዳ​ችሁ ወዴት እንደ ሆነ ዕወቁ፤” አለ። እነ​ር​ሱም፥ “እነሆ፥ በዶ​ታ​ይን አለ” ብለው ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="14">ወደ​ዚ​ያም ፈረ​ሶ​ች​ንና ሰረ​ገ​ሎ​ችን ብዙም ጭፍራ ላከ፤ በሌ​ሊ​ትም መጥ​ተው ከተ​ማ​ዪ​ቱን ከበ​ቡ​አት።</verse>
				<verse number="15">የኤ​ል​ሳ​ዕም ሎሌ ማለዳ ነቃ፤ ተነ​ሥ​ቶም በወጣ ጊዜ፥ እነሆ፥ በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዙሪያ ጭፍ​ሮች ከተ​ማ​ዋን ከብ​በ​ዋት አየ። ፈረ​ሶ​ችና ሰረ​ገ​ሎ​ችም ነበሩ። ሎሌ​ውም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! ምን እና​ድ​ርግ?” አለው።</verse>
				<verse number="16">እር​ሱም፥ “ከእኛ ጋር ያሉት ከእ​ነ​ርሱ ጋር ካሉት ይበ​ል​ጣ​ሉና አት​ፍራ” አለው።</verse>
				<verse number="17">ኤል​ሳ​ዕም፥ “አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዐይ​ኖ​ቹን፥ እባ​ክህ፥ ግለጥ” ብሎ ጸለየ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የብ​ላ​ቴ​ና​ውን ዐይ​ኖች ገለጠ፤ እነ​ሆም፥ የእ​ሳት ፈረ​ሶ​ችና ሰረ​ገ​ሎች በኤ​ል​ሳዕ ዙሪያ ተራ​ራ​ውን ሞል​ተ​ውት አየ።</verse>
				<verse number="18">ወደ እር​ሱም በወ​ረዱ ጊዜ ኤል​ሳዕ፥ “አቤቱ፥ እነ​ዚ​ህን ሰዎች አሳ​ው​ራ​ቸው” ብሎ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለየ። ኤል​ሳ​ዕም እንደ ተና​ገ​ረው ቃል አሳ​ወ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">ኤል​ሳ​ዕም፥ “መን​ገዱ በዚህ አይ​ደ​ለም፥ ከተ​ማ​ዪ​ቱም ይህች አይ​ደ​ለ​ችም፤ የም​ት​ሹ​ትን ሰው አሳ​ያ​ችሁ ዘንድ ተከ​ተ​ሉኝ” አላ​ቸው፤ ወደ ሰማ​ር​ያም ወሰ​ዳ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">ወደ ሰማ​ር​ያም በገቡ ጊዜ ኤል​ሳዕ፥ “አቤቱ፥ ያዩ ዘንድ የእ​ነ​ዚ​ህን ሰዎች ዐይ​ኖች ግለጥ” አለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ገለጠ፤ እነ​ር​ሱም አዩ። እነ​ሆም፥ በሰ​ማ​ርያ መካ​ከል እን​ዳሉ ዐወቁ።</verse>
				<verse number="21">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ባያ​ቸው ጊዜ ኤል​ሳ​ዕን፥ “አባቴ ሆይ፥ ልግ​ደ​ላ​ቸ​ውን?” አለው።</verse>
				<verse number="22">እር​ሱም፥ “በሰ​ይ​ፍ​ህና በቀ​ስ​ትህ የማ​ረ​ክ​ሃ​ቸ​ውን ግደል እንጂ በሰ​ይ​ፍ​ህና በቀ​ስ​ትህ የማ​ረ​ክ​ሃ​ቸው አይ​ደ​ሉ​ምና አት​ግ​ደ​ላ​ቸው። ይል​ቁ​ንስ እን​ጀ​ራና ውኃ በፊ​ታ​ቸው አቅ​ር​ብ​ላ​ቸው፤ በል​ተ​ውና ጠጥ​ተ​ውም ወደ ጌታ​ቸው ይመ​ለሱ” አለው።</verse>
				<verse number="23">ብዙም መብል አዘ​ጋ​ጀ​ላ​ቸው፤ በበ​ሉና በጠጡ ጊዜም አሰ​ና​በ​ታ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ወደ ጌታ​ቸው ሄዱ። ከዚ​ያም በኋላ የሶ​ር​ያ​ው​ያን አደጋ ጣዮች ዳግ​መኛ ወደ እስ​ራ​ኤል ሀገር አል​መ​ጡም።</verse>
				<verse number="24">ከዚ​ያም በኋላ የሶ​ርያ ንጉሥ ወልደ አዴር ሠራ​ዊ​ቱን ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ ወጥ​ቶም ሰማ​ር​ያን ከበ​ባት፤ በዚ​ያም ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="25">በሰ​ማ​ር​ያም ታላቅ ራብ ሆኖ ነበር፤ እነ​ሆም፥ የአ​ህያ ራስ በኀ​ምሳ ብር፥ የድ​ርጎ አንድ አራ​ተኛ የሚ​ሆን ኵስሐ ርግ​ብም በአ​ም​ስት ብር እስ​ኪ​ሽጥ ድረስ ከበ​ቡ​አት።</verse>
				<verse number="26">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በቅ​ጥር ላይ ሲመ​ላ​ለስ አን​ዲት ሴት፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ርዳኝ” ብላ ወደ እርሱ ጮኸች።</verse>
				<verse number="27">እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካል​ረ​ዳሽ እኔ እን​ዴት እረ​ዳ​ሻ​ለሁ? ከአ​ው​ድ​ማው ወይስ ከመ​ጭ​መ​ቂ​ያው ነውን?” አለ።</verse>
				<verse number="28">ንጉ​ሡም፥ “ምን ሆነ​ሻል?” አላት፤ እር​ስ​ዋም፥ “ይህች ሴት፦ ዛሬ እን​ድ​ን​በ​ላው ልጅ​ሽን አምጪ፤ ነገም ልጄን እን​በ​ላ​ለን አለ​ችኝ።</verse>
				<verse number="29">ልጄ​ንም ቀቅ​ለን በላ​ነው፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም፦ እን​ድ​ን​በ​ላው ልጅ​ሽን አምጪ አል​ኋት፤ ልጅ​ዋ​ንም ሸሸ​ገ​ችው” ብላ መለ​ሰ​ች​ለት።</verse>
				<verse number="30">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ የሴ​ቲ​ቱን ቃል ሰምቶ ልብ​ሱን ቀደደ፤ በቅ​ጥ​ርም ይመ​ላ​ለስ ነበር፤ ሕዝ​ቡም በስ​ተ​ው​ስጥ በሥ​ጋው ላይ ለብ​ሶት የነ​በ​ረ​ውን ማቅ አዩ።</verse>
				<verse number="31">ንጉ​ሡም፥ “የሣ​ፋጥ ልጅ የኤ​ል​ሳዕ ራስ ዛሬ በላዩ ያደረ እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ያድ​ር​ገኝ እን​ዲ​ህም ይግ​ደ​ለኝ” አለ።</verse>
				<verse number="32">ኤል​ሳዕ ግን በቤቱ ተቀ​ምጦ ነበር፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ከእ​ርሱ ጋር ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ ንጉ​ሡም በፊቱ ከሚ​ቆ​ሙት አንድ ሰው ላከ፤ መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውም ገና ሳይ​ደ​ርስ ለሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች፥ “ይህ የነ​ፍሰ ገዳይ ልጅ ራሴን ይቈ​ርጥ ዘንድ እንደ ላከ እዩ፤ መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውም በመጣ ጊዜ ደጁን ዘግ​ታ​ችሁ ከል​ክ​ሉት፤ በደ​ጅም ይቆም ዘንድ ተዉት፤ የጌ​ታው የእ​ግሩ ኮቴ በኋ​ላው ነው” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="33">ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሲነ​ጋ​ገር እነሆ፥ መል​እ​ክ​ተ​ኛው ወደ እርሱ ደረሰ፤ እር​ሱም፥ “እነሆ፥ ይህ ክፉ ነገር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ገና እጠ​ብቅ ዘንድ ምን​ድን ነኝ?” አለ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">ኤል​ሳ​ዕም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ነገ በዚህ ጊዜ በሰ​ማ​ርያ በር፥ ሁለት መስ​ፈ​ሪያ ገብስ በአ​ንድ ሰቅል አንድ መስ​ፈ​ሪያ መል​ካም ዱቄ​ትም በአ​ንድ ሰቅል ይሸ​መ​ታል” አለው።</verse>
				<verse number="2">ንጉ​ሡም በእጁ ተደ​ግ​ፎት የሚ​ቆም የነ​በረ ያ ብላ​ቴና ለኤ​ል​ሳዕ መልሶ፥ “እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማይ የእ​ህል ሿሿቴ ቢያ​ደ​ርግ ይህ ነገር ይሆ​ና​ልን?” አለው። ኤል​ሳ​ዕም፥ “እነሆ፥ በዐ​ይ​ኖ​ችህ ታየ​ዋ​ለህ፤ ከዚያ ግን አት​ቀ​ም​ስም” አለ።</verse>
				<verse number="3">በከ​ተ​ማ​ዋም በር አራት ለም​ጻ​ሞች ሰዎች ነበሩ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “እስ​ክ​ን​ሞት ድረስ በዚህ ለምን እን​ቀ​መ​ጣ​ለን?</verse>
				<verse number="4">ወደ ከተማ ብን​ገባ ራብ በከ​ተማ አለና፥ በዚያ እን​ሞ​ታ​ለን፤ በዚ​ህም ብን​ቀ​መጥ እን​ሞ​ታ​ለን። እን​ግ​ዲህ ኑ፥ ወደ ሶር​ያ​ው​ያን ሰፈር እን​ሂድ፤ በሕ​ይ​ወት ቢያ​ኖ​ሩን እን​ኖ​ራ​ለን፤ ቢገ​ድ​ሉ​ንም እን​ሞ​ታ​ለን” ተባ​ባሉ።</verse>
				<verse number="5">በጨ​ለ​ማም ወደ ሶር​ያ​ው​ያን ሰፈር ይሄዱ ዘንድ ተነሡ፤ ወደ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ሰፈር መጀ​መ​ሪያ ዳርቻ በመጡ ጊዜ፥ እነሆ፥ በዚያ ማንም ሰው አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሶ​ር​ያ​ው​ያን የሰ​ረ​ገላ ድምፅ፥ የፈ​ረስ ድም​ፅና የብዙ ጭፍራ ድምፅ አሰ​ምቶአ​ቸ​ዋ​ልና፥ እርስ በር​ሳ​ቸው “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ይከ​ቡን ዘንድ የኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንና የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንን ነገ​ሥት ቀጥሮ አም​ጥ​ቶ​ብ​ናል” ይባ​ባሉ ነበር።</verse>
				<verse number="7">ስለ​ዚ​ህም ተነ​ሥ​ተው በጨ​ለማ ሸሹ፤ ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንና ፈረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን፥ አህ​ዮ​ቻ​ቸ​ው​ንና ሰፈ​ሩን እን​ዳለ ትተው ነፍ​ሳ​ቸ​ውን ያድኑ ዘንድ ሸሹ።</verse>
				<verse number="8">እነ​ዚ​ያም ለም​ጻ​ሞች ወደ ሰፈሩ መጀ​መ​ሪያ ዳርቻ በመጡ ጊዜ ወደ አንድ ድን​ኳን ገብ​ተው በሉ፤ ጠጡም፤ ከዚ​ያም ወር​ቅና ብር ልብ​ስም ወሰዱ፤ ሄደ​ውም ሸሸ​ጉት፤ ተመ​ል​ሰ​ውም ወደ ሌላ ድን​ኳን ገቡ፤ ከዚ​ያም ደግሞ ወስ​ደው ሸሸጉ።</verse>
				<verse number="9">ከዚ​ያም ወዲያ እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “መል​ካም አላ​ደ​ረ​ግ​ንም፤ ዛሬ የመ​ል​ካም ምሥ​ራች ቀን ነው፤ እኛ ዝም ብለ​ናል፤ እስ​ኪ​ነ​ጋም ድረስ ብን​ቆይ በደ​ለ​ኞች እን​ሆ​ና​ለን፤ ኑ፥ እን​ሂድ፤ ለን​ጉሥ ቤተ​ሰ​ብም እን​ና​ገር” ተባ​ባሉ።</verse>
				<verse number="10">ገብ​ተ​ውም በከ​ተ​ማው በር ጮኹ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ተና​ገሩ፥ “ወደ ሶር​ያ​ው​ያን ሰፈር ገባን፤ እነ​ሆም፥ ፈረ​ሶ​ችና አህ​ዮች ታስ​ረው፥ ድን​ኳ​ኖ​ችም ተተ​ክ​ለው ነበር እንጂ ያገ​ኘ​ነው አል​ነ​በ​ረም፤ የሰ​ውም ድምፅ አል​ነ​በ​ረም።”</verse>
				<verse number="11">የደ​ጁም ጠባ​ቂ​ዎች ለን​ጉሡ ይነ​ግሩ ዘንድ ወደ ውስጥ ገቡ፤ ለን​ጉ​ሡም ቤት አወሩ።</verse>
				<verse number="12">ንጉ​ሡም በሌ​ሊት ተነ​ሥቶ ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “ሶር​ያ​ው​ያን ያደ​ረ​ጉ​ብ​ንን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ እንደ ተራ​ብን ያው​ቃሉ፤ ስለ​ዚህ፦ ከከ​ተ​ማ​ይቱ በወጡ ጊዜ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው እን​ይ​ዛ​ቸ​ዋ​ለን፤ ወደ ከተ​ማም እን​ገ​ባ​ለን ብለው በሜዳ ይሸ​ሸጉ ዘንድ ከሰ​ፈሩ ወጥ​ተ​ዋል” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አንዱ መልሶ፥ “እዚህ ከቀ​ሩት ፈረ​ሶች አም​ስት ይው​ሰዱ፤ እነሆ፥ እነ​ርሱ በቀ​ሩት በእ​ስ​ራ​ኤል ቍጥር ናቸው፥ እን​ስ​ደ​ድና ይዩ” አለ።</verse>
				<verse number="14">ሁለት ፈረ​ሰ​ኞ​ች​ንም ወሰዱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥም፥ “ሄዳ​ችሁ እዩ” ብሎ የሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንን ንጉሥ ይከ​ተ​ሉት ዘንድ ላከ።</verse>
				<verse number="15">በኋ​ላ​ቸ​ውም እስከ ዮር​ዳ​ኖስ ድረስ ተከ​ት​ለ​ዋ​ቸው ሄዱ፤ እነ​ሆም፥ ሶር​ያ​ው​ያን ሲሸሹ የጣ​ሉት ልብ​ስና ዕቃ መን​ገ​ዱን ሁሉ ሞልቶ አገኙ። እነ​ዚያ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ተመ​ል​ሰው ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="16">ሕዝ​ቡም ወጥቶ የሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንን ሰፈር በዘ​በዘ፤ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል አንድ መስ​ፈ​ሪያ መል​ካም ዱቄት በአ​ንድ ሰቅል፥ ሁለት መስ​ፈ​ሪያ ገብ​ስም በአ​ንድ ሰቅል ተሸ​መተ።</verse>
				<verse number="17">ንጉ​ሡም ያን እጁን ይደ​ግ​ፈው የነ​በ​ረ​ውን ብላ​ቴና በሩን ይጠ​ብቅ ዘንድ አቆ​መው። ሕዝ​ቡም በበሩ ረገ​ጠው፥ መል​እ​ክ​ተ​ኛው ወደ እርሱ በወ​ረደ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ተና​ገ​ረ​ውም ሞተ።</verse>
				<verse number="18">ኤል​ሳ​ዕም ለን​ጉሡ፥ “ነገ በዚህ ጊዜ በሰ​ማ​ርያ በር ሁለት መስ​ፈ​ሪያ ገብስ በአ​ንድ ሰቅል፥ አንድ መስ​ፈ​ሪያ መል​ካም ዱቄ​ትም በአ​ንድ ሰቅል፥ ይሸ​መ​ታል” ብሎ እንደ ተና​ገ​ረው ነገር እን​ዲሁ ሆነ።</verse>
				<verse number="19">ያም ሎሌ ለኤ​ል​ሳዕ መልሶ፥ “እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማይ የእ​ህል ሿሿቴ ቢያ​ወ​ርድ ይህ ነገር ይሆ​ና​ልን?” ብሎ ነበር፤ ኤል​ሳ​ዕም፥ “እነሆ፥ በዐ​ይ​ኖ​ችህ ታየ​ዋ​ለህ፥ ከዚ​ያም አት​ቀ​ም​ስም” ብሎት ነበር።</verse>
				<verse number="20">እን​ዲ​ሁም ሆነ፤ ሕዝ​ቡም በበሩ ረገ​ጠ​ውና ሞተ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">ኤል​ሳ​ዕም ልጅ​ዋን ያስ​ነ​ሣ​ላ​ትን ሴት፥ “አንቺ ከቤተ ሰብሽ ጋር ተነ​ሥ​ተሽ ሂጂ፤ በም​ታ​ገ​ኚ​ውም ስፍራ ተቀ​መጪ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ራብን ጠር​ቶ​አ​ልና፤ ሰባት ዓመ​ትም በም​ድር ላይ ይቆ​ያል” ብሎ ተና​ገ​ራት።</verse>
				<verse number="2">ሴቲ​ቱም ተነ​ሥታ ኤል​ሳዕ እንደ ነገ​ራት አደ​ረ​ገች፤ ከቤተ ሰብ​ዋም ጋር ሄዳ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሀገር ሰባት ዓመት ተቀ​መ​ጠች።</verse>
				<verse number="3">ሰባ​ቱም ዓመት ካለፈ በኋላ ያች ሴት ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሀገር ተመ​ለ​ሰች፤ ሄዳም ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ልት​ጮህ ወደ ንጉሡ ወጣች።</verse>
				<verse number="4">ንጉ​ሡም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው የኤ​ል​ሳዕ ሎሌ ግያ​ዝን፥ “ኤል​ሳዕ ያደ​ረ​ገ​ውን ታላ​ላቅ ተአ​ም​ራት ሁሉ ንገ​ረኝ” እያለ ይነ​ጋ​ገር ነበር።</verse>
				<verse number="5">እር​ሱም የሞ​ተ​ውን ሕፃን እንደ አስ​ነሣ ለን​ጉሡ ሲና​ገር፥ እነሆ፥ ልጅ​ዋን ያስ​ነ​ሣ​ላት ያች ሴት መጥታ ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ወደ ንጉሥ ጮኸች፥ ግያ​ዝም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ሴቲቱ ይህች ናት፤ ኤል​ሳ​ዕም ያስ​ነ​ሣው ልጅዋ ይህ ነው፤” አለ።</verse>
				<verse number="6">ንጉ​ሡም ሴቲ​ቱን ጠየ​ቃት፤ እር​ስ​ዋም ነገ​ረ​ችው። ንጉ​ሡም ከባ​ለ​ሟ​ሎቹ አን​ዱን ሰጣት፤ “እህ​ል​ዋ​ንና ገን​ዘ​ብ​ዋን ሁሉ ሀገ​ሩን ከተ​ወች ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የሄደ ቦታ​ዋን ሁሉ መል​ስ​ላት” አለው።</verse>
				<verse number="7">ኤል​ሳ​ዕም ወደ ደማ​ስቆ ሄደ፤ የሶ​ር​ያም ንጉሥ ወልደ አዴር ታምሞ ነበር፤ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ​ዚህ መጥ​ቶ​አል” ብለ​ውም ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="8">ንጉ​ሡም አዛ​ሄ​ልን፥ “ገጸ በረ​ከት በእ​ጅህ ወስ​ደህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው ተቀ​በ​ለው፤ ከዚ​ህም በሽታ እድን እንደ ሆነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ጠይ​ቀው” አለው።</verse>
				<verse number="9">አዛ​ሄ​ልም ሊገ​ና​ኘው ሄደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ከደ​ማ​ስቆ መል​ካ​ሙን ነገር ሁሉ የአ​ርባ ግመል ጭነት ገጸ በረ​ከት ወሰደ፤ መጥ​ቶም በፊቱ ቆመና፥ “ልጅህ የሶ​ርያ ንጉሥ ወልደ አዴር፦ ከዚህ በሽታ እድ​ና​ለ​ሁን? ሲል ወደ አንተ ልኮ​ኛል” አለው።</verse>
				<verse number="10">ኤል​ሳ​ዕም፥ “ሂድ፥ መዳ​ንስ ትድ​ና​ለህ በለው፤ ነገር ግን እን​ዲ​ሞት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​ይ​ቶ​ኛል” አለው።</verse>
				<verse number="11">እስ​ኪ​ያ​ፍ​ርም ድረስ ትኩር ብሎ ፊቱን ተመ​ለ​ከ​ተው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው አለ​ቀሰ።</verse>
				<verse number="12">አዛ​ሄ​ልም፥ “ጌታ​ዬን ምን ያስ​ለ​ቅ​ሰ​ዋል?” አለ። ኤል​ሳ​ዕም፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ክፋት ስለ​ማ​ውቅ ነው፤ ምሽ​ጎ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በሰ​ይፍ ትገ​ድ​ላ​ለህ፤ ሕፃ​ና​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትፈ​ጠ​ፍ​ጣ​ለህ፤ እር​ጉ​ዞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትሰ​ነ​ጥ​ቃ​ለህ፤” አለው።</verse>
				<verse number="13">አዛ​ሄ​ልም፥ “ይህን ታላቅ ነገር አደ​ርግ ዘንድ እኔ የሞተ ውሻ አገ​ል​ጋ​ይህ ምን​ድን ነኝ?” አለ። ኤል​ሳ​ዕም፥ “አንተ በሶ​ርያ ላይ ንጉሥ እን​ድ​ት​ሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​ይ​ቶ​ኛል” አለው።</verse>
				<verse number="14">ከኤ​ል​ሳ​ዕም ወጥቶ ወደ ጌታው መጣ፤ እር​ሱም፥ “ኤል​ሳዕ ምን አለህ?” አለው፤ እር​ሱም አለው፥ “መዳ​ንን ትድ​ና​ለህ በለው አለኝ።”</verse>
				<verse number="15">ከዚ​ህም በኋላ በነ​ጋው ለሐፍ ወስዶ በውኃ ነከ​ረው፤ በፊ​ቱም ላይ ሸፈ​ነው፥ ሞተም። አዛ​ሄ​ልም በፋ​ን​ታው ነገሠ።</verse>
				<verse number="16">በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በአ​ክ​ዓብ ልጅ በኢ​ዮ​ራም በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጅ ኢዮ​ራም በይ​ሁዳ ነገሠ።</verse>
				<verse number="17">መን​ገ​ሥም በጀ​መረ ጊዜ የሠ​ላሳ ሁለት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ስም​ንት ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="18">የአ​ክ​ዓ​ብ​ንም ልጅ አግ​ብቶ ነበ​ርና የአ​ክ​ዓብ ቤት እን​ዳ​ደ​ረገ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መን​ገድ ሄደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="19">ነገር ግን ለእ​ር​ሱና ለል​ጆቹ በዘ​መኑ ሁሉ መብ​ራት ይሰ​ጠው ዘንድ ተስፋ እንደ አደ​ረ​ገ​ለት፥ ስለ ባሪ​ያው ስለ ዳዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁ​ዳን ያጠፋ ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም።</verse>
				<verse number="20">በእ​ር​ሱም ዘመን የኤ​ዶ​ም​ያስ ሰዎች ሸፍ​ተው የይ​ሁዳ ሰዎ​ችን ከዱ​አ​ቸው፤ በላ​ያ​ቸ​ውም ንጉሥ አነ​ገሡ።</verse>
				<verse number="21">ኢዮ​ራ​ምም ከሰ​ረ​ገ​ሎቹ ሁሉ ጋር ወደ ሲሆር አለፈ፤ ተነ​ሥ​ቶም እር​ሱ​ንና የሰ​ረ​ገ​ሎ​ችን አለ​ቆች ከብ​በው የነ​በ​ሩ​ትን የኤ​ዶ​ም​ያ​ስን ሰዎች አጠ​ፋ​ቸው፤ ሕዝቡ ግን ወደ እየ​ቤቱ ሸሸ።</verse>
				<verse number="22">ኤዶ​ም​ያስ ግን ለይ​ሁዳ እን​ዳ​ይ​ገ​ብር እስከ ዛሬ ድረስ በይ​ሁዳ ላይ ሸፈተ። በዚ​ያም ዘመን ደግሞ የሎ​ምና ሰዎች ሸፈቱ።</verse>
				<verse number="23">የተ​ረ​ፈ​ውም የኢ​ዮ​ራም ነገር ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="24">ኢዮ​ራ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ፤ በፋ​ን​ታ​ውም ልጁ አካ​ዝ​ያስ ነገሠ።</verse>
				<verse number="25">በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በአ​ክ​ዓብ ልጅ በኢ​ዮ​ራም በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ራም ልጅ አካ​ዝ​ያስ ነገሠ።</verse>
				<verse number="26">መን​ገ​ሥም በጀ​መረ ጊዜ አካ​ዝ​ያስ የሃያ ሁለት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አንድ ዓመት ነገሠ። እና​ቱም ጎቶ​ልያ የተ​ባ​ለች የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የዘ​ን​በሪ ልጅ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="27">በአ​ክ​ዓ​ብም ቤት መን​ገድ ሄደ፤ እንደ አክ​ዓ​ብም ቤት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="28">ከአ​ክ​ዓ​ብም ልጅ ከኢ​ዮ​ራም ጋር የሶ​ር​ያን ንጉሥ አዛ​ሄ​ልን በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ ሊጋ​ጠም ሄደ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ኢዮ​ራ​ምን አቈ​ሰ​ሉት።</verse>
				<verse number="29">ንጉ​ሡም ኢዮ​ራም ከሶ​ርያ ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል ጋር በተ​ዋጋ ጊዜ ሶር​ያ​ው​ያን በሬ​ማት ያቈ​ሰ​ሉ​ትን ቍስል ይታ​ከም ዘንድ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ተመ​ለሰ። የአ​ክ​ዓ​ብም ልጅ ኢዮ​ራም ታምሞ ነበ​ርና የኢ​ዮ​ራም ልጅ አካ​ዝ​ያስ ሊያ​የው ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ወረደ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">ነቢ​ዩም ኤል​ሳዕ ከነ​ቢ​ያት ልጆች አን​ዱን ጠርቶ እን​ዲህ አለው፥ “ወገ​ብ​ህን ታጥ​ቀህ ይህን የዘ​ይት ቀንድ በእ​ጅህ ያዝ፤ ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓ​ድም ሂድ።</verse>
				<verse number="2">በዚ​ያም በደ​ረ​ስህ ጊዜ የና​ሜ​ሲን ልጅ የኢ​ዮ​ሣ​ፍ​ጥን ልጅ ኢዩን ታገ​ኘ​ዋ​ለህ፤ ገብ​ተ​ህም ከወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል አስ​ነ​ሣው፤ ወደ ጓዳም አግ​ባው።</verse>
				<verse number="3">የዘ​ይ​ቱ​ንም ቀንድ ይዘህ በራሱ ላይ አፍ​ስ​ሰ​ውና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባ​ሁህ በለው፤ ከዚ​ህም በኋላ በሩን ከፍ​ተህ ሽሽ፥ አት​ዘ​ግ​ይም።”</verse>
				<verse number="4">እን​ዲ​ሁም ጐል​ማ​ሳው ነቢይ ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ሄደ።</verse>
				<verse number="5">በገ​ባም ጊዜ፥ እነሆ፥ የሠ​ራ​ዊት አለ​ቆች ተቀ​ም​ጠው አገኘ፤ እር​ሱም፥ “አለቃ ሆይ፥ የም​ና​ገ​ረው መል​እ​ክት አለኝ” አለ። ኢዩም፥ “ከማ​ን​ኛ​ችን ጋር ነው?” አለ። እር​ሱም፥ “አለቃ ሆይ፥ ከአ​ንተ ጋር ነው” አለ።</verse>
				<verse number="6">ተነ​ሥ​ቶም ወደ ቤቱ ገባ፥ ዘይ​ቱ​ንም በራሱ ላይ አፍ​ስሶ እን​ዲህ አለው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባ​ሁህ።</verse>
				<verse number="7">የባ​ሪ​ያ​ዎቼን የነ​ቢ​ያ​ትን ደም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ባሪ​ያ​ዎች ሁሉ ደም ከኤ​ል​ዛ​ቤል እጅና ከአ​ክ​ዓብ ቤት ሁሉ እጅ እበ​ቀል ዘንድ የጌ​ታ​ህን የአ​ክ​ዓ​ብን ቤት ታጠ​ፋ​ለህ።</verse>
				<verse number="8">የአ​ክ​ዓ​ብን ቤት ሁሉ ታጠ​ፋ​ለህ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ አጥር ተጠ​ግቶ እስ​ከ​ሚ​ሸን የቀ​ረ​በ​ውን ሁሉና ከእ​ነ​ርሱ የቀ​ረ​ውን ሁሉ ታጠ​ፋ​ለህ።</verse>
				<verse number="9">የአ​ክ​ዓ​ብ​ንም ቤት እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ቤት፥ እንደ አኪ​ያም ልጅ እንደ ባኦስ ቤት አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">ኤል​ዛ​ቤ​ል​ንም በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል እርሻ ውሾች ይበ​ሉ​አ​ታል፥ የሚ​ቀ​ብ​ራ​ትም አታ​ገ​ኝም።” በሩ​ንም ከፍቶ ሸሸ።</verse>
				<verse number="11">ኢዩም ወደ ጌታው ብላ​ቴ​ኖች ወጣ፤ እነ​ር​ሱም፥ “ደኅና ነውን? ይህ እብድ ለምን ወደ አንተ መጣ?” አሉት። እር​ሱም፥ “ሰው​ዬው ፌዝ እን​ደ​ሚ​ና​ገር አታ​ው​ቁ​ምን?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">እነ​ር​ሱም፥ “ዋሸ​ኸን፤ ነገር ግን ንገ​ረን” አሉት፤ ኢዩም፦ ለጌ​ታው ልጆች፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባ​ሁህ ብሎ እን​ዲ​ህና እን​ዲህ ነገ​ረኝ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">በሰ​ሙም ጊዜ ሁሉም ፈጥ​ነው ልብ​ሳ​ቸ​ውን ወሰዱ፤ በሰ​ገ​ነቱ መውጫ እር​ከን ላይም ከእ​ግሩ በታች አነ​ጠ​ፉት፥ መለ​ከ​ትም እየ​ነፉ፥ “ኢዩ ነግ​ሦ​አል” አሉ።</verse>
				<verse number="14">እን​ዲ​ሁም የና​ሜሲ ልጅ የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጅ ኢዩ ኢዮ​ራ​ምን ከዳው። ኢዮ​ራ​ምና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ከሶ​ርያ ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል የተ​ነሣ ሬማት ዘገ​ለ​ዓ​ድን ይጠ​ብቁ ነበር።</verse>
				<verse number="15">ንጉሡ ኢዮ​ራም ግን ከሶ​ርያ ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል ጋር በተ​ዋጋ ጊዜ ሶር​ያ​ው​ያን ያቈ​ሰ​ሉ​ትን ቍስል ይታ​ከም ዘንድ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ተመ​ልሶ ነበር። ኢዩም ከእ​ርሱ ጋር ለነ​በ​ሩት እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ከእኔ ጋር ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለሞት መስ​ጠት ትች​ላ​ላ​ች​ሁን? እን​ግ​ዲህ ማንም የሚ​ያ​መ​ል​ጣ​ችሁ፥ ከከ​ተ​ማ​ች​ሁም የሚ​ወጣ እን​ዳ​ይ​ኖ​ርና በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል እን​ዳ​ያ​ወራ ተጠ​ን​ቀቁ።”</verse>
				<verse number="16">የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ኢዮ​ራ​ምም ከሶ​ርያ ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል ጋር በተ​ዋጋ ጊዜ አረ​ማ​ው​ያን የሶ​ርያ ሰዎች በሬ​ማት ያቈ​ሰ​ሉ​ትን ቍስል በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ይታ​ከም ስለ ነበረ ኢዩ በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ተቀ​ምጦ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ሄደ። ጠን​ካ​ራና ኀይ​ለኛ ሰው ነበ​ርና፤ የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ አካ​ዝ​ያስ ኢዮ​ራ​ምን ለማ​የት ወርዶ ነበር።</verse>
				<verse number="17">ሰላ​ይም ያያ​ቸው ዘንድ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ግንብ ላይ ቆመ፤ ሲመ​ጡም የእ​ነ​ኢ​ዩን አቧራ አየ። “እነ​ሆም፥ አቧራ አያ​ለሁ” አለ። ኢዮ​ራ​ምም፥ “ይገ​ና​ኛ​ቸው ዘንድ አንድ ፈረ​ሰኛ ይሂድ፤ እር​ሱም፦ ሰላም ነውን? ይበ​ላ​ቸው” አለ።</verse>
				<verse number="18">ፈረ​ሰ​ኛ​ውም ሊቀ​በ​ላ​ቸው ሄዶ፥ “ንጉሡ እን​ዲህ ይላል፦ ሰላም ነውን?” አላ​ቸው። ኢዩም፥ “አንተ ከሰ​ላም ጋር ምን አለህ? ወደ ኋላዬ ተመ​ል​ሰህ ተከ​ተ​ለኝ” አለ። ሰላ​ዩም፥ “መል​እ​ክ​ተ​ኛው ደረ​ሰ​ባ​ቸው፥ ነገር ግን አል​ተ​መ​ለ​ሰም” ብሎ ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="19">ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ፈረ​ሰኛ ሰደደ፤ ወደ እነ​ር​ሱም ደርሶ ንጉሡ እን​ዲህ ይላል፥ “ሰላም ነውን?” አላ​ቸው። ኢዩም፥ “አንተ ከሰ​ላም ጋር ምን አለህ? ወደ ኋላዬ ተመ​ል​ሰህ ተከ​ተ​ለኝ” አለ።</verse>
				<verse number="20">ሰላ​ዩም፥ “መል​እ​ክ​ተ​ኛው ደረ​ሰ​ባ​ቸው፥ ነገር ግን አል​ተ​መ​ለ​ሰም፤ የሚ​መ​ራው ግን እንደ ናሜሲ ልጅ እንደ ኢዩ ይመ​ራል በች​ኮላ ይሄ​ዳ​ልና” ብሎ ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="21">ኢዮ​ራ​ምም፥ “ሰረ​ገላ አዘ​ጋጁ” አለ፤ ሰረ​ገ​ላ​ው​ንም አዘ​ጋ​ጁ​ለት። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኢዮ​ራ​ምና የይ​ሁዳ ንጉሥ አካ​ዝ​ያስ ሁለ​ቱም በሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸው ተቀ​ም​ጠው ወጡ፤ ኢዩ​ንም ሊገ​ና​ኙት ሄዱ፤ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊ​ውም በና​ቡቴ እርሻ ውስጥ አገ​ኙት።</verse>
				<verse number="22">ኢዮ​ራ​ምም ኢዩን ባየ ጊዜ “ኢዩ ሆይ፥ ሰላም ነውን?” አለ። እር​ሱም፥ “የእ​ና​ትህ የኤ​ል​ዛ​ቤል ግል​ሙ​ት​ና​ዋና መተቷ ሲበዛ ምን ሰላም አለ?” ብሎ መለሰ።</verse>
				<verse number="23">ኢዮ​ራ​ምም መልሶ ነዳና ሸሸ፤ አካ​ዝ​ያ​ስ​ንም፥ “አካ​ዝ​ያስ ሆይ፥ ዐመፅ ነው” አለው።</verse>
				<verse number="24">ኢዩም በእጁ ቀስ​ቱን ለጠጠ፤ ኢዮ​ራ​ም​ንም በጫ​ን​ቃው መካ​ከል ወጋው ፤ ፍላ​ጻ​ውም በልቡ አለፈ፤ ወደ ሰረ​ገ​ላ​ውም ውስጥ በጕ​ል​በቱ ላይ ወደቀ።</verse>
				<verse number="25">ኢዩም ጋሻ​ጃ​ግ​ሬ​ውን ቢድ​ቃ​ርን እን​ዲህ አለው፥ “አን​ሥ​ተህ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው በና​ቡቴ እርሻ ጣለው፤ አን​ተና እኔ ጎን ለጎን በፈ​ረስ ተቀ​ም​ጠን አባ​ቱን አክ​ዓ​ብን በተ​ከ​ተ​ልን ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ይህን መከራ እንደ ተና​ገ​ረ​በት እኔ አስ​ባ​ለ​ሁና አን​ተም ታው​ቃ​ለ​ህና፤</verse>
				<verse number="26">በእ​ው​ነት የና​ቡ​ቴ​ንና የል​ጆ​ቹን ደም ትና​ን​ትና አይ​ቻ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ በዚ​ህም እርሻ እበ​ቀ​ለ​ዋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ረው ቃል ወስ​ደህ በእ​ር​ሻው ውስጥ ጣለው።”</verse>
				<verse number="27">የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ አካ​ዝ​ያስ ያን ባየ ጊዜ በአ​ት​ክ​ልት ቤት መን​ገድ ሸሸ። ኢዩም፥ “እር​ሱ​ንም ደግሞ አል​ተ​ወ​ውም” ብሎ ተከ​ተ​ለው። በይ​ብ​ላ​ሄ​ምም አቅ​ራ​ቢያ ባለ​ችው በጋይ አቀ​በት በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ወጋው። ወደ መጊ​ዶም ሸሸ፥ በዚ​ያም ሞተ።</verse>
				<verse number="28">ብላ​ቴ​ኖ​ቹም በሰ​ረ​ገ​ላው ጭነው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወሰ​ዱት፥ በዳ​ዊ​ትም ከተማ በመ​ቃ​ብሩ ቀበ​ሩት።</verse>
				<verse number="29">በአ​ክ​ዓ​ብም ልጅ በኢ​ዮ​ራም በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ዓመት አካ​ዝ​ያስ በይ​ሁዳ ላይ ነገሠ።</verse>
				<verse number="30">ኢዩም ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ሄደ፤ ኤል​ዛ​ቤ​ልም ይህን በሰ​ማች ጊዜ ዐይ​ን​ዋን ተኳ​ለች፤ ራስ​ዋ​ንም አስ​ጌ​ጠች፤ በመ​ስ​ኮ​ትም ዘልቃ ትመ​ለ​ከት ነበር።</verse>
				<verse number="31">ኢዩም ወደ ከተማ በገባ ጊዜ፥ “ጌታ​ውን የገ​ደለ ዘምሪ ሰላም ነውን?” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="32">ፊቱ​ንም አቅ​ንቶ በመ​ስ​ኮቱ አያት። “አንቺ ማን ነሽ? ወደ​ዚህ ወደ እኔ ውረጂ” አላት። ከዚ​ህም በኋላ ሁለት ጃን​ደ​ረ​ቦች ወደ እርሱ ተመ​ለ​ከቱ።</verse>
				<verse number="33">እር​ሱም፥ “ወደ ታች ወር​ው​ሩ​አት” አላ​ቸው፤ ወረ​ወ​ሩ​አ​ትም፥ ደም​ዋም በግ​ን​ቡና በፈ​ረ​ሶች መግ​ሪያ ላይ ተረጨ፥ ረገ​ጡ​አ​ትም።</verse>
				<verse number="34">ኢዩም ገብቶ በላ፤ ጠጣም፥ ከዝ​ያም በኋላ፥ “ሂዱ፥ ይህ​ችን የተ​ረ​ገ​መች እዩ​አት፤ የን​ጉሥ ልጅ ናትና ቅበ​ሩ​አት” አለ።</verse>
				<verse number="35">ሊቀ​ብ​ሩ​አ​ትም በሄዱ ጊዜ ከአ​ና​ቷና ከእ​ግ​ርዋ ተረ​ከዝ ከመ​ዳ​ፍ​ዋም በቀር ምንም አላ​ገ​ኙም።</verse>
				<verse number="36">ተመ​ል​ሰ​ውም ለኢዩ ነገ​ሩት፤ እር​ሱም፥ “በባ​ሪ​ያው በቴ​ስ​ብ​ያ​ዊው ኤል​ያስ እጅ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል እርሻ የኤ​ል​ዛ​ቤ​ልን ሥጋ ውሾች ይበ​ላሉ፥</verse>
				<verse number="37">የኤ​ል​ዛ​ቤ​ልም ሬሳ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል እርሻ መሬት ላይ እንደ ፍግ ይሆ​ና​ልና ማንም፦ ይህች ኤል​ዛ​ቤል ናት ይል ዘንድ አይ​ች​ልም ብሎ የተ​ና​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው” አለ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">ለአ​ክ​አ​ብም በሰ​ማ​ርያ ሰባ ልጆች ነበ​ሩት፤ ኢዩም ደብ​ዳቤ ጽፎ፥ የአ​ክ​አ​ብን ልጆች ለሚ​ያ​ሳ​ድጉ፥ ለሰ​ማ​ርያ አለ​ቆ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወደ ሰማ​ርያ ላከ።</verse>
				<verse number="2">እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህ ደብ​ዳቤ አሁን በደ​ረ​ሳ​ችሁ ጊዜ የጌ​ታ​ችሁ ልጆች ሰረ​ገ​ሎ​ቹና ፈረ​ሶ​ቹም፥ የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞ​ቹም፥ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ዎ​ቹም በእ​ና​ንተ ዘንድ አሉ፤</verse>
				<verse number="3">ከጌ​ታ​ችሁ ልጆች ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኛ​ች​ሁ​ንና የሚ​ሻ​ላ​ች​ሁን ምረጡ፤ በአ​ባ​ቱም ዙፋን አስ​ቀ​ም​ጡት፤ ስለ ጌታ​ች​ሁም ቤት ተዋጉ።”</verse>
				<verse number="4">እነ​ር​ሱም እጅግ ፈር​ተው፥ “እነሆ፥ ሁለቱ ነገ​ሥ​ታት በፊቱ ይቆሙ ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ እኛስ እን​ዴት በፊቱ መቆም እን​ች​ላ​ለን?” አሉ።</verse>
				<verse number="5">የአ​ክ​አ​ብም የቤቱ አለ​ቆች፥ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም አለ​ቆች፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹና ልጆ​ቹ​ንም የሚ​ያ​ሳ​ድጉ፥ “እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ነን፤ ያዘ​ዝ​ኸ​ን​ንም ሁሉ እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ የም​ና​ነ​ግ​ሠው ሰው የለም፤ የም​ት​ወ​ድ​ደ​ውን አድ​ርግ” ብለው ወደ ኢዩ ላኩ።</verse>
				<verse number="6">ከዚ​ህም በኋላ ኢዩ፥ “ወገ​ኖ​ቼስ ከሆ​ና​ችሁ፥ ነገ​ሬ​ንም ከሰ​ማ​ችሁ የጌ​ታ​ች​ሁን ልጆች ራስ ቍረጡ፤ ነገም በዚህ ሰዓት ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ወደ እኔ ይዛ​ችሁ ኑ” ብሎ ሁለ​ተኛ ደብ​ዳቤ ጻፈ​ላ​ቸው። የን​ጉ​ሡም ልጆች ሰባው ሰዎች በሚ​ያ​ሳ​ድ​ጓ​ቸው በከ​ተ​ማ​ዪቱ ታላ​ላ​ቆች ዘንድ ነበሩ።</verse>
				<verse number="7">ደብ​ዳ​ቤ​ውም በደ​ረ​ሳ​ቸው ጊዜ የሀ​ገሩ ሰዎች የን​ጉ​ሡን ልጆች ሰባ​ውን ሰዎች ይዘው ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም በቅ​ር​ጫት አድ​ር​ገው ወደ እርሱ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ላኩ።</verse>
				<verse number="8">መል​እ​ክ​ተ​ኛም መጥቶ፥ “የን​ጉ​ሡን ልጆች ራስ ይዘው መጥ​ተ​ዋል” ብሎ ነገ​ረው። ንጉ​ሡም፥ “እስከ ነገ ድረስ በበሩ አደ​ባ​ባይ ሁለት ክምር አድ​ር​ጋ​ችሁ አኑ​ሩ​አ​ቸው” አለ።</verse>
				<verse number="9">በነ​ጋ​ውም ንጉሡ ወጥቶ ቆመ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ፥ “እና​ንተ ንጹ​ሓን ናችሁ፤ እነሆ፥ የጌ​ታ​ዬን ቤት የወ​ነ​ጀ​ልሁ የገ​ደ​ል​ኋ​ቸ​ውም እኔ ነኝ፤ እነ​ዚ​ህ​ንስ ሁሉ የገ​ደለ ማን ነው?</verse>
				<verse number="10">እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ክ​አብ ቤት ላይ ከተ​ና​ገ​ረው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በም​ድር ላይ አን​ዳች እን​ዳ​ይ​ወ​ድቅ አሁን ዕወቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በባ​ሪ​ያው በኤ​ል​ያስ ቃል የተ​ና​ገ​ረ​ውን አድ​ር​ጎ​አል” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ኢዩም ከአ​ክ​አብ ቤት በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል የቀ​ረ​ውን ሁሉ፥ ታላ​ላ​ቆ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ወዳ​ጆ​ቹ​ንና ካህ​ና​ቱን ሁሉ ገደ​ላ​ቸው፤ ከእ​ነ​ርሱ አን​ድስ እንኳ አላ​ስ​ቀ​ረም።</verse>
				<verse number="12">ተነ​ሥ​ቶም ወደ ሰማ​ርያ ሄደ፤ በመ​ን​ገ​ድም ወዳ​ለው ወደ በግ ጠባ​ቂ​ዎች ቤት በደ​ረሰ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="13">ኢዩ ከይ​ሁዳ ንጉሥ ከአ​ካ​ዝ​ያስ ወን​ድ​ሞች ጋር ተገ​ና​ኝቶ፥ “እና​ንተ እነ​ማን ናችሁ?” አለ፤ እነ​ር​ሱም፥ “እኛ የይ​ሁዳ ንጉሥ የአ​ካ​ዝ​ያስ ወን​ድ​ሞች ነን፤ የን​ጉ​ሡ​ንና የእ​ቴ​ጌ​ዪ​ቱን ልጆች ደኅ​ን​ነት እን​ነ​ግ​ረው ዘንድ ወረ​ድን” አሉት።</verse>
				<verse number="14">እር​ሱም፥ “በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው ያዙ​አ​ቸው” ብሎ አዘዘ። በበግ ጠባ​ቂ​ዎች ቤትም አጠ​ገብ አርባ ሁለ​ቱን ሰዎች ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ሰው እንኳ አላ​ስ​ቀ​ረም።</verse>
				<verse number="15">ከዚ​ያም በሄደ ጊዜ የሬ​ካ​ብን ልጅ ኢዮ​ና​ዳ​ብን በመ​ን​ገድ አገ​ኘው፤ ተቀ​ብ​ሎም መረ​ቀው፤ ኢዩም፥ “ልቤ ከል​ብህ ጋር ቅን እንደ ሆነ ያህል ልብህ ከልቤ ጋር በቅ​ን​ነት ነውን?” አለው። ኢዮ​ና​ዳ​ብም፥ “አዎን” አለው። ኢዩም፥ “እው​ነ​ት​ህስ ከሆነ እጅ​ህን ስጠኝ” አለ። እጁ​ንም ሰጠው፤ ወደ እር​ሱም ወደ ሰረ​ገ​ላው አወ​ጣው።</verse>
				<verse number="16">“ከእኔ ጋር ና፥ ለሠ​ራ​ዊት ጌታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ደ​ም​ቀና ታያ​ለህ” አለው። ከእ​ር​ሱም ጋር በሰ​ረ​ገ​ላው አስ​ቀ​መ​ጠው።</verse>
				<verse number="17">ወደ ሰማ​ር​ያም ገብቶ ለኤ​ል​ያስ እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋው ድረስ በሰ​ማ​ርያ የቀ​ረ​ውን የአ​ክ​አ​ብን ሰው ገደለ።</verse>
				<verse number="18">ኢዩም ሕዝ​ቡን ሁሉ ሰብ​ስቦ፥ “አክ​አብ በዓ​ልን በጥ​ቂቱ አመ​ለ​ከው፤ ኢዩ ግን በብዙ ያመ​ል​ከ​ዋል።</verse>
				<verse number="19">አሁ​ንም የበ​ዓ​ልን ነቢ​ያት ሁሉ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ካህ​ና​ቱ​ንም ሁሉ ወደ እኔ ጥሩ፤ ማንም እን​ዳ​ይ​ቀር፤ ለበ​ዓል ታላቅ መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ር​ባ​ለሁ፤ የቀ​ረ​ውም ሁሉ በሕ​ይ​ወት አይ​ኖ​ርም” አላ​ቸው። ኢዩ ግን የበ​ዓ​ልን አገ​ል​ጋ​ዮች ያጠፋ ዘንድ በተ​ን​ኮል ይህን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="20">ኢዩም፥ “ለበ​ዓል መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን አንጹ” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም አዋጅ ነገሩ።</verse>
				<verse number="21">ኢዩም ወደ እስ​ራ​ኤል ሀገ​ሮች ሁሉ ላከ፤ የበ​ዓ​ልም አገ​ል​ጋ​ዮች ሁሉ፥ ካህ​ና​ቱም ሁሉ፥ ነቢ​ያ​ቶ​ቹም ሁሉ መጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ሳይ​መጣ የቀረ አንድ ሰው እንኳ አል​ነ​በ​ረም። ሁሉም ወደ በዓል ቤት ገቡ፤ የበ​ዓ​ል​ንም ቤት ከዳር እስከ ዳር ድረስ ሞሉት።</verse>
				<verse number="22">የዕቃ ቤቱ​ንም ሹም፥ “ለበ​ዓል አገ​ል​ጋ​ዮች ሁሉ ልብ​ስን አውጣ” አለው። የሚ​ያ​ለ​ብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ልብ​ሱን አወ​ጣ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">ኢዩና የሬ​ካብ ልጅ ኢዮ​ና​ዳ​ብም ወደ በዓል ቤት ገቡ። የበ​ዓ​ል​ንም አገ​ል​ጋ​ዮች፥ “መር​ምሩ፥ ከበ​ዓል አገ​ል​ጋ​ዮች ብቻ በቀር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከሚ​ያ​መ​ልኩ ወገን በእ​ና​ንተ ዘንድ አንድ እንኳ እን​ዳ​ይ​ኖር ተመ​ል​ከቱ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና ሌላ መሥ​ዋ​ዕ​ትም ያቀ​ርቡ ዘንድ ገቡ፤ ኢዩም፥ “በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፌ ከም​ሰ​ጣ​ችሁ ሰዎች አንድ ሰው ያመ​ለጠ እንደ ሆነ ነፍሱ በዚያ እን​ዲ​ያ​መ​ልጥ ባደ​ረ​ገው ሰው ነፍስ ፋንታ ትሆ​ና​ለች” ብሎ በውጭ ሰማ​ንያ ሰዎ​ችን አዘ​ጋ​ጅቶ ነበር።</verse>
				<verse number="25">የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ር​በው በፈ​ጸሙ ጊዜ ኢዩ ዘበ​ኞ​ቹ​ንና አለ​ቆ​ቹን፥ “ግቡና ግደ​ሉ​አ​ቸው፤ አን​ድም አያ​ም​ልጥ” አላ​ቸው። በሰ​ይ​ፍም ስለት ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ ዘበ​ኞ​ችና አለ​ቆ​ችም ወደ ውጭ ጣሉ​አ​ቸው፤ ወደ በዓ​ልም ቤት ከተማ ሄዱ።</verse>
				<verse number="26">ከበ​ዓ​ልም ቤት ሐው​ል​ቶ​ቹን አወጡ፤ አቃ​ጠ​ሉ​አ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="27">የበ​ዓ​ልን ሐው​ልት ቀጠ​ቀጡ፤ የበ​ዓ​ል​ንም ቤት አፈ​ረሱ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የው​ዳቂ መጣያ አደ​ረ​ጉት።</verse>
				<verse number="28">እን​ዲ​ሁም ኢዩ በዓ​ልን ከእ​ስ​ራ​ኤል አጠፋ።</verse>
				<verse number="29">ነገር ግን እስ​ራ​ኤ​ልን ካሳ​ተው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት ኢዩ አል​ራ​ቀም፥ በቤ​ቴ​ልና በዳን የነ​በ​ሩ​ትን የወ​ርቅ እን​ቦ​ሶ​ች​ንም፥ አላ​ስ​ወ​ገ​ደም።</verse>
				<verse number="30">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢዩን፥ “በፊቴ ቅን ነገር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ በል​ቤም ያለ​ውን ሁሉ በአ​ክ​አብ ቤት ላይ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ልጆ​ችህ እስከ አራት ትው​ልድ ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን ላይ ይቀ​መ​ጣሉ” አለው።</verse>
				<verse number="31">ኢዩ ግን በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ በፍ​ጹም ልቡ ይሄድ ዘንድ አል​ተ​ጠ​ነ​ቀ​ቀም፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ካሳ​ተው ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት አል​ራ​ቀም።</verse>
				<verse number="32">በዚ​ያም ወራት እዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ራ​ኤ​ልን ያጠፋ ጀመረ፤ አዛ​ሄ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል ዳርቻ ሁሉ መታ​ቸው።</verse>
				<verse number="33">በዮ​ር​ዳ​ኖስ ምሥ​ራቅ ያለ​ውን የገ​ለ​ዓ​ድን ሀገር ሁሉ፥ በአ​ር​ኖን ወንዝ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ የጋ​ድ​ንና የሮ​ቤ​ልን የም​ና​ሴ​ንም ሀገር፥ ገለ​ዓ​ድ​ንና ባሳ​ንን መታ።</verse>
				<verse number="34">የቀ​ረ​ውም የኢዩ ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ ኀይ​ሉም ሁሉ፥ የገ​ደ​ለ​ውም ሁሉ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="35">ኢዩም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በሰ​ማ​ር​ያም ቀበ​ሩት። በፋ​ን​ታ​ውም ልጁ ኢዩ​አ​ካዝ ነገሠ።</verse>
				<verse number="36">ኢዩም በሰ​ማ​ርያ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ የነ​ገ​ሠ​በት ዘመን ሃያ ስም​ንት ዓመት ነበረ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">የአ​ካ​ዝ​ያ​ስም እናት ጎቶ​ልያ ልጅዋ እንደ ሞተ ባየች ጊዜ ተነ​ሥታ የመ​ን​ግ​ሥ​ትን ዘር ሁሉ አጠ​ፋች።</verse>
				<verse number="2">የን​ጉሡ የኢ​ዮ​ራም ልጅ የአ​ካ​ዝ​ያስ እኅት ኢዮ​ሳ​ቡ​ሄም የአ​ካ​ዝ​ያ​ስን ልጅ ኢዮ​አ​ስን ከተ​ገ​ደ​ሉት ከን​ጉሡ ልጆች መካ​ከል ሰርቃ ወሰ​ደ​ችው፤ እር​ሱ​ንና ሞግ​ዚ​ቱ​ንም ወደ እል​ፍኝ ወሰ​ደች፤ ከጎ​ቶ​ል​ያም ሸሸ​ገ​ችው፤ አል​ገ​ደ​ሉ​ት​ምም።</verse>
				<verse number="3">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ስድ​ስት ዓመት ሸሸ​ገ​ችው። ጎቶ​ል​ያም በሀ​ገሩ ላይ ነገ​ሠች።</verse>
				<verse number="4">በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ዮዳሄ ልኮ፥ በኮ​ራ​ው​ያ​ንና በዘ​በ​ኞች ላይ ያሉ​ትን የመቶ አለ​ቆች ወሰደ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አገ​ባ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አማ​ላ​ቸው፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ልጅ አሳ​ያ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “እን​ዲህ አድ​ርጉ፤ በሰ​ን​በት ቀን ከም​ት​ገ​ቡት ከእ​ና​ንተ ከሦ​ስት አንዱ እጅ በበር ተቀ​ም​ጣ​ችሁ የን​ጉ​ሡን ቤት ዘብ ጠብቁ፤</verse>
				<verse number="6">ሌላ​ውም ከሦ​ስት አንዱ እጅ በሰ​ፊው መን​ገድ በበሩ በኩል ተቀ​መጡ፤ ሦስ​ተ​ኛ​ውም እጅ ከዘ​በ​ኞች ቤት በኋላ ባለው በር ሁኑ፤ ቤቱ​ንም አጽ​ን​ታ​ችሁ ጠብቁ፤</verse>
				<verse number="7">ከእ​ና​ን​ተም በሰ​ን​በት ቀን የም​ት​ወ​ጡት ሁለቱ እጅ ንጉሥ ያለ​በ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ጠብቁ።</verse>
				<verse number="8">ንጉ​ሡ​ንም በዙ​ሪ​ያው ክበ​ቡት፤ የጦር ዕቃ​ች​ሁም በእ​ጃ​ችሁ ይሁን፤ በሰ​ል​ፋ​ች​ሁም መካ​ከል የሚ​ገባ ይገ​ደል፤ ንጉ​ሡም በወ​ጣና በገባ ጊዜ ከእ​ርሱ ጋር ሁኑ።”</verse>
				<verse number="9">መቶ አለ​ቆ​ችም ብልሁ ዮዳሄ ያዘ​ዛ​ቸ​ውን ሁሉ አደ​ረጉ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም እያ​ን​ዳ​ንዱ በሰ​ን​በት ይገቡ የነ​በ​ሩ​ትን፥ በሰ​ን​በ​ትም ይወጡ የነ​በ​ሩ​ትን ሰዎች ይዘው ወደ ካህኑ ወደ ዮዳሄ መጡ።</verse>
				<verse number="10">ዮዳ​ሄም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የነ​በ​ረ​ውን የን​ጉ​ሡን የዳ​ዊ​ትን ሰይ​ፍና ጦር ሁሉ ለመቶ አለ​ቆች ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ዘበ​ኞ​ቹም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው የጦር ዕቃ​ቸ​ውን በእ​ጃ​ቸው ይዘው በን​ጉሡ ዙሪያ ከቤቱ ቀኝ እስከ ቤቱ ግራ ድረስ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውና በቤቱ አጠ​ገብ ቆሙ።</verse>
				<verse number="12">የን​ጉ​ሡ​ንም ልጅ አው​ጥቶ ዘው​ዱን ጫነ​በት፤ ምስ​ክ​ሩ​ንም ሰጠው፤ ቀብ​ቶም አነ​ገ​ሠው፥ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይን​ገሥ” እያሉ በእ​ጃ​ቸው አጨ​በ​ጨቡ።</verse>
				<verse number="13">ጎቶ​ል​ያም ሲሮጡ የሕ​ዝ​ቡን ድምፅ በሰ​ማች ጊዜ ወደ ሕዝቡ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ገባች።</verse>
				<verse number="14">እነ​ሆም፥ ንጉ​ሡን እንደ ተለ​መ​ደው በዓ​ምዱ አጠ​ገብ ቆሞ፥ ከን​ጉ​ሡም ጋር መዘ​ም​ራ​ንና መለ​ከ​ተ​ኞች ቆመው አየች፤ የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ ብሎ​አ​ቸው መለ​ከት ይነፉ ነበር። ጎቶ​ል​ያም ልብ​ስ​ዋን ቀድዳ፥ “ዐመፅ ነው፥ ዐመፅ ነው፥” ብላ ጮኸች።</verse>
				<verse number="15">ካህ​ኑም ዮዳሄ በጭ​ፍ​ራው ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን የመቶ አለ​ቆች፥ “ወደ ሰልፉ መካ​ከል አው​ጡ​አት፤ የሚ​ከ​ተ​ላ​ት​ንም በሰ​ይፍ ግደ​ሉት” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፤ ካህኑ፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አት​ገ​ደል” ብሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="16">እር​ስ​ዋ​ንም ይዘው በን​ጉሡ ቤት አጠ​ገብ ወደ አለ ወደ ፈረ​ሶች መግ​ቢያ መን​ገድ ወሰ​ዱ​አት፤ በዚ​ያም ገደ​ሉ​አት።</verse>
				<verse number="17">ዮዳ​ሄም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በን​ጉሡ፥ በሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ ደግ​ሞም በን​ጉ​ሡና በሕ​ዝቡ መካ​ከል ቃል ኪዳን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="18">የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በዓል ቤት ሄደው ሰበ​ሩት፤ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አፈ​ረሱ፤ ምስ​ሎ​ቹ​ንም አደ​ቀቁ፥ የበ​ዓ​ል​ንም ካህን ማታ​ንን በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት ገደ​ሉት። ካህኑ ዮዳ​ሄም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ጠባ​ቂ​ዎ​ችን ሾመ።</verse>
				<verse number="19">መቶ አለ​ቆ​ቹ​ንና ኮራ​ው​ያ​ንን፥ ዘበ​ኞ​ች​ንና የሀ​ገ​ሩ​ንም ሕዝብ ሁሉ ወሰ​ዳ​ቸው፤ ንጉ​ሡ​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አወ​ጣው፤ በዘ​በ​ኞ​ችም በር መን​ገድ ወደ ንጉሡ ቤት አመ​ጡት፤ በነ​ገ​ሥ​ታ​ቱም ዙፋን አስ​ቀ​መ​ጡት።</verse>
				<verse number="20">የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ደስ አላ​ቸው፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱም ፀጥ አለች። ጎቶ​ል​ያ​ንም በን​ጉሡ ቤት አጠ​ገብ በሰ​ይፍ ገደ​ሉ​አት።</verse>
				<verse number="21">ኢዮ​አ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሰ​ባት ዓመት ልጅ ነበረ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">ኢዩ በነ​ገሠ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ኢዮ​አስ ነገሠ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አርባ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ሳቢያ የተ​ባ​ለች የቤ​ር​ሳ​ቤህ ሴት ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="2">ካህኑ ዮዳሄ ያስ​ተ​ም​ረው በነ​በረ ዘመን ሁሉ ኢዮ​አስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="3">ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ያሉ የጣ​ዖት መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ ሕዝ​ቡም ገና በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ባሉት የጣ​ዖት መስ​ገ​ጃ​ዎች ይሠ​ዋና ያጥን ነበር።</verse>
				<verse number="4">ኢዮ​አ​ስም ካህ​ና​ቱን፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​ገ​ባ​ውን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ገን​ዘብ ሁሉ፥ ስለ ነፍ​ሱም ዋጋ የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን ገን​ዘብ፥ በል​ባ​ቸ​ውም ፈቃድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​ያ​መ​ጡ​ትን ገን​ዘብ ሁሉና፥</verse>
				<verse number="5">እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ከሚ​ያ​መ​ጣው ካህ​ናቱ ለራ​ሳ​ቸው ይው​ሰዱ፤ በመ​ቅ​ደ​ስም ውስጥ የተ​ና​ዱ​ትን ይጠ​ግ​ኑ​በት” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">ነገር ግን እስከ ንጉሡ እስከ ኢዮ​አስ እስከ ሃያ ሦስ​ተ​ኛው ዓመት ድረስ ከመ​ቅ​ደሱ ውስጥ የተ​ና​ዱ​ትን ካህ​ናቱ አል​ጠ​ገ​ኑ​ትም ነበር።</verse>
				<verse number="7">ኢዮ​አ​ስም ካህ​ኑን ዮዳ​ሄ​ንና ካህ​ና​ቱን ጠርቶ፥ “በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ የተ​ና​ዱ​ትን ስፍ​ራ​ዎች ስለ ምን አል​ጠ​ገ​ና​ች​ሁም? ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ገን​ዘቡ ለቤቱ መጠ​ገኛ ይሰጥ እንጂ ከሚ​ያ​መ​ጡት ሰዎች አት​ቀ​በሉ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">ካህ​ና​ቱም “ከሕ​ዝቡ ገን​ዘ​ቡን አን​ወ​ስ​ድም፤ በቤ​ቱም ውስጥ የተ​ና​ዱ​ትን አን​ጠ​ግ​ንም፥” ብለው ተስ​ማሙ።</verse>
				<verse number="9">ካህኑ ዮዳሄ ግን አንድ ሣጥን ወስዶ መክ​ደ​ኛ​ውን ነደ​ለው፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም አጠ​ገብ ሰው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሚ​ገ​ባ​በት መግ​ቢያ በስ​ተ​ቀኝ አኖ​ረው፤ ደጁ​ንም የሚ​ጠ​ብቁ ካህ​ናት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​መ​ጣ​ውን ገን​ዘብ ሁሉ በሚ​ዛን አስ​ገቡ።</verse>
				<verse number="10">በሣ​ጥ​ኑም ውስጥ የተ​ገ​ኘው ወርቅ ብዙ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ የን​ጉሡ ጸሓ​ፊና የካ​ህ​ናቱ አለቃ ይመጡ ነበር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የተ​ገ​ኘ​ውን ገን​ዘብ ሁሉ ቈጥ​ረው በከ​ረ​ጢት ውስጥ ያኖ​ሩት ነበር።</verse>
				<verse number="11">የተ​ሰ​በ​ሰ​በ​ው​ንም ገን​ዘብ ሥራ​ውን በሚ​ሠ​ሩና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት በሚ​ጠ​ብ​ቁት እጅ ይሰጡ ነበር። እነ​ር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለሚ​ሠሩ ግን​በ​ኞ​ችና አና​ጢ​ዎች ይሰጡ ነበር።</verse>
				<verse number="12">የተ​ና​ደ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለመ​ጠ​ገን መክ​ፈል ለሚ​ያ​ሻው ሁሉ ድን​ጋ​ይ​ንና እን​ጨ​ትን ይገዙ ዘንድ፥ ለግ​ን​በ​ኞ​ችና ለድ​ን​ጋይ ወቃ​ሪ​ዎች ይሰ​ጡት ነበር።</verse>
				<verse number="13">ነገር ግን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ከሚ​መ​ጣው ገን​ዘብ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​ሆኑ የብር መዝ​ጊ​ያ​ዎች፥ ጽዋ​ዎ​ችና ጕጠ​ቶች፥ ድስ​ቶ​ችም፥ መለ​ከ​ቶ​ችም፥ የወ​ር​ቅና የብር ዕቃ​ዎ​ችም አል​ተ​ሠ​ሩም ነበር።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን ለሚ​ሠ​ሩት ይሰ​ጡት ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ጠገ​ኑ​በት።</verse>
				<verse number="15">ለሠ​ራ​ተ​ኞ​ችም ይከ​ፍሉ ዘንድ ገን​ዘ​ቡን የሚ​ወ​ስ​ዱ​ትን ሰዎች አይ​ቈ​ጣ​ጠ​ሩ​አ​ቸ​ውም ነበር፤ በታ​ማ​ኝ​ነት ይሠሩ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="16">ስለ በደ​ልና ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​ያ​መ​ጡት ገን​ዘ​ብም ለካ​ህ​ናት ነበር።</verse>
				<verse number="17">በዚ​ያም ወራት የሶ​ርያ ንጉሥ አዛ​ሄል ዘመተ፤ ጌት​ንም ወግቶ ያዛት፤ አዛ​ሄ​ልም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ው​ጣት ፊቱን አቀና።</verse>
				<verse number="18">የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ኢዮ​አስ አባ​ቶቹ የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥና ኢዮ​ራም፥ አካ​ዝ​ያ​ስም የቀ​ደ​ሱ​ትን ቅዱስ ነገር፥ እር​ሱም የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤትና በን​ጉ​ሡም ቤተ መዛ​ግ​ብት የተ​ገ​ኘ​ውን ወርቅ ሁሉ ወሰደ፤ ወደ ሶር​ያም ንጉሥ ወደ አዛ​ሄል ላከው። እር​ሱም ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="19">የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​አስ ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ታሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="20">አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ተነ​ሥ​ተው ዐመ​ፁ​በት፥ ወደ ሲላ በሚ​ወ​ር​ደ​ውም መን​ገድ በመ​ሀሎ ቤት ኢዮ​አ​ስን ገደ​ሉት።</verse>
				<verse number="21">አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም የኢ​ያ​ሙ​ሃት ልጅ ኢያ​ዜ​ክ​ርና የሳ​ሜር ልጅ ኢያ​ዛ​ብድ መቱት፤ ሞተም፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ቀበ​ሩት፤ ልጁም አሜ​ስ​ያስ በፋ​ን​ታው ነገሠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">በይ​ሁዳ ንጉሥ በአ​ካ​ዝ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አስ በሃያ ሦስ​ተ​ኛው ዓመት የኢዩ ልጅ ኢዮ​አ​ካዝ በሰ​ማ​ርያ ነገሠ፤ ዐሥራ ሰባት ዓመ​ትም ነገሠ።</verse>
				<verse number="2">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ያሳ​ተ​ውን የና​ባ​ጥን ልጅ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምን ኀጢ​አት ተከ​ተለ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም አል​ራ​ቀም።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በጣም ተቈጣ፤ በዘ​መ​ኑም ሁሉ በሶ​ር​ያው ንጉሥ በአ​ዛ​ሄል እጅ፥ በአ​ዛ​ሄ​ልም ልጅ በወ​ልደ አዴር እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ኢዮ​አ​ካ​ዝም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመነ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሶ​ርያ ንጉሥ እስ​ራ​ኤ​ልን ያስ​ጨ​ነ​ቀ​በ​ትን ጭን​ቀት አይ​ቶ​አ​ልና ሰማው።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእ​ስ​ራ​ኤል ታዳ​ጊን ሰጠ፤ ከሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንም እጅ ዳኑ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እንደ ቀድ​ሞው ጊዜ በድ​ን​ኳ​ና​ቸው ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="6">ነገር ግን በእ​ር​ስዋ ሄዱ እንጂ እስ​ራ​ኤ​ልን ካሳ​ተ​በት ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት ኀጢ​አት አል​ራ​ቁም፤ ደግ​ሞም የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ በሰ​ማ​ርያ ቆሞ ነበረ።</verse>
				<verse number="7">ለኢ​ዮ​አ​ካ​ዝም ከኀ​ምሳ ፈረ​ሰ​ኞች፥ ከዐ​ሥ​ርም ሰረ​ገ​ሎች፥ ከዐ​ሥር ሺህም እግ​ረ​ኞች በቀር ሕዝብ አል​ቀ​ረ​ለ​ትም፤ የሶ​ርያ ንጉሥ አጥ​ፍ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና፥ በአ​ው​ድ​ማም እን​ዳለ ዕብቅ አድ​ቅ​ቆ​አ​ቸ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="8">የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​አ​ካዝ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ ኀይ​ሉም፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="9">ኢዮ​አ​ካ​ዝም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በሰ​ማ​ር​ያም ቀበ​ሩት፥ ልጁም ዮአስ በፋ​ን​ታው ነገሠ።</verse>
				<verse number="10">በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​አስ በሠ​ላሳ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት የኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ ዮአስ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ ዐሥራ ስድ​ስት ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="11">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልን ካሳ​ተው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት አል​ራ​ቀም፤ ነገር ግን በእ​ር​ስዋ ሄደ።</verse>
				<verse number="12">የቀ​ረ​ውም የዮ​አስ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ ከይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ከአ​ሜ​ስ​ያስ ጋር የተ​ዋ​ጋ​በት ኀይሉ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="13">ዮአ​ስም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም በዙ​ፋኑ ላይ ተቀ​መጠ፤ ዮአ​ስም በሰ​ማ​ርያ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት ጋር ተቀ​በረ።</verse>
				<verse number="14">ኤል​ሳ​ዕም በሚ​ሞ​ት​በት በሽታ ታመመ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዮአስ ወደ እርሱ ወርዶ በፊቱ አለ​ቀ​ሰና፥ “አባቴ ሆይ፥ አባቴ ሆይ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰረ​ገ​ላ​ቸ​ውና ፈረ​ሰ​ኛ​ቸው” አለ።</verse>
				<verse number="15">ኤል​ሳ​ዕም፥ “ቀስ​ት​ህ​ንና ፍላ​ጻ​ዎ​ች​ህን ውሰድ” አለው፤ ቀስ​ቱ​ንና ፍላ​ጻ​ዎ​ቹ​ንም ወሰደ።</verse>
				<verse number="16">የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ንጉሥ አለው፥ “እጅ​ህን በቀ​ስቱ ላይ ጫን።” ዮአ​ስም እጁን በቀ​ስቱ ላይ ጫነ፤ ኤል​ሳ​ዕም እጁን በን​ጉሡ እጅ ላይ ጫነ፦</verse>
				<verse number="17">“የም​ሥ​ራ​ቁ​ንም መስ​ኮት ክፈት” አለ፤ ከፈ​ተ​ውም። ኤል​ሳ​ዕም፥ “ወር​ውር” አለው፤ ወረ​ወ​ረ​ውም እር​ሱም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መድ​ኀ​ኒት ፍላጻ ነው፤ ከሶ​ርያ የመ​ዳን ፍላጻ ነው፤ እስ​ክ​ታ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም ድረስ ሶር​ያ​ው​ያ​ንን በአ​ፌቅ ትመ​ታ​ለህ” አለ።</verse>
				<verse number="18">ኤል​ሳ​ዕም ደግሞ፥ “ፍላ​ጻ​ዎ​ች​ህን ውሰድ” አለው ወሰ​ዳ​ቸ​ውም። የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ንጉሥ፥ “ምድ​ሩን ምታው” አለው። ንጉ​ሡም ሦስት ጊዜ መትቶ ቆመ።</verse>
				<verse number="19">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው አዝኖ፥ “አም​ስት ወይም ስድ​ስት ጊዜ መት​ተ​ኸው ቢሆን ኖሮ ሶር​ያ​ው​ያ​ንን እስ​ክ​ታ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ በመ​ታ​ኻ​ቸው ነበር፤ አሁን ግን ሦስት ጊዜ ብቻ ሶር​ያን ትመ​ታ​ለህ” አለ።</verse>
				<verse number="20">ኤል​ሳ​ዕም ሞተ፤ ቀበ​ሩ​ትም። ከሞ​ዓ​ብም አደጋ ጣዮች በየ​ዓ​መቱ መጀ​መ​ሪያ ወደ ሀገሩ ይገቡ ነበር።</verse>
				<verse number="21">ሰዎ​ችም አንድ ሰው ሲቀ​ብሩ አደጋ ጣዮ​ችን አዩ፤ ሬሳ​ው​ንም በኤ​ል​ሳዕ መቃ​ብር ላይ ጣሉት፤ የኤ​ል​ሳ​ዕ​ንም አጥ​ንት በነካ ጊዜ ሰው​ዬው ድኖ በእ​ግሩ ቆመ።</verse>
				<verse number="22">አዛ​ሄ​ልም በኢ​ዮ​አ​ካዝ ዘመን ሁሉ እስ​ራ​ኤ​ልን አስ​ጨ​ነቀ፤</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ራራ​ላ​ቸው፤ ማራ​ቸ​ውም፤ ከአ​ብ​ር​ሃ​ምና ከይ​ስ​ሐቅ፥ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ጋር ስላ​ደ​ረ​ገው ቃል ኪዳን እነ​ር​ሱን ተመ​ለ​ከተ፤ ሊያ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም አል​ወ​ደ​ደም፤ ፈጽ​ሞም ከፊቱ አል​ጣ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="24">የሶ​ር​ያም ንጉሥ አዛ​ሄል ሞተ፤ ልጁም ወልደ አዴር በፋ​ን​ታው ነገሠ።</verse>
				<verse number="25">አዛ​ሄ​ልም ከአ​ባቱ ከኢ​ዮ​አ​ካዝ እጅ በሰ​ልፍ የወ​ሰ​ዳ​ቸ​ውን ከተ​ሞች የኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ ዮአስ መልሶ ከአ​ዛ​ሄል ልጅ ከወ​ልደ አዴር እጅ ወሰደ። ዮአ​ስም ሦስት ጊዜ መታው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ከተ​ሞች መለሰ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ በዮ​አስ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​አስ ልጅ አሜ​ስ​ያስ ነገሠ።</verse>
				<verse number="2">መን​ገ​ሥም በጀ​መረ ጊዜ ዕድ​ሜው ሃያ አም​ስት ዓመት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ። እና​ቱም ዮአ​ድም የተ​ባ​ለች የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="3">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ፤ ነገር ግን አባቱ ኢዮ​አስ እን​ዳ​ደ​ረገ ሁሉ እንጂ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት አላ​ደ​ረ​ገም።</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ያሉ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎች አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ ሕዝ​ቡም ገና በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ባሉት መስ​ገ​ጃ​ዎች ይሠ​ዋና ያጥን ነበር።</verse>
				<verse number="5">መን​ግ​ሥ​ቱም በእጁ በጸ​ና​ለት ጊዜ አባ​ቱን የገ​ደ​ሉ​ትን አገ​ል​ጋ​ዮች ገደለ።</verse>
				<verse number="6">በሙሴ ሕግ መጽ​ሐ​ፍም እንደ ተጻፈ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሁሉ በኀ​ጢ​አቱ ይሙት እንጂ አባ​ቶች ስለ ልጆች አይ​ሙቱ፤ ልጆ​ችም ስለ አባ​ቶች አይ​ሙቱ” ብሎ እን​ዳ​ዘዘ የነ​ፍሰ ገዳ​ዮ​ቹን ልጆች አል​ገ​ደ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="7">እር​ሱም በጨው ሸለቆ ከኤ​ዶ​ም​ያስ ዐሥር ሺህ ሰው ገደለ፤ ሴላ​ንም በጦ​ር​ነት ወስዶ ስም​ዋን እስከ ዛሬ ድረስ “ዮቅ​ት​ኤል” ብሎ ጠራት።</verse>
				<verse number="8">በዚ​ያን ጊዜም አሜ​ስ​ያስ፥ “ና እርስ በር​ሳ​ችን ፊት ለፊት እን​ተ​ያይ” ብሎ ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮ​አ​ካዝ ልጅ ወደ ዮአስ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ።</verse>
				<verse number="9">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዮአስ፥ “የሊ​ባ​ኖስ ኵር​ን​ችት፦ ልጅ​ህን ለልጄ ሚስት አድ​ር​ገህ ስጠው ብሎ ወደ ሊባ​ኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊ​ባ​ኖ​ስም አውሬ አልፎ ኵር​ን​ች​ቱን ረገጠ።</verse>
				<verse number="10">ኤዶ​ም​ያ​ስን በእ​ው​ነት መታህ፤ ልብ​ህ​ንም ከፍ ከፍ አደ​ረ​ግህ፤ በዚያ ተመካ፤ በቤ​ት​ህም ተቀ​መጥ፤ አንተ፥ ይሁ​ዳም ከአ​ንተ ጋር ትወ​ድቁ ዘንድ ስለ ምን መከ​ራን ትሻ​ለህ?” ብሎ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜ​ስ​ያስ ላከ።</verse>
				<verse number="11">አሜ​ስ​ያስ ግን አል​ሰ​ማም፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዮአስ ዘመተ፤ እር​ሱና የይ​ሁዳ ንጉሥ አሜ​ስ​ያ​ስም በይ​ሁዳ ባለች በቤ​ት​ሳ​ሚስ ፊት ለፊት ተያዩ።</verse>
				<verse number="12">ይሁ​ዳም በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ተመታ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ ድን​ኳኑ ሸሸ።</verse>
				<verse number="13">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዮአስ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የአ​ካ​ዝ​ያ​ስን ልጅ የኢ​ዮ​አ​ስን ልጅ አሜ​ስ​ያ​ስን በቤ​ት​ሳ​ሚስ ይዞ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቅጥር ከኤ​ፍ​ሬም በር ጀምሮ እስከ ማዕ​ዘኑ በር ድረስ አራት መቶ ክንድ አፈ​ረሰ።</verse>
				<verse number="14">ወር​ቁ​ንና ብሩን ሁሉ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤትና በን​ጉሥ ቤተ መዛ​ግ​ብት የነ​በ​ሩ​ትን ዕቃ​ዎች ሁሉ፤ በመ​ያ​ዣም የተ​ያ​ዙ​ትን ልጆች ወስዶ ወደ ሰማ​ርያ ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="15">የቀ​ረ​ውም ያደ​ረ​ገው የዮ​አስ ነገር፥ ኀይ​ሉም፥ ከይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ከአ​ሜ​ስ​ያስ ጋር እንደ ተዋጋ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="16">ዮአ​ስም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በሰ​ማ​ር​ያም ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት ጋር ተቀ​በረ፤ ልጁም ኢዮ​ር​ብ​ዓም በፋ​ን​ታው ነገሠ።</verse>
				<verse number="17">የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​አስ ልጅ አሜ​ስ​ያስ ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ከኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ ከዮ​አስ ሞት በኋላ ዐሥራ አም​ስት ዓመት ኖረ።</verse>
				<verse number="18">የቀ​ረ​ውም የአ​ሜ​ስ​ያስ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="19">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የዐ​መፅ መሐላ አደ​ረ​ጉ​በት፤ እር​ሱም ወደ ለኪሶ ኮበ​ለለ፤ ወደ ለኪ​ሶም ተከ​ተ​ሉት፤ በዚ​ያም ገደ​ሉት።</verse>
				<verse number="20">በድ​ኑ​ንም በፈ​ረስ ጭነው አመ​ጡት፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ቀበ​ሩት።</verse>
				<verse number="21">የይ​ሁ​ዳም ሕዝብ ሁሉ የዐ​ሥራ ስድ​ስት ዓመት ልጅ የነ​በ​ረ​ውን ዓዛ​ር​ያ​ስን ወስ​ደው በአ​ባቱ በአ​ሜ​ስ​ያስ ፋንታ አነ​ገ​ሡት።</verse>
				<verse number="22">ንጉ​ሡም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ከአ​ን​ቀ​ላፋ በኋላ፥ ኤላ​ትን ሠርቶ ወደ ይሁዳ መለ​ሳት።</verse>
				<verse number="23">በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​አስ ልጅ በአ​ሜ​ስ​ያስ በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የዮ​አስ ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም በሰ​ማ​ርያ መን​ገሥ ጀመረ፤ አርባ አንድ ዓመ​ትም ነገሠ።</verse>
				<verse number="24">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገር አደ​ረገ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ካሳ​ታ​ቸው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት ሁሉ አል​ራ​ቀም።</verse>
				<verse number="25">በጋ​ት​ሔ​ፌር በነ​በ​ረው በአ​ማቴ ልጅ በባ​ሪ​ያው በነ​ቢዩ በዮ​ናስ አፍ እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እስ​ራ​ኤል አም​ላክ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ድን​በር ከሔ​ማት መግ​ቢያ ጀምሮ እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ መለሰ።</verse>
				<verse number="26">በቍ​ጥር እን​ዳ​ነሱ፥ የታ​ሰ​ረ​ውና የተ​ለ​ቀ​ቀ​ውም እንደ ጠፋ፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም የሚ​ረዳ እን​ዳ​ል​ነ​በረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅግ የመ​ረ​ረ​ውን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጭን​ቀት አየ።</verse>
				<verse number="27">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ዘር ከሰ​ማይ በታች ይደ​መ​ስስ ዘንድ አል​ተ​ና​ገ​ረም፤ ነገር ግን በዮ​አስ ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም እጅ አዳ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="28">የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ ኀይ​ሉም፥ የይ​ሁዳ የነ​በ​ረ​ውን ደማ​ስ​ቆ​ንና ሔማ​ትን ለእ​ስ​ራ​ኤል እንደ መለሰ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="29">ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም እንደ አባ​ቶቹ እንደ እስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት አን​ቀ​ላፋ፤ ልጁም ዘካ​ር​ያስ በፋ​ን​ታው ነገሠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የአ​ሜ​ስ​ያስ ልጅ ዓዛ​ር​ያስ ነገሠ።</verse>
				<verse number="2">ዓዛ​ር​ያ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የዐ​ሥራ ስድ​ስት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አምሳ ሁለት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ኮልያ የተ​ባ​ለች የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="3">አባቱ አሜ​ስ​ያስ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ቶች ላይ የነ​በ​ሩ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎች አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ ሕዝ​ቡም ገና በኮ​ረ​ብ​ቶች ላይ በነ​በ​ሩት መስ​ገ​ጃ​ዎች ይሠ​ዋና ያጥን ነበር።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ንጉ​ሡን በደዌ ዳሰ​ሰው፤ እስ​ከ​ሚ​ሞ​ት​በ​ትም ቀን ለም​ጻም ሆነ፤ በተ​ለየ ቤትም ይቀ​መጥ ነበር፤ የን​ጉ​ሡም ልጅ ኢዮ​አ​ታም በን​ጉሡ ቤት ላይ ሠል​ጥኖ ለሀ​ገሩ ሕዝብ ይፈ​ርድ ነበር።</verse>
				<verse number="6">የቀ​ረ​ውም የዓ​ዛ​ር​ያስ ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="7">ዓዛ​ር​ያ​ስም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ፥ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ቀበ​ሩት፤ ልጁም ኢዮ​አ​ታም በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።</verse>
				<verse number="8">በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በዓ​ዛ​ር​ያስ በሠ​ላሳ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመት የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ልጅ ዘካ​ር​ያስ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ ስድ​ስት ወር ነገሠ።</verse>
				<verse number="9">አባ​ቶ​ቹም እን​ዳ​ደ​ረ​ጉት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ካሳ​ታ​ቸው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት አል​ራ​ቀም።</verse>
				<verse number="10">የኢ​ያ​ቢ​ስም ልጅ ሴሎም፤ ሌሎ​ችም ከዱት፤ በይ​ብ​ል​ዓም መት​ተው ገደ​ሉት፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ሴሎም ነገሠ።</verse>
				<verse number="11">የቀ​ረ​ውም የዘ​ካ​ር​ያስ ነገር፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="12">ለኢዩ፥ “ልጆ​ችህ እስከ አራት ትው​ልድ ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን ላይ ይቀ​መ​ጣሉ” ተብሎ የተ​ነ​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነበረ፤ እን​ዲ​ሁም ሆነ።</verse>
				<verse number="13">በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በዓ​ዛ​ር​ያስ በሠ​ላሳ ዘጠ​ነ​ኛው ዓመት የኢ​ያ​ቢስ ልጅ ሴሎም ነገሠ፤ በሰ​ማ​ር​ያም አንድ ወር ነገሠ።</verse>
				<verse number="14">የጋ​ዲም ልጅ ምና​ሔም ከቴ​ር​ሳ​ላቅ ወጥቶ ወደ ሰማ​ርያ ሄደ፤ በሰ​ማ​ር​ያም የኢ​ያ​ቢ​ስን ልጅ ሴሎ​ምን መታ፤ ገደ​ለ​ውም፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ነገሠ።</verse>
				<verse number="15">የቀ​ረ​ውም የሴ​ሎም ነገር፥ የተ​ማ​ማ​ለ​ውም ዐመፅ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሓፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="16">በዚያ ጊዜም ምና​ሔም ቴር​ሳን፥ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ሁሉ፥ ዳር​ቻ​ዋ​ንም መታ፤ ይከ​ፍ​ቱ​ለ​ትም ዘንድ አል​ወ​ደ​ዱ​ምና መታት፤ በእ​ር​ስ​ዋም የነ​በ​ሩ​ትን እር​ጉ​ዞች ሁሉ ሰነ​ጠ​ቃ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">በይ​ሁዳ ንጉሥ በዓ​ዛ​ር​ያስ በሠ​ላሳ ዘጠ​ነ​ኛው ዓመት የጋዲ ልጅ ምና​ሔም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ ዐሥር ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="18">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልን ካሳ​ተው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አ​ትም አል​ራ​ቀም።</verse>
				<verse number="19">በዘ​መ​ኑም የአ​ሶር ንጉሥ ፎሐ በም​ድ​ሪቱ ላይ ወጣ፤ ምና​ሔ​ምም የፎሐ እጅ ከእ​ርሱ ጋር እን​ዲ​ሆን አንድ ሺህ መክ​ሊት ብር ሰጠው።</verse>
				<verse number="20">ምና​ሔ​ምም ብሩን ለአ​ሶር ንጉሥ ይሰጥ ዘንድ በእ​ስ​ራ​ኤል ባለ​ጠ​ጎች ሁሉ ላይ በእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ላይ አምሳ ሰቅል ብር አስ​ገ​ብሮ አወጣ። የአ​ሶ​ርም ንጉሥ ተመ​ለሰ፤ በሀ​ገ​ሪ​ቱም አል​ተ​ቀ​መ​ጠም።</verse>
				<verse number="21">የቀ​ረ​ውም የም​ና​ሔም ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="22">ምና​ሔ​ምም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ፤ ልጁም ፋቂ​ስ​ያስ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።</verse>
				<verse number="23">በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በዓ​ዛ​ር​ያስ በአ​ም​ሳ​ኛው ዓመት የም​ና​ሔም ልጅ ፋቂ​ስ​ያስ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ መን​ገሥ ጀመረ፤ ሁለት ዓመ​ትም ነገሠ።</verse>
				<verse number="24">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልን ካሳ​ተው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አ​ትም አል​ራ​ቀም።</verse>
				<verse number="25">የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ ከዳው፤ በሰ​ማ​ር​ያም በን​ጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ከአ​ር​ጎ​ብና ከአ​ርያ ጋር መታው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ከገ​ለ​ዓ​ዳ​ው​ያን አምሳ ሰዎች ነበሩ፤ ገደ​ለ​ውም፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ነገሠ።</verse>
				<verse number="26">የቀ​ረ​ውም የፋ​ቂ​ስ​ያስ ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="27">በይ​ሁዳ ንጉሥ በዓ​ዛ​ር​ያስ በአ​ምሳ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ መን​ገሥ ጀመረ፤ ሃያ ዓመ​ትም ነገሠ።</verse>
				<verse number="28">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልን ካሳ​ተው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አ​ትም አል​ራ​ቀም።</verse>
				<verse number="29">በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በፋ​ቁሔ ዘመን የአ​ሶር ንጉሥ ቴል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶር መጣ፤ ኢዮ​ንና አቤ​ል​ቤ​ት​መ​ዓ​ካን፥ ያኖ​ዋ​ንም፥ ቃዴ​ስ​ንና አሶ​ር​ንም፥ ገለ​ዓ​ድ​ንና ገሊ​ላ​ንም፥ የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶ​ርም አፈ​ለ​ሳ​ቸው።</verse>
				<verse number="30">በዖ​ዝ​ያ​ንም ልጅ በኢ​ዮ​አ​ታም በሃ​ያ​ኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በሮ​ሜ​ልዮ ልጅ በፋ​ቁሔ ላይ ዐመ​ፀ​በት፤ መት​ቶም ገደ​ለው፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ነገሠ።</verse>
				<verse number="31">የቀ​ረ​ውም የፋ​ቁሔ ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="32">በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በሮ​ሜ​ልዩ ልጅ በፋ​ቁሔ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የይ​ሁዳ ንጉሥ የዓ​ዛ​ር​ያስ ልጅ ኢዮ​አ​ታም ነገሠ።</verse>
				<verse number="33">መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ ሃያ አም​ስት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ ስድ​ስት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም የሳ​ዶቅ ልጅ ኢየ​ሩሳ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="34">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ፤ አባቱ ዓዛ​ር​ያስ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ እን​ዲሁ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="35">ነገር ግን የጣ​ዖ​ታ​ቱን ቤት አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ ሕዝ​ቡም ገና በኮ​ረ​ብ​ቶች ላይ ይሠ​ዉና ያጥኑ ነበር። እር​ሱም የላ​ይ​ኛ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት በር ሠራ።</verse>
				<verse number="36">የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​አ​ታም ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="37">በዚ​ያም ወራት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሶ​ር​ያን ንጉሥ ረአ​ሶ​ን​ንና የሮ​ሜ​ል​ዩን ልጅ ፋቁ​ሔን በይ​ሁዳ ላይ መላክ ጀመረ።</verse>
				<verse number="38">ኢዮ​አ​ታ​ምም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ፥ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ፤ ልጁም አካዝ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">በሮ​ሜ​ልዩ ልጅ በፋ​ቁሔ በዐ​ሥራ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​አ​ታም ልጅ አካዝ ነገሠ።</verse>
				<verse number="2">አካዝ መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ ስድ​ስት ዓመት ነገሠ፤ እንደ አባ​ቱም እንደ ዳዊት በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በታ​ማ​ኝ​ነት ቅን ነገ​ርን አላ​ደ​ረ​ገም።</verse>
				<verse number="3">ነገር ግን በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መን​ገድ ሄደ፤ ደግ​ሞም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ዳ​ሳ​ደ​ዳ​ቸው እንደ አሕ​ዛብ ርኵ​ሰት ልጁን በእ​ሳት ሠዋው።</verse>
				<verse number="4">በመ​ስ​ገ​ጃ​ዎ​ቹና በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ በለ​መ​ለ​መ​ውም ዛፍ ሁሉ በታች ይሠ​ዋና ያጥን ነበር።</verse>
				<verse number="5">ያን ጊዜም የሶ​ርያ ንጉሥ ረአ​ሶ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ ሊዋጉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጡ፤ አካ​ዝ​ንም ከበ​ቡት፥ ሊያ​ሸ​ን​ፉት ግን አል​ቻ​ሉም።</verse>
				<verse number="6">በዚ​ያም ዘመን የሶ​ርያ ንጉሥ ረአ​ሶን ኤላ​ትን ወደ ሶርያ መለ​ሰ​ላ​ቸው፥ አይ​ሁ​ድ​ንም ከኤ​ላት አሳ​ደደ፤ ኤዶ​ማ​ው​ያ​ንም ወደ ኤላት መጥ​ተው እስከ ዛሬ ድረስ በዚያ ይኖ​ራሉ።</verse>
				<verse number="7">አካ​ዝም፥ “እኔ ባሪ​ያ​ህና ልጅህ ነኝ፤ መጥ​ተህ ከተ​ነ​ሡ​ብኝ ከሶ​ርያ ንጉ​ሥና ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እጅ አድ​ነኝ” ብሎ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ቴል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶር መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ።</verse>
				<verse number="8">አካ​ዝም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና በን​ጉሡ ቤተ መዛ​ግ​ብት የተ​ገ​ኘ​ውን ብርና ወርቅ ወስዶ ወደ አሦር ንጉሥ ገጸ በረ​ከት አድ​ርጎ ሰደ​ደው።</verse>
				<verse number="9">የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ሰማው፤ የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ወደ ደማ​ስቆ ወጣ፤ ያዛ​ትም፤ ሕዝ​ብ​ዋ​ንም ወደ ቂር አፈ​ለ​ሳ​ቸው፤ ረአ​ሶ​ን​ንም ገደ​ለው።</verse>
				<verse number="10">የይ​ሁዳ ንጉሥ አካ​ዝም የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ቴል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶ​ርን ሊገ​ና​ኘው ወደ ደማ​ስቆ ሄደ፤ በደ​ማ​ስቆ የነ​በ​ረ​ው​ንም መሠ​ዊያ አየ፤ ንጉ​ሡም አካዝ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ምሳ​ሌና የአ​ሠ​ራ​ሩን መልክ ወደ ካህኑ ወደ ኦርያ ላከው።</verse>
				<verse number="11">ካህ​ኑም ኦርያ ንጉሡ አካዝ ከደ​ማ​ስቆ እንደ ላከ​ለት መሠ​ዊ​ያ​ውን ሁሉ ሠራ፤ እን​ዲ​ሁም ካህኑ ኦርያ ንጉሡ አካዝ ከደ​ማ​ስቆ እስ​ኪ​መጣ ድረስ ሠራው።</verse>
				<verse number="12">ንጉ​ሡም ከደ​ማ​ስቆ በመጣ ጊዜ መሠ​ዊ​ያ​ውን አየ፤ ንጉ​ሡም ወደ መሠ​ዊ​ያው ወጣ።</verse>
				<verse number="13">የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን አሳ​ረገ፤ የመ​ጠ​ጡ​ንም ቍር​ባን አፈ​ሰሰ፤ የደ​ኅ​ን​ነ​ቱ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ደም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ረጨ።</verse>
				<verse number="14">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት የነ​በ​ረ​ውን የና​ሱን መሠ​ዊያ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት ከመ​ሠ​ዊ​ያ​ውና ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መካ​ከል ፈቀቅ አድ​ርጎ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ በሰ​ሜን በኩል አኖ​ረው።</verse>
				<verse number="15">ንጉ​ሡም አካዝ፥ “የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን የጥ​ዋት መሥ​ዋ​ዕት፥ የማ​ታ​ው​ንም የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የን​ጉ​ሡ​ንም መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ሁሉ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን፥ የመ​ጠ​ጡ​ንም ቍር​ባን በታ​ላቁ መሠ​ዊያ ላይ አቅ​ርብ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ደም ሁሉ፥ የሌ​ላ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ደም ሁሉ በእ​ርሱ ላይ ርጭ​በት፤ የናሱ መሠ​ዊያ ግን በየ​ጥ​ዋቱ ለእኔ ይሁን” ብሎ ካህ​ኑን ኦር​ያን አዘ​ዘው።</verse>
				<verse number="16">ካህኑ ኦር​ያም ንጉሡ አካዝ እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ እን​ዲሁ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="17">ንጉሡ አካ​ዝም የመ​ቀ​መ​ጫ​ዎ​ችን ክፈፍ ቈረጠ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰኖች ወሰደ፤ ኵሬ​ው​ንም ከበ​ታቹ ከነ​በ​ሩት ከናሱ በሬ​ዎች አወ​ረ​ደው፤ በጠ​ፍ​ጣ​ፋ​ውም ድን​ጋይ ላይ አኖ​ረው።</verse>
				<verse number="18">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የዙ​ፋ​ኑን መሠ​ረት ሠራ፤ ስለ አሦ​ርም ንጉሥ በውጭ ያለ​ውን የን​ጉ​ሡን መግ​ቢያ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አዞ​ረው።</verse>
				<verse number="19">የቀ​ረ​ውም አካዝ ያደ​ረ​ገው ነገር እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="20">አካ​ዝም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ፥ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ተቀ​በረ፤ ልጁም ሕዝ​ቅ​ያስ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">የይ​ሁዳ ንጉሥ አካዝ በነ​ገሠ በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="2">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ ነገር ግን ከእ​ርሱ አስ​ቀ​ድሞ እንደ ነበ​ሩት እንደ እስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት አል​ሆ​ነም።</verse>
				<verse number="3">የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ስል​ም​ና​ሶር በእ​ርሱ ላይ ዘመተ፤ ሆሴ​ዕም ተገ​ዛ​ለት፤ ግብ​ርም አመ​ጣ​ለት።</verse>
				<verse number="4">የአ​ሦ​ርም ንጉሥ በሆ​ሴዕ ላይ ዐመፅ አገኘ፤ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ች​ን ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ሴጎር ልኮ ነበ​ርና፤ እንደ ልማ​ዱም በየ​ዓ​መቱ ለአ​ሦር ንጉሥ ግብር አል​ሰ​ጠ​ምና፤ ስለ​ዚህ የአ​ሦር ንጉሥ ተዋ​ጋው፤ ይዞም በወ​ህኒ ቤት አሰ​ረው።</verse>
				<verse number="5">የአ​ሦ​ርም ንጉሥ በም​ድር ሁሉ ላይ ወጣ፤ ወደ ሰማ​ር​ያም ወጥቶ ሦስት ዓመት ከበ​ባት።</verse>
				<verse number="6">በሆ​ሴ​ዕም በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመት የአ​ሦር ንጉሥ ሰማ​ር​ያን ያዘ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ወደ አሶር አፈ​ለሰ፤ በአ​ላ​ሔና በአ​ቦር፤ በጎ​ዛ​ንም ወንዝ፤ በሜ​ዶ​ንም ከተ​ሞች አኖ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከግ​ብፅ ንጉሥ ከፈ​ር​ዖን እጅ፥ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ቸ​ውን አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በድ​ለው ነበ​ርና፥ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት አም​ል​ከው ነበ​ርና፤</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት በአ​ሳ​ደ​ዳ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ ሥር​ዐት፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ሥ​ታት ባደ​ረ​ጓት ሥር​ዐት ሄደው ነበ​ርና እን​ደ​ዚህ ሆነ።</verse>
				<verse number="9">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በአ​ም​ላ​ካ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ቅን ያል​ሆ​ነን ነገር በስ​ውር አደ​ረጉ፤ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ከዘ​በ​ኞች ግንብ ጀምሮ እስከ ተመ​ሸ​ገች ከተማ ድረስ በከ​ፍ​ታ​ዎች ላይ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን ሠሩ።</verse>
				<verse number="10">በረ​ጃ​ጅሙ ኮረ​ብታ ሁሉ ላይ፥ በለ​መ​ለ​መ​ውም ዛፍ ሁሉ በታች ሐው​ል​ቶ​ች​ንና የማ​ም​ለ​ኪያ ዐም​ዶ​ችን ተከሉ፤</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፊ​ታ​ቸው ያወ​ጣ​ቸው አሕ​ዛብ እን​ዳ​ደ​ረ​ጉት፥ በኮ​ረ​ብ​ቶቹ መስ​ገ​ጃ​ዎች ሁሉ ላይ ያጥኑ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያስ​ቈጡ ዘንድ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ች​ንና ሐው​ል​ቶ​ችን አደ​ረጉ፤</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ይህን አታ​ድ​ርጉ” ብሎ የከ​ለ​ከ​ላ​ቸ​ውን ጣዖ​ቶች አመ​ለኩ።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ከክፉ መን​ገ​ዳ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁት፥ በባ​ሪ​ያ​ዎቼ በነ​ቢ​ያት የላ​ክ​ሁ​ላ​ች​ሁን ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሥር​ዐ​ቴን፥ ሕጌ​ንም ሁሉ ጠብቁ” ብሎ በነ​ቢዩ ሁሉና በባለ ራእዩ አፍ ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ መሰ​ከረ።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ላ​መኑ ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አን​ገት ይልቅ አን​ገ​ታ​ቸ​ውን አደ​ነ​ደኑ እንጂ አል​ሰ​ሙም።</verse>
				<verse number="15">የገ​ባ​ላ​ቸ​ው​ንም ቃል ኪዳን ሁሉ አል​ጠ​በ​ቁም። ከንቱ ነገ​ር​ንም ተከ​ተሉ፤ ከን​ቱም ሆኑ፤ እንደ እነ​ር​ሱም እን​ዳ​ይ​ሠሩ ያዘ​ዛ​ቸ​ውን በዙ​ሪ​ያ​ቸው ያሉ​ትን አሕ​ዛብ ተከ​ተሉ።</verse>
				<verse number="16">የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ሁሉ ተዉ፤ ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም የሁ​ለ​ቱን እን​ቦ​ሶች ምስ​ሎች አደ​ረጉ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ድ​ንም ተከሉ፤ ለሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ ሰገዱ፤ በዓ​ል​ንም አመ​ለኩ።</verse>
				<verse number="17">ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ሥዉ​አ​ቸው፤ ምዋ​ር​ተ​ኞ​ችና አስ​ማ​ተ​ኞ​ችም ሆኑ፤ ያስ​ቈ​ጡ​ትም ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገር ለማ​ድ​ረግ ራሳ​ቸ​ውን ሸጡ።</verse>
				<verse number="18">ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ እጅግ ተቈጣ፤ ከፊ​ቱም ጣላ​ቸው፤ ከይ​ሁ​ዳም ነገድ ብቻ በቀር ማንም አል​ቀ​ረም።</verse>
				<verse number="19">ይሁ​ዳም ደግሞ እስ​ራ​ኤል ባደ​ረ​ጋት ሥር​ዐት ሄደ እንጂ የአ​ም​ላ​ኩን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ አል​ጠ​በ​ቀም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ተዉት።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘር ሁሉ ተቈጣ፤ አስ​ጨ​ነ​ቃ​ቸ​ውም፤ ከፊ​ቱም እስ​ኪ​ጥ​ላ​ቸው ድረስ በበ​ዝ​ባ​ዦች እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">እስ​ራ​ኤ​ልም ከዳ​ዊት ቤት ተለዩ፤ የና​ባ​ጥ​ንም ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምን አነ​ገሡ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ከ​ተል እስ​ራ​ኤ​ልን መለሰ፤ ታላ​ቅም ኀጢ​አት አሠ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ኢዮ​ር​ብ​ዓም ባደ​ረ​ገው ኀጢ​አት ሁሉ ሄዱ፤</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሪ​ያ​ዎቹ በነ​ቢ​ያት ሁሉ አፍ እንደ ተና​ገ​ረው እስ​ራ​ኤ​ልን ከፊቱ እስ​ኪ​ያ​ወጣ ድረስ ከእ​ር​ስዋ አል​ራ​ቁም። እስ​ራ​ኤ​ልም እስከ ዛሬ ድረስ ከም​ድሩ ወደ አሦር ፈለሰ።</verse>
				<verse number="24">የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ከባ​ቢ​ሎ​ንና ከኩታ፥ ከአ​ዋና ከሐ​ማት፥ ከሴ​ፌ​ር​ዋ​ይም ሰዎ​ችን አመጣ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ፋንታ በሰ​ማ​ርያ ከተ​ሞች አኖ​ራ​ቸው፤ ሰማ​ር​ያ​ንም ወረ​ሱ​አት፤ በከ​ተ​ሞ​ች​ዋም ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="25">በዚ​ያም መቀ​መጥ በጀ​መሩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አይ​ፈ​ሩ​ትም ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​በ​ሶ​ችን ሰደ​ደ​ባ​ቸው፤ ይገ​ድ​ሉ​አ​ቸ​ውም ነበር።</verse>
				<verse number="26">ስለ​ዚ​ህም ለአ​ሦር ንጉሥ፥ “ያፈ​ለ​ስ​ኻ​ቸው፥ በሰ​ማ​ር​ያም ከተ​ሞች ያኖ​ር​ኻ​ቸው ሕዝ​ቦች የሀ​ገ​ሩን አም​ላክ ሕግ አላ​ወ​ቁም፤ የሀ​ገ​ሩን አም​ላክ ሕግ አላ​ወ​ቁ​ምና አን​በ​ሶ​ችን ሰድ​ዶ​ባ​ቸ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ እየ​ገ​ደ​ሉ​አ​ቸው ነው” ብለው ተና​ገ​ሩት።</verse>
				<verse number="27">የአ​ሦ​ርም ንጉሥ፥ “ከዚያ ካመ​ጣ​ኋ​ቸው ካህ​ናት አን​ዱን ውሰዱ፤ ሄዶም በዚያ ይቀ​መጥ፤ የሀ​ገ​ሩ​ንም አም​ላክ ሕግ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው” ብሎ አዘዘ።</verse>
				<verse number="28">ከሰ​ማ​ር​ያም ካፈ​ለ​ሱ​አ​ቸው ካህ​ናት አን​ዱን ወስ​ደው በቤ​ቴል አኖ​ሩት፤ ያም ካህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዴት እን​ደ​ሚ​ፈ​ሩት ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="29">በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸ​ውም አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን አደ​ረጉ፤ ሳም​ራ​ው​ያ​ንም በሠ​ሯቸው በኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች ሕዝቡ ሁሉ በሚ​ኖ​ሩ​ባቸው ከተ​ሞ​ቻ​ቸው አኖ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="30">የባ​ቢ​ሎ​ንም ሰዎች ሴኬ​ቤ​ቴ​ና​ሆ​ምን ሠሩ፤ የኩ​ታም ሰዎች ኤር​ጌ​ትን ሠሩ፤</verse>
				<verse number="31">የሐ​ማ​ትም ሰዎች አሲ​ማ​ትን ሠሩ፤ አዋ​ው​ያ​ንም ኤል​ባ​ዝ​ር​ንና ተር​ታ​ቅን ሠሩ፤ የሴ​ፌ​ር​ዋ​ይም ሰዎች ለሴ​ፌ​ር​ዋ​ይም አማ​ል​ክት ለአ​ድ​ራ​ሜ​ሌ​ክና ለአ​ኔ​ሜ​ሌክ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ሳት ይሠዉ ነበር።</verse>
				<verse number="32">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ይፈሩ ነበር፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በሚ​ኖ​ሩ​በት ከተማ በሰ​ማ​ርያ በሠ​ሩት በከ​ፍ​ታው ቦታ ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አኖሩ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ይፈሩ ነበር፤ ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ለኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች ካህ​ና​ትን አደ​ረጉ፤ በኮ​ረ​ብ​ታ​ውም መስ​ገ​ጃ​ዎች ይሠዉ ነበር።</verse>
				<verse number="33">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሲፈሩ ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው እንደ ፈለ​ሱት እንደ አሕ​ዛብ ልማድ አም​ላ​ካ​ቸ​ውን ያመ​ልኩ ነበር።</verse>
				<verse number="34">እስከ ዛሬም ድረስ እንደ ልማ​ዳ​ቸው ያደ​ር​ጋሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ይፈ​ራሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስ​ራ​ኤል ብሎ የጠ​ራ​ውን የያ​ዕ​ቆ​ብን ልጆች እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው ሥር​ዐ​ትና ፍርድ፥ ሕግና ትእ​ዛ​ዝም ያደ​ር​ጋሉ።</verse>
				<verse number="35">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው፤ አት​ስ​ገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፤ አታ​ም​ል​ኩ​አ​ቸ​ውም፤ አት​ሠ​ዉ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="36">ነገር ግን በታ​ላቅ ኀይል በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እር​ሱን ፍሩ፤ ለእ​ር​ሱም ስገዱ፤ ለእ​ር​ሱም ሠዉ።</verse>
				<verse number="37">የጻ​ፈ​ላ​ች​ሁ​ንም ሥር​ዐ​ትና ፍርድ፥ ሕግና ትእ​ዛ​ዝም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ፤ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት አት​ፍሩ።</verse>
				<verse number="38">ከእ​ና​ን​ተም ጋር ያደ​ረ​ገ​ውን ቃል ኪዳን አት​ርሱ፤ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት አት​ፍሩ።</verse>
				<verse number="39">ነገር ግን አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍሩ፤ እር​ሱም ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸሁ ሁሉ እጅ ያድ​ና​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="40">ነገር ግን እነ​ርሱ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጉት ልማ​ዳ​ቸ​ውን አት​ስሙ።</verse>
				<verse number="41">እነ​ዚ​ህም አሕ​ዛብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈሩ ነበር፤ ደግ​ሞም የተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ያመ​ልኩ ነበር፤ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም፥ የልጅ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም አባ​ቶ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ደ​ረጉ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋሉ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የኤላ ልጅ ሆሴዕ በነ​ገሠ በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የአ​ካዝ ልጅ ሕዝ​ቅ​ያስ ነገሠ።</verse>
				<verse number="2">መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜም የሃያ አም​ስት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም የዘ​ካ​ር​ያስ ልጅ አቡ ትባል ነበር።</verse>
				<verse number="3">እር​ሱም አባቱ ዳዊት እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="4">በኮ​ረ​ብ​ታም ያሉ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎች አስ​ወ​ገደ፤ ሐው​ል​ቶ​ች​ንም ሰባ​በረ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ች​ንም ነቃ​ቀለ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እስ​ከ​ዚህ ዘመን ድረስ ያጥ​ኑ​ለት ነበ​ርና ሙሴ የሠ​ራ​ውን የና​ሱን እባብ አጠፋ፤ ስሙ​ንም “ነሑ​ስ​ታን” ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="5">በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመነ፤ ከእ​ርሱ በፊት ከነ​በ​ሩት ከይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ሁሉ እር​ሱን የሚ​መ​ስል አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ተከ​ተለ፤ እር​ሱ​ንም ከመ​ከ​ተል አል​ራ​ቀም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙሴ ያዘ​ዘ​ውን ትእ​ዛ​ዛ​ቱን ጠበቀ።</verse>
				<verse number="7">በሚ​ሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ በአ​ሦ​ርም ንጉሥ ላይ ዐመፀ፤ አል​ተ​ገ​ዛ​ለ​ት​ምም።</verse>
				<verse number="8">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም እስከ ጋዛና እስከ ዳር​ቻዋ ድረስ፥ ከዘ​በ​ኞች ግንብ ጀምሮ እስከ ምሽጉ ከተማ ድረስ አጠፋ።</verse>
				<verse number="9">ሕዝ​ቅ​ያስ በነ​ገሠ በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የኤላ ልጅ ሆሴዕ በነ​ገሠ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት፥ የአ​ሦር ንጉሥ ስል​ም​ና​ሶር ወደ ሰማ​ርያ ወጣ፤ ከበ​ባ​ትም።</verse>
				<verse number="10">በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ያዛት፤ በሕ​ዝ​ቅ​ያስ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በሆ​ሴዕ በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመተ መን​ገ​ሥት፥ ሰማ​ርያ ተያ​ዘች።</verse>
				<verse number="11">የአ​ሦ​ርም ንጉሥ እስ​ራ​ኤ​ልን ወደ አሦር አፈ​ለሰ፤ በአ​ላ​ሔና በአ​ቦር በጎ​ዛ​ንም ወንዝ፥ በሜ​ዶ​ንም አው​ራ​ጃ​ዎች አኖ​ራ​ቸው፤</verse>
				<verse number="12">የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ሙ​ምና፥ ቃል ኪዳ​ኑ​ንም አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባሪያ ሙሴ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አል​ሰ​ሙ​ምና፤ አላ​ደ​ረ​ጉ​ም​ምና።</verse>
				<verse number="13">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በነ​ገሠ በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ዓመት የአ​ሦር ንጉሥ ሰና​ክ​ሬም ወደ ይሁዳ ወደ ተመ​ሸ​ጉት ከተ​ሞች ሁሉ ወጣ፤ ወሰ​ዳ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="14">የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ሕዝ​ቅ​ያስ፥ “በድ​ያ​ለሁ፥ ከእኔ ተመ​ለስ፤ የም​ት​ጭ​ን​ብ​ኝ​ንም ሁሉ እሸ​ከ​ማ​ለሁ” ብሎ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ለኪሶ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ። የአ​ሦ​ርም ንጉሥ በይ​ሁዳ ንጉሥ በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ላይ ሦስት መቶ መክ​ሊት ብርና ሠላሳ መክ​ሊት ወርቅ ጫነ​በት።</verse>
				<verse number="15">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና በን​ጉሡ ቤተ መዛ​ግ​ብት የተ​ገ​ኘ​ውን ብር ሁሉ ሰጠው።</verse>
				<verse number="16">በዚ​ያን ጊዜም ሕዝ​ቅ​ያስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ ደጆ​ችና የይ​ሁዳ ንጉሥ ሕዝ​ቅ​ያስ ከለ​በ​ጣ​ቸው መቃ​ኖች ወር​ቁን ቈረጠ፤ ለአ​ሦ​ርም ንጉሥ ሰጠው።</verse>
				<verse number="17">የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ተር​ታ​ን​ንና ራፌ​ስን ራፋ​ስ​ቂ​ስ​ንም ከብዙ ሠራ​ዊት ጋር ከለ​ኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ላካ​ቸው። ወጥ​ተ​ውም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ደረሱ፤ በአ​ጣ​ቢ​ውም እርሻ መን​ገድ ባለ​ችው በላ​ዪ​ኛ​ዪቱ ኩሬ መስኖ አጠ​ገብ ቆሙ።</verse>
				<verse number="18">ሕዝ​ቅ​ያ​ስ​ንም ጠሩ፤ የቤ​ቱም አዛዥ የኬ​ል​ቅዩ ልጅ ኤል​ያ​ቄም ጸሓ​ፊ​ውም ሳም​ናስ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እነ​ርሱ ወጡ።</verse>
				<verse number="19">ራፋ​ስ​ቂ​ስም አላ​ቸው፥ “ለሕ​ዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦ ታላቁ ንጉሥ የአ​ሦር ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፦ ይህ የም​ት​ተ​ማ​መ​ን​በት መተ​ማ​መኛ ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="20">የከ​ን​ፈር ቃል ለሰ​ልፍ ምክ​ርና ኀይል እን​ደ​ሚ​ሆን ትና​ገ​ራ​ለህ፤ አሁ​ንም በእኔ ላይ ያመ​ፅ​ኸው በማን ተማ​ም​ነህ ነው?</verse>
				<verse number="21">እነሆ፥ በዚህ በተ​ቀ​ጠ​ቀጠ በሸ​ም​በቆ በትር በግ​ብፅ ትታ​መ​ና​ለህ፤ ሰው ቢመ​ረ​ኰ​ዘው ተሰ​ብሮ በእጁ ይገ​ባል፥ ያቈ​ስ​ለ​ው​ማል፤ የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን ለሚ​ታ​መ​ኑ​በት ሁሉ እን​ዲሁ ነው።</verse>
				<verse number="22">እና​ን​ተም፦ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ታ​መ​ና​ለን ብት​ሉኝ፥ ሕዝ​ቅ​ያስ ይሁ​ዳ​ንና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለው በዚህ መሠ​ዊያ ፊት ስገዱ ብሎ የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቹ​ንና መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹን ያስ​ፈ​ረሰ ይህ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="23">አሁ​ንም እን​ግ​ዲህ ከጌ​ታዬ ከአ​ሦር ንጉሥ ጋር ተወ​ራ​ረድ፤ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ው​ንም ሰዎች ማግ​ኘት ቢቻ​ልህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረ​ሶች እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="24">ስለ ሰረ​ገ​ሎ​ችና ስለ ፈረ​ሶች በግ​ብፅ ስት​ታ​መን፥ ከጌ​ታዬ አገ​ል​ጋ​ዮች የሚ​ያ​ን​ሰ​ውን የአ​ን​ዱን አለቃ ፊት ትመ​ልስ ዘንድ እን​ዴት ይቻ​ል​ሃል?</verse>
				<verse number="25">አሁን በውኑ ያለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ይህን ስፍራ እና​ጠፋ ዘንድ ወጥ​ተ​ና​ልን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ​ዚች ሀገር ወጥ​ታ​ችሁ አጥ​ፉ​አት አለን።”</verse>
				<verse number="26">የኬ​ል​ቅ​ዩም ልጅ ኤል​ያ​ቄም ሳም​ና​ስም ዮአ​ስም ራፋ​ስ​ቂ​ስን፥ “እኛ እን​ሰ​ማ​ለ​ንና በሱ​ር​ስት ቋንቋ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ተና​ገር፤ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስ​ጥም ቋንቋ አት​ና​ገ​ረን፤ በቅ​ጥ​ርም ላይ ያለው ሕዝብ በሚ​ሰ​ማው ቋንቋ ለምን ትና​ገ​ራ​ለህ?” አሉት።</verse>
				<verse number="27">ራፋ​ስ​ቂስ ግን፥ “በውኑ ጌታዬ ይህን ቃል እና​ገር ዘንድ ወደ እና​ን​ተና ወደ ጌታ​ችሁ ልኮ​ኛ​ልን? ከእ​ና​ንተ ጋር ኵሳ​ቸ​ውን ይበሉ ዘንድ ሽን​ታ​ቸ​ው​ንም ይጠጡ ዘንድ በቅ​ጥር ላይ ወደ ተቀ​መ​ጡት ሰዎች አይ​ደ​ለ​ምን?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="28">ራፋ​ስ​ቂ​ስም ቆሞ በታ​ላቅ ድምፅ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ እን​ዲህ ብሎ ጮኸ፥ “የታ​ላ​ቁን የአ​ሦር ንጉሥ ቃል ስሙ፤</verse>
				<verse number="29">ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፦ ከእጄ ያድ​ና​ችሁ ዘንድ አይ​ች​ል​ምና ሕዝ​ቅ​ያስ አያ​ታ​ል​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="30">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ር​ግጥ ያድ​ነ​ናል፤ ይህ​ች​ንም ከተማ የአ​ሦር ንጉሥ ሊይ​ዛት አይ​ች​ልም እያለ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ድ​ት​ታ​መኑ አያ​ድ​ር​ጋ​ችሁ።</verse>
				<verse number="31">ሕዝ​ቅ​ያ​ስ​ንም አት​ስሙ፤ የአ​ሶር ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፦ ከእኔ ጋር ታረቁ፤ ወደ እኔም ውጡ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም ከወ​ይ​ና​ች​ሁና ከበ​ለ​ሳ​ችሁ ብሉ፤ ከጕ​ድ​ጓ​ዳ​ች​ሁም ውኃ ጠጡ፤</verse>
				<verse number="32">ይህም መጥቼ ምድ​ራ​ች​ሁን ወደ​ም​ት​መ​ስ​ለው ምድር፥ እህ​ልና የወ​ይን ጠጅ፥ እን​ጀ​ራና ወይን፥ ወይ​ራና ማር ወዳ​ለ​ባት ምድር እስ​ካ​ፈ​ል​ሳ​ችሁ ድረስ በሕ​ይ​ወት እን​ድ​ት​ኖሩ፥ እን​ዳ​ት​ሞ​ቱም ነው። ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ና​ች​ኋል ብሎ ያታ​ል​ላ​ች​ኋ​ልና አት​ስ​ሙት።</verse>
				<verse number="33">በውኑ የአ​ሕ​ዛብ አማ​ል​ክት አገ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ አድ​ነ​ዋ​ቸ​ዋ​ልን?</verse>
				<verse number="34">የኤ​ማ​ትና የአ​ር​ፋድ አማ​ል​ክት ወዴት አሉ? የሴ​ፋ​ሩ​ዋ​ይ​ምና የሄና የዒ​ዋም አማ​ል​ክት ወዴት አሉ? ስማ​ር​ያን ከእጄ አድ​ነ​ዋ​ታ​ልን?</verse>
				<verse number="35">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ከእጄ ያድ​ናት ዘንድ ከሀ​ገ​ሮቹ አማ​ል​ክት ሁሉ ሀገ​ሩን ከእጄ ያዳነ ማን ነው?”</verse>
				<verse number="36">ሕዝ​ቡም ዝም አሉ፥ አን​ዳ​ችም ቃል አል​መ​ለ​ሱ​ለ​ትም፤ ንጉሡ እን​ዳ​ይ​መ​ል​ሱ​ለት አዝዞ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="37">የቤቱ አዛዥ የኬ​ል​ቅዩ ልጅ ኤል​ያ​ቄም፥ ጸሓ​ፊው ሳም​ናስ፥ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሳፍ ልጅ ዮአስ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀድ​ደው ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ገቡ፥ የራ​ፋ​ስ​ቂ​ስ​ንም ቃል ነገ​ሩት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">ንጉ​ሡም ሕዝ​ቅ​ያስ ይህን በሰማ ጊዜ ልብ​ሱን ቀደደ፥ ማቅም ለበሰ፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ገባ።</verse>
				<verse number="2">የቤ​ቱ​ንም አዛዥ ኤል​ያ​ቄ​ምን ጸሓ​ፊ​ው​ንም ሳም​ና​ስን የካ​ህ​ና​ቱ​ንም አለ​ቆች ማቅ ለብ​ሰው ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳ​ይ​ያስ ይሄዱ ዘንድ ላካ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">እነ​ር​ሱም አሉት፥ “ሕዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመ​ከ​ራና የተ​ግ​ሣጽ የዘ​ለ​ፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚ​ወ​ለ​ዱ​በት ጊዜ ደር​ሶ​አል፤ እና​ትም ለማ​ማጥ ኀይል የላ​ትም።</verse>
				<verse number="4">ምና​ል​ባት በሕ​ያው አም​ላክ ላይ ይገ​ዳ​ደር ዘንድ ጌታው የአ​ሦር ንጉሥ የላ​ከ​ውን የራ​ፋ​ስ​ቂ​ስን ቃል ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰማ እን​ደ​ሆነ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ሰማው ቃል ይገ​ሥ​ጸው እንደ ሆነ፥ ስለ​ዚህ ለቀ​ረው ቅሬታ ጸልይ።”</verse>
				<verse number="5">እን​ዲሁ የን​ጉሡ የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ብላ​ቴ​ኖች ወደ ኢሳ​ይ​ያስ መጡ።</verse>
				<verse number="6">ኢሳ​ይ​ያ​ስም አላ​ቸው፥ “ለጌ​ታ​ችሁ እን​ዲህ በሉት፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ሦር ንጉሥ ብላ​ቴ​ኖች ስለ ተሳ​ደ​ቡት፥ ስለ ሰማ​ኸው ቃል አት​ፍራ።</verse>
				<verse number="7">እነሆ፥ በላዩ መን​ፈ​ስን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ወሬ​ንም ይሰ​ማል፤ ወደ ምድ​ሩም ይመ​ለ​ሳል፤ በም​ድ​ሩም በሰ​ይፍ እን​ዲ​ወ​ድቅ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ በሉት።”</verse>
				<verse number="8">የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ከለ​ኪሶ እንደ ራቀ ሰምቶ ነበ​ርና ራፋ​ስ​ቂስ ተመ​ልሶ በሎ​ምና ሲዋጋ አገ​ኘው።</verse>
				<verse number="9">እር​ሱም፥ “የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንጉሥ ቲር​ሐቅ ሊወ​ጋህ መጥ​ቶ​አል” የሚል ወሬ በሰማ ጊዜ ተመ​ልሶ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እን​ዲህ ሲል፦</verse>
				<verse number="10">“ለይ​ሁዳ ንጉሥ ለሕ​ዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በአ​ሦር ንጉሥ እጅ አት​ሰ​ጥም ብሎ የም​ት​ታ​መ​ን​በት አም​ላ​ክህ አያ​ታ​ል​ልህ።</verse>
				<verse number="11">እነሆ፥ የአ​ሦር ነገ​ሥ​ታት በም​ድር ሁሉ ላይ ያደ​ረ​ጉ​ትን፥ እን​ዴ​ትስ እን​ዳ​ጠ​ፉ​አ​ቸው ሰም​ተ​ሃል፤ አን​ተስ ትድ​ና​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="12">አባ​ቶች ያጠ​ፉ​አ​ቸ​ውን፥ ጎዛ​ንን፥ ካራ​ንን፥ ራፌ​ስን በታ​ኤ​ሴ​ቴም የነ​በ​ሩ​ት​ንም የዔ​ድ​ንን ልጆች፥ የአ​ሕ​ዛብ አማ​ል​ክት አዳ​ኑ​አ​ቸ​ውን?</verse>
				<verse number="13">የሐ​ማት ንጉሥ፥ የአ​ር​ፋድ ንጉሥ፥ የሴ​ፋ​ሩ​ሄም ከተማ ንጉሥ፥ የኤ​ናና የዓዋ ንጉሥ ወዴት አሉ?”</verse>
				<verse number="14">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ደብ​ዳ​ቤ​ውን ከመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞች እጅ ተቀ​ብሎ አነ​በ​በው፤ ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወጥቶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዘረ​ጋው።</verse>
				<verse number="15">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ጸለየ፥ “በኪ​ሩ​ቤል ላይ የም​ት​ቀ​መጥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ፥ አንተ ብቻ​ህን የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ አም​ላክ ነህ፤ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ፈጥ​ረ​ሃል ።</verse>
				<verse number="16">አቤቱ፥ ጆሮ​ህን አዘ​ን​ብ​ልና ስማ፥ አቤቱ፥ ዐይ​ን​ህን ክፈ​ትና እይ፤ በሕ​ያው አም​ላክ ላይ ይገ​ዳ​ደር ዘንድ የላ​ከ​ውን የሰ​ና​ክ​ሬ​ምን ቃል ስማ።</verse>
				<verse number="17">አቤቱ፥ በእ​ው​ነት የአ​ሦር ነገ​ሥት አሕ​ዛ​ብን አጥ​ፍ​ተ​ዋል፤</verse>
				<verse number="18">አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ላይ ጥለ​ዋል፤ የእ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ የሰው እጅ ሥራ ነበሩ እንጂ አማ​ል​ክት አል​ነ​በ​ሩ​ምና፤ ስለ​ዚህ አጥ​ፍ​ተ​ዋ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="19">እን​ግ​ዲ​ህም አም​ላ​ካ​ችን አቤቱ፥ የም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ አንተ ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እንደ ሆንህ ያውቁ ዘንድ ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ አድ​ነን።”</verse>
				<verse number="20">የአ​ሞ​ጽም ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ እን​ዲህ ብሎ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ላከ፥ “የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰና​ክ​ሬም ወደ እኔ የለ​መ​ን​ኸ​ውን ሰም​ቻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="21">ድን​ግ​ሊቱ የጽ​ዮን ልጅ፥ ሰድ​ቦ​ሻ​ልና ንቆ​ሻ​ል​ምና፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ልጅ፥ በአ​ንቺ ላይ ራሱን ነቅ​ን​ቋ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ርሱ ላይ የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው፦</verse>
				<verse number="22">የተ​ገ​ዳ​ደ​ር​ኸው፥ የሰ​ደ​ብ​ኸ​ውስ ማን ነው? ቃል​ህ​ንስ ከፍ ከፍ ያደ​ረ​ግ​ኸው፥ ዐይ​ን​ህ​ንም ወደ ላይ ያነ​ሣ​ኸው በማን ላይ ነው? በእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ላይ ነው።</verse>
				<verse number="23">አን​ተስ በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችህ እጅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ተገ​ዳ​ደ​ርህ፤ እን​ዲ​ህም አልህ፦ በሰ​ረ​ገ​ላዬ ብዛት ወደ ተራ​ሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባ​ኖስ ጥግ እወ​ጣ​ለሁ፤ ረጃ​ጅ​ሞ​ች​ንም ዝግ​ባ​ዎች የተ​መ​ረ​ጡ​ት​ንም ጥዶች እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤ ወደ ሀገ​ሩም ዳር​ቻና ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ዱር እገ​ባ​ለሁ።</verse>
				<verse number="24">ዕረ​ፍት አደ​ረ​ግሁ፤ የባ​ዕድ ውኃ​ንም ጠጣሁ፥ የተ​ገ​ደ​በ​ው​ንም ውኃ ሁሉ በእ​ግሬ ጫማ አደ​ር​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="25">“እኔ ጥን​ቱን እንደ ሠራ​ሁት፥ ቀድ​ሞ​ው​ንም እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ሁት አል​ሰ​ማ​ህ​ምን? አሁ​ንም የተ​መ​ሸ​ጉ​ትን ከተ​ሞች የፍ​ር​ስ​ራሽ ክምር እስ​ኪ​ሆኑ ድረስ እን​ድ​ታ​ፈ​ርስ አደ​ረ​ግ​ሁህ።</verse>
				<verse number="26">ስለ​ዚ​ህም የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸው ሰዎች እጆ​ቻ​ቸው ዝለ​ዋል፤ ደን​ግ​ጠ​ውም አፍ​ረ​ዋል፤ እንደ ምድረ በዳ ሣር፥ እንደ ለም​ለ​ምም ቡቃያ፥ በሰ​ገ​ነ​ትም ላይ እን​ዳለ ሣር፥ ሳይ​ሸት ዋግ እንደ መታ​ውም እህል ሆነ​ዋል።</verse>
				<verse number="27">እኔ ግን መቀ​መ​ጫ​ህ​ንና መው​ጫ​ህን መግ​ቢ​ያ​ህ​ንም፥ በእ​ኔም ላይ የተ​ቈ​ጣ​ኸ​ውን ቍጣ ዐው​ቄ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="28">ቍጣ​ህና ትዕ​ቢ​ትህ ወደ ጆሮዬ ደር​ሶ​አ​ልና ስለ​ዚህ ስና​ጋ​ዬን በአ​ፍ​ን​ጫህ፥ ልጓ​ሜ​ንም በከ​ን​ፈ​ርህ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በመ​ጣ​ህ​በት መን​ገ​ድም እመ​ል​ስ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="29">“ይህም ለአ​ንተ ምል​ክት ይሆ​ን​ል​ሃል፤ በዚህ ዓመት የገ​ቦ​ውን፥ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ከገ​ቦው የበ​ቀ​ለ​ውን ትበ​ላ​ለህ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ትዘ​ራ​ለህ፤ ታጭ​ድ​ማ​ለህ፥ ወይ​ንም ትተ​ክ​ላ​ለህ፤ ፍሬ​ው​ንም ትበ​ላ​ለህ።</verse>
				<verse number="30">የዳ​ነው የይ​ሁዳ ቤት ቅሬታ ሥሩን ወደ ታች ይሰ​ድ​ዳል፤ ወደ ላይም ያፈ​ራል።</verse>
				<verse number="31">ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅሬታ፥ ከጽ​ዮ​ንም ተራራ የዳነ ይወ​ጣ​ልና፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅን​አት ይህን ያደ​ር​ጋል።”</verse>
				<verse number="32">እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለ​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አሦር ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፥ “ወደ​ዚች ከተማ አይ​ገ​ባም፥ ፍላ​ጻ​ንም አይ​ወ​ረ​ው​ር​ባ​ትም፤ በጋ​ሻም አይ​መ​ጣ​ባ​ትም፥ የአ​ፈ​ር​ንም ድል​ድል አይ​ደ​ለ​ድ​ል​ባ​ትም።</verse>
				<verse number="33">በመ​ጣ​በት መን​ገድ በዚያ ይመ​ለ​ሳል እንጂ፥ ወደ​ዚ​ህ​ችም ከተማ አይ​ገ​ባም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="34">ስለ እኔም፥ ስለ ባሪ​ያዬ ስለ ዳዊ​ትም ይህ​ችን ከተማ እጋ​ር​ዳ​ታ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="35">በዚ​ያ​ችም ሌሊት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ መጣ፤ ከአ​ሦ​ራ​ው​ያ​ንም ሰፈር መቶ ሰማ​ንያ አም​ስት ሺህ ገደለ፤ ማለ​ዳም በተ​ነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድ​ኖች ነበሩ።</verse>
				<verse number="36">የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ሰና​ክ​ሬም ተነ​ሥቶ ሄደ፤ ተመ​ል​ሶም በነ​ነዌ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="37">በአ​ም​ላ​ኩም በሲ​ድ​ራክ ቤት ሲሰ​ግድ ልጆቹ አድ​ራ​ሜ​ሌ​ክና ሶር​ሶር በሰ​ይፍ ገደ​ሉት፤ ወደ አራ​ራ​ትም ሀገር ኰበ​ለሉ። ልጁም አስ​ራ​ዶን በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">በዚ​ያም ወራት ሕዝ​ቅ​ያስ ታመመ፤ ለሞ​ትም ደረሰ። ነቢ​ዩም የአ​ሞጽ ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ ወደ እርሱ መጥቶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ በሕ​ይ​ወት አት​ኖ​ር​ምና ቤት​ህን አስ​ተ​ካ​ክል” አለው።</verse>
				<verse number="2">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ፊቱን ወደ ግድ​ግ​ዳው መልሶ እን​ዲህ ሲል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለየ፦</verse>
				<verse number="3">“አቤቱ፥ በፊ​ትህ በእ​ው​ነ​ትና በፍ​ጹም ልብ እንደ ሄድሁ፥ መል​ካም ነገ​ርም እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ አስብ።” ሕዝ​ቅ​ያ​ስም እጅግ አለ​ቀሰ።</verse>
				<verse number="4">ኢሳ​ይ​ያ​ስም ወደ መካ​ከ​ለ​ኛው አደ​ባ​ባይ ሲደ​ርስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገ​ረው፤ እን​ዲ​ህም አለው፦</verse>
				<verse number="5">“ተመ​ል​ሰህ የሕ​ዝ​ቤን ንጉሥ ሕዝ​ቅ​ያ​ስን እን​ዲህ በለው፦ የአ​ባ​ትህ የዳ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጸሎ​ት​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፥ እን​ባ​ህ​ንም አይ​ቻ​ለሁ፤ እነሆ፥ እኔ እፈ​ው​ስ​ሃ​ለሁ፤ እስከ ሦስት ቀንም ድረስ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ትወ​ጣ​ለህ።</verse>
				<verse number="6">በዕ​ድ​ሜ​ህም ላይ ዐሥራ አም​ስት ዓመት እጨ​ም​ራ​ለሁ፤ አን​ተ​ንና ይህ​ችን ከተማ ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ እታ​ደ​ጋ​ለሁ፤ ስለ እኔ፥ ስለ ባሪ​ያ​ዬም ስለ ዳዊት ይህ​ችን ከተማ አጋ​ር​ዳ​ታ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="7">ኢሳ​ይ​ያ​ስም አለው፥ “የበ​ለስ ጥፍ​ጥፍ አም​ጥ​ተህ በእ​ባ​ጭህ ላይ አድ​ርግ ትፈ​ወ​ሳ​ለ​ህም።”</verse>
				<verse number="8">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ኢሳ​ይ​ያ​ስን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲ​ፈ​ው​ሰኝ፥ እኔስ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እን​ድ​ወጣ ምል​ክቱ ምን​ድን ነው?” አለው።</verse>
				<verse number="9">ኢሳ​ይ​ያ​ስም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር እን​ዲ​ፈ​ጽ​መው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ምል​ክቱ ይህ ይሆ​ን​ል​ሃል፤ ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት ይሂ​ድን? ወይስ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላው ይመ​ለስ?” አለ።</verse>
				<verse number="10">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ኢሳ​ይ​ያ​ስን፥ “ጥላው ዐሥር ደረጃ ቢጨ​ምር ቀላል ነገር ነው፤ እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ይመ​ለሰ” አለው።</verse>
				<verse number="11">ነቢ​ዩም ኢሳ​ይ​ያስ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፤ ጥላ​ውም ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="12">በዚ​ያም ወራት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ መሮ​ዳህ ሕዝ​ቅ​ያስ እንደ ታመመ ሰምቶ ነበ​ርና የበ​ል​ዳ​ንን ልጅ በል​ዳ​ንን ከመ​ጻ​ሕ​ፍ​ትና እጅ መንሻ ጋር ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ላከ።</verse>
				<verse number="13">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በእ​ነ​ርሱ ደስ አለው፤ ግምጃ ቤቱ​ንም ሁሉ፥ ብሩ​ንና ወር​ቁ​ንም፥ ሽቱ​ው​ንና የከ​በ​ረ​ው​ንም ዘይት፥ መሣ​ሪ​ያም ያለ​በ​ትን ቤት በቤተ መዛ​ግ​ብ​ቱም የተ​ገ​ኘ​ውን ሁሉ አሳ​ያ​ቸው፤ በቤ​ቱና በግ​ዛቱ ሁሉ ካለው ሕዝ​ቅ​ያስ ያላ​ሳ​ያ​ቸው የለም።</verse>
				<verse number="14">ነቢዩ ኢሳ​ይ​ያ​ስም ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ መጥቶ፥ “እነ​ዚህ ሰዎች ምን አሉ? ከወ​ዴ​ትስ ወደ አንተ መጡ?” አለው። ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “ከሩቅ ሀገር ከባ​ቢ​ሎን ወደ እኔ መጡ” አለው።</verse>
				<verse number="15">እር​ሱም፥ “ምን አዩ?” አለው ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “በቤቴ ያለ​ውን ሁሉ አይ​ተ​ዋል፤ በቤተ መዛ​ግ​ብ​ቴም ካለው ያላ​ሳ​የ​ኋ​ቸው የለም” አለው።</verse>
				<verse number="16">ኢሳ​ይ​ያ​ስም ሕዝ​ቅ​ያ​ስን አለው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ።</verse>
				<verse number="17">እነሆ፥ በቤ​ትህ ያለው ሁሉ፥ አባ​ቶ​ች​ህም እስከ ዛሬ ያከ​ማ​ቹት ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን የሚ​ፈ​ል​ስ​በት ወራት ይመ​ጣል፤ ምንም አይ​ቀ​ርም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="18">ከአ​ን​ተም ከሚ​ወ​ጡት ከም​ት​ወ​ል​ዳ​ቸው ልጆ​ችህ ማር​ከው ይወ​ስ​ዳሉ፤ በባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ቤት ውስጥ ጃን​ደ​ረ​ቦች ይሆ​ናሉ።”</verse>
				<verse number="19">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ኢሳ​ይ​ያ​ስን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረው ቃል መል​ካም ነው። ደግ​ሞም በዘ​መኔ ሰላም ይሁን” አለው።</verse>
				<verse number="20">የቀ​ረ​ውም የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ነገር፥ ኀይ​ሉም ሁሉ፥ ኵሬ​ው​ንና መስ​ኖ​ውን እንደ ሠራ፥ ውኃ​ው​ንም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ እን​ዳ​መጣ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ታሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="21">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊት ከተ​ማም ቀበ​ሩት። ልጁ ምና​ሴም በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">ምና​ሴም በነ​ገሠ ጊዜ ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ኀምሳ አም​ስት ዓመት ነገሠ፤ የእ​ና​ቱም ስም ሐፍ​ሴባ ነበረ።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ዳ​ራ​ቃ​ቸው እንደ አሕ​ዛብ ርኵ​ሰት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="3">አባ​ቱም ሕዝ​ቅ​ያስ ያፈ​ረ​ሳ​ቸ​ውን የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎች መልሶ ሠራ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አክ​ዓብ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ለበ​ዓል መሠ​ዊ​ያን ሠራ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ድ​ንም ተከለ፤ ለሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ ሰገደ አመ​ለ​ካ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ስሜን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አኖ​ራ​ለሁ” ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መሠ​ዊ​ያን ሠራ።</verse>
				<verse number="5">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በሁ​ለቱ ወለ​ሎች ላይ ለሰ​ማይ ሠራ​ዊት ሁሉ መሠ​ዊ​ያን ሠራ።</verse>
				<verse number="6">ልጁ​ንም በእ​ሳት ሠዋ፤ ሞራ ገላ​ጭም ሆነ፤ አስ​ማ​ትም አደ​ረገ፤ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ች​ንም ሰበ​ሰበ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ ኣስ​ቈ​ጣ​ውም።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለዳ​ዊ​ትና ለልጁ ለሰ​ሎ​ሞን፥ “በዚህ ቤት ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገድ ሁሉ በመ​ረ​ጥ​ኋት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስሜን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አኖ​ራ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="8">ያዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ፥ ባሪ​ያ​ዬም ሙሴ ያዘ​ዛ​ቸ​ውን ሕግ ሁሉ ቢያ​ደ​ርጉ ቢጠ​ብ​ቁም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ከሰ​ጠ​ኋት ምድር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን እግር እን​ደ​ገና አላ​ን​ቀ​ሳ​ቅ​ስም” ባለው ቤት የሠ​ራ​ውን የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ው​ንም ምስል አቆመ።</verse>
				<verse number="9">ነገር ግን አል​ሰ​ሙም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ካጠ​ፋ​ቸው ከአ​ሕ​ዛብ ይልቅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖች ፊት ክፉ ይሠሩ ዘንድ ምናሴ አሳ​ታ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሪ​ያ​ዎቹ በነ​ቢ​ያት ቃል እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፦</verse>
				<verse number="11">“የይ​ሁዳ ንጉሥ ምናሴ ከእ​ርሱ በፊት የነ​በሩ አሞ​ራ​ው​ያን ከሠ​ሩት ሁሉ ይልቅ ይህን ክፉ ርኵ​ሰት አድ​ር​ጎ​አ​ልና፥ ይሁ​ዳ​ንም ደግሞ በጣ​ዖ​ታቱ አስ​ቶ​አ​ልና፥</verse>
				<verse number="12">ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የሚ​ሰ​ማ​ውን ሁሉ ሁለቱ ጆሮ​ቹን ጭው የሚ​ያ​ደ​ርግ ክፉ ነገ​ርን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ላይ አመ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">የሰ​ማ​ር​ያ​ንም ገመድ የአ​ክ​ዓ​ብ​ንም ቤት ቱንቢ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ የሽቱ ዕቃ እን​ዲ​ወ​ለ​ወል ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ወል​ውዬ በፊቷ እገ​ለ​ብ​ጣ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">የሕ​ዝ​ቡ​ንም ቅሬታ እጥ​ላ​ለሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ምር​ኮና ብዝ​በዛ ይሆ​ናሉ፤</verse>
				<verse number="15">አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ከግ​ብፅ ከአ​ወ​ጣ​ኋ​ቸው ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በፊቴ ክፉ ሠር​ተ​ዋ​ልና፥ አስ​ቈ​ጥ​ተ​ው​ኝ​ማ​ልና።”</verse>
				<verse number="16">ደግ​ሞም ምናሴ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖች ፊት ክፉ ይሠራ ዘንድ ይሁ​ዳን ካሳ​ተ​በት ኀጢ​አት ሌላ ከዳር እስከ ዳር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እስ​ኪ​ሞ​ላት ድረስ እጅግ ብዙ ንጹሕ ደምን አፈ​ሰሰ።</verse>
				<verse number="17">የም​ና​ሴም የቀ​ረው ነገ​ርና የሠ​ራው ሥራ ሁሉ፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ኀጢ​አት፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="18">ምና​ሴም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በቤ​ቱም አጠ​ገብ ባለው በዖዛ አት​ክ​ልት ቦታ ተቀ​በረ፤ ልጁም አሞጽ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።</verse>
				<verse number="19">አሞ​ጽም በነ​ገሠ ጊዜ ሃያ ሁለት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሁለት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም የዮ​ጥባ ሰው የሐ​ሩስ ልጅ ሚሱ​ላም ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="20">አባቱ ምና​ሴም እን​ዳ​ደ​ረገ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ሠራ።</verse>
				<verse number="21">አባ​ቱም በሄ​ደ​በት መን​ገድ ሁሉ ሄደ፤ አባ​ቱም ያመ​ለ​ካ​ቸ​ውን ጣዖ​ታት አመ​ለከ፥ ሰገ​ደ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="22">የአ​ባ​ቶ​ቹ​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተወ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ገድ አል​ሄ​ደም።</verse>
				<verse number="23">የአ​ሞ​ጽም ብላ​ቴ​ኖች አሴ​ሩ​በት፤ ንጉ​ሡ​ንም በቤቱ ውስጥ ገደ​ሉት።</verse>
				<verse number="24">የሀ​ገሩ ሕዝብ ግን በን​ጉሡ በአ​ሞጽ ላይ ያሴ​ሩ​ትን ሁሉ ገደሉ፤ የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ልጁን ኢዮ​ስ​ያ​ስን በእ​ርሱ ፋንታ አነ​ገ​ሡት።</verse>
				<verse number="25">የአ​ሞ​ጽም የቀ​ረው ነገ​ርና የሠ​ራው ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="26">በዖ​ዛም የአ​ት​ክ​ልት ቦታ ባለው መቃ​ብሩ ቀበ​ሩት፤ ልጁም ኢዮ​ስ​ያስ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">ኢዮ​ስ​ያ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የስ​ም​ንት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሠላሳ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ከባ​ሱ​ሮት የሆነ የአ​ዳያ ልጅ ይዲያ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="2">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት መን​ገድ ሁሉ ሄደ፤ ቀኝም ግራም አላ​ለም።</verse>
				<verse number="3">በን​ጉ​ሡም በኢ​ዮ​ስ​ያስ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በስ​ም​ን​ተ​ኛው ወር ንጉሡ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ጸሓፊ የሜ​ሱ​ላ​ምን ልጅ የኤ​ሴ​ል​ዩን ልጅ ሳፋ​ንን እን​ዲህ ሲል ላከው፦</verse>
				<verse number="4">“ወደ ታላቁ ካህን ወደ ኬል​ቅዩ ወጥ​ተህ ደጃ​ፉን የሚ​ጠ​ብቁ ከሕ​ዝቡ የሰ​በ​ሰ​ቡ​ትን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የገ​ባ​ውን ወርቅ ቍጠር።</verse>
				<verse number="5">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ላሉት ሠራ​ተ​ኞች አለ​ቆች ይስ​ጡት፤ እነ​ር​ሱም የተ​ና​ደ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለሚ​ጠ​ግ​ኑት ሠራ​ተ​ኞች፥</verse>
				<verse number="6">ለአ​ና​ጢ​ዎ​ችና ለጠ​ራ​ቢ​ዎች፥ ለድ​ን​ጋ​ይም ወቃ​ሪ​ዎች፥ መቅ​ደ​ሱ​ንም ለመ​ጠ​ገን እን​ጨ​ት​ንና የተ​ወ​ቀ​ረ​ውን ድን​ጋይ ለሚ​ገዙ ይክ​ፈ​ሉት።”</verse>
				<verse number="7">ነገር ግን እነ​ርሱ በእ​ም​ነት ይሠሩ ነበ​ርና የሰ​ጡ​አ​ቸ​ውን ገን​ዘብ አይ​ቈ​ጣ​ጠ​ሩ​አ​ቸ​ውም ነበር።</verse>
				<verse number="8">ታላቁ ካህ​ንም ኬል​ቅ​ያስ ጸሓ​ፊ​ውን ሳፋ​ንን፥ “የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አግ​ኝ​ቻ​ለሁ” አለው፤ ኬል​ቅ​ያ​ስም መጽ​ሐ​ፉን ለሳ​ፋን ሰጠው፥ እር​ሱም አነ​በ​በው።</verse>
				<verse number="9">ጸሓ​ፊ​ውም ሳፋን ወደ ንጉሡ መጣ፤ ለን​ጉ​ሡም፥ “በመ​ቅ​ደሱ የተ​ገ​ኘ​ውን ገን​ዘብ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ አፈ​ሰ​ሱት፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ሥራ ለመ​ሥ​ራት ለተ​መ​ደ​ቡት ሰዎች ሰጡት” ብሎ ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="10">ጸሓ​ፊው ሳፋ​ንም ለን​ጉሡ፥ “ካህኑ ኬል​ቅ​ያስ የሕግ መጽ​ሐፍ ሰጥ​ቶ​ኛል” ብሎ ነገ​ረው። ሳፋ​ንም በን​ጉሡ ፊት አነ​በ​በው።</verse>
				<verse number="11">ንጉ​ሡም የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ ቃል በሰማ ጊዜ ልብ​ሱን ቀደደ።</verse>
				<verse number="12">ንጉ​ሡም ካህ​ኑን ኬል​ቅ​ያ​ስን፥ የሳ​ፋ​ን​ንም ልጅ አኪ​ቃ​ምን፥ የሚ​ክ​ዩ​ንም ልጅ ዓክ​ቦ​ርን፥ ጸሓ​ፊ​ው​ንም ሳፋ​ንን፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ብላ​ቴና ዓስ​ያን እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፦</verse>
				<verse number="13">“አባ​ቶ​ቻ​ችን በእ​ር​ስዋ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ ይሠሩ ዘንድ የዚ​ህ​ችን መጽ​ሐፍ ቃል ስላ​ል​ሰሙ በላ​ያ​ችን የነ​ደደ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ እጅግ ነውና ሄዳ​ችሁ ስለ እኔና ስለ ሕዝቡ ስለ ይሁ​ዳም ሁሉ ስለ​ዚ​ችም ስለ​ተ​ገ​ኘ​ችው መጽ​ሐፍ ቃል ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠይቁ።</verse>
				<verse number="14">እን​ዲ​ሁም ካህኑ ኬል​ቅ​ያ​ስና አኪ​ቃም ዓክ​ቦ​ርም ሳፋ​ንና ዓሳ​ያም ወደ ልብስ ጠባ​ቂው ወደ ሓስራ ልጅ ወደ ቴቁዋ ልጅ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢ​ዪቱ ወደ ሕል​ዳና ሄዱ፤ እር​ስ​ዋም በዚያ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሁ​ለ​ተ​ኛው ክፍል ተቀ​ምጣ ነበር፤ ለእ​ር​ስ​ዋም ነገ​ሩ​አት።</verse>
				<verse number="15">እር​ስ​ዋም አለ​ቻ​ቸው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ እኔ ለላ​ካ​ችሁ ሰው እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የይ​ሁዳ ንጉሥ እን​ዳ​ነ​በ​በው እን​ደ​ዚህ መጽ​ሐፍ ቃል ሁሉ በዚህ ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ ክፉ ነገር አመ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="17">በእ​ጃ​ችሁ ሥራ ሁሉ ታስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ትታ​ች​ሁ​ኛ​ልና፥ ለሌ​ሎች አማ​ል​ክ​ትም ዐጥ​ና​ች​ኋ​ልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነ​ድ​ዳል፥ አይ​ጠ​ፋ​ምም።</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመ​ጠ​የቅ ለላ​ካ​ችሁ ለይ​ሁዳ ንጉሥ ግን እን​ዲህ በሉት፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ስለ ሰማ​ኸው ቃል፥</verse>
				<verse number="19">ልብ​ህን አላ​ደ​ነ​ደ​ን​ህ​ምና፥ እነ​ር​ሱም ለጥ​ፋ​ትና ለመ​ር​ገም እን​ዲ​ሆኑ በዚህ ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ሰም​ተህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ ልብ​ስ​ህን ቀድ​ደ​ሃ​ልና፥ በፊ​ቴም አል​ቅ​ሰ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="20">ነገሩ እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ ወደ አባ​ቶ​ችህ እሰ​በ​ስ​ብ​ሃ​ለሁ፥ በሰ​ላ​ምም ወደ መቃ​ብ​ርህ ትሰ​በ​ሰ​ባ​ለህ፤ በዚ​ህም ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ የማ​መ​ጣ​ውን ክፉ ነገር ዐይ​ኖ​ችህ አያ​ዩም።” ይህ​ንም ለን​ጉሡ ነገ​ሩት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="23">
				<verse number="1">ንጉ​ሡም ላከ፤ የይ​ሁ​ዳ​ንና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ወደ እርሱ ሰበ​ሰ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">ንጉ​ሡም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወጣ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የይ​ሁዳ ሰዎች ሁሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ኖሩ ሁሉ፥ ካህ​ና​ቱና ነቢ​ያ​ቱም፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ ከታ​ና​ሾቹ ጀምሮ እስከ ታላ​ቆቹ ድረስ ወጡ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የተ​ገ​ኘ​ውን የቃል ኪዳ​ኑን መጽ​ሐፍ ቃል ሁሉ በጆ​ሮ​አ​ቸው አነ​በበ።</verse>
				<verse number="3">ንጉ​ሡም በዓ​ምደ ወርቁ አጠ​ገብ ቆሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይከ​ተሉ ዘንድ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንና ምስ​ክ​ሩ​ንም ሥር​ዐ​ቱ​ንም በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውና በፍ​ጹም ነፍ​ሳ​ቸው ይጠ​ብቁ ዘንድ፥ በዚ​ህም መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን የቃል ኪዳን ቃል ያጸኑ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በቃል ኪዳን ጸኑ።</verse>
				<verse number="4">ንጉ​ሡም የካ​ህ​ና​ቱን አለቃ ኬል​ቅ​ያ​ስን በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም መዓ​ርግ ያሉ​ትን ካህ​ናት በረ​ኞ​ቹ​ንም፥ ለበ​ዓ​ልና ለማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ ለሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ የተ​ሠ​ሩ​ትን ዕቃ​ዎች ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ ያወጡ ዘንድ አዘ​ዛ​ቸው፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ውጭ በቄ​ድ​ሮን ሜዳ አቃ​ጠ​ሉት፤ አመ​ዱ​ንም ወደ ቤቴል ወሰ​ዱት።</verse>
				<verse number="5">የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታ​ትም በይ​ሁዳ ከተ​ሞች በነ​በ​ሩት በኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዙሪያ ባሉ መስ​ገ​ጃ​ዎች ያጥኑ ዘንድ ያኖ​ሩ​አ​ቸ​ውን የጣ​ዖ​ቱን ካህ​ናት፥ ለበ​ዓ​ልና ለፀ​ሐይ፥ ለጨ​ረ​ቃና ለከ​ዋ​ክ​ብት ለሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ ያጥኑ የነ​በ​ሩ​ትን አቃ​ጠ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ድ​ንም ጣዖት ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ውጭ ወደ ቄድ​ሮን ፈፋ አወ​ጣው፤ በቄ​ድ​ሮ​ንም ፈፋ አጠ​ገብ አቃ​ጠ​ለው፤ አድ​ቅ​ቆም ትቢያ አደ​ረ​ገው፥ ትቢ​ያ​ው​ንም በሕ​ዝብ መቃ​ብር ላይ ጨመ​ረው።</verse>
				<verse number="7">ሴቶ​ቹም ለማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ መጋ​ረጃ ይፈ​ት​ሉ​ባ​ቸው የነ​በ​ሩ​ትን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ ያሉ​ትን የሰ​ዶ​ማ​ው​ያ​ንን ቤቶች አፈ​ረሰ።</verse>
				<verse number="8">ካህ​ና​ቱ​ንም ሁሉ ከይ​ሁዳ ከተ​ሞች አወ​ጣ​ቸው፤ ከጌ​ባ​ልም ጀምሮ እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ ካህ​ናት ያጥ​ኑ​በት የነ​በ​ረ​ውን የኮ​ረ​ብታ መስ​ገጃ ሁሉ ርኩስ አደ​ረ​ገው። በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በር በግራ በኩል በነ​በ​ረው በከ​ተ​ማ​ዪቱ ሹም በኢ​ያሱ በር መግ​ቢያ አጠ​ገብ የነ​በ​ሩ​ትን የበ​ሮ​ቹን መስ​ገ​ጃ​ዎች አፈ​ረሰ።</verse>
				<verse number="9">የኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች ካህ​ናት ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወዳ​ለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ አይ​መ​ጡም ነበር፤ ብቻ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው መካ​ከል ቂጣ እን​ጀራ ይበሉ ነበር።</verse>
				<verse number="10">ሰው ሁሉ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን ለሞ​ሎክ በእ​ሳት እን​ዲ​ሠዋ በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ቆሞ የነ​በ​ረ​ውን ጣፌ​ትን ርኩስ አደ​ረ​ገው።</verse>
				<verse number="11">የይ​ሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መግ​ቢያ አጠ​ገብ በከ​ተ​ማው አቅ​ራ​ቢያ በነ​በ​ረው በን​ጉሡ ጃን​ደ​ረባ በና​ታን መኖ​ሪያ አጠ​ገብ ለፀ​ሐይ የሰ​ጡ​አ​ቸ​ውን ፈረ​ሶች አቃ​ጠለ፤ የፀ​ሐ​ይ​ንም ሰረ​ገ​ሎች በእ​ሳት አቃ​ጠለ።</verse>
				<verse number="12">የይ​ሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት ያሠ​ሩ​ትን በአ​ካዝ ቤት ሰገ​ነት ላይ የነ​በ​ሩ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ዎች፥ ምና​ሴም ያሠ​ራ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሁ​ለቱ ወለ​ሎች ላይ የነ​በ​ሩ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ዎች ንጉሡ አስ​ፈ​ረ​ሳ​ቸው፤ ከዚ​ያም አወ​ረ​ዳ​ቸው፤ አደ​ቀ​ቃ​ቸ​ውም፥ ትቢ​ያ​ቸ​ው​ንም በቄ​ድ​ሮን ፈፋ ጣለ።</verse>
				<verse number="13">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ፊት ለፊት በር​ኵ​ስት ተራራ ቀኝ የነ​በ​ሩ​ትን፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሰሎ​ሞን ለሲ​ዶ​ና​ው​ያን ርኵ​ስት ለአ​ስ​ታ​ሮት፥ ለሞ​ዓ​ብም ርኵ​ሰት ለካ​ሞሽ፥ ለአ​ሞ​ንም ልጆች ርኵ​ሰት ለሞ​ሎክ ያሠ​ራ​ቸ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎች ንጉሡ ርኩስ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="14">ሐው​ል​ቶ​ቹ​ንም ሁሉ አደ​ቀቀ፥ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ቹ​ንም ሁሉ ቈረጠ፤ በስ​ፍ​ራ​ቸ​ውም የሙ​ታ​ንን አጥ​ንት ሞላ​በት።</verse>
				<verse number="15">ደግ​ሞም በቤ​ቴል ኮረ​ብታ የነ​በ​ረ​ውን መሠ​ዊያ፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ያሳተ የና​ባጥ ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ያሠ​ራ​ውን የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገጃ፥ ይህ​ንም መሠ​ዊ​ያና መስ​ገጃ አፈ​ረሰ፤ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ሰባ​በረ፤ አድ​ቅ​ቆም ትቢያ አደ​ረ​ገው፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዱ​ንም አቃ​ጠ​ለው።</verse>
				<verse number="16">ኢዮ​ስ​ያ​ስም ዘወር ብሎ በከ​ተ​ማው የነ​በ​ሩ​ትን መቃ​ብ​ሮች አየ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም በበ​ዓል ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ ልኮ ከመ​ቃ​ብ​ሮቹ አጥ​ን​ቶ​ቹን አስ​ወጣ፥ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይም አቃ​ጠ​ላ​ቸው፥ አረ​ከ​ሰ​ውም። ዘወ​ርም ብሎ ይህን ቃል ወደ ተና​ገ​ረው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው መቃ​ብር ዐይ​ኖ​ቹን አቀና። እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="17">“ይህ የማ​የው የተ​ቀ​በረ ነገር ምን​ድን ነው?” አለ የዚ​ያ​ችም ከተማ ሰዎች፥ “ከይ​ሁዳ መጥቶ በቤ​ቴል መሠ​ዊያ ላይ ይህን ያደ​ረ​ግ​ኸ​ውን ነገር የተ​ና​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው መቃ​ብር ነው” ብለው ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="18">እር​ሱም፥ “ተዉት፥ ማንም አጥ​ን​ቱን አያ​ን​ቀ​ሳ​ቅ​ሰው” አለ፤ አጥ​ን​ቶ​ቹም ከሰ​ማ​ርያ ከመ​ጣው ከነ​ቢዩ አጥ​ንት ጋር ዳኑ።</verse>
				<verse number="19">በሰ​ማ​ር​ያም ከተ​ሞች የነ​በ​ሩ​ትን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያስ​ቈ​ጡት ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የሠ​ሩ​ትን የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎች ኢዮ​ስ​ያስ አስ​ወ​ገ​ዳ​ቸው፤ በቤ​ቴ​ልም እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ነገር ሁሉ እን​ዲሁ አደ​ረ​ገ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">በዚ​ያም የነ​በ​ሩ​ትን የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎች ካህ​ናት ሁሉ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዎቹ ላይ ገደ​ላ​ቸው፥ የሰ​ዎ​ቹ​ንም አጥ​ንት በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዎቹ ላይ አቃ​ጠለ። ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="21">ንጉ​ሡም ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ “በዚህ በቃል ኪዳኑ መጽ​ሐፍ እንደ ተጻ​ፈው ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲ​ካን አድ​ርጉ” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">እን​ደ​ዚ​ህም ያለ ፋሲካ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ይፈ​ርዱ ከነ​በሩ ከመ​ሳ​ፍ​ንት ዘመን ጀምሮ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ዘመን ሁሉ አል​ተ​ደ​ረ​ገም።</verse>
				<verse number="23">ነገር ግን በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመት ይህ ፋሲካ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተደ​ረገ።</verse>
				<verse number="24">ደግ​ሞም ካህኑ ኬል​ቅ​ያስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ባገ​ኘው መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን የሕ​ጉን ቃል ያጸና ዘንድ፥ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ቹ​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ቹን ተራ​ፊ​ም​ንና ጣዖ​ታ​ት​ንም በይ​ሁዳ ሀገ​ርና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ገ​ኘ​ውን ርኵ​ሰት ሁሉ ኢዮ​ስ​ያስ አስ​ወ​ገደ።</verse>
				<verse number="25">እንደ ሙሴም ሕግ ሁሉ በፍ​ጹም ልቡ በፍ​ጹ​ምም ነፍሱ በፍ​ጹ​ምም ኀይሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ለሰ እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ ከእ​ርሱ አስ​ቀ​ድሞ አል​ነ​በ​ረም፤ እንደ እር​ሱም ያለ ንጉሥ ከእ​ርሱ በኋላ አል​ተ​ነ​ሣም።</verse>
				<verse number="26">ነገር ግን ምናሴ ስላ​ስ​ቈ​ጣው ነገር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በይ​ሁዳ ላይ ከነ​ደ​ደው ከታ​ላቁ ቍጣው ትኵ​ሳት አል​ተ​መ​ለ​ሰም።</verse>
				<verse number="27">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “እስ​ራ​ኤ​ልን እን​ዳ​ራ​ቅ​ሁት ይሁ​ዳን ከፊቴ አር​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ይህ​ች​ንም የመ​ረ​ጥ​ኋ​ትን ከተማ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንና፦ ስሜ በዚያ ይሆ​ናል ያል​ሁ​ት​ንም ቤት እጥ​ላ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="28">የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​ስ​ያስ ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="29">በእ​ር​ሱም ዘመን የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን ኒካዑ ከአ​ሦር ንጉሥ ጋር ሊጋ​ጠም ወደ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ወጣ፤ ንጉ​ሡም ኢዮ​ስ​ያስ ከእ​ርሱ ጋር ሊጋ​ጠም ወጣ፤ ፈር​ዖ​ንም በተ​ገ​ና​ኘው ጊዜ በመ​ጊዶ ገደ​ለው።</verse>
				<verse number="30">አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም በድ​ኑን በሰ​ረ​ገ​ላው አድ​ር​ገው ከመ​ጊዶ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመ​ጡት፤ በመ​ቃ​ብ​ሩም ቀበ​ሩት። የሀ​ገ​ሩም ሰዎች የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስን ልጅ ዮአ​ክ​ስን ወሰ​ዱት። ቀብ​ተ​ውም በአ​ባቱ ፋንታ አነ​ገ​ሡት።</verse>
				<verse number="31">ዮአ​ክ​ስም በነ​ገሠ ጊዜ ሃያ ሦስት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሦስት ወር ነገሠ። እና​ቱም አሚ​ጣል ትባል ነበር፥ እር​ስ​ዋም የሎ​ብና ሰው የኤ​ር​ም​ያስ ልጅ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="32">እር​ሱም አባ​ቶቹ እንደ አደ​ረጉ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="33">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እን​ዳ​ይ​ነ​ግሥ ፈር​ዖን ኒካዑ በኤ​ማት ምድር ባለ​ችው በዴ​ብ​ላታ አሰ​ረው፤ በም​ድ​ሩም ላይ መቶ መክ​ሊት ብርና አንድ መቶ መክ​ሊት ወርቅ ፈሰሴ ጣለ​በት።</verse>
				<verse number="34">ፈር​ዖን ኒካ​ዑም የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስን ልጅ ኤል​ያ​ቄ​ምን በአ​ባቱ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ፋንታ አነ​ገሠ፤ ስሙ​ንም ኢዮ​አ​ቄም ብሎ ለወ​ጠው። ዮአ​ክ​ስ​ንም ወስዶ ወደ ግብፅ አፈ​ለ​ሰው፤ በዚ​ያም ሞተ።</verse>
				<verse number="35">ኢዮ​አ​ቄ​ምም ብሩ​ንና ወር​ቁን ለፈ​ር​ዖን ሰጠው፤ እንደ ፈር​ዖ​ንም ትእ​ዛዝ ገን​ዘብ ይሰጥ ዘንድ ምድ​ሩን አስ​ገ​በረ፤ ለፈ​ር​ዖን ኒካ​ዑም ግብር ይሰጥ ዘንድ ከሀ​ገሩ ሕዝብ ሁሉ እንደ ግም​ጋ​ሜው ብርና ወርቅ አስ​ከ​ፈለ።</verse>
				<verse number="36">ኢዮ​አ​ቄ​ምም በነ​ገሠ ጊዜ ሃያ አም​ስት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ሄል​ድፍ ትባል ነበር፤ እር​ስ​ዋም የሩማ ሰው የፈ​ዳያ ልጅ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="37">አባ​ቶ​ቹም እን​ዳ​ደ​ረጉ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="24">
				<verse number="1">በእ​ር​ሱም ዘመን የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወጣ፤ ኢዮ​አ​ቄ​ምም ሦስት ዓመት ተገ​ዛ​ለት፤ ከዚ​ያም በኋላ ዘወር አለና ዐመ​ፀ​በት።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን አደጋ ጣዮች፥ የሶ​ር​ያ​ው​ያ​ን​ንም አደጋ ጣዮች፥ የሞ​ዓ​ባ​ው​ያ​ን​ንም አደጋ ጣዮች፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች አደጋ ጣዮች ሰደ​ደ​በት፤ በባ​ሪ​ያ​ዎቹ በነ​ቢ​ያት ቃል እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ያጠ​ፉት ዘንድ በይ​ሁዳ ላይ ሰደ​ዳ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ምና​ሴም ስላ​ደ​ረ​ገው ኀጢ​አት ሁሉ ከፊቱ ያር​ቀው ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በይ​ሁዳ ላይ ሆነ፤</verse>
				<verse number="4">ጻድ​ቁ​ንም ስለ ገደለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም በን​ጹሕ ደም ስለ ሞላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይራራ ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም።</verse>
				<verse number="5">የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​አ​ቄም ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="6">ኢዮ​አ​ቄ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በኦ​ዛም የአ​ት​ክ​ልት ቦታ ተቀ​በረ ልጁም ዮአ​ኪን በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።</verse>
				<verse number="7">የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ለግ​ብፅ ንጉሥ የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ከግ​ብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ ወስዶ ነበ​ርና የግ​ብፅ ንጉሥ ከዚያ ወዲህ ከሀ​ገሩ አል​ወ​ጣም።</verse>
				<verse number="8">ዮአ​ኪ​ንም በነ​ገሠ ጊዜ ዐሥራ ስም​ንት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሦስት ወር ነገሠ፤ እና​ቱም ኒስታ ትባል ነበር፤ እር​ስ​ዋም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሰው የኤ​ል​ና​ታን ልጅ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="9">አባ​ቶ​ቹም እን​ዳ​ደ​ረጉ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="10">በዚ​ያም ወራት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ የና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ሠራ​ዊት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጡ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱም ተከ​በ​በች።</verse>
				<verse number="11">የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ መጣ። ሠራ​ዊ​ቱም ከበ​ቡ​አት።</verse>
				<verse number="12">የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ዮአ​ኪን ከእ​ናቱ፥ ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም፥ ከአ​ለ​ቆ​ቹም፥ ከጃ​ን​ደ​ረ​ቦ​ቹም ጋር ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ ወጣ፤ የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በነ​ገሠ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ዓመት ያዘው።</verse>
				<verse number="13">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ መዛ​ግ​ብት ሁሉ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤተ መዛ​ግ​ብት ከዚያ አወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ የሠ​ራ​ውን የወ​ር​ቁን ዕቃ ሁሉ ሰባ​በረ።</verse>
				<verse number="14">ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም አጠ​ፋት፥ አለ​ቆ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ጽኑ​ዓ​ኑ​ንና ኀያ​ላ​ኑን ሁሉ፥ ጠራ​ቢ​ዎ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ብረት ሠራ​ተ​ኞ​ቹ​ንም ሁሉ ዐሥር ሺህ ምር​ኮ​ኞ​ችን ሁሉ አፈ​ለሰ፤ ከሀ​ገሩ ድሆች በቀር ማንም አል​ቀ​ረም።</verse>
				<verse number="15">ዮአ​ኪ​ን​ንም ወደ ባቢ​ሎን አፈ​ለሰ፤ የን​ጉ​ሡ​ንም እናት፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ሚስ​ቶች፥ ጃን​ደ​ረ​ቦ​ቹ​ንም፥ የሀ​ገ​ሩ​ንም ታላ​ላ​ቆች ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ባቢ​ሎን ማረከ።</verse>
				<verse number="16">የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ሰባት ሺህ ያህል፥ ብር​ቱ​ዎ​ች​ንና ሰልፍ የሚ​ች​ሉ​ትን ሁሉ፥ ኀያ​ላ​ኑን ሁሉ አንድ ሺህ የሚ​ሆኑ ጠራ​ቢ​ዎ​ች​ንና ብረት ሠራ​ተ​ኞ​ች​ንም ወደ ባቢ​ሎን ማረከ።</verse>
				<verse number="17">የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ የዮ​አ​ኪ​ንን አጎት ማታ​ን​ያን በእ​ርሱ ፋንታ አነ​ገሠ፤ ስሙ​ንም ሴዴ​ቅ​ያስ ብሎ ለወ​ጠው።</verse>
				<verse number="18">ሴዴ​ቅ​ያ​ስም በነ​ገሠ ጊዜ ሃያ አንድ ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም አሚ​ጣል የተ​ባ​ለች የሎ​ብና ሰው የኤ​ር​ም​ያስ ልጅ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="19">ኢዮ​አ​ቄ​ምም እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="20">ከፊቱ አው​ጥቶ እስ​ኪ​ጥ​ላ​ቸው ድረስ ይህ ነገር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ላይ ሆኖ​አ​ልና፤ ሴዴ​ቅ​ያ​ስም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="25">
				<verse number="1">ሴዴ​ቅ​ያ​ስም በነ​ገሠ በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከሠ​ራ​ዊቱ ሁሉ ጋር ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጥቶ ሰፈ​ረ​ባት፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ዕርድ ሠራ​ባት።</verse>
				<verse number="2">ከተ​ማ​ዪ​ቱም እስከ ንጉሡ እስከ ሴዴ​ቅ​ያስ ዐሥራ አን​ደ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት እስከ አራ​ተ​ኛው ወር እስከ ዘጠ​ነ​ኛው ቀን ድረስ ተከ​ብባ ነበር።</verse>
				<verse number="3">በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ራብ ጸንቶ ነበ​ርና ለሀ​ገሩ ሰዎች እህል ታጣ።</verse>
				<verse number="4">ከተ​ማ​ዪ​ቱም ተሰ​በ​ረች፤ ሰል​ፈ​ኞ​ችም ሁሉ በሁ​ለት ቅጥር መካ​ከል ባለው በር ወደ ንጉሡ አት​ክ​ልት በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ በሌ​ሊት ሸሹ፤ ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዙሪያ ነበሩ፤ ወደ ምድረ በዳ በሚ​ወ​ስ​ደ​ውም መን​ገድ ሄዱ።</verse>
				<verse number="5">የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ሠራ​ዊት ንጉ​ሡን ተከ​ተሉ፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም በኩል ባለው ሜዳ ያዙት፤ ሠራ​ዊ​ቱም ሁሉ ከእ​ርሱ ተለ​ይ​ተው ተበ​ት​ነው ነበር።</verse>
				<verse number="6">ንጉ​ሡ​ንም ይዘው የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ወዳ​ለ​በት የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ክፍል ወደ​ም​ት​ሆን ወደ ዴብ​ላታ ወሰ​ዱት፤ ፍር​ድም ፈረ​ዱ​በት።</verse>
				<verse number="7">የሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስ​ንም ልጆች በፊቱ ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ የሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስ​ንም ዐይ​ኖች አወጡ፤ በሰ​ን​ሰ​ለ​ትም አሰ​ሩት፤ ወደ ባቢ​ሎ​ንም ወሰ​ዱት።</verse>
				<verse number="8">በባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በዐ​ሥራ ዘጠ​ነ​ኛው ዓመት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ፊት የሚ​ቆ​መው የአ​በ​ዛ​ዎች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣ።</verse>
				<verse number="9">የን​ጉ​ሡም የአ​በ​ዛ​ዎች አለቃ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የን​ጉ​ሡን ቤት አቃ​ጠለ። የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቤቶች ሁሉ በእ​ሳት አቃ​ጠለ።</verse>
				<verse number="10">የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሠራ​ዊት ሁሉ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን የአ​ን​ባ​ዋን ቅጥር ዙሪ​ያ​ዋን አፈ​ረሱ።</verse>
				<verse number="11">የአ​በ​ዛ​ዎች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ውስጥ የቀ​ረ​ውን ሕዝብ፥ ሸሽ​ተ​ውም ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ የተ​ጠ​ጉ​ትን፥ የቀ​ሩ​ት​ንም ሕዝብ ሁሉ ማርኮ ወሰደ።</verse>
				<verse number="12">የአ​በ​ዛ​ዎ​ችም አለቃ ከሀ​ገሩ ድሆች ወይን ተካ​ዮ​ችና አራ​ሾች እን​ዲ​ሆኑ አስ​ቀረ።</verse>
				<verse number="13">ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ የነ​በ​ሩ​ትን የናስ ዓም​ዶች፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የነ​በ​ሩ​ትን መቀ​መ​ጫ​ዎ​ችና የናስ ኵሬ​ዎች ሰባ​በሩ፤ ናሱ​ንም ወደ ባቢ​ሎን ወሰዱ።</verse>
				<verse number="14">ምን​ቸ​ቶ​ቹ​ንና ማን​ካ​ዎ​ቹ​ንም፥ መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንና ጭል​ፋ​ዎ​ቹ​ንም የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ት​ንም የናስ ዕቃ ሁሉ ወሰዱ።</verse>
				<verse number="15">የአ​በ​ዛ​ዎች አለ​ቃም ጥና​ዎ​ቹን ከወ​ር​ቅና ከብር የተ​ሠሩ መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ንም ወሰደ።</verse>
				<verse number="16">ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሠ​ራ​ቸ​ውን ሁለ​ቱን ዓም​ዶች፥ አን​ዱ​ንም ኵሬ መቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹ​ንም ወሰደ፤ ለእ​ነ​ዚ​ህም ዕቃ​ዎች ሁሉ ናስ ሚዛን አል​ነ​በ​ረ​ውም።</verse>
				<verse number="17">የአ​ን​ዱም ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስም​ንት ክንድ ነበረ፥ የና​ስም ጕል​ላት ነበ​ረ​በት፤ የጕ​ል​ላ​ቱም ርዝ​መት ሦስት ክንድ ነበረ፥ በጕ​ል​ላ​ቱም ላይ በዙ​ሪ​ያው የናስ መር​በ​ብና ሮማ​ኖች ነበሩ፤ እን​ዲ​ሁም ደግሞ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓምድ ላይ መር​በብ ነበ​ረ​በት።</verse>
				<verse number="18">የአ​በ​ዛ​ዎ​ችም አለቃ ታላ​ቁን ካህን ሠራ​ያን ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ካህን ሶፎ​ን​ያ​ስን ሦስ​ቱ​ንም በረ​ኞች ማርኮ ወሰደ።</verse>
				<verse number="19">ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በሰ​ል​ፈ​ኞች ላይ ተሾ​መው ከነ​በ​ሩት አን​ዱን ጃን​ደ​ረባ፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም የተ​ገ​ኙ​ትን በን​ጉሡ ፊት የሚ​ቆ​ሙ​ትን አም​ስ​ቱን ሰዎች፥ የሀ​ገ​ሩ​ንም ሕዝብ የሚ​ያ​ሰ​ልፍ የሠ​ራ​ዊ​ቱን አለቃ ጸሓፊ፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ከተ​ገ​ኙት ከሀ​ገሩ ሕዝብ ስድሳ ሰዎ​ችን ወሰደ።</verse>
				<verse number="20">የአ​በ​ዛ​ዎ​ቹም አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ማርኮ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ወዳ​ለ​በት ወደ ዴብ​ላታ አመ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ መታ​ቸው፥ በኤ​ማ​ትም ምድር ባለ​ችው በዴ​ብ​ላታ ገደ​ላ​ቸው። እን​ዲ​ሁም ይሁዳ ከሀ​ገሩ ተማ​ረከ።</verse>
				<verse number="22">የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በይ​ሁዳ ምድር በቀ​ረው ሕዝብ ላይ የሳ​ፋ​ንን ልጅ የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያን ሾመው።</verse>
				<verse number="23">የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለ​ቆች ሁሉ ሰዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ የና​ታ​ንዩ ልጅ እስ​ማ​ኤል፥ የቃ​ሬ​ያን ልጅ ዮሐ​ናን፥ የነ​ጦ​ፋ​ዊ​ውም የተ​ን​ሑ​ሜት ልጅ ሴሪያ፥ የማ​ዕ​ካ​ታ​ዊው ልጅ አዛ​ንያ፥ ሰዎ​ቻ​ቸ​ውም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ጎዶ​ል​ያን እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ ወደ ጎዶ​ልያ ወደ መሴፋ መጡ።</verse>
				<verse number="24">ጎዶ​ል​ያም፥ “ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሎሌ​ዎች የተ​ነሣ አት​ፍሩ፤ በሀ​ገሩ ተቀ​መጡ፤ ለባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ተገዙ፤ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል” ብሎ ለእ​ነ​ር​ሱና ለሰ​ዎ​ቻ​ቸው ማለ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ግን የመ​ን​ግ​ሥት ዘር የነ​በረ የኤ​ል​ሴማ ልጅ የና​ታ​ንዩ ልጅ እስ​ማ​ኤል መጣ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ዐሥር ሰዎች ነበሩ፤ ጎዶ​ል​ያ​ንም መታው፤ ሞተም፤ ከእ​ር​ሱም ጋር በመ​ሴፋ የነ​በ​ሩ​ትን አይ​ሁ​ድ​ንና ከለ​ዳ​ው​ያ​ን​ንም ገደ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">ከለ​ዳ​ው​ያ​ን​ንም ፈር​ተው ነበ​ርና ከታ​ናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሕዝቡ ሁሉ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለ​ቆች ተነ​ሥ​ተው ወደ ግብፅ ገቡ።</verse>
				<verse number="27">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የይ​ሁዳ ንጉሥ ዮአ​ኪን በተ​ማ​ረከ በሠ​ላሳ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ቀን የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ዮር​ማ​ሮ​ዴቅ በነ​ገሠ በአ​ን​ደ​ኛው ዓመት የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ዮአ​ኪ​ንን ከፍ አደ​ረ​ገው፤ ከወ​ህኒ ቤትም አወ​ጣው፤</verse>
				<verse number="28">መል​ካም ነገ​ር​ንም ተና​ገ​ረው፥ ዙፋ​ኑ​ንም ከእ​ርሱ ጋር በባ​ቢ​ሎን ከነ​በ​ሩት ነገ​ሥ​ታት ዙፋን በላይ አደ​ረ​ገ​ለት።</verse>
				<verse number="29">በወ​ህ​ኒም ውስጥ ለብ​ሶት የነ​በ​ረ​ውን ልብስ ለወ​ጠ​ለት፤ ዮአ​ኪ​ንም በሕ​ይ​ወቱ ዘመን ሁሉ በፊቱ ሁል​ጊዜ እን​ጀራ ይበላ ነበር።</verse>
				<verse number="30">ቀለ​ቡ​ንም ሁል​ጊዜ ከን​ጉሡ ቤት ይቀ​በል ነበር፤ በሕ​ይ​ወ​ቱም ዘመን ሁሉ የዘ​ወ​ትር ቀለ​ቡን ዕለት ዕለት ይሰ​ጡት ነበር።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="13">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">አዳም፥ ሴት፥ ሄኖስ፥</verse>
				<verse number="2">ቃይ​ናን፥ መላ​ል​ኤል፥ ያሬድ፥</verse>
				<verse number="3">ሄኖክ፥ ማቱ​ሳላ፥ ላሜሕ፥</verse>
				<verse number="4">ኖኅ፥ ልጆ​ቹም ሴም፥ ካም፥ ያፌት።</verse>
				<verse number="5">የያ​ፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዳይ፥ ይሕ​ያን፥ ኤልሳ፥ ቶቤል፥ ሞሳ​ሕና ቲራም።</verse>
				<verse number="6">የጋ​ሜ​ርም ልጆች አስ​ካ​ናስ፥ ሪፋት፥ ቶር​ጋማ።</verse>
				<verse number="7">የይ​ሕያ ልጆች ኤልሳ፥ ተር​ሴስ፥ ኬቲም፥ ሮድኢ።</verse>
				<verse number="8">የካ​ምም ልጆች፤ ኩሽ፥ ምስ​ራ​ይም፥ ፉጥ፥ ከነ​ዓን።</verse>
				<verse number="9">የኩ​ሽም ልጆች፤ ሳባ፥ ኤው​ላጥ፥ ሳበታ፥ ሬግ​ማን፥ ሱቦን። የሬ​ግ​ማ​ንም ልጆች፤ ሴባ፥ ዳዳን።</verse>
				<verse number="10">ኩሽም ናም​ሩ​ድን ወለደ፤ እር​ሱም በም​ድር ላይ አዳ​ኝና ኀያል መሆ​ንን ጀመረ።</verse>
				<verse number="11">ምሥ​ራ​ይም ሎዲ​አ​ምን፥ ዐና​ኒ​ምን፥ ሎቢ​ንን፥ ንፍ​ታ​ሌ​ምን፥</verse>
				<verse number="12">ጴጥ​ሮ​ሳ​ኒ​ኤ​ምን፥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን የወ​ጡ​በ​ትን ከሰ​ሎ​ን​ኤ​ምን፥ ከፋ​ቱ​ሪ​ምን ወለደ።</verse>
				<verse number="13">ከነ​ዓን የበ​ኵር ልጁን ሲዶ​ንን፥ ኬጤ​ዎ​ንን፥</verse>
				<verse number="14">ኤያ​ቡ​ሴ​ዎ​ንን፥ አሞ​ሬ​ዎ​ንን፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ንን፥</verse>
				<verse number="15">አዌ​ዎ​ንን፥ አረ​ቄ​ዎ​ንን፥ ኤሴ​ነ​ዎ​ንን፥</verse>
				<verse number="16">አራ​ዴ​ዎ​ንን፥ ሰማ​ሬ​ዎ​ንን፥ አማ​ቲን ወለደ።</verse>
				<verse number="17">የሴ​ምም ልጆች፤ አይ​ላም፥ አሡር፥ አር​ፋ​ክ​ስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ የአ​ራ​ምም ልጆች፤ ኡስ፥ ዑል፥ ጋቴር፥ ሞሳክ።</verse>
				<verse number="18">አር​ፋ​ክ​ስ​ድም ቃይ​ና​ንን ወለደ፤ ቃይ​ና​ንም ሳላን ወለደ፤ ሳላም ኤቦ​ርን ወለደ።</verse>
				<verse number="19">ለኤ​ቦ​ርም ሁለት ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ በዘ​መኑ ምድር ተከ​ፋ​ፍ​ላ​ለ​ችና የአ​ን​ደ​ኛው ስም ፋሌቅ ተባለ፤ የወ​ን​ድ​ሙም ስም ዮቅ​ጣን ነበረ፤</verse>
				<verse number="20">ዮቅ​ጣ​ንም ኤል​ሞ​ዳ​ድን፥ ሣሌ​ፍን፥ ኤራ​ሞ​ትን፥ ያራ​ሕን፥</verse>
				<verse number="21">ቄዱ​ራ​ምን፥ ኤዜ​ልን፥ ዲቅ​ላ​ምን፥</verse>
				<verse number="22">ጌማ​ሄ​ልን፥ ኤል​ሜ​ሄ​ልን፥ ሳባን፥</verse>
				<verse number="23">ኦፌ​ርን፥ ሄው​ላን፥ ኦራ​ምን፥ ዑካ​ብን ወለደ፤ እነ​ዚህ ሁሉ የዮ​ቅ​ጣን ልጆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="24">የሴ​ምም ልጆች፤ አይ​ላም፥ አሡር፥ አር​ፋ​ክ​ስድ፥ ሳላን፥ ቃይ​ናን፥</verse>
				<verse number="25">ዔቦር፥ ፋሌቅ፥ ራግው፥</verse>
				<verse number="26">ሴሮሕ፥ ናኮር፥ ታራ፥</verse>
				<verse number="27">አብ​ር​ሃም የተ​ባ​ለው አብ​ራም።</verse>
				<verse number="28">የአ​ብ​ር​ሃ​ምም ልጆች፤ ይስ​ሐቅ፥ ይስ​ማ​ኤል።</verse>
				<verse number="29">ትው​ል​ዳ​ቸ​ውም እን​ደ​ዚህ ነው። የይ​ስ​ማ​ኤል በኵር ልጅ ናቢ​ዎት፤ ቄዳር፥ ቢዲ​ሄል፥ ሙባ​ሳን፥</verse>
				<verse number="30">ሚስ​ማዕ፥ ይዱማ፥ ማሴ፥ ኬዲድ፥ ቴማን፤</verse>
				<verse number="31">የጡር፥ ናፌስ፥ ቂዳማ፤ እነ​ዚህ የይ​ስ​ማ​ኤል ልጆች ናቸው።</verse>
				<verse number="32">የአ​ብ​ር​ሃም ዕቅ​ብት ኬጡራ የወ​ለ​ደ​ች​ለት ልጆች፤ ዘም​ራን፥ ዮቅ​ሳን፥ ሜዳም፥ ምድ​ያን፥ ዮሳ​ብቅ፥ ስዌሕ፥ የዮ​ቅ​ሳ​ንም ልጆች፤ ሳባ፥ ዳዳን።</verse>
				<verse number="33">የም​ድ​ያ​ምም ልጆች፤ ጌፌር፥ ዔፌር፥ ሄኖሕ፥ አቢ​ዳን፥ ኤል​ዳን። እነ​ዚህ ሁሉ የኬ​ጡራ ልጆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="34">አብ​ር​ሃ​ምም ይስ​ሐ​ቅን ወለደ። የይ​ስ​ሐ​ቅም ልጆች ዔሳ​ውና ያዕ​ቆብ ነበሩ።</verse>
				<verse number="35">የዔ​ሳው ልጆች፤ ዔል​ፋዝ፥ ራጉ​ኤል፥ ይዑል፥ ይጉ​ሎም፥ ቆሬ።</verse>
				<verse number="36">የኤ​ል​ፋዝ ልጆች፤ ቴማን፥ ኦማር፥ ሳፍር፥ ጎታም፥ ቄኔዝ፥ ቴም​ናስ፥ አማ​ሌቅ።</verse>
				<verse number="37">የራ​ጉ​ኤል ልጆች፤ ናቦት፥ ዛራ፥ ሴዴት፥ ሞዛ።</verse>
				<verse number="38">የሴ​ይ​ርም ልጆች፤ ሎጣን፥ ሳባን፥ ሴቤ​ጎን፥ ዓናን፥ ዴሶን፥ አሦር፥ ዴሳን።</verse>
				<verse number="39">የሎ​ጣ​ንም ልጆች፤ ሖሪ፥ ኤማን፤ ታም​ናን የሎ​ጣን እኅት ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="40">የሦ​ባል ልጆች፤ ጎለም፥ ማኔ​ሐት፥ ኔባል፥ ሳፍር፥ አናን፤ የሴ​ቤ​ጎን ልጆች፤ ሐያን፥ አናም፤</verse>
				<verse number="41">የአ​ናም ልጆች፤ ዴሶን፥ የአ​ናም ሴት ልጅ ኤሌማ፥ የዴ​ሶ​ንም ልጆች፤ አም​ዳን፥ ኤስ​ቦን፥ ኢይ​ት​ራን፥ ካራን፥ እሊህ ናቸው።</verse>
				<verse number="42">የአ​ሦር ልጆች፤ በለ​ዓን፥ ዛዕ​ዋን፥ ኢይ​ዓ​ቃን። የዴ​ሶን ልጆች፤ ዖስ፥ አራን።</verse>
				<verse number="43">በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ላይ ገና ንጉሥ ሳይ​ነ​ግሥ በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድር የነ​ገሡ ነገ​ሥ​ታት እነ​ዚህ ናቸው። የቢ​ዖር ልጅ ባላቅ፤ የከ​ተ​ማ​ውም ስም ዲናባ ነበረ።</verse>
				<verse number="44">ባላ​ቅም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ የባ​ሶራ ሰው የዛራ ልጅ ኢዮ​ባብ ነገሠ።</verse>
				<verse number="45">ኢዮ​ባ​ብም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ የቴ​ማን ሀገር ሰው አሶም ነገሠ፤</verse>
				<verse number="46">አሶ​ምም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ በሞ​ዓብ ሜዳ ምድ​ያ​ምን የመ​ታው የባ​ራድ ልጅ አዳድ ነገሠ፤ የከ​ተ​ማ​ውም ስም ጌቴም ነበረ።</verse>
				<verse number="47">አዳ​ድም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ የማ​ስቃ ሰው ስማዓ ነገሠ።</verse>
				<verse number="48">ስማ​ዓም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ በወ​ንዙ አጠ​ገብ ያለ​ችው የረ​ኆ​ቦት ሰው ሳኦል ነገሠ።</verse>
				<verse number="49">ሳኦ​ልም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ የአ​ክ​ቦር ልጅ በኣ​ል​ሐ​ናን ነገሠ።</verse>
				<verse number="50">የአ​ክ​ቦር ልጅ በኣ​ል​ሐ​ና​ንም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ የባ​ራድ ልጅ አዳድ ነገሠ፤ የከ​ተ​ማ​ውም ስም ፌጎር ነበረ፤ ሚስ​ቱም የሚ​ዛ​ሃብ ልጅ የመ​ጥ​ሬድ ልጅ መሄ​ጣ​ብ​ኤል ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="51">አዳ​ድም ሞተ፤ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም አለ​ቆች እነ​ዚህ ነበሩ፤ ቴም​ናዕ አለቃ፥ ጎለም አለቃ፥ የቴት አለቃ፥</verse>
				<verse number="52">አህ​ሊ​ባማ አለቃ፥ ኤላ አለቃ፥ ፌኖን አለቃ፥</verse>
				<verse number="53">ቄኔዝ አለቃ፥ ቴማን አለቃ፥ መብ​ሳር አለቃ፥</verse>
				<verse number="54">መግ​ዴ​ኤል አለቃ፥ ዛፎ​አል አለቃ፤ እነ​ዚህ የኤ​ዶ​ም​ያስ አለ​ቆች ነበሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ስሞች እነ​ዚህ ናቸው፤ ሮቤል፥ ስም​ዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳ​ኮር፥ ዛብ​ሎን፤</verse>
				<verse number="2">ዳን፥ ዮሴፍ፥ ብን​ያም፥ ንፍ​ታ​ሌም፥ ጋድ፥ አሴር።</verse>
				<verse number="3">የይ​ሁዳ ልጆች፤ ዔር፥ አው​ናን፥ ሴሎም፤ እነ​ዚህ ሦስቱ ከከ​ነ​ዓ​ና​ዊቱ ሴት ከሴዋ ልጅ ተወ​ለ​ዱ​ለት። የይ​ሁ​ዳም የበ​ኵር ልጅ ዔር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ ገደ​ለ​ውም።</verse>
				<verse number="4">ምራ​ቱም ትዕ​ማር ፋሬ​ስ​ንና ዛራን ወለ​ደ​ች​ለት፤ የይ​ሁ​ዳም ልጆች ሁሉ አም​ስት ነበሩ።</verse>
				<verse number="5">የፋ​ሬስ ልጆች፤ ኤስ​ሮም፥ ያሙ​ሔል።</verse>
				<verse number="6">የዛ​ራም ልጆች፤ ዘምሪ፥ ኤታን፥ ኤማን፥ ካል​ኮል፥ ዳራ፤ ሁሉም አም​ስት ነበሩ።</verse>
				<verse number="7">የዘ​ም​ሪም ልጅ ከርሚ ነው፤ የከ​ር​ሚም ልጅ እስ​ራ​ኤ​ልን ያስ​ጨ​ነቀ፥ እር​ሙን ሰርቆ የበ​ደለ አካን ነበረ።</verse>
				<verse number="8">የኤ​ታ​ንም ልጅ አዛ​ርያ ነበረ።</verse>
				<verse number="9">ለኤ​ስ​ሮም የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት ልጆች፤ ኢያ​ሬ​ሄም፥ አራም፥ ካሌብ ነበሩ።</verse>
				<verse number="10">አራ​ምም አሚ​ና​ዳ​ብን ወለደ፤ አሚ​ና​ዳ​ብም የይ​ሁ​ዳን ልጆች አለቃ ነአ​ሶ​ንን ወለደ፤</verse>
				<verse number="11">ነአ​ሶ​ንም ሰል​ሞ​ንን ወለደ፤ ሰል​ሞን ቦዔ​ዝን ወለደ፤</verse>
				<verse number="12">ቦዔ​ዝም ኢዮ​ቤ​ድን ወለደ፤ ኢዮ​ቤ​ድም እሴ​ይን ወለደ፤</verse>
				<verse number="13">እሴ​ይም የበ​ኵር ልጁን ኤል​ያ​ብን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም አሚ​ና​ዳ​ብን፥ ሦስ​ተ​ኛ​ው​ንም ሣማን፥</verse>
				<verse number="14">አራ​ተ​ኛ​ው​ንም ናት​ና​ኤ​ልን፥ አም​ስ​ተ​ኛ​ው​ንም ራዳ​ይን፥</verse>
				<verse number="15">ስድ​ስ​ተ​ኛ​ው​ንም አሶ​ንን፥ ሰባ​ተ​ኛ​ው​ንም ዳዊ​ትን ወለደ፤</verse>
				<verse number="16">እኅ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሶር​ህ​ያና አቢ​ግያ ነበሩ። የሶ​ር​ህ​ያም ልጆች አቢሳ፥ ኢዮ​አብ፥ አሣ​ሄል እኒህ ሦስቱ ነበሩ።</verse>
				<verse number="17">አቢ​ግ​ያም አሜ​ሳ​ይን ወለ​ደች፤ የአ​ሜ​ሳ​ይም አባት እስ​ማ​ኤ​ላ​ዊው ይት​ኤር ነበረ።</verse>
				<verse number="18">የኤ​ስ​ሮ​ምም ልጅ ካሌብ ዐዙባ የም​ት​ባል ሚስት አገባ፥ ይሪ​ዖ​ት​ንም አገባ፤ ልጆ​ች​ዋም ያሳር፥ ሶባብ፥ ኤር​ኖን ነበሩ።</verse>
				<verse number="19">ዐዙ​ባም ሞተች፥ ካሌ​ብም ኤፍ​ራ​ታን አገባ፤ እር​ስ​ዋም ኦርን ወለ​ደ​ች​ለት።</verse>
				<verse number="20">ኦርም ኡሪን ወለደ፥ ኡሪም ባስ​ል​ኤ​ልን ወለደ።</verse>
				<verse number="21">ከዚ​ያም በኋላ ኤስ​ሮም ስድሳ ዓመት በሆ​ነው ጊዜ ወደ አገ​ባት ወደ ገለ​ዓድ አባት ወደ ማኬር ልጅ ገባ፤ ሴጉ​ብ​ንም ወለ​ደ​ች​ለት።</verse>
				<verse number="22">ሴጉ​ብም ኢያ​ኤ​ርን ወለደ፤ ለእ​ር​ሱም በገ​ለ​ዓድ ምድር ሃያ ሦስት ከተ​ሞች ነበ​ሩት።</verse>
				<verse number="23">ኤስ​ሮ​ምም ጌሱ​ር​ንና አራ​ምን የኢ​ያ​ዔ​ርን ከተ​ሞች ከቄ​ና​ትና ከመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ ጋር ስድ​ሳ​ውን ከተ​ሞች ወሰደ። እነ​ዚህ ሁሉ የገ​ለ​ዓድ አባት የማ​ኪር ልጆች ከተ​ሞች ነበሩ።</verse>
				<verse number="24">ኤስ​ሮ​ምም ከሞተ በኋላ ካሌብ ወደ ኤፍ​ራታ መጣ። የኤ​ስ​ሮ​ምም ሚስት አብያ የቴ​ቁ​ሔን አባት አስ​ሖ​ርን ወለ​ደ​ች​ለት።</verse>
				<verse number="25">የኤ​ስ​ሮ​ምም የበ​ኵር ልጁ የኢ​ያ​ሬ​ም​ሄል ልጆች በኵሩ ራም፥ በአ​ናን፥ አራን፥ አሶም፥ አኪያ ነበሩ።</verse>
				<verse number="26">ለኢ​ያ​ሬ​ም​ሄ​ልም አጥራ የተ​ባ​ለች ሌላ ሚስት ነበ​ረ​ችው፤ እር​ስ​ዋም የአ​ናም እናት ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="27">የኢ​ያ​ሬ​ም​ሄል የበ​ኵሩ የራም ልጆች ማኦስ፥ ኢያ​ቢን ዔቄር ነበሩ።</verse>
				<verse number="28">የአ​ና​ምም ልጆች ሸማ​ይና ያዳይ ነበሩ። የሸ​ማ​ይም ልጆች ናዳ​ብና አቢ​ሱር ነበሩ።</verse>
				<verse number="29">የአ​ቢ​ሱ​ርም ሚስት ስም አቢ​ካ​ኤል ነበረ፤ እር​ስ​ዋም፥ አዛ​ቡ​ር​ንና ሞሊ​ድን ወለ​ደ​ች​ለት።</verse>
				<verse number="30">የና​ዳ​ብም ልጆች ሴሌ​ድና አፋ​ይም ነበሩ፤ ሴሌ​ድም ልጆ​ችን ሳይ​ወ​ልድ ሞተ።</verse>
				<verse number="31">የአ​ፋ​ይ​ምም ልጅ ይሲ፥ የይ​ሲም ልጅ ሶሳን፥ የሶ​ሳ​ንም ልጅ አሕ​ላይ ነበረ። የአ​ሕ​ላ​ይም ልጅ ይዳይ ነበረ።</verse>
				<verse number="32">የይ​ዳይ ልጆች አክ​ሲም፥ ዮቴ​ርና ዮና​ታን ነበሩ፤ ዮቴ​ርም ልጆ​ችን ሳይ​ወ​ልድ ሞተ።</verse>
				<verse number="33">የዮ​ና​ታ​ንም ልጆች ፋሌ​ትና አዛዝ ነበሩ፤ እነ​ዚ​ህም የኢ​ያ​ሬ​ም​ሔል ልጆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="34">ለሶ​ሳ​ንም ሴቶች ልጆች እንጂ ወን​ዶች ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​ትም፤ ለሶ​ሳ​ንም ኢዮ​ሄል የተ​ባለ ግብ​ፃዊ አገ​ል​ጋይ ነበ​ረው።</verse>
				<verse number="35">ሶሳ​ንም ለአ​ገ​ል​ጋዩ ለኢ​ዮ​ሄል ልጁን አጋ​ባት፥ እር​ስ​ዋም ያቲን ወለ​ደ​ች​ለት።</verse>
				<verse number="36">ያቲም ናታ​ንን ወለደ፤ ናታ​ንም ዛቤ​ትን ወለደ፤</verse>
				<verse number="37">ዛቤ​ትም አው​ፋ​ልን ወለደ፤ አው​ፋ​ልም ዖቤ​ድን ወለደ፤</verse>
				<verse number="38">ዖቤ​ድም ኢያ​ሁን ወለደ፤ ኢያ​ሁም አዛ​ር​ያ​ስን ወለደ፤</verse>
				<verse number="39">አዛ​ር​ያ​ስም ኬሌ​ስን ወለደ፤ ኬሌ​ስም ኤል​ዓ​ሳን ወለደ፤</verse>
				<verse number="40">ኤል​ዓ​ሳም ሲስ​ማ​ኤ​ልን ወለደ፤ ሲስ​ማ​ኤ​ልም ሱላ​ምን ወለደ፤</verse>
				<verse number="41">ሱላ​ምም ኢዮ​ቆ​ምን ወለደ፤ ኢዮ​ቆ​ምም ኤል​ሳ​ማን ወለደ።</verse>
				<verse number="42">የኢ​ያ​ሬ​ም​ሄል ወን​ድም የካ​ሌብ ልጆች በኵር የዚፍ አባት ማሪስ ነው፤ የኬ​ብ​ሮ​ንም አባት የማ​ሪስ ልጆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="43">የኬ​ብ​ሮ​ንም ልጆች፤ ቆሬ፥ ተፋ፥ ሬቆ​ምና፥ ሴማዓ ነበሩ።</verse>
				<verse number="44">ሴማ​ዓም የኤ​ር​ቃ​ምን አባት ራኤ​ምን ወለደ፤ ኤር​ቃ​ምም ሰማ​ኤ​ምን ወለደ።</verse>
				<verse number="45">የሰ​ማ​ኤ​ምም ልጅ ማዖን ነበረ፤ ማዖ​ንም የቤት ሱር አባት ነበረ።</verse>
				<verse number="46">የካ​ሌ​ብም ዕቅ​ብት ጌፋ አራ​ንን፥ ሞሳን፥ ጋዜ​ዝን ወለ​ደች። አራ​ንም ጊዚ​ኢን ወለደ።</verse>
				<verse number="47">የያ​ዳ​ይም ልጆች፤ ሬጌም፥ ዮታም፥ ጌር​ሶም፥ ፋሌጥ፥ ጌፋና፥ ሰጋፍ ነበሩ።</verse>
				<verse number="48">የካ​ሌ​ብም ዕቅ​ብት ማዕካ ሴብ​ር​ንና ቲር​ሐ​ናን ወለ​ደች።</verse>
				<verse number="49">ደግ​ሞም የም​ድ​ሜ​ናን አባት ስጋ​ብን የመ​ክ​ቢ​ና​ንና የጌ​ባ​ልን አባት ሳዑ​ልን ወለ​ደች፤ የካ​ሌ​ብም ሴት ልጅ አስካ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="50">የካ​ሌ​ብም ልጆች እነ​ዚህ ነበሩ፤ የኤ​ፍ​ራታ የበ​ኵሩ የኦር ልጅ የቀ​ር​ያ​ታ​ርም አባት ሶባል ነበር፥</verse>
				<verse number="51">የቤተ ልሔም አባት ሰል​ሞን፥ የቤት ጋዲር አባት ኦሪ።</verse>
				<verse number="52">የቀ​ር​ያ​ታ​ር​ምም አባት የሶ​ባል ልጆች አረኤ፥ ሃጼ፥ አማ​ኒት ነበሩ።</verse>
				<verse number="53">የቀ​ር​ያ​ታ​ርም ወገ​ኖች፤ ይት​ራ​ው​ያን፥ ፋታ​ው​ያን፥ ሹማ​ታ​ው​ያን፥ ሚሸ​ራ​ው​ያን፤ ከእ​ነ​ዚ​ህም ሶራ​ሐ​ው​ያ​ንና ኤሽ​ታ​አ​ላ​ው​ያን ወጡ።</verse>
				<verse number="54">የሰ​ል​ሞ​ንም ልጆች ቤተ ልሔም፥ ነጦ​ፋ​ው​ያን፥ አጦ​ሮት ቤት​ዮ​አብ፥ የመ​ና​ሕ​ታ​ው​ያን እኩ​ሌታ፥ ሰራ​ዓ​ው​ያ​ንም ነበሩ።</verse>
				<verse number="55">በያ​ቤ​ጽም የተ​ቀ​መጡ የጸ​ሓ​ፊ​ዎች ወገ​ኖች፤ ቴር​ዓ​ው​ያን፥ ሹማ​ታ​ው​ያን፥ ሡካ​ታ​ው​ያን ነበሩ፤ እነ​ዚህ ከሬ​ካብ ቤት አባት ከሐ​ማት የወጡ ቄና​ው​ያን ናቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">በኬ​ብ​ሮን ለዳ​ዊት የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። በኵሩ አም​ኖን ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊቱ ከአ​ኪ​ና​ሆም፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዶለ​ህያ ከቀ​ር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊቱ ከአ​ቢ​ግያ፥</verse>
				<verse number="2">ሦስ​ተ​ኛው አቤ​ሴ​ሎም ከጌ​ድ​ሶር ንጉሥ ከተ​ል​ማይ ልጅ ከመ​ዓካ፥ አራ​ተ​ኛው አዶ​ን​ያስ ከአ​ጊት፥</verse>
				<verse number="3">አም​ስ​ተ​ኛው ሰፋ​ጥ​ያስ ከአ​ቢ​ጣል፥ ስድ​ስ​ተ​ኛው ይት​ር​ኃም ከሚ​ስቱ ከዔ​ግላ።</verse>
				<verse number="4">እነ​ዚህ ስድ​ስቱ በኬ​ብ​ሮን ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ በዚ​ያም ሰባት ዓመት ከስ​ድ​ስት ወር ነገሠ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="5">እነ​ዚህ ደግሞ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ ከዓ​ሚል ልጅ ከቤ​ር​ሳ​ቤህ ስማዕ፥ ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎ​ሞን፥ አራት፤</verse>
				<verse number="6">ኢያ​ቤ​ሔር፥ ኤል​ሳማ፥ ኤሊ​ፋ​ላት፥</verse>
				<verse number="7">ናጌል፥ ናፌቅ፥ ያፍያ፥</verse>
				<verse number="8">ኤል​ሳማ፥ ኤሊዳ፥ ኤል​ፋ​ሌጥ፥ ዘጠኝ።</verse>
				<verse number="9">እነ​ዚህ ሁሉ ከቁ​ባ​ቶቹ ልጆች በቀር የዳ​ዊት ልጆች ነበሩ፤ ትዕ​ማ​ርም እኅ​ታ​ቸው ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="10">የሰ​ሎ​ሞ​ንም ልጅ ሮብ​ዓም ነበረ፤ ልጁ አቢያ፥ ልጁ አሳ፥ ልጁ ኢዮ​ሣ​ፍጥ፥</verse>
				<verse number="11">ልጁ ኢዮ​ራም፥ ልጁ አካ​ዝ​ያስ፥ ልጁ ኢዮ​አስ፥</verse>
				<verse number="12">ልጁ አሜ​ስ​ያስ፥ ልጁ ዓዛ​ር​ያስ፥ ልጁ ኢዮ​አ​ታም፥</verse>
				<verse number="13">ልጁ አካዝ፥ ልጁ ሕዝ​ቅ​ያስ፥ ልጁ ምናሴ፥</verse>
				<verse number="14">ልጁ አሞጽ፥ ልጁ ኢዮ​ስ​ያስ።</verse>
				<verse number="15">የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስም ልጆች፤ በኵሩ ዮሐ​ናን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ኢዮ​አ​ቄም፥ ሦስ​ተ​ኛ​ውም ሴዴ​ቅ​ያስ፥ አራ​ተ​ኛ​ውም ሰሎም።</verse>
				<verse number="16">የኢ​ዮ​አ​ቄ​ምም ልጆች፤ ልጁ ኢኮ​ን​ያን፥ ልጁ ሴዴ​ቅ​ያስ።</verse>
				<verse number="17">የኢ​ኮ​ን​ያ​ንም ልጆች አሤር፥ ሰላ​ት​ያል፥</verse>
				<verse number="18">መል​ኪ​ራም፥ ፈዳያ፥ ሳን​ሳሮ፥ ይቃ​ምያ፥ ሆሻማ፥ ነዳ​ብያ ነበሩ።</verse>
				<verse number="19">የፈ​ዳ​ያም ልጆች ዘሩ​ባ​ቤ​ልና ሰሜኤ ነበሩ፤ የዘ​ሩ​ባ​ቤ​ልም ልጆች፤ ሜሱ​ላም፥ ሐና​ንያ፥ እኅ​ታ​ቸ​ውም ሰሎ​ሚት።</verse>
				<verse number="20">አሱባ፥ አሄል፥ በራ​ክያ፥ ሐሳ​ድያ፥ አስ​ቦ​ሴድ አም​ስት ናቸው።</verse>
				<verse number="21">የሐ​ና​ን​ያም ልጆች ፈላ​ጥ​ያና ልጁ ኢያ​ሴያ ነበሩ። ረፋያ ልጁ፥ አርና ልጁ፥ አብ​ድዩ ልጁ፥ ሴኬ​ንያ ልጁ።</verse>
				<verse number="22">የሴ​ኬ​ን​ያም ልጅ ሰማ​ዕያ ነበረ። የሰ​ማ​ዕ​ያም ልጆች ሐጡስ፥ ኢዮ​ሔል፥ ቤር​ያሕ፥ ነዋ​ድያ፥ ሳፌጥ ስድ​ስት ነበሩ።</verse>
				<verse number="23">የነ​ዋ​ድያ ልጆች ኤል​ዮ​ዔ​ንኢ፥ ሕዝ​ቅ​ያስ፥ ዓዝ​ሪ​ቃም ሦስት ነበሩ።</verse>
				<verse number="24">የኤ​ል​ዮ​ዔ​ና​ኢም ልጆች አዳ​ይያ፥ ኤል​ያ​ሴብ፥ ፈላያ፥ ዓቁብ፥ ዮሐ​ናን፥ ዶላያ፥ ዓናኒ ሰባት ነበሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">የይ​ሁዳ ልጆች ፋሬስ፥ ኤስ​ሮም ከርሚ፥ ሆርና ሱባል ናቸው።</verse>
				<verse number="2">የሱ​ባ​ልም ልጅ ራያ ኢኤ​ትን ወለደ፤ ኢኤ​ትም አሑ​ማ​ይ​ንና ላሃ​ድን ወለደ። እነ​ዚህ የሰ​ራ​አ​ው​ያን ትው​ል​ዶች ናቸው።</verse>
				<verse number="3">እነ​ዚ​ህም የኤ​ጣም ልጆች ናቸው፤ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል፥ ይሰማ፥ ኤጋ​ቢስ፥ እኅ​ታ​ቸ​ውም ኤሴ​ል​ፎን።</verse>
				<verse number="4">የጌ​ዶ​ርም አባት ፋኑ​ኤል፥ የአ​ሶን አባት አዜር፤ እነ​ዚህ የቤተ ልሔም አባት የኤ​ፍ​ራታ የበ​ኵሩ የሆር ልጆች ናቸው።</verse>
				<verse number="5">ለቴ​ቁ​ሄም አባት ለአ​ስ​ሑር ሔላና ነዓራ የተ​ባሉ ሁለት ሚስ​ቶች ነበ​ሩት።</verse>
				<verse number="6">ነዓ​ራም አሑ​ዛ​ምን፥ ኦፌ​ርን፥ ቴማ​ን​ንና አስ​ት​ራን ወለ​ደ​ች​ለት። እነ​ዚህ የነ​ዓራ ልጆች ናቸው።</verse>
				<verse number="7">የሔ​ላም ልጆች ሴሬት፥ ይጽ​ሐ​ርና ኢት​ናን ናቸው።</verse>
				<verse number="8">ቆስ፥ ኢኖ​ብን፥ ሲባ​ባን፥ የሃ​ሩ​ም​ንም ልጅ የሬ​ካ​ብን ወን​ድም ወገ​ኖች ወለደ።</verse>
				<verse number="9">ያግ​ቤ​ጽም ከወ​ን​ድ​ሞቹ ይልቅ የተ​ከ​በረ ነበረ፤ እና​ቱም፦ በጣር ወል​ጄ​ዋ​ለ​ሁና ብላ ስሙን፦ ያግ​ቤጽ ብላ ጠራ​ችው።</verse>
				<verse number="10">ያግ​ቤ​ጽም፥ “እባ​ክህ፥ መባ​ረ​ክን ባር​ከኝ፥ ሀገ​ሬ​ንም አስ​ፋው፤ እጅ​ህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እን​ዳ​ያ​ሳ​ዝ​ነ​ኝም ምል​ክት አድ​ር​ግ​ልኝ” ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ጠራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የለ​መ​ነ​ውን ሰጠው።</verse>
				<verse number="11">የሱ​ሃም ወን​ድም ካሌብ የኤ​ስ​ቶ​ንን አባት ማኪ​ርን ወለደ።</verse>
				<verse number="12">ኤስ​ቶ​ንም ቤቶ​ራ​ፋ​ንና ፋሲ​ሓን፥ የቄ​ኔ​ዛ​ዊው የኤ​ሴ​ሎ​ምን ወን​ድም የነ​ዓስ ከተማ አባት ታሒ​ናን ወለደ፤ እነ​ዚህ የራፋ ሰዎች ናቸው።</verse>
				<verse number="13">የቄ​ኔ​ዝም ልጆች ጎቶ​ን​ያ​ልና ሠራ​ኢያ ነበሩ። የጎ​ቶ​ን​ያ​ልም ልጅ አታት ነበረ።</verse>
				<verse number="14">መና​ቲም ጎፍ​ራን ወለደ። ሠራ​ኢ​ያም የጌ​ራ​ሲ​ምን አባት ኢዮ​አ​ብን ወለደ፤ እነ​ር​ሱም ጠራ​ቢ​ዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="15">የዮ​ፎ​ኒም ልጅ የካ​ሌብ ልጆች ዔሩ፥ ኤላ፥ ነዓም ነበሩ። የኤ​ላም ልጅ ቄኔዝ ነበረ።</verse>
				<verse number="16">የኢ​ያ​ል​ኤል ልጆች ዜፍ፥ ዚፋ፥ ቲርያ፥ አሣ​ር​ኤል ነበሩ።</verse>
				<verse number="17">የኤ​ዜ​ራ​ስም ልጆች፤ ኢያ​ቴር፥ ሞራድ፥ ጋፌር፥ ኢያ​ሎን ነበሩ፤ ኢያ​ቴ​ርም ማሮ​ንን፥ ሰማ​ዒን፥ የኢ​ስ​ቲ​ሞ​ንን አባት ይስ​ባ​ኤ​ልን ወለደ።</verse>
				<verse number="18">ሚስቱ አይ​ሂ​ዳም የጌ​ዶ​ርን አባት ያሬ​ድን፥ የሦ​ኮ​ንም አባት ሔቤ​ርን፥ የዛ​ኖ​ዋ​ንም አባት ይቁ​ቲ​ኤ​ልን ወለ​ደች። እነ​ዚህ ሞሬድ ያገ​ባት የፈ​ር​ዖን ልጅ የቢ​ትያ ልጆች ናቸው።</verse>
				<verse number="19">የሆ​ድያ ሚስት የነ​ሐም እኅት ልጆች የገ​ር​ሜው የቅ​ዔላ አባ​ትና ማዕ​ካ​ታ​ዊው ኤሲ​ት​ሞዓ ነበሩ።</verse>
				<verse number="20">የሴ​ሞ​ንም ልጆች አም​ኖን፥ የአ​ናን ልጆች ሬኖ​ንና ቲሎን ነበሩ፤ የይ​ስ​ቴም ልጆች ዘካ​ትና የዘ​ካት ልጆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="21">የይ​ሁ​ዳም ልጅ የሴ​ሎም ልጆች የሌካ አባት ዔር፥ የመ​ሪሳ አባት ለዓዳ፥ ከአ​ስ​ቤዓ ቤት የሚ​ሆኑ ጥሩ በፍታ የሚ​ሠሩ ወገ​ኖች፥</verse>
				<verse number="22">ኢዮ​አ​ቄም፥ የካ​ዚባ ሰዎች፥ ኢዮ​አስ፥ በሞ​ዓብ አድሮ ስማ​ቸ​ውን፥ አብ​ዶ​ራ​ንና ተቂ​ኤም ብሎ የመ​ለሰ ሣራፍ ነበሩ።</verse>
				<verse number="23">እነ​ዚህ በነ​ጣ​ዔ​ምና በጋ​ዲራ ከን​ጉሡ ጋር የሚ​ቀ​መጡ ሸክላ ሠራ​ተ​ኞች ነበሩ። እነ​ር​ሱም በመ​ን​ግ​ሥቱ ጸን​ተው በዚያ ይኖሩ ነበር።</verse>
				<verse number="24">የስ​ም​ዖ​ንም ልጆች፤ ነሙ​ኤል፥ ያሚን፥ ያሪብ፥ ዛራ፥ ሳኡል፤</verse>
				<verse number="25">ልጁ ሳሌም፥ ልጁ መብ​ሳም፥ ልጁ ማስ​ማዕ።</verse>
				<verse number="26">የማ​ስ​ማ​ዕም ልጆች፤ ልጁ ሃሙ​ኤል፥ ልጁ ሳባድ፥ ልጁ ዝኩር፥ ልጁ ሰሜኢ።</verse>
				<verse number="27">ለሰ​ሜ​ኢም ዐሥራ ስድ​ስት ወን​ዶ​ችና ስድ​ስት ሴቶች ልጆች ነበ​ሩት፤ ለወ​ን​ድ​ሞቹ ግን ብዙ ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​አ​ቸ​ውም፥ ወገ​ና​ቸ​ውም ሁሉ እንደ ይሁዳ ልጆች አል​ተ​ባ​ዙም።</verse>
				<verse number="28">በቤ​ር​ሳ​ቤ​ህም፥ በሰ​ም​ዓም፥ በሞ​ላዳ፥ በሐ​ጸ​ር​ሱ​ዓል፥</verse>
				<verse number="29">በቤ​ልሃ፥ በዔ​ጼም፥ በቶ​ላድ፤</verse>
				<verse number="30">በቤ​ቱ​ኤል፥ በሔ​ርማ፥ በሤ​ቄ​ላቅ፤</verse>
				<verse number="31">በቤ​ት​ማ​ር​ካ​ቦት፥ በሐ​ጸ​ር​ሱ​ሲም፥ በቤ​ት​ቢሪ፥ በሰ​ዓ​ራ​ይም ይቀ​መጡ ነበር። እስከ ዳዊ​ትም መን​ግ​ሥት ድረስ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ነበሩ።</verse>
				<verse number="32">መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ኤጣም፥ ዓይን፥ ሬሞን፥ ቶኪን፥ ዓሻን፥ አም​ስቱ ከተ​ሞች፤</verse>
				<verse number="33">መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ እስከ በኣል ድረስ በእ​ነ​ዚህ ከተ​ሞች ዙሪያ ነበሩ። መቀ​መ​ጫ​ቸ​ውና ድር​ሻ​ቸ​ውም ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="34">መሶ​ባብ፥ የም​ሌክ፥ የአ​ሚ​ስ​ያስ ልጅ ኢዮ​ስያ፤</verse>
				<verse number="35">ኢዮ​ኤል፥ የዮ​ስ​ብያ ልጅ፥ የሠ​ራያ ልጅ የአ​ሣ​ኤል ልጅ ኢዩ፤</verse>
				<verse number="36">ኤል​ዮ​ዔ​ናይ፥ ያዕ​ቀባ፥ የሰ​ሐያ፥ ዓሣያ፥ ዓዲ​ዔል፥ ይስ​ማ​ኤል፥ በና​ያስ፤</verse>
				<verse number="37">የሳ​ፋኤ ልጅ ዙዛ፥ የአ​ሎን ልጅ የይ​ዳያ ልጅ የሰ​ማሪ ልጅ የሰ​ማያ ልጅ፤</verse>
				<verse number="38">እነ​ዚህ በስ​ማ​ቸው የተ​ጠሩ በወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ላይ አለ​ቆች ነበሩ፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች በዝ​ተው ነበር።</verse>
				<verse number="39">ለመ​ን​ጎ​ቻ​ቸው መሰ​ማ​ርያ ይሹ ዘንድ ወደ ጌራራ እስ​ኪ​ደ​ርሱ ድረስ ወደ ጋይ ምሥ​ራቅ ሄዱ።</verse>
				<verse number="40">ብዙና እጅግ ያማረ መሰ​ማ​ር​ያም አገኙ፤ ምድ​ሪ​ቱም በፊ​ታ​ቸው ሰፊና ጸጥ​ተኛ ሰላም ያላ​ትም ነበ​ረች፤ በቀ​ድ​ሞም ጊዜ በዚያ ተቀ​ም​ጠው የነ​በሩ ከካም ወገን ነበሩ።</verse>
				<verse number="41">በስ​ማ​ቸው የተ​ጻፉ እነ​ዚ​ህም በይ​ሁዳ ንጉሥ በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ዘመን መጥ​ተው ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንና በዚያ የተ​ገ​ኙ​ትን ምዑ​ና​ው​ያ​ንን መቱ፥ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽ​መው አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ በዚ​ያም ለመ​ን​ጎ​ቻ​ቸው መሰ​ማ​ሪያ ነበ​ርና በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="42">ከስ​ም​ዖ​ንም ልጆች አም​ስት መቶ ሰዎች ወደ ሴይር ተራራ ሄዱ፤ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም የይ​ሰዔ ልጆች ፥ ፈላ​ጥያ፥ ነዓ​ርያ፥ ረፋያ፥ ዑዝ​ኤል ነበሩ።</verse>
				<verse number="43">ያመ​ለ​ጡ​ት​ንም የአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ቅሬታ መቱ፥ በዚ​ያም እስከ ዛሬ ድረስ ተቀ​ም​ጠ​ዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም በኵር የሮ​ቤል ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። እርሱ የበ​ኵር ልጅ ነበረ፤ ነገር ግን ወደ አባቱ ምን​ጣፍ ስለ ወጣ አባቱ እስ​ራ​ኤል በረ​ከ​ቱን ለልጁ ለዮ​ሴፍ ሰጠ፤ ብኵ​ር​ናም አል​ተ​ቈ​ጠ​ረ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="2">ይሁ​ዳም በወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል በረታ፥ አለ​ቃም ከእ​ርሱ ሆነ፤ በረ​ከት ግን ለዮ​ሴፍ ነበረ።</verse>
				<verse number="3">የእ​ስ​ራ​ኤል በኵር የሮ​ቤል ልጆች፤ ሄኖኅ፥ ፍሎስ፥ አስ​ሮን፥ ከርሚ ነበሩ።</verse>
				<verse number="4">የኢ​ዩ​ኤል ልጆች፤ ልጁ ሰማያ፥ ልጁ ጎግ፥ ልጁ ሰሜኢ፤</verse>
				<verse number="5">ልጁ ሚካ፥ ልጁ ሬካ፥ ልጁ ቤኤል፥</verse>
				<verse number="6">የአ​ሦር ንጉሥ ቴል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶር የማ​ረ​ከው ልጁ ብኤራ፤ እርሱ የሮ​ቤል ነገድ አለቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="7">ወን​ድ​ሞቹ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የት​ው​ል​ዶ​ቻ​ቸው መዝ​ገብ በተ​ቈ​ጠረ ጊዜ፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸው ኢዩ​ኤ​ልና ዘካ​ር​ያስ ነበሩ።</verse>
				<verse number="8">እስከ ናባ​ውና እስከ በኣ​ል​ሜ​ዎን ድረስ በአ​ሮ​ዔር የተ​ቀ​መ​ጠው የኢ​ዩ​ኤል ልጅ የሰ​ማዕ ልጅ የዖ​ዛዝ ልጅ ቤላ፤</verse>
				<verse number="9">በገ​ለ​ዓድ ምድር እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸው በዝ​ተው ነበ​ርና በም​ሥ​ራቅ በኩል ከኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምድረ በዳው መግ​ቢያ ድረስ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="10">በሳ​ኦ​ልም ዘመን ከስ​ደ​ተ​ኞች ጋር ተዋጉ፥ እነ​ር​ሱም በእ​ጃ​ቸው ተመ​ት​ተው ወደቁ፤ በገ​ለ​ዓድ ምሥ​ራቅ በኩል ባለው ሀገር ሁሉ በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸው ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="11">የጋ​ድም ልጆች በባ​ሳን ምድር እስከ ሰልካ ድረስ በአ​ፋ​ዛ​ዣ​ቸው ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="12">በኵሩ ኢዩ​ኤል፥ ሁለ​ተ​ኛው ሳፋም፥ ጸሓ​ፊው ያና​ይን፥ ሳፋ​ጥም በባ​ሳን ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="13">የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ወን​ድ​ሞች ሚካ​ኤል፥ ሜሱ​ላም፥ ሳባ፥ ዮራይ፥ ያካን፥ ዙኢ፥ ኦቤድ እነ​ዚህ ሰባት ነበሩ።</verse>
				<verse number="14">እነ​ዚ​ህም የቡዝ ልጅ የዮ​ዳይ ልጅ የኢ​ዮ​ሳይ ልጅ የሚ​ካ​ኤል ልጅ የገ​ለ​ዓድ ልጅ የኤ​ዳይ ልጅ የዑሪ ልጅ የአ​ቢ​ካ​ኤል ልጆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="15">የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች አለቃ የጎኔ ልጅ የአ​ብ​ዲ​ኤል ልጅ ወን​ድም ነበር።</verse>
				<verse number="16">በገ​ለ​ዓ​ድም ምድር በባ​ሳን በመ​ን​ደ​ሮ​ቹም በሳ​ሮ​ንም መሰ​ማ​ር​ያ​ዎች ሁሉ እስከ ዳር​ቻ​ቸው ድረስ ተቀ​ም​ጠው ነበር።</verse>
				<verse number="17">እነ​ዚህ ሁሉ በት​ው​ል​ዶ​ቻ​ቸው በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​አ​ታም ዘመ​ንና በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ዘመን ተቈ​ጠሩ።</verse>
				<verse number="18">የሮ​ቤ​ልና የጋድ ልጆች የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ፥ ጽኑ​ዓን ጋሻና ሰይፍ የሚ​ይዙ፥ ቀስ​ተ​ኞ​ችም፥ ሰልፍ የሚ​ያ​ውቁ ሰል​ፈ​ኞ​ችም፥ አርባ አራት ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ ነበሩ።</verse>
				<verse number="19">ከአ​ጋ​ራ​ው​ያ​ንና ከኢ​ጣ​ር​ዮን ከና​ፋ​ስ​ዮ​ንና ከና​ዳ​ብ​ዮን ጋር ተዋጉ።</verse>
				<verse number="20">በሚ​ዋ​ጉ​በ​ትም ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ​ዋ​ልና በእ​ር​ሱም ታም​ነ​ዋ​ልና አዳ​ና​ቸው፤ በላ​ያ​ቸ​ውም በረ​ቱ​ባ​ቸው፥ አጋ​ራ​ው​ያ​ንና ከእ​ነ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትም ሁሉ በእ​ጃ​ቸው ተሰጡ።</verse>
				<verse number="21">ከከ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አምሳ ሺህ ግመ​ሎች፥ ሁለት መቶ አምሳ ሺህም በጎች፥ ሁለት ሺህም አህ​ዮች፥ ከሰ​ዎ​ችም መቶ ሺህ ማረኩ።</verse>
				<verse number="22">ሰልፉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበ​ረና ብዙ ሰዎች ተገ​ድ​ለው ወደቁ፤ እስከ ምር​ኮም ዘመን ድረስ በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="23">የም​ና​ሴም የነ​ገድ እኩ​ሌታ ልጆች፤ ከባ​ሳን ጀምሮ እስከ በኣ​ል​አ​ር​ሞ​ንና እስከ ሳኔር እስከ አር​ሞ​ን​ኤም ተራራ እስከ ሊባ​ኖስ ድረስ ተቀ​መጡ፤ እነ​ር​ሱም በዙ።</verse>
				<verse number="24">የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች አለ​ቆች እነ​ዚህ ነበሩ፤ ዔፌር፥ ይስዔ፥ ኤሊ​ኤል፥ ዓዝ​ር​ኤል፥ ኢይ​ር​ምያ፥ ሆዳ​ይዋ፥ ኢየ​ድ​ኤል፤ እነ​ርሱ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን የታ​ወቁ ሰዎች የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች አለ​ቆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="25">የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ በደሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፊ​ታ​ቸው ባጠ​ፋ​ቸው በም​ድሩ አሕ​ዛብ አማ​ል​ክት አመ​ነ​ዘሩ።</verse>
				<verse number="26">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ የፋ​ሎ​ክን መን​ፈስ፥ የአ​ሦ​ር​ንም ንጉሥ የቴ​ል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶ​ርን መን​ፈስ አስ​ነሣ፤ የሮ​ቤ​ል​ንና የጋ​ድን ልጆች የም​ና​ሴ​ንም ነገድ እኩ​ሌታ አፈ​ለሰ፥ እስከ ዛሬም ወዳ​ሉ​በት ወደ አላ​ሔና ወደ ኦቦር፥ ወደ ሃራ​ንና ወደ ጎዛን ወንዝ አመ​ጣ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">የሌዊ ልጆች፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት ሜራሪ።</verse>
				<verse number="2">የቀ​ዓ​ትም ልጆች፤ እን​በ​ረም፥ ይስ​ዓር፥ ኬብ​ሮን፥ ዑዝ​ኤል።</verse>
				<verse number="3">የእ​ን​በ​ረ​ምም ልጆች፤ አሮን፥ ሙሴ፥ ማር​ያም። የአ​ሮ​ንም ልጆች፤ ናዳብ፥ አብ​ዩድ፥ አል​ዓ​ዛር፥ ኢታ​ምር።</verse>
				<verse number="4">አል​ዓ​ዛር ፊን​ሐ​ስን ወለደ፤ ፊን​ሐ​ስም አቢ​ሱን ወለደ፤</verse>
				<verse number="5">አቢ​ሱም ቡቂን ወለደ፤ ቡቂም ኦዚን ወለደ፤</verse>
				<verse number="6">ኦዚም ዘራ​እ​ያን ወለደ፤ ዘራ​እ​ያም መራ​ዮ​ትን ወለደ፤</verse>
				<verse number="7">መራ​ዮ​ትም አማ​ር​ያን ወለደ፤ አማ​ር​ያም አኪ​ጦ​ብን ወለደ፤</verse>
				<verse number="8">አኪ​ጦ​ብም ሳዶ​ቅን ወለደ፤ ሳዶ​ቅም አኪ​ማ​ኦ​ስን ወለደ፤</verse>
				<verse number="9">አኪ​ማ​ኦ​ስም ዓዛ​ር​ያን ወለደ፤ አዛ​ር​ያም ዮሐ​ና​ንን ወለደ፤</verse>
				<verse number="10">ዮሐ​ና​ንም ዓዛ​ር​ያ​ስን ወለደ፤ እር​ሱም ሰሎ​ሞን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሠ​ራው ቤት ካህን ነበረ፤</verse>
				<verse number="11">ዓዛ​ር​ያ​ስም አማ​ር​ያን ወለደ፤ አማ​ር​ያም አኪ​ጦ​ብን ወለደ፤</verse>
				<verse number="12">አኪ​ጦ​ብም ሳዶ​ቅን ወለደ፤ ሳዶ​ቅም ሳሎ​ምን ወለደ፤</verse>
				<verse number="13">ሳሎ​ምም ኬል​ቅ​ያ​ስን ወለደ፤ ኬል​ቅ​ያ​ስም ዓዛ​ር​ያ​ስን ወለደ፤</verse>
				<verse number="14">ዓዛ​ር​ያ​ስም ሠራ​ያን ወለደ፤ ሠራ​ያም ኢዮ​ሴ​ዴ​ቅን ወለደ፤</verse>
				<verse number="15">ኢዮ​ሴ​ዴ​ቅም፥ ይሁ​ዳና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ በተ​ማ​ረኩ ጊዜ ተማ​ርኮ ሄደ።</verse>
				<verse number="16">የሌዊ ልጆች፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።</verse>
				<verse number="17">የጌ​ድ​ሶ​ንም ልጆች ስም ይህ ነው፤ ሎቤኒ፥ ሰሜኢ።</verse>
				<verse number="18">የቀ​ዓ​ትም ልጆች፤ እን​በ​ረም፥ ይስ​ዓር፥ ኬብ​ሮን፥ ዑዝ​ኤል ነበሩ።</verse>
				<verse number="19">የሜ​ራ​ሪም ልጆች፤ ሞሐሊ፥ ሙሲ፥ የሌ​ዋ​ው​ያን ወገ​ኖች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="20">ከጌ​ድ​ሶን፤ ልጁ ሎቤኒ፥ ልጁ ኢኤት፥ ልጁ ዛማት፤</verse>
				<verse number="21">ልጁ ዮአክ፥ ልጁ አዶ፥ ልጁ ዛራ፥ ልጁ ያት​ራይ።</verse>
				<verse number="22">የቀ​ዓት ልጆች፤ ልጁ አሚ​ና​ዳብ፥ ልጁ ቆሬ፥ ልጁ አሴር፤</verse>
				<verse number="23">ልጁ ሕል​ቃና፥ ልጁ አቢ​ሳፍ፥ ልጁ አሴር፤</verse>
				<verse number="24">ልጁ ተአት፥ ልጁ ኡር​ኤል፥ ልጁ ዖዝያ፥ ልጁ ሳውል።</verse>
				<verse number="25">የሕ​ል​ቃ​ናም ልጆች፤ አማሤ፥ አኪ​ሞት።</verse>
				<verse number="26">ልጁ ሕል​ቃና፤ ልጁ ሱፌ፤ ልጁ ናሔት፤</verse>
				<verse number="27">ልጁ ኤል​ያብ፤ ልጁ ኢያ​ሬ​ም​ያል፤ ልጁ ሕል​ቃና፤ ልጁ ሳሙ​ኤል።</verse>
				<verse number="28">የሳ​ሙ​ኤ​ልም ልጆች፤ በኵሩ ኢዮ​ኤል፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም አብያ።</verse>
				<verse number="29">የሜ​ራሪ ልጆች፤ ሞሓሊ፥ ልጁ ሎቤኒ፥ ልጁ ሰሜኢ፥ ልጁ ዖዛ፥</verse>
				<verse number="30">ልጁ ሳምዓ፥ ልጁ ሐግያ፥ ልጁ ዓሣያ።</verse>
				<verse number="31">ዳዊ​ትም ታቦቷ በም​ታ​ር​ፍ​በት ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ያቆ​ማ​ቸው የመ​ዘ​ም​ራን አለ​ቆች እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="32">ሰሎ​ሞ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እስ​ኪ​ሠራ ድረስ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ማደ​ሪያ ፊት በበ​ገና እያ​ዜሙ ያገ​ለ​ግሉ ነበር፤ በየ​ተ​ራ​ቸ​ውም ለአ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ይቆሙ ነበር።</verse>
				<verse number="33">አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹና ልጆቹ እነ​ዚህ ነበሩ፤ ከቀ​ዓት ልጆች ዘማ​ሪው ኤማን ነበረ፤ እር​ሱም የኢ​ዩ​ኤል ልጅ፥ የሳ​ሙ​ኤል ልጅ፤</verse>
				<verse number="34">የሕ​ል​ቃና ልጅ፥ የይ​ሮ​ዓም ልጅ፥ የኤ​ላ​ኤል ልጅ፥ የቶዋ ልጅ፤</verse>
				<verse number="35">የሱፍ ልጅ፥ የሕ​ል​ቃና ልጅ፥ የመ​ሐት ልጅ፥ የአ​ማሤ ልጅ፤</verse>
				<verse number="36">የሕ​ል​ቃና ልጅ፥ የኢ​ዩ​ኤል ልጅ፥ የዓ​ዛ​ር​ያስ ልጅ፥ የሶ​ፎ​ን​ያስ ልጅ፤</verse>
				<verse number="37">የታ​ሐት ልጅ፥ የአ​ሴር ልጅ፥ የአ​ብ​ያ​ሳፍ ልጅ፥ የቆሬ ልጅ፥</verse>
				<verse number="38">የይ​ሰ​አር ልጅ፥ የቀ​ዓት ልጅ፥ የሌዊ ልጅ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጅ ነው።</verse>
				<verse number="39">በቀ​ኙም የሚ​ቆ​መው ወን​ድሙ አሳፍ ነበረ፤ አሳ​ፍም የበ​ራ​ክያ ልጅ፥ የሳ​ምዓ ልጅ፤</verse>
				<verse number="40">የሚ​ካ​ኤል ልጅ፤ የበ​ዓ​ሣያ ልጅ፥ የመ​ል​ክያ ልጅ፤</verse>
				<verse number="41">የኤ​ትኒ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥ የዓ​ዳያ ልጅ፤</verse>
				<verse number="42">የኤ​ታን ልጅ፥ የዛማ ልጅ፥ የሰ​ሜኢ ልጅ፤</verse>
				<verse number="43">የኢ​ያ​ኤት ልጅ፥ የጌ​ድ​ሶን ልጅ፥ የሌዊ ልጅ ነው።</verse>
				<verse number="44">በግ​ራ​ቸ​ውም በኩል የሚ​ቆሙ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው የሜ​ራሪ ልጆች ነበሩ፤ ኤታን የቄሳ ልጅ፥ የአ​ብዲ ልጅ፥ የማ​ሎክ ልጅ፤</verse>
				<verse number="45">የአ​ሳቢ ልጅ፥ የአ​ሜ​ስ​ያስ ልጅ፥ የኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ፤</verse>
				<verse number="46">የአ​ማሴ ልጅ፥ የባኒ ልጅ፥ የሴ​ሜር ልጅ፤</verse>
				<verse number="47">የሞ​አሊ ልጅ፥ የሙሲ ልጅ፥ የሜ​ራሪ ልጅ፥ የሌዊ ልጅ።</verse>
				<verse number="48">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ሌዋ​ው​ያን እንደ እየ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሥራ አገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ ተሰጡ።</verse>
				<verse number="49">አሮ​ንና ልጆቹ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ሥራ ሁሉ ስለ እስ​ራ​ኤ​ልም ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ ለሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ላይ ይሠዉ ነበር፥ በዕ​ጣ​ኑም መሠ​ዊያ ላይ ያጥኑ ነበር።</verse>
				<verse number="50">የአ​ሮ​ንም ልጆች ስሞች እነ​ዚህ ናቸው፤ ልጁ አል​ዓ​ዛር፥ ልጁ ፊን​ሐስ፥ ልጁ አቢሱ፤</verse>
				<verse number="51">ልጁ ቡቂ፥ ልጁ ኦዚ፥ ልጁ ዘራ​እያ፤</verse>
				<verse number="52">ልጁ መራ​ዮት፥ ልጁ አማ​ርያ፥ ልጁ አኪ​ጦብ፥</verse>
				<verse number="53">ልጁ ሳዶቅ፥ ልጁ አኪ​ማ​ኦስ።</verse>
				<verse number="54">ማደ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም በየ​ሰ​ፈ​ራ​ቸው በየ​ዳ​ር​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው፤ ለአ​ሮን ልጆች ለቀ​ዓት ወገ​ኖች አን​ደ​ኛው ዕጣ ነበረ።</verse>
				<verse number="55">ለእ​ነ​ርሱ በይ​ሁዳ ሀገር ያለ​ች​ውን ኬብ​ሮ​ንን፥ በእ​ር​ስ​ዋም ዙሪያ የነ​በ​ረ​ውን መሰ​ማ​ሪያ ሰጡ፤</verse>
				<verse number="56">የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱን እርሻ ግን መን​ደ​ሮ​ች​ዋ​ንም ለዮ​ፎኒ ልጅ ለካ​ሌብ ሰጡ።</verse>
				<verse number="57">ለአ​ሮ​ንም ልጆች የመ​ማ​ፀ​ኛ​ውን ከተ​ሞች፥ ኬብ​ሮ​ንን፥ ልብ​ና​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ሴል​ና​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፤ ኤስ​ት​ሞ​ዓ​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን ሰጡ።</verse>
				<verse number="58">የኢ​ያ​ቴ​ርን ከተ​ማና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፥ ዳቤ​ር​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፤</verse>
				<verse number="59">ዓሳ​ን​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፥ ቤት​ሳ​ሚ​ስ​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፤</verse>
				<verse number="60">ከብ​ን​ያ​ምም ነገድ ጌባ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ጋሌ​ማ​ት​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፥ ዓና​ቶ​ት​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን ሰጡ። ከተ​ሞ​ቻ​ቸው ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።</verse>
				<verse number="61">ለቀ​ሩ​ትም ለቀ​ዓት ልጆች ከም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ዐሥር ከተ​ሞች በዕጣ ተሰጡ።</verse>
				<verse number="62">ለጌ​ድ​ሶ​ንም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ከይ​ሳ​ኮር ነገድ፥ ከአ​ሴ​ርም ነገድ፥ ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምም ነገድ፥ በባ​ሳ​ንም ካለው ከም​ናሴ ነገድ፥ ዐሥራ ሦስት ከተ​ሞች ተሰጡ።</verse>
				<verse number="63">ለሜ​ራ​ሪም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ከሮ​ቤል ነገድ፥ ከጋ​ድም ነገድ፥ ከዛ​ብ​ሎ​ንም ነገድ፥ ዐሥራ ሁለት ከተ​ሞች በዕጣ ተሰጡ።</verse>
				<verse number="64">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለሌ​ዋ​ው​ያን ከተ​ሞ​ችን ከመ​ሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ጋር ሰጡ።</verse>
				<verse number="65">ከይ​ሁ​ዳም ልጆች ነገድ፥ ከስ​ም​ዖ​ንም ልጆች ነገድ፥ ከብ​ን​ያ​ምም ልጆች ነገድ፥ እነ​ዚ​ህን በስ​ማ​ቸው የተ​ጠ​ሩ​ትን ከተ​ሞች በዕጣ ሰጡ።</verse>
				<verse number="66">ከቀ​ዓ​ትም ልጆች ወገ​ኖች ለአ​ን​ዳ​ን​ዶቹ ከኤ​ፍ​ሬም ነገድ ከተ​ሞች ድርሻ ነበ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="67">በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ያሉ​ትን የመ​ማ​ፀ​ኛ​ውን ከተ​ሞች ሴኬ​ም​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፥ ደግ​ሞም ጋዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፤</verse>
				<verse number="68">ዮቅ​ም​ዓ​ም​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፥ ቤት​ሖ​ሮ​ን​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፤</verse>
				<verse number="69">ኤሎ​ን​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፥ ጋት​ሪ​ሞ​ን​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን ሰጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="70">ከም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ዓኔ​ር​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፥ ቤል​ዓ​ም​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፥ ከቀ​ዓት ልጆች ወገን ለቀ​ሩት ሰጡ።</verse>
				<verse number="71">ለጌ​ድ​ሶን ልጆች ከም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ወገን በባ​ሳን ያለ​ችው ጋው​ሎ​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፥ አስ​ታ​ሮ​ትና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፤</verse>
				<verse number="72">ከይ​ሳ​ኮ​ርም ነገድ ቃዴ​ስና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፥ ዳብ​ራ​ትና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፤</verse>
				<verse number="73">ራሞ​ትና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፥ ዓኔ​ምና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፤</verse>
				<verse number="74">ከአ​ሴ​ርም ነገድ መዓ​ሳ​ልና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፥ ዓብ​ዶ​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፤</verse>
				<verse number="75">ሐቆ​ቅና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፥ ረዓ​ብና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፤</verse>
				<verse number="76">ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምም ነገድ በገ​ሊላ ያለ​ችው ቃዴ​ስና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፥ ሐሞ​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፥ ቄር​ያ​ታ​ይ​ምና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ ተሰጡ።</verse>
				<verse number="77">ለቀ​ሩ​ትም ለሜ​ራሪ ልጆች ከዛ​ብ​ሎን ነገድ ሬሞ​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፥ ታቦ​ርና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፤</verse>
				<verse number="78">ከሮ​ቤ​ልም ነገድ በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በም​ሥ​ራቅ በኩል በም​ድረ በዳ ያለ​ችው ቦሶ​ርና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፥ ያሶ​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፤</verse>
				<verse number="79">ቅዴ​ሞ​ትና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፥ ሜፍ​ዓ​ትና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፤</verse>
				<verse number="80">ከጋ​ድም ነገድ በገ​ለ​ዓድ ያለ​ችው ሬማ​ትና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፥ መሃ​ና​ይ​ምና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፤</verse>
				<verse number="81">ሐሴ​ቦ​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፥ ኢያ​ዜ​ርና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ ተሰጡ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">የይ​ሳ​ኮ​ርም ልጆች፤ ቶላ፥ ፋዋ፥ ያሱብ፥ ሰም​ሮን፥ አራት ናቸው።</verse>
				<verse number="2">የቶ​ላም ልጆች፤ ኦዚ፥ ረፋያ፥ ይሪ​ኤል፥ የሕ​ማይ፥ ይብ​ሣም፥ ሰሙ​ኤል፥ የአ​ባ​ታ​ቸው የቶላ ቤት አለ​ቆች፥ በት​ው​ል​ዳ​ቸው ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ነበሩ፤ በዳ​ዊት ዘመን ቍጥ​ራ​ቸው ሃያ ሁለት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበረ።</verse>
				<verse number="3">የኦ​ዚም ልጆች ይዝ​ረ​ሕያ፤ የይ​ዝ​ረ​ሕ​ያም ልጆች ሚካ​ኤል፥ አብ​ድዩ፥ ኢዩ​ኤል፥ ይሴያ አም​ስት ናቸው፤ ሁሉም አለ​ቆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="4">ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ለሰ​ልፍ የተ​ዘ​ጋጁ የሠ​ራ​ዊት ጭፍ​ሮች ነበሩ፤ ብዙም ሴቶ​ችና ልጆች ነበ​ሩ​አ​ቸ​ውና ሠላሳ ስድ​ስት ሺህ ነበሩ።</verse>
				<verse number="5">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም በይ​ሳ​ኮር ወገ​ኖች ሁሉ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች በት​ው​ል​ዳ​ቸው ሁሉ የተ​ቈ​ጠሩ ሰማ​ንያ ሰባት ሺህ ነበሩ።</verse>
				<verse number="6">የብ​ን​ያም ልጆች ቤላ፥ ቤኬር፥ ይድ​ኤል ሦስት ነበሩ።</verse>
				<verse number="7">የቤ​ላም ልጆች፥ ኤሲ​ቦን፥ ኦዚ፥ ዑዝ​ኤል፥ ኢያ​ሬ​ሙት፥ ዔሪ አም​ስት ነበሩ፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች፥ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ነበሩ፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም ሃያ ሁለት ሺህ ሠላሳ አራት ነበሩ።</verse>
				<verse number="8">የቤ​ኬ​ርም ልጆች ዝሜራ፥ ኢዮ​አስ፥ አል​ዓ​ዛር፥ ኤል​ዮ​ኤ​ናይ፥ ዖምሪ፥ ኢያ​ሪ​ሙት፥ ዓብያ፥ ዓና​ቶት፤ ዓሌ​ሜት፤ እነ​ዚህ ሁሉ የቤ​ኬር ልጆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="9">በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸ​ውም መዝ​ገብ የተ​ቈ​ጠሩ፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች፥ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ሃያ ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="10">የይ​ዴ​ኤ​ልም ልጅ ቢል​ሐን ነበረ፤ የቢ​ል​ሐ​ንም ልጆች የዑስ፥ ብን​ያም፥ ኤሁድ፥ ክን​ዓና፥ ዜታን፥ ተር​ሴስ፥ አኬ​ሳ​አር ነበሩ።</verse>
				<verse number="11">እነ​ዚህ ሁሉ የይ​ዴ​ኤል ልጆች ነበሩ፤ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች፥ ጭፍራ እየ​ሆኑ ወደ ሰልፍ የሚ​ወጡ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ዐሥራ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="12">ደግ​ሞም ሳፊን፥ ሑፊም የዔር ልጆች፥ ሑሲም የአ​ሔር ልጅ ነበረ።</verse>
				<verse number="13">የን​ፍ​ታ​ሌ​ምም ልጆች፥ ያሕ​ጽ​ኤል፥ ጎኒ፥ ዬጽር፥ ሼሌም፥ እነ​ዚህ አራቱ የባላ ልጆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="14">የም​ናሴ ልጆች ሶሪ​ያ​ዪቱ ቁባቱ የወ​ለ​ደ​ች​ለት አስ​ር​ኤ​ልና የገ​ለ​ዓድ አባት ማኪር ናቸው።</verse>
				<verse number="15">ማኪ​ርም ከሑ​ፊ​ምና ከሳ​ፊን ወገን ሚስት አገባ፤ የእ​ኅ​ት​የ​ዋም ስም መዓካ ነበረ፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ስም ሰለ​ጰ​ዓድ ነበረ፤ ለሰ​ለ​ጰ​ዓ​ድም ሴቶች ልጆች ነበ​ሩት።</verse>
				<verse number="16">የማ​ኪ​ርም ሚስት መዓካ ልጅ ወለ​ደች፥ ስሙ​ንም ፋሬስ ብላ ጠራ​ችው፤ የወ​ን​ድ​ሙም ስም ሱሮስ ነበረ፤ ልጆ​ቹም ኡላ​ምና ራቄም ነበሩ።</verse>
				<verse number="17">የኡ​ላ​ምም ልጅ ባዳን ነበረ፤ እነ​ዚህ የም​ናሴ ልጅ የማ​ኪር ልጅ የገ​ለ​ዓድ ልጆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="18">እኅቱ መለ​ኪት ኢሱ​ድን፥ አቢ​ዔ​ዜ​ርን፥ መሕ​ላን ወለ​ደች።</verse>
				<verse number="19">የሰ​ሜ​ራም ልጆች አሒ​ያን፥ ሴኬም፥ ሌቅሔ፥ አኔ​ዓም ነበሩ።</verse>
				<verse number="20">የኤ​ፍ​ሬም ልጆች፤ ሱቱላ፥ ልጁ ባሬድ፥ ልጁ ታሐት፥ ልጁ ኤል​ዓዳ፥ ልጁ ታክት፤</verse>
				<verse number="21">ልጁ ዛባድ፥ ልጁ ሹቱላ፥ ልጁ ኤድር፥ ልጁ ኤል​ዓድ ነበሩ፤ የሀ​ገ​ሩም ተወ​ላ​ጆች የጌት ሰዎች ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሊወ​ስዱ ወር​ደው ነበ​ርና ገደ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">አባ​ታ​ቸው ኤፍ​ሬ​ምም ብዙ ቀን አለ​ቀሰ፤ ወን​ድ​ሞ​ቹም ሊያ​ጽ​ና​ኑት መጡ።</verse>
				<verse number="23">ወደ ሚስ​ቱም ገባ፥ አረ​ገ​ዘ​ችም፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች፤ በቤ​ቴም መከራ ሆኖ​አ​ልና ሲል ስሙን በሪዓ ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="24">የሴት ልጁም ስም ሲአራ ነበረ፤ በዚ​ያም በቀ​ሩት ታች​ኛ​ው​ንና ላይ​ኛ​ውን ቤት​ሖ​ሮ​ንን ሠራ የኡ​ዛ​ንም ልጁ ሠይራ ነበረ፤</verse>
				<verse number="25">ወን​ዶች ልጆ​ቹም ራፋኢ፥ ሳራፍ፥ ልጁ ቴላ፥ ልጁ ታሐን፤</verse>
				<verse number="26">ልጁ ለአ​ዳን፥ ልጁ ዓሜ​ሁድ፥ ልጁ ኤሌ​ሳማ፤</verse>
				<verse number="27">ልጁ ነዌ፥ ልጁ ኢያሱ።</verse>
				<verse number="28">ግዛ​ታ​ቸ​ውና ማደ​ሪ​ያ​ቸው ቤቴ​ልና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ነዓ​ራን፥ በም​ዕ​ራ​ብም በኩል ጌዝ​ርና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ ደግ​ሞም ሴኬ​ምና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ እስከ ጋዛና እስከ መን​ደ​ሮ​ችዋ ድረስ፤</verse>
				<verse number="29">በም​ና​ሴም ልጆች ዳርቻ ቤት​ሳ​ንና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ ታዕ​ና​ክና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ መጊ​ዶና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ ዶርና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በላ​ድና መን​ደ​ሮ​ችዋ ነበሩ፤ በእ​ነ​ዚህ ያዕ​ቆብ የተ​ባለ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጅ የዮ​ሴፍ ልጆች ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="30">የአ​ሴር ልጆች፤ ኢያ​ምና፥ የሱዋ፥ የሱዊ፥ በሬዓ፥ እኅ​ታ​ቸ​ውም ሤራሕ ነበሩ።</verse>
				<verse number="31">የበ​ሪ​ዓም ልጆች፤ ሔቤ​ርና፥ የቤ​ር​ዛ​ዊት አባት የነ​በ​ረው መል​ኪ​ኤል ናቸው።</verse>
				<verse number="32">ሔቤ​ርም ያፍ​ሌ​ጥን፥ ሳሜ​ርን፥ ኮታ​ምን፥ እኅ​ታ​ቸ​ው​ንም ሶላን ወለደ።</verse>
				<verse number="33">የያ​ፍ​ሌ​ጥም ልጆች፤ ፋሴክ፥ ቢም​ሃል፥ ዓሴት ነበሩ፤ እነ​ዚህ የያ​ፍ​ሌጥ ልጆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="34">የሳ​ሜ​ርም ልጆች፤ አኪ፥ ሮኦጋ፥ ይሁባ፥ አራም ነበሩ።</verse>
				<verse number="35">የወ​ን​ድ​ሙም የኡ​ላም ልጆች ጾፋ፥ ይምና፥ ሰሌስ፥ ዓማል ነበሩ።</verse>
				<verse number="36">የጾ​ፋም ልጆች፤ ሴዋ፥ ሐር​ኔ​ፍር፥ ሦአል፥ ቤሪ፥ ይምራ፥</verse>
				<verse number="37">ቤጼር፥ ሆድ፦ ሳማ፦ ሰሌሳ፥ ይት​ራን፦ ብኤራ ነበሩ።</verse>
				<verse number="38">የዬ​ቴ​ርም ልጆች፤ ያፊና፥ ፊስጳ፥ አራ ነበሩ።</verse>
				<verse number="39">የዑላ ልጆች፤ ኤራ፥ ሐኔ​ኤል፥ ሪጽያ ነበሩ።</verse>
				<verse number="40">እነ​ዚህ ሁሉ የአ​ሴር ልጆች፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች፥ የተ​መ​ረጡ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች፥ የመ​ኳ​ን​ንቱ አለ​ቆች ነበሩ። በት​ው​ል​ዳ​ቸ​ውም በሰ​ልፍ ለመ​ዋ​ጋት የተ​ቈ​ጠሩ ሃያ ስድ​ስት ሺህ ሰዎች ነበሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">ብን​ያ​ምም በኵ​ሩን ቤላን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም አስ​ቤ​ልን፥ ሦስ​ተ​ኛ​ው​ንም አሐ​ራን፤</verse>
				<verse number="2">አራ​ተ​ኛ​ው​ንም ኖሐን፥ አም​ስ​ተ​ኛ​ው​ንም ራፋን ወለደ።</verse>
				<verse number="3">ለቤ​ላም ልጆች ነበ​ሩት፤ አዳር፥ ጌራ፥ አቤ​ሁድ፤</verse>
				<verse number="4">አቤሱ፥ ናዕ​ማን፥ አሖዋ፤</verse>
				<verse number="5">ጌራ፥ ሰፉ​ፋም፥ ሑራም።</verse>
				<verse number="6">እነ​ዚህ የኤ​ሁድ ልጆች ናቸው፤ እነ​ዚህ በጌባ የሚ​ቀ​መጡ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች ናቸው፤ ወደ መነ​ሐ​ትም ተማ​ረኩ፤</verse>
				<verse number="7">ናዕ​ማን፥ አኪያ፥ ጌራ፥ እነ​ር​ሱም ተማ​ረኩ። ዖዛ​ንና አሂ​ሑ​ድን ወለደ።</verse>
				<verse number="8">ሰሐ​ራ​ይ​ምም ሚስ​ቶ​ቹን ሑሴ​ም​ንና በዕ​ራን ከሰ​ደደ በኋላ በሞ​ዓብ ሜዳ ልጆ​ችን ወለደ።</verse>
				<verse number="9">ከሚ​ስቱ ከሖ​ዲሽ ዮባ​ብን፥ ዲብ​ያን፥ ማሴን፥ ማል​ካ​ምን፤</verse>
				<verse number="10">ኢያ​ሱ​ብን፥ ሻክ​ያን፥ ሜር​ማን ወለደ። እነ​ዚ​ህም ልጆች የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="11">ከሑ​ሲ​ምም አቢ​ጡ​ብ​ንና ኤል​ፍ​ዓ​ልን ወለደ።</verse>
				<verse number="12">የኤ​ል​ፍ​ዓ​ልም ልጆች ዖቤድ፥ ሚሳም፥ ኦኖ​ንና ሎድን፥ መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም የሠራ ሳሜር፤</verse>
				<verse number="13">በሪዓ፥ ሰማዕ ነበሩ፤ እነ​ር​ሱም የጌ​ትን ነዋ​ሪ​ዎች ያሳ​ደዱ የኤ​ሎን ሰዎች የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች ነበሩ፤</verse>
				<verse number="14">ወን​ድ​ሞ​ቹም ሶሲ​ቅና ይሬ​ሞት፤</verse>
				<verse number="15">ዝባ​ድያ፥ ዓራድ፥ ዔዴር፤</verse>
				<verse number="16">ሚካ​ኤል፥ የሴፋ፥ ዮሐ፥ የበ​ሪ​ዓም ልጆች፤</verse>
				<verse number="17">ዝባ​ድያ፥ ሜሱ​ላም፥ ሕዝቂ፥ ሔቤር፤</verse>
				<verse number="18">ይሰ​ም​ራይ፥ ይዝ​ሊያ፥ ዮባብ፥</verse>
				<verse number="19">የኤ​ል​ፍ​ዓል ልጆች ያቂም፥ ዝክሪ፥ ዘብዲ፥</verse>
				<verse number="20">ኤሊ​ዔ​ናይ፥ ጼል​ታይ፥ ኤሊ​ኤል፤</verse>
				<verse number="21">ዓዳያ፥ ብራያ፥ ሲም​ራት፥ የሰ​ሜኤ ልጆች፤</verse>
				<verse number="22">ይሰ​ጳን፥ ዖቤድ፥ ኤሊ​ኤል፤</verse>
				<verse number="23">ዓብ​ዶን፥ ዝክሪ፥ ሐናን፤</verse>
				<verse number="24">ሐና​ንያ፥ አን​በሪ፥ ኤላም፤ አና​ቶ​ትያ፥</verse>
				<verse number="25">ይቲን፥ ይፍ​ዴያ፥ ፋኑ​ኤል፥ የሶ​ሴቅ ልጆች፤</verse>
				<verse number="26">ሸም​ሸ​ራይ፥ ሸሃ​ሪያ፥ ጎቶ​ልያ፤</verse>
				<verse number="27">ያሬ​ሽያ፥ ኤል​ያስ፥ ዝክሪ፥ የይ​ሮ​ሐም ልጆች።</verse>
				<verse number="28">እነ​ዚህ በት​ው​ል​ዶ​ቻ​ቸው አለ​ቆች ነበሩ፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች ነበሩ፤ እነ​ዚህ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="29">የገ​ባ​ዖን አባት በገ​ባ​ዖን ይኖር ነበር የሚ​ስ​ቱም ስም መዓካ ነበር፤</verse>
				<verse number="30">የበ​ኵር ልጁ ዓብ​ዶን፥ ሱር፥ ቂስ፥ በኣል፥ ኔር፥ ናዳብ፥</verse>
				<verse number="31">ጌዶ​ርና፥ ወን​ድሙ ዛኪር ሜቅ​ሎት፤</verse>
				<verse number="32">ሜቅ​ሎ​ትም ሳም​አን ወለደ፤ እነ​ርሱ ደግሞ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ፊት ለፊት ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="33">ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦ​ልን ወለደ፤ ሳኦ​ልም ዮና​ታ​ንን፥ ሜል​ኪ​ሳን፥ አሚ​ና​ዳ​ብን፥ አስ​በ​ኣ​ልን ወለደ።</verse>
				<verse number="34">የዮ​ና​ታ​ንም ልጅ መሪ​በ​ኣል ነበረ፤ መሪ​በ​ኣ​ልም ሚካን ወለደ።</verse>
				<verse number="35">የሚ​ካም ልጆች ፒቶን፥ ሜሌክ፥ ታሬዓ፥ አካዝ ነበሩ።</verse>
				<verse number="36">አካ​ዝም ይሆ​ዓ​ዳን ወለደ፤ ይሆ​ዓ​ዳም ዓሌ​ሜ​ትን፥ ዓዝ​ሞ​ትን፥ ዘም​ሪን ወለደ፤ ዘም​ሪም ማሴ​ዕን ወለደ።</verse>
				<verse number="37">ማሴ​ዕም በዓ​ናን ወለደ፤ ልጁም ራፋያ ነበረ፤ ልጁ ኤል​ዓሣ፥ ልጁ ኤሴል፤</verse>
				<verse number="38">ለኤ​ሴ​ልም ስድ​ስት ልጆች ነበ​ሩት፤ ስማ​ቸ​ውም ይህ ነበረ፤ ዓዝ​ሪ​ቃም፥ በኬ​ርዩ፥ እስ​ማ​ኤል፥ ሰዓ​ርያ፥ አብ​ድዩ፥ ሐናን፤ እነ​ዚህ ሁሉ የአ​ሴል ልጆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="39">የወ​ን​ድ​ሙም የአ​ሴል ልጆች፤ በኵሩ ኡላም፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ኤያስ፥ ሦስ​ተ​ኛ​ውም ኤሊ​ፋ​ላት።</verse>
				<verse number="40">የኡ​ላም ልጆች ጽኑ​ዓን ኀያ​ላ​ንና ቀስ​ተ​ኞች ነበሩ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም መቶ አምሳ የሚ​ያ​ህሉ ብዙ ልጆ​ችና የልጅ ልጆች ነበ​ሩ​አ​ቸው፤ እነ​ዚህ ሁሉ የብ​ን​ያም ልጆች ነበሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው ወደ ባቢ​ሎን ከተ​ማ​ረኩ በኋላ፥ በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው ተቈ​ጠሩ፤ እነ​ሆም በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት መጽ​ሐፍ ተጽ​ፈ​ዋል።</verse>
				<verse number="2">በእ​ስ​ራ​ኤል ከተ​ሞ​ችና በአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ቻ​ቸው መጀ​መ​ሪያ የተ​ቀ​መጡ ካህ​ናት፥ ሌዋ​ው​ያ​ንም፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ነበሩ።</verse>
				<verse number="3">ከይ​ሁዳ ልጆ​ችና ከብ​ን​ያም ልጆች፥ ከኤ​ፍ​ሬ​ምና ከም​ናሴ ልጆች በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="4">ከይ​ሁዳ ልጅ ከፋ​ሬስ ልጆች የባኔ ልጅ የአ​ምሪ ልጅ የዖ​ምሪ ልጅ የዓ​ሚ​ሁድ ልጅ ዑታይ ደግሞ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="5">ከሴ​ሎ​ና​ው​ያ​ንም በኵሩ ዓሣ​ያና ልጆቹ።</verse>
				<verse number="6">ከዛ​ራም ልጆች ኢያ​ሄ​ልና ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው፥ ስድ​ስት መቶ ዘጠና።</verse>
				<verse number="7">ከብ​ን​ያ​ምም ልጆች የሐ​ስ​ኑአ ልጅ የሆ​ዳ​ይዋ ልጅ የሜ​ሱ​ላም ልጅ ሰሎ፤</verse>
				<verse number="8">የይ​ሮ​ሐም ልጅ ኢያ​ብ​ናአ፤ የሚ​ክሪ ልጅ የኦዚ ልጅ ኤላ፤ የበ​ን​ያስ ልጅ የራ​ጉ​ኤል ልጅ የሰ​ፋ​ጥ​ያስ ልጅ ሜሱ​ላም፤</verse>
				<verse number="9">በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸ​ውም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ዘጠኝ መቶ አምሳ ስድ​ስት ነበሩ፤ እነ​ዚህ ሰዎች ሁሉ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="10">ከካ​ህ​ና​ቱም ዮዳኤ፥ ዮአ​ሪብ፥ ያኪን፤</verse>
				<verse number="11">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አለቃ የአ​ኪ​ጦብ ልጅ፥ የመ​ራ​ዩት ልጅ፥ የሳ​ዶቅ ልጅ፥ የሜ​ሱ​ላም ልጅ የኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ ዓዛ​ር​ያስ፤</verse>
				<verse number="12">የመ​ል​ክያ ልጅ፥ የጳ​ስ​ኮር ልጅ፥ የይ​ሮ​ሐም ልጅ፥ አዳያ፤ የኤ​ሜር ልጅ የም​ስ​ል​ሞት ልጅ፥ የሜ​ሱ​ላም ልጅ፥ የኤ​ሕ​ዜራ ልጅ፥ የዓ​ዴ​ኤል ልጅ መዕ​ሣይ፤</verse>
				<verse number="13">የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች አለ​ቆች ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ ነበሩ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትም ማገ​ል​ገል ሥራ እጅግ ብቁ​ዎች ሰዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="14">ከሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ልጆች ከሜ​ራሪ ልጆች የአ​ሳ​ብያ ልጅ፥ የዓ​ዝ​ሪ​ቃም ልጅ፥ የአ​ሱብ ልጅ ሸማያ፤</verse>
				<verse number="15">በቀ​ባ​ቃር፥ ኤሬስ፥ ጋላል፥ የአ​ሳፍ ልጅ የዝ​ክሪ ልጅ የሜካ ልጅ ማታ​ን​ያስ፤ የኤ​ዶ​ታም ልጅ የጋ​ላል ልጅ የሰ​ማያ ልጅ አብ​ድያ፤</verse>
				<verse number="16">በነ​ጦ​ፋ​ው​ያ​ንም መን​ደ​ሮች የተ​ቀ​መ​ጠው የሕ​ል​ቃና ልጅ የአሳ ልጅ በራ​ክያ።</verse>
				<verse number="17">በረ​ኞ​ችም ሰሎም፥ ዓቁብ፥ ጤል​ሞን፥ አሒ​ማን፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ነበሩ፤ ሰሎ​ምም አለቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="18">እስ​ከ​ዛ​ሬም ድረስ በን​ጉሥ በር በም​ሥ​ራቅ በኩል ነበሩ፤ ለሌዊ ልጆች ሰፈር በረ​ኞች ነበሩ።</verse>
				<verse number="19">የቆ​ሬም ልጅ የአ​ብ​ያ​ሳፍ ልጅ የቆሬ ልጅ ሰሎም ከአ​ባቱ ቤት የነ​በሩ ወን​ድ​ሞቹ ቆሬ​ያ​ው​ያን በማ​ገ​ል​ገል ሥራ ላይ ነበሩ፤ የድ​ን​ኳ​ኑ​ንም መድ​ረክ ይጠ​ብቁ ነበር። አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰፈር መግ​ቢያ ይጠ​ብቁ ነበር።</verse>
				<verse number="20">አስ​ቀ​ድ​ሞም የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ አለ​ቃ​ቸው ነበረ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነበረ።</verse>
				<verse number="21">የሜ​ሱ​ላም ልጅ ዘካ​ር​ያስ የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ በረኛ ነበረ።</verse>
				<verse number="22">የመ​ድ​ረኩ በረ​ኞች ይሆኑ ዘንድ የተ​መ​ረጡ እነ​ዚህ ሁሉ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ነበሩ። እነ​ዚህ በመ​ን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው ተቈ​ጠሩ። ዳዊ​ትና ነቢዩ ሳሙ​ኤል ታማ​ኝ​ነ​ታ​ቸ​ውን አይ​ተው በሥ​ራ​ቸው አቆ​ሙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">እነ​ር​ሱና ልጆ​ቻ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በድ​ን​ኳኑ ደጆች ላይ በረ​ኞች ነበሩ።</verse>
				<verse number="24">በአ​ራቱ ማዕ​ዘ​ኖች፥ በም​ሥ​ራቅ፥ በም​ዕ​ራብ፥ በሰ​ሜን፥ በደ​ቡብ በሮች ነበሩ።</verse>
				<verse number="25">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም በመ​ን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ሆነው፥ በየ​ሰ​ባቱ ቀን ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሊሆኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይገቡ ነበር።</verse>
				<verse number="26">እነ​ዚህ አራቱ ኀያ​ላን ሰዎች ለአ​ራቱ በሮች ኀላ​ፊ​ዎች ነበሩ። ሌዋ​ው​ያ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ባሉ ጓዳ​ዎ​ችና ቤተ መዛ​ግ​ብት ላይ የተ​ሾሙ ነበሩ።</verse>
				<verse number="27">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት መክ​ፈቻ የሚ​ይዙ፥ ጥዋት ጥዋ​ትም ደጆ​ቹን የሚ​ከ​ፍቱ እነ​ርሱ ነበ​ሩና።</verse>
				<verse number="28">ዕቃ​ው​ንም በቍ​ጥር ያገ​ቡና ያወጡ ነበ​ርና ከእ​ነ​ዚህ አን​ዳ​ን​ዶቹ በማ​ገ​ል​ገ​ያው ዕቃ ላይ ሹሞች ነበሩ።</verse>
				<verse number="29">ከእ​ነ​ርሱ አን​ዳ​ን​ዶቹ በአ​ገ​ል​ግ​ሎቱ ዕቃ​ዎች በመ​ቅ​ደሱ ዕቃ ሁሉ፥ በመ​ል​ካ​ሙም ዱቄት፥ በወ​ይን ጠጁም፥ በዘ​ይ​ቱም፥ በዕ​ጣ​ኑም፥ በሽ​ቱ​ውም ላይ ሹሞች ነበሩ።</verse>
				<verse number="30">ከካ​ህ​ና​ቱም ልጆች አን​ዳ​ን​ዶቹ ዕጣ​ኑ​ንና የሽ​ቱ​ውን ቅባት ያዘ​ጋጁ ነበር።</verse>
				<verse number="31">የቆ​ሬ​ያ​ዊ​ውም የሰ​ሎም በኵር ሌዋ​ዊው ማቲ​ትያ ለታ​ላቁ ሊቀ ካህ​ናት በም​ጣድ በሚ​ጋ​ገ​ረው ነገር ላይ ሹም ነበረ።</verse>
				<verse number="32">በየ​ሰ​ን​በ​ቱም ያዘ​ጋጁ ዘንድ ቀዓ​ታ​ዊው በን​ያ​ስና ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው በገጹ ኅብ​ስት ላይ ሹሞች ነበሩ።</verse>
				<verse number="33">ከሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ወገን የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች የነ​በሩ መዘ​ም​ራን በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው አገ​ል​ጋ​ዮ​ችና ሹሞች ነበሩ፤ ሥራ​ቸ​ውም ሌሊ​ትና ቀን ነበረ።</verse>
				<verse number="34">እነ​ዚህ ከሌ​ዋ​ው​ያን የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው አለ​ቆች ነበሩ። እነ​ዚ​ህም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይቀ​መጡ ነበር።</verse>
				<verse number="35">የሚ​ስቱ ስም መዓካ የነ​በ​ረው የገ​ባ​ዖን አባት ይዒ​ኤል በገ​ባ​ዖን ይቀ​መጥ ነበረ።</verse>
				<verse number="36">የበ​ኵር ልጁም ስም ዓብ​ዶን፥ሁለ​ተ​ኛው ሲር፥ ሦስ​ተ​ኛው ቂስ፥ አራ​ተ​ኛው በኣል፥ አም​ስ​ተ​ኛው ኔር፥ ስድ​ስ​ተ​ኛ​ውም ናዳብ፤</verse>
				<verse number="37">ሰባ​ተ​ኛው ግዱር፥ ወን​ድሙ ዘካ​ር​ያ​ስም፥ ሜቅ​ሎ​ትም።</verse>
				<verse number="38">ሜቅ​ሎ​ትም ሳም​አን ወለደ፤ እነ​ር​ሱም ደግሞ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው መካ​ከል ይቀ​መጡ ነበር።</verse>
				<verse number="39">ኔርም ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦ​ልን ወለደ፤ ሳኦ​ልም ዮና​ታ​ንን፥ ሜል​ኪ​ሳን፥ አሚ​ና​ዳ​ብን፥ አስ​በ​ኣ​ልን ወለደ።</verse>
				<verse number="40">የዮ​ና​ታ​ንም ልጅ መሪ​በ​ኣል ነበረ፤ መሪ​በ​ኣ​ልም ሚካን ወለደ።</verse>
				<verse number="41">የሚ​ካም ልጆች ፒቶን፥ ሜሌክ፥ ታራ፥ አካዝ ነበሩ፤</verse>
				<verse number="42">አካ​ዝም ኢያ​ዳ​ዕን ወለደ፤ ኢያ​ዳ​ዕም ጋሌ​ሜ​ትን፥ ጋዝ​ሞ​ትን፥ ዘም​ሪን ወለደ፤ ዘም​ሪም ማሳ​ዕን ወለደ።</verse>
				<verse number="43">ማሳ​ዕም በዓ​ናን ወለደ፥ ልጁ ረፋያ ነበረ፥ ልጁ ኤል​ዓሣ፥ ልጁ ኤሴል፤</verse>
				<verse number="44">ለኤ​ሴ​ልም ስድ​ስት ልጆች ነበ​ሩት፤ ስማ​ቸ​ውም ይህ ነበረ፤ ዓዝ​ሪ​ቃም፥ ቦኬ​ርዩ፥ እስ​ማ​ኤል፥ ሰዓ​ርያ፥ አብ​ድዩ፥ ሐናን፤ እነ​ዚህ የኤ​ሴል ልጆች ነበሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">በዚ​ያም ወራት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ተዋጉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ሸሹ፥ ተወ​ግ​ተ​ውም በጌ​ላ​ቡሄ ተራራ ላይ ወደቁ።</verse>
				<verse number="2">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሳኦ​ል​ንና ልጆ​ቹን በእ​ግር በእ​ግ​ራ​ቸው ተከ​ት​ለው አባ​ረ​ሩ​አ​ቸው፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የሳ​ኦ​ልን ልጆች ዮና​ታ​ን​ንና አሚ​ና​ዳ​ብን ሜል​ኪ​ሳ​ንም ገደሉ።</verse>
				<verse number="3">ሰል​ፍም በሳ​ኦል ላይ ጠነ​ከረ። ቀስ​ተ​ኞ​ችም አግ​ኝ​ተው ወጉት፤ ከቀ​ስ​ቶ​ችም ኀይል የተ​ነሣ ተጨ​ነቀ።</verse>
				<verse number="4">ሳኦ​ልም ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን፥ “እነ​ዚህ ቈላ​ፋን መጥ​ተው እን​ዳ​ይ​ዘ​ብ​ቱ​ብኝ ሰይ​ፍ​ህን መዝ​ዘህ ውጋኝ” አለው። ጋሻ ጃግ​ሬው ግን እጅግ ፈርቶ ነበ​ርና እንቢ አለ። ሳኦ​ልም ሰይ​ፉን ወስዶ በላዩ ወደቀ።</verse>
				<verse number="5">ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም ሳኦል እንደ ሞተ ባየ ጊዜ እርሱ ደግሞ በሰ​ይፉ ላይ ወድቆ ሞተ።</verse>
				<verse number="6">ሳኦ​ልና ሦስ​ቱም ልጆቹ የቤ​ቱም ሰዎች ሁሉ በዚ​ያች ቀን በአ​ንድ ላይ ሞቱ።</verse>
				<verse number="7">በሸ​ለ​ቆ​ውም የነ​በ​ሩት የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ እስ​ራ​ኤል እንደ ሸሹ፥ ሳኦ​ልና ልጆ​ቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ለቅ​ቀው ሸሹ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም መጥ​ተው ተቀ​መ​ጡ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">በነ​ጋ​ውም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን የሞ​ቱ​ትን ለመ​ግ​ፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦ​ል​ንና ልጆ​ቹን በጌ​ላ​ቡሄ ተራራ ላይ ወድ​ቀው አገ​ኙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ሳኦ​ል​ንም ገፈ​ፉት፥ ራሱ​ንም ቈር​ጠው መሣ​ሪ​ያ​ው​ንም አን​ሥ​ተው ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ለሕ​ዝቡ የም​ሥ​ራች ይወ​ስዱ ዘንድ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገር ዙሪያ ሰደዱ።</verse>
				<verse number="10">መሣ​ሪ​ያ​ው​ንም በአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው ቤት ውስጥ አኖሩ፤ ራሱ​ንም በዳ​ጎን ቤት ውስጥ አኖ​ሩት፤</verse>
				<verse number="11">የገ​ለ​ዓ​ድም ሰዎች ሁሉ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን በሳ​ኦ​ልና በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ያደ​ረ​ጉ​ትን ሁሉ ሰሙ።</verse>
				<verse number="12">ጽኑ​ዓን ሰዎች ሁሉ ከገ​ለ​ዐድ ተነ​ሥ​ተው የሳ​ኦ​ልን ሬሳ የል​ጆ​ቹ​ንም ሬሳ​ዎች ወሰዱ፥ ወደ ኢያ​ቢ​ስም አመ​ጡ​አ​ቸው፤ በኢ​ያ​ቢ​ስም ካለው ከት​ልቁ ዛፍ በታች አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ቀበሩ፥ ሰባት ቀንም ጾሙ።</verse>
				<verse number="13">እን​ዲሁ ሳኦል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ስላ​ደ​ረ​ገው ኀጢ​አት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስላ​ል​ጠ​በቀ ሞተ። ደግ​ሞም መና​ፍ​ስት ጠሪን ጠየቀ።</verse>
				<verse number="14">ነቢዩ ሳሙ​ኤ​ልም መለ​ሰ​ለት፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ለስ ዘንድ አል​ሰ​ማ​ውም፥ ስለ​ዚህ ገደ​ለው፤ መን​ግ​ሥ​ቱ​ንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት አሳ​ለ​ፈው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በኬ​ብ​ሮን ወደ ዳዊት ተሰ​ብ​ስ​በው እን​ዲህ አሉት፥ “እነሆ፥ እኛ የአ​ጥ​ን​ትህ ፍላጭ የሥ​ጋህ ቍራጭ ነን፤</verse>
				<verse number="2">አስ​ቀ​ድሞ ሳኦል ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስ​ራ​ኤ​ልን የም​ታ​ወ​ጣና የም​ታ​ገባ አንተ ነበ​ርህ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን አንተ ትጠ​ብ​ቃ​ለህ፤ በሕ​ዝ​ቤም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ ትሆ​ና​ለህ” አለህ።</verse>
				<verse number="3">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ወደ ኬብ​ሮን መጡ፤ ንጉሥ ዳዊ​ትም በኬ​ብ​ሮን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቃል ኪዳን ከእ​ነ​ርሱ ጋር አደ​ረገ፤ በሳ​ሙ​ኤ​ልም እጅ እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ ዳዊ​ትን ቀቡት።</verse>
				<verse number="4">ዳዊ​ትና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ኢያ​ቡስ ወደ​ም​ት​ባል ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሄዱ፤ በሀ​ገ​ሩም የተ​ቀ​መጡ ኢያ​ቡ​ሳ​ው​ያን በዚያ ነበሩ።</verse>
				<verse number="5">በኢ​ያ​ቡ​ስም የተ​ቀ​መጡ ዳዊ​ትን፥ “ወደ​ዚህ አት​ገ​ባም” አሉት፤ ዳዊት ግን አን​ባ​ዪ​ቱን ጽዮ​ንን ያዘ፤ እር​ስ​ዋም የዳ​ዊት ከተማ ናት።</verse>
				<verse number="6">ዳዊ​ትም ኢያ​ቡ​ሳ​ው​ያ​ንን አስ​ቀ​ድሞ የሚ​መታ ሰው አለ​ቃና መኰ​ንን ይሆ​ናል አለ። የሶ​ር​ህ​ያም ልጅ ኢዮ​አብ አስ​ቀ​ድሞ ወጣና ወጋ​ቸው፥ አለ​ቃም ሆነ።</verse>
				<verse number="7">ዳዊ​ትም በአ​ን​ባ​ዪቱ ውስጥ ተቀ​መጠ፤ ስለ​ዚ​ህም “የዳ​ዊት ከተማ” ብለው ጠሩ​አት።</verse>
				<verse number="8">ዳዊ​ትም የከ​ተ​ማ​ዋን ዙሪያ ቀጸረ፤ ተዋ​ግ​ቶም እጅ አደ​ረ​ጋት።</verse>
				<verse number="9">ዳዊ​ትም ሁሉን ቻይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነበ​ረና እየ​በ​ረታ ሄደ።</verse>
				<verse number="10">ለዳ​ዊ​ትም የነ​በ​ሩት ኀያ​ላን አለ​ቆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ስለ እስ​ራ​ኤል እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ያነ​ግ​ሡት ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ጋር በመ​ን​ግ​ሥቱ አጸ​ኑት።</verse>
				<verse number="11">የዳ​ዊ​ትም ኀያ​ላን ቍጥር ይህ ነበረ፤ የሠ​ላ​ሳው አለቃ የአ​ኪ​ማን ልጅ ኢያ​ቡ​ስቴ ነበረ፤ እርሱ ጦሩን አን​ሥቶ ሦስት መቶ ሰው በአ​ንድ ጊዜ ገደለ።</verse>
				<verse number="12">ከእ​ር​ሱም በኋላ በሦ​ስቱ ኀያ​ላን መካ​ከል የነ​በረ የአ​ሆ​ሃ​ዊው የዱዲ ልጅ አል​ዓ​ዛር ነበረ።</verse>
				<verse number="13">እርሱ ከዳ​ዊት ጋር በፋ​ሶ​ደ​ሚን ነበረ፥ በዚ​ያም ገብስ በሞ​ላ​በት እርሻ ውስጥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ለሰ​ልፍ ተሰ​ብ​ስ​በው ነበር፤ ሕዝ​ቡም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ሸሹ።</verse>
				<verse number="14">በእ​ር​ሻ​ውም መካ​ከል ቆመው ጠበ​ቁት፥ ያች​ንም ቦታ አዳ​ናት፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ገደ​ላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በታ​ላቅ ማዳን አዳ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="15">ከሠ​ላ​ሳ​ውም አለ​ቆች ሦስቱ ወር​ደው ዳዊት ወዳ​ለ​በት ወደ ዓለቱ ወደ ዓዶ​ላም ዋሻ መጡ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍራ በኀ​ያ​ላን ሸለቆ ሰፍሮ ነበር።</verse>
				<verse number="16">በዚ​ያም ጊዜ ዳዊት በም​ሽጉ ውስጥ ነበረ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍራ በቤተ ልሔም ነበረ።</verse>
				<verse number="17">ዳዊ​ትም፥ “በበሩ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ማን ይሰ​ጠ​ኛል?” ብሎ ተመኘ።</verse>
				<verse number="18">እነ​ዚህ ሦስቱ ኀያ​ላን የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ሰፈር ሰን​ጥ​ቀው ሄዱ፥ በበ​ሩም አጠ​ገብ ካለ​ችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ቀዱ፤ ይዘ​ውም ለዳ​ዊት አመ​ጡ​ለት። እርሱ ግን ሊጠጣ አል​ወ​ደ​ደም፥ ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ​ስሶ፦</verse>
				<verse number="19">“ይህን አደ​ርግ ዘንድ አም​ላኬ ሆይ፥ ለእኔ አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ለሞት አሳ​ል​ፈው አም​ጥ​ተ​ው​ታ​ልና የእ​ነ​ዚ​ህን ሰዎች ደም እጠ​ጣ​ለ​ሁን?” አለ። ስለ​ዚ​ህም ዳዊት ይጠ​ጣው ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም። ሦስ​ቱም ኀያ​ላን ያደ​ረ​ጉት ይህ ነው።</verse>
				<verse number="20">የኢ​ዮ​አ​ብም ወን​ድም አቢሳ የሦ​ስቱ አለቃ ነበረ፤ ሰይ​ፉ​ንም በሦ​ስት መቶ ላይ አን​ሥቶ በአ​ንድ ጊዜ ገደ​ላ​ቸው፤ በሦ​ስ​ቱም መካ​ከል ስሙ የተ​ጠራ ነበረ።</verse>
				<verse number="21">በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ተራ በሆ​ኑት በሦ​ስቱ መካ​ከል የከ​በረ ነበረ፥ አለ​ቃ​ቸ​ውም ሆነ፤ ነገር ግን ወደ ፊተ​ኞቹ ወደ ሦስቱ አል​ደ​ረ​ሰም።</verse>
				<verse number="22">በቀ​በ​ሳ​ኤል የነ​በ​ረው፥ ታላቅ ሥራ ያደ​ረ​ገው የጽ​ኑዕ ሰው የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ እንደ አን​በሳ ኀያ​ላን የነ​በ​ሩ​ትን ሁለት የሞ​ዓብ ሰዎች ገደለ፤ በአ​መ​ዳ​ይም ወራት ወርዶ በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ አን​በሳ ገደለ።</verse>
				<verse number="23">ቁመ​ቱም አም​ስት ክንድ የነ​በ​ረ​ውን ረጅ​ሙን ግብ​ፃ​ዊ​ውን ሰው ገደለ፤ በግ​ብ​ፃ​ዊ​ውም እጅ የሸ​ማኔ መጠ​ቅ​ለያ የመ​ሰለ ጦር ነበረ፤ እርሱ ግን በትር ይዞ ወደ እርሱ ወረደ፥ ከግ​ብ​ፃ​ዊ​ውም እጅ ጦሩን ቀምቶ በገዛ ጦሩ ገደ​ለው።</verse>
				<verse number="24">የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ ያደ​ረ​ገው ይህ ነው፤ ስሙም በሦ​ስቱ ኀያ​ላን መካ​ከል የተ​ጠራ ነበረ።</verse>
				<verse number="25">እነሆ፥ ከሠ​ላ​ሳው ይልቅ የከ​በረ ነበረ፤ ነገር ግን ወደ ፊተ​ኞቹ ወደ ሦስቱ አል​ደ​ረ​ሰም። ዳዊ​ትም በና​ያ​ስን በሀ​ገሩ ላይ ሾመው።</verse>
				<verse number="26">ደግ​ሞም በጭ​ፍ​ሮቹ ዘንድ የነ​በ​ሩት ኀያ​ላን እነ​ዚህ ናቸው፤ የኢ​ዮ​አብ ወን​ድም አሣ​ሄል፥ የቤተ ልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤል​ያ​ናን፤</verse>
				<verse number="27">ሃሮ​ራ​ዊው ሳሞት፥ ፈሎ​ና​ዊው ኬሌስ፤</verse>
				<verse number="28">የቴ​ቁሔ ሰው የአ​ቂስ ልጅ ኦራ፥ ዓና​ቶ​ታ​ዊው አቤ​ዔ​ዜር፤</verse>
				<verse number="29">ኩሳ​ታ​ዊው ሰቦ​ካይ፥ የአ​ሆ​ሂው ዔላይ፤</verse>
				<verse number="30">ነጦ​ፋ​ዊው ሜሐሪ፥ የነ​ጦ​ፋ​ዊው የበ​ዓና ልጅ ሔሌድ፤</verse>
				<verse number="31">ከብ​ን​ያም ወገን ከጊ​ብዓ የሪ​ባይ ልጅ ኢታይ፥ ፈር​ኖ​ታ​ዊው ባን​ያስ፤</verse>
				<verse number="32">የገ​ዓዝ ወንዝ ሰው ኡሪ፥ ገራ​ባ​ታ​ዊው አብ​ኤል፥</verse>
				<verse number="33">ባሮ​ማ​ዊው ዓዝ​ሞት፥ ሰዓ​ል​ቦ​ና​ዊው ኤሊ​ያ​ሕባ፤</verse>
				<verse number="34">የጊ​ዞ​ን​ያ​ዊው የኤ​ሳም ልጅ፥ የአ​ሩ​ራ​ዊው የሶላ ልጅ ዮና​ታን፤</verse>
				<verse number="35">የአ​ሮ​ራ​ዊው የሳ​ኮር ልጅ አህ​ያም፥ የኤር ልጅ ኤሊ​ፋል፤</verse>
				<verse number="36">መከ​ራ​ታ​ዊው ኦፌር፥ ፍሎ​ና​ዊው አኪያ፤</verse>
				<verse number="37">ቀር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊው ሴራይ፥ የኤ​ዝ​ባይ ልጅ ናራይ፤</verse>
				<verse number="38">የና​ታ​ንም ወን​ድም ኢዩ​ኤል፥ የሐ​ገሪ ልጅ ሚብ​ሐር፤</verse>
				<verse number="39">አሞ​ና​ዊው ሴሌቅ፥ የሦ​ር​ህያ ልጅ የኢ​ዮ​አብ ጋሻ ጃግሬ ቤሮ​ታ​ዊው ናኮር፤</verse>
				<verse number="40">ይት​ራ​ዊው ዔራ፥ ይት​ራ​ዊው ጋሬብ፤</verse>
				<verse number="41">ኬጢ​ያ​ዊው ዑር​ያስ፥ የአ​ሕ​ላይ ልጅ ዘባት፤</verse>
				<verse number="42">የሮ​ቤ​ላ​ዊው የሲዛ ልጅ ዓዲና፥ እርሱ የሮ​ቤ​ላ​ው​ያን አለቃ ነበረ ከእ​ር​ሱም ጋር ሠላሳ ሰዎች ነበሩ፤</verse>
				<verse number="43">የሞካ ልጅ ሐናን፥ ሚት​ና​ዊው ኢዮ​ሣ​ፍጥ፤</verse>
				<verse number="44">አስ​ታ​ሮ​ታ​ዊው ዖዝያ፥ የአ​ሮ​ዔ​ራ​ዊው የኮ​ታም ልጆች ሳማና ይዒ​ኤል፤</verse>
				<verse number="45">የሳ​ምሪ ልጅ ይዳ​ኤል፥ ወን​ድ​ሙም ቲዳ​ዊው ዮዛሔ፥</verse>
				<verse number="46">መዓ​ዊው ኤሊ​ኤል፤ ኢያ​ር​ባኢ፥ ልጁ ዮሳኢ፥ ኤል​ነ​ዓ​ምና ሞዓ​ባ​ዊው ይትማ፤</verse>
				<verse number="47">ኤሊ​ኤል፥ ዖቤድ፥ ምሶ​ባ​ዊው ኢያ​ስ​ኤል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">በሴ​ቅ​ላ​ቅም ከቂስ ልጅ ከሳ​ኦል በተ​ሸ​ሸገ ጊዜ ወደ ዳዊት የመጡ እነ​ዚህ ናቸው፤ በጦ​ር​ነ​ትም ባገ​ዙት ኀያ​ላን መካ​ከል ነበሩ።</verse>
				<verse number="2">ቀስ​ተ​ኞ​ችም ነበሩ፤ በቀ​ኝና በግ​ራም እጃ​ቸው ድን​ጋይ ሊወ​ነ​ጭፉ፥ ፍላ​ጻም ሊወ​ረ​ውሩ ይችሉ ነበር፤ ከብ​ን​ያም ወገን የሳ​ኦል ወን​ድ​ሞች ነበሩ።</verse>
				<verse number="3">አለ​ቃ​ቸ​ውም አኬ​ዘር ነበረ፤ የጊ​ብ​ዓ​ዊው የሰ​ማዓ ልጅ ኢዮ​አስ፥ የዓ​ዝ​ሞት ልጆች ኢዮ​ኤ​ልና ፋሌጥ፥ በራ​ኪ​ያና ዓና​ቶ​ታ​ዊው ኢዩ፤</verse>
				<verse number="4">ገባ​ዖ​ና​ዊው ሰማ​ያስ፥ እርሱ በሠ​ላ​ሳው መካ​ከ​ልና በሠ​ላ​ሳው ላይ ኀያል ሰው ነበረ፤ ኤር​ም​ያስ፥ ሕዝ​ኤል፥ ዮሐ​ናን፥ ገድ​ሮ​ታዊ ዮዛ​ባት፤</verse>
				<verse number="5">ኤል​ዮዝ፥ ኢያ​ሪ​ሙት፥ በዓ​ልያ፥ ሰማ​ራያ፥ ሐሩ​ፋ​ዊው ሰፋ​ጥ​ያስ፤</verse>
				<verse number="6">ቆሬ​ያ​ው​ያን ሕል​ቃና፥ ኢሰያ፥ ዓዘ​ር​ኤል፥ ዮዛር፥ ይሰ​ከ​አም።</verse>
				<verse number="7">የግ​ዶር ሰው የይ​ሮ​ሐም ልጆች ዮዔላ፥ ዝባ​ድያ።</verse>
				<verse number="8">ዳዊ​ትም በም​ድረ በዳ ውስጥ ባለ​ችው በአ​ን​ባ​ዪቱ ሳለ ከጋድ ወገን የሆኑ እነ​ዚህ ጋሻና ጦር የሚ​ይዙ፥ ጽኑ​ዓን፥ ኀያ​ላን ሰል​ፈ​ኞች፥ ወደ እርሱ ተጠጉ፤ ፊታ​ቸ​ውም እንደ አን​በሳ ፊት ነበረ፤ በተ​ራ​ራም ላይ እን​ደ​ሚ​ዘ​ልል ሚዳቋ ፈጣ​ኖች ነበሩ።</verse>
				<verse number="9">አለ​ቃው አዝር፥ ሁለ​ተ​ኛው አብ​ድያ፥ ሦስ​ተ​ኛው ኤል​ያብ፤</verse>
				<verse number="10">አራ​ተ​ኛው መስ​መና፥ አም​ስ​ተ​ኛው ኤር​ም​ያስ፥</verse>
				<verse number="11">ስድ​ስ​ተ​ኛው ኤቲ፥ ሰባ​ተ​ኛው ኤሊ​ኤል፥</verse>
				<verse number="12">ስም​ን​ተ​ኛው ዮሐ​ናን፥ ዘጠ​ነ​ኛው ኤል​ዛ​ባድ፥</verse>
				<verse number="13">ዐሥ​ረ​ኛው ኤር​ም​ያስ፥ ዐሥራ አን​ደ​ኛው መክ​በ​ናይ።</verse>
				<verse number="14">እነ​ዚህ የጋድ ልጆች የጭ​ፍራ አለ​ቆች ነበሩ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ታናሹ የመቶ አለቃ ታላቁ የሺህ አለቃ ነበር።</verse>
				<verse number="15">በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ዮር​ዳ​ኖስ ከዳር እስከ ዳር ሞልቶ በነ​በረ ጊዜ የተ​ሻ​ገ​ሩት እነ​ዚህ ናቸው፤ በሸ​ለ​ቆ​ውም ውስጥ በም​ሥ​ራ​ቅና በም​ዕ​ራብ በኩል የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ሁሉ አባ​ረሩ።</verse>
				<verse number="16">ዳዊ​ትም ወደ ነበ​ረ​ባት ወደ አን​ባ​ዪቱ ከብ​ን​ያ​ምና ከይ​ሁዳ ወገን ሰዎች ዳዊ​ትን ለመ​ር​ዳት መጡ።</verse>
				<verse number="17">ዳዊ​ትም ሊገ​ና​ኛ​ቸው ወጥቶ፥ “በሰ​ላም ወደ እኔ መጥ​ታ​ችሁ እንደ ሆነ ልቤ ከእ​ና​ንተ ጋር አንድ ይሆ​ናል፤ ለጠ​ላ​ቶቼ አሳ​ል​ፋ​ችሁ ልት​ሰ​ጡኝ መጥ​ታ​ችሁ እንደ ሆነ ግን፥ በእጄ ዓመፅ የለ​ብ​ኝ​ምና የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ ይመ​ል​ከ​ተው፥ ይፍ​ረ​ደ​ውም፤” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">መን​ፈ​ስም በሠ​ላ​ሳው አለቃ በዓ​ማ​ሣይ ላይ መጣ፤ እር​ሱም፥ “ዳዊት ሆይ፥ እኛ ያንተ ነን፤ የእ​ሴይ ልጅ ሆይ፥ እኛ ከአ​ንተ ጋር ነን፤ ውጣ አም​ላ​ክህ ይረ​ዳ​ሃ​ልና ሰላም ሰላም ለአ​ንተ ይሁን፤ ለሚ​ረ​ዱ​ህም ሰላም ይሁን” አለ። ዳዊ​ትም ተቀ​በ​ላ​ቸው፤ የጭ​ፍ​ራም አለ​ቆች አደ​ረ​ጋ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">ዳዊ​ትም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ሳኦ​ልን ሊወጋ በመጣ ጊዜ ከም​ናሴ ወገን ሰዎች ወደ ዳዊት ከዱ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች ግን፥ “በራ​ሳ​ችን ላይ ጉዳት አድ​ርጎ ወደ ጌታው ወደ ሳኦል ይመ​ለ​ሳል” ሲሉ ተማ​ክ​ረው ሰድ​ደ​ው​ታ​ልና እርሱ አል​ረ​ዳ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="20">ዳዊ​ትም ወደ ሴቄ​ላቅ ሲሄድ ከም​ናሴ ወገን የም​ናሴ ሻለ​ቆች የነ​በሩ ዓድና፥ ዮዛ​ባት፥ ይዲ​ኤል፥ ሚካ​ኤል፥ ዮዛ​ባት፥ ኤሊ​ሁና ጼል​ታይ ወደ እርሱ ከዱ።</verse>
				<verse number="21">ሁሉም ጽኑ​ዓን ኀያ​ላ​ንና በሠ​ራ​ዊቱ ላይ አለ​ቆች ነበ​ሩና በአ​ደጋ ጣዮች ላይ ዳዊ​ትን አገ​ዙት።</verse>
				<verse number="22">እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሠራ​ዊት ታላቅ ሠራ​ዊት እስ​ኪ​ሆን ድረስ ዳዊ​ትን ለመ​ር​ዳት ዕለት ዕለት ይመጡ ነበር።</verse>
				<verse number="23">እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል የሳ​ኦ​ልን መን​ግ​ሥት ወደ እርሱ ይመ​ልሱ ዘንድ በኬ​ብ​ሮን ሳለ ወደ ዳዊት የመ​ጡት የሠ​ራ​ዊቱ አለ​ቆች ቍጥር ይህ ነው።</verse>
				<verse number="24">ጋሻና ጦር ተሸ​ክ​መው ለሰ​ልፍ የተ​ዘ​ጋጁ የይ​ሁዳ ልጆች ስድ​ስት ሺህ ስም​ንት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="25">ለሰ​ልፍ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች የነ​በሩ የስ​ም​ዖን ልጆች ሰባት ሺህ አንድ መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="26">የሌዊ ልጆች አራት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="27">የአ​ሮ​ንም ቤት አለቃ ዮዳሄ ነበረ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ፤</verse>
				<verse number="28">ከእ​ር​ሱም ጋር ጽኑዕ ኀያል ጐል​ማሳ ሳዶቅ ነበረ፤ ከአ​ባ​ቱም ቤት ሃያ ሁለት አለ​ቆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="29">የሳ​ኦ​ልም ወን​ድ​ሞች ከሆኑ ከብ​ን​ያም ልጆች ሦስት ሺህ ነበሩ። የሚ​በ​ል​ጠው ክፍል የሳ​ኦ​ልን ቤት ይጠ​ብቁ ነበሩ።</verse>
				<verse number="30">ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን የሆኑ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤት የታ​ወቁ የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ሃያ ሺህ ስም​ንት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="31">በየ​ስ​ማ​ቸው የተ​ጻፉ ዳዊ​ትን ያነ​ግ​ሡት ዘንድ የመጡ የም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ዐሥራ ስም​ንት ሺህ ነበሩ።</verse>
				<verse number="32">እስ​ራ​ኤ​ልም የሚ​ገ​ባ​ውን ያደ​ርግ ዘንድ ዘመ​ኑን የሚ​ያ​ውቁ ጥበ​በ​ኞች ሰዎች የይ​ሳ​ኮር ልጆች አለ​ቆች ሁለት መቶ ነበሩ፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበሩ።</verse>
				<verse number="33">በጭ​ፍ​ራ​ውም ውስጥ ዳዊ​ትን ለመ​ር​ዳት የወጡ የተ​ዘ​ጋጁ፥ መሣ​ሪ​ያም ሁሉ የያዙ የዛ​ብ​ሎን ሰዎች አምሳ ሺህ ነበሩ፤ ከእ​ነ​ርሱ አን​ድስ እንኳ ደካማ አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="34">የን​ፍ​ታ​ሌ​ምም አለ​ቆች አንድ ሺህ ነበሩ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ጋሻና ጦር የሚ​ይዙ ሠላሳ ሰባት ሺህ ነበሩ።</verse>
				<verse number="35">ለሰ​ል​ፍም የተ​ዘ​ጋጁ የዳን ሰዎች ሃያ ስም​ንት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="36">በጭ​ፍ​ራ​ውም ውስጥ የሚ​ወጡ፥ ለሰ​ል​ፍም የተ​ዘ​ጋጁ የአ​ሴር ሰዎች አርባ ሺህ ነበሩ።</verse>
				<verse number="37">በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ ካሉ ከሮ​ቤ​ልና ከጋድ ሰዎች ከም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ንም ሁሉ ይዘው የመጡ መቶ ሃያ ሺህ ነበሩ።</verse>
				<verse number="38">እነ​ዚህ ሁሉ ዳዊ​ትን በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ ያነ​ግ​ሡት ዘንድ አር​በ​ኞ​ችና ሰል​ፈ​ኞች እየ​ሆኑ በፍ​ጹም ልባ​ቸው ወደ ኬብ​ሮን መጡ፤ ደግ​ሞም ከእ​ስ​ራ​ኤል የቀ​ሩት ሁሉ ዳዊ​ትን ያነ​ግ​ሡት ዘንድ አንድ ልብ ነበሩ።</verse>
				<verse number="39">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ው​ላ​ቸው ነበ​ርና እየ​በ​ሉና እየ​ጠጡ በዚያ ከዳ​ዊት ጋር ሦስት ቀን ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="40">ደግ​ሞም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ደስታ ሆኖ​አ​ልና እስከ ይሳ​ኮ​ርና እስከ ዛብ​ሎን እስከ ንፍ​ታ​ሌ​ምም ድረስ ለእ​ርሱ አቅ​ራ​ቢያ የነ​በሩ በአ​ህ​ያና በግ​መል በበ​ቅ​ሎና በበሬ ላይ እን​ጀ​ራና ዱቄት የበ​ለስ ጥፍ​ጥ​ፍና የዘ​ቢብ ዘለላ የወ​ይ​ንም ጠጅ፥ ዘይ​ትም በሬ​ዎ​ች​ንና በጎ​ች​ንም፥ ፍየ​ሎ​ች​ንም በብዙ አድ​ር​ገው ያመጡ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">ዳዊ​ትም ከሻ​ለ​ቆ​ችና ከመቶ አለ​ቆች፥ ከአ​ለ​ቆ​ቹም ሁሉ ጋር ተማ​ከረ።</verse>
				<verse number="2">ዳዊ​ትም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጉባኤ ሁሉ፥ “መል​ካም መስሎ የታ​ያ​ችሁ እንደ ሆነ፥ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፈቅዶ እንደ ሆነ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ሀገር ሁሉ ለቀ​ሩት ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውና በመ​ሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ለሚ​ቀ​መጡ ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን ወደ እኛ ይሰ​በ​ሰቡ ዘንድ እን​ላክ።</verse>
				<verse number="3">ከሳ​ኦ​ልም ዘመን ጀምሮ አል​ፈ​ለ​ጓ​ት​ምና የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወደ እኛ እን​መ​ል​ሳት” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ነገ​ሩም በሕ​ዝቡ ሁሉ ዐይን ዘንድ ቅን ነበ​ረና የእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ፥ “እን​ዲሁ እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አሉ።</verse>
				<verse number="5">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ከቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ያመጡ ዘንድ ዳዊት እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ከግ​ብፅ ዳርቻ ጀምሮ እስከ ኤማት መግ​ቢያ ድረስ ሰበ​ሰበ።</verse>
				<verse number="6">ዳዊ​ትም፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በኪ​ሩ​ቤል ላይ የተ​ቀ​መ​ጠ​ውን፥ ስሙም በእ​ር​ስዋ የተ​ጠ​ራ​ባ​ትን የአ​ም​ላ​ክን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ከዚያ ያወጡ ዘንድ በይ​ሁዳ ወዳ​ለ​ችው ቂር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ሄዱ።</verse>
				<verse number="7">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ከአ​ሚ​ና​ዳብ ቤት በተ​ገኘ በአ​ዲስ ሰረ​ገላ ላይ አኖ​ሩ​አት። ዖዛና ወን​ድ​ሞ​ቹም ሰረ​ገ​ላ​ውን ይነዱ ነበር።</verse>
				<verse number="8">ዳዊ​ትና እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከመ​ዘ​ም​ራን ጋር በበ​ገና፥ በመ​ሰ​ን​ቆና በከ​በሮ፥ በጸ​ና​ጽ​ልና በመ​ለ​ከት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሙሉ ኀይ​ላ​ቸው ይዘ​ምሩ ነበር።</verse>
				<verse number="9">ወደ አው​ድማ ዳርም በደ​ረሱ ጊዜ ላሞቹ ሰረ​ገ​ላ​ውን ሲስቡ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ዘን​በል ብላ​ለ​ችና ታቦ​ቷን ሊይዝ ዖዛ እጁን ዘረጋ።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዖዛ ላይ ተቈጣ። እጁ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ስለ ዘረጋ ቀሠ​ፈው፤ በዚ​ያም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሞተ።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዖዛን ስለ ሰበ​ረው ዳዊት አዘነ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የዚ​ያን ስፍራ ስም “የዖዛ ስብ​ራት” ብሎ ጠራው።</verse>
				<verse number="12">በዚ​ያም ቀን ዳዊት፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወደ እኔ እን​ዴት አመ​ጣ​ለሁ?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈራ።</verse>
				<verse number="13">ዳዊ​ትም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወደ ጌት ሰው ወደ አቢ​ዳራ ቤት አሳ​ለ​ፋት እንጂ ወደ እርሱ ወደ ዳዊት ከተማ አላ​መ​ጣ​ትም።</verse>
				<verse number="14">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት በጌት ሰው በአ​ቢ​ዳራ ቤት ውስጥ ሦስት ወር ተቀ​መ​ጠች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አቢ​ዳ​ራ​ንና ቤተ ሰቡን ሁሉ ባረከ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">የጢ​ሮ​ስም ንጉሥ ኪራም ቤት ይሠ​ሩ​ለት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን፥ የዝ​ግባ እን​ጨ​ት​ንም፥ ጠራ​ቢ​ዎ​ች​ንም፥ አና​ጢ​ዎ​ች​ንም ወደ ዳዊት ላከ።</verse>
				<verse number="2">ስለ ሕዝ​ቡም ስለ እስ​ራ​ኤል፥ መን​ግ​ሥቱ እጅግ ከፍ ብሎ​አ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ እን​ዲ​ሆን እን​ዳ​ዘ​ጋ​ጀው ዳዊት ዐወቀ።</verse>
				<verse number="3">ዳዊ​ትም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሌሎች ሚስ​ቶ​ችን ጨምሮ አገባ፤ ሌሎች ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ችም ተወ​ለ​ዱ​ለት።</verse>
				<verse number="4">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት የል​ጆቹ ስም ይህ ነው፤ ሳማ፥ ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎ​ሞን፤</verse>
				<verse number="5">በዓር፥ ኤሊ​ሳዒ፥ ኤሌ​ፋ​ላት፤</verse>
				<verse number="6">ናጌት፥ ናፋት፥ ያፍያ፥</verse>
				<verse number="7">ኤሊ​ሳማ፥ በለ​ዓዳ፥ ኤሊ​ፋ​ላት።</verse>
				<verse number="8">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ዳዊት በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ ንጉሥ ሆኖ እንደ ተቀባ ሰሙ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ዳዊ​ትን ሊፈ​ልጉ ወጡ፤ ዳዊ​ትም በሰማ ጊዜ ሊጋ​ጠ​ማ​ቸው ወጣ።</verse>
				<verse number="9">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም መጥ​ተው በኀ​ያ​ላን ሸለቆ ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="10">ዳዊ​ትም፥ “ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ልው​ጣን? በእ​ጄስ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ህን?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ውጣ” አለው።</verse>
				<verse number="11">ዳዊ​ትም ወደ በኣ​ል​ፐ​ራ​ሲን ወጣ፤ በዚ​ያም ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ​ቸው። ዳዊ​ትም፥ “ውኃ እን​ዲ​ያ​ጠፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶ​ቼን በእጄ አጠ​ፋ​ቸው” አለ። ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያን ስፍራ ስም በኣ​ል​ፐ​ራ​ሲን ብለው ጠሩት።</verse>
				<verse number="12">አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በዚያ ተዉ፤ ዳዊ​ትም፥ “በእ​ሳት አቃ​ጥ​ሉ​አ​ቸው” ብሎ አዘዘ።</verse>
				<verse number="13">ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ደግሞ በኀ​ያ​ላን ሸለቆ ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="14">ዳዊ​ትም እንደ ገና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አት​ውጣ፥ በኋ​ላ​ቸ​ውም አት​ከ​ተ​ላ​ቸው፤ ነገር ግን ከኋ​ላ​ቸው ዙረህ ቅረ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">በሾ​ላ​ውም ዛፍ ራስ ውስጥ የሽ​ው​ሽ​ውታ ድምፅ ስት​ሰማ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ጭፍራ ሊመታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ትህ ይወ​ጣ​ልና በዚ​ያን ጊዜ ወደ ሰልፍ ውጣ” አለው።</verse>
				<verse number="16">ዳዊ​ትም አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረገ፤ ከገ​ባ​ዖ​ንም ጀምሮ እስከ ጌዝር ድረስ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ጭፍራ መታ።</verse>
				<verse number="17">የዳ​ዊ​ትም ዝና በየ​ሀ​ገሩ ሁሉ ወጣ፤ መፈ​ራ​ቱ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ዘንድ አደ​ረገ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">ዳዊ​ትም በከ​ተ​ማው ለራሱ ቤቶ​ችን ሠራ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ስፍራ አዘ​ጋጀ፤ ድን​ኳ​ንም ተከ​ለ​ላት።</verse>
				<verse number="2">በዚ​ያን ጊዜም ዳዊት፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ይሸ​ከሙ ዘንድ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም ያገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከመ​ረ​ጣ​ቸው ከሌ​ዋ​ው​ያን በቀር ማንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ይሸ​ከም ዘንድ አይ​ገ​ባ​ውም” አለ።</verse>
				<verse number="3">ዳዊ​ትም ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ላት ስፍራ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ያመጣ ዘንድ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሰበ​ሰበ።</verse>
				<verse number="4">ዳዊ​ትም የአ​ሮ​ንን ልጆ​ችና ሌዋ​ው​ያ​ንን ሰበ​ሰበ።</verse>
				<verse number="5">ከቀ​ዓት ልጆች፤ አለ​ቃው ኡር​ኤል፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም መቶ ሃያ፤</verse>
				<verse number="6">ከሜ​ራሪ ልጆ​ችም፤ አለ​ቃው ዓሣያ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም ሁለት መቶ ኀምሳ፤</verse>
				<verse number="7">ከጌ​ድ​ሶን ልጆች፤ አለ​ቃው ኢዮ​ሔት፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም መቶ ሠላሳ፤</verse>
				<verse number="8">ከኤ​ል​ሳ​ፋን ልጆች፤ አለ​ቃው ሰማያ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም ሁለት መቶ፤</verse>
				<verse number="9">ከኬ​ብ​ሮን ልጆች፤ አለ​ቃው ኢዮ​ሔል፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም ሰማ​ንያ፤</verse>
				<verse number="10">ከዑ​ዝ​ኤል ልጆች፤ አለ​ቃው አሚ​ና​ዳብ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም መቶ ዐሥራ ሁለት።</verse>
				<verse number="11">ዳዊ​ትም ካህ​ና​ቱን ሳዶ​ቅ​ንና አብ​ያ​ታ​ርን፥ ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም፥ ኡር​ኤ​ልን፥ ዓሣ​ያን፥ ኢዮ​ኤ​ልን፥ ሰማ​ያን፥ ኤሊ​ኤ​ልን፥ አሚ​ና​ዳ​ብ​ንም ጠርቶ፦</verse>
				<verse number="12">“እና​ንተ የሌ​ዋ​ው​ያን አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ናችሁ፤ ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ላት ስፍራ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ታመጡ ዘንድ እና​ን​ተና ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ተቀ​ደሱ።</verse>
				<verse number="13">በቀ​ድሞ ሥራ​ችን አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርስ በር​ሳ​ችን አላ​ጠ​ፋ​ንም፤ በጦ​ር አል​ፈ​ለ​ገ​ን​ምና” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ያመጡ ዘንድ ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያኑ ራሳ​ቸ​ውን አነጹ።</verse>
				<verse number="15">በመ​ጽ​ሐ​ፍም እንደ ተጻፈ ሙሴ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ አዘ​ዛ​ቸው የሌ​ዋ​ው​ያን ልጆች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት በት​ከ​ሻ​ቸው ላይ በመ​ሎ​ጊ​ያ​ዎቹ ተሸ​ከሙ። መባ​እና ቍር​ባ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበረ።</verse>
				<verse number="16">ዳዊ​ትም በዜማ ዕቃ፥ በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገና፥ በጸ​ና​ጽ​ልም እን​ዲ​ያ​ዜሙ፥ ድም​ፃ​ቸ​ው​ንም በደ​ስታ ከፍ እን​ዲ​ያ​ደ​ርጉ መዘ​ም​ራ​ኑን “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ሹሙ” ብሎ ለሌ​ዋ​ው​ያን አለ​ቆች ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="17">ሌዋ​ው​ያ​ኑም የኢ​ዩ​ኤ​ልን ልጅ ኤማ​ንን፥ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹም የበ​ራ​ክ​ያን ልጅ አሳ​ፍን፥ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ከሜ​ራሪ ልጆች የቂ​ሳ​ንን ልጅ ኢታ​ንን፥</verse>
				<verse number="18">ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር በሁ​ለ​ተ​ኛው ተራ የሆ​ኑ​ትን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ዘካ​ር​ያ​ስን፥ ቤንን፥ አዝ​ኤ​ልን፥ ስሜ​ራ​ሞ​ትን፥ ኢያ​ሄ​ልን፥ ኡኒን፥ ኤል​ያ​ብን፥ በና​እ​ያን፥ መዕ​ሤ​ያን፥ መታ​ት​ያን፥ ኤል​ፋ​ይን፥ ሜቄ​ድ​ያን፥ በረ​ኞ​ች​ንም አብ​ዲ​ዶ​ምን፥ ኢያ​ኤ​ል​ንና ዖዝ​ያ​ስን አቆሙ።</verse>
				<verse number="19">መዘ​ም​ራ​ንም ኤማ​ንና አሳፍ ኤታ​ንም በናስ ጸና​ጽል ከፍ አድ​ር​ገው ያሰሙ ነበር።</verse>
				<verse number="20">ዘካ​ር​ያስ፥ አዝ​ኤል፥ ሰሚ​ራ​ሞት፥ ኢያ​ሔል፥ ዑኒ፥ ኤል​ያብ፥ መዕ​ሤያ፥ በና​ያስ በመ​ሰ​ንቆ በል​ዑል ቃል ያዜሙ ነበር።</verse>
				<verse number="21">ማታ​ት​ያስ፥ ኤል​ፋ​ላይ፥ ሜቄ​ድ​ያስ፥ አብ​ዴ​ዶም፥ ይዒ​ኤል፥ ዖዝ​ያ​ስም ስም​ንት አው​ታር ባለው በገና ይዘ​ምሩ ነበር።</verse>
				<verse number="22">የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም አለቃ ኮነ​ን​ያስ በዜማ ላይ ተሾሞ ነበር። ብል​ሃ​ተኛ ነበ​ረና።</verse>
				<verse number="23">በራ​ክ​ያና ሕል​ቃ​ናም ለታ​ቦቷ በረ​ኞች ነበሩ።</verse>
				<verse number="24">ካህ​ና​ቱም ሰበ​ንያ፥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ፥ ናት​ና​ኤል፥ ዓማ​ሣይ፥ ዘካ​ር​ያስ፥ በና​ያስ፥ አል​ዓ​ዛ​ርም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት መለ​ከት ይነፉ ነበር። አብ​ዲ​ዶ​ምና ኢያ​ኤ​ያም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት በረ​ኞች ነበሩ።</verse>
				<verse number="25">ዳዊ​ትም፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ የሻ​ለ​ቆ​ችም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ከአ​ቢ​ዳራ ቤት በደ​ስታ ያመጡ ዘንድ ሄዱ።</verse>
				<verse number="26">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ኪዳን ታቦት የተ​ሸ​ከ​ሙ​ትን ሌዋ​ው​ያ​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​በ​ረ​ታ​ቸው ጊዜ ሰባት በሬ​ዎ​ች​ንና ሰባት አውራ በጎ​ችን ሠዉ።</verse>
				<verse number="27">ዳዊ​ትም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ሌዋ​ው​ያ​ንም ሁሉ፥ መዘ​ም​ራ​ኑም፥ የመ​ዘ​ም​ራ​ኑም አለቃ ኮኖ​ን​ያስ የጥሩ በፍታ ቀሚስ ለብ​ሰው ነበር፤ ዳዊ​ትም የከ​በረ ልብስ ለብሶ ነበረ።</verse>
				<verse number="28">እን​ዲሁ እስ​ራ​ኤል ሁሉ በይ​ባቤ፥ ቀንደ መለ​ከ​ትና እን​ቢ​ልታ እየ​ነፉ፥ ጸና​ጽ​ልና መሰ​ን​ቆም፥ በገ​ናም እየ​መቱ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ።</verse>
				<verse number="29">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ኪዳን ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደ​ረ​ሰች ጊዜ የሳ​ኦል ልጅ ሜል​ኮል በመ​ስ​ኮት ሆና ተመ​ለ​ከ​ተች፤ ንጉ​ሡም ዳዊት ሲዘ​ፍ​ንና ሲጫ​ወት አይታ በል​ብዋ ናቀ​ችው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ይዘው ገቡ፤ ዳዊ​ትም በተ​ከ​ለ​ላት ድን​ኳን ውስጥ አኖ​ሩ​አት፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቀ​ረቡ።</verse>
				<verse number="2">ዳዊ​ትም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ማቅ​ረብ በፈ​ጸመ ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ሕዝ​ቡን ባረከ።</verse>
				<verse number="3">ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ለወ​ን​ዱም ለሴ​ቱም ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አን​ዳ​ንድ እን​ጀራ፥ አን​ዳ​ን​ድም ቍራጭ ሥጋ፥ አን​ዳ​ን​ድም የዘ​ቢብ ጥፍ​ጥፍ አካ​ፈለ።</verse>
				<verse number="4">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ፊት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያወ​ድ​ሱት ዘንድ፥ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ትና ያከ​ብ​ሩ​ትም ዘንድ ከሌ​ዋ​ው​ያን ወገን አቆመ።</verse>
				<verse number="5">አለ​ቃ​ውም አሳፍ ነበረ፤ ከእ​ር​ሱም ቀጥሎ ዘካ​ር​ያስ፥ ኢያ​ሔል፥ ሰሜ​ራ​ሞት፥ ይሔ​ኤል፥ ማታ​ትያ፥ ኤል​ያብ፥ በና​ያስ፥ አብ​ዲ​ዶም፥ ይዒ​ኤል በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገና፥ አሳ​ፍም በጸ​ና​ጽል ይዘ​ምሩ ነበር።</verse>
				<verse number="6">ካህ​ና​ቱም በና​ያ​ስና የሕ​ዜ​ኤል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ሁል​ጊዜ መለ​ከት ይነፉ ነበር።</verse>
				<verse number="7">በዚ​ያም ቀን ዳዊት በአ​ሳ​ፍና በወ​ን​ድ​ሞቹ እጅ እግ​ዝ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲ​ያ​መ​ሰ​ግኑ አስ​ቀ​ድሞ ትእ​ዛ​ዝን ሰጠ።</verse>
				<verse number="8">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት የዘ​መ​ር​ዋት መዝ​ሙር ይህች ናት፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፤ ስሙ​ንም ጥሩ፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ሥራ​ውን አውሩ።</verse>
				<verse number="9">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቀ​ኙ​ለት፥ ዘም​ሩ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ራ​ቱን ሁሉ ተና​ገሩ።</verse>
				<verse number="10">በቅ​ዱስ ስሙ ክበሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ልግ ልብ ደስ ይበ​ለው።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈል​ጉት፥ ትጸ​ና​ላ​ች​ሁም፤ ሁል​ጊዜ ፊቱን ፈልጉ።</verse>
				<verse number="12">የሠ​ራ​ትን ድንቅ አስቡ፥ ተአ​ም​ራ​ቱ​ንም፥ የአ​ፉ​ንም ፍርድ፤</verse>
				<verse number="13">ባሪ​ያ​ዎቹ የእ​ስ​ራ​ኤል ዘር፥ ለእ​ር​ሱም የተ​መ​ረ​ጣ​ችሁ የያ​ዕ​ቆብ ልጆች ሆይ፥</verse>
				<verse number="14">እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችን ነው፤ ፍርዱ በም​ድር ሁሉ ነው።</verse>
				<verse number="15">ቃል ኪዳ​ኑን ለዘ​ለ​ዓ​ለም፥ እስከ ሺህ ትው​ልድ ያዘ​ዘ​ውን ቃሉን አሰበ፥</verse>
				<verse number="16">ለአ​ብ​ር​ሃም ያደ​ረ​ገ​ውን፥ ለይ​ስ​ሐ​ቅም የማ​ለ​ውን፤</verse>
				<verse number="17">ለያ​ዕ​ቆብ ሥር​ዐት እን​ዲ​ሆን ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የዘ​ለ​ዓ​ለም ኪዳን እን​ዲ​ሆን አጸና፤</verse>
				<verse number="18">እን​ዲ​ህም አለ፥ “ለአ​ንተ የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር የር​ስ​ታ​ች​ሁን ገመድ እሰ​ጣ​ለሁ፤”</verse>
				<verse number="19">ይህም የሆ​ነው እነ​ርሱ በቍ​ጥር ጥቂ​ቶች ሰዎች፥ እጅግ ጥቂ​ቶ​ችና ስደ​ተ​ኞች ሲሆኑ ነው።</verse>
				<verse number="20">ከሕ​ዝብ ወደ ሕዝብ፥ ከመ​ን​ግ​ሥ​ትም ወደ ሌላ ሕዝብ አለፉ።</verse>
				<verse number="21">ሰው ግፍ ያደ​ር​ግ​ባ​ቸው ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደም፤ ስለ እነ​ር​ሱም ነገ​ሥ​ታ​ትን ገሠጸ።</verse>
				<verse number="22">“የቀ​ባ​ኋ​ቸ​ውን አት​ንኩ፥ በነ​ቢ​ያ​ቴም ክፉ አታ​ድ​ርጉ” ብሎ፥</verse>
				<verse number="23">ምድር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤ ዕለት ዕለ​ትም ማዳ​ኑን አውሩ።</verse>
				<verse number="24">ክብ​ሩን ለአ​ሕ​ዛብ፥ ተአ​ም​ራ​ቱ​ንም ለወ​ገ​ኖች ሁሉ ንገሩ።</verse>
				<verse number="25">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ፥ ምስ​ጋ​ና​ውም ብዙ ነውና፤ በአ​ማ​ል​ክ​ትም ሁሉ ላይ የተ​ፈራ ነው።</verse>
				<verse number="26">የአ​ሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ሁሉ ጣዖ​ታት ናቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሰማ​ያ​ትን ሠራ።</verse>
				<verse number="27">ክብ​ርና ግርማ በፊቱ፥ ኀይ​ልና ደስ​ታም በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ናቸው።</verse>
				<verse number="28">እና​ንተ የአ​ሕ​ዛብ ወገ​ኖች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፥ ክብ​ር​ንና ኀይ​ልን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ።</verse>
				<verse number="29">ለስሙ የሚ​ገባ ክብ​ርን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፤ ቍር​ባ​ንን ይዛ​ችሁ በአ​ደ​ባ​ባዩ ግቡ፤ በቅ​ድ​ስ​ና​ውም ስፍራ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስገዱ።</verse>
				<verse number="30">ምድር ሁሉ በፊቱ ትነ​ዋ​ወ​ጣ​ለች፤ ዓለ​ም​ንም እን​ዳ​ት​ነ​ዋ​ወጥ አጸ​ናት።</verse>
				<verse number="31">ሰማ​ያት ደስ ይበ​ላ​ቸው፥ ምድ​ርም ሐሤ​ትን ታድ​ርግ፤ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነገሠ” በሉ።</verse>
				<verse number="32">ባሕር በሞ​ላዋ ትና​ወ​ጣ​ለች፤ በረሃ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ ሁሉ ሐሤ​ትን ያድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="33">በም​ድር ሊፈ​ርድ ይመ​ጣ​ልና፥ የዱር ዛፎች በዚ​ያን ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደስ ይላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="34">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ። ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።</verse>
				<verse number="35">የመ​ዳ​ና​ችን አም​ላክ ሆይ፥ አድ​ነን፤ ቅዱስ ስም​ህን እና​መ​ሰ​ግን ዘንድ፥ በም​ስ​ጋ​ና​ህም እን​መካ ዘንድ፥ ከአ​ሕ​ዛብ ሰብ​ስ​በህ ታደ​ገን በሉ።</verse>
				<verse number="36">ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም፥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ረክ። ሕዝቡ ሁሉ አሜን ይበሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያመ​ስ​ግኑ።</verse>
				<verse number="37">እን​ዲ​ሁም በየ​ቀኑ እን​ደ​ሚ​ገ​ባ​ቸው በታ​ቦቱ ፊት ዘወ​ትር ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ አሳ​ፍ​ንና ወን​ድ​ሞ​ቹን ተዋ​ቸው።</verse>
				<verse number="38">አብ​ዲ​ዶ​ም​ንም፥ ስድሳ ስም​ን​ቱ​ንም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን፤ የኤ​ዶ​ታ​ምም ልጅ አብ​ዲ​ዶ​ምና ሖሳ በረ​ኞች ይሆኑ ዘንድ ተዋ​ቸው፤</verse>
				<verse number="39">ካህ​ኑን ሳዶ​ቅ​ንና ካህ​ና​ቱን ወን​ድ​ሞ​ቹን በገ​ባ​ዖን በኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪያ ፊት አቆ​ማ​ቸው፥</verse>
				<verse number="40">ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ይነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ አገ​ል​ጋዩ ሙሴን እንደ አዘ​ዘው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ እንደ ተጻፈ ሁሉ ለሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ላይ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ሁል​ጊዜ ጥዋ​ትና ማታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ርቡ ዘንድ።</verse>
				<verse number="41">ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ ኤማ​ን​ንና ኤዶ​ታ​ምን፥ በስ​ማ​ቸው የተ​ጻ​ፉ​ትን ተመ​ር​ጠው የቀ​ሩ​ትን ከእ​ነ​ርሱ ጋር አቆመ።</verse>
				<verse number="42">ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ካህ​ናቱ ከፍ አድ​ር​ገው ለማ​ሰ​ማት መለ​ከ​ትና ጸና​ጽል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መዝ​ሙ​ራት የዜማ ዕቃ ይዘው ነበር፤ የኤ​ዶ​ታም ልጆች ግን በረ​ኞች ነበሩ።</verse>
				<verse number="43">ሕዝቡ ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ቤቱ ሄደ፤ ዳዊ​ትም ቤቱን ይባ​ርክ ዘንድ ተመ​ለሰ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት በቤቱ በተ​ቀ​መጠ ጊዜ ዳዊት ነቢዩ ናታ​ንን፥ “እነሆ፥ ከዝ​ግባ በተ​ሠራ ቤት ተቀ​ም​ጫ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት ግን በመ​ጋ​ረ​ጃ​ዎች ውስጥ ተቀ​ም​ጣ​ለች” አለው።</verse>
				<verse number="2">ናታ​ንም ዳዊ​ትን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና በል​ብህ ያለ​ውን ሁሉ አድ​ርግ” አለው።</verse>
				<verse number="3">በዚ​ያም ሌሊት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ናታን መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፦</verse>
				<verse number="4">“ሂድ፥ ለአ​ገ​ል​ጋዬ ለዳ​ዊት ንገ​ረው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በው​ስጡ እኖ​ር​በት ዘንድ ቤትን የም​ት​ሠ​ራ​ልኝ አንተ አይ​ደ​ለ​ህም፤</verse>
				<verse number="5">ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ሁ​በት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በድ​ን​ኳ​ንና በማ​ደ​ሪያ ኖርሁ እንጂ በቤት ውስጥ አል​ኖ​ር​ሁም።</verse>
				<verse number="6">ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ጋር ባለ​ፍ​ሁ​በት ስፍራ ሁሉ፥ ስለ ምን ቤትን ከዝ​ግባ እን​ጨት አል​ሠ​ራ​ች​ሁ​ል​ኝም? ብዬ ሕዝ​ቤን ይጠ​ብቅ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ፈራ​ጆች ላዘ​ዝ​ሁት ለአ​ንዱ በውኑ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁን?</verse>
				<verse number="7">አሁ​ንም አገ​ል​ጋ​ዬን ዳዊ​ትን እን​ዲህ በለው፦ ሁሉን ቻይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አንተ መን​ጋ​ውን ስት​ከ​ተል በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ መርጬ ወሰ​ድ​ሁህ።</verse>
				<verse number="8">በሄ​ድ​ህ​በ​ትም ሁሉ ከአ​ንተ ጋር ነበ​ርሁ፥ ጠላ​ቶ​ች​ህ​ንም ሁሉ ከፊ​ትህ አጠ​ፋሁ፤ በም​ድ​ርም ላይ እን​ዳሉ እንደ ታላ​ላ​ቆች ስም ለአ​ንተ ስምን አደ​ረ​ግሁ።</verse>
				<verse number="9">ለሕ​ዝ​ቤም ለእ​ስ​ራ​ኤል ስፍራ አደ​ር​ግ​ለ​ታ​ለሁ፥ በዚ​ያም እተ​ክ​ለ​ዋ​ለሁ፥ በስ​ፍ​ራ​ውም ይቀ​መ​ጣል፤ ከዚ​ያም በኋላ አይ​ና​ወ​ጥም፤ የኀ​ጢ​አ​ትም ልጆች እንደ ቀድ​ሞው አያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​ትም፤</verse>
				<verse number="10">በሕ​ዝ​ቤም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈራ​ጆ​ችን ካስ​ነ​ሣ​ሁ​በት ጊዜ ጀምሮ ጠላ​ቶ​ች​ህን ሁሉ አዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አን​ተ​ንም ከፍ ከፍ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደግሞ ቤትን ይሠ​ራ​ል​ሃል።</verse>
				<verse number="11">ወደ አባ​ቶ​ች​ህም ትሄድ ዘንድ ዕድ​ሜህ በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ ከአ​ብ​ራ​ክህ የተ​ወ​ለደ ዘር​ህን ከአ​ንተ በኋላ አስ​ነ​ሣ​ለሁ ፤ መን​ግ​ሥ​ቱ​ንም አጸ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">እርሱ ቤትን ይሠ​ራ​ል​ኛል ፤ ዙፋ​ኑ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጸ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">እኔም አባት እሆ​ነ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ልጄ ይሆ​ነ​ኛል፤ ከአ​ንተ አስ​ቀ​ድሞ ከነ​በ​ሩት እን​ዳ​ራ​ቅሁ፥ ምሕ​ረ​ቴን ከእ​ርሱ አላ​ር​ቅም።</verse>
				<verse number="14">ለቤ​ቴም ታማኝ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ መን​ግ​ሥ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነው፤ ዙፋ​ኑም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጸ​ናል።”</verse>
				<verse number="15">እን​ደ​ዚህ ነገር ሁሉ እን​ደ​ዚ​ህም ራእይ ሁሉ ነቢዩ ናታን ለዳ​ዊት ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="16">ንጉ​ሡም ዳዊት ገባ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ተቀ​ምጦ እን​ዲህ አለ፥ “አቤቱ አም​ላክ ሆይ፥ ለዘ​ለ​ዓም የወ​ደ​ድ​ኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="17">አም​ላክ ሆይ፥ ይህ በፊ​ትህ ጥቂት ነበረ፤ ስለ አገ​ል​ጋ​ይህ ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተና​ገ​ርህ፤ እንደ አንድ ባለ ማዕ​ረግ ሰው ተመ​ለ​ከ​ት​ኸኝ። አቤቱ፥ አም​ላክ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደ​ረ​ግ​ኸኝ።</verse>
				<verse number="18">አንተ ባሪ​ያ​ህን ታው​ቀ​ዋ​ለ​ህና ለባ​ሪ​ያህ ስለ ተደ​ረ​ገው ክብር ዳዊት ጨምሮ የሚ​ለው ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="19">እንደ ልብ​ህም ይህን ታላቅ ነገር ሁሉ ለእኔ አደ​ረ​ግህ።</verse>
				<verse number="20">አቤቱ፥ እን​ዳ​ንተ ያለ የለም፤ በጆ​ሮ​አ​ች​ንም እንደ ሰማን ሁሉ ከአ​ንተ በቀር አም​ላክ የለም።</verse>
				<verse number="21">አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ ካወ​ጣ​ኸው ከሕ​ዝ​ብህ ፊት አሕ​ዛ​ብን በማ​ሳ​ደድ ታላ​ቅና የከ​በረ ስምን ለአ​ንተ ታደ​ርግ ዘንድ፥ ለአ​ን​ተም ሕዝብ ትቤዥ ዘንድ እንደ መራ​ኸው እንደ አንተ ሕዝብ እንደ እስ​ራ​ኤል ያለ በም​ድር ላይ ሌላ ሕዝብ የለም።</verse>
				<verse number="22">ሕዝ​ብ​ህ​ንም እስ​ራ​ኤ​ልን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕዝ​ብህ አደ​ረ​ግ​ኸው፤ አን​ተም አቤቱ፥ አም​ላክ ሆን​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">አሁ​ንም፥ አቤቱ፥ ስለ ባሪ​ያ​ህና ስለ ቤቱ የተ​ና​ገ​ር​ኸው ቃል ለዘ​ለ​ዓ​ለም የታ​መነ ይሁን፤ እንደ ተና​ገ​ር​ህም አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="24">ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ነው፤ በእ​ው​ነት የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ነው ይባል ዘንድ ስምህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጽኑና ታላቅ ይሁን፤ የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህም የዳ​ዊት ቤት በፊ​ትህ የጸና ይሁን።</verse>
				<verse number="25">አም​ላኬ ሆይ፥ ቤት እን​ድ​ት​ሠ​ራ​ለት ለባ​ሪ​ያህ በጆሮው ገል​ጠ​ሃ​ልና ስለ​ዚህ አገ​ል​ጋ​ይህ ወደ አንተ ይጸ​ልይ ዘንድ ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን አገኘ።</verse>
				<verse number="26">አሁ​ንም፥ አቤቱ፥ አንተ አም​ላክ ነህ፤ ይህ​ንም መል​ካም ነገር ለባ​ሪ​ያህ ተና​ግ​ረ​ሃል።</verse>
				<verse number="27">አሁ​ንም በፊ​ትህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖር ዘንድ የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ቤት ትባ​ርክ ዘንድ ጀም​ረ​ሃል፤ አን​ተም አቤቱ፥ ባር​ከ​ኸ​ዋል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ቡሩክ ይሆ​ናል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ፤ አዋ​ረ​ዳ​ቸ​ውም፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ ጌት​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን ወሰደ።</verse>
				<verse number="2">ሞዓ​ብ​ንም መታ፤ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት።</verse>
				<verse number="3">ዳዊ​ትም በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ የነ​በ​ረ​ውን ግዛ​ቱን ለማ​ጽ​ናት በሄደ ጊዜ ሔማ​ታ​ዊ​ውን የሱ​ባን ንጉሥ አድ​ር​አ​ዛ​ርን መታ።</verse>
				<verse number="4">ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ አንድ ሺህ ሰረ​ገ​ሎች፥ ሰባት ሺህም ፈረ​ሰ​ኞች፥ ሃያ ሺህም እግ​ረ​ኞች ወሰደ፤ ዳዊ​ትም ለመቶ ሰረ​ገ​ሎች የሚ​ሆ​ኑ​ትን ብቻ አስ​ቀ​ርቶ የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹን ፈረ​ሶች ቋንጃ ቈረጠ።</verse>
				<verse number="5">ከደ​ማ​ስ​ቆም ሶር​ያ​ው​ያን የሱ​ባን ንጉሥ አድ​ር​አ​ዛ​ርን ሊረዱ በመጡ ጊዜ ዳዊት ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን ገደለ።</verse>
				<verse number="6">ዳዊ​ትም በደ​ማ​ስቆ ሶርያ ጭፍ​ሮ​ችን አኖረ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሄ​ደ​በት ሁሉ ያድ​ነው ነበር።</verse>
				<verse number="7">ዳዊ​ትም ለአ​ድ​ር​አ​ዛር አገ​ል​ጋ​ዮች የነ​በ​ሩ​ትን የወ​ርቅ ማር​ዳ​ዎች ወሰደ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ይዞ​አ​ቸው መጣ።</verse>
				<verse number="8">ከሚ​ጢ​ብ​ሐ​ትና ከተ​መ​ረ​ጡት ከአ​ድ​ር​አ​ዛር ከተ​ሞች ዳዊት እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ፤ ከዚ​ህም ሰሎ​ሞን የና​ሱን ኩሬና ዓም​ዶች የና​ሱ​ንም ዕቃ ሠራ።</verse>
				<verse number="9">የኤ​ማ​ትም ንጉሥ ቶዑ ዳዊት የሱ​ባን ንጉሥ አድ​ር​አ​ዛ​ርን፥ ጭፍ​ራ​ው​ንም ሁሉ እንደ መታ ሰማ።</verse>
				<verse number="10">ቶዑም ከአ​ድ​ር​አ​ዛር ጋር ሁል​ጊዜ ይዋጋ ነበ​ርና ዳዊት አድ​ር​አ​ዛ​ርን ወግቶ ስለ መታው ደኅ​ን​ነ​ቱን ይጠ​ይ​ቀ​ውና ይመ​ር​ቀው ዘንድ ልጁን አዶ​ራ​ምን ወደ ዳዊት ላከው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የወ​ር​ቅና የብር፥ የና​ስም ዕቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="11">ንጉ​ሡም ዳዊት ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ከኤ​ዶ​ምና ከሞ​ዓብ፥ ከአ​ሞ​ንም ልጆች፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥ ከአ​ማ​ሌ​ቅም ከማ​ረ​ከው ብርና ወርቅ ጋር እነ​ዚ​ህን ደግሞ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀደሰ።</verse>
				<verse number="12">ደግሞ የሶ​ር​ህያ ልጅ አቢሳ ከኤ​ዶ​ማ​ው​ያን በጨው ሸለቆ ውስጥ ዐሥራ ስም​ንት ሺህ ሰዎች ገደለ።</verse>
				<verse number="13">በዚ​ያም ሸለቆ ምሽግ ሠርቶ ጭፍ​ሮ​ችን አኖረ፥ ኤዶ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሄ​ደ​በት ሁሉ ያድ​ነው ነበር።</verse>
				<verse number="14">ዳዊ​ትም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤ ለሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">የሶ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አ​ብም የሠ​ራ​ዊት አለቃ ነበረ፤ የአ​ሔ​ሉ​ድም ልጅ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ታሪክ ጸሓፊ ነበረ።</verse>
				<verse number="16">የአ​ኪ​ጦ​ብም ልጅ ሳዶ​ቅና የአ​ብ​ያ​ታር ልጅ አቤ​ሜ​ሌክ ካህ​ናት ነበሩ፤ ሱሳ ጸሓፊ ነበረ።</verse>
				<verse number="17">የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ በከ​ሊ​ታ​ው​ያ​ንና በፈ​ሊ​ታ​ው​ያን ላይ ሹም ነበረ፤ የዳ​ዊ​ትም ልጆች በን​ጉሡ አጠ​ገብ አለ​ቆች ነበሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ የአ​ሞን ልጆች ንጉሥ ናዖስ ሞተ፤ ልጁም በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።</verse>
				<verse number="2">ዳዊ​ትም፥ “አባቱ ስላ​ደ​ረ​ገ​ልኝ ወረታ እኔ ለና​ዖስ ልጅ ለሐ​ናን ቸር​ነት አደ​ር​ጋ​ለሁ” አለ። ዳዊ​ትም አባቱ ስለ ሞተ ሊያ​ጽ​ና​ናው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ የዳ​ዊ​ትም አገ​ል​ጋ​ዮች ሊያ​ጽ​ና​ኑት ወደ ሐናን ወደ አሞን ልጆች ምድር መጡ።</verse>
				<verse number="3">የአ​ሞን ልጆች አለ​ቆች ግን ሐና​ንን፥ “ዳዊት የሚ​ያ​ጽ​ና​ኑ​ህን ወደ አንተ የላከ አባ​ት​ህን በማ​ክ​በር ነውን? አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹስ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ለመ​መ​ር​መ​ርና ሀገ​ሪ​ቱ​ንም ለመ​ሰ​ለል ወደ አንተ የመጡ አይ​ደ​ሉ​ምን?” አሉት።</verse>
				<verse number="4">ሐና​ንም የዳ​ዊ​ትን አገ​ል​ጋ​ዮች ወስዶ የጢ​ማ​ቸ​ውን ግማሽ አስ​ላ​ጫ​ቸው፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም እስከ ወገ​ባ​ቸው ድረስ ለሁ​ለት ቀድዶ ሰደ​ዳ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">ሰዎ​ችም ሄደው በሰ​ዎቹ ላይ የተ​ደ​ረ​ገ​ውን ለዳ​ዊት አስ​ታ​ወ​ቁት። ሰዎ​ቹም በብዙ አፍ​ረ​ዋ​ልና ይቀ​በ​ሏ​ቸው ዘንድ ሰዎ​ችን ላኩ፤ ንጉ​ሡም፥ “ጢማ​ችሁ እስ​ኪ​ያ​ድግ ድረስ በኢ​ያ​ሪኮ ተቀ​መጡ፥ ከዚ​ያም በኋላ ተመ​ለሱ” አለ።</verse>
				<verse number="6">የአ​ሞ​ንም ልጆች የዳ​ዊት ሰዎች እን​ዳ​ፈሩ ባዩ ጊዜ ሐናን የአ​ሞን ልጆች ንጉሥ ከሶ​ርያ መስ​ጴ​ጦ​ምያ፥ ከሶ​ርያ ሞዓካ፥ ከሱ​ባም ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ይቀ​ጥሩ ዘንድ አንድ ሺህ መክ​ሊት ብር ላከ።</verse>
				<verse number="7">ሠላሳ ሁለ​ትም ሺህ ሰረ​ገ​ሎ​ችን የሞ​ዓ​ካን ንጉ​ሥና ሕዝ​ቡ​ንም ቀጠሩ፤ መጥ​ተ​ውም በሜ​ድባ ፊት ለፊት ሰፈሩ። የአ​ሞ​ንም ልጆች ከየ​ከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ተሰ​ብ​ስ​በው ወደ ሰልፍ መጡ።</verse>
				<verse number="8">ዳዊ​ትም ይህን በሰማ ጊዜ ኢዮ​አ​ብ​ንና የኀ​ያ​ላ​ኑን ሠራ​ዊት ሁሉ ላከ።</verse>
				<verse number="9">የአ​ሞ​ንም ልጆች ወጥ​ተው በከ​ተ​ማ​ዪቱ በር አጠ​ገብ ተሰ​ለፉ፤ የመ​ጡ​ትም ነገ​ሥ​ታት ለብ​ቻ​ቸው በሜ​ዳው ላይ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="10">ኢዮ​አ​ብም በፊ​ቱና በኋ​ላው ሰልፍ እንደ ከበ​በው ባየ ጊዜ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጐል​ማ​ሶ​ችን መረጠ፤ እነ​ር​ሱም ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ጋር ተዋጉ።</verse>
				<verse number="11">የቀ​ረ​ው​ንም ሕዝብ ለወ​ን​ድሙ ለአ​ቢሳ ሰጠው፤ እነ​ር​ሱም በአ​ሞን ልጆች ላይ ተሰ​ለፉ።</verse>
				<verse number="12">ኢዮ​አ​ብም፥ “ሶር​ያ​ው​ያን ቢበ​ረ​ቱ​ብኝ ርዳኝ፤ የአ​ሞ​ንም ልጆች ቢበ​ረ​ቱ​ብህ እረ​ዳ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">አይ​ዞህ፥ በርታ፤ ስለ ሕዝ​ባ​ች​ንና ስለ አም​ላ​ካ​ች​ንም ከተ​ሞች እን​በ​ርታ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፊቱ ደስ ያሰ​ኘ​ውን ያድ​ርግ” አለ።</verse>
				<verse number="14">ኢዮ​አ​ብና ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ረው ሕዝብ ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ጋር ተዋጉ፤ እነ​ር​ሱም ከፊ​ታ​ቸው ሸሹ።</verse>
				<verse number="15">የአ​ሞ​ንም ልጆች ሶር​ያ​ው​ያን ከኢ​ዮአብ ፊት እንደ ሸሹ ባዩ ጊዜ እነ​ርሱ ደግሞ ከወ​ን​ድሙ ከአ​ቢሳ ፊት ሸሹ፤ ወደ ከተ​ማ​ዪ​ቱም ገቡ። ኢዮ​አ​ብም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ።</verse>
				<verse number="16">ሶር​ያ​ው​ያ​ንም እስ​ራ​ኤል ድል እን​ዳ​ደ​ረ​ጓ​ቸው ባዩ ጊዜ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ልከው በወ​ንዝ ማዶ የነ​በ​ሩ​ትን ሶር​ያ​ው​ያን አስ​መጡ፤ የአ​ድ​ር​አ​ዛ​ርም ሠራ​ዊት አለቃ ሶፋክ በፊ​ታ​ቸው ነበረ።</verse>
				<verse number="17">ዳዊ​ትም በተ​ነ​ገ​ረው ጊዜ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ግሮ መጣ​ባ​ቸው፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ተዋጋ፤ ዳዊ​ትም ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ጋር ተዋጋ፥ እነ​ር​ሱም ከእ​ርሱ ጋር ተዋጉ።</verse>
				<verse number="18">ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ከዳ​ዊት ፊት ሸሹ፤ ዳዊ​ትም ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ሰባት ሺህ ሰረ​ገ​ለ​ኞ​ችን፥ አርባ ሺህም እግ​ረ​ኞ​ችን ገደለ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱ​ንም አለቃ ሶፋ​ክን ገደለ።</verse>
				<verse number="19">የአ​ድ​ር​አ​ዛ​ርም አገ​ል​ጋ​ዮች በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት እንደ ተሸ​ነፉ ባዩ ጊዜ ከዳ​ዊት ጋር ታረቁ፤ ተገ​ዙ​ለ​ትም፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ከዚያ ወዲያ የአ​ሞ​ንን ልጆች ይረዱ ዘንድ እንቢ አሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዓ​መት መጨ​ረሻ ነገ​ሥ​ታት ወደ ሰልፍ በሚ​ወ​ጡ​በት ጊዜ ኢዮ​አብ የሠ​ራ​ዊ​ቱን ኀይል አወጣ፤ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች ሀገር አጠፋ፤ መጥ​ቶም አራ​ቦ​ትን ከበበ። ዳዊ​ትም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​ምጦ ነበር። ኢዮ​አ​ብም አራ​ቦ​ትን መትቶ አፈ​ረ​ሳት።</verse>
				<verse number="2">ዳዊ​ትም የን​ጉ​ሣ​ቸ​ውን የሞ​ል​ኮ​ልን ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ፤ ክብ​ደ​ቱም አንድ መክ​ሊት ወርቅ ያህል ሆኖ ተገኘ፤ ክቡር ዕን​ቍም ነበ​ረ​በት፤ በዳ​ዊ​ትም ራስ ላይ አስ​ቀ​መ​ጡት፤ ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰደ።</verse>
				<verse number="3">በው​ስ​ጥ​ዋም የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ አው​ጥተው በመ​ጋዝ ተረ​ተ​ሩ​አ​ቸው፤ በመ​ጥ​ረ​ቢ​ያም ቈራ​ረ​ጡ​አ​ቸው። ዳዊ​ትም በአ​ሞን ልጆች ከተ​ሞች ሁሉ እን​ዲሁ አደ​ረገ። ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="4">ከዚ​ህም በኋላ በጋ​ዜር ላይ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ጦር​ነት እንደ ገና ሆነ፤ ያን​ጊ​ዜም ኡሳ​ታ​ዊው ሴቦ​ቃይ ከኀ​ያ​ላን ወገን የነ​በ​ረ​ውን ሲፋ​ይን ገድሎ ጣለው።</verse>
				<verse number="5">ደግ​ሞም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ሰልፍ ነበረ፤ የያ​ዔ​ርም ልጅ ኤል​ያ​ናን የጌት ሰው የጎ​ል​ያ​ድን ወን​ድም ለሕ​ሜን ገደለ። የጦሩ የቦም እንደ ሸማኔ መጠ​ቅ​ለያ ሆኖ ተገኘ።</verse>
				<verse number="6">ደግሞ በጌት ላይ ሰልፍ ሆነ ፤ በዚ​ያም በእ​ጁና በእ​ግሩ ስድ​ስት ስድ​ስት ጣቶች በጠ​ቅ​ላ​ላው ሃያ አራት ጣቶች ያሉት አንድ ረዥም ሰው ነበረ፤ እር​ሱም ደግሞ ከኀ​ያ​ላን የተ​ወ​ለደ ነበረ።</verse>
				<verse number="7">እስ​ራ​ኤ​ል​ንም በተ​ገ​ዳ​ደረ ጊዜ የዳ​ዊት ወን​ድም የሳ​ምዓ ልጅ ዮና​ታን ገደ​ለው።</verse>
				<verse number="8">እነ​ዚ​ህም በጌት ውስጥ ከኀ​ያ​ላን የተ​ወ​ለዱ ነበሩ፤ እነ​ር​ሱም አራት ኀያ​ላን ነበሩ፤ በዳ​ዊ​ትም እጅ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም እጅ ወደቁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">ያን​ጊ​ዜም ሰይ​ጣን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ተነሣ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ይቈ​ጥር ዘንድ ዳዊ​ትን አነ​ሣ​ሣው።</verse>
				<verse number="2">ዳዊ​ትም ኢዮ​አ​ብ​ንና የሕ​ዝ​ቡን አለ​ቆች ሁሉ፥ “ሂዱ፥ ከቤ​ር​ሳ​ቤህ ጀምሮ እስከ ዳን ድረስ እስ​ራ​ኤ​ልን ቍጠሩ፤ ድም​ራ​ቸ​ው​ንም አውቅ ዘንድ አስ​ታ​ው​ቁኝ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ኢዮ​አ​ብም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ላይ አሁን ባለ​በት መቶ እጥፍ ይጨ​ምር፤ የጌ​ታዬ የን​ጉሥ ዐይ​ኖ​ችም ይዩ፤ ሁሉም የጌ​ታዬ አገ​ል​ጋ​ዮች ናቸው፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በደል ይሆን ዘንድ ይህን ነገር ጌታዬ ለምን ይሻል?” አለ።</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን የን​ጉሡ ቃል በኢ​ዮ​አብ ላይ አሸ​ነፈ፤ ኢዮ​አ​ብም ወጥቶ በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ ተዘ​ዋ​ወረ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም መጣ።</verse>
				<verse number="5">ኢዮ​አ​ብም የቈ​ጠ​ራ​ቸ​ውን የሕ​ዝ​ቡን ድምር ለዳ​ዊት ሰጠ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አንድ ሚሊ​ዮን አንድ መቶ ሺህ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ሰዎች ተገኙ፤ ከይ​ሁ​ዳም አራት መቶ ሰባ ሺህ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ሰዎች ተገኙ።</verse>
				<verse number="6">የን​ጉሡ ትእ​ዛዝ ግን በኢ​ዮ​አብ ዘንድ የተ​ጠላ ነበ​ረና ሌዊና ብን​ያም ከእ​ነ​ርሱ ጋር አል​ተ​ቈ​ጠ​ሩም።</verse>
				<verse number="7">ይህም ነገር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ሆነ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ መቅ​ሠ​ፍ​ትን አመጣ።</verse>
				<verse number="8">ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “ይህን በማ​ድ​ረ​ግ እ​ጅ​ግ በ​ድ​ያ​ለሁ፤ አሁ​ንም ታላቅ ስን​ፍና አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና የባ​ሪ​ያ​ህን ኀጢ​አት ታስ​ወ​ግድ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለነ​ቢዩ ለጋድ እን​ዲህ አለው፦</verse>
				<verse number="10">“ሂድ፥ ለዳ​ዊት፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሦስ​ቱን ነገ​ሮች በፊ​ትህ አኖ​ራ​ለሁ፤ አደ​ር​ግ​ብህ ዘንድ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዱን ምረጥ ብለህ ንገ​ረው።”</verse>
				<verse number="11">ጋድም ወደ ዳዊት መጥቶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የም​ት​ወ​ድ​ደ​ውን ምረጥ።</verse>
				<verse number="12">የሦ​ስት ዓመት ራብ፥ ወይም ሦስት ወር የጠ​ላ​ቶ​ችህ ሰይፍ እን​ዲ​ያ​ገ​ኝህ ከጠ​ላ​ቶ​ችህ መሰ​ደ​ድን፥ ወይም ሦስት ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ፥ ቸነ​ፈ​ርም በም​ድር ላይ መሆ​ንን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር ሁሉ ማጥ​ፋ​ትን ምረጥ፤ አሁ​ንም ለላ​ከኝ ምን እን​ደ​ም​መ​ልስ አስ​ረ​ዳኝ” አለው።</verse>
				<verse number="13">ዳዊ​ትም ጋድን፥ “እነ​ዚህ ሦስት ነገ​ሮች እጅግ ይከ​ብ​ዱ​ኛል፥ እጅ​ግም ተጨ​ን​ቄ​አ​ለሁ፤ አሁ​ንም ምሕ​ረቱ ብዙ ነውና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ መው​ደቅ ይሻ​ለ​ኛል፤ በሰው እጅ ግን አል​ው​ደቅ” አለው።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ቸነ​ፈ​ርን ሰደደ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰባ ሺህ ሰዎች ወደቁ።</verse>
				<verse number="15">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያጠ​ፋት ዘንድ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መል​አ​ክን ሰደደ፤ ሊያ​ጠ​ፋ​ትም በቀ​ረበ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይቶ ከመ​ቅ​ሠ​ፍቱ ይቅር አለ፤ የሚ​ያ​ጠ​ፋ​ው​ንም መል​አክ፥ “በቃህ፤ አሁን እጅ​ህን መልስ” አለው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በኢ​ያ​ቡ​ሳ​ዊው በኦ​ርና አው​ድማ አጠ​ገብ ቆሞ ነበር።</verse>
				<verse number="16">ዳዊ​ትም ዐይ​ኖ​ቹን አነሣ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በም​ድ​ርና በሰ​ማይ መካ​ከል ቆሞ፥ የተ​መ​ዘ​ዘም ሰይፍ በእጁ ሆኖ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተዘ​ር​ግቶ አየ። ዳዊ​ትና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹም ማቅ ለብ​ሰው በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደፉ።</verse>
				<verse number="17">ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “ሕዝቡ ይቈ​ጠር ዘንድ ያዘ​ዝሁ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? የበ​ደ​ል​ሁና ክፉ የሠ​ራሁ እኔ ነኝ፤ እነ​ዚህ በጎች ግን ምን አድ​ር​ገ​ዋል? አቤቱ አም​ላኬ ሆይ፥ እጅህ በእ​ኔና በአ​ባቴ ቤት ላይ ትሁን፤ ነገር ግን አቤቱ በሕ​ዝ​ብህ ላይ ለጥ​ፋት አት​ሁን” አለው።</verse>
				<verse number="18">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ዳዊት ወጥቶ በኢ​ያ​ቡ​ሳ​ዊው በኦ​ርና አው​ድማ ላይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ይሠራ ዘንድ ለዳ​ዊት እን​ዲ​ነ​ግ​ረው ጋድን አዘ​ዘው።</verse>
				<verse number="19">ዳዊ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም እንደ ተና​ገ​ረው እንደ ጋድ ነገር ወጣ።</verse>
				<verse number="20">ኦር​ናም ዘወር ብሎ ንጉሡ ዳዊ​ትን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ተሸ​ሽ​ገው የነ​በሩ አራ​ቱን ብላ​ቴ​ኖ​ቹን አየ። ኦር​ናም ስንዴ ያበ​ራይ ነበር።</verse>
				<verse number="21">ዳዊ​ትም ወደ ኦርና መጣ፤ ኦር​ናም ከአ​ው​ድ​ማው ወጥቶ ዳዊ​ትን ተቀ​በ​ለው። በም​ድ​ርም ላይ ወድቆ ሰገ​ደ​ለት።</verse>
				<verse number="22">ዳዊ​ትም ኦር​ናን፥ “በላዩ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ እሠራ ዘንድ ይህን የአ​ው​ድማ ስፍራ ስጠኝ፤ በሙሉ ዋጋ ሽጥ​ልኝ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ቱም ከሕ​ዝቤ ይከ​ለ​ከ​ላል” አለው።</verse>
				<verse number="23">ኦር​ናም ዳዊ​ትን፥ “ለአ​ንተ ውሰ​ደው፤ ጌታዬ ንጉ​ሡም በፊቱ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን ያድ​ርግ፤ እነሆ፥ ለሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት በሬ​ዎ​ቹን፥ ለእ​ን​ጨ​ትም የአ​ው​ድ​ማ​ውን ዕቃ፥ ለእ​ህ​ልም ቍር​ባን ስን​ዴ​ውን እሰ​ጥ​ሀ​ለሁ፥ ሁሉን እሰ​ጣ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="24">ንጉ​ሡም ዳዊት ኦር​ናን፥ “አይ​ደ​ለም፥ ነገር ግን ለአ​ንተ ያለ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ጥቼ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በከ​ንቱ አላ​ቀ​ር​ብ​ምና በተ​ገ​ቢው ዋጋ እገ​ዛ​ዋ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="25">ዳዊ​ትም ስለ ስፍ​ራው ስድ​ስት መቶ ሰቅል ወርቅ በሚ​ዛን ለኦ​ርና ሰጠው።</verse>
				<verse number="26">ዳዊ​ትም በዚያ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሠራ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱ​ንም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ጠራ፤ ከሰ​ማ​ይም ለሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ላይ በእ​ሳት መለ​ሰ​ለት፤ እሳ​ቱም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት በላ።</verse>
				<verse number="27">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አ​ኩን አዘ​ዘው፤ ሰይ​ፉ​ንም በአ​ፎቱ ከተ​ተው።</verse>
				<verse number="28">በዚ​ያም ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​ያ​ቡ​ሳ​ዊው በኦ​ርና አው​ድማ እንደ ሰማው ዳዊት ባየ ጊዜ፥ በዚያ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋ።</verse>
				<verse number="29">ሙሴም በም​ድረ በዳ የሠ​ራት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪ​ያና ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ በዚ​ያን ጊዜ በገ​ባ​ዖን ባለው በኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ ነበሩ።</verse>
				<verse number="30">ዳዊት ግን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ሰይፍ የተ​ነሣ ስለ ፈራ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመ​ጠ​የቅ ወደ​ዚያ ይሄድ ዘንድ አል​ቻ​ለም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">ዳዊ​ትም፥ “ይህ የአ​ም​ላኬ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ነው፤ ይህም ለእ​ስ​ራ​ኤል ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ነው” አለ።</verse>
				<verse number="2">ዳዊ​ትም በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር የነ​በ​ሩ​ትን መጻ​ተ​ኞች ይሰ​በ​ስቡ ዘንድ አዘዘ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ለመ​ሥ​ራት የሚ​ወ​ቀ​ሩ​ትን ድን​ጋ​ዮች ይወ​ቅሩ ዘንድ ጠራ​ቢ​ዎ​ችን አኖረ።</verse>
				<verse number="3">ዳዊ​ትም ለበ​ሮቹ ሳንቃ ለሚ​ሆኑ ለም​ስ​ማ​ርና ለመ​ጠ​ረ​ቂያ ብዙ ብረት፥ ከብ​ዛ​ቱም የተ​ነሣ የማ​ይ​መ​ዘን ናስ አዘ​ጋጀ።</verse>
				<verse number="4">ሲዶ​ና​ው​ያ​ንና የጢ​ሮስ ሰዎ​ችም ብዙ የዝ​ግባ እን​ጨት ለዳ​ዊት ያመጡ ነበ​ርና ቍጥር የሌ​ላ​ቸ​ውን የዝ​ግባ እን​ጨ​ቶች አዘ​ጋጀ።</verse>
				<verse number="5">ዳዊ​ትም፥ “ልጄ ሰሎ​ሞን ታና​ሽና ለጋ ብላ​ቴና ነው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ሠ​ራው ቤት እጅግ ማለ​ፊ​ያና በሀ​ገሩ ሁሉ ስሙና ክብሩ እን​ዲ​ጠራ ይሆን ዘንድ ይገ​ባል፤ ስለ​ዚህ አዘ​ጋ​ጅ​ለ​ታ​ለሁ” አለ። ዳዊ​ትም ሳይ​ሞት አስ​ቀ​ድሞ ብዙ አዘ​ጋጀ።</verse>
				<verse number="6">ልጁ​ንም ሰሎ​ሞ​ንን ጠርቶ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት ይሠራ ዘንድ አዘ​ዘው።</verse>
				<verse number="7">ዳዊ​ትም ሰሎ​ሞ​ንን እን​ዲህ አለው፥ “ልጄ ሆይ፥ እኔ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት እሠራ ዘንድ በልቤ አስቤ ነበር።</verse>
				<verse number="8">ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እን​ዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ እጅግ ብዙ ደም አፍ​ስ​ሰ​ሃል፤ ታላ​ቅም ሰልፍ አድ​ር​ገ​ሃል፤ በፊ​ቴም በም​ድር ላይ ብዙ ደም አፍ​ስ​ሰ​ሃ​ልና ለስሜ ቤት አት​ሠ​ራም።</verse>
				<verse number="9">እነሆ፥ ልጅ ይወ​ለ​ድ​ል​ሃል፤ የዕ​ረ​ፍት ሰውም ይሆ​ናል፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ካሉ ከጠ​ላ​ቶቹ ሁሉ አሳ​ር​ፈ​ዋ​ለሁ፤ ስሙ ሰሎ​ሞን ይባ​ላ​ልና፥ በዘ​መ​ኑም ሰላ​ም​ንና ጸጥ​ታን ለእ​ስ​ራ​ኤል እሰ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">እርሱ ለስሜ ቤት ይሠ​ራል፤ ልጅም ይሆ​ነ​ኛል፤ እኔም አባት እሆ​ነ​ዋ​ለሁ፤ የመ​ን​ግ​ሥ​ቱ​ንም ዙፋን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጸ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">አሁ​ንም ልጄ ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ይሁን፤ ስለ አን​ተም እንደ ተና​ገ​ረው ያከ​ና​ው​ን​ልህ፤ የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሥራ።</verse>
				<verse number="12">ብቻ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን ይስ​ጥህ፤ መን​ግ​ሥ​ት​ህ​ንም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ያጽና።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እስ​ራ​ኤል ሙሴን ያዘ​ዘ​ውን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ ብት​ጠ​ነ​ቀቅ በዚ​ያን ጊዜ ይከ​ና​ወ​ን​ል​ሃል፤ አይ​ዞህ፥ በርታ፤ አት​ፍራ፤ አት​ደ​ን​ግ​ጥም።</verse>
				<verse number="14">አሁ​ንም፥ እነሆ፥ በድ​ህ​ነቴ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መቶ ሺህ መክ​ሊት ወር​ቅና አንድ ሚሊ​ዮን መክ​ሊት ብር፥ ሚዛ​ንም የሌ​ላ​ቸው ብዙ ናስና ብረት አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ፤ ደግ​ሞም የማ​ይ​ቈ​ጠር ብዙ የዝ​ግባ እን​ጨ​ትና ድን​ጋ​ዮች አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ፤ አን​ተም ልጄ ከዚያ በላይ ጨምር።</verse>
				<verse number="15">አን​ተም ብዙ ሠራ​ተ​ኞ​ችን፥ ድን​ጋ​ይና እን​ጨት ወቃ​ሪ​ዎ​ች​ንና ጠራ​ቢ​ዎ​ችን፥ ሥራ​ው​ንም ሁሉ ለማ​ድ​ረግ ጠቢ​ባን ሰዎ​ችን አብ​ዝ​ተህ ጨምር።</verse>
				<verse number="16">ቍጥር በሌ​ለው በወ​ር​ቅና ብር፥ በና​ስና ብረት ተነ​ሥ​ተህ ሥራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ንተ ጋር ይሁን።”</verse>
				<verse number="17">ዳዊ​ትም ደግሞ ልጁን ሰሎ​ሞ​ንን ይቀ​በ​ሉ​ትና ያግ​ዙት ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አለ​ቆች ሁሉ እን​ዲህ ሲል አዘ​ዛ​ቸው፦</verse>
				<verse number="18">“አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር አይ​ደ​ለ​ምን? በም​ድ​ርም የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና፥ ምድ​ርም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በሕ​ዝቡ ፊት ተገ​ዝ​ታ​ለ​ችና በዙ​ሪ​ያ​ችሁ ከአሉ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ ዕረ​ፍ​ትን ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="19">አሁ​ንም አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትፈ​ልጉ ዘንድ ልባ​ች​ሁ​ንና ነፍ​ሳ​ች​ሁን ስጡ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም ወደ​ሚ​ሠ​ራው ቤት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦ​ትና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ንዋየ ቅድ​ሳት ታመጡ ዘንድ ተነ​ሥ​ታ​ችሁ የአ​ም​ላ​ክን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መቅ​ደስ ሥሩ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="23">
				<verse number="1">ዳዊ​ትም በሸ​መ​ገለ ጊዜ፥ ዕድ​ሜ​ንም በጠ​ገበ ጊዜ ልጁን ሰሎ​ሞ​ንን በእ​ርሱ ፋንታ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አነ​ገ​ሠው።</verse>
				<verse number="2">የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አለ​ቆች ሁሉ፥ ካህ​ና​ቱ​ንም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም ሰበ​ሰበ።</verse>
				<verse number="3">ሌዋ​ው​ያ​ንም ከሠ​ላሳ ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ ተቈ​ጠሩ፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም በእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ነፍስ ወከፍ ሲቈ​ጠሩ ሠላሳ ስም​ንት ሺህ ነበረ።</verse>
				<verse number="4">ከእ​ነ​ዚ​ህም ውስጥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሥራ የሚ​ያ​ሠ​ሩት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ፤ ስድ​ስቱ ሺህም ጻፎ​ችና ፈራ​ጆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="5">አራቱ ሺህም በረ​ኞች ነበሩ፤ አራቱ ሺህም ለም​ስ​ጋና በተ​ሠ​ሩት በዜማ ዕቃ​ዎች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ነበር።</verse>
				<verse number="6">ዳዊ​ትም እንደ ሌዊ ልጆች እንደ ጌድ​ሶ​ንና እንደ ቀዓት እንደ ሜራ​ሪም በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው መደ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">ከጌ​ድ​ሶ​ና​ው​ያን ለአ​ዳ​ንና ሰሜኢ ነበሩ።</verse>
				<verse number="8">የለ​አ​ዳን ልጆች አለ​ቃው አድ​ሔ​ኤል፥ ዜቶም፥ ዮሔል ሦስት ነበሩ።</verse>
				<verse number="9">የሰ​ሜኢ ልጆች ሰሎ​ሚት፥ ሐዝ​ኤል፥ ሐራን ሦስት ነበሩ። እነ​ዚህ የለ​ያአ​ዳን አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="10">የሰ​ሜኢ ልጆች ኤኢት፥ ዚዛ፥ ኢያ​አስ፥ በሪዓ ነበሩ። እነ​ዚህ አራቱ የሰ​ሜኢ ልጆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="11">አለ​ቃው ኤኢት ነበረ፤ ሁለ​ተ​ኛው ዚዛ ነበረ፤ ኢያ​አ​ስና በሪዓ ግን ብዙ ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​አ​ቸ​ውም፤ ስለ​ዚህ እንደ አንድ አባት ቤት ሆነው ተቈ​ጠሩ።</verse>
				<verse number="12">የቀ​ዓት ልጆች እን​በ​ረም፥ ይስ​ዓር፦ ኬብ​ሮን፥ ዑዝ​ኤል አራት ነበሩ።</verse>
				<verse number="13">የእ​ን​በ​ረም ልጆች አሮ​ንና ሙሴ ነበሩ፤ አሮ​ንም ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን የተ​ቀ​ደሰ ይሆን ዘንድ ተመ​ረጠ፤ እር​ሱና ልጆቹ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያጥ​ኑና ያገ​ለ​ግሉ ነበር፤ በስ​ሙም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይባ​ርኩ ነበር።</verse>
				<verse number="14">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው ሙሴና ልጆቹ በሌዊ ነገድ ተቈ​ጠሩ።</verse>
				<verse number="15">የሙሴ ልጆ​ችም ጌር​ሳ​ምና አል​ዓ​ዛር ነበሩ።</verse>
				<verse number="16">የጌ​ር​ሳም ልጆች አለቃ ሱባ​ኤል ነበረ።</verse>
				<verse number="17">የአ​ል​ዓ​ዛ​ርም ልጆች አለቃ ረዓ​ብያ ነበረ፤ አል​ዓ​ዛ​ርም ሌሎች ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​ትም፤ የረ​ዓ​ብያ ልጆች እጅግ ብዙ ነበሩ።</verse>
				<verse number="18">የይ​ስ​ዓር ልጆች አለ​ቃው ሰሎ​ሚት ነበረ።</verse>
				<verse number="19">የኬ​ብ​ሮን ልጆች አለ​ቃው ኢያ​ኤ​ርያ፥ ሁለ​ተ​ኛው አማ​ርያ፥ ሦስ​ተ​ኛው ኢያ​ዝ​ሔል፥ አራ​ተ​ኛው ኢያ​ቄ​ም​ያስ ነበሩ።</verse>
				<verse number="20">የዑ​ዝ​ኤል ልጆች አለ​ቃው ሚካ፥ ሁለ​ተ​ኛው ይስያ ነበሩ።</verse>
				<verse number="21">የሜ​ራሪ ልጆች ሞዓ​ሊና ሐሙሲ ነበሩ። የሞ​ዓሊ ልጆች አል​ዓ​ዛ​ርና ቂስ ነበሩ።</verse>
				<verse number="22">አል​ዓ​ዛ​ርም ሴቶች ልጆች ብቻ እንጂ ወን​ዶች ልጆች ሳይ​ወ​ልድ ሞተ፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም የቂስ ልጆች አገ​ቡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">የሐ​ሙሲ ልጆች፤ ሞዓሊ፥ አዴር፥ ኢያ​ሪ​ሞት ሦስት ነበሩ።</verse>
				<verse number="24">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት አገ​ል​ግ​ሎት በሠሩ ከሃያ አም​ስት ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ በነ​በሩ በእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በስ​ማ​ቸው በተ​ቈ​ጠ​ሩት ላይ የአ​ባ​ቶች ቤት አለ​ቆች የሆ​ኑት በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት የሌዊ ልጆች እነ​ዚህ ነበሩ።</verse>
				<verse number="25">ዳዊ​ትም እን​ዲህ አለ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ ዕረ​ፍት ሰጥ​ቶ​አል፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይቀ​መ​ጣል።</verse>
				<verse number="26">ሌዋ​ው​ያ​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ማደ​ሪ​ያ​ው​ንና የማ​ገ​ል​ገያ ዕቃ​ውን ሁሉ አይ​ሽ​ከ​ሙም።”</verse>
				<verse number="27">በመ​ጨ​ረ​ሻ​ውም በዳ​ዊት ትእ​ዛዝ ከሃያ አም​ስት ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉት የሌዊ ልጆች ተቈ​ጠሩ።</verse>
				<verse number="28">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት በየ​አ​ደ​ባ​ባ​ዩና በየ​መ​ጋ​ረ​ጃው ውስጥ ለማ​ገ​ል​ገል፥ ቅዱ​ሱ​ንም ዕቃ ሁሉ ለማ​ን​ጻት፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ለመ​ሥ​ራት ከአ​ሮን ልጆች እጅ በታች ሹሞ​አ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="29">ደግ​ሞም ገጸ ኅብ​ስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በም​ጣ​ድም ቢጋ​ገር፥ ቢለ​ወ​ስም ለእ​ህል ቍር​ባን በሆ​ነው በመ​ል​ካሙ ዱቄት በመ​ስ​ፈ​ሪ​ያና በልክ ሁሉ ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ሹሞ​አ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="30">በየ​ጥ​ዋ​ቱና በየ​ማ​ታው ቆመው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​መ​ስ​ገ​ንና ለማ​ክ​በር፥</verse>
				<verse number="31">በየ​ሰ​ን​በ​ታ​ቱም፥ በየ​መ​ባ​ቻ​ዎ​ቹም፥ በየ​በ​ዓ​ላ​ቱም እንደ ሥር​ዐቱ ቍጥር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዘወ​ትር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ሁሉ ለማ​ቅ​ረብ፥</verse>
				<verse number="32">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሥር​ዐት፥ የወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን የአ​ሮ​ንን ልጆች ሥር​ዐት ለመ​ጠ​በቅ ሹሞ​አ​ቸው ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="24">
				<verse number="1">የአ​ሮ​ንም ልጆች ሰሞን ይህ ነው። የአ​ሮን ልጆች ናዳብ፥ አብ​ዩድ፥ አል​ዓ​ዛር፥ ኢታ​ምር ነበሩ።</verse>
				<verse number="2">ናዳ​ብና አብ​ዩድ ግን ልጆች ሳይ​ወ​ልዱ ከአ​ባ​ታ​ቸው በፊት ሞቱ፤ የአ​ሮን ልጆች አል​ዓ​ዛ​ርና ኢታ​ም​ርም ካህ​ናት ሆነው አገ​ለ​ገሉ።</verse>
				<verse number="3">ዳዊ​ትም ከአ​ል​ዓ​ዛር ልጆች ሳዶ​ቅን፥ ከኢ​ታ​ም​ርም ልጆች አቤ​ሜ​ሌ​ክን እንደ ቍጥ​ራ​ቸው፥ እንደ አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውና እንደ እየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ከፍሎ መደ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">የአ​ል​ዓ​ዛ​ርም ልጆች አለ​ቆች ከኢ​ታ​ምር ልጆች አለ​ቆች በል​ጠው ተገኙ፤ እን​ዲ​ህም ተመ​ደቡ፤ ከአ​ል​ዓ​ዛር ልጆች እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ዐሥራ ስድ​ስት አለ​ቆች፥ ከኢ​ታ​ም​ርም ልጆች እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ስም​ንት አለ​ቆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="5">ከአ​ል​ዓ​ዛ​ርና ከኢ​ታ​ም​ርም ልጆች መካ​ከል የን​ዋ​ያተ ቅዱ​ሳ​ቱና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አለ​ቆች ነበ​ሩና እነ​ዚ​ህና እነ​ዚያ እን​ዲህ በዕጣ ተመ​ደቡ።</verse>
				<verse number="6">ከሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ወገን የነ​በ​ረው የና​ት​ና​ኤል ልጅ ጸሓ​ፊው ሳም​ያስ በን​ጉ​ሡና በአ​ለ​ቆቹ ፊት ፥ በካ​ህኑ በሳ​ዶ​ቅና በአ​ብ​ያ​ታ​ርም ልጅ በአ​ቤ​ሜ​ሌክ ፊት ፥ በካ​ህ​ና​ቱና በሌ​ዋ​ው​ያኑ አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ፊት ጻፋ​ቸው፤ አን​ዱ​ንም የአ​ባት ቤት ለአ​ል​ዓ​ዛር፥ አን​ዱ​ንም ለኢ​ታ​ምር ጻፈ።</verse>
				<verse number="7">መጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ዕጣ ለኢ​ያ​ሬብ ወጣ፤ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ለኢ​ያ​ድያ፥</verse>
				<verse number="8">ሦስ​ተ​ኛ​ውም ለካ​ሬም፥ አራ​ተ​ኛ​ውም ለሴ​ዓ​ሪን፥</verse>
				<verse number="9">አም​ስ​ተ​ኛ​ውም ለመ​ል​ክያ፥ ስድ​ስ​ተ​ኛ​ውም ለሜ​ዒ​ያ​ኢም፥</verse>
				<verse number="10">ሰባ​ተ​ኛ​ውም ለአ​ቆስ፥ ስም​ን​ተ​ኛው ለአ​ብያ፥</verse>
				<verse number="11">ዘጠ​ነ​ኛው ለኢ​ያሱ፥ ዐሥ​ረ​ኛው ለሴ​ኬ​ንያ፥</verse>
				<verse number="12">ዐሥራ አን​ደ​ኛው ለኤ​ል​ያ​ሴብ፥ ዐሥራ ሁለ​ተ​ኛው ለኤ​ል​ያ​ቄም፥</verse>
				<verse number="13">ዐሥራ ሦስ​ተ​ኛው ለኦ​ፋዕ፥ ዐሥራ አራ​ተ​ኛው ለኤ​ሳ​ባእ፥</verse>
				<verse number="14">ዐሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ለቤ​ል​ጋዕ፥ ዐሥራ ስድ​ስ​ተ​ኛው ለኤ​ሜር፥</verse>
				<verse number="15">ዐሥራ ሰባ​ተ​ኛው ለኢ​ያ​ዜር፥ ዐሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ለአ​ፌስ፥</verse>
				<verse number="16">ዐሥራ ዘጠ​ነ​ኛው ለፈ​ታ​ሕያ፥ ሃያ​ኛው ለሕ​ዝ​ቄል፥</verse>
				<verse number="17">ሃያ አን​ደ​ኛው ለአ​ኬኖ፥ ሃያ ሁለ​ተ​ኛው ለጋ​ሙ​ሄል፥</verse>
				<verse number="18">ሃያ ሦስ​ተ​ኛው ለደ​ላ​ኢያ፥ ሃያ አራ​ተ​ኛው ለሙ​ዓዚ።</verse>
				<verse number="19">የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘዘ፥ በአ​ባ​ታ​ቸው በአ​ሮን እጅ እንደ ተሰ​ጣ​ቸው ሥር​ዐት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ይገቡ ዘንድ እንደ እየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ቍጥ​ራ​ቸው ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="20">ከቀ​ሩ​ትም የሌዊ ልጆች፤ ከእ​ን​በ​ረም ልጆች ስባ​ሄል፤ ከስ​ባ​ሄል ልጆች ኢያ​ዳ​እያ፤</verse>
				<verse number="21">ከአ​ረ​ብ​ያም ልጆች የአ​ረ​ብያ ልጅ አራ​ድያ፥ አለ​ቃው ኢያ​ስ​ያስ፤</verse>
				<verse number="22">ከኢ​ስ​ዓ​ራ​ው​ያን ሰሎ​ሞት፤ ከሰ​ሎ​ሞት ልጆች ኤናት፤</verse>
				<verse number="23">ከኢ​ዩ​ዲዩ ልጆች አለ​ቃው ይሪያ፥ ሁለ​ተ​ኛው አማ​ርያ፥ ሦስ​ተ​ኛው ኢያ​ዚ​ሄል፥ አራ​ተ​ኛው ኢያ​ቁ​ምያ፤</verse>
				<verse number="24">የኢ​ያ​ዝ​ሄል ልጅ ሚካ፤ የሚካ ልጅ ሳሜር፤</verse>
				<verse number="25">የሚካ ወን​ድም ኢሳ​እያ፤ የኢ​ሳ​እያ ልጅ ዘካ​ር​ያስ፤</verse>
				<verse number="26">የሜ​ራሪ ልጆች ሞዓ​ሊና ሐሙሲ፤ የዖ​ዝ​ያስ ልጅ ባኒ፤</verse>
				<verse number="27">የሜ​ራሪ ልጆች፤ ከዖ​ዝያ ይሰ​ዓም፥ ዝኩር፥ አብዲ፤</verse>
				<verse number="28">የሞ​ዓሊ ልጅ አል​ዓ​ዛር፥ እር​ሱም ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​ትም፤</verse>
				<verse number="29">ከቂስ፤ የቂስ ልጅ አራ​ሜ​ሄል፤</verse>
				<verse number="30">የሐ​ሙሲ ልጆች፤ ሞዓሊ፥ ኤዳር፥ ኢያ​ሪ​ሞት። እነ​ዚህ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች የሌ​ዋ​ው​ያን ልጆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="31">እነ​ዚ​ህም ደግሞ በን​ጉሡ በዳ​ዊ​ትና በሳ​ዶቅ በአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክም በሌ​ዋ​ው​ያ​ንና በካ​ህ​ናት አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ፊት፥ ታላ​ላ​ቆች እንደ ታና​ናሽ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው፥ እንደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣ​ጣሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="25">
				<verse number="1">ዳዊ​ትና የሠ​ራ​ዊቱ አለ​ቆ​ችም ከአ​ሳ​ፍና ከኤ​ማን ከኤ​ዶ​ት​ምም ልጆች በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገና፥ በጸ​ና​ጽ​ልም የሚ​ዘ​ምሩ ሰዎ​ችን ለማ​ገ​ል​ገል ለዩ፤ በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውም ሥራ የሚ​ሠሩ ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="2">ከአ​ሳፍ ልጆች፤ ዘኩር፥ ዮሴፍ፥ ናታ​ንያ፥ ኤራ​ኤል፤ እነ​ዚህ የአ​ሳፍ ልጆች የን​ጉሡ ቀራ​ቢ​ዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="3">ከኤ​ዶ​ትም የኤ​ዶ​ትም ልጆች፤ ጎዶ​ል​ያስ፥ ሱሪ፥ የሻያ፥ ሰሜኢ፥ ሐሸ​ብያ፥ መታ​ትያ፥ እነ​ዚህ ስድ​ስቱ ከአ​ባ​ታ​ቸው ከኤ​ዶ​ትም ጋር በበ​ገና እየ​ዘ​መሩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ነበር።</verse>
				<verse number="4">ከኤ​ማን የኤ​ማን ልጆች፤ ቡቅያ፥ መታ​ንያ፥ ዓዛ​ር​ዔል፥ ሱባ​ኤል፥ ኢየ​ሪ​ሙት፥ ሐና​ንያ፥ ሐናኒ፥ ኤል​ያታ፥ ጌዶ​ላቲ፥ ሮማ​ን​ቴ​ዔ​ዜር፥ ዮስ​ብ​ቃሳ፥ ሜኤ​ላቴ፥ ሆቴር፥ መሐ​ዝ​ዮት፤</verse>
				<verse number="5">እነ​ዚህ ሁሉ ቀንደ መለ​ከ​ቱን ከፍ ያደ​ርጉ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በን​ጉሡ ፊት የሚ​ዘ​ም​ረው የኤ​ማን ልጆች ነበሩ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለኤ​ማን ዐሥራ አራት ወን​ዶች ልጆ​ች​ንና ሦስት ሴቶች ልጆ​ችን ሰጠው።</verse>
				<verse number="6">እነ​ዚህ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በጸ​ና​ጽ​ልና በበ​ገና፥ በመ​ሰ​ን​ቆም ከአ​ባ​ታ​ቸው ጋራ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለማ​ገ​ል​ገል ወደ ንጉሡ ቀር​በው ያመ​ሰ​ግኑ ነበር። አሳ​ፍም ኤዶ​ት​ምም ኤማ​ንም ያመ​ሰ​ግኑ ነበር።</verse>
				<verse number="7">የብ​ል​ሃ​ተ​ኞ​ቹም ቍጥር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​መ​ስ​ገን ከሚ​ያ​ውቁ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር ሁለት መቶ ሰማ​ንያ ስም​ንት ነበረ።</verse>
				<verse number="8">ሁሉም ተካ​ክ​ለው፥ ታና​ሹም ታላ​ቁም፥ ለሰ​ሞ​ና​ቸው ዕጣ ተጣ​ጣሉ እነ​ር​ሱም ፍጹ​ማ​ንና የተ​ማሩ ነበሩ።</verse>
				<verse number="9">የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዕጣ ለአ​ሳፍ ወገን ለዮ​ሴፍ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹና ለል​ጆቹ ለዐ​ሥራ ሁለቱ ደረ​ሳ​ቸው፤ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለጎ​ዶ​ል​ያስ ለል​ጆ​ቹና ለወ​ን​ድ​ሞቹ ለዐ​ሥራ ሁለቱ ደረ​ሳ​ቸው፤</verse>
				<verse number="10">ሦስ​ተ​ኛው ለዘ​ኩር ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ፤</verse>
				<verse number="11">አራ​ተ​ኛው ለይ​ጽሪ ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ፤</verse>
				<verse number="12">አም​ስ​ተ​ኛው ለና​ታ​ን​ያስ ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ።</verse>
				<verse number="13">ስድ​ስ​ተ​ኛው ለቡ​ቅያ ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ፤</verse>
				<verse number="14">ሰባ​ተ​ኛው ለይ​ስ​ር​ኤል ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ፤</verse>
				<verse number="15">ስም​ን​ተ​ኛው ለኢ​ያ​ስያ ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ፤</verse>
				<verse number="16">ዘጠ​ነ​ኛው ለማ​ታ​ን​ያስ ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ፤</verse>
				<verse number="17">ዐሥ​ረ​ኛው ለሰ​ሜኢ ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ፤</verse>
				<verse number="18">ዐሥራ አን​ደ​ኛው ለዓ​ዛ​ር​ኤል ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ፤</verse>
				<verse number="19">ዐሥራ ሁለ​ተ​ኛው ለኢ​ሰ​ብያ ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ፤</verse>
				<verse number="20">ዐሥራ ሦስ​ተ​ኛው ለሱ​ባ​ኤል ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ፤</verse>
				<verse number="21">ዐሥራ አራ​ተ​ኛው ለማ​ታ​ት​ያስ ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ፤</verse>
				<verse number="22">ዐሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ለኢ​የ​ሪ​ሙት ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ፤</verse>
				<verse number="23">ዐሥራ ስድ​ስ​ተ​ኛው ለሐ​ና​ንያ ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ፤</verse>
				<verse number="24">ዐሥራ ሰባ​ተ​ኛው ለዮ​ስ​ባ​ቃጥ ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ፤</verse>
				<verse number="25">ዐሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ለሐ​ናኒ ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ፤</verse>
				<verse number="26">ዐሥራ ዘጠ​ነ​ኛው ለማ​ኤ​ላቲ ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ፤</verse>
				<verse number="27">ሃያ​ኛው ለኤ​ል​ያታ ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ፤</verse>
				<verse number="28">ሃያ አን​ደ​ኛው ለኦ​ትሪ ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ፤</verse>
				<verse number="29">ሃያ ሁለ​ተ​ኛው ለጌ​ዶ​ላቲ ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ፤</verse>
				<verse number="30">ሃያ ሦስ​ተ​ኛው ለመ​ሐ​ዝ​ዮት ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ፤</verse>
				<verse number="31">ሃያ አራ​ተ​ኛው ለሮ​ማ​ን​ቴ​ዔ​ዜር ለል​ጆ​ቹም ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም ለዐ​ሥራ ሁለቱ ወጣ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="26">
				<verse number="1">በረ​ኞ​ችም እን​ደ​ዚህ ተመ​ደቡ፤ ከቆ​ሬ​ያ​ው​ያን ከአ​ሳፍ ልጆች የቆሬ ልጅ ሜሱ​ላም።</verse>
				<verse number="2">ሜሱ​ላ​ምም ልጆች ነበ​ሩት፤ በኵሩ ዘካ​ር​ያስ፥ ሁለ​ተ​ኛው ይዲ​ኤል፥ ሦስ​ተ​ኛው ዘባ​ድያ፥ አራ​ተ​ኛው የት​ን​ኤል፤</verse>
				<verse number="3">አም​ስ​ተ​ኛው ኤላም፥ ስድ​ስ​ተ​ኛው ይሆ​ሐ​ናን፥ ሰባ​ተ​ኛው ኤሊ​ሆ​ዔ​ናይ።</verse>
				<verse number="4">ዖቤ​ድ​ኤ​ዶ​ምም ልጆች ነበ​ሩት፤ በኵሩ ሰማያ፥ ሁለ​ተ​ኛው ዮዛ​ባት፥ ሦስ​ተ​ኛው ኢዮ​አስ፥ አራ​ተ​ኛው ሣካር፥ አም​ስ​ተ​ኛው ናት​ና​ኤል፤</verse>
				<verse number="5">ስድ​ስ​ተ​ኛው ዓሚ​ኤል፥ ሰባ​ተ​ኛው ይሳ​ኮር፥ ስም​ን​ተ​ኛው ፒላቲ ነበሩ፤ አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባር​ኮ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="6">ለልጁ ለሰ​ማ​ያም ከበ​ኵር ልጁ ከሮሲ ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ እነ​ር​ሱም በአ​ባ​ታ​ቸው ቤት የሠ​ለ​ጠኑ እጅ​ግም ኀያ​ላን ነበሩ።</verse>
				<verse number="7">የሰ​ማያ ልጆች ዖትኒ፥ ራፋ​ኤል፥ ዖቤድ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም ኀያ​ላን የነ​በሩ ኤል​ዛ​ባድ፥ ኤሊሁ፥ ሰማ​ክያ፥ ኢስ​ባ​ኮም።</verse>
				<verse number="8">እነ​ዚህ ሁሉ የዖ​ቤ​ድ​ኤ​ዶም ልጆች ነበሩ፤ እነ​ር​ሱም፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ለማ​ገ​ል​ገል ኀያ​ላን የነ​በሩ የዖ​ቤ​ድ​ኤ​ዶም ልጆች ስድሳ ሁለት ነበሩ።</verse>
				<verse number="9">ለሜ​ሱ​ላ​ምም ኀያ​ላን የነ​በሩ ዐሥራ ስም​ንት ልጆ​ችና ወን​ድ​ሞች ነበ​ሩት።</verse>
				<verse number="10">ከሜ​ራ​ሪም ልጆች ለነ​በ​ረው ለሖሳ ፊተ​ኛ​ውን በር የሚ​ጠ​ብቁ ልጆች ነበ​ሩት፤ አለ​ቃ​ውም ሰምሪ ነበረ፤ በኵር አል​ነ​በ​ረም፤ አባቱ ግን አለቃ አደ​ረ​ገው፤</verse>
				<verse number="11">ሁለ​ተ​ኛ​ውም ኬል​ቅ​ያስ፥ ሦስ​ተ​ኛ​ውም ጥበ​ልያ፥ አራ​ተ​ኛ​ውም ዘካ​ር​ያስ ነበረ፤ የሖሳ ልጆ​ችና ወን​ድ​ሞች ሁሉ ዐሥራ ሦስት ነበሩ።</verse>
				<verse number="12">እንደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ሆነው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ የበ​ረ​ኞች አለ​ቆች በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው የሚ​ጠ​ብቁ እነ​ዚህ ነበሩ።</verse>
				<verse number="13">በበ​ሩም ሁሉ ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ታና​ሹና ታላቁ ተካ​ክ​ለው ዕጣ ተጣ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="14">የም​ሥ​ራ​ቁም በር ዕጣ ለሰ​ሌ​ም​ያና ለዘ​ካ​ርያ ወደቀ። የዮ​አ​ስም ልጆች ለም​ል​ክያ ዕጣ ጣሉ፤ ዕጣ​ውም በሰ​ሜን በኩል ወጣ።</verse>
				<verse number="15">ለአ​ብ​ዲ​ዶም በደ​ቡብ በኩል በዕቃ ቤት አን​ጻር ዕጣ ወጣ።</verse>
				<verse number="16">ለሶ​ፊ​ምና ለሖ​ሳም በም​ዕ​ራብ በኩል በዐ​ቀ​በቱ መን​ገድ ባለው በሸ​ለ​ኬት በር በኩል ጥበቃ በጥ​በቃ ላይ ዕጣ ወጣ።</verse>
				<verse number="17">በም​ሥ​ራቅ በኩል ለየ​ዕ​ለቱ ስድ​ስት፥ በሰ​ሜን በኩል ለየ​ዕ​ለቱ አራት፥ በደ​ቡብ በኩል ለየ​ዕ​ለቱ አራት፥ ለዕቃ ቤትም ሁለት ሁለት ነበሩ።</verse>
				<verse number="18">በኦ​ሳም በም​ዕ​ራብ በኩል በሸ​ለ​ኬት በር ሦስት፥ በም​ሥ​ራቅ በኩል በዐ​ቀ​በቱ በር ከጥ​በቃ በላይ ጥበቃ በቀን ስድ​ስት፥ በሰ​ሜን በኩል አራት፥ በደ​ቡብ በኩል አራት፥ በዕቃ ቤቱ በኩል ተቀ​ባ​ባ​ዮች ሁለት ሁለት፥ በም​ዕ​ራብ በኩል አራት በመ​ተ​ላ​ለ​ፊ​ያ​ውም መን​ገድ ተቀ​ባ​ባ​ዮች ሁለት ሁለት።</verse>
				<verse number="19">ከቆ​ሬና ከሜ​ራሪ ልጆች የነ​በሩ የበ​ረ​ኞች ሰሞን ይህች ናት።</verse>
				<verse number="20">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ሌዋ​ው​ያ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሚ​ሆኑ ቤተ መዛ​ግ​ብ​ትና በን​ዋየ ቅድ​ሳቱ ቤተ መዛ​ግ​ብት ላይ ተሹ​መው ነበር።</verse>
				<verse number="21">የለ​አ​ዳን ልጆች፤ ለለ​አ​ዳን የሆኑ የጌ​ድ​ሶ​ና​ው​ያን ልጆች፥ ለጌ​ድ​ሶ​ና​ዊው ለለ​አ​ዳን የሆኑ፥ የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ይሔ​ኤሊ፤</verse>
				<verse number="22">የይ​ሔ​ኤሊ ልጆች፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በሚ​ሆኑ ቤተ መዛ​ግ​ብት ላይ የነ​በሩ ዜቶም፥ ወን​ድ​ሙም ኢዮ​ኤል ነበረ።</verse>
				<verse number="23">ከእ​ን​በ​ረ​ማ​ው​ያን፥ ከይ​ስ​ዓ​ራ​ው​ያን፥ ከኬ​ብ​ሮ​ና​ው​ያን፥ ከዑ​ዝ​ኤ​ላ​ው​ያን፤</verse>
				<verse number="24">የሙሴ ልጅ የጌ​ር​ሳም ልጅ ሱባ​ኤል በቤተ መዛ​ግ​ብት ላይ ተሾሞ ነበር።</verse>
				<verse number="25">ወን​ድ​ሞ​ቹም፤ ከአ​ል​ዓ​ዛር ልጁ ረዓ​ብያ፥ ልጁም የሳያ፥ ልጁም ኢዮ​ራም፥ ልጁም ዝክሪ፥ ልጁም ሰሎ​ሚት ነበሩ።</verse>
				<verse number="26">ይህ ሰሎ​ሚ​ትና ወን​ድ​ሞቹ፥ ንጉሡ ዳዊ​ትና የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች፥ ሻለ​ቆ​ችና የመቶ አለ​ቆች፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለ​ቆች፥ በቀ​ደ​ሱት በን​ዋየ ቅድ​ሳቱ ቤተ መዛ​ግ​ብት ሁሉ ላይ ተሹ​መው ነበር።</verse>
				<verse number="27">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደስ ሕንጻ ወደ ኋላ እን​ዳ​ይል ዳዊት ከየ​ሀ​ገሩ በማ​ረ​ካ​ቸ​ውና በሰ​በ​ሰ​ባ​ቸው በቀ​ደ​ሳ​ቸ​ውም ላይ የተ​ሾሙ ናቸው።</verse>
				<verse number="28">ነቢዩ ሳሙ​ኤል፥ የቂ​ስም ልጅ ሳኦል፥ የኔ​ርም ልጅ አበ​ኔር፥ የሶ​ር​ህ​ያም ልጅ ኢዮ​አብ የቀ​ደ​ሱት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንዋየ ቅድ​ሳት ሁሉ ከሰ​ሎ​ሚ​ትና ከወ​ን​ድ​ሞቹ እጅ በታች ነበረ።</verse>
				<verse number="29">ከይ​ሰ​ዓ​ራ​ው​ያን ከና​ን​ያና ልጆቹ ጻፎ​ችና ፈራ​ጆች ይሆኑ ዘንድ በው​ጭው ሥራ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ተሾ​መው ነበር።</verse>
				<verse number="30">ከኬ​ብ​ሮ​ና​ው​ያን ሐሳ​ብ​ያና ወን​ድ​ሞቹ፥ ጽኑ​ዓን የነ​በ​ሩት ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ሁሉ፥ ለን​ጉ​ሡም አገ​ል​ግ​ሎት በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በም​ዕ​ራብ በኩል ባለው በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ተሾ​መው ነበር።</verse>
				<verse number="31">ከኬ​ብ​ሮ​ና​ው​ያ​ንም እንደ አባ​ቶች ቤቶች ትው​ል​ዶች የኬ​ብ​ሮ​ና​ው​ያን አለቃ ኤር​ያስ ነበረ። ዳዊት በነ​ገሠ በአ​ር​ባ​ኛው ዓመት ይፈ​ል​ጉ​አ​ቸው ነበረ፤ በእ​ነ​ር​ሱም መካ​ከል በገ​ለ​ዓድ ኢያ​ዜር ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ተገኙ፤</verse>
				<verse number="32">ወን​ድ​ሞ​ቹም ጽኑ​ዓን የነ​በ​ሩት የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። ንጉ​ሡም ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሁሉና በን​ጉሡ ትእ​ዛዝ ሁሉ በሮ​ቤ​ላ​ው​ያ​ንና በጋ​ዳ​ው​ያን፥ በም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ላይ ሹሞች አደ​ረ​ጋ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="27">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆ​ችና የሺህ አለ​ቆች፥ የመቶ አለ​ቆ​ችም ለን​ጉ​ሡና ለን​ጉሡ ትእ​ዛዝ ሁሉ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ሹማ​ምት እንደ ቍጥ​ራ​ቸው በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸው እነ​ዚህ ነበሩ። እነ​ዚ​ህም ክፍ​ሎች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ሃያ አራት ሺህ ሆነው በዓ​መቱ ወራት ሁሉ በየ​ወሩ ይገ​ቡና ይወጡ ነበር።</verse>
				<verse number="2">ለመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በአ​ን​ደ​ኛው ክፍል ላይ የዘ​ብ​ድ​ኤል ልጅ ያሶ​ብ​አም ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።</verse>
				<verse number="3">እር​ሱም ከፋ​ሬስ ልጆች ነበረ፤ ለመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በጭ​ፍራ አለ​ቆች ሁሉ ላይ ተሾሞ ነበር።</verse>
				<verse number="4">በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር ክፍል ላይ የኤቲ ልጅ ዶድያ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሚኮ​ሎት አለቃ ነበር፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።</verse>
				<verse number="5">በሦ​ስ​ተ​ኛው ወር ሦስ​ተ​ኛው የጭ​ፍራ አለቃ የካ​ህኑ የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሽህ ጭፍራ ነበረ።</verse>
				<verse number="6">ይህ በና​ያስ ከሠ​ላ​ሳው መካ​ከል ኀያል ሆኖ በሠ​ላ​ሳው ላይ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ልጁ ዓሚ​ዛ​ባድ ነበረ።</verse>
				<verse number="7">በአ​ራ​ተ​ኛው ወር አራ​ተ​ኛው አለቃ የኢ​ዮ​አብ ወን​ድም አሳ​ሄል ነበረ፤ ከእ​ር​ሱም በኋላ ልጁ ዝባ​ድ​ያና ወን​ድ​ሞቹ ነበሩ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።</verse>
				<verse number="8">በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር አም​ስ​ተ​ኛው አለቃ ይዝ​ራ​ዊው ሰማ​ኦት ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።</verse>
				<verse number="9">በስ​ድ​ስ​ተ​ኛ​ውም ወር ስድ​ስ​ተ​ኛው አለቃ የቴ​ቁ​ሓ​ዊው የአ​ቂስ ልጅ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።</verse>
				<verse number="10">በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ሰባ​ተ​ኛው አለቃ ከኤ​ፍ​ሬም ልጆች የሆነ ፍሎ​ሳ​ዊው ከሊስ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።</verse>
				<verse number="11">በስ​ም​ን​ተ​ኛው ወር ስም​ን​ተ​ኛው አለቃ ከዛ​ራ​ው​ያን የነ​በ​ረው ኩሳ​ታ​ዊው ሲቦ​ካይ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።</verse>
				<verse number="12">በዘ​ጠ​ነ​ኛው ወር ዘጠ​ነ​ኛው አለቃ ከብ​ን​ያ​ማ​ው​ያን የነ​በ​ረው ዓና​ቶ​ታ​ዊው አቢ​ዔ​ዜር ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።</verse>
				<verse number="13">በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር ዐሥ​ረ​ኛው አለቃ ከዛ​ራ​ው​ያን የነ​በ​ረው ነጦ​ፋ​ዊው መዐ​ርኢ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።</verse>
				<verse number="14">በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ወር ዐሥራ አን​ደ​ኛው አለቃ ከኤ​ፍ​ሬም ልጆች የነ​በ​ረው ፍር​ዓ​ቶ​ና​ዊው በና​ያስ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።</verse>
				<verse number="15">በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ወር ዐሥራ ሁለ​ተ​ኛው አለቃ ከጎ​ቶ​ን​ያል ወገን የነ​በ​ረው ነጦ​ፋ​ታ​ዊው ኬል​ዳይ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።</verse>
				<verse number="16">በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ዶች ላይ እነ​ዚህ ነበሩ፦ በሮ​ቤ​ላ​ው​ያን ላይ የዝ​ክሪ ልጅ ኤል​ያ​ዛር አለቃ ነበረ፤ በስ​ም​ዖ​ና​ው​ያን ልጅ የመ​ዓካ ልጅ ሰፋ​ጥ​ያስ ነበረ፤</verse>
				<verse number="17">በሌዊ ወገን ላይ የቀ​ሙ​ኤል ልጅ አሰ​ብያ፤ በአ​ሮን ወገን ላይ ሳዶቅ፤</verse>
				<verse number="18">በይ​ሁዳ ወገን ላይ ከዳ​ዊት ወን​ድ​ሞች ኤል​ያብ፤ በይ​ሳ​ኮር ወገን ላይ የሚ​ካ​ኤል ልጅ ዖምሪ፤</verse>
				<verse number="19">በዛ​ብ​ሎን ወገን ላይ የአ​ብ​ድዩ ልጅ ሶማ​ዒ​ያስ፤ በን​ፍ​ታ​ሌም ወገን ላይ የዖ​ዜ​ሄል ልጅ ኢያ​ሪ​ሙት፤</verse>
				<verse number="20">በኤ​ፍ​ሬም ልጆች ላይ የአ​ዛ​ዝያ ልጅ ሆሴዕ፤ በም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ላይ የፈ​ዳያ ልጅ ኢዩ​ኤል፤</verse>
				<verse number="21">በገ​ለ​ዓድ ምድር ባለው በም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ላይ የዘ​ብ​ድ​ያስ ልጅ ኢዮ​ዳኢ፤ በብ​ን​ያ​ምም ልጆች ላይ የአ​በ​ኔር ልጅ አሳ​ሄል፤</verse>
				<verse number="22">በዳን ወገ​ንም ላይ የኢ​ዮ​ራም ልጅ ዓዛ​ር​ኤል፤ እነ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች አለ​ቆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="23">ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝቡ እስ​ራ​ኤ​ልን እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት ያበዛ ዘንድ ተና​ግሮ ነበ​ርና ዳዊት ከሃያ ዓመት በታች የነ​በ​ሩ​ትን አል​ቈ​ጠ​ረም።</verse>
				<verse number="24">የሶ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አ​ብም መቍ​ጠር ጀመረ፤ ነገር ግን አል​ፈ​ጸ​መም፤ ስለ​ዚህ ነገር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ቍጣ ሆነ፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም በን​ጉሡ በዳ​ዊት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ አል​ተ​ጻ​ፈም።</verse>
				<verse number="25">በን​ጉ​ሡም ቤተ መዛ​ግ​ብት ላይ የዓ​ዳ​ኤል ልጅ ዓዝ​ሞት ሹም ነበረ፤ በሜ​ዳ​ውም፥ በከ​ተ​ሞ​ቹም፥ በመ​ን​ደ​ሮ​ቹም፥ በግ​ን​ቦ​ቹም ቤተ መዛ​ግ​ብት ላይ የዖ​ዝያ ልጅ ዮና​ታን ሹም ነበረ፤</verse>
				<verse number="26">መሬ​ቱን በሚ​ያ​በ​ጃ​ጁ​ትና እር​ሻ​ውን በሚ​ያ​ር​ሱት ላይ የክ​ሉብ ልጅ ዔዝሪ ሹም ነበረ፤</verse>
				<verse number="27">በወ​ይ​ንም ቦታ​ዎች ላይ ራማ​ታ​ዊው ሰሜኢ ሹም ነበረ፤ ለወ​ይ​ንም ጠጅ ዕቃ ቤት በሚ​ሆ​ነው በወ​ይኑ ሰብል ላይ የሳ​ፍ​ኒው ዘብዲ ሹም ነበረ።</verse>
				<verse number="28">በቈ​ላ​ውም ውስጥ ባሉት በወ​ይ​ራ​ውና በሾ​ላው ዛፎች ላይ ጌድ​ራ​ዊው በአ​ል​ሐ​ናን ሹም ነበረ፤ በዘ​ይ​ቱም ቤቶች ላይ ኢዮ​አስ ሹም ነበረ፤</verse>
				<verse number="29">በሳ​ሮ​ንም በሚ​ሰ​ማሩ ከብ​ቶች ላይ ሳሮ​ና​ዊው ሰጥ​ራይ ሹም ነበረ፤ በሸ​ለ​ቆ​ዎ​ቹም ውስጥ በነ​በ​ሩት ከብ​ቶች ላይ የዓ​ድ​ላይ ልጅ ሳፋጥ ሹም ነበረ፤</verse>
				<verse number="30">በግ​መ​ሎ​ቹም ላይ እስ​ማ​ኤ​ላ​ዊው ኤቢ​ያስ ሹም ነበረ፤ በአ​ህ​ዮ​ቹም ላይ ሜሮ​ኖ​ታ​ዊው ኢያ​ድስ ሹም ነበረ፤</verse>
				<verse number="31">በበ​ጎ​ችም ላይ አጋ​ራ​ዊው ያዚዝ ሹም ነበረ። እነ​ዚህ ሁሉ በን​ጉሡ በዳ​ዊት ሀብት ላይ ሹሞች ነበሩ።</verse>
				<verse number="32">አስ​ተ​ዋ​ይና ጸሓፊ የነ​በ​ረው በአ​ባቱ በኩል የዳ​ዊት አጎት ዮና​ታን አማ​ካሪ ነበረ፤ የአ​ክ​ማ​ኔም ልጅ ኢያ​ሔ​ኤል ከን​ጉሡ ልጆች ጋር ነበረ፤</verse>
				<verse number="33">አኪ​ጦ​ፌ​ልም የን​ጉሡ አማ​ካሪ ነበረ። አር​ካ​ዊው ኩሲም የን​ጉሡ አን​ደኛ ወዳጅ ነበረ፤</verse>
				<verse number="34">ከአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልም ቀጥሎ የበ​ና​ያስ ልጅ ዮዳ​ሔና አብ​ያ​ታር ነበሩ፤ ኢዮ​አ​ብም የን​ጉሡ ሠራ​ዊት አለቃ ነበረ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="28">
				<verse number="1">ዳዊ​ትም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አለ​ቆች ሁሉና የፍ​ርድ አለ​ቆ​ችን፥ ንጉ​ሡ​ንም በየ​ተራ የሚ​ጠ​ብ​ቁ​ትን አለ​ቆ​ቹን፥ ሻለ​ቆ​ቹ​ንም፥ የመቶ አለ​ቆ​ቹ​ንም፥ በን​ጉ​ሡና በል​ጆቹ ሀብ​ትና ንብ​ረት ላይ፥ መባ ባለ​በት ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን ጃን​ደ​ረ​ቦ​ች​ንም፥ ኀያ​ላ​ኑ​ንና ሰል​ፈ​ኞ​ቹን ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሰበ​ሰበ።</verse>
				<verse number="2">ንጉ​ሡም ዳዊት በጉ​ባ​ኤው መካ​ከል ቆሞ እን​ዲህ አለ፥ “ወን​ድ​ሞቼና ሕዝቤ ሆይ፥ ስሙኝ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለቃል ኪዳኑ ታቦ​ትና ለአ​ም​ላ​ካ​ችን እግር ማረ​ፊያ የዕ​ረ​ፍት ቤት ለመ​ሥ​ራት አሳብ በልቤ መጣ​ብኝ፤ ለዚ​ህም ሥራ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ውን አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን፦ የሰ​ልፍ ሰው ነህና፥ ብዙ ደምም አፍ​ስ​ሰ​ሃ​ልና ስሜ የሚ​ጠ​ራ​በ​ትን ቤት አት​ሠ​ራም ብሎ​ኛል።</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ የዘ​ለ​ዓ​ለም ንጉሥ እሆን ዘንድ ከአ​ባቴ ቤት ሁሉ መር​ጦ​ኛል፤ ይሁ​ዳ​ንም አለቃ ይሆን ዘንድ መር​ጦ​ታል፤ ከይ​ሁ​ዳም ቤት የአ​ባ​ቴን ቤት መር​ጦ​አል፤ ከአ​ባ​ቴም ልጆች መካ​ከል በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ ያነ​ግ​ሠኝ ዘንድ እኔን ሊመ​ር​ጠኝ ወደደ።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብዙ ልጆች ሰጥ​ቶ​ኛ​ልና ከል​ጆቼ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ዙፋን ላይ ተቀ​ምጦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ይነ​ግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎ​ሞ​ንን መር​ጦ​ታል።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፦ ልጅ ይሆ​ነኝ ዘንድ መር​ጬ​ዋ​ለ​ሁና፥ እኔም አባት እሆ​ነ​ዋ​ለ​ሁና ልጅህ ሰሎ​ሞን ቤቴ​ንና አደ​ባ​ባ​ዮ​ቼን ይሠ​ራል።</verse>
				<verse number="7">ትእ​ዛ​ዜ​ንና ፍር​ዴ​ንም መጠ​በቅ ቢች​ልና እንደ ዛሬው ቢጸና መን​ግ​ሥ​ቱን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጸ​ና​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">አሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጉባኤ እስ​ራ​ኤል ሁሉ እያዩ፥ አም​ላ​ካ​ች​ንም እየ​ሰማ፥ ይህ​ችን መል​ካ​ሚ​ቱን ምድር ትወ​ርሱ ዘንድ፥ ለል​ጆ​ቻ​ች​ሁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታወ​ር​ሱ​አት ዘንድ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ሁሉ ጠብቁ፤ ፈል​ጉም።</verse>
				<verse number="9">“አን​ተም ልጄ ሰሎ​ሞን ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብን ሁሉ ይመ​ረ​ም​ራ​ልና፥ የነ​ፍ​ስ​ንም አሳብ ሁሉ ያው​ቃ​ልና የአ​ባ​ቶ​ች​ህን አም​ላክ ዕወቅ፤ በፍ​ጹም ልብና በነ​ፍ​ስህ ፈቃ​ድም ተገ​ዛ​ለት፤ ብት​ፈ​ል​ገው ታገ​ኘ​ዋ​ለህ፤ ብት​ተ​ወው ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይተ​ው​ሃል።</verse>
				<verse number="10">አሁ​ንም፥ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ቅ​ደስ የሚ​ሆን ቤትን ትሠራ ዘንድ መር​ጦ​ሃ​ልና ጠን​ክ​ረህ ፈጽ​መው።”</verse>
				<verse number="11">ዳዊ​ትም ለመ​ቅ​ደሱ ወለል፥ ለቤ​ቱም፥ ለቤተ መዛ​ግ​ብ​ቱም፥ ለደ​ር​ቡና ለው​ስ​ጡም ጓዳ​ዎች፥ ለስ​ር​የ​ቱም መክ​ደኛ መቀ​መጫ ምሳ​ሌ​ውን ለልጁ ለሰ​ሎ​ሞን ሰጠው።</verse>
				<verse number="12">ደግ​ሞም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባ​ዮ​ችና በዙ​ሪ​ያው ለሚ​ሆኑ ጓዳ​ዎች፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ለሚ​ሆኑ ቤተ መዛ​ግ​ብት፥ ለን​ዋየ ቅድ​ሳ​ቱም ለሚ​ሆኑ ዕቃ ቤቶች፥ ለቀ​ሩ​ትም በመ​ን​ፈሱ ላሰ​በው ሁሉ ምሳ​ሌን ሰጠው።</verse>
				<verse number="13">የካ​ህ​ና​ቱ​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑ​ንም ክፍ​ላ​ቸ​ውን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በት ሥራ ሁሉ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በት ዕቃ ሁሉ፥ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ ለሚ​ሆ​ነ​ውም፥</verse>
				<verse number="14">ለወ​ርቁ ዕቃ ወር​ቁን በሚ​ዛን ሰጠው፤ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ ለሚ​ሆ​ነ​ውም ለብር ዕቃ ሁሉ ብሩን በሚ​ዛን ሰጠው፤</verse>
				<verse number="15">ለወ​ር​ቁም መቅ​ረ​ዞ​ችና ለቀ​ን​ዲ​ሎ​ችም ወር​ቁን በየ​መ​ቅ​ረ​ዙና በየ​ቀ​ን​ዲሉ በሚ​ዛን ሰጠው፤ ለብ​ሩም መቅ​ረ​ዞች እንደ መቅ​ረዙ ሁሉ ሥራ ብሩን በየ​መ​ቅ​ረ​ዙና በየ​ቀ​ን​ዲሉ በሚ​ዛን ሰጠው፤</verse>
				<verse number="16">ዳግ​መ​ኛም ለገጹ ኅብ​ስት ገበ​ታ​ዎች ወር​ቁን በሚ​ዛን ለገ​በ​ታ​ዎቹ ሁሉ፥ ብሩ​ንም ለብሩ ገበ​ታ​ዎች እን​ደ​ዚሁ ሰጠው፤</verse>
				<verse number="17">ለሥጋ ሜን​ጦ​ዎ​ቹና ለድ​ስ​ቶቹ፥ ለመ​ጠጥ ቍር​ባን መቅ​ጃ​ዎ​ቹም ጥሩ​ውን ወርቅ፥ ለወ​ር​ቁም ጽዋ​ዎች ወር​ቁን በየ​ጽ​ዋው ሁሉ በሚ​ዛን ሰጠው፤ ለብ​ሩም ጽዋ​ዎች ብሩን በየ​ጽ​ዋው በሚ​ዛን ሰጠው።</verse>
				<verse number="18">ለዕ​ጣ​ኑም መሠ​ዊያ ጥሩ​ውን ወርቅ በሚ​ዛን፥ ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ዘር​ግ​ተው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት የሸ​ፈ​ኑ​ትን የኪ​ሩ​ቤ​ልን የወ​ርቅ ሰረ​ገላ ምሳሌ አሳ​የው።</verse>
				<verse number="19">ዕው​ቀት እንደ ተሰ​ጠው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ይሠራ ዘንድ ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ የተ​ጻ​ፈ​ውን ለልጁ ለሰ​ሎ​ሞን ሰጠው።</verse>
				<verse number="20">ዳዊ​ትም ልጁን ሰሎ​ሞ​ንን፥ “ጠን​ክር፤ ሰው ሁን፤ አይ​ዞህ፥ አድ​ር​ገ​ውም፤ አም​ላኬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና አት​ፍራ፤ አት​ደ​ን​ግ​ጥም፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ሆ​ነ​ውን ሥራ ሁሉ እስ​ክ​ት​ፈ​ጽም ድረስ እርሱ አይ​ተ​ው​ህም፤ አይ​ጥ​ል​ህ​ምም። እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሕንጻ ምሳሌ፥ የአ​ደ​ባ​ባዩ፥ የቤተ መዛ​ግ​ብቱ፥ የሰ​ገ​ነቱ፥ የው​ስጡ ቤተ መዛ​ግ​ብት፥ የስ​ር​የት ቤቱና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ምሳሌ።</verse>
				<verse number="21">እነ​ሆም፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ የሚ​ሆኑ የካ​ህ​ና​ትና የሌ​ዋ​ው​ያን ክፍ​ሎች በዚህ አሉ፤ ለሁ​ሉም ዓይ​ነት አገ​ል​ግ​ሎ​ትና ሥራ በጥ​በ​ብና በነ​ፍሱ ፈቃድ የሚ​ሠራ ሁሉ ከአ​ንተ ጋር ይሆ​ናል፤ አለ​ቆ​ችና ሕዝ​ቡም ሁሉ ፈጽ​መው ይታ​ዘ​ዙ​ሃል” አለው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="29">
				<verse number="1">ንጉሡ ዳዊ​ትም ለጉ​ባ​ኤው ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ​ውን የመ​ረ​ጠው ልጄ ሰሎ​ሞን ገና ለጋ ብላ​ቴና ነው፤ ሕን​ጻው ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላክ ነው እንጂ ለሰው አይ​ደ​ለ​ምና ሥራው ታላቅ ነው።</verse>
				<verse number="2">እኔም እንደ ጉል​በቴ ሁሉ ለአ​ም​ላኬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወር​ቅን፥ ብርን፥ ናስን፥ ብረ​ትን፥ እን​ጨ​ትን፥ ደግ​ሞም መረ​ግ​ድ​ንና በፈ​ርጥ የሚ​ገባ ድን​ጋ​ይን፥ የሚ​ለ​ጠፍ ድን​ጋ​ይን፥ ልዩ ልዩ መልክ ያለ​ው​ንም ድን​ጋይ፥ የከ​በ​ረ​ው​ንም ድን​ጋይ ከየ​ዓ​ይ​ነቱ፥ ብዙም እብነ በረድ አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">ከዚ​ህም በላይ ደግሞ የአ​ም​ላ​ኬን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ስለ ወደ​ድሁ፥ ለመ​ቅ​ደሱ ከሰ​በ​ሰ​ብ​ሁት ሁሉ ሌላ የግል ገን​ዘቤ የሚ​ሆን ወር​ቅና ብር አለ​ኝና እነሆ፥ ለአ​ም​ላኬ ቤት ሰጥ​ቼ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ግን​ቦች ይለ​በ​ጡ​በት ዘንድ ከኦ​ፌር ወርቅ ሦስት ሺህ መክ​ሊት ወርቅ፥ ሰባት ሺህ መክ​ሊ​ትም ጥሩ ብር፤</verse>
				<verse number="5">በሠ​ራ​ተ​ኞች እጅ ለሚ​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ ለወ​ርቁ ዕቃ ወር​ቁን፥ ለብ​ሩም ዕቃ ብሩን ሰጥ​ቻ​ለሁ። ዛሬ በዚች ቀን በፈ​ቃዱ አገ​ል​ግ​ሎ​ቱን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ፈ​ጽም ማን ነው?”</verse>
				<verse number="6">የአ​ባ​ቶ​ችም ቤቶች አለ​ቆች፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አለ​ቆች፥ ሻለ​ቆ​ችም፥ የመቶ አለ​ቆ​ችም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሥራ የተ​ሾ​ሙና የን​ጉሡ ግን​በ​ኞች በፈ​ቃ​ዳ​ቸው አቀ​ረቡ።</verse>
				<verse number="7">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ሥራ አም​ስት ሺህ መክ​ሊት ወር​ቅና ዐሥር ሺህ ዳሪክ፥ ዐሥር ሺህም መክ​ሊት ብር፥ ዐሥራ ስም​ንት ሺህም መክ​ሊት ናስ፥ መቶ ሺህም መክ​ሊት ብረት ሰጡ።</verse>
				<verse number="8">የከ​በረ ዕን​ቍም ያላ​ቸው ሰዎች ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ለሆ​ነው ቤተ መዛ​ግ​ብት በጌ​ድ​ሶ​ና​ዊው በኢ​ዩ​ኤል እጅ ሰጡ።</verse>
				<verse number="9">ሕዝ​ቡም ፈቅ​ደው ሰጥ​ተ​ዋ​ልና፥ በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃ​ዳ​ቸው አቅ​ር​በ​ዋ​ልና ደስ አላ​ቸው፤ ንጉ​ሡም ዳዊት ደግሞ ታላቅ ደስታ ደስ አለው።</verse>
				<verse number="10">ንጉሡ ዳዊ​ትም በጉ​ባ​ኤው ሁሉ ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገነ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አባ​ታ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ቡሩክ ነህ።</verse>
				<verse number="11">አቤቱ፥ በሰ​ማ​ይና በም​ድር ያለው ሁሉ የአ​ንተ ነውና ታላ​ቅ​ነ​ትና ኀይል፥ ክብ​ርም፥ ድልና ጽንዕ የአ​ንተ ነው፤ ነገ​ሥ​ታ​ቱና ሕዝቡ ሁሉ በፊ​ትህ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="12">ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትና ክብር ከአ​ንተ ዘንድ ነው፤ አቤቱ፥ አን​ተም ሁሉን ትገ​ዛ​ለህ፤ የሥ​ል​ጣን ሁሉ ጌታ ነህ፤ ኀይ​ልና ብር​ታት በእ​ጅህ ነው፤ ኀያል ነህ፤ ታላቅ ለማ​ድ​ረግ፥ ለሁ​ሉም ኀይ​ልን ለመ​ስ​ጠት ዓለ​ምን ሁሉ በእ​ጅህ የያ​ዝህ ነህ።</verse>
				<verse number="13">አሁ​ንም እን​ግ​ዲህ፥ አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ እን​ገ​ዛ​ል​ሃ​ለን፤ ለክ​ቡር ስም​ህም ምስ​ጋና እና​ቀ​ር​ባ​ለን።</verse>
				<verse number="14">ሁሉ ከአ​ንተ ዘንድ ነውና፥ ከእ​ጅ​ህም የተ​ቀ​በ​ል​ነ​ውን ሰጥ​ተ​ን​ሃ​ልና ይህን ያህል ችለን ልና​ቀ​ር​ብ​ልህ እኔ ማን ነኝ? ሕዝ​ቤስ ማን ነው?</verse>
				<verse number="15">አባ​ቶ​ቻ​ችን ስደ​ተ​ኞች እንደ ነበሩ እኛ በፊ​ትህ ስደ​ተ​ኞ​ችና መጻ​ተ​ኞች ነን፤ ዘመ​ና​ች​ንም በም​ድር ላይ እንደ ጥላ ናት፤ አት​ጸ​ና​ምም።</verse>
				<verse number="16">አቤቱ አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ለቅ​ዱስ ስምህ ቤት እሠራ ዘንድ ይህ ያዘ​ጋ​ጀ​ሁት ባለ​ጠ​ግ​ነት ሁሉ ከእ​ጅህ የመጣ ነው፤ ሁሉም የአ​ንተ ነው።</verse>
				<verse number="17">አም​ላኬ ሆይ፥ ልብን እን​ደ​ም​ት​መ​ረ​ምር፥ ጽድ​ቅ​ንም እን​ደ​ም​ት​ወ​ድድ አው​ቃ​ለሁ፤ እኔም በልቤ ቅን​ነ​ትና በፈ​ቃዴ ይህን ሁሉ አቅ​ር​ቤ​አ​ለሁ፤ አሁ​ንም በዚህ ያለው ሕዝ​ብህ በፈ​ቃዱ እን​ዳ​ቀ​ረ​በ​ልህ በደ​ስታ አይ​ቻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="18">አቤቱ፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐቅ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ሆይ፥ ይህን አሳብ በሕ​ዝ​ብህ ልብ ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጠብቅ፤ ልባ​ቸ​ው​ንም ወደ አንተ አቅና።</verse>
				<verse number="19">ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንም ያደ​ርግ ዘንድ፥ ምስ​ክ​ር​ህ​ንም፥ ሥር​ዐ​ት​ህ​ንም ይጠ​ብቅ ዘንድ፥ ያዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ለ​ት​ንም ቤት ይሠራ ዘንድ ለልጄ ለሰ​ሎ​ሞን ቅን ልብን ስጠው።”</verse>
				<verse number="20">ዳዊ​ትም ጉባ​ኤ​ውን ሁሉ፥ “አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ” አላ​ቸው። ጉባ​ኤ​ውም ሁሉ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ፥ በጕ​ል​በ​ታ​ቸ​ውም ተን​በ​ር​ክ​ከው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገዱ፤ ደግ​ሞም ለን​ጉሡ።</verse>
				<verse number="21">በነ​ጋ​ውም ዳዊት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት ሠዋ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቀ​ረበ፤ አንድ ሺህ ወይ​ፈን፥ አንድ ሺህም አውራ በጎች፥ አንድ ሺህም የበግ ጠቦ​ቶች፥ የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንም፥ ስለ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ብዙ መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ።</verse>
				<verse number="22">በዚ​ያም ቀን በታ​ላቅ ደስታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሉ፥ ጠጡም። የዳ​ዊ​ት​ንም ልጅ ሰሎ​ሞ​ንን ሁለ​ተኛ ጊዜ አነ​ገ​ሡት፤ እር​ሱ​ንም ንጉሥ ይሆን ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀቡት፤ ሳዶ​ቅም በካ​ህ​ናት ላይ ተሾመ።</verse>
				<verse number="23">ሰሎ​ሞ​ንም በአ​ባቱ በዳ​ዊት ዙፋን ላይ ተቀ​መጠ፤ በሁ​ሉም ዘንድ ተወ​ዳጅ ሆነ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ታዘ​ዙ​ለት።</verse>
				<verse number="24">አለ​ቆ​ቹም ሁሉ፥ ኀያ​ላ​ኑም፥ ደግ​ሞም የን​ጉሡ የአ​ባቱ የዳ​ዊት ልጆች ሁሉ ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን ተገ​ዙ​ለት።</verse>
				<verse number="25">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰሎ​ሞ​ንን በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት እጅግ አገ​ነ​ነው፤ ከእ​ርሱ በፊ​ትም ለነ​በ​ሩት ነገ​ሥ​ታት ያል​ሆ​ነ​ውን የመ​ን​ግ​ሥት ክብር ሰጠው።</verse>
				<verse number="26">የእ​ሴ​ይም ልጅ ዳዊት በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ አርባ ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="27">ሰባት ዓመት በኬ​ብ​ሮን፥ ሠላሳ ሦስ​ትም ዓመት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነገሠ።</verse>
				<verse number="28">ዕድ​ሜም፥ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትም፥ ክብ​ርም ጠግቦ በመ​ል​ካም ሽም​ግ​ልና ሞተ፤ ልጁም ሰሎ​ሞን በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።</verse>
				<verse number="29">የን​ጉ​ሡም የዳ​ዊት የፊ​ተ​ኛ​ውና የኋ​ለ​ኛው ነገር፥ እነሆ፥ በባ​ለ​ራ​እዩ በሳ​ሙ​ኤል ታሪክ፥ በነ​ቢ​ዩም በና​ታን ታሪክ፥ በባለ ራእ​ዩም በጋድ ታሪክ ተጽ​ፎ​አል።</verse>
				<verse number="30">እን​ደ​ዚ​ሁም የመ​ን​ግ​ሥቱ ነገ​ርና ኀይሉ ሁሉ በእ​ር​ሱም፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም፥ በም​ድ​ርም መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ ያለ​ፉት ዘመ​ናት ተጽ​ፈ​ዋል።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="14">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">የዳ​ዊት ልጅ ሰሎ​ሞ​ንም በመ​ን​ግ​ሥቱ በረታ፤ አም​ላ​ኩም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ እጅ​ግም አከ​በ​ረው፤ አገ​ነ​ነ​ውም።</verse>
				<verse number="2">ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ ለሻ​ለ​ቆች ለመቶ አለ​ቆ​ችም፥ ለፈ​ራ​ጆ​ችም፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ዘንድ ለነ​በሩ መሳ​ፍ​ንት ሁሉ፥ ለአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ሁሉ ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="3">ሰሎ​ሞ​ንም ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪያ ሙሴ በም​ድረ በዳ የሠ​ራው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ስ​ክር ድን​ኳን በዚያ ነበ​ረና በገ​ባ​ዖን ወዳ​ለው የኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ ሄዱ።</verse>
				<verse number="4">ዳዊት ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ከቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም አወ​ጣት። ለእ​ርሷ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ድን​ኳን አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ላት ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="5">የሆ​ርም ልጅ የኡሪ ልጅ ባስ​ል​ኤል የሠ​ራው የናስ መሠ​ዊያ በዚያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪያ ፊት ነበረ፤ ሰሎ​ሞ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጉባኤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ይፈ​ል​ጓት ነበር።</verse>
				<verse number="6">ሰሎ​ሞ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በድ​ን​ኳኑ አጠ​ገብ ወዳ​ለው ወደ ናሱ መሠ​ዊያ ወጣ፤ በዚ​ያም አንድ ሺህ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ።</verse>
				<verse number="7">በዚ​ያ​ችም ሌሊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰ​ሎ​ሞን ታየው፥ “የም​ሰ​ጥ​ህን ከእኔ ለምን” አለው።</verse>
				<verse number="8">ሰሎ​ሞ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ከአ​ባቴ ከዳ​ዊት ጋር ታላቅ ምሕ​ረ​ትን አድ​ር​ገ​ሃል፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ አን​ግ​ሠ​ኸ​ኛል።</verse>
				<verse number="9">አሁ​ንም አቤቱ አም​ላኬ፥ ቍጥሩ እንደ ምድር አሸዋ በሆ​ነው በብዙ ሕዝብ ላይ አን​ግ​ሠ​ኸ​ኛ​ልና ስምህ የታ​መነ ይሁን።</verse>
				<verse number="10">አሁ​ንም በዚህ ሕዝብ ፊት እወ​ጣና እገባ ዘንድ ጥበ​ብ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን ስጠኝ፤ በዚህ በታ​ላቅ ሕዝብ ላይ መፍ​ረድ የሚ​ቻ​ለው የለ​ምና።”</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰሎ​ሞ​ንን አለው፥ “ይህ በል​ብህ ነበ​ረና፥ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትን፥ ሀብ​ትን፥ ክብ​ርን፥ የጠ​ላ​ቶ​ች​ህ​ንም ነፍስ፥ ረጅ​ምም ዕድ​ሜን አል​ለ​መ​ን​ህም፤ ነገር ግን ባነ​ገ​ሥ​ሁህ በሕ​ዝቤ ላይ ትፈ​ርድ ዘንድ ጥብ​ብ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን ለራ​ስህ ለም​ነ​ሃል።</verse>
				<verse number="12">ጥበ​ብ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ። ካንተ በፊት ለነ​በሩ ነገ​ሥ​ታት ያል​ተ​ሰ​ጠ​ውን፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ለሚ​ነሡ የማ​ይ​ሰ​ጠ​ውን ብል​ፅ​ግ​ናን፥ ገን​ዘ​ብ​ንና ክብ​ርን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="13">ሰሎ​ሞ​ንም በገ​ባ​ዖን ካለው ኮረ​ብታ ከም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ነገሠ።</verse>
				<verse number="14">ሰሎ​ሞ​ንም ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ሰበ​ሰበ፤ አንድ ሺህ አራት መቶ ሰረ​ገ​ሎች፥ ዐሥራ ሁለት ሺህም ፈረ​ሰ​ኞች ነበ​ሩት፤ በሰ​ረ​ገ​ሎች ከተ​ሞ​ችም አስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው። ሕዝ​ቡም ከን​ጉሡ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነበሩ።</verse>
				<verse number="15">ንጉ​ሡም ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ ድን​ጋይ፥ የዝ​ግ​ባ​ንም እን​ጨት በብ​ዛት በቆላ እን​ደ​ሚ​ገኝ ሾላ በይ​ሁዳ አኖረ።</verse>
				<verse number="16">የሰ​ሎ​ሞን ፈረ​ሶች መምጫ ከግ​ብ​ፅና ከቴ​ቁሄ ምድር ነበር። በዋጋ ገዝ​ተው ከቴ​ቁሄ የሚ​ያ​መ​ጡ​አ​ቸ​ውም ከሀ​ገር ሽማ​ግ​ሌ​ዎች የሆኑ የሰ​ሎ​ሞን ነጋ​ዴ​ዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="17">ሄደ​ውም ከግ​ብፅ አንድ ሰረ​ገላ በስ​ድ​ስት መቶ ብር፥ አን​ድ​ንም ፈረስ በመቶ አምሳ ሰቅል ብር አመጡ፤ እን​ዲ​ሁም ለኬ​ጢ​ያ​ው​ያ​ንና ለሦ​ርያ ነገ​ሥ​ታት ሁሉ በየ​ተ​ራ​ቸው ያመ​ጡ​ላ​ቸው ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት፥ ለራ​ሱም ቤተ መን​ግ​ሥት ልሥራ አለ።</verse>
				<verse number="2">ሰሎ​ሞ​ንም የሚ​ሸ​ከ​ሙ​ትን ሰባ ሺህ፥ ከተ​ራ​ሮ​ችም ድን​ጋ​ዮ​ችን የሚ​ጠ​ር​ቡ​ትን ሰማ​ንያ ሺህ፥ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን ሦስት ሺህ ስድ​ስት መቶ ሰዎች ሰበ​ሰበ።</verse>
				<verse number="3">ሰሎ​ሞ​ንም እን​ዲህ ሲል ወደ ጢሮስ ንጉሥ ወደ ኪራም ላከ፥ “ከአ​ባቴ ከዳ​ዊት ጋር እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ፥ የሚ​ቀ​መ​ጥ​በ​ት​ንም ቤት ይሠራ ዘንድ የዝ​ግባ እን​ጨት እንደ ላክ​ህ​ለት፥ እን​ዲሁ ለእኔ አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="4">እነሆ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ለዘ​ለ​ዓ​ለም እንደ ታዘ​ዘው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የጣ​ፋ​ጩን ሽቱ ዕጣን ለማ​ጠን፥ የገ​ጹ​ንም ኅብ​ስት ለማ​ኖር፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት በጥ​ዋ​ትና በማታ፥ በሰ​ን​በ​ታ​ቱም፥ በመ​ባ​ቻ​ዎ​ቹም፥ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ላት ለማ​ቅ​ረብ እኔ ልጁ ለአ​ም​ላኬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት እሠ​ራ​ለሁ፤ እር​ሱ​ንም እቀ​ድ​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ማ​ል​ክት ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነውና የም​ሠ​ራው ቤት ታላቅ ነው።</verse>
				<verse number="6">ነገር ግን ሰማ​ይና ከሰ​ማ​ያት በላይ ያለ ሰማይ ክብ​ሩን ይሸ​ከም ዘንድ አይ​ች​ል​ምና ለእ​ርሱ ቤት ይሠራ ዘንድ ማን ይች​ላል? በፊቱ ዕጣን ከማ​ጠን በቀር ቤት እሠ​ራ​ለት ዘንድ እኔ ማን ነኝ?</verse>
				<verse number="7">አሁ​ንም በወ​ር​ቅና በብር፥ በና​ስና በብ​ረት፥ በሐ​ም​ራ​ዊና በቀይ፥ በሰ​ማ​ያ​ዊም ግምጃ መለ​በጥ የሚ​ች​ልና፥ አባቴ ዳዊት ካዘ​ጋ​ጃ​ቸው በእኔ ዘንድ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ካሉት ብል​ሃ​ተ​ኞች ጋር ቅርጽ ማው​ጣት የሚ​ያ​ውቅ ብል​ሃ​ተኛ ሰውን ላክ​ልኝ።</verse>
				<verse number="8">ደግ​ሞም አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ከሊ​ባ​ኖስ እን​ጨት መቍ​ረጥ እን​ዲ​ያ​ውቁ እኔ አው​ቃ​ለ​ሁና ከሊ​ባ​ኖስ የዝ​ግ​ባና የጥድ፥ የሰ​ን​ደ​ልም እን​ጨት ላክ​ልኝ።</verse>
				<verse number="9">የም​ሠ​ራ​ውም ቤት እጅግ ታላ​ቅና ክቡር ይሆ​ና​ልና ብዙ እን​ጨት ያዘ​ጋ​ጁ​ልኝ ዘንድ፥ እነሆ፥ አገ​ል​ጋ​ዮች ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ጋር ይወ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="10">እነ​ሆም፥ እን​ጨ​ቱን ለሚ​ቈ​ርጡ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ሃያ ሺህ የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ የተ​በ​ጠረ ስንዴ፥ ሃያ ሺህም የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ገብስ፥ ሃያ ሺህም የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ የወ​ይን ጠጅ፥ ሃያ ሺህም የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ ዘይት በነጻ እሰ​ጣ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="11">የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራ​ምም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ወድ​ዶ​አ​ልና በላ​ያ​ቸው አነ​ገ​ሠህ” ሲል ለሰ​ሎ​ሞን ጻፈ​ለት።</verse>
				<verse number="12">የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራ​ምም ደግሞ አለ፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ለመ​ን​ግ​ሥ​ቱም ቤት ይሠራ ዘንድ ጥበ​በ​ኛና ብል​ሃ​ተኛ፥ አስ​ተ​ዋ​ይም ልጅ ለን​ጉሡ ለዳ​ዊት የሰጠ፥ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን የፈ​ጠረ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ ይሁን።</verse>
				<verse number="13">አሁ​ንም ብል​ሃ​ተ​ኛና አስ​ተ​ዋይ ሰው አቢ​ኪ​ራ​ምን ልኬ​ል​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">እናቱ ከዳን ልጆች ናት፤ አባ​ቱም የጢ​ሮስ ሰው ነው፤ በወ​ር​ቅና በብር፥ በና​ስና በብ​ረት፥ ድን​ጋ​ዩ​ንና እን​ጨ​ቱን መለ​በጥ፥ ሐም​ራ​ዊ​ው​ንና ሰማ​ያ​ዊ​ውን፥ ቀዩ​ንም ግምጃ፥ ጥሩ​ው​ንም በፍታ መሥ​ራት፥ ቅር​ጽም፥ ሌላም ነገር ሁሉ ማድ​ረግ ያው​ቃል። ከብ​ል​ሃ​ተ​ኞ​ችህ ጋር ከጌ​ታ​ዬም ከአ​ባ​ትህ ከዳ​ዊት ብል​ሃ​ተ​ኞች ጋር ሥራ ብለህ የም​ት​ሰ​ጠ​ውን ሁሉ አስቦ መሥ​ራት ይች​ላል።</verse>
				<verse number="15">አሁ​ንም ጌታዬ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ስን​ዴ​ው​ንና ገብ​ሱን ዘይ​ቱ​ንና የወ​ይን ጠጁን ወደ አገ​ል​ጋ​ዮቹ ይላክ፤</verse>
				<verse number="16">እኛም ከሊ​ባ​ኖስ የም​ት​ሻ​ውን ያህል እን​ጨት እን​ቈ​ር​ጣ​ለን፤ በታ​ን​ኳም አድ​ር​ገን በባ​ሕር ላይ ወደ አንተ ወደ ኢዮጴ እን​ል​ካ​ለን፤ አን​ተም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ታስ​ወ​ስ​ደ​ዋ​ለህ።”</verse>
				<verse number="17">ሰሎ​ሞ​ንም አባቱ ዳዊት ከቈ​ጠ​ራ​ቸው ጋር ያል​ተ​ቈ​ጠሩ በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር የነ​በ​ሩ​ትን መጻ​ተ​ኞች ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ ቍጠ​ራ​ቸ​ውም መቶ ኀምሳ ሦስት ሺህ ስድ​ስት መቶ ሆኖ ተገኘ።</verse>
				<verse number="18">ከእ​ነ​ር​ሱም የሚ​ሸ​ከ​ሙ​ትን ሰባ ሺህ፥ በተ​ራ​ሮ​ቹም ላይ የሚ​ጠ​ር​ቡ​ትን ሰማ​ንያ ሺህ፥ በሕ​ዝ​ቡም ሥራ ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን ሦስት ሺህ ስድ​ስት መቶ አደ​ረገ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ሰሎ​ሞ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባቱ ለዳ​ዊት በተ​ገ​ለ​ጠ​በት በአ​ሞ​ሪያ ተራራ ዳዊት ባዘ​ጋ​ጀው ስፍራ በኢ​ያ​ቡ​ሳ​ዊው በኦ​ርና አው​ድማ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መሥ​ራት ጀመረ።</verse>
				<verse number="2">በነ​ገ​ሠም በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር መሥ​ራት ጀመረ።</verse>
				<verse number="3">ሰሎ​ሞ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ይሠራ ዘንድ የጣ​ለው መሠ​ረት ይህ ነው፤ ርዝ​መ​ቱም በዱ​ሮው ስፍር ስድሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="4">በቤ​ቱም ፊት የነ​በ​ረው ወለል ርዝ​መቱ እንደ ቤቱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ቁመ​ቱም መቶ ሃያ ክንድ ነበረ፤ ውስ​ጡ​ንም በጥሩ ወርቅ ለበ​ጠው።</verse>
				<verse number="5">ታላ​ቁ​ንም ቤት በዝ​ግባ እን​ጨት ከደ​ነው፤ በጥ​ሩም ወርቅ ለበ​ጠው፤ የዘ​ን​ባ​ባና የሰ​ን​ሰ​ለት አም​ሳ​ልም ቀረ​ጸ​በት።</verse>
				<verse number="6">ቤቱ​ንም በከ​በ​ረና በተ​መ​ረጠ ዕንቍ፥ በወ​ር​ቅም አስ​ጌ​ጠው፤ ወር​ቁም የፋ​ሩ​ሔም ወርቅ ነበረ።</verse>
				<verse number="7">ቤቱ​ንም፥ ሰረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም፥ መድ​ረ​ኮ​ቹ​ንም፥ ግን​ቦ​ቹ​ንም፥ ደጆ​ቹ​ንም በወ​ርቅ ለበጠ፤ በግ​ን​ቦ​ቹም ላይ ኪሩ​ቤ​ልን ቀረጸ።</verse>
				<verse number="8">ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑ​ንም ሠራ፤ ርዝ​መ​ቱም እንደ ቤቱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ክንድ ነበረ፤ ስድ​ስት መቶ መክ​ሊት በሚ​ያ​ህል በጥሩ ወር​ቅም ኪሩ​ቤ​ልን ለበ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">የም​ስ​ማ​ሮ​ቹም ሚዛን ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አምሳ ሰቅል ወርቅ ነበረ። የደ​ር​ቡ​ንም ጓዳ​ዎች በወ​ርቅ ለበጠ።</verse>
				<verse number="10">በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ንም ውስጥ ከእ​ን​ጨት ሥራ ሁለ​ቱን ኪሩ​ቤል ሠራ፤ በወ​ር​ቅም ለበ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">የኪ​ሩ​ቤ​ልም ክን​ፎች ሃያ ክንድ ሙሉ ተዘ​ር​ግ​ተው ነበር፤ የአ​ንዱ የኪ​ሩብ ክንፍ ርዝ​መት አም​ስት ክንድ ነበረ፤ የቤ​ቱ​ንም ግንብ ይነካ ነበር፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ክንፍ ርዝ​መት አም​ስት ክንድ ነበረ፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ው​ንም ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር።</verse>
				<verse number="12">የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ኪሩብ አንዱ ክንፍ አም​ስት ክንድ ነበረ፤ የቤ​ቱ​ንም ግንብ ይነካ ነበር፤ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ክንፍ አም​ስት ክንድ ነበረ፤ የሌ​ላ​ው​ንም ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር።</verse>
				<verse number="13">የእ​ነ​ዚ​ህም ኪሩ​ቤል ክን​ፎች ሃያ ክንድ ሙሉ ተዘ​ር​ግ​ተው ነበር፤ በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም ቆመው ነበር፤ ፊቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ይመ​ለ​ከቱ ነበር።</verse>
				<verse number="14">ከሰ​ማ​ያ​ዊ​ውም፥ ከሐ​ም​ራ​ዊ​ውም፥ ከቀ​ዩም ሐር፥ ከጥ​ሩም በፍታ መጋ​ረ​ጃ​ውን ሠራ፤ ኪሩ​ቤ​ል​ንም ጠለ​ፈ​በት።</verse>
				<verse number="15">በቤ​ቱም ፊት ቁመ​ታ​ቸው ሠላሳ አም​ስት ክንድ የነ​በ​ረ​ውን ሁለ​ቱን ዐም​ዶች ሠራ፤ በእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም ላይ የነ​በ​ረው ጕል​ላት አም​ስት ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="16">እንደ ድሪ ያሉ ሰን​ሰ​ለ​ቶ​ች​ንም ሠርቶ በአ​ዕ​ማዱ ራስ ላይ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ መቶም ሮማ​ኖች ሠርቶ በሰ​ን​ሰ​ለቱ ላይ አደ​ረ​ጋ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">አዕ​ማ​ዶ​ቹ​ንም አን​ደ​ኛ​ውን በቀኝ፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም በግራ በመ​ቅ​ደሱ ፊት አቆ​ማ​ቸው፤ በቀ​ኝም የነ​በ​ረ​ውን ስም ርትዕ በግ​ራም የነ​በ​ረ​ውን ስም ጽንዕ ብሎ ጠራ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ርዝ​መ​ቱም ሃያ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ክንድ፥ ቁመ​ቱም ዐሥር ክንድ የነ​በ​ረ​ውን የና​ሱን መሠ​ዊያ ሠራ።</verse>
				<verse number="2">ዳግ​መ​ኛም ከቀ​ለጠ ናስ ከዳር እስከ ዳር ዐሥር ክንድ፥ ቁመ​ት​ዋም አም​ስት ክንድ፥ ዙሪ​ያ​ዋም ሠላሳ ክንድ የሆነ ኵሬ ሠራ።</verse>
				<verse number="3">በበ​ታ​ች​ዋም፥ በዙ​ሪ​ያዋ በዐ​ሥሩ ክንድ የበ​ሬ​ዎች ምስ​ሎች ነበሩ። ኵሬ​ዋ​ንም ይከ​ብ​ቡ​አት ነበር። በሬ​ዎ​ቹም በሁ​ለት ተራ ሁነው ከኵ​ሬው ጋር በአ​ን​ድ​ነት ቀል​ጠው የተ​ሠሩ ነበሩ።</verse>
				<verse number="4">ዐሥራ ሁለት በሬ​ዎ​ችን ሠሩ​ላ​ቸው። ከእ​ነ​ር​ሱም ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስቱ ወደ ምዕ​ራብ፥ ሦስ​ቱም ወደ ደቡብ፥ ሦስ​ቱም ወደ ምሥ​ራቅ ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ ቀልጣ የተ​ሠ​ራች ኵሬም በላ​ያ​ቸው ነበ​ረች፤ የሁ​ሉም ጀር​ባ​ቸው በስ​ተ​ው​ስጥ ነበረ።</verse>
				<verse number="5">ውፍ​ረ​ት​ዋም አንድ ጋት ያህል ነበረ፤ ከን​ፈ​ሯም እንደ ጽዋ ከን​ፈር፥ እንደ ሱፍ አበባ ሆኖ ተሠ​ርቶ ነበር፤ ሦስት ሺህም ማድጋ ትይዝ ነበር ሠር​ቶም ፈጸ​ማት፤</verse>
				<verse number="6">ደግ​ሞም ዐሥር የመ​ታ​ጠ​ቢያ ሰኖ​ችን ሠራ፤ ለሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ቀ​ር​በው ነገር ሁሉ ይታ​ጠ​ብ​ባ​ቸው ዘንድ አም​ስ​ቱን በቀኝ፥ አም​ስ​ቱ​ንም በግራ አኖ​ራ​ቸው፤ ባሕሩ ግን ካህ​ናት ይታ​ጠ​ቡ​በት ነበር።</verse>
				<verse number="7">ዐሥ​ሩ​ንም የወ​ርቅ መቅ​ረ​ዞች እንደ ሥር​ዐ​ታ​ቸው ሠራ፤ አም​ስ​ቱን በቀኝ፥ አም​ስ​ቱ​ንም በግራ በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ አኖ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">ዐሥ​ሩ​ንም የወ​ርቅ ገበ​ታ​ዎች ሠርቶ አም​ስ​ቱን በቀኝ፥ አም​ስ​ቱ​ንም በግራ በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ አኖ​ራ​ቸው። አንድ መቶም የወ​ርቅ ጽዋ​ዎ​ችን ሠራ።</verse>
				<verse number="9">ደግ​ሞም የካ​ህ​ና​ቱን አደ​ባ​ባይ ፥ ታላ​ቁ​ንም አደ​ባ​ባይ፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ደጆች ሠራ፤ ደጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በናስ ለበጠ።</verse>
				<verse number="10">ኵሬ​ው​ንም በቤተ መቅ​ደሱ መዓ​ዝን በስ​ተ​ቀኝ በኩል በም​ሥ​ራቅ አቅ​ጣጫ አኖ​ረው።</verse>
				<verse number="11">ኪራ​ምም ምን​ቸ​ቶ​ቹ​ንና መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹን፥ በመ​ሠ​ዊ​ያው ቤት ያሉ ማን​ኪ​ያ​ዎ​ች​ንና የመ​ገ​ል​ገ​ያ​ውን ዕቃ ሁሉ ሠራ። ኪራ​ምም ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ ጨረሰ።</verse>
				<verse number="12">ሁለት ዐም​ዶ​ች​ንና በሁ​ለቱ ዐም​ዶች ላይ ጕል​ላ​ቶ​ችን፥ በዐ​ም​ዶ​ቹም ራሶች ላይ ያሉ​ትን ጕል​ላ​ቶች የሚ​ሸ​ፍኑ ሁለት መር​በ​ቦ​ችን ሠራ።</verse>
				<verse number="13">በሁ​ለ​ቱም መር​በ​ቦች አራት መቶ የወ​ርቅ ሻኵ​ራ​ዎ​ች​ንና በዐ​ም​ዶቹ ላይ ያሉ​ትን ሁለት ጕል​ላ​ቶች በሁ​ለት ጎኖች የሚ​ሸ​ፍ​ኑ​ትን ሮማ​ኖች ሠራ።</verse>
				<verse number="14">ዐሥር መቀ​መ​ጫ​ዎ​ች​ንና በመ​ቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹም ላይ መታ​ጠ​ቢ​ያ​ዎ​ችን ሠራ፤</verse>
				<verse number="15">አን​ድ​ዋ​ንም ኵሬ፥ በበ​ታ​ች​ዋም ያሉ​ትን ዐሥራ ሁለት በሬ​ዎች ሠራ።</verse>
				<verse number="16">የእ​ግር መታ​ጠ​ቢ​ያ​ዎ​ችን፥ የእጅ መታ​ጠ​ቢ​ያ​ዎ​ችን፥ ጋኖ​ችን፥ የሥጋ ማውጫ ሜን​ጦ​ዎ​ች​ንና ኪራም የሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ ከን​ጹሕ ናስ ሠርቶ ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አቀ​ረ​በ​ለት።</verse>
				<verse number="17">ንጉ​ሡም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ሜዳ በሱ​ኮ​ትና በሴ​ድራ መካ​ከል ባለው በወ​ፍ​ራሙ መሬት ውስጥ አቀ​ለ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">ሰሎ​ሞ​ንም እነ​ዚ​ህን ዕቃ​ዎች ሁሉ እጅግ አብ​ዝቶ ሠራ፤ የና​ሱም ብዛት አይ​ቈ​ጠ​ርም ነበር።</verse>
				<verse number="19">ሰሎ​ሞ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የነ​በ​ረ​ውን ዕቃ ሁሉ፥ የወ​ር​ቁ​ንም መሠ​ዊያ፥ ኅብ​ስተ ገጽ የነ​በ​ረ​ባ​ቸ​ውን ገበ​ታ​ዎች ሠራ።</verse>
				<verse number="20">በመ​ቅ​ደሱ ፊት እንደ ሥር​ዐ​ታ​ቸው የሚ​ያ​በሩ መቅ​ረ​ዞ​ች​ንና ቀን​ዲ​ሎ​ች​ንም ከጥሩ ወርቅ ሠራ።</verse>
				<verse number="21">የመ​ብ​ራ​ቶች መቅ​ረ​ዞ​ች​ንና በላ​ያ​ቸው ያሉ መብ​ራ​ቶ​ችን፥ ጽዋ​ዎ​ቹን፥ ማን​ኪ​ያ​ዎ​ቹን፥ ሥራ የሚ​ሠ​ሩ​ባ​ቸው ጻሕ​ሎ​ች​ንም ከጥሩ ወርቅ ሠራ።</verse>
				<verse number="22">ውስ​ጠ​ኛው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ደጅና ወደ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ መግ​ቢያ የሚ​ወ​ስ​ደው የው​ስ​ጠ​ኛ​ውም የቤተ መቅ​ደሱ ደጆች የወ​ርቅ ነበሩ። እን​ዲ​ሁም ሰሎ​ሞን ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሠ​ራው ሥራ ሁሉ ተፈ​ጸመ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">ሰሎ​ሞ​ንም አባቱ ዳዊት የቀ​ደ​ሰ​ውን ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ የመ​ገ​ል​ገያ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ አም​ጥቶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በነ​በ​ረው ግምጃ ቤት አገባ።</verse>
				<verse number="2">በዚያ ጊዜም ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳ​ዊት ከተማ ከጽ​ዮን ያወጡ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና የነ​ገድ አለ​ቆ​ችን ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች አባ​ቶች ቤቶች መሳ​ፍ​ንት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሰበ​ሰበ።</verse>
				<verse number="3">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር በበ​ዓሉ ጊዜ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎ​ሞን ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="4">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ መጡ፤ ሌዋ​ው​ያ​ንም ሁሉ ታቦ​ቷን አነሡ።</verse>
				<verse number="5">የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን፥ በድ​ን​ኳ​ኑም ውስጥ የነ​በ​ረ​ውን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ዕቃ ሁሉ አወጡ፤ ታቦ​ቷ​ንም ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያኑ አወጡ።</verse>
				<verse number="6">ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈሩ ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት በታ​ቦቷ ፊት ሆነው ከብ​ዛት የተ​ነሣ የማ​ይ​ቈ​ጠ​ሩ​ት​ንና የማ​ይ​መ​ጠ​ኑ​ትን በጎ​ችና በሬ​ዎች ይሠዉ ነበር።</verse>
				<verse number="7">ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ቤትዋ አም​ጥ​ተው በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ውስጥ ከኪ​ሩ​ቤል ክንፍ በታች በነ​በ​ረው መቅ​ደስ አኖ​ሯት።</verse>
				<verse number="8">ኪሩ​ቤ​ልም በታ​ቦቷ ስፍራ ላይ ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ዘር​ግ​ተው ነበር፤ ኪሩ​ቤ​ልም ታቦ​ቷ​ንና መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹን በስ​ተ​ላዩ በኩል ይሸ​ፍኑ ነበር።</verse>
				<verse number="9">መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹም ረጃ​ጅ​ሞች ነበ​ሩና በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ፊት ከመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ጫፎ​ቻ​ቸው ይታዩ ነበር፤ ነገር ግን ከውጭ አይ​ታ​ዩም ነበር፤ እስከ ዛሬም ድረስ እዚያ አሉ።</verse>
				<verse number="10">በታ​ቦ​ቷም ውስጥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር በወጡ ጊዜ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደ​ረገ ጊዜ ሙሴ በኮ​ሬብ ካስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው ከሁ​ለቱ ጽላት በቀር ምንም አል​ነ​በ​ረ​ባ​ትም።</verse>
				<verse number="11">ከመ​ቅ​ደ​ስም ከወጡ በኋላ በዚያ የነ​በ​ሩት ካህ​ናት ሁሉ ተቀ​ድ​ሰው ነበር፤ በሰ​ሞ​ና​ቸ​ውም አል​ተ​ከ​ፈ​ሉም ነበር።</verse>
				<verse number="12">መዘ​ም​ራ​ንም የነ​በ​ሩት ሌዋ​ው​ያን ሁሉ፥ ከአ​ሳ​ፍና ከኤ​ማን፥ ከኤ​ዶ​ት​ምም ልጆች ጋር ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም፥ ጥሩ በፍታ ለብ​ሰው ጸና​ጽ​ልና ከበሮ፥ መሰ​ን​ቆም እየ​መቱ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ በም​ሥ​ራቅ በኩል ቆመው ነበር፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር መቶ ሃያ ካህ​ናት መለ​ከት ይነፉ ነበር።</verse>
				<verse number="13">መለ​ከ​ቱ​ንም የሚ​ነፉ መዘ​ም​ራኑ በአ​ን​ድ​ነት ሆነው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገ​ኑና እያ​ከ​በሩ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ” እያሉ በአ​ንድ ቃል ድም​ፃ​ቸ​ውን ወደ ላይ ከፍ አድ​ር​ገው በመ​ለ​ከ​ትና በጸ​ና​ጽል፥ በዜ​ማም ዕቃ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ባመ​ሰ​ገኑ ጊዜ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የክ​ብሩ ደመና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሞላው።</verse>
				<verse number="14">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሞል​ቶት ነበ​ርና ካህ​ናቱ ከደ​መ​ናው የተ​ነሣ መቆ​ምና ማገ​ል​ገል አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">ያን​ጊ​ዜም ሰሎ​ሞን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በጨ​ለማ ውስጥ እኖ​ራ​ለሁ ብሎ​አል።</verse>
				<verse number="2">እኔም ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ኖ​ር​በት ዝግ​ጁና ቅዱስ ቤት ለስሙ ሠራሁ” አለ።</verse>
				<verse number="3">ንጉሡ ሰሎ​ሞ​ንም ፊቱን መልሶ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጉባኤ ሁሉ መረቀ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጉባኤ ሁሉ ቆመው ነበር።</verse>
				<verse number="4">እር​ሱም አለ፥ “ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት በአፉ የተ​ና​ገረ፥ በእ​ጁም የፈ​ጸመ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።</verse>
				<verse number="5">እርሱ፦ ሕዝ​ቤን ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ሁ​በት ጊዜ ጀምሮ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ በዚያ ለስሜ ቤት ይሠ​ራ​በት ዘንድ ከተ​ማን አል​መ​ረ​ጥ​ሁም። በሕ​ዝቤ እስ​ራ​ኤል ላይም ይነ​ግሥ ዘንድ ሰውን አል​መ​ረ​ጥ​ሁም።</verse>
				<verse number="6">ነገር ግን ስሜ በዚያ እን​ዲ​ጠ​ራ​ባት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን መር​ጫ​ለሁ። በሕ​ዝ​ቤም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ እን​ዲ​ሆን ዳዊ​ትን መር​ጫ​ለሁ ብሎ​አል።</verse>
				<verse number="7">አባ​ቴም ዳዊት ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ይሠራ ዘንድ በልቡ አስቦ ነበር።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አባ​ቴን ዳዊ​ትን፦ ለስሜ ቤት ትሠራ ዘንድ በል​ብህ አስ​በ​ሃ​ልና ይህን በል​ብህ ማሰ​ብህ መል​ካም አደ​ረ​ግህ።</verse>
				<verse number="9">ነገር ግን ከወ​ገ​ብህ የሚ​ወ​ጣው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤትን ይሠ​ራል እንጂ አንተ አት​ሠ​ራ​ል​ኝም አለው።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ፈጸመ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ በአ​ባቴ በዳ​ዊት ፋንታ ተተ​ካሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዙፋን ላይ ተቀ​መ​ጥሁ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት ሠራሁ።</verse>
				<verse number="11">ከሕ​ዝ​ቡም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ያደ​ረ​ገው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ያለ​ባ​ትን ታቦት በዚ​ያው ውስጥ አኖ​ርሁ።”</verse>
				<verse number="12">ሰሎ​ሞ​ንም በእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ ፊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ አን​ጻር ቆሞ እጆ​ቹን ዘረጋ።</verse>
				<verse number="13">ሰሎ​ሞ​ንም ርዝ​መቱ አም​ስት ክንድ፥ ወር​ዱም አም​ስት ክንድ፥ ቁመ​ቱም ሦስት ክንድ የሆነ የናስ መድ​ረክ ሠርቶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ መካ​ከል ተክ​ሎት ነበር፤ በላ​ዩም ቆመ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጉባኤ ሁሉ ፊት በጕ​ል​በቱ ተን​በ​ር​ክኮ እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤</verse>
				<verse number="14">እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ በሰ​ማ​ይም በም​ድ​ርም አን​ተን የሚ​መ​ስል አም​ላክ የለም፤ በፍ​ጹም ልባ​ቸው በፊ​ትህ ለሚ​ሄዱ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ቃል ኪዳ​ን​ንና ምሕ​ረ​ትን የም​ታ​ጸ​ናና የም​ት​ጠ​ብቅ አንተ ነህ።</verse>
				<verse number="15">ለባ​ሪ​ያህ ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት እን​ዲህ ብለህ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን የጠ​በ​ቅህ፥ በአ​ፍህ ተና​ገ​ርህ፤ ዛሬም እንደ ሆነው በእ​ጆ​ችህ ፈጸ​ም​ኸው።</verse>
				<verse number="16">አሁ​ንም አቤቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ አንተ በፊቴ እንደ ሄድህ ልጆ​ችህ በሕጌ ይሄዱ ዘንድ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ቢጠ​ብቁ በእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን የሚ​ቀ​መጥ ሰው በፊቴ አይ​ታ​ጣም ብለህ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ለባ​ሪ​ያህ ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት ጠብቅ፤ አጽ​ናም።</verse>
				<verse number="17">አሁ​ንም፥ አቤቱ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ለባ​ሪ​ያህ ለዳ​ዊት የተ​ና​ገ​ር​ኸው ቃል ይጽና።</verse>
				<verse number="18">“በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰው ጋር በም​ድር ላይ ይኖ​ራ​ልን? እነሆ፥ ሰማይ ሰማየ ሰማ​ያ​ትም ይወ​ስ​ንህ ዘንድ አይ​ች​ልም፤ እን​ግ​ዲ​ያስ እኔ የሠ​ራ​ሁት ይህ ቤት ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="19">ነገር ግን አቤቱ አም​ላኬ ሆይ፥ ወደ ባሪ​ያህ ጸሎ​ትና ልመና ተመ​ል​ከት፤ ባሪ​ያህ በዚች ዕለት በፊ​ትህ የሚ​ጸ​ል​የ​ውን ጸሎ​ትና ልመ​ና​ውን ስማ።</verse>
				<verse number="20">ባሪ​ያህ በዚህ ቤት የሚ​ጸ​ል​የ​ውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፦ በዚያ ስሜ ይሆ​ናል ወዳ​ል​ኸው ስፍራ፥ ወደ​ዚህ ቤት ዐይ​ኖ​ችህ ቀንና ሌሊት የተ​ገ​ለጡ ይሁኑ።</verse>
				<verse number="21">ባሪ​ያ​ህና ሕዝ​ብህ እስ​ራ​ኤል በዚህ ስፍራ የሚ​ጸ​ል​ዩ​ትን ልመና ስማ፤ በተ​ዘ​ጋ​ጀው በማ​ደ​ሪ​ያህ በሰ​ማይ ስማ፤ ሰም​ተ​ህም ይቅር በል።</verse>
				<verse number="22">“ሰው ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ቢበ​ድል፥ ይም​ልም ዘንድ በላዩ መሐላ ቢጭ​ን​በት፥ እር​ሱም መጥቶ በዚህ ቤት በመ​ሠ​ዊ​ያህ ፊት ቢና​ዘዝ፥</verse>
				<verse number="23">በሰ​ማይ ስማ፤ አድ​ር​ግም፤ በባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህም ላይ ዳኛ ሁን፤ በበ​ደ​ለ​ኛ​ውም ላይ ፍረድ፤ መን​ገ​ዱ​ንም በራሱ ላይ መል​ስ​በት፤ ንጹ​ሑ​ንም አጽ​ድ​ቀው፤ እንደ ጽድ​ቁም ክፈ​ለው።</verse>
				<verse number="24">“ሕዝ​ብህ እስ​ራ​ኤል አን​ተን ስለ በደሉ በጠ​ላት ፊት ድል ተመ​ት​ተው ወደ አንተ ቢመ​ለሱ፥ ስም​ህ​ንም ቢያ​ከ​ብሩ፥ በዚ​ህም ቤት በፊ​ትህ ቢጸ​ል​ዩና ቢለ​ም​ኑህ፥</verse>
				<verse number="25">አንተ በሰ​ማይ ስማ፤ የሕ​ዝ​ብ​ህ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ኀጢ​አት ይቅር በል፤ ለእ​ነ​ር​ሱም፥ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ሰጠ​ሃት ምድር መል​ሳ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">“አን​ተን ስለ በደሉ ሰማ​ያት በተ​ዘጉ ጊዜ፥ ዝና​ብም ባል​ዘ​ነበ ጊዜ፥ በዚህ ስፍራ ቢጸ​ልዩ፥ ስም​ህ​ንም ቢያ​ከ​ብሩ፥ ባዋ​ረ​ድ​ሃ​ቸ​ውም ጊዜ ከኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ቢመ​ለሱ፥</verse>
				<verse number="27">አንተ በሰ​ማይ ስማ፤ የባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህ​ንና የሕ​ዝ​ብ​ህን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ኀጢ​አት ይቅር በል፥ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መል​ካም መን​ገድ አሳ​ያ​ቸው፤ ለሕ​ዝ​ብ​ህም ርስት አድ​ር​ገህ ለሰ​ጠ​ሃት ምድር ዝና​ብን ስጥ።</verse>
				<verse number="28">“በም​ድር ላይ ራብ፥ ወይም ቸነ​ፈር፥ ወይም ዋግ፥ ወይም አረ​ማሞ፥ ወይም አን​በጣ፥ ወይም ኩብ​ኩባ ቢሆን፥ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የሀ​ገ​ሩን ከተ​ሞች ከብ​በው ቢያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ቸው፥ ማና​ቸ​ውም መቅ​ሠ​ፍ​ትና ደዌ ቢሆን፥</verse>
				<verse number="29">ማንም ሰው ወይም ሕዝ​ብህ እስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ ማና​ቸ​ውም ሰው ሕማ​ሙ​ንና ኀዘ​ኑን ዐውቆ ጸሎ​ትና ልመና ቢያ​ደ​ርግ፥ እጆ​ቹ​ንም ወደ​ዚህ ቤት ቢዘ​ረጋ፥</verse>
				<verse number="30">አንተ በተ​ዘ​ጋ​ጀው በማ​ደ​ሪ​ያህ በሰ​ማይ ስማው፤ ይቅ​ርም በለው፤ ልቡን ለም​ታ​ው​ቀው ሰው ሁሉ እንደ መን​ገዱ ሁሉ መጠን ክፈ​ለው፤ አንተ ብቻ የሰ​ውን ልጆች ልብ ታው​ቃ​ለ​ህና።</verse>
				<verse number="31">ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን በሰ​ጠ​ኸው ምድር ላይ በሚ​ኖ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ ይፈ​ሩህ ዘንድ በመ​ን​ገ​ዶ​ች​ህም ይሄዱ ዘንድ።</verse>
				<verse number="32">“ከሕ​ዝ​ብህ ከእ​ስ​ራ​ኤል ያል​ሆነ እን​ግዳ ስለ ታላቁ ስምህ፥ ስለ ብር​ቱ​ውም እጅህ፥ ስለ ተዘ​ረ​ጋ​ውም ክን​ድህ፥ ከሩቅ ሀገር መጥቶ በዚህ ቤት በጸ​ለየ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="33">አንተ በማ​ደ​ሪ​ያህ በሰ​ማይ ስማ፤ የም​ድ​ርም አሕ​ዛብ ሁሉ ስም​ህን ያውቁ ዘንድ፥ እንደ ሕዝ​ብ​ህም እንደ እስ​ራ​ኤል ይፈ​ሩህ ዘንድ፥ በዚ​ህም በሠ​ራ​ሁት ቤት ስምህ እንደ ተጠራ ያውቁ ዘንድ፥ እን​ግ​ዳው የሚ​ለ​ም​ን​ህን ሁሉ አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="34">“ሕዝ​ብ​ህም ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ለመ​ው​ጋት አንተ በም​ት​ል​ካ​ቸው መን​ገድ ቢወጡ፥ አን​ተም ወደ መረ​ጥ​ሃት ወደ​ዚ​ህች ከተማ፥ እኔም ለስ​ምህ ወደ ሠራ​ሁት ቤት ለአ​ንተ ቢጸ​ልዩ፥</verse>
				<verse number="35">ጸሎ​ታ​ቸ​ው​ንና ልመ​ና​ቸ​ውን በሰ​ማይ ስማ፤ ፍር​ድ​ንም ፍረ​ድ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="36">“የማ​ይ​በ​ድል ሰው የለ​ምና አን​ተን ቢበ​ድሉ፥ ብት​ቈ​ጣ​ቸ​ውም፥ ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አሳ​ል​ፈህ ብት​ሰ​ጣ​ቸው፥ ሩቅም ወይም ቅርብ ወደ ሆነ ሀገር ጠላ​ቶ​ቻ​ቸው ቢማ​ር​ኩ​አ​ቸው፥</verse>
				<verse number="37">በተ​ማ​ረ​ኩ​ባ​ትም ሀገር ሆነው በል​ባ​ቸው ንስሓ ቢገቡ፥ በም​ር​ኮ​አ​ቸ​ውም ሀገር ሳሉ ተመ​ል​ሰው፦ ኀጢ​አት ሠር​ተ​ናል፥ በድ​ለ​ን​ማል፥ ክፉም አድ​ር​ገ​ናል ብለው ቢለ​ም​ኑህ፤</verse>
				<verse number="38">በተ​ማ​ረ​ኩ​በ​ትም ሀገር ሳሉ በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውና በፍ​ጹም ነፍ​ሳ​ቸው ወደ አንተ ቢመ​ለሱ፥ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ሰጠ​ሃት ወደ ምድ​ራ​ቸው፥ ወደ መረ​ጥ​ሃ​ትም ከተማ፥ ለስ​ም​ህም ወደ ሠራ​ሁት ቤት ቢጸ​ልዩ፥</verse>
				<verse number="39">ጸሎ​ታ​ቸ​ው​ንና ልመ​ና​ቸ​ውን በተ​ዘ​ጋጀ በማ​ደ​ሪ​ያህ በሰ​ማይ ስማ፤ ፍር​ድ​ንም አድ​ር​ግ​ላ​ቸው፤ አን​ተ​ንም የበ​ደ​ሉ​ህን ሕዝ​ብ​ህን ይቅር በል።</verse>
				<verse number="40">“አሁ​ንም አም​ላኬ ሆይ፥ በዚህ ስፍራ ወደ​ሚ​ሆ​ነው ጸሎት ዐይ​ኖ​ችህ የተ​ገ​ለጡ፥ ጆሮ​ዎ​ች​ህም የሚ​ያ​ደ​ምጡ ይሁኑ።</verse>
				<verse number="41">አሁ​ንም አቤቱ አም​ላክ ሆይ፥ ከኀ​ይ​ልህ ታቦት ጋር ወደ ዕረ​ፍ​ትህ ተነሣ፤ አቤቱ አም​ላክ ሆይ፥ ካህ​ና​ትህ ደኅ​ን​ነ​ትን ይል​በሱ፤ ቅዱ​ሳ​ን​ህም በደ​ስታ ደስ ይበ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="42">አቤቱ አም​ላክ ሆይ፥ ከቀ​ባ​ኸው ሰው ፊት​ህን አት​መ​ልስ፤ ለባ​ሪ​ያ​ህም ለዳ​ዊት ምሕ​ረ​ትን አስብ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">ሰሎ​ሞ​ንም ይህን ጸሎት በፈ​ጸመ ጊዜ እሳት ከሰ​ማይ ወርዶ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን ቍር​ባ​ንና መሥ​ዋ​ዕ​ቱን ሁሉ በላ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ቤቱን ሞላ።</verse>
				<verse number="2">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሞል​ቶት ነበ​ርና ካህ​ናቱ በዚ​ያች ዕለት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መግ​ባት አል​ቻ​ሉም።</verse>
				<verse number="3">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እሳቱ ሲወ​ርድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር፤ ድን​ጋይ በተ​ነ​ጠ​ፈ​በ​ትም ምድር በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደ​ፍ​ተው ሰገዱ፥ “እርሱ ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና” እያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ።</verse>
				<verse number="4">ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕዝብ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርቡ ነበር።</verse>
				<verse number="5">በዚ​ያ​ችም ዕለት ንጉሡ ሰሎ​ሞን ሃያ ሁለት ሺህ በሬ​ዎ​ች​ንና መቶ ሃያ ሺህ በጎ​ችን ሠዋ። እን​ዲሁ ንጉ​ሡና ሕዝቡ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ቅዳሴ አከ​በሩ።</verse>
				<verse number="6">ካህ​ና​ቱም በየ​ሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ሌዋ​ው​ያ​ኑም ደግሞ፥ “ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ” የሚ​ለ​ውን የዳ​ዊ​ትን መዝ​ሙር እየ​ዘ​መሩ፥ ንጉሡ ዳዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​መ​ስ​ገን የሠ​ራ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የዜማ ዕቃ ይዘው ቆመው ነበር፤ ካህ​ና​ቱም በፊ​ታ​ቸው መለ​ከት ይነፉ ነበር፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ቆመው ነበር።</verse>
				<verse number="7">ሰሎ​ሞ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት የነ​በ​ረ​ውን የአ​ደ​ባ​ባ​ዩን ውስጥ ቀደሰ፤ ሰሎ​ሞ​ንም የሠ​ራው የናስ መሠ​ዊያ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ ስቡ​ንም መያዝ አል​ቻ​ለ​ምና የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱ​ንም መሥ​ዋ​ዕት፥ ስብ በዚያ አቀ​ረበ።</verse>
				<verse number="8">ሰሎ​ሞ​ንም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እጅግ ታላቅ ጉባኤ የሆኑ ከኤ​ማት መግ​ቢያ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ያሉ እስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ በዚያ ጊዜ ሰባት ቀን በዓል አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="9">መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ቀድሶ፥ ሰባት ቀን በዓል አድ​ርጎ ነበ​ርና በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን የፍ​ጻሜ በዓል አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="10">በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር በሃያ ሦስ​ተ​ኛው ቀን ሕዝ​ቡን ወደ ድን​ኳ​ና​ቸው አሰ​ና​በተ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዳ​ዊ​ትና ለሰ​ሎ​ሞን፥ ለሕ​ዝ​ቡም ለእ​ስ​ራ​ኤል ስላ​ደ​ረ​ገው ቸር​ነት በል​ባ​ቸው ደስ ብሎ​አ​ቸው ሄዱ።</verse>
				<verse number="11">ሰሎ​ሞ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የን​ጉ​ሡን ቤት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና በራሱ ቤት ይሠ​ራው ዘንድ በልቡ ያሰ​በ​ውን ሁሉ ጨረሰ፤ አከ​ና​ወ​ነም።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሰ​ሎ​ሞን በሌ​ሊት ተገ​ልጦ እን​ዲህ አለው፥ “ ጸሎ​ት​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፤ ይህ​ንም ስፍራ ለራሴ ለመ​ሥ​ዋ​ዕት ቤት መር​ጫ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">ዝናብ እን​ዳ​ይ​ወ​ርድ ሰማ​ያ​ቱን ብዘጋ፥ ወይም የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን እን​ጨት ሁሉ ይበላ ዘንድ አን​በ​ጣን ባዝ​ዘው፥ ወይም በሕ​ዝቤ ላይ ቸነ​ፈር ብሰ​ድድ፥</verse>
				<verse number="14">በስሜ የተ​ጠ​ሩት ሕዝቤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን አዋ​ር​ደው ቢጸ​ልዩ፥ ፊቴ​ንም ቢፈ​ልጉ፥ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም ቢመ​ለሱ፥ በሰ​ማይ ሆኜ እሰ​ማ​ለሁ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይቅር እላ​ለሁ፤ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም እፈ​ው​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">አሁ​ንም በዚህ ስፍራ ለሚ​ጸ​ለይ ጸሎት ዐይ​ኖች ይገ​ለ​ጣሉ፤ ጆሮ​ዎ​ችም ያዳ​ም​ጣሉ።</verse>
				<verse number="16">አሁ​ንም ስሜ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መር​ጫ​ለሁ፤ ቀድ​ሻ​ለ​ሁም፤ ዐይ​ኖ​ችና ልቤም ዘወ​ትር በዚያ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="17">አን​ተም ደግሞ አባ​ትህ ዳዊት እንደ ሄደ በፊቴ ብት​ሄድ፥ እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁም ሁሉ ብታ​ደ​ርግ፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንና ፍር​ዴ​ንም ብት​ጠ​ብቅ፥</verse>
				<verse number="18">ከአ​ባ​ትህ ከዳ​ዊት ጋር፦ ‘በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ የሚ​ሆን ከዘ​ርህ አይ​ታ​ጣም’ ብዬ ቃል ኪዳን እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ የመ​ን​ግ​ሥ​ት​ህን ዙፋን አጸ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">“እና​ንተ ግን ብት​መ​ለሱ፥ የሰ​ጠ​ኋ​ች​ሁን ሥር​ዐ​ቴ​ንና ትእ​ዛ​ዜን ብት​ተዉ፥ ሄዳ​ች​ሁም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ብታ​መ​ልኩ፥ ብት​ሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፥</verse>
				<verse number="20">እኔም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ከሰ​ጠ​ኋ​ቸው ምድር እነ​ቅ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ለስ​ሜም የቀ​ደ​ስ​ሁ​ትን ይህን ቤት ከፊቴ እጥ​ለ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ መካ​ከል ምሳ​ሌና ተረት አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="21">ከፍ ከፍ ብሎ የነ​በ​ረ​ው​ንም ይህን ቤት እያየ በዚያ የሚ​ያ​ልፍ መን​ገ​ደኛ ሁሉ፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ሀገ​ርና በዚህ ቤት ስለ ምን እን​ዲህ አደ​ረገ?’ ብሎ ይደ​ነ​ቃል።</verse>
				<verse number="22">መል​ሰ​ውም፦ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ቸ​ውን ያባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተው ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ስለ ተከ​ተሉ፥ ስለ ሰገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፥ ስለ አመ​ለ​ኩ​አ​ቸ​ውም፥ ስለ አገ​ለ​ገ​ሏ​ቸ​ውም፥ ስለ​ዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመ​ጣ​ባ​ቸው” ይላሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የራ​ሱን ቤት የሠ​ራ​በት ሃያ ዓመት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="2">ኪራም ለሰ​ሎ​ሞን የሰ​ጠ​ውን ከተ​ሞች ሰሎ​ሞን ሠራ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች አኖ​ረ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ሰሎ​ሞ​ንም ወደ ኤማ​ት​ሱባ ሄደ፤ በረ​ታ​ባ​ትም።</verse>
				<verse number="4">በም​ድረ በዳም ያለ​ውን ተድ​ሞ​ርን፥ በኤ​ማ​ትም የጸኑ ከተ​ሞ​ችን ሁሉ ሠራ።</verse>
				<verse number="5">ደግ​ሞም ቅጥ​ርና መዝ​ጊያ፥ መወ​ር​ወ​ሪ​ያም የነ​በ​ራ​ቸ​ውን የተ​መ​ሸ​ጉ​ትን ከተ​ሞች ላይ​ኛ​ውን ቤት​ሖ​ርን፥ ታች​ኛ​ው​ንም ቤት​ሖ​ርን ሠራ።</verse>
				<verse number="6">ባዕ​ላ​ት​ንም፥ ለሰ​ሎ​ሞ​ንም የነ​በ​ሩ​ትን የዕቃ ቤት ከተ​ሞች ሁሉ፥ የሰ​ረ​ገ​ላ​ው​ንም ከተ​ሞች ሁሉ፥ የፈ​ረ​ሰ​ኞ​ች​ንም ከተ​ሞች፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም፥ በሊ​ባ​ኖ​ስም፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ቱም ምድር ሁሉ ሰሎ​ሞን ይሠራ ዘንድ የወ​ደ​ደ​ውን ሁሉ ሠራ።</verse>
				<verse number="7">ከኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ከአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ከፌ​ር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ከኤ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ከኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም የቀ​ሩ​ትን፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ወገን ያል​ሆ​ኑ​ትን ሕዝብ ሁሉ፥</verse>
				<verse number="8">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ያላ​ጠ​ፉ​አ​ቸ​ውን፥ በኋ​ላ​ቸ​ውም በም​ድር ላይ የቀ​ሩ​ትን ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ሰሎ​ሞን እስከ ዛሬ ድረስ ገባ​ሮች አደ​ረ​ጋ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ሰሎ​ሞ​ንም በመ​ን​ግ​ሥቱ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማን​ንም አገ​ል​ጋይ አላ​ደ​ረ​ገም፤ እነ​ርሱ ሰል​ፈ​ኞች፥ የሹ​ሞ​ችም አለ​ቆች፥ የሰ​ረ​ገ​ሎ​ችና የፈ​ረ​ሰ​ኞች ባል​ደ​ራ​ሶች ነበ​ሩና።</verse>
				<verse number="10">እነ​ዚ​ህም በሕ​ዝቡ ላይ ያለ​ውን ሥራ የሚ​ቈ​ጣ​ጠሩ የን​ጉሡ የሰ​ሎ​ሞን ዓይ​ነ​ተ​ኞች አለ​ቆች ሁለት መቶ አምሳ ነበሩ።</verse>
				<verse number="11">ሰሎ​ሞ​ንም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት የገ​ባ​ች​በት ስፍራ ቅዱስ ነውና ሚስቴ በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በዳ​ዊት ቤት አት​ቀ​መ​ጥም” ሲል የፈ​ር​ዖ​ንን ልጅ ከዳ​ዊት ከተማ ወደ ሠራ​ላት ቤት አወ​ጣት።</verse>
				<verse number="12">በዚያ ጊዜም ሰሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት በሠ​ራው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ላይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ።</verse>
				<verse number="13">ሙሴም እን​ዳ​ዘዘ እንደ ሥር​ዐ​ታ​ቸው በየ​ቀኑ ሁሉ፥ በየ​ሰ​ን​በ​ታ​ቱም፥ በየ​መ​ባ​ቻ​ዎ​ቹም፥ በየ​በ​ዓ​ላ​ቱም፥ በየ​ዓ​መቱ ሦስት ጊዜ በየ​ቂ​ጣው በዓ​ልና በየ​ሰ​ባቱ ሱባዔ በዓል፥ በየ​ዳ​ሱም በዓል ቍር​ባን ያቀ​ርቡ ነበር።</verse>
				<verse number="14">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው ዳዊት እን​ዲህ አዝዞ ነበ​ርና ካህ​ና​ቱን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሥር​ዐት በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ሰሞን ከፈ​ላ​ቸው፤ ሌዋ​ው​ያ​ንም እንደ ሥር​ዐ​ታ​ቸው ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ፥ በካ​ህ​ና​ቱም ፊት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ከፈ​ላ​ቸው፤ በረ​ኞ​ቹ​ንም ደግሞ በየ​በሩ ሁሉ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ከፈ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">እነ​ር​ሱም ንጉሡ ስለ ነገሩ ሁሉና ስለ መዝ​ገቡ ካህ​ና​ቱ​ንና ሌዋ​ው​ያ​ኑን ያዘ​ዘ​ውን ነገር ሁሉ አል​ተ​ላ​ለ​ፉም።</verse>
				<verse number="16">እነሆ፥ መሠ​ረቱ ከተ​ጣለ ጀምሮ ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት እስከ ፈጸመ ድረስ ሥራው ሁሉ የተ​ዘ​ጋጀ ነበረ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ተፈ​ጸመ።</verse>
				<verse number="17">ሰሎ​ሞ​ንም የዚ​ያን ጊዜ በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድር በባ​ሕር ዳር ወዳሉ ወደ ጋሴ​ዎ​ን​ጋ​ብ​ርና ወደ ኤላት ሄደ።</verse>
				<verse number="18">ኪራ​ምም መር​ከ​ቦ​ች​ንና የባ​ሕ​ርን ነገር የሚ​ያ​ው​ቁ​ትን መር​ከ​በ​ኞች በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ እጅ ላከ​ለት፤ እነ​ር​ሱም ከሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ጋር ወደ ሴፌር መጡ፤ ከዚ​ያም አራት መቶ አምሳ መክ​ሊት ወርቅ ወስ​ደው ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎ​ሞን አመጡ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">የሳ​ባም ንግ​ሥት የሰ​ሎ​ሞ​ንን ዝና በሰ​ማች ጊዜ በግ​መ​ሎች ላይ ሽቱና ብዙ ወርቅ፥ የከ​በ​ረም ዕንቍ አስ​ጭና ከታ​ላቅ ጓዝ ጋር ሰሎ​ሞ​ንን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በእ​ን​ቆ​ቅ​ልሽ ትፈ​ት​ነው ዘንድ መጣች፤ ወደ ሰሎ​ሞ​ንም በገ​ባች ጊዜ በል​ብዋ ያለ​ውን ሁሉ አጫ​ወ​ተ​ችው።</verse>
				<verse number="2">ሰሎ​ሞ​ንም የጠ​የ​ቀ​ች​ውን ሁሉ ፈታ​ላት፤ ሰሎ​ሞ​ንም ያል​ፈ​ታው ነገር አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="3">የሳ​ባም ንግ​ሥት የሰ​ሎ​ሞ​ንን ጥበብ፥ ሠር​ቶ​ትም የነ​በ​ረ​ውን ቤት፤</verse>
				<verse number="4">የማ​ዕ​ዱ​ንም መብል፥ የብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹ​ንም አቀ​ማ​መጥ፥ የሎ​ሌ​ዎ​ቹ​ንም ሥር​ዐት፥ አለ​ባ​በ​ሳ​ቸ​ው​ንም፥ ጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ቹ​ንም፥ አለ​ባ​በ​ሳ​ቸ​ው​ንም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የሚ​ያ​ሳ​ር​ገ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ባየች ጊዜ ተደ​ነ​ቀች።</verse>
				<verse number="5">ንጉ​ሡ​ንም አለ​ችው፥ “ስለ ነገ​ር​ህና ስለ ጥበ​ብህ በሀ​ገሬ ሳለሁ የሰ​ማ​ሁት ዝና እው​ነት ነው።</verse>
				<verse number="6">እኔ ግን መጥቼ በዐ​ይኔ እስ​ካ​የሁ ድረስ የነ​ገ​ሩ​ኝን አላ​መ​ን​ሁም፤ እነሆ፥ የጥ​በ​ብ​ህን ታላ​ቅ​ነት እኩ​ሌታ አል​ነ​ገ​ሩ​ኝም፤ በሀ​ገሬ ከሰ​ማ​ሁ​ትም ዝና ይልቅ ጨመ​ር​ህ​ልኝ።</verse>
				<verse number="7">እነ​ዚህ ሰዎ​ችህ ምስ​ጉ​ኖች ናቸው፤ በፊ​ትህ ሁል​ጊዜ የሚ​ቆ​ሙና ጥበ​ብ​ህን የሚ​ሰሙ እነ​ዚህ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህም ምስ​ጉ​ኖች ናቸው።</verse>
				<verse number="8">በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ንጉሥ እን​ድ​ት​ሆን በዙ​ፋኑ ላይ ያስ​ቀ​ም​ጥህ ዘንድ የወ​ደ​ደህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ ይሁን፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ራ​ኤ​ልን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያጸ​ና​ቸው ዘንድ ወድ​ዶ​አ​ቸ​ዋ​ልና ስለ​ዚህ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን ታደ​ርግ ዘንድ በላ​ያ​ቸው አነ​ገ​ሠህ።”</verse>
				<verse number="9">ለን​ጉ​ሡም መቶ ሃያ መክ​ሊት ወርቅ፥ እጅ​ግም ብዙ ሽቱ፥ የከ​በ​ረም ዕንቍ ሰጠ​ችው፤ የሳ​ባም ንግ​ሥት ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን እንደ ሰጠ​ችው ያለ ሽቱ ከቶ አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="10">የኪ​ራም አገ​ል​ጋ​ዮ​ችና የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ከሴ​ፌር ለሰ​ሎ​ሞን ወርቅ አመጡ፤ የሰ​ን​ደል እን​ጨ​ትና የከ​በረ ዕን​ቍም ደግሞ አመጡ።</verse>
				<verse number="11">ንጉ​ሡም ከሰ​ን​ደሉ እን​ጨት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና ለን​ጉሡ ቤት ደርብ፥ ለመ​ዘ​ም​ራ​ኑም መሰ​ን​ቆና በገና አደ​ረገ፤ እን​ደ​ዚ​ህም ያለ በይ​ሁዳ ምድር ከቶ አል​ታ​የም ነበር።</verse>
				<verse number="12">እር​ስ​ዋም ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን ካመ​ጣ​ችው የበ​ለጠ፥ ንጉሡ ሰሎ​ሞን የወ​ደ​ደ​ች​ውን ሁሉ፥ ከእ​ር​ሱም የለ​መ​ነ​ች​ውን ሁሉ ለሳባ ንግ​ሥት ሰጣት፤ እር​ስ​ዋም ተመ​ልሳ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችዋ ጋር ወደ ሀገ​ርዋ ሄደች።</verse>
				<verse number="13">በየ​ዓ​መ​ቱም ወደ ሰሎ​ሞን የሚ​መጣ የወ​ርቅ ሚዛን ስድ​ስት መቶ ስድሳ ስድ​ስት መክ​ሊት ወርቅ ነበረ።</verse>
				<verse number="14">ነጋ​ድ​ራ​ሶ​ችና ነጋ​ዴ​ዎች ከሚ​ያ​መ​ጡት ሌላ የዓ​ረብ ነገ​ሥ​ታት ሁሉ፥ የም​ድ​ሩም ሹሞች ወደ ንጉሡ ሰሎ​ሞን ወር​ቅና ብር ያመጡ ነበር</verse>
				<verse number="15">ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን በጥ​ፍ​ጥፍ ወርቅ ሁለት መቶ አላ​ባሽ አግሬ ጋሻ አሠራ፤ በየ​አ​ን​ዳ​ን​ዱም አላ​ባሽ አግሬ ጋሻ ውስጥ የገ​ባው የጠራ ወርቅ ስድ​ስት መቶ ሰቅል ነበረ።</verse>
				<verse number="16">ከጥ​ፍ​ጥ​ፍም ወርቅ ሦስት መቶ ጋሻ አሠራ፤ በየ​አ​ን​ዳ​ን​ዱም ጋሻ የገ​ባው ወርቅ ሦስት መቶ ሰቅል ነበረ፤ ንጉ​ሡም የሊ​ባ​ኖስ ዱር በተ​ባ​ለው ቤት ውስጥ አኖ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">ንጉ​ሡም ደግሞ ከዝ​ሆን ጥርስ ታላቅ ዙፋን አሠራ፤ በጥሩ ወር​ቅም ለበ​ጠው።</verse>
				<verse number="18">ወደ ዙፋ​ኑም የሚ​ያ​ስ​ሄዱ፥ በወ​ርቅ የተ​ለ​በጡ ስድ​ስት እር​ከ​ኖች ነበሩ፤ በዚ​ህና በዚያ በመ​ቀ​መ​ጫው አጠ​ገብ ሁለት የክ​ንድ መደ​ገ​ፊ​ያ​ዎች ነበ​ሩ​በት፤ በመ​ደ​ገ​ፊ​ያ​ዎ​ቹም አጠ​ገብ ሁለት አን​በ​ሶች ቆመው ነበር።</verse>
				<verse number="19">በስ​ድ​ስ​ቱም እር​ከ​ኖች ላይ በዚ​ህና በዚያ ዐሥራ ሁለት አን​በ​ሶች ቆመው ነበር፤ በመ​ን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ እን​ዲህ ያለ ሥራ አል​ተ​ሠ​ራም።</verse>
				<verse number="20">ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን የሚ​ጠ​ጣ​በት ዕቃ ሁሉ የወ​ርቅ ነበረ፤ የሊ​ባ​ኖስ ዱር በተ​ባ​ለ​ውም ቤቱ የሚ​ገ​ለ​ገ​ል​በት ዕቃ ሁሉ ጥሩ ወርቅ ነበረ፤ በሰ​ሎ​ሞ​ንም ዘመን ብር ከቶ አይ​ቈ​ጠ​ርም ነበር።</verse>
				<verse number="21">ለን​ጉ​ሡም ከኪ​ራም አገ​ል​ጋ​ዮች ጋር ወደ ተር​ሴስ የሚ​ሄዱ መር​ከ​ቦች ነበ​ሩት፤ በሦ​ስት በሦ​ስት ዓመ​ትም አንድ ጊዜ የተ​ር​ሴስ መር​ከ​ቦች ወር​ቅና ብር፥ የዝ​ሆ​ንም ጥር​ስና ዝን​ጀሮ ይዘው ይመጡ ነበር።</verse>
				<verse number="22">ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ከም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ በባ​ለ​ጠ​ግ​ነ​ትና በጥ​በብ በለጠ።</verse>
				<verse number="23">የም​ድ​ርም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በልቡ ያኖ​ረ​ውን ጥበ​ቡን ይሰሙ ዘንድ የሰ​ሎ​ሞ​ንን ፊት ሊያዩ ይመኙ ነበር።</verse>
				<verse number="24">ከእ​ነ​ር​ሱም እያ​ን​ዳ​ንዱ ገጸ በረ​ከ​ቱን፥ የወ​ር​ቅ​ንና የብ​ርን ዕቃ፥ ልብ​ስ​ንና የጦር መሣ​ሪ​ያን፥ ሽቱ​ው​ንም፥ ፈረ​ሶ​ች​ንና በቅ​ሎ​ዎ​ችን እየ​ያዘ በየ​ዓ​መቱ ያመጣ ነበር።</verse>
				<verse number="25">ሰሎ​ሞ​ንም ለሰ​ረ​ገ​ሎች አራት ሺህ እን​ስት ፈረ​ሶ​ችና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረ​ሰ​ኞች ነበ​ሩት፤ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም ከተ​ሞች፥ ከን​ጉሡ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አኖ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">ከኤ​ፍ​ራ​ጥ​ስም ወንዝ ጀምሮ እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ምድ​ርና እስከ ግብፅ ዳርቻ ድረስ ባሉ ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ ነገሠ።</verse>
				<verse number="27">ንጉ​ሡም ወር​ቁ​ንና ብሩን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ ድን​ጋይ፥ የዝ​ግ​ባ​ው​ንም እን​ጨት በቆላ እን​ደ​ሚ​በ​ቅል ሾላ ብዛት አደ​ረ​ገው።</verse>
				<verse number="28">ለሰ​ሎ​ሞ​ንም ፈረ​ሶች ከግ​ብ​ፅና ከየ​ሀ​ገሩ ሁሉ ይመ​ጡ​ለት ነበር።</verse>
				<verse number="29">የቀ​ረ​ውም ፊተ​ኛ​ውና ኋለ​ኛው የሰ​ሎ​ሞን ነገር በነ​ቢዩ በና​ታን ታሪክ፥ በሴ​ሎ​ና​ዊ​ውም በአ​ኪያ ትን​ቢት፥ ስለ ናባ​ጥም ልጅ ስለ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ባየው በባለ ራእዩ በኢ​ዩ​ሔል ራእይ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="30">ሰሎ​ሞ​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ አርባ ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="31">ሰሎ​ሞ​ንም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ቀበ​ሩት፤ ልጁም ሮብ​ዓም በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ያነ​ግ​ሡት ዘንድ ወደ ሴኬም መጥ​ተው ነበ​ርና ሮብ​ዓም ወደ ሴኬም ሄደ።</verse>
				<verse number="2">የና​ባጥ ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ከን​ጉሡ ከሰ​ሎ​ሞን ፊት ሸሽቶ በግ​ብፅ ይኖር ነበ​ርና ይህን በሰማ ጊዜ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ከግ​ብፅ ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="3">ልከ​ውም ጠሩት፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምና እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ወደ ሮብ​ዓም መጥ​ተው እን​ዲህ አሉት፦</verse>
				<verse number="4">“አባ​ትህ ቀን​በር አክ​ብ​ዶ​ብን ነበር፤ አሁ​ንም አንተ ጽኑ​ውን የአ​ባ​ት​ህን አገ​ዛዝ፥ በላ​ያ​ች​ንም የጫ​ነ​ውን የከ​በ​ደ​ውን ቀን​በር አቅ​ል​ል​ልን፥ እኛም እን​ገ​ዛ​ል​ሃ​ለን።”</verse>
				<verse number="5">እር​ሱም፥ “ሂዱ ከሦ​ስት ቀን በኋላ ወደ እኔ ተመ​ለሱ” አላ​ቸው። ሕዝ​ቡም ሄዱ።</verse>
				<verse number="6">ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም፥ “ለዚህ ሕዝብ እመ​ል​ስ​ለት ዘንድ የም​ት​መ​ክ​ሩኝ ምን​ድን ነው?” ብሎ አባቱ ሰሎ​ሞን በሕ​ይ​ወት ሳለ በፊቱ ይቆሙ የነ​በ​ሩ​ትን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሰበ​ሰበ።</verse>
				<verse number="7">እነ​ር​ሱም፥ “በዚች ዕለት ለዚህ ሕዝብ ቸር​ነት ብታ​ደ​ር​ግ​ላ​ቸው፥ ደስም ብታ​ሰ​ኛ​ቸው፥ መል​ካም ነገ​ር​ንም ብት​ና​ገ​ራ​ቸው፥ ሁል​ጊዜ አገ​ል​ጋ​ዮች ይሆ​ኑ​ል​ሃል” ብለው ተና​ገ​ሩት።</verse>
				<verse number="8">እርሱ ግን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች የመ​ከ​ሩ​ትን ነገር ትቶ ከእ​ርሱ ጋር ካደ​ጉ​ትና በፊቱ ይቆሙ ከነ​በ​ሩት ብላ​ቴ​ኖች ጋር ተማ​ከረ።</verse>
				<verse number="9">እር​ሱም፥ “አባ​ትህ የጫ​ነ​ብ​ንን ቀን​በር አቅ​ል​ል​ልን ለሚ​ሉኝ ሕዝብ እመ​ል​ስ​ላ​ቸው ዘንድ የም​ት​መ​ክ​ሩኝ ምን​ድን ነው?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">ከእ​ር​ሱም ጋር ያደ​ጉት ብላ​ቴ​ኖች፥ “አባ​ትህ ቀን​በር አክ​ብ​ዶ​ብን ነበር፤ አንተ ግን አቅ​ል​ል​ልን ለሚ​ሉህ ሕዝብ፦ ታና​ሺቱ ጣቴ ከአ​ባቴ ወገብ ትወ​ፍ​ራ​ለች፤</verse>
				<verse number="11">አሁ​ንም አባቴ ከባድ ቀን​በር ጭኖ​ባ​ችሁ ነበር፤ እኔ ግን በቀ​ን​በ​ራ​ችሁ ላይ እጨ​ም​ራ​ለሁ፤ አባቴ በአ​ለ​ንጋ ገር​ፎ​አ​ችሁ ነበር፤ እኔ ግን በጊ​ንጥ እገ​ር​ፋ​ች​ኋ​ለሁ በላ​ቸው” ብለው ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="12">ንጉ​ሡም፥ “በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ወደ እኔ ተመ​ለሱ” ብሎ እንደ ተና​ገረ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምና ሕዝቡ ሁሉ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ወደ ሮብ​ዓም መጡ።</verse>
				<verse number="13">ንጉ​ሡም ጽኑ ምላሽ መለ​ሰ​ላ​ቸው፤ ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም የሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹን ምክር ትቶ፦</verse>
				<verse number="14">“አባቴ ቀን​በር አክ​ብ​ዶ​ባ​ችሁ ነበር፤ እኔ ግን እጨ​ም​ር​በ​ታ​ለሁ፤ አባቴ በአ​ለ​ንጋ ገር​ፎ​አ​ችሁ ነበር፤ እኔ ግን በጊ​ንጥ እገ​ር​ፋ​ች​ኋ​ለሁ” ብሎ እንደ ብላ​ቴ​ኖቹ ምክር ተና​ገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሴ​ሎ​ና​ዊው በአ​ኪያ ቃል ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮ​ር​ብ​ዓም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃሉን እን​ዲ​ያ​ጸና ለውጡ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበ​ርና ንጉሡ ሕዝ​ቡን አል​ሰ​ማም።</verse>
				<verse number="16">ንጉሡ ስላ​ል​ሰ​ማ​ቸው ሕዝቡ፥ “በዳ​ዊት ዘንድ ምን ክፍል አለን? በእ​ሴ​ይም ልጅ ዘንድ ምን ርስት አለን? እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ወደ እየ​ድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ ዳዊት ሆይ፥ አሁን ቤት​ህን ተመ​ል​ከት” ብለው ለን​ጉሡ መለ​ሱ​ለት። እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ወደ እየ​ድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸው ሄዱ።</verse>
				<verse number="17">በይ​ሁዳ ከተ​ሞች የተ​ቀ​መ​ጡት የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ግን ሮብ​ዓ​ምን በላ​ያ​ቸው አነ​ገሡ።</verse>
				<verse number="18">ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም አስ​ገ​ባ​ሪ​ውን አዶ​ራ​ምን ወደ እነ​ርሱ ላከው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በድ​ን​ጋይ ወገ​ሩት፤ ሞተም፤ ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም ፈጥኖ ወደ ሰረ​ገ​ላው ወጣ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሸሸ።</verse>
				<verse number="19">እስ​ራ​ኤ​ልም እስከ ዛሬ ድረስ ከዳ​ዊት ቤት ሸፈተ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">ሮብ​ዓ​ምም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በመጣ ጊዜ እስ​ራ​ኤ​ልን ወግ​ተው መን​ግ​ሥ​ቱን ወደ ሮብ​ዓም ይመ​ልሱ ዘንድ ከይ​ሁ​ዳና ከብ​ን​ያም ቤት የተ​መ​ረ​ጡ​ትን አንድ መቶ ሰማ​ንያ ሺህ ሰል​ፈ​ኞች ጐል​ማ​ሶ​ችን ሰበ​ሰበ።</verse>
				<verse number="2">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ ሰማያ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="3">“ለይ​ሁዳ ንጉሥ ለሰ​ሎ​ሞን ልጅ ለሮ​ብ​ዓም፥ በይ​ሁ​ዳና በብ​ን​ያ​ምም ላሉት ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ፦</verse>
				<verse number="4">‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህ ነገር ከእኔ ዘንድ ነውና አት​ውጡ፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁ​ንም አት​ውጉ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ ቤቱ ይመ​ለስ’ ብለህ ንገ​ራ​ቸው።” የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ሰሙ፤ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ላይ ከመ​ሄድ ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="5">ሮብ​ዓ​ምም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መጠ፤ በይ​ሁ​ዳም የተ​መ​ሸ​ጉ​ትን ከተ​ሞች ሠራ።</verse>
				<verse number="6">በይ​ሁ​ዳና በብ​ን​ያም ያሉ​ት​ንም የተ​መ​ሸ​ጉ​ትን ከተ​ሞች፥ ቤተ ልሔ​ምን፥ ኤጣ​ምን፥ ቴቁ​ሔን፤</verse>
				<verse number="7">ቤተ​ሱ​ራን፥ ሱላ​ኮን፥ ዓዶ​ላ​ምን፥</verse>
				<verse number="8">ጌትን፥ መሪ​ሳን፥ ዚፍን፥</verse>
				<verse number="9">አዶ​ራ​ይ​ምን፥ ለኪ​ስን፥ ዓዚ​ቃን፤</verse>
				<verse number="10">ሶር​ዓን፥ ኤሎ​ንን፥ ኬብ​ሮ​ንን ሠራ።</verse>
				<verse number="11">ምሽ​ጎ​ቹ​ንም አጠ​ነ​ከረ፤ አለ​ቆ​ች​ንም አኖ​ረ​ባ​ቸው፤ ምግ​ቡ​ንም፥ ዘይ​ቱ​ንም፥ የወ​ይን ጠጁ​ንም አከ​ማ​ቸ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">በከ​ተ​ሞቹ ሁሉ አላ​ባሽ አግሬ ጋሻና ጦርን አኖረ፤ ከተ​ሞ​ቹ​ንም እጅግ አጠ​ነ​ከ​ራ​ቸው፤ ይሁ​ዳና ብን​ያ​ምም የእ​ርሱ ወገን ነበሩ።</verse>
				<verse number="13">በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ዘንድ የነ​በሩ ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን ከየ​ሀ​ገ​ራ​ቸው ሁሉ ወደ እርሱ መጡ።</verse>
				<verse number="14">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ካህ​ናት እን​ዳ​ይ​ሆኑ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምና ልጆቹ አስ​ለ​ቅ​ቀ​ዋ​ቸው ነበ​ርና ሌዋ​ው​ያን መሰ​ም​ሪ​ያ​ቸ​ውን ትተው ወደ ይሁ​ዳና ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጡ።</verse>
				<verse number="15">እርሱ ግን ለኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች፥ ከንቱ ለሆኑ ጣዖ​ታ​ቱም፥ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ለሠ​ራ​ቸው እን​ቦ​ሶ​ችም ካህ​ና​ትን አቆመ።</verse>
				<verse number="16">ደግ​ሞም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሠዉ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመ​ፈ​ለግ ልባ​ቸ​ውን የሰጡ ሁሉ እነ​ር​ሱን ተከ​ት​ለው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጡ።</verse>
				<verse number="17">ሦስት ዓመ​ትም በዳ​ዊ​ትና በሰ​ሎ​ሞን መን​ገድ ይሄድ ነበ​ርና ሦስት ዓመት የይ​ሁ​ዳን መን​ግ​ሥት አበ​ረቱ፤ የሰ​ሎ​ሞ​ን​ንም ልጅ ሮብ​ዓ​ምን አጸኑ።</verse>
				<verse number="18">ሮብ​ዓ​ምም የዳ​ዊ​ትን ልጅ የኢ​ያ​ሪ​ሙ​ትን ሴት ልጅ ሞላ​ትን አገባ፤ እና​ቷም የእ​ሴይ ልጅ የኤ​ል​ያብ ልጅ አቢ​ካ​ኤል ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="19">እር​ስ​ዋም የዑ​ስን፥ ሰማ​ር​ያ​ንና፥ ዘሃ​ምን ወን​ዶች ልጆች ወለ​ደ​ች​ለት።</verse>
				<verse number="20">ከእ​ር​ስ​ዋም በኋላ የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምን ልጅ መዓ​ካን አገባ፤ እር​ስ​ዋም አብ​ያን፥ ኢያ​ቲን፥ ዚዛን፥ ሰሎ​ሚ​ትን ወለ​ደ​ች​ለት።</verse>
				<verse number="21">ሮብ​ዓ​ምም ከሚ​ስ​ቶ​ቹና ከቁ​ባ​ቶቹ ሁሉ ይልቅ የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምን ልጅ መዓ​ካን ወደደ፤ ዐሥራ ስም​ን​ትም ሚስ​ቶ​ችና ስድሳ ቁባ​ቶች ነበ​ሩት፤ ሃያ ስም​ንት ወን​ዶ​ችና ስድሳ ሴቶች ልጆ​ች​ንም ወለደ።</verse>
				<verse number="22">ሮብ​ዓ​ምም ያነ​ግ​ሠው ዘንድ አስ​ቦ​አ​ልና የመ​ዓ​ካን ልጅ አብ​ያን በወ​ን​ድ​ሞቹ ላይ አለቃ አድ​ርጎ ሾመው።</verse>
				<verse number="23">ብል​ሃ​ተ​ኛም ሆነ፤ ልጆ​ቹ​ንም ሁሉ በይ​ሁ​ዳና በብ​ን​ያም ሀገር ሁሉ በም​ሽጉ ከተ​ሞች ሁሉ ከፋ​ፈ​ላ​ቸው፤ ብዙም ምግብ ሰጣ​ቸው፤ ብዙም ሚስ​ቶች ፈለ​ገ​ላ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የሮ​ብ​ዓም መን​ግ​ሥት በጸ​ናች ጊዜ፥ እር​ሱም በበ​ረታ ጊዜ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ረሳ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ረሱ።</verse>
				<verse number="2">ሮብ​ዓም በነ​ገሠ በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ዓመት የግ​ብፅ ንጉሥ ሱስ​ቀም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በድ​ለ​ዋ​ልና፤</verse>
				<verse number="3">ሺህ ሁለት መቶ ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ስድሳ ሺህ ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ይዞ መጣ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ከግ​ብፅ ለመ​ጣው ሕዝብ ቍጥር አል​ነ​በ​ረ​ውም፤ እነ​ር​ሱም የል​ብያ ሰዎች፥ ሞጠ​ግ​ሊ​ያ​ና​ው​ያን፥ የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያም ሰዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="4">በይ​ሁ​ዳም የነ​በ​ሩ​ትን ምሽ​ጎች ከተ​ሞች ያዙ። እስከ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ደረሱ።</verse>
				<verse number="5">ነቢ​ዩም ሰማያ ወደ ሮብ​ዓ​ምና ከሱ​ስ​ቀም ሸሽ​ተው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ተሰ​በ​ሰ​ቡት ወደ ይሁዳ መሳ​ፍ​ንት መጥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እና​ንተ ተዋ​ች​ሁኝ፤ ስለ​ዚህ እኔ ደግሞ በግ​ብፅ ንጉሥ በሱ​ስ​ቀም እጅ ተው​ኋ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="6">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መሳ​ፍ​ን​ትና ንጉሡ አፈሩ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድቅ ነው” አሉ።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተመ​ለ​ሱና እንደ ተፀ​ፀቱ ባየ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ “ከተ​መ​ለሱ አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ ከጥ​ቂት ቀንም በኋላ አድ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቍጣ​ዬም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ አይ​ፈ​ስ​ስም” ሲል ወደ ሰማያ መጣ።</verse>
				<verse number="8">ለእኔ መገ​ዛ​ት​ንና ለም​ድር ነገ​ሥ​ታት መገ​ዛ​ትን ያው​ቃ​ሉና አገ​ል​ጋ​ዮች ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="9">የግ​ብፅ ንጉሥ ሱስ​ቀ​ምም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤተ መዛ​ግ​ብ​ትና የን​ጉ​ሡን ቤተ መዛ​ግ​ብት ወሰደ፤ ሁሉ​ንም ወሰደ፤ ደግ​ሞም ሰሎ​ሞን የሠ​ራ​ቸ​ውን የወ​ር​ቁን አላ​ባሽ አግሬ ጋሻ​ዎ​ችን ወሰደ።</verse>
				<verse number="10">ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም በእ​ነ​ርሱ ፋንታ የናስ አላ​ባሽ አግሬ ጋሻ​ዎ​ችን ሠራ፤ ሮብ​ዓ​ምም የን​ጉ​ሡን ቤት ደጅ በሚ​ጠ​ብቁ በዘ​በ​ኞች አለቃ እጅ አኖ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ንጉ​ሡም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በገባ ቍጥር ዘበ​ኞች መጥ​ተው ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸው ነበር፤ መል​ሰ​ውም በዘ​በ​ኞች ቤት ውስጥ ያኖ​ሩ​አ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="12">በተ​ፀ​ፀ​ተም ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ከእ​ርሱ ዘንድ ራቀ፤ ፈጽ​ሞም አላ​ጠ​ፋ​ውም፤ በይ​ሁዳ መል​ካም ነገር ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="13">ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጸና፤ ንጉ​ሥም ሆነ፤ ሮብ​ዓ​ምም በነ​ገሠ ጊዜ የአ​ርባ አንድ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስሙን ያኖ​ር​ባት ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሀገር ሁሉ በመ​ረ​ጣት ከተማ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዐሥራ ሰባት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም የአ​ሞን ሴት ንዑማ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ይሻ ዘንድ ልቡን አላ​ቀ​ናም ነበ​ርና ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="15">የሮ​ብ​ዓ​ምም የፊ​ተ​ኛ​ውና የኋ​ለ​ኛው ነገር እነሆ፥ በነ​ቢዩ ሰማ​ያና በባለ ራእዩ በአዶ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን? ሮብ​ዓ​ምም ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ጋር በዘ​መኑ ሁሉ ይዋጋ ነበር።</verse>
				<verse number="16">ሮብ​ዓ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ተቀ​በረ፤ ልጁም አብያ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">ንጉ​ሡም ኢዮ​ር​ብ​ዓም በነ​ገሠ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመት አብያ በይ​ሁዳ ላይ ንጉሥ ሆነ።</verse>
				<verse number="2">ሦስት ዓመ​ትም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነገሠ፤ የእ​ና​ቱም ስም መዓካ ነበረ፤ የገ​ባ​ዖን ሰው የኡ​ር​ኤል ልጅ ነበ​ረች። በአ​ብ​ያና በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም መካ​ከ​ልም ሰልፍ ነበረ።</verse>
				<verse number="3">አብ​ያም የተ​መ​ረ​ጡ​ትን አራት መቶ ሺህ ኀያ​ላን ሰል​ፈ​ኞች ይዞ ወደ ሰልፍ ወጣ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም የተ​መ​ረ​ጡ​ትን ስም​ንት መቶ ሺህ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ይዞ በእ​ርሱ ላይ ተሰ​ለፈ።</verse>
				<verse number="4">አብ​ያም በኤ​ፍ​ሬም ተራራ ባለው በሳ​ም​ሮን ተራራ ላይ ቆሞ እን​ዲህ አለ፥ “ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምና እስ​ራ​ኤል ሁሉ ሆይ፥ ስሙኝ፤</verse>
				<verse number="5">የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ መን​ግ​ሥ​ትን ለዳ​ዊ​ትና ለል​ጆቹ በጨው ቃል ኪዳን ለዘ​ለ​ዓ​ለም እንደ ሰጠ በውኑ አታ​ው​ቁ​ምን?</verse>
				<verse number="6">የዳ​ዊት ልጅ የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋይ የና​ባጥ ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ግን ተነ​ሥቶ በጌ​ታው ላይ ዐመፀ።</verse>
				<verse number="7">ክፉ​ዎች ሰዎ​ችና የሕግ ተላ​ላ​ፊ​ዎች ልጆ​ችም ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሮብ​ዓም ሕፃን በነ​በ​ረና በልቡ ድፍ​ረት ባል​ነ​በ​ረው ጊዜ፥ ሊቋ​ቋ​መ​ውም ባል​ቻ​ለ​በት ጊዜ፥ በሰ​ሎ​ሞን ልጅ በሮ​ብ​ዓም ላይ በረ​ታ​በት።</verse>
				<verse number="8">አሁ​ንም በዳ​ዊት ልጆች እጅ የሚ​ሆ​ነ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ልት​ቋ​ቋሙ እን​ዲህ ትላ​ላ​ችሁ። እና​ን​ተም እጅግ ታላቅ ሕዝብ ናችሁ፥ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም አማ​ል​ክት አድ​ርጎ የሠ​ራ​ላ​ችሁ የወ​ርቅ እን​ቦ​ሶች ከእ​ና​ንተ ጋር ናቸው።</verse>
				<verse number="9">የአ​ሮ​ንን ልጆች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን አላ​ሳ​ደ​ዳ​ች​ሁ​ምን? ከም​ድ​ርም አሕ​ዛብ ሁሉ ለራ​ሳ​ችሁ ካህ​ና​ትን አላ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ምን? አንድ ወይ​ፈ​ንና ሰባት አውራ በጎ​ችን ይዞ ራሱን ይቀ​ድስ ዘንድ የሚ​መጣ ሁሉ አማ​ል​ክት ላል​ሆ​ኑት ለእ​ነ​ዚያ ካህን ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="10">እኛ ግን አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ተ​ው​ነ​ውም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋ​ዮች የአ​ሮን ልጆች ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያኑ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ያገ​ለ​ግ​ሉ​ታል።</verse>
				<verse number="11">በየ​ጥ​ዋ​ቱና በየ​ማ​ታ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ጣፋ​ጩን ዕጣን ያሳ​ር​ጋሉ፤ የገ​ጹ​ንም ኅብ​ስት በን​ጹሕ ገበታ ላይ፥ የወ​ር​ቁን መቅ​ረ​ዝና ቀን​ዲ​ሎ​ቹ​ንም ማታ ማታ እን​ዲ​ያ​በሩ ያዘ​ጋ​ጃሉ፤ እኛም የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ እን​ጠ​ብ​ቃ​ለን፤ እና​ንተ ግን ትታ​ች​ሁ​ታል።</verse>
				<verse number="12">እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኛ ላይ አለቃ ነው፤ መለ​ከ​ቱ​ንም የሚ​ነፉ ካህ​ናቱ ከእኛ ጋር ናቸው፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ ይጮ​ኻሉ። የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ፥ አይ​በ​ጃ​ች​ሁ​ምና ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አቷጉ።”</verse>
				<verse number="13">ኢዮ​ር​ብ​ዓም ግን በስ​ተ​ኋ​ላ​ቸው ይመ​ጣ​ባ​ቸው ዘንድ ድብቅ ጦር አዞ​ረ​ባ​ቸው፤ እነ​ርሱ በይ​ሁዳ ሰፈር ፊት ሳሉ ድብቅ ጦሩ በስ​ተ​ኋ​ላ​ቸው ከበ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ወደ ኋላ​ቸው በተ​መ​ለ​ከቱ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰልፉ በፊ​ታ​ቸ​ውና በኋ​ላ​ቸው ነበረ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጮኹ፤ ካህ​ና​ቱም መለ​ከ​ቱን ነፉ።</verse>
				<verse number="15">የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ጮኹ፤ የይ​ሁ​ዳም ሰዎች በጮኹ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ም​ንና እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ በይ​ሁዳ ንጉሥ በአ​ብ​ያና በሕ​ዝቡ ፊት መታ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከይ​ሁዳ ሰዎች ፊት ሸሹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ጃ​ቸው አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">አብ​ያና ሕዝ​ቡም ታላቅ አመ​ታት መቱ​አ​ቸው፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ስት መቶ ሺህ የተ​መ​ረጡ ሰዎች ተገ​ድ​ለው ወደቁ።</verse>
				<verse number="18">በዚ​ያም ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተዋ​ረዱ፤ የይ​ሁ​ዳም ልጆች በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታም​ነው ነበ​ርና አሸ​ነፉ።</verse>
				<verse number="19">አብ​ያም ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምን ተከ​ትሎ አሳ​ደ​ደው፤ ከእ​ር​ሱም ከተ​ሞ​ቹን ቤቴ​ል​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ ይሳ​ና​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ ዔፍ​ሮ​ን​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን ወሰደ።</verse>
				<verse number="20">ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ከዚያ በኋላ በአ​ብያ ዘመን አል​በ​ረ​ታም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀሠ​ፈው፤ ሞተም።</verse>
				<verse number="21">አብ​ያም ጸና፤ ዐሥራ አራት ሚስ​ቶ​ች​ንም አገባ፤ ሃያ ሁለ​ትም ወን​ዶች ልጆ​ች​ንና ዐሥራ ስድ​ስት ሴቶች ልጆ​ችን ወለደ።</verse>
				<verse number="22">የአ​ብ​ያም የቀ​ረው ነገ​ርና አካ​ሄዱ የተ​ና​ገ​ራ​ቸ​ውም ቃሎች በነ​ቢዩ በአዶ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፈ​ዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">አብ​ያም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት፤ ልጁም አሳ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ። በእ​ር​ሱም ዘመን ምድ​ሪቱ ዐሥር ዓመት ያህል ዐረ​ፈች።</verse>
				<verse number="2">አሳም በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካ​ምና ቅን ነገር አደ​ረገ፤</verse>
				<verse number="3">የእ​ን​ግ​ዶ​ቹ​ንም አማ​ል​ክት መሠ​ዊያ፥ የኮ​ረ​ብ​ታ​ው​ንም መስ​ገ​ጃ​ዎች አፈ​ረሰ፤ ሐው​ል​ቶ​ቹ​ንም ሰበረ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ አፀ​ዶ​ቹ​ንም ቈረጠ፤</verse>
				<verse number="4">የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይሹ ዘንድ፥ ሕጉ​ንና ትእ​ዛ​ዙ​ንም ያደ​ርጉ ዘንድ የይ​ሁ​ዳን ሕዝብ አዘዘ።</verse>
				<verse number="5">ከይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ሁሉ የጣ​ዖት መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ች​ንና ምስ​ሎ​ችን አስ​ወ​ገደ፤ መን​ግ​ሥ​ቱም በእ​ርሱ ሥር በሰ​ላም ተቀ​መ​ጠች።</verse>
				<verse number="6">በይ​ሁ​ዳም ምሽ​ጎች ከተ​ሞ​ችን ሠራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዕረ​ፍት ስለ ሰጠው ምድ​ሪቱ ጸጥ ብላ ነበር፤ በዚ​ያም ዘመን ጦር​ነት አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="7">እር​ሱም የይ​ሁ​ዳን ሰዎች፥ “እነ​ዚ​ህን ከተ​ሞች እን​ሥራ፤ ቅጥ​ርም፥ ግን​ብም፥ መዝ​ጊ​ያም፥ መወ​ር​ወ​ሪ​ያም እና​ድ​ር​ግ​ባ​ቸው፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም እን​ገ​ዛ​ታ​ለን፤ አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ ፈለ​ግ​ነው እር​ሱም ይፈ​ል​ገ​ና​ልና፤ እር​ሱም በዙ​ሪ​ያ​ችን ዕረ​ፍት ሰጥ​ቶ​ናል፤ ሁሉ​ንም አከ​ና​ወ​ነ​ልን” አለ።</verse>
				<verse number="8">ለአ​ሳም አላ​ባሽ አግሬ ጋሻና ጦር የሚ​ሸ​ከሙ ሦስት መቶ ሺህ የይ​ሁዳ ሠራ​ዊት፥ ወን​ጭፍ የሚ​ወ​ነ​ጭፉ፥ ቀስ​ትም የሚ​ገ​ትሩ ሁለት መቶ ሰማ​ንያ ሺህ የብ​ን​ያም ሰዎች ነበ​ሩት፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="9">የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያም ንጉሥ ዝሪ አንድ ሚሊ​ዮን ሰዎ​ችና ሦስት መቶ ሰረ​ገ​ሎች ይዞ ወጣ​ባ​ቸው፤ ወደ መሪ​ሳም መጣ።</verse>
				<verse number="10">የይ​ሁዳ ንጉሥ አሳም ሊጋ​ጠ​መው ወጣ፤ በመ​ሪ​ሳም ደቡብ አጠ​ገብ ባለው ሸለቆ ውስጥ ተሰ​ለፉ።</verse>
				<verse number="11">አሳም፥ “አቤቱ፥ በብ​ዙም ሆነ በጥ​ቂቱ ማዳን አይ​ሳ​ን​ህም፤ አቤቱ፥ አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ በአ​ንተ ታም​ነ​ና​ልና፥ በስ​ም​ህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥ​ተ​ና​ልና ርዳን፤ አቤቱ፥ አም​ላ​ካ​ችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያ​ሸ​ን​ፍ​ህም” ብሎ ወደ አም​ላኩ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሳና በይ​ሁዳ ሕዝብ ፊት ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያ​ንን መታ፤ ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያ​ንም ሸሹ።</verse>
				<verse number="13">አሳም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ያለው ሕዝብ እስከ ጌዶር ሀገር ድረስ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያ​ንም ፈጽ​መው እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ ወደቁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በሠ​ራ​ዊቱ ፊት ተሰ​ባ​ብ​ረ​ዋ​ልና፤ እጅ​ግም ብዙ ምርኮ ወሰዱ።</verse>
				<verse number="14">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ ታላቅ ድን​ጋጤ ስለ ወደ​ቀ​ባ​ቸው በጌ​ዶር ዙሪያ የነ​በ​ሩ​ትን ከተ​ሞች ሁሉ መቱ፤ በከ​ተ​ሞ​ቹም ውስጥ እጅግ ብዙ ምር​ኮና ብዝ​በዛ ነበ​ርና ከተ​ሞ​ቹን ሁሉ ማረኩ።</verse>
				<verse number="15">የከ​ብ​ቶ​ቹ​ንም በረት አፈ​ረሱ፤ እጅግ ብዙ በጎ​ች​ንና ግመ​ሎ​ች​ንም ወሰዱ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተመ​ለሱ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በአ​ዳድ ልጅ በአ​ዛ​ር​ያስ ላይ መላ፤</verse>
				<verse number="2">እር​ሱም ንጉ​ሡን አሳን፥ የይ​ሁ​ዳ​ንና የብ​ን​ያ​ምን ሕዝብ ሁሉ ሊገ​ናኝ ወጣ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አሳ ይሁ​ዳና ብን​ያም ሁሉ ሆይ፥ ስሙኝ፤ እና​ንተ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ብት​ሆኑ እርሱ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሆ​ናል፤ ብት​ፈ​ል​ጉ​ትም ይገ​ኝ​ላ​ች​ኋል፤ ብት​ተ​ዉት ግን ይተ​ዋ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="3">እስ​ራ​ኤ​ልም ብዙ ዘመን እው​ነ​ተ​ኛ​ውን አም​ላክ ሳያ​መ​ልኩ፥ ያለ አስ​ተ​ማ​ሪም ካህን፥ ያለ ሕግም ይኖ​ራሉ።</verse>
				<verse number="4">በመ​ከ​ራ​ቸ​ውም ጊዜ ወደ እስ​ራ​ኤል አም​ላክ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ል​ሰው ይፈ​ል​ጉ​ታል፤ እር​ሱም ይገ​ኝ​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="5">በዚ​ያም ዘመን ለሚ​ወ​ጣ​ውና ለሚ​ገ​ባው ሰላም አይ​ሆ​ን​ለ​ትም፤ በሀ​ገ​ሮ​ችም በሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ላይ ታላቅ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ከ​ራው ሁሉ ያስ​ጨ​ን​ቃ​ቸ​ዋ​ልና ሕዝብ ከሕ​ዝብ ጋር፥ ከተ​ማም ከከ​ተማ ጋር ይዋ​ጋል። ።</verse>
				<verse number="7">እና​ንተ ግን ለሥ​ራ​ችሁ ዋጋ ይሆ​ን​ላ​ች​ኋ​ልና በርቱ፤ እጆ​ቻ​ች​ሁም አይ​ላሉ።”</verse>
				<verse number="8">አሳም ይህን ቃልና የነ​ቢ​ዩን የአ​ዳ​ድን ልጅ የአ​ዛ​ር​ያ​ስን ትን​ቢት በሰማ ጊዜ ጸና፤ ከይ​ሁ​ዳና ከብ​ን​ያ​ምም ሀገር ሁሉ በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ከያ​ዛ​ቸው ከተ​ሞች ርኵ​ሰ​ትን ሁሉ አስ​ወ​ገደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ፊት የነ​በ​ረ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መሠ​ዊያ አደሰ።</verse>
				<verse number="9">አም​ላ​ኩም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተጠ​ግ​ተው ነበ​ርና እርሱ ይሁ​ዳ​ንና ብን​ያ​ምን ሁሉ፥ ከኤ​ፍ​ሬ​ምና ከም​ና​ሴም፥ ከስ​ም​ዖ​ንም ፈል​ሰው ከእ​ነ​ርሱ ጋር የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ሰበ​ሰበ።</verse>
				<verse number="10">አሳም በነ​ገሠ በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ዓመት በሦ​ስ​ተ​ኛው ወር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="11">በዚ​ያም ቀን ካመ​ጡት ምርኮ ሰባት መቶ በሬ​ዎ​ች​ንና ሰባት ሺህ በጎ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠዋ።</verse>
				<verse number="12">በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውና በፍ​ጹም ነፍ​ሳ​ቸው የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይሹ ዘንድ ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤</verse>
				<verse number="13">የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የማ​ይ​ፈ​ልግ፥ ታናሽ ወይም ታላቅ፥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን፥ ይገ​ደል ዘንድ ማሉ።</verse>
				<verse number="14">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በታ​ላቅ ድም​ፅና በእ​ል​ልታ፥ በእ​ን​ቢ​ል​ታና በቀ​ንደ መለ​ከት ማሉ።</verse>
				<verse number="15">በፍ​ጹ​ምም ልባ​ቸው ምለ​ዋ​ልና፥ በፍ​ጹ​ምም ሕሊ​ና​ቸው ፈል​ገ​ው​ታ​ልና፥ እር​ሱም ተገ​ኝ​ቶ​ላ​ቸ​ዋ​ልና ይሁዳ ሁሉ በመ​ሐ​ላው ደስ አላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዙ​ሪ​ያ​ቸው ዕረ​ፍ​ትን ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">ንጉ​ሡም አሳ እና​ቱን መዓ​ካን ለአ​ስ​ጣ​ር​ቴስ ስለ ሰገ​ደች ከእ​ቴ​ጌ​ነቷ አወ​ረ​ዳት፤ አሳም ምስ​ሉን ቈርጦ ቀጠ​ቀ​ጠው፤ በቄ​ድ​ሮ​ንም ወንዝ አጠ​ገብ አቃ​ጠ​ለው።</verse>
				<verse number="17">በኮ​ረ​ብታ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎች ግን ከእ​ስ​ራ​ኤል አላ​ራ​ቀም። ገና በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ እስከ አሁን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ የአሳ ልብ በዘ​መኑ ሁሉ ፍጹም ነበረ።</verse>
				<verse number="18">አባ​ቱም ዳዊት የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ እር​ሱም የቀ​ደ​ሰ​ውን ወር​ቁ​ንና ብሩን፥ ልዩ ልዩ​ው​ንም ዕቃ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት​አ​ገባ።</verse>
				<verse number="19">አሳም በነ​ገ​ሠ​በት ዘመን እስከ ሠላሳ አም​ስ​ተ​ኛው ዓመት ድረስ ጦር​ነት አል​ነ​በ​ረም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">አሳ በነ​ገሠ በሠ​ላሳ ስድ​ስ​ተ​ኛው ዓመት የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ባኦስ በይ​ሁዳ ላይ ዘመተ፥ ወደ ይሁ​ዳም ንጉሥ ወደ አሳ ማንም መው​ጣ​ትና መግ​ባት እን​ዳ​ይ​ችል ራማን ሠራት።</verse>
				<verse number="2">አሳም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና ከን​ጉሥ ቤት መዝ​ገብ ብርና ወርቅ ወስዶ፦ በደ​ማ​ስቆ ወደ ተቀ​መ​ጠው ወደ ሶርያ ንጉሥ ወደ ወልደ አዴር ላከ። እን​ዲ​ህም አለው፦</verse>
				<verse number="3">“በአ​ባ​ቴና በአ​ባ​ትህ መካ​ከል እንደ ነበ​ረው ቃል ኪዳን በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል አድ​ርግ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ባኦስ ከእኔ ዘንድ እን​ዲ​ርቅ መጥ​ተህ ትወ​ጋው ዘንድ እነሆ፥ ወር​ቅና ብር ልኬ​ል​ሃ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="4">ወልደ አዴ​ርም ንጉ​ሡን አሳን ሰማው፤ የሠ​ራ​ዊ​ቱ​ንም አለ​ቆች በእ​ስ​ራ​ኤል ከተ​ሞች ላይ ሰደደ፤ እነ​ር​ሱም አእ​ዮ​ን​ንና ዳንን፥ አቤ​ል​ማ​ይ​ም​ንና የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም አው​ራጃ ከተ​ሞች ሁሉ መቱ።</verse>
				<verse number="5">ባኦ​ስም በሰማ ጊዜ ራማን መሥ​ራት ተወ፤ ሥራ​ው​ንም አቋ​ረጠ።</verse>
				<verse number="6">የይ​ሁዳ ንጉሥ አሳም የይ​ሁ​ዳን ሰዎች ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ ባኦስ ይሠ​ራ​በት የነ​በ​ረ​ውን የራ​ማን ድን​ጋ​ይና እን​ጨት ወሰደ፤ እር​ሱም ገባ​ዖ​ን​ንና መሴ​ፋን ሠራ​በት።</verse>
				<verse number="7">በዚ​ያን ጊዜም ነቢዩ አናኒ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ መጥቶ እን​ዲህ አለው፥ “በሶ​ርያ ንጉሥ ታም​ነ​ሃ​ልና፥ በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ታ​መ​ን​ህ​ምና ስለ​ዚህ የሶ​ርያ ንጉሥ ጭፍራ ከእ​ጆ​ችህ አም​ል​ጠ​ዋል።</verse>
				<verse number="8">ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያ​ንና የል​ብያ ሰዎች እጅግ ብዙ ሰረ​ገ​ሎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች የነ​በ​ሩ​አ​ቸው እጅግ ታላቅ ጭፍራ አል​ነ​በ​ሩ​ምን? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ታመ​ንህ በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡ በእ​ርሱ ዘንድ ፍጹም የሆ​ነ​ውን ያጸና ዘንድ ዐይ​ኖቹ በም​ድር ሁሉ ይመ​ለ​ከ​ታ​ሉና። አሁ​ንም ባለ​ማ​ወ​ቅህ በድ​ለ​ሃል፤ ስለ​ዚ​ህም ከዛሬ ጀምሮ ጦር​ነት ይሆ​ን​ብ​ሃል።”</verse>
				<verse number="10">አሳም በነ​ቢዩ በአ​ናኒ ላይ ተቈጣ፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር ተቈ​ጥ​ቶ​አ​ልና በግ​ዞት አኖ​ረው፤ በዚ​ያን ጊዜም አሳ ከሕ​ዝቡ አያሌ ሰዎ​ችን አስ​ጨ​ነቀ።</verse>
				<verse number="11">የአ​ሳም የፊ​ተ​ኛ​ውና የኋ​ለ​ኛው ነገር፥ እነሆ፥ በይ​ሁ​ዳና በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።</verse>
				<verse number="12">አሳም በነ​ገሠ በሠ​ላሳ ዘጠ​ነ​ኛው ዓመት እግ​ሩን ታመመ፤ ደዌ​ውም ጸና​በት፤ ነገር ግን በሕ​ማሙ ጊዜ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶ​ችን እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ፈ​ለ​ገም።</verse>
				<verse number="13">አሳም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በነ​ገ​ሠም በአ​ርባ አን​ደ​ኛው ዓመት ሞተ።</verse>
				<verse number="14">ለእ​ር​ሱም ለራሱ በሠ​ራው መቃ​ብር በዳ​ዊት ከተማ ቀበ​ሩት፤ በቀ​ማሚ ብል​ሃት የተ​ሰ​ናዳ ልዩ ልዩ መል​ካም ሽቱ በተ​ሞላ አልጋ ላይም አኖ​ሩት፤ እጅ​ግም ታላቅ የሆነ የቀ​ብር ሥር​ዐት አደ​ረ​ጉ​ለት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">ከአ​ሳም በኋላ ልጁ ኢዮ​ሳ​ፍጥ ነገሠ፤ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ጠነ​ከረ።</verse>
				<verse number="2">በተ​መ​ሸ​ጉ​ትም በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ሁሉ ሠራ​ዊ​ቱን አኖረ፤ በይ​ሁ​ዳም ሀገር፥ አባ​ቱም አሳ በወ​ሰ​ዳ​ቸው በኤ​ፍ​ሬም ከተ​ሞች መሳ​ፍ​ን​ቱን አስ​ቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ ጋር ነበረ፤ በፊ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም በአ​ባቱ በዳ​ዊት መን​ገድ ሄዶ​አ​ልና፥ ጣዖ​ት​ንም አል​ፈ​ለ​ገ​ምና፤</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን የአ​ባ​ቱን አም​ላክ ፈለገ፤ በአ​ባ​ቱም ትእ​ዛዝ ሄደ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሥራ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥ​ቱን በእጁ አጸና፤ ይሁ​ዳም ሁሉ እጅ መንሻ ለኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ አመጣ፤ እጅ​ግም ብዙ ብል​ጥ​ግ​ናና ክብር ሆነ​ለት።</verse>
				<verse number="6">ልቡም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገድ ከፍ ከፍ አለ፤ የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችና የማ​ም​ለ​ኪያ አፀ​ዱ​ንም ከይ​ሁዳ አስ​ወ​ገደ።</verse>
				<verse number="7">በነ​ገ​ሠም በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ መሳ​ፍ​ን​ቱ​ንና ኀያ​ላ​ኑን ሰዎች አብ​ድ​ያ​ስን፥ ዘካ​ር​ያ​ስን፥ ናት​ና​ኤ​ልን፥ ሚኪ​ያ​ስን ላከ።</verse>
				<verse number="8">ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሌዋ​ው​ያ​ንን ሸማ​ያን፥ ነታ​ን​ያን፥ ዛባ​ድ​ያን፥ አሣ​ሄ​ልን፥ ሰሚ​ራ​ሞ​ትን፥ ዮና​ታ​ንን፥ አዶ​ን​ያ​ስን፥ ጦብ​ያን፥ ጦባ​ዶ​ን​ያ​ስን ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ካህ​ና​ቱን ኤሊ​ሳ​ማ​ንና ኢዮ​ራ​ምን ላከ።</verse>
				<verse number="9">እነ​ር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ ይዘው በይ​ሁዳ ያስ​ተ​ምሩ ነበር፤ ወደ ይሁ​ዳም ከተ​ሞች ሁሉ ተመ​ላ​ል​ሰው ሕዝ​ቡን አስ​ተ​ማሩ።</verse>
				<verse number="10">በይ​ሁ​ዳም ዙሪያ በነ​በሩ የም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ድን​ጋጤ ሆነ፤ ከኢ​ዮ​ሳ​ፍ​ጥም ጋር አል​ተ​ዋ​ጉም።</verse>
				<verse number="11">ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ለኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ እጅ መን​ሻና የብር ግብር ያመጡ ነበር፤ ዐረ​ባ​ው​ያ​ንም ደግሞ ከመ​ን​ጎ​ቻ​ቸው ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ በጎ​ች​ንና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ ፍየ​ሎ​ችን ያመ​ጡ​ለት ነበር።</verse>
				<verse number="12">ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም እየ​በ​ረ​ታና እጅ​ግም እየ​ከ​በረ ሄደ፤ በይ​ሁ​ዳም ግን​ቦ​ች​ንና የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞ​ችን ሠራ።</verse>
				<verse number="13">በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ብዙ ሥራ ሠራ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰል​ፈ​ኞች ነበ​ሩት።</verse>
				<verse number="14">ቍጥ​ራ​ቸ​ውም እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ይህ ነበረ፤ ከይ​ሁዳ ሻለ​ቆች አለ​ቃው ዓድ​ናስ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሦስት መቶ ሺህ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ነበሩ፤</verse>
				<verse number="15">ከእ​ር​ሱም በኋላ አለ​ቃው ኢዮ​አ​ናን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሁለት መቶ ሰማ​ንያ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤</verse>
				<verse number="16">ከእ​ር​ሱም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግል የዝ​ክሪ ልጅ ማስ​ያስ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሁለት መቶ ሺህ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="17">ከብ​ን​ያ​ምም ጽኑዕ ኀያል የነ​በ​ረው ኤሊ​ያዳ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ቀስት የሚ​ገ​ትሩ፥ ወን​ጭፍ የሚ​ወ​ነ​ጭፉ ሁለት መቶ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤</verse>
				<verse number="18">ከእ​ር​ሱም በኋላ ዮዛ​ባድ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ለሰ​ልፍ የተ​ዘ​ጋጁ መቶ ሰማ​ንያ ሺህ ሰዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="19">ንጉሡ በተ​መ​ሸጉ በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ሁሉ ካኖ​ራ​ቸ​ውም ሌላ እነ​ዚህ ንጉ​ሡን ያገ​ለ​ግሉ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">ለኢ​ዮ​ሣ​ፍ​ጥም ብዙ ብል​ጥ​ግ​ናና ክብር ነበ​ረው፤ ከአ​ክ​ዓ​ብም ወገን ሚስት አገባ።</verse>
				<verse number="2">ከጥ​ቂት ዓመ​ታት በኋ​ላም ወደ አክ​ዓብ ወደ ሰማ​ርያ ወረደ። አክ​ዓ​ብም ለእ​ር​ሱና ከእ​ርሱ ጋር ለነ​በ​ሩት ሕዝብ ብዙ በጎ​ች​ንና በሬ​ዎ​ችን አረደ፤ ወደ​ደ​ውም፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ይሄድ ዘንድ አባ​በ​ለው።</verse>
				<verse number="3">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አክ​ዓብ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ከእኔ ጋር ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ትሄ​ዳ​ለ​ህን?” አለው። እር​ሱም፥ “እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝ​ቤም ለሰ​ልፍ እንደ ሕዝ​ብህ ናቸው፤” ብሎ መለ​ሰ​ለት።</verse>
				<verse number="4">ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ፥ “ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠይቅ” አለው።</verse>
				<verse number="5">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ከነ​ቢ​ያቱ አራት መቶ ሰዎ​ችን ሰብ​ስቦ፥ “ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ለሰ​ልፍ ልሂ​ድን? ወይስ ልቅር?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በን​ጉሥ እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ታ​ልና ውጣ” አሉት።</verse>
				<verse number="6">ኢዮ​ሣ​ፍጥ ግን፥ “እን​ጠ​ይ​ቀው ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ የሆነ ሌላ ሰው በዚህ አይ​ገ​ኝ​ምን?” አለ።</verse>
				<verse number="7">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ን​ጠ​ይ​ቅ​በት አንድ ሰው አለ፤ ነገር ግን ሁል​ጊዜ ክፉ እንጂ ከቶ መል​ካም ትን​ቢት አይ​ና​ገ​ር​ል​ኝ​ምና እጠ​ላ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም የይ​ምላ ልጅ ሚክ​ያስ ነው” አለው። ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም፥ “ንጉሡ እን​ዲህ አይ​በል” አለው።</verse>
				<verse number="8">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አንድ ጃን​ደ​ረባ ጠርቶ፥ “የይ​ም​ላን ልጅ ሚክ​ያ​ስን ፈጥ​ነህ አም​ጣው” አለው።</verse>
				<verse number="9">የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥና የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ልብሰ መን​ግ​ሥት ለብ​ሰው በሰ​ማ​ርያ በር መግ​ቢያ አጠ​ገብ በአ​ደ​ባ​ባይ በዙ​ፋ​ኖ​ቻ​ቸው ላይ ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ ነቢ​ያ​ትም ሁሉ በፊ​ታ​ቸው ትን​ቢት ይና​ገሩ ነበር።</verse>
				<verse number="10">የካ​ህ​ናን ልጅ ሴዴ​ቅ​ያ​ስም የብ​ረት ቀን​ዶች ሠርቶ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሶር​ያ​ው​ያ​ንን እስ​ክ​ታ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ በእ​ነ​ዚህ ትወ​ጋ​ለህ” አለ።</verse>
				<verse number="11">ነቢ​ያ​ትም ሁሉ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በን​ጉሡ እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ታ​ልና ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ውጣና ተከ​ና​ወን” እያሉ እን​ዲሁ ትን​ቢት ይና​ገሩ ነበር።</verse>
				<verse number="12">ሚክ​ያ​ስ​ንም ሊጠራ የሄደ መል​እ​ክ​ተኛ፥ “እነሆ፥ ነቢ​ያት በአ​ንድ አፍ ሆነው ለን​ጉሡ መል​ካም ይና​ገ​ራሉ፤ ቃል​ህም እንደ ቃላ​ቸው እን​ዲ​ሆን መል​ካም እን​ድ​ት​ና​ገር እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="13">ሚክ​ያ​ስም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! አም​ላኬ የሚ​ለ​ውን እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="14">ወደ ንጉ​ሡም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፥ “ሚክ​ያስ ሆይ፥ ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ለሰ​ልፍ ልሂ​ድን? ወይስ ልቅር?” አለው።</verse>
				<verse number="15">ነቢዩ ሚክ​ያ​ስም፥ “ውጣ፤ ተከ​ና​ወን፤ በእ​ጅ​ህም አል​ፈው ይሰ​ጣሉ” አለ። ንጉ​ሡም፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ከእ​ው​ነት በቀር እን​ዳ​ት​ነ​ግ​ረኝ ስንት ጊዜ አም​ል​ሃ​ለሁ?” አለው።</verse>
				<verse number="16">እር​ሱም፥ “እስ​ራ​ኤል ሁሉ ጠባቂ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው በጎች በተ​ራ​ሮች ላይ ተበ​ት​ነው አየሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ለእ​ነ​ዚህ ጌታ የላ​ቸ​ውም፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም በሰ​ላም ወደ ቤቱ ይመ​ለስ አለ” ብሎ ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="17">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ክፉ እንጂ መል​ካም ትን​ቢት አይ​ና​ገ​ር​ል​ኝም አላ​ል​ሁ​ህ​ምን?” አለው።</verse>
				<verse number="18">ሚክ​ያ​ስም አለ፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ፋኑ ተቀ​ምጦ፥ የሰ​ማይ ሠራ​ዊት ሁሉ በቀ​ኙና በግ​ራው፤ ቆመው አየሁ።”</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ወጥቶ በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ ይወ​ድቅ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ አክ​ዓ​ብን የሚ​ያ​ታ​ልል ማን ነው?” አለ። አን​ዱም እን​ደ​ዚህ፥ ሌላ​ውም እን​ደ​ዚያ ያለ ነገር ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="20">መን​ፈ​ስም መጣ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቆሞ፥ “እኔ አታ​ል​ለ​ዋ​ለሁ” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በምን ታታ​ል​ለ​ዋ​ለህ?” አለው።</verse>
				<verse number="21">እር​ሱም፥ “ወጥቼ በነ​ቢ​ያት ሁሉ አፍ የሐ​ሰት መን​ፈስ እሆ​ና​ለሁ” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ታታ​ል​ለ​ዋ​ለህ፤ ይቀ​ና​ሃል፥ ውጣ፤ እን​ዲ​ህም አድ​ርግ” አለው።</verse>
				<verse number="22">“አሁ​ንም እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ነ​ዚህ በነ​ቢ​ያ​ትህ አፍ የሐ​ሰት መን​ፈ​ስን አድ​ር​ጎ​አል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ንተ ላይ ክፉ ተና​ግ​ሮ​ብ​ሃል።”</verse>
				<verse number="23">የካ​ህ​ና​ንም ልጅ ሴዴ​ቅ​ያስ ቀረበ፤ ሚክ​ያ​ስ​ንም በጥፊ መታ​ውና፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ከአ​ንተ ጋር ይና​ገር ዘንድ በምን መን​ገድ ከእኔ አለፈ?” አለው።</verse>
				<verse number="24">ሚክ​ያ​ስም፥ “እነሆ፥ በዚያ ቀን ልት​ሸ​ሸግ ከእ​ል​ፍኝ ወደ እል​ፍኝ ስት​ሄድ ታያ​ለህ” አለ።</verse>
				<verse number="25">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ እን​ዲህ አለ፥ “ሚክ​ያ​ስን ውሰዱ፤ ወደ ከተ​ማ​ዪ​ቱም አለቃ ወደ ኤሜር፥ ወደ ንጉ​ሡም ልጆች አለቃ ወደ ኢዮ​አስ መል​ሱት</verse>
				<verse number="26">እን​ዲ​ህም በሉ​አ​ቸው፦ ንጉሡ እን​ዲህ ይላል፦ በደ​ኅና እስ​ክ​መ​ለስ ድረስ ይህን ሰው በግ​ዞት አኑ​ሩት፤ የመ​ከ​ራም እን​ጀራ መግ​ቡት፤ የመ​ከ​ራም ውኃ አጠ​ጡት።”</verse>
				<verse number="27">ሚክ​ያ​ስም፥ “በደ​ኅና ብት​መ​ለስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኔ አል​ተ​ና​ገ​ረም” አለ። “ደግ​ሞም እና​ንተ ሕዝቡ ሁሉ ስሙኝ” አለ።</verse>
				<verse number="28">የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥና የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ወጡ።</verse>
				<verse number="29">የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥም ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ልብ​ሴን ለውጬ ወደ ጦር​ነት እገ​ባ​ለሁ፤ አንተ ግን የእ​ኔን ልብስ ልበስ” አለው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ልብ​ሱን ለወጠ፤ ወደ ሰል​ፍም ገባ።</verse>
				<verse number="30">የሶ​ር​ያም ንጉሥ ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትን የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹን አለ​ቆች፦ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በቀር ትንሽ ቢሆን ወይም ትልቅ ከማ​ና​ቸ​ውም ጋር አት​ጋ​ጠሙ ብሎ አዝዞ ነበር።</verse>
				<verse number="31">የሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም አለ​ቆች ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን ባዩ ጊዜ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ነው” አሉ፤ ሊጋ​ጠ​ሙ​ትም ከበ​ቡት፤ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ግን ጮኸ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አዳ​ነው፤ አም​ላ​ኩም ከእ​ርሱ መለ​ሳ​ቸው።</verse>
				<verse number="32">የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹም አለ​ቆች የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እን​ዳ​ል​ሆነ ባዩ ጊዜ ከእ​ርሱ ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="33">አንድ ሰውም ቀስ​ቱን በድ​ን​ገት ገትሮ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ በጥ​ሩሩ መጋ​ጠ​ሚያ በኩል ሳን​ባ​ውን ወጋው። ሰረ​ገ​ለ​ኛ​ው​ንም፥ “ተወ​ግ​ቻ​ለ​ሁና እጅ​ህን ግታ፤ ከጦ​ር​ነት ውስጥ አው​ጣኝ” አለው።</verse>
				<verse number="34">በዚ​ያም ቀን ጦር​ነት በረታ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በሶ​ር​ያ​ው​ያን ፊት እስከ ማታ ድረስ በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ራሱን ይደ​ግፍ ነበር፤ ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ ሞተ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ወደ ቤቱ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በሰ​ላም ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="2">ነቢዩ የአ​ናኒ ልጅ ኢዩ ሊገ​ና​ኘው ወጣ፤ ንጉ​ሡ​ንም ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ታግ​ዛ​ለ​ህን? ወይስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ጠ​ላ​ውን ትወ​ድ​ዳ​ለ​ህን? ስለ​ዚ​ህም ነገር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ቍጣ መጥ​ቶ​ብ​ሃል።</verse>
				<verse number="3">ነገር ግን የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ችን ከም​ድረ ይሁዳ አስ​ወ​ግ​ደ​ሃ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ትፈ​ልግ ዘንድ ልብ​ህን አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ሃ​ልና መል​ካም ነገር ተገ​ኝ​ቶ​ብ​ሃል” አለው።</verse>
				<verse number="4">ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መጠ፤ ደግ​ሞም ከቤ​ር​ሳ​ቤህ ጀምሮ እስከ ተራ​ራ​ማው እስከ ኤፍ​ሬም ሀገር ድረስ ወደ ሕዝቡ ወጥቶ ወደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መለ​ሳ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">በተ​መ​ሸ​ጉት በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ሁሉ በእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ከተማ ውስጥ ፈራ​ጆ​ችን ሾመ።</verse>
				<verse number="6">ፈራ​ጆ​ቹ​ንም፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንጂ ለሰው አት​ፈ​ር​ዱ​ምና፥ የፍ​ር​ድም ነገር ከእ​ና​ንተ ጋር ነውና የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን ተመ​ል​ከቱ።</verse>
				<verse number="7">አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት በእ​ና​ንተ ላይ ይሁን፤ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በደ​ልና ለሰው ፊት ማድ​ላት፥ መማ​ለ​ጃም መው​ሰድ የለ​ምና ሁሉን ተጠ​ን​ቅ​ቃ​ችሁ አድ​ርጉ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ከሌ​ዋ​ው​ያ​ንና ከካ​ህ​ናት፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሚ​ኖሩ ላይ ፍር​ድን እን​ዲ​ፈ​ርዱ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሾመ።</verse>
				<verse number="9">እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ፍ​ራት፥ በቅ​ን​ነ​ትም፥ በፍ​ጹ​ምም ልብ አድ​ርጉ።”</verse>
				<verse number="10">በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ከተ​ቀ​መ​ጡት ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ በደ​ምና በደም መካ​ከል፥ በሕ​ግና በት​እ​ዛዝ፥ በሥ​ር​ዐ​ትና በፍ​ር​ድም መካ​ከል ያለ ማና​ቸ​ውም ሰው ለፍ​ርድ ወደ እና​ንተ ቢመጣ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ይ​በ​ድሉ፥ ቍጣም በእ​ና​ን​ተና በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ላይ እን​ዳ​ይ​መጣ አስ​ጠ​ን​ቅ​ቁ​አ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም ብታ​ደ​ርጉ በደ​ለ​ኞች አት​ሆ​ኑም።</verse>
				<verse number="11">እነ​ሆም፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ሆ​ነው ነገር ሁሉ የካ​ህ​ናቱ አለቃ አማ​ርያ፥ በን​ጉ​ሡም ነገር ሁሉ የይ​ሁዳ ቤት አለቃ የይ​ስ​ማ​ኤል ልጅ ዝባ​ድ​ያስ በላ​ያ​ችሁ ተሾ​መ​ዋል፤ ጸሐ​ፍ​ቱና ሌዋ​ው​ያኑ ደግሞ በፊ​ታ​ችሁ አሉ፤ በር​ት​ታ​ች​ሁም አድ​ርጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካም ከሚ​ያ​ደ​ርግ ጋር ይሁን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከዚህ በኋላ የሞ​ዓ​ብና የአ​ሞን ልጆች ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ምዑ​ና​ው​ያን ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን ሊወጉ መጡ።</verse>
				<verse number="2">ሰዎ​ችም መጥ​ተው፥ “ከባ​ሕሩ ማዶ ከሶ​ርያ ታላቅ ሠራ​ዊት መጥ​ቶ​ብ​ሃል፤ እነ​ሆም፥ ዓይ​ን​ጋዲ በተ​ባ​ለች በሐ​ሴ​ሶን ታማር ናቸው” ብለው ለኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="3">ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ፈራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሊፈ​ልግ ፊቱን አቀና፤ በይ​ሁ​ዳም ሁሉ ጾም አወጀ።</verse>
				<verse number="4">ይሁ​ዳም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ልግ ዘንድ ተሰ​በ​ሰበ፤ ከይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ልጉ ዘንድ መጡ።</verse>
				<verse number="5">ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጉባኤ መካ​ከል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በአ​ዲሱ አደ​ባ​ባይ ፊት ቆመ፤</verse>
				<verse number="6">እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ ሆይ፥ በሰ​ማይ ያለህ አም​ላክ አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? የአ​ሕ​ዛ​ብ​ንስ መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ የም​ት​ገዛ አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? ኀይ​ልና ችሎታ በእ​ጅህ ነው፤ ሊቋ​ቋ​ም​ህም የሚ​ችል የለም።</verse>
				<verse number="7">አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ በዚህ ምድር የነ​በ​ሩ​ትን አሕ​ዛብ ከሕ​ዝ​ብህ ከእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ያሳ​ደ​ድህ፥ ለወ​ዳ​ጅ​ህም ለአ​ብ​ር​ሃም ዘር ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሰ​ጠ​ሃት አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን?</verse>
				<verse number="8">እነ​ርሱ ተቀ​መ​ጡ​ባት፤ ለስ​ም​ህም መቅ​ደ​ስን ሠሩ​ባት።</verse>
				<verse number="9">እን​ዲ​ህም አሉ፦ ክፉ ነገር፥ የፍ​ርድ ሰይፍ ወይም ቸነ​ፈር ወይም ራብ፥ ቢመ​ጣ​ብን በዚህ ቤት ፊትና በፊ​ትህ እን​ቆ​ማ​ለን፤ ስምህ በዚህ ቤት ላይ ነውና፤ በመ​ከ​ራ​ች​ንም ወደ አንተ እን​ጮ​ኻ​ለን፥ አን​ተም ሰም​ተህ ታድ​ነ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="10">አሁ​ንም እነሆ፥ እስ​ራ​ኤል ከግ​ብዕ ምድር በወጡ ጊዜ ያል​ፉ​ባ​ቸው ዘንድ ያል​ፈ​ቀ​ድ​ህ​ላ​ቸው የአ​ሞ​ንና የሞ​ዓብ ልጆች፥ የሴ​ይ​ርም ተራራ ሰዎች እን​ዳ​ያ​ጠ​ፉ​አ​ቸው ከእ​ነ​ርሱ ፈቀቅ ብለው ነበር።</verse>
				<verse number="11">እነሆ፥ አሁን ለወ​ሮ​ታ​ችን ክፋት ይመ​ል​ሱ​ል​ናል፤ ከሰ​ጠ​ኸ​ንም ርስት ያወ​ጡን ዘንድ መጥ​ተ​ዋል።</verse>
				<verse number="12">አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ አንተ አት​ፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ው​ምን? ይህን የመ​ጣ​ብ​ንን ታላቅ ወገን መቃ​ወም እን​ችል ዘንድ ኀይል የለ​ንም፤ የም​ና​ደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ው​ንም አና​ው​ቅም፤ ነገር ግን ዐይ​ኖ​ቻ​ችን ወደ አንተ ናቸው።”</verse>
				<verse number="13">የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ሁሉ ከሚ​ስ​ቶ​ቻ​ቸው፥ ከል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆመው ነበር።</verse>
				<verse number="14">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ ከአ​ሳፍ ወገን በነ​በ​ረው በሌ​ዋ​ዊው በም​ታ​ን​ያስ ልጅ በኢ​ያ​ሔል ልጅ በብ​ል​አ​ንያ ልጅ በዘ​ካ​ር​ያስ ልጅ በኡ​ዝ​ሔል ላይ በጉ​ባ​ኤው መካ​ከል መጣ፤</verse>
				<verse number="15">እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይሁዳ ሁሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የም​ት​ኖሩ፥ አን​ተም ንጉሡ ኢዮ​ሣ​ፍጥ! ስሙ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ች​ኋል፦ ሰልፉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው እንጂ የእ​ና​ንተ አይ​ደ​ለ​ምና ከዚህ ታላቅ ወገን የተ​ነሣ አት​ፍሩ፤ አት​ደ​ን​ግ​ጡም።</verse>
				<verse number="16">ነገ በእ​ነ​ርሱ ላይ ውረዱ፤ እነሆ፥ በአ​ሲስ ዐቀ​በት ይወ​ጣሉ፤ በሸ​ለ​ቆ​ውም መጨ​ረሻ በኢ​ያ​ር​ሔል ምድረ በዳ ፊት ለፊት ታገ​ኙ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="17">እና​ንተ የም​ቷጉ አይ​ደ​ላ​ች​ሁም፤ ይሁ​ዳና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ተሰ​ለፉ፤ ዝም ብላ​ችሁ ቁሙ፤ የሚ​ሆ​ነ​ው​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማዳን እዩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ና​ንተ ጋር ነውና አት​ፍሩ፤ አት​ደ​ን​ግ​ጡም፤ ነገም ውጡ​ባ​ቸው።”</verse>
				<verse number="18">ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም በም​ድር ላይ ሰገደ፤ ይሁ​ዳም ሁሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ኖሩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደቁ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰገዱ።</verse>
				<verse number="19">ሌዋ​ው​ያ​ንም፥ ከቀ​ዓት ልጆ​ችና ከቆሬ ልጆች የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከፍ ባለ ታላቅ ድምፅ ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ ቆሙ።</verse>
				<verse number="20">ማል​ደ​ውም ተነሡ፤ ወደ ቴቁ​ሔም ምድረ በዳ ወጡ፤ ሲወ​ጡም ኢዮ​ሣ​ፍጥ ቆመና፥ “ይሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ት​ኖሩ ሆይ፥ ስሙኝ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እመኑ፥ ትጸ​ኑ​ማ​ላ​ችሁ፤ በነ​ቢ​ዩም እመኑ፤ ነገ​ሩም ይቀ​ና​ላ​ች​ኋል” አለ።</verse>
				<verse number="21">ከሕ​ዝ​ቡም ጋር ተማ​ክሮ በሠ​ራ​ዊቱ ፊት የሚ​ሄ​ዱ​ትን፥ “ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ” የሚ​ሉ​ት​ንም፥ በቅ​ድ​ስና የሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑ​ትን፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ዘ​ም​ሩ​ትን መዘ​ም​ራን አቆመ።</verse>
				<verse number="22">ዝማ​ሬ​ው​ንና ምስ​ጋ​ና​ው​ንም በጀ​መሩ ጊዜ ይሁ​ዳን ሊወጉ በመ​ጡት በአ​ሞ​ንና በሞ​ዓብ ልጆች በሴ​ይ​ርም ተራራ ሰዎች ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይ​ልን ሰጣ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ተመቱ።</verse>
				<verse number="23">የአ​ሞ​ንና የሞ​ዓብ ልጆ​ችም በሴ​ይር ተራራ በሚ​ኖ​ሩት ላይ ፈጽ​መው ይገ​ድ​ሉ​አ​ቸው ዘንድ፥ ያጠ​ፉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ ተነ​ሥ​ተ​ው​ባ​ቸው ነበር፤ በሴ​ይ​ርም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ካጠፉ በኋላ እርስ በር​ሳ​ቸው ሊጠ​ፋፉ ተነሡ።</verse>
				<verse number="24">የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ወደ ምድረ በዳው መጠ​በ​ቂያ ግንብ በመጡ ጊዜ ሕዝ​ቡን አዩ፤ እነ​ሆም፥ በም​ድሩ ሁሉ ሬሳ ሞልቶ ነበር፤ ያመ​ለ​ጠም ሰው አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="25">ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥና ሕዝ​ቡም ምርኮ ይወ​ስዱ ዘንድ መጡ፤ ብዙ ከብ​ትና ልዩ ልዩ ዕቃም፥ ልብ​ስም፥ እጅ​ግም ያማረ ዕቃ አገኙ፤ ማረ​ኩ​ትም፤ ምር​ኮ​ውም ብዙ ነበ​ርና ምር​ኮ​ውን እየ​ሰ​በ​ሰቡ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ቈዩ።</verse>
				<verse number="26">በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ቀን በበ​ረ​ከት ሸለቆ ውስጥ ተሰ​በ​ሰቡ፤ በዚ​ያም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ፤ ስለ​ዚ​ህም ያ ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ የበ​ረ​ከት ሸለቆ ተባለ።</verse>
				<verse number="27">የይ​ሁዳ ሰዎች ሁሉ፥ ንጉ​ሣ​ቸ​ውም ኢዮ​ሣ​ፍጥ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ላይ ደስ አሰ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና በደ​ስታ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="28">በበ​ገ​ናና በመ​ሰ​ንቆ፥ በመ​ለ​ከ​ትም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ገቡ።</verse>
				<verse number="29">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጠላ​ቶች እንደ ወጋ በሰሙ ጊዜ በም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍር​ሀት ሆነ።</verse>
				<verse number="30">የኢ​ዮ​ሣ​ፍ​ጥም መን​ግ​ሥት ሰላም ሆነች፤ አም​ላ​ኩም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ሪ​ያው ካሉ አሳ​ረ​ፈው።</verse>
				<verse number="31">ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም በይ​ሁዳ ላይ ነገሠ፤ መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜም የሠ​ላሳ አም​ስት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሃያ አም​ስት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም የሳሊ ልጅ አዙባ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="32">በአ​ባ​ቱም በአሳ መን​ገድ ሄደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን የሆ​ነ​ውን ነገር ከማ​ድ​ረግ ፈቀቅ አላ​ለም።</verse>
				<verse number="33">ነገር ግን ኮረ​ብ​ታ​ዎች ገና በዚያ ነበሩ፤ ሕዝ​ቡም ገና ልባ​ቸ​ውን ወደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አላ​ቀ​ኑም ነበር።</verse>
				<verse number="34">የቀ​ረ​ውም የፊ​ተ​ኞ​ቹና የኋ​ለ​ኞቹ የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ነገ​ሮች፥ እነሆ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ነገ​ሥ​ታት ታሪክ በጻ​ፈው በአ​ናኒ ልጅ በነ​ቢዩ በኢዩ ታሪክ ተጽ​ፈ​ዋል።</verse>
				<verse number="35">ከዚ​ህም በኋላ የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ከአ​ካ​ዝ​ያስ ጋር ተባ​በረ፤ ይህም በደ​ልን የሠራ ነበር፦</verse>
				<verse number="36">ወደ ተር​ሴ​ስም የሚ​ሄ​ዱ​ትን መር​ከ​ቦች ያሠራ ዘንድ ከእ​ርሱ ጋር አንድ ሆነ፤ መር​ከ​ቦ​ቹ​ንም በጋ​ሲ​ዮ​ን​ጋ​ብር አሠሩ።</verse>
				<verse number="37">የማ​ር​ሶስ ሰው የኢ​ያ​ድያ ልጅ አል​ዓ​ዛር፥ “ከአ​ካ​ዝ​ያስ ጋር ተባ​ብ​ረ​ሃ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ​ህን አፍ​ር​ሶ​ታል” ብሎ በኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ላይ ትን​ቢት ተና​ገረ። መር​ከ​ቦ​ቹም ተሰ​በሩ፤ ወደ ተር​ሴ​ስም ይሄዱ ዘንድ አል​ቻ​ሉም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ተቀ​በረ፤ ልጁም ኢዮ​ራም በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።</verse>
				<verse number="2">ለእ​ር​ሱም የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጆች አዛ​ር​ያስ፥ ኢይ​ሔል፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ዔዛ​ር​ያስ፥ ሚካ​ኤል፥ ሰፋ​ጥ​ያስ የሚ​ባሉ ስድ​ስት ወን​ድ​ሞች ነበ​ሩት፤ እነ​ዚህ ሁሉ የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="3">አባ​ታ​ቸ​ውም ብዙ ስጦታ፥ ብርና ወርቅ፥ የከ​በ​ረም ዕቃ፥ በይ​ሁ​ዳም የተ​መ​ሸ​ጉ​ትን ከተ​ሞች ሰጣ​ቸው፤ መን​ግ​ሥ​ቱን ግን የበ​ኵር ልጁ ስለ​ሆነ ለኢ​ዮ​ራም ሰጠው።</verse>
				<verse number="4">ኢዮ​ራ​ምም በአ​ባቱ መን​ግ​ሥት ላይ ተነ​ሥቶ በጸና ጊዜ ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ፥ ሌሎ​ች​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን መሳ​ፍ​ንት በሰ​ይፍ ገደለ።</verse>
				<verse number="5">ኢዮ​ራ​ምም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሠ​ላሳ ሁለት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ስም​ንት ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="6">የአ​ክ​ዓ​ብ​ንም ልጅ አግ​ብቶ ነበ​ርና የአ​ክ​ዓብ ቤት እን​ዳ​ደ​ረገ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መን​ገድ ሄደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="7">ነገር ግን ከዳ​ዊት ጋር ስላ​ደ​ረ​ገው ቃል ኪዳን፥ ለእ​ር​ሱና ለል​ጆ​ቹም በዘ​መ​ናት ሁሉ መብ​ራ​ትን ይሰ​ጠው ዘንድ ስለ ሰጠው ተስፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዳ​ዊ​ትን ቤት ያጠፋ ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም።</verse>
				<verse number="8">በእ​ነ​ዚ​ያም ዘመ​ናት የኤ​ዶ​ም​ያስ ሰዎች በይ​ሁዳ ላይ ዐመፁ፤ ለራ​ሳ​ቸ​ውም ንጉሥ አነ​ገሡ።</verse>
				<verse number="9">ኢዮ​ራ​ምም ከአ​ለ​ቆ​ቹና ከሰ​ረ​ገ​ሎቹ ሁሉ ጋር ተሻ​ገረ፤ በሌ​ሊ​ትም ተነ​ሥቶ እር​ሱ​ንና የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹን አለ​ቆች ከብ​በው የነ​በ​ሩ​ትን የኤ​ዶ​ም​ያስ ሰዎ​ችን መታ፤ ሕዝ​ቡም ወደ ድን​ኳ​ና​ቸው ሸሹ።</verse>
				<verse number="10">ኤዶ​ም​ያስ ግን በይ​ሁዳ ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ዐመፀ፤ በዚ​ያም ዘመን ልብና ደግሞ በእ​ርሱ ላይ ዐመፀ፤ የአ​ባ​ቶ​ቹን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትቶ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="11">ደግ​ሞም በይ​ሁዳ ተራ​ሮች ላይ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን ሠራ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን እን​ዲ​ያ​መ​ነ​ዝሩ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም ሰዎች አሳ​ታ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">ከነ​ቢ​ዩም ከኤ​ል​ያስ እን​ዲህ የሚል ጽሕ​ፈት መጣ​በት፥ “የአ​ባ​ትህ የዳ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በአ​ባ​ትህ በኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ መን​ገድ፥ በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በአሳ መን​ገድ አል​ሄ​ድ​ህ​ምና፥</verse>
				<verse number="13">በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መን​ገድ ግን ሄደ​ሃ​ልና፥ የአ​ክ​ዓ​ብም ቤት እን​ዳ​ደ​ረገ ይሁ​ዳ​ንና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትን እን​ዲ​ያ​መ​ነ​ዝሩ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ ከአ​ን​ተም የሚ​ሻ​ሉ​ትን የአ​ባ​ት​ህን ቤት ወን​ድ​ሞ​ች​ህን ገድ​ለ​ሃ​ልና፥</verse>
				<verse number="14">እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ብ​ህ​ንና ልጆ​ች​ህን፥ ሚስ​ቶ​ች​ህ​ንም፥ ያለ​ህ​ንም ንብ​ረት ሁሉ በታ​ላቅ መቅ​ሠ​ፍት ይቀ​ሥ​ፋል።</verse>
				<verse number="15">አን​ተም ከደ​ዌው ጽናት የተ​ነሣ አን​ጀ​ትህ በየ​ዕ​ለቱ እስ​ኪ​ወጣ ድረስ በክፉ የአ​ን​ጀት ደዌ ትታ​መ​ማ​ለህ።”</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንና በኢ​ት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያን አጠ​ገብ የሚ​ኖ​ሩ​ትን የዓ​ረ​ብ​ያን ሰዎች በኢ​ዮ​ራም ላይ አስ​ነሣ።</verse>
				<verse number="17">ወደ ይሁ​ዳም ወጡ፤ በረ​ቱ​ባ​ቸ​ውም፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ወን​ዶች ልጆ​ቹ​ንም፥ ሴቶች ልጆ​ቹ​ንም ወሰዱ፤ ከታ​ና​ሹም ልጅ ከአ​ካ​ዝ​ያስ በቀር ልጅ አል​ቀ​ረ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="18">ከዚ​ህም ሁሉ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መድ​ኀ​ኒት በማ​ይ​ገ​ኝ​ለት ደዌ አን​ጀ​ቱን ቀሠ​ፈው።</verse>
				<verse number="19">ከቀ​ንም ወደ ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ ከሁ​ለት ዓመት በኋላ ከደ​ዌው ጽናት የተ​ነሣ አን​ጀቱ ወጣ፤ በክ​ፉም ደዌ ሞተ። ሕዝ​ቡም ለአ​ባ​ቶቹ ያደ​ር​ገው እንደ ነበረ ለእ​ርሱ የመ​ቃ​ብር ወግ አላ​ደ​ረ​ገም።</verse>
				<verse number="20">መን​ገ​ሥም በጀ​መረ ጊዜ የሠ​ላሳ ሁለት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ስም​ንት ዓመት ነገሠ፤ ማንም ሳያ​ዝ​ን​ለት ሄደ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ እንጂ በነ​ገ​ሥ​ታት መቃ​ብር አል​ቀ​በ​ሩ​ትም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የነ​በ​ሩት ታና​ሹን ልጁን አካ​ዝ​ያ​ስን በእ​ርሱ ፋንታ አነ​ገ​ሡት። የመ​ጣ​ባ​ቸው የዓ​ረ​ብና የአ​ሊ​ማ​ዞን የሽ​ፍ​ቶች ጭፍራ የእ​ር​ሱን ታላ​ቆች ወን​ድ​ሞች ገድ​ለ​ዋ​ቸው ነበ​ርና የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ራም ልጅ አካ​ዝ​ያስ ነገሠ።</verse>
				<verse number="2">አካ​ዝ​ያ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ ዕድ​ሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበረ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ጎቶ​ልያ የተ​ባ​ለች የዘ​ን​በሪ ልጅ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="3">እና​ቱም ክፉ እን​ዲ​ያ​ደ​ርግ ትመ​ክ​ረው ነበ​ርና እርሱ ደግሞ በአ​ክ​ዓብ ቤት መን​ገድ ሄደ።</verse>
				<verse number="4">ከአ​ባ​ቱም ሞት በኋላ የአ​ክ​ዓብ ቤት እን​ዳ​ደ​ረገ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ፤ ያጠ​ፉት ዘንድ መካ​ሪ​ዎች ነበ​ሩ​ትና።</verse>
				<verse number="5">በም​ክ​ራ​ቸ​ውም ሄደ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ከአ​ክ​ዓብ ልጅ ከኢ​ዮ​ራም ጋር የሶ​ር​ያን ንጉሥ አዛ​ሄ​ልን በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ ሊዋጋ ሄደ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ኢዮ​ራ​ምን አቈ​ሰ​ሉት።</verse>
				<verse number="6">ከሶ​ር​ያም ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል ጋር በተ​ዋጋ ጊዜ ሶር​ያ​ው​ያን በሬ​ማት ያቈ​ሰ​ሉ​ትን ቍስል ይታ​ከም ዘንድ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ተመ​ለሰ፤ ታም​ሞም ነበ​ርና የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ራም ልጅ አካ​ዝ​ያስ የአ​ክ​ዓ​ብን ልጅ ኢዮ​ራ​ምን ያይ ዘንድ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ወረደ።</verse>
				<verse number="7">ወደ ኢዮ​ራም በመ​ም​ጣ​ቱም የአ​ካ​ዝ​ያስ ጥፋት ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆነ፤ በመ​ጣም ጊዜ ከኢ​ዮ​ራም ጋር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ክ​ዓ​ብን ቤት ያጠፋ ዘንድ ወደ ቀባው ወደ ናሚሲ ልጅ ወደ ኢዩ ወጣ።</verse>
				<verse number="8">ኢዩም የአ​ክ​ዓ​ብን ቤት ይበ​ቀል ዘንድ የይ​ሁ​ዳን መሳ​ፍ​ን​ትና አካ​ዝ​ያ​ስን ያገ​ለ​ግሉ የነ​በ​ሩ​ትን የአ​ካ​ዝ​ያ​ስን ወን​ድ​ሞች አግ​ኝቶ ገደ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">አካ​ዝ​ያ​ስ​ንም ፈለ​ገው፤ በሰ​ማ​ር​ያም እየ​ታ​ከመ ሳለ አገ​ኙት፤ ወደ ኢዩም አመ​ጡት፤ እር​ሱም ገደ​ለው፦ እነ​ር​ሱም፥ “በፍ​ጹም ልብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የፈ​ለ​ገው የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጅ ነው” ብለው ቀበ​ሩት። ከአ​ካ​ዝ​ያ​ስም ቤት ማንም መን​ግ​ሥ​ትን ይይዝ ዘንድ የሚ​ችል አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="10">የአ​ካ​ዝ​ያ​ስም እናት ጎቶ​ልያ ልጅዋ እንደ ሞተ ባየች ጊዜ ተነ​ሥታ የይ​ሁ​ዳን ቤተ መን​ግ​ሥት ዘር ሁሉ አጠ​ፋች።</verse>
				<verse number="11">የን​ጉሡ ልጅ ዮሳ​ቤት ግን ከተ​ገ​ደ​ሉት ከን​ጉሡ ልጆች መካ​ከል የአ​ካ​ዝ​ያ​ስን ልጅ ኢዮ​አ​ስን ሰርቃ ወሰ​ደች፤ እር​ሱ​ንና ሞግ​ዚ​ቱን በእ​ል​ፍኝ ውስጥ አኖ​ረ​ቻ​ቸው፤ የን​ጉሡ የኢ​ዮ​ራም ልጅ የአ​ካ​ዝ​ያስ እኅት የካ​ህኑ የዮ​ዳሄ ሚስት ዮሳ​ቤት ከጎ​ቶ​ልያ ፊት ሸሸ​ገ​ችው፤ እር​ስ​ዋም አል​ገ​ደ​ለ​ች​ውም።</verse>
				<verse number="12">ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ተሸ​ሽጎ ስድ​ስት ዓመት ያህል ተቀ​መጠ፤ ጎቶ​ል​ያም በም​ድር ላይ ነገ​ሠች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="23">
				<verse number="1">በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ኢዮ​አዳ በረታ፤ የመቶ አለ​ቆ​ቹ​ንም፥ የኢ​ዮ​ራ​ምን ልጅ አዛ​ር​ያ​ስን፥ የኢ​ዮ​አ​ና​ንም ልጅ እስ​ማ​ኤ​ልን፥ የዖ​ቤ​ድ​ንም ልጅ አዛ​ር​ያን፥ የኢ​ዳ​ኢ​ንም ልጅ መዓ​ስ​ያን፥ የዘ​ካ​ር​ያ​ስ​ንም ልጅ ኤሊ​ሳ​ፋ​ጥን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ።</verse>
				<verse number="2">ይሁ​ዳ​ንም ዞሩ፤ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ሁሉ ሌዋ​ው​ያ​ን​ንና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ሰብ​ስ​በው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጡ።</verse>
				<verse number="3">የይ​ሁ​ዳም ጉባኤ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ ከን​ጉሥ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ። የን​ጉ​ሥ​ንም ልጅ አሳ​ያ​ቸው፤ አላ​ቸ​ውም፥ “እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ዳዊት ቤት እንደ ተና​ገረ የን​ጉሡ ልጅ ይነ​ግ​ሣል።</verse>
				<verse number="4">እነሆ፥ የም​ታ​ደ​ር​ጉት ይህ ነው፤ በሰ​ን​በት ቀን ከም​ት​ገ​ቡት ከእ​ና​ንተ ከካ​ህ​ና​ትና ከሌ​ዋ​ው​ያን ከሦ​ስት አንድ እጅ በመ​ግ​ቢያ በሮች በረ​ኞች ሁኑ፤</verse>
				<verse number="5">ከሦ​ስት አንድ እጅም በን​ጉሡ ቤት ሁኑ፤ ሌላ​ውም ከሦ​ስት አንድ እጅ በመ​ካ​ከ​ለ​ኛው በር ሁኑ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ ይሁኑ።</verse>
				<verse number="6">ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ግን ከካ​ህ​ና​ትና ከሌ​ዋ​ው​ያን ከሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም አገ​ል​ጋ​ዮች በቀር ማንም አይ​ግባ፤ እነ​ርሱ ቅዱ​ሳን ናቸ​ውና ይግቡ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ይጠ​ብቅ።</verse>
				<verse number="7">ሌዋ​ው​ያ​ንም የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን በእ​ጃ​ቸው ይዘው ንጉ​ሡን በዙ​ሪ​ያው ይክ​በ​ቡት፤ ወደ ቤቱም የሚ​ገባ ይገ​ደል፤ ንጉ​ሡም ሲገ​ባና ሲወጣ ከእ​ርሱ ጋር ሁኑ።”</verse>
				<verse number="8">ሌዋ​ው​ያ​ንና ይሁ​ዳም ሁሉ ካህኑ ኢዮ​አዳ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረጉ፤ ካህ​ኑም ኢዮ​አዳ ሰሞ​ነ​ኞ​ቹን አላ​ሰ​ና​በ​ተም ነበ​ርና እያ​ን​ዳ​ንዱ ከሰ​ን​በት መጀ​መ​ሪያ እስከ ሰን​በት መጨ​ረሻ ሰዎ​ችን ወሰደ።</verse>
				<verse number="9">ካህ​ኑም ኢዮ​አዳ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የነ​በ​ረ​ውን የን​ጉ​ሡን የዳ​ዊ​ትን ሰይ​ፍና ጦር፥ አላ​ባሽ አግ​ሬ​ው​ንም ጋሻ ለመቶ አለ​ቆች ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">ሕዝ​ቡም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ውን በእጁ እየ​ያዘ በን​ጉሡ ዙሪያ ከቤተ መቅ​ደሱ ቀኝ እስከ ቤተ መቅ​ደሱ ግራ ድረስ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውና በመ​ቅ​ደሱ አጠ​ገብ እን​ዲ​ቆም አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="11">የን​ጉ​ሡ​ንም ልጅ አው​ጥቶ ዘው​ዱን ጫነ​በት፤ ምስ​ክ​ሩ​ንም ሰጠው፤ አነ​ገ​ሡ​ትም፤ ኢዮ​አ​ዳና ልጆ​ቹም አነ​ገ​ሡት፥ “ንጉሡ በሕ​ይ​ወት ይኑር” እያ​ሉም ቀቡት።</verse>
				<verse number="12">ጎቶ​ል​ያም የሚ​ሮ​ጡ​ት​ንና ንጉ​ሡን የሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑ​ትን የሕ​ዝ​ቡን ድምፅ በሰ​ማች ጊዜ ወደ ሕዝቡ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መጣች።</verse>
				<verse number="13">እነ​ሆም፥ ንጉሡ በመ​ግ​ቢ​ያው በዓ​ምዱ አጠ​ገብ ሆኖ በን​ጉ​ሡም ዙሪያ አለ​ቆ​ችና መለ​ከ​ተ​ኞች፥ መኳ​ን​ን​ትም ቆመው አየች። ሕዝ​ቡም ሁሉ ደስ ብሎ​አ​ቸው መለ​ከ​ቱን ይነፉ ነበር፤ መዘ​ም​ራ​ንም በዜማ ዕቃ እያ​ዜሙ የም​ስ​ጋና መዝ​ሙር ይዘ​ምሩ ነበር። ጎቶ​ል​ያም ልብ​ስ​ዋን ቀድዳ፥ “ዐመፅ ነው! ዐመፅ ነው!” ብላ ጮኸች።</verse>
				<verse number="14">ካህ​ኑም ኢዮ​አዳ ወጥቶ በጭ​ፍ​ራው ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን አለ​ቆ​ችና የመቶ አለ​ቆች፥ “ከቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ውጭ አው​ጡ​አት፤ የሚ​ከ​ተ​ላ​ትም በሰ​ይፍ ይገ​ደል” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው። ካህኑ፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ አት​ገ​ደል” ብሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="15">ገለ​ልም ብለው አሳ​ለ​ፉ​አት፤ እር​ስ​ዋም ወደ ፈረሱ በር መግ​ቢያ ወደ ንጉሡ ቤት ሄደች፤ በዚ​ያም ገደ​ሉ​አት።</verse>
				<verse number="16">ካህኑ ኢዮ​አ​ዳም በእ​ር​ሱና በሕ​ዝቡ ሁሉ፥ በን​ጉ​ሡም መካ​ከል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ ቃል ኪዳን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="17">የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በዓል ቤት ሄደው አፈ​ረ​ሱት፤ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹ​ንና ምስ​ሎ​ቹ​ንም አደ​ቀቁ፤ የበ​ዓ​ል​ንም ካህን ማታ​ንን በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት ገደ​ሉት።</verse>
				<verse number="18">ካህኑ ኢዮ​አ​ዳም በሙሴ ሕግ እንደ ተጻ​ፈው እንደ ዳዊት ትእ​ዛዝ በደ​ስ​ታና በመ​ዝ​ሙር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርቡ ዘንድ ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የከ​ፈ​ላ​ቸ​ውን ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ላይ ሾመ።</verse>
				<verse number="19">በማ​ና​ቸ​ውም ነገር ሁሉ ርኩስ የሆነ ሰው እን​ዳ​ይ​ገባ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በር በረ​ኞ​ችን አኖረ።</verse>
				<verse number="20">የመቶ አለ​ቆ​ች​ንም፥ ከበ​ር​ቴ​ዎ​ች​ንም፥ የሕ​ዝ​ቡ​ንም አለ​ቆች፥ የሀ​ገ​ሩ​ንም ሕዝብ ሁሉ ወሰደ፤ ንጉ​ሡ​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አወ​ረ​ዱት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በው​ስ​ጠ​ኛው በር በኩል ወደ ንጉሡ ቤት አመ​ጡት፤ ንጉ​ሡ​ንም በመ​ን​ግ​ሥቱ ዙፋን ላይ አስ​ቀ​መ​ጡት።</verse>
				<verse number="21">የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ አላ​ቸው፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱም ጸጥ አለች፤ ጎቶ​ል​ያ​ንም በሰ​ይፍ ገደ​ሉ​አት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="24">
				<verse number="1">ኢዮ​አ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሰ​ባት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አርባ ዓመት ነገሠ፤ እናቱ ሳብያ የተ​ባ​ለች የቤ​ር​ሳ​ቤህ ሴት ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="2">ኢዮ​አ​ስም በካ​ህኑ በኢ​ዮ​አዳ ዘመን ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="3">ኢዮ​አ​ዳም ሁለት ሚስ​ቶ​ችን አጋ​ባው፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ንም ወለደ።</verse>
				<verse number="4">ከዚ​ህም በኋላ ኢዮ​አስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ይጠ​ግን ዘንድ አሰበ።</verse>
				<verse number="5">ካህ​ና​ት​ንና ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም ሰብ​ስቦ፥ “ወደ ይሁዳ ከተ​ሞች ውጡ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም ቤት በየ​ዓ​መቱ ለማ​ደስ የሚ​በቃ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ገን​ዘ​ብን ሰብ​ስቡ፤ ነገ​ሩ​ንም ፈጥ​ና​ችሁ አድ​ርጉ” አላ​ቸው። ሌዋ​ው​ያን ግን አላ​ፋ​ጠ​ኑም።</verse>
				<verse number="6">ንጉሡ ኢዮ​አ​ስም አለ​ቃ​ውን ኢዮ​አ​ዳን ጠርቶ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪያ ሙሴ እስ​ራ​ኤ​ልን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን በሰ​በ​ሰበ ጊዜ እን​ዲ​ያ​ዋጣ ያዘ​ዘ​ውን ግብር ከይ​ሁ​ዳና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያመጡ ዘንድ ስለ ምን ሌዋ​ው​ያ​ንን አል​ተ​ከ​ታ​ተ​ል​ህም?” አለው።</verse>
				<verse number="7">ጎቶ​ልያ ከሐ​ዲት ነበ​ረ​ችና ልጆ​ች​ዋም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ተቀ​ድሶ የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ለበ​ኣ​ሊም ሰጥ​ተ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="8">ንጉ​ሡም ሣጥን ሠር​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በር አጠ​ገብ በስ​ተ​ውጭ ያኖ​ሩት ዘንድ አዘዘ።</verse>
				<verse number="9">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባሪያ ሙሴ በም​ድረ በዳ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ያዘ​ዘ​ውን ግብር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያመጡ ዘንድ፥ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ አዘዘ።</verse>
				<verse number="10">አለ​ቆ​ቹና ሕዝ​ቡም ሁሉ ሰጡ፤ እስ​ኪ​ሞ​ላም ድረስ በሣ​ጥኑ ውስጥ አስ​ገ​ቡት።</verse>
				<verse number="11">ሣጥ​ኑም በሌ​ዋ​ው​ያን እጅ ወደ ንጉሡ ሹሞች በደ​ረሰ ጊዜ፥ ብዙ ገን​ዘ​ብም እን​ዳ​ለ​በት ባዩ ጊዜ፥ የን​ጉሡ ጸሓ​ፊና የሊቀ ካህ​ናቱ ሹም እየ​መጡ ብሩን ከሣ​ጥን ያወጡ ነበር፤ ሣጥ​ኑ​ንም ደግሞ ወደ ስፍ​ራው ይመ​ል​ሱት ነበር። እን​ዲ​ሁም በየ​ቀኑ ያደ​ርጉ ነበር፤ ብዙም ገን​ዘብ ሰበ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="12">ንጉ​ሡና ኢዮ​አ​ዳም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሥራ ላይ ለተ​ሾ​ሙት ሰጡ​አ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት የሚ​ጠ​ግ​ኑ​ትን ጠራ​ቢ​ዎ​ች​ንና አና​ጢ​ዎ​ችን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት የሚ​ያ​ድ​ሱ​ትን የብ​ረ​ትና የናስ ሠራ​ተ​ኞ​ችን ይቀ​ጥ​ሩ​በት ነበር።</verse>
				<verse number="13">ሠራ​ተ​ኞ​ችም ሠሩ፤ ሥራ​ውም ሁሉ በእ​ጃ​ቸው ተፈ​ጸመ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት እንደ ቀድ​ሞው ሥራ መለሱ፤ አጽ​ን​ተ​ውም አቆ​ሙት።</verse>
				<verse number="14">በጨ​ረ​ሱም ጊዜ የተ​ረ​ፈ​ውን ገን​ዘብ ወደ ንጉ​ሡና ወደ ካህኑ ኢዮ​አዳ ፊት አመጡ፤ እነ​ር​ሱም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ዕቃ፥ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎ​ትና ለቍ​ር​ባን ዕቃ፥ ለጭ​ል​ፋ​ዎ​ችም፥ ለወ​ር​ቅና ለብ​ርም ዕቃ አደ​ረ​ጉት። በኢ​ዮ​አ​ዳም ዘመን ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ሁል​ጊዜ ያቀ​ርቡ ነበር።</verse>
				<verse number="15">ኢዮ​አ​ዳም ሸመ​ገለ፤ ዕድ​ሜም ጠግቦ ሞተ፤ በሞ​ተም ጊዜ ዕድ​ሜው መቶ ሠላሳ ዓመት ነበረ።</verse>
				<verse number="16">ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጋር፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ከቤ​ቱም ጋር መል​ካም ሠር​ቶ​አ​ልና በዳ​ዊት ከተማ ከነ​ገ​ሥ​ታቱ ጋር ቀበ​ሩት።</verse>
				<verse number="17">ካህኑ ኢዮ​አ​ዳም ከሞተ በኋላ የይ​ሁዳ አለ​ቆች ገብ​ተው ለን​ጉሡ ሰገዱ፤ ንጉ​ሡም ሰማ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ትተው ባዕድ አም​ላ​ክ​ንና ጣዖ​ታ​ትን አመ​ለኩ፤ በዚ​ያም ወራት በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ቍጣ ወረደ።</verse>
				<verse number="19">ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ል​ሱ​አ​ቸው ዘንድ ነቢ​ያ​ትን ይሰ​ድ​ድ​ላ​ቸው ነበር፤ መሰ​ከ​ሩ​ባ​ቸ​ውም፤ እነ​ርሱ ግን አላ​ደ​መ​ጡም።</verse>
				<verse number="20">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በካ​ህኑ በኢ​ዮ​አዳ ልጅ በአ​ዛ​ር​ያስ ላይ መጣ፤ እር​ሱም በሕ​ዝቡ ፊት ቆመና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ለምን ትተ​ላ​ለ​ፋ​ላ​ችሁ? መል​ካ​ምም አይ​ሆ​ን​ላ​ች​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ተዋ​ችሁ እርሱ ትቶ​አ​ች​ኋል” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">ወደ እር​ሱም ሮጡ በን​ጉ​ሡም ትእ​ዛዝ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ ውስጥ በድ​ን​ጋይ ደበ​ደ​ቡት።</verse>
				<verse number="22">እን​ዲ​ሁም ንጉሡ ኢዮ​አስ አባቱ ኢዮ​አዳ ያደ​ረ​ገ​ለ​ትን ቸር​ነት አላ​ሰ​በም፤ ልጁ​ንም አዛ​ር​ያ​ስን አስ​ገ​ደ​ለው፤ እር​ሱም ሲሞት፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይየው፤ ይፍ​ረ​ደ​ውም” አለ።</verse>
				<verse number="23">ዓመ​ቱም ካለፈ በኋላ የሶ​ር​ያ​ው​ያን ሠራ​ዊት መጡ​በት፤ ወደ ይሁ​ዳና ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም መጥ​ተው ከሕ​ዝቡ መካ​ከል የሕ​ዝ​ቡን አለ​ቆች ሁሉ አጠፉ፤ ምር​ኮ​አ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ለደ​ማ​ስቆ ንጉሥ ላኩ።</verse>
				<verse number="24">የሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንም ሠራ​ዊት ቍጥር ጥቂት ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ብዙ​ው​ንና ጠን​ካ​ራ​ውን ሠራ​ዊት አሳ​ልፎ በእ​ጃ​ቸው ሰጣ​ቸው፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዘን​ግ​ተ​ዋ​ልና። በኢ​ዮ​አ​ስም ላይ ፈረ​ደ​በት።</verse>
				<verse number="25">ከእ​ር​ሱም ዘንድ አል​ፈው ከሄዱ በኋላ እጅግ ታሞ ሳለ ተዉት፤ የገዛ ባሪ​ያ​ዎ​ቹም ስለ ካህኑ ስለ ኢዮ​አዳ ልጅ ደም ተበ​ቅ​ለው በአ​ል​ጋው ላይ ገደ​ሉት፤ ሞተም፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት፤ ነገር ግን በነ​ገ​ሥ​ታት መቃ​ብር አል​ቀ​በ​ሩ​ትም።</verse>
				<verse number="26">የገ​ደ​ሉ​ትም የአ​ሞ​ና​ዊቱ የሰ​ማት ልጅ ዘቡድ፥ የሞ​ዓ​ባ​ዊ​ቱም የሰ​ማ​ሪት ልጅ ኢዮ​ዛ​ብድ ነበሩ።</verse>
				<verse number="27">የል​ጆ​ቹና በእ​ርሱ ላይ የተ​ደ​ረ​ገው ነገር፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ማደሱ፥ እነሆ በነ​ገ​ሥ​ታቱ የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል። ልጁም አሜ​ስ​ያስ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="25">
				<verse number="1">አሜ​ስ​ያ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አም​ስት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፤ እናቱ ኢዮ​ዓ​ዲን የተ​ባ​ለች የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="2">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ፤ ነገር ግን በፍ​ጹም ልብ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="3">መን​ግ​ሥ​ትም በእጁ በጸ​ና​ለት ጊዜ ንጉ​ሡን አባ​ቱን የገ​ደ​ሉ​ትን ባሪ​ያ​ዎች ገደለ።</verse>
				<verse number="4">እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ቃል ኪዳን እንደ ተጻፈ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሰው ሁሉ በገዛ ኀጢ​አቱ ይሙት እንጂ አባ​ቶች በል​ጆ​ቻ​ቸው፥ ልጆ​ችም በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ፋንታ አይ​ሙቱ” ብሎ እን​ዳ​ዘዘ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ግን አል​ገ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="5">ንጉሡ አሜ​ስ​ያ​ስም የይ​ሁ​ዳን ሕዝብ ሰበ​ሰበ፤ እንደ እየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች አቆ​ማ​ቸው፤ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሁሉ የሽህ አለ​ቆ​ች​ንና የመቶ አለ​ቆ​ችን አደ​ረገ፤ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉ​ትን ሁሉ ቈጠረ፤ ለሰ​ል​ፍም የሚ​ወጡ፥ ጋሻና ጦርም የሚ​ይዙ ሦስት መቶ ሺህ የተ​መ​ረጡ ሰዎ​ችን አገኘ።</verse>
				<verse number="6">ደግ​ሞም ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ መቶ ሺህ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎ​ችን በመቶ መክ​ሊት ብር ቀጠረ።</verse>
				<verse number="7">አንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ግን ወደ እርሱ መጥቶ፥ “ንጉሥ ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልና ከኤ​ፍ​ሬም ልጆች ሁሉ ጋር አይ​ደ​ለ​ምና የእ​ስ​ራ​ኤል ጭፍራ ከአ​ንተ ጋር አይ​ውጣ።</verse>
				<verse number="8">ብት​ሄድ ግን፥ በእ​ነ​ር​ሱም ማሸ​ነ​ፍን ብታ​ስብ፥ የማ​ጽ​ና​ትና የመ​ጣል ኀይል ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጠ​ላ​ቶ​ችህ ፊት ይጥ​ል​ሃል” አለው።</verse>
				<verse number="9">አሜ​ስ​ያ​ስም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ጭፍራ የሰ​ጠ​ሁት መቶ መክ​ሊት ምን ይሁን?” አለው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው፥ “ከዚህ አብ​ልጦ ይሰ​ጥህ ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ሳ​ነ​ውም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።</verse>
				<verse number="10">ንጉሡ አሜ​ስ​ያ​ስም ከኤ​ፍ​ሬም ከተ​ሞች የመጡ ጭፍ​ሮች ወደ ስፍ​ራ​ቸው ይመ​ለሱ ዘንድ ለይቶ አሰ​ና​በ​ታ​ቸው፤ ስለ​ዚ​ህም ቍጣ​ቸው በይ​ሁዳ ላይ ጸና፤ ወደ ስፍ​ራ​ቸ​ውም በጽኑ ቍጣ ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="11">አሜ​ስ​ያ​ስም በረታ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ሰብ​ስቦ ወደ ጨው ሸለቆ ሄደ፤ ከሴ​ይ​ርም ልጆች ዐሥር ሺህ ገደለ።</verse>
				<verse number="12">የይ​ሁ​ዳም ልጆች ደግሞ ዐሥር ሺህ ሰዎ​ችን ማረኩ። ወደ ዐለ​ቱም ራስ ላይ አመ​ጡ​አ​ቸው፤ ከዐ​ለ​ቱም ራስ ላይ ጣሉ​አ​ቸው፤ ሁሉም ተፈ​ጠ​ፈጡ።</verse>
				<verse number="13">አሜ​ስ​ያስ ግን ከእ​ርሱ ጋር ወደ ሰልፍ እን​ዳ​ይ​ሄዱ ያሰ​ና​በ​ታ​ቸው ጭፍ​ሮ​ችም ከሰ​ማ​ርያ ጀም​ረው እስከ ቤት​ሮን ድረስ በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ላይ አደጋ ጣሉ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ሦስት ሺህ ገደሉ፤ ብዙም ምርኮ ማረኩ።</verse>
				<verse number="14">አሜ​ስ​ያ​ስም የኤ​ዶ​ም​ያ​ስን ሰዎች ከገ​ደለ በኋላ የሴ​ይ​ርን ልጆች አማ​ል​ክት አመጣ፤ የእ​ር​ሱም አማ​ል​ክት ይሆኑ ዘንድ አቆ​ማ​ቸው፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ይሰ​ግ​ድ​ላ​ቸ​ውና ይሠ​ዋ​ላ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="15">ስለ​ዚ​ህም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በን​ጉሡ በአ​ሜ​ስ​ያስ ላይ መጣ፤ እን​ዲ​ህም ሲል ነቢ​ይን ላከ​በት፥ “ሕዝ​ባ​ቸ​ውን ከአ​ንተ እጅ ያላ​ዳ​ኑ​ትን የአ​ሕ​ዛ​ብን አማ​ል​ክት ስለ​ምን ፈለ​ግ​ሃ​ቸው?”</verse>
				<verse number="16">እር​ሱም ይህን ሲና​ገር ንጉሡ አሜ​ስ​ያስ፥ “በውኑ የን​ጉሡ አማ​ካሪ ልት​ሆን ሹሜ​ሃ​ለ​ሁን? ቅጣት እን​ዳ​ያ​ገ​ኝህ ተጠ​ን​ቀቅ” አለው። ነቢ​ዩም፥ “ይህን አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ ምክ​ሬ​ንም አል​ሰ​ማ​ህ​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ጠ​ፋህ እን​ዳ​ሰበ አወ​ቅሁ” ብሎ ዝም አለ።</verse>
				<verse number="17">የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ አሜ​ስ​ያስ ምክር አደ​ረ​ገና፥ “ና፥ እርስ በር​ሳ​ችን ፊት ለፊት እን​ተ​ያይ” ብሎ ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮ​አ​ካዝ ልጅ ወደ ኢዮ​አስ ላከ።</verse>
				<verse number="18">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኢዮ​አስ፦ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜ​ስ​ያስ እን​ዲህ ሲል ላከ፥ “የሊ​ባ​ኖስ ኵር​ን​ችት ልጅ​ህን ለልጄ ሚስት አድ​ር​ገህ ስጠው” ብሎ ወደ ሊባ​ኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊ​ባ​ኖ​ስም ዱር አው​ሬ​ዎች መጥ​ተው ኵር​ን​ች​ቱን ረገ​ጡት።</verse>
				<verse number="19">አን​ተም፦ እነሆ፥ ኤዶ​ም​ያ​ስን መት​ቻ​ለሁ ብለህ በል​ብህ ኰር​ተ​ሃል፤ በቤ​ትህ ተቀ​መጥ፤ አንተ ከይ​ሁዳ ጋር ትወ​ድቅ ዘንድ ስለ​ምን መከ​ራን በራ​ስህ ትሻ​ለህ?”</verse>
				<verse number="20">የኤ​ዶ​ም​ያ​ስ​ንም አማ​ል​ክት ስለ ፈለጉ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ይህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበ​ረና አሜ​ስ​ያስ አል​ሰ​ማም።</verse>
				<verse number="21">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኢዮ​አስ ወጣ፤ እር​ሱና የይ​ሁዳ ንጉሥ አሜ​ስ​ያ​ስም በይ​ሁዳ ባለች በቤ​ት​ሳ​ሚስ ላይ እርስ በር​ሳ​ቸው ተያዩ።</verse>
				<verse number="22">ይሁ​ዳም በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ድል ሆኑ፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም ወደ ድን​ኳ​ና​ቸው ሸሹ።</verse>
				<verse number="23">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኢዮ​አስ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የአ​ካ​ዝ​ያ​ስን ልጅ የኢ​ዮ​አ​ስን ልጅ አሜ​ስ​ያ​ስን በቤ​ት​ሳ​ሚስ ይዞ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመ​ጣው፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቅጥር ከኤ​ፍ​ሬም በር ጀምሮ እስከ ማዕ​ዘኑ በር ድረስ አራት መቶ ክንድ አፈ​ረሰ።</verse>
				<verse number="24">ወር​ቁ​ንና ብሩን ሁሉ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በአ​ብ​ዲ​ዶም እጅ የነ​በ​ሩ​ትን ዕቃ​ዎች ሁሉ፥ በን​ጉ​ሡም ቤተ መዛ​ግ​ብት የተ​ገ​ኘ​ውን፥ በመ​ያዣ የተ​ያ​ዙ​ት​ንም ልጆች ወስዶ ወደ ሰማ​ርያ ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="25">የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​አስ ልጅ አሜ​ስ​ያስ ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ከኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ ከኢ​ዮ​አስ ሞት በኋላ ዐሥራ አም​ስት ዓመት ኖረ።</verse>
				<verse number="26">የቀ​ሩ​ትም የፊ​ተ​ኞ​ቹና የኋ​ለ​ኞቹ የአ​ሜ​ስ​ያስ ነገ​ሮች፥ እነሆ፥ በይ​ሁ​ዳና በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="27">አሜ​ስ​ያ​ስም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ከ​ተል በራቀ ጊዜ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የዐ​መፅ መሐላ አደ​ረ​ጉ​በት፤ ወደ ለኪ​ሶም ኮበ​ለለ፤ በስ​ተ​ኋ​ላ​ውም ወደ ለኪሶ ላኩ፤ በዚ​ያም ገደ​ሉት።</verse>
				<verse number="28">በፈ​ረ​ስም ጭነው አመ​ጡት፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ቀበ​ሩት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="26">
				<verse number="1">የይ​ሁ​ዳም ሕዝብ ሁሉ የዐ​ሥራ ስድ​ስት ዓመት ጐል​ማሳ የነ​በ​ረ​ውን ዖዝ​ያ​ንን ወስ​ደው በአ​ባቱ በአ​ሜ​ስ​ያስ ፋንታ አነ​ገ​ሡት።</verse>
				<verse number="2">ንጉሥ አባ​ቱም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ከአ​ን​ቀ​ላፋ በኋላ ዖዝ​ያን ኤላ​ትን ሠራ፤ ወደ ይሁ​ዳም መለ​ሳት።</verse>
				<verse number="3">ዖዝ​ያ​ንም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የዐ​ሥራ ስድ​ስት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አምሳ ሁለት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ኢዮ​ኮ​ል​ያስ የተ​ባ​ለች የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="4">አባ​ቱም አሜ​ስ​ያስ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መፍ​ራት ባስ​ተ​ማረ በዘ​ካ​ር​ያስ ዘመን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ልግ ዘንድ ልብ አደ​ረገ፤ በዘ​መ​ኑም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈለገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነገ​ሩን አከ​ና​ወ​ነ​ለት።</verse>
				<verse number="6">ወጥ​ቶም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ተዋጋ፤ የጌ​ትን ቅጥር፥ የኢ​ያ​ቢ​ስ​ንም ቅጥር፥ የአ​ዛ​ጦ​ን​ንም ቅጥር አፈ​ረሰ፤ በአ​ዛ​ጦ​ንና በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሀገር ከተ​ሞ​ችን ሠራ።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንና በዓ​ለት ላይ በሚ​ኖሩ ዓረ​ባ​ው​ያን፥ በም​ዕ​ዑ​ና​ው​ያ​ንም ላይ አጸ​ናው።</verse>
				<verse number="8">አሞ​ና​ው​ያ​ንም ለዖ​ዝ​ያን ገበሩ፤ እጅ​ግም በር​ትቶ ነበ​ርና ዝናው እስከ ግብፅ መግ​ቢያ ድረስ ተሰማ።</verse>
				<verse number="9">ዖዝ​ያ​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በማ​ዕ​ዘኑ በርና በሸ​ለ​ቆው በር፥ ቅጥ​ሩም በዞ​ረ​በት ማዕ​ዘን አጠ​ገብ ግን​ቦ​ችን ሠርቶ መሸ​ጋ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">በም​ድረ በዳ​ውም ግን​ቦ​ችን ሠራ፤ ብዙ ጕድ​ጓ​ድም ማሰ፤ በቆ​ላ​ውና በደ​ጋው ብዙ እን​ስ​ሶች ነበ​ሩ​ትና፤ ደግ​ሞም እርሻ ይወ​ድድ ነበ​ርና በተ​ራ​ራ​ማ​ውና በፍ​ሬ​ያ​ማው ስፍራ አራ​ሾ​ችና የወ​ይን አት​ክ​ል​ተ​ኞች ነበ​ሩት።</verse>
				<verse number="11">ደግ​ሞም ለዖ​ዝ​ያን የሰ​ልፍ ሠራ​ዊት ነበ​ሩት፤ በን​ጉሡ አለቃ በሐ​ና​ንያ ትእ​ዛዝ፥ በአ​ለ​ቃው በመ​ዕ​ሤ​ያና በጸ​ሓ​ፊው በኢ​ዮ​ሔል እጅ እንደ ተቈ​ጠሩ ወደ ሰልፍ በየ​ቍ​ጥ​ራ​ቸው ይወጡ ነበር።</verse>
				<verse number="12">የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች አለ​ቆች በሰ​ልፍ ጽኑ​ዓ​ንና ኀያ​ላን የሆኑ ሁሉ ቍጥ​ራ​ቸው ሁለት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበረ።</verse>
				<verse number="13">ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ወደ ሰልፍ የሚ​ወጡ ሦስት መቶ ሰባት ሺህ አም​ስት መቶ ሠራ​ዊት ነበሩ፤ እነ​ዚ​ህም ንጉ​ሡን በጠ​ላቱ ላይ የሚ​ያ​ግዙ፥ በታ​ላቅ ኀይል ወደ ሰልፍ የሚ​ወጡ ጽኑ​ዓን ነበሩ።</verse>
				<verse number="14">ዖዝ​ያ​ንም ለጭ​ፍ​ራው ሁሉ ጋሻና ጦር፥ ራስ ቍርና ጥሩር፥ ቀስ​ትና የሚ​ወ​ነ​ጭ​ፉ​ትን ድን​ጋይ አዘ​ጋ​ጀ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በብ​ል​ሃ​ተ​ኞች እጅ የተ​ሠ​ሩ​ትን ፥ በግ​ን​ብና በቅ​ጥር ላይ የሚ​ኖ​ሩ​ትን፥ ፍላ​ጻና መርግ የሚ​ወ​ረ​ወ​ር​ባ​ቸ​ውን መሣ​ሪ​ያ​ዎች አደ​ረገ፤ እስ​ኪ​በ​ረ​ታም ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በድ​ንቅ ረድ​ቶ​ታ​ልና የመ​ሣ​ሪ​ያ​ዎቹ ዝና እስከ ሩቅ ድረስ ተሰማ።</verse>
				<verse number="16">ነገር ግን በበ​ረታ ጊዜ ለጥ​ፋት ልቡ ታበየ፤ አም​ላ​ኩ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በደለ፤ በዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ ያጥን ዘንድ ወደ መቅ​ደስ ገባ።</verse>
				<verse number="17">ካህ​ኑም ዓዛ​ር​ያስ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ጽኑ​ዓን የነ​በሩ ሰማ​ንያ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካህ​ናት ተከ​ት​ለው ገቡ።</verse>
				<verse number="18">ንጉ​ሡ​ንም ዖዝ​ያ​ንን እየ​ተ​ቃ​ወሙ፥ “ዖዝ​ያን ሆይ፥ ዕጣን ማጠን ለተ​ቀ​ደ​ሱት ለአ​ሮን ልጆች ለካ​ህ​ናቱ ነው እንጂ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታጥን ዘንድ ለአ​ንተ አይ​ገ​ባ​ህም፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርቀ​ሃ​ልና ከመ​ቅ​ደሱ ውጣ፤ ይህም በአ​ም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ ለአ​ንተ ክብር አይ​ሆ​ን​ህም” አሉት።</verse>
				<verse number="19">ዖዝ​ያ​ንም ተቈጣ፤ በመ​ቅ​ደ​ስም የሚ​ያ​ጥ​ን​በት ጥና በእጁ ነበረ፤ ካህ​ና​ቱ​ንም በተ​ቈጣ ጊዜ በካ​ህ​ናቱ ፊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በዕ​ጣኑ መሠ​ዊያ አጠ​ገብ ሳለ በግ​ን​ባሩ ላይ ለምጽ ታየ።</verse>
				<verse number="20">ታላቁ ካህን ዓዛ​ር​ያስ፥ ካህ​ና​ቱም ሁሉ ተመ​ለ​ከ​ቱት፤ እነ​ሆም፥ በግ​ን​ባሩ ላይ ለምጽ ነበረ፤ ፈጥ​ነ​ውም አባ​ረ​ሩት፤ እር​ሱም ደግሞ እግ​ዝ​አ​ብ​ሔር ቀሥ​ፎት ነበ​ርና ይወጣ ዘንድ ቸኰለ።</verse>
				<verse number="21">ንጉ​ሡም ዖዝ​ያን እስ​ኪ​ሞት ድረስ ለም​ጻም ነበረ፤ ለም​ጻ​ምም ሆኖ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ርቆ​አ​ልና በተ​ለየ ቤት ይቀ​መጥ ነበር፤ ልጁም ኢዮ​አ​ታም በቤተ መን​ግ​ሥቱ ሆኖ በም​ድሩ ሕዝብ ላይ ይፈ​ርድ ነበር።</verse>
				<verse number="22">የቀ​ሩ​ትም የፊ​ተ​ኞ​ቹና የኋ​ለ​ኞቹ የዖ​ዝ​ያን ነገ​ሮች በነ​ቢዩ በኢ​ሳ​ይ​ያስ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፈ​ዋል።</verse>
				<verse number="23">ዖዝ​ያ​ንም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ ለም​ጻም ነው ብለ​ዋ​ልና የነ​ገ​ሥ​ታቱ መቃ​ብር ባል​ሆነ እርሻ ውስጥ ቀበ​ሩት፤ ልጁም ኢዮ​አ​ታም በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="27">
				<verse number="1">ኢዮ​አ​ታ​ምም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አም​ስት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ ስድ​ስት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም የሳ​ዶቅ ልጅ ኢየ​ሩሳ ትባል ነበር።</verse>
				<verse number="2">አባ​ቱም ዖዝ​ያን እን​ዳ​ደ​ረገ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ፤ ነገር ግን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ አል​ገ​ባም፤ ሕዝ​ቡም ገና ይበ​ድል ነበር።</verse>
				<verse number="3">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት የላ​ይ​ኛ​ውን በር ሠራ፤ በዖ​ፌ​ልም ቅጥር ላይ ብዙ ሠራ።</verse>
				<verse number="4">በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በይ​ሁዳ ሀገር ላይ ከተ​ሞ​ችን ሠራ፤ በዱር ስፍ​ራ​ዎ​ችም አም​ባ​ዎ​ች​ንና ግን​ቦ​ችን ሠራ።</verse>
				<verse number="5">ከአ​ሞ​ንም ልጆች ንጉሥ ጋር ተዋጋ፤ አሸ​ነ​ፋ​ቸ​ውም። በዚ​ያም ዓመት የአ​ሞን ልጆች መቶ መክ​ሊት ብር፥ ዐሥር ሺህም የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ስንዴ፥ ዐሥር ሺህም የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ገብስ ግብር ሰጡት። እን​ዲ​ሁም ደግሞ የአ​ሞን ልጆ​ችና ንጉ​ሣ​ቸው በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው፥ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውና በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት ሰጡት።</verse>
				<verse number="6">ኢዮ​አ​ታ​ምም በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መን​ገ​ዱን አቅ​ን​ቶ​አ​ልና በረታ።</verse>
				<verse number="7">የቀ​ሩ​ትም የኢ​ዮ​አ​ታም ነገ​ሮች፥ ሰል​ፉም ሁሉ፥ ሥራ​ውም፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።</verse>
				<verse number="8">መን​ገ​ሥም በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አም​ስት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ ስድ​ስት ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="9">ኢዮ​አ​ታ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት፤ ልጁም አካዝ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="28">
				<verse number="1">አካ​ዝም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ ስድ​ስት ዓመት ነገሠ፤ እንደ አባ​ቱም እንደ ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገር አላ​ደ​ረ​ገም።</verse>
				<verse number="2">ነገር ግን በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መን​ገድ ሄደ፤ ደግ​ሞም ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ትን ምስ​ሎች ሠራ።</verse>
				<verse number="3">ደግ​ሞም በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ለም​ስሉ ሠዋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ዳ​ሳ​ደ​ዳ​ቸው እንደ አሕ​ዛ​ብም ክፉ ልማድ ልጆ​ቹን በእ​ሳት አቃ​ጠለ።</verse>
				<verse number="4">በኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችና በተ​ራ​ሮች ላይ በለ​መ​ለ​መ​ውም ዛፍ ሁሉ በታች ያጥን ነበር።</verse>
				<verse number="5">ስለ​ዚህ አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሶ​ርያ ንጉሥ እጅ አሳ​ልፎ ሰጠው፤ እር​ሱም መታው፤ ከእ​ር​ሱም ብዙ ምር​ኮ​ኞ​ችን ወሰደ፤ ወደ ደማ​ስ​ቆም አመ​ጣው። ደግ​ሞም በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እጅ አሳ​ልፎ ሰጠው፤ እር​ሱም በታ​ላቅ አመ​ታት መታው።</verse>
				<verse number="6">የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተው ነበ​ርና የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ በአ​ንድ ቀን ከይ​ሁዳ ጽኑ​ዓን የነ​በሩ መቶ ሃያ ሺህ ሰል​ፈ​ኞ​ችን ገደለ፤</verse>
				<verse number="7">ከኤ​ፍ​ሬም ወገን የነ​በ​ረው ኀያል ሰው ዝክ​ሪም የን​ጉ​ሡን ልጅ ማዓ​ሥ​ያ​ንና የቤ​ቱን አዛዥ ዓዝ​ሪ​ቃ​ምን፥ ለን​ጉ​ሡም በማ​ዕ​ርግ ሁለ​ተኛ የሆ​ነ​ውን ሕል​ቃ​ናን ገደለ።</verse>
				<verse number="8">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ሦስት መቶ ሺህ ሴቶ​ችን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ንም ማረኩ፤ እጅ​ግም ምርኮ ከእ​ነ​ርሱ ወስ​ደው ወደ ሰማ​ርያ አገቡ።</verse>
				<verse number="9">በዚ​ያም ዖዴድ የተ​ባለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ ነበረ፤ ወደ ሰማ​ር​ያም የሚ​መ​ጣ​ውን ጭፍራ ሊገ​ና​ኘው ወጣ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፤ “እነሆ፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁ​ዳን ስለ ተቈጣ በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ እና​ን​ተም ወደ ሰማይ በሚ​ደ​ርስ ቍጣ ገደ​ላ​ች​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">አሁ​ንም የይ​ሁ​ዳ​ንና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ልጆች ባሪ​ያ​ዎች አድ​ር​ገን እን​ግዛ ትላ​ላ​ችሁ፤ የፈ​ጣ​ሪ​ያ​ችሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክር የም​ሆን እኔም ከእ​ና​ንተ ጋር ያለሁ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="11">አሁ​ንም ስሙ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በላ​ያ​ችሁ ነድ​ዶ​አ​ልና ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ የወ​ሰ​ዳ​ች​ኋ​ቸ​ውን ምር​ኮ​ኞች መልሱ።”</verse>
				<verse number="12">ደግ​ሞም ከኤ​ፍ​ሬም ልጆች አለ​ቆች የአ​ናን ልጅ ዓዛ​ር​ያስ፥ የመ​ስ​ለ​ሞት ልጅ በራ​ክያ፥ የሳ​ሎም ልጅ ሕዝ​ቅ​ያስ፥ የአ​ዳሊ ልጅ አማ​ስያ ከሰ​ልፍ የተ​መ​ለ​ሱ​ትን ተቃ​ወ​ሙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">“ደግ​ሞም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በእኛ ላይ በደል ታመ​ጡ​ብ​ና​ላ​ች​ሁና፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ን​ንና በደ​ላ​ች​ንን ታበ​ዙ​ብ​ና​ላ​ች​ሁና የተ​ማ​ረ​ኩ​ትን ወደ​ዚህ አታ​ግቡ፤ በደ​ላ​ችን ታላቅ ነውና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የመ​ቅ​ሠ​ፍቱ ቍጣ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ነውና” አሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">ሰል​ፈ​ኞ​ቹም ምር​ኮ​ኞ​ቹ​ንና ምር​ኮ​ውን በአ​ለ​ቆ​ችና በጉ​ባኤ ሁሉ ፊት ተዉ።</verse>
				<verse number="15">በስ​ማ​ቸ​ውም የተ​ጻፉ ሰዎች ተነ​ሥ​ተው ምር​ኮ​ኞ​ቹን ወሰዱ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ራቁ​ታ​ቸ​ውን ለነ​በ​ሩት ሁሉ ከም​ር​ኮው አለ​በ​ሱ​አ​ቸው፤ አጐ​ና​ጸ​ፉ​አ​ቸ​ውም፤ ጫማም በእ​ግ​ራ​ቸው አደ​ረ​ጉ​ላ​ቸው፤ መገ​ቡ​አ​ቸ​ውም፤ አጠ​ጡ​አ​ቸ​ውም፤ ቀቡ​አ​ቸ​ውም፤ ደካ​ሞ​ቹ​ንም ሁሉ በአ​ህ​ዮች ላይ አስ​ቀ​መ​ጡ​አ​ቸው፤ ዘን​ባ​ባም ወዳ​ለ​በት ከተማ ወደ ኢያ​ሪኮ ወደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው አመ​ጡ​አ​ቸው፤ ወደ ሰማ​ር​ያም ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="16">በዚ​ያም ጊዜ ንጉሡ አካዝ ርዳታ ፈልጎ ወደ አሦር ንጉሥ ላከ፤</verse>
				<verse number="17">የኤ​ዶ​ም​ያስ ሰዎች ዳግ​መኛ መጥ​ተው፥ ይሁ​ዳ​ንም መት​ተው ብዙ ምር​ኮኛ ወስ​ደው ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="18">ደግ​ሞም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን በቆ​ላ​ውና በደ​ቡብ በኩል ባሉት በይ​ሁዳ ከተ​ሞች አደጋ ጥለው ነበር፤ ቤት​ሳ​ሚ​ስ​ንና ኤሎ​ንን፥ ጋቤ​ሮ​ት​ንም፥ ሠካ​ዕ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ ቴም​ና​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋ​ንም፥ ጋማ​ዚ​እ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን ወስ​ደው በዚያ ተቀ​ም​ጠው ነበር።</verse>
				<verse number="19">በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በአ​ካዝ ምክ​ን​ያት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁ​ዳን አዋ​ረ​ደው፤ እርሱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅግ ርቆ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="20">የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ቴል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶር መጥቶ አስ​ጨ​ነ​ቀው።</verse>
				<verse number="21">አካ​ዝም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ከን​ጉ​ሡና ከአ​ለ​ቆ​ቹም ቤት የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ወሰደ፤ ለአ​ሦ​ርም ንጉሥ ሰጠ፥ ነገር ግን አስ​ጨ​ነ​ቀው እንጂ አል​ረ​ዳ​ውም።</verse>
				<verse number="22">ዳግ​መ​ኛም ንጉሡ አካዝ ፈጽሞ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራቀ።</verse>
				<verse number="23">ንጉ​ሡም፥ “የመ​ቱ​ኝን የደ​ማ​ስ​ቆን አማ​ል​ክት እፈ​ል​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የሶ​ር​ያን ንጉሥ እር​ሱን ረድ​ተ​ው​ታ​ልና እኔ​ንም ይረ​ዱኝ ዘንድ እሠ​ዋ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለ። ነገር ግን ለእ​ር​ሱና ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዕን​ቅ​ፋት ሆኑ።</verse>
				<verse number="24">አካ​ዝም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ዕቃ​ዎች ሁሉ ወስዶ ሰባ​በ​ራ​ቸው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ደጆች ዘጋ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ማዕ​ዘን ሁሉ ለራሱ መሠ​ዊያ ሠራ።</verse>
				<verse number="25">በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ሁሉ ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት ያጥን ዘንድ የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን አሠራ፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አስ​ቈጣ።</verse>
				<verse number="26">የቀ​ሩ​ትም ነገ​ሮ​ቹና ሥራው ሁሉ፥ የፊ​ተ​ኞ​ቹና የኋ​ለ​ኞቹ እነሆ፥ በይ​ሁ​ዳና በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መጽ​ሐፍ ተጽ​ፈ​ዋል።</verse>
				<verse number="27">አካ​ዝም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት፤ ነገር ግን ወደ እስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መቃ​ብር አላ​ገ​ቡ​ትም፤ ልጁም ሕዝ​ቅ​ያስ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="29">
				<verse number="1">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም የሃያ አም​ስት ዓመት ጐል​ማሳ በነ​በረ ጊዜ መን​ገሥ ጀመረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም የዘ​ካ​ር​ያስ ልጅ አብያ ትባል ነበር።</verse>
				<verse number="2">አባ​ቱም ዳዊት እን​ዳ​ደ​ረገ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="3">በመ​ን​ግ​ሥ​ቱም በጸና ጊዜ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ደጆች ከፈተ፤ አደ​ሳ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="4">ካህ​ና​ቱ​ንና ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም አስ​መጣ፤ በም​ሥ​ራቅ በኩል ባለው አደ​ባ​ባ​ይም ሰበ​ሰ​ባ​ቸው፤</verse>
				<verse number="5">እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ሌዋ​ው​ያን ሆይ፥ ስሙኝ፤ ራሳ​ች​ሁን አንጹ፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ቀድሱ፤ ርኩ​ስን ነገር ሁሉ ከመ​ቅ​ደሱ አስ​ወ​ግዱ።</verse>
				<verse number="6">አባ​ቶ​ቻ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርቀ​ዋል፤ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አድ​ር​ገ​ዋል፤ እር​ሱ​ንም ረስ​ተ​ዋል፤ ፊታ​ቸ​ው​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መል​ሰ​ዋል፤ ጀር​ባ​ቸ​ው​ንም አዙ​ረ​ዋል፤</verse>
				<verse number="7">ደግ​ሞም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ደጆች ዘግ​ተ​ዋል፤ መብ​ራ​ቶ​ቹ​ንም አጥ​ፍ​ተ​ዋል፤ በመ​ቅ​ደ​ሱም ውስጥ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አላ​ጠ​ኑም፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አላ​ቀ​ረ​ቡም።</verse>
				<verse number="8">“ስለ​ዚ​ህም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ሆነ፤ በዐ​ይ​ና​ች​ሁም እን​ደ​ም​ታዩ ለድ​ን​ጋ​ጤና ለመ​ደ​ነ​ቂያ፥ ለመ​ዘ​በ​ቻም አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">እነ​ሆም፥ ስለ​ዚህ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ በሰ​ይፍ ወደቁ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም፥ ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁም የእ​ነ​ርሱ ሀገር ወዳ​ል​ሆነ ተማ​ረኩ፤ እስከ ዛሬም በዚያ ይኖ​ራሉ።</verse>
				<verse number="10">አሁ​ንም የቍ​ጣ​ውን መቅ​ሠ​ፍት ከእኛ እን​ዲ​መ​ልስ ከእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ቃል ኪዳን አደ​ርግ ዘንድ በልቤ አስ​ቤ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">አሁ​ንም በፊቱ ትቆ​ሙና ታገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ትሆኑ ዘንድ፥ ታጥ​ኑ​ለ​ትም ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መር​ጦ​አ​ች​ኋ​ልና ቸል አት​በሉ።”</verse>
				<verse number="12">ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ ከቀ​ዓት ልጆች የአ​ሜ​ሳእ ልጅ መኤ​ትና የዓ​ዛ​ር​ያስ ልጅ ኢዮ​ሔል፥ ከሜ​ራ​ሪም ልጆች የአ​ብዲ ልጅ ቂስና የያ​ሃ​ሌ​ል​ኤል ልጅ ዓዛ​ር​ያስ፥ ከጌ​ድ​ሶ​ንም ልጆች የዛ​ማት ልጅ ዮአ​ክና የዮ​አክ ልጅ ኢዮ​አድ፤</verse>
				<verse number="13">ከኤ​ል​ሳ​ፋ​ንም ልጆች ሳም​ሪና ኢዮ​ሔል፥ ከአ​ሳ​ፍም ልጆች ዘካ​ር​ያ​ስና ማታ​ን​ያስ፤</verse>
				<verse number="14">ከኤ​ማ​ንም ልጆች ኢዮ​ሔ​ልና ሰሜኢ፥ ከኢ​ዱ​ቱ​ንም ልጆች ሰማ​ዕ​ያና ኡዝ​ሔል ተነሡ።</verse>
				<verse number="15">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሰብ​ስ​በው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ንጉሡ ትእ​ዛዝ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ያነጹ ዘንድ ራሳ​ቸ​ውን አነጹ።</verse>
				<verse number="16">ካህ​ና​ቱም ያነ​ጹት ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ውስጥ ገቡ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መቅ​ደስ ያገ​ኙ​ትን ርኩስ ነገር ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ አወ​ጡት። ሌዋ​ው​ያ​ንም ወስ​ደው ወደ ሜዳ ወደ ቄድ​ሮን ወንዝ ጣሉት።</verse>
				<verse number="17">በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ያነጹ ጀመር፤ በዚ​ያ​ውም ወር በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወለል ደረሱ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት በስ​ም​ንት ቀን አነጹ፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ ስድ​ስ​ተ​ኛው ቀን ፈጸሙ።</verse>
				<verse number="18">ወደ ውስ​ጡም ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ገብ​ተው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሁሉ፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊ​ያና ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ የኅ​ብ​ስተ ገጹ​ንም ገበ​ታና ዕቃ​ውን ሁሉ አን​ጽ​ተ​ናል፤</verse>
				<verse number="19">ንጉ​ሡም አካዝ ነግሦ ሳለ በመ​ተ​ላ​ለፉ ያረ​ከ​ሰ​ውን ዕቃ ሁሉ አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ናል፤ ቀድ​ሰ​ና​ልም፤ እነ​ሆም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ፊት ሆነ​ዋል” አሉት።</verse>
				<verse number="20">ንጉ​ሡም ሕዝ​ቅ​ያስ ማልዶ ተነሣ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቤት አለ​ቆች ሰበ​ሰበ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ወጣ።</verse>
				<verse number="21">ስለ መን​ግ​ሥ​ቱና ስለ መቅ​ደ​ሱም፥ ስለ ሕዝ​ቡም ስለ እስ​ራ​ኤል ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሰባት ወይ​ፈ​ኖች፥ ሰባ​ትም አውራ በጎች፥ ሰባ​ትም የበግ ጠቦ​ቶች፥ ሰባ​ትም አውራ ፍየ​ሎች አመጡ። የአ​ሮ​ን​ንም ልጆች ካህ​ና​ቱን፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ውጡ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">ወይ​ፈ​ኖ​ቹ​ንም አረዱ፤ ካህ​ና​ቱም ደሙን ተቀ​ብ​ለው በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ረጩት፤ አውራ በጎ​ቹ​ንም አረዱ፤ ደሙ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ረጩት፤ ጠቦ​ቶ​ቹ​ንም አረዱ፤ ደሙ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ረጩት።</verse>
				<verse number="23">የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ኑ​ት​ንም አውራ ፍየ​ሎች በን​ጉ​ሡና በጉ​ባ​ኤው ፊት አቀ​ረቡ፤ እጃ​ቸ​ው​ንም ጫኑ​ባ​ቸው፤</verse>
				<verse number="24">ካህ​ና​ቱም አረ​ዱ​አ​ቸው፤ ንጉ​ሡም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ እን​ዲ​ደ​ረግ አዝዞ ነበ​ርና ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ማስ​ተ​ስ​ረያ ያደ​ርጉ ዘንድ ደማ​ቸ​ውን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ አቀ​ረቡ።</verse>
				<verse number="25">ይህ​ንም ትእ​ዛዝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በነ​ቢ​ያቱ እጅ አዝ​ዞ​አ​ልና እንደ ዳዊ​ትና እንደ ንጉሡ ባለ ራእይ እንደ ጋድ፥ እንደ ነቢ​ዩም እንደ ናታን ትእ​ዛዝ፥ ጸና​ጽ​ልና በገና፥ መሰ​ን​ቆም አስ​ይዞ ሌዋ​ው​ያ​ንን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቆመ።</verse>
				<verse number="26">ሌዋ​ው​ያ​ንም የዳ​ዊ​ትን የዜማ ዕቃ ይዘው፥ ካህ​ና​ቱም መለ​ከ​ቱን ይዘው ቆመው ነበር።</verse>
				<verse number="27">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ አሳ​ርጉ” አለ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ማሳ​ረግ በተ​ጀ​መረ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዝ​ሙር ደግሞ ተጀ​መረ፤ መለ​ከ​ቱም ተነፋ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ የዳ​ዊት ዜማ ዕቃ ተመታ።</verse>
				<verse number="28">የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም መሥ​ዋ​ዕት እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ ጉባ​ኤው ሁሉ ይሰ​ግዱ ነበር፤ መዘ​ም​ራ​ኑም ይዘ​ምሩ ነበር፤ መለ​ከ​ተ​ኞ​ችም ይነፉ ነበር።</verse>
				<verse number="29">ማቅ​ረ​ቡ​ንም በፈ​ጸሙ ጊዜ ንጉሡ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሁሉ አጐ​ነ​በሱ፤ ሰገ​ዱም።</verse>
				<verse number="30">ንጉሡ ሕዝ​ቅ​ያ​ስና አለ​ቆ​ቹም በዳ​ዊ​ትና በነ​ቢዩ በአ​ሳፍ ቃል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ ሌዋ​ው​ያ​ንን አዘዙ። በደ​ስ​ታም አመ​ሰ​ገኑ፤ አጐ​ነ​በ​ሱም፤ ሰገ​ዱም።</verse>
				<verse number="31">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “አሁን እጃ​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አን​ጽ​ታ​ችሁ ቅረቡ፤ መሥ​ዋ​ዕ​ቱ​ንና የም​ስ​ጋ​ና​ውን መሥ​ዋ​ዕት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አምጡ” ብሎ ተና​ገረ። ጉባ​ኤ​ውም መሥ​ዋ​ዕ​ቱ​ንና የም​ስ​ጋ​ና​ውን መሥ​ዋ​ዕት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አመጡ፤ ልባ​ቸ​ውም የፈ​ቀደ ሁሉ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አመጡ።</verse>
				<verse number="32">ጉባ​ኤ​ውም ያመ​ጡት የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ቍጥር ሰባ ወይ​ፈን፥ መቶም አውራ በጎች፥ ሁለት መቶም የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ ይህ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነበረ።</verse>
				<verse number="33">የተ​ቀ​ደ​ሱ​ትም ቍጥር ስድ​ስት መቶ በሬ​ዎች፥ ሦስት ሺህም በጎች ነበረ።</verse>
				<verse number="34">ነገር ግን ካህ​ናቱ ጥቂ​ቶች ነበ​ሩና የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ለመ​ግ​ፈፍ አይ​ች​ሉም ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም ሌዋ​ው​ያን በቅን ልብ ከካ​ህ​ናት ይልቅ ይቀ​ደሱ ነበ​ርና ሥራው እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ፥ ካህ​ና​ቱም እስ​ኪ​ቀ​ደሱ ድረስ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ሌዋ​ው​ያን ያግ​ዙ​አ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="35">የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም መሥ​ዋ​ዕት ከደ​ኅ​ን​ነቱ መሥ​ዋ​ዕት ስብና ለሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም መሥ​ዋ​ዕት ከሚ​ቀ​ር​በው የመ​ጠጥ ቍር​ባን ጋር ብዙ ነበረ። እን​ዲ​ሁም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ተዘ​ጋጀ።</verse>
				<verse number="36">ሕዝ​ቅ​ያ​ስና ሕዝ​ቡም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ ስላ​ዘ​ጋ​ጀው ነገር ደስ አላ​ቸው። ይህ ነገር በድ​ን​ገት ተደ​ር​ጎ​አ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="30">
				<verse number="1">ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲካ ያደ​ርጉ ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዲ​መጡ ሕዝ​ቅ​ያስ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ላከ፤ ደግ​ሞም ወደ ኤፍ​ሬ​ምና ወደ ምናሴ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ችን ጻፈ።</verse>
				<verse number="2">ንጉ​ሡና አለ​ቆቹ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ያለ የእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር ፋሲ​ካ​ውን ያደ​ርጉ ዘንድ ተማ​ከሩ።</verse>
				<verse number="3">ካህ​ናቱ በሚ​በቃ ቍጥር ስላ​ል​ተ​ቀ​ደሱ፥ ሕዝ​ቡም ገና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስላ​ል​ተ​ሰ​በ​ሰቡ በጊ​ዜው ያደ​ር​ጉት ዘንድ አል​ቻ​ሉም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="4">ነገ​ሩም ንጉ​ሡ​ንና ጉባ​ኤ​ውን ሁሉ ደስ የሚ​ያ​ሰኝ ሆነ።</verse>
				<verse number="5">እንደ ተጻ​ፈም ብዙ​ዎቹ አላ​ደ​ረ​ጉ​ትም ነበ​ርና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፋሲካ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያደ​ርጉ ዘንድ እን​ዲ​መጡ ከቤ​ር​ሳ​ቤህ ጀምሮ እስከ ዳን ድረስ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ አዋጅ እን​ዲ​ነ​ገር ወሰኑ።</verse>
				<verse number="6">እንደ ንጉ​ሡም ትእ​ዛዝ መል​እ​ክ​ተ​ኞቹ እን​ዲህ የሚ​ለ​ውን የን​ጉ​ሡ​ንና የአ​ለ​ቆ​ቹን ደብ​ዳቤ ይዘው ወደ እስ​ራ​ኤ​ልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ፈጥ​ነው ሄዱ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ ወዳ​መ​ለጠ ቅሬ​ታ​ችሁ እን​ዲ​መ​ለስ ወደ አብ​ር​ሃ​ምና ወደ ይስ​ሐቅ ወደ ያዕ​ቆ​ብም አም​ላክ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="7">እና​ን​ተም እን​ደ​ም​ታዩ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ በደሉ፥ ለጥ​ፋ​ትም እንደ ሰጣ​ቸው እንደ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁና እንደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ አት​ሁኑ።</verse>
				<verse number="8">አሁ​ንም እንደ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ አን​ገ​ታ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ስጡ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ወደ ተቀ​ደ​ሰው ወደ መቅ​ደሱ ግቡ፤ ጽኑ ቍጣ​ው​ንም ከእ​ና​ንተ እን​ዲ​መ​ልስ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዙ።</verse>
				<verse number="9">አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸርና መሓሪ ነውና፥ ወደ እር​ሱም ብን​መ​ለስ ፊቱን ከእኛ አያ​ዞ​ር​ምና ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብት​መ​ለሱ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁና ልጆ​ቻ​ችሁ በማ​ረ​ኩ​አ​ቸው ፊት ምሕ​ረ​ትን ያገ​ኛሉ፤ ደግ​ሞም ወደ​ዚ​ህች ምድር ይመ​ል​ሳ​ቸ​ዋል።”</verse>
				<verse number="10">መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹም ከከ​ተማ ወደ ከተማ በኤ​ፍ​ሬ​ምና በም​ናሴ ሀገር እስከ ዛብ​ሎን ሄዱ፤ እነ​ዚያ ግን በን​ቀት ሳቁ​ባ​ቸው፤ አፌ​ዙ​ባ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="11">ነገር ግን ከአ​ሴ​ርና ከም​ናሴ፥ ከዛ​ብ​ሎ​ንም አያሌ ሰዎች ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን አዋ​ረዱ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም መጡ።</verse>
				<verse number="12">ደግ​ሞም አንድ ልብ ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል የሆ​ነ​ውን የን​ጉ​ሡ​ንና የአ​ለ​ቆ​ቹን ትእ​ዛዝ ያደ​ርጉ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ነ​ርሱ ላይ ሆነ።</verse>
				<verse number="13">በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር የቂ​ጣ​ውን በዓል ያደ​ርጉ ዘንድ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ብዙ ሕዝብ ተሰ​በ​ሰቡ፤ እጅ​ግም ታላቅ ጉባኤ ነበረ።</verse>
				<verse number="14">ተነ​ሥ​ተ​ውም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የነ​በ​ሩ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ችና ለጣ​ዖ​ታት የሚ​ያ​ጥ​ኑ​በ​ትን ዕቃ ሁሉ አስ​ወ​ገዱ፤ በቄ​ድ​ሮ​ንም ወንዝ ጣሉት።</verse>
				<verse number="15">በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ አረዱ፤ ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም ተዘ​ጋጁ ነጹም። ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አመጡ።</verse>
				<verse number="16">እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው እንደ ሙሴ ሕግ በቦ​ታ​ቸ​ውና በሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ቆሙ፤ ካህ​ና​ቱም ከሌ​ዋ​ው​ያን እጅ የተ​ቀ​በ​ሉ​ትን ደም ይረጩ ነበር።</verse>
				<verse number="17">በጉ​ባ​ኤ​ውም ያል​ነጹ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ስለ​ዚ​ህም ሌዋ​ው​ያን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሳ​ቸ​ውን ላላ​ነ​ጹት ሁሉ የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ ያር​ዱ​ላ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="18">እንደ ትእ​ዛ​ዙም ሳይ​ሆን ከኤ​ፍ​ሬ​ምና ከም​ናሴ፥ ከይ​ሳ​ኮ​ርና ከዛ​ብ​ሎ​ንም ወገን እጅግ ሰዎች ሳይ​ነጹ ፋሲ​ካ​ውን በሉ።</verse>
				<verse number="19">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ስለ እነ​ርሱ እን​ዲህ ሲል ጸለየ፥ “ምንም እንደ መቅ​ደሱ ማን​ጻት ባይ​ነጻ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመ​ፈ​ለግ ልቡን የሚ​ያ​ቀ​ና​ውን ሁሉ ቸሩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ይበ​ለው።”</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕዝ​ቅ​ያ​ስን ሰማው፤ ሕዝ​ቡ​ንም አዳ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="21">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተገ​ኝ​ተው የነ​በሩ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በየ​ቀኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገኑ የቂ​ጣ​ውን በዓል በታ​ላቅ ደስታ ሰባት ቀን አደ​ረጉ፤ ሌዋ​ው​ያ​ኑና ካህ​ና​ቱም በዜማ ዕቃ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ነበር።</verse>
				<verse number="22">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ግ​ሎት አስ​ተ​ዋ​ዮች የነ​በ​ሩ​ትን ሌዋ​ው​ያ​ንን ሁሉ ያጽ​ናና ነበር። የደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት እያ​ቀ​ረቡ፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ እያ​መ​ሰ​ገኑ ሰባት ቀን በዓል አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="23">ጉባ​ኤው ሁሉ እንደ ገና ሰባት ቀን በዓል ያደ​ርጉ ዘንድ ተማ​ከሩ፤ በደ​ስ​ታም እንደ ገና ሰባት ቀን በዓል አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="24">ንጉሡ ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ስለ ቍር​ባን ሺህ ወይ​ፈ​ኖ​ች​ንና ሰባት ሺህ በጎ​ችን ለይ​ሁ​ዳና ለጉ​ባ​ኤው ሰጥቶ ነበር፤ አለ​ቆ​ቹም ሺህ ወይ​ፈ​ኖ​ች​ንና ዐሥር ሺህ በጎ​ችን ለጉ​ባ​ኤው ሰጥ​ተው ነበር፤ ከካ​ህ​ናቱ እጅግ ብዙ ተቀ​ድ​ሰው ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="25">የይ​ሁ​ዳም ጉባኤ ሁሉ ፥ ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያኑ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የመጡ ጉባኤ ሁሉ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሀገር የመ​ጡ​ትና በይ​ሁዳ የኖ​ሩት እን​ግ​ዶች ደስ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ታላቅ ደስታ ሆነ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ከዳ​ዊት ልጅ ከን​ጉሥ ሰሎ​ሞን ዘመን ጀምሮ እን​ደ​ዚህ ያለ በዓል በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አል​ተ​ደ​ረ​ገም ነበር።</verse>
				<verse number="27">ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም ተነ​ሥ​ተው ሕዝ​ቡን ባረኩ፤ ድም​ፃ​ቸ​ውም ተሰማ፥ ጸሎ​ታ​ቸ​ውም ወደ ቅዱስ ማደ​ሪ​ያው ወደ ሰማይ ዐረገ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="31">
				<verse number="1">ይህም ሁሉ በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ በይ​ሁዳ ከተ​ሞች የተ​ገኙ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ወጥ​ተው ዐም​ዶ​ቹን ሰበሩ፤ ዐፀ​ዶ​ች​ንም ኮረ​ብ​ታ​ዎ​ች​ንም አፈ​ረሱ፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም አጠፉ። በይ​ሁ​ዳና በብ​ን​ያ​ምም ሁሉ ደግ​ሞም በኤ​ፍ​ሬ​ምና በም​ናሴ የነ​በ​ሩ​ትን ፈጽ​መው እስከ ዘለ​ዓ​ለሙ አጠ​ፉ​አ​ቸው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ወደ ርስ​ታ​ቸ​ውና ወደ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="2">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም የካ​ህ​ና​ት​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ንን ሰሞን በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸ​ውና በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ በሮች የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡና ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ፥ ያመ​ሰ​ግ​ኑም፥ ያከ​ብ​ሩም ዘንድ ካህ​ና​ቱ​ንና ሌዋ​ው​ያ​ኑን መደበ።</verse>
				<verse number="3">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ እንደ ተጻፈ በጥ​ዋ​ትና በማታ በሰ​ን​በ​ታ​ቱም፥ በመ​ባ​ቻ​ዎ​ቹም፥ በበ​ዓ​ላ​ትም ለሚ​ቀ​ር​በው ለሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ንጉሡ ከገ​ን​ዘቡ የሚ​ከ​ፍ​ለ​ውን ወሰነ።</verse>
				<verse number="4">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት እን​ዲ​ጸኑ ለካ​ህ​ና​ቱና ለሌ​ዋ​ው​ያን ድር​ሻ​ቸ​ውን ይሰጡ ዘንድ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሕዝብ አዘዘ።</verse>
				<verse number="5">ይህ​ንም ነገር እን​ዳ​ዘዘ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የእ​ህ​ሉ​ንና የወ​ይ​ኑን፥ የዘ​ይ​ቱ​ንና የማ​ሩ​ንም፥ የእ​ር​ሻ​ው​ንም ፍሬ መጀ​መ​ሪያ ሁሉ ሰጡ፤ የሁ​ሉ​ንም ዐሥ​ራት አብ​ዝ​ተው አቀ​ረቡ።</verse>
				<verse number="6">በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች የሚ​ኖሩ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልና የይ​ሁዳ ልጆች የበ​ሬ​ዉ​ንና የበ​ጉን፥ የፍ​የ​ሉ​ንም ዐሥ​ራት አመጡ፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀደ​ሱት፤ ከም​ረ​ውም አኖ​ሩት።</verse>
				<verse number="7">በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ወር መከ​መር ጀመሩ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ጨረሱ።</verse>
				<verse number="8">ሕዝ​ቅ​ያ​ስና አለ​ቆ​ቹም መጥ​ተው ክም​ሩን ባዩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ። ሕዝ​ቡን እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ባረኩ።</verse>
				<verse number="9">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ካህ​ና​ቱ​ንና ሌዋ​ው​ያ​ኑን ስለ ክምሩ ጠየቀ።</verse>
				<verse number="10">ከሳ​ዶ​ቅም ወገን የሆነ ታላቁ ካህን ዓዛ​ር​ያስ፥ “ሕዝቡ መባ​ውን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ማቅ​ረብ ከጀ​መረ ወዲህ በል​ተ​ናል፤ ጠጥ​ተ​ና​ልም፤ ጠግ​በ​ና​ልም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕዝ​ቡን ባር​ኮ​አ​ልና ብዙ ተር​ፎ​አል፤ ከዚ​ህም ገና ብዙ ተረፈ” ብሎ ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="11">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ጎተራ ያዘ​ጋጁ ዘንድ አዘዘ፤ እነ​ር​ሱም አዘ​ጋጁ።</verse>
				<verse number="12">መባ​ኡ​ንና ዐሥ​ራ​ቱን፥ የተ​ቀ​ደ​ሱ​ት​ንም በእ​ም​ነት ወደ​ዚያ አገቡ። ሌዋ​ዊ​ውም ኮክ​ን​ያስ ተሾ​መ​ባ​ቸው፥ ወን​ድ​ሙም ሰሜኢ በማ​ዕ​ርግ ሁለ​ተኛ ነበረ፤</verse>
				<verse number="13">ንጉ​ሡም ሕዝ​ቅ​ያ​ስና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አለቃ ዓዛ​ር​ያስ እንደ አዘዙ ኢዮ​ኤል፥ ዓዛ​ዝያ፥ አና​ኤት፥ ኡሳ​ሄል፥ ኢያ​ሪ​ሞት፥ ኢዮ​ዛ​ብድ፥ ኤል​ሄል፥ ሰማ​ኪያ፥ መሐት፥ በና​ያ​ስና ልጆቹ፥ ከኮ​ክ​ን​ያ​ስና ከወ​ን​ድሙ ከሰ​ሜኢ እጅ በታች ተቈ​ጣ​ጣ​ሪ​ዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="14">የሌ​ዋ​ዊ​ውም የይ​ም​ላእ ልጅ የም​ሥ​ራቁ ደጅ በረኛ ቆሬ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መባና የተ​ቀ​ደ​ሱ​ትን ነገ​ሮች እን​ዲ​ያ​ካ​ፍል ሕዝቡ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ቀ​ረ​ቡት ላይ ተሾመ።</verse>
				<verse number="15">በካ​ህ​ና​ቱም ከተ​ሞች ለታ​ላ​ላ​ቆ​ችና ለታ​ና​ና​ሾች ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ክፍ​ላ​ቸ​ውን በእ​ም​ነት ይሰጡ ዘንድ ኤዶም፥ ብን​ያስ፥ ኢያሱ፥ ሴሚ፥ አማ​ርያ፥ ኮክ​ን​ያስ ከእጁ በታች ነበሩ።</verse>
				<verse number="16">ከሦ​ስ​ትም ዓመት ወደ ላይ ላሉ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ለሥ​ራ​ቸ​ውና ለአ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ዕለት ዕለት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ለሚ​ገቡ ወን​ዶች ሁሉ፥</verse>
				<verse number="17">በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤት ለተ​ቈ​ጠሩ ካህ​ናት፥ ከሃያ ዓመ​ትም ወደ ላይ ላሉ በየ​ሥ​ር​ዐ​ታ​ቸ​ውና በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ለተ​ቈ​ጠሩ ሌዋ​ው​ያን፥</verse>
				<verse number="18">በማ​ኅ​በ​ራ​ቸ​ውም ሁሉ በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው ለተ​ቈ​ጠሩ ለሚ​ስ​ቶ​ቻ​ቸው፥ ለወ​ን​ዶ​ችና ለሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ይሰጡ ነበር፤ በእ​ም​ነት ፈጽ​መው ተቀ​ድ​ሰ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="19">ክህ​ነት ለሚ​ገ​ባ​ቸው ለአ​ሮን ልጆች ለካ​ህ​ናቱ፥ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ዙሪያ ባሉ መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ችና በሌ​ሎ​ችም ከተ​ሞች ላሉ ለወ​ን​ዶች ሁሉ፥ ከሌ​ዋ​ው​ያን ጋራ ለተ​ቈ​ጠሩ ሰዎ​ችም ሁሉ ከፍ​ለው ይሰጡ ዘንድ በስም የተ​ጠሩ ሰዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="20">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በይ​ሁዳ ሁሉ እን​ዲህ አደ​ረገ፤ በአ​ም​ላ​ኩም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካ​ም​ንና ቅን ነገ​ርን እው​ነ​ት​ንም አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="21">ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት በጀ​መ​ረው ሥራ ሁሉ፥ በሕ​ጉና በት​እ​ዛ​ዙም አም​ላ​ኩን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በፍ​ጹም ልቡ ፈለ​ገው፤ ሥራ​ውም ሁሉ ተከ​ና​ወ​ነ​ለት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="32">
				<verse number="1">ከእ​ነ​ዚ​ህም ነገ​ሮ​ችና ከዚህ እው​ነት በኋላ የአ​ሦር ንጉሥ ሰና​ክ​ሬም መጥቶ ወደ ይሁዳ ገባ፤ በተ​መ​ሸ​ጉ​ትም ከተ​ሞች ፊት ሰፈረ፤ ሊወ​ስ​ዳ​ቸ​ውም አሰበ።</verse>
				<verse number="2">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ሰና​ክ​ሬም እንደ መጣ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ሊወጋ ፊቱን እን​ዳ​ቀና አየ፤</verse>
				<verse number="3">ከከ​ተ​ማ​ዪቱ በስ​ተ​ውጭ ያለ​ውን የው​ኃ​ውን ምንጭ ይደ​ፍኑ ዘንድ ከአ​ለ​ቆ​ቹና ከኀ​ያ​ላኑ ጋር ተማ​ከረ፤ እነ​ር​ሱም ምክ​ሩን ወደዱ።</verse>
				<verse number="4">ብዙ ሰዎ​ች​ንም ሰበ​ሰበ፥ “የአ​ሦ​ርም ንጉሥ እን​ዳ​ይ​መ​ጣና ብዙ ውኃ አግ​ኝቶ እን​ዳ​ይ​ጠ​ነ​ክር” ብሎ የውኃ ምን​ጮ​ች​ንና በከ​ተ​ማ​ዪቱ የሚ​ፈ​ስ​ሱ​ትን ወን​ዞች ደፈነ።</verse>
				<verse number="5">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ሰው​ነ​ቱን አጽ​ናና፤ የፈ​ረ​ሰ​ው​ንም ቅጥር ሁሉ ጠገነ፤ በላ​ዩም ግንብ ሠራ​በት፤ ከእ​ር​ሱም በስ​ተ​ውጭ ሌላ ቅጥር ሠራ፤ ወደ ዳዊ​ትም ከተማ የሚ​ያ​ወ​ጣ​ውን በር አጠ​ነ​ከረ፤ ብዙም መሣ​ሪ​ያና ጋሻ አዘ​ጋጀ።</verse>
				<verse number="6">የጦር አለ​ቆ​ቹ​ንም በሕ​ዝቡ ላይ ሾመ፤ ሁሉ​ንም በሸ​ለ​ቆው በኩል ባለው በከ​ተ​ማ​ዪቱ በር አደ​ባ​ባይ ወደ እርሱ ሰበ​ሰበ፤ እን​ዲ​ህም ብሎ ልባ​ቸ​ውን አጸና፦</verse>
				<verse number="7">“ጽኑ፥ አይ​ዞ​አ​ችሁ፤ ከእኛ ጋር ያለው ከእ​ርሱ ጋር ካለው ይበ​ል​ጣ​ልና ከአ​ሦር ንጉ​ሥና ከእ​ርሱ ጋር ካለው ጭፍራ ሁሉ የተ​ነሣ አት​ፍሩ፤ አት​ደ​ን​ግ​ጡም።</verse>
				<verse number="8">ከእ​ርሱ ጋር የሥጋ ክንድ ነው፤ ከእኛ ጋር ያለው ግን የሚ​ረ​ዳን የሚ​ዋ​ጋ​ል​ንም አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።” ሕዝ​ቡም በይ​ሁዳ ንጉሥ በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ቃል ተጽ​ናና።</verse>
				<verse number="9">ከዚ​ህም በኋላ የአ​ሦር ንጉሥ ሰና​ክ​ሬም ከሠ​ራ​ዊቱ ሁሉ ጋር በለ​ኪሶ ፊት ሳለ ባሪ​ያ​ዎ​ቹን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሕዝ​ቅ​ያ​ስና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ነበሩ ወደ ይሁዳ ሕዝብ ሁሉ እን​ዲህ ሲል ላከ፦</verse>
				<verse number="10">“የአ​ሦር ንጉሥ ሰና​ክ​ሬም እን​ዲህ ይላል፦ እና​ንተ በማን ተማ​ም​ና​ችሁ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ምሽግ ትቀ​መ​ጣ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="11">አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ ያድ​ነ​ናል እያለ ለራብ፥ ለጥ​ምና ለሞት አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ የሚ​ያ​ሳ​ስ​ታ​ችሁ ሕዝ​ቅ​ያስ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="12">በዚህ መሠ​ዊያ ፊት ስገዱ፤ በእ​ር​ሱም ላይ ዕጠኑ፤ እያለ የይ​ሁ​ዳን ሕዝ​ብና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ነዋ​ሪ​ዎች አዝዞ፥ የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችና መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹን ያፈ​ረሰ ይህ ሕዝ​ቅ​ያስ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="13">እኔና አባ​ቶች በም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ ያደ​ረ​ግ​ነ​ውን አላ​ወ​ቃ​ች​ሁ​ምን? የም​ድ​ርስ ሁሉ አሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ሀገ​ራ​ቸ​ውን ከእጄ ያድኑ ዘንድ በውኑ ተቻ​ላ​ቸ​ውን?</verse>
				<verse number="14">አም​ላ​ካ​ች​ሁስ ከእጄ እና​ን​ተን ለማ​ዳን ይችል ዘንድ አባ​ቶች ካጠ​ፉ​አ​ቸው ከአ​ሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ሁሉ ሕዝ​ቡን ከእጄ ያድን ዘንድ የቻለ ማን ነው?</verse>
				<verse number="15">አሁ​ንም ሕዝ​ቅ​ያስ አያ​ስ​ታ​ችሁ፤ በእ​ነ​ዚ​ህም ቃላት እን​ድ​ት​ተ​ማ​መኑ አያ​ድ​ር​ጋ​ችሁ፤ አት​መ​ኑ​ትም፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብና ከመ​ን​ግ​ሥ​ታት አማ​ል​ክት ሁሉ ሕዝ​ቡን ከእ​ጄና ከአ​ባ​ቶች እጅ ያድን ዘንድ ማንም አል​ቻ​ለም፤ ስለ​ዚ​ህም አም​ላ​ካ​ችሁ ከእጄ ያድ​ና​ችሁ ዘንድ አይ​ች​ልም።”</verse>
				<verse number="16">ባሪ​ያ​ዎ​ቹም ደግሞ በአ​ም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በባ​ሪ​ያው በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ላይ ሌላ ብዙ ነገር ተና​ገሩ።</verse>
				<verse number="17">ደግ​ሞም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እየ​ተ​ገ​ዳ​ደረ በእ​ር​ሱም ላይ እየ​ተ​ና​ገረ፥ “የም​ድር አሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ሕዝ​ባ​ቸ​ውን ከእጄ ያድኑ ዘንድ እን​ዳ​ል​ቻሉ፥ እን​ዲሁ የሕ​ዝ​ቅ​ያስ አም​ላክ ሕዝ​ቡን ከእጄ ያድን ዘንድ አይ​ች​ልም” የሚል ደብ​ዳቤ ጻፈ።</verse>
				<verse number="18">ቅጥ​ሩን እን​ዲ​ያ​ፈ​ርሱ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም እን​ዲ​ወ​ስዱ፥ በቅ​ጥር ላይ የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ሕዝብ ያስ​ፈ​ራ​ቸ​ውና ያስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ቸው ዘንድ በታ​ላቅ ድምፅ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ ይጮ​ኽ​ባ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="19">በሰ​ውም እጅ በተ​ሠሩ በም​ድር አሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ላይ እን​ደ​ሚ​ና​ገር መጠን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አም​ላክ ላይ ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="20">ንጉሡ ሕዝ​ቅ​ያ​ስና የአ​ሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳ​ይ​ያስ ስለ​ዚህ ተግ​ዳ​ሮት ጸለዩ፤ ወደ ሰማ​ይም ጮኹ።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አ​ኩን ላከ፤ እር​ሱም ጽኑ​ዓን ኀያ​ላ​ኑ​ንና መሳ​ፍ​ን​ቱን አለ​ቆ​ቹ​ንም ከአ​ሦር ንጉሥ ሰፈር አጠፋ። የአ​ሦ​ርም ንጉሥ አፍሮ ወደ ሀገሩ ተመ​ለሰ። ወደ አም​ላ​ኩም ቤት በገባ ጊዜ ከወ​ገቡ የወ​ጡት ልጆቹ በዚያ በሰ​ይፍ ገደ​ሉት።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕዝ​ቅ​ያ​ስ​ንና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ከአ​ሦር ንጉሥ ከስ​ና​ክ​ሬም እጅና ከሁ​ሉም እጅ አዳ​ና​ቸው፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ካለው ሁሉ አሳ​ረ​ፋ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">ብዙ​ዎ​ቹም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ ይዘው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይመጡ ነበር፤ ለይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ለሕ​ዝ​ቅ​ያስ እጅ መንሻ ይሰጡ ነበር፤ እር​ሱም ከዚህ ነገር በኋላ በሕ​ዝብ ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አለ።</verse>
				<verse number="24">በዚ​ያም ወራት ሕዝ​ቅ​ያስ እስከ ሞት ድረስ ታመመ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸለየ፤ እር​ሱም ሰማው፤ ምል​ክ​ትም ሰጠው።</verse>
				<verse number="25">ሕዝ​ቅ​ያስ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰጠው ቸር​ነት መጠን አላ​ደ​ረ​ገም፤ ልቡም ኮራ፤ ስለ​ዚ​ህም በእ​ር​ሱና በይ​ሁዳ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ላይ ቍጣ ሆነ።</verse>
				<verse number="26">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከሚ​ኖሩ ሰዎች ጋር ስለ ልቡ ኵራት ሰው​ነ​ቱን አዋ​ረደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ዘመን ቍጣ​ውን አላ​መ​ጣ​ባ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="27">ለሕ​ዝ​ቅ​ያ​ስም እጅግ ብዙ ሀብ​ትና ክብር ነበ​ረው፤ ለብ​ርና ለወ​ር​ቅም፥ ለከ​በ​ረው ዕን​ቍና ለሽ​ቱው፥ ለጋ​ሻ​ውና ውድ ለሆ​ነው ዕቃ ሁሉ ግምጃ ቤቶ​ችን ሠራ።</verse>
				<verse number="28">ለእ​ህ​ልና ለወ​ይን ጠጅም ለዘ​ይ​ትም ዕቃ ቤቶች፥ ለልዩ ልዩም እን​ስሳ ጋጥ፥ ለመ​ን​ጎ​ችም በረት ሠራ።</verse>
				<verse number="29">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅግ ብዙ ጥሪት ሰጥ​ቶት ነበ​ርና ከተ​ሞ​ችን ለራሱ ሠራ፤ ብዙም የበ​ግና የላም መንጋ ሰበ​ሰበ።</verse>
				<verse number="30">ይህም ሕዝ​ቅ​ያስ የላ​ይ​ኛ​ውን የግ​ዮ​ንን ውኃ ምንጭ ደፈነ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ በም​ዕ​ራብ በኩል አቅ​ንቶ አወ​ረ​ደው። ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በሥ​ራው ሁሉ ተከ​ና​ወነ።</verse>
				<verse number="31">ነገር ግን የባ​ቢ​ሎን መሳ​ፍ​ንት መል​እ​ክ​ተ​ኞች በሀ​ገሩ ላይ ስለ ተደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት ይጠ​ይ​ቁት ዘንድ ወደ እርሱ በተ​ላኩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ት​ነ​ውና በልቡ ያለ​ውን ሁሉ ያውቅ ዘንድ ተወው።</verse>
				<verse number="32">የሕ​ዝ​ቅ​ያ​ስም የቀ​ሩት ነገ​ሮች፥ ቸር​ነ​ቱም፥ እነሆ፥ በአ​ሞጽ ልጅ በነ​ቢዩ በኢ​ሳ​ይ​ያስ ራእይ በይ​ሁ​ዳና በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ሥ​ታት መጽ​ሐፍ ተጽ​ፈ​ዋል።</verse>
				<verse number="33">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ልጆች መቃ​ብር በላ​ይ​ኛው ክፍል ቀበ​ሩት፤ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትም ሁሉ በሞቱ አከ​በ​ሩት። ልጁም ምናሴ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="33">
				<verse number="1">ምና​ሴም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የዐ​ሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አምሳ አም​ስት ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ዳ​ወ​ጣ​ቸው እንደ አሕ​ዛብ ያለ ርኵ​ሰት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="3">አባ​ቱም ሕዝ​ቅ​ያስ ያፈ​ረ​ሳ​ቸ​ውን የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎች መልሶ ሠራ፤ ለበ​ዓ​ሊ​ምም መሠ​ዊያ ሠራ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ች​ንም ተከለ፤ ለሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ ሰገደ፤ አመ​ለ​ካ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ስሜ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል” ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የጣ​ዖት መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ችን ሠራ።</verse>
				<verse number="5">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በሁ​ለቱ አደ​ባ​ባ​ዮች ላይ ለሰ​ማይ ሠራ​ዊት ሁሉ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ችን ሠራ።</verse>
				<verse number="6">በሄ​ኖ​ምም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ልጆ​ቹን በእ​ሳት አቃ​ጠለ፤ ሞራ ገላ​ጭም ሆነ፤ አስ​ማ​ትም አደ​ረገ። መተ​ተ​ኛም ነበረ፤ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ች​ንም ሰበ​ሰበ፤ ያስ​ቈ​ጣ​ውም ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለዳ​ዊ​ትና ለልጁ ለሰ​ሎ​ሞን፥ “በዚህ ቤትና ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ በመ​ረ​ጥ​ኋት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስሜን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አኖ​ራ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="8">ያዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ው​ንም ሁሉ፥ በሙሴ የተ​ሰ​ጠ​ውን ሕግና ሥር​ዐት ፍር​ድ​ንም ሁሉ ቢያ​ደ​ርጉ ቢጠ​ብ​ቁም፥ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ከሰ​ጠ​ኋት ምድር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን እግር እንደ ገና አላ​ር​ቅም” ባለ​በት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ የሠ​ራ​ውን ጣዖ​ትና የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል አቆመ።</verse>
				<verse number="9">ምና​ሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ካጠ​ፋ​ቸው ከአ​ሕ​ዛብ ይልቅ ክፉ ይሠሩ ዘንድ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትን አሳተ።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምና​ሴ​ንና ሕዝ​ቡን ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ግን አል​ሰ​ሙ​ትም።</verse>
				<verse number="11">ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ሠራ​ዊት አለ​ቆች አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ ምና​ሴ​ንም በዛ​ን​ጅር ያዙት፤ በሰ​ን​ሰ​ለ​ትም አስ​ረው ወደ ባቢ​ሎን ወሰ​ዱት።</verse>
				<verse number="12">በተ​ጨ​ነ​ቀም ጊዜ አም​ላ​ኩን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈለገ፤ በአ​ባ​ቶ​ቹም አም​ላክ ፊት ሰው​ነ​ቱን እጅግ አዋ​ረደ።</verse>
				<verse number="13">የን​ጉሡ የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ልጅ ምና​ሴም ጸለየ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="14">“ዓለ​ምን ሁሉ የም​ት​ገዛ፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐቅ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም የጻ​ድ​ቃን ልጆ​ቻ​ቸ​ውም አም​ላክ ሆይ፥ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ከዓ​ለ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር የፈ​ጠ​ርህ፥</verse>
				<verse number="15">በቃ​ልህ ትእ​ዛዝ ባሕ​ርን የገ​ሠ​ጽ​ሃት፥ ቀላ​ዮ​ችን የዘ​ጋህ፥ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ው​ንም የወ​ሰ​ንህ፥</verse>
				<verse number="16">ይኸ​ውም በተ​መ​ሰ​ገ​ነው ስምህ ነው፤ ኀይ​ልህ ከመ​ገ​ለጡ የተ​ነሣ ሁሉ የሚ​ር​ድና የሚ​ን​ቀ​ጠ​ቀጥ፤</verse>
				<verse number="17">ለክ​ብ​ርህ ከፍ​ተ​ኛ​ነት ፍጻሜ የለ​ው​ምና፥ የቍ​ጣ​ህም መቅ​ሠ​ፍት በኃ​ጥ​አን ላይ ግሩም ነው።</verse>
				<verse number="18">በት​እ​ዛ​ዝህ ለሚ​ሆ​ነው ይቅ​ርታ ስፍር ቍጥር የለ​ውም፤ ገናና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ ብቻ ነህና፥ ይቅር ባይ፥ ከቍጣ የራ​ቅህ፥ ይቅ​ር​ታህ የበዛ፥ የሰ​ው​ንም ኀጢ​አት የም​ታ​ስ​ተ​ሰ​ርይ አንተ ነህ።</verse>
				<verse number="19">አሁ​ንም አቤቱ፥ የጻ​ድ​ቃን አም​ላ​ካ​ቸው አንተ ነህ። ንስ​ሓን የፈ​ጠ​ርህ ለጻ​ድቅ ሰው አይ​ደ​ለ​ምና፥ አን​ተን ላል​በ​ደሉ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም አይ​ደ​ለ​ምና፤ ነገር ግን የእ​ኔን የኃ​ጥ​ኡን ንስሓ ወደ ማየት ተመ​ለስ።</verse>
				<verse number="20">ቍጥሩ ከባ​ሕር አሸዋ የሚ​በ​ልጥ በደ​ልን በድ​ያ​ለ​ሁና፥ ኀጢ​አ​ቴም ብዙ ነውና፤ ከበ​ደ​ሌም ብዛት የተ​ነሣ ቀና ብዬ የሰ​ማ​ይን ርዝ​መት አይ ዘንድ አገ​ባቤ አይ​ደ​ለም። ሰው​ነ​ቴን ከኀ​ጢ​አቴ አሳ​ር​ፋት ዘንድ በብ​ረት ቀፎ ደከ​ምሁ፤ በዚ​ህም ደግሞ አላ​ረ​ፍ​ሁም፤ መዓ​ት​ህን አነ​ሣ​ሥ​ቻ​ለ​ሁና፥</verse>
				<verse number="21">ከን​ቱ​ውን ስመ​ለ​ከት የማ​ይ​ጠ​ቅ​መ​ኝ​ንም ነገር ሳበዛ በፊ​ትህ ክፉ ሥራን ሠር​ቻ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="22">አሁ​ንም ቸር​ነ​ት​ህን እየ​ለ​መ​ንሁ በልቤ ጕል​በት እሰ​ግ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="23">አቤቱ፥ ጌታዬ፥ ፈጽሜ በደ​ልሁ፤ ኀጢ​አ​ቴ​ንም አም​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="24">አን​ተ​ንም እማ​ል​ዳ​ለሁ፤ እለ​ም​ን​ህ​ማ​ለሁ፤ ይቅር በለኝ፤ አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፤ ለኀ​ጢ​አ​ቴም አሳ​ል​ፈህ አት​ስ​ጠኝ።</verse>
				<verse number="25">ለዘ​ለ​ዓ​ለም ክፋ​ቴን አት​መ​ል​ከ​ት​ብኝ፤ በም​ድር ጥል​ቀ​ትም አት​በ​ቀ​ለኝ፤ አቤቱ፥ በን​ስሓ ለሚ​መ​ለሱ ሰዎች፥ አም​ላ​ካ​ቸው አንተ ነህና፥ ቸር​ነ​ትህ በእኔ ላይ ይገ​ለጥ፤ መዳን የማ​ይ​ገ​ባኝ ሲሆን በይ​ቅ​ር​ታህ ብዛት አዳ​ን​ኸኝ።</verse>
				<verse number="26">በየ​ጊ​ዜ​ውና በሕ​ይ​ወቴ ዘመን ሁሉ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ። የሰ​ማ​ያት ኀይል ሁሉ አን​ተን ያመ​ሰ​ግ​ና​ሉና፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ምስ​ጋና ለአ​ንተ ይገ​ባል፤” አሜን። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምናሴ ባለ​ማ​ወቅ ከአ​ደ​ረ​ገው ክፉ ሥራው እንደ ተመ​ለሰ ባየ ጊዜ ይቅር አለው፤ ጸሎ​ቱ​ንም ሰማው፤ ልመ​ና​ው​ንም ተቀ​በ​ለው፤ ወደ መን​ግ​ሥ​ቱም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መለ​ሰው፤ ምና​ሴም እርሱ አም​ላክ እንደ ሆነ ዐወቀ።</verse>
				<verse number="27">ከዚህ በኋላ በዳ​ዊት ከተማ በስ​ተ​ው​ጭው ከግ​ዮን ሰሜ​ናዊ ምዕ​ራብ በሸ​ለ​ቆው ውስጥ እስከ ዓሣ በር መግ​ቢያ ድረስ ቅጥር ሠራ። እስከ ዖፌ​ልም አዞ​ረ​በት፤ እጅ​ግም ከፍ አደ​ረ​ገው፤ በተ​መ​ሸ​ጉ​ትም በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ሁሉ የጭ​ፍራ አለ​ቆ​ችን አኖረ።</verse>
				<verse number="28">እን​ግ​ዶ​ች​ንም አማ​ል​ክ​ትና ጣዖ​ታ​ቱ​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አራቀ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ባለ​በት ተራራ ላይና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሠ​ራ​ቸ​ውን መሠ​ዊ​ያ​ዎች ሁሉ ወስዶ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ በስ​ተ​ውጭ ጣላ​ቸው።</verse>
				<verse number="29">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መሠ​ዊያ ደግሞ አደሰ፤ የደ​ኅ​ነ​ት​ንና የም​ስ​ጋ​ና​ንም መሥ​ዋ​ዕት ሠዋ​በት፤ የይ​ሁ​ዳም ሕዝብ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲ​ያ​መ​ልኩ አዘዘ።</verse>
				<verse number="30">ሕዝቡ ግን ከአ​ም​ላ​ካ​ቸው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈጽ​መው ርቀው ገና በኮ​ረ​ብ​ታ​ዎች ላይ ይሠዉ ነበር፥</verse>
				<verse number="31">የም​ና​ሴም የቀ​ሩት ነገ​ሮች፥ ወደ አም​ላ​ኩም የጸ​ለ​የው ጸሎት፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የነ​ገ​ሩት የነ​ቢ​ያት ቃል፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መጽ​ሐፍ ተጽ​ፈ​ዋል።</verse>
				<verse number="32">ደግ​ሞም ጸሎ​ቱን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰማው፥ ኀጢ​አ​ቱና መተ​ላ​ለፉ ሁሉ፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሳይ​መ​ለስ ኮረ​ብ​ታ​ውን የሠ​ራ​በት ዐፀ​ዱ​ንና የተ​ቀ​ረ​ጹ​ት​ንም ምስ​ሎች የተ​ከ​ለ​በት ስፍራ፥ እነሆ፥ በባለ ራእዩ የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፈ​ዋል።</verse>
				<verse number="33">ምና​ሴም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በቤ​ቱም አት​ክ​ልት ቦታ ቀበ​ሩት፤ ልጁም አሞጽ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።</verse>
				<verse number="34">አሞጽ መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ ሁለት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሁለት ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="35">አባ​ቱም ምናሴ እን​ዳ​ደ​ረገ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ፤ አሞ​ጽም አባቱ ምናሴ ለሠ​ራ​ቸው ለተ​ቀ​ረ​ጹት ምስ​ሎች ሁሉ ሠዋ፤ አመ​ለ​ካ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="36">አባ​ቱም ምናሴ ሰው​ነ​ቱን እን​ዳ​ዋ​ረደ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሰው​ነ​ቱን አላ​ዋ​ረ​ደም፤ ነገር ግን አሞጽ መተ​ላ​ለ​ፉን እጅግ አበዛ።</verse>
				<verse number="37">አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ተነ​ሡ​በት፤ በቤ​ቱም ገደ​ሉት።</verse>
				<verse number="38">የሀ​ገሩ ሕዝብ ግን በን​ጉሡ በአ​ሞጽ ላይ የተ​ነ​ሡ​ትን ሁሉ ገደሉ፤ የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ልጁን ኢዮ​ስ​ያ​ስን በእ​ርሱ ፋንታ አነ​ገሡ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="34">
				<verse number="1">ኢዮ​ስ​ያ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የስ​ም​ንት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሠላሳ አንድ ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="2">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት መን​ገድ ሄደ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላ​ለም።</verse>
				<verse number="3">በነ​ገ​ሠም በስ​ም​ን​ተ​ኛው ዓመት ገና ብላ​ቴና ሳለ የአ​ባ​ቱን የዳ​ዊ​ትን አም​ላክ ይፈ​ልግ ጀመረ፤ በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ይሁ​ዳ​ንና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ከኮ​ረ​ብ​ታ​ውና ከዐ​ፀ​ዶቹ፥ ከተ​ቀ​ረ​ጹ​ትና ቀል​ጠው ከተ​ሠ​ሩት ምስ​ሎች ያነጻ ጀመር።</verse>
				<verse number="4">የበ​ዓ​ሊ​ም​ንም መሠ​ዊ​ያ​ዎች በፊቱ አፈ​ረሰ፤ በላ​ዩም የነ​በ​ሩ​ትን ኮረ​ብ​ታ​ዎ​ችን ዐፀ​ዶ​ቹ​ንም ቈረጠ፤ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ት​ንና ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም ምስ​ሎች ሰባ​በረ፤ አደ​ቀ​ቃ​ቸ​ውም፤ ይሠ​ዉ​ላ​ቸው በነ​በ​ሩት ሰዎች መቃ​ብ​ርም ላይ በተ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="5">የካ​ህ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም አጥ​ንት በመ​ሠ​ዊ​ያ​ቸው ላይ አቃ​ጠለ። ይሁ​ዳ​ንና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም አነጻ።</verse>
				<verse number="6">የም​ና​ሴ​ንና የኤ​ፍ​ሬ​ም​ንም፥ የስ​ም​ዖ​ንና የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ከተ​ሞች፥ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ያለ​ውን ቦታ እን​ዲሁ አነጻ።</verse>
				<verse number="7">መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አፈ​ረሰ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ቹ​ንና የተ​ቀ​ረ​ጹ​ትን ምስ​ሎ​ችም አደ​ቀቀ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሀገር ሁሉ የኮ​ረ​ብ​ታ​ዎ​ችን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ች​አ​ጠፋ። ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="8">በነ​ገ​ሠም በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመት ምድ​ሪ​ቱ​ንና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ካነጻ በኋላ፥ የሴ​ልያ ልጅ ሳፋን፥ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም አለቃ መዕ​ሴያ፥ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ ኢዮ​አክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የአ​ም​ላ​ኩን ቤት ይጠ​ግኑ ዘንድ ሰደ​ዳ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ወደ ታላ​ቁም ካህን ወደ ኬል​ቅ​ያስ መጡ፤ ሌዋ​ው​ያ​ኑም በረ​ኞች ከም​ና​ሴና ከኤ​ፍ​ሬም፥ ከአ​ለ​ቆ​ችም፥ ከቀ​ረ​ውም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ ከይ​ሁ​ዳና ከብ​ን​ያም ሁሉ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ከሚ​ኖ​ሩት የሰ​በ​ሰ​ቡ​ትን፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የቀ​ረ​በ​ውን ገን​ዘብ ሰጡት።</verse>
				<verse number="10">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት በሚ​ሠ​ሩት ላይ ለተ​ሾ​ሙት ሰጡ፤ እነ​ር​ሱም ይጠ​ግ​ኑና ያድሱ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለሚ​ሠሩ ሠራ​ተ​ኞች ሰጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ላፈ​ረ​ሱት ቤት ሰረ​ገ​ሎች ያደ​ርጉ ዘንድ፥ ለማ​ጋ​ጠ​ሚ​ያም እን​ጨት፥ የተ​ጠ​ረ​በ​ው​ንም ድን​ጋይ ይገዙ ዘንድ ለአ​ና​ጢ​ዎ​ችና ለጠ​ራ​ቢ​ዎች ሰጡ።</verse>
				<verse number="12">ሰዎ​ቹም ሥራ​ውን በመ​ታ​መን አደ​ረጉ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ የተ​ሾ​ሙት፥ ሥራ​ው​ንም የሚ​ያ​ሠ​ሩት ሌዋ​ው​ያን ከሜ​ራሪ ልጆች ይኤ​ትና አብ​ድ​ያስ፥ ከቀ​ዓ​ትም ልጆች ዘካ​ር​ያ​ስና ሜሱ​ላም ነበሩ። ከሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ወገን በዜማ ዕቃ ዐዋ​ቂ​ዎች፥ የነ​በሩ ሁሉ፥</verse>
				<verse number="13">በተ​ሸ​ካ​ሚ​ዎ​ችና ልዩ ልዩ ሥራ በሚ​ሠሩ ላይ ተሾ​መው ነበር፤ ጸሓ​ፊ​ዎ​ቹና አለ​ቆ​ቹም በረ​ኞ​ቹም ከሌ​ዋ​ው​ያን ወገን ነበሩ።</verse>
				<verse number="14">ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የቀ​ረ​በ​ውን ገን​ዘብ ባመጡ ጊዜ ካህኑ ኬል​ቅ​ያስ በሙሴ እጅ የተ​ሰ​ጠ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ መጽ​ሐፍ አገኘ።</verse>
				<verse number="15">ኬል​ቅ​ያ​ስም ጸሓ​ፊ​ውን ሳፋ​ንን፥ “የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አግ​ኝ​ቼ​አ​ለሁ” ብሎ ነገ​ረው። ኬል​ቅ​ያ​ስም መጽ​ሐ​ፉን ለሳ​ፋን ሰጠው።</verse>
				<verse number="16">ሳፋ​ንም መጽ​ሐ​ፉን ወደ ንጉሡ አመጣ፤ ለን​ጉ​ሡም ዳግ​መኛ እን​ዲህ አለው፥ “ወር​ቁ​ንና ብሩን፥ መባ​ው​ንም ሁሉ የቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ለሚ​ሠሩ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በእ​ጃ​ቸው ሰጧ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የተ​ገ​ኘ​ውን ገን​ዘብ አፈ​ሰሱ፤ በሥ​ራው ላይ ለተ​ሾ​ሙ​ትና ለሠ​ራ​ተ​ኞ​ቹም በእ​ጃ​ቸው ሰጡ።”</verse>
				<verse number="18">ጸሓ​ፊ​ውም ሳፋን ለን​ጉሡ፥ “ካህኑ ኬል​ቅ​ያስ መጽ​ሐፍ ሰጠኝ” ብሎ ነገ​ረው። ሳፋ​ንም በን​ጉሡ ፊት አነ​በ​በው።</verse>
				<verse number="19">ንጉ​ሡም የሕ​ጉን ቃል በሰማ ጊዜ ልብ​ሱን ቀደደ።</verse>
				<verse number="20">ንጉ​ሡም ኬል​ቅ​ያ​ስን፥ የሳ​ፋ​ን​ንም ልጅ አኪ​ቃ​ምን፥ የሚ​ክ​ያ​ስ​ንም ልጅ አብ​ዶ​ንን፥ ጸሓ​ፊ​ው​ንም ሳፋ​ንን፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ብላ​ቴና ዔሴ​ኢ​ያን፦</verse>
				<verse number="21">“በዚህ መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ ያደ​ርጉ ዘንድ አባ​ቶ​ቻ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስላ​ል​ጠ​በቁ፥ በላ​ያ​ችን የነ​ደደ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ እጅግ ነውና ሄዳ​ችሁ ስለ ተገ​ኘው የመ​ጽ​ሐፍ ቃል ስለ​እኔ፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ስለ​ቀ​ሩ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠይቁ” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">ኬል​ቅ​ያ​ስና እነ​ዚያ ንጉሡ ያዘ​ዛ​ቸው ወደ ልብስ ጠባ​ቂው ወደ ሐስራ ልጅ ወደ ቴቁዋ ልጅ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢ​ይቱ ወደ ሕል​ዳና ሄዱ፤ እር​ስ​ዋም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በከ​ተ​ማ​ዪቱ በሁ​ለ​ተ​ኛው ክፍል ተቀ​ምጣ ነበር፤ ይህ​ንም ነገር ነገ​ሩ​አት።</verse>
				<verse number="23">እር​ስ​ዋም አለ​ቻ​ቸው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ እኔ ለላ​ካ​ችሁ ሰው እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦</verse>
				<verse number="24">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህ ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ በይ​ሁዳ ንጉሥ ፊት በተ​ነ​በ​በው መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፉ​ትን ቃላት ሁሉ፥ ማለት ክፉ ነገ​ርን አመ​ጣ​ለሁ፥</verse>
				<verse number="25">በእ​ጃ​ቸው ሥራ ሁሉ ሊያ​ስ​ቈ​ጡኝ ትተ​ው​ኛ​ልና፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት አጥ​ነ​ዋ​ልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነ​ድ​ዳል፤ አይ​ጠ​ፋ​ምም።</verse>
				<verse number="26">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመ​ጠ​የቅ ለላ​ካ​ችሁ ለይ​ሁዳ ንጉሥ እን​ዲህ በሉት፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ስለ ሰማ​ኸው ቃል ልብህ ደን​ግ​ጦ​አ​ልና፥</verse>
				<verse number="27">በፊ​ቴም ራስ​ህን አዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ በዚ​ህም ስፍራ በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ ቃሌን በሰ​ማህ ጊዜ ራስ​ህን አዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ ልብ​ስ​ህ​ንም ቀድ​ደህ በፊቴ አል​ቅ​ሰ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="28">እነሆ፥ ወደ አባ​ቶ​ችህ እሰ​በ​ስ​ብ​ሃ​ለሁ፤ በሰ​ላ​ምም ወደ መቃ​ብ​ርህ ትሰ​በ​ሰ​ባ​ለህ፤ በዚ​ህም ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ የማ​መ​ጣ​ውን ክፉ ነገር ሁሉ ዐይ​ኖ​ችህ አያ​ዩም” ያለ​ቻ​ቸ​ው​ንም ነገር ለን​ጉሡ አስ​ረ​ዱት።</verse>
				<verse number="29">ንጉ​ሡም ላከ፤ የይ​ሁ​ዳ​ንና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ሰበ​ሰበ።</verse>
				<verse number="30">ንጉ​ሡም፥ የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ሁሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ኖ​ሩና ካህ​ናቱ፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ ከታ​ናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወጡ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የተ​ገ​ኘ​ውን የቃል ኪዳ​ኑን መጽ​ሐፍ ቃል ሁሉ በጆ​ሮ​አ​ቸው አነ​በበ።</verse>
				<verse number="31">ንጉ​ሡም በዐ​ምዱ ቆሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተከ​ትሎ እን​ዲ​ሄድ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንና ምስ​ክ​ሩን፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም በፍ​ጹም ልቡና በፍ​ጹም ነፍሱ እን​ዲ​ጠ​ብቅ፥ በዚ​ህም መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን የቃል ኪዳን ቃል እን​ዲ​ያ​ደ​ርግ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቃል ኪዳን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="32">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በብ​ን​ያ​ምም ሀገር የተ​ገ​ኙ​ትን ሁሉ በዚህ ነገር አማለ። በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ኖሩ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ቃል ኪዳን አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="33">ኢዮ​ስ​ያ​ስም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ምድር ሁሉ ርኩ​ሱን ሁሉ አስ​ወ​ገደ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የተ​ገ​ኙ​ትን ሁሉ አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲ​ያ​መ​ልኩ አደ​ረገ። በዘ​መኑ ሁሉ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ከ​ተል አል​ራ​ቁም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="35">
				<verse number="1">ኢዮ​ስ​ያ​ስም ለአ​ም​ላኩ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ፋሲካ አደ​ረገ፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ አረዱ።</verse>
				<verse number="2">ካህ​ና​ቱ​ንም በየ​ሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው አቆመ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ አጸ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="3">በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ መሥ​ራት የሚ​ች​ሉ​ትን ሌዋ​ው​ያን ራሳ​ቸ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲ​ያ​ነ​ጹና ቅድ​ስ​ቲ​ቱ​ንም ታቦት የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የዳ​ዊት ልጅ ሰሎ​ሞን በሠ​ራው ቤት ውስጥ እን​ዲ​ያ​ኖሩ አዘ​ዛ​ቸው። ንጉ​ሡም ኢዮ​ስ​ያስ አለ፥ “በት​ከ​ሻ​ችሁ የም​ት​ሸ​ከ​ሙት አን​ዳች ነገር አይ​ኑር፤ አሁ​ንም አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ሕዝ​ቡን እስ​ራ​ኤ​ልን አገ​ል​ግሉ፤</verse>
				<verse number="4">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዳዊት እንደ አዘዘ፥ ልጁም ሰሎ​ሞን እንደ አዘዘ በየ​ሰ​ሞ​ና​ች​ሁና በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ቤቶች ተዘ​ጋጁ፤</verse>
				<verse number="5">እንደ ሕዝ​ቡም ልጆች እንደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ በየ​አ​ባ​ቶች ቤቶች አከ​ፋ​ፈል በመ​ቅ​ደሱ ቁሙ፤ እን​ዲ​ሁም ለሌ​ዋ​ው​ያን በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት አከ​ፋ​ፈል ይሁን፤</verse>
				<verse number="6">የፋ​ሲ​ካ​ው​ንም በግ እረዱ፤ እና​ን​ተም ተቀ​ደሱ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሙሴ እጅ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ታደ​ርጉ ዘንድ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ አዘ​ጋጁ።”</verse>
				<verse number="7">ኢዮ​ስ​ያ​ስም ለፋ​ሲ​ካው መሥ​ዋ​ዕት እን​ዲ​ሆን በዚያ ለነ​በ​ሩት ለሕ​ዝቡ ልጆች ከመ​ን​ጋው ሠላሳ ሺህ የበ​ግና የፍ​የል ጠቦ​ቶች፥ ሦስት ሺህም ወይ​ፈ​ኖች ሰጣ​ቸው፤ እነ​ዚ​ህም ከን​ጉሡ ሀብት ነበሩ።</verse>
				<verse number="8">አለ​ቆ​ቹም ለሕ​ዝ​ቡና ለካ​ህ​ናቱ፥ ለሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ሰጡ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አለ​ቆች፥ ኬል​ቅ​ያስ፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ኢዮ​ሔል፥ ለፋ​ሲ​ካው መሥ​ዋ​ዕት እን​ዲ​ሆን ሁለት ሺህ ስድ​ስት መቶ በጎ​ች​ንና ፍየ​ሎ​ችን፥ ሦስት መቶም በሬ​ዎ​ችን ለካ​ህ​ናቱ ሰጡ።</verse>
				<verse number="9">የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም አለ​ቆች ኮኒ​ን​ያስ በን​ያ​ስም፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም ሰማ​ዕ​ያ​ስና ናት​ና​ኤል፥ ሰብ​ን​ያስ፥ ኢዮ​ሄል፥ ኢዮ​ዛ​ብድ ለፋ​ሲ​ካው መሥ​ዋ​ዕት እን​ዲ​ሆን አም​ስት ሺህ በጎ​ችን፥ አም​ስት መቶም በሬ​ዎ​ችን ለሌ​ዋ​ው​ያን ሰጡ።</verse>
				<verse number="10">አገ​ል​ግ​ሎ​ቱም ተዘ​ጋጀ፤ ካህ​ና​ቱም በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸው፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸው እንደ ንጉሡ ትእ​ዛዝ ቆሙ።</verse>
				<verse number="11">የፋ​ሲ​ካ​ው​ንም በግ አረዱ፤ ካህ​ና​ቱም ከእ​ጃ​ቸው የተ​ቀ​በ​ሉ​ትን ደም ረጩ፤ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ቍር​በ​ቱን ገፈፉ።</verse>
				<verse number="12">በሙ​ሴም መጽ​ሐፍ እንደ ተጻፈ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ርቡ ዘንድ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች እንደ ክፍ​ላ​ቸው ለሕ​ዝቡ ልጆች እን​ዲ​ሰጡ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ለዩ። እን​ዲ​ሁም በበ​ሬ​ዎቹ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="13">የፋ​ሲ​ካ​ው​ንም በግ እንደ ሙሴ ሥር​ዐት በእ​ሳት ጠበሱ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ቍር​ባን በም​ን​ቸ​ትና በሰ​ታቴ፥ በድ​ስ​ትም ቀቀሉ፤ ተከ​ና​ወ​ነ​ላ​ቸ​ውም፤ ለሕ​ዝ​ቡም ልጆች ሁሉ በፍ​ጥ​ነት አደ​ረሱ።</verse>
				<verse number="14">ከዚ​ያም በኋላ ለራ​ሳ​ቸ​ውና ከእ​ነ​ርሱ ጋር ላሉ ለካ​ህ​ናቱ አዘ​ጋጁ፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ስቡን ለማ​ቅ​ረብ እስከ ሌሊት ድረስ ይሠሩ ነበ​ርና ስለ​ዚህ ሌዋ​ው​ያን ለራ​ሳ​ቸ​ውና ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ለአ​ሮን ልጆች ለካ​ህ​ናቱ አዘ​ጋጁ።</verse>
				<verse number="15">የአ​ሳ​ፍም ልጆች መዘ​ም​ራን እንደ ዳዊት፥ እንደ አሳ​ፍም፥ እንደ ኤማ​ንም የን​ጉ​ሡም ባለ ራእይ እንደ ነበ​ረው እንደ ኤዶ​ትም ትእ​ዛዝ በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸው ነበሩ፤ በረ​ኞ​ቹም በሮ​ቹን ሁሉ ይጠ​ብቁ ነበር፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ሌዋ​ው​ያን ያዘ​ጋ​ጁ​ላ​ቸው ነበ​ርና ከአ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ይርቁ ዘንድ አያ​ስ​ፈ​ል​ጋ​ቸ​ውም ነበር።</verse>
				<verse number="16">እንደ ንጉ​ሡም እንደ ኢዮ​ስ​ያስ ትእ​ዛዝ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ላይ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርቡ ዘንድ፥ ፋሲ​ካ​ው​ንም ያደ​ርጉ ዘንድ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ በዚያ ቀን ተዘ​ጋጀ።</verse>
				<verse number="17">የተ​ገ​ኙ​ትም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በዚያ ቀን ፋሲ​ካ​ውን፥ ሰባት ቀንም የቂ​ጣ​ውን በዓል አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="18">ከነ​ቢ​ዩም ከሳ​ሙ​ኤል ዘመን ጀምሮ እን​ደ​ዚህ ያለ ፋሲካ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ከቶ አል​ተ​ደ​ረ​ገም፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ኢዮ​ስ​ያ​ስና ካህ​ናቱ፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ በዚ​ያም የተ​ገኙ የይ​ሁ​ዳና የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ኖ​ሩት እን​ዳ​ደ​ረ​ጉት ያለ ፋሲካ ያደ​ረገ የለም።</verse>
				<verse number="19">ይህም ፋሲካ ኢዮ​ስ​ያስ በነ​ገሠ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመት ተደ​ረገ። ‘ሀ’ ንጉሡ ኢዮ​ስ​ያስ ካህኑ ኬል​ቅ​ያስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ባገ​ኘው መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፉ​ትን ቃላት ሁሉ ለመ​ጠ​በቅ አስ​ማ​ተ​ኞ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን፥ ሟር​ተ​ኞ​ች​ንና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ምድ​ርና በይ​ሁዳ የሚ​ገ​ኙ​ትን ምስ​ሎ​ችና ቃሪ​ያ​ሲም የተ​ባሉ ጣዖ​ታ​ትን በእ​ሳት አቃ​ጠለ። ‘ለ’ እንደ ሙሴ ሕግ ሁሉ በፍ​ጹም ልቡ፥ በፍ​ጹም ነፍሱ፥ በፍ​ጹም ኀይሉ ከእ​ርሱ በፊት ከነ​በ​ሩት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ለሰ የሚ​መ​ስ​ለው ሰው አል​ነ​በ​ረም። ከእ​ር​ሱም በኋላ የሚ​መ​ስ​ለው አል​ተ​ነ​ሣም። ‘ሐ’ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጉሥ ምናሴ በይ​ሁዳ ላይ በአ​ደ​ረ​ገ​ውና በአ​ነ​ሣ​ሣው ጥፋት ሁሉ ከአ​ስ​ከ​ተ​ለው ታላቅ ቍጣ አል​ተ​መ​ለ​ሰም። ‘መ’ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “እስ​ራ​ኤ​ልን እን​ዳ​ራ​ቅሁ ይሁ​ዳን ከፊቴ አር​ቃ​ለሁ። የመ​ረ​ጥ​ኋ​ት​ንም ከተማ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንና ስሜ በዚያ ይጠ​ራ​በ​ታል ያል​ሁ​ትን ቤት እጥ​ላ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="20">ከዚ​ህም ሁሉ በኋላ፥ ኢዮ​ስ​ያ​ስም ቤተ መቅ​ደ​ሱን ካሰ​ናዳ በኋላ፥ የግ​ብጽ ንጉሥ ፈር​ዖን ኒካዑ በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ይዋጋ ዘንድ ወጣ፤ ኢዮ​ስ​ያ​ስም ሊጋ​ጠ​መው ወጣ።</verse>
				<verse number="21">እር​ሱም፥ “የይ​ሁዳ ንጉሥ ሆይ፥ ከአ​ንተ ጋር ምን አለኝ? በም​ዋ​ጋ​በት በሌላ ቤት ላይ ነው እንጂ በአ​ንተ ላይ ዛሬ አል​መ​ጣ​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ድ​ቸ​ኩል አዝ​ዞ​ኛል፤ ከእኔ ጋር ያለው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋህ ተጠ​ን​ቀቅ” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ​በት።</verse>
				<verse number="22">ኢዮ​ስ​ያስ ግን ይዋ​ጋው ዘንድ ተጽ​ናና እንጂ ፊቱን ከእ​ርሱ አል​መ​ለ​ሰም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አፍ የተ​ነ​ገ​ረ​ውን የኒ​ካ​ዑን ቃል አል​ሰ​ማም፤ በመ​ጊ​ዶ​ንም ሸለቆ ይዋጋ ዘንድ መጣ።</verse>
				<verse number="23">ቀስ​ተ​ኞ​ቹም ንጉ​ሡን ኢዮ​ስ​ያ​ስን ወጉት፤ ንጉ​ሡም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “እጅግ ቈስ​ያ​ለ​ሁና ከሰ​ልፉ ውስጥ አው​ጡኝ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">ብላ​ቴ​ኖ​ቹም ከሰ​ረ​ገ​ላው አው​ር​ደው ለእ​ርሱ በነ​በ​ረው በሁ​ለ​ተ​ኛው ሰረ​ገላ ውስጥ አስ​ቀ​መ​ጡት፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አመ​ጡት፤ እር​ሱም በዚያ ሞተ፤ በአ​ባ​ቶ​ቹም መቃ​ብር ተቀ​በረ፤ ይሁ​ዳና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሁሉ ለኢ​ዮ​ስ​ያስ አለ​ቀሱ።</verse>
				<verse number="25">ኤር​ም​ያ​ስም ለን​ጉሡ ለኢ​ዮ​ስ​ያስ የል​ቅሶ ግጥም ገጠ​መ​ለት፤ እስከ ዛሬም ድረስ ወን​ዶ​ችና ሴቶች መዘ​ም​ራን ሁሉ በል​ቅሶ ግጥ​ማ​ቸው ስለ ኢዮ​ስ​ያስ ይና​ገሩ ነበር፤ ይህም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዘንድ ወግ ሆኖ በል​ቅሶ ግጥም ተጽ​ፎ​አል።</verse>
				<verse number="26">የቀ​ሩ​ትም የኢ​ዮ​ስ​ያስ ነገ​ሮች፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ እንደ ተጻፈ ያደ​ረ​ገው ቸር​ነት፥</verse>
				<verse number="27">የፊ​ተ​ኛ​ውና የኋ​ለ​ኛ​ውም ነገሩ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት መጽ​ሐፍ ተጽ​ፈ​ዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="36">
				<verse number="1">የሀ​ገ​ሩም ሰዎች የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስን ልጅ ኢዮ​አ​ክ​ስን ወስ​ደው በአ​ባቱ ፋንታ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አነ​ገ​ሡት።</verse>
				<verse number="2">ኢዮ​አ​ክ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ ሦስት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሦስት ወር ነገሠ። ‘ሀ’ የእ​ና​ቱም ስም ከሎ​ቤና የኤ​ር​ም​ያስ ልጅ አሚ​ጣል ነበ​ረች። ‘ለ’ አባ​ቶቹ እንደ ሠሩት ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ሥራን ሠራ። በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እን​ዳ​ይ​ነ​ግሥ በኤ​ማት ምድር በዴ​ብ​ላታ ፈር​ዖን ኒካዑ ማርኮ አሰ​ረው።</verse>
				<verse number="3">ንጉ​ሡም ወደ ግብፅ ወሰ​ደው፤ በሀ​ገ​ሩም ላይ መቶ መክ​ሊት ብርና አንድ መክ​ሊት ወርቅ ግብር ጣለ​በት።</verse>
				<verse number="4">የግ​ብ​ፅም ንጉሥ ፈር​ዖን ኒካዑ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስን ልጅ ኤል​ያ​ቄ​ምን በአ​ባቱ ፋንታ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ አነ​ገሠ፤ ስሙ​ንም ኢዮ​አ​ቄም ብሎ ለወጠ፤ ፈር​ዖን ኒካ​ዑም ወን​ድ​ሙን ኢዮ​አ​ክ​ስን ይዞ ወደ ግብፅ ወሰ​ደው። በዚ​ያም ሞተ። ‘ሀ’ ወር​ቅ​ንና ብርን ለፈ​ር​ዖን ሰጠ። በዚ​ያን ጊዜም ምድር በፈ​ር​ዖን ትእ​ዛዝ ብር መገ​በ​ሯን ጀመ​ረች። ‘ለ’ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም እን​ደ​ሚ​ች​ለው ለፈ​ር​ዖን ኒካዑ እን​ዲ​ገ​ብር ከሀ​ገ​ሪቱ ሕዝብ ወር​ቅ​ንና ብርን ጠየቀ።</verse>
				<verse number="5">ኢዮ​አ​ቄ​ምም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አም​ስት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ዘካራ የም​ት​ባል የኔ​ሬ​ያሳ ልጅ የራማ ሴት ነበ​ረች፤ አባ​ቶ​ቹም እን​ዳ​ደ​ረጉ በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ። ‘ሀ’ በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወደ​ዚያ ሀገር መጣና ሦስት ዓመት ተገ​ዛ​ለት። ከእ​ር​ሱም ከዳ። ‘ለ’ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ን​ንና የሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንን፥ የሞ​ዓ​ባ​ው​ያ​ን​ንና የአ​ሞ​ና​ው​ያ​ንን ልጆ​ችና የሰ​ማ​ር​ያን አደጋ ጣዮች ላከ​በት፤ ከዚ​ህም በኋላ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ በነ​ቢ​ያት እንደ ተነ​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ራቁ። ‘ሐ’ ነገር ግን ምናሴ ስለ​ሠ​ራ​ቸው ኀጢ​አ​ቶ​ችና ኢዮ​አ​ቄም ስላ​ፈ​ሰ​ሰው ንጹሕ ደም፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም በን​ጹሕ ደም ስለ ሞላት ከፊቱ ይርቁ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በይ​ሁዳ ላይ ነበር። ‘መ’ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው አል​ፈ​ለ​ገም ነበር።</verse>
				<verse number="6">የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በእ​ርሱ ላይ ወጥቶ ወደ ባቢ​ሎን ይወ​ስ​ደው ዘንድ በሰ​ን​ሰ​ለት አሰ​ረው።</verse>
				<verse number="7">ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ዕቃ አያ​ሌ​ውን አው​ጥቶ ወደ ባቢ​ሎን ወሰደ፤ በባ​ቢ​ሎ​ንም በጣ​ዖቱ ቤት ውስጥ አኖ​ረው።</verse>
				<verse number="8">የቀ​ሩ​ትም የኢ​ዮ​አ​ቄም ነገ​ሮች፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ርኵ​ሰት፥ በእ​ር​ሱም የተ​ገ​ኘው ሁሉ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት መጽ​ሐፍ ተጽ​ፈ​ዋል፤ ኢዮ​አ​ቄ​ምም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ፤ ከአ​ባ​ቶ​ቹም ጋር በጋ​ኖ​ዛን ከተማ ተቀ​በረ። ልጁም ኢኮ​ን​ያን ከእ​ርሱ ቀጥሎ ነገሠ።</verse>
				<verse number="9">ኢኮ​ን​ያ​ንም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የዐ​ሥራ ስም​ንት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሦስት ወር ከዐ​ሥር ቀን ነገሠ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="10">ዓመ​ቱም ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ልኮ ወደ ባቢ​ሎን ወሰ​ደው፤ የከ​በ​ረ​ው​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ዕቃ ከእ​ርሱ ጋር አስ​ወ​ሰደ፤ የአ​ባ​ቱን የኢ​ዮ​አ​ቄ​ምን ወን​ድም ሴዴ​ቅ​ያ​ስን በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ አነ​ገሠ።</verse>
				<verse number="11">ሴዴ​ቅ​ያ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አንድ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ።</verse>
				<verse number="12">በአ​ም​ላ​ኩም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ፤ ከነ​ቢዩ ከኤ​ር​ም​ያስ ፊት፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል የተ​ነሣ አላ​ፈ​ረም።</verse>
				<verse number="13">ደግ​ሞም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም አም​ሎት በነ​በ​ረው በን​ጉሡ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ላይ ዐመፀ፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ይ​መ​ለስ አን​ገ​ቱን አደ​ነ​ደነ፤ ልቡ​ንም አጠ​ነ​ከረ።</verse>
				<verse number="14">የይ​ሁ​ዳም ታላ​ላቅ ሰዎች ካህ​ና​ቱና የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ በአ​ሕ​ዛብ ርኵ​ሰት ሁሉ መተ​ላ​ለ​ፍን አበዙ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት አረ​ከሱ።</verse>
				<verse number="15">የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝ​ቡና ለማ​ደ​ሪ​ያው ስላ​ዘነ ማለዳ ተነ​ሥቶ በነ​ቢ​ያቱ እጅ ወደ እነ​ርሱ ይልክ ነበር።</verse>
				<verse number="16">እነ​ርሱ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በሕ​ዝቡ ላይ እስ​ኪ​ወጣ ድረስ፥ ፈው​ስም እስ​ከ​ማ​ይ​ገ​ኝ​ላ​ቸው ድረስ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​እ​ክ​ተ​ኞች ይሳ​ለቁ፥ ቃሉ​ንም ያቃ​ልሉ፥ በነ​ቢ​ያ​ቱም ላይ ያፌዙ ነበር።</verse>
				<verse number="17">ስለ​ዚ​ህም የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ንጉሥ አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ እር​ሱም ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን በቤተ መቅ​ደሱ ውስጥ በሰ​ይፍ ገደ​ላ​ቸው፤ለን​ጉ​ሣ​ቸው ለሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስም አል​ራ​ራ​ለ​ትም፤ ደና​ግ​ሉ​ንም አል​ማ​ረም፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ወሰ​ዳ​ቸው፤ ሁሉ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ አሳ​ልፎ ሰጠው።</verse>
				<verse number="18">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ታላ​ቁ​ንና ታና​ሹን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት መዝ​ገብ፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤት መዝ​ገብ፥ የአ​ለ​ቆ​ቹ​ንም ቤት መዝ​ገብ፥ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን ወሰደ።</verse>
				<verse number="19">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤተ መቅ​ደስ አቃ​ጠለ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቅጥር አፈ​ረሰ፤ አዳ​ራ​ሾ​ች​ዋ​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠለ፤ መል​ካ​ሙ​ንም ዕቃ​ዋን ሁሉ አጠፋ።</verse>
				<verse number="20">የተ​ረ​ፉ​ት​ንም ወደ ባቢ​ሎን ማረ​ካ​ቸው፤ የሜ​ዶ​ንም ንጉሥ እስ​ኪ​ነ​ግሥ ድረስ ለን​ጉ​ሡና ለል​ጆቹ ባሪ​ያ​ዎች ሆኑ፤</verse>
				<verse number="21">በኤ​ር​ም​ያስ አፍ የተ​ነ​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እን​ዲ​ፈ​ጸም፥ ምድ​ሪቱ ሰን​በ​ትን በማ​ድ​ረ​ግዋ እስ​ክ​ታ​ርፍ ድረስ፥ በተ​ፈ​ታ​ች​በ​ትም ዘመን ሁሉ፥ ሰባ ዓመት እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ፥ ሰን​በ​ትን አገ​ኘች።</verse>
				<verse number="22">በኤ​ር​ም​ያ​ስም አፍ የተ​ና​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ በፋ​ርስ ንጉሥ በቂ​ሮስ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዓመት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፋ​ር​ስን ንጉሥ የቂ​ሮ​ስን መን​ፈስ አስ​ነሣ፤ በመ​ን​ግ​ሥ​ቱም ሁሉ አዋጅ ይነ​ገር ዘንድ በጽ​ሕ​ፈት እን​ዲህ ሲል አዘዘ፤</verse>
				<verse number="23">“የፋ​ርስ ንጉሥ ቂሮስ እን​ዲህ ይላል፦ የሰ​ማይ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ርን መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ሰጥ​ቶ​ኛል፤ እር​ሱም በይ​ሁዳ ባለ​ችው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቤትን እሠ​ራ​ለት ዘንድ አዝ​ዞ​ኛል፤ ከሕ​ዝ​ቡም ሁሉ በእ​ና​ንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ይሁን፤ እር​ሱም ይውጣ።”</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="15">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በኤ​ር​ም​ያስ አፍ የተ​ና​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ በፋ​ርስ ንጉሥ በቂ​ሮስ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዓመት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፋ​ር​ስን ንጉሥ የቂ​ሮ​ስን መን​ፈስ አስ​ነሣ፤ እር​ሱም በመ​ን​ግ​ሥቱ ሁሉ አዋጅ አስ​ነ​ገረ፤ ደግ​ሞም በጽ​ሕ​ፈት እን​ዲህ አለ፦</verse>
				<verse number="2">“የፋ​ርስ ንጉሥ ቂሮስ እን​ዲህ ይላል፦ የሰ​ማይ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ርን መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ሰጥ​ቶ​ኛል፤ በይ​ሁ​ዳም ባለ​ችው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቤትን እሠ​ራ​ለት ዘንድ እን​ዳ​ስብ አደ​ረ​ገኝ፤</verse>
				<verse number="3">ከሕ​ዝቡ ሁሉ በእ​ና​ንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አም​ላኩ ከእ​ርሱ ጋር ይሁን፤ እር​ሱም በይ​ሁዳ ወዳ​ለ​ችው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይውጣ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ለሚ​ኖ​ረው አም​ላክ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትን ይሥራ፤</verse>
				<verse number="4">በስ​ደት በሚ​ኖ​ር​ባ​ቸው ከተ​ሞች ሁሉ ለቀ​ረው ሰው ሁሉ የሀ​ገሩ ሰዎች በብ​ርና በወ​ርቅ፥ በዕ​ቃም፥ በእ​ን​ስ​ሳም ይር​ዱት፤ ይህም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላለው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ሌላ ይሁን።”</verse>
				<verse number="5">የይ​ሁ​ዳና የብ​ን​ያም የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆ​ችም፥ ካህ​ና​ቱም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለመ​ሥ​ራት ይወጡ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ሳ​ቸ​ውን ያነ​ሣ​ሣው ሁሉ ተነሡ።</verse>
				<verse number="6">በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ያሉ ሁሉ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ካቀ​ረ​ቡት ሁሉ ሌላ በብር ዕቃና በወ​ርቅ፥ በገ​ን​ዘ​ቦ​ችና በእ​ን​ስ​ሶች፥ በሌ​ላም ስጦታ ይረ​ዷ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="7">ንጉሡ ቂሮ​ስም ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወስዶ በአ​ም​ላኩ ቤት ያኖ​ራ​ቸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ መቅ​ደስ ዕቃ​ዎች አወጣ።</verse>
				<verse number="8">የፋ​ርስ ንጉሥ ቂሮ​ስም የመ​ዝ​ገብ ሐላፊ በነ​በ​ረው በሚ​ት​ሪ​ዳጡ እጅ አወ​ጣ​ቸው፤ ለይ​ሁ​ዳም መስ​ፍን ለሲ​ሳ​ብ​ሳር ቈጠ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ቍጥ​ራ​ቸ​ውም ይህ ነው፤ ሠላሳ የወ​ርቅ ሳሕ​ኖች፥ አንድ ሺህም የብር ሳሕ​ኖች፥ ሃያ ዘጠ​ኝም ቢላ​ዋ​ዎች፥ ሠላሳ የወ​ርቅ ዳካ​ዎች፥</verse>
				<verse number="10">አራት መቶ ዐሥ​ርም ሌላ ዓይ​ነት የብር ዳካ​ዎች፥ አንድ ሺህም ሌላ ዕቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="11">የወ​ር​ቁና የብሩ ዕቃ​ዎች ሁሉ አም​ስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ሁሉ ሲሳ​ብ​ሳር ከባ​ቢ​ሎን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ከተ​መ​ለሱ ምር​ኮ​ኞች ጋር ወሰደ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወደ ባቢ​ሎን ከማ​ረ​ካ​ቸው ምር​ኮ​ኞች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየ​ከ​ተ​ማ​ቸው የተ​መ​ለ​ሱት የሀ​ገር ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="2">ከዘ​ሩ​ባ​ቤል፥ ከኢ​ያሱ፥ ከነ​ህ​ምያ፥ ከሠ​ራያ፥ ከሮ​ሃ​ልያ፥ ከመ​ር​ዶ​ክ​ዮስ፥ ከበ​ላ​ሳን፥ ከመ​ሴ​ፋር፥ ከበ​ጎ​ዋይ፥ ከሬ​ሁም፥ ከበ​ዓና ጋር መጡ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤</verse>
				<verse number="3">የፋ​ሮስ ልጆች ሁለት ሺህ መቶ ሰባ ሁለት።</verse>
				<verse number="4">የሰ​ፋ​ጥ​ያስ ልጆች ሦስት መቶ ሰባ ሁለት።</verse>
				<verse number="5">የኤ​ራስ ልጆች ሰባት መቶ ሰባ አም​ስት።</verse>
				<verse number="6">ከያ​ሱ​ኤና ከዮ​አብ ልጆች የሆ​ኑት የፈ​ሐት ሞዓብ ልጆች ሁለት ሺህ ስም​ንት መቶ ዐሥራ ሁለት።</verse>
				<verse number="7">የኤ​ላም ልጆች ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት።</verse>
				<verse number="8">የዛ​ቱዕ ልጆች ዘጠኝ መቶ አርባ አም​ስት።</verse>
				<verse number="9">የዘ​ካይ ልጆች ሰባት መቶ ስድሳ።</verse>
				<verse number="10">የባኒ ልጆች ስድ​ስት መቶ አርባ ሁለት።</verse>
				<verse number="11">የቢ​ባይ ልጆች ስድ​ስት መቶ ሃያ ሦስት።</verse>
				<verse number="12">የዓ​ዝ​ጋድ ልጆች ሺህ ሁለት መቶ ሃያ ሁለት።</verse>
				<verse number="13">የአ​ዶ​ኒ​ቃም ልጆች ስድ​ስት መቶ ስድሳ ስድ​ስት።</verse>
				<verse number="14">የበ​ጕ​ዋይ ልጆች ሁለት ሺህ አምሳ ስድ​ስት።</verse>
				<verse number="15">የዓ​ዲን ልጆች አራት መቶ አምሳ አራት።</verse>
				<verse number="16">ከሕ​ዝ​ቅ​ያስ ወገን የአ​ጤር ልጆች ዘጠና ስም​ንት።</verse>
				<verse number="17">የቤ​ሳይ ልጆች ሦስት መቶ ሃያ ሦስት።</verse>
				<verse number="18">የዮራ ልጆች መቶ ዐሥራ ሁለት።</verse>
				<verse number="19">የሐ​ሱም ልጆች ሁለት መቶ ሃያ ሦስት።</verse>
				<verse number="20">የጋ​ቤር ልጆች ዘጠና አም​ስት።</verse>
				<verse number="21">የቤተ ልሔም ልጆች መቶ ሃያ ሦስት።</verse>
				<verse number="22">የነ​ጦፋ ልጆች አምሳ ስድ​ስት።</verse>
				<verse number="23">የዓ​ና​ቶት ልጆች መቶ ሃያ ስም​ንት።</verse>
				<verse number="24">የዓ​ዝ​ሞት ልጆች አርባ ሁለት።</verse>
				<verse number="25">የቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪ​ምና የቃ​ፌር፥ የብ​ኤ​ሮ​ትም ልጆች ሰባት መቶ አርባ ሦስት።</verse>
				<verse number="26">የራ​ማና የጋ​ባዕ ልጆች ስድ​ስት መቶ ሃያ አንድ።</verse>
				<verse number="27">የመ​ኪ​ማስ ሰዎች መቶ ሃያ ሁለት።</verse>
				<verse number="28">የቤ​ቴ​ልና የጋይ ሰዎች ሁለት መቶ ሃያ ሦስት።</verse>
				<verse number="29">የና​ባው ልጆች አምሳ ሁለት።</verse>
				<verse number="30">የመ​ጌ​ባስ ልጆች መቶ አምሳ ስድ​ስት።</verse>
				<verse number="31">የኤ​ላ​ማር ልጆች ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት።</verse>
				<verse number="32">የኤ​ላም ልጆች ሦስት መቶ ሃያ።</verse>
				<verse number="33">የሎድ፥ የሐ​ዲ​ድና የኦ​ኖም ልጆች ሰባት መቶ ሃያ አም​ስት።</verse>
				<verse number="34">የኢ​ያ​ሪኮ ልጆች ሦስት መቶ አርባ አም​ስት።</verse>
				<verse number="35">የሴ​ዓ​ናህ ልጆች ሦስት ሺህ ስድ​ስት መቶ ሠላሳ።</verse>
				<verse number="36">ካህ​ናቱ ከኢ​ያሱ ወገን የዮ​ዳኤ ልጆች ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት።</verse>
				<verse number="37">የኢ​ሜር ልጆች ሺህ አምሳ ሁለት።</verse>
				<verse number="38">የፋ​ስ​ኮር ልጆች ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት።</verse>
				<verse number="39">የኤ​ረም ልጆች ሺህ ዐሥራ ሰባት።</verse>
				<verse number="40">ሌዋ​ው​ያኑ፤ ከሁ​ድያ ልጆች ወገን የኢ​ዮ​ስ​ስና የቀ​ዳ​ም​ሔል ልጆች ሰባ አራት።</verse>
				<verse number="41">መዘ​ም​ራኑ የአ​ሳፍ ልጆች መቶ ሃያ ስም​ንት።</verse>
				<verse number="42">የበ​ረ​ኞች ልጆች፥ የሰ​ሎም ልጆች፥ የአ​ጤር ልጆች፥ የጤ​ል​ሞን ልጆች፥ የዓ​ቁብ ልጆች፥ የሐ​ጢጣ ልጆች፥ የሰ​በ​ዋይ ልጆች ሁሉ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ።</verse>
				<verse number="43">ናታ​ኒም፤ የሲሓ ልጆች፥ የሐ​ሡፊ ልጆች፥ የጠ​ብ​ዖት ልጆች፤</verse>
				<verse number="44">የቃ​ዴስ ልጆች፥ የሲ​ሔል ልጆች፥ የፋ​ዶን ልጆች፤</verse>
				<verse number="45">የል​ባና ልጆች፥ የአ​ጋባ ልጆች፥ የዓ​ቁብ ልጆች፥</verse>
				<verse number="46">የአ​ጋብ ልጆች፥ የሰ​ላሚ ልጆች፥ የሐ​ናን ልጆች፤</verse>
				<verse number="47">የጋ​ዱል ልጆች፥ የጋ​ሐር ልጆች፥ የራ​እያ ልጆች፤</verse>
				<verse number="48">የረ​አ​ሶን ልጆች፥ የኒ​ቆዳ ልጆች፥ የጋ​ሴም ልጆች፤</verse>
				<verse number="49">የዓ​ዝ​ያት ልጆች፥ የፋ​ሒስ ልጆች፥ የባሲ ልጆች፤</verse>
				<verse number="50">የአ​ሲና ልጆች፥ የም​ዑ​ና​ው​ያን ልጆች፥ የና​ፌ​ሶን ልጆች፤</verse>
				<verse number="51">የበ​ቅ​ቡቅ ልጆች፥ የሐ​ቁፋ ልጆች፥ የሐ​ር​ሑር ልጆች፤</verse>
				<verse number="52">የበ​ስ​ሎት ልጆች፥ የማ​ሁድ ልጆች፥ የአ​ሪስ ልጆች፤</verse>
				<verse number="53">የበ​ር​ቆስ ልጆች፥ የሲ​ሣራ ልጆች፥ የቴማ ልጆች፥</verse>
				<verse number="54">የን​ስያ ልጆች፥ የአ​ጡፋ ልጆች።</verse>
				<verse number="55">የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ልጆች፤ የሳጢ ልጆች፥ የሰ​ፌ​ርታ ልጆች፥ የፋ​ዱ​ርሓ ልጆች፤</verse>
				<verse number="56">የኢ​ያ​ሔል ልጆች፥ የደ​ር​ቆን ልጆች፥ የጌ​ዴል ልጆች፤</verse>
				<verse number="57">የሰ​ፋ​ጥ​ያስ ልጆች፥ የአ​ጤል ልጆች፥ የፎ​ኬ​ርት ልጆች፥ የሐ​ፂ​ባ​ይም ልጆች፥ የአሚ ልጆች።</verse>
				<verse number="58">እነ​ዚህ ናታ​ኒም ሁሉና የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ።</verse>
				<verse number="59">ከቲ​ል​ሜላ፥ ከቴ​ላ​ርሳ፥ ከክ​ሩብ፥ ከሐ​ዳን፥ ከኤ​ሜር የወጡ እነ​ዚህ ነበሩ፤ ነገር ግን የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ቤቶ​ችና ዘራ​ቸ​ውን ወይም ከእ​ስ​ራ​ኤል ወገን መሆ​ና​ቸ​ውን ያስ​ታ​ውቁ ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤</verse>
				<verse number="60">የዳ​ላያ ልጆች፥ የጦ​ብያ ልጆች፥ የኒ​ቆዳ ልጆች፥ ስድ​ስት መቶ አምሳ ሁለት ነበሩ።</verse>
				<verse number="61">ከካ​ህ​ና​ቱም ልጆች፤ የአ​ብያ ልጆች፥ የአ​ቆስ ልጆች፥ ከገ​ለ​ዓ​ዳ​ዊው ከቤ​ር​ዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ፥ በስ​ማ​ቸ​ውም የተ​ጠራ የቤ​ር​ዜሊ ልጆች።</verse>
				<verse number="62">እነ​ዚህ በት​ው​ልድ መጽ​ሐፍ ትው​ል​ዳ​ቸ​ውን ፈለጉ፤ ነገር ግን አል​ተ​ገ​ኘም፤ ከክ​ህ​ነ​ትም ተከ​ለ​ከሉ።</verse>
				<verse number="63">ሐቲ​ር​ሰ​ስ​ታም፥ “በኡ​ሪ​ምና በቱ​ሚም የሚ​ፈ​ርድ ካህን እስ​ኪ​ነሣ ድረስ ከቅ​ዱሰ ቅዱ​ሳኑ አት​በ​ሉም” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="64">ጉባ​ኤው ሁሉ አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ ነበሩ።</verse>
				<verse number="65">ይኸ​ውም ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ከነ​በሩ ከሎ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውና ከገ​ረ​ዶ​ቻ​ቸው ሌላ ሁለት መቶ ወን​ዶች መዘ​ም​ራ​ንና ሴቶች መዘ​ም​ራ​ትም ነበ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="66">ፈረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ሰባት መቶ ሠላሳ ስድ​ስት፥ በቅ​ሎ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ሁለት መቶ አርባ አም​ስት፥</verse>
				<verse number="67">ግመ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም አራት መቶ ሠላሳ አም​ስት፥ አህ​ዮ​ቻ​ቸ​ውም ስድ​ስት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ ነበሩ።</verse>
				<verse number="68">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወዳ​ለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በመጡ ጊዜ ከአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች አያ​ሌ​ዎች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በስ​ፍ​ራው ይሠ​ሩት ዘንድ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ሰጡ።</verse>
				<verse number="69">ስድሳ አንድ ሺህም የወ​ርቅ ዳሪክ፥ አም​ስት ሺህም ምናን ብር፥ አንድ መቶም የካ​ህ​ናት ልብስ እንደ ችሎ​ታ​ቸው ወደ ሥራው ቤተ መዛ​ግ​ብት አቀ​ረቡ።</verse>
				<verse number="70">ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ ከሕ​ዝ​ቡም አያ​ሌ​ዎች፥ መዘ​ም​ራ​ኑና በረ​ኞ​ቹም፥ ናታ​ኒ​ምም በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ተቀ​መጡ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ሰባ​ተ​ኛ​ውም ወር በደ​ረሰ ጊዜ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ሳሉ፥ ሕዝቡ እንደ አንድ ሰው ሆነው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="2">የኢ​ዮ​ሴ​ዴ​ቅም ልጅ ኢያሱ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም ካህ​ናቱ፥ የሰ​ላ​ት​ያ​ልም ልጅ ዘሩ​ባ​ቤል፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም ተነ​ሥ​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡ​በት ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ መሠ​ዊያ ሠሩ።</verse>
				<verse number="3">በሀ​ገ​ሩም ካሉት አሕ​ዛብ ፈር​ተው ነበ​ርና መሠ​ዊ​ያ​ውን በስ​ፍ​ራው ላይ አስ​ቀ​መ​ጡት፤ በጥ​ዋ​ትና በማ​ታም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቀ​ረ​ቡ​በት።</verse>
				<verse number="4">እንደ ተጻ​ፈ​ውም የዳስ በዓል አደ​ረጉ፤ እንደ ሥር​ዐ​ቱም ለየ​ዕ​ለቱ የተ​ገ​ባ​ውን የየ​ዕ​ለ​ቱን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በቍ​ጥር አቀ​ረቡ።</verse>
				<verse number="5">ከዚ​ያም በኋላ ዘወ​ትር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የመ​ባ​ቻ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት፥ የተ​ቀ​ደ​ሱ​ት​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ላት ሁሉ መሥ​ዋ​ዕት፥ ሰውም ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃድ የሰ​ጠ​ውን ቍር​ባን አቀ​ረቡ።</verse>
				<verse number="6">በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ማቅ​ረብ ጀመሩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ ግን ገና አል​ተ​መ​ሠ​ረ​ተም ነበር።</verse>
				<verse number="7">ለጠ​ራ​ቢ​ዎ​ችና ለአ​ና​ጢ​ዎ​ችም ብር ሰጡ፤ የፋ​ር​ስም ንጉሥ ቂሮስ እንደ ፈቀ​ደ​ላ​ቸው የዝ​ግባ ዛፍ ከሊ​ባ​ኖስ በባ​ሕር ወደ ኢዮጴ ያመጡ ዘንድ ለሲ​ዶ​ናና ለጢ​ሮስ ሰዎች መብ​ልና መጠጥ፥ ዘይ​ትም ሰጡ።</verse>
				<verse number="8">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወዳ​ለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በመጡ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር የሰ​ላ​ት​ያል ልጅ ዘሩ​ባ​ቤል፥ የኢ​ዮ​ሴ​ዴ​ቅም ልጅ ኢያሱ፥ የቀ​ሩ​ትም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን፥ ከም​ርኮ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​መ​ለ​ሱት ሁሉ ጀመሩ፤ ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሥራ እን​ዲ​ያ​ሠ​ሩት ሾሙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ኢያ​ሱም፥ ልጆ​ቹም ተሾሙ፤ ወን​ድ​ሞ​ቹም፥ የይ​ሁ​ዳም ልጆች ቀደ​ም​ያ​ልና ልጆቹ፥ የኢ​ን​ሐ​ዳ​ድም ልጆች፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ውና ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ሌዋ​ው​ያ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት የሚ​ሠ​ሩ​ትን ያሠሩ ዘንድ በአ​ን​ድ​ነት ቆሙ።</verse>
				<verse number="10">አና​ጢ​ዎ​ቹም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መቅ​ደስ ይሠሩ ዘንድ መሠ​ረት በጣሉ ጊዜ ካህ​ናቱ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ለብ​ሰው መለ​ከ​ቱን ይዘው፥ የአ​ሳ​ፍም ልጆች ሌዋ​ው​ያን ጸና​ጽል ይዘው እንደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ እንደ ዳዊት ሥር​ዐት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ ቆሙ።</verse>
				<verse number="11">ደግሞ፥ “ቸር ነውና፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና” እያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገ​ኑና እያ​ከ​በሩ እርስ በር​ሳ​ቸው ያስ​ተ​ዛ​ዝሉ ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በተ​መ​ሠ​ረተ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​ከ​በሩ በታ​ላቅ ድምፅ ዘመሩ።</verse>
				<verse number="12">የፊ​ተ​ኛ​ውን ቤት ያዩ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች የሆኑ ብዙ ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን፥ የአ​ባ​ቶ​ችም ቤቶች አለ​ቆች ግን ይህ መቅ​ደስ በፊ​ታ​ቸው በተ​መ​ሠ​ረተ ጊዜ በታ​ላቅ ድምፅ ያለ​ቅሱ ነበር፤ ብዙ ሰዎ​ችም እየ​ዘ​መሩ በደ​ስታ ይጮኹ ነበር፤</verse>
				<verse number="13">ደስ ብሎ​አ​ቸው የሚ​ጮ​ኹ​ትን ድምፅ ከሕ​ዝቡ ልቅሶ ድምፅ መለ​የት የሚ​ችል አል​ነ​በ​ረም፥ ሕዝቡ በታ​ላቅ ድምፅ ይጮኽ ነበ​ርና ድም​ፁም ከሩቅ ይሰማ ነበ​ርና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">የይ​ሁ​ዳና የብ​ን​ያ​ምም ጠላ​ቶች፥ የም​ር​ኮ​ኞቹ ልጆች ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ እን​ደ​ሚ​ሠሩ ሰሙ።</verse>
				<verse number="2">ወደ ዘሩ​ባ​ቤ​ልና ወደ አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆ​ችም ቀር​በው፥ “የአ​ሦር ንጉሥ አስ​ራ​ዶን ወደ​ዚህ ካመ​ጣን ቀን ጀምሮ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ እን​ሠ​ዋ​ለ​ንና፥ እንደ እና​ን​ተም እን​ፈ​ል​ገ​ዋ​ለ​ንና ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ሥራ” አሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ዘሩ​ባ​ቤ​ልና ኢያ​ሱም፥ የቀ​ሩ​ትም የእ​ስ​ራ​ኤል አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች፥ “የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ቤት መሥ​ራት ለእ​ኛና ለእ​ና​ንተ አይ​ደ​ለም፤ እኛ ራሳ​ችን ግን የፋ​ርስ ንጉሥ ቂሮስ እን​ዳ​ዘ​ዘን ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እን​ሠ​ራ​ለን” አሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ የይ​ሁ​ዳን ሕዝብ እጅግ ያዳ​ክሙ ነበር፤ እን​ዳ​ይ​ሠ​ሩም ከለ​ከ​ሉ​አ​ቸው፤</verse>
				<verse number="5">ምክ​ራ​ቸ​ው​ንም ያፈ​ርሱ ዘንድ በፋ​ርሱ ንጉሥ በቂ​ሮስ ዘመን ሁሉ እስከ ፋርስ ንጉሥ እስከ ዳር​ዮስ መን​ግ​ሥት ድረስ መካ​ሪ​ዎ​ችን ገዙ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">በአ​ሕ​ሳ​ዊ​ሮ​ስም መን​ግ​ሥት፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ቱም በመ​ጀ​መ​ሪያ ዘመን፥ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሚ​ኖ​ሩት ላይ ደብ​ዳቤ ጻፉ።</verse>
				<verse number="7">በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ ዘመን በሴ​ሌም፥ ሜት​ሪ​ዳጡ፥ ጣብ​ሄል፥ የቀ​ሩት ተባ​ባ​ሪ​ው​ቻ​ቸ​ውም ለፋ​ርስ ንጉሥ ለአ​ር​ተ​ሰ​ስታ ጻፉ፤ ደብ​ዳ​ቤ​ውም በሶ​ርያ ፊደ​ልና በሶ​ርያ ቋንቋ ተጽፎ ነበር።</verse>
				<verse number="8">አዛዡ ሬሁም፥ ጸሓ​ፊ​ውም ሲም​ሳይ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ለን​ጉሡ ለአ​ር​ተ​ሰ​ስታ አንድ የክስ ደብ​ዳቤ ጻፉ።</verse>
				<verse number="9">አዛዡ ሬሁም፥ ጸሓ​ፊ​ውም ሲም​ሳይ፥ የቀ​ሩ​ትም ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸው፥ ዲና​ው​ያን፥ አፈ​ር​ሳ​ት​ካ​ዋ​ያን፥ ጠር​ፈ​ላ​ው​ያን፥ አፈ​ር​ሳ​ው​ያን፥ አር​ካ​ው​ያን፥ ባቢ​ሎ​ና​ው​ያን፥ ሱስ​ና​ካ​ው​ያን፥ ዴሐ​ው​ያን፥ ኤላ​ማ​ው​ያን፥</verse>
				<verse number="10">ታላ​ቁና ኀይ​ለ​ኛው አስ​ና​ፍር ያፈ​ለ​ሳ​ቸው፥ በሰ​ማ​ር​ያና በወ​ንዝ ማዶ ያኖ​ራ​ቸው፥ የቀ​ሩ​ትም አሕ​ዛብ ደብ​ዳ​ቤ​ውን ጻፉ።</verse>
				<verse number="11">ለን​ጉሡ ለአ​ር​ተ​ሰ​ስታ የላ​ኩት የደ​ብ​ዳቤ ቃልም ይህ ነው፥ “በወ​ንዝ ማዶ ያሉት ሰዎች ባሪ​ያ​ዎ​ችህ፤</verse>
				<verse number="12">አሁ​ንም ከአ​ንተ ዘንድ የወጡ አይ​ሁድ ወደ እኛ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ መጡ ጌታ​ቸው ንጉሡ ይወቅ፤ ዐመ​ፀ​ኛ​ዪ​ቱ​ንና እጅ​ግም የከ​ፋ​ች​ቱን ከተማ ይሠ​ራሉ፤ ቅጥ​ር​ዋ​ንም ያድ​ሳሉ፤ መሠ​ረ​ቷ​ንም ጠገኑ።</verse>
				<verse number="13">አሁ​ንም ይህች ከተማ የተ​ሠ​ራች እንደ ሆነ፥ ቅጥ​ር​ዋም የታ​ደሰ እንደ ሆነ፥ ግብ​ርና ቀረጥ መጥ​ንም እን​ደ​ማ​ይ​ሰጡ፥ ንጉሡ ይወቅ፤ ይህም መን​ግ​ሥ​ትን ይጐ​ዳል።</verse>
				<verse number="14">ንጉ​ሡ​ንም ሲያ​ቃ​ል​ሉት ማየት አይ​ገ​ባ​ን​ምና ስለ​ዚህ ልከን ለን​ጉሡ አስ​ታ​ው​ቀ​ናል፤</verse>
				<verse number="15">በአ​ባ​ቶ​ችህ ታሪክ መጽ​ሐፍ ምር​መራ ይደ​ረግ፤ በዚ​ያም በታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ይህች ከተማ ዐመ​ፀኛ እንደ ሆነች፥ ነገ​ሥ​ታ​ት​ንና አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ንም እንደ ጎዳች፥ ከጥ​ን​ቱም የገ​ባ​ሮች ሽፍ​ት​ነት በእ​ር​ስዋ እንደ ተጀ​መረ ታገ​ኛ​ለህ፤ ታው​ቃ​ለ​ህም፤ ስለ​ዚ​ህም ይህች ከተማ ፈርሳ ነበር።</verse>
				<verse number="16">ይህ​ችም ከተማ የተ​ሠ​ራች እንደ ሆነ፥ ቅጥ​ር​ዋም የታ​ደሰ እንደ ሆነ፥ ሰላም እን​ደ​ማ​ይ​ኖ​ርህ ለን​ጉሡ እና​ስ​ታ​ው​ቃ​ለን።”</verse>
				<verse number="17">ንጉ​ሡም ለአ​ዛዡ ለሬ​ሁም፥ ለጸ​ሓ​ፊ​ውም ለሲ​ም​ሳይ፥ በሰ​ማ​ር​ያና በወ​ንዝ ማዶም ለተ​ቀ​መ​ጡ​ትና ለቀ​ሩት ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸው እን​ዲህ የሚ​ለ​ውን መልስ ላከ፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን።</verse>
				<verse number="18">አሁ​ንም ወደ እኛ የላ​ካ​ች​ሁት መል​እ​ክ​ተኛ ወደ እኔ ደረሰ</verse>
				<verse number="19">እኔም አዝ​ዣ​ለሁ፤ ተመ​ረ​መ​ረም፤ ይህ​ችም ከተማ ከጥ​ንት ጀምራ በነ​ገ​ሥ​ታት ላይ ዐመ​ፀኛ እንደ ነበ​ረች፥ በእ​ር​ስ​ዋም ዐመ​ፅና ሽፍ​ት​ነት እንደ ተደ​ረገ ተገኘ።</verse>
				<verse number="20">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እጅግ ኀያ​ላን ነገ​ሥ​ታት ነበሩ፤ በወ​ን​ዝም ማዶ ያለ​ውን ሀገር ሁሉ ይገዙ ነበር፤ ግብ​ር​ንና እጅ መን​ሻ​ንም ይቀ​በሉ ነበር።</verse>
				<verse number="21">አሁ​ንም እነ​ዚህ ሰዎች ሥራ​ውን እን​ዲ​ተዉ፥ ይህ​ችም ከተማ እን​ዳ​ት​ሠራ ትእ​ዛዝ ስጡ።</verse>
				<verse number="22">በዚ​ህም ነገር እን​ዳ​ት​ሳ​ሳቱ፥ በነ​ገ​ሥ​ታ​ቱም ጕዳ​ትና ጥፋት እን​ዳ​ይ​በዛ ተጠ​ን​ቀቁ።”</verse>
				<verse number="23">የን​ጉ​ሡም የአ​ር​ተ​ሰ​ስታ መል​እ​ክ​ተኛ በደ​ረሰ ጊዜ በአ​ዛዡ በሬ​ሁ​ምና በጸ​ሓ​ፊው በሲ​ም​ሳይ፥ በተ​ባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ፊት መል​እ​ክ​ቱን ባነ​በበ ጊዜ ፈጥ​ነው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አይ​ሁድ በፈ​ረስ ሄዱ፤ በኀ​ይ​ልም አስ​ተ​ዉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">በዚ​ያን ጊዜም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሥራ ተቋ​ረጠ፤ እስከ ፋር​ስም ንጉሥ እስከ ዳር​ዮስ መን​ግ​ሥት እስከ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት ድረስ ተጓ​ጐለ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">ነቢ​ያቱ ሐጌና የአዶ ልጅ ዘካ​ር​ያስ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለነ​በሩ አይ​ሁድ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ስም ትን​ቢት ተና​ገ​ሩ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">በዚ​ያን ጊዜም የሰ​ላ​ት​ያል ልጅ ዘሩ​ባ​ቤል የኢ​ዮ​ሴ​ዴ​ቅም ልጅ ኢያሱ ተነ​ሥ​ተው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መሥ​ራት ጀመሩ፤ የሚ​ያ​ግ​ዙ​አ​ቸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢ​ያት ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበሩ።</verse>
				<verse number="3">በዚ​ያም ጊዜ በወ​ንዝ ማዶ የነ​በ​ረው ገዥ ተን​ት​ናይ፥ ደግሞ አስ​ተ​ር​ቡ​ዝ​ናይ ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ወደ እነ​ርሱ መጥ​ተው፥ “ይህን ቤት ትሠሩ ዘንድ ማን አዘ​ዛ​ችሁ? የም​ት​ሠ​ሩ​በ​ት​ንስ ሥል​ጣን ማን ሰጣ​ችሁ?” አሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ደግ​ሞም፥ “ይህ​ችን ከተ​ማስ የሚ​ሠሩ ሰዎች ስም ማን ማን ነው?” ብለው ጠየ​ቁ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይን ግን በይ​ሁዳ ምር​ኮ​ኞች ላይ ነበረ፤ ይህም ነገር ወደ ዳር​ዮስ እስ​ኪ​ደ​ርስ ድረስ፥ መል​ሱም በመ​ል​እ​ክ​ተኛ እስ​ኪ​መጣ ድረስ አል​ከ​ለ​ከ​ሉ​አ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="6">በወ​ንዙ ማዶ የነ​በ​ረው ገዥ ተን​ት​ናይ፥ ደግሞ አስ​ተ​ር​ቡ​ዝ​ናይ፥ ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ በወ​ንዙ ማዶ የነ​በ​ሩት አፈ​ር​ስ​ካ​ው​ያ​ንም ወደ ንጉሡ ወደ ዳር​ዮስ የላ​ኩት የደ​ብ​ዳ​ቤው ቃል ይህ ነበረ።</verse>
				<verse number="7">እን​ዲ​ህም የሚል ደብ​ዳቤ ላኩ​ለት፥ “ለን​ጉሡ ለዳ​ር​ዮስ ሙሉ ሰላም ይሁን፤</verse>
				<verse number="8">ወደ ይሁዳ ሀገር ወደ ታላ​ቁም አም​ላክ ቤት እንደ ሄድን ንጉሡ ይወቅ፤ እር​ሱም በጥሩ ድን​ጋይ ይሠ​ራል፤ በቅ​ጥ​ሩም ውስጥ ልዩ እን​ጨት ይደ​ረ​ጋል፤ ያም ሥራ በት​ጋት ይሠ​ራል፤ በእ​ጃ​ቸ​ውም ይከ​ና​ወ​ናል።</verse>
				<verse number="9">እነ​ዚ​ያ​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፦ ‘ይህን ቤት ትሠሩ ዘንድ ማን አዘ​ዛ​ችሁ? የም​ት​ሠ​ሩ​በ​ት​ንስ ሥል​ጣን ማን ሰጣ​ችሁ?’ ብለን ጠየ​ቅ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="10">ደግ​ሞም እና​ስ​ታ​ው​ቅህ ዘንድ፥ በእ​ነ​ር​ሱም ያሉ​ትን ሹሞች ስም እን​ጽ​ፍ​ልህ ዘንድ ስማ​ቸ​ውን ጠየ​ቅን።</verse>
				<verse number="11">እን​ደ​ዚ​ህም ብለው መለ​ሱ​ልን፦ እኛ የሰ​ማ​ይና የም​ድር አም​ላክ ባሪ​ያ​ዎች ነን፥ ከብ​ዙም ዘመን ጀምሮ ተሠ​ርቶ የነ​በ​ረ​ውን፥ ታላ​ቁም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሠርቶ ፈጽ​ሞ​ላ​ቸው የነ​በ​ረ​ውን ቤት እን​ሠ​ራ​ለን።</verse>
				<verse number="12">አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም የሰ​ማ​ይን አም​ላክ ከአ​ስ​ቈጡ በኋላ በከ​ለ​ዳ​ዊው በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ እር​ሱም ይህን ቤት አፈ​ረሰ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ወደ ባቢ​ሎን አፈ​ለሰ።</verse>
				<verse number="13">ነገር ግን በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በቂ​ሮስ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዓመት ንጉሡ ቂሮስ ይህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ይሠሩ ዘንድ አዘዘ።</verse>
				<verse number="14">ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከነ​በ​ረው መቅ​ደስ የወ​ሰ​ደ​ውን፥ ወደ ባቢ​ሎ​ንም መቅ​ደስ ያፈ​ለ​ሰ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት የወ​ር​ቁ​ንና የብ​ሩን ዕቃ ንጉሡ ቂሮስ ከባ​ቢ​ሎን መቅ​ደስ አው​ጥቶ ለቤተ መዛ​ግ​ብቱ ሹም ለሲ​ሳ​ብ​ሳር ሰጠ​ውና፦</verse>
				<verse number="15">‘ይህን ዕቃ ይዘህ ሂድ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ባለው መቅ​ደስ በቦ​ታው አኑ​ረው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በስ​ፍ​ራው ይሠራ’ አለው።</verse>
				<verse number="16">በዚያ ጊዜም ይህ ሲሳ​ብ​ሳር መጣ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መሠ​ረተ፤ ከዚ​ያም ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እየ​ተ​ሠራ አል​ተ​ጨ​ረ​ሰም።</verse>
				<verse number="17">አሁ​ንም ይህ ነገር በን​ጉሡ ዐይን መል​ካም ቢሆን ይህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይሠራ ዘንድ ከን​ጉሡ ከቂ​ሮስ ታዝዞ እንደ ሆነ በባ​ቢ​ሎን ባለው በን​ጉሡ ቤተ መዛ​ግ​ብት ይመ​ር​መር፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር ንጉሡ ፈቃ​ዱን ይላ​ክ​ልን።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">በዚያ ጊዜም ንጉሡ ዳር​ዮስ በባ​ቢ​ሎን ቤተ መዛ​ግ​ብት ያሉ የታ​ሪክ መጻ​ሕ​ፍት እን​ዲ​መ​ረ​መሩ አዘዘ።</verse>
				<verse number="2">በሜ​ዶን አው​ራጃ ባለው ባሪ በሚ​ባል ከተማ በን​ጉሡ ቤት ውስጥ አንድ ጥቅ​ልል ተገኘ፤ በው​ስ​ጡም ይህ ነገር ለመ​ታ​ሰ​ቢያ ተጽፎ ነበር።</verse>
				<verse number="3">በን​ጉሡ በቂ​ሮስ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዓመት ንጉሡ ቂሮስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስላ​ለው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደስ እን​ዲህ ብሎ አዘዘ፥ “ይህ ቤት ይሠራ መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ቀ​ር​ብ​በ​ትም ቦታ ይሠራ፤ ቁመ​ቱም ስድሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ስድሳ ክንድ ይሁን።</verse>
				<verse number="4">በሦ​ስት ተራ ታላ​ላቅ ድን​ጋይ፥ በአ​ንድ ተራ እን​ጨት ይደ​ረግ፤ ወጭ​ውም ከን​ጉሡ ቤት ይሰጥ።</verse>
				<verse number="5">ናቡ​ከ​ደ​ነ​ዖ​ርም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ካለው መቅ​ደስ ወስዶ ወደ ባቢ​ሎን ያመ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የወ​ር​ቅና የብር ዕቃ ይሰጥ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወዳ​ለው መቅ​ደስ ወደ ስፍ​ራው ይወ​ሰድ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ይኑር።</verse>
				<verse number="6">“አሁ​ንም አንተ በወ​ንዝ ማዶ ያለ​ኸው የሀ​ገሩ ገዥ ተን​ት​ናይ ደግሞ አሰ​ተ​ር​ቡ​ዝ​ናይ በወ​ንዝ ማዶም ያሉ ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ችሁ አፈ​ር​ስ​ካ​ው​ያን ከዚያ ራቁ፤</verse>
				<verse number="7">ይህም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ይሠራ ዘንድ ተዉ፤ የአ​ይ​ሁ​ድም አለ​ቆ​ችና የአ​ይ​ሁድ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ይህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት በስ​ፍ​ራው ይሥሩ።</verse>
				<verse number="8">ይህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ይሠሩ ዘንድ ለአ​ይ​ሁድ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን፥ በወ​ንዝ ማዶ ካለው ሀገር ከሚ​መ​ጣው ግብር ከን​ጉሡ ገን​ዘብ ለእ​ነ​ዚህ ሰዎች ወጭ​ውን በት​ጋት እን​ድ​ት​ሰ​ጡ​አ​ቸው፥ ሥራም እን​ዳ​ታ​ስ​ፈ​ቱ​አ​ቸው አዝ​ዣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">ለሰ​ማይ አም​ላክ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ውን ወይ​ፈ​ኖ​ችና አውራ በጎች፥ ጠቦ​ቶ​ችም፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እን​ዳሉ እንደ ካህ​ናቱ ቃል ስን​ዴና ጨው፥ የወ​ይን ጠጅና ዘይት የሚ​ጠ​ይ​ቋ​ች​ሁን ዕለት ዕለት ስጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">ይኸ​ውም ለሰ​ማይ አም​ላክ በጎ መዓዛ የሆ​ነ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርቡ ዘንድ፥ ለን​ጉ​ሡና ለል​ጆ​ቹም ዕድሜ ይጸ​ልዩ ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="11">ይህ​ንም ትእ​ዛዝ የሚ​ለ​ውጥ ሁሉ ምሰ​ሶው ከቤቱ ተነ​ቅሎ እርሱ ይሰ​ቀ​ል​በት፤ በላ​ዩም ይገ​ደል፤ ቤቱም የጕ​ድፍ መጣያ ይደ​ረግ ብዬ አዝ​ዣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">ስሙ በዚያ የሚ​ኖር አም​ላክ ይህን ይለ​ውጡ ዘንድ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ው​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ያፈ​ር​ሱት ዘንድ እጃ​ቸ​ውን የሚ​ዘ​ረ​ጉ​ትን ነገ​ሥ​ታ​ትና አሕ​ዛብ ሁሉ ያጥፋ። እኔ ዳር​ዮስ ይህን አዝ​ዣ​ለሁ፤ በት​ጋት ይፈ​ጸም።”</verse>
				<verse number="13">ንጉ​ሡም ዳር​ዮስ እንደ ላከው ቃል፥ በዚ​ያን ጊዜ በወ​ንዝ ማዶ ያለ ገዥ ተን​ት​ናይ ደግሞ አስ​ተ​ር​ቡ​ዝ​ናይ ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም እን​ዲሁ ተግ​ተው አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="14">የአ​ይ​ሁድ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ሌዋ​ው​ያ​ንም በነ​ቢዩ በሐ​ጌና በአዶ ልጅ በዘ​ካ​ር​ያስ ትን​ቢት መሠ​ረት ሠሩ፤ ተከ​ና​ወ​ነ​ላ​ቸ​ውም። እንደ እስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ትእ​ዛዝ፥ እንደ ፋር​ስም ነገ​ሥ​ታት እንደ ቂሮ​ስና እንደ ዳር​ዮስ፥ እንደ አር​ተ​ሰ​ስ​ታም ትእ​ዛዝ ሠር​ተው ፈጸሙ።</verse>
				<verse number="15">ይህም ቤት በን​ጉሡ በዳ​ር​ዮስ መን​ግ​ሥት በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ዓመት አዳር በሚ​ባል ወር በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ተፈ​ጸመ።</verse>
				<verse number="16">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያኑ፥ የቀ​ሩ​ትም የም​ር​ኮ​ኞች ልጆች የዚ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ቅዳሴ በደ​ስታ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="17">በዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ቅዳሴ መቶ ወይ​ፈ​ኖ​ችና ሁለት መቶ አውራ በጎች፥ አራት መቶም የበግ ጠቦ​ቶች አቀ​ረቡ፤ ስለ ኀጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት እንደ እስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ቍጥር ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየ​ሎች አቀ​ረቡ።</verse>
				<verse number="18">በሙ​ሴም መጽ​ሐፍ እንደ ተጻ​ፈው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ግ​ሎት ላይ ካህ​ና​ቱን በየ​ማ​ዕ​ር​ጋ​ቸው፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸው አቆሙ።</verse>
				<verse number="19">የም​ር​ኮ​ኞ​ቹም ልጆች በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን ፋሲ​ካ​ውን አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="20">ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም አንድ ሆነው ነጽ​ተው ነበር፤ ሁሉም ንጹ​ሓን ነበሩ፤ ለም​ር​ኮ​ኞ​ቹም ልጆች ሁሉ፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ለካ​ህ​ናቱ፥ ለራ​ሳ​ቸ​ውም የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ ዐረዱ።</verse>
				<verse number="21">ከም​ር​ኮም ተመ​ል​ሰው የመ​ጡት የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ልጉ ዘንድ ራሳ​ቸ​ውን ከም​ድር አሕ​ዛብ ርኵ​ሰት ለይ​ተው ወደ እነ​ርሱ መጥ​ተው የነ​በ​ሩት ሁሉ ፋሲ​ካ​ውን በሉ፤</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደስ አሰ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለመ​ሥ​ራት እጃ​ቸ​ውን ያጸና ዘንድ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ልብ ወደ እነ​ርሱ መል​ሶ​አ​ልና የቂ​ጣ​ውን በዓል ሰባት ቀን በደ​ስታ አደ​ረጉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">ከዚ​ህም ነገር በኋላ በፋ​ርስ ንጉሥ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ መን​ግ​ሥት ዕዝራ የሠ​ራያ ልጅ፥ የዓ​ዛ​ር​ያስ ልጅ፥ የኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ፥</verse>
				<verse number="2">የሰ​ሎም ልጅ፥ የሳ​ዶቅ ልጅ፥ የአ​ኪ​ጦብ ልጅ፥</verse>
				<verse number="3">የአ​ማ​ርያ ልጅ፥ የዓ​ዛ​ር​ያስ ልጅ፥ የመ​ራ​ዮት ልጅ፥</verse>
				<verse number="4">የዘ​ራ​እያ ልጅ፥ የኡዚ ልጅ፥ የቡቂ ልጅ፥</verse>
				<verse number="5">የአ​ቢሱ ልጅ፥ የፊ​ን​ሐስ ልጅ፥ የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ፥ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ካህን የአ​ሮን ልጅ፥</verse>
				<verse number="6">ይህም ዕዝራ ከባ​ቢ​ሎን ወጣ፤ እር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ የሰ​ጠ​ውን ሕግ ዐዋቂ ነበረ፤ የአ​ም​ላ​ኩም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረ​ችና ንጉሡ ያሻ​ውን ሁሉ ሰጠው።</verse>
				<verse number="7">ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከካ​ህ​ና​ቱም፥ ከሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም፥ ከመ​ዘ​ም​ራ​ኑም፥ ከበ​ረ​ኞ​ቹም፥ ከና​ታ​ኒ​ምም በን​ጉሡ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ዐያ​ሌ​ዎች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጡ።</verse>
				<verse number="8">በን​ጉ​ሡም በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ደረሱ።</verse>
				<verse number="9">በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በአ​ን​ደ​ኛው ቀን ከባ​ቢ​ሎን ሊወጡ ጀመሩ፤ መል​ካ​ሚ​ቱም የአ​ም​ላኩ እጅ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረ​ችና በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ደረሱ።</verse>
				<verse number="10">ዕዝ​ራም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ይፈ​ል​ግና ያደ​ርግ ዘንድ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሥር​ዐ​ት​ንና ፍር​ድን ያስ​ተ​ምር ዘንድ ልቡን አዘ​ጋ​ጅቶ ነበር።</verse>
				<verse number="11">ንጉ​ሡም አር​ተ​ሰ​ስታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ቃልና ለእ​ስ​ራ​ኤል የሆ​ነ​ውን ሥር​ዐት ይጽፍ ለነ​በ​ረው ለጸ​ሓ​ፊው ለካ​ህኑ ለዕ​ዝራ የሰ​ጠው የደ​ብ​ዳ​ቤው ቃል ይህ ነው፦</verse>
				<verse number="12">“ከን​ጉሠ ነገ​ሥት ከአ​ር​ተ​ሰ​ስታ ለሰ​ማይ አም​ላክ ሕግ ጸሓፊ ለካ​ህኑ ለዕ​ዝራ፥ ሰላም ይሁን፤</verse>
				<verse number="13">በመ​ን​ግ​ሥ​ቴም ውስጥ ካሉ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ከካ​ህ​ና​ቱና ከሌ​ዋ​ው​ያኑ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይሄድ ዘንድ የሚ​ወ​ድድ ሁሉ ከአ​ንተ ጋር እን​ዲ​ሄድ አዝ​ዣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">ንጉ​ሡና ሰባቱ አማ​ካ​ሪ​ዎቹ በእ​ጅህ እን​ዳ​ለ​ችው እንደ አም​ላ​ክህ ሕግ ይሁ​ዳ​ንና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ትጐ​በኝ ዘንድ አዝ​ዘ​ዋል፤</verse>
				<verse number="15">ንጉ​ሡና አማ​ካ​ሪ​ዎ​ቹም መኖ​ሪ​ያው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለሆ​ነው ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ያቀ​ረ​ቡ​ትን ብርና ወርቅ፥</verse>
				<verse number="16">በባ​ቢ​ሎ​ንም አው​ራጃ ሁሉ የም​ታ​ገ​ኘ​ውን ብርና ወርቅ ሁሉ፥ ሕዝ​ቡና ካህ​ና​ቱም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላለው ለአ​ም​ላ​ካ​ቸው ቤት በፈ​ቃ​ዳ​ቸው የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡ​ትን ትወ​ስድ ዘንድ አዝ​ዘ​ዋል፤</verse>
				<verse number="17">ስለ​ዚህ በዚህ መጽ​ሐፍ ያዘ​ዝ​ሁህ ትእ​ዛዝ ይህ ነው። በዚህ ገን​ዘብ ወይ​ፈ​ኖ​ች​ንና አውራ በጎ​ችን፥ ጠቦ​ቶ​ች​ንም፥ የእ​ህ​ላ​ቸ​ው​ንና የመ​ጠ​ጣ​ቸ​ውን ቍር​ባን ተግ​ተህ ግዛ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ባለው በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ቤት መሠ​ዊያ ላይ አቅ​ር​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">ከቀ​ረ​ውም ብርና ወርቅ አን​ተና ወን​ድ​ሞ​ችህ ለማ​ድ​ረግ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኛ​ች​ሁን ነገር እንደ አም​ላ​ካ​ችሁ ፈቃድ አድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="19">ስለ አም​ላ​ክ​ህም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት የተ​ሰ​ጠ​ህን ዕቃ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አም​ላክ ፊት አሳ​ል​ፈህ ስጥ።</verse>
				<verse number="20">ከዚ​ህም በላይ ለማ​ው​ጣት የሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ግ​ህን ለአ​ም​ላ​ክህ ቤት የሚ​ያ​ሻ​ውን ነገር ከን​ጉሡ ቤተ መዛ​ግ​ብት ስጥ።</verse>
				<verse number="21">እኔም ንጉሡ አር​ተ​ሰ​ስታ በወ​ንዝ ማዶ ላሉት ግምጃ ቤቶች ሁሉ ይህን ትእ​ዛዝ ሰጥ​ቻ​ለሁ፦ የሰ​ማይ አም​ላክ ሕግ ጸሓፊ ካህኑ ዕዝራ ከእ​ና​ንተ የሚ​ፈ​ል​ገ​ውን ሁሉ አዘ​ጋ​ጁ​ለት፤</verse>
				<verse number="22">እስከ መቶ መክ​ሊት ብርም ቢሆን፥ እስከ መቶም የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ስንዴ፥ እስከ መቶም የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ የወ​ይን ጠጅ፥ እስከ መቶም የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ ዘይት ቢሆን፥ ጨውም ያለ ልክ ቢሆን፤</verse>
				<verse number="23">በን​ጉሡ መን​ግ​ሥ​ትና በል​ጆቹ ላይ ቍጣ እን​ዳ​ይ​ሆን፥ የሰ​ማይ አም​ላክ ያዘ​ዘው ሁሉ ይደ​ረግ፤ ለሰ​ማይ አም​ላክ ቤት የታ​ዘ​ዘ​ው​ንም እን​ዳ​ታ​ቋ​ርጡ ተጠ​ን​ቀቁ።</verse>
				<verse number="24">ደግ​ሞም በካ​ህ​ና​ቱና በሌ​ዋ​ው​ያኑ፥ በመ​ዘ​ም​ራ​ኑም፥ በበ​ረ​ኞ​ቹም፥ በና​ታ​ኒ​ምም በዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሚ​ሠሩ አገ​ል​ጋ​ዮች ላይ ግብ​ርና ቀረጥ እን​ዳ​ይ​ጣል፥ የም​ት​ገ​ዙ​አ​ቸ​ውም አገ​ዛዝ እን​ዳ​ይ​ኖር ብለን እና​ስ​ታ​ው​ቃ​ች​ኋ​ለን።</verse>
				<verse number="25">አን​ተም ዕዝራ፥ በእ​ጅህ እን​ዳ​ለው እንደ አም​ላ​ክህ ጥበብ መጠን በወ​ንዝ ማዶ ባሉ ሕዝብ ሁሉ፥ የአ​ም​ላ​ክ​ህን ሕግ በሚ​ያ​ውቁ ሁሉ ላይ ይፈ​ርዱ ዘንድ ጻፎ​ች​ንና ፈራ​ጆ​ችን ሹም፤ የማ​ያ​ው​ቁ​ት​ንም አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም ሕግ፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ሕግ በማ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ላይ ሞት፥ ወይም ስደት፥ ወይም ገን​ዘብ መወ​ረስ፥ ወይም ግዞት በፍ​ጥ​ነት ይፈ​ረ​ድ​በት።”</verse>
				<verse number="27">ያባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ያከ​ብር ዘንድ ይህን ነገር በን​ጉሡ ልብ ያኖረ፥</verse>
				<verse number="28">በን​ጉሡ ፊት በሚ​መ​ክ​ሩ​ትም፥ በኀ​ያ​ላ​ኑም፥ በን​ጉሡ አለ​ቆች ሁሉ ፊት በእኔ ላይ ምሕ​ረ​ቱን ላከ። እኔም በእኔ ላይ ባለ​ችው በአ​ም​ላኬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በረ​ታሁ፤ ከእ​ኔም ጋራ ይወጡ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል አለ​ቆ​ቹን ሰበ​ሰ​ብሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">በን​ጉሡ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ መን​ግ​ሥት ከእኔ ጋር ከባ​ቢ​ሎን የወጡ የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ትው​ል​ዳ​ቸ​ውም ይህ ነው፤</verse>
				<verse number="2">ከፊ​ን​ሐስ ልጆች ጌር​ሶም፥ ከኢ​ታ​ምር ልጆች ዳን​ኤል፥ ከዳ​ዊት ልጆች ሐጡስ፥</verse>
				<verse number="3">ከሴ​ኬ​ንያ ልጆች፥ ከፋ​ሮስ ልጆች ዘካ​ር​ያስ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የተ​ቈ​ጠሩ መቶ አምሳ ወን​ዶች ናቸው።</verse>
				<verse number="4">ከፋ​ሐት ሞዓብ ልጆች የዘ​ር​ህያ ልጅ ኤሊ​ሆ​ዔ​ናይ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሁለት መቶ ወን​ዶች።</verse>
				<verse number="5">ከዘ​ቱ​ኤስ ልጆች የአ​ዚ​ኤል ልጅ ሴኬ​ንያ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሦስት መቶ ወን​ዶች።</verse>
				<verse number="6">ከዓ​ዴን ልጆች የዮ​ና​ታን ልጅ ዔቤድ፥ ከእ​ር​ሱም ጋራ አምሳ ወን​ዶች።</verse>
				<verse number="7">ከኤ​ሌም ልጆች የጎ​ቶ​ልያ ልጅ የሻያ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሰባ ወን​ዶች።</verse>
				<verse number="8">ከሰ​ፋ​ጥ​ያስ ልጆች የሚ​ካ​ኤል ልጅ ዘብ​ድያ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሰማ​ንያ ወን​ዶች።</verse>
				<verse number="9">ከኢ​ዮ​አብ ልጆች የያ​ሔ​ኤል ልጅ አብ​ድያ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሁለት መቶ ዐሥራ ስም​ንት ወን​ዶች።</verse>
				<verse number="10">ከበ​ዐኛ ልጆች የዮ​ሴ​ፍያ ልጅ ሰሎ​ሚት፥ ከእ​ር​ሱም ጋር መቶ ስድሳ ወን​ዶች።</verse>
				<verse number="11">ከቤ​ባይ ልጆች የቤ​ባይ ልጅ ዘካ​ር​ያስ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሃያ ስም​ንት ወን​ዶች።</verse>
				<verse number="12">ከዓ​ዝ​ጋድ ልጆች የአ​ቃ​ጦን ልጅ፤ ዮሓ​ናን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር መቶ ዐሥር ወን​ዶች።</verse>
				<verse number="13">ከኋ​ለ​ኞቹ ከአ​ዶ​ኒ​ቃም ልጆች ስማ​ቸው ይህ ነው፤ ኤሊ​ፋ​ልጥ፥ ይኢ​ኤል፥ ሰማ​አያ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ስድሳ ወን​ዶች።</verse>
				<verse number="14">ከባ​ጎዊ ልጆች ውታ​ይና ዘቡድ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሰባ ወን​ዶች።</verse>
				<verse number="15">ወደ አኅ​ዋም ወደ​ሚ​ፈ​ስስ ወንዝ ሰበ​ሰ​ብ​ኋ​ቸው፤ በዚ​ያም ሦስት ቀን ሰፈ​ርን፤ ሕዝ​ቡ​ንና ካህ​ና​ቱ​ንም ስቈ​ጥ​ራ​ቸው በዚያ ከሌዊ ልጆች ማን​ንም አላ​ገ​ኘ​ሁም።</verse>
				<verse number="16">ወደ አለ​ቆ​ቹም ወደ አል​ዓ​ዛር፥ ወደ አር​ኤል፥ ወደ ሰማ​አያ፥ ወደ ሀሎ​ናም፥ ወደ ያሪብ፥ ወደ ሄል​ና​ታን፥ ወደ ናታን፥ ወደ ዘካ​ር​ያስ፥ ወደ ሜሱ​ላም፥ ደግ​ሞም ወደ ዐዋ​ቂ​ዎቹ ወደ ዮያ​ሪ​ብና ወደ ሄል​ና​ታን ላክሁ።</verse>
				<verse number="17">በካ​ሲ​ፍያ ስፍራ ወደ ነበ​ረው ወደ አለ​ቃው ወደ አዶ ላክ​ኋ​ቸው፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤትም አገ​ል​ጋ​ዮ​ችን ያመ​ጡ​ልን ዘንድ በካ​ሲ​ፍያ ስፍራ ለሚ​ኖ​ሩት ለአ​ዶና ለወ​ን​ድ​ሞቹ ለና​ታ​ኒም የሚ​ነ​ግ​ሩ​አ​ቸ​ውን በአ​ፋ​ቸው አደ​ረ​ግሁ።</verse>
				<verse number="18">በላ​ያ​ች​ንም መል​ካም በሆ​ነው በአ​ም​ላ​ካ​ችን እጅ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጅ ከሌዊ ልጅ ከሞ​ሐሊ ልጆች ወገን የነ​በ​ረ​ውን አስ​ተ​ዋይ ሰው ሰራ​ብ​ያን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ዐሥራ ስም​ን​ቱን ልጆ​ቹ​ንና ወን​ድ​ሞ​ቹን አመ​ጡ​ልን።</verse>
				<verse number="19">ደግ​ሞም አሴ​ብ​ያ​ስን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ከሜ​ራሪ ልጆች ወገን የነ​በ​ረ​ውን ኢሳ​ይ​ያ​ስን፥ ሃያ​ውን ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንና ልጆ​ቻ​ቸ​ውን።</verse>
				<verse number="20">ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ዳዊ​ትና አለ​ቆቹ ከሰ​ጡ​አ​ቸው ናታ​ኒም ውስጥ ሁለት መቶ ሃያ ናታ​ኒ​ምን አመጡ፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ በስም በስ​ማ​ቸው ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="21">በአ​ም​ላ​ካ​ችን ፊት ራሳ​ች​ንን እና​ዋ​ርድ ዘንድ፥ ከእ​ር​ሱም የቀ​ና​ውን መን​ገድ ለእ​ኛና ለል​ጆ​ቻ​ችን፥ ለን​ብ​ረ​ታ​ች​ንም ሁሉ እን​ለ​ምን ዘንድ በዚያ በአ​ኅዋ ወንዝ አጠ​ገብ ጾምን አወ​ጅሁ።</verse>
				<verse number="22">ንጉ​ሡ​ንም፥ “የአ​ም​ላ​ካ​ችን እጅ በሚ​ሹት ሁሉ ላይ ለመ​ል​ካም ነው፤ ኀይ​ሉና ቍጣው ግን እር​ሱን በሚ​ተዉ ሁሉ ላይ ነው” ብለን ተና​ግ​ረን ነበ​ርና፤ በመ​ን​ገድ ካለው ጠላት ያድ​ኑን ዘንድ ጭፍ​ራና ፈረ​ሰ​ኞች ከን​ጉሡ እለ​ምን ዘንድ አፍሬ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="23">ስለ​ዚ​ህም ነገር ጾምን፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለመ​ንን፤ እር​ሱ​ም​ሰ​ማን።</verse>
				<verse number="24">ከካ​ህ​ና​ቱም አለ​ቆች ዐሥራ ሁለት ሰዎ​ችን፥ ሰራ​ብ​ያ​ንና ሐሳ​ብ​ያን፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ዐሥር ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ለየሁ፤</verse>
				<verse number="25">ንጉ​ሡና አማ​ካ​ሪ​ዎቹ፥ አለ​ቆ​ቹም፥ በዚ​ያም የተ​ገ​ኙት እስ​ራ​ኤል ሁሉ ያቀ​ረ​ቡ​ትን፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤት የቀ​ረ​በ​ውን ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ ዕቃ​ው​ንም መዝኜ ሰጠ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">ስድ​ስት መቶ አምሳ መክ​ሊት ብር፥ አንድ መቶም መክ​ሊት የብር ዕቃ​ዎች፥ አንድ መቶም መክ​ሊት ወርቅ፥</verse>
				<verse number="27">ሃያም ባለ ሺህ ዳሪክ የወ​ርቅ ጽዋ​ዎች፥ ሁለ​ትም እንደ ወርቅ የከ​በሩ ከጥ​ሩና ከሚ​ያ​ን​ጸ​በ​ርቅ ናስ የተ​ሠሩ ዕቃ​ዎ​ችን መዝኜ በእ​ጃ​ቸው ሰጠሁ።</verse>
				<verse number="28">እኔም “እና​ንተ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቀ​ድ​ሳ​ች​ኋል፤ ዕቃ​ዎ​ቹም ቅዱ​ሳን ናቸው፤ ብሩና ወር​ቁም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃድ የቀ​ረበ ነው፤</verse>
				<verse number="29">በካ​ህ​ና​ትና በሌ​ዋ​ው​ያን አለ​ቆች፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ፊት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ጓዳ​ዎች ውስጥ እስ​ክ​ት​መ​ዝኑ ድረስ ተግ​ታ​ችሁ ጠብቁ” አል​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="30">ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት ይወ​ስ​ዱት ዘንድ ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ ዕቃ​ዎ​ቹ​ንም በሚ​ዛን ተቀ​በሉ።</verse>
				<verse number="31">በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ቀን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ሄድ ዘንድ ከአ​ኅዋ ወንዝ ተነ​ሣን፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም እጅ በላ​ያ​ችን ነበረ፤ በመ​ን​ገ​ድም ከጠ​ላ​ትና ከሚ​ሸ​ምቅ ሰው እጅ አዳ​ነን።</verse>
				<verse number="32">ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ደረ​ስን፤ በዚ​ያም ሦስት ቀን ተቀ​መ​ጥን።</verse>
				<verse number="33">በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ቀን ብሩና ወርቁ፥ ዕቃ​ዎ​ቹም በአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤት በካ​ህኑ በኦ​ርያ ልጅ በሜ​ሪ​ሞት እጅ ተመ​ዘኑ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የፊ​ን​ሐስ ልጅ አል​ዓ​ዛር ነበረ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሌዋ​ው​ያን የኢ​ያሱ ልጅ ኢዮ​ዛ​ብ​ድና የቤ​ንዊ ልጅ ናሕ​ድያ ነበሩ።</verse>
				<verse number="34">ሁሉም በቍ​ጥ​ርና በሚ​ዛን ተመ​ዘነ፤ ሚዛ​ኑም ሁሉ በዚያ ጊዜ ተጻፈ።</verse>
				<verse number="35">ከም​ር​ኮም የወ​ጡት የም​ር​ኮ​ኞች ልጆች ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ስለ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት ወይ​ፈ​ኖች፥ ዘጠና ስድ​ስ​ትም አውራ በጎች፥ ሰባ ሰባ​ትም ጠቦ​ቶች፥ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየ​ሎ​ችን አቀ​ረቡ። ይህ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነበረ።</verse>
				<verse number="36">የን​ጉ​ሡ​ንም ትእ​ዛዝ በወ​ንዙ ማዶ ላሉት ለን​ጉሡ ሹሞ​ችና ገዢ​ዎች ሰጡ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝ​ቡ​ንና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት አከ​በሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">ይህም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ የሕ​ዝቡ አለ​ቆች ወደ እኔ ቀር​በው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ካህ​ና​ቱም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ እንደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን፥ እንደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያን፥ እንደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያን፦ እንደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያን፥ እንደ አሞ​ና​ው​ያን፥ እንደ ሞዓ​ባ​ው​ያን፥ እንደ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንና እንደ አሞ​ራ​ው​ያን ርኵ​ሰት ያደ​ር​ጋሉ እንጂ ከም​ድር አሕ​ዛብ አል​ተ​ለ​ዩም፤</verse>
				<verse number="2">ለራ​ሳ​ቸ​ውና ለል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ወስ​ደ​ዋል፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ዘር ከም​ድር አሕ​ዛብ ጋር ደባ​ል​ቀ​ዋል፤ አስ​ቀ​ድ​ሞም አለ​ቆ​ቹና ሹሞቹ በዚህ መተ​ላ​ለፍ መጀ​መ​ሪያ ሆነ​ዋል” አሉኝ።</verse>
				<verse number="3">ይህ​ንም ነገር በሰ​ማሁ ጊዜ ልብ​ሴ​ንና መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ዬን ቀደ​ድሁ፤ አዘ​ን​ሁም፤ የራ​ሴ​ንና የጢ​ሜ​ንም ጠጕር ነጨሁ፤ ደን​ግ​ጬም ተቀ​መ​ጥሁ።</verse>
				<verse number="4">ስለ ምር​ኮ​ኞ​ቹም መተ​ላ​ለፍ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ቃል የሚ​ፈሩ ሁሉ ወደ እኔ ተሰ​በ​ሰቡ፤ እኔም እስከ ሠርክ መሥ​ዋ​ዕት ድረስ ዐዝኜ ተቀ​መ​ጥሁ።</verse>
				<verse number="5">በሠ​ር​ክም መሥ​ዋ​ዕት ጊዜ ልብ​ሴና መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያዬ እንደ ተቀ​ደደ ሆኖ ከመ​ዋ​ረዴ ተነ​ሣሁ፤ በጕ​ል​በ​ቴም ተን​በ​ር​ክኬ ወደ አም​ላኬ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጄን ዘረ​ጋሁ።</verse>
				<verse number="6">እን​ዲ​ህም አልሁ፥ “አም​ላኬ ሆይ፥ ኀጢ​አ​ታ​ችን በራ​ሳ​ችን ላይ በዝ​ቶ​አ​ልና፥ በደ​ላ​ች​ንም ወደ ሰማይ ከፍ ብሎ​አ​ልና አም​ላኬ ሆይ፥ ፊቴን ወደ አንተ አነሣ ዘንድ አፍ​ራ​ለሁ፤ እፈ​ራ​ማ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ዘመን ጀም​ረን እስከ ዛሬ ድረስ እጅግ በድ​ለ​ናል፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን እኛና ልጆ​ቻ​ችን ንጉ​ሦ​ቻ​ችን፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ች​ንም ለሰ​ይ​ፍና ለም​ርኮ፥ ለብ​ዝ​በ​ዛና ለዕ​ፍ​ረት በአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት እጅ ተጣ​ልን፤ እስከ ዛሬም ድረስ በፊ​ታ​ችን እፍ​ረት እን​ኖ​ራ​ለን።</verse>
				<verse number="8">አሁ​ንም ቅሬታ ይተ​ዉ​ልን ዘንድ፥ በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ስፍ​ራው ኀይ​ልን ይሰ​ጠን ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ች​ንም ዐይ​ና​ች​ንን ያበራ ዘንድ፥ በባ​ር​ነ​ትም ሳለን ጥቂት የሕ​ይ​ወት መታ​ደ​ስን ይሰ​ጠን ዘንድ ለጥ​ቂት ጊዜ ከአ​ም​ላ​ካ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥቂት ዕረ​ፍ​ትን አገ​ኘን።</verse>
				<verse number="9">ባሪ​ያ​ዎቹ ነንና፥ አም​ላ​ካ​ችን ግን በባ​ር​ነ​ታ​ችን አል​ተ​ወ​ንም፤ ቀለ​ባ​ች​ንን ይሰ​ጡን ዘንድ፥ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ን​ንም ቤት ከፍ ከፍ ያደ​ርጉ ዘንድ፥ የተ​ፈ​ታ​ው​ንም ይጠ​ግኑ ዘንድ፥ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቅጥር ያደ​ር​ጉ​ልን ዘንድ በፋ​ርስ ነገ​ሥ​ታት ፊት ሞገ​ስን ሰጠን።</verse>
				<verse number="10">አሁ​ንስ ከዚህ በኋላ ምን እን​ላ​ለን? አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ትእ​ዛ​ዝ​ህን ትተ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="11">በባ​ሮ​ችህ በነ​ቢ​ያት እጅ ያዘ​ዝ​ሃ​ትን እን​ዲህ ስትል፦ ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ የም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር በም​ድር አሕ​ዛብ ርኵ​ሰት የረ​ከ​ሰች ናት፤ በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውም ከዳር እስከ ዳር​ቻዋ ድረስ መል​ተ​ዋ​ታል።</verse>
				<verse number="12">አሁ​ንም ትበ​ረቱ ዘንድ፥ የም​ድ​ሩ​ንም ፍሬ ትበሉ ዘንድ፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይወ​ር​ሱ​አት ዘንድ፥ ሴቶ​ችን ልጆ​ቻ​ች​ሁን ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸው አት​ስጡ፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ችሁ አት​ው​ሰዱ፤ ሰላ​ማ​ቸ​ው​ንና ደኅ​ን​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አትሹ።</verse>
				<verse number="13">ስለ ክፉ ሥራ​ች​ንና ስለ ታላቁ በደ​ላ​ችን ካገ​ኘን ነገር ሁሉ በኋላ፥ አንተ አም​ላ​ካ​ችን እንደ ኀጢ​አ​ታ​ችን ብዛት አል​ቀ​ሠ​ፍ​ኸ​ንም፤ ነገር ግን ድኅ​ነ​ትን ሰጠ​ኸን።</verse>
				<verse number="14">ትእ​ዛ​ዝ​ህን እና​ፈ​ርስ ዘንድ ተመ​ል​ሰ​ና​ልና፥ ርኵስ ሥራ ከሚ​ሠሩ ከእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ጋርም ተጋ​ብ​ተ​ና​ልና ከእኛ ከሞት የሚ​ያ​መ​ልጥ እስ​ከ​ማ​ይ​ኖር ድረስ ፈጽ​መህ አት​ቈ​ጣን።</verse>
				<verse number="15">አቤቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ዛሬም እንደ ሆነው እኛ አም​ል​ጠን ቀር​ተ​ናል፤ እነሆ በፊ​ትህ በበ​ደ​ላ​ችን አለን፤ ስለ​ዚህ በፊ​ትህ ሊቆም የሚ​ችል የለም።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">ዕዝ​ራም እያ​ለ​ቀ​ሰና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እየ​ወ​ደቀ በጸ​ለ​የና በተ​ና​ዘዘ ጊዜ ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ የወ​ን​ድና የሴት፥ የሕ​ፃ​ና​ትም እጅግ ታላቅ ጉባኤ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰበ፤ ሕዝ​ቡም እጅግ አለ​ቀሱ።</verse>
				<verse number="2">ከኤ​ላም ልጆች ወገን የነ​በ​ረ​ውም የኢ​ያ​ሔል ልጅ ሴኬ​ንያ ዕዝ​ራን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፥ “አም​ላ​ካ​ች​ንን በድ​ለ​ናል፤ የም​ድ​ር​ንም አሕ​ዛብ እን​ግ​ዶች ሴቶ​ችን አግ​ብ​ተ​ናል፤ አሁን ግን ስለ​ዚህ ነገር ገና ለእ​ስ​ራ​ኤል ተስፋ አለ።</verse>
				<verse number="3">አሁ​ንም እንደ ጌታ​ዬና የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ትእ​ዛዝ እን​ደ​ሚ​ፈ​ሩት ምክር፥ ሴቶ​ችን ሁሉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ወ​ለ​ዱ​ትን እን​ሰ​ድድ ዘንድ ከአ​ም​ላ​ካ​ችን ጋር ቃል ኪዳን እና​ድ​ርግ። ተነሥ እንደ አም​ላ​ካ​ች​ንም ትእ​ዛዝ ገሥ​ፃ​ቸው፤ እንደ ሕጉም ያድ​ርጉ፤</verse>
				<verse number="4">ይህም ነገር ለአ​ንተ ይገ​ባ​ልና፥ እኛም ከአ​ንተ ጋር ነንና ተነሣ፤ በርታ፤ አድ​ር​ገ​ውም።”</verse>
				<verse number="5">ዕዝ​ራም ተነሣ፤ አለ​ቆ​ቹ​ንና ካህ​ና​ቱ​ንም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም፥ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ እን​ደ​ዚህ ቃል ያደ​ርጉ ዘንድ አማ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ማሉ።</verse>
				<verse number="6">ዕዝ​ራም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት ተነ​ሥቶ ወደ ኤሊ​ያ​ሴብ ልጅ ወደ ዮሐ​ናን ጓዳ ገባ፤ ስለ ምር​ኮ​ኞ​ቹም ኀጢ​አት ያለ​ቅስ ነበ​ርና ገብቶ እን​ጀራ አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም።</verse>
				<verse number="7">የም​ርኮ ልጆች ሁሉም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይሰ​በ​ሰቡ ዘንድ ወደ ይሁ​ዳና ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ዐዋጅ ነገረ</verse>
				<verse number="8">“እስከ ሦስት ቀን ድረስ የማ​ይ​መጣ ሁሉ እንደ ሽማ​ግ​ሎ​ችና እን​ዳ​ለ​ቆች ምክር ከብቱ ሁሉ ይበ​ዝ​በዝ፤ እር​ሱም ከም​ር​ኮው ጉባኤ ይለይ” ብሎ ዐዋጅ አስ​ነ​ገረ።</verse>
				<verse number="9">ሦስት ቀንም ሳያ​ልፍ በዘ​ጠ​ነ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሃ​ያ​ኛው ቀን የይ​ሁ​ዳና የብ​ን​ያም ሰዎች ሁሉ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተሰ​በ​ሰቡ። ሕዝ​ቡም ሁሉ ስለ​ዚህ ነገ​ርና ስለ ታላቁ ዝናብ እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት ባለው አደ​ባ​ባይ ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="10">ካህ​ኑም ዕዝራ ተነ​ሥቶ፥ “ተላ​ል​ፋ​ች​ኋል፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን በደል ታበዙ ዘንድ እን​ግ​ዶ​ችን ሴቶች አግ​ብ​ታ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="11">አሁ​ንም የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ው​ንም አድ​ርጉ፤ ከም​ድ​ርም አሕ​ዛ​ብና ከእ​ን​ግ​ዶች ሴቶች ተለዩ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">ጉባ​ኤ​ውም ሁሉ በታ​ላቅ ድምፅ መል​ሰው እን​ዲህ አሉ፥ “እንደ ተና​ገ​ር​ኸን እና​ደ​ርግ ዘንድ ይገ​ባ​ናል።</verse>
				<verse number="13">ነገር ግን የሕ​ዝቡ ቍጥር ብዙ ነው፤ ጊዜ​ውም የት​ልቅ ዝናብ ጊዜ ነው፤ በሜ​ዳም ልን​ቆም አን​ች​ልም፤ በዚ​ህም ነገር እጅግ በድ​ለ​ና​ልና ይህ ሥራ የአ​ንድ ወይም የሁ​ለት ቀን ሥራ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="14">አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም በጉ​ባ​ኤው ፋንታ ሁሉ ይቁሙ፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር የአ​ም​ላ​ካ​ችን ጽኑ ቍጣ ከእኛ ይመ​ለስ ዘንድ እን​ግ​ዶ​ቹን ሴቶች ያገ​ቡት በከ​ተ​ሞ​ቻ​ችን ያሉት ሁሉ በተ​ቀ​ጠ​ረው ጊዜ ይምጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የከ​ተ​ማው ሁሉ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ፈራ​ጆች ይምጡ።”</verse>
				<verse number="15">ነገር ግን የአ​ሣ​ሄል ልጅ ዮና​ታ​ንና የቴ​ቁዋ ልጅ የሐ​ዝያ ስለ​ዚህ ነገር ከእኔ ጋር ናቸው፤ ሜሱ​ላ​ምና ሌዋ​ዊው ሰባ​ታ​ይም ይረ​ዱ​አ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="16">የስ​ደ​ተ​ኞ​ቹም ልጆች እን​ዲህ አደ​ረጉ፤ ካህኑ ዕዝራ፥ የአ​ባ​ቶ​ችም ቤቶች አለ​ቆች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ሁሉም በየ​ስ​ማ​ቸው ተለዩ፤ በዐ​ሥ​ረ​ኛ​ውም ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ነገ​ሩን ይመ​ረ​ምሩ ዘንድ ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="17">እስከ መጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር እስከ መጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ድረስ ሠር​ተው እን​ግ​ዶ​ቹን ሴቶች ያገ​ቡ​ትን ሰዎች ሁሉ መር​ም​ረው ጨረሱ።</verse>
				<verse number="18">ከካ​ህ​ና​ቱም ወገን ልጆች እን​ግ​ዶ​ቹን ሴቶች ያገቡ ሰዎች ተገኙ፤ ከኢ​ዮ​ሴ​ዴቅ ልጅ ከኢ​ያሱ ልጆ​ችና ከወ​ን​ድ​ሞቹ ማዓ​ሥያ፥ አል​ዓ​ዛር፥ ኦሬም፥ ገዳ​ልያ።</verse>
				<verse number="19">ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ይፈቱ ዘንድ እጃ​ቸ​ውን ሰጡ፤ ስለ በደ​ላ​ቸ​ውም ከመ​ን​ጋው አንድ አውራ በግ ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ።</verse>
				<verse number="20">ከኢ​ሚር ልጆ​ችም አና​ኒና ዝብ​ድያ።</verse>
				<verse number="21">ከኤ​ራም ልጆ​ችም መሳ​ሔል፥ ኤልያ፥ ሴሚያ፥ ያሔል፥ ዖዝያ።</verse>
				<verse number="22">ከጳ​ሰ​ኮር ልጆ​ችም ኤል​ዮና፥ መሐ​ሰዓ፥ ይስ​ማ​ኤል፥ ናት​ና​ኤል፥ ኢዮ​ዛ​ባድ፥ ኤልሣ።</verse>
				<verse number="23">ከሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ኢዮ​ዛ​ባድ፥ ሰሜኢ፥ ቆሊ​ጣስ የሚ​ባል ቆልያ፥ ፈዲሓ፥ ይሁዳ፥ አል​ዓ​ዛር።</verse>
				<verse number="24">ከመ​ዘ​ም​ራ​ንም ኤል​ያ​ሴብ፤ ከበ​ረ​ኞ​ችም ሰሎም፥ ጤሎም፥ ኡሪ።</verse>
				<verse number="25">ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ከፋ​ሮስ ልጆች ራምያ፥ ዖዝያ፥ መል​ክያ፥ ሚያ​ሚን፥ አል​ዓ​ዛር፥ መል​ክያ፥ ቤን​ያህ።</verse>
				<verse number="26">ከኤ​ላም ልጆ​ችም መታ​ንያ፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ኢያ​ኤል፥ አብዲ፥ ይሬ​ሞት፥ ኤልያ።</verse>
				<verse number="27">ከዛቱ ልጆ​ችም ዔሊ​ዔ​ናይ፥ ኤል​ያ​ሴብ፥ መታ​ንያ፥ ኤር​ሞት፥ ዛባድ፥ ዓዚዛ።</verse>
				<verse number="28">ከቤ​ባይ ልጆ​ችም ዮሐ​ናን፥ ሐና​ንያ፥ ዘባይ፥ አጥ​ላይ።</verse>
				<verse number="29">ከባኒ ልጆ​ችም ሜሱ​ላም፥ መሉክ፥ ዓዳያ፥ ያሱብ፥ ሳዓል፥ ራሞት።</verse>
				<verse number="30">ከፈ​ሐት ሞዓብ ልጆ​ችም ዓድና፥ ክላል፥ በና​ያስ፥ ማዕ​ሴያ፥ መታ​ንያ፥ ባስ​ል​ኤል፥ በነዊ፥ ምናሴ።</verse>
				<verse number="31">ከኤ​ራም ልጆ​ችም አል​ዓ​ዛር፥ ይሲያ፥ ሚል​ክያ፥ ሰማያ፥ ስም​ዖን፥</verse>
				<verse number="32">ብን​ያም፥ መሉክ፥ ሰማ​ርያ።</verse>
				<verse number="33">ከሐ​ሱም ልጆ​ችም መታ​ንያ፥ መታታ፥ ዛባድ፥ ኤሊ​ፋ​ልጥ፥ ይሬ​ማይ፥ ምናሴ፥ ሰሜኢ።</verse>
				<verse number="34">ከባኒ ልጆ​ችም ማዕ​ዳይ፥ ዓም​ራም፥ ኡኤል፥</verse>
				<verse number="35">በና​ያስ፥ በዳያ፥ ኬል​ቅያ፥</verse>
				<verse number="36">ውንያ፥ መሪ​ሙት፥ ኤል​ያ​ሴብ፤</verse>
				<verse number="37">መታ​ንያ፥ መት​ናይ፥ የዕሡ፤</verse>
				<verse number="38">የባ​ኔይ ልጆ​ችና የሰ​ሜይ ልጆች፤</verse>
				<verse number="39">ሰሌ​ምያ፥ ናታን፥ ሐዳያ፤</verse>
				<verse number="40">መክ​ነ​ድ​ባይ፥ ሴሴይ፥ ሰራይ፤</verse>
				<verse number="41">ኤዛ​ር​ኤል፥ ሰሌ​ምያ፥ ሰማ​ርያ፥</verse>
				<verse number="42">ሰሎም፥ አማ​ርያ፥ ዮሴፍ።</verse>
				<verse number="43">ከናቡ ልጆ​ችም ይዒ​ኤል፥ መታ​ትያ፥ ዛባድ፥ ዛብ​ንያ፥ ያዳይ፥ ኢዮ​ኤል፥ በና​ያስ።</verse>
				<verse number="44">እነ​ዚህ ሁሉ እን​ግ​ዶ​ቹን ሚስ​ቶች አግ​ብ​ተው ነበር፤ ከእ​ነ​ዚ​ህም ሚስ​ቶች ዐያ​ሌ​ዎቹ ልጆ​ችን ወል​ደው ነበር።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="16">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">የኬ​ል​ቅያ ልጅ የነ​ህ​ምያ ቃል። በሃ​ያ​ኛው ዓመት በካ​ሴሎ ወር እን​ዲህ ሆነ፤ እኔ በሱሳ ግንብ ሳለሁ፥</verse>
				<verse number="2">ከወ​ን​ድ​ሞች አንዱ ሐናኒ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሌሎች ሰዎች ከይ​ሁዳ መጡ፤ እኔም የዳ​ኑ​ትን፥ ከም​ር​ኮም የተ​ረ​ፉ​ትን የአ​ይ​ሁ​ድን ነገር፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ነገር ጠየ​ቅ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">እነ​ር​ሱም፥ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከም​ርኮ የተ​ረ​ፉት ቅሬ​ታ​ዎች በታ​ላቅ መከ​ራና ስድብ አሉ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቅጥር ፈር​ሶ​አል፥ በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ለ​ዋል” አሉኝ።</verse>
				<verse number="4">ይህ​ንም ቃል በሰ​ማሁ ጊዜ ተቀ​ምጬ አለ​ቀ​ስሁ፤ አያሌ ቀንም አዝን ነበር፤ በሰ​ማ​ይም አም​ላክ ፊት እጾ​ምና እጸ​ልይ ነበር፤ እን​ዲ​ህም አልሁ፦</verse>
				<verse number="5">“አቤቱ የሰ​ማይ አም​ላክ ሆይ፥ ለሚ​ወ​ድ​ዱ​ህና ትእ​ዛ​ዝ​ህን ለሚ​ያ​ደ​ርጉ ቃል ኪዳ​ን​ንና ምሕ​ረ​ትን የም​ት​ጠ​ብቅ፥ ታላ​ቅና የተ​ፈ​ራህ አም​ላክ ሆይ፥</verse>
				<verse number="6">እኔ ባሪ​ያህ ዛሬ በፊ​ትህ ስለ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆች ሌሊ​ትና ቀን የም​ጸ​ል​የ​ውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ጆሮ​ዎ​ችህ ያድ​ምጡ፤ ዐይ​ኖ​ች​ህም ይከ​ፈቱ፤ በአ​ንተ ላይም ያደ​ረ​ግ​ነ​ውን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ኀጢ​አት ለአ​ንተ እን​ና​ዘ​ዛ​ለን፤ እኔም፥ የአ​ባ​ቴም ቤት በድ​ለ​ናል።</verse>
				<verse number="7">እኛም በአ​ንተ ላይ እጅግ ክፉ ሠር​ተ​ናል፤ ለባ​ሪ​ያ​ህም ለሙሴ ያዘ​ዝ​ኸ​ውን ትእ​ዛ​ዝና ሥር​ዐት፥ ሕጉ​ንም አል​ጠ​በ​ቅ​ንም።</verse>
				<verse number="8">“አሁ​ንም ለሙሴ ለባ​ሪ​ያህ እን​ዲህ ስትል ያዘ​ዝ​ሃ​ትን ነገር አስብ። ብት​በ​ድ​ሉም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እበ​ት​ና​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">ወደ እኔ ብት​መ​ለሱ ግን፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ብት​ጠ​ብቁ፥ ብታ​ደ​ር​ጓ​ትም ምንም ከእ​ና​ንተ ሰዎች እስከ ሰማይ ዳርቻ ቢበ​ተኑ፥ ከዚያ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ስሜም ይኖ​ር​በት ዘንድ ወደ መረ​ጥ​ሁት ስፍራ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">“እነ​ዚ​ህም በታ​ላቅ ኀይ​ል​ህና በብ​ርቱ እጅህ የተ​ቤ​ዥ​ሃ​ቸው ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህና ሕዝ​ብህ ናቸው።</verse>
				<verse number="11">ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባ​ሪ​ያ​ህን ጸሎት፥ ስም​ህ​ንም ይፈሩ ዘንድ የሚ​ወ​ድ​ዱ​ትን የባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህን ጸሎት ያድ​ምጥ፤ ዛሬም ለባ​ሪ​ያህ አከ​ና​ው​ን​ለት፤ በዚ​ህም ሰው ፊት ምሕ​ረ​ትን ስጠው።” እኔም ለን​ጉሡ ጠጅ አሳ​ላፊ ነበ​ርሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">በን​ጉሡ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ በሃ​ያ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በኔ​ሳን ወር የወ​ይን ጠጅ በፊቱ ነበር፤ ጠጁ​ንም አን​ሥቼ ለን​ጉሡ ሰጠ​ሁት። በፊ​ቱም ሌላ ሰው አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="2">ንጉ​ሡም፥ “ሳት​ታ​መም ፊትህ ለምን አዘነ? ይህ የልብ ኀዘን ነው እንጂ ሌላ አይ​ደ​ለም” አለኝ። እጅ​ግም ብዙ አድ​ርጌ ፈራሁ።</verse>
				<verse number="3">ንጉ​ሡ​ንም፥ “ንጉሡ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኑር፤ የአ​ባ​ቶች መቃ​ብር ያለ​ባት ከተማ ተፈ​ት​ታ​ለ​ችና፥ በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ለ​ዋ​ልና ፊቴ ስለ ምን አያ​ዝን?” አል​ሁት።</verse>
				<verse number="4">ንጉ​ሡም፥ “ምን ትለ​ም​ነ​ኛ​ለህ?” አለኝ። እኔም ወደ ሰማይ አም​ላክ ጸለ​ይሁ።</verse>
				<verse number="5">ንጉ​ሡ​ንም፥ “ንጉ​ሡን ደስ ቢያ​ሰ​ኝህ፥ ባሪ​ያ​ህም በፊ​ትህ ሞገስ ቢያ​ገኝ፥ እሠ​ራው ዘንድ ወደ ይሁዳ ወደ አባ​ቶች መቃ​ብር ከተማ ስደ​ደኝ” አል​ሁት።</verse>
				<verse number="6">ንግ​ሥ​ቲ​ቱም፦ በአ​ጠ​ገቡ ተቀ​ምጣ ሳለች ንጉሡ፥ “መን​ገ​ድህ እስከ መቼ ድረስ ይሆ​ናል? መቼስ ትመ​ለ​ሳ​ለህ?” አለኝ። ንጉ​ሡም ይሰ​ድ​ደኝ ዘንድ ደስ አለው፤ እኔም ጊዜ​ውን ነገ​ር​ሁት፤ እር​ሱም አሰ​ና​በ​ተኝ።</verse>
				<verse number="7">ንጉ​ሡ​ንም፥ “ንጉሥ ደስ ቢለው፥ እስከ ይሁዳ ሀገር እን​ዲ​ያ​ደ​ር​ሱኝ በወ​ንዝ ማዶ ላሉት ገዦች ደብ​ዳቤ ይስ​ጠኝ፤</verse>
				<verse number="8">በቤ​ቱም አጠ​ገብ ላለው ለግ​ንብ በሮች፥ ለከ​ተ​ማ​ውም ቅጥር፥ ለም​ገ​ባ​በ​ትም ቤት እን​ጨት እን​ዲ​ሰ​ጠኝ ለን​ጉሡ ዱር ጠባቂ ለአ​ሳፍ ደብ​ዳቤ ይሰ​ጠኝ” አል​ሁት። ንጉ​ሡም ሁሉን ሰጠኝ። የከ​በ​ረች የአ​ም​ላኬ እጅ ከእኔ ጋር ነበ​ረ​ችና።</verse>
				<verse number="9">በወ​ን​ዙም ማዶ ወዳ​ሉት ሀገረ ገዦች መጥቼ የን​ጉ​ሡን ደብ​ዳ​ቤ​ዎች ሰጠ​ኋ​ቸው። ንጉ​ሡም ከእኔ ጋር የሠ​ራ​ዊ​ቱን አለ​ቆ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች ልኮ ነበር።</verse>
				<verse number="10">ሖሮ​ና​ዊ​ውም ሰን​ባ​ላ​ጥና አገ​ል​ጋዩ አሞ​ና​ዊው ጦብያ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መል​ካ​ምን ነገር የሚሻ ሰው እንደ መጣ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተበ​ሳጩ።</verse>
				<verse number="11">ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ደረ​ስሁ፤ በዚ​ያም ሦስት ቀን ተቀ​መ​ጥሁ።</verse>
				<verse number="12">በሌ​ሊ​ትም ተነ​ሣሁ፤ ከእ​ኔም ጋር ጥቂት ሰዎች ነበሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ር​ገው ዘንድ በልቤ ያኖ​ረ​ውን ለማ​ንም አላ​ስ​ታ​ወ​ቅ​ሁም፤ ተቀ​ም​ጬ​በት ከነ​በ​ረው እን​ስሳ በቀር ከእኔ ጋር ምንም እን​ስሳ አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="13">በሸ​ለ​ቆ​ውም በር ወጣሁ፤ ወደ በለ​ስም ምን​ጭና ወደ ጕድፍ መጣ​ያው በር ሄድሁ፤ የፈ​ረ​ሰ​ው​ንም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ቅጥር፥ በእ​ሳ​ትም የተ​ቃ​ጠ​ሉ​ትን በሮ​ች​ዋን ተመ​ለ​ከ​ትሁ።</verse>
				<verse number="14">ወደ ምን​ጩም በርና ወደ ንጉ​ሡም መዋኛ አለ​ፍሁ፤ ተቀ​ም​ጬ​በት የነ​በ​ረው እን​ስ​ሳም የሚ​ያ​ል​ፍ​በት ስፍራ አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="15">በሌ​ሊ​ትም በፈ​ፋው በኩል ወጥቼ ቅጥ​ሩን ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ በሸ​ለ​ቆ​ውም በር ገባሁ፤ እን​ዲ​ሁም ተመ​ለ​ስሁ።</verse>
				<verse number="16">ጠባ​ቆች ግን ወዴት እንደ ሄድሁ፥ ምን እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ሁም አላ​ወ​ቁም ነበር፤ ለአ​ይ​ሁ​ድና ለካ​ህ​ናቱ፥ ለታ​ላ​ላ​ቆ​ችና ለሹ​ሞ​ቹም፥ ሥራም ይሠሩ ለነ​በ​ሩት ለሌ​ሎች እስ​ከ​ዚያ ጊዜ ገና አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁም ነበር።</verse>
				<verse number="17">እኔም፥ “እኛ ያለ​ን​በ​ትን ጕስ​ቍ​ልና፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ ፈረ​ሰች፥ በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት እንደ ተቃ​ጠሉ ታያ​ላ​ችሁ። አሁ​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ መሳ​ለ​ቂያ እን​ዳ​ን​ሆን ኑና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ቅጥር እን​ሥራ” አል​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">የአ​ም​ላ​ኬም እጅ በእኔ ላይ መል​ካም እንደ ሆነች፥ ንጉ​ሡም የነ​ገ​ረ​ኝን ቃል ነገ​ር​ኋ​ቸው። “ተነሡ እን​ሥራ” አል​ኋ​ቸው። እጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለበጎ ሥራ አበ​ረቱ።</verse>
				<verse number="19">ሖሮ​ና​ዊ​ውም ሰን​ባ​ላጥ፥ አገ​ል​ጋ​ዩም አሞ​ና​ዊው ጦቢያ፥ ዓረ​ባ​ዊ​ውም ጌሳም በሰሙ ጊዜ በን​ቀት ሳቁ​ብን፤ ቀላል አድ​ር​ገ​ው​ንም ወደ እኛ መጡና፥ “ይህ የም​ታ​ደ​ር​ጉት ነገር ምን​ድን ነው? በውኑ በን​ጉሡ ላይ ትሸ​ፍቱ ዘንድ ትወ​ድ​ዳ​ላ​ች​ሁን?” አሉ።</verse>
				<verse number="20">እኔም መልሼ፥ “የሰ​ማይ አም​ላክ ያከ​ና​ው​ን​ል​ናል፤ እኛም ንጹ​ሓን ባሪ​ያ​ዎቹ ተነ​ሥ​ተን እን​ሠ​ራ​ለን፤ እና​ንተ ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዕድል ፋን​ታና መብት፥ መታ​ሰ​ቢ​ያም የላ​ች​ሁም” አል​ኋ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ታላ​ቁም ካህን ኤል​ያ​ሴ​ብና ወን​ድ​ሞቹ ካህ​ናት ተነ​ሥ​ተው የበግ በር ሠሩ፤ ቀደ​ሱ​ትም፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆሙ፤ እስከ መቶ ግን​ብና እስከ ሐና​ን​ኤል ግንብ ድረስ ቀደ​ሱት።</verse>
				<verse number="2">በአ​ጠ​ገ​ቡም የኢ​ያ​ሪኮ ሰዎች ሠሩ፤ በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የአ​ምሪ ልጅ የዘ​ኩር ልጆች ሠሩ።</verse>
				<verse number="3">የአ​ስ​ናሃ ልጆ​ችም የዓሣ በር ሠሩ፤ ሠረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም አኖሩ፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆሙ፥ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="4">በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የቆስ ልጅ የኡ​ርያ ልጅ ሚራ​ሞት ይሠራ ጀመረ። በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የሜ​ሴ​ዜ​ቤል ልጅ የበ​ራ​ክያ ልጅ ሜሱ​ላም ይሠራ ጀመረ። በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የበ​ሃና ልጅ ሳዶቅ ይሠራ ጀመረ።</verse>
				<verse number="5">በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም ቴቁ​ሓ​ው​ያን ይሠሩ ጀመሩ፤ ታላ​ላ​ቆ​ቻ​ቸው ግን ለሥ​ራው አን​ገ​ታ​ቸ​ውን አላ​ዋ​ረ​ዱም።</verse>
				<verse number="6">የፋ​ሴሓ ልጅ ኢዮ​ዳ​ሄና የበ​ሶ​ድያ ልጅ ሜሱ​ላም አሮ​ጌ​ውን በር አደሱ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቹን አኖሩ፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆሙ፤ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="7">በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም ገባ​ዖ​ና​ዊው መል​ጥ​ያና ሜሮ​ና​ታ​ዊው ያዴን፥ እስከ ወን​ዙም ማዶ አለቃ ግዛት የሆኑ የገ​ባ​ዖ​ንና የመ​ሴፋ ሰዎች ሠሩ።</verse>
				<verse number="8">በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም ወርቅ አን​ጥ​ረ​ኛው የሐ​ሬ​ህያ ልጅ ዑዝ​ኤል ሠራ። በአ​ጠ​ገ​ቡም ከሽቱ ቀማ​ሚ​ዎች የነ​በረ ሐና​ንያ ሠራ፤ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ጠገኑ።</verse>
				<verse number="9">በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ግዛት እኩ​ሌታ አለቃ የሆር ልጅ ረፋያ ሠራ።</verse>
				<verse number="10">በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የኤ​ር​ማፍ ልጅ ይዳያ በቤቱ አን​ጻር ያለ​ውን ሠራ። በአ​ጠ​ገ​ቡም የአ​ሰ​ብ​ን​ብ​ሔም ልጅ ሐጡስ ሠራ።</verse>
				<verse number="11">የካ​ሪም ልጅ መል​ክያ፥ የፈ​ሐት ሞዓብ ልጅም አሱብ ሌላ​ውን ክፍ​ልና የእ​ቶ​ኑን ግንብ ሠሩ።</verse>
				<verse number="12">በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ግዛት እኩ​ሌታ ገዢ የአ​ሎ​ኤስ ልጅ ሰሎ​ምና ሴቶች ልጆቹ ሠሩ።</verse>
				<verse number="13">ሐኖ​ንና የዘ​ናን ሰዎ​ችም የሸ​ለ​ቆ​ውን በር አደሱ፤ ሠሩት፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆሙ፥ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረጉ፤ ደግ​ሞም እስከ ጕድፍ መጣያ በር ድረስ አንድ ሺህ ክንድ የሚ​ሆን ቅጥር ሠሩ።</verse>
				<verse number="14">የቤ​ት​ሐ​ካ​ሪ​ምም ግዛት ገዢ የሬ​ካብ ልጅ መል​ክያ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹና ከል​ጆቹ ጋር የጕ​ድፍ መጣ​ያ​ውን በር ሠራ፤ ከደ​ነው፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆመ፤ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="15">የመ​ሴ​ፋም ገዢ የኮ​ል​ሐዜ ልጅ ሰሎም የም​ን​ጩን በር አደሰ፤ ሠራው፤ ከደ​ነ​ውም፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆመ፤ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረገ፤ ከዳ​ዊ​ትም ከተማ እስ​ከ​ሚ​ወ​ር​ደው ደረጃ ድረስ በን​ጉሡ አት​ክ​ልት አጠ​ገብ ያለ​ውን የመ​ዋኛ ቅጥር ሠራ።</verse>
				<verse number="16">ከእ​ር​ሱም በኋላ የቤ​ሶር ግዛት እኩ​ሌታ ገዢ የዓ​ዛ​ቡህ ልጅ ነህ​ምያ በዳ​ዊት መቃ​ብር አን​ጻር እስ​ካ​ለው ስፍራ፥ እስከ ተሠ​ራ​ውም መዋኛ፥ እስከ ኀያ​ላ​ኑም ቤት ድረስ ሠራ።</verse>
				<verse number="17">ከእ​ር​ሱም በኋላ ሌዋ​ው​ያ​ንና የባኒ ልጅ ሬሁም ሠሩ። በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የቅ​ዒላ ግዛት እኩ​ሌ​ታና የአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ችዋ ገዢ አሰ​ብያ ሠራ።</verse>
				<verse number="18">ከእ​ር​ሱም በኋላ የቅ​ዔላ ግዛት እኩ​ሌታ ገዢ የኤ​ን​ሐ​ዳድ ልጅ ቤኒ​ይና ወን​ድ​ሞቹ ሠሩ።</verse>
				<verse number="19">በአ​ጠ​ገ​ቡም የመ​ሴፋ ገዢ የኢ​ያሱ ልጅ አዙር በማ​ዕ​ዘኑ አጠ​ገብ በመ​ወ​ጣ​ጫው ግንብ አን​ጻር ያለ​ውን ሌላ​ውን ክፍል ሠራ።</verse>
				<verse number="20">ከእ​ር​ሱም በኋላ የዘ​ቡር ልጅ ባሮክ ከማ​ዕ​ዘኑ ጀምሮ እስከ ታላቁ ካህን እስከ ኤል​ያ​ሴብ ቤት መግ​ቢያ ድረስ ሌላ​ውን ክፍል ተግቶ ሠራ።</verse>
				<verse number="21">ከእ​ር​ሱም በኋላ የአ​ቆስ ልጅ የኡ​ርያ ልጅ ሚራ​ሞት ከኤ​ል​ያ​ሴብ ቤት መግ​ቢያ ጀምሮ እሰከ ኤል​ያ​ሴብ ቤት መጨ​ረሻ ድረስ ሌላ​ውን ክፍል ሠራ።</verse>
				<verse number="22">ከእ​ር​ሱም በኋላ የአ​ካ​ባ​ቢው ሰዎች ካህ​ናቱ ሠሩ።</verse>
				<verse number="23">ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ብን​ያ​ምና አሴብ በቤ​ታ​ቸው አን​ጻር ያለ​ውን ሠሩ። ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ የሐ​ና​ንያ ልጅ የመ​ዓ​ስያ ልጅ ዓዛ​ር​ያስ በቤቱ አጠ​ገብ ያለ​ውን ሠራ።</verse>
				<verse number="24">ከእ​ር​ሱም በኋላ የኢ​ን​ሓ​ዳድ ልጅ ባኒ ከዓ​ዛ​ር​ያስ ቤት ጀምሮ እስከ ማዕ​ዘኑ እስከ ግን​ቡ​መ​ዞ​ሪያ ድረስ ያለ​ውን ሌላ​ውን ክፍል ሠራ።</verse>
				<verse number="25">የኡ​ዛይ ልጅ ፋልል በማ​ዕ​ዘኑ አን​ጻር ያለ​ው​ንና በዘ​በ​ኞች አደ​ባ​ባይ አጠ​ገብ ከላ​ይ​ኛው የን​ጉሡ ቤት ወጥቶ የቆ​መ​ውን ግንብ ሠራ። ከእ​ር​ሱም በኋላ የፋ​ሮስ ልጅ ፈዳያ ሠራ።</verse>
				<verse number="26">ናታ​ኒ​ምም በዖ​ፌል በው​ኃው በር አን​ጻር በም​ሥ​ራቅ በኩል ወጥቶ በቆ​መው ግንብ አጠ​ገብ እስ​ካ​ለው ስፍራ ድረስ ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="27">ከእ​ር​ሱም በኋላ ቴቁ​ሐ​ው​ያን ወጥቶ በቆ​መው በታ​ላቁ ግንብ አን​ጻር ያለ​ውን እስከ ዖፌል ቅጥር ድረስ ሌላ​ውን ክፍል ሠሩ።</verse>
				<verse number="28">ከፈ​ረ​ሶች በር በላይ ካህ​ናቱ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በየ​ቤ​ታ​ቸው አን​ጻር ሠሩ።</verse>
				<verse number="29">ከዚ​ያም በኋላ የሄ​ሜር ልጅ ሳዶቅ በቤቱ አን​ጻር ያለ​ውን ሠራ። ከእ​ር​ሱም በኋላ የም​ሥ​ራቁ በር ጠባቂ የሴ​ኬ​ንያ ልጅ ሰማያ ሠራ።</verse>
				<verse number="30">ከእ​ር​ሱም በኋላ የሰ​ሎ​ምያ ልጅ ሐና​ን​ያና የሴ​ሌፍ ስድ​ስ​ተ​ኛው ልጁ ሐኖን ሌላ​ውን ክፍል ሠሩ። ከዚ​ያም በኋላ የበ​ራ​ክያ ልጅ ሜሱ​ላም በሙ​ዳየ ምጽ​ዋቱ አን​ጻር ያለ​ውን ሠራ።</verse>
				<verse number="31">ከእ​ር​ሱም በኋላ የሰ​ራፊ ልጅ መል​ክያ እስከ ናታ​ኒ​ምና እስከ ነጋ​ዴ​ዎቹ ቤት ድረስ በሐ​ሜ​ፍ​ቃድ በር አን​ጻር ያለ​ውን እስከ ማዕ​ዘኑ መውጫ ድረስ ሠራ።</verse>
				<verse number="32">ከማ​ዕ​ዘ​ኑም መውጫ ጀም​ረው እስከ በጎች በር ድረስ ወርቅ አን​ጥ​ረ​ኞ​ችና ነጋ​ዴ​ዎች ሠሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ሰን​ባ​ላ​ጥም ቅጥ​ሩን እንደ ሠራን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤ ተበ​ሳ​ጨም፤ በአ​ይ​ሁ​ድም ሳቀ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">በወ​ን​ድ​ሞ​ቹና በሰ​ማ​ርያ ሠራ​ዊ​ትም ፊት፥ “ከተ​ማ​ቸ​ውን የሚ​ሠሩ እነ​ዚህ ደካ​ሞች አይ​ሁድ ኀይ​ላ​ቸው ምን​ድን ነው? ይተ​ዉ​ላ​ቸ​ዋ​ልን? ይሠ​ዋ​ሉን? በአ​ንድ ቀንስ ይጨ​ር​ሳ​ሉን? የተ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንስ ድን​ጋይ ከፍ​ር​ስ​ራሹ መል​ሰው ያድ​ኑ​ታ​ልን?” ብሎ ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="3">አሞ​ና​ዊ​ውም ጦቢያ ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “በድ​ን​ጋይ በሚ​ሠ​ሩት ቅጥ​ራ​ቸው ላይ ቀበሮ ቢወ​ጣ​በት ያፈ​ር​ሰ​ዋል” አለ።</verse>
				<verse number="4">አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ተን​ቀ​ና​ልና ስማ፤ ስድ​ባ​ቸ​ውን በራ​ሳ​ቸው ላይ መል​ስ​ባ​ቸው፤ በም​ርኮ ሀገር ለብ​ዝ​በዛ አሳ​ል​ፈህ ስጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">በደ​ላ​ቸ​ው​ንም አት​ክ​ደን፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ከፊ​ትህ አይ​ደ​ም​ሰስ፤ በሠ​ራ​ተ​ኞች ፊት አስ​ቈ​ጥ​ተ​ው​ሃ​ልና።</verse>
				<verse number="6">ቅጥ​ሩ​ንም ሠራን፤ ቅጥ​ሩም ሁሉ እስከ እኩ​ሌ​ታው ድረስ ተጋ​ጠመ፤ ሕዝቡ ከልብ ይሠራ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="7">ሰን​ባ​ላ​ጥና ጦብ​ያም፥ ዓረ​ባ​ው​ያ​ንም፥ አሞ​ና​ው​ያ​ንም፥ አዛ​ጦ​ና​ው​ያ​ንም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅጥር እየ​ታ​ደሰ እንደ ሄደ፥ የፈ​ረ​ሰ​ውም ሊጠ​ገን እንደ ተጀ​መረ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቈጡ።</verse>
				<verse number="8">መጥ​ተ​ውም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ይወ​ጉና ያፈ​ር​ሷት ዘንድ ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="9">እኛም ወደ አም​ላ​ካ​ችን ጸለ​ይን፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ነሣ በአ​ን​ጻ​ራ​ቸው ተጠ​ባ​ባ​ቂ​ዎ​ችን በሌ​ሊ​ትና በቀን አደ​ረ​ግን።</verse>
				<verse number="10">ይሁ​ዳም፥ “የተ​ሸ​ካ​ሚ​ዎች ኀይል ደከመ፤ ፍር​ስ​ራ​ሹም ብዙ ነው፤ ቅጥ​ሩ​ንም እን​ሠራ ዘንድ አን​ች​ልም” አሉ።</verse>
				<verse number="11">ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ “ወደ መካ​ከ​ላ​ቸው እስ​ክ​ን​መ​ጣና እስ​ክ​ን​ገ​ድ​ላ​ቸው ድረስ፥ ሥራ​ቸ​ው​ንም እስ​ክ​ና​ስ​ተ​ጓ​ጕል ድረስ አያ​ው​ቁም፤ አያ​ዩም” አሉ።</verse>
				<verse number="12">በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የተ​ቀ​መ​ጡት አይ​ሁድ መጥ​ተው፥ “ከስ​ፍ​ራው ሁሉ ይመ​ጡ​ብ​ናል ብለው ዐሥር ጊዜ ነገ​ሩን።”</verse>
				<verse number="13">ከቅ​ጥ​ሩም በስ​ተ​ኋላ በኩል ባለው በታ​ች​ኛው ክፍል በሰ​ዋራ ስፍራ ሰይ​ፋ​ቸ​ው​ንና ጦራ​ቸ​ውን፥ ቀስ​ታ​ቸ​ው​ንም አስ​ይዤ ሕዝ​ቡን በየ​ወ​ገ​ና​ቸው አቆ​ም​ኋ​ቸው፤</verse>
				<verse number="14">አይ​ችም ተነ​ሣሁ፤ ታላ​ላ​ቆ​ቹ​ንና ሹሞ​ቹ​ንም፥ የቀ​ሩ​ት​ንም ሕዝብ፥ “አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው፤ ታላ​ቁ​ንና የተ​ፈ​ራ​ውን አም​ላ​ካ​ች​ንን አስቡ፤ ስለ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁም፥ ስለ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም፥ ስለ ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁም፥ ስለ ቤቶ​ቻ​ች​ሁም ተዋጉ” አል​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንም እንደ ዐወ​ቅ​ን​ባ​ቸው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምክ​ራ​ቸ​ውን ከንቱ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሰሙ፤ እኛም ሁላ​ችን ወደ ቅጥሩ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችን ወደ ሥራ​ችን ተመ​ለ​ስን።</verse>
				<verse number="16">ከዚ​ያም ቀን ጀምሮ እኩ​ሌ​ቶቹ ብላ​ቴ​ኖች ሥራ ይሠሩ ነበር፤ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም ጋሻና ጦር፥ ቀስ​ትና ጥሩ​ርም ይዘው በፊ​ትና በኋላ ይጠ​ብቁ ነበር፤ አለ​ቆ​ቹም ከይ​ሁዳ ቤት ሁሉ በኋላ ይቆሙ ነበር።</verse>
				<verse number="17">ቅጥ​ሩ​ንም የሚ​ሠ​ሩ​ትና ሸክም ተሸ​ካ​ሚ​ዎቹ በአ​ንድ እጃ​ቸው ይሠሩ ነበር፤ በአ​ንድ እጃ​ቸ​ውም የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይይዙ ነበር።</verse>
				<verse number="18">አና​ጢ​ዎ​ቹም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰይ​ፉን በወ​ገቡ ታጥቆ ይሠራ ነበር፤ ቀንደ መለ​ከ​ትም የሚ​ነፋ በአ​ጠ​ገቤ ነበረ።</verse>
				<verse number="19">ታላ​ላ​ቆ​ቹ​ንና ሹሞ​ቹን፥ የቀ​ሩ​ት​ንም ሕዝብ፥ “ሥራው ታላ​ቅና ሰፊ ነው፤ እኛም በቅ​ጥሩ ላይ ተበ​ታ​ት​ነ​ናል፤ አን​ዱም ከሁ​ለ​ተ​ኛው ርቆ​አል፤</verse>
				<verse number="20">የቀ​ንደ መለ​ከ​ቱን ድምፅ ወደ​ም​ት​ሰ​ሙ​በት ስፍራ ወደ​ዚያ ወደ እኛ ተሰ​ብ​ሰቡ፤ አም​ላ​ካ​ችን ስለ እኛ ይዋ​ጋል” አል​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">ሥራ​ው​ንም እን​ሠራ ነበር፤ ከማ​ለዳ ወገ​ግ​ታም ጀምሮ ከዋ​ክ​ብት እስ​ኪ​ወጡ ድረስ እኩ​ሌ​ቶቹ ጦር ይይዙ ነበር።</verse>
				<verse number="22">ደግ​ሞም በዚያ ጊዜ ሕዝ​ቡን፥ “ሁላ​ችሁ ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቻ​ችሁ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ እደሩ፤ በሌ​ሊ​ትም ጠባ​ቂ​ዎች ሁኑ​ልን፤ በቀ​ንም ሥሩ” አል​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">እኔና ወን​ድ​ሞ​ችም፥ ብላ​ቴ​ኖ​ችም በኋ​ላ​ዬም የነ​በ​ሩት ጠባ​ቂ​ዎች ልብ​ሳ​ች​ንን አና​ወ​ል​ቅም ነበር። ወደ ውኃም ስን​ሄድ መሣ​ሪ​ያ​ች​ንን እን​ደ​ታ​ጠ​ቅን እን​ሄድ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም በአ​ይ​ሁድ ላይ ትልቅ የሕ​ዝ​ቡና የሚ​ስ​ቶ​ቻ​ቸው ጩኸት ሆነ።</verse>
				<verse number="2">“ከወ​ን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችን ጋር ብዙ​ዎች ነን፤ በል​ተ​ንም በሕ​ይ​ወት እን​ድ​ን​ኖር እህ​ልን እን​ሸ​ምት” የሚሉ ነበሩ።</verse>
				<verse number="3">“ከራብ የተ​ነ​ሣም እህ​ልን እን​ሸ​ምት ዘንድ እር​ሻ​ች​ን​ንና ወይ​ና​ች​ንን፥ ቤታ​ች​ን​ንም አስ​ይ​ዘ​ናል” የሚሉ ነበሩ።</verse>
				<verse number="4">ሌሎ​ቹም “ለን​ጉሡ ግብር እር​ሻ​ች​ን​ንና ወይ​ና​ች​ንን አስ​ይ​ዘን ገን​ዘብ ተበ​ድ​ረ​ናል፤</verse>
				<verse number="5">አሁ​ንም ሥጋ​ችን እንደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሥጋ፥ ልጆ​ቻ​ች​ንም እንደ ልጆ​ቻ​ቸው ናቸው፤ እነ​ሆም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችን ባሪ​ያ​ዎች ይሆኑ ዘንድ ሰጥ​ተ​ናል፤ ከሴ​ቶ​ችም ልጆ​ቻ​ችን ባሪ​ያ​ዎች ሆነው የሚ​ኖሩ አሉ፤ ታላ​ላ​ቆ​ችም እር​ሻ​ች​ን​ንና ወይ​ና​ች​ንን ይዘ​ዋ​ልና ልና​ድ​ና​ቸው አን​ች​ልም” የሚሉ ነበሩ።</verse>
				<verse number="6">እኔም ጩኸ​ታ​ቸ​ው​ንና ይህን ቃል በሰ​ማሁ ጊዜ እጅግ ዐዘ​ንሁ።</verse>
				<verse number="7">በል​ቤም አሰ​ብሁ፤ ታላ​ላ​ቆ​ቹ​ንና ሹሞ​ቹ​ንም፥ “ሁላ​ችሁ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ወለድ ትወ​ስ​ዳ​ላ​ችሁ” ብዬ ተጣ​ላ​ኋ​ቸው፤ ትል​ቅም ጉባኤ ሰበ​ሰ​ብ​ሁ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">እኔም፥ “ለአ​ሕ​ዛብ የተ​ሸ​ጡ​ትን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንን አይ​ሁ​ድን በፈ​ቃ​ዳ​ችን ተቤ​ዠን፤ እና​ን​ተስ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ትሸ​ጣ​ላ​ች​ሁን? እነ​ር​ሱስ ለእኛ የተ​ሸጡ ይሆ​ና​ሉን?” አል​ኋ​ቸው። እነ​ር​ሱም ዝም አሉ፤ መል​ስም አላ​ገ​ኙም።</verse>
				<verse number="9">ደግ​ሞም አልሁ፥ “የም​ታ​ደ​ር​ጉት ነገር መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ችን አሕ​ዛብ እን​ዳ​ይ​ሰ​ድ​ቡን አም​ላ​ካ​ች​ንን በመ​ፍ​ራት ትሄዱ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ች​ሁ​ምን?</verse>
				<verse number="10">እኔ ደግሞ፥ ወን​ድ​ሞ​ችም፥ ብላ​ቴ​ኖ​ችም ገን​ዘ​ብና እህል ለእ​ነ​ርሱ አበ​ድ​ረ​ናል፤ እባ​ካ​ችሁ፥ ይህን ወለድ እን​ተ​ው​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">እር​ሻ​ቸ​ውን፥ የወ​ይ​ና​ቸ​ው​ንና የወ​ይ​ራ​ቸ​ውን ቦታ፥ ቤታ​ቸ​ው​ንም፥ ከእ​ነ​ር​ሱም የወ​ሰ​ዳ​ች​ሁ​ትን ገን​ዘ​ቡ​ንና እህ​ሉን፥ ወይን ጠጁ​ንና ዘይ​ቱን እባ​ካ​ችሁ ዛሬ መል​ሱ​ላ​ቸው።”</verse>
				<verse number="12">እነ​ር​ሱም፥ “እን​መ​ል​ስ​ላ​ቸ​ዋ​ለን፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ምንም አን​ሻም፤ እን​ደ​ተ​ና​ገ​ርህ እን​ዲሁ እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አሉ። ካህ​ና​ቱ​ንም ጠርቼ እን​ደ​ዚህ ነገር ያደ​ርጉ ዘንድ አማ​ል​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">ደግ​ሞም ልብ​ሴን አራ​ገ​ፍ​ሁና፥ “ይህን ነገር የማ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ሰው ከቤ​ቱና ከሥ​ራው እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያራ​ግ​ፈው፤ እን​ዲሁ የተ​ራ​ገ​ፈና ባዶ ይሁን” አልሁ። ጉባ​ኤ​ውም ሁሉ፥ “አሜን” አሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገኑ፤ ሕዝ​ቡም እን​ደ​ዚህ ነገር አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="14">ንጉ​ሡም በይ​ሁዳ ምድር ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ካዘ​ዘኝ ጊዜ ጀምሮ ከን​ጉሡ ከአ​ር​ተ​ሰ​ስታ ከሃ​ያ​ኛው ዓመት እስከ ሠላሳ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት ድረስ ዐሥራ ሁለት ዓመት ያህል እኔና ወን​ድ​ሞች ለአ​ለቃ የሚ​ገ​ባ​ውን ቀለብ አል​በ​ላ​ንም።</verse>
				<verse number="15">ከእኔ አስ​ቀ​ድ​መው የነ​በ​ሩት አለ​ቆች ግን በሕ​ዝቡ ላይ አክ​ብ​ደው ነበር፤ ስለ እን​ጀ​ራ​ውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወ​ስዱ ነበር፤ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ በሕ​ዝቡ ላይ ይሰ​ለ​ጥኑ ነበር። እኔ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ፈራሁ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ግ​ሁም።</verse>
				<verse number="16">ደግ​ሞም የቅ​ጥ​ሩን ሥራ ሠራሁ፤ እር​ሻም አል​ገ​ዛ​ሁም፤ ብላ​ቴ​ኖ​ችም ሁሉ ወደ​ዚ​ያው ወደ ሥራው ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="17">ደግ​ሞም በዙ​ሪ​ያ​ችን ካሉት አሕ​ዛብ ወደ እኛ ከመ​ጡት ሌላ ከአ​ይ​ሁ​ድና ከሹ​ሞቹ መቶ አምሳ ሰዎች በገ​በ​ታዬ ነበሩ።</verse>
				<verse number="18">ለአ​ንድ ቀን አንድ በሬና ስድ​ስት የሰቡ በጎች፥ አንድ ፍየ​ልም፥ በዐ​ሥር በዐ​ሥር ቀንም ብዙ ልዩ ልዩ ዓይ​ነት ወይን ጠጅ ይዘ​ጋ​ጅ​ልኝ ነበር፤ ነገር ግን አገ​ዛዝ በሕ​ዝቡ ላይ ከብዶ ነበ​ርና ለአ​ለቃ የሚ​ገ​ባ​ውን ቀለብ አል​ሻም ነበር።</verse>
				<verse number="19">አም​ላኬ ሆይ፥ ለዚህ ሕዝብ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ሁሉ ለበ​ጎ​ነት አስ​ብ​ልኝ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ቅጥ​ሩን እንደ ሠራሁ፥ ከፍ​ራ​ሹም አን​ዳች እን​ዳ​ል​ቀ​ረ​በት ሰን​ባ​ላ​ጥና ጦቢያ ዓረ​ባ​ዊ​ውም ጌሳም የቀ​ሩ​ትም ጠላ​ቶ​ቻ​ችን ሰሙ፤ ነገር ግን እስ​ከ​ዚያ ጊዜ ድረስ በበ​ሮቹ ውስጥ ሳን​ቃ​ዎ​ቹን አላ​ቆ​ም​ሁም ነበር።</verse>
				<verse number="2">ሰን​ባ​ላ​ጥና ጌሳም፥ “መጥ​ተህ በኦኖ ቈላ ውስጥ ባሉት መን​ደ​ሮች እን​ገ​ናኝ” ብለው ላኩ​ብኝ፤ ነገር ግን ክፉ ያደ​ር​ጉ​ብኝ ዘንድ ይመ​ክሩ ነበር።</verse>
				<verse number="3">እኔም እን​ዲህ ስል መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላክ​ሁ​ባ​ቸው፥ “እኔ ታላቅ ሥራ እሠ​ራ​ለሁ፤ እወ​ር​ድም ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ኝም። ስለ​ምን ወደ እና​ንተ በመ​ም​ጣ​ቴና በመ​ው​ረዴ ሥራው ይታ​ጐ​ላል? ሥራ​ውን እንደ ፈጸ​ምሁ እመ​ጣ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="4">እን​ዲ​ህም ቃል አራት ጊዜ ላኩ​ብኝ፤ እኔም እንደ ፊተ​ኛው ቃል መለ​ስ​ሁ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">ሰን​ባ​ላ​ጥም እንደ ፊተ​ኛው ብላ​ቴ​ና​ውን አም​ስ​ተኛ ጊዜ ላከ​ብኝ፤ በእ​ጁም ውስጥ እን​ዲህ የሚል ግልጥ ደብ​ዳቤ ነበረ፦</verse>
				<verse number="6">“አን​ተና አይ​ሁድ ዓመፃ እን​ድ​ታ​ስቡ፥ ስለ​ዚ​ህም ቅጥ​ሩን እን​ድ​ት​ሠራ፥ ንጉ​ሣ​ቸ​ውም ትሆን ዘንድ እን​ድ​ት​ወ​ድድ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ተሰ​ም​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="7">ደግ​ሞም፦ ንጉሥ በይ​ሁዳ አለ ብለው ስለ አንተ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይና​ገሩ ዘንድ ነቢ​ያ​ትን አቁ​መ​ሃል፤ አሁ​ንም ለን​ጉሡ ይህን ቃል ያወ​ሩ​ለ​ታል፤ እን​ግ​ዲህ መጥ​ተህ በአ​ን​ድ​ነት እን​ማ​ከር።”</verse>
				<verse number="8">እኔም፥ “አንተ ከል​ብህ ፈጥ​ረ​ኸ​ዋል እንጂ እንደ ተና​ገ​ር​ኸው ነገር አይ​ደ​ለም” ብዬ ላክ​ሁ​በት።</verse>
				<verse number="9">እነ​ር​ሱም ሁሉ ሥራው እን​ዳ​ይ​ፈ​ጸም፥ “እጃ​ቸው ይደ​ክ​ማል” ብለው አስ​ፈ​ራ​ሩን፤ ስለ​ዚ​ህም እጆ​ችን አበ​ረ​ታሁ።</verse>
				<verse number="10">እኔም ወደ መሔ​ጣ​ብ​ኤል ልጅ ወደ ዶልያ ልጅ ወደ ሴሜይ ቤት ገባሁ፤ እር​ሱም ተዘ​ግቶ ነበ​ርና፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ እን​ግባ፤ የመ​ቅ​ደ​ሱ​ንም ደጆች እን​ዝጋ፤ እነ​ርሱ በሌ​ሊት ይገ​ድ​ሉህ ዘንድ ይመ​ጣ​ሉና” አለኝ።</verse>
				<verse number="11">እኔም፥ “እንደ እኔ ያለ ሰው የሸ​ሸና፥ ነፍ​ሱ​ንስ ያድን ዘንድ ወደ መቅ​ደስ የገባ ማን ነው? እኔስ አል​ገ​ባም” አል​ሁት።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልኮት እን​ዳ​ል​ነ​በረ፥ በእኔ ላይ ግን ትን​ቢት እንደ ተና​ገረ፥ እነሆ፥ ዐወ​ቅሁ፤ ጦብ​ያና ሰን​ባ​ላ​ጥም ገዝ​ተ​ውት ነበር።</verse>
				<verse number="13">ይህ​ንም ነገር አደ​ር​ግና እበ​ድል ዘንድ፥ በእ​ኔም ላይ ክፋት እን​ዲ​ና​ገ​ሩና እን​ዲ​ያ​ላ​ግጡ ያስ​ፈ​ራ​ራኝ ዘንድ ተገ​ዝቶ ነበር።</verse>
				<verse number="14">አም​ላኬ ሆይ፥ ስለ​ዚህ ሥራ​ቸው ጦቢ​ያ​ንና ሰን​ባ​ላ​ጥን፥ ነቢ​ይ​ቱ​ንም ኖዓ​ድ​ያን ያስ​ፈ​ራ​ሩኝ ዘንድ የፈ​ለ​ጉ​ትን፥ የቀ​ሩ​ት​ንም ነቢ​ያት አስብ።</verse>
				<verse number="15">ቅጥ​ሩም በኤ​ሉል ወር በሃያ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን በአ​ምሳ ሁለት ቀን ውስጥ ተጨ​ረሰ።</verse>
				<verse number="16">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ችን ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ በዙ​ሪ​ያ​ችን የነ​በሩ አሕ​ዛብ ሁሉ ፈሩ፤ አይ​ተ​ውም እጅግ ተደ​ና​ገጡ፤ ይህም ሥራ በአ​ም​ላ​ካ​ችን እንደ ተፈ​ጸመ አወቁ።</verse>
				<verse number="17">በዚ​ያም ወራት ብዙ የይ​ሁዳ አለ​ቆች ወደ ጦብያ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ችን ይልኩ ነበር፤ የጦ​ብ​ያም ደብ​ዳ​ቤ​ዎች ወደ እነ​ርሱ ይመጡ ነበር።</verse>
				<verse number="18">ጦብያ የአ​ራሄ ልጅ የሴ​ኬ​ንያ አማች ስለ ነበረ፥ ልጁም ዮሐ​ናን የቤ​ራ​ክ​ያን ልጅ የሜ​ሱ​ላ​ምን ሴት ልጅ ስላ​ገባ፥ በይ​ሁዳ ብዙ ሰዎች ከእ​ርሱ ጋር ተማ​ም​ለው ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="19">ደግ​ሞም በፊቴ ስለ እርሱ መል​ካ​ም​ነት ይና​ገሩ ነበር፤ የእ​ር​ሱን ነገር ወደ እኔ ያመጡ ነበር፤ የእ​ኔ​ንም ቃል ወደ እርሱ ይወ​ስዱ ነበር፤ ጦቢ​ያም ሊያ​ስ​ፈ​ራ​ራኝ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ችን ይልክ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ቅጥሩ ከተ​ሠራ በኋላ፥ ሳን​ቃ​ዎ​ቹን አቆ​ምሁ፤ በረ​ኞ​ቹ​ንና መዘ​ም​ራ​ኑን፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም ሾምሁ፤</verse>
				<verse number="2">ወን​ድ​ሜን ሃና​ኒ​ንና የግ​ን​ቡን አለቃ ሐና​ን​ያ​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ሾም​ኋ​ቸው፤ እር​ሱም እው​ነ​ተኛ ከሌ​ሎ​ቹም ይልቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው ነበረ።</verse>
				<verse number="3">እኔም፥ “ፀሐይ እስ​ኪ​ሞቅ ድረስ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሮች አይ​ከ​ፈቱ፤ እነ​ር​ሱም ቆመው ሳሉ ደጆ​ቹን ይዝጉ፤ ይቈ​ል​ፉም፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሰዎች አን​ዳ​ን​ዱን በየ​ተ​ራው፥ አን​ዳ​ን​ዱ​ንም በየ​ቤቱ አን​ጻር ጠባ​ቂ​ዎ​ችን አስ​ቀ​ምጡ” አል​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ከተ​ማ​ዪ​ቱም ሰፊና ታላቅ ነበ​ረች፤ በው​ስ​ጥዋ የነ​በሩ ሕዝብ ግን ጥቂ​ቶች ነበሩ፤ ቤቶ​ቹም ገና አል​ተ​ሠ​ሩም ነበር።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታላ​ላ​ቆ​ቹ​ንና ሹሞ​ቹን፥ ሕዝ​ቡ​ንም ሰብ​ስቤ በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው እቈ​ጥ​ራ​ቸው ዘንድ ልቤን አነ​ሣሣ፤ አስ​ቀ​ድ​መው የመ​ጡ​ት​ንም ሰዎች የት​ው​ልድ መጽ​ሐ​ፋ​ቸ​ውን አገ​ኘሁ፤ በእ​ር​ሱም እን​ደ​ዚህ ተጽፎ አገ​ኘሁ።</verse>
				<verse number="6">የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከማ​ረ​ካ​ቸው ምር​ኮ​ኞች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየ​ከ​ተ​ማ​ቸው የተ​መ​ለ​ሱት የሀ​ገር ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="7">ከዘ​ሩ​ባ​ቤል፥ ከኢ​ያሱ፥ ከነ​ህ​ምያ፥ ከአ​ዛ​ር​ያስ፥ ከረ​ዓ​ምያ፥ ከሄ​ሜ​ኔስ፥ ከመ​ር​ዶ​ክ​ዮስ፥ ከበ​ል​ሰማ፥ ከሚ​ስ​ፌ​ሬት፥ ከዕ​ዝራ፥ ከበ​ጉ​ዋይ፥ ከነ​ሑም፥ ከበ​ዓና፥ ከመ​ስ​ፈር ጋር መጡ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕዝብ የወ​ን​ዶች ቍጥር ይህ ነው፥</verse>
				<verse number="8">የፋ​ሮስ ልጆች ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሰባ ሁለት።</verse>
				<verse number="9">የሰ​ፋ​ጥ​ያስ ልጆች ሦስት መቶ ሰባ ሁለት።</verse>
				<verse number="10">የኤራ ልጆች ስድ​ስት መቶ አምሳ ሁለት።</verse>
				<verse number="11">ከኢ​ያ​ሱና ከኢ​ዮ​አብ ልጆች የሆኑ የፈ​ሐት ሞዓብ ልጆች ሁለት ሺህ ስም​ንት መቶ ዐሥራ ስም​ንት።</verse>
				<verse number="12">የኤ​ላም ልጆች ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት።</verse>
				<verse number="13">የዘ​ቱዕ ልጆች ስም​ንት መቶ አርባ አም​ስት።</verse>
				<verse number="14">የዘ​ካይ ልጆች ሰባት መቶ ስድሳ።</verse>
				<verse number="15">የበ​ኑይ ልጆች ስድ​ስት መቶ አርባ ስም​ንት።</verse>
				<verse number="16">የቤ​ባይ ልጆች ስድ​ስት መቶ ሃያ ስም​ንት።</verse>
				<verse number="17">የአ​ዝ​ጌድ ልጆች ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ሃያ ሁለት።</verse>
				<verse number="18">የአ​ዶ​ኒ​ቃም ልጆች ስድ​ስት መቶ ስድሳ ሰባት።</verse>
				<verse number="19">የበ​ጉ​ዋይ ልጆች ሁለት ሺህ ስድሳ ሰባት።</verse>
				<verse number="20">የዓ​ዴን ልጆች ስድ​ስት መቶ አምሳ አም​ስት።</verse>
				<verse number="21">የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ወገን የአ​ጤር ልጆች ዘጠና ስም​ንት።</verse>
				<verse number="22">የሐ​ሱም ልጆች ሦስት መቶ ሃያ ስም​ንት።</verse>
				<verse number="23">የቤ​ሳይ ልጆች ሦስት መቶ ሃያ አራት።</verse>
				<verse number="24">የሐ​ሪፍ ልጆች መቶ ዐሥራ ሁለት።</verse>
				<verse number="25">የገ​ባ​ዖን ልጆች ዘጠና አም​ስት።</verse>
				<verse number="26">የቤተ ልሔ​ምና የነ​ጦ​ፍያ ሰዎች መቶ ሰማ​ንያ ስም​ንት።</verse>
				<verse number="27">የዓ​ና​ቶት ሰዎች መቶ ሃያ ስም​ንት።</verse>
				<verse number="28">የቤ​ት​አ​ዝ​ሞት ሰዎች አርባ ሁለት።</verse>
				<verse number="29">የቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪ​ምና የቃ​ፌር፥ የቤ​ሮ​ትም ሰዎች ሰባት መቶ አርባ ሦስት።</verse>
				<verse number="30">የሐ​ራ​ማና የገ​ቢኣ ሰዎች ስድ​ስት መቶ ሃያ አንድ።</verse>
				<verse number="31">የማ​ኬ​ማስ ሰዎች መቶ ሃያ ሁለት።</verse>
				<verse number="32">የቤ​ቴ​ልና የጋይ ሰዎች መቶ ሃያ ሦስት።</verse>
				<verse number="33">የና​ብያ ሰዎች መቶ አምሳ ሁለት።</verse>
				<verse number="34">የኤ​ላም ሰዎች ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት።</verse>
				<verse number="35">የኤ​ራም ልጆች ሦስት መቶ ሃያ።</verse>
				<verse number="36">የኢ​ያ​ሪኮ ልጆች ሦስት መቶ አርባ አም​ስት።</verse>
				<verse number="37">የሎ​ድና ሐዲድ የሐ​ኖም ልጆች ሰባት መቶ ሃያ አንድ።</verse>
				<verse number="38">የሴ​ናዓ ልጆች ሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ።</verse>
				<verse number="39">ካህ​ናቱ ከኢ​ያሱ ወገን፦ የዮ​ዳሔ ልጆች ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት።</verse>
				<verse number="40">የኤ​ሜር ልጆች ሺህ አምሳ ሁለት።</verse>
				<verse number="41">የፋ​ስ​ኮር ልጆች ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት።</verse>
				<verse number="42">የሐ​ራም ልጆች ሺህ ዐሥራ ሰባት።</verse>
				<verse number="43">ሌዋ​ው​ያ​ኑም ከሆ​ዳ​ይዋ ወገን የኢ​ያ​ሱና የቀ​ድ​ም​ኤል ልጆች ሰባ አራት።</verse>
				<verse number="44">መዘ​ም​ራኑ የአ​ሳፍ ልጆች መቶ አርባ ስም​ንት።</verse>
				<verse number="45">በረ​ኞቹ የሴ​ሎ​ምያ ልጆች፥ የአ​ጤር ልጆች፥ የጤ​ል​ማና ልጆች፥ የዓ​ቁብ ልጆች፥ የሐ​ጢጣ ልጆች፥ የሶ​ባይ ልጆች መቶ አርባ ስም​ንት።</verse>
				<verse number="46">ናታ​ኒም የሲአ ልጆች፥ የሐ​ሡፋ ልጆች፥ የጠ​ብ​ዓት ልጆች፤</verse>
				<verse number="47">የቄ​ራስ ልጆች፥ የአ​ሲያ ልጆች፥ የፋ​ዶን ልጆች፤</verse>
				<verse number="48">የል​ባና ልጆች፥ የአ​ጋባ ልጆች፥ የሰ​ል​ማይ ልጆች፤</verse>
				<verse number="49">የሐ​ናን ልጆች፥ የጌ​ዴል ልጆች፥ የጋ​ኤር ልጆች፤</verse>
				<verse number="50">የር​አያ ልጆች፥ የረ​አ​ሶን ልጆች፥ የኔ​ቆዳ ልጆች፤</verse>
				<verse number="51">የጋ​ሴም ልጆች፥ የኡዚ ልጆች፥ የፋ​ሴሓ ልጆች፤</verse>
				<verse number="52">የቤ​ሳይ ልጆች፥ የም​ዑ​ና​ው​ያን ልጆች፥ የኔ​ፋ​ሴ​ስም ልጆች፤</verse>
				<verse number="53">የበ​ቅ​ቡቅ ልጆች፥ የሐ​ቀፋ ልጆች፥ የሐ​ሩር ልጆች፤</verse>
				<verse number="54">የበ​ስ​ሎት ልጆች፥ የም​ሒዳ ልጆች፥ የሐ​ርሳ ልጆች፤</verse>
				<verse number="55">የበ​ር​ቆስ ልጆች፥ የሲ​ሣራ ልጆች፥ የታ​ማህ ልጆች፥</verse>
				<verse number="56">የነ​ስያ ልጆች፥ የሐ​ጤፋ ልጆች።</verse>
				<verse number="57">የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ልጆች፤ የሦ​ጠይ ልጆች፥ የሰ​ፋ​ሬት ልጆች፥ የፈ​ሪዳ ልጆች፥</verse>
				<verse number="58">የየ​ዕላ ልጆች፥ የደ​ር​ቆን ልጆች፥ የጌ​ዴል ልጆች፤</verse>
				<verse number="59">የሰ​ፋ​ጥ​ያስ ልጆች፥ የሐ​ጢል ልጆች፥ የፈ​ከ​ራት ልጆች፥ የሰ​ባ​ይም ልጆች፥ የአ​ሞን ልጆች።</verse>
				<verse number="60">ናታ​ኒም ሁሉና የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ።</verse>
				<verse number="61">ከቲ​ል​ሜል፥ ከቲ​ላ​ሬስ፥ ከኪ​ሩብ፥ ከአ​ዶን፥ ከኢ​ሜር የወጡ እነ​ዚህ ናቸው፤ ነገር ግን የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ቤቶ​ችና ዘራ​ቸ​ውን ወይም ከእ​ስ​ራ​ኤል ወገን መሆ​ና​ቸ​ውን ያስ​ታ​ውቁ ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤</verse>
				<verse number="62">የዳ​ላያ ልጆች፥ የጦ​ብያ ልጆች፥ የኔ​ቆዳ ልጆች ስድ​ስት መቶ አርባ ሁለት።</verse>
				<verse number="63">ከካ​ህ​ና​ቱም የአ​ብያ ልጆች፥ የአ​ቆስ ልጆች፥ ከገ​ለ​ዓ​ዳ​ዊው ከቤ​ር​ዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ፥ በስ​ሙም የተ​ጠራ የቤ​ር​ዜሊ ልጆች።</verse>
				<verse number="64">እነ​ዚህ በት​ው​ልድ መጽ​ሐፍ ትው​ል​ዳ​ቸ​ውን ፈለጉ፤ ነገር ግን አል​ተ​ገ​ኘም፤ ከክ​ህ​ነ​ትም ተከ​ለ​ከሉ።</verse>
				<verse number="65">ሐቴ​ር​ሰ​ታም፥ “በኡ​ሪ​ምና በቱ​ሚም የሚ​ፈ​ርድ ካህን እስ​ኪ​ነሣ ድረስ ከተ​ቀ​ደ​ሰው ነገር አት​በ​ሉም” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="66">ጉባ​ኤ​ውም ሁሉ አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ ነበሩ፤</verse>
				<verse number="67">ይኸ​ውም ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ከነ​በሩ ከሎ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውና ከገ​ረ​ዶ​ቻ​ቸው ሌላ ሁለት መቶም አርባ አም​ስት ወን​ዶች መዘ​ም​ራ​ንና ሴቶች መዘ​ም​ራት ነበ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="68">ፈረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ሰባት መቶ ሠላሳ ስድ​ስት፥ በቅ​ሎ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ሁለት መቶ አርባ አም​ስት፤</verse>
				<verse number="69">ግመ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም አራት መቶ ሠላሳ አም​ስት፥ አህ​ዮ​ቻ​ቸ​ውም ስድ​ስት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ ነበሩ።</verse>
				<verse number="70">ከአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆ​ችም ስለ ሥራው ስጦታ ሰጡ። ሐቴ​ር​ሰ​ታም አንድ ሺህ የወ​ርቅ ዳሪክ፥ አም​ሳም ድስ​ቶች፥ አም​ስት መቶ ሠላ​ሳም የካ​ህ​ናት ልብስ በቤተ መዛ​ግ​ብት ውስጥ ሰጠ።</verse>
				<verse number="71">ከአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆ​ችም ዐያ​ሌ​ዎቹ በሥ​ራው ቤተ መዛ​ግ​ብት ውስጥ ሃያ ሺህ የወ​ርቅ ዳሪክ፥ ሁለት ሺህ ሁለት መቶም ምናን ብር ሰጡ።</verse>
				<verse number="72">የቀ​ሩ​ትም ሕዝብ የሰ​ጡት ሃያ ሺህ የወ​ርቅ ዳሪ​ክና ሁለት ሺህ ምናን ብር፥ ስድሳ ሰባ​ትም የካ​ህ​ናት ልብስ ነበረ።</verse>
				<verse number="73">ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ በረ​ኞ​ቹና መዘ​ም​ራ​ኑም፥ ከሕ​ዝ​ቡም ዐያ​ሌ​ዎቹ፥ ናታ​ኒ​ምም፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ተቀ​መጡ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">ሰባ​ተ​ኛ​ውም ወር በደ​ረሰ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ነበሩ። ሕዝ​ቡም ሁሉ በው​ኃው በር ፊት ወዳ​ለው አደ​ባ​ባይ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእ​ስ​ራ​ኤል ያዘ​ዘ​ውን የሙ​ሴን ሕግ መጽ​ሐፍ ያመጣ ዘንድ ጸሓ​ፊ​ውን ዕዝ​ራን ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="2">ካህ​ኑም ዕዝራ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ሕጉን በወ​ን​ዶ​ችና በሴ​ቶች ጉባኤ፥ አስ​ተ​ው​ለ​ውም በሚ​ሰ​ሙት ሁሉ ፊት አመ​ጣው።</verse>
				<verse number="3">በው​ኃ​ውም በር ፊት ባለው አደ​ባ​ባይ ላይ ቆሞ፥ በወ​ን​ዶ​ችና በሴ​ቶች በሚ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉ​ትም ፊት፥ ከማ​ለዳ ጀምሮ እስከ ቀትር ድረስ አነ​በ​በው፤ የሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ጆሮ የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ ለመ​ስ​ማት ያደ​ምጥ ነበር።</verse>
				<verse number="4">ጸሓ​ፊ​ውም ዕዝራ ስለ​ዚህ ነገር በተ​ሠራ በዕ​ን​ጨት መረ​ባ​ርብ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአ​ጠ​ገቡ መቲ​ትያ፥ ሰምያ፥ ሐና​ንያ፤ ኦርያ፥ ሕል​ቅያ፥ መዕ​ሢያ በቀኙ በኩል፥ ፈድያ፥ ሚሳ​ኤል፥ ሚል​ክያ፥ ሐሱም፥ ሐስ​በ​ዳና፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ሜሱ​ላም በግ​ራው በኩል ቆመው ነበር።</verse>
				<verse number="5">ዕዝ​ራም የሕ​ዝቡ ሁሉ የበ​ላይ ነበ​ረና በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት መጽ​ሐ​ፉን ገለጠ፤ በገ​ለ​ጠ​ውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ።</verse>
				<verse number="6">ዕዝ​ራም ታላ​ቁን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገነ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ እጃ​ቸ​ውን እየ​ዘ​ረጉ፥ “አሜን፥ አሜን” ብለው መለሱ። ራሳ​ቸ​ው​ንም አዘ​ነ​በሉ፤ በግ​ን​ባ​ራ​ቸ​ውም ወደ ምድር ተደ​ፍ​ተው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገዱ።</verse>
				<verse number="7">ደግሞ ኢያ​ሱና ባኒ፥ ሰራ​ብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሳባ​ታይ፥ ሆዲያ፥ መዕ​ሤያ፥ ቆሊጣ፥ ዓዛ​ርያ፥ ኢዮ​ዛ​ባድ፥ ሐናን፥ ፌል​ዕያ፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ሕጉን ለሕ​ዝቡ ያስ​ተ​ምሩ ነበር፤ ሕዝ​ቡም በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸው ቆመው ነበር።</verse>
				<verse number="8">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሕግ መጽ​ሐፍ አነ​በቡ፤ ዕዝ​ራም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማወቅ ያስ​ተ​ም​ርና ያስ​ታ​ውቅ ነበር፤ ሕዝ​ቡም የሚ​ነ​በ​በ​ውን ያስ​ተ​ውሉ ነበር።</verse>
				<verse number="9">ሕቴ​ር​ሰታ ነህ​ም​ያም፥ ጸሓ​ፊ​ውም ካህኑ ዕዝራ፥ ሕዝ​ቡ​ንም የሚ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ሌዋ​ው​ያን ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ “ዛሬ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ቀን ነው፤ አት​ዘኑ፤ አታ​ል​ቅ​ሱም” አሉ​አ​ቸው፤ ሕዝቡ ሁሉ የሕ​ጉን ቃል በሰሙ ጊዜ ያለ​ቅሱ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="10">እር​ሱም፥ “ሂዱ፤ የሰ​ባ​ው​ንም ብሉ፤ ጣፋ​ጩ​ንም ጠጡ፤ ለእ​ነ​ዚ​ያም ምንም ለሌ​ላ​ቸው እድል ፈን​ታ​ቸ​ውን ላኩ፤ ዛሬ ለጌ​ታ​ችን የተ​ቀ​ደሰ ቀን ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይ​ላ​ችን ነውና አት​ዘኑ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ሌዋ​ው​ያ​ንም “ቀኑ የተ​ቀ​ደሰ ነውና ዝም በሉ፤ አት​ዘ​ኑም” እያሉ ሕዝ​ቡን ሁሉ ጸጥ ያደ​ርጉ ነበር።</verse>
				<verse number="12">ሕዝ​ቡም ሁሉ የተ​ነ​ገ​ራ​ቸ​ውን ቃል አስ​ተ​ው​ለ​ዋ​ልና ሊበ​ሉና ሊጠጡ፥ እድል ፈን​ታም ሊልኩ፥ ደስ​ታም ሊያ​ደ​ርጉ ሄዱ።</verse>
				<verse number="13">በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከሕ​ዝቡ ሁሉ የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች፥ ካህ​ና​ቱም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም የሕ​ጉን ቃል ይተ​ረ​ጕ​ም​ላ​ቸው ዘንድ ወደ ጸሓ​ፊው ወደ ዕዝራ ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="14">በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ባለው በዓል የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በዳስ ይቀ​መጡ ዘንድ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ይና​ገ​ሩና ያውጁ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ እን​ዳ​ዘዘ በሕጉ ውስጥ ተጽፎ አገኙ።</verse>
				<verse number="15">ዕዝ​ራም አላ​ቸው፥ “ወደ ተራራ ሂዱ፤ የዘ​ይ​ትና የበ​ረሃ ወይራ፥ የባ​ር​ሰ​ነ​ትም፥ የዘ​ን​ባ​ባም፥ የለ​መ​ለ​መ​ው​ንም ዛፍ ቅር​ን​ጫፍ አምጡ፤ እንደ ተጻ​ፈ​ውም ዳሶ​ችን ሥሩ።”</verse>
				<verse number="16">ሕዝ​ቡም ወጥ​ተው አመጡ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም በቤቱ ሰገ​ነት ላይ፥ በአ​ደ​ባ​ባ​ዩም ላይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አደ​ባ​ባይ ላይ፥ በው​ኃ​ውም በር አደ​ባ​ባ​ይና በኤ​ፍ​ሬም በር አደ​ባ​ባይ ላይ ዳስ ሠሩ።</verse>
				<verse number="17">ከም​ር​ኮም የተ​መ​ለ​ሱት ማኅ​በር ሁሉ ዳስ ሠሩ፤ በዳ​ሱም ውስጥ ተቀ​መጡ። ከነ​ዌም ልጅ ከኢ​ያሱ ዘመን ጀምሮ እስ​ከ​ዚያ ቀን ድረስ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ያለ አላ​ደ​ረ​ጉም ነበር። እጅ​ግም ታላቅ ደስታ ሆነ።</verse>
				<verse number="18">ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ቀን ጀምሮ እስከ መጨ​ረ​ሻው ቀን ድረስ ዕለት ዕለት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ መጽ​ሐፍ ያነ​ብብ ነበር። በዓ​ሉ​ንም ሰባት ቀን ያህል አደ​ረጉ፤ በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን እንደ ሕጋ​ቸው ወጡ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">በዚ​ህም ወር በሃያ አራ​ተ​ኛው ቀን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጾመው፥ ማቅም ለብ​ሰው፥ በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ ትቢያ ነስ​ን​ሰው ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="2">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከባ​ዕድ ሕዝብ ሁሉ ራሳ​ቸ​ውን ለዩ፤ ቆመ​ውም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንና የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ኀጢ​አት ተና​ዘዙ።</verse>
				<verse number="3">በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸ​ውም ቆመው የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሕግ መጽ​ሐፍ አነ​በቡ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተና​ዘዙ፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገዱ።</verse>
				<verse number="4">ሌዋ​ው​ያ​ኑም ኢያ​ሱና የቀ​ድ​ም​ኤል ልጆች፥ የሰ​ራ​ብያ ልጅ ሴኬ​ንያ፥ የከ​ናኒ ልጆ​ችም በደ​ረ​ጃ​ዎች ላይ ቆመው ወደ አም​ላ​ካ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በታ​ላቅ ድምፅ ጮኹ።</verse>
				<verse number="5">ሌዋ​ው​ያ​ኑም ኢያ​ሱና ቀድ​ም​ኤል፥ እን​ዲህ አሉ፥ “ቆማ​ችሁ ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ። የከ​በረ ስሙ​ንም አመ​ስ​ግኑ፤ በበ​ረ​ከ​ትና በም​ስ​ጋ​ናም ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አድ​ር​ጉት።”</verse>
				<verse number="6">ዕዝ​ራም እን​ዲህ አለ፥ “አንተ ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነህ፤ ሰማ​ዩ​ንና የሰ​ማ​ያት ሰማ​ይን፥ ሠራ​ዊ​ታ​ቸ​ው​ንም ሁሉ፥ ምድ​ር​ንና በእ​ር​ስዋ ላይ ያሉ​ትን ሁሉ፥ ባሕ​ሮ​ቹ​ንና በእ​ነ​ርሱ ውስጥ ያለ​ውን ሁሉ ፈጥ​ረ​ሃል፤ ሁሉ​ንም ሕያው አድ​ር​ገ​ኸ​ዋል፤ የሰ​ማ​ዩም ሠራ​ዊት ለአ​ንተ ይሰ​ግ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="7">አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነህ፤ አብ​ራ​ምን መረ​ጥህ፤ ከዑር ከላ​ው​ዴ​ዎ​ንም አወ​ጣ​ኸው፤ ስሙ​ንም አብ​ር​ሃም አል​ኸው፤</verse>
				<verse number="8">ልቡም በፊ​ትህ የታ​መነ ሆኖ አገ​ኘ​ኸው፤ የከ​ነ​ዓ​ና​ዊ​ው​ንና የኬ​ጤ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ የፌ​ር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ የኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ የጌ​ር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ምድር ለእ​ር​ሱና ለዘሩ ትሰጥ ዘንድ ከእ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረ​ግህ፤ አን​ተም ጻድቅ ነህና ቃል​ህን አጸ​ናህ።</verse>
				<verse number="9">“በግ​ብ​ጽም ሳሉ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንን መከራ አየህ፤ በኤ​ር​ትራ ባሕ​ርም ሳሉ ጩኸ​ታ​ቸ​ውን ሰማህ፤</verse>
				<verse number="10">እንደ ታበ​ዩ​ባ​ቸ​ውም ዐው​ቀህ ነበ​ርና በፈ​ር​ዖ​ንና በባ​ሪ​ያ​ዎቹ ሁሉ፥ በም​ድ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ላይ ምል​ክ​ት​ንና ተአ​ም​ራ​ትን አሳ​የህ፤ ዛሬም እንደ ሆነው ስም​ህን አስ​ጠ​ራህ።</verse>
				<verse number="11">ከፊ​ታ​ቸ​ውም ባሕ​ሩን ከፈ​ልህ፤ በባ​ሕ​ሩም መካ​ከል በደ​ረቅ ዐለፉ፤ የተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውን ግን ድን​ጋይ በጥ​ልቅ ውኃ እን​ዲ​ጣል በቀ​ላይ ውስጥ ጣል​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መን​ገድ ታበ​ራ​ላ​ቸው ዘንድ ቀን በደ​መና ዐምድ፥ ሌሊ​ትም በእ​ሳት ዐምድ መራ​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">ወደ ሲናም ተራራ ወረ​ድህ፤ ከሰ​ማ​ይም ተና​ገ​ር​ሃ​ቸው፤ ቅኑን ፍር​ድና እው​ነ​ቱን ሕግ፥ መል​ካ​ሙ​ንም ሥር​ዐ​ትና ትእ​ዛዝ ሰጠ​ሃ​ቸው፤</verse>
				<verse number="14">የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ሰን​በ​ት​ህን አስ​ታ​ወ​ቅ​ሃ​ቸው፤ ትእ​ዛ​ዝ​ንና ሥር​ዐ​ትን፥ ሕግ​ንም በባ​ሪ​ያህ በሙሴ እጅ አዘ​ዝ​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">ለራ​ባ​ቸ​ውም ከሰ​ማይ እን​ጀ​ራን ሰጠ​ሃ​ቸው፤ ለጥ​ማ​ታ​ቸ​ውም ከዓ​ለቱ ውኃን አወ​ጣ​ህ​ላ​ቸው፤ ትሰ​ጣ​ቸ​ውም ዘንድ እጅ​ህን የዘ​ረ​ጋ​ህ​ባ​ትን ምድር ገብ​ተው ይወ​ር​ሷት ዘንድ አዘ​ዝ​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">“ነገር ግን እነ​ር​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ችን ታበዩ፤ አን​ገ​ታ​ቸ​ው​ንም አደ​ነ​ደኑ፤ ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንም አል​ሰ​ሙም፥</verse>
				<verse number="17">ለመ​ስ​ማ​ትም እንቢ አሉ፤ ያደ​ረ​ግ​ህ​ላ​ቸ​ው​ንም ተአ​ም​ራት አላ​ሰ​ቡም፤ አን​ገ​ታ​ቸ​ው​ንም አደ​ነ​ደኑ፤ ለባ​ር​ነ​ታ​ቸ​ውም ወደ ግብፅ ይመ​ለሱ ዘንድ አለ​ቃን ሾሙ፤ አንተ ግን መሓ​ሪና ይቅር ባይ አም​ላክ፥ ለቍ​ጣም የም​ት​ዘ​ገይ፥ ምሕ​ረ​ት​ንም የም​ታ​በዛ ነህ፤ አል​ተ​ው​ሃ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="18">ዳግ​መ​ኛም ቀልጦ የተ​ሠ​ራ​ውን እን​ቦሳ አድ​ር​ገው፦ ‘ከግ​ብፅ ያወ​ጡን አም​ላ​ኮ​ቻ​ችን እሊህ ናቸው’ አሉ፤ እጅ​ግም አስ​ቈ​ጡህ፤</verse>
				<verse number="19">አንተ ግን ምሕ​ረ​ትህ ብዙ ነውና በም​ድረ በዳ አል​ተ​ው​ሃ​ቸ​ውም፤ በመ​ን​ገ​ድም ይመ​ራ​ቸው ዘንድ የደ​መና ዓም​ድን በቀን፥ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መን​ገድ ያበ​ራ​ላ​ቸው ዘንድ የእ​ሳት ዓም​ድን በሌ​ሊት ከእ​ነ​ርሱ አላ​ራ​ቅ​ህም።</verse>
				<verse number="20">ያስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ውም ዘንድ መል​ካ​ሙን መን​ፈ​ስ​ህን ሰጠ​ሃ​ቸው፤ መና​ህ​ንም ከአ​ፋ​ቸው አል​ከ​ለ​ከ​ል​ህም፤ ለጥ​ማ​ታ​ቸ​ውም ውኃን ሰጠ​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">አርባ ዓመ​ትም በም​ድረ በዳ መገ​ብ​ሃ​ቸው፤ ምንም አላ​ሳ​ጣ​ሃ​ቸ​ውም፤ ልብ​ሳ​ቸ​ውም አላ​ረ​ጀም፤ እግ​ራ​ቸ​ውም አላ​በ​ጠም።</verse>
				<verse number="22">“መን​ግ​ሥ​ታ​ት​ንና አሕ​ዛ​ብን ዕድል ፈንታ አድ​ር​ገህ ሰጠ​ሃ​ቸው፤ የሐ​ሴ​ቦ​ንን ንጉሥ የሴ​ዎ​ንን ምድር፥ የባ​ሳ​ን​ንም ንጉሥ የዐ​ግን ምድር ወረሱ።</verse>
				<verse number="23">ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አበ​ዛህ፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ተና​ገ​ር​ህ​ላ​ቸው ምድር አገ​ባ​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">እነ​ር​ሱም ወረ​ሱ​አት፤ በከ​ነ​ዓን ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም ሰዎች በፊ​ታ​ቸው አጠ​ፋ​ሃ​ቸው፤ የሚ​ወ​ድ​ዱ​ት​ንም ነገር ያደ​ር​ጉ​ባ​ቸው ዘንድ እነ​ር​ሱ​ንና ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ የም​ድ​ሩ​ንም አሕ​ዛብ በእ​ጃ​ቸው አሳ​ል​ፈህ ሰጠ​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">ምሽ​ጎ​ቹ​ንም ከተ​ሞች፥ መል​ካ​ምን ነገር የሞ​ሉ​ትን ቤቶች፥ የተ​ማ​ሱ​ት​ንም ጕድ​ጓ​ዶች፥ የወ​ይ​ኖ​ቹ​ንና የወ​ይ​ራ​ዎ​ቹን ቦታ​ዎች፥ ብዙ​ዎ​ቹ​ንም የፍሬ ዛፎች ወረሱ፤ በሉም፤ ጠገ​ቡም፤ ወፈ​ሩም፤ በታ​ላቅ በጎ​ነ​ት​ህም ደስ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">“ነገር ግን ተመ​ል​ሰው ዐመ​ፁ​ብህ፤ ሕግ​ህ​ንም ወደ ኋላ​ቸው ጣሉት፤ ወደ አን​ተም ይመ​ለሱ ዘንድ የመ​ሰ​ከ​ሩ​ባ​ቸ​ውን ነቢ​ያ​ት​ህን ገደሉ፤ እጅ​ግም አስ​ቈ​ጡህ።</verse>
				<verse number="27">ስለ​ዚህ በሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸው ሰዎች እጅ አሳ​ል​ፈህ ሰጠ​ሃ​ቸው፤ አስ​ጨ​ነ​ቋ​ቸ​ውም፤ በመ​ከ​ራ​ቸ​ውም ጊዜ ወደ አንተ ጮኹ፤ ከሰ​ማ​ይም ሰማ​ሃ​ቸው፤ እንደ ምሕ​ረ​ት​ህም ብዛት ታዳ​ጊ​ዎ​ችን ሰጠ​ሃ​ቸው፤ ከሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸ​ውም እጅ አዳ​ን​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="28">ባረ​ፉም ጊዜ ተመ​ል​ሰው በፊ​ትህ ክፉ አደ​ረጉ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅ ተው​ሃ​ቸው፤ ገዙ​አ​ቸ​ውም፤ ተመ​ል​ሰ​ውም ወደ አንተ በጮኹ ጊዜ ከሰ​ማይ ሰማ​ሃ​ቸው፤ እንደ ምሕ​ረ​ት​ህም ብዛት ታደ​ግ​ሃ​ቸው፤</verse>
				<verse number="29">ወደ ሕግ​ህም ትመ​ል​ሳ​ቸው ዘንድ አስ​መ​ሰ​ከ​ር​ህ​ባ​ቸው፤ ነገር ግን አል​ሰ​ሙ​ህም፤ ሰውም ባደ​ረ​ገው ጊዜ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንና ፍር​ድ​ህን ተላ​ለፉ፤ ጀር​ባ​ቸ​ውን ሰጡ፤ አን​ገ​ታ​ቸ​ው​ንም አደ​ነ​ደኑ፤ አል​ሰ​ሙ​ምም።</verse>
				<verse number="30">ነገር ግን ብዙ ዓመ​ታት ታገ​ሥ​ሃ​ቸው፤ በነ​ቢ​ያ​ት​ህም እጅ በመ​ን​ፈ​ስህ መሰ​ከ​ር​ህ​ባ​ቸው፤ አላ​ደ​መ​ጡም፤ ስለ​ዚ​ህም በም​ድር አሕ​ዛብ እጅ አሳ​ል​ፈህ ሰጠ​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="31">ነገር ግን አንተ ኀያል፥ ቸርና መሓሪ አም​ላክ ነህና በም​ሕ​ረ​ትህ ብዛት ፈጽ​መህ አላ​ጠ​ፋ​ሃ​ቸ​ውም፤ አል​ተ​ው​ሃ​ቸ​ው​ምም።</verse>
				<verse number="32">“አሁ​ንም አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ቃል ኪዳ​ን​ንና ምሕ​ረ​ትን የም​ት​ጠ​ብቅ ታላ​ቅና ኀያል ጽኑ​ዕና የተ​ፈ​ራ​ኸው አም​ላክ ሆይ፥ ከአ​ሦር ነገ​ሥ​ታት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ በእ​ኛና በነ​ገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ችን፥ በአ​ለ​ቆ​ቻ​ች​ንም፥ በካ​ህ​ና​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ በነ​ቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ በሕ​ዝ​ብህ ሁሉ ላይ የደ​ረ​ሰው መከራ ሁሉ በፊ​ትህ ጥቂት መስሎ አይ​ታ​ይህ።</verse>
				<verse number="33">በደ​ረ​ሰ​ብ​ንም ነገር ሁሉ አንተ ጻድቅ ነህ፤ አንተ እው​ነት አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ እኛም እጅግ በድ​ለ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="34">ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ችን፥ አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሕግ​ህን አል​ጠ​በ​ቁም፤ ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንና የመ​ሰ​ከ​ር​ህ​ባ​ቸ​ውን ምስ​ክ​ር​ህ​ንም አል​ሰ​ሙም።</verse>
				<verse number="35">በመ​ን​ግ​ሥ​ት​ህም በሰ​ጠ​ሃ​ቸው ታላቅ በጎ​ነ​ትህ፥ በፊ​ታ​ቸ​ውም በሰ​ጠ​ሃ​ቸው በሰ​ፊ​ውና በሰ​ባው ምድር አል​ተ​ገ​ዙ​ል​ህም፤ ከክ​ፉም ሥራ​ቸው አል​ተ​መ​ለ​ሱም።</verse>
				<verse number="36">እነሆ፥ ዛሬ ባሪ​ያ​ዎች ነን፤ ፍሬ​ዋ​ንና በረ​ከ​ቷን ይበሉ ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን በሰ​ጠ​ሃት ምድር እነሆ፥ በእ​ር​ስዋ ባሪ​ያ​ዎች ነን፥</verse>
				<verse number="37">ስለ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንም ለሾ​ም​ህ​ብን ነገ​ሥ​ታት በረ​ከ​ቷን ታበ​ዛ​ለች፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ን​ንም ይገ​ዛሉ፤ በእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ች​ንም የሚ​ወ​ድ​ዱ​ትን ያደ​ር​ጋሉ፤ እኛም በጽኑ መከራ ላይ ነን።</verse>
				<verse number="38">ስለ​ዚ​ህም ሁሉ የታ​መ​ነ​ውን ቃል ኪዳን አድ​ር​ገን እን​ጽ​ፋ​ለን፤ አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኖ​ቻ​ች​ንም፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ች​ንም ያት​ሙ​በ​ታል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">ያተ​ሙ​ትም እነ​ዚህ ናቸው፤ የሐ​ካ​ልያ ልጅ ሐቴ​ር​ሰታ ነህ​ምያ፥ ሴዴ​ቅ​ያስ፤</verse>
				<verse number="2">ኦርያ፥ ዓዛ​ርያ፥ ኤር​ም​ያስ፤</verse>
				<verse number="3">ፋሲ​ኩር፥ አማ​ርያ፥ ሚል​ክያ፤</verse>
				<verse number="4">ሐጡስ፥ ሰባ​ንያ፥ መሉክ፤</verse>
				<verse number="5">ካሪም፥ ሚራ​ሞት፥ አብ​ድያ፤</verse>
				<verse number="6">ዳን​ኤል፥ ገን​ቶን፥ ባሩክ፤</verse>
				<verse number="7">ሜሱ​ላም፥ አብ​ድያ፥ ሚያ​ሚን፤</verse>
				<verse number="8">መዓ​ዝያ፥ ቤል​ጋይ፥ ሰማያ፤ እነ​ዚህ ካህ​ናት ነበሩ።</verse>
				<verse number="9">ሌዋ​ው​ያ​ኑም የአ​ዛ​ንያ ልጅ ኢያሱ፥ ከኢ​ን​ሐ​ዳድ ልጆች ባንዩ፥ ቀዳ​ም​ኤል፤</verse>
				<verse number="10">ወን​ድ​ሞ​ቹም ሰባ​ንያ፥ ሆዲያ፥ ቆሊጣ፥ ፌል​ዕያ፥ ሐናን፤</verse>
				<verse number="11">ሚካ፥ ሬሆብ፥ ሐሳ​ብያ፤</verse>
				<verse number="12">ዘኩር፥ ሰራ​ብያ፥ ሰባ​ንያ፤</verse>
				<verse number="13">ሆድያ፥ ባኒ፥ ባኑን።</verse>
				<verse number="14">የሕ​ዝቡ አለ​ቆች ፋሮስ፥ ፈሐት ሞዓብ፥ ኤላም፥ ዛቱያ፥ ባኒ፤</verse>
				<verse number="15">ቡኒ፥ ዓዝ​ጋድ፥ ቤባይ፤</verse>
				<verse number="16">አዶ​ን​ያስ፥ በጉ​ዋይ፥ ዓዲን፤</verse>
				<verse number="17">አጤር፥ ሕዝ​ቅ​ያስ፥ ዓዙር፤</verse>
				<verse number="18">አሆ​ዲያ፥ ሐሱም፥ ቤሳይ፤</verse>
				<verse number="19">ሐሪፍ፥ ዓና​ቶት፥ ኖባይ፤</verse>
				<verse number="20">መግ​ፈ​አስ፥ ሜሱ​ላም፥ ኤዚር፤</verse>
				<verse number="21">ሜሴ​ዜ​ቤል፥ ሳዶቅ፥ ያዱአ፤</verse>
				<verse number="22">ፈላ​ጥያ፥ ሐናን፥ ዓናያ፤</verse>
				<verse number="23">ሆሴዕ፥ ሐና​ንያ፥ አሱብ፥</verse>
				<verse number="24">አሎ​ኤስ፥ ፈሊሃ፥ ሶቤቅ፤</verse>
				<verse number="25">ሬሁም፥ ሐሰ​ብና፥ መዕ​ሤያ፤</verse>
				<verse number="26">አሂያ፥ ሐናን፥ ዓናን፥፤</verse>
				<verse number="27">መሎክ፥ ሔራም፥ ባዕና።</verse>
				<verse number="28">የቀ​ሩ​ትም ሕዝብ፥ ካህ​ና​ቱም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ በረ​ኞ​ቹም፥ መዘ​ም​ራ​ንም፥ ናታ​ኒ​ምም፥ ከም​ድ​ርም አሕ​ዛብ ራሳ​ቸ​ውን የለ​ዩና ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ የገቡ ሁሉ፥ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም፥ የሚ​ያ​ው​ቁ​ትና የሚ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉ​ትም ሁሉ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንና ታላ​ላ​ቆ​ቻ​ቸ​ውን አበ​ረ​ታቱ፤</verse>
				<verse number="29">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባሪያ በሙሴ እጅ በተ​ሰ​ጠው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ሁሉ፥ ፍር​ዱ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ይጠ​ብ​ቁና ያደ​ርጉ ዘንድ ርግ​ማ​ን​ንና መሐ​ላን አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="30">ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ን​ንም ለም​ድር አሕ​ዛብ አን​ሰ​ጥም፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለል​ጆ​ቻ​ችን አን​ወ​ስ​ድም፤</verse>
				<verse number="31">የም​ድ​ር​ንም አሕ​ዛብ ሸቀ​ጥና ልዩ ልዩ እህል ሊገ​በዩ በሰ​ን​በት ቀን ቢያ​መጡ በሰ​ን​በት ወይም በተ​ቀ​ደ​ሰው ቀን ከእ​ነ​ርሱ አን​ገ​ዛም፤ ሰባ​ተ​ኛ​ው​ንም ዓመት እና​ከ​ብ​ራ​ለን፤ ከሰ​ውም ዕዳ ማስ​ከ​ፈ​ልን እን​ተ​ዋ​ለን።</verse>
				<verse number="32">ስለ አም​ላ​ካ​ች​ንም ቤት ሥራ ሁሉ በየ​ዓ​መቱ የሰ​ቅል ሢሶ እና​መጣ ዘንድ ሥር​ዐት በራ​ሳ​ችን ላይ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።</verse>
				<verse number="33">ስለ አም​ላ​ካ​ች​ንም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት፥ ስለ ኅብ​ስተ ገጽም፥ ዘወ​ት​ርም በሰ​ን​በ​ትና በመ​ባቻ ስለ ማቅ​ረብ ስለ እህሉ ቍር​ባ​ንና ስለ​ሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት፥ ስለ በዓ​ላ​ትም፥ ስለ ተቀ​ደ​ሱ​ትም ነገ​ሮች፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ስለ​ሚ​ያ​ስ​ተ​ሰ​ር​የው ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥</verse>
				<verse number="34">እኛም ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያኑ ሕዝ​ቡም፥ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ችን ቤቶች በተ​ወ​ሰነ ጊዜ በየ​ዓ​መቱ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት አም​ጥ​ተን በሕጉ እንደ ተጻፈ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ላይ ይቃ​ጠል ዘንድ ስለ ዕን​ጨት ቍር​ባን ዕጣ ተጣ​ጣ​ልን፤</verse>
				<verse number="35">በየ​ዓ​መ​ቱም የመ​ሬ​ታ​ች​ንን እህል ቀዳ​ም​ያት፥ የሁሉ ዓይ​ነት ዛፍ የፍሬ ቀዳ​ም​ያት ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እና​መጣ ዘንድ፥</verse>
				<verse number="36">በሕ​ጉም እንደ ተጻፈ የል​ጆ​ቻ​ች​ን​ንና የእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ች​ንን በኵ​ራት፥ የበ​ሬ​ዎ​ቻ​ች​ን​ንና የበ​ጎ​ቻ​ች​ንን በኵ​ራት በአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤት ወደ​ሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉት ካህ​ናት ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት እና​መጣ ዘንድ፥</verse>
				<verse number="37">የእ​ህ​ላ​ች​ን​ንም ቀዳ​ም​ያት፥ የዛ​ፉን ሁሉ ፍሬ፥ የወ​ይ​ኑ​ንና የዘ​ይ​ቱ​ንም ፍሬ ወደ ካህ​ናቱ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት ጓዳ​ዎች እና​መጣ ዘንድ፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ችን እርሻ ሁሉ ዐሥ​ራት ይቀ​በ​ላ​ሉና የመ​ሬ​ታ​ች​ንን ዐሥ​ራት ወደ ሌዋ​ው​ያን እና​መጣ ዘንድ ማልን።</verse>
				<verse number="38">ሌዋ​ው​ያ​ኑም ዐሥ​ራ​ቱን በተ​ቀ​በሉ ጊዜ የአ​ሮን ልጅ ካህኑ ከሌ​ዋ​ው​ያን ጋር ይሁን፤ ሌዋ​ው​ያ​ኑም የዐ​ሥ​ራ​ቱን ዐሥ​ራት ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት ወደ ጓዳ​ዎች ወደ ዕቃ ቤት ያም​ጡት።</verse>
				<verse number="39">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና የሌዊ ልጆ​ችም የእ​ህ​ሉ​ንና የወ​ይ​ኑን፥ የዘ​ይ​ቱ​ንም ቀዳ​ም​ያት፥ የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ​ዎ​ችና የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉት ካህ​ናት፥ በረ​ኞ​ቹና መዘ​ም​ራኑ ወዳ​ሉ​ባ​ቸው ጓዳ​ዎች ያግ​ቡት፤ እን​ዲ​ሁም የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ቤት ከቶ አን​ተ​ውም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">የሕ​ዝ​ቡም አለ​ቆች በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መጡ፤ ከቀ​ሩ​ትም ሕዝብ ከዐ​ሥሩ ክፍል አንዱ በቅ​ድ​ስ​ቲቱ ከተማ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ዘጠ​ኙም በሌ​ሎች ከተ​ሞች ይቀ​መጡ ዘንድ ዕጣ ተጣ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="2">ሕዝ​ቡም በፈ​ቃ​ዳ​ቸው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ቀ​መጥ የወ​ደ​ዱ​ትን ሰዎች ሁሉ ባረኩ።</verse>
				<verse number="3">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​ቀ​መ​ጡት የሀ​ገሩ አለ​ቆች እነ​ዚህ ናችው፤ እስ​ራ​ኤል ግን ካህ​ና​ቱም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ ናታ​ኒ​ምም፥ የሰ​ሎ​ሞ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮች ልጆች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በየ​ር​ስ​ታ​ቸ​ውና በየ​ከ​ተ​ማ​ቸው በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="4">ከይ​ሁ​ዳና ከብ​ን​ያ​ምም ልጆች እነ​ዚህ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መጡ። ከይ​ሁዳ ልጆች፤ ከፋ​ሬስ ልጆች የመ​ላ​ል​ኤል ልጅ፥ የሰ​ፋ​ጥ​ያስ ልጅ፥ የሰ​ማ​ርያ ልጅ፥ የዘ​ካ​ር​ያስ ልጅ፥ የዖ​ዝያ ልጅ አታያ፤</verse>
				<verse number="5">የሴሎ ልጅ፥ የዘ​ካ​ር​ያስ ልጅ፥ የዮ​ያ​ሪብ ልጅ፥ የዓ​ዳያ ልጅ፥ የዖ​ዝያ ልጅ፥ የኮ​ል​ሖዜ ልጅ፥ የባ​ሩክ ልጅ መዕ​ሤያ።</verse>
				<verse number="6">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ቀ​መ​ጡት የፋ​ሬስ ልጆች ሁሉ አራት መቶ ስድሳ ስም​ንት ጽኑ​ዓን ነበሩ።</verse>
				<verse number="7">የብ​ን​ያ​ምም ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ የይ​ሳ​ዕያ ልጅ፥ የአ​ት​ያል ልጅ፥ የመ​ዕ​ሤያ ልጅ፥ የቆ​ላያ ልጅ፥ የፈ​ዳያ ልጅ፥ የዮ​ሐድ ልጅ፥ የሜ​ሱ​ላም ልጅ ሴሎ።</verse>
				<verse number="8">ከእ​ር​ሱም በኋላ ጌቤና ሴል ዘጠኝ መቶ ሃያ ስም​ንት ነበሩ።</verse>
				<verse number="9">አለ​ቃ​ቸ​ውም የዝ​ክሪ ልጅ ኢዮ​ኤል ነበረ፤ የሰ​ኑ​ዋም ልጅ ይሁዳ በከ​ተ​ማው ላይ ሁለ​ተኛ ነበረ።</verse>
				<verse number="10">ከካ​ህ​ና​ቱም የዮ​ያ​ሬብ ልጅ ይዳ​እ​ያና ያኪን፤</verse>
				<verse number="11">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አለቃ የአ​ኪ​ጦብ ልጅ፥ የማ​ር​ዮት ልጅ፥ የሳ​ዶቅ ልጅ፥ የሜ​ሱ​ላም ልጅ፥ የኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ ሣርያ፥</verse>
				<verse number="12">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የቤ​ቱን ሥራ የሠሩ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ስም​ንት መቶ ሃያ ሁለት የመ​ል​ክያ ልጅ፥ የፋ​ስ​ኩር ልጅ፥ የዘ​ካ​ር​ያስ ልጅ፥ የአ​ማሴ ልጅ፥ የፈ​ላ​ልያ ልጅ፥ የይ​ሮ​ሖም ልጅ ዓዳያ፥</verse>
				<verse number="13">ወን​ድ​ሞ​ቹም የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ሁለት መቶ አርባ ሁለት፤ የኢ​ሜር ልጅ፥ የሜ​ሱ​ላ​ሙት ልጅ፥ የአ​ሐዚ ልጅ፥ የኤ​ዝ​ር​ኤል ልጅ ሐማ​ስያ፥</verse>
				<verse number="14">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም መቶ ሃያ ስም​ንት ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን፤ አለ​ቃ​ቸ​ውም የሐ​ጊ​ዶ​ሌም ልጅ ዘብ​ዲ​ሔል ነበረ።</verse>
				<verse number="15">ከሌ​ዋ​ው​ያ​ንም የቡኒ ልጅ፥ የአ​ሳ​ብያ ልጅ፥ የዓ​ዝ​ሪ​ቃም ልጅ፥ የሐ​ሱብ ልጅ ሰማያ፤</verse>
				<verse number="16">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በውጭ በነ​በ​ረው ሥራ ላይ የነ​በሩ የሌ​ዋ​ው​ያን አለ​ቆች ሴቤ​ታ​ይና ኢዮ​ዛ​ብድ፤</verse>
				<verse number="17">በጸ​ሎ​ትም ጊዜ ምስ​ጋ​ናን የሚ​ጀ​ምሩ አለ​ቃው የአ​ሳፍ ልጅ፥ የዛ​ብዲ ልጅ፥ የሚካ ልጅ ማታ​ንያ፥ በወ​ን​ድ​ሞ​ቹም መካ​ከል ሁለ​ተኛ የነ​በረ ቦቂ​ቦ​ቅያ፥ የኢ​ዶ​ትም ልጅ፥ የጌ​ላል ልጅ፥ የሰ​ሙዓ ልጅ አብ​ድያ።</verse>
				<verse number="18">በቅ​ድ​ስ​ቲቱ ከተማ የነ​በሩ ሌዋ​ው​ያን ሁሉ ሁለት መቶ ሰማ​ንያ አራት ነበሩ።</verse>
				<verse number="19">በሮ​ቹ​ንም የሚ​ጠ​ብቁ በረ​ኞች፥ ዓቁ​ብና ጤል​ሞን፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም መቶ ሰባ ሁለት ነበሩ።</verse>
				<verse number="20">ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የቀ​ሩት ከካ​ህ​ና​ትና ከሌ​ዋ​ው​ያ​ንም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በየ​ር​ስ​ታ​ቸው በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ሁሉ ውስጥ ነበሩ።</verse>
				<verse number="21">ናታ​ኒ​ምም በዖ​ፌል ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ ሲሐና ጊስ​ፋም በና​ታ​ኒም ላይ ነበሩ።</verse>
				<verse number="22">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ሥራ ላይ ከነ​በሩ መዘ​ም​ራን ከአ​ሳፍ ልጆች ወገን የሚካ ልጅ፥ የመ​ታ​ንያ ልጅ፥ የሐ​ሳ​ብያ ልጅ፥ የባኒ ልጅ ኦዚ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሌ​ዋ​ው​ያን አለቃ ነበረ።</verse>
				<verse number="23">በእ​ነ​ር​ሱም ላይ የን​ጉሥ ትእ​ዛዝ ነበረ፤ የመ​ዘ​ም​ራ​ኑም ሥር​ዐት ለየ​ዕ​ለቱ የተ​ሠራ ነበረ።</verse>
				<verse number="24">ከይ​ሁ​ዳም ልጅ ከዛራ ወገን የባ​ስ​ያ​ዘ​ብ​ኤል ልጅ ፈታያ ስለ ሕዝቡ ነገር ሁሉ በን​ጉሡ አጠ​ገብ ነበረ።</verse>
				<verse number="25">ስለ መን​ደ​ሮ​ቹና ስለ እር​ሻ​ዎ​ቻ​ቸው ከይ​ሁዳ ልጆች ዐያ​ሌ​ዎች በቂ​ር​ያ​ት​አ​ር​ባ​ቅና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በዲ​ቦ​ንና በመ​ን​ደ​ሮ​ች​ዋም፥ በቃ​ጽ​ብ​ኤ​ልና በመ​ን​ደ​ሮ​ች​ዋም፥</verse>
				<verse number="26">በኢ​ያሱ፥ በሞ​ላዳ፥ በቤ​ተ​ፋ​ሌጥ፥</verse>
				<verse number="27">በሐ​ጸ​ር​ሱ​ዓል፥ በቤ​ር​ሳ​ቤ​ህና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥</verse>
				<verse number="28">በጼ​ቅ​ላቅ፥ በመ​ኮ​ናና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥</verse>
				<verse number="29">በዓ​ይ​ን​ሪ​ሞን፥ በጼ​ርህ፥ በየ​ር​ሙት፥</verse>
				<verse number="30">በዛ​ኖህ፥ በዓ​ዶ​ላም፥ በመ​ን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም፥ በለ​ኪ​ሶና በእ​ር​ሻ​ዎ​ችዋ፥ በዓ​ዜ​ቃና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ ተቀ​መጡ። እን​ዲሁ ከቤ​ር​ሳ​ቤህ ጀምሮ እስከ ሄኖም ሸለቆ ድረስ ሰፈሩ።</verse>
				<verse number="31">የብ​ን​ያ​ምም ልጆች ከጌባ ጀምሮ በማ​ኬ​ማስ፥ በአ​ያል፥ በቤ​ቴ​ልና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥</verse>
				<verse number="32">በዓ​ና​ቶት፥ በኖብ፥ በሐ​ና​ንያ፥</verse>
				<verse number="33">በሐ​ጾር፥ በራማ፥ በጌ​ትም፤</verse>
				<verse number="34">በሐ​ዲድ፥ በሰ​ቡ​ኢም፥ በነ​ብ​ላት፥</verse>
				<verse number="35">በሎድ፥ በኣ​ውኖ፥ በጌ​ሐ​ራ​ሲም ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="36">ከሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ተከ​ፍ​ለው በይ​ሁ​ዳና በብ​ን​ያም ነበሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">ከሰ​ላ​ት​ያል ልጅ ከዘ​ሩ​ባ​ቤ​ልና ከኢ​ያሱ ጋር የወ​ጡት ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን እነ​ዚህ ነበሩ፤ ሠራ​ህያ፥ ኤር​ም​ያስ፥ ዔዝራ፤</verse>
				<verse number="2">አማ​ርያ፥ መሎክ፥ ሐጡስ፥</verse>
				<verse number="3">ሴኬ​ንያ፥ ሬሁም፥ ሜራ​ሞት፤</verse>
				<verse number="4">አዶ፥ ጌን​ቶን፥ አብያ፤</verse>
				<verse number="5">ሚያ​ሚን፥ መዓ​ድያ፥ ቤልጋ፤</verse>
				<verse number="6">ሰማ​ዕያ፥ ዮያ​ሪብ፥ ዮዳ​ኤያ፤</verse>
				<verse number="7">ሳሎም፥ ዓሞቅ፥ ሔል​ቅ​ያስ፥ ኢዳ​ዕያ፤ እነ​ዚህ በኢ​ያሱ ዘመን የካ​ህ​ና​ቱና የወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው አለ​ቆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="8">ሌዋ​ው​ያ​ኑም ኢያሱ፥ በንዊ፥ ቀድ​ም​ኤል፥ ሰራ​ብያ፥ ይሁዳ፥ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹም ጋር በመ​ዘ​ም​ራን ላይ የተ​ሾመ ማታ​ንያ።</verse>
				<verse number="9">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም በቅ​ቡ​ቅ​ያና ዑኒ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው በአ​ን​ጻ​ራ​ቸው ነበሩ።</verse>
				<verse number="10">ኢያ​ሱም ዮአ​ቂ​ምን ወለደ፤ ዮአ​ቂ​ምም ኤሊ​ያ​ሴ​ብን ወለደ፤ ኤሊ​ያ​ሴ​ብም ዮሐ​ዳን ወለደ፤</verse>
				<verse number="11">ዮሐ​ዳም ዮና​ታ​ንን ወለደ፤ ዮና​ታ​ንም ይዱ​ዕን ወለደ።</verse>
				<verse number="12">በዮ​አ​ቂ​ምም ዘመን የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ወን​ድ​ሞቹ ካህ​ናቱ ነበሩ፤ ከሠ​ራያ ምራያ፥ ከኤ​ር​ም​ያስ ሐና​ንያ፤</verse>
				<verse number="13">ከዕ​ዝራ ሜሱ​ላም፥ ከአ​ማ​ርያ ዮሐ​ናን፤</verse>
				<verse number="14">ከማ​ሎክ ዮና​ታን፥ ከሴ​ብ​ንያ ዮሴፍ፤</verse>
				<verse number="15">ከሐ​ሪም ዓድና፥ ከመ​ራ​ዮት ሔል​ቃይ፤</verse>
				<verse number="16">ከአዶ ዘካ​ር​ያስ፥ ከጌ​ን​ቶን ሜሱ​ላም፤</verse>
				<verse number="17">ከአ​ብያ ዝክሪ፥ ከሚ​ያ​ሚ​ንና ከሞ​ዓ​ድያ፥ ፈል​ጣይ፤</verse>
				<verse number="18">ከቤ​ልጋ ሳሙኣ፥ ከሰ​ማ​ዕያ ዮና​ታን፤</verse>
				<verse number="19">ከዮ​ያ​ሬብ መት​ናይ፥ ከዮ​ዳ​ኤያ ኦዚ፤</verse>
				<verse number="20">ከሳ​ላይ ቃላይ፥ ከዓ​ሞቅ ዔቤር፤</verse>
				<verse number="21">ከኬ​ል​ቅ​ያስ ሐሳ​ብያ፥ ከኢ​ዳ​ዕያ ናት​ና​ኤል።</verse>
				<verse number="22">ከሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም በኤ​ል​ያ​ሴ​ብና በዮ​ሐዳ፥ በዮ​ሐ​ና​ንና በያ​ዱዕ ዘመን የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ተጻፉ፤ ካህ​ና​ቱም በፋ​ር​ሳ​ዊው በዳ​ር​ዮስ መን​ግ​ሥት ዘመን ተጻፉ።</verse>
				<verse number="23">የሌዊ ልጆች የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች እስከ ኤል​ያ​ሴብ ልጅ እስከ ዮሐ​ናን ዘመን ድረስ በታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጻፉ።</verse>
				<verse number="24">የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም አለ​ቆች አሳ​ብያ፥ ሰር​ብያ፥ ኢያሱ፥ የቀ​ድ​ም​ኤ​ልም ልጆች፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ዳዊት ትእ​ዛዝ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው በእ​ነ​ርሱ ፊት ያከ​ብ​ሩና ያመ​ሰ​ግኑ ነበር።</verse>
				<verse number="25">መታ​ንያ፥ በቅ​ቡ​ቅያ፥ አብ​ድያ፥ ሜሱ​ላም፥ ጤል​ሞን፥ ዓቁብ በበ​ሮች አጠ​ገብ የሚ​ገ​ኙ​ትን ዕቃ ቤቶች ለመ​ጠ​በቅ በረ​ኞች ነበሩ።</verse>
				<verse number="26">እነ​ዚ​ህም በኢ​ዮ​ሴ​ዴቅ ልጅ በኢ​ያሱ ልጅ በዮ​አ​ቂም በአ​ለ​ቃ​ውም በነ​ህ​ምያ፥ በጸ​ሓ​ፊ​ውም በካ​ህኑ በዕ​ዝራ ዘመን ነበሩ።</verse>
				<verse number="27">የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቅጥር በተ​መ​ረቀ ጊዜ ምረ​ቃ​ውን በደ​ስ​ታና በም​ስ​ጋና፥ በመ​ዝ​ሙ​ርም፥ በጸ​ና​ጽ​ልም፥ በበ​ገ​ናም፥ በመ​ሰ​ን​ቆም ለማ​ድ​ረግ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ጡ​አ​ቸው ዘንድ ሌዋ​ው​ያ​ኑን በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸው ሁሉ ፈለጉ።</verse>
				<verse number="28">የመ​ዘ​ም​ራ​ኑም ልጆች ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዙር​ያና ከሌ​ሎ​ችም መን​ደ​ሮች ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="29">ከቤት ጌል​ጋ​ልና ከጌባ፥ ከአ​ዝ​ማ​ዊ​ትም እርሻ መዘ​ም​ራኑ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዙርያ ለራ​ሳ​ቸው መን​ደ​ሮች ሠር​ተ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="30">ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም ራሳ​ቸ​ውን አነጹ፤ ሕዝ​ቡ​ንም፥ በረ​ኞ​ች​ንም ቅጥ​ሩ​ንም አነጹ።</verse>
				<verse number="31">የይ​ሁ​ዳ​ንም አለ​ቆች ወደ ቅጥሩ አወ​ጣ​ኋ​ቸው፤ አመ​ስ​ጋ​ኞ​ቹ​ንም በሁ​ለት ታላ​ላቅ ተርታ አቆ​ም​ኋ​ቸው፤ የአ​ን​ዱም ተርታ ሰዎች ወደ ቀኝ በቅ​ጥሩ ላይ ወደ ጉድፍ መጣ​ያው በር ሄዱ።</verse>
				<verse number="32">ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ሆሴዕ የይ​ሁ​ዳም አለ​ቆች እኩ​ሌታ፤</verse>
				<verse number="33">ዓዛ​ርያ፥ ዕዝራ፥ ሜሱ​ላም፥</verse>
				<verse number="34">ይሁዳ፥ ብን​ያም፥ ሰማ​ዕያ፥ ኤር​ም​ያስ፤</verse>
				<verse number="35">መለ​ከ​ትም ይዘው ከካ​ህ​ናቱ ልጆች አያ​ሌ​ዎች፥ የአ​ሳ​ፍም ልጅ የዘ​ኩር ልጅ የሚ​ካያ ልጅ የመ​ታ​ንያ ልጅ የሰ​ማ​ዕያ ልጅ የዮ​ና​ታን ልጅ ዘካ​ር​ያስ፤</verse>
				<verse number="36">ወን​ድ​ሞ​ቹም ሰማ​ዕያ፥ አዘ​ር​ኤል፥ ማዕ​ላይ፥ ጌላ​ላይ፥ መዓይ፥ ናት​ና​ኤል፥ ይሁዳ፥ አናኒ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው የዳ​ዊ​ትን የዜ​ማ​ውን ዕቃ ይዘው ሄዱ፤ ጸሓ​ፊ​ውም ዕዝራ በፊ​ታ​ቸው ነበረ።</verse>
				<verse number="37">በም​ን​ጭም በር አቅ​ን​ተው ሄዱ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ደረጃ፥ በቅ​ጥ​ሩም መውጫ፥ ከዳ​ዊ​ትም ቤት በላይ እስከ ውኃው በር ድረስ በም​ሥ​ራቅ በኩል ሄዱ።</verse>
				<verse number="38">ሁለ​ተ​ኛ​ውም የአ​መ​ስ​ጋ​ኞቹ ክፍል ወደ ግራ ሄደ፤ እኔና የሕ​ዝ​ቡም እኩ​ሌታ በስ​ተ​ኋ​ላ​ቸው ነበ​ርን፤ በቅ​ጥ​ሩም ላይ፥ በእ​ቶኑ ግንብ በላይ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ፥</verse>
				<verse number="39">ከኤ​ፍ​ሬ​ምም በር በላይ፥ በአ​ሮ​ጌው በርና በዓሣ በር፥ በአ​ና​ን​ኤ​ልም ግንብ፥ በሃ​ሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፤ በዘ​በ​ኞ​ችም በር አጠ​ገብ ቆሙ።</verse>
				<verse number="40">እን​ዲሁ ሁለቱ የአ​መ​ስ​ጋ​ኞች ክፍ​ሎች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ቆሙ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር እኔና የአ​ለ​ቆች እኩ​ሌታ ነበ​ርን፤</verse>
				<verse number="41">ካህ​ና​ቱም ኤል​ያ​ቄም፥ መዕ​ሤያ፥ ሚን​ያ​ሚን፥ ሚካያ፥ ኤል​ዮ​ዔ​ናይ፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ሐና​ንያ መለ​ከት ይዘው፥</verse>
				<verse number="42">መዕ​ሤያ፥ ሰማ​ዕያ፥ ኤል​የ​ዜር፥ ኦዚ፥ ዮሐ​ናን፥ ሚል​ክያ፥ ኤላም፥ ኤዝር፥ መዘ​ም​ራ​ኑም በታ​ላቅ ድምፅ ዘመሩ፤ አለ​ቃ​ቸ​ውም ይዝ​ረ​አያ ነበረ።</verse>
				<verse number="43">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በታ​ላቅ ደስታ ደስ አሰ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ፤ ደስም አላ​ቸው፤ ሴቶ​ቹና ልጆ​ቹም ደግሞ ደስ አላ​ቸው፤ ደስ​ታ​ቸ​ውም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከሩቅ ተሰማ።</verse>
				<verse number="44">የይ​ሁ​ዳም ሕዝብ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን ደስ ስላ​ላ​ቸው፥ የካ​ህ​ና​ቱ​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑን ዕድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከ​ተ​ሞች እር​ሻ​ዎች ያከ​ማቹ ዘንድ ለቀ​ዳ​ም​ያት፥ ለዐ​ሥ​ራ​ትም በየ​ዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎ​ችን ሾሙ።</verse>
				<verse number="45">እነ​ር​ሱም መዘ​ም​ራ​ኑና በረ​ኞ​ቹም የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን ሥር​ዐት የመ​ን​ጻ​ታ​ቸ​ውን ሥር​ዐት እንደ ዳዊ​ትና እንደ ልጁ እንደ ሰሎ​ሞን ትእ​ዛዝ ጠበቁ።</verse>
				<verse number="46">በዳ​ዊ​ትም ዘመን አሳፍ የመ​ዘ​ም​ራን አለቃ ነበር፤ እነ​ር​ሱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በዜማ ያመ​ሰ​ግኑ ነበር።</verse>
				<verse number="47">እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በዘ​ሩ​ባ​ቤ​ልና በነ​ህ​ምያ ዘመን ለመ​ዘ​ም​ራ​ኑና ለበ​ረ​ኞቹ ፈን​ታ​ቸ​ውን በየ​ዕ​ለቱ ይሰጡ ነበር፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ነገር ለሌ​ዋ​ው​ያን ሰጡ፤ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ከተ​ቀ​ደ​ሰው ነገር ለአ​ሮን ልጆች ሰጡ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">በዚ​ያም ቀን የሙ​ሴን መጽ​ሐፍ በሕ​ዝቡ ጆሮ አነ​በቡ፤ አሞ​ና​ው​ያ​ንና ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጉባኤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዳ​ይ​ገቡ የሚል በዚያ አገኙ።</verse>
				<verse number="2">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በእ​ን​ጀ​ራና በውኃ አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​አ​ቸ​ው​ምና፥ ይረ​ግ​ማ​ቸ​ውም ዘንድ በለ​ዓ​ምን ገዝ​ተ​ው​ባ​ቸ​ዋ​ልና፤ ነገር ግን አም​ላ​ካ​ችን ርግ​ማ​ኑን ወደ በረ​ከት መለ​ሰው።</verse>
				<verse number="3">ሕጉ​ንም በሰሙ ጊዜ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር የተ​ደ​ባ​ለ​ቀ​ውን ሕዝብ ሁሉ ለዩ።</verse>
				<verse number="4">ከዚ​ህም አስ​ቀ​ድሞ በአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤት ጓዳ​ዎች ላይ ተሾሞ የነ​በ​ረው ካህኑ ኤል​ያ​ሴብ ከጦ​ብያ ጋር ተወ​ዳ​ጅቶ፥</verse>
				<verse number="5">ለሌ​ዋ​ው​ያን፥ ለመ​ዘ​ም​ራ​ንና ለበ​ረ​ኞቹ እንደ ሕጉ የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ንና ዕጣ​ኑን፥ ዕቃ​ዎ​ቹ​ንም፥ የእ​ህ​ሉ​ንና የወ​ይ​ኑን፥ የዘ​ይ​ቱ​ንም ዐሥ​ራት፥ ለካ​ህ​ና​ቱም የሆ​ነ​ውን ቀዳ​ም​ያ​ቱን አስ​ቀ​ድሞ ያስ​ቀ​መ​ጡ​በ​ትን ታላቅ ዕቃ ቤት አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ለት ነበር።</verse>
				<verse number="6">እኔ ግን በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ በሠ​ላሳ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት ወደ ንጉሡ ሄጄ ነበ​ርና በዚህ ጊዜ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አል​ነ​በ​ር​ሁም። ከጥ​ቂት ዘመ​ንም በኋላ የን​ጉ​ሡን ፈቃድ ለመ​ንሁ፤</verse>
				<verse number="7">ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም መጣሁ፤ ኤል​ያ​ሴ​ብም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ ለጦ​ቢያ ዕቃ ቤቱን በማ​ዘ​ጋ​ጀት ያደ​ረ​ገ​ውን ክፉ ነገር አስ​ተ​ዋ​ልሁ።</verse>
				<verse number="8">እጅ​ግም አስ​ከ​ፋኝ፤ የጦ​ብ​ያ​ንም የቤ​ቱን ዕቃ ሁሉ ከዕቃ ቤት ወደ ውጭ ጣልሁ።</verse>
				<verse number="9">ዕቃ ቤቶ​ቹ​ንም እን​ዲ​ያ​ነጹ አዘ​ዝሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ዕቃ​ዎች፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን፥ ዕጣ​ኑ​ንም መልሼ በዚያ አገ​ባሁ።</verse>
				<verse number="10">ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ፈን​ታ​ቸው እን​ዳ​ል​ተ​ሰጠ፥ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​ትም ሌዋ​ው​ያ​ንና መዘ​ም​ራን እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ እር​ሻው እንደ ሄደ ተመ​ለ​ከ​ትሁ።</verse>
				<verse number="11">እኔም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ስለ ምን ተተወ?” ብዬ ከአ​ለ​ቆቹ ጋር ተከ​ራ​ከ​ርሁ። ሰበ​ሰ​ብ​ኋ​ቸ​ውም፤ በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸ​ውም አቆ​ም​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">ይሁ​ዳም ሁሉ የእ​ህ​ሉ​ንና የወ​ይ​ኑን የዘ​ይ​ቱ​ንም ዐሥ​ራት ወደ ዕቃ ቤቶች አመጡ።</verse>
				<verse number="13">በዕቃ ቤቶ​ችም ላይ ካህ​ኑን ሰሌ​ም​ያን፥ ጸሓ​ፊ​ው​ንም ሳዶ​ቅን፥ ከሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም ፈዳ​ያን ሾምሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የመ​ታ​ንያ ልጅ የዘ​ኩር ልጅ ሐናን ነበረ፤ እነ​ር​ሱም የታ​መኑ ሆነው ተገኙ፤ ሥራ​ቸ​ውም ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ማከ​ፋ​ፈል ነበረ።</verse>
				<verse number="14">አም​ላኬ ሆይ፥ ስለ​ዚህ አስ​በኝ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ወረ​ታ​ዬን አታ​ጥፋ።</verse>
				<verse number="15">በዚ​ያም ወራት በይ​ሁዳ በሰ​ን​በት ቀን የወ​ይን መጭ​መ​ቂ​ያን የሚ​ረ​ግ​ጡ​ትን፥ ነዶም የሚ​ከ​ም​ሩ​ትን፥ የወ​ይ​ኑን ጠጅና የወ​ይ​ኑን ዘለላ፤ በለ​ሱ​ንም፥ ልዩ ልዩም ዓይ​ነት ሸክም በአ​ህ​ዮች ላይ የሚ​ጭ​ኑ​ትን፥ በሰ​ን​በ​ትም ቀን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ያ​ስ​ገ​ቡ​ትን አየሁ፤ ገበ​ያም ባደ​ረ​ጉ​በት ቀን አስ​መ​ሰ​ከ​ር​ሁ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">ደግ​ሞም በእ​ር​ስዋ የተ​ቀ​መጡ ነበሩ፤ እነ​ር​ሱም ዓሣ​ዎ​ችን፥ ልዩ ልዩም ዓይ​ነት ሸቀጥ አም​ጥ​ተው በሰ​ን​በት ቀን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለይ​ሁዳ ልጆች ይሸጡ ነበር።</verse>
				<verse number="17">ከይ​ሁ​ዳም አለ​ቆ​ችና ታላ​ላ​ቆች ጋር ተከ​ራ​ከ​ር​ሁና እን​ዲህ አል​ኋ​ቸው፥ “ይህ የም​ታ​ደ​ር​ጉት ክፉ ነገር ምን​ድን ነው? የሰ​ን​በ​ት​ንስ ቀን ታረ​ክ​ሳ​ላ​ች​ሁን?</verse>
				<verse number="18">አባ​ቶ​ቻ​ችሁ እን​ደ​ዚህ አድ​ር​ገው አል​ነ​በ​ረ​ምን? አም​ላ​ካ​ች​ንስ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ በእ​ኛና በዚች ከተማ ላይ አም​ጥቶ አል​ነ​በ​ረ​ምን? እና​ን​ተስ ሰን​በ​ትን በማ​ር​ከ​ሳ​ችሁ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ መዓ​ትን ትጨ​ም​ራ​ላ​ችሁ?”</verse>
				<verse number="19">ከዚህ በኋላ ሰን​በት ከመ​ግ​ባቱ በፊት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሮች ድን​ግ​ዝ​ግ​ዝታ በሆነ ጊዜ በሮ​ችዋ እን​ዲ​ዘጉ፥ ሰን​በ​ትም እስ​ኪ​ያ​ልፍ ድረስ እን​ዳ​ይ​ከ​ፈቱ አዘ​ዝሁ። በሰ​ን​በ​ትም ቀን ሸክም እን​ዳ​ይ​ገባ ከብ​ላ​ቴ​ኖች በዐ​ያ​ሌ​ዎቹ በሮ​ች​ዋን አስ​ጠ​በ​ቅሁ።</verse>
				<verse number="20">ሁሉም አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውጭ አድ​ረው ገበያ አድ​ር​ገው ነበር።</verse>
				<verse number="21">እኔም አስ​መ​ሰ​ከ​ር​ሁ​ባ​ቸ​ውና፥ “ከቅ​ጥሩ ውጭ ለምን ታድ​ራ​ላ​ችሁ? እንደ ገና ብታ​ደ​ር​ጉት እጆ​ችን አነ​ሣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ” አል​ኋ​ቸው። ከዚ​ያም ጊዜ ጀምሮ በሰ​ን​በት ቀን እንደ ገና አል​መ​ጡም።</verse>
				<verse number="22">ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም ራሳ​ቸ​ውን እን​ዲ​ያ​ነጹ፥ መጥ​ተ​ውም በሮ​ቹን እን​ዲ​ጠ​ብቁ፥ የሰ​ን​በ​ት​ንም ቀን እን​ዲ​ቀ​ድሱ ነገ​ር​ኋ​ቸው። “አም​ላኬ ሆይ፥ ስለ​ዚህ ደግሞ አስ​በኝ፥ እንደ ምሕ​ረ​ት​ህም ብዛት ራራ​ልኝ” አልሁ።</verse>
				<verse number="23">ደግ​ሞም በዚያ ወራት የአ​ዛ​ጦ​ን​ንና የአ​ሞ​ንን፥ የሞ​ዓ​ብ​ንም ሴቶች ያገ​ቡ​ትን አይ​ሁድ አየሁ።</verse>
				<verse number="24">ከል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም እኩ​ሌ​ቶቹ በአ​ዛ​ጦን ቋንቋ ይና​ገሩ ነበር፤ በሌ​ሎች ሕዝብ ቋንቋ የሚ​ና​ገ​ሩም ነበሩ፤ በአ​ይ​ሁ​ድም ቋንቋ መና​ገር አያ​ው​ቁም ነበር።</verse>
				<verse number="25">እነ​ር​ሱ​ንም ተቈ​ጣ​ኋ​ቸው፤ ረገ​ም​ኋ​ቸ​ውም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ዐያ​ሌ​ዎ​ቹን መታሁ፤ ጠጕ​ራ​ቸ​ው​ንም ነጨሁ፤ እን​ዲ​ህም ብዬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አማ​ል​ኋ​ቸው፥ “ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸው አት​ስጡ፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ችሁ አት​ው​ሰዱ።</verse>
				<verse number="26">የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሰሎ​ሞን በዚህ ነገር ኀጢ​አት አድ​ርጎ የለ​ምን? በብዙ አሕ​ዛ​ብም መካ​ከል እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም፤ በአ​ም​ላ​ኩም ዘንድ የተ​ወ​ደደ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ አን​ግ​ሦት ነበር፤ እር​ሱ​ንም እንኳ እን​ግ​ዶች ሴቶች አሳ​ቱት።</verse>
				<verse number="27">እን​ዲሁ እን​ግ​ዲህ ይህን ሁሉ ታላቅ ክፋት ስት​ሠሩ፥ እን​ግ​ዶ​ች​ንም ሴቶች በማ​ግ​ባት አም​ላ​ካ​ች​ንን ስት​በ​ድሉ አን​ስ​ማ​ባ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="28">ከዋ​ነ​ኛ​ውም ካህን ከኤ​ል​ያ​ሴብ ልጅ ከዮ​ዳሔ ልጆች አንዱ ለሐ​ሮ​ና​ዊው ለሰ​ን​ባ​ላጥ አማች ነበረ፤ ከእ​ኔም ዘንድ አባ​ረ​ር​ሁት።</verse>
				<verse number="29">“አም​ላኬ ሆይ፥ ክህ​ነ​ትን የክ​ህ​ነ​ት​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ን​ንም ቃል ኪዳን ስላ​ፈ​ረሱ አስ​ባ​ቸው።”</verse>
				<verse number="30">ከእ​ን​ግዳ ነገ​ርም ሁሉ አነ​ጻ​ኋ​ቸው፤ ለካ​ህ​ና​ቱና ለሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው፥</verse>
				<verse number="31">በየ​ጊ​ዜ​ውም ዕን​ጨት ለሚ​ሸ​ከሙ ሰዎች ቍር​ባን፥ ለበ​ኵ​ራ​ቱም ሥር​ዐት አደ​ረ​ግሁ። “አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ በመ​ል​ካም አስ​በኝ።”</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="17">
			<chapter number="1">
			</chapter>
			<chapter number="2">
			</chapter>
			<chapter number="3">
			</chapter>
			<chapter number="4">
			</chapter>
			<chapter number="5">
			</chapter>
			<chapter number="6">
			</chapter>
			<chapter number="7">
			</chapter>
			<chapter number="8">
			</chapter>
			<chapter number="9">
			</chapter>
			<chapter number="10">
			</chapter>
		</book>
		<book number="18">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">አው​ስ​ጢድ በሚ​ባል ሀገር ስሙ ኢዮብ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ቅን፥ ንጹ​ሕና ጻድቅ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ፈራ፥ ከክፉ ሥራም ሁሉ የራቀ ነበር።</verse>
				<verse number="2">ሰባ​ትም ወን​ዶች፥ ሦስ​ትም ሴቶች ልጆች ነበ​ሩት።</verse>
				<verse number="3">ከብ​ቶ​ቹም፦ ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመ​ሎች፥ አም​ስት መቶም ጥማድ በሬ፥ አም​ስት መቶም እን​ስት አህ​ዮች ነበሩ፤ እጅግ ብዙም አገ​ል​ጋ​ዮች ነበ​ሩት፤ ሥራ​ውም በም​ድር ላይ ታላቅ ነበረ፤ ያም ሰው በም​ሥ​ራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ገናና ነበረ።</verse>
				<verse number="4">ወን​ዶች ልጆ​ቹም ሄደው በየ​ተራ በእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ቤት ግብዣ ያደ​ርጉ ነበር፤ ሦስቱ እኅ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይወ​ስ​ዱ​አ​ቸው ነበር፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ይበ​ሉና ይጠጡ ነበር።</verse>
				<verse number="5">የግ​ብ​ዣ​ውም ቀኖች በተ​ፈ​ጸሙ ጊዜ ኢዮብ ይል​ክና ይቀ​ድ​ሳ​ቸው ነበር፤ በማ​ለ​ዳም ገሥ​ግሦ፦ ስለ ልጆቹ በቍ​ጥ​ራ​ቸው መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርብ ነበር፤ አንድ ወይ​ፈን ስለ ነፍ​ሳ​ቸው የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርብ ነበር፤ ኢዮብ፥ “ምና​ል​ባት ልጆቼ በል​ባ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ክፉ ነገር ያስቡ ይሆ​ናል” ይል ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="6">ከዕ​ለ​ታት አንድ ቀንም እን​ዲህ ሆነ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለመ​ቆም መጡ፤ ሰይ​ጣ​ንም ደግሞ ከእ​ነ​ርሱ ጋር መጣ።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰይ​ጣ​ንን፥ “ከወ​ዴት መጣህ?” አለው። ሰይ​ጣ​ንም፥ “ምድ​ርን ሁሉ ዞር​ሁ​አት፥ ከሰ​ማይ በታ​ችም ተመ​ላ​ለ​ስ​ሁና መጣሁ።” ብሎ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መለሰ።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰይ​ጣ​ንን አለው፥ “በባ​ሪ​ያዬ በኢ​ዮብ ላይ የም​ታ​ስ​በው ነገር እን​ዳ​ይ​ኖር ተጠ​ን​ቀቅ! በም​ድር ላይ እንደ እርሱ ቅን፥ ንጹ​ሕና ጻድቅ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ፈራ፥ ከክፉ ሥራም ሁሉ የራቀ ሰው የለ​ምና።”</verse>
				<verse number="9">ሰይ​ጣ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዲህ ብሎ መለሰ፥ “በውኑ ኢዮብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​መ​ል​ከው በከ​ንቱ ነውን?</verse>
				<verse number="10">አንተ ቤቱን በው​ስ​ጥም በው​ጭም፥ በዙ​ሪ​ያው ያለ​ው​ንም ሁሉ አል​ሞ​ላ​ህ​ለ​ት​ምን? የእ​ጁ​ንም ሥራ ባር​ከ​ህ​ለ​ታል፥ ከብ​ቱ​ንም በም​ድር ላይ አብ​ዝ​ተ​ህ​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="11">ነገር ግን እጅ​ህን ዘር​ግ​ተህ ያለ​ውን ሁሉ ዳስስ፤ በእ​ው​ነት በፊ​ትህ ይሰ​ድ​ብ​ሃል።”</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰይ​ጣ​ንን፥ “እነሆ፥ ለእ​ርሱ ያለ​ውን ሁሉ በእ​ጅህ ሰጠ​ሁህ፥ ነገር ግን በእ​ርሱ ላይ እጅ​ህን አት​ዘ​ርጋ” አለው። ሰይ​ጣ​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወጣ።</verse>
				<verse number="13">አንድ ቀንም እን​ዲህ ሆነ፤ የኢ​ዮብ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች በታ​ላቅ ወን​ድ​ማ​ቸው ቤት ይበ​ሉና የወ​ይን ጠጅ ይጠጡ ነበር።</verse>
				<verse number="14">መል​እ​ክ​ተ​ኛም ወደ ኢዮብ መጥቶ፥ “ጥምድ በሬ​ዎ​ችህ እርሻ ያርሱ ነበር፥ በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም ሴቶች አህ​ዮ​ችህ ይሰ​ማሩ ነበር፤</verse>
				<verse number="15">ማራ​ኪ​ዎ​ችም መጥ​ተው ወሰ​ዱ​አ​ቸው፥ ብላ​ቴ​ኖ​ች​ህ​ንም በሰ​ይፍ ስለት ገደሉ፥ እኔም ብቻ​ዬን አም​ልጬ እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ” አለው።</verse>
				<verse number="16">እር​ሱም ገና ይህን ሲና​ገር ሌላ መል​እ​ክ​ተኛ መጥቶ፦ ለኢ​ዮብ እን​ዲህ አለው፥ “እሳት ከሰ​ማይ ወደ​ቀች፥ በጎ​ች​ህ​ንም አቃ​ጠ​ለች፥ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ህ​ንም በላች፤ እኔም ብቻ​ዬን አም​ልጬ እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ።”</verse>
				<verse number="17">እር​ሱም ገና ይህን ሲና​ገር ሦስ​ተ​ኛው መል​እ​ክ​ተኛ መጥቶ ለኢ​ዮብ እን​ዲህ አለው፥ “ፈረ​ሰ​ኞች በሦ​ስት ረድፍ ከብ​በው ግመ​ሎ​ችን ማር​ከው ወሰዱ፥ ብላ​ቴ​ኖ​ች​ህ​ንም በሰ​ይፍ ስለት ገደሉ፤ እኔም ብቻ​ዬን አም​ልጬ እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ።”</verse>
				<verse number="18">እር​ሱም ገና ይህን ሲና​ገር አራ​ተ​ኛው መል​እ​ክ​ተኛ መጥቶ ለኢ​ዮብ እን​ዲህ አለው፥ “ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ችህ በታ​ላቅ ወን​ድ​ማ​ቸው ቤት ሲበ​ሉና የወ​ይን ጠጅ ሲጠጡ፥</verse>
				<verse number="19">እነሆ፥ ዐውሎ ነፋስ ከም​ድረ በዳ ድን​ገት መጥቶ ቤቱን በአ​ራት ማዕ​ዘኑ መታው፥ ቤቱም በብ​ላ​ቴ​ኖቹ ላይ ወደቀ፥ እነ​ር​ሱም ሞቱ፤ እኔም ብቻ​ዬን አም​ልጬ እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ።”</verse>
				<verse number="20">ኢዮ​ብም ተነሣ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ው​ንም ቀደደ፥ ራሱ​ንም ተላጨ፥ በም​ድ​ርም ላይ ተደ​ፍቶ ሰገደ፤</verse>
				<verse number="21">እን​ዲ​ህም አለ፥ “ከእ​ናቴ ማኅ​ፀን ራቁ​ቴን ወጥ​ቻ​ለሁ፥ ራቁ​ቴ​ንም ወደ ምድር እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰጠ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነሣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ፈቀደ ሆነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ብ​ሔር ስም የተ​ባ​ረከ ይሁን።”</verse>
				<verse number="22">በዚ​ህም በደ​ረ​ሰ​በት ሁሉ ኢዮብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አል​በ​ደ​ለም፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስን​ፍ​ናን አል​ሰ​ጠም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ከዕ​ለ​ታት አንድ ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት መጥ​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆሙ፥ ሰይ​ጣን ደግሞ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለመ​ቆም ከእ​ነ​ርሱ ጋር መጣ።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰይ​ጣ​ንን፥ “ከወ​ዴት መጣህ?” አለው። ሰይ​ጣ​ንም፥ “ከሰ​ማይ በታች በም​ድር ላይ ዞርሁ፥ በእ​ር​ስ​ዋም ተመ​ላ​ለ​ስሁ” ብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መለሰ።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰይ​ጣ​ንን አለው፥ “በባ​ሪ​ያዬ በኢ​ዮብ ላይ እን​ዲህ እን​ዳ​ታ​ስብ ተጠ​ን​ቀቅ፤ በም​ድር ላይ እንደ እርሱ ያለ ገር፥ ጻድ​ቅና ንጹሕ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ፥ ከክ​ፋ​ትም ሁሉ የራቀ፥ ዳግ​መ​ኛም ቅን የሆነ ሰው የለ​ምና፤ አንተ ግን ሀብ​ቱን በከ​ንቱ አጠፋ ዘንድ ነገ​ር​ኸኝ።”</verse>
				<verse number="4">ሰይ​ጣ​ንም መልሶ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ቍር​በት ስለ ቍር​በት ነው፤ ሰው ያለ​ውን ሁሉ ስለ ሕይ​ወቱ ይሰ​ጣል።</verse>
				<verse number="5">ነገር ግን አሁን እጅ​ህን ዘር​ግ​ተህ አጥ​ን​ቱ​ንና ሥጋ​ውን ዳስስ፤ በእ​ው​ነት በፊ​ትህ ይሰ​ድ​ብ​ሃል” ብሎ መለሰ።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰይ​ጣ​ንን አለው፥ “እነሆ፥ ሥጋ​ው​ንና አጥ​ን​ቱን በእ​ጅህ ሰጠ​ሁህ። ነገር ግን ሕይ​ወ​ቱን ተው።”</verse>
				<verse number="7">ሰይ​ጣ​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወጣ፥ ኢዮ​ብ​ንም ከእ​ግሩ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ በክፉ ቍስል መታው።</verse>
				<verse number="8">ቍስ​ሉ​ንም ያክ​ክ​በት ዘንድ ገል ወሰደ፥ ከከ​ተ​ማም ወጥቶ በአ​መድ ላይ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="9">ብዙ ወራ​ትም ካለፈ በኋላ ሚስቱ እን​ዲህ አለ​ችው፥ “እስከ መቼ ትታ​ገ​ሣ​ለህ? ‘ሀ’ ዳግ​መ​ኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጥቂት ወራት ደጅ እጠ​ና​ዋ​ለሁ፤ ዳግ​መ​ኛም መከ​ራ​ውን እታ​ገ​ሠ​ዋ​ለሁ፤ የቀ​ድ​ሞው ኑሬ​ዬ​ንም ተስፋ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ ትላ​ለ​ህን? ‘ለ’ እን​ደ​ዚ​ህስ እን​ዳ​ትል ከዚህ ዓለም እነሆ ስም አጠ​ራ​ርህ ጠፋ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆቼም ሞቱ፥ ማኅ​ፀ​ኔም በምጥ ተጨ​ነቀ፥ በከ​ን​ቱም ደከ​ምሁ። ‘ሐ’ አን​ተም በመ​ግ​ልና በትል ትኖ​ራ​ለህ፤ ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ ትዛ​ብ​ራ​ለህ። ‘መ’ እኔ ግን እየ​ዞ​ርሁ እቀ​ላ​ው​ጣ​ለሁ። ከአ​ንዱ መን​ደር ወደ አንዱ መን​ደር፥ ከአ​ንዱ ቤትም ወደ አንዱ ቤት እሄ​ዳ​ለሁ፤ ከድ​ካ​ሜና በእኔ ላይ ካለ ችግ​ሬም ዐርፍ ዘንድ ፀሐይ እስ​ኪ​ገባ ድረስ እጠ​ብ​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን አሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስደ​ብና ሙት።”</verse>
				<verse number="10">እርሱ ግን፦ ወደ እር​ስዋ ተመ​ለ​ከ​ተና እን​ዲህ አላት፥ “አንቺ ከሰ​ነ​ፎች ሴቶች እንደ አን​ዲቱ ተና​ገ​ርሽ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ መል​ካ​ሙን ተቀ​በ​ልን፥ ክፉ​ውን ነገ​ርስ አን​ታ​ገ​ሥ​ምን?” በዚህ በደ​ረ​ሰ​በት ሁሉ ኢዮብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በከ​ን​ፈሩ አል​በ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="11">ሦስ​ቱም የኢ​ዮብ ወዳ​ጆች ይህን የደ​ረ​ሰ​በ​ትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰም​ተው ከየ​ሀ​ገ​ራ​ቸው ወደ እርሱ መጡ፤ እነ​ር​ሱም ቴማ​ና​ዊው ንጉሥ ኤል​ፋዝ፥ አው​ኬ​ና​ዊው መስ​ፍን በል​ዳ​ዶስ፥ አሜ​ና​ዊው ንጉሥ ሶፋር ነበሩ። እነ​ር​ሱም ሊጐ​በ​ኙ​ትና ሊያ​ጽ​ና​ኑት በአ​ን​ድ​ነት ወደ እርሱ መጡ።</verse>
				<verse number="12">ከሩ​ቅም ሆነው ባዩት ጊዜ አላ​ወ​ቁ​ትም፤ በታ​ላቅ ድም​ፅም ጮኸው አለ​ቀሱ፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ቸ​ው​ንም ቀደዱ፥ በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ ትቢያ ነሰ​ነሱ።</verse>
				<verse number="13">ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊ​ትም በአ​ጠ​ገቡ ተቀ​መጡ፤ ሕማሙ እጅግ አስ​ፈ​ሪና ታላቅ እንደ ነበረ አይ​ተ​ዋ​ልና ከእ​ነ​ርሱ አንድ ቃል የሚ​ና​ገ​ረው አል​ነ​በ​ረም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ከዚ​ያም በኋላ ኢዮብ አፉን ከፈተ፥ የተ​ወ​ለ​ደ​ባ​ት​ንም ቀን ረገመ።</verse>
				<verse number="2">እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="3">“ያች የተ​ወ​ለ​ድ​ሁ​ባት ቀን ትጥፋ፥ ያችም፦ ወንድ ልጅ ነው ያሉ​ባት ሌሊት።</verse>
				<verse number="4">ያች ቀን ጨለማ ትሁን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከላይ አይ​መ​ል​ከ​ታት፥ ብር​ሃ​ንም አይ​ብ​ራ​ባት።</verse>
				<verse number="5">ጨለ​ማና የሞት ጥላ ያግ​ኙ​አት፤ ጭጋ​ግም ይም​ጣ​ባት፤</verse>
				<verse number="6">ያች ቀንም የተ​ረ​ገ​መች ትሁን። ያችም ሌሊት ጨለማ ይም​ጣ​ባት፤ በዓ​መቱ ቀኖች መካ​ከል አት​ኑር፤ በወ​ሮች ቀኖች ውስ​ጥም ገብታ አት​ቈ​ጠር።</verse>
				<verse number="7">ለዚ​ያም ሌሊት ጭንቅ ይሁን፥ እል​ልታ ወይም ደስታ አይ​ግ​ባ​ባት።</verse>
				<verse number="8">ነገር ግን ሌዋ​ታ​ንን ለመ​ግ​ደል የተ​ዘ​ጋጀ ያችን ቀን የሚ​ረ​ግም ይር​ገ​ማት።</verse>
				<verse number="9">የዚያ ሌሊት ኮከ​ቦች ይጨ​ልሙ፤ ሌሊ​ቱም በጨ​ለማ ይኑር፤ ወደ ብር​ሃ​ንም አይ​ምጣ፤ የን​ጋት ኮከ​ብም ሲወጣ አይይ፤</verse>
				<verse number="10">የእ​ና​ቴን ማኅ​ፀን ደጅ አል​ዘ​ጋ​ምና፥ መከ​ራ​ው​ንም ከዐ​ይኔ አል​ሰ​ወ​ረ​ምና።</verse>
				<verse number="11">በማ​ኅ​ፀን ሳለሁ ስለ ምን አል​ሞ​ት​ሁም? ከሆ​ድስ በወ​ጣሁ ጊዜ ወዲ​ያ​ውኑ ስለ ምን አል​ጠ​ፋ​ሁም?</verse>
				<verse number="12">ጕል​በ​ቶች ስለ ምን ደገ​ፉኝ? ጡትስ ስለ ምን ጠባሁ?</verse>
				<verse number="13">አሁ​ንም ተኝቼ ዝም ባልሁ ነበር፤ አን​ቀ​ላ​ፍ​ቼም ባረ​ፍሁ ነበር፤</verse>
				<verse number="14">በሰ​ይ​ፋ​ቸው ከከ​በሩ ከም​ድር ነገ​ሥ​ታ​ትና መካ​ሮች ጋር፥</verse>
				<verse number="15">ወይም ወር​ቅን ካበዙ፥ ቤታ​ቸ​ው​ንም ብር ከሞሉ አለ​ቆች ጋር፥</verse>
				<verse number="16">ወይም ከእ​ናቱ ማኅ​ፀን እንደ ወጣ ጭን​ጋፍ፥ ብር​ሃ​ንም እን​ዳ​ላዩ ሕፃ​ናት በሆ​ንሁ ነበር።</verse>
				<verse number="17">ኃጥ​ኣን በዚያ በቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ይቃ​ጠ​ላሉ፤ በዚ​ያም በሥ​ጋ​ቸው የተ​ጨ​ነ​ቁት ያር​ፋሉ።</verse>
				<verse number="18">በዚ​ያም የጥ​ንት ዘመን ሰዎች በአ​ን​ድ​ነት፥ የአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ውን ድምፅ አይ​ሰ​ሙም።</verse>
				<verse number="19">ታና​ሹና ታላቁ በዚያ አሉ፤ ጌታ​ውን ያገ​ለ​ገለ ባሪ​ያም በዚያ አለ።</verse>
				<verse number="20">በመ​ራ​ራ​ነት ላሉት ብር​ሃን፥ በነ​ፍስ ለተ​ጨ​ነ​ቁ​ትም ሕይ​ወት፥</verse>
				<verse number="21">የተ​ሰ​ወረ ሀብ​ትን ከሚ​ቈ​ፍሩ ይልቅ፥ ሞትን ለሚ​መኙ ለማ​ያ​ገ​ኙ​ትም፥</verse>
				<verse number="22">ባገ​ኙ​ትም ጊዜ ደስ ለሚ​ላ​ቸው፥ ሕይ​ወት ስለ ምን ተሰጠ?</verse>
				<verse number="23">ሞት ለሰው ዕረ​ፍቱ ነው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ከለ​ከ​ለው።</verse>
				<verse number="24">ከአ​ዝ​መ​ራዬ በፊት ልቅ​ሶዬ መጥ​ቶ​አ​ልና፥ ስለ ደረ​ሰ​ብ​ኝም አስ​ፈሪ ነገር ሁል​ጊዜ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="25">የተ​ጠ​ራ​ጠ​ር​ሁት ነገር መጥ​ቶ​ብ​ኛ​ልና፥ ያሰ​ብ​ሁ​ትም ደር​ሶ​ብ​ኛል።</verse>
				<verse number="26">ተዘ​ልዬ አል​ተ​ቀ​መ​ጥ​ሁም፥ ፀጥ​ታም አላ​ገ​ኘ​ሁም፥ አላ​ረ​ፍ​ሁም። ነገር ግን መከራ ደረ​ሰ​ች​ብኝ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ቴማ​ና​ዊ​ውም ኤል​ፋዝ መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“በመ​ከራ ሳለህ ነገር አታ​ብዛ፥ የነ​ገር ብዛት ምን ይጠ​ቅ​ም​ሃል?</verse>
				<verse number="3">እነሆ፥ አንተ ብዙ​ዎ​ችን ታስ​ተ​ምር ነበር፥ የደ​ከ​ሙ​ት​ንም እጆች ታበ​ረታ ነበር፥</verse>
				<verse number="4">በቃ​ልህ በሽ​ተ​ኞ​ችን ታስ​ነሣ ነበር፥ የሚ​ብ​ረ​ከ​ረ​ከ​ው​ንም ጕል​በት ታጸና ነበር።</verse>
				<verse number="5">አሁን ግን ሕማም በአ​ንተ ላይ መጥቶ ዳሰ​ሰህ። አን​ተም ተቸ​ገ​ርህ።</verse>
				<verse number="6">ጥን​ቱን ፍር​ሀ​ትህ፥ ተስ​ፋ​ህም፥ የመ​ን​ገ​ድ​ህም ጠማ​ማ​ነት፥ ስን​ፍና አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="7">እባ​ክህ አስብ፥ ንጹሕ ሆኖ የጠፋ ማን ነው? ከጻ​ድ​ቃ​ንስ የተ​ደ​መ​ሰሰ ማን ነው?</verse>
				<verse number="8">እኔ እን​ዳ​የሁ፥ ኀጢ​ኣ​ትን የሚ​ያ​ርሱ፥ የሚ​ዘ​ሩ​አ​ትም መከ​ራን ለራ​ሳ​ቸው ያጭ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="9">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ይጠ​ፋሉ፥ በቍ​ጣ​ውም መን​ፈስ ያል​ቃሉ።</verse>
				<verse number="10">የአ​ን​በ​ሳው ጩኸት፥ የአ​ን​በ​ሳ​ዪ​ቱም ድምፅ፥ የእ​ባ​ቦ​ችም አስ​ፈሪ ጩኸት ጠፉ።</verse>
				<verse number="11">“ገብረ ጉን​ዳን ምግብ በማ​ጣት አለቀ፥ የአ​ን​በ​ሳ​ዪቱ ግል​ገ​ሎ​ችም እርስ በእ​ር​ሳ​ቸው ተላ​ለቁ።</verse>
				<verse number="12">ነገር ግን አንተ አን​ዳች እው​ነት አድ​ር​ገህ ቢሆን ኖሮ፥ ይህ ሁሉ ባል​ደ​ረ​ሰ​ብ​ህም ነበር። በእኔ ዘንድ ነገር ይነ​ሣል፤ ዦሮ​ዬም ከእ​ርሱ ድም​ፅን ትሰ​ማ​ለች፤ ጥን​ቱን የነ​ገ​ረ​ኝን አላ​ም​ነ​ው​ምን?</verse>
				<verse number="13">በሰ​ዎች ላይ ፍር​ሀት በወ​ደቀ ጊዜ በሌ​ሊት ከፍ​ር​ሀ​ትና ከድ​ምፅ ጋር</verse>
				<verse number="14">ድን​ጋ​ጤና መን​ቀ​ጥ​ቀጥ ያዙኝ፤ አጥ​ን​ቶቼም ሁሉ እጅግ ተነ​ዋ​ወጡ፤</verse>
				<verse number="15">መን​ፈ​ሴም በፊቴ ዐለፈ፥ ሥጋ​ዬም፥ ጠጕ​ሬም ተቈጣ።</verse>
				<verse number="16">ተነ​ሣሁ፤ ነገር ግን አላ​ወ​ቅ​ሁም፥ ተመ​ለ​ከ​ትሁ፥ በዐ​ይ​ኖ​ቼም ፊት መልክ አል​ነ​በ​ረም። ነገር ግን ጥላን አያ​ለሁ፤ ድም​ፅ​ንም እሰ​ማ​ለሁ፦</verse>
				<verse number="17">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ንጹሕ የሚ​ሆን ሟች ማን ነው? በሥ​ራ​ውስ የሚ​ጸ​ድቅ ሰው ማን ነው?</verse>
				<verse number="18">እነሆ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም አይ​ተ​ማ​መ​ና​ቸ​ውም፥ መላ​እ​ክ​ቱ​ንም በጭ​ንቅ ይጠ​ራ​ጠ​ራ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="19">ይል​ቁ​ንም ከአ​ንድ ዐይ​ነት ጭቃ የተ​ፈ​ጠ​ርን እኛ፥ በተ​ፈ​ጠ​ር​ን​በት የጭቃ ቤት የሚ​ኖ​ሩ​ትን እንደ ብል ይጨ​ፈ​ል​ቃ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="20">ከጥ​ዋት እስከ ማታ አይ​ኖ​ሩም። ራሳ​ቸ​ውን ማዳ​ንና መር​ዳት አይ​ች​ሉ​ምና ጠፉ።</verse>
				<verse number="21">እፍ ብሎ​ባ​ቸ​ዋ​ልና ይደ​ር​ቃሉ፥ ጥበ​ብም የላ​ቸ​ው​ምና ይጠ​ፋሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">“አሁ​ንም የሚ​መ​ል​ስ​ልህ ካለ ጥራ፥ ከቅ​ዱ​ሳን መላ​እ​ክ​ትም የም​ታ​የው ካለ?</verse>
				<verse number="2">ሰነ​ፉን ሰው ቍጣ ይገ​ድ​ለ​ዋ​ልና፥ ቅን​ዓ​ትም ሰነ​ፉን ያጠ​ፋ​ዋል።</verse>
				<verse number="3">ሰነ​ፎ​ችን ሥር ሰድ​ደው አየ​ኋ​ቸው፥ በድ​ን​ገ​ትም መኖ​ሪ​ያ​ቸው ጠፋች።</verse>
				<verse number="4">ልጆ​ቻ​ቸው ከደ​ኅ​ን​ነት ርቀ​ዋል፥ በበ​ርም ውስጥ ይቀ​ጠ​ቅ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ መከ​ራም ያጸ​ኑ​ባ​ቸ​ዋል፥ የሚ​ታ​ደ​ጋ​ቸ​ውም የለም።</verse>
				<verse number="5">እነ​ርሱ የሰ​በ​ሰ​ቡ​ት​ንም ጻድ​ቃን ይበ​ሉ​ታል። እነ​ር​ሱን ግን ክፋት ቷጋ​ቸ​ዋ​ለች፥ ኀይ​ላ​ቸ​ውም ይደ​ክ​ማል።</verse>
				<verse number="6">ችግር ከም​ድር አይ​ወ​ጣ​ምና፥ መከ​ራም ከተ​ራ​ሮች አይ​በ​ቅ​ል​ምና፤</verse>
				<verse number="7">የአ​ሞራ ግል​ገ​ሎች ግን ወደ ላይ እየ​በ​ረሩ ከፍ እን​ዲሉ፥ ሰው እን​ዲሁ ለድ​ካም ተወ​ል​ዶ​አል።</verse>
				<verse number="8">“እኔ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እለ​ም​ነው ነበር፥ የሁሉ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም እጠ​ራው ነበር።</verse>
				<verse number="9">እርሱ የማ​ይ​መ​ረ​መ​ረ​ውን ታላቅ ነገ​ርና የማ​ይ​ቈ​ጠ​ረ​ውን የከ​በ​ረና ድንቅ ነገር ያደ​ር​ጋል።</verse>
				<verse number="10">በም​ድር ላይ ዝና​ብን ይሰ​ጣል፥ ከሰ​ማ​ይም በታች ውኃን ይል​ካል።</verse>
				<verse number="11">የተ​ዋ​ረ​ዱ​ትን ከፍ ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፥ የወ​ደ​ቁ​ት​ንም ያነ​ሣ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="12">የተ​ን​ኰ​ለ​ኞ​ችን ምክር ይለ​ው​ጣል፥ እጆ​ቻ​ቸ​ውም ቅን አይ​ሠ​ሩም።</verse>
				<verse number="13">ጠቢ​ባ​ን​ንም በተ​ን​ኰ​ላ​ቸው ይይ​ዛ​ቸ​ዋል፤ ምክ​ርን የሚ​ጐ​ነ​ጉኑ ሰዎ​ችን አሳብ ያጠ​ፋል።</verse>
				<verse number="14">በቀን ጨለማ ያገ​ኛ​ቸ​ዋል፥ በቀ​ት​ርም ጊዜ በሌ​ሊት እን​ዳሉ ይር​መ​ሰ​መ​ሳሉ።</verse>
				<verse number="15">በጦ​ር​ነት ይጠ​ፋሉ፤ ደካ​ማ​ውም ከኀ​ያሉ እጅ ያመ​ል​ጣል።</verse>
				<verse number="16">ለም​ስ​ኪ​ኑ ተስፋ አለ​ውና፤ የዐ​መ​ጸ​ኛም አፍ ይዘ​ጋ​ልና።</verse>
				<verse number="17">“ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ገ​ሥ​ጸው ሰው ብፁዕ ነው፤ ስለ​ዚህ ሁሉን የሚ​ች​ለ​ውን የአ​ም​ላ​ክን ተግ​ሣጽ አት​ናቅ።</verse>
				<verse number="18">እርሱ ይሰ​ብ​ራል፥ ዳግ​መ​ኛም ይጠ​ግ​ናል፤ ይቀ​ሥ​ፋል፥ እጆ​ቹም ይፈ​ው​ሳሉ።</verse>
				<verse number="19">ስድ​ስት ጊዜ ከክፉ ነገር ያድ​ን​ሃል፥ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ጊዜ ክፋት አት​ነ​ካ​ህም።</verse>
				<verse number="20">በራብ ጊዜ ከሞት ያድ​ን​ሃል፥ በጦ​ር​ነ​ትም ጊዜ ከሰ​ይፍ እጅ ያድ​ን​ሃል።</verse>
				<verse number="21">ከም​ላስ ጅራፍ ይሰ​ው​ር​ሃል፥ ከም​ት​መ​ጣ​ብ​ህም ክፋት አት​ፈ​ራም።</verse>
				<verse number="22">በኃ​ጥ​ኣ​ንና በዐ​መ​ጸ​ኞች ላይ ትስ​ቅ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ከም​ድረ በዳ አራ​ዊ​ትም አት​ፈ​ራም፤</verse>
				<verse number="23">የም​ድረ በዳ አራ​ዊ​ትም ከአ​ንተ ጋር ይስ​ማ​ማሉ።</verse>
				<verse number="24">ያን​ጊዜ ቤትህ በሰ​ላም እን​ዲ​ሆን ታው​ቃ​ለህ፤ ከን​ብ​ረ​ት​ህም አን​ዳች አይ​ጐ​ድ​ልም።</verse>
				<verse number="25">ዘር​ህም ብዙ እን​ዲ​ሆን፥ ልጆ​ች​ህም እንደ አማረ መስክ ሣር እን​ዲ​ሆኑ ታው​ቃ​ለህ።</verse>
				<verse number="26">በወ​ራቱ የደ​ረሰ አዝ​መራ እን​ዲ​ሰ​በ​ሰብ፥ የእ​ህሉ ነዶም በወ​ቅቱ ወደ አው​ድማ እን​ዲ​ገባ፥ በረ​ዥም ዕድሜ ወደ መቃ​ብር ትገ​ባ​ለህ።</verse>
				<verse number="27">እነሆ፥ ይህን ዐው​ቀን መረ​መ​ርን፥ የሰ​ማ​ነ​ውም ይህ ነው፤ አንተ ግን አን​ዳች ሠር​ተህ እንደ ሆነ ለራ​ስህ ዕወቅ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">ኢዮ​ብም መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“ከእ​ና​ንተ አንዱ መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ምነው በመ​ዘነ ኖሮ! መከ​ራ​ዬ​ንም በአ​ን​ድ​ነት ምነው በሚ​ዛን ላይ ባኖ​ረው ኖሮ!</verse>
				<verse number="3">ከባ​ሕር አሸዋ ይልቅ ይከ​ብድ ነበ​ርና፤ ነገር ግን ቃሌ ሐሰ​ትን ይመ​ስ​ላል።</verse>
				<verse number="4">እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍላጻ በሥ​ጋዬ ላይ ነው፤ መር​ዙም ደሜን ይመ​ጥ​ጣል። ለመ​ና​ገር ስጀ​ም​ርም ይወ​ጋ​ኛል።</verse>
				<verse number="5">በውኑ የሜዳ አህያ ሣር እያ​ለው በከ​ንቱ ይጮ​ኻ​ልን? የሚ​በ​ላ​ውን ፈልጎ አይ​ደ​ለ​ምን? ወይስ በሬ በበ​ረት ውስጥ ገለባ ሳለው ይጮ​ኻ​ልን?</verse>
				<verse number="6">ምግብ ያለ ጨው ይበ​ላ​ልን? የጎ​መን ዘር ጭማ​ቂስ ይጣ​ፍ​ጣ​ልን? ወይስ ለከ​ንቱ ጣዕም አለ​ውን?</verse>
				<verse number="7">ሰው​ነቴ ማረፍ አል​ቻ​ለ​ችም፤ የሥ​ጋ​ዬን ክር​ፋት እንደ አን​በሳ ክር​ፋት እመ​ለ​ከ​ተ​ዋ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="8">ልመ​ናዬ ምነው በደ​ረ​ሰ​ልኝ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተስ​ፋ​ዬን ምነው በሰ​ጠኝ!</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያቈ​ስ​ለኝ ዘንድ ጀመረ፥ ነገር ግን እስከ መጨ​ረ​ሻው አላ​ጠ​ፋ​ኝም።</verse>
				<verse number="10">መቃ​ብሬ በግ​ንቡ የም​መ​ላ​ለ​ስ​በት ከተ​ማዬ ይሁን፥ ከእ​ር​ሱም ፈቀቅ አል​ልም የአ​ም​ላ​ኬን ቅዱስ ቃል አል​ካ​ድ​ሁ​ምና።</verse>
				<verse number="11">እታ​ገሥ ዘንድ ጕል​በቴ ምን​ድን ነው? ነፍ​ሴም ትጽ​ናና ዘንድ ዘመኔ ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="12">ጕል​በቴ የድ​ን​ጋይ ጉል​በት ነውን? በውኑ ሥጋ​ዬስ እንደ ናስ ነውን?</verse>
				<verse number="13">በእ​ርሱ የታ​መ​ንሁ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ረድ​ኤቱ ከእኔ ለምን ራቀ?</verse>
				<verse number="14">ምሕ​ረቱ ቸል አለኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ጐ​በ​ኘ​ኝም አል​ተ​መ​ለ​ከ​ተ​ኝም።</verse>
				<verse number="15">“ወን​ድ​ሞ​ቼም እንደ ደረቅ ወንዝ፥ እንደ አለፈ ማዕ​በ​ልም አላ​ወ​ቁ​ኝም።</verse>
				<verse number="16">ያከ​ብ​ሩኝ የነ​በሩ እነ​ዚያ፥ አሁን እንደ በረ​ዶና እንደ ረጋ አመ​ዳይ ሆኑ​ብኝ፤</verse>
				<verse number="17">ወደ ሙቀት ሲቀ​ርብ በቀ​ለጠ ጊዜ ምን እንደ ነበረ አይ​ታ​ወ​ቅም።</verse>
				<verse number="18">እን​ደ​ዚ​ሁም እኔ ከሁሉ ተለ​ይቼ ጠፋሁ፥ ከቤ​ቴም ወጥቼ የተ​ጣ​ልሁ ሆንሁ።</verse>
				<verse number="19">የቴ​ማ​ና​ው​ያ​ንን መን​ገ​ዶች፥ የሳ​ባ​ው​ያ​ንን ክፋ​ትና ቸል​ተ​ኝ​ነት ተመ​ል​ከቱ።</verse>
				<verse number="20">በከ​ተ​ሞ​ችና በገ​ን​ዘ​ቦች የሚ​ታ​መኑ ያፍ​ራሉ።</verse>
				<verse number="21">አሁ​ንም እና​ንተ ያለ ምሕ​ረት መጣ​ችሁ፤ ቍስ​ሌ​ንም አይ​ታ​ችሁ ፈራ​ችሁ።</verse>
				<verse number="22">ለምን? በውኑ፦ ከእ​ና​ንተ አን​ዳች ነገር ጠየ​ቅ​ሁን? ወይስ፦ ከእ​ና​ንተ ኀይ​ልን ተመ​ኘ​ሁን?</verse>
				<verse number="23">ወይስ ከጠ​ላ​ቶች እጅ ታስ​ጥ​ሉኝ ዘንድ ከኀ​ይ​ለ​ኞ​ችም እጅ ታድ​ኑኝ ዘንድ።</verse>
				<verse number="24">“አስ​ተ​ም​ሩኝ፥ እኔም አዳ​ም​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ የተ​ሳ​ሳ​ት​ሁ​ትም ካለ አስ​ረ​ዱኝ።</verse>
				<verse number="25">የእ​ው​ነ​ተኛ ሰው ቃል ሐሰ​ትን ይመ​ስ​ላል፥ ከእ​ና​ንተ ዘንድ ኀይ​ልን የም​ጠ​ይቅ አይ​ደ​ለ​ምና።</verse>
				<verse number="26">የን​ግ​ግ​ራ​ች​ሁም ማጽ​ና​ናት ዕረ​ፍ​ትን አይ​ሰ​ጠ​ኝም፤ የአ​ን​ደ​በ​ታ​ች​ሁም ቅል​ጥ​ፍና ደስ አያ​ሰ​ኘ​ኝም።</verse>
				<verse number="27">በድሃ አደጉ ላይ ትስ​ቃ​ላ​ች​ሁና፥ ወዳ​ጃ​ች​ሁ​ንም ትሰ​ድ​ባ​ላ​ች​ሁና።</verse>
				<verse number="28">አሁ​ንም፥ ፊታ​ች​ሁን አይቼ ሐሰት አል​ና​ገ​ርም።</verse>
				<verse number="29">አሁ​ንም ተቀ​መጡ፤ በደ​ልም አይ​ኑር፤ ዳግ​መ​ኛም ከጻ​ድቁ ጋር አንድ ሁኑ።</verse>
				<verse number="30">በአ​ን​ደ​በቴ በደል የለ​ምና አፌ ጕሮ​ሮ​ዬም ጥበ​ብን ይና​ገ​ራል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">“ጥን​ቱን በም​ድር ላይ የሰው ሕይ​ወት ጥላ አይ​ደ​ለ​ምን? ኑሮ​ውስ እንደ ቀን ምን​ደኛ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="2">ወይም ጌታ​ውን እን​ደ​ሚ​ፈራ አገ​ል​ጋይ ጥላ​ው​ንም እን​ደ​ሚ​መኝ፥ ወይም ደመ​ወ​ዙን እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቅ ምን​ደኛ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="3">እን​ዲሁ እኔ የከ​ንቱ ወራ​ትን ታገ​ሥሁ፥ የፃ​ዕ​ርም ሌሊት ተወ​ሰ​ነ​ች​ልኝ።</verse>
				<verse number="4">በተ​ኛ​ሁም ጊዜ፦ መቼ ይነ​ጋል? እላ​ለሁ፤ በተ​ነ​ሣ​ሁም ጊዜ ዳግ​መኛ መቼ ይመ​ሻል? እላ​ለሁ፤ ከማታ እስከ ጥዋት ድረስ መከ​ራን ጠገ​ብሁ።</verse>
				<verse number="5">ሥጋዬ በት​ልና በመ​ግል በስ​ብ​ሶ​አል፥ ቍስ​ሌን በገል እያ​ከ​ክሁ አለ​ቅሁ። ዐመ​ድም ሆንሁ።</verse>
				<verse number="6">ሕይ​ወቴ እንደ ሸማኔ መወ​ር​ወ​ርያ፥ ቀላል ሆነች በከ​ንቱ ተስ​ፋም ጠፋሁ።</verse>
				<verse number="7">ሕይ​ወቴ እስ​ት​ን​ፋስ እንደ ሆነች አስብ፤ ዐይ​ኔም መል​ካም ነገ​ርን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ዳግ​መኛ አታ​ይም።</verse>
				<verse number="8">የሚ​ያ​የኝ ሰው ዐይን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አያ​የ​ኝም፤ ዐይ​ንህ በእኔ ላይ ይሆ​ናል፤ እኔም አል​ገ​ኝም።</verse>
				<verse number="9">ደመና ከሰ​ማይ ተበ​ትኖ እን​ደ​ሚ​ጠፋ፥ እን​ዲሁ ወደ መቃ​ብር የሚ​ወ​ርድ ሰው ዳግ​መኛ አይ​ወ​ጣም።</verse>
				<verse number="10">ወደ ቤቱም ዳግ​መኛ አይ​መ​ለ​ስም፥ ስፍ​ራ​ውም ዳግ​መኛ እር​ሱን አያ​ው​ቀ​ውም።</verse>
				<verse number="11">ስለ​ዚ​ህም እኔ አፌን አል​ከ​ለ​ክ​ልም፤ በመ​ን​ፈሴ ጭን​ቀ​ትን እና​ገ​ራ​ለሁ፤ የነ​ፍ​ሴ​ንም ምሬት በኀ​ዘን እገ​ል​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">ጠባቂ አዝ​ዘ​ህ​ብ​ኛ​ልና፥ እኔ ባሕር ወይስ አን​በሪ ነኝን?</verse>
				<verse number="13">እኔም፦ አል​ጋዬ ያጽ​ና​ናኝ ይሆን? መኝ​ታ​ዬስ ደስ ያሰ​ኘኝ ይሆን? እላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">አን​ተም በሕ​ልም ታስ​ፈ​ራ​ራ​ኛ​ለህ፥ በራ​እ​ይም ታስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ኛ​ለህ፤</verse>
				<verse number="15">ሕይ​ወ​ትን ከመ​ን​ፈሴ ትለ​ያ​ለህ። አጥ​ን​ቶ​ቼ​ንም ከሞት ትጠ​ብ​ቃ​ለህ።</verse>
				<verse number="16">እን​ድ​ታ​ገሥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እኖ​ራ​ለ​ሁን? ሕይ​ወቴ ከንቱ ነውና ከእኔ ራቅ።</verse>
				<verse number="17">ሰው ምን​ድን ነው? ከፍ ከፍ ታደ​ር​ገው ዘንድ፥ ልቡ​ና​ው​ንም ትጐ​በ​ኘው ዘንድ፥</verse>
				<verse number="18">ማለዳ ማለ​ዳስ ትጐ​በ​ኘው ዘንድ፥ በዕ​ረ​ፍ​ቱም ትፈ​ር​ድ​ለት ዘንድ፥</verse>
				<verse number="19">የማ​ታ​ሳ​ር​ፈኝ እስከ መቼ ነው? ምራ​ቄ​ንስ እስ​ክ​ውጥ ድረስ የማ​ት​ለ​ቅ​ቀኝ እስከ መቼ ነው?</verse>
				<verse number="20">የሰ​ውን ልብ፦ የም​ታ​ውቅ ሆይ፥ በድ​ዬስ እንደ ሆነ እን​ግ​ዲህ ምን ላደ​ር​ግ​ልህ እች​ላ​ለሁ? ስለ​ምን እኔን ለመ​ከራ አደ​ረ​ግ​ኸኝ? ስለ ምን በአ​ንተ ላይ እን​ድ​ና​ገር በአ​ም​ሳ​ልህ ፈጠ​ር​ኸኝ? ስለ ምንስ እኔ ሸክም ሆን​ሁ​ብህ?</verse>
				<verse number="21">ስለ ምን መተ​ላ​ለ​ፌን ይቅር አት​ልም? ኀጢ​አ​ቴ​ንስ ስለ ምን አታ​ነ​ጻም? አሁን በም​ድር ውስጥ እተ​ኛ​ለሁ፤ በማ​ለ​ዳም አል​ነ​ቃም።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">አው​ኬ​ና​ዊው በል​ዳ​ዶስ መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“እስከ መቼ ይህን ነገር ትና​ገ​ራ​ለህ? ወይስ ነገ​ርን የማ​ብ​ዛት መን​ፈስ በአ​ፍህ አለን?</verse>
				<verse number="3">በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዐ​መፅ ይፈ​ር​ዳ​ልን? ሁሉን የፈ​ጠረ አም​ላ​ክስ ጽድ​ቅን ያጣ​ም​ማ​ልን?</verse>
				<verse number="4">ልጆ​ችህ በፊቱ በድ​ለው እንደ ሆነ፥ እርሱ በበ​ደ​ላ​ቸው እጅ ጥሎ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="5">“አንተ ግን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገሥ​ግሥ፥ ሁሉን ወደ​ሚ​ች​ለው አም​ላ​ክም ጸልይ፥</verse>
				<verse number="6">ንጹ​ሕና ጻድቅ ብት​ሆን፥ ልመ​ና​ህን ፈጥኖ ይሰ​ማ​ሃል፥ የጽ​ድ​ቅ​ህ​ንም ብድ​ራት ፈጽሞ ይሰ​ጥ​ሃል።</verse>
				<verse number="7">ጅማ​ሬ​ህም ታናሽ ቢሆ​ንም እንኳ ፍጻ​ሜህ ቍጥር አይ​ኖ​ረ​ውም።</verse>
				<verse number="8">ስለ​ዚህ የቀ​ደ​መ​ውን ትው​ልድ ጠይቅ፥ አባ​ቶ​ች​ንም በየ​ወ​ገ​ና​ቸው በት​ጋት መር​ምር፥</verse>
				<verse number="9">እኛ የት​ና​ንት ብቻ ነን ምንም አና​ው​ቅም፤ ሕይ​ወ​ታ​ችን በም​ድር ላይ እንደ ጥላ ነውና</verse>
				<verse number="10">እነ​ርሱ የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩ​ህና የሚ​ነ​ግ​ሩህ፥ ቃል​ንም ከል​ባ​ቸው የሚ​ያ​ወጡ አይ​ደ​ሉ​ምን?</verse>
				<verse number="11">“በውኑ ደን​ገል ረግ​ረግ በሌ​ለ​በት መሬት ይበ​ቅ​ላ​ልን? ወይስ ቄጠማ ውኃ በሌ​ለ​በት ቦታ ይለ​መ​ል​ማ​ልን?</verse>
				<verse number="12">ገና በሥሩ ሳለ፥ ሳይ​ቈ​ረ​ጥም፥ ውኃ የማ​ይ​ጠጣ ተክል ሁሉ ይደ​ር​ቃል።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ረሱ ሁሉ ፍጻ​ሜ​አ​ቸው እን​ዲሁ ነው፤ የዝ​ንጉ ሰውም ተስፋ ትጠ​ፋ​ለች፤</verse>
				<verse number="14">ቤቱም ያለ ነዋሪ ይቀ​ራል፥ ማደ​ሪ​ያ​ውም የሸ​ረ​ሪት ድር ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="15">ቤቱን ቢደ​ግ​ፈ​ውም አይ​ቆ​ም​ለ​ትም፤ የጀ​መ​ረ​ው​ንም አይ​ፈ​ጽ​ምም።</verse>
				<verse number="16">ከፀ​ሐይ በታች ይሻ​ግ​ታል፤ ጫፉም በአ​ት​ክ​ልት ቦታ ይወ​ጣል።</verse>
				<verse number="17">በድ​ን​ጋይ ክምር ላይ ያድ​ራል፤ በድ​ን​ጋ​ዮ​ቹም መካ​ከል ይኖ​ራል።</verse>
				<verse number="18">ቦታው ቢው​ጠው፦ እን​ደ​ዚህ ያለ አላ​የ​ሁም ብሎ ይክ​ደ​ዋል።</verse>
				<verse number="19">ኀጢ​አ​ተ​ኞች እን​ዲሁ ይጠ​ፋ​ሉና፤ ሌሎ​ችም ከመ​ሬት ይበ​ቅ​ላሉ።</verse>
				<verse number="20">እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዋ​ሁን ሰው አይ​ጥ​ለ​ውም፥ የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞ​ች​ንም እጅ አያ​በ​ረ​ታም። የዝ​ን​ጉ​ዎ​ች​ንም መባ አይ​ቀ​በ​ልም።</verse>
				<verse number="21">የቅ​ኖ​ችን አፍ ሳቅ ይሞ​ላል፥ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም ምስ​ጋና ይሞ​ላል።</verse>
				<verse number="22">ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ኀፍ​ረ​ትን ይለ​ብ​ሳሉ፤ የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞ​ችም ቤት ይጠ​ፋል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">ኢዮ​ብም እን​ዲህ ሲል መለሰ፦</verse>
				<verse number="2">“በእ​ው​ነት እን​ዲህ እንደ ሆነ ዐወ​ቅሁ፤ ሰውስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጻድቅ መሆን እን​ዴት ይች​ላል?</verse>
				<verse number="3">ከእ​ርሱ ጋር ይከ​ራ​ከር ዘንድ ቢወ​ድድ፥ ከሺህ ነገር አን​ዱን መመ​ለስ አይ​ች​ልም።</verse>
				<verse number="4">በልቡ ጠቢብ ነው፥ ኀይ​ለ​ኛም፥ ታላ​ቅም ነው፤ ክፉስ ሆኖ በፊቱ የቆመ ማን ነው?</verse>
				<verse number="5">ተራ​ሮ​ችን ይነ​ቅ​ላል፤ አያ​ው​ቁ​ት​ምም፤ በቍ​ጣ​ውም ይገ​ለ​ብ​ጣ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">ምድ​ርን ከሰ​ማይ በታች ከመ​ሠ​ረቷ ያና​ው​ጣ​ታል፥ ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ዋም ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="7">ፀሐ​ይን ያዝ​ዛ​ታል፥ አት​ወ​ጣ​ምም፤ ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም ያት​ማል።</verse>
				<verse number="8">ሰማ​ያ​ትን ብቻ​ውን ይዘ​ረ​ጋል፥ በም​ድር ላይ እን​ደ​ሚ​ሄድ በማ​ዕ​በል ላይ ይሄ​ዳል።</verse>
				<verse number="9">ድብ የሚ​ባ​ለ​ውን ኮከ​ብና ኦሪ​ዮን የሚ​ባ​ለ​ውን ኮከብ፥ የአ​ጥ​ቢያ ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም፥ በአ​ዜ​ብም በኩል ያሉ​ትን የከ​ዋ​ክ​ብት ማደ​ሪ​ያ​ዎች ፈጥ​ሮ​አል።</verse>
				<verse number="10">ታላ​ቁ​ንና የማ​ይ​መ​ረ​መ​ረ​ውን ነገር፥ እን​ዲ​ሁም የከ​በ​ረ​ው​ንና እጅግ መል​ካም የሆ​ነ​ውን የማ​ይ​ቈ​ጠ​ረ​ው​ንም ተአ​ም​ራት አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="11">እነሆ፥ ቢመ​ጣ​ብኝ አላ​የ​ውም፤ ቢያ​ል​ፍ​ብ​ኝም አላ​ው​ቀ​ውም።</verse>
				<verse number="12">እርሱ ቢያ​ርቅ የሚ​መ​ልስ ማን ነው? እር​ሱ​ንስ፦ ምን ታደ​ር​ጋ​ለህ? የሚ​ለው ማን ነው?</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔን ከመ​ቅ​ጣት አል​ተ​መ​ለ​ሰም፥ ከእ​ር​ሱም የተ​ነሣ ከሰ​ማይ በታች ያሉ አና​ብ​ርት ይዋ​ረ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="14">ቃሌን እን​ዴት ይሰ​ማ​ኛል? እን​ዴ​ትስ ይተ​ረ​ጕ​መ​ዋል?</verse>
				<verse number="15">በጽ​ድቅ ብጠ​ራው፥ ባይ​ሰ​ማ​ኝም፥ የእ​ር​ሱን ፍርድ እለ​ም​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">ብጠ​ራው፥ እር​ሱም ቢመ​ል​ስ​ልኝ ኖሮ፥ እንደ ሰማኝ አላ​ም​ንም ነበር።</verse>
				<verse number="17">“በዐ​ውሎ ነፋስ ይቀ​ጠ​ቅ​ጠ​ኛል፤ ያለ ምክ​ን​ያት ብዙ ጊዜ ያቈ​ስ​ለ​ኛል።</verse>
				<verse number="18">እተ​ነ​ፍስ ዘንድ አይ​ተ​ወ​ኝም፤ ነገር ግን መራራ ነገ​ርን አጥ​ግ​ቦ​ኛል።</verse>
				<verse number="19">እርሱ በኀ​ይል ይይ​ዛ​ልና፤ ፍር​ዱን ማን ይቃ​ወ​ማል?</verse>
				<verse number="20">ጻድቅ ብሆን አፌ ይወ​ቅ​ሰ​ኛል፤ ፍጹ​ምም ብሆን ጠማማ ያደ​ር​ገ​ኛል።</verse>
				<verse number="21">ንጹሕ ነኝ፤ ራሴ​ንም አላ​ው​ቅም፤ ነገር ግን ሕይ​ወቴ ጠፋች።</verse>
				<verse number="22">“ስለ​ዚህ እን​ዲህ እላ​ለሁ፦ ታላ​ቁና ኀያሉ መቅ​ሠ​ፍ​ትን ይል​ካል።</verse>
				<verse number="23">የኃ​ጥ​ኣን ሞታ​ቸው ክፉ ነውና፥ በጻ​ድ​ቃን ይስ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="24">በኃ​ጥ​ኣን እጅ ተሰ​ጥ​ተ​ዋ​ልና፤ የም​ድር ፈራ​ጆ​ችን ፊት ይሸ​ፍ​ናል፤ እርሱ ካል​ሆነ ማን ነው?</verse>
				<verse number="25">ሕይ​ወቴ ከሚ​ሮጥ ሰው ይልቅ ይፈ​ጥ​ናል፤ ይሸ​ሻል፥ መል​ካ​ም​ንም አያ​ይም።</verse>
				<verse number="26">የመ​ር​ከብ መን​ገድ ፍለጋ፥ ወይም የሚ​በ​ርና የሚ​በ​ላ​ውን የሚ​ፈ​ልግ የን​ስር ፍለጋ እን​ደ​ማ​ይ​ታ​ወቅ ሕይ​ወቴ እን​ዲሁ ሆነ።</verse>
				<verse number="27">እኔ ብና​ገር የሚ​ጠ​ቅ​መኝ የለም፤ ፊቴም በጩ​ኸት ወደቀ፤</verse>
				<verse number="28">ሰው​ነ​ቶቼ ሁሉ ተነ​ዋ​ወጡ፤ እን​ግ​ዲህ ንጹሕ አድ​ር​ገህ እን​ደ​ማ​ት​ተ​ወኝ አው​ቃ​ለሁ፥</verse>
				<verse number="29">“ኃጢ​ኣ​ተኛ ሰው ከሆ​ንሁ፤ ስለ ምን አል​ሞ​ት​ሁም?</verse>
				<verse number="30">ብታ​ጠብ፥ እንደ በረ​ዶም ብነጻ፥ እጆ​ቼ​ንም እጅግ ባነጻ፥</verse>
				<verse number="31">በአ​ዘ​ቅት ውስጥ ታሰ​ጥ​መ​ኛ​ለህ፤ ልብ​ሴም ይጸ​የ​ፈ​ኛል።</verse>
				<verse number="32">የሚ​ከ​ራ​ከ​ረኝ ሰው ቢሆን ኖሮ፥ ወደ አደ​ባ​ባይ በአ​ን​ድ​ነት በሄ​ድን ነበር!</verse>
				<verse number="33">ማዕ​ከ​ላዊ ዳኛ ቢኖር፥ በሁ​ለ​ታ​ች​ንም መካ​ከል የሚ​ሰማ ቢገኝ ኖሮ፥</verse>
				<verse number="34">በትሩ ከእኔ ላይ በራቀ ነበር፤ ግር​ማ​ውም ባላ​ስ​ፈ​ራኝ ነበር።</verse>
				<verse number="35">እና​ገ​ርም ነበር፤ አል​ፈ​ራ​ምም ነበር፤ የማ​ው​ቀ​ውም ነገር የለም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">“ነፍሴ ስለ ተጨ​ነ​ቀች ቃሌን በእ​ን​ጕ​ር​ጕሮ አሰ​ማ​ለሁ፤ ነፍ​ሴም እየ​ተ​ጨ​ነ​ቀች በም​ሬት እና​ገ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲህ እለ​ዋ​ለሁ፦ ኀጢ​ኣ​ተኛ እን​ድ​ሆን አታ​ስ​ተ​ም​ረኝ፤ ለም​ንስ እን​ደ​ዚህ ፈረ​ድ​ህ​ብኝ?</verse>
				<verse number="3">ኀጢ​ኣ​ተኛ ብሆን በአ​ንተ ዘንድ መል​ካም ነውን? የእ​ጅ​ህን ሥራ ቸል ብለ​ሃ​ልና፤ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም ምክር ተመ​ል​ክ​ተ​ሃ​ልና።</verse>
				<verse number="4">በውኑ የሰው ዐይን አለ​ህን? ወይስ መዋቲ ሰው እን​ደ​ሚ​ያይ ታያ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="5">ዘመ​ንህ እንደ ሰው ዘመን ነውን? ወይስ ዓመ​ታ​ትህ እንደ ሰው ዓመ​ታት ናቸ​ውን?</verse>
				<verse number="6">ክፋ​ቴን ትፈ​ላ​ለግ ዘንድ፥ ኀጢ​ኣ​ቴ​ንም ትመ​ረ​ምር ዘንድ፥</verse>
				<verse number="7">ከዚህ በላይ በደ​ለኛ እን​ዳ​ል​ሆ​ንሁ፥ አንተ ታው​ቃ​ለህ። ነግር ግን ከእ​ጅህ የሚ​ያ​መ​ልጥ ማን ነው?</verse>
				<verse number="8">“እጆ​ችህ ፈጠ​ሩኝ፤ ሠሩ​ኝም፤ ከዚ​ያም በኋላ ዞረህ ጣል​ኸኝ።</verse>
				<verse number="9">ከጭቃ እንደ ፈጠ​ር​ኸኝ አስብ፤ ዳግ​መ​ኛም ወደ ትቢያ ትመ​ል​ሰ​ኛ​ለህ፤</verse>
				<verse number="10">በውኑ እንደ ወተት አላ​ፈ​ሰ​ስ​ኸ​ኝ​ምን? እንደ እር​ጎስ አላ​ረ​ጋ​ኸ​ኝ​ምን?</verse>
				<verse number="11">ቍር​በ​ትና ሥጋን አለ​በ​ስ​ኸኝ፤ በአ​ጥ​ን​ትና በዥ​ማ​ትም አጠ​ነ​ከ​ር​ኸኝ።</verse>
				<verse number="12">ሕይ​ወ​ትና ቸር​ነ​ትን ሰጠ​ኸኝ። መጐ​ብ​ኘ​ት​ህም መን​ፈ​ሴን ጠበ​ቀ​ልኝ።</verse>
				<verse number="13">ይህ ሁሉ በአ​ንተ ዘንድ አለ። ሁሉን ነገር ማድ​ረግ እን​ደ​ም​ት​ችል፥ የሚ​ሳ​ን​ህም እንደ ሌለ አው​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">ኀጢ​ኣት ብሠራ አንተ ትጠ​ባ​በ​ቀ​ኛ​ለህ፤ ከኀ​ጢ​ኣ​ቴም ንጹሕ አታ​ደ​ር​ገ​ኝም።</verse>
				<verse number="15">በደ​ለኛ ብሆን ወዮ​ልኝ፤ ጻድ​ቅም ብሆን ራሴን አላ​ነ​ሣም፤ ጕስ​ቍ​ል​ና​ንም ጠገ​ብ​ኋት።</verse>
				<verse number="16">ለመ​ገ​ደል እንደ አን​በሳ ታደ​ንሁ። ተመ​ል​ሰ​ህም ፈጽ​መህ ታጠ​ፋ​ኛ​ለህ።</verse>
				<verse number="17">ዳግ​መ​ኛም ከጥ​ንት ጀምሮ ትመ​ረ​ም​ረ​ኛ​ለህ፤ ታላቅ መቅ​ሠ​ፍ​ትን አመ​ጣ​ህ​ብኝ። ፈተ​ና​ዎ​ች​ንም ላክ​ህ​ብኝ።</verse>
				<verse number="18">“ስለ ምን ከማ​ኅ​ፀን አወ​ጣ​ኸኝ? ዐይ​ንም ሳያ​የኝ ለምን አል​ሞ​ት​ሁም?</verse>
				<verse number="19">እን​ዳ​ል​ነ​በ​ረስ ለምን አል​ሆ​ን​ሁም? ከማ​ኅ​ፀ​ንም ወደ መቃ​ብር ለምን አል​ወ​ረ​ድ​ሁም?</verse>
				<verse number="20">የሕ​ይ​ወቴ ዘመን አጭር አይ​ደ​ለ​ምን? ጥቂት አርፍ ዘንድ ተወኝ፤</verse>
				<verse number="21">ወደ​ማ​ል​መ​ለ​ስ​በት ስፍራ፥ ወደ ጨለ​ማና ወደ ጭጋግ ምድር፥</verse>
				<verse number="22">የዘ​ለ​ዓ​ለም ጨለ​ማም ወደ አለ​ባት፥ ብር​ሃ​ንም ወደ​ሌ​ለ​ባት፥ ማንም የሟ​ችን ሕይ​ወት ወደ​ማ​ያ​ይ​ባት ምድር ሳል​ሄድ ጥቂት አርፍ ዘንድ ተወኝ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">አሜ​ና​ዊው ሶፋር መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“ብዙ እን​ደ​ም​ት​ና​ገር እን​ዲሁ መስ​ማት አለ​ብህ። ወይስ በን​ግ​ግ​ርህ ብዛት ጻድቅ የም​ት​ሆን ይመ​ስ​ል​ሃ​ልን? ከሴ​ቶች የሚ​ወ​ለድ ዘመኑ ጥቂት የሆነ ቡሩክ ነው።</verse>
				<verse number="3">ንግ​ግር አታ​ብዛ፤ የሚ​ከ​ራ​ከ​ርህ የለ​ምና።</verse>
				<verse number="4">አንተ፦ በሥ​ራዬ ንጹሕ ነኝ በፊ​ቱም ጻድቅ ነኝ አት​በል።</verse>
				<verse number="5">ምነው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢና​ገ​ርህ! በአ​ን​ተም ላይ ከን​ፈ​ሩን ቢከ​ፍት!</verse>
				<verse number="6">የጥ​በ​ቡን ኀይል ቢገ​ል​ጥ​ልህ! ባንተ ላይ ያለው እጥፍ ነውና። ያን​ጊ​ዜም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በበ​ደ​ልህ ያገ​ኘህ ትክ​ክል እንደ ሆነ ታው​ቃ​ለህ።</verse>
				<verse number="7">“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍለጋ ልት​መ​ረ​ምር ትች​ላ​ለ​ህን? ወይስ ሁሉን የሚ​ችል አም​ላክ ወደ ፈጠ​ረው ፍጥ​ረት ፍጻሜ ትደ​ር​ሳ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="8">ሰማይ ከፍ ያለ ነው፤ ምን ልታ​ደ​ርግ ትች​ላ​ለህ? ከሲ​ኦ​ልም ይልቅ የጠ​ለቁ ነገ​ሮች አሉ፤ ምን ታው​ቃ​ለህ?</verse>
				<verse number="9">ርዝ​መቱ ከም​ድር ይልቅ ይረ​ዝ​ማል፥ ከባ​ሕ​ርም ይልቅ ይሰ​ፋል።</verse>
				<verse number="10">እርሱ ሁሉን ቢገ​ለ​ብጥ፥ ምን አደ​ረ​ግህ? የሚ​ለው ማን ነው?</verse>
				<verse number="11">እርሱ የኃ​ጥ​ኣን ሰዎች ሥራን ያው​ቃል፤ በደ​ል​ንም ቢያይ ዝም ብሎ አይ​መ​ለ​ከ​ትም፤ ይህ​ንም አስ​ተ​ዋይ ሰው ያስ​ተ​ው​ላል።</verse>
				<verse number="12">ነገር ግን በከ​ንቱ ነገ​ርን የሚ​ፈ​ልግ ሰው፥ ከሴ​ትም የሚ​ወ​ለድ ሟች የሜዳ አህ​ያን ይመ​ስ​ላል።</verse>
				<verse number="13">አንተ ልብ​ህን ንጹሕ ብታ​ደ​ርግ፥ እጆ​ች​ህ​ንም ወደ እርሱ ብት​ዘ​ረጋ፥</verse>
				<verse number="14">በእ​ጆ​ችህ በደል ቢኖር ካንተ አር​ቀው፤ በል​ብ​ህም ኀጢ​አት አይ​ኑር፤</verse>
				<verse number="15">በዚ​ያን ጊዜ ፊትህ በን​ጹሕ ውኃ እንደ ታጠበ ያበ​ራል፥ መተ​ዳ​ደ​ፍ​ህ​ንም ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ፥ አት​ፈ​ራ​ምም።</verse>
				<verse number="16">መከ​ራ​ህ​ንም እን​ዳ​ለፈ ማዕ​በል ትረ​ሳ​ለህ፥ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ አት​ደ​ነ​ግ​ጥም።</verse>
				<verse number="17">ጸሎ​ትህ እንደ አጥ​ቢያ ኮከብ ይሆ​ናል። ሕይ​ወ​ት​ህም እንደ ቀትር ብር​ሃን ያበ​ራል።</verse>
				<verse number="18">ተስ​ፋ​ህ​ንም ታገኝ ዘንድ ተዘ​ል​ለህ ትቀ​መ​ጣ​ለህ፤ ያለ ኀዘ​ንና ጭን​ቀ​ትም በደ​ኅ​ን​ነት ትኖ​ራ​ለህ።</verse>
				<verse number="19">ታር​ፋ​ለህ፥ የሚ​ዋ​ጋ​ህም የለም፤ ብዙ ሰዎ​ችም ይመ​ጣሉ፤ ልመ​ናም ያቀ​ር​ቡ​ል​ሃል።</verse>
				<verse number="20">የኃ​ጥ​ኣን መድ​ኀ​ኒ​ታ​ቸው ታል​ቃ​ለች። ተስ​ፋ​ቸ​ው​ንም ያጣሉ፥ የዝ​ን​ጉ​ዎች ዐይ​ኖ​ችም ይጠ​ፋሉ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">ኢዮ​ብም መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“በእ​ር​ግጥ እና​ንተ ዓይ​ነ​ተ​ኞች ሰዎች ናችሁ፤ ጥበ​ብም በእ​ና​ንተ ዘንድ ትፈ​ጸ​ማ​ለች።</verse>
				<verse number="3">ነገር ግን እኔ ደግሞ እንደ እና​ንተ ልብ አለኝ። እኔ ከእ​ና​ንተ የማ​ንስ አይ​ደ​ለ​ሁም፥ እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ነገር የሚ​ያ​ውቅ ማነው?</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የጠ​ራሁ እር​ሱም የመ​ለ​ሰ​ልኝ እኔ፥ ለባ​ል​ን​ጀ​ራው መሣ​ለ​ቂያ እን​ደ​ሚ​ሆን ሰው ሆኛ​ለሁ፤ ጻድ​ቁና ንጹሑ ሰው መሣ​ለ​ቂያ ሆኖ​አል።</verse>
				<verse number="5">እርሱ በተ​ወ​ሰ​ነው ዕድሜ በሌ​ሎች እን​ዲ​ወ​ድቅ፥ ቤቱም በኃ​ጥ​ኣን እን​ዲ​ፈ​ርስ ተዘ​ጋ​ጅቶአል። ነገር ግን ማንም ክፉ ሆኖ ንጹሕ እን​ደ​ሚ​ሆን አይ​መን።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​ስ​ቈ​ጡ​ትን ሰዎች፥ እርሱ የሚ​መ​ረ​ም​ራ​ቸው አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="7">“አሁን ግን እን​ስ​ሶ​ችን ጠይቅ፥ ያስ​ተ​ም​ሩ​ህ​ማል፤ የሰ​ማ​ይ​ንም ወፎች ጠይቅ፥ ይነ​ግ​ሩ​ህ​ማል።</verse>
				<verse number="8">ለም​ድር ንገ​ራት፥ እር​ስ​ዋም ትተ​ረ​ጕ​ም​ል​ሃ​ለች፤ የባ​ሕ​ርም ዓሣ​ዎች ያስ​ረ​ዱ​ሃል።</verse>
				<verse number="9">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ይህን ሁሉ እን​ዳ​ደ​ረገ ከእ​ነ​ዚህ ሁሉ የማ​ያ​ውቅ ማን ነው?</verse>
				<verse number="10">የሕ​ያ​ዋን ሁሉ ነፍስ፥ የሰ​ውም ሁሉ መን​ፈስ በእጁ ናትና።</verse>
				<verse number="11">ዦሮ ነገ​ርን የሚ​ለይ አይ​ደ​ለ​ምን? ጕረ​ሮስ መብ​ልን የሚ​ቀ​ምስ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="12">በረ​ዥም ዘመን ጥበብ፥ በመ​ኖር ብዛ​ትም ዕው​ቀት ይገ​ኛል።</verse>
				<verse number="13">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ጥበ​ብና ኀይል አለ፤ ለእ​ርሱ ምክ​ርና ማስ​ተ​ዋል አለው።</verse>
				<verse number="14">እነሆ፥ እርሱ ቢያ​ፈ​ርስ፥ ማን ይሠ​ራል? በሰ​ውም ላይ ቢዘ​ጋ​በት ማን ይከ​ፍ​ታል?</verse>
				<verse number="15">እነሆ፥ ዝና​ብን ከሰ​ማይ ቢከ​ለ​ክል ምድ​ርን ያደ​ር​ቃ​ታል፤ እን​ደ​ገና ቢተ​ዋ​ትም ትጠ​ፋ​ለች፤ ትገ​ለ​በ​ጣ​ለ​ችም።</verse>
				<verse number="16">ኀይ​ልና ብር​ታት በእ​ርሱ ዘንድ ናቸው፤ ዕው​ቀ​ትና ማስ​ተ​ዋ​ልም ለእ​ርሱ ናቸው።</verse>
				<verse number="17">መካ​ሮ​ች​ንም እን​ዲ​ማ​ረኩ ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ የም​ድር ፈራ​ጆ​ች​ንም አላ​ዋ​ቆች ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="18">ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም በዙ​ፋን ያስ​ቀ​ም​ጣ​ቸ​ዋል፤ ወገ​ባ​ቸ​ው​ንም በኀ​ይል መታ​ጠ​ቂያ ያስ​ታ​ጥ​ቃ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="19">ካህ​ናተ ጣዖ​ትን እን​ዲ​ማ​ረኩ ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ የም​ድር ኀያ​ላ​ን​ንም ይገ​ለ​ብ​ጣ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="20">ከታ​መኑ ሰዎ​ችም ቋን​ቋን ይለ​ው​ጣል፤ የሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ች​ንም ምክር ያው​ቃል።</verse>
				<verse number="21">በአ​ለ​ቆች ላይ ውር​ደ​ትን ያመ​ጣል፥ ትሑ​ታ​ን​ንም ያድ​ና​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="22">ጥልቅ ነገ​ርን ከጨ​ለማ ይገ​ል​ጣል፤ የሞ​ት​ንም ጥላ ወደ ብር​ሃን ያወ​ጣል።</verse>
				<verse number="23">አሕ​ዛ​ብን ያቅ​በ​ዘ​ብ​ዛ​ቸ​ዋል፤ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ልም፤ አሕ​ዛ​ብ​ንም ይገ​ለ​ብ​ጣ​ቸ​ዋል፤ ያፈ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ልም።</verse>
				<verse number="24">የም​ድር አለ​ቆች ማስ​ተ​ዋ​ልን ይለ​ው​ጣል። በማ​ያ​ው​ቁት መን​ገ​ድም ያቅ​በ​ዘ​ብ​ዛ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="25">ብር​ሃ​ንም ሳይ​ኖር በጨ​ለማ ይር​መ​ሰ​መ​ሳሉ፤ እንደ ሰካ​ራ​ምም ይፍ​ገ​መ​ገ​ማሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">“እነሆ፥ ይህን ሁሉ ዐይኔ አየች፤ ጆሮ​የም ሰማች።</verse>
				<verse number="2">እና​ንተ የም​ታ​ው​ቁ​ትን እኔ ደግሞ አው​ቃ​ለሁ፤ ከእ​ና​ን​ተም የም​ሰ​ንፍ አይ​ደ​ለ​ሁም።</verse>
				<verse number="3">ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ከፈ​ቀ​ደም በፊቱ እዋ​ቀ​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">እና​ንተ ግን የዐ​መፅ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶች፥ ሁላ​ች​ሁም የክ​ፋት ፈዋ​ሾች ናችሁ።</verse>
				<verse number="5">ላዳ​ም​ጣ​ችሁ አይ​ገ​ባ​ኝም፥ ጥበብ ከእ​ና​ንተ ጠፍ​ታ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="6">“አሁን የአ​ፌን ክር​ክር ስሙ፥ የከ​ን​ፈ​ሬ​ንም ፍርድ አድ​ምጡ።</verse>
				<verse number="7">በውኑ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የም​ት​ና​ገሩ አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን? በፊቱ ሽን​ገ​ላን ታወ​ራ​ላ​ች​ሁን?</verse>
				<verse number="8">ከእ​ርሱ ወደ ኋላ ትመ​ለ​ሳ​ላ​ች​ሁን? እስኪ ራሳ​ችሁ ፍረዱ።</verse>
				<verse number="9">እርሱ ቢመ​ረ​ም​ራ​ችሁ መል​ካም ነው፥ ይህን ሁሉ በኀ​ይ​ላ​ችሁ ስታ​ደ​ርጉ ራሳ​ች​ሁን ከእ​ርሱ ጋር አንድ ታደ​ር​ጋ​ላ​ች​ሁና።</verse>
				<verse number="10">በስ​ውር ለሰው ፊት ብታ​ደሉ ዘለፋ ይዘ​ል​ፋ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="11">ጥን​ቱን ኀይሉ አያ​ስ​ፈ​ራ​ች​ሁ​ምን? ግር​ማስ ከእ​ርሱ ዘንድ አይ​ወ​ድ​ቅ​ባ​ች​ሁ​ምን?</verse>
				<verse number="12">ምሳ​ሌ​ያ​ችሁ እንደ አመድ ዐላፊ ነው፤ ሥጋ​ች​ሁም እንደ ትቢያ ነው።</verse>
				<verse number="13">ዝም በሉ፤ እና​ገ​ርም ዘንድ ተዉኝ፤ ከቍ​ጣ​ዬም ልረፍ።</verse>
				<verse number="14">ሥጋ​ዬን በጥ​ርሴ እይ​ዛ​ለሁ፤ ሕይ​ወ​ቴ​ንም በእጄ አጥ​ብቄ አኖ​ራ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">እነሆ፥ ኀያሉ እጁን በእኔ ላይ ቢጭን፥ እርሱ እንደ ጀመረ እና​ገ​ራ​ለሁ፥ በፊ​ቱም እዋ​ቀ​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">ዝንጉ ሰው በፊቱ አይ​ገ​ባ​ምና እርሱ መድ​ኀ​ኒት ይሆ​ን​ል​ኛል።</verse>
				<verse number="17">ነገ​ሬን ስሙ ስሙ፥ እኔ በጆ​ሮ​አ​ችሁ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="18">እነሆ፥ ወደ ፍርዴ ቀር​ቤ​አ​ለሁ። ጽድ​ቄም እን​ደ​ም​ት​ገ​ለጥ አው​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">አሁን ፈጽሜ ዝም እል ዘንድ፥ ከእኔ ጋር የሚ​ፋ​ረድ ማን ነው?</verse>
				<verse number="20">“ነገር ግን ሁለት ነገ​ርን ስጠኝ፤ የዚ​ያን ጊዜ ከፊ​ትህ አል​ሰ​ወ​ርም፤</verse>
				<verse number="21">እጅ​ህን ከእኔ አርቅ፤ ግር​ማ​ህም አታ​ስ​ደ​ን​ግ​ጠኝ።</verse>
				<verse number="22">ከዚ​ህም በኋላ ትጠ​ራ​ኛ​ለህ፥ እኔም እመ​ል​ስ​ል​ሃ​ለሁ። ወይም አንተ ተና​ገር፥ አኔም እመ​ል​ስ​ል​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="23">ኀጢ​አ​ቶ​ችና በደሌ ምን ያህል ናቸው? ምን ያህል እንደ ሆኑ አስ​ታ​ው​ቀኝ።</verse>
				<verse number="24">“ፊት​ህን ከእኔ የሰ​ወ​ርህ፥ እንደ ጠላ​ት​ህም የቈ​ጠ​ር​ኸኝ ስለ​ምን ነው?</verse>
				<verse number="25">በነ​ፋስ እንደ ረገፈ ቅጠል ታፍ​ሰ​ኛ​ለ​ህን? ወይስ ነፋስ እን​ደ​ሚ​ወ​ስ​ደው ዕብቅ ታሳ​ድ​ደ​ኛ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="26">ክፉ ነገ​ርን ጽፈ​ህ​ብ​ኛ​ልና፤ የል​ጅ​ነ​ቴ​ንም ኀጢ​አት ተቈ​ጣ​ጥ​ረህ አስ​ታ​ጥ​ቀ​ኸ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="27">እግ​ሮ​ች​ንም በድጥ አሰ​ነ​ካ​ከ​ልህ፥ ሥራ​ዬ​ንም ሁሉ መር​ም​ረ​ሃል፤ እግ​ሬም በቆ​መች ጊዜ ተው​ኸኝ።</verse>
				<verse number="28">እኔ እንደ አረጀ ረዋት፥ ብልም እን​ደ​ሚ​በ​ላው ልብስ ነኝ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">“ከሴት የተ​ወ​ለደ ሟች ሰው የሕ​ይ​ወቱ ዘመን ጥቂት ነው፥ የቍጣ መከ​ራ​ንም የተ​ሞላ ነው።</verse>
				<verse number="2">እንደ አበባ ይወ​ጣል፥ ይረ​ግ​ፋ​ልም፤ እንደ ጥላም ያል​ፋል፥ እር​ሱም አይ​ኖ​ርም።</verse>
				<verse number="3">እን​ደ​ዚ​ህስ ያለ​ውን ሰው አንተ የም​ት​መ​ረ​ም​ረው አይ​ደ​ለ​ምን? በፊ​ት​ህስ እር​ሱን ወደ ፍርድ ታገ​ባ​ዋ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="4">ከር​ኵ​ሰት የሚ​ነጻ ማን ነው? አንድ ስንኳ የለም።</verse>
				<verse number="5">በም​ድር ላይ አንድ ቀንም እንኳ ቢኖር፤ ወሮ​ቹም በአ​ንተ ዘንድ የተ​ቈ​ጠሩ ናቸው፤ ዘመ​ኑ​ንም ወስ​ነህ ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ፤ እር​ሱም ከዚያ አያ​ል​ፍም።</verse>
				<verse number="6">“እንደ ምን​ደኛ ሕይ​ወ​ቱን እን​ዲ​ጠ​ባ​በ​ቃት፥ ያርፍ ዘንድ ከእ​ርሱ ዘወር በል።</verse>
				<verse number="7">ዛፍ ቢቈ​ረጥ ደግሞ ያቈ​ጠ​ቍጥ ዘንድ፥ ተስፋ አለው፤ ቅር​ን​ጫ​ፉም አያ​ል​ቅም።</verse>
				<verse number="8">ሥሩም በም​ድር ውስጥ ቢያ​ረጅ፥ ግን​ዱም በጭ​ንጫ ውስጥ ቢሞት፥</verse>
				<verse number="9">ከውኃ ሽታ የተ​ነሣ ያቈ​ጠ​ቍ​ጣል፤ እንደ አዲስ ተክ​ልም ያፈ​ራል።</verse>
				<verse number="10">ሰው ግን ከሞተ ፈጽሞ ይተ​ላል፤ ሟች ሰው ከሞተ በኋላ እን​ግ​ዲህ አይ​ኖ​ርም።</verse>
				<verse number="11">ባሕር ይጐ​ድ​ላል፤ ወን​ዙም ይነ​ጥ​ፋል፤ ይደ​ር​ቅ​ማል።</verse>
				<verse number="12">ሰውም ከተኛ በኋላ ሰማይ እስ​ኪ​ያ​ልፍ ድረስ አይ​ነ​ቃም፤ ከእ​ን​ቅ​ል​ፉም አይ​ነ​ሣም።</verse>
				<verse number="13">“በመ​ቃ​ብር ውስጥ ምነው በጠ​በ​ቅ​ኸኝ ኖሮ! ቍጣህ እስ​ኪ​በ​ር​ድም ድረስ በሸ​ሸ​ግ​ኸኝ ኖሮ! እስ​ከ​ም​ታ​ስ​በ​ኝም ምነው ቀጠሮ በሰ​ጠ​ኸኝ ኖሮ!</verse>
				<verse number="14">ሰው የሕ​ይ​ወ​ቱን ዘመን ፈጽሞ ከሞተ በኋላ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖር ቢሆን ዳግ​መኛ እስ​ክ​ወ​ለድ ድረስ፥ በት​ዕ​ግ​ሥት በተ​ጠ​ባ​በ​ቅሁ ነበር።</verse>
				<verse number="15">በጠ​ራ​ኸ​ኝም ጊዜ በመ​ለ​ስ​ሁ​ልህ ነበር፤ የእ​ጅ​ህ​ንም ሥራ አት​ና​ቀኝ።</verse>
				<verse number="16">አሁን ግን ኀጢ​አ​ቶ​ችን ቈጥ​ረ​ሃል፤ ከበ​ደ​ሌም እን​ዲ​ቱ​ንስ እንኳ አል​ረ​ሳ​ህም።</verse>
				<verse number="17">መተ​ላ​ለ​ፌን በከ​ረ​ጢት ውስጥ አት​መ​ሃል፥ ኀጢ​አ​ቴ​ንም ለብ​ጠ​ህ​ባ​ታል።</verse>
				<verse number="18">ተራራ ሲወ​ድቅ ይጠ​ፋል፥ ዓለ​ቱም ከስ​ፍ​ራው ይፈ​ል​ሳል፤</verse>
				<verse number="19">“ውኆች ድን​ጋ​ዮ​ችን ይፍ​ቃሉ፤ ፈሳ​ሾ​ቹም የም​ድ​ሩን አፈር ይወ​ስ​ዳሉ፤ እን​ዲሁ አንተ የሰ​ውን ተስፋ ታጠ​ፋ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="20">ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታስ​ወ​ግ​ደ​ዋ​ለህ፥ እር​ሱም ያል​ፋል፤ ፊት​ህን ትመ​ል​ስ​በ​ታ​ለህ፥ እር​ሱ​ንም ትሰ​ድ​ደ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="21">ልጆቹ ቢበዙ አያ​ያ​ቸ​ውም ቢያ​ን​ሱም አያ​ው​ቃ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="22">ነገር ግን የገዛ ሥጋው በሕ​ማም ይሠ​ቃ​ያል፥ ነፍ​ሱም ታለ​ቅ​ሳ​ለች።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">ቴማ​ና​ዊ​ውም ኤል​ፋዝ መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“በውኑ ጠቢብ ሰው እንደ ነፋስ በሆነ ዕው​ቀት ይመ​ል​ሳ​ልን? ሆዱ​ንስ በሥ​ቃይ ይሞ​ላ​ልን?</verse>
				<verse number="3">ከከ​ንቱ ነገር፥ ወይስ ከማ​ይ​ጠ​ቅም ንግ​ግር ጋር ይዋ​ቀ​ሳ​ልን?</verse>
				<verse number="4">አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ትተ​ሃ​ልን? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ፊት እን​ዲህ ያለ​ውን ቃል ትና​ገ​ራ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="5">ከአ​ፍህ ንግ​ግር የተ​ነሣ መጠ​ንህ ይታ​ወ​ቃል፥ የኀ​ያ​ላ​ኑ​ንም ቃል አል​ለ​የ​ህም።</verse>
				<verse number="6">የሚ​ፈ​ር​ድ​ብህ አፍህ ነው እንጂ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ከን​ፈ​ሮ​ች​ህም ይመ​ሰ​ክ​ሩ​ብ​ሃል።</verse>
				<verse number="7">በውኑ ከሰው ቀድ​መህ የተ​ፈ​ጠ​ርህ ሰው አንተ ነህን? ወይስ ከተ​ራ​ሮች በፊት ተፀ​ነ​ስ​ህን?</verse>
				<verse number="8">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንስ ትእ​ዛዝ ሰም​ተ​ሃ​ልን? ወይስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አማ​ካ​ሪው አድ​ር​ጎ​ሃ​ልን? ወይስ ጥበ​ብን ለብ​ቻህ አድ​ር​ገ​ሃ​ልን?</verse>
				<verse number="9">እኛ የማ​ና​ው​ቀ​ውን አንተ ምን ታው​ቃ​ለህ? እኛስ የማ​ና​ስ​ተ​ው​ለ​ውን አንተ ምን ታስ​ተ​ው​ላ​ለህ?</verse>
				<verse number="10">በዕ​ድሜ ከአ​ባ​ትህ የሚ​በ​ልጡ፥ ሽበ​ትም ያላ​ቸው ሽማ​ግ​ሎች ከእኛ ጋር አሉ።</verse>
				<verse number="11">ጥቂት ብት​በ​ድል ተገ​ረ​ፍህ፥ ይህም የተ​ና​ገ​ር​ኸው ነገር በዐ​ቅ​ምህ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="12">“ልብ​ህስ ለምን ይደ​ፍ​ራል? ዐይ​ኖ​ች​ህስ ለምን ይገ​ላ​ም​ጣሉ?</verse>
				<verse number="13">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በቍጣ ትመ​ልስ ዘንድ፤ እን​ደ​ዚ​ህስ ያለ ነገር ከአ​ፍህ ታወጣ ዘንድ፤</verse>
				<verse number="14">ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሟች ሰው ማን ነው? ጻድ​ቅስ ይሆን ዘንድ ከሴት የተ​ወ​ለደ ማን ነው?</verse>
				<verse number="15">እነሆ፥ በቅ​ዱ​ሳኑ እንኳ አይ​ታ​መ​ንም፤ ሰማ​ይም በፊቱ ንጹሕ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="16">ይል​ቁ​ንስ አስ​ጸ​ያ​ፊና የረ​ከሰ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም እንደ ውኃ የሚ​ጠጣ ሰው ምንኛ ያንስ?</verse>
				<verse number="17">“ስማኝ ልን​ገ​ርህ፥ እነ​ሆም ያየ​ሁ​ትን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="18">ጠቢ​ባን የተ​ና​ገ​ሩ​ትን፥ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ያል​ሰ​ወ​ሩ​ትን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">ምድር ለእ​ነ​ርሱ ብቻ ተሰ​ጥ​ታ​ለ​ችና፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም እን​ግዳ ሕዝብ አል​ገ​ባ​ባ​ቸ​ው​ምና።</verse>
				<verse number="20">የኃ​ጥእ ሰው ዕድ​ሜው በጭ​ንቅ ያል​ፋል፥ ለግ​ፈኛ የተ​መ​ደቡ ዓመ​ታ​ቱም ሁሉ የተ​ቈ​ጠሩ ናቸው።</verse>
				<verse number="21">የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግጥ ድም​ፅም በጆ​ሮው ነው፤ በደ​ኅ​ን​ነ​ትም ይኖር ዘንድ ተስፋ በሚ​ያ​ደ​ር​ግ​በት ጊዜ ጥፋት ይመ​ጣ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="22">ከጨ​ለማ ተመ​ልሶ እን​ዲ​ወጣ ተስፋ የለ​ውም፥ ለሰ​ይ​ፍም ኀይል ፈጽሞ ተዳ​ር​ጎ​አል።</verse>
				<verse number="23">ለአ​ሞ​ራ​ዎ​ችም ምግብ ሆኖ ተሰ​ጥ​ቶ​አል በድን ሆኖ እን​ደ​ሚ​ቈ​ይም እርሱ ራሱ ያው​ቃል። የጨ​ለማ ቀንም እንደ አውሎ ነፋስ ትወ​ስ​ደ​ዋ​ለች።</verse>
				<verse number="24">መከ​ራና ጭን​ቀት ይመ​ጡ​በ​ታል፤ በፊት እንደ ተሰ​ለፈ መኰ​ንን ይወ​ድ​ቃል።</verse>
				<verse number="25">እጁን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዘር​ግ​ቶ​አ​ልና፥ ሁሉን በሚ​ችል አም​ላክ ፊትም አን​ገ​ቱን አደ​ን​ድ​ኖ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="26">በደ​ን​ዳና አን​ገ​ቱና በወ​ፍ​ራሙ በጋ​ሻው ጕብ​ጕብ፥ ከው​ር​ደት ጋር እየ​ሰ​ገገ ይመ​ጣ​በ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="27">በስ​ብም ፊቱን ከድ​ኖ​አ​ልና ስቡ​ንም በወ​ገቡ ላይ አድ​ር​ጎ​አ​ልና፥</verse>
				<verse number="28">በተ​ፈ​ቱም ከተ​ሞች ውስጥ ይኖ​ራል፥ ሰውም በሌ​ለ​ባ​ቸው ቤቶች ይገ​ባል፥ እርሱ ያዘ​ጋ​ጀ​ው​ንም ሌሎች ይወ​ስ​ዱ​ታል።</verse>
				<verse number="29">“እርሱ ባለ​ጠጋ አይ​ሆ​ንም፤ ሀብ​ቱም አይ​ጸ​ናም፤ ጥላ​ው​ንም በም​ድር ላይ አይ​ጥ​ልም፤</verse>
				<verse number="30">ከጨ​ለማ በም​ንም አያ​መ​ል​ጥም፤ ነፋ​ስም ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹን ያደ​ር​ቃ​ቸ​ዋል፥ አበ​ባ​ዎ​ቹም ይረ​ግ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="31">ለመ​ኖር ተስፋ አያ​ደ​ር​ግም፤ ፍጻ​ሜው ከንቱ ይሆ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="32">ቀኑ ሳይ​ደ​ርስ መከሩ ይጠ​ፋል፥ ቅር​ን​ጫ​ፉም አይ​ለ​መ​ል​ምም።</verse>
				<verse number="33">ጮር​ቃ​ውም ይረ​ግ​ፋል፤ እንደ ወይ​ራም አበባ ይወ​ድ​ቃል።</verse>
				<verse number="34">ለኃ​ጥ​ኣን ሁሉ ሞት ምስ​ክ​ራ​ቸው ነው፥ እሳት የጉቦ ተቀ​ባ​ዮ​ችን ቤት ይበ​ላል።</verse>
				<verse number="35">በሆ​ዳ​ቸው ጭን​ቅ​ትን ይፀ​ን​ሳሉ፥ ከንቱ ነገ​ር​ንም ይወ​ል​ዳሉ። ሆዳ​ቸ​ውም ተን​ኰ​ልን ያዘ​ጋ​ጃል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">ኢዮ​ብም መለሰ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“እን​ደ​ዚህ ያለ ብዙ ነገር ሰማሁ፤ እና​ንተ ሁላ​ችሁ የም​ታ​ደ​ክሙ አጽ​ና​ኞች ናችሁ።</verse>
				<verse number="3">የመ​ጣ​ላ​ች​ሁን ሁሉ ያለ ልክ ትና​ገ​ራ​ላ​ችሁ፦ ትከ​ራ​ከ​ሩኝ ዘን​ድስ ምን አስ​ቸ​ገ​ር​ኋ​ችሁ?</verse>
				<verse number="4">እኔ ደግሞ እና​ንተ እን​ደ​ም​ት​ና​ገሩ እና​ገር ነበር፤ ነፍ​ሳ​ችሁ በነ​ፍሴ ፋንታ ብት​ሆን ኖሮ፥</verse>
				<verse number="5">እኔም ነገ​ርን እነ​ግ​ራ​ችሁ ነበር፤ ራሴ​ንም በእ​ና​ንተ ላይ እነ​ቀ​ንቅ ነበር።</verse>
				<verse number="6">ባፌም ኀይል ቢኖ​ረኝ ኖሮ፥ ከን​ፈ​ሬን ባል​ገ​ታ​ሁም ነበር፥ የም​ና​ገ​ረ​ው​ንም ባሻ​ሻ​ልሁ ነበር፤</verse>
				<verse number="7">እኔ ብና​ገር ቍስሌ አይ​ድ​ንም፤ ዝም ብልም ሕማሜ ይብ​ስ​ብ​ኛል።</verse>
				<verse number="8">አሁን ግን የዕ​ብድ ቍር​ጥ​ራ​ጭና ብጥ​ስ​ጣሽ አደ​ረ​ግ​ኸኝ፤ እኔ​ንም መያ​ዝህ ምስ​ክር ሆነ​ች​ብኝ፤</verse>
				<verse number="9">ሐሰ​ቴም በእኔ ላይ ተነ​ሣች፤ በፊ​ቴም ተከ​ራ​ከ​ረ​ች​ብኝ።</verse>
				<verse number="10">በቍ​ጣው ጣለኝ፤ ጥር​ሶ​ቹ​ንም አፋ​ጨ​ብኝ፤ ፍላ​ጻ​ዎ​ቹ​ንም በእኔ ላይ ፈተነ።</verse>
				<verse number="11">ዐይ​ኖ​ችን አፍ​ዝዞ ጋረ​ደኝ፤ በተ​ሳለ ጦርም ጕል​በ​ቴን ወግቶ ጣለኝ። በአ​ን​ድ​ነ​ትም ከበ​ቡኝ።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጠ​ማማ ሰው አሳ​ልፎ ሰጠኝ፤ በክ​ፉ​ዎ​ችም እጅ ጣለኝ።</verse>
				<verse number="13">ተዘ​ልዬ ስኖ​ርም ጣለኝ፤ የራስ ጠጕ​ሬን ይዞ ነጨው፤ እንደ ዓላ​ማም አድ​ርጎ አቆ​መኝ፤ እንደ ጉበ​ኛም ተመ​ለ​ከ​ተኝ።</verse>
				<verse number="14">በጦር ከበ​ቡኝ፤ ኵላ​ሊ​ቴ​ንም ወጉኝ፤ እነ​ር​ሱም አል​ራ​ሩ​ል​ኝም፤ ሐሞ​ቴ​ንም በም​ድር ላይ አፈ​ሰሱ።</verse>
				<verse number="15">በው​ድ​ቀት ላይ ውድ​ቀ​ትን አደ​ረ​ሱ​ብኝ፤ ኀያ​ላኑ እየ​ሠ​ገጉ ሮጡ​ብኝ።</verse>
				<verse number="16">በቍ​ር​በቴ ላይ ማቅ ሰፉ፤ መከ​ራዬ በመ​ሬት ላይ በዛች።</verse>
				<verse number="17">ሆዴ በል​ቅሶ ተቃ​ጠለ፤ የሞት ጥላን በቅ​ን​ድ​ቦች ላይ አያ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="18">ነገር ግን በእጄ ዐመፅ የለም፤ ጸሎ​ቴም ንጹሕ ነው።</verse>
				<verse number="19">መሬት ሥጋ​ዬን ይሸ​ፍ​ነው ይሆን? ደሜስ ይፈ​ስስ ይሆን? የም​ጮ​ህ​በ​ትስ ቦታ አላ​ገኝ ይሆን?</verse>
				<verse number="20">“አሁ​ንም፥ እነሆ፥ ምስ​ክሬ በሰ​ማይ አለ፤ የሚ​ያ​ው​ቅ​ል​ኝም በአ​ር​ያም ነው።</verse>
				<verse number="21">ጸሎቴ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትድ​ረስ፥ ዐይ​ኔም በፊቱ እንባ ታፍ​ስስ።</verse>
				<verse number="22">የሰው ልጅ ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ጋር እን​ደ​ሚ​ም​ዋ​ገት፥ ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለመ​ሟ​ገት ምነው በቻለ!</verse>
				<verse number="23">የተ​ቈ​ጠሩ ዘመ​ኖች ደረሱ፤ እኔም ወደ​ማ​ል​መ​ለ​ስ​በት መን​ገድ እሄ​ዳ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">ነፍ​ሴን የሚ​ያ​ወ​ጣት ያስ​ጨ​ን​ቀ​ኛል መቃ​ብ​ር​ንም እመ​ኘ​ዋ​ለሁ፤ ግን አላ​ገ​ኘ​ውም፤</verse>
				<verse number="2">እየ​ለ​መ​ንሁ ደከ​ምሁ፤ ምንስ አደ​ር​ጋ​ለሁ? ባዕ​ዳ​ንም ገን​ዘ​ቤን ሰረ​ቁኝ።</verse>
				<verse number="3">ከእኔ ጋር አጋና የሚ​ማታ ማን ነው?</verse>
				<verse number="4">ልባ​ቸ​ው​ንም ከጥ​በብ ሰው​ረ​ኸ​ዋል፤ ስለ​ዚህ ከፍ ከፍ አታ​ደ​ር​ጋ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="5">ለብ​ዝ​በዛ ባል​ን​ጀ​ሮ​ቹን አሳ​ልፎ የሚ​ሰጥ ሰው፥ የል​ጆቹ ዐይ​ኖች ይጨ​ል​ማሉ።</verse>
				<verse number="6">ለአ​ሕ​ዛ​ብም ምሳሌ አደ​ረ​ግ​ኸኝ፤ መሳ​ቂ​ያና መዘ​ባ​በ​ቻም ሆን​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">ዐይ​ኖች ከእ​ንባ የተ​ነሣ ፈዘዙ፥ ሁሉም እጅግ ተጸ​የ​ፉኝ።</verse>
				<verse number="8">ደስ​ታ​ዬን ተማ​ም​ኛት ነበር፤ ነገር ግን ጠፋ​ች​ብኝ፤ አግ​ባ​ብስ ወደ ኃጥ​ኣን ትመ​ለስ ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="9">ነገር ግን ወደ መን​ገዴ እንደ ምመ​ለስ እተ​ማ​መ​ና​ለሁ፤ እጆ​ችም የነጹ ናቸ​ውና፤ ደስ​ታ​ዬን አገ​ኛ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">ነገር ግን እና​ንተ ሁሉ ወደ​ዚህ መጥ​ታ​ችሁ ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ፤ በእ​ና​ንተ ዘንድ እው​ነ​ትን አላ​ገ​ኘ​ሁ​ምና።</verse>
				<verse number="11">“ዘመ​ኖች በጩ​ኸት አለቁ፤ የልቤ ሥርም ተቈ​ረጠ።</verse>
				<verse number="12">ቀኑ ሌሊት ሆነ​ብኝ። ከጨ​ለ​ማ​ውም የተ​ነሣ ብር​ሃኑ አጭር ነው።</verse>
				<verse number="13">ብዘ​ገ​ይም ሲኦል ቤቴ ናት፤ ምን​ጣ​ፌም በጨ​ለማ ተነ​ጥ​ፎ​አል።</verse>
				<verse number="14">ሞትን፦ አንተ አባቴ ነህ አል​ሁት፤ ትሎ​ች​ንም እና​ንተ እና​ቴም ወን​ድ​ሞቼም ናችሁ አል​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">እን​ግ​ዲህ ተስ​ፋዬ ወዴት ናት? ዳግ​መ​ኛስ መል​ካም ነገ​ርን አያ​ታ​ለ​ሁን?</verse>
				<verse number="16">ከእ​ኔስ ጋር ወደ መቃ​ብር ትወ​ር​ዳ​ለ​ችን? አብ​ረ​ንስ በመ​ሬት ውስጥ እን​ቀ​በ​ራ​ለ​ንን?”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">አው​ኬ​ና​ዊው በል​ዳ​ዶስ መለሰ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“ዝም የማ​ት​ለው እስከ መቼ ነው? እኛም እን​ድ​ን​ነ​ግ​ርህ ታገሥ።</verse>
				<verse number="3">ስለ ምንስ እንደ እን​ስሳ በፊ​ትህ ዝም አልን?</verse>
				<verse number="4">መከ​ራው ይገ​ባ​ሃል፤ አን​ተስ የሞ​ትህ እንደ ሆነ ምን​ድን ነው? ከሰ​ማይ በታች ምድር ስለ አንተ ባድማ ትሆ​ና​ለ​ችን? ወይስ ተራ​ራ​ዎች ከመ​ሠ​ረ​ታ​ቸው ይና​ወ​ጣ​ሉን?</verse>
				<verse number="5">“የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞች መብ​ራት ይጠ​ፋል፥ ነበ​ል​ባ​ላ​ቸ​ውም ብልጭ አይ​ልም።</verse>
				<verse number="6">ብር​ሃኑ በድ​ን​ኳኑ ውስጥ ይጨ​ል​ማል፤ መብ​ራ​ቱም በላዩ ይጠ​ፋል።</verse>
				<verse number="7">የተ​ዋ​ረዱ ሰዎች ንብ​ረ​ቱን ይወ​ስ​ዳሉ፤ ምክ​ሩም ትጥ​ለ​ዋ​ለች።</verse>
				<verse number="8">እግሩ በወ​ጥ​መድ ትያ​ዛ​ለች፤ በመ​ረ​ብም ትታ​ሠ​ራ​ለች፤</verse>
				<verse number="9">አሽ​ክ​ላ​ዎች በላዩ ይመ​ጣሉ፤ የተ​ጠ​ሙ​ትም በእ​ርሱ ይበ​ረ​ታሉ፤</verse>
				<verse number="10">በም​ድር ላይ የሸ​ም​ቀቆ ገመዱ ተሰ​ው​ራ​ለች፤ የሚ​ጐ​ት​ተ​ውም በመ​ን​ገዱ ላይ ነው።</verse>
				<verse number="11">መከራ በዙ​ሪ​ያው ታጠ​ፋ​ዋ​ለች፤ ብዙ ጠላ​ቶ​ችም ከእ​ግሩ በታች ይመ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="12">ኀይሉ በራብ ትደ​ክ​ማ​ለች። አስ​ጨ​ናቂ መቅ​ሠ​ፍ​ትም ተዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="13">ጭኖቹ ይበ​ሰ​ብ​ሳሉ። ሞትም መል​ካም ሕዋ​ሶ​ቹን ይበ​ላል።</verse>
				<verse number="14">ጤን​ነት ከሥ​ጋው ትር​ቃ​ለች። መከ​ራው ትጸ​ና​ለች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይበ​ቀ​ለ​ዋል።</verse>
				<verse number="15">በሌ​ሊት በድ​ን​ኳኑ ውስጥ ለእ​ርሱ የማ​ይ​ሆ​ነው ይኖ​ራል፤ የእ​ር​ሱም መል​ካም ነገር በዲን ይበ​ተ​ናል።</verse>
				<verse number="16">ሥሩ ከበ​ታቹ ይደ​ር​ቃል፤ ፍሬ​ውም ከላዩ ይረ​ግ​ፋል።</verse>
				<verse number="17">መታ​ሰ​ቢ​ያ​ውም ከም​ድር ይጠ​ፋል፤ በም​ድ​ርም ስም አይ​ቀ​ር​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="18">ከብ​ር​ሃን ወደ ጨለማ አር​ቀው ያፈ​ል​ሱ​ታል።</verse>
				<verse number="19">ከሕ​ዝቡ መካ​ከል የሚ​ራ​ራ​ለት የለም፤ ቤቱ ከሰ​ማይ በታች አይ​ቀ​ር​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="20">ነገር ግን ባዕድ በን​ብ​ረቱ ላይ ተድላ ያደ​ር​ጋል፤ ድሃው በእ​ርሱ ያጕ​ረ​መ​ር​ማል። ፊተ​ኞ​ቹም ይደ​ነ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="21">የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞች ቤት እን​ዲህ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የማ​ያ​ውቁ ሰዎች ስፍራ ይህ ነው።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">ኢዮ​ብም መለሰ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“ነፍ​ሴን የም​ት​ነ​ዘ​ን​ዙ​አት፥ በቃ​ላ​ች​ሁስ የም​ታ​ደ​ቅ​ቁኝ እስከ መቼ ነው? ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ብኝ ዕወቁ፤</verse>
				<verse number="3">ዐሥር ጊዜ ትና​ገ​ሩ​ኛ​ላ​ችሁ፥ ትሰ​ድ​ቡ​ኛ​ላ​ች​ሁም፤ በሰ​ው​ነቴ ላይ በጠ​ላ​ት​ነት ስት​ነ​ሡ​ብኝ አታ​ፍ​ሩም።</verse>
				<verse number="4">በእ​ው​ነት እኔ ከበ​ደ​ልሁ፤ ስሕ​ተቴ ከእኔ ጋር ትኖ​ራ​ለች። የማ​ላ​ው​ቀ​ው​ንም ነገር ተና​ገ​ርሁ፤ ነገ​ሬም ስን​ፍና ነው እንጂ በየ​ጊ​ዜው አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="5">ወዮ​ልኝ! አፋ​ች​ሁን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ ታደ​ር​ጋ​ላ​ች​ሁና፤ ትጓ​ደ​ዱ​ብ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ትዘ​ል​ፉ​ኛ​ላ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="6">እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አወ​ከኝ፥ መዓ​ቱ​ንም በእኔ ላይ እንደ አበዛ ዕወቁ።</verse>
				<verse number="7">እነሆ፥ በዘ​ለፋ እደ​ክ​ማ​ለሁ፤ አል​ና​ገ​ር​ምም፤ አሰ​ም​ቼም እጮ​ኻ​ለሁ፤ ነገር ግን ፍርድ የለ​ኝም።</verse>
				<verse number="8">ዙሪ​ያዬ ታጥ​ሯል፤ መተ​ላ​ለ​ፊ​ያም የለ​ኝም፤ በፊ​ቴም ጨለ​ማን ጋር​ዶ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="9">ክብ​ሬን ገፈ​ፈኝ፤ ዘው​ዴ​ንም ከራሴ ላይ ወሰደ።</verse>
				<verse number="10">በዚ​ህና በዚያ አፈ​ረ​ሰኝ፤ እኔም ሄድሁ፤ ተስ​ፋ​ዬ​ንም እንደ ዛፍ ቈረ​ጠው።</verse>
				<verse number="11">በታ​ላቅ ቍጣም ያዘኝ እንደ ጠላ​ትም ቈጠ​ረኝ።</verse>
				<verse number="12">ሠራ​ዊቱ አብ​ረው በእኔ ላይ መጡ፥ የሚ​ሸ​ም​ቁ​ብ​ኝም መን​ገ​ዴን ከበቡ፥</verse>
				<verse number="13">“ወን​ድ​ሞች ተለ​ዩኝ፥ ከእኔ ይልቅ ባዕ​ዳ​ንን ወደዱ። ጓደ​ኞ​ችም አላ​ዘ​ኑ​ል​ኝም።</verse>
				<verse number="14">ዘመ​ዶች አል​ተ​ረ​ዱ​ኝም፥ ስሜ​ንም የሚ​ያ​ውቁ ረሱኝ።</verse>
				<verse number="15">ቤተ​ሰ​ቦ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮች ሊያ​ዩኝ አል​ፈ​ቀ​ዱም፤ እንደ መጻ​ተ​ኛም አስ​መ​ሰ​ሉኝ።</verse>
				<verse number="16">አገ​ል​ጋ​ዮ​ችን እጠ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ርሱ ግን ቸል ይሉ​ኛል፤ በአ​ፌም እለ​ማ​መ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="17">ሚስ​ቴን እለ​ማ​መ​ጣ​ታ​ለሁ፤ እር​ስዋ ግን ትጠ​ቃ​ቀ​ስ​ብ​ኛ​ለች፤ የቤ​ተ​ሰ​ቤ​ንም ልጆች ፈጽሜ አቈ​ላ​ም​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="18">ለዘ​ለ​ዓ​ለም ተስፋ ቈረ​ጡ​ብኝ። ብነ​ሣም በእኔ ላይ ሐሜት ይና​ገ​ራሉ።</verse>
				<verse number="19">ያዩኝ ሁሉ ተጸ​የ​ፉኝ፤ እኔ የም​ወ​ድ​ዳ​ቸ​ውም በላዬ ተነሡ።</verse>
				<verse number="20">ቍር​በቴ ከሥ​ጋዬ ጋር ይበ​ጣ​ጠ​ሳል። አጥ​ን​ቶቼም ይፋ​ጩ​ብ​ኛል።</verse>
				<verse number="21">እና​ንተ ወዳ​ጆቼ ሆይ፤ ማሩኝ፤ ማሩኝ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ዳስ​ሳ​ኛ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="22">ስለ ምን እና​ንተ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታሳ​ድ​ዱ​ኛ​ላ​ችሁ? ከሥ​ጋ​ዬስ ስለ​ምን አት​ጠ​ግ​ቡም?</verse>
				<verse number="23">ቃሌን ማን በጻ​ፈው! ማንስ በመ​ጽ​ሐፍ ውስጥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባተ​መው!</verse>
				<verse number="24">ማን በብ​ረት ብር​ዕና በእ​ር​ሳስ፥ በዓ​ለት ላይ በቀ​ረ​ፀው!</verse>
				<verse number="25">እኔን ግን የሚ​ቤ​ዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፥ በመ​ጨ​ረ​ሻም ዘመን በም​ድር ላይ እን​ዲ​ቆም፥</verse>
				<verse number="26">ይህ ቍር​በ​ቴም ከጠፋ በኋላ፥ በዚያ ጊዜ ከሥ​ጋዬ ተለ​ይቼ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳይ አው​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="27">እኔ ራሴ አየ​ዋ​ለሁ፤ ዐይ​ኖቼም ይመ​ለ​ከ​ቱ​ታል፤ ከእ​ኔም ሌላ አይ​ደ​ለም። ሁሉም በብ​ብቴ ተፈ​ጸመ።</verse>
				<verse number="28">“በፊቱ ምን እን​ና​ገ​ራ​ለን? የነ​ገሩ ሥርም በእ​ርሱ ዘንድ ተገ​ኝ​ቶ​አል ብትሉ፥</verse>
				<verse number="29">እና​ንተ ሐሣ​ርን ፍሩ​አት፥ ቍጣ በኃ​ጥ​ኣን ላይ ይመ​ጣ​ልና፤ ያን​ጊ​ዜም ክፋ​ታ​ቸው ከየት እንደ ሆነ ያው​ቃሉ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">አሜ​ና​ዊ​ውም ሶፋር መለሰ፤ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“እን​ደ​ዚህ እን​ደ​ም​ት​መ​ልስ አል​ጠ​ረ​ጠ​ር​ሁ​ህም ነበር፤ በዕ​ው​ቀ​ትም ከእኔ አት​ሻ​ልም።</verse>
				<verse number="3">የት​ም​ህ​ር​ቴን ጥበብ ልን​ገ​ርህ፤ ስማኝ፤ የማ​ስ​ተ​ዋ​ሌም መን​ፈስ ይመ​ል​ስ​ል​ኛል።</verse>
				<verse number="4">ሰው በም​ድር ላይ ከተ​ፈ​ጠረ፥ ከድሮ ዘመን ጀምሮ፥ በአ​ን​ተስ ዘመን እን​ደ​ዚህ ያለ ነገር ታው​ቃ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="5">የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞች ደስታ ታላቅ ሰልፍ ነው፥ የዝ​ን​ጉ​ዎ​ችም ደስታ ጥፋት ነው።</verse>
				<verse number="6">መባው ወደ ሰማይ ቢወጣ፥ መሥ​ዋ​ዕ​ቱም እስከ ደመና ቢደ​ርስ፥</verse>
				<verse number="7">እነሆ ተደ​ላ​ድ​ያ​ለሁ በሚ​ል​በት ጊዜ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጠ​ፋል። የሚ​ያ​ው​ቁ​ትም ወዴት ነው? ይላሉ።</verse>
				<verse number="8">እንደ ሕልም ይበ​ር​ራል፤ እር​ሱም አይ​ገ​ኝም፤ ሲነ​ጋም እን​ደ​ማ​ይ​ታ​ወቅ እንደ ሌሊት ራእይ ይሰ​ደ​ዳል።</verse>
				<verse number="9">ዐይን አየ​ችው፤ ነገር ግን ዳግ​መኛ አታ​የ​ውም፤ ስፍ​ራ​ው​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አያ​ው​ቀ​ውም።</verse>
				<verse number="10">የተ​ዋ​ረዱ ሰዎች ልጆ​ቹን ያጠ​ፋሉ፤ እጆ​ቹም የኀ​ዘን እሳ​ትን ያቀ​ጣ​ጥ​ላሉ።</verse>
				<verse number="11">ጭን​ቀት በአ​ጥ​ን​ቶቹ ሞል​ቶ​አል፤ ነገር ግን ሕማሙ ከእ​ርሱ ጋር በመ​ሬት ውስጥ ይተ​ኛል።</verse>
				<verse number="12">“ክፋት በአፉ ውስጥ ብት​ጣ​ፍ​ጠው፤ ከም​ላ​ሱም በታች ቢሰ​ው​ራት፥</verse>
				<verse number="13">ቢጠ​ብ​ቃ​ትም፥ ባይ​ተ​ዋ​ትም፤ በጕ​ሮ​ሮ​ውም መካ​ከል ቢይ​ዛት፥ መብሉ በአ​ን​ጀቱ ውስጥ ይገ​ላ​በ​ጣል፤</verse>
				<verse number="14">ፈጽሞ ራሱን መር​ዳት አይ​ች​ልም። የእ​ፉ​ኝ​ትም መርዝ ከከ​ን​ፈሩ በታች አለ።</verse>
				<verse number="15">በዐ​መፅ የሚ​ሰ​በ​ሰብ ሀብ​ትም ይጠ​ፋል፤ የሞት መል​አ​ክም ከቤቱ ውስጥ እያ​ዳፋ ያወ​ጣ​ዋል።</verse>
				<verse number="16">የእ​ባ​ብን መርዝ ይጠ​ባል፤ የእ​ፉ​ኝ​ትም ምላስ ይገ​ድ​ለ​ዋል።</verse>
				<verse number="17">የመ​ን​ጋ​ዎ​ቹ​ንም ጥጆች፥ የማ​ሩ​ንና የቅ​ቤ​ው​ንም ፈሳሽ አይ​መ​ለ​ከ​ትም።</verse>
				<verse number="18">ለማ​ይ​ቀ​ም​ሰው፥ ለማ​ይ​ታ​ኘ​ክና ለማ​ይ​ዋጥ ሀብት በከ​ንቱ ይደ​ክ​ማል።</verse>
				<verse number="19">የደ​ካ​ሞ​ችን ቤቶች አፍ​ር​ሶ​አ​ልና፤ ያል​ሠ​ራ​ው​ንም ቤት በዝ​ብ​ዞ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="20">ለን​ብ​ረቱ ጥበቃ የለ​ውም፤ የወ​ደ​ደ​ው​ንም ነገር አያ​ገ​ኝም።</verse>
				<verse number="21">ለሀ​ብቱ ትርፍ የለ​ውም፤ ስለ​ዚህ በረ​ከቱ አት​ከ​ና​ወ​ን​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="22">በጠ​ገበ ጊዜ ይጨ​ነ​ቃል፤ መከ​ራም ሁሉ ያገ​ኘ​ዋል።</verse>
				<verse number="23">“ሆዱን ቢያ​ጠ​ግብ፥ የመ​ዓት መቅ​ሠ​ፍት ይጨ​መ​ር​በ​ታል፤ የሕ​ማ​ሙም ሥቃይ ይጸ​ና​በ​ታል።</verse>
				<verse number="24">ከሰ​ይ​ፍም ኀይል አያ​መ​ል​ጥም፤ የና​ስም ቀስት ይወ​ጋ​ዋል።</verse>
				<verse number="25">ቀስ​ቱም በሥ​ጋው ውስጥ ያል​ፋል። ክፉም ነገር በሰ​ው​ነቱ ይመ​ላ​ለ​ሳል፤ ፍር​ሀ​ትም ይወ​ድ​ቅ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="26">ጨለማ ሁሉ ይጠ​ብ​ቀ​ዋል፤ ዕፍ የማ​ይ​ባል እሳ​ትም ይበ​ላ​ዋል፤ እን​ግ​ዳም ቤቱን ያጠ​ቃ​ዋል።</verse>
				<verse number="27">ሰማይ ኀጢ​ኣ​ቱን ይገ​ል​ጥ​በ​ታል፤ ምድ​ርም በእ​ርሱ ላይ ትነ​ሣ​ለች።</verse>
				<verse number="28">ጥፋ​ትም ቤቱን ወደ ፍጻሜ ያመ​ጣ​ታል። የቍጣ ቀንም ትመ​ጣ​በ​ታ​ለች።</verse>
				<verse number="29">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የኀ​ጢ​አ​ተኛ ሰው እድል ፋን​ታው፥ ከሚ​ያ​የው ከፈ​ጣ​ሪ​ውም የተ​መ​ደበ ርስቱ ይህ ነው።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">ኢዮ​ብም መለሰ፤ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“እኛ አጽ​ና​ና​ነው እን​ዳ​ት​ሉኝ፥ ስሙ፤ ቃሌን ስሙ።</verse>
				<verse number="3">እና​ገር ዘንድ ዝም በሉ፤ ከተ​ና​ገ​ርሁ በኋላ ትስ​ቁ​ብ​ኛ​ላ​ች​ሁና፤</verse>
				<verse number="4">ሰው የሚ​ዘ​ል​ፈኝ አይ​ደ​ለም፤ ስለ ምንስ አል​ቈ​ጣም?</verse>
				<verse number="5">ወደ እኔ ተመ​ል​ከቱ፥ ተደ​ነ​ቁም፤ እጃ​ች​ሁ​ንም በጕ​ን​ጫ​ችሁ ላይ አኑሩ።</verse>
				<verse number="6">እኔ ባሰ​ብሁ ቍጥር እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ ጻዕ​ርም ሥጋ​ዬን ይይ​ዛል።</verse>
				<verse number="7">ስለ ምን ኀጢ​ኣ​ተ​ኞች በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራሉ? በባ​ለ​ጠ​ግ​ነ​ትስ ስለ ምን ያረ​ጃሉ?</verse>
				<verse number="8">ዘራ​ቸው በፊ​ታ​ቸው ከእ​ነ​ርሱ ጋር ጸንቶ ይኖ​ራል፤ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም በዐ​ይ​ና​ቸው ፊት ናቸው።</verse>
				<verse number="9">ቤታ​ቸው በብ​ል​ፅ​ግና የተ​ሞላ ነው፤ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ቸ​ውም የለም። ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ መቅ​ሠ​ፍት አይ​መ​ጣ​ባ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="10">በሬ​ዎ​ቻ​ቸው አይ​መ​ክ​ኑም፤ ላሞ​ቻ​ቸ​ውም አይ​ጨ​ነ​ግ​ፉም፤ በደ​ኅ​ናም ይወ​ል​ዳሉ።</verse>
				<verse number="11">እነ​ር​ሱም እንደ በጎች ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጠ​በ​ቃሉ፤ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም በፊ​ታ​ቸው ይዘ​ፍ​ናሉ።</verse>
				<verse number="12">በገ​ናና መሰ​ንቆ ይዘው ይዘ​ም​ራሉ፤ በመ​ዝ​ሙ​ራ​ቸ​ውም ደስ ይላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="13">ዕድ​ሜ​ያ​ቸ​ው​ንም በተ​ድላ ይፈ​ጽ​ማሉ፤ በሲ​ኦል ማረ​ፊ​ያም ይጋ​ደ​ማሉ።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፦ እን​ዲህ ይሉ​ታል፦ ከእኛ ዘንድ ራቅ፤ መን​ገ​ድ​ህ​ንም እና​ውቅ ዘንድ አን​ወ​ድ​ድም።</verse>
				<verse number="15">እን​ገ​ዛ​ለ​ትስ ዘንድ እርሱ ምን ይች​ላል? ወይስ ወደ እርሱ ብን​ቀ​ርብ ምን ይጠ​ቅ​መ​ናል?</verse>
				<verse number="16">“እነሆ፥ በጎ​ነ​ታ​ቸው በእ​ጃ​ቸው ውስጥ አለች፤ የኃ​ጥ​ኣ​ንን ሥራ አይ​መ​ለ​ከ​ትም።</verse>
				<verse number="17">የኃ​ጥ​ኣን መብ​ራት ትጠ​ፋ​ለች፤ መቅ​ሠ​ፍ​ትም ትመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለች። የበ​ቀል ቍጣም ይይ​ዛ​ቸ​ዋል፤</verse>
				<verse number="18">በነ​ፋ​ስም ፊት እንደ ገለባ፥ አውሎ ነፋ​ስም እን​ደ​ሚ​ወ​ስ​ደው ትቢያ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="19">ልጆቹ ሀብ​ቱን አያ​ገ​ኙም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብድ​ራ​ቱን ይከ​ፍ​ለ​ዋል። እር​ሱም ያን​ጊዜ ያው​ቃል።</verse>
				<verse number="20">ዐይ​ኖቹ ልጆቹ ሲወጉ ያያሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አያ​ድ​ና​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="21">የወ​ደ​ደ​ውን በቤቱ ውስጥ ያደ​ር​ጋል። ወራ​ቶ​ቹም ከቍ​ጥር ድን​ገት ይጐ​ድ​ላሉ።</verse>
				<verse number="22">ጥን​ቱን ዕው​ቀ​ት​ንና ምክ​ርን የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ምን? በነ​ፍሰ ገዳ​ዩስ የሚ​ፈ​ርድ እርሱ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="23">አንድ ሰው በሰ​ላም ተዘ​ልሎ ሲቀ​መጥ፥ በሁ​ሉም ፈጽሞ ደስ ብሎት ሳለ ይሞ​ታል።</verse>
				<verse number="24">በው​ስጡ ስብ ሞል​ቶ​አል፥ የአ​ጥ​ን​ቶ​ቹም ቅል​ጥም ፈስ​ሶ​አል።</verse>
				<verse number="25">ሌላ​ውም ሰው መል​ካ​ምን ነገር ከቶ ሳይ​በላ በተ​መ​ረ​ረች ነፍሱ ይሞ​ታል።</verse>
				<verse number="26">ሁሉም በአ​ፈር ውስጥ በአ​ንድ ላይ ይተ​ኛሉ፤ ትሎ​ችም ይሸ​ፍ​ኗ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="27">እነሆ፥ ደፍ​ራ​ችሁ፥ በእኔ ላይ በጠ​ላ​ት​ነት እንደ ተነ​ሣ​ችሁ ዐው​ቄ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="28">እና​ንተ፦ የአ​ለ​ቃው ቤት የት ነው? ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ያደ​ረ​በት ድን​ኳን የት ነው? ብላ​ች​ኋ​ልና።</verse>
				<verse number="29">መን​ገድ ዐላ​ፊ​ዎ​ችን ጠይ​ቋ​ቸው፤ ምል​ክ​ታ​ቸ​ው​ንም አታ​ገ​ኙም።</verse>
				<verse number="30">ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ክፉ ቀን ትጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለች፤ በቍጣ ቀንም ይወ​ስ​ዱ​ታል።</verse>
				<verse number="31">መን​ገ​ዱን በፊቱ የሚ​ና​ገር ማን ነው? እርሱ የሠ​ራ​ው​ንስ የሚ​መ​ል​ስ​በት ማን ነው?</verse>
				<verse number="32">እር​ሱን ግን ወደ መቃ​ብር ይወ​ስ​ዱ​ታል፤ በመ​ቃ​ብ​ሩም ውስጥ ይጠ​በ​ቃል።</verse>
				<verse number="33">የሸ​ለ​ቆው ጓል ይጣ​ፍ​ጥ​ለ​ታል፤ በኋ​ላ​ውም ሰው ሁሉ ይወ​ጣል፤ በፊ​ቱም ቍጥር የሌ​ለው ሰው አለ።</verse>
				<verse number="34">ለምን በከ​ንቱ ታጽ​ና​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ? በእ​ና​ንተ ዘንድ ግን ዕረ​ፍት የለ​ኝም።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">ቴማ​ና​ዊ​ውም ኤል​ፋዝ መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“በውኑ ማስ​ተ​ዋ​ል​ንና ዕው​ቀ​ትን የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="3">አንተ በሥ​ራህ ንጹሕ ከሆ​ንህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምን ያገ​ደ​ዋል? መን​ገ​ድ​ህ​ንስ ብታ​ቀና ምን ይጠ​ቅ​መ​ዋል?</verse>
				<verse number="4">አን​ተ​ንስ ተቈ​ጣ​ጥሮ ይዘ​ል​ፍ​ሃ​ልን? ወደ ፍር​ድስ ከአ​ንተ ጋር ይገ​ባ​ልን?</verse>
				<verse number="5">“ክፋ​ት​ህስ የበዛ አይ​ደ​ለ​ምን? ኀጢ​አ​ት​ህስ ቍጥር የሌ​ለው አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="6">የወ​ን​ድ​ሞ​ች​ህን መያዣ በከ​ንቱ ወስ​ደ​ሃል፥ የታ​ረ​ዘ​ው​ንም ልብ​ሱን ገፍ​ፈ​ሃል።</verse>
				<verse number="7">ለተ​ጠማ ውኃ አላ​ጠ​ጣ​ህም፥ የራ​ብ​ተ​ኛ​ው​ንም ጕርሻ ነጥ​ቀ​ሃል፥ ምድ​ርን የሚ​ዘራ ሰውም በው​ስጧ ድን​በ​ርን ያኖ​ራል።</verse>
				<verse number="8">ፊታ​ቸ​ውን አይ​ተህ ያደ​ነ​ቅ​ሃ​ቸው አሉ፥ በም​ድ​ርም ላይ ድሆ​ችን በዐ​መፅ ጠላህ</verse>
				<verse number="9">መበ​ለ​ቶ​ችን ባዶ​አ​ቸ​ውን ሰድ​ደ​ሃ​ቸ​ዋል፥ ድሃ​አ​ደ​ጎ​ች​ንም አስ​ጨ​ን​ቀ​ሃ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="10">ስለ​ዚህ አሽ​ክላ ከብ​ቦ​ሃል፥ ከባድ ጦር​ነ​ትም አና​ው​ጦ​ሃል።</verse>
				<verse number="11">ብር​ሃ​ኑም ጨለማ ሆነ​ብህ፥ ተኝ​ተ​ህም ሳለህ ውኃው አሰ​ጠ​መህ።</verse>
				<verse number="12">“ልዑል የወ​ደ​ደ​ውን ያደ​ርግ ዘንድ የሚ​ገ​ባው አይ​ደ​ለ​ምን? ትዕ​ቢ​ተ​ኞ​ች​ንስ አያ​ዋ​ር​ዳ​ቸ​ው​ምን?</verse>
				<verse number="13">አን​ተም እን​ዲህ ብለ​ሃል፦ ኀያል እርሱ ምን ያው​ቃል? በድ​ቅ​ድቅ ጨለማ ውስጥ ሆኖ ሊፈ​ርድ ይች​ላ​ልን?</verse>
				<verse number="14">የጠ​ቈረ ደመና ጋር​ዶ​ታል አያ​ይ​ምም፤ በሰ​ማይ ክበብ ላይ ይራ​መ​ዳል።</verse>
				<verse number="15">በውኑ ጻድ​ቃን ሰዎች የረ​ገ​ጡ​አ​ትን የዱ​ሮ​ይ​ቱን መን​ገድ ትጠ​ብ​ቃ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="16">ጊዜ​ያ​ቸው ሳይ​ደ​ርስ ተነ​ጠቁ፤ መሠ​ረ​ታ​ቸ​ውም እንደ ፈሳሽ ውኃ ፈሰሰ።</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን ያደ​ር​ገ​ናል? ሁሉን የሚ​ችል አም​ላ​ክስ ምን ያመ​ጣ​ብ​ናል? ይላሉ።</verse>
				<verse number="18">ነገር ግን ቤታ​ቸ​ውን በመ​ል​ካም ነገር ሞላ፤ የኃ​ጥ​ኣን ምክር ከእ​ርሱ የራ​ቀች ናት።</verse>
				<verse number="19">ጻድ​ቃ​ንም አይ​ተው ሳቁ፤ ንጹ​ሓ​ንም በን​ቀት ይዘ​ባ​በ​ቱ​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="20">በእ​ው​ነት ሀብ​ታ​ቸው ጠፋ፥ የቀ​ረ​ው​ንም እሳት በላች።</verse>
				<verse number="21">“አሁ​ንም መታ​ገሥ ትችል እንደ ሆነ፥ ፍሬ​ህም ይበጅ እንደ ሆነ እስኪ ጽኑ ሁን።</verse>
				<verse number="22">ከአ​ፉም ሕጉን ተቀ​በል፥ በል​ብ​ህም ቃሉን አኑር፤</verse>
				<verse number="23">ብት​መ​ለስ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ራስ​ህን ብታ​ዋ​ርድ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም ከል​ብህ ብታ​ርቅ፥</verse>
				<verse number="24">በዓ​ለቱ ቋጥኝ ላይ ለራ​ስህ መዝ​ገ​ብን ታኖ​ራ​ለህ። የሶ​ፎ​ርም ወርቅ እንደ ጅረት ድን​ጋይ ይሆ​ን​ል​ሃል።</verse>
				<verse number="25">ሁሉን የሚ​ችል አም​ላ​ክም ከጠ​ላ​ቶ​ችህ ይረ​ዳ​ሃል። ንጽ​ሕ​ና​ንም በእ​ሳት እንደ ተፈ​ተነ ብር አድ​ርጎ ይመ​ል​ስ​ል​ሃል።</verse>
				<verse number="26">በዚ​ያን ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሞገ​ስን ታገ​ኛ​ለህ። ወደ ሰማ​ይም በደ​ስታ ትመ​ለ​ከ​ታ​ለህ።</verse>
				<verse number="27">ወደ እር​ሱም ትጸ​ል​ያ​ለህ፥ እር​ሱም ይሰ​ማ​ሃል፤ ስእ​ለ​ት​ህ​ንም ይሰ​ጠ​ሃል።</verse>
				<verse number="28">የጽ​ድ​ቅ​ህ​ንም ብድ​ራት ይሰ​ጥ​ሃል። ብር​ሃ​ንም በመ​ን​ገ​ድህ ላይ ይበ​ራል።</verse>
				<verse number="29">ራስ​ህን ብታ​ዋ​ርድ ሰውም ኰራ​ብኝ ብትል፥ ራሱን የሚ​ያ​ዋ​ር​ደ​ውን ሰው ያድ​ነ​ዋል።</verse>
				<verse number="30">ንጹ​ሕን ሰው ያድ​ነ​ዋል፤ በእ​ጅ​ህም ንጽ​ሕና ትድ​ና​ለህ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="23">
				<verse number="1">ኢዮ​ብም መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“ዛሬም ዘለ​ፋዬ ከእጄ እንደ ሆነ ዐወ​ቅሁ። እጁ​ንም በእኔ ላይ አከ​በደ፥ አስ​ለ​ቀ​ሰ​ኝም።</verse>
				<verse number="3">እር​ሱን ወዴት እን​ደ​ማ​ገ​ኘው ምነው ባወ​ቅሁ! ወደ ነገሩ ፍጻ​ሜም ምነው በደ​ረ​ስሁ!</verse>
				<verse number="4">የሠ​ራ​ሁት ቢኖር ይነ​ግ​ረኝ ነበረ፥ ስከ​ራ​ከ​ርም አፌ ዝም አይ​ልም ነበር።</verse>
				<verse number="5">የሚ​ሰ​ጠ​ኝ​ንም ፈውስ አውቅ ነበር፥ የሚ​ለ​ኝ​ንም አስ​ተ​ውል ነበር።</verse>
				<verse number="6">በኀ​ይሉ ብዛት ቢመ​ጣ​ብ​ኝም እንኳ በቍ​ጣው አያ​ስ​ፈ​ራ​ራ​ኝም ነበር።</verse>
				<verse number="7">እው​ነ​ትና ቅን​ነት ከእ​ርሱ ዘንድ ናቸ​ውና። ከፍ​ር​ዴም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያሳ​ር​ፈኝ ነበር።</verse>
				<verse number="8">እነሆ፥ ወደ ፊት እሄ​ዳ​ለሁ፥ እን​ግ​ዲ​ህም አል​ኖ​ርም፤ ስለ ፍጻ​ሜ​ውም አላ​ው​ቅም፤</verse>
				<verse number="9">ወደ​ሚ​ሠ​ራ​በ​ትም ወደ ግራ ብሄድ አል​መ​ለ​ከ​ተ​ውም፤ ቀኝ እጁ ይከ​ብ​በ​ኛል፤ ነገር ግን አላ​የ​ውም።</verse>
				<verse number="10">መን​ገ​ዴን ፈጽሞ ዐወቀ፥ እንደ ወር​ቅም ፈተ​ነኝ</verse>
				<verse number="11">እንደ ትእ​ዛዙ እወ​ጣ​ለሁ፥ መን​ገ​ዱ​ንም ጠብ​ቄ​አ​ለሁ፥ ፈቀ​ቅም አላ​ል​ሁም።</verse>
				<verse number="12">ከት​እ​ዛ​ዙም አላ​ለ​ፍ​ሁም፤ ቃሉን በልቤ ሰው​ሬ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">“ስለ ፍርድ የሚ​ከ​ራ​ከር ማን ነው? እርሱ የወ​ደ​ደ​ውን ያደ​ር​ጋ​ልና።</verse>
				<verse number="14">ስለ​ዚ​ህም እኔ ስለ እርሱ ቸኰ​ልሁ፤ በተ​ገ​ሠ​ጽ​ሁም ጊዜ አሰ​ብ​ሁት።</verse>
				<verse number="15">ስለ​ዚህ በፊቱ ደነ​ገ​ጥሁ፤ አስ​በ​ዋ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም የተ​ነሣ እፈ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ልቤን አቀ​ለ​ጠው፥ ሁሉን የሚ​ችል አም​ላ​ክም አስ​ጨ​ን​ቆ​ኛል።</verse>
				<verse number="17">ጨለ​ማም እን​ደ​ሚ​መ​ጣ​ብኝ፥ ድቅ​ድ​ቁም ጨለማ ፊቴን እን​ደ​ሚ​ከ​ድን አላ​ወ​ቅ​ሁም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="24">
				<verse number="1">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘመ​ኖ​ችን ለምን ረሳ​ቸው?</verse>
				<verse number="2">ኃጥ​ኣን የድ​ን​በ​ሩን ምል​ክት አለፉ፤ እረ​ኛ​ው​ንም ከመ​ን​ጋ​ዎቹ ጋር ይነ​ጥ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="3">የድ​ሃ​አ​ደ​ጎ​ቹን አህያ ይነ​ዳሉ የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም በሬ ስለ መያዣ ይወ​ስ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="4">ደካ​ሞ​ችን ከእ​ው​ነት መን​ገድ ያወ​ጣሉ፤ የም​ድ​ርም የዋ​ሃን ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ይሸ​ሸ​ጋሉ።</verse>
				<verse number="5">እነሆ፥ በም​ድረ በዳ እን​ዳሉ እንደ ሜዳ አህ​ዮች ሆኑ። ስለ እኔም ሥራ​ቸ​ውን ትተው ይወ​ጣሉ፤ መብል፦ ከል​ጅ​ነ​ታ​ቸው ጀምሮ ይጥ​ማ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">“የራ​ሳ​ቸው ያል​ሆ​ነ​ውን እርሻ ያለ ሰዓቱ ያጭ​ዳሉ። ኃጥ​ኣን ድሆ​ችን በወ​ይ​ና​ቸው ቦታ ያለ ዋጋና ያለ ቀለብ ያሠ​ሩ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">ብዙ​ዎ​ችን የተ​ራ​ቈ​ቱ​ት​ንም ያለ ልብስ ያሳ​ድ​ሩ​አ​ቸ​ዋል። መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ቸ​ው​ንም ይገ​ፍ​ፏ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="8">በካ​ፊ​ያና ከተ​ራ​ሮች በሚ​ወ​ርድ ጠል ይረ​ጥ​ባሉ፤ መጠ​ጊ​ያም የላ​ቸ​ው​ምና ቋጥ​ኙን ተተ​ገኑ።</verse>
				<verse number="9">ድሃ​አ​ደ​ጉን ልጅ ከጡቱ ይነ​ጥ​ላሉ፤ ችግ​ረ​ኛ​ው​ንም ያሠ​ቃ​ያሉ።</verse>
				<verse number="10">ችግ​ረ​ኞ​ችን በደ​ሉ​አ​ቸው፥ ጣሉ​አ​ቸ​ውም፤ ከተ​ራ​ቡ​ትም የሚ​ጐ​ር​ሱ​ትን ነጠ​ቋ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">በጠ​ባብ ቦታ በዐ​መፅ ይሸ​ም​ቃሉ፥ የጽ​ድ​ቅ​ንም መን​ገድ አያ​ው​ቁም።</verse>
				<verse number="12">ድሆ​ችን ከከ​ተ​ማ​ውና ከገዛ ቤቶ​ቻ​ቸው አባ​ረ​ሩ​አ​ቸው የሕ​ፃ​ና​ት​ንም ነፍስ እጅግ አስ​ጮሁ፤</verse>
				<verse number="13">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እነ​ዚ​ህን ለምን አል​ገ​ሠ​ጻ​ቸ​ውም? በም​ድር ላይ ሳሉ አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም፥ የቅ​ን​ነት መን​ገ​ድ​ንም አላ​ዩም። በአ​ደ​ባ​ባ​ይ​ዋም አል​ሄ​ዱም።</verse>
				<verse number="14">ሥራ​ቸ​ው​ንም ዐውቆ ለጨ​ለማ ዳረ​ጋ​ቸው። በሌ​ሊ​ትም እንደ ሌባ ናቸው።</verse>
				<verse number="15">የአ​መ​ን​ዝ​ራም ዐይን ድግ​ዝ​ግ​ዝ​ታን ይጠ​ብ​ቃል፦ የማ​ንም ዐይን አያ​የ​ኝም ይላል፥ ፊቱ​ንም ይሸ​ፍ​ናል።</verse>
				<verse number="16">በጨ​ለማ ቤቶ​ችን ይነ​ድ​ላል፤ በቀን ይሸ​ሸ​ጋሉ፤ ብር​ሃ​ን​ንም አያ​ዩም።</verse>
				<verse number="17">የጥ​ዋት ብር​ሃን ለእ​ነ​ርሱ ሁሉ እንደ ሞት ጥላ ነው፤ የሚ​ሆ​ነ​ውን ድን​ጋጤ ያው​ቃ​ሉና። ሞት​ንም ይጠ​ራ​ጠ​ራ​ሉና።</verse>
				<verse number="18">እርሱ በውኃ ፊት ላይ በርሮ ያል​ፋል፤ እድል ፋን​ታ​ውም በም​ድር ላይ የተ​ረ​ገ​መች ናት፤</verse>
				<verse number="19">ተክ​ላ​ቸው በም​ድር ላይ ሲደ​ርቅ ያያሉ። ያላ​ቸ​ውም ድሀ​ኣ​ደ​ጉን በዘ​በ​ዙት።</verse>
				<verse number="20">ከዚ​ህም በኋላ ኀጢ​አ​ቱን ያስ​ባል። እንደ ጤዛ ትነት ይጠ​ፋል። እንደ ሥራ​ውም ይከ​ፈ​ለ​ዋል። ዐመ​ፀ​ኛም ሁሉ እንደ በሰ​በሰ ዛፍ ይሰ​በ​ራል።</verse>
				<verse number="21">ለማ​ት​ወ​ል​ደው ለመ​ካ​ኒቱ በጎ​ነ​ትን አላ​ደ​ረ​ገ​ላ​ትም፤ ለም​ት​ወ​ል​ደ​ውም አል​ራ​ራም።</verse>
				<verse number="22">ነገር ግን ረዳት የሌ​ላ​ቸ​ውን በቍ​ጣው አጠ​ፋ​ቸው። እር​ሱም በተ​ነሣ ጊዜ ሰው በሕ​ይ​ወቱ አይ​ታ​መ​ንም።</verse>
				<verse number="23">በታ​መ​መም ጊዜ መዳ​ንን ተስፋ አያ​ደ​ር​ግም። ነገር ግን እርሱ በሕ​ማሙ ይሞ​ታል።</verse>
				<verse number="24">ከፍ ከፍ ባለ ጊዜም ብዙ​ዎ​ችን አስ​ጨ​ነ​ቃ​ቸው። እንደ አመ​ድ​ማዶ በሙ​ቀት ይጠ​ወ​ል​ጋል። ከቃ​ር​ሚ​ያው እን​ደ​ሚ​ወ​ድቅ እሸ​ትም ይቈ​ረ​ጣል።</verse>
				<verse number="25">እን​ዲ​ህስ ባይ​ሆን ሐሰ​ተኛ ነህ የሚ​ለኝ፥ ነገ​ሬ​ንስ እንደ ኢም​ንት የሚ​ያ​ደ​ር​ገው ማን ነው?”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="25">
				<verse number="1">አው​ኬ​ና​ዊ​ውም በል​ዳ​ዶስ መለሰ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“ጥን​ቱን መፈ​ራት በእ​ርሱ ዘንድ ያለ አይ​ደ​ለ​ምን? በከ​ፍ​ታ​ውም ሁሉን ነገር አድ​ራጊ ነው።</verse>
				<verse number="3">ለሌ​ቦች ዕረ​ፍ​ትን የሚ​ሰጥ እን​ዳለ የሚ​መ​ስ​ለው አይ​ኑር። የክ​ፋ​ቱስ ወጥ​መድ የማ​ይ​መ​ጣ​በት ማን ነው?</verse>
				<verse number="4">ጻድቅ ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዴት ንጹሕ ይሆ​ናል? ከሴ​ትስ የተ​ወ​ለደ ራሱን ንጹሕ ማድ​ረግ እን​ዴት ይች​ላል?</verse>
				<verse number="5">እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ይሰ​ወ​ራል፤ አያ​በ​ራ​ምም፤ ከዋ​ክ​ብ​ትም በፊቱ ንጹ​ሓን አይ​ደ​ሉም።</verse>
				<verse number="6">ይል​ቁ​ንስ ፈራሽ የሆነ ሰው፥ ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ!”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="26">
				<verse number="1">ኢዮ​ብም መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“ማንን ትደ​ግ​ፋ​ለህ? ማን​ንስ ልት​ረዳ ትወ​ድ​ዳ​ለህ? ጥን​ቱን ኀይሉ ብዙ፥ ክን​ዱም ጽኑ የሆነ እርሱ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="3">ለማ​ንስ ታማ​ክ​ራ​ለህ? ጥበብ ሁሉ ለእ​ርሱ አይ​ደ​ለ​ምን? ማን​ንስ ትከ​ተ​ላ​ለህ? ታላቅ ኀይል ያለው እርሱ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="4">ነገ​ርን ለማን ትና​ገ​ራ​ለህ? የማ​ንስ መን​ፈስ ከአ​ንተ ዘንድ ይወ​ጣል?</verse>
				<verse number="5">ኀያ​ላን ከው​ኆች በታች፥ በው​ኆ​ችም ውስጥ ከሚ​ኖሩ ይወ​ለ​ዳ​ሉን?</verse>
				<verse number="6">ሲኦል በፊቱ ራቁ​ቱን ነው፥ ሞት​ንም ከእ​ርሱ የሚ​ጋ​ር​ደው የለም።</verse>
				<verse number="7">ሰማ​ይን በባዶ ስፍራ ላይ ይዘ​ረ​ጋል፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አን​ዳች አልባ ያን​ጠ​ለ​ጥ​ላል።</verse>
				<verse number="8">ውኃ​ውን በደ​መና ውስጥ ይቋ​ጥ​ራል፥ ደመ​ና​ውም ከታች አይ​ቀ​ደ​ድም።</verse>
				<verse number="9">የዙ​ፋ​ኑን ፊት ይከ​ድ​ናል፥ ደመ​ና​ው​ንም ይዘ​ረ​ጋ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="10">ብር​ሃን ከጨ​ለማ እስ​ከ​ሚ​ለ​ይ​በት ዳርቻ ድረስ፥ የው​ኃ​ውን ፊት በተ​ወ​ሰነ ትእ​ዛዙ ከበ​በው።</verse>
				<verse number="11">የሰ​ማይ አዕ​ማድ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፥ ከተ​ግ​ሣ​ጹም የተ​ነሣ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="12">በኀ​ይሉ ባሕ​ርን ጸጥ ያደ​ር​ጋል፥ በማ​ስ​ተ​ዋ​ሉም ዐን​በ​ሪ​ውን ይገ​ለ​ብ​ጠ​ዋል።</verse>
				<verse number="13">የሲ​ኦል በረ​ኞች ለእ​ርሱ አደሉ። በት​እ​ዛ​ዙም ዐመ​ፀ​ኛ​ውን እባብ ገደ​ለው።</verse>
				<verse number="14">እነሆ ይህ የመ​ን​ገዱ ክፍል ነው፤ የቀ​ሩ​ት​ንም ነገ​ሮ​ቹን እን​ሰ​ማ​ለን፤ በሚ​ያ​ደ​ር​ግ​በ​ትስ ጊዜ የነ​ጐ​ድ​ጓ​ዱን ኀይል የሚ​ያ​ውቅ ማን ነው?”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="27">
				<verse number="1">ኢዮ​ብም ምሳ​ሌ​ውን ይመ​ስል ዘንድ ደገመ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“እን​ደ​ዚህ የፈ​ረ​ደ​ብኝ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ነፍ​ሴ​ንም መራራ ያደ​ረገ ሁሉን የሚ​ችል ሕያው አም​ላ​ክን!</verse>
				<verse number="3">እስ​ት​ን​ፋሴ በእኔ ውስጥ ገና ሳለች፥ የሚ​ያ​ና​ግ​ረ​ኝም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በአ​ፍ​ን​ጫዬ ውስጥ ገና ሳለ፥</verse>
				<verse number="4">አን​ደ​በቴ ዐመ​ፅን አይ​ና​ገ​ርም፤ ነፍ​ሴም የዐ​መፅ አሳ​ብን አት​ማ​ርም፤</verse>
				<verse number="5">እና​ን​ተን ማጽ​ደቅ ከእኔ ዘንድ ይራቅ፤ እስ​ክ​ሞ​ትም ድረስ ፍጹ​ም​ነ​ቴን ከእኔ አላ​ር​ቅ​ምና።</verse>
				<verse number="6">ጽድ​ቅን እየ​ሠ​ራሁ አል​ጠ​ፋም፤ ያደ​ረ​ግ​ሁት ክፉ ነገር አይ​ታ​ወ​ቀ​ኝ​ምና።</verse>
				<verse number="7">ጠላ​ቶች እንደ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ውድ​ቀት፥ በእኔ ላይም የሚ​ነሡ እንደ በደ​ለ​ኞች ጥፋት ይሁኑ።</verse>
				<verse number="8">“ኀጢ​አ​ተኛ ድኅ​ነ​ትን ተስፋ ያደ​ርግ ዘንድ ለምን ደጅ ይጠ​ናል? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ የማ​ያ​ምን ይድ​ና​ልን? እንጃ!</verse>
				<verse number="9">በውኑ መከራ በመ​ጣ​በ​ትስ ጊዜ፥ ጸሎ​ቱን ይሰ​ማ​ዋ​ልን?</verse>
				<verse number="10">በእ​ርሱ ዘን​ድስ ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን ያገ​ኛ​ልን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንስ በጠራ ጊዜ ይመ​ል​ስ​ለ​ታ​ልን?</verse>
				<verse number="11">እኔ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ምን እን​ዳለ አስ​ተ​ም​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሁሉን በሚ​ችል አም​ላክ ዘንድ ያለ​ው​ንም አል​ዋ​ሽም።</verse>
				<verse number="12">እነሆ፥ ሁላ​ች​ሁም፥ በክ​ፉ​ዎች ላይ ክፋት እን​ደ​ም​ት​መ​ጣ​ባ​ቸው ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="13">ይህች ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የኀ​ጢ​አ​ተኛ እድል ፋንታ ናት፥ ግፈ​ኞ​ችም ሁሉን ከሚ​ችል አም​ላክ ዘንድ የሚ​ቀ​በ​ሏት ሀብት ናት።</verse>
				<verse number="14">ልጆቹ ቢበዙ ለጥ​ፋት ይሆ​ናሉ፤ ቢያ​ድ​ጉም ለማ​ኞች ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="15">ለእ​ር​ሱም የቀ​ሩት ፈጽ​መው ይሞ​ታሉ። ለመ​በ​ለ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የሚ​ያ​ዝ​ን​ላ​ቸው የለም።</verse>
				<verse number="16">እርሱ ብርን እንደ አፈር ቢሰ​በ​ስብ፥ ወር​ቅ​ንም እንደ ጭቃ ቢያ​ዘ​ጋጅ፥</verse>
				<verse number="17">ይህን ሁሉ ጻድ​ቃን ይወ​ስ​ዱ​ታል። ሀብ​ቱ​ንም ቅኖች ይከ​ፋ​ፈ​ሉ​ታል።</verse>
				<verse number="18">ቤቱ እንደ ሸረ​ሪት ድር፥ ቅን​ቅ​ንም እን​ደ​ሚ​በ​ላው ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="19">ባለ​ጠጋ ይተ​ኛል፥ የሚ​ያ​ነ​ቃ​ውም የለም፤ ዐይ​ኖ​ቹን ይከ​ፍ​ታል፥ ይደ​ነ​ቃ​ልም።</verse>
				<verse number="20">ሥቃይ እንደ ጎርፍ ታገ​ኘ​ዋ​ለች፤ በሌ​ሊ​ትም ዐውሎ ነፋስ ትነ​ጥ​ቀ​ዋ​ለች።</verse>
				<verse number="21">የሚ​ያ​ቃ​ጥል ነፋስ ያነ​ሣ​ዋል፥ እር​ሱም ያል​ፋል፤ ከቦ​ታ​ውም ይጠ​ር​ገ​ዋል።</verse>
				<verse number="22">በእ​ር​ሱም ላይ የማ​ያ​ው​ቀው ይመ​ጣ​በ​ታል፤ አይ​ራ​ራ​ለ​ትም፥ ከእ​ጁም ፈጥኖ መሸሽ ይወ​ድ​ዳል።</verse>
				<verse number="23">በእ​ር​ሱም እጁን ያጨ​በ​ጭ​ብ​በ​ታል፤ ከስ​ፍ​ራ​ውም በፉ​ጨት ጎትቶ ያወ​ጣ​ዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="28">
				<verse number="1">“በእ​ው​ነቱ ብር የሚ​ወ​ጣ​በት ቦታ አለ፥ ወር​ቅም የሚ​ነ​ጠ​ር​በት ስፍራ አለ።</verse>
				<verse number="2">ብረ​ትም ከመ​ሬት ውስጥ ይወ​ጣል፤ መዳ​ብም እንደ ድን​ጋይ ይፈ​ለ​ጣል።</verse>
				<verse number="3">ለጨ​ለማ ወሰ​ንን ያደ​ር​ጋል፤ እርሱ ሁሉን ይመ​ረ​ም​ራል፥ የጨ​ለ​ማ​ንና የሞት ጥላ ድን​ጋ​ይ​ንም ይመ​ረ​ም​ራል።</verse>
				<verse number="4">በአ​ፈር ምክ​ን​ያት እን​ደ​ሚ​ከ​ፈል ወንዝ የጽ​ድ​ቅን መን​ገድ የረሱ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ይደ​ክ​ማሉ። ከሰ​ዎ​ችም መካ​ከል ይለ​ያሉ።</verse>
				<verse number="5">እን​ጀራ ከም​ድር ውስጥ ይወ​ጣል፤ በእ​ሳ​ትም እን​ደ​ሚ​ሆን ታች​ኛው ይገ​ለ​በ​ጣል።</verse>
				<verse number="6">ድን​ጋ​ይዋ እንደ ሰን​ፔር፥ ወር​ቅ​ዋም እንደ አፈር የሆነ መሬት አለች።</verse>
				<verse number="7">መን​ገ​ድ​ዋን ዎፍ አያ​ው​ቀ​ውም፥ የን​ስ​ርም ዐይን አላ​የ​ውም።</verse>
				<verse number="8">የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞች ልጆች አል​ረ​ገ​ጡ​አ​ትም፥ ደቦል አን​በ​ሳም በው​ስ​ጥዋ አላ​ለ​ፈ​ባ​ትም።</verse>
				<verse number="9">ሰው ወደ ቡላድ ድን​ጋይ እጁን ይዘ​ረ​ጋል፥ ተራ​ራ​ዎ​ች​ንም ከመ​ሠ​ረ​ታ​ቸው ይገ​ለ​ብ​ጣ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="10">ከድ​ን​ጋይ ውስጥ መን​ዶ​ል​ዶያ ይወ​ቅ​ራል፤ ዐይ​ኔም የከ​በ​ረ​ውን ነገር ሁሉ ታያ​ለች።</verse>
				<verse number="11">የፈ​ሳ​ሹ​ንም ጥል​ቀት ይገ​ል​ጣል። ኀይ​ሉ​ንም በብ​ር​ሃን ይገ​ል​ጣል።</verse>
				<verse number="12">“ነገር ግን ጥበብ ወዴት ትገ​ኛ​ለች? የጥ​በ​ብስ ሀገ​ርዋ ወዴት ነው?</verse>
				<verse number="13">ሟች ሰው መን​ገ​ድ​ዋን አያ​ው​ቅም፤ በሰ​ዎ​ችም ዘንድ አት​ገ​ኝም።</verse>
				<verse number="14">ቀላይ፦ በእኔ ውስጥ የለ​ችም ትላ​ለች። ባሕ​ርም፦ በእኔ ዘንድ የለ​ችም ይላል።</verse>
				<verse number="15">ስለ እር​ስ​ዋም ማንም ምዝ​ምዝ ወርቅ አይ​ሰ​ጥም ብርም በእ​ር​ስዋ ለውጥ አይ​መ​ዘ​ንም።</verse>
				<verse number="16">ከአ​ፌር ወር​ቅም ጋር አት​ወ​ዳ​ደ​ርም። በከ​በረ መረ​ግ​ድና በሰ​ን​ፔር አት​ገ​መ​ትም።</verse>
				<verse number="17">ወር​ቅና ብር​ጭቆ አይ​ወ​ዳ​ደ​ሩ​አ​ትም፥ የወ​ር​ቅም ጥሬ ዕቃ የእ​ር​ስዋ ለውጥ አይ​ሆ​ንም።</verse>
				<verse number="18">ዛጎ​ልና አል​ማዝ አይ​ታ​ሰ​ቡም። አንተ ግን እጅግ ከከ​በሩ ነገ​ሮች ሁሉ ይልቅ ጥበ​ብን አቅ​ር​ባት።</verse>
				<verse number="19">የኢ​ት​ዮ​ጵያ ሉል አይ​ተ​ካ​ከ​ላ​ትም፥ በጥ​ሩም ወርቅ አት​ገ​መ​ትም።</verse>
				<verse number="20">“እን​ግ​ዲያ ጥበብ ከወ​ዴት ትገ​ኛ​ለች? የማ​ስ​ተ​ዋ​ልስ ሀገሯ ወዴት ነው?</verse>
				<verse number="21">በሰው ሁሉ ዘንድ ተረ​ስ​ታ​ለች፥ ከሰ​ማይ ወፎ​ችም ተሰ​ው​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="22">ሞትና ሲኦል ወሬ​ዋን በጆ​ሮ​ቻ​ችን ሰማን ብለ​ዋል።</verse>
				<verse number="23">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገ​ድ​ዋን አሳ​መረ፥ እር​ሱም ስፍ​ራ​ዋን ያው​ቃል።</verse>
				<verse number="24">እር​ሱም በሰ​ማይ ያለ​ውን ይመ​ለ​ከ​ታል፥ በም​ድ​ርም ያለ​ውን ሁሉ ያው​ቃል።</verse>
				<verse number="25">ለነ​ፋስ ሚዛ​ንን ለው​ሆ​ችም መስ​ፈ​ሪ​ያን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="26">እነ​ዚ​ህን በፈ​ጠረ ጊዜ እን​ዲሁ ዐውቆ ቈጠ​ራ​ቸው። ለዝ​ናም ሥር​ዐ​ትን ለነ​ጐ​ድ​ጓድ መብ​ረ​ቅም መን​ገ​ድን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="27">በዚ​ያን ጊዜ አያት፥ ገለ​ጣ​ትም፤ አዘ​ጋ​ጃ​ትም፥ አከ​በ​ራት፥ ደግ​ሞም መረ​መ​ራት።</verse>
				<verse number="28">ሰው​ንም፦ ‘እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ጥበብ ነው፤ ከክፉ መራ​ቅም ማስ​ተ​ዋል ነው’ ” አለው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="29">
				<verse number="1">ኢዮ​ብም ምሳ​ሌ​ውን ይመ​ስል ዘንድ ደገመ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ብ​ቀኝ እንደ ነበ​ረው ጊዜ፥ ወደ ፊተ​ኛው ወራት ማን በመ​ለ​ሰኝ?</verse>
				<verse number="3">በራ​ስ​ጌዬ ላይ መብ​ራቴ በበራ ጊዜ፥ እኔም ጨለ​ማ​ውን ዐልፌ በብ​ር​ሃኑ በሄ​ድሁ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="4">በበ​ረ​ከት ሁሉ በነ​በ​ርሁ ጊዜ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤቴን በጐ​በኘ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="5">ባለ ሀብት በነ​በ​ርሁ ጊዜ፥ ልጆ​ችም በዙ​ሪ​ያዬ በነ​በሩ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="6">ቅቤ በመ​ን​ገዴ ይፈ​ስስ በነ​በረ ጊዜ፥ ወተት በተ​ራ​ራዬ ይፈ​ስ​ስ​ልኝ በነ​በረ ጊዜ።</verse>
				<verse number="7">ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ገሥ​ግሼ በወ​ጣሁ ጊዜ፥ በአ​ደ​ባ​ባ​ዩም ወን​በ​ሬን ባኖ​ሩ​ልኝ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="8">ጐበ​ዛ​ዝት እኔን አይ​ተው ተሸ​ሸጉ፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው ቆሙ።</verse>
				<verse number="9">ኀያ​ላ​ኑም ከመ​ና​ገር ዝም አሉ፥ እጃ​ቸ​ው​ንም በአ​ፋ​ቸው ላይ ጫኑ።</verse>
				<verse number="10">የሰ​ሙ​ኝም ብፁዕ ይሉ​ኛል። ምላ​ሳ​ቸ​ውም በት​ና​ጋ​ቸው ተጠጋ።</verse>
				<verse number="11">የሰ​ማ​ች​ኝም ጆሮ ብፁዕ አለ​ችኝ፥ ያየ​ች​ኝም ዐይን ገለል አለች፤</verse>
				<verse number="12">ድሃ​ውን ከሚ​ጨ​ቁ​ነው እጅ አድ​ኛ​ለ​ሁና። ረዳት የሌ​ለ​ውን ደሃ​አ​ደ​ጉ​ንም ረድ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="13">ለሞት የቀ​ረ​በው መረ​ቀኝ፤ የባ​ል​ቴ​ቲ​ቱም አፍ ባረ​ከኝ፤</verse>
				<verse number="14">ጽድ​ቅን ለበ​ስሁ፥ ቅን​ነ​ት​ንም እንደ መጎ​ና​ጸ​ፊያ ተሸ​ለ​ምሁ፤ ፍር​ድ​ንም እንደ ኩፋር ተቀ​ዳ​ጀ​ኋት</verse>
				<verse number="15">ለዕ​ው​ራን ዐይን፥ ለአ​ን​ካ​ሳ​ዎ​ችም እግር ነበ​ርሁ።</verse>
				<verse number="16">ለድ​ሃ​ዎች አባት ነበ​ርሁ፥ የማ​ላ​ው​ቀ​ው​ንም ሰው ክር​ክር መረ​መ​ርሁ።</verse>
				<verse number="17">የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችን መን​ጋጋ ሰበ​ርሁ፥ የነ​ጠ​ቁ​ት​ንም ከጥ​ር​ሳ​ቸው ውስጥ አስ​ጣ​ልሁ።</verse>
				<verse number="18">እኔም እን​ደ​ም​ሸ​መ​ግ​ልና እን​ደ​ማ​ረጅ፥ እንደ ረዥም ዘን​ባ​ባም ረዥም ዘመን እን​ደ​ም​ኖር፥ እንደ አሸ​ዋም ዘመ​ኔን እን​ደ​ማ​በዛ ዐሰ​ብሁ።</verse>
				<verse number="19">ውኃ በሥሬ ላይ ይፈ​ስ​ሳል፥ ጠልም በአ​ዝ​መ​ራዬ ላይ ይወ​ር​ዳል፤</verse>
				<verse number="20">ክብሬ በእኔ ዘንድ ታድ​ሶ​አል፥ ቀስ​ቴም በእጄ ውስጥ ሳለ እሄ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="21">“ሰዎች እኔን ይሰ​ሙ​ኛል፥ ያዳ​ም​ጡ​ኝ​ማል፥ በም​ክ​ሬም ዝም ይላሉ።</verse>
				<verse number="22">በነ​ገሬ ላይ ደግ​መው አይ​ና​ገ​ሩም፤ ባነ​ጋ​ገ​ር​ኋ​ቸ​ውም ጊዜ ደስ ይላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="23">የተ​ጠ​ማች ምድር ዝና​ምን ተስፋ እን​ደ​ም​ታ​ደ​ርግ፥ እን​ደ​ዚ​ሁም እነ​ርሱ ንግ​ግ​ሬን ይጠ​ባ​በ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="24">በእ​ነ​ርሱ ብስቅ አያ​ም​ኑም፤ የፊ​ቴም ብር​ሃን አል​ወ​ደ​ቀም።</verse>
				<verse number="25">መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን መረ​መ​ርሁ፤ እንደ አለ​ቃም ሆኜ ተቀ​መ​ጥሁ፤ ንጉሥ በሠ​ራ​ዊቱ መካ​ከል እን​ደ​ሚ​ኖር ኖርሁ፤ በሚ​ያ​ዝ​ኑም ጊዜ በእኔ ይጽ​ናኑ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="30">
				<verse number="1">“አሁን ግን በዕ​ድሜ ከእኔ የሚ​ያ​ንሱ ለመ​ዘ​ባ​በት በእኔ ላይ ሳቁ፤ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን የና​ቅ​ሁ​ባ​ቸ​ውና እንደ መን​ጋዬ ውሾች ያል​ቈ​ጠ​ር​ኋ​ቸው ዛሬ ለብ​ቻ​ቸው ይገ​ሥ​ጹ​ኛል።</verse>
				<verse number="2">የእ​ጃ​ቸው ብር​ታት ለእኔ ምን​ድን ነው? ሞት በላ​ያ​ቸው ይምጣ።</verse>
				<verse number="3">ትላ​ንት በድ​ካ​ምና በው​ር​ደት ከም​ድረ በዳ ያመ​ለጡ፥ ከረ​ኃብ የተ​ነሣ ተሰ​ድ​ደው ይለ​ም​ናሉ።</verse>
				<verse number="4">እየ​ዞሩ የሚ​ለ​ም​ኑና የሚ​በሉ በቅ​ል​ው​ጥም የሚ​ኖሩ ወራ​ዶች፥ ዐመ​ፀ​ኞ​ችና ከበጎ ነገ​ሮች ሁሉ የተ​ቸ​ገሩ ናቸው። ከታ​ላቅ ረኃ​ብም የተ​ነሣ ጨው ጨው የሚ​ለ​ውን የእ​ን​ጨት ሥር ይበ​ላሉ።</verse>
				<verse number="5">“ሌቦች በእኔ ላይ ተነሡ፥</verse>
				<verse number="6">በሸ​ለ​ቆው ፈረ​ፈ​ርና በም​ድር ጕድ​ጓድ ውስጥ በዓ​ለ​ትም ዋሻ ውስጥ ይኖ​ራሉ፤</verse>
				<verse number="7">በገ​ደል ማሚ​ቶው መካ​ከል ይጮ​ኻሉ፤ በሳማ ውስ​ጥም ይሸ​ሸ​ጋሉ።</verse>
				<verse number="8">የሰ​ነ​ፎ​ችና የክ​ፉ​ዎች ሰዎች ልጆች ናቸው፤ ስማ​ቸ​ውና ክብ​ራ​ቸው ከም​ድር የጠፋ ነው።</verse>
				<verse number="9">አሁ​ንም እኔ መዝ​ፈ​ኛና መተ​ረቻ ሆን​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">ተጸ​የ​ፉኝ፥ ከእ​ኔም ራቁ፤ ምራ​ቃ​ቸ​ው​ንም በፊቴ መት​ፋ​ትን አል​ታ​ከ​ቱም።</verse>
				<verse number="11">የቀ​ስ​ቱን አፎት ከፍቶ ክፉ አደ​ረ​ገ​ብኝ፤ በፊ​ቴም ልጓ​ሙን ሰደደ።</verse>
				<verse number="12">በኀ​ይሉ ቀኝ ተነ​ሣ​ብኝ፤ እግ​ሮ​ቹ​ንም ዘረ​ጋ​ብኝ፤ የሞ​ት​ንም መን​ገድ በእኔ ላይ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="13">ፍለ​ጋ​ዬን አጠፋ፤ ልብ​ሴን ገፈ​ፈኝ፥ በቀ​ስ​ቱም ነደ​ፈኝ።</verse>
				<verse number="14">እንደ ወደደ አደ​ረ​ገ​ብኝ፤ በመ​ከ​ራም እዛ​ብ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">ድን​ጋጤ በላዬ ተመ​ላ​ለ​ሰ​ች​ብኝ፥ ነፍሴ ከእኔ ላይ እለይ እለይ አለች፥ ደኅ​ን​ነ​ቴም እንደ ተበ​ተነ ደመና አለ​ፈች።</verse>
				<verse number="16">“አሁ​ንም ነፍሴ በው​ስጤ ፈሰ​ሰች፤ ጭን​ቀ​ትም በእኔ ላይ ሞላ፤</verse>
				<verse number="17">በሌ​ሊት ሁሉ አጥ​ን​ቶች በደዌ ይነ​ድ​ዳሉ፥ ጅማ​ቶ​ችም ይቀ​ል​ጣሉ።</verse>
				<verse number="18">ከታ​ላቁ ደዌ ኀይል የተ​ነሣ ልብሴ ተበ​ላ​ሸች፤ የል​ብሴ ክሳድ አነ​ቀ​ችኝ፥ ቀሚ​ሴም በአ​ን​ገቴ ተጣ​በቀ።</verse>
				<verse number="19">እርሱ እንደ ጭቃ ረገ​ጠኝ፥ ዕድል ፋን​ታ​ዬም አፈ​ርና አመድ ሆነ።</verse>
				<verse number="20">ወደ አንተ ጮኽሁ፥ አል​ሰ​ማ​ኸ​ኝ​ምም፤ እነ​ርሱ ግን ቆመው ተመ​ለ​ከ​ቱኝ።</verse>
				<verse number="21">ምሕ​ረት የሌ​ላ​ቸው ሰዎች ደበ​ደ​ቡኝ፥ የገ​ረ​ፈ​ችኝ እጅም በረ​ታች።</verse>
				<verse number="22">በኀ​ዘን አኖ​ር​ኸኝ፥ ከሕ​ይ​ወ​ቴም አራ​ቅ​ኸኝ።</verse>
				<verse number="23">ሞት እን​ደ​ሚ​ያ​ጠ​ፋኝ አው​ቃ​ለ​ሁና ለሟ​ችም ሁሉ ማደ​ሪ​ያው ምድር ናትና።</verse>
				<verse number="24">እኔ ራሴ ልታ​ነቅ በወ​ደ​ድሁ ነበር ይህም ባይ​ሆን ሌላው እን​ዲሁ እን​ዲ​ያ​ደ​ር​ግ​ልኝ እለ​ም​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="25">ረዳት ለሌ​ለው ሰው አለ​ቀ​ስሁ የተ​ቸ​ገረ ሰውን ባየሁ ጊዜ ጮኽሁ።</verse>
				<verse number="26">ነገር ግን በጎ ነገ​ርን በተ​ጠ​ባ​በ​ቅ​ኋት ጊዜ እነሆ ክፉ ቀኖች መጡ​ብኝ፤ ብር​ሃ​ንን ተስፋ አደ​ረ​ግሁ፥ ጨለ​ማም መጣ​ብኝ።</verse>
				<verse number="27">ሆዴ ፈላች፥ አላ​ረ​ፈ​ች​ምም፤ የች​ግ​ርም ዘመን መጣ​ች​ብኝ።</verse>
				<verse number="28">በጠ​ባቡ ሄድሁ፥ የሚ​ያ​ሰ​ፋ​ል​ኝም አጣሁ፥ በጉ​ባ​ኤም መካ​ከል ቆሜ እጮ​ኻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="29">ለሌ​ሊት ዎፍ ወን​ድም፥ ለሰ​ጎ​ንም ባል​ን​ጀራ ሆንሁ።</verse>
				<verse number="30">ቍር​በቴ እጅግ ጠቈረ፥ አጥ​ን​ቶቼም ከት​ኩ​ሳት የተ​ነሣ ተቃ​ጠሉ።</verse>
				<verse number="31">ስለ​ዚህ ሕማሜ መሰ​ንቆ፥ ልቅ​ሶ​ዬም በገና ሆነ​ብኝ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="31">
				<verse number="1">“ከዐ​ይኔ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረ​ግሁ፥ ድን​ግ​ሊ​ቱ​ንም አል​ተ​መ​ለ​ከ​ት​ሁም፤</verse>
				<verse number="2">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እድል ፋንታ ከላይ፥ ሁሉ​ንም የሚ​ችል የአ​ም​ላክ ርስት ከአ​ር​ያም ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="3">ሞት ለዐ​መ​ፀኛ፥ መለ​የ​ትም ኀጢ​አ​ትን ለሚ​ሠሩ ነው።</verse>
				<verse number="4">እርሱ መን​ገ​ዴን የሚ​ያይ አይ​ደ​ለ​ምን? እር​ም​ጃ​ዬ​ንስ ሁሉ የሚ​ቈ​ጥር አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="5">ከፌ​ዘ​ኞች ጋር ሄጄ እንደ ሆነ፥ እግ​ሬም ከመ​ን​ገዱ ገለል ብላ እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="6">በእ​ው​ነ​ተኛ ሚዛን ልመ​ዘን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቅን​ነ​ቴን ያው​ቃል።</verse>
				<verse number="7">እር​ም​ጃዬ ከመ​ን​ገዱ ፈቀቅ ብሎ እንደ ሆነ፥ ልቤም ዐይ​ኔን ተከ​ትሎ እንደ ሆነ፥ ጉቦም በእጄ ተጣ​ብቆ እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="8">እኔ ልዝራ፥ ሌላ ሰውም ይብ​ላው፤ በም​ድር ላይ ሥሬ ይነ​ቀል።</verse>
				<verse number="9">ልቤ ወደ ሌላ ወንድ ሚስት ተከ​ትሎ እንደ ሆነ፥ በደ​ጅ​ዋም አድ​ብቼ እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="10">ሚስቴ ሌላ​ውን ሰው ደስ ታሰኝ። ልጆ​ቼም ይዋ​ረዱ።</verse>
				<verse number="11">የሌ​ላ​ውን ወንድ ሚስት ማር​ከስ፥ የማ​ይ​ቈ​ጣ​ጠ​ሩት የቍጣ መቅ​ሠ​ፍት ነው።</verse>
				<verse number="12">ይህ በሕ​ዋ​ሳት ሁሉ የሚ​ነ​ድድ እሳት፥ የገ​ባ​በ​ት​ንም ሁሉ ከሥር የሚ​ነ​ቅል ነውና።</verse>
				<verse number="13">“ወንድ ባሪ​ያዬ ወይም ሴት ባሪ​ያዬ በእኔ ዘንድ በተ​ም​ዋ​ገቱ ጊዜ፥ ፍር​ዳ​ቸ​ውን አዳ​ልቼ እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ረ​መ​ረኝ ጊዜ ምን አደ​ር​ጋ​ለሁ? በጐ​በ​ኘኝ ጊዜስ በፊቱ ምን እመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለሁ?</verse>
				<verse number="15">እኔን በማ​ኅ​ፀን የፈ​ጠረ እነ​ር​ሱ​ንስ የፈ​ጠረ አይ​ደ​ለ​ምን? በማ​ኅ​ፀ​ንስ ውስጥ የሠ​ራን አንድ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="16">“ድሆች የሚ​ሹ​ትን እን​ዳ​ያ​ገኙ አድ​ርጌ እንደ ሆነ፥ የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም ዐይን አጨ​ልሜ እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="17">እን​ጀ​ራ​ዬን ለብ​ቻዬ በልቼ እንደ ሆነ፥ ለድ​ሃ​አ​ደ​ጉም ደግሞ ከእ​ርሱ አላ​ካ​ፈ​ልሁ እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="18">እር​ሱን ከታ​ና​ሽ​ነቱ ጀምሮ እንደ አባቱ ከእ​ኔው ጋር አሳ​ድ​ጌው ነበር፤ ከእ​ና​ቱም ማኅ​ፀን ከተ​ወ​ለደ ጀምሮ አሳ​ደ​ግ​ሁት።</verse>
				<verse number="19">ራቁ​ቱን የሆ​ነው ሰው በብ​ርድ ሲሞት አይቼ፥ አላ​ለ​በ​ስ​ሁት እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="20">ድሆች አል​መ​ረ​ቁኝ እንደ ሆነ፥ በበ​ጎ​ቼም ጠጕር ትከ​ሻ​ቸው አል​ሞቀ እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="21">ብዙ ረዳት እን​ዳ​ለኝ ተማ​ምኜ በድ​ሃ​አ​ደጉ ላይ እጄን አን​ሥቼ እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="22">ትከ​ሻዬ ከመ​ሠ​ረቷ ትው​ደቅ፥ ክን​ዴም ከመ​ገ​ና​ኛዋ ትሰ​በር።</verse>
				<verse number="23">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግርማ አስ​ደ​ን​ግ​ጦ​ኛ​ልና፤ በእ​ር​ሱም ከመ​ያዝ በም​ክ​ን​ያት ማም​ለጥ አል​ቻ​ል​ሁም።</verse>
				<verse number="24">“ወር​ቄን በመ​ሬት ውስጥ ቀብሬ እንደ ሆነ፥ ዋጋው ብዙ በሆነ ዕንቍ ታም​ኜም እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="25">ሀብቴ በበዛ ጊዜ፥ ደስ ብሎኝ እንደ ሆነ፥ ስፍር ቍጥር በሌ​ለ​ውም መዝ​ገብ ላይ እጄን ጨምሬ እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="26">የሚ​ያ​በራ ፀሐይ እን​ደ​ሚ​ጠፋ ጨረ​ቃም እን​ደ​ም​ት​ጨ​ልም አላ​ይ​ምን? በራ​ሳ​ቸው ለመ​ኖር ኀይል የላ​ቸ​ው​ምና፥</verse>
				<verse number="27">ልቤ በስ​ውር ተታ​ልሎ እንደ ሆነ፥ በአ​ፌም ላይ እጄን አኑሬ ስሜ እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="28">በል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዋ​ሸሁ ነበ​ርና ይህ ደግሞ ትልቅ በደል ይሁ​ን​ብኝ።</verse>
				<verse number="29">በጠ​ላቴ ውድ​ቀት ደስ ብሎኝ እንደ ሆነ፥ በል​ቤም እሰይ ብዬ እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="30">ጆሮዬ መር​ገ​ሜን ትስማ፤ በወ​ገ​ኔም መካ​ከል ክፉ ስም ይው​ጣ​ልኝ።</verse>
				<verse number="31">“ቤተ ሰቦቼ እኔ ስራ​ራ​ላ​ቸው፥ ሥጋ​ውን እን​በላ ዘንድ ማን በሰ​ጠን ብለው እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="32">መጻ​ተ​ኛው ግን በሜዳ አያ​ድ​ርም ነበር፥ ደጄ​ንም ለመ​ጣው ሁሉ እከ​ፍት ነበር፤</verse>
				<verse number="33">ታላቅ በደ​ልም በድዬ እንደ ሆነ፥ ኀጢ​አ​ቴ​ንም ሰውሬ እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="34">ከብዙ ሕዝብ የተ​ነሣ በፊ​ታ​ቸው ለመ​ና​ገር አፍሬ እንደ ሆነ፥ ድሃ​ውም ከደጄ ባዶ​ውን ወጥቶ እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="35">የሚ​ያ​ደ​ም​ጠ​ኝን ማን በሰ​ጠኝ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም እጅ አል​ፈ​ራሁ እንደ ሆነ፥ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ር​ድ​ብኝ የክስ ጽሑፍ ምነው በኖ​ረኝ!</verse>
				<verse number="36">በት​ከ​ሻዬ ላይ እሸ​ከ​መው ነበር፥ አክ​ሊ​ልም አድ​ርጌ በራሴ አስ​ረው ነበር፥ በብ​ዙ​ዎ​ችም መካ​ከል አነ​ብ​በው ነበር፤</verse>
				<verse number="37">ከባለ ዕዳዬ የም​ቀ​በ​ለው ሳይ​ኖር ቀድ​ጀው እመ​ለ​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="38">“እር​ሻዬ በእኔ ላይ ጮኻ እንደ ሆነ፥ ትል​ሞ​ች​ዋም በአ​ንድ ላይ አል​ቅ​ሰው እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="39">ፍሬ​ዋን ለብ​ቻዬ ያለ ዋጋ በልቼ እንደ ሆነ፥ ባለ መሬ​ቱ​ንም አባ​ርሬ ነፍ​ሱን አሳ​ዝኜ እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="40">በስ​ንዴ ፋንታ እን​ክ​ር​ዳድ፥ በገ​ብ​ስም ፋንታ ኵር​ን​ችት ይብ​ቀ​ል​ብኝ።” ኢዮ​ብም ነገ​ሩን ፈጸመ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="32">
				<verse number="1">ኢዮ​ብም በፊ​ታ​ቸው ራሱን ጻድቅ አድ​ርጎ ነበ​ርና እነ​ዚያ ሦስቱ ወዳ​ጆቹ ለኢ​ዮብ ለመ​መ​ለስ ዝም አሉ።</verse>
				<verse number="2">ከአ​ው​ስ​ጢድ ሀገር ከአ​ራም ወገን የሆነ የቡ​ዛ​ዊው የባ​ር​ክ​ኤል ልጅ ኤሊ​ዩስ ተቈጣ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ራሱን ጻድቅ አድ​ርጎ ነበ​ርና ኢዮ​ብን ተቈ​ጣው።</verse>
				<verse number="3">ደግ​ሞም እንደ ኀጢ​አ​ተኛ አደ​ረ​ጉት እንጂ ለኢ​ዮብ የሚ​ገባ መልስ መመ​ለስ ስላ​ል​ቻሉ በሦ​ስቱ ባል​ን​ጀ​ሮቹ ላይ ተቈጣ።</verse>
				<verse number="4">ኤሊ​ዩስ ግን ከእ​ርሱ ይልቅ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ነበ​ሩና ለኢ​ዮብ መልስ ለመ​ስ​ጠት ጠብቆ ነበር።</verse>
				<verse number="5">ኤሊ​ዩ​ስም በእ​ነ​ዚህ በሦ​ስቱ ሰዎች አፍ መልስ እን​ደ​ሌለ ባየ ጊዜ በቍ​ጣው ተቈ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">የቡ​ዛ​ዊው የባ​ር​ክ​ኤል ልጅ ኤል​ዩ​ስም መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እኔ በዕ​ድ​ሜዬ ታናሽ ነኝ፥ እና​ንተ ግን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ናችሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ዕው​ቀ​ቴን እገ​ል​ጥ​ላ​ችሁ ዘንድ ፈርቼ ዝም አልሁ።</verse>
				<verse number="7">እን​ደ​ዚ​ህም አልሁ፥ “የሚ​ና​ገሩ ዓመ​ታት አይ​ደ​ሉም፥ በዓ​መ​ታት ብዛት ሰዎች ጥበ​ብን አያ​ው​ቋ​ትም።</verse>
				<verse number="8">ነገር ግን በሟች ሰው ውስጥ መን​ፈስ አለ፥ ሁሉን የሚ​ችል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ስም ያስ​ተ​ም​ራል።</verse>
				<verse number="9">በዕ​ድሜ ያረጁ ጠቢ​ባን አይ​ደ​ሉም፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ፍር​ድን አያ​ስ​ተ​ው​ሉም።</verse>
				<verse number="10">ነገር ግን፦ ስሙኝ፤ እኔ ደግሞ የማ​ው​ቀ​ውን እገ​ል​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ አልሁ።</verse>
				<verse number="11">እነሆ፥ ንግ​ግ​ሬን አድ​ም​ጡኝ፤ የም​ት​ና​ገ​ሩ​ትን ነገር እስ​ክ​ት​መ​ረ​ምሩ ድረስ እየ​ሰ​ማ​ች​ሁት እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">እን​ዲ​ሁም ልብ አደ​ረ​ግሁ፤ እነ​ሆም፥ ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ኢዮ​ብን የገ​ሠጸ፥ ወይም ለተ​ና​ገ​ረው ቃልን የመ​ለሰ የለም።</verse>
				<verse number="13">እና​ን​ተም፦ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብን አግ​ኝ​ተ​ናል፤ አብ​ዝ​ተ​ና​ልም እን​ዳ​ትሉ ተጠ​ን​ቀቁ።</verse>
				<verse number="14">እና​ንተ ግን እን​ዲህ ያለ ነገር እን​ዲ​ና​ገር ለሰው መብት ሰጣ​ች​ሁት።</verse>
				<verse number="15">“እና​ንተ ፈራ​ችሁ፥ ዳግ​መ​ኛም አል​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም፤ ከአ​ፋ​ች​ሁም ቁም ነገር ጠፋ።</verse>
				<verse number="16">እኔ በት​ዕ​ግ​ሥት ጠበ​ቅሁ እንጂ አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁም። እና​ንተ ዝም ብላ​ችሁ ቆማ​ችሁ፥ አል​መ​ለ​ሳ​ች​ሁ​ምና።”</verse>
				<verse number="17">ኤል​ዩ​ስም መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦ “ደግሜ እና​ገ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="18">እኔ ቃል ተሞ​ል​ቻ​ለ​ሁና፥ በው​ስ​ጤም ያለ መን​ፈስ አስ​ጨ​ን​ቆ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="19">በተሃ ጠጅ እንደ ተሞ​ላና ሊቀ​ደድ እንደ ቀረበ አቁ​ማዳ፥ ወይም እንደ አን​ጥ​ረኛ ወናፍ እነሆ፥ አን​ጀቴ ሆነ።</verse>
				<verse number="20">ጥቂት እን​ድ​ተ​ነ​ፍስ እና​ገ​ራ​ለሁ። ከን​ፈ​ሬ​ንም ገልጬ እመ​ል​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="21">ከሰው የተ​ነሣ አላ​ፍ​ር​ምና፥ ከሟች ሰውም የተ​ነሣ አላ​ፈ​ገ​ፍ​ግ​ምና።</verse>
				<verse number="22">ለሰው ፊት ማድ​ላ​ትን አላ​ው​ቅም፤ ከሰ​ውም የተ​ነሣ የማ​ፍ​ረው ካለ ትሎች ይብ​ሉኝ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="33">
				<verse number="1">“ነገር ግን፥ ኢዮብ ሆይ፥ ቃሌን ስማ፥ ነገ​ሬ​ንም አድ​ምጥ።</verse>
				<verse number="2">እነሆ፥ አፌን ከፍ​ቻ​ለሁ፥ አን​ደ​በ​ቴም ይና​ገ​ራል።</verse>
				<verse number="3">ልቤም ንጹሕ ነገ​ርን ያስ​ባል፥ የከ​ን​ፈ​ሮ​ችም ማስ​ተ​ዋል ንጹሕ ነገ​ርን ይመ​ረ​ም​ራል።</verse>
				<verse number="4">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ፈጠ​ረኝ፥ ሁሉ​ንም የሚ​ችል የአ​ም​ላክ እስ​ት​ን​ፋስ ያስ​ተ​ም​ረ​ኛል።</verse>
				<verse number="5">በዚህ ነገር ልት​መ​ል​ስ​ልኝ ትችል እንደ ሆነ ታገ​ሠኝ፥ እኔም እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም መል​ስ​ልኝ።</verse>
				<verse number="6">አንተ እንደ እኔ ከጭቃ የተ​ፈ​ጠ​ርህ ነህ፥ የሁ​ላ​ች​ንም ተፈ​ጥሮ ከዚ​ያው ነው።</verse>
				<verse number="7">እነሆ፥ ግር​ማዬ አታ​ስ​ፈ​ራ​ህም፥ እጄም አት​ከ​ብ​ድ​ብ​ህም።</verse>
				<verse number="8">ግፍ​ህን ተና​ግ​ረ​ሃል፥ የቃ​ል​ህ​ንም ድምፅ ሰም​ቻ​ለሁ፥ እን​ዲ​ህም ብለ​ሃል፦</verse>
				<verse number="9">እኔ ንጹሕ ነኝ፥ አል​በ​ደ​ል​ሁ​ምና፤ እኔ ጻድቅ ነኝ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም አል​ሠ​ራ​ሁም።</verse>
				<verse number="10">እነሆ፥ ምክ​ን​ያት አግ​ኝ​ቶ​ብ​ኛል፥ እንደ ጠላ​ትም ቈጥ​ሮ​ኛል፤</verse>
				<verse number="11">እግ​ሬን በግ​ንድ አጣ​በቀ፥ መን​ገ​ዴ​ንም ሁሉ ጠበቀ።</verse>
				<verse number="12">እነሆ፥ እኔ ጻድቅ ነኝ፥ ቃሌ​ንም አይ​ሰ​ማ​ኝም እን​ዴት ትላ​ለህ? ከሟች ሰው በላይ ያለ እርሱ ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ነውና።</verse>
				<verse number="13">አንተ፦ ‘ቃሌን ሁሉ ለምን አይ​ሰ​ማ​ኝም?’ ትላ​ለህ።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ልም ወይም በሌ​ሊት ራእይ፥ አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ የተ​ና​ገረ እን​ደ​ሆነ፥</verse>
				<verse number="15">በአ​ልጋ ላይ ተኝ​ተው ሳሉ፥ በሰ​ዎች ላይ ታላቅ ድን​ጋ​ጤን ያመ​ጣል።</verse>
				<verse number="16">በዚ​ያን ጊዜ የሰ​ዎ​ችን ማስ​ተ​ዋል ይከ​ፍ​ታል፥ ግርማ ባለው ራእ​ይም ያስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ቸ​ዋል፤</verse>
				<verse number="17">ሰውን ከኀ​ጢ​አቱ ይመ​ል​ሰው ዘንድ፥ ሥጋ​ው​ንም ከው​ድ​ቀት ያድ​ነው ዘንድ፥</verse>
				<verse number="18">ነፍ​ሱን ከሞት ያድ​ና​ታል፤ በሰ​ይ​ፍም እን​ዳ​ይ​ጠፋ ይጠ​ብ​ቀ​ዋል።</verse>
				<verse number="19">“ደግሞ በአ​ልጋ ላይ በደዌ ይገ​ሥ​ጸ​ዋል፥ አጥ​ን​ቱም ሁሉ ይን​ቋ​ቋል።</verse>
				<verse number="20">ማን​ኛ​ው​ንም መብል መቅ​መስ አይ​ች​ልም። ሰው​ነቱ ግን መብ​ልን ትበላ ዘንድ ትመ​ኛ​ለች።</verse>
				<verse number="21">ሥጋው እስ​ከ​ሚ​ያ​ልቅ ድረስ፥ አጥ​ን​ቱም ባዶ​ውን እስ​ከ​ሚ​ታይ ድረስ፥</verse>
				<verse number="22">ሰው​ነቱ ለሞት፥ ሕይ​ወ​ቱም ወደ ሲኦል ቀር​ባ​ለች።</verse>
				<verse number="23">የሞት መላ​እ​ክት ምንም ሺህ ቢሆኑ፥ በልቡ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊመ​ለስ ቢያ​ስብ፥ ኀጢ​አ​ቱን ለሰው ቢና​ገር፥ በደ​ሉ​ንም ቢገ​ልጥ፥ ከእ​ነ​ርሱ አንዱ እንኳ አይ​ገ​ድ​ለ​ውም፤</verse>
				<verse number="24">በሞት እን​ዳ​ይ​ጠፋ ይጠ​ብ​ቀ​ዋል፥ ሰው​ነ​ቱ​ንም እንደ ግድ​ግዳ ምርግ ያድ​ሳ​ታል። አጥ​ን​ቶ​ቹ​ንም በመ​ቅን ይሞ​ላል።</verse>
				<verse number="25">ሥጋ​ውን እንደ ሕፃን ሥጋ ያለ​መ​ል​ማል፤ ከሰ​ዎ​ችም ይልቅ ወደ ጕብ​ዝ​ናው ዘመን ይመ​ል​ሰ​ዋል።</verse>
				<verse number="26">ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ል​ያል፥ ጸሎ​ቱም ተቀ​ባ​ይ​ነ​ትን ያገ​ኛል። በደ​ስ​ተ​ኛም ፊት እያ​መ​ሰ​ገነ ይገ​ባል፥ ለሰ​ውም ጽድ​ቁን ይመ​ል​ስ​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="27">ያን​ጊ​ዜም ሰው ራሱን ይነ​ቅ​ፋል፤ እን​ዲ​ህም ይላል፦ ‘እኔ ምን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ? እንደ ኀጢ​አ​ቶ​ችም መጠን አል​ቀ​ጣ​ኝም፤</verse>
				<verse number="28">ነፍሴ ወደ ጥፋት እን​ዳ​ት​ወ​ርድ አድ​ኖ​አ​ታል፥ ሕይ​ወ​ቴም ብር​ሃ​ንን ታያ​ለች።’</verse>
				<verse number="29">“እነሆ፦ ሁሉን የሚ​ችል እርሱ፥ ይህን ሁሉ ሦስት ጊዜ ከሰው ጋር ያደ​ር​ጋል፤</verse>
				<verse number="30">ሕይ​ወ​ቴም በብ​ር​ሃን ውስጥ ታመ​ሰ​ግን ዘንድ፥ እርሱ ነፍ​ሴን ከሞት አድ​ኖ​አ​ታል።</verse>
				<verse number="31">ኢዮብ ሆይ፥ አድ​ምጥ፥ እኔ​ንም ስማ፤ ዝም በል፥ እኔም እና​ገ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="32">ነገር ቢኖ​ርህ ተና​ገር፤ ትጸ​ድቅ ዘንድ እወ​ድ​ዳ​ለ​ሁና ተና​ገር።</verse>
				<verse number="33">ያለ​ዚ​ያም እኔን ስማ፤ ዝም በል፥ እኔም ጥበ​ብን አስ​ተ​ም​ር​ሃ​ለሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="34">
				<verse number="1">ኤል​ዩስ ደግሞ መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“እና​ንተ ጥበ​በ​ኞች፥ ቃሌን ስሙ፤ እና​ን​ተም ዐዋ​ቂ​ዎች፥ መል​ካም ነገ​ርን አድ​ምጡ።</verse>
				<verse number="3">ጆሮ ቃልን ትለ​ያ​ለ​ችና፥ ጕሮ​ሮም የመ​ብ​ልን ጣዕም ይለ​ያል።</verse>
				<verse number="4">ፍር​ድን ለራ​ሳ​ችን እን​ም​ረጥ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ች​ንም ምን እን​ደ​ሚ​ሻል እን​ወቅ።</verse>
				<verse number="5">ኢዮብ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፦ እኔ ጻድቅ ነኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ፍር​ዴን አስ​ወ​ገደ፤</verse>
				<verse number="6">ፍር​ዴን ሐሰ​ተኛ አደ​ረ​ገ​ብኝ፤ በደ​ልም ሳይ​ኖ​ር​ብኝ በግ​ፍዕ መከ​ራን እቀ​በ​ላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">መሣ​ለ​ቅን እንደ ውኃ የሚ​ጠ​ጣት፥ እንደ ኢዮብ ያለ ሰው ማን ነው?</verse>
				<verse number="8">ፈጽሞ ያል​በ​ደለ፥ ግፍን ከሚ​ሠ​ሩም ጋር ያል​ተ​ባ​በረ፥ ከኃ​ጥ​ኣ​ንም ጋር ያል​ሄደ፥ ማን ነው?</verse>
				<verse number="9">ሰው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጕብ​ኝት ሲኖ​ረው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ጐ​በ​ኘ​ውም አት​በል።</verse>
				<verse number="10">“ሰለ​ዚህ እና​ንተ አእ​ምሮ ያላ​ቸሁ ሰዎች ስሙኝ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ ትበ​ድሉ ዘንድ አት​ው​ደዱ። ሁሉን በሚ​ችል አም​ላክ ፊትም ጻድ​ቁን አታ​ው​ኩት።</verse>
				<verse number="11">ለሰው ሁሉ እንደ ሥራው ይመ​ል​ስ​ለ​ታል፥ ሰው​ንም እንደ መን​ገዱ ያገ​ኘ​ዋል።</verse>
				<verse number="12">በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ግፍ እን​ደ​ሚ​ሠራ ታደ​ር​ገ​ዋ​ለ​ህን? ወይስ ምድ​ርን የፈ​ጠረ ሁሉን የሚ​ችል አም​ላክ ፍር​ድን ያጣ​ም​ማ​ልን?</verse>
				<verse number="13">ከሰ​ማይ በታች ያለ​ውን ዓለም፥ በው​ስ​ጡም ያሉ​ትን ነገ​ሮች ሁሉ የፈ​ጠረ ማን ነው?</verse>
				<verse number="14">በእ​ርሱ ያለ መን​ፈ​ሱን፥ ሊያ​ጸ​ናና ሊይዝ ቢወ​ድድ፥</verse>
				<verse number="15">ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ይሞ​ታል፥ ሟችም ሁሉ ወደ ተፈ​ጠ​ረ​በት መሬት ይመ​ለ​ሳል።</verse>
				<verse number="16">ያለ​ዚያ ግን ተመ​ከር፥ ይህ​ንም ስማ፤ የን​ግ​ግ​ሬ​ንም ቃል አድ​ምጥ።</verse>
				<verse number="17">ግፍን የሚ​ጠላ፥ ክፉ​ዎ​ች​ንም የሚ​ያ​ጠፋ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጻድቅ ነው።</verse>
				<verse number="18">ንጉ​ሡን፦ በደ​ለኛ ነህ የሚ​ለው፥ መኳ​ን​ን​ቱ​ንም፦ ክፉ​ዎች ናችሁ የሚ​ላ​ቸው ኀጢ​አ​ተኛ ነው</verse>
				<verse number="19">እርሱ ግን የክ​ቡ​ርን ሰው ፊት አያ​ፍ​ርም። ለታ​ላ​ቁም ክብር መስ​ጠ​ትን አያ​ው​ቅም፥ ከፊ​ታ​ቸ​ውም አይ​ሸ​ሽም።</verse>
				<verse number="20">የሚ​ጮ​ኸ​ው​ንና ሰውን የማ​ይ​ሰ​ማ​ውን ከንቱ ነገር ያገ​ኘ​ዋል፥ በድ​ሆች ላይ ክፉ አድ​ር​ጎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="21">እርሱ የሰ​ዎ​ችን ሥራ ይመ​ረ​ም​ራል፥ ከሚ​ሠ​ሩ​ትም ሁሉ ከእ​ርሱ የሚ​ሰ​ወር ምንም የለም።</verse>
				<verse number="22">ኀጢ​አ​ትን የሚ​ሠሩ የሚ​ሰ​ወ​ሩ​በት ቦታ የለም።</verse>
				<verse number="23">ሁሉን ከሚ​ያይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አያ​መ​ል​ጡ​ምና።</verse>
				<verse number="24">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ታች ወደ ሰዎች ይመ​ለ​ከ​ታል፥ ሊመ​ረ​መሩ የማ​ይ​ችሉ ነገ​ሮ​ችን ሁሉ፥ ቍጥር የሌ​ላ​ቸ​ውን የተ​ከ​በ​ሩ​ት​ንና ድን​ቆ​ች​ንም ያስ​ተ​ው​ላል።</verse>
				<verse number="25">ሥራ​ቸ​ውን ያው​ቃል፥ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ ሌሊ​ትን ያመ​ጣል፥ መከ​ራ​ንም ያጸ​ና​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="26">ኃጥ​ኣ​ንን ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፥ ጻድ​ቃን ግን በፊቱ ናቸው።</verse>
				<verse number="27">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ፈቀቅ ያሉ፥ ፍር​ዱን አያ​ው​ቁም።</verse>
				<verse number="28">እር​ሱም የድ​ሆ​ችን ጩኸት በእ​ነ​ርሱ ላይ ይመ​ል​ሳል፥ የች​ግ​ረ​ኞ​ች​ንም ልቅሶ ይሰ​ማል።</verse>
				<verse number="29">“እርሱ ዕረ​ፍ​ትን ይሰ​ጣል፤ የሚ​ፈ​ር​ድስ ማን ነው? በሕ​ዝብ ወይም በሰው ዘንድ ፊቱን ቢሰ​ውር የሚ​ያ​የው ማን ነው?</verse>
				<verse number="30">ስለ ሕዝ​ቡም ክፋት፥ ግብዝ ሰውን ያነ​ግ​ሣል።</verse>
				<verse number="31">“ኀያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፦ እን​ዲህ የሚል አለ፥ እኔ በረ​ከ​ትን ተቀ​በ​ልሁ፥ መያ​ዣ​ው​ንም አል​ወ​ስ​ድም።</verse>
				<verse number="32">እኔ ራሴ አያ​ለሁ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም ሠርቼ እንደ ሆነ፥ ሐሰ​ት​ንም ተና​ግሬ እንደ ሆነ፥ ደግሜ እን​ዳ​ል​ሠራ አንተ አሳ​የኝ።</verse>
				<verse number="33">በውኑ አንተ ከእኔ ትርቅ ዘንድ፥ እኔ ከአ​ንተ የተ​ቀ​በ​ል​ሁት አለን? አንተ ትመ​ር​ጣ​ለህ እንጂ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና፤ ስለ​ዚህ የም​ታ​ው​ቀው ካለ ተና​ገር።</verse>
				<verse number="34">የልብ ጥበ​በ​ኞች እን​ዲህ ይላ​ሉና፦ ጠቢብ ሰው ነገ​ሬን ይሰ​ማ​ኛል።</verse>
				<verse number="35">ኢዮብ እንደ ጠቢብ በዕ​ው​ቀት አይ​ና​ገ​ርም፥ ቃሉም እንደ ምሁር አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="36">ነገር ግን ኢዮብ ሆይ፥ ተማር። እንደ ሰነ​ፎ​ችም አት​መ​ልስ፥</verse>
				<verse number="37">በኀ​ጢ​አ​ቶ​ችህ ላይ እን​ዳ​ት​ጨ​ምር፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ብዙ መና​ገር በደል ይሆ​ን​ብ​ሃል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="35">
				<verse number="1">ኤል​ዩ​ስም ደግሞ መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“አንተ ተዋ​ቅ​ሰህ ምን ትላ​ለህ? ወይስ፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እኔ ጻድቅ ነኝ የም​ትል አንተ ማን ነህ?</verse>
				<verse number="3">ኀጢ​አት ብሠ​ራስ ምን አደ​ር​ጋ​ለሁ? ትላ​ለህ።</verse>
				<verse number="4">እኔ ለአ​ን​ተና ለሦ​ስቱ ወዳ​ጆ​ችህ እመ​ል​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">ወደ ሰማይ ተመ​ል​ከት፥ እይም፤ ደመ​ናም ከአ​ንተ በላይ ምን ያህል ከፍ እን​ዳለ ዕወቅ።</verse>
				<verse number="6">ኀጢ​አት ብት​ሠራ በእ​ርሱ ላይ ምን ታደ​ር​ጋ​ለህ? ብዙም ብት​በ​ድል ምን ማድ​ረግ ትች​ላ​ለህ?</verse>
				<verse number="7">ጻድ​ቅስ ብት​ሆን ምን ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ? ወይስ ከእ​ጅህ ምንን ይቀ​በ​ላል?</verse>
				<verse number="8">እንደ አንተ ያለ​ውን ሰው ክፋ​ትህ ይጎ​ዳ​ዋል፤ ለሰ​ውም ልጅ ጽድ​ቅህ ይጠ​ቅ​መ​ዋል።</verse>
				<verse number="9">ከግ​ፈ​ኞች ብዛት የተ​ነሣ ሰዎች ይጮ​ኻሉ፤ ከብ​ዙ​ዎች ክንድ የተ​ነ​ሣም ለር​ዳታ ይጠ​ራሉ።</verse>
				<verse number="10">ነገር ግን በሌ​ሊት ጥበ​ቃን የሚ​ያ​ዝዝ ፈጣ​ሪዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዴት ነው? የሚል የለም፤</verse>
				<verse number="11">እር​ሱም ከም​ድር እን​ስ​ሶች ይልቅ፥ ከሰ​ማ​ይም ወፎች ይልቅ የሚ​ለ​የኝ ነው።</verse>
				<verse number="12">በዚያ ስለ ክፉ ሰዎች ስድብ ይጮ​ኻሉ፥ እርሱ ግን አይ​ሰ​ማ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ው​ነት ክፉ ነገ​ርን ሊያይ አይ​ወ​ድም። እርሱ ሁሉን የሚ​ችል ዐዋቂ አም​ላክ ነውና።</verse>
				<verse number="14">ክፉ የሚ​ሠ​ሩ​ትን አይ​ሰ​ማ​ቸ​ውም፥ እኔ​ንም ያድ​ነ​ኛል፤ አንተ አሁን የሚ​ቻል እንደ መሆኑ መጠን ልታ​መ​ሰ​ግ​ነው ትችል እንደ ሆነ እስኪ በፊቱ ተዋ​ቀስ።</verse>
				<verse number="15">አሁን ቍጣ​ውን የሚ​ያ​ውቅ የለ​ምና፥ ታላቅ ኀጢ​አ​ቱ​ንም የሚ​ያ​ስብ የለ​ምና።</verse>
				<verse number="16">ኢዮብ ግን አፉን በከ​ንቱ ይከ​ፍ​ታል፥ ያለ ዕው​ቀ​ትም ቃሉን ያበ​ዛል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="36">
				<verse number="1">ኤል​ዩ​ስም ደግሞ መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“ገና የም​ና​ገ​ረው ነገር አለ​ኝና ጥቂት ታገ​ሠኝ፥ እኔም አስ​ተ​ም​ር​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">ዕው​ቀ​ቴን ከሩቅ አመ​ጣ​ለሁ፥ ሥራ​ዬ​ንም እው​ነት ነው እላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">ቃሌ ሐሰት ያይ​ደለ እው​ነት ነው። አን​ተም የዐ​መፅ ቃላ​ትን አት​ሰ​ማም።</verse>
				<verse number="5">“በጥ​በብ ብር​ቱና ኀያል የሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ የዋ​ሁን ሰው እን​ደ​ማ​ይ​ጥ​ለው ዕወቅ።</verse>
				<verse number="6">እርሱ የበ​ደ​ለ​ኞ​ችን ሕይ​ወት አያ​ድ​ንም፤ ለች​ግ​ረ​ኞች ግን ፍር​ዱን ይሰ​ጣል።</verse>
				<verse number="7">ዐይ​ኑን ከጻ​ድ​ቃን ላይ አያ​ር​ቅም፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ከነ​ገ​ሥ​ታት ጋር በዙ​ፋን ላይ ያስ​ቀ​ም​ጣ​ቸ​ዋል፥ በድል አድ​ራ​ጊ​ነ​ትም ያኖ​ራ​ቸ​ዋል። እነ​ር​ሱም ከፍ ከፍ ይላሉ።</verse>
				<verse number="8">በሰ​ን​ሰ​ለት እጃ​ቸ​ውን የታ​ሠሩ በች​ግር ገመድ ይያ​ዛሉ።</verse>
				<verse number="9">ሥራ​ቸ​ው​ንና መተ​ላ​ለ​ፋ​ቸ​ውን ይነ​ግ​ራ​ቸ​ዋል፥ ብዙ ነውና።</verse>
				<verse number="10">ጻድ​ቃ​ንን ግን ይሰ​ማ​ቸ​ዋል፥ ከኀ​ጢ​አ​ትም ይመ​ለሱ ዘንድ ያዝ​ዛ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="11">ቢሰ​ሙና ቢያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​ትም፥ ዕድ​ሜ​አ​ቸ​ውን በመ​ል​ካም፥ ዘመ​ና​ቸ​ው​ንም በተ​ድላ ይፈ​ጽ​ማሉ።</verse>
				<verse number="12">ኃጥ​ኣ​ንን ግን አያ​ድ​ና​ቸ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያዩ ዘንድ አይ​ወ​ዱ​ምና፥ ሲገ​ሥ​ፃ​ቸ​ውም አይ​ሰ​ሙ​ምና።</verse>
				<verse number="13">“ግብ​ዞች ግን በል​ባ​ቸው ቍጣን ያዘ​ጋ​ጃሉ፤ እር​ሱም ባሰ​ራ​ቸው ጊዜ አይ​ጮ​ኹም።</verse>
				<verse number="14">ስለ​ዚ​ህም በሕ​ፃ​ን​ነ​ታ​ቸው ሳሉ ሰው​ነ​ታ​ቸው ትጠ​ፋ​ለች፥ ሕይ​ወ​ታ​ቸ​ው​ንም መላ​እ​ክት ያጠ​ፉ​አ​ታል።</verse>
				<verse number="15">የተ​ቸ​ገ​ረ​ው​ንና ረዳት የሌ​ለ​ውን አስ​ጨ​ን​ቀ​ዋ​ልና፥ የየ​ዋ​ሃ​ን​ንም ፍርድ ለው​ጠ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="16">አን​ተን ግን ከጠ​ላ​ትህ አፍ አድ​ኖ​ሃል፥ በበ​ታ​ች​ህም ጥልቅ ባሕር፥ ፈሳሽ ምን​ጭም አለ፥ ማዕ​ድ​ህም በስብ ተሞ​ልታ ትወ​ር​ዳ​ለች።</verse>
				<verse number="17">ፍር​ድን ለጻ​ድ​ቃን አያ​ዘ​ገ​ይ​ምና።</verse>
				<verse number="18">ይበ​ድሉ ዘንድ በተ​ቀ​በ​ሉት መማ​ለጃ ኀጢ​አት ምክ​ን​ያት ቍጣ በኃ​ጥ​ኣን ላይ ትመ​ጣ​ለች።</verse>
				<verse number="19">በጭ​ን​ቀት ካሉ ከች​ግ​ረ​ኞች ልመና የተ​ነሣ አእ​ም​ሮህ በፈ​ቃድ አያ​ስ​ትህ</verse>
				<verse number="20">በእ​ነ​ርሱ ፋንታ ወገ​ኖች እን​ዲ​ገቡ፥ ኀያ​ላን ሰዎ​ችን ሁሉ በሌ​ሊት አታ​ስ​ወጣ።</verse>
				<verse number="21">መል​ካ​ምን አድ​ርግ እንጂ፥ ክፉን እን​ዳ​ት​ሠራ ተጠ​ን​ቀቅ። ስለ​ዚ​ህም ከች​ግር ትድ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="22">“እነሆ፥ ኀያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኀ​ይሉ ያጸ​ናል። እንደ እር​ሱስ ያለ ኀያል ማን ነው?</verse>
				<verse number="23">ሥራ​ው​ንስ የሚ​መ​ረ​ምር ማን ነው? ወይስ፦ ክፉ ሠር​ተ​ሃል የሚ​ለው ማን ነው?</verse>
				<verse number="24">ሰዎች ሊሠ​ሩት ከሞ​ከ​ሩት በላይ፥ ሥራው ታላቅ እንደ ሆነ አስብ።</verse>
				<verse number="25">ሰው ሁሉ ራሱ፥ ኃጥ​ኣን ሙታን እንደ ሆኑ ያስ​ባል።</verse>
				<verse number="26">እነሆ፥ ኀያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አና​ው​ቀ​ውም፤ የዘ​መ​ኑም ቍጥር አይ​መ​ረ​መ​ርም።</verse>
				<verse number="27">የዝ​ና​ቡም ነጠ​ብ​ጣ​ቦች በእ​ርሱ ይቈ​ጠ​ራሉ። ዝና​ብም ከደ​መና ይን​ጠ​ባ​ጠ​ባል፤</verse>
				<verse number="28">የጥ​ንቱ ይበ​ቅ​ላል። ደመ​ናም በሟች ላይ ይጋ​ር​ዳል፥ ስፍር ቍጥር የሌ​ለው ዝናብ ይዘ​ን​ባል፥</verse>
				<verse number="29">አንድ ሰው የደ​መ​ና​ውን መዘ​ር​ጋት፥ ወይም የማ​ደ​ሪ​ያ​ውን ልክ ቢያ​ውቅ፥</verse>
				<verse number="30">እነሆ፥ በዙ​ሪ​ያው ብር​ሃ​ኑን ይዘ​ረ​ጋል የባ​ሕ​ሩ​ንም ጥል​ቀት ይከ​ድ​ነ​ዋል።</verse>
				<verse number="31">በእ​ነ​ዚህ በአ​ሕ​ዛብ ላይ ይፈ​ር​ዳል፤ ለኀ​ይ​ለ​ኛ​ውም ምግ​ቡን ይሰ​ጠ​ዋል።</verse>
				<verse number="32">በእጁ ብር​ሃ​ንን ይሰ​ው​ራል፥ አደጋ የሚ​ጥ​ል​ባ​ት​ንም አዘዘ።</verse>
				<verse number="33">ስለ እር​ሱም ወዳጁ፥ በዐ​መ​ፃው ያገ​ኘ​ች​ውን ይና​ገ​ራል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="37">
				<verse number="1">“ስለ​ዚ​ህም ልቤ ደነ​ገ​ጠ​ች​ብኝ፥ ከስ​ፍ​ራ​ዋም ተን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰች።</verse>
				<verse number="2">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቍ​ጣ​ውን ድምፅ ስማ፥ ከአ​ፉም የሚ​ወ​ጣ​ውን ጕር​ም​ር​ምታ አድ​ምጥ።</verse>
				<verse number="3">እር​ሱን ወደ ሰማ​ያት ሁሉ ታች፥ ብር​ሃ​ኑ​ንም ወደ ምድር ዳርቻ ይሰ​ድ​ዳል።</verse>
				<verse number="4">በስ​ተ​ኋ​ላው ድምፅ ይጮ​ኻል፤ በግ​ር​ማ​ውም ድምፅ ያን​ጐ​ደ​ጕ​ዳል፤ ድም​ፁም በተ​ሰማ ጊዜ ሰዎች እን​ዲ​ጠፉ አያ​ደ​ር​ግም።</verse>
				<verse number="5">ኀያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በድ​ምፁ ድንቅ አድ​ርጎ ያን​ጐ​ደ​ጕ​ዳል፤ ለእ​ን​ስ​ሳት በየ​ጊ​ዜው ምግ​ባ​ቸ​ውን ያዘ​ጋ​ጃል፥ የሚ​ተ​ኙ​በ​ት​ንም ጊዜ ያው​ቃሉ፤ በዚህ ሁሉ ልብህ አይ​ደ​ን​ግ​ጥ​ብህ፤ ሥጋ​ህም ልብ​ህም ከግ​ዘፉ አይ​ለ​ወ​ጥ​ብህ፤ እር​ሱም እኛ የማ​ና​ው​ቀ​ውን ታላቅ ነገር ያደ​ር​ጋል።</verse>
				<verse number="6">በረ​ዶ​ው​ንና ውሽ​ን​ፍ​ሩን፥ ብር​ቱ​ው​ንም ዝናብ በም​ድር ላይ እን​ዲ​ወ​ርድ ያዝ​ዛል።</verse>
				<verse number="7">ሰው ሁሉ ደካ​ማ​ነ​ቱን ያውቅ ዘንድ፥ የሰ​ውን ሁሉ እጅ ያት​ማል።</verse>
				<verse number="8">አው​ሬ​ዎ​ቹም ወደ ጫካው ይገ​ባሉ፥ በዋ​ሾ​ቻ​ቸ​ውም ያር​ፋሉ።</verse>
				<verse number="9">ከተ​ሰ​ወረ ማደ​ሪ​ያ​ውም ችግር፥ ከተ​ራ​ሮች ጫፍም ብርድ ይመ​ጣል።</verse>
				<verse number="10">ከኀ​ያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ት​ን​ፋስ ውርጭ ይመ​ጣል። ውኃ​ው​ንም እንደ ወደደ ይመ​ራ​ዋል።</verse>
				<verse number="11">የተ​መ​ረ​ጡ​ትን በደ​መና ይሰ​ው​ራል፤ ብር​ሃ​ኑም ደመ​ና​ውን ይበ​ት​ናል፤</verse>
				<verse number="12">እር​ሱም ሰው በሚ​ኖ​ር​በት ዓለም ላይ፥ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ያደ​ርግ ዘንድ፥ ፈቃዱ ወደ መራ​ችው ይዞ​ራል።</verse>
				<verse number="13">ይኸ​ውም፥ ለተ​ግ​ሣጽ ወይም ለም​ድሩ ወይም በም​ሕ​ረት ለሚ​ያ​ገ​ኘው እን​ዲ​ሆን ነው።</verse>
				<verse number="14">“ኢዮብ ሆይ፥ ይህን ስማ፤ ቁም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይል ተገ​ሠጽ።</verse>
				<verse number="15">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ​ውን እን​ዳ​ከ​ና​ወነ ከጨ​ለ​ማም ለይቶ ብር​ሃ​ንን እንደ ፈጠረ እና​ው​ቃ​ለን።</verse>
				<verse number="16">የደ​መ​ና​ትን ክፍ​ሎች፥ አስ​ፈሪ የሆ​ነ​ው​ንም የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችን አወ​ዳ​ደቅ ያው​ቃል።</verse>
				<verse number="17">የአ​ዜብ ነፋስ በተ​ኮሰ ጊዜ ያንተ ልብ​ስህ የሞቀ ነው። እን​ግ​ዲህ በም​ድር ላይ ፀጥ በል።</verse>
				<verse number="18">እንደ ቀለጠ መስ​ተ​ዋት ብርቱ የሆ​ኑ​ትን ሰማ​ያት ከእ​ርሱ ጋር ልት​ዘ​ረጋ ትች​ላ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="19">ስለ​ዚህ ንገ​ረኝ! ምን እን​ለ​ዋ​ለን? እን​ግ​ዲህ ዝም እን​በል፥ ብዙም አን​ና​ገር፥</verse>
				<verse number="20">“ሰው በእኔ ዘንድ ሲቆም ዝም እል ዘንድ፥ መጽ​ሐፍ ወይም ጸሓፊ አለ​ኝን?</verse>
				<verse number="21">“ብር​ሃን ለሁሉ የሚ​ታይ አይ​ደ​ለም ብር​ሃን በእ​ርሱ ዘንድ በደ​መና ውስጥ ሆኖ ከሩቅ በሰ​ማ​ያት ያበ​ራል።</verse>
				<verse number="22">ከሰ​ሜን እንደ ወርቅ የሚ​ያ​በራ ደመና ይወ​ጣል፤ በዚ​ህም ሁሉን የሚ​ችል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ክብ​ርና ምስ​ጋና አለ።</verse>
				<verse number="23">በኀ​ይል ከእ​ርሱ ጋር እኩል የሚ​ሆን፥ እው​ነ​ት​ንም የሚ​ፈ​ርድ ሌላ አና​ገ​ኝም። እርሱ እን​ደ​ማ​ይ​ሰማ ታስ​ባ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="24">ስለ​ዚህ ሰዎች ይፈ​ሩ​ታል፤ በል​ባ​ቸ​ውም ጠቢ​ባን የሆኑ ሁሉ ይፈ​ሩ​ታል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="38">
				<verse number="1">ኤል​ዩስ ንግ​ግ​ሩን ካቆመ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በደ​መ​ናና በዐ​ውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ኢዮ​ብን ጠየ​ቀው፤ እን​ዲ​ህም አለው፦</verse>
				<verse number="2">“ከእኔ ምክ​ርን የሚ​ሸ​ሽግ፥ በል​ቡም ነገ​ርን የሚ​ደ​ብቅ ማን ነው? ከእኔ ይሰ​ው​ረ​ዋ​ልን?</verse>
				<verse number="3">እን​ግ​ዲህ እንደ ሰው ወገ​ብ​ህን ታጠቅ፤ እጠ​ይ​ቅ​ሃ​ለሁ፥ አን​ተም መል​ስ​ልኝ።</verse>
				<verse number="4">ምድ​ርን በመ​ሠ​ረ​ትሁ ጊዜ አንተ ወዴት ነበ​ርህ? ታስ​ተ​ውል እንደ ሆነ ንገ​ረኝ።</verse>
				<verse number="5">ብታ​ውቅ መስ​ፈ​ሪ​ያ​ዋን የወ​ሰነ፥ በላ​ይ​ዋስ የመ​ለ​ኪያ ገመ​ድን የዘ​ረጋ ማን ነው?</verse>
				<verse number="6">መሠ​ረ​ቶ​ችዋ በምን ላይ ተተ​ክ​ለው ነበር? የማ​ዕ​ዘ​ን​ዋ​ንስ ድን​ጋይ ያቆመ ማን ነው?</verse>
				<verse number="7">ከዋ​ክ​ብት በተ​ፈ​ጠሩ ጊዜ መላ​እ​ክቴ ሁሉ በታ​ላቅ ድምፅ አመ​ሰ​ገ​ኑኝ</verse>
				<verse number="8">ከእ​ናቷ ማኅ​ፀን በወ​ጣች ጊዜ፥ ባሕ​ርን በመ​ዝ​ጊ​ያ​ዎች ዘጋ​ኋት፤</verse>
				<verse number="9">ደመ​ና​ውን ልብስ አደ​ረ​ግ​ሁ​ላት። በጭ​ጋ​ግም ጠቀ​ለ​ል​ኋት።</verse>
				<verse number="10">ድን​በ​ርም አደ​ረ​ግ​ሁ​ላት። መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ንና መዝ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ንም አኖ​ርሁ።</verse>
				<verse number="11">እስ​ከ​ዚህ ድረስ ድረሺ፥ ከወ​ሰ​ን​ሽም አት​ለፊ፤ ነገር ግን ማዕ​በ​ልሽ በመ​ካ​ከ​ልሽ ይገ​ደብ አል​ኋት።</verse>
				<verse number="12">“የን​ጋት ወገ​ግታ በአ​ንተ ተፈ​ጥ​ሮ​አ​ልን? የአ​ጥ​ቢያ ኮከ​ብስ ትእ​ዛ​ዙን በአ​ንተ ዐው​ቋ​ልን?</verse>
				<verse number="13">የም​ድ​ርን ዳርቻ ይይዝ ዘንድ፥ ከእ​ር​ስ​ዋም ኃጥ​ኣ​ንን ያና​ውጥ ዘንድ።</verse>
				<verse number="14">አንተ ጭቃ​ውን ከመ​ሬት ወስ​ደህ ሕያው ፍጥ​ረ​ትን ፈጥ​ረ​ሃ​ልን? በም​ድ​ርስ ላይ እን​ዲ​ና​ገር አድ​ር​ገ​ሃ​ልን?</verse>
				<verse number="15">የኃ​ጥ​ኣ​ንን ብር​ሃ​ና​ቸ​ውን ከል​ክ​ለ​ሃ​ልን? የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ች​ንስ ክንድ ሰብ​ረ​ሃ​ልን?</verse>
				<verse number="16">ወደ ባሕር ምን​ጭስ ውስጥ ገብ​ተ​ሃ​ልን? በጥ​ል​ቁስ መሠ​ረት ውስጥ ተመ​ላ​ል​ሰ​ሃ​ልን</verse>
				<verse number="17">ከግ​ር​ማ​ህስ የተ​ነሣ የሞት በሮች ተከ​ፍ​ተ​ው​ል​ሃ​ልን? የሲ​ኦል በረ​ኞ​ችስ አን​ተን አይ​ተው ይደ​ነ​ግ​ጣ​ሉን?</verse>
				<verse number="18">ከሰ​ማይ በታች ያለ የም​ድ​ር​ንስ ስፋት አስ​ተ​ው​ለ​ሃ​ልን? መጠ​ኑም ምን ያህል እንደ ሆነ እስኪ ንገ​ረኝ!</verse>
				<verse number="19">“የብ​ር​ሃን ማደ​ር​ያው ቦታ የት ነው? የጨ​ለ​ማስ ቦታው ወዴት አለ?</verse>
				<verse number="20">ትችል እንደ ሆነ፥ መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንም ታውቅ እን​ደ​ሆነ፥ ወደ ዳር​ቻ​ቸው እስኪ ውሰ​ደኝ።</verse>
				<verse number="21">በዚ​ያን ጊዜ ተወ​ል​ደህ ነበ​ርና፥ የዕ​ድ​ሜ​ህም ቍጥር ብዙ ነውና፥ በእ​ው​ነት አንተ ሳታ​ውቅ አት​ቀ​ርም።</verse>
				<verse number="22">በውኑ ወደ በረ​ዶው ቤተ መዛ​ግ​ብት ገብ​ተ​ሃ​ልን? የበ​ረ​ዶ​ው​ንስ ቅን​ጣት ቤተ መዛ​ግ​ብት አይ​ተ​ሃ​ልን?</verse>
				<verse number="23">ይህስ በጠ​ላ​ትህ ጊዜ ለሰ​ል​ፍና ለጦ​ር​ነት ቀን ይጠ​በ​ቅ​ል​ሃ​ልን?</verse>
				<verse number="24">አመ​ዳይ ከየት ይወ​ጣል? ከሰ​ማይ በታች ያለ የአ​ዜብ ነፋ​ስስ እን​ዴት ይበ​ተ​ናል?</verse>
				<verse number="25">ለኀ​ይ​ለ​ኛው ዝናብ መው​ረ​ጃ​ውን፥ ወይስ ለሚ​ያ​ን​ጐ​ዳ​ጕ​ደው መብ​ረቅ መን​ገ​ድን ያዘ​ጋጀ ማን​ነው?</verse>
				<verse number="26">ማንም በሌ​ለ​በት ምድር ላይ፥ ሰውም በማ​ይ​ኖ​ር​በት ምድረ በዳ ይዘ​ንም ዘንድ፥</verse>
				<verse number="27">ባድ​ማ​ው​ንና ውድ​ማ​ውን ያጠ​ግብ ዘንድ፥ ሣሩ​ንም በም​ድረ በዳ ያበ​ቅል ዘንድ፥</verse>
				<verse number="28">የዝ​ናብ አባቱ ማን ነው? ወይስ የጠ​ልን ነጠ​ብ​ጣብ የወ​ለደ ማን ነው?</verse>
				<verse number="29">በረ​ዶስ ከማን ማኅ​ፀን ይወ​ጣል? የሰ​ማ​ዩ​ንስ አመ​ዳይ ማን ወለ​ደው?</verse>
				<verse number="30">እር​ሱም እንደ ፈሳሽ ውኃ ይወ​ር​ዳል። ውኆች እንደ ድን​ጋይ ጠነ​ከሩ፥ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንስ ፊት ማን አዋ​ረደ?</verse>
				<verse number="31">“በውኑ የሰ​ባ​ቱን ከዋ​ክ​ብት ዘለላ ታስር ዘንድ፥ ወይስ ኦሪ​ዮን የሚ​ባ​ለ​ውን ኮከብ ትፈታ ዘንድ ትች​ላ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="32">ወይስ ማዛ​ሮት የሚ​ባ​ሉ​ትን ከዋ​ክ​ብት በጊ​ዜ​ያ​ቸው ታወጣ ዘንድ፥ ወይስ የም​ሽ​ቱን ኮከብ ከል​ጆቹ ጋር ትመራ ዘንድ ትች​ላ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="33">የሰ​ማ​ይን ሥር​ዐት፥ ከሰ​ማይ በታ​ችስ የሚ​ሆ​ነ​ውን ታው​ቃ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="34">ደመ​ና​ውን በቃ​ልህ ትጠ​ራ​ዋ​ለ​ህን? ብዙ ውኃስ እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጠ ይመ​ል​ስ​ል​ሃ​ልን?</verse>
				<verse number="35">መብ​ረ​ቁን ትል​ከ​ዋ​ለ​ህን? እር​ሱስ ይሄ​ዳ​ልን? ደስ​ታ​ህስ ምን​ድን ነው ይል​ሃ​ልን?</verse>
				<verse number="36">ለሴ​ቶች የፈ​ት​ልን ጥበ​ብና የተ​ለ​ያዩ የጥ​ልፍ ሥራ​ዎ​ችን ዕው​ቀት ማን ሰጠ?</verse>
				<verse number="37">የሰ​ማ​ይን ደመና በጥ​በቡ ሊቈ​ጥር የሚ​ችል ማን ነው? ሰማ​ይ​ንም ወደ ምድር ያዘ​ነ​በለ ማን ነው?</verse>
				<verse number="38">እንደ ትቢያ በም​ድር ተዘ​ር​ግቷል፤ እንደ ዓለት ድን​ጋ​ይም አጣ​በ​ቅ​ሁት።</verse>
				<verse number="39">“ለአ​ን​በ​ሳ​ዪቱ አደን ታድ​ና​ለ​ህን? የእ​ባ​ቦ​ች​ንስ ነፍስ ታጠ​ግ​ባ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="40">በዋ​ሾ​ቻ​ቸው ውስጥ ተጋ​ድ​መው በጫ​ካም ውስጥ አድ​ብ​ተው ይቀ​መ​ጣ​ሉና።</verse>
				<verse number="41">ልጆቹ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሲጮኹ፥ የሚ​በ​ሉ​ትም ፈል​ገው ሲቅ​በ​ዘ​በዙ፥ ለቍራ መብ​ልን የሚ​ሰ​ጠው ማን ነው?</verse>
			</chapter>
			<chapter number="39">
				<verse number="1">“ዋልያ የም​ት​ወ​ል​ድ​በ​ትን ጊዜ ታው​ቃ​ለ​ህን? የም​ታ​ም​ጥ​በ​ት​ንስ ጊዜ ትመ​ለ​ከ​ታ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="2">እር​ስዋ የም​ት​ወ​ል​ድ​በ​ት​ንስ ሙሉ ወራት ትቈ​ጥ​ራ​ለ​ህን? ከም​ጥስ ትገ​ላ​ግ​ላ​ታ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="3">ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንስ ያለ ፍር​ሃት አሳ​ድ​ገ​ሃ​ልን? መከ​ራ​ቸ​ው​ንስ አስ​ወ​ግ​ደ​ሃ​ልን?</verse>
				<verse number="4">ልጆ​ቻ​ቸው ያመ​ል​ጣሉ። ይባ​ዛሉ፥ ይዋ​ለ​ዳ​ሉም። ይወ​ጣሉ፥ ወደ እነ​ር​ሱም አይ​መ​ለ​ሱም።</verse>
				<verse number="5">“የሜ​ዳ​ው​ንስ አህያ ነጻ​ነት ማን አወ​ጣው? ከእ​ስ​ራ​ቱስ ማን ፈታው?</verse>
				<verse number="6">በረ​ሃ​ውን ለእ​ርሱ ቤት፥ መኖ​ሪ​ያ​ው​ንም በጨው ምድር አድ​ርጌ ሰጠ​ሁት።</verse>
				<verse number="7">በከ​ተ​ማው ሕዝብ ውካታ ይዘ​ብ​ታል፤ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ው​ንም ጩኸት አይ​ሰ​ማም።</verse>
				<verse number="8">ተራ​ራ​ውን እንደ መሰ​ም​ሪ​ያው ይመ​ለ​ከ​ተ​ዋል፥ ለም​ለ​ሙ​ንም ሁሉ ይፈ​ል​ጋል።</verse>
				<verse number="9">“ጎሽ ያገ​ለ​ግ​ልህ ዘንድ ይፈ​ቅ​ዳ​ልን? ወይስ በግ​ር​ግ​ምህ አጠ​ገብ ያድ​ራ​ልን?</verse>
				<verse number="10">በቀ​ን​በር ትጠ​ም​ደ​ዋ​ለ​ህን? በእ​ር​ሻ​ህስ ውስጥ ትልም ያር​ስ​ል​ሃ​ልን?</verse>
				<verse number="11">ጕል​በ​ቱስ ብርቱ ስለ​ሆነ ትታ​መ​ነ​ዋ​ለ​ህን? ተግ​ባ​ር​ህ​ንስ ለእ​ርሱ ትተ​ዋ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="12">ዘር​ህ​ንስ ይመ​ል​ስ​ልህ ዘንድ፥ በአ​ው​ድ​ማ​ህስ ያከ​ማ​ች​ልህ ዘንድ ትታ​መ​ነ​ዋ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="13">“ሰጎን ክን​ፍ​ዋን በደ​ስታ ታን​ቀ​ሳ​ቅ​ሳ​ለች፥ በፀ​ነ​ሰ​ችም ጊዜ ልት​በላ ትመ​ኛ​ለች፥</verse>
				<verse number="14">ዕን​ቍ​ላ​ልን በመ​ሬት ላይ ትጥ​ላ​ለች፥ በአ​ፈ​ርም ውስጥ ታሞ​ቀ​ዋ​ለች፥</verse>
				<verse number="15">እግር ይሰ​ብ​ረው ዘንድ፥ የም​ድረ በዳም አውሬ ይረ​ግ​ጠው ዘንድ ትረ​ሳ​ለች።</verse>
				<verse number="16">የእ​ር​ስዋ እን​ዳ​ል​ሆኑ በል​ጆ​ችዋ ላይ ትጨ​ክ​ና​ለች፤ ያለ ፍር​ሀ​ትም በከ​ንቱ ትሠ​ራ​ለች፤</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብን ከእ​ር​ስዋ ከል​ክ​ሎ​አ​ልና፥ ማስ​ተ​ዋ​ል​ንም አል​ሰ​ጣ​ት​ምና።</verse>
				<verse number="18">በዘ​መ​ንዋ ወደ ላይ ራስ​ዋን ከፍ ከፍ ታደ​ር​ጋ​ለች፥ በፈ​ረ​ሱና በፈ​ረ​ሰ​ኛው ትሣ​ለ​ቃ​ለች።</verse>
				<verse number="19">“ለፈ​ረስ አንተ ጕል​በ​ቱን ሰጥ​ተ​ኸ​ዋ​ልን? አን​ገ​ቱ​ንስ ጋማ አል​ብ​ሰ​ኸ​ዋ​ልን?</verse>
				<verse number="20">በፍ​ጹም የጦር መሣ​ሪያ አስ​ጊ​ጠ​ኸ​ዋ​ልን? እም​ቢ​ያ​ው​ንስ በብ​ር​ታት የከ​በረ አድ​ር​ገ​ኸ​ዋ​ልን?</verse>
				<verse number="21">በኮ​ቴው በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ይጐ​ደ​ፍ​ራል፥ በጕ​ል​በ​ቱም ወደ ሜዳ ይወ​ጣል።</verse>
				<verse number="22">በሚ​ገ​ና​ኘው ፍላጻ ላይ ይስ​ቃል። ከሰ​ይ​ፍም ፊት አይ​መ​ለ​ስም።</verse>
				<verse number="23">ቀስ​ትና ጦር በእ​ርሱ ላይ ይበ​ረ​ታሉ፥</verse>
				<verse number="24">በቍ​ጣ​ውም መሬ​ትን ያጠ​ፋል፤ የመ​ለ​ከ​ትም ድምፅ እስ​ከ​ሚ​ሰ​ማው አያ​ም​ንም።</verse>
				<verse number="25">የመ​ለ​ከ​ትም ድምፅ ሲሰማ፦ እሰይ ይላል፤ ከሩ​ቅም ሆኖ ሰል​ፍ​ንና የአ​ለ​ቆ​ችን ጩኸት፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱ​ንም ውካታ ያሸ​ታል።</verse>
				<verse number="26">“በውኑ ከጥ​በ​ብህ የተ​ነሣ ጭል​ፊት ያን​ዣ​ብ​ባ​ልን? ወይስ ክን​ፎ​ቹን ወደ ደቡብ ይዘ​ረ​ጋ​ልን?</verse>
				<verse number="27">በአ​ፍህ ትእ​ዛዝ ንስር ከፍ ከፍ ይላ​ልን? ጆፌ አሞ​ራስ ልጆ​ቹን አቅፎ ያድ​ራ​ልን?</verse>
				<verse number="28">በዓ​ለቱ ገደል ላይ ይኖ​ራል፤ በገ​ደሉ ገመ​ገ​ምና በጥጉ ያድ​ራል።</verse>
				<verse number="29">በዚ​ያም ሆኖ የሚ​በ​ላ​ውን ይፈ​ል​ጋል፤ ዐይ​ኖ​ቹም በሩቁ ይመ​ለ​ከ​ታሉ።</verse>
				<verse number="30">ጫጭ​ቶ​ቹም ወደ ደም ይሮ​ጣሉ፥ በድን ወደ አለ​በ​ትም ስፍራ ወዲ​ያ​ውኑ ይደ​ር​ሳሉ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="40">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መለሰ፥ ኢዮ​ብ​ንም እን​ዲህ አለው፦</verse>
				<verse number="2">“በውኑ የሚ​ከ​ራ​ከር ሰው ሁሉን ከሚ​ችል አም​ላክ ጋር ይከ​ራ​ከ​ራ​ልን? ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር የሚ​ዋ​ቀስ እርሱ ይመ​ል​ስ​ለት።”</verse>
				<verse number="3">ኢዮ​ብም መለሰ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም እን​ዲህ አለው፦</verse>
				<verse number="4">“አንተ ስታ​ስ​ተ​ም​ረኝ እኔ የም​መ​ል​ሰው ምን አለኝ? ይህ​ንስ እየ​ሰ​ማሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር እከ​ራ​ከር ዘንድ እኔ ምን​ድን ነኝ? እጄን በአፌ ላይ ከማ​ኖር በቀር የም​መ​ል​ሰው ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="5">አንድ ጊዜ ተና​ገ​ርሁ፥ ሁለ​ተኛ ጊዜም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አል​ና​ገ​ርም።”</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ደ​ገና በደ​መና ውስጥ ሆኖ ለኢ​ዮብ መለ​ሰ​ለት፥ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="7">“እን​ግ​ዲህ እንደ ወንድ ወገ​ብ​ህን ታጠቅ፤ እጠ​ይ​ቅ​ሃ​ለሁ፥ አን​ተም መል​ስ​ልኝ።</verse>
				<verse number="8">ወይም ፍር​ዴን መቃ​ወ​ም​ህን ተው፥ ጽድ​ቅህ እን​ድ​ት​ገ​ለጥ እንጂ እኔ በሌላ መን​ገድ የም​ፈ​ር​ድ​ብህ ይመ​ስ​ል​ሃ​ልን?</verse>
				<verse number="9">እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክንድ ያለ ክንድ አለ​ህን? ወይስ እንደ እርሱ ባለ ድምፅ ታን​ጐ​ደ​ጕ​ዳ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="10">እስኪ ልዕ​ል​ና​ንና ኀይ​ልን ተላ​በስ፤ በክ​ብ​ርና በግ​ር​ማም ተጐ​ና​ጸፍ።</verse>
				<verse number="11">የቍ​ጣ​ህን መላ​እ​ክት ላክ፤ ትዕ​ቢ​ተ​ኛ​ው​ንም ሁሉ አዋ​ር​ደው።</verse>
				<verse number="12">ትዕ​ቢ​ተ​ኛ​ውን ሰው ዝቅ ዝቅ አድ​ር​ገው፤ ዝን​ጉ​ዎ​ች​ንም በአ​ንድ ጊዜ አጥ​ፋ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">በአ​ፈር ውስጥ በአ​ን​ድ​ነት ሰው​ራ​ቸው፤ ፊታ​ቸ​ው​ንም በኀ​ፍ​ረት ሙላ።</verse>
				<verse number="14">በዚ​ያን ጊዜ ቀኝ እጅህ ታድ​ንህ ዘንድ እን​ድ​ት​ችል፥ እኔ ደግሞ እመ​ሰ​ክ​ር​ል​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">“እነሆ፥ በአ​ንተ ዘንድ የዱር አውሬ አለ፤ እንደ በሬ ሣር ይበ​ላል።</verse>
				<verse number="16">እነሆ፥ ብር​ታቱ በወ​ገቡ ውስጥ ነው፤ ኀይ​ሉም በሆዱ እን​ብ​ርት ውስጥ ነው።</verse>
				<verse number="17">ጅራ​ቱን እንደ ጥድ ዛፍ ያወ​ዛ​ው​ዛል፤ የወ​ር​ቹም ጅማት የተ​ጐ​ነ​ጐነ ነው።</verse>
				<verse number="18">የጐ​ድን አጥ​ንቱ እንደ ናስ ነው፤ የጀ​ር​ባው አጥ​ን​ቶ​ችም እንደ ብረት ዘን​ጎች ናቸው።</verse>
				<verse number="19">ይህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፍ​ጥ​ረቱ አውራ ነው። ከተ​ፈ​ጠ​ረም በኋላ መላ​እ​ክት ሣቁ​በት።</verse>
				<verse number="20">ወደ ረዥም ተራራ በወጣ ጊዜም በሜ​ዳው ላሉ እን​ስ​ሳት በጥ​ልቁ ስፍራ ደስ​ታን ያደ​ር​ጋል።</verse>
				<verse number="21">ጥላ ካለው ዛፍ በታች፥ በደ​ን​ገል፥ በቄ​ጠ​ማና በሸ​ን​በቆ ሥር ይተ​ኛል።</verse>
				<verse number="22">ጥላ ያለው ዛፍ በጥ​ላው ይሰ​ው​ረ​ዋል፤ የወ​ንዝ አኻያ ዛፎ​ችም ይከ​ብ​ቡ​ታል።</verse>
				<verse number="23">እነሆ፥ ወንዙ ቢጐ​ርፍ አይ​ደ​ነ​ግ​ጥም፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስም እስከ አፉ ድረስ ቢፈ​ስስ እርሱ ይተ​ማ​መ​ናል።</verse>
				<verse number="24">ዐይኑ እያየ በገ​መድ ይያ​ዛ​ልን? አፍ​ን​ጫ​ውስ ይበ​ሳ​ልን?</verse>
				<verse number="25">“በውኑ ዘን​ዶ​ውን በመ​ቃ​ጥን ታወ​ጣ​ለ​ህን? በአ​ፍ​ን​ጫ​ውስ ገመድ ታስ​ራ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="26">ወይስ ስናጋ በጕ​ንጩ ታደ​ር​ጋ​ለ​ህን? ወይስ በች​ን​ካር ከን​ፈ​ሩን ትበ​ሳ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="27">በውኑ ወደ አንተ እጅግ ይለ​ም​ና​ልን? በጣ​ፈጠ ቃልስ ይና​ገ​ር​ሃ​ልን?</verse>
				<verse number="28">በውኑ ከአ​ንተ ጋር ቃል ኪዳን ይገ​ባ​ልን? ወይስ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባሪያ ይሆን ዘንድ ትወ​ስ​ደ​ዋ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="29">ከዎፍ ጋር እን​ደ​ም​ት​ጫ​ወት ከእ​ርሱ ጋር ትጫ​ወ​ታ​ለ​ህን? ወይስ እንደ ልጆች መጫ​ወቻ ዎፍ ታስ​ረ​ዋ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="30">አሕ​ዛብ ይመ​ገ​ቡ​ታ​ልን? ወይስ የፊ​ንቄ ሰዎች ይካ​ፈ​ሉ​ታ​ልን?</verse>
				<verse number="31">ጀል​ባ​ዎች ሁሉ ቢሰ​በ​ሰቡ የጅ​ራ​ቱን ቍር​በት ሊሸ​ከ​ሙት አይ​ች​ሉም። አጥ​ማ​ጆ​ችም ራሱን በመ​ረብ መያዝ አይ​ች​ሉም።</verse>
				<verse number="32">እጅ​ህን በላዩ ጫን፤ በአፉ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ጦር​ነት አስብ፥ እን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አት​ድ​ገም፥ አላ​የ​ህ​ምን? ስለ እር​ሱስ የተ​ባ​ለ​ውን አላ​ደ​ነ​ቅ​ህ​ምን?</verse>
			</chapter>
			<chapter number="41">
				<verse number="1">አት​ፈ​ራ​ምን? ለእኔ አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ሃ​ልና። የሚ​ቃ​ወ​መ​ኝስ ማን ነው?</verse>
				<verse number="2">የሚ​ከ​ራ​ከ​ረ​ኝና በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ርስ ማን ነው? ከሰ​ማይ በታች ያለ​ውም ሁሉ የእኔ ነው።</verse>
				<verse number="3">ስለ እርሱ ዝም አል​ልም፥ የኀ​ይል ቃልም እንደ እርሱ ያለ​ውን ይቅር ይለ​ዋል።</verse>
				<verse number="4">የፊ​ቱን መጋ​ረጃ ማን ይገ​ል​ጣል? ወደ ደረቱ መጋ​ጠ​ሚያ ውስ​ጥስ ማን ይገ​ባል?</verse>
				<verse number="5">የፊ​ቱ​ንስ ደጆች የሚ​ከ​ፍት ማን ነው? በጥ​ር​ሶቹ ዙሪ​ያም ግርማ አለ።</verse>
				<verse number="6">አን​ጀ​ቶቹ የናስ አራ​ዊት ናቸው፤ የቆ​ዳ​ውም ጽናት እንደ ዓለት ድን​ጋይ ነው።</verse>
				<verse number="7">እርስ በር​ሳ​ቸው የተ​ጣ​በቁ ናቸ​ውና፥ ነፋ​ስም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው መግ​ባት አይ​ች​ልም።</verse>
				<verse number="8">ሰውን ከወ​ን​ድሙ ጋር አንድ ያደ​ር​ጋል፤ እርስ በር​ሳ​ቸው የተ​ገ​ጣ​ጠሙ ናቸው፤ ሊለ​ያ​ዩም አይ​ች​ሉም።</verse>
				<verse number="9">እን​ጥ​ሽ​ታው ብል​ጭ​ታን ያወ​ጣል፥ ዐይ​ኖ​ቹም እንደ አጥ​ቢያ ኮከብ ናቸው።</verse>
				<verse number="10">ከአፉ የሚ​ቃ​ጠል መብ​ራት ይወ​ጣል የእ​ሳ​ትም ፍን​ጣሪ ይረ​ጫል።</verse>
				<verse number="11">የከ​ሰል እሳት እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠ​ል​በት ምድጃ ከአ​ፍ​ን​ጫው ጢስ ይወ​ጣል።</verse>
				<verse number="12">እስ​ት​ን​ፋሱ እንደ ፍም ናት። ነበ​ል​ባ​ልም ከአፉ ይወ​ጣል።</verse>
				<verse number="13">በአ​ን​ገቱ ኀይል ታድ​ራ​ለች፤ ለሚ​ያ​የ​ውም በፊቱ ሞት ይው​ላል።</verse>
				<verse number="14">የአ​ካሉ ሥጋም የተ​ነ​ባ​በረ ነው፤ ጎጂ ነገ​ርን ቢያ​ፈ​ስ​ሱ​በ​ትም አይ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ስም፤</verse>
				<verse number="15">ልቡ እንደ ዋሻ ድን​ጋይ የደ​ነ​ደነ ነው፤ እንደ ወፍጮ ድን​ጋ​ይም የጸና ነው።</verse>
				<verse number="16">በተ​መ​ለ​ሰም ጊዜ አራ​ዊ​ትና እን​ስሳ ይፈ​ራሉ፥ በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀሱ ሁሉ ይሸ​በ​ራሉ።</verse>
				<verse number="17">ሰይ​ፍና ጦር፥ ፍላ​ጻና መው​ጊ​ያም ቢያ​ገ​ኙት ምንም አያ​ደ​ር​ጉ​ትም።</verse>
				<verse number="18">በእ​ርሱ ዘንድ መው​ጊ​ያና የብ​ረት ልብስ እንደ ገለባ ናቸው። ናስም እንደ ነቀዘ እን​ጨት ነው።</verse>
				<verse number="19">የናስ ፍላጻ ሊበ​ሳው አይ​ች​ልም፤ የወ​ን​ጭፍ ድን​ጋ​ዮ​ችም በእ​ርሱ ዘንድ እንደ ገለባ ናቸው።</verse>
				<verse number="20">ድጅኖ ቀሰም ይመ​ስ​ለ​ዋል በታ​ላ​ላቅ ድን​ጋ​ዮች ላይ ይሥ​ቃል።</verse>
				<verse number="21">መኝ​ታው እንደ ስለ​ታም ድን​ጋይ ነው፤ የባ​ሕር ወርቅ ሁሉ በእ​ርሱ ዘንድ እን​ደ​ማ​ይ​ቈ​ጠር ጭቃ ነው።</verse>
				<verse number="22">ቀላ​ይ​ዋን እንደ ብረት ድስት ያፈ​ላ​ታል፤ ባሕ​ሩም ምድረ በዳ ይመ​ስ​ለ​ዋል።</verse>
				<verse number="23">የሲ​ኦ​ልም ጥል​ቀት እንደ ምርኮ ነው። ቀላ​ዩ​ንም እንደ መመ​ላ​ለሻ መን​ገድ ያደ​ር​ጋል።</verse>
				<verse number="24">በተ​ፈ​ጠረ ጊዜ መላ​እ​ክቴ የሣ​ቁ​በት፥ እንደ እርሱ ያለ በም​ድር ላይ ምንም የለም።</verse>
				<verse number="25">ከፍ ያለ​ውን ሁሉ ይመ​ለ​ከ​ታል፤ በውኃ ውስ​ጥም ላሉ ሁሉ ንጉሥ ነው።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="42">
				<verse number="1">ኢዮ​ብም መለሰ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም እን​ዲህ አለው፦</verse>
				<verse number="2">“ሁሉን ታደ​ርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ የሚ​ሳ​ን​ህም እን​ደ​ሌለ ዐወ​ቅሁ።</verse>
				<verse number="3">ምክ​ርን ከአ​ንተ የሚ​ሰ​ውር፥ ቃሉ​ንም ከአ​ንተ የሚ​ሸ​ል​ግና የሚ​ሸ​ሽግ የሚ​መ​ስ​ለው ማን ነው? የማ​ላ​ስ​ተ​ው​ለ​ው​ንና የማ​ላ​ው​ቀ​ው​ንም ታላ​ቅና ድንቅ ነገር የሚ​ነ​ግ​ረኝ ማን ነው?</verse>
				<verse number="4">“ጌታ ሆይ፥ እባ​ክህ፥ ስማኝ፥ እኔም ልና​ገር፤ እጠ​ይ​ቅ​ህ​ማ​ለሁ፥ አን​ተም አስ​ተ​ም​ረኝ።</verse>
				<verse number="5">መስ​ማ​ት​ንስ ስለ አንተ ቀድሞ በጆ​ሮዬ ሰምቼ ነበር፤ አሁን ግን ዐይኔ አየ​ችህ፤</verse>
				<verse number="6">ስለ​ዚህ ራሴን እን​ቃ​ለሁ፤ ሰው​ነ​ቴም ቀለጠ። እኔ አፈ​ርና አመድ እንደ ሆንሁ አው​ቃ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይህን ቃል ለኢ​ዮብ ከተ​ና​ገረ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቴማ​ና​ዊ​ውን ኤል​ፋ​ዝን እን​ዲህ አለው፥ “እንደ ባሪ​ያዬ እንደ ኢዮብ አን​ዲት ቅን ነገ​ርን በፊቴ አል​ተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁ​ምና አን​ተና ሁለቱ ባል​ን​ጀ​ሮ​ችህ በድ​ላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="8">አሁን እን​ግ​ዲህ ሰባት ወይ​ፈ​ኖ​ች​ንና ሰባት አውራ በጎ​ችን ይዛ​ችሁ ወደ ባሪ​ያዬ ወደ ኢዮብ ዘንድ ሂዱ፥ እር​ሱም የሚ​ቃ​ጠ​ልን መሥ​ዋ​ዕት ስለ ራሳ​ችሁ ያሳ​ር​ግ​ላ​ችሁ። ባሪ​ያ​ዬም ኢዮብ ስለ እና​ንተ ይጸ​ልይ፥ እኔም ፊቱን እቀ​በ​ላ​ለሁ። ስለ እርሱ ባይ​ሆን ባጠ​ፋ​ኋ​ችሁ ነበር። በባ​ሪ​ያዬ በኢ​ዮብ ላይ ቅን ነገ​ርን በፊቴ አል​ተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁ​ምና።”</verse>
				<verse number="9">ቴማ​ና​ዊ​ውም ኤል​ፋዝ፥ አው​ኬ​ና​ዊው በል​ዳ​ዶ​ስና፥ አሜ​ና​ዊው ሶፋር ሄደው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው አደ​ረጉ፤ ስለ ኢዮ​ብም ሲል ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይቅር አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢዮ​ብን አዳ​ነው። ኢዮ​ብም ስለ ወዳ​ጆቹ ጸለየ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ተወ​ላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀድሞ በነ​በ​ረው ገን​ዘቡ ሁሉ ፋንታ ሁለት እጥፍ ከዚ​ያም በላይ አድ​ርጎ ለኢ​ዮብ ሰጠው።</verse>
				<verse number="11">ወን​ድ​ሞ​ቹና እኅ​ቶቹ ቀድ​ሞም ያው​ቁት የነ​በ​ሩት ሁሉ የሆ​ነ​ውን ሁሉ በሰሙ ጊዜ ወደ እርሱ መጡ፥ በቤ​ቱም ከእ​ርሱ ጋር እን​ጀራ በሉ፥ ጠጡም፤ አጽ​ና​ኑ​ትም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባመ​ጣ​በት ክፉ ነገር ሁሉ አደ​ነቁ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም ጥማድ በሬ፥ አራት ድራ​ህማ የሚ​መ​ዝን ወር​ቅና ብር ሰጡት።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፊ​ተ​ኛው ይልቅ የኋ​ለ​ኛ​ውን ለኢ​ዮብ ባረከ፤ መን​ጋ​ዎ​ቹም ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፥ ስድ​ስት ሺህም ግመ​ሎች፥ አንድ ሺህም ጥማድ በሬ​ዎች፥ አንድ ሺህም እን​ስት አህ​ዮች ነበሩ።</verse>
				<verse number="13">ደግ​ሞም ሰባት ወን​ዶ​ችና ሦስት ሴቶች ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት።</verse>
				<verse number="14">የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ይ​ቱን ስም ዕለት፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ይ​ቱ​ንም ስም ቃስያ፥ የሦ​ስ​ተ​ኛ​ይ​ቱ​ንም ስም አማ​ል​ት​ያ​ስ​ቂ​ራስ ብሎ ሰየ​ማ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">ከሰ​ማይ በታች እንደ ኢዮብ ሴቶች ልጆች ያሉ የተ​ዋቡ ሴቶች በሀ​ገሩ ሁሉ አል​ተ​ገ​ኙም፤ አባ​ታ​ቸ​ውም ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር ርስት ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">ኢዮ​ብም ከደ​ዌው ከዳነ በኋላ መቶ ሰባ ዓመት ኖረ፥ ኢዮ​ብም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ሁለት መቶ አርባ ነው። ልጆ​ቹ​ንና የልጅ ልጆ​ቹ​ንም እስከ አራት ትው​ልድ ድረስ አየ።</verse>
				<verse number="17">ኢዮ​ብም ሸም​ግሎ ዕድ​ሜም ጠግቦ ሞተ።</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ያ​ነ​ሣ​ቸው ሰዎች ጋር ዳግ​መኛ እን​ደ​ሚ​ነሣ የተ​ጻፈ ነው።</verse>
				<verse number="19">ይህ ሰው በሶ​ር​ያው መጽ​ሐፍ እን​ደ​ዚህ ተገ​ል​ጦ​አል። የኖ​ረ​በ​ትም ሀገሩ በኤ​ዶ​ም​ያ​ስና በዐ​ረብ አው​ራጃ ያለ አው​ስ​ጢድ ነው።</verse>
				<verse number="20">ስሙም ቀድሞ ኢዮ​ባብ ነበረ፥ ዐረ​ባ​ዊት ሴት​ንም አገባ። ስሙ ሄኖን የሚ​ባል ልጅ​ንም ወለ​ደ​ች​ለት። እር​ሱም የኤ​ሳው የልጅ ልጅ የዛራ ልጅ ነው። እና​ቱም ባሱ​ራስ ትባል ነበር።</verse>
				<verse number="21">እር​ሱም ከአ​ብ​ር​ሃም አም​ስ​ተኛ ነው። እር​ሱም በገ​ዛት ሀገር በኤ​ዶ​ም​ያስ የነ​ገሡ ነገ​ሥ​ታት እነ​ዚህ ነበሩ።</verse>
				<verse number="22">አስ​ቀ​ድሞ የነ​ገሠ የቢ​ዖር ልጅ ባላቅ ነው። የከ​ተ​ማ​ዋም ስም ዲናባ ነበር።</verse>
				<verse number="23">ከባ​ላ​ቅም በኋላ ስሙ ኢዮብ ይባል የነ​በ​ረው ኢዮ​ባብ ነገሠ። ከእ​ር​ሱም በኋላ በቴ​ማን ሀገር የነ​ገሠ አሶም ነበር።</verse>
				<verse number="24">ከእ​ር​ሱም በኋላ በሞ​ዓብ ምድረ በዳ የም​ድ​ያ​ምን ሰዎች የገ​ደ​ላ​ቸው የበ​ራድ ልጅ አዳድ ነበር፥ የከ​ተ​ማ​ውም ስም ጌቴም ነበር።</verse>
				<verse number="25">ወደ እርሱ የመጡ ወዳ​ጆ​ቹም አንዱ ከዔ​ሳው ልጆች የተ​ወ​ለደ በቴ​ማ​ኖን የነ​ገ​ሠው ኤል​ፋዝ፥ በአ​ው​ኪ​ኒ​ዮን የተ​ሾ​መው በል​ዳ​ዶ​ስና የአ​ሜ​ኔ​ዎን ንጉሥ ሶፋር ነበሩ።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="19">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">ምስ​ጉን ነው፥ በዝ​ን​ጉ​ዎች ምክር ያል​ሄደ፥ በኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችም መን​ገድ ያል​ቆመ፥ በዋ​ዘ​ኞ​ችም ወን​በር ያል​ተ​ቀ​መጠ ሰው።</verse>
				<verse number="2">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ብቻ ፈቃዱ የሆነ፥ ሕጉ​ንም በቀ​ንና በሌ​ሊት የሚ​ያ​ስብ፥</verse>
				<verse number="3">እር​ሱም በውኃ ፈሳ​ሾች ዳር እንደ ተተ​ከ​ለች፥ ፍሬ​ዋን በየ​ጊ​ዜዋ እን​ደ​ም​ት​ሰጥ፥ ቅጠ​ል​ዋም እን​ደ​ማ​ይ​ረ​ግፍ ዛፍ ይሆ​ናል፤ የሚ​ሠ​ራ​ውም ሁሉ ይከ​ና​ወ​ን​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="4">ኃጥ​ኣን እን​ዲህ አይ​ደ​ሉም፥ እን​ዲህ አይ​ደ​ሉም። ነገር ግን ነፋስ ከገጸ ምድር ጠርጎ እን​ደ​ሚ​ወ​ስ​ደው ትቢያ ናቸው።</verse>
				<verse number="5">ስለ​ዚህ ዝን​ጉ​ዎች በፍ​ርድ፥ ኃጥ​ኣ​ንም በጻ​ድ​ቃን ምክር አይ​ቆ​ሙም።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጻ​ድ​ቃ​ንን መን​ገድ ያው​ቃ​ልና፥ የኃ​ጥ​ኣን መን​ገድ ግን ትጠ​ፋ​ለች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">አሕ​ዛብ ለምን ዶለቱ? ወገ​ኖ​ችስ ለምን ከንቱ ይና​ገ​ራሉ?</verse>
				<verse number="2">የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ተነሡ፥ አለ​ቆ​ችም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በመ​ሲሑ ላይ እን​ዲህ ሲሉ በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="3">“ማሰ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ከእኛ እን​በ​ጥስ፥ ቀን​በ​ራ​ቸ​ው​ንም ከእኛ ላይ እን​ጣል።”</verse>
				<verse number="4">በሰ​ማይ የሚ​ኖር እርሱ ይሥ​ቅ​ባ​ቸ​ዋል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሣ​ለ​ቅ​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="5">በዚ​ያን ጊዜ በቍ​ጣው ይና​ገ​ራ​ቸ​ዋል፥ በመ​ዓ​ቱም ያው​ካ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">እኔ ግን በእ​ነ​ርሱ ላይ ንጉሥ ሆኜ ተሾ​ምሁ በተ​ቀ​ደሰ ተራ​ራው በጽ​ዮን ላይ።</verse>
				<verse number="7">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ እና​ገር ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አለኝ፥ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔም ዛሬ ወለ​ድ​ሁህ።</verse>
				<verse number="8">ለም​ነኝ፥ አሕ​ዛ​ብን ለር​ስ​ትህ የም​ድ​ር​ንም ዳርቻ፥ ለግ​ዛ​ትህ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">በብ​ረት በትር ትጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃም ትቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።”</verse>
				<verse number="10">አሁ​ንም እና​ንት ነገ​ሥ​ታት፥ ልብ አድ​ርጉ፤ እና​ንት የም​ድር ፈራ​ጆ​ችም፥ ተገ​ሠጹ።</verse>
				<verse number="11">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፍ​ር​ሀት ተገዙ፥ በረ​ዓ​ድም ደስ ይበ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="12">ጥበ​ብን አጽ​ኑ​አት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ይ​ቈጣ፥ እና​ን​ተም ከጽ​ድቅ መን​ገድ እን​ዳ​ት​ጠፉ፥ ቍጣው ፈጥና በነ​ደ​ደች ጊዜ፥ በእ​ርሱ የታ​መኑ ሁሉ ብፁ​ዓን ናቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">አቤቱ፥ የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ምንኛ በዙ! በእኔ ላይ የሚ​ቆ​ሙት ብዙ ናቸው።</verse>
				<verse number="2">ብዙ ሰዎች ነፍ​ሴን አል​ዋት፦ “አም​ላ​ክሽ አያ​ድ​ን​ሽም።”</verse>
				<verse number="3">አንተ ግን አቤቱ፥ መጠ​ጊ​ያዬ ነህ፤ ክብ​ሬና ራሴን ከፍ ከፍ የም​ታ​ደ​ር​ገው አንተ ነህ።</verse>
				<verse number="4">በቃሌ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኽሁ፤ ከተ​ቀ​ደሰ ተራ​ራ​ውም ሰማኝ።</verse>
				<verse number="5">እኔ ተኛሁ፤ አን​ቀ​ላ​ፋ​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​ሥ​ቶ​ኛ​ልና ተነ​ሣሁ።</verse>
				<verse number="6">ከሚ​ከ​ብ​ቡ​ኝና በእኔ ላይ ከሚ​ነሡ ከአ​እ​ላፍ አሕ​ዛብ አል​ፈ​ራም።</verse>
				<verse number="7">ተነሥ፥ አቤቱ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ አድ​ነኝ፤ አንተ በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ሉ​ኝን ሁሉ መት​ተ​ሃ​ልና፥ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም ጥርስ ሰብ​ረ​ሃ​ልና።</verse>
				<verse number="8">ማዳን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥ በረ​ከ​ት​ህም በሕ​ዝ​ብህ ላይ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በጠ​ራ​ሁት ጊዜ ጽድ​ቄን ሰማኝ፥ ከጭ​ን​ቀ​ቴም አሰ​ፋ​ልኝ፤ ይቅር አለኝ፥ ጸሎ​ቴ​ንም ሰማኝ።</verse>
				<verse number="2">እና​ንት የሰው ልጆች፥ እስከ መቼ ድረስ ልባ​ች​ሁን ታከ​ብ​ዳ​ላ​ችሁ? ከንቱ ነገ​ርን ለምን ትወ​ድ​ዳ​ላ​ችሁ? ሐሰ​ት​ንም ለምን ትሻ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጻ​ድቁ እንደ ተገ​ለጠ ዕወቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ እርሱ በጮ​ኽሁ ጊዜ ይሰ​ማ​ኛል።</verse>
				<verse number="4">ተቈጡ፥ ነገር ግን አት​በ​ድሉ፤ በመ​ኝ​ታ​ችሁ ሳላ​ችሁ በል​ባ​ችሁ የም​ታ​ስ​ቡት ይታ​ወ​ቃ​ችሁ።</verse>
				<verse number="5">የጽ​ድ​ቅን መሥ​ዋ​ዕት ሠዉ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታመኑ።</verse>
				<verse number="6">“በጎ​ውን ማን ያሳ​የ​ናል?” የሚሉ ብዙ​ዎች ናቸው። አቤቱ፥ የፊ​ትህ ብር​ሃን በላ​ያ​ችን ታወቀ።</verse>
				<verse number="7">በል​ባ​ችን ደስ​ታን ጨመ​ርህ፤ ከስ​ንዴ ፍሬና ከወ​ይን፥ ከዘ​ይ​ትም ይልቅ በዛ።</verse>
				<verse number="8">በእ​ርሱ በሰ​ላም እተ​ኛ​ለሁ፥ አን​ቀ​ላ​ፋ​ለ​ሁም፤ አቤቱ፥አንተ ብቻ​ህን በተ​ስፋ አሳ​ድ​ረ​ኸ​ኛ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">አቤቱ፥ ቃሌን አድ​ምጥ፥ ጩኸ​ቴ​ንም አስ​ተ​ውል፤</verse>
				<verse number="2">የል​መ​ና​ዬን ቃል አድ​ምጥ፥ ንጉ​ሤና አም​ላኬ ሆይ፥ አቤቱ፥ ወደ አንተ እጸ​ል​ያ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="3">በማ​ለዳ ቃሌን ስማኝ፥ በማ​ለዳ በፊ​ትህ እቆ​ማ​ለሁ፥ እገ​ለ​ጥ​ል​ሃ​ለ​ሁም።</verse>
				<verse number="4">አንተ በደ​ልን የሚ​ወ​ድድ አም​ላክ አይ​ደ​ለ​ህ​ምና፤ ክፉ​ዎች ከአ​ንተ ጋር አያ​ድ​ሩም።</verse>
				<verse number="5">ዐመ​ፀ​ኞ​ችም በዐ​ይ​ኖ​ችህ ፊት አይ​ኖ​ሩም፤ ዐመፅ አድ​ራ​ጊ​ዎ​ችን ሁሉ ጠላህ።</verse>
				<verse number="6">ሐሰ​ትን የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን ሁሉ ትጥ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ደም አፍ​ሳ​ሹ​ንና ሸን​ጋ​ዩን ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​የ​ፋል።</verse>
				<verse number="7">እኔ ግን በም​ሕ​ረ​ትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገ​ባ​ለሁ፤ አን​ተን በመ​ፍ​ራት በቤተ መቅ​ደ​ስህ እሰ​ግ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">አቤቱ፥ በጽ​ድ​ቅህ ምራኝ፤ ስለ ጠላ​ቶቼ መን​ገ​ዴን በፊ​ትህ አቅና።</verse>
				<verse number="9">በአ​ፋ​ቸው እው​ነት የለ​ምና፥ ልባ​ቸ​ውም ከንቱ ነው፥ ጕሮ​ሮ​ኣ​ቸው እንደ ተከ​ፈተ መቃ​ብር ነው፤ በም​ላ​ሳ​ቸው ይሸ​ነ​ግ​ላሉ።</verse>
				<verse number="10">አቤቱ፥ ፍረ​ድ​ባ​ቸው፥ በነ​ገረ ሠሪ​ነ​ታ​ቸ​ውም ይው​ደቁ፤ እንደ ሐሰ​ታ​ቸ​ውም ብዛት አሳ​ድ​ዳ​ቸው፥ አቤቱ፥ እነ​ርሱ አሳ​ዝ​ነ​ው​ሃ​ልና።</verse>
				<verse number="11">በአ​ንተ የሚ​ታ​መ​ኑት ሁሉ ግን ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ በእ​ነ​ር​ሱም ታድ​ራ​ለህ። ስም​ህ​ንም የሚ​ወ​ድዱ ሁሉ በአ​ንተ ይመ​ካሉ።</verse>
				<verse number="12">አንተ ጻድ​ቁን ትባ​ር​ከ​ዋ​ለ​ህና፤ አቤቱ፥ እንደ አላ​ባሽ ጋሻ ከለ​ል​ኸን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">አቤቱ፥ በቍ​ጣህ አት​ቅ​ሠ​ፈኝ፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ት​ህም አት​ገ​ሥ​ጸኝ።</verse>
				<verse number="2">ድውይ ነኝና አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፤ አጥ​ን​ቶቼ ታው​ከ​ዋ​ልና ፈው​ሰኝ።</verse>
				<verse number="3">ነፍ​ሴም እጅግ ታወ​ከች፤ አን​ተም አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?</verse>
				<verse number="4">አቤቱ፥ ተመ​ለስ ነፍ​ሴ​ንም አድ​ናት፥ ስለ ቸር​ነ​ት​ህም አድ​ነኝ።</verse>
				<verse number="5">በሞት የሚ​ያ​ስ​ብህ የለ​ምና፥ በሲ​ኦ​ልም የሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ንህ ማን ነው?</verse>
				<verse number="6">በጭ​ን​ቀቴ ደክ​ሜ​አ​ለሁ፤ ሌሊ​ቱን ሁሉ አል​ጋ​ዬን አጥ​ባ​ለሁ፥ በዕ​ን​ባ​ዬም መኝ​ታ​ዬን አር​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">ዐይኔ ከቍጣ የተ​ነሣ ታወ​ከች፤ ከጠ​ላ​ቶቼ ሁሉ የተ​ነሣ አረ​ጀሁ።</verse>
				<verse number="8">ዐመ​ፃን የም​ታ​ደ​ርጉ ሁሉ፥ ከእኔ ራቁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የል​ቅ​ሶ​ዬን ቃል ሰም​ቶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልመ​ና​ዬን ሰማኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸሎ​ቴን ተቀ​በለ።</verse>
				<verse number="10">ጠላ​ቶቼ ሁሉ ይፈሩ፥ ይጐ​ስ​ቁ​ሉም፤ ወደ ኋላ​ቸው ይመ​ለሱ፥ በፍ​ጥ​ነ​ትም እጅግ ይፈሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ በአ​ንተ ታመ​ንሁ፥ አት​ጣ​ለ​ኝም፤ ከሚ​ከ​ብ​ቡኝ ሁሉ አድ​ነ​ኝና አው​ጣኝ፥</verse>
				<verse number="2">ነፍ​ሴን እንደ አን​በሳ እን​ዳ​ይ​ነ​ጥ​ቋት፥ የሚ​ያ​ድ​ንና የሚ​ታ​ደግ ሳይ​ኖር።</verse>
				<verse number="3">አቤቱ አም​ላኬ፥ እን​ዲ​ህስ ካደ​ረ​ግሁ፥ ዐመ​ፃም በእጄ ቢኖር፥</verse>
				<verse number="4">ክፉ ላደ​ረ​ጉ​ብ​ኝም ክፉን መል​ሼ​ላ​ቸው ብሆን፥ ጠላ​ቶቼ ዕራ​ቁ​ቴን ይጣ​ሉኝ።</verse>
				<verse number="5">ጠላት ነፍ​ሴን ያሳ​ድ​ዳት፤ ያግ​ኛ​ትም፥ ሕይ​ወ​ቴን በም​ድር ላይ ይር​ገ​ጣት፤ ክብ​ሬ​ንም በት​ቢያ ላይ ያዋ​ር​ደው።</verse>
				<verse number="6">አቤቱ፥ በመ​ዓ​ትህ ተነሥ፤ በጠ​ላ​ቶቼ ላይ ተነ​ሣ​ባ​ቸው፤ አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ ባዘ​ዝ​ኸው ሥር​ዐት ተነሥ።</verse>
				<verse number="7">የአ​ሕ​ዛ​ብም ጉባኤ ይከ​ብ​ብ​ሃል፤ ስለ​ዚ​ህም ወደ አር​ያም ተመ​ለስ።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝብ ላይ ይፈ​ር​ዳል፤ አቤቱ አም​ላኬ፥ እንደ ጽድ​ቅህ ፍረ​ድ​ልኝ፤ እንደ የዋ​ህ​ነ​ቴም ይሁ​ን​ልኝ።</verse>
				<verse number="9">የኃ​ጥ​ኣን ክፋት ያል​ቃል፥ ጻድ​ቃ​ንን ግን ታቃ​ና​ቸ​ዋ​ለህ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡ​ና​ንና ኵላ​ሊ​ትን ይመ​ረ​ም​ራል።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ው​ነት ይረ​ዳ​ኛል ልበ ቅኖ​ችን የሚ​ያ​ድ​ና​ቸው እርሱ ነው።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ው​ነት ዳኛ ነው፤ ኀይ​ለ​ኛም ታጋ​ሽም ነው፤ ሁል​ጊ​ዜም ጥፋ​ትን አያ​መ​ጣም።</verse>
				<verse number="12">ባት​መ​ለሱ ግን ሰይ​ፉን ይመ​ዝ​ዛል፥ ቀስ​ቱን ገተረ አዘ​ጋ​ጀም፤</verse>
				<verse number="13">የሚ​ገ​ድል መር​ዝ​ንም አዘ​ጋ​ጀ​በት፤ ፍላ​ጻ​ዎ​ቹ​ንም የሚ​ቃ​ጠሉ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="14">እነሆ፥ ዐመ​ፀኛ በዐ​መፁ ተጨ​ነቀ፤ ጭን​ቅን ፀነሰ፤ ኀጢ​አ​ት​ንም ወለደ።</verse>
				<verse number="15">ጕድ​ጓ​ድ​ንም ማሰ፥ ቈፈ​ረም። ባደ​ረ​ገ​ውም ጕድ​ጓድ ይወ​ድ​ቃል።</verse>
				<verse number="16">ጉዳቱ በራሱ ይመ​ለ​ሳል፥ ዐመ​ፃ​ውም በአ​ናቱ ላይ ትወ​ር​ዳ​ለች።</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ ጽድቁ መጠን አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥ ለል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም እዘ​ም​ራ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">አቤቱ ጌታ​ችን፥ ስምህ በም​ድር ሁሉ እጅግ ተመ​ሰ​ገነ፥ ምስ​ጋ​ናህ በሰ​ማ​ዮች ላይ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="2">ከሕ​ፃ​ና​ትና ከሚ​ጠቡ ልጆች አፍ ምስ​ጋ​ናን አዘ​ጋ​ጀህ፥ ስለ ጠላት፥ ጠላ​ት​ንና ግፈ​ኛን ታጠ​ፋው ዘንድ።</verse>
				<verse number="3">የጣ​ቶ​ች​ህን ሥራ ሰማ​ዮ​ችን፥ አንተ የሠ​ራ​ሃ​ቸ​ውን፥ ጨረ​ቃ​ንና ከዋ​ክ​ብ​ትን እና​ያ​ለ​ንና።</verse>
				<verse number="4">ታስ​በው ዘንድ ሰው ምን​ድን ነው? ትጐ​በ​ኘ​ውም ዘንድ የሰው ልጅ ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="5">ከመ​ላ​እ​ክት ጥቂት አሳ​ነ​ስ​ኸው፤ በክ​ብ​ርና በም​ስ​ጋና ዘውድ ከለ​ል​ኸው።</verse>
				<verse number="6">በእ​ጆ​ች​ህም ሥራ ሁሉ ላይ ሾም​ኸው፤ ሁሉን ከእ​ግ​ሮቹ በታች አስ​ገ​ዛ​ህ​ለት፥</verse>
				<verse number="7">በጎ​ች​ንም በሬ​ዎ​ች​ንም ሁሉ፥ ደግ​ሞም የም​ድረ በዳ​ውን እን​ስ​ሶች፥</verse>
				<verse number="8">የሰ​ማ​ይ​ንም ወፎች፥ የባ​ሕ​ር​ንም ዓሦች፥ በባ​ሕር መን​ገድ የሚ​ሄ​ደ​ው​ንም ሁሉ።</verse>
				<verse number="9">አቤቱ፥ ጌታ​ችን፥ ስምህ በም​ድር ሁሉ እጅግ ተመ​ሰ​ገነ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">አቤቱ፥ በፍ​ጹም ልቤ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥ ታም​ራ​ት​ህ​ንም ሁሉ እና​ገ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">በአ​ንተ ደስ ይለ​ኛል፥ ሐሤ​ት​ንም አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ልዑል ሆይ፥ ለስ​ምህ እዘ​ም​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">ጠላ​ቶቼ ወደ ኋላ​ቸው በተ​መ​ለሱ ጊዜ፥ ይታ​መሙ፥ ከፊ​ት​ህም ይጥፉ።</verse>
				<verse number="4">ፍር​ዴ​ንና በቀ​ሌን አድ​ር​ገ​ህ​ል​ኛ​ልና፤ የጽ​ድቅ ፈራጅ ሆይ፥ በዙ​ፋ​ንህ ላይ ተቀ​መ​ጥህ።</verse>
				<verse number="5">አሕ​ዛ​ብን ገሠ​ጽህ፥ ዝን​ጉ​ዎ​ችም ጠፉ፥ ስማ​ቸ​ው​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ደመ​ሰ​ስህ።</verse>
				<verse number="6">ጠላ​ቶች በጦር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጠፉ፥ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም አፈ​ረ​ስህ፥ ዝክ​ራ​ቸ​ው​ንም በአ​ን​ድ​ነት ታጠ​ፋ​ለህ።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል፥ ዙፋ​ኑ​ንም ለመ​ፍ​ረድ አዘ​ጋጀ፤</verse>
				<verse number="8">እር​ሱም ዓለ​ምን በጽ​ድቅ ይዳ​ኛ​ታል። አሕ​ዛ​ብ​ንም በቅ​ን​ነት ይዳ​ኛ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለድ​ሆች መጠ​ጊያ ሆና​ቸው፥ እር​ሱም በመ​ከ​ራ​ቸው ጊዜ ረዳ​ታ​ቸው ነው።</verse>
				<verse number="10">ስም​ህን የሚ​ወዱ ሁሉ በአ​ንተ ይታ​መ​ናሉ፥ አቤቱ፥ የሚ​ሹ​ህን አት​ተ​ዋ​ቸ​ው​ምና።</verse>
				<verse number="11">በጽ​ዮን ለሚ​ኖር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ፥ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ሥራ​ውን ንገሩ፤</verse>
				<verse number="12">ደማ​ቸ​ውን የሚ​መ​ራ​መር እርሱ አስ​ቦ​አ​ልና፥ የድ​ሆ​ች​ንም ጩኸት አል​ረ​ሳ​ምና።</verse>
				<verse number="13">አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፥ ጠላ​ቶቼም የሚ​ያ​መ​ጡ​ብ​ኝን መከራ እይ፥ ከሞት ደጆች ከፍ ከፍ የሚ​ያ​ደ​ር​ገኝ፤</verse>
				<verse number="14">ምስ​ጋ​ና​ውን ሁሉ እና​ገር ዘንድ፤ በጽ​ዮን ልጅ በደ​ጆ​ችዋ፥ በማ​ዳ​ንህ ደስ ይለ​ናል።</verse>
				<verse number="15">አሕ​ዛብ በሠ​ሩት በደ​ላ​ቸው ጠፉ፥ በዚ​ያ​ችም በሸ​ሸ​ጓት ወጥ​መድ እግ​ራ​ቸው ተጠ​መደ።</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍር​ድን ማድ​ረግ ያው​ቃል፤ ኀጢ​አ​ተ​ኛው በእ​ጆቹ ሥራ ተጠ​መደ።</verse>
				<verse number="17">ኀጢ​አ​ተ​ኞች ወደ ሲኦል ይመ​ለሱ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ረሱ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ።</verse>
				<verse number="18">ድሃ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ረሳ አይ​ደ​ለ​ምና፥ ችግ​ረ​ኞ​ችም ተስ​ፋ​ቸ​ውን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አያ​ጡም።</verse>
				<verse number="19">አቤቱ፥ ተነሥ፥ ሰውም አይ​በ​ርታ፥ አሕ​ዛ​ብም በፊ​ትህ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">አቤቱ፥ የሕግ መም​ህ​ርን በላ​ያ​ቸው ላይ ሹም፤ አሕ​ዛ​ብም ሰዎች እንደ ሆኑ ይወቁ።</verse>
				<verse number="21">አቤቱ፥ ለምን ርቀህ ቆምህ? በመ​ከ​ራም ጊዜ ለምን ቸል ትላ​ለህ?</verse>
				<verse number="22">በኀ​ጢ​አ​ተኛ ትዕ​ቢት ድሃ ይና​ደ​ዳል፤ ባሰ​ቡት ተን​ኮ​ላ​ቸው ይጠ​መ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="23">ኀጢ​አ​ተኛ በነ​ፍሱ ፈቃድ ይወ​ደ​ሳል፥ ዐመ​ፀ​ኛም ይባ​ረ​ካል።</verse>
				<verse number="24">ኀጢ​አ​ተኛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አበ​ሳ​ጨው፥ እንደ ቍጣ​ውም ብዛት አይ​መ​ራ​መ​ረ​ውም፤ በእ​ርሱ ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የለም።</verse>
				<verse number="25">መን​ገዱ ሁሉ የረ​ከሰ ነው፥ ፍር​ድ​ህም በፊቱ የፈ​ረሰ ነው፥ ጠላ​ቶ​ቹ​ንም ሁሉ ይገ​ዛ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="26">በልቡ ይላል፥ “ለልጅ ልጅ አል​ታ​ወ​ክም ክፉም አያ​ገ​ኘ​ኝም።”</verse>
				<verse number="27">አፉ መር​ገ​ም​ንና ሽን​ገ​ላን የተ​መላ ነው፤ ከም​ላሱ በታች ድካ​ምና መከራ ነው።</verse>
				<verse number="28">ከባ​ለ​ጸ​ጎች ጋር ይሸ​ም​ቃል፥ ያድ​ድ​ና​ልም ንጹ​ሑን በስ​ውር ይገ​ድል ዘንድ፥ ዐይ​ኖ​ቹም ወደ ድሃው ይመ​ለ​ከ​ታሉ።</verse>
				<verse number="29">እንደ አን​በሳ በጕ​ድ​ጓድ በስ​ውር ይሸ​ም​ቃል፤ ድሃ​ውን ለመ​ን​ጠቅ ያደ​ባል፤ ድሃ​ውን ይነ​ጥ​ቀ​ዋል፥ ይስ​በ​ዋ​ልም።</verse>
				<verse number="30">በወ​ጥ​መ​ዱም ያዋ​ር​ደ​ዋል፥ ይጐ​ብ​ጣል፥ ድሃ​ው​ንም በገ​ዛው ጊዜ ይወ​ድ​ቃል።</verse>
				<verse number="31">በል​ቡም ይላል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረስ​ቶ​ኛል፤ ፈጽ​ሞም እን​ዳ​ያይ ፊቱን መለሰ።”</verse>
				<verse number="32">አቤቱ፥ አም​ላክ ሆይ፥ ተነሥ፥ እጅ​ህም ከፍ ከፍ ትበል፤ ድሆ​ች​ንም አት​ርሳ።</verse>
				<verse number="33">ኀጢ​አ​ተኛ ስለ ምን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አስ​ቈ​ጣው? በልቡ፥ “አይ​መ​ራ​መ​ረ​ኝም” ይላ​ልና።</verse>
				<verse number="34">አንተ ድካ​ም​ንና ቍጣን እን​ድ​ት​መ​ለ​ከት ታያ​ለ​ህን? በእ​ጅህ አሳ​ል​ፈህ እን​ድ​ት​ሰ​ጠው፥ እን​ግ​ዲህ ድሃ በአ​ንተ ላይ ተጣ​ለን? ለድሃ አደ​ግም ረዳቱ አንተ ነህ?</verse>
				<verse number="35">የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛ​ንና የክ​ፉን ክንድ ስበር፥ ስለ እር​ሱም ኀጢ​አቱ ትመ​ረ​መ​ራ​ለች፥ አት​ገ​ኝ​ምም።</verse>
				<verse number="36">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይነ​ግ​ሣል፤ አሕ​ዛብ ከም​ድር ይጠ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="37">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የድ​ሆ​ችን ምኞት ሰማ፥ ጆሮ​ውም የል​ባ​ቸ​ውን ዐሳብ አደ​መ​ጠች፥</verse>
				<verse number="38">ፍርዱ ለድሃ አደ​ግና ለች​ግ​ረኛ ይደ​ረግ ዘንድ፥ ሰዎች በም​ድር ላይ አፋ​ቸ​ውን ከፍ ከፍ ማድ​ረ​ግን እን​ዳ​ይ​ደ​ግሙ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመ​ንሁ፤ ነፍ​ሴን፥ እንደ ወፍ ወደ ተራ​ሮች ተቅ​በ​ዝ​በዢ እን​ዴት ትሉ​አ​ታ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="2">ኀጢ​አ​ተ​ኞች እነሆ፥ ቀስ​ታ​ቸ​ውን ገት​ረ​ዋ​ልና፥ ፍላ​ጻ​ቸ​ው​ንም በአ​ው​ታር አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ዋ​ልና፥ ልበ ቅኖ​ቹን በስ​ውር ይነ​ድፉ ዘንድ።</verse>
				<verse number="3">አንተ የሠ​ራ​ኸ​ውን እነሆ፥ እነ​ርሱ አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና፤ ጻድቅ ግን ምን አደ​ረገ?</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቤተ መቅ​ደሱ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋኑ በሰ​ማይ ነው፤ ዐይ​ኖ​ቹም ወደ ድሃ ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤ ቅን​ድ​ቦ​ቹም የሰው ልጆ​ችን ይመ​ረ​ም​ራሉ።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድ​ቁ​ንና ኃጥ​ኡን ይመ​ረ​ም​ራል፤ ዐመ​ፃን የወ​ደ​ዳት ግን ነፍ​ሱን ጠል​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="6">ወጥ​መድ በኃ​ጥ​ኣን ላይ ይዘ​ን​ባል፤ እሳ​ትና ዲን፥ ዐውሎ ነፋ​ስም የጽ​ዋ​ቸው እድል ፋንታ ነው።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድቅ ነውና፥ ጽድ​ቅ​ንም ይወ​ድ​ዳል፤ ቅን​ነት ግን ፊቱን ታየ​ዋ​ለች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">አቤቱ፥ አድ​ነኝ፥ ደግ ሰው አል​ቆ​አ​ልና፥ ከሰው ልጆ​ችም መተ​ማ​መን ጐድ​ሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="2">እርስ በር​ሳ​ቸው ከንቱ ነገ​ርን ይና​ገ​ራሉ፤ በሽ​ን​ገላ ከን​ፈር ሁለት ልብ ሆነው ይና​ገ​ራሉ።</verse>
				<verse number="3">የሽ​ን​ገ​ላን ከን​ፈ​ሮች ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፥ ታላቅ ነገ​ርን የም​ት​ና​ገ​ረ​ው​ንም ምላስ፤</verse>
				<verse number="4">“ምላ​ሳ​ች​ንን እና​በ​ረ​ታ​ለን፤ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ችን የእኛ ናቸው፥ ጌታ​ችን ማን ነው?” የሚ​ሉ​ትን።</verse>
				<verse number="5">“ስለ ድሆች መከራ፥ ስለ እስ​ረ​ኞ​ችም ጩኸት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይላል፥ አሁን እነ​ሣ​ለሁ፤ መድ​ኀ​ኒ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ፥ በእ​ር​ሱም እገ​ል​ጣ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="6">በም​ድር ላይ እንደ ተፈ​ተነ፥ ሰባት ጊዜም እንደ ተጣራ ብር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ንጹሕ ቃል ነው።</verse>
				<verse number="7">አቤቱ፥ አንተ ጠብ​ቀን፥ ከዚ​ህ​ችም ትው​ልድ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታደ​ገን።</verse>
				<verse number="8">ዝን​ጉ​ዎች በዙ​ሪ​ያው ይመ​ላ​ለ​ሳሉ። እንደ ገና​ና​ነ​ትህ መጠን የሰው ልጆ​ችን አጸ​ና​ሃ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">አቤቱ፥ እስከ መቼ ፈጽ​መህ ትረ​ሳ​ኛ​ለህ? እስከ መቼስ ፊት​ህን ከእኔ ትመ​ል​ሳ​ለህ?</verse>
				<verse number="2">እስከ መቼ በነ​ፍሴ ኀዘ​ንን አኖ​ራ​ለሁ? እስከ መቼ ልቤ ሁል​ጊዜ ትጨ​ነ​ቅ​ብ​ኛ​ለች? እስከ መቼ ጠላ​ቶች በላዬ ይታ​በ​ያሉ?</verse>
				<verse number="3">አቤቱ አም​ላኬ፥ ተመ​ል​ከ​ተኝ ስማ​ኝም፤ ለሞ​ትም እን​ዳ​ያ​ን​ቀ​ላፉ ዐይ​ኖቼን አብ​ራ​ቸው። ጠላ​ቶ​ቼም አሸ​ነ​ፍ​ነው እን​ዳ​ይሉ፥</verse>
				<verse number="4">የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​ኝም እኔ ብና​ወጥ ደስ እን​ዳ​ይ​ላ​ቸው፥</verse>
				<verse number="5">እኔ ግን በቸ​ር​ነ​ትህ ታመ​ንሁ፥ ልቤም በማ​ዳ​ንህ ደስ ይለ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">የረ​ዳ​ኝን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ፤ ለል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስምም እዘ​ም​ራ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">ሰነፍ በልቡ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የለም” ይላል። በሥ​ራ​ቸው ረከሱ፥ ጐሰ​ቈ​ሉም፤ በጎ ነገ​ርን የሚ​ሠ​ራት የለም። አን​ድም እንኳ የለም።</verse>
				<verse number="2">የሚ​ያ​ስ​ተ​ውል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ፈ​ልግ እን​ዳለ ያይ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ የሰው ልጆ​ችን ተመ​ለ​ከተ።</verse>
				<verse number="3">ሁሉ ተስ​ተ​ካ​ክሎ በአ​ን​ድ​ነት ዐመፀ፤ በጎ ነገ​ርን የሚ​ሠ​ራት የለም፤ አን​ድም እንኳ የለም።</verse>
				<verse number="4">ጕሮ​ሮ​ኣ​ቸው እንደ መቃ​ብር የተ​ከ​ፈተ ነው፥ በም​ላ​ሳ​ቸው ሸነ​ገሉ፤</verse>
				<verse number="5">ከከ​ን​ፈ​ራ​ቸው በታች የእ​ባብ መርዝ አለ፤ አፋ​ቸው መራራ ነው፥ መር​ገ​ም​ንም ተሞ​ል​ቶ​አል፤</verse>
				<verse number="6">ደምን ለማ​ፍ​ሰስ እግ​ራ​ቸው ፈጣን ነው፤ ጥፋ​ትና ጕስ​ቍ​ልና በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው አለ፥ የሰ​ላ​ምን መን​ገድ አላ​ወ​ቁ​አ​ት​ምና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት በዐ​ይ​ና​ቸው ፊት የለም።</verse>
				<verse number="7">ሕዝ​ቤን እንደ እን​ጀራ የሚ​በሉ፥ ኀጢ​አ​ትን የሚ​ሠሩ ሁሉ አያ​ው​ቁም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አይ​ጠ​ሩ​ትም።</verse>
				<verse number="8">በዚ​ያም ፈሩ፥ የማ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ውም አስ​ፈ​ራ​ቸው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጻ​ድ​ቃን ትው​ልድ ዘንድ ነውና።</verse>
				<verse number="9">የድ​ሆ​ችን ምክር አሳ​ፈ​ራ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ተስ​ፋ​ቸው ነው።</verse>
				<verse number="10">ከጽ​ዮን መድ​ኀ​ኒ​ትን ለእ​ስ​ራ​ኤል ማን ይሰ​ጣል? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሕ​ዝ​ቡን ምርኮ በመ​ለሰ ጊዜ፥ ያዕ​ቆብ ደስ ይለ​ዋል፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">አቤቱ፥ በድ​ን​ኳ​ንህ ውስጥ ማን ያድ​ራል? በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ተራ​ራህ ማን ይኖ​ራል?</verse>
				<verse number="2">በቅ​ን​ነት የሚ​ሄድ፥ ጽድ​ቅ​ንም የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በል​ቡም እው​ነ​ትን የሚ​ና​ገር።</verse>
				<verse number="3">በአ​ን​ደ​በቱ የማ​ይ​ሸ​ነ​ግል፥ በባ​ል​ን​ጀ​ራው ላይ ክፋ​ትን የማ​ያ​ደ​ርግ፥ ዘመ​ዶ​ቹ​ንም የማ​ያ​ሰ​ድብ።</verse>
				<verse number="4">ኀጢ​አ​ተኛ በፊቱ የተ​ናቀ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ፈ​ሩ​ትን የሚ​ያ​ከ​ብር፥ ለባ​ል​ን​ጀ​ራው ምሎ የማ​ይ​ከዳ።</verse>
				<verse number="5">ገን​ዘ​ቡን በአ​ራጣ የማ​ያ​በ​ድር፥ በን​ጹሑ ላይ መማ​ለ​ጃን የማ​ይ​ቀ​በል። እን​ዲህ የሚ​ያ​ደ​ርግ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ታ​ወ​ክም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">አቤቱ፥ በአ​ንተ ታም​ኛ​ለ​ሁና ጠብ​ቀኝ።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ሁት፥ “አንተ ጌታዬ ነህ፤ በጎ​ነ​ቴን አት​ሻ​ት​ምና።</verse>
				<verse number="3">ፈቃ​ድህ ሁሉ በም​ድር ባሉት ቅዱ​ሳን ላይ ተገ​ለጠ።</verse>
				<verse number="4">ደዌ​ያ​ቸው በዛ፤ ከዚ​ያም በኋላ ተፋ​ጠኑ፤ በደም ማኅ​በ​ራ​ቸው አል​ተ​ባ​በ​ርም። ስማ​ቸ​ው​ንም በአፌ አል​ጠ​ራም።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የር​ስቴ ዕድል ፋን​ታና ጽዋዬ ነው፥ ርስ​ቴን የም​ት​መ​ልስ አንተ ነህ።</verse>
				<verse number="6">ይይ​ዙኝ ዘንድ ገመድ ጣሉ​ብኝ፥ ርስቴ ግን ተያ​ዘ​ልኝ።”</verse>
				<verse number="7">እን​ዳ​ስ​ተ​ውል ያደ​ረ​ገ​ኝን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ፤ ደግ​ሞም በሌ​ሊት ኵላ​ሊ​ቶች ይገ​ሥ​ጹ​ኛል።</verse>
				<verse number="8">ሁል​ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በፊቴ አየ​ዋ​ለሁ፤ እን​ዳ​ል​ታ​ወክ በቀኜ ነውና።</verse>
				<verse number="9">ስለ​ዚህ ልቤን ደስ አለው፥ ምላ​ሴም ሐሤት አደ​ረገ፤ ሥጋዬ ደግሞ በተ​ስ​ፋው ያድ​ራል፤</verse>
				<verse number="10">ነፍ​ሴን በሲ​ኦል አት​ተ​ዋ​ት​ምና፥ ጻድ​ቅ​ህ​ንም መበ​ስ​በ​ስን ያይ ዘንድ አት​ተ​ወ​ውም።</verse>
				<verse number="11">የሕ​ይ​ወ​ትን መን​ገድ አሳ​የ​ኸኝ፤ ከፊ​ትህ ጋር ደስ​ታን አጠ​ገ​ብ​ኸኝ፥ በቀ​ኝ​ህም የዘ​ለ​ዓ​ለም ፍስሓ አለ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">አቤቱ፥ ጽድ​ቄን ስማኝ፥ ልመ​ና​ዬ​ንም አድ​ም​ጠኝ፤ በተ​ን​ኰ​ለ​ኛም ከን​ፈር ያል​ሆ​ነ​ውን ጸሎ​ቴን አድ​ም​ጠኝ፤</verse>
				<verse number="2">ፍርዴ ከፊ​ትህ ይወ​ጣል፥ ዐይ​ኖ​ቼም ጽድ​ቅ​ህን አዩ።</verse>
				<verse number="3">በሌ​ሊ​ትም ጐበ​ኘ​ኸኝ፤ ልቤ​ንም ፈተ​ን​ኸው፥ ፈተ​ን​ኸኝ፥ ዐመ​ፅም አል​ተ​ገ​ኘ​ብ​ኝም።</verse>
				<verse number="4">የሰ​ውን ሥራ አፌ እን​ዳ​ይ​ና​ገር፥ ስለ ከን​ፈ​ሮ​ችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መን​ገ​ዶ​ችን ጠበ​ቅሁ።</verse>
				<verse number="5">ሰኰ​ናዬ እን​ዳ​ይ​ና​ወጥ አረ​ማ​መ​ዴን በመ​ን​ገ​ድህ አጽና።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰም​ቶ​ኛ​ልና እኔ ጮኽሁ፤ ጆሮ​ህን ወደ እኔ አዘ​ን​ብል፤ ቃሌ​ንም ስማ።</verse>
				<verse number="7">ቀኝ​ህን ከሚ​ቃ​ወ​ሟት፥ የሚ​ያ​ም​ኑ​ብ​ህን የሚ​ያ​ድ​ና​ቸ​ውን ቸር​ነ​ት​ህን ግለ​ጠው።</verse>
				<verse number="8">እንደ ዐይን ብሌን ጠብ​ቀኝ፤ በክ​ን​ፎ​ችህ ጥላ ሰው​ረኝ፤</verse>
				<verse number="9">ከሚ​ያ​ጐ​ሳ​ቍ​ሉኝ ኃጥ​ኣን ፊት፥ ጠላ​ቶቼ ግን ነፍ​ሴን ተመ​ለ​ከ​ት​ዋት፤</verse>
				<verse number="10">አን​ጀ​ታ​ቸ​ውን ቋጠሩ፥ አፋ​ቸ​ውም ትዕ​ቢ​ትን ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="11">አሁ​ንም አባ​ረ​ሩኝ፤ ከበ​ቡ​ኝም፤ ዐይ​ና​ቸ​ው​ንም ወደ ምድር ዝቅ ዝቅ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="12">እነ​ርሱ ለን​ጥ​ቂያ እን​ደ​ሚ​ሸ​ምቅ አን​በሳ፥ ተሰ​ው​ሮም እን​ደ​ሚ​ኖር እንደ አን​በሳ ግል​ገል ተቀ​በ​ሉኝ።</verse>
				<verse number="13">አቤቱ፥ ተነሥ፥ ደር​ሰህ አሰ​ና​ክ​ላ​ቸው፤ ነፍ​ሴ​ንም ከጦር አድ​ናት።</verse>
				<verse number="14">ሰይ​ፍህ በእ​ጅህ ጠላ​ቶች ላይ ናት። አቤቱ፥ በም​ድር ካነሱ ሰዎች፥ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው ከፋ​ፍ​ላ​ቸው፥ ከሰ​ወ​ር​ኸው ሆዳ​ቸው ጠገ​በች፤ ልጆ​ቻ​ቸው ጠገቡ። የተ​ረ​ፋ​ቸ​ው​ንም ለሕ​ፃ​ና​ቶ​ቻ​ቸው ተዉ።</verse>
				<verse number="15">እኔ ግን በጽ​ድ​ቅህ ፊት​ህን አያ​ለሁ፤ ክብ​ር​ህን በማ​የ​ትም እጠ​ግ​ባ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">አቤቱ፥ በኀ​ይሌ እወ​ድ​ድ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይሌ፥ አም​ባዬ፥ መድ​ኀ​ኒቴ፥ አም​ላኬ፥ በእ​ር​ሱም የም​ተ​ማ​መ​ን​በት ረዳቴ፥ መታ​መ​ኛ​ዬና የደ​ኅ​ን​ነቴ ቀንድ፥ መጠ​ጊ​ያ​ዬም ነው።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በጠ​ራ​ሁት ጊዜ ከጠ​ላ​ቶቼ እድ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">የሞት ጣር ያዘኝ፥ የዐ​መፅ ፈሳ​ሽም አወ​ከኝ፤</verse>
				<verse number="5">የሲ​ኦል ጣር ከበ​በኝ፤ የሞት ወጥ​መ​ድም ደረ​ሰ​ብኝ።</verse>
				<verse number="6">በጨ​ነ​ቀኝ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠራ​ሁት፥ ወደ አም​ላ​ኬም ጮኽሁ፤ በቤተ መቅ​ደ​ሱም ቃሌን ሰማኝ፥ ጩኸ​ቴም በፊቱ ወደ ጆሮው ገባ።</verse>
				<verse number="7">ምድ​ርም ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠች፥ ተና​ወ​ጠ​ችም፥ የተ​ራ​ሮ​ችም መሠ​ረ​ቶች ተነ​ቃ​ነቁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቈ​ጥ​ቶ​አ​ልና ተን​ቀ​ጠ​ቀጡ።</verse>
				<verse number="8">ከቍ​ጣው ጢስ ወጣ፥ ከፊ​ቱም እሳት ነደደ፤ ፍምም ከእ​ርሱ በራ።</verse>
				<verse number="9">ሰማ​ዮ​ችን ዝቅ ዝቅ አደ​ረገ፥ ወረ​ደም፥ ጭጋግ ከእ​ግሩ በታች ነበረ።</verse>
				<verse number="10">በኪ​ሩ​ቤ​ልም ላይ ተቀ​ምጦ በረረ፥ በነ​ፋ​ስም ክንፍ በረረ።</verse>
				<verse number="11">መሰ​ወ​ሪ​ያ​ውን ጨለማ አደ​ረገ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ድን​ኳኑ፤ ውኃ​ዎች በደ​መ​ና​ዎች ውስጥ ጠቈሩ።</verse>
				<verse number="12">በፊቱ ካለው ብር​ሃን የተ​ነሣ ደመ​ና​ትና በረዶ የእ​ሳት ፍምም በፊቱ አለፉ።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ማ​ያት አን​ጐ​ደ​ጐደ፥ ልዑ​ልም ቃሉን ሰጠ።</verse>
				<verse number="14">ፍላ​ጻ​ውን ላከ፥ በተ​ና​ቸ​ውም፤ መብ​ረ​ቆ​ችን አበዛ አወ​ካ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="15">አቤቱ፥ ከተ​ግ​ሣ​ጽህ፥ ከመ​ዓ​ት​ህም መን​ፈስ እስ​ት​ን​ፋስ የተ​ነሣ፥ የው​ኆች ምን​ጮች ታዩ፥ የዓ​ለም መሠ​ረ​ቶ​ችም ተገ​ለጡ።</verse>
				<verse number="16">ከአ​ር​ያም ላከ፥ ወሰ​ደ​ኝም፥ ከብዙ ውኆ​ችም አወ​ጣኝ።</verse>
				<verse number="17">ከብ​ር​ቱ​ዎች ጠላ​ቶቼ ከሚ​ጠ​ሉ​ኝም አዳ​ነኝ፥ በር​ት​ተ​ው​ብኝ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="18">በመ​ከ​ራዬ ቀን ደረ​ሱ​ብኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን መጠ​ጊ​ያዬ ሆነ።</verse>
				<verse number="19">ወደ ሰፊ ሥፍ​ራም አወ​ጣኝ፤ ወድ​ዶ​ኛ​ልና አዳ​ነኝ።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ጽድቄ ይሰ​ጠ​ኛል፤ እንደ እጆቼ ንጽ​ሕ​ናም ይከ​ፍ​ለ​ኛል።</verse>
				<verse number="21">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ጠብ​ቄ​አ​ለ​ሁና፥ አም​ላ​ኬ​ንም አል​በ​ደ​ል​ሁም።</verse>
				<verse number="22">ፍርዱ ሁሉ ሁል​ጊዜ በፊቴ ነበ​ረና፥ ጽድ​ቁም ከእኔ አል​ራ​ቀም።</verse>
				<verse number="23">ከእ​ርሱ ጋር ንጹሕ እሆ​ና​ለሁ። ከኀ​ጢ​አ​ቴም እጠ​በ​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="24">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ጽድቄ ይሰ​ጠ​ኛል። እንደ እጆ​ቼም ንጽ​ሕና በዐ​ይ​ኖቹ ፊት ይከ​ፍ​ለ​ኛል።</verse>
				<verse number="25">ከጻ​ድቅ ሰው ጋር ጻድቅ ትሆ​ና​ለህ፤ ከቅን ሰው ጋርም ቅን ትሆ​ና​ለህ፤</verse>
				<verse number="26">ከን​ጹ​ሕም ሰው ጋር ንጹሕ ትሆ​ና​ለህ፤ ከጠ​ማ​ማም ጋር ጠማማ ትሆ​ና​ለህ፥</verse>
				<verse number="27">አንተ የተ​ዋ​ረ​ደ​ውን ሕዝብ ታድ​ና​ለ​ህና፥ የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችን ዐይ​ኖች ግን ታዋ​ር​ዳ​ለህ።</verse>
				<verse number="28">አቤቱ አንተ መብ​ራ​ቴን ታበ​ራ​ለ​ህና፤ አም​ላኬ ጨለ​ማ​ዬን ያበ​ራል።</verse>
				<verse number="29">በአ​ንተ ከጥ​ፋት እድ​ና​ለ​ሁና፥ በአ​ም​ላ​ኬም ቅጥ​ሩን እዘ​ል​ላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="30">የአ​ም​ላኬ መን​ገዱ ንጹሕ ነው፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል የነ​ጠረ ነው፥ በእ​ርሱ ለሚ​ታ​መ​ኑት ሁሉ መታ​መ​ኛ​ቸው ነው።</verse>
				<verse number="31">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀር አም​ላክ ማን ነው? ከአ​ም​ላ​ካ​ች​ንስ በቀር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማን ነው?</verse>
				<verse number="32">ኀይ​ልን የሚ​ያ​ስ​ታ​ጥ​ቀኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥ መን​ገ​ዴ​ንም ንጹሕ የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት፥</verse>
				<verse number="33">እግ​ሮ​ቼን እንደ ዋልያ እግ​ሮች የሚ​ያ​ረታ በከ​ፍ​ታም ቦታ የሚ​ያ​ቆ​መኝ፥</verse>
				<verse number="34">እጆ​ቼን ሰልፍ የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር፤ ለክ​ን​ዴም የናስ ቀስት አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="35">ለደ​ኅ​ን​ነ​ቴም መታ​መ​ኛን ሰጠኝ። ቀኝ​ህም ተቀ​በ​ለኝ፥ ትም​ህ​ር​ት​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያጠ​ና​ኛል። የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ረ​ኝም ተግ​ሣ​ጽህ ነው።</verse>
				<verse number="36">አረ​ማ​መ​ዴን በበ​ታቼ አሰ​ፋህ፥ ሰኰ​ና​ዬም አል​ደ​ከ​መም።</verse>
				<verse number="37">ጠላ​ቶ​ቼን አሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ እይ​ዛ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም፥ እስ​ካ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም ድረስ አል​መ​ለ​ስም።</verse>
				<verse number="38">አስ​ጨ​ን​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ መቆ​ምም አይ​ች​ሉም፥ ከእ​ግ​ሬም በታች ይወ​ድ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="39">በሰ​ል​ፍም ኀይ​ልን ታስ​ታ​ጥ​ቀ​ኛ​ለህ፤ በበ​ላዬ የቆ​ሙ​ትን ሁሉ በበ​ታቼ ትጥ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="40">የጠ​ላ​ቶቼን ጀርባ ሰጠ​ኸኝ፥ የሚ​ጠ​ሉ​ኝ​ንም አጠ​ፋ​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="41">ጮኹ፥ የሚ​ረ​ዳ​ቸ​ውም አጡ። ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጮኹ፥ አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="42">በነ​ፋስ ፊት እን​ዳለ ትቢያ እፈ​ጫ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ እንደ አደ​ባ​ባ​ይም ጭቃ እረ​ግ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="43">ከሕ​ዝብ ክር​ክር አድ​ነኝ፥ የአ​ሕ​ዛ​ብም ራስ አድ​ር​ገህ ትሾ​መ​ኛ​ለህ፥ የማ​ላ​ው​ቀው ሕዝ​ብም ይገ​ዛ​ል​ኛል።</verse>
				<verse number="44">በጆሮ ሰም​ተው ተገ​ዙ​ልኝ፤ የባ​ዕድ ልጆች ዋሹኝ።</verse>
				<verse number="45">የባ​ዕድ ልጆች አረጁ፥ በመ​ገ​ን​ዳ​ቸ​ውም ተሰ​ና​ከሉ።</verse>
				<verse number="46">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕያው ነው፥ አም​ላ​ኬም ቡሩክ ነው፥ የመ​ድ​ኀ​ኒ​ቴም አም​ላክ ከፍ ከፍ አለ።</verse>
				<verse number="47">አም​ላኬ በቀ​ሌን ይመ​ል​ስ​ል​ኛል። አሕ​ዛ​ብን በበ​ታቼ ያስ​ገ​ዛ​ል​ኛል።</verse>
				<verse number="48">ከጥ​ፉ​ዎች ጠላ​ቶቼ የሚ​ታ​ደ​ገኝ እርሱ ነው፤ በእኔ ላይ ከቆ​ሙ​ትም ከፍ ከፍ የሚ​ያ​ደ​ር​ገኝ እርሱ ነው፥ ከግ​ፈኛ ሰው አድ​ነኝ።</verse>
				<verse number="49">አቤቱ፥ ስለ​ዚህ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥ ለስ​ም​ህም እዘ​ም​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="50">የን​ጉ​ሡን መድ​ኀ​ኒት ታላቅ ያደ​ር​ጋ​ታል፥ ቸር​ነ​ቱ​ንም ለቀ​ባው ለዳ​ዊት፥ ለዘ​ሩም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ያደ​ር​ጋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">ሰማ​ያት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ይና​ገ​ራሉ፥ የሰ​ማ​ይም ጠፈር የእ​ጁን ሥራ ያወ​ራል።</verse>
				<verse number="2">ቀን ለቀን ነገ​ርን ታወ​ጣ​ለች፥ ሌሊ​ትም ለሌ​ሊት ጥበ​ብን ትና​ገ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="3">ቃላ​ቸው ያል​ተ​ሰ​ማ​በት ነገር የለም፥ መና​ገ​ርም የለም፥</verse>
				<verse number="4">ቃላ​ቸው ወደ ምድር ሁሉ ወጣ። ነገ​ራ​ቸ​ውም እስከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ።</verse>
				<verse number="5">በፀ​ሐይ ውስጥ ድን​ኳ​ኑን አደ​ረገ፥ እር​ሱም እንደ ሙሽራ ከእ​ል​ፍኙ ይወ​ጣል፤ በመ​ን​ገዱ እን​ደ​ሚ​ራ​መድ አር​በኛ ደስ ይለ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">አወ​ጣጡ ከሰ​ማ​ያት ዳርቻ ነው፥ መግ​ቢ​ያ​ውም እስከ ዓለም ዳርቻ ነው፤ ከት​ኩ​ሳ​ቱም የሚ​ሰ​ወር የለም።</verse>
				<verse number="7">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ንጹሕ ነው፤ ነፍ​ስ​ንም ይመ​ል​ሳል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክር የታ​መነ ነው፤ ሕፃ​ና​ት​ንም ጠቢ​ባን ያደ​ር​ጋል።</verse>
				<verse number="8">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥር​ዐት ቅን ነው፥ ልብ​ንም ደስ ያሰ​ኛል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ብሩህ ነው፥ ዐይ​ኖ​ች​ንም ያበ​ራል።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ንጹሕ ነው፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ይኖ​ራል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ እው​ነ​ትና ቅን​ነት በአ​ን​ድ​ነት ነው።</verse>
				<verse number="10">ከወ​ር​ቅና ከክ​ቡር ዕንቍ ይልቅ ይወ​ደ​ዳል፤ ከማ​ርና ከማር ወለ​ላም ይልቅ ይጣ​ፍ​ጣል።</verse>
				<verse number="11">ባሪ​ያህ ደግሞ ይጠ​ብ​ቀ​ዋል፤ በመ​ጠ​በ​ቁም ብዙ ዋጋ ይቀ​በ​ላል።</verse>
				<verse number="12">ስሕ​ተ​ትን ማን ያስ​ተ​ው​ላ​ታል? ከተ​ሰ​ወረ ኀጢ​አቴ አን​ጻኝ።</verse>
				<verse number="13">ከልዩ ሰው ባሪ​ያ​ህን አድ​ነው። ካል​ገ​ዙኝ የዚ​ያን ጊዜ ፍጹም እሆ​ና​ለሁ፥ ከታ​ላ​ቁም ኀጢ​አቴ እነ​ጻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">የአ​ን​ደ​በቴ ቃል ያማረ ይሁን፤ የልቤ ዐሳ​ብም ሁል​ጊዜ በፊቴ ነው አቤቱ ረድ​ኤቴ መድ​ኀ​ኒ​ቴም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">በመ​ከ​ራህ ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይስ​ማህ፤ የያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ ስምም ይቁ​ም​ልህ።</verse>
				<verse number="2">ከመ​ቅ​ደሱ ረድ​ኤ​ትን ይላ​ክ​ልህ፥ ከጽ​ዮ​ንም ይቀ​በ​ልህ።</verse>
				<verse number="3">መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን ያስ​ብ​ልህ፤ ቍር​ባ​ን​ህ​ንም ያለ​ም​ል​ም​ልህ።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ልብህ ይስ​ጥህ ፈቃ​ድ​ህ​ንም ሁሉ ይፈ​ጽ​ም​ልህ።</verse>
				<verse number="5">በማ​ዳ​ንህ ደስ ይለ​ናል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ም​ላ​ካ​ችን ስም ከፍ ከፍ እን​ላ​ለን፤ ልመ​ና​ህን ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ጽ​ም​ልህ።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ባ​ውን እን​ዳ​ዳ​ነው ዛሬ ዐወ​ቅሁ፤ ከሰ​ማይ መቅ​ደሱ ይመ​ል​ስ​ለ​ታል በቀኙ የማ​ዳን ኀይል።</verse>
				<verse number="7">እነ​ዚያ በፈ​ረ​ሶ​ችና በሰ​ረ​ገ​ላ​ዎች ይታ​መ​ናሉ፤ እኛ ግን በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ከፍ ከፍ እን​ላ​ለን።</verse>
				<verse number="8">እነ​ርሱ ተሰ​ነ​ካ​ክ​ለው ወደቁ፤ እኛ ግን ተነ​ሣን፥ ጸን​ተ​ንም ቆምን።</verse>
				<verse number="9">አቤቱ፥ ንጉ​ሥን አድ​ነው፥ በም​ን​ጠ​ራ​ህም ቀን ስማን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">አቤቱ፥ በኀ​ይ​ልህ ንጉሥ ደስ ይለ​ዋል፤ በማ​ዳ​ን​ህም እጅግ ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋል።</verse>
				<verse number="2">የል​ቡን ፈቃድ ሰጠ​ኸው፥ የከ​ን​ፈ​ሮ​ቹ​ንም ልመና አል​ከ​ለ​ከ​ል​ኸ​ውም።</verse>
				<verse number="3">በበጎ በረ​ከት ደር​ሰ​ህ​ለ​ታ​ልና፤ ከክ​ቡር ዕንቍ የሆነ ዘው​ድ​ንም በራሱ ላይ አኖ​ርህ።</verse>
				<verse number="4">ሕይ​ወ​ትን ለመ​ነህ፥ ሰጠ​ኸ​ውም፥ ለረ​ዥም ዘመን ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ።</verse>
				<verse number="5">በማ​ዳ​ንህ ክብሩ ታላቅ ነው፤ ክብ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን ጨመ​ር​ህ​ለት።</verse>
				<verse number="6">የዘ​ለ​ዓ​ለም በረ​ከ​ትን ሰጥ​ተ​ኸ​ዋ​ልና፥ በፊ​ት​ህም ደስታ ደስ ታሰ​ኘ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="7">ንጉሥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተማ​ም​ኖ​አ​ልና፥ በል​ዑ​ልም ምሕ​ረት አይ​ና​ወ​ጥም።</verse>
				<verse number="8">እጅህ ጠላ​ቶ​ች​ህን ሁሉ ታግ​ኛ​ቸው፥ ቀኝ​ህም የሚ​ጠ​ሉ​ህን ሁሉ ታግ​ኛ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ፊትህ በተ​ቈጣ ጊዜ እንደ እሳት እቶን አድ​ር​ጋ​ቸው፤ አቤቱ፥ በቍ​ጣህ አው​ካ​ቸው፥ እሳ​ትም ትብ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">ፍሬ​ያ​ቸ​ውን ከም​ድር፥ ዘራ​ቸ​ው​ንም ከሰው ልጆች አጥፋ።</verse>
				<verse number="11">ክፋ​ትን በአ​ንተ ላይ ዘር​ግ​ተ​ዋ​ልና፥ መወ​ሰን የማ​ይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ንም ምክር ዐሰቡ።</verse>
				<verse number="12">ወደ ኋላ​ቸው ትመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ፊታ​ቸ​ውን ለመ​ዓ​ትህ ጊዜ ታዘ​ጋ​ጃ​ለህ።</verse>
				<verse number="13">አቤቱ፥ በኀ​ይ​ልህ ከፍ ከፍ አልህ፤ ጽና​ት​ህ​ንም እና​መ​ሰ​ግ​ና​ለን፤ እን​ዘ​ም​ር​ማ​ለን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">አም​ላኬ፥ አም​ላኬ፥ ተመ​ል​ከ​ተኝ፥ ለምን ተው​ኸኝ? የኀ​ጢ​አቴ ቃል እኔን ከማ​ዳን የራቀ ነው።</verse>
				<verse number="2">አም​ላኬ፥ በቀን ወደ አንተ እጮ​ኻ​ለሁ፥ አል​ሰ​ማ​ኸ​ኝም። በሌ​ሊ​ትም በፊ​ትህ አላ​ሰ​ብ​ከ​ኝም።</verse>
				<verse number="3">በእ​ስ​ራ​ኤል የተ​መ​ሰ​ገ​ንህ አንተ ግን በቅ​ዱ​ሳ​ንህ ትኖ​ራ​ለህ።</verse>
				<verse number="4">አባ​ቶ​ቻ​ችን አን​ተን አመኑ፥ አመኑ፥ አን​ተም አዳ​ን​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">ወደ አንተ ጮኹ፥ ዳኑም፥ አን​ተ​ንም አመኑ፥ አላ​ፈ​ሩም።</verse>
				<verse number="6">እኔ ግን ትል ነኝ፥ ሰውም አይ​ደ​ለ​ሁም፤ በሰው ዘንድ የተ​ና​ቅሁ፥ በሕ​ዝ​ብም ዘንድ የተ​ዋ​ረ​ድሁ ነኝ።</verse>
				<verse number="7">የሚ​ያ​ዩኝ ሁሉ ይጠ​ቃ​ቀ​ሱ​ብ​ኛል፤ ራሳ​ቸ​ውን እየ​ነ​ቀ​ነቁ በከ​ን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸው እን​ዲህ ይላሉ፦</verse>
				<verse number="8">“በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አመነ፥ እር​ሱ​ንም ያድ​ነው፤ ከወ​ደ​ደው ያድ​ነው።”</verse>
				<verse number="9">አንተ ከሆድ አው​ጥ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፥ በእ​ናቴ ጡት ሳለ​ሁም በአ​ንተ ታመ​ንሁ።</verse>
				<verse number="10">ከማ​ኅ​ፀን ጀምሮ በአ​ንተ ላይ ተጣ​ልሁ፤ ከእ​ናቴ ማኅ​ፀን ጀም​ረህ አንተ አም​ላኬ ነህ።</verse>
				<verse number="11">ልጨ​ነቅ ቀር​ቤ​አ​ለ​ሁና፥ የሚ​ረ​ዳ​ኝም የለ​ምና ከእኔ አት​ራቅ።</verse>
				<verse number="12">ብዙ በሬ​ዎች ከበ​ቡኝ፥ የሰ​ቡ​ትም ፍሪ​ዳ​ዎች ያዙኝ፤</verse>
				<verse number="13">ለመ​ን​ጠቅ እን​ደ​ሚ​ያ​ሸ​ምቅ አን​በሳ በላዬ አፋ​ቸ​ውን ከፈቱ።</verse>
				<verse number="14">እንደ ውኃ ፈሰ​ስሁ አጥ​ን​ቶቼም ሁሉ ተለ​ያዩ፤ ልቤ እንደ ሰም ሆነ፥ በሆ​ዴም መካ​ከል ቀለጠ።</verse>
				<verse number="15">ኀይሌ እንደ ገል ደረቀ፥ ምላ​ሴም በጕ​ሮ​ሮዬ ተጣጋ፥ ወደ ሞትም አፈር አወ​ረ​ድ​ኸኝ፤</verse>
				<verse number="16">ብዙ ውሾ​ችም ከበ​ቡኝ፤ የክ​ፉ​ዎች ማኅ​በ​ርም ያዙኝ፤ እጆ​ቼ​ንና እግ​ሮቼን ቸነ​ከ​ሩኝ።</verse>
				<verse number="17">አጥ​ን​ቶ​ቼን ሁሉ ቈጠሩ፤ እነ​ር​ሱም ዐው​ቀው ቸል አሉኝ።</verse>
				<verse number="18">ልብ​ሶ​ቼን ለራ​ሳ​ቸው ተከ​ፋ​ፈሉ፥ በቀ​ሚ​ሴም ላይ ዕጣ ተጣ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="19">አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ከእኔ አት​ራቅ፥ እኔን ለመ​ር​ዳት ተመ​ል​ከት።</verse>
				<verse number="20">ነፍ​ሴን ከሰ​ይፍ አድ​ናት፥ ብቸ​ኝ​ነ​ቴ​ንም ከው​ሾች እጅ።</verse>
				<verse number="21">ከአ​ን​በሳ አፍ አድ​ነኝ። ብቸ​ኝ​ነ​ቴ​ንም ከቀ​ን​ዶች አንድ ቀንድ ካለው።</verse>
				<verse number="22">ስም​ህን ለወ​ን​ድ​ሞቼ እነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ በጉ​ባ​ኤም መካ​ከል አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈሩ፥ አመ​ስ​ግ​ኑት፤ የያ​ዕ​ቆብ ዘር ሁላ​ችሁ፥ አክ​ብ​ሩት፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘር ሁላ​ችሁ፥ ፍሩት።</verse>
				<verse number="24">የድ​ሃ​ውን ልመና አል​ና​ቀ​ምና፥ ቸልም አላ​ለ​ምና፤ ፊቱ​ንም ከእኔ አል​መ​ለ​ሰ​ምና፥ ነገር ግን ወደ እርሱ በጮ​ኽሁ ጊዜ ሰማኝ።</verse>
				<verse number="25">በታ​ላቅ ጉባኤ ክብሬ ከአ​ንተ ዘንድ ነው፤ እር​ሱን በሚ​ፈ​ሩት ፊት ስእ​ለ​ቴን እሰ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="26">ችግ​ረ​ኞች ይበ​ላሉ፥ ይጠ​ግ​ባ​ሉም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ሹት ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤ ልባ​ቸ​ውም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕያው ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="27">የም​ድር ዳር​ቻ​ዎች ሁሉ ያስቡ፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ለሱ፤ የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ዶች ሁሉ በፊቱ ይሰ​ግ​ዳሉ፤</verse>
				<verse number="28">መን​ግ​ሥት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና፥ እርሱ አሕ​ዛ​ብን ይገ​ዛል።</verse>
				<verse number="29">የም​ድር ደን​ዳ​ኖች ሁሉ ይበ​ላሉ ይሰ​ግ​ዳ​ሉም፤ ወደ መሬት የሚ​ወ​ር​ዱት ሁሉ በፊቱ ይሰ​ግ​ዳሉ፤ ነፍ​ሴም ስለ እርሱ በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="30">ዘሬም ይገ​ዛ​ለ​ታል፤ የም​ት​መ​ጣው ትው​ልድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትነ​ግ​ረ​ዋ​ለች፤</verse>
				<verse number="31">ለሚ​ወ​ለ​ደው ሕዝብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ረ​ገ​ውን ጽድ​ቁን ይና​ገ​ራሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ብ​ቀ​ኛል፥ የሚ​ያ​ሳ​ጣ​ኝም የለም።</verse>
				<verse number="2">በለ​መ​ለመ መስክ ያሳ​ድ​ረ​ኛል፤ በዕ​ረ​ፍት ውኃ ዘንድ አሳ​ደ​ገኝ።</verse>
				<verse number="3">ነፍ​ሴን መለ​ሳት፥ ስለ ስሙም በጽ​ድቅ መን​ገድ መራኝ።</verse>
				<verse number="4">በሞት ጥላ መካ​ከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አል​ፈ​ራም፤ በት​ር​ህና ምር​ኩ​ዝህ እነ​ርሱ ያጽ​ና​ኑ​ኛል።</verse>
				<verse number="5">በፊቴ ገበ​ታን አዘ​ጋ​ጀ​ህ​ልኝ፥ በሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩኝ ሰዎች፤ ፊት ለፊት ራሴን በዘ​ይት ቀባህ፥ ጽዋ​ህም የተ​ት​ረ​ፈ​ረፈ ነው፥ ያረ​ካ​ልም።</verse>
				<verse number="6">ምሕ​ረ​ትህ በሕ​ይ​ወቴ ዘመን ሁሉ ይከ​ተ​ለኝ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ለረ​ዥም ዘመን እኖር ዘንድ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="23">
				<verse number="1">ምድር በሞ​ላዋ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናት፥ ዓለ​ምም በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖሩ ሁሉ።</verse>
				<verse number="2">እርሱ በባ​ሕ​ሮች መሥ​ር​ቶ​አ​ታ​ልና፥ በፈ​ሳ​ሾ​ችም አጽ​ን​ቶ​አ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="3">ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ ማን ይወ​ጣል? በተ​ቀ​ደሰ ስፍ​ራ​ውስ ማን ይቆ​ማል?</verse>
				<verse number="4">ልቡ ንጹሕ የሆነ፥ እጆ​ቹም የነጹ፥ በነ​ፍሱ ላይ ከን​ቱን ያል​ወ​ሰደ፥ ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ውም በሽ​ን​ገላ ያል​ማለ።</verse>
				<verse number="5">እርሱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በረ​ከ​ትን ይቀ​በ​ላል፥ ምሕ​ረ​ቱም ከአ​ም​ላኩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="6">ይህች ትው​ልድ እር​ሱን ትፈ​ል​ገ​ዋ​ለች፥ የያ​ዕ​ቆ​ብን አም​ላክ ፊት ትፈ​ል​ጋ​ለች።</verse>
				<verse number="7">እና​ንተ መኳ​ን​ንት! በሮ​ችን ክፈቱ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም ደጆ​ችም ይከ​ፈቱ፥ የክ​ብ​ርም ንጉሥ ይግባ።</verse>
				<verse number="8">ይህ የክ​ብር ንጉሥ ማን ነው? ብር​ቱና ኀያል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጦ​ር​ነት ኀያል ነው።</verse>
				<verse number="9">እና​ንት መኳ​ን​ንት፥ በሮ​ችን ክፈቱ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም ደጆ​ችም ይከ​ፈቱ፥ የክ​ብ​ርም ንጉሥ ይግባ።</verse>
				<verse number="10">ይህ የክ​ብር ንጉሥ ማን ነው? የኀ​ያ​ላን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እርሱ የክ​ብር ንጉሥ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="24">
				<verse number="1">አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ ወደ አንተ ነፍ​ሴን አነ​ሣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">አቤቱ፥ አን​ተን ታመ​ንሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አል​ፈር፤ ጠላ​ቶቼ በእኔ አይ​ሣ​ቁ​ብኝ።</verse>
				<verse number="3">አን​ተን ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ርጉ አያ​ፍ​ሩ​ምና። በከ​ንቱ የሚ​በ​ድሉ ሁሉ ዘወ​ትር ይፈሩ።</verse>
				<verse number="4">አቤቱ፥ መን​ገ​ድ​ህን አመ​ል​ክ​ተኝ፤ ፍለ​ጋ​ህ​ንም አስ​ተ​ም​ረኝ።</verse>
				<verse number="5">በእ​ው​ነ​ትህ ምራኝ፤ አስ​ተ​ም​ረ​ኝም፤ አንተ አም​ላ​ኪ​ዬና መድ​ኀ​ኒቴ ነህና፥ ዘወ​ት​ርም አን​ተን ተስፋ አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="6">አቤቱ፥ ቸር​ነ​ት​ህን ዐስብ፥ ምሕ​ረ​ትህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።</verse>
				<verse number="7">የል​ጅ​ነ​ቴን ኀጢ​አ​ትና ስን​ፍ​ና​የን አታ​ስ​ብ​ብኝ። አቤቱ፥ ስለ ቸር​ነ​ትህ ብዛት፥ እንደ ምሕ​ረ​ትህ ዐስ​በኝ።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር ጻድ​ቅም ነው፤ ስለ​ዚህ የሚ​ሳ​ሳ​ቱ​ትን በመ​ን​ገድ ይመ​ራ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="9">ለየ​ዋ​ሃን ፍር​ድን ያስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ዋል፤ ለየ​ዋ​ሃን መን​ገ​ድን ያመ​ለ​ክ​ታ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="10">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገድ ሁሉ ይቅ​ር​ታና እው​ነት ነው፤ ቃል ኪዳ​ኑ​ንና ምስ​ክ​ሩን ለሚ​ፈ​ልጉ።</verse>
				<verse number="11">አቤቱ፥ ስለ ስምህ ብለህ፥ ኀጢ​አ​ቴን ሁሉ ይቅር በለኝ፥ ብዙ ነውና።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው ማን ነው? እርሱ በሚ​መ​ር​ጠው መን​ገድ ይመ​ራ​ዋል።</verse>
				<verse number="13">ነፍሱ በመ​ል​ካም ታድ​ራ​ለች፥ ዘሩም ምድ​ርን ይወ​ር​ሳል።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ፈ​ሩት ኀይ​ላ​ቸው ነው፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም ለሚ​ጠ​ሩት ነው። ሕጉ​ንም ያስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="15">ዐይ​ኖቼ ሁል​ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናቸው፤ እርሱ እግ​ሮ​ችን ከወ​ጥ​መድ ያወ​ጣ​ቸ​ዋ​ልና፥</verse>
				<verse number="16">ፊት​ህን ወደ እኔ አድ​ርግ ማረ​ኝም፥ እኔ ብቸ​ኛና ድሃ ነኝና።</verse>
				<verse number="17">የልቤ ኀዘን ብዙ ነው፤ ከጭ​ን​ቀቴ አው​ጣኝ።</verse>
				<verse number="18">ድካ​ሜ​ንና መከ​ራ​ዬን እይ፥ ኀጢ​አ​ቴ​ንም ሁሉ ይቅር በለኝ።</verse>
				<verse number="19">ጠላ​ቶቼ እንደ በዙ እይ፥ በግ​ፍም ጥልን ጠል​ተ​ው​ኛል።</verse>
				<verse number="20">ነፍ​ሴን ጠብ​ቃት አድ​ና​ትም፥ አን​ተን ታም​ኛ​ለ​ሁና አል​ፈር።</verse>
				<verse number="21">አቤቱ፥ አን​ተን ተስፋ አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና የዋ​ሃ​ንና ቅኖች ተከ​ተ​ሉኝ።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ራ​ኤ​ልን ከመ​ከ​ራው ሁሉ ያድ​ነ​ዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="25">
				<verse number="1">አቤቱ፥ እኔ በየ​ዋ​ህ​ነቴ እኖ​ራ​ለ​ሁና ፍረ​ድ​ልኝ፤ እን​ዳ​ል​ደ​ክም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አመ​ንሁ።</verse>
				<verse number="2">አቤቱ፥ ፈት​ነኝ መር​ም​ረ​ኝም፤ ኵላ​ሊ​ቴ​ንና ልቤን ፈትን።</verse>
				<verse number="3">ምሕ​ረ​ትህ በዐ​ይኔ ፊት ነው፥ በማ​ዳ​ን​ህም ደስ አለኝ፤</verse>
				<verse number="4">በከ​ንቱ ሸንጎ አል​ተ​ቀ​መ​ጥ​ሁም፥ ከዐ​መ​ፀ​ኞ​ችም ጋር አል​ገ​ባ​ሁም።</verse>
				<verse number="5">የክ​ፉ​ዎ​ችን ማኅ​በር ጠላሁ፥ ከከ​ዳ​ተ​ኞች ጋር አል​ቀ​መ​ጥም።</verse>
				<verse number="6">እጆቼን በን​ጽ​ሕና አጥ​ባ​ለሁ፤ አቤቱ፥ መሠ​ዊ​ያ​ህን እዞ​ራ​ለሁ፥</verse>
				<verse number="7">የም​ስ​ጋ​ና​ህን ቃል እሰማ ዘንድ፥ ተአ​ም​ራ​ት​ህ​ንም ሁሉ እነ​ግር ዘንድ።</verse>
				<verse number="8">አቤቱ፥ የቤ​ት​ህን ጌጥ የክ​ብ​ር​ህ​ንም ማደ​ሪያ ቦታ ወደ​ድሁ።</verse>
				<verse number="9">ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ጋር ነፍ​ሴን፥ ከደም ሰዎ​ችም ጋር ሕይ​ወ​ቴን አት​ጣ​ላት።</verse>
				<verse number="10">በእ​ጃ​ቸው ተን​ኮል አለ​ባ​ቸው፥ ቀኛ​ቸ​ውም መማ​ለ​ጃን ተሞ​ል​ታ​ለች።</verse>
				<verse number="11">እኔ ግን በየ​ዋ​ህ​ነቴ እኖ​ራ​ለሁ፤ አቤቱ፦ አድ​ነኝ ይቅ​ርም በለኝ።</verse>
				<verse number="12">እግ​ሮቼ በቅ​ን​ነት ቆመ​ዋ​ልና፤ አቤቱ፥ በማ​ኅ​በር አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="26">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያበ​ራ​ል​ኛል፥ ያድ​ነ​ኛ​ልም፤ ምን ያስ​ፈ​ራ​ኛል? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሕ​ይ​ወቴ መታ​መ​ኛዋ ነው፤ ምን ያስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ኛል?</verse>
				<verse number="2">ክፉ​ዎች ሥጋ​ዬን ይበሉ ዘንድ በቀ​ረቡ ጊዜ፥ የሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩኝ እነ​ዚያ ጠላ​ቶቼ ደከሙ፥ ወደ​ቁም።</verse>
				<verse number="3">ሠራ​ዊ​ትም ቢጠ​ላኝ ልቤ አይ​ፈ​ራ​ብ​ኝም፤ ሠራ​ዊ​ትም ቢከ​ቡኝ በእ​ርሱ እተ​ማ​መ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አን​ዲት ነገር ለመ​ን​ሁት፥ እር​ስ​ዋ​ንም እሻ​ለሁ፤ በሕ​ይ​ወቴ ዘመን ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ው​ንም አይ ዘንድ፥ በቤተ መቅ​ደ​ሱም አገ​ለ​ግል ዘንድ።</verse>
				<verse number="5">በመ​ከ​ራዬ ቀን በድ​ን​ኳኑ ሸሽ​ጎ​ኛ​ልና፥ በድ​ን​ኳ​ኑም መሸ​ሸ​ጊያ ሰው​ሮ​ኛ​ልና፥ በዓ​ለ​ትም ላይ ከፍ ከፍ አድ​ር​ጎ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="6">እነሆ፥ አሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጠ​ላ​ቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደ​ረገ፤ ዞርሁ በድ​ን​ኳ​ኑም መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋሁ፥ እል​ልም አል​ሁ​ለት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥ እዘ​ም​ር​ለ​ት​ማ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮ​ኽ​ሁ​ትን ቃሌን ስማኝ፤ ማረኝ፥ አድ​ም​ጠ​ኝም።</verse>
				<verse number="8">ልቤ አን​ተን አለ፦ ፊት​ህን ፈለ​ግሁ፥ አቤቱ፥ ፊት​ህን እሻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">ፊት​ህን ከእኔ አት​መ​ልስ፥ ተቈ​ጥ​ተህ ከባ​ሪ​ያህ ፈቀቅ አት​በል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አት​ጣ​ለ​ኝም፥ አም​ላ​ኪ​ዬና መድ​ኀ​ኒቴ ሆይ፥ ቸል አት​በ​ለኝ።</verse>
				<verse number="10">አባ​ቴና እናቴ ጥለ​ው​ኛ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ተቀ​በ​ለኝ።</verse>
				<verse number="11">አቤቱ መን​ገ​ድ​ህን አስ​ተ​ም​ረኝ፥ ስለ ጠላ​ቶ​ቼም በቀና መን​ገድ ምራኝ።</verse>
				<verse number="12">ለሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ፈቃድ አት​ስ​ጠኝ፥ የዐ​መፅ ምስ​ክ​ሮች ተነ​ሥ​ተ​ው​ብ​ኛ​ልና፥ ሐሰ​ትም የዐ​መፅ ራስ ነው።</verse>
				<verse number="13">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቸር​ነት በሕ​ያ​ዋን ምድር አይ ዘንድ አም​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተስፋ አድ​ርግ፤ በርታ፥ ልብ​ህ​ንም አጽና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ተስፋ አድ​ርግ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="27">
				<verse number="1">አቤቱ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ ወደ አንተ እጮ​ኻ​ለሁ፤ ቸልም አት​በ​ለኝ። ቸል ብት​ለኝ ግን ወደ ጕድ​ጓድ እን​ደ​ሚ​ወ​ር​ዱት እሆ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">በቤተ መቅ​ደ​ስህ እጆ​ችን ባነ​ሣሁ ጊዜ፥ ወደ አንተ የጮ​ኽ​ሁ​ትን የል​መ​ና​ዬን ቃል ስማ።</verse>
				<verse number="3">ከኃ​ጥ​ኣን ጋር ነፍ​ሴን አት​ው​ሰ​ዳት፤ ክፋ​ትም በል​ባ​ቸው እያለ ከባ​ል​ን​ጀ​ራ​ቸው ጋር ሰላ​ምን ከሚ​ና​ገሩ ዐመፅ አድ​ራ​ጊ​ዎች ጋር አት​ጣ​ለኝ።</verse>
				<verse number="4">እንደ ሥራ​ቸ​ውና እንደ ዐሳ​ባ​ቸው ክፋት ስጣ​ቸው፤ እንደ እጃ​ቸ​ውም ሥራ ክፈ​ላ​ቸው፤ ፍዳ​ቸ​ውን በራ​ሳ​ቸው ላይ መልስ።</verse>
				<verse number="5">ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ወደ እጆ​ቹም ተግ​ባር አላ​ሰ​ቡ​ምና አፍ​ር​ሳ​ቸው፥ አት​ሥ​ራ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="6">የል​መ​ና​ዬን ቃል ሰም​ቶ​ኛ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳ​ቴና መታ​መ​ኛዬ ነው፤ ልቤ በእ​ርሱ ታመነ፥ እር​ሱም ይረ​ዳ​ኛል፤ ሥጋ​ዬም ለመ​ለመ፥ ፈቅ​ጄም አም​ነ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ ኀይ​ላ​ቸው ነው፥ ለመ​ሲሑ የመ​ድ​ኀ​ኒቱ መታ​መኛ ነው።</verse>
				<verse number="9">ሕዝ​ብ​ህን አድን፥ ርስ​ት​ህ​ንም ባርክ፥ ጠብ​ቃ​ቸው፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም ከፍ ከፍ አድ​ር​ጋ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="28">
				<verse number="1">የአ​ማ​ል​ክት ልጆች ሆይ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፥ የጊ​ደ​ሮ​ችን ጥጃ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ። ክብ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፥</verse>
				<verse number="2">የስ​ሙን ክብር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፥ በቅ​ድ​ስ​ናው ስፍራ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስገዱ።</verse>
				<verse number="3">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በው​ኆች ላይ ነው። የክ​ብር አም​ላክ አን​ጐ​ደ​ጐደ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በብዙ ውኆች ላይ ነው።</verse>
				<verse number="4">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በኀ​ይል ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በታ​ላቅ ክብር ነው።</verse>
				<verse number="5">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ዝግ​ባን ይሰ​ብ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሊ​ባ​ኖ​ስን ዝግባ ይቀ​ጠ​ቅ​ጣል።</verse>
				<verse number="6">እንደ ሊባ​ኖስ ላም ያከ​ሳ​ዋል። ተወ​ዳጅ ግን አንድ ቀንድ እን​ዳ​ለው ርኤም ልጅ ነው።</verse>
				<verse number="7">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል የእ​ሳ​ቱን ነበ​ል​ባል ይቈ​ር​ጣል።</verse>
				<verse number="8">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ምድረ በዳ​ውን ያና​ው​ጣል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃ​ዴ​ስን ምድረ በዳ ያና​ው​ጣል።</verse>
				<verse number="9">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ዋሊ​ያ​ዎ​ችን ያጠ​ነ​ክ​ራ​ቸ​ዋል፥ ዛፎ​ች​ንም ይገ​ል​ጣል፤ ሁሉም በመ​ቅ​ደሱ፦ ምስ​ጋና ይላል።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጥ​ፋት ውኃን ሰብ​ስ​ቦ​አል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ንጉሥ ሆኖ ይቀ​መ​ጣል።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ ኀይ​ልን ይሰ​ጣል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን በሰ​ላም ይባ​ር​ካ​ቸ​ዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="29">
				<verse number="1">አቤቱ፥ ተቀ​ብ​ለ​ኸ​ኛ​ልና፥ የጠ​ላ​ቶቼ መዘ​ባ​በቻ አላ​ደ​ረ​ግ​ኸ​ኝ​ምና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">አቤቱ አም​ላኬ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ይቅ​ርም አል​ኸኝ።</verse>
				<verse number="3">አቤቱ፥ ነፍ​ሴን ከሲ​ኦል አወ​ጣ​ሃት፥ ወደ ጕድ​ጓ​ድም ከሚ​ወ​ር​ዱት ለይ​ተህ አዳ​ን​ኸኝ።</verse>
				<verse number="4">ጻድ​ቃን ሆይ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ፥ ለቅ​ድ​ስ​ና​ውም መታ​ሰ​ቢያ አመ​ስ​ግኑ።</verse>
				<verse number="5">መቅ​ሠ​ፍቱ ከቍ​ጣው ነውና፥ መዳ​ንም ከፈ​ቃዱ ነውና፤ ማታ ልቅሶ ይሰ​ማል፥ ጥዋት ግን ደስታ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="6">እኔም በደ​ስ​ታዬ፥ “ለዘ​ለ​ዓ​ለም አል​ታ​ወ​ክም” አልሁ።</verse>
				<verse number="7">አቤቱ፥ በፈ​ቃ​ድህ ለሕ​ይ​ወቴ ኀይ​ልን ስጣት፤ ፊት​ህን መለ​ስህ፥ እኔም ደነ​ገ​ጥሁ።</verse>
				<verse number="8">አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ወደ አም​ላ​ኬም ለመ​ንሁ።</verse>
				<verse number="9">ወደ ጥፋት ብወ​ርድ በደሜ ምን ጥቅም አለ? አፈር ያመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ልን? ጽድ​ቅ​ህ​ንም ይና​ገ​ራ​ልን?</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰማ፥ ይቅ​ርም አለኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳቴ ሆነኝ።</verse>
				<verse number="11">ልቅ​ሶ​ዬን መል​ሰህ ደስ አሰ​ኘ​ኸኝ። ማቄን ቀድ​ደህ ደስ​ታን አስ​ታ​ጠ​ቅ​ኸኝ።</verse>
				<verse number="12">ክብሬ እን​ዲ​ዘ​ም​ር​ልህ እን​ዳ​ል​ደ​ነ​ግ​ጥም፥ አቤቱ፥ አም​ላኬ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="30">
				<verse number="1">አቤቱ፥ አን​ተን ታመ​ንሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አል​ፈር፤ በጽ​ድ​ቅ​ህም አስ​ጥ​ለኝ፥ አድ​ነ​ኝም።</verse>
				<verse number="2">ጆሮ​ህን ወደ እኔ አዘ​ን​ብል፥ ፈጥ​ነ​ህም አድ​ነኝ፤ ታድ​ነኝ ዘንድ አም​ላኬ መድ​ኀ​ኒ​ቴና የመ​ጠ​ጊ​ያዬ ቤት ሁነኝ።</verse>
				<verse number="3">ኀይ​ሌና መጠ​ጊ​ያዬ አንተ ነህና ስለ ስምህ ምራኝ፥ መግ​በ​ኝም፤</verse>
				<verse number="4">አቤቱ፥ አንተ ረዳቴ ነህና ከሰ​ወ​ሩ​ብኝ ከዚች ወጥ​መድ አው​ጣኝ።</verse>
				<verse number="5">በእ​ጅህ ነፍ​ሴን አደራ እሰ​ጣ​ለሁ፤ የጽ​ድቅ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ተቤ​ዠኝ።</verse>
				<verse number="6">ከን​ቱን ነገር የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውን ሁሉ ሁል​ጊዜ ጠላህ፤ እኔ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመ​ንሁ።</verse>
				<verse number="7">በት​ድ​ግ​ናህ ደስ ይለ​ኛል፤ ሐሴ​ትም አደ​ር​ጋ​ለሁ። መከ​ራ​ዬን አይ​ተ​ሃ​ልና፥ ነፍ​ሴ​ንም ከጭ​ን​ቀት አድ​ነ​ሃ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="8">በጠ​ላቴ እጅ አል​ዘ​ጋ​ኸኝም፥ በሰ​ፊም ስፍራ እግ​ሮ​ቼን አቆ​ምህ።</verse>
				<verse number="9">ተቸ​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና አቤቱ ይቅር በለኝ፥ ዐይ​ኔም ከቍጣ የተ​ነሣ ታወ​ከች፥ ነፍ​ሴም፥ ሆዴም።</verse>
				<verse number="10">ሕይ​ወቴ በመ​ከራ አል​ቋ​ልና፥ ዘመ​ኔም በጩ​ኸት፤ ኀይሌ በች​ግር ደከመ፥ አጥ​ን​ቶቼም ሁሉ ተነ​ዋ​ወጡ።</verse>
				<verse number="11">በጠ​ላ​ቶቼ ሁሉ ዘንድ ተሰ​ደ​ብሁ፥ ይል​ቁ​ንም በጎ​ረ​ቤ​ቶቼ ዘንድ፥ ለዘ​መ​ዶ​ቼም አስ​ፈሪ ሆንሁ፤ በሜዳ ያዩ​ኝም ከእኔ ሸሹ።</verse>
				<verse number="12">እንደ ሞተ ሰው ከልብ ረሱኝ፥ እንደ ጠፋ ዕቃም ሆንሁ።</verse>
				<verse number="13">በዙ​ሪ​ያዬ የከ​በ​ቡ​ኝን ድምፅ ሰም​ቻ​ለ​ሁና፤ በላዬ በአ​ን​ድ​ነት በተ​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ፥ ነፍ​ሴን ለመ​ን​ጠቅ በተ​ማ​ከሩ ጊዜ።</verse>
				<verse number="14">አቤቱ፥ እኔ ግን በአ​ንተ ታመ​ንሁ፤ አንተ አም​ላኬ ነህ አልሁ።</verse>
				<verse number="15">ርስቴ በእ​ጅህ ነው፤ ከጠ​ላ​ቶቼ እጅና ከከ​በ​ቡኝ አድ​ነኝ።</verse>
				<verse number="16">ፊት​ህን በባ​ሪ​ያህ ላይ አብራ፥ ስለ ምሕ​ረ​ት​ህም አድ​ነኝ።</verse>
				<verse number="17">አቤቱ፥ አን​ተን ጠር​ቻ​ለ​ሁና አል​ፈር፤ ሸን​ጋ​ዮች ይፈሩ፥ ወደ ሲኦ​ልም ይው​ረዱ።</verse>
				<verse number="18">በት​ዕ​ቢ​ትና በመ​ናቅ በጻ​ድቅ ላይ ዐመ​ፃን የሚ​ና​ገሩ የሽ​ን​ገላ ከን​ፈ​ሮች ወዮ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">አቤቱ፥ እንደ ቸር​ነ​ትህ ብዛት የሚ​ፈ​ሩ​ህን ሰወ​ር​ኻ​ቸው፥ በሰው ልጆች ፊት የሚ​ታ​መ​ኑ​ብ​ህ​ንም አዳ​ን​ኻ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">በፊ​ትህ ጥላ ከሰው ክር​ክር ትጋ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለህ፥ በመ​ጋ​ረ​ጃ​ህም ከአ​ን​ደ​በት ሽን​ገላ ትሸ​ፍ​ና​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="21">በመ​ከ​ራዬ ብዛት ጊዜ ምሕ​ረ​ቱን በእኔ ላይ የገ​ለጠ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።</verse>
				<verse number="22">እኔስ ከዐ​ይ​ኖ​ችህ ፊት ተጣ​ልሁ ብዬ ነበር። ስለ​ዚህ ወደ እርሱ የጮ​ኽ​ሁ​ትን የል​መ​ና​ዬን ቃል ሰማኝ።</verse>
				<verse number="23">ጻድ​ቃን ሁላ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ውደ​ዱት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቅን ይሻ​ልና፥ ትዕ​ቢ​ት​ንም የሚ​ሹ​ትን ፈጽሞ ይበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="24">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ታ​ምኑ ሁላ​ችሁ፥ ታገሡ ልባ​ች​ሁ​ንም አጽኑ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="31">
				<verse number="1">ኀጢ​አ​ታ​ቸው የተ​ተ​ወ​ላ​ቸው፥ በደ​ላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ያል​ቈ​ጠ​ረ​ባ​ቸው ብፁ​ዓን ናቸው።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በደ​ሉን የማ​ይ​ቈ​ጥ​ር​በት በል​ቡም ሽን​ገላ የሌ​ለ​በት ሰው ብፁዕ ነው።</verse>
				<verse number="3">ሁል​ጊዜ ከመ​ጮኼ የተ​ነሣ ዝም ብያ​ለ​ሁና አጥ​ን​ቶቼ አረጁ፤</verse>
				<verse number="4">በቀ​ንና በሌ​ሊት እጅህ ከብ​ዳ​ብ​ኛ​ለ​ችና፥ እሾህ በወ​ጋኝ ጊዜ ወደ ጕስ​ቍ​ልና ተመ​ለ​ስሁ።</verse>
				<verse number="5">ኀጢ​አ​ቴን ነገ​ርሁ፤ በደ​ሌ​ንም አል​ሸ​ሸ​ግ​ሁም፤ ስለ ኀጢ​አቴ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሴን እከ​ስ​ሳ​ለሁ አልሁ፤ አን​ተም የል​ቤን ሽን​ገላ ተው​ልኝ።</verse>
				<verse number="6">ስለ​ዚህ ጻድቅ ሁሉ በምቹ ጊዜ ወደ አንተ ይጸ​ል​ያል፤ ነገር ግን ብዙ የጥ​ፋት ውኃ ወደ አንተ አይ​ቀ​ር​ብም።</verse>
				<verse number="7">አንተ ካገ​ኘ​ችኝ ከዚች መከ​ራዬ መሸ​ሸ​ጊ​ያዬ ነህ፥ ከከ​በ​ቡ​ኝም ታድ​ነኝ ዘንድ ደስ​ታዬ ነህ።</verse>
				<verse number="8">አስ​ተ​ም​ር​ሃ​ለሁ፥ በም​ት​ሄ​ድ​ባ​ትም በዚች መን​ገድ አጸ​ና​ሃ​ለሁ። ዐይ​ኖ​ቼን በአ​ንተ ላይ አጸ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">ወደ አንተ እን​ዳ​ይ​ቀ​ርቡ በል​ባ​ብና በል​ጓም ጉን​ጫ​ቸ​ውን እን​ደ​ሚ​ለ​ጕ​ሙ​አ​ቸው፥ ልብ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው እንደ ፈረ​ስና እንደ በቅሎ አት​ሁኑ።</verse>
				<verse number="10">የኃ​ጥ​ኣን መቅ​ሠ​ፍ​ታ​ቸው ብዙ ነው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ታ​መ​ኑ​ትን ግን ይቅ​ርታ ይከ​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="11">ጻድ​ቃን ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፥ ሐሤ​ትም አድ​ርጉ፤ ልባ​ች​ሁም የቀና ሁላ​ችሁ፥ በእ​ርሱ ተመኩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="32">
				<verse number="1">ጻድ​ቃን ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ለቅ​ኖ​ችም ክብር ይገ​ባል።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በመ​ሰ​ንቆ አመ​ስ​ግ​ኑት፥ ዐሥር አው​ታ​ርም ባለው በገና ዘም​ሩ​ለት።</verse>
				<verse number="3">አዲስ ምስ​ጋ​ና​ንም አመ​ስ​ግ​ኑት፥ በእ​ል​ል​ታም መል​ካም ዝማሬ ዘም​ሩ​ለት፤</verse>
				<verse number="4">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እው​ነት ነውና ሥራ​ውም ሁሉ በእ​ም​ነት ነውና።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቅ​ንና ምጽ​ዋ​ትን ይወ​ድ​ዳል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታው ምድ​ርን ሞላ።</verse>
				<verse number="6">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሰማ​ዮች ጸኑ፥ ሠራ​ዊ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ በአፉ እስ​ት​ን​ፋስ፤</verse>
				<verse number="7">የባ​ሕ​ሩን ውኃ እንደ ረዋት የሚ​ሰ​በ​ስ​በው፥ በቀ​ላ​ዮ​ችም መዝ​ገ​ቦች የሚ​ያ​ኖ​ረው።</verse>
				<verse number="8">ምድር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትፈ​ራ​ዋ​ለች፥ በዓ​ለም የሚ​ኖሩ ሁሉም ከእ​ርሱ የተ​ነሣ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="9">እርሱ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና፥ ሆኑ፤ እርሱ አዘዘ፤ ተፈ​ጠ​ሩም።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ሕ​ዛ​ብን ምክር ይመ​ል​ሳል፥ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ዐሳብ ይመ​ል​ሳል። የአ​ለ​ቆ​ችን ምክ​ራ​ቸ​ውን ያስ​ረ​ሳ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="11">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክር ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል፥ የል​ቡም ዐሳብ ለልጅ ልጅ ነው።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኩ የሚ​ሆ​ን​ለት ሕዝብ ብፁዕ ነው፥ እርሱ ለር​ስቱ የመ​ረ​ጠው ሕዝብ።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ተመ​ለ​ከተ፥ የሰ​ው​ንም ልጆች ሁሉ አየ።</verse>
				<verse number="14">ከተ​ዘ​ጋ​ጀው የመ​ቅ​ደሱ አዳ​ራሽ ሆኖ በም​ድር ወደ​ሚ​ኖሩ ሁሉ ተመ​ለ​ከተ፤</verse>
				<verse number="15">እርሱ ብቻ​ውን ልባ​ቸ​ውን የሠራ፥ ሥራ​ቸ​ው​ንም ሁሉ የሚ​ያ​ውቅ እርሱ ነው።</verse>
				<verse number="16">ንጉሥ በሠ​ራ​ዊቱ ብዛት አይ​ድ​ንም፥ ኀያ​ልም በኀ​ይሉ ብዛት አይ​ድ​ንም።</verse>
				<verse number="17">ፈረ​ስም ከንቱ ነው፥ አያ​ድ​ንም፤ በኀ​ይ​ሉም ብዛት አያ​መ​ል​ጥም።</verse>
				<verse number="18">እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖች ወደ​ሚ​ፈ​ሩት ናቸው፤ በም​ሕ​ረ​ቱም ወደ​ሚ​ታ​መኑ፥</verse>
				<verse number="19">ነፍ​ሳ​ቸ​ውን ከሞት ያድ​ና​ታል፥ በራ​ብም ጊዜ ይመ​ግ​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="20">ነፍ​ሳ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተስፋ ታደ​ር​ገ​ዋ​ለች፥ ረዳ​ታ​ች​ንና መጠ​ጊ​ያ​ችን እርሱ ነውና።</verse>
				<verse number="21">ልባ​ችን በእ​ርሱ ደስ ይለ​ዋ​ልና፥ በቅ​ዱስ ስሙም ታም​ነ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="22">አቤቱ፥ በአ​ንተ እንደ ታመ​ንን፥ ምሕ​ረ​ትህ በላ​ያ​ችን ትሁን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="33">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሁል​ጊዜ አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ። ምስ​ጋ​ና​ውም ዘወ​ትር በአፌ ነው።</verse>
				<verse number="2">ነፍ​ሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትከ​ብ​ራ​ለች፥ ገሮ​ችም ይስሙ፥ ደስም ይበ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከእኔ ጋር ከፍ ከፍ አድ​ር​ጉት፥ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ስሙን ከፍ ከፍ እና​ድ​ርግ።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈለ​ግ​ሁት መለ​ሰ​ል​ኝም፥ ከመ​ከ​ራ​ዬም ሁሉ አዳ​ነኝ።</verse>
				<verse number="5">ወደ እርሱ ቅረቡ ያበ​ራ​ላ​ች​ሁ​ማል፥ ፊታ​ች​ሁም አያ​ፍ​ርም።</verse>
				<verse number="6">ይህ ችግ​ረኛ ጮኸ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማው፥ ከመ​ከ​ራ​ውም ሁሉ አዳ​ነው።</verse>
				<verse number="7">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ በሚ​ፈ​ሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰ​ፍ​ራል፥ ያድ​ና​ቸ​ው​ማል።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ፥ ዕወ​ቁም፤ በእ​ርሱ የሚ​ታ​መን ሰው ብፁዕ ነው።</verse>
				<verse number="9">ለሚ​ፈ​ሩት ችግር የለ​ባ​ቸ​ው​ምና ቅዱ​ሳን ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍሩት።</verse>
				<verse number="10">ባለ​ጠ​ጎች ደኸዩ፥ ተራ​ቡም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ል​ጉት ግን ከመ​ል​ካም ነገር ሁሉ አል​ተ​ቸ​ገ​ሩም።</verse>
				<verse number="11">ልጆቼ ኑ፥ ስሙኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት አስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ዘንድ፤</verse>
				<verse number="12">ሕይ​ወ​ትን የሚ​ፈ​ቅድ ሰው ማን ነው? በጎ ዘመ​ን​ንም ለማ​የት የሚ​ወ​ድድ ማን ነው?</verse>
				<verse number="13">አን​ደ​በ​ት​ህን ከክፉ ከል​ክል፥ ከን​ፈ​ሮ​ች​ህም ሽን​ገ​ላን እን​ዳ​ይ​ና​ገሩ።</verse>
				<verse number="14">ከክፉ ሽሽ፥ መል​ካ​ም​ንም አድ​ርግ፤ ሰላ​ምን ሻት፥ ተከ​ተ​ላ​ትም።</verse>
				<verse number="15">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖች ወደ ጻድ​ቃኑ፥ ጆሮ​ቹም ወደ ልመ​ና​ቸው ናቸ​ውና።</verse>
				<verse number="16">መታ​ሰ​ቢ​ያ​ቸ​ውን ከም​ድር ያጠፋ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉን በሚ​ያ​ደ​ርጉ ላይ ነው።</verse>
				<verse number="17">ጻድ​ቃን ጮኹ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማ​ቸው፥ ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም ሁሉ አዳ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በል​ባ​ቸው የዋ​ሃን ለሆኑ ቅርብ ነው፥ በመ​ን​ፈስ ትሑ​ታን የሆ​ኑ​ት​ንም ያድ​ና​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="19">የጻ​ድ​ቃን መከ​ራ​ቸው ብዙ ነው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሁሉ ያድ​ና​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ ይጠ​ብ​ቃል፥ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ አይ​ሰ​በ​ርም።</verse>
				<verse number="21">የኃ​ጥእ ሞቱ ክፉ ነው ጽድ​ቅ​ንም የሚ​ጠሉ ይጸ​ጸ​ታሉ።</verse>
				<verse number="22">የባ​ሪ​ያ​ዎ​ቹን ነፍስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቤ​ዣል፥ በእ​ር​ሱም የሚ​ያ​ምኑ ሁሉ አይ​ጸ​ጸ​ቱም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="34">
				<verse number="1">አቤቱ፥ የሚ​በ​ድ​ሉ​ኝን በድ​ላ​ቸው፥ የሚ​ዋ​ጉ​ኝ​ንም ተዋ​ጋ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">ጋሻና ጦር ያዝ፥ እኔ​ንም ለመ​ር​ዳት ተነሥ።</verse>
				<verse number="3">ሰይ​ፍ​ህን ምዘዝ፥ የሚ​ከ​ብ​ቡ​ኝ​ንም ክበ​ባ​ቸው ነፍ​ሴን፦ ረዳ​ትሽ እኔ ነኝ በላት።</verse>
				<verse number="4">ነፍ​ሴን የሚሹ ሁሉ ይፈሩ ይጐ​ሳ​ቈ​ሉም፤ ክፋ​ትን በእኔ ላይ የሚ​መ​ክሩ ይፈሩ፥ ወደ ኋላ​ቸ​ውም ይመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="5">በነ​ፋስ ፊት እን​ዳለ ትቢያ ይሁኑ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ያስ​ጨ​ን​ቃ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">መን​ገ​ዳ​ቸው ዳጥና ጨለማ ትሁን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ያሳ​ድ​ዳ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">በከ​ንቱ ያጠ​ፉኝ ዘንድ ወጥ​መ​ዳ​ቸ​ውን ሸሽ​ገ​ው​ብ​ኛ​ልና፥ ነፍ​ሴን በከ​ንቱ አበ​ሳ​ጭ​ተ​ዋ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="8">ያላ​ወ​ቋት ወጥ​መድ ትም​ጣ​ባ​ቸው፥ የሸ​ሸ​ጓ​ትም ወጥ​መድ ትያ​ዛ​ቸው፤ በዚ​ህ​ችም ወጥ​መድ ውስጥ ይው​ደቁ።</verse>
				<verse number="9">ነፍሴ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይላ​ታል፥ በማ​ዳ​ኑም ሐሤት ታደ​ር​ጋ​ለች።</verse>
				<verse number="10">አጥ​ን​ቶች ሁሉ እን​ዲህ ይሉ​ሃል፦ “አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? ድሃ​ውን ከሚ​ቀ​ማው እጅ ድሃ​ው​ንና ችግ​ረ​ኛ​ው​ንም ከሚ​ነ​ጥ​ቀው እጅ ታድ​ነ​ዋ​ለህ።”</verse>
				<verse number="11">የዐ​መፃ ምስ​ክ​ሮች ተነ​ሡ​ብኝ፥ የማ​ላ​ው​ቀ​ንም በእኔ ላይ ተና​ገሩ።</verse>
				<verse number="12">ስለ በጎ ፋንታ ክፉን መለ​ሱ​ልኝ፥ ሰው​ነ​ቴ​ንም ልጆ​ችን አሳ​ጡ​አት።</verse>
				<verse number="13">እኔስ ባሠ​ቃ​ዩኝ ጊዜ ማቅ ለበ​ስሁ፥ ነፍ​ሴ​ንም በጾም አደ​ከ​ም​ኋት፤ ጸሎ​ቴም ወደ ብብቴ ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="14">ለወ​ዳ​ጆቼና ለወ​ን​ድ​ሞቼ እን​ደ​ማ​ደ​ርግ አደ​ረ​ግሁ፤ እን​ደ​ሚ​ያ​ለ​ቅ​ስና እን​ደ​ሚ​ተ​ክዝ ራሴን ዝቅ ዝቅ አደ​ረ​ግሁ።</verse>
				<verse number="15">በእኔ ላይ ተሰ​በ​ሰቡ፥ ደስም አላ​ቸው፤ ይገ​ር​ፉኝ ዘንድ ተማ​ከሩ፥ እኔ ግን አላ​ወ​ቅ​ሁም። ተሰ​በሩ፥ አል​ደ​ነ​ገ​ጡ​ምም።</verse>
				<verse number="16">ፈተ​ኑኝ፥ በእኔ ላይም ዘበ​ቱ​ብኝ፥ ሣቁ​ብ​ኝም፤ ጥር​ሳ​ቸ​ው​ንም በእኔ ላይ አን​ቀ​ጫ​ቀጩ።</verse>
				<verse number="17">አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ትፈ​ር​ድ​ል​ኛ​ለህ? ነፍ​ሴን ከክፉ ሥራ​ቸው፥ ብቸ​ኝ​ነ​ቴ​ንም ከአ​ን​በ​ሶች አድ​ናት፥</verse>
				<verse number="18">አቤቱ፥ በታ​ላቁ ጉባኤ ውስጥ እገ​ዛ​ል​ሃ​ለሁ፥ በብዙ ሕዝብ መካ​ከ​ልም አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">በግፍ የሚ​ጠ​ሉኝ በላዬ ደስ አይ​በ​ላ​ቸው፥ በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ሉ​ኝና በዐ​ይ​ና​ቸው የሚ​ጠ​ቃ​ቀ​ሱ​ብ​ኝም።</verse>
				<verse number="20">ለእ​ኔስ ሰላ​ምን ይና​ገ​ሩ​ኛ​ልና፥ በግ​ር​ፋ​ትም ያጠ​ፉኝ ዘንድ ይመ​ክ​ራሉ።</verse>
				<verse number="21">አፋ​ቸ​ው​ንም በእኔ ላይ አላ​ቀቁ፤ እሰይ፥ እሰይ፥ በዐ​ይ​ና​ችን አየ​ነው ይላሉ።</verse>
				<verse number="22">አቤቱ፥ አንተ እይ፥ ዝምም አት​በል፤ አቤቱ፥ ከእኔ አት​ራቅ።</verse>
				<verse number="23">አቤቱ ተነሥ፥ ፍር​ዴ​ንም አድ​ምጥ፥ አም​ላኬ ጌታ​ዬም፥ በክ​ር​ክሬ ጊዜ ተነሥ፥</verse>
				<verse number="24">አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ እንደ ጽድ​ቅህ ፍረ​ድ​ልኝ፥ በእ​ኔም ላይ ደስ አይ​በ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">በል​ባ​ቸ​ውም በሰ​ው​ነቴ ላይ፥ “እሰይ እሰይ፥” አይ​በሉ፤ “ዋጥ​ነ​ውም” አይ​በሉ።</verse>
				<verse number="26">በመ​ከ​ራዬ ደስ የሚ​ላ​ቸው ይፈሩ፥ ይጐ​ስ​ቍ​ሉም፤ በእኔ ላይ ነገ​ርን የሚ​ያ​በዙ እፍ​ረ​ት​ንና ጕስ​ቍ​ል​ናን ይል​በሱ።</verse>
				<verse number="27">ጽድ​ቄን የሚ​ወ​ድ​ዱ​አት ደስ ይበ​ላ​ቸው፥ ሐሤ​ት​ንም ያድ​ርጉ፤ የባ​ሪ​ያ​ህን ሰላም የሚ​ወዱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁል​ጊዜ ታላቅ ነው ይበሉ።</verse>
				<verse number="28">ምላሴ ጽድ​ቅ​ህን፥ ሁል​ጊ​ዜም ምስ​ጋ​ና​ህን ይና​ገ​ራል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="35">
				<verse number="1">ኀጢ​አ​ተኛ ራሱን የሚ​ያ​ስ​ት​በ​ትን ነገር ይና​ገ​ራል፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍር​ሀት በዐ​ይ​ኖቹ ፊት የለም።</verse>
				<verse number="2">በአ​ን​ደ​በቱ ሸን​ግ​ሎ​አ​ልና፤ ኀጢ​አቱ ባገ​ኘ​ችው ጊዜ ይጠ​ላ​ታል።</verse>
				<verse number="3">የአፉ ቃል ዐመ​ፅና ሽን​ገላ ነው፤ በጎ ሥራን ይሠራ ዘንድ ማስ​ተ​ዋ​ልን አል​ወ​ደ​ደም።</verse>
				<verse number="4">በመ​ኝ​ታው ዐመ​ፅን ዐሰበ፤ በሁሉ ነገር መል​ካም ባል​ሆ​ነች መን​ገድ ቆሞ​አል፤ ክፋ​ት​ንም አይ​ሰ​ለ​ቻ​ትም።</verse>
				<verse number="5">አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ትህ በሰ​ማይ ነው፥ እው​ነ​ት​ህም እስከ ደመ​ናት ትደ​ር​ሳ​ለች።</verse>
				<verse number="6">ጽድ​ቅ​ህም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራ​ሮች ናት፤ ፍር​ድ​ህም እጅግ ጥልቅ ናት።</verse>
				<verse number="7">አቤቱ፥ ሰው​ንና እን​ስ​ሳን ታድ​ና​ለህ። አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ት​ህን እንደ አበ​ዛህ፥ የሰው ልጆች በክ​ን​ፎ​ችህ ጥላ ይታ​መ​ናሉ።</verse>
				<verse number="8">ከቤ​ትህ ጠል ይረ​ካሉ። ከደ​ስ​ታ​ህም ፈሳሽ ታጠ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="9">የሕ​ይ​ወት ምንጭ ከአ​ንተ ዘንድ ነውና፤ በብ​ር​ሃ​ንህ ብር​ሃ​ንን እና​ያ​ለን።</verse>
				<verse number="10">ምሕ​ረ​ት​ህን በሚ​ያ​ው​ቁህ ላይ፥ ጽድ​ቅ​ህ​ንም በልበ ቅኖች ላይ ዘርጋ።</verse>
				<verse number="11">የት​ዕ​ቢት እግር አይ​ም​ጣ​ብኝ፥ የኀ​ጢ​አ​ተኛ እጅም አያ​ው​ከኝ።</verse>
				<verse number="12">ዐመ​ፃን የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ በዚያ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ይሰ​ደ​ዳሉ፥ መቆ​ምም አይ​ች​ሉም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="36">
				<verse number="1">በክ​ፉ​ዎች ላይ አት​ቅና፥ ዐመ​ፃ​ንም በሚ​ያ​ደ​ርጉ ላይ አት​ቅና፤</verse>
				<verse number="2">እንደ ሣር ፈጥ​ነው ይደ​ር​ቃ​ሉና፥ እንደ ለመ​ለመ ቅጠ​ልም ፈጥ​ነው ይረ​ግ​ፋ​ሉና።</verse>
				<verse number="3">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመን፥ መል​ካ​ም​ንም አድ​ርግ፥ በም​ድ​ርም ያሳ​ድ​ር​ሃል፥ በሀ​ብ​ት​ዋም ያሰ​ማ​ር​ሃል።</verse>
				<verse number="4">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ልህ፥ የል​ብ​ህ​ንም መሻት ይሰ​ጥ​ሃል።</verse>
				<verse number="5">መን​ገ​ድ​ህን ለአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግለጥ፥ በእ​ር​ሱም ታመን፥ እር​ሱም ያደ​ር​ግ​ል​ሃል።</verse>
				<verse number="6">ጽድ​ቅ​ህን እንደ ብር​ሃን፥ ፍር​ድ​ህ​ንም እንደ ቀትር ያመ​ጣ​ታል።</verse>
				<verse number="7">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዛ አገ​ል​ግ​ለ​ውም። በሕ​ይ​ወቱ ደስ ባለ​ውና ዐመ​ፃን በሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው ላይ አት​ቅና።</verse>
				<verse number="8">መዓ​ትን ተዋት፤ ቍጣ​ንም ጣላት፥ እን​ዳ​ት​በ​ድ​ልም አት​ቅና።</verse>
				<verse number="9">ክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎች ይጠ​ፋ​ሉና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ግን እነ​ርሱ ምድ​ርን ይወ​ር​ሳሉ።</verse>
				<verse number="10">ኀጢ​አ​ተ​ኛም ገና ጥቂት አይ​ኖ​ርም፤ ትፈ​ል​ገ​ዋ​ለህ፥ ቦታ​ው​ንም አታ​ገ​ኝም።</verse>
				<verse number="11">የዋ​ሆች ግን ምድ​ርን ይወ​ር​ሳሉ፥ በብ​ዙም ሰላም ደስ ይላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="12">ኀጢ​አ​ተኛ ጻድ​ቁን ይመ​ለ​ካ​ከ​ተ​ዋል፥ ጥር​ሱ​ንም በእ​ርሱ ላይ ያፋ​ጫል።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ይሥ​ቅ​በ​ታል፥ ቀኑ እን​ደ​ሚ​ደ​ርስ አስ​ቀ​ድሞ ዐው​ቆ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="14">ኃጥ​ኣን ሰይ​ፋ​ቸ​ውን መዘዙ፥ ቀስ​ታ​ቸ​ው​ንም ገተሩ ድሃ​ው​ንና ችግ​ረ​ኛ​ውን ይገ​ድሉ ዘንድ፥ ልበ ቅኖ​ች​ንም ይወጉ ዘንድ፤</verse>
				<verse number="15">ሰይ​ፋ​ቸው ወደ ልባ​ቸው ይግባ፥ ቀስ​ታ​ቸ​ውም ይሰ​በር።</verse>
				<verse number="16">በእ​ው​ነት ያለ ጥቂት ከብዙ የኃ​ጥ​ኣን ሀብት ይበ​ል​ጣል።</verse>
				<verse number="17">የኃ​ጥ​ኣን ኀይ​ላ​ቸው ይሰ​በ​ራ​ልና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድ​ቃ​ንን ይደ​ግ​ፋ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="18">የን​ጹ​ሓ​ንን መን​ገድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያው​ቃል፥ ርስ​ታ​ቸ​ውም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነው፤</verse>
				<verse number="19">በክፉ ዘመ​ንም አያ​ፍ​ሩም፤ በራብ ዘመ​ንም ይጠ​ግ​ባሉ።</verse>
				<verse number="20">ኃጥ​ኣን ግን ይጠ​ፋሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶች በከ​በ​ሩና ከፍ ከፍ ባሉ ጊዜ እንደ ጢስ ይጠ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="21">ኀጢ​አ​ተኛ ይበ​ደ​ራል፥ አይ​ከ​ፍ​ል​ምም፤ ጻድቅ ግን ይራ​ራል፥ ይሰ​ጣ​ልም።</verse>
				<verse number="22">እር​ሱን የሚ​ባ​ር​ኩት ምድ​ርን ይወ​ር​ሳ​ሉና፤ የሚ​ረ​ግ​ሙት ግን ይጠ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="23">የሰው አካ​ሄዱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይጸ​ናል፥ መን​ገ​ዱ​ንም እጅግ ይወ​ድ​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="24">ቢወ​ድ​ቅም አይ​ደ​ነ​ግ​ጥም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጁን ይዞ ይደ​ግ​ፈ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="25">ጐለ​መ​ስሁ፥ አረ​ጅ​ሁም፤ ጻድቅ ግን ሲጠፋ አላ​የ​ሁም፤ ዘሩም እህ​ልን አይ​ቸ​ገ​ርም።</verse>
				<verse number="26">ሁል​ጊዜ ይራ​ራል፤ ያበ​ድ​ራ​ልም፤ ዘሩም በበ​ረ​ከት ይኖ​ራል።</verse>
				<verse number="27">ከክፉ ሽሽ፥ መል​ካ​ሙ​ንም አድ​ርግ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ትኖ​ራ​ለህ።</verse>
				<verse number="28">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቅን ይወ​ድ​ዳ​ልና፥ ጻድ​ቃ​ኑ​ንም አይ​ጥ​ላ​ቸ​ው​ምና፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ይጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋል፤ ለን​ጹ​ሓ​ንም ይበ​ቀ​ል​ላ​ቸ​ዋል፤ የኃ​ጥ​ኣ​ንን ዘር ግን ያጠ​ፋል።</verse>
				<verse number="29">ጻድ​ቃን ምድ​ርን ይወ​ር​ሳሉ፥ በእ​ር​ስ​ዋም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራሉ።</verse>
				<verse number="30">የጻ​ድቅ አፉ ጥበ​ብን ይማ​ራል፥ አን​ደ​በ​ቱም ጽድ​ቅን ይና​ገ​ራል።</verse>
				<verse number="31">የአ​ም​ላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው፥ ሰኰ​ና​ውም አይ​ሰ​ና​ከ​ልም።</verse>
				<verse number="32">ኀጢ​አ​ተኛ ጻድ​ቁን ይመ​ለ​ከ​ተ​ዋል፥ ሊገ​ድ​ለ​ውም ይወ​ድ​ዳል።</verse>
				<verse number="33">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በእጁ አይ​ተ​ወ​ውም፥ በተ​ፋ​ረ​ደ​ውም ጊዜ አያ​ሸ​ን​ፈ​ውም።</verse>
				<verse number="34">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደጅ ጥናው፥ መን​ገ​ዱ​ንም ጠብቅ፥ ምድ​ር​ንም ትወ​ርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ግ​ሃል፤ ኃጥ​ኣ​ንም ሲጠፉ ታያ​ለህ።</verse>
				<verse number="35">ኀጢ​አ​ተ​ኛን ከፍ ከፍ ብሎ፥ እንደ ሊባ​ኖስ ዛፍም ረዝሞ አየ​ሁት።</verse>
				<verse number="36">ብመ​ለስ ግን አጣ​ሁት፤ ፈለ​ግ​ሁት፥ ቦታ​ው​ንም አላ​ገ​ኘ​ሁ​ትም።</verse>
				<verse number="37">ቅን​ነ​ትን ጠብቅ፥ ጽድ​ቅ​ንም እይ፤ ለሰ​ላም ሰው ቅሬት አለ​ውና።</verse>
				<verse number="38">ዐመ​ፀ​ኞች ግን በአ​ን​ድ​ነት ይጠ​ፋሉ፤ የኃ​ጥ​ኣ​ንም ቅሬ​ቶች ይጠ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="39">የጻ​ድ​ቃን መድ​ኀ​ኒ​ታ​ቸው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነው፤ በመ​ከ​ራ​ቸ​ውም ጊዜ ጠባ​ቂ​ያ​ቸው እርሱ ነው።</verse>
				<verse number="40">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይረ​ዳ​ቸ​ዋል፥ ያድ​ና​ቸ​ዋ​ልም፥ ከኃ​ጥ​ኣ​ንም እጅ ያወ​ጣ​ቸ​ዋል፥ ያድ​ና​ቸ​ዋ​ልም፥ በእ​ርሱ ታም​ነ​ዋ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="37">
				<verse number="1">አቤቱ፥ በመ​ዓ​ትህ አት​ቅ​ሠ​ፈኝ፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ት​ህም አት​ገ​ሥ​ጸኝ።</verse>
				<verse number="2">ፍላ​ጾ​ችህ ወግ​ተ​ው​ኛ​ልና፥ እጅ​ህ​ንም በእኔ ላይ አክ​ብ​ደ​ህ​ብ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="3">ከቍ​ጣህ ፊት የተ​ነሣ ለሥ​ጋዬ ድኅ​ነት የለ​ውም፤ ከኀ​ጢ​አ​ቴም ፊት የተ​ነሣ ለአ​ጥ​ን​ቶቼ ሰላም የላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="4">ኀጢ​አቴ ከራሴ ጠጕር በዝ​ቷ​ልና፥ እንደ ከባድ ሸክ​ምም በላዬ ከብ​ዶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="5">ከስ​ን​ፍ​ና​ዬም ፊት የተ​ነሣ አጥ​ን​ቶቼ ሸተቱ፥ በሰ​በ​ሱም፤</verse>
				<verse number="6">እጅግ ጐሰ​ቈ​ልሁ፥ ጐበ​ጥ​ሁም፥ ሁል​ጊ​ዜም በት​ካዜ እመ​ላ​ለ​ሳ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="7">ነፍሴ ስድ​ብን ጠግ​ባ​ለ​ችና፥ ለሥ​ጋ​ዬም ድኅ​ነ​ትን አጣሁ።</verse>
				<verse number="8">ታመ​ምሁ እጅ​ግም ተሠ​ቃ​የሁ፥ ከል​ቤም ኀዘን የተ​ነሣ እጮ​ኻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">አቤቱ፥ ፈቃዴ ሁሉ በፊ​ትህ ነው፥ ጩኸ​ቴም ከአ​ንተ አይ​ሰ​ወ​ርም።</verse>
				<verse number="10">ልቤ ደነ​ገ​ጠ​ብኝ፥ ኀይ​ሌም ተወኝ፥ የዐ​ይ​ኖ​ቼም ብር​ሃን ፈዘ​ዘ​ብኝ።</verse>
				<verse number="11">ወዳ​ጆቼም ባል​ን​ጀ​ሮ​ቼም ባላ​ጋራ ሆኑኝ፥ ከበ​ውም ደበ​ደ​ቡኝ፥ ዘመ​ዶቼም ተስፋ ቈር​ጠው ተለ​ዩኝ።</verse>
				<verse number="12">ነፍ​ሴ​ንም የሚ​ሹ​አት በረ​ቱ​ብኝ፥ መከ​ራ​ዬ​ንም የሚ​ፈ​ልጉ ከን​ቱን ተና​ገሩ፥ ሁል​ጊ​ዜም ያጠ​ፉኝ ዘንድ በሽ​ን​ገላ ይመ​ክ​ራሉ።</verse>
				<verse number="13">እኔ ግን እን​ደ​ማ​ይ​ሰማ ደን​ቆሮ፥ አፉ​ንም እን​ደ​ማ​ይ​ከ​ፍት ዲዳ ሆንሁ።</verse>
				<verse number="14">እን​ደ​ማ​ይ​ሰማ ሰው፥ በአ​ፉም መና​ገር እን​ደ​ማ​ይ​ችል ሰው ሆንሁ።</verse>
				<verse number="15">አቤቱ፥ በአ​ንተ ታም​ኛ​ለ​ሁና፤ አቤቱ አም​ላኬ፥ አንተ ስማኝ።</verse>
				<verse number="16">የጠ​ላ​ቶቼ መዘ​ባ​በቻ አታ​ድ​ር​ገኝ ብያ​ለ​ሁና፥ እግ​ሬም ቢሰ​ና​ከል በእኔ ላይ ብዙ ነገ​ርን ይና​ገ​ራሉ።</verse>
				<verse number="17">እኔ​ንስ ይገ​ር​ፉኝ ዘንድ አቈ​ዩኝ፥ ቍስሌ ሁል​ጊዜ በፊቴ ነውና።</verse>
				<verse number="18">በደ​ሌን እና​ገ​ራ​ለ​ሁና፥ ስለ ኀጢ​አ​ቴም እተ​ክ​ዛ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">ጠላ​ቶቼ ሕያ​ዋን ናቸው፥ ይበ​ረ​ቱ​ብ​ኛ​ልም፥ በዐ​መ​ፃም የሚ​ጠ​ሉኝ በዙ።</verse>
				<verse number="20">በበጎ ፋንታ ክፉን የሚ​መ​ል​ሱ​ልኝ ጽድ​ቅን ስለ ተከ​ተ​ልሁ ይከ​ስ​ሱ​ኛል። እንደ ርኩስ በድን ወን​ድ​ማ​ቸ​ውን ጣሉ፥</verse>
				<verse number="21">አቤቱ፥ አንተ አት​ጣ​ለኝ፤ አም​ላኬ፥ ከእኔ አት​ራቅ።</verse>
				<verse number="22">አቤቱ፥ የመ​ድ​ኀ​ኒቴ አም​ላክ ሆይ፥ እኔን ለመ​ር​ዳት ፍጠን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="38">
				<verse number="1">“በአ​ን​ደ​በቴ እን​ዳ​ል​ስት አፌን እጠ​ብ​ቃ​ለሁ፤ ኃጥ​ኣን በፊቴ በተ​ቃ​ወ​ሙኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖ​ራ​ለሁ” አልሁ፤</verse>
				<verse number="2">ዝም አልሁ ራሴ​ንም አዋ​ረ​ድሁ፥ ለበጎ ነገ​ርም ዝም አልሁ፥ ቍስ​ሌም ታደ​ሰ​ብኝ።</verse>
				<verse number="3">ልቤም በው​ስጤ ሞቀ​ብኝ፤ ከመ​ና​ገ​ሬም የተ​ነሣ እሳት ነደደ፥ በአ​ን​ደ​በ​ቴም ተና​ገ​ርሁ፦</verse>
				<verse number="4">“አቤቱ፥ ፍጻ​ሜ​ዬን አስ​ታ​ው​ቀኝ” አልሁ፥ የዘ​መኔ ቍጥ​ሮች ምን ያህል ናቸው? ዐውቅ ዘን​ድስ ለምን ወደ ኋላ እላ​ለሁ?</verse>
				<verse number="5">እነሆ፥ ዘመ​ኖቼን አስ​ረ​ጀ​ሃ​ቸው፤ አካ​ሌም በፊ​ትህ እንደ ኢም​ንት ነው። ነገር ግን የሰው ልጅ ሁሉ ከንቱ ነው።</verse>
				<verse number="6">ሰው ሁሉ እንደ ጥላ ይመ​ላ​ለ​ሳል፥ ነገር ግን በከ​ንቱ ይታ​ወ​ካሉ። ያከ​ማ​ቻሉ የሚ​ሰ​በ​ስ​ቡ​ለ​ት​ንም አያ​ው​ቁም።</verse>
				<verse number="7">አሁ​ንስ ተስ​ፋዬ ማን ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ምን? ትዕ​ግ​ሥ​ቴም ከአ​ንተ ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="8">ከኀ​ጢ​አቴ ሁሉ አዳ​ን​ኸኝ፥ ለሰ​ነ​ፎ​ችም ስድብ አደ​ረ​ግ​ኸኝ።</verse>
				<verse number="9">ዝም አልሁ አፌ​ንም አል​ከ​ፈ​ት​ሁም። አንተ ፈጥ​ረ​ኸ​ኛ​ልና፤</verse>
				<verse number="10">መቅ​ሠ​ፍ​ት​ህን ከእኔ አርቅ፥ ከእ​ጅህ ብር​ታት የተ​ነሣ አል​ቄ​አ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="11">በተ​ግ​ሣ​ጽህ ስለ ኀጢ​አቱ ሰውን ዘለ​ፍ​ኸው፥ ሰው​ነ​ቱ​ንም እንደ ሸረ​ሪት አቀ​ለ​ጥ​ኻት፤ ነገር ግን ሰዎች ሁሉ በከ​ንቱ ይታ​ወ​ካሉ።</verse>
				<verse number="12">አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን ስማ፥ ልመ​ና​ዬ​ንም አድ​ምጥ፥ ልቅ​ሶ​ዬ​ንም አድ​ምጥ፥ ቸልም አት​በ​ለኝ፤ እኔ በም​ድር ላይ መጻ​ተኛ ነኝና፥ እንደ አባ​ቶ​ችም ሁሉ እን​ግዳ ነኝና።</verse>
				<verse number="13">ወደ​ማ​ል​መ​ለ​ስ​በት ሳል​ሄድ ዐርፍ ዘንድ ተወኝ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="39">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በት​ዕ​ግ​ሥት ደጅ ጠና​ሁት፥ እር​ሱም ተመ​ልሶ ሰማኝ፥ የል​መ​ና​ዬ​ንም ቃል ሰማኝ።</verse>
				<verse number="2">ከጥ​ፋት ጕድ​ጓድ ከረ​ግ​ረግ ጭቃም አወ​ጣኝ፥ እግ​ሮ​ቼ​ንም በዓ​ለት ላይ አቆ​ማ​ቸው፥ አረ​ማ​መ​ዴ​ንም አጸና።</verse>
				<verse number="3">አዲስ ምስ​ጋ​ናን በአፌ ጨመረ፥ ይህም የአ​ም​ላ​ካ​ችን ምስ​ጋ​ናው ነው፤ ብዙ​ዎች አይ​ተው ይፍሩ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይታ​መኑ።</verse>
				<verse number="4">መታ​መ​ኛው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የሆነ፥ ወደ ከንቱ ነገር፥ ወደ ቍጣና ወደ ሐሰ​ትም፥ ያል​ተ​መ​ለ​ከተ ሰው ብፁዕ ነው።</verse>
				<verse number="5">አቤቱ አም​ላኬ፥ ብዙ ተአ​ም​ራ​ት​ህን አደ​ረ​ግህ፥ አሳ​ብ​ህ​ንም ምንም የሚ​መ​ስ​ለው የለም፤ አወ​ራሁ፥ ተና​ገ​ርሁ፥ ከቍ​ጥ​ርም በዛ።</verse>
				<verse number="6">መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና ቍር​ባ​ንን አል​ወ​ደ​ድ​ሁም፤ ሥጋ​ህን አን​ጻ​ልኝ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንና ስለ ኀጢ​አት የሚ​ቀ​ር​በ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አል​ወ​ደ​ድ​ሁም።</verse>
				<verse number="7">በዚ​ያን ጊዜ አልሁ፥ “እነሆ፥ መጣሁ፤ ስለ እኔ በመ​ጽ​ሐፍ ራስ ተጽ​ፎ​አል፤</verse>
				<verse number="8">አም​ላኬ ሆይ፥ ፈቃ​ድ​ህን ለማ​ድ​ረግ መከ​ርሁ፥ ሕግ​ህም በልቤ ውስጥ ነው።”</verse>
				<verse number="9">በታ​ላቅ ጉባኤ ጽድ​ቅ​ህን አወ​ራሁ፤ እነሆ፥ ከን​ፈ​ሮ​ችን አል​ከ​ለ​ክ​ልም፤ አቤቱ፥ አንተ ጽድ​ቄን ታው​ቃ​ለህ።</verse>
				<verse number="10">ቅን​ነ​ት​ህን በልቤ ውስጥ አል​ሰ​ወ​ር​ሁም፥ ማዳ​ን​ህ​ንም ተና​ገ​ርሁ፤ ይቅ​ር​ታ​ህ​ንና ምሕ​ረ​ት​ህን ከታ​ላቅ ጉባኤ አል​ሰ​ወ​ር​ሁም።</verse>
				<verse number="11">አቤቱ አንተ ይቅ​ር​ታ​ህን ከእኔ አታ​ርቅ፤ ቸር​ነ​ት​ህና እው​ነ​ትህ ዘወ​ትር ያግ​ኙኝ።</verse>
				<verse number="12">ቍጥር የሌ​ላት ክፋት አግ​ኝ​ታ​ኛ​ለ​ችና፤ ኀጢ​አ​ቶቼ ተገ​ና​ኙኝ፥ ማየ​ትም ተስ​ኖ​ኛል፤ ከራሴ ጠጕር ይልቅ በዙ፥ ልቤም ተወኝ።</verse>
				<verse number="13">አቤቱ፥ ታድ​ነኝ ዘንድ ፍቀድ፤ አቤቱ፥ እኔን ለመ​ር​ዳት ተመ​ል​ከት።</verse>
				<verse number="14">ነፍ​ሴን ለማ​ጥ​ፋት የሚ​ወ​ድዱ ይፈሩ፥ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ይጐ​ስ​ቍሉ፤ በእኔ ላይ ክፋ​ትን ለማ​ድ​ረግ የሚ​ወ​ድዱ ወደ ኋላ​ቸው ይመ​ለሱ፥ ይፈ​ሩም።</verse>
				<verse number="15">እሰይ፥ እሰይ የሚ​ሉኝ እፍ​ረ​ታ​ቸ​ውን ወዲ​ያ​ውኑ ይከ​ፈሉ።</verse>
				<verse number="16">አቤቱ፥ የሚ​ፈ​ል​ጉህ ሁሉ በአ​ንተ ደስ ይበ​ላ​ቸው፥ ሐሤ​ት​ንም ያድ​ርጉ፤ ሁል​ጊዜ ማዳ​ን​ህን የሚ​ወዱ ዘወ​ትር፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው ይበሉ።</verse>
				<verse number="17">እኔ ድሃና ምስ​ኪን ነኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ያስ​ብ​ል​ኛል፤ አንተ ረዳ​ቴና መድ​ኀ​ኒቴ ነህ፤ አም​ላኬ ሆይ፥ አት​ዘ​ግይ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="40">
				<verse number="1">ለድ​ሃና ለም​ስ​ኪን የሚ​ያ​ስብ ብፁዕ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከክፉ ቀን ያድ​ነ​ዋል።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ብ​ቀ​ዋል፥ ሕያ​ውም ያደ​ር​ገ​ዋል፥ በም​ድር ላይም ያስ​መ​ሰ​ግ​ነ​ዋል፥ በጠ​ላ​ቶቹ እጅ አሳ​ልፎ አይ​ሰ​ጠ​ውም።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በደ​ዌው አልጋ ሳለ ይረ​ዳ​ዋል፤ መኝ​ታ​ው​ንም ሁሉ ከበ​ሽ​ታው የተ​ነሣ ይለ​ው​ጥ​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="4">እኔስ፥ “አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፤ አን​ተን በድ​ያ​ለ​ሁና ለነ​ፍሴ አስ​ተ​ስ​ር​ይ​ላት” አልሁ።</verse>
				<verse number="5">ጠላ​ቶ​ቼም በላዬ ክፋ​ትን ይና​ገ​ራሉ፦ “መቼ ይሞ​ታል? ስሙስ መቼ ይሻ​ራል?” ይላሉ።</verse>
				<verse number="6">ከን​ቱን የሚ​ና​ገር ይግ​ባና ይይ፤ ልቡ በላዩ ላይ ኀጢ​አ​ትን ሰበ​ሰበ፤ ወደ ሜዳ ይወ​ጣል ይና​ገ​ራ​ልም፥ በእ​ኔም ላይ ይተ​ባ​በ​ራል።</verse>
				<verse number="7">ጠላ​ቶ​ቼም ሁሉ ይጠ​ቃ​ቀ​ሱ​ብ​ኛል፥ በእኔ ላይም ክፋ​ትን ይመ​ክ​ራሉ።</verse>
				<verse number="8">የበ​ደ​ልን ነገር በእኔ አወጡ። የተኛ ሰው ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​ነ​ቃ​ምን?</verse>
				<verse number="9">ደግሞ የሰ​ላሜ ሰው የታ​መ​ን​ሁ​በት፥ እን​ጀ​ራ​ዬን የበላ በእኔ ላይ ተረ​ከ​ዙን አነሣ።</verse>
				<verse number="10">አንተ ግን አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፥ እመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ውም ዘንድ አስ​ነ​ሣኝ።</verse>
				<verse number="11">ስለ​ዚህ እንደ ወደ​ድ​ኸኝ ዐወ​ቅሁ። ጠላ​ቶቼ በእኔ ደስ አላ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="12">እኔን ግን ስለ የዋ​ህ​ነቴ ተቀ​በ​ል​ኸኝ፥ በፊ​ት​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጸ​ና​ኸኝ።</verse>
				<verse number="13">የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ይሁን፥ ይሁን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="41">
				<verse number="1">ዋሊያ ወደ ውኃ ምን​ጮች እን​ደ​ሚ​ና​ፍቅ፥ እን​ዲሁ ነፍሴ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትና​ፍ​ቃ​ለች።</verse>
				<verse number="2">ነፍሴ ወደ ሕያው አም​ላኬ ተጠ​ማች፤ መቼ እደ​ር​ሳ​ለሁ? የአ​ም​ላ​ኬ​ንስ ፊት መቼ አያ​ለሁ?</verse>
				<verse number="3">ዘወ​ትር፥ “አም​ላ​ክህ ወዴት ነው?” ይሉ​ኛ​ልና እን​ባዬ በቀ​ንና በሌ​ሊት ምግብ ሆነኝ።</verse>
				<verse number="4">ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰ​ሰች፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ምስ​ጋና መኖ​ሪያ ስፍራ እገ​ባ​ለ​ሁና፤ በዓ​ልን የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሰዎች በም​ስ​ጋ​ናና በደ​ስታ ቃል ሲያ​መ​ሰ​ግኑ ተሰሙ።</verse>
				<verse number="5">ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝ​ኛ​ለሽ? ለም​ንስ ታው​ኪ​ኛ​ለሽ? የፊ​ቴን መድ​ኀ​ኒት አም​ላ​ኬን አመ​ሰ​ግ​ነው ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኚ።</verse>
				<verse number="6">ነፍሴ በእኔ ውስጥ ታወ​ከች፤ ስለ​ዚህ አቤቱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ምድር፥ በአ​ር​ሞ​ን​ኤ​ምም በታ​ናሹ ተራራ አስ​ብ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">በፍ​ዋ​ፍ​ዋ​ቴህ ድምፅ ቀላይ ቀላ​ይን ትጠ​ራ​ዋ​ለች፤ ማዕ​በ​ል​ህና ሞገ​ድህ ሁሉ በላዬ አለፈ።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀን ይቅ​ር​ታ​ውን ያዝ​ዛል፥ በሌ​ሊ​ትም እር​ሱን ይና​ገ​ራል፤ ከእኔ ዘንድ የሕ​ይ​ወቴ ብፅ​ዐት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ሁት፥ “አንተ አም​ላኬ ነህ፤ ለምን ረሳ​ኸኝ? ጠላ​ቶቼ ሲያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ለምን ተው​ኸኝ? ለም​ንስ አዝኜ እመ​ለ​ሳ​ለሁ?” ጠላ​ቶቼ ሁሉ አጥ​ን​ቶ​ቼን እየ​ቀ​ለ​ጣ​ጠሙ ሰደ​ቡኝ።</verse>
				<verse number="10">ሁል​ጊዜ፥ “አም​ላ​ክህ ወዴት ነው?” ይሉ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="11">ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝ​ኛ​ለሽ? ለም​ንስ ታው​ኪ​ኛ​ለሽ? የፊ​ቴን መድ​ኀ​ኒት አም​ላ​ኬን አመ​ሰ​ግ​ነው ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኚ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="42">
				<verse number="1">አቤቱ፥ ፍረ​ድ​ልኝ፥ ከጽ​ድቅ ከወጡ ሕዝ​ብም በቀ​ሌን ተበ​ቀል። ከዐ​መ​ፀ​ኛና ከሸ​ን​ጋይ ሰው አድ​ነኝ።</verse>
				<verse number="2">አንተ አም​ላኬ፥ ኀይ​ሌም ነህና፥ ለምን ትተ​ወ​ኛ​ለህ? ጠላ​ቶቼ ቢያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ለምን አዝኜ እመ​ለ​ሳ​ለሁ?</verse>
				<verse number="3">ብር​ሃ​ን​ህ​ንና ጽድ​ቅ​ህን ላክ፤ እነ​ር​ሱም ይም​ሩኝ፥ አቤቱ ወደ መቅ​ደ​ስህ ተራ​ራና ወደ ማደ​ሪ​ያህ ይው​ሰ​ዱኝ።</verse>
				<verse number="4">ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ፥ ጐል​ማ​ስ​ነ​ቴ​ንም ደስ ወዳ​ሰ​ኛት ወደ አም​ላኬ እገ​ባ​ለሁ፤ አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ በመ​ሰ​ንቆ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝ​ኛ​ለሽ? ለም​ንስ ታው​ኪ​ኛ​ለሽ? የፊ​ቴን መድ​ኀ​ኒት አም​ላ​ኬን አመ​ሰ​ግ​ነው ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኚ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="43">
				<verse number="1">አቤቱ፥ በጆ​ሮ​አ​ችን ሰማን፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም በዘ​መ​ና​ቸው በቀ​ድሞ ዘመን የሠ​ራ​ኸ​ውን ሥራ ነገ​ሩን።</verse>
				<verse number="2">እጅህ ጠላ​ትን አጠ​ፋች፥ እነ​ር​ሱ​ንም ተከ​ልህ፤ አሕ​ዛ​ብን አሠ​ቃ​የ​ኻ​ቸው፥ አሳ​ደ​ድ​ኻ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="3">በጦ​ራ​ቸው ምድ​ርን አል​ወ​ረ​ሱም፥ ክን​ዳ​ቸ​ውም አላ​ዳ​ና​ቸ​ውም፤ ቀኝ​ህና ክን​ድህ የፊ​ት​ህም ብር​ሃን ነው እንጂ፤ ይቅር ብለ​ሃ​ቸ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="4">አም​ላ​ኬና ንጉሤ አንተ ነህ፤ ለያ​ዕ​ቆብ መድ​ኀ​ኒ​ትን ያዘ​ዝህ።</verse>
				<verse number="5">በአ​ንተ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንን ሁሉ እን​ወ​ጋ​ቸ​ዋ​ለን፥ በስ​ም​ህም በላ​ያ​ችን የቆ​ሙ​ትን እና​ዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለን።</verse>
				<verse number="6">በቀ​ስቴ የም​ታ​መን አይ​ደ​ለ​ሁም፥ ጦሬም አያ​ድ​ነ​ኝም፤</verse>
				<verse number="7">አንተ ግን ከከ​በ​ቡን አዳ​ን​ኸን፥ የሚ​ጠ​ሉ​ን​ንም ሁሉ አሳ​ፈ​ር​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">ሁል​ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ከ​ብ​ራ​ለን፥ ስም​ህ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም እና​መ​ሰ​ግ​ና​ለን።</verse>
				<verse number="9">አሁን ግን ጣል​ኸን፥ አሳ​ፈ​ር​ኸ​ንም፥ አም​ላ​ካ​ችን፥ ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ችን ጋር አት​ወ​ጣም።</verse>
				<verse number="10">በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን ዘንድ ወደ ኋላ​ችን መለ​ስ​ኸን፥ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንም ተነ​ጣ​ጠ​ቁን።</verse>
				<verse number="11">እንደ በጎች ሊበ​ሉን ሰጠ​ኸን፥ ወደ አሕ​ዛ​ብም በተ​ን​ኸን፥</verse>
				<verse number="12">ሕዝ​ብ​ህን ያለ ዋጋ ሰጠህ፥ ለእ​ል​ል​ታ​ች​ንም ብዛት የለ​ውም።</verse>
				<verse number="13">ለጎ​ረ​ቤ​ቶ​ቻ​ችን ስድብ፥ በዙ​ሪ​ያ​ች​ንም ላሉ መሣ​ቂ​ያና መዘ​በቻ አደ​ረ​ግ​ኸን።</verse>
				<verse number="14">ለአ​ሕ​ዛብ ተረት፥ ለሕ​ዝ​ቡም የራስ መነ​ቅ​ነ​ቂያ አደ​ረ​ግ​ኸን።</verse>
				<verse number="15">እፍ​ረቴ ሁል​ጊዜ በፊቴ ነው፥ እፍ​ረት ፊቴን ሸፈ​ነኝ።</verse>
				<verse number="16">ከሚ​ሳ​ደ​ብና ከሚ​ላ​ገድ ቃል የተ​ነሣ፥ ከሚ​ከ​ብብ ጠላት ፊት የተ​ነሣ ነው።</verse>
				<verse number="17">ይህ ሁሉ በእኛ ላይ ደረሰ፥ አል​ረ​ሳ​ን​ህም፥ ኪዳ​ን​ህ​ንም አላ​ፈ​ረ​ስ​ንም።</verse>
				<verse number="18">ልባ​ች​ንም ወደ ኋላው አል​ተ​መ​ለ​ሰም፥ ፍለ​ጋ​ች​ንም ከመ​ን​ገ​ድህ ፈቀቅ አላ​ለም፤</verse>
				<verse number="19">በክፉ ስፍራ አዋ​ር​ደ​ኸ​ና​ልና፥ የሞት ጥላም ሰው​ሮ​ና​ልና፥</verse>
				<verse number="20">የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ስም ረስ​ተ​ንስ ቢሆን፥ እጃ​ች​ን​ንም ወደ ሌላ አም​ላክ አን​ሥ​ተ​ንስ ቢሆን፥</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን በተ​መ​ራ​መ​ረው ነበር! እርሱ ልባ​ችን የሰ​ወ​ረ​ውን ያው​ቃ​ልና።</verse>
				<verse number="22">ስለ እርሱ ሁል​ጊዜ ይገ​ድ​ሉ​ና​ልና፥ እን​ደ​ሚ​ታ​ረ​ዱም በጎች ሆነ​ናል።</verse>
				<verse number="23">አቤቱ፥ ንቃ፤ ለም​ንስ ትተ​ኛ​ለህ? ተነሥ፥ ለዘ​ወ​ት​ርም አት​ጣ​ለን።</verse>
				<verse number="24">ለም​ንስ ፊት​ህን ከእኛ ትመ​ል​ሳ​ለህ? መከ​ራ​ች​ን​ንና ችግ​ራ​ች​ን​ንስ ለምን ትረ​ሳ​ለህ?</verse>
				<verse number="25">ነፍ​ሳ​ችን በመ​ሬት ላይ ተጐ​ሳ​ቍ​ላ​ለ​ችና፥ ሆዳ​ች​ንም ወደ ምድር ተጣ​ብ​ቃ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="26">አቤቱ፥ ተነ​ሥና ርዳን፥ ስለ ስም​ህም ተቤ​ዥን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="44">
				<verse number="1">ልቤ መል​ካም ነገ​ርን ተና​ገረ፥ እኔም ሥራ​ዬን ለን​ጉሥ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ አን​ደ​በቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው።</verse>
				<verse number="2">ውበቱ ከሰው ልጆች ይልቅ ያም​ራል፤ ሞገስ ከከ​ን​ፈ​ሮ​ችህ ፈሰሰ፤ ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባረ​ከህ።</verse>
				<verse number="3">ኀያል ሆይ፥ በደም ግባ​ት​ህና በው​በ​ትህ፥ ሰይ​ፍ​ህን በወ​ገ​ብህ ታጠቅ።</verse>
				<verse number="4">ስለ ቅን​ነ​ትና ስለ የዋ​ህ​ነት ስለ ጽድ​ቅም አቅና፥ ተከ​ና​ወን፥ ንገ​ሥም፤ ቀኝ​ህም በክ​ብር ይመ​ራ​ሃል።</verse>
				<verse number="5">ኀያል ሆይ፥ ፍላ​ጻ​ዎ​ችህ የተ​ሳሉ ናቸው፥ አሕ​ዛብ በበ​ታ​ችህ ይወ​ድ​ቃሉ። በን​ጉሥ ጠላ​ቶች ልብ ውስጥ ይገ​ባሉ፥</verse>
				<verse number="6">አም​ላክ ሆይ፥ ዙፋ​ንህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነው፤ በትረ መን​ግ​ሥ​ትህ የጽ​ድቅ በትር ነው።</verse>
				<verse number="7">ጽድ​ቅን ወደ​ድህ፥ ዐመ​ፃ​ንም ጠላህ፤ ስለ​ዚህ ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ችህ ይልቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ የደ​ስታ ዘይ​ትን ቀባህ።</verse>
				<verse number="8">ከር​ቤና ሽቱ ዝባ​ድም በል​ብ​ሶ​ችህ ናቸው።</verse>
				<verse number="9">የን​ግ​ሥት ሴቶች ልጆች ለክ​ብ​ርህ ናቸው፤ በወ​ርቅ ልብስ ተጐ​ና​ጽ​ፋና ተሸ​ፋ​ፍና ንግ​ሥ​ቲቱ በቀ​ኝህ ትቆ​ማ​ለች።</verse>
				<verse number="10">ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ፥ ጆሮ​ሽ​ንም አዘ​ን​ብዪ፤ ወገ​ን​ሽን ያባ​ት​ሽ​ንም ቤት እርሺ፤</verse>
				<verse number="11">ንጉሥ ውበ​ት​ሽን ወድ​ዶ​አ​ልና፥ እርሱ ጌታሽ ነውና።</verse>
				<verse number="12">የጢ​ሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መን​ሻን ይዘው ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል። የም​ድር ባለ​ጠ​ጎች አሕ​ዛብ ሁሉ በፊ​ትሽ ይማ​ለ​ላሉ።</verse>
				<verse number="13">ለሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ ሴት ልጅ ሁሉ ክብ​ርዋ ነው፤ በወ​ርቀ ዘቦ ልብስ የተ​ጐ​ና​ጸ​ፈ​ችና የተ​ሸ​ፋ​ፈ​ነች ናት።</verse>
				<verse number="14">በኋ​ላዋ ደና​ግ​ሉን ለን​ጉሡ ይወ​ስ​ዳሉ፥ ባል​ን​ጀ​ሮ​ች​ዋ​ንም ወደ አንተ ያቀ​ር​ባሉ፤</verse>
				<verse number="15">በደ​ስ​ታና በሐ​ሤት ይወ​ስ​ዱ​አ​ቸ​ዋል። ወደ ንጉሥ እል​ፍ​ኝም ያስ​ገ​ቡ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="16">በአ​ባ​ቶ​ችሽ ፋንታ ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ልሽ፥ በም​ድ​ርም ሁሉ ላይ ገዥ​ዎች አድ​ር​ገሽ ትሾ​ሚ​ያ​ቸ​ዋ​ለሽ።</verse>
				<verse number="17">ለልጅ ልጅ ሁሉ ስም​ሽን ያሳ​ስ​ባሉ፤ አቤቱ፥ ስለ​ዚህ ለዓ​ለ​ምና ለዘ​ለ​ዓ​ለም። አሕ​ዛብ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="45">
				<verse number="1">አም​ላ​ካ​ችን መጠ​ጊ​ያ​ች​ንና ኀይ​ላ​ችን ነው፤ ባገ​ኘን በታ​ላቅ መከ​ራም ጊዜ ረዳ​ታ​ችን ነው።</verse>
				<verse number="2">ስለ​ዚህ ምድር ብት​ነ​ዋ​ወጥ፥ ተራ​ሮ​ችም ወደ ባሕር ልብ ቢፈ​ልሱ አን​ፈ​ራም።</verse>
				<verse number="3">ውኆ​ቻ​ቸው ጮኹ ደፈ​ረ​ሱም፥ ተራ​ሮ​ችም ከኀ​ይሉ የተ​ነሣ ተና​ወጡ።</verse>
				<verse number="4">ፈሳሽ ወንዝ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከተማ ደስ ያሰ​ኛል፤ ልዑል ማደ​ሪ​ያ​ውን ቀደሰ።</verse>
				<verse number="5">እን​ዳ​ት​ታ​ወ​ክም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ልዋ ነው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔርም ፊት ለፊት ይረ​ዳ​ታል።</verse>
				<verse number="6">አሕ​ዛብ ደነ​ገጡ ነገ​ሥ​ታ​ትም ተመ​ለሱ፤ ልዑል ቃሉን ሰጠ፥ ምድ​ርም ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠች።</verse>
				<verse number="7">የሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፤ የያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ መጠ​ጊ​ያ​ችን ነው።</verse>
				<verse number="8">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ፥ በም​ድር ያደ​ረ​ገ​ው​ንም ተአ​ም​ራት እን​ድ​ታዩ ኑ።</verse>
				<verse number="9">ከም​ድር ዳርቻ ጦር​ነ​ትን ይሽ​ራል፤ ቀስ​ትን ይሰ​ብ​ራል፥ ጋሻ​ንም ይቀ​ጠ​ቅ​ጣል፥ በእ​ሳ​ትም የጦር መሣ​ሪ​ያን ያቃ​ጥ​ላል።</verse>
				<verse number="10">ልብ አድ​ርጉ፥ እኔም አም​ላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ፤ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላ​ለሁ፥ በም​ድ​ርም ላይ ከፍ ከፍ እላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">የሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፤ የያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ መጠ​ጊ​ያ​ችን ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="46">
				<verse number="1">አሕ​ዛብ ሁላ​ችሁ፥ እጆ​ቻ​ች​ሁን አጨ​ብ​ጭቡ፥ በደ​ስታ ቃልም ለአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እልል በሉ።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልዑል፥ ግሩ​ምም ነውና፥ በም​ድር ሁሉ ላይም ታላቅ ንጉሥ ነውና።</verse>
				<verse number="3">አሕ​ዛ​ብን ከእኛ በታች፥ ወገ​ኖ​ች​ንም ከእ​ግ​ራ​ችን በታች አስ​ገ​ዛ​ልን።</verse>
				<verse number="4">ለር​ስቱ እኛን መረ​ጠን፥ የያ​ዕ​ቆ​ብን ውበት የወ​ደደ።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ል​ልታ፥ ጌታ​ች​ንም በመ​ለ​ከት ድምፅ ዐረገ።</verse>
				<verse number="6">ዘምሩ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ዘምሩ፤ ዘምሩ፥ ለን​ጉ​ሣ​ችን ዘምሩ።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለም​ድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤ በማ​ስ​ተ​ዋል ዘምሩ፤</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ሕ​ዛብ ላይ ነገሠ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቅ​ዱስ ዙፋኑ ላይ ይቀ​መ​ጣል።</verse>
				<verse number="9">የአ​ሕ​ዛብ አለ​ቆች ከአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ ጋር ተሰ​በ​ሰቡ፤ የም​ድር ኀይ​ለ​ኞች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ከፍ ብለ​ዋ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="47">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው፤ በአ​ም​ላ​ካ​ችን ከተማ በመ​ቅ​ደሱ ተራራ ምስ​ጋ​ናው ብዙ ነው።</verse>
				<verse number="2">ለም​ድር ሁሉ ደስ​ታን የሚ​ያ​ዝዝ፥ የጽ​ዮን ተራ​ራ​ዎች በመ​ስዕ በኩል ናቸው። የታ​ላቁ ንጉሥ ከተማ ናት።</verse>
				<verse number="3">በተ​ቀ​በ​ሏት ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በረ​ከ​ት​ዋን ያው​ቃል</verse>
				<verse number="4">እነሆ፥ የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ተሰ​ብ​ስ​በው በአ​ን​ድ​ነት መጥ​ተ​ዋል።</verse>
				<verse number="5">እነ​ር​ሱስ ይህን አይ​ተው አደ​ነቁ፥ ደነ​ገጡ፥ ፈሩም።</verse>
				<verse number="6">መን​ቀ​ጥ​ቀ​ጥም ያዛ​ቸው፥ እንደ ወላ​ድም በዚያ አማጡ።</verse>
				<verse number="7">በኀ​ይ​ለኛ ነፋስ የተ​ር​ሴ​ስን መር​ከ​ቦች ትቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="8">እን​ደ​ሰ​ማን እን​ዲሁ አየን፥ በሠ​ራ​ዊት ጌታ ከተማ፥ በአ​ም​ላ​ካ​ችን ከተማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያጸ​ና​ታል።</verse>
				<verse number="9">አም​ላክ ሆይ፥ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይቅ​ር​ታ​ህን ተቀ​በ​ልን።</verse>
				<verse number="10">አም​ላክ ሆይ፥ እንደ ስምህ እን​ዲ​ሁም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስ​ጋ​ናህ ነው። ቀኝህ ጽድ​ቅን የተ​መላ ነው።</verse>
				<verse number="11">አቤቱ፥ ስለ ፍር​ድህ የጽ​ዮን ተራ​ሮች ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ የይ​ሁ​ዳም ሴቶች ልጆች ሐሤት ያደ​ር​ጋሉ።</verse>
				<verse number="12">ጽዮ​ንን ክበ​ቡ​አት፥ ዕቀ​ፉ​አ​ትም። በቅ​ጥ​ሮ​ች​ዋም ተና​ገሩ፤</verse>
				<verse number="13">በብ​ር​ታቷ ልባ​ች​ሁን አኑሩ፤ በረ​ከ​ቷ​ንም ትካ​ፈ​ላ​ላ​ችሁ ለሚ​መ​ጣ​ውም ትው​ልድ ትነ​ግሩ ዘንድ።</verse>
				<verse number="14">ለዓ​ለ​ምና ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይህ አም​ላ​ካ​ችን እንደ ሆነ፥ እር​ሱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጠ​ብ​ቀ​ናል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="48">
				<verse number="1">አሕ​ዛብ ሁላ​ችሁ፥ ይህን ስሙ፤ በዓ​ለም የም​ት​ኖ​ሩም ሁላ​ችሁ፥ አድ​ምጡ፤</verse>
				<verse number="2">የሰው ልጆች ባለ​ጠ​ጎ​ችና ድሆች፥ በየ​ሀ​ገ​ራ​ችሁ በአ​ን​ድ​ነት።</verse>
				<verse number="3">አፌ ጥበ​ብን ይና​ገ​ራል፥ የል​ቤም ዐሳብ ምክ​ርን፥</verse>
				<verse number="4">በጆ​ሮዬ ምሳሌ አደ​ም​ጣ​ለሁ፥ በበ​ገ​ናም ነገ​ሬን እገ​ል​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">ከክፉ ቀን ለምን እፈ​ራ​ለሁ? ኀጢ​አት ተረ​ከ​ዜን ከበ​በኝ፤</verse>
				<verse number="6">በኀ​ይ​ላ​ቸው የሚ​ታ​መኑ፥ በባ​ለ​ጠ​ግ​ነ​ታ​ቸ​ውም ብዛት የሚ​ኮሩ፤</verse>
				<verse number="7">ወን​ድም ወን​ድ​ሙን አያ​ድ​ንም፥ ሰውም አያ​ድ​ንም፤ ቤዛ​ው​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ሰ​ጥም፥</verse>
				<verse number="8">የነ​ፍ​ሱ​ንም ዋጋ ለውጥ፥</verse>
				<verse number="9">በዓ​ለም የደ​ከመ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይድ​ናል፥ ጥፋ​ትን አያ​ይ​ምና።</verse>
				<verse number="10">ጠቢ​ባ​ንን ሲሞቱ ባየ​ሃ​ቸው ጊዜ፥ እን​ደ​ዚሁ ልብ የሌ​ላ​ቸው ሰነ​ፎች ይጠ​ፋሉ፥ ገን​ዘ​ባ​ቸ​ው​ንም ለሌ​ሎች ይተ​ዋሉ።</verse>
				<verse number="11">መቃ​ብ​ራ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቤታ​ቸው ነው፥ ማደ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ለልጅ ልጅ ነው፤ በየ​ሀ​ገ​ራ​ቸ​ውም ስማ​ቸው ይጠ​ራል።</verse>
				<verse number="12">ሰው ግን ክቡር ሆኖ ሳለ አላ​ወ​ቀም፤ ልብ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው እን​ስ​ሶ​ችም ሆነ፥ መሰ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="13">በአ​ፋ​ቸው ሲወዱ፥ ራስዋ መን​ገ​ዳ​ቸው መሰ​ና​ክ​ላ​ቸው ናት፥</verse>
				<verse number="14">እንደ በጎች ሞት በሲ​ኦል ይጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋል፥ ቅኖ​ችም በማ​ለዳ ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፥ ረድ​ኤ​ታ​ቸ​ውም ከክ​ብ​ራ​ቸው ተለ​ይታ በሲ​ኦል ትጠ​ፋ​ለች።</verse>
				<verse number="15">ነገር ግን በሚ​ወ​ስ​ዱኝ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነፍ​ሴን ከሲ​ኦል እጅ ያድ​ና​ታል።</verse>
				<verse number="16">በበ​ለ​ጸገ ጊዜ፥ የቤ​ቱም ክብር በበዛ ጊዜ ሰውን አት​ፍ​ራው፥</verse>
				<verse number="17">በሚ​ሞት ጊዜ ከእ​ርሱ ጋር ምንም አይ​ወ​ስ​ድ​ምና፥ የቤ​ቱም ክብር ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር አይ​ወ​ር​ድ​ምና።</verse>
				<verse number="18">በሕ​ይ​ወቱ ሳለ ሰው​ነቱ ደስ ብሎ​አ​ታ​ልና ሰው መል​ካም ብታ​ደ​ር​ግ​ለት ያመ​ሰ​ግ​ን​ሃል።</verse>
				<verse number="19">ወደ አባ​ቶ​ቹም ዓለም ይወ​ር​ዳል፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ብር​ሃ​ንን አያ​ይም።</verse>
				<verse number="20">ሰው ግን ክቡር ሲሆን አላ​ወ​ቀም። ልብ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው እን​ስ​ሶ​ችም ሆነ፥ መሰ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="49">
				<verse number="1">የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገረ፥ ምድ​ር​ንም ጠራት፤ ከፀ​ሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግ​ቢ​ያዋ ድረስ።</verse>
				<verse number="2">ከክ​ብሩ ውበት ከጽ​ዮ​ንም፥</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ልጥ ይመ​ጣል። አም​ላ​ካ​ች​ንም ዝም አይ​ልም፤ እሳት በፊቱ ይነ​ድ​ዳል፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ብዙ ዐውሎ አለ።</verse>
				<verse number="4">በላይ ያለ​ውን ሰማ​ይን ምድ​ር​ንም በሕ​ዝቡ ለመ​ፍ​ረድ ይጠ​ራል፥</verse>
				<verse number="5">እንደ ሕጉ መሥ​ዋ​ዕ​ትን የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡ​ትን፥ ጻድ​ቃ​ኑን ሰብ​ስ​ቡ​ለት።</verse>
				<verse number="6">ሰማ​ያት ጽድ​ቁን ይና​ገ​ራሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራጅ ነውና።</verse>
				<verse number="7">ሕዝቤ፥ ስማኝ ልን​ገ​ርህ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም እመ​ሰ​ክ​ር​ብ​ሃ​ለሁ፤ አም​ላ​ክስ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝ።</verse>
				<verse number="8">ስለ መሥ​ዋ​ዕ​ትህ የም​ዘ​ል​ፍህ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ የሚ​ቃ​ጠል ቍር​ባ​ን​ህም ሁል​ጊዜ በፊቴ ነው።</verse>
				<verse number="9">ከቤ​ትህ ፍሪ​ዳን፥ ከመ​ን​ጋ​ህም ጊደ​ርን አል​ወ​ስ​ድም፤</verse>
				<verse number="10">የዱር አራ​ዊት ሁሉ፥ የም​ድረ በዳ እን​ስ​ሶ​ችና ላሞች ሁሉ የእኔ ናቸ​ውና።</verse>
				<verse number="11">የሰ​ማ​ይን አዕ​ዋፍ ሁሉ አው​ቃ​ለሁ፥ የዱር ውበ​ትም በእኔ ዘንድ አለ።</verse>
				<verse number="12">ብራ​ብም አል​ለ​ም​ን​ህም፥ ዓለም ሁሉ በመ​ላው የእኔ ነውና።</verse>
				<verse number="13">የፍ​ሪ​ዳ​ውን ሥጋ አል​በ​ላም፥ የፍ​የ​ሉ​ንም ደም አል​ጠ​ጣም።</verse>
				<verse number="14">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ስ​ጋ​ናን መሥ​ዋ​ዕት ሠዋ፥ ለል​ዑ​ልም ጸሎ​ት​ህን ስጥ፤</verse>
				<verse number="15">በመ​ከ​ራህ ቀን ትጠ​ራ​ኛ​ለህ አድ​ን​ህ​ማ​ለሁ፥ አን​ተም ታከ​ብ​ረ​ኛ​ለህ።</verse>
				<verse number="16">ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አለው፦ “ለምን አንተ ሕጌን ትና​ገ​ራ​ለህ? ኪዳ​ኔ​ንም በአ​ፍህ ለምን ትወ​ስ​ዳ​ለህ?</verse>
				<verse number="17">አን​ተስ ተግ​ሣ​ጼን ጠላህ፥ ቃሌ​ንም ወደ ኋላህ መለ​ስኽ።</verse>
				<verse number="18">ሌባ​ውን ባየህ ጊዜ ከእ​ርሱ ጋር ትሮ​ጣ​ለህ፥ ዕድል ፋን​ታ​ህ​ንም ከአ​መ​ን​ዝ​ሮች ጋር አደ​ረ​ግህ።</verse>
				<verse number="19">አፍህ ክፋ​ትን አበ​ዛች፥ አን​ደ​በ​ት​ህም ሽን​ገ​ላን ተበ​ተ​ባት።</verse>
				<verse number="20">ተቀ​ም​ጠህ ወን​ድ​ም​ህን ታማ​ዋ​ለህ፥ ለእ​ና​ት​ህም ልጅ ዕን​ቅ​ፋ​ትን አኖ​ርህ።</verse>
				<verse number="21">ይህን አድ​ር​ገህ ዝም አል​ሁህ፤ ኀጢ​አት አማ​ረ​ች​ህን? እኔ እን​ዳ​ንተ እሆን ዘንድ ጠረ​ጠ​ርህ? በፊ​ትህ ቆሜ ልዝ​ለ​ፍህ?</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ረሱ እና​ንተ፥ ይህን አስ​ተ​ውሉ፤ አለ​ዚያ ግን ይነ​ጥ​ቃል፥ የሚ​ያ​ድ​ንም የለም።</verse>
				<verse number="23">የከ​በ​ረች መሥ​ዋ​ዕት ታከ​ብ​ረ​ኛ​ለች፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማዳ​ኑን ያሳ​የ​ባት መን​ገድ በዚያ አለች።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="50">
				<verse number="1">አቤቱ፥ እንደ ቸር​ነ​ትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕ​ረ​ት​ህም ብዛት ኀጢ​አ​ቴን ደም​ስስ።</verse>
				<verse number="2">ከበ​ደሌ ፈጽሞ እጠ​በኝ፥ ከኀ​ጢ​አ​ቴም አን​ጻኝ፤</verse>
				<verse number="3">እኔ በደ​ሌን አው​ቃ​ለ​ሁና፥ ኀጢ​አ​ቴም ሁል​ጊዜ በፊቴ ነውና።</verse>
				<verse number="4">አን​ተን ብቻ በደ​ልሁ፥ በፊ​ት​ህም ክፋ​ትን አደ​ረ​ግሁ፥ በነ​ገ​ርህ ትጸ​ድቅ ዘንድ በፍ​ር​ድ​ህም ታሸ​ንፍ ዘንድ።</verse>
				<verse number="5">እነሆ፥ በኀ​ጢ​አት ተፀ​ነ​ስሁ፥ እና​ቴም በዐ​መፃ ወለ​ደ​ችኝ።</verse>
				<verse number="6">እነሆ፥ እው​ነ​ትን ወደ​ድህ፤ የማ​ይ​ነ​ገር ስውር ጥበ​ብ​ህን አስ​ታ​ወ​ቅ​ኸኝ።</verse>
				<verse number="7">በሂ​ሶጵ እር​ጨኝ፥ እነ​ጻ​ማ​ለሁ፤ እጠ​በኝ፥ ከበ​ረ​ዶም ይልቅ ነጭ እሆ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">ሐሤ​ት​ንና ደስ​ታን አሰ​ማኝ፥ የጻ​ድ​ቃን አጥ​ን​ቶች ደስ ይላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="9">ከኀ​ጢ​አቴ ፊት​ህን መልስ፥ በደ​ሌ​ንም ሁሉ ደም​ስ​ስ​ልኝ።</verse>
				<verse number="10">አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠ​ር​ልኝ፥ የቀ​ና​ው​ንም መን​ፈስ በው​ስጤ አድስ።</verse>
				<verse number="11">ከፊ​ትህ አት​ጣ​ለኝ፥ ቅዱስ መን​ፈ​ስ​ህ​ንም ከእኔ ላይ አት​ው​ሰ​ድ​ብኝ።</verse>
				<verse number="12">ደስ​ታ​ንና ማዳ​ን​ህን ስጠኝ፥ በጽኑ መን​ፈ​ስም አጽ​ናኝ።</verse>
				<verse number="13">መን​ገ​ድ​ህን ለኃ​ጥ​ኣን አስ​ተ​ም​ራ​ቸው ዘንድ፥ ዝን​ጉ​ዎ​ችም ወደ አንተ ይመ​ለሱ ዘንድ።</verse>
				<verse number="14">የመ​ድ​ኀ​ኒቴ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ከደም አድ​ነኝ፥ አን​ደ​በ​ቴም በአ​ንተ ጽድቅ ደስ ይለ​ዋል።</verse>
				<verse number="15">አቤቱ፥ ከን​ፈ​ሮ​ችን ክፈት፥ አፌም ምስ​ጋ​ና​ህን ያወ​ራል።</verse>
				<verse number="16">መሥ​ዋ​ዕ​ትን ብት​ወ​ድ​ድስ በሰ​ጠ​ሁህ ነበር፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አት​ወ​ድ​ድም።</verse>
				<verse number="17">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የዋህ መን​ፈስ ነው፥ የተ​ዋ​ረ​ደ​ው​ንና የዋ​ሁን ልብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ን​ቅም።</verse>
				<verse number="18">አቤቱ፥ በው​ዴ​ታህ ጽዮ​ንን አሰ​ማ​ም​ራት፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቅጽ​ሮች ይታ​ነጹ።</verse>
				<verse number="19">የጽ​ድ​ቁን መሥ​ዋ​ዕት፥ መባ​ው​ንም፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት በወ​ደ​ድህ ጊዜ፥ ያን​ጊዜ በመ​ሠ​ዊ​ያህ ላይ ፍሪ​ዳ​ዎ​ችን ይሠ​ዋሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="51">
				<verse number="1">ኀያል ሆይ፥ በክ​ፋት ለምን ትኰ​ራ​ለህ? ሁል​ጊ​ዜስ ለምን ትበ​ድ​ላ​ለህ?</verse>
				<verse number="2">ልብህ ኀጢ​አ​ትን ያስ​ባል፤ እንደ ተሳለ ምላጭ ሽን​ገ​ላን አደ​ረ​ግህ።</verse>
				<verse number="3">ከመ​ል​ካም ይልቅ ክፋ​ትን፥ ጽድ​ቅ​ንም ከመ​ና​ገር ይልቅ ዐመ​ፃን ወደ​ድህ።</verse>
				<verse number="4">የሚ​ያ​ሰ​ጥም የም​ላስ ነገ​ርን ሁሉ ወደ​ድህ።</verse>
				<verse number="5">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያፈ​ር​ስ​ሃል፤ ከቤ​ት​ህም ይነ​ቅ​ል​ሃል፥ ያፈ​ል​ስ​ሃ​ልም፥ ሥር​ህ​ንም ከሕ​ያ​ዋን ምድር።</verse>
				<verse number="6">ጻድ​ቃን አይ​ተው ይፍሩ፤ በእ​ር​ሱም ይሳቁ እን​ዲ​ህም ይበሉ፦</verse>
				<verse number="7">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረዳቱ ያላ​ደ​ረገ፥ በባ​ለ​ጠ​ግ​ነ​ቱም ብዛት የታ​መነ፥ በከ​ንቱ ነገ​ርም የበ​ረታ ያ ሰው እነሆ።”</verse>
				<verse number="8">እኔስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እንደ ለመ​ለመ እንደ ወይራ ዛፍ ነኝ፤ ለዓ​ለ​ምና ለዘ​ለ​ዓ​ለም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሕ​ረት ታመ​ንሁ።</verse>
				<verse number="9">አድ​ር​ገ​ህ​ል​ኛ​ልና ለዘ​ለ​ዓ​ለም አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥ በጻ​ድ​ቃ​ን​ህም ዘንድ መል​ካም ነውና ምሕ​ረ​ት​ህን ተስፋ አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="52">
				<verse number="1">ሰነፍ በልቡ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የለም ይላል። ረከሱ፥ በበ​ደ​ላ​ቸ​ውም ጐሰ​ቈሉ፤ በጎ ነገ​ርን የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት የለም።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ልግ አስ​ተ​ዋይ እን​ዳለ ያይ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ የሰው ልጆ​ችን ተመ​ለ​ከተ።</verse>
				<verse number="3">ሁሉ ተካ​ክሎ በአ​ን​ድ​ነት በደለ፤ አንድ ስንኳ በጎ ነገ​ርን የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት የለም።</verse>
				<verse number="4">ሕዝ​ቤን እን​ጀ​ራን እንደ መብ​ላት የሚ​በሉ ግፍ አድ​ራ​ጊ​ዎች ሁሉ አያ​ው​ቁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አይ​ጠ​ሩ​ትም።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የግ​ብ​ዞ​ችን አጥ​ን​ቶች በት​ኖ​አ​ልና በዚያ የሚ​ያ​ስ​ፈራ ሳይ​ኖር እጅግ ፈሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዋ​ር​ዶ​አ​ቸ​ዋ​ልና አፈሩ።</verse>
				<verse number="6">መድ​ኀ​ኒ​ትን ከጽ​ዮን ለእ​ስ​ራ​ኤል ማን ይሰ​ጣል? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሕ​ዝ​ቡን ምርኮ በመ​ለሰ ጊዜ፥ ያዕ​ቆብ ደስ ይለ​ዋል እስ​ራ​ኤ​ልም ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="53">
				<verse number="1">አቤቱ፥ በስ​ምህ አድ​ነኝ፥ በኀ​ይ​ል​ህም ፍረ​ድ​ልኝ።</verse>
				<verse number="2">አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን ስማኝ፥ የአ​ፌ​ንም ቃል አድ​ምጥ፤</verse>
				<verse number="3">ባዕ​ዳን በእኔ ላይ ቆመ​ዋ​ልና፥ ኀያ​ላ​ንም ነፍ​ሴን ሽተ​ዋ​ታ​ልና። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በፊ​ታ​ቸው አላ​ደ​ረ​ጉ​ትም።</verse>
				<verse number="4">እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይረ​ዳ​ኛል፥ ጌታ​ዬም ነፍ​ሴን ያድ​ና​ታል።</verse>
				<verse number="5">ክፋ​ትን ወደ ጠላ​ቶች ይመ​ል​ሳ​ታል፤ በእ​ው​ነ​ት​ህም አጥ​ፋ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">ከፈ​ቃዴ የተ​ነሣ እሠ​ዋ​ል​ሃ​ለሁ፤ አቤቱ፥ መል​ካም ነውና፥ ስም​ህን አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፤</verse>
				<verse number="7">ከመ​ከራ ሁሉ አድ​ኖ​ኛ​ልና፥ ዐይ​ኔም በጠ​ላ​ቶቼ ላይ አይ​ታ​ለ​ችና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="54">
				<verse number="1">አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን አድ​ም​ጠኝ፥ ልመ​ና​ዬ​ንም ቸል አት​በ​ለኝ።</verse>
				<verse number="2">ተመ​ል​ከ​ተኝ፥ ስማ​ኝም፤ አዘ​ንሁ፥ ደነ​ገ​ጥሁ፥ ተና​ወ​ጥ​ሁም፤</verse>
				<verse number="3">ከጠ​ላት ድምፅ፥ ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኛም ማሠ​ቃ​የት የተ​ነሣ፥ ዐመ​ፃን በላዬ መል​ሰ​ው​ብ​ኛ​ልና፥ ሊያ​ጠ​ፉ​ኝም ተነ​ሥ​ተ​ው​ብ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="4">ልቤ በላዬ ደነ​ገ​ጠ​ብኝ፥ የሞት ድን​ጋ​ጤም መጣ​ብኝ።</verse>
				<verse number="5">ፍር​ሃ​ትና እን​ቅ​ጥ​ቅጥ ያዙኝ፥ ጨለ​ማም ሸፈ​ነኝ።</verse>
				<verse number="6">በርሬ ዐርፍ ዘንድ እንደ ርግብ ክን​ፍን ማን በሰ​ጠኝ አልሁ፥</verse>
				<verse number="7">እነሆ፥ ኮብ​ልዬ በራ​ቅሁ፥ በም​ድረ በዳም በኖ​ርሁ፤</verse>
				<verse number="8">እንደ ዐውሎ ነፋስ ከሆ​ነው ከነ​ፍሴ መቅ​በ​ዝ​በዝ የሚ​ያ​ድ​ነ​ኝን ተስፋ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">አቤቱ፥ ዐመ​ፃ​ንና ጠብን በከ​ተማ ውስጥ አይ​ች​አ​ለ​ሁና አስ​ጥ​ማ​ቸው፥ አን​ደ​በ​ታ​ቸ​ው​ንም ቍረጥ።</verse>
				<verse number="10">በቀ​ንና በሌ​ሊት በቅ​ጥ​ርዋ ይከ​ብ​ቡ​አ​ታል፤ ዐመ​ፃና ድካም ኀጢ​አ​ትም በመ​ካ​ከ​ልዋ ነው፤</verse>
				<verse number="11">ሽን​ገላ ከአ​ደ​ባ​ባ​ይዋ አይ​ር​ቅም።</verse>
				<verse number="12">ጠላ​ትስ ቢሰ​ድ​በኝ፥ በታ​ገ​ሥሁ ነበር፤ የሚ​ጠ​ላ​ኝም አፉን በላዬ ከፍ ከፍ ቢያ​ደ​ርግ፥ ከእ​ርሱ በተ​ሸ​ሸ​ግሁ ነበር።</verse>
				<verse number="13">አንተ ሰው፥ አንተ ግን እንደ ራሴ ነበ​ርህ፥ ባል​ን​ጀ​ራ​ዬና የማ​ው​ቅህ ወዳ​ጄም ነበ​ርህ፤</verse>
				<verse number="14">መብ​ልን ከእኔ ጋር በአ​ን​ድ​ነት ያጣ​ፈ​ጥህ ነበ​ርህ፤ በአ​ንድ ልብ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ተራ​መ​ድን።</verse>
				<verse number="15">ሞት ይም​ጣ​ባ​ቸው፤ በሕ​ይ​ወት ሳሉም ወደ ሲኦል ይው​ረዱ፤ ክፋት በማ​ደ​ሪ​ያ​ቸ​ውና በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ነውና።</verse>
				<verse number="16">እኔ ግን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኽሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማኝ።</verse>
				<verse number="17">በማ​ታና በጥ​ዋት በቀ​ት​ርም እና​ገ​ራ​ለሁ አስ​ረ​ዳ​ለሁ፥ ቃሌ​ንም አይ​ሰ​ሙ​ኝም።</verse>
				<verse number="18">ከእኔ ጋር ካሉት ይበ​ዛ​ሉና ከሚ​ቃ​ረ​ቡኝ ነፍ​ሴን በሰ​ላም አድ​ናት።</verse>
				<verse number="19">ቤዛ የላ​ቸ​ው​ምና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ፈ​ሩ​ት​ምና ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር የነ​በረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰምቶ ያጐ​ሰ​ቍ​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="20">ፍዳን ለማ​ም​ጣት እጁን ዘረጋ፤ ኪዳ​ኑ​ንም አረ​ከሱ።</verse>
				<verse number="21">ከፊ​ቱም ቍጣ የተ​ነሣ ተለ​ያዩ፥ ልቡም ቀረበ፤ ቃሉም ከቅቤ ይልቅ ለሰ​ለሰ፤ እነ​ርሱ ግን እን​ደ​ሚ​ያ​ሰ​ጥም ማዕ​በል ናቸው።</verse>
				<verse number="22">ትካ​ዜ​ህን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ጣል፥ እር​ሱም ይመ​ግ​ብ​ሃል፤ ለጻ​ድ​ቁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሁከ​ትን አይ​ሰ​ጠ​ውም።</verse>
				<verse number="23">አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ወደ ሞት ጕድ​ጓድ አው​ር​ዳ​ቸው፤ የደም ሰዎ​ችና ሸን​ጋ​ዮች ዘመ​ና​ቸ​ውን አያ​ጋ​ም​ሱም፤ እኔ ግን፥ አቤቱ እታ​መ​ን​ሃ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="55">
				<verse number="1">አቤቱ፥ ሰው ረግ​ጦ​ኛ​ልና ይቅር በለኝ፤ ሁል​ጊ​ዜም ሰልፍ አስ​ጨ​ን​ቆ​ኛል።</verse>
				<verse number="2">ሁል​ጊዜ ቀኑን ሁሉ ጠላ​ቶች ረገ​ጡኝ፥ የሚ​ዋ​ጉኝ በዝ​ተ​ዋ​ልና ፈራሁ።</verse>
				<verse number="3">እኔ ግን አቤቱ በአ​ንተ ታመ​ንሁ።</verse>
				<verse number="4">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃሉን አከ​ብ​ራ​ለሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመ​ንሁ፥ አል​ፈ​ራም፤ ሰው ምን ያደ​ር​ገ​ኛል?</verse>
				<verse number="5">ሁል​ጊዜ ቃሎ​ችን ይጸ​የ​ፉ​ብ​ኛል፤ በእኔ ላይም የሚ​መ​ክ​ሩት ሁሉ ለክፉ ነው።</verse>
				<verse number="6">ይሸ​ም​ቁ​ብ​ኛል፥ ይሸ​ሸ​ጉ​ኝ​ማል፥ እነ​ር​ሱም ተረ​ከ​ዜን ይመ​ለ​ካ​ከ​ታሉ፥ ሁል​ጊ​ዜም ነፍ​ሴን ይሸ​ም​ቁ​ባ​ታል።</verse>
				<verse number="7">በም​ንም ምን አታ​ድ​ና​ቸ​ውም፤ አሕ​ዛ​ብን በመ​ዓ​ትህ ትጥ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="8">አም​ላኬ ሆይ፥ ሕይ​ወ​ቴን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤ እን​ባ​ዬ​ንም እንደ ትእ​ዛ​ዝህ በፊ​ትህ አኖ​ርሁ።</verse>
				<verse number="9">በጠ​ራ​ሁህ ጊዜ ጠላ​ቶች ወደ ኋላ​ቸው ይመ​ለሱ፤ አንተ አም​ላኬ እንደ ሆንህ እነሆ፥ ዐወ​ቅሁ።</verse>
				<verse number="10">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃሌን አከ​ብ​ራ​ለሁ፤ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይከ​ብ​ራል።</verse>
				<verse number="11">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመ​ንሁ፥ አል​ፈ​ራም፥ ሰው ምን ያደ​ር​ገ​ኛል?</verse>
				<verse number="12">አቤቱ፥ የም​ስ​ጋና ስእ​ለት የም​ሰ​ጥህ ከእኔ ዘንድ ነው፤</verse>
				<verse number="13">ነፍ​ሴን ከሞት፥ ዐይ​ኖ​ቼን ከዕ​ንባ፥ እግ​ሮቼ​ንም ከድጥ አድ​ነ​ሃ​ልና፥ በሕ​ያ​ዋን ሀገር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ አሰ​ኘው ዘንድ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="56">
				<verse number="1">ይቅር በለኝ፥ አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፥ ነፍሴ አን​ተን ታም​ና​ለ​ችና፤ ኀጢ​አት እስ​ክ​ታ​ልፍ ድረስ በክ​ን​ፎ​ችህ ጥላ እታ​መ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">ወደ ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ወደ​ሚ​ረ​ዳኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጮ​ኻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">ከሰ​ማይ ልኮ አዳ​ነኝ፥ ለረ​ገ​ጡ​ኝም ውር​ደ​ትን ሰጣ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር​ነ​ቱ​ንና ጽድ​ቁን ላከ።</verse>
				<verse number="4">ነፍ​ሴን ከአ​ን​በ​ሶች መካ​ከል አዳ​ናት። ደን​ግ​ጬም ተኛሁ፤ የሰው ልጆች ጥር​ሳ​ቸው ጦርና ፍላጻ ነው፥ አን​ደ​በ​ታ​ቸ​ውም የተ​ሳለ ሾተል ነው።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማ​ያት ላይ ከፍ ከፍ አለ፥ ክብ​ሩም በም​ድር ሁሉ ላይ ነው።</verse>
				<verse number="6">ለእ​ግ​ሮቼ ወጥ​መ​ድን አዘ​ጋጁ፥ ሰው​ነ​ቴ​ንም አጐ​በ​ጡ​አት፤ ጕድ​ጓ​ድን በፊቴ ቈፈሩ፥ በው​ስ​ጡም ወደቁ።</verse>
				<verse number="7">ልቤ ጽኑዕ ነው፥ አቤቱ ልቤ ጽኑዕ ነው፥ አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥ እዘ​ም​ራ​ለ​ሁም።</verse>
				<verse number="8">ክብሬ ይነሣ፥ በበ​ገ​ናና በመ​ሰ​ንቆ ይነሣ፤ እኔም ማልጄ እነ​ሣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">አቤቱ፥ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥ በወ​ገ​ኖ​ችም ዘንድ እዘ​ም​ር​ል​ሃ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="10">ምሕ​ረ​ትህ እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ብላ​ለ​ችና፥ ጽድ​ቅ​ህም እስከ ደመ​ናት ድረስ።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማ​ያት ላይ ከፍ ከፍ አለ፥ ክብ​ሩም በም​ድር ሁሉ ላይ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="57">
				<verse number="1">በእ​ው​ነት ጽድ​ቅን ብት​ና​ገ​ሩስ፥ የሰው ልጆች ሆይ፥ በቅን ትፈ​ር​ዳ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="2">በል​ባ​ችሁ በም​ድር ላይ ኀጢ​አ​ትን ትሠ​ራ​ላ​ች​ሁና፥ እጆ​ቻ​ች​ሁም ሽን​ገ​ላን ይታ​ታ​ሉና።</verse>
				<verse number="3">ኀጥ​ኣን ከማ​ኅ​ፀን ጀም​ረው ተለዩ፤ ከሆ​ድም ጀም​ረው ሳቱ፥ ሐሰ​ት​ንም ተና​ገሩ።</verse>
				<verse number="4">ቍጣ​ቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፥ ጆሮ​ዋም እንደ ደነ​ቈረ እባብ፥</verse>
				<verse number="5">ዐዋቂ ሲደ​ግ​ም​ባት የአ​ስ​ማ​ተ​ኛ​ውን ቃል እን​ደ​ማ​ት​ሰማ።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥር​ሳ​ቸ​ውን በአ​ፋ​ቸው ውስጥ ይሰ​ብ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ን​በ​ሶ​ቹን መን​ጋ​ጋ​ቸ​ውን ያደ​ቅ​ቃል።</verse>
				<verse number="7">እን​ደ​ሚ​ፈ​ስስ ውኃ ይቀ​ል​ጣሉ፤ እስ​ከ​ሚ​ያ​ደ​ክ​ማ​ቸው ድረስ ፍላ​ጻ​ቹን ይገ​ት​ራል።</verse>
				<verse number="8">እን​ደ​ሚ​ቀ​ልጥ ሰም ያል​ቃሉ፤ እሳት ወደ​ቀች፥ ፀሐ​ይ​ንም አላ​የ​ኋ​ትም።</verse>
				<verse number="9">እሾ​ኻ​ችሁ ሳይ​ታ​ወቅ በትር ሆነ፤ ሕያ​ዋን ሳላ​ችሁ በመ​ዓቱ ይው​ጣ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="10">ጻድቅ በቀ​ልን ባየ ጊዜ ደስ ይለ​ዋል፤ በኀ​ጢ​አ​ተ​ኛው ደምም እጁን ይታ​ጠ​ባል።</verse>
				<verse number="11">ሰውም፥ “በእ​ው​ነት ለጻ​ድቅ ፍሬ አለው፤ በእ​ው​ነት በም​ድር ላይ የሚ​ፈ​ርድ አም​ላክ አለ” ይላል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="58">
				<verse number="1">አም​ላኬ ሆይ፥ ከጠ​ላ​ቶች አድ​ነኝ፤ በላ​ዬም ከቆ​ሙት አስ​ጥ​ለኝ።</verse>
				<verse number="2">ከዐ​መፅ አድ​ራ​ጊ​ዎች ታደ​ገኝ፥ ከደም ሰዎ​ችም አድ​ነኝ።</verse>
				<verse number="3">እነሆ፥ ነፍ​ሴን አድ​ድ​ነ​ዋ​ታ​ልና፥ ብር​ቱ​ዎ​ችም በላዬ ተነሡ፤ አቤቱ፥ በበ​ደ​ሌም አይ​ደ​ለም፥ በኀ​ጢ​አ​ቴም አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="4">ያለ በደል ሮጥሁ ተዘ​ጋ​ጀ​ሁም፤ ተነሥ፥ ተቀ​በ​ለኝ፥ እይም።</verse>
				<verse number="5">አን​ተም አቤቱ፥ የኀ​ያ​ላን አም​ላክ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ፥ አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ጐብ​ኛ​ቸው፥ ይቅ​ርም በላ​ቸው፤ ዐመፅ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ሁሉ ግን አት​ማ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">ማታ ይመ​ለሱ እንደ ውሾ​ችም ይራቡ፥ በከ​ተ​ማም ይዙሩ።</verse>
				<verse number="7">እነሆ፥ በአ​ፋ​ቸው ይና​ገ​ራሉ፤ ሰይ​ፍም በከ​ን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸው አለ፤</verse>
				<verse number="8">የም​ት​ሰ​ማ​ቸው አንተ ግን አቤቱ፥ ትሥ​ቅ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፥ አሕ​ዛ​ቡ​ንም ሁሉ ትን​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ፥</verse>
				<verse number="9">ኀይ​ሌን ወደ አንተ አስ​ጠ​ጋ​ለሁ፥ አንተ አም​ላ​ኬና መጠ​ጊ​ያዬ ነህና።</verse>
				<verse number="10">የአ​ም​ላኬ ይቅ​ር​ታው ይድ​ረ​ሰኝ አም​ላኬ በጠ​ላ​ቶቼ ላይ አሳ​የኝ።</verse>
				<verse number="11">ሕግ​ህን እን​ዳ​ይ​ረሱ አት​ግ​ደ​ላ​ቸው፤ አቤቱ፥ አም​ላ​ኬና ረዳቴ፥ በኀ​ይ​ልህ በት​ና​ቸው፥ አዋ​ር​ዳ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="12">ስለ አፋ​ቸው ኀጢ​አት ስለ ከን​ፈ​ራ​ቸ​ውም ቃል፥ በት​ዕ​ቢ​ታ​ቸው ይጠ​መዱ ከመ​ር​ገ​ማ​ቸ​ውና ከሐ​ሰ​ታ​ቸው የተ​ነሣ፥ ፍጻ​ሜ​ያ​ቸው ይታ​ወ​ቃል።</verse>
				<verse number="13">ኋላ በሚ​መጣ መቅ​ሠ​ፍት ያል​ቃሉ፤ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ እን​ዲ​ገዛ ይወቁ።</verse>
				<verse number="14">ማታ ይመ​ለሱ እንደ ውሾ​ችም ይራቡ፥ በከ​ተ​ማም ይዙሩ።</verse>
				<verse number="15">እነ​ር​ሱም መብል ለመ​ፈ​ለግ ይበ​ተኑ፤ የጠ​ገቡ እንደ ሆነም ያን​ጐ​ራ​ጕ​ራሉ።</verse>
				<verse number="16">እኔ ግን ለኀ​ይ​ልህ እቀ​ኛ​ለሁ፤ በም​ሕ​ረ​ት​ህም በማ​ለዳ ደስ ይለ​ኛል፤ በመ​ከ​ራዬ ቀን መጠ​ጊ​ያ​ዬና አም​ባዬ ሆነ​ኽ​ል​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="17">አንተ ረዳቴ ነህ፥ ለአ​ን​ተም ለአ​ም​ላኬ እዘ​ም​ራ​ለሁ፤ አንተ፥ አም​ላኬ፥ መጠ​ጊ​ያዬ ነህና አም​ላ​ኪዬ ምሕ​ረ​ቴም ነህና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="59">
				<verse number="1">አቤቱ፥ ጣል​ኸን አፈ​ረ​ስ​ኸ​ንም፤ ገረ​ፍ​ኸን፥ ይቅ​ርም አል​ኸን።</verse>
				<verse number="2">ምድ​ርን አና​ወ​ጥ​ሃት፥ አወ​ክ​ሃ​ትም፤ ተና​ው​ጣ​ለ​ችና ቍስ​ል​ዋን ፈወ​ስ​ኻት።</verse>
				<verse number="3">ለሕ​ዝ​ብህ ጭን​ቅን አሳ​የ​ሃ​ቸው፥ አስ​ደ​ን​ጋ​ጩ​ንም ወይን አጠ​ጣ​ኸን።</verse>
				<verse number="4">ለሚ​ፈ​ሩህ ምል​ክ​ትን ሰጠ​ሃ​ቸው፥ ከቀ​ስት ፊት ያመ​ልጡ ዘንድ።</verse>
				<verse number="5">ወዳ​ጆ​ች​ህም፥ እን​ዲ​ድኑ በቀ​ኝህ አድን፥ ስማ​ኝም።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ቅ​ደሱ ተና​ገረ፤ ደስ ይለ​ኛል፥ ምር​ኮ​ንም እካ​ፈ​ላ​ለሁ፥ የሸ​ለቆ ቦታ​ዎ​ችን እሰ​ፍ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">ገለ​ዓድ የእኔ ነው፥ ምና​ሴም የእኔ ነው፤ ኤፍ​ሬም የራሴ መጠ​ጊያ ነው። ይሁዳ ንጉሤ ነው፤</verse>
				<verse number="8">ካህን ሞአ​ብም ተስ​ፋዬ ነው በኤ​ዶ​ም​ያስ ላይ ጫማ​ዬን እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ምም ይገ​ዙ​ል​ኛል።</verse>
				<verse number="9">ቅጥር ወደ አለ​ባት ወደ ጽኑ ከተማ ማን ይወ​ስ​ደ​ኛል? ማንስ እስከ ኤዶ​ም​ያስ ይመ​ራ​ኛል?</verse>
				<verse number="10">አቤቱ፥ የጣ​ል​ኸን አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ችን ጋር አት​ወ​ጣም።</verse>
				<verse number="11">በመ​ከ​ራ​ችን ረድ​ኤ​ትን ስጠን፥ በሰ​ውም መታ​መን ከንቱ ነው።</verse>
				<verse number="12">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይ​ልን እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ እር​ሱም የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​ንን ያዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="60">
				<verse number="1">አም​ላኬ ሆይ፥ ልመ​ና​ዬን ስማኝ፥ ጸሎ​ቴ​ንም አድ​ም​ጠኝ።</verse>
				<verse number="2">ልቤ ተስፋ በቈ​ረጠ ጊዜ ከም​ድር ዳርቻ ወደ አንተ እጮ​ኻ​ለሁ፤ በድ​ን​ጋይ ላይ ከፍ ከፍ አደ​ረ​ግ​ኸኝ።</verse>
				<verse number="3">በጠ​ላት ፊት ጽኑ ግንብ ነህ፤ ተስ​ፋ​ዬም ሆነ​ኽ​ል​ኛ​ልና መራ​ኸኝ።</verse>
				<verse number="4">በድ​ን​ኳ​ንህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እኖ​ራ​ለሁ፤ በክ​ን​ፎ​ችህ ጥላም እጋ​ረ​ዳ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="5">አም​ላኬ፥ አንተ ጸሎ​ቴን ሰም​ተ​ሃ​ልና፤ ለሚ​ፈ​ሩ​ህም ርስ​ትን ሰጠ​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">ለን​ጉሥ ከቀን በላይ ቀንን ትጨ​ም​ራ​ለህ፥ ዓመ​ታ​ቱም ከት​ው​ልድ ወደ ትው​ልድ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="7">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል፤ ይቅ​ር​ታ​ው​ንና ጽድ​ቁን ማን ይፈ​ል​ጋል?</verse>
				<verse number="8">እን​ዲሁ ለስ​ምህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እዘ​ም​ራ​ለሁ ምኞ​ቴን ሁል​ጊዜ ትሰ​ጠኝ ዘንድ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="61">
				<verse number="1">ነፍሴ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ት​ገዛ አይ​ደ​ለ​ች​ምን? መድ​ኀ​ኒቴ ከእ​ርሱ ዘንድ ናትና።</verse>
				<verse number="2">እርሱ አም​ላኬ መድ​ኀ​ኒ​ቴም ነውና፤ እርሱ ረዳቴ ነው ሁል​ጊ​ዜም አል​ታ​ወ​ክም።</verse>
				<verse number="3">እስከ መቼ በሰው ላይ ትቆ​ማ​ላ​ችሁ? እና​ንተ ሁላ​ችሁ እን​ዳ​ዘ​ነ​በለ ግድ​ግዳ እንደ ፈረ​ሰም ቅጥር ትገ​ድ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን ክብ​ሬን ይሽሩ ዘንድ መከሩ፥ በጥ​ሜም ሮጥሁ፤ በአ​ፋ​ቸው ይባ​ር​ካሉ፥ በል​ባ​ቸ​ውም ይረ​ግ​ማሉ።</verse>
				<verse number="5">ነገር ግን ነፍሴ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትገ​ዛ​ለች፥ ተስ​ፋዬ ከእ​ርሱ ዘንድ ናትና።</verse>
				<verse number="6">እርሱ አም​ላኬ መድ​ኃ​ኒ​ቴም ነውና፤ እርሱ ረዳቴ ነውና፥ አል​ታ​ወ​ክም።</verse>
				<verse number="7">መድ​ኃ​ኒቴ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ክብ​ሬም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥ የረ​ድ​ኤቴ አም​ላክ፥ ተስ​ፋ​ዬም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።</verse>
				<verse number="8">የአ​ሕ​ዛብ ማኅ​በር ሁላ​ችሁ፥ በእ​ርሱ ታመኑ፥ ልባ​ች​ሁ​ንም በፊቱ አፍ​ስሱ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳ​ታ​ችን ነው።</verse>
				<verse number="9">ነገር ግን የሰው ልጆች ሁሉ ከንቱ ናቸው፥ የሰው ልጆ​ችም ሐሰ​ተ​ኞች ናቸው፤ በሚ​ዛ​ንም ይበ​ድ​ላሉ፥ እነ​ር​ሱስ በፍ​ጹም ከንቱ ናቸው።</verse>
				<verse number="10">ዐመ​ፃን ተስፋ አታ​ድ​ርጉ፥ ቅሚ​ያ​ንም አት​ተ​ማ​መ​ኑት፤ ባለ​ጠ​ግ​ነት ቢበዛ ልባ​ች​ሁን አታ​ኩሩ።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንድ ጊዜ ተና​ገረ፥ እኔም ይህን ብቻ ሰማሁ፤ ይቅ​ርታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና፥</verse>
				<verse number="12">አቤቱ፥ ኀይ​ልም ያንተ ነው፤ አንተ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ እንደ ሥራው ትከ​ፍ​ለ​ዋ​ለ​ህና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="62">
				<verse number="1">አም​ላኬ፥ አም​ላኬ፥ ወደ አንተ እገ​ሠ​ግ​ሣ​ለሁ፤ ነፍሴ አን​ተን ተጠ​ማች፥ እን​ጨ​ትና ውኃ በሌ​ለ​በት ምድረ በዳ ሥጋ​ዬን ለአ​ንተ እን​ዴት ልዘ​ር​ጋ​ልህ</verse>
				<verse number="2">ኀይ​ል​ህ​ንና ክብ​ር​ህን ዐውቅ ዘንድ እን​ዲሁ በመ​ቅ​ደስ ውስጥ ተመ​ለ​ከ​ት​ሁህ።</verse>
				<verse number="3">ምሕ​ረ​ትህ ከሕ​ይ​ወት ይሻ​ላ​ልና፥ ከን​ፈ​ሮቼ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል።</verse>
				<verse number="4">እን​ዲህ በሕ​ይ​ወቴ ዘመን አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥ በአ​ን​ተም ስም እጆ​ችን አነ​ሣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">ነፍሴ በቅ​ቤና በስብ እን​ደ​ሚ​ጠ​ግቡ ትጠ​ግ​ባ​ለች፥ ደስ​ተ​ኞች ከን​ፈ​ሮቼም ስም​ህን ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።</verse>
				<verse number="6">በመ​ኝ​ታ​ዬም አስ​ብ​ሃ​ለሁ፥ በማ​ለ​ዳም እና​ገ​ር​ል​ሃ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="7">ረዳቴ ሆነ​ኽ​ል​ኛ​ልና፥ በክ​ን​ፎ​ች​ህም ጥላ እታ​መ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">ነፍሴ በኋ​ላህ ተከ​ታ​ተ​ለች፥ እኔ​ንም ቀኝህ ተቀ​በ​ለ​ችኝ።</verse>
				<verse number="9">እነ​ርሱ ግን ነፍ​ሴን ለከ​ንቱ ፈለ​ጓት፤ ወደ ምድር ጥልቅ ይግቡ።</verse>
				<verse number="10">በሰ​ይፍ እጅ አል​ፈው ይሰጡ፥ የቀ​በ​ሮ​ዎ​ችም ዕድል ፋንታ ይሁኑ።</verse>
				<verse number="11">ንጉሥ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይለ​ዋል፤ በእ​ር​ሱም የሚ​ምል ሁሉ ይከ​ብ​ራል፥ ዐመ​ፅን የሚ​ና​ገር አፍ ይዘ​ጋ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="63">
				<verse number="1">አቤቱ፥ ወደ አንተ የለ​መ​ን​ሁ​ትን ጸሎ​ቴን ስማኝ፥ ከጠ​ላ​ትም ጥር​ጥር ነፍ​ሴን አድ​ናት።</verse>
				<verse number="2">ከክ​ፉ​ዎች ሴራ ከብ​ዙ​ዎች ዐመፅ አድ​ራ​ጊ​ዎች ሰው​ረኝ።</verse>
				<verse number="3">እንደ እባብ ምላ​ሳ​ቸ​ውን አሰሉ፤ መራራ ነገ​ርን ለማ​ድ​ረግ፥</verse>
				<verse number="4">ንጹ​ሕ​ንም በስ​ውር ለመ​ግ​ደል ቀስ​ትን ገተሩ፤ በድ​ን​ገት ይነ​ድ​ፏ​ቸ​ዋል አይ​ፈ​ሩ​ምም።</verse>
				<verse number="5">ለእ​ነ​ርሱ ለራ​ሳ​ቸው ክፉ ነገ​ርን አጸኑ፤ ወጥ​መ​ድን ይሰ​ውሩ ዘንድ ተማ​ከሩ፤ የሚ​ያ​ም​ንም የለም ይላሉ።</verse>
				<verse number="6">ዐመ​ፃን ፈለ​ጓት፥ ሲፈ​ት​ኑም ሲጀ​ም​ሩም አለቁ፤ ሰው በጥ​ልቅ ልብ ውስጥ ይገ​ባል፥</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፍ ከፍ ይላል። መቅ​ሠ​ፍ​ታ​ቸው እንደ ልጆች ሕንፃ ሆነ፤</verse>
				<verse number="8">አን​ደ​በ​ታ​ቸው በላ​ያ​ቸው ደከመ፥ የሚ​ያ​ዩ​አ​ቸ​ውም ሁሉ ደነ​ገጡ።</verse>
				<verse number="9">ሰው ሁሉ ፈራ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥራ ተና​ገሩ፥ ሥራ​ው​ንም ዐወቁ።</verse>
				<verse number="10">ጻድቅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይለ​ዋል፥ በእ​ር​ሱም ይታ​መ​ናል፤ ልባ​ቸ​ውም የቀና ሁሉ ይከ​ብ​ራሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="64">
				<verse number="1">አቤቱ፥ በጽ​ዮን ለአ​ንተ ምስ​ጋና ይገ​ባል፥ ለአ​ን​ተም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጸሎት ይቀ​ር​ባል።</verse>
				<verse number="2">ወደ አንተ የሚ​መጣ የሰ​ውን ሁሉ ጸሎት ስማ</verse>
				<verse number="3">የዐ​መ​ፀ​ኞች ነገር በረ​ታ​ብን፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ን​ንስ አንተ ይቅር ትላ​ለህ።</verse>
				<verse number="4">አንተ የመ​ረ​ጥ​ኸው በአ​ደ​ባ​ባ​ዮ​ች​ህም ለማ​ሳ​ደር የተ​ቀ​በ​ል​ኸው ብፁዕ ነው፤ አቤቱ፥ ከቤ​ትህ በረ​ከት ጠገ​ብን።</verse>
				<verse number="5">ቤተ መቅ​ደ​ስህ ቅዱስ ነው በጽ​ድ​ቅም ድንቅ ነው። በም​ድር ዳርቻ ሁሉና በሩቅ ባሕር ውስጥ ላሉ ተስ​ፋ​ቸው የሆ​ንህ፥ አም​ላ​ካ​ች​ንና መድ​ኃ​ኒ​ታ​ችን ሆይ ስማን።</verse>
				<verse number="6">በኀ​ይ​ልህ ተራ​ሮ​ችን አጸ​ና​ሃ​ቸው፥ እነ​ር​ሱም በኀ​ይል ታጥ​ቀ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">የባ​ሕ​ሩን ዓሣ አን​በሪ የሚ​ያ​ው​ከው እርሱ ነው የሞ​ገ​ድ​ዋ​ንም ድምፅ የሚ​ቃ​ወ​መው ማን ነው?</verse>
				<verse number="8">ከተ​አ​ም​ራ​ትህ የተ​ነሣ አሕ​ዛብ ይደ​ን​ግ​ጣሉ፥ በም​ድር ዳር​ቻም የሚ​ኖሩ ይፈ​ራሉ፤ በጥ​ዋት ይወ​ጣሉ፥ ማታም ይደ​ሰ​ታሉ።</verse>
				<verse number="9">ምድ​ርን ጐበ​ኘ​ሃት አረ​ካ​ሃ​ትም፥ ብል​ጽ​ግ​ና​ዋ​ንም እጅግ አበ​ዛህ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወንዝ ውኆ​ችን የተ​መላ ነው፤ ምግ​ባ​ቸ​ውን አዘ​ጋ​ጀህ፥ እን​ዲሁ ታሰ​ና​ዳ​ለ​ህና።</verse>
				<verse number="10">ትል​ም​ዋን አር​ካው፥ መከ​ሯ​ንም አብ​ጀው፤ በነ​ጠ​ብ​ጣ​ብ​ህም ደስ ብሏት ትበ​ቅ​ላ​ለች</verse>
				<verse number="11">የም​ሕ​ረ​ት​ህን ዓመት አክ​ሊል ትባ​ር​ካ​ለህ ምድረ በዳ​ዎ​ችም ጠልን ይጠ​ግ​ባሉ።</verse>
				<verse number="12">የም​ድረ በዳ ተራ​ሮች ይረ​ካሉ፥ ኮረ​ብ​ቶ​ችም በደ​ስታ ይታ​ጠ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="13">የበ​ጎች አው​ራ​ዎ​ችም ስብን ይለ​ብ​ሳሉ፥ ሸለ​ቆ​ዎ​ችም ስን​ዴን ይመ​ላሉ፤ እየ​ጮሁ ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="65">
				<verse number="1">በም​ድር ያላ​ቸሁ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እልል በሉ፥</verse>
				<verse number="2">ለስ​ሙም ዘምሩ፥ ለክ​ብ​ሩም ምስ​ጋ​ናን ስጡ።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲህ በሉት፥ “ሥራህ ግሩም ነው፤ ኀይ​ልህ ብዙ ሲሆን ጠላ​ቶ​ችህ ዋሹ​ብህ።”</verse>
				<verse number="4">ምድር ሁላ ለአ​ንተ ትሰ​ግ​ዳ​ለች፥ ለአ​ን​ተም ትገ​ዛ​ለች፥ ለስ​ም​ህም ትዘ​ም​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="5">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ታዩ ዘንድ ኑ። ምክሩ ከሰው ልጆች ይልቅ ግሩም ነው።</verse>
				<verse number="6">ባሕ​ርን የብስ አደ​ረ​ጋት፥ ወን​ዙ​ንም በእ​ግር ተሻ​ገሩ፤ በዚያ በእ​ርሱ ደስ ይለ​ናል።</verse>
				<verse number="7">በኀ​ይሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይገ​ዛል፤ ዐይ​ኖቹ ወደ አሕ​ዛብ ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤ የም​ታ​ውቁ ራሳ​ች​ሁን ከፍ ከፍ አታ​ድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="8">አሕ​ዛብ ሆይ፥ አም​ላ​ካ​ች​ንን አመ​ስ​ግኑ፥ የም​ስ​ጋ​ና​ው​ንም ቃል አድ​ምጡ።</verse>
				<verse number="9">ነፍ​ሴን በሕ​ይ​ወት ያኖ​ራ​ታል፥ ለእ​ግ​ሮቼም ሁከ​ትን አል​ሰ​ጠም።</verse>
				<verse number="10">አቤቱ፥ ፈት​ነ​ኸ​ና​ልና፥ ብር​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ነ​ጥ​ሩት አን​ጥ​ረ​ኸ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="11">ወደ ወጥ​መ​ድም አገ​ባ​ኸን፥ በፊ​ታ​ች​ንም መከ​ራን አመ​ጣህ።</verse>
				<verse number="12">በራ​ሳ​ችን ላይ ሰውን አስ​ጫ​ንህ፤ በእ​ሳ​ትና በውኃ መካ​ከል አሳ​ለ​ፍ​ኸን፥ ወደ ዕረ​ፍ​ትም አወ​ጣ​ኸን።</verse>
				<verse number="13">መባ​ዬን ይዤ ወደ ቤትህ እገ​ባ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="14">በመ​ከ​ራዬ ጊዜ በአፌ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን በከ​ን​ፈ​ሮ​ቼም ያል​ሁ​ትን ስእ​ለ​ቴን ለአ​ንተ እሰ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">ከዕ​ጣ​ንና ከሙ​ክ​ቶች ጋር ነውር የሌ​ለ​በት ንጹሕ መሥ​ዋ​ዕ​ትን አቀ​ር​ብ​ል​ሃ​ለሁ፤ ላሞ​ች​ንና ፍየ​ሎ​ች​ንም እሠ​ዋ​ል​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈ​ሩት ሁሉ፥ ኑ፥ ስሙኝ፤ ለነ​ፍሴ ያደ​ረ​ገ​ላ​ትን ልን​ገ​ራ​ችሁ።</verse>
				<verse number="17">በአፌ ወደ እርሱ ጮኽሁ፥ በአ​ን​ደ​በ​ቴም ከፍ ከፍ አደ​ረ​ግ​ሁት።</verse>
				<verse number="18">በል​ቤስ በደ​ልን አይቶ ቢሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ሰ​ማ​ኝም ነበር።</verse>
				<verse number="19">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰማኝ፤ የል​መ​ና​ዬ​ንም ድምፅ አደ​መጠ።</verse>
				<verse number="20">ጸሎ​ቴን ያል​ከ​ለ​ከ​ለኝ፥ ምሕ​ረ​ቱ​ንም ከእኔ ያላ​ራቀ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="66">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይማ​ረን ይባ​ር​ከ​ንም፥ ፊቱ​ንም በላ​ያ​ችን ያብራ፤ እኛም በሕ​ይ​ወት እን​ኑር</verse>
				<verse number="2">መን​ገ​ድ​ህን በም​ድር፥ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ዘንድ ማዳ​ን​ህን እና​ውቅ ዘንድ፥</verse>
				<verse number="3">አቤቱ፥ አሕ​ዛብ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፥ አሕ​ዛብ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል። አሕ​ዛብ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ ሐሤ​ትም ያደ​ር​ጋሉ።</verse>
				<verse number="4">ለአ​ሕ​ዛብ በቅን ትፈ​ር​ድ​ላ​ቸ​ዋ​ለ​ህና፥ አሕ​ዛ​ብ​ንም በም​ድር ላይ ትመ​ራ​ለ​ህና</verse>
				<verse number="5">አቤቱ፥ አሕ​ዛብ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል። አሕ​ዛብ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል።</verse>
				<verse number="6">ምድር ፍሬ​ዋን ሰጠች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ች​ንም ይባ​ር​ከ​ናል፥ የም​ድ​ርም ዳርቻ ሁሉ ይፈ​ሩ​ታል።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ር​ከ​ናል፥ የም​ድ​ርም ዳር​ቻ​ዎች ሁሉ ይፈ​ሩ​ታል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="67">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይነሣ፥ ጠላ​ቶ​ቹም ይበ​ተኑ፥ የሚ​ጠ​ሉ​ትም ከፊቱ ይሽሹ።</verse>
				<verse number="2">ጢስ እን​ደ​ሚ​በ​ንን እን​ዲሁ ይብ​ነኑ፤ ሰም በእ​ሳት ፊት እን​ደ​ሚ​ቀ​ልጥ፥ እን​ዲሁ ኃጥ​ኣን ከአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይጥፉ።</verse>
				<verse number="3">ጻድ​ቃን ግን ደስ ይበ​ላ​ቸው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ሐሤ​ትን ያድ​ርጉ፥ በደ​ስ​ታም ደስ ይበ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤ ለስ​ሙም ዘምሩ፤ ወደ ምዕ​ራብ ለወ​ጣው መን​ገ​ድን አብጁ፤ ስሙ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥ በፊ​ቱም ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ከፊ​ቱም የተ​ነሣ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቅ​ዱስ ቦታው ለድሃ አደ​ጎች አባት፥ ለባ​ል​ቴ​ቶ​ችም ዳኛ ነው።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቸ​ኞ​ችን በቤቱ ያሳ​ድ​ራ​ቸ​ዋል፥ እስ​ረ​ኞ​ች​ንም በኀ​ይሉ ያወ​ጣ​ቸ​ዋል፤ በመ​ቃ​ብር የሚ​ኖሩ ኀዘ​ን​ተ​ኞ​ች​ንም እን​ዲሁ።</verse>
				<verse number="7">አቤቱ፥ በሕ​ዝ​ብህ ፊት በወ​ጣህ ጊዜ፥ በም​ድረ በዳም ባለ​ፍህ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="8">ከሲና አም​ላክ ፊት፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ፊት ምድር ተና​ወ​ጠች፥ ሰማ​ያ​ትም አን​ጠ​ባ​ጠቡ።</verse>
				<verse number="9">አቤቱ፥ በፈ​ቃ​ድህ ዝና​ብን ለር​ስ​ትህ ለየህ፥ በደ​ከ​መም ጊዜ አንተ ታጸ​ና​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="10">እን​ስ​ሶ​ችህ በው​ስጡ ያድ​ራሉ፤ አቤቱ፥ በቸ​ር​ነ​ትህ ለድ​ሆች አዘ​ጋ​ጀህ።</verse>
				<verse number="11">ብዙ ኀይ​ልን ለሚ​ያ​ወሩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃሉን ሰጠ፤</verse>
				<verse number="12">ለኀ​ያ​ላን ንጉሥ ለወ​ዳጁ፤ ለወ​ዳ​ጁና ለቤ​ትህ ውበት ምር​ኮን ተካ​ፈ​ልን።</verse>
				<verse number="13">በር​ስ​ቶች መካ​ከል ብታ​ድሩ፥ ከብር እንደ ተሠሩ እንደ ርግብ ክን​ፎች፥ በቅ​ጠ​ልያ ወር​ቅም እንደ ተለ​በጡ ላባ​ዎ​ችዋ ትሆ​ና​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="14">ሰማ​ያዊ ንጉሥ በላ​ይዋ ባዘዘ ጊዜ፥ በሰ​ል​ሞን ላይ በረዶ ይዘ​ን​ማል።</verse>
				<verse number="15">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ የለ​መ​ለመ ተራራ ነው፤ የጸና ተራ​ራና የለ​መ​ለመ ተራራ ነው።</verse>
				<verse number="16">የጸኑ ተራ​ራ​ዎች ለምን ይነ​ሣሉ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ር​በት ዘንድ የወ​ደ​ደው ተራራ ይህ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያድ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="17">የብዙ ብዙ ሺህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰረ​ገ​ላ​ዎች ደስ​ተ​ኞች ናቸው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ቅ​ደሱ በሲና በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ነው።</verse>
				<verse number="18">ምር​ኮን ማር​ከህ ወደ ሰማይ ወጣህ ስጦ​ታ​ህ​ንም ለሰ​ዎች ሰጠህ፥ ያድሩ ዘንድ ይክዱ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ቡሩክ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በየ​ዕ​ለቱ ቡሩክ ነው፤ አም​ላ​ካ​ች​ንና መድ​ኃ​ኒ​ታ​ችን ይረ​ዳ​ናል።</verse>
				<verse number="20">አም​ላ​ካ​ች​ንስ የማ​ዳን አም​ላክ ነው፤ የሞት መን​ገድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።</verse>
				<verse number="21">ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጠ​ላ​ቶ​ቹን ራስ ይሰ​ብ​ራል፥ በጠ​ጉ​ራ​ቸው ጫፍም በደ​ላ​ቸው ይሄ​ዳል።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አለ፦ ወጥቼ እመ​ለ​ሳ​ለሁ፥ በባ​ሕ​ሩም ጥልቅ እመ​ለ​ሳ​ለሁ፥</verse>
				<verse number="23">እግ​ሮ​ችህ በደም ይነ​ከሩ ዘንድ፥ የው​ሾ​ችህ ምላስ በጠ​ላ​ቶ​ችህ ላይ ነው።</verse>
				<verse number="24">አቤቱ፥ መን​ገ​ድህ ተገ​ለጠ። የአ​ም​ላ​ካ​ችን የን​ጉሡ መን​ገድ በመ​ቅ​ደሱ</verse>
				<verse number="25">አለ​ቆች ደረሱ፥ መዘ​ም​ራ​ንም አሏ​ቸው ከበ​ሮን በሚ​መቱ በደ​ና​ግል መካ​ከል።</verse>
				<verse number="26">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በጉ​ባኤ፥ አም​ላ​ካ​ች​ን​ንም በእ​ስ​ራ​ኤል ምን​ጮች አመ​ሰ​ገ​ኑት።</verse>
				<verse number="27">ወጣቱ ብን​ያም በጉ​ል​በቱ በዚያ አለ፥ ገዦ​ቻ​ቸው የይ​ሁዳ አለ​ቆች፥ የዛ​ብ​ሎን አለ​ቆ​ችና የን​ፍ​ታ​ሌ​ምም አለ​ቆች።</verse>
				<verse number="28">አቤቱ፥ በኀ​ይ​ልህ እዘዝ፤ አቤቱ፥ ይህን ለእኛ የሠ​ራ​ኸ​ውን አጽ​ናው።</verse>
				<verse number="29">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለው መቅ​ደ​ስህ ነገ​ሥ​ታት እጅ መን​ሻን ለአ​ንተ ያመ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="30">በቀ​ር​ካሃ ውስጥ ያሉ​ትን አራ​ዊት፥ በሕ​ዝብ ጊደ​ሮች መካ​ከል የበ​ሬ​ዎ​ችን ጉባኤ ገሥጽ፥ እንደ ብር የተ​ፈ​ተ​ኑት አሕ​ዛብ እን​ዳ​ይ​ዘጉ፤ ሰል​ፍን የሚ​ወ​ድ​ዱ​ትን አሕ​ዛ​ብን በት​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="31">መል​እ​ክ​ተ​ኞች ከግ​ብፅ ይምጡ፤ ኢት​ዮ​ጵያ እጆ​ች​ዋን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትዘ​ረ​ጋ​ለች።</verse>
				<verse number="32">የም​ድር ነገ​ሥ​ታት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም ዘምሩ።</verse>
				<verse number="33">በም​ሥ​ራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማ​ያት ለወጣ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ፤ የኀ​ይል ቃል የሆነ ቃሉን፥ እነሆ፥ ይሰ​ጣል።</verse>
				<verse number="34">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋ​ናን ስጡ፤ ግር​ማው በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ፥ ኀይ​ሉም እስከ ደመ​ናት ነው።</verse>
				<verse number="35">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቅ​ዱ​ሳኑ ላይ ድንቅ ነው፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እርሱ ኀይ​ልን ብር​ታ​ት​ንም ለሕ​ዝቡ ይሰ​ጣል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="68">
				<verse number="1">አቤቱ፥ ውኃ እስከ ነፍሴ ደር​ሶ​ብ​ኛ​ልና አድ​ነኝ።</verse>
				<verse number="2">በጥ​ልቅ ረግ​ረግ ጠለ​ቅሁ ኀይ​ልም የለ​ኝም፤ ወደ ጥልቁ ባሕ​ርም ደረ​ስሁ ማዕ​በ​ሉም አሰ​ጠ​መኝ።</verse>
				<verse number="3">በጩ​ኸት ደከ​ምሁ፥ ጉሮ​ሮ​ዬም ሻከረ፤ አም​ላ​ኬን ተስፋ ሳደ​ርግ ዐይ​ኖቼ ፈዘዙ።</verse>
				<verse number="4">በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ሉኝ ከራሴ ጠጉር በዙ፤ በዐ​መፅ የሚ​ከ​ብ​ቡኝ ጠላ​ቶቼ በረቱ፤ ያል​ወ​ሰ​ድ​ሁ​ትን ይከ​ፈ​ሉ​ኛል።</verse>
				<verse number="5">አቤቱ፥ አንተ ስን​ፍ​ና​ዬን ታው​ቃ​ለህ፥ ኃጢ​አ​ቴም ከአ​ንተ አል​ተ​ሰ​ወ​ረም።</verse>
				<verse number="6">አቤቱ፥ የሠ​ራ​ዊት አም​ላክ፥ የሚ​ሹህ በእኔ አይ​ፈሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉህ በእኔ አይ​ነ​ወሩ።</verse>
				<verse number="7">ስለ አንተ ስድ​ብን ታግ​ሻ​ለ​ሁና፥ እፍ​ረ​ትም ፊቴን ሸፍ​ኖ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="8">ለወ​ን​ድ​ሞቼ እንደ ባዕድ፥ ለአ​ባ​ቴና ለእ​ና​ቴም ልጆች እንደ እን​ግዳ ሆን​ሁ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">የቤ​ትህ ቅን​ዓት በል​ቶ​ኛ​ልና፥ የሚ​ሰ​ድ​ቡ​ህም ስድብ በላዬ ወድ​ቆ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="10">ሰው​ነ​ቴን በጾም አደ​ከ​ም​ኋት፥ ስድ​ብ​ንም ሆነ​ብኝ።</verse>
				<verse number="11">ማቅ ለበ​ስሁ መተ​ረ​ቻም ሆን​ሁ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">በደጅ የሚ​ቀ​መጡ በእኔ ይጫ​ወ​ታሉ፤ ወይን የሚ​ጠ​ጡም በእኔ ይዘ​ፍ​ናሉ።</verse>
				<verse number="13">እኔስ በጸ​ሎቴ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታው በጊ​ዜው ነው፤ ይቅ​ር​ታህ ብዙ ሲሆን መድ​ኃ​ኒቴ ሆይ፥ በእ​ው​ነት አድ​ነኝ።</verse>
				<verse number="14">እን​ዳ​ይ​ው​ጠኝ ከረ​ግ​ረግ አው​ጣኝ፤ ከጠ​ላ​ቶ​ችና ከጥ​ልቅ ውኃ አስ​ጥ​ለኝ።</verse>
				<verse number="15">የውኃ ማዕ​በል አያ​ስ​ጥ​መኝ፥ ጥል​ቁም አይ​ዋ​ጠኝ፥ ጕድ​ጓ​ዶ​ችም አፋ​ቸ​ውን በኔ ላይ አይ​ክ​ፈቱ፤</verse>
				<verse number="16">አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ትህ መል​ካም ናትና ስማኝ፤ እንደ ይቅ​ር​ታ​ህም ብዛት ወደ እኔ ተመ​ል​ከት፤</verse>
				<verse number="17">ከባ​ሪ​ያ​ህም ፊት​ህን አት​መ​ልስ፤ ተጨ​ን​ቄ​አ​ለ​ሁና ፈጥ​ነህ ስማኝ።</verse>
				<verse number="18">ነፍ​ሴን ተመ​ል​ክ​ተህ ተቤ​ዣት፤ ስለ ጠላ​ቶ​ችም አድ​ነኝ።</verse>
				<verse number="19">አንተ ስድ​ቤን፥ እፍ​ረ​ቴ​ንም፥ ነው​ሬ​ንም ታው​ቃ​ለህ፤ በሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ሁሉ ፊት።</verse>
				<verse number="20">ሰው​ነቴ ስድ​ብ​ንና ውር​ደ​ትን ታገ​ሠች፤ አዝኜ ተቀ​መ​ጥሁ፥ የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ኝ​ም አጣሁ።</verse>
				<verse number="21">በመ​ብሌ ውስጥ ሐሞ​ትን ጨመሩ፥ ለጥ​ማ​ቴም ሆም​ጣ​ጤን አጠ​ጡኝ።</verse>
				<verse number="22">ማዕ​ዳ​ቸው በፊ​ታ​ቸው ለወ​ጥ​መድ፥ ለፍ​ዳና ለዕ​ን​ቅ​ፋት ትሁ​ን​ባ​ቸው፤</verse>
				<verse number="23">ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ያዩ ይጨ​ልሙ፥ ጀር​ባ​ቸ​ውም ዘወ​ትር ይጉ​በጥ።</verse>
				<verse number="24">መዓ​ት​ህን በላ​ያ​ቸው አፍ​ስስ፥ የቍ​ጣህ መቅ​ሠ​ፍ​ትም ያግ​ኛ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">ከተ​ማ​ቸው በረሃ ትሁን፥ በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም የሚ​ቀ​መጥ አይ​ገኝ፤</verse>
				<verse number="26">አንተ የቀ​ሠ​ፍ​ኸ​ውን እነ​ርሱ ተከ​ት​ለ​ዋ​ልና፥ በቍ​ስ​ሌም ላይ ቍስ​ልን ጨመ​ሩ​ብኝ።</verse>
				<verse number="27">በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ላይ ኃጢ​አ​ትን ጨም​ር​ባ​ቸው፥ በጽ​ድ​ቅ​ህም አይ​ግቡ።</verse>
				<verse number="28">ከሕ​ያ​ዋን መጽ​ሐፍ ይደ​ም​ሰሱ፥ ከጻ​ድ​ቃ​ንም ጋር አይ​ጻፉ።</verse>
				<verse number="29">እኔ ድሃና ቍስ​ለኛ ነኝ፤ የፊቴ፥ መድ​ኀ​ኒት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቀ​በ​ለኝ።</verse>
				<verse number="30">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም በዝ​ማሬ አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥ በም​ስ​ጋ​ናም ከፍ ከፍ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="31">ቀን​ድና ጥፍር ካላ​በ​ቀለ ከእ​ም​ቦሳ ይልቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ አሰ​ኘ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="32">ድሆች ይዩ ደስም ይበ​ላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈል​ጉት፥ ነፍ​ሳ​ች​ሁም ትድ​ና​ለች።</verse>
				<verse number="33">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድሆ​ችን ሰም​ቶ​እ​ቸ​ዋ​ልና፥ እስ​ረ​ኞ​ች​ንም አል​ና​ቃ​ቸ​ው​ምና።</verse>
				<verse number="34">ሰማ​ይና ምድር፥ ባሕ​ርም፥ በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀሱ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።</verse>
				<verse number="35">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዮ​ንን አድ​ኗ​ታ​ልና፥ የይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ይሠ​ራ​ሉና፤ በዚ​ያም ይቀ​መ​ጣሉ ይወ​ር​ሷ​ታ​ልም።</verse>
				<verse number="36">የባ​ሪ​ያ​ዎ​ችህ ዘሮች ይኖ​ሩ​ባ​ታል፥ ስም​ህን የሚ​ወ​ድዱ በው​ስጧ ይቀ​መ​ጣሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="69">
				<verse number="1">አቤቱ፥ እኔን ለማ​ዳን ተመ​ል​ከት፤ አቤቱ፥ እኔን ለመ​ር​ዳት ፍጠን።</verse>
				<verse number="2">ነፍ​ሴን የሚ​ሹ​አት ይፈሩ፥ ይጐ​ስ​ቍ​ሉም፥ ክፉ​ንም የሚ​መ​ክ​ሩ​ብኝ ወደ​ኋ​ላ​ቸው ይመ​ለሱ፥ ይፈ​ሩም።</verse>
				<verse number="3">እሰይ! እሰይ! የሚ​ሉኝ አፍ​ረው ወዲ​ያው ወደ ኋላ​ቸው ይመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="4">አቤቱ፥ የሚ​ሹህ ሁሉ በአ​ንተ ሐሤት ያድ​ርጉ፥ ደስም ይበ​ላ​ቸው፤ ሁል​ጊዜ ማዳ​ን​ህን የሚ​ወ​ድዱ፥ “ዘወ​ትር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው” ይበሉ።</verse>
				<verse number="5">እኔ ድሃና ምስ​ኪን ነኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይረ​ዳ​ኛል፤ ረዳቴ መጠ​ጊ​ያ​ዬም አንተ ነህ፥ አቤቱ አም​ላኬ አት​ዘ​ግይ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="70">
				<verse number="1">አቤቱ፥ አን​ተን ታመ​ንሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አላ​ፍ​ርም።</verse>
				<verse number="2">በጽ​ድ​ቅህ አስ​ጥ​ለኝ፥ ታደ​ገ​ኝም፤ ጆሮ​ህን ወደ እኔ አዘ​ን​ብል፥ ፈጥ​ነ​ህም አድ​ነኝ።</verse>
				<verse number="3">በጠ​ን​ካራ ቦታ ታድ​ነኝ ዘንድ አም​ላ​ኬና መድ​ኀ​ኒቴ ሁነኝ፤ ኀይ​ሌና መጠ​ጊ​ያዬ አንተ ነህና።</verse>
				<verse number="4">አም​ላኬ ከኃ​ጥ​ኣን እጅ፥ ከዐ​መ​ፀ​ኛና ከግ​ፈ​ኛም እጅ አድ​ነኝ።</verse>
				<verse number="5">አቤቱ፥ አንተ ተስ​ፋዬ ነህና፥ ጌታዬ ሆይ፥ ከታ​ና​ሽ​ነቴ ጀምሬ ተስፋ አደ​ረ​ግ​ሁህ።</verse>
				<verse number="6">በእ​ናቴ ማኅ​ፀን በአ​ንተ ጸናሁ፥ በማ​ኅ​ፀን ውስ​ጥም አንተ ሸሸ​ግ​ኸኝ፤ ሁል​ጊ​ዜም ስም አጠ​ራሬ አንተ ነህ።</verse>
				<verse number="7">ለብ​ዙ​ዎች እንደ ጥንግ ሆንሁ፤ አንተ ግን ረዳ​ቴና ኀይሌ ነህ።</verse>
				<verse number="8">አፌን በም​ስ​ጋና ምላ ሁል​ጊዜ ምስ​ጋ​ና​ህ​ንና የክ​ብ​ር​ህን ገና​ና​ነት አመ​ሰ​ግን ዘንድ።</verse>
				<verse number="9">በእ​ር​ጅ​ናዬ ዘመን አት​ጣ​ለኝ፥ ጉል​በ​ቴም ባለቀ ጊዜ አም​ላኬ አት​ተ​ወኝ።</verse>
				<verse number="10">ጠላ​ቶቼ በእኔ ላይ ተና​ግ​ረ​ዋ​ልና፥ ነፍ​ሴ​ንም የሚ​ሹ​አት በአ​ን​ድ​ነት ተማ​ክ​ረ​ዋ​ልና፥ እን​ዲ​ህም አሉ፦</verse>
				<verse number="11">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቶ​ታል፤ የሚ​ያ​ድ​ነው የለ​ምና ተከ​ት​ላ​ችሁ ያዙት።”</verse>
				<verse number="12">አም​ላኬ ሆይ፥ ከእኔ አት​ራቅ፤ አም​ላኬ ሆይ፥ እኔን ለመ​ር​ዳት ተመ​ል​ከት።</verse>
				<verse number="13">ነፍ​ሴን የሚ​ያ​ጣ​ሏት ይፈሩ፥ ይዋ​ረ​ዱም፥ ጉዳ​ቴ​ንም የሚ​ፈ​ልጉ ዕፍ​ረ​ት​ንና ኃሣ​ርን ይል​በሱ።</verse>
				<verse number="14">እኔ ግን አቤቱ ሁል​ጊዜ ተስፋ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፥ በም​ስ​ጋ​ና​ህም ሁሉ ላይ እጨ​ም​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">አፌ ጽድ​ቅ​ህን፥ ሁል​ጊ​ዜም ማዳ​ን​ህን ይና​ገ​ራል። ሥራን አላ​ው​ቅ​ምና</verse>
				<verse number="16">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል እገ​ባ​ለሁ፤ አቤቱ፥ ጽድ​ቅ​ህን ብቻ አስ​ባ​ለሁ።</verse>
				<verse number="17">አም​ላኬ ከታ​ና​ሽ​ነቴ ጀም​ረህ አስ​ተ​ማ​ር​ኸኝ፤ እስከ ዛሬም ክብ​ር​ህን እና​ገ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="18">አም​ላኬ ሆይ እስ​ክ​ሸ​መ​ግ​ልም ድረስ፥ ለሚ​መጣ ትው​ል​ድም ሁሉ ክን​ድ​ህን ኀይ​ል​ህ​ንም ጽድ​ቅ​ህ​ንም እስ​ክ​ነ​ግር ድረስ፥ አት​ተ​ወኝ።</verse>
				<verse number="19">አቤቱ፥ እስከ አር​ያም ታላ​ላቅ ነገ​ሮ​ችን አደ​ረ​ግህ፤ አም​ላክ ሆይ፥ እን​ዳ​ንተ ያለ ማን ነው?</verse>
				<verse number="20">ብዙ ጭን​ቀ​ት​ንና መከ​ራን አሳ​ይ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፥ ተመ​ል​ሰ​ህም ሕያው አደ​ረ​ግ​ኸኝ፤ ከም​ድር ጥል​ቅም እን​ደ​ገና አወ​ጣ​ኸኝ።</verse>
				<verse number="21">ጽድ​ቅ​ህ​ንም አበ​ዛ​ኸው። ደስ ታሰ​ኘ​ኝም ዘንድ ተመ​ለ​ስህ። ከም​ድር ጥል​ቅም እንደ ገና አወ​ጣ​ኸኝ።</verse>
				<verse number="22">እኔም በመ​ዝ​ሙር መሣ​ሪያ ስለ እው​ነ​ትህ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ አም​ላክ ሆይ፥ በመ​ሰ​ንቆ እዘ​ም​ር​ል​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="23">ዝማ​ሬን ባቀ​ረ​ብ​ሁ​ልህ ጊዜ ከን​ፈ​ሮ​ቼን ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ ነፍ​ሴ​ንም አንተ አዳ​ን​ሃት።</verse>
				<verse number="24">ክፉን ለእኔ የሚሹ ባፈ​ሩና በተ​ነ​ወሩ ጊዜ፥ አን​ደ​በቴ ደግሞ ሁል​ጊዜ ጽድ​ቅ​ህን ይና​ገ​ራል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="71">
				<verse number="1">አቤቱ፥ ፍር​ድ​ህን ለን​ጉሥ ስጠው፥ ጽድ​ቅ​ህ​ንም ለን​ጉሥ ልጅ፥</verse>
				<verse number="2">ሕዝ​ብ​ህን በጽ​ድቅ፥ ድሆ​ች​ህ​ንም በፍ​ርድ ይዳኝ ዘንድ።</verse>
				<verse number="3">ተራ​ሮ​ችና ኮረ​ብ​ቶች የሕ​ዝ​ብ​ህን ሰላም ይቀ​በሉ።</verse>
				<verse number="4">ለድ​ሆች ሕዝ​ብህ በጽ​ድቅ ፍረድ፥ የድ​ሆ​ች​ንም ልጆች አድ​ና​ቸው። ትዕ​ቢ​ተ​ኛ​ው​ንም አዋ​ር​ደው።</verse>
				<verse number="5">ፀሐይ በሚ​ኖ​ር​በት ዘመን ሁሉ፥ በጨ​ረ​ቃም ፊት ለልጅ ልጅ ይኑር።</verse>
				<verse number="6">እንደ ጠል በባ​ዘቶ ላይ፥ በም​ድ​ርም ላይ እን​ደ​ሚ​ን​ጠ​ባ​ጠብ ጠብታ ይወ​ር​ዳል።</verse>
				<verse number="7">በዘ​መ​ኑም ጽድቅ ይበ​ቅ​ላል፥ ጨረ​ቃም እስ​ኪ​ያ​ልፍ ድረስ ሰላም ብዙ ነው።</verse>
				<verse number="8">ከባ​ሕር እስከ ባሕር ድረስ፥ ከወ​ን​ዝም እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ይገ​ዛል።</verse>
				<verse number="9">በፊ​ቱም ኢት​ዮ​ጵያ ይሰ​ግ​ዳሉ፥ ጠላ​ቶ​ቹም አፈ​ርን ይል​ሳሉ።</verse>
				<verse number="10">የተ​ር​ሴ​ስና የደ​ሴ​ቶች ነገ​ሥ​ታት ስጦ​ታን ያመ​ጣሉ፤ የሳ​ባና የዓ​ረብ ነገ​ሥ​ታት እጅ መን​ሻን ያመ​ጣሉ፤</verse>
				<verse number="11">የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል ፥ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ ይገ​ዙ​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="12">ድሃ​ውን ከሚ​ቀ​ማው እጅ፥ ረዳት የሌ​ለ​ው​ንም ምስ​ኪን ያድ​ነ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="13">ለድ​ሃና ለም​ስ​ኪን ይራ​ራል፥ የድ​ሆ​ች​ንም ነፍስ ያድ​ናል።</verse>
				<verse number="14">ከአ​ራ​ጣና ከቅ​ሚያ ነፍ​ሳ​ቸ​ውን ያድ​ና​ታል፤ ስሙም በፊ​ታ​ቸው ክቡር ነው።</verse>
				<verse number="15">እርሱ ይኖ​ራል፥ ከዓ​ረ​ብም ወር​ቅን ይሰ​ጡ​ታል፤ ሁል​ጊ​ዜም ስለ እርሱ ይጸ​ል​ያሉ፥ ዘወ​ት​ርም ይመ​ር​ቁ​ታል።</verse>
				<verse number="16">በተ​ራ​ሮች ራስ ላይ ለም​ድር ሁሉ መጠ​ጊያ ይሆ​ናል፤ ፍሬ​ውም ከሊ​ባ​ኖስ ዛፍ ይልቅ ከፍ ከፍ ይላል፤ እንደ ምድር ሣር በከ​ተማ ይበ​ቅ​ላል።</verse>
				<verse number="17">ስሙ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቡሩክ ነው፥ ከፀ​ሓ​ይም አስ​ቀ​ድሞ ስሙ ነበረ፤ የም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ በእ​ርሱ ይባ​ረ​ካሉ፥ ሕዝቡ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።</verse>
				<verse number="18">ብቻ​ውን ተአ​ም​ራ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።</verse>
				<verse number="19">የም​ስ​ጋ​ናው ስም ለዓ​ለ​ምና ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይባ​ረክ፤ ምስ​ጋ​ና​ውም ምድ​ርን ሁሉ ይምላ። ይሁን፤ ይሁን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="72">
				<verse number="1">ልባ​ቸው ለቀና ለእ​ስ​ራ​ኤል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅግ ቸር ነው።</verse>
				<verse number="2">እኔ ግን እግ​ሮች ሊሰ​ና​ከሉ፥ አረ​ማ​መ​ዴም ሊወ​ድቅ ጥቂት ቀረ።</verse>
				<verse number="3">የዐ​መ​ፀ​ኞ​ችን ሰላም አይቼ በኃ​ጥ​ኣን ላይ ቀንቼ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="4">ለሞ​ታ​ቸው እረ​ፍት የለ​ው​ምና፤ ለመ​ቅ​ሠ​ፍ​ታ​ቸ​ውም ኀይል የለ​ው​ምና፤</verse>
				<verse number="5">በድ​ካ​ምም ጠላት አል​ሆ​ኑም። ከሰው ጋርም አል​ተ​ገ​ረ​ፉም።</verse>
				<verse number="6">ስለ​ዚ​ህም ትዕ​ቢት ያዛ​ቸው፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንና በደ​ላ​ቸ​ውን ተጐ​ና​ጸ​ፉ​አት።</verse>
				<verse number="7">መቅን ከቅ​ል​ጥም እን​ደ​ሚ​ወጣ ኀጢ​አ​ታ​ቸው ይወ​ጣል። ልባ​ቸ​ውም ከት​ዕ​ቢት አለፈ።</verse>
				<verse number="8">ዐስ​በው ከንቱ ነገ​ርን ተና​ገሩ። በአ​ር​ያ​ምም ዐመ​ፃን ተና​ገሩ።</verse>
				<verse number="9">አፋ​ቸ​ው​ንም በሰ​ማይ አኖሩ፥ አን​ደ​በ​ታ​ቸ​ውም በም​ድር ላይ ተመ​ላ​ለሰ።</verse>
				<verse number="10">ስለ​ዚህ ሕዝቤ ወደ​ዚህ ይመ​ለ​ሳሉ፤ ፍጹም ጊዜም በላ​ያ​ቸው ይገ​ኛል፤</verse>
				<verse number="11">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዴት ያው​ቃል? በአ​ር​ያ​ምስ በውኑ የሚ​ያ​ውቅ አለን?” ይላሉ።</verse>
				<verse number="12">እነሆ፥ እነ​ዚህ ኃጥ​ኣን ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ሁል​ጊ​ዜም ባለ​ጠ​ግ​ነ​ታ​ቸ​ውን ያጸ​ኗ​ታል፤</verse>
				<verse number="13">እን​ዲ​ህም አልሁ፥ “በውኑ ልቤን በከ​ንቱ አጸ​ደ​ቅ​ሁ​አ​ትን?” እጆ​ቼ​ንም በን​ጽ​ሕና አጠ​ብሁ።</verse>
				<verse number="14">ሁል​ጊ​ዜም የተ​ገ​ረ​ፍሁ ሆንሁ፥ መሰ​ደ​ቤም በማ​ለዳ ነው።</verse>
				<verse number="15">እን​ደ​ዚህ ብዬ ብና​ገር ኖሮ፥ እነሆ፥ የል​ጆ​ች​ህን ትው​ልድ በበ​ደ​ልሁ ነበር።</verse>
				<verse number="16">አው​ቅም ዘንድ ተቀ​በ​ል​ኸኝ፥ ይህ ግን በፊቴ ድካም ነው።</verse>
				<verse number="17">ፍጻ​ሜ​አ​ቸ​ውን አውቅ ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ እስ​ክ​ገባ ድረስ፥</verse>
				<verse number="18">ነገር ግን ስለ ሽን​ገ​ላ​ቸው አቈ​የ​ሃ​ቸው፥ በመ​ነ​ሣ​ታ​ቸ​ውም ጣል​ኻ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">እን​ዴት ለጥ​ፋት ሆኑ! በድ​ን​ገት አለቁ፥ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ጠፉ።</verse>
				<verse number="20">ከእ​ን​ቅ​ልፍ እን​ደ​ሚ​ነቃ፥ አቤቱ፥ በከ​ተ​ማህ ምል​ክ​ታ​ቸ​ውን ታስ​ነ​ው​ራ​ለህ።</verse>
				<verse number="21">ልቤ ነድ​ዶ​አል፥ ኵላ​ሊ​ቴም ቀል​ጦ​አ​ልና፤</verse>
				<verse number="22">እኔ የተ​ና​ቅሁ ነኝ፥ አላ​ወ​ቅ​ሁ​ምም፥ በአ​ንተ ዘንድ እንደ እን​ስሳ ሆንሁ።</verse>
				<verse number="23">እኔ ግን ዘወ​ትር ከአ​ንተ ጋር ነኝ፥ ቀኝ እጄ​ንም ያዝ​ኸኝ።</verse>
				<verse number="24">በአ​ንተ ምክር መራ​ኸኝ፤ በክ​ብ​ርም ተቀ​በ​ል​ኸኝ።</verse>
				<verse number="25">በሰ​ማይ ያለኝ ምን​ድን ነው? በም​ድ​ርስ ውስጥ ከአ​ንተ በቀር ምን እሻ​ለሁ?</verse>
				<verse number="26">የመ​ድ​ኀ​ኒቴ አም​ላክ ሆይ፥ ልቤና ሥጋዬ አለቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዕድል ፋን​ታዬ ነው።</verse>
				<verse number="27">እነሆ፥ ከአ​ንተ የሚ​ርቁ ይጠ​ፋ​ሉና፤ ከአ​ንተ ርቀው የሚ​ያ​መ​ነ​ዝ​ሩ​ት​ንም ሁሉ አጠ​ፋ​ኻ​ቸው።</verse>
				<verse number="28">ለእኔ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መከ​ተል ይሻ​ለ​ኛል፤ መታ​መ​ኛ​ዬም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ነው በጽ​ዮን ልጅ በሮች ምስ​ጋ​ና​ህን ሁሉ እና​ገር ዘንድ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="73">
				<verse number="1">አቤቱ፥ ስለ ምን ለዘ​ወ​ትር ጣል​ኸን? በማ​ሰ​ማ​ሪ​ያህ በጎች ላይስ ቍጣ​ህን ለምን ተቈ​ጣህ?</verse>
				<verse number="2">አስ​ቀ​ድ​መህ የፈ​ጠ​ር​ሃ​ትን ማኅ​በ​ር​ህን፥ የተ​ቤ​ዠ​ሃ​ት​ንም የር​ስ​ት​ህን በትር፥ በው​ስ​ጥዋ ያደ​ር​ህ​ባ​ትን የጽ​ዮ​ንን ተራራ ዐስብ።</verse>
				<verse number="3">ጠላት በቅ​ዱ​ሳ​ንህ ላይ እንደ ከፋ መጠን፥ ሁል​ጊዜ በት​ዕ​ቢ​ታ​ቸው ላይ እጅ​ህን አንሣ።</verse>
				<verse number="4">ጠላ​ቶ​ችህ በበ​ዓ​ልህ መካ​ከል ተመኩ፤ የማ​ያ​ው​ቁ​ት​ንም ምል​ክት ምል​ክ​ታ​ቸው አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="5">እንደ ላይ​ኛው መን​ገድ፥ በዱር እን​ዳ​ሉም እን​ጨ​ቶች፥ በገ​ጀሞ በሮ​ች​ዋን ሰበሩ።</verse>
				<verse number="6">እን​ዲሁ በመ​ጥ​ረ​ቢ​ያና በመ​ዶሻ ሰበ​ሩ​አት።</verse>
				<verse number="7">መቅ​ደ​ስ​ህ​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠሉ፤ የስ​ም​ህ​ንም ማደ​ሪያ በም​ድር ውስጥ አረ​ከሱ።</verse>
				<verse number="8">አንድ ሆነው በል​ባ​ቸው በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸው አሉ፦ “ኑ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በዓ​ላት ከም​ድር እን​ሻር</verse>
				<verse number="9">ምል​ክ​ቱ​ንም አና​ው​ቅም፥ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ነቢይ የለም፤ እኛም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አና​ው​ቅም።”</verse>
				<verse number="10">አቤቱ፥ ጠላት እስከ መቼ ይሳ​ደ​ባል? ስም​ህ​ንስ ጠላት ሁል​ጊዜ ያስ​ቈ​ጣ​ዋል?</verse>
				<verse number="11">አቤቱ፥ እጅ​ህን ፈጽ​መህ ለምን ትመ​ል​ሳ​ለህ? ቀኝ​ህ​ንም በብ​ብ​ትህ መካ​ከል፥</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ከዓ​ለም አስ​ቀ​ድሞ ንጉሥ ነው፥ በም​ድ​ርም መካ​ከል መድ​ኀ​ኒ​ትን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="13">አንተ ባሕ​ርን በኀ​ይ​ልህ አጸ​ና​ሃት፤ አንተ የእ​ባ​ቡን ራስ በውኃ ውስጥ ሰበ​ርህ።</verse>
				<verse number="14">አን​ተም የዘ​ን​ዶ​ውን ራሶች ቀጠ​ቀ​ጥህ፤ ለኢ​ት​ዮ​ጵያ ሕዝ​ብም ምግ​ባ​ቸ​ውን ሰጠ​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">አንተ ፈሳ​ሾ​ቹ​ንና ምን​ጮ​ቹን ሰነ​ጠ​ቅህ።</verse>
				<verse number="16">ቀኑ የአ​ንተ ነው፥ ሌሊ​ቱም የአ​ንተ ነው፤ አንተ ፀሐ​ይ​ንና ጨረ​ቃን ፈጠ​ርህ።</verse>
				<verse number="17">አንተ የም​ድር ዳር​ቻ​ዎ​ችን ሁሉ ሠራህ፤ በጋ​ንና ክረ​ም​ትን አንተ አደ​ረ​ግህ።</verse>
				<verse number="18">ይህን ፍጥ​ረ​ት​ህን ዐስብ። ጠላት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተገ​ዳ​ደ​ረው። ሰነፍ ሕዝ​ብም ስሙን አስ​ቈጣ።</verse>
				<verse number="19">የም​ት​ገ​ዛ​ል​ህን ነፍስ ለአ​ራ​ዊት አት​ስ​ጣት፤ የድ​ሆ​ች​ህ​ንም ነፍስ ለዘ​ወ​ትር አት​ርሳ።</verse>
				<verse number="20">ወደ ኪዳ​ን​ህም ተመ​ል​ከት፥ የም​ድር የጨ​ለማ ስፍ​ራ​ዎች በኃ​ጥ​ኣን ቤቶች ተሞ​ል​ተ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="21">ችግ​ረኛ አፍሮ አይ​መ​ለስ፤ ድሃና ምስ​ኪን ስም​ህን ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።</verse>
				<verse number="22">አቤቱ፥ ተነሥ፥ በቀ​ሌ​ንም ተበ​ቀል፤ ሰነ​ፎች ሁል​ጊዜ የተ​ገ​ዳ​ደ​ሩ​ህን ዐስብ።</verse>
				<verse number="23">የባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህን ቃል አት​ርሳ፤ የጠ​ላ​ቶ​ችህ ኵራት ሁል​ጊዜ ወደ አንተ ይውጣ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="74">
				<verse number="1">አቤቱ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፤ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ ስም​ህ​ንም እጠ​ራ​ለሁ፤ ተአ​ም​ራ​ት​ህን ሁሉ እና​ገ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">ጊዜ​ውን ባገ​ኘሁ ጊዜ እኔ በቅን እፈ​ር​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">ምድ​ርና በእ​ር​ስዋ ውስጥ የሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ቀለጡ፥ እኔም ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ዋን አጸ​ናሁ።</verse>
				<verse number="4">ኃጥ​ኣ​ንን አል​ኋ​ቸው፥ “አት​በ​ድሉ” የሚ​በ​ድ​ሉ​ት​ንም አል​ኋ​ቸው፥ “ቀን​ዳ​ች​ሁን አታ​ንሡ፥</verse>
				<verse number="5">ቀን​ዳ​ች​ሁን እስከ አር​ያም አታ​ንሡ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐመ​ፃን አት​ና​ገሩ።”</verse>
				<verse number="6">ክብር ከም​ሥ​ራቅ ወይም ከም​ዕ​ራብ ወይም ከም​ድረ በዳ የለ​ምና፤</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራጅ ነውና ይህን ያዋ​ር​ዳል ይህ​ንም ያከ​ብ​ራል።</verse>
				<verse number="8">ጽዋ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ነውና፤ ያል​ተ​ቀ​ላ​ቀለ የወ​ይን ጠጅ ሞላ​በት፤ ከዚህ ወደ​ዚህ አቃ​ዳው፥ ነገር ግን አተ​ላው አል​ፈ​ሰ​ሰም፤ የም​ድር ኃጥ​ኣን ሁሉ ይጠ​ጡ​ታል።</verse>
				<verse number="9">እኔ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ደስ ይለ​ኛል፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እዘ​ም​ራ​ለሁ፥</verse>
				<verse number="10">የኃ​ጥ​ኣ​ንን ቀን​ዶች ሁሉ እሰ​ብ​ራ​ለሁ። የጻ​ድ​ቃን ቀን​ዶች ግን ከፍ ከፍ ይላሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="75">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በይ​ሁዳ ታወቀ፥ ስሙም በእ​ስ​ራ​ኤል ታላቅ ሆነ።</verse>
				<verse number="2">በሀ​ገ​ሩም በሰ​ላም ኖረ፥ ማደ​ሪ​ያ​ውም በጽ​ዮን ነው፤</verse>
				<verse number="3">በዚ​ያም የቀ​ስ​ትን ኀይል፥ ጋሻን፥ ጦር​ንና ሰል​ፍ​ንም ሰበረ፤ በዚ​ያም ቀን​ዶ​ችን ሰበረ።</verse>
				<verse number="4">አንተ በዘ​ለ​ዓ​ለም ተራ​ሮች ሆነህ በድ​ንቅ ታበ​ራ​ለህ።</verse>
				<verse number="5">ልበ ሰነ​ፎች ሁሉ ደነ​ገጡ፥ ሕል​ምን አለሙ፥ ያገ​ኙት ግን የለም፤ ሰው ሁሉ ለእጁ ባለ​ጠ​ግ​ነት ነው።</verse>
				<verse number="6">የያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ ሆይ፥ ከተ​ግ​ሣ​ጽህ የተ​ነሣ ፈረ​ሰ​ኞች ሁሉ አን​ቀ​ላፉ።</verse>
				<verse number="7">አንተ ግን፥ ግሩም ነህ፤ ቍጣ​ህን ማን ይቃ​ወ​ማል?</verse>
				<verse number="8">ፍር​ድን ከሰ​ማይ ታሰ​ማ​ለህ። ምድር ፈራች፥ ዝምም አለች፥</verse>
				<verse number="9">ልበ የዋ​ሃ​ንን ሁሉ ያድን ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለፍ​ርድ በተ​ነሣ ጊዜ።</verse>
				<verse number="10">ሰው በፈ​ቃዱ ያመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ልና፥ ከሕ​ሊ​ና​ቸው ትር​ፍም በዓ​ል​ህን ያደ​ር​ጋሉ።</verse>
				<verse number="11">ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለ​ትን ሰጡ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ያሉ ሁሉ እጅ መን​ሻን ለሚ​ያ​ስ​ፈ​ራው ያገ​ባሉ።</verse>
				<verse number="12">የአ​ለ​ቆ​ችን ነፍስ ያወ​ጣል፤ በም​ድ​ርም ነገ​ሥ​ታት ዘንድ ያስ​ፈ​ራል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="76">
				<verse number="1">በቃሌ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኽሁ፥ ቃሌም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥ እር​ሱም አደ​መ​ጠኝ።</verse>
				<verse number="2">በመ​ከ​ራዬ ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈለ​ግ​ሁት፤ እጆ​ቼም በሌ​ሊት በፊቱ ናቸው፥ ጠላ​ቶ​ቼም አል​ረ​ገ​ጡ​ኝም። ነፍሴ ግን ደስ​ታን አጣች።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዐሰ​ብ​ሁት፥ ደስ አለ​ኝም፤ ተና​ገ​ርሁ፥ ነፍ​ሴም ፈዘ​ዘች። የጠ​ላ​ቶ​ቼን ሁሉ ሰዓ​ቶች ዐወ​ቅ​ኋ​ቸው</verse>
				<verse number="4">ደነ​ገ​ጥሁ አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁ​ምም።</verse>
				<verse number="5">የድ​ሮ​ውን ዘመን ዐሰ​ብሁ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙን ዓመ​ታት ዐሰ​ብሁ፤ አነ​በ​ብ​ኹም፤</verse>
				<verse number="6">በሌ​ሊት ከልቤ ጋር ተጫ​ወ​ትሁ፥ መን​ፈ​ሴ​ንም አነ​ቃ​ቃ​ኋት።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም በውኑ ይጥ​ላ​ልን? እን​ግ​ዲ​ህስ ይቅ​ር​ታ​ውን አይ​ጨ​ም​ር​ምን?</verse>
				<verse number="8">ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምስ ምሕ​ረ​ቱን ለልጅ ልጅ ይቈ​ር​ጣ​ልን?</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታን ይረ​ሳ​ልን? በቍ​ጣ​ውስ ምሕ​ረ​ቱን ዘጋ​ውን?</verse>
				<verse number="10">እነሆ፥ ዛሬ ጀመ​ርሁ አልሁ፥ ልዑል ቀኙን እን​ደ​ሚ​ያ​ፈ​ራ​ርቅ።</verse>
				<verse number="11">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ አስ​ታ​ወ​ስሁ፤ የቀ​ደ​መ​ውን ተአ​ም​ራ​ት​ህን አስ​ታ​ው​ሳ​ለ​ሁና፤</verse>
				<verse number="12">በም​ግ​ባ​ር​ህም ሁሉ እና​ገ​ራ​ለሁ፥ በሥ​ራ​ህም እጫ​ወ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">አቤቱ፥ መን​ገ​ድህ በመ​ቅ​ደስ ውስጥ ነው፤ እንደ አም​ላ​ካ​ችን ያለ ታላቅ አም​ላክ ማን ነው?</verse>
				<verse number="14">ተአ​ም​ራ​ትን የም​ታ​ደ​ርግ አም​ላክ አንተ ብቻ ነህ፤ ለሕ​ዝ​ብህ ኀይ​ል​ህን አሳ​የ​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንና የዮ​ሴ​ፍን ልጆች፥ ሕዝ​ብ​ህን በክ​ን​ድህ አዳ​ን​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">አቤቱ፥ ውኆች አዩህ፥ ውኆች አይ​ተው ፈሩ፤ የው​ኆች ጥል​ቆች ተነ​ዋ​ወጡ፥ ውኆ​ቻ​ቸ​ውም ጮኹ።</verse>
				<verse number="17">ደመ​ናት ድም​ፅን ሰጡ፥ ፍላ​ጾ​ች​ህም ወጡ።</verse>
				<verse number="18">የነ​ጐ​ድ​ጓ​ድህ ድምፅ በሰ​ረ​ገላ ነበረ፤ መብ​ረ​ቆች ለዓ​ለም አበሩ፤ ምድር ተና​ወ​ጠች፥ ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠ​ችም።</verse>
				<verse number="19">መን​ገ​ድህ በባ​ሕር ውስጥ ነው፥ ፍለ​ጋ​ህም በብዙ ውኆች ነው፥ ፍለ​ጋ​ህም አይ​ታ​ወ​ቅም።</verse>
				<verse number="20">በሙ​ሴና በአ​ሮን እጅ ሕዝ​ብ​ህን እንደ በጎች መራ​ሃ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="77">
				<verse number="1">ሕዝቤ ሆይ፥ ሕጌን አድ​ምጡ፥ ጆሮ​አ​ች​ሁ​ንም ወደ አፌ ቃል አዘ​ን​ብሉ።</verse>
				<verse number="2">አፌን በም​ሳሌ እከ​ፍ​ታ​ለሁ፤ ከቀ​ድሞ ጀምሮ ያለ​ው​ንም ምሳሌ እና​ገ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">የሰ​ማ​ነ​ው​ንና ያየ​ነ​ውን፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም የነ​ገ​ሩ​ንን፥ ለሚ​መጣ ትው​ልድ ከል​ጆ​ቻ​ቸው አል​ሰ​ወ​ሩም።</verse>
				<verse number="4">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ጋና ተና​ገሩ፥ ኀይ​ሉ​ንና ያደ​ረ​ገ​ው​ንም ተአ​ም​ራት።</verse>
				<verse number="5">ለያ​ዕ​ቆብ ያቆ​መ​ውን ምስ​ክር፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የሠ​ራ​ውን ሕግ፥ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ያዘ​ዘ​ውን ለል​ጆ​ቻ​ቸው ይነ​ግሩ ዘንድ፥</verse>
				<verse number="6">የሚ​መጣ ትው​ልድ የሚ​ወ​ለ​ዱም ልጆች ያውቁ ዘንድ፥ ተነ​ሥ​ተ​ውም ለል​ጆ​ቻ​ቸው ይነ​ግ​ራሉ።</verse>
				<verse number="7">ተስ​ፋ​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲ​ያ​ደ​ርጉ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥራ እን​ዳ​ይ​ረሱ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም እን​ዲ​ፈ​ልጉ፤</verse>
				<verse number="8">እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ይ​ሆኑ፥ ጠማ​ማና የም​ታ​ስ​መ​ርር ትው​ልድ፥ ልብ​ዋን ያላ​ቀ​ናች ትው​ልድ፥ መን​ፈ​ስዋ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ያል​ታ​መ​ነች።</verse>
				<verse number="9">የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ቀስ​ታ​ቸ​ውን ገት​ረው ይወጉ ነበር። በሰ​ልፍ ቀን ወደ ኋላ ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="10">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ኪዳን አል​ጠ​በ​ቁ​ምና፥ በሕ​ጉም ለመ​ሄድ እንቢ አሉ፤</verse>
				<verse number="11">ረድ​ኤ​ቱ​ንና ያሳ​ያ​ቸ​ውን ተአ​ም​ራ​ቱን ረሱ፥</verse>
				<verse number="12">በግ​ብጽ ሀገ​ርና በጣ​ኔ​ዎስ በረሃ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ፊት የሠ​ራ​ውን ተአ​ም​ራት።</verse>
				<verse number="13">ባሕ​ርን ከፍሎ አሳ​ለ​ፋ​ቸው፤ ውኆ​ችን እንደ ረዋት ውኃ አቆመ።</verse>
				<verse number="14">ቀን በደ​መና መራ​ቸው፥ ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ በእ​ሳት ብር​ሃን።</verse>
				<verse number="15">ዓለ​ቱን በም​ድረ በዳ ሰነ​ጠቀ፤ ከብዙ ጥልቅ እን​ደ​ሚ​ገኝ ያህል አጠ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">ውኃ​ንም እንደ ወን​ዞች አፈ​ሰሰ። ውኃ​ንም ከዓ​ለት አፈ​ለቀ፥</verse>
				<verse number="17">ነገር ግን እር​ሱን መበ​ደ​ልን እን​ደ​ገና ደገሙ፥ ልዑ​ል​ንም በም​ድረ በዳ አስ​መ​ረ​ሩት።</verse>
				<verse number="18">ለነ​ፍ​ሳ​ቸው መብ​ልን ይፈ​ልጉ ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በል​ባ​ቸው ፈተ​ኑት።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲህ ብለው አሙት፦ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድረ በዳ ማዕ​ድን ያሰ​ናዳ ዘንድ</verse>
				<verse number="20">ዓለ​ቱን ይመታ ዘንድ ውኃ​ንም ያፈስ ዘንድ ይች​ላ​ልን? እን​ጀ​ራን መስ​ጠ​ትና ለሕ​ዝ​ቡስ ማዕ​ድን መሥ​ራት ይች​ላ​ልን?”</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይህን ሰምቶ ተቈጣ፤ በያ​ዕ​ቆ​ብም ላይ እሳት ነደደ፥ መቅ​ሠ​ፍ​ትም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ወጣ፤</verse>
				<verse number="22">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አላ​መ​ኑ​ምና፥ በማ​ዳ​ኑም አል​ተ​ማ​መ​ኑ​ምና።</verse>
				<verse number="23">ደመ​ና​ው​ንም ከላይ አዘዘ፥ የሰ​ማ​ይ​ንም ደጆች ከፈተ፤</verse>
				<verse number="24">ይበ​ሉም ዘንድ መናን አዘ​ነ​በ​ላ​ቸው፥ የሰ​ማ​ይ​ንም እን​ጀራ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">የመ​ላ​እ​ክ​ት​ንም እን​ጀራ የሰው ልጆች በሉ። የሚ​በ​ቃ​ቸው ስን​ቅ​ንም ላከ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">ከሰ​ማይ ዐዜ​ባዊ ነፋ​ስን አስ​ነሣ፥ በኀ​ይ​ሉም መስ​ዓዊ ነፋ​ስን አመጣ፤</verse>
				<verse number="27">ሥጋን እንደ አፈር፥ የሚ​በ​ር​ሩ​ት​ንም ወፎች እንደ ባሕር አሸዋ አዘ​ነ​በ​ላ​ቸው፤</verse>
				<verse number="28">በሰ​ፈ​ራ​ቸው መካ​ከል፥ በድ​ን​ኳ​ና​ቸ​ውም ዙሪያ ወደቀ።</verse>
				<verse number="29">በሉ፥ እጅ​ግም ጠገቡ፤ ለም​ኞ​ታ​ቸ​ውም ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="30">ከወ​ደ​ዱ​ትም አላ​ሳ​ጣ​ቸ​ውም፤ መብ​ላ​ቸ​ውም ገና በአ​ፋ​ቸው ሳለ፥</verse>
				<verse number="31">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ሠ​ፍት በላ​ያ​ቸው መጣ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ብዙ​ዎ​ቹን ገደለ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ምር​ጦች አሰ​ና​ከለ።</verse>
				<verse number="32">ከዚ​ህም ሁሉ ጋር እንደ ገና እር​ሱን በደሉ፥ ተአ​ም​ራ​ቱ​ንም አላ​መ​ኑም፤</verse>
				<verse number="33">ቀኖ​ቻ​ቸ​ውም በከ​ንቱ አለቁ፥ ዓመ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም በች​ኮላ አለፉ።</verse>
				<verse number="34">በገ​ደ​ላ​ቸ​ውም ጊዜ ወዲ​ያው ፈለ​ጉት፤ ተመ​ለሱ፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ገሠ​ገሡ፤</verse>
				<verse number="35">ረዳ​ታ​ቸ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ መድ​ኀ​ኒ​ታ​ቸ​ውም ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነ ዐሰቡ።</verse>
				<verse number="36">በአ​ፋ​ቸው ብቻ ወደ​ዱት፤ በአ​ን​ደ​በ​ታ​ቸ​ውም ዋሹ​በት፤</verse>
				<verse number="37">ልባ​ቸ​ውም ከእ​ርሱ ጋር አል​ቀ​ናም፥ በቃል ኪዳ​ኑም አል​ተ​ማ​መ​ኑ​ትም።</verse>
				<verse number="38">እርሱ ግን መሐሪ ነው፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ይቅር አላ​ቸው፥ አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ው​ምም፤ ቍጣ​ው​ንም መመ​ለስ አበዛ፥ መዓ​ቱ​ንም ሁሉ አላ​ቃ​ጠ​ለም።</verse>
				<verse number="39">ሥጋም እንደ ሆኑ ዐሰበ። መን​ፈስ ከወጣ በኋላ አይ​መ​ለ​ስም</verse>
				<verse number="40">በም​ድረ በዳ ምን ያህል አስ​ቈ​ጡት፥ በበ​ረ​ሃም አሳ​ዘ​ኑት።</verse>
				<verse number="41">ተመ​ለሱ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ፈተ​ኑት፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቅዱስ አሳ​ዘ​ኑት።</verse>
				<verse number="42">እነ​ር​ሱም እጁን አላ​ሰ​ቡም፥ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ ያዳ​ነ​በ​ትን፥</verse>
				<verse number="43">በግ​ብፅ ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ራ​ቱን፥ በጣ​ኔ​ዎ​ስም በረሃ ያደ​ረ​ገ​ውን ድን​ቁን።</verse>
				<verse number="44">ወን​ዞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ወደ ደም ለወጠ፥ ምን​ጮ​ቻ​ቸ​ው​ንም ደግሞ እን​ዳ​ይ​ጠጡ።</verse>
				<verse number="45">ዝን​ቦ​ች​ንም በላ​ያ​ቸው ሰደ​ደ​ባ​ቸው፥ በሉ​አ​ቸ​ውም፤ ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ችን ሰደደ፥ አረ​ከ​ሳ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="46">ፍሬ​ያ​ቸ​ውን ለኩ​ብ​ኩባ፥ ሥራ​ቸ​ው​ንም ለአ​ን​በጣ ሰጠ።</verse>
				<verse number="47">ወይ​ና​ቸ​ው​ንም በበ​ረዶ፥ በለ​ሳ​ቸ​ው​ንም በው​ርጭ አጠፋ።</verse>
				<verse number="48">እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን ለበ​ረዶ፥ ሀብ​ታ​ቸ​ው​ንም ለእ​ሳት ሰጠ።</verse>
				<verse number="49">የመ​ዓ​ቱን መቅ​ሠ​ፍት በላ​ያ​ቸው ሰደደ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ትን፥ መዓ​ት​ንም መከ​ራ​ንም በክ​ፉ​ዎች መላ​እ​ክት ሰደደ።</verse>
				<verse number="50">ለቍ​ጣው መን​ገ​ድን ጠረገ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም ከሞት አላ​ዳ​ና​ትም፥ እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በሞት ውስጥ ዘጋ፤</verse>
				<verse number="51">በኵ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ በግ​ብፅ ምድር፥ የድ​ካ​ማ​ቸ​ው​ንም መጀ​መ​ሪያ በቤ​ቶ​ቻ​ቸው ውስጥ ገደለ።</verse>
				<verse number="52">ሕዝ​ቡን ግን እንደ በጎች አሰ​ማ​ራ​ቸው፥ እንደ መን​ጋም ወደ ምድረ በዳ አወ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="53">በተ​ስ​ፋም መራ​ቸው አል​ፈ​ሩ​ምም፥ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ባሕር ደፈ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="54">ወደ መቅ​ደ​ሱም ተራራ ወሰ​ዳ​ቸው፥ ቀኙ ወደ ፈጠ​ረ​ችው ተራራ፤</verse>
				<verse number="55">ከፊ​ታ​ቸ​ውም አሕ​ዛ​ብን አባ​ረረ፥ ርስ​ቱ​ንም በገ​መድ አካ​ፈ​ላ​ቸው፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ወገ​ኖች በቤ​ታ​ቸው አኖረ።</verse>
				<verse number="56">ነገር ግን ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈተ​ኑት፥ አሳ​ዘ​ኑ​ትም፥ ምስ​ክ​ሩ​ንም አል​ጠ​በ​ቁም፤</verse>
				<verse number="57">ተመ​ለ​ሱም፥ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከዱ፤ እንደ ጠማማ ቀስ​ትም ሆኑ፤</verse>
				<verse number="58">በኮ​ረ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አስ​ቈ​ጡት፥ በተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም አስ​ቀ​ኑት።</verse>
				<verse number="59">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይህን ሰምቶ ተቈጣ። እስ​ራ​ኤ​ል​ንም እጅግ ናቃ​ቸው፤</verse>
				<verse number="60">የሴ​ሎ​ም​ንም ድን​ኳን ተዋት፥ በሰ​ዎች መካ​ከል ያደ​ረ​ባ​ትን ድን​ኳ​ኑን።</verse>
				<verse number="61">ኀይ​ላ​ቸ​ውን ለም​ርኮ፥ ጌጣ​ቸ​ው​ንም በጠ​ላት እጅ ሰጠ።</verse>
				<verse number="62">ሕዝ​ቡ​ንም በጦር ውስጥ ዘጋ​ቸው፥ ርስ​ቱ​ንም ቸል አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="63">ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን እሳት በላ​ቻ​ቸው፥ ቈነ​ጃ​ጅ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አላ​ለ​ቀ​ሱም።</verse>
				<verse number="64">ካህ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም በሰ​ይፍ ወደቁ፥ ባል​ቴ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አላ​ለ​ቀ​ሱ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="65">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ን​ቅ​ልፍ እን​ደ​ሚ​ነቃ ተነሣ፥ የወ​ይን ስካር እንደ ተወው እንደ ኀያ​ልም ሰው፤</verse>
				<verse number="66">ጠላ​ቶ​ቹ​ንም በኋ​ላው ገደለ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ም​ንም ኀሣር ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="67">የዮ​ሴ​ፍ​ንም ድን​ኳን ተዋት፥ የኤ​ፍ​ሬ​ም​ንም ወገን አል​መ​ረ​ጠ​ውም፤</verse>
				<verse number="68">የይ​ሁ​ዳን ወገን ግን መረጠ፥ የወ​ደ​ደ​ውን የጽ​ዮ​ንን ተራራ።</verse>
				<verse number="69">መቅ​ደ​ሱን እንደ አር​አ​ያም ሠራ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም በም​ድር ውስጥ መሠ​ረ​ታት።</verse>
				<verse number="70">ባሪ​ያው ዳዊ​ት​ንም መረ​ጠው፥ ከበ​ጎ​ቹም መንጋ ውስጥ ወሰ​ደው፤</verse>
				<verse number="71">ከሚ​ያ​ጠቡ በጎ​ችም በኋላ፥ ባሪ​ያ​ውን ያዕ​ቆ​ብን ርስ​ቱን እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ይጠ​ብቅ ዘንድ ወሰ​ደው።</verse>
				<verse number="72">በልቡ ቅን​ነት ጠበ​ቃ​ቸው፥ በእ​ጁም ጥበብ መራ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="78">
				<verse number="1">አቤቱ፥ አሕ​ዛብ ወደ ርስ​ትህ ገቡ፤ ቤተ መቅ​ደ​ስ​ህ​ንም አረ​ከሱ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም እንደ ተክል ጠባቂ ጎጆ አደ​ረ​ጉ​አት።</verse>
				<verse number="2">የባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህ​ንም በድ​ኖች ለሰ​ማይ ወፎች መብል አደ​ረጉ፥ የጻ​ድ​ቃ​ን​ህ​ንም ሥጋ ለም​ድር አራ​ዊት፤</verse>
				<verse number="3">ደማ​ቸ​ው​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዙሪያ እንደ ውኃ አፈ​ሰሱ፥ የሚ​ቀ​ብ​ራ​ቸ​ውም አጡ።</verse>
				<verse number="4">ለጎ​ረ​ቤ​ቶ​ቻ​ች​ንም ስድብ ሆንን፥ በዙ​ሪ​ያ​ች​ንም ላሉ ሣቅና መዘ​በቻ።</verse>
				<verse number="5">አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ትቈ​ጣ​ለህ? ቅን​ዐ​ት​ህም እንደ እሳት ይነ​ድ​ዳል?</verse>
				<verse number="6">በማ​ያ​ው​ቁ​ህም አሕ​ዛብ ላይ ስም​ህ​ንም በማ​ት​ጠራ መን​ግ​ሥት ላይ መዓ​ት​ህን አፍ​ስስ፤</verse>
				<verse number="7">ያዕ​ቆ​ብን በል​ተ​ው​ታ​ልና፥ ስፍ​ራ​ው​ንም ባድማ አድ​ር​ገ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="8">የቀ​ደ​መ​ውን በደ​ላ​ች​ንን አታ​ስ​ብ​ብን፥ አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ትህ በቶሎ ያግ​ኘን፥ እጅግ ተቸ​ግ​ረ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="9">አም​ላ​ካ​ች​ንና መድ​ኀ​ኒ​ታ​ችን ሆይ፥ ርዳን፥ ስለ ስምህ ክብር አቤቱ፥ ታደ​ገን፥ ስለ ስም​ህም ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን አስ​ተ​ስ​ር​ይ​ልን።</verse>
				<verse number="10">አሕ​ዛብ፥ “አም​ላ​ካ​ቸው ወዴት ነው?” እን​ዳ​ይ​ሉን፥ የፈ​ሰ​ሰ​ውን የባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህን ደም በቀል በዐ​ይ​ኖ​ቻ​ችን ፊት አሕ​ዛብ ይዩ።</verse>
				<verse number="11">የእ​ስ​ረ​ኞች ጩኸት ወደ ፊትህ ይግባ፤ እንደ ክን​ድ​ህም ታላ​ቅ​ነት የተ​ገ​ደ​ሉ​ትን ሰዎች ልጆች ጠብ​ቃ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">አቤቱ፥ የተ​ገ​ዳ​ደ​ሩ​ህን መገ​ዳ​ደ​ራ​ቸ​ውን፥ ለጎ​ረ​ቤ​ቶ​ቻ​ችን ሰባት እጥፍ በብ​ብ​ታ​ቸው ክፈ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">እኛ ሕዝ​ብህ ግን፥ የማ​ሰ​ማ​ሪ​ያ​ህም በጎች፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እና​መ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለን፤ ለልጅ ልጅም ምስ​ጋ​ና​ህን እን​ና​ገ​ራ​ለን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="79">
				<verse number="1">ዮሴ​ፍን እንደ መንጋ የም​ት​መራ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ጠባቂ ሆይ፥ አድ​ምጥ፤ በኪ​ሩ​ቤል ላይ የም​ት​ቀ​መጥ፥ ተገ​ለጥ።</verse>
				<verse number="2">በኤ​ፍ​ሬ​ምና በብ​ን​ያም በም​ና​ሴም ፊት ኀይ​ል​ህን አንሣ፥ እኛ​ንም ለማ​ዳን ና።</verse>
				<verse number="3">የኀ​ያ​ላን አም​ላክ፥ መል​ሰን፥ ፊት​ህ​ንም አብራ፥ እኛም እን​ድ​ና​ለን።</verse>
				<verse number="4">የኀ​ያ​ላን አም​ላክ አቤቱ፥ በባ​ሪ​ያህ ጸሎት ላይ እስከ መቼ ትቈ​ጣ​ለህ?</verse>
				<verse number="5">የእ​ን​ባ​ች​ንን እን​ጀራ ትመ​ግ​በ​ና​ለህ፥ እን​ባ​ች​ን​ንም በስ​ፍር ታጠ​ጣ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="6">ለጎ​ረ​ቤ​ቶ​ቻ​ችን መነ​ጋ​ገ​ሪያ አደ​ረ​ግ​ኸን፥ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንም በላ​ያ​ችን ተሳ​ለ​ቁ​ብን።</verse>
				<verse number="7">የኀ​ያ​ላን አም​ላክ አቤቱ፥ መል​ሰን፥ ፊት​ህ​ንም አብራ፥ እኛም እን​ድ​ና​ለን።</verse>
				<verse number="8">ከግ​ብፅ የወ​ይ​ንን ግንድ አመ​ጣህ፤ አሕ​ዛ​ብን አባ​ረ​ርህ፥ እር​ስ​ዋ​ንም ተከ​ልህ።</verse>
				<verse number="9">በፊ​ቷም መን​ገ​ድን ጠረ​ግህ፥ ሥሮ​ች​ዋ​ንም ተከ​ልህ፥ ምድ​ር​ንም ሞላች።</verse>
				<verse number="10">ጥላዋ ተራ​ሮ​ችን ከደነ፥ ጫፎ​ች​ዋም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዝግባ ሆኑ።</verse>
				<verse number="11">ቅር​ን​ጫ​ፎ​ች​ዋ​ንም እስከ ባሕር፥ ቡቃ​ያ​ዋ​ንም እስከ ወንዙ ዘረ​ጋች።</verse>
				<verse number="12">አጥ​ር​ዋን ለምን አፈ​ረ​ስህ? መን​ገድ አላ​ፊም ሁሉ ይበ​ላ​ታል።</verse>
				<verse number="13">የበ​ረሃ እርያ አረ​ከ​ሳት፥ የዱር አው​ሬም ተሰ​ማ​ራ​ባት።</verse>
				<verse number="14">የኀ​ያ​ላን አም​ላክ ሆይ፥ እባ​ክህ ተመ​ለስ፤ ከሰ​ማይ ተመ​ል​ከት፥ እይም፥ ይህ​ች​ንም የወ​ይን ግንድ ይቅር በላት።</verse>
				<verse number="15">በሰው ልጅ ለአ​ንተ ያጸ​ና​ኻ​ትን ቀኝህ የተ​ከ​ላ​ትን አጽ​ን​ተህ አነ​ሣ​ሣት።</verse>
				<verse number="16">በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ላ​ለች፥ ተነ​ቅ​ላ​ማ​ለች ከፊ​ትህ ተግ​ሣ​ጽም የተ​ነሣ ይጠ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="17">ለአ​ንተ ባጸ​ና​ኸው በሰው ልጅ ላይ፥ በቀ​ኝህ ሰው ላይ እጅህ ይሁን።</verse>
				<verse number="18">ከአ​ን​ተም አን​ራቅ፤ አድ​ነን፥ ስም​ህ​ንም እን​ጠ​ራ​ለን።</verse>
				<verse number="19">የኀ​ያ​ላን አም​ላክ አቤቱ፥ መል​ሰን፥ ፊት​ህ​ንም አብራ፥ እኛም እን​ድ​ና​ለን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="80">
				<verse number="1">በረ​ዳ​ታ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እልል በሉ።</verse>
				<verse number="2">ዝማ​ሬ​ውን አንሡ ከበ​ሮ​ው​ንም ስጡ፥ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን በገና ከመ​ሰ​ንቆ ጋር፤</verse>
				<verse number="3">በመ​ባቻ ቀን በታ​ወ​ቀ​ችው በዓ​ላ​ችን ቀን መለ​ከ​ትን ንፉ፤</verse>
				<verse number="4">ለእ​ስ​ራ​ኤል ሥር​ዐቱ ነውና፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ ፍርድ ነውና።</verse>
				<verse number="5">ወደ ግብፅ ሀገር በሄደ ጊዜ ለዮ​ሴፍ ምስ​ክ​ርን አቆመ። የማ​ያ​ው​ቀ​ውን ቋንቋ ሰማ።</verse>
				<verse number="6">ጀር​ባ​ውን ከመ​ስ​ገ​ጃ​ቸው መለሰ፥ እጆ​ቹም በቅ​ር​ጫት ተገዙ።</verse>
				<verse number="7">በመ​ከ​ራህ ጊዜ ጠራ​ኸኝ፥ አዳ​ን​ሁ​ህም፥ በተ​ሰ​ወረ ዐው​ሎም መለ​ስ​ሁ​ልህ፥ በክ​ር​ክር ውኃ ዘን​ድም ፈተ​ን​ሁህ።</verse>
				<verse number="8">ሕዝቤ ሆይ፥ ስማኝ እነ​ግ​ር​ሃ​ለ​ሁም፤ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እመ​ሰ​ክ​ር​ል​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">አን​ተስ ብት​ሰ​ማኝ የድ​ን​ገት አም​ላክ አል​ሆ​ን​ህም፥ ለሌላ አም​ላ​ክም አት​ስ​ገድ።</verse>
				<verse number="10">ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ሁህ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝና፤ አፍ​ህን አስፋ፥ እሞ​ላ​ዋ​ለ​ሁም።</verse>
				<verse number="11">ሕዝቤ ግን ቃሌን አል​ሰ​ሙ​ኝም፥ እስ​ራ​ኤ​ልም አላ​ደ​መ​ጡ​ኝም።</verse>
				<verse number="12">እንደ ሥራ​ቸው ላክ​ሁ​ባ​ቸው፥ በል​ባ​ቸ​ውም ዐሳብ ሄዱ።</verse>
				<verse number="13">ሕዝ​ቤስ ቃሌን ሰም​ተ​ውኝ ቢሆን፥ እስ​ራ​ኤ​ልም በመ​ን​ገዴ ሄደው ቢሆን፤</verse>
				<verse number="14">ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ፈጥኜ ባዋ​ረ​ድ​ኋ​ቸው ነበር፥ በሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቋ​ቸ​ውም ላይ እጄን በጣ​ልሁ ነበር፤</verse>
				<verse number="15">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶ​ችስ ዋሽ​ተ​ውት ነበር፥ ዘመ​ና​ቸ​ውም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይሆ​ናል፤</verse>
				<verse number="16">ከስ​ን​ዴም ስብ አበ​ላ​ቸው፥ ከዓ​ለ​ቱም ማር አጠ​ገ​ባ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="81">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ማ​ል​ክት ማኅ​በር ቆመ፥ በአ​ማ​ል​ክ​ትም መካ​ከል ይፈ​ር​ዳል።</verse>
				<verse number="2">እስከ መቼ ዐመ​ፃን ትፈ​ር​ዳ​ላ​ችሁ? እስከ መቼስ ለኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ፊት ታደ​ላ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="3">ለድ​ሆ​ችና ለድሃ አደ​ጎች ፍረዱ፤ ለተ​ገ​ፋ​ውና ለም​ስ​ኪኑ ጽድ​ቅን አድ​ርጉ፤</verse>
				<verse number="4">ብቸ​ኛ​ው​ንና ችግ​ረ​ኛ​ውን አድኑ፤ ከኃ​ጥ​ኣ​ንም እጅ አስ​ጥ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">አያ​ው​ቁም፥ አያ​ስ​ተ​ው​ሉ​ምም፤ በጨ​ለማ ውስ​ጥም ይመ​ላ​ለ​ሳሉ፤ የም​ድር መሠ​ረ​ቶች ሁሉ ተና​ወጡ።</verse>
				<verse number="6">እኔ ግን እላ​ለሁ፥ “አማ​ል​ክት ናችሁ፥ ሁላ​ች​ሁም የል​ዑል ልጆች ናችሁ፤”</verse>
				<verse number="7">እና​ንተ ግን እንደ ሰው ትሞ​ታ​ላ​ችሁ፥ ከአ​ለ​ቆ​ችም እንደ አንዱ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="8">አቤቱ፥ ተነሥ፥ በም​ድር ላይ ፍረድ፥ አንተ አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ትወ​ር​ሳ​ለ​ህና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="82">
				<verse number="1">አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? አቤቱ፥ ዝም አት​በል፥ ቸልም አት​በል።</verse>
				<verse number="2">እነሆ፥ ጠላ​ቶ​ችህ ጮኸ​ዋ​ልና፥ ጠላ​ቶ​ች​ህም ራሳ​ቸ​ውን አን​ሥ​ተ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="3">ሕዝ​ብ​ህን በም​ክር ሸነ​ገ​ሉ​አ​ቸው፥ በቅ​ዱ​ሳ​ን​ህም ላይ ተማ​ከሩ።</verse>
				<verse number="4">“ኑ ከሕ​ዝብ ለይ​ተን እና​ጥ​ፋ​ቸው፥ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ስም አያ​ስቡ” አሉ።</verse>
				<verse number="5">በአ​ን​ድ​ነት ተካ​ክ​ለው ተማ​ክ​ረ​ዋ​ልና፤ በአ​ንተ ላይ ሤራ ቈረጡ፤ ቃል ኪዳ​ንም አደ​ረጉ፤</verse>
				<verse number="6">የኤ​ዶ​ም​ያስ ወገ​ኖች፥ እስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም፥ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም፥ አጋ​ራ​ው​ያ​ንም፥</verse>
				<verse number="7">ጌባል፥ አሞ​ንም፥ አማ​ሌ​ቅም፥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ከጢ​ሮስ ሰዎች ጋር፤</verse>
				<verse number="8">አሦ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ተባ​በረ፥ ለሎጥ ልጆ​ችም ረዳት ሆኑ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">እንደ ምድ​ያ​ምና እንደ ሲሣራ፥ በቂ​ሶ​ንም ወንዝ እንደ ኢያ​ቢስ አድ​ር​ግ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">እንደ ዕን​ዶር ሰዎች ይጥፉ እንደ ምድር ትቢያ ይሁኑ።</verse>
				<verse number="11">አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውን እንደ ሔሬ​ብና እንደ ዜብ፥ ታላ​ላ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ እንደ ዛብ​ሄ​ልና እንደ ስል​ማና አድ​ር​ጋ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መሠ​ዊያ እን​ወ​ር​ሳ​ለን የሚ​ሉ​ትን።</verse>
				<verse number="13">አም​ላኬ ሆይ፥ እንደ መን​ኰ​ራ​ኵር፥ በእ​ሳት ፊትም እንደ አለ ገለባ አድ​ር​ጋ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">እሳት ዱርን እን​ደ​ሚ​ያ​ቃ​ጥል፥ ነበ​ል​ባ​ልም ተራ​ሮ​ችን እን​ደ​ሚ​ያ​ነ​ድድ፥</verse>
				<verse number="15">እን​ዲሁ በቍ​ጣህ አሳ​ድ​ዳ​ቸው፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ት​ህም አስ​ደ​ን​ግ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">በፊ​ታ​ቸው እፍ​ረ​ትን ሙላ፥ አቤቱ፥ ስም​ህን ይወቁ።</verse>
				<verse number="17">ይፈሩ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም ይታ​ወኩ፤ ይጐ​ስ​ቍሉ፥ ይጥ​ፉም።</verse>
				<verse number="18">ስም​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነ፥ በም​ድር ሁሉ ላይም አንተ ብቻ ልዑል እንደ ሆንህ ይወቁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="83">
				<verse number="1">የኀ​ያ​ላን አም​ላክ ሆይ፥ ማደ​ሪ​ያ​ዎ​ችህ እጅግ የተ​ወ​ደዱ ናቸው።</verse>
				<verse number="2">አቤቱ፥ ነፍሴ አደ​ባ​ባ​ዮ​ች​ህን በመ​ው​ደድ ደስ አላት፤ ልቤም ሥጋ​ዬም በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ወፍ ለእ​ር​ስዋ ቤትን አገ​ኘች፥ ዋኖ​ስም ጫጩ​ቶ​ች​ዋን የም​ታ​ኖ​ር​በት ቤት አገ​ኘች፤ የኀ​ያ​ላን አም​ላክ ንጉ​ሤም አም​ላ​ኬም ሆይ፥ እርሱ መሠ​ዊ​ያህ ነው።</verse>
				<verse number="4">በቤ​ትህ የሚ​ኖሩ ሁሉ ብፁ​ዓን ናቸው፤ ለዓ​ለ​ምና ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያመ​ስ​ግ​ኑ​ሃል።</verse>
				<verse number="5">አቤቱ፥ ርዳ​ታው ከአ​ንተ ዘንድ የሆ​ነ​ለት፥ በል​ቡም የላ​ይ​ኛ​ውን መን​ገድ የሚ​ያ​ስብ ሰው ብፁዕ ነው።</verse>
				<verse number="6">በል​ቅሶ ሸለቆ ውስጥ በወ​ሰ​ን​ኻ​ቸው ስፍራ የሕግ መም​ህር በረ​ከ​ትን ይሰ​ጣ​ልና።</verse>
				<verse number="7">ከኀ​ይል ወደ ኀይ​ልም ይሄ​ዳል፥ የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ በጽ​ዮን ይታ​ያል።</verse>
				<verse number="8">የኀ​ያ​ላን አም​ላክ አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን ስማኝ፤ የያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ ሆይ፥ አድ​ም​ጠኝ።</verse>
				<verse number="9">አቤቱ፥ መታ​መ​ኔን እይ​ልኝ፥ ወደ ቀባ​ኸ​ውም ፊት ተመ​ል​ከት።</verse>
				<verse number="10">ከአ​እ​ላፍ ይልቅ በአ​ደ​ባ​ባ​ዮ​ችህ አን​ዲት ቀን ትሻ​ላ​ለች፤ በኃ​ጥ​ኣን ድን​ኳ​ኖች ከመ​ቀ​መጥ ይልቅ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እጣል ዘንድ መረ​ጥሁ።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ምጽ​ዋ​ት​ንና እው​ነ​ትን ይወ​ድ​ዳ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ርና ሞገ​ስን ይሰ​ጣል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቅ​ን​ነት የሚ​ሄ​ዱ​ትን ከበ​ረ​ከቱ አያ​ሳ​ጣ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="12">አቤቱ የኀ​ያ​ላን አም​ላክ ሆይ፥ በአ​ንተ የታ​መነ ሰው ብፁዕ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="84">
				<verse number="1">አቤቱ፦ ምድ​ር​ህን ይቅር አልኽ። የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንም ምርኮ መለ​ስህ።</verse>
				<verse number="2">የሕ​ዝ​ብ​ህን ኀጢ​አት ይቅር አልህ፤ ዐበ​ሳ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ሰወ​ርህ።</verse>
				<verse number="3">መዓ​ት​ህ​ንም ሁሉ አስ​ወ​ገ​ድህ፤ ከቍ​ጣህ መቅ​ሠ​ፍት ተመ​ለ​ስህ።</verse>
				<verse number="4">አም​ላ​ካ​ች​ንና መድ​ኀ​ኒ​ታ​ችን ሆይ፥ መል​ሰን፥ ቍጣ​ህ​ንም ከእኛ መልስ።</verse>
				<verse number="5">ለዘ​ለ​ዓ​ለም አት​ቈ​ጣን፥ ቍጣ​ህ​ንም ለልጅ ልጅ አታ​ስ​ረ​ዝም።</verse>
				<verse number="6">አንተ አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ተመ​ለ​ስ​ልን፥ አድ​ነ​ንም፤ ሕዝ​ብ​ህም በአ​ንተ ደስ ይላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ት​ህን አሳ​የን፥ አቤቱ፥ ማዳ​ን​ህን ስጠን።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኬ የሚ​ና​ገ​ረ​ኝን አደ​ም​ጣ​ለሁ፤ ሰላ​ምን ለሕ​ዝ​ቡና ለጻ​ድ​ቃኑ፥ ልባ​ቸ​ው​ንም ወደ እርሱ ለሚ​መ​ልሱ ይና​ገ​ራ​ልና።</verse>
				<verse number="9">ነገር ግን ክብር በም​ድ​ራ​ችን ያድር ዘንድ ማዳኑ ለሚ​ፈ​ሩት ቅርብ ነው።</verse>
				<verse number="10">ይቅ​ር​ታና ቅን​ነት ተገ​ናኙ፤ ጽድ​ቅና ሰላም ተስ​ማሙ።</verse>
				<verse number="11">ቅን​ነት ከም​ድር በቀ​ለች፥ ጽድ​ቅም ከሰ​ማይ ተመ​ለ​ከተ።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምሕ​ረ​ቱን ይሰ​ጣል፥ ምድ​ርም ፍሬ​ዋን ትሰ​ጣ​ለች።</verse>
				<verse number="13">ጽድቅ በፊቱ ይሄ​ዳል፥ ፍለ​ጋ​ው​ንም በመ​ን​ገድ ውስጥ ይተ​ዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="85">
				<verse number="1">አቤቱ፥ ጆሮ​ህን ወደ እኔ አዘ​ን​ብል ስማ​ኝም፥ ድሃና ምስ​ኪን ነኝና።</verse>
				<verse number="2">እኔ የዋህ ነኝና ነፍ​ሴን ጠብ​ቃት፤ አም​ላኬ ሆይ፥ አን​ተን የታ​መ​ነ​ውን ባሪ​ያ​ህን አድ​ነው።</verse>
				<verse number="3">አቤቱ፥ ቀኑን ሁሉ ወደ አንተ እጮ​ኻ​ለ​ሁና ይቅር በለኝ።</verse>
				<verse number="4">የባ​ሪ​ያ​ህን ነፍስ ደስ አሰ​ኛት፥ ነፍ​ሴን ወደ አንተ አነ​ሣ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="5">አቤቱ፥ አንተ መሓ​ሪና ይቅር ባይ ነህና፥ ይቅ​ር​ታ​ህም ለሚ​ጠ​ሩህ ሁሉ ብዙ ነውና።</verse>
				<verse number="6">አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን አድ​ምጥ፥ የል​መ​ና​ዬ​ንም ቃል ስማ።</verse>
				<verse number="7">ትሰ​ማ​ኛ​ለ​ህና በመ​ከ​ራዬ ቀን ወደ አንተ እጮ​ኻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">አቤቱ፥ ከአ​ማ​ል​ክት የሚ​መ​ስ​ልህ የለም፥ እንደ ሥራ​ህም ያለ የለም።</verse>
				<verse number="9">የፈ​ጠ​ር​ሃ​ቸው አሕ​ዛብ ሁሉ ይምጡ፥ አቤቱ፥ በፊ​ት​ህም ይስ​ገዱ፥ ስም​ህ​ንም ያክ​ብሩ፤</verse>
				<verse number="10">አቤቱ፥ ድን​ቅን የም​ታ​ደ​ርግ አንተ ታላቅ ነህና፥ አን​ተም ብቻ​ህን ታላቅ አም​ላክ ነህና፥</verse>
				<verse number="11">አቤቱ መን​ገ​ድ​ህን ምራኝ፥ በእ​ው​ነ​ት​ህም እሄ​ዳ​ለሁ፤ ስም​ህ​ንም ለመ​ፍ​ራት ልቤን ደስ ይለ​ዋል።</verse>
				<verse number="12">አቤቱ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ በልቤ ሁሉ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ። ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ስም​ህን አከ​ብ​ራ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="13">ምሕ​ረ​ትህ በእኔ ላይ ታላቅ ናትና፥ ነፍ​ሴ​ንም ከታ​ች​ኛ​ዪቱ ሲኦል አድ​ነ​ሃ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="14">አም​ላኬ ሆይ፥ ዐመ​ፅ​ኞች በእኔ ላይ ተነ​ሥ​ተ​ዋል፥ የክ​ፉ​ዎ​ችም ማኅ​በር ነፍ​ሴን ፈለ​ጉ​አት፤ አን​ተ​ንም በፊ​ታ​ቸው አላ​ደ​ረ​ጉ​ህም።</verse>
				<verse number="15">አቤቱ፥ አንተ መሓ​ሪና ይቅር ባይ ነህ፤ መዓ​ትህ የራቀ፥ ምሕ​ረ​ት​ህም የበዛ፥ እው​ነ​ተ​ኛም ነህ።</verse>
				<verse number="16">ወደ እኔ ተመ​ል​ከት፥ ይቅር በለ​ኝም፤ ለባ​ሪ​ያህ ኀይ​ልን ስጠው፥ የሴት ባሪ​ያ​ህ​ንም ልጅ አድን።</verse>
				<verse number="17">ምል​ክ​ት​ንም ለመ​ል​ካም ከእኛ ጋር አድ​ርግ፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንም ይዩ፥ ይፈ​ሩም፥ አቤቱ፥ አንተ ረድ​ተ​ኸ​ና​ልና፥ ደስም አሰ​ኝ​ተ​ኸ​ና​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="86">
				<verse number="1">መሠ​ረ​ቶ​ችዋ በተ​ቀ​ደሱ ተራ​ሮች ናቸው፤</verse>
				<verse number="2">ከያ​ዕ​ቆብ ድን​ኳ​ኖች ይልቅ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ዮ​ንን ደጆች ይወ​ድ​ዳ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="3">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተማ ሆይ፥ ስለ አንቺ የተ​ነ​ገ​ረው ነገር ድንቅ ነው።</verse>
				<verse number="4">የሚ​ያ​ው​ቁ​ኝን ረዓ​ብ​ንና ባቢ​ሎ​ንን አስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነሆ፥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን፥ ጢሮ​ስም የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያም ሕዝብ፥ እነ​ዚህ በዚያ ተወ​ለዱ።</verse>
				<verse number="5">ሰው እና​ታ​ችን ጽዮን ይላል፥ በው​ስ​ጥ​ዋም ሰው ተወ​ለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠ​ረ​ታት።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ፥ በው​ስ​ጥ​ዋም ለተ​ወ​ለ​ዱት አለ​ቆ​ችዋ በመ​ጽ​ሐፍ ይነ​ግ​ራ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">በአ​ንቺ የሚ​ኖሩ ሁሉ ደስ እን​ደ​ሚ​ላ​ቸው ይነ​ግ​ራ​ቸ​ዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="87">
				<verse number="1">የድ​ኅ​ነቴ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ በቀ​ንና በሌ​ሊት በፊ​ትህ ጮኽሁ፤</verse>
				<verse number="2">ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትግባ፥ ጆሮ​ህ​ንም ወደ ልመ​ናዬ አዘ​ን​ብል፤</verse>
				<verse number="3">ነፍሴ መከ​ራን ጠግ​ባ​ለ​ችና፥ ሕይ​ወ​ቴም ለሞት ቀር​ባ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="4">ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ተቈ​ጠ​ርሁ፥ ረዳ​ትም እን​ደ​ሌ​ለው ሰው ሆንሁ።</verse>
				<verse number="5">እንደ ተገ​ደ​ሉና በመ​ቃ​ብር ውስጥ እንደ ተጣሉ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ደ​ማ​ታ​ስ​ባ​ቸው በሙ​ታን መካ​ከል የተ​ጣ​ልሁ ሆንሁ፤ እነ​ርሱ ከእ​ጅህ ርቀ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="6">በጨ​ለ​ማና በሞት ጥላ ውስጥ፥ በታ​ች​ኛው ጕድ​ጓድ አስ​ቀ​መ​ጡኝ።</verse>
				<verse number="7">በእኔ ላይ ቍጣህ ጸና፥ መቅ​ሠ​ፍ​ት​ህን ሁሉ በእኔ ላይ አመ​ጣህ።</verse>
				<verse number="8">የሚ​ያ​ው​ቁ​ኝን ከእኔ አራ​ቅህ፤ በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ርኩስ አደ​ረ​ግ​ኸኝ፤ ያዙኝ፥ መው​ጫም የለ​ኝም።</verse>
				<verse number="9">ዐይ​ኖቼም በች​ግር ፈዘዙ፤ አቤቱ፥ ሁል​ጊዜ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ እጆ​ቼንም ወደ አንተ ዘረ​ጋሁ።</verse>
				<verse number="10">በውኑ ለሙ​ታን ድን​ቅን ታደ​ር​ጋ​ለ​ህን? ወይስ ያመ​ሰ​ግ​ኑህ ዘንድ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶች ያነ​ሡ​አ​ቸ​ዋ​ልን?</verse>
				<verse number="11">በመ​ቃ​ብ​ርስ ውስጥ ያሉት ቸር​ነ​ት​ህን፥ እው​ነ​ት​ህ​ንስ በሞት ስፍራ ይና​ገ​ራ​ሉን?</verse>
				<verse number="12">ተአ​ም​ራ​ትህ በጨ​ለማ ይታ​ወ​ቃ​ልን? ቅን​ነ​ት​ህስ በም​ድር ተረ​ሳን?</verse>
				<verse number="13">አቤቱ፥ እኔ ግን ወደ አንተ ጮኽሁ፤ በጥ​ዋት ጸሎቴ ወደ አንተ ትድ​ረስ።</verse>
				<verse number="14">አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን ለምን ትጥ​ላ​ለህ? ፊት​ህ​ንስ ከእኔ ለምን ትመ​ል​ሳ​ለህ።</verse>
				<verse number="15">እኔ ድሃ ነኝ፥ ከሕ​ፃ​ን​ነቴ ጀምሮ ደከ​ምሁ። ከፍ ከፍ ካልሁ በኋላ ተዋ​ረ​ድሁ፥ ተና​ቅ​ሁም።</verse>
				<verse number="16">መቅ​ሠ​ፍት በላዬ አለፈ፥ ግር​ማ​ህም አስ​ደ​ነ​ገ​ጠኝ።</verse>
				<verse number="17">ሁል​ጊዜ እንደ ውኃ ከበ​ቡኝ፥ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ያዙኝ።</verse>
				<verse number="18">ወዳ​ጆ​ቼ​ንና ባል​ን​ጀ​ሮ​ቼን ዘመ​ዶ​ቼ​ንም ከች​ግሬ የተ​ነሣ ከእኔ አራ​ቅህ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="88">
				<verse number="1">አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ት​ህን ለዘ​ለ​ዓ​ለም እዘ​ም​ራ​ለሁ። ጽድ​ቅ​ህ​ንም በአፌ ለልጅ ልጅ እና​ገ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">“ምሕ​ረ​ትን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አን​ጻ​ለሁ” ብለ​ሃ​ልና፥ ጽድ​ቅህ በሰ​ማይ ጸና።</verse>
				<verse number="3">ከመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረ​ግሁ፥ ለባ​ሪ​ያ​ዬም ለዳ​ዊት ማልሁ፥</verse>
				<verse number="4">ዘር​ህን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አዘ​ጋ​ጃ​ለሁ፥ ዙፋ​ን​ህ​ንም ለልጅ ልጅ አጸ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">አቤቱ፥ ሰማ​ያት ክብ​ር​ህን ጽድ​ቅ​ህ​ንም ደግሞ በቅ​ዱ​ሳን ማኅ​በር ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በደ​መ​ናት ማን ይተ​ካ​ከ​ለ​ዋል? ከአ​ማ​ል​ክ​ትስ ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማን ይመ​ስ​ለ​ዋል?</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቅ​ዱ​ሳን ምክር ክቡር ነው፤ በዙ​ሪ​ያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላ​ቅና ግሩም ነው።</verse>
				<verse number="8">አቤቱ የኀ​ያ​ላን አም​ላክ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? አቤቱ፥ አንተ ብርቱ ነህ፥ እው​ነ​ትም ይከ​ብ​ብ​ሃል።</verse>
				<verse number="9">የባ​ሕ​ርን ኀይል አንተ ትገ​ዛ​ለህ፥ የሞ​ገ​ዱ​ንም መና​ወጥ አንተ ዝም ታሰ​ኘ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="10">አንተ ትዕ​ቢ​ተ​ኛ​ውን እንደ ተገ​ደለ አዋ​ረ​ድ​ኸው፥ በኀ​ይ​ል​ህም ክንድ ጠላ​ቶ​ች​ህን በተ​ን​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ሰማ​ያት የአ​ንተ ናቸው፥ ምድ​ርም የአ​ንተ ናት፤ ዓለ​ምን በሙሉ አንተ መሠ​ረ​ትህ።</verse>
				<verse number="12">ባሕ​ር​ንና መስ​ዕን አንተ ፈጠ​ርህ፤ ታቦ​ርና አር​ሞ​ን​ኤም በስ​ምህ ደስ ይላ​ቸ​ዋል። ስም​ህ​ንም ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።</verse>
				<verse number="13">ክን​ድህ ከኀ​ይ​ልህ ጋር ነው፤ እጅህ በረ​ታች፥ ቀኝ​ህም ከፍ ከፍ አለች።</verse>
				<verse number="14">የዙ​ፋ​ንህ መሠ​ረት ፍት​ሕና ርትዕ ነው፤ ምሕ​ረ​ትና እው​ነት በፊ​ትህ ይሄ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="15">እል​ል​ታን የሚ​ያ​ውቅ ሕዝብ ብፁዕ ነው፤ አቤቱ፥ በፊ​ትህ ብር​ሃን ይሄ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="16">በስ​ምህ ቀኑን ሁሉ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ በጽ​ድ​ቅ​ህም ከፍ ከፍ ይላሉ፤</verse>
				<verse number="17">የኀ​ይ​ላ​ቸው ትም​ክ​ሕት አንተ ነህና፥ በይ​ቅ​ር​ታ​ህም ቀን​ዳ​ችን ከፍ ከፍ ይላ​ልና።</verse>
				<verse number="18">ረድ​ኤ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና። ንጉ​ሣ​ች​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ነውና።</verse>
				<verse number="19">በዚያ ጊዜ ለል​ጆ​ችህ በራ​እይ ተና​ገ​ርህ፥ እን​ዲ​ህም አልህ፥ “ረድ​ኤ​ትን በኀ​ይል ላይ አኖ​ርሁ፤ ከሕ​ዝቤ የመ​ረ​ጥ​ሁ​ትን ከፍ ከፍ አደ​ረ​ግሁ።</verse>
				<verse number="20">ባሪ​ያ​ዬን ዳዊ​ትን አገ​ኘ​ሁት፥ የተ​ቀ​ደሰ ዘይ​ት​ንም ቀባ​ሁት።</verse>
				<verse number="21">እጄም ትረ​ዳ​ዋ​ለች፥ ክን​ዴም ታጸ​ና​ዋ​ለች፥</verse>
				<verse number="22">ጠላት በእ​ርሱ ላይ አይ​ጠ​ቀ​ምም፥ የዐ​መፃ ልጅም መከራ አይ​ጨ​ም​ር​በ​ትም።</verse>
				<verse number="23">ጠላ​ቶ​ቹን ከፊቱ አጠ​ፋ​ለሁ፥ የሚ​ጠ​ሉ​ት​ንም አዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="24">እው​ነ​ቴና ምሕ​ረ​ቴም ከእ​ርሱ ጋር ነው፥ በስ​ሜም ቀንዱ ከፍ ከፍ ይላል።</verse>
				<verse number="25">እጁን በባ​ሕር ላይ ቀኙ​ንም በወ​ን​ዞች ላይ አኖ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="26">እርሱ “አባቴ አንተ ነህ፥ አም​ላኬ ረዳ​ቴና መድ​ኃ​ኒ​ቴም ነህ” ይላል።</verse>
				<verse number="27">እኔም ደግሞ በኵሬ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፥ ከም​ድር ነገ​ሥ​ታ​ትም ከፍ ይላል።</verse>
				<verse number="28">ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይቅ​ር​ታ​ዬን ለእ​ርሱ እጠ​ብ​ቃ​ለሁ፥ ለኪ​ዳ​ኔም እርሱ የታ​መነ ነው።</verse>
				<verse number="29">ዘሩ​ንም ለዓ​ለ​ምና ለዘ​ለ​ዓ​ለም፥ ዙፋ​ኑ​ንም እንደ ሰማይ ዘመን አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="30">“ልጆቹ ግን ሕጌን ቢተዉ፥ በፍ​ር​ዴም ባይ​ሄዱ፤</verse>
				<verse number="31">ሥር​ዐ​ቴ​ንም ቢያ​ረ​ክሱ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ባይ​ጠ​ብቁ፤</verse>
				<verse number="32">ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን በበ​ትር፥ በደ​ላ​ቸ​ው​ንም በመ​ቅ​ሠ​ፍት እጐ​በ​ኛ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="33">ይቅ​ር​ታ​ዬን ግን ከእ​ርሱ አላ​ር​ቅም፥ በእ​ው​ነ​ቴም አል​በ​ድ​ልም፤</verse>
				<verse number="34">ኪዳ​ኔ​ንም አላ​ረ​ክ​ስም፥ ከአ​ፌም የወ​ጣ​ውን አል​ለ​ው​ጥም።</verse>
				<verse number="35">ዳዊ​ትን እን​ዳ​ል​ዋ​ሸው አንድ ጊዜ በቅ​ዱ​ስ​ነቴ ማልሁ።</verse>
				<verse number="36">ዘሩ ለዘ​ለ​ዓ​ለም፥ ዙፋ​ኑም በፊቴ እንደ ፀሐይ ይኖ​ራል።</verse>
				<verse number="37">ለዘ​ለ​ዓ​ለም እንደ ጨረቃ ይጸ​ናል። ምስ​ክ​ር​ነ​ቱም በሰ​ማይ የታ​መነ ነው።”</verse>
				<verse number="38">አንተ ግን ናቅ​ኸው፥ ጣል​ኸ​ውም፥ የቀ​ባ​ኸ​ው​ንም አቃ​ለ​ል​ኸው።</verse>
				<verse number="39">የባ​ሪ​ያ​ህ​ንም ኪዳን አፈ​ረ​ስህ፥ መቅ​ደ​ሱ​ንም በም​ድር አረ​ከ​ስህ።</verse>
				<verse number="40">ቅጥ​ሩን ሁሉ አፈ​ራ​ረ​ስህ፥ አም​ባ​ዎ​ቹ​ንም የሚ​ያ​ስ​ፈሩ አደ​ረ​ግህ።</verse>
				<verse number="41">መን​ገድ አላ​ፊም ሁሉ ተና​ጠ​ቀው፥ ለጎ​ረ​ቤ​ቶ​ቹም ስድብ ሆነ።</verse>
				<verse number="42">የጠ​ላ​ቶ​ቹ​ንም ቀኝ ከፍ ከፍ አደ​ረ​ግህ። ጠላ​ቶ​ቹ​ንም ሁሉ ደስ አሰ​ኘህ።</verse>
				<verse number="43">የሰ​ይ​ፉ​ንም ረድ​ኤት መለ​ስህ፥ በሰ​ል​ፍም ውስጥ አል​ደ​ገ​ፍ​ኸ​ውም።</verse>
				<verse number="44">ከን​ጽ​ሕ​ና​ውም ሻር​ኸው፥ ዙፋ​ኑ​ንም በም​ድር ጣልህ።</verse>
				<verse number="45">የዙ​ፋ​ኑ​ንም ዘመን አሣ​ነ​ስህ፥ በላ​ዩም እፍ​ረ​ትን ጨመ​ርህ።</verse>
				<verse number="46">አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ፊት​ህን ትመ​ል​ሳ​ለህ? እስከ መቼስ ቍጣህ እንደ እሳት ይነ​ድ​ዳል?</verse>
				<verse number="47">ኀይሌ ምን እንደ ሆነ ዐስብ፤ በውኑ የሰ​ውን ልጅ ሁሉ ለከ​ንቱ ፈጠ​ር​ኸ​ውን?</verse>
				<verse number="48">ሕያው ሆኖ የሚ​ኖር፥ ሞት​ንስ የማ​ያይ ሰው ማን ነው? ነፍ​ሱ​ንስ ከሲ​ኦል እጅ የሚ​ያ​ድ​ናት ማን ነው?</verse>
				<verse number="49">አቤቱ፥ የቀ​ድሞ ይቅ​ር​ታህ ወዴት ነው? ለባ​ሪ​ያህ ለዳ​ዊት በእ​ው​ነት የማ​ልህ፥</verse>
				<verse number="50">አቤቱ፦ ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህን የሰ​ደ​ቡ​አ​ቸ​ውን ስድብ፥ በብ​ብቴ ብዙ አሕ​ዛ​ብን የተ​ቀ​በ​ል​ሁ​ትን፥</verse>
				<verse number="51">አቤቱ፥ ጠላ​ቶ​ችህ የሰ​ደ​ቡ​ትን የቀ​ባ​ኸ​ውን ዘመን የሰ​ደ​ቡ​ትን ስድብ ዐስብ።</verse>
				<verse number="52">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይመ​ስ​ገን። ይሁን ይሁን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="89">
				<verse number="1">አቤቱ፥ አንተ ለልጅ ልጅ ሁሉ መጠ​ጊያ ሆን​ህ​ልን።</verse>
				<verse number="2">ተራ​ሮች ሳይ​ወ​ለዱ፥ ምድ​ርም ዓለ​ምም ሳይ​ሠሩ፥ ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ መቼም መች አንተ ነህ።</verse>
				<verse number="3">ሰውን ወደ ኀሣር አት​መ​ል​ሰው፤ የሰው ልጆች ሆይ፥ ተመ​ለሱ ትላ​ለህ፤</verse>
				<verse number="4">ሺህ ዓመት በፊ​ትህ እን​ዳ​ለ​ፈች እንደ ትና​ንት ቀን፥ እንደ ሌሊ​ትም ሰዓት ነውና።</verse>
				<verse number="5">ዘመ​ኖች በፊ​ትህ የተ​ናቁ ናቸው፥ በማ​ለ​ዳም እንደ ሣር ያል​ፋል።</verse>
				<verse number="6">ማልዶ ይበ​ቅ​ላል ያል​ፋ​ልም፥ በሠ​ር​ክም ጠው​ል​ጎና ደርቆ ይወ​ድ​ቃል።</verse>
				<verse number="7">እኛ በቍ​ጣህ አል​ቀ​ና​ልና፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ት​ህም ደን​ግ​ጠ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="8">ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን በፊ​ትህ አስ​ቀ​መ​ጥህ፥ ዓለ​ማ​ች​ንም በፊ​ትህ ብር​ሃን ነው።</verse>
				<verse number="9">ዘመ​ና​ችን ሁሉ አል​ፎ​አ​ልና፥ እኛም በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ትህ አል​ቀ​ና​ልና፤ ዘመ​ኖ​ቻ​ች​ንም እንደ ሸረ​ሪት ድር ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="10">የዘ​መ​ኖ​ቻ​ች​ንም ዕድሜ ሰባ ዓመት ነው፥ ቢበ​ዛም ሰማ​ንያ ዓመት ነው፤ ከእ​ነ​ዚህ ቢበዛ ግን ድካ​ምና መከራ ነው፤ የዋ​ህ​ነት ከእኛ አል​ፋ​ለ​ችና፥ እኛም ተገ​ሥ​ጸ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="11">የመ​ቅ​ሠ​ፍ​ት​ህን ኀይል ማን ያው​ቃል? ከቍ​ጣህ ግርማ የተ​ነሣ አለቁ።</verse>
				<verse number="12">ጥበ​ብን በልብ ለተ​ማሩ፥ ቀኝ​ህን እን​ዲህ ግለጥ።</verse>
				<verse number="13">አቤቱ፥ ተመ​ለስ፥ እስከ መቼስ ነው? ስለ ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህም ተሟ​ገት።</verse>
				<verse number="14">በማ​ለዳ ምሕ​ረ​ት​ህን እን​ጠ​ግ​ባ​ለ​ንና፤ በዘ​መ​ና​ችን ሁሉ ደስ ይለ​ናል፥ ሐሤ​ትም እና​ደ​ር​ጋ​ለን።</verse>
				<verse number="15">መከ​ራን ባሳ​የ​ኸን ዘመን ፋንታ፥ ክፉ​ንም ባየ​ን​ባት ዘመን ፋንታ ደስ ይለ​ናል።</verse>
				<verse number="16">ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህ​ንና ሥራ​ህን እይ፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ምራ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብር​ሃን በላ​ያ​ችን ይሁን። የእ​ጆ​ቻ​ች​ን​ንም ሥራ ያቃ​ና​ል​ናል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="90">
				<verse number="1">በል​ዑል ረድ​ኤት የሚ​ያ​ድር፥ በሰ​ማይ አም​ላክ ጥላ ውስጥ የሚ​ቀ​መጥ፥</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “አንተ መጠ​ጊ​ያ​ዬና አም​ባዬ ነህ፤ አም​ላ​ኬና ረዳቴ ነው፥ በእ​ር​ሱም እታ​መ​ና​ለሁ” ይለ​ዋል።</verse>
				<verse number="3">እርሱ ከአ​ዳኝ ወጥ​መድ፥ ከሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጥም ነገር ያድ​ነ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="4">በላ​ባ​ዎቹ ይጋ​ር​ድ​ሃል፥ በክ​ን​ፎ​ቹም በታች ትተ​ማ​መ​ና​ለህ፤ እው​ነት እንደ ጋሻ ይከ​ብ​ብ​ሃል።</verse>
				<verse number="5">ከሌ​ሊት ግርማ፥ በመ​ዓ​ልት ከሚ​በ​ርር ፍላጻ፥</verse>
				<verse number="6">በጨ​ለማ ከሚ​ሄድ ክፉ ሥራ፥ ከአ​ደ​ጋና ከቀ​ትር ጋኔን አት​ፈ​ራም።</verse>
				<verse number="7">በአ​ጠ​ገ​ብህ ሺህ፥ በቀ​ኝ​ህም ዐሥር ሺህ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ወደ አንተ ግን አይ​ቀ​ር​ቡም።</verse>
				<verse number="8">በዐ​ይ​ኖ​ችህ ብቻ ትመ​ለ​ከ​ታ​ለህ፥ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም ፍዳ ታያ​ለህ።</verse>
				<verse number="9">አቤቱ፥ አንተ ተስ​ፋዬ ነህና፤ ልዑ​ልን መጠ​ጊ​ያህ አደ​ረ​ግህ።</verse>
				<verse number="10">ክፉ ነገር ወደ አንተ አይ​ቀ​ር​ብም፥ መቅ​ሠ​ፍ​ትም ወደ ቤትህ አይ​ገ​ባም።</verse>
				<verse number="11">በመ​ን​ገ​ድህ ሁሉ ይጠ​ብ​ቁህ ዘንድ መላ​እ​ክ​ቱን ስለ አንተ ያዝ​ዛ​ቸ​ዋ​ልና፤</verse>
				<verse number="12">እግ​ር​ህም በድ​ን​ጋይ እን​ዳ​ት​ሰ​ና​ከል በእ​ጆ​ቻ​ቸው ያነ​ሡ​ሃል።</verse>
				<verse number="13">በተ​ኵ​ላና በእ​ባብ ላይ ትጫ​ና​ለህ፤ አን​በ​ሳ​ው​ንና ዘን​ዶ​ውን ትረ​ግ​ጣ​ለህ።</verse>
				<verse number="14">በእኔ ተማ​ም​ኖ​አ​ልና አድ​ነ​ዋ​ለሁ ስሜ​ንም አው​ቆ​አ​ልና እጋ​ር​ደ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">ይጠ​ራ​ኛል እመ​ል​ስ​ለ​ት​ማ​ለሁ፥ በመ​ከ​ራ​ውም ጊዜ ከእ​ርሱ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ አድ​ነ​ዋ​ለሁ አከ​ብ​ረ​ው​ማ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">ረዥም ዕድ​ሜን አጠ​ግ​በ​ዋ​ለሁ፥ ማዳ​ኔ​ንም አሳ​የ​ዋ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="91">
				<verse number="1">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​መን ይሻ​ላል፥ ልዑል ሆይ፥ ለስ​ም​ህም መዘ​መር፤</verse>
				<verse number="2">በማ​ለዳ ምሕ​ረ​ት​ህን፥ በሌ​ሊ​ትም እው​ነ​ት​ህን መና​ገር፥</verse>
				<verse number="3">ዐሥር አው​ታር ባለው በበ​ገና፥ ከም​ስ​ጋና ጋርም በመ​ሰ​ንቆ።</verse>
				<verse number="4">አቤቱ፥ በሥ​ራህ ደስ አሰ​ኝ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፤ በእ​ጆ​ች​ህም ሥራ ደስ ይለ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="5">አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ትልቅ ነው፥ አሳ​ብ​ህም እጅግ ጥልቅ ነው።</verse>
				<verse number="6">ሰነፍ ሰው አያ​ው​ቅም፥ ልብ የሌ​ለ​ውም ይህን አያ​ስ​ተ​ው​ለ​ውም።</verse>
				<verse number="7">ኃጥ​ኣን እንደ ሣር በበ​ቀሉ ጊዜ፥ ዐመ​ፃን የሚ​ያ​ደ​ር​ጉም ሁሉ በለ​መ​ለሙ ጊዜ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዓለም እን​ደ​ሚ​ጠፉ ነው።</verse>
				<verse number="8">አቤቱ፥ አንተ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ልዑል ነህ፤</verse>
				<verse number="9">አቤቱ፥ እነሆ፥ ጠላ​ቶ​ችህ ይጠ​ፋ​ሉና፥ ዐመ​ፃ​ንም የሚ​ሠሩ ሁሉ ይበ​ተ​ና​ሉና።</verse>
				<verse number="10">ቀንዴ አንድ ቀንድ እን​ዳ​ለው ከፍ ከፍ ይላል፥ ሽም​ግ​ል​ና​ዬም በዘ​ይት ይለ​መ​ል​ማል።</verse>
				<verse number="11">ዐይ​ኔም በጠ​ላ​ቶቼ ላይ አየች፥ ጆሮ​ዬም በእኔ ላይ በቆሙ በክ​ፉ​ዎች ላይ ሰማች።</verse>
				<verse number="12">ጻድቅ ግን እንደ ዘን​ባባ ያፈ​ራል፥ እንደ ሊባ​ኖስ ዝግ​ባም ይበ​ዛል፥</verse>
				<verse number="13">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ የተ​ተ​ከሉ ናቸው፥ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም አደ​ባ​ባይ ውስጥ ይበ​ቅ​ላሉ።</verse>
				<verse number="14">ያን​ጊዜ በመ​ል​ካም ሽም​ግ​ልና ይበ​ዛሉ፤ ዕረ​ፍት ያላ​ቸ​ውም ሆነው ይኖ​ራሉ።</verse>
				<verse number="15">አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተኛ እንደ ሆነ ይና​ገ​ራሉ፥ በእ​ር​ሱም ዘንድ ዐመፃ የለም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="92">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነገሠ፥ ክብ​ሩ​ንም ለበሰ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይ​ልን ለበሰ፥ ታጠ​ቀም፤ ዓለ​ም​ንም እን​ዳ​ት​ና​ወጥ አጸ​ናት።</verse>
				<verse number="2">አቤቱ፥ ዙፋ​ንህ ከጥ​ንት ጀምሮ የተ​ዘ​ጋጀ ነው፥ አን​ተም መቼም መች እስከ ዘለ​ዓ​ለም ነህ።</verse>
				<verse number="3">አቤቱ፥ ወን​ዞች ከፍ ከፍ አደ​ረጉ፥ ወን​ዞች ቃሎ​ቻ​ቸ​ውን ከፍ ከፍ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="4">ከብዙ ውኆች ድምፅ የተ​ነሣ የባ​ሕር እን​ቅ​ስ​ቃ​ሴዋ ድንቅ ነው። ድን​ቅስ በል​ዕ​ልና የሚ​ኖር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።</verse>
				<verse number="5">ምስ​ክ​ርህ እጅግ የታ​መነ ነው፤ አቤቱ፥ እስከ ረዥም ዘመን ድረስ ለቤ​ትህ ምስ​ጋና ይገ​ባል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="93">
				<verse number="1">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተበ​ቃይ ነው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ልጥ ተበ​ቃይ ነው።</verse>
				<verse number="2">የም​ድር ፈራጅ፥ ከፍ ከፍ አለ፤ ለት​ዕ​ቢ​ተ​ኞች ፍዳ​ቸ​ውን ክፈ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">አቤቱ፥ ኃጥ​ኣን እስከ መቼ? ኃጥ​ኣን እስከ መቼ ይታ​በ​ያሉ?</verse>
				<verse number="4">ይከ​ራ​ከ​ራሉ፥ ዐመ​ፃ​ንም ይና​ገ​ራሉ፤ ዐመ​ፃ​ንም የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ይና​ገ​ራሉ።</verse>
				<verse number="5">አቤቱ፥ ሕዝ​ብ​ህን አዋ​ረዱ፥ ርስ​ት​ህ​ንም አሠ​ቃዩ።</verse>
				<verse number="6">ባል​ቴ​ቲ​ቱ​ንና ድሃ አደ​ጉን ገደሉ፥ ስደ​ተ​ኛ​ው​ንም ገደሉ።</verse>
				<verse number="7">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አያ​ይም፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ አያ​ው​ቅም” አሉ።</verse>
				<verse number="8">ሰነ​ፎች ሕዝብ ሆይ፥ ልብ አድ​ርጉ፤ ሰነ​ፎ​ችም መቼ ይጠ​በ​ባሉ?</verse>
				<verse number="9">ጆሮን የተ​ከ​ለው አይ​ሰ​ማ​ምን? ዐይ​ንን የሠ​ራው አያ​ይ​ምን?</verse>
				<verse number="10">አሕ​ዛ​ብ​ንስ የሚ​ገ​ሥ​ጸው፥ ለሰ​ዎ​ችም ዕው​ቀ​ትን የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ረው እርሱ አይ​ዘ​ል​ፍ​ምን?</verse>
				<verse number="11">የጠ​ቢ​ባን ዐሳብ ከንቱ እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያው​ቃል።</verse>
				<verse number="12">አቤቱ፥ አንተ የገ​ሠ​ጽ​ኸው ሕግ​ህ​ንም ያስ​ተ​ማ​ር​ኸው ሰው ብፁዕ ነው።</verse>
				<verse number="13">ከክ​ፉ​ዎች ዘመ​ናት ይወ​ገድ ዘንድ ለኃ​ጥ​ኣን ጕድ​ጓድ እስ​ኪ​ቆ​ፈር ድረስ።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን አይ​ጥ​ላ​ቸ​ው​ምና፥ ርስ​ቱ​ንም አይ​ተ​ዋ​ቸ​ው​ምና</verse>
				<verse number="15">ፍርድ ለእ​ው​ነ​ተኛ እስ​ኪ​መ​ለስ ድረስ፥ ልበ ቅኖ​ችም ሁሉ ይከ​ተ​ሉ​አ​ታል።</verse>
				<verse number="16">ስለ ክፉ​ዎች ማን ይከ​ራ​ከ​ር​ል​ኛል? ዐመ​ፃ​ንስ ስለ​ሚ​ያ​ደ​ርጉ ማን ይቆ​ም​ል​ኛል?</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የረ​ዳኝ ባይ​ሆን ነፍሴ ለጥ​ቂት ጊዜ በሲ​ኦል ባደ​ረች ነበር።</verse>
				<verse number="18">እግ​ሮች ተሰ​ና​ከሉ ባልሁ ጊዜ፥ አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ትህ ረዳኝ።</verse>
				<verse number="19">አቤቱ ለልቤ እንደ መከ​ራዋ ብዛት፥ ማጽ​ና​ና​ትህ ነፍ​ሴን ደስ አሰ​ኛት።</verse>
				<verse number="20">በሕግ ላይ ድካ​ምን የሚ​ፈ​ጥር፥ የዐ​መፃ ዙፋን አይ​ቃ​ወ​ም​ህም፥</verse>
				<verse number="21">የጻ​ድ​ቅን ነፍስ ያድ​ና​ታል፥ በን​ጹሕ ደምም ይፈ​ር​ዳል።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መጠ​ጊ​ያዬ ሆነኝ፥ አም​ላኬ የተ​ስ​ፋ​ዬም ረዳት ነው።</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ክፋ​ታ​ቸው ፍዳ​ቸ​ውን ይከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋል፥ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="94">
				<verse number="1">ኑ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ለን፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ንና ለመ​ድ​ኀ​ኒ​ታ​ች​ንም እልል እን​በል፥</verse>
				<verse number="2">በእ​ም​ነት ወደ ፊቱ እን​ድ​ረስ፥ በዝ​ማ​ሬም ለእ​ርሱ እልል እን​በል፤</verse>
				<verse number="3">አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነውና፥ በአ​ማ​ል​ክ​ትም ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ ነውና።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን አይ​ጥ​ላ​ቸ​ው​ምና፤ የም​ድር ዳር​ቻ​ዎ​ችም ሁሉ በእጁ ውስጥ ናቸ​ውና፥ ረዣ​ዥም ተራ​ሮች የእ​ርሱ ናቸ​ውና።</verse>
				<verse number="5">ባሕር የእ​ርሱ ናትና፥ እር​ሱም ፈጥ​ሯ​ታ​ልና። የብ​ስ​ንም በእጁ ፈጥ​ሯ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="6">ኑ፥ እን​ስ​ገድ ለእ​ር​ሱም እን​ገዛ፤ በእ​ርሱ በፈ​ጠ​ረን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እና​ል​ቅስ፤</verse>
				<verse number="7">እርሱ አም​ላ​ካ​ችን ነውና፥ እኛ ግን ሕዝቡ የማ​ሰ​ማ​ር​ያ​ውም በጎች ነን።</verse>
				<verse number="8">በም​ድረ በዳ እንደ ተፈ​ታ​ተ​ኑ​ትና እን​ዳ​ስ​ቈ​ጡት ጊዜ፥ ዛሬ ድም​ፁን ብት​ሰሙ ልባ​ች​ሁን አታ​ጽኑ።</verse>
				<verse number="9">የተ​ፈ​ታ​ተ​ኑኝ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ፈተ​ኑኝ፥ ሥራ​ዬ​ንም አዩ።</verse>
				<verse number="10">“ይችን ትው​ልድ አርባ ዓመ​ታት ተቈ​ጥ​ቻት ነበር፥ ሁል​ጊዜ ልባ​ቸው ይስ​ታል፥ እነ​ር​ሱም መን​ገ​ዴን አላ​ወ​ቁም” አልሁ።</verse>
				<verse number="11">ወደ ዕረ​ፍ​ቴም እን​ዳ​ይ​ገቡ በቍ​ጣዬ ማልሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="95">
				<verse number="1">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዲስ ምስ​ጋ​ናን አመ​ስ​ግኑ፤ ምድር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ስ​ግ​ኑት፥ ስሙ​ንም ባርኩ፥ ዕለት ዕለ​ትም ማዳ​ኑን አውሩ።</verse>
				<verse number="3">ክብ​ሩን ለአ​ሕ​ዛብ፥ ተአ​ም​ራ​ቱ​ንም ለወ​ገ​ኖች ሁሉ ንገሩ፤</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ፥ ምስ​ጋ​ና​ውም ብዙ ነውና፥ በአ​ማ​ል​ክ​ትም ሁሉ ላይ የተ​ፈራ ነውና።</verse>
				<verse number="5">የአ​ሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ሁሉ አጋ​ን​ንት ናቸ​ውና፤ እግ​ዝ​አ​ብ​ሔር ግን ሰማ​ያ​ትን ፈጠረ።</verse>
				<verse number="6">እም​ነ​ትና በጎ​ነት በፊቱ፥ ቅድ​ስ​ናና የክ​ብር ገና​ና​ነት በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ናቸው።</verse>
				<verse number="7">የአ​ሕ​ዛብ ወገ​ኖች፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፥ ክብ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፤</verse>
				<verse number="8">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለስሙ ክብ​ርን አምጡ፤ መሥ​ዋ​ዕት ያዙ ወደ አደ​ባ​ባ​ዮ​ችም ግቡ።</verse>
				<verse number="9">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቅ​ድ​ስ​ናው ቦታ ስገዱ፤ ምድር በመ​ላዋ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ነሣ ትነ​ዋ​ወ​ጣ​ለች።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንደ ነገሠ ለአ​ሕ​ዛብ ንገ​ሩ​አ​ቸው፥ እን​ዳ​ይ​ና​ወ​ጥም ዓለ​ሙን ሁሉ አጸ​ናው፥ አሕ​ዛ​ብ​ንም በቅ​ን​ነት ይገ​ዛል።</verse>
				<verse number="11">ሰማ​ያት ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ ምድ​ርም ሐሤ​ትን ታደ​ር​ጋ​ለች፤ ባሕር ሞላዋ ትና​ወ​ጣ​ለች፤</verse>
				<verse number="12">በረሃ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ ሁሉ ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋሉ፤ የዱር ዛፎች ሁሉ በዚ​ያን ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤</verse>
				<verse number="13">ይመ​ጣ​ልና፤ በም​ድር ላይ ሊፈ​ርድ ይመ​ጣ​ልና፤ እር​ሱም ዓለ​ምን በጽ​ድቅ አሕ​ዛ​ብ​ንም በቅ​ን​ነት ይገ​ዛል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="96">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነገሠ፥ ምድር ሐሤ​ትን ታደ​ር​ጋ​ለች፥ ብዙ ደሴ​ቶ​ችም ደስ ይላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="2">ደመ​ናና ጭጋ​ግም በዙ​ሪ​ያው ናቸው፤ ፍት​ሕና ርትዕ የዙ​ፋኑ መሠ​ረት ናቸው፤</verse>
				<verse number="3">እሳት በፊቱ ይሄ​ዳል፥ ነበ​ል​ባ​ሉም ጠላ​ቶ​ቹን ይከ​ብ​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="4">መብ​ረ​ቆቹ ለዓ​ለም አበሩ፤ ምድር ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠች ተና​ወ​ጠ​ችም።</verse>
				<verse number="5">ተራ​ሮ​ችም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ነሣ እንደ ሰም ቀለጡ፥ ምድር ሁሉ ከአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ነሣ ቀለ​ጠች።</verse>
				<verse number="6">ሰማ​ያት የእ​ር​ሱን ጽድቅ አወሩ፥ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ ክብ​ሩን አዩ።</verse>
				<verse number="7">ለተ​ቀ​ረጸ ምስል የሚ​ሰ​ግዱ ሁሉ፥ በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የሚ​መኩ ይፈሩ፤ መላ​እ​ክ​ቱም ሁሉ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="8">አቤቱ፥ ስለ ፍር​ድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፥ የይ​ሁ​ዳም ሴቶች ልጆች ሐሤት አደ​ረጉ፤</verse>
				<verse number="9">አንተ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ በም​ድር ላይ ሁሉ ብቻ​ህን ልዑል ነህና፥ በአ​ማ​ል​ክ​ትም ሁሉ ላይ እጅግ ከፍ ከፍ ብለ​ሃ​ልና።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ወ​ድዱ፥ ክፋ​ትን ጥሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጻ​ድ​ቃ​ኑን ነፍ​ሶች ይጠ​ብ​ቃል፥ ከኃ​ጥ​ኣ​ንም እጅ ያድ​ና​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="11">ብር​ሃን ለጻ​ድ​ቃን፥ ደስ​ታም ለልበ ቅኖች ወጣ።</verse>
				<verse number="12">ጻድ​ቃን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይላ​ቸ​ዋል። ለቅ​ድ​ስ​ና​ውም መታ​ሰ​ቢያ ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="97">
				<verse number="1">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዲስ ምስ​ጋ​ናን አመ​ስ​ግኑ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ፥ የቀኙ ማዳን፥ የተ​ቀ​ደሰ ክን​ዱም ድንቅ ነውና።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማዳ​ኑን አሳየ። በአ​ሕ​ዛ​ብም ፊት ቃል ኪዳ​ኑን ገለጠ።</verse>
				<verse number="3">ለያ​ዕ​ቆብ ይቅ​ር​ታ​ውን ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት እው​ነ​ቱን አሰበ፤ የም​ድር ዳር​ቻ​ዎች ሁሉ፥ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ማዳን እዩ።</verse>
				<verse number="4">በም​ድር ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እልል በሉ፤ አመ​ስ​ግኑ፥ ደስም ይበ​ላ​ችሁ፥ ዘም​ሩም።</verse>
				<verse number="5">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ሰ​ንቆ፥ በመ​ሰ​ን​ቆና በዝ​ማሬ ድምፅ ዘምሩ።</verse>
				<verse number="6">በነ​ጋ​ሪ​ትና በመ​ለ​ከት ድምፅ፥ በን​ጉሡ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እልል በሉ።</verse>
				<verse number="7">ባሕር በሞ​ላዋ፥ ዓለ​ምም በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖሩ ሁሉ ይና​ወጡ።</verse>
				<verse number="8">ወን​ዞ​ችም በአ​ን​ድ​ነት በእጅ ያጨ​ብ​ጭቡ፥ ተራ​ሮች ደስ ይበ​ላ​ቸው፥</verse>
				<verse number="9">ለም​ድር በዚያ ይፈ​ረ​ድ​ላ​ታ​ልና። ለዓ​ለ​ምም በእ​ው​ነት ይፈ​ረ​ድ​ላ​ታ​ልና። ለአ​ሕ​ዛ​ብም በቅ​ን​ነት ይፈ​ረ​ዳል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="98">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነገሠ፥ አሕ​ዛብ ደነ​ገጡ፤ በኪ​ሩ​ቤል ላይ የተ​ቀ​መጠ፥ ምድ​ርን አነ​ዋ​ወ​ጣት።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ታላቅ ነው፤ እር​ሱም በአ​ሕ​ዛቡ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ።</verse>
				<verse number="3">ሁሉ ታላቅ ስም​ህን ያመ​ሰ​ግ​ናል፥ ግሩ​ምና ቅዱስ ነውና።</verse>
				<verse number="4">ክቡር ንጉሥ ፍር​ድን ይወ​ድ​ዳል፤ አንተ በኀ​ይ​ልህ ጽድ​ቅን አጸ​ናህ፥ ለያ​ዕ​ቆብ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን አንተ አደ​ረ​ግህ።</verse>
				<verse number="5">ፈጣ​ሪ​ያ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ከፍ አለ፥ ከእ​ግሩ መረ​ገጫ በታ​ችም ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="6">ሙሴና አሮን በክ​ህ​ነ​ታ​ቸው ቅዱ​ሳን ናቸ​ውና ሳሙ​ኤ​ልም ስሙን ከሚ​ጠ​ሩት ጋራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠሩት፥ እር​ሱም መለ​ሰ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">በደ​መና ዐም​ድም ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ምስ​ክ​ሩ​ንና የሰ​ጣ​ቸ​ውን ትእ​ዛዝ ጠበቁ።</verse>
				<verse number="8">አቤቱ፥ አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ አንተ ሰማ​ሃ​ቸው፤ አቤቱ፥ አንተ ማር​ሃ​ቸው፥ በሥ​ራ​ቸው ሁሉ ግን ትበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="9">አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ከፍ አለ፥ በተ​ቀ​ደ​ሰው ተራራ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ነውና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="99">
				<verse number="1">በም​ድር ሁሉ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እልል በሉ፥</verse>
				<verse number="2">በደ​ስ​ታም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዙ፥ በሐ​ሤ​ትም ወደ ፊቱ ግቡ።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላ​ካ​ችን እንደ ሆነ ዕወቁ፤ እርሱ ፈጠ​ረን፥ እኛም አይ​ደ​ለ​ንም፤ እኛስ ሕዝቡ የመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ውም በጎች ነን።</verse>
				<verse number="4">ወደ ደጆቹ በመ​ገ​ዛት፥ ወደ አደ​ባ​ባ​ዮ​ቹም በም​ስ​ጋና ግቡ፤ አመ​ስ​ግ​ኑት፥ ስሙ​ንም አክ​ብሩ፥</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም፥ እው​ነ​ቱም ለልጅ ልጅ ነውና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="100">
				<verse number="1">አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ት​ንና ፍር​ድን እዘ​ም​ር​ል​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">እዘ​ም​ራ​ለሁ፥ ንጹሕ መን​ገ​ድ​ንም አስ​ተ​ው​ላ​ለሁ፤ ወደ እኔ መቼ ትመ​ጣ​ለህ? በቤቴ መካ​ከል በልቤ ቅን​ነት እሄ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">በዐ​ይኔ ፊት ክፉ ነገ​ርን አላ​ኖ​ር​ሁም፤ ዐመፃ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ጠላሁ።</verse>
				<verse number="4">ጠማማ ልብም አል​ተ​ከ​ተ​ለ​ኝም፤ ክፉ ከእኔ በራቀ ጊዜ አላ​ወ​ቅ​ሁም።</verse>
				<verse number="5">ባል​ን​ጀ​ራ​ውን በስ​ውር የሚ​ያ​ማን እር​ሱን አሳ​ደ​ድሁ፤ በዐ​ይኑ ትዕ​ቢ​ተኛ የሆ​ነ​ውና ልቡ የሚ​ሳ​ሳው ከእኔ ጋር አይ​ተ​ባ​በ​ርም።</verse>
				<verse number="6">ከእኔ ጋር አኖ​ራ​ቸው ዘንድ ዐይ​ኖቼ ወደ ምድር ምእ​መ​ናን ናቸው፤ በን​ጹሕ መን​ገድ የሚ​ሄድ እርሱ ያገ​ለ​ግ​ለ​ኛል።</verse>
				<verse number="7">ትዕ​ቢ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ በቤቴ መካ​ከል አይ​ኖ​ርም፥ ዐመ​ፃን የሚ​ና​ገር በፊቴ አይ​ጸ​ናም።</verse>
				<verse number="8">ዐመ​ፃን የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተማ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ፥ የም​ድ​ርን ኀጢ​አ​ተ​ኞች ሁሉ በማ​ለዳ እገ​ድ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="101">
				<verse number="1">አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን ስማኝ፥ ጩኸ​ቴም ወደ ፊትህ ይድ​ረስ።</verse>
				<verse number="2">በመ​ከ​ራዬ ቀን ፊት​ህን ከእኔ አት​መ​ልስ፤ ጆሮ​ህን ወደ እኔ አዘ​ን​ብል፤ በጠ​ራ​ሁህ ቀን ፈጥ​ነህ ስማኝ።</verse>
				<verse number="3">ዘመኔ እንደ ጢስ አል​ቋ​ልና፥ አጥ​ን​ቶቼም እንደ ሣር ደር​ቀ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="4">ተቀ​ሠ​ፍሁ ልቤም እንደ ሣር ደረቀ። እህል መብ​ላት ተረ​ስ​ቶ​ኛ​ልና</verse>
				<verse number="5">ከጩ​ኸቴ ድምፅ የተ​ነሣ ሥጋዬ በአ​ጥ​ን​ቶቼ ላይ ተጣ​በቀ።</verse>
				<verse number="6">እንደ ሜዳ አህያ ሆንኹ፤ ሌሊት በወና ቤት እን​ዳለ እንደ ጕጕት ሆንሁ።</verse>
				<verse number="7">ተጋሁ፥ በሰ​ገ​ነ​ትም እን​ደ​ሚ​ኖር ብቸኛ ድን​ቢጥ ሆንሁ።</verse>
				<verse number="8">ጠላ​ቶቼ ሁል​ጊዜ ይሰ​ድ​ቡ​ኛል፥ የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​ኝም ተማ​ማ​ሉ​ብኝ።</verse>
				<verse number="9">አመ​ድን እንደ እህል ቅሜ​አ​ለ​ሁና፥ መጠ​ጤ​ንም ከእ​ን​ባዬ ጋር ጠጥ​ቻ​ለ​ሁና፥</verse>
				<verse number="10">ከቍ​ጣህ መቅ​ሠ​ፍት የተ​ነሣ፥ አን​ስ​ተኽ ጥለ​ኸ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="11">ዘመ​ኔም እንደ ጥላ አለፈ፤ እኔም እንደ ሣር ደር​ቄ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ትኖ​ራ​ለህ፥ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ህም ለልጅ ልጅ ነው።</verse>
				<verse number="13">አንተ ተነሥ፥ ጽዮ​ን​ንም ይቅር በላት፥ ይቅር ትላት ዘንድ ጊዜዋ ነውና፥ ዘመ​ን​ዋም ደር​ሶ​አ​ልና፤</verse>
				<verse number="14">ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ድን​ጋ​ዮ​ች​ዋን ወድ​ደ​ዋ​ልና፥ መሬ​ቷ​ንም አክ​ብ​ረ​ው​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="15">አቤቱ፥ አሕ​ዛብ ስም​ህን፥ ነገ​ሥ​ታ​ትም ሁሉ ክብ​ር​ህን ይፍሩ፤</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዮ​ንን ይሠ​ራ​ታ​ልና፥ በክ​ብ​ሩም ይገ​ለ​ጣ​ልና።</verse>
				<verse number="17">ወደ ድሆች ጸሎት ተመ​ለ​ከተ፥ ልመ​ና​ቸ​ው​ንም አል​ና​ቀም፥</verse>
				<verse number="18">ይህ​ችም ለሚ​መጣ ትው​ልድ ተጻ​ፈች፥ የሚ​ፈ​ጠ​ርም ሕዝብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ነ​ዋል፤</verse>
				<verse number="19">ከሰ​ማይ ሆኖ መቅ​ደ​ሱን ተመ​ል​ክ​ቶ​አ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ሆኖ ምድ​ርን ጐብ​ኝ​ቶ​አ​ልና፤</verse>
				<verse number="20">የእ​ስ​ረ​ኞ​ችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፥ የተ​ገ​ደ​ሉ​ት​ንም ሰዎች ልጆች ያድን ዘንድ፤</verse>
				<verse number="21">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም በጽ​ዮን ምስ​ጋ​ና​ው​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይነ​ግሩ ዘንድ፤</verse>
				<verse number="22">አሕ​ዛብ በአ​ን​ድ​ነት በተ​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ ነገ​ሥ​ታ​ትም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገዙ ዘንድ።</verse>
				<verse number="23">በኀ​ይሉ ጎዳና መለ​ሳ​ቸው፥ የዘ​መ​ኔን ማነስ ንገ​ረኝ።</verse>
				<verse number="24">በዘ​መኔ አኩ​ሌታ አት​ው​ሰ​ደኝ፤ ዓመ​ቶ​ችህ ለልጅ ልጅ ናቸው።</verse>
				<verse number="25">አቤቱ፥ አንተ አስ​ቀ​ድ​መህ ምድ​ርን መሠ​ረ​ትህ፥ ሰማ​ያ​ትም የእ​ጅህ ሥራ ናቸው።</verse>
				<verse number="26">እነ​ርሱ ይጠ​ፋሉ፥ አንተ ግን ትኖ​ራ​ለህ፥ ሁሉ እንደ ልብስ ያረ​ጃል፥ እንደ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያም ትለ​ው​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ፥ ይለ​ወ​ጡ​ማል፤</verse>
				<verse number="27">አንተ ግን ያው አንተ ነህ፥ ዓመ​ት​ህም ከቶ አያ​ል​ቅም።</verse>
				<verse number="28">የባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህም ልጆች ይኖ​ራሉ፥ ዘራ​ቸ​ውም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጸ​ናል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="102">
				<verse number="1">ነፍሴ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለች። አጥ​ን​ቶ​ቼም ሁሉ የተ​ቀ​ደሰ ስሙን።</verse>
				<verse number="2">ነፍሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለች፥ ምስ​ጋ​ና​ው​ንም ሁሉ አት​ረ​ሳም።</verse>
				<verse number="3">ኀጢ​አ​ት​ህን ሁሉ ይቅር የሚ​ል​ልህ፤ ደዌ​ህ​ንም ሁሉ የሚ​ፈ​ው​ስህ፥</verse>
				<verse number="4">ሕይ​ወ​ት​ህን ከጥ​ፋት የሚ​ያ​ድ​ናት፥ በይ​ቅ​ር​ታ​ውና በም​ሕ​ረቱ የሚ​ከ​ል​ልህ፥</verse>
				<verse number="5">ምኞ​ት​ህን ከበ​ረ​ከቱ የሚ​ያ​ጠ​ግ​ባት፥ ጐል​ማ​ስ​ነ​ት​ህን እንደ ንስር የሚ​ያ​ድ​ሳት፥</verse>
				<verse number="6">እግ​ዝ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ርታ አድ​ራጊ ነው፤ ለተ​በ​ደሉ ሁሉ ይፈ​ር​ዳል።</verse>
				<verse number="7">ለሙሴ መን​ገ​ዱን አሳየ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ፈቃ​ዱን።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓ​ሪና ይቅር ባይ ነው፥ ከቍጣ የራቀ ምሕ​ረ​ቱም የበዛ ጻድቅ ነው።</verse>
				<verse number="9">ሁል​ጊ​ዜም አይ​ቀ​ሥ​ፍም፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አይ​ቈ​ጣም።</verse>
				<verse number="10">እንደ ኀጢ​አ​ታ​ችን አላ​ደ​ረ​ገ​ብ​ንም፥ እንደ በደ​ላ​ች​ንም አል​ከ​ፈ​ለ​ንም።</verse>
				<verse number="11">ሰማይ ከም​ድር ከፍ እን​ደ​ሚል፥ እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሕ​ረ​ቱን በሚ​ፈ​ሩት ላይ አጸና።</verse>
				<verse number="12">ምሥ​ራቅ ከም​ዕ​ራብ እን​ደ​ሚ​ርቅ፥ እን​ዲሁ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን ከእኛ አራቀ።</verse>
				<verse number="13">አባት ለል​ጆቹ እን​ደ​ሚ​ራራ፥ እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ፈ​ሩት ይራ​ራ​ላ​ቸ​ዋል፤</verse>
				<verse number="14">ፍጥ​ረ​ታ​ች​ንን እርሱ ያው​ቃ​ልና፤ አቤቱ፥ እኛ አፈር እንደ ሆንን አስብ።</verse>
				<verse number="15">ሰውስ በዘ​መኑ እንደ ሣር ነው፤ እንደ ዱር አበባ እን​ዲሁ ያብ​ባል፤</verse>
				<verse number="16">ነፍሱ ከእ​ርሱ ይወ​ጣ​ልና፥ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አይ​ኖ​ር​ምና ስፍ​ራ​ው​ንም ደግሞ አያ​ው​ቀ​ው​ምና።</verse>
				<verse number="17">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታው ግን ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም በሚ​ፈ​ሩት ላይ፥ ጽድ​ቁም በልጅ ልጆች ላይ ነው፤</verse>
				<verse number="18">ሕጉን በሚ​ጠ​ብቁ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ያደ​ርጉ ዘንድ በሚ​ያ​ስቡ ላይ ነው።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋ​ኑን በሰ​ማይ አዘ​ጋጀ፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ቱም ሁሉን ይገ​ዛል።</verse>
				<verse number="20">ቃሉን የም​ት​ፈ​ጽሙ፥ ብር​ቱ​ዎ​ችና ኀያ​ላን፥ የቃ​ሉ​ንም ድምፅ የም​ት​ሰሙ መላ​እ​ክቱ ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፤</verse>
				<verse number="21">ሠራ​ዊቱ ሁሉ፥ ፈቃ​ዱን የሚ​ያ​ደ​ርጉ አገ​ል​ጋ​ዮቹ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።</verse>
				<verse number="22">ፍጥ​ረ​ቶቹ ሁሉ በግ​ዛቱ ስፍራ ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል። ነፍሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="103">
				<verse number="1">ነፍሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለች፤ አቤቱ አም​ላኬ ሆይ፥ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ፤ መታ​መ​ን​ንና የጌ​ት​ነ​ትን ክብር ለበ​ስህ።</verse>
				<verse number="2">ብር​ሃ​ንን እንደ ልብስ ተጐ​ና​ጸ​ፍህ፤ ሰማ​ይ​ንም እንደ መጋ​ረጃ ዘረ​ጋህ፤</verse>
				<verse number="3">እል​ፍ​ኙን በውኃ የሚ​ሠራ፥ ደመ​ናን መሄ​ጃው የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በነ​ፋስ ክን​ፍም የሚ​ሄድ፥</verse>
				<verse number="4">መላ​እ​ክ​ቱን መን​ፈስ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም የእ​ሳት ነበ​ል​ባል የሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዳ​ት​ና​ወጥ፥ ምድ​ርን መሠ​ረ​ታት፥ አጸ​ና​ትም።</verse>
				<verse number="6">ጥል​ቁም እንደ ልብስ ክዳኗ ነው፥ በተ​ራ​ሮ​ችም ላይ ውኆች ይቆ​ማሉ።</verse>
				<verse number="7">ከተ​ግ​ሣ​ጽ​ህም የተ​ነሣ ይሸ​ሻሉ፥ ከነ​ጐ​ድ​ጓ​ድ​ህም ድምፅ የተ​ነሣ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ፤</verse>
				<verse number="8">ወደ ተራ​ሮች ይወ​ጣሉ፥ ወደ ሜዳ፥ ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ህ​ላ​ቸው ስፍ​ራም ይወ​ር​ዳሉ፥</verse>
				<verse number="9">እን​ዳ​ያ​ል​ፉ​ትም ድን​በር አደ​ረ​ግ​ህ​ላ​ቸው፥ ምድ​ርን ይከ​ድኑ ዘንድ እን​ዳ​ይ​መ​ለሱ።</verse>
				<verse number="10">ምን​ጮ​ችን ወደ ቆላ​ዎች የሚ​ልክ፤ በተ​ራ​ሮች መካ​ከል ውኆች ያል​ፋሉ፤</verse>
				<verse number="11">የዱር አራ​ዊ​ትን ሁሉ ያጠ​ጣሉ፥ የበ​ረሃ አህ​ዮ​ችም ጥማ​ታ​ቸ​ውን ያረ​ካሉ።</verse>
				<verse number="12">የሰ​ማይ ወፎ​ችም በዚያ ይኖ​ራሉ፤ በዋ​ሻው መካ​ከ​ልም ይጮ​ኻሉ።</verse>
				<verse number="13">ተራ​ሮ​ችን ከው​ስ​ጣ​ቸው የሚ​ያ​ጠ​ጣ​ቸው፤ ከሥ​ራህ ፍሬ ምድር ትጠ​ግ​ባ​ለች።</verse>
				<verse number="14">እህ​ልን ከም​ድር ያወጣ ዘንድ፥ ለም​ለ​ሙን ለሰው ልጆች አገ​ል​ግ​ሎት፥ ሣር​ንም ለእ​ን​ስሳ ያበ​ቅ​ላል።</verse>
				<verse number="15">ወይን የሰ​ውን ልብ ደስ ያሰ​ኛል፥ ዘይ​ትም ፊትን ለማ​ብ​ራት ነው። እህ​ልም የሰ​ውን ኀይል ያጠ​ነ​ክ​ራል።</verse>
				<verse number="16">የዱር ዛፎች ሁሉ፥ የተ​ከ​ል​ኸው የሊ​ባ​ኖስ ዝግ​ባም ይጠ​ግ​ባሉ።</verse>
				<verse number="17">በዚ​ያም ዎፎች ይዋ​ለ​ዳሉ፥ የሸ​መላ ቤትም ይጐ​ራ​በ​ታ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="18">ረጃ​ጅም ተራ​ራ​ዎች ለዋ​ሊ​ያ​ዎች፥ ድን​ጋ​ዮ​ችም ለአ​ሽ​ኮ​ኮ​ዎች መሸሻ ናቸው።</verse>
				<verse number="19">ጨረ​ቃን በጊ​ዜው ፈጠ​ርህ፤ ፀሐ​ይም መግ​ቢ​ያ​ውን ያው​ቃል።</verse>
				<verse number="20">ጨለ​ማን ታመ​ጣ​ለህ ሌሊ​ትም ይሆ​ናል፤ በእ​ር​ሱም የዱር አራ​ዊት ሁሉ ይወ​ጡ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="21">የአ​ን​በ​ሶች ግል​ገ​ሎች ያገ​ሣሉ፥ ይነ​ጥ​ቃ​ሉም፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምግ​ባ​ቸ​ውን ይሻሉ።</verse>
				<verse number="22">ፀሐይ ስት​ወጣ ይገ​ባሉ፥ በየ​ዋ​ሻ​ቸ​ውም ይው​ላሉ።</verse>
				<verse number="23">ሰው ወደ ተግ​ባሩ ይሰ​ማ​ራል፥ እስ​ኪ​መ​ሽም ድረስ ሲሠራ ይው​ላል።</verse>
				<verse number="24">አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ታላቅ ነው፤ ሁሉን በጥ​በብ አደ​ረ​ግህ፥ የፈ​ጠ​ር​ኸ​ውም ፍጥ​ረት ምድ​ርን ሞላ።</verse>
				<verse number="25">ይህች ባሕር ታላ​ቅና ሰፊ ናት፤ በዚያ ስፍር ቍጥር የሌ​ለው ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ፥ ታላ​ላ​ቆ​ችና ታና​ና​ሾች እን​ስ​ሶች አሉ።</verse>
				<verse number="26">በዚያ ላይ መር​ከ​ቦች ይሄ​ዳሉ፥ በዚ​ያም ላይ የፈ​ጠ​ር​ኸው ዘንዶ ይጫ​ወ​ታል።</verse>
				<verse number="27">ምግ​ባ​ቸ​ውን በየ​ጊ​ዜው ትሰ​ጣ​ቸው ዘንድ እነ​ዚህ ሁሉ አን​ተን ተስፋ ያደ​ር​ጋሉ።</verse>
				<verse number="28">በሰ​ጠ​ሃ​ቸ​ውም ጊዜ ይሰ​በ​ስ​ባሉ፤ እጅ​ህን ፈት​ተህ ከቸ​ር​ነ​ትህ የተ​ነሣ ሁሉን ታጠ​ግ​ባ​ለህ።</verse>
				<verse number="29">ፊት​ህን ብት​መ​ልስ ግን ይደ​ነ​ግ​ጣሉ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውን ታወ​ጣ​ለህ፥ ይሞ​ታ​ሉም፥ ወደ አፈ​ራ​ቸ​ውም ይመ​ለ​ሳሉ።</verse>
				<verse number="30">መን​ፈ​ስ​ህን ትል​ካ​ለህ፥ ይፈ​ጠ​ራ​ሉም፥ የም​ድ​ር​ንም ፊት ታድ​ሳ​ለህ።</verse>
				<verse number="31">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይሁን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሥ​ራው ደስ ይለ​ዋል።</verse>
				<verse number="32">ምድ​ርን ያያል፥ እን​ድ​ት​ን​ቀ​ጠ​ቀ​ጥም ያደ​ር​ጋል፤ ተራ​ሮ​ችን ይዳ​ስ​ሳል፥ ይጤ​ሳ​ሉም።</verse>
				<verse number="33">በሕ​ይ​ወቴ ሳለሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ፥ ለአ​ም​ላ​ኬም በም​ኖ​ር​በት ዘመን ሁሉ እዘ​ም​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="34">በቃ​ሌም ደስ አሰ​ኘ​ዋ​ለሁ፥ እኔም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይለ​ኛል።</verse>
				<verse number="35">ኃጥ​ኣን ከም​ድር ይጠ​ፋሉ፥ ዐመ​ፀ​ኞ​ችም እን​ግ​ዲህ አይ​ኖ​ሩም። ነፍሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="104">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፥ ስሙ​ንም ጥሩ፥ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ሥራ​ውን ንገሩ።</verse>
				<verse number="2">ተቀ​ኙ​ለት፥ ዘም​ሩ​ለት፥ ተአ​ም​ራ​ቱ​ንም ሁሉ ተና​ገሩ።</verse>
				<verse number="3">በቅ​ዱስ ስሙም ትከ​ብ​ራ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ልግ ልብ ደስ ይበ​ለው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈል​ጉት፥ ትጸ​ና​ላ​ች​ሁም፤ ሁል​ጊዜ ፊቱን ፈልጉ።</verse>
				<verse number="5">የሠ​ራ​ውን ድንቅ ዐስቡ፥ ተአ​ም​ራ​ቱን፥ የአ​ፉ​ንም ፍርድ።</verse>
				<verse number="6">ባሪ​ያ​ዎቹ የአ​ብ​ር​ሃም ዘር፥ ለእ​ር​ሱም የተ​መ​ረ​ጣ​ችሁ የያ​ዕ​ቆብ ልጆች ሆይ፥</verse>
				<verse number="7">እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችን ነው፤ ፍርዱ በም​ድር ሁሉ ነው።</verse>
				<verse number="8">ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ኖር ቃል ኪዳ​ኑን፥ እስከ ሺህ ትው​ልድ ያዘ​ዘ​ውን ቃሉን ዐሰበ።</verse>
				<verse number="9">ለአ​ብ​ር​ሃም የሠ​ራ​ለ​ትን፥ ለይ​ስ​ሐ​ቅም የማ​ለ​ውን፤</verse>
				<verse number="10">ለያ​ዕ​ቆብ ምስ​ክ​ር​ነ​ትን አጸና።</verse>
				<verse number="11">ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ኖር ኪዳ​ኑን፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ለአ​ንተ የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር፥ የር​ስ​ታ​ችሁ ገመድ ትሆ​ና​ችሁ ዘንድ እሰ​ጣ​ለሁ፤”</verse>
				<verse number="12">እነ​ርሱ በቍ​ጥር እጅግ ጥቂ​ቶ​ችና፥ በው​ስጧ ስደ​ተ​ኞች ሲሆኑ።</verse>
				<verse number="13">ከሕ​ዝብ ወደ ሕዝብ፥ ከነ​ገ​ሥ​ታት ወደ ሌላ ሕዝብ አለፉ።</verse>
				<verse number="14">ሰው ግፍ ያደ​ር​ግ​ባ​ቸው ዘንድ አል​ተ​ወም፥ ስለ እነ​ር​ሱም ነገ​ሥ​ታ​ቱን ገሠጸ።</verse>
				<verse number="15">የቀ​ባ​ኋ​ቸ​ውን አት​ዳ​ስሱ፥ በነ​ቢ​ያ​ቴም ላይ ክፉ አታ​ድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="16">በም​ድር ላይ ራብን አመጣ፥ የእ​ህ​ልን ኀይል ሁሉ አጠፋ።</verse>
				<verse number="17">በፊ​ታ​ቸው ሰውን ላከ፤ ዮሴፍ ተሸጠ፥ አገ​ል​ጋ​ይም ሆነ።</verse>
				<verse number="18">እግ​ሮ​ቹም በእ​ግር ብረት ሰለ​ሰሉ፥ ሰው​ነ​ቱም ከብ​ረት አመ​ለ​ጠች።</verse>
				<verse number="19">ቃሉ ሳይ​ደ​ርስ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ፈተ​ነው።</verse>
				<verse number="20">ንጉሥ ላከ፥ ፈታ​ውም፥ የሕ​ዝ​ብም አለቃ አድ​ርጎ ሾመው።</verse>
				<verse number="21">የቤቱ ጌታም አደ​ረ​ገው፥ በገ​ን​ዘቡ ሁሉ ላይ ገዢ አደ​ረ​ገው፥</verse>
				<verse number="22">አለ​ቆ​ቹን ሁሉ እንደ እርሱ ይገ​ሥጽ ዘንድ፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹ​ንም እንደ እርሱ ጥበ​በ​ኞች ያደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ።</verse>
				<verse number="23">እስ​ራ​ኤ​ልም ወደ ግብፅ ገባ፥ ያዕ​ቆ​ብም በካም ምድር ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="24">ሕዝ​ቡ​ንም እጅግ አበ​ዛ​ቸው፥ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ይልቅ አበ​ረ​ታ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">ሕዝ​ቡን ይጠሉ ዘንድ በባ​ሪ​ያ​ዎ​ቹም ላይ ይተ​ነ​ኰሉ ዘንድ ልባ​ቸ​ውን ለወጠ።</verse>
				<verse number="26">ባሪ​ያ​ውን ሙሴን፥ የመ​ረ​ጠ​ው​ንም አሮ​ንን ላከ።</verse>
				<verse number="27">የተ​አ​ም​ራ​ቱን ቃል በላ​ያ​ቸው ድን​ቁ​ንም በካም ምድር አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="28">ጨለ​ማ​ንም ላከ ጨለ​መ​ባ​ቸ​ውም፤ ቃሉ​ንም መራራ አደ​ረ​ጉት።</verse>
				<verse number="29">ውኃ​ቸ​ውን ደም አደ​ረገ፥ ዓሦ​ቻ​ቸ​ው​ንም ገደለ።</verse>
				<verse number="30">ምድ​ራ​ቸው በን​ጉ​ሦ​ቻ​ቸው ቤቶች ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ችን አወ​ጣች።</verse>
				<verse number="31">እርሱ ተና​ገረ፥ የውሻ ዝንብ ትን​ኝም በም​ድ​ራ​ቸው ሁሉ መጡ።</verse>
				<verse number="32">ዝና​ባ​ቸ​ውን በረዶ አደ​ረ​ገው፥ እሳ​ትም በም​ድ​ራ​ቸው ነደደ።</verse>
				<verse number="33">ወይ​ና​ቸ​ው​ንና በለ​ሳ​ቸ​ውን መታ፥ የሀ​ገ​ራ​ቸ​ው​ንም ዛፍ ሁሉ ሰበረ።</verse>
				<verse number="34">ተና​ገረ፥ አን​በ​ጣም፥ ስፍር ቍጥር የሌ​ለ​ውም ኵብ​ኵባ መጣ፥</verse>
				<verse number="35">የም​ድ​ራ​ቸ​ው​ንም ፍሬ ሁሉ በላ የተ​ግ​ባ​ራ​ቸ​ውን ሁሉ መጀ​መ​ሪያ በላ፥</verse>
				<verse number="36">የሀ​ገ​ራ​ቸ​ው​ንም በኵር ሁሉ ገደለ።</verse>
				<verse number="37">ከወ​ር​ቅና ከብር ጋርም አወ​ጣ​ቸው፥ በወ​ገ​ና​ቸ​ውም ውስጥ ደዌ አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="38">ፈር​ተ​ዋ​ቸው ነበ​ርና ግብፅ በመ​ው​ጣ​ታ​ቸው ደስ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="39">ደመ​ናን ጋርዶ ሰወ​ራ​ቸው። እሳ​ት​ንም በሌ​ሊት ያበ​ራ​ላ​ቸው ዘንድ ዘረጋ።</verse>
				<verse number="40">ለመኑ፥ ድር​ጭ​ትም መጣ፥ የሰ​ማ​ይ​ንም እን​ጀራ አጠ​ገ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="41">ዓለ​ቱን ሰነ​ጠቀ ውኃ​ንም አመ​ነጨ፤ በበ​ረሃ ወን​ዞች ውስጥ ሄዱ፤</verse>
				<verse number="42">ለባ​ሪ​ያው ለአ​ብ​ር​ሃም የነ​ገ​ረ​ውን ቅዱስ ቃሉን ዐስ​ቦ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="43">ሕዝ​ቡ​ንም በደ​ስታ የመ​ረ​ጣ​ቸ​ው​ንም በሐ​ሤት አወጣ።</verse>
				<verse number="44">የአ​ሕ​ዛ​ብ​ንም ሀገ​ሮች ሰጣ​ቸው፥ የባ​ዕ​ድን ድካም ወረሱ፥</verse>
				<verse number="45">ሕጉን ይጠ​ብቁ ዘንድ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ይፈ​ልጉ ዘንድ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="105">
				<verse number="1">ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ።</verse>
				<verse number="2">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ኀይል ማን ይና​ገ​ራል? ምስ​ጋ​ና​ው​ንስ ሁሉ ይሰማ ዘንድ ማን ያደ​ር​ጋል?</verse>
				<verse number="3">ፍር​ድን የሚ​ጠ​ብቁ፥ ጽድ​ቅ​ንም ሁል​ጊዜ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ብፁ​ዓን ናቸው።</verse>
				<verse number="4">አቤቱ፥ ሕዝ​ብ​ህን በይ​ቅ​ር​ታህ ዐስ​በን፥ በማ​ዳ​ን​ህም ይቅር በለን፤</verse>
				<verse number="5">የመ​ረ​ጥ​ሃ​ቸ​ውን በጎ​ነት እናይ ዘንድ፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም ደስታ ደስ ይለን ዘንድ፥ ከር​ስ​ት​ህም ጋር እን​ከ​ብር ዘንድ።</verse>
				<verse number="6">ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ጋር ኃጢ​አት ሠራን፥ ዐመ​ፅ​ንም፥ በደ​ል​ንም።</verse>
				<verse number="7">አባ​ቶ​ቻ​ችን በግ​ብፅ ሀገር ሳሉ ተአ​ም​ራ​ት​ህን አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም፥ የም​ሕ​ረ​ት​ህ​ንም ብዛት አላ​ሰ​ቡም፤ በኤ​ር​ትራ ባሕር ባለፉ ጊዜ አስ​መ​ረ​ሩህ።</verse>
				<verse number="8">ኀይ​ሉን ያሳ​ያ​ቸው ዘንድ ስለ ስሙ አዳ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="9">የኤ​ር​ት​ራ​ንም ባሕር ገሠ​ጻት፥ ደረ​ቀ​ችም፤ እንደ ምድረ በዳ በጥ​ልቅ መራ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅ አዳ​ና​ቸው፥ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅ ተቤ​ዣ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ያሳ​ደ​ዱ​አ​ቸ​ው​ንም ውኃ ደፈ​ና​ቸው፥ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ስንኳ አል​ቀ​ረም።</verse>
				<verse number="12">ያን​ጊ​ዜም በቃሉ አመኑ፥ በም​ስ​ጋ​ና​ውም አመ​ሰ​ገ​ኑት።</verse>
				<verse number="13">ፈጥ​ነ​ውም ሥራ​ውን ረሱ፥ በም​ክ​ሩም አል​ጸ​ኑም።</verse>
				<verse number="14">በም​ድረ በዳም ምኞ​ትን ተመኙ፥ በበ​ረ​ሃም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አሳ​ዘ​ኑት።</verse>
				<verse number="15">የለ​መ​ኑ​ት​ንም ሰጣ​ቸው፤ ለነ​ፍ​ሳ​ች​ውም ጥጋ​ብን ላከ።</verse>
				<verse number="16">ሙሴ​ንም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ደ​ሰ​ውን አሮ​ን​ንም በሰ​ፈር አስ​ቈ​ጧ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">ምድር ተከ​ፈ​ተች፥ ዳታ​ን​ንም ዋጠ​ችው፥ የአ​ቤ​ሮ​ን​ንም ወገን ደፈ​ነች፤</verse>
				<verse number="18">በማ​ኅ​በ​ራ​ቸው እሳት ነደ​ደች፥ ነበ​ል​ባ​ልም ኃጥ​ኣ​ንን አቃ​ጠ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">በኮ​ሬ​ብም ጥጃን ሠሩ፥ ቀልጦ ለተ​ሠራ ምስ​ልም ሰገዱ።</verse>
				<verse number="20">ሣር​ንም በሚ​በላ በበሬ ምሳሌ ክብ​ራ​ቸ​ውን ለወጡ።</verse>
				<verse number="21">ያዳ​ና​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረሱ። ታላቅ ነገ​ር​ንም በግ​ብፅ፥</verse>
				<verse number="22">ድን​ቅ​ንም በካም ምድር፥ ግሩም ነገ​ር​ንም በኤ​ር​ትራ ባሕር ያደ​ረ​ገ​ውን።</verse>
				<verse number="23">እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው የቍ​ጣ​ውን መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ልስ ዘንድ የተ​መ​ረ​ጠው ሙሴ በመ​ቅ​ሠ​ፍት ጊዜ በፊቱ ባይ​ቆም ኖሮ፥ ባጠ​ፋ​ቸው ነበር አለ።</verse>
				<verse number="24">የተ​ወ​ደ​ደ​ች​ው​ንም ምድር ናቁ፥ በቃ​ሉም አል​ታ​መ​ኑም፥</verse>
				<verse number="25">በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ውስጥ አን​ጐ​ራ​ጐሩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል አል​ሰ​ሙም።</verse>
				<verse number="26">እጁ​ንም አነ​ሣ​ባ​ቸው። በም​ድረ በዳ ይጥ​ላ​ቸው ዘንድ፥</verse>
				<verse number="27">ዘራ​ቸ​ው​ንም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይጥል ዘንድ፥ በየ​ሀ​ገ​ሩም ይበ​ት​ና​ቸው ዘንድ።</verse>
				<verse number="28">በብ​ዔል ፌጎ​ርም ዐለቁ፥ የሞተ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም በሉ፤</verse>
				<verse number="29">በሥ​ራ​ቸ​ውም አነ​ሣ​ሱት ቸነ​ፈ​ርም በላ​ያ​ቸው በዛ።</verse>
				<verse number="30">ፊን​ሐ​ስም ተነ​ሥቶ አዳ​ና​ቸው፥ ቸነ​ፈ​ሩም ተወ።</verse>
				<verse number="31">ያም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ለልጅ ልጅ ጽድቅ ሆኖ ተቈ​ጠ​ረ​ለት።</verse>
				<verse number="32">በክ​ር​ክር ውኃ ዘን​ድም አስ​ቈ​ጡት፥ ስለ እነ​ር​ሱም ሙሴ ተበ​ሳጨ፤</verse>
				<verse number="33">መን​ፈ​ሱን አስ​መ​ር​ረ​ዋ​ታ​ልና፤ በከ​ን​ፈ​ሮ​ቹም አዘዘ።</verse>
				<verse number="34">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ላ​ቸው አሕ​ዛ​ብን አላ​ጠ​ፉም፤</verse>
				<verse number="35">ከአ​ሕ​ዛብ ጋር ተደ​ባ​ለቁ፥ ሥራ​ቸ​ው​ንም ተማሩ።</verse>
				<verse number="36">ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ተገዙ፥ በደ​ልም ሆነ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="37">ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለአ​ጋ​ን​ንት ሠዉ፤</verse>
				<verse number="38">ንጹሕ ደም​ንም አፈ​ሰሱ፥ የወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና የሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ደም፥ ለከ​ነ​ዓን ጣዖ​ቶች ሠዉ፥ ምድ​ርም በደም ታለ​ለች።</verse>
				<verse number="39">በሥ​ራ​ቸ​ውም ረከ​ሰች፥ በጣ​ዖ​ታ​ቸ​ውም አመ​ነ​ዘሩ።</verse>
				<verse number="40">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ዝቡ ላይ ቍጣን ተቈጣ፥ ርስ​ቱ​ንም ተጸ​የፈ።</verse>
				<verse number="41">በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው። የሚ​ጠ​ሉ​አ​ቸ​ውም ገዙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="42">ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸው፥ ከእ​ጃ​ቸ​ውም በታች ተዋ​ረዱ።</verse>
				<verse number="43">ብዙ ጊዜ አዳ​ና​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን በም​ክ​ራ​ቸው አስ​መ​ረ​ሩት፥ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም መከራ ተቀ​በሉ።</verse>
				<verse number="44">እንደ ተጨ​ነ​ቁም ተመ​ለ​ከ​ታ​ቸው፥ ጸሎ​ታ​ቸ​ው​ንም ሰማ​ቸው፤</verse>
				<verse number="45">ለእ​ነ​ር​ሱም ኪዳ​ኑን አሰበ፥ እንደ ምሕ​ረ​ቱም ብዛት አዘ​ነ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="46">በማ​ረ​ኩ​አ​ቸ​ውም ሁሉ ፊት ይቅ​ር​ታን ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="47">አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ አድ​ነን፤ ቅዱስ ስም​ህን እና​መ​ሰ​ግን ዘንድ፥ በም​ስ​ጋ​ና​ህም እን​መካ ዘንድ፥ ከአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ሰብ​ስ​በን።</verse>
				<verse number="48">ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ይሁን ይሁን ይበል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="106">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዳ​ና​ቸው፥ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ ያዳ​ና​ቸው ይና​ገሩ።</verse>
				<verse number="3">ከም​ሥ​ራ​ቅና ከም​ዕ​ራብ፥ ከመ​ስ​ዕና ከባ​ሕር፥ ከየ​ሀ​ገሩ ሰበ​ሰ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ውኃ በሌ​ለ​በት ምድረ በዳ ተቅ​በ​ዘ​በዙ፤ የሚ​ኖ​ሩ​በ​ት​ንም ከተማ መን​ገድ አላ​ገ​ኙም።</verse>
				<verse number="5">ተራቡ፥ ተጠ​ሙም፥ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውም በላ​ያ​ቸው አለ​ቀች።</verse>
				<verse number="6">በተ​ጨ​ነቁ ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፥ ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው፤</verse>
				<verse number="7">ወደ​ሚ​ኖ​ሩ​በ​ትም ሀገር ይሄዱ ዘንድ የቀና መን​ገ​ድን መራ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሕ​ረት ለሰው ልጆ​ችም ያደ​ረ​ገ​ውን ድን​ቁን ንገሩ፤</verse>
				<verse number="9">የተ​ራ​በ​ችን ነፍስ አጥ​ግ​ቦ​አ​ልና፥ የተ​ራ​ቈ​ተ​ች​ንም ነፍስ በበ​ረ​ከት ሞል​ቶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="10">በጨ​ለ​ማና በሞ​ትም ጥላ የተ​ቀ​መጡ፥ በች​ግር በብ​ረ​ትም የታ​ሰሩ፥</verse>
				<verse number="11">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስለ አማ​ረሩ፥ የል​ዑ​ል​ንም ምክር ስለ አስ​ቈጡ፥</verse>
				<verse number="12">ልባ​ቸው በመ​ከራ ደከመ፤ ታመሙ የሚ​ረ​ዳ​ቸ​ው​ንም አጡ።</verse>
				<verse number="13">በተ​ጨ​ነቁ ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፥ ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="14">ከጨ​ለ​ማና ከሞት ጥላ አወ​ጣ​ቸው፥ እግር ብረ​ታ​ቸ​ው​ንም ሰበረ።</verse>
				<verse number="15">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሕ​ረት ለሰው ልጆ​ችም ያደ​ረ​ገ​ውን ድን​ቁን ንገሩ፤</verse>
				<verse number="16">የና​ሱን ደጆች ሰብ​ሮ​አ​ልና፥ የብ​ረ​ቱ​ንም መወ​ር​ወ​ሪያ ቀጥ​ቅ​ጦ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="17">ከበ​ደ​ላ​ቸው ጎዳና ተቀ​በ​ላ​ቸው፥ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ተሠ​ቃ​ይ​ተ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="18">ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውም መብ​ልን ሁሉ ተጸ​የ​ፈች፥ ወደ ሞትም ደጆች ቀረቡ።</verse>
				<verse number="19">በተ​ጨ​ነ​ቁም ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፥ ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="20">ቃሉን ልኮ ፈወ​ሳ​ቸው፥ ከጥ​ፋ​ታ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="21">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሕ​ረት ለሰው ልጆ​ችም ያደ​ረ​ገ​ውን ድን​ቁን ንገሩ፤</verse>
				<verse number="22">የም​ስ​ጋና መሥ​ዋ​ዕ​ትም ይሠ​ዉ​ለት፥ በደ​ስ​ታም ሥራ​ውን ይን​ገሩ።</verse>
				<verse number="23">በመ​ር​ከ​ቦች ወደ ባሕር የሚ​ወ​ርዱ፥ በብዙ ውኃ ሥራ​ቸ​ውን የሚ​ሠሩ፥</verse>
				<verse number="24">እነ​ርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ፥ በጥ​ል​ቅም ያለ​ች​ውን ድን​ቁን ዐወቁ።</verse>
				<verse number="25">ተና​ገረ፥ ዐውሎ ነፋ​ስም ተነሣ፥ ሞገ​ድም ከፍ ከፍ አለ።</verse>
				<verse number="26">ወደ ሰማይ ይወ​ጣሉ፥ ወደ ጥል​ቅም ይወ​ር​ዳሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውም በመ​ከራ ቀለ​ጠች።</verse>
				<verse number="27">ደነ​ገጡ፥ እንደ ሰካ​ራ​ምም ተን​ገ​ዳ​ገዱ፥ ጥበ​ባ​ቸ​ውም ሁሉ ተዋጠ።</verse>
				<verse number="28">በተ​ጨ​ነቁ ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፥ ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="29">ዐውሎ ነፋ​ሱ​ንም ጸጥ አደ​ረገ፥ ባሕ​ሩም ዝም አለ።</verse>
				<verse number="30">ማዕ​በ​ሉም ዝም አለ፥ አር​ፈ​ዋ​ልና ደስ አላ​ቸው። ወደ ፈለ​ጉ​ትም ወደብ መራ​ቸው።</verse>
				<verse number="31">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሕ​ረ​ቱን ለሰው ልጆ​ችም ድን​ቁን ንገሩ።</verse>
				<verse number="32">በአ​ሕ​ዛብ ጉባኤ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጉ​ታል፥ በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ሸንጎ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።</verse>
				<verse number="33">ወን​ዞ​ችን ምድረ በዳ አደ​ረገ፥ የው​ኃ​ው​ንም ምን​ጮች ደረቅ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤</verse>
				<verse number="34">በተ​ቀ​መ​ጡ​ባት ሰዎች ክፋት ፍሬ​ያ​ማ​ዋን ምድር ጨው አደ​ረ​ጋት።</verse>
				<verse number="35">ምድረ በዳ​ውን ለውኃ መው​ረጃ፥ ደረ​ቁ​ንም ምድር የውኃ ምን​ጮች አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="36">በዚ​ያም ራብ​ተ​ኞ​ችን አስ​ቀ​መጠ፥ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸ​ው​ንም ከተ​ሞች ሠሩ።</verse>
				<verse number="37">እር​ሻ​ዎ​ች​ንም ዘሩ፥ ወይ​ኖ​ች​ንም ተከሉ፥ የእ​ህ​ል​ንም ሰብል አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="38">ባረ​ካ​ቸ​ውም፥ እጅ​ግም በዙ፤ እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አላ​ሳ​ነ​ሰ​ባ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="39">እነ​ርሱ በክፉ መከ​ራና በጭ​ን​ቀት ተሠ​ቃዩ፥ እያ​ነ​ሱም ሄዱ፤</verse>
				<verse number="40">በአ​ለ​ቆ​ችም ላይ ኀሣር ፈሰሰ፥ መን​ገ​ድም በሌ​ለ​በት በም​ድረ በዳ አሳ​ታ​ቸው።</verse>
				<verse number="41">ችግ​ረ​ኛ​ንም በች​ግሩ ረዳው፤ እንደ ሀገር በጎች አደ​ረ​ገው።</verse>
				<verse number="42">ቅኖች ይዩ፥ ደስም ይበ​ላ​ቸው፤ ዐመ​ፃም ሁሉ አፍ​ዋን ትዘ​ጋ​ለች።</verse>
				<verse number="43">ይህን የሚ​ጠ​ብቅ ጥበ​በኛ ማን ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ባይ እንደ ሆነ ያው​ቃል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="107">
				<verse number="1">ልቤ ጽኑዕ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጽኑዕ ነው፤ አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ እዘ​ም​ራ​ለ​ሁም።</verse>
				<verse number="2">ክብ​ሬም ይመ​ለ​ስ​ል​ኛል፥ በበ​ገ​ናና በመ​ሰ​ንቆ እነ​ሣ​ለሁ፤ ማል​ጄም እነ​ሣ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="3">አቤቱ፥ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፤ በወ​ገ​ኖ​ችም መካ​ከል እዘ​ም​ር​ል​ሃ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="4">ምሕ​ረ​ትህ በሰ​ማይ ላይ ታላቅ ናትና፥ እው​ነ​ት​ህም እስከ ደመ​ናት ድረስ ነውና።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ማ​ያት ላይ ከፍ ከፍ አለ፥ ክብ​ሩም በም​ድር ሁሉ ላይ ነው።</verse>
				<verse number="6">ወዳ​ጆ​ችህ ይድኑ ዘንድ በቀ​ኝህ አድን፥ አድ​ም​ጠ​ኝም።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ቅ​ደሱ ተና​ገረ፥ ደስ ይለ​ኛል፥ ሰቂ​ማ​ንም እካ​ፈ​ላ​ለሁ፥ የሸ​ለቆ ቦታ​ዎ​ችን እሰ​ፍ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">ገለ​ዓድ የእኔ ነው፥ ምና​ሴም የእኔ ነው፤ ኤፍ​ሬም የራሴ መጠ​ጊያ ነው። ይሁዳ ንጉሤ ነው፤</verse>
				<verse number="9">ካህን ሞዓ​ብም ተስ​ፋዬ ነው፥ በኤ​ዶ​ም​ያስ ላይም ጫማ​ዬን እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ምም ይገ​ዙ​ል​ኛል።</verse>
				<verse number="10">ወደ ጽኑ ከተማ ማን ይወ​ስ​ደ​ኛል? ማንስ እስከ ኤዶ​ም​ያስ ይመ​ራ​ኛል?</verse>
				<verse number="11">አቤቱ፥ የጣ​ል​ኸን አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ችን ጋር አት​ወ​ጣም።</verse>
				<verse number="12">በመ​ከ​ራ​ችን ረድ​ኤ​ትን ስጠን፤ በሰ​ውም መታ​መን ከንቱ ነው።</verse>
				<verse number="13">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይ​ልን እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ እር​ሱም የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​ንን ያዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="108">
				<verse number="1">አቤቱ፥ ልመ​ና​ዬን ቸል አት​በል፥</verse>
				<verse number="2">የዐ​መ​ፀኛ አፍና የኀ​ጢ​አ​ተኛ አፍ በላዬ ተላ​ቅ​ቀ​ዋ​ልና። በሽ​ን​ገላ አን​ደ​በ​ትም በላዬ ተና​ገሩ፤</verse>
				<verse number="3">በጥል ከበ​ቡኝ፥ በከ​ን​ቱም ተዋ​ጉኝ።</verse>
				<verse number="4">በወ​ደ​ድ​ኋ​ቸው ፋንታ አጣ​ሉኝ፥ እኔ ግን እጸ​ል​ያ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">በመ​ል​ካም ፋንታ ክፉን ከፈ​ሉኝ። በወ​ደ​ድ​ኋ​ቸ​ውም ፋንታ ጠሉኝ።</verse>
				<verse number="6">በላዩ ኀጢ​አ​ተ​ኛን ሹም፤ ሰይ​ጣ​ንም በቀኙ ይቁም።</verse>
				<verse number="7">በሚ​ከ​ራ​ከ​ርም ጊዜ ተረ​ትቶ ይውጣ፤ ጸሎ​ቱም በደል ትሁ​ን​በት።</verse>
				<verse number="8">ዘመ​ኖ​ቹም ጥቂት ይሁኑ፤ ሹመ​ቱ​ንም ሌላ ይው​ሰድ።</verse>
				<verse number="9">ልጆ​ቹም ድሃ አደ​ጎች ይሁኑ፥ ሚስ​ቱም መበ​ለት ትሁን።</verse>
				<verse number="10">ልጆ​ቹም ታው​ከው ይሰ​ደዱ፥ ይለ​ም​ኑም፥ ከቤ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ያባ​ር​ሯ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ባለ ዕዳም ገን​ዘ​ቡን ሁሉ ይበ​ር​ብ​ረው፥ የደ​ከ​መ​በ​ት​ንም ሁሉ ባዕድ ይበ​ዝ​ብ​ዘው።</verse>
				<verse number="12">የሚ​ረ​ዳ​ው​ንም አያ​ግኝ፤ ለድሃ አደግ ልጆ​ቹም የሚ​ራራ አይ​ኑር።</verse>
				<verse number="13">ልጆ​ቹም ይጥፉ፤ በአ​ን​ዲት ትው​ልድ ስሙ ትጥፋ።</verse>
				<verse number="14">የአ​ባቱ ኀጢ​አት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትታ​ሰብ፤ የእ​ና​ቱም ኀጢ​አት አይ​ደ​ም​ሰስ።</verse>
				<verse number="15">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ሁል​ጊዜ ይኑር፤ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ውም ከም​ድር ይጥፋ።</verse>
				<verse number="16">ምጽ​ዋ​ትን ያደ​ርግ ዘንድ አላ​ሰ​በ​ምና ድሃ​ንና ምስ​ኪ​ን​ንም ሰው አሳ​ዷ​ልና ልቡም ሰውን ለመ​ግ​ደል የጨ​ከነ ነውና።</verse>
				<verse number="17">መር​ገ​ምን መረ​ጣት፥ ወደ እር​ሱም ትምጣ፤ በረ​ከ​ት​ንም አል​መ​ረ​ጣ​ትም ከእ​ር​ሱም ትራቅ።</verse>
				<verse number="18">መር​ገ​ምን እንደ ልብስ ለበ​ሳት፥ እንደ ውኃም ወደ አን​ጀቱ፥ እንደ ቅባ​ትም ወደ አጥ​ንቱ ገባች።</verse>
				<verse number="19">እን​ደ​ሚ​ለ​ብ​ሰው ልብስ፥ ሁል​ጊ​ዜም እን​ደ​ሚ​ታ​ጠ​ቀው ትጥቅ ትሁ​ነው።</verse>
				<verse number="20">ይህ ሥራ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በሚ​ያ​ጣ​ሉኝ በነ​ፍ​ሴም ላይ ክፉን በሚ​ና​ገሩ ነው።</verse>
				<verse number="21">አንተ ግን አቤቱ፥ ጌታዬ፥ ስለ ስምህ ምሕ​ረ​ት​ህን በእኔ ላይ አድ​ርግ፤ ምሕ​ረ​ትህ መል​ካም ናትና አድ​ነኝ።</verse>
				<verse number="22">እኔ ድሃና ምስ​ኪን ነኝና፥ ልቤም በው​ስጤ ደነ​ገ​ጠ​ብኝ።</verse>
				<verse number="23">እን​ዳ​ለፈ ጥላ አለ​ቅሁ፥ እንደ አን​በ​ጣም ረገ​ፍሁ።</verse>
				<verse number="24">ጕል​በ​ቶች በጾም ደከሙ፤ ሥጋ​ዬም ቅባት በማ​ጣት ከሳ።</verse>
				<verse number="25">እኔም በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ተሰ​ደ​ብሁ፤ ባዩኝ ጊዜም ራሳ​ቸ​ውን ነቀ​ነቁ።</verse>
				<verse number="26">አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ ርዳኝ፥ ስለ ምሕ​ረ​ት​ህም አድ​ነኝ።</verse>
				<verse number="27">አቤቱ፥ እጅህ ይህች እንደ ሆነች፥ አን​ተም ይህ​ችን እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ ይወቁ።</verse>
				<verse number="28">እነ​ርሱ ይራ​ገ​ማሉ፥ አንተ ግን ባርክ፤ በእኔ ላይ የሚ​ነ​ሡም ይፈሩ፥ ባሪ​ያህ ግን ደስ ይበ​ለው።</verse>
				<verse number="29">የሚ​ያ​ጣ​ሉኝ እፍ​ረ​ት​ንና ውር​ደ​ትን ይል​በሱ፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን እንደ መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይል​በ​ሱ​አት።</verse>
				<verse number="30">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በአፌ እጅግ አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ። በብ​ዙ​ዎ​ችም መካ​ከል አከ​ብ​ረ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="31">ነፍ​ሴን ከሚ​ከ​ብ​ቡ​አት ያድን ዘንድ በእኔ በድ​ሃው ቀኝ ቆሞ​አ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="109">
				<verse number="1">ጌታ ጌታ​ዬን፥ “ጠላ​ቶ​ች​ህን ለእ​ግ​ርህ መረ​ገጫ እስ​ካ​ደ​ር​ግ​ልህ ድረስ በቀኜ ተቀ​መጥ” አለው።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኀ​ይ​ልን በትር ከጽ​ዮን ይል​ክ​ል​ሃል፤ በጠ​ላ​ቶ​ች​ህም መካ​ከል ትገ​ዛ​ለህ።</verse>
				<verse number="3">ቀዳ​ማዊ፦ በኀ​ይል ቀን፥ በቅ​ዱ​ሳን ብር​ሃን ከአ​ንተ ጋር ነበር፥ ከአ​ጥ​ቢያ ኮከብ አስ​ቀ​ድሞ ከሆድ ወለ​ድ​ሁህ።</verse>
				<verse number="4">እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት አንተ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ካህን ነህ ብሎ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማለ አይ​ጸ​ጸ​ት​ምም።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ኝህ ነው፥ ነገ​ሥ​ታ​ትን በቍ​ጣው ቀን ይቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይፈ​ር​ዳል፥ ሬሳ​ዎ​ች​ንም ያበ​ዛል፤ በም​ድር ላይ የብ​ዙ​ዎ​ችን ራሶች ይቀ​ጠ​ቅ​ጣል።</verse>
				<verse number="7">በመ​ን​ገድ ከፈ​ሳሽ ውኃ ጠጡ፤ ስለ​ዚህ ራስ ከፍ ከፍ ይላል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="110">
				<verse number="1">አቤቱ፥ በቅ​ኖች ሸንጎ በጉ​ባ​ኤም በፍ​ጹም ልቤ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ታላቅ ናት፥ በፈ​ቃ​ዱም ሁሉ የተ​ፈ​ለ​ገች ናት።</verse>
				<verse number="3">ሥራው ምስ​ጋ​ናና የጌ​ት​ነት ክብር ነው። ጽድ​ቁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።</verse>
				<verse number="4">ለጌ​ት​ነቱ መታ​ሰ​ቢ​ያን አደ​ረገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓ​ሪና ይቅር ባይ ነው።</verse>
				<verse number="5">ለሚ​ፈ​ሩት ምግ​ብን ሰጣ​ቸው፤ ኪዳ​ኑ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያስ​ባል።</verse>
				<verse number="6">የአ​ሕ​ዛ​ብን ርስት ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ለሕ​ዝቡ የሥ​ራ​ውን ብር​ታት አሳየ።</verse>
				<verse number="7">የእ​ጆቹ ሥራ እው​ነ​ትና ቅን ነው፤ ትእ​ዛ​ዙም ሁሉ የታ​መነ ነው፥</verse>
				<verse number="8">ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም የጸና ነው፥ በእ​ው​ነ​ትና በቅ​ንም የተ​ሠራ ነው።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መድ​ኀ​ኒ​ትን ለሕ​ዝቡ ላከ፥ ኪዳ​ኑ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አዘዘ፤ ስሙ የተ​ቀ​ደ​ሰና የተ​ፈራ ነው።</verse>
				<verse number="10">የጥ​በብ መጀ​መ​ሪያ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ነው፥ ለሚ​ያ​ደ​ር​ጋት ሁሉ ምክር መል​ካም ናት ምስ​ጋ​ና​ውም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="111">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም እጅግ የሚ​ወ​ድድ ሰው ብፁዕ ነው።</verse>
				<verse number="2">ዘሩ በም​ድር ላይ ኀያል ይሆ​ናል፤ የጻ​ድ​ቃን ትው​ል​ዶች ይባ​ረ​ካሉ።</verse>
				<verse number="3">ክብ​ርና ባለ​ጠ​ግ​ነት በቤቱ ነው፥ ጽድ​ቁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።</verse>
				<verse number="4">ለቅ​ኖች ብር​ሃን በጨ​ለማ ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓ​ሪና ይቅር ባይ ነው፤ አም​ላ​ካ​ች​ንም ጻድቅ ነው።</verse>
				<verse number="5">ርኅ​ሩኅ፥ ይቅር ባይና ቸር ሰው ነገ​ሩን በፍ​ርድ ይፈ​ጽ​ማል።</verse>
				<verse number="6">ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ታ​ወ​ክም፤ የጻ​ድቅ መታ​ሰ​ቢያ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።</verse>
				<verse number="7">ከክፉ ነገ​ርም አይ​ፈ​ራም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ታ​መን ልቡ የጸና ነው።</verse>
				<verse number="8">በጠ​ላ​ቶቹ ላይ እስ​ኪ​ያይ ድረስ ልቡ ጽኑዕ ነው፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አይ​ታ​ወ​ክም።</verse>
				<verse number="9">በተነ፥ ለች​ግ​ረ​ኞ​ችም ሰጠ፤ ጽድቁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዓለም ይኖ​ራል፤ ቀን​ዱም በክ​ብር ከፍ ከፍ ይላል።</verse>
				<verse number="10">ኀጢ​አ​ተ​ኛም አይቶ ይቈ​ጣል፥ ጥር​ሱ​ንም ያፋ​ጫል፥ ይቀ​ል​ጣ​ልም፤ የኃ​ጥ​ኣ​ንም ምኞት ትጠ​ፋ​ለች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="112">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪ​ያ​ዎች ሆይ፥ አመ​ስ​ግ​ኑት፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም አመ​ስ​ግኑ።</verse>
				<verse number="2">ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ቡሩክ ይሁን።</verse>
				<verse number="3">ከፀ​ሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግ​ቢ​ያው ድረስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ይመ​ስ​ገን።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ልዑል ነው፥ ክብ​ሩም ከሰ​ማ​ያት በላይ ነው።</verse>
				<verse number="5">እንደ አም​ላ​ካ​ችን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማን ነው? በል​ዕ​ልና የሚ​ኖር።</verse>
				<verse number="6">በሰ​ማ​ይና በም​ድር የተ​ዋ​ረ​ዱ​ትን የሚ​ያይ፤</verse>
				<verse number="7">ድሃ​ውን ከም​ድር የሚ​ያ​ነሣ፥ ምስ​ኪ​ኑ​ንም ከመ​ሬት ከፍ ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ፤</verse>
				<verse number="8">ከአ​ለ​ቆች ጋር ከሕ​ዝ​ቡም አለ​ቆች ጋር ያኖ​ረው ዘንድ</verse>
				<verse number="9">መካ​ኒ​ቱን በቤቱ የሚ​ያ​ኖ​ራት፥ ደስ የተ​ሰ​ኘ​ችም የል​ጆች እናት የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="113">
				<verse number="1">እስ​ራ​ኤል ከግ​ብፅ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም ወገን ከጠ​ላት ሕዝብ በወጡ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="2">ይሁዳ መመ​ስ​ገ​ኛው፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ግዛቱ ሆነ።</verse>
				<verse number="3">ባሕር አየች፥ ሸሸ​ችም፥ ዮር​ዳ​ኖ​ስም ወደ​ኋ​ላው ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="4">ተራ​ሮች እንደ ኮር​ማ​ዎች፥ ኮረ​ብ​ቶ​ችም እንደ በጎች ጠቦ​ቶች ዘለሉ።</verse>
				<verse number="5">አንቺ ባሕር የሸ​ሸሽ፥ አን​ተም ዮር​ዳ​ኖስ ወደ ኋላህ የተ​መ​ለ​ስህ፥ ምን ሁና​ችሁ ነው?</verse>
				<verse number="6">እና​ን​ተም ተራ​ሮች፥ እንደ ኮር​ማ​ዎች፥ ኮረ​ብ​ቶ​ችስ፥ እንደ በጎች ጠቦ​ቶች ለምን ዘለ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="7">ከያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ ፊት፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ምድር ተና​ወ​ጠች፤</verse>
				<verse number="8">ዐለ​ቱን ወደ ውኃ ምንጭ፥ ባል​ጭ​ቱ​ንም ወደ ውኃ ኩሬ የለ​ወጠ።</verse>
				<verse number="9">ለእኛ አይ​ደ​ለም፥ አቤቱ፥ ለእኛ አይ​ደ​ለም፥ ነገር ግን ለስ​ምህ፥ ስለ ምሕ​ረ​ት​ህና ስለ እው​ነ​ት​ህም ምስ​ጋ​ናን እን​ስጥ</verse>
				<verse number="10">አሕ​ዛብ፥ “አም​ላ​ካ​ቸው ወዴት ነው?” አይ​በሉ።</verse>
				<verse number="11">አም​ላ​ካ​ች​ንስ በላይ በሰ​ማይ ነው፤ በሰ​ማ​ይም በም​ድ​ርም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፈ​ቀ​ደ​ውን ሁሉ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="12">የአ​ሕ​ዛብ ጣዖ​ታ​ቶች የወ​ር​ቅና የብር፥ የሰው እጅ ሥራ ናቸው።</verse>
				<verse number="13">አፍ አላ​ቸው ግን አይ​ና​ገ​ሩም፤ ዐይን አላ​ቸው ግን አያ​ዩም፤</verse>
				<verse number="14">ጆሮ አላ​ቸው ግን አይ​ሰ​ሙም፤ አፍ​ንጫ አላ​ቸው ግን አያ​ሸ​ት​ቱም፤</verse>
				<verse number="15">እጅ አላ​ቸው ግን አይ​ዳ​ስ​ሱም፤ እግር አላ​ቸው ግን አይ​ሄ​ዱም፤ በጉ​ሮ​ሮ​አ​ቸ​ውም አይ​ና​ገ​ሩም።</verse>
				<verse number="16">በአ​ፋ​ቸው ትን​ፋሽ የለም፥ የሚ​ሠ​ሩ​አ​ቸ​ውም የሚ​ያ​ም​ኑ​ባ​ቸ​ውም ሁሉ እንደ እነ​ርሱ ይሁኑ።</verse>
				<verse number="17">የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኑ፤ ረዳ​ታ​ቸ​ውና መታ​መ​ኛ​ቸው እርሱ ነው።</verse>
				<verse number="18">የአ​ሮን ወገ​ኖች ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኑ፤ ረዳ​ታ​ቸ​ውና መታ​መ​ኛ​ቸው እርሱ ነው።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈሩ ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኑ፤ ረዳ​ታ​ቸ​ውና መታ​መ​ኛ​ቸው እርሱ ነው።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ አስ​በን ባር​ከ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ወገ​ኖች ባርክ፥ የአ​ሮ​ን​ንም ወገ​ኖች ባርክ።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ሩ​ትን፥ ትን​ን​ሾ​ች​ንና ትል​ል​ቆ​ችን ሁሉ ባር​ካ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላ​ያ​ችሁ፥ በላ​ያ​ች​ሁና በል​ጆ​ቻ​ችሁ ላይ ይጨ​ምር።</verse>
				<verse number="23">እና​ንተ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ለሠራ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ረ​ካ​ችሁ ናችሁ።</verse>
				<verse number="24">የሰ​ማ​ዮች ሰማይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ምድ​ርን ግን ለሰው ልጆች ሰጠ።</verse>
				<verse number="25">አቤቱ፥ ሙታን የሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑህ አይ​ደ​ሉም፥ ወደ ሲኦ​ልም የሚ​ወ​ርዱ ሁሉ፤</verse>
				<verse number="26">እኛ ሕያ​ዋን ግን ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ሰ​ግ​ና​ለን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="114">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የል​መ​ና​ዬን ድምፅ ሰም​ቶ​አ​ልና ወደ​ድ​ሁት።</verse>
				<verse number="2">ጆሮ​ውን ወደ እኔ አዘ​ን​ብ​ሎ​አ​ልና በዘ​መኔ ሁሉ እጠ​ራ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">የሞት ጣር ያዘኝ፥ የሲ​ኦ​ልም ሕማም አገ​ኘኝ፤ ጭን​ቀ​ትና መከራ አገ​ኘኝ።</verse>
				<verse number="4">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ጠራሁ፦ አቤቱ፥ ነፍ​ሴን አድ​ናት።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓ​ሪና ጻድቅ ነው። አም​ላ​ካ​ችን ይቅር ባይ ነው።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕፃ​ና​ትን ይጠ​ብ​ቃል፤ ተቸ​ገ​ርሁ እር​ሱም አዳ​ነኝ።</verse>
				<verse number="7">ነፍሴ ሆይ፥ ወደ ዕረ​ፍ​ትሽ ተመ​ለሺ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳ​ትሽ ነውና፤</verse>
				<verse number="8">ነፍ​ሴን ከሞት፥ ዓይ​ኔ​ንም ከእ​ንባ፥ እግ​ሬ​ንም ከድጥ አድ​ኖ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="9">በሕ​ያ​ዋን ሀገር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ አሰ​ኘው ዘንድ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="115">
				<verse number="1">በተ​ና​ገ​ር​ሁት አመ​ንሁ፤ እኔም እጅግ ታመ​ምሁ።</verse>
				<verse number="2">እኔም ከራሴ ጀምሮ፥ “ሰው ሁሉ ሐሰ​ተኛ ነው” አልሁ።</verse>
				<verse number="3">ስላ​ደ​ረ​ገ​ልኝ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምንን እከ​ፍ​ለ​ዋ​ለሁ?</verse>
				<verse number="4">የሕ​ይ​ወ​ትን ጽዋ እቀ​በ​ላ​ለሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም እጠ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት ስእ​ለ​ቴን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሰ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="6">የጻ​ድቅ ሞት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የከ​በረ ነው።</verse>
				<verse number="7">አቤቱ፥ እኔ ባሪ​ያህ ነኝ፥ ባሪ​ያህ ነኝ፥ የሴት ባሪ​ያ​ህም ልጅ ነኝ፤ ሰን​ሰ​ለ​ቴን ሰበ​ርህ።</verse>
				<verse number="8">ለአ​ንተ የም​ስ​ጋና መሥ​ዋ​ዕ​ትን እሠ​ዋ​ለሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም እጠ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት ስእ​ለ​ቴን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሰ​ጣ​ለሁ፥</verse>
				<verse number="10">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ሽም። ሃሌ ሉያ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="116">
				<verse number="1">አሕ​ዛብ ሁላ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፥ ወገ​ኖ​ችም ሁሉ ያመ​ስ​ግ​ኑት፤</verse>
				<verse number="2">ምሕ​ረቱ በእኛ ላይ ጸን​ታ​ለ​ችና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እው​ነት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ትኖ​ራ​ለች። ሃሌ ሉያ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="117">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፥ ቸር ነውና፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።</verse>
				<verse number="2">ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እንደ ሆነ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ወገን ንገሩ።</verse>
				<verse number="3">ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እንደ ሆነ፥ የአ​ሮን ወገን ንገሩ።</verse>
				<verse number="4">ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እንደ ሆነ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈሩ ሁሉ ንገሩ።</verse>
				<verse number="5">በተ​ጨ​ነ​ቅሁ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠራ​ሁት፤ ሰማኝ፥ አሰ​ፋ​ል​ኝም።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳቴ ነው፥ አል​ፈ​ራም፤ ሰው ምን ያደ​ር​ገ​ኛል?</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳቴ ነው፥ እነሆ፥ በጠ​ላ​ቶቼ ላይ አያ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">በሰው ከመ​ታ​መን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​መን ይሻ​ላል።</verse>
				<verse number="9">በአ​ለ​ቆች ተስፋ ከማ​ድ​ረግ ይልቅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተስፋ ማድ​ረግ ይሻ​ላል።</verse>
				<verse number="10">አሕ​ዛብ ሁሉ ከበ​ቡኝ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም አሸ​ነ​ፍ​ኋ​ቸው፤</verse>
				<verse number="11">መክ​በ​ቡ​ንስ ከበ​ቡኝ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም አሸ​ነ​ፍ​ኋ​ቸው፤</verse>
				<verse number="12">ንብ ማርን እን​ደ​ሚ​ከ​ብብ ከበ​ቡኝ፥ እሳ​ትም በእ​ሾህ ውስጥ እን​ደ​ሚ​ነ​ድድ ነደዱ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም አሸ​ነ​ፍ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">ለመ​ው​ደ​ቅም ተን​ገ​ደ​ገ​ድሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን አነ​ሣኝ።</verse>
				<verse number="14">ኀይ​ሌም ስም አጠ​ራ​ሬም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥ እር​ሱም አዳኜ ሆነኝ።</verse>
				<verse number="15">የደ​ስታ ድምፅ በጻ​ድ​ቃን ማደ​ሪ​ያ​ዎች ነው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀኝ ኀይ​ልን አደ​ረ​ገች።</verse>
				<verse number="16">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀኝ ከፍ ከፍ አደ​ረ​ገ​ችኝ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀኝ ኀይ​ልን አደ​ረ​ገች።</verse>
				<verse number="17">አል​ሞ​ትም በሕ​ይ​ወት እኖ​ራ​ለሁ እንጂ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥራ እና​ገ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="18">መገ​ሠ​ጽስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገሠ​ጸኝ፤ ለሞት ግን አሳ​ልፎ አል​ሰ​ጠ​ኝም።</verse>
				<verse number="19">የጽ​ድ​ቅን ደጆች ክፈ​ቱ​ልኝ፤ ወደ እነ​ርሱ ገብቼ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግን ዘንድ።</verse>
				<verse number="20">ይህች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደጅ ናት፤ ወደ እር​ስዋ ጻድ​ቃን ይገ​ባሉ።</verse>
				<verse number="21">ሰም​ተ​ኸ​ኛ​ልና፥ አዳ​ኜም ሆነ​ኸ​ኛ​ልና አቤቱ፥ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="22">ግን​በ​ኞች የና​ቋት ድን​ጋይ፥ እርሷ የማ​ዕ​ዘን ራስ ሆነች፥</verse>
				<verse number="23">ይህች ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ሆነች፥ ለዐ​ይ​ኖ​ቻ​ች​ንም ድንቅ ናት።</verse>
				<verse number="24">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሠ​ራት ቀን ይህች ናት፤ በእ​ር​ስዋ ደስ ይበ​ለን፥ ሐሤ​ት​ንም እና​ድ​ር​ግ​ባት።</verse>
				<verse number="25">አቤቱ፥ እባ​ክህ፥ አሁን አድን፤ አቤቱ፥ እባ​ክህ፥ አሁን አቅና።</verse>
				<verse number="26">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የሚ​መጣ ቡሩክ ነው፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መረ​ቅ​ና​ችሁ።</verse>
				<verse number="27">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገ​ለ​ጠ​ልን፤ እስከ መሠ​ዊ​ያው ቀን​ዶች ድረስ በሚ​ያ​ስ​ተ​ነ​ት​ኑ​በት በደ​ስታ በዓ​ልን አድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="28">አንተ አም​ላኬ ነህ፥ አመ​ሰ​ግ​ን​ህ​ማ​ለሁ። አንተ አም​ላኬ ነህ፥ ከፍ ከፍም አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ ሰም​ተ​ኸ​ኛ​ልና፥ አዳ​ኜም ሆነ​ኸ​ኛ​ልና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="29">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፥ ቸር ነውና፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="118">
				<verse number="1">በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ንጹ​ሓን የሆኑ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ የሚ​ሄዱ ብፁ​ዓን ናቸው።</verse>
				<verse number="2">ምስ​ክ​ሩን የሚ​ፈ​ልጉ፥ በፍ​ጹም ልብ የሚ​ሹት ብፁ​ዓን ናቸው፤</verse>
				<verse number="3">ዐመ​ፃን የሚ​ያ​ደ​ርጉ ግን በመ​ን​ገዱ አይ​ሄ​ዱም።</verse>
				<verse number="4">ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህን እጅግ ይጠ​ብቁ ዘንድ አንተ አዘ​ዝህ።</verse>
				<verse number="5">ሥር​ዐ​ት​ህን እጠ​ብቅ ዘንድ የሚ​ቀ​ናስ ከሆነ መን​ገዴ ይቅና።</verse>
				<verse number="6">ትእ​ዛ​ዝ​ህን ሁሉ ስመ​ለ​ከት በዚ​ያን ጊዜ አላ​ፍ​ርም።</verse>
				<verse number="7">አቤቱ፥ የጽ​ድ​ቅ​ህን ፍርድ ስማር በቅን ልብ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">ሥር​ዐ​ት​ህ​ንም እጠ​ብ​ቃ​ለሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አት​ጣ​ለኝ።</verse>
				<verse number="9">ጐል​ማሳ መን​ገ​ዱን በምን ያቀ​ናል? ቃል​ህን በመ​ጠ​በቅ ነው።</verse>
				<verse number="10">በፍ​ጹም ልቤ ፈለ​ግ​ሁህ፥ ከት​እ​ዛ​ዝህ አታ​ር​ቀኝ።</verse>
				<verse number="11">አን​ተን እን​ዳ​ል​በ​ድል፥ ቃል​ህን በልቤ ሰወ​ርሁ።</verse>
				<verse number="12">አቤቱ፥ አንተ ቡሩክ ነህ፤ ሥር​ዐ​ት​ህ​ንም አስ​ተ​ም​ረኝ።</verse>
				<verse number="13">የአ​ፍ​ህን ፍርድ ሁሉ በከ​ን​ፈሬ ነገ​ርሁ።</verse>
				<verse number="14">እንደ ብል​ጥ​ግና ሁሉ በም​ስ​ክ​ርህ መን​ገድ ደስ አለኝ።</verse>
				<verse number="15">ትእ​ዛ​ዝ​ህን አሰ​ላ​ሰ​ልሁ፥ መን​ገ​ድ​ህ​ንም እፈ​ል​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">ትእ​ዛ​ዞ​ች​ህን አነ​ብ​ባ​ለሁ፤ ቃል​ህ​ንም አል​ረ​ሳም።</verse>
				<verse number="17">ሕያው እን​ድ​ሆን ቃል​ህ​ንም እን​ድ​ጠ​ብቅ ለባ​ሪ​ያህ ስጠው።</verse>
				<verse number="18">ዓይ​ኖ​ችን ክፈት፥ ከሕ​ግ​ህም ድንቅ ነገ​ርን አያ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">እኔ በም​ድር ስደ​ተኛ ነኝ፤ ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህን ከእኔ አት​ሰ​ውር።</verse>
				<verse number="20">ነፍሴ ሁል​ጊዜ ፍር​ድ​ህን እጅግ ናፈ​ቀች። ትዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችን ገሠ​ጽ​ኻ​ቸው፥</verse>
				<verse number="21">ከት​እ​ዛ​ዛ​ትህ የሚ​ርቁ ርጉ​ማን ናቸው።</verse>
				<verse number="22">ትእ​ዛ​ዝ​ህን ፈል​ጌ​አ​ለ​ሁና ስድ​ብ​ንና ነው​ርን ከእኔ አርቅ።</verse>
				<verse number="23">አለ​ቆች ደግሞ ተቀ​ም​ጠው እኔን አሙኝ፤ ባሪ​ያህ ግን ፍር​ድ​ህን ያሰ​ላ​ስል ነበር።</verse>
				<verse number="24">ምስ​ክ​ር​ህም ትም​ህ​ርቴ ነው፥ ሥር​ዐ​ት​ህም መካሬ ነው።</verse>
				<verse number="25">ሰው​ነቴ ወደ ምድር ተጣ​በ​ቀች፤ እንደ ቃልህ ሕያው አድ​ር​ገኝ።</verse>
				<verse number="26">መን​ገ​ድ​ህ​ንና ምስ​ክ​ር​ህን ነገ​ርሁ፥ ፍር​ድ​ህን አስ​ተ​ም​ረኝ።</verse>
				<verse number="27">የእ​ው​ነ​ት​ህን መን​ገድ እን​ዳ​ስ​ተ​ውል አድ​ር​ገኝ፥ ተአ​ም​ራ​ት​ህ​ንም አሰ​ላ​ስ​ላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="28">ከኀ​ዘን የተ​ነሣ ሰው​ነቴ አን​ቀ​ላ​ፋች፤ በቃ​ልህ አጠ​ን​ክ​ረኝ።</verse>
				<verse number="29">የዐ​መ​ፃን መን​ገድ ከእኔ አርቅ፥ በሕ​ግ​ህም ይቅር በለኝ፤</verse>
				<verse number="30">የእ​ው​ነ​ት​ህን መን​ገድ መረ​ጥሁ፥ ፍር​ድ​ህ​ንም አል​ረ​ሳ​ሁም።</verse>
				<verse number="31">አቤቱ፥ ምስ​ክ​ር​ህን ተከ​ተ​ልሁ፥ አታ​ሳ​ፍ​ረኝ።</verse>
				<verse number="32">ልቤን ባሰ​ፋ​ኸው ጊዜ፥ በት​እ​ዛ​ዝህ መን​ገድ ሮጥሁ።</verse>
				<verse number="33">አቤቱ፥ የእ​ው​ነ​ት​ህን መን​ገድ አስ​ተ​ም​ረኝ፥ ሁል​ጊ​ዜም እፈ​ል​ጋ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="34">እን​ዳ​ስ​ተ​ውል አድ​ር​ገኝ፥ ሕግ​ህ​ንም እፈ​ል​ጋ​ለሁ፤ በፍ​ጹም ልቤም እጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="35">እር​ስ​ዋን ወድ​ጃ​ለ​ሁና የት​እ​ዛ​ዝ​ህን መን​ገድ ምራኝ።</verse>
				<verse number="36">ልቤን ወደ ምስ​ክ​ርህ መልስ፥ ወደ ቅሚ​ያም አይ​ሁን።</verse>
				<verse number="37">ከንቱ ነገ​ርን እን​ዳ​ያዩ ዐይ​ኖ​ቼን መልስ፤ በመ​ን​ገ​ድ​ህም ሕያው አድ​ር​ገኝ።</verse>
				<verse number="38">እን​ዲ​ፈ​ራህ ለባ​ሪ​ያህ በቃ​ልህ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን አጽና።</verse>
				<verse number="39">ፍር​ድህ መል​ካም ነውና የተ​ጠ​ራ​ጠ​ር​ሁ​ትን ስድብ ከእኔ አርቅ።</verse>
				<verse number="40">እነሆ፥ ትእ​ዛ​ዝ​ህን ናፈ​ቅሁ፥ በጽ​ድ​ቅ​ህም ሕያው አድ​ር​ገኝ።</verse>
				<verse number="41">አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ትህ ይም​ጣ​ልኝ፥ አቤቱ፥ ማዳ​ንህ እንደ ቃልህ ነው።</verse>
				<verse number="42">በቃ​ልህ ታም​ኛ​ለ​ሁና ለሚ​ሰ​ድ​ቡኝ በነ​ገር እመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="43">በፍ​ር​ድ​ህም ታም​ኛ​ለ​ሁና የእ​ው​ነ​ትን ቃል ከአፌ ፈጽ​መህ አታ​ርቅ።</verse>
				<verse number="44">ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዓለም ሁል​ጊዜ ሕግ​ህን እጠ​ብ​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="45">ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህ​ንም ፈል​ጌ​አ​ለ​ሁና አስ​ፍቼ እሄ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="46">በነ​ገ​ሥ​ታት ፊት ምስ​ክ​ር​ህን እና​ገ​ራ​ለሁ፥ አላ​ፍ​ር​ምም፤</verse>
				<verse number="47">እጅ​ግም የወ​ደ​ድ​ኋ​ቸ​ውን ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህን እና​ገ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="48">እጆ​ቼ​ንም ወደ ወደ​ድ​ኋ​ቸው ወደ ትእ​ዛ​ዛ​ትህ አነ​ሣ​ለሁ፤ ፍር​ድ​ህ​ንም አሰ​ላ​ስ​ላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="49">ለባ​ሪ​ያህ ተስፋ ያስ​ደ​ረ​ግ​ኸ​ውን ቃል​ህን አስብ።</verse>
				<verse number="50">ቃልህ ሕያው አድ​ር​ጎ​ኛ​ልና። ይህች በመ​ከ​ራዬ ደስ አሰ​ኘ​ችኝ።</verse>
				<verse number="51">ትዕ​ቢ​ተ​ኞች እጅግ ዐመፁ፤ እኔ ግን ከሕ​ግህ አል​ራ​ቅ​ሁም።</verse>
				<verse number="52">ከጥ​ንት የነ​በ​ረ​ውን ፍር​ድ​ህን ዐሰ​ብሁ፥ አቤቱ፥ደስ አለኝ።</verse>
				<verse number="53">ሕግ​ህን ከተዉ ኃጥ​ኣን የተ​ነሣ ኀዘን ያዘኝ።</verse>
				<verse number="54">በእ​ን​ግ​ድ​ነቴ ሀገር ፍር​ድህ መዝ​ሙር ሆነኝ።</verse>
				<verse number="55">አቤቱ፥ በሌ​ሊት ስም​ህን ዐሰ​ብሁ፥ ሕግ​ህ​ንም ጠበ​ቅሁ።</verse>
				<verse number="56">ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህ​ንም ፈል​ጌ​አ​ለ​ሁና ይህች ሆነ​ች​ልኝ።</verse>
				<verse number="57">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክፍሌ ነው፤ ሕግ​ህን ይጠ​ብቁ አልሁ።</verse>
				<verse number="58">አቤቱ በፍ​ጹም ልቤ ወደ ፊትህ ለመ​ንሁ፤ እንደ ቃልህ ይቅር በለኝ።</verse>
				<verse number="59">ስለ መን​ገ​ዶ​ችህ ዐሰ​ብሁ፥ እግ​ሬ​ንም ወደ ምስ​ክ​ርህ መለ​ስሁ።</verse>
				<verse number="60">ትእ​ዛ​ዝ​ህን ለመ​ጠ​በቅ ጨከ​ንሁ፥ አል​ተ​ጠ​ራ​ጠ​ር​ሁ​ምም።</verse>
				<verse number="61">የኃ​ጥ​ኣን ገመ​ዶች ተተ​በ​ተ​ቡ​ብኝ፤ ሕግ​ህን ግን አል​ረ​ሳ​ሁም።</verse>
				<verse number="62">ስለ ጽድ​ቅህ ፍርድ፥ አመ​ሰ​ግ​ንህ ዘንድ በእ​ኩለ ሌሊት እነ​ሣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="63">እኔ ለሚ​ፈ​ሩህ ሁሉ፥ ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንም ለሚ​ጠ​ብቁ ባል​ን​ጀራ ነኝ።</verse>
				<verse number="64">አቤቱ፥ ይቅ​ር​ታህ በም​ድር ሁሉ ሞላች፤ ሥር​ዐ​ት​ህ​ንም አስ​ተ​ም​ረኝ።</verse>
				<verse number="65">አቤቱ፥ እንደ ቃልህ ለባ​ሪ​ያህ መል​ካም አደ​ረ​ግህ።</verse>
				<verse number="66">በት​እ​ዛ​ዛ​ትህ ታም​ኛ​ለ​ሁና መል​ካም ምክ​ር​ንና ጥበ​ብን አስ​ተ​ም​ረኝ።</verse>
				<verse number="67">እኔ ሳል​ጨ​ነቅ ተጸ​ጸ​ትሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ቃል​ህን ጠበ​ቅሁ።</verse>
				<verse number="68">አቤቱ፥ አንተ ቸር ነህ፥ በቸ​ር​ነ​ት​ህም ፍር​ድ​ህን አስ​ተ​ም​ረኝ።</verse>
				<verse number="69">የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞች ዐመፃ በላዬ በዛ፤ እኔ ግን በፍ​ጹም ልቤ ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህን እፈ​ል​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="70">ልባ​ቸው እንደ ወተት ረጋ፤ እኔ ግን ሕግ​ህን አነ​ብ​ባ​ለሁ</verse>
				<verse number="71">ፍር​ድ​ህን አውቅ ዘንድ ያስ​ጨ​ነ​ቅ​ኸኝ መል​ካም ሆነ​ልኝ።</verse>
				<verse number="72">ከአ​እ​ላ​ፋት ወር​ቅና ብር ይልቅ። የአ​ፍህ ሕግ ይሻ​ለ​ኛል።</verse>
				<verse number="73">እጆ​ችህ ሠሩኝ፥ አበ​ጃ​ጁ​ኝም፤ እን​ዳ​ስ​ተ​ውል አድ​ር​ገኝ፥ ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህ​ንም እማ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="74">በቃ​ልህ ታም​ኛ​ለ​ሁና የሚ​ፈ​ሩህ እኔን አይ​ተው ደስ ይላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="75">አቤቱ፥ ፍር​ድህ ጽድቅ እንደ ሆነች፥ በሚ​ገ​ባም እን​ዳ​ስ​ጨ​ነ​ቅ​ኸኝ ዐወ​ቅሁ።</verse>
				<verse number="76">ምሕ​ረ​ትህ ለደ​ስ​ታዬ ይሁ​ነኝ፥ እንደ ቃል​ህም ለባ​ሪ​ያህ ይሁ​ነው።</verse>
				<verse number="77">ሕግህ ትም​ህ​ርቴ ነውና ቸር​ነ​ትህ ይም​ጣ​ልኝ፥ በሕ​ይ​ወ​ትም ልኑር።</verse>
				<verse number="78">ትዕ​ቢ​ተ​ኞች ዐመ​ፃን መክ​ረ​ው​ብ​ኛ​ልና ይፈሩ፤ እኔ ግን ትእ​ዛ​ዝ​ህን አሰ​ላ​ስ​ላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="79">የሚ​ፈ​ሩ​ህና ምስ​ክ​ሮ​ች​ህን የሚ​ያ​ውቁ ወደ እኔ ይመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="80">እን​ዳ​ላ​ፍር ልቤ በፍ​ር​ድህ ንጹሕ ይሁን።</verse>
				<verse number="81">ነፍሴ ወደ ማዳ​ንህ አለ​ፈች፤ በቃ​ል​ህም ታመ​ንሁ።</verse>
				<verse number="82">መቼ ታጽ​ና​ና​ኛ​ለህ እያ​ልሁ ዐይ​ኖቼ ትድ​ግ​ና​ህን በመ​ጠ​በቅ ፈዘዙ።</verse>
				<verse number="83">በው​ርጭ እን​ዳለ ረዋት ሆኛ​ለ​ሁና፤ ፍር​ድ​ህን ግን አል​ረ​ሳ​ሁም።</verse>
				<verse number="84">የባ​ሪ​ያህ ዘመ​ኖች ምን ያህል ናቸው? በሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​ኝስ ላይ መቼ ትፈ​ር​ድ​ል​ኛ​ለህ?</verse>
				<verse number="85">ኃጥ​ኣን ዋዛ-ፈዛ​ዛን ነገ​ሩኝ፥ አቤቱ፥ እንደ ሕግህ ግን አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="86">ትእ​ዛ​ዝ​ትህ ሁሉ እው​ነት ናቸው፤ በዐ​መፃ አሳ​ድ​ደ​ው​ኛል፤ ርዳኝ።</verse>
				<verse number="87">ከም​ድር ሊያ​ጠ​ፉኝ ጥቂት ቀር​ቶ​አ​ቸው ነበር፤ እኔ ግን ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህን አል​ተ​ው​ሁም።</verse>
				<verse number="88">እንደ ምሕ​ረ​ትህ ሕያው አድ​ር​ገኝ፤ የአ​ፍ​ህ​ንም ምስ​ክር እጠ​ብ​ቃ​ለሁ። ላሜድ።</verse>
				<verse number="89">አቤቱ፥ ቃልህ በሰ​ማይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።</verse>
				<verse number="90">እው​ነ​ትህ ለልጅ ልጅ ናት፤ ምድ​ርን መሠ​ረ​ት​ሃት፥ እር​ስ​ዋም ትኖ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="91">ሁሉን ገዝ​ተ​ሃ​ልና ቀኑ በት​እ​ዛ​ዝህ ይኖ​ራል።</verse>
				<verse number="92">ሕግህ ትም​ህ​ርቴ ባይ​ሆን፥ ቀድሞ በጕ​ስ​ቍ​ል​ናዬ በጠ​ፋሁ ነበር።</verse>
				<verse number="93">በእ​ርሱ ሕያው አድ​ር​ገ​ኸ​ኛ​ልና ፍር​ድ​ህን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አል​ረ​ሳም።</verse>
				<verse number="94">እኔ የአ​ንተ ነኝ፥ ፍር​ድ​ህን ፈል​ጌ​አ​ለ​ሁና አድ​ነኝ።</verse>
				<verse number="95">ኃጥ​ኣን ያጠ​ፉኝ ዘንድ ጠበ​ቁኝ፤ ምስ​ክ​ር​ህን አስ​ተ​ው​ያ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="96">የሥ​ራ​ውን ሁሉ ፍጻሜ አየሁ፤ ትእ​ዛ​ዝህ ግን እጅግ ሰፊ ነው።</verse>
				<verse number="97">አቤቱ፥ ሕግ​ህን እን​ደ​ምን እጅግ ወደ​ድሁ! ቀኑን ሁሉ እርሱ ትም​ህ​ርቴ ነው።</verse>
				<verse number="98">ለዘ​ለ​ዓ​ለም ለእኔ ነውና ትእ​ዛ​ዝህ ከጠ​ላ​ቶቼ ይልቅ አስ​ተ​ዋይ አደ​ረ​ገኝ።</verse>
				<verse number="99">ትእ​ዛ​ዝህ ትም​ህ​ርቴ ነውና ካስ​ተ​ማ​ሩኝ ሁሉ ይልቅ አስ​ተ​ዋ​ልሁ።</verse>
				<verse number="100">ትእ​ዛ​ዝ​ህን ፈል​ጌ​አ​ለ​ሁና ከሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች ይልቅ አስ​ተ​ዋ​ልሁ።</verse>
				<verse number="101">ቃል​ህን እጠ​ብቅ ዘንድ ከክፉ መን​ገድ ሁሉ እግ​ሬን ከለ​ከ​ልሁ።</verse>
				<verse number="102">አንተ አስ​ተ​ም​ረ​ኸ​ኛ​ልና ከፍ​ር​ድህ አል​ራ​ቅ​ሁም።</verse>
				<verse number="103">ቃልህ ለጕ​ሮ​ሮዬ ጣፋጭ ነው፤ ከማ​ርና ከወ​ለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈ​ጠኝ።</verse>
				<verse number="104">ከት​እ​ዛ​ዝህ የተ​ነሣ አስ​ተ​ዋ​ልሁ፤ ስለ​ዚህ የዐ​መ​ፃን መን​ገድ ጠላሁ።</verse>
				<verse number="105">ሕግህ ለእ​ግሬ መብ​ራት፥ ለመ​ን​ገ​ዴም ብር​ሃን ነው።</verse>
				<verse number="106">የጽ​ድ​ቅ​ህን ፍርድ እጠ​ብቅ ዘንድ ማልሁ፥ አጸ​ና​ሁም።</verse>
				<verse number="107">እጅግ መከራ ተቀ​በ​ልሁ፥ አቤቱ፥ እንደ ቃልህ ሕያው አድ​ር​ገኝ።</verse>
				<verse number="108">አቤቱ፥ ከአፌ የሚ​ወ​ጣ​ውን ቃል ውደድ፥ ፍር​ድ​ህ​ንም አስ​ተ​ም​ረኝ።</verse>
				<verse number="109">ነፍሴ ሁል​ጊዜ በእ​ጅህ ውስጥ ናት፤ ሕግ​ህን ግን አል​ረ​ሳ​ሁም።</verse>
				<verse number="110">ኃጥ​ኣን ወጥ​መ​ድን ዘረ​ጉ​ብኝ፤ ከት​እ​ዛ​ዝህ ግን አል​ሳ​ት​ሁም።</verse>
				<verse number="111">የልቤ ደስታ ነውና ምስ​ክ​ር​ህን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ወረ​ስሁ።</verse>
				<verse number="112">ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያለ ነቀፋ ትእ​ዛ​ዝ​ህን አደ​ርግ ዘንድ ልቤን መለ​ስሁ።</verse>
				<verse number="113">ዐመ​ፀ​ኞ​ችን ጠላሁ፥ ሕግ​ህን ግን ወደ​ድሁ።</verse>
				<verse number="114">አንተ ረዳ​ቴና መጠ​ጊ​ያዬ ነህ፥ በቃ​ል​ህም ተማ​መ​ንሁ።</verse>
				<verse number="115">እና​ንተ ዐመ​ፀ​ኞች፥ ከእኔ ራቁ፥ የአ​ም​ላ​ኬ​ንም ትእ​ዛዝ ልፈ​ልግ።</verse>
				<verse number="116">እንደ ቃልህ ተቀ​በ​ለኝ፥ ሕያ​ውም እሆ​ና​ለሁ፤ ከተ​ስ​ፋ​ዬም አታ​ሳ​ፍ​ረኝ።</verse>
				<verse number="117">ርዳ​ኝም፥ አድ​ነ​ኝም፥ ሁል​ጊ​ዜም ፍር​ድ​ህን አነ​ብ​ባ​ለሁ።</verse>
				<verse number="118">ምኞ​ታ​ቸው ዐመፃ ነውና ከሥ​ር​ዐ​ትህ የሚ​ር​ቁ​ትን ሁሉ አጐ​ሳ​ቈ​ል​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="119">የም​ድር ኃጥ​ኣን ሁሉ ወን​ጀ​ለ​ኞች ናቸው፤ ስለ​ዚህ ምስ​ክ​ር​ህን ወደ​ድሁ።</verse>
				<verse number="120">መፈ​ራ​ት​ህን በሥ​ጋዬ ውስጥ አስ​ማማ፤ ከፍ​ር​ድህ የተ​ነሣ ፈር​ቻ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="121">ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን ሠራህ፤ ለሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ አሳ​ል​ፈህ አት​ስ​ጠኝ።</verse>
				<verse number="122">ባሪ​ያ​ህን በመ​ል​ካም ጠብ​ቀው፤ ትዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችም አይ​ጋ​ፉኝ።</verse>
				<verse number="123">ዐይ​ኖቼ ለማ​ዳ​ንህ፥ ለጽ​ድ​ቅ​ህም ቃል ፈዘዙ።</verse>
				<verse number="124">ለባ​ሪ​ያህ እንደ ምሕ​ረ​ትህ አድ​ርግ፥ ፍር​ድ​ህ​ንም አስ​ተ​ም​ረኝ።</verse>
				<verse number="125">እኔ ባሪ​ያህ ነኝ፤ እን​ዳ​ስ​ተ​ውል አድ​ር​ገኝ፥ ምስ​ክ​ር​ህ​ንም አው​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="126">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሥራ ጊዜ አለው፥ ሕግ​ህ​ንም ሻሩት።</verse>
				<verse number="127">ስለ​ዚህ ከወ​ር​ቅና ከዕ​ንቍ ይልቅ ትእ​ዛ​ዝ​ህን ወደ​ድሁ።</verse>
				<verse number="128">ስለ​ዚህ ወደ ትእ​ዛ​ዝህ ሁሉ አቀ​ናሁ፥ የዐ​መ​ፃ​ንም መን​ገድ ሁሉ ጠላሁ።</verse>
				<verse number="129">ምስ​ክ​ርህ ድንቅ ነው፤ ስለ​ዚህ ነፍሴ ፈለ​ገ​ችው።</verse>
				<verse number="130">የቃ​ልህ ነገር ያበ​ራል፥ ሕፃ​ና​ት​ንም አስ​ተ​ዋ​ዮች ያደ​ር​ጋል።</verse>
				<verse number="131">አፌን ከፈ​ትሁ፥ ልቡ​ና​ዬ​ንም አሰ​ፋሁ፤ ትእ​ዛ​ዝ​ህን ወድ​ጃ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="132">ስም​ህን ለሚ​ወ​ድዱ እን​ደ​ም​ታ​ደ​ር​ገው ፍርድ፥ ወደ እኔ ተመ​ል​ከት፥ ይቅ​ርም በለኝ።</verse>
				<verse number="133">መን​ገ​ዴ​ንና አካ​ሄ​ዴን እንደ ቃልህ አቅና፤ ኀጢ​አ​ትም ሁሉ ድል አይ​ን​ሳኝ።</verse>
				<verse number="134">ከሰው ቅሚያ አድ​ነኝ፤ ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንም እጠ​ብ​ቃ​ለሁ ።</verse>
				<verse number="135">በባ​ሪ​ያህ ላይ ፊት​ህን አብራ፥ ፍር​ድ​ህ​ንም አስ​ተ​ም​ረኝ።</verse>
				<verse number="136">ሕግ​ህን አል​ጠ​በ​ቅ​ሁ​ምና የውኃ ፈሳሽ ከዐ​ይ​ኖች ፈሰሰ።</verse>
				<verse number="137">አቤቱ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፥ ፍር​ድ​ህም ቅን ነው።</verse>
				<verse number="138">ምስ​ክ​ር​ህን በጽ​ድቅ አዘ​ዝህ፥ እጅ​ግም ቅን ነው።</verse>
				<verse number="139">ጠላ​ቶቼ ትእ​ዛ​ዝ​ህን ረስ​ተ​ዋ​ልና የቤ​ትህ ቅን​ዓት አቀ​ለ​ጠኝ።</verse>
				<verse number="140">ቃልህ እጅግ የጋለ ነው፥ ባሪ​ያህ ግን ወደ​ደው።</verse>
				<verse number="141">እኔ ታና​ሽና የተ​ና​ቅሁ ነኝ፥ ሕግ​ህን ግን አል​ረ​ሳ​ሁም።</verse>
				<verse number="142">ጽድ​ቅ​ህም የዘ​ለ​ዓ​ለም ጽድቅ ነው፥ ቃል​ህም የታ​መነ ነው።</verse>
				<verse number="143">መከ​ራና ችግር አገ​ኙኝ፤ ትእ​ዛ​ዝህ ግን ትም​ህ​ርቴ ነው።</verse>
				<verse number="144">ምስ​ክ​ርህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እው​ነት ነው፤ እን​ዳ​ስ​ተ​ውል አድ​ር​ገኝ፥ በሕ​ይ​ወ​ትም አኑ​ረኝ።</verse>
				<verse number="145">በፍ​ጹም ልቤ ጮኽሁ፥ አቤቱ ስማኝ፤ ፍር​ድ​ህ​ንም ፈለ​ግሁ።</verse>
				<verse number="146">ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ስማኝ አድ​ነ​ኝም። ምስ​ክ​ር​ህ​ንም ልጠ​ብቅ።</verse>
				<verse number="147">ወደ ተራ​ሮች ደረ​ስሁ፥ ጮኽ​ሁም። ቃል​ህን ተስፋ አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="148">ዐይ​ኖቼ ለመ​ማ​ለድ ደረሱ፥ ቃል​ህን እና​ገር ዘንድ።</verse>
				<verse number="149">አቤቱ፥ እንደ ይቅ​ር​ታህ ቃሌን ስማ፤ እንደ ፍር​ድህ ሕያው አድ​ር​ገኝ።</verse>
				<verse number="150">በዐ​መፃ የከ​በ​ቡኝ ቀረቡ፥ ከሕ​ግህ ግን ራቁ።</verse>
				<verse number="151">አቤቱ አንተ ቅርብ ነህ፥ መን​ገ​ዶ​ች​ህም ሁሉ የቀኑ ናቸው።</verse>
				<verse number="152">ለዘ​ለ​ዓ​ለም እንደ መሠ​ረ​ት​ሃ​ቸው ከቀ​ድሞ ጀምሮ ምስ​ክ​ሮ​ች​ህን ዐወ​ቅሁ።</verse>
				<verse number="153">ሕግ​ህን አል​ረ​ሳ​ሁ​ምና ችግ​ሬን ተመ​ል​ከት፥ አድ​ነ​ኝም።</verse>
				<verse number="154">ፍር​ዴን ፍረድ አድ​ነ​ኝም፤ ስለ ቃል​ህም ሕያው አድ​ር​ገኝ።</verse>
				<verse number="155">ሕይ​ወት ከኃ​ጥ​ኣን የራቀ ነው፥ ፍር​ድ​ህን አል​ፈ​ለ​ጉ​ምና።</verse>
				<verse number="156">አቤቱ፥ ይቅ​ር​ታህ እጅግ የበዛ ነው፤ እንደ ፍር​ድ​ህም ሕያው አድ​ር​ገኝ።</verse>
				<verse number="157">የከ​በ​ቡ​ኝና ያስ​ጨ​ነ​ቁኝ ብዙ​ዎች ናቸው፤ ከም​ስ​ክ​ርህ ግን ፈቀቅ አላ​ል​ሁም።</verse>
				<verse number="158">ቃል​ህን አል​ጠ​በ​ቁ​ምና ሰነ​ፎ​ችን አይቼ አዘ​ንሁ።</verse>
				<verse number="159">ትእ​ዛ​ዝ​ህን እንደ ወደ​ድሁ ተመ​ል​ከት፤ አቤቱ፥ በይ​ቅ​ር​ታህ ሕያው አድ​ር​ገኝ።</verse>
				<verse number="160">የቃ​ልህ መጀ​መ​ሪያ እው​ነት ነው፥ ፍር​ድ​ህም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እው​ነት ነው።</verse>
				<verse number="161">አለ​ቆች በከ​ንቱ አሳ​ደ​ዱኝ፤ ከቃ​ልህ የተ​ነሣ ግን ልቤ ደን​ገ​ጠ​ብኝ።</verse>
				<verse number="162">ብዙ ምርኮ እን​ዳ​ገኘ በቃ​ልህ ደስ አለኝ።</verse>
				<verse number="163">ዐመ​ፃን ጠላሁ ተጸ​የ​ፍ​ሁም፤ ሕግ​ህን ግን ወደ​ድሁ።</verse>
				<verse number="164">ስለ እው​ነት ፍር​ድህ ሰባት ጊዜ በቀን አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="165">ስም​ህን ለሚ​ወ​ድዱ ብዙ ሰላም ነው፥ ዕን​ቅ​ፋት የለ​ባ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="166">አቤቱ፥ ማዳ​ን​ህን ተስፋ አደ​ረ​ግሁ፥ ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህ​ንም ጠበ​ቅሁ።</verse>
				<verse number="167">ነፍሴ ምስ​ክ​ር​ህን ጠበ​ቀች፥ እጅ​ግም ወደ​ደ​ችው።</verse>
				<verse number="168">አቤቱ፥ መን​ገ​ዶ​ችህ ሁሉ በፊ​ትህ ናቸ​ውና። ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንና ምስ​ክ​ር​ህን ጠበ​ቅሁ።</verse>
				<verse number="169">አቤቱ፥ ልመ​ናዬ ወደ አንተ ትቅ​ረብ፤ እንደ ቃል​ህም አስ​ተ​ዋይ አድ​ር​ገኝ።</verse>
				<verse number="170">አቤቱ፥ ምል​ጃዬ ወደ ፊትህ ትድ​ረስ፤ እንደ ቃል​ህም አድ​ነኝ።</verse>
				<verse number="171">ፍር​ድ​ህን አስ​ተ​ም​ረ​ኸ​ኛ​ልና ከን​ፈ​ሮች ምስ​ጋ​ና​ህን ይና​ገ​ራሉ።</verse>
				<verse number="172">ትእ​ዛ​ዛ​ትህ ሁሉ ጽድቅ ናቸ​ውና፥ አን​ደ​በቴ ቃል​ህን ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="173">ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህን ወድ​ጃ​ለ​ሁና ቀኝህ የሚ​ያ​ድ​ነኝ ይሁን።</verse>
				<verse number="174">አቤቱ፥ ማዳ​ን​ህን ናፈ​ቅሁ፤ ሕግ​ህም ትም​ህ​ርቴ ነው።</verse>
				<verse number="175">ነፍሴ ትኑ​ር​ልኝ ላመ​ስ​ግ​ን​ህም፥ ፍር​ድ​ህም ይር​ዳኝ።</verse>
				<verse number="176">እንደ ጠፋ በግ ተዘ​ነ​ጋሁ፤ ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህን አል​ረ​ሳ​ሁ​ምና ባሪ​ያ​ህን ፈል​ገው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="119">
				<verse number="1">አቤቱ፥ በተ​ጨ​ነ​ቅሁ ጊዜ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ሰማ​ኸ​ኝም።</verse>
				<verse number="2">ከዐ​መ​ፀኛ ከን​ፈር፥ ከሸ​ን​ጋ​ይም አን​ደ​በት፥ አቤቱ፥ ነፍ​ሴን አድ​ናት።</verse>
				<verse number="3">ስለ ሽን​ገላ አን​ደ​በት ምንን ይሰ​ጡ​ሃል? ምንስ ይጨ​ም​ሩ​ል​ሃል?</verse>
				<verse number="4">እንደ በረሃ ቋያ የኀ​ያል ፍላ​ጾች የተ​ሳሉ ናቸው።</verse>
				<verse number="5">መኖ​ሪ​ያዬ የራቀ እኔ ወዮ​ልኝ፤ በዘ​ላን ድን​ኳ​ኖች አደ​ርሁ።</verse>
				<verse number="6">ሰላ​ምን ከሚ​ጠሉ ጋር ነፍሴ ብዙ ጊዜ ታገ​ሠች።</verse>
				<verse number="7">እኔ ሰላ​ማዊ ስሆን በተ​ና​ገ​ር​ኋ​ቸው ጊዜ በከ​ንቱ ይጠ​ሉ​ኛል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="120">
				<verse number="1">ዐይ​ኖቼን ወደ ተራ​ሮች አነ​ሣሁ፤ ረድ​ኤቴ ከወ​ዴት ይምጣ?</verse>
				<verse number="2">ረድ​ኤቴ ሰማ​ይና ምድ​ርን ከፈ​ጠረ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="3">ለእ​ግ​ሮ​ችህ ሁከ​ትን አይ​ሰ​ጣ​ቸ​ውም፤ የሚ​ጠ​ብ​ቅ​ህም አይ​ተ​ኛም።</verse>
				<verse number="4">እነሆ፥ እስ​ራ​ኤ​ልን የሚ​ጠ​ብቅ አይ​ተ​ኛም፥ አያ​ን​ቀ​ላ​ፋ​ምም።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ብ​ቅህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀኝ እጁ ይጋ​ር​ድህ።</verse>
				<verse number="6">ፀሐይ በቀን አያ​ቃ​ጥ​ልህ፤ ጨረ​ቃም በሌ​ሊት።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከክፉ ሁሉ ይጠ​ብ​ቅህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነፍ​ስ​ህ​ንም ይጠ​ብ​ቃት።</verse>
				<verse number="8">ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መው​ጣ​ት​ህ​ንና መግ​ባ​ት​ህን ይጠ​ብቅ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="121">
				<verse number="1">ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እን​ሂድ ስላ​ሉኝ ደስ አለኝ።</verse>
				<verse number="2">ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ እግ​ሮ​ቻ​ችን በአ​ደ​ባ​ባ​ዮ​ችሽ ቆሙ።</verse>
				<verse number="3">ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምስ እንደ ከተማ የታ​ነ​ጸች ናት።</verse>
				<verse number="4">እንደ እርሷ ያሉት በአ​ን​ድ​ነት ከእ​ርሷ ጋር ናቸው። አቤቱ፥ ለስ​ምህ ይገዙ ዘንድ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ምስ​ክር የሚ​ሆኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወገ​ኖች አሕ​ዛብ ወደ​ዚያ ይወ​ጣ​ሉና።</verse>
				<verse number="5">ለመ​ፍ​ረድ ዙፋ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን በዚያ አስ​ቀ​ም​ጠ​ዋ​ልና፥ የዳ​ዊት ቤት ዙፋ​ኖች።</verse>
				<verse number="6">የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ደኅ​ን​ነ​ት​ዋን፥ ተነ​ጋ​ገሩ። ስም​ህን ለሚ​ወ​ድዱ ደስ​ታ​ቸው ነው።</verse>
				<verse number="7">በኀ​ይ​ልህ ሰላም ይሁን፥ በክ​ብ​ርህ ቦታ ደስታ አለ።</verse>
				<verse number="8">ስለ ወን​ድ​ሞቼና ስለ ባል​ን​ጀ​ሮቼ ስለ አን​ቺም፥ ሰላ​ምን ይና​ገ​ራሉ።</verse>
				<verse number="9">ስለ አም​ላኬ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ደኅ​ን​ነ​ት​ሽን ፈለ​ግሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="122">
				<verse number="1">በሰ​ማይ የም​ት​ኖር ሆይ፥ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ንን ወደ አንተ አነ​ሣን።</verse>
				<verse number="2">እነሆ፥ የባ​ሪ​ያ​ዎች ዐይ​ኖች ወደ ጌቶ​ቻ​ቸው እጅ እንደ ሆኑ፥ የባ​ሪ​ያ​ዪ​ቱም ዐይን ወደ እመ​ቤቷ እጅ እንደ ሆነ፥ እን​ዲ​ሁም ይቅር እስ​ከ​ሚ​ለን ድረስ ዐይ​ኖ​ቻ​ችን ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናቸው።</verse>
				<verse number="3">ማረን፥ አቤቱ፥ ማረን፤ ስድ​ብን እጅግ ጠግ​በ​ና​ልና፤</verse>
				<verse number="4">የባ​ለ​ጠ​ጎ​ችን ስድ​ብና የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችን ውር​ደት ነፍ​ሳ​ችን እጅግ ጠገ​በች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="123">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር ባይ​ሆን እስ​ራ​ኤል እን​ዲህ ይበል፦</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር ባይ​ሆን ሰዎች በእኛ ላይ በተ​ነሡ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="3">የመ​ዓት ቍጣ​ቸ​ውን በላ​ያ​ችን ባነሡ ጊዜ፥ ሕያ​ዋን ሳለን በዋ​ጡን ነበር ብዬ በተ​ጠ​ራ​ጠ​ርሁ ነበር፥</verse>
				<verse number="4">በውኃ ባሰ​ጠ​ሙን ነበር ብዬ በተ​ጠ​ራ​ጠ​ርሁ ነበር፤</verse>
				<verse number="5">ነፍ​ሳ​ች​ንም ከጐ​ርፍ አመ​ለ​ጠች፤ ነፍ​ሳ​ችን ከክ​ር​ክር ውኃ አመ​ለ​ጠች፤</verse>
				<verse number="6">ወደ ከባቢ ወጥ​መ​ዳ​ቸው ያላ​ገ​ባን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።</verse>
				<verse number="7">ሰው​ነ​ታ​ችን ግን እንደ ወፍ ከአ​ዳኝ ወጥ​መድ አመ​ለ​ጠች፤ ወጥ​መድ ተሰ​በ​ረች፥ እኛ ግን ዳን።</verse>
				<verse number="8">ረድ​ኤ​ታ​ችን ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በፈ​ጠረ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="124">
				<verse number="1">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መኑ እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖር ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ታ​ወ​ክም።</verse>
				<verse number="2">ተራ​ሮች ይከ​ቧ​ታል፥ ከዛሬ ጀምሮ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ይመ​ግ​ባል።</verse>
				<verse number="3">ጻድ​ቃን እጃ​ቸ​ውን በዐ​መፃ እን​ዳ​ይ​ዘ​ረጉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኃ​ጥ​ኣ​ንን በትር በጻ​ድ​ቃን ዕጣ ላይ አይ​ተ​ው​ምና።</verse>
				<verse number="4">አቤቱ፥ ለቸ​ሮች፥ ልባ​ቸ​ውም ለቀና መል​ካ​ምን አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="5">ወደ ጠማ​ማ​ነት የሚ​መ​ለ​ሱ​ትን ግን ዐመ​ፃን ከሚ​ሠ​ሩት ጋር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይወ​ስ​ዳ​ቸ​ዋል። ሰላም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ይሁን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="125">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ዮ​ንን ምርኮ በመ​ለሰ ጊዜ፥ እጅግ ደስ​ተ​ኞች ሆንን።</verse>
				<verse number="2">በዚ​ያን ጊዜ አፋ​ችን ደስ​ታን ሞላ፥ አን​ደ​በ​ታ​ች​ንም ሐሤ​ትን አደ​ረገ፤ በዚ​ያን ጊዜ አሕ​ዛብ፦ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነገ​ርን አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው” አሉ።</verse>
				<verse number="3">ደስ​ተ​ኞ​ችም ሆን።</verse>
				<verse number="4">አቤቱ፥ በአ​ዜብ እን​ዳሉ ፈሳ​ሾች ምር​ኮ​አ​ች​ንን መልስ።</verse>
				<verse number="5">በል​ቅሶ የሚ​ዘሩ በደ​ስታ ይሰ​በ​ስ​ባሉ።</verse>
				<verse number="6">በሄዱ ጊዜ፥ ዘራ​ቸ​ውን ተሸ​ክ​መው እያ​ለ​ቀሱ ተሰ​ማሩ፤ በተ​መ​ለሱ ጊዜ ግን ነዶ​አ​ቸ​ውን ተሸ​ክ​መው ደስ እያ​ላ​ቸው ይመ​ጣሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="126">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትን ካል​ሠራ፥ ቤትን የሚ​ሠሩ በከ​ንቱ ይደ​ክ​ማሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተ​ማን ካል​ጠ​በቀ፥ የሚ​ጠ​ብቁ በከ​ንቱ ይተ​ጋሉ።</verse>
				<verse number="2">በማ​ለዳ መገ​ሥ​ገ​ሣ​ች​ሁም ከንቱ ነው። ለወ​ዳ​ጆቹ እን​ቅ​ል​ፍን በሰጠ ጊዜ፥ እና​ንተ የመ​ከ​ራን እን​ጀራ የም​ት​በሉ፥ ከተ​ቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​በት ተነሡ።</verse>
				<verse number="3">እነሆ፥ ልጆች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጦታ ናቸው፥ የሆ​ድም ፍሬ የእ​ርሱ ዋጋ ነው።</verse>
				<verse number="4">በኀ​ያል እጅ እን​ዳሉ ፍላ​ጾች፥ የተ​ጣሉ ሰዎች ልጆች እን​ዲሁ ናቸው።</verse>
				<verse number="5">ከእ​ነ​ርሱ ዘንድ ምኞ​ቱን የሚ​ፈ​ጽም ሰው ብፁዕ ነው፤ ጠላ​ቶ​ቹን በአ​ደ​ባ​ባይ በተ​ና​ገረ ጊዜ እርሱ አያ​ፍ​ርም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="127">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ሩት ሁሉ፥ በመ​ን​ገ​ዶ​ቹም የሚ​ሄዱ ብፁ​ዓን ናቸው።</verse>
				<verse number="2">የድ​ካ​ም​ህን ፍሬ ትመ​ገ​ባ​ለህ፤ ብፁዕ ነህ፥ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ል​ሃል።</verse>
				<verse number="3">ሚስ​ትህ በቤ​ትህ እል​ፍኝ ውስጥ እን​ደ​ሚ​ያ​ፈራ ወይን ትሆ​ና​ለች፤ ልጆ​ች​ህም በማ​ዕ​ድህ ዙሪያ እንደ አዲስ የወ​ይራ ተክል ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="4">እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው እን​ዲህ ይባ​ረ​ካል።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጽ​ዮን ይባ​ር​ክህ፤ በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን መል​ካ​ም​ነት ታያ​ለህ።</verse>
				<verse number="6">የል​ጆ​ች​ህ​ንም ልጆች ታያ​ለህ። በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ሰላም ይሁን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="128">
				<verse number="1">እስ​ራ​ኤል እን​ዲህ ይበል፥ “ከት​ን​ሽ​ነቴ ጀምሮ ሁል​ጊዜ ተሰ​ለ​ፉ​ብኝ፤</verse>
				<verse number="2">ከት​ን​ሽ​ነቴ ጀምሮ ሁል​ጊዜ ተሰ​ለ​ፉ​ብኝ፤ ነገር ግን አል​ቻ​ሉ​ኝም።</verse>
				<verse number="3">ኃጥ​ኣን በጀ​ር​ባዬ ላይ መቱኝ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም አበ​ዙ​አት።”</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድቅ ነው፤ የኃ​ጥ​ኣ​ንን አን​ገ​ታ​ቸ​ውን ቈረጠ።</verse>
				<verse number="5">ጽዮ​ንን የሚ​ጠሉ ሁሉ ይፈሩ፥ ወደ ኋላ​ቸ​ውም ይመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="6">በሰ​ገ​ነት ላይ እንደ በቀለ ሣር፥ ሳይ​ነ​ቀል እን​ደ​ሚ​ደ​ርቅ፥</verse>
				<verse number="7">ለሚ​ያ​ጭ​ደው እጁን፥ ነዶ​ዎ​ቹን ለሚ​ሰ​በ​ስ​ብም እቅ​ፉን እን​ደ​ማ​ይ​ሞላ ይሁኑ።</verse>
				<verse number="8">በመ​ን​ገ​ድም የሚ​ያ​ልፉ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በረ​ከት በእ​ና​ንተ ላይ ይሁን፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም እን​መ​ር​ቃ​ች​ኋ​ለን” አይ​በሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="129">
				<verse number="1">አቤቱ፥ አን​ተን ከጥ​ልቅ ጠራ​ሁህ።</verse>
				<verse number="2">አቤቱ፥ ቃሌን ስማኝ፤ ጆሮ​ህም የል​መ​ና​ዬን ቃል የሚ​ያ​ደ​ምጥ ይሁን።</verse>
				<verse number="3">አቤቱ፥ ኀጢ​አ​ት​ንስ ብት​ጠ​ባ​በቅ፥ አቤቱ፥ ማን ይቆ​ማል?</verse>
				<verse number="4">ይቅ​ርታ ከአ​ንተ ዘንድ ነውና።</verse>
				<verse number="5">አቤቱ፥ ስለ ስምህ ተስፋ አደ​ረ​ግ​ሁህ፤ ነፍሴ በሕ​ግህ ታገ​ሠች።</verse>
				<verse number="6">ከማ​ለ​ዳው ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊት ነፍሴ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመ​ነች። ከማ​ለዳ ጀምሮ እስ​ራ​ኤል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመነ።</verse>
				<verse number="7">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይቅ​ርታ፥ በእ​ር​ሱም ዘንድ ብዙ ማዳን አለና፥</verse>
				<verse number="8">እር​ሱም እስ​ራ​ኤ​ልን ከኀ​ጢ​አቱ ሁሉ ያድ​ነ​ዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="130">
				<verse number="1">አቤቱ፥ ልቤ አይ​ታ​በ​ይ​ብ​ኝ፥ ዐይ​ኖ​ቼም ከፍ ከፍ አይ​በ​ሉ​ብኝ፤ ከት​ል​ል​ቆች ጋር፥ ከእ​ኔም ይልቅ ከሚ​ከ​ብሩ ጋር አል​ሄ​ድ​ሁም።</verse>
				<verse number="2">ራሴን አዋ​ረ​ድሁ እንጂ። ለነ​ፍሴ ዋጋ​ዋን ትሰ​ጣት ዘንድ፤ የእ​ና​ቱ​ንም ጡት እን​ዳ​ስ​ጣ​ሉት በቃሌ ጮኽሁ።</verse>
				<verse number="3">ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም እስ​ራ​ኤል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይታ​መ​ናል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="131">
				<verse number="1">አቤቱ፥ ዳዊ​ትን፥ ገር​ነ​ቱ​ንም ሁሉ ዐስብ፤</verse>
				<verse number="2">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ማለ፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እንደ ተሳለ፦</verse>
				<verse number="3">“ወደ ቤቴ ድን​ኳን አል​ገ​ባም፥ ወደ መኝ​ታ​ዬም አልጋ አል​ወ​ጣም፥</verse>
				<verse number="4">ለዐ​ይ​ኖቼም መኝ​ታን፥ ለቅ​ን​ድ​ቦ​ቼም እን​ቅ​ል​ፍን፥ ለጕ​ን​ጮ​ቼም ዕረ​ፍ​ትን አል​ሰ​ጥም፥</verse>
				<verse number="5">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቦታ፥ የያ​ዕ​ቆብ አም​ላ​ክን ማደ​ሪያ እስ​ካ​ገኝ ድረስ” ብሎ እንደ ተሳለ ዐስብ።</verse>
				<verse number="6">እነሆ፥ በኤ​ፍ​ራታ ሰማ​ነው፥ ዛፍ በበ​ዛ​በ​ትም ቦታ አገ​ኘ​ነው።</verse>
				<verse number="7">እን​ግ​ዲ​ህስ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪ​ያ​ዎች እን​ገ​ባ​ለን፤ የጌ​ታ​ችን እግ​ሮቹ በሚ​ቆ​ሙ​በት ቦታ እን​ሰ​ግ​ዳ​ለን።</verse>
				<verse number="8">አቤቱ፥ ወደ ዕረ​ፍ​ትህ ተነሥ፥ አን​ተና የመ​ቅ​ደ​ስህ ታቦት።</verse>
				<verse number="9">ካህ​ና​ትህ ጽድ​ቅን ይለ​ብ​ሳሉ፥ ጻድ​ቃ​ን​ህም ደስ ይላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="10">ስለ ባሪ​ያህ ስለ ዳዊት ቀብ​ተህ ካነ​ገ​ሥ​ኸው ፊት​ህን አት​መ​ልስ።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዳ​ዊት እን​ዲህ ሲል በእ​ው​ነት ማለ፥ አይ​ጸ​ጸ​ት​ምም፥ “ከሆ​ድህ ፍሬ በዙ​ፋ​ንህ ላይ አስ​ቀ​ም​ጣ​ለ​ሁና</verse>
				<verse number="12">ልጆ​ችህ ኪዳ​ኔን፥ ይህ​ንም የማ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ውን ምስ​ክ​ሬን ቢጠ​ብቁ፥ ልጆ​ቻ​ቸው በዙ​ፋ​ንህ ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይቀ​መ​ጣሉ።”</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዮ​ንን መር​ጦ​አ​ታ​ልና፥ ማደ​ሪ​ያ​ውም ትሆ​ነው ዘንድ ወድ​ዶ​አ​ታ​ልና፥</verse>
				<verse number="14">“ይህች ለዘ​ለ​ዓ​ለም ማረ​ፊ​ያዬ ናት፤ መር​ጫ​ታ​ለ​ሁና በዚ​ህች አድ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">ባል​ቴ​ቶ​ች​ዋን እጅግ እባ​ር​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ድሆ​ች​ዋ​ንም እህ​ልን አጠ​ግ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፥</verse>
				<verse number="16">ካህ​ና​ቷ​ንም ደኅ​ን​ነ​ትን አለ​ብ​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ጻድ​ቃ​ኖ​ች​ዋም እጅግ ደስ ይላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="17">በዚያ ለዳ​ዊት ቀን​ድን አበ​ቅ​ላ​ለሁ፥ ቀብቼ ላነ​ገ​ሥ​ሁ​ትም መብ​ራ​ትን አዘ​ጋ​ጃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="18">ጠላ​ቶ​ቹ​ንም እፍ​ረ​ትን አለ​ብ​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ር​ሱም ቅድ​ስ​ናዬ ያፈ​ራል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="132">
				<verse number="1">ወን​ድ​ሞች በኅ​ብ​ረት ቢቀ​መጡ፥ እነሆ፥ መል​ካም ነው፥ እነ​ሆም፥ ያማረ ነው።</verse>
				<verse number="2">ከራሱ ጀምሮ እስከ ጢሙ፥ በል​ብሱ መደ​ረ​ቢያ ላይ፥ እስ​ከ​ሚ​ወ​ር​ደው እስከ አሮን ጢም ድረስ እን​ደ​ሚ​ፈስ ሽቱ ነው።</verse>
				<verse number="3">በጽ​ዮን ተራ​ሮች እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ እንደ አር​ሞ​ን​ዔ​ምም ጠል ነው፤ በዚያ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በረ​ከ​ቱን ሕይ​ወ​ት​ንም ከዛሬ ጀምሮ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አዝ​ዞ​አ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="133">
				<verse number="1">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት፥ በአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤት አደ​ባ​ባ​ዮች የም​ት​ቆሙ እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪ​ያ​ዎች ሁላ​ችሁ፥ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ።</verse>
				<verse number="2">በሌ​ሊት በቤተ መቅ​ደስ እጆ​ቻ​ች​ሁን አንሡ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ስ​ግ​ኑት።</verse>
				<verse number="3">ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን የሠራ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጽ​ዮን ይባ​ር​ክህ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="134">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም አመ​ስ​ግኑ፤ እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪ​ያ​ዎች ሆይ፥ አመ​ስ​ግ​ኑት።</verse>
				<verse number="2">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ፥ በአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤት አደ​ባ​ባይ የም​ት​ቆሙ።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤ ለስሙ ዘምሩ፥ መል​ካም ነውና፤</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዕ​ቆ​ብን ለራሱ፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ርስቱ እን​ዲ​ሆን መር​ጦ​ታ​ልና፤</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ እንደ ሆነ፥ አም​ላ​ካ​ች​ንም ከአ​ማ​ል​ክት ሁሉ እን​ዲ​በ​ልጥ አው​ቃ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="6">በሰ​ማ​ይና በም​ድር፥ በባ​ሕ​ርና በጥ​ል​ቆ​ችም ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የወ​ደ​ደ​ውን ሁሉ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="7">ከም​ድር ዳር ደመ​ና​ትን ያወ​ጣል፤ ለዝ​ናም ጊዜም መብ​ረ​ቅን አደ​ረገ፤ ነፋ​ሳ​ት​ንም ከመ​ዛ​ግ​ብቱ ያወ​ጣል።</verse>
				<verse number="8">የግ​ብ​ፅን በኵር ልጆች ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ ድረስ ገደለ።</verse>
				<verse number="9">ግብፅ ሆይ፥ በመ​ካ​ከ​ልሽ በፈ​ር​ዖ​ንና በባ​ሪ​ያ​ዎቹ ሁሉ ላይ ተአ​ም​ራ​ት​ንና ድን​ቅን ሰደደ።</verse>
				<verse number="10">ብዙ አሕ​ዛ​ብን መታ፥ ብር​ቱ​ዎ​ች​ንም ነገ​ሥ​ታት ገደለ።</verse>
				<verse number="11">የአ​ሞ​ራ​ው​ያ​ንን ንጉሥ ሴዎ​ንን፥ የባ​ሳ​ን​ንም ንጉሥ ዐግን፥ የከ​ነ​ዓ​ንን ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ገደለ፤</verse>
				<verse number="12">ርስት ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም ለሕ​ዝቡ ለእ​ስ​ራ​ኤል ርስት አድ​ርጎ ሰጠ።</verse>
				<verse number="13">አቤቱ፥ ስምህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነው፥ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ህም ለልጅ ልጅ ነው፤</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ ይፈ​ር​ዳ​ልና፥ ባሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ያጽ​ና​ና​ልና።</verse>
				<verse number="15">የአ​ሕ​ዛብ ጣዖ​ታት የብ​ርና የወ​ርቅ፥ የሰው እጅ ሥራ ናቸው።</verse>
				<verse number="16">አፍ አላ​ቸው፥ ግን አይ​ና​ገ​ሩም፤ ዐይን አላ​ቸው፥ ግን አያ​ዩም፤</verse>
				<verse number="17">ጆሮ አላ​ቸው፥ ግን አይ​ሰ​ሙም፤ አፍ​ንጫ አላ​ቸው፥ ግን አያ​ሸ​ቱም፤ እጅ አላ​ቸው፥ ግን አይ​ዳ​ስ​ሱም፤ እግር አላ​ቸው፥ ግን አይ​ሄ​ዱም፤ በጕ​ሮ​ሮ​አ​ቸው አይ​ና​ገ​ሩም፥ እስ​ት​ን​ፋ​ስም በአ​ፋ​ቸው የለም።</verse>
				<verse number="18">የሚ​ሠ​ሩ​አ​ቸው ሁሉ፥ የሚ​ታ​መ​ኑ​ባ​ቸ​ውም ሁሉ እንደ እነ​ርሱ ይሁኑ።</verse>
				<verse number="19">የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፤ የአ​ሮን ወገ​ኖች ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፤</verse>
				<verse number="20">የሌዊ ወገ​ኖች ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈ​ሩት ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት።</verse>
				<verse number="21">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ያ​ድር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን የተ​መ​ሰ​ገነ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="135">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፥ ቸር ነውና፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።</verse>
				<verse number="2">የአ​ማ​ል​ክ​ትን አም​ላክ አመ​ስ​ግኑ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።</verse>
				<verse number="3">የጌ​ቶ​ችን ጌታ አመ​ስ​ግኑ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤</verse>
				<verse number="4">እርሱ ብቻ​ውን ታላቅ ተአ​ም​ራ​ትን ያደ​ረገ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤</verse>
				<verse number="5">ሰማ​ያ​ትን በጥ​በቡ የሠራ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤</verse>
				<verse number="6">ምድ​ርን በውኃ ላይ ያጸና፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤</verse>
				<verse number="7">ብቻ​ውን ታላ​ላቅ ብር​ሃ​ና​ትን የሠራ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤</verse>
				<verse number="8">ለፀ​ሐይ ቀንን ያስ​ገ​ዛው፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤</verse>
				<verse number="9">ለጨ​ረ​ቃና ለከ​ዋ​ክ​ብት ሌሊ​ትን ያስ​ገ​ዛ​ቸው፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤</verse>
				<verse number="10">ከበ​ኵ​ራ​ቸው ጋር ግብ​ፅን የገ​ደለ፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤</verse>
				<verse number="11">እስ​ራ​ኤ​ልን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ያወጣ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤</verse>
				<verse number="12">በጸ​ናች እጅ በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤</verse>
				<verse number="13">የኤ​ር​ት​ራን ባሕር ፈጽሞ የከ​ፈለ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤</verse>
				<verse number="14">እስ​ራ​ኤ​ልን በመ​ካ​ከሉ ያሳ​ለፈ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤</verse>
				<verse number="15">ፈር​ዖ​ን​ንና ሠራ​ዊ​ቱን በኤ​ር​ትራ ባሕር ውስጥ የጣለ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤</verse>
				<verse number="16">ሕዝ​ቡን በም​ድረ በዳ የመራ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤ ከዓ​ለት ውኃን ያፈ​ለቀ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤</verse>
				<verse number="17">ታላ​ላቅ ነገ​ሥ​ታ​ትን የገ​ደለ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤</verse>
				<verse number="18">ጽኑ​ዓን ነገ​ሥ​ታ​ትን የገ​ደለ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤</verse>
				<verse number="19">የአ​ሞ​ራ​ው​ያ​ንን ንጉሥ ሴዎ​ንን፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፥</verse>
				<verse number="20">የባ​ሳ​ንን ንጉሥ ዐግን፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤</verse>
				<verse number="21">ርስት ምድ​ራ​ቸ​ውን ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፥ ለባ​ሪ​ያው ለእ​ስ​ራ​ኤል ርስት አድ​ርጎ የሰጠ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኛን በመ​ዋ​ረ​ዳ​ችን ዐስ​ቦ​ና​ልና፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤</verse>
				<verse number="23">ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ንም እጅ አድ​ኖ​ና​ልና፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤</verse>
				<verse number="24">ለሥጋ ሁሉ ምግ​ብን የሚ​ሰጥ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።</verse>
				<verse number="25">የሰ​ማ​ይን አም​ላክ አመ​ስ​ግኑ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="136">
				<verse number="1">በባ​ቢ​ሎን ወን​ዞች አጠ​ገብ በዚያ ተቀ​መ​ጥን፤ ጽዮ​ን​ንም ባሰ​ብ​ናት ጊዜ አለ​ቀ​ስን።</verse>
				<verse number="2">በአ​ኻያ ዛፎ​ችዋ ላይ በገ​ና​ዎ​ቻ​ች​ንን ሰቀ​ልን።</verse>
				<verse number="3">የማ​ረ​ኩን በዚያ የዝ​ማሬ ቃል ጠይ​ቀ​ው​ና​ልና፥ የወ​ሰ​ዱ​ንም፥ “የጽ​ዮ​ንን ዝማሬ ዘም​ሩ​ልን” አሉን።</verse>
				<verse number="4">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዝማሬ በባ​ዕድ ምድር እን​ዴት እን​ዘ​ም​ራ​ለን?</verse>
				<verse number="5">ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ብረ​ሳሽ፥ ቀኜ ትር​ሳኝ።</verse>
				<verse number="6">ባላ​ስ​ብሽ፥ ምላሴ በጕ​ሮ​ሮዬ ይጣ​በቅ፤ ከደ​ስ​ታዬ ሁሉ በላይ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ባል​ወ​ድድ።</verse>
				<verse number="7">አቤቱ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቀን፦ “እስከ መሠ​ረቷ ድረስ አፍ​ርሱ አፍ​ርሱ” ያሉ​አ​ትን የኤ​ዶ​ምን ልጆች ዐስብ።</verse>
				<verse number="8">አንቺ ወራዳ የባ​ቢ​ሎን ልጅ ሆይ፥ ስለ ተበ​ቀ​ል​ሽን የሚ​በ​ቀ​ልሽ ብፁዕ ነው።</verse>
				<verse number="9">ሕፃ​ና​ቶ​ች​ሽን ይዞ በዓ​ለት ላይ የሚ​ፈ​ጠ​ፍ​ጣ​ቸው ብፁዕ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="137">
				<verse number="1">አቤቱ፥ በፍ​ጹም ልቤ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥ የአ​ፌን ነገር ሁሉ ሰም​ተ​ኸ​ኛ​ልና፤ በመ​ላ​እ​ክት ፊት እዘ​ም​ር​ል​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">በቤተ መቅ​ደ​ስ​ህም እሰ​ግ​ዳ​ለሁ፤ ስለ ምሕ​ረ​ት​ህና ስለ እው​ነ​ት​ህም ስም​ህን አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስም​ህን ከፍ ከፍ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና።</verse>
				<verse number="3">በጠ​ራ​ሁህ ቀን በፍ​ጥ​ነት አድ​ም​ጠኝ፤ ነፍ​ሴን በኀ​ይ​ልህ በብዙ አጸ​ና​ሃት።</verse>
				<verse number="4">አቤቱ፥ የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፤ የአ​ፍ​ህን ቃል ሁሉ ሰም​ተ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="5">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምስ​ጋና ይዘ​ም​ራሉ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ታላቅ ነውና።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ያለ ነውና፥ የተ​ዋ​ረ​ዱ​ት​ንም ይመ​ለ​ከ​ታ​ልና፤ ትቢ​ተ​ኛ​ው​ንም ከሩቁ ያው​ቀ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">በመ​ከራ መካ​ከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ታድ​ነ​ኛ​ለህ፤ በጠ​ላ​ቶች ቍጣ ላይ እጆ​ች​ህን ትዘ​ረ​ጋ​ለህ፥ ቀኝ​ህም ያድ​ነ​ኛል</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይበ​ቀ​ል​ል​ኛል፤ አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ትህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነው፤ አቤቱ የእ​ጅ​ህን ሥራ ቸል አት​በል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="138">
				<verse number="1">አቤቱ፥ ፈተ​ን​ኸኝ፥ ዐወ​ቅ​ኸ​ኝም።</verse>
				<verse number="2">አንተ መቀ​መ​ጤ​ንና መነ​ሣ​ቴን ታው​ቃ​ለህ። የል​ቤን ዐሳብ ሁሉ ከሩቁ ታስ​ተ​ው​ላ​ለህ።</verse>
				<verse number="3">ፍለ​ጋ​ዬ​ንና መን​ገ​ዴን አንተ ትመ​ረ​ም​ራ​ለህ፤ መን​ገ​ዶ​ቼን ሁሉ አስ​ቀ​ድ​መህ ዐወ​ቅህ፥</verse>
				<verse number="4">የዐ​መፃ ቃል በአ​ን​ደ​በቴ እን​ደ​ሌለ።</verse>
				<verse number="5">አቤቱ፥ አንተ እነሆ፥ የቀ​ድ​ሞ​ው​ንና የኋ​ላ​ውን ሁሉ ዐወ​ቅህ፤ አንተ ፈጠ​ር​ኸኝ፥ እጅ​ህ​ንም በላዬ አደ​ረ​ግህ።</verse>
				<verse number="6">ዕው​ቀ​ትህ በእኔ ላይ ተደ​ነ​ቀች፤ በረ​ታ​ች​ብኝ፥ ወደ እር​ሷም ለመ​ድ​ረስ አል​ች​ልም።</verse>
				<verse number="7">ከመ​ን​ፈ​ስህ ወዴት እሄ​ዳ​ለሁ? ከፊ​ት​ህስ ወዴት እሸ​ሻ​ለሁ?</verse>
				<verse number="8">ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ አለህ፤ ወደ ጥል​ቁም ብወ​ርድ፥ አንተ በዚያ አለህ፤</verse>
				<verse number="9">እንደ ንስ​ርም ክን​ፍን ብወ​ስድ፥ እስከ ባሕር መጨ​ረ​ሻም ብበ​ርር፥</verse>
				<verse number="10">በዚያ እጅህ ትመ​ራ​ኛ​ለች፥ ቀኝ​ህም ታኖ​ረ​ኛ​ለች።</verse>
				<verse number="11">በእ​ው​ነት ጨለማ ይሸ​ፍ​ነ​ኛል ብል፥ ሌሊት በደ​ስ​ታዬ ብር​ሃን ይሆ​ናል፤</verse>
				<verse number="12">ጨለማ በአ​ንተ ዘንድ አይ​ጨ​ል​ም​ምና፥ ሌሊ​ትም እንደ ቀን ታበ​ራ​ለ​ችና፤ እንደ ጨለ​ማዋ እን​ዲሁ ብር​ሃ​ንዋ ነው።</verse>
				<verse number="13">አቤቱ፥ አንተ ኵላ​ሊ​ቴን ፈጥ​ረ​ሃ​ልና፥ ከእ​ናቴ ማኅ​ፀን ጀምሮ ተቀ​በ​ል​ኸኝ።</verse>
				<verse number="14">በመ​ፈ​ራት የተ​ደ​ነ​ቅህ ነህና አቤቱ፥ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍ​ሴም እጅግ ትረ​ዳ​ዋ​ለች።</verse>
				<verse number="15">በስ​ውር የሠ​ራ​ኸው አጥ​ንቴ ከአ​ንተ አል​ተ​ሰ​ወ​ረም፥ አካ​ሌም ከም​ድር በታች፥</verse>
				<verse number="16">ያል​ተ​ሠራ አካ​ሌ​ንም ዐይ​ኖ​ችህ አዩ፤ ሁሉም በመ​ጽ​ሐ​ፍህ ተጻፉ፥ በቀን ይፈ​ጠ​ራሉ፥ ነገር ግን ከእ​ነ​ርሱ አንድ ስንኳ አይ​ኖ​ርም።</verse>
				<verse number="17">አቤቱ፥ ወዳ​ጆ​ችህ በእኔ ዘንድ እጅግ የከ​በሩ ናቸው፤ ከቀ​ደ​ም​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅግ ጸኑ።</verse>
				<verse number="18">እቈ​ጥ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ከአ​ሸ​ዋም ይልቅ ይበ​ዛሉ፤ ተነ​ሣሁ፥ ገናም ከአ​ንተ ጋር ነኝ።</verse>
				<verse number="19">አቤቱ፥ አንተ ኃጥ​ኣ​ንን የም​ት​ገ​ድል ከሆ​ን​ህስ፥ የደም ሰዎች ሆይ፥ ከእኔ ፈቀቅ በሉ።</verse>
				<verse number="20">በዐ​ሳ​ባ​ቸው ይኰ​ራ​ሉና፤ ከተ​ሞ​ች​ህ​ንም በከ​ንቱ ይወ​ስ​ዷ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="21">አቤቱ፥ የሚ​ጠ​ሉ​ህን እኔ የጠ​ላሁ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ስለ ጠላ​ቶ​ች​ህም አል​ጠ​ፋ​ሁ​ምን?</verse>
				<verse number="22">ፍጹም ጥልን ጠላ​ኋ​ቸው፥ ጠላ​ቶ​ችም ሆኑኝ።</verse>
				<verse number="23">አቤቱ፥ መር​ም​ረኝ፥ ልቤ​ንም ፈትን፤ ፈት​ነኝ፥ መን​ገ​ዶ​ች​ንም ዕወቅ፤</verse>
				<verse number="24">በደ​ልም በእኔ ላይ ቢገኝ እይ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ም​ንም መን​ገድ ምራኝ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="139">
				<verse number="1">“አቤቱ፥ ከክፉ ሰው አድ​ነኝ፥ ከዐ​መ​ፀኛ ሰውም ታደ​ገኝ፥</verse>
				<verse number="2">ሁል​ጊዜ በል​ባ​ቸው ዐመ​ፃን የሚ​መ​ክሩ፥ ይገ​ድ​ሉኝ ዘንድ ይከ​ብ​ቡ​ኛል።</verse>
				<verse number="3">ምላ​ሳ​ቸ​ውን እንደ እባብ ሳሉ፤ ከከ​ን​ፈ​ራ​ቸው በታች የእ​ባብ መርዝ አለ።</verse>
				<verse number="4">አቤቱ፥ ከኃ​ጥ​ኣን እጅ ጠብ​ቀኝ፥ እር​ም​ጃ​ዬ​ንም ሊያ​ሰ​ና​ክሉ ከመ​ከሩ ከዐ​መ​ፀ​ኞች ሰዎች አድ​ነኝ።</verse>
				<verse number="5">ትዕ​ቢ​ተ​ኞች ወጥ​መ​ድን ሰወ​ሩ​ብኝ፥ ለእ​ግ​ሮ​ቼም የወ​ጥ​መድ ገመ​ድን ዘረጉ፤ በመ​ን​ገ​ዴም ዕን​ቅ​ፋ​ትን አኖሩ።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፥ “አንተ አም​ላኬ ነህ፤ የል​መ​ና​ዬን ቃል፥ አቤቱ፥ አድ​ምጥ” አል​ሁት።</verse>
				<verse number="7">አቤቱ፥ ጌታዬ፥ የድ​ኅ​ነቴ ኀይል፥ በጦ​ር​ነት ቀን በራሴ ላይ ሁነህ ሰወ​ር​ኸኝ።</verse>
				<verse number="8">አቤቱ፥ ጌታዬ፥ ከም​ኞቴ የተ​ነሣ ለኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች አት​ስ​ጠኝ፤ በላዬ ተማ​ከሩ፥ እን​ዳ​ይ​ታ​በ​ዩም አት​ተ​ወኝ።</verse>
				<verse number="9">የአ​ሽ​ክ​ላ​ቸው ራስ የከ​ን​ፈ​ራ​ቸ​ውም ክፋት ይድ​ፈ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="10">የእ​ሳት ፍም በላ​ያ​ቸው ይው​ደቅ፤ መቆም እን​ዳ​ይ​ችሉ በች​ግር ወደ ምድር ይው​ደቁ።</verse>
				<verse number="11">ተና​ጋሪ ሰው በም​ድር ውስጥ አይ​ጸ​ናም፤ ዐመ​ፀኛ ሰውን ክፋት ለጥ​ፋት ታድ​ነ​ዋ​ለች።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለድ​ሆች ዳኝ​ነ​ትን ለች​ግ​ረ​ኞ​ችም ፍር​ድን እን​ዲ​ያ​ደ​ርግ ዐወ​ቅሁ።</verse>
				<verse number="13">ጻድ​ቃን ግን በእ​ው​ነት ስም​ህን ያመ​ሰ​ግ​ናሉ፤ ቅኖ​ችም በፊ​ትህ ይኖ​ራሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="140">
				<verse number="1">አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፤ ስማኝ፤ ወደ አንተ ስጮ​ኽም የል​መ​ና​ዬን ቃል አድ​ምጥ።</verse>
				<verse number="2">ጸሎ​ቴን በፊ​ትህ እንደ ዕጣን ተቀ​በ​ል​ልኝ፥ እጆቼ የሠ​ርክ መሥ​ዋ​ዕ​ትን አነሡ።</verse>
				<verse number="3">አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ፥ ለከ​ን​ፈ​ሮ​ቼም ጽኑዕ መዝ​ጊ​ያን አኑር።</verse>
				<verse number="4">ልቤን ወደ ክፉ ነገር አት​መ​ል​ሰው፥ ዐመ​ፃን ከሚ​ያ​ደ​ርጉ ሰዎች ጋር ለኀ​ጢ​አት ምክ​ን​ያት እን​ዳ​ል​ሰጥ፤ ከም​ር​ጦ​ቻ​ቸ​ውም ጋር አል​ተ​ባ​በር።</verse>
				<verse number="5">በጽ​ድቅ ገሥ​ጸኝ፥ በም​ሕ​ረ​ትም ዝለ​ፈኝ፥ የኀ​ጢ​አ​ተኛ ዘይ​ትን ግን ራሴን አል​ቀ​ባም፤ ዳግ​መ​ኛም ጸሎቴ ይቅር እን​ዳ​ት​ላ​ቸው ነውና።</verse>
				<verse number="6">ኀያ​ላ​ኖ​ቻ​ቸው በዓ​ለት አጠ​ገብ ተጣሉ፥ ተች​ሎ​ኛ​ልና ቃሌን ስሙኝ።</verse>
				<verse number="7">እንደ ጓል በም​ድር ላይ ተሰ​ነ​ጣ​ጠቁ እን​ዲሁ አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸው በሲ​ኦል ተበ​ተኑ፥</verse>
				<verse number="8">አቤቱ፥ ጌታዬ፥ ዐይ​ኖቼ ወደ አንተ ናቸ​ውና፤ በአ​ንተ ታመ​ንሁ፥ ነፍ​ሴን አታ​ው​ጣት።</verse>
				<verse number="9">ከሰ​ወ​ሩ​ብኝ ወጥ​መድ፥ ዐመ​ፃ​ንም ከሚ​ያ​ደ​ርጉ ሰዎች እን​ቅ​ፋት ጠብ​ቀኝ።</verse>
				<verse number="10">እኔ ብቻ​ዬን እስ​ካ​ልፍ ድረስ ኃጥ​ኣን በወ​ጥ​መ​ዳ​ቸው ይው​ደቁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="141">
				<verse number="1">በቃሌ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኽሁ፤ በቃሌ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ንሁ።</verse>
				<verse number="2">ልመ​ና​ዬን በፊቱ አፈ​ስ​ሳ​ለሁ፤ መከ​ራ​ዬ​ንም በፊቱ እና​ገ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">ሰው​ነቴ በላዬ ላይ ባለ​ቀች ጊዜ አቤቱ፥ መን​ገ​ዴን አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ በም​ሄ​ድ​ባት በዚ​ያች መን​ገድ ወጥ​መ​ድን ሰወ​ሩ​ብኝ።</verse>
				<verse number="4">ወደ ቀኝም ተመ​ልሼ አየሁ፥ የሚ​ያ​ው​ቀ​ኝም አጣሁ፤ መሸ​ሸ​ጊ​ያም የለ​ኝም፥ ስለ ሰው​ነ​ቴም የሚ​መ​ራ​መር የለም።</verse>
				<verse number="5">አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፦ “አንተ ተስ​ፋዬ ነህ፥ በሕ​ያ​ዋ​ንም ምድር አንተ ዕድል ፋን​ታዬ ነህ” አልሁ።</verse>
				<verse number="6">እጅግ ተዋ​ር​ጃ​ለ​ሁና ወደ ልመ​ናዬ ተመ​ል​ከት፤ በር​ት​ተ​ው​ብ​ኛ​ልና ከከ​በ​ቡኝ አድ​ነኝ።</verse>
				<verse number="7">አቤቱ፥ ስም​ህን አመ​ሰ​ግን ዘንድ ሰው​ነ​ቴን ከእ​ሥ​ራት አው​ጣት፤ ዋጋ​ዬን እስ​ክ​ት​ሰ​ጠኝ ድረስ ጻድ​ቃን እኔን ይጠ​ብ​ቃሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="142">
				<verse number="1">አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን ስማ፥ በእ​ው​ነ​ትህ ልመ​ና​ዬን አድ​ምጥ፥ በጽ​ድ​ቅ​ህም መል​ስ​ልኝ።</verse>
				<verse number="2">ሕያው ሁሉ በፊ​ትህ አይ​ጸ​ድ​ቅ​ምና ከባ​ሪ​ያህ ጋር ወደ ክር​ክር አት​ግባ።</verse>
				<verse number="3">ጠላት ነፍ​ሴን ከብ​ቦ​አ​ታ​ልና ሕይ​ወ​ቴ​ንም በም​ድር ውስጥ አዋ​ር​ዶ​አ​ታል፥ ቀድሞ እንደ ሞተ ሰው በጨ​ለማ አኖ​ሩኝ።</verse>
				<verse number="4">ሰው​ነቴ በላዬ አለ​ቀ​ች​ብኝ፥ ልቤም በው​ስጤ ደነ​ገ​ጠ​ብኝ።</verse>
				<verse number="5">የቀ​ድ​ሞ​ውን ዘመን ዐሰ​ብሁ፥ ሥራ​ህ​ንም ሁሉ አነ​በ​ብሁ፤ የእ​ጅ​ህ​ንም ሥራ አነ​ብ​ባ​ለሁ።</verse>
				<verse number="6">እጆ​ቼን ወደ አንተ ዘረ​ጋሁ፤ ነፍ​ሴም እንደ ምድረ በዳ አን​ተን ተጠ​ማች።</verse>
				<verse number="7">አቤቱ፥ ፈጥ​ነህ ስማኝ፥ ሰው​ነቴ አል​ቃ​ለች፤ ፊት​ህ​ንም ከእኔ አት​መ​ልስ፥ ወደ ጕድ​ጓ​ድም እን​ደ​ሚ​ወ​ርዱ አል​ሁን።</verse>
				<verse number="8">አቤቱ፥ አን​ተን ታም​ኛ​ለ​ሁና፥ በማ​ለዳ ምሕ​ረ​ት​ህን አሰ​ማኝ፤ አቤቱ፥ ነፍ​ሴን ወደ አንተ አን​ሥ​ቻ​ለ​ሁና የም​ሄ​ድ​ባ​ትን መን​ገድ ምራኝ።</verse>
				<verse number="9">አቤቱ፥ ወደ አንተ ተማ​ጽ​ኛ​ለ​ሁና ከጠ​ላ​ቶቼ አድ​ነኝ።</verse>
				<verse number="10">አቤቱ፥ አንተ አም​ላኬ ነህና ፈቃ​ድ​ህን ለማ​ድ​ረግ አስ​ተ​ም​ረኝ፤ ቅዱስ መን​ፈ​ስ​ህም በጽ​ድቅ ምድር ይም​ራኝ።</verse>
				<verse number="11">አቤቱ፥ ስለ ስምህ ሕያው አድ​ር​ገኝ፤ ስለ ጽድ​ቅ​ህም ነፍ​ሴን ከመ​ከ​ራዋ አው​ጣት።</verse>
				<verse number="12">በፈ​ቃ​ድህ ጠላ​ቶቼን አጥ​ፋ​ቸው፥ እኔ ባሪ​ያህ ነኝና ነፍ​ሴን የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ትን ሁሉ አጥ​ፋ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="143">
				<verse number="1">ለእ​ጆቼ ጠብን፥ ለጣ​ቶ​ቼም ሰል​ፍን ያስ​ተ​ማ​ራ​ቸው አም​ላኬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤</verse>
				<verse number="2">የሚ​ም​ረኝ፥ መሸ​ሸ​ጊ​ያዬ፥ መጠ​ጊ​ያ​ዬና አዳኜ፤ መታ​መ​ኛ​ዬም፤ እር​ሱን ታመ​ንሁ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ከእኔ በታች የሚ​ያ​ስ​ገ​ዛ​ልኝ።</verse>
				<verse number="3">አቤቱ፥ ለእ​ርሱ ትገ​ለ​ጥ​ለት ዘንድ ሰው ምን​ድን ነው? ታስ​በው ዘን​ድስ የሰው ልጅ ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="4">ሰው ከንቱ ነገ​ርን ይመ​ስ​ላል፤ ዘመ​ኑም እንደ ጥላ ያል​ፋል።</verse>
				<verse number="5">አቤቱ፥ ሰማ​ዮ​ች​ህን ዝቅ ዝቅ አድ​ር​ጋ​ቸው፥ ውረ​ድም፤ ተራ​ሮ​ችን ዳስ​ሳ​ቸው፥ ይጢ​ሱም።</verse>
				<verse number="6">መብ​ረ​ቆ​ች​ህን ብልጭ አድ​ር​ጋ​ቸው፥ በት​ና​ቸ​ውም፤ ፍላ​ጾ​ች​ህን ላካ​ቸው፥ አስ​ደ​ን​ግ​ጣ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="7">እጅ​ህን ከአ​ር​ያም ላክ፥ ከብዙ ውኃም አድ​ነኝ፤ ከባ​ዕድ ልጆ​ችም እጅ፥</verse>
				<verse number="8">አፋ​ቸው ከንቱ ነገ​ርን ከሚ​ና​ገር፥ ቀኛ​ቸ​ውም የዐ​መፃ ቀኝ ከሆነ አስ​ጥ​ለኝ።</verse>
				<verse number="9">አቤቱ፥ በአ​ዲስ ምስ​ጋና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፤ ዐሥር አው​ታር ባለው በገ​ናም እዘ​ም​ር​ል​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">ለነ​ገ​ሥ​ታት መድ​ኀ​ኒ​ትን የሚ​ሰጥ፥ ባሪ​ያው ዳዊ​ትን ከክፉ ጦር የሚ​ያ​ድ​ነው እርሱ ነው።</verse>
				<verse number="11">አፋ​ቸ​ውም ከንቱ ነገ​ርን ከሚ​ና​ገር፥ ቀኛ​ቸ​ውም የዐ​መፃ ቀኝ ከሆነ፥ ከባ​ዕድ ልጆች እጅ አድ​ነኝ፥ አስ​ጥ​ለ​ኝም።</verse>
				<verse number="12">ልጆ​ቻ​ቸው በጐ​ል​ማ​ስ​ነ​ታ​ቸው እንደ አዲስ ተክል የሆኑ፥ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም እንደ እል​ፍኝ ያማ​ሩና ያጌጡ፤</verse>
				<verse number="13">ዕቃ ቤቶ​ቻ​ቸ​ውም በያ​ይ​ነቱ ዕቃ የተ​ሞሉ ናቸው፥ በጎ​ቻ​ቸ​ውም ብዙ የሚ​ወ​ልዱ፥ በመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ቸ​ውም የሚ​በዙ፥</verse>
				<verse number="14">ላሞ​ቻ​ቸ​ውም የሰቡ፤ ለቅ​ጥ​ራ​ቸ​ውም መፍ​ረስ የሌ​ለው፥ የሚ​ገ​ባ​ባ​ቸ​ውም የሌለ፥ በአ​ደ​ባ​ባ​ዮ​ቻ​ቸ​ውም ዋይታ የሌ​ለ​ባ​ቸው፤</verse>
				<verse number="15">እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ሕዝብ አመ​ስ​ግ​ኑት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኩ የሆነ ሕዝብ ብፁዕ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="144">
				<verse number="1">አም​ላኬ ንጉሤ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፥ ስም​ህ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዓለም አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">በየ​ቀኑ ሁሉ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥ ለስ​ም​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዓለም ምስ​ጋና አቀ​ር​ባ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው፥ ምስ​ጋ​ና​ውም እጅግ ብዙ ነው፤ ለታ​ላ​ቅ​ነ​ቱም ዳርቻ የለ​ውም።</verse>
				<verse number="4">የልጅ ልጆች ሥራ​ህን ያደ​ን​ቃሉ፥ ኀይ​ል​ህ​ንም ይና​ገ​ራሉ፥</verse>
				<verse number="5">የቅ​ድ​ስ​ና​ህ​ንም ክብር ታላ​ቅ​ነት ይና​ገ​ራሉ፥ ተአ​ም​ራ​ት​ህ​ንም ያስ​ረ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="6">“ኀይ​ልህ ግሩም ነው” ይላሉ፥ ግር​ማ​ህ​ንም ይነ​ጋ​ገ​ራሉ፥ ብር​ታ​ት​ህ​ንም ያስ​ረ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="7">የቸ​ር​ነ​ት​ህን ብዛት መታ​ሰ​ቢያ ይና​ገ​ራሉ፥ በጽ​ድ​ቅ​ህም ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋሉ።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ባይና መሓሪ ነው፥ መዐቱ የራቀ፥ ምሕ​ረቱ የበዛ እው​ነ​ተኛ ነው፤</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ታ​ገ​ሡት ቸር ነው። ይቅ​ር​ታ​ውም በሥ​ራው ሁሉ ላይ ነው።</verse>
				<verse number="10">አቤቱ፥ ፍጥ​ረ​ትህ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፥ ጻድ​ቃ​ን​ህም ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል።</verse>
				<verse number="11">“ለመ​ን​ግ​ሥ​ትህ ክብር ይገ​ባል” ይላሉ፥ ኀይ​ል​ህ​ንም ይነ​ጋ​ገ​ራሉ፥</verse>
				<verse number="12">ለሰው ልጆች ኀይ​ል​ህን የመ​ን​ግ​ሥ​ት​ህ​ንም ክብር ታላ​ቅ​ነት ያስ​ታ​ውቁ ዘንድ።</verse>
				<verse number="13">መን​ግ​ሥ​ትህ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሁሉ መን​ግ​ሥት ናት፥ ግዛ​ት​ህም ለልጅ ልጅ ነው።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቃሉ ሁሉ የታ​መነ ነው፥ በሥ​ራ​ውም ሁሉ ጻድቅ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ፍ​ገ​መ​ገ​ሙ​ትን ሁሉ ይደ​ግ​ፋ​ቸ​ዋል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የወ​ደ​ቁ​ትን ያነ​ሣ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="15">የሰው ሁሉ ዐይን አን​ተን ተስፋ ያደ​ር​ጋል፤ አን​ተም ምግ​ባ​ቸ​ውን በየ​ጊ​ዜው ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="16">ቀኝ እጅ​ህን ትዘ​ረ​ጋ​ለህ፤ በሥ​ር​ዐ​ትህ ለሚ​ኖሩ እን​ስሳ ሁሉ ታጠ​ግ​ባ​ለህ።</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ን​ገዱ ሁሉ ጻድቅ ነው በሥ​ራ​ውም ሁሉ ቸር ነው።</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ጠ​ሩት ሁሉ፥ በእ​ው​ነት ለሚ​ጠ​ሩት ሁሉ ቅርብ ነው።</verse>
				<verse number="19">ለሚ​ፈ​ሩት ፈቃ​ዳ​ቸ​ውን ያደ​ር​ጋል፥ ልመ​ና​ቸ​ው​ንም ይሰ​ማል፥ ያድ​ና​ቸ​ዋ​ልም።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ወ​ድ​ዱ​ትን ሁሉ ይጠ​ብ​ቃል፤ ኀጢ​አ​ተ​ኞ​ች​ንም ሁሉ ያጠ​ፋል።</verse>
				<verse number="21">አፌ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ጋና ይና​ገ​ራል፤ ሥጋም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዓለም የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ስሙን ያመ​ሰ​ግ​ናል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="145">
				<verse number="1">ነፍሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለች።</verse>
				<verse number="2">በሕ​ይ​ወቴ ሳለሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ፤ በም​ኖ​ር​በት ዘመን መጠን ለአ​ም​ላኬ እዘ​ም​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">ማዳን በማ​ይ​ችሉ በአ​ለ​ቆ​ችና በሰው ልጆች አት​ታ​መኑ።</verse>
				<verse number="4">ነፍ​ሳ​ቸው ትወ​ጣ​ለች፥ ወደ መሬ​ትም ይመ​ለ​ሳሉ፤ ያን​ጊዜ ምክ​ራ​ቸው ሁሉ ይጠ​ፋል።</verse>
				<verse number="5">የያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ ረዳቱ የሆነ፥ መታ​መ​ኛ​ውም በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆነ ሰው ብፁዕ ነው።</verse>
				<verse number="6">እር​ሱም ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ባሕ​ር​ንም፥ በእ​ነ​ርሱ ውስጥ ያለ​ው​ንም ሁሉ የፈ​ጠረ፤ እው​ነ​ትን ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ጠ​ብቅ፤</verse>
				<verse number="7">ለተ​በ​ደ​ሉ​ትም የሚ​ፈ​ር​ድ​ላ​ቸው፥ ለተ​ራቡ ምግ​ብን የሚ​ሰጥ ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​ሰ​ሩ​ትን ይፈ​ታ​ቸ​ዋል፤</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የወ​ደ​ቁ​ትን ያነ​ሣ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዕው​ሮ​ችን ጥበ​በ​ኞች ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድ​ቃ​ንን ይወ​ድ​ዳ​ቸ​ዋል፤</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስደ​ተ​ኞ​ችን ይጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋል፤ ድሃ አደ​ጎ​ች​ንና ባል​ቴ​ቶ​ችን ይቀ​በ​ላ​ቸ​ዋል፤ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም መን​ገድ ያጠ​ፋል።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይነ​ግ​ሣል፤ ጽዮን ሆይ፥ አም​ላ​ክሽ ለልጅ ልጅ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="146">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፥ መዝ​ሙር መል​ካም ነውና። ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም ምስ​ጋና ማቅ​ረብ ያማረ ነው።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ይሠ​ራ​ታል፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የተ​በ​ተ​ኑ​ትን ይሰ​በ​ስ​ባል።</verse>
				<verse number="3">ልባ​ቸው የቈ​ሰ​ለ​ውን ይፈ​ው​ሳል፥ ቍስ​ላ​ቸ​ው​ንም ያደ​ር​ቅ​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="4">ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም በሙሉ ይቈ​ጥ​ራ​ቸ​ዋል፥ ሁሉ​ንም በየ​ስ​ማ​ቸው ይጠ​ራ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው፥ ኀይ​ሉም ታላቅ ነው፥ ለጥ​በ​ቡም ቍጥር የለ​ውም።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዋ​ሃ​ንን ያነ​ሣ​ቸ​ዋል፥ ኃጥ​አ​ንን ግን እስከ ምድር ድረስ ያዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ስ​ጋና ዘምሩ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በመ​ሰ​ንቆ ዘምሩ፤</verse>
				<verse number="8">ሰማ​ዩን በደ​መ​ናት የሚ​ሸ​ፍን፥ ለም​ድ​ርም ዝና​ምን የሚ​ያ​ዘ​ጋጅ፥ ሣርን በተ​ራ​ሮች ላይ፥ ልም​ላ​ሜ​ው​ንም ለሰው ልጆች አገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ያ​በ​ቅል፥</verse>
				<verse number="9">ለእ​ን​ስ​ሶ​ችና ለሚ​ጠ​ሩት ለቍ​ራ​ዎች ጫጩ​ቶች፥ ምግ​ባ​ቸ​ውን የሚ​ሰ​ጣ​ቸው እርሱ ነው።</verse>
				<verse number="10">የፈ​ረ​ስን ኀይል አይ​ወ​ድ​ድም፥ በሰ​ውም ጕል​በት ደስ አይ​ለ​ውም።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ፈ​ሩት፥ በም​ሕ​ረ​ቱም በሚ​ታ​መኑ ደስ ይለ​ዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="147">
				<verse number="1">ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኚ፥</verse>
				<verse number="2">ጽዮ​ንም ሆይ፥ አም​ላ​ክ​ሽን አመ​ስ​ግኚ፤ የደ​ጆ​ች​ሽን መወ​ር​ወ​ሪያ አጽ​ን​ቶ​አ​ልና፥ ልጆ​ች​ሽ​ንም በው​ስ​ጥሽ ባር​ኮ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="3">ለወ​ሰ​ኖ​ች​ሽም ሰላ​ምን አደ​ረገ፥ የስ​ን​ዴ​ንም ስብ አጠ​ገ​በሽ።</verse>
				<verse number="4">ቃሉን ወደ ምድር ይል​ካል፥ ነገ​ሩም እጅግ ፈጥኖ ይሮ​ጣል።</verse>
				<verse number="5">በረ​ዶ​ውን እንደ ባዘቶ ይሰ​ጣል፤ ጉሙን እንደ አመድ ይበ​ት​ነ​ዋል፤</verse>
				<verse number="6">በረ​ዶ​ውን እንደ ፍር​ፋሪ ያወ​ር​ዳል፤ ቅዝ​ቃ​ዜ​ው​ንስ ማን ይቋ​ቋ​ማል?</verse>
				<verse number="7">ቃሉን ልኮ ያቀ​ል​ጠ​ዋል፤ ነፋ​ሱን ያነ​ፍ​ሳል፥ ውኆ​ች​ንም ያፈ​ስ​ሳል።</verse>
				<verse number="8">ቃሉን ለያ​ዕ​ቆብ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንና ፍር​ዱ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ይና​ገ​ራል።</verse>
				<verse number="9">ለሌ​ሎች አሕ​ዛብ ሁሉ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ገም፥ ፍር​ዱ​ንም አል​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="148">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከሰ​ማ​ያት አመ​ስ​ግ​ኑት፤ በአ​ር​ያም ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤</verse>
				<verse number="2">መላ​እ​ክቱ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤ ሠራ​ዊቱ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።</verse>
				<verse number="3">ፀሐ​ይና ጨረቃ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤ ከዋ​ክ​ብ​ትና ብር​ሃን ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።</verse>
				<verse number="4">ሰማየ ሰማ​ያት፥ ከሰ​ማ​ያት በላይ ያለ ውኃም ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።</verse>
				<verse number="5">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ያመ​ሰ​ግ​ናሉ። እርሱ ብሎ​አ​ልና፥ ሆኑ፤ እርሱ አዝ​ዞ​አ​ልና፥ ተፈ​ጠሩ፤</verse>
				<verse number="6">ለዘ​ለ​ዓ​ለም አቆ​ማ​ቸው፤ ትእ​ዛ​ዝን ሰጣ​ቸው፥ አላ​ለ​ፉ​ምም።</verse>
				<verse number="7">እባ​ቦ​ችና ጥል​ቆች ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከም​ድር አመ​ስ​ግ​ኑት፤</verse>
				<verse number="8">እሳ​ትና በረዶ፥ አመ​ዳ​ይና ውርጭ፥ ቃሉን የሚ​ያ​ደ​ርግ ዐውሎ ነፋ​ስም፤</verse>
				<verse number="9">ተራ​ሮ​ችና ኮረ​ብ​ቶ​ችም ሁሉ፥ የሚ​ያ​ፈ​ራም ዛፍ ዝግ​ባም ሁሉ፤</verse>
				<verse number="10">አራ​ዊ​ትም፥ እን​ስ​ሳ​ትም ሁሉ፥ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችም፥ የሚ​በ​ርሩ ወፎ​ችም፤</verse>
				<verse number="11">የም​ድር ነገ​ሥ​ታት፥ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ፥ አለ​ቆች፥ የም​ድ​ርም ፈራ​ጆች ሁሉ፤</verse>
				<verse number="12">ጐል​ማ​ሶ​ችና ደና​ግል፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ልጆች፤</verse>
				<verse number="13">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ያመ​ሰ​ግ​ናሉ። ስሙ ብቻ​ውን ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፥ በሰ​ማ​ይና በም​ድር ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።</verse>
				<verse number="14">የሕ​ዝ​ቡ​ንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋል፤ የጻ​ድ​ቃ​ኑ​ንም ሁሉ ምስ​ጋና ወደ እርሱ ለቀ​ረበ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="149">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አዲስ ምስ​ጋ​ናን አመ​ስ​ግ​ኑት፤ ምስ​ጋ​ና​ውም በጻ​ድ​ቃኑ ጉባኤ ነው።</verse>
				<verse number="2">እስ​ራ​ኤል በፈ​ጣ​ሪው ደስ ይለ​ዋል፥ የጽ​ዮ​ንም ልጆች በን​ጉ​ሣ​ቸው ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋሉ።</verse>
				<verse number="3">ስሙን በደ​ስታ ያመ​ሰ​ግ​ናሉ፥ በከ​በ​ሮና በበ​ገና ይዘ​ም​ሩ​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ደስ ብሎ​ታ​ልና፥ የዋ​ሃ​ን​ንም በማ​ዳኑ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋ​ልና።</verse>
				<verse number="5">ጻድ​ቃን በክ​ብሩ ይመ​ካሉ፤ በመ​ኝ​ታ​ቸ​ውም ላይ ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋሉ።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በጕ​ሮ​ሮ​አ​ቸው ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤ ሁለት አፍ ያለ​ውም ሰይፍ በእጁ ነው፥</verse>
				<verse number="7">በአ​ሕ​ዛብ ላይ በቀ​ልን ያደ​ርግ ዘንድ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ይዘ​ል​ፋ​ቸው ዘንድ፤</verse>
				<verse number="8">ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ግር ብረት፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በሰ​ን​ሰ​ለት ያስ​ራ​ቸው ዘንድ፤</verse>
				<verse number="9">የተ​ጻ​ፈ​ውን ፍርድ በእ​ነ​ርሱ ላይ ያደ​ርግ ዘንድ። ይህች ክብር ለጻ​ድ​ቃኑ ሁሉ ናት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="150">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በተ​ቀ​ደሱ ቦታ​ዎች አመ​ስ​ግ​ኑት፤ በኀ​ይሉ ጽናት አመ​ስ​ግ​ኑት።</verse>
				<verse number="2">በከ​ሃ​ሊ​ነቱ አመ​ስ​ግ​ኑት፤ እንደ ታላ​ቅ​ነቱ ብዛት አመ​ስ​ግ​ኑት።</verse>
				<verse number="3">በመ​ለ​ከት ድምፅ አመ​ስ​ግ​ኑት፤ በበ​ገ​ናና በመ​ሰ​ንቆ አመ​ስ​ግ​ኑት፤</verse>
				<verse number="4">በከ​በ​ሮና በሽ​ብ​ሸባ አመ​ስ​ግ​ኑት፤ አው​ታር በአ​ለው መሣ​ሪ​ያና በእ​ን​ዚራ አመ​ስ​ግ​ኑት።</verse>
				<verse number="5">ድምፁ መል​ካም በሆነ ጸና​ጽል አመ​ስ​ግ​ኑት፤ በጸ​ና​ጽ​ልና በእ​ል​ልታ አመ​ስ​ግ​ኑት።</verse>
				<verse number="6">እስ​ት​ን​ፋስ ያለው ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ስ​ግ​ነው። ሃሌ ሉያ።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="20">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">ለእስራኤል የነገሠ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን ምሳሌዎች፤</verse>
				<verse number="2">ጥበብንና ተግሣጽን ለማወቅ፥ የጥበብንም ቃል ለማወቅ፥</verse>
				<verse number="3">የቃልን መልስ ለመቀበል በእውነት ጽድቅንም ለማወቅ ፍርድንም ለማቃናት፥</verse>
				<verse number="4">ብልሃትን ለየውሃን ይሰጥ ዘንድ ለሕፃናትና ለወጣቶችም አእምሮንና ዕውቀትን፥</verse>
				<verse number="5">ጠቢብ እነዚህን በመስማት ጥበብን ይጨምራል፥ አስተዋይ ግን ምክርን ገንዘብ ያደርጋል።</verse>
				<verse number="6">ምሳሌንና የተሸሸገውን ነገር፥ የጠቢባንን ቃልና ዕንቈቅልሾችን ያውቃል።</verse>
				<verse number="7">የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ዕውቀት ለሚያደርጋት ሁሉ መልካም ናት። እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፥ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።</verse>
				<verse number="8">ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናትህንም ትእዛዝ ቸል አትበል፤</verse>
				<verse number="9">ለራስህ የክብር ዘውድን ለአንገትህም የወርቅ ድሪ ታገኛለህና።</verse>
				<verse number="10">ልጄ ሆይ፥ ዝንጉዎች ሰዎች አያስቱህ፤ እሽም አትበላቸው።</verse>
				<verse number="11">“ና ከእኛ ጋር ደምን በማፍሰስ አንድ ሁን፥ ጻድቅ ሰውንም በምድር እንቅበር፥ ብለው ቢማልዱህ፥</verse>
				<verse number="12">በሕይወት ሳለ እንደ ሲኦል እንዋጠው፥ መታሰቢያውንም ከምድር እናጥፋ፤</verse>
				<verse number="13">ብዙ ሀብቱን እንሰብስብ፥ ከምርኮውም ቤታችንን እንሙላ፤</verse>
				<verse number="14">ዕጣህን ከእኛ ጋር ጣል፤ ለሁላችንም አንድ ከረጢትና አንድ አቁማዳ ይሁንልን” ቢሉ፥</verse>
				<verse number="15">ልጄ ሆይ፥ ከእነርሱ ጋር በመንገድ አትሂድ፥ ከጎዳናቸውም እግርህን ፈቀቅ አድርግ፤</verse>
				<verse number="16">እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉና፥ ደም ለማፍሰስም ይፈጥናሉና።</verse>
				<verse number="17">ወጥመድን ለወፎች በከንቱ የሚያጠምዱ አይደለምና፥</verse>
				<verse number="18">መግደልን የለመዱ እነርሱ ክፋትን ለራሳቸው ይሰበስባሉ። የኀጢአተኞች ሰዎች አወዳደቃቸው ክፉ ነው።</verse>
				<verse number="19">ይህ መንገድ ኀጢአትን የሚፈጽሙ ሁሉ ነው። ቅሚያ ነፍሳቸውን ታጠፋለች።</verse>
				<verse number="20">ጥበብ በጎዳና ትመሰገናለች፤ በአደባባይም ድምፅዋን ትሰጣለች።</verse>
				<verse number="21">በግንብ ድምድማት ትሰብካለች፥ በኀያላን በሮች ታገለግላለች። በከተማ በሮች በድፍረት እንዲህ ትላለች፦</verse>
				<verse number="22">“ይህን ያህል ዘመን የዋሃን ጽድቅን ሲከተሉ አያፍሩም። ሰነፎች፥ እስከ መቼ ድረስ ስሕተትን ትወዳላችሁ? ሰነፎች ስድብን የሚወዱ ናቸው፥ ሰነፎችም ሆነው ዕውቀትን ጠሉ። ለሚዘልፏቸው የተመቹ ሆኑ፤</verse>
				<verse number="23">እነሆ፥ የቃሌን መንፈስ እነግራችኋለሁ፤ ቃሌንም አስተምራችኋለሁ።</verse>
				<verse number="24">በጠራሁ ጊዜ አልሰማችሁኝምና እጄን ዘረጋሁ፥ ማንም አላስተዋለም ነገርንም አበዛሁ፥ አልመለሳችሁልኝም፥</verse>
				<verse number="25">“ምክሬን ሁሉ ናቃችሁ፥ ዘለፋዬንም አልተመለከታችሁም፥</verse>
				<verse number="26">ስለዚህ እኔ በጥፋታችሁ እሥቃለሁ፤ ጥፋትም በመጣባችሁ ጊዜ ደስ ይለኛል።</verse>
				<verse number="27">ጭቅጭቅ ድንገት በመጣባችሁ ጊዜ፥ እንደዚሁም ጥፋታችሁ እንደ ዓውሎ ነፋስ በመጣባችሁ ጊዜ፥ ችግርና ምርኮ በደረሰባችሁ ጊዜ፥ እኔ ከዚያ አለሁ።</verse>
				<verse number="28">ግን በጠራችሁኝ ጊዜ እኔ አልሰማችሁም፤ ክፉዎች ይሹኛል፥ ነገር ግን አያገኙኝም።</verse>
				<verse number="29">ዕውቀትን ጠልተዋልና፥ እግዚአብሔርንም መፍራትን አልመረጡምና።</verse>
				<verse number="30">ምክሬን ይመለከቱ ዘንድ አልፈቀዱምና፥ ዘለፋዬንም ሁሉ ንቀዋልና፤</verse>
				<verse number="31">ስለዚህ የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉ፥ በራሳቸውም ኀጢአት ይጠግባሉ።</verse>
				<verse number="32">አላዋቂዎችን አለመመለሳቸው ትገድላቸዋለችና፥ ሰነፎችንም ምርመራቸው ትገድላቸዋለች።</verse>
				<verse number="33">የሚሰማኝ ግን በተስፋ ይኖራል፥ ከክፉም ሁሉ ያለ ድንጋጤ ያርፋል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ብትቀበል፥ ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት፥</verse>
				<verse number="2">ጆሮህ ጥበብን ትሰማለች፥ ልብህንም ወደ ማስተዋል ታዘነብላለህ። ልብህንም ልጅህን ለመምከር ታቀርባለህ፥</verse>
				<verse number="3">ጥበብን ብትጠራት፥ ቃልህንም ለማስተዋል ብትሰጥ፥ ዕውቀትንም በታላቅ ቃል ብትፈልጋት፥</verse>
				<verse number="4">እርስዋንም እንደ ብር ብትፈልጋት፥ እርስዋንም እንደ ተቀበረ ገንዘብ ብትሻት፤</verse>
				<verse number="5">የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፥ አምላክን ማወቅንም ታገኛለህ።</verse>
				<verse number="6">እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከፊቱም ዕውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ፤</verse>
				<verse number="7">እርሱ ቅንነትን ለሚያደርጉ ደኅንነትን ያከማቻል፤ በመንገዳቸውም ይቆምላቸዋል።</verse>
				<verse number="8">የጽድቅን ጎዳና ይጠብቃል፤ የሚፈሩትንም መንገድ ያጸናል።</verse>
				<verse number="9">የዚያን ጊዜ ጽድቅንና ፍርድን ታውቃለህ፤ መልካም መንገድንም ሁሉ ታቃናለህ።</verse>
				<verse number="10">ጥበብ ወደ ልብህ በመጣች ጊዜ፥ ዕውቀትም ለነፍስህ መልካምና ክብር በሆነች ጊዜ፥</verse>
				<verse number="11">መልካም ምክር ትጠብቅሃለች፤ የተቀደሰች ማስተዋልም ትጋርድሃለች።</verse>
				<verse number="12">አንተን ከክፉ መንገድ፥ ምንም የሚታመን ነገርን ከማይናገር ሰውም ታድንህ ዘንድ፥</verse>
				<verse number="13">እነርሱ በጨለማ መንገድ ይሄዱ ዘንድ የቀናውን ጎዳና ለሚተዉ፥</verse>
				<verse number="14">ክፉ በመሥራት ደስ ለሚላቸው ክፋትንም በመመለስ ሐሤትን ለሚያደርጉ፥</verse>
				<verse number="15">መንገዳቸው ጐጻጕጽ፥ አካሄዳቸው ጠማማ ለሆኑ ወዮላቸው!</verse>
				<verse number="16">ከቀናች መንገድ እንዳያርቁህ፥ እውነትንም ከማወቅ የተለየህ እንዳያደርጉህ፤ ልጄ ሆይ፥ በሕፃንነትህ ትምህርትን የምታስተው፥ ክፉ ምክር አታግኝህ፤</verse>
				<verse number="17">ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ጠብቅ፥ ቃሏን ከምታለዝብ ከሌላዪቱ ክፉ ሴት፥ የሕፃንንነት ባልዋን ከምትተው፥ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ከምትረሳ፤ ይጠብቅህ ዘንድ፤</verse>
				<verse number="18">ቤቷን በሞት አጠገብ አኖረች፥ አካሄድዋንም ከኀያላን ጋር ከምድር ወደ ሲኦል አቀናች።</verse>
				<verse number="19">ወደ እርስዋ የሚገቡ ሁሉ አይመለሱም፥ ቀና መንገዶችንም አያገኙም፥ ሕይወት በአለው ዘመንም አይገኙም።</verse>
				<verse number="20">ቀና መንገዶችን ቢሄዱ ለስላሳ የጽድቅ መንገዶችን ባገኙ ነበር።</verse>
				<verse number="21">ደጋግ ሰዎች በምድር ላይ ይቀመጣሉ፥ ጻድቃንም በእርስዋ ይኖራሉ፤</verse>
				<verse number="22">የክፉዎች መንገዶች ከምድር ላይ ይጠፋሉ፤ ዓመፀኞችም ከእርስዋ ይሰደዳሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ልጄ ሆይ! ሕጎቼን አትርሳ፥ ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ።</verse>
				<verse number="2">ብዙ ዘመናትንና ረጅም ዕድሜን ሰላምንም ይጨምሩልሃልና።</verse>
				<verse number="3">ምጽዋትና ሃይማኖት ከአንተ አይራቁ፤ በአንገትህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላትም ጻፋቸው፤</verse>
				<verse number="4">ባላሟልነትን ታገኛለህና፥ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት መልካምን ዐስብ።</verse>
				<verse number="5">በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታምነህ ኑር፥ በራስህም ጥበብ አትደገፍ፤</verse>
				<verse number="6">በመንገድህ ሁሉ ጥበብን ዕወቃት፥ እርስዋም መንገድህን ታቃናልሃለች።</verse>
				<verse number="7">በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን፤ እግዚአብሔርን ፍራው፥ ከክፋትም ሁሉ ራቅ፤</verse>
				<verse number="8">ይህም ለሥጋህ ፈውስ፥ ለአጥንትህም ጠገን ይሆንልሃል።</verse>
				<verse number="9">እግዚአብሔርን በእውነት በአገኘኸው ሀብትህ አክብረው። ከእውነተኛ ፍሬህም ሁሉ ቀዳምያቱን አግባለት።</verse>
				<verse number="10">ጐተራህም እህልን ይሞላል። የወይን መጥመቂያህም ወይን ይሞላል።</verse>
				<verse number="11">ልጄ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ ቸል አትበል፥ በመገሠጹም ከእርሱ የተነሣ አትመረር።</verse>
				<verse number="12">አባት የሚወድደውን ልጁን እንደሚገሥጽ እግዚአብሔር የሚወድደውን ይገሥጻል፥ የሚቀበላቸውን ልጆቹን ይገርፋልና።</verse>
				<verse number="13">ጥበብን የሚያገኝ፥ ማስተዋልንም የሚያውቅ መዋቲ ሰው ብፁዕ ነው።</verse>
				<verse number="14">በወርቅና በብር፥ በብዙም መዛግብት ከመነገድ ይልቅ በእርስዋ መነገድ ይሻላልና።</verse>
				<verse number="15">ዋጋው ብዙ ከሆነ ዕንቍም የከበረች ናት። ክፉ ነገር አይቃወማትም፥ ለሚቀርቧትም መልካም ናት። ክብርም ሁሉ አይተካከላትም።</verse>
				<verse number="16">ረጅም ዕድሜና የሕይወት ዘመን በቀኝዋ ነው። ባለጠግነትና ክብርም በግራዋ፥ ከአፏ ጽድቅ ይወጣል። ሕግንና ምጽዋትንም በአንደበትWa ትለብሳለች።</verse>
				<verse number="17">መንገዶችዋ መልካም መንገዶች ናቸው። ጎዳናዋም ሁሉ ሰላም ነው።</verse>
				<verse number="18">እርስዋ ለሚመረኰዛት ሁሉ የሕይወት ዛፍ ናት፥ የሚታመኑባትም በእግዚአብሔር እንደ ጸና ሰው ናቸው።</verse>
				<verse number="19">እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሠረተ፥ በማስተዋልም ሰማያትን አዘጋጀ።</verse>
				<verse number="20">በዕውቀቱ ቀላያት መነጩ፥ ደመናትም ጠልን ያንጠባጥባሉ።</verse>
				<verse number="21">ልጄ ሆይ፥ ቸል አትበል ዐሳቤንና ምክሬን ጠብቅ፤</verse>
				<verse number="22">ነፍስህ ትድን ዘንድ፥ ለአንገትህም ሞገስ ይሆንህ ዘንድ። ለሥጋህ ፈውስ፥ ለአጥንትህም ጠገን ይሆንልሃል።</verse>
				<verse number="23">በመንገድህም ሁሉ በመተማመን ትሄዳለህ፥ እግሮችህም አይሰነካከሉም።</verse>
				<verse number="24">በተቀመጥህም ጊዜ አትፈራም፤ ብትተኛም መልካም እንቅልፍ ትተኛለህ።</verse>
				<verse number="25">ከሚመጣብህም አስደንጋጭ ነገር፥ ከሚመጣውም የክፉዎች ሰዎች አደጋ አትፈራም፤</verse>
				<verse number="26">እግዚአብሔር በመንገድህ ሁሉ ይኖራልና፥ እግሮችህም እንዳይነዋወጡ ያቆማቸዋልና።</verse>
				<verse number="27">ለተቸገረው ሰው በጎ ነገር ማድረግን ቸል አትበል፥ በእጅህ ያለውን ያህል ርዳው።</verse>
				<verse number="28">በጎ ነገርን ማድረግ ሲቻልህ፥ ወዳጅህን፦ “ሂድና ተመለስ፤ ነገ እሰጥሃለሁ” አትበለው፥ ነገ የምትወልደውን አታውቅምና።</verse>
				<verse number="29">እርሱ ተማምኖብህ ከአንተ ጋር ተቀምጦ ሳለ፥ እንደገና በወዳጅህ ላይ ክፉ አታስብ፤</verse>
				<verse number="30">እርሱ በላይህ የሠራው ክፉ ነገር ከሌለ፥ ከሰው ጋር በከንቱ አትጣላ።</verse>
				<verse number="31">ከክፉ ሰዎች ዘንድ ሽሙጥን ገንዘብ አታድርግ፥ በመንገዳቸውም አትቅና።</verse>
				<verse number="32">ኀጢአተኛ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና፤ ከጻድቃንም ጋር አንድ አይሆንም።</verse>
				<verse number="33">የእግዚአብሔር መርገም በክፉዎች ቤት ነው፥ በጻድቃን ቤት ግን በረከት አለ።</verse>
				<verse number="34">እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማቸዋል፤ ለትሑታን ግን ክብርን ይሰጣል።</verse>
				<verse number="35">ጠቢባን ክብርን ይወርሳሉ፤ ሰነፎች ግን ውርደታቸውን ከፍ ከፍ ያደርጋሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ልጆች ሆይ፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፤</verse>
				<verse number="2">መልካም ስጦታን እሰጣችኋለሁና፥ ሕጌን አትተዉ።</verse>
				<verse number="3">እኔም አባቴን የምሰማ ልጅ ነበርሁና፥ በእናቴም ፊት እወደድ ነበር።</verse>
				<verse number="4">ያስተምሩኝም ነበር፥ እንዲህም ይሉኝ ነበር፦ ቃላችን በልብህ ይኑር፤ ትእዛዞቻችንንም ጠብቅ፥ አትርሳቸውም።</verse>
				<verse number="5">የአፌንም ቃል ቸል አትበል።</verse>
				<verse number="6">አትተዋት፥ ትደግፍህማለች፤ ውደዳት፥ ትጠብቅህማለች።</verse>
				<verse number="7">ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ፤ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ።</verse>
				<verse number="8">ጠብቃት፥ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ አክብራት፥ እርስዋም ታቅፍሃለች።</verse>
				<verse number="9">ለራስህ የሞገስ አክሊልን ትሰጥሃለች፥ በደስታ አክሊልም ትጠብቅሃለች።</verse>
				<verse number="10">ልጄ ሆይ፥ ስማ፥ ንግግሬንም ተቀበል፤ የሕይወትህም ዓመታት ይበዙልሃል፥ የሕይወትህ መንገድ ይበዛ ዘንድ።</verse>
				<verse number="11">የጥበብን መንገዶች አስተምርሃለሁና፤ በቀናች ጎዳና መራሁህ።</verse>
				<verse number="12">ብትሄድ ፍለጋህ አይጠፋም፤ በሮጥህም ጊዜ አትሰናከልም።</verse>
				<verse number="13">ምክሬን ያዝ፥ አትተውም፤ ለራስህ ጠብቃት፥ እርሷ ሕይወትህ ናትና።</verse>
				<verse number="14">በክፉዎች መንገድ አትሂድ፥ በክፉ ሰዎችም ጎዳና አትቅና።</verse>
				<verse number="15">በተጓዙበትም ቦታ አትሂድ፤ ከእነርሱ ፈቀቅ በል ተመለስም።</verse>
				<verse number="16">ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፥ ከዐይናቸው እንቅልፋቸው ይወገዳል አይተኙምም።</verse>
				<verse number="17">የኀጢአት መብልን ይበላሉ፥ በግፍ የወይን ጠጅም ይሰክራሉ።</verse>
				<verse number="18">የጻድቃን መንገዶች ግን እንደ ብርሃን ይበራሉ። ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየጨመሩ ይበራሉ።</verse>
				<verse number="19">የኃጥኣን መንገዶች ግን ጨለማ ናቸው። እንዴት እንደሚሰናከሉም አያውቁም።</verse>
				<verse number="20">ልጄ ሆይ፥ ንግግሬን አድምጥ፤ ጆሮህንም ወደ ቃሌ አዘንብል።</verse>
				<verse number="21">ምንጮችህ እንዳይደርቁ፥ በልብህ ጠብቃቸው።</verse>
				<verse number="22">ለሚያገኙአቸው ሕይወት፥ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ናቸውና።</verse>
				<verse number="23">ልብህን አጥብቀህ ጠብቅ፥ የሕይወት መገኛ ከእርሱ ነውና።</verse>
				<verse number="24">ክፉ አፍን ከአንተ አርቅ፥ ሐሰተኞች ከንፈሮችንም ከአንተ አስወግድ።</verse>
				<verse number="25">ዐይኖችህም አቅንተው ይዩ፥ ሽፋሽፍቶችህም ወደ እውነት ያመልክቱ።</verse>
				<verse number="26">ለእግርህ ቀና መሄጃ ሥራ፥ መንገዶችህንም አቅና።</verse>
				<verse number="27">ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፤ እግርህንም ከመጥፎ መንገድ መልስ። እግዚአብሔር የቀኝ መንገዶችን ያውቃልና፥ የግራ መንገዶች ግን ጠማሞች ናቸው። እርሱም መሄጃህን የቀና ያደርጋል፥ አካሄድህንም በሰላም ያሳምራል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">ልጄ ሆይ፥ ጥበቤን ተመልከት፤ ጆሮህም ወደ ቃሌ ያድምጥ፥</verse>
				<verse number="2">መልካም ዐሳብን ትጠብቅ ዘንድ በከንፈሮቼ የማዝዝህን ዕወቅ።</verse>
				<verse number="3">ከአመንዝራ ሴት ከንፈር ማር ይንጠባጠባልና፥ ወደ አመንዝራ ሴት አትመልከት፥ ለጊዜው ጕሮሮህን ያጣፍጣል፥</verse>
				<verse number="4">ፍጻሜው ግን እንደ ሐሞት የመረረ ነው፥ ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ይልቅም የተሳለ ነው።</verse>
				<verse number="5">እግሮችዋም ወደ ስንፍና ይወርዳሉ፥ አረማመድዋም ወደ ሞትና ወደ ሲኦል ያደርሳል። ፍለጋዋ ከኀጢአት ቦታ አይርቅም፥</verse>
				<verse number="6">በሕይወት መንገድም አትሄድም። መሮጫዋ ሰንከልካላ ነው፥ የሚታወቅም አይደለም።</verse>
				<verse number="7">አሁንም ልጄ ሆይ፥ ስማኝ፥ ቃሌንም የተናቀ አታድርግ</verse>
				<verse number="8">መንገድህን ከእርስዋ አርቅ፥ ወደ ቤቷም ደጅ አትቅረብ፥</verse>
				<verse number="9">ሕይወትህን ለሌላ እንዳትሰጥ፥ ንብረትህንም ምሕረት ለሌላቸው፤</verse>
				<verse number="10">ባዕዳን በሀብትህ እንዳይጠግቡ፥ የድካምህም ፍሬ በባዕድ ሰው ቤት እንዳይገባ።</verse>
				<verse number="11">ሰውነትህ በደከመ ጊዜ፥ ኋላ ትጸጸታለህ፥</verse>
				<verse number="12">እንዲህም ትላለህ፦ “እንዴት ትምህርትን ጠላሁ! ልቤም ከተግሣጽ እንዴት ራቀ!</verse>
				<verse number="13">የአስተማሪዎቼንም ቃል አልሰማሁም፥ ጆሮዎቼንም ወደ አስተማሪዎቼ አላዘነበልሁም።</verse>
				<verse number="14">በማኅበርና በጉባኤ መካከል፥ ወደ ክፉ ሁሉ ለመድረስ ጥቂት ቀረኝ።”</verse>
				<verse number="15">ከማድጋህ ውኃ፥ ከምንጭህም የሚፈልቀውን ውኃ ጠጣ።</verse>
				<verse number="16">ከምንጮችህ ውኆች ወደ ሜዳ አይፍሰሱ። ውኃዎችም ወደ አደባባዮች አይሂዱ፥</verse>
				<verse number="17">ለአንተ ብቻ ይሁኑ፥ ከአንተ ጋር ላሉ እንግዶችም አይሁኑ።</verse>
				<verse number="18">የውኃ ምንጭህ ለአንተ ይሁንልህ፤ ከልጅነት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ።</verse>
				<verse number="19">በዋሊያና በውርንጭላ ፍቅር፥ ከሚስትህ ጋር ተፋቀር፥ የፍቅርዋ ሞገስ ያርካህ፥ ለአንተ ትሁንህ፥ ሁልጊዜም ከአንተ ጋር ትኑር፤ በዚች ፍቅር ስትፋቀር ብዙ ትሆናለህ።</verse>
				<verse number="20">ልጄ ሆይ፥ ከሌላዪቱ ሴት ጋር አትኑር፤ የአንተ ወዳልሆነችውም እጅህን አትዘርጋ።</verse>
				<verse number="21">የሰው መንገድ በእግዚአብሔር ዐይኖች ፊት ነውና፥ አካሄዱንም ሁሉ እርሱ ይመለከታልና።</verse>
				<verse number="22">ኀጢአት ሰውን ያጠምዳል፥ ሁሉም በኀጢአቱ ልባብ ይታሰራል።</verse>
				<verse number="23">እርሱ ከሰነፎች ጋር ይሞታል፤ ከስንፍናውም ብዛት የተነሣ ሕይወቱ ይጣላል፤ ስለ ስንፍናውም ይጠፋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">ልጄ ሆይ፥ ለወዳጅህ ዋስ ብትሆን፥ እጅህን ለባላጋራህ ትሰጣለህ፤</verse>
				<verse number="2">የሰው ከንፈሩ ጽኑ ወጥመድ ነው፤ በአፉ ቃል ይጠፋል።</verse>
				<verse number="3">ልጄ ሆይ፥ እኔ የማዝዝህን አድርግ፤ ራስህንም አድን፤ ስለ ወዳጅህ በክፉዎች እጅ ወድቀሃልና፤ ሰነፍ አትሁን፥ የተዋስኸውን ወዳጅህን አነሣሣው።</verse>
				<verse number="4">ለዐይንህ እንቅልፍን፥ ለሽፋሽፍቶችህም ሸለብታን አትስጥ፤</verse>
				<verse number="5">እንደ ሚዳቋ ከወጥመድ፥ እንደ ወፍም ከጭራ ወጥመድ ትድን ዘንድ።</verse>
				<verse number="6">አንተ ታካች፥ ወደ ገብረ ጕንዳን ሂድ፥ መንገዱንም ተመልክተህ ቅና። ከእርሱም ይልቅ ብልህ ሁን።</verse>
				<verse number="7">ጌታ ሳይኖረው፥ መሰማርያ ሳይኖረው፥ የሚያሠራውም ሳይኖረው፥</verse>
				<verse number="8">መብሉን በበጋ ይሰበስባል፥ በመከርም ጊዜ በሰፊ ቦታ ያስቀምጣል። ወይም ወደ ንብ ሂድ፥ ሠራተኛ እንደ ሆነች፥ መልካም ሥራንም እንደምትሠራ ዕወቅ፥ የደከመችበትንም ነገሥታትና ሌሎች ሰዎች ለጤንነት ይወስዱታል። በሁሉም ዘንድ የተወደደች ናት፥ የከበረችም ናት። በአካሏ ደካማ ናት፥ በሥራዋ ግን የጸናች ናት፥ ጥበብን አክብራ አሳየች።</verse>
				<verse number="9">አንተ ታካች እስከ መቼ ትተኛለህ? ከእንቅልፍህስ መቼ ትነሣለህ?</verse>
				<verse number="10">ጥቂት ትተኛለህ፥ ጥቂትም ትቀመጣለህ፥ ጥቂት ታሸልባለህ፥ ጥቂትም እጆችህን በደረትህ ታጥፋለህ፤</verse>
				<verse number="11">እንግዲህ ድህነት እንደ ክፉ መልእክተኛ፥ ችግርም እንደ ደኅና ርዋጭ ይመጣብሃል። ሰነፍ ባትሆን ግን ባለጸግነትህ እንደምንጭ ይመጣልሃል፤ ችግርም እንደ ክፉ ርዋጭ ከአንተ ይርቃል።</verse>
				<verse number="12">ዓመፀኛና ሰነፍ የሆነ ሰው ቀና ያልሆኑ መንገዶችን ይሄዳል፤</verse>
				<verse number="13">በዐይኑ ይጠቅሳል፥ በእግሩ ይናገራል፥ በጣቱ ጥቅሻ ያመለክታል፤</verse>
				<verse number="14">ጠማማ ልቡ ሁልጊዜ ክፋትን ያስባል፤ እንደዚህም ያለ ሰው ጠብን በከተማ ላይ ይዘራል።</verse>
				<verse number="15">ስለዚህ የማይድን ውድቀትና መመታት፥ ጥፋትም ድንገት ይደርስበታል፤ እግዚአብሔር በሚጠላቸው ሁሉ ደስ ይለዋልና፤ ስለ ነፍሱ ርኵሰትም ይደቅቃልና፥</verse>
				<verse number="16">እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ናቸው፥ ሰባተኛውንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤</verse>
				<verse number="17">ትዕቢተኛ ዐይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ የጻድቁን ደም የምታፈስስ እጅ፥</verse>
				<verse number="18">ክፉ ዐሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ክፉዉን ለማድረግ ወዲህና ወዲያ የምትሮጥ እግር፥</verse>
				<verse number="19">ሐሰተኛ ምስክርን የሚያቀጣጥል፥ በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።</verse>
				<verse number="20">ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ሕጎች ጠብቅ፥ የእናትህንም ትእዛዝ ቸል አትበል፤</verse>
				<verse number="21">ሁልጊዜ በልብህ አኑረው፥ በአንገትህም እሰረው።</verse>
				<verse number="22">ስትሄድም ይመራሃል፤ ከአንተም ጋር ይኖር ዘንድ ውሰደው። ስትተኛ ይጠብቅሃል፤ ስትነሣም ያነጋግርሃል።</verse>
				<verse number="23">ትእዛዝ መብራት፥ ሕግም ብርሃን ነውና፥ ትምህርትና ተግሣጽም የሕይወት መንገድ ነውና፥</verse>
				<verse number="24">ከጐልማሳ ሚስት፥ ከሌላዪቱም አንደበት ነገረ ሠሪነት ትጠብቅህ ዘንድ ትእዛዜን ጠብቅ፥</verse>
				<verse number="25">ውበቷ ድል አይንሣህ። በዐይኖችዋ አትጠመድ፥ በቅንድቧም አትማረክ።</verse>
				<verse number="26">የአመንዝራ ሴት ክብር እስከ አንዲት እንጀራ ነው፤ አመንዝራ ሴትም የተከበሩ ወንዶች ነፍስን ታጠምዳለች።</verse>
				<verse number="27">በጕያው እሳትን የሚታቀፍ፥ ልብሶቹስ የማይቃጠሉ ማን ነው?</verse>
				<verse number="28">ወይም በፍም ላይ የሚሄድ፥ እግሮቹስ የማይቃጠሉ ማን ነው?</verse>
				<verse number="29">ወደ ጐልማሳ ሚስት የሚገባም እንዲሁ ነው፤ የሚነካትም ሁሉ አይነጻም።</verse>
				<verse number="30">የሚሰርቅ ሌባ ቢያዝ የሚደንቅ አይደለም፥ የተራበች ነፍሱን ሊያጠግብ ይሰርቃልና፤</verse>
				<verse number="31">ቢያዝም ሰባት እጥፍ ይከፍላል፥ ነፍሱንም ያድን ዘንድ ገንዘቡን ሁሉ ይሰጣል።</verse>
				<verse number="32">አመንዝራ ግን በአእምሮው ጉድለት፥ ነፍሱ የሚጠፋበትን ጥፋት ይሠራል።</verse>
				<verse number="33">ቍስልንና ውርደትን ያገኛል፥ ስድቡም ለዘለዓለም አይደመሰስም።</verse>
				<verse number="34">ባሏ ቅንዐትንና ቍጣን የተመላ ነውና፥ በፍርድ ቀን አይራራለትም።</verse>
				<verse number="35">የጠብ ካሣ በምንም አይለወጥም፥ በገንዘብ ብዛትም አይታረቀውም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ጠብቅ፥ ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽግ።</verse>
				<verse number="2">ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔርን አክብረው ትጸናለህም። ከእርሱ በቀር ሌላውን አትፍራ፥ ከእርሱ በቀር የሚገድልህም የሚያድንህም የለምና። ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ፤ ቃሌንም እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቅ፤</verse>
				<verse number="3">በጣቶችህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላትም ጻፋቸው።</verse>
				<verse number="4">ጥበብን፦ “አንቺ እኅቴ ነሽ” በላት፥ ማስተዋልንም፦ “ወዳጄ” ብለህ ጥራት፥</verse>
				<verse number="5">ከባዕድና ከክፉ ሴት ዋዛ ነገርንም ከምታመጣብህ ትጠብቅህ ዘንድ።</verse>
				<verse number="6">በቤትWa መስኮት ሆና ወደ ዐደባባይ ትመለከታለችና፤</verse>
				<verse number="7">ከአላዋቂዎች ወጣቶች መካከል ከዕውቅት ድሃ የሆነውን ጐልማሳ ብታይ፥</verse>
				<verse number="8">በቤቷም አቅራቢያ ባለው መንገድ ሲሄድ ሲናገርም፤</verse>
				<verse number="9">ማታ ሲመሽ፥ ውድቅትም ሲሆን፥ በሌሊት በጽኑ ጨለማ፥</verse>
				<verse number="10">የምንዝር ጌጥ ያላት የጐልማሶችን ልብ እንዲሰቀል የምታደርግ ሴት ያንጊዜ ትገናኘዋለች። እርስዋ የምትበርር መዳራትንም የምትወድ ናት።</verse>
				<verse number="11">ሁከተኛና አበያ ናት፥ እግሮችዋም በቤቷ አያርፉም፥</verse>
				<verse number="12">አንድ ጊዜ በጎዳና፥ በሌላ ጊዜም በአደባባይ፥ በማዕዘኑም ሁሉ ታደባለች።</verse>
				<verse number="13">ያዘችውም ሳመችውም፤ ፊቷም ያለ እፍረት ሆኖ እንዲህ አለችው፦</verse>
				<verse number="14">“የፍቅሬ መሥዋዕት ነው፤ ዛሬ ስእለቴን እሰጣለሁ።</verse>
				<verse number="15">ስለዚህ እንድገናኝህ መጣሁ፥ ፊትህንም ለማየት ስሻ አገኘሁህ።</verse>
				<verse number="16">በአልጋዬ ላይ ማለፊያ ሰርፍ ዘርግቼበታለሁ፥ የግብፅንም ሸመልመሌ ምንጣፍ።</verse>
				<verse number="17">በመኝታዬ ከርቤንና ዓልሙን ቀረፋም ረጭቼበታለሁ።</verse>
				<verse number="18">ና፥ እስኪነጋ ድረስ በፍቅር እንርካ። በመልካም መተቃቀፍም ደስ ይበለን።</verse>
				<verse number="19">ባለቤቴ በቤቱ የለምና፥ ወደ ሩቅ መንገድ ሄዶአልና፤</verse>
				<verse number="20">በእጁም የወርቅ ከረጢት ይዞአል፤ ወደ ቤቱ ቢመለስም ከብዙ ጊዜ በኋላ ነው።”</verse>
				<verse number="21">በብዙ ጨዋታዋ እንዲስት ታደርገዋለች፤ በከንፈርዋ ወጥመድም ትጐትተዋለች።</verse>
				<verse number="22">እርሱ አንገቱን ደፍቶ ይከተላታል፥ ለመታረድ እንደሚነዳ በሬ፥ ወደ እስራት እንደሚሄድ ውሻ፥ ሆዱ እንደ ተወጋ ዋሊያ፥</verse>
				<verse number="23">ወደ ወጥመድ እንደሚቸኩል ዎፍ፥ ሳያውቅም ለነፍሱ ጥፋት እንደሚሮጥ።</verse>
				<verse number="24">ልጄ ሆይ፥ አሁን እንግዲህ ስማኝ፥ ወደ አፌ ቃል አድምጥ።</verse>
				<verse number="25">ልብህ ወደ መንገድዋ አያዘንብል፤ በጎዳናዋ አትሳት።</verse>
				<verse number="26">ብዙዎችን ወግታ አስታለች፤ እርስዋም የገደለቻቸው ቍጥር የላቸውም።</verse>
				<verse number="27">ቤቷ ወደ ሞት ጓዳ የሚያወርድ የሲኦል መንገድ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">አንተስ ጥበብን አስተምር፥ ማስተዋል ትመልስልህ ዘንድ፤</verse>
				<verse number="2">በተራሮች ጫፍ ላይ ናትና፥ በጎዳና መካከልም ትቆማለች።</verse>
				<verse number="3">በኀያላን በሮች ትጠብቃለች፥ በመግቢያዉም ትመሰገናለች፥</verse>
				<verse number="4">እናንተ ሰዎች እናንተን እለምናለሁ፥ ቃሌንም ለሰዎች ልጆች እናገራለሁ።</verse>
				<verse number="5">እናንተ የዋሆች፥ ጥበብን አስተውሉ፤ እናንተም ሰነፎች፥ ዕውቀትን ገንዘብ አድርጉ፤</verse>
				<verse number="6">የተወደደች ነገርን እናገራለሁና ስሙ፤ ከከንፈሮቼም ቅን ነገርን አወጣለሁ፤</verse>
				<verse number="7">አንደበቴ እውነትን ታስተምራለችና፥ የሐሰት ከንፈሮችም በፊቴ የረከሱ ናቸውና።</verse>
				<verse number="8">የአፌ ቃላት ሁሉ እውነት ናቸው፤ ጠማማና እንቅፋት በውስጣቸው የለም።</verse>
				<verse number="9">በሚያውቁ ፊት ሁሉ የቀና ነው፥ ዕውቀትንም ለሚያገኙ ሰዎች የቀና ነው።</verse>
				<verse number="10">ከብር ይልቅ ትምህርትን፥ ከተፈተነ ወርቅም ይልቅ ዕውቀትን ተቀበሉ።</verse>
				<verse number="11">ዋጋው ብዙ ከሆነ ዕንቍ ጥበብ ትበልጣለችና፥ የከበረ ነገር ሁሉ አይተካከላትም።</verse>
				<verse number="12">እኔ ጥበብ ምክርን አሳደርሁ፥ ዕውቀትንና ዐሳብንም እኔ ጠራሁ።</verse>
				<verse number="13">እግዚአብሔርን የሚፈራ ዐመፃን ይጠላል፤ ጥልንና ትዕቢትን፥ ክፉ መንገድንም ይጠላል። የክፉ ሰዎችንም ጠማማ መንገድ ጠላሁ።</verse>
				<verse number="14">ምክርና ሥልጣን የእኔ ናቸው፤ ማስተዋል የእኔ ነው፥ ብርታትም የእኔ ነው።</verse>
				<verse number="15">ነገሥታት በእኔ ይነግሣሉ፥ ሹማምቶችም እውነትን ይጽፋሉ።</verse>
				<verse number="16">ታላላቆች በእኔ ይከብራሉ። መኳንንት በእኔ ምድርን ይይዛሉ፥</verse>
				<verse number="17">እኔ የሚወድዱኝን እወድዳለሁ፥ እኔንም የሚሹ ሞገስን ያገኛሉ።</verse>
				<verse number="18">ብልጥግናና ክብር ብዙ ሃብትና ጽድቅም በእኔ ዘንድ አሉ።</verse>
				<verse number="19">ከወርቅና ከከበረ ዕንቍ ይልቅ እኔን መምረጥ ይሻላል፥ ፍሬዬም ከጠራ ብር ይሻላል።</verse>
				<verse number="20">እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፥ በፍርድ ጎዳና መካከልም እመላለሳለሁ፥</verse>
				<verse number="21">ለሚወድዱኝ ሀብትን እከፍላቸው ዘንድ ቤተ መዛግብታቸውንም በመልካም ነገር እሞላ ዘንድ። የሚሆነውን ነገር በየቀኑ ብነግራችሁ ከጥንት ጀምሮ የነበረውን ቍጥር አስባለሁ።</verse>
				<verse number="22">እግዚአብሔር ለሥራው የመንገዱ መጀመሪያ አድርጎ ፈጠረኝ፥</verse>
				<verse number="23">ምድርን ሳይፈጥር አስቀድሞ ከዓለም በፊት ሠራኝ፥</verse>
				<verse number="24">ቀላያትን ሳይፈጥር፥ የውኃ ምንጮችም ሳይፈልቁ፥</verse>
				<verse number="25">ተራሮች ሳይመሠረቱ፥ ከኮረብቶች በፊት ወለደኝ፥</verse>
				<verse number="26">እግዚአብሔር ከሰማይ በታች የሚታደርባቸውን ሀገሮችንና ዳርቻዎችን ሳይፈጥር።</verse>
				<verse number="27">ሰማዮችን በዘረጋ ጊዜ አብሬ ነበርሁ፥ ዙፋኑን በነፋሳት ላይ ባጸና ጊዜ፥</verse>
				<verse number="28">ደመናትን በላይ ባጸና ጊዜ፥ የቀላያትን ምንጮች ባጸና ጊዜ፥</verse>
				<verse number="29">ለባሕርም ዳርቻን በወሰነ ጊዜ ውኃ ከትእዛዙ እንዳያልፍ፥ የምድርን መሠረት ባጸና ጊዜ፥</verse>
				<verse number="30">እኔ ከእርሱ ጋር እሠራ ነበር፤ ደስም አሰኘው ነበር፥ በየዕለቱ ሁልጊዜ በፊቱ ደስ ይለኝ ነበር።</verse>
				<verse number="31">ዓለምንም ፈጥሮ በፈጸመና ደስ ባለው ጊዜ፥ ደስታዬ በሰው ልጆች መካከል ነበር።</verse>
				<verse number="32">አሁንም ልጄ ሆይ፥ ስማኝ፥ መንገዴን የሚጠብቁ ብፁዓን ናቸው።</verse>
				<verse number="33">ጥበብን ስሙ፥ ጠቢባንም ሁኑ፥ ቸልም አትበሉት።</verse>
				<verse number="34">የሚሰማኝ ሰው ብፁዕ ነው፥ መንገዴን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው፥ ዕለት ዕለት በቤቴ መግቢያ የሚተጋ፥ የደጄንም መድረክ የሚጠብቅ።</verse>
				<verse number="35">መንገዶቼ የሕይወት መንገዶች ናቸውና። እኔን ያገኘ ሕይወትን አገኘ፤ ፈቃዱም በእግዚአብሔር ዘንድ ይዘጋጃል።</verse>
				<verse number="36">በእኔ ላይ በደልን የሚፈጽሙ ራሳቸውን ይበድላሉ፤ የሚጠሉኝም ሞትን ይወድዳሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">ጥበብ ለራስዋ ቤቷን ሠራች፥ ሰባቱንም ምሰሶዎችዋን አቆመች።</verse>
				<verse number="2">ፍሪዳዋን አረደች፥ የወይን ጠጅዋንም በማድጋዋ ጨመረች። ማዕድዋን አዘጋጀች።</verse>
				<verse number="3">አገልጋዮችዋን ልካ በከፍተኛ ዐዋጅ ወደ ማዕድዋ ጠራች። እንዲህም አለች፦</verse>
				<verse number="4">“አላዋቂ የሆነ ወደ እኔ ይምጣ፤” አእምሮ የጎደላቸውንም እንዲህ አለች፦</verse>
				<verse number="5">“ኑ፥ እንጀራዬን ብሉ፥ የጠመቅሁላችሁን የወይን ጠጅም ጠጡ።</verse>
				<verse number="6">ስንፍናን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ፥ በሕይወትም ትኖሩ ዘንድ ዕውቀትን ፈልጉ፥ በመረዳትም ዕውቀትን አቅኑ።”</verse>
				<verse number="7">ክፉዎችን የሚያስተምር ለራሱ ውርደትን ይቀበላል፥ ኃጥእንም የሚገሥጽ ራሱን ያዋርዳል።</verse>
				<verse number="8">ሰነፎችን አትገሥጽ እንዳይጠሉህ፥ ጠቢብን ገሥጽ ይወድድህማል።</verse>
				<verse number="9">ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ጥበብንም ያበዛል፤ ጻድቅንም አስተምረው፥ ዕውቀትንም ያበዛል።</verse>
				<verse number="10">የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ የቅዱሳንም ምክር ዕውቀት ነው፥ ሕግንም ማወቅ ለልብ ደግ ነው።</verse>
				<verse number="11">በዚህ ሥርዐት ብዙ ዘመን ትኖራለህ፥ የሕይወትህም ዓመታት ይጨመሩልሃል።</verse>
				<verse number="12">ልጄ ሆይ፥ ለራስህ ጠቢብ ብትሆን ለባልንጀራህም ጠቢብ ትሆናለህ፥ ክፉም ብትሆን ክፋትን ለብቻህ ትሸከማለህ። ሐሰትን የሚያዘጋጅ ሰው ነፋሳትን እንደሚያዘጋጅ ሰው ይመስላል። እርሱም የሚበርር ዎፍን እንደሚከተል ነው። የወይኑ ቦታ መንገዱን ተወ፤ የሚሰማራባትን መንገድ ዘነጋ፤ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፥ ለጥም ወደ ተሠራች ምድርም ይሄዳል፤ የማያፈራና የማይጠቅም ገንዘብንም በእጁ ይሰበስባል።</verse>
				<verse number="13">ሰነፍና ነዝናዛ፥ እንጀራንም ያጣች ሴት ኀፍረትን የማታውቅ ትሆናለች።</verse>
				<verse number="14">በቤቷ ደጅ በአደባባይ በወንበር ላይ በግልጥ ተቀምጣ፥</verse>
				<verse number="15">በመንገድ የሚያልፉትን አካሄዳቸውንም ያቀኑትን ትጠራለች።</verse>
				<verse number="16">ከእነርሱ ወገን ሰነፍ የሆነው ወደ እርሷ ይቀርባል። አእምሮ የጐደለውንም እንዲህ ብላ ታዝዘዋለች፦</verse>
				<verse number="17">“የተሸሸገ እንጀራን አሰማምረህ ዳስስ። ጣፋጭ የስርቆት ውኃንም ጠጣ፥”</verse>
				<verse number="18">ነገር ግን እርሱ ከኀያላን ወገን በእርሷ ዘንድ የሚጠፉ እንዳሉ፥ የሲኦል ወጥመድም በቤቷ እንደሚገኝ አያውቅም። ነገር ግን ፈጥነህ ሂድ፥ በቦታዋም አትዘግይ፥ የባዕድን ውኃ እንደምትሻገር በዐይንህ ወደ እርሷ መመልከትን አታዘውትር። ከባዕድ ውኃ ራቅ፥ ብዙ ዘመን ትኖር ዘንድ ከባዕድ ምንጭ ውኃ አትጠጣ። የሕይወትህም ዓመታት ይጨመሩልሃል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሰነፍ ልጅ ግን እናቱን ያሳዝናታል።</verse>
				<verse number="2">የሀብት ድልብ ለኃጥኣን አይጠቅምም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች።</verse>
				<verse number="3">እግዚአብሔር ጻድቅት ነፍስን አያስርብም፤ የኃጥኣንን ሕይወት ግን ከምድር ያስወግዳል።</verse>
				<verse number="4">የሐኬተኛ እጅ ችግረኛ ያደርጋል፤ የትጉህ እጅ ግን ባለጠጋ ያደርጋል።</verse>
				<verse number="5">የተማረ ልጅ ብልህ ይሆናል። ሰነፍ ልጅ ግን ራሱን ተገዥ ያደርጋል። ብልህ ልጅ ከቃጠሎ ይድናል፤ ኀጢአተኛ ልጅ ግን በአውድማ ነፋስ የሚጨብጥ ይሆናል። ብልህ ልጅ በመከር ጊዜ ይሠራል። ሰነፍ ልጅ ግን በመከር ጊዜ ይተኛል።</verse>
				<verse number="6">የእግዚአብሔር በረከት በጻድቃን ራስ ላይ ነው። የኃጥኣንን አፍ ግን ኀዘን በድንገት ይዘጋዋል።</verse>
				<verse number="7">የጻድቃን መታሰቢያ ከምስጋና ጋር ነው። የኃጥኣን ስም ግን ይጠፋል።</verse>
				<verse number="8">በልቡ ጠቢብ የሆነ ትእዛዝን ይቀበላል፤ በከንፈሩ የማይታገሥ ግን በመሰናክል ይወድቃል።</verse>
				<verse number="9">በየውሃት የሚሄድ ተማምኖ ይኖራል፤ መንገዱን የሚያጣምም ግን ይታወቃል።</verse>
				<verse number="10">ለክፋት በዐይኑ የሚጠቃቀስ ለሰው ኀዘንን ይሰበስባል፥ በግልጽ የሚገሥጽ ግን ሰላምን ያደርጋል።</verse>
				<verse number="11">የሕይወት ምንጭ በጻድቃን አፍ ነው፥ የኃጥኣንን አፍ ግን ጥፋት ይከድነዋል።</verse>
				<verse number="12">ቍጣ ጥልን ያነሣሣል። ፍቅር ግን የማይጣሉትን ሁሉ ይሸፍናቸዋል።</verse>
				<verse number="13">ብልህ ሰው ከከንፈሩ ጥበብን ያወጣል፤ አእምሮ የጐደለውንም ሰው በበትር ይመታል።</verse>
				<verse number="14">ጠቢብ ዕውቀትን ይሸሽጋል፤ የችኩል አፍ ግን ለጥፋት ይቀርባል።</verse>
				<verse number="15">የባለጠጋ ሀብት የጸናች ከተማ ናት፤ የዕውቀት ድህነት ግን የኀጢአተኞች ጥፋት ነው።</verse>
				<verse number="16">የጻድቃን ሥራ ሕይወትን ያደርጋል፤ የኃጥኣን ፍሬ ግን ኀጢአት ነው።</verse>
				<verse number="17">ተግሣጽ የሕይወትን መንገድ ይጠብቃታል፤ በተግሣጽ የማይዘለፍ ግን ይስታል።</verse>
				<verse number="18">ልዝብ ከንፈሮች ጥልን ይሸፍናሉ፤ ስድብን የሚያወጡ ግን ሰነፎች ናቸው።</verse>
				<verse number="19">ኃጥእ ከነገር ብዛት የተነሣ ከኀጢአት አያመልጥም፤ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።</verse>
				<verse number="20">የጻድቅ ምላስ የተፈተነ ብር ነው፤ የኃጥኣን ልብ ግን ይጐድላል።</verse>
				<verse number="21">የጻድቃን ከንፈሮች የሩቁን ያውቃሉ፤ ሰነፎች ግን በድህነት ይሞታሉ።</verse>
				<verse number="22">የእግዚአብሔር በረከት በጻድቃን ራስ ላይ ሆና ባለጠጋ ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ወደ ልብ አታመጣም።</verse>
				<verse number="23">ሰነፍ ሰው በመሳቁ ክፉን ይሠራል፤ ጥበብ ግን ለሰው ዕውቀትን ትወልዳለች።</verse>
				<verse number="24">ኃጥእ ወደ ጥፋት ይመለሳል፥ የጻድቅ ምኞቱ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደች ናት።</verse>
				<verse number="25">ኃጥእ እንደ ዐውሎ ነፋስ ኅልፈት ይጠፋል፤ ጻድቅ ግን ተሰውሮ ለዘለዓለም ይድናል።</verse>
				<verse number="26">ጨርቋ ለጥርስ፥ ጢስም ለዐይን ጎጂ እንደ ሆነ፥ ኀጢአትም ለሚሠሯት እንዲሁ ናት።</verse>
				<verse number="27">እግዚአብሔርን መፍራት ዘመንን ያረዝማል፤ የኃጥኣን ዕድሜ ግን ያጥራል።</verse>
				<verse number="28">ደስታ ከጻድቃን ጋር ትኖራለች፤ የኃጥኣን ተስፋ ግን ትጠፋለች።</verse>
				<verse number="29">እግዚአብሔርን መፍራት ለደግ ሰው ብርታት ነው፥ ጥፋት ግን ክፋት ለሚያደርጉ ነው።</verse>
				<verse number="30">ጻድቃን ለዘለዓለም አይናወጡም፤ ኃጥኣን ግን በምድር ላይ አይቀመጡም።</verse>
				<verse number="31">የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል፤ የዐመፀኛ ምላስ ግን ይጠፋል።</verse>
				<verse number="32">የጻድቃን ከንፈሮች ሞገስን ያፈስሳሉ፤ የኃጥኣን አፍ ግን ከዕውቀት ይከለከላል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">አባይ ሚዛን በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነው፤ እውነተኛ ሚዛን ግን በእርሱ ዘንድ የተመረጠ ነው።</verse>
				<verse number="2">ትዕቢት ባለበት በዚያ ውርደት አለ፤ የየዋሃን አፍ ግን ጥበብን ይማራል።</verse>
				<verse number="3">ጻድቃንን ፍጻሜያቸው ትመራቸዋለች፤ ኃጥኣንን ግን መሰነካከላቸው ትማርካቸዋለች።</verse>
				<verse number="4">በቍጣ ቀን ገንዘብ አይጠቅምም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች። ጻድቅ በሞተ ጊዜ ጸጸትን ይተዋል፥ የኀጢአተኛ ሞት ግን በእጅ የተያዘና ሣቅ ይሆናል።</verse>
				<verse number="5">የፍጹም ሰው ጽድቁ መንገዱን ያቀናለታል፤ ኀጢአት ግን በክፉዎች ላይ ትወርዳለች።</verse>
				<verse number="6">ቅኖች ሰዎችን ጽድቃቸው ይታደጋቸዋል፤ ኃጥኣን ግን ባለማወቃቸው ይጠመዳሉ።</verse>
				<verse number="7">ጻድቅ ሰው በሞተ ጊዜ ተስፋውን አያጣም፥ የክፉዎች ትምክሕታቸው ግን ትጠፋለች።</verse>
				<verse number="8">ጻድቅ ከወጥመድ ያመልጣል፥ ኀጢአተኛ ግን በእርሱ ፋንታ ይሰጣል።</verse>
				<verse number="9">በክፉዎች አፍ የሀገር ወጥመድ አለ፥ የጻድቃን ዕውቀት ግን መልካም ጎዳና ናት።</verse>
				<verse number="10">በጻድቃን ደግነት ከተማ ትቀናለች፥ በክፉዎችም ጥፋት ደስ ይላታል።</verse>
				<verse number="11">በቅኖች በረከት ከተማ ከፍ ከፍ ትላለች፤ በኃጥኣን አፍ ግን ትገለበጣለች።</verse>
				<verse number="12">ጥበብ የጐደለው የሀገሩን ሰው ይንቃል። ብልህ ሰው ግን ጸጥታን ያመጣል።</verse>
				<verse number="13">ሁለት ምላስ የሆነ ሰው የጉባኤን ምሥጢር ይገልጣል፤ በአንደበቱ የታመነ ግን ነገርን ይሰውራል።</verse>
				<verse number="14">መምህር የሌላቸው እንደ ቅጠል ይወድቃሉ። በምክር ብዛት ግን ደኅንነት ይኖራል።</verse>
				<verse number="15">ክፉ ሰው ከጻድቅ ጋር በተቀላቀለ ጊዜ ይከፋል፥ የሰላም ድምፅንም ይጠላል።</verse>
				<verse number="16">ደግ ሴት ለባሏ ክብርን ታስገኛለች፥ ጽድቅን የምትጠላ ሴት ግን የውርደት ወንበር ናት። ሐኬተኞች ከብልጽግና ይደኸያሉ፥ ብርቱዎች ግን ብልጽግናን ይከተላሉ።</verse>
				<verse number="17">ቸር ሰው ለነፍሱ መልካም ያደርጋል፤ ጨካኝ ግን ሥጋውን ይጐዳል።</verse>
				<verse number="18">ክፉ ሰው የበደልን ሥራ ይሠራል፤ ለጻድቃን ዘር ግን የታመነ ዋጋ አለው።</verse>
				<verse number="19">ጻድቅ ልጅ ለሕይወት ይወለዳል፤ የኃጥኣን መወለድ ግን ለሞት ነው።</verse>
				<verse number="20">ጠማማ መንገድ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ በመንገዳቸው ፍጹማን የሆኑ ግን በፊቱ የተመረጡ ናቸው።</verse>
				<verse number="21">በሐሰት እጅን በእጅ የሚመታ አይድንም፤ ጽድቅን የሚዘራ ግን የታመነ ዋጋን ያገኛል።</verse>
				<verse number="22">የወርቅ ቀለበት በእርያ አፍንጫ እንደ ሆነ፥ የክፉ ሴትም ውበትWa እንዲሁ ነው።</verse>
				<verse number="23">የጻድቃን ምኞት መልካም ነው፤ የኃጥኣን ተስፋ ግን ይጠፋል።</verse>
				<verse number="24">የየራሳቸውን የሚዘሩና የሚያበዙ አሉ፤ እየሰበሰቡ የሚያጐድሉም አሉ።</verse>
				<verse number="25">የተባረከች ሰውነት ሁሉ ትጠግባለች፥ ቍጡ ሰው ግን ክፉ ነው።</verse>
				<verse number="26">ስንዴውን የሚያደልብ ለአሕዛብ ይተወዋል። በረከት ግን በሚሰጥ ሰው ራስ ላይ ነው።</verse>
				<verse number="27">መልካምን የሚያስብ መልካም ክብርን ይወድዳል። ክፋትን የሚፈልግን ግን ክፋት ታገኘዋለች።</verse>
				<verse number="28">በባለጠግነቱ የሚተማመን ሰው ይወድቃል፤ ጻድቃንን የሚቀበል ግን ይለመልማል።</verse>
				<verse number="29">ቤቱን የማያውቅ ሰው ነፋስን ይወርሳል፥ ሰነፍም ለጠቢብ ተገዥ ይሆናል።</verse>
				<verse number="30">ከጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ይወጣል። የዐመፀኞች ነፍሳት ግን በድንገት ይወገዳሉ።</verse>
				<verse number="31">እነሆ፥ ጻድቅ በምድር ላይ በጭንቅ የሚድን ከሆነ፥ ይልቁንስ ኃጥእና ዐመፀኛ በወዴት ይገለጣሉ?</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">ተግሣጽን የሚወድድ ዕውቀትን ይወድዳል፤ ተግሣጽን የሚጠላ ግን ሰነፍ ነው።</verse>
				<verse number="2">የተሻለ ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን ያገኛል። ዐመፀኛ ሰው ግን ቸል ይባላል።</verse>
				<verse number="3">ከዐመፃ የማይርቅ ሰው ይጠፋል፤ የጻድቃን ሥር ግን አይነቀልም።</verse>
				<verse number="4">ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት፤ ክፉ ሴት ግን ነቀዝ እንጨትን እንደሚበላ እንዲዚሁ ባሏን ትጐዳለች።</verse>
				<verse number="5">የጻድቃን አሳብ ቅን ነው፤ ኃጥኣን ግን ሽንገላን ያስተምራሉ።</verse>
				<verse number="6">የኃጥኣን ምክር ተንኮል ነው። የቅኖች አፍ ግን ይታደጋቸዋል።</verse>
				<verse number="7">ኀጢአተኛ በተገለበጠበት ይጠፋል፥ የጻድቃን ቤቶች ግን ጸንተው ይኖራሉ።</verse>
				<verse number="8">የብልህ ሰው አንደበት በሰው ሁሉ ዘንድ ይመሰገናል፤ ልበ ጠማማ የሆነ ሰው ግን ይናቃል።</verse>
				<verse number="9">ለራሱ ባሪያ ሆኖ የተጠቃ ሰው እንጀራ ጐድሎት ራሱን ካከበረው ሰው ይሻላል።</verse>
				<verse number="10">ጻድቅ ሰው ለእንስሳው ነፍስ ይራራል፤ የኃጥኣን ምሕረት ግን አለመመጽወት ነው።</verse>
				<verse number="11">ምድሩን የሚያርሳት ሰው እንጀራን ይጠግባል፤ ቦዘኔነትን የሚከተል ግን የአእምሮ ድህነትን ይሰበስባል። በወይን ግብዣ ራሱን ደስ የሚያሰኝ ሰው በሰውነቱ ውርደትን ያመጣል።</verse>
				<verse number="12">የኃጥኣን ምኞት ክፋት ናት። የጻድቃን ሥር ግን የጸና ነው።</verse>
				<verse number="13">ኀጢአተኛ ሰው በከንፈሩ ኀጢአት ወደ ወጥመድ ይወድቃል፤ ጻድቅ ግን ከእርሱ ያመልጣል። አስፍቶ የሚመለከት ሰው ብዙ ምሕረትን ያገኛል። ድንገት በበር የሚገናኝ ግን ነፍሳትን ያስጨንቃል።</verse>
				<verse number="14">የሰው ነፍስ ከአፉ ፍሬ መልካም ነገርን ትጠግባለች፥ ሰውም የከንፈሩን ዋጋ ይቀበላል።</verse>
				<verse number="15">የሰነፎች መንገድ በፊታቸው የቀናች ናት፤ ጠቢብ ግን ምክርን ይሰማል።</verse>
				<verse number="16">ሰነፍ ቍጣውን በየቀኑ ይናገራል፤ ብልህ ሰው ግን ነውርን ይሰውራል።</verse>
				<verse number="17">ጻድቅ ሰው የተገለጠ እውነትን ያስተምራል፤ የክፉዎች ምስክርነት ግን ውሸት ነው።</verse>
				<verse number="18">በሐሰት የሚመሰክሩ በሰይፍ ይገድላሉ፤ በአፋቸው ሰይፍ አለና። የጠቢባን ምላስ ግን የቈሰለውን ይፈውሳል።</verse>
				<verse number="19">የጻድቃን ከንፈሮች ምስክርነትን ያቀናሉ፥ የሚቸኩል ምስክር ግን ክፉ አንደበት አለው።</verse>
				<verse number="20">ክፉን በሚያስብ ልብ ውስጥ ማታለል አለ፤ ሰላምን የሚወዱ ግን ደስ ይላቸዋል፥</verse>
				<verse number="21">ጻድቅን ምንም ክፉ ነገር ደስ አያሰኘውም፤ ክፉዎች ግን ክፋትን የተሞሉ ናቸው።</verse>
				<verse number="22">ሐሰተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው።</verse>
				<verse number="23">ብልህ ሰው የጥበብ መንበር ነው፤ የሰነፎች ልብ ግን መርገምን ያገኛል።</verse>
				<verse number="24">የተመረጡ ሰዎች እጅ ፈጥኖ ይገዛል፤ ሐሰተኞች ሰዎች ግን ለምርኮ ይሆናሉ።</verse>
				<verse number="25">የሚያስደነግጥ ቃል የጻድቅ ሰው ልቡናን ያውካል፤ መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል።</verse>
				<verse number="26">ራሱን የሚያውቅ ሰው ለራሱ ጻድቅ ነው፤ የክፉዎች ሥራ ግን መልካም አይደለም። የሚበድሉ ሰዎችን ክፉ ይከተላቸዋል፥ የኃጥኣን መንገዳቸውም ታስታቸዋለች።</verse>
				<verse number="27">ታካች ሰው አድኖ አይዝም። ንጹሕ ሰው ግን ክቡር ሀብት ነው።</verse>
				<verse number="28">በጽድቅ መንገድ ሕይወት አለ፥ ክፉን የሚያስቡ ሰዎች መንገዶች ግን ወደ ሞት ያወርዳሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">ዐዋቂ ልጅ የአባቱን ተግሣጽ ይሰማል፤ የማይሰማ ልጅ ግን ይጠፋል።</verse>
				<verse number="2">ደግ ሰው ከጽድቅ ፍሬ መልካምን ይበላል፤ የዐመፀኞች ነፍሳት ግን በጨርቋነታቸው ይጠፋሉ።</verse>
				<verse number="3">አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ በከንፈሩ የሚቸኩል ግን ራሱን ይጥላል።</verse>
				<verse number="4">የማይሠራ ሁሉ በምኞት ይኖራል። የደጋጎች እጅ ግን ይተጋል።</verse>
				<verse number="5">ጻድቅ የሐሰትን ቃል ይጠላል፤ ኀጢአተኛ ግን ያፍራል፥ ተገልጦም አይመጣም።</verse>
				<verse number="6">መንገዳቸው ቀና የሆነውን የዋሃንን ጽድቅ ትጠብቃቸዋለች፤ ኀጢአተኞችን ግን ኀጢአታቸው በደለኛ ታደርጋቸዋለች።</verse>
				<verse number="7">ምንም ሳይኖራቸው ራሳቸውን ባለጠጎች የሚያደርጉ አሉ፥ ባለጠግነታቸው ብዙ ሲሆን ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉም አሉ።</verse>
				<verse number="8">ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፤ ድሃ ግን ቍጣን አይቃወምም።</verse>
				<verse number="9">ለጻድቃን ሁልጊዜ ብርሃን ነው፤ የኃጥኣን መብራት ግን ትጠፋለች። የሐሰተኞች ነፍሳት በኀጢአት ይስታሉ። ጻድቃን ግን ይራራሉ፥ ይመጸውታሉም።</verse>
				<verse number="10">ክፉ ሰው ከመሳደብ ጋር ክፋትን ይሠራል፤ ራሳቸውን የሚያውቁ ግን ብልሆች ናቸው።</verse>
				<verse number="11">በኀጢአት በችኮላ የሚገኝ ሀብት ይጐድላል፥ በእውነት ለራሱ የሚሰበስብ ግን ይበዛለታል። ጻድቅ ይራራል፥ ያበድራልም።</verse>
				<verse number="12">ከሚበለጽግና በተስፋ ከሚቈይ ሰውነቱን ሊረዳ የሚጀምር ይሻላል። መልካም ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ናት።</verse>
				<verse number="13">የእግዚአብሔርን ሥራ የሚያቃልለውን እርሱ ያቃልለዋል፥ ትእዛዙን የሚሰማ ግን በእርሱ በሕይወት ይኖራል። ለውሸተኛ ልጅ ምንም ደግነት የለም፥ ለብልህ አገልጋይ ግን ሥራው መልካም ይሆናል። መንገዱም ይቃናል።</verse>
				<verse number="14">የብልህ ሰው ሕግ የሕይወት ምንጭ ነው። ማስተዋል የሌለው ግን በኀጢአት ይሞታል።</verse>
				<verse number="15">መልካም ዕውቀት ሞገስንና ጥበብን ይሰጣል፤ የቸለልተኞች መንገድ ግን በጥፋት ውስጥ ነው።</verse>
				<verse number="16">ብልህ ሁሉ በዕውቀት ይሠራል፤ ሰነፍ ግን ክፋቱን ይገልጣል።</verse>
				<verse number="17">ሰነፍ መልእክተኛ በክፉ ላይ ይወድቃል፤ ብልህ መልእክተኛ ግን ራሱን ያድናል።</verse>
				<verse number="18">ትምህርት ድህነትንና ጕስቍልናን ያስወግዳል፤ ተግሣጽን የሚጠብቅ ግን ይከብራል።</verse>
				<verse number="19">የደጋግ ሰዎች ምኞት ነፍስን ያድናል፤ የሰነፎች ሥራ ግን ከዕውቀት የራቀ ነው።</verse>
				<verse number="20">ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤ ከአላዋቂዎች ጋር የሚሄድ ግን አላዋቂ ይሆናል።</verse>
				<verse number="21">በደለኞችን ክፉ ነገር ይከተላቸዋል፤ ጻድቃንን ግን መልካም ነገር ያገኛቸዋል።</verse>
				<verse number="22">ደግ ሰው ለልጅ ልጅ ያወርሳል፥ የኀጢአተኞች ብልጽግና ግን ለጻድቃን ይደልባል።</verse>
				<verse number="23">ጻድቃን ለብዙ ዓመት በብልጽግና ይኖራሉ፤ ዐመፀኞች ግን ፈጥነው ይጠፋሉ።</verse>
				<verse number="24">በበትር ከመምታት የሚራራ ሰው ልጁን ይጠላል፤ ልጁን የሚወድድ ግን በጥንቃቄ ይቀጣዋል።</verse>
				<verse number="25">ጻድቅ ሰውነቱ እስክትጠግብ ድረስ ይበላል፤ የኃጥኣን ሰውነት ግን ትቸገራለች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">ብልሆች ሴቶች ቤቶችን ይሠራሉ፤ ሰነፎች ሴቶች ግን በእጃቸው ያፈርሳሉ።</verse>
				<verse number="2">በቅንነት የሚሄድ ሰው እግዚአብሔርን ይፈራል፤ መንገዱን የሚያጣምም ግን ይናቃል።</verse>
				<verse number="3">ከሰነፎች አፍ የስድብ በትር ይወጣል፤ የጠቢባን ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች።</verse>
				<verse number="4">በሬዎች በሌሉበት ስፍራ በረቱ ንጹሕ ነው፤ ብዙ እህል ግን በበሬዎች ኀይል ይገኛል።</verse>
				<verse number="5">የታመነ ምስክር አይዋሽም፤ የሐሰት ምስክር ግን ሐሰትን ያቀጣጥላል።</verse>
				<verse number="6">በክፉዎች ዘንድ ጥበብን ትፈልጋለህ፥ አታገኛትምም፤ ዕውቀት ግን በብልሆች ዘንድ በቀላሉ ይገኛል።</verse>
				<verse number="7">በሰነፍ ሰው ፊት ሁሉ ጠማማ ነው፥ የብልሆች ከንፈር ግን የዕውቀት ጋሻ ነው።</verse>
				<verse number="8">የዐዋቂዎች ጥበብ መንገዳቸውን ታውቃለች፤ የሰነፎች ስንፍና ግን ወደ ስሕተት ይመራል።</verse>
				<verse number="9">የኃጥኣን ቤቶች መንጻትን ይሻሉ፥ የጻድቃን ቤቶች ግን የተወደዱ ናቸው።</verse>
				<verse number="10">የዐዋቂ ሰው ልብ ለሰውነቱ ኀዘን ነው፤ ደስ ባለውም ጊዜ ከጥል ጋር ግንኙነት የለውም።</verse>
				<verse number="11">የክፉዎች ቤቶች ይፈርሳሉ፤ የቅኖች ማደሪያዎች ግን ይጸናሉ።</verse>
				<verse number="12">በሰዎች ዘንድ ቅን የምትመስል መንገድ አለች፤ ፍጻሜዋ ግን ወደ ሲኦል ጕድጓድ ታደርሳለች።</verse>
				<verse number="13">ከደስታ ጋር ኀዘን አይቀላቀልም፥ የደስታ ፍጻሜ ግን ወደ ኀዘን ይመለሳል።</verse>
				<verse number="14">ልበ ትዕቢተኛ ከራሱ መንገድ ይጠግባል። ደግ ሰውም ከራሱ ዐሳብ ይጠግባል።</verse>
				<verse number="15">የዋህ ነገርን ሁሉ ያምናል፤ ዐዋቂ ግን ወደ ንስሓ ይመለሳል።</verse>
				<verse number="16">ብልህ ሰው ፈርቶ ከክፉ ይሸሻል፤ አላዋቂ ግን ራሱን ተማምኖ ከኃጥኣን ጋር አንድ ይሆናል።</verse>
				<verse number="17">ቍጡ ሰው ያለምክር ይሠራል፤ ብልህ ግን ብዙ ይታገሣል።</verse>
				<verse number="18">አላዋቂዎች ሰዎች ክፋትን ይካፈላሉ፤ ዐዋቂዎች ሰዎች ግን ማስተዋልን ፈጥነው ይይዟታል።</verse>
				<verse number="19">ክፉዎች በደጎች ፊት ይሰነካከላሉ፥ ኃጥኣን ግን በጻድቃን በር ያገለግላሉ።</verse>
				<verse number="20">ባለጠጎች ወዳጆች ድሆች ወዳጆችን ይጠላሉ፤ የባለጠጎች ወዳጆች ግን ብዙዎች ናቸው።</verse>
				<verse number="21">ድሃውን የሚንቅ ኀጢአትን ይሠራል፤ ለድሃ የሚራራ ግን ብፁዕ ነው።</verse>
				<verse number="22">ስሕተተኞች ክፉን ያስባሉ፤ ደጋጎች ግን ምሕረትንና እውነትን ያስባሉ። ክፋትንም የሚሠሩ ምሕረትንና ይቅርታን አያውቁም። ነገር ግን ታማኝነትና ቸርነት ደግ በሚሠሩ ዘንድ ናቸው።</verse>
				<verse number="23">በሁሉ ነገር ጠንቃቃ ለሆነ ብዙ ትርፍ አለው። ደስታን ፈላጊና ሰነፍ ግን ችግረኛ ነው።</verse>
				<verse number="24">ዐዋቂ ሰው የጠቢባን ዘውድ ነው፤ የአላዋቂዎች ተግባር ግን ክፉ ነው።</verse>
				<verse number="25">እውነተኛ ምስክር ነፍስን ከክፉ ያድናል፥ ሐሰተኛ ግን ሐሰትን ያቀጣጥላል።</verse>
				<verse number="26">እግዚአብሔርን ለሚፈራ ጽኑዕ ተስፋ አለው፥ ለልጆቹም መጠጊያን ይተዋል።</verse>
				<verse number="27">የእግዚአብሔር ትእዛዝ የሕይወት ምንጭ ነው። ሰዎችንም ከሞት ወጥመድ እንዲያመልጡ ያደርጋል።</verse>
				<verse number="28">የንጉሥ ክብር በሕዝብ ብዛት ነው፤ የገዥ ውድቀት ግን በሕዝብ ማነስ ነው።</verse>
				<verse number="29">ትዕግሥተኛ ሰው ጥበብ የበዛለት ይሆናል፤ ትዕግሥት የጐደለው ሰው ግን ሰነፍ ነው፤</verse>
				<verse number="30">የሚያስታርቅ ሰው የልብ ፈዋሽ ነው፤ ቀናተኛ ልብ ግን ለአጥንት ነቀዝ ነው።</verse>
				<verse number="31">ድሃን የሚያስጨንቅ ፈጣሪውን ያስቈጣዋል፤ ፈጣሪውን የሚያከብር ግን ለድሃ ምሕረትን ያደርጋል።</verse>
				<verse number="32">ኃጥእ በክፋቱ ይወገዳል፤ በቸርነቱ የሚታመን ግን ጻድቅ ነው።</verse>
				<verse number="33">በደግ ሰው ልብ ጥበብ ታድራለች፤ በአላዋቂ ሰው ልብ ግን አትታወቅም።</verse>
				<verse number="34">ጽድቅ ሕዝብን ከፍ ከፍ ታደርጋለች፤ ኀጢአት ግን ሕዝብን ታሳንሳለች።</verse>
				<verse number="35">አስተዋይ መልእክተኛ በንጉሥ ዘንድ የተወደደ ነው፤ በመልካም ጠባዩም ውርደትን ከራሱ ያርቃል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">ቍጣ ጥበበኞችን ታጠፋለች፤ የለዘበ ቃል ቍጣን ይመልሳል፥ ሻካራ ቃል ግን ጠብን ያነሣሣል።</verse>
				<verse number="2">የጠቢባን ምላስ መልካም ነገርን ታውቃለች፤ የአላዋቂዎች አፍ ግን ክፋትን ይናገራል።</verse>
				<verse number="3">የእግዚአብሔር ዐይኖች በሁሉ ቦታ ናቸው፤ ክፉዎችንና ደጎችንም ይመለከታሉ።</verse>
				<verse number="4">ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፤ የሚጠብቀው ግን የዕውቀት መንፈስን ይሞላል።</verse>
				<verse number="5">አላዋቂ ልጅ የአባቱን ተግሥጽ ያቃልላል፤ ተግሣጽን የሚጠብቅ ግን ዐዋቂ ነው። እውነት ከበዛ ዘንድ ብዙ ኀይል አለ፥ ኀጢአተኞች ግን ከምድር ገጽ ይጠፋሉ፥</verse>
				<verse number="6">በጻድቃን ቤቶች ብዙ ኀይል አለ፥ የኀጢአተኞች ፍሬ ግን ይጠፋል።</verse>
				<verse number="7">የጠቢባን ከንፈሮች በዕውቀት የታሰሩ ናቸው፤ የሰነፎች ልብ ግን የጸና አይደለም።</verse>
				<verse number="8">የክፉዎች መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ ነው፤ የቅኖች ጸሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው።</verse>
				<verse number="9">የክፉዎች መንገድ በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ ነው፤ ጽድቅን የሚከተሉትን ግን እግዚአብሔር ይወድዳቸዋል።</verse>
				<verse number="10">የቅኖች ትምህርት በሚያልፉ ሰዎች ትታወቃለች። ተግሣጽን የሚጠሉ ግን በውርደት ይሞታሉ።</verse>
				<verse number="11">ሲኦልና ሞት በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቁ ናቸው፤ የሰዎች ልብማ እንዴት የታወቀ አይሆን?</verse>
				<verse number="12">አላዋቂ ሰው የሚዘልፈውን አይወድድም፥ ከጠቢባንም ጋር አይነጋገርም።</verse>
				<verse number="13">ልብ ደስ ሲለው ፊት ይበራል፤ ልብ ሲያዝን ግን ፊት ይጠቍራል።</verse>
				<verse number="14">ቀና ልብ ዕውቀትን ትፈልጋለች። የአላዋቂዎች አፍ ግን ክፋትን ይናገራል።</verse>
				<verse number="15">የክፉዎች ዐይኖች ሁልጊዜ ክፋትን ይመለከታሉ፤ ደጋግ ሰዎች ግን ሁልጊዜ ዝም ይላሉ።</verse>
				<verse number="16">እግዚአብሔርን በመፍራት የሚገኝ ጥቂት ሀብት እግዚአብሔርን ባለመፍራት ከሚገኝ ብዙ መዝገብ ይሻላል።</verse>
				<verse number="17">ጥል ካለበት የሰባ ፊሪዳ፥ ደስታና ፍቅር ያለበት የጎመን ወጥ ይሻላል።</verse>
				<verse number="18">ቍጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ ትዕግሥተኛ ሰው ግን የሆነውን ስንኳ ያጠፋል። ትዕግሥተኛ ሰው ክርክርን ያጠፋል፥ ኀጢአተኛ ሰው ግን ጠብን ፈጽሞ ያነሣል።</verse>
				<verse number="19">የሰነፎች መንገዶች እሾህ የተከሰከሰባቸው ናቸው፥ የጽኑዓን መንገዶች ግን ጥርጊያ ናቸው።</verse>
				<verse number="20">ብልህ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ አላዋቂ ልጅ ግን እናቱን ያሰድባል።</verse>
				<verse number="21">የአላዋቂ ሰው መንገዶች ጠማሞች ናቸው፤ ብልህ ሰው ግን አቅንቶ ይሄዳል።</verse>
				<verse number="22">ማኅበርን የሚያከብሩ ማስተዋልን ገንዘብ ያደርጋሉ። ምክርም በመካሮች ልብ ትኖራለች።</verse>
				<verse number="23">ክፉ ሰው ግን ምክርን አይሰማትም፤ ለማኅበሩም መልካምና መጥፎ ነው የሚለው የለም።</verse>
				<verse number="24">ሸሽቶ ከሲኦል ያመልጥ ዘንድ፥ የአስተዋይ ሰው ልብ የሕይወት መንገድ ነው።</verse>
				<verse number="25">እግዚአብሔር የትዕቢተኞችን ቤት ያፈርሳል፤ የመበለቷን ወሰን ግን ያጸናል።</verse>
				<verse number="26">ዐመፃን ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ የተናቀ ነው፤ የንጹሓን ቃል ግን ያማረ ነው።</verse>
				<verse number="27">መማለጃን የሚቀበል ራሱን ያጠፋል፤ መማለጃ መቀበልን የሚጠላ ግን ይድናል። በምጽዋትና በእምነት ኀጢአት ይሰረያል። እግዚአብሔርንም በመፍራት ክፉ ሁሉ ይወገዳል።</verse>
				<verse number="28">የጻድቃን ልብ ታማኝነትን ይማራል፤ የኃአጥኣን አፍ ግን ክፋትን ይመልሳል። የደጋግ ሰዎች መንገዶች በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደዱ ናቸው፥ ስለ እነርሱም ጠላቶች ወዳጆችን ይሆናሉ።</verse>
				<verse number="29">እግዚአብሔር ከኃጥኣን ፈጽሞ ይርቃል፤ የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል። ከዐመፃ ጋር ካለ ብዙ ሀብት ይልቅ፥ ከእውነት ጋር ያለ ጥቂት ሀብት ይሻላል። አካሄዱ ከእግዚአብሔር ይቃናለት ዘንድ፥ የደግ ሰው ልብ እውነትን ያስባል።</verse>
				<verse number="30">መልካምን ነገር የሚያይ ዐይን ልብን ደስ ያሰኛል፥ መልካም ዜናም አጥንትን ያለመልማል።</verse>
				<verse number="31">የብልህን ተግሣጽ የሚሰማ ሰው ከጠቢባን ጋራ አንድ ይሆናል።</verse>
				<verse number="32">ከተግሣጽ የሚከላከል ራሱን ይጠላል። ተግሣጽን የሚወድድ ግን ራሱን ይወድዳል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">እግዚአብሔርን መፍራት በጎ ዕውቀትና ጥበብ ነው። ለሚመልስላትም የክብር መጀመሪያ ናት፥ የዋሃንንም ክብር ትከተላቸዋለች።</verse>
				<verse number="2">የትሑት ሰው ሥራ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ ነው፥</verse>
				<verse number="3">ኃጥኣን ግን በክፉ ቀን ይጠፋሉ።</verse>
				<verse number="4">በልቡ የታበየ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነው። በዐመፃ እጅን በእጅ የሚመታ አይነጻም።</verse>
				<verse number="5">የደግ መንገድ መጀመሪያ እውነት መሥራት ነው፥ እርሱም መሥዋዕትን ከመሠዋት ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ የተወደደ ነው።</verse>
				<verse number="6">እግዚአብሔርን የሚፈልግ ዕውቀትን ከጽድቅ ጋር ያገኛል፥</verse>
				<verse number="7">ቅንነትን የሚሹ ሰላምን ያገኛሉ።</verse>
				<verse number="8">የእግዚአብሔር ሥራ ሁሉ ከእውነት ጋር ነው።</verse>
				<verse number="9">ኃጥእ ለክፉ ቀን ይጠበቃል።</verse>
				<verse number="10">ጥበብ በንጉሥ አፍ አለ፥ አፉም በፍርድ አይሳሳትም።</verse>
				<verse number="11">የእግዚአብሔር ፍርድ እንደ ሚዛን ውልብልቢት ነው፤ ሥራውም የከረጢት ደንጊያ ነው።</verse>
				<verse number="12">ክፉን የሚሠራም በንጉሥ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ የፍርድ ዙፋን በጽድቅ ይጸናልና።</verse>
				<verse number="13">የእውነት ከንፈር በንጉሥ ዘንድ የተወደደ ነው፥ ቅን ነገርንም ይወድዳል።</verse>
				<verse number="14">የንጉሥ ቍጣ እንደ መልአከ ሞት ነው፤ ብልህ ሰው ግን ያቈላምጠዋል።</verse>
				<verse number="15">የንጉሥ ልጅ እንደ ሕይወት ብርሃን ነው፥ በማያስደስቱትም ዘንድ የማታ ደመና ነው።</verse>
				<verse number="16">ጥበብን ገንዘብ ማድረግ ከወርቅ ይመረጣል። ዕውቀትንም ገንዘብ ማድረግ ከብር ይሻላል።</verse>
				<verse number="17">የሕይወት መንገዶች ከክፉ ያርቃሉ፤ የጽድቅ ጎዳና የዘመን ብዛት ነው። ትምህርትን የሚቀበል በበጎ ይኖራል። ተግሣጽን የሚጠብቅም ብልሃተኛ ይሆናል። መንገዶቹን የሚጠብቅ ሰውነቱን ይጠብቃል፥ ሕይወትንም የሚወድድ አፉን ይጠብቃል።</verse>
				<verse number="18">ከጥል በፊት ስድብ ይቀድማል፥ ከመውደቅም በፊት ክፋትን ማወቅ።</verse>
				<verse number="19">ከተሳዳቢዎች ጋር ምርኮን ከሚካፈል፥ በትሕትና ቍጣን የሚያርቅ ይሻላል።</verse>
				<verse number="20">በሥራ ዐዋቂ የሆነ መልካም ነገርን ያገኛል፤ በእግዚአብሔርም የታመነ ብፁዕ ነው።</verse>
				<verse number="21">ጠቢብን ሰዎች ዐዋቂ ይሉታል፥ ነገሩም ጣፋጭ የሆነውን እጅግ ያደምጡታል።</verse>
				<verse number="22">በጎ ዐሳብ ገንዘብ ላደረጋት ሰው የሕይወት ምንጭ ናት፤ የሰነፎች ትምህርት ግን ክፉ ናት።</verse>
				<verse number="23">የጠቢብ ልብ ከአፉ ይታወቃል፥ በከንፈሩም ዕውቀትን ይለብሳል።</verse>
				<verse number="24">ያማረ ቃል የማር ወለላ ነው፤ ጣፋጭነቱም የነፍስ መድኀኒት ነው።</verse>
				<verse number="25">ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች፤ ፍጻሜዋ ግን የሲኦል ጕድጓዶችን ይመለከታል።</verse>
				<verse number="26">ሰው በድካሙ ለራሱ ይደክማል፥ ከራሱም ጥፋትን ያርቃል። ጠማማ ግን በአፉ ጥፋትን ይለብሳል።</verse>
				<verse number="27">አላዋቂ ሰው ለራሱ ክፋትን ይምሳል፥ በከንፈሩም እሳትን ይሰበስባል።</verse>
				<verse number="28">ጠማማ ሰው ክፋትን ይዘራል፥ የሐሰት መብራት ክፉዎችን ታቃጥላቸዋለች፥ ወዳጆችንም ትለያለች።</verse>
				<verse number="29">ክፉ ሰው ወዳጆቹን ይዋሻል፥ መልካምም ወዳልሆኑ መንገዶች ይመራቸዋል።</verse>
				<verse number="30">በዐይኑ ትኩር ብሎ የሚመለከት፥ ጠማማ ዐሳብን ያስባል፤ በከንፈሩም ክፉውን ሁሉ የሚያደርግ የክፋት ምድጃ ነው።</verse>
				<verse number="31">መልካም ሽምግልና የክብር አክሊል ነው፥ እርሱም በጽድቅ መንገድ ይገኛል።</verse>
				<verse number="32">ትዕግሥተኛ ሰው ከኀያል፥ ጥበብ ያለው ሰውም ሰፊ ርስት ካለው፥ በመንፈሱ የሠለጠነ ሰውም ሀገርን ከሚገዛ ሰው ይሻላል።</verse>
				<verse number="33">የበደለኛ ሰው በደሉ ሁሉ ወደ ጕያው ይመለሳል። ጽድቅ ሁሉ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">ብዙ ደስታ ከሞላበትና ከክርክር ጋር የዐመፃ ፍሪዳ ካለበት ቤት ይልቅ፥ ከሰላም ጋር ደረቅ ቍራሽ ይሻላል።</verse>
				<verse number="2">ብልህ አገልጋይ አላዋቂዎች ጌቶችን ይገዛል፥ ከወንድማማች ጋርም ርስትን ይካፈላል።</verse>
				<verse number="3">ብርና ወርቅ በከውር እንዲፈተን፥ የተመረጡ ሰዎች ልብም በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲሁ ነው።</verse>
				<verse number="4">ክፉ ሰው ከሕግ ውጭ የሆኑትን ሰዎች አንደበት ይሰማል፤ ጻድቅ ግን የሐሰት ከንፈሮችን አይመለከትም። ለሚያምን በዓለም ያለው ገንዘቡ ነው፥ ለማያምን ግን መሐለቅ የለውም፥</verse>
				<verse number="5">በድሃ የሚያላግጥ ፈጣሪውን ያነሣሣዋል፥ በሚጠፋም ላይ ደስ የሚለው ከፍርድ አይነጻም፥ የሚራራ ግን ምሕረትን ያገኛል።</verse>
				<verse number="6">የሽማግሌዎች አክሊል የልጅ ልጆች ናቸው፤ የልጆችም ክብር አባቶቻቸው ናቸው።</verse>
				<verse number="7">የታመነች ከንፈር ለሰነፍ፥ የሐሰት ከንፈርም ለጻድቅ አትስማማውም።</verse>
				<verse number="8">ትምህርት ገንዘብ ለሚያደርጓት የባለሟልነት ዋጋ ናት፥ ወደ ተመለሰችበትም መንገድን ታቀናለታለች።</verse>
				<verse number="9">በደሉን የሚሰውር ሰው ዕርቅን ይሻል፤ በደሉን መሰወር የሚጠላ ግን ቤተሰቦችንና ወዳጆችን ይለያያል።</verse>
				<verse number="10">ትምክሕት የአስተዋይ ሰው ልቡናን ያሳዝነዋል፥ አላዋቂ ግን ተገርፎ ግርፋቱ አይታወቀውም፥</verse>
				<verse number="11">ክፉ ሰው ሁሉ ጠብን ያነሣሣል፤ እግዚአብሔርም ምሕረት የሌለውን መልአክ ይልክበታል።</verse>
				<verse number="12">ዐዋቂ ሰው በትካዜ ውስጥ ይወድቃል፥ አላዋቂዎች ግን ክፉን ያስባሉ።</verse>
				<verse number="13">በመልካም ፋንታ ክፉን የሚመልስ፥ ክፉ ነገር ከቤቱ አይርቅም።</verse>
				<verse number="14">የጠብ መጀመሪያ ውኃን መድፈን ነው። የጽድቅ መጀመሪያ በነገር መሠልጠንን ይሰጣል፥ የችጋር አበጋዝ ጠብና ክርክር ነው።</verse>
				<verse number="15">ኃጥኡን ጻድቅ፥ ጻድቁንም ኃጥእ ብሎ መፍረድ በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰና የተናቀ ነው።</verse>
				<verse number="16">ለአላዋቂ ሰው ገንዘብ ለምንድን ነው? አላዋቂ ሰው ጥበብን ገንዘብ ማድረግ አይችልምና፥ ቤቱን የሚያስረዝም ሰው ለራሱ ጥፋትን ይሻል፤ ለመማርም የሚጨንቀው ወደ ክፉ ይወድቃል።</verse>
				<verse number="17">ሁልጊዜ ወዳጅ ይኑርህ፥ ወንድሞች በመከራ ጊዜ ጠቃሚዎች ይሆናሉ፥ ስለዚህ ይወለዳሉና።</verse>
				<verse number="18">አላዋቂ ሰው አጋና ይመታል፥ ለባልንጀራውም ዋስ እንደሚሆን በራሱ ደስ ይለዋል።</verse>
				<verse number="19">ክርክርን የሚወድድ በጠብ ደስ ይለዋል።</verse>
				<verse number="20">ጠማማ ልብ ያለው መልካም ነገርን አያገኝም፥ አንደበቱን የሚለዋውጥም በክፉ ላይ ይወድቃል።</verse>
				<verse number="21">የሰነፍ ልብ ገንዘብ ላደረጋት ኀዘን ናት፥ አባት ባልተማረ ልጁ ደስ አይለውም፥ ብልህ ልጅ ግን እናቱን ደስ ያሰኛል።</verse>
				<verse number="22">ደስ ያላት ልብ ፈውስን ታገኛለች፤ ኀዘንተኛ ሰው ግን አጥንቱን ያደርቃል።</verse>
				<verse number="23">መማለጃን በዐመፃ በብብቱ የሚቀበል መንገዶቹን አያቀናም፥ ክፉ ሰውም ከጽድቅ መንገዶች ይርቃል።</verse>
				<verse number="24">የብልህ ሰው ፊት ዐዋቂ ነው፤ የአላዋቂ ሰው ዐይኖች ግን በምድር ዳርቻ ናቸው።</verse>
				<verse number="25">አላዋቂ ልጅ ለአባቱ ፀፀት ነው፥ ለወለደችውም ኀዘን ነው።</verse>
				<verse number="26">ጻድቅን ሰው ማዋረድ መልካም አይደለም። በእውነት ለሚፈርዱም መዋሸት መልካም አይደለም።</verse>
				<verse number="27">ሻካራ ቃልን ከመናገር የሚከለክል ዐዋቂ ነው፥ ትዕግሥተኛ ሰውም ብልህ ነው።</verse>
				<verse number="28">አላዋቂ ጥበብን ቢጠይቅ ጥበብ ይሆነዋል፤ ዝም የሚል ሰውም ጥበበኛን ይመስላል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">ከወዳጆቹ መለየትን የሚወድድ ሰው ምክንያትን ይፈልጋል፥ ሁልጊዜም ለሽሙጥ ይሆናል።</verse>
				<verse number="2">የዕውቀት ድሃ ጥበብን አይወድድም፤ ነገር ግን ስንፍና ይገዛዋል።</verse>
				<verse number="3">ኀጢአተኛ ወደ ጥፋት ጥልቅ በመጣ ጊዜ ቸል ይላል፥ ውርደትና ሽሙጥም በላዩ ይመጣል።</verse>
				<verse number="4">ቃል በብልህ ሰው ልብ ውስጥ የጠለቀ ውኃ ነው፥ የሚፈልቅም የሕይወት ምንጭና ፈሳሽ ወንዝ ነው።</verse>
				<verse number="5">የኃጥኣንን ፊት ማድነቅ መልካም አይደለም። በፍርድ ጊዜም እውነትን ማራቅ መልካም አይደለም፥</verse>
				<verse number="6">አላዋቂን ከንፈሮቹ ወደ ክፉ ያደርሱታል፥ የችኩል አፍም ሞትን ይጠራል።</verse>
				<verse number="7">የአላዋቂ አፍ ለራሱ ጥፋት ነው፥ ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው።</verse>
				<verse number="8">ፍርሀት ሰነፎችን ይጥላል፥ የተቸገሩ ሰዎች ሰውነትም ይራባል።</verse>
				<verse number="9">በሥራው ራሱን የማያድን፥ ራሱን ለሚያጠፋ ወንድም ነው።</verse>
				<verse number="10">የእግዚአብሔር ስም ታላቅ ኀይል ነው፤ ጻድቃንም እርሱን በመከተል ከፍ ከፍ ይላሉ።</verse>
				<verse number="11">የባለጠጋ ሰው ሀብቱ የጸናች ከተማ ናት፥ ክብሯም እንደ ትልቅ ጥላ ታጠላለች።</verse>
				<verse number="12">ከመውደቅ በፊት የሰው ልቡ ከፍ ከፍ ይላል፥ ሳይከብርም ይዋረዳል።</verse>
				<verse number="13">ሳይሰማ ነገርን የሚመልስ ስንፍናና እፍረት ይሆንበታል።</verse>
				<verse number="14">ብልህ አገልጋይ የጌታውን ቍጣ ያበርዳል፥ አእምሮ የጐደለውን ሰው ማን ይችለዋል?</verse>
				<verse number="15">የብልህ ልብ ዕውቀትን ገንዘብ ያደርጋል፥ የጠቢባን ጆሮም ዕውቀትን ትፈልጋለች።</verse>
				<verse number="16">ሀብት ሰውን ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ ከመኳንንት ጋርም ያኖረዋል።</verse>
				<verse number="17">ከፍርድ በፊት ራሱን የሚከስስ ጻድቅ ነው፥ ያመጣው ባላጋራውም ይገሠጻል።</verse>
				<verse number="18">ዕጣ ክርክርን ያስተዋል፥ በኀያላንም መካከል ይለያል።</verse>
				<verse number="19">ወንድሙን የሚረዳ ወንድም እንደ ጸናችና ከፍ እንዳለች ከተማ ነው። በጽኑ መሠረትም እንደ ታነጸ ሕንጻ የጸና ነው።</verse>
				<verse number="20">ሰው ሆዱን ከአፉ ፍሬ ይሞላል፥ ከከንፈሩም ፍሬ ይጠግባል።</verse>
				<verse number="21">ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚያጸኑአትም ፍሬዋን ይበላሉ።</verse>
				<verse number="22">ደግ ሚስትን ያገኘ ሞገስን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ደስታን ተቀበለ። ደግ ሴትን የፈታ ደስታን አጣ፥ አመንዝራዪቱንም የሚያኖር አላዋቂና ኀጢአተኛ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">በከንፈሩ ከሚወሳልት አላዋቂ ይልቅ፥ ያለ ነውር የሚሄድ ድሃ ይሻላል።</verse>
				<verse number="2">ነፍስ ዕውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ እግሩንም የሚያፈጥን ከመንገድ ይስታል።</verse>
				<verse number="3">የሰው ስንፍናው መንገዱን ያጣምምበታል፥ በልቡም እግዚአብሔርን ገፋኢ ያደርገዋል።</verse>
				<verse number="4">ባለጠጋ ብዙ ወዳጆችን ይጨምራል፤ ድሃ ግን ያን ያለውን ያጣል።</verse>
				<verse number="5">ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይቀርም፥ በግፍዕ የሚከስም አያመልጥም።</verse>
				<verse number="6">ብዙ ሰዎች በነገሥታት ፊት ያገለግላሉ፥ ነገር ግን የሰው ጽድቁና ሀብቱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ናቸው፤ ክፉ ሁሉም የሰው መዘባበቻ ይሆናል።</verse>
				<verse number="7">ድሃ ወንድሙንም የሚጠላ ሰው ሁሉ፥ ከወንድምነቱ የራቀ ነው። በጎ ዕውቀትም ወደሚያውቋት ትቀርባለች። ብልህ ሰውም ያገኛታል። ብዙ ክፋትን የሚሠራ ክፋትን ይፈጽማል፥ ስቅጥጥ የሚያደርግ ነገርን የሚናገርም አይድንም።</verse>
				<verse number="8">ጥበብን የሚያገኝ ራሱን ይወድዳል፥ ማስተዋልንም የሚጠብቅ መልካም ነገርን ያገኛል።</verse>
				<verse number="9">ሐሰተኛ ምስክር ከቅጣት አይድንም፤ ክፋትን የሚያቀጣጥላትም ይጠፋባታል።</verse>
				<verse number="10">ለአላዋቂ ቅምጥልነት አይገባውም፥ አገልጋይም ከስድብ ጋር ቢገዛ ይበረታል።</verse>
				<verse number="11">ይቅር ባይ ሰው ይታገሣል፥ መመካቱም ኀጢአተኞችን ይቃወማቸዋል፥</verse>
				<verse number="12">የንጉሥ ቍጣ እንደ አንበሳ ግሣት ነው፥ ሞገሱም በመስክ ላይ እንዳለ ጠል ነው።</verse>
				<verse number="13">አላዋቂ ልጅ ለአባቱ ኀፍረት ነው፥ ከዐስበ ደነስ ጋር የሚቀርብ ስእለትም ንጹሕ አይደለም።</verse>
				<verse number="14">አባቶች ለልጆቻቸው ቤትንና ሀብትን ያወርሳሉ፤ ሚስት ግን በእግዚአብሔር ከባልዋ ጋር አንድ ትሆናለች።</verse>
				<verse number="15">ችግረኛን ሰው ሽብር ይይዘዋል፥ የማይሠራ ሰውም ይራባል።</verse>
				<verse number="16">ትእዛዛትን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ መንገዶቹን የሚያቃልል ግን ይጠፋል።</verse>
				<verse number="17">ለድሃ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ እንደ ስጦታውም መልሶ ይከፍለዋል።</verse>
				<verse number="18">ለተስፋ ይሆንህ ዘንድ ልጅህን ግረፍ፥ ለመሳደብ ግን እጅህን አታንሣ፥</verse>
				<verse number="19">ዐሳበ ክፉ ሰው ብዙ ያጠፋል፤ ጽኑ ደፋር ቢሆን ግን ነፍሱን ይጨምራል።</verse>
				<verse number="20">ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ በፍጻሜህ ጠቢብ ትሆን ዘንድ።</verse>
				<verse number="21">በሰው ልብ ብዙ ዐሳብ አለ፤ የእግዚአብሔር ምክር ግን ለዘለዓለም ይኖራል።</verse>
				<verse number="22">ምጽዋት ለሰው ፍሬ ነው፤ ከሐሰተኛ ባለጠጋም እውነተኛ ድሃ ይሻላል።</verse>
				<verse number="23">እግዚአብሔርን መፍራት የሰው ሕይወት ነው፤ የማይፈራው ግን ዕውቀት በሌለበት ቦታ ውስጥ ይኖራል።</verse>
				<verse number="24">ታካች ሰው እጁን በብብቱ ይሸሽጋል፥ ወደ አፉ ስንኳ አይመልሳትም።</verse>
				<verse number="25">ፌዘኛን ብትገርፈው አላዋቂው ብልሃተኛ ይሆናል፤ አስተዋይን ሰው ብትገሥጸው ግን ዕውቀትን ያገኛል።</verse>
				<verse number="26">አባቱን የሚያዋርድ እናቱንም የሚያሳድድ፥ አሳፋሪና ጐስቋላ ልጅ ይሆናል።</verse>
				<verse number="27">የአባቱን ትምህርት ከመጠበቅ የሚከለከል ልጅ፥ ክፉ ቃልን ይማራል።</verse>
				<verse number="28">ለአላዋቂ ልጅ የሚዋስ ፍርድን ያስነቅፋል፥ የኃጥኣንም አፍ ክፉ ቅጣትን ይውጣል።</verse>
				<verse number="29">ለክፉዎች ሰዎች መቅሠፍት ተዘጋጅቶላቸዋል፥ ለሰነፎችም እንደዚሁ ቅጣት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">ለተሳዳቢና ለሰካራም ወይን ክፉ ነው፥ ጽዋውንም መላልሶ የሚጨልጥ ጠቢብ አይደለም፥ እንደዚህ ያለ አላዋቂም ሁሉ አንድ ይሆናል።</verse>
				<verse number="2">የንጉሥ ቍጣ ከአንበሳ ቍጣ አያንስም፤ የሚያስቈጣውም ሰው የራሱን ነፍስ ይበድላል።</verse>
				<verse number="3">የሰው ክብሩ ከስድብ መከልከል ነው፤ ሰነፍ ሁሉ ግን እንዲህ ባለ ነገር ይጣመራል።</verse>
				<verse number="4">ታካች ሰው ሲያሽሟጥጡት አያፍርም፤ ስለዚህ በመከር ጊዜ ይለምናል፥ የሚሰጠውም የለም። በክምሩ እያለ ስንዴ የሚበደር እንደዚሁ ነው።</verse>
				<verse number="5">ምክር በሰው ልብ እንደ ጥልቅ ውኃ ነው፤ አእምሮ ያለው ሰው ግን ይቀዳዋል።</verse>
				<verse number="6">ይቅር ባይ ሰው ታላቅና ክቡር ነው፤ ነገር ግን የታመነ ሰው የሚገኘው በድካም ነው።</verse>
				<verse number="7">ያለ ነውር ወደ እውነት በንጹሕ የሚሄድ፥ ልጆቹን ብፁዓን ያደርጋቸዋል።</verse>
				<verse number="8">እውነተኛ ንጉሥ በዙፋኑ በተቀመጠ ጊዜ በዐይኖቹ ፊት ምንም ክፉ አይቃወመውም።</verse>
				<verse number="9">ንጹሕ ልብ አለኝ ብሎ የሚመካ ማን ነው? ከኀጢአትስ ንጹሕ ሆኖ የሚታይ ማን ነው?</verse>
				<verse number="10">ሁለት ዐይነት ሚዛንና ሁለት ዐይነት መስፈሪያ፥ ሁለቱ በእግዚአብሔር ፊት ርኩሳን ናቸው። የሚሠራቸውም በሥራው ይሰነካከላል።</verse>
				<verse number="11">የእውነተኛ ጐልማሳ መንገዱ የቀና ነው።</verse>
				<verse number="12">የሚሰማ ጆሮና የሚያይ ዓይን፥ ሁለቱ የእግዚአብሔር ሥራ ናቸው።</verse>
				<verse number="13">እንዳትወገድ ማማትን አትውደድ። ድሃም እንዳትሆን እንቅልፍን አትውደድ ዐይንህን ክፈት፥ እንጀራም ትጠግባለህ።</verse>
				<verse number="14">የሚገዛ ሰው፦ “ክፉ ነው፥ ክፉ ነው” ይላል፤ በሄደ ጊዜ ግን ይመካል።</verse>
				<verse number="15">ወርቅና ብዙ ቀይ ዕንቍ ይገኛል፤ የዕውቀት ከንፈር ግን የከበረች ጌጥ ናት።</verse>
				<verse number="16">ለማያውቀው ከተዋሰ ሰው ልብሱን ውሰድ፥ ለእንግዳ የተዋሰውንም እርሱን አግተው።</verse>
				<verse number="17">የሐሰት እንጀራ ለሰው የጣፈጠ ነው፤ ከዚህ በኋላ ግን አፉ ጭንጫ ይሞላል።</verse>
				<verse number="18">ዐሳብ በምክር ትጸናለች፥ በመልካምም ምክር ሰልፍ አድርግ።</verse>
				<verse number="19">ዘዋሪ ሐሜተኛ ምሥጢርን ይገልጣል፤ በከንፈሩ የሚያባብል ሰውን አትገናኘው።</verse>
				<verse number="20">አባቱንና እናቱን የሚያማ ብርሃኑ ይጠፋል፥ የዐይኖቹ ብሌንም ጨለማን ያያል።</verse>
				<verse number="21">አስቀድሞ ለርስት የሚቸኩል፥ በፍጻሜው አይባረክም።</verse>
				<verse number="22">ጠላቴን እበቀለዋለሁ አትበል፤ ነገር ግን እንዲረዳህ እግዚአብሔርን ተማመን።</verse>
				<verse number="23">ሁለት ዓይነት ሚዛን በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ ሐሰተኛ ሚዛንም መልካም አይደለም።</verse>
				<verse number="24">የሰው አካሄዱ በእግዚአብሔር ዘንድ ይቃናል፤ ሟች ግን መንገዱን እንዴት ያውቃል?</verse>
				<verse number="25">ሰው ከገንዘቡ በችኮላ የተቀደሰ ነው ብሎ ቢሳል፥ ከተሳለም በኋላ ቢፀፀት ወጥመድ ይሆንበታል።</verse>
				<verse number="26">ብልህ ንጉሥ የኃጥኣን መንሽ ነው፥ በእነርሱ ላይም መንኰራኵርን ይነዳባቸዋል።</verse>
				<verse number="27">የሰው መንፈስ የሆድን መዛግብት የሚመረምር፥ የእግዚአብሔር መብራት ነው።</verse>
				<verse number="28">ቸርነትና እውነት ንጉሥን ይጠብቁታል፤ ዙፋኑንም በእውነት ይከቡታል።</verse>
				<verse number="29">ለጐልማሶች ጌጣቸው ጥበብ ነው። ለሽማግሌዎችም ክብራቸው ሽበት ነው።</verse>
				<verse number="30">ሽብርና ስደት ክፉዎችን ድንገት ይገናኛቸዋል፥ ግርፋትም ወደ ሆድ ዕቃ ይገባል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሽ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ወደ ወደደውም ይመልሳታል፥ በዚያም ትቈያለች።</verse>
				<verse number="2">ሰው ሁሉ ለራሱ ጻድቅ መስሎ ይታያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያቀናል።</verse>
				<verse number="3">ጽድቅንና ቅን ፍርድን ማድረግ መሥዋዕት ከመሠዋት ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ ነው።</verse>
				<verse number="4">ለስድብ በልብ አለመቸኮል ታላቅ ዕውቀት ነው የኃጥኣንም ብርሃናቸው ኀጢአት ነው።</verse>
				<verse number="5">የትጉህ ዐሳብ ወደ ጥጋብ ያደርሳል፥ ችኩል ሰው ሁሉ ግን ለመጕደል ይቸኩላል።</verse>
				<verse number="6">በሐሰተኛ ምላስ ሀብትን የሚያከማች ከንቱ ነገርን ይከተላል፥ ወደ ሞት ወጥመድም ያደርሰዋል።</verse>
				<verse number="7">ጽድቅን ያደርጉ ዘንድ አይወድዱምና የኃጥኣን ጥፋት ከሩቅ ይመጣል።</verse>
				<verse number="8">እግዚአብሔር ለጠማሞች ጠማማ ሥራን ይልክባቸዋል፤ ሥራው የቀናና ንጹሕ ነውና።</verse>
				<verse number="9">ከነዝናዛ ሴት ጋር በተለሰነ ቤት ከመቀመጥ ይልቅ፥ ከቤት ውጭ በማዕዘን ላይ መቀመጥ ይሻላል።</verse>
				<verse number="10">የኀጢአተኛ ነፍስ በአንድ ሰው እንኳ ይቅር አትባልም።</verse>
				<verse number="11">ክፉ ሰው ሲዋረድ የዋህ ሰው ዐዋቂ ይሆናል፤ ጥበብን የሚረዳ ሰውም ዕውቀትን ይቀበላል።</verse>
				<verse number="12">የክፉዎች ልብ ጽድቅን አያውቅም፥ ክፋትም ኃጥአንን ያከፋቸዋል።</verse>
				<verse number="13">ድሃን እንዳይሰማ ጆሮውን የሚደፍን ሰው፥ እርሱ ራሱ ይጣራል፥ የሚሰማውም የለም።</verse>
				<verse number="14">በስውር ያለ ስጦታ ቍጣን ይመልሳል፥ ስጦታን የሚሸልግ ግን ጽኑ ቍጣን ያስነሣል።</verse>
				<verse number="15">ፍርድን ማድረግ ለጻድቃን ደስታ ነው፤ ጻድቅ ሰው ግን ክፉ በሚሠሩ ዘንድ የረከሰ ነው።</verse>
				<verse number="16">ከጽድቅ መንገድ የሚሳሳት ሰው፥ በረዐይት ጉባኤ ያርፋል።</verse>
				<verse number="17">ደስታን የሚወድድ ድሃን ይሆናል፥ የወይን ጠጅንና ዘይትን የሚወድድም ባለጠጋ አይሆንም።</verse>
				<verse number="18">ኃጥእ በጻድቅ ዘንድ የተናቀ ነው፥ ኃጥእም የጻድቅ ቤዛ ነው።</verse>
				<verse number="19">ከቍጡ፥ ከነዝናዛና ከነገረኛ ሴት ጋር ከመቀመጥ ይልቅ በምድረ በዳ መቀመጥ ይሻላል።</verse>
				<verse number="20">የተወደደ መዝገብ በጠቢባን አፍ ያርፋል፤ አላዋቂዎች ግን ያጡታል።</verse>
				<verse number="21">ጽድቅንና ምሕረትን የሚከተል ሕይወትንና ክብርን ያገኛል።</verse>
				<verse number="22">ጠቢብ የጸናች ከተማን ይገባባታል፥ ክፉዎች የሚተማመኑበትንም ኀይል ያፈርሳል።</verse>
				<verse number="23">አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ነፍሱን ከመከራ ይጠብቃል።</verse>
				<verse number="24">የችኩል፥ የነዝናዛና የነገረኛ ሰው ስሙ ቸነፈር ነው፥ ክፉን የሚያስብም ኃጥእ ነው።</verse>
				<verse number="25">ታካችን ምኞቱ ትገድለዋለች፥ እጆቹ ምንም ይሠሩ ዘንድ አይፈቅዱምና።</verse>
				<verse number="26">ኃጥእ ቀኑን ሁሉ ክፉ ምኞትን ይመኛል፥ ጻድቅ ግን ዐውቆ ይራራል፥ ይመጸውታልም።</verse>
				<verse number="27">የኃጥኣን መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ በክፋት ያቀርቡታልና።</verse>
				<verse number="28">ሐሰተኛ ምስክር ይጠፋል፤ የሚሰማ ሰው ግን ተጠንቅቆ ይናገራል።</verse>
				<verse number="29">ኃጥእ ሰው ያለ ኀፍረት ፊት ለፊት ይቃወማል፤ ቅን ሰው ግን መንገዱን ይረዳል።</verse>
				<verse number="30">ጥበብና ብርታት፥ ምክርም፥ በኃጥእ ዘንድ የሉም።</verse>
				<verse number="31">ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤ ረድኤት ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">መልካም ስም ከብዙ ባለ ጠግነት ይሻላል፥ መልካም ሞገስም ከብርና ከወርቅ ይበልጣል።</verse>
				<verse number="2">ባለ ጠጋና ድሃ በአንድነት ተገናኙ፤ ሁለቱንም እግዚአብሔር ፈጠራቸው።</verse>
				<verse number="3">ዐዋቂ ሰው ክፉ ሰው በኀይል ሲቀጣ አይቶ ይገሠጻል፥ አላዋቂዎች ግን ሲያልፉ ይጐዳሉ።</verse>
				<verse number="4">እግዚአብሔርን መፍራት፥ ጥበብን ባለጠግነትንና ክብርን፥ ሕይወትንም ትወልዳለች።</verse>
				<verse number="5">እሾህና ወጥመድ በጠማማ ሰው መንገድ ናቸው፤ ነፍሱን የሚጠብቅ ግን ከእነርሱ ያመልጣል።</verse>
				<verse number="6">ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም።</verse>
				<verse number="7">ድሆች ባለጠጎችን ይገዛሉ፥ አገልጋዮችም ለጌቶቻቸው ያበድራሉ።</verse>
				<verse number="8">ሐሰትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፥ የሥራውንም መቅሠፍት ይፈጽማል። እግዚአብሔር ደስ ብሎት የሚሰጥ ሰውን ይወድዳል፥ ከንቱ ሥራውን ግን ይጠላል።</verse>
				<verse number="9">ለድሃ የሚራራ እርሱ ይበላል እንጀራውን ለድሃ ሰጥቶአልና። ለሰጠው ሀብታምም የሚከፍል አይደለምና። መማለጃን የሰጠ ሰው ድል መንሣትንና ሞገስን ያገኛል፥ ነገር ግን የተቀበለውን ነፍስ ያጠፋል።</verse>
				<verse number="10">ነፍሰ ገዳይን ከጉባኤ አውጣ፥ ከእርሱም ጋር ክርክር ይወጣል፥ በጉባኤ በሚቀመጥበት ጊዜ ሁሉን ያዋርዳልና።</verse>
				<verse number="11">እግዚአብሔር የልብን የውሀት ይወድዳል። ንጹሓንም ሁሉ በእርሱ ዘንድ የተመረጡ ናቸው። ንጉሥ በከንፈሩ ይገዛል።</verse>
				<verse number="12">የእግዚአብሔር ዐይኖች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤ ኃጥእ ግን የጥበብን ቃል ይንቃል።</verse>
				<verse number="13">ታካች ሰው በላኩት ጊዜ ያመካኛል፥ እንዲህም ይላል፦ “አንበሳ በመንገድ አለ፥ በአደባባይም ግድያ አለ።”</verse>
				<verse number="14">የዐመፀኛ አፍ ጥልቅ ጕድጓድ ነው፤ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተጠላ በእርሱ ውስጥ ይወድቃል። በሰው ፊት ክፉዎች መንገዶች አሉ፥ ከእነርሱም ይርቅ ዘንድ አይወድድም። ከክፉና ከጠማማ መንገድም መራቅ አግባብ ነው።</verse>
				<verse number="15">አለማወቅ የጐልማሳን ልብ ከፍ ከፍ አደረገች፤ በትርና ተግሣጽ ከእርሱ ርቀዋልና።</verse>
				<verse number="16">ድሃን የሚቀማ ገንዘቡን ብዙ ያደርግለታል፥ በችግሩ ጊዜም ለባለጠጋ ይሰጣል።</verse>
				<verse number="17">ለመስማት ጆሮህን ወደ ጠቢባን ቃል አዘንብል፥ የእኔንም ቃል ስማ፥ መልካምንም ታውቅ ዘንድ ልብህን አቅርብ።</verse>
				<verse number="18">እነርሱን በልብህ ብትጠብቅ፥ በከንፈሮችህ በአንድነት ደስ ያሰኙሃል።</verse>
				<verse number="19">ተስፋህ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ፥ መንገዱን ያሳውቅሃል።</verse>
				<verse number="20">ለዕውቀትና ለምክር ይሆኑህ ዘንድ ሦስት ነገሮችን እነሆ ጻፍሁልህ። አንተም በልብህ ሰሌዳነት ጻፋቸው።</verse>
				<verse number="21">በጎ ዕውቀትን ትሰማ ዘንድ፥ ለሚጠይቁህም የእውነት ቃልን ትመልስ ዘንድ ነዋሪ ቃልን አስተምርሃለሁ።</verse>
				<verse number="22">ድሃን በግድ አትበለው፥ ድሃ ነውና ችግረኛውንም በበር አትግፋው፤</verse>
				<verse number="23">እግዚአብሔር ፍርዱን ይፈርድለታልና። አንተም ነፍስህን በሰላም ታድናለህ።</verse>
				<verse number="24">ከቍጡ ሰው ጋር ባልንጀራ አትሁን፥ ከነዝናዛም ጓደኛ ጋር አትኑር።</verse>
				<verse number="25">መንገዱን እንዳትማር፥ ለነፍስህም ወጥመድ እንዳያገኝህ።</verse>
				<verse number="26">የሰውን ፊት በማፈር ራስህን ለዋስትና አትስጥ።</verse>
				<verse number="27">የምትከፍለው ባይኖርህ፥ ምንጣፍህን ከጎንህ ይወስዱብሃልና።</verse>
				<verse number="28">አባቶችህ የሠሩትን የቀድሞውን ድንበር አታፍርስ።</verse>
				<verse number="29">ነገርን የሚረዳ፥ በሥራውም ብልህ የሆነ ሰው፥ ወደ ነገሥታት ይቀርባል፤ በተዋረዱ ሰዎችም ፊት አይቆምም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="23">
				<verse number="1">በመኳንንት ማዕድ ለመብላት በተቀመጥህ ጊዜ፥ ያቀረቡልህን ፈጽመህ ዕወቅ፤</verse>
				<verse number="2">በእጅህ ተቀበል፥ እንደዚህም ታዘጋጅ ዘንድ እንዳለህ ዕወቅ።</verse>
				<verse number="3">ብትሳሳ ግን ምግቡን አትውደድ እርሱ የሐሰት እንጀራ ነውና።</verse>
				<verse number="4">አንተም ድሃ ስትሆን ከባለጠጋ ጋር አትወዳደር። በዐሳብህም ራቅ።</verse>
				<verse number="5">በእርሱ ላይ ዐይንህን ብታተኩር አታገኘውም፥ ለእርሱ የንስር ክንፍ ተዘጋጅቶለታልና። ወደሚቆምበትም ቤት ይመለሳልና።</verse>
				<verse number="6">ከስስታም ሰው ጋር አትመገብ፥ ምግቡንም አትመኝ፤</verse>
				<verse number="7">ሣርን እንደሚበላ ይበላል፥ ይጠጣልም፤ ወደ አንተም አታስገባው፥ ከእርሱ ጋርም እንጀራን አትብላ፥ ብላ፥ ጠጣ ይልሃል፥ ልቡ ግን ከአንተ ጋር አይደለም።</verse>
				<verse number="8">የበላኸውን ትተፋለህ፥ ያማረውንም ቃልህን ታጠፋለህ።</verse>
				<verse number="9">በሰነፍ ጆሮ አንዳች አትናገር፥ የነገርህን ጥበብ እንዳይንቅብህ።</verse>
				<verse number="10">አባቶችህ ያኖሩትን የድንበር ምልክት አታፍልስ፤ ወደ ድሃ አደጎች እርሻም አትግባ፤</verse>
				<verse number="11">ታዳጊአቸው እግዚአብሔር ጽኑ ነውና፥ እርሱም ፍርዳቸውን ከአንተ ጋር ይፋረዳልና።</verse>
				<verse number="12">ልብህን ለተግሣጽ ስጥ፥ ጆሮህንም ለዕውቀት ቃል አዘጋጅ።</verse>
				<verse number="13">ሕፃናትን ከመቅጣት ቸል አትበል፥ በበትር ብትመታቸው አይሞቱምና።</verse>
				<verse number="14">አንተ በበትር ትመታቸዋለህ፥ ነፍሳቸውን ግን ከሞት ታድናለህ።</verse>
				<verse number="15">ልጄ ሆይ፥ ልብህ ጠቢብ ይሁን ልቤን ደግሞ ደስ ያሰኛል፤</verse>
				<verse number="16">በከንፈሮችህ ቃሌ ብትኖር ለከንፈሮቼ የቀኑ ይሆናሉ።</verse>
				<verse number="17">ልብህ በኀጢአተኞች አይቅና፤ ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር፤</verse>
				<verse number="18">ብትጠብቃቸው ዘመድ ይሆኑሃል፥ ተስፋህም አትጠፋም።</verse>
				<verse number="19">ልጄ ሆይ፥ ስማ፥ ጠቢብም ሁን፥ የልብህንም ዐሳብ አቅና።</verse>
				<verse number="20">የወይን ጠጅ ጠጭ አትሁን፤ ለሥጋም አትሳሳ</verse>
				<verse number="21">ሰካራምና አመንዝራ ይደኸያል፥ እንቅልፋምም ሁሉ የተቦጫጨቀ ጨርቅ ይለብሳል።</verse>
				<verse number="22">ልጄ ሆይ፥ የወለደህን አባትህን ስማ፥ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት።</verse>
				<verse number="23">እውነትን ግዛ፥ አትሽጣትም፥ ጥበብንና ተግሣጽን፥ ማስተዋልንም።</verse>
				<verse number="24">ጻድቅ አባት በመልካም ያሳድጋል፥ በብልህ ልጅም ነፍሱ ደስ ይላታል።</verse>
				<verse number="25">አባትህና እናትህ በአንተ ደስ ይላቸዋል፥ አንተንም የወለደች ደስ ይላታል።</verse>
				<verse number="26">ልጄ ሆይ፥ ልብህን ስጠኝ፥ ዐይኖችህም መንገዴን ይጠብቁ።</verse>
				<verse number="27">አመንዝራ ሴት የተነደለች ማድጋ ናት፥ ሌላዪቱም ሴት የጠበበች ጕድጓድ ናት።</verse>
				<verse number="28">ወደ እርሷ የሄደ ፈጥኖ ይጠፋል፥ ጠማማ ሰውም ሁሉ ያልቃል።</verse>
				<verse number="29">ልጄ ሆይ፥ ዋይታ ለማን ነው? ጠብ ለማን ነው? ጩኸት ለማን ነው? ያለ ምክንያት መቍሰል ለማን ነው? የዐይን ቅላት ለማን ነው?</verse>
				<verse number="30">የወይን ጠጅ በመጠጣት ለሚዘገዩ አይደለምን? የወይንን ፍለጋ ለሚከተሉስ አይደለምን? ግብዣ ከተደረገ ዘንድ በወይን አትስከሩ፥ ነገር ግን ከደጋግ ሰዎች ጋር በመደማመጥ ተነጋገሩ።</verse>
				<verse number="31">ወደ ጽዋዎችና ወደ ብርሌ ዐይንህን ብትሰጥ፥ በኋላ እንደ ግንብ ዕራቁትህን ትሄዳለህ፤</verse>
				<verse number="32">በመጨረሻም እባብ እንደ ነደፈው፥ የእፉኝትም መርዝ እንደ ተሰራጨበት ትዘረጋለህ።</verse>
				<verse number="33">ዐይኖችህ ጋለሞታዎችን ያያሉ፥ ያንጊዜም አፍህ ጠማማ ነገርን ይናገራል።</verse>
				<verse number="34">በጥልቅ ባሕር ውስጥ እንደሚተኛ ትሆናለህ፥ በብዙ ማዕበል ውስጥም እንደሚቀዝፍ።</verse>
				<verse number="35">“መቱኝ፥ ያውም አልተሰማኝም፤ ዘበቱብኝ፥ እኔም አላወቅሁም። ከእኔ ጋር የሚሄዱትን መጥቼ እፈልግ ዘንድ መቼ ጧት ይሆናል?” ትላለህ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="24">
				<verse number="1">ልጄ ሆይ፥ በክፉ ሰዎች አትቅና፥ ከእነርሱም ጋር መኖርን አትውደድ፤</verse>
				<verse number="2">ልባቸው ሐሰትን ይማራልና። ከንፈራቸውም ምቀኝነትን ይናገራልና።</verse>
				<verse number="3">ቤት በጥበብ ይሠራል፥ በዕውቀትም ይጸናል።</verse>
				<verse number="4">በዕውቀት ከከበረውና ካማረው ሀብት ሁሉ ጓዳዎች ይሞላሉ።</verse>
				<verse number="5">ጠቢብ ሰው ከብርቱ ይሻላል፥ ከታላቅ ርስትም ይልቅ ዕውቀት ያለው ይበልጣል።</verse>
				<verse number="6">በአስተዳደር ጦርነት ይደረጋል፤ ርዳታም ከምትመክር ልብ ጋር ይሆናል።</verse>
				<verse number="7">ጥበብና መልካም ዕውቀት በብልሆች በር ትገኛለች፤ ብልሆች ከእግዚአብሔር ቃል አይርቁም።</verse>
				<verse number="8">ነገር ግን በአንድነት ያስባሉ፥ ሰነፎችንም ድንገት ሞት ያገኛቸዋል።</verse>
				<verse number="9">ሰነፍ በኀጢአት ይሞታል፤ ነፍሰ ገዳይ ሰውን ርኵሰቱ፥</verse>
				<verse number="10">በመከራ ቀንና በክፉ ቀን እስኪያልቅ ድረስ ያረክሰዋል።</verse>
				<verse number="11">ወደ ሞት የሚነዱትን ታደግ፤ የሚገደሉትንም መዋረዳቸውን ቸል አትበል።</verse>
				<verse number="12">እነሆ፥ ይህን አላውቅም ብትል፥ እግዚአብሔር የሁሉን ልብ እንዲያውቅ ዕወቅ። ለሁሉ እስትንፋስን የፈጠረ እርሱ ሁሉን ያውቃል። ለሁሉም እንደ ሥራው ይከፍለዋል።</verse>
				<verse number="13">ልጄ ሆይ፥ ማር ብላ፥ ወለላ ጕሮሮህን ያጣፍጥልህ ዘንድ መልካም ነውና።</verse>
				<verse number="14">እንዲሁም ጥበብን በሰውነትህ ተማር፥ ብታገኛት ፍጻሜህ መልካም ይሆናል፥ ተስፋህም አይጠፋም።</verse>
				<verse number="15">ኃጥኣንን ወደ ጻድቃን ቦታ አትውሰድ፤ በሆድህ ጥጋብም አትሳሳት፥</verse>
				<verse number="16">ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃል፥ ሰባት ጊዜም ይነሣል። ኃጥኣን ግን በክፉ ደዌ ይያዛሉ።</verse>
				<verse number="17">ጠላትህ ቢወድቅ ደስ አይበልህ፥ በመሰናከሉም አትታበይ።</verse>
				<verse number="18">እግዚአብሔር ያያልና፥ ደስም አያሰኘውምና፥ ቍጣውን ከእርሱ ይመልሳል።</verse>
				<verse number="19">ክፋትን በሚያደርጉ ሰዎች ደስ አይበልህ፥ በክፉዎችም አትቅና።</verse>
				<verse number="20">ዘመኑ ለክፉዎች አይሆንምና የኃጥኣንም መብራት ይጠፋልና።</verse>
				<verse number="21">ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔርንና ንጉሥን ፍራ፥ ከእነርሱ ለአንዱ ስንኳ እንቢ አትበል።</verse>
				<verse number="22">እነርሱ ኀጢአተኞችን ድንገት ይበቀሏቸዋልና፤ የሁለቱንስ ፍርድ ማን ያውቃል?</verse>
				<verse number="23">የነገሩትን የሚጠብቅ ልጅ ከጥፋት የራቀ ነው፥ የሚቀበልም እርሱን ይቀበለዋል።</verse>
				<verse number="24">ከንጉሥ አንደበት ምንም ሐሰት ይነገራል አይባልም፥ ከአንደበቱም የሚወጣ ሐሰት የለም።</verse>
				<verse number="25">የንጉሥ ቃል ሰይፍ ናት፥ ለጥፋት የተሰጠችውን ሰው ሰውነት ታጠፋዋለች እንጂ አንድን አካል ብቻ የምታጠፋ አይደለም።</verse>
				<verse number="26">ሰይፈ መዓቱ ብትሳል ግን ከዘሮቹ ጋር ሰውን ታጠፋለች፤ የሰውንም አጥንት ትቈረጥማለች።</verse>
				<verse number="27">በአሞሮች ጫጩት የማይበላ እስኪሆን ድረስ፥ እንደ እሳት ነበልባል ታቃጥላለች።</verse>
				<verse number="28">ልጄ ሆይ፥ ነገሬን ፍራ፥ ተቀበለው፥ ንስሓም ግባ፤ ይህንም በእግዚአብሔር ለሚያምኑ ተናግሬ ፈጸምሁ።</verse>
				<verse number="29">እኔ ከሰው ሁሉ ይልቅ ሰነፍ ነኝና፥ የሰውም ማስተዋል በእኔ ላይ አልነበረምና።</verse>
				<verse number="30">እግዚአብሔር ጥበብን አስተማረኝ፥ የቅዱሳንንም ዕውቀት ዐወቅሁ።</verse>
				<verse number="31">ወደ ሰማይ የወጣ፥ የወረደስ ማን ነው? ነፋስንስ በብብቱ የሰበሰበ ማን ነው? ውኃንስ በልብሱ የቋጠረ ማን ነው? የምድርንስ ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ፥ ስሙ ማን ነው? የልጁስ ስም ማን ነው?</verse>
				<verse number="32">የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ የጋለ ነው፤ እርሱን ለሚታመኑት ጋሻ ነው።</verse>
				<verse number="33">እንዳይዘልፍህ፥ ሐሰተኛም እንዳትሆን በቃሉ አንዳች አትጨምር።</verse>
				<verse number="34">ሁለትን ነገር ከአንተ እለምናለሁ፥ ሳልሞትም የሰጠኸኝን ጸጋህን አትከልክለኝ፤</verse>
				<verse number="35">ከንቱነትንና ሐሰተኛነትን ከእኔ አርቃቸው፤ ባለጠግነትንና ድህነትንም አትስጠኝ፤ ነገር ግን የሚያስፈልገኝንና የሚበቃኝን ስጠኝ፥</verse>
				<verse number="36">እጅግ ጠግቤ ሐሰተኛ እንዳልሆን፦ እግዚአብሔርስ ማን ነው? እንዳልል፤ ድሃም እንዳልሆን፥ እንዳልሰርቅም፥ በአምላኬም ስም በሐሰት እንዳልምል።</verse>
				<verse number="37">አገልጋይን በጌታው እጅ አሳልፈህ አትስጥ እንዳይረግምህና እንዳትጠፋ።</verse>
				<verse number="38">ክፉ ልጅ አባቱን ይረግማል፥ እናቱንም አያመሰግንም።</verse>
				<verse number="39">ክፉ ልጅ የራሱን ጽድቅ ይፈርዳል ነገር ግን መውጫውን አይረዳም።</verse>
				<verse number="40">ክፉ ትውልድ ትዕቢተኛ ዐይን አለው፥ ቅንድቦቹንም ከፍ ከፍ ያደርጋል።</verse>
				<verse number="41">ድሆችን ከምድር ላይ ችግረኞችንም ከሰው መካከል ያጠፋና ይጨርስ ዘንድ፥ ጥርሶቹ ሰይፍ፥ መንጋጎቹም መጋዝ የሆኑ ክፉ ትውልድ አለ።</verse>
				<verse number="42">በፍርድ ጊዜ የሰውን ፊት ማፈር መልካም እንዳይደለ ታውቁ ዘንድ ለጥበበኞች ይህን እነግራችኋለሁ።</verse>
				<verse number="43">ኃጥኡን፦ “ጻድቅ ነህ” የሚለውን ወገኖች ይረግሙታል፥ አሕዛብም ይጠሉታል፤</verse>
				<verse number="44">የሚዘልፉት ግን መታየትን ያሳምራሉ፥ በላያቸውም መልካም በረከት ትመጣላቸዋለች።</verse>
				<verse number="45">በቀና ነገር የሚመልስ ከንፈር ይሳማል።</verse>
				<verse number="46">ለመንገድህ ሥራህን አሰናዳ፥ ወደ እርሻ ተዘጋጅ፤ በኋላዬም ተከተልና ቤትህን ሥራ።</verse>
				<verse number="47">በባልንጀራህ ላይ በሐሰት ምስክር አትሁን፥ በከንፈርህም አትሳት።</verse>
				<verse number="48">እንዳደረገብኝ እንዲሁ አደርግበታለሁ፥ እንደ ገፋኝም እመልስበታለሁ አትበል።</verse>
				<verse number="49">በሰነፍ ሰው እርሻ አለፍሁ። አእምሮ በጐደለውም ሰው የወይን ቦታ ሔድሁ።</verse>
				<verse number="50">እነሆም፥ በላዩ እሾህ በቅሎበታል፥ ሣሩም ፈጽሞ ደርቋል፥ ምድረ በዳም ሆኖአል፤ የድንጋዩ ቅጥርም ፈርሶአል።</verse>
				<verse number="51">እኔ ንስሓ ከገባሁ በኋላ ተግሣጽን እመርጥ ዘንድ ተመለከትሁ።</verse>
				<verse number="52">ጥቂት ትተኛለህ፥ ጥቂትም ታንቀላፋለህ፥ ትተኛም ዘንድ ጥቂት እጅህን ወደ ብብትህ ትሰበስባለህ።</verse>
				<verse number="53">እንግዲህ ይህን ብታደርግ ድህነት እየቀደመች፥ ችግርም እንደ በጎ ሯጭ ትመጣብሃለች።</verse>
				<verse number="54">ለአልቅት ሦስት የሚዋደዱ ሴቶች ልጆች አሏት። ሦስቱም የማይጠግቡ ናቸው፤ አራተኛዪቱም በቃኝ ማለት ተሳናት፤</verse>
				<verse number="55">እነርሱም ሲኦልና የሴት ፍቅር፥ የማትወልድ ማኅፀን፥ ውኃ የማትጠግብየምድር ጕድጓድ፥ በቃኝ የማይሉ ውኃና እሳት ናቸው።</verse>
				<verse number="56">በአባቱ የሚሥቅ፥ የእናቱንም እርጅና የሚያክፋፋ ዐይንን የሸለቆ ቍራዎች ያወልቁታል፥ የአሞራዎች ግልገሎችም ይበሉታል።</verse>
				<verse number="57">ላውቃቸው የማልችል ሦስት ናቸው፥ አራተኛውንም ከቶ አላስተውለውም።</verse>
				<verse number="58">እነርሱም የሚበርር ንስር ዱካ፥ የእባብ መንገድ በድንጋይ ላይ፥ የመርከብ ዱካ በባሕር ላይ ሲሄድ፥ የሰውም መንገድ በወጣትነቱ፥</verse>
				<verse number="59">ሠርታ የምትታጠብ፦ ያደረግሁት አንዳች ክፉ ነገር የለም የምትል የአመንዝራ ሴት መንገድም እንዲሁ ነው።</verse>
				<verse number="60">በሦስት ነገር ምድር ትናወጣለች፥ አራተኛውንም ትሸከም ዘንድ አይቻላትም።</verse>
				<verse number="61">ባሪያ በነገሠ ጊዜ፥ ሰነፍም እንጀራን በጠገበ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="62">የተጠላች ሴት ቸር ባል ባገኘች ጊዜ፥ ሴት ባሪያም እመቤቷን በወረሰች ጊዜ።</verse>
				<verse number="63">በምድር ላይ አራት ጥቃቅን ፍጥረቶች አሉ፤ እነርሱ ግን እጅግ ጠቢባን ናቸው፤</verse>
				<verse number="64">ገብረ ጕንዳን ኀይል የሌላቸው ናቸው፥ ነገር ግን በመከር ጊዜ መኖዋቸውን ይሰበስባሉ።</verse>
				<verse number="65">ሽኮኮዎች ያልበረቱ ሕዝቦች ናቸው፥ ቤታቸውን ግን በቋጥኝ ድንጋይ ውስጥ ያደርጋሉ።</verse>
				<verse number="66">አንበጣ ያለ መንግሥት ነው፥ ነገር ግን በአንድ ትእዛዝ አብሮ ይሄዳል።</verse>
				<verse number="67">እንሽላሊት በእጅ የሚሄድ ደካማ ሲሆን፥ በነገሥታት ቤት ይኖራል።</verse>
				<verse number="68">መልካም አራማመድን የሚራመዱ ሦስት ፍጥረቶች አሉ፥ አራተኛውም መልካም አካሄድን ይሄዳል፤</verse>
				<verse number="69">የአንበሳ ደቦል ከእንስሳ ሁሉ የሚበረታ፥ የማይመለስ፥ እንስሳንም የማይፈራ፤</verse>
				<verse number="70">ክንፉን እያማታ በእንስቶች ዶሮዎች መካከል የሚሄድ አውራ ዶሮ፤ መንጋን የሚመራ አውራ ፍየል፤ ንጉሥ ሕዝብን ሲገሥጽ።</verse>
				<verse number="71">ራስህን ለቦዘኔነት ብትሰጥ፥ እጅህንም ለክርክር ብትዘረጋ ቷረዳለህ።</verse>
				<verse number="72">ወተትን እለብ ቅቤ ይሆንልሃል፥ አፍንጫንም ብትጨምቅ ደም ይወጣል፤ እንዲሁም ነገርን መጐተት ጭቅጭቅንና ቅጣትን ያወጣል።</verse>
				<verse number="73">የእኔ ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ተነገረ። እናቱ ያስተማረችው የንጉሥ ቃል።</verse>
				<verse number="74">ልጄ ሆይ፥ የእግዚአብሔር ቃል ምን እንደሆነ ዐውቀህ ተጠበቅ። የበኸር ልጄ ሆይ፥ ምንድን ነው? የማኅፀኔ ልጅ ሆይ፥ ምንድን ነው? የስእለቴ ልጅ ሆይ፥ ምንድን ነው? ለእግዚአብሔርና ለንጉሥ የማይገባውን አታድርግ።</verse>
				<verse number="75">ኋላ እንዳትጸጸት ገንዘብህን፥ ልብህንና ጕልበትህን፥ ለሴቶች አትስጥ።</verse>
				<verse number="76">ከምክር ጋር ሁሉን አድርግ፥ ከምክር ጋር ወይን ጠጣ፥ መኳንንት ቍጡዎች ናቸው፥ ነገር ግን ወይን አይጠጡ።</verse>
				<verse number="77">ወይንን በመጠጣት ጥበብን እንዳይዘነጓት ለድሆች ፍርድን ማቃናት አይችሉምና።</verse>
				<verse number="78">ለኀዘንተኞች ወይንን ስጧቸው፥ የተከዙም ወይንን ይጠጡ።</verse>
				<verse number="79">ኀዘናቸውን ይረሱ ዘንድ፥ መከራንም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳያስቡ።</verse>
				<verse number="80">አፍህን በእግዚአብሔር ቃል ክፈት፥ ለሕያዋንም ሁሉ ፍረድ።</verse>
				<verse number="81">አፍህን ክፈት፥ በእውነትም ፍረድ፤ ለድሃና ለምስኪን ፍረድ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="25">
			</chapter>
			<chapter number="26">
			</chapter>
			<chapter number="27">
			</chapter>
			<chapter number="28">
			</chapter>
			<chapter number="29">
			</chapter>
			<chapter number="30">
			</chapter>
			<chapter number="31">
			</chapter>
		</book>
		<book number="21">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለእ​ስ​ራ​ኤል የነ​ገሠ የዳ​ዊት ልጅ የሰ​ባ​ኪው የሰ​ሎ​ሞን ቃል።</verse>
				<verse number="2">ሰባ​ኪው፥ “ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከ​ንቱ ከንቱ ሁሉ ከንቱ ነው” ይላል።</verse>
				<verse number="3">ከፀ​ሐይ በታች በሚ​ደ​ክ​ም​በት ድካም ሁሉ የሰው ትርፉ ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="4">ትው​ልድ ያል​ፋል፥ ትው​ል​ድም ይመ​ጣል፤ ምድር ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጸንታ ትኖ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="5">ፀሐይ ይወ​ጣል፥ ፀሐ​ይም ይገ​ባል፥ ወደ​ሚ​ወ​ጣ​በ​ትም ስፍራ ይመ​ለ​ሳል፤</verse>
				<verse number="6">ወደ ቀኝ ይመ​ለ​ሳል፥ ወደ ሰሜ​ንም ይዞ​ራል፤ ነፋስ ዙሪ​ያ​ዉን ዙሮ ይሄ​ዳል፥ ነፋ​ስም በዙ​ረቱ ይመ​ለ​ሳል።</verse>
				<verse number="7">ፈሳ​ሾች ሁሉ ወደ ባሕር ይሄ​ዳሉ፥ ባሕሩ ግን አይ​ሞ​ላም፤ ፈሳ​ሾች ወደ​ሚ​ሄ​ዱ​በት ስፍራ እንደ ገና ወደ​ዚያ ይመ​ለ​ሳሉ።</verse>
				<verse number="8">ነገር ሁሉ ያደ​ክ​ማል፤ ሰውም ይና​ገ​ረው ዘንድ አይ​ች​ልም፥ ዐይን በማ​የት አይ​ጠ​ግ​ብም፥ ጆሮም በመ​ስ​ማት አይ​ሞ​ላም።</verse>
				<verse number="9">የሆ​ነው ነገር እርሱ የሚ​ሆን ነው፥ የተ​ደ​ረ​ገ​ውም ነገር እርሱ የሚ​ደ​ረግ ነው፥ ከፀ​ሐ​ይም በታች ከተ​ደ​ረ​ገው ሁሉ አዲስ ነገር የለም።</verse>
				<verse number="10">እነሆ፥ “ይህ ነገር አዲስ ነው” ብሎ የሚ​ና​ገር ማን ነው? እርሱ ከእኛ በፊት በነ​በ​ሩት ዘመ​ናት ተደ​ር​ጓል።</verse>
				<verse number="11">ለፊ​ተ​ኞቹ ነገ​ሮች መታ​ሰ​ቢያ የላ​ቸ​ውም፤ ለኋ​ለ​ኞ​ቹም ነገ​ሮች ከእ​ነ​ርሱ በኋላ በሚ​ነ​ሡት ሰዎች ዘንድ መታ​ሰ​ቢያ አይ​ገ​ኝ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="12">እኔ ሰባ​ኪው በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ንጉሥ ነበ​ርሁ።</verse>
				<verse number="13">ከሰ​ማ​ይም በታች ስለ​ተ​ደ​ረ​ገው ሁሉ በጥ​በብ ለመ​መ​ር​መ​ርና ለመ​ፈ​ተን ልቤን አተ​ጋሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይደ​ክ​ሙ​በት ዘንድ ክፉ ድካ​ምን ለሰው ልጆች ሰጥ​ት​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="14">ከፀ​ሐይ በታች የተ​ሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እነ​ሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።</verse>
				<verse number="15">ጠማማ ይቀና ዘንድ አይ​ች​ልም፤ ጐደ​ሎም ይቈ​ጠር ዘን​ድ​አ​ይ​ች​ልም።</verse>
				<verse number="16">እኔ በልቤ፥ “እነሆ፥ ከእኔ አስ​ቀ​ድ​መው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ከነ​በ​ሩት ሁሉ ይልቅ ጥበ​ብን አበ​ዛሁ፤ ልቤ​ንም ለጥ​በ​ብና ለዕ​ው​ቀት ሰጠሁ፥” በማ​ለት ተና​ገ​ርሁ።</verse>
				<verse number="17">ልቤም ብዙ ጥበ​ብ​ንና አእ​ም​ሮን፥ ምሳ​ሌ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን ተመ​ለ​ከ​ተች። ይህም ነፋ​ስን መከ​ተል እንደ ሆነ አስ​ተ​ዋ​ልሁ።</verse>
				<verse number="18">በጥ​በብ መብ​ዛት ትካዜ ይበ​ዛ​ልና፤ ዕው​ቀ​ት​ንም የሚ​ያ​በዛ መከ​ራን ያበ​ዛ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">እኔ በልቤ፥ “ና በደ​ስ​ታም እፈ​ት​ን​ሃ​ለሁ፥ እነሆ፥ መል​ካ​ም​ንም እይ” አልሁ፤ ይህም እነሆ፥ ከንቱ ነበረ።</verse>
				<verse number="2">ሣቅን፥ “ሽን​ገላ ነህ፤ ደስ​ታ​ንም፦ ምን ታደ​ር​ጋ​ለህ?” አል​ሁት።</verse>
				<verse number="3">የሰው ልጆች በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው ዘመን ሁሉ ከፀ​ሐይ በታች የሚ​ሠ​ሩት መል​ካም ነገር ምን እንደ ሆነ እስ​ካይ ድረስ ልቤ በጥ​በብ እየ​መ​ራኝ፥ ሰው​ነ​ቴን በወ​ይን ደስ ለማ​ሰ​ኘት፥ ስን​ፍ​ና​ንም ለመ​ያዝ በልቤ መረ​መ​ርሁ።</verse>
				<verse number="4">እኔ ሥራ​ዬን አበ​ዛሁ፥ ቤቶ​ች​ንም ለእኔ ሠራሁ፥ ወይ​ንም ተከ​ልሁ።</verse>
				<verse number="5">የወ​ይ​ንና የአ​ት​ክ​ልት ቦታን አደ​ረ​ግሁ፥ ወይ​ንና ልዩ ልዩ ፍሬ ያለ​ባ​ቸ​ው​ንም ዛፎች ተከ​ል​ሁ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">የሚ​ያ​ፈራ እን​ጨ​ት​ንና የተ​ተ​ከ​ሉ​ትን ዛፎች አጠ​ጣ​በት ዘንድ የውኃ ማጠ​ራ​ቀ​ሚ​ያን አደ​ረ​ግሁ።</verse>
				<verse number="7">ወን​ዶ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ችን ገዛሁ፤ በቤት የተ​ወ​ለዱ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ነበ​ሩኝ፤ ከእኔ አስ​ቀ​ድ​መው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከነ​በ​ሩት ሁሉ ይልቅ ብዙ የበ​ጎ​ችና የከ​ብ​ቶች መን​ጋ​ዎች ነበ​ሩኝ።</verse>
				<verse number="8">ብር​ንና ወር​ቅን፥ የከ​በ​ረ​ው​ንም የነ​ገ​ሥ​ታ​ት​ንና የአ​ው​ራ​ጆ​ችን መዝ​ገብ ለራሴ ሰበ​ሰ​ብሁ፤ ሴቶ​ችና ወን​ዶች አዝ​ማ​ሪ​ዎ​ችን፥ የሰ​ዎች ልጆ​ች​ንም ተድላ አደ​ረ​ግሁ፤ የወ​ይን ጠጅ ጠማ​ቂ​ዎ​ች​ንና አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ች​ንም አበ​ዛሁ።</verse>
				<verse number="9">ከእ​ኔም አስ​ቀ​ድ​መው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከነ​በ​ሩት ሁሉ ይልቅ ከበ​ርሁ፥ ታላ​ቅም ሆንሁ። ጥበ​ቤም ከእኔ ጋር ጸና​ች​ልኝ።</verse>
				<verse number="10">ዐይ​ኖቼ ከፈ​ለ​ጉት ሁሉ አላ​ጣ​ሁም፥ ልቤ​ንም ከደ​ስታ ሁሉ አል​ከ​ለ​ከ​ል​ሁ​ትም፤ ልቤ በድ​ካሜ ሁሉ ደስ ይለው ነበ​ርና፤ ከድ​ካ​ሜም ሁሉ ይህ ዕድል ፋን​ታዬ ሆነ።</verse>
				<verse number="11">እጄ የሠ​ራ​ቻ​ትን ሥራ​ዬን ሁሉ፥ የደ​ከ​ም​ሁ​በ​ት​ንም ድካ​ሜን ሁሉ ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነሆ፥ ሁሉ ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነበረ፥ ከፀ​ሐይ በታ​ችም ትርፍ አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="12">እኔም ጥበ​ብን፥ ሽን​ገ​ላ​ንና ስን​ፍ​ናን አይ ዘንድ ተመ​ለ​ከ​ትሁ ፥ ምክ​ርን የሚ​ከ​ተል፥ ምሳ​ሌ​ንስ ሁሉ የሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ላት ሰው ማን ነው?</verse>
				<verse number="13">እኔም ብር​ሃን ከጨ​ለማ እን​ደ​ሚ​በ​ልጥ እን​ዲሁ ከአ​ላ​ዋቂ ይልቅ ለብ​ልህ ብልጫ እን​ዳ​ለው ተመ​ለ​ከ​ትሁ።</verse>
				<verse number="14">የጠ​ቢብ ዐይ​ኖች በራሱ ላይ ናቸ​ውና፤ አላ​ዋቂ ግን በጨ​ለማ ይሄ​ዳል፤ ደግሞ የሁ​ለ​ቱም መጨ​ረ​ሻ​ቸው አንድ እንደ ሆነ አስ​ተ​ዋ​ልሁ።</verse>
				<verse number="15">እኔም በልቤ፥ “አላ​ዋ​ቂን የሚ​ያ​ገ​ኘው እን​ዲሁ እኔ​ንም ያገ​ኘ​ኛል፤ እኔም ለምን እጅግ ጠቢብ ሆንሁ?” አልሁ፤ የዚ​ያን ጊዜም በልቤ፥ “ይህ ደግሞ ከንቱ ነው” አልሁ፥ አላ​ዋቂ በከ​ንቱ መና​ገ​ርን ያበ​ዛ​ልና።</verse>
				<verse number="16">ለብ​ልህ ከአ​ላ​ዋቂ ጋር ለዘ​ለ​ዓ​ለም መታ​ሰ​ቢያ የለ​ውም፤ እነሆ፥ ዘመን ይመ​ጣ​ልና ሁሉም ይረ​ሳል፤ ብል​ህስ ከአ​ላ​ዋቂ ጋር እን​ዴት ይሞ​ታል?</verse>
				<verse number="17">ከፀ​ሐ​ይም በታች የተ​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ በእኔ ላይ ክፉ ነውና ሕይ​ወ​ትን ጠላሁ፥ ሁሉም ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።</verse>
				<verse number="18">ከእኔ በኋላ ለሚ​ወ​ለድ ሰው እተ​ወ​ዋ​ለ​ሁና ከፀ​ሐይ በታች እኔ የደ​ከ​ም​ሁ​በ​ትን ድካም ሁሉ ጠላ​ሁት።</verse>
				<verse number="19">ጠቢብ ወይም አላ​ዋቂ እን​ደ​ሚ​ሆን ከፀ​ሐይ በታ​ችም በደ​ከ​ም​ሁ​በ​ትና ጠቢብ በሆ​ን​ሁ​በት በድ​ካሜ ሁሉ ይሰ​ለ​ጥን እንደ ሆነ የሚ​ያ​ውቅ ሰው ማን ነው? ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።</verse>
				<verse number="20">እኔም ተመ​ልሼ ልቤን ከፀ​ሐይ በታች በደ​ከ​ም​ሁ​በት ድካም ሁሉ ተስፋ አስ​ቈ​ረ​ጥ​ሁት።</verse>
				<verse number="21">ሰው በጥ​በ​ብና በዕ​ው​ቀት በብ​ር​ታ​ትም ከደ​ከመ በኋላ ለሌላ ላል​ደ​ከ​መ​በት ሰው ዕድ​ሉን ያወ​ር​ሳ​ልና፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ትል​ቅም መከራ ነው።</verse>
				<verse number="22">ከፀ​ሐይ በታች በደ​ከ​መ​በት ድካ​ምና በልቡ ዐሳብ ሁሉ ለሰው አይ​ሆ​ን​ለ​ት​ምና፤</verse>
				<verse number="23">ዘመኑ ሁሉ መከራ፥ ቍጣም፥ ቅሚ​ያም ነው፤ ልቡም በሌ​ሊት አይ​ተ​ኛም፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።</verse>
				<verse number="24">ለሰው ከመ​ብ​ላ​ትና ከመ​ጠ​ጣት በድ​ካ​ሙም ለሰ​ው​ነቱ መል​ካም ነገር ከሚ​ያ​ሳ​ያት በቀር በጎ ነገር የለም፤ ይህ ደግሞ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ እንደ ተሰጠ አየሁ።</verse>
				<verse number="25">ያለ እርሱ ፈቃድ የሚ​በላ ወይም የሚ​ጠጣ ማን ነው?</verse>
				<verse number="26">እርሱ በፊቱ ደግ ለሆነ ሰው ጥበ​ብ​ንና ዕው​ቀ​ትን፥ ደስ​ታ​ንም ይሰ​ጠ​ዋል፤ ለኀ​ጢ​አ​ተኛ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደግ ለሆነ ይሰጥ ዘንድ እን​ዲ​ሰ​በ​ስ​ብና እን​ዲ​ያ​ከ​ማች ጥረ​ትን ይሰ​ጠ​ዋል። ይህ ደግሞ ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከፀ​ሐይ በታ​ችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።</verse>
				<verse number="2">ለመ​ፅ​ነስ ጊዜ አለው፥ ለመ​ው​ለ​ድም ጊዜ አለው፤ ለመ​ኖር ጊዜ አለው፥ ለመ​ሞ​ትም ጊዜ አለው፤ ለመ​ት​ከል ጊዜ አለው፥ የተ​ተ​ከ​ለ​ው​ንም ለመ​ን​ቀል ጊዜ አለው።</verse>
				<verse number="3">ለመ​ግ​ደል ጊዜ አለው፥ ለመ​ፈ​ወ​ስም ጊዜ አለው፤ ለማ​ፍ​ረስ ጊዜ አለው፥ ለመ​ሥ​ራ​ትም ጊዜ አለው፤</verse>
				<verse number="4">ለማ​ል​ቀስ ጊዜ አለው፥ ለመ​ሣ​ቅም ጊዜ አለው፤ ዋይ ለማ​ለት ጊዜ አለው፥ ለመ​ዝ​ፈ​ንም ጊዜ አለው።</verse>
				<verse number="5">ድን​ጋ​ይን ለመ​ወ​ር​ወር ጊዜ አለው፥ ድን​ጋ​ይ​ንም ለመ​ሰ​ብ​ሰብ ጊዜ አለው፤ ለመ​ተ​ቃ​ቀፍ ጊዜ አለው፥ ከመ​ተ​ቃ​ቀ​ፍም ለመ​ራቅ ጊዜ አለው፤</verse>
				<verse number="6">ለመ​ፈ​ለግ ጊዜ አለው፥ ለማ​ጥ​ፋ​ትም ጊዜ አለው፤ ለመ​ጠ​በቅ ጊዜ አለው፥ ለመ​ጣ​ልም ጊዜ አለው፤</verse>
				<verse number="7">ለመ​ቅ​ደድ ጊዜ አለው፥ ለመ​ስ​ፋ​ትም ጊዜ አለው፤ ዝም ለማ​ለት ጊዜ አለው፥ ለመ​ና​ገ​ርም ጊዜ አለው፤</verse>
				<verse number="8">ለመ​ው​ደድ ጊዜ አለው፥ ለመ​ጥ​ላ​ትም ጊዜ አለው፤ ለጦ​ር​ነት ጊዜ አለው፥ ለሰ​ላ​ምም ጊዜ አለው።</verse>
				<verse number="9">ለሠ​ራ​ተኛ የድ​ካሙ ትርፍ ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ልጆች ይደ​ክ​ሙ​በት ዘንድ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ድካም ሁሉ አይ​ቻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">የሠ​ራው ሥራ ሁሉ በጊ​ዜው መል​ካም ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከጥ​ንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠ​ራ​ውን ሥራ ሰው መር​ምሮ እን​ዳ​ያ​ገኝ ዘለ​ዓ​ለ​ም​ነ​ትን በልቡ ሰጠው።</verse>
				<verse number="12">ሰው ደስ ከሚ​ለ​ውና በሕ​ይ​ወቱ ሳለ መል​ካ​ምን ነገር ከሚ​ያ​ደ​ርግ በቀር በው​ስ​ጣ​ቸው መል​ካም ነገር እን​ደ​ሌለ ዐወ​ቅሁ።</verse>
				<verse number="13">ደግ​ሞም ሰው ሁሉ ይበ​ላና ይጠጣ ዘንድ በድ​ካ​ሙም ሁሉ መል​ካ​ምን ያይ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጦታ ነው።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ረ​ገው ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዲ​ኖር ዐወ​ቅሁ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ መጨ​መር ከእ​ነ​ር​ሱም ማጕ​ደል አይ​ቻ​ልም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፊቱ ይፈሩ ዘንድ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="15">በፊት የተ​ደ​ረ​ገው አሁን አለ። ይደ​ረግ ዘንድ ያለ​ውም እነሆ ተደ​ር​ጓል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያለ​ፈ​ውን መልሶ ይሻ​ዋል።</verse>
				<verse number="16">ደግ​ሞም ከፀ​ሐይ በታች በጻ​ድቅ ስፍራ ኃጥእ፥ በኃ​ጥ​እም ስፍራ ጻድቅ እን​ዳለ አየሁ።</verse>
				<verse number="17">እኔም በልቤ፥ “በዚያ ለነ​ገር ሁሉና ለሥራ ሁሉ ጊዜ አለ​ውና በጻ​ድ​ቁና በኀ​ጢ​አ​ተ​ኛው ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ዳል” አልሁ።</verse>
				<verse number="18">እኔ በልቤ ስለ ሰው ልጆች ነገር፥ “እንደ እን​ስሳ መሆ​ና​ቸ​ውን ያሳይ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋል” አልሁ።</verse>
				<verse number="19">ለሰው ልጆች ሞት አለ​ባ​ቸው፥ ለእ​ን​ስ​ሳም ሞት አለ​ባ​ቸው፤ አንድ ሞት አለ​ባ​ቸው፤ አንዱ እን​ደ​ሚ​ሞት ሌላ​ውም እን​ዲሁ ይሞ​ታል፤ ለሁ​ሉም አንድ እስ​ት​ን​ፋስ አላ​ቸው፥ ሰው ከእ​ን​ስሳ ብል​ጫው ምን​ድን ነው? ሁሉም ከንቱ ነውና ምንም የለ​ውም።</verse>
				<verse number="20">ሁሉም ወደ አንድ ቦታ ይሄ​ዳል፤ ሁሉ ከአ​ፈር ተገኘ፥ ሁሉም ወደ አፈር ይመ​ለ​ሳል።</verse>
				<verse number="21">የሰው ልጆች ነፍስ ወደ ላይ እን​ደ​ም​ት​ወጣ፥ የእ​ን​ስ​ሳም ነፍስ ወደ ታች ወደ ምድር እን​ደ​ም​ት​ወ​ርድ የሚ​ያ​ውቅ ማን ነው?</verse>
				<verse number="22">ያም ዕድል ፋን​ታው ነውና ሰው በሥ​ራው ደስ ከሚ​ለው በቀር ሌላ መል​ካም ነገር እን​ደ​ሌ​ለው አየሁ፤ ከእ​ርሱ በኋ​ላስ የሚ​ሆ​ነ​ውን ያይ ዘንድ የሚ​ያ​መ​ጣው ማን ነው?</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ እነ​ሆም፥ የተ​ገ​ፉት ሰዎች እንባ ነበረ፤ የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ቸ​ውም አል​ነ​በ​ረም፤ በሚ​ገ​ፉ​አ​ቸ​ውም እጅ ኀይል ነበረ። እነ​ር​ሱን ግን የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ቸው አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="2">እኔም እስከ ዛሬ በሕ​ይ​ወት ካሉት ሕያ​ዋን ይልቅ በቀ​ድሞ ዘመን የሞ​ቱ​ትን አመ​ሰ​ገ​ን​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ከእ​ነ​ዚ​ህም ከሁ​ለቱ ይልቅ ገና ያል​ተ​ወ​ለ​ደው ከፀ​ሓ​ይም በታች የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ክፉ ሥራ ሁሉ ያላየ ይሻ​ላል።</verse>
				<verse number="4">እኔ ድካ​ምን ሁሉና የብ​ል​ሃት ሥራ​ውን ተመ​ለ​ከ​ትሁ፥ ለሰ​ውም በባ​ል​ን​ጀ​ራው ዘንድ ቅን​አ​ትን እን​ዲ​ያ​ስ​ነሣ አየሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።</verse>
				<verse number="5">ሰነፍ እጆ​ቹን ኰር​ትሞ ይቀ​መ​ጣል፥ የገዛ ሥጋ​ው​ንም ይበ​ላል።</verse>
				<verse number="6">በድ​ካ​ምና ነፋ​ስን በመ​ከ​ተል ከሁ​ለት እጅ ሙሉ ይልቅ አንድ እጅ ሙሉ በዕ​ረ​ፍት ይሻ​ላል።</verse>
				<verse number="7">እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም ከንቱ ነገ​ርን አየሁ።</verse>
				<verse number="8">አንድ ሰው ብቻ​ውን አለ፥ ሁለ​ተ​ኛም የለ​ውም፥ ልጅም ሆነ ወን​ድም የለ​ውም፤ ለድ​ካሙ ግን መጨ​ረሻ የለ​ውም፥ ዐይ​ኖ​ቹም ከባ​ለ​ጠ​ግ​ነት አይ​ጠ​ግ​ቡም። ለማን እደ​ክ​ማ​ለሁ? ሰው​ነ​ቴ​ንስ ከደ​ስታ ለምን እነ​ፍ​ጋ​ታ​ለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር፥ ክፉም ጥረት ነው።</verse>
				<verse number="9">ድካ​ማ​ቸው መል​ካም ዋጋ አለ​ውና አንድ ብቻ ከመ​ሆን ሁለት መሆን ይሻ​ላል።</verse>
				<verse number="10">አንዱ ቢወ​ድቅ ሁለ​ተ​ኛው ያነ​ሣ​ዋ​ልና፥ አንድ ብቻ​ውን ሆኖ በወ​ደቀ ጊዜ ግን የሚ​ያ​ነ​ሣው ሁለ​ተኛ የለ​ው​ምና ወዮ​ለት።</verse>
				<verse number="11">ሁለ​ቱም በአ​ን​ድ​ነት ቢተኙ ይሞ​ቃ​ቸ​ዋል፤ አንድ ብቻ​ውን ግን እን​ዴት ይሞ​ቀ​ዋል?</verse>
				<verse number="12">አን​ዱም ሌላ​ውን ቢያ​ሸ​ንፍ ሁለቱ በፊቱ ይቆ​ማሉ፤ በሦ​ስ​ትም የተ​ገ​መደ ገመድ ፈጥኖ አይ​በ​ጠ​ስም።</verse>
				<verse number="13">ድሃና ጠቢብ ብላ​ቴና ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ተግ​ሣ​ጽን መቀ​በል ከማ​ያ​ውቅ ከሰ​ነፍ ሽማ​ግሌ ንጉሥ ይሻ​ላል።</verse>
				<verse number="14">በመ​ን​ግ​ሥቱ ችግ​ረኛ ቢሆ​ንም ከግ​ዞት ቤት ለመ​ን​ገሥ ወጥ​ቶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="15">ከፀ​ሓይ በታች የሚ​ሄ​ዱ​ትን ሕያ​ዋን ሁሉ በእ​ርሱ ፋንታ ከሚ​ነ​ሣው ከሌ​ላው ጐል​ማሳ ጋር ሆነው አየሁ።</verse>
				<verse number="16">ከእ​ርሱ በፊት የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ቍጥር የላ​ቸ​ውም፤ በኋላ የሚ​መ​ጡት ግን በእ​ርሱ ደስ አይ​ላ​ቸ​ውም። ይህ ደግሞ ከንቱ ነው፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በም​ት​ሄ​ድ​በት ጊዜ እግ​ር​ህን ጠብቅ፤ የጠ​ቢ​ባ​ን​ንም ትም​ህ​ርት ለመ​ስ​ማት ቅረብ፤ ዳግ​መ​ኛም ከሰ​ነ​ፎች ስጦታ መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገህ ከመ​ቀ​በል ተጠ​በቅ፤ እነ​ርሱ መል​ካም ለመ​ሥ​ራት ዐዋ​ቂ​ዎች አይ​ደ​ሉ​ምና።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማይ፥ አን​ተም በም​ድር ነህና በአ​ፍህ አት​ፍ​ጠን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቃልን ይና​ገር ዘንድ ልብህ አይ​ቸ​ኩል፤ ስለ​ዚ​ህም ቃልህ ጥቂት ይሁን።</verse>
				<verse number="3">ሕልም በብዙ መከራ፥ እን​ዲ​ሁም የሰ​ነፍ ቃል በብዙ ነገር ይመ​ጣ​ልና።</verse>
				<verse number="4">ፈቃዱ አይ​ደ​ለ​ምና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለት በተ​ሳ​ልህ ጊዜ ትፈ​ጽ​መው ዘንድ አት​ዘ​ግይ፤ አንተ ግን እንደ ተሳ​ልህ ስእ​ለ​ት​ህን ስጥ።</verse>
				<verse number="5">ተስ​ለህ የማ​ት​ፈ​ጽም ከሆነ ባት​ሳል ይሻ​ላል።</verse>
				<verse number="6">ለሥ​ጋህ በደል አፍ​ህን አት​ስጥ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት፥ “ባለ​ማ​ወቅ ነው” አት​በል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ቃልህ እን​ዳ​ይ​ቈጣ፥ የእ​ጅ​ህ​ንም ሥራ እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ብህ፤</verse>
				<verse number="7">ብዙ ሕልም፥ እን​ዲሁ ደግሞ ብዙ ቃል ከንቱ ነውና፤ አንተ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽ​መህ ፍራ።</verse>
				<verse number="8">ከፍ ካለው በላይ ከፍ ያለ ይጠ​ብ​ቅ​ሃ​ልና፥ ከእ​ነ​ር​ሱም በላይ ደግሞ ሌሎች ከፍ ይላ​ሉና በሀ​ገሩ ድሃ ሲበ​ደል፥ ፍር​ድና ጽድ​ቅም ሲነ​ጠቅ ብታይ በሥ​ራው አታ​ድ​ንቅ።</verse>
				<verse number="9">የም​ድር ጥቅም ለሁሉ ነው፥ የን​ጉ​ሥም ጥቅም በእ​ርሻ ነው።</verse>
				<verse number="10">ብርን የሚ​ወ​ድድ ሰው ብርን አይ​ጠ​ግ​ብም፤ ብዙ እህ​ል​ንም የሚ​ወ​ድድ እን​ዲሁ ነው፤ ይህም ከንቱ ነው።</verse>
				<verse number="11">ሀብት ሲበዛ የሚ​በ​ሉት ይበ​ዛሉ፤ በዐ​ይ​ኑም ከማ​የት በቀር ለባ​ለ​ቤቱ ምን ይጠ​ቅ​መ​ዋል?</verse>
				<verse number="12">ብዙ ወይም ጥቂት ቢበላ የአ​ገ​ል​ጋይ እን​ቅ​ልፉ ጣፋጭ ነው፤ ብል​ጽ​ግ​ናን ያበዛ ሰውን ግን ይተኛ ዘንድ የሚ​ተ​ወው የለም።</verse>
				<verse number="13">ከፀ​ሓይ በታች ያየ​ሁት ክፉ ደዌ አለ፤ ለመ​ከ​ራው በባ​ለ​ቤቱ ዘንድ የተ​ቈ​ጠ​በች ባለ​ጠ​ግ​ነት ናት።</verse>
				<verse number="14">ያችም ባለ​ጠ​ግ​ነት በክፉ ንጥ​ቂያ ትጠ​ፋ​ለች፤ ልጅ​ንም ቢወ​ልድ በእጁ ምንም የለ​ውም።</verse>
				<verse number="15">ከእ​ናቱ ሆድ ራቁ​ቱን እንደ ወጣ እን​ዲሁ እንደ መጣው ይመ​ለ​ሳል፤ ከጥ​ረ​ቱም በእጁ ሊወ​ስድ የሚ​ች​ለው ምንም የለም።</verse>
				<verse number="16">ይህም ደግሞ የሚ​ያ​ሳ​ዝን ክፉ ደዌ ነው፥ እንደ መጣ እን​ዲሁ ይሄ​ዳ​ልና፥ ለሰ​ው​ነቱ ለሚ​ደ​ክም ሰው ትርፉ ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="17">ዘመኑ ሁሉ በጨ​ለማ በል​ቅ​ሶና በብዙ ብስ​ጭት በደ​ዌና በኀ​ዘን ነውና።</verse>
				<verse number="18">እነሆ፥ እኔ ያየ​ሁት መል​ካ​ምና የተ​ዋበ ነገር፦ ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ጠው በሕ​ይ​ወቱ ዘመን ሁሉ ይበ​ላና ይጠጣ ዘንድ፥ ከፀ​ሐይ በታ​ችም በሚ​ደ​ክ​ም​በት ድካም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ ነው፤ ይህ ዕድል ፈን​ታው ነውና።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ሁሉ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ት​ንና ሀብ​ትን መስ​ጠቱ፥ ከእ​ር​ስ​ዋም ይበ​ላና ዕድል ፈን​ታ​ውን ይወ​ስድ ዘንድ፥ በድ​ካ​ሙም ደስ ይለው ዘንድ ማሠ​ል​ጠኑ ይህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጦታ ነው።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በልቡ ደስታ ስለ​ሚ​ያ​ደ​ክ​መው እርሱ የሕ​ይ​ወ​ቱን ዘመን ሁሉ እጅግ አያ​ስ​ብም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">ከፀ​ሐይ በታች ያየ​ሁት ክፉ ነገር አለ፥ እር​ሱም በሰው ላይ እጅግ የበዛ ነው።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ሀብ​ት​ንና ጥሪ​ትን ክብ​ር​ንም ሰጠው፥ ከወ​ደ​ደ​ውም ሁሉ ለሰ​ው​ነቱ የከ​ለ​ከ​ላት የለም፤ ነገር ግን ሌላ ሰው ይበ​ላ​ዋል እንጂ ከእ​ርሱ ይበላ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አላ​ሠ​ለ​ጠ​ነ​ውም፤ ይህም ከን​ቱና ክፉ ደዌ ነው።</verse>
				<verse number="3">ሰው መቶ ልጆች ቢወ​ልድ፥ ብዙ ዘመ​ንም በሕ​ይ​ወት ቢኖር፥ ዕድ​ሜ​ውም ብዙ ዓመት ቢሆን፥ ነገር ግን ነፍሱ መል​ካ​ምን ባት​ጠ​ግብ፥ መቃ​ብ​ር​ንም ባያ​ገኝ፥ እኔ ስለ እርሱ፥ “ከእ​ርሱ ይልቅ ጭን​ጋፍ ይሻ​ላል” አልሁ።</verse>
				<verse number="4">በከ​ንቱ መጥ​ቶ​አል፥ በጨ​ለ​ማም ይሄ​ዳል፥ ስሙ በጨ​ለማ ይሸ​ፈ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="5">ደግ​ሞም ፀሐ​ይን አላ​የም፥ አላ​ወ​ቀ​ምም፤ ስለ​ዚህ ከዚያ ይልቅ ለዚህ ዕረ​ፍት አለው።</verse>
				<verse number="6">ሺህ ዓመት ሁለት ጊዜ በሕ​ይ​ወት ቢኖር፥ መል​ካ​ም​ንም ባያይ፥ ሁሉ ወደ አንድ ስፍራ የሚ​ሄድ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="7">የሰው ድካም ሁሉ በአፉ ነው፥ ነፍሱ ግን አት​ጠ​ግ​ብም።</verse>
				<verse number="8">ከአ​ላ​ዋቂ ይልቅ ለጠ​ቢብ ጥቅሙ ምን​ድር ነው? በሕ​ያ​ዋን ፊትስ መሄ​ድን ለሚ​ያ​ውቅ ለድሃ ጥቅሙ ምን​ድር ነው?</verse>
				<verse number="9">በዐ​ይን ማየት በነ​ፍስ ከመ​ቅ​በ​ዝ​በዝ ይሻ​ላል፥ ይህ ደግሞ ከንቱ ነው፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።</verse>
				<verse number="10">የሆ​ነው ሁሉ እነሆ፥ ስሙ አስ​ቀ​ድሞ ተጠራ፥ ሰውም እንደ ሆነ ታወቀ፤ ከእ​ር​ሱም ከሚ​በ​ረ​ታው ጋር ይፋ​ረድ ዘንድ አይ​ች​ልም።</verse>
				<verse number="11">ከን​ቱን የሚ​ያ​በዛ ብዙ ነገር አለና፥ ለሰው ጥቅሙ ምን​ድር ነው?</verse>
				<verse number="12">ሰው በከ​ንቱ ወራቱ ቍጥ​ርና እንደ ጥላ በሚ​ያ​ሳ​ል​ፈው ዘመኑ በሕ​ይ​ወቱ ሳለ ለሰው የሚ​ሻ​ለ​ውን የሚ​ያ​ውቅ ማን ነው? ወይስ ለሰው ከፀ​ሓይ በታች ከእ​ርሱ በኋላ የሚ​ሆ​ነ​ውን ማን ይነ​ግ​ረ​ዋል?</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">ከመ​ል​ካም ሽቱ መል​ካም ስም፥ ከመ​ወ​ለድ ቀንም የሞት ቀን ይሻ​ላል።</verse>
				<verse number="2">ወደ ግብዣ ቤትም ከመ​ሄድ ወደ ልቅሶ ቤት መሄድ ይሻ​ላል፤ እርሱ የሰው ሁሉ ፍጻሜ ነውና፥ ሕያ​ውም የሆነ ይህን መል​ካም ነገር በልቡ ያኖ​ረ​ዋል።</verse>
				<verse number="3">ከሣቅ ኀዘን ይሻ​ላል፥ ከፊት ኀዘን የተ​ነሣ ልብ ደስ ይሰ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="4">የጠ​ቢ​ባን ልብ በል​ቅሶ ቤት ነው፤ የሰ​ነ​ፎች ልብ ግን በደ​ስታ ቤት ነው።</verse>
				<verse number="5">ለሰው የሰ​ነ​ፎ​ችን ዘፈን ከሚ​ሰማ ይልቅ የጠ​ቢ​ባ​ንን ተግ​ሣጽ መስ​ማት ይሻ​ለ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">ከድ​ስት በታች እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠል እሾህ ድምፅ የሰ​ነፍ ሣቅ እን​ዲሁ ነው፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።</verse>
				<verse number="7">ግፍ ጠቢ​ብን ያሳ​ብ​ደ​ዋል፥ የል​ቡ​ንም ትዕ​ግ​ሥት ያጠ​ፋ​ዋል።</verse>
				<verse number="8">የነ​ገር ፍጻሜ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ይሻ​ላል፤ ታጋ​ሽም ከልብ ትዕ​ቢ​ተኛ ይሻ​ላል።</verse>
				<verse number="9">በመ​ን​ፈ​ስህ ለቍጣ ችኩል አት​ሁን፥ ቍጣ በሰ​ነ​ፎች ብብት ያር​ፋ​ልና።</verse>
				<verse number="10">ከዚህ ዘመን ይልቅ ያለ​ፈው ዘመን ለምን ተሻለ? ብለህ አት​ና​ገር፤ የዚ​ህን ነገር በጥ​በብ አት​ጠ​ይ​ቅ​ምና።</verse>
				<verse number="11">ጥበብ ከር​ስት ጋር መል​ካም ነው፤ ፀሓ​ይ​ንም ለሚ​ያዩ ሰዎች ትር​ፍን ይሰ​ጣል።</verse>
				<verse number="12">የጥ​በብ ጥላ ከብር ጥላ ይሻ​ላል፤ የጥ​በ​ብ​ንም ዕው​ቀት ማብ​ዛት ገን​ዘብ ላደ​ረ​ጋት ሕይ​ወ​ትን ትሰ​ጠ​ዋ​ለች።</verse>
				<verse number="13">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ተመ​ል​ከት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠማማ ያደ​ረ​ገ​ውን ማን ሊያ​ቀ​ናው ይች​ላል?</verse>
				<verse number="14">በመ​ል​ካም ቀን ደስ ይበ​ልህ ፤ በክ​ፉም ቀን ተመ​ል​ከት፤ ሰው ከእ​ርሱ በኋላ መር​ምሮ ምንም እን​ዳ​ያ​ገኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ንም ያንም እን​ደ​ዚያ ሠራ።</verse>
				<verse number="15">ጻድቅ በጽ​ድቁ ሲጠፋ፥ ኃጥ​እም በክ​ፋቱ ሲኖር፥ ይህን ሁሉ በከ​ንቱ ዘመኔ አየሁ።</verse>
				<verse number="16">እጅግ ጻድቅ አት​ሁን፥ እጅ​ግም ጠቢብ አት​ሁን፥ እን​ዳ​ት​በ​ድል።</verse>
				<verse number="17">እጅግ ክፉ አት​ሁን፥ እል​ከ​ኛም አት​ሁን፥ ያለ ጊዜህ እን​ዳ​ት​ሞት።</verse>
				<verse number="18">ይህን ብት​ይዝ ለአ​ንተ መል​ካም ነው፤ በዚ​ህም እጅ​ህን አታ​ር​ክስ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ከሁሉ ይወ​ጣ​ልና።</verse>
				<verse number="19">በከ​ተማ ከሚ​ኖሩ ዐሥር ገዢ​ዎች ይልቅ ጥበብ ጠቢ​ብን ትረ​ዳ​ዋ​ለች።</verse>
				<verse number="20">በም​ድር ላይም መል​ካ​ምን የሚ​ሠራ ኀጢ​አ​ት​ንም የማ​ያ​ደ​ርግ ጻድቅ ሰው አይ​ገ​ኝ​ምና።</verse>
				<verse number="21">አገ​ል​ጋ​ይህ ሲረ​ግ​ምህ እን​ዳ​ት​ሰማ በሚ​ጫ​ወ​ቱ​በት ቃል ሁሉ ልብ​ህን አት​ጣል።</verse>
				<verse number="22">ብዙ ጊዜ ያበ​ሳ​ጭ​ሃ​ልና፤ በብዙ መን​ገ​ድም ልብ​ህን ያስ​ከ​ፋ​ታ​ልና፥ አንተ ደግሞ ሌሎ​ችን እንደ ረገ​ምህ ታው​ቃ​ለ​ህና።</verse>
				<verse number="23">ይህን ሁሉ በጥ​በብ ፈተ​ንሁ፥ ጠቢ​ብም እሆ​ና​ለሁ አልሁ፥ እር​ስዋ ግን ከእኔ ራቀች።</verse>
				<verse number="24">ርቃና እጅግ ጠልቃ ሳለች መር​ምሮ የሚ​ያ​ገ​ኛት ማን ነው?</verse>
				<verse number="25">አው​ቅና እመ​ረ​ምር ዘንድ ጥበ​ብ​ንና የነ​ገ​ሩን ሁሉ መደ​ም​ደ​ሚያ እፈ​ልግ ዘንድ፥ የክ​ፉ​ዎ​ች​ንም ስን​ፍ​ናና ዕብ​ደት አውቅ ዘንድ እኔ በልቤ ዞርሁ።</verse>
				<verse number="26">እኔም ከሞት ይልቅ የመ​ረ​ረች ነገ​ርን አገ​ኘሁ፤ እር​ስ​ዋም ልብዋ ወጥ​መ​ድና መረብ የሆነ፥ በእ​ጆ​ች​ዋም ማሰ​ሪያ ያላት ሴት ናት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ደግ የሆነ ከእ​ርሷ ያመ​ል​ጣል። ኀጢ​አ​ተኛ ግን ይጠ​መ​ድ​ባ​ታል።</verse>
				<verse number="27">እነሆ፥ ይህን ነገር አገ​ኘሁ ይላል ሰባ​ኪው፥ መደ​ም​ደ​ሚ​ያን ለማ​ግ​ኘት አን​ዲ​ቱን በአ​ን​ዲቱ ጨምሬ ወደ ነገሩ ሁሉ መደ​ም​ደ​ሚያ እደ​ርስ ዘንድ ብመ​ረ​ምር፥</verse>
				<verse number="28">ነፍሴ የፈ​ለ​ገ​ች​ውን አላ​ገ​ኘ​ሁም፤ ከሺህ ወን​ዶች አንድ አገ​ኘሁ፥ ከእ​ነ​ዚያ ሁሉ መካ​ከል ግን አን​ዲት ሴት አላ​ገ​ኘ​ሁም።</verse>
				<verse number="29">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጊ​ዜው ሰዎ​ችን ቅኖች አድ​ርጎ እንደ ሠራ​ቸው እነሆ፥ ይህን ብቻ አገ​ኘሁ፥ እነ​ርሱ ግን ብዙ ዕው​ቀ​ትን ይሻሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">ዐዋ​ቂ​ዎ​ችን ማን ያው​ቃ​ቸ​ዋል? ቃላ​ቸ​ው​ንስ መተ​ር​ጐም የሚ​ያ​ውቅ ማን ነው? የሰው ጥበቡ ፊቱን ታበ​ራ​ለች፥ በፊ​ቱም ኀፍ​ረት የሌ​ለው ሰው ይጠ​ላል።</verse>
				<verse number="2">ልጄ ሆይ፥ የን​ጉ​ሥን አፍ ጠብቅ፤ ለመ​ሐላ ቃልም አት​ቸ​ኩል።</verse>
				<verse number="3">የወ​ደ​ደ​ውን ሁሉ ያደ​ር​ጋ​ልና ከፊቱ ሂድ፥ በክፉ ነገ​ርም አት​ቁም፥</verse>
				<verse number="4">ንጉሥ እንደ መሆኑ ኀይል አለ​ውና፤ ይህ​ንስ ለምን ታደ​ር​ጋ​ለህ? ማን ይለ​ዋል?</verse>
				<verse number="5">ትእ​ዛ​ዝን የሚ​ጠ​ብቅ ክፉን ነገር አያ​ው​ቅም፤ የጠ​ቢ​ብም ልብ የፍ​ር​ድን ጊዜ ያው​ቃል።</verse>
				<verse number="6">የሰው ዕው​ቀት በእ​ርሱ ላይ ታላቅ ስለ ሆነ ለነ​ገር ሁሉ ጊዜና ፍርድ አለ​ውና።</verse>
				<verse number="7">የሚ​ሆ​ነ​ው​ንም ምንም የሚ​ያ​ውቅ የለም፤ እን​ዴ​ትስ እን​ደ​ሚ​ሆን የሚ​ነ​ግ​ረው ማን ነው?</verse>
				<verse number="8">መን​ፈ​ስን ለማ​ስ​ቀ​ረት በመ​ን​ፈሱ ላይ ሥል​ጣን ያለው ሰው የለም፤ በሞ​ትም ቀን ሥል​ጣን የለ​ውም፤ በጦ​ር​ነ​ትም ጊዜ ስን​ብት የለም፥ ኀጢ​አ​ትም ሠሪ​ውን አያ​ድ​ነ​ውም።</verse>
				<verse number="9">ይህን ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት አየሁ፥ ከፀ​ሓ​ይም በታች ወደ ተደ​ረ​ገው ሥራ ሁሉ ልቤን ሰጠሁ፤ ሰውም ሰውን ለመ​ጕ​ዳት ገዥ የሚ​ሆ​ን​በት ጊዜ አለ።</verse>
				<verse number="10">እን​ዲ​ሁም ያን​ጊዜ ኃጥ​ኣን ወደ ጽኑ መቃ​ብር ሲገቡ አየሁ፥ ከቅ​ድ​ስት ስፍ​ራም ወጥ​ተው ተለዩ፤ እነ​ር​ሱም በከ​ተ​ማዋ ተመ​ሰ​ገኑ፥ እን​ዲህ ሠር​ተ​ዋ​ልና፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።</verse>
				<verse number="11">ክፉን ከሚ​ያ​ደ​ርጉ ወገን ፈጥኖ ክር​ክ​ርን የሚ​ያ​ደ​ርግ የለ​ምና፤ ስለ​ዚህ የሰው ልጆች ልብ በእ​ነ​ርሱ ክፉን ለመ​ሥ​ራት ጠነ​ከረ።</verse>
				<verse number="12">የበ​ደለ ከጥ​ንት ጀምሮ ከዚ​ያም በፊት ኀጢ​አ​ትን አድ​ር​ጓል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለሚ​ፈ​ሩት በፊ​ቱም ለሚ​ፈ​ሩት ደኅ​ን​ነት እን​ዲ​ሆን አው​ቃ​ለ​ሁና፤</verse>
				<verse number="13">ለኃ​ጥእ ግን ደኅ​ን​ነት የለ​ውም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት አይ​ፈ​ራ​ምና ዘመኑ እንደ ጥላ አት​ረ​ዝ​ምም።</verse>
				<verse number="14">ከፀ​ሓይ በታች በም​ድር የሚ​ደ​ረግ ከንቱ ነገር አለ፥ በኃ​ጥ​ኣን የሚ​ደ​ረ​ገው ሥራ የሚ​ደ​ር​ስ​ባ​ቸው ጻድ​ቃን አሉ፥ ለጻ​ድ​ቃ​ንም የሚ​ደ​ረ​ገው ሥራ የሚ​ደ​ር​ስ​ላ​ቸው ኃጥ​ኣን አሉ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው አልሁ።</verse>
				<verse number="15">ከሚ​በ​ላ​ውና ከሚ​ጠ​ጣው፥ ደስም ከሚ​ለው በቀር ለሰው ከፀ​ሓይ በታች ሌላ መል​ካም ነገር የለ​ው​ምና እኔ ደስ​ታን አመ​ሰ​ገ​ንሁ፤ ይህም ከፀ​ሓይ በታች ከድ​ካሙ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ይ​ወቱ ዘመን ለእ​ርሱ የሰ​ጠው ነው።</verse>
				<verse number="16">ጥበ​ብን አውቅ ዘንድ በም​ድር የሚ​ሆ​ነ​ው​ንም ድካም አይ ዘንድ ልቤን ሰጠሁ፥ በቀ​ንና በሌ​ሊት እን​ቅ​ል​ፍን በዐ​ይኑ የሚ​ያይ የለ​ምና።</verse>
				<verse number="17">ከፀ​ሓ​ይም በታች የተ​ደ​ረ​ገ​ውን ሥራ መር​ምሮ ያገኝ ዘንድ ለሰው እን​ዳ​ይ​ቻ​ለው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ሁሉ አየሁ። ሰውም ሊፈ​ልግ እጅግ ቢደ​ክም መር​ምሮ አያ​ገ​ኘ​ውም፤ ደግ​ሞም ጠቢብ ሰው፥ “ይህን ዐወ​ቅሁ” ቢል እርሱ ያገ​ኘው ዘንድ አይ​ች​ልም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">ይህን ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ለልቤ ሰጠሁ፥ ጻድ​ቃ​ንና ጠቢ​ባን ሥራ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ እንደ ሆኑ፥ ይህን ሁሉ ልቤ ተመ​ለ​ከ​ተች፤ ፍቅር ወይም ጥል ቢሆን ሰው አያ​ው​ቅም፥ ሁሉ ወደ ፊታ​ቸው ነው።</verse>
				<verse number="2">በሁ​ሉም ከን​ቱ​ነት አለ፥ የጻ​ድ​ቁና የበ​ደ​ለ​ኛው፥ የመ​ል​ካ​ሙና የክ​ፉው፥ የን​ጹ​ሑና የር​ኩሱ፥ መሥ​ዋ​ዕ​ትን የሚ​ሠ​ዋ​ውና የማ​ይ​ሠ​ዋው፥ የመ​ል​ካ​ሙና እን​ዲሁ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛው፥ የመ​ሐ​ላ​ኛ​ውና እን​ዲሁ መሐ​ላን የሚ​ፈ​ራው ድርሻ አንድ ነው።</verse>
				<verse number="3">ከፀ​ሓይ በታች የተ​ደ​ረ​ገው ክፉ ሁሉ ለሁሉ ነው፤ የሁሉ ድርሻ አንድ ነውና። ደግ​ሞም የሰው ልጆች ልብ ክፋ​ትን ትሞ​ላ​ለች፥ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው ሳሉ ሁከት በል​ባ​ቸው አለ፥ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሙታን ይወ​ር​ዳሉ።</verse>
				<verse number="4">ከሕ​ያ​ዋን ጋር አን​ድ​ነት ያለው ማንም ሰው ተስፋ አለ​ውና ከሞተ አን​በሳ ያል​ሞተ ውሻ ይሻ​ላል።</verse>
				<verse number="5">ሕያ​ዋን እን​ዲ​ሞቱ ያው​ቃ​ሉና፤ ሙታን ግን አን​ዳች አያ​ው​ቁም፤ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ቸ​ውም ተረ​ስ​ቶ​አ​ልና ከዚህ በኋላ ዋጋ የላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="6">ፍቅ​ራ​ቸ​ውና ጥላ​ቸው ቅን​አ​ታ​ቸ​ውም በአ​ን​ድ​ነት እነሆ፥ ጠፍ​ቶ​አል፤ ከፀ​ሓይ በታ​ችም በሚ​ሠ​ራው ነገር ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዕድል ፈንታ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ​ህን ተቀ​ብ​ሎ​ታ​ልና፦ ና እን​ጀ​ራ​ህን በደ​ስታ ብላ፥ በበጎ ልቡ​ናም የወ​ይን ጠጅ​ህን ጠጣ።</verse>
				<verse number="8">ሁል​ጊዜ ልብ​ስህ ነጭ ይሁን፤ ቅባ​ትም ከራ​ስህ ላይ አይ​ታጣ።</verse>
				<verse number="9">በሕ​ይ​ወ​ትህ፥ አን​ተም ከፀ​ሓይ በታች በም​ት​ደ​ክ​ም​በት ድካም ይህ ዕድል ፈን​ታህ ነውና ከንቱ በሆነ በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ፥ ከፀ​ሓይ በታች በሰ​ጠህ፥ በከ​ንቱ ዘመ​ንህ ሁሉ፥ ከም​ት​ወ​ድ​ዳት ሚስ​ትህ ጋር ደስ ይበ​ልህ።</verse>
				<verse number="10">አንተ በም​ት​ሄ​ድ​በት በሲ​ኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕው​ቀ​ትና ጥበብ አይ​ገ​ኙ​ምና እጅህ ለማ​ድ​ረግ የም​ት​ች​ለ​ውን ሁሉ እንደ ኀይ​ልህ አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="11">እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም ሩጫ ለፈ​ጣ​ኖች፥ ጦር​ነ​ትም ለኀ​ያ​ላን፥ እን​ጀ​ራም ለጠ​ቢ​ባን፥ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትም ለአ​ስ​ተ​ዋ​ዮች፥ ሞገ​ስም ለዐ​ዋ​ቂ​ዎች እን​ዳ​ል​ሆነ አየሁ፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ያገ​ና​ኛ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="12">ሰውም ጊዜ​ውን አያ​ው​ቅም፤ በክፉ መረብ እንደ ተጠ​መዱ ዓሣ​ዎች ፥ በወ​ጥ​መ​ድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እን​ዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድ​ን​ገት ሲወ​ድ​ቅ​ባ​ቸው ይጠ​መ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="13">ከፀ​ሓይ በታ​ችም ጥበ​ብን አየሁ፥ እር​ስ​ዋም በእኔ ዘንድ ታላቅ ናት።</verse>
				<verse number="14">ታናሽ ከተማ ነበ​ረች፥ ጥቂ​ቶች ሰዎ​ችም ነበ​ሩ​ባት፤ ታላቅ ንጉ​ሥም መጣ​ባት፥ ከበ​ባ​ትም፥ ታላቅ ግን​ብ​ንም ሠራ​ባት።</verse>
				<verse number="15">ጠቢብ ድሃ ሰውም በው​ስ​ጥዋ ተገ​ኘ​ባት፥ ያች​ንም ከተማ በጥ​በቡ አዳ​ናት፤ ያን ድሃ ሰው ግን ማንም አላ​ሰ​በ​ውም።</verse>
				<verse number="16">እኔም፥ “ከኀ​ይል ይልቅ ጥበብ ትበ​ል​ጣ​ለች፤ የድ​ሃው ጥበብ ግን ተና​ቀች ቃሉም አል​ተ​ሰ​ማ​ችም” አልሁ።</verse>
				<verse number="17">በስ​ን​ፍና ከሚ​ፈ​ርዱ ፈራ​ጆች ጩኸት ይልቅ የጠ​ቢ​ባን ቃል በጸ​ጥታ ትሰ​ማ​ለች።</verse>
				<verse number="18">ከጦር መሣ​ሪ​ያ​ዎች ይልቅ ጥበብ ትሻ​ላ​ለች፤ አንድ ኀጢ​አ​ተኛ ግን ብዙ መል​ካ​ምን ያጠ​ፋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">የሞቱ ዝን​ቦች የተ​ቀ​መ​መ​ውን የዘ​ይት ሽቱ ያገ​ሙ​ታል፤ በስ​ን​ፍ​ናም ካለ ታላቅ ክብር ይልቅ ትንሽ ጥበብ ትበ​ል​ጣ​ለች።</verse>
				<verse number="2">የጠ​ቢብ ልብ በስ​ተ​ቀኙ ነው፥ የሰ​ነፍ ልብ ግን በስ​ተ​ግ​ራው ነው።</verse>
				<verse number="3">ደግ​ሞም ሰነፍ በልቡ ፈቃ​ድና መን​ገድ በሚ​ሄድ ጊዜ አእ​ምሮ ይጐ​ድ​ለ​ዋል፥ የሚ​ያ​ስ​በ​ውም ሁሉ ሰን​ፍና ነው።</verse>
				<verse number="4">ትዕ​ግ​ሥት ታላ​ቁን ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ር​ያ​ልና የገዢ ቍጣ የተ​ነ​ሣ​ብህ እንደ ሆነ ስፍ​ራ​ህን አት​ል​ቀቅ።</verse>
				<verse number="5">ከፀ​ሓይ በታች ያየ​ሁት ክፉ ነገር አለ፥ እር​ሱም ከገዢ ባለ​ማ​ወቅ የሚ​ወጣ ስሕ​ተት ነው፥</verse>
				<verse number="6">ሰነፍ በታ​ላቅ ማዕ​ርግ ላይ ተሾመ፥ ባለ​ጠ​ጎች ግን በተ​ዋ​ረደ ስፍራ ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="7">አገ​ል​ጋ​ዮች በፈ​ረስ ላይ ሲቀ​መጡ፥ መኳ​ን​ን​ትም እንደ አገ​ል​ጋ​ዮች በም​ድር ላይ በእ​ግ​ራ​ቸው ሲሄዱ አየሁ።</verse>
				<verse number="8">ለባ​ል​ን​ጀ​ራው ጕድ​ጓ​ድን የሚ​ምስ ይወ​ድ​ቅ​በ​ታል፥ ቅጥ​ር​ንም የሚ​ያ​ፈ​ር​ስን እባብ ትነ​ድ​ፈ​ዋ​ለች።</verse>
				<verse number="9">ድን​ጋ​ይን የሚ​ፈ​ነ​ቅል ይታ​መ​ም​በ​ታል፥ ዕን​ጨ​ት​ንም የሚ​ፈ​ልጥ ይጐ​ዳ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="10">ምሣሩ ከዛ​ቢ​ያው ቢወ​ልቅ ሰው​የው ፊቱን ወዲ​ያና ወዲህ ይላል፤ ብዙ ኀይ​ልም ያስ​ፈ​ል​ገ​ዋል። ጥበብ ግን ለብ​ርቱ ሰው ትርፉ ነው፤</verse>
				<verse number="11">እባብ ቢነ​ድፍ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ትም ባያ​ድን ባለ መድ​ኀ​ኒቱ አይ​ጠ​ቀ​ምም።</verse>
				<verse number="12">የጠ​ቢብ ሰው የአፉ ቃል ሞገስ ናት፤ የሰ​ነፍ ከን​ፈ​ሮች ግን ራሱን ይው​ጡ​ታል።</verse>
				<verse number="13">የአፉ ቃል መጀ​መ​ሪያ ስን​ፍና ነው፥ የን​ግ​ግ​ሩም ፍጻሜ ክፉ ነው።</verse>
				<verse number="14">ሰነፍ ነገ​ርን ያበ​ዛል፤ ሰውም የሆ​ነ​ው​ንና ወደ ፊት የሚ​ሆ​ነ​ውን አያ​ው​ቅም፤ ከእ​ርሱ በኋላ የሚ​ሆ​ነ​ው​ንስ ማን ይነ​ግ​ረ​ዋል?</verse>
				<verse number="15">የሰ​ነፍ ድካሙ ያሠ​ቃ​የ​ዋል፥ ወደ ከተማ መሄ​ድን አያ​ው​ቅ​ምና።</verse>
				<verse number="16">ንጉ​ሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳ​ን​ን​ቶ​ች​ሽም ማል​ደው የሚ​በሉ፥ አንቺ ሀገር ሆይ፥ ወዮ​ልሽ!</verse>
				<verse number="17">ንጉ​ሥሽ የጌታ ልጅ የሆነ፥ መኳ​ን​ን​ቶ​ች​ሽም ለብ​ር​ታት በጊዜ የሚ​በሉ፥ የማ​ያ​ፍ​ሩም፥ አንቺ ሀገር ሆይ፥ የተ​መ​ሰ​ገ​ንሽ ነሽ።</verse>
				<verse number="18">በሰ​ዎች ስን​ፍ​ናና ቦዘ​ኔ​ነት የቤት ጣራ ይዘ​ብ​ጣል፥ በእ​ጆች ስን​ፍ​ናም ቤት ያፈ​ስ​ሳል።</verse>
				<verse number="19">ሰነ​ፎች ሰዎች እን​ጀ​ራን ለሣቅ ያደ​ር​ጉ​ታል፥ የወ​ይን ጠጅም ሕያ​ዋ​ንን ደስ ያሰ​ኛል፥ ሁሉም ለገ​ን​ዘብ ይገ​ዛል።</verse>
				<verse number="20">የሰ​ማይ ዎፍ ቃል​ህን ያወ​ጣ​ዋ​ልና፥ ክንፍ ያለ​ውም ነገ​ር​ህን ያወ​ራ​ዋ​ልና በል​ብህ ዐሳብ እን​ኳን ቢሆን ንጉ​ሥን አት​ሳ​ደብ፥ በመ​ኝታ ቤት​ህም ባለ​ጠ​ጋን አት​ሳ​ደብ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">እን​ጀ​ራ​ህን በውኃ ፊት ላይ ጣለው፥ ከብዙ ቀን በኋላ ታገ​ኝ​ኘ​ዋ​ለ​ህና።</verse>
				<verse number="2">ለሰ​ባት፥ ደግ​ሞም ለስ​ም​ን​ት​ዕ​ድል ፈን​ታን ስጥ፥ በም​ድር ላይ የሚ​ሆ​ነ​ውን ክፉ ነገር ምን እንደ ሆነ አታ​ው​ቅ​ምና።</verse>
				<verse number="3">ደመ​ናት ዝናም በሞሉ ጊዜ በም​ድር ላይ ያፈ​ስ​ሱ​ታል፤ ዛፍም ወደ ደቡብ ወይም ወደ ሰሜን ቢወ​ድቅ፥ ዛፉ በወ​ደ​ቀ​በት ስፍራ በዚያ ይኖ​ራል።</verse>
				<verse number="4">ነፋ​ስን የሚ​ጠ​ባ​በቅ አይ​ዘ​ራም፥ ደመ​ና​ት​ንም የሚ​መ​ለ​ከት አያ​ጭ​ድም።</verse>
				<verse number="5">የነ​ፋስ መን​ገድ እን​ዴት እንደ ሆነች፥ አጥ​ን​ትም በእ​ር​ጉዝ ሆድ እን​ዴት እን​ድትዋ​ደድ እን​ደ​ማ​ታ​ውቅ፥ እን​ዲ​ሁም ሁሉን የሚ​ሠ​ራ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ አታ​ው​ቅም።</verse>
				<verse number="6">ይህ ወይም ያ ማና​ቸው እን​ዲ​በ​ቅል ወይም ሁለቱ መል​ካም እንደ ሆኑ አታ​ው​ቅ​ምና በማ​ለዳ ዘር​ህን ዝራ፥ በማ​ታም እጅ​ህን አት​ተው።</verse>
				<verse number="7">ብር​ሃን ጣፋጭ ነው፥ ፀሓ​ይ​ንም ማየት ለዐ​ይን መል​ካም ነው።</verse>
				<verse number="8">ሰው ብዙ ዘመን በሕ​ይ​ወት ቢኖር፥ በሁ​ሉም ደስ ቢለው፤ የጨ​ለ​ማ​ውን ዘመን ያስብ፥ ብዙ ቀን ይሆ​ና​ልና። የሚ​መ​ጣ​ውም ነገር ሁሉ ከንቱ ነው።</verse>
				<verse number="9">አንተ ጐበዝ፥ በጕ​ብ​ዝ​ናህ ደስ ይበ​ልህ፥ በጕ​ብ​ዝ​ና​ህም ወራት ልብ​ህን ደስ ይበ​ለው፥ በል​ብ​ህም መን​ገድ፥ ዐይ​ኖ​ች​ህም በሚ​ያ​ዩት ሂድ፤ ዳሩ ግን ስለ​ዚህ ነገር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ፍርድ እን​ዲ​ያ​መ​ጣህ ዕወቅ።</verse>
				<verse number="10">ሕፃ​ን​ነ​ትና ጕብ​ዝና፥ አለ​ማ​ወ​ቅም ከንቱ ናቸ​ውና ከል​ብህ ቍጣን አርቅ፥ ከሰ​ው​ነ​ት​ህም ክፉ ነገ​ርን አስ​ወ​ግድ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">የጭ​ን​ቀት ቀን ሳይ​መጣ በጕ​ብ​ዝ​ናህ ወራት ፈጣ​ሪ​ህን ዐስብ፤ ደስ አያ​ሰ​ኙም የም​ት​ላ​ቸው ዓመ​ታት ሳይ​ደ​ርሱ፥</verse>
				<verse number="2">ፀሓ​ይና ብር​ሃን፥ ጨረ​ቃና ከዋ​ክ​ብ​ትም ሳይ​ጨ​ልሙ፥ ደመ​ና​ትም ከዝ​ናብ በኋላ ሳይ​መ​ለሱ፥</verse>
				<verse number="3">ቤት ጠባ​ቆች በሚ​ን​ቀ​ጠ​ቀ​ጡ​በት፥ ኀያ​ላን ሰዎ​ችም በሚ​ጐ​ብ​ጡ​በት፥ ጥቂ​ቶች ሆነ​ዋ​ልና ፈጭ​ታ​ዎች ሥራ በሚ​ፈ​ቱ​በት፥ በመ​ስ​ኮ​ትም ሆነው የሚ​መ​ለ​ከቱ በሚ​ጨ​ል​ሙ​በት፥</verse>
				<verse number="4">በአ​ደ​ባ​ባ​ይም ደጆቹ በሚ​ዘ​ጉ​በት ቀን፥ የወ​ፍጮ ድምፅ ሲላሽ፥ ከዎፍ ድምፅ የተ​ነሣ ሰው ሲነሣ፥ ዜማም የሚ​ጮኹ ሴቶች ልጆች ሁሉ ዝግ ሲሉ፤</verse>
				<verse number="5">ከፍ ያለ​ውን ተመ​ል​ክ​ተው ደግሞ ሲፈሩ፥ ድን​ጋ​ጤም በመ​ን​ገድ ላይ ሲሆን፤ ለው​ዝም ሲያ​ብብ፥ አን​በ​ጣም እንደ ሸክም ሲከ​ብድ፥ ፍሬም ሳይ​በ​ተን፤ ሰው ወደ ዘለ​ዓ​ለም ቤቱ ሲሄድ፥ አል​ቃ​ሾ​ችም በአ​ደ​ባ​ባይ ሲዞሩ፤</verse>
				<verse number="6">የብር ድሪ ሳይ​በ​ጠስ፥ የወ​ር​ቅም ኵስ​ኵ​ስት ሳይ​ሰ​በር፥ ማድ​ጋ​ውም በም​ንጭ አጠ​ገብ ሳይ​ከ​ሰ​ከስ፥ ወደ መስ​ኮት የሚ​ያዩ ዐይ​ኖች ሳይ​ጠፉ፥ የአ​ደ​ባ​ባይ ደጆች ሳይ​ዘጉ፥ ስለ ቃላት ድን​ጋጤ ከጠ​ላት ቃል የተ​ነሣ የሚ​ጮኹ ሳይ​ነሡ፥ በአ​ዳም ልጆች ሁሉ ወዮታ ሳይ​ሆን፥ ወደ ላይም ሳይ​መ​ለ​ከቱ፥ በመ​ን​ገ​ድም ፍር​ሀት ሳይ​መጣ፥ እሳ​ትም ወደ ላይ ከፍ ማለ​ትን በወ​ደደ ጊዜ ሳይ​ታይ፥ በአ​ደ​ባ​ባይ ልቅሶ ሳይ​ሰማ፥ የብር መልኩ ሳይ​ለ​ወጥ፥ የወ​ር​ቅም መልኩ ሳይ​ጠፋ፥ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሩም በጕ​ድ​ጓድ ላይ ሳይ​ሰ​በር፥</verse>
				<verse number="7">አፈ​ርም ወደ ነበ​ረ​በት ምድር ሳይ​መ​ለስ፥ ነፍ​ስም ወደ ሰጠው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሳይ​መ​ለስ በሥ​ጋም በነ​በ​ረ​በት ጊዜ መል​ካም ወይም ክፉ ቢሆን ስለ ሠራው ሁሉ መልስ ሳይ​ሰጥ ፈጣ​ሪ​ህን አስብ።</verse>
				<verse number="8">ሰባ​ኪው አለ፥ “ሁሉ ከንቱ፥ የከ​ንቱ ከንቱ ነው።”</verse>
				<verse number="9">ሰባ​ኪ​ውም ጠቢብ ስለ ሆነ ለሕ​ዝቡ ዕው​ቀ​ትን አስ​ተ​ማረ፥ ጆሮ​ውም እን​ቆ​ቅ​ል​ሽን መረ​መረ።</verse>
				<verse number="10">ሰባ​ኪ​ውም ያማ​ረ​ውን በቅ​ንም የተ​ጻ​ፈ​ውን እው​ነ​ተ​ኛ​ው​ንም ቃል መር​ምሮ ለማ​ግ​ኘት ፈለገ።</verse>
				<verse number="11">የጠ​ቢ​ባን ቃል እንደ በሬ መው​ጊያ ነው፥ የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡ​ትም ከአ​ንድ እረኛ የተ​ሰ​ጡት ቃላት እንደ ተቸ​ነ​ከሩ ችን​ካ​ሮች ናቸው።</verse>
				<verse number="12">ከዚ​ህም ሁሉ በላይ፥ ልጄ ሆይ፥ ተግ​ሣ​ጽን ስማ፥ ፍጻሜ የሌ​ላ​ቸው ብዙ መጻ​ሕ​ፍ​ትን አታ​ድ​ርግ። እጅ​ግም ምር​ምር ሰው​ነ​ትን ያደ​ክ​ማል።</verse>
				<verse number="13">የነ​ገ​ሩን ሁሉ ፍጻሜ ስማ፤ ይህ የሰው ሁለ​ን​ተ​ናው ነውና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ጠብቅ።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራን ሁሉ የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም ነገር ሁሉ፥ መል​ካ​ምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመ​ጣ​ዋ​ልና።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="22">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">ከመ​ዝ​ሙር ሁሉ የሚ​በ​ልጥ የሰ​ሎ​ሞን መዝ​ሙር።</verse>
				<verse number="2">በአፉ አሳ​ሳም ይስ​መ​ኛል፥ ጡቶ​ችሽ ከወ​ይን ይልቅ ያማሩ ናቸው።</verse>
				<verse number="3">የሽ​ቱሽ መዓዛ ከሽቱ ሁሉ መዓዛ ያማረ ነው፥ ስምህ እን​ደ​ሚ​ፈ​ስስ ሽቱ ነው፤ ስለ​ዚህ ደና​ግል ወደ​ዱህ።</verse>
				<verse number="4">ከወደ ኋላ​ህም ሳቡህ፥ በሽ​ቱህ መዓ​ዛም እን​ሮ​ጣ​ለን፤ ንጉሡ ወደ እል​ፍኙ አገ​ባኝ፤ በአ​ንቺ ደስ ይለ​ኛል፥ ሐሤ​ትም እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ ከወ​ይን ጠጅ ይልቅ ጡቶ​ች​ሽን እን​ወ​ዳ​ለን፤ አን​ቺ​ንም መው​ደድ የተ​ገባ ነው።</verse>
				<verse number="5">እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ፤ ነገር ግን ውብ ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድን​ኳ​ኖች እንደ ሰሎ​ሞ​ንም መጋ​ረ​ጃ​ዎች።</verse>
				<verse number="6">ፀሓይ መል​ኬን አክ​ስ​ሎ​ታ​ልና ጥቁር ስለ ሆንሁ አት​ዩኝ፤ የእ​ናቴ ልጆች ስለ እኔ ተጣሉ፥ የወ​ይን ቦታ​ዎ​ች​ንም ጠባቂ አደ​ረ​ጉኝ፤ ነገር ግን የእ​ኔን የወ​ይን ቦታ አል​ጠ​በ​ቅ​ሁም።</verse>
				<verse number="7">ነፍሴ የወ​ደ​ደ​ችህ አንተ ንገ​ረኝ፤ በባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ችህ መን​ጎች መካ​ከል የተ​ቅ​በ​ዘ​በ​ዝሁ እን​ዳ​ል​ሆን፥ ወዴት ታሰ​ማ​ራ​ለህ? በቀ​ት​ርስ ጊዜ ወዴት ትመ​ሰ​ጋ​ለህ?</verse>
				<verse number="8">አንቺ በሴ​ቶች ዘንድ የተ​ዋ​ብሽ ሆይ፥ ያላ​ወ​ቅሽ እንደ ሆነ የመ​ን​ጎ​ችን ፍለጋ ተከ​ት​ለሽ ውጪ፥ የፍ​የል ግል​ገ​ሎ​ች​ሽ​ንም በእ​ረ​ኞች ድን​ኳ​ኖች አጠ​ገብ አሰ​ማሪ።</verse>
				<verse number="9">ወዳጄ ሆይ፥ በፈ​ር​ዖን ሰረ​ገ​ሎች እን​ዳለ ፈረሴ መሰ​ል​ሁሽ።</verse>
				<verse number="10">ጕን​ጮ​ችሽ እንደ ዋኖስ እጅግ ያማሩ ናቸው፥ አን​ገ​ት​ሽም በዕ​ንቍ ድሪ ያማረ ነው።</verse>
				<verse number="11">ባለ ብር ጕብ​ጕብ የሆነ የወ​ርቅ ጠል​ሰም ያድ​ር​ጉ​ልሽ።</verse>
				<verse number="12">ንጉሡ በማ​ዕድ እስ​ከ​ሚ​ቀ​ርብ ድረስ፥ የእኔ ናር​ዶስ መዓ​ዛ​ውን ሰጠ።</verse>
				<verse number="13">ውዴ ለእኔ በጡ​ቶች መካ​ከል እን​ደ​ሚ​ያ​ርፍ እንደ ተቋ​ጠረ ከርቤ ነው።</verse>
				<verse number="14">ልጅ ወን​ድሜ ለእኔ በዐ​ይ​ን​ጋዲ ወይን ቦታ እን​ዳለ እንደ አበባ ዕቅፍ ነው።</verse>
				<verse number="15">ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፤ እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ፤ ዐይ​ኖ​ች​ሽም እንደ ርግ​ቦች ናቸው።</verse>
				<verse number="16">ልጅ ወን​ድሜ ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ውብ ነህ፥ መልከ መል​ካ​ምም ነህ፤ አል​ጋ​ች​ንም ለም​ለም ነው።</verse>
				<verse number="17">የቤ​ታ​ችን ሰረ​ገላ የዝ​ግባ ዛፍ ነው፥ የጣ​ሪ​ያ​ች​ንም ማዋ​ቀ​ሪያ የጥድ ዛፍ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">እኔ የዱር ጽጌ​ረዳ፥ የቈ​ላም የሱፍ አበባ ነኝ።</verse>
				<verse number="2">በእ​ሾህ መካ​ከል እን​ዳለ የሱፍ አበባ፥ እን​ዲሁ ወዳጄ በቈ​ነ​ጃ​ጅት መካ​ከል ነሽ።</verse>
				<verse number="3">በዱር እን​ዳለ እን​ኮይ፥ እን​ዲሁ ውዴ በወ​ን​ድ​ሞች መካ​ከል ነው። ከጥ​ላው በታች እጅግ ወድጄ ተቀ​መ​ጥሁ፥ ፍሬ​ውም ለጕ​ሮ​ሮዬ ጣፋጭ ነው።</verse>
				<verse number="4">ወደ ወይን ቤት አገ​ቡኝ፥ በእ​ኔም ላይ ፍቅ​ርን አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="5">በሽቱ አጸ​ኑኝ፥ በእ​ን​ኮ​ይም አበ​ረ​ታ​ቱኝ፥ በፍ​ቅሩ ተነ​ድ​ፌ​አ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="6">ቀኙ ታቅ​ፈ​ኛ​ለች። ግራ​ውም ከራሴ በታች ናት፥</verse>
				<verse number="7">እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ ወድዶ እስ​ኪ​ነሣ ድረስ፥ ፍቅ​ሬን እን​ዳ​ት​ቀ​ሰ​ቅ​ሱ​ትና እን​ዳ​ታ​ስ​ነ​ሡት፥ በም​ድረ በዳው ኀይ​ልና ጽናት አም​ላ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">እነሆ፥ የልጅ ወን​ድሜ ቃል በተ​ራ​ሮች ላይ ሲዘ​ልል፥ በኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም ላይ ሲወ​ረ​ወር ይመ​ጣል።</verse>
				<verse number="9">ልጅ ወን​ድሜ በቤ​ቴል ተራ​ሮች ላይ ሚዳ​ቋን ወይም የዋ​ሊ​ያን እን​ም​ቦሳ ይመ​ስ​ላል፤ እነሆ፥ በመ​ስ​ኮ​ቶች ሲጐ​በኝ፥ በዐ​ይነ ርግ​ብም ሲመ​ለ​ከት፥ እርሱ ከቅ​ጥ​ራ​ችን በኋላ ቆሞ​አል።</verse>
				<verse number="10">ልጅ ወን​ድሜ እን​ዲህ ብሎ መለ​ሰ​ልኝ፦ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፥ መል​ካ​ምዋ ርግቤ ሆይ፥ ነዪ።</verse>
				<verse number="11">እነሆ፥ ክረ​ምቱ ዐለፈ፥ ዝና​ሙም አልፎ ሄደ፤</verse>
				<verse number="12">አበባ በም​ድር ላይ ታየ፥ የመ​ከ​ርም ጊዜ ደረሰ፥ የቍ​ር​ዬ​ውም ቃል በም​ድ​ራ​ችን ተሰማ።</verse>
				<verse number="13">በለሱ ጐመራ፥ ወይ​ኖ​ችም አበቡ፥ መዓ​ዛ​ቸ​ው​ንም ሰጡ፤ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፤ መል​ካ​ምዋ ርግቤ ሆይ፥ ነዪ። በዐ​ለት ንቃ​ቃ​ትና በገ​ደል መሸ​ሸ​ጊያ ወዳ​ለው ጥላ ነዪ።</verse>
				<verse number="14">ፊት​ህን አሳ​የኝ፥ ቃል​ህ​ንም አሰ​ማኝ፤ ቃልህ ያማረ፥ ፊት​ህም የተ​ዋበ ነውና።</verse>
				<verse number="15">የወ​ይን ቦታ​ችን ያብብ ዘንድ፥ የወ​ይ​ና​ች​ንን ቦታ የሚ​ያ​ጠ​ፉ​ትን ጥቃ​ቅ​ኑን ቀበ​ሮች አጥ​ም​ዳ​ችሁ ያዙ​ልን።</verse>
				<verse number="16">ልጅ ወን​ድሜ የእኔ ነው፥ እኔም የእ​ርሱ ነኝ፤ በሱፍ አበ​ባ​ዎች መካ​ከ​ልም መን​ጋ​ውን ያሰ​ማ​ራል።</verse>
				<verse number="17">ልጅ ወን​ድሜ ሆይ፥ ቀኑ እስ​ኪ​ነ​ፍስ፥ ጥላ​ውም እስ​ኪ​ሸሽ ድረስ ተመ​ለስ፤ በቅ​መም ተራራ ላይ ሚዳ​ቋ​ውን ወይም የዋ​ላ​ውን እን​ቦሳ ምሰል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ሌሊት በም​ን​ጣፌ ላይ ነፍሴ የወ​ደ​ደ​ች​ውን ፈለ​ግ​ሁት፤ ፈለ​ግ​ሁት አላ​ገ​ኘ​ሁ​ትም። ጠራ​ሁት አል​መ​ለ​ሰ​ል​ኝም።</verse>
				<verse number="2">እነ​ሣ​ለሁ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም እዞ​ራ​ለሁ፥ ነፍሴ የወ​ደ​ደ​ች​ውን በገ​በ​ያና በአ​ደ​ባ​ባይ እፈ​ል​ጋ​ለሁ፤ ፈለ​ግ​ሁት አላ​ገ​ኘ​ሁ​ትም። ጠራ​ሁት አል​መ​ለ​ሰ​ል​ኝም።</verse>
				<verse number="3">ከተ​ማ​ዪ​ቱን የሚ​ጠ​ብ​ቁት ጠባ​ቂ​ዎች አገ​ኙኝ፤ ነፍሴ የወ​ደ​ደ​ች​ውን አያ​ች​ሁ​ትን? አል​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ከእ​ነ​ር​ሱም ጥቂት እልፍ ብዬ ያን​ጊዜ ነፍሴ የወ​ደ​ደ​ች​ውን አገ​ኘ​ሁት፥ ያዝ​ሁ​ትም፤ ወደ እና​ቴም ቤት፥ ወደ ወላጅ እና​ቴም እል​ፍኝ እስ​ካ​ገ​ባው ድረስ አል​ተ​ው​ሁ​ትም።</verse>
				<verse number="5">እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ ወድዶ እስ​ኪ​ነሣ ፍቅ​ሬን እን​ዳ​ት​ቀ​ሰ​ቅ​ሱ​ትና እን​ዳ​ታ​ስ​ነ​ሡት፥ በም​ድረ በዳው ኀይ​ልና ጽን​ዐት አም​ላ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="6">መዓ​ዛዋ እንደ ከር​ቤና እንደ ዕጣን የሆ​ነው፥ ከልዩ የሽቱ ቅመም ሁሉ የሆ​ነው፥ ይህች ከም​ድረ በዳ እንደ ጢስ ዐምድ የወ​ጣ​ችው ማን ናት?</verse>
				<verse number="7">እነሆ፥ የሰ​ሎ​ሞን አልጋ ናት፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ኀያ​ላን ስድሳ ኀያ​ላን በዙ​ሪ​ያዋ ናቸው።</verse>
				<verse number="8">ሁሉም ሰይፍ የያ​ዙና ሰልፍ የተ​ማሩ ናቸው፤ በሌ​ሊት ከሚ​ወ​ድ​ቀው ፍር​ሀት የተ​ነሣ ሰው ሁሉ ሰይፉ በወ​ገቡ አለ።</verse>
				<verse number="9">ንጉሡ ሰሎ​ሞን መሸ​ከ​ሚ​ያን ከሊ​ባ​ኖስ እን​ጨት ለራሱ አሠራ።</verse>
				<verse number="10">ምሰ​ሶ​ዎ​ቹን የብር አደ​ረገ፥ መደ​ገ​ፊ​ያ​ው​ንም የወ​ርቅ፥ መቀ​መ​ጫ​ው​ንም ሐም​ራዊ ግምጃ አደ​ረገ፤ ውስጡ ሰን​ፔር በሚ​ባል ዕንቍ የተ​ለ​በጠ ነው። ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ይልቅ እወ​ድ​ደ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">እና​ንት የጽ​ዮን ቈነ​ጃ​ጅት፥ እናቱ በሠ​ርጉ ቀን በልቡ ደስታ ቀን ያቀ​ዳ​ጀ​ች​ውን አክ​ሊል ደፍቶ ንጉሥ ሰሎ​ሞ​ንን ታዩ ዘንድ ውጡ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፤ እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ፤ ከዝ​ም​ታሽ በቀር ዐይ​ኖ​ችሽ እንደ ርግ​ቦች ናቸው፤ ጠጕ​ርሽ በገ​ለ​ዓድ ተራራ እን​ደ​ሚ​ታይ እንደ ፍየል መንጋ ነው።</verse>
				<verse number="2">ጥር​ሶ​ችሽ ከመ​ታ​ጠ​ቢያ ወጥ​ተው እንደ ተሸ​ለቱ ሁሉም መንታ መንታ እንደ ወለዱ ከእ​ነ​ር​ሱም መካን እን​ደ​ሌ​ለ​ባ​ቸው መን​ጎች ናቸው።</verse>
				<verse number="3">ከን​ፈ​ሮ​ችሽ እንደ ቀይ ሐር ፈትል ናቸው፥ ቃል​ሽም ያማረ ነው፤ ከዝ​ም​ታሽ በቀር ጕን​ጮ​ችሽ እንደ ተከ​ፈለ ሮማን ናቸው።</verse>
				<verse number="4">አን​ገ​ትሽ ለሰ​ልፍ ዕቃ መስ​ቀያ እንደ ተሠራ እንደ ዳዊት ግንብ ነው፤ በው​ስ​ጡም ሺህ የጦር ዕቃና የኀ​ያ​ላን መሣ​ሪያ ሁሉ ተሰ​ቅ​ሎ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="5">ሁለቱ ጡቶ​ችሽ መንታ እንደ ተወ​ለዱ፥ በሱፍ አበባ መካ​ከል እን​ደ​ሚ​ሰ​ማሩ እንደ ሚዳቋ ግል​ገ​ሎች ናቸው።</verse>
				<verse number="6">ቀኑ እስ​ኪ​ነ​ፍስ ጥላ​ውም እስ​ኪ​ያ​ልፍ ድረስ፥ ወደ ከር​ቤው ተራራ ወደ ዕጣ​ኑም ኰረ​ብታ እሄ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">ወዳጄ ሆይ፥ ሁለ​ን​ተ​ናሽ ውብ ነው፥ ምንም ነውር የለ​ብ​ሽም።</verse>
				<verse number="8">ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ከሊ​ባ​ኖስ ነዪ፤ ከሊ​ባ​ኖስ ነዪ፤ ከሃ​ይ​ማ​ኖት ራስ ከሳ​ኔ​ርና ከኤ​ር​ሞን ራስ፥ ከአ​ን​በ​ሶች ጕድ​ጓድ፥ ከነ​ብ​ሮ​ችም ተራራ ተመ​ል​ከቺ።</verse>
				<verse number="9">እኅቴ ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ልቤን ማረ​ክ​ሽው፤ አንድ ጊዜ በዐ​ይ​ኖ​ችሽ፥ ከአ​ን​ገ​ት​ሽም ድሪ በአ​ንዱ፥ ልቤን ማረ​ክ​ሽው።</verse>
				<verse number="10">እኅቴ ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ጡቶ​ችሽ እን​ዴት ያማሩ ናቸው? ጡቶ​ችሽ ከወ​ይን ይልቅ እጅግ ያማሩ ናቸው። የሽ​ቱ​ሽም መዓ​ዛው ከሽቱ ሁሉ ይልቅ እጅግ ያማረ ነው።</verse>
				<verse number="11">ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ከከ​ን​ፈ​ሮ​ችሽ የማር ወለላ ይን​ጠ​ባ​ጠ​ባል፤ ከም​ላ​ስ​ሽም በታች ማርና ወተት አለ፥ የል​ብ​ስ​ሽም መዓዛ እንደ ዕጣን መዓዛ ነው።</verse>
				<verse number="12">እኅቴ ሙሽ​ሪት የተ​ቈ​ለ​ፈች ገነት፥ የተ​ዘ​ጋች ገነት፥ የታ​ተ​መ​ችም ጕድ​ጓድ ናት።</verse>
				<verse number="13">መን​ገ​ድ​ሽም ሮማ​ንና የተ​መ​ረጠ ፍሬ፥ ቆዕ ከና​ር​ዶስ ጋር ያለ​በት ገነት ነው፥</verse>
				<verse number="14">ናር​ዶስ ከቀጋ ጋር፥ የሽቱ ሣርና ቀረ​ፋም፥ ከሊ​ባ​ኖስ እን​ጨ​ቶች ጋር፥ ከር​ቤና እሬት ከክ​ቡር ሽቱ ሁሉ ጋር።</verse>
				<verse number="15">አንቺ የገ​ነት ምንጭ፥ የሕ​ይ​ወት ውኃ ጕድ​ጓድ፥ ከሊ​ባ​ኖ​ስም የሚ​ፈ​ስስ ወንዝ ነሽ።</verse>
				<verse number="16">የሰ​ሜን ነፋስ ሆይ፥ ተነሥ፥ የደ​ቡ​ብም ነፋስ ና፤ በገ​ነቴ ላይ ንፈስ፥ ሽቱ​ዬም ይፍ​ሰስ፤ ልጅ ወን​ድሜ ወደ ገነቱ ይው​ረድ፥ መል​ካ​ሙ​ንም ፍሬ ይብላ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">እኅቴ ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ወደ ገነቴ ገባሁ፥ ከር​ቤ​ዬን ከሽ​ቱዬ ጋር ለቀ​ምሁ፥ እን​ጀ​ራ​ዬን ከማሬ ጋር በላሁ፥ የወ​ይን ጠጄን ከወ​ተቴ ጋር ጠጣሁ። ባል​ን​ጀ​ሮች በሉ፥ ጠገ​ቡም፤ የወ​ን​ድ​ሞች ልጆች ጠጡ፥ ሰከ​ሩም፥ ልባ​ቸው የጠፋ ነውና።</verse>
				<verse number="2">እኔ ተኝቼ ነበር፥ ልቤ ግን ነቅታ ነበር፤ ልጅ ወን​ድሜ ቃል ደጅ እየ​መታ መጣ፥ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ መደ​ም​ደ​ሚ​ያዬ ሆይ፥ በራሴ ጠል፥ በቍ​ን​ዳ​ላ​ዬም የሌ​ሊት ነጠ​ብ​ጣብ ሞል​ቶ​በ​ታ​ልና ክፈ​ች​ልኝ።</verse>
				<verse number="3">ቀሚ​ሴን አወ​ለ​ቅሁ፥ እን​ዴት እለ​ብ​ሰ​ዋ​ለሁ? እግ​ሬን ታጠ​ብሁ፥ እን​ዴት አሳ​ድ​ፈ​ዋ​ለሁ?</verse>
				<verse number="4">ልጅ ወን​ድሜ እጁን በቀ​ዳዳ ሰደደ፥ አን​ጀ​ቴም ስለ እርሱ ታወ​ከች።</verse>
				<verse number="5">ለልጅ ወን​ድሜ እከ​ፍ​ት​ለት ዘንድ ተነ​ሣሁ፤ እጆች በደጁ መወ​ር​ወ​ሪያ ላይ ከር​ቤን አፈ​ሰሱ፥ ጣቶች ፈሳ​ሹን ከርቤ አን​ጠ​ባ​ጠቡ።</verse>
				<verse number="6">ለልጅ ወን​ድሜ ከፈ​ት​ሁ​ለት፥ ልጅ ወን​ድሜ ግን ሂዶ ነበር። ነፍሴ ከቃሉ የተ​ነሣ ደነ​ገ​ጠች፤ ፈለ​ግ​ሁት፥ አላ​ገ​ኘ​ሁ​ትም፤ ጠራ​ሁት፥ አል​መ​ለ​ሰ​ል​ኝም።</verse>
				<verse number="7">ከተ​ማ​ዪ​ቱን የሚ​ዞ​ሩት ጠባ​ቂ​ዎች አገ​ኙኝ፤ መቱኝ፥ አቈ​ሰ​ሉ​ኝም፤ ቅጥር ጠባ​ቂ​ዎ​ችም የዐ​ይነ ርግብ መሸ​ፈ​ኛ​ዬን ከራሴ ላይ ወሰ​ዱት።</verse>
				<verse number="8">እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ በም​ድረ በዳ ኀይ​ልና ጽን​ዐት አም​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ልጅ ወን​ድ​ሜን ያገ​ኛ​ች​ሁት እንደ ሆነ፥ እኔ ከፍ​ቅር የተ​ነሣ መታ​መ​ሜን ትነ​ግ​ሩት ዘንድ።</verse>
				<verse number="9">አንቺ በሴ​ቶች ዘንድ የተ​ዋ​ብሽ ሆይ፥ ከወ​ን​ድ​ሞች ልጆች ይልቅ ልጅ ወን​ድ​ምሽ ማን ነው? ይህን ያህል መሐላ አም​ለ​ሽ​ና​ልና ከወ​ን​ድ​ሞች ልጆች ይልቅ ልጅ ወን​ድ​ምሽ ማን ነው?</verse>
				<verse number="10">ወን​ድሜ ነጭና ቀይ ነው፥ ከአ​እ​ላፍ የተ​መ​ረጠ ነው።</verse>
				<verse number="11">ራሱ ምዝ​ምዝ ወርቅ ነው፤ ቈን​ዳ​ላው የተ​ዝ​ረ​ፈ​ረፈ ነው፥ እንደ ቍራ ጥቍ​ረ​ትም ጥቁር ነው።</verse>
				<verse number="12">ዐይ​ኖቹ በሙሉ የውኃ ኵሬ አጠ​ገብ እን​ዳሉ በወ​ተት እንደ ታጠቡ በኵሬ ውኃ አጠ​ገብ እንደ ተቀ​መጡ፥ እንደ ርግ​ቦች ናቸው።</verse>
				<verse number="13">ጕን​ጮቹ ሽቱን የሚ​ያ​ፈ​ስሱ የሽቱ መደብ ናቸው። ከን​ፈ​ሮቹ እንደ አበ​ቦች ናቸው፥ የሚ​ፈ​ስስ ከር​ቤ​ንም ያን​ጠ​ባ​ጥ​ባሉ።</verse>
				<verse number="14">እጆቹ የተ​ር​ሴስ ፈርጥ እን​ዳ​ለ​ባ​ቸው እንደ ለዘቡ የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች ናቸው፤ ሆዱ በሰ​ን​ፔር ዕንቍ እን​ዳ​ጌጠ እንደ ዝሆን ጥርስ ነው፥</verse>
				<verse number="15">እግ​ሮቹ በም​ዝ​ምዝ ወርቅ እንደ ተመ​ሠ​ረቱ እንደ ዕብነ በረድ ምሰ​ሶ​ዎች ናቸው፤ መልኩ እንደ ሊባ​ኖ​ስና እንደ ዝግባ ዛፍ የተ​መ​ረጠ ነው።</verse>
				<verse number="16">ጕሮ​ሮው እጅግ ጣፋጭ ነው፥ ሁለ​ን​ተ​ና​ውም የተ​ወ​ደደ ነው፤ እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ ልጅ ወን​ድሜ ይህ ነው፥ ወዳ​ጄም ይህ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">አንቺ በሴ​ቶች ዘንድ የተ​ዋ​ብሽ ሆይ፥ ከአ​ንቺ ጋር እን​ፈ​ል​ገው ዘንድ ልጅ ወን​ድ​ምሽ ወዴት ሄደ? ልጅ ወን​ድ​ም​ሽስ ወዴት ፈቀቅ አለ?</verse>
				<verse number="2">ልጅ ወን​ድሜ በገ​ነቱ መን​ጋ​ውን ይጠ​ብቅ ዘንድ፥ አበ​ባ​ው​ንም ይሰ​በ​ስብ ዘንድ ወደ ሽቱ መደብ ወደ ገነቱ ወረደ።</verse>
				<verse number="3">እኔ የልጅ ወን​ድሜ ነኝ፥ ልጅ ወን​ድ​ሜም የእኔ ነው፤ በሱፍ አበባ መካ​ከል መን​ጋ​ውን ያሰ​ማ​ራል።</verse>
				<verse number="4">ወዳጄ ሆይ፥ እንደ ቴርሳ ውብ ነሽ፥ እንደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ያማ​ርሽ ነሽ፤ ዓላማ ይዞ እንደ ተሰ​ለፈ ሠራ​ዊት ታስ​ፈ​ር​ያ​ለሽ።</verse>
				<verse number="5">ዐይ​ኖ​ች​ሽን ከፊቴ መልሺ፤ እነ​ርሱ አስ​ፈ​ር​ተ​ው​ኛ​ልና፤ ጠጕ​ርሽ ከገ​ለ​ዓድ እንደ ታየ እንደ ፍየል መንጋ ነው።</verse>
				<verse number="6">ጥር​ሶ​ችሽ ታጥ​በው እንደ ወጡ ሁሉም መንታ እንደ ወለዱ ከእ​ነ​ር​ሱም መካን እን​ደ​ሌ​ለ​ባ​ቸው መን​ጎች ናቸው። ከን​ፈ​ሮ​ችሽ እንደ ቀይ ሐር ናቸው፥ ቃልሽ ያማረ ነው።</verse>
				<verse number="7">ከዝ​ም​ታሽ በቀር ጕን​ጮ​ችሽ እንደ ተከ​ፈለ ሮማን ናቸው።</verse>
				<verse number="8">ስድሳ ንግ​ሥ​ታት፥ ሰማ​ን​ያም ቁባ​ቶች ቍጥር የሌ​ላ​ቸ​ውም ቈነ​ጃ​ጅት አሉ።</verse>
				<verse number="9">ርግቤ መደ​ም​ደ​ሚ​ያ​ዬም አን​ዲት ናት፤ ለእ​ናቷ አን​ዲት ናት፥ ለወ​ለ​ደ​ቻ​ትም የተ​መ​ረ​ጠች ናት። ቈነ​ጃ​ጅ​ትም አይ​ተው አሞ​ገ​ሱ​አት፥ ንግ​ሥ​ታ​ትና ቁባ​ቶ​ችም አመ​ሰ​ገ​ኑ​አት።</verse>
				<verse number="10">ይህች እንደ ማለዳ ብር​ሃን የም​ት​ጐ​በኝ፥ እንደ ጨረቃ የተ​ዋ​በች እንደ ፀሓ​ይም የጠ​ራች፥ ዓላማ ይዞ እንደ ተሰ​ለፈ ሠራ​ዊት የም​ታ​ስ​ፈራ ማን ናት?</verse>
				<verse number="11">ልጅ ወን​ድሜ የወ​ን​ዙን ዳር ልም​ላሜ ያይ ዘንድ ወይኑ አብቦ ሮማ​ኑም አፍ​ርቶ እንደ ሆነ ይመ​ለ​ከት ዘንድ ወደ ገውዝ ገነት ወረደ።</verse>
				<verse number="12">በዚያ ጡቶ​ችን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፥ ሰው​ነ​ቴም አላ​ወ​ቀ​ችም፥ እንደ አሚ​ና​ዳብ ሰረ​ገላ አደ​ረ​ገኝ አለች። ብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አይ ዘንድ ... ወረ​ድሁ” ይላል። ወይኑ አብቦ ሮማ​ኑም አፍ​ርቶ እንደ ሆነ ይመ​ለ​ከት ዘንድ ወደ ገውዝ ገነት ወረደ።</verse>
				<verse number="13">በዚያ ጡቶ​ችን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፥ ሰው​ነ​ቴም አላ​ወ​ቀ​ችም፥ እንደ አሚ​ና​ዳብ ሰረ​ገላ አደ​ረ​ገኝ አለች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">አንቺ ሱላ​ማ​ጢስ ሆይ፥ ተመ​ለሽ፥ ተመ​ለሽ፤ እና​ይ​ሽም ዘንድ ተመ​ለሽ፥ ተመ​ለሽ። በሱ​ላ​ማ​ጢስ ምን ታያ​ላ​ችሁ? እር​ስዋ በሩቁ እን​ደ​ም​ት​ታይ እንደ ማኅ​በር ማሕ​ሌት ናት።</verse>
				<verse number="2">አንቺ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ሆይ፥ በጫማ አካ​ሄ​ድሽ እጅግ ያማረ ነው። የዳ​ሌ​ዎ​ችሽ አቀ​ማ​መጥ በአ​ን​ጥ​ረኛ እጅ እንደ ተሠሩ እንደ ዕን​ቍ​ዎች ይመ​ስ​ላል።</verse>
				<verse number="3">እን​ብ​ር​ትሽ የወ​ይን ጠጅ እን​ደ​ማ​ይ​ጐ​ድ​ል​በት እንደ ተነ​ጠጠ ጽዋ ነው፤ ሆድሽ እንደ ስንዴ ክምር፥ በአ​በ​ባም እንደ ታጠረ ነው።</verse>
				<verse number="4">ሁለቱ ጡቶ​ችሽ እንደ ሁለት መንታ እንደ ሚዳቋ ግል​ገ​ሎች ናቸው።</verse>
				<verse number="5">አን​ገ​ትሽ እንደ ዝሆን ጥርስ ግንብ ነው፤ ዐይ​ኖ​ችሽ በሐ​ሴ​ቦን ውስጥ በብ​ዙ​ዎች ልጅ በሮች አጠ​ገብ እን​ዳሉ እንደ ውኃ ኵሬ​ዎች ናቸው፤ አፍ​ን​ጫሽ ወደ ደማ​ስቆ አፋ​ዛዥ እን​ደ​ሚ​መ​ለ​ከት እንደ ሊባ​ኖስ ግንብ ነው።</verse>
				<verse number="6">በራ​ስሽ ላይ ያለው ጠጕ​ርሽ እንደ ቀር​ሜ​ሎስ ተራራ ነው፤ የጠ​ጕ​ር​ሽም ሹርባ እንደ ሐም​ራዊ ሐር ነው፥ ንጉ​ሡም በሹ​ር​ባው ታስ​ሯል።</verse>
				<verse number="7">ወዳጄ ሆይ፥ እን​ዴት የተ​ዋ​ብሽ ነሽ! እን​ዴ​ትስ ደስ ታሰ​ኛ​ለሽ! ደስ​ታ​ሽ​ንም እወ​ድ​ደ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">ይህ ቁመ​ትሽ የዘ​ን​ባባ ዛፍ ይመ​ስ​ላል፥ ጡቶ​ች​ሽም የወ​ይን ዘለላ ይመ​ስ​ላሉ።</verse>
				<verse number="9">ወደ ዘን​ባ​ባው ዛፍ እወ​ጣ​ለሁ ጫፉ​ንም እይ​ዛ​ለሁ አልሁ፤ ጡቶ​ችሽ እንደ ወይን ዘለላ ናቸው፥ የአ​ፍ​ን​ጫ​ሽም ሽታ እንደ እን​ኮይ ነው።</verse>
				<verse number="10">ጕሮ​ሮ​ሽም ለልጅ ወን​ድሜ እየ​ጣ​ፈጠ እን​ደ​ሚ​ገባ፥ ለከ​ን​ፈ​ሮ​ችና ለም​ላሴ እን​ደ​ሚ​ስ​ማማ እንደ ማለ​ፊያ የወ​ይን ጠጅ ነው።</verse>
				<verse number="11">እኔ የልጅ ወን​ድሜ ነኝ፥ የእ​ር​ሱም መመ​ለ​ሻው ወደ እኔ ነው።</verse>
				<verse number="12">ልጅ ወን​ድሜ ሆይ፥ ና፥ ወደ መስክ እን​ውጣ፥ በመ​ን​ደ​ሮ​ችም እን​ደር።</verse>
				<verse number="13">ወደ ወይኑ ቦታ ማልደን እንሂድ፤ ወይኑ አብቦ፥ አበባውም ፍሬ አንዠርግጎ ሮማኑም አፍርቶ እንደ ሆነ እንይ፤ በዚያ ጡቶቼን እሰጥሃለሁ።</verse>
				<verse number="14">ትርንጎዎች መዓዛን ስጡ፤ መልካሞች ፍሬዎች ሁሉ፥ አሮጌው ከአዲሱ ጋር፥ በደጃችን አሉ፤ ልጅ ወንድሜ ሆይ፥ ሁሉን ለአንተ ጠበቅሁልህ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">ልጅ ወን​ድሜ ሆይ፥ የእ​ና​ቴን ጡት ትጠባ ዘንድ ማን በሰ​ጠህ? በሜዳ ባገ​ኘ​ሁህ ጊዜ በሳ​ም​ሁህ፥ ማንም ባል​ና​ቀ​ኝም ነበር።</verse>
				<verse number="2">ይዤ ወደ እናቴ ቤት፥ ወደ ወላጅ እና​ቴም እል​ፍኝ ባገ​ባ​ሁህ፥ እኔ ከመ​ል​ካሙ የወ​ይን ጠጄ ከሮ​ማ​ኔም ውኃ ባጠ​ጣ​ሁህ ነበር።</verse>
				<verse number="3">ቀኙ ባቀ​ፈ​ችኝ ግራ​ውም ከራሴ በታች በሆ​ነች ነበር።</verse>
				<verse number="4">እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ ወድዶ እስ​ኪ​ነሣ ድረስ ፍቅ​ሬን እን​ዳ​ት​ቀ​ሰ​ቅ​ሱ​ትና እን​ዳ​ታ​ስ​ነ​ሡት በም​ድረ በዳው ኀይ​ልና ጽን​ዐት አም​ላ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">በልጅ ወን​ድ​ምዋ ላይ ተደ​ግፋ እንደ ማለዳ ደም​ቃና አብ​ርታ የም​ት​ወጣ ይህች ማን ናት? ልጅ ወን​ድሜ ሆይ፥ ከእ​ን​ኮይ በታች አስ​ነ​ሣ​ሁህ፤ በዚያ እና​ትህ አማ​ጠ​ችህ፥ በዚ​ያም ወላጅ እና​ትህ ወለ​ደ​ችህ።</verse>
				<verse number="6">እንደ ቀለ​በት በል​ብህ፥ እንደ ቀለ​በ​ትም ማኅ​ተም በክ​ን​ድህ አኑ​ረኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበ​ረ​ታች ናትና፥ ቅን​ዐ​ትም እንደ ሲኦል የጨ​ከ​ነች ናትና። ላን​ቃዋ እንደ እሳት ላንቃ እንደ ነበ​ል​ባል ነው።</verse>
				<verse number="7">ብዙ ውኃ ፍቅ​ርን ያጠ​ፋት ዘንድ አይ​ች​ልም፥ ፈሳ​ሾ​ችም አያ​ሰ​ጥ​ሙ​አ​ትም፤ ሰው የቤ​ቱን ሀብት ሁሉ ስለ ፍቅር ቢሰጥ ፈጽሞ አይ​ን​ቁ​ትም።</verse>
				<verse number="8">እኅ​ታ​ችን ትንሽ ናት፥ ጡትም የላ​ትም፤ ስለ እር​ስዋ በሚ​ና​ገ​ሩ​ባት ቀን ለእ​ኅ​ታ​ችን ምን እና​ድ​ር​ግ​ላት?</verse>
				<verse number="9">እር​ስዋ ቅጥር ብት​ሆን የብር ግንብ በላ​ይዋ እን​ሥራ፤ ደጅ​አ​ፍም ብት​ሆን የዝ​ግባ ሳንቃ እን​ሥ​ራ​ላት።</verse>
				<verse number="10">እኔ ቅጥር ነኝ፥ ጡቶ​ችም እንደ ግንብ ናቸው፤ በዚያ ጊዜ በፊቱ ሰላ​ምን እን​ደ​ም​ታ​ገኝ ሆንሁ።</verse>
				<verse number="11">ለሰ​ሎ​ሞን በብ​ኤ​ላ​ሞን የወ​ይን ቦታ ነበ​ረው፤ የወ​ይ​ኑን ቦታ ፍሬ​ውን ለሚ​ጠ​ብቁ አከ​ራ​የው፤ ሰው ሁሉ በየ​ጊ​ዜው ለፍ​ሬው አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር ያመ​ጣል።</verse>
				<verse number="12">ለእኔ ያለኝ የወ​ይን ቦታ በፊቴ ነው፤ አንዱ ሺህ ለሰ​ሎ​ሞን፥ ሁለቱ መቶ ፍሬ​ውን ለሚ​ጠ​ብቁ ነው።</verse>
				<verse number="13">በአ​ት​ክ​ልቱ ቦታ ሲኖር ሌሎች አዩት፥ ቃል​ህን አሰ​ማኝ።</verse>
				<verse number="14">ልጅ ወን​ድሜ ሆይ፥ ፍጠን፤ በቅ​መም ተራራ ላይ ሚዳ​ቋን ወይም የዋ​ሊ​ያን እን​ቦሳ ምሰል።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="23">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት በዖ​ዝ​ያ​ንና በኢ​ዮ​አ​ታም፥ በአ​ካ​ዝና በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ዘመን ስለ ይሁ​ዳና ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያየው የአ​ሞጽ ልጅ የኢ​ሳ​ይ​ያስ ራእይ።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና፥ “ሰማይ ስማ፤ ምድ​ርም አድ​ምጪ፤ ልጆ​ችን ወለ​ድሁ፤ አሳ​ደ​ግ​ሁም፤ እነ​ር​ሱም ዐመ​ፁ​ብኝ።</verse>
				<verse number="3">በሬ ገዢ​ውን አህ​ያም የጌ​ታ​ውን ጋጥ ዐወቀ፤ እስ​ራ​ኤል ግን አላ​ወ​ቁ​ኝም፤ ሕዝ​ቤም አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉ​ኝም።”</verse>
				<verse number="4">ኀጢ​አ​ተኛ ወገ​ንና ዐመፅ የተ​ሞ​ላ​በት ሕዝብ፥ የክ​ፉ​ዎች ዘር፥ በደ​ለ​ኞች ልጆች ሆይ፥ ወዮ​ላ​ችሁ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተዋ​ች​ሁት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቅዱስ አስ​ቈ​ጣ​ች​ሁት።</verse>
				<verse number="5">እን​ግ​ዲህ በበ​ደል ላይ በደል እየ​ጨ​መ​ራ​ችሁ ለምን ትቀ​ሠ​ፋ​ላ​ችሁ? ራስ ሁሉ ለሕ​ማም፥ ልብም ሁሉ ለኀ​ዘን ሆኖ​አል።</verse>
				<verse number="6">ከእ​ግር ጫማ አን​ሥቶ እስከ ራስ ድረስ ጤና የለ​ውም፤ ቍስ​ልና እበጥ የሚ​መ​ግ​ልም ነው፤ አል​ፈ​ረ​ጠም፤ አል​ተ​ጠ​ገ​ነ​ምም፤ በዘ​ይ​ትም አል​ለ​ዘ​በም።</verse>
				<verse number="7">ምድ​ራ​ችሁ ባድማ ናት፤ ከተ​ሞ​ቻ​ችሁ በእ​ሳት ተቃ​ጠሉ፤ እር​ሻ​ች​ሁ​ንም በፊ​ታ​ችሁ ባዕ​ዳን ይበ​ሉ​ታል፤ ጠላ​ትም ያጠ​ፋ​ዋል፤ ባድ​ማም ያደ​ር​ገ​ዋል።</verse>
				<verse number="8">የጽ​ዮ​ንም ሴት ልጅ በወ​ይን ቦታ እን​ዳለ ዳስ፥ እንደ አዝ​መራ ጠባ​ቂም ጎጆ፥ እንደ ተከ​በ​በ​ችም ከተማ ሆና ቀረች።</verse>
				<verse number="9">የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘርን ባያ​ስ​ቀ​ር​ልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆ​ንን፥ እንደ ገሞ​ራም በመ​ሰ​ልን ነበር።</verse>
				<verse number="10">እና​ንተ የሰ​ዶም አለ​ቆች ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ እና​ንተ የገ​ሞራ ሕዝብ ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ አድ​ምጡ።</verse>
				<verse number="11">“የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችሁ ብዛት ለእኔ ምን​ድን ነው?” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን የአ​ውራ በግ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና የፍ​ሪ​ዳን ስብ ጠግ​ቤ​አ​ለሁ፤ የበ​ሬና የአ​ውራ ፍየ​ልም ደም ደስ አያ​ሰ​ኘ​ኝም።</verse>
				<verse number="12">በእኔ ፊት ልት​ታዩ ብት​መጡ፥ ይህን ከእ​ጃ​ችሁ የሚሻ ማን ነው? እን​ግ​ዲህ አደ​ባ​ባ​ዬን ደግ​ማ​ችሁ አት​ረ​ግ​ጡም።</verse>
				<verse number="13">መል​ካ​ሙን የስ​ንዴ ዱቄት ብታ​መጡ እንኳ ከንቱ ነው፤ ዕጣ​ና​ችሁ በእኔ ዘንድ አስ​ጸ​ያፊ ነው፤ መባ​ቻ​ዎ​ቻ​ች​ሁ​ንና ሰን​በ​ቶ​ቻ​ች​ሁን፥ ታላ​ቋን፥ ቀና​ች​ሁን፥ ጾማ​ች​ሁ​ንና ሥራ መፍ​ታ​ታ​ች​ሁን አል​ወ​ድም።</verse>
				<verse number="14">መባ​ቻ​ች​ሁ​ንና በዓ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ነፍሴ ጠል​ታ​ለች፤ አስ​ጸ​ያፊ ሆና​ች​ሁ​ብ​ኛል፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁ​ንም ይቅር አል​ልም።</verse>
				<verse number="15">እጃ​ች​ሁን ወደ እኔ ብት​ዘ​ረጉ፥ ዐይ​ኖ​ችን ከእ​ና​ንተ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ምህ​ላ​ንም ብታ​በዙ አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ እጆ​ቻ​ችሁ ደምን ተሞ​ል​ተ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="16">ታጠቡ፤ ንጹ​ሓ​ንም ሁኑ፤ የሰ​ው​ነ​ታ​ች​ሁን ክፋት ከዐ​ይ​ኖች ፊት አስ​ወ​ግዱ፤ ክፉ ማድ​ረ​ግ​ንም ተዉ፤</verse>
				<verse number="17">መል​ካም መሥ​ራ​ትን ተማሩ፤ ፍር​ድን ፈልጉ፤ የተ​ገ​ፋ​ውን አድኑ፤ ለድ​ሃ​አ​ደጉ ፍረ​ዱ​ለት፤ ስለ መበ​ለ​ቲ​ቱም ተሙ​አ​ገቱ።”</verse>
				<verse number="18">“ኑና እን​ዋ​ቀስ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ እንደ አለላ ቢሆን እንደ በረዶ አነ​ጻ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ደምም ቢቀላ እንደ ባዘቶ አጠ​ራ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">እሽ ብት​ሉና ብት​ሰ​ሙኝ የም​ድ​ርን በረ​ከት ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="20">እንቢ ብት​ሉና ባት​ሰ​ሙኝ ግን ሰይፍ ትበ​ላ​ች​ኋ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ ይህን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="21">ፍርድ መል​ቶ​ባት የነ​በረ የታ​መ​ነ​ች​ይቱ የጽ​ዮን ከተማ እን​ዴት ጋለ​ሞታ ሆነች! ጽድቅ አድ​ሮ​ባት ነበር፤ አሁን ግን ወን​በ​ዴ​ዎ​ችና ነፍሰ ገዳ​ዮች አሉ​ባት።</verse>
				<verse number="22">ወር​ቅ​ሽና ብርሽ ዛገ፥ የወ​ይን ጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ች​ሽም በወ​ይን ጠጅሽ ላይ ውኃን ይደ​ባ​ል​ቃሉ።</verse>
				<verse number="23">አለ​ቆ​ችሽ ዐመ​ፀ​ኞ​ችና የሌ​ቦች ባል​ን​ጀ​ሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወ​ድ​ዳሉ፤ ፍር​ድ​ንም ሊያ​ጣ​ምሙ ይፈ​ል​ጋሉ፤ ለሙት ልጅ አይ​ፈ​ር​ዱም፤ የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም አቤ​ቱታ አያ​ዳ​ም​ጡም።</verse>
				<verse number="24">ስለ​ዚህ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ኀያ​ላን ወዮ​ላ​ቸው! በጠ​ላ​ቶች ላይ ቍጣዬ አይ​በ​ር​ድም፤ ጠላ​ቶ​ች​ንም እበ​ቀ​ላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="25">እጄ​ንም በአ​ንቺ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ አግ​ል​ሻ​ለሁ፤ ዝገ​ት​ሽ​ንም አነ​ጻ​ለሁ፤ ቆር​ቆ​ሮ​ሽ​ንም ሁሉ አስ​ወ​ግ​ዳ​ለሁ፤ ዐመ​ፀ​ኞ​ችን አጠ​ፋ​ለሁ፤ ሕገ ወጦ​ች​ንም ከአ​ንቺ አስ​ወ​ግ​ዳ​ለሁ፤ ትዕ​ቢ​ተ​ኞ​ች​ንም አዋ​ር​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="26">ፈራ​ጆ​ች​ሽ​ንም እንደ ቀድሞ፥ አማ​ካ​ሪ​ዎ​ች​ሽ​ንም እንደ መጀ​መ​ሪያ ጊዜ አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ የጽ​ድቅ ከተማ፥ የታ​መ​ነ​ችም ጽዮን ርእሰ ከተማ ተብ​ለሽ ትጠ​ሪ​ያ​ለሽ።</verse>
				<verse number="27">ምር​ኮ​ኞ​ችሽ በእ​ው​ነ​ትና በም​ጽ​ዋት ይድ​ናሉ።</verse>
				<verse number="28">በደ​ለ​ኞ​ችና ኀጢ​አ​ተ​ኞች ግን በአ​ን​ድ​ነት ይቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ተ​ዉት ሁሉ ይጠ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="29">በወ​ደ​ዱ​አ​ቸው ጣዖ​ታት ያፍ​ራ​ሉና፥ በፈ​ለ​ጉ​አ​ቸ​ውም የአ​ድ​ባር ዛፎች ዕፍ​ረት ይይ​ዛ​ቸ​ዋ​ልና፤</verse>
				<verse number="30">ቅጠ​ልዋ እንደ ረገፈ የጠ​ር​ቤ​ን​ቶስ ዛፍ፥ ውኃም እን​ደ​ሌ​ለ​በት የአ​ት​ክ​ልት ቦታ ይሆ​ና​ሉና።</verse>
				<verse number="31">ኀይ​ላ​ቸ​ውም እንደ መቃ መስዬ፥ ሥራ​ቸ​ውም እንደ ጠለ​ሸት ይሆ​ናል፤ ኃጥ​አ​ንና ዐማ​ፅ​ያ​ንም አብ​ረው ይቃ​ጠ​ላሉ፤ እሳ​ቱ​ንም የሚ​ያ​ጠ​ፋ​ላ​ቸው ያጣሉ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ስለ ይሁ​ዳና ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አሞፅ ልጅ ወደ ኢሳ​ይ​ያስ የመጣ ቃል።</verse>
				<verse number="2">በኋላ ዘመን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በተ​ራ​ሮች ራስ ላይ ይታ​ያል፤ ከኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ አሕ​ዛ​ቡም ሁሉ ወደ እርሱ ይመ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="3">ሕግ ከጽ​ዮን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይወ​ጣ​ልና ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ መጥ​ተው፥ “ኑ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ፥ ወደ ያዕ​ቆብ አም​ላክ ቤት እን​ውጣ፤ እር​ሱም መን​ገ​ዱን ያስ​ተ​ም​ረ​ናል፤ በጎ​ዳ​ና​ውም እን​ሄ​ዳ​ለን” ይላሉ።</verse>
				<verse number="4">በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ይፈ​ር​ዳል፤ ብዙ አሕ​ዛ​ብ​ንም ይዘ​ል​ፋ​ቸ​ዋል፤ ሰይ​ፋ​ቸ​ው​ንም ማረሻ፥ ጦራ​ቸ​ው​ንም ማጭድ ለማ​ድ​ረግ ይቀ​ጠ​ቅ​ጣሉ፤ ሕዝ​ብም በሕ​ዝብ ላይ ሰይ​ፍን አያ​ነ​ሣም፤ ሰል​ፍ​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​ማ​ሩም።</verse>
				<verse number="5">አሁ​ንም የያ​ዕ​ቆብ ቤት ሆይ፥ ኑ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብር​ሃን እን​መ​ላ​ለስ።</verse>
				<verse number="6">ሕዝ​ቡን የያ​ዕ​ቆ​ብን ቤት ትቶ​አ​ልና፤ ምድ​ራ​ቸው እንደ ቀድ​ሞው እንደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ምድር በሟ​ርት ተሞ​ል​ቶ​አ​ልና፤ እንደ ባዕድ ልጆ​ችም ሆነ​ዋ​ልና፤ ብዙ እን​ግ​ዶች ልጆ​ችም ተወ​ል​ደ​ው​ላ​ቸ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="7">ምድ​ራ​ቸ​ውም በብ​ርና በወ​ርቅ ተሞ​ል​ታ​ለች፤ ለመ​ዛ​ግ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቍጥር የለ​ውም፤ ምድ​ራ​ቸ​ውም ደግሞ በፈ​ረ​ሶች ተሞ​ል​ታ​ለች፤ ለሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም ቍጥር የለ​ውም።</verse>
				<verse number="8">ምድ​ራ​ቸ​ውም በእ​ጆ​ቻ​ቸው በሠ​ሩ​አ​ቸው ጣዖ​ታት ተሞ​ል​ታ​ለች፤ በጣ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ለሠ​ሩ​አ​ቸው ይሰ​ግ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="9">ታና​ሹም ሰው ዝቅ ብሎ​አል፤ ታላ​ቁም ሰው ተዋ​ር​ዶ​አል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይቅር አል​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="10">አሁ​ንም ምድ​ርን ያነ​ዋ​ው​ጣት ዘንድ በተ​ነሣ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ፍ​ራ​ትና ከግ​ር​ማው ክብር የተ​ነሣ ወደ ድን​ጋይ ዋሻ ግቡ፤ በመ​ሬት ውስ​ጥም ተሸ​ሸጉ።</verse>
				<verse number="11">የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞች ሰዎች ዐይ​ኖች ይዋ​ረ​ዳሉ፤ የሰ​ዎ​ችም ኵራት ትወ​ድ​ቃ​ለች፥ በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።</verse>
				<verse number="12">የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን በት​ዕ​ቢ​ተ​ኛ​ውና በኵ​ራ​ተ​ኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለ​ውም ላይ ይሆ​ናል፤ እነ​ር​ሱም ይዋ​ረ​ዳሉ፤</verse>
				<verse number="13">ደግ​ሞም በረ​ጅሙ ከፍ ባለ​ውም በሊ​ባ​ኖስ ዝግባ ሁሉ ላይ፥ በባ​ሳ​ንም ዛፍ ሁሉ ላይ፥</verse>
				<verse number="14">በረ​ጅ​ሙም ተራራ ሁሉ ላይ፥ ከፍ ባለ​ውም ኮረ​ብታ ሁሉ ላይ፥</verse>
				<verse number="15">በረ​ጅ​ሙም ግንብ ሁሉ ላይ፥ በተ​መ​ሸ​ገ​ውም ቅጥር ሁሉ ላይ፥</verse>
				<verse number="16">በባ​ሕ​ሩም መር​ከብ ሁሉ ላይ፥ በተ​ጌጡ ጣዖ​ታ​ትም ምስል ሁሉ ላይ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="17">ሰውም ሁሉ ይዋ​ረ​ዳል፤ የሰ​ውም ኵራት ይወ​ድ​ቃል፤ በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።</verse>
				<verse number="18">በእጅ የተ​ሠሩ ጣዖ​ታ​ትን ሁሉ ይሰ​ው​ራሉ፤</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምድ​ርን ያና​ውጥ ዘንድ በተ​ነሣ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ፍ​ራ​ትና ከግ​ር​ማው ክብር የተ​ነሣ ወደ ድን​ጋይ ዋሻና ወደ ምድር ንቃ​ቃት ውስጥ ያገ​ቡ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="20">በዚ​ያም ቀን ሰው ይሰ​ግ​ድ​ላ​ቸው ዘንድ ያበ​ጁ​አ​ቸ​ውን የብ​ሩ​ንና የወ​ር​ቁን ጣዖ​ቶ​ቹን ለፍ​ል​ፈ​ልና ለሌ​ሊት ወፍ ይጥ​ላል።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምድ​ርን ያና​ውጥ ዘንድ በተ​ነሣ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ፍ​ራ​ትና ከግ​ር​ማው ክብር የተ​ነሣ ወደ ድን​ጋይ ዋሻና ወደ ተሰ​ነ​ጠቁ ዓለ​ቶች ውስጥ ያገ​ባሉ።</verse>
				<verse number="22">እስ​ት​ን​ፋሱ በአ​ፍ​ን​ጫው ያለ​በ​ትን ሰው ተዉት፤ እርሱ ስለ ምን ይቈ​ጠ​ራል?</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">እነሆ፥ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና ከይ​ሁዳ ኀይ​ለ​ኛ​ውን ወን​ድና ኀይ​ለ​ኛ​ዋን ሴት፥ የእ​ን​ጃ​ራን ኀይል ሁሉ፥ የው​ኃ​ው​ንም ኀይል ሁሉ ያስ​ወ​ግ​ዳል፤</verse>
				<verse number="2">ኀያ​ሉ​ንም፥ ተዋ​ጊ​ው​ንም፥ ፈራ​ጁ​ንም፥ ነቢ​ዩ​ንም፥ ዐዋ​ቂ​ው​ንም፥ ሽማ​ግ​ሌ​ው​ንም፥</verse>
				<verse number="3">የአ​ምሳ አለ​ቃ​ው​ንም፥ የተ​ከ​በረ አማ​ካ​ሪ​ው​ንም፥ ጠቢ​ቡ​ንም፥ የአ​ና​ጢ​ዎ​ቹ​ንም አለቃ፥ አስ​ተ​ዋይ አድ​ማ​ጩ​ንም ያስ​ወ​ግ​ዳል።</verse>
				<verse number="4">በእ​ነ​ርሱ ላይ አለ​ቆ​ቻ​ቸው እን​ዲ​ሆኑ ጐል​ማ​ሶ​ችን እሾ​ም​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ዘባ​ቾ​ችም ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="5">ሕዝብ በሕ​ዝብ ላይ፥ ሰው በሰው ላይ፥ ሰውም በባ​ል​ን​ጀ​ራው ላይ ይገ​ፋ​ፋል፤ ብላ​ቴ​ና​ውም በሽ​ማ​ግ​ሌው ላይ፥ የተ​ጠ​ቃ​ውም በከ​በ​ር​ቴው ላይ ይታ​በ​ያል።</verse>
				<verse number="6">ሰውም በአ​ባቱ ቤተ ሰብእ ውስጥ ወን​ድ​ሙን ይዞ፥ “አንተ ልብስ አለህ፥ አለ​ቃም ሁን​ልን፥ ምግ​ባ​ች​ንም ከእ​ጅህ በታች ትሁን” ቢለው፥</verse>
				<verse number="7">በዚያ ቀን ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ፥ “እኔ በቤቴ ውስጥ እን​ጀራ ወይም ልብስ የለ​ኝ​ምና ለሕ​ዝቡ አለቃ አል​ሆ​ንም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።</verse>
				<verse number="8">ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተፈ​ት​ታ​ለ​ችና፥ ይሁ​ዳም ወድ​ቃ​ለ​ችና፥ አን​ደ​በ​ታ​ቸ​ውም ዐመ​ፅን ስለ​ሚ​ና​ገር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ታ​ዘ​ዙም።</verse>
				<verse number="9">ዛሬም ክብ​ራ​ቸው ተዋ​ር​ዷ​ልና፥ ፊታ​ቸ​ውም አፍ​ሯ​ልና ኀጢ​አ​ታ​ቸው እንደ ሰዶ​ምና እንደ ገሞራ ኀጢ​አት ተቃ​ወ​መ​ቻ​ቸው፤ በላ​ያ​ቸ​ውም ተገ​ልጣ ታወ​ቀች።</verse>
				<verse number="10">ክፉ ምክ​ርን መክ​ረ​ዋ​ልና ለነ​ፍ​ሳ​ቸው ወዮ​ላት! እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ጻድ​ቁን እን​ሻ​ረው፤ ሸክም ሆኖ​ብ​ና​ልና፤” ስለ​ዚህ የእ​ጃ​ቸ​ውን ሥራ ፍሬ ይበ​ላሉ።</verse>
				<verse number="11">እንደ እጁ ሥራ ፍዳው ይደ​ረ​ግ​በ​ታ​ልና ለበ​ደ​ለኛ ወዮ! ክፉም ይደ​ር​ስ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="12">ሕዝቤ ሆይ፥ ገዥ​ዎ​ቻ​ችሁ ያስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ች​ኋል፤ አስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች ሴቶ​ችም በላ​ያ​ችሁ ይሠ​ለ​ጥ​ኑ​ባ​ች​ኋል። ሕዝቤ ሆይ፥ የሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑ​አ​ችሁ ያስ​ቱ​አ​ች​ኋል፤ የም​ት​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መን​ገድ ያጠ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="13">ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ለፍ​ርድ ይነ​ሣል፤ በሕ​ዝ​ቡም ላይ ሊፈ​ርድ ይነ​ሣል።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሕ​ዝቡ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ከአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸው ጋር ለፍ​ርድ ይመ​ጣል፤ እን​ዲ​ህም ይላል፥ “ወይ​ኔን አቃ​ጥ​ላ​ች​ኋል፤ ከድ​ሃው የበ​ዘ​በ​ዛ​ች​ሁ​ትም በቤ​ታ​ችሁ አለ፤</verse>
				<verse number="15">ሕዝ​ቤ​ንስ ለምን ትገ​ፋ​ላ​ችሁ? የድ​ሃ​ውን ፊትስ ለምን ታሳ​ፍ​ሩ​ታ​ላ​ችሁ?”</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አለ፥ “የጽ​ዮን ቆነ​ጃ​ጅት ኰር​ተ​ዋ​ልና፥ አን​ገ​ታ​ቸ​ውን እያ​ሰ​ገጉ በዐ​ይ​ና​ቸ​ውም እያ​ጣ​ቀሱ፥ በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም እያ​ረ​ገዱ፥ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም እየ​ጐ​ተቱ፥ በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም እያ​ማቱ ይሄ​ዳ​ሉና፤</verse>
				<verse number="17">ስለ​ዚህ ጌታ የጽ​ዮን ታላ​ላቅ ሴቶች ልጆ​ችን ያዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚያ ቀን ልብ​ሳ​ቸ​ውን ይገ​ል​ጣል።</verse>
				<verse number="18">በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ግር አል​ቦ​ውን ክብር፥ መር​በ​ቡ​ንም፥ ጨረቃ የሚ​መ​ስ​ለ​ው​ንም ጌጥ፥</verse>
				<verse number="19">የጆሮ እን​ጥ​ል​ጥ​ሉ​ንም፥ አን​ባ​ሩ​ንም፥ መሸ​ፈ​ኛ​ው​ንም፥ ቀጸ​ላ​ው​ንም፥</verse>
				<verse number="20">ሰን​ሰ​ለ​ቱ​ንም፥ መቀ​ነ​ቱ​ንም፥ የሽ​ቱ​ው​ንም ዕቃ፥ አሸ​ን​ክ​ታ​ቡ​ንም፥</verse>
				<verse number="21">የእ​ጅና የአ​ፍ​ንጫ ቀለ​በ​ቱ​ንም፥</verse>
				<verse number="22">የዓ​መት በዓ​ል​ንም ልብስ፥ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ው​ንም፥ ልግ​ም​በ​ገ​ላ​ው​ንም፥ ከረ​ጢ​ቱ​ንም፥</verse>
				<verse number="23">መስ​ተ​ዋ​ቱ​ንም ከጥሩ በፍታ የተ​ሠ​ራ​ው​ንም ልብስ፥ ራስ ማሰ​ሪ​ያ​ው​ንም፥ ዐይነ ርግ​ቡ​ንም ያስ​ወ​ግ​ዳል።</verse>
				<verse number="24">እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ስለ ሥራሽ ክፋት በሽቱ ፋንታ ትቢያ ይሁ​ን​ብሽ፤ በወ​ርቅ መታ​ጠ​ቂ​ያ​ሽም ፋንታ ገመድ ታጠቂ፤ በራስ ወርቅ ቀጸ​ላ​ሽም ፋንታ ቡሃ​ነት ይው​ጣ​ብሽ፤ በሐር መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያሽ ፋንታ ማቅ ልበሽ።</verse>
				<verse number="25">የም​ት​ወ​ጂው ትልቁ ልጅሽ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃል፤ ኀያ​ላ​ን​ሽም በው​ጊያ ይወ​ድ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="26">የጌ​ጦ​ች​ሽም ሣጥ​ኖች ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ይዋ​ረ​ዳ​ሉም፤ ብቻ​ሽ​ንም ትቀ​ሪ​ያ​ለሽ፤ ከም​ድ​ርም ጋር ትቀ​ላ​ቀ​ያ​ለሽ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">በዚ​ያም ቀን ሰባት ሴቶች፥ “የገዛ እን​ጀ​ራ​ች​ንን እን​በ​ላ​ለን፤ የገዛ ልብ​ሳ​ች​ን​ንም እን​ለ​ብ​ሳ​ለን፤ ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፤ መሰ​ደ​ባ​ች​ን​ንም አር​ቅ​ልን” ብለው አን​ዱን ወንድ ይይ​ዙ​ታል።</verse>
				<verse number="2">በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል የተ​ረ​ፉ​ትን ያከ​ብ​ርና ከፍ ያደ​ርግ ዘንድ በጌ​ት​ነቱ ምክር በም​ድር ላይ ያበ​ራል።</verse>
				<verse number="3">በጽ​ዮን የቀሩ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​ረፉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለሕ​ይ​ወት የተ​ጻፉ ሁሉ፥ ቅዱ​ሳን ይባ​ላሉ።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ዮ​ንን ሴቶች ልጆ​ችና ወን​ዶች ልጆች እድፍ ያጥ​ባ​ልና፥ በፍ​ርድ መን​ፈ​ስና በሚ​ያ​ቃ​ጥል መን​ፈ​ስም ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ደምን ያነ​ጻ​ልና።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ጣል፤ በጽ​ዮን ተራራ ላይ ባለ ቦታ ሁሉ፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ላይ ደመና በቀን እንደ ጢስ፥ በሌ​ሊ​ትም እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠል የእ​ሳት ብር​ሃን ይጋ​ር​ዳል፤ በክ​ብ​ርም ሁሉ ላይ መጋ​ረጃ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="6">ከሙ​ቀት ለጥላ፥ ከዐ​ውሎ ነፋ​ስና ከዝ​ና​ብም ለመ​ጠ​ጊ​ያና ለመ​ሸ​ሸ​ጊያ ጎጆ ይሆ​ናል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">አሁን የወ​ይ​ኔን ቦታ በተ​መ​ለ​ከተ የወ​ዳ​ጄን መዝ​ሙር ለወ​ዳጄ እዘ​ም​ራ​ለሁ። ለወ​ዳጄ በፍ​ሬ​ያ​ማው ቦታ ላይ የወ​ይን ቦታ ነበ​ረው።</verse>
				<verse number="2">አጥር አጠ​ርሁ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ቈፈ​ርሁ፤ ድን​ጋ​ዮ​ች​ንም ለቅሜ አወ​ጣሁ፤ ምርጥ የሆ​ነ​ው​ንም ወይን ተከ​ልሁ፤ በመ​ካ​ከ​ሉም ግንብ ሠራሁ፤ ደግ​ሞም የመ​ጥ​መ​ቂያ ጕድ​ጓድ ማስ​ሁ​ለት፤ ወይ​ን​ንም ያፈራ ዘንድ ጠበ​ቅ​ሁት፤ ዳሩ ግን እሾ​ህን አፈራ።</verse>
				<verse number="3">አሁ​ንም እና​ንተ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ት​ኖ​ሩና የይ​ሁዳ ሰዎች ሆይ፥ በእ​ኔና በወ​ይኑ ቦታዬ መካ​ከል እስኪ ፍረዱ።</verse>
				<verse number="4">ለወ​ይኔ ያላ​ደ​ረ​ግ​ሁ​ለት፥ ከዚህ ሌላ አደ​ር​ግ​ለት ዘንድ የሚ​ገ​ባኝ ምን​ድን ነው? ወይ​ንን ያፈ​ራል ብዬ ጠበ​ቅ​ሁት፤ ነገር ግን እሾ​ህን አፈራ።</verse>
				<verse number="5">አሁ​ንም በወ​ይኔ ላይ የማ​ደ​ር​ገ​ውን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ አጥ​ሩን እነ​ቅ​ላ​ለሁ፤ ለብ​ዝ​በ​ዛም ይሆ​ናል፤ ቅጥ​ሩ​ንም አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ ለመ​ራ​ገ​ጫም ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="6">ባድማ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ አይ​ገ​ረ​ዝም፤ አይ​ኰ​ተ​ኰ​ትም፤ እንደ ጠፍ ቦታ ኵር​ን​ች​ትና እሾህ ይበ​ቅ​ል​በ​ታል፤ ዝና​ብ​ንም እን​ዳ​ያ​ዘ​ን​ቡ​በት ደመ​ና​ዎ​ችን አዝ​ዛ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወይን ቦታ እርሱ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ነው፤ ተወ​ዳጁ አዲስ ተክ​ልም የይ​ሁዳ ሰዎች ናቸው፤ ፍር​ድን ያደ​ር​ጋል ብየ እጠ​ብቅ ነበር፤ እነ​ሆም፥ ዐመ​ፅን አደ​ረገ፤ ጽድ​ቅ​ንም አይ​ደ​ለም፥ ጩኸ​ትን እንጂ።</verse>
				<verse number="8">ከጎ​ረ​ቤ​ቶ​ቻ​ቸው እርሻ ይወ​ስዱ ዘንድ፥ ምድ​ር​ንም ለብ​ቻ​ቸው ይይ​ዟት ዘንድ፥ ቤትን ከቤት ጋር ለሚ​ያ​ያ​ይዙ፥ እር​ሻ​ንም ከእ​ርሻ ጋር ለሚ​ያ​ቀ​ራ​ርቡ ወዮ​ላ​ቸው!</verse>
				<verse number="9">ይህ በሠ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጆሮ ተሰ​ም​ቶ​አ​ልና፦ ቤቶች ቢሠሩ ባድማ ይሆ​ናሉ፤ ታላ​ላ​ቅና የሚ​ያ​ምሩ ቤቶ​ችም የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው አይ​ኖ​ርም።</verse>
				<verse number="10">ዐሥር ጥማድ በሬ ካረ​ሰው የወ​ይን ቦታ አንድ ፊቀን ወይን ጠጅ ይወ​ጣል፤ ስድ​ስት መስ​ፈ​ሪያ የዘራ ሦስት መሥ​ፈ​ሪያ ብቻ ያገ​ባል።</verse>
				<verse number="11">በጥ​ዋት ወደ መሸታ ቤት ለሚ​ገ​ሠ​ግ​ሡና በመ​ጠጥ ቤት ለሚ​ውሉ ወዮ​ላ​ቸው! ወይኑ ያቃ​ጥ​ላ​ቸ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="12">በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገና፥ በከ​በ​ሮና በእ​ም​ቢ​ል​ታም እየ​ዘ​ፈኑ የወ​ይን ጠጅን ይጠ​ጣሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ግን አል​ተ​መ​ለ​ከ​ቱም፤ የእ​ጁ​ንም ሥራ አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም።</verse>
				<verse number="13">ስለ​ዚ​ህም ሕዝቤ ወደ ምርኮ ሄዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ወ​ቁ​ት​ምና፤ ብዙ​ዎቹ በረ​ኃ​ብና በውኃ ጥም ሞቱ፤</verse>
				<verse number="14">ሲኦ​ልም ሆድ​ዋን አስ​ፍ​ታ​ለች፤ አፍ​ዋ​ንም ያለ ልክ ከፍ​ታ​ለች፤ የተ​ከ​በ​ሩና ታላ​ላቅ ሰዎች ባለ​ጠ​ጎ​ቻ​ቸ​ውና ድሆ​ቻ​ቸ​ውም ወደ እር​ስዋ ይወ​ር​ዳሉ።</verse>
				<verse number="15">ታናሹ ሰውም ይጐ​ሰ​ቍ​ላል፤ ታላቁ ሰውም ይዋ​ረ​ዳል፤ የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችም ዐይ​ኖች ይዋ​ረ​ዳሉ፤</verse>
				<verse number="16">የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በፍ​ርድ ከፍ ከፍ ይላል፤ ቅዱ​ሱም አም​ላክ በጽ​ድቅ ይከ​ብ​ራል።</verse>
				<verse number="17">የተ​ማ​ረኩ እንደ በሬ​ዎች ይሰ​ማ​ራሉ፤ የተ​ረ​ሱ​ትም ምግ​ባ​ቸ​ውን ሲፈ​ልጉ እንደ በግ ጠቦ​ቶች በማ​ሰ​ማ​ር​ያ​ቸው ይሰ​ማ​ራሉ።</verse>
				<verse number="18">በደ​ልን እንደ ረዥም ገመድ ለሚ​ስቡ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም እንደ በሬ ቀን​በር ለሚ​ያ​ስሩ ወዮ​ላ​ቸው!</verse>
				<verse number="19">“እናይ ዘንድ፥ ሥራ​ውን ያፋ​ጥን፤ እና​ው​ቃ​ትም ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ምክር፥ ትምጣ” ለሚሉ ወዮ​ላ​ቸው!</verse>
				<verse number="20">ክፉ​ውን መል​ካም መል​ካ​ሙ​ንም ክፉ ለሚሉ፥ ጨለ​ማ​ውን ብር​ሃን ብር​ሃ​ኑ​ንም ጨለማ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ፥ ጣፋ​ጩን መራራ መራ​ራ​ው​ንም ጣፋጭ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ ወዮ​ላ​ቸው!</verse>
				<verse number="21">ለክ​ፋት ጥበ​በ​ኞች ለሆኑ፥ እኛ ጠቢ​ባን ነን ለሚ​ሉም ወዮ​ላ​ቸው!</verse>
				<verse number="22">የወ​ይን ጠጅ ለሚ​ጠጡ ኀያ​ላን፥ የሚ​ያ​ሰ​ክ​ረ​ው​ንም መጠጥ ለሚ​ደ​ባ​ልቁ ጽኑ​ዓን ወዮ​ላ​ቸው!</verse>
				<verse number="23">በደ​ለ​ኛ​ውን ስለ ጉቦ ጻድቅ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ፥ የጻ​ድ​ቁ​ንም ጽድቅ ለሚ​ያ​ስ​ወ​ግ​ዱ​በት ወዮ​ላ​ቸው!</verse>
				<verse number="24">ስለ​ዚህ ገለባ በእ​ሳት ፍም እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠል፥ በነ​በ​ል​ባ​ልም እን​ደ​ሚ​በላ፥ እን​ዲሁ የእ​ነ​ርሱ ሥር የበ​ሰ​በሰ ይሆ​ናል፤ አበ​ባ​ቸ​ውም እንደ ትቢያ ይበ​ን​ናል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ጥለ​ዋ​ልና፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቅዱስ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አቃ​ል​ለ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="25">ስለ​ዚህ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ላይ ታላቅ ቍጣን ተቈጣ፤ እጁ​ንም በላ​ያ​ቸው ዘር​ግቶ መት​ቶ​አ​ቸ​ዋል፤ ተራ​ሮ​ችም ተን​ቀ​ጠ​ቀጡ፤ ሬሳ​ቸ​ውም በመ​ን​ገድ መካ​ከል እንደ ጕድፍ ሆኖ​አል። በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="26">በሩቅ ላሉ አሕ​ዛ​ብም ምል​ክ​ትን ያቆ​ማል፤ ከም​ድ​ርም ዳርቻ በፉ​ጨት ይጠ​ራ​ቸ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ እየ​ተ​ጣ​ደፉ ፈጥ​ነው ይመ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="27">አይ​ራ​ቡም፤ አይ​ጠ​ሙ​ምም፤ አይ​ደ​ክ​ሙም፤ አይ​ተ​ኙም፤ የወ​ገ​ባ​ቸ​ውን መታ​ጠ​ቂያ አይ​ፈ​ቱም፤ የጫ​ማ​ቸ​ውም ማዘ​ቢያ አይ​በ​ጠ​ስም።</verse>
				<verse number="28">ፍላ​ጾ​ቻ​ቸው ተስ​ለ​ዋል፤ ቀስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ተለ​ጥ​ጠ​ዋል፤ የፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ኮቴ እንደ ቡላድ፥ የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም መን​ኰ​ራ​ኵር እንደ ዐውሎ ነፋስ ይቈ​ጠ​ራል።</verse>
				<verse number="29">ጩኸ​ታ​ቸው እንደ አን​በሳ ነው፤ እንደ አን​በሳ ደቦ​ሎ​ችም ይቆ​ማሉ፤ ከጕ​ድ​ጓዱ እን​ደ​ሚ​ወጣ አው​ሬም ይነ​ጥ​ቃሉ፤ ይጮ​ሃሉ፤ የሚ​ድ​ንም የለም።</verse>
				<verse number="30">በዚ​ያም ቀን እንደ ባሕር መት​መም ይተ​ም​ሙ​ባ​ቸ​ዋል፤ ወደ ምድ​ርም ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤ ድቅ​ድቅ ጨለ​ማን ያያሉ፤ ይጨ​ነ​ቃ​ሉም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ ንጉሡ ዖዝ​ያን በሞ​ተ​በት ዓመት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በረ​ዥ​ምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀ​ምጦ አየ​ሁት፤ ምስ​ጋ​ና​ውም ቤቱን ሞል​ቶት ነበር።</verse>
				<verse number="2">ሱራ​ፌ​ልም በዙ​ሪ​ያው ቆመው ነበር፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ስድ​ስት ክንፍ ነበ​ረው፤ በሁ​ለቱ ክን​ፎ​ቻ​ቸው ፊታ​ቸ​ውን ይሸ​ፍኑ ነበር፤ በሁ​ለ​ቱም ክን​ፎ​ቻ​ቸው እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ይሸ​ፍኑ ነበር፤ በሁ​ለ​ቱም ክን​ፎ​ቻ​ቸው ይበ​ርሩ ነበር።</verse>
				<verse number="3">አን​ዱም ለአ​ንዱ፥ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ምድር ሁሉ ከክ​ብሩ ተሞ​ል​ታ​ለች” እያለ ይጮኽ ነበር።</verse>
				<verse number="4">የመ​ድ​ረ​ኩም መሠ​ረት ከጩ​ኸ​ታ​ቸው ድምፅ የተ​ነሣ ተና​ወጠ፤ ቤቱ​ንም ጢስ ሞላ​በት።</verse>
				<verse number="5">እኔም፥ “ከን​ፈ​ሮች የረ​ከ​ሱ​ብኝ ሰው በመ​ሆኔ፥ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸው በረ​ከ​ሱ​ባ​ቸው ሕዝብ መካ​ከል በመ​ቀ​መጤ ዐይ​ኖች የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ ንጉ​ሡን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ አዩ ጠፍ​ቻ​ለ​ሁና ወዮ​ልኝ!” አልሁ።</verse>
				<verse number="6">ከሱ​ራ​ፌል አንዱ ወደ እኔ ተላከ፤ በእ​ጁም ከመ​ሠ​ዊ​ያው በጕ​ጠት የወ​ሰ​ደው ፍም ነበረ።</verse>
				<verse number="7">አፌ​ንም ዳሰ​ሰ​በ​ትና፥ “እነሆ፥ ይህ ከን​ፈ​ሮ​ች​ህን ነክ​ቶ​አል፤ በደ​ል​ህም ከአ​ንተ ተወ​ገደ፤ ኀጢ​አ​ት​ህም ተሰ​ረ​የ​ልህ” አለኝ።</verse>
				<verse number="8">የጌ​ታ​ንም ድምፅ፥ “ማንን እል​ካ​ለሁ? ማንስ ወደ​ዚያ ሕዝብ ይሄ​ድ​ል​ናል?” ሲል ሰማሁ? እኔም፥ “እነ​ሆኝ፥ ጌታዬ፥ እኔን ላከኝ” አልሁ።</verse>
				<verse number="9">እር​ሱም፥ “ሂድ፤ ይህን ሕዝብ፦ መስ​ማ​ትን ትሰ​ማ​ላ​ችሁ፥ አታ​ስ​ተ​ው​ሉ​ምም፤ ማየ​ት​ንም ታያ​ላ​ችሁ፥ አት​መ​ለ​ከ​ቱ​ምም” በላ​ቸው አለኝ።</verse>
				<verse number="10">እነ​ዚህ ሕዝ​ቦች በዐ​ይ​ና​ቸው እን​ዳ​ያዩ፥ በጆ​ሮ​አ​ቸ​ውም እን​ዳ​ይ​ሰሙ፥ በል​ባ​ቸ​ውም እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ውሉ ተመ​ል​ሰ​ውም እን​ዳ​ል​ፈ​ው​ሳ​ቸው፥ ልባ​ቸ​ውን አደ​ን​ድ​ነ​ዋ​ልና፥ ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም ደፍ​ነ​ዋ​ልና፥ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም ጨፍ​ነ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="11">እኔም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?” አልሁ። እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አለኝ፥ “ከተ​ሞች የሚ​ኖ​ር​ባ​ቸ​ውን አጥ​ተው እስ​ኪ​ፈ​ርሱ ድረስ፥ ቤቶ​ችም ሰው አልቦ እስ​ኪ​ሆኑ፥ ምድ​ርም ፈጽሞ ባድማ ሆና እስ​ክ​ት​ቀር ድረስ ነው፤”</verse>
				<verse number="12">ከዚ​ያም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰዎ​ችን ያር​ቃል፤ በም​ድ​ርም የቀ​ሩት ይበ​ዛሉ።</verse>
				<verse number="13">በእ​ር​ስ​ዋም ዘንድ ዐሥ​ረኛ እጅ ቀርቶ እንደ ሆነ እርሱ ደግሞ ይቃ​ጠ​ላል፤ ቅጠ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም በረ​ገፉ ጊዜ እንደ ግራ​ርና እንደ ኮም​በል ዛፍ ሁነው ይቀ​ራሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በይ​ሁዳ ንጉሥ በዖ​ዝ​ያን ልጅ በኢ​ዮ​አ​ታም ልጅ በአ​ካዝ ዘመን የአ​ራም ንጉሥ ረአ​ሶን፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ሊወጉ ወጡ፤ ሊይ​ዙ​አ​ትም አል​ቻ​ሉም።</verse>
				<verse number="2">ለዳ​ዊት ቤትም፥ “አራም ከኤ​ፍ​ሬም ጋር ተባ​ብ​ረ​ዋል” የሚል ወሬ ተነ​ገረ፤ የእ​ር​ሱም ልብ የሕ​ዝ​ቡም ልብ የዱር ዛፍ በነ​ፋስ እን​ደ​ሚ​ና​ወጥ ተና​ወጠ።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢሳ​ይ​ያ​ስን አለው፥ “አን​ተና ልጅህ ያሱብ አካ​ዝን ትገ​ና​ኙት ዘንድ በል​ብስ አጣ​ቢው እርሻ መን​ገድ ወዳ​ለው ወደ ላይ​ኛው መታ​ጠ​ቢያ ቦታ ውጡ፤</verse>
				<verse number="4">እን​ዲ​ህም በለው፥ “ተጠ​በቅ፥ ዝምም በል፤ አት​ፍራ፤ ከእ​ነ​ዚህ ከሚ​ጤሱ ሁለት የእ​ን​ጨት ጠለ​ሸ​ቶች፥ የተ​ነሣ ልብህ አይ​ደ​ን​ግጥ፤ ከተ​ቈ​ጣሁ በኋላ ይቅር እላ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="5">የአ​ራም ልጅና የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ፦ ክፉ ምክ​ርን ተማ​ከ​ሩ​ብህ እን​ዲህ ብለው፦</verse>
				<verse number="6">ወደ ይሁዳ እን​ው​ጣና እን​ነ​ጋ​ገ​ራ​ቸው፤ ወደ እኛም እን​መ​ል​ሳ​ቸው፤ የጣ​ብ​ኤ​ል​ንም ልጅ እና​ን​ግ​ሥ​ባ​ቸው፤”</verse>
				<verse number="7">የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ይህ ምክር አይ​ጸ​ና​ምና አይ​ሆ​ንም።</verse>
				<verse number="8">የአ​ራም ራስ ደማ​ስቆ ነው፤ የደ​ማ​ስ​ቆም ራስ ረአ​ሶን ነው፤ በስ​ድሳ አም​ስት ዓመት ውስጥ የኤ​ፍ​ሬም መን​ግ​ሥት ከሕ​ዝብ ይጠ​ፋል፤</verse>
				<verse number="9">የኤ​ፍ​ሬ​ምም ራስ ሳም​ሮን ነው፤ የሳ​ም​ሮ​ንም ራስ የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ ነው። ባታ​ምኑ አት​ጸ​ኑም።”</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ አካ​ዝን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦</verse>
				<verse number="11">“ከጥ​ልቁ ወይም ከከ​ፍ​ታው ቢሆን ከአ​ም​ላ​ክህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምል​ክ​ትን ለአ​ንተ ለምን።”</verse>
				<verse number="12">አካ​ዝም፥ “አል​ለ​ም​ንም፤ አም​ላኬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ፈ​ታ​ተ​ንም” አለ።</verse>
				<verse number="13">እር​ሱም አለ፥ “እና​ንተ የዳ​ዊት ቤት ሆይ፥ ስሙ፤ በውኑ ሰውን ማድ​ከ​ማ​ችሁ ቀላል ነውን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታደ​ክ​ማ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="14">ስለ​ዚህ ጌታ ራሱ ምል​ክት ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ እነሆ፥ ድን​ግል ትፀ​ን​ሳ​ለች፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ዳ​ለች፤ ስሙ​ንም አማ​ኑ​ኤል ብላ ትጠ​ራ​ዋ​ለች።</verse>
				<verse number="15">ሕፃኑ ክፉን ለመ​ጥ​ላት መል​ካ​ሙ​ንም ለመ​ም​ረጥ ሳያ​ውቅ ቅቤና ማር ይበ​ላል።</verse>
				<verse number="16">ሕፃኑ ክፉን ለመ​ጥ​ላት፥ መል​ካ​ሙን ለመ​ም​ረጥ ሳያ​ውቅ፥ የፈ​ራ​ሃ​ቸው የሁ​ለቱ ነገ​ሥ​ታት ሀገር ባድማ ትሆ​ና​ለች።</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኤፍ​ሬም ከይ​ሁዳ ከተ​ለ​የ​በት ቀን ጀምሮ ያል​መ​ጣ​ውን ዘመን በአ​ን​ተና በሕ​ዝ​ብህ በአ​ባ​ት​ህም ቤት ላይ ያመ​ጣል፤ እር​ሱም የአ​ሦር ንጉሥ መም​ጣት ነው።”</verse>
				<verse number="18">በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብፅ ወንዝ ዳርቻ ያለ​ውን ዝንብ፥ በአ​ሦ​ርም ሀገር ያለ​ውን ንብ በፉ​ጨት ይጠ​ራል።</verse>
				<verse number="19">ይመ​ጡ​ማል፤ እነ​ር​ሱም ሁሉ በሸ​ለቆ፥ በመ​ን​ደ​ሮች፥ በም​ድር ጕድ​ጓድ፥ በድ​ን​ጋ​ይም ዋሻ ውስጥ በጫካ ሁሉ ላይ ይሰ​ፍ​ራሉ።</verse>
				<verse number="20">በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከወ​ንዙ ማዶ ባመ​ጣው ታላቅ ምላጭ በአ​ሦር ንጉሥ የራ​ሱ​ንና የእ​ግ​ሩን ጠጕር ይላ​ጨ​ዋል፤ ምላ​ጩም ጢሙን ደግሞ ይላ​ጫል።</verse>
				<verse number="21">በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ሰው ከላ​ሞቹ አን​ዲት ጊደ​ር​ንና ሁለት በጎ​ችን ያሳ​ድ​ጋል፤ የአ​ን​ዲት በግ ወተ​ትም ሁለት ሰዎ​ችን ያጠ​ግ​ባል።</verse>
				<verse number="22">ወተ​ትም ይበ​ዛል፤ በሀ​ገ​ሪቱ መካ​ከል የቀረ ሁሉ ቅቤና ማር ይበ​ላል።</verse>
				<verse number="23">በዚ​ያም ወራት እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ወይን በሀ​ገሩ ሁሉ የበጀ ይሆ​ናል፤ የአ​ንድ ሺህ የወ​ይን ዳስ ዋጋ አንድ ሺህ የብር ሰቅል ይሆ​ናል። ከዚህ በኋላ ዳግ​መኛ ምድር ሁሉ ትጠ​ፋ​ለች፤ እሾ​ህ​ንና ኵር​ን​ች​ት​ንም ትሞ​ላ​ለች፤ ፍር​ሀ​ትም ይመ​ጣል።</verse>
				<verse number="24">በፍ​ላ​ጻና በቀ​ስት ይገ​ቡ​ባ​ታል፤ ምድ​ሪቱ ሁሉ ትጠ​ፋ​ለ​ችና፥ እሾ​ህ​ንና ኵር​ን​ች​ት​ንም ትሞ​ላ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="25">በሚ​ታ​ረ​ሰ​ውም ተራራ ሁሉ ላይ ፍር​ሀት ይመ​ጣል፤ የበ​ጎች መሰ​ማ​ርያ ይሆ​ናል፤ በሬ​ዎ​ችም ይረ​ግ​ጡ​ታል፤ እሾ​ህና ኵር​ን​ች​ትም ያጠ​ፋ​ዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “ታላቅ አዲስ ሰሌዳ ወስ​ደህ፦ ‘ቸኩ​ለህ ማርክ፤ ፈጥ​ነ​ህም በዝ​ብዝ’ ብለህ በሰው ብርዕ ጻፍ​በት።</verse>
				<verse number="2">የታ​መ​ኑ​ትን ሰዎች ካህ​ኑን ኦር​ያ​ንና የበ​ራ​ክ​ዩን ልጅ ዘካ​ር​ያ​ስን ምስ​ክ​ሮች አድ​ር​ግ​ልኝ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ አድ​ሮ​ባ​ቸ​ዋ​ልና፤”</verse>
				<verse number="3">ወደ ነቢ​ዪ​ቱም ቀረ​ብሁ፤ እር​ስ​ዋም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “ስሙን ‘ቸኩ​ለህ ማርክ፤ ፈጥ​ነ​ህም በዝ​ብዝ’ ብለህ ጥራው።</verse>
				<verse number="4">ሕፃኑ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን መጥ​ራት ሳያ​ውቅ የደ​ማ​ስ​ቆን ሀብ​ትና የሰ​ማ​ር​ያን ምርኮ በአ​ሦር ንጉሥ ፊት ይወ​ስ​ዳ​ልና።”</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ ተና​ገ​ረኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፦</verse>
				<verse number="6">“እኒህ ሕዝብ በቀ​ስታ በሚ​ሄ​ደው በሰ​ሊ​ሆም ውኃ ቍርጥ ምክ​ርን መከሩ፤ ረአ​ሶ​ን​ንና የሮ​ሜ​ል​ዩን ልጅ ያነ​ግ​ሡ​ላ​ቸው ዘንድ ይወ​ዳ​ሉና።</verse>
				<verse number="7">ስለ​ዚህ፥ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብር​ቱና ብዙ የሆ​ነ​ውን የወ​ንዝ ውኃ፥ የአ​ሦ​ርን ንጉ​ሥና ክብ​ሩን ሁሉ ያመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋል፤ ወን​ዙም ሞልቶ ይወ​ጣል፤ በዳ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ላይ ይፈ​ስ​ሳል፤</verse>
				<verse number="8">ከይ​ሁዳ ወንድ ሰውን ሁሉ ያጠ​ፋል፤ ኀያ​ላ​ኑ​ንም ይጨ​ር​ሳል፤ ሰፈ​ሩም በሰ​ፊው ምድ​ርና በሀ​ገ​ሮ​ቻ​ቸው ሁሉ ይሞ​ላል፤” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር ነውና።</verse>
				<verse number="9">አሕ​ዛብ ሆይ፥ ዕወ​ቁና ደን​ግጡ፤ እስከ ምድር ዳር​ቻም ስሙ፤ ኀያ​ላን! ድል ሁኑ፤ ዳግ​መ​ኛም ብት​በ​ረቱ እንደ ገና ድል ትሆ​ና​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="10">ምክ​ርን ብት​መ​ክ​ሩም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክ​ራ​ች​ሁን ይለ​ው​ጣል፤ የተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁ​ትም ነገር አይ​ሆ​ን​ላ​ች​ሁም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር ነውና።</verse>
				<verse number="11">የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽኑ እጅ እን​ዲህ ተና​ገ​ረኝ፤ በዚ​ህም ሕዝብ መን​ገድ እን​ዳ​ል​ሄድ አስ​ጠ​ነ​ቀ​ቀኝ፤</verse>
				<verse number="12">እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “ይህ ሕዝብ፦ ከባድ ነው የሚ​ለ​ውን ሁሉ፦ ከባድ ነው አት​በሉ፤ መፈ​ራ​ታ​ቸ​ው​ንም አት​ፍሩ፤ አት​ደ​ን​ግ​ጡም።</verse>
				<verse number="13">ነገር ግን የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቀድ​ሱት፤ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ች​ሁና የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ች​ሁም እርሱ ይሁን።</verse>
				<verse number="14">ብታ​ም​ን​በት ይቀ​ድ​ስ​ሃል፤ እንደ ድን​ጋይ ዕን​ቅ​ፋ​ትም አያ​ደ​ና​ቅ​ፍ​ህም፤ እን​ደ​ሚ​ያ​ድጥ ዓለ​ትም አይ​ሆ​ን​ብ​ህም፤ ሁለቱ የያ​ዕ​ቆብ ቤቶች ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በወ​ጥ​መ​ድና በአ​ሽ​ክላ ተይ​ዘው ይኖ​ራሉ።</verse>
				<verse number="15">ስለ​ዚ​ህም ከእ​ነ​ርሱ ብዙ​ዎች በእ​ርሱ ይሰ​ና​ከ​ላሉ፤ ይወ​ድ​ቁ​ማል፤ ይሰ​በ​ሩ​ማል፤ ይጠ​መ​ዱ​ማል፤ ይያ​ዙ​ማል።”</verse>
				<verse number="16">እን​ዳ​ይ​ማ​ሩ​አት ሕግን የሚ​ያ​ጠ​ፉ​አት ሰዎች ያን​ጊዜ ይገ​ለ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="17">ከያ​ዕ​ቆ​ብም ቤት ፊቱን የመ​ለ​ሰ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጠ​ብ​ቃ​ለሁ፥ እተ​ማ​መ​ን​በ​ት​ማ​ለሁ።</verse>
				<verse number="18">እነሆ፥ እኔና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠኝ ልጆች ለእ​ስ​ራ​ኤል በጽ​ዮን ተራራ ከሚ​ኖ​ረው ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ምል​ክ​ትና ተአ​ም​ራት ነን።</verse>
				<verse number="19">እነ​ር​ሱም፥ “ድም​ፃ​ቸ​ውን ዝቅ አድ​ር​ገው የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን ጠይቁ” ባሉ​አ​ችሁ ጊዜ፥ ሕዝቡ ከአ​ም​ላኩ መጠ​የቅ አይ​ገ​ባ​ው​ምን? ወይስ ለሕ​ያ​ዋን ሲሉ ሙታ​ንን ይጠ​ይ​ቃ​ሉን?</verse>
				<verse number="20">ነገሩ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም ይሉ ዘንድ፥ ለእ​ር​ሱም ግብር እን​ዳ​ይ​ሰጡ ሕግን ለር​ዳታ ሰጥ​ቶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="21">በዚ​ህም በር​ግጥ ጽኑ ረኃብ ይመ​ጣ​ባ​ች​ኋል፤ በተ​ራ​ባ​ች​ሁም ጊዜ ትጨ​ነ​ቃ​ላ​ችሁ፤ በአ​ለ​ቆ​ችና በመ​ኳ​ን​ን​ቱም ላይ ክፉ ትና​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤ ወደ ላይ ወደ ሰማይ ትመ​ለ​ከ​ታ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="22">ወደ ታችም ወደ ምድር ትመ​ለ​ከ​ታ​ላ​ችሁ፤ ድቅ​ድቅ ጨለ​ማ​ንም ታያ​ላ​ችሁ፤ ታላቅ መከ​ራ​ንም ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ፤ ትጨ​ነ​ቃ​ላ​ችሁ፤ ትቸ​ገ​ራ​ላ​ች​ሁም፤ በፊ​ታ​ች​ሁም ጨለማ ይሆ​ናል፤ አታ​ዩ​ምም፤ በመ​ከ​ራም ያለ ጊዜው እስ​ኪ​ደ​ርስ አይ​ድ​ንም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">የዚ​ህም ጊዜው እስ​ከ​ሚ​ደ​ርስ የተ​ቸ​ገ​ረው ሁሉ አያ​መ​ል​ጥም፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዘመን የዛ​ብ​ሎ​ን​ንና የን​ፍ​ታ​ሌ​ምን ምድር አቃ​ለለ፤ በኋ​ለ​ኛው ዘመን ግን በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በባ​ሕር መን​ገድ ያለ​ውን የአ​ሕ​ዛ​ብን ገሊላ ያከ​ብ​ራል።</verse>
				<verse number="2">በጨ​ለማ የሄደ ሕዝብ ታላቅ ብር​ሃን አየ፤ በሞት ጥላና በጨ​ለማ ሀገ​ርም ለነ​በሩ ብር​ሃን ወጣ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ብዙ ሕዝ​ብን በደ​ስታ አወ​ረ​ድህ፤ በመ​ከር ደስ እን​ደ​ሚ​ላ​ቸው፥ ምር​ኮ​ንም እን​ደ​ሚ​ካ​ፈሉ በፊ​ትህ ደስ ይላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="4">በም​ድ​ያም ጊዜ እንደ ሆነ በላ​ያ​ቸው የነ​በ​ረው ቀን​በር ተነ​ሥ​ቶ​አ​ልና፥ በጫ​ን​ቃ​ቸው የነ​በ​ረ​ው​ንም፥ የአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎ​ች​ንም በትር መል​ሶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="5">በደም የተ​ለ​ወሰ ልብስ በእ​ሳት ከሚ​ቃ​ጠል በቀር ለም​ንም አይ​ጠ​ቅ​ምም።</verse>
				<verse number="6">ሕፃን ተወ​ል​ዶ​ል​ና​ልና፥ ወንድ ልጅም ተሰ​ጥ​ቶ​ና​ልና፤ አለ​ቅ​ነ​ትም በጫ​ን​ቃው ላይ ይሆ​ናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኀያል አም​ላክ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም አባት፥ የሰ​ላም አለቃ ተብሎ ይጠ​ራል፤</verse>
				<verse number="7">ለአ​ለ​ቆች ሰላ​ምን ለእ​ር​ሱም ሕይ​ወ​ትን አመ​ጣ​ለ​ሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ በፍ​ር​ድና በጽ​ድቅ ያጸ​ና​ውና ይደ​ግ​ፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆ​ናል፤ በዳ​ዊት ዙፋን መን​ግ​ሥቱ ትጸ​ና​ለች፤ ለሰ​ላ​ሙም ፍጻሜ የለ​ውም። የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅን​ዐት ይህን ያደ​ር​ጋል።</verse>
				<verse number="8">ጌታ በያ​ዕ​ቆብ ላይ ሞትን ላከ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ወደቀ።</verse>
				<verse number="9">የኤ​ፍ​ሬም ሕዝብ ሁሉና በሰ​ማ​ርያ የሚ​ኖሩ ያው​ቃሉ፤ በት​ዕ​ቢ​ትና በልብ ኵራ​ትም እን​ዲህ ይላሉ፦</verse>
				<verse number="10">“ጡቡ ወደቀ፤ ነገር ግን ኑ፥ ድን​ጋይ እን​ው​ቀር፤ ሾላው ነቀዘ፤ ነገር ግን ፅድን እን​ቍ​ረጥ፤ ለራ​ሳ​ች​ንም ግን​ብን እን​ሥራ።”</verse>
				<verse number="11">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ተራራ ላይ እር​ሱን በመ​ቃ​ወም የሚ​ነ​ሡ​ትን ይበ​ት​ና​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="12">ጠላ​ቶ​ቹን ሶር​ያ​ው​ያ​ን​ንም ከም​ሥ​ራቅ፥ አረ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ከም​ዕ​ራብ ያን​ቀ​ሳ​ቅ​ስ​በ​ታል፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም በተ​ከ​ፈተ አፍ ይበ​ሉ​ታል። በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="13">ሕዝቡ ግን እስ​ከ​ተ​ቀ​ሠፉ ድረስ አል​ተ​መ​ለ​ሱም፤ የሠ​ራ​ዊ​ት​ንም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ፈ​ለ​ጉም።</verse>
				<verse number="14">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራስ​ንና ጅራ​ትን፥ ታላ​ቁ​ንና ታና​ሹን በአ​ንድ ቀን ከእ​ስ​ራ​ኤል ይቈ​ር​ጣል።</verse>
				<verse number="15">ሽማ​ግ​ሌ​ውና ለፊት የሚ​ያ​ደ​ላው እርሱ ራስ ነው፤ ዐመ​ፅ​ንም የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር ነቢይ እርሱ ጅራት ነው።</verse>
				<verse number="16">ይህን ሕዝብ የሚ​ያ​መ​ሰ​ግኑ ያስ​ቱ​አ​ቸ​ዋል፤ ይበ​ሉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ ያስ​ቱ​አ​ቸ​ዋል፤</verse>
				<verse number="17">ሰው ሁሉ ክፉና በደ​ለኛ ነውና፥ አፍም ሁሉ ዐመ​ፅን ይና​ገ​ራ​ልና፥ ስለ​ዚህ ጌታ በጐ​ል​ማ​ሶ​ቻ​ቸው ደስ አይ​ለ​ውም፤ ለሙት ልጆ​ቻ​ቸ​ውና ለመ​በ​ለ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አይ​ራ​ራም። በዚህ ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="18">ኀጢ​አት እንደ እሳት ይነ​ድ​ዳል፤ እሳት እንደ በላ​ችው ደረቅ ሣር ይቃ​ጠ​ላል፤ እንደ ዱር ሣርም ይቃ​ጠ​ላል፤ በተ​ራ​ራ​ዎች ዙሪያ ያለው ሁሉ አብሮ ይቃ​ጠ​ላል።</verse>
				<verse number="19">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ምድር ሁሉ ትቃ​ጠ​ላ​ለች፤ ሕዝ​ቡም እሳት እን​ደ​ሚ​በ​ላው እን​ጨት ሆኖ​አል፤ ሰውም ለወ​ን​ድሙ አይ​ራ​ራም።</verse>
				<verse number="20">ነገር ግን ሰው ወደ ቀኙ ይመ​ለ​ሳል፤ ይራ​ባ​ልና፤ በግ​ራም በኩል ይበ​ላል፤ አይ​ጠ​ግ​ብ​ምም፤</verse>
				<verse number="21">እያ​ን​ዳ​ን​ዱም የክ​ን​ዱን ሥጋ ይበ​ላል፤ ምናሴ ኤፍ​ሬ​ምን፥ ኤፍ​ሬ​ምም ምና​ሴን ይበ​ላል፤ እነ​ርሱ በአ​ን​ድ​ነት የይ​ሁዳ ጠላ​ቶች ይሆ​ና​ሉና። በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">ክፉ​ንም ጽሕ​ፈት ለሚ​ጽፉ ወዮ​ላ​ቸው!</verse>
				<verse number="2">መበ​ለ​ቶች ቅሚ​ያ​ቸው እን​ዲ​ሆኑ፥ የሙት ልጆ​ች​ንም ብዝ​በ​ዛ​ቸው እን​ዲ​ያ​ደ​ርጉ፥ የድ​ሃ​ውን ፍርድ ያጣ​ምሙ ዘንድ፥ የች​ግ​ረ​ኛ​ው​ንም ሕዝ​ቤን ፍርድ ያጐ​ድሉ ዘንድ የግ​ፍን ትእ​ዛ​ዛት ለሚ​ያ​ዝዙ ወዮ​ላ​ቸው!</verse>
				<verse number="3">በተ​ጐ​በ​ኛ​ች​ሁ​በት ቀን፥ ምን ታደ​ርጉ ይሆን? መከራ ከሩቅ ይመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ልና፥ ለረ​ድ​ኤ​ትስ ወደ ማን ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="4">በሐ​ሣር እን​ዳ​ት​ወ​ድቁ፥ ክብ​ራ​ች​ሁን ወዴት ትተ​ዉ​ታ​ላ​ችሁ? በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="5">ለቍ​ጣዬ በትር ለሆኑ፥ ለመ​ዓ​ቴም ጨን​ገር በእ​ጃ​ቸው ላለ ለአ​ሦ​ራ​ው​ያን ወዮ​ላ​ቸው!</verse>
				<verse number="6">ቍጣ​ዬን በኀ​ጢ​አ​ተኛ ሕዝብ ላይ እል​ካ​ለሁ፤ ይማ​ር​ኳ​ቸ​ውና ይበ​ዘ​ብ​ዙ​አ​ቸው ዘንድ፥ ከተ​ሞ​ች​ንም ይረ​ግ​ጡ​አ​ቸ​ውና እንደ ትቢያ ያደ​ር​ጓ​ቸው ዘንድ ሕዝ​ቤን አዝ​ዛ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">እርሱ በልቡ እን​ዲህ አይ​መ​ስ​ለ​ውም፤ እን​ዲ​ህም አያ​ስ​ብም፤ ነገር ግን ማጥ​ፋት፥ ጥቂት ያይ​ደ​ሉ​ት​ንም አሕ​ዛብ መቍ​ረጥ በልቡ አለ።</verse>
				<verse number="8">“አንተ ብቻ​ህን አለቃ ነህን?” ቢሉ​ትም፥ የሔ​ማ​ትን መን​ደር ወሰ​ድሁ ይላል።</verse>
				<verse number="9">እንደ ሔማት አር​ፋድ፥ እንደ አር​ፋድ ሴፋ​ሩ​ሔም፥ እንደ ሴፋ​ሩ​ሔም ካሌና፥ እንደ ካሌ​ናም ደማ​ስቆ፥ እንደ ደማ​ስ​ቆም ሰማ​ርያ አይ​ደ​ለ​ች​ምን?</verse>
				<verse number="10">ይሁ​ዳ​ንም እን​ዲሁ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በሰ​ማ​ርያ የሚ​ያ​ድን ጣዖት አለን?</verse>
				<verse number="11">በሰ​ማ​ር​ያና በጣ​ዖ​ቶ​ች​ዋም እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ፥ እን​ዲሁ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በጣ​ዖ​ቶ​ችዋ አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">ስለ​ዚህ እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ጌታ ሥራ​ውን ሁሉ በጽ​ዮን ተራ​ራና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ በፈ​ጸመ ጊዜ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ የኵሩ ልብን ፍሬ፥ የዐ​ይ​ኑ​ንም ከፍታ ትም​ክ​ሕት ይቀ​ጣል።</verse>
				<verse number="13">እርሱ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በኀ​ይሌ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በማ​ስ​ተ​ዋል ጥበ​ቤም የአ​ሕ​ዛ​ብን ድን​በ​ሮች አር​ቃ​ለሁ፤ ሀብ​ታ​ቸ​ው​ንም እዘ​ር​ፋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="14">የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ው​ንም ከተ​ሞች አና​ው​ጣ​ለሁ። በእ​ጄም ዓለ​ምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰ​በ​ስ​ባ​ለሁ፤ እንደ ተተወ እን​ቍ​ላ​ልም እወ​ስ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከእ​ኔም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም፤ የሚ​ቃ​ወ​መ​ኝም የለም።</verse>
				<verse number="15">“በውኑ መጥ​ረ​ቢያ በሚ​ቈ​ር​ጥ​በት ሰው ላይ ይነ​ሣ​ልን? ወይስ መጋዝ በሚ​ስ​በው ሰው ላይ ይጓ​ደ​ዳ​ልን? ይህም ዘንግ በሚ​መ​ቱ​በት ላይ እንደ መነ​ሣት፥ በት​ርም ዕን​ጨት አይ​ደ​ለ​ሁም እንደ ማለት ነው።”</verse>
				<verse number="16">ስለ​ዚ​ህም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በክ​ብ​ርህ ላይ ውር​ደ​ትን፥ በጌ​ጥህ ላይም የሚ​ነ​ድና የሚ​ያ​ቃ​ጥል እሳ​ትን ይሰ​ድ​ዳል።</verse>
				<verse number="17">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ብር​ሃን እንደ እሳት ይሆ​ናል፤ በሚ​ነ​ድድ እሳ​ትም ይቀ​ድ​ሰ​ዋል፤ ዛፉ​ንም እንደ ሣር ያቃ​ጥ​ለ​ዋል።</verse>
				<verse number="18">ያን​ጊዜ ተራ​ሮ​ችና ኮረ​ብ​ቶች፥ ዛፎ​ችም ይጠ​ፋሉ። ነፍ​ስና ሥጋ​ንም ይበ​ላል፤ የሚ​ሸ​ሽም ከሚ​ነ​ድድ የእ​ሳት ነበ​ል​ባል እን​ደ​ሚ​ሸሽ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="19">የቀ​ሩ​ትም የዱር ዛፎች በቍ​ጥር ጥቂት ይሆ​ናሉ፤ ታናሽ ብላ​ቴ​ናም ይጽ​ፋ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="20">በዚ​ያም ጊዜ እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅሬታ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ቤት የዳ​ኑት ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በአ​ቈ​ሰ​ሉ​አ​ቸው ላይ አይ​ደ​ገ​ፉም፤ ነገር ግን በእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ በእ​ው​ነት ይደ​ገ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="21">የያ​ዕ​ቆ​ብም ቅሬታ በኀ​ያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ናሉ።</verse>
				<verse number="22">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕዝብ ቍጥር እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆን የቀ​ሩት ይድ​ናሉ።</verse>
				<verse number="23">የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያለ​ቀና የተ​ቈ​ረጠ ነገ​ርን በዓ​ለም ሁሉ በእ​ው​ነት ይፈ​ጽ​ማል።</verse>
				<verse number="24">ስለ​ዚህ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በጽ​ዮን የም​ት​ኖር ሕዝቤ ሆይ፥ ከአ​ሦር የተ​ነሣ አት​ፍራ፤ በበ​ትር ይመ​ቱ​ሃ​ልና፥ የግ​ብ​ፅ​ንም መን​ገድ ታይ ዘንድ መቅ​ሠ​ፍ​ቴን አመ​ጣ​ብ​ሃ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="25">ለጥ​ቂት ጊዜ ቍጣዬ ይበ​ር​ዳል፤ ነገር ግን መዓቴ በም​ክ​ራ​ቸው ላይ ይሆ​ናል።”</verse>
				<verse number="26">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምድ​ያ​ምን በመ​ከ​ራው ቦታ እንደ መታው ጅራ​ፍን ያነ​ሣ​በ​ታል፤ ቍጣ​ውም በባ​ሕሩ መን​ገ​ድና በግ​ብፅ መን​ገድ በኩል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="27">በዚ​ያም ቀን ቀን​በሩ ከጫ​ን​ቃህ፥ ፍር​ሀ​ቱም ከአ​ንተ ላይ ይወ​ር​ዳል፤ ቀን​በ​ሩም ከጫ​ን​ቃህ ወርዶ ይሰ​በ​ራል።</verse>
				<verse number="28">ወደ አን​ጋይ ከተማ ይመ​ጣል፤ በመ​ጌ​ዶን በኩል ያል​ፋል፤ በማ​ክ​ማ​ስም ውስጥ ዕቃ​ውን ያኖ​ራል፤</verse>
				<verse number="29">በቆላ ያል​ፋል፤ ወደ አን​ጋ​ይም በደ​ረሰ ጊዜ ሬማ​ትና የሳ​ኦል ከተማ ገባ​ዖን ይፈ​ራሉ፤</verse>
				<verse number="30">የጋ​ሊም ልጅ ትሸ​ሻ​ለች፤ ላይ​ሳም ትሰ​ማ​ለች፤ አና​ቶ​ትም ትሰ​ማ​ለች።</verse>
				<verse number="31">መደ​ቤ​ናና በጌ​ቤር የሚ​ኖሩ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="32">ዛሬ በእጁ እን​ዲ​ኖሩ በመ​ን​ገዱ ለምኑ፤ የጽ​ዮን ልጅ ተራ​ራ​ንና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ኮረ​ብ​ቶች አጽኑ።</verse>
				<verse number="33">እነሆ፥ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክቡ​ራ​ንን በኀ​ይል ያው​ካ​ቸ​ዋል፤ ታላ​ላ​ቆ​ች​ንም በሐ​ሣር ይቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋል፤ ከፍ ያሉ​ትም ይዋ​ረ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="34">ታላ​ላ​ቆ​ችም በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ሊባ​ኖ​ስም ከረ​ዣ​ዥም ዛፎች ጋር ይወ​ድ​ቃል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">ከእ​ሴይ ሥር በትር ትወ​ጣ​ለች፤ አበ​ባም ከግ​ንዱ ይወ​ጣል።</verse>
				<verse number="2">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ፥ የጥ​በ​ብና የማ​ስ​ተ​ዋል መን​ፈስ፥ የም​ክ​ርና የኀ​ይል መን​ፈስ፥ የዕ​ው​ቀ​ትና የእ​ው​ነት መን​ፈስ ያር​ፍ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የመ​ፍ​ራት መን​ፈስ ይሞ​ላ​በ​ታል፤ በፍ​ርድ አያ​ዳ​ላም፤ በነ​ገ​ርም አይ​ከ​ራ​ከ​ርም፤</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን ለድ​ሆች በጽ​ድቅ ይፈ​ር​ዳል፤ ለም​ድ​ርም የዋ​ሆች በቅ​ን​ነት ይበ​ይ​ናል፤ በአ​ፉም ቃል ምድ​ርን ይመ​ታል፤ በከ​ን​ፈ​ሩም እስ​ት​ን​ፋስ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ያጠ​ፋ​ዋል።</verse>
				<verse number="5">ወገ​ቡን በጽ​ድቅ ይታ​ጠ​ቃል፤ እው​ነ​ት​ንም በጎኑ ይጐ​ና​ጸ​ፋል።</verse>
				<verse number="6">ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይሰ​ማ​ራል፤ ነብ​ርም ከፍ​የል ጠቦት ጋር ይተ​ኛል፤ ጥጃና በሬ የአ​ን​በሳ ደቦ​ልም በአ​ን​ድ​ነት ይሰ​ማ​ራሉ፤ ታና​ሽም ልጅ ይመ​ራ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">ላምና ድብ አብ​ረው ይሰ​ማ​ራሉ፤ ግል​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም በአ​ን​ድ​ነት ያድ​ጋሉ፤ አን​በ​ሳም እንደ በሬ ገለባ ይበ​ላል።</verse>
				<verse number="8">የሚ​ጠ​ባ​ውም ሕፃን በእ​ባብ ጕድ​ጓ​ድና በእ​ፉ​ኝት ቤት ላይ እጁን ይጭ​ናል።</verse>
				<verse number="9">እነ​ር​ሱም አይ​ጐ​ዱ​ትም፤ በተ​ቀ​ደ​ሰው ተራ​ራዬ ሁሉ ላይ ማን​ንም አይ​ጐ​ዱም፤ አያ​ጠ​ፉ​ምም፤ ብዙ ውኃ ባሕ​ርን እን​ደ​ሚ​ሸ​ፍን ምድር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በማ​ወቅ ትሞ​ላ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="10">በዚ​ያም ቀን የእ​ሴይ ሥር ይቆ​ማል፤ የተ​ሾ​መ​ውም የአ​ሕ​ዛብ አለቃ ይሆ​ናል፤ አሕ​ዛ​ብም በእ​ርሱ ተስፋ ያደ​ር​ጋሉ፤ ማረ​ፊ​ያ​ውም የተ​ከ​በረ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="11">በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ከአ​ሦ​ርና ከግ​ብፅ፥ ከባ​ቢ​ሎ​ንና ከኢ​ት​ዮ​ጵያ፥ ከኤ​ላ​ሜ​ጤን፥ ከም​ሥ​ራ​ቅና ከም​ዕ​ራብ ለቀ​ሩት ለሕ​ዝቡ ቅሬታ ይቀና ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገና እጁን ይገ​ል​ጣል።</verse>
				<verse number="12">ለአ​ሕ​ዛ​ብም ምል​ክ​ትን ያቆ​ማል፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የቀ​ሩ​ትን ይሰ​በ​ስ​ባል፤ ከይ​ሁ​ዳም የተ​በ​ተ​ኑ​ትን ከአ​ራቱ የም​ድር ማዕ​ዘ​ኖች ያከ​ማ​ቻል።</verse>
				<verse number="13">የኤ​ፍ​ሬ​ምም ቅናት ይሻ​ራል፤ የይ​ሁ​ዳም ጠላ​ቶች ይጠ​ፋሉ፤ ኤፍ​ሬ​ምም በይ​ሁዳ አይ​ቀ​ናም፤ ይሁ​ዳም ኤፍ​ሬ​ምን አያ​ስ​ጨ​ን​ቅም።</verse>
				<verse number="14">በባ​ሕ​ርም በኩል በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መር​ከ​ቦች ላይ እየ​በ​ረሩ ይወ​ር​ዳሉ፤ የም​ሥ​ራቅ ሰዎ​ች​ንና ኤዶ​ም​ያ​ስን በአ​ን​ድ​ነት ይዘ​ር​ፋሉ፤ በሞ​ዓብ ላይ ቀድ​መው እጃ​ቸ​ውን ይዘ​ረ​ጋሉ፤ የአ​ሞ​ንም ልጆች ቀድ​መው ለእ​ነ​ርሱ ይታ​ዘ​ዛሉ።</verse>
				<verse number="15">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የግ​ብ​ፅን ባሕር ያደ​ር​ቃል፤ በኀ​ይ​ለ​ኛም ነፋስ እጁን በወ​ንዙ ላይ ያነ​ሣል፤ ሰባት ፈሳ​ሾ​ች​ንም ይመ​ታል፤ ሰዎ​ችም በጫ​ማ​ቸው እን​ዲ​ሻ​ገሩ ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="16">ከግ​ብ​ፅም በወጣ ጊዜ ለእ​ስ​ራ​ኤል እንደ ነበረ፥ በአ​ሦር ለቀ​ረው ለሕ​ዝቡ ጎዳና ይሆ​ናል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ትላ​ለህ፥ “አቤቱ፥ ተቈ​ጥ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፥ ቍጣ​ህ​ንም ከእኔ መል​ሰ​ሃ​ልና፥ ዳግ​መ​ኛም ይቅር ብለ​ኸ​ኛ​ልና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">እነሆ፥ አም​ላኬ መድ​ኀ​ኒቴ ነው፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ሬና ዝማ​ሬዬ ነው፤ መድ​ኀ​ኒ​ቴም ሆኖ​አ​ልና በእ​ርሱ ታም​ኜ​አ​ለሁ፤ አል​ፈ​ራ​ምም።”</verse>
				<verse number="3">ውኃ​ው​ንም ከሕ​ይ​ወት ምን​ጮች በደ​ስታ ትቀ​ዳ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="4">በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ትላ​ላ​ችሁ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤ ስሙ​ንም ጥሩ፤ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ክብ​ሩን አስ​ታ​ውቁ፤ ስሙ ከፍ ያለ እንደ ሆነ አስ​ታ​ውሱ።</verse>
				<verse number="5">ታላቅ ሥራ ሠር​ቶ​አ​ልና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ዘምሩ፤ ይህ​ንም በም​ድር ሁሉ ላይ አስ​ታ​ውቁ።</verse>
				<verse number="6">አንቺ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፤ ሐሤ​ትም አድ​ርጊ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ በመ​ካ​ከ​ልሽ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">የአ​ሞጽ ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ በባ​ቢ​ሎን ላይ ያየው ራእይ።</verse>
				<verse number="2">ምድረ በዳ በሆነ ተራራ ላይ ምል​ክ​ትን አቁሙ፤ ድም​ፃ​ች​ሁ​ንም ከፍ አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ አለ​ቆች በእጅ ጥቀሱ። በሮ​ች​ንም ክፈቱ።</verse>
				<verse number="3">እኔ አዝዤ ቅዱ​ሳ​ኔን አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ኀያ​ላ​ኔ​ንም አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ደስ እያ​ላ​ቸ​ውም ይመ​ጣሉ፤ ቍጣ​ዬ​ንም ይፈ​ጽ​ማሉ፤ ያዋ​ር​ዱ​አ​ቸ​ዋ​ልም።</verse>
				<verse number="4">በተ​ራ​ሮች ላይ እንደ ታላቅ ሕዝብ ድምፅ የሆነ የብዙ ሰው ድምፅ አለ። የተ​ሰ​በ​ሰቡ ነገ​ሥ​ታ​ትና የአ​ሕ​ዛብ ድም​ፅም አለ። የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተዋ​ጊ​ዎች አሕ​ዛብ ይመጡ ዘንድ አዘዘ።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና የቍ​ጣው ሠራ​ዊት ዓለ​ምን ያጠ​ፉ​አት ዘንድ ከሩቅ ሀገር ከሰ​ማይ ዳርቻ ይመ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="6">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ቀር​ቦ​አ​ልና አል​ቅሱ፤ ጥፋ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይመ​ጣል።</verse>
				<verse number="7">ስለ​ዚህ እጅ ሁሉ ትዝ​ላ​ለች፤ ሰውም ሁሉ ይደ​ነ​ግ​ጣል፤</verse>
				<verse number="8">ሽማ​ግ​ሎች ይደ​ነ​ግ​ጣሉ፤ እን​ደ​ም​ት​ወ​ልድ ሴትም ምጥ ይይ​ዛ​ቸ​ዋል፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ይገ​ዳ​ደ​ላሉ፤ ይደ​ነ​ቃሉ፤ ፊታ​ቸ​ውም እንደ እሳት ይን​በ​ለ​በ​ላል።</verse>
				<verse number="9">እነሆ፥ ምድ​ሪ​ቱን ባድማ ሊያ​ደ​ርግ፥ ኀጢ​አ​ተ​ኞ​ች​ዋ​ንም ከእ​ር​ስዋ ዘንድ ሊያ​ጠፋ በመ​ዓ​ትና በጽኑ ቍጣ ተሞ​ልቶ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ይመ​ጣል።</verse>
				<verse number="10">የሰ​ማ​ይም ከዋ​ክ​ብ​ትና ኦሪ​ዎን፥ የሰ​ማይ ሠራ​ዊ​ትም ሁሉ ብር​ሃ​ና​ቸ​ውን አይ​ሰ​ጡም፤ ፀሐ​ይም በወ​ጣች ጊዜ ትጨ​ል​ማ​ለች፤ ጨረ​ቃም በብ​ር​ሃኑ አያ​በ​ራም።</verse>
				<verse number="11">በዓ​ለም ሁሉ ላይ ክፋ​ትን አዝ​ዛ​ለሁ፤ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ች​ንም ኀጢ​አት እጐ​በ​ኛ​ለሁ፤ የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ች​ንም ኵራት እሽ​ራ​ለሁ፤ የጨ​ካ​ኞ​ቹ​ንም ኵራት አዋ​ር​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">የተ​ረ​ፉ​ትም ከጥሩ ወርቅ ይልቅ የከ​በሩ ይሆ​ናሉ፤ ሰውም ከሰ​ን​ፔር ዕንቍ ይልቅ የከ​በረ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="13">ስለ​ዚህ በሠ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓት በጽኑ ቍጣው ቀንም ሰማ​ያት ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ምድ​ርም ከመ​ሠ​ረቷ ትና​ወ​ጣ​ለች።</verse>
				<verse number="14">የተ​ረ​ፉ​ትም ሁሉ እንደ ተባ​ረረ ሚዳቋ፥ እንደ ባዘነ በግም ይሆ​ናሉ። የሚ​ሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ውም የለም፤ እን​ዲ​ሁም ሰው ሁሉ ወደ ወገኑ ይመ​ለ​ሳል፤ ሁሉም ሰው ወደ ሀገሩ ይሸ​ሻል።</verse>
				<verse number="15">የተ​በ​ተ​ኑት ሁሉ ይሞ​ታሉ፤ የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡ​ትም ሁሉ በጦር ይወ​ድ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="16">ሕፃ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም በፊ​ታ​ቸው ይጨ​ፈ​ጭ​ፋሉ፤ ቤቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይበ​ዘ​ብ​ዛሉ፤ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ያስ​ነ​ው​ራሉ።</verse>
				<verse number="17">እነሆ፥ ብር የማ​ይ​ሹ​ትን፥ ወር​ቅም የማ​ያ​ም​ራ​ቸ​ውን ሜዶ​ና​ው​ያ​ንን በእ​ና​ንተ ላይ አስ​ነ​ሣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="18">ፍላ​ጾ​ቻ​ቸ​ውም ጐበ​ዞ​ችን ይጨ​ፈ​ጭ​ፋሉ፤ ሕፃ​ኖ​ቻ​ች​ሁ​ንም አይ​ም​ሩም፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ለል​ጆ​ቻ​ችሁ አይ​ራ​ሩም።</verse>
				<verse number="19">የመ​ን​ግ​ሥ​ታት ክብር፥ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም የት​ዕ​ቢ​ታ​ቸው ትም​ክ​ሕት የሆ​ነች ባቢ​ሎ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገለ​በ​ጣ​ቸው እንደ ሰዶ​ምና እንደ ገሞራ ትሆ​ና​ለች።</verse>
				<verse number="20">ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባት አይ​ገ​ኝም፤ ከት​ው​ል​ድም እስከ ትው​ልድ ድረስ ሰው አይ​ኖ​ር​ባ​ትም፤ ዓረ​ባ​ው​ያ​ንም በእ​ርሷ አያ​ል​ፉም፤ እረ​ኞ​ችም በው​ስ​ጥዋ አያ​ር​ፉም።</verse>
				<verse number="21">በዚ​ያም የም​ድረ በዳ አራ​ዊት ያር​ፋሉ፤ ጕጕ​ቶ​ችም በቤ​ቶ​ቻ​ቸው ይሞ​ላሉ፤ ሰጎ​ኖ​ችም በዚያ ይኖ​ራሉ፤ በዚ​ያም አጋ​ን​ንት ይዘ​ፍ​ናሉ።</verse>
				<verse number="22">ተኵ​ላ​ዎ​ችም በዚያ ያድ​ራሉ፤ ቀበ​ሮ​ዎ​ችም በሚ​ያ​ማ​ምሩ አዳ​ራ​ሾ​ቻ​ቸው ይዋ​ለ​ዳሉ፤ ይህም ሁሉ ፈጥኖ ይሆ​ናል፤ አይ​ዘ​ገ​ይ​ምም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዕ​ቆ​ብን ይም​ረ​ዋል፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ደግሞ ይመ​ር​ጠ​ዋል፤ በሀ​ገ​ራ​ቸ​ውም ያር​ፋሉ፤ መጻ​ተ​ኞ​ችም ከእ​ነ​ርሱ ጋር አንድ ይሆ​ናሉ፤ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ቤት ጋር ይጨ​መ​ራሉ።</verse>
				<verse number="2">አሕ​ዛ​ብም ይዘው ወደ ስፍ​ራ​ቸው ያመ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወገ​ኖች ይካ​ፈ​ሏ​ቸ​ዋል፤ በዚ​ያም ሀገር ይበ​ዛሉ፤ በዚ​ያም ወን​ዶች ባሮ​ችና ሴቶች ባሮች ይሆ​ናሉ። ማር​ከው የወ​ሰ​ዷ​ቸ​ውም ለእ​ነ​ርሱ ምር​ኮ​ኞች ይሆ​ናሉ፤ የገ​ዙ​አ​ቸ​ውም ይገ​ዙ​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="3">በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከኀ​ዘ​ን​ህና ከመ​ከ​ራህ፥ ከተ​ገ​ዛ​ህ​ለ​ትም ከጽኑ ባር​ነት ያሳ​ር​ፍ​ሃል።</verse>
				<verse number="4">ይህ​ንም ሙሾ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ላይ ታነ​ሣ​ለህ፤ እን​ዲ​ህም ትላ​ለህ፥ “አስ​ጨ​ናቂ እን​ዴት ዐረፈ! አስ​ገ​ባ​ሪም እን​ዴት ጸጥ አለ!</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችን ቀን​በ​ርና የአ​ለ​ቆ​ችን ቀን​በር ሰብ​ሮ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት አሕ​ዛ​ብን ገር​ፎ​አ​ቸ​ዋ​ልና፥ ከቍ​ጣ​ውም መቅ​ሠ​ፍት አል​ራ​ራ​ላ​ቸ​ው​ምና።</verse>
				<verse number="7">ምድ​ርም ሁሉ ዐርፋ በጸ​ጥታ ተቀ​ም​ጣ​ለች፤ እል​ልም ብላ​ለች።</verse>
				<verse number="8">የሊ​ባ​ኖስ ዛፎች፦ አንተ ከተ​ዋ​ረ​ድህ ጀምሮ ማንም ይቈ​ር​ጠን ዘንድ አል​ወ​ጣ​ብ​ንም ብለው በአ​ንተ ደስ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">“ሲኦ​ልም በመ​ም​ጣ​ትህ ልት​ገ​ና​ኝህ በታች ታወ​ከች፤ የአ​ሕ​ዛ​ብን ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ከዙ​ፋ​ና​ቸው ያስ​ነሡ፥ ምድ​ርን የገ​ዙ​አት አር​በ​ኞች ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት በአ​ንተ ላይ ተነሡ።</verse>
				<verse number="10">እነ​ዚህ ሁሉ፦ አንተ ደግሞ እንደ እኛ ተይ​ዘ​ሃል፤ እንደ እኛም ተቈ​ጥ​ረ​ሃል።</verse>
				<verse number="11">ከክ​ብ​ርህ ወደ ሲኦል ወደ​ቅህ፤ በበ​ታ​ች​ህም ብል ተነ​ጥ​ፎ​አል፤ ትልም መደ​ረ​ቢ​ያህ ሆኖ​አል” ብለው ይመ​ል​ሱ​ል​ሃል።</verse>
				<verse number="12">“አንተ በን​ጋት የሚ​ወጣ የአ​ጥ​ቢያ ኮከብ ሆይ፥ እን​ዴት ከሰ​ማይ ወደ​ቅህ! ወደ አሕ​ዛ​ብም መል​እ​ክ​ትን የላ​ክህ አንተ ሆይ፥ እን​ዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀ​ጠ​ቀ​ጥህ!</verse>
				<verse number="13">አን​ተም በል​ብህ፦ ወደ ሰማይ ዐር​ጋ​ለሁ፤ ዙፋ​ኔ​ንም ከሰ​ማይ ከዋ​ክ​ብት በላይ ከፍ ከፍ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በሰ​ሜ​ንም ዳርቻ በረ​ዣ​ዥም ተራ​ሮች ላይ እቀ​መ​ጣ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="14">ከደ​መ​ና​ዎች ከፍታ በላይ ዐር​ጋ​ለሁ፤ በል​ዑ​ልም እመ​ሰ​ላ​ለሁ አልህ።</verse>
				<verse number="15">ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወ​ድ​ቃ​ለህ፤ ወደ ምድር ጥል​ቅም ትወ​ር​ዳ​ለህ።</verse>
				<verse number="16">የሚ​መ​ለ​ከ​ቱ​ህም ይደ​ነ​ቃሉ፤ እን​ዲ​ህም ይላሉ፦ በውኑ ምድ​ርን ያን​ቀ​ጠ​ቀጠ፥ መን​ግ​ሥ​ታ​ት​ንም ያና​ወጠ፥</verse>
				<verse number="17">ዓለ​ሙን ሁሉ ባድማ ያደ​ረገ፥ ከተ​ሞ​ች​ንም ያፈ​ረሰ፥ ምር​ኮ​ኞ​ቹ​ንም ወደ ቤታ​ቸው ያል​ሰ​ደደ ሰው ይህ ነውን?</verse>
				<verse number="18">“የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት ሁሉ በየ​ቤ​ታ​ቸው በክ​ብር አን​ቀ​ላ​ፍ​ተ​ዋል።</verse>
				<verse number="19">አንተ ግን በጦር ተወ​ግ​ተው ወደ መቃ​ብር ከሚ​ወ​ርዱ ብዙ ሙታን ጋር እንደ ረከሰ ሬሳ በተ​ራ​ሮች ላይ ትጣ​ላ​ለህ።</verse>
				<verse number="20">ንጹሕ እን​ዳ​ል​ሆ​ነና በደም እንደ ረከሰ ልብስ አን​ተም ንጹሕ አይ​ደ​ለ​ህም። ምድ​ሬን አጥ​ፍ​ተ​ሃ​ልና፥ ሕዝ​ቤ​ንም ገድ​ለ​ሃ​ልና ክፉ ዘር አንተ እን​ግ​ዲህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አት​ኖ​ርም።</verse>
				<verse number="21">እን​ዳ​ይ​ነ​ሡም፥ ምድ​ር​ንም እን​ዳ​ይ​ወ​ርሱ፥ የዓ​ለ​ሙ​ንም ፊት በጦ​ር​ነት እን​ዳ​ይ​ሞሉ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው በደል ይገ​ድ​ሉ​አ​ቸው ዘንድ ልጆ​ች​ህን አዘ​ጋጅ።”</verse>
				<verse number="22">“በእ​ነ​ርሱ ላይ እነ​ሣ​ለሁ” ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “ስም​ንና ቅሬ​ታን፥ ዘር​ንና ትው​ል​ድ​ንም አጠ​ፋ​ለሁ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="23">“ባቢ​ሎ​ንን የወ​ፎች መኖ​ሪያ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ እንደ ኢም​ን​ትም ትሆ​ና​ለች፤ በጥ​ፋ​ትም እንደ ረግ​ረግ ጭቃ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ” ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="24">የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ምሎ​አል፥ “እንደ ተና​ገ​ርሁ በእ​ር​ግጥ ይሆ​ናል፤ እንደ መከ​ር​ሁም እን​ዲሁ ይጸ​ናል።</verse>
				<verse number="25">አሦ​ርን በም​ድሬ ላይ እሰ​ብ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በተ​ራ​ራ​ዬም ላይ እረ​ግ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ ቀን​በ​ሩም ከእ​ነ​ርሱ ላይ ይነ​ሣል፤ ሸክ​ሙም ከጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ ይወ​ገ​ዳል።”</verse>
				<verse number="26">በም​ድር ሁሉ ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሰ​በው ዐሳብ ይህ ነው፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ የተ​ዘ​ረ​ጋች እጅ ይህች ናት።</verse>
				<verse number="27">ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን መክ​ሮ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምክር የሚ​መ​ልስ ማን ነው? የተ​ዘ​ረ​ጋች እጁ​ንስ የሚ​መ​ል​ሳት ማን ነው?</verse>
				<verse number="28">ንጉሡ አካዝ በሞ​ተ​በት ዓመት ይህ ነገር ሆነ።</verse>
				<verse number="29">ፍል​ስ​ጥ​ኤም ሆይ፥ ከእ​ባቡ ዘር እፉ​ኝት ይወ​ጣ​ልና፥ ፍሬ​ውም የሚ​በ​ር​ርና እሳት የሚ​መ​ስል እባብ ይሆ​ና​ልና፥ የኀ​ይ​ላ​ችሁ ቀን​በር ተሰ​ብ​ሮ​አ​ልና ሁላ​ች​ሁም ደስ አይ​በ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="30">ድሆ​ችም በው​ስ​ጣ​ችሁ ይሰ​ማ​ራሉ፤ ድሆች ሰዎ​ችም በሰ​ላም ያር​ፋሉ፤ ዘራ​ች​ሁ​ንም ረኃብ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፤ ከእ​ና​ን​ተም የቀ​ሩት ያል​ቃሉ።</verse>
				<verse number="31">እና​ንተ የከ​ተ​ሞች በሮች ሆይ፥ ወዮ በሉ፤ እና​ን​ተም ከተ​ሞች ሆይ፥ ደን​ግጡ፥ ጩኹም፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሆይ፥ ሁላ​ች​ሁም ቀል​ጣ​ች​ኋል፤ ጢስ ከሰ​ሜን ይወ​ጣ​ልና፥ እን​ግ​ዲ​ህም አት​ኖ​ሩ​ምና።</verse>
				<verse number="32">የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት ምን ይመ​ል​ሳሉ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዮ​ንን መሠ​ረ​ታት፤ ትሑ​ታን የሆ​ኑ​ት​ንም ሕዝብ አዳ​ና​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">ስለ ሞዓብ የተ​ነ​ገረ ቃል። ሞዓብ በሌ​ሊት ትጠ​ፋ​ለች፤ የሞ​ዓ​ብም ምሽግ በሌ​ሊት ይፈ​ር​ሳል።</verse>
				<verse number="2">ለራ​ሳ​ችሁ እዘኑ፤ ጣዖ​ታ​ች​ሁና መሠ​ዊ​ያ​ችሁ ያሉ​ባት ዲቦን ትጠ​ፋ​ለ​ችና፤ ወደ​ዚ​ያም ወጥ​ታ​ችሁ በሞ​ዓብ ናባው አል​ቅሱ፤ ወዮም በሉ፤ ራስ ሁሉ በራ ይሆ​ናል፤ ክን​ድም ሁሉ ይቈ​ረ​ጣል።</verse>
				<verse number="3">በየ​መ​ን​ገ​ድዋ ማቅ ታጠቁ፤ በየ​ሰ​ገ​ነ​ቶ​ች​ዋም አል​ቅሱ፤ በየ​አ​ደ​ባ​ባ​ዮ​ች​ዋም እን​ባን እጅግ እያ​ፈ​ሰ​ሳ​ችሁ ወዮ በሉ።</verse>
				<verse number="4">ሐሴ​ቦ​ንና ኤል​ያሊ ጮኹ፤ ድም​ፃ​ቸ​ውም እስከ ያሳ ድረስ ይሰ​ማል፤ ስለ​ዚህ የሞ​ዓብ ወገብ ይታ​መ​ማል።</verse>
				<verse number="5">ሞዓብ ራሷን ይዛ ትጮ​ኻ​ለች፤ ለል​ቧም ይረ​ዳ​ታል፤ እስከ ሴጎ​ርም ድረስ ብቻ​ዋን ታለ​ቅ​ሳ​ለች። ሞዓብ እንደ ሦስት ዓመት ጥጃ ናትና በሉ​ሒት ዐቀ​በት ትጮ​ኻ​ለች። በአ​ሮ​ሜ​ዎን መን​ገ​ድም ይመ​ለ​ሳሉ፤ ይጮ​ኻ​ሉም፥ ጥፋ​ትና መና​ወ​ጥም ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="6">የኔ​ም​ሬም ውኃ ይነ​ጥ​ፋል፤ ሣሯም ይደ​ር​ቃል፤ በው​ስ​ጧም ልም​ላሜ አይ​ገ​ኝም።</verse>
				<verse number="7">ስለ​ዚህ ሞዓብ ይድ​ና​ልን? ዐረ​ባ​ው​ያ​ንን ወደ ሸለ​ቆው አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፤ እነ​ር​ሱም ይወ​ስ​ዷ​ታል።</verse>
				<verse number="8">ጩኸት የሞ​ዓ​ብን ዳርቻ ሁሉ ዞረ፤ ልቅ​ሶ​ዋም ወደ ኤግ​ላ​ይ​ምና ወደ ኢሊም ጕድ​ጓድ ደረሰ።</verse>
				<verse number="9">የዲ​ሞ​ንም ውኃ ደም ተሞ​ል​ታ​ለች፤ በዲ​ሞን ላይ ዐረ​ባ​ው​ያ​ንን አመ​ጣ​ለ​ሁና፤ የሞ​ዓ​ብ​ንና የአ​ር​ያ​ልን ዘር፥ ከኤ​ዶ​ም​ያ​ስም የተ​ረ​ፉ​ትን ወስጄ እንደ አራ​ዊት በም​ድር ላይ እሰ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">የጽ​ዮን ሴት ልጅ ተራራ ምድረ በዳ አይ​ደ​ለ​ች​ምን?</verse>
				<verse number="2">ጫጩ​ቶ​ች​ዋን አሳ​ድጋ እንደ ተወች ወፍ ሆና​ለ​ችና፤ የሞ​ዓብ ሴት ልጅም እንደ ሰባ የበግ ጠቦት ሆነች።</verse>
				<verse number="3">አር​ኖ​ንም በም​ት​ኖ​ር​በት ምሽግ መጠ​ለ​ያን ትሠራ ዘንድ ብዙ ትመ​ክ​ራ​ለች፤ በቀ​ትር ጊዜ እንደ ሌሊት ደን​ግ​ጠው ይሸ​ሻሉ፤ ወደ እና​ን​ተም አታ​ስ​ገ​ቡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ከሚ​ከ​ቧ​ችሁ ጋር ጠላ​ቶች እን​ዳ​ይ​ሆ​ኗ​ችሁ ከሞ​ዓብ የተ​ሰ​ደ​ዱ​ትን ከእ​ና​ንተ ጋር አታ​ስ​ቀ​ምጡ፤ ሰል​ፈ​ኞች አል​ቀ​ዋ​ልና፤ በሀ​ገ​ሪቱ ሁሉ የነ​በ​ረ​ውም አለቃ ጠፍ​ቶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="5">ዙፋን በም​ሕ​ረት ይጸ​ናል፥ በዚ​ያም ላይ በዳ​ዊት ቤት ፍር​ድን የሚሻ ጽድ​ቅ​ንም የሚ​ያ​ፋ​ጥን ፈራጅ በእ​ው​ነት ይቀ​መ​ጣል፤ ይፈ​ር​ዳ​ልም።</verse>
				<verse number="6">የሞ​ዓ​ብን ትዕ​ቢ​ትና እጅግ መኵ​ራ​ቱን ሰም​ተ​ናል፤ ትዕ​ቢ​ቱ​ንም አስ​ወ​ገ​ድሁ፤ ጥን​ቈ​ላህ እን​ዲህ አይ​ደ​ለ​ምና፥ እን​ዲ​ህም አይ​ደ​ለም፤</verse>
				<verse number="7">ሞዓብ ዋይ በሉ፤ ሁሉም በሞ​ዓብ ዋይ ይላ​ሉና፤ በዴ​ሴት የሚ​ኖ​ሩም አያ​መ​ል​ጡም፤ ጠብን ያጭ​ራሉ፤ ያፍ​ራ​ሉም።</verse>
				<verse number="8">የሐ​ሴ​ቦን እር​ሻ​ዎ​ችና የሴ​ባማ ወይን ግን​ዶች አዝ​ነ​ዋል። የአ​ሕ​ዛብ አለ​ቆች የሰ​ባ​በ​ሩ​አ​ቸው ቅር​ን​ጫ​ፎች እስከ ኢያ​ዜር ደር​ሰው ወደ ምድረ በዳ ወጥ​ተው ነበር፤ ቍጥ​ቋ​ጦ​ቹም ተዘ​ር​ግ​ተው ባሕ​ርን ተሻ​ግ​ረው ነበር።</verse>
				<verse number="9">ስለ​ዚህ በኢ​ያ​ዜር ልቅሶ ስለ ሴባማ ወይን ግንድ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ፤ ሐሴ​ቦ​ንና ኤል​ያሊ ሆይ፥ ዛፎ​ችሽ ወድ​ቀ​ዋል፤ የዛ​ፍ​ሽን ፍሬና የወ​ይ​ን​ሽን መከር እረ​ግ​ጣ​ለሁ፤ ተክ​ሎ​ችሽ ሁሉ ይወ​ድ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="10">ደስ​ታና ሐሤ​ትም ከወ​ይን ቦታሽ ተወ​ስ​ዶ​አል፤ በወ​ይ​ን​ሽም ቦታ​ዎች ፈጽ​መው ደስ አይ​ላ​ቸ​ውም፤ በመ​ጥ​መ​ቂ​ያ​ውም ወይ​ንን አይ​ረ​ግ​ጡም፤ ረጋ​ጮ​ቹን አጥ​ፍ​ቻ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="11">ስለ​ዚህ ልቤ ስለ ሞዓብ እንደ መሰ​ንቆ ትጮ​ኻ​ለች። አጥ​ን​ቶ​ችም እንደ ተመ​ረገ ግድ​ግዳ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="12">ለኀ​ፍ​ረት ይሆ​ን​ብ​ሃል፤ ሞዓብ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዎ​ችዋ ደክ​ማ​ለ​ችና፤ ለጸ​ሎ​ትም ወደ ጣዖ​ቶ​ችዋ ትሄ​ዳ​ለች፤ ሊያ​ድ​ኑ​አ​ትም አይ​ች​ሉም።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሞ​ዓብ ላይ በድሮ ዘመን የተ​ና​ገ​ረው ነገር ይህ ነው።</verse>
				<verse number="14">አሁ​ንም እን​ዲህ እላ​ለሁ፤ በሦ​ስት ዓመት ውስጥ እንደ ምን​ደኛ ዓመት የሞ​ዓብ ክብር ከብዙ ሀብ​ትዋ ጋር ይዋ​ረ​ዳል፤ በቍ​ጥ​ርም ጥቂት ይቀ​ራል፤ ክብ​ር​ዋም አይ​ገ​ኝም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">ስለ ደማ​ስቆ የተ​ነ​ገረ ቃል። “እነሆ፥ ደማ​ስቆ ከከ​ተ​ሞች መካ​ከል ተለ​ይታ ትጠ​ፋ​ለች፤ ትፈ​ር​ሳ​ለ​ችም።</verse>
				<verse number="2">ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​ፈ​ታች ትሆ​ና​ለች፤ ለመ​ንጋ ማሰ​ማ​ር​ያም ትሆ​ና​ለች፤ የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዳ​ቸ​ውም የለም።</verse>
				<verse number="3">ኤፍ​ሬም የሚ​ጠ​ጋ​በት ምሽግ አይ​ኖ​ርም፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ ንጉሥ በደ​ማ​ስቆ አይ​ነ​ግ​ሥም። የሶ​ርያ ቅሬታ ሆይ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከክ​ብ​ራ​ቸው የም​ት​ሻል አይ​ደ​ለ​ህም” ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="4">“በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ የያ​ዕ​ቆብ ክብር ይደ​ክ​ማል፤ የሚ​በዛ የክ​ብሩ ብል​ጽ​ግ​ናም ይነ​ዋ​ወ​ጣል።</verse>
				<verse number="5">አጫጅ የቆ​መ​ውን እህል ሰብ​ስቦ ዛላ​ውን እን​ደ​ሚ​ያ​ጭድ ይሆ​ናል፤ በሸ​ለቆ እሸ​ትን እን​ደ​ሚ​ሰ​በ​ስ​ብም እን​ዲሁ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="6">ወይራ በተ​መታ ጊዜ ሁለት ወይም ሦስት ፍሬ በራሱ ላይ እን​ደ​ሚ​ቀር፥ አራት ወይም አም​ስት በዛ​ፊቱ ጫፍ እን​ደ​ሚ​ገኝ፥ በእ​ርሱ ዘንድ ቃር​ሚያ ይቀ​ራል” ይላል የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="7">በዚ​ያም ቀን ሰው በፈ​ጣ​ሪው ይታ​መ​ናል፤ ዐይ​ኖ​ቹም ወደ እስ​ራ​ኤል ቅዱስ ያያሉ።</verse>
				<verse number="8">በጣ​ዖ​ታ​ቸ​ውና ጣቶ​ቻ​ቸው በሠ​ሩ​አ​ቸው የእ​ጃ​ቸው ሥራ​ዎች አይ​ተ​ማ​መ​ኑም፤ ለር​ኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውም ዛፎ​ችን አይ​ቈ​ር​ጡም።</verse>
				<verse number="9">በዚ​ያም ቀን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት የአ​ሞ​ራ​ው​ያ​ንና የኤ​ዌ​ዎ​ያ​ው​ያን ከተ​ሞች እንደ ተፈቱ፥ እን​ዲሁ ከተ​ሞ​ችህ ይፈ​ታሉ፤ ባድ​ማም ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="10">አዳ​ኝህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተ​ኸ​ዋ​ልና፥ ረዳ​ትህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አላ​ስ​ብ​ኸ​ውም፤ ስለ​ዚህ የሐ​ሰ​ትን ተክል ተክ​ለ​ሃል፤ የሐ​ሣ​ር​ንም ዘር ዘር​ተ​ሃል።</verse>
				<verse number="11">ተክ​ልን በተ​ከ​ል​ህ​በት ቀን ትበ​ድ​ላ​ለህ፤ የዘ​ራ​ኸ​ውም በበ​ነ​ጋው በም​ታ​ወ​ር​ስ​በት ቀን ይበ​ቅ​ላል፤ አባ​ትም ለልጁ እን​ደ​ሚ​ያ​ወ​ርስ አን​ተም ለል​ጆ​ችህ ታወ​ር​ሳ​ለህ።</verse>
				<verse number="12">እንደ ውኃ ለሞሉ፥ ከተ​ራራ በመ​ከ​ታ​ተል እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ የውኃ ፈሳሽ ለሆ​ኑም ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ ወዮ​ላ​ቸው!</verse>
				<verse number="13">ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ እንደ ብዙ ውኃ ናቸው፤ ከፏ​ፏቴ ውስጥ በኀ​ይል እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ እንደ ብዙ ውኃ ፈሳሽ ይጮ​ኻሉ፤ ያጠ​ፉ​ታ​ልም፤ እነ​ር​ሱም ከሩቅ ይወ​ር​ዳሉ፤ በተ​ራ​ራም ላይ እን​ዳለ እብቅ፥ በነ​ፋስ ፊት ዐውሎ ነፋስ እን​ደ​ሚ​ያ​ዞ​ረው እንደ መን​ኰ​ራ​ኵር ትቢ​ያም ይበ​ተ​ናሉ።</verse>
				<verse number="14">በመ​ሸም ጊዜ ሳይ​ነጋ ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ያን​ጊ​ዜም የይ​ሁዳ ወገ​ኖች “ይህ የወ​ራ​ሾች ርስት ነው፤ የበ​ዘ​በ​ዙ​ንም ዕድል ፋንታ ይህ ነው” ይላሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">በኢ​ት​ዮ​ጵያ ወን​ዞች ማዶ ላለች፥ ክንፍ ያላ​ቸው መር​ከ​ቦች ላሉ​ባት ምድር ወዮ​ላት!</verse>
				<verse number="2">መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን በባ​ሕር ላይ፥ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ች​ንም በውኃ ላይ ይል​ካል። ፈጣ​ኖች መል​እ​ክ​ተ​ኞች ወደ ረዥ​ምና ወደ ባዕድ፥ ወደ ክፉም ሕዝብ ይሄ​ዳ​ሉና፤ ተስፋ የቈ​ረ​ጡና የተ​ረ​ገጡ ሕዝብ እነ​ማን ናቸው? ዛሬ ግን የም​ድር ወን​ዞች ሁሉ፥ ሰዎች እን​ደ​ሚ​ኖ​ሩ​ባት ሀገር ይኖ​ራሉ።</verse>
				<verse number="3">በየ​ሀ​ገ​ራ​ቸው ይቀ​መ​ጣሉ፤ ከተ​ራ​ሮች ራሶ​ችም እንደ ዓላማ ይይ​ዙ​ታል፤ እንደ መለ​ከት ድም​ፅም ይሰ​ማል።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “እንደ ቀትር ብር​ሃን፥ በአ​ጨ​ዳም ወራት እንደ ጠል ደመና በማ​ደ​ሪ​ያዬ ጸጥታ ይሆ​ናል” ብሎ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="5">እርሱ ከመ​ከር በፊት አበባ በረ​ገፈ ጊዜ የወ​ይ​ንም ፍሬ ጨርቋ ሲይዝ የወ​ይ​ኑን ቀጫ​ጭን ዘንግ በማ​ጭድ ይቈ​ር​ጣል፤ ጫፎ​ቹ​ንም ይመ​ለ​ም​ላል፤ ያስ​ወ​ግ​ድ​ማል።</verse>
				<verse number="6">ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አው​ሬ​ዎ​ችም በአ​ን​ድ​ነት ይቀ​ራሉ፤ የሰ​ማይ ወፎ​ችና የም​ድር አው​ሬ​ዎ​ችም ሁሉ ይሰ​በ​ሰ​ቡ​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">በዚያ ዘመን ለሠ​ራ​ዊት ጌታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከተ​ዋ​ረ​ደና ከደ​ከመ ሕዝብ፥ ከዛሬ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ታላቅ ከሆነ ወገን፥ ተስፋ ከሚ​ያ​ደ​ር​ግና ከሚ​ረ​ገጥ፥ በሀ​ገሩ ወንዝ ዳር ከሚ​ኖር ሕዝብ ዘንድ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም በተ​ጠ​ራ​በት በደ​ብረ ጽዮን እጅ መንሻ ይቀ​ር​ባል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">ስለ ግብፅ የተ​ነ​ገረ ራእይ። እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ጣን ደመና ተቀ​ምጦ ወደ ግብፅ ይመ​ጣል፤ የግ​ብ​ፅም የእ​ጆ​ቻ​ቸው ሥራ​ዎች በፊቱ ይዋ​ረ​ዳሉ፤ የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ልብ በው​ስ​ጣ​ቸው ይቀ​ል​ጣል።</verse>
				<verse number="2">“ግብ​ፃ​ው​ያን በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ይነ​ሣሉ፤ ወን​ድ​ምም ወን​ድ​ሙን፥ ሰውም ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ይገ​ድ​ላል፤ ከተ​ማም ከተ​ማን፥ መን​ግ​ሥ​ትም መን​ግ​ሥ​ትን ይወ​ጋል።</verse>
				<verse number="3">የግ​ብ​ፅም መን​ፈስ በው​ስ​ጣ​ቸው ትደ​ነ​ግ​ጣ​ለች፤ ምክ​ራ​ቸ​ውን አጠ​ፋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ ድም​ፃ​ቸ​ውን ዝቅ አድ​ር​ገው የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይጠ​ይ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="4">ግብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም በጨ​ካኝ ጌቶች እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ጨካ​ኞች ነገ​ሥ​ታ​ትም ይገ​ዟ​ቸ​ዋል” ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="5">ግብ​ፃ​ው​ያን ከባ​ሕር ውኃን ይጠ​ጣሉ፤ ወን​ዙም ያን​ሳል፤ ደረ​ቅም ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="6">ወን​ዞ​ችም ይነ​ጥ​ፋሉ። ቦዮ​ችና መስ​ኖች ያን​ሳሉ፤ ይደ​ር​ቃ​ሉም፤ ደን​ገ​ልና ቄጤማ ይጠ​ወ​ል​ጋሉ።</verse>
				<verse number="7">በዓ​ባይ ወንዝ ዳር ያለው መስክ፥ በዓ​ባ​ይም ወንዝ አጠ​ገብ የተ​ዘራ እርሻ ሁሉ በነ​ፋስ ይመ​ታል፤ ይደ​ር​ቃ​ልም፤</verse>
				<verse number="8">ዓሣ አጥ​ማ​ጆቹ ያዝ​ናሉ፤ በዓ​ባ​ይም ወንዝ መቃ​ጥን የሚ​ጥ​ሉት ሁሉ ያለ​ቅ​ሳሉ፤ በው​ኆ​ችም ላይ መረብ የሚ​ዘ​ረ​ጉት ያለ​ቅ​ሳሉ።</verse>
				<verse number="9">የተ​ቈ​ራ​ረ​ጠ​ው​ንም መረብ የሚ​ጠ​ግኑ፥ ነጩ​ንም ልብስ የሚ​ሠሩ ሸማ​ኔ​ዎች ያፍ​ራሉ።</verse>
				<verse number="10">በእ​ነ​ር​ሱም የሚ​ሠሩ ይሠ​ቃ​ያሉ፤ በሐር ኩብ የሚ​ነ​ግዱ ሁሉ ይቀ​ል​ጣሉ፤ ልቡ​ና​ቸ​ውም ያዝ​ናል።</verse>
				<verse number="11">የጣ​ኔ​ዎስ አለ​ቆች ሰነ​ፎች ይሆ​ናሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ትን የሚ​መ​ክሩ ጥበ​በ​ኞ​ችም ምክ​ራ​ቸው ስን​ፍና ትሆ​ና​ለች። ንጉ​ሥን፥ “እኛ የጥ​በ​በ​ኞች ልጆች፥ የቀ​ደሙ ነገ​ሥ​ታ​ትም ልጆች ነን እን​ዴት ትሉ​ታ​ላ​ችሁ?”</verse>
				<verse number="12">አሁን ጥበ​በ​ኞ​ችህ የት አሉ? አሁን ያብ​ስ​ሩህ፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብፅ ላይ ያሰ​በ​ውን እስኪ ይን​ገ​ሩህ።</verse>
				<verse number="13">የጣ​ኔ​ዎስ አለ​ቆች አለቁ፤ የሜ​ም​ፎ​ስም አለ​ቆች ከፍ ከፍ አሉ፤ ግብ​ፃ​ው​ያን በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ተሳ​ሳቱ።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ስት መን​ፈ​ስን ልኮ​ባ​ቸ​ዋ​ልና፤ ሰካ​ርም፥ ደም ያዞ​ረ​ውም እን​ዲ​ስት እን​ዲሁ ግብ​ፃ​ው​ያን በሥ​ራ​ቸው ሁሉ ሳቱ።</verse>
				<verse number="15">ለግ​ብ​ፃ​ው​ያን ራስ ወይም ጅራት፥ መጀ​መ​ሪያ ወይም መጨ​ረሻ ያለው ሥራ የላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="16">በዚ​ያም ቀን የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ያ​ወ​ር​ድ​ባ​ቸው ፍር​ሀ​ትና መን​ቀ​ጥ​ቀጥ የተ​ነሣ ግብ​ፃ​ው​ያን እንደ ሴቶች ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="17">የይ​ሁ​ዳም ምድር ግብ​ፅን የም​ታ​ስ​ደ​ነ​ግጥ ትሆ​ና​ለች፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከመ​ከ​ረ​ባት ምክር የተ​ነሣ ስም​ዋን የሚ​ሰማ ሁሉ ይፈ​ራል።</verse>
				<verse number="18">በዚያ ቀን አም​ስት የግ​ብፅ ከተ​ሞች በከ​ነ​ዓን ቋንቋ ይና​ገ​ራሉ፤ በሠ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም ይጠሩ ዘንድ ከተ​ሞች አንድ ይሆ​ናሉ፤ ከእ​ነ​ዚ​ህም አን​ዲቱ የጽ​ድቅ ከተማ ተብላ ትጠ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="19">በዚያ ቀን በግ​ብፅ ምድር መካ​ከል አን​ዲቱ ከተማ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ትሆ​ና​ለች፤ በዳ​ር​ቻ​ዋም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ዐ​ምድ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="20">ይህም ለሠ​ራ​ዊት ጌታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብፅ ምድር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ምል​ክት ይሆ​ናል፤ ከሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቋ​ቸው የተ​ነሣ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጮ​ኻ​ሉና፥ እር​ሱም የሚ​ያ​ድ​ና​ቸ​ውን ሰው ይል​ክ​ላ​ቸ​ዋል፤ ይፈ​ር​ዳል፤ ያድ​ና​ቸ​ዋ​ልም።</verse>
				<verse number="21">በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብፅ የታ​ወቀ ይሆ​ናል፤ በዚ​ያም ጊዜ ግብ​ፃ​ው​ያን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያው​ቃሉ፤ መሥ​ዋ​ዕ​ትም ያቀ​ር​ቡ​ለ​ታል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስእ​ለት ይሳ​ላሉ፤ መባ​ኡ​ንም ያገ​ባሉ።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብ​ፅን በታ​ላቅ መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ታ​ታል፤ ይፈ​ው​ሳ​ታ​ልም፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ለ​ሳሉ፤ እር​ሱም ይሰ​ማ​ቸ​ዋል፤ ይፈ​ው​ሳ​ቸ​ው​ማል።</verse>
				<verse number="23">በዚ​ያም ወራት ከግ​ብፅ ወደ አሦር መን​ገድ ይሆ​ናል፤ አሦ​ራ​ዊ​ውም ወደ ግብፅ፥ ግብ​ፃ​ዊ​ውም ወደ አሦር ይገ​ባል፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ለአ​ሦ​ራ​ው​ያን ይገ​ዛሉ።</verse>
				<verse number="24">በዚ​ያም ወራት እስ​ራ​ኤል ለግ​ብ​ፅና ለአ​ሦር ሦስ​ተኛ ይሆ​ናል፤ በም​ድ​ርም መካ​ከል በረ​ከት ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="25">የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “በግ​ብፅ ውስጥ ያለ ሕዝቤ፥ በአ​ሦር መካ​ከ​ልም ያለ ሕዝቤ፥ ርስ​ቴም እስ​ራ​ኤል የተ​ባ​ረከ ይሁን” ብሎ ይባ​ር​ካ​ቸ​ዋ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">የአ​ሦር ንጉሥ አርና ጣን​ታ​ንን በሰ​ደደ ጊዜ፥ እር​ሱም ወደ አዛ​ጦን በመጣ ጊዜ፥ አዛ​ጦ​ን​ንም ወግቶ በያ​ዛት ጊዜ፥</verse>
				<verse number="2">በዚያ ዓመት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ሞ​ጽን ልጅ ኢሳ​ይ​ያ​ስን፥ “ሂድ፥ ማቅ​ህን ከወ​ገ​ብህ አውጣ፤ ጫማ​ህ​ንም ከእ​ግ​ርህ አው​ልቅ፤ ያለ​ጫ​ማም በባዶ እግ​ርህ ሂድ” ብሎ ተና​ገ​ረው። እን​ዲ​ህም አደ​ረገ፤ ራቁ​ቱ​ንም ያለ ጫማ ሄደ።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “ባሪ​ያዬ ኢሳ​ይ​ያስ ሦስት ዓመት ራቁ​ቱን በባዶ እግሩ እንደ ሄደ፥ እን​ዲሁ በግ​ብ​ፅና በኢ​ት​ዮ​ጵያ ላይ ሦስት ዓመት ምል​ክ​ትና ተአ​ም​ራት ይደ​ረ​ጋል።</verse>
				<verse number="4">እን​ዲሁ የአ​ሦር ንጉሥ የግ​ብ​ፅ​ንና የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያን ምርኮ፥ ጐበ​ዛ​ዝ​ቱ​ንና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹን ራቁ​ታ​ቸ​ው​ንና ባዶ እግ​ራ​ቸ​ውን አድ​ርጎ፥ ገላ​ቸ​ው​ንም ገልጦ ለግ​ብፅ ኀፍ​ረት ይነ​ዳ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="5">ግብ​ፃ​ው​ያን ከኢ​ት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያን ጋር ይሸ​ነ​ፋሉ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ከታ​መ​ኑ​ባ​ቸው ጋር ይፈ​ራሉ፤ ያፍ​ሩ​ማል።</verse>
				<verse number="6">በዚ​ያም ቀን በዚች ደሴት የሚ​ቀ​መጡ፦ እነሆ፥ ለር​ዳታ ወደ እነ​ርሱ የሸ​ሸ​ን​በት ተስ​ፋ​ችን ይህ ነበረ፤ ከአ​ሦር ንጉሥ ራሳ​ቸ​ውን ያላ​ዳኑ እኛን እን​ዴት ያድ​ኑ​ናል?” ይላሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">ስለ ምድረ በዳ የተ​ነ​ገረ ቃል፤ ዐውሎ ነፋስ በም​ድረ በዳ እን​ደ​ሚ​ያ​ልፍ፥ እን​ዲሁ ከሚ​ያ​ስ​ፈራ ሀገር ከም​ድረ በዳ ይመ​ጣል።</verse>
				<verse number="2">ከባድ ራእይ ተነ​ገ​ረኝ፤ ወን​ጀ​ለ​ኛው ይወ​ነ​ጅ​ላል፤ በደ​ለ​ኛ​ውም ይበ​ድ​ላል። የኤ​ላም ሰዎ​ችና የሜ​ዶን መል​እ​ክ​ተኛ በእኔ ላይ ይመ​ጣሉ። ዛሬ ግን እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ እረ​ጋ​ጋ​ለ​ሁም።</verse>
				<verse number="3">ስለ​ዚ​ህም ወገቤ ሕማም ተሞላ፤ እን​ደ​ም​ት​ወ​ልድ ሴትም ምጥ ያዘኝ፤ ከሕ​ማሜ የተ​ነሣ አል​ሰ​ማም፤ ከድ​ን​ጋ​ጤም የተ​ነሣ አላ​ይም።</verse>
				<verse number="4">ልቤ ሳተ፤ ኀጢ​አ​ቴም አሰ​ጠ​መኝ፤ ሰው​ነ​ቴም ደነ​ገ​ጠ​ብኝ።</verse>
				<verse number="5">ማዕ​ዱን አዘ​ጋጁ፤ ብሉ፤ ጠጡ፤ እና​ንተ አለ​ቆች ሆይ፥ ተነሡ፤ ጋሻ​ው​ንም አዘ​ጋጁ።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ​ኛ​ልና፥ “ፈጥ​ነህ ሂድ፤ ጕበ​ኛ​ንም አቁም፤ የሚ​ያ​የ​ው​ንም ይና​ገር፤ የሚ​ሰ​ማ​ው​ንም ያውራ።</verse>
				<verse number="7">ሁለት ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ሲጋ​ልቡ አየሁ፤ አንዱ በአ​ህያ ላይ፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም በግ​መል ላይ ተቀ​ምጦ ነበር፤ ድም​ፃ​ቸው ግን እንደ ብዙ​ዎች ፈረ​ሰ​ኞች ድምፅ ነበረ።”</verse>
				<verse number="8">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጕበኛ ኦር​ያስ ተጠራ፤ እር​ሱም፥ “እነሆ እኔ አለሁ፤ መላ መዓ​ል​ቱ​ንና መላ ሌሊ​ቱን በማማ ላይ ቆሜ አለሁ።</verse>
				<verse number="9">እነ​ሆም፥ በፈ​ረ​ሶች የሚ​ቀ​መጡ፥ ሁለት ሁለት ሆነው የሚ​ሄዱ ፈረ​ሰ​ኞች ይመ​ጣሉ” ብሎ ጮኸ፤ እር​ሱም መልሶ፥ “ባቢ​ሎን ወደ​ቀች! ወደ​ቀች! ጣዖ​ቶ​ች​ዋም ሁሉ፥ የእ​ጆ​ች​ዋም ሥራ​ዎች ሁሉ በም​ድር ላይ ተጥ​ለው ደቀቁ” አለ።</verse>
				<verse number="10">እና​ንተ የተ​ረ​ፋ​ች​ሁና መከራ የም​ት​ቀ​በሉ ሆይ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የነ​ገ​ረ​ኝ​ንና የሰ​ማ​ሁ​ትን ስሙ።</verse>
				<verse number="11">ስለ ኤዶ​ም​ያስ የተ​ነ​ገረ ነገር። አንዱ ከሴ​ይር፥ “ጕበኛ ሆይ፥ ሌሊቱ ምን ያህል ነው? ጕበኛ ሆይ፥ ሌሊቱ ምን ያህል ነው?” ብሎ ጠራኝ።</verse>
				<verse number="12">ጕበ​ኛ​ውም፥ “ይነ​ጋል፤ ደግ​ሞም ይመ​ሻል፤ ትጠ​ይቁ ዘንድ ብት​ወ​ድዱ ጠይቁ፤ ተመ​ል​ሳ​ች​ሁም ኑ፥” አለ።</verse>
				<verse number="13">ሌሊ​ትም በዲ​ዳ​ና​ው​ያን ጎዳና በዛ​ፎች ውስጥ ታድ​ራ​ለህ፤</verse>
				<verse number="14">በቴ​ማን የም​ት​ኖሩ ሆይ፥ ወደ ተጠ​ሙት ሰዎች ውኃ አምጡ፤</verse>
				<verse number="15">እን​ጀራ ይዛ​ችሁ ከሰ​ልፍ ከሸሹ ከብዙ ሰዎ​ችና በጦር ከጠፉ ከብዙ ሰዎች፥ ፍላጻ ከያዙ ከብዙ ሰዎ​ችና ጦር ከያዙ ከብዙ ሰዎች፥ ቀስ​ቶ​ቻ​ቸው ከተ​ሳ​ቡና በሰ​ልፍ ከወ​ደቁ ከብዙ ሰዎች ያመ​ለ​ጡ​ትን ተቀ​በ​ሏ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገና እን​ዲህ ብሎ​ኛ​ልና፥ “እንደ ምን​ደኛ ዓመት በአ​ንድ ዓመት ውስጥ የቄ​ዳር ልጆች ክብር ሁሉ ይጠ​ፋል፤</verse>
				<verse number="17">ከቀ​ስ​ተ​ኞች ቍጥር የቀ​ሩት፥ የቄ​ዳር ልጆች ኀያ​ላን፥ ያን​ሳሉ፤” የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">ስለ ጽዮን ሸለቆ የተ​ነ​ገረ ቃል። እና​ንተ ሁላ​ችሁ፥ ዛሬ ወደ ሰገ​ነት በከ​ንቱ መው​ጣ​ታ​ችሁ ምን ሆና​ች​ኋል?</verse>
				<verse number="2">ጩኸ​ትና ፍጅ​ትም የተ​ሞ​ላ​ብሽ ከተማ ሆይ፥ ቍስ​ለ​ኞ​ችሽ በሰ​ይፍ የቈ​ሰሉ አይ​ደ​ሉም፤ በአ​ንቺ ውስጥ የተ​ገ​ደ​ሉ​ትም በሰ​ልፍ የተ​ገ​ደሉ አይ​ደ​ሉም።</verse>
				<verse number="3">ነገር ግን አለ​ቆ​ችሽ ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ሸሹ፤ የተ​ማ​ረ​ኩ​ት​ንም በእ​ግር ብረት አሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸው፤ ኀይ​ለ​ኞ​ች​ሽም ርቀው ሸሹ።</verse>
				<verse number="4">ስለ​ዚህ፥ “ተዉኝ እኔ መራራ ልቅሶ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋ​ትም ታጽ​ና​ኑኝ ዘንድ አት​ድ​ከሙ፥” አልሁ።</verse>
				<verse number="5">ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሁ​ከ​ትና የጥ​ፋት፥ የመ​ረ​ገ​ጥና የስ​ብ​ራ​ትም ቀን በጽ​ዮን ሸለቆ ውስጥ ሆኖ​አል። ታና​ሹና ታላ​ቁም ሸሽ​ተው በተ​ራራ ላይ ይቅ​በ​ዘ​በ​ዛሉ።</verse>
				<verse number="6">የኤ​ላ​ምም ሰዎች አፎ​ታ​ቸ​ውን ተሸ​ከሙ፤ በፈ​ረስ የተ​ቀ​መ​ጡና አር​በ​ኞች ሰዎች፥ የአ​ር​በ​ኞ​ችም ሠራ​ዊት ነበሩ።</verse>
				<verse number="7">መል​ካ​ሞ​ቹን ሸለ​ቆ​ች​ሽ​ንም ሰረ​ገ​ሎች ሞሉ​ባ​ቸው፤ ፈረ​ሰ​ኞ​ችም መቆ​ሚ​ያ​ቸ​ውን በበ​ሮ​ችሽ ላይ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="8">የይ​ሁ​ዳ​ንም በሮች ይከ​ፍ​ታሉ፤ በዚ​ያም ቀን የከ​ተ​ማ​ይ​ቱን መኳ​ን​ንት ቤቶች ይበ​ረ​ብ​ራሉ። የዳ​ዊት ቤት መዛ​ግ​ብ​ት​ንም ይከ​ፍ​ታሉ።</verse>
				<verse number="9">የዳ​ዊ​ትም ከተማ ፍራ​ሾች እን​ደ​በዙ አይ​ታ​ች​ኋል፤ የታ​ች​ኛ​ው​ንም ኵሬ ውኃ በከ​ተማ አከ​ማ​ች​ታ​ች​ኋል፤</verse>
				<verse number="10">የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቤቶች ቈጠ​ራ​ችሁ፤ ቅጥ​ሩ​ንም ለማ​ጽ​ናት ቤቶ​ችን አፈ​ረ​ሳ​ችሁ።</verse>
				<verse number="11">በአ​ሮ​ጌው ኵሬ ላለው ውኃ በሁ​ለቱ ቅጥር መካ​ከል መከ​ማቻ ሠራ​ችሁ፤ ይህን ያደ​ረ​ገ​ውን ግን አል​ተ​መ​ለ​ከ​ታ​ች​ሁም፤ ቀድሞ የሠ​ራ​ው​ንም አላ​ያ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="12">በዚ​ያም ቀን የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቅ​ሶ​ንና ዋይ​ታን፥ ራስን መን​ጨ​ት​ንና ማቅን መል​በ​ስን ጠራ።</verse>
				<verse number="13">እነ​ሆም፥ በዓ​ልን፥ ደስ​ታ​ንና ሐሴ​ትን አደ​ረ​ጋ​ችሁ፤ በሬ​ዎ​ች​ንና በጎ​ች​ንም አረ​ዳ​ችሁ፤ “ነገ እን​ሞ​ታ​ለን፤ እን​ብላ፤ እን​ጠ​ጣም፤” እያ​ላ​ችሁ ሥጋን በላ​ችሁ፤ ወይ​ን​ንም ጠጣ​ችሁ።</verse>
				<verse number="14">ይህም ነገር በሠ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጆሮ ተሰማ፥ “እስ​ክ​ት​ሞቱ ድረስ ይህ በደል በእ​ው​ነት አይ​ሰ​ረ​ይ​ላ​ች​ሁም” ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="15">የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አለኝ፥ “ወደ ገን​ዘብ ጠባ​ቂው ወደ ሳም​ናስ ሂድ እን​ዲ​ህም በለው፦</verse>
				<verse number="16">መቃ​ብር በዚያ ያስ​ወ​ቀ​ርህ፥ ከፍ ባለው ስፍራ መቃ​ብር ያሠ​ራህ፥ በድ​ን​ጋ​ይም ውስጥ ለራ​ስህ መኖ​ርያ ያሳ​ነ​ጽህ ወደ​ዚህ ለምን መጣህ? ለም​ንስ በዚህ ተደ​ፋ​ፈ​ርህ?</verse>
				<verse number="17">እነሆ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኀ​ይል ወር​ውሮ ይጥ​ል​ሃል፤ ያጠ​ፋ​ሃ​ልም፤ ልብ​ስ​ህ​ንና የክ​ብር አክ​ሊ​ል​ህ​ንም ይገ​ፍ​ሃል፤</verse>
				<verse number="18">ወደ መከራ ሀገር ይጥ​ል​ሃል፤ በዚ​ያም ትሞ​ታ​ለህ፤ ያማረ ሰረ​ገ​ላ​ህ​ንም ያጐ​ሰ​ቍ​ለ​ዋል፤ የአ​ለ​ቃ​ህም ቤት ይረ​ገ​ጣል።</verse>
				<verse number="19">ከአ​ዛ​ዥ​ነት ሥራ​ህና ከሥ​ል​ጣ​ንህ ትሻ​ራ​ለህ።</verse>
				<verse number="20">በዚ​ያም ቀን ባሪ​ያ​ዬን የኬ​ል​ቅ​ዩን ልጅ ኤል​ያ​ቄ​ምን እጠ​ራ​ዋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="21">መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ህ​ንም አለ​ብ​ሰ​ዋ​ለሁ፤ አክ​ሊ​ል​ህ​ንም እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ ሹመ​ት​ህ​ንም በእጁ አሳ​ልፌ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ለሚ​ኖ​ሩና በይ​ሁ​ዳም ለሚ​ኖሩ አባት ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="22">የዳ​ዊ​ት​ንም ክብር እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ ይገ​ዛል፤ በአ​ገ​ዛ​ዝም የሚ​በ​ል​ጠው የለም። የዳ​ዊ​ት​ንም ቤት መክ​ፈቻ በጫ​ን​ቃው ላይ አኖ​ራ​ለሁ፤ እር​ሱም ይከ​ፍ​ታል፤ የሚ​ዘ​ጋም የለም፤ እር​ሱም ይዘ​ጋል የሚ​ከ​ፍ​ትም የለም።</verse>
				<verse number="23">በታ​መነ ስፍራ እንደ ችን​ካር እተ​ክ​ለ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ባ​ቱም ቤት የክ​ብር ዙፋን አስ​ቀ​ም​ጠ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="24">የአ​ባ​ቱ​ንም ቤት ክብር ሁሉ፥ ልጆ​ቹ​ንም፥ የልጅ ልጆ​ቹ​ንም፥ ከጽዋ ዕቃ ጀምሮ እስከ ማድጋ ዕቃ ድረስ፥ ታና​ና​ሹ​ንና ታላ​ላ​ቁን ሁሉ ይሰ​ቅ​ሉ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="25">በዚያ ቀን፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ በታ​መ​ነው ስፍራ የተ​ተ​ከ​ለው ችን​ካር ይወ​ል​ቃል፤ ተሰ​ብ​ሮም ይወ​ድ​ቃል፤ በእ​ር​ሱም ላይ የተ​ሰ​ቀ​ለው ሸክም ይጠ​ፋል፤” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="23">
				<verse number="1">ስለ ጢሮስ የተ​ነ​ገረ ትን​ቢት። የኬ​ል​ቀ​ዶን መር​ከ​ቦች ሆይ፥ አል​ቅሱ፤ ጠፍ​ተ​ዋ​ልና፤ እን​ግ​ዲ​ህም ከኬ​ጤ​ዎን ሀገር አይ​መ​ጡ​ምና ማር​ከ​ውም ይወ​ስ​ዱ​አ​ቸ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="2">በደ​ሴት የሚ​ኖሩ በባ​ሕር የሚ​ሻ​ገሩ የፊ​ኒቄ ስደ​ተ​ኞች ምን ይመ​ስ​ላሉ?</verse>
				<verse number="3">የገቡ ስደ​ተ​ኞች አሕ​ዛብ በመ​ከር ጊዜ እን​ደ​ሚ​ለ​ወጥ ዘር ናቸው።</verse>
				<verse number="4">ሲዶና ሆይ፥ ባሕር፥ የባ​ሕር ምሽግ፥ “አላ​ማ​ጥ​ሁም፥ አል​ወ​ለ​ድ​ሁም፤ ጐበ​ዛ​ዝ​ት​ንም አላ​ሳ​ደ​ግ​ሁም፥ ደና​ግ​ል​ንም አላ​ሳ​ደ​ግ​ሁም” ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና እፈሪ።</verse>
				<verse number="5">ወሬዋ ወደ ግብፅ በደ​ረሰ ጊዜ ስለ ጢሮስ ምጥ ይይ​ዛ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">ወደ ኬል​ቄ​ዶን ተሻ​ገሩ፤ እና​ንተ በደ​ሴት የም​ት​ኖሩ፥ አል​ቅሱ።</verse>
				<verse number="7">ተማ​ር​ካ​ችሁ ሂዱ እንጂ ይህች ዕረ​ፍት የእ​ና​ንተ አይ​ደ​ለ​ችም።</verse>
				<verse number="8">በጢ​ሮስ ላይ ይህን የመ​ከረ ማን ነው? እር​ስዋ ከሁሉ የም​ት​ሻ​ልና የም​ት​በ​ልጥ አይ​ደ​ለ​ች​ምን? ነጋ​ዴ​ዎ​ችዋ የከ​በሩ የም​ድር አለ​ቆች ናቸው።</verse>
				<verse number="9">የክ​ቡ​ራ​ንን ትዕ​ቢት ይሽር ዘንድ፥ የም​ድ​ር​ንም ክቡ​ራን ሁሉ ያዋ​ርድ ዘንድ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወስ​ኖ​ታል።</verse>
				<verse number="10">ምድ​ር​ህን እረስ፤ እን​ግ​ዲህ መር​ከ​ቦች ከኬ​ል​ቀ​ዶን አይ​መ​ጡ​ምና።</verse>
				<verse number="11">ነገ​ሥ​ታ​ቱን ያበ​ሳ​ጨ​ቻ​ቸው የባ​ሕር ሰዎች እጃ​ቸው ትደ​ክ​ማ​ለች፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የከ​ነ​ዓ​ንን ኀይል ያጠፉ ዘንድ አዘዘ።</verse>
				<verse number="12">እር​ሱም፥ “አንቺ የተ​በ​ደ​ልሽ የሲ​ዶና ድን​ግል ልጅ ሆይ፥ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ደስ አይ​በ​ልሽ፤ ተነ​ሥ​ተሽ ወደ ኪቲም ተሻ​ገሪ፤ በዚ​ያም ደግሞ አታ​ር​ፊም” አለ።</verse>
				<verse number="13">እነሆ፥ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ሀገር አሦ​ራ​ው​ያን አጥ​ፍ​ተ​ዋ​ታ​ልና፤ ግን​ብ​ዋም ወድ​ቆ​አል፤</verse>
				<verse number="14">እና​ንተ የኬ​ል​ቀ​ዶን መር​ከ​ቦች ሆይ፥ ምሽ​ጋ​ችሁ ፈር​ሶ​አ​ልና ዋይ በሉ።</verse>
				<verse number="15">በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ጢሮስ እንደ አንድ ንጉሥ ዘመን ወይም እንደ አንድ ሰው ዘመን ሰባ ዓመት ያህል የተ​ረ​ሳች ትሆ​ና​ለች፤ ከሰባ ዓመት በኋላ ግን ለጢ​ሮስ በጋ​ለ​ሞታ ዘፈን እን​ደ​ሚ​ሆን እን​ዲሁ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="16">አንቺ የተ​ረ​ሳሽ ጋለ​ሞታ ሆይ፥ መሰ​ንቆ ያዢ፤ በከ​ተማ ላይም ዙሪ፤ መታ​ሰ​ቢ​ያም ይሆ​ን​ልሽ ዘንድ ዜማን አሳ​ምሪ፤ ዘፈ​ን​ሽ​ንም አብዢ።</verse>
				<verse number="17">ከሰባ ዓመ​ትም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጢሮ​ስን በይ​ቅ​ርታ ይጐ​በ​ኛ​ታል፤ ወደ ጥን​ቷም ትመ​ለ​ሳ​ለች፤ ደግ​ሞም ለዓ​ለም መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ መና​ገ​ሻና መና​ገጃ ትሆ​ና​ለች።</verse>
				<verse number="18">ንግ​ድ​ዋና ዋጋዋ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ይሆ​ናል፤ ንግ​ድ​ዋም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለሚ​ኖሩ ለመ​ብ​ላ​ትና ለመ​ጠ​ጣት፥ ለመ​ጥ​ገ​ብም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ለመ​ታ​ሰ​ቢያ ይሆ​ናል እንጂ ለእ​ነ​ርሱ አይ​ሰ​በ​ሰ​ብም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="24">
				<verse number="1">እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዓለ​ምን ያጠ​ፋ​ታል፤ ባድ​ማም ያደ​ር​ጋ​ታል፤ ይገ​ለ​ብ​ጣ​ት​ማል፤ በእ​ር​ስ​ዋም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ይበ​ት​ናል።</verse>
				<verse number="2">ሕዝቡ እንደ ካህኑ፥ ባሪ​ያ​ውም እንደ ጌታው ባሪ​ያ​ይ​ቱም እንደ እመ​ቤቷ፥ የሚ​ሸ​ጠ​ውም እን​ደ​ሚ​ገ​ዛው፥ ተበ​ዳ​ሪ​ውም እንደ አበ​ዳ​ሪው፥ ዕዳ ከፋ​ዩም እንደ ዕዳ አስ​ከ​ፋዩ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="3">እነሆ፥ ምድር መፈ​ታ​ትን ትፈ​ታ​ለች፤ ፈጽ​ማም ትበ​ረ​በ​ራ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ እን​ዲህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="4">ምድ​ርም አለ​ቀ​ሰች፤ ጠፋ​ችም፤ ዓለም ተገ​ለ​በ​ጠች፤ የም​ድ​ርም ታላ​ላ​ቆች አለ​ቀሱ።</verse>
				<verse number="5">ምድ​ርም በሚ​ቀ​መ​ጡ​ባት ሰዎች ምክ​ን​ያት በደ​ለች፤ ሕጉን ተላ​ል​ፈ​ዋ​ልና፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ለው​ጠ​ዋ​ልና፥ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙ​ንም ቃል ኪዳን አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="6">ስለ​ዚህ ምድር ትው​ጣ​ቸ​ዋ​ለች፤ በእ​ር​ስዋ የተ​ቀ​መጡ በድ​ለ​ዋ​ልና፤ በም​ድር የሚ​ኖሩ ሰዎ​ችም ይቸ​ገ​ራሉ፤ ጥቂት ሰዎ​ችም ይቀ​ራሉ።</verse>
				<verse number="7">የወ​ይን ጠጅ አለ​ቀ​ሰች፤ የወ​ይን ግንድ ደከ​መች፤ ልባ​ቸው ደስ ያለው ሁሉ ተከዙ።</verse>
				<verse number="8">የከ​በ​ሮ​አ​ቸው ደስታ አል​ቆ​አል፤ መታ​ጀ​ራ​ቸ​ውም አል​ቃ​ለች፤ የኃ​ጥ​ኣን ሀብት አል​ቆ​አል፤ የመ​ሰ​ንቆ ድም​ፅም ቀር​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="9">ወይ​ንን የሚ​ጠ​ጡት አፈሩ፤ የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥም ለሚ​ጠ​ጡት መራራ ሆነ።</verse>
				<verse number="10">ከተ​ሞች ሁሉ ምድረ በዳ ሆኑ፤ ቤቶ​ችም ሁሉ ማንም እን​ዳ​ይ​ገ​ባ​ባ​ቸው ተዘጉ።</verse>
				<verse number="11">ስለ ወይ​ኑም ጠጅ በአ​ደ​ባ​ባይ አል​ቅሱ፤ የም​ድር ደስታ ሁሉ ጨል​ሞ​አ​ልና፥ የም​ድ​ርም ሐሤት ፈል​ሶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="12">ከተ​ሞ​ችም ባድማ ይሆ​ናሉ፤ ቤቶ​ችም ባዶ ሆነው ይቀ​ራሉ፤ ይጠ​ፋ​ሉም።</verse>
				<verse number="13">ይህ ሁሉ በሀ​ገር ውስጥ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይሆ​ናል። የወ​ይራ ፍሬ ለቀማ ባለቀ ጊዜ በቃ​ር​ሚ​ያው ውስጥ የወ​ይራ ፍሬ እን​ደ​ሚ​ለ​ቀም እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ይቃ​ር​ሟ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="14">እነ​ዚህ ድም​ፃ​ቸ​ውን ያነ​ሣሉ፤ በም​ድር የቀ​ሩ​ትም ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር በአ​ን​ድ​ነት ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ የባ​ሕ​ርም ውኃ ይና​ወ​ጣል።</verse>
				<verse number="15">ስለ​ዚ​ህም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር በባ​ሕር ደሴ​ቶች ይሆ​ናል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም ይከ​ብ​ራል።</verse>
				<verse number="16">የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ የጻ​ድ​ቁን ድንቅ ተስፋ ከም​ድር ዳርቻ ሰም​ተ​ናል። እነ​ርሱ ግን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ለሚ​ያ​ፈ​ርሱ ወን​ጀ​ለ​ኞች ወዮ​ላ​ቸው!” አሉ።</verse>
				<verse number="17">በም​ድር ላይ በሚ​ኖሩ፥ ፍር​ሀ​ትና ገደል ወጥ​መ​ድም አሉ።</verse>
				<verse number="18">የሰ​ማይ መስ​ኮ​ቶ​ችም ተከ​ፍ​ተ​ዋ​ልና፥ የም​ድ​ርም መሠ​ረት ተና​ው​ጣ​ለ​ችና ከፍ​ር​ሀት ድምፅ የሸሸ በገ​ደል ይወ​ድ​ቃል፤ ከገ​ደ​ልም የወጣ በወ​ጥ​መድ ይያ​ዛል።</verse>
				<verse number="19">ምድር ደነ​ገ​ጠች፤ ታወ​ከ​ችም፤ ምድር ጐሰ​ቈ​ለች፤ ተነ​ዋ​ወ​ጠ​ችም።</verse>
				<verse number="20">ምድር በወ​ይን እንደ ሰከረ ሰው ትን​ገ​ዳ​ገ​ዳ​ለች፤ እንደ ዳስም ትወ​ዛ​ወ​ዛ​ለች፤ ሕግን መተ​ላ​ለ​ፍ​ዋም ይከ​ብ​ድ​ባ​ታል፤ ትወ​ድ​ቅ​ማ​ለች፤ ደግ​ማም አት​ነ​ሣም።</verse>
				<verse number="21">በዚ​ያም ቀን እን​ደ​ዚህ ይሆ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማይ ሠራ​ዊ​ትና በም​ድር ነገ​ሥ​ታት ላይ እጁን ይጥ​ላል።</verse>
				<verse number="22">እነ​ር​ሱም ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ተዘ​ግ​ቶ​ባ​ቸ​ውም በግ​ዞት ቤት ይኖ​ራሉ፤ ከብዙ ትው​ል​ድም በኋላ ይጐ​በ​ኛሉ።</verse>
				<verse number="23">ጣራ​ቸው ይፈ​ር​ሳል፤ ግድ​ግ​ዳ​ቸ​ውም ይወ​ድ​ቃል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ተራ​ራና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ይነ​ግ​ሣ​ልና፥ በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹም ፊት ይከ​ብ​ራ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="25">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኬ፥ ድንቅ ነገ​ርን የዱሮ እው​ነ​ተኛ ምክ​ርን አድ​ር​ገ​ሃ​ልና አከ​ብ​ር​ሃ​ለሁ፤ ስም​ህ​ንም አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">ከተ​ሞ​ችን ትቢያ አደ​ረ​ግህ፤ የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞ​ችን፥ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም መሠ​ረት አፈ​ረ​ስህ፤ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ሠ​ሩም።</verse>
				<verse number="3">ስለ​ዚህ ድሆች ወገ​ኖች ያከ​ብ​ሩ​ሃል፤ የተ​ገፉ ሰዎች ከተ​ሞ​ችም ያከ​ብ​ሩ​ሃል።</verse>
				<verse number="4">ለተ​ዋ​ረዱ ሰዎች ከተ​ሞች ረዳት ሆነ​ሃ​ልና፥ በች​ግ​ራ​ቸው የተ​ጨ​ነ​ቁ​ትን በደ​ስታ ጋረ​ድ​ሃ​ቸው፤ ከክ​ፉ​ዎች ሰዎ​ችም አዳ​ን​ሃ​ቸው፤ ለተ​ጠ​ሙት ጥላ ሆን​ሃ​ቸው፤ ለተ​ገ​ፉ​ትም ሕይ​ወት ሆን​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">ለእ​ነ​ርሱ አሳ​ል​ፈህ ከሰ​ጠ​ኸን ከኃ​ጥ​ኣን ሰዎች የተ​ነሣ በጽ​ዮን እንደ ተጠሙ አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን እን​ዳጡ ሰዎች ሆነ​ናል።</verse>
				<verse number="6">የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሕ​ዝቡ ሁሉ ግብ​ዣን ያደ​ር​ጋል፤ በዚህ ተራራ ላይ ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋሉ፤ የወ​ይን ጠጅ​ንም ይጠ​ጣሉ፤ ዘይ​ት​ንም ይቀ​ባሉ።</verse>
				<verse number="7">በዚ​ህም ተራራ ላይ ይህን ሁሉ ለአ​ሕ​ዛብ ሰጠ፤ ምክሩ ለአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ናትና።</verse>
				<verse number="8">ሞት ሰዎ​ችን ዋጠ፤ በረ​ታም፤ እንደ ገናም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊት ሁሉ እን​ባን ያብ​ሳል፤ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ስድብ ከም​ድር ሁሉ ላይ ያስ​ወ​ግ​ዳል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአፉ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="9">በዚ​ያም ቀን፥ “እነሆ፥ አም​ላ​ካ​ችን ይህ ነው፤ ተስፋ አድ​ር​ገ​ነ​ዋል፤ ያድ​ና​ልም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ ነው፤ ጠብ​ቀ​ነ​ዋል፤ በመ​ዳ​ና​ች​ንም ደስ ይለ​ናል፤ ሐሤ​ትም እና​ደ​ር​ጋ​ለን” ይላሉ።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ተራራ ላይ ዕረ​ፍ​ትን ይሰ​ጠ​ናል፤ እህ​ልም በመ​ን​ኰ​ራ​ኵር ጭድም በጭቃ እን​ደ​ሚ​በ​ራይ እን​ዲሁ ሞዓብ ይረ​ገ​ጣል።</verse>
				<verse number="11">እርሱ ክፉ እንደ አደ​ረ​ገና እንደ አጠፋ በእ​ርሱ ላይ እጁን ያነ​ሣል፤ በእ​ር​ሱም ላይ እጁን ያነ​ሣው ስድ​ብን ይሽ​ራል።</verse>
				<verse number="12">የተ​መ​ሸ​ገ​ው​ንና ከፍ ከፍ ያለ​ው​ንም ቅጥ​ር​ህን ዝቅ ያደ​ር​ገ​ዋል። ያዋ​ር​ደ​ው​ማል፤ ወደ መሬ​ትም እስከ አፈር ድረስ ይጥ​ለ​ዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="26">
				<verse number="1">በዚ​ያም ቀን ይህን ቅኔ በይ​ሁዳ ምድር ይዘ​ም​ራሉ፤ እነ​ሆም፥ የጸ​ና​ችና የም​ታ​ድን፥ ቅጥ​ር​ንና ምሽ​ግ​ንም የም​ታ​ደ​ርግ ከተማ አለ​ችን።</verse>
				<verse number="2">ፍት​ሕን የሚ​ጠ​ብ​ቅና ጽድ​ቅን የሚ​ያ​ደ​ርግ ሕዝብ ይገባ ዘንድ በሮ​ችን ክፈቱ።</verse>
				<verse number="3">በአ​ንተ ላይ ታም​ና​ለ​ችና በአ​ንተ የም​ት​ደ​ገፍ ነፍ​ስን ፈጽ​መህ በሰ​ላም ትጠ​ብ​ቃ​ታ​ለህ።</verse>
				<verse number="4">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዘ​ለ​ዓ​ለም አንባ ነውና ለዘ​ለ​ዓ​ለም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኑ።</verse>
				<verse number="5">በከ​ፍታ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሰዎች ዝቅ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ የተ​መ​ሸ​ጉ​ት​ንም ከተ​ሞች ትጥ​ላ​ለህ፤ እስከ ምድ​ርም ድረስ ታወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="6">የየ​ዋ​ሃ​ንና የት​ሑ​ታን እግ​ሮች ይረ​ግ​ጡ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">የጻ​ድ​ቃን መን​ገድ የቀና ትሆ​ና​ለች፤ የቅ​ኖ​ችም መን​ገድ ትጠ​ረ​ጋ​ለች።</verse>
				<verse number="8">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገድ የቀና ነው፤ በቅ​ዱስ ስሙም ታመን፤ ነፍ​ሳ​ችን የተ​መ​ኘ​ች​ው​ንም አገ​ኘን።</verse>
				<verse number="9">አቤቱ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ ትእ​ዛ​ዝህ በም​ድር ላይ ብር​ሃን ነውና ነፍሴ በሌ​ሊት ወደ አንተ ትገ​ሠ​ግ​ሣ​ለች። በም​ድር የም​ት​ኖ​ሩም ጽድቅ መሥ​ራ​ትን ተማሩ።</verse>
				<verse number="10">በም​ድር ጽድ​ቅን የማ​ይ​ማ​ርና መል​ካ​ምን የማ​ያ​ደ​ርግ ኃጥእ አል​ቆ​አ​ልና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር እን​ዳ​ያይ ኀጢ​አ​ተ​ኛን ያስ​ወ​ግ​ዱ​ታል።</verse>
				<verse number="11">አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክን​ድ​ህን አላ​ወ​ቁም፤ ካወቁ ግን ያፍ​ራሉ። አላ​ዋ​ቆች ሰዎ​ችን ቅን​አት ያዛ​ቸው፤ አሁ​ንም እሳት ጠላ​ቶ​ችን ትበ​ላ​ለች።</verse>
				<verse number="12">አቤቱ፥ አም​ላ​ካ​ችን ሁሉን ሰጥ​ተ​ኸ​ና​ልና ሰላ​ምን ስጠን።</verse>
				<verse number="13">አቤቱ፥ አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ አንተ ግዛን፤ ከአ​ንተ በቀር ሌላ አና​ው​ቅ​ምና፤ ስም​ህ​ንም እን​ጠ​ራ​ለን።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን ሙታን ሕይ​ወ​ትን አያ​ዩ​አ​ትም፤ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶ​ችም አያ​ስ​ነ​ሡም፤ ስለ​ዚ​ህም አንተ አም​ጥ​ተ​ሃ​ቸ​ዋል፤ አጥ​ፍ​ተ​ሃ​ቸ​ው​ማል፤ ወን​ዶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አስ​ወ​ግ​ደ​ሃል።</verse>
				<verse number="15">አቤቱ፥ ክፋ​ትን ጨም​ር​ባ​ቸው፤ ለም​ድር ክቡ​ራን ክፋ​ትን ጨም​ር​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">አቤቱ፥ በመ​ከ​ራዬ ጊዜ አሰ​ብ​ኹህ፤ በጥ​ቂት መከ​ራም ገሠ​ጽ​ኸኝ።</verse>
				<verse number="17">የፀ​ነ​ሰች ሴት ለመ​ው​ለድ ስት​ቀ​ርብ እን​ደ​ም​ት​ጨ​ነ​ቅና በምጥ እን​ደ​ም​ት​ጮህ፥ አቤቱ፥ እን​ዲሁ በፊ​ትህ ለወ​ዳ​ጅህ ሆነ​ናል።</verse>
				<verse number="18">አን​ተን በመ​ፍ​ራት አቤቱ፥ እኛ ፀን​ሰ​ናል፤ ምጥም ይዞ​ናል፤ በም​ድ​ርም የማ​ዳ​ን​ህን መን​ፈስ ወለ​ድን፤ በዓ​ለ​ምም የሚ​ኖሩ ይወ​ድ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="19">ሙታን ይነ​ሣሉ፤ በመ​ቃ​ብር ያሉም ይድ​ናሉ። በም​ድ​ርም የሚ​ኖሩ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ከአ​ንተ የሚ​ገኝ ጠል መድ​ኀ​ኒ​ታ​ቸው ነውና፤ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም ምድር ታጠ​ፋ​ለህ።</verse>
				<verse number="20">ሕዝቤ ሆይ፥ ና፤ ወደ ቤት​ህም ግባ፤ ደጅ​ህን በኋ​ላህ ዝጋ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ እስ​ኪ​ያ​ልፍ ድረስ ጥቂት ጊዜ ተሸ​ሸግ።</verse>
				<verse number="21">እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር በሚ​ኖ​ሩት ላይ ከመ​ቅ​ደሱ መቅ​ሠ​ፍ​ቱን ያመ​ጣል፤ ምድ​ርም ደም​ዋን ትገ​ል​ጣ​ለች፤ ሙታ​ኖ​ች​ዋ​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አት​ከ​ድ​ንም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="27">
				<verse number="1">በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ጣኑ እባብ ደራ​ጎን ላይ፥ በክ​ፉ​ውም እባብ ደራ​ጎን ላይ ልዩ፥ ታላ​ቅና ብርቱ ሰይ​ፍን ያመ​ጣል። በባ​ሕ​ርም ውስጥ ያለ​ውን ዘንዶ ይገ​ድ​ለ​ዋል።</verse>
				<verse number="2">በዚ​ያም ቀን ለተ​ወ​ደ​ደው የወ​ይን ቦታ ተቀ​ኙ​ለት።</verse>
				<verse number="3">እኔ የጸ​ናች ከተማ ነኝ፤ አን​ድ​ዋን ከተማ ይወ​ጋሉ። በከ​ንቱ አጠ​ጣ​ኋት፤ በሌ​ሊት ትጠ​መ​ዳ​ለች፤ በቀ​ንም ግድ​ግ​ዳዋ ይወ​ድ​ቃል፤ የሚ​ያ​ነ​ሣ​ትም የለም።</verse>
				<verse number="4">ስለ ጠቡ በእ​ሳት አቃ​ጥ​ለው ዘንድ ቀር​ቃ​ሃና ሣርን ማን በሰ​ጠኝ! አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ዛሬ አደ​ረገ፤ እነ​ርሱ ተቃ​ጥ​ለ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="5">በው​ስጧ የሚ​ኖሩ ይጮ​ሃሉ፤ ከእ​ርሱ ጋር ሰላ​ምን እና​ድ​ርግ፤ ከእ​ርሱ ጋር ሰላ​ምን እና​ድ​ርግ።</verse>
				<verse number="6">በሚ​መ​ጣው ዘመን የያ​ዕ​ቆብ ልጆች ሥር ይሰ​ድ​ዳሉ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ያብ​ባል፤ በፍ​ሬ​ያ​ቸ​ውም የዓ​ለ​ሙን ፊት ይሞ​ላሉ።</verse>
				<verse number="7">በውኑ የመ​ቱ​ትን እንደ መታ እን​ዲሁ እር​ሱን መታ​ውን? ወይስ እነ​ርሱ እንደ ተገ​ደ​ሉ​በት መገ​ደል እርሱ ተገ​ድ​ሎ​አ​ልን?</verse>
				<verse number="8">በጠ​ብና በን​ቀት ይሰ​ዳ​ቸ​ዋል፤ በቍ​ጣና በክፉ መን​ፈስ ትገ​ሥ​ጻ​ቸው ዘንድ ትጀ​ም​ራ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="9">ስለ​ዚ​ህም የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ችና የፀ​ሐይ ምስ​ሎች ዳግ​መኛ እን​ዳ​ይ​ነሡ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ድን​ጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድን​ጋይ ባደ​ረገ ጊዜ ፥ እን​ዲሁ የያ​ዕ​ቆብ በደል ይሰ​ረ​ያል፤ ይህም ኀጢ​አ​ትን የማ​ስ​ወ​ገድ ፍሬ ሁሉ ነው።</verse>
				<verse number="10">በዚ​ያም የተ​ሰ​ማ​ራው መንጋ እንደ ተተወ መንጋ ይሆ​ናል፤ ምድ​ሩም ለብዙ ዘመን መሰ​ማ​ሪያ ይሆ​ናል፤ በዚ​ያም መን​ጋው ይሰ​ማ​ራል፤ ያር​ፋ​ልም።</verse>
				<verse number="11">ዘግ​ይቶ ይደ​ር​ቃል፤ በው​ስ​ጡም ልም​ላሜ ሁሉ አይ​ገ​ኝም፤ ከቲ​ኣሳ የም​ት​መጡ ሴቶች፥ ኑና ለሕ​ዝቤ አል​ቅሱ፤ የማ​ያ​ስ​ተ​ውል ሕዝብ ነውና፤ ስለ​ዚህ ፈጣ​ሪው አይ​ራ​ራ​ለ​ትም፤ ሠሪ​ውም ምሕ​ረት አያ​ደ​ር​ግ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="12">በዚያ ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከወ​ንዝ ፈሳሽ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ዐጥር ያጥ​ራል፤ እና​ን​ተም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ፥ አንድ በአ​ንድ ትሰ​በ​ሰ​ባ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="13">በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ታላቅ መለ​ከት ይነ​ፋል፤ በአ​ሦ​ርም የጠፉ፥ በግ​ብፅ ምድ​ርም የተ​ሰ​ደዱ ይመ​ጣሉ፤ በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ተራራ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ግ​ዳሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="28">
				<verse number="1">ለኤ​ፍ​ሬም ምን​ደ​ኞች ትዕ​ቢት አክ​ሊል፥ ያለ ወይን ጠጅ ለሰ​ከሩ፥ በወ​ፍ​ራም ተራራ ራስ ላይ ላለ​ችም ለረ​ገ​ፈች ለክ​ብር ጌጥ አበባ ወዮ!</verse>
				<verse number="2">እነሆ፥ ኀያል ብርቱ የሆነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ሠ​ፍት በኀ​ይል እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ የበ​ረዶ ወጨፎ፥ እን​ደ​ሚ​ያ​ጠ​ፋም ዐውሎ ነፋስ፥ እን​ደ​ሚ​ያ​ጥ​ለ​ቀ​ል​ቅም እንደ ብዙ ውኃ ፈሳሽ በጠ​ነ​ከረ እጅ ወደ ምድር ይጥ​ላል።</verse>
				<verse number="3">የኤ​ፍ​ሬም ምን​ደ​ኞች ትዕ​ቢት አክ​ሊል በእ​ጅና በእ​ግር ይረ​ገ​ጣል፤</verse>
				<verse number="4">በረ​ዥም ተራራ ራስ ላይ ያለች የረ​ገ​ፈች የክ​ብሩ ተስፋ አበባ አስ​ቀ​ድማ እን​ደ​ም​ት​በ​ስል በለስ ትሆ​ና​ለች፤ ሰውም ባያት ጊዜ በእጁ ሳይ​ቀ​በ​ላት ይበ​ላት ዘንድ ይፈ​ጥ​ናል።</verse>
				<verse number="5">በዚያ ቀን የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለተ​ረ​ፉት ሕዝቡ የክ​ብር የተ​ጐ​ነ​ጐነ ዘው​ድና የተ​ስፋ አክ​ሊል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="6">ለፍ​ር​ድና ከጥ​ፋት ለሚ​ያ​ድ​ና​ቸው ኀይል በፍ​ርድ መን​ፈስ ይቀ​ራሉ።</verse>
				<verse number="7">እነ​ዚ​ህም ደግሞ ከወ​ይን ጠጅ የተ​ነሣ ይስ​ታሉ፤ ከሚ​ያ​ሰ​ክ​ርም መጠጥ የተ​ነሣ አላ​ዋ​ቆች ይሆ​ናሉ፤ ካህ​ኑና ነቢዩ ከሚ​ያ​ሰ​ክር መጠጥ የተ​ነሣ ይስ​ታሉ፤ በወ​ይን ጠጅም ይዋ​ጣሉ፤ ከሚ​ያ​ሰ​ክ​ርም መጠጥ የተ​ነሣ ይበ​ድ​ላሉ፤ ይህም የዐ​ይን ምት​ሐት ነው፤ በፍ​ርድ ይሰ​ና​ከ​ላሉ።</verse>
				<verse number="8">ማዕ​ዱም ሁሉ ትፋ​ት​ንና ርኵ​ሰ​ትን ተሞ​ል​ቶ​አል፤ ንጹሕ ስፍራ እን​ኳን የለም።</verse>
				<verse number="9">ክፉን ለማን ተና​ገ​ርን? ወሬን ለማን አወ​ራን? ወተ​ትን ለተዉ ወይስ ጡትን ለጣሉ ነውን?</verse>
				<verse number="10">ሕማ​ምን በሕ​ማም ላይ፥ ተስ​ፋ​ንም በተ​ስፋ ላይ ተቀ​በሉ፤ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ነው።</verse>
				<verse number="11">በባ​ዕድ አፍ በል​ዩም ልሳን ለዚህ ሕዝብ ይና​ገ​ራል፤</verse>
				<verse number="12">እር​ሱም፥ “ይህ​ችም ለደ​ከመ ዕረ​ፍት ናት፤ ይህ​ችም መቅ​ሠ​ፍት ናት፤” አላ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን መስ​ማ​ትን እንቢ አሉ።</verse>
				<verse number="13">ስለ​ዚህ ሄደው ወደ ኋላ እን​ዲ​ወ​ድቁ፥ እን​ዲ​ሰ​በ​ሩም፥ ተጠ​ም​ደ​ውም እን​ዲ​ቸ​ገሩ፥ የግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃሉ በሕ​ማም ላይ ሕማም፥ በተ​ስፋ ላይ ተስፋ፥ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="14">ስለ​ዚህ የተ​ጨ​ነ​ቃ​ችሁ ሰዎ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን ሕዝብ የም​ት​ገዙ አለ​ቆች ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።</verse>
				<verse number="15">እና​ን​ተም “ከሲ​ኦል ጋር ተማ​ም​ለ​ናል፤ ከሞ​ትም ጋር ቃል ኪዳን አድ​ር​ገ​ናል፤ ሐሰ​ት​ንም መሸ​ሸ​ጊ​ያን አድ​ር​ገ​ና​ልና፥ በሐ​ሰ​ትም ተሰ​ው​ረ​ና​ልና፥ ዐውሎ ነፋ​ስም ባለፈ ጊዜ አይ​ደ​ር​ስ​ብ​ንም” ትላ​ላ​ች​ሁና፥</verse>
				<verse number="16">ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ በጽ​ዮን ድን​ጋ​ይን ለመ​ሠ​ረት አስ​ቀ​ም​ጣ​ለሁ፤ ዋጋው ብዙ የሆ​ነ​ውን፥ የተ​መ​ረ​ጠ​ውን፥ የከ​በ​ረ​ው​ንና መሠ​ረቱ የጸ​ና​ውን የማ​ዕ​ዘን ድን​ጋይ አኖ​ራ​ለሁ፤ በእ​ር​ሱም የሚ​ያ​ምን አያ​ፍ​ርም።</verse>
				<verse number="17">ፍር​ዴን ለተ​ስፋ ይቅ​ር​ታ​ዬ​ንም ለት​ክ​ክ​ለኛ ሚዛን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በከ​ን​ቱና በሐ​ሰት የሚ​ታ​መኑ ከዐ​ውሎ ነፋስ አያ​መ​ል​ጡም።</verse>
				<verse number="18">ከሞ​ትም ጋር ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ቃል ኪዳን ይፈ​ር​ሳል፤ ከኢ​ኦ​ልም ጋር የተ​ማ​ማ​ላ​ች​ሁት መሐላ አይ​ጸ​ናም፤ የሚ​ያ​ልፍ ዐውሎ ነፋስ በመጣ ጊዜ ይረ​ግ​ጣ​ች​ኋል፤ ትደ​ክ​ማ​ላ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="19">ባለ​ፈም ጊዜ ይወ​ስ​ዳ​ች​ኋል፤ ማለዳ ማለዳ በቀን ያል​ፋል፤ በሌ​ሊት ክፉ ተስፋ ይሆ​ናል፤ እና​ንተ ያዘ​ና​ችሁ፥ መስ​ማ​ትን ተማሩ።”</verse>
				<verse number="20">መዋ​ጋ​ትን አን​ች​ልም፤ እና​ን​ተ​ንም ለመ​ሰ​ብ​ሰብ ደካ​ሞች ነን።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በኃ​ጥ​ኣን ተራራ እንደ ነበረ ይነ​ሣል፤ በገ​ባ​ዖን ሸለ​ቆም ይኖ​ራል፤ ሥራ​ውን ማለት መራራ ሥራ​ውን በቍጣ ይሠ​ራል፤ ቍጣ​ውም ድን​ቅን ያደ​ር​ጋል፤ መር​ዙም ልዩ ነው።</verse>
				<verse number="22">አሁ​ንም በም​ድር ሁሉ ላይ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ያለ​ቀና የተ​ቈ​ረጠ ነገ​ርን ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ሰም​ቻ​ለ​ሁና እስ​ራ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ጸ​ና​ባ​ችሁ እና​ንተ ደስ አይ​በ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="23">አድ​ምጡ፤ ድም​ፄ​ንም ስሙ፤ ልብ አድ​ርጉ፤ ንግ​ግ​ሬ​ንም ስሙ።</verse>
				<verse number="24">በውኑ ገበሬ ሊዘራ ሁል​ጊዜ ያር​ሳ​ልን? ወይስ ምድ​ሩን ከማ​ረሱ አስ​ቀ​ድሞ ዘርን ይዘ​ራ​ልን? ጓሉ​ንስ ይከ​ሰ​ክ​ሳ​ልን?</verse>
				<verse number="25">እር​ሻ​ውን ባስ​ተ​ካ​ከለ ጊዜ ጥቂት ጥቍ​ሩን አዝ​ሙድ፥ ከሙ​ኑ​ንም፥ ዳግ​መ​ኛም ስን​ዴ​ውን፥ ገብ​ሱ​ንም፥ አጃ​ው​ንም በየ​ስ​ፍ​ራው የሚ​ዘራ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="26">ምድ​ርም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍርድ ተምራ ደስ ይላ​ታል።</verse>
				<verse number="27">ጥቍ​ሩን አዝ​ሙድ በተ​ሳ​ለች ማሄጃ አያ​ሄ​ድም፤ የሰ​ረ​ገ​ላም መን​ኰ​ራ​ኵር በከ​ሙን ላይ አይ​ዞ​ርም፤ ነገር ግን ጥቍ​ሩን አዝ​ሙድ በሽ​መል፥ ከሙ​ኑ​ንም በበ​ትር ይወ​ቃል።</verse>
				<verse number="28">እኔ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በእ​ና​ንተ ላይ አል​ቈ​ጣም፤ የም​ሕ​ረ​ቴም ድምፅ አያ​ጠ​ፋ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="29">ይህም ደግሞ ድንቅ ምክ​ርን ከሚ​መ​ክር በግ​ብ​ሩም ገናና ከሆ​ነው ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወጥ​ቶ​አል። እና​ንተ ግን ከንቱ መጽ​ና​ና​ትን ታበዙ ዘንድ ትሻ​ላ​ችሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="29">
				<verse number="1">ዳዊት ለሰ​ፈ​ረ​ባት ከተማ ለአ​ር​ኤል ወዮ​ላት! የዓ​መ​ቱን አዝ​መራ ሰብ​ስቡ፤ ከሞ​ዓብ ጋር ትበ​ላ​ላ​ች​ሁና።</verse>
				<verse number="2">አር​ኤ​ል​ንም አስ​ጨ​ን​ቃ​ለሁ፤ ይህ​ችም ኀይል፥ ይህ​ችም ብዕል የእኔ ትሆ​ና​ለች፥</verse>
				<verse number="3">እንደ ዳዊ​ትም እከ​ብ​ሻ​ለሁ፤ በቅ​ጥ​ርም አጥ​ር​ሻ​ለሁ፤ አን​ባም በላ​ይሽ አቆ​ማ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">ነገ​ር​ሽም በም​ድር ውስጥ ይሰ​ጥ​ማል፤ ቃል​ሽም ከም​ድር በታች እን​ደ​ሚ​ና​ገር ይሆ​ናል፤ ትደ​ክ​ሚ​ያ​ለሽ፤ ቃል​ሽም በም​ድር ውስጥ ዝቅ ይላል።</verse>
				<verse number="5">ነገር ግን የኃ​ጥ​አን ብል​ጽ​ግና እንደ ደቀቀ ትቢያ፥ የጠ​ላ​ቶ​ች​ሽም ብዛት ነፋስ እን​ደ​ሚ​ያ​መ​ጣው ገለባ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="6">ድን​ገ​ትም ፈጥኖ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በነ​ጐ​ድ​ጓድ፥ በም​ድ​ርም መና​ወጥ፥ በታ​ላቅ ድምፅ፥ በዐ​ውሎ ነፋ​ስም፥ በወ​ጨ​ፎም፥ በም​ት​በ​ላም በእ​ሳት ነበ​ል​ባል ይጐ​በ​ኛ​ታል።</verse>
				<verse number="7">በአ​ር​ኤ​ልም ላይ የሚ​ዋጉ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም የሚ​ወጉ፥ በእ​ር​ሻ​ዋም ላይ የሚ​ሰ​በ​ሰቡ የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቋ​ትም፥ የአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ብል​ጽ​ግና እን​ደ​ሚ​ያ​ልም ሰው ሕልም ነው።</verse>
				<verse number="8">ሰዎች ተር​በው ሌሊት በሕ​ል​ማ​ቸው ይበ​ላሉ፤ ይጠ​ጣ​ሉም፤ በተ​ነሡ ጊዜ ግን ሕል​ማ​ቸው ከንቱ ነው። የተ​ጠማ ሰውም እን​ደ​ሚ​ጠጣ ያል​ማል፤ በነ​ቃም ጊዜ እንደ ተጠማ ነው፤ ነፍ​ሱም በከ​ንቱ ትመ​ኛ​ለች። ደብረ ጽዮ​ንን የሚ​ዋጉ የአ​ሕ​ዛብ ብል​ጽ​ግ​ናም እን​ደ​ዚሁ ነው።</verse>
				<verse number="9">ደከሙ፤ ደነ​ገ​ጡም፤ ሰከ​ሩም፤ በወ​ይን አይ​ይ​ደ​ለም፤ በጠ​ጅም አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ን​ቅ​ልፍ መን​ፈ​ስን አፍ​ስ​ሶ​ባ​ቸ​ዋል፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን፥ የነ​ቢ​ያ​ት​ንም ዐይን፥ የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም የሚ​ያዩ የአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውን ዐይን ጨፍ​ኖ​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="11">ይህም ሁሉ ነገር እንደ ታተመ መጽ​ሐፍ ቃል ሆኖ​ባ​ቸ​ዋል፤ ማን​በ​ብ​ንም ለሚ​ያ​ውቅ፥ “ይህን አን​ብብ” ብለው በሰ​ጡት ጊዜ እርሱ፥ “ታት​ሟ​ልና ማን​በብ አል​ች​ልም” ይላ​ቸ​ዋል፤</verse>
				<verse number="12">ደግ​ሞም መጽ​ሐ​ፉን ማን​በ​ብን ለማ​ያ​ውቅ፥ “ይህን አን​ብብ” ብለው በሰ​ጡት ጊዜ እርሱ፥ “ማን​በብ አላ​ው​ቅም” ይላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="13">ጌታም አለ፥ “ይህ ሕዝብ በከ​ን​ፈ​ሮቹ ያከ​ብ​ረ​ኛ​ልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና፥ በከ​ንቱ ያመ​ል​ኩ​ኛል፤ ሰው ሠራሽ ትም​ህ​ር​ትም ያስ​ተ​ም​ራሉ፤</verse>
				<verse number="14">ስለ​ዚህ፥ እነሆ፥ ይህ ሕዝብ በድ​ጋሚ እን​ዲ​ፈ​ልስ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ አፈ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም፤ የጥ​በ​በ​ኞ​ች​ንም ጥበብ አጠ​ፋ​ለሁ፤ የአ​ስ​ተ​ዋ​ዮ​ች​ንም ማስ​ተ​ዋል እሰ​ው​ራ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="15">ምክ​ራ​ቸ​ውን ጥልቅ አድ​ር​ገው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ሰ​ውሩ ወዮ​ላ​ቸው! ሥራ​ቸ​ው​ንም በጨ​ለማ ውስጥ አድ​ር​ገው፥ “ማን ያየ​ናል? ወይስ ማን ያው​ቀ​ናል?” ለሚሉ ወዮ​ላ​ቸው!</verse>
				<verse number="16">ይህ የእ​ና​ንተ ጠማ​ም​ነት ነው፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃ የም​ት​ቈ​ጠሩ አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን? በውኑ ሥራ ሠሪ​ውን፥ “አል​ሠ​ራ​ኸ​ኝም” ይለ​ዋ​ልን? ወይስ የተ​ደ​ረገ አድ​ራ​ጊ​ውን፥ “በማ​ስ​ተ​ዋል አላ​ሳ​መ​ር​ኸ​ኝም” ይለ​ዋ​ልን?</verse>
				<verse number="17">ሊባ​ኖስ እንደ ፍሬ​ያማ እርሻ ሊለ​ወጥ፥ ፍሬ​ያ​ማ​ውም እርሻ እንደ ዱር ሊቈ​ጠር ጥቂት ዘመን የቀረ አይ​ይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="18">በዚ​ያም ቀን ደን​ቆ​ሮች የመ​ጽ​ሐ​ፍን ቃል ይሰ​ማሉ፤ በጨ​ለ​ማና በጭ​ጋግ ውስ​ጥም የዕ​ው​ሮች ዐይ​ኖች ያያሉ።</verse>
				<verse number="19">ነዳ​ያን ደስ​ታ​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያበ​ዛሉ፤ በሰ​ዎች መካ​ከል ተስፋ የሌ​ላ​ቸ​ውም ሐሤ​ትን በእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ያደ​ር​ጋሉ።</verse>
				<verse number="20">ኃጥእ ሰው አል​ቆ​አ​ልና፥ ትዕ​ቢ​ተ​ኛ​ውም ጠፍ​ቶ​አ​ልና፥ በክ​ፋት የበ​ደ​ሉም ሁሉ ይነ​ቀ​ላ​ሉና፤</verse>
				<verse number="21">እነ​ዚ​ህም ሰውን በነ​ገር በደ​ለኛ የሚ​ያ​ደ​ርጉ፥ በበ​ርም ለሚ​ገ​ሥ​ጸው አሽ​ክላ የሚ​ያ​ኖሩ፥ ጻድ​ቁ​ንም በከ​ንቱ ነገር የሚ​ያ​ስቱ ናቸው።</verse>
				<verse number="22">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ብ​ር​ሃም ስለ ለየው ስለ ያዕ​ቆብ ቤት እን​ዲህ ይላል፥ “ያዕ​ቆብ አሁን አታ​ፍ​ርም፤ ፊት​ህም አሁን አይ​ለ​ወ​ጥም።</verse>
				<verse number="23">ነገር ግን ልጆ​ቻ​ቸው የእ​ጄን ሥራ ባዩ ጊዜ ስለ እኔ ስሜን ይቀ​ድ​ሳሉ፤ የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንም ቅዱስ ይቀ​ድ​ሳሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ ይፈ​ራሉ።</verse>
				<verse number="24">በመ​ን​ፈ​ስም የሳቱ ማስ​ተ​ዋ​ልን ያው​ቃሉ፤ የሚ​ያ​ጕ​ረ​መ​ር​ሙም መታ​ዘ​ዝን ይማ​ራሉ፤ ዲዳ አን​ደ​በ​ትም ሰላም መና​ገ​ርን ይማ​ራል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="30">
				<verse number="1">ለዐ​መ​ፀ​ኞች ልጆች ወዮ​ላ​ቸው! ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከእኔ ዘንድ ያል​ሆ​ነን ምክር ይመ​ክ​ራሉ፤ ኀጢ​አ​ት​ንም በኀ​ጢ​አት ላይ ይጨ​ምሩ ዘንድ ከመ​ን​ፈሴ ዘንድ ያል​ሆ​ነ​ውን ቃል ኪዳን ያደ​ር​ጋሉ።</verse>
				<verse number="2">እኔን ሳይ​ጠ​ይቁ በፈ​ር​ዖን ኀይል ይረዱ ዘንድ በግ​ብ​ፅም ይጠ​በቁ ዘንድ ወደ ግብፅ ይሄ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="3">ስለ​ዚህ የፈ​ር​ዖን ኀይል እፍ​ረት፥ በግ​ብፅ መታ​መ​ንም ስድብ ይሆ​ን​ባ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="4">አለ​ቆች ምንም በጣ​ኔ​ዎስ ቢሆኑ፥ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ምንም ወደ ሓኔስ ቢደ​ርሱ፥</verse>
				<verse number="5">ሁላ​ቸው ይጠ​ቅ​ሙ​አ​ቸው ዘንድ ስለ​ማ​ይ​ችሉ፥ እፍ​ረ​ትና ስድብ እንጂ ረድ​ኤ​ትና ረብ ስለ​ማ​ይ​ሆኑ ሕዝብ ያፍ​ራሉ።</verse>
				<verse number="6">ተባ​ትና እን​ስት አን​በሳ፥ እፉ​ኝ​ትም፥ ነዘር እባ​ብም፥ በሚ​ወ​ጡ​ባት በመ​ከ​ራና በጭ​ን​ቀት ምድር በኩል ብል​ጽ​ግ​ና​ቸ​ውን በአ​ህ​ዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛ​ግ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በግ​መ​ሎች ሻኛ ላይ እየ​ጫኑ ወደ​ማ​ይ​ጠ​ቅ​ሙ​አ​ቸው ሕዝብ ይሄ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="7">የግ​ብፅ ርዳታ ከን​ቱና ባዶ ነው፤ ስለ​ዚህ፥ “ምክ​ራ​ችሁ ከንቱ ነው” ብለህ ንገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">አሁን ተቀ​መጥ፤ ለሚ​መ​ጣ​ውም ዘመን ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዲ​ሆን በሰ​ሌዳ ላይ በመ​ጽ​ሐ​ፍም ውስጥ ጻፍ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ዐመ​ፀኛ ወገን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ለመ​ስ​ማት እምቢ ያሉ የሐ​ሰት ልጆች ናቸ​ውና፤</verse>
				<verse number="10">ነቢ​ያ​ትን፥ “አት​ን​ገ​ሩን፤ ባለ ራእ​ዮ​ች​ንም አታ​ው​ሩን፤ ነገር ግን ሌላ​ውን ስሕ​ተት አስ​ረ​ዱን፤ ንገ​ሩ​ንም” ይላሉ፤</verse>
				<verse number="11">“ከዚህ መን​ገድ መል​ሱን፤ ከዚ​ህም ፈቀቅ አድ​ር​ጉን በሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቅዱስ ትም​ህ​ርት ከእኛ ዘንድ አስ​ወ​ግዱ” ይሏ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="12">ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ እን​ዲህ ይላል፥ “ይህ​ችን ቃል አቃ​ል​ላ​ች​ኋ​ልና፥ በሐ​ሰ​ትና በጠ​ማ​ማ​ነት ተስፋ አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና፥ አጕ​ረ​ም​ር​ማ​ች​ኋ​ል​ምና፥ በዚ​ህም ቃል ታም​ና​ች​ኋ​ልና፤</verse>
				<verse number="13">ስለ​ዚህ ይህ በደል አዘ​ብ​ዝቦ ለመ​ፍ​ረስ እንደ ቀረበ፥ አፈ​ራ​ረ​ሱም ፈጥኖ ድን​ገት እን​ደ​ሚ​መጣ እንደ ከተማ ቅጥር ይሆ​ን​ባ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="14">አወ​ዳ​ደ​ቁም እንደ ሸክላ ሠሪ ገንቦ የደ​ቀቀ ይሆ​ናል፤ ሳይ​ራ​ራም ያደ​ቅ​ቀ​ዋል፤ ከስ​ባ​ሪ​ውም እሳት ከማ​ን​ደጃ የሚ​ወ​ስ​ዱ​በት፥ ወይም ውኃ ከጕ​ድ​ጓድ የሚ​ቀ​ዱ​በት ገል አይ​ገ​ኝም።”</verse>
				<verse number="15">የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “ብት​ጸ​ጸ​ትና ብታ​ለ​ቅስ ትድ​ና​ለህ፤ የት እን​ዳ​ለ​ህም ታው​ቃ​ለህ፤ በከ​ንቱ ታም​ነ​ሃ​ልና፤ ኀይ​ላ​ች​ሁም ከንቱ ይሆ​ናል፤ እና​ንተ ግን መስ​ማ​ትን እንቢ አላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="16">ነገር ግን፥ በፈ​ረስ ላይ ተቀ​ም​ጠን እን​ሸ​ሻ​ለን እንጂ እን​ዲህ አይ​ሆ​ንም አላ​ችሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ፤ ደግ​ሞም በፈ​ጣን ፈረስ ላይ እን​ቀ​መ​ጣ​ለን አላ​ችሁ፤ ስለ​ዚ​ህም የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ችሁ ፈጣ​ኖች ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="17">ከአ​ንድ ሰው ዛቻ የተ​ነሣ ሺህ ሰዎች ይሸ​ሻሉ፤ እና​ን​ተም በተ​ራራ ራስ ላይ እን​ዳለ ምሰሶ፥ በኮ​ረ​ብ​ታም ላይ እን​ዳለ ምል​ክት ሆና​ችሁ እስ​ክ​ት​ቀሩ ድረስ፥ ከአ​ም​ስት ሰዎች ዛቻ የተ​ነሣ ብዙ​ዎች ይሸ​ሻሉ።”</verse>
				<verse number="18">አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራጅ ነውና ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይራ​ራ​ላ​ችሁ ዘንድ ይታ​ገ​ሣል፤ ይም​ራ​ች​ሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እር​ሱን በመ​ተ​ማ​መን የሚ​ጠ​ባ​በቁ ሁሉ ብፁ​ዓን ናቸው።</verse>
				<verse number="19">ቅዱስ ሕዝብ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ በጽ​ዮን ይኖ​ራል፤ ልቅ​ሶን አል​ቅሺ፤ ይቅር በለ​ኝም በዪ፤ ልቅ​ሶ​ሽን ባየ ጊዜ ይቅር ይል​ሻል፤ ሰም​ቶ​ሻ​ልና።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የጭ​ን​ቀ​ትን እን​ጀ​ራና የመ​ከ​ራን ውኃ ይሰ​ጥ​ሃል። የሚ​ያ​ሳ​ስ​ቱ​ህም እን​ግ​ዲህ ወደ አንተ አይ​ቀ​ር​ቡም፤ ዐይ​ኖ​ችህ ግን የሚ​ያ​ሳ​ስ​ቱ​ህን ያያሉ፤</verse>
				<verse number="21">ወደ ቀኝም ቢሆን ወደ ግራም ቢሆን በኋ​ላህ በዚህ መን​ገድ እን​ሂድ የሚ​ሉና የሚ​ሳ​ሳቱ ሰዎ​ችን ድምፅ ጆሮ​ዎ​ችህ ይሰ​ማሉ።</verse>
				<verse number="22">በብ​ርም ወደ ተለ​በጡ፥ በወ​ር​ቅም ወደ አጌጡ ወደ ጣዖ​ታቱ እን​ሂድ የሚሉ ናቸው፤ ያን​ጊዜ እንደ ትቢያ የደ​ቀቁ ይሆ​ናሉ፤ እንደ ውኃም ይደ​ፈ​ር​ሳሉ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ጥራ​ጊ​ዎ​ችን ይጥ​ሉ​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="23">በም​ድ​ርም ለተ​ዘ​ራው ዘርህ ዝናም ይዘ​ን​ማል፤ ከም​ድ​ርም ፍሬ የሚ​ወጣ እን​ጀራ ወፍ​ራ​ምና ብዙ ይሆ​ናል። በዚ​ያም ቀን ከብ​ቶ​ችህ በሰ​ፊና በለ​መ​ለመ መስክ ይሰ​ማ​ራሉ፤</verse>
				<verse number="24">መሬ​ት​ንም የሚ​ያ​ርሱ በሬ​ዎ​ችና አህ​ዮች በመ​ን​ሽና በወ​ን​ፊት የነ​ጻ​ውን ከገ​ብስ ጋር የተ​ቀ​ላ​ቀ​ለ​ውን ገፈራ ይበ​ላሉ።</verse>
				<verse number="25">በታ​ላ​ቅም እል​ቂት ቀን ግን​ቦች በወ​ደቁ ጊዜ፥ በረ​ዥሙ ተራራ ሁሉ ከፍ ባለ​ውም ኮረ​ብታ ሁሉ ላይ፥ ወን​ዞ​ችና የውኃ ፈሳ​ሾች ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="26">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሕ​ዝ​ቡን ስብ​ራት በጠ​ገነ ዕለት፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍቱ የቈ​ሰ​ለ​ው​ንም በፈ​ወሰ ዕለት፥ የጨ​ረቃ ብር​ሃን እንደ ፀሐይ ብር​ሃን፥ የፀ​ሐ​ይም ብር​ሃን እንደ ሰባት ቀን ብር​ሃን ሰባት እጥፍ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="27">እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ከብዙ ጊዜ በኋላ ይመ​ጣል፤ ቍጣ​ውም ከከ​ን​ፈ​ሮቹ ቃል ክብር ጋር ይነ​ድ​ዳል፤ ቃሉም ቍጣን የተ​መላ ነው፤ የቍ​ጣ​ውም መቅ​ሠ​ፍት እን​ደ​ም​ት​በላ እሳት ናት፤</verse>
				<verse number="28">እስ​ት​ን​ፋ​ሱም አሕ​ዛ​ብን ስለ ከንቱ ስሕ​ተ​ታ​ቸው ሊከ​ፋ​ፍ​ላ​ቸው በሸ​ለቆ እን​ደ​ሚ​ያ​ጥ​ለ​ቀ​ልቅ፥ እስከ አን​ገ​ትም እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ስና እን​ደ​ሚ​ከ​ፋ​ፍል ውኃ ይጐ​ር​ፋል፤ ስሕ​ተ​ታ​ቸ​ውም ይከ​ተ​ላ​ቸ​ዋል፤ ይወ​ስ​ዳ​ቸ​ዋ​ልም።</verse>
				<verse number="29">በዐ​ልን እን​ደ​ሚ​ያ​ከ​ብሩ፥ ሁል​ጊዜ ደስ ሊላ​ችሁ፥ ወደ ተቀ​ደ​ሰው ቦታ​የም ልት​ሄዱ አይ​ገ​ባ​ች​ሁ​ምን? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ ደስ እን​ደ​ሚ​ላ​ቸው በእ​ን​ቢ​ልታ ወደ እስ​ራ​ኤል ቅዱስ ልት​ሄዱ ይገ​ባ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="30">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የድ​ም​ፁን ክብር ያሰ​ማል፤ የክ​ን​ዱ​ንም መፈ​ራት፥ በጽኑ ቍጣና በም​ት​በላ እሳት፥ በወ​ጀ​ብም፥ በዐ​ውሎ ነፋ​ስም፥ በበ​ረ​ዶም ድን​ጋይ ይገ​ል​ጣል።</verse>
				<verse number="31">አሦ​ርም በመ​ቅ​ሠ​ፍቱ ከመ​ታው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድምፅ የተ​ነሣ ይደ​ነ​ግ​ጣል።</verse>
				<verse number="32">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላዩ የሚ​ያ​ወ​ር​ድ​በት የታ​ዘ​ዘ​በቱ የበ​ትር ድብ​ደባ ሁሉ በከ​በ​ሮና በመ​ሰ​ንቆ ይሆ​ናል፤ በጦ​ር​ነ​ትም ክን​ዱን አን​ሥቶ ይዋ​ጋ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="33">ከቀ​ድ​ሞም ጀምሮ የማ​ቃ​ጠያ ስፍራ ተዘ​ጋ​ጅ​ታ​ለች፤ ለን​ጉ​ሥም ተበ​ጅ​ታ​ለች፤ ጥል​ቅና ሰፊም አድ​ር​ጎ​አ​ታል፤ እሳ​ትና ብዙ ማገዶ ተከ​ም​ሮ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃ​ጥ​ለ​ዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="31">
				<verse number="1">ርዳታ ለመ​ፈ​ለግ ወደ ግብፅ ለሚ​ወ​ርዱ፥ በፈ​ረ​ሶ​ችና በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም ለሚ​ታ​መኑ ወዮ​ላ​ቸው! ፈረ​ሰ​ኞቹ ብዙ​ዎች ናቸ​ውና፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቅዱስ አል​ታ​መ​ኑ​ምና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ፈ​ለ​ጉ​ምና።</verse>
				<verse number="2">እርሱ ግን ጠቢብ ነው፤ ክፉ​ንም ነገር በላ​ያ​ቸው ያመ​ጣል፤ ቃሉ​ንም አይ​መ​ል​ስም፤ በክ​ፉ​ዎ​ችም ሰዎች ቤት ላይ በከ​ንቱ ተስ​ፋ​ቸ​ውም ላይ ይነ​ሣል።</verse>
				<verse number="3">ግብ​ፃ​ው​ያን ሰዎች እንጂ አም​ላክ አይ​ደ​ሉም፤ ፈረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ሥጋ እንጂ መን​ፈስ አይ​ደ​ሉም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ነ​ርሱ ላይ እጁን በዘ​ረጋ ጊዜ፥ ረጂው ይሰ​ና​ከ​ላል፤ ተረ​ጂ​ውም ይወ​ድ​ቃል፤ ሁሉም በአ​ንድ ላይ ይጠ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይለ​ኛ​ልና፥ “አን​በሳ ወይም የአ​ን​በሳ ደቦል በን​ጥ​ቂ​ያው ላይ እን​ደ​ሚ​ያ​ገሣ፥ ድም​ፁም ተራ​ሮ​ችን እስ​ኪ​ሞላ በእ​ርሱ ላይ እን​ደ​ሚ​ጮህ፥ እረ​ኞ​ችም ሁሉ ሲጮ​ሁ​በት ከብ​ዛ​ታ​ቸው የተ​ነሣ እን​ደ​ማ​ይ​ፈራ፥ ከድ​ም​ፃ​ቸ​ውም የተ​ነሣ እን​ደ​ማ​ይ​ደ​ነ​ግጥ፥ እነ​ር​ሱም ከቍ​ጣው ብዛት የተ​ነሣ ድል እን​ደ​ሚ​ሆ​ኑና እን​ደ​ሚ​ደ​ነ​ግጡ፥ እን​ዲሁ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ተራ​ራና በኮ​ረ​ብ​ታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወ​ር​ዳል።</verse>
				<verse number="5">እን​ደ​ሚ​በ​ርር ወፍ እን​ዲሁ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ይጋ​ር​ዳ​ታል፤ ይከ​ል​ላ​ታ​ልም፤ ይታ​ደ​ጋ​ታል፤ አል​ፎም ያድ​ና​ታል።</verse>
				<verse number="6">ትበ​ድሉ ዘንድ ጥልቅ ምክ​ርን የም​ት​መ​ክሩ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ፥ ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="7">በዚ​ያም ቀን እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው እጆ​ቻ​ቸው የሠ​ሩ​አ​ቸ​ውን የብ​ሩ​ንና የወ​ር​ቁን ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ይጥ​ላሉ።</verse>
				<verse number="8">አሦ​ርም ይወ​ድ​ቃል፤ የሚ​ወ​ድ​ቀ​ውም በሰው ሰይፍ አይ​ደ​ለም፤ የም​ት​በ​ላ​ቸ​ውም የሰው ሰይፍ አይ​ደ​ለ​ችም፤ የሚ​ሸ​ሹም ከሰ​ይፍ ፊት አይ​ደ​ለም ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸው ግን ይሸ​ነ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="9">ዓለ​ትም ትው​ጣ​ቸ​ዋ​ለች ድልም ይሆ​ናሉ የሸ​ሸም ይያ​ዛል። በጽ​ዮን ዘርእ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቤቶች ያሉት ብፁዕ ነው” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="32">
				<verse number="1">እነሆ፥ ጻድቅ ንጉሥ ይነ​ግ​ሣል፤ መሳ​ፍ​ን​ትም በፍ​ርድ ይገ​ዛሉ።</verse>
				<verse number="2">ሰውም ቃሉን ይሰ​ው​ራል፤ በውኃ እን​ደ​ሚ​ጠ​ል​ቅም ይሰ​ወ​ራል፤ ክብ​ሩም በደ​ረቅ ምድር እን​ደ​ሚ​ፈ​ስስ ውኃ በጽ​ዮን ይገ​ለ​ጣል።</verse>
				<verse number="3">እን​ግ​ዲህ በሰው አይ​ታ​መ​ኑም፤ በጆ​ሮ​አ​ቸው ያዳ​ም​ጣሉ እንጂ።</verse>
				<verse number="4">የደ​ካ​ሞች ሰዎች ልብ ዕው​ቀ​ትን ትሰ​ማ​ለች፤ የተ​ብ​ታ​ቦ​ችም ምላስ ፈጥና የሰ​ላ​ምን ነገር ትማ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="5">ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ሰነ​ፍን አለቃ ይሆን ዘንድ ግድ አይ​ሉ​ትም፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ሎሌህ ዝም በል አይ​ል​ህም።</verse>
				<verse number="6">ሰነፍ ግን ስን​ፍ​ናን ይና​ገ​ራል፤ ልቡም ዐመ​ፅን ያደ​ርግ ዘንድ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ስሕ​ተ​ትን ይና​ገር ዘንድ፥ የተ​ራ​በ​ች​ው​ንም ሰው​ነት ይበ​ትን ዘንድ፥ የተ​ጠ​ማ​ች​ንም ነፍስ ባዶ ያደ​ርግ ዘንድ ከን​ቱን ያስ​ባል።</verse>
				<verse number="7">በዐ​መ​ፃ​ቸው ነገር ድሃ​ውን ይገ​ድ​ሉት ዘንድ፥ የድ​ሆ​ች​ንም ፍርድ ይገ​ለ​ብጡ ዘንድ የክ​ፉ​ዎች ሕሊና ዐመ​ፅን ትመ​ክ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="8">ጻድ​ቃን ግን ጥበ​ብን ይመ​ክ​ራሉ፤ ምክ​ራ​ቸ​ውም ትጸ​ና​ለች።</verse>
				<verse number="9">እና​ንተ ባለ​ጸ​ጎች ሴቶች ሆይ፥ ተነሡ፤ ድም​ፄ​ንም ስሙ፤ እና​ንተ ተማ​ም​ና​ችሁ የም​ት​ቀ​መጡ ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ንግ​ግ​ሬን አድ​ምጡ።</verse>
				<verse number="10">በየ​ዓ​መቱ የኀ​ዘን በዓል መታ​ሰ​ቢያ አድ​ርጉ፤ ወይን መቍ​ረጥ አል​ፎ​አል፤ ፍሬ ማከ​ማ​ች​ትም አል​ቆ​አል፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አይ​መ​ጣም።</verse>
				<verse number="11">እና​ንተ ተማ​ም​ና​ችሁ የም​ት​ቀ​መጡ ደን​ግጡ፤ ሴቶች ሆይ፥ እዘኑ፤ ልብ​ሳ​ች​ሁ​ንም አው​ልቁ፤ ዕራ​ቁ​ታ​ች​ሁ​ንም ሁኑ፤ ወገ​ባ​ች​ሁ​ንም በማቅ ታጠቁ።</verse>
				<verse number="12">ስለ ተወ​ደ​ደ​ችዉ እርሻ ስለ​ሚ​ያ​ፈ​ራ​ውም ወይን ደረ​ታ​ች​ሁን ድቁ።</verse>
				<verse number="13">በሕ​ዝቤ ምድር ላይ በእ​ር​ሻ​ቸ​ውም ላይ እሾ​ህና አሜ​ከላ ይበ​ቅ​ላሉ፤ ደስ​ታም ከቤ​ታ​ቸው ሁሉ ይጠ​ፋል።</verse>
				<verse number="14">የበ​ለ​ጸ​ገች ከተ​ማና ቤቶ​ችዋ ምድረ በዳ ይሆ​ናሉ። የከ​ተ​ማ​ውን ሀብ​ትና ያማሩ ቤቶ​ችን ይተ​ዋሉ፤ አን​ባ​ዎ​ችም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዋሻ፥ የም​ድረ በዳም አህያ ደስታ፥ የመ​ን​ጎ​ችም ማሰ​ማ​ሪያ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="15">ይህም፥ መን​ፈስ ከላይ እስ​ኪ​መ​ጣ​ላ​ችሁ፥ ምድረ በዳ​ውም ፍሬ​ያማ እርሻ እስ​ኪ​ሆን፥ ፍሬ​ያ​ማ​ውም እርሻ ዱር ተብሎ እስ​ኪ​ቈ​ጠር ድረስ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="16">ከዚያ በኋላ ፍርድ በም​ድረ በዳ ይኖ​ራል፤ ጽድ​ቅም በፍ​ሬ​ያ​ማው እርሻ ያድ​ራል።</verse>
				<verse number="17">የጽ​ድ​ቅም ሥራ ሰላም ይሆ​ናል፤ ጽድ​ቅም የዕ​ረ​ፍት ቦታን ይይ​ዛል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ይታ​መ​ኑ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="18">ሕዝ​ቤም በሰ​ላም ከተማ ይኖ​ራል። ተዘ​ል​ሎም በው​ስ​ጥዋ ያድ​ራል፤ በብ​ል​ጽ​ግ​ናም ያር​ፋል።</verse>
				<verse number="19">በረዶ ቢወ​ርድ አይ​ደ​ር​ስ​ባ​ች​ሁም፤ በዛፍ ሥር የሚ​ኖሩ ሰዎች በበ​ረሃ እን​ደ​ሚ​ኖሩ ሰዎች ታም​ነው ይኖ​ራሉ።</verse>
				<verse number="20">ውኃ ባለ​በት፥ በሬና አህ​ያም በሚ​ረ​ግ​ጠው ቦታ የሚ​ዘሩ ብፁ​ዓን ናቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="33">
				<verse number="1">ለሚ​ያ​ዋ​ር​ዱ​አ​ችሁ ወዮ​ላ​ቸው! እና​ን​ተን ግን የሚ​ያ​ዋ​ር​ዳ​ችሁ የለም፤ የሚ​ወ​ነ​ጅ​ላ​ችሁ እና​ን​ተን የሚ​ወ​ነ​ጅል አይ​ደ​ለም፤ ወን​ጀ​ለ​ኞች ይጠ​መ​ዳሉ፤ ይያ​ዛ​ሉም፤ ብል እን​ደ​በ​ላው ልብ​ስም ያል​ቃሉ።</verse>
				<verse number="2">አቤቱ፥ ማረን፤ አን​ተን ተማ​ም​ነ​ና​ልና፤ የዐ​ላ​ው​ያን ዘራ​ቸው ለጥ​ፋት ነው፤ በመ​ከ​ራም ጊዜ መድ​ኀ​ኒ​ታ​ችን አንተ ነህ።</verse>
				<verse number="3">ከቃ​ልህ ግርማ የተ​ነሣ አሕ​ዛብ ፈር​ተው ሸሹ፤ አሕ​ዛ​ብም ተበ​ተኑ።</verse>
				<verse number="4">አን​በጣ እን​ደ​ሚ​ሰ​በ​ሰብ ትን​ሹም ትል​ቁም ምር​ኮ​አ​ችሁ እን​ዲሁ ይሰ​በ​ሰ​ብ​ላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="5">በአ​ር​ያም የሚ​ኖር ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ይኖ​ራል፤ ጽዮ​ንም ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን ተሞ​ላች።</verse>
				<verse number="6">በድ​ኅ​ነ​ታ​ችን መዝ​ገብ በሕግ ይሰ​በ​ስ​ቡ​አ​ቸ​ዋል፤ ጥበ​ብና ምክር፥ ጽድ​ቅም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ናቸው፤ እነ​ዚ​ህም የጽ​ድቅ መዝ​ገ​ቦች ናቸው።</verse>
				<verse number="7">እነሆ እና​ንተ ቀድሞ ትፈ​ሩ​አ​ቸው የነ​በሩ በግ​ር​ማ​ችሁ ይፈ​ሩ​አ​ች​ኋል፤ ከእ​ና​ን​ተም የተ​ነሣ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ። መል​እ​ክ​ተ​ኞች መራራ ልቅ​ሶን እያ​ለ​ቀሱ ይላ​ካሉ፤ ሰላ​ም​ንም ይለ​ም​ናሉ።</verse>
				<verse number="8">መን​ገ​ዶች ባድማ ሆኑ፤ የአ​ሕ​ዛ​ብም መፈ​ራት ቀረ፤ ቃል ኪዳ​ና​ቸ​ውም ፈረሰ፤ እንደ ሰውም አል​ተ​መ​ለ​ከ​ታ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="9">ምድር አለ​ቀ​ሰች፤ ሊባ​ኖስ አፈረ፤ ሳሮ​ንም እንደ ምድረ በዳ ሆነ፤ ገሊ​ላና ቀር​ሜ​ሎስ ታወቁ።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “አሁን እነ​ሣ​ለሁ፤ አሁን እከ​ብ​ራ​ለሁ፤ አሁን ከፍ ከፍ እላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">ዛሬ ታያ​ላ​ችሁ፤ ዛሬ ታደ​ን​ቃ​ላ​ችሁ፤ የመ​ን​ፈ​ሳ​ች​ሁም ኀይል ከንቱ ይሆ​ናል፤ እሳ​ትም ትበ​ላ​ች​ኋ​ለች።</verse>
				<verse number="12">አሕ​ዛ​ብም በእ​ርሻ ውስጥ ተቈ​ርጦ እንደ ተጣ​ለና በእ​ሳት እንደ ተቃ​ጠለ እሾህ የተ​ቃ​ጠሉ ይሆ​ናሉ።”</verse>
				<verse number="13">በሩቅ ያሉ የሠ​ራ​ሁ​ትን ይሰ​ማሉ፤ በቅ​ር​ብም ያሉ ኀይ​ሌን ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="14">በጽ​ዮን ያሉ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ፈሩ፤ መን​ቀ​ጥ​ቀጥ ዝን​ጉ​ዎ​ችን ያዘ፤ እሳት እን​ደ​ሚ​ነ​ድድ የሚ​ነ​ግ​ራ​ችሁ ማን ነው? የዘ​ለ​ዓ​ለም ሀገ​ር​ንስ የሚ​ነ​ግ​ራ​ችሁ ማን ነው?</verse>
				<verse number="15">በጽ​ድቅ የሚ​ሄድ፥ ቅን ነገ​ር​ንም የሚ​ና​ገር፥ በደ​ል​ንና ኀጢ​አ​ትን የሚ​ጠላ፥ መማ​ለ​ጃን ከመ​ጨ​በጥ እጁን የሚ​ያ​ራ​ግፍ፥ ደም ማፍ​ሰ​ስን ከመ​ስ​ማት ጆሮ​ቹን የሚ​ደ​ፍን፥ ክፋ​ት​ንም ከማ​የት ዐይ​ኖ​ቹን የሚ​ጨ​ፍን ነው።</verse>
				<verse number="16">እርሱ ከፍ ባለ በጽ​ኑዕ ዓለት ዋሻ ይኖ​ራል፤ እን​ጀ​ራም ይሰ​ጠ​ዋል፤ ውኃ​ውም የታ​መ​ነች ትሆ​ና​ለች።</verse>
				<verse number="17">ንጉ​ሥን በክ​ብሩ ታዩ​ታ​ላ​ችሁ፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም በሩቅ ያለች ምድ​ርን ያዩ​አ​ታል።</verse>
				<verse number="18">ልባ​ች​ሁም፥ “ጸሓ​ፊ​ዎች ወዴት አሉ? መማ​ክ​ር​ትስ ወዴት አሉ? የት​ን​ሹና የት​ልቁ ዐማ​ፅ​ያን ብዛ​ትስ ወዴት አለ?” ብሎ ፍር​ሀ​ትን ያስ​ባል።</verse>
				<verse number="19">የማ​ታ​ው​ቋ​ቸ​ውን አሕ​ዛብ አመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ንት ዐማ​ፅ​ያን ሕዝብ፥ ጥልቅ ነገ​ርን ትሰ​ማ​ላ​ችሁ። የሚ​ሰ​ማም ማስ​ተ​ዋል እን​ደ​ሌ​ለው ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="20">እነሆ፥ የመ​ድ​ኀ​ኒ​ታ​ች​ንን ከተማ ጽዮ​ንን ተመ​ል​ከት፤ ዐይ​ኖ​ች​ህም ድን​ኳ​ኖ​ችዋ የማ​ይ​ና​ወጡ፥ ካስ​ማ​ዎ​ችዋ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የማ​ይ​ነ​ቀሉ፥ አው​ታ​ሮ​ች​ዋም ሁሉ የማ​ይ​በ​ጠሱ፥ የበ​ለ​ጸ​ገች ከተማ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ያያሉ።</verse>
				<verse number="21">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ለእ​ና​ንተ ታላቅ ነው፤ ሀገ​ራ​ች​ሁም የሰፉ ወን​ዞ​ችና ታላቅ የመ​ስኖ ስፍራ ይሆ​ናል፤ በዚ​ህች መን​ገድ አት​ሄ​ድም፤ መር​ከ​ቦ​ችም አይ​ሄ​ዱም።</verse>
				<verse number="22">አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነውና ቸል አይ​ለ​ንም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራ​ጃ​ችን ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችን ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጉ​ሣ​ችን ነው፤ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ነ​ናል።</verse>
				<verse number="23">ገመ​ዶ​ችሽ ተበ​ጥ​ሰ​ዋል፤ ጥን​ካሬ የላ​ቸ​ው​ምና፤ ደቀ​ልሽ ዘመመ፤ ሸራ​ው​ንም መዘ​ር​ጋት አል​ቻ​ለም፤ እስ​ከ​ሚ​ያ​ዝም ድረስ አላ​ማ​ውን አል​ተ​ሸ​ከ​መም። በዚ​ያን ጊዜ የብዙ ምርኮ ተከ​ፈለ፤ ብዙ አን​ካ​ሶች እንኳ ምር​ኮ​ውን ማረኩ።</verse>
				<verse number="24">በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም የሚ​ቀ​መጥ ሕዝብ፦ ደክ​ሜ​አ​ለሁ አይ​ልም፥ በደ​ላ​ቸው ይቅር ይባ​ል​ላ​ቸ​ዋ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="34">
				<verse number="1">እና​ንተ አሕ​ዛብ ሆይ፥ ቅረቡ፤ እና​ን​ተም አለ​ቆች ሆይ፥ አድ​ምጡ፤ ምድ​ርና በው​ስ​ጥ​ዋም ያሉ፥ ዓለ​ምና በው​ስ​ጥ​ዋም ያሉ ሕዝብ ሁሉ ይስሙ።</verse>
				<verse number="2">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ነውና፤ መቅ​ሠ​ፍ​ቱም ያጠ​ፋ​ቸ​ውና ለጦር ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ በቍ​ጥ​ራ​ቸው ልክ ነው።</verse>
				<verse number="3">ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ገ​ደ​ሉት በድ​ና​ቸው ይጣ​ላል፤ የሬ​ሳ​ቸ​ውም ግማት ይሸ​ታል፤ ተራ​ሮ​ቹም ከደ​ማ​ቸው የተ​ነሣ ይር​ሳሉ።</verse>
				<verse number="4">ሰማ​ያት እንደ መጽ​ሐፍ ጥቅ​ልል ይጠ​ቀ​ለ​ላሉ፤ ከወ​ይ​ንና ከበ​ለ​ስም ቅጠል እን​ደ​ሚ​ረ​ግፍ ከዋ​ክ​ብት ሁሉ ይረ​ግ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="5">ሰይፌ በሰ​ማይ ሆና ሰከ​ረች፤ እነሆ፥ በኤ​ዶ​ም​ያ​ስና በሚ​ጠ​ፉት ሕዝብ ላይ ለፍ​ርድ ትወ​ር​ዳ​ለች።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት በባ​ሶራ፥ ታላ​ቅም እርድ በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድር አለ​ውና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ በደም ተሞ​ል​ታ​ለች፤ በበግ ስብ፥ በፍ​የል ደምም፥ በአ​ው​ራም በግ ስብ ወፍ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="7">ኀያ​ላን ከእ​ነ​ርሱ ጋር፥ ወይ​ፈ​ኖ​ችም ከኮ​ር​ማ​ዎች ጋር ይወ​ድ​ቃሉ፤ ምድ​ራ​ቸ​ውም በደም ትሰ​ክ​ራ​ለች፤ በስ​ባ​ቸ​ውም ትወ​ፍ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="8">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፍ​ርዱ ቀን፥ ስለ ጽዮ​ንም ፍርድ የብ​ድ​ራት ዓመት ነውና።</verse>
				<verse number="9">ሸለ​ቆ​ዎ​ችዋ ዝፍት ሆነው ይወ​ጣሉ፤ አፈ​ር​ዋም ዲን ይሆ​ናል፤ መሬ​ቷም በቀ​ንና በሌ​ሊት እንደ ዝፍት ይቃ​ጠ​ላል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አይ​ጠ​ፋም፤</verse>
				<verse number="10">ጢሱም ወደ​ላይ ይወ​ጣል፤ ከት​ው​ልድ እስከ ትው​ል​ድም ድረስ ባድማ ሆና ትኖ​ራ​ለች፤ ለብዙ ዘመ​ና​ትም ትጠ​ፋ​ለች።</verse>
				<verse number="11">ጭል​ፊ​ቶ​ችና ጃርት፥ ጕጕ​ትና ቍራም ይኖ​ሩ​ባ​ታል፤ መሠ​ረ​ቷ​ንም በመ​ፍ​ረስ ገመድ ይለ​ካሉ። አጋ​ን​ን​ትም ያድ​ሩ​ባ​ታል፤</verse>
				<verse number="12">አለ​ቆ​ችዋ ያል​ቃሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ቷና መሳ​ፍ​ንቷ ይጠ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="13">በከ​ተ​ማ​ዎ​ች​ዋም እሾህ፥ በቅ​ጥ​ሮ​ች​ዋም አሜ​ከላ ይበ​ቅ​ሉ​ባ​ታል፤ የአ​ጋ​ን​ንት ማደ​ሪ​ያና የሰ​ጎን ስፍራ ትሆ​ና​ለች።</verse>
				<verse number="14">በዚ​ያም አጋ​ን​ን​ትና ጂኖች ይገ​ና​ኛሉ፤ እነ​ር​ሱም እርስ በር​ሳ​ቸው ይጠ​ራ​ራሉ፤ ጂኖ​ችም በዚያ ይኖ​ራሉ፤ ለራ​ሳ​ቸ​ውም ማረ​ፊ​ያን ያገ​ኛሉ።</verse>
				<verse number="15">በዚያ ጃር​ቶች ይዋ​ለ​ዳሉ፤ ምድ​ርም ልጆ​ች​ዋን በኀ​ይል ታድ​ና​ለች፤ ዋሊ​ያ​ዎች በዚያ ይገ​ና​ኛሉ፤ ፊት ለፊ​ትም ይተ​ያ​ያሉ።</verse>
				<verse number="16">በየ​ቍ​ጥ​ራ​ቸው ያል​ፋሉ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ አይ​ጠ​ፋም፤ እርስ በር​ሳ​ቸው አይ​ተ​ጣ​ጡም፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዝ​ዞ​አ​ቸ​ዋ​ልና መን​ፈ​ሱም ሰብ​ስ​ቦ​አ​ቸ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="17">እር​ሱም ዕጣ ጣለ​ባ​ቸው፤ እጁም ከፈ​ለ​ች​ላ​ቸው፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይሰ​ማ​ሩ​ባ​ታል፤ ከት​ው​ል​ድም እስከ ትው​ልድ ድረስ ይወ​ር​ሱ​አ​ታል፤ በው​ስ​ጥ​ዋም ያር​ፉ​ባ​ታል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="35">
				<verse number="1">የተ​ጠ​ማው ምድረ በዳ ደስ ይለ​ዋል፤ በረ​ሃ​ውም ሐሤት ያደ​ር​ጋል፤ እንደ ጽጌ​ረ​ዳም ያብ​ባል።</verse>
				<verse number="2">የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ምድረ በዳ ያብ​ባል፤ ሐሤ​ት​ንም ያደ​ር​ጋል፤ የሊ​ባ​ኖስ ክብ​ርና የቀ​ር​ሜ​ሎስ ክብር ይሰ​ጠ​ዋል፤ ሕዝ​ቤም የጌ​ታን ክብር፥ የአ​ም​ላ​ክ​ንም ግርማ ያያሉ።</verse>
				<verse number="3">ደካ​ሞች እጆ​ችና አን​ካ​ሶች ጕል​በ​ቶች፥ ጽኑ።</verse>
				<verse number="4">እና​ንተ አእ​ምሮ የሌ​ላ​ችሁ፥ ልቡ​ና​ች​ሁን አረ​ጋጉ፤ ጽኑ፤ አት​ፍሩ፤ እነሆ፥ አም​ላ​ካ​ችን ፍር​ድን ይመ​ል​ሳል፤ ይበ​ቀ​ላ​ልም፤ እር​ሱም መጥቶ ያድ​ነ​ናል።</verse>
				<verse number="5">በዚ​ያን ጊዜም የዕ​ው​ሮች ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው ይገ​ለ​ጣሉ፤ የደ​ን​ቆ​ሮ​ዎ​ችም ጆሮ​ዎች ይሰ​ማሉ።</verse>
				<verse number="6">በዚ​ያን ጊዜ አን​ካ​ሳ​ዎች እንደ ሚዳቋ ይዘ​ል​ላሉ፤ የዲ​ዳ​ዎ​ችም ምላስ ርቱዕ ይሆ​ናል፤ በም​ድረ በዳ ውኃ፥ በተ​ጠማ መሬ​ትም ፈሳሽ ይፈ​ል​ቃ​ልና።</verse>
				<verse number="7">ደረ​ቂቱ ምድር ኩሬ፥ የተ​ጠ​ማች ምድ​ርም የውኃ ምንጭ ትሆ​ና​ለች፤ የዎ​ፎች መኖ​ሪ​ያም ሸን​በ​ቆና ደን​ገል ይሆ​ን​በ​ታል።</verse>
				<verse number="8">በዚ​ያም ንጹሕ መን​ገድ ይሆ​ናል፤ እር​ሱም የተ​ቀ​ደሰ መን​ገድ ይባ​ላል፤ በዚ​ያም ንጹ​ሓን ያል​ሆኑ አያ​ል​ፉ​በ​ትም፤ ርኩስ መን​ገ​ድም በዚያ አይ​ኖ​ርም፤ የተ​በ​ተ​ኑ​ትም በእ​ርሱ ይሄ​ዳሉ፤ አይ​ሳ​ሳ​ቱ​ምም።</verse>
				<verse number="9">አን​በሳ አይ​ኖ​ር​በ​ትም፤ ክፉ አው​ሬም አይ​ወ​ጣ​በ​ትም፤ በዚ​ያም አይ​ገ​ኙም፤ የዳ​ኑት ግን በዚያ ይሄ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="10">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡም ይመ​ለ​ሳሉ፤ በደ​ስ​ታም ተመ​ል​ሰው ወደ ጽዮን ይመ​ጣሉ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም ደስ​ታም በራ​ሳ​ቸው ላይ ይሆ​ናል፤ ሐሤ​ት​ንና ደስ​ታ​ንም ያገ​ኛሉ፤ መከራ፥ ኀዘ​ንና ትካ​ዜም ይጠ​ፋሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="36">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በን​ጉሡ በሕ​ዝ​ቅ​ያስ በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የአ​ሦር ንጉሥ ሰና​ክ​ሬም ወደ ይሁዳ ወደ ተመ​ሸ​ጉት ከተ​ሞች ሁሉ ወጥቶ ወሰ​ዳ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ራፋ​ስ​ቂ​ስን ከብዙ ሠራ​ዊት ጋር ከለ​ኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ላከው፤ እር​ሱም በአ​ጣ​ቢው እርሻ መን​ገድ ባለ​ችው በላ​ይ​ኛ​ዪቱ ኵሬ መስኖ አጠ​ገብ ቆመ።</verse>
				<verse number="3">የቤ​ቱም አዛዥ የኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ ኤል​ያ​ቄም፥ ጸሓ​ፊ​ውም ሳም​ናስ፥ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እርሱ ወጡ።</verse>
				<verse number="4">ራፋ​ስ​ቂ​ስም አላ​ቸው፥ “ለሕ​ዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦ ታላቁ የአ​ሦር ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፦ በማን ትተ​ማ​መ​ና​ለህ?</verse>
				<verse number="5">በም​ክ​ርና በከ​ን​ፈር ንግ​ግር ጦር​ነት ይሆ​ና​ልን? አሁ​ንም በእኔ ላይ ያመ​ፅ​ኸው በማን ተማ​ም​ነህ ነው?</verse>
				<verse number="6">እነሆ፥ በዚያ በተ​ቀ​ጠ​ቀጠ በሸ​ን​በቆ በትር በግ​ብፅ ትታ​መ​ና​ለህ፤ ሰው ቢመ​ረ​ኰ​ዘው ተሰ​ብሮ በእጁ ይገ​ባል፤ የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን ለሚ​ታ​መ​ኑ​በት ሁሉ እን​ዲሁ ነው።</verse>
				<verse number="7">አን​ተም፦ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ታ​መ​ና​ለን ብትል፥ ሕዝ​ቅ​ያስ ይሁ​ዳ​ንና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ በዚህ መሥ​ዊያ ፊት ስገዱ ብሎ የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቹ​ንና መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹን ያስ​ፈ​ረሰ ይህ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="8">አሁን እን​ግ​ዲህ ከጌ​ታዬ ከአ​ሦር ንጉሥ ጋር ተስ​ማማ፤ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ው​ንም ሰዎች ማግ​ኘት ቢቻ​ልህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረ​ሶ​ችን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">ከታ​ና​ና​ሾቹ ከጌ​ታዬ አገ​ል​ጋ​ዮች የሚ​ያ​ን​ሰ​ውን የአ​ን​ዱን ጭፍራ ፊት መመ​ለስ እን​ዴት ትች​ላ​ለህ? ስለ ሰረ​ገ​ሎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች በግ​ብፅ የሚ​ታ​መኑ ለጌ​ታዬ ባሮች ናቸው።</verse>
				<verse number="10">አሁ​ንም በውኑ ያለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ እና​ጠ​ፋ​ችሁ ዘንድ ወደ​ዚህ ሀገር ዘም​ተ​ና​ልን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ ሀገ​ራ​ቸው ዘም​ታ​ችሁ አጥ​ፉ​አ​ቸው” አለን።</verse>
				<verse number="11">ኤል​ያ​ቄ​ምና ሳም​ናስ፥ ዮአ​ስም ራፋ​ስ​ቂ​ስን፥ “እኛ እን​ሰ​ማ​ለ​ንና እባ​ክህ፥ በሶ​ርያ ቋንቋ ለባ​ሪ​ያ​ዎ​ችህ ተና​ገር፤ በቅ​ጥ​ርም ላይ ባለው ሕዝብ ጆሮ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ አት​ና​ገ​ረን” አሉት።</verse>
				<verse number="12">ራፋ​ስ​ቂስ ግን፥ “ጌታዬ ይህን ቃል እና​ገር ዘንድ ወደ እና​ን​ተና ወደ ጌታ​ችሁ ልኮ​ኛ​ልን? ከእ​ና​ንተ ጋር ኵሳ​ቸ​ውን ይበሉ ዘንድ፥ ሽን​ታ​ቸ​ው​ንም ይጠጡ ዘንድ በቅ​ጥር ላይ ለተ​ቀ​መ​ጡት ሰዎች እነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ አይ​ደ​ለ​ምን?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">ራፋ​ስ​ቂ​ስም ቆሞ በታ​ላቅ ድምፅ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ እን​ዲህ ብሎ ጮኸ፥ “የታ​ላ​ቁን የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ቃል ስሙ።</verse>
				<verse number="14">ንጉሡ እን​ዲህ ይላል፦ ያድ​ና​ችሁ ዘንድ በማ​ይ​ችል ቃል ሕዝ​ቅ​ያስ አያ​ታ​ል​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="15">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ር​ግጥ ያድ​ና​ች​ኋል፤ ይህ​ችም ከተማ በአ​ሦር ንጉሥ እጅ አት​ሰ​ጥም አይ​በ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="16">ሕዝ​ቅ​ያ​ስ​ንም አት​ስሙ፤ የአ​ሦር ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፦ በሕ​ይ​ወት ልት​ኖሩ ብት​ወ​ድዱ ሁላ​ችሁ ወደ እኔ ውጡ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም ከወ​ይ​ና​ች​ሁና ከበ​ለ​ሳ​ችሁ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ከጕ​ድ​ጓ​ዳ​ች​ሁም ውኃ ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="17">ይህም መጥቼ ምድ​ራ​ች​ሁን ወደ​ም​ት​መ​ስ​ለው ምድር፥ እህ​ልና የወ​ይን ጠጅ፥ እን​ጀ​ራና ወይን ወዳ​ለ​ባት ምድር እስ​ካ​ፈ​ል​ሳ​ችሁ ድረስ ነው።</verse>
				<verse number="18">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ነ​ናል ብሎ አያ​ታ​ል​ላ​ችሁ። በውኑ የአ​ሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ሀገ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ አድ​ነ​ዋ​ቸ​ዋ​ልን?</verse>
				<verse number="19">የሐ​ማ​ትና የአ​ር​ፋድ አማ​ል​ክት ወዴት አሉ? ሰማ​ር​ያን ከእጄ አድ​ነ​ዋ​ታ​ልን?</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ከእጄ ያድን ዘንድ ከእ​ነ​ዚህ ሀገ​ሮች አማ​ል​ክት ሁሉ ሀገ​ሩን ከእጄ ያዳነ አለን?”</verse>
				<verse number="21">እነ​ር​ሱም ዝም አሉ፤ አን​ዳ​ችም አል​መ​ለ​ሱ​ለ​ትም፤ ንጉሡ እን​ዳ​ይ​መ​ል​ሱ​ለት አዝዞ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="22">የቤቱ አዛዥ የኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ ኤል​ያ​ቄም፥ የሠ​ራ​ዊቱ ጸሓፊ ሳም​ናስ፥ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሳፍ ልጅ ዮአስ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀድ​ደው ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ መጡ፤ የራ​ፋ​ስ​ቂ​ስ​ንም ቃል ነገ​ሩት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="37">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ንጉሡ ሕዝ​ቅ​ያስ ይህን በሰማ ጊዜ ልብ​ሱን ቀደደ፤ ማቅም ለበሰ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ገባ።</verse>
				<verse number="2">የቤ​ቱ​ንም አዛዥ ኤል​ያ​ቄ​ምን፥ ጸሓ​ፊ​ው​ንም ሳም​ና​ስን፥ የካ​ህ​ና​ቱ​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ማቅ ለብ​ሰው ወደ ነቢዩ ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ኢሳ​ይ​ያስ ይሄዱ ዘንድ ላካ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">እነ​ር​ሱም፥ “ሕዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመ​ከ​ራና የተ​ግ​ሣጽ፥ የዘ​ለ​ፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚ​ወ​ለ​ዱ​በት ጊዜ ደር​ሶ​አል፤ ለመ​ው​ለ​ድም ኀይል የለም።</verse>
				<verse number="4">ምና​ል​ባት በሕ​ያው አም​ላክ ላይ ይገ​ዳ​ደር ዘንድ ጌታው የአ​ሦር ንጉሥ የላ​ከ​ውን የራ​ፋ​ስ​ቂ​ስን ቃል አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰማ እንደ ሆነ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ሰማው ቃል ይገ​ሥ​ጸው እንደ ሆነ፥ ስለ​ዚህ ለቀ​ረው ቅሬታ ጸልይ” አሉት።</verse>
				<verse number="5">እን​ዲሁ የን​ጉሡ የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ብላ​ቴ​ኖች ወደ ኢሳ​ይ​ያስ በመጡ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="6">ኢሳ​ይ​ያስ፥ “ለጌ​ታ​ችሁ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ሦር ንጉሥ ባሪ​ያ​ዎች ስለ ሰደ​ቡኝ፥ ስለ ሰማ​ኸው ቃል አት​ፍራ።</verse>
				<verse number="7">እነሆ፥ መን​ፈ​ስን በላዩ እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ወሬ​ንም ይሰ​ማል፤ ወደ ምድ​ሩም ይመ​ለ​ሳል፤ በም​ድ​ሩም በሰ​ይፍ እን​ዲ​ወ​ድቅ አደ​ር​ጋ​ለሁ በሉት” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ከለ​ኪሶ እንደ ራቀ ሰምቶ ነበ​ርና ራፋ​ስ​ቂስ ተመ​ልሶ በል​ብና ሲዋጋ አገ​ኘው።</verse>
				<verse number="9">እር​ሱም፥ “የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንጉሥ ቲር​ሐቅ ሊዋ​ጋህ መጥ​ቶ​አል” የሚል ወሬ ሰማ። በሰ​ማም ጊዜ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እን​ዲህ ሲል፦</verse>
				<verse number="10">“ለይ​ሁዳ ንጉሥ ለሕ​ዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በአ​ሦር ንጉሥ እጅ አት​ሰ​ጥም ብሎ የም​ት​ታ​መ​ን​በት አም​ላ​ክህ አያ​ታ​ል​ልህ።</verse>
				<verse number="11">እነሆ፥ የአ​ሦር ነገ​ሥ​ታት በም​ድር ሁሉ ላይ ያደ​ረ​ጉ​ትን እን​ዴ​ትስ እን​ዳ​ጠ​ፉ​አ​ቸው አል​ሰ​ማ​ህ​ምን? አን​ተስ ትድ​ና​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="12">አባ​ቶች ያጠ​ፉ​አ​ቸ​ውን በቴ​ማን ያሉ​ትን ጎዛ​ን​ንና ካራ​ንን፥ ራፌ​ስ​ንም የአ​ሕ​ዛብ አማ​ል​ክት አዳ​ኑ​አ​ቸ​ውን?</verse>
				<verse number="13">የሔ​ማ​ትና የአ​ር​ፋድ፥ የሴ​ፈ​ር​ዋይ ከተማ፥ የሄ​ናና የዒዋ ነገ​ሥ​ታት ወዴት አሉ?”</verse>
				<verse number="14">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ደብ​ዳ​ቤ​ውን ከመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞች እጅ ተቀ​ብሎ አነ​በ​በው፤ ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወጥቶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዘረ​ጋው።</verse>
				<verse number="15">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ጸለየ፦</verse>
				<verse number="16">“አቤቱ፥ በኪ​ሩ​ቤል ላይ የም​ት​ቀ​መጥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ ሆይ፥ አንተ ብቻ​ህን የም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ አም​ላክ ነህ፤ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ፈጥ​ረ​ሃል።</verse>
				<verse number="17">አቤቱ፥ ጆሮ​ህን አዘ​ን​ብ​ልና ስማ፤ አቤቱ፥ ዐይ​ን​ህን ክፈ​ትና በሕ​ያው አም​ላክ ላይ ይገ​ዳ​ደር ዘንድ የላ​ከ​ውን የሰ​ና​ክ​ሬ​ምን ቃል ተመ​ል​ከት።</verse>
				<verse number="18">አቤቱ፥ በእ​ው​ነት የአ​ሦር ነገ​ሥ​ታት ዓለ​ሙን ሁሉ ሀገ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም አፍ​ር​ሰ​ዋል፤</verse>
				<verse number="19">አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት አቃ​ጥ​ለ​ዋል፤ የእ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ የሰው እጅ ሥራም ነበሩ እንጂ አማ​ል​ክት አል​ነ​በ​ሩ​ምና ስለ​ዚህ አጥ​ፍ​ተ​ዋ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="20">እን​ግ​ዲህ አም​ላ​ካ​ችን አቤቱ፥ የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ አንተ ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንህ ያውቁ ዘንድ ከእጁ አድ​ነን።”</verse>
				<verse number="21">የአ​ሞጽ ልጅ ኢሳ​ይ​ያ​ስም ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ተላከ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰና​ክ​ሬም ወደ እኔ የጸ​ለ​ይ​ኸ​ውን ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እርሱ የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው፦ ድን​ግ​ሊቱ የጽ​ዮን ልጅ ቀላል አድ​ር​ጋ​ሃ​ለች፤ በን​ቀ​ትም ሥቃ​ብ​ሃ​ለች፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ልጅ ራስ​ዋን ነቅ​ን​ቃ​ብ​ሃ​ለች።</verse>
				<verse number="23">የተ​ገ​ዳ​ደ​ር​ኸው፥ የሰ​ደ​ብ​ኸ​ውስ ማንን ነው? ቃል​ህ​ንስ ከፍ ከፍ ያደ​ረ​ግ​ህ​በት፥ ዐይ​ን​ህ​ንስ ወደ ላይ ያነ​ሣ​ህ​በት ማን ነው? በእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ላይ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="24">አን​ተም በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችህ በኩል እን​ዲህ ብለህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተገ​ዳ​ደ​ር​ኸው፦ በሰ​ረ​ገ​ላዬ ብዛት ወደ ተራ​ሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባ​ኖስ ራስ ወጥ​ቻ​ለሁ፤ ረዣ​ዥ​ሞ​ቹ​ንም ዝግ​ባ​ዎች፥ የተ​መ​ረ​ጡ​ት​ንም ጥዶች እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤ ወደ ከፍ​ታ​ውም ዳርቻ ወደ ዱሩ እገ​ባ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="25">ገድ​ቤም ውኃ​ው​ንና የው​ኃ​ውን ኩሬ አደ​ር​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="26">“እኔ ጥንት የሠ​ራ​ሁ​ትን አል​ሰ​ማ​ህ​ምን? እኔ በቀ​ድሞ ዘመን እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ሁት፥ አሁ​ንም አሕ​ዛ​ብን በም​ሽ​ጎ​ቻ​ቸው፥ በጽኑ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም ያጠፉ ዘንድ አዘ​ዝሁ።</verse>
				<verse number="27">እጃ​ቸ​ው​ንም አዝ​ላ​ለሁ፤ ይደ​ር​ቃ​ሉም፤ በሰ​ገ​ነት ላይ እን​ዳለ ደረቅ ሣርም ሳያ​ሸት ዋግ እንደ መታው እህ​ልም ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="28">አሁን ግን እኔ መቀ​መ​ጫ​ህ​ንና መው​ጫ​ህን፥ መግ​ቢ​ያ​ህ​ንም ዐው​ቄ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="29">የተ​ቈ​ጣ​ኸው ቍጣና ትዕ​ቢ​ትህ ወደ ጆሮዬ ደር​ሶ​አ​ልና ሰለ​ዚህ ስና​ጋ​ዬን በአ​ፍ​ን​ጫህ፥ ልጓ​ሜ​ንም በከ​ን​ፈ​ርህ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በመ​ጣ​ህ​በ​ትም መን​ገድ እመ​ል​ስ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="30">“ይህም ምል​ክት ይሆ​ን​ሃል፤ በዚህ ዓመት የዘ​ራ​ኸ​ውን፥ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ከገ​ቦው የበ​ቀ​ለ​ውን ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ትዘ​ራ​ላ​ቸሁ፤ ታጭ​ዱ​ማ​ላ​ችሁ፤ ወይ​ን​ንም ትተ​ክ​ላ​ላ​ችሁ፤ ፍሬ​ው​ንም ትበ​ላ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="31">ያመ​ለ​ጠው የይ​ሁዳ ቤት ቅሬታ ሥሩን ወደ ታች ይሰ​ድ​ዳል፤ ወደ ላይም ያፈ​ራል።</verse>
				<verse number="32">ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅሬታ ከጽ​ዮ​ንም ተራራ ያመ​ለ​ጡት ይድ​ና​ሉና፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅን​አት ይህን ያደ​ር​ጋል።</verse>
				<verse number="33">ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አሦር ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፦ ወደ​ዚች ከተማ አይ​መ​ጣም፤ ፍላ​ጻ​ንም አይ​ወ​ረ​ው​ር​ባ​ትም፤ በጋ​ሻም አይ​መ​ጣ​ባ​ትም፥ አያ​ጥ​ራ​ት​ምም።</verse>
				<verse number="34">በመ​ጣ​በ​ትም መን​ገድ በዚያ ይመ​ለ​ሳል፤ ወደ​ዚ​ህም ከተማ አይ​መ​ጣም ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤</verse>
				<verse number="35">ስለ እኔም፥ ስለ ባሪ​ያ​ዬም ስለ ዳዊት ይህ​ችን ከተማ እረ​ዳ​ታ​ለሁ አድ​ና​ታ​ለ​ሁም።”</verse>
				<verse number="36">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ወጣ፤ ከአ​ሦ​ራ​ው​ያ​ንም ሰፈር መቶ ሰማ​ንያ አም​ስት ሺህ ሰዎ​ችን ገደለ፤ ማለ​ዳም በተ​ነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉም በድ​ኖች ሆነው አገ​ኙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="37">የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ሰና​ክ​ሬም ተነ​ሥቶ ሄደ፤ ተመ​ል​ሶም በነ​ነዌ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="38">በአ​ም​ላ​ኩም በና​ሳ​ራክ ቤት ሲሰ​ግድ ልጆቹ አድ​ራ​ሜ​ሌ​ክና ሳራ​ሳር በሰ​ይፍ ገደ​ሉት፤ ወደ አራ​ራ​ትም ሀገር ኰበ​ለሉ። ልጁም አስ​ራ​ዶን በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="38">
				<verse number="1">በዚ​ያም ወራት ሕዝ​ቅ​ያስ ለሞት እስ​ኪ​ደ​ርስ ታመመ። ነቢ​ዩም የአ​ሞጽ ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ ወደ እርሱ መጥቶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ በሕ​ይ​ወት አት​ኖ​ር​ምና ቤት​ህን አስ​ተ​ካ​ክል” አለው።</verse>
				<verse number="2">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ፊቱን ወደ ግድ​ግ​ዳው መልሶ እን​ዲህ ሲል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለየ፦</verse>
				<verse number="3">“አቤቱ፥ በፊ​ትህ በእ​ው​ነ​ትና በቅን ልብ እንደ ሄድሁ፥ በፊ​ት​ህም ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ አስብ።” ሕዝ​ቅ​ያ​ስም እጅግ ታላቅ ልቅ​ሶን አለ​ቀሰ።</verse>
				<verse number="4">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ኢሳ​ይ​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፤</verse>
				<verse number="5">“ሂድ፤ ሕዝ​ቅ​ያ​ስን እን​ዲህ በለው፦ የአ​ባ​ትህ የዳ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጸሎ​ት​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፤ እን​ባ​ህ​ንም አይ​ቻ​ለሁ፤ እነሆ፥ በዕ​ድ​ሜህ ላይ ዐሥራ አም​ስት ዓመት እጨ​ም​ራ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="6">አን​ተ​ንና ይህ​ች​ንም ከተማ ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ አድ​ና​ለሁ፤ ለዚ​ችም ከተማ እቆ​ም​ላ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር እን​ዲ​ፈ​ጽ​መው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ምል​ክቱ ይህ ይሆ​ን​ል​ሃል።</verse>
				<verse number="8">እነሆ፥ በአ​ባ​ትህ የጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ ከፀ​ሐይ ጋራ የወ​ረ​ደ​ውን በደ​ረ​ጃ​ዎች ያለ​ውን ጥላ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እን​ዲ​መ​ለስ አደ​ር​ጋ​ለሁ።” ፀሐ​ይም በጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ የወ​ረ​ደ​በት ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="9">የይ​ሁዳ ንጉሥ ሕዝ​ቅ​ያስ ታምሞ ከደ​ዌው በተ​ፈ​ወሰ ጊዜ የጸ​ለ​የው ጸሎት ይህ ነው፦</verse>
				<verse number="10">እኔ እን​ዲህ አልሁ፥ “በሕ​ይ​ወት ዘመኔ መካ​ከል ወደ ሲኦል በሮች እገ​ባ​ለሁ፤ የቀ​ረ​ው​ንም ዘመ​ኔን ተውሁ።</verse>
				<verse number="11">ደግ​ሞም፦ በሕ​ያ​ዋን ምድር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማዳን፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም መዳን በም​ድር ላይ አላ​ይም፤ ከዘ​መ​ዶ​ችም ሰውን አላ​ይም።</verse>
				<verse number="12">የቀ​ረ​ው​ንም ኑሬ​ዬን አጣሁ። ከእ​ኔም ወጣች፥ ተለ​የ​ችም። ድን​ኳ​ኑን ተክሎ እን​ደ​ሚ​ያ​ድ​ርና እን​ደ​ሚ​ሄድ፥ ሊቈ​ረጥ እንደ ተቃ​ረበ ሸማም እን​ዲሁ ነፍሴ በላዬ ሆነች።</verse>
				<verse number="13">በዚያ ወራት እስ​ኪ​ነጋ ድረስ እንደ አን​በሳ ታወ​ክሁ፤ እን​ደ​ዚ​ሁም አጥ​ን​ቶች ተቀ​ጠ​ቀ​ጡ​ብኝ፤ ከማ​ለዳ ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ተጨ​ነ​ቅሁ።</verse>
				<verse number="14">እንደ ሸመላ እን​ዲሁ ጮህሁ፤ እንደ ርግ​ብም አጕ​ረ​መ​ረ​ምሁ፤</verse>
				<verse number="15">ዐይ​ኖች ደከሙ፤ ወደ ሰማ​ይም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማየት አል​ቻ​ል​ሁም። ጌታ ሆይ፦ ይቅር በለኝ፤ የሰ​ው​ነ​ቴ​ንም መከራ አር​ቅ​ልኝ።</verse>
				<verse number="16">ጌታ ሆይ፥ ስለ እር​ስዋ እን​ዲህ አል​ሁህ፤ ነፍ​ሴን አዳ​ን​ሃት፤ ደስ አለኝ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ኖርሁ።</verse>
				<verse number="17">ሰው​ነ​ቴ​ንም እን​ዳ​ት​ጠፋ ይቅር አል​ሃት፤ ኀጢ​አ​ቴ​ንም ሁሉ ወደ ኋላዬ ጣልህ።</verse>
				<verse number="18">በመ​ቃ​ብር የሚ​ኖሩ አያ​መ​ሰ​ግ​ኑ​ህ​ምና፤ ሙታ​ንም የሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑህ አይ​ደ​ሉ​ምና፤ በሲ​ኦ​ልም የሚ​ኖሩ ይቅ​ር​ታ​ህን ተስፋ አያ​ደ​ር​ጉ​ምና።</verse>
				<verse number="19">እኔ ዛሬ እን​ደ​ማ​ደ​ርግ ሕያ​ዋን ብቻ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፤ ከዛሬ ጀምሮ ጽድ​ቅ​ህን የሚ​ና​ገሩ ልጆ​ችን እወ​ል​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">ጌታዬ ሆይ አንተ መድ​ኀ​ኒቴ ነህ፤ ስለ​ዚህ በሕ​ይ​ወቴ ዘመን ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አው​ታር ባለው ዕቃ አን​ተን ማመ​ስ​ገ​ንን አላ​ቋ​ር​ጥም።”</verse>
				<verse number="21">ኢሳ​ይ​ያ​ስም ሕዝ​ቅ​ያ​ስን እን​ዲህ አለው፥ “የበ​ለስ ጥፍ​ጥፍ አም​ጥ​ተህ በእ​ባጩ ላይ ለብ​ጠው፤ አን​ተም ትፈ​ወ​ሳ​ለህ።”</verse>
				<verse number="22">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እወጣ ዘንድ ምል​ክቱ ምን​ድን ነው?” ብሎ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="39">
				<verse number="1">በዚ​ያም ወራት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ የባ​ል​ዳን ልጅ መሮ​ዳክ ባል​ዳን ሕዝ​ቅ​ያስ ታምሞ እንደ ተፈ​ወሰ ሰምቶ ነበ​ርና ደብ​ዳ​ቤና እጅ መን​ሻን፥ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ች​ንም ላከ​ለት።</verse>
				<verse number="2">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ስለ እነ​ርሱ እጅግ ደስ አለው፤ ግምጃ ቤቱ​ንም፥ ወር​ቁ​ንና ብሩን፥ ከር​ቤ​ው​ንና ዕጣ​ኑን፥ ዘይ​ቱ​ንም፥ መሣ​ሪ​ያም ያለ​በ​ትን ቤት ሁሉ፥ ልብ​ሱ​ንና ዕን​ቍ​ውን ሁሉ፥ በቤተ መዛ​ግ​ብ​ቱም የተ​ገ​ኘ​ውን ሁሉ አሳ​ያ​ቸው፤ በቤ​ቱና በግ​ዛቱ ሁሉ ካለው ሕዝ​ቅ​ያስ ያላ​ሳ​ያ​ቸው የለም።</verse>
				<verse number="3">ነቢ​ዩም ኢሳ​ይ​ያስ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ መጥቶ፥ “እነ​ዚህ ሰዎች ምን አሉ? ከወ​ዴ​ትስ መጡ?” አለው። ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “ከሩቅ ሀገር ከባ​ቢ​ሎን መጡ” አለው።</verse>
				<verse number="4">ኢሳ​ይ​ያ​ስም፥ “በቤ​ትህ ያዩት ምን​ድን ነው?” አለው፤ ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “በቤቴ ያለ​ውን ሁሉ አይ​ተ​ዋል፤ በቤቴ፥ እን​ዲ​ሁም በቤተ መዛ​ግ​ብቴ ካለው ያላ​ሳ​የ​ኋ​ቸው የለም” አለው።</verse>
				<verse number="5">ኢሳ​ይ​ያ​ስም ሕዝ​ቅ​ያ​ስን፥ “የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ።</verse>
				<verse number="6">እነሆ፥ በቤ​ትህ ያለው ሁሉ፥ አባ​ቶ​ች​ህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከ​ማ​ቹት ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን የሚ​ፈ​ል​ስ​በት ወራት ይመ​ጣል፤ ምንም አያ​ስ​ቀ​ሩ​ል​ህም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="7">ከአ​ንተ ከሚ​ወ​ጡት ከም​ት​ወ​ል​ዳ​ቸው ልጆ​ችህ ማር​ከው ይወ​ስ​ዳሉ፤ በባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ቤት ውስጥ ጃን​ደ​ረ​ቦ​ችና የቤት አሽ​ከ​ሮች ይሆ​ናሉ” አለው።</verse>
				<verse number="8">ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ኢሳ​ይ​ያ​ስን፥ “እርሱ የተ​ና​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል መል​ካም ነው፤ ነገር ግን፦ በዘ​መኔ ሰላ​ምና ጽድቅ ይሁን” አለው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="40">
				<verse number="1">አጽ​ናኑ፤ ሕዝ​ቤን አጽ​ናኑ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤</verse>
				<verse number="2">ካህ​ናት ሆይ፥ ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ልቧ የሚ​ገባ ነገ​ርን ተና​ገሩ፤ ውር​ደቷ እንደ ተፈ​ጸመ፥ ኀጢ​አ​ቷም እንደ ተሰ​ረየ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ ስለ ኀጢ​አቷ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀ​በ​ለች አጽ​ና​ኑ​አት።</verse>
				<verse number="3">የዐ​ዋጅ ነጋሪ ቃል በም​ድረ በዳ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ጥረጉ፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም ጎዳና በበ​ረሃ አስ​ተ​ካ​ክሉ።</verse>
				<verse number="4">ሸለ​ቆው ሁሉ ይሙላ፤ ተራ​ራ​ውና ኮረ​ብ​ታ​ውም ሁሉ ዝቅ ይበል፤ ጠማ​ማ​ውም ይቅና፤ ሰር​ጓ​ጕ​ጡም ሜዳ ይሁን፤</verse>
				<verse number="5">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ይገ​ለጥ፤ ሥጋ ለባ​ሹም ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትድ​ግና ይይ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።”</verse>
				<verse number="6">“ጩኽ” የሚል ሰው ቃል፤ “ምን ብዬ ልጩኽ?” አልሁ። “ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፤ የሰ​ውም ክብሩ ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነው።</verse>
				<verse number="7">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ት​ን​ፋስ ይነ​ፍ​ስ​በ​ታ​ልና ሣሩ ይደ​ር​ቃል፤ አበ​ባ​ውም ይረ​ግ​ፋል፤ በእ​ው​ነት ሕዝቡ ሣር ነው።</verse>
				<verse number="8">ሣሩ ይደ​ር​ቃል፤ አበ​ባ​ውም ይረ​ግ​ፋል፤ የአ​ም​ላ​ካ​ችን ቃል ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጸንቶ ይኖ​ራል።”</verse>
				<verse number="9">ለጽ​ዮን የም​ሥ​ራ​ችን የም​ት​ነ​ግር ሆይ፥ ከፍ ወዳ​ለው ተራራ ውጣ፤ ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ሥ​ራ​ችን የም​ት​ነ​ግር ሆይ፥ ድም​ፅ​ህን በኀ​ይል አንሣ፤ አት​ፍራ፤ ለይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች፦ እነሆ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ! ብለህ ንገር።</verse>
				<verse number="10">እነሆ፥ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኀ​ይሉ ይመ​ጣል፤ በክ​ን​ዱም ይገ​ዛል፤ እነሆ፥ ዋጋው ከእ​ርሱ ጋር ሥራ​ውም በፊቱ ነው።</verse>
				<verse number="11">መን​ጋ​ውን እንደ እረኛ ያሰ​ማ​ራል፤ ጠቦ​ቶ​ቹን በክ​ንዱ ሰብ​ስቦ በብ​ብቱ ይሸ​ከ​ማል፤ የሚ​ያ​ጠ​ቡ​ት​ንም በቀ​ስታ ይመ​ራል።</verse>
				<verse number="12">ውኆ​ችን በእ​ፍኙ የሰ​ፈረ፥ ሰማ​ይ​ንም በስ​ን​ዝሩ የለካ፥ ምድ​ር​ንም ሁሉ ሰብ​ስቦ በእጁ የያዘ፥ ተራ​ሮ​ችን በሚ​ዛን፥ ኮረ​ብ​ቶ​ች​ንም በሚ​ዛ​ኖች የመ​ዘነ ማን ነው?</verse>
				<verse number="13">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕሊና ያወቀ ወይስ አማ​ካሪ ሆኖ ያማ​ከ​ረው ማን ነው?</verse>
				<verse number="14">ወይስ ከማን ጋር ተመ​ካ​ከረ? ወይስ ማን መከ​ረው? ፍር​ድ​ንስ ማን አስ​ተ​ማ​ረው? የጥ​በ​ብ​ንስ መን​ገድ ማን አሳ​የው?</verse>
				<verse number="15">እነሆ፥ አሕ​ዛብ በገ​ንቦ እን​ዳ​ለች ጠብታ ናቸው፤ እንደ ሚዛ​ንም ውል​ብ​ል​ቢት ተቈ​ጥ​ረ​ዋል፤ እንደ ኢም​ን​ትም ናቸው።</verse>
				<verse number="16">ሊባ​ኖስ ለማ​ን​ደጃ እን​ስ​ሶ​ች​ዋም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አይ​በ​ቁም።</verse>
				<verse number="17">አሕ​ዛብ ሁሉ በፊቱ እን​ዳ​ል​ነ​በሩ ናቸው፤ እንደ ከንቱ ነገ​ርም ይመ​ስ​ላሉ።</verse>
				<verse number="18">እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በማን ትመ​ስ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስ​ተ​ያ​ዩ​ታ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="19">እን​ጨት ጠራቢ በሠ​ራው ምስል፥ ወይስ አን​ጥ​ረኛ መትቶ በሠ​ራው ወርቅ፥ በወ​ር​ቅም ለብጦ በሠ​ራው ምስል ትመ​ስ​ሉ​ታ​ላ​ች​ሁን?</verse>
				<verse number="20">ጠራ​ቢው የማ​ይ​ነ​ቅ​ዘ​ውን እን​ጨት ይመ​ር​ጣል፤ ምስ​ሉም እን​ዳ​ይ​ና​ወጥ ያቆ​መው ዘንድ ብልህ ሠራ​ተ​ኛን ይፈ​ል​ጋል።</verse>
				<verse number="21">አላ​ወ​ቃ​ች​ሁ​ምን? ወይስ አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምን? ከጥ​ን​ትስ አል​ተ​ወ​ራ​ላ​ች​ሁ​ምን? ወይስ ምድር ከተ​መ​ሠ​ረ​ተች ጀምሮ አላ​ስ​ተ​ዋ​ላ​ች​ሁ​ምን?</verse>
				<verse number="22">እርሱ የም​ድ​ርን ክበብ ያጸ​ናል፤ በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖ​ሩት እንደ አን​በጣ ናቸው፤ ሰማ​ያ​ትን እንደ መጋ​ረጃ የሚ​ዘ​ረ​ጋ​ቸው፥ እንደ ድን​ኳ​ንም ለመ​ኖ​ሪያ የሚ​ዘ​ረ​ጋ​ቸው፤</verse>
				<verse number="23">አለ​ቆ​ች​ንም የሚ​ገ​ዛ​ላ​ቸው እን​ዳ​ይ​ኖር የሚ​ያ​ደ​ርግ ምድ​ር​ንም እንደ ኢም​ንት የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት እርሱ ነው።</verse>
				<verse number="24">በእ​ር​ሱም ላይ ዛፉ​ንና ሣሩን፥ የማ​ይ​ቈ​ጠር ሌላ​ው​ንም ብዙ ፍጥ​ረት የፈ​ጠረ እርሱ ነው። ነፋ​ስም በነ​ፈ​ሰ​ባ​ቸው ጊዜ ይደ​ር​ቃሉ፤ ዐውሎ ነፋ​ስም እንደ ገለባ ይጠ​ር​ጋ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="25">እን​ግ​ዲህ እተ​ካ​ከ​ለው ዘንድ በማን መሰ​ላ​ች​ሁኝ? ይላል ቅዱሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="26">ዐይ​ና​ች​ሁን ወደ ሰማይ አን​ሥ​ታ​ችሁ ተመ​ል​ከቱ፤ ይህን ሁሉ የፈ​ጠረ ማን ነው? ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም በሙሉ የሚ​ቈ​ጥ​ራ​ቸው እርሱ ነው፤ በየ​ጊ​ዜ​ያ​ቸው ያመ​ጣ​ቸ​ዋል፤ ሁሉ​ንም በየ​ስ​ማ​ቸው ይጠ​ራ​ቸ​ዋል፤ በክ​ብሩ ብዛ​ትና በች​ሎቱ ብር​ታት አን​ድስ እንኳ አይ​ታ​ጣ​ውም።</verse>
				<verse number="27">ያዕ​ቆብ ሆይ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሆይ፥ መን​ገዴ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተሰ​ው​ራ​ለች፤ አም​ላ​ኬም ከእኔ ርቋል፤ ፍር​ዴ​ንም ትት​ዋል፤ ለምን ትላ​ለህ? ለም​ንስ እን​ዲህ ትና​ገ​ራ​ለህ?</verse>
				<verse number="28">አሁ​ንም አላ​ወ​ቅ​ህ​ምን? አል​ሰ​ማ​ህ​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዘ​ለ​ዓ​ለም አም​ላክ፥ የም​ድ​ር​ንም ዳርቻ የፈ​ጠረ አም​ላክ ነው፤ አይ​ራ​ብም፤ አይ​ጠ​ማም፤ አይ​ደ​ክ​ምም፤ ማስ​ተ​ዋ​ሉም አይ​መ​ረ​መ​ርም።</verse>
				<verse number="29">ለደ​ካ​ሞች ኀይ​ልን ይሰ​ጣል፤ መከራ የሚ​ቀ​በ​ሉ​ት​ንም አያ​ሳ​ዝ​ና​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="30">ብላ​ቴ​ኖች ይራ​ባሉ፤ ጐል​ማ​ሶች ይታ​ክ​ታሉ፤ ጐበ​ዛ​ዝ​ቱም ፈጽሞ ይዝ​ላሉ።</verse>
				<verse number="31">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉና የሚ​ታ​ገሡ ግን ኀይ​ላ​ቸ​ውን ያድ​ሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወ​ጣሉ፤ ይሮ​ጣሉ፤ አይ​ታ​ክ​ቱ​ምም፤ ይሄ​ዳሉ፤ አይ​ራ​ቡ​ምም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="41">
				<verse number="1">ደሴ​ቶች ሆይ፥ ወደ እኔ ተመ​ለሱ፤ አለ​ቆች ኀይ​ላ​ቸ​ውን ያድ​ሳ​ሉና በአ​ን​ድ​ነት ቀር​በው ፍር​ድን ይና​ገሩ።</verse>
				<verse number="2">ከም​ሥ​ራቅ ጽድ​ቅን ያስ​ነሣ፥ ይከ​ተ​ለ​ውም ዘንድ ወደ እግሩ የጠ​ራው ማን ነው? በአ​ሕ​ዛ​ብና በነ​ገ​ሥ​ታት ፊት ድን​ጋ​ጤን ያመ​ጣል። ጦሮ​ቻ​ቸ​ውን በም​ድር ያስ​ጥ​ላ​ቸ​ዋል፤ ቀስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እንደ ገለባ ይረ​ግ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="3">ያሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ልም፤ እግ​ሮ​ቹም በሰ​ላም መን​ገድ ይሄ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="4">ይህን የሠ​ራና ያደ​ረገ፥ ትው​ል​ድ​ንም ከጥ​ንት የጠራ ማን ነው? እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊተ​ኛ​ውና ኋለ​ኛው እኔ ነኝ።</verse>
				<verse number="5">አሕ​ዛብ አይ​ተው ፈሩ። የም​ድ​ርም ዳር​ቾች ቀረቡ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ቀረቡ፤ መጡም።</verse>
				<verse number="6">ሁሉም ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ይከ​ራ​ከ​ራል፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ ወን​ድሙ ይረ​ዳው ነበር፤ ወን​ድ​ሙ​ንም፦ አይ​ዞህ ይለው ነበር።</verse>
				<verse number="7">አና​ጢ​ውም አን​ጥ​ረ​ኛ​ውን፥ በመ​ዶ​ሻም የሚ​ያ​ሳ​ሳ​ውን መስፍ መች​ውን አጽ​ናና፤ ስለ ማጣ​በቅ ሥራ​ውም፥ “መል​ካም ነው” አለ፤ እን​ዳ​ይ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ስም በች​ን​ካር አጋ​ጠ​መው።</verse>
				<verse number="8">ባሪ​ያዬ እስ​ራ​ኤል፥ የመ​ረ​ጥ​ሁህ ያዕ​ቆብ፥ የወ​ዳጄ የአ​ብ​ር​ሃም ዘር ሆይ፥</verse>
				<verse number="9">አንተ ከም​ድር ዳርቻ የያ​ዝ​ሁህ፥ ከማ​ዕ​ዘ​ን​ዋም የጠ​ራ​ሁህ ነህና፦ አንተ ባሪ​ያዬ ነህ፤ መር​ጬ​ሃ​ለሁ፤ አል​ጥ​ል​ህም፤ ያል​ሁህ ሆይ፥</verse>
				<verse number="10">እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፤ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝና አት​ደ​ን​ግጥ፤ አበ​ረ​ታ​ሃ​ለሁ፤ እረ​ዳ​ህ​ማ​ለሁ፤ በጽ​ድ​ቄም ቀኝ ደግፌ እይ​ዝ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">እነሆ፥ የሚ​ቃ​ወ​ሙህ ሁሉ ያፍ​ራሉ፤ ይዋ​ረ​ዱ​ማል፤ እን​ዳ​ል​ነ​በ​ሩም ይሆ​ናሉ፤ ጠላ​ቶ​ች​ህም ይጠ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="12">የሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩ​ህ​ንም ሰዎች ትሻ​ቸ​ዋ​ለህ፤ አታ​ገ​ኛ​ቸ​ው​ምም፤ እን​ዳ​ል​ነ​በሩ ይሆ​ና​ሉና፤ የሚ​ዋ​ጋ​ህም የለም።</verse>
				<verse number="13">ቀኝ እጅ​ህን የያ​ዝ​ሁህ፥ እን​ዲ​ህም የም​ልህ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝና።</verse>
				<verse number="14">ያዕ​ቆብ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ በቍ​ጥር ጥቂት የነ​በ​ርህ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እኔ እረ​ዳ​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የሚ​ቤ​ዥ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ነው።</verse>
				<verse number="15">እነሆ፥ እንደ ተሳ​ለች እንደ አዲስ ባለ ጥርስ ማሄጃ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ ተራ​ሮ​ች​ንም ታሄ​ዳ​ለህ፤ ኮረ​ብ​ቶ​ች​ንም ታደ​ቅ​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ እንደ ገለ​ባም ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="16">ታበ​ጥ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ነፋ​ስም ይጠ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ ዐውሎ ነፋ​ስም ይበ​ት​ና​ቸ​ዋል፤ አን​ተም በእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ደስ ይል​ሃል።</verse>
				<verse number="17">ድሆ​ችና ምስ​ኪ​ኖች ውኃ ይሻሉ፤ አያ​ገ​ኙ​ምም፤ ምላ​ሳ​ቸ​ውም በጥ​ማት ደር​ቋል፤ እኔ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሰ​ማ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እኔ አል​ተ​ዋ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="18">በተ​ራ​ሮች ላይ ወን​ዞ​ችን፥ በሸ​ለ​ቆ​ችም መካ​ከል ምን​ጮ​ችን እከ​ፍ​ታ​ለሁ፤ ምድረ በዳ​ውን ለውኃ መቆ​ሚያ፥ የተ​ጠ​ማ​ች​ው​ንም ምድር ለውኃ መፍ​ለ​ቂያ አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">በም​ድረ በዳ ዝግ​ባ​ው​ንና ግራ​ሩን፥ ባር​ሰ​ነ​ቱ​ንና የዘ​ይ​ቱን ዛፍ አበ​ቅ​ላ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="20">ይኸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ይህን ሁሉ እንደ ሠራ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቅዱስ ይህን እንደ አሳየ ያውቁ ዘንድ፥ ያስ​ተ​ው​ሉም ዘንድ፥ ይረ​ዱም ዘንድ፥ ያም​ኑም ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="21">ፍር​ዳ​ችሁ ቀረ​በች፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ፤ ምክ​ራ​ች​ሁም ቀረበ፥ ይላል የያ​ዕ​ቆብ ንጉሥ።</verse>
				<verse number="22">ይምጡ፤ የሚ​ደ​ር​ስ​ባ​ች​ሁ​ንም ይን​ገ​ሩን፤ ልብም እና​ደ​ርግ ዘንድ፤ ፍጻ​ሜ​አ​ቸ​ው​ንም እና​ውቅ ዘንድ፥ የቀ​ደ​ሙት ነገ​ሮች ምን እንደ ሆኑ ንገ​ሩን፤ የሚ​መ​ጡ​ት​ንም አሳ​ዩን።</verse>
				<verse number="23">አማ​ል​ክ​ትም መሆ​ና​ች​ሁን እና​ውቅ ዘንድ በኋላ የሚ​መ​ጡ​ትን ተና​ገሩ፤ እና​ደ​ን​ቃ​ች​ሁም ዘንድ፥ በአ​ን​ድ​ነ​ትም እናይ ዘንድ መል​ካ​ሙን ወይም ክፉ​ውን አድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="24">እና​ንተ ከየት ናችሁ? ከየ​ትስ ሠሯ​ችሁ? ከም​ድር የሚ​መ​ር​ጧ​ች​ሁም የረ​ከሱ አይ​ደ​ሉ​ምን?</verse>
				<verse number="25">ከሰ​ሜ​ንና ከፀ​ሐይ መውጫ የሚ​መ​ጡ​ትን አስ​ነ​ሣሁ፤ በስ​ሜም ይጠ​ራሉ፤ አለ​ቆች ይምጡ፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃና ጭቃን እን​ደ​ሚ​ረ​ግጥ ሸክላ ሠሪ እን​ዲሁ ይረ​ግ​ጡ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="26">እና​ውቅ ዘንድ፥ ከጥ​ንት የተ​ነ​ገ​ረው፦ እው​ነት ነው እን​ልም ዘንድ ቀድሞ የተ​ና​ገ​ረው ማን ነው? ከመ​ሆኑ በፊት የሚ​ና​ገር የለም፤ የሚ​ገ​ል​ጥም የለም፤ ቃላ​ች​ሁን የሚ​ሰማ የለም።</verse>
				<verse number="27">በመ​ጀ​መ​ሪያ ለጽ​ዮን፦ ግዛ​ትን እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ወደ መን​ገ​ድዋ እመ​ል​ሳ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="28">ከአ​ሕ​ዛ​ብና ከአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸው የሚ​ና​ገር የለ​ምና፥ ከየ​ትም እንደ ሆኑ ብጠ​ይ​ቃ​ቸው አይ​መ​ል​ሱ​ል​ኝም።</verse>
				<verse number="29">የሚ​ሠ​ሩ​አ​ቸ​ውም በከ​ንቱ ይሠ​ሩ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="42">
				<verse number="1">እነሆ፥ ደግፌ የያ​ዝ​ሁት ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ፤ ነፍሴ የተ​ቀ​በ​ለ​ችው ምርጤ እስ​ራ​ኤ​ልም፤ በእ​ርሱ ላይ መን​ፈ​ሴን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ እር​ሱም ለአ​ሕ​ዛብ ፍር​ድን ያመ​ጣል።</verse>
				<verse number="2">አይ​ጮ​ኽም፤ ቃሉ​ንም አያ​ነ​ሣም፤ ድም​ፁ​ንም በሜዳ አያ​ሰ​ማም።</verse>
				<verse number="3">የተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ሸን​በ​ቆን አይ​ሰ​ብ​ርም፤ የሚ​ጤ​ስ​ንም ክር አያ​ጠ​ፋም፤ ነገር ግን በእ​ው​ነት ፍር​ድን ያመ​ጣል።</verse>
				<verse number="4">በም​ድ​ርም ፍር​ድን እስ​ኪ​ያ​ደ​ርግ ድረስ ያበ​ራል እንጂ አይ​ጠ​ፋም፤ አሕ​ዛ​ብም በስሙ ይታ​መ​ናሉ።</verse>
				<verse number="5">ሰማ​ይን የፈ​ጠረ፥ የዘ​ረ​ጋ​ውም፥ ምድ​ር​ንና በው​ስ​ጥዋ ያለ​ውን ሁሉ ያጸና፥ በእ​ር​ስዋ ላይ ለሚ​ኖሩ ሕዝብ እስ​ት​ን​ፋ​ስን፥ ለሚ​ሄ​ዱ​ባ​ትም መን​ፈ​ስን የሚ​ሰጥ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="6">“እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ በጽ​ድቅ ጠር​ቼ​ሃ​ለሁ፤ በእ​ጄም እይ​ዝ​ሃ​ለሁ፤ አበ​ረ​ታ​ሃ​ለ​ሁም፤ ለልጅ ልጅ ቃል ኪዳን፥ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ብር​ሃን አድ​ርጌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">የዕ​ው​ራ​ን​ንም ዐይን ትከ​ፍት ዘንድ፥ የተ​ጋ​ዙ​ት​ንም ከግ​ዞት ቤት፥ በጨ​ለ​ማም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከወ​ህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ።</verse>
				<verse number="8">እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው፤ ክብ​ሬን ለሌላ፥ ምስ​ጋ​ና​ዬ​ንም ለተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎች አል​ሰ​ጥም።</verse>
				<verse number="9">እነሆ የቀ​ድ​ሞው ነገር ተፈ​ጸመ፤ አዲስ ነገ​ር​ንም እና​ገ​ራ​ለሁ፤ አስ​ቀ​ድ​ሞም ሳይ​ነ​ገር እር​ሱን አስ​ታ​ው​ቃ​ች​ኋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="10">ወደ ባሕር የም​ት​ወ​ርዱ፥ በእ​ር​ስ​ዋም ውስጥ የም​ት​ጓዙ ሁሉ፥ ደሴ​ቶ​ችና በእ​ነ​ር​ሱም ላይ የም​ት​ኖሩ ሆይ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዲስ መዝ​ሙር ዘምሩ፤ ከም​ድ​ርም ዳርቻ ስሙን አክ​ብሩ።</verse>
				<verse number="11">ምድረ በዳ​ውና ከተ​ሞ​ችዋ፥ የቄ​ዳ​ርም ነዋ​ሪ​ዎ​ችና መን​ደ​ሮች ድም​ፃ​ቸ​ውን ያንሡ፤ በዋ​ሻም የሚ​ኖሩ እልል ይበሉ፤ በተ​ራ​ሮ​ችም ራስ ላይ ሆነው ይጩኹ።</verse>
				<verse number="12">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ርን ይስጡ፤ ምስ​ጋ​ና​ው​ንም በደ​ሴ​ቶች ይና​ገሩ።</verse>
				<verse number="13">የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይወ​ጣል፤ ኀይ​ለ​ኛ​ው​ንም ያጠ​ፋል፤ ቅን​አ​ት​ንም ያስ​ነ​ሣል፤ በጠ​ላ​ቶ​ቹም ላይ በኀ​ይል ይጮ​ኻል።</verse>
				<verse number="14">ከድሮ ዘመን ጀምሮ ዝም ብያ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዝም እላ​ለ​ሁን? አሁን ምጥ እንደ ያዛት ሴት እታ​ገ​ሣ​ለሁ፤ አጠ​ፋ​ለሁ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም እጨ​ር​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">ተራ​ሮ​ች​ንና ኮረ​ብ​ቶ​ችን አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ ቡቃ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አደ​ር​ቃ​ለሁ፤ ወን​ዞ​ች​ንም ደሴ​ቶች አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ኩሬ​ዎ​ች​ንም አደ​ር​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">ዕው​ሮ​ች​ንም በማ​ያ​ው​ቋት መን​ገድ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የማ​ያ​ው​ቋ​ት​ንም ጎዳና እን​ዲ​ረ​ግጡ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ጨለ​ማ​ውን ብር​ሃን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ጠማ​ማ​ው​ንም አቀ​ና​ለሁ። ይህ​ንም አደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አል​ተ​ዋ​ቸ​ው​ምም።</verse>
				<verse number="17">በተ​ቀ​ረ​ጹ​ትም ምስ​ሎች የሚ​ታ​መኑ፥ ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም ምስ​ሎች፥ “አም​ላ​ኮ​ቻ​ችን ናችሁ” የሚሉ ወደ ኋላ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ፤ ፈጽ​መ​ውም ያፍ​ራሉ።</verse>
				<verse number="18">እና​ንተ ደን​ቆ​ሮች፥ ስሙ፤ እና​ን​ተም ዕው​ሮች እዩ፤ ተመ​ል​ከ​ቱም።</verse>
				<verse number="19">ከባ​ሪ​ያ​ዎች በቀር ዕውር ማን ነው? ከአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውስ በቀር ደን​ቆሮ የሆነ ማን ነው? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪ​ያ​ዎች ታወሩ።</verse>
				<verse number="20">ብዙ ነገ​ርን ታያ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን አት​ጠ​ባ​በ​ቁ​ትም፤ ጆሮ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ተከ​ፍ​ተ​ዋል፤ ነገር ግን አት​ሰ​ሙም።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ምስ​ጋ​ና​ውን ያጸ​ድ​ቅና ከፍ ያደ​ርግ ዘንድ መከረ።</verse>
				<verse number="22">እነሆ፥ ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ ሕዝቡ የተ​በ​ዘ​በ​ዘና የተ​ዘ​ረፈ ነው፤ ወጥ​መድ በሁ​ሉም ቦታ በዋ​ሻ​ዎ​ችና እነ​ር​ሱን በሸ​ሸ​ጉ​ባ​ቸው ቤቶች ተጠ​ም​ዶ​አል፤ ብዝ​በዛ ሆነ​ዋል፤ የሚ​ያ​ድ​ንም የለም፤ ምር​ኮም ሆነ​ዋል፤ የሚ​ያ​ስ​ጥ​ላ​ቸ​ውም የለም።</verse>
				<verse number="23">ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ይህን የሚ​ያ​ደ​ምጥ፥ ለሚ​መ​ጣ​ውም ጊዜ የሚ​ሰማ ማን ነው?</verse>
				<verse number="24">ያዕ​ቆ​ብን እን​ዲ​ማ​ር​ኩት፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም እን​ዲ​በ​ዘ​ብ​ዙት ያደ​ረገ ማን ነው? እነ​ር​ሱም የበ​ደ​ሉት፥ በመ​ን​ገ​ዱም ይሄዱ ዘንድ ያል​ወ​ደ​ዱት፥ ሕጉ​ንም ያል​ሰ​ሙት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="25">ስለ​ዚህ የቍ​ጣ​ውን መዓ​ትና የሰ​ል​ፉን ጽናት አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸው አቃ​ጠ​ላ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን አላ​ወ​ቁም፤ በል​ባ​ቸ​ውም አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="43">
				<verse number="1">አሁ​ንም ያዕ​ቆብ ሆይ፥ የፈ​ጠ​ረህ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሆይ፥ የሠ​ራህ እግ​ዝ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ተቤ​ዥ​ች​ሃ​ለ​ሁና አት​ፍራ፤ በስ​ም​ህም ጠር​ቼ​ሃ​ለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ።</verse>
				<verse number="2">በውኃ ውስጥ ባለ​ፍህ ጊዜ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ ወን​ዞ​ችም አያ​ሰ​ጥ​ሙ​ህም፤ በእ​ሳ​ትም ውስጥ በሄ​ድህ ጊዜ አት​ቃ​ጠ​ልም፤ ነበ​ል​ባ​ሉም አይ​ፈ​ጅ​ህም።</verse>
				<verse number="3">እኔ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መድ​ኀ​ኒ​ትህ ነኝ፤ ግብ​ፅ​ንና ኢት​ዮ​ጵ​ያን ለአ​ንተ ቤዛ አድ​ርጌ፥ ሴዎ​ን​ንም ለአ​ንተ ፋንታ ሰጥ​ቻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">በፊቴ የከ​በ​ር​ህና የተ​መ​ሰ​ገ​ንህ ነህና፥ እኔም ወድ​ጄ​ሃ​ለ​ሁና ስለ​ዚህ ብዙ ሰዎ​ችን ለአ​ንተ ቤዛ፥ አለ​ቆ​ች​ንም ለራ​ስህ እሰ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፤ ዘር​ህ​ንም ከም​ሥ​ራቅ አመ​ጣ​ዋ​ለሁ፤ ከም​ዕ​ራ​ብም እሰ​በ​ስ​ብ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="6">ሰሜ​ንን፦ መል​ሰህ አምጣ፤ ደቡ​ብ​ምን፦ አት​ከ​ል​ክል፤ ወን​ዶች ልጆ​ችን ከሩቅ፥ ሴቶች ልጆ​ች​ንም ከም​ድር ዳርቻ፥</verse>
				<verse number="7">በስሜ የተ​ጠ​ራ​ውን ለክ​ብ​ሬም የፈ​ጠ​ር​ሁ​ትን፥ የሠ​ራ​ሁ​ት​ንና ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ሁሉ አምጣ” እለ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">ዐይ​ኖች እያ​ሉ​አ​ቸው የማ​ያዩ ዕው​ሮ​ችን ሕዝብ፥ ጆሮ​ችም እያ​ሉ​አ​ቸው የማ​ይ​ሰሙ ደን​ቆ​ሮ​ዎ​ችን አወ​ጣሁ።</verse>
				<verse number="9">አሕ​ዛብ ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​በ​ሰቡ፤ አለ​ቆ​ችም ተከ​ማቹ፤ ይህን ማን ይና​ገ​ራል? የቀ​ድ​ሞ​ው​ንስ ማን ይነ​ግ​ራ​ች​ኋል? ይጸ​ድቁ ዘንድ ምስ​ክ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ያምጡ፤ ሰም​ተ​ውም፦ እው​ነ​ትን ይና​ገሩ።</verse>
				<verse number="10">ታው​ቁና ታም​ኑ​ብኝ ዘንድ እኔም እንደ ሆንሁ ታስ​ተ​ውሉ ዘንድ፥ እና​ንተ፥ የመ​ረ​ጥ​ሁ​ትም ባሪ​ያዬ ምስ​ክ​ሮች ሁኑ፤ እኔም ምስ​ክር እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ፤ ከእኔ በፊት አም​ላክ አል​ነ​በ​ረም፤ ከእ​ኔም በኋላ አይ​ኖ​ርም።</verse>
				<verse number="11">እኔ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከእኔ ሌላ የሚ​ያ​ድን አም​ላክ የለም።</verse>
				<verse number="12">ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አድ​ኜ​ማ​ለሁ፤ መክ​ሬ​ማ​ለሁ፤ በእ​ና​ን​ተም ዘንድ ባዕድ አም​ልኮ አል​ነ​በ​ረም፤ ስለ​ዚህ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እንደ ሆንሁ እና​ንተ ራሳ​ችሁ ምስ​ክ​ሮች ናችሁ፤</verse>
				<verse number="13">ከጥ​ንት ጀምሮ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከእ​ጄም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም፤ እሠ​ራ​ለሁ፤ ወደ ኋላስ የሚ​መ​ልስ ማን ነው?</verse>
				<verse number="14">የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ፥ የሚ​ቤ​ዣ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ስለ እና​ንተ ወደ ባቢ​ሎን ሰድ​ጃ​ለሁ፤ ስደ​ተ​ኞ​ችን አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም በመ​ር​ከብ ውስጥ ይታ​ሰ​ራሉ።</verse>
				<verse number="15">ቅዱ​ሳ​ችሁ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ፈጣሪ፥ ንጉ​ሣ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እኔ ነኝ።”</verse>
				<verse number="16">በባ​ሕር ውስጥ መን​ገ​ድን በኀ​ይ​ለ​ኛም ውኃ ውስጥ መተ​ላ​ለ​ፊ​ያን ያደ​ረገ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እን​ዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰረ​ገ​ላ​ው​ንና ፈረ​ሱን ሠራ​ዊ​ቱ​ንና አር​በ​ኛ​ውን ያወ​ጣል፤ እነ​ርሱ ግን በአ​ን​ድ​ነት ተኝ​ተ​ዋል፤ አይ​ነ​ሡም፤ ቀር​ተ​ዋል፤ እንደ ጥዋፍ ኩስ​ታ​ሪም ጠፍ​ተ​ዋል፤</verse>
				<verse number="18">የፊ​ተ​ኛ​ውን ነገር አታ​ስ​ታ​ውሱ፤ የጥ​ን​ቱ​ንም ነገር አታ​ስቡ።</verse>
				<verse number="19">እነሆ፥ አዲስ ነገ​ርን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እር​ሱም አሁን ይበ​ቅ​ላል፤ እና​ን​ተም አታ​ው​ቁ​ትም፤ በም​ድረ በዳም መን​ገ​ድን፥ በበ​ረ​ሃም ወን​ዞ​ችን አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">የም​ድረ በዳ አራ​ዊት፥ ቀበ​ሮ​ችና ሰጎ​ኖች፥ ያከ​ብ​ሩ​ኛል። የመ​ረ​ጥ​ሁ​ትን ሕዝ​ቤን አጠጣ ዘንድ በም​ድረ በዳ ውኃን፥ በበ​ረ​ሃም ወን​ዞ​ችን ሰጥ​ቻ​ለ​ሁና፤</verse>
				<verse number="21">እነ​ር​ሱም ምስ​ጋ​ና​ዬን እን​ዲ​ና​ገሩ ለእኔ የፈ​ጠ​ር​ኋ​ቸው ሕዝብ ናቸው፤</verse>
				<verse number="22">ያዕ​ቆብ ሆይ፥ እነሆ፥ አል​ጠ​ራ​ሁ​ህም፤ አን​ተም እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ አል​ዘ​በ​ዘ​ብ​ሁ​ህም፤</verse>
				<verse number="23">ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በጎ​ች​ህን አላ​ቀ​ረ​ብ​ህ​ል​ኝም፤ በሌ​ላም በሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትህ አላ​ከ​በ​ር​ኸ​ኝም፤ በእ​ህ​ልም ቍር​ባን አላ​ስ​ቸ​ገ​ር​ሁ​ህም፤ በዕ​ጣ​ንም አላ​ደ​ከ​ም​ሁ​ህም።</verse>
				<verse number="24">ዕጣ​ንም በገ​ን​ዘብ አል​ገ​ዛ​ህ​ል​ኝም፤ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ት​ህ​ንም ስብ አል​ተ​መ​ኘ​ሁም፤ ነገር ግን በኀ​ጢ​አ​ት​ህና በበ​ደ​ልህ በፊቴ ቁመ​ሃል።</verse>
				<verse number="25">መተ​ላ​ለ​ፍን፦ ስለ እኔ ስለ ራሴ ስል የም​ደ​መ​ስስ እኔ ነኝ፤ ኀጢ​አ​ት​ህ​ንም አላ​ስ​ብም።</verse>
				<verse number="26">አሳ​ስ​በኝ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ሆነን እን​ፋ​ረድ፤ እን​ድ​ት​ጸ​ድቅ አስ​ቀ​ድ​መህ በደ​ል​ህን ተና​ገር።</verse>
				<verse number="27">በመ​ጀ​መ​ሪያ አባ​ቶ​ችህ፥ ቀጥ​ሎም አለ​ቆ​ችህ በድ​ለ​ው​ኛል።</verse>
				<verse number="28">አለ​ቆች መቅ​ደ​ሴን አረ​ከሱ፤ ስለ​ዚ​ህም ያዕ​ቆ​ብን ለጥ​ፋት፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ለው​ር​ደት ሰጠሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="44">
				<verse number="1">አሁ​ንም ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ የመ​ረ​ጥ​ሁ​ህም እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ።</verse>
				<verse number="2">የፈ​ጠ​ረህ ከማ​ኅ​ፀ​ንም የሠ​ራህ የሚ​ረ​ዳ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እን​ዲህ ይላል፥ “ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ የመ​ረ​ጥ​ሁ​ህም ወዳጄ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ አት​ፍራ።</verse>
				<verse number="3">በደ​ረቅ መሬት ላይ ለሚ​ሄ​ድና ለተ​ጠማ ውኃን እሰ​ጣ​ለሁ፤ መን​ፈ​ሴን በዘ​ርህ ላይ፥ በረ​ከ​ቴ​ንም በል​ጆ​ችህ ላይ አኖ​ራ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="4">በውኃ መካ​ከል እን​ዳለ ቄጠማ በፈ​ሳ​ሾ​ችም አጠ​ገብ እን​ደ​ሚ​በ​ቅሉ እንደ አኻያ ዛፎች ይበ​ቅ​ላሉ።</verse>
				<verse number="5">ይህ፦ እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ ይላል፤ ያም በያ​ዕ​ቆብ ስም ይጠ​ራል፤ ይህም፦ እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ ብሎ በእጁ ይጽ​ፋል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ስም ይጠ​ራል።”</verse>
				<verse number="6">የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ የሚ​ቤ​ዥም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ ፊተኛ ነኝ፤ እኔም ኋለኛ ነኝ፤ ከእኔ ሌላም አም​ላክ የለም።</verse>
				<verse number="7">እንደ እኔ ያለ አዳኝ ማን ነው? ይነ​ሣና ይጥራ፤ ይና​ገ​ርም፤ ሰውን ከፈ​ጠ​ር​ሁ​በት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለሙ የሚ​ሆ​ነ​ውን ያዘ​ጋ​ጅ​ልኝ፤ የሚ​መ​ጣ​ውም ነገር ሳይ​ደ​ርስ ይና​ገር።</verse>
				<verse number="8">ራሳ​ች​ሁን አት​ደ​ብቁ፤ ከጥ​ንት ጀምሮ አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምን? አል​ነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁ​ምን? ከእኔ ሌላ አም​ላክ እንደ ሌለ ምስ​ክ​ሮች ናችሁ።”</verse>
				<verse number="9">ጣዖ​ታ​ትን የሚ​ቀ​ርጹ ያን​ጊዜ አይ​ኖ​ሩም፤ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል የሚ​ሠ​ሩም ሁሉ ከን​ቱ​ዎች ናቸው፤ የማ​ይ​ረ​ባ​ቸ​ውን የራ​ሳ​ቸ​ውን ፍላ​ጎት የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ያፍ​ራሉ።</verse>
				<verse number="10">ጣዖ​ታ​ትን የሚ​ሠሩ፥ የማ​ይ​ጠ​ቅ​ማ​ቸ​ውን ምስል የሚ​ቀ​ር​ጹና በእ​ነ​ር​ሱም የተ​ሠሩ ሁሉ ይደ​ር​ቃሉ።</verse>
				<verse number="11">ከሰ​ዎች መካ​ከል ደን​ቆ​ሮ​ዎች ሁሉ ይሰ​ብ​ሰቡ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ይቁሙ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ያፍ​ራሉ፤ ይዋ​ረ​ዳ​ሉም።</verse>
				<verse number="12">ብረት ሠሪ መጥ​ረ​ቢ​ያ​ውን ይስ​ላል፤ ጣዖ​ቱን በመ​ጥ​ረ​ቢያ ይቀ​ር​ጸ​ዋል፤ በመ​ዶ​ሻም መትቶ ቅርጽ ይሰ​ጠ​ዋል፤ በክ​ን​ዱም ኀይል ይሠ​ራ​ዋል፤ እር​ሱም ይራ​ባል፤ ይደ​ክ​ም​ማል፤ ውኃም አይ​ጠ​ጣም።</verse>
				<verse number="13">ጠራ​ቢ​ውም እን​ጨት ቈርጦ በልኩ ያቆ​መ​ዋል፤ በማ​ጣ​በ​ቂ​ያም ያያ​ይ​ዘ​ዋል፤ በሰው አም​ሳ​ልና በሰው ውበት ያስ​መ​ስ​ለ​ዋል፤ በቤ​ትም ውስጥ ያቆ​መ​ዋል።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያበ​ቀ​ለ​ውን፥ በዝ​ና​ምም ያሳ​ደ​ገ​ውን ዛፍ ከዱር ይቈ​ር​ጣል።</verse>
				<verse number="15">ለሰ​ውም ማገዶ ይሆ​ናል፤ ከእ​ር​ሱም ወስዶ ይሞ​ቃል፤ አን​ድ​ዶም እን​ጀራ ይጋ​ግ​ር​በ​ታል፤ ከእ​ር​ሱም የተ​ረ​ፈ​ውን ጣዖ​ታ​ትን አበ​ጅቶ ይሰ​ግ​ድ​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="16">ግማ​ሹን በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላል፤ በዚ​ያም በግ​ማሹ ሥጋ ይጠ​ብ​ሳል፤ ጥብ​ሱ​ንም ይበ​ላና ይጠ​ግ​ባል፤ ይሞ​ቃ​ልና፥ “እሰይ ሞቅሁ፥ እሳ​ቱን አይ​ቻ​ለሁ” ይላል።</verse>
				<verse number="17">የቀ​ረ​ው​ንም እን​ጨት ጣዖት አድ​ርጎ ምስል ይቀ​ር​ጽ​በ​ታል፤ በፊ​ቱም ተጐ​ን​ብሶ ይሰ​ግ​ዳል፤ ወደ እር​ሱም እየ​ጸ​ለየ፥ “አም​ላኬ ነህና አድ​ነኝ” ይላል።</verse>
				<verse number="18">አያ​ው​ቁም፤ አያ​ስ​ቡም፤ እን​ዳ​ያዩ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው፥ እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉም ልቦ​ቻ​ቸው ተጋ​ር​ደ​ዋል።</verse>
				<verse number="19">ማንም በልቡ አያ​ስ​ብም፥ “ግማ​ሽ​ዋን በእ​ሳት አቃ​ጥ​ያ​ለሁ፤ በፍ​ም​ዋም ላይ እን​ጀ​ራን ጋግ​ሬ​አ​ለሁ፤ ሥጋም ጠብሼ በል​ቻ​ለሁ፤ የቀ​ረ​ው​ንም አስ​ጸ​ያፊ ነገር አደ​ር​ጋ​ለ​ሁን? ለዛ​ፍስ ግንድ እሰ​ግ​ዳ​ለ​ሁን? እን​ዲ​ልም ዕው​ቀ​ትና ማስ​ተ​ዋል የለ​ውም።</verse>
				<verse number="20">እን​ግ​ዲህ ልባ​ቸው አመድ እንደ ሆነና እንደ በደሉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ነፍ​ሱን ለማ​ዳን የሚ​ችል ማንም እን​ደ​ሌለ ዕወቁ፤ በቀኝ እጄ ሐሰት አለ” የሚ​ልም እን​ደ​ሌለ ተመ​ል​ከቱ።</verse>
				<verse number="21">ያዕ​ቆብ ሆይ፥ አን​ተም እስ​ራ​ኤል፥ አገ​ል​ጋዬ ነህና ይህን ዐስብ፤ እኔ ፈጥ​ሬ​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም ባሪ​ያዬ ነህ፤ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ አት​ር​ሳኝ።</verse>
				<verse number="22">መተ​ላ​ለ​ፍ​ህን እንደ ደመና፥ ኀጢ​አ​ት​ህ​ንም እንደ ጭጋግ ደም​ስ​ሼ​አ​ለሁ፤ ተቤ​ዥ​ች​ሃ​ለ​ሁና ወደ እኔ ተመ​ለስ።</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ምሕ​ረ​ትን አድ​ር​ጎ​አ​ልና ሰማ​ያት ደስ ይበ​ላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዕ​ቆ​ብን ተቤ​ዥ​ቶ​አ​ልና፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ይከ​በ​ራ​ልና የም​ድር መሠ​ረ​ቶች መለ​ከ​ትን ይንፉ፤ ተራ​ሮ​ችና ኮረ​ብ​ቶች በው​ስ​ጣ​ቸው ያሉ ዛፎች ሁሉ፥ እልል ይበሉ።</verse>
				<verse number="24">ከማ​ኅ​ፀን የሠ​ራህ፥ የሚ​ቤ​ዥህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሁሉን ለብ​ቻዬ የፈ​ጠ​ርሁ፥ ሰማ​ያ​ትን የዘ​ረ​ጋሁ፥ ምድ​ር​ንም ያጸ​ናሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ፤</verse>
				<verse number="25">በሟ​ርት ሙት እና​ስ​ነ​ሣ​ለን የሚ​ሉ​ትን፥ ከል​ባ​ቸ​ውም አን​ቅ​ተው ሐሰት የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን ሰዎች ምል​ክት የሚ​ለ​ውጥ ማን ነው? ጥበ​በ​ኞ​ቹ​ንም ወደ ኋላ ይመ​ል​ሳል፤ ምክ​ራ​ቸ​ው​ንም ስን​ፍና ያደ​ር​ጋል።</verse>
				<verse number="26">የባ​ር​ያ​ውን ቃል ያጸ​ናል፤ የመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹ​ንም ምክር ይፈ​ጽ​ማል። ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ የሰው መኖ​ሪያ ትሆ​ኛ​ለሽ፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም ከተ​ሞች ትታ​ነ​ጻ​ላ​ችሁ፤ ምድረ በዳ​ዎ​ች​ዋም ይለ​መ​ል​ማሉ፤” ይላል፤</verse>
				<verse number="27">ቀላ​ይ​ዋ​ንም፥ “ደረቅ ሁኚ ፈሳ​ሾ​ች​ሽም ይድ​ረቁ” ይላል፤</verse>
				<verse number="28">ቂሮ​ስ​ንም፥ “ብልህ ሁን፤ እር​ሱም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ ትታ​ነ​ጺ​ያ​ለሽ ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም እመ​ሠ​ር​ታ​ለሁ ብሎ ፈቃ​ዴን ሁሉ ይፈ​ጽ​ማል” ይላል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="45">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ለቀ​ባ​ሁት፥ አሕ​ዛ​ብ​ንም በፊቱ አስ​ገዛ ዘንድ የነ​ገ​ሥ​ታ​ት​ንም ኀይል እጥል ዘንድ፥ በሮ​ቹም እን​ዳ​ይ​ዘጉ መዝ​ጊ​ያ​ዎ​ቹን በፊቱ እከ​ፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያ​ዝ​ሁት ለቂ​ሮስ እን​ዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="2">“በፊ​ትህ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ተራ​ሮ​ች​ንም ዝቅ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የና​ሱ​ንም ደጆች እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ የብ​ረ​ቱ​ንም መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎች እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="3">በስ​ም​ህም የም​ጠ​ራህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨ​ለማ የነ​በ​ሩ​ትን መዛ​ግ​ብት እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ የማ​ይ​ታ​የ​ው​ንም የተ​ደ​በ​ቀ​ውን ሀብት እገ​ል​ጥ​ል​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">ስለ አገ​ል​ጋዬ ስለ ያዕ​ቆብ፥ ስለ መረ​ጥ​ሁ​ትም ስለ እስ​ራ​ኤል ብዬ በስ​ምህ ጠር​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ተቀ​በ​ል​ሁ​ህም፤ አንተ ግን አላ​ወ​ቅ​ኸ​ኝም።</verse>
				<verse number="5">እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነኝ፤ ከእ​ኔም በቀር ሌላ አም​ላክ የለም፤ አጸ​ና​ሁህ፤ አንተ ግን አላ​ወ​ቅ​ኸ​ኝም።</verse>
				<verse number="6">በፀ​ሐይ መው​ጫና በም​ዕ​ራብ ያሉ ከእኔ በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ያውቁ ዘንድ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነኝ፤ ከእ​ኔም ሌላ አም​ላክ የለም።</verse>
				<verse number="7">ብር​ሃ​ንን ፈጠ​ርሁ፤ ጨለ​ማ​ው​ንም ፈጠ​ርሁ፤ ሰላ​ም​ንም አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ክፋ​ት​ንም አመ​ጣ​ለሁ፤ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ያደ​ረ​ግሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ።</verse>
				<verse number="8">“ሰማይ በላይ ደስ ይበ​ለው፤ ደመ​ና​ትም ጽድ​ቅን ያዝ​ንቡ፤ ምድ​ርም መድ​ኀ​ኒ​ትን ታብ​ቅል፤ ጽድ​ቅም በአ​ን​ድ​ነት ይብ​ቀል፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ፈጥ​ሬ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">“እንደ ሸክላ ሠሪ ሥራ ውብ አድ​ርጌ ሠራ​ሁህ፤ ምድ​ርን የሚ​ያ​ርስ ሁል​ጊዜ ያር​ሳ​ልን? ጭቃ ሠሪ​ውን፦ ምን ትሠ​ራ​ለህ? እጅ የለ​ህ​ምና መሥ​ራት አት​ች​ልም ይለ​ዋ​ልን? ጭቃ ሠሪ​ውን ይከ​ራ​ከ​ረ​ዋ​ልን?</verse>
				<verse number="10">አባ​ቱን፦ ለምን ወለ​ድ​ኸኝ? እና​ቱ​ንም፦ ለምን አም​ጠሽ ወለ​ድ​ሽኝ? ለሚል ወዮ!</verse>
				<verse number="11">“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቅዱስ የሚ​መ​ጣ​ው​ንም የፈ​ጠረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እን​ዲህ ይላል፦ ስለ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች ጠይ​ቁኝ፤ ስለ እጄም ሥራ እዘ​ዙኝ።</verse>
				<verse number="12">እኔ ምድ​ርን ሠር​ቻ​ለሁ፤ ሰው​ንም በእ​ር​ስዋ ላይ ፈጥ​ሬ​አ​ለሁ፤ እኔ በእጄ ሰማ​ያ​ትን አጽ​ን​ቼ​አ​ለሁ፤ ከዋ​ክ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አዝ​ዣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">እኔ ቂሮ​ስን በጽ​ድቅ አስ​ነ​ሥ​ቼ​ዋ​ለሁ፤ መን​ገ​ዱ​ንም ሁሉ አቀ​ና​ለሁ፤ እርሱ ከተ​ማ​ዬን ይሠ​ራል፤ በዋ​ጋም ወይም በጉቦ ሳይ​ሆን ምር​ኮ​ኞ​ችን ያወ​ጣል፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”</verse>
				<verse number="14">የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ግብ​ፅና የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንግ​ዶች ደከሙ፤ ቁመተ ረዥ​ሞች የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያል​ፋሉ፤ ለአ​ን​ተም ይገ​ዙ​ል​ሃል፤ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ታስ​ረው በኋ​ላህ ይከ​ተ​ሉ​ሃል፤ በፊ​ት​ህም ያል​ፋሉ፤ ለአ​ን​ተም እየ​ሰ​ገዱ፦ በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው፤ ከእ​ር​ሱም ሌላ አም​ላክ የለም ብለው ይለ​ም​ኑ​ሃል።</verse>
				<verse number="15">አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነህ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መድ​ኀ​ኒት አም​ላክ እንደ ሆንህ አላ​ወ​ቅ​ን​ህም።</verse>
				<verse number="16">የሚ​ቃ​ወ​ሙት ሁሉም ያፍ​ራሉ፤ ይዋ​ረ​ዱ​ማል፤ አፍ​ረ​ውም ይሄ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="17">ደሴ​ቶች ሆይ፥ ወደ እኔ ተመ​ለሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እስ​ራ​ኤ​ልን በዘ​ለ​ዓ​ለ​ማዊ መድ​ኀ​ኒት ያድ​ነ​ዋል፤ እና​ን​ተም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አታ​ፍ​ሩ​ምና አቷ​ረ​ዱም።”</verse>
				<verse number="18">ሰማ​ይን የፈ​ጠረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እር​ሱም ምድ​ርን የሠ​ራና ያደ​ረገ ያጸ​ና​ትም፥ መኖ​ሪ​ያም ልት​ሆን እንጂ ለከ​ንቱ እን​ድ​ት​ሆን ያል​ፈ​ጠ​ራት አም​ላክ፥ እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለም።</verse>
				<verse number="19">በስ​ውር ወይም በጨ​ለማ ስፍራ አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁም፤ ለያ​ዕ​ቆብ ዘር፦ በከ​ንቱ ፈል​ጉኝ አላ​ል​ሁም፤ ጽድ​ቅን የም​ና​ገር፥ ቅን ነገ​ር​ንም የም​ና​ገር እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።</verse>
				<verse number="20">እና​ንተ ከአ​ሕ​ዛብ ወገን ሆና​ችሁ ያመ​ለ​ጣ​ችሁ፥ ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ ኑ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ተማ​ከሩ፤ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን የም​ስ​ላ​ቸ​ውን እን​ጨት የሚ​ሸ​ከ​ሙና ያድን ዘንድ ወደ​ማ​ይ​ችል አም​ላክ የሚ​ጸ​ልዩ ዕው​ቀት የላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="21">የሚ​ና​ገሩ ከሆነ ከጥ​ንት ጀምሮ ይህን ምስ​ክ​ር​ነት ያደ​ረገ ማን እንደ ሆነ በአ​ን​ድ​ነት ያውቁ ዘንድ ይቅ​ረቡ። ያሳ​የ​ሁም የተ​ና​ገ​ር​ሁም እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ከእ​ኔም በቀር ሌላ አም​ላክ የለም፤ እኔ ጻድቅ አም​ላ​ክና መድ​ኀ​ኒት ነኝ፥ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።</verse>
				<verse number="22">እና​ንተ በም​ድር ዳርቻ ያላ​ችሁ ሁሉ፥ እኔ አም​ላክ ነኝና፥ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለ​ምና ወደ እኔ ተመ​ለሱ፤ ትድ​ኑ​ማ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="23">ቃሌ ከአፌ በጽ​ድቅ ወጥ​ታ​ለች፤ አት​መ​ለ​ስ​ምም፤ ጕል​በት ሁሉ ለእኔ ይን​በ​ረ​ከ​ካል፤ ምላ​ስም ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይም​ላል ብዬ በራሴ ምያ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="24">ክብ​ርና ጽድቅ ወደ እርሱ ይመ​ጣሉ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ርቁ ሁሉ ያፍ​ራሉ።</verse>
				<verse number="25">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዘር ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ድ​ቃሉ፤ ይከ​ብ​ራ​ሉም ይባ​ላል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="46">
				<verse number="1">ቤል ወደቀ፤ ዳጎን ተሰ​ባ​በረ፤ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም እንደ ትቢያ ሆኑ፤ አራ​ዊ​ትና እን​ስ​ሳም ይረ​ግ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ እንደ ፋን​ድ​ያም ሸክም የሚ​ያ​ጸ​ይፉ ናቸ​ውና አያ​ነ​ሡ​አ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="2">ደካ​ሞች ናቸው፤ ኀይ​ልም የላ​ቸ​ውም፤ ከጦ​ር​ነ​ትም ራሳ​ቸ​ውን ለማ​ዳን አል​ቻ​ሉም፤ ራሳ​ቸው ግን ተማ​ረኩ።</verse>
				<verse number="3">እና​ንተ የያ​ዕ​ቆብ ቤት ሆይ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ቅሬታ ሁሉ፥ ከማ​ኅ​ፀ​ንም ጀምሮ የተ​ሸ​ከ​ም​ኋ​ችሁ፥ ከሕ​ፃ​ን​ነ​ትም ጀምሮ ያስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ችሁ፥ ስሙኝ።</verse>
				<verse number="4">እስከ ሽም​ግ​ልና ድረስ እኔ ነኝ፤ እስከ ሽበ​ትም ድረስ እኔ ነኝ፤ እኔ እታ​ገ​ሣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ ሠር​ቻ​ለሁ፤ እኔም ይቅር እላ​ለሁ፤ እኔም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">እን​ግ​ዲህ በማን ትመ​ስ​ሉ​ኛ​ላ​ችሁ? የም​ት​ሳ​ሳቱ እና​ንተ ሁላ​ችሁ፥ እዩ፤ አስ​ተ​ው​ሉም።</verse>
				<verse number="6">ወር​ቁ​ንና ብሩን ከኮ​ሮጆ የሚ​ያ​ወ​ጡና በሚ​ዛን የሚ​መ​ዝኑ እነ​ርሱ አን​ጥ​ረ​ኛ​ውን ይቀ​ጥ​ራሉ፤ እር​ሱም ጣዖት አድ​ርጎ ይሠ​ራ​ዋል፤ ለዚ​ያም ይጐ​ነ​በ​ሱ​ለ​ታል፤ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ት​ማል።</verse>
				<verse number="7">በጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ ተሸ​ክ​መ​ውት ይሄ​ዳሉ፤ በስ​ፍ​ራ​ውም በአ​ኖ​ሩት ጊዜ በዚያ ይቆ​ማል፤ ከስ​ፍ​ራ​ውም ፈቀቅ አይ​ልም፤ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮህ አይ​ሰ​ማ​ውም፤ ከክ​ፉም አያ​ድ​ነ​ውም።</verse>
				<verse number="8">ይህን ዐስ​ቡና አል​ቅሱ፤ የተ​ሳ​ሳ​ታ​ችሁ ሆይ፥ ንስሓ ግቡ፤ ልባ​ች​ሁ​ንም መልሱ።</verse>
				<verse number="9">እኔ አም​ላክ ነኝና፤ ያለ እኔም ሌላ የለ​ምና የቀ​ድ​ሞ​ው​ንና የጥ​ን​ቱን ነገር ዐስቡ። እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።</verse>
				<verse number="10">በመ​ጀ​መ​ሪያ መጨ​ረ​ሻ​ውን፥ ከጥ​ን​ትም ያል​ተ​ደ​ረ​ገ​ውን እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ምክሬ ትጸ​ና​ለች፤ የመ​ከ​ር​ሁ​ት​ንም ሁሉ አደ​ር​ጋ​ለሁ እላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">ከም​ሥ​ራ​ቅና ከሩቅ ሀገር ስለ መከ​ር​ሁት ምክር ዎፍን እጠ​ራ​ለሁ፤ ተና​ገ​ርሁ፤ አመ​ጣ​ሁም፤ ፈጠ​ርሁ፤ አደ​ረ​ግ​ሁም፤ አመ​ጣ​ሁት፤ መን​ገ​ዱ​ንም አቀ​ና​ሁ​ለት።</verse>
				<verse number="12">እና​ንተ ከጽ​ድቅ የራ​ቃ​ችሁ ልበ ጥፉ​ዎች፥ ስሙኝ፤</verse>
				<verse number="13">ጽድ​ቄን አመ​ጣ​ኋት፤ ከእኔ ዘንድ የም​ት​ገኝ መድ​ኀ​ኒ​ት​ንም አላ​ዘ​ገ​ይም፤ ከጽ​ዮን ለክ​ብር እን​ዲ​ሆን መድ​ኀ​ኒ​ትን ለእ​ስ​ራ​ኤል ሰጥ​ቻ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="47">
				<verse number="1">አንቺ ድን​ግል የባ​ቢ​ሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ፤ በት​ቢ​ያም ላይ ተቀ​መጪ፤ የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ ለስ​ላ​ሳና ቅም​ጥል አት​ባ​ዪ​ምና ያለ ዙፋን በመ​ሬት ላይ ተቀ​መጪ።</verse>
				<verse number="2">ወፍጮ ወስ​ደሽ ዱቄ​ትን ፍጪ፤ ክን​ብ​ን​ብ​ሽን ግለጪ፤ ሽበ​ትሽ ይታይ፤ ባት​ሽን ግለጪ፤ ወን​ዙ​ንም ተሻ​ገሪ።</verse>
				<verse number="3">ኀፍ​ረ​ትሽ ይገ​ለ​ጣል፤ ውር​ደ​ት​ሽም ይታ​ያል፤ ጽድቅ ከአ​ንቺ ይወ​ሰ​ዳል፤ እን​ዲ​ሁም በአ​ንቺ ፋንታ ሰውን አሳ​ልፌ አል​ሰ​ጥም።</verse>
				<verse number="4">ታዳ​ጊሽ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ስሙ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ነው።</verse>
				<verse number="5">የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ፥ “የመ​ን​ግ​ሥ​ታት እመ​ቤት” አት​ባ​ዪ​ምና በድ​ን​ጋጤ ዝም ብለሽ ተቀ​መጪ፤ ወደ ጨለ​ማም ውስጥ ግቢ።</verse>
				<verse number="6">በሕ​ዝቤ ላይ ተቈ​ጥቼ ነበር፤ ርስ​ቴ​ንም አረ​ከ​ስሽ፤ በእ​ጅ​ሽም አሳ​ልፌ ሰጠ​ኋ​ቸው፤ ለሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸው አል​ራ​ራ​ሽም፤ ቀን​በ​ራ​ቸ​ው​ንም እጅግ አክ​ብ​ደ​ሻል።</verse>
				<verse number="7">አን​ቺም፥ “እኔ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እመ​ቤት እሆ​ና​ለሁ” ብለ​ሻል፤ ይህ​ንም በል​ብሽ አላ​ሰ​ብ​ሽም፤ ፍጻ​ሜ​ው​ንም አላ​ስ​ታ​ወ​ስ​ሽም።</verse>
				<verse number="8">አሁ​ንም አንቺ ቅም​ጥል ተዘ​ል​ለሽ የም​ት​ቀ​መጪ፥ በል​ብ​ሽም፥ “እኔ ነኝ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለም፤ መበ​ለ​ትም ሆኜ አል​ኖ​ርም፤ የወ​ላድ መካ​ን​ነ​ት​ንም አላ​ው​ቅም” የም​ትዪ፥ ይህን ስሚ፤</verse>
				<verse number="9">አሁን ግን በአ​ንድ ቀን እነ​ዚህ ሁለት ነገ​ሮች በድ​ን​ገት ይመ​ጡ​ብ​ሻል፤ የወ​ላድ መካ​ን​ነ​ትና መበ​ለ​ት​ነት ስለ መተ​ቶ​ችሽ ብዛ​ትና ስለ አስ​ማ​ቶ​ችሽ ጽናት ፈጽ​መው ይመ​ጡ​ብ​ሻል።</verse>
				<verse number="10">በክ​ፋ​ትሽ ታም​ነ​ሻል፤ አንቺ ግን፥ “እኔ ነኝ፤ ከእኔ በቀር ሌላ የለም” ብለ​ሻል፤ በዝ​ሙ​ትሽ ኀፍ​ረት ያሰ​ብ​ሽ​ው​ንም ዕወቂ፤ በል​ብሽ፥ “እኔ ነኝ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለም” ብለ​ሻ​ልና።</verse>
				<verse number="11">ስለ​ዚህ ምክ​ን​ያት ጥፋት ይመ​ጣ​ብ​ሻል፤ ጥል​ቀ​ቱን አታ​ው​ቂም፤ በው​ስ​ጡም ትወ​ድ​ቂ​ያ​ለሽ፤ ጕስ​ቁ​ልና ይመ​ጣ​ብ​ሻል፤ ማም​ለ​ጥም አይ​ቻ​ል​ሽም፤ ሞት ድን​ገት ይመ​ጣ​ብ​ሻል፤ አታ​ው​ቂ​ምም።</verse>
				<verse number="12">ምና​ል​ባ​ትም ሊያ​ድ​ንሽ የሚ​ችል እንደ አለ፥ ከአ​ስ​ማ​ቶ​ች​ሽና ከሕ​ፃ​ን​ነ​ትሽ ጀም​ረሽ ከተ​ማ​ር​ሽው ከመ​ተ​ቶ​ችሽ ብዛት ጋር ቁሚ።</verse>
				<verse number="13">በክፉ ምክ​ርሽ ደክ​መ​ሻል፤ አሁ​ንም የሰ​ማ​ይን ከዋ​ክ​ብት የሚ​ቈ​ጥሩ፥ ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም የሚ​መ​ለ​ከቱ ይነሡ፤ ያድ​ኑ​ሽም፤ ምን እን​ደ​ሚ​መ​ጣ​ብ​ሽም ይን​ገ​ሩሽ፤</verse>
				<verse number="14">እነሆ፥ ሁሉም እንደ እብቅ እሳት ይቃ​ጠ​ላሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ከነ​በ​ል​ባል ኀይል አያ​ድ​ኑም፤ እንደ እሳ​ትም ፍም ይሆ​ኑ​ብ​ሻል፤ በላ​ያ​ቸ​ውም ትቀ​መ​ጫ​ለሽ።</verse>
				<verse number="15">እነ​ርሱ ረዳ​ቶ​ችሽ ይሆ​ናሉ፤ ከሕ​ፃ​ን​ነ​ትሽ ጀም​ረሽ ደከ​ምሽ፤ ሰው በራሱ ይሳ​ሳ​ታል፤ ለአ​ንቺ ግን መድ​ኀ​ኒት የለ​ሽም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="48">
				<verse number="1">እና​ንተ በእ​ስ​ራ​ኤል ስም የተ​ጠ​ራ​ችሁ፥ ከይ​ሁ​ዳም የወ​ጣ​ችሁ፥ በእ​ው​ነት ሳይ​ሆን፥ በጽ​ድ​ቅም ሳይ​ሆን እር​ሱን እየ​ጠ​ራ​ችሁ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የም​ት​ምሉ የያ​ዕ​ቆብ ቤት ሆይ፥ ይህን ስሙ፤</verse>
				<verse number="2">በቅ​ድ​ስት ከተማ ስም የተ​ጠ​ራ​ችሁ፥ ስሙም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ባል በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የም​ት​ደ​ገፉ፥ ይህን ስሙ።</verse>
				<verse number="3">የቀ​ድ​ሞ​ውን ነገር ከጥ​ንት ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ ከአ​ፌም ወጥ​ቶ​አል፤ ድን​ገ​ትም ያደ​ረ​ግ​ሁት ምስ​ክር ሆኖ​አል፤ እር​ሱም ተፈ​ጽ​ሞ​አል።</verse>
				<verse number="4">አንተ እል​ከኛ፥ አን​ገ​ት​ህም የብ​ረት ጅማት፥ ግን​ባ​ር​ህም ናስ እንደ ሆነ ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="5">ስለ​ዚህ፥ አንተ፥ “ጣዖቴ ይህን አድ​ር​ጎ​አል፤ የተ​ቀ​ረ​ጸው ምስ​ሌና ቀልጦ የተ​ሠ​ራው ምስ​ሌም ይህን አዘ​ዙኝ” እን​ዳ​ትል፥ የሚ​ሆ​ነ​ውን ከመ​ሆኑ በፊት ነገ​ር​ሁህ፤ አስ​ረ​ዳ​ሁ​ህም፤</verse>
				<verse number="6">ሁሉን ሰም​ተ​ሃ​ሃል፤ አላ​ወ​ቅ​ህም፤ ከዛሬ ጀምሮ የሚ​ሆ​ነ​ውን አዲስ ነገር ገለ​ጥ​ሁ​ልህ።</verse>
				<verse number="7">እነ​ር​ሱም አሁን እንጂ ከጥ​ንት አል​ተ​ፈ​ጠ​ሩም፤ አን​ተም፥ “እነሆ፥ ዐው​ቄ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ” እን​ዳ​ትል ከዛሬ በፊት አል​ሰ​ማ​ሃ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="8">አላ​ወ​ቅ​ህም፤ አላ​ስ​ተ​ዋ​ል​ህም፤ ጆሮ​ህን ከጥ​ንት አል​ከ​ፈ​ት​ሁ​ል​ህም፤ አንተ ፈጽሞ ወን​ጀ​ለኛ እንደ ሆንህ፥ ከማ​ኅ​ፀ​ንም ጀም​ረህ ተላ​ላፊ ተብ​ለህ እንደ ተጠ​ራህ ዐው​ቄ​አ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="9">ስለ ስሜ ቍጣ​ዬን አሳ​ይ​ሃ​ለሁ፤ እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋ​ህም ግር​ማ​ዬን አመ​ጣ​ብ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">እነሆ፥ ለወ​ጥ​ሁህ፤ ነገር ግን በብር አይ​ደ​ለም፤ ከመ​ከ​ራም እቶን አው​ጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">ስለ እኔ፥ ስለ ራሴ ይህን ለአ​ንተ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ስሜ ተነ​ቅ​ፎ​አ​ልና፤ ክብ​ሬ​ንም ለሌላ አል​ሰ​ጥም።</verse>
				<verse number="12">ያዕ​ቆብ ሆይ፥ የጠ​ራ​ሁ​ህም እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማኝ፤ እኔ ፊተ​ኛው ነኝ፤ እኔም ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ነኝ።</verse>
				<verse number="13">እጄም ምድ​ርን መሥ​ር​ታ​ለች፤ ቀኜም ሰማ​ያ​ትን አጽ​ን​ታ​ለች፤ እጠ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም መጥ​ተው ይቆ​ማሉ።</verse>
				<verse number="14">ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​ብ​ስ​በው ይሰ​ማሉ፤ ይህን ማን ነገ​ራ​ቸው? አን​ተን በመ​ው​ደድ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ዘር አስ​ወ​ግድ ዘንድ ፈቃ​ድ​ህን በባ​ቢ​ሎን ላይ አደ​ረ​ግሁ።</verse>
				<verse number="15">እኔ ራሴ ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ እኔ ጠር​ቼ​ዋ​ለሁ፤ አም​ጥ​ቼ​ዋ​ለሁ፤ መን​ገ​ዱም ትከ​ና​ወ​ን​ለ​ታ​ለች።</verse>
				<verse number="16">ወደ እኔ ቅረቡ፤ ይህ​ንም ስሙ፤ እኔ ከጥ​ንት ጀምሬ በስ​ውር አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁም፤ ከሆ​ነ​በት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበ​ርሁ፤ አሁ​ንም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና መን​ፈሱ ልከ​ው​ኛል።</verse>
				<verse number="17">ታዳ​ጊህ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ፥ እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ የሚ​ረ​ባ​ህን ነገር የማ​ስ​ተ​ም​ርህ የም​ት​ሄ​ድ​ባ​ት​ንም መን​ገድ እን​ዴት እን​ደ​ም​ታ​ገኝ የም​መ​ራህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።</verse>
				<verse number="18">ትእ​ዛ​ዜን ብት​ሰማ ኖሮ፥ ሰላ​ምህ እንደ ወንዝ ጽድ​ቅ​ህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር፤</verse>
				<verse number="19">ዘር​ህም እንደ አሸዋ የሆ​ድ​ህም ትው​ልድ እንደ ምድር ትቢያ በሆነ ነበር፤ አሁ​ንም ስምህ ከፊቴ ባል​ጠ​ፋና ባል​ፈ​ረሰ ነበር።</verse>
				<verse number="20">ከባ​ቢ​ሎን ውጡ፤ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ኰብ​ልሉ፤ በእ​ል​ልታ ድምፅ ተና​ገሩ፤ ይህም ይሰማ፤ እስከ ምድ​ርም ዳርቻ ድረስ አው​ሩና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባር​ያ​ውን ያዕ​ቆ​ብን ታድ​ጎ​ታል” በሉ።</verse>
				<verse number="21">በም​ድረ በዳም በተ​ጠሙ ጊዜ፥ ውኃን ከዓ​ለቱ ውስጥ ያፈ​ል​ቅ​ላ​ቸው ነበር፤ ዓለ​ቱም ተሰ​ነ​ጠቀ፤ ውኃ​ውም ይፈ​ስ​ስ​ላ​ቸው ነበር፤ ሕዝ​ቤም ይጠጡ ነበር።</verse>
				<verse number="22">እን​ግ​ዲህ ኃጥ​ኣን ደስታ አያ​ደ​ር​ጉም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="49">
				<verse number="1">ደሴ​ቶች ሆይ፥ ስሙኝ፤ እና​ን​ተም አሕ​ዛብ፥ አድ​ምጡ፤ ከረ​ዥም ዘመን በኋላ እን​ዲህ ይሆ​ናል ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከእ​ና​ቴም ሆድ ጀምሮ ስሜን ጠር​ቶ​አል፤</verse>
				<verse number="2">አፌ​ንም እንደ ተሳለ ሰይፍ አድ​ር​ጎ​አል፤ በእጁ ጥላ ሰው​ሮ​ኛል፤ እንደ ተሳለ ፍላ​ጻም አድ​ር​ጎ​ኛል፤ በሰ​ገ​ባው ውስ​ጥም ሸሽ​ጎ​ኛል።</verse>
				<verse number="3">እር​ሱም፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ አንተ ባር​ያዬ ነህ፤ በአ​ን​ተም እከ​በ​ራ​ለሁ” አለኝ።</verse>
				<verse number="4">እኔ ግን፥ “በከ​ንቱ ደከ​ምሁ፤ ምንም ጥቅም ለሌ​ለ​ውና ለከ​ንቱ ጕል​በ​ቴን ፈጀሁ፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ል​ኛል፤ መከ​ራ​ዬም በአ​ም​ላኬ ፊት ነው” አልሁ።</verse>
				<verse number="5">አሁ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከብ​ሬ​አ​ለ​ሁና፥ አም​ላ​ኬም ጕል​በት ሆኖ​ኛ​ልና ያዕ​ቆ​ብን ወደ እርሱ እን​ድ​መ​ልስ፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ወደ እርሱ እን​ድ​ሰ​በ​ስብ ባርያ እሆ​ነው ዘንድ ከማ​ኅ​ፀን ጀምሮ የፈ​ጠ​ረኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል።</verse>
				<verse number="6">እር​ሱም፥ “የያ​ዕ​ቆ​ብን ነገ​ዶች እን​ደ​ገና እን​ድ​ታ​ስ​ነሣ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የተ​በ​ተ​ኑ​ትን ወደ አባ​ቶች ቃል ኪዳን እን​ድ​ት​መ​ልስ ባር​ያዬ ትሆን ዘንድ ለአ​ንተ እጅግ ታላቅ ነገር ነውና፥ እስከ ምድር ዳር ድረስ መድ​ኀ​ኒት ትሆን ዘንድ ለአ​ሕ​ዛብ ብር​ሃን አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ” ይላል።</verse>
				<verse number="7">ታዳ​ጊህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሕይ​ወ​ቱን የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ትን፥ በአ​ሕ​ዛብ የተ​ጠ​ላ​ውን የአ​ለ​ቆ​ችን ባርያ ቀድ​ሱት፤ ነገ​ሥ​ታት ያዩ​ታል፤ አለ​ቆ​ችም ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብለው ተነ​ሥ​ተው ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መር​ጨ​ሃ​ለ​ሁና።”</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በተ​መ​ረ​ጠ​ችው ዕለት ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ድኅ​ነት በሚ​ደ​ረ​ግ​በ​ትም ቀን ረድ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ቃል ኪዳን አድ​ርጌ ለሕ​ዝቡ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ምድ​ር​ንም ታቀና ዘንድ፥ ውድማ የሆ​ኑ​ትን ርስ​ቶች ትወ​ርስ ዘንድ፤</verse>
				<verse number="9">የተ​ጋ​ዙ​ት​ንም፦ ውጡ፤ በጨ​ለ​ማም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን፦ ተገ​ለጡ፤ ትል ዘንድ።” በመ​ን​ገ​ድም ሁሉ ላይ ይሰ​ማ​ራሉ፤ ማሰ​ማ​ሪ​ያ​ቸ​ውም በጥ​ር​ጊያ ጎዳና ሁሉ ላይ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="10">የሚ​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም ያጽ​ና​ና​ቸ​ዋ​ልና፥ በውኃ ምን​ጮ​ችም በኩል ይመ​ራ​ቸ​ዋ​ልና አይ​ራ​ቡም፤ አይ​ጠ​ሙም፤ የፀ​ሐይ ትኩ​ሳ​ትም አይ​ጐ​ዳ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="11">ተራ​ሮ​ች​ንም ሁሉ መን​ገድ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ጎዳ​ና​ዎ​ችም ሁሉ መሰ​ማ​ርያ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="12">እነሆ፥ እነ​ዚህ ከሩቅ፥ እነ​ሆም፥ እነ​ዚህ ከሰ​ሜ​ንና ከም​ዕ​ራብ፥ እነ​ዚ​ህም ከፋ​ርስ ሀገር ይመ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ይቅር ብሎ​አ​ልና፥ ከሕ​ዝ​ቡም ችግ​ረ​ኞ​ቹን አጽ​ን​ቶ​አ​ልና። ሰማ​ያት ሆይ፥ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ምድ​ርም ደስ ይበ​ላት፤ ተራ​ሮ​ችም እልል ይበሉ።</verse>
				<verse number="14">ጽዮን ግን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቶ​ኛል፤ ጌታም ረስ​ቶ​ኛል” አለች።</verse>
				<verse number="15">“በውኑ ሴት፥ ልጅ​ዋን ትረ​ሳ​ለ​ችን? ከማ​ኅ​ፀ​ንዋ ለተ​ወ​ለ​ደ​ውስ አት​ራ​ራ​ምን? ሴት ይህን ብት​ረሳ፥ እኔ አን​ቺን አል​ረ​ሳ​ሽም።</verse>
				<verse number="16">እነሆ፥ እኔ በእጄ ግን​ቦ​ች​ሽን ሣልሁ፤ አን​ቺም ሁል​ጊዜ በፊቴ ነሽ።</verse>
				<verse number="17">ከአ​ፈ​ረ​ሱሽ በኋላ ፈጥ​ነሽ ትታ​ነ​ጺ​ያ​ለሽ፤ ያፈ​ረ​ሱሽ ከአ​ንቺ ይወ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="18">ዐይ​ን​ሽን አን​ሥ​ተሽ በዙ​ሪ​ያሽ ተመ​ል​ከቺ፤ እነ​ዚህ ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ። እኔ ሕያው ነኝና እነ​ዚ​ህን ሁሉ እንደ ጌጥ ትለ​ብ​ሻ​ቸ​ዋ​ለሽ፤ እንደ ሙሽ​ራም ትጐ​ና​ጸ​ፊ​አ​ቸ​ዋ​ለሽ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="19">ፈር​ሰ​ሻ​ልና፥ ፈጽ​መ​ሽም ጠፍ​ተ​ሻ​ልና በአ​ንቺ ለሚ​ኖሩ ሰዎች ዛሬ ጠባብ ትሆ​ኚ​ባ​ቸ​ዋ​ለሽ፤ ያጠ​ፉ​ሽም ከአ​ንቺ ይር​ቃሉ።</verse>
				<verse number="20">አጥ​ተ​ሻ​ቸው የነ​በ​ሩት ልጆ​ች​ሽም በጆ​ሮሽ፦ ስፍራ ጠብ​ቦ​ና​ልና የም​ን​ቀ​መ​ጥ​በት ቦታ አስ​ፊ​ልን ይላሉ።</verse>
				<verse number="21">አን​ቺም በል​ብሽ፦ የወ​ላድ መካን ሆኛ​ለ​ሁና፥ እኔም መበ​ለት ነኝና እነ​ዚ​ህን ማን ወለ​ደ​ልኝ? እነ​ዚ​ህ​ንስ ማን አሳ​ደ​ጋ​ቸው? እነሆ፥ ብቻ​ዬን ቀርቼ ነበር፤ እነ​ዚ​ህስ ከወ​ዴት መጡ?” ትያ​ለሽ።</verse>
				<verse number="22">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ እጄን ወደ አሕ​ዛብ አነ​ሣ​ለሁ፤ ዓር​ማ​ዬ​ንም ወደ ደሴ​ቶች አቆ​ማ​ለሁ፤ ወን​ዶች ልጆ​ች​ሽ​ንም በብ​ብ​ታ​ቸው ታቅ​ፈው ያመ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ ሴቶች ልጆ​ች​ሽ​ንም በጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="23">ነገ​ሥ​ታ​ትም አሳ​ዳ​ጊ​ዎች አባ​ቶ​ችሽ ይሆ​ናሉ፤ እቴ​ጌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ሞግ​ዚ​ቶ​ችሽ ይሆ​ናሉ፤ ግን​ባ​ራ​ቸ​ው​ንም ወደ ምድር ዝቅ አድ​ር​ገው ይሰ​ግ​ዱ​ል​ሻል፤ የእ​ግ​ር​ሽ​ንም ትቢያ ይል​ሳሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቂ​ያ​ለሽ፤ እኔ​ንም በመ​ተ​ማ​መን የሚ​ጠ​ባ​በቁ አያ​ፍ​ሩም።”</verse>
				<verse number="24">በውኑ ምር​ኮን ከኀ​ይ​ለኛ እጅ መቀ​ማት ይቻ​ላ​ልን? በግፍ የተ​ማ​ረ​ከስ ይድ​ና​ልን?</verse>
				<verse number="25">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እን​ዲህ ይላል፥ “በኀ​ያ​ላን የተ​ማ​ረኩ ይወ​ሰ​ዳሉ፤ የጨ​ካ​ኞ​ችም ብዝ​በዛ ያመ​ል​ጣል፤ እኔም ፍር​ድ​ሽን እፈ​ር​ድ​ል​ሻ​ለሁ፤ ልጆ​ች​ሽ​ንም አድ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="26">የአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎ​ች​ሽ​ንም ሥጋ​ቸ​ውን ይበ​ላሉ፤ እንደ ጣፋጭ ወይን ጠጅም ደማ​ቸ​ውን ጠጥ​ተው ይሰ​ክ​ራሉ፤ ሥጋ ለባ​ሹም ሁሉ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መድ​ኀ​ኒ​ት​ሽና ታዳ​ጊሽ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብን ኀይል የም​ደ​ግፍ እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="50">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እና​ታ​ች​ሁን የፈ​ታ​ሁ​በት የፍ​ችዋ ደብ​ዳቤ የት አለ? ወይስ እና​ን​ተን የሸ​ጥሁ ከአ​በ​ዳ​ሪ​ዎች ለማን ነው? እነሆ፥ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ ተሸ​ጣ​ች​ኋል፤ ስለ በደ​ላ​ች​ሁም እና​ታ​ችሁ ተፈ​ት​ታ​ለች።</verse>
				<verse number="2">እነሆ፥ መጣሁ፤ ሰውም አል​ነ​በ​ረም፤ ተጣ​ራሁ፤ የሚ​መ​ል​ስም አል​ነ​በ​ረም፤ እጄ ለማ​ዳን ጠን​ካራ አይ​ደ​ለ​ምን? ወይስ ለማ​ዳን አል​ች​ል​ምን? እነሆ፥ በገ​ሠ​ጽሁ ጊዜ ባሕ​ርን አደ​ር​ቃ​ለሁ፤ ወን​ዞ​ች​ንም ምድረ በዳ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ውኃም በማ​ጣት ዐሣ​ዎ​ቻ​ቸው ይሞ​ታሉ፤ በጥ​ማ​ትም ያል​ቃሉ።</verse>
				<verse number="3">ሰማ​ይን በጨ​ለማ እሸ​ፍ​ነ​ዋ​ለሁ፤ መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም ማቅ አደ​ር​ጋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="4">የም​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አውቅ ዘንድ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጥ​በብ ምላ​ስን ሰጥ​ቶ​ኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነ​ቃ​ኛል፤ ለመ​ስ​ማ​ትም ጆሮን ሰጥ​ቶ​ኛል።</verse>
				<verse number="5">የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተግ​ሣ​ጽም ጆሮ​ዬን ከፍ​ቶ​አል፤ እኔም ዐመ​ፀኛ አል​ነ​በ​ር​ሁም፤ አል​ተ​ከ​ራ​ከ​ር​ሁም።</verse>
				<verse number="6">ጀር​ባ​ዬን ለግ​ር​ፋት፥ ጕን​ጬ​ንም ለጽ​ፍ​ዐት ሰጠሁ፤ ፊቴ​ንም ከም​ራቅ ኀፍ​ረት አል​መ​ለ​ስ​ሁም።</verse>
				<verse number="7">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳኝ፤ ስለ​ዚ​ህም አላ​ፈ​ር​ሁም፤ ፊቴ​ንም እንደ ባል​ጩት ድን​ጋይ አድ​ር​ጌ​ዋ​ለሁ፤ እን​ዳ​ላ​ፍ​ርም አው​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">የሚ​ያ​ጸ​ድ​ቀኝ ቅርብ ነው፤ ከእ​ኔስ ጋር የሚ​ከ​ራ​ከር ማን ነው? እስቲ በእኔ ላይ ይነሣ፤ የሚ​ከ​ራ​ከ​ረ​ኝስ ማን ነው? ወደ እኔ ይቅ​ረብ።</verse>
				<verse number="9">እነሆ፥ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይረ​ዳ​ኛል፤ ማን ይጎ​ዳ​ኛል? እነሆ፥ ሁላ​ችሁ እንደ ልብስ ታረ​ጃ​ላ​ችሁ፤ ብልም ይበ​ላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="10">ከእ​ና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ፥ ማን ነው? የባ​ሪ​ያ​ው​ንም ቃል ይስማ፤ በጨ​ለ​ማም የም​ት​ሄዱ፥ ብር​ሃ​ንም የሌ​ላ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ታመኑ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተደ​ገፉ፤</verse>
				<verse number="11">እነሆ፥ እሳት የም​ታ​ነ​ድዱ፥ የእ​ሳ​ት​ንም ነበ​ል​ባል ከፍ ያደ​ረ​ጋ​ችሁ ሁላ​ችሁ፥ በእ​ሳ​ታ​ችሁ ብር​ሃ​ንና ባነ​ደ​ዳ​ች​ሁት ነበ​ል​ባል ሂዱ፤ ስለ እኔ ይህ ይሆ​ን​ባ​ች​ኋል፤ በኀ​ዘ​ንም ትተ​ኛ​ላ​ችሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="51">
				<verse number="1">እና​ንተ ጽድ​ቅን የም​ት​ከ​ተሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የም​ትሹ፥ ስሙኝ፤ የተ​ቈ​ረ​ጣ​ች​ሁ​በ​ትን ጽኑዕ ዓለት የተ​ቈ​ፈ​ራ​ች​ሁ​ባ​ት​ንም ጥልቅ ጕድ​ጓድ ተመ​ል​ከቱ።</verse>
				<verse number="2">ወደ አባ​ታ​ችሁ ወደ አብ​ር​ሃም፥ ወደ ወለ​ደ​ቻ​ች​ሁም ወደ ሳራ ተመ​ል​ከቱ፤ አንድ ብቻ​ውን በሆነ ጊዜ ጠራ​ሁት፤ ባረ​ክ​ሁ​ትም፤ ወደ​ድ​ሁ​ትም፤ አበ​ዛ​ሁ​ትም።</verse>
				<verse number="3">ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ደስ አሰ​ኝ​ሻ​ለሁ፤ ባድ​ማ​ሽ​ንም ሁሉ ደስ አሰ​ኛ​ለሁ፤ ምድረ በዳ​ሽ​ንም እንደ ዔድን፥ በረ​ሃ​ዎ​ች​ሽ​ንም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነት አደ​ር​ጋ​ለሁ። ደስ​ታና ተድላ እም​ነ​ትና የዝ​ማሬ ድምፅ በው​ስጧ ይገ​ኝ​ባ​ታል።</verse>
				<verse number="4">ሕዝቤ ሆይ፥ ስሙኝ፤ ስሙኝ፤ እና​ን​ተም ነገ​ሥ​ታት ተግ​ሣ​ጼን አድ​ም​ጡኝ፤ ሕግ ከእኔ ይወ​ጣ​ልና፥ ፍር​ዴም ለአ​ሕ​ዛብ ብር​ሃን ይሆ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="5">ጽድቄ ፈጥና ትመ​ጣ​ለች፤ ማዳ​ኔም እንደ ብር​ሃን ትደ​ር​ሳ​ለች፤ አሕ​ዛብ በክ​ንዴ ይታ​መ​ናሉ፤ ደሴ​ቶች እኔን ተስፋ ያደ​ር​ጋሉ፤ በክ​ን​ዴም ይታ​መ​ናሉ።</verse>
				<verse number="6">ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ሁን ወደ ሰማይ አንሡ፤ ወደ ታችም ወደ ምድር ተመ​ል​ከቱ፤ ሰማ​ያት እንደ ጢስ በን​ነው ይጠ​ፋሉ፤ ምድ​ርም እንደ ልብስ ታረ​ጃ​ለች፤ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም እን​ዲሁ ይሞ​ታሉ፤ ማዳ​ኔም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ናት፤ ጽድ​ቄም አታ​ል​ቅም።</verse>
				<verse number="7">ፍር​ድን የም​ታ​ውቁ፥ ሕጌም በል​ባ​ችሁ ያለ ሕዝብ ሆይ፥ ስሙኝ፤ የሰ​ዎ​ችን ስድ​ብና ማስ​ፈ​ራ​ራት አት​ፍሩ፤ አት​ሸ​ነ​ፉም።</verse>
				<verse number="8">እንደ ልብስ ፈጥ​ነው ያረ​ጃ​ሉና አይ​ቈ​ዩም፤ ብል እንደ በላ​ውም ይሆ​ናሉ፤ ጽድቄ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም፥ ማዳ​ኔም ለልጅ ልጅ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="9">ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ የክ​ን​ድ​ሽ​ንም ኀይል ልበሺ፤ እንደ ቀድ​ሞ​ውም ዘመን እንደ ጥንቱ ትው​ልድ ተነሺ።</verse>
				<verse number="10">ባሕ​ሩን ያደ​ረ​ቅሽ፥ ጥል​ቁ​ንም ውኃ ያደ​ረ​ቅ​ሽው፥ የዳ​ኑ​ትም ይሻ​ገሩ ዘንድ ጥል​ቁን ባሕር ጥር​ጊያ ጎዳና ያደ​ረ​ግሽ አይ​ደ​ለ​ሽ​ምን?</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቤ​ዣ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ፤ ወደ ጽዮ​ንም በደ​ስ​ታና በሐ​ሤት ይመ​ጣሉ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ክብር በራ​ሳ​ቸው ላይ ይሆ​ናል፤ ደስ​ታ​ንና ተድ​ላን ያገ​ኛሉ፤ ኀዘ​ንና ልቅ​ሶም ይወ​ገ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="12">እኔ ነኝ፤ የማ​ጽ​ና​ናሽ እኔ ነኝ፤ አንቺ እን​ግ​ዲህ ዕወቂ፤ ማንን ፈራሽ? የሚ​ሞ​ተ​ውን ሰው እንደ ሣርም የሚ​ጠ​ወ​ል​ገ​ውን የሰው ልጅ ነውን?</verse>
				<verse number="13">አንቺ ግን ሰማ​ያ​ትን የፈ​ጠ​ረ​ውን፥ ምድ​ር​ንም የመ​ሠ​ረ​ታ​ትን ፈጣ​ሪ​ሽን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረስ​ተ​ሻል፤ ያጠ​ፋሽ ዘንድ ባዘ​ጋጀ ጊዜ ከአ​ስ​ጨ​ና​ቂው ቍጣ የተ​ነሣ ሁል​ጊዜ ቀኑን ሁሉ ፈር​ተ​ሻል፤ ይቈ​ጣሽ ዘንድ መክ​ሮ​አ​ልና፤ አሁን የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቅሽ ቍጣው የት አለ?</verse>
				<verse number="14">ከዳ​ንሽ በኋላ እን​ግ​ዲህ አይ​ኖ​ር​ምና፥ አይ​ዘ​ገ​ይ​ም​ምና።</verse>
				<verse number="15">ባሕ​ርን የማ​ና​ውጥ፥ ሞገ​ዱም እን​ዲ​ተ​ምም የማ​ደ​ርግ አማ​ላ​ክሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝና፥ ስሜም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።</verse>
				<verse number="16">ቃሌን በአ​ፍሽ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ሰማ​ይን በዘ​ረ​ጋ​ሁ​በ​ትና ምድ​ርን በመ​ሠ​ረ​ት​ሁ​በት በእጄ ጥላ እጋ​ር​ድ​ሻ​ለሁ፤ ጽዮ​ን​ንም አንቺ ሕዝቤ ነሽ እላ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="17">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ የቍ​ጣ​ውን ጽዋ የጠ​ጣሽ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ቁሚ፤ የሚ​ያ​ን​ገ​ደ​ግ​ድ​ሽን የቍ​ጣ​ውን ጽዋ ጠጥ​ተ​ሻ​ልና፥ ጨል​ጠ​ሽ​ው​ማ​ልና።</verse>
				<verse number="18">ከወ​ለ​ድ​ሻ​ቸው ልጆ​ችሽ ሁሉ የሚ​ያ​ረ​ጋ​ጋሽ አጣሽ፤ ከአ​ሳ​ደ​ግ​ሻ​ቸ​ውም ልጆ​ችሽ ሁሉ እጁን ሰጥቶ የሚ​ያ​ነ​ሣሽ የለም።</verse>
				<verse number="19">አሁ​ንም እነ​ዚህ ሁለቱ ይጠ​ብ​ቁ​ሻል፤ ማን ያስ​ተ​ዛ​ዝ​ን​ሻል? እነ​ር​ሱም ጥፋ​ትና ውድ​ቀት ራብና ሰይፍ ናቸው፤ እን​ግ​ዲህ የሚ​ያ​ጽ​ና​ናሽ ማን ነው?</verse>
				<verse number="20">ልጆ​ችሽ ዝለ​ዋል፤ እንደ ጠወ​ለገ ቅጠ​ልም በየ​መ​ን​ገዱ ዳር ወድ​ቀ​ዋል፤ በአ​ም​ላ​ክሽ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣና ተግ​ሣጽ ተሞ​ል​ተ​ዋል።</verse>
				<verse number="21">ስለ​ዚ​ህም ያለ ወይን ጠጅ የሰ​ከ​ርሽ አንቺ የተ​ዋ​ረ​ድሽ፥ ይህን ስሚ፤</verse>
				<verse number="22">ለወ​ገኑ የሚ​ፈ​ርድ አም​ላ​ክሽ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ የሚ​ያ​ን​ገ​ደ​ግ​ድ​ሽን ጽዋ የቍ​ጣ​ዬ​ንም ጽዋ ከእ​ጅሽ ወስ​ጃ​ለሁ፤ ደግ​መ​ሽም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አት​ጠ​ጪ​ውም።</verse>
				<verse number="23">ወደ በደ​ሉ​ሽና ወደ አጐ​ሰ​ቈ​ሉሽ ሰዎች እጅ፥ ሰው​ነ​ት​ሽ​ንም ዝቅ በዪ፥ ድል​ድይ አድ​ር​ገን እን​ሻ​ገ​ር​ብሽ ወደ​ሚ​ሏት ሰዎች እጅ እመ​ል​ሰ​ዋ​ለሁ።” በም​ድ​ርም ላይ በሆ​ድሽ አስ​ተ​ኙሽ፤ መን​ገ​ደ​ኞ​ችም ሁሉ ረገ​ጡሽ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="52">
				<verse number="1">ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፤ ጽዮን ሆይ፥ ኀይ​ል​ሽን ልበሺ፤ አን​ቺም ቅድ​ስ​ቲቱ ከተማ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ያል​ተ​ገ​ረ​ዘና ርኩስ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ወደ አንቺ አያ​ል​ፍ​ምና ክብ​ር​ሽን ልበሺ።</verse>
				<verse number="2">ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ትቢ​ያን አራ​ግፊ፤ ተነሺ፥ ተቀ​መጪ፤ ምር​ኮ​ኛ​ዪቱ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ የአ​ን​ገ​ት​ሽን እስ​ራት ፍቺ።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በከ​ንቱ ተሸ​ጣ​ችሁ ነበር፤ ያለ ወር​ቅም እቤ​ዣ​ች​ኋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="4">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሕዝቤ አስ​ቀ​ድሞ ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዚ​ያም በስ​ደት ኖሩ፤ ከዚ​ያም ወደ አሦር በግድ ተወ​ሰዱ።</verse>
				<verse number="5">ሕዝቤ በከ​ንቱ ተወ​ስ​ዶ​አ​ልና አሁን ከዚህ ምን አቆ​ማ​ችሁ?” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “ታደ​ን​ቃ​ላ​ችሁ፤ ትጮ​ሃ​ላ​ች​ሁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ስሜም በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ሁል​ጊዜ ይሰ​ደ​ባል።</verse>
				<verse number="6">ስለ​ዚህ ሕዝቤ ስሜን ያው​ቃል፤ የም​ና​ገ​ርና ያለሁ እኔ እንደ ሆንሁ በዚያ ቀን ያው​ቃሉ።”</verse>
				<verse number="7">ሰላ​ምን የሚ​ያ​ወራ፥ መል​ካም የም​ሥ​ራ​ች​ንም የሚ​ና​ገር፥ መድ​ኀ​ኒ​ት​ንም የሚ​ያ​ወራ፥ ጽዮ​ን​ንም፥ “አም​ላ​ክሽ ነግ​ሦ​አል” የሚል ሰው እግሩ በተ​ራ​ሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው።</verse>
				<verse number="8">እነሆ፥ የሚ​ጠ​ብ​ቁሽ ሰዎች ድምፅ ከፍ ከፍ ይላ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጽዮ​ንን ይቅር ባላት ጊዜ ዐይን በዐ​ይን ይተ​ያ​ያ​ሉና በአ​ን​ድ​ነት በቃ​ላ​ቸው ደስ ይላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="9">የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ፍር​ስ​ራ​ሾች ደስ ይበ​ላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ብሎ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን አድ​ኖ​አ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ክን​ዱን በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ፊት ገል​ጦ​አል፤ በም​ድር ዳርቻ የሚ​ኖ​ሩ​ትም ሁሉ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ማዳን ያያሉ።</verse>
				<verse number="11">እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዕቃ የም​ት​ሸ​ከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፤ እልፍ በሉ፤ ከዚያ ውጡ፤ ርኩ​ስን ነገር አት​ንኩ፤ ከመ​ካ​ከ​ልዋ ውጡ፤ ራሳ​ች​ሁን ለዩ።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ታ​ችሁ ይሄ​ዳ​ልና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ይሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ልና በች​ኮላ አት​ወ​ጡም፤ በመ​ኮ​ብ​ለ​ልም አት​ሄ​ዱም።</verse>
				<verse number="13">እነሆ፥ አገ​ል​ጋዬ ያስ​ተ​ው​ላል፤ ከፍ ከፍ ይላል፥ ይከ​ብ​ራ​ልም፤ እጅ​ግም ደስ ይለ​ዋል።</verse>
				<verse number="14">ፊቱ ከሰ​ዎች ሁሉ ይልቅ፥ መል​ኩም ከሰ​ዎች ልጆች ይልቅ ያለ ክብር ነውና ብዙ ሰዎች ስለ እርሱ ያደ​ን​ቃሉ፤</verse>
				<verse number="15">ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ እር​ሱን ያደ​ን​ቃሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ትም አፋ​ቸ​ውን ይዘ​ጋሉ፤ ስለ እርሱ ያል​ተ​ወ​ራ​ላ​ቸው ያው​ቁ​ታ​ልና፥ ያል​ሰ​ሙ​ትም ያስ​ተ​ው​ሉ​ታ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="53">
				<verse number="1">ጌታ ሆይ፥ ነገ​ራ​ች​ንን ማን ያም​ነ​ናል? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ክንድ ለማን ተገ​ል​ጦ​አል?</verse>
				<verse number="2">ነገ​ራ​ችን በፊቱ እንደ ሕፃን፥ በደ​ረቅ መሬ​ትም እን​ዳለ ሥር ሆነ፤ መል​ክና ውበት የለ​ውም፤ እነሆ፥ አየ​ነው፤ ደም ግባት የለ​ውም፤ ውበ​ትም የለ​ውም።</verse>
				<verse number="3">መል​ኩም የተ​ናቀ፥ ከሰ​ውም ልጆች ሁሉ የተ​ዋ​ረደ፥ የተ​ገ​ረፈ ሰው፥ መከ​ራ​ንም የተ​ቀ​በለ ነው፤ ፊቱ​ንም መል​ሶ​አ​ልና አቃ​ለ​ሉት፥ አላ​ከ​በ​ሩ​ት​ምም።</verse>
				<verse number="4">እርሱ ግን በእ​ው​ነት ደዌ​ያ​ች​ንን ተቀ​በለ፤ ሕመ​ማ​ች​ን​ንም ተሸ​ከመ፤ ስለ እኛም ታመመ፤ እኛም እንደ ታመመ፥ እንደ ተገ​ረ​ፈም ቈጠ​ር​ነው።</verse>
				<verse number="5">እርሱ ግን ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ቈሰለ፤ ስለ በደ​ላ​ች​ንም ታመመ፤ የሰ​ላ​ማ​ች​ንም ተግ​ሣጽ በእ​ርሱ ላይ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ቍስል እኛ ተፈ​ወ​ስን።</verse>
				<verse number="6">እኛ ሁላ​ችን እንደ በጎች ተቅ​በ​ዝ​ብ​ዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ገዛ መን​ገዱ አዘ​ነ​በለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ለሞት አሳ​ልፎ ሰጠው።</verse>
				<verse number="7">እርሱ ግን በመ​ከ​ራው ጊዜ አፉን አል​ከ​ፈ​ተም፤ እንደ በግ ወደ መታ​ረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦ​ትም በሸ​ላ​ቾቹ ፊት ዝም እን​ደ​ሚል፥ እን​ዲሁ አፉን አል​ከ​ፈ​ተም።</verse>
				<verse number="8">በው​ር​ደቱ ፍርዱ ተወ​ገደ፤ ሕይ​ወቱ ከም​ድር ተወ​ግ​ዷ​ልና ልደ​ቱን ማን ይና​ገ​ራል? ስለ ሕዝቤ ኀጢ​አት ለሞት ደረሰ።</verse>
				<verse number="9">ክፉ​ዎ​ች​ንም ስለ መቃ​ብሩ፥ ባለ​ጸ​ጎ​ች​ንም ስለ ሞቱ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ኀጢ​አ​ትን አላ​ደ​ረ​ገ​ምና፥ ከአ​ፉም ሐሰት አል​ተ​ገ​ኘ​በ​ት​ምና።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ር​ፋቱ ያነ​ጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ብታ​ቀ​ርቡ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ረዥም ዕድሜ ያለ​ውን ዘር ታያ​ለች።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሰ​ው​ነቱ ሕማ​ምን ያርቅ ዘንድ ይወ​ዳል፤ ብር​ሃ​ን​ንም ያሳ​የ​ዋል፤ በጥ​በ​ቡም ይለ​የ​ዋል፤ ለጽ​ድ​ቅና ለበጎ ነገር የሚ​ገ​ዛ​ውን ጻድ​ቁን ያጸ​ድ​ቀ​ዋል። የብ​ዙ​ዎ​ች​ንም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን እርሱ ይደ​መ​ስ​ሳል።</verse>
				<verse number="12">ስለ​ዚ​ህም እርሱ ብዙ​ዎ​ችን ይወ​ር​ሳል፤ ከኀ​ያ​ላ​ንም ጋር ምር​ኮን ይከ​ፋ​ፈ​ላል፤ ነፍ​ሱን ለሞት አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና፥ ከዐ​መ​ፀ​ኞ​ችም ጋር ተቈ​ጥ​ሮ​አ​ልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎ​ችን ኀጢ​አት ተሸ​ከመ፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ተሰጠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="54">
				<verse number="1">አንቺ ያል​ወ​ለ​ድሽ መካን ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፤ አንቺ ያላ​ማ​ጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፤ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆ​ነ​ቺቱ ልጆች በዝ​ተ​ዋ​ልና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="2">የድ​ን​ኳ​ን​ሽን ስፍራ አስፊ፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ች​ሽ​ንም ዘርጊ፤ አት​ቈ​ጥቢ፤ አው​ታ​ሮ​ች​ሽን አስ​ረ​ዝሚ፤ ካስ​ሞ​ች​ሽ​ንም ትከዪ።</verse>
				<verse number="3">እንደ ገና​ም​በ​ቀ​ኝና በግራ ተስ​ፋፊ፤ ዘርሽ አሕ​ዛ​ብን ይወ​ር​ሳ​ሉና፥ የፈ​ረ​ሱ​ት​ንም ከተ​ሞች መኖ​ሪያ ታደ​ር​ጊ​ያ​ለ​ሽና።</verse>
				<verse number="4">አታ​ፍ​ሪ​ምና አት​ፍሪ፤ አቷ​ረ​ጂ​ምና አት​ደ​ን​ግጪ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም እፍ​ረ​ት​ሽ​ንም ትረ​ሺ​ዋ​ለሽ፤ የመ​በ​ለ​ት​ነ​ት​ሽ​ንም ስድብ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አታ​ስ​ቢም።</verse>
				<verse number="5">ፈጣ​ሪሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ስሙም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ታዳ​ጊሽ ነው፤ እር​ሱም በም​ድር ሁሉ እን​ደ​ዚሁ ይጠ​ራል።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተተ​ወ​ችና እንደ ተበ​ሳ​ጨች፥ በል​ጅ​ነ​ቷም እንደ ተጠ​ላች ሴት የጠ​ራሽ አይ​ደ​ለም፥ ይላል አም​ላ​ክሽ።</verse>
				<verse number="7">ጥቂት ጊዜ ተው​ሁሽ፤ በታ​ላቅ ምሕ​ረ​ትም ይቅር እል​ሻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">በጥ​ቂት ቍጣ ፊቴን ከአ​ንቺ ሰወ​ርሁ፤ በዘ​ለ​ዓ​ለም ቸር​ነት ይቅር እል​ሻ​ለሁ፥ ይላል ታዳ​ጊሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="9">ከኖኅ ዘመን ውኃ ጀምሮ ይህ ለእኔ ምስ​ክር ነው፤ ቀድሞ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ምድ​ርን እን​ዳ​ል​ቈ​ጣት እንደ ማልሁ፥</verse>
				<verse number="10">ተራ​ሮ​ችን እን​ዳ​ል​ቀ​ሥ​ፋ​ቸው እን​ዳ​ላ​ፈ​ል​ሳ​ቸ​ውም፥ ኮረ​ብ​ቶ​ችም እን​ዳ​ይ​ነ​ዋ​ወጡ እንደ ማልሁ እን​ዲሁ ከእኔ ዘንድ ያለሽ ይቅ​ርታ አያ​ል​ቅም፤ የሰ​ላ​ምሽ ቃል ኪዳ​ንም አይ​ጠ​ፋም፤ መሓ​ሪሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="11">አንቺ የተ​ቸ​ገ​ርሽ የተ​ና​ወ​ጥሽ ያል​ተ​ጽ​ና​ና​ሽም፥ እነሆ፥ ድን​ጋ​ዮ​ች​ሽን የሚ​ያ​በሩ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ መሠ​ረ​ት​ሽ​ንም የሰ​ን​ፔር አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">ግን​ብ​ሽ​ንም በቀይ ዕንቍ፥ በሮ​ች​ሽ​ንም ቢረሌ በተ​ባለ ዕንቍ፥ ዳር​ቻ​ዎ​ች​ሽ​ንም በከ​በረ ዕንቍ እሠ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">ልጆ​ች​ሽም ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ማሩ ይሆ​ናሉ፤ ልጆ​ች​ሽም በብዙ ሰላም ይኖ​ራሉ።</verse>
				<verse number="14">እነሆ፥ በጽ​ድቅ ትታ​ነ​ጺ​ያ​ለሽ፤ ከግፍ ራቂ፤ አት​ፈ​ሪም፤ ድን​ጋ​ጤም ወደ አንቺ አይ​ቀ​ር​ብም።</verse>
				<verse number="15">እነሆ፥ መጻ​ተ​ኞች በእኔ ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፤ በአ​ን​ቺም ይማ​ጸ​ናሉ።</verse>
				<verse number="16">እነሆ፥ ፍሙን በወ​ናፍ እን​ደ​ሚ​ያ​ናፋ፥ ለሥ​ራ​ውም መሣ​ሪያ እን​ደ​ሚ​ያ​ወጣ ብረት ሠሪ የፈ​ጠ​ር​ሁሽ አይ​ደ​ለም፤ እኔ ግን ለመ​ል​ካም ፈጠ​ር​ሁሽ እንጂ ለጥ​ፋት አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="17">በአ​ንቺ ላይ የተ​ሠራ መሣ​ሪያ ሁሉ እን​ዲ​ከ​ና​ወን አላ​ደ​ር​ግም፤ በአ​ንቺ ላይ ለፍ​ርድ የሚ​ነ​ሣ​ውን ድምፅ ሁሉ ታጠ​ፊ​ያ​ለሽ፤ ጠላ​ቶ​ች​ሽም ሁሉ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ርስት አላ​ቸው፤ ጻድ​ቃ​ኔም ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="55">
				<verse number="1">እና​ንተ የተ​ጠ​ማ​ችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ሂዱ፤ ገን​ዘ​ብም የሌ​ላ​ችሁ ሂዱና ግዙ፤ ብሉ፤ ያለ ገን​ዘ​ብም ያለ ዋጋም የወ​ይን ጠጅና ወተት ጠጡ።</verse>
				<verse number="2">ገን​ዘ​ብን እን​ጀራ ላይ​ደለ፥ የድ​ካ​ማ​ች​ሁ​ንም ዋጋ ለማ​ያ​ጠ​ግብ ነገር ለምን ትመ​ዝ​ና​ላ​ችሁ? አድ​ም​ጡኝ፤ በረ​ከ​ት​ንም ብሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁም በበ​ረ​ከት ደስ ይበ​ለው።</verse>
				<verse number="3">ስሙኝ፤ ጎዳ​ና​ዬን ተከ​ተሉ፤ አድ​ም​ጡ​ኝም፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁም በበ​ረ​ከት ትኖ​ራ​ለች፤ የታ​መ​ነ​ች​ዪ​ቱን የዳ​ዊ​ትን ምሕ​ረት፥ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምን ቃል ኪዳን ከእ​ና​ንተ ጋር አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">እነሆ፥ ለአ​ሕ​ዛብ ምስ​ክር፥ ለወ​ገ​ኖ​ችም አለ​ቃና አዛዥ እን​ዲ​ሆን አደ​ረ​ግ​ሁት።</verse>
				<verse number="5">እነሆ፥ የማ​ያ​ው​ቁህ ሕዝብ ይጠ​ሩ​ሃል፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ አክ​ብ​ሮ​ሃ​ልና ስለ አም​ላ​ክህ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የማ​ያ​ው​ቁህ ሕዝብ በአ​ንተ ይማ​ጠ​ናሉ።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ገ​ኝ​በት ጊዜ ፈል​ጉት፤ ቀር​ቦም ሳለ ጥሩት፤</verse>
				<verse number="7">ክፉ ሰው መን​ገ​ዱን፥ በደ​ለ​ኛም ዐሳ​ቡን ይተው፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ለስ፤ እር​ሱም ይም​ረ​ዋል፤ እርሱ ብዙ በደ​ላ​ች​ሁን ይተ​ው​ላ​ች​ኋ​ልና።</verse>
				<verse number="8">ዐሳቤ እንደ ዐሳ​ባ​ችሁ፥ መን​ገ​ዴም እንደ መን​ገ​ዳ​ችሁ አይ​ደ​ለ​ምና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="9">ሰማይ ከም​ድር እን​ደ​ሚ​ርቅ፥ እን​ዲሁ መን​ገዴ ከመ​ን​ገ​ዳ​ችሁ፥ ዐሳ​ቤም ከዐ​ሳ​ባ​ችሁ የራቀ ነው።</verse>
				<verse number="10">ብዙ ዝና​ምና በረዶ ከሰ​ማይ እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ፥ ምድ​ርን እን​ደ​ሚ​ያ​ረ​ካት፥ ታበ​ቅ​ልና ታፈ​ራም ዘንድ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጋት፥ ዘርን ለሚ​ዘራ፥ እህ​ል​ንም ለም​ግብ እን​ደ​ሚ​ሰጥ እንጂ ወደ ሰማይ እን​ደ​ማ​ይ​መ​ለስ፥</verse>
				<verse number="11">ከአፌ የሚ​ወጣ ቃሌ እን​ዲሁ ነው፤ የም​ሻ​ውን እስ​ኪ​ያ​ደ​ርግ ድረስ ወደ እኔ በከ​ንቱ አይ​መ​ለ​ስም፤ መን​ገ​ዴ​ንና ትእ​ዛ​ዜን አከ​ና​ው​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">እና​ን​ተም በደ​ስታ ትወ​ጣ​ላ​ችሁ፤ በሐ​ሤ​ትም ትማ​ራ​ላ​ችሁ፤ ተራ​ሮ​ችና ኮረ​ብ​ቶች በደ​ስታ ሊቀ​በ​ሏ​ችሁ ይዘ​ላሉ፤ የሜ​ዳም ዛፎች ሁሉ በቅ​ር​ን​ጫ​ፎ​ቻ​ቸው ያጨ​በ​ጭ​ባሉ።</verse>
				<verse number="13">በእ​ሾ​ህም ፋንታ ጥድ፥ በኵ​ር​ን​ች​ትም ፋንታ ባር​ሰ​ነት ይበ​ቅ​ላል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም ለዘ​ለ​ዓ​ለም በማ​ይ​ጠፋ ምል​ክት ይመ​ሰ​ገ​ናል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="56">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ማዳኔ ሊመጣ ምሕ​ረ​ቴም ሊገ​ለጥ ቀር​ቦ​አ​ልና ፍር​ድን ጠብቁ፤ ጽድ​ቅ​ንም አድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="2">ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ በእ​ር​ሱም ጸንቶ የሚ​ኖር፥ ሰን​በ​ታ​ት​ንም የሚ​ጠ​ብ​ቅና የማ​ያ​ረ​ክስ፥ እጁ​ንም ክፋት ከማ​ድ​ረግ የሚ​ጠ​ብቅ ሰው ብፁዕ ነው።”</verse>
				<verse number="3">ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ጠጋ መጻ​ተኛ፥ “በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሕ​ዝቡ ይለ​የ​ኛል” አይ​በል፤ ጃን​ደ​ረ​ባም፥ “እነሆ፥ እኔ እንደ ደረቀ ዛፍ ነኝ” አይ​በል።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጃ​ን​ደ​ረ​ቦች እን​ዲህ ይላል፥ “ሰን​በ​ቴን ቢጠ​ብቁ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ኝ​ንም ነገር ቢመ​ርጡ፥ በቃል ኪዳ​ኔም ጸን​ተው ቢኖሩ፥</verse>
				<verse number="5">በቤ​ቴና በቅ​ጥሬ ውስጥ ከወ​ን​ዶ​ችና ከሴ​ቶች ልጆች ይልቅ የሚ​በ​ልጥ ስም የሚ​ያ​ስ​ጠራ ቦታን እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የማ​ይ​ጠፋ የዘ​ለ​ዓ​ለም ስም​ንም እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="6">ከሌ​ላም ሕዝብ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ለ​ሱ​ትን ለእ​ር​ሱም ባሪ​ያ​ዎች የሆ​ኑ​ትን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም የወ​ደ​ዱ​ትን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎቹ የሆ​ኑ​ትን፥ “ሰን​በ​ታ​ቴን የሚ​ጠ​ብ​ቁ​ት​ንና የማ​ያ​ረ​ክ​ሱ​ትን፥ በቃል ኪዳ​ኔም ጸን​ተው የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ፥</verse>
				<verse number="7">ወደ ተቀ​ደሰ ተራ​ራዬ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በጸ​ሎ​ቴም ቤት ደስ አሰ​ኛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቤቴ ለአ​ሕ​ዛብ ሁሉ የሚ​ሆን የጸ​ሎት ቤት ይባ​ላ​ልና፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውና ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም በመ​ሠ​ዊ​ያዬ ላይ የተ​መ​ረጠ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="8">ከእ​ስ​ራ​ኤል የተ​በ​ተ​ኑ​ትን የሚ​ሰ​በ​ስብ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ ተሰ​በ​ሰ​ቡት ሌሎ​ችን እሰ​በ​ስ​ብ​ለ​ታ​ለሁ” ይላል።</verse>
				<verse number="9">እና​ንተ የም​ድረ በዳ አራ​ዊት ሁሉ ኑ፤ እና​ንተ የዱር አራ​ዊት ሁሉ ብሉ።</verse>
				<verse number="10">ሁሉም ዕው​ራን እንደ ሆኑ ኑና እዩ፤ ሁሉ ያለ ዕው​ቀት ናቸው፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው፤ ይጮ​ኹም ዘንድ አይ​ች​ሉም፤ በመ​ኝ​ታ​ቸ​ውም ሕል​ምን ያል​ማሉ፤ ማን​ቀ​ላ​ፋ​ት​ንም ይወ​ድ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="11">ሁሉም ከቶ የማ​ይ​ጠ​ግቡ የረ​ከሱ ውሾች ናቸው፤ እነ​ር​ሱም ያስ​ተ​ውሉ ዘንድ የማ​ይ​ችሉ ክፉ​ዎች ናቸው፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው እንደ ፈቃ​ዳ​ቸው መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለ​ዋል።</verse>
				<verse number="12">ኑ፤ የወ​ይን ጠጅ እን​ው​ሰድ፤ በሚ​ያ​ሰ​ክ​ርም መጠጥ እን​ርካ፤ ዛሬም እንደ ሆነ እን​ዲሁ ነገ ይሆ​ናል፤ ከዛ​ሬም ይልቅ እጅግ ይበ​ል​ጣል ይላሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="57">
				<verse number="1">ጻድቅ ሰው እን​ደ​ጠፋ አያ​ችሁ፤ ይህ​ንም በል​ባ​ችሁ አላ​ሰ​ባ​ች​ሁም፤ ጻድ​ቃን ሰዎች ይወ​ገ​ዳሉ፤ ጻድ​ቅም ከክ​ፋት ፊት እንደ ተወ​ገደ ማንም አያ​ስ​ተ​ው​ልም።</verse>
				<verse number="2">መቃ​ብሩ በሰ​ላም ይሆ​ናል፤ ከመ​ካ​ከ​ልም ይወ​ሰ​ዳል።</verse>
				<verse number="3">እና​ንተ የኃ​ጥ​ኣን ልጆች፥ የዘ​ማ​ው​ያ​ንና የጋ​ለ​ሞ​ታ​ዪቱ ዘር፥ ወደ​ዚህ ቅረቡ።</verse>
				<verse number="4">በማን ታላ​ግ​ጣ​ላ​ችሁ? በማ​ንስ ላይ አፋ​ች​ሁን ታላ​ቅ​ቃ​ላ​ችሁ? ምላ​ሳ​ች​ሁ​ንስ በማን ላይ ታስ​ረ​ዝ​ማ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="5">እና​ንተ በለ​መ​ለመ ዛፍ ሁሉ በታች በጣ​ዖት ደስ የም​ት​ሰኙ፥ እና​ን​ተም በሸ​ለ​ቆች ውስጥ በዓ​ለ​ትም ስን​ጣ​ቂ​ዎች በታች ልጆ​ቻ​ች​ሁን የም​ት​ሠዉ፥ እና​ንተ የጥ​ፋት ልጆ​ችና የዐ​መ​ፀ​ኞች ዘሮች አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን?</verse>
				<verse number="6">በሸ​ለቆ ውስጥ ያሉ የለ​ዘቡ ድን​ጋ​ዮች ዕድል ፋን​ታሽ ናቸው፤ እነ​ር​ሱም ዕጣሽ ናቸው፤ ለእ​ነ​ር​ሱም የመ​ጠጥ ቍር​ባን አፍ​ስ​ሰ​ሻል፤ የእ​ህ​ል​ንም ቍር​ባን አቅ​ር​በ​ሻል። እን​ግ​ዲህ በዚህ ነገር አል​ቈ​ጣ​ምን?</verse>
				<verse number="7">ከፍ ባለ​ውና በረ​ዘ​መ​ውም ተራራ ላይ መኝ​ታ​ሽን አደ​ረ​ግሽ፤ በዚ​ያም መሥ​ዋ​ዕ​ት​ሽን ሠዋሽ።</verse>
				<verse number="8">ከመ​ዝ​ጊ​ያው በኋላ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ሽን አደ​ረ​ግሽ፤ እኔን ብት​ተዪ የሚ​ጠ​ቅ​ምሽ መሰ​ለ​ሽን? ከእ​ኔም ይልቅ ከአ​ንቺ ጋራ የሚ​ተ​ኙ​ትን መረ​ጥሽ።</verse>
				<verse number="9">ዝሙ​ት​ሽን ከእ​ነ​ርሱ ጋር አበ​ዛሽ፤ ከአ​ንቺ የራቁ ብዙ​ዎ​ች​ንም ተጐ​ዳ​ኘሽ። መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ች​ሽ​ንም ወደ ሩቅ ላክሽ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ተወ​ገ​ድሽ፤ እስከ ሲኦ​ልም ድረስ ተዋ​ረ​ድሽ።</verse>
				<verse number="10">በመ​ን​ገ​ድ​ሽም ብዛት ደከ​ምሽ፤ ዳግ​መ​ኛም ጕል​በት እያ​ለኝ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ይህን መን​ገድ አል​ተ​ውም አላ​ል​ሽም፤ ይህ​ንም ስላ​ደ​ረ​ግሽ አላ​ፈ​ር​ሽም።</verse>
				<verse number="11">ሐሰት የተ​ና​ገ​ር​ሽው፥ እኔ​ንም ያላ​ሰ​ብ​ሽው፥ በል​ብ​ሽም ነገ​ሩን ያላ​ኖ​ር​ሽው ማንን ሰግ​ተሽ ነው? ማን​ንስ ፈር​ተሽ ነው? እኔም ዝም አል​ሁሽ፤ አን​ቺም አል​ፈ​ራ​ሽ​ኝም።</verse>
				<verse number="12">እን​ግ​ዲህ እኔ ጽድ​ቄ​ንና የማ​ይ​ረ​ባ​ሽን የአ​ን​ቺን በደል እና​ገ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">በች​ግ​ርሽ ቀን በጮ​ኽሽ ጊዜ እስኪ ይታ​ደ​ጉሽ፤ እነሆ፥ ዐውሎ ይወ​ስ​ዳ​ቸ​ዋል፤ ነፋ​ስም ሁሉን ያስ​ወ​ግ​ዳ​ቸ​ዋል። ወደ እኔ የሚ​ጠጉ ግን ምድ​ሪ​ቱን ይገ​ዛሉ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ተራ​ራ​ዬ​ንም ይወ​ር​ሳሉ።</verse>
				<verse number="14">እር​ሱም፥ “በፊቱ፥ መን​ገ​ድን ጥረጉ፤ ከሕ​ዝ​ቤም መን​ገድ ዕን​ቅ​ፋ​ትን አስ​ወ​ግዱ” ይላል።</verse>
				<verse number="15">ለዘ​ለ​ዓ​ለም በአ​ር​ያም የሚ​ኖር ስሙም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን የሆነ፥ በቅ​ዱ​ሳን አድሮ የሚ​ኖር፥ ለተ​ዋ​ረ​ዱት ትዕ​ግ​ሥ​ትን የሚ​ሰጥ፥ ልባ​ቸ​ውም ለተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="16">“መን​ፈስ ከእኔ ይወ​ጣ​ልና፥ የሁ​ሉ​ንም ነፍስ ፈጥ​ሬ​አ​ለ​ሁና ለዘ​ለ​ዓ​ለም አል​ቀ​ስ​ፋ​ች​ሁም፤ ሁል​ጊ​ዜም አል​ቈ​ጣ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="17">ስለ ኀጢ​አቱ ጥቂት ጊዜ መከራ አመ​ጣ​ሁ​በት፤ ቀሠ​ፍ​ሁ​ትም፤ ፊቴ​ንም ከእ​ርሱ መለ​ስሁ፤ እር​ሱም አዘነ። እያ​ዘ​ነም ሄደ።</verse>
				<verse number="18">ከዚ​ህም በኋላ መን​ገ​ዱን አይ​ቻ​ለሁ፤ ፈወ​ስ​ሁ​ትም፤ አጽ​ና​ና​ሁት፤ እው​ነ​ተኛ ደስ​ታ​ንም ሰጠ​ሁት።</verse>
				<verse number="19">በሩ​ቅም በቅ​ር​ብም ላሉ በሰ​ላም ላይ ሰላም ይሁን፤ እፈ​ው​ሳ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="20">“ኃጥ​ኣን ግን እን​ዲህ ይገ​ለ​በ​ጣሉ፤ ዕረ​ፍ​ት​ንም አያ​ገ​ኙም።</verse>
				<verse number="21">ለኃ​ጥ​አን ደስታ የላ​ቸ​ውም” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="58">
				<verse number="1">በኀ​ይ​ልህ ጩኽ፤ አት​ቈ​ጥብ፤ ድም​ፅ​ህን እንደ መለ​ከት አንሣ፤ ለሕ​ዝቤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን፥ ለያ​ዕ​ቆብ ቤትም በደ​ላ​ቸ​ውን ንገር።</verse>
				<verse number="2">ነገር ግን ጽድ​ቅን እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርግ የአ​ም​ላ​ኩ​ንም ፍርድ እን​ደ​ማ​ይ​ተው ሕዝብ ዕለት ዕለት ይሹ​ኛል፤ መን​ገ​ዴ​ንም ያውቁ ዘንድ ይወ​ድ​ዳሉ። አሁ​ንም እው​ነ​ተ​ኛ​ውን ፍርድ ይለ​ም​ኑ​ኛል፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለመ​ቅ​ረብ ይወ​ድ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="3">“ስለ ምን ጾምን፥ አን​ተም አል​ተ​መ​ለ​ከ​ት​ኸ​ንም? ሰው​ነ​ታ​ች​ን​ንስ ስለ ምን አዋ​ረ​ድን፥ አን​ተም አላ​ወ​ቅ​ኸ​ንም?” ይላሉ። እነሆ፥ በጾ​ማ​ችሁ ቀን ፈቃ​ዳ​ች​ሁን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ፥ ሠራ​ተ​ኞ​ቻ​ች​ሁ​ንም ሁሉ ታስ​ጨ​ን​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="4">እነሆ፥ ለጠ​ብና ለክ​ር​ክር ትጾ​ማ​ላ​ችሁ፤ ድሃ​ው​ንም በጡጫ ትማ​ታ​ላ​ችሁ፤ በም​ት​ጮ​ኹ​በት ጊዜ ድም​ፃ​ችሁ እን​ዲ​ሰማ ለእኔ ትጾ​ማ​ላ​ች​ሁን? ድም​ፃ​ች​ሁ​ንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እን​ደ​ም​ት​ጾ​ሙት አት​ጾ​ሙም።</verse>
				<verse number="5">እኔ ይህን ጾም የመ​ረ​ጥሁ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ እን​ደ​ዚ​ችም ባለች ቀን ሰው ራሱን ቢያ​ሳ​ዝን፥ አን​ገ​ቱ​ንም እንደ ቀለ​በት ቢያ​ቀ​ጥን፥ ማቅ ለብሶ በአ​መድ ላይ ቢተ​ኛም፥ ይህ ጾም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​መ​ረጠ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="6">ይህን ጾም የመ​ረ​ጥሁ አይ​ደ​ለም ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን የበ​ደ​ልን እስ​ራት ፍታ፤ ጠማ​ማ​ውን ሁሉ አቅና፤ የተ​ጨ​ነ​ቀ​ው​ንም ሁሉ አድን፤ የዐ​መፃ ደብ​ዳ​ቤ​ንም ተው።</verse>
				<verse number="7">ለተ​ራ​በ​ውም እን​ጀ​ራ​ህን አጥ​ግ​በው፤ ድሆ​ችን ወደ ቤትህ አስ​ገ​ብ​ተህ አሳ​ድ​ራ​ቸው፤ የተ​ራ​ቈ​ተ​ው​ንም ብታይ አል​ብ​ሰው፤ ከሥጋ ዘመ​ድህ አት​ሸ​ሽግ።</verse>
				<verse number="8">ያን ጊዜ ብር​ሃ​ንህ እንደ ንጋት ይበ​ራል፤ ፈው​ስ​ህም ፈጥኖ ይወ​ጣል፤ ጽድ​ቅ​ህም በፊ​ትህ ይሄ​ዳል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ይጋ​ር​ድ​ሃል።</verse>
				<verse number="9">ያን ጊዜ ትጠ​ራ​ለህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሰ​ማ​ሃል፤ ትጮ​ኻ​ለህ፤ እር​ሱም፦ እነ​ሆኝ፥ ይል​ሃል። የዐ​መፅ እስ​ራ​ትን ከመ​ካ​ከ​ልህ ብታ​ርቅ፥ ጣት​ህ​ንም መጥ​ቀስ ማን​ጐ​ራ​ጐ​ር​ንም ብት​ተው፥</verse>
				<verse number="10">ከም​ግ​ብ​ህም ለተ​ራበ ብታ​ካ​ፍል፥ የተ​ራ​በች ሰው​ነ​ት​ንም ብታ​ጠ​ግብ፥ ያን​ጊዜ ብር​ሃ​ንህ በጨ​ለማ ይወ​ጣል፤ ጨለ​ማ​ህም እንደ ቀትር ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሁል​ጊዜ ከአ​ንተ ጋር ይኖ​ራል፤ እንደ ነፍ​ስ​ህም ፍላ​ጎት ያጠ​ግ​ብ​ሃል፤ አጥ​ን​ት​ህ​ንም ያለ​መ​ል​ማል፤ አን​ተም እን​ደ​ሚ​ጠጣ ገነት፥ ውኃ​ውም እን​ደ​ማ​ያ​ቋ​ርጥ ምንጭ ትሆ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="12">ከድሮ ዘመን የፈ​ረ​ሱት ስፍ​ራ​ዎ​ችህ ይሠ​ራሉ፤ መሠ​ረ​ት​ህም ለልጅ ልጅ ዘመን ይሆ​ናል፤ አን​ተም፦ ሰባ​ራ​ውን ጠጋኝ፥ የመ​ኖ​ሪያ መን​ገ​ድ​ንም አዳሽ ትባ​ላ​ለህ።</verse>
				<verse number="13">ፈቃ​ድ​ህን በተ​ቀ​ደ​ሰው ቀኔ ከማ​ድ​ረግ እግ​ር​ህን ከሰ​ን​በት ብት​መ​ልስ፥ ሰን​በ​ት​ንም ደስታ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቀ​ደሰ ብታ​ደ​ር​ገው፥ ክፉ ሥራን ለመ​ሥ​ራት እግ​ር​ህን ባታ​ነሣ፥ በአ​ፍ​ህም ክፉ ነገ​ርን ባት​ና​ገር፥</verse>
				<verse number="14">በዚ​ያን ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትታ​መ​ና​ለህ፤ በም​ድ​ርም በረ​ከት ላይ ያወ​ጣ​ሃል፤ የአ​ባ​ትህ የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንም ርስት ይመ​ግ​ብ​ሃል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ እን​ደ​ዚህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="59">
				<verse number="1">በውኑ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ማዳን አት​ች​ል​ምን? ጆሮ​ውስ አይ​ሰ​ማ​ምን?</verse>
				<verse number="2">ነገር ግን በደ​ላ​ችሁ በእ​ና​ን​ተና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መካ​ከል ለይ​ታ​ለች፤ ይቅ​ርም እን​ዳ​ይ​ላ​ችሁ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ ፊቱን ከእ​ና​ንተ ሰው​ሮ​ታል።</verse>
				<verse number="3">እጃ​ችሁ በደም ጣታ​ች​ሁም በኀ​ጢ​አት ተሞ​ል​ት​ዋል፤ ከን​ፈ​ራ​ች​ሁም ዐመ​ፅን ተና​ግ​ሮ​አል፤ ምላ​ሳ​ች​ሁም ኀጢ​አ​ትን አሰ​ም​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="4">ጽድ​ቅን የሚ​ና​ገር በእ​ው​ነ​ትም የሚ​ፈ​ርድ የለም፤ በከ​ንቱ ነገር ታም​ነ​ዋል፤ የማ​ይ​ጠ​ቅ​ማ​ቸ​ው​ንም ተና​ግ​ረ​ዋል፤ ኀጢ​አ​ትን ፀን​ሰ​ዋል፤ በደ​ል​ንም ወል​ደ​ዋል።</verse>
				<verse number="5">የእ​ባ​ብን ዕን​ቍ​ላል ቀፈ​ቀፉ፤ የሸ​ረ​ሪ​ት​ንም ድር አደሩ፤ እን​ቁ​ላ​ላ​ቸ​ው​ንም የሚ​በላ ሰው ፈጥኖ ይሞ​ታል፤ እን​ቍ​ላ​ሉም ሲሰ​በር እባብ ይወ​ጣል።</verse>
				<verse number="6">የሸ​ረ​ሪ​ቶች ድር ልብስ አይ​ሆ​ንም፤ በሥ​ራ​ቸ​ውም ራሳ​ቸ​ውን አያ​ለ​ብ​ሱም፤ ሥራ​ቸው የግፍ ሥራ ነውና።</verse>
				<verse number="7">እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ለተ​ን​ኮል ይሮ​ጣሉ፤ ደምን ለማ​ፍ​ሰ​ስም ይፈ​ጥ​ናሉ፤ ሰውን ለመ​ግ​ደል ይመ​ክ​ራሉ፤ ጕስ​ቍ​ል​ናና ቅጥ​ቃጤ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው አለ።</verse>
				<verse number="8">የሰ​ላ​ምን መን​ገድ አያ​ው​ቁም፤ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸ​ውም ፍርድ የለም፤ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ትም መን​ገድ ጠማማ ነው፤ ሰላ​ም​ንም አያ​ው​ቁም።</verse>
				<verse number="9">ስለ​ዚህ ፍርድ ከእ​ነ​ርሱ ዘንድ ርቆ​አል፤ ጽድ​ቅም አላ​ገ​ኛ​ቸ​ውም፤ ብር​ሃ​ንን ሲጠ​ባ​በቁ ብር​ሃ​ና​ቸው ጨለማ ሆነ​ባ​ቸው፤ ብር​ሃ​ን​ንም ሲጠ​ባ​በቁ በጨ​ለማ ሄዱ፤</verse>
				<verse number="10">እንደ ዕው​ሮች ወደ ቅጥሩ ተር​መ​ሰ​መሱ፤ ዐይ​ንም እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው ተር​መ​ሰ​መሱ፤ በቀ​ት​ርም ጊዜ በመ​ን​ፈቀ ሌሊት እን​ዳለ ሰው ተሰ​ና​ከሉ፤ እንደ ሙታ​ንም ይጨ​ነ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="11">እንደ ድብና እንደ ርግብ በአ​ን​ድ​ነት ይሄ​ዳሉ፤ ፍር​ድን እን​ጠ​ባ​በቅ ነበር፤ መዳ​ንም የለም፤ ከእ​ኛም ርቆ​አል።</verse>
				<verse number="12">ዐመ​ፃ​ችን በአ​ንተ ፊት በዝ​ቶ​አ​ልና፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንም መስ​ክ​ሮ​ብ​ና​ልና፥ ዐመ​ፃ​ችን ከእኛ ጋር ነውና፥ ጽድ​ቅ​ንም አላ​ወ​ቅ​ን​ምና።</verse>
				<verse number="13">በድ​ለ​ናል፤ ዋሽ​ተ​ና​ልም፤ አም​ላ​ካ​ች​ን​ንም መከ​ተል ትተ​ናል፤ ዐመ​ፃን ተና​ግ​ረ​ናል፤ ከድ​ተ​ን​ሃ​ልም፤ የኀ​ጢ​አ​ት​ንም ቃል ፀን​ሰን፤ ከልብ አው​ጥ​ተ​ናል።</verse>
				<verse number="14">ፍር​ድን ከመ​ከ​ተል ወደ ኋላ ርቀ​ናል፤ ጽድ​ቅም በሩቅ ቆሞ​አል፤ እው​ነ​ትም ከመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ታጥ​ቶ​አል፤ በቀና መን​ገ​ድም መሄድ አል​ቻ​ሉም።</verse>
				<verse number="15">ከእ​ው​ነት ተወ​ግ​ደ​ዋል፤ እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉም ልባ​ቸ​ውን መል​ሰ​ዋል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አየ፤ ፍር​ድም ስለ​ሌለ ደስ አላ​ለ​ውም።</verse>
				<verse number="16">ሰውም እን​ደ​ሌለ አየ፤ የሚ​ረ​ዳም ሰው እን​ደ​ሌለ ተረዳ፤ ሰለ​ዚህ በክ​ንዱ ደገ​ፋ​ቸው፤ በይ​ቅ​ር​ታ​ውም አጸ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="17">ጽድ​ቅ​ንም እንደ ጥሩር ለበሰ፤ በራ​ሱም ላይ የማ​ዳ​ንን ራስ ቍር አደ​ረገ፤ የበ​ቀ​ል​ንም ልብስ ለበሰ።</verse>
				<verse number="18">ጠላ​ቶ​ቹ​ንም ያዋ​ር​ዳ​ቸው ዘንድ የበ​ቀ​ልና የፍ​ዳን መጐ​ና​ጸ​ፊያ ተጐ​ና​ጸፈ።</verse>
				<verse number="19">በም​ዕ​ራብ ያሉት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም፥ በፀ​ሐይ መው​ጫም ያሉት ክብ​ሩን ይፈ​ራሉ። መቅ​ሠ​ፍ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እንደ ኀይ​ለኛ ፈሳሽ በቍጣ ይመ​ጣል።</verse>
				<verse number="20">ከጽ​ዮን ታዳጊ ይመ​ጣል፤ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ኀጢ​አ​ትን ያር​ቃል።</verse>
				<verse number="21">“ከእ​ነ​ርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “በአ​ንተ ላይ ያለው መን​ፈሴ በአ​ፍ​ህም ውስጥ ያደ​ረ​ግ​ሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ ከአ​ፍህ፥ ከዘ​ር​ህም አፍ፥ ከዘር ዘር​ህም አፍ አይ​ጠ​ፋም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="60">
				<verse number="1">ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ብር​ሃ​ንሽ መጥ​ቶ​አ​ልና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብር​ሃን በአ​ንቺ ላይ ወጥ​ቶ​አ​ልና አብሪ፤ አብሪ።</verse>
				<verse number="2">እነሆ፥ ጨለማ ምድ​ርን፥ ድቅ​ድቅ ጨለ​ማም አሕ​ዛ​ብን ይሸ​ፍ​ናል፤ ነገር ግን በአ​ንቺ ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገ​ለ​ጣል፤ ክብ​ሩም በአ​ንቺ ላይ ይታ​ያል፤</verse>
				<verse number="3">ነገ​ሥ​ታት በብ​ር​ሃ​ንሽ፥ አሕ​ዛ​ብም በፀ​ዳ​ልሽ ይሄ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="4">ዐይ​ኖ​ች​ሽን አን​ሥ​ተሽ በዙ​ሪ​ያሽ ተመ​ል​ከቺ፤ ልጆ​ች​ሽም እንደ ተሰ​በ​ሰቡ እነሆ፥ እዪ፤ ወን​ዶች ልጆ​ችሽ ከሩቅ ይመ​ጣሉ፤ ሴቶች ልጆ​ች​ሽ​ንም በጫ​ንቃ ላይ ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="5">በዚያ ጊዜ አይ​ተሽ ትፈ​ሪ​ያ​ለሽ፤ የአ​ሕ​ዛ​ብና የሀ​ገ​ሮች ብል​ጽ​ግና ወደ አንቺ ይመ​ለ​ሳ​ልና፥ ልብሽ ይደ​ነ​ግ​ጣል።</verse>
				<verse number="6">የግ​መ​ሎች መንጋ ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፤ የም​ድ​ያ​ምና የኤፋ ግመ​ሎች ይሸ​ፍ​ኑ​ሻል፤ ሁሉ ከሳባ ወር​ቅ​ንና ዕጣ​ንን ይዘው ይመ​ጣሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ማዳን ያበ​ሥ​ራሉ።</verse>
				<verse number="7">የቄ​ዳር በጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ የነ​ባ​ዮ​ትም አውራ በጎች ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፤ በመ​ሠ​ዊ​ያዬ ላይም የተ​መ​ረ​ጠው መሥ​ዋ​ዕት ይቀ​ር​ባል፤ የጸ​ሎቴ ቤትም ይከ​ብ​ራል።</verse>
				<verse number="8">እንደ ደመና፥ ከጫ​ጩ​ቶ​ችዋ ጋር ወደ መስ​ኮቷ እን​ደ​ም​ት​ገባ ርግ​ብም የሚ​በ​ርሩ እነ​ዚህ እነ​ማን ናቸው?</verse>
				<verse number="9">ደሴ​ቶች እኔን ተስፋ ያደ​ር​ጋሉ፤ የተ​ር​ሴ​ስም መር​ከ​ቦች አስ​ቀ​ድ​መው ይመ​ጣሉ፤ ልጆ​ችሽ ስለ ከበ​ረው ስለ እስ​ራ​ኤል ቅዱስ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ወር​ቅና ብር ይዘው ከሩቅ ሀገር ይመ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="10">በቍ​ጣዬ ቀሥፌ በይ​ቅ​ር​ታዬ አቅ​ር​ቤ​ሻ​ለ​ሁና መጻ​ተ​ኞች ቅጥ​ር​ሽን ይሠ​ራሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም በፊ​ትሽ ይቆ​ማሉ።</verse>
				<verse number="11">በሮ​ች​ሽም ሁል​ጊዜ ይከ​ፈ​ታሉ፤ ሰዎች የአ​ሕ​ዛ​ብን ብል​ጽ​ግና፥ የተ​ማ​ረ​ኩ​ት​ንም ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ወደ አንቺ ያመጡ ዘንድ ሌሊ​ትና ቀን አይ​ዘ​ጉም።</verse>
				<verse number="12">ለአ​ን​ቺም የማ​ይ​ገዙ ነገ​ሥ​ታት ይሞ​ታሉ፤ እነ​ዚ​ያም አሕ​ዛብ ፈጽ​መው ይጠ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="13">የመ​ቅ​ደ​ሴ​ንም ስፍራ ያከ​ብሩ ዘንድ የሊ​ባ​ኖስ ክብር፥ ጥዱና አስ​ታው፥ ባር​ሰ​ነ​ቱም ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፥</verse>
				<verse number="14">የአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎ​ች​ሽም ልጆች እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፤ የና​ቁ​ሽም ሁሉ ወደ እግ​ርሽ ጫማ ይሰ​ግ​ዳሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተማ፥ ጽዮን ተብ​ለ​ሽም ትጠ​ሪ​ያ​ለሽ።</verse>
				<verse number="15">የተ​ተ​ው​ሽና የተ​ጠ​ላሽ ሆነ​ሻ​ልና የሚ​ረ​ዳሽ አጣሽ፤ ነገር ግን የዘ​ለ​ዓ​ለም ደስ​ታን ለልጅ ልጅ እሰ​ጥ​ሻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">የአ​ሕ​ዛ​ብ​ንም ወተት ትጠ​ጫ​ለሽ፤ የነ​ገ​ሥ​ታ​ት​ንም ብል​ጽ​ግና ትበ​ያ​ለሽ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ፥ መድ​ኀ​ኒ​ት​ሽና ታዳ​ጊሽ እንደ ሆንሁ ታው​ቂ​ያ​ለሽ።</verse>
				<verse number="17">በናስ ፋንታ ወር​ቅን፥ በብ​ረ​ትም ፋንታ ብርን፥ በእ​ን​ጨ​ትም ፋንታ ናስን፥ በድ​ን​ጋ​ይም ፋንታ ብረ​ትን እሰ​ጥ​ሻ​ለሁ። ለአ​ለ​ቆ​ች​ሽም ሰላ​ምን፥ ለመ​ኳ​ን​ን​ት​ሽም ፍር​ድን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="18">እን​ግ​ዲህ በም​ድ​ርሽ ውስጥ ግፍ፥ በዳ​ር​ቻ​ሽም ውስጥ ጕስ​ቍ​ል​ናና ቅጥ​ቃጤ አይ​ሰ​ማም፤ ቅጥ​ሮ​ችሽ ድኅ​ነት ይባ​ላሉ፤ በሮ​ች​ሽም በጥ​ርብ ድን​ጋይ ይሠ​ራሉ።</verse>
				<verse number="19">ፀሐይ በቀን የሚ​ያ​በ​ራ​ልሽ አይ​ደ​ለም፤ በሌ​ሊ​ትም ጨረቃ የሚ​ወ​ጣ​ልሽ አይ​ደ​ለም፤ ለአ​ን​ቺስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዘ​ለ​ዓ​ለም ብር​ሃ​ንሽ፥ አም​ላ​ክ​ሽም ክብ​ርሽ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዘ​ለ​ዓ​ለም ብር​ሃ​ንሽ ይሆ​ና​ልና፥ የል​ቅ​ሶ​ሽም ወራት ያል​ፋ​ልና፤ ፀሐ​ይሽ ከዚህ በኋላ አት​ጠ​ል​ቅም፤ ጨረ​ቃ​ሽም አይ​ቋ​ረ​ጥም።</verse>
				<verse number="21">ሕዝ​ብሽ ሁሉ ጻድ​ቃን ይሆ​ናሉ፤ ምድ​ር​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይወ​ር​ሳሉ፤ እር​ሱ​ንም ለማ​መ​ስ​ገን የእ​ጆ​ቹን ሥራ ይጠ​ብ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="22">ታናሹ ሺህ፥ የሁ​ሉም ታናሽ ታላቅ ሕዝብ ይሆ​ናል፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዘ​መ​ና​ቸው ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="61">
				<verse number="1">የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድ​ሆች የም​ሥ​ራ​ችን እሰ​ብክ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀብ​ቶ​ኛ​ልና፤ ልባ​ቸው የተ​ሰ​በ​ረ​ውን እጠ​ግን ዘንድ፥ ለተ​ማ​ረ​ኩ​ትም ነጻ​ነ​ትን፥ ለታ​ሰ​ሩ​ትም መፈ​ታ​ትን፥ ለዕ​ው​ራ​ንም ማየ​ትን እና​ገር ዘንድ ልኮ​ኛል።</verse>
				<verse number="2">የተ​ወ​ደ​ደ​ች​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ዓመት የተ​መ​ረ​ጠች ብዬ እጠ​ራት ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ች​ንም የሚ​በ​ቀ​ል​በ​ትን ቀን እና​ገር ዘንድ፥ የሚ​ያ​ለ​ቅ​ሱ​ት​ንም ሁሉ አጽ​ናና ዘንድ፥</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለክ​ብሩ የተ​ከ​ላ​ቸው የጽ​ድቅ ዛፎች እን​ዲ​ባሉ ለጽ​ዮን አል​ቃ​ሾች አደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ፥ በአ​መ​ድም ፋንታ አክ​ሊ​ልን፥ በል​ቅ​ሶም ፋንታ የደ​ስ​ታን ዘይት፥ በኀ​ዘ​ንም መን​ፈስ ፋንታ የም​ስ​ጋ​ናን መጐ​ና​ጸ​ፊያ እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ልኮ​ኛል።</verse>
				<verse number="4">ከጥ​ንት ጀምሮ የፈ​ረ​ሱ​ትን ይሠ​ራሉ፤ ከቀ​ድሞ ጀምሮ የፈ​ረ​ሱ​ት​ንም ያቆ​ማሉ፤ ባድማ የነ​በ​ሩ​ት​ንና ከብዙ ትው​ልድ በፊት የፈ​ረ​ሱ​ትን ከተ​ሞች እንደ ገና ያድ​ሳሉ።</verse>
				<verse number="5">መጻ​ተ​ኞ​ችም መጥ​ተው በጎ​ቻ​ች​ሁን ይጠ​ብ​ቃሉ፥ ሌሎች ወገ​ኖ​ችም አራ​ሾ​ችና ወይን ጠባ​ቂ​ዎች ይሆ​ኑ​ላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="6">እና​ንተ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካህ​ናት ትባ​ላ​ላ​ችሁ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም አገ​ል​ጋ​ዮች ተብ​ላ​ችሁ ትጠ​ራ​ላ​ችሁ፤ የአ​ሕ​ዛ​ብን ሀብት ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በሀ​ብ​ታ​ቸ​ውም ትመ​ካ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="7">ሌላ ምድ​ርን ይወ​ር​ሳሉ፤ በራ​ሳ​ቸ​ውም ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ደስታ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቅን የም​ወ​ድድ፥ ስር​ቆ​ት​ንና ቅሚ​ያን የም​ጠላ ነኝ፤ እንደ ሥራ​ቸ​ውም ለጻ​ድ​ቃን እከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምን ቃል ኪዳን አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">ዘራ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም በወ​ገ​ኖች መካ​ከል የታ​ወቁ ይሆ​ናሉ፤ ያያ​ቸው ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የባ​ረ​ካ​ቸው ዘር እንደ ሆኑ ያው​ቃል፤</verse>
				<verse number="10">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅግ ደስ ይላ​ቸ​ዋል። ነፍ​ሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሐሤት ታደ​ር​ጋ​ለች። ሽል​ማ​ትን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽል​ማ​ቷም እን​ዳ​ጌ​ጠች ሙሽራ፥ የማ​ዳ​ንን ልብስ አል​ብ​ሶ​ኛ​ልና፥ የደ​ስ​ታ​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ደር​ቦ​ል​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="11">ምድ​ርም ቡቃ​ያ​ውን እን​ደ​ም​ታ​ወጣ፥ ገነ​ትም ዘሩን እን​ደ​ሚ​ያ​በ​ቅል፥ እን​ዲሁ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቅ​ንና ደስ​ታን በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ፊት ያበ​ቅ​ላል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="62">
				<verse number="1">ጽድቄ እንደ ብር​ሃን፥ ማዳ​ኔም እን​ደ​ሚ​በራ ፋና እስ​ኪ​ወጣ ድረስ ስለ ጽዮን ዝም አል​ልም፤ ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ጸጥ አል​ልም።</verse>
				<verse number="2">አሕ​ዛብ ጽድ​ቅ​ሽን፥ ነገ​ሥ​ታ​ትም ሁሉ ክብ​ር​ሽን ያያሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አፍ በሚ​ጠ​ራ​በት በአ​ዲሱ ስም ትጠ​ሪ​ያ​ለሽ።</verse>
				<verse number="3">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ያማረ አክ​ሊል፥ በአ​ም​ላ​ክ​ሽም እጅ የመ​ን​ግ​ሥት ዘውድ ትሆ​ኛ​ለሽ።</verse>
				<verse number="4">ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ፥ “የተ​ተ​ወች” አት​ባ​ዪም፤ ምድ​ር​ሽም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ፥ “ውድማ” አት​ባ​ልም፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ንቺ ደስ ብሎ​ታ​ልና፥ ምድ​ር​ሽም ባል ታገ​ባ​ለ​ችና አንቺ፥ “ደስ​ታዬ የሚ​ኖ​ር​ባት” ትባ​ያ​ለሽ፤ ምድ​ር​ሽም፥ “ባል ያገ​ባች” ትባ​ላ​ለች።</verse>
				<verse number="5">ጐል​ማ​ሳም ከድ​ን​ግ​ሊቱ ጋር እን​ደ​ሚ​ኖር፥ እን​ዲሁ ልጆ​ችሽ ከአ​ንቺ ጋር ይኖ​ራሉ፤ ሙሽ​ራም በሙ​ሽ​ራ​ዪቱ ደስ እን​ደ​ሚ​ለው፥ እን​ዲሁ አም​ላ​ክሽ በአ​ንቺ ደስ ይለ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ሽን በቅ​ጥ​ርሽ ላይ ቀንና ሌሊት አቁ​ሜ​አ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​ስቡ ከቶ ዝም አይ​ሉም፤</verse>
				<verse number="7">ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እስ​ኪ​ያ​ጸና፥ በም​ድ​ርም ላይ ምስ​ጋና እስ​ኪ​ያ​ደ​ር​ጋት ድረስ ዝም አት​በሉ።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በእ​ር​ግጥ ለጠ​ላ​ቶ​ችሽ መብል ይሆን ዘንድ እህ​ል​ሽን አል​ሰ​ጥም፥ መጻ​ተ​ኞ​ችም የደ​ከ​ም​ሽ​በ​ትን ወይ​ን​ሽን አይ​ጠ​ጡም፤” ብሎ በጌ​ት​ነ​ቱና በክ​ንዱ ኀይል ምሎ​አል።</verse>
				<verse number="9">ነገር ግን የሰ​በ​ሰ​ቡት ይበ​ሉ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያመ​ሰ​ግ​ናሉ፤ ያከ​ማ​ቹ​ት​ንም ወይን በመ​ቅ​ደሴ አደ​ባ​ባይ ላይ ይጠ​ጡ​ታል።</verse>
				<verse number="10">ሂዱና በበሬ ውስጥ ግቡ፤ ለሕ​ዝ​ቤም መን​ገ​ድን ጥረጉ፤ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ከጎ​ዳ​ናው አስ​ወ​ግዱ፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም አላማ ያዙ።</verse>
				<verse number="11">እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስከ ምድር ዳርቻ አዋጅ እን​ዲህ ብሎ ነግ​ሮ​አል፥ “ለጽ​ዮን ልጅ፦ እነሆ፥ መድ​ኀ​ኒ​ትሽ ይመ​ጣል፤ እነሆ፥ ዋጋው ከእ​ርሱ ጋር ሥራ​ውም በፊቱ አለ በሉ​አት።”</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “የተ​ቤ​ዣ​ቸው፥ የተ​ቀ​ደሰ ሕዝብ” ብለው ይጠ​ሩ​አ​ቸ​ዋል፤ አን​ቺም፥ “የተ​ተ​ወች ያይ​ደ​ለች የተ​ወ​ደ​ደች ቅድ​ስት ከተማ” ትባ​ያ​ለሽ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="63">
				<verse number="1">ከኤ​ዶ​ም​ያስ፥ ከባ​ሶራ የሚ​መጣ፥ ልብ​ሱም የቀላ፥ የሚ​መካ ኀይ​ለኛ፥ አለ​ባ​በ​ሱም ያማረ፥ ይህ ማን ነው? ስለ ጽድቅ የም​ከ​ራ​ከር፥ ስለ ማዳ​ንም የም​ፈ​ርድ እኔ ነኝ።</verse>
				<verse number="2">ቀሚ​ስህ ስለ ምን ቀላ? ልብ​ስ​ህስ በወ​ይን መጭ​መ​ቂያ እን​ደ​ሚ​ረ​ግጥ ሰው ልብስ ስለ ምን መሰለ?</verse>
				<verse number="3">መጭ​መ​ቂ​ያ​ውን ብቻ​ዬን ረግ​ጫ​ለሁ፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አል​ነ​በ​ረም፤ በቍ​ጣ​ዬም ረገ​ጥ​ኋ​ቸው፤ በመ​ዓ​ቴም ወደ መሬት ጣል​ጥ​ህ​ዋ​ቸው፤ ደማ​ቸ​ው​ንም በም​ድር ላይ አፈ​ሰ​ስሁ፤ ልብ​ሴም ሁሉ በደም ታለለ።</verse>
				<verse number="4">የም​በ​ቀ​ል​በት ቀን ደር​ሶ​ባ​ቸ​ዋ​ልና፥ የም​ቤ​ዥ​በ​ትም ዐመት ደር​ሶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="5">የሚ​ረ​ዳም እን​ደ​ሌለ አየሁ፤ የሚ​ያ​ግ​ዝም እን​ደ​ሌለ ዐወ​ቅሁ፤ ስለ​ዚህ በገዛ ክንዴ አድ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቍጣ​ዬም ወደ​ቀ​ች​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">በመ​ቅ​ሠ​ፍቴ ረገ​ጥ​ኋ​ቸው፤ ደማ​ቸ​ው​ንም ወደ ምድር አፈ​ሰ​ስ​ሁት።</verse>
				<verse number="7">በስ​ጦ​ታው ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቸር​ነ​ትና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ጋና ዐሰ​ብሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች እው​ነ​ተኛ ፈራጅ ነው፤ እንደ ቸር​ነ​ቱና እንደ ጽድቁ ብዛ​ትም ይቅ​ር​ታ​ውን ያመ​ጣ​ል​ናል።</verse>
				<verse number="8">እር​ሱም፥ “ሕዝቤ ልጆች አይ​ደ​ሉ​ምን? ካል​ከ​ዱ​ኝስ ከመ​ከ​ራ​ቸው ሁሉ አድ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="9">በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኛም አይ​ደ​ለም፤ በመ​ል​አ​ክም አይ​ደ​ለም፤ እርሱ ራሱ ያድ​ና​ቸ​ዋል እንጂ። እርሱ ይወ​ዳ​ቸ​ዋ​ልና፥ ይራ​ራ​ላ​ቸ​ዋ​ል​ምና እርሱ ተቤ​ዣ​ቸው፤ ተቀ​በ​ላ​ቸ​ውም፤ በዘ​መ​ና​ቸ​ውም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አከ​በ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">እነ​ርሱ ግን ዐመ​ፁ​በት፤ ቅዱስ መን​ፈ​ሱ​ንም አስ​መ​ረሩ፤ ስለ​ዚህ ተመ​ልሶ ጠላት ሆና​ቸው፤ እር​ሱም ተዋ​ጋ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">እር​ሱም እን​ዲህ ብሎ የቀ​ደ​መ​ውን ዘመን ዐሰበ፥ “በበ​ጎቹ እረኛ እጅ ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ መል​አ​ኬን በፊ​ታ​ቸው ላክሁ።</verse>
				<verse number="12">በሙ​ሴም ቀኝ እጅ ውኃ​ውን ከፈ​ልሁ፤” ውኃ​ውም ተከ​ፍሎ በፊቱ ጸና፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም ስም​ንም አደ​ረ​ገ​ለት።</verse>
				<verse number="13">ፈረስ በም​ድረ በዳ እን​ደ​ሚ​ያ​ልፍ፥ በቀ​ላይ ውስጥ አሳ​ለ​ፋ​ቸው፥ እነ​ር​ሱም አል​ደ​ከ​ሙም።</verse>
				<verse number="14">ወደ ሸለቆ እን​ደ​ሚ​ወ​ርዱ ከብ​ቶች፥ እን​ዲሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ወደ ዕረ​ፍት አመ​ጣ​ቸው፤ እን​ዲ​ሁም ለራ​ስህ የከ​በረ ስምን ታደ​ርግ ዘንድ ሕዝ​ብ​ህን መራህ።</verse>
				<verse number="15">ከሰ​ማይ ተመ​ለስ፤ ከቅ​ድ​ስ​ና​ህና ከክ​ብ​ርህ ማደ​ሪ​ያም ተመ​ል​ከት፤ ቅን​አ​ት​ህና ኀይ​ል​ህስ ወዴት ነው? የቸ​ር​ነ​ት​ህና የይ​ቅ​ር​ታህ ብዛት ወዴት ነው? ቸል ብለ​ሃ​ልና።</verse>
				<verse number="16">አንተ አባ​ታ​ችን ነህ፤ አብ​ር​ሃም ግን አላ​ወ​ቀ​ንም፤ እስ​ራ​ኤ​ልም አል​ተ​ገ​ነ​ዘ​በ​ንም፤ ነገር ግን አንተ አባ​ታ​ችን አድ​ነን፤ ስም​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም በእኛ ላይ ነው።</verse>
				<verse number="17">አቤቱ፥ ከመ​ን​ገ​ድህ ለምን አሳ​ት​ኸን? እን​ዳ​ን​ፈ​ራ​ህም ልባ​ች​ንን ለምን አጸ​ና​ህ​ብን? ስለ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ስለ ርስ​ትህ ነገ​ዶች ተመ​ለስ፤</verse>
				<verse number="18">በተ​ቀ​ደ​ሰው ተራ​ራህ ከር​ስ​ትህ ጥቂት ክፍል እና​ገኝ ዘንድ።</verse>
				<verse number="19">ከጥ​ንት እን​ዳ​ል​ገ​ዛ​ኸን ስም​ህም በእኛ ላይ እን​ዳ​ል​ተ​ጠራ ሆነ​ና​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="64">
				<verse number="1">ሰማ​ይን ብት​ከ​ፍት ከአ​ንተ የተ​ነሣ ተራ​ሮች ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ይቀ​ል​ጣ​ሉም።</verse>
				<verse number="2">አደሮ ማር በእ​ሳት ፊት እን​ደ​ሚ​ቀ​ልጥ እን​ዲሁ ጠላ​ቶ​ች​ህን እሳት ትበ​ላ​ቸ​ዋ​ለች፤ ስም​ህም በእ​ነ​ርሱ ላይ ይታ​ወ​ቃል፤ አሕ​ዛ​ብም በፊ​ትህ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="3">የክ​ብ​ር​ህ​ንም ሥራ ባደ​ረ​ግህ ጊዜ፥ ተራ​ሮች በፊ​ትህ ተን​ቀ​ጠ​ቀጡ።</verse>
				<verse number="4">ከጥ​ንት ጀምሮ ይቅ​ር​ታ​ህን ለሚ​ጠ​ባ​በቁ ምሕ​ረ​ትን ከም​ታ​ደ​ር​ግ​ላ​ቸው ከአ​ንተ በቀር ሌላ አም​ላክ አላ​የ​ንም፤ አል​ሰ​ማ​ን​ምም።</verse>
				<verse number="5">በቸ​ር​ነ​ትህ የሚ​ታ​ገሡ መን​ገ​ድ​ህ​ንም የሚ​ያ​ስቡ ይገ​ና​ኙ​ሃል፤ እነሆ፥ አንተ ተቈ​ጣህ፤ እኛም ኀጢ​አት ሠራን፤ ስለ​ዚ​ህም ተሳ​ሳ​ትን።</verse>
				<verse number="6">ሁላ​ችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነ​ናል፤ ጽድ​ቃ​ች​ንም ሁሉ እንደ መር​ገም ጨርቅ ነው፤ በኀ​ጢ​አ​ታ​ችን ምክ​ን​ያት እንደ ቅጠል ረግ​ፈ​ናል፤ እን​ዲ​ሁም ነፋስ ጠራ​ርጎ ወስ​ዶ​ናል።</verse>
				<verse number="7">ስም​ህ​ንም የሚ​ጠራ፥ አን​ተ​ንም የሚ​ያ​ስብ የለም፤ ፊት​ህ​ንም ከእኛ መል​ሰ​ሃል፤ ለኀ​ጢ​አ​ታ​ች​ንም አሳ​ል​ፈህ ሰጥ​ተ​ኸ​ናል።</verse>
				<verse number="8">አሁን ግን፥ ጌታ ሆይ፥ አንተ አባ​ታ​ችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን፤ አን​ተም ሠሪ​ያ​ችን ነህ፤ እኛም ሁላ​ችን የእ​ጅህ ሥራ ነን።</verse>
				<verse number="9">አቤቱ፥ እጅግ አት​ቈጣ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን አታ​ስብ፤ አሁ​ንም እባ​ክህ፥ ወደ እኛ ተመ​ል​ከት፤ እኛ ሁላ​ችን ሕዝ​ብህ ነን።</verse>
				<verse number="10">የተ​ቀ​ደሱ ከተ​ሞ​ችህ ምድረ በዳ ሆነ​ዋል፤ ጽዮን ምድረ በዳ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ውድማ ሆና​ለች።</verse>
				<verse number="11">አባ​ቶ​ቻ​ችን ያከ​በ​ሩት ክብ​ራ​ችን ቤተ መቅ​ደ​ስህ በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ሎ​አል፤ ያማ​ረ​ውም ስፍ​ራ​ችን ፈር​ሶ​አል።</verse>
				<verse number="12">አቤቱ፥ በዚህ ነገር ሁሉ ታገ​ሥ​ኸን፤ ዝም አል​ኸን፤ እጅ​ግም አዋ​ረ​ድ​ኸን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="65">
				<verse number="1">ያል​ፈ​ለ​ጉኝ አገ​ኙኝ፤ ላል​ጠ​የ​ቁ​ኝም ተገ​ኘሁ፤ ስሜን ላል​ጠራ ሕዝብ፥ “እነ​ሆኝ” አል​ሁት።</verse>
				<verse number="2">በጽ​ድቅ መን​ገድ ወደ​ማ​ይ​ሄዱ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ወደ​ሚ​ከ​ተሉ ዐመ​ፀ​ኞች ሕዝብ ቀኑን ሁሉ እጆ​ችን ዘረ​ጋሁ።</verse>
				<verse number="3">እኒህ ሕዝብ ዘወ​ትር የሚ​ያ​ስ​ቈ​ጡኝ ናቸው፤ እነ​ርሱ በአ​ት​ክ​ልት ውስጥ የሚ​ሠዉ በጡ​ብም ላይ ለአ​ጋ​ን​ንት የሚ​ያ​ጥኑ፥</verse>
				<verse number="4">በመ​ቃ​ብ​ርም መካ​ከል የሚ​ተኙ፥ በዋሻ ውስጥ የሚ​ያ​ልሙ፥ የእ​ሪያ ሥጋም የሚ​በሉ ናቸው። የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ደምና ዕቃ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ያረ​ክ​ሳሉ።</verse>
				<verse number="5">“እኔ ንጹሕ ነኝና ከእኔ ራቁ፥ ወደ እኔም አት​ቅ​ረቡ” ይላሉ። ስለ​ዚ​ህም የቍ​ጣዬ ጢስ በዘ​መኑ ሁሉ እንደ እሳት ይነ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">እነሆ፥ በፊቴ ተጽ​ፎ​አል፦ ኀጢ​አ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንና የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ኀጢ​አት በአ​ንድ ላይ ወደ ብብ​ታ​ቸው ፍዳ አድ​ርጌ እመ​ል​ሳ​ለሁ እንጂ ዝም አል​ልም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤</verse>
				<verse number="7">በተ​ራ​ሮ​ችም ላይ ስላ​ጠኑ፥ በኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም ላይ ስለ አሽ​ሟ​ጠ​ጡኝ ስለ​ዚህ አስ​ቀ​ድ​መው የሠ​ሩ​ትን ሥራ​ቸ​ውን በብ​ብ​ታ​ቸው እሰ​ፍ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የወ​ይን ፍሬ በዘ​ለ​ላው በተ​ገ​ኘች ጊዜ፦ በረ​ከት በእ​ር​ስዋ ላይ አለና አታ​ጥ​ፉት እን​ደ​ሚ​ባ​ለው፥ ሁሉን እን​ዳ​ላ​ጠፋ ስለ ባሪ​ያ​ዎች እን​ዲህ አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">የያ​ዕ​ቆ​ብን ዘርና የይ​ሁ​ዳን ዘር አመ​ጣ​ለሁ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰው ተራ​ራ​ዬ​ንም ይወ​ር​ሳሉ፤ እኔ የመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸ​ውና ባሪ​ያ​ዎ​ችም ይወ​ር​ሱ​አ​ታል፤ በዚ​ያም ይኖ​ራሉ።</verse>
				<verse number="10">በመ​ን​ጋው መሰ​ማ​ሪ​ያና በዛፍ መካ​ከል በአ​ኮር ሸለ​ቆና በቆ​ላ​ውም የላ​ሞች መመ​ሰ​ግያ ለፈ​ለ​ጉኝ ሕዝቤ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="11">“እና​ንተ ግን እኔን ተዋ​ች​ሁኝ፤ ቅዱ​ሱ​ንም ተራ​ራ​ዬን ረሳ​ችሁ፥ ለአ​ጋ​ን​ን​ትም ማዕድ አዘ​ጋ​ጃ​ችሁ፤ ዕድል ለተ​ባለ ጣዖ​ትም የወ​ይን ጠጅ ለመ​ጠጥ ቍር​ባን ቀዳ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="12">እኔም ለሰ​ይፍ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሁላ​ች​ሁም በሰ​ይፍ ትገ​ደ​ላ​ላ​ችሁ፤ በፊቴ ክፉ ነገር አደ​ረ​ጋ​ችሁ፤ ያል​ወ​ደ​ድ​ሁ​ት​ንም መረ​ጣ​ችሁ እንጂ በጠ​ራ​ኋ​ችሁ ጊዜ አል​መ​ለ​ሳ​ች​ሁ​ል​ኝ​ምና፥ በተ​ና​ገ​ር​ሁም ጊዜ አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝ​ምና።”</verse>
				<verse number="13">ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ ባሪ​ያ​ዎች ይበ​ላሉ፤ እና​ንተ ግን ትራ​ባ​ላ​ችሁ፤ እነሆ፥ ባሪ​ያ​ዎች ይጠ​ጣሉ፤ እና​ንተ ግን ትጠ​ማ​ላ​ችሁ፤ እነሆ፥ ባሪ​ያ​ዎች ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ እና​ንተ ግን ትጐ​ሰ​ቍ​ላ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="14">እነሆ፥ ባሪ​ያ​ዎች ሐሤት ያደ​ር​ጋሉ፤ እና​ንተ ግን ከል​ባ​ችሁ ኀዘን የተ​ነሣ ትጮ​ኻ​ላ​ችሁ፤ መን​ፈ​ሳ​ች​ሁም ስለ ተሰ​በረ ወዮ! ትላ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="15">ስማ​ች​ሁ​ንም እኔ ለመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው ሕዝቤ ጥጋብ አድ​ር​ጋ​ችሁ ትተ​ዋ​ላ​ችሁ፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያጠ​ፋ​ች​ኋል፤ ባሪ​ያ​ዎች ግን በሐ​ዲስ ስም ይጠ​ራሉ።</verse>
				<verse number="16">እን​ዲ​ሁም በም​ድር ላይ የተ​ባ​ረኩ ይሆ​ናሉ፤ እው​ነ​ተ​ኛ​ውን አም​ላክ ያመ​ሰ​ግ​ና​ሉና፥ በም​ድ​ርም ላይ በእ​ው​ነ​ተ​ኛው አም​ላክ ይም​ላ​ሉና፤ የቀ​ድ​ሞ​ው​ንም ጭን​ቀት ረስ​ተ​ዋ​ልና፤ በል​ቡ​ና​ቸ​ውም አያ​ስ​ቡ​ት​ምና።</verse>
				<verse number="17">“እነሆ፥ አዲስ ሰማ​ይና አዲስ ምድር ይሆ​ና​ልና፤ የቀ​ደ​ሙ​ትም አይ​ታ​ሰ​ቡም፤ ወደ ልብም አይ​ገ​ቡም።</verse>
				<verse number="18">ነገር ግን በው​ስ​ጥዋ ደስ​ታ​ንና ሐሤ​ትን ያገ​ኛሉ፤ እኔም ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ደስ​ታን ለሕ​ዝ​ቤም ሐሤ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">እኔም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሐሤ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በሕ​ዝ​ቤም ደስ ይለ​ኛል፤ ከዚ​ያም ወዲያ የል​ቅሶ ድም​ፅና የዋ​ይታ ድምፅ በው​ስ​ጥዋ አይ​ሰ​ማም።</verse>
				<verse number="20">ከዚ​ያም ወዲያ ጥቂት ዘመን ብቻ የሚ​ኖር ሕፃን፥ ወይም ዕድ​ሜ​ውን ያል​ፈ​ጸመ ሽማ​ግሌ አይ​ገ​ኝም፤ ጐል​ማ​ሳው የመቶ ዓመት ሆኖት ይሞ​ታ​ልና፥ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም የመቶ ዓመት ሆኖት የተ​ረ​ገመ ይሆ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="21">ቤቶ​ች​ንም ይሠ​ራሉ፤ ይቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ው​ማል፤ ወይ​ኑን ይተ​ክ​ላሉ፤ ፍሬ​ው​ንም ይበ​ላሉ።</verse>
				<verse number="22">ሌላ እን​ዲ​ቀ​መ​ጥ​በት አይ​ሠ​ሩም፤ ሌላም እን​ዲ​በ​ላው አይ​ተ​ክ​ሉም፤ የሕ​ዝቤ ዕድሜ እንደ ሕይ​ወት ዛፍ ዕድሜ ይሆ​ና​ልና፥ እኔም የመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው በእ​ጃ​ቸው ሥራ ረዥም ዘመን ደስ ይላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="23">እነ​ርሱ ከእ​ነ​ል​ጆ​ቻ​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩ​ካን ዘር ናቸ​ውና በከ​ንቱ አይ​ደ​ክ​ሙም፤ ለር​ግ​ማ​ንም አይ​ወ​ል​ዱም።</verse>
				<verse number="24">“እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ሳይ​ጠሩ እመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ገናም ሲና​ገሩ እነሆ፥ አለሁ እላ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="25">ያን​ጊዜ ተኵ​ላና በግ በአ​ን​ድ​ነት ይሰ​ማ​ራሉ፤ አን​በ​ሳም እንደ በሬ ገለባ ይበ​ላል፤ የእ​ባ​ብም መብል ትቢያ ይሆ​ናል። በተ​ቀ​ደ​ሰው ተራ​ራዬ ሁሉ አይ​ጐ​ዱም፤ አያ​ጠ​ፉ​ምም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="66">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድ​ርም የእ​ግሬ መረ​ገጫ ናት፤ የም​ት​ሠ​ሩ​ልኝ ቤት ምን ዓይ​ነት ነው? የማ​ር​ፍ​በ​ትስ ስፍራ ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="2">ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “ወደ የዋ​ሁና ወደ ጸጥ​ተ​ኛው፥ ከቃ​ሌም የተ​ነሣ ወደ​ሚ​ን​ቀ​ጠ​ቀጥ ሰው ከአ​ል​ሆነ በቀር ወደ ማን እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ?</verse>
				<verse number="3">በሬን የሚ​ሠ​ዋ​ልኝ ኃጥእ ውሻን እን​ደ​ሚ​ያ​ር​ድ​ልኝ ነው፤ የእ​ህ​ልን ቍር​ባን የሚ​ያ​ቀ​ር​ብም የእ​ሪ​ያን ደም እን​ደ​ሚ​ያ​ቀ​ርብ ነው፤ ዕጣ​ን​ንም ለመ​ታ​ሰ​ቢያ የሚ​ያ​ጥን አም​ላ​ክን እን​ደ​ሚ​ፀ​ርፍ ነው፤ እነ​ዚህ የገዛ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን መረጡ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸው ደስ ይላ​ታል።</verse>
				<verse number="4">እኔ ግን አዋ​ር​ዳ​ቸው ዘንድ፥ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም እበ​ቀ​ላ​ቸው ዘንድ እፈ​ቅ​ዳ​ለሁ፤ እኔ በጠ​ራሁ ጊዜ አል​መ​ለ​ሱ​ል​ኝ​ምና፥ በተ​ና​ገ​ር​ሁም ጊዜ አል​ሰ​ሙ​ኝም፤ በፊ​ቴም ክፉ ነገ​ርን አደ​ረጉ፤ ያል​ወ​ደ​ድ​ሁ​ት​ንም መረጡ።”</verse>
				<verse number="5">በቃሉ የም​ት​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ይከ​ብር ዘንድ፦ ደስ​ታ​ች​ሁም ይገ​ለጥ ዘንድ፥ እነ​ር​ሱም ያፍሩ ዘንድ የሚ​ጠ​ሏ​ች​ሁ​ንና የሚ​ጸ​የ​ፉ​አ​ች​ሁን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን በሏ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">የጩ​ኸት ድምፅ ከከ​ተማ፥ ድም​ፅም ከመ​ቅ​ደስ፥ በጠ​ላ​ቶ​ቹም ላይ ፍዳን የሚ​ያ​መጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድምፅ ተሰ​ም​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="7">“ሳታ​ምጥ ወለ​ደች፤ ምጥም ሳያ​ገ​ኛት ወንድ ልጅን ወለ​ደች።</verse>
				<verse number="8">ከቶ እን​ዲህ ያለ ነገ​ርን ማን ሰም​ቶ​አል? እን​ዲ​ህስ ያለ ነገ​ርን ማን አይ​ቶ​አል? በውኑ ሀገር በአ​ንድ ቀን ታም​ጣ​ለ​ችን? ወይስ በአ​ንድ ጊዜ ሕዝብ ይወ​ለ​ዳ​ልን? ጽዮን እን​ዳ​ማ​ጠች ወዲ​ያው ልጆ​ች​ዋን ወል​ዳ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="9">እኔ ተስ​ፋን ሰጠ​ሁሽ፤ አንቺ ግን አላ​ሰ​ብ​ሽ​ኝም ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ሴት እን​ድ​ት​ወ​ልድ፥ መካ​ንም እን​ዳ​ት​ሆን የማ​ደ​ርግ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን?” ይላል አም​ላ​ክሽ።</verse>
				<verse number="10">ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ ደስ ይበ​ልሽ፤ እር​ስ​ዋ​ንም የም​ት​ወ​ድ​ዱ​አት ሁሉ፥ በአ​ን​ድ​ነት ሐሤት አድ​ርጉ፤ ስለ እር​ስ​ዋም ያለ​ቀ​ሳ​ችሁ ሁሉ፥ ከእ​ር​ስዋ ጋር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="11">ትጠቡ ዘንድ ከማ​ጽ​ና​ና​ቷም ጡት ትጠ​ግቡ ዘንድ እጅግ ጠጥ​ታ​ችሁ በክ​ብ​ርዋ ሙላት ደስ ይላ​ችሁ ዘንድ።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “እነሆ፥ ሰላ​ምን እንደ ወንዝ፥ የአ​ሕ​ዛ​ብ​ንም ክብር እን​ደ​ሚ​ጐ​ርፍ ፈሳሽ እመ​ል​ስ​ላ​ታ​ለሁ፤ ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸ​ዋል፤ በጕ​ል​በ​ታ​ቸ​ውም ላይ እያ​ስ​ቀ​መጡ ያቀ​ማ​ጥ​ሏ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="13">እናት ልጅ​ዋን እን​ደ​ም​ታ​ጽ​ናና እን​ዲሁ አጽ​ና​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ውስጥ ትጽ​ና​ና​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="14">ታያ​ላ​ችሁ፤ ልባ​ች​ሁም ሐሤት ታደ​ር​ጋ​ለች፤ አጥ​ን​ታ​ች​ሁም እንደ ለም​ለም ሣር ትበ​ቅ​ላ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ ለሚ​ፈ​ሩት ትታ​ወ​ቃ​ለች፤ ዐላ​ው​ያ​ን​ንም ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል።”</verse>
				<verse number="15">እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓ​ቱን በቍጣ፥ ዘለ​ፋ​ው​ንም በእ​ሳት ነበ​ል​ባል ይመ​ልስ ዘንድ እንደ እሳት ይመ​ጣል፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="16">ምድ​ርም ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሳት ሰውም ሁሉ በሰ​ይፉ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተቀ​ሥ​ፈው የሞ​ቱት ይበ​ዛሉ።</verse>
				<verse number="17">“በአ​ት​ክ​ልት ቦታ ውስጥ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን የሚ​ያ​ጠ​ሩና የሚ​ያ​ነጹ፥ በም​ግብ ቦታም የእ​ሪ​ያን ሥጋ፥ አስ​ጸ​ያፊ ነገ​ር​ንም አይ​ጥ​ንም የሚ​በሉ በአ​ን​ድ​ነት ይጠ​ፋሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="18">“ሥራ​ቸ​ው​ንና አሳ​ባ​ቸ​ውን ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤ እነ​ሆም እኔ እመ​ጣ​ለሁ፤ አሕ​ዛ​ብ​ንና ልሳ​ና​ት​ንም ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይመ​ጣሉ፤ ክብ​ሬ​ንም ያያሉ።</verse>
				<verse number="19">በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ምል​ክት አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ከሞት የዳ​ኑ​ትን ዝና​ዬን ወዳ​ል​ሰሙ፥ ክብ​ሬ​ንም ወዳ​ላዩ ወደ አሕ​ዛብ ወደ ተር​ሴስ፥ ወደ ፉጥ፥ ወደ ሉድ፥ ወደ ሞሳሕ፥ ወደ ቶቤል፥ ወደ ኤላድ በሩቅ ወዳሉ ደሴ​ቶች እል​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ክብ​ሬን ይና​ገ​ራሉ።</verse>
				<verse number="20">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን በም​ስ​ጋና ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እን​ደ​ሚ​ያ​መጡ፥ እን​ዲሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን ይሆን ዘንድ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ሁሉ፥ በፈ​ረ​ሶ​ችና በሰ​ረ​ገ​ሎች፥ በአ​ል​ጋ​ዎ​ችና በበ​ቅ​ሎ​ዎች፥ በጠ​ያር ግመ​ሎ​ችም ላይ አድ​ር​ገው፥ ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ወደ ተቀ​ደ​ሰ​ችው ከተማ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="21">ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን እን​ዲ​ሆኑ ከእ​ነ​ርሱ እወ​ስ​ዳ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="22">“እኔ የም​ሠ​ራ​ቸው አዲስ ሰማ​ይና አዲስ ምድር በፊቴ ጸን​ተው እን​ደ​ሚ​ኖሩ፥ እን​ዲሁ ዘራ​ች​ሁና ስማ​ችሁ ጸን​ተው ይኖ​ራሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="23">እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፦ በየ​መ​ባ​ቻ​ውና በየ​ሰ​ን​በቱ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በፊቴ ይሰ​ግድ ዘንድ ዘወ​ትር ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="24">ወጥ​ተ​ውም በእኔ ያመ​ፁ​ብ​ኝን ሰዎች ሬሳ​ቸ​ውን ያያሉ፤ ትላ​ቸው አይ​ሞ​ትም፤ እሳ​ታ​ቸ​ውም አይ​ጠ​ፋም፤ ለሥጋ ለባ​ሽም ሁሉ ምሳሌ ይሆ​ናሉ።”</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="24">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በብ​ን​ያም ሀገር በዓ​ና​ቶት ከነ​በሩ ካህ​ናት ወገን ወደ ሆነ ወደ ኬል​ቅ​ያስ ልጅ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል።</verse>
				<verse number="2">በይ​ሁዳ ንጉሥ በአ​ሞጽ ልጅ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ዘመን በመ​ን​ግ​ሥቱ በዐ​ሥራ ሦስ​ተ​ኛው ዓመት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል መጣ​ለት።</verse>
				<verse number="3">በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮ​ስ​ያስ ልጅ እስከ ሴዴ​ቅ​ያስ እስከ ዐሥራ አን​ደ​ኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እስከ ተማ​ረ​ከ​ች​በት እስከ አም​ስ​ተ​ኛው ወር ድረስ መጣ።</verse>
				<verse number="4">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="5">“በእ​ና​ትህ ሆድ ሳል​ሠ​ራህ አው​ቄ​ሃ​ለሁ፤ ከማ​ኅ​ፀ​ንም ሳት​ወጣ ቀድ​ሼ​ሃ​ለሁ፥ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ነቢይ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="6">እኔም፥ “ወዮ​ልኝ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እነሆ ሕፃን ነኝና እና​ገር ዘንድ አል​ች​ልም” አልሁ።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እን​ዲህ አለኝ፥ “ወደ​ም​ል​ክህ ሁሉ ዘንድ ትሄ​ዳ​ለ​ህና፥ የማ​ዝ​ዝ​ህ​ንም ሁሉ ትና​ገ​ራ​ለ​ህና፦ ሕፃን ነኝ አት​በል።</verse>
				<verse number="8">እኔ አድ​ንህ ዘንድ ከአ​ንተ ጋራ ነኝና ከፊ​ታ​ቸው የተ​ነሣ አት​ፍራ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጁን ዘር​ግቶ አፌን ዳሰሰ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “እነሆ፥ ቃሌን በአ​ፍህ ውስጥ አኑ​ሬ​አ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="10">እነሆ ትነ​ቅ​ልና ታፈ​ርስ ዘንድ፥ ታጠ​ፋና ትገ​ለ​ብጥ ዘንድ፥ ትሠ​ራና ትተ​ክል ዘንድ በአ​ሕ​ዛ​ብና በመ​ን​ግ​ሥ​ታት ላይ ዛሬ ሾሜ​ሃ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="11">ደግሞ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ “ኤር​ም​ያስ ሆይ! ምን ታያ​ለህ?” እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም፥ “የሎሚ በትር አያ​ለሁ” አልሁ።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን እፈ​ጽ​መው ዘንድ እተ​ጋ​ለ​ሁና መል​ካም አይ​ተ​ሃል” አለኝ።</verse>
				<verse number="13">ሁለ​ተ​ኛም ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “ምን ታያ​ለህ?” እኔም፥ “የሚ​ፈላ አፍ​ላል አያ​ለሁ፤ ፊቱም ወደ ሰሜን ወገን ነው” አልሁ።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ከሰ​ሜን ወገን ክፉ ነገር በም​ድ​ሪቱ በተ​ቀ​መጡ ሁሉ ላይ ይፈ​ስ​ሳል።</verse>
				<verse number="15">እነሆ እኔ በሰ​ሜን ያሉ​ትን የመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቱን ወገ​ኖች ሁሉ እጠ​ራ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ር​ሱም ይመ​ጣሉ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በር መግ​ቢያ በዙ​ሪ​ያ​ዋና በቅ​ጥ​ርዋ ሁሉ ላይ፥ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ሁሉ ላይ ዙፋ​ና​ቸ​ውን ያስ​ቀ​ም​ጣሉ።</verse>
				<verse number="16">ስለ ክፋ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ፥ እኔን ስለ ተዉ፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት ስለ ሠዉ፥ ለእ​ጃ​ቸ​ውም ሥራ ስለ ሰገዱ፥ ፍር​ዴን በእ​ነ​ርሱ ላይ እና​ገ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="17">አንተ ግን ወገ​ብ​ህን ታጠቅ፤ ተነ​ሥም፤ ያዘ​ዝ​ሁ​ህ​ንም ሁሉ ንገ​ራ​ቸው፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ አት​ፍራ። በፊ​ታ​ቸ​ውም አት​ደ​ን​ግጥ አድ​ንህ ዘንድ እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="18">እነሆ በም​ድ​ሪቱ ሁሉ ላይ፥ በይ​ሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት በአ​ለ​ቆ​ች​ዋና በካ​ህ​ናቷ ላይ፥ በም​ድ​ሪ​ቱም ሕዝብ ላይ እንደ ተመ​ሸ​ገች ከተማ፥ እንደ ብረ​ትም ዓምድ፥ እንደ ናስም ቅጥር ዛሬ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">ከአ​ንተ ጋር ይዋ​ጋሉ፤ ነገር ግን አድ​ንህ ዘንድ እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና ድል አይ​ነ​ሡ​ህም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“ሂድ፤ እን​ዲህ ብለህ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጆሮ ተና​ገር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የብ​ላ​ቴ​ን​ነ​ት​ሽን ምሕ​ረት፥ የታ​ጨ​ሽ​በ​ት​ንም ፍቅር፥ በም​ድረ በዳ ዘር ባል​ተ​ዘ​ራ​በት ምድር እንደ ተከ​ተ​ል​ሽኝ አስ​ቤ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">እስ​ራ​ኤል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ነበረ፤ የቡ​ቃ​ያው በኵ​ራ​ትም ነበረ፤ የበ​ሉት እንደ በደ​ለ​ኞች ይቈ​ጠ​ራሉ፤ ክፉም ነገር ያገ​ኛ​ቸ​ዋል፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”</verse>
				<verse number="4">የያ​ዕ​ቆብ ቤት የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ወገ​ኖች ሁሉ ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ ከን​ቱ​ነ​ት​ንም የተ​ከ​ተሉ፥ ከን​ቱም የሆኑ ምን ክፋት አግ​ኝ​ተ​ው​ብኝ ነው?</verse>
				<verse number="6">እነ​ር​ሱም፥ “ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣን፥ በም​ድረ በዳና በባ​ድማ፥ ዕን​ጨ​ትና ውኃ፥ የእ​ን​ጨት ፍሬም በሌ​ለ​በት ምድር፥ ሰው በማ​ያ​ል​ፍ​በ​ትና የሰው ልጅም በማ​ይ​ቀ​መ​ጥ​በት ምድር የመ​ራን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዴት አለ? አላ​ሉም።</verse>
				<verse number="7">ፍሬ​ዋ​ንና በረ​ከ​ቷ​ንም ትበሉ ዘንድ ወደ ቀር​ሜ​ሎስ አገ​ባ​ኋ​ችሁ፤ ነገር ግን በገ​ባ​ችሁ ጊዜ ምድ​ሬን አረ​ከ​ሳ​ችሁ፤ ርስ​ቴ​ንም አጐ​ሳ​ቈ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="8">ካህ​ና​ቱም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዴት አለ? አላ​ሉም፤ ሕጌን የተ​ማ​ሩ​ትም አላ​ወ​ቁ​ኝም፤ ጠባ​ቂ​ዎ​ችም ዐመ​ፁ​ብኝ፤ ነቢ​ያ​ትም በበ​ዐል ትን​ቢት ተና​ገሩ፤ የማ​ይ​ጠ​ቅ​ማ​ቸ​ው​ንም ነገር ተከ​ተሉ።</verse>
				<verse number="9">“ስለ​ዚህ እንደ ገና ከእ​ና​ንተ ጋር እከ​ራ​ከ​ራ​ለሁ፤ ከል​ጆ​ቻ​ች​ሁም ልጆች ጋር እከ​ራ​ከ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">ወደ ኬቲም ደሴ​ቶች እለ​ፉና ተመ​ል​ከቱ፤ ወደ ቄዳ​ርም ላኩና እጅግ መር​ምሩ፤ እን​ደ​ዚ​ህም ያለ ነገር ሆኖ እንደ ሆነ እዩ።</verse>
				<verse number="11">አሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ያል​ሆኑ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ይለ​ውጡ አንደ ሆነ እዩ፤ ነገር ግን ሕዝቤ ክብ​ራ​ቸ​ውን ለማ​ይ​ረባ ነገር ለወጡ።</verse>
				<verse number="12">ሰማይ በዚህ ደነ​ገጠ፤ እጅ​ግም ተን​ቀ​ጠ​ቀጠ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="13">ሕዝቤ ሁለት ክፉ ነገ​ሮ​ችን አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፤ የሕ​ይ​ወት ውኃ ምንጭ እኔን ትተ​ው​ኛል፥ የተ​ነ​ደ​ሉ​ትን ውኃ​ው​ንም ይይዙ ዘንድ የማ​ይ​ች​ሉ​ትን ጕድ​ጓ​ዶች ለራ​ሳ​ቸው ቈፍ​ረ​ዋል።</verse>
				<verse number="14">“በውኑ እስ​ራ​ኤል ባሪያ ነውን? ወይስ የቤት ውላጅ ነውን? ስለ ምን ምርኮ ሆነ?</verse>
				<verse number="15">የአ​ን​በሳ ደቦ​ሎች በእ​ርሱ ላይ አገሡ፤ በእ​ር​ሱም ላይ ደነፉ፤ ምድ​ሩ​ንም ባድማ አደ​ረጉ፤ ከተ​ሞ​ቹ​ንም አፈ​ረሱ፤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸ​ውም የለም።</verse>
				<verse number="16">የሜ​ም​ፎ​ስና የጣ​ፍ​ናስ ልጆች አስ​ነ​ወ​ሩሽ፤ አላ​ገ​ጡ​ብ​ሽም።</verse>
				<verse number="17">ይህን ሁሉ ያመ​ጣ​ብሽ እኔን መር​ሳ​ትሽ አይ​ደ​ለ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክሽ።</verse>
				<verse number="18">አሁ​ንስ የግ​ዮ​ንን ውኃ ትጠጪ ዘንድ በግ​ብፅ መን​ገድ ምን ጉዳይ አለሽ? የወ​ን​ዞ​ች​ንም ውኃ ትጠጪ ዘንድ በአ​ሦር መን​ገድ ምን ጉዳይ አለሽ?</verse>
				<verse number="19">ክፋ​ትሽ ይገ​ሥ​ጽ​ሻል፤ ክዳ​ት​ሽም ይዘ​ል​ፍ​ሻል፤ እኔን መተ​ው​ሽም ክፉና መራራ ነገር መሆ​ኑን ታው​ቂ​ያ​ለሽ፤ ትረ​ጂ​ማ​ለሽ” ይላል አም​ላ​ክሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “መፈ​ራ​ቴም በአ​ንቺ ዘንድ የለም፤ ይህም ደስ አላ​ሰ​ኘ​ኝም” ይላል አም​ላ​ክሽ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="20">ከጥ​ንት ጀምሬ ቀን​በ​ር​ሽን ሰብ​ሬ​አ​ለሁ፤ እስ​ራ​ት​ሽ​ንም ቈር​ጫ​ለሁ፤ አን​ቺም፦ አላ​ገ​ለ​ግ​ልም አልሽ፤ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረ​ብታ ሁሉ ላይ፤ ከለ​ም​ለ​ምም ዛፍ ሁሉ በታች ለማ​መ​ን​ዘር ተጋ​ደ​ምሽ።</verse>
				<verse number="21">እኔ የተ​መ​ረ​ጠች ወይን፥ ፍጹ​ምም እው​ነ​ተኛ ዘር አድ​ርጌ ተክ​ዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን ተለ​ው​ጠሽ እን​ዴት መራራ የእ​ን​ግዳ ወይን ግንድ ሆንሽ?</verse>
				<verse number="22">በእ​ን​ዶድ ብት​ታ​ጠ​ቢም፥ ለራ​ስ​ሽም ሳሙና ብታ​በዢ፥ በእኔ ፊት በኀ​ጢ​አ​ትሽ ረክ​ሰ​ሻል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="23">አን​ቺስ፦ አል​ረ​ከ​ስ​ሁም፤ በዓ​ሊ​ም​ንም አል​ተ​ከ​ተ​ል​ሁም፤ እን​ዴት ትያ​ለሽ? በሸ​ለቆ ያለ​ውን መን​ገ​ድ​ሽን ተመ​ል​ከቺ፤ ያደ​ረ​ግ​ሽ​ው​ንም ዕወቂ። ማታ ማታ በመ​ን​ገ​ዶች ትጮ​ኻ​ለች፤</verse>
				<verse number="24">በም​ድረ በዳ ባሉ ውኃ​ዎች ተዘ​ረ​ጋች፤ በሰ​ው​ነ​ቷም ምኞት ትወ​ሰ​ዳ​ለች፤ ይይ​ዟ​ታል፤ የሚ​መ​ል​ሳት ግን የለም፤ የሚ​ሹ​አ​ትም አይ​ደ​ክ​ሙም፤ በተ​ዋ​ረ​ደ​ች​በ​ትም ጊዜ ያገ​ኙ​አ​ታል።</verse>
				<verse number="25">እግ​ር​ሽን ከሰ​ን​ከ​ል​ካላ መን​ገድ፥ ጕሮ​ሮ​ሽ​ንም ከውኃ ጥም ከል​ክዪ፤ እር​ስዋ ግን፥ “እጨ​ክ​ና​ለሁ፤ እን​ግ​ዶ​ች​ንም ወድ​ጄ​አ​ለሁ” ብላ ተከ​ተ​ለ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">ሌባ በተ​ያዘ ጊዜ እን​ደ​ሚ​ያ​ፍር፤ እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ እነ​ር​ሱና ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ውም፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፥ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ያፍ​ራሉ።</verse>
				<verse number="27">ግን​ዱን፥ “አንተ አባቴ ነህ፤ ድን​ጋ​ዩ​ንም፦ አንተ ወለ​ድ​ኸኝ” ይላሉ፤ ፊታ​ቸ​ው​ንም ሳይ​ሆን ጀር​ባ​ቸ​ውን ሰጡኝ፤ በመ​ከ​ራ​ቸው ጊዜ ግን፥ “ተነ​ሥ​ተህ አድ​ነን ይላሉ።</verse>
				<verse number="28">ለአ​ንተ የሠ​ራ​ሃ​ቸው አማ​ል​ክ​ትህ ግን ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ፥ አማ​ል​ክ​ትህ እንደ ከተ​ሞ​ችህ ቍጥር እን​ዲሁ ናቸ​ውና ይነሡ፤ በመ​ከ​ራ​ህም ጊዜ ያድ​ኑህ። በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በመ​ን​ገ​ዶ​ችዋ ቍጥር ለጣ​ዖት ሠዉ።</verse>
				<verse number="29">“ከእኔ ጋር ለምን ትከ​ራ​ከ​ራ​ላ​ችሁ? ሁላ​ችሁ ክዳ​ች​ሁ​ኛል፤ ሁላ​ች​ሁም ዐም​ፃ​ች​ሁ​ብ​ኛል” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="30">ልጆ​ቻ​ች​ሁን በከ​ንቱ ቀሥ​ፌ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ተግ​ሣ​ጼን አል​ተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁም፤ ሰይ​ፋ​ችሁ እን​ደ​ሚ​ሰ​ብር አን​በሳ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁን በል​ቶ​አል፤ በዚ​ህም አል​ፈ​ራ​ች​ሁ​ኝም።</verse>
				<verse number="31">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ። በውኑ ለእ​ስ​ራ​ኤል ምድረ በዳ ወይስ የጨ​ለ​መች ምድር ሆን​ሁ​በ​ትን? ሕዝ​ቤስ ስለ ምን፦ እኛ አን​ገ​ዛ​ል​ህም፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ወደ አንተ አን​መ​ለ​ስም ይላል?</verse>
				<verse number="32">በውኑ ሙሽራ ጌጥ​ዋን ወይስ ድን​ግል ዝር​ግፍ ጌጥ​ዋን ትረ​ሳ​ለ​ችን? ሕዝቤ ግን ለማ​ይ​ቈ​ጠር ወራት ረስ​ቶ​ኛል።</verse>
				<verse number="33">ፍቅ​ርን ለመ​ሻት እን​ግ​ዲህ በመ​ን​ገ​ድሽ የም​ት​ፈ​ል​ጊው መል​ካም ምን​ድን ነው? እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ መን​ገ​ድ​ሽን ታረ​ክሺ ዘንድ ዳግ​መኛ በደ​ልሽ።</verse>
				<verse number="34">በእ​ጆ​ች​ሽም የን​ጹ​ሓን ድሆች ደም ተገ​ኝ​ቶ​አል፤ በዛፍ ሁሉ ላይ በግ​ልጥ አገ​ኘ​ሁት እንጂ በጕ​ድ​ጓድ ፈልጌ አላ​ገ​ኘ​ሁ​ትም።</verse>
				<verse number="35">አንቺ ግን፦ ንጹሕ ነኝ፤ በእ​ው​ነት ቍጣው ከእኔ ይመ​ለስ አልሽ። እነሆ ኀጢ​አት አል​ሠ​ራ​ሁም ብለ​ሻ​ልና እፋ​ረ​ድ​ሻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="36">መን​ገ​ድ​ሽን እጥፍ ታደ​ርጊ ዘንድ ለምን እጅግ ትሮ​ጫ​ለሽ? በአ​ሦር እን​ዳ​ፈ​ርሽ በግ​ብ​ፅም ታፍ​ሪ​ያ​ለሽ።</verse>
				<verse number="37">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተስ​ፋ​ሽን አስ​ቈ​ር​ጦ​ሻ​ልና፥ በእ​ር​ሱም አይ​ከ​ና​ወ​ን​ል​ሽ​ምና እጅ​ሽን በራ​ስሽ ላይ አድ​ር​ገሽ ከዚያ ደግሞ ትወ​ጫ​ለሽ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">“ሰው ሚስ​ቱን ቢፈታ፥ ከእ​ር​ሱም ዘንድ ሄዳ ሌላ ወንድ ብታ​ገባ፥ በውኑ ደግሞ ወደ እርሱ ትመ​ለ​ሳ​ለ​ችን? ያች ሴት እጅግ የረ​ከ​ሰች አይ​ደ​ለ​ች​ምን? አን​ቺም ከብዙ እረ​ኞች ጋር አመ​ን​ዝ​ረ​ሻል፤ ወደ እኔም ትመ​ለ​ሻ​ለ​ሽን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="2">ዐይ​ኖ​ች​ሽን አቅ​ን​ተሽ አንሺ፤ ያል​ተ​ጋ​ደ​ም​ሽ​በት ስፍራ እን​ዳ​ለም ተመ​ል​ከች። እንደ ምድረ በዳ ቍራ​ዎች በመ​ን​ገድ ላይ ተቀ​ም​ጠሽ በዝ​ሙ​ት​ሽና በክ​ፋ​ትሽ ምድ​ሪ​ቱን አር​ክ​ሰ​ሻ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="3">ለጕ​ስ​ቍ​ል​ናሽ ከብ​ዙ​ዎች እረ​ኞች ጋር ኖርሽ የአ​መ​ን​ዝ​ራም ሴት ፊት ነበ​ረ​ብሽ፥ በሁ​ሉም ዘንድ ያለ ኀፍ​ረት ሄድሽ። ስለ​ዚህ የመ​ከ​ርና የበ​ልግ ዝናም ተከ​ለ​ከለ።</verse>
				<verse number="4">አሁ​ንም፦ እንደ ጌታ​ሽና እንደ አባ​ትሽ፥ እንደ ልጅ​ነት ባል​ሽም አል​ጠ​ራ​ሽ​ኝ​ምን?</verse>
				<verse number="5">ቍጣው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራ​ልን? እስከ ፍጻ​ሜስ ድረስ ይጠ​ብ​ቀ​ዋ​ልን? እነሆ እን​ዲህ ብለሽ ተና​ገ​ርሽ፤ እንደ ተቻ​ለ​ሽም መጠን ክፉን ነገር አደ​ረ​ግሽ።”</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በን​ጉሡ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ዘመን እን​ዲህ አለኝ፥ “ከዳ​ተ​ኛ​ዪቱ እስ​ራ​ኤል ያደ​ረ​ገ​ች​ውን አየ​ህን? ወደ ረዘ​መው ተራራ ሁሉ፥ ወደ ለመ​ለመ ዛፍም ሁሉ በታች ሄደች፤ በዚ​ያም አመ​ነ​ዘ​ረች።</verse>
				<verse number="7">ይህ​ንም ሁሉ ካደ​ረ​ገች በኋላ፦ ወደ እኔ ተመ​ለሽ አል​ኋት፤ ነገር ግን አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ አታ​ላይ እኅቷ ይሁ​ዳም አየች።</verse>
				<verse number="8">ከዳ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም እስ​ራ​ኤል እን​ዳ​መ​ነ​ዘ​ረች አየሁ፤ የፍ​ች​ዋ​ንም ደብ​ዳቤ በእ​ጅዋ ሰጥቼ ሰደ​ድ​ኋት፤ ጎስ​ቋላ እኅቷ ይሁዳ ግን በዚያ አል​ፈ​ራ​ችም፤ እር​ስ​ዋም ደግሞ ሄዳ አመ​ነ​ዘ​ረች።</verse>
				<verse number="9">ዝሙ​ቷም ከንቱ ሆነ፤ እር​ስ​ዋም ከድ​ን​ጋ​ይና ከግ​ንድ ጋር አመ​ነ​ዘ​ረች።</verse>
				<verse number="10">በዚ​ህም ሁሉ ከዳ​ተ​ኛ​ዪቱ ይሁዳ በሐ​ሰት እንጂ በፍ​ጹም ልብዋ ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ከጎ​ስ​ቋ​ላዋ ይሁዳ ይልቅ ከዳ​ተ​ኛ​ዪቱ እስ​ራ​ኤል ራስ​ዋን አጸ​ደ​ቀች።</verse>
				<verse number="12">ሂድና ይህን ቃል ወደ ሰሜን ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በል፦ ከዳ​ተ​ኛ​ዪቱ እስ​ራ​ኤል ሆይ! ወደ እኔ ተመ​ለሽ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ መሓሪ ነኝና፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አል​ቈ​ጣ​ምና በእ​ና​ንተ ላይ ፊቴን አላ​ጸ​ናም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="13">በአ​ም​ላ​ክሽ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ እን​ዳ​መ​ፅሽ፥ መን​ገ​ድ​ሽ​ንም ከለ​መ​ለመ ዛፍ ሁሉ በታች ለእ​ን​ግ​ዶች እንደ ዘረ​ጋሽ፥ ቃሌ​ንም እን​ዳ​ል​ሰ​ማሽ ኀጢ​አ​ት​ሽን ብቻ ዕወቂ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="14">ከዳ​ተ​ኞች ልጆች ሆይ! እኔ እገ​ዛ​ች​ኋ​ለ​ሁና ተመ​ለሱ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። አን​ዱ​ንም ከአ​ን​ዲት ከተማ ሁለ​ቱ​ንም ከአ​ንድ ወገን እወ​ስ​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወደ ጽዮ​ንም አመ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="15">እንደ ልቤም የሚ​ሆኑ ጠባ​ቂ​ዎ​ችን እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዕ​ው​ቀ​ትና በማ​ስ​ተ​ዋ​ልም ይጠ​ብ​ቁ​አ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="16">“በበ​ዛ​ችሁ ጊዜ፥ በም​ድ​ርም ላይ በረ​ባ​ችሁ ጊዜ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በዚያ ዘመን፦ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት እነ​ኋት አይ​ሉም፤ በል​ባ​ቸ​ውም አያ​ስ​ቧ​ትም፤ በአ​ፋ​ቸ​ውም አይ​ጠ​ሯ​ትም፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም አይ​ሿ​ትም።</verse>
				<verse number="17">ያን​ጊ​ዜም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋን ብለው ይጠ​ሩ​አ​ታል፤ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ክፉ​ውን እል​ከኛ ልባ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለው አይ​ሄ​ዱም።</verse>
				<verse number="18">በዚ​ያም ዘመን የይ​ሁዳ ቤት ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት ይሄ​ዳል፤ በአ​ን​ድም ሆነው ከሰ​ሜን ምድር ርስት አድ​ርጌ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ወደ ሰጠ​ኋት ምድር ይመ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="19">“እኔም፦ ይሁን አልሁ፤ በወ​ን​ዶች ልጆች መካ​ከል እሾ​ም​ሃ​ለሁ፤ አሕ​ዛ​ብን የሚ​ገዛ ሁሉን ቻይ የሆነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ርስት የተ​መ​ረ​ጠ​ች​ውን ምድር ለአ​ንተ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ አባቴ ትለ​ኛ​ለህ፤ ከእ​ኔም አት​መ​ለ​ስም አልሁ ብለ​ሃ​ልና።</verse>
				<verse number="20">ሚስት ባል​ዋን እን​ደ​ም​ት​ከዳ እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ከዱኝ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="21">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ዐም​ጸ​ዋ​ልና፥ ቅዱስ አም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም ረስ​ተ​ዋ​ልና ከብዙ ሰዎች ድምፅ ተሰማ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ልቅ​ሶና ጩኸ​ትም ተሰማ።</verse>
				<verse number="22">“ከዳ​ተ​ኞች ልጆች ሆይ! ተመ​ለሱ፤ ቍስ​ላ​ች​ሁ​ንም እፈ​ው​ሳ​ለሁ። እነሆ እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እን​ሆ​ና​ለን፤ አንተ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነህና።</verse>
				<verse number="23">በእ​ው​ነት የተ​ራ​ሮች ኀይል፥ የኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም ኀይል ሐሰት ነው፤ ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤል መዳን በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="24">ነገር ግን ከት​ን​ሽ​ነ​ታ​ችን ጀምሮ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንን ሥራ፥ በጎ​ቻ​ቸ​ው​ንና ላሞ​ቻ​ቸ​ውን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ እፍ​ረት በል​ቶ​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="25">ከት​ን​ሽ​ነ​ታ​ችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባ​ቶ​ቻ​ችን በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኀጢ​አት ሠር​ተ​ና​ልና፥ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ን​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ን​ምና በእ​ፍ​ረ​ታ​ችን ተኝ​ተ​ናል፤ ውር​ደ​ታ​ች​ንም ሸፍ​ኖ​ናል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">እስ​ራ​ኤል ወደ እኔ ቢመ​ለስ ይመ​ለስ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ርኵ​ሰ​ቱ​ንም ከአፉ ቢያ​ስ​ወ​ግድ፤ ከፊ​ቴም የተ​ነሣ ቢፈራ፥</verse>
				<verse number="2">ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ብሎ በእ​ው​ነ​ትና በቅ​ን​ነት፤ በጽ​ድ​ቅም ቢምል፥ አሕ​ዛብ በእ​ርሱ ይባ​ረ​ካሉ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለይ​ሁዳ ወን​ዶ​ችና ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነዋ​ሪ​ዎች እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ልባ​ች​ሁን አድሱ በእ​ሾ​ህም ላይ አት​ዝሩ።</verse>
				<verse number="4">እና​ን​ተም የይ​ሁዳ ሰዎች በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ት​ኖሩ ሆይ፥ ስለ ሥራ​ችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እን​ዳ​ይ​ወጣ የሚ​ያ​ጠ​ፋ​ውም ሳይ​ኖር እን​ዳ​ይ​ነድ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ተገ​ረዙ፤ የል​ባ​ች​ሁ​ንም ሸለ​ፈት አስ​ወ​ግዱ።</verse>
				<verse number="5">በይ​ሁዳ ዘንድ ተና​ገሩ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ላይ አው​ሩና፦ በሀ​ገ​ሪቱ ላይ መለ​ከት ንፉ በሉ፤ ጮኻ​ች​ሁም፦ ሁላ​ችሁ ተሰ​ብ​ሰቡ፤ ወደ ተመ​ሸ​ጉ​ትም ከተ​ሞች እን​ግባ በሉ።</verse>
				<verse number="6">ከሰ​ሜን ክፉ ነገ​ር​ንና ጽኑ ጥፋ​ትን አመ​ጣ​ለ​ሁና ዓላ​ማ​ች​ሁን አንሡ፤ ወደ ጽዮ​ንም ሽሹ፥ ፍጠኑ፥ አት​ዘ​ግዩ።</verse>
				<verse number="7">አን​በሳ ከጕ​ድ​ጓዱ ወጥ​ቶ​አል፤ አሕ​ዛ​ብ​ንም ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው የሚ​ዘ​ርፍ ተነ​ሥ​ቶ​አል፤ ምድ​ር​ሽን ባድማ ያደ​ርግ ዘንድ፥ ከተ​ሞ​ች​ሽ​ንም ሰው እን​ዳ​ይ​ኖ​ር​ባ​ቸው ያፈ​ር​ሳ​ቸው ዘንድ ከስ​ፍ​ራው ወጥ​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="8">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽኑ ቍጣ ከእኛ ዘንድ አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ምና ማቅ ልበሱ፤ አል​ቅ​ሱም፤ ዋይም በሉ።</verse>
				<verse number="9">በዚ​ያም ቀን ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የን​ጉ​ሡና የመ​ኳ​ን​ንቱ ልብ ይጠ​ፋል፤ ካህ​ና​ቱም ይደ​ነ​ግ​ጣሉ፤ ነቢ​ያ​ቱም ያደ​ን​ቃሉ።</verse>
				<verse number="10">እኔም፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ወዮ! አንተ ሰይፍ እስከ ሰው​ነ​ታ​ቸው ድረስ እስ​ክ​ት​ደ​ርስ ሰላም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል” ብለህ ይህን ሕዝ​ብና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እጅግ አታ​ለ​ልህ አልሁ።</verse>
				<verse number="11">በዚያ ጊዜ ለዚህ ሕዝ​ብና ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዲህ ይሏ​ቸ​ዋል፦ በም​ድረ በዳ የሚ​ያ​ስት ጋኔን አለ፤ የሕ​ዝቤ ሴት ልጅ መን​ገ​ድም ለን​ጽ​ሕና ወይም ለቅ​ድ​ስና አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="12">አሳች ጋኔን ይመ​ጣል፤ አሁ​ንም እኔ ፍር​ዴን በእ​ነ​ርሱ ላይ እና​ገ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">እነሆ! እንደ ደመና ይወ​ጣል፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው፤ ፈረ​ሶ​ቹም ከን​ስር ይልቅ ፈጣ​ኖች ናቸው። ተዋ​ር​ደ​ና​ልና ወዮ​ልን።</verse>
				<verse number="14">ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ! ትድኚ ዘንድ ልብ​ሽን ከክፉ ነገር እጠቢ። ክፉ አሳብ የሚ​ኖ​ር​ብሽ እስከ መቼ ነው?</verse>
				<verse number="15">የወሬ ነጋሪ ድምፅ ከዳን ይመ​ጣል፥ ከኤ​ፍ​ሬ​ምም ተራ​ሮች መከራ ይሰ​ማል።</verse>
				<verse number="16">ለአ​ሕ​ዛብ አሳ​ስቡ፥ “እነሆ፥ መጡ! ጠላ​ቶች ከሩቅ ሀገር ይመ​ጣሉ፤ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ላይ ይጮ​ኻሉ ብላ​ችሁ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ አውጁ።</verse>
				<verse number="17">በእኔ ላይ ዐመ​ፀኛ ሆና​ለ​ችና በዙ​ሪ​ያዋ ከብ​በው እንደ እርሻ ጠባ​ቂ​ዎች ሆነ​ው​ባ​ታል” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="18">መን​ገ​ድ​ሽና ክፉ ሥራሽ ይህን አድ​ር​ጎ​ብ​ሻል፤ ይህ ክፋ​ትሽ መራራ ነው፤ ወደ ልብ​ሽም ደር​ሶ​አል።</verse>
				<verse number="19">አን​ጀቴ! አን​ጀቴ! ልቤ በጣም ታም​ሞ​አል፤ ነፍ​ሴም አእ​ም​ሮ​ዋን አጥ​ታ​ለች፤ በው​ስ​ጤም ልቤ ታው​ኮ​ብ​ኛል፤ ነፍ​ሴም የመ​ለ​ከ​ትን ድም​ፅና የሰ​ል​ፍን ውካታ ሰም​ታ​ለ​ችና ዝም እል ዘንድ አል​ች​ልም።</verse>
				<verse number="20">መከራ በመ​ከራ ላይ ተጠ​ር​ቶ​አል፤ ምድር ሁሉ ተዋ​ር​ዳ​ለ​ችና፤ በድ​ን​ገ​ትም ድን​ኳኔ ጠፋ፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችም ተቀ​ዳ​ደዱ።</verse>
				<verse number="21">የሚ​ሸ​ሹ​ትን የም​መ​ለ​ከት፥ የመ​ለ​ከ​ቱ​ንስ ድምፅ የም​ሰማ እስከ መቼ ነው?</verse>
				<verse number="22">የሕ​ዝቤ አለ​ቆች አላ​ወ​ቁ​ኝም፤ እነ​ርሱ ሰነ​ፎች ልጆች ናቸው፤ ማስ​ተ​ዋ​ልም የላ​ቸ​ውም፤ ክፉ ነገ​ርን ለማ​ድ​ረግ ብል​ሃ​ተ​ኞች ናቸው፤ በጎ ነገ​ርን ማድ​ረግ ግን አያ​ው​ቁም።</verse>
				<verse number="23">ምድ​ሪ​ቱን ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነ​ሆም ባዶ ነበ​ረች፤ ሰማ​ያ​ት​ንም ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ ብር​ሃ​ንም አል​ነ​በ​ረ​በ​ትም።</verse>
				<verse number="24">ተራ​ሮ​ችን ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነ​ሆም ይን​ቀ​ጠ​ቀጡ ነበር፤ ኮረ​ብ​ቶ​ችም ሁሉ ይና​ወጡ ነበር።</verse>
				<verse number="25">ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነ​ሆም ሰው አል​ነ​በ​ረም፤ የሰ​ማ​ይም ወፎች ሁሉ ሸሽ​ተው ነበር።</verse>
				<verse number="26">ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነ​ሆም ቀር​ሜ​ሎስ ምድረ በዳ ሆነች፤ ከተ​ሞ​ችም ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ነሣ በእ​ሳት ተቃ​ጠሉ፤ ከጽኑ ቍጣ​ውም የተ​ነሣ ፈጽ​መው ጠፉ።</verse>
				<verse number="27">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላል፦ ምድር ሁሉ ባድማ ትሆ​ና​ለች፤ ነገር ግን ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋ​ትም።</verse>
				<verse number="28">ስለ​ዚህ ምድር ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ በላ​ይም ሰማይ ይጠ​ቍ​ራል፤ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና፤ አል​ጸ​ጸ​ትም ወደ​ፊት እሮ​ጣ​ለሁ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም አል​መ​ለ​ስም።</verse>
				<verse number="29">ከፈ​ረ​ሰ​ኞ​ችና ከቀ​ስ​ተ​ኞች ድምፅ የተ​ነሣ ሀገሯ ሁሉ ሸሽ​ታ​ለች፤ ወደ ዋሻ​ዎች ይገ​ባሉ፥ በዛፍ ሥር ተሸ​ሸጉ፥ በቋ​ጥ​ኝም ላይ ይወ​ጣሉ፤ ከተ​ማዋ ሁሉ ተለ​ቅ​ቃ​ለች፤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም ሰው የለም።</verse>
				<verse number="30">አን​ቺስ ምን ታደ​ር​ጊ​ያ​ለሽ? ቀይ በለ​በ​ስሽ ጊዜ፥ በወ​ርቅ አን​ባ​ርም ባጌ​ጥሽ ጊዜ፥ ዐይ​ን​ሽ​ንም በኵል በተ​ኳ​ልሽ ጊዜ፥ በከ​ንቱ ታጌ​ጫ​ለሽ፤ ፍቅ​ረ​ኞ​ችሽ አቃ​ለ​ሉሽ፥ ነፍ​ስ​ሽን ይሹ​አ​ታል።</verse>
				<verse number="31">እን​ደ​ም​ታ​ምጥ፥ የበ​ኵር ልጅ​ዋ​ንም እን​ደ​ም​ት​ወ​ልድ ሴት ጩኸት፥ ጩኸ​ት​ሽን ሰም​ቻ​ለ​ሁና፤ የጽ​ዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድ​ካም ሰለለ፤ እጆ​ች​ዋ​ንም ትዘ​ረ​ጋ​ለች፤ ተገ​ድ​ለው ከሞ​ቱት የተ​ነሣ ነፍሴ ዝላ​ለ​ችና ወዮ​ልኝ! አለች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">“በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መን​ገ​ዶች ሩጡ፤ ተመ​ል​ከ​ቱም፤ ዕወ​ቁም፤ በአ​ደ​ባ​ባ​ይ​ዋም ፈልጉ፤ ፍር​ድን የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን እው​ነ​ት​ንም የሚ​ሻ​ውን ሰው ታገኙ እንደ ሆነ ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="2">እነ​ር​ሱም፦ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ቢሉ የሚ​ም​ሉት በሐ​ሰት ነው።”</verse>
				<verse number="3">አቤቱ! ዐይ​ኖ​ችህ ለሃ​ይ​ማ​ኖት አይ​ደ​ሉ​ምን? አንተ ቀሥ​ፈ​ሃ​ቸ​ዋል፤ ነገር ግን አላ​ዘ​ኑም፤ ቀጥ​ቅ​ጠ​ሃ​ቸ​ው​ማል፤ ነገር ግን ተግ​ሣ​ጽን እንቢ አሉ፤ ፊታ​ቸ​ውን ከድ​ን​ጋይ ይልቅ አጠ​ን​ክ​ረ​ዋል፤ ይመ​ለ​ሱም ዘንድ እንቢ አሉ።</verse>
				<verse number="4">እኔም እን​ዲህ አልሁ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገ​ድና የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን ፍርድ አላ​ወ​ቁ​ምና እነ​ዚህ በእ​ው​ነት ድሆ​ችና ደካ​ሞች ናቸው፤</verse>
				<verse number="5">ወደ ታላ​ላ​ቆቹ እሄ​ዳ​ለሁ እና​ገ​ራ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ እነ​ርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገ​ድና የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን ፍርድ ያው​ቃ​ሉና።” እነ​ዚህ ግን ቀን​በ​ሩን በአ​ን​ድ​ነት ሰብ​ረ​ዋል፤ እስ​ራ​ቱ​ንም ቈር​ጠ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">ስለ​ዚህ ኀጢ​አ​ታ​ቸው በዝ​ቶ​አ​ልና፥ የዐ​መ​ፃ​ቸ​ውም ብዛት ጸን​ቶ​አ​ልና አን​በሳ ከዱር ወጥቶ ይሰ​ብ​ራ​ቸ​ዋል፤ የበ​ረ​ሃም ተኵላ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፥ ነብ​ርም በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ላይ ይተ​ጋል፤ ከዚ​ያም የሚ​ወጣ ሁሉ ይነ​ጠ​ቃል።</verse>
				<verse number="7">“ከእ​ነ​ዚህ ነገ​ሮች በየ​ት​ኛው ይቅር እል​ሻ​ለሁ? ልጆ​ችሽ ትተ​ው​ኛል፤ አማ​ል​ክ​ትም ባል​ሆኑ ምለ​ዋል፤ አጠ​ገ​ብ​ኋ​ቸ​ውም፤ እነ​ርሱ ግን አመ​ነ​ዘሩ፤ በአ​መ​ን​ዝ​ራ​ዎ​ቹም ቤት ዐደሩ።</verse>
				<verse number="8">እንደ አለሌ ፈረ​ሶች ሆኑ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም የባ​ል​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ሚስ​ቶች አረ​ከሱ።</verse>
				<verse number="9">በውኑ ስለ እነ​ዚህ ነገ​ሮች አል​ቀ​ሥ​ፍ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነፍ​ሴስ እን​ደ​ዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አት​በ​ቀ​ል​ምን?</verse>
				<verse number="10">“ወደ ቅጥ​ርዋ ወጥ​ታ​ችሁ አፍ​ርሱ፤ ነገር ግን ፈጽ​ማ​ችሁ አታ​ጥፉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናቸ​ውና መጠ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋን አት​ርፉ።</verse>
				<verse number="11">የእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና የይ​ሁዳ ቤት በእኔ ላይ እጅግ ወን​ጅ​ለ​ዋል” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="12">የይ​ሁ​ዳም ወገ​ኖች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዋሹ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ ክፉ ነገ​ርም አይ​መ​ጣ​ብ​ንም ሰይ​ፍ​ንና ራብ​ንም አና​ይም፤</verse>
				<verse number="13">ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ችን ነፋስ ናቸው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል በእ​ነ​ርሱ ዘንድ የለም፤ እን​ዲ​ህም ይደ​ረ​ግ​ባ​ቸ​ዋል።”</verse>
				<verse number="14">ስለ​ዚ​ህም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እን​ደ​ዚህ ያለ ቃል ተና​ግ​ራ​ች​ኋ​ልና እነሆ በአ​ፍህ ውስጥ ቃሌን እሳት፥ ይህ​ንም ሕዝብ እን​ጨት አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ትበ​ላ​ቸ​ው​ማ​ለች።</verse>
				<verse number="15">የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እነሆ ሕዝ​ብን ከሩቅ አመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ኀያል ጥን​ታዊ ሕዝብ ነው፤ ቋን​ቋ​ቸ​ው​ንም የማ​ታ​ው​ቀው፥ የሚ​ና​ገ​ሩ​ት​ንም የማ​ታ​ስ​ተ​ው​ለው ሕዝብ ነው።</verse>
				<verse number="16">ከን​ፈ​ራ​ቸ​ውም እንደ ተከ​ፈተ መቃ​ብር ነው፤ ሁሉም ኀያ​ላን ናቸው።</verse>
				<verse number="17">መከ​ር​ህ​ንና እን​ጀ​ራ​ህን ይበ​ላሉ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ህ​ንም ይበ​ሉ​አ​ቸ​ዋል፤ በጎ​ች​ህ​ንና ላሞ​ች​ህ​ንም ይበ​ላሉ፤ ወይ​ን​ህ​ንና በለ​ስ​ህ​ንም፥ ዘይ​ት​ህ​ንም ይበ​ላሉ፤ የም​ት​ታ​መ​ና​ቸ​ውን የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞ​ች​ህ​ንም በሰ​ይፍ ያጠ​ፋሉ።”</verse>
				<verse number="18">ነገር ግን “በዚያ ዘመን ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋ​ች​ሁም።”</verse>
				<verse number="19">እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ እና​ንተ፥ “አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ነገር ሁሉ ስለ ምን አደ​ረ​ገ​ብን?” ብትሉ፥ አንተ፥ “እንደ ተዋ​ች​ሁኝ፥ በሀ​ገ​ራ​ች​ሁም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት እን​ዳ​መ​ለ​ካ​ችሁ፥ እን​ዲሁ ለእ​ና​ንተ ባል​ሆነ ሀገር ለሌ​ሎች ሰዎች ትገ​ዛ​ላ​ችሁ” ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="20">ይህ​ንም በያ​ዕ​ቆብ ቤት አውሩ፤ በይ​ሁ​ዳም አሰሙ፦</verse>
				<verse number="21">እና​ንተ ሰነ​ፎች ልበ ቢሶች፥ ዐይን እያ​ላ​ችሁ የማ​ታዩ፥ ጆሮም እያ​ላ​ችሁ የማ​ት​ሰሙ ሕዝብ ሆይ! ይህን ስሙ።</verse>
				<verse number="22">በውኑ እኔን አት​ፈ​ሩ​ምን? ከፊ​ቴስ አት​ደ​ነ​ግ​ጡ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እን​ዳ​ያ​ልፍ አሸ​ዋን በዘ​ለ​ዓ​ለም ትእ​ዛዝ ለባ​ሕር ዳርቻ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ ሞገ​ዱም ቢት​ረ​ፈ​ረ​ፍና ቢጮኽ ከእ​ርሱ አያ​ል​ፍም።</verse>
				<verse number="23">ለዚ​ህም ሕዝብ የማ​ይ​ሰ​ማና የዐ​መፀ ልብ አላ​ቸው፤ ተመ​ል​ሰ​ውም ሄደ​ዋል።</verse>
				<verse number="24">በል​ባ​ቸ​ውም፦ የመ​ከ​ሩ​ንና የበ​ል​ጉን ዝናብ በጊዜ የሚ​ሰ​ጠ​ውን፥ ለመ​ከ​ርም የተ​መ​ደ​ቡ​ትን ወራት የሚ​ጠ​ብ​ቅ​ል​ንን አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ፍራ አላ​ሉም።</verse>
				<verse number="25">በደ​ላ​ች​ሁም እነ​ዚ​ህን አስ​ቀ​ር​ታ​ለች፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም መል​ካ​ምን ነገር ከእ​ና​ንተ አር​ቃ​ለች።</verse>
				<verse number="26">በሕ​ዝቤ መካ​ከል ክፉ​ዎች ሰዎች ተገ​ኝ​ተ​ዋል፤ ሰዎ​ች​ንም ይዘው ይገ​ድሉ ዘንድ ወጥ​መ​ድን ይዘ​ረ​ጋሉ።</verse>
				<verse number="27">ቀፎ ወፎ​ችን እን​ደ​ሚ​ሞላ፥ እን​ዲሁ ቤታ​ቸው ሽን​ገ​ላን ሞል​ታ​ለች፤ በዚ​ህም ከብ​ረ​ዋል ባለ​ጸ​ጎ​ችም ሆነ​ዋል።</verse>
				<verse number="28">ፍር​ድን አጣ​መሙ ለድ​ሃ​አ​ደ​ጎች ፍር​ድን አል​ፈ​ረ​ዱም፤ ለመ​በ​ለ​ቷም አል​ተ​ሟ​ገ​ቱም።</verse>
				<verse number="29">በውኑ ስለ እነ​ዚህ ነገ​ሮች አል​ቀ​ሥ​ፍ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነፍ​ሴስ እን​ደ​ዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አት​በ​ቀ​ል​ምን?</verse>
				<verse number="30">የም​ት​ሰ​ቀ​ጥ​ጥና የም​ታ​ስ​ደ​ነ​ግጥ ነገር በም​ድር ላይ ሆና​ለች፤</verse>
				<verse number="31">ነቢ​ያት በሐ​ሰት ትን​ቢት ይና​ገ​ራሉ፥ ካህ​ና​ትም በእ​ጃ​ቸው ያጨ​በ​ጭ​ባሉ፥ ሕዝ​ቤም እን​ዲህ ያለ​ውን ነገር ይወ​ድ​ዳሉ፤ በፍ​ጻ​ሜ​ውስ ምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">እና​ንተ የብ​ን​ያም ልጆች፥ ክፉ ነገር፥ ታላ​ቅም ጥፋት ከመ​ስዕ ይጐ​በ​ኛ​ልና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ ለመ​ሸሽ ጽኑ፤ በቴ​ቁሔ መለ​ከ​ቱን ንፉ፤ በቤ​ት​ካ​ሪም ላይ ምል​ክ​ትን አንሡ።</verse>
				<verse number="2">ቅም​ጥል የጽ​ዮን ልጅ ሆይ! ውበ​ትሽ ይጐ​ሳ​ቈ​ላል።</verse>
				<verse number="3">እረ​ኞ​ችና መን​ጎ​ቻ​ቸው ወደ እር​ስዋ ይመ​ጣሉ፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ይተ​ክ​ሉ​ባ​ታል፤ በእ​ጃ​ቸ​ውም መን​ጋ​ቸ​ውን ያሰ​ማ​ራሉ።</verse>
				<verse number="4">በእ​ር​ስዋ ላይ ሰልፍ አዘ​ጋጁ፤ ተነሡ፥ በቀ​ት​ርም እን​ውጣ። ቀኑ መሽ​ቶ​አ​ልና፥ የቀ​ኑም ጥላ አል​ፎ​አ​ልና ወዮ​ልን።</verse>
				<verse number="5">ተነሡ በሌ​ሊ​ትም እን​ውጣ፤ መሠ​ረ​ቶ​ች​ዋ​ንም እና​ፍ​ርስ።</verse>
				<verse number="6">ኀያል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ዛፎ​ች​ዋን ቍረጡ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ላይ ኀይ​ልን አፍ​ስሱ ይህች ከተማ የሐ​ሰት ከተማ ናት፤ መካ​ከ​ልዋ ሁሉ ግፍ ብቻ ነው።</verse>
				<verse number="7">በጕ​ድ​ጓድ ውኃ እን​ደ​ሚ​ፈ​ልቅ፥ እን​ዲሁ ክፋቷ ከእ​ር​ስዋ ዘንድ ይፈ​ል​ቃል፤ ግፍና ቅሚያ በእ​ር​ስዋ ዘንድ ይሰ​ማል፤ ደዌና ቍስ​ልም ሁል​ጊዜ በፊቷ አለ።</verse>
				<verse number="8">ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፤ ነፍሴ ከአ​ንቺ እን​ዳ​ት​ለይ፥ አን​ቺ​ንም ባድ​ማና ወና እን​ዳ​ላ​ደ​ር​ግሽ፥ ተግ​ሣ​ጽን ተቀ​በዪ።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰው ወይ​ንን እን​ደ​ሚ​ቃ​ርም፥ እን​ዲሁ ከእ​ስ​ራ​ኤል የቀ​ሩ​ትን ይቃ​ር​ሙ​አ​ቸ​ዋል፤ እጅ​ህን እንደ ወይን ለቃሚ ወደ እን​ቅብ ዘርጋ።</verse>
				<verse number="10">ይሰ​ሙ​ኝስ ዘንድ ለማን እና​ገ​ራ​ለሁ? ለማ​ንስ አዳ​ኛ​ለሁ? እነሆ፥ ጆሮ​አ​ቸው ያል​ተ​ገ​ረ​ዘች ናት፤ ለመ​ስ​ማ​ትም አይ​ች​ሉም፤ እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ለስ​ድብ ሆኖ​ባ​ቸ​ዋል፥ ይሰ​ሙት ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ዱ​ምና።</verse>
				<verse number="11">ስለ​ዚህ ቍጣ​ዬን መላ​ሁ​ባ​ቸው፤ ታገ​ሥሁ፤ ፈጽ​ሜም አላ​ጠ​ፋ​ኋ​ቸ​ውም፤ በሜዳ በሕ​ፃ​ናት ላይ በጐ​ል​ማ​ሶ​ችም ጉባኤ ላይ መዓ​ቴን በአ​ን​ድ​ነት አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ባል ከሚ​ስቱ ጋር ሽማ​ግ​ሌ​ውም ከጎ​በዙ ጋር ይያ​ያ​ዛ​ልና።</verse>
				<verse number="12">እጄን በዚች ምድር በሚ​ኖሩ ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለ​ሁና ቤቶ​ቻ​ቸዉ፥ እር​ሻ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ ሴቶ​ቻ​ቸ​ውም በአ​ን​ድ​ነት ለሌ​ሎች ይሰ​ጣሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤</verse>
				<verse number="13">ከታ​ናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ኀጢ​አ​ትን አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፥ ከሐ​ሳዊ ነቢይ ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ሐሰ​ትን አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="14">የሕ​ዝ​ቤ​ንም ስብ​ራት በጥ​ቂቱ ይፈ​ው​ሳሉ፤ ሰላም ሳይ​ሆን፦ ሰላም ሰላም ይላሉ።</verse>
				<verse number="15">ርኩስ ነገ​ርን ስለ ሠሩ አፍ​ረ​ዋ​ልን? ምንም አላ​ፈ​ሩም፤ ውር​ደ​ት​ንም አላ​ወ​ቁም፤ ስለ​ዚ​ህም ከሚ​ወ​ድቁ ጋር ይወ​ድ​ቃሉ፤ በጐ​በ​ኘ​ኋ​ቸው ጊዜ ይዋ​ረ​ዳሉ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በመ​ን​ገድ ላይ ቁሙ ተመ​ል​ከ​ቱም፤ የቀ​ደ​መ​ች​ው​ንም መን​ገድ ጠይቁ፤ መል​ካ​ሚቱ መን​ገድ ወዴት እንደ ሆነች ዕወቁ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ላይ ሂዱ፤ ለነ​ፍ​ሳ​ች​ሁም መድ​ኀ​ኒ​ትን ታገ​ኛ​ላ​ችሁ፤” እነ​ርሱ ግን፥ “አን​ሄ​ድ​ባ​ትም” አሉ።</verse>
				<verse number="17">እኔም፥ “የመ​ለ​ከ​ቱን ድምፅ አድ​ምጡ” ብዬ ጠባ​ቂ​ዎ​ችን ሾም​ሁ​ባ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን፥ “አና​ዳ​ም​ጥም” አሉ።</verse>
				<verse number="18">አሕ​ዛ​ብና የመ​ን​ጋው ጠባ​ቂ​ዎች ሆይ፥ ስለ​ዚህ ስሙ።</verse>
				<verse number="19">ምድር ሆይ፥ ስሚ! እነሆ ቃሌን ስላ​ል​ሰሙ፥ ሕጌ​ንም ስለ ጣሉ፥ እኔ​ንም ስለ ናቁ በዚህ ሕዝብ ላይ እንደ ሥራ​ቸው ፍሬ፥ ክፉን ነገር አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">ስለ ምንስ ከሳባ ዕጣ​ንን፥ ከሩ​ቅም ሀገር ቀረ​ፋን ታቀ​ር​ቡ​ል​ኛ​ላ​ችሁ? የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን አል​ቀ​በ​ለ​ውም፤ ቍር​ባ​ና​ች​ሁም ደስ አያ​ሰ​ኘ​ኝም።</verse>
				<verse number="21">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በዚህ ሕዝብ ላይ ደዌን አሳ​ድ​ራ​ለሁ፤ አባ​ቶ​ችና ልጆ​ችም በአ​ን​ድ​ነት ይታ​መ​ማሉ፤ ጎረ​ቤ​ትና ባል​ን​ጀ​ራም ይጠ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ሕዝብ ከሰ​ሜን ሀገር ይመ​ጣል፤ ታላቅ ሕዝ​ብም ከም​ድር ዳርቻ ይነ​ሣል።</verse>
				<verse number="23">ቀስ​ት​ንና ጦርን ይይ​ዛሉ፤ ጨካ​ኞች ናቸው፤ ምሕ​ረ​ትም አያ​ደ​ር​ጉም፤ ድም​ፃ​ቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይተ​ም​ማል፤ በሰ​ረ​ገ​ላና በፈ​ረ​ሶ​ችም ላይ ይቀ​መ​ጣሉ፤ የጽ​ዮን ሴት ልጅ ሆይ! እንደ እሳት ያጠ​ፉ​ሻል።</verse>
				<verse number="24">ጩኸ​ታ​ቸ​ውን ሰም​ተን፥ እጃ​ችን ደክ​ማ​ለች፤ ወላ​ድን ሴት ምጥ እን​ደ​ሚ​ይ​ዛት ጭን​ቀት ይዞ​ናል።</verse>
				<verse number="25">የጠ​ላት ሰይፍ ከብ​በ​ዋ​ች​ኋ​ልና ወደ ሜዳ አት​ውጡ፤ በመ​ን​ገ​ድም ላይ አት​ሂዱ።</verse>
				<verse number="26">የሕ​ዝቤ ልጅ ሆይ፥ ማቅ ልበሺ፤ በራ​ስ​ሺም ላይ አመድ ነስ​ንሺ፥ አጥፊ በላ​ያ​ችን በድ​ን​ገት ይመ​ጣ​ብ​ና​ልና ለተ​ወ​ዳጅ ልጅ እን​ደ​ሚ​ደ​ረግ ልቅሶ መራራ ልቅሶ አል​ቅሺ።</verse>
				<verse number="27">በተ​ፈ​ታኝ ሕዝቤ መካ​ከል ፈታኝ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንም በፈ​ተ​ንሁ ጊዜ ታው​ቀ​ኛ​ለህ።</verse>
				<verse number="28">እነ​ርሱ ሁሉ እጅግ ደን​ቆ​ሮ​ዎች ናቸው፤ በጠ​ማ​ማ​ነት ይሄ​ዳሉ፤ ሁሉም እንደ ናስና ብረት የዛጉ ናቸው።</verse>
				<verse number="29">ወና​ፉን የሚ​አ​ና​ፋው ደከመ፤ እር​ሳ​ሱም በእ​ሳት ቀለጠ፤ አን​ጥ​ረ​ኛ​ውም መልሶ በከ​ንቱ ያቀ​ል​ጠ​ዋል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም አል​ተ​ወ​ገ​ደም።</verse>
				<verse number="30">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንቆ​አ​ቸ​ዋ​ልና የተ​ናቀ ብር ብላ​ችሁ ጥሩ​አ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፤ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በር ቁም፤ ይህ​ንም ቃል እን​ዲህ ብለህ ተና​ገር፦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትሰ​ግዱ ዘንድ በእ​ነ​ዚህ በሮች የም​ት​ገቡ ከይ​ሁዳ ያላ​ችሁ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።</verse>
				<verse number="3">የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና ሥራ​ች​ሁን አቅኑ፤ በዚ​ህም ስፍራ አሳ​ድ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ ይህ ነው እያ​ላ​ችሁ በሐ​ሰት ቃል በራ​ሳ​ችሁ አት​ታ​መኑ።</verse>
				<verse number="5">መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና ሥራ​ች​ሁን ፈጽ​ማ​ችሁ ብታ​ቃኑ፥ በሰ​ውና በጓ​ደ​ኛው መካ​ከል ቅን ፍርድ ብት​ፈ​ርዱ፤</verse>
				<verse number="6">መጻ​ተ​ኛ​ው​ንና ድሃ​አ​ደ​ጉን፥ መበ​ለ​ቲ​ቱ​ንም ባት​ገፉ፥ በዚ​ህም ስፍራ ንጹሕ ደምን ባታ​ፈ​ስሱ፥ ክፉም ሊሆ​ን​ባ​ችሁ እን​ግ​ዶ​ችን አማ​ል​ክት ባት​ከ​ተሉ፤</verse>
				<verse number="7">ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ በሰ​ጠ​ኋ​ቸው ምድር በዚህ ስፍራ አሳ​ድ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">“እነሆ በማ​ት​ጠ​ቀ​ሙ​በት በሐ​ሰት ቃል ብት​ተ​ማ​መ​ኑም፤</verse>
				<verse number="9">ብት​ገ​ድ​ሉም፥ ብታ​መ​ነ​ዝ​ሩም፥ ብት​ሰ​ር​ቁም፥ በሐ​ሰ​ትም ብት​ምሉ፥ ለበ​አ​ልም ብታ​ጥኑ፥ የማ​ታ​ው​ቋ​ቸ​ው​ንም እን​ግ​ዶች አማ​ል​ክት ብት​ከ​ተሉ ክፉ ያገ​ኛ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="10">መጥ​ታ​ች​ሁም ስሜ በተ​ጠ​ራ​በት በዚህ ቤት በፊቴ ብት​ቆሙ፦ ይህን አስ​ጸ​ያፊ የሆነ ነገ​ርን ሁሉ ከማ​ድ​ረግ ተለ​ይ​ተ​ናል ብትሉ፥</verse>
				<verse number="11">ይህ ስሜ የተ​ጠ​ራ​በት ቤት በዐ​ይ​ና​ችሁ የሌ​ቦች ዋሻ ነውን? እነሆ፥ እኔ አይ​ቻ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="12">“ነገር ግን በቀ​ድሞ ዘመን ስሜን ወዳ​ሳ​ደ​ር​ሁ​በት በሴሎ ወደ ነበ​ረው ስፍ​ራዬ ሂዱ፤ ከሕ​ዝ​ቤም ከእ​ስ​ራ​ኤል ክፋት የተ​ነሣ ያደ​ረ​ግ​ሁ​በ​ትን እዩ።</verse>
				<verse number="13">አሁ​ንም ይህን ነገር ሁሉ ስላ​ደ​ረ​ጋ​ችሁ፥ ተና​ገ​ር​ኋ​ችሁ፤ ነገር ግን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ ጠራ​ኋ​ች​ሁም፤ ነገር ግን አል​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም፤</verse>
				<verse number="14">ስለ​ዚህ በሴሎ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እን​ዲሁ ስሜ በተ​ጠ​ራ​በት፥ እና​ን​ተም በም​ት​ተ​ማ​መ​ኑ​በት ቤት ለእ​ና​ን​ተና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በሰ​ጠ​ኋ​ችሁ ስፍራ እን​ዲሁ አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን የኤ​ፍ​ሬ​ምን ዘር ሁሉ፥ እንደ ጣልሁ፥ እን​ዲሁ ከፊቴ እጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “ስለ​ዚህ ሕዝብ አንተ አት​ጸ​ልይ፤ ይቅር እላ​ቸው ዘንድ አት​ማ​ል​ደኝ፤ የእ​ነ​ር​ሱን ነገር አል​ሰ​ማ​ህ​ምና ትለ​ም​ን​ላ​ቸው ዘንድ ወደ እኔ አት​ምጣ።”</verse>
				<verse number="17">እነ​ር​ሱስ በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ውስ​ጥና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መን​ገ​ዶች የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን አታ​ይ​ምን?</verse>
				<verse number="18">ያስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ፥ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት እን​ጎቻ እን​ዲ​ያ​ደ​ርጉ፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት የመ​ጠጥ ቍር​ባን እን​ዲ​ያ​ፈ​ስሱ ልጆች እን​ጨት ይሰ​በ​ስ​ባሉ፤ አባ​ቶ​ችም እሳት ያነ​ድ​ዳሉ፤ ሴቶ​ችም ዱቄት ይለ​ው​ሳሉ።</verse>
				<verse number="19">እኔን ያስ​ቈ​ጣ​ሉን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ፊታ​ቸው ያፍር ዘንድ ለራ​ሳ​ቸው አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="20">እን​ግ​ዲህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ቍጣ​ዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ፥ በሰ​ውና በእ​ን​ስሳ ላይ፥ በዱር ዛፎ​ችና በም​ድር ፍሬ ላይ ይፈ​ስ​ሳል፤ ይነ​ድ​ዳል፤ አይ​ጠ​ፋ​ምም።”</verse>
				<verse number="21">የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ከቍ​ር​ባ​ና​ችሁ ጋር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን ጨምሩ፤ ሥጋ​ው​ንም ብሉ።</verse>
				<verse number="22">ከግ​ብፅ ምድር ባወ​ጣ​ኋ​ችሁ ቀን ስለ​ሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና ስለ ቍር​ባን ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁ​ምና፥ አላ​ዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ው​ምም።</verse>
				<verse number="23">ነገር ግን፦ ቃሌን ስሙ፤ እኔ አም​ላክ እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ሕዝብ ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ፤ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ላ​ችሁ ዘንድ ባዘ​ዝ​ኋ​ችሁ መን​ገድ ሂዱ ብዬ በዚህ ነገር አዘ​ዝ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">ነገር ግን በክፉ ልባ​ቸው አሳ​ብና እል​ከ​ኝ​ነት ሄዱ፤ ወደ​ፊ​ትም ሳይ​ሆን ወደ ኋላ​ቸው ሄዱ እንጂ አል​ሰ​ሙ​ኝም ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም አላ​ዘ​ነ​በ​ሉም።</verse>
				<verse number="25">አባ​ቶ​ቻ​ቸው ከግ​ብፅ ምድር ከወ​ጡ​በት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፤ በቀ​ንና በሌ​ሊት ባሪ​ያ​ዎ​ችን ነቢ​ያ​ትን ሁሉ ልኬ​ባ​ቸው ነበር፤ አዎ ልኬ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="26">ነገር ግን አን​ገ​ታ​ቸ​ውን አደ​ነ​ደኑ እንጂ አል​ሰ​ሙ​ኝም፤ ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም አላ​ዘ​ነ​በ​ሉም፤ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከአ​ደ​ረ​ጉት ይልቅ የባሰ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="27">“ይህን ሁሉ ቃል ለዚህ ሕዝብ ትነ​ግ​ራ​ለህ፤ ነገር ግን አይ​ሰ​ሙ​ህም፤ ትጠ​ራ​ቸ​ው​ማ​ለህ፤ ነገር ግን አይ​መ​ል​ሱ​ል​ህም።</verse>
				<verse number="28">አን​ተም፦ የአ​ም​ላ​ኩን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ያል​ሰማ፥ ተግ​ሣ​ጽ​ንም ያል​ተ​ቀ​በለ ሕዝብ ይህ ነው፤ እው​ነት ጠፍ​ቶ​አል፤ ከአ​ፋ​ቸ​ውም ተቈ​ር​ጦ​አል ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="29">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቍ​ጣ​ውን ትው​ልድ ጥሎ​አ​ልና፥ ትቶ​ታ​ል​ምና ጠጕ​ር​ሽን ቈር​ጠሽ፥ ጣዪው፤ በከ​ን​ፈ​ሮ​ች​ሽም ሙሾ አው​ርጂ።</verse>
				<verse number="30">የይ​ሁዳ ልጆች በፊቴ ክፉ ነገ​ርን ሠር​ተ​ዋል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ያረ​ክ​ሱ​ትም ዘንድ ስሜ በተ​ጠ​ራ​በት ቤት ርኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውን አኑ​ረ​ዋል።</verse>
				<verse number="31">እኔም ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ት​ንና በልቤ ያላ​ሰ​ብ​ሁ​ትን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ሳት ያቃ​ጥሉ ዘንድ በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ያለ​ች​ውን የቶ​ፌ​ትን መሥ​ዊ​ያ​ዎች ሠር​ተ​ዋል።</verse>
				<verse number="32">“ስለ​ዚህ እነሆ ስፍራ ከማ​ጣት የተ​ነሣ በቶ​ፌት ይቀ​በ​ራ​ሉና የታ​ረ​ዱት ሰዎች ሸለቆ ይባ​ላል እንጂ የቶ​ፌት ኮረ​ብታ ወይም የሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ዳግ​መኛ የማ​ይ​ባ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="33">የዚህ ሕዝብ ሬሳ ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት መብል ይሆ​ናል፥ የሚ​ቀ​ብ​ራ​ቸው የለ​ምና።</verse>
				<verse number="34">ምድ​ሪ​ቱም ባድማ ትሆ​ና​ለ​ችና ከይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ የእ​ል​ል​ታን ድም​ፅና የደ​ስ​ታን ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽ​ራን ድም​ፅና የሴት ሙሽ​ራን ድምፅ አጠ​ፋ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">“በዚ​ያም ዘመን ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታ​ትን አጥ​ን​ትና የመ​ኳ​ን​ን​ቱን አጥ​ንት፥ የካ​ህ​ና​ቱን አጥ​ን​ትና የነ​ቢ​ያ​ቱን አጥ​ንት፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ሰዎች አጥ​ንት ከመ​ቃ​ብ​ሮ​ቻ​ቸው ያወ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="2">በወ​ደ​ዱ​አ​ቸ​ውና በአ​መ​ለ​ኳ​ቸው፥ በተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውና በፈ​ለ​ጓ​ቸው፥ በሰ​ገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም በፀ​ሐ​ይና በጨ​ረቃ፥ በከ​ዋ​ክ​ብ​ትም፥ በሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ ፊት ይዘ​ረ​ጓ​ቸ​ዋል፤ አያ​ለ​ቅ​ሱ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ቀ​ብ​ሯ​ቸ​ው​ምም፤ በም​ድ​ርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="3">እኔም ባሳ​ደ​ድ​ኋ​ቸው ስፍራ ሁሉ የቀሩ፥ ከዚ​ህች ክፉ ትው​ልድ የተ​ረፉ ቅሬ​ቶች ሁሉ፥ ከሕ​ይ​ወት ይልቅ ሞትን ይመ​ር​ጣሉ።”</verse>
				<verse number="4">እን​ዲ​ህም ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የወ​ደቀ አይ​ነ​ሣ​ምን? የሳ​ተስ አይ​መ​ለ​ስ​ምን?</verse>
				<verse number="5">ሕዝቤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስለ ምን ወደ ኋላ​ቸው ተመ​ለሱ? ዐመ​ፅን ዐም​ፀ​ዋል፥ መመ​ለ​ስ​ንም እንቢ ብለ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">አደ​መ​ጥሁ፤ ሰማ​ሁም፤ ቅንን ነገር አል​ተ​ና​ገ​ሩም፤ ማና​ቸ​ውም፦ ምን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ? ብሎ ከክ​ፋቱ ንስሓ የገባ የለም፤ የሚ​ሮ​ጠ​ውም ወደ ሰልፍ እን​ደ​ሚ​ሮጥ ፈረስ ሲሮጥ ደከመ።</verse>
				<verse number="7">ሽመላ በሰ​ማይ ጊዜ​ዋን አው​ቃ​ለች፤ ዋኖ​ስና ጨረባ፥ ዋሊ​ያም የመ​ም​ጣ​ታ​ቸ​ውን ጊዜ ይጠ​ብ​ቃሉ፤ ሕዝቤ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍርድ አላ​ወ​ቁም።</verse>
				<verse number="8">“እና​ን​ተስ፦ ጥበ​በ​ኞች ነን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ ከእኛ ጋር ነው እን​ዴት ትላ​ላ​ችሁ? እነሆ ጸሓ​ፊ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ከንቱ ሆኑ፤ በሐ​ሰ​ትም ብርዕ ተጠ​ቀሙ።</verse>
				<verse number="9">ጥበ​በ​ኞች አፍ​ረ​ዋል፤ ደን​ግ​ጠ​ው​ማል፤ ተማ​ር​ከ​ው​ማል፤ እነሆ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ጥለ​ዋል፤ ምን ዓይ​ነት ጥበብ አላ​ቸው?</verse>
				<verse number="10">ከታ​ናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስ​ትን ያስ​ባ​ሉና፥ ከነ​ቢ​ዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ በተ​ን​ኰል ያደ​ር​ጋ​ሉና ስለ​ዚህ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ለሌ​ሎች፥ እር​ሻ​ቸ​ው​ንም ለሚ​ወ​ር​ሱ​ባ​ቸው እሰ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">የሕ​ዝ​ቤ​ንም ሴት ልጅ ስብ​ራት በማ​ቃ​ለል ይፈ​ው​ሳሉ፤ ሰላም ሳይ​ሆን፦ ሰላም ሰላም ይላሉ።</verse>
				<verse number="12">አስ​ጸ​ያፊ ነገ​ርን ስለ ሠሩ አፍ​ረ​ዋ​ልን? ምንም አላ​ፈ​ሩም፤ እፍ​ረ​ት​ንም አላ​ወ​ቁም፤ ስለ​ዚህ ከሚ​ወ​ድቁ ጋር ይወ​ድ​ቃሉ፤ በጐ​በ​ኘ​ኋ​ቸ​ውም ጊዜ ይዋ​ረ​ዳሉ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="13">አዝ​መ​ራ​ቸ​ውን ይሰ​በ​ስ​ባሉ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን በወ​ይን ላይ ፍሬ፥ በበ​ለስ ዛፍ ላይ በለስ የለም፤ ቅጠ​ልም ይረ​ግ​ፋል፤ ሰጠ​ኋ​ቸው፤ አለ​ፈ​ባ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="14">“ዝም ብለን ለምን እን​ቀ​መ​ጣ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ በደ​ልን አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አጥ​ፍ​ቶ​ና​ልና፥ የሐ​ሞ​ት​ንም ውኃ አጠ​ጥ​ቶ​ና​ልና ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ ወደ ተመ​ሸጉ ከተ​ሞች እን​ግባ በዚ​ያም እን​ጥፋ።</verse>
				<verse number="15">ሰላ​ምን በተ​ስፋ ተጠ​ባ​በ​ቅን፤ ለይ​ቅ​ር​ታም ጊዜ መል​ካም ነገ​ርን አጣን፤ እነ​ሆም ድን​ጋጤ ሆነ።</verse>
				<verse number="16">የፈ​ረ​ሶ​ቹን የሩጫ ድምፅ ከዳን ሰማን፤ ከሠ​ራ​ዊቱ ፈረ​ሶች ሩጫ ድምፅ የተ​ነ​ሣም ምድር በመ​ላዋ ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠች፤ መጥ​ተ​ውም ምድ​ሪ​ቱ​ንና በእ​ር​ስ​ዋም ያለ​ውን ሁሉ፥ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንና የተ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ት​ንም በሉ።</verse>
				<verse number="17">እነሆ አስ​ማት የማ​ይ​ከ​ለ​ክ​ላ​ቸ​ውን የሚ​ገ​ድሉ እባ​ቦ​ችን እሰ​ድ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይነ​ድ​ፉ​አ​ች​ኋል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="18">ልባ​ች​ሁን ታም​ማ​ችሁ ትቅ​በ​ዘ​በ​ዛ​ላ​ችሁ። ከሚ​ያ​ቅ​በ​ዘ​ብዝ የልብ ሕመ​ማ​ችሁ የሚ​ያ​ድ​ና​ችሁ የለም።</verse>
				<verse number="19">እነሆ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን የለ​ምን? ወይስ ንጉ​ሥዋ በእ​ር​ስዋ ዘንድ የለ​ምን? የሚል የወ​ገኔ ሴት ልጅ ጩኸት ድምፅ ከሩቅ ሀገር ተሰማ። በተ​ቀ​ረፁ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውና በባ​ዕድ ከን​ቱ​ነ​ትስ ያስ​ቈ​ጡኝ ስለ ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="20">መከሩ አል​ፎ​አል፤ በጋ​ውም ዐል​ቋል፤ እኛም አል​ዳ​ን​ንም።</verse>
				<verse number="21">በሕ​ዝቤ ሴት ልጅ ስብ​ራት እኔ ወድቄ ተሰ​ብ​ሬ​አ​ለሁ፤ ጠቍ​ሬ​ማ​ለሁ፤ ራስ ማዞ​ርም ይዞ​ኛል፤ ምጥ እን​ደ​ያ​ዛ​ትም ሴት በመ​ከ​ራው እጨ​ነ​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="22">በገ​ለ​ዓድ መድ​ኀ​ኒት የለ​ምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለ​ምን? የወ​ገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለ ምን አል​ሆ​ነም?</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">ስለ ተገ​ደሉ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊ​ትና ቀን አለ​ቅስ ዘንድ ለራሴ ውኃን፥ ለዐ​ይ​ኔም የዕ​ን​ባን ምንጭ ማን በሰ​ጠኝ?</verse>
				<verse number="2">ሁሉም አመ​ን​ዝ​ሮች፥ የዐ​መ​ጸ​ኞች ጉባኤ ናቸ​ውና ሕዝ​ቤን እተ​ዋ​ቸው ዘንድ ከእ​ነ​ር​ሱም እለይ ዘንድ በም​ድረ በዳ ማደ​ሪ​ያን ማን በሰ​ጠኝ?</verse>
				<verse number="3">“ምላ​ሳ​ቸ​ውን ለሐ​ሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በም​ድ​ርም በረቱ፤ ነገር ግን ለእ​ው​ነት አይ​ደ​ለም፤ ከክ​ፋት ወደ ክፋት ይሄ​ዳ​ሉና፥ እኔ​ንም አላ​ወ​ቁ​ምና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="4">ወን​ድ​ምም ሁሉ ያሰ​ና​ክ​ላ​ልና፥ ባል​ን​ጀ​ራም ሁሉ በጠ​ማ​ማ​ነት ይሄ​ዳ​ልና እና​ንተ ሁሉ ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ፤ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁም አት​ታ​መኑ።</verse>
				<verse number="5">እያ​ን​ዳ​ንዱ በባ​ል​ን​ጀ​ራው ላይ ይሣ​ለ​ቃል በእ​ው​ነ​ትም አይ​ና​ገ​ርም፤ ሐሰት መና​ገ​ር​ንም ምላ​ሳ​ቸው ተም​ሮ​አል፤ በደሉ መመ​ለ​ስ​ንም እንቢ አሉ።</verse>
				<verse number="6">አራ​ጣ​ንም በአ​ራጣ ላይ ይቀ​በ​ላሉ፤ ተን​ኰ​ልን በተ​ን​ኰል ላይ ይሠ​ራሉ፤ “እኔ​ንም ያው​ቁኝ ዘንድ እንቢ ብለ​ዋል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="7">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ አቀ​ል​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እፈ​ት​ና​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት እን​ደ​ዚሁ አደ​ር​ጋ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="8">ምላ​ሳ​ቸው የተ​ሳለ ፍላጻ ነው፤ ንግ​ግ​ራ​ቸው ሽን​ገላ ነው፤ ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ቸው ሰላ​ምን ይና​ገ​ራሉ፤ በል​ባ​ቸው ግን ጥላ​ቻን ይይ​ዛሉ።</verse>
				<verse number="9">በውኑ ስለ​ዚህ ነገር በመ​ቅ​ሠ​ፍት አል​ጐ​በ​ኝ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነፍ​ሴስ እን​ደ​ዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አት​በ​ቀ​ል​ምን?</verse>
				<verse number="10">በተ​ራ​ሮቹ ላይ አል​ቅሱ፤ በም​ድረ በዳም ጎዳና ላይ እዘኑ፤ ሰው ጠፍ​ት​ዋ​ልና፤ የሚ​መ​ላ​ለ​ስም የለ​ምና ሙሾ​ው​ንም አሙሹ፤ የሰ​ማይ ወፍ ድም​ፅ​ንም እስከ ከብት ድምፅ ድረስ አይ​ሰ​ሙም፤ ደን​ግ​ጠ​ውም ተማ​ር​ከው ሄዱ።</verse>
				<verse number="11">ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም የፍ​ር​ስ​ራሽ ክምር፥ የቀ​በ​ሮም ማደ​ሪያ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም ከተ​ሞች ሰው እን​ዳ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">ይህን የሚ​ያ​ስ​ተ​ውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? ያወ​ራስ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ ለማን ተና​ገረ? ሰው እን​ዳ​ያ​ል​ፍ​ባት ምድ​ርስ ስለ ምን ጠፋች፤ እንደ ምድረ በዳስ ስለ ምን ተቃ​ጠ​ለች?</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፦ ሕዝቤ በፊ​ታ​ቸው የሰ​ጠ​ኋ​ቸ​ውን ሕጌን ትተ​ዋል፤ ቃሌ​ንም አል​ሰ​ሙም።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን የል​ባ​ቸ​ውን ምኞ​ትና አባ​ቶ​ቻ​ቸው ያስ​ተ​ማ​ሩ​አ​ቸ​ውን ጣዖት ተከ​ት​ለ​ዋል፤</verse>
				<verse number="15">ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ፥ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ይህን ሕዝብ መከ​ራን አበ​ላ​ዋ​ለሁ፤ የሐ​ሞ​ት​ንም ውኃ አጠ​ጣ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">እነ​ር​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም በአ​ላ​ወ​ቋ​ቸው አሕ​ዛብ መካ​ከል እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እስከ አጠ​ፋ​ቸ​ውም ድረስ በስተ ኋላ​ቸው ሰይ​ፍን እሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እን​ዲ​መጡ አል​ቃ​ሾች ሴቶ​ችን ጥሩ፤ ወደ ብል​ሃ​ተ​ኞች ሴቶ​ችም ላኩ፤ መጥ​ተ​ውም ይን​ገ​ሩ​አ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="18">ፈጥ​ነ​ውም ሙሾ ያሙ​ሹ​ላ​ችሁ፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም እን​ባን ያፍ​ስሱ፤ ከዐ​ይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም ሽፋ​ሽ​ፍ​ቶች ውኃ ይፍ​ለቅ።</verse>
				<verse number="19">ምድ​ርን ትተ​ና​ልና፥ ቤቶ​ቻ​ች​ን​ንም ጥለን ሄደ​ና​ልና እን​ዴት ጐሰ​ቈ​ልን! እን​ዴት አፈ​ርን! የሚል የል​ቅሶ ድምፅ በጽ​ዮን ተሰ​ም​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="20">እና​ንተ ሴቶች ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ ጆሮ​አ​ች​ሁም የአ​ፉን ቃል ትቀ​በል፤ ለሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም ልቅ​ሶ​ውን፥ እያ​ን​ዳ​ን​ድ​ዋም ለባ​ል​ን​ጀ​ራዋ ዋይ​ታን ታስ​ተ​ምር።</verse>
				<verse number="21">ሕፃ​ና​ቱ​ንም በመ​ን​ገድ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቹ​ንም በአ​ደ​ባ​ባ​ዮ​ቻ​ችን ያጠፋ ዘንድ ሞት በመ​ስ​ኮ​ቶ​ቻ​ችን ወደ ሀገ​ራ​ችን ገብ​ቶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="22">የሰ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ሬሳ እንደ ጕድፍ በእ​ርሻ ላይ፥ ማንም እን​ደ​ማ​ይ​ሰ​በ​ስ​በው ከአ​ጫ​ጆች በኋላ እን​ደ​ሚ​ቀር ቃር​ሚያ ይወ​ድ​ቃል።</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ጠቢብ በጥ​በቡ አይ​መካ፤ ኀያ​ልም በኀ​ይሉ አይ​መካ፤ ባለ​ጠ​ጋም በብ​ል​ጥ​ግ​ናው አይ​መካ፤</verse>
				<verse number="24">ነገር ግን የሚ​መ​ካው፦ ምሕ​ረ​ት​ንና ፍር​ድን፥ ጽድ​ቅ​ንም በም​ድር ላይ የማ​ደ​ርግ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሆ​ኔን በማ​ወ​ቁና በማ​ስ​ተ​ዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘኝ ይህ ነውና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="25">“እነሆ ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። የተ​ገ​ረ​ዙ​ት​ንና ያል​ተ​ገ​ረ​ዙ​ትን ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት እጐ​በ​ኛ​ለሁ።</verse>
				<verse number="26">አሕ​ዛብ ሁሉ ያል​ተ​ገ​ረዙ ናቸ​ውና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ ልባ​ቸው ያል​ተ​ገ​ረዘ ነውና የተ​ገ​ረ​ዙ​ትን ሁሉ፥ ግብ​ጽ​ንና ይሁ​ዳን፥ ኤዶ​ም​ያ​ስ​ንም፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች፥ ሞዓ​ብ​ንም፥ በም​ድረ በዳም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ጠጕ​ራ​ቸ​ውን በዙ​ሪያ የተ​ላ​ጩ​ት​ንም ሁሉ የም​ጐ​በ​ኝ​በት ዘመን እነሆ ይመ​ጣል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ና​ንተ ላይ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ስሙ።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የአ​ሕ​ዛ​ብን መን​ገድ አት​ማሩ፤ ከሰ​ማይ ምል​ክ​ትም አት​ፍሩ፤ አሕ​ዛብ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ነሣ ይፈ​ራ​ሉና።</verse>
				<verse number="3">የአ​ሕ​ዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፥ ከዱር በመ​ጥ​ረ​ቢያ እን​ደ​ሚ​ቈ​ረጥ፥ በሠ​ራ​ተ​ኛም እጅ እን​ደ​ሚ​ሠራ እን​ጨት ነው።</verse>
				<verse number="4">በብ​ርና በወ​ርቅ ይለ​ብ​ጡ​ታል፤ እን​ዳ​ይ​ና​ወ​ጥም በች​ን​ካ​ርና በመ​ዶሻ ይቸ​ነ​ክ​ሩ​ታል።</verse>
				<verse number="5">እንደ ተቀ​ረጸ ብር ናቸው፤ እነ​ር​ሱም አይ​ና​ገ​ሩም፤ መራ​መ​ድም አይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸ​ዋል። ክፉ መሥ​ራ​ትም አይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና፥ ደግ​ሞም መል​ካም ይሠሩ ዘንድ አይ​ች​ሉ​ምና አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው።”</verse>
				<verse number="6">አቤቱ! እንደ አንተ ያለ የለም፤ አንተ ታላቅ ነህ ስም​ህም በኀ​ይል ታላቅ ነው።</verse>
				<verse number="7">የአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ ሆይ! በአ​ሕ​ዛብ ጥበ​በ​ኞች ሁሉ መካ​ከል፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለ​ሌለ፥ ለአ​ንተ ክብር ይገ​ባ​ልና አን​ተን የማ​ይ​ፈራ ማን ነው?</verse>
				<verse number="8">በአ​ንድ ጊዜ ሰን​ፈ​ዋል፥ ደን​ቍ​ረ​ው​ማል፤ ጣዖ​ታት የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩት የእ​ን​ጨት ነገር ብቻ ነው።</verse>
				<verse number="9">የሠ​ራ​ተ​ኛና የአ​ን​ጥ​ረኛ እጅ ሥራ የሆነ ከተ​ር​ሴስ ጥፍ​ጥፍ ብር፥ ከአ​ፌ​ዝም ወርቅ ይመ​ጣል፤ ልብ​ሳ​ቸ​ውም ሰማ​ያ​ዊና ቀይ ግምጃ ነው፤ ሁሉም የብ​ል​ሃ​ተ​ኞች ሥራ ናቸው።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እው​ነ​ተኛ አም​ላክ ነው፤ እር​ሱም ሕያው አም​ላ​ክና የዘ​ለ​ዓ​ለም ንጉሥ ነው፤ ከቍ​ጣው የተ​ነሣ ምድር ትን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣ​ለች፤ አሕ​ዛ​ብም መዓ​ቱን አይ​ች​ሉም።</verse>
				<verse number="11">እና​ን​ተም፦ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ያል​ፈ​ጠሩ እነ​ዚህ አማ​ል​ክት ከም​ድር ላይ፥ ከሰ​ማ​ይም በታች ፈጽ​መው ይጥፉ ትሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="12">ምድ​ርን በኀ​ይሉ የፈ​ጠረ፥ ዓለ​ሙን በጥ​በቡ ያጸና፥ ሰማ​ያ​ት​ንም በማ​ስ​ተ​ዋሉ የዘ​ረጋ እርሱ ነው።</verse>
				<verse number="13">በላይ በሰ​ማይ ውኆ​ችን ይሰ​በ​ስ​ባል፤ ከም​ድ​ርም ዳርቻ ደመ​ና​ትን ከፍ ያደ​ር​ጋል፤ ለዝ​ና​ብም መብ​ረ​ቅን ያደ​ር​ጋል፤ ነፋ​ስ​ንም ከቤተ መዛ​ግ​ብቱ ያወ​ጣል።</verse>
				<verse number="14">ሰው ሁሉ ዕው​ቀት አጥቶ ሰን​ፎ​አል፤ አን​ጥ​ረ​ኛም ሁሉ ከቀ​ረ​ጸው ምስል የተ​ነሣ አፍ​ሮ​አል፤ ቀልጦ የተ​ሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስ​ት​ን​ፋ​ስም የለ​ው​ምና።</verse>
				<verse number="15">አገ​ጣ​ጥ​መው የሚ​ሠ​ሩት ሥራ ከንቱ ነው፤ በተ​ጐ​በኙ ጊዜም ይጠ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="16">የያ​ዕ​ቆብ ዕድል ፈንታ እንደ እነ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ እርሱ ሁሉን የፈ​ጠረ ነውና እስ​ራ​ኤ​ልም የር​ስቱ ነገድ ነውና፤ ስሙም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።</verse>
				<verse number="17">በም​ሽግ ውስጥ የተ​ቀ​መ​ጥሽ ሆይ! ኀይ​ል​ሽን ከውጭ ሰብ​ስቢ፤</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ እነሆ በም​ድ​ሪቱ የሚ​ኖ​ሩ​ትን በመ​ከራ አሰ​ና​ክ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ት​ሽም እን​ዲ​ያ​ገ​ኛ​ቸው አስ​ጨ​ን​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">ስለ ስብ​ራቴ ወዮ​ልኝ! ቍስ​ሌም ክፉ ነው፤ እኔ ግን፦ በእ​ው​ነት የመ​ከራ ቁስሌ ነው፤ እር​ሱ​ንም መሸ​ከም ይገ​ባ​ኛል አልሁ።</verse>
				<verse number="20">ድን​ኳ​ኔም ተበ​ዘ​በዘ፤ አው​ታ​ሬም ሁሉ ተቈ​ረጠ፤ ልጆ​ችና በጎ​ችም የሉም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ለድ​ን​ኳ​ኔም ቦታ የለም ለመ​ን​ጎ​ችም መሰ​ማ​ሪያ የለም፤</verse>
				<verse number="21">እረ​ኞች አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን አጥ​ተ​ዋ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ፈ​ለ​ጉ​ት​ምና፤ ስለ​ዚ​ህም መሰ​ማ​ሪ​ያ​ውን አላ​ወ​ቁም፤ መን​ጎ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ተበ​ት​ነ​ዋል።</verse>
				<verse number="22">የወሬ ድምፅ ተሰማ፤ እነ​ሆም የይ​ሁ​ዳን ከተ​ሞች ባድ​ማና የሰ​ገኖ ማደ​ሪያ ያደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ ከሰ​ሜን ምድር ታላቅ መነ​ዋ​ወጥ መጥ​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="23">አቤቱ! የሰው መን​ገድ ከራሱ እንደ አይ​ደለ አው​ቃ​ለሁ፤ ሰውም አይ​ሄ​ድ​ባ​ትም፤ መን​ገ​ዱ​ንም ጥር​ጊያ አላ​ደ​ረ​ገም።</verse>
				<verse number="24">አቤቱ! ቅጣን፤ ነገር ግን ፈጽ​መህ እን​ዳ​ታ​ጠ​ፋን በፍ​ር​ድህ ይሁን እንጂ በቍ​ጣህ አይ​ሁን።</verse>
				<verse number="25">ያዕ​ቆ​ብን በል​ተ​ው​ታ​ልና፥ አጥ​ፍ​ተ​ው​ት​ማ​ልና፥ ማደ​ሪ​ያ​ው​ንም አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና በማ​ያ​ው​ቁህ አሕ​ዛብ፥ ስም​ህ​ንም በማ​ይ​ጠሩ ትው​ልድ ላይ መዓ​ት​ህን አፍ​ስስ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው ቃል ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">የዚ​ህን ቃል ኪዳን ቃል ስሙ፤ ለይ​ሁ​ዳም ሰዎች በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ለሚ​ኖሩ ተና​ገሩ፤</verse>
				<verse number="3">እን​ደ​ዚ​ህም በሏ​ቸው፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የዚ​ህን ቃል ኪዳን ቃል የማ​ይ​ሰማ ሰው ርጉም ይሁን፤</verse>
				<verse number="4">ከግ​ብፅ ሀገር ከብ​ረት ምድጃ ባወ​ጣ​ኋ​ቸው ቀን ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ያዘ​ዝ​ሁ​ትን፥ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁ​ንም ሁሉ አድ​ርጉ፤ እን​ዲ​ሁም እና​ንተ ሕዝብ ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ” ያል​ሁ​ትን ቃሌን ስሙ።</verse>
				<verse number="5">ይህም ዛሬ እንደ ሆነ ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ የማ​ል​ሁ​ትን መሐላ አጸና ዘንድ ነው። እኔም፥ “አቤቱ! ጌታ ሆይ! ይሁን” ብዬ መለ​ስ​ሁ​ለት።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ይህ​ችን ቃል ሁሉ በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በል፦ የዚ​ህን ቃል ኪዳን ቃል ስሙ፤ አድ​ር​ጉ​ትም።</verse>
				<verse number="7">አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ከግ​ብፅ ምድር ከአ​ወ​ጣ​ሁ​በት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፥ በማ​ለዳ ተነ​ሥቼ እያ​ስ​ጠ​ነ​ቀ​ቅሁ፦ ቃሌን ስሙ በማ​ለት አስ​ጠ​ን​ቅ​ቄ​አ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="8">እነ​ርሱ ሁሉ ግን በክፉ ልባ​ቸው እል​ከ​ኝ​ነት ሄዱ እንጂ አል​ሰ​ሙም፤ ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም አላ​ዘ​ነ​በ​ሉም፤ ስለ​ዚህ ያዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ውን እነ​ር​ሱም ያላ​ደ​ረ​ጉ​ትን የዚ​ህን ቃል ኪዳን ቃል ሁሉ አመ​ጣ​ሁ​ባ​ቸው።”</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፦ በይ​ሁዳ ሰዎ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሚ​ኖሩ ዘንድ አድማ ተገ​ኝ​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="10">ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ ወደ አሉ ወደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ኀጢ​አት ተመ​ለሱ፥ ያመ​ል​ኩ​አ​ቸ​ውም ዘንድ እን​ግ​ዶ​ችን አማ​ል​ክት ተከ​ተሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና የይ​ሁዳ ቤት ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን አፈ​ረሱ።</verse>
				<verse number="11">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ሊያ​መ​ል​ጡት የማ​ይ​ች​ሉ​ትን ክፉ ነገር በዚህ ሕዝብ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ ወደ እኔም ይጮ​ኻሉ፤ እኔ ግን አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="12">በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖሩ ሄደው ወደ​ሚ​ያ​ጥ​ኑ​ላ​ቸው፥ በመ​ከ​ራ​ቸው ጊዜ ከቶ ወደ​ማ​ያ​ድ​ኗ​ቸው አማ​ል​ክት ይጮ​ኻሉ።</verse>
				<verse number="13">ይሁዳ ሆይ! አማ​ል​ክ​ትህ እንደ ከተ​ሞ​ችህ ቍጥር እን​ዲሁ ናቸው፤ እንደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም መን​ገ​ዶች ቍጥር ለነ​ው​ረኛ ነገር ለበ​ዓል ታጥ​ኑ​ባ​ቸው ዘንድ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ችን አድ​ር​ጋ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="14">አን​ተም ስለ​ዚህ ሕዝብ አት​ጸ​ልይ፤ በመ​ከ​ራ​ቸው ቀን ወደ እኔ በጮኹ ጊዜ አል​ሰ​ማ​ቸ​ው​ምና ስለ እነ​ርሱ አት​ጸ​ልይ፤ በም​ል​ጃና በጸ​ሎት አት​ማ​ልድ።</verse>
				<verse number="15">ወዳጄ በቤቴ ውስጥ ለምን ርኵ​ሰ​ትን አደ​ረ​ገች? ስእ​ለት ወይም የተ​ቀ​ደሰ ሥጋ ክፋ​ት​ሽን ከአ​ንቺ ያስ​ወ​ግ​ዳ​ልን? ወይስ በእ​ነ​ዚህ ታመ​ል​ጫ​ለ​ሽን?</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም​ሽን፦ በመ​ል​ካም ፍሬ የተ​ዋ​በ​ችና የለ​መ​ለ​መች የወ​ይራ ዛፍ ብሎ ጠራው፤ ከመ​ቈ​ረ​ጥ​ዋም ድምፅ የተ​ነሣ በላ​ይዋ እሳት ነደ​ደ​ባት፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ች​ዋም ተሰ​ብ​ረ​ዋል።</verse>
				<verse number="17">ለበ​ዓ​ልም በማ​ጠ​ና​ቸው ያስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ለራ​ሳ​ቸው ስለ ሠሩ​አት ስለ እስ​ራ​ኤ​ልና ስለ ይሁዳ ቤት ክፋት የተ​ከ​ለሽ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክፉን ነገር ተና​ግ​ሮ​ብ​ሻል።</verse>
				<verse number="18">ጌታ ሆይ! አስ​ታ​ው​ቀኝ፤ እኔም አው​ቃ​ለሁ፤ ያን​ጊ​ዜም ሥራ​ቸ​ውን ገለ​ጥ​ህ​ልኝ።</verse>
				<verse number="19">እኔም ለመ​ታ​ረድ እን​ደ​ሚ​ነዳ እንደ የዋህ ጠቦት በግ ሆንሁ፤ እነ​ር​ሱም በእ​ን​ጀ​ራው ዕን​ጨት እን​ጨ​ምር ስሙም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ እን​ዳ​ይ​ታ​ሰብ ከሕ​ያ​ዋን ምድር እና​ጥ​ፋው ብለው ክፉ ምክ​ርን እን​ዳ​ሰ​ቡ​ብኝ አላ​ወ​ቅ​ሁም ነበር።</verse>
				<verse number="20">ኵላ​ሊ​ት​ንና ልብን የም​ት​ፈ​ትን፥ በቅ​ንም የም​ት​ፈ​ርድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! ክር​ክ​ሬን ገል​ጬ​ል​ሃ​ለ​ሁና ከእ​ነ​ርሱ ፍረ​ድ​ልኝ።</verse>
				<verse number="21">ስለ​ዚ​ህም፥ “በእ​ጃ​ችን እን​ዳ​ት​ሞት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ትን​ቢት አት​ና​ገር” ብለው ነፍ​ሴን ስለ​ሚሹ ስለ አና​ቶት ሰዎች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="22">ስለ​ዚህ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በመ​ዓት እጐ​በ​ኛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ጐበ​ዛ​ዝ​ቶ​ቻ​ቸው በሰ​ይፍ ይሞ​ታሉ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም በራብ ይሞ​ታሉ፤</verse>
				<verse number="23">በም​ጐ​በ​ኛ​ቸ​ውም ዓመት በዓ​ና​ቶት ሰዎች ላይ ክፉ ነገር አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ማንም ከእ​ነ​ርሱ የሚ​ተ​ርፍ የለም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">አቤቱ! ከአ​ንተ ጋር በተ​ም​ዋ​ገ​ትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአ​ንተ ጋር ስለ ፍርድ ልና​ገር። የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች መን​ገድ ስለ ምን ይቀ​ናል? በደ​ል​ንስ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ስለ ምን ደስ ይላ​ቸ​ዋል?</verse>
				<verse number="2">አንተ ተክ​ለ​ሃ​ቸ​ዋል፤ ሥር ሰድ​ደ​ዋል፤ ወል​ደ​ዋል አፍ​ር​ተ​ው​ማል፤ በአ​ፋ​ቸ​ውም አንተ ቅርብ ነህ፤ ከል​ባ​ቸው ግን ሩቅ ነህ።</verse>
				<verse number="3">አንተ ግን አቤቱ! ዐው​ቀ​ኸ​ኛል፤ አይ​ተ​ኸ​ኛል፤ ልቤ​ንም በፊ​ትህ ፈት​ነ​ሃል፤ እንደ በጎች ለመ​ታ​ረድ ጐት​ተህ ለያ​ቸው፤ ለመ​ታ​ረ​ድም ቀን አዘ​ጋ​ጃ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">በሚ​ኖ​ሩ​ባት ሰዎች ክፋት ምድ​ሪቱ የም​ታ​ለ​ቅ​ሰ​ውና የዱሩ ሣርስ ሁሉ የሚ​ደ​ር​ቀው እስከ መቼ ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍጻ​ሜ​ያ​ች​ንን አያ​ይም ብለ​ዋ​ልና እን​ስ​ሶ​ችና ወፎ​ችም ጠፍ​ተ​ዋል።</verse>
				<verse number="5">እግ​ሮ​ችህ ሮጠው ይደ​ክ​ማሉ፤ ፈረ​ሶ​ችን ለምን ታስ​ጌ​ጣ​ለህ? በሰ​ላ​ምም ምድር ላይ ለምን ትታ​መ​ና​ለህ? በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስስ ጩኸት ለምን እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ለህ?</verse>
				<verse number="6">ወን​ድ​ሞ​ች​ህና የአ​ባ​ትህ ቤት እነ​ርሱ ጭምር ክደ​ው​ሃ​ልና፥ ጮኸ​ውም በስ​ተ​ኋ​ላህ ተሰ​በ​ሰቡ፤ በመ​ል​ካ​ምም ቢና​ገ​ሩህ አት​መ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="7">ቤቴን ትች​አ​ለሁ፤ ርስ​ቴ​ንም ጥያ​ለሁ፤ ነፍሴ የም​ት​ወ​ድ​ዳ​ት​ንም በጠ​ላ​ቶ​ችዋ እጅ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">ርስቴ በዱር እንደ አለ አን​በሳ ሆና​ብ​ኛ​ለች፤ ድም​ፅ​ዋ​ንም አን​ሥ​ታ​ብ​ኛ​ለች፤ ስለ​ዚህ ጠል​ቻ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">ርስቴ እንደ ጅብ ጕድ​ጓድ ናትን? ወይስ በዙ​ሪ​ያዋ የሚ​ከ​ቡ​አት የሽ​ፍ​ቶች ዋሻ ናትን? የም​ድር አራ​ዊት ሁሉ ይበ​ሉ​አት ዘንድ ተሰ​ብ​ስ​በው ይመ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="10">ብዙ እረ​ኞች የወ​ይ​ኑን ቦታ​ዬን አጥ​ፍ​ተ​ዋል፤ እድል ፈን​ታ​ዬ​ንም አር​ክ​ሰ​ዋል፤ የም​ወ​ድ​ዳ​ት​ንም እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድ​ር​ገ​ዋ​ታል።</verse>
				<verse number="11">እር​ስ​ዋም ለፍ​ጹም ጥፋት ሆና​ለች፤ ስለ እኔም ምድር ሁሉ ባድማ ሆና​ለች፤ በል​ቡም የሚ​ያ​ኖ​ራት የለም።</verse>
				<verse number="12">ወራ​ዶች ወደ ዱር ሁሉ መጥ​ተ​ዋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ ከም​ድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይበ​ላ​ልና፤ ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም።</verse>
				<verse number="13">ስን​ዴን ትዘ​ራ​ላ​ችሁ፤ እሾ​ህ​ንም ታጭ​ዳ​ላ​ችሁ፤ ዕጣ​ች​ሁም ምንም አይ​ጠ​ቅ​ማ​ች​ሁም፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽኑ ቍጣ የተ​ነሣ በአ​ዝ​መ​ራ​ችሁ ታፍ​ራ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ያወ​ረ​ስ​ሁ​ትን ርስት ለሚ​ነ​ኩት ክፉ​ዎች ጎረ​ቤ​ቶች ሁሉ እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “እነሆ ከም​ድ​ራ​ቸው እነ​ቅ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም ቤት ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው እነ​ቅ​ለ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">ከነ​ቀ​ል​ኋ​ቸ​ውም በኋላ መልሼ ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ሁላ​ቸ​ው​ንም በር​ስ​ታ​ቸው፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ው​ንም በም​ድ​ራ​ቸው አኖ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">በበ​ዓል ይምሉ ዘንድ ሕዝ​ቤን እን​ዳ​ስ​ተ​ማሩ በስሜ፦ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ብለው ይምሉ ዘንድ የሕ​ዝ​ቤን መን​ገድ ፈጽ​መው ቢማሩ፥ በዚያ ጊዜ በሕ​ዝቤ መካ​ከል ይመ​ሠ​ረ​ታሉ።</verse>
				<verse number="17">ባይ​መ​ለሱ ግን ያን ሕዝብ እነ​ቅ​ለ​ዋ​ለሁ፤ አስ​ወ​ግ​ደ​ዋ​ለሁ፤ አጠ​ፋ​ው​ማ​ለሁ፤” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይለ​ኛል፦ ሂድ፥ ከተ​ልባ እግር የተ​ሠ​ራ​ችን መታ​ጠ​ቂያ ለአ​ንተ ግዛ፤ ወገ​ብ​ህ​ንም ታጠ​ቅ​ባት፤ በው​ኃ​ውም ውስጥ አት​ን​ከ​ራት።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ለኝ የተ​ልባ እግር መታ​ጠ​ቂ​ያን ገዛሁ፤ ወገ​ቤ​ንም ታጠ​ቅ​ሁ​ባት።</verse>
				<verse number="3">ዳግ​መ​ኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረኝ፦</verse>
				<verse number="4">“ለወ​ገ​ብህ የገ​ዛ​ሃ​ትን ያቺን መታ​ጠ​ቂያ ወስ​ደህ ተነሥ፤ ወደ ኤፍ​ራ​ጥ​ስም ሂድ፤ በዚ​ያም በተ​ሰ​ነ​ጠቀ ዓለት ውስጥ ሸሽ​ጋት።”</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘኝ ሄድሁ፤ በኤ​ፍ​ራ​ጥ​ስም ወንዝ አጠ​ገብ ሸሸ​ግ​ኋት።</verse>
				<verse number="6">ከብዙ ቀንም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ተነ​ሥ​ተህ ወደ ኤፍ​ራ​ጥስ ሂድ፥ በዚ​ያም ትሸ​ሽ​ጋት ዘንድ ያዘ​ዝ​ሁ​ህን መታ​ጠ​ቂያ ከዚያ ውስጥ ውሰድ” አለኝ።</verse>
				<verse number="7">እኔም ወደ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ሄድሁ፤ ቈፈ​ር​ሁም፤ ከቀ​በ​ር​ሁ​በ​ትም ስፍራ መታ​ጠ​ቂ​ያ​ዪ​ቱን ወሰ​ድሁ። እነ​ሆም መታ​ጠ​ቂ​ያ​ዪቱ ተበ​ላ​ሽታ ነበር፤ ለም​ንም አል​ረ​ባ​ችም።</verse>
				<verse number="8">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፤</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እን​ዲሁ የይ​ሁ​ዳን ትዕ​ቢት፥ ታላ​ቁ​ንም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ትዕ​ቢት አበ​ላ​ሻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ የሚሉ፥ በክፉ ልባ​ቸ​ውም እል​ከ​ኝ​ነት የሚ​ሄዱ፥ ያገ​ለ​ግ​ሏ​ቸ​ውና ይሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸው ዘንድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ተከ​ት​ለው የሚ​ሄዱ እነ​ዚህ ክፉ ሕዝብ አን​ዳች እን​ደ​ማ​ት​ረባ እን​ደ​ዚች መታ​ጠ​ቂያ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="11">መታ​ጠ​ቂያ በሰው ወገብ ላይ እን​ደ​ም​ት​ጣ​በቅ፥ እን​ዲሁ ለስም፥ ለመ​መ​ኪ​ያና ለክ​ብር ሕዝብ ይሆ​ኑ​ልኝ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ሁሉ፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ቤት ሁሉ ከእኔ ጋር አጣ​ብ​ቄ​አ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን አል​ሰ​ሙም።”</verse>
				<verse number="12">ስለ​ዚህ፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ማድጋ ሁሉ የወ​ይን ጠጅ ይሞ​ላል” ብለህ ትነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ፤ እነ​ር​ሱም፥ “ማድጋ ሁሉ የወ​ይን ጠጅ እን​ዲ​ሞላ በውኑ እኛ አና​ው​ቅ​ምን?” ቢሉህ፤</verse>
				<verse number="13">አን​ተም እን​ዲህ ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በዚ​ህች ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ፥ በዳ​ዊት ዙፋን የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን ነገ​ሥ​ታት፥ ካህ​ና​ቱ​ንም፥ ነቢ​ያ​ቱ​ንም፥ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ሁሉ በስ​ካር እሞ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">ሰው​ንና ወን​ድ​ሙን፥ አባ​ቶ​ች​ንና ልጆ​ችን በአ​ንድ ላይ እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ አል​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም፤ አላ​ዝ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ አል​ም​ራ​ቸ​ው​ምም።”</verse>
				<verse number="15">ስሙ፤ አድ​ምጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና አት​ታ​በዩ።</verse>
				<verse number="16">ሳይ​ጨ​ል​ም​ባ​ችሁ፥ ጨለ​ማም ባለ​ባ​ቸው ተራ​ሮች እግ​ሮ​ቻ​ችሁ ሳይ​ሰ​ነ​ካ​ከሉ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ርን ስጡ፤ በዚ​ያም የሞት ጥላ አለና በጨ​ለ​ማ​ውም ውስጥ ያኖ​ራ​ች​ኋ​ልና ብር​ሃ​ንን ተስፋ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="17">ይህን ባት​ሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕ​ቢ​ታ​ችሁ በስ​ውር ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መንጋ ተሰ​ብ​ሮ​አ​ልና ዐይኔ ታነ​ባ​ለች፤ እን​ባ​ንም ታፈ​ስ​ሳ​ለች።</verse>
				<verse number="18">ለነ​ገ​ሥ​ታ​ቱና ለመ​ኳ​ን​ንቱ፦ የክ​ብ​ራ​ችሁ አክ​ሊል ከራ​ሳ​ችሁ ወር​ዶ​አ​ልና ራሳ​ች​ሁን አዋ​ር​ዳ​ችሁ ተቀ​መጡ በላ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">የደ​ቡብ ከተ​ሞች ተዘ​ግ​ተ​ዋል፤ የሚ​ከ​ፍ​ታ​ቸ​ውም የለም፤ ይሁዳ ሁሉ ተሰ​ድ​ዶ​አል፤ ፈጽ​ሞም ተሰ​ድ​ዶ​አል።</verse>
				<verse number="20">ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ! ዐይ​ን​ሽን አን​ሥ​ተሽ እነ​ዚ​ህን ከሰ​ሜን የሚ​መ​ጡ​ትን ተመ​ል​ከቺ፤ ለአ​ንቺ የሰ​ጠ​ሁሽ መንጋ፤ የክ​ብር በጎ​ችሽ ወዴት አሉ?</verse>
				<verse number="21">አንቺ ትም​ህ​ርት ያስ​ተ​ማ​ር​ሻ​ቸው አለ​ቆ​ችሽ ሆነው በጐ​በ​ኙሽ ጊዜ ምን ትያ​ለሽ? እንደ ወላድ ሴት ምጥ አይ​ዝ​ሽ​ምን?</verse>
				<verse number="22">በል​ብ​ሽም፦ እን​ዲህ ያለ ነገር ስለ ምን ደረ​ሰ​ብኝ? ብትዪ፥ ከኀ​ጢ​አ​ትሽ ብዛት የተ​ነሣ ልብ​ስሽ በስ​ተ​ኋ​ላሽ ተገ​ፎ​አል፤ ተረ​ከ​ዝ​ሽም ተገ​ል​ጦ​አል።</verse>
				<verse number="23">በውኑ ኢት​ዮ​ጵ​ያዊ መል​ኩን ወይስ ነብር ዝን​ጕ​ር​ጕ​ር​ነ​ቱን ይለ​ውጥ ዘንድ ይች​ላ​ልን? በዚያ ጊዜ ክፋ​ትን የለ​መ​ዳ​ችሁ እና​ንተ ደግሞ በጎ ለማ​ድ​ረግ ትች​ላ​ላ​ች​ሁን?</verse>
				<verse number="24">ነፋስ በም​ድረ በዳ እን​ደ​ሚ​በ​ት​ነው እብቅ እበ​ት​ና​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="25">ረስ​ተ​ሽ​ኛ​ልና፥ በሐ​ሰ​ትም ታም​ነ​ሻ​ልና ዕጣ​ሽና እድል ፈን​ታሽ ይህ ነው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="26">ስለ​ዚ​ህም የል​ብ​ስ​ሽን ዘርፍ በስ​ተ​ኋ​ላሽ ወደ ፊትሽ እገ​ል​ጣ​ለሁ እፍ​ረ​ት​ሽም ይታ​ያል።</verse>
				<verse number="27">አስ​ጸ​ያፊ ሥራ​ሽን፥ ምን​ዝ​ር​ና​ሽን፥ ማሽ​ካ​ካ​ት​ሽን፥ የዝ​ሙ​ት​ሽ​ንም መዳ​ራት በኮ​ረ​ብ​ቶች ላይ፥ በሜ​ዳም ላይ አይ​ቻ​ለሁ። ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ! ወዮ​ልሽ! ለመ​ን​ጻት እንቢ ብለ​ሻል፤ ይህስ እስከ መቼ ነው?</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">ስለ ድርቅ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">ይሁዳ አለ​ቀ​ሰች፤ ደጆ​ች​ዋም ባዶ ሆኑ፤ በም​ድ​ርም ላይ ጨለሙ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ጩኸት ከፍ ከፍ ብሎ​አል።</verse>
				<verse number="3">ታላ​ላ​ቆ​ች​ዋም ብላ​ቴ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ወደ ውኃ ሰደዱ፤ ወደ ጕድ​ጓድ መጡ፤ ውኃም አላ​ገ​ኙም፤ ዕቃ​ቸ​ው​ንም ባዶ​ውን መለሱ፤ ዐፈ​ሩም፤ ተዋ​ረ​ዱም፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ተከ​ና​ነቡ።</verse>
				<verse number="4">በም​ድር ላይ አል​ዘ​ነ​በ​ምና መሬቱ ስን​ጥ​ቅ​ጥቅ ስለ ሆነ አራ​ሾች ዐፈሩ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ተከ​ና​ነቡ።</verse>
				<verse number="5">ዋሊ​ያ​ዎች ደግሞ በም​ድረ በዳ ወለዱ፤ ሣርም የለ​ምና ግል​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ተዉ።</verse>
				<verse number="6">የሜዳ አህ​ዮ​ችም በወና ኮረ​ብታ ላይ ቆመ​ዋል፤ እንደ ሰገ​ኖም ወደ ነፋስ አለ​ከ​ለኩ፤ ሣርም የለ​ምና ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው ጠወ​ለጉ።</verse>
				<verse number="7">አቤቱ! ኀጢ​አ​ታ​ችን ብዙ ነውና፥ በአ​ን​ተም ላይ ኀጢ​አት ሠር​ተ​ና​ልና ኀጢ​አ​ታ​ችን ተቃ​ው​ሞ​ናል፤ ነገር ግን ስለ ስምህ ብለህ አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="8">ጌታ ሆይ! አንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ተስፋ ነህ፤ በመ​ከ​ራም ጊዜ ታድ​ነ​ዋ​ለህ፤ በም​ድር እንደ እን​ግዳ፥ ወደ ማደ​ሪ​ያም ዘወር እን​ደ​ሚል መን​ገ​ደኛ ስለ ምን ትሆ​ና​ለህ?</verse>
				<verse number="9">እን​ዳ​ን​ቀ​ላፋ ሰው፥ ያድ​ንም ዘንድ እን​ደ​ማ​ይ​ችል ኀያል ስለ ምን ትሆ​ና​ለህ? አንተ ግን አቤቱ! በመ​ካ​ከ​ላ​ችን ነህ፤ ስም​ህም በእኛ ላይ ተጠ​ር​ት​ዋል፤ አት​ር​ሳ​ንም።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዚህ ሕዝብ እን​ዲህ ይላል፥ “መቅ​በ​ዝ​በ​ዝን ወድ​ደ​ዋል፤ እግ​ራ​ቸ​ው​ንም አል​ከ​ለ​ከ​ሉም፤ ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ነ​ርሱ ደስ አይ​ለ​ውም፤ በደ​ላ​ቸ​ው​ንም አሁን ያስ​ባል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይጐ​በ​ኛል።”</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “ለዚህ ሕዝብ ስለ መል​ካም አት​ጸ​ል​ይ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">ቢጾሙ ጸሎ​ታ​ቸ​ውን አል​ሰ​ማም፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን ቢያ​ቀ​ር​ቡም ደስ አል​ሰ​ኝ​ባ​ቸ​ውም፤ በሰ​ይ​ፍና በራብ በቸ​ነ​ፈ​ርም አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="13">እኔም፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! ወዮ! እነሆ ነቢ​ያት፦ እው​ነ​ት​ንና ሰላ​ምን በዚህ ስፍራ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ ሰይ​ፍን አታ​ዩም፤ ራብም አያ​ገ​ኛ​ች​ሁም ይሉ​አ​ቸ​ዋል” አልሁ።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ነቢ​ያቱ በስሜ የሐ​ሰት ትን​ቢት ይና​ገ​ራሉ፤ አላ​ክ​ኋ​ቸ​ውም፤ አላ​ዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ውም፤ አል​ተ​ና​ገ​ር​ኋ​ቸ​ውም፤ የሐ​ሰ​ቱን ራእይ፥ ምዋ​ር​ት​ንም፥ ከን​ቱ​ንም ነገር፥ በል​ባ​ቸ​ውም የፈ​ጠ​ሩ​ትን ይተ​ነ​ብ​ዩ​ላ​ች​ኋል።”</verse>
				<verse number="15">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በስሜ የሐ​ሰት ትን​ቢት ስለ​ሚ​ና​ገሩ ነቢ​ያት ስላ​ላ​ክ​ኋ​ቸው፦ በዚ​ህች ሀገር ሰይ​ፍና ረሃብ አይ​ሆ​ንም ስለ​ሚሉ ነቢ​ያት እን​ዲህ ይላል፥ “እነ​ዚያ ነቢ​ያት በሰ​ይ​ፍና በራብ ይጠ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="16">ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ላ​ቸ​ውም ሰዎች ከራ​ብና ከሰ​ይፍ የተ​ነሣ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መን​ገ​ዶች ይበ​ተ​ናሉ፤ ክፋ​ታ​ቸ​ው​ንም አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና እነ​ር​ሱ​ንና ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም የሚ​ቀ​ብ​ራ​ቸው አይ​ገ​ኝም።</verse>
				<verse number="17">“እን​ደ​ዚ​ህም ብለህ ትነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ፦ የወ​ገኔ ልጅ ድን​ግ​ሊቱ በታ​ላቅ ስብ​ራ​ትና እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰ​ብ​ራ​ለ​ችና ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ ሌሊ​ትና ቀን ሳያ​ቋ​ርጡ እን​ባን ያፍ​ስሱ።</verse>
				<verse number="18">ወደ ሜዳ ብወጣ፥ እነሆ በሰ​ይፍ የሞቱ አሉ፤ ወደ ከተ​ማም ብገባ፥ እነሆ በራብ የከሱ አሉ፤ ነቢ​ዩና ካህኑ ወደ​ማ​ያ​ው​ቋት ሀገር ሄደ​ዋ​ልና።”</verse>
				<verse number="19">በውኑ ይሁ​ዳን ፈጽ​መህ ጥለ​ኸ​ዋ​ልን? ነፍ​ስ​ህስ ጽዮ​ንን ጠል​ታ​ታ​ለ​ችን? ስለ ምን መታ​ኸን? ፈው​ስስ ስለ ምን የለ​ንም? ስለ ምን ተስፋ አደ​ረ​ግን? ነገር ግን መል​ካም ነገር አል​ተ​ገ​ኘም፤ የፈ​ው​ስን ጊዜ ተስፋ አደ​ረ​ግን፤ ነገር ግን ድን​ጋጤ ሆነ።</verse>
				<verse number="20">አቤቱ በአ​ንተ ላይ ኀጢ​አ​ትን ሠር​ተ​ና​ልና ክፋ​ታ​ች​ን​ንና የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንን በደል እና​ው​ቃ​ለን።</verse>
				<verse number="21">ስለ ስምህ ብለህ ተመ​ለ​ስ​ልን፤ የክ​ብ​ር​ህ​ንም ዙፋን አታ​ጥፋ፤ ከእኛ ጋርም ያደ​ረ​ግ​ኸ​ውን ቃል ኪዳ​ን​ህን አስብ እንጂ አታ​ፍ​ርስ።</verse>
				<verse number="22">በውኑ በአ​ሕ​ዛብ ጣዖ​ታት መካ​ከል ያዘ​ንብ ዘንድ የሚ​ችል ይገ​ኛ​ልን? ወይስ ሰማይ ዝናብ ሊሰ​ጥና ሊያ​ጠ​ግብ ይች​ላ​ልን? አቤቱ አም​ላ​ካ​ችን ሆይ አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? አንተ ይህን ነገር ሁሉ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ስለ​ዚህ አን​ተን በተ​ስፋ እን​ጠ​ባ​በ​ቃ​ለን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ሙሴና ሳሙ​ኤል በፊቴ ቢቆ​ሙም፥ ልቤ ወደ​ዚህ ሕዝብ አያ​ዘ​ነ​ብ​ልም፤ እነ​ዚ​ህን ሕዝ​ቦች ከፊቴ አባ​ር​ራ​ቸው፤ ይውጡ።</verse>
				<verse number="2">እነ​ር​ሱም፦ ወዴት እን​ሂድ ቢሉህ፥ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ለሞት የሆነ ወደ ሞት፥ ለሰ​ይ​ፍም የሆነ ወደ ሰይፍ፥ ለራ​ብም የሆነ ወደ ራብ፥ ለም​ር​ኮም የሆነ ወደ ምርኮ ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="3">ሰይ​ፍን ለመ​ግ​ደል፥ ውሾ​ች​ንም ለመ​ጐ​ተት፥ የሰ​ማ​ያ​ት​ንም ወፎች፥ የም​ድ​ር​ንም አራ​ዊት ለመ​ብ​ላ​ትና ለማ​ጥ​ፋት፥ አራ​ቱን ዓይ​ነት ጥፋት አዝ​ዝ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="4">የይ​ሁዳ ንጉሥ የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ልጅ ምናሴ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስለ አደ​ረ​ገው ሁሉ በም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ መካ​ከል ለመ​ከራ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">“ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ! የሚ​ራ​ራ​ልሽ ማን ነው? የሚ​ያ​ዝ​ን​ል​ሽስ ማን ነው? ወይስ ስለ ደኅ​ን​ነ​ትሽ ይጠ​ይቅ ዘንድ ፈቀቅ የሚል ማን ነው?</verse>
				<verse number="6">አንቺ እኔን ከድ​ተ​ሽ​ኛል፤ እኔ​ንም መከ​ተል ትተ​ሻል፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ወደ ኋላ​ሽም ተመ​ል​ሰ​ሻል፤ ስለ​ዚህ እጄን በአ​ንቺ ላይ ዘር​ግቼ አጠ​ፋ​ሻ​ለሁ፤ ይቅ​ርም አል​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="7">ሕዝ​ቤ​ንም ወደ ዳርቻ ፈጽሜ እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የወ​ላድ መካን አድ​ር​ጌ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ሕዝ​ቤ​ንም ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው አጥ​ፍ​ቻ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከመ​ን​ገ​ዳ​ቸ​ውም አል​ተ​መ​ለ​ሱም።</verse>
				<verse number="8">መበ​ለ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከባ​ሕር አሸዋ ይልቅ በዝ​ተ​ዋል፤ በብ​ላ​ቴ​ኖች እናት ላይ በቀ​ትር ጊዜ አጥ​ፊ​ውን አም​ጥ​ቻ​ለሁ፤ ጭን​ቀ​ት​ንና ድን​ጋ​ጤን በድ​ን​ገት አም​ጥ​ቼ​ባ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">ሰባት የወ​ለ​ደች ባዶ ቀረች፤ ነፍ​ስ​ዋም ተጨ​ን​ቃ​ለች፤ በቀ​ትር ጊዜ ፀሐ​ይዋ ገብ​ታ​ባ​ታ​ለች፤ አፍ​ራ​ለች፤ ተዋ​ር​ዳ​ማ​ለች፤ የተ​ረ​ፉ​ት​ንም በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ፊት ለሰ​ይፍ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="10">እናቴ ሆይ! ለም​ድር ሁሉ የክ​ር​ክ​ርና የጥል ሰው የሆ​ን​ሁ​ትን እኔን ወል​ደ​ሽ​ኛ​ልና ወዮ​ልኝ! ለማ​ንም አል​ጠ​ቀ​ም​ሁም፤ ማንም እኔን አል​ጠ​ቀ​መ​ኝም፤ ከሚ​ረ​ግ​ሙ​ኝም የተ​ነሣ ኀይሌ አለቀ።</verse>
				<verse number="11">አቤቱ! በመ​ከ​ራ​ቸ​ውና በጭ​ን​ቃ​ቸው ጊዜ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ዘንድ ስለ እነ​ርሱ በጎ ነገር በአ​ንተ ፊት የቆ​ምሁ ባል​ሆን ይህ ለእ​ነ​ርሱ መከ​ና​ወን ይሁን።</verse>
				<verse number="12">በውኑ ብረ​ትን፥ የሰ​ሜ​ንን ብረት፥ ናስ​ንም የሚ​ሰ​ብር አለን?</verse>
				<verse number="13">በዳ​ር​ቻህ ሁሉ ስላለ ኀጢ​አ​ትህ ሁሉ ፋንታ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ት​ህ​ንና መዝ​ገ​ብ​ህን ለመ​በ​ዝ​በዝ በከ​ንቱ እሰ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">እሳት ከቍ​ጣዬ ትነ​ድ​ዳ​ለ​ችና፥ እና​ን​ተ​ንም ታቃ​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለ​ችና በማ​ታ​ው​ቀው ሀገር ለጠ​ላ​ቶ​ችህ አስ​ገ​ዛ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">አቤቱ! አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ አስ​በኝ፤ ጐብ​ኘ​ኝም፤ ከሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​ኝም አድ​ነኝ እንጂ፥ አት​ታ​ገ​ሣ​ቸው፤ ስለ አንተ እንደ ሰደ​ቡኝ አስብ።</verse>
				<verse number="16">ቃልህ ተገ​ኝ​ቶ​አል፤ እኔም በል​ች​ዋ​ለሁ፤ አቤቱ! የሠ​ራ​ዊት አም​ላክ ሆይ! ቃል​ህን የከዱ ሰዎ​ችን አጥ​ፋ​ቸው፤ ስምህ በእኔ ላይ ተጠ​ር​ት​ዋ​ልና፥ ቃልህ ሐሤ​ትና የልብ ደስታ ሆነኝ።</verse>
				<verse number="17">በዋ​ዘ​ኞች ጉባኤ አል​ተ​ቀ​መ​ጥ​ሁም፤ ነገር ግን በእ​ጅህ ፊት ፈር​ቻ​ለሁ፤ ምሬ​ትን ሞል​ተ​ህ​ብ​ኛ​ልና ለብ​ቻዬ ተቀ​መ​ጥሁ።</verse>
				<verse number="18">የሚ​ያ​ሳ​ዝ​ኑኝ በእኔ ላይ ለምን ይበ​ረ​ታሉ? ቍስ​ሌስ ስለ ምን የማ​ይ​ፈ​ወስ ሆነ? ስለ ምንስ አል​ሽ​ርም አለ? እንደ ሐሰ​ተኛ ምንጭ፥ እን​ዳ​ል​ታ​መ​ነች ውኃም ሆነ​ብኝ።</verse>
				<verse number="19">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ብት​መ​ለስ እመ​ል​ስ​ሃ​ለሁ፤ በፊ​ቴም ትቆ​ማ​ለህ፤ የከ​በ​ረ​ው​ንም ከተ​ዋ​ረ​ደው ብት​ለይ እንደ አፌ ትሆ​ና​ለህ፤ እነ​ርሱ ወደ አንተ ይመ​ለ​ሳሉ፤ አንተ ግን ወደ እነ​ርሱ አት​መ​ለ​ስም።</verse>
				<verse number="20">ለዚ​ህም ሕዝብ የተ​መ​ሸገ የናስ ቅጥር አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ ይዋ​ጉ​ሃል፤ እኔ ግን ለማ​ዳን ከአ​ንተ ጋር ነኝና አያ​ሸ​ን​ፉ​ህም።</verse>
				<verse number="21">ከክፉ ሰዎ​ችም እጅ እታ​ደ​ግ​ሃ​ለሁ፤ ከጨ​ካ​ኞ​ችም ጡጫ እቤ​ዥ​ሃ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">በዚህ ስፍራ ሚስት አታ​ግባ፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ንም አት​ው​ለድ።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ስፍራ ስለ ተወ​ለዱ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች፥ ስለ ወለ​ዱ​አ​ቸ​ውም ስለ እና​ቶ​ቻ​ቸው፥ በዚ​ህ​ችም ምድር ስለ ወለ​ዱ​አ​ቸው ስለ አባ​ቶ​ቻ​ቸው እን​ዲህ ይላ​ልና፦</verse>
				<verse number="4">“በክፉ ሞት ይሞ​ታሉ፤ አይ​ለ​ቀ​ስ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ቀ​በ​ሩ​ምም፤ ነገር ግን በመ​ሬት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆ​ናሉ፤ በሰ​ይ​ፍም ይወ​ድ​ቃሉ፤ በራ​ብም ይጠ​ፋሉ፤ ሬሳ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለዱር አራ​ዊት መብል ይሆ​ናሉ።”</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰላ​ሜን፥ ቸር​ነ​ቴ​ንና ምሕ​ረ​ቴን፥ ከዚህ ሕዝብ አስ​ወ​ግ​ጄ​አ​ለ​ሁና ልቅሶ ወዳ​ለ​በት ቤት አት​ግባ፤ ታለ​ቅ​ስና ታዝ​ንም ዘንድ አት​ሂድ።</verse>
				<verse number="6">ታላ​ላ​ቆ​ችና ታና​ና​ሾች በዚች ምድር ይሞ​ታሉ ፥ አይ​ቀ​በ​ሩም ሰዎ​ችም አያ​ለ​ቅ​ሱ​ላ​ቸ​ውም፤ ስለ እነ​ር​ሱም ፊት አይ​ነ​ጩ​ላ​ቸ​ውም፤ ራስ​ንም አይ​ላ​ጩ​ላ​ቸ​ውም፤</verse>
				<verse number="7">ሰዎ​ችም ስለ ሞቱት ለማ​ጽ​ና​ናት የእ​ዝን እን​ጀራ አይ​ቈ​ር​ሱ​ላ​ቸ​ውም፤ ስለ አባ​ታ​ቸ​ውና ስለ እና​ታ​ቸ​ውም የመ​ጽ​ና​ናት ጽዋ አያ​ጠ​ጡ​አ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="8">ትበ​ላና ትጠጣ ዘንድ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ለመ​ቀ​መጥ ወደ ግብዣ ቤት አት​ግባ።”</verse>
				<verse number="9">ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት በዘ​መ​ና​ች​ሁም የእ​ል​ል​ታን ድም​ፅና የደ​ስ​ታን ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽ​ራን ድም​ፅና የሴት ሙሽ​ራን ድምፅ ከዚህ ስፍራ አስ​ቀ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">“ለዚ​ህም ሕዝብ ይህን ቃል ሁሉ በተ​ና​ገ​ርህ ጊዜ፦ ይህን ሁሉ ትልቅ የሆነ ክፉ ነገ​ርን ስለ ምን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገ​ረ​ብን? በደ​ላ​ች​ንስ ምን​ድን ነው? በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያደ​ረ​ግ​ነው ኀጢ​አት ምን​ድን ነው? ቢሉህ፥</verse>
				<verse number="11">አንተ እን​ዲህ ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፦ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ እኔን ስለ ተዉ ነው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት ተከ​ተሉ፤ አመ​ለ​ኩ​አ​ቸ​ውም፤ ሰገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፤ እነ​ር​ሱም ትተ​ው​ኛል፤ ሕጌ​ንም አል​ጠ​በ​ቁም፤</verse>
				<verse number="12">እና​ን​ተም ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ይልቅ ክፉ አድ​ር​ጋ​ች​ኋል፤ እነ​ሆም ሁላ​ችሁ እንደ ክፉ ልባ​ችሁ ፍላ​ጎት ሄዳ​ች​ኋል፤ እኔ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="13">ስለ​ዚህ ከዚች ምድር እና​ን​ተና አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ወደ አላ​ወ​ቃ​ች​ኋት ምድር እጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ምሕ​ረ​ትን ለማ​ያ​ደ​ር​ጉ​ላ​ችሁ ሌሎች አማ​ል​ክት ቀንና ሌሊት ታገ​ለ​ግ​ላ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="14">ስለ​ዚህ እነሆ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ያወጣ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ዳግ​መኛ የማ​ይ​ባ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤</verse>
				<verse number="15">ነገር ግን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከሰ​ሜን ምድር፥ ከተ​ሰ​ደ​ዱ​በ​ትም ምድር ሁሉ ያወጣ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ይባ​ላል፤ እኔም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ወደ ሰጠ​ኋት ወደ ምድ​ራ​ቸው እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">“እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥ​ማ​ጆ​ችን እል​ካ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ር​ሱም ያጠ​ም​ዱ​አ​ቸ​ዋል፤ ከዚ​ያም በኋላ ብዙ አድ​ዳ​ኞ​ችን እል​ካ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ከየ​ተ​ራ​ራ​ውና ከየ​ኮ​ረ​ብ​ታው ሁሉ ከየ​ድ​ን​ጋ​ዩም ስን​ጣቂ ውስጥ ያድ​ድ​ኑ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="17">ዐይ​ኖች በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ሁሉ ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤ ከፊ​ቴም አል​ተ​ሰ​ወ​ሩም፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ከዐ​ይ​ኖች አል​ተ​ሸ​ሸ​ገም።</verse>
				<verse number="18">ምድ​ሬ​ንም በተ​ጠሉ በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸው ሬሳ​ዎች አር​ክ​ሰ​ዋ​ልና፥ ርስ​ቴ​ንም አስ​ጸ​ያፊ በሆኑ ነገ​ሮች ሞል​ተ​ዋ​ልና አስ​ቀ​ድሜ የበ​ደ​ላ​ቸ​ው​ንና የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ዕዳ ሁለት እጥፍ እከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="19">ጌታ ሆይ! አንተ ኀይ​ሌና ረዳቴ፥ በመ​ከ​ራም ቀን መጠ​ጊ​ያዬ ነህ፤ ከም​ድር ዳርቻ አሕ​ዛብ ወደ አንተ መጥ​ተው፥ “በእ​ው​ነት አባ​ቶ​ቻ​ችን ውሸ​ት​ንና ከን​ቱን ነገር ለም​ንም የማ​ይ​ረ​ባ​ቸ​ውን ጣዖ​ትን ሠር​ተ​ዋል” ይላሉ።</verse>
				<verse number="20">በውኑ ሰው አማ​ል​ክት ያል​ሆ​ኑ​ትን ለራሱ አማ​ል​ክ​ትን አድ​ርጎ ይሠ​ራ​ልን?</verse>
				<verse number="21">“ስለ​ዚህ እነሆ በዚህ ወራት አስ​ታ​ው​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እጄ​ንና ኀይ​ሌ​ንም አሳ​ያ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ስሜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነ ያው​ቃሉ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">የይ​ሁዳ ኀጢ​አት በብ​ረት ብርዕ በደ​ን​ጊያ ሰሌዳ ተጽ​ፎ​አል፤ በል​ባ​ቸው ጽላ​ትና በመ​ሠ​ዊ​ያ​ቸው ቀን​ዶ​ችም ተቀ​ር​ጾ​አል።</verse>
				<verse number="2">ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ከለ​መ​ለሙ ዛፎች በታ​ችና በረ​ዘ​ሙት ኮረ​ብ​ቶች ላይ ያሉ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ቸ​ው​ንና የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዳ​ቸ​ውን ያስ​ባሉ።</verse>
				<verse number="3">በሜዳ ያለው ተራ​ራዬ ሆይ! ባለ​ጠ​ግ​ነ​ት​ህ​ንና መዝ​ገ​ብ​ህን ሁሉ፥ የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ች​ህ​ንም ስለ ኀጢ​አ​ትህ በድ​ን​በ​ሮ​ችህ ሁሉ ለመ​በ​ዝ​በዝ እሰ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">አን​ተም የሰ​ጠ​ሁ​ህን ርስት ትለ​ቅ​ቃ​ለህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም በማ​ታ​ው​ቃት ምድር ለጠ​ላ​ቶ​ችህ አስ​ገ​ዛ​ሃ​ለሁ፤ ቍጣዬ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እንደ እሳት ትነ​ድ​ዳ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በሰው የሚ​ታ​መን የሥጋ ክን​ዱ​ንም በእ​ርሱ የሚ​ያ​ስ​ደ​ግፍ፥ ልቡም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ርቅ ሰው ርጉም ነው።</verse>
				<verse number="6">በም​ድረ በዳ እንደ አለ ቍጥ​ቋጦ ይሆ​ናል፤ መል​ካ​ምም በመጣ ጊዜ አያ​ይም፤ ሰውም በማ​ይ​ኖ​ር​በት፥ ጨው ባለ​በት ምድር በም​ድረ በዳ በደ​ረቅ ስፍራ ይቀ​መ​ጣል።</verse>
				<verse number="7">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ታ​መን፥ ተስ​ፋ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው።</verse>
				<verse number="8">በውኃ አጠ​ገብ እንደ ተተ​ከለ፥ በወ​ን​ዝም ዳር ሥሩን እን​ደ​ሚ​ዘ​ረጋ፥ ሙቀ​ትም ሲመጣ እን​ደ​ማ​ይ​ፈራ፥ ቅጠ​ሉም እን​ደ​ሚ​ለ​መ​ልም፥ በድ​ርቅ ዓመ​ትም እን​ደ​ማ​ይ​ሠጋ ፍሬ​ው​ንም እን​ደ​ማ​ያ​ቋ​ርጥ ዛፍ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="9">“የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ጥልቅ ነው፤ ማንስ ያው​ቀ​ዋል?</verse>
				<verse number="10">እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ሁሉ እንደ መን​ገ​ዱና፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመ​ረ​ም​ራ​ለሁ፤ ኵላ​ሊ​ት​ንም እፈ​ት​ና​ለሁ።”</verse>
				<verse number="11">ቆቅ ጮኸች፤ ያል​ወ​ለ​ደ​ች​ው​ንም ዐቀ​ፈች፤ በዐ​መፅ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትን የሚ​ሰ​በ​ስብ ሰውም እን​ደ​ዚሁ ነው፤ በእ​ኩ​ሌታ ዘመኑ ይተ​ወ​ዋል፤ በፍ​ጻ​ሜ​ውም ሰነፍ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="12">የመ​ቅ​ደ​ሳ​ችን ስፍራ ከጥ​ንት ጀምሮ ከፍ ያለ የክ​ብር ዙፋን ነው።</verse>
				<verse number="13">አቤቱ! የእ​ስ​ራ​ኤል ተስፋ ሆይ! የሚ​ተ​ዉህ ሁሉ ያፍ​ራሉ፤ ከአ​ን​ተም የሚ​ለዩ የሕ​ይ​ወ​ትን ውኃ ምንጭ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተ​ዋ​ልና በም​ድር ላይ ይጻ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="14">አቤቱ! ፈው​ሰኝ፤ እኔም እፈ​ወ​ሳ​ለሁ፤ አድ​ነኝ፤ እኔም እድ​ና​ለሁ፤ አንተ መመ​ኪ​ያዬ ነህና።</verse>
				<verse number="15">እነሆ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወዴት አለ? አሁን ይምጣ ይሉ​ኛል።</verse>
				<verse number="16">እኔም አን​ተን ተከ​ትዬ አል​ደ​ከ​ም​ሁም፥ የሰ​ው​ንም ቀን አል​ተ​መ​ኘ​ሁም፤ አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ ከከ​ን​ፈሬ የወ​ጣ​ውም በፊ​ትህ ነው።</verse>
				<verse number="17">እን​ግዳ አት​ሁ​ን​ብኝ፤ በክ​ፉም ቀን አንተ መጠ​ጊ​ያዬ ነህ።</verse>
				<verse number="18">አሳ​ዳ​ጆች ይፈሩ፤ እኔ ግን አል​ፈር፤ እነ​ርሱ ይደ​ን​ግጡ፤ እኔ ግን አል​ደ​ን​ግጥ፤ ክፉ​ንም ቀን አም​ጣ​ባ​ቸው፤ በሁ​ለት እጥፍ ጥፋት ቀጥ​ቅ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይለ​ኛል፥ “ሂድ፤ የይ​ሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት በሚ​ገ​ቡ​በ​ትና በሚ​ወ​ጡ​በት በሕ​ዝ​ብህ ልጆች በር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በሮች ሁሉ ቁም።”</verse>
				<verse number="20">እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፥ “በእ​ነ​ዚህ በሮች የም​ት​ገቡ እና​ንተ የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት፥ ይሁ​ዳም ሁሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የም​ት​ኖሩ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።”</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ራሳ​ች​ሁን ጠብቁ፥ በሰ​ን​በ​ትም ቀን ምንም ሸክም አት​ሸ​ከሙ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በሮች አታ​ግቡ፤</verse>
				<verse number="22">ከቤ​ቶ​ቻ​ችሁ በሰ​ን​በት ቀን ሸክ​ምን አታ​ውጡ፤ ሥራ​ንም ሁሉ አት​ሥሩ፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኋ​ቸው የሰ​ን​በ​ትን ቀን ቀድሱ።</verse>
				<verse number="23">እነ​ርሱ ግን አል​ሰ​ሙም፤ ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም አላ​ዘ​ነ​በ​ሉም፤ እን​ዳ​ይ​ሰ​ሙና ተግ​ሣ​ጼን እን​ዳ​ይ​ቀ​በ​ሉም ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ይልቅ አን​ገ​ታ​ቸ​ውን አደ​ነ​ደኑ።”</verse>
				<verse number="24">እኔን ፈጽሞ ብት​ሰሙ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በሰ​ን​በ​ትም ቀን በዚ​ህች ከተማ በሮች ሸክም ባታ​ገቡ፥ የሰ​ን​በ​ት​ንም ቀን ብት​ቀ​ድሱ፥ ሥራ​ንም ሁሉ ባት​ሠ​ሩ​ባት፥</verse>
				<verse number="25">በዳ​ዊት ዙፋን ላይ የሚ​ቀ​መጡ ነገ​ሥ​ታ​ትና መሳ​ፍ​ንት በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችና በፈ​ረ​ሶች ላይ እየ​ተ​ቀ​መጡ በዚ​ህች ከተማ በሮች ይገ​ባሉ፤ እነ​ር​ሱና አለ​ቆ​ቻ​ቸው የይ​ሁ​ዳም ሰዎች፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ቀ​መጡ ይገ​ባሉ፤ ይህ​ችም ከተማ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሰው መኖ​ሪያ ትሆ​ና​ለች።</verse>
				<verse number="26">የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን፥ እጅ መን​ሻ​ው​ንና ዕጣ​ኑን፥ የም​ስ​ጋ​ና​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ይዘው ከይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዙሪያ፥ ከብ​ን​ያ​ምም ሀገር፥ ከቆ​ላ​ውም፥ ከደ​ጋ​ውም፥ ከደ​ቡ​ብም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ይመ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="27">ነገር ግን የሰ​ን​በ​ትን ቀን እን​ድ​ት​ቀ​ድሱ፥ በሰ​ን​በ​ትም ቀን ሸክ​ምን ተሸ​ክ​ማ​ችሁ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሮች እን​ዳ​ት​ገቡ የነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁን ባት​ሰ​ሙኝ፥ በበ​ሮ​ችዋ ላይ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ግን​ቦች ትበ​ላ​ለች፤ አት​ጠ​ፋ​ምም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል፥ እን​ዲ​ህም አለው፦</verse>
				<verse number="2">“ተነ​ሥ​ተህ ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ውረድ፤ በዚ​ያም ቃሌን አሰ​ማ​ሃ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="3">ወደ ሸክላ ሠሪ​ውም ቤት ወረ​ድሁ፤ እነ​ሆም ሥራ​ውን በዓ​ለት ላይ ሲሠራ አገ​ኘ​ሁት።</verse>
				<verse number="4">ከጭ​ቃም ይሠ​ራው የነ​በ​ረው ዕቃ ከሸ​ክላ ሠሪው እጅ ወደቀ፤ ሸክላ ሠሪ​ውም እንደ ወደደ ዳግ​መኛ ሌላ ዕቃ አድ​ርጎ ሠራው።</verse>
				<verse number="5">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ።</verse>
				<verse number="6">“የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ይህ ሸክላ ሠሪ እን​ደ​ሚ​ሠራ በውኑ እኔ በእ​ና​ንተ ዘንድ መሥ​ራት አይ​ቻ​ለ​ኝ​ምን? እነሆ ጭቃው በሸ​ክላ ሠሪ እጅ እን​ዳለ፥ እን​ዲሁ እና​ንተ በእኔ እጅ አላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="7">አጠ​ፋ​ቸ​ውና እደ​መ​ስ​ሳ​ቸው ዘንድ በሕ​ዝብ ላይና በመ​ን​ግ​ሥት ላይ ቍርጥ ነገ​ርን ተና​ገ​ርሁ፤</verse>
				<verse number="8">ስለ እነ​ርሱ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ባ​ቸው ሕዝብ ከክ​ፋ​ታ​ቸው ቢመ​ለሱ፥ እኔ አደ​ር​ግ​ባ​ቸው ዘንድ ካሰ​ብ​ሁት ክፉ ነገር እጸ​ጸ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">በሕ​ዝ​ብም በመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ትም ላይ እሠ​ራ​ቸ​ውና እተ​ክ​ላ​ቸው ዘንድ ቍርጥ ነገ​ርን እና​ገ​ራ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="10">በፊቴ ክፉን ነገር ቢያ​ደ​ርጉ ቃሌ​ንም ባይ​ሰሙ፥ እኔ አደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ ስለ ተና​ገ​ር​ሁት መል​ካም ነገር እጸ​ጸ​ታ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="11">አሁን እን​ግ​ዲህ ለይ​ሁዳ ሰዎ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለሚ​ኖሩ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ ክፉ ነገር እፈ​ጥ​ር​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ምክ​ር​ንም እመ​ክ​ር​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ አሁ​ንም ሁላ​ችሁ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና ሥራ​ች​ሁ​ንም አቅኑ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው።”</verse>
				<verse number="12">እነ​ርሱ ግን፥ “እን​ጨ​ክ​ና​ለን፤ ክዳ​ታ​ች​ንን ተከ​ት​ለን እን​ሄ​ዳ​ለን፥ ሁላ​ች​ንም ክፉ ልባ​ች​ንን ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኛ​ትን እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አሉ።</verse>
				<verse number="13">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ያደ​ረ​ገ​ች​ውን በጣም የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ውን ነገር የሚ​ሰ​ሙት እን​ዳለ አሕ​ዛ​ብን ጠይቁ።”</verse>
				<verse number="14">ምንጭ ከዓ​ለት ይጠ​ፋ​ልን? በረ​ዶስ ከሊ​ባ​ኖስ ይጠ​ፋ​ልን? ወራጅ ውኃስ በኀ​ይ​ለኛ ነፋስ ይመ​ለ​ሳ​ልን?</verse>
				<verse number="15">ሕዝቤ ግን ረስ​ተ​ው​ኛል፤ ለከ​ንቱ ነገ​ርም አጥ​ነ​ዋል፤ የቀ​ድ​ሞ​ውን ጐዳና ትተው ወደ ጠማ​ማ​ውና ወደ ሰን​ከ​ል​ካ​ላው መን​ገድ ለመ​ሄድ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ተሰ​ና​ከሉ።</verse>
				<verse number="16">ምድ​ራ​ቸ​ውን ለጥ​ፋ​ትና ለዘ​ለ​ዓ​ለም ማፍ​ዋጫ አድ​ር​ገ​ዋል፤ የሚ​ያ​ል​ፍ​ባት ሁሉ ይደ​ነ​ቃል፤ ራሱ​ንም ያነ​ቃ​ን​ቃል።</verse>
				<verse number="17">በጠ​ላት ፊት እንደ በረሃ ዐውሎ ነፋስ እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በጥ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ቀን ጀር​ባ​ዬን እንጂ ፊቴን አላ​ሳ​ያ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="18">እነ​ር​ሱም፥ “ሕግ ከካ​ህን፥ ምክ​ርም ከጠ​ቢብ፥ ቃልም ከነ​ቢይ አይ​ጠ​ፋ​ምና ኑ፤ በኤ​ር​ም​ያስ ላይ ምክ​ርን እን​ም​ከር። ኑ፤ በም​ላስ እን​ም​ታው፤ ቃሉ​ንም ሁሉ አና​ዳ​ምጥ” አሉ።</verse>
				<verse number="19">“አቤቱ! አድ​ም​ጠኝ፤ የክ​ር​ክ​ሬ​ንም ቃል ስማ።</verse>
				<verse number="20">ለሰ​ው​ነቴ ጕድ​ጓ​ድን ቈፍ​ረ​ዋል፤ በውኑ በመ​ል​ካም ፈንታ ክፉ ይመ​ለ​ሳ​ልን? ስለ እነ​ርሱ በመ​ል​ካም እና​ገር ዘንድ፥ ቍጣ​ህ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ትመ​ልስ ዘንድ በፊ​ትህ እንደ ቆምሁ አስብ።</verse>
				<verse number="21">ስለ​ዚህ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለራብ ስጥ፤ ለሰ​ይ​ፍም እጅ አሳ​ል​ፈህ ስጣ​ቸው፤ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የወ​ላድ መካ​ንና መበ​ለ​ቶች ይሁኑ፤ ወን​ዶ​ቻ​ቸ​ውም በሞት ይጥፉ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም በጦ​ር​ነት ጊዜ በሰ​ይፍ ይመቱ።</verse>
				<verse number="22">ሊይ​ዙኝ ጕድ​ጓድ ቈፍ​ረ​ዋ​ልና፥ ለእ​ግ​ሮ​ችም ወጥ​መድ ሸሽ​ገ​ዋ​ልና፥ በቤ​ታ​ቸው ጩኸት ይሰማ፤ ድን​ገ​ትም በላ​ያ​ቸው ወን​በ​ዴን አም​ጣ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">አንተ ግን አቤቱ! ይገ​ድ​ሉኝ ዘንድ በላዬ የመ​ከ​ሩ​ትን ምክር ሁሉ ታው​ቃ​ለህ፤ በደ​ላ​ቸ​ው​ንም ይቅር አት​በል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ከፊ​ትህ አት​ደ​ም​ስስ፤ በፊ​ት​ህም ይው​ደቁ፤ በቍ​ጣህ ጊዜ እን​ዲሁ አድ​ር​ግ​ባ​ቸው።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ሂድ፤ የሸ​ክላ ሠሪ የሠ​ራ​ውን ገምቦ ግዛ፤ ከሕ​ዝ​ቡም ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ከካ​ህ​ናት ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ከአ​ንተ ጋር ውሰድ፤</verse>
				<verse number="2">በከ​ር​ሲት በር መግ​ቢያ አጠ​ገብ ወዳ​ለው ወደ ሄኖም ልጅ ሸለቆ ሂድ፥ በዚ​ያም የም​ነ​ግ​ር​ህን ቃል አን​ብብ፤ እን​ዲ​ህም በል፦</verse>
				<verse number="3">“የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታ​ትና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ት​ኖሩ ሆይ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በዚህ ስፍራ ክፉ ነገ​ርን አመ​ጣ​ለሁ፤ የሰ​ማ​ውም ሰው ሁሉ ይደ​ነ​ግ​ጣል፤ ጆሮ​ዎ​ቹ​ንም ይይ​ዛል።</verse>
				<verse number="4">ትተ​ው​ኛ​ልና፥ ይህ​ንም ስፍራ እን​ግዳ አድ​ር​ገ​ው​ታ​ልና፥ እነ​ር​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ለማ​ያ​ው​ቋ​ቸው ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት ዐጥ​ነ​ዋ​ልና፥ የይ​ሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት ይህን ስፍራ በን​ጹ​ሓን ደም ሞል​ተ​ዋ​ልና፥</verse>
				<verse number="5">እኔም ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ትን፥ ያል​ተ​ና​ገ​ር​ሁ​ት​ንም፥ ወደ ልቤም ያል​ገ​ባ​ውን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገው ለበ​ዓል ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ሳት ያቃ​ጥሉ ዘንድ የበ​ዓ​ልን የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎች ሠር​ተ​ዋ​ልና፤</verse>
				<verse number="6">ስለ​ዚህ እነሆ ይህ ስፍራ የእ​ርድ ሸለቆ ይባ​ላል እንጂ ቶፌት ወይም የሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ዳግ​መኛ የማ​ይ​ባ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="7">በዚ​ህም ስፍራ የይ​ሁ​ዳ​ንና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ምክር አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ፊት በጦ​ርና ነፍ​ሳ​ቸ​ውን በሚ​ሹት እጅ እጥ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ሬሳ​ቸ​ው​ንም ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት መብል አድ​ርጌ እሰ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">ይህ​ች​ንም ከተማ ለጥ​ፋ​ትና ለማ​ፍ​ዋጫ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ያ​ልፍ ሁሉ ስለ ተደ​ረ​ገ​ባት መቅ​ሠ​ፍት ሁሉ ይደ​ነ​ግ​ጣል፤ ያፍ​ዋ​ጫ​ልም።</verse>
				<verse number="9">የወ​ን​ዶ​ችና የሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሥጋ አበ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ነፍ​ሳ​ቸ​ውን የሚ​ሹት በሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቋ​ቸው ጭን​ቀ​ትና መከ​በብ የባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ሥጋ ይበ​ላሉ።</verse>
				<verse number="10">“ገም​ቦ​ው​ንም ከአ​ንተ ጋር በሚ​ሄዱ ሰዎች ፊት ትሰ​ብ​ራ​ለህ፤</verse>
				<verse number="11">እን​ዲ​ህም ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፦ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሸ​ክላ ማድጋ እን​ደ​ሚ​ሰ​ባ​በር ደግ​ሞም ይጠ​ገን ዘንድ እን​ደ​ማ​ይ​ቻል፥ እን​ዲሁ ይህን ሕዝ​ብና ይህ​ችን ከተማ እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ የሚ​ቀ​በ​ሩ​በ​ትም ስፍራ ሌላ የለ​ምና በቶ​ፌት ይቀ​በ​ራሉ።</verse>
				<verse number="12">እን​ዲሁ በዚህ ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ይህ​ች​ንም ከተማ እንደ ቶፌት አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ አፈ​ር​ሳ​ታ​ለ​ሁም።</verse>
				<verse number="13">የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቤቶ​ችና የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ቤቶች እንደ ቶፌት የረ​ከሱ ይሆ​ናሉ፤ እነ​ዚ​ያም በሰ​ገ​ነ​ታ​ቸው ላይ ለሰ​ማይ ሠራ​ዊት ሁሉ ያጠ​ኑ​ባ​ቸው፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት የመ​ጠጥ ቍር​ባን ያፈ​ሰ​ሱ​ባ​ቸው ቤቶች ሁሉ ይፈ​ር​ሳሉ።”</verse>
				<verse number="14">ኤር​ም​ያ​ስም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትን​ቢት ሊና​ገር ወደ​ዚያ ልኮት ከነ​በ​ረው ስፍራ ከቶ​ፌት ተመ​ለሰ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አደ​ባ​ባይ ቆሞ ለሕ​ዝቡ ሁሉ እን​ዲህ አላ​ቸው፦</verse>
				<verse number="15">የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ቃሌን እን​ዳ​ይ​ሰሙ አን​ገ​ታ​ቸ​ውን አደ​ን​ድ​ነ​ዋ​ልና እነሆ በዚች ከተ​ማና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ ሁሉ ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ባ​ትን ክፉ ነገር ሁሉ አመ​ጣ​ለሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የተ​ሾ​መው አለቃ የካ​ህኑ የኢ​ሜር ልጅ ጳስ​ኮር ኤር​ም​ያስ በዚህ ነገር ትን​ቢት ሲና​ገር ሰማ።</verse>
				<verse number="2">ጳስ​ኮ​ርም ነቢ​ዩን ኤር​ም​ያ​ስን ገረ​ፈው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በነ​በ​ረው በላ​ይ​ኛው በብ​ን​ያም በር ባለው አዘ​ቅት ውስጥ ጣለው።</verse>
				<verse number="3">በነ​ጋ​ውም ጳስ​ኮር ኤር​ም​ያ​ስን ከአ​ዘ​ቅት ውስጥ አወ​ጣው። ኤር​ም​ያ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም​ህን፦ ዘዋሪ ስደ​ተኛ እንጂ ጳስ​ኮር ብሎ አይ​ጠ​ራ​ህም።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ እነሆ አን​ተን ከወ​ዳ​ጆ​ችህ ሁሉ ጋር አፈ​ል​ስ​ሃ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ሰይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ዐይ​ኖ​ች​ህም ያያሉ፤ አን​ተ​ንና ይሁ​ዳ​ንም ሁሉ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እር​ሱም ወደ ባቢ​ሎን ያፈ​ል​ሳ​ቸ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፍም ይገ​ድ​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="5">የዚ​ች​ንም ከተማ ኀይል ሁሉ፥ ጥሪ​ቷ​ንም ሁሉ፥ ክብ​ር​ዋ​ንም ሁሉ፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ነገ​ሥ​ታት መዝ​ገብ ሁሉ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እነ​ርሱ ይበ​ዘ​ብ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ ይዘ​ውም ወደ ባቢ​ሎን ያስ​ገ​ቡ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">አን​ተም ጳስ​ኮር ሆይ! በቤ​ት​ህም የሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ተማ​ር​ካ​ችሁ ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ፤ አን​ተም በሐ​ሰት ትን​ቢት የተ​ና​ገ​ር​ህ​ላ​ቸው ወዳ​ጆ​ችህ ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን ትገ​ባ​ላ​ችሁ፤ በዚ​ያም ትሞ​ታ​ላ​ችሁ፤ በዚ​ያም ትቀ​በ​ራ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="7">አቤቱ! አታ​ለ​ል​ኸኝ፤ እኔም ተታ​ለ​ልሁ፤ ከእ​ኔም በረ​ታህ አሸ​ነ​ፍ​ህም፤ ቀኑን ሁሉ መሳ​ቂያ ሆኛ​ለሁ፤ ሁሉም ያፌ​ዙ​ብ​ኛል።</verse>
				<verse number="8">በተ​ና​ገ​ርሁ ቍጥር እጮ​ኻ​ለሁ፤ ግፍና ጥፋት ብዬ እጠ​ራ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ቀኑን ሁሉ ስድ​ብና ዋዛ ሆኖ​ብ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="9">እኔም እን​ዲህ አልሁ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም አላ​ነ​ሣም፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በስሙ አል​ና​ገ​ርም፥” በአ​ጥ​ን​ቶች ውስጥ እንደ ገባ እን​ደ​ሚ​ነ​ድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነ​ብኝ፤ ደከ​ምሁ፤ መሸ​ከ​ምም አል​ቻ​ል​ሁም።</verse>
				<verse number="10">በእኔ ላይ የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡና የከ​በ​ቡ​ኝን የብዙ ሰዎ​ችን ስድብ ሰም​ቻ​ለሁ፤ መው​ደ​ቄን የሚ​ጠ​ብቁ የሰ​ላሜ ሰዎች ሁሉ፥ “ምና​ል​ባት ይታ​ለል እንደ ሆነ፥ እና​ሸ​ን​ፈ​ውም እንደ ሆነ፥ እር​ሱ​ንም እን​በ​ቀል እንደ ሆነ፥ ተነሡ እኛም እን​ነ​ሣ​ለን” ይላሉ።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለ​ዚህ አሳ​ዳ​ጆች ይሰ​ና​ከ​ላሉ፤ አያ​ሸ​ን​ፉም፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም የማ​ይ​ረሳ ጕስ​ቍ​ል​ና​ቸ​ውን አላ​ወ​ቁ​ምና ፈጽ​መው አፈሩ።</verse>
				<verse number="12">አቤቱ! ጽድ​ቅን የም​ት​ፈ​ትን ኵላ​ሊ​ት​ንና ልብን የም​ት​መ​ረ​ምር የሠ​ራ​ዊት ጌታ ሆይ! ክር​ክ​ሬን ገል​ጬ​ል​ሃ​ለ​ሁና ፍረ​ድ​ልኝ።</verse>
				<verse number="13">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ፤ አመ​ስ​ግ​ኑ​ትም፤ የች​ግ​ረ​ኛ​ውን ነፍስ ከክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎች እጅ አድ​ኖ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="14">የተ​ወ​ለ​ድ​ሁ​ባት ቀን፥ እናቴ እኔን የወ​ለ​ደ​ች​ባት ቀን የተ​ረ​ገ​መች ትሁን፤ የተ​ባ​ረ​ከ​ችም አት​ሁን።</verse>
				<verse number="15">ወንድ ልጅ ተወ​ል​ዶ​ል​ሃል ብሎ ለአ​ባቴ የም​ሥ​ራች ነግሮ ደስ ያሰ​ኘው ሰው የተ​ረ​ገመ ይሁን።</verse>
				<verse number="16">ያም ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣው እንደ ገለ​በ​ጣ​ቸው፥ ይቅ​ርም እንደ አላ​ላ​ቸው ከተ​ሞች ይሁን፥ በማ​ለ​ዳም ልቅ​ሶን፥ በቀ​ት​ርም ጩኸ​ትን ይስማ፤</verse>
				<verse number="17">እናቴ መቃ​ብር ትሆ​ነኝ ዘንድ፥ ማኅ​ፀ​ን​ዋም ዘወ​ትር ይዞኝ ያቈይ ዘንድ በማ​ኅ​ፀን ውስጥ አል​ገ​ደ​ለ​ኝ​ምና።</verse>
				<verse number="18">ድካ​ም​ንና ጣርን አይ ዘንድ፥ ዘመ​ኔም በእ​ፍ​ረት ታልቅ ዘንድ ስለ ምን ከማ​ኅ​ፀን ወጣሁ?</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ የመ​ል​ክ​ያን ልጅ ጳስ​ኮ​ር​ንና የካ​ህ​ኑን የመ​ዕ​ሴ​ይን ልጅ ሶፎ​ን​ያ​ስን ወደ ኤር​ም​ያስ በላከ ጊዜ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ይወ​ጋን ዘንድ መጥ​ቶ​አ​ልና ከእኛ ይመ​ለስ ዘንድ፥ ምና​ል​ባ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር እንደ ተአ​ም​ራቱ ሁሉ ያደ​ርግ እንደ ሆነ ስለ እኛ፥ እባ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠይቅ።”</verse>
				<verse number="3">ኤር​ም​ያ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስን እን​ዲህ በሉት፦</verse>
				<verse number="4">የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ በቅ​ጥ​ርም ውጭ የከ​በ​ቡ​አ​ች​ሁን ከለ​ዳ​ው​ያ​ንን የም​ት​ወ​ጉ​በ​ትን በእ​ጃ​ችሁ ያለ​ውን የጦር መሣ​ሪ​ያ​ች​ሁን እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እነ​ዚ​ያ​ንም በዚ​ህች ከተማ መካ​ከል እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">እኔም በተ​ዘ​ረ​ጋች እጅና በብ​ርቱ ክንድ፥ በቍ​ጣና በመ​ዓት፥ በታ​ላ​ቅም መቅ​ሠ​ፍት አወ​ጋ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="6">በዚ​ህ​ችም ከተማ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ሰዎ​ች​ንና እን​ስ​ሶ​ችን እመ​ታ​ለሁ፤ በጽ​ኑም ቸነ​ፈር ይሞ​ታሉ።</verse>
				<verse number="7">ከዚህ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስ​ንና አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ ከቸ​ነ​ፈ​ርና ከሰ​ይፍ፥ ከራ​ብም በዚ​ህች ከተማ የቀ​ሩ​ትን ሕዝ​ቡ​ንም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ፥ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም በሚ​ሹት እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም በሰ​ይፍ ስለት ይመ​ታ​ቸ​ዋል፤ አያ​ዝ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ም​ራ​ቸ​ውም።”</verse>
				<verse number="8">ለዚ​ህም ሕዝብ እን​ዲህ በል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በፊ​ታ​ችሁ የሕ​ይ​ወ​ትን መን​ገ​ድና የሞ​ትን መን​ገድ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">በዚ​ህች ከተማ ውስጥ የሚ​ቀ​መጥ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ይሞ​ታል፤ ወጥቶ ወደ ከበ​ቡ​አ​ችሁ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን የሚ​ገባ ግን በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፤ ሰው​ነ​ቱም ምርኮ ትሆ​ና​ለች።</verse>
				<verse number="10">ለመ​ል​ካም ሳይ​ሆን ለክፉ ፊቴን በዚ​ህች ከተማ ላይ አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና፤ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ ትሰ​ጣ​ለች፤ እር​ሱም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላ​ታል።”</verse>
				<verse number="11">የይ​ሁዳ ንጉሥ ቤት ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።</verse>
				<verse number="12">የዳ​ዊት ቤት ሆይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ስለ ሥራ​ችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እን​ዳ​ይ​ነ​ድ​ድና ማንም ሳያ​ጠ​ፋው እን​ዳ​ያ​ቃ​ጥል፥ በማ​ለዳ ፍር​ድን አድ​ርጉ፤ የተ​ነ​ጠ​ቀ​ው​ንም ከአ​ስ​ጨ​ና​ቂው እጅ አድኑ።</verse>
				<verse number="13">እነሆ በሜዳ ላይ ባለው ድን​ጋ​ያማ ሸለቆ የም​ት​ቀ​መጥ ሆይ! እኔ በአ​ንተ ላይ ነኝ፤ እና​ን​ተም፦ የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጠን ወይም ወደ መኖ​ሪ​ያ​ችን የሚ​ገባ ማን ነው? የም​ትሉ ሆይ! እኔ በእ​ና​ንተ ላይ ነኝ፤</verse>
				<verse number="14">እንደ ሥራ​ች​ሁም ፍሬ እቀ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዱ​ር​ዋም ውስጥ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ያለ​ውን ሁሉ ይበ​ላል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤት ውረድ፤ በዚ​ያም ይህን ቃል ተና​ገር፥ እን​ዲ​ህም በል፦</verse>
				<verse number="2">በዳ​ዊት ዙፋን የም​ት​ቀ​መጥ የይ​ሁዳ ንጉሥ ሆይ! አን​ተና አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በእ​ነ​ዚ​ህም በሮች የሚ​ገባ ሕዝ​ብህ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን አድ​ርጉ፤ የተ​ነ​ጠ​ቀ​ው​ንም ከአ​ስ​ጨ​ና​ቂው እጅ አድኑ፤ መጻ​ተ​ኛ​ው​ንና ድሃ​አ​ደ​ጉን፥ ባል​ቴ​ቲ​ቱ​ንም አት​በ​ድሉ፤ አታ​ም​ፁ​ባ​ቸ​ውም፤ በዚ​ህም ስፍራ ንጹሕ ደምን አታ​ፍ​ስሱ።</verse>
				<verse number="4">ይህ​ንም ነገር ብታ​ደ​ርጉ፥ በዳ​ዊት ዙፋን የሚ​ቀ​መጡ ነገ​ሥ​ታት በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችና በፈ​ረ​ሶች ላይ ተቀ​ም​ጠው፥ በዚህ ቤት በሮች ይገ​ባሉ፤ እነ​ር​ሱም፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቻ​ቸ​ውም፥ ሕዝ​ቡም እን​ዲሁ ይገ​ባሉ።</verse>
				<verse number="5">ነገር ግን ይህን ቃል ባት​ሰሙ፥ ይህ ቤት ወና እን​ዲ​ሆን በራሴ ምያ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ቤት እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “አንተ በእኔ ዘንድ እንደ ገለ​ዓ​ድና እንደ ሊባ​ኖስ ራስ ነህ፤ በር​ግጥ ምድረ በዳና ማንም የማ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው ከተ​ሞች አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">የሚ​አ​ጠ​ፋ​ህን ሰው በአ​ንተ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ የሚ​ያ​ም​ረ​ውን ዛፍ​ህ​ንም በም​ሳር ይቈ​ር​ጣል፤ በእ​ሳ​ትም ያቃ​ጥ​ላል።</verse>
				<verse number="8">ብዙ አሕ​ዛ​ብም በዚች ከተማ ላይ ያል​ፋሉ፤ ሁሉም ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚች ታላቅ ከተማ ለምን እን​ዲህ አደ​ረገ? ይላሉ።</verse>
				<verse number="9">እነ​ር​ሱም፦ የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ትተው ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት ስለ ሰገዱ፥ ስለ አመ​ለ​ኳ​ቸ​ውም ነው ብለው ይመ​ል​ሳሉ።”</verse>
				<verse number="10">ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​መ​ለ​ስ​ምና፥ የተ​ወ​ለ​ደ​ባ​ት​ንም ሀገር አያ​ይ​ምና ለሚ​ወጣ እጅግ አል​ቅሱ እንጂ ለሞተ አታ​ል​ቅሱ፤ አት​ዘ​ኑ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="11">በአ​ባቱ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ፋንታ ስለ ነገ​ሠው፥ ከዚ​ህም ስፍራ ስለ ወጣ​ውና ስለ​ማ​ይ​መ​ለ​ሰው ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮ​ስ​ያስ ልጅ፥ ስለ ሳሌም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦</verse>
				<verse number="12">“በተ​ማ​ረ​ከ​በት ሀገር ይሞ​ታል፤ እን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ሀገ​ሩን አያ​ይም።”</verse>
				<verse number="13">ቤቱን በዐ​መፅ፥ አዳ​ራ​ሹ​ንም ያለ እው​ነት ለሚ​ሠራ፥ ባል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም እን​ዲ​ያው በከ​ንቱ ለሚ​ያ​ሠራ፥ ዋጋ​ው​ንም ለማ​ይ​ሰ​ጠው ወዮ​ለት!</verse>
				<verse number="14">“ለራሴ ሰፊ ቤት፥ ትል​ቅም ሰገ​ነት እሠ​ራ​ለሁ ለሚል፥ መስ​ኮ​ት​ንም ለሚ​ያ​ወጣ፥ በዝ​ግ​ባም ሥራ ለሚ​ያ​ስ​ጌጥ፥ በቀይ ቀለ​ምም ለሚ​ቀ​ባው ወዮ​ለት፤</verse>
				<verse number="15">በአ​ባ​ትህ ዝግባ አዳ​ራሽ ስለ ሠራህ በውኑ ትነ​ግ​ሣ​ለ​ህን? በውኑ አባ​ትህ አይ​በ​ላና አይ​ጠ​ጣም ነበ​ርን? ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅ​ንስ አያ​ደ​ር​ግም ነበ​ርን? በዚ​ያም ጊዜ መል​ካም ሆኖ​ለት ነበር።</verse>
				<verse number="16">የድ​ሃ​ው​ንና የች​ግ​ረ​ኛ​ውን ፍርድ ይፈ​ርድ ነበር፤ በዚ​ያም ጊዜ መል​ካም ሆኖ ነበር። ይህ እኔን ማወቅ አይ​ደ​ለ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="17">እነሆ ዐይ​ን​ህና ልብህ መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ለቅ​ሚያ፥ ንጹሕ ደም​ንም ለማ​ፍ​ሰስ፥ ግድ​ያ​ንና ግፍ​ንም ለመ​ሥ​ራት ብቻ ነው።”</verse>
				<verse number="18">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮ​ስ​ያስ ልጅ ስለ ኢዮ​አ​ቄም እን​ዲህ ይላል፥ “ወን​ድሜ ሆይ፥ ወዮ! ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! እያለ የሚ​ያ​ለ​ቅ​ስ​ለት ለሌ​ለው ለዚያ ሰው ወዮ​ለት!</verse>
				<verse number="19">አህ​ያም እን​ደ​ሚ​ቀ​በር ይቀ​በ​ራል፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በር ወደ ውጭ ተጐ​ትቶ፥ በው​ራጅ ጨርቅ ተጠ​ቅ​ልሎ ይጣ​ላል።”</verse>
				<verse number="20">ወዳ​ጆ​ችሽ ሁሉ ጠፍ​ተ​ዋ​ልና ወደ ሊባ​ኖስ ወጥ​ተሽ ጩኺ፤ በባ​ሳ​ንም ላይ ድም​ፅ​ሽን አንሺ፤ በባ​ሕ​ሩም ማዶ ጩኺ።</verse>
				<verse number="21">በጐ​ሰ​ቈ​ልሽ ጊዜ ተና​ገ​ር​ሁሽ፤ አን​ቺም፦ አል​ሰ​ማም አልሽ፤ ከሕ​ፃ​ን​ነ​ትሽ ጀምሮ ቃሌን አለ​መ​ስ​ማ​ትሽ መን​ገ​ድሽ ነው።</verse>
				<verse number="22">በግ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ሽን ሁሉ ነፋስ ይወ​ስ​ዳ​ቸ​ዋል፤ ወዳ​ጆ​ች​ሽም ተማ​ር​ከው ይሄ​ዳሉ፤ በዚ​ያን ጊዜም ስለ ክፋ​ትሽ ሁሉ ታፍ​ሪ​ያ​ለሽ፤ በወ​ዳ​ጆ​ች​ሽም ፊት ቷረ​ጃ​ለሽ።</verse>
				<verse number="23">አንቺ በሊ​ባ​ኖስ የም​ት​ቀ​መጪ፥ በዝ​ግባ ዛፍም ውስጥ የም​ታ​ለ​ቅሺ ሆይ! ምጥ እንደ ያዛት ሴት ሕማም በያ​ዘሽ ጊዜ እን​ዴት ትጨ​ነ​ቂ​ያ​ለሽ!</verse>
				<verse number="24">“እኔ ሕያው ነኝ የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​አ​ቄም ልጅ ኢኮ​ን​ያን ሆይ፥ አን​ተን በሰ​ወ​ር​ሁ​በት ቀኝ እጄ እን​ዳለ ማሕ​ተም ነበ​ርህ፤ እን​ግ​ዲህ ወዲህ ግን እን​ደ​ማ​ት​ኖር እኔ ሕያው ነኝ፤” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤</verse>
				<verse number="25">ነፍ​ስ​ህ​ንም ለሚ​ሹ​አት፥ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ለም​ት​ፈ​ራ​ቸው እጅ፥ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርና ለከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም እጅ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="26">አን​ተ​ንም፥ የወ​ለ​ደ​ች​ህን እና​ት​ህ​ንም ወዳ​ል​ተ​ወ​ለ​ዳ​ች​ሁ​ባት ወደ ሌላ ሀገር እጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ትሞ​ታ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="27">ነፍ​ሳ​ች​ሁም ወደ​ም​ት​መ​ኛት ወደ​ዚ​ያች ምድር አት​መ​ለ​ሱም።</verse>
				<verse number="28">ኢኮ​ን​ያን ተዋ​ረደ፤ ለም​ንም እን​ደ​ማ​ይ​ጠ​ቅም የሸ​ክላ ዕቃ ሆነ፤ እር​ሱ​ንና ዘሩን ወደ​ማ​ያ​ው​ቀው ሀገር ወር​ው​ረው ጥለ​ው​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="29">ምድር ሆይ! ምድር ሆይ! ምድር ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሚ።</verse>
				<verse number="30">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በዘ​መኑ አይ​ከ​ና​ወ​ን​ምና፥ ከዘ​ሩም በዳ​ዊት ዙፋን የሚ​ቀ​መጥ አይ​ነ​ሣ​ምና፥ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ለይ​ሁዳ ገዢ አይ​ሾ​ም​ምና ይህን ሰው እንደ ሞተ ቍጠ​ሪው” አለ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="23">
				<verse number="1">“የማ​ሰ​ማ​ር​ያ​ዬን በጎች ለሚ​ያ​ጠ​ፉና ለሚ​በ​ትኑ እረ​ኞች ወዮ​ላ​ቸው!” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="2">ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቤን ስለ​ሚ​ጠ​ብቁ እረ​ኞች እን​ዲህ ይላል፥ “በጎ​ችን በት​ና​ች​ኋል፤ አባ​ር​ራ​ች​ኋ​ቸ​ው​ማል፥ አል​ጐ​በ​ኛ​ች​ኋ​ቸ​ው​ምም፤ እነሆ! እንደ ሥራ​ችሁ ክፋት እጐ​በ​ኛ​ች​ኋ​ለሁ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="3">የሕ​ዝ​ቤን ቅሬታ ከበ​ተ​ን​ኋ​ቸው ምድር ሁሉ ወደ መሰ​ማ​ሪ​ያ​ቸው ሰብ​ስቤ እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይበ​ዛሉ፤ ይባ​ዛ​ሉም።</verse>
				<verse number="4">የሚ​ጠ​ብ​ቋ​ቸ​ውን እረ​ኞች አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ዳግ​መ​ኛም አይ​ፈ​ሩም፤ አይ​ደ​ነ​ግ​ጡ​ምም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="5">“እነሆ ለዳ​ዊት የጽ​ድቅ ቍጥ​ቋጥ የማ​ስ​ነ​ሣ​በት ዘመን ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ንጉሥ ይነ​ግ​ሣል፤ ያስ​ባል፤ በም​ድ​ርም ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን ያደ​ር​ጋል።</verse>
				<verse number="6">በዘ​መ​ኑም ይሁዳ ይድ​ናል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ተዘ​ልሎ ይቀ​መ​ጣል፤ ይህም ስም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በነ​ቢ​ያት ኢዮ​ሴ​ዴቅ ብሎ የጠ​ራው ነው።</verse>
				<verse number="7">ስለ​ዚህ እነሆ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሕዝብ ከግ​ብፅ ምድር ያወጣ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ዳግ​መኛ የማ​ይ​ባ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤</verse>
				<verse number="8">ነገር ግን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ዘር ከሰ​ሜን ሀገ​ርና ካሳ​ደ​ዷ​ቸ​ውም ሀገር ሁሉ ያወ​ጣና የመራ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን!” ይባ​ላል፤ በም​ድ​ራ​ቸ​ውም መልሶ ያኖ​ራ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="9">ስለ ነቢ​ያት ልቤ በው​ስጤ ተሰ​ብ​ሮ​አል፤ አጥ​ን​ቶ​ችም ሁሉ ታው​ከ​ዋል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ነሣ፤ ከጌ​ት​ነ​ቱም ክብር የተ​ነሣ እኔም በመ​ከራ እንደ ተቀ​ጠ​ቀጠ ሰው፥ የወ​ይን ጠጅ እን​ዳ​ሸ​ነ​ፈ​ውም እንደ ሰካ​ራም ሰው ሆኛ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">ዝሙ​ታ​ቸው ምድ​ርን ሞል​ት​ዋ​ልና፥ ከመ​ር​ገም ፊት የተ​ነሣ ምድር አል​ቅ​ሳ​ለች፤ የም​ድረ በዳ ማሰ​ሪ​ያው ሁሉ ደር​ቆ​አል፤ ሥራ​ቸ​ውና ድካ​ማ​ቸው ከንቱ ሆነ።</verse>
				<verse number="11">“ነቢ​ዩና ካህ​ኑም ረክ​ሰ​ዋ​ልና፥ በቤ​ቴም ውስጥ ክፋ​ታ​ቸ​ውን አግ​ኝ​ቻ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="12">ስለ​ዚህ መን​ገ​ዳ​ቸው ድጥና ጨለማ ትሆ​ን​ባ​ቸ​ዋ​ለች፤ እነ​ር​ሱም ፍግ​ም​ግም ብለው ይወ​ድ​ቁ​ባ​ታል፤ እኔም በም​ጐ​በ​ኛ​ቸው ዓመት ክፉ ነገ​ርን አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="13">በበ​ዓል ትን​ቢት የተ​ና​ገ​ሩ​በ​ትን የሰ​ማ​ር​ያን ነቢ​ያት ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን አይ​ቻ​ለሁ፤ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ል​ንም አሳ​ት​ዋ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ነቢ​ያት ላይ የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጥን ነገር አይ​ቻ​ለሁ፤ ያመ​ነ​ዝ​ራሉ፤ በሐ​ሰ​ትም ይሄ​ዳሉ፤ ማንም ከክ​ፋቱ እን​ዳ​ይ​መ​ለስ የክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎ​ችን እጅ ያበ​ረ​ታሉ፤ ሁሉም እንደ ሰዶም፥ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም እንደ ገሞራ ሆኑ​ብኝ።</verse>
				<verse number="15">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነቢ​ያት ዘንድ ርኵ​ሰት በም​ድር ሁሉ ላይ ወጥ​ቶ​አ​ልና ሕማ​ምን አበ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ መራራ ውኃ​ንም አጠ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="16">ኀያል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ላ​ች​ሁን የነ​ቢ​ያ​ትን ቃል አት​ስሙ፤ ከን​ቱ​ነ​ትን ያስ​ተ​ም​ሩ​አ​ች​ኋል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ ሳይ​ሆን ከገዛ ልባ​ቸው የወ​ጣ​ውን ራእይ ይና​ገ​ራሉ።</verse>
				<verse number="17">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ለሚ​ያ​ቃ​ልሉ ሰላም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፥ በፍ​ላ​ጎ​ታ​ቸ​ውና በል​ቡ​ና​ቸው ክፋት ለሚ​ሄ​ዱም ሁሉ፦ ክፉ ነገር አያ​ገ​ኛ​ች​ሁም” ይላሉ።</verse>
				<verse number="18">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክር የሚ​ቆም፥ ቃሉን የሚ​ያ​ይና የሚ​ሰማ ማን ነው? ቃሉ​ንስ ያዳ​መጠ፥ የሰ​ማስ ማን​ነው?</verse>
				<verse number="19">እነሆ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ንው​ጽ​ው​ጽታ ይመ​ጣል፤ ኃጥ​ኣ​ንን ያነ​ዋ​ው​ጣ​ቸ​ውና ይገ​ለ​ብ​ጣ​ቸው ዘንድ መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋል፤ የዐ​መ​ፀ​ኞ​ችን ራስ ይገ​ለ​ባ​ብ​ጣል።</verse>
				<verse number="20">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ የል​ቡን ዐሳብ ሠርቶ እስ​ኪ​ፈ​ጽም ድረስ አይ​መ​ለ​ስም፤ በኋ​ለ​ኛ​ውም ዘመን ያው​ቁ​ታል።</verse>
				<verse number="21">“እኔ ሳል​ል​ካ​ቸው እነ​ዚህ ነቢ​ያት ሮጡ፤ እኔም ሳል​ነ​ግ​ራ​ቸው ትን​ቢ​ትን ተና​ገሩ።</verse>
				<verse number="22">በቃሌ ቢቆ​ሙና ምክ​ሬን ቢሰሙ ኖሮ ግን ሕዝ​ቤን ከክፉ ሥራ​ቸው በመ​ለ​ሱ​አ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="23">“እኔ ቅርብ አም​ላክ ነኝ እንጂ ሩቅ አም​ላክ አይ​ደ​ለ​ሁም ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="24">ሰው በስ​ውር ቦታ ቢሸ​ሸግ፥ እኔ አላ​የ​ው​ምን? ሰማ​ይ​ንና ምድ​ር​ንስ የሞ​ላሁ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="25">ሕል​ምን አለ​ምን እያሉ በስሜ ሐሰ​ተኛ ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን የነ​ቢ​ያ​ትን ነገር ሰም​ቻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="26">ትን​ቢ​ትን በሐ​ሰት በሚ​ና​ገሩ፥ የል​ባ​ቸ​ው​ንም ሽን​ገላ በሚ​ና​ገሩ በነ​ቢ​ያት ልብ ይህ የሚ​ሆ​ነው እስከ መቼ ነው?</verse>
				<verse number="27">አባ​ቶ​ቻ​ቸው ስለ በዓል ስሜን እንደ ረሱ፥ እያ​ን​ዳ​ንዱ ለባ​ል​ን​ጀ​ራው በሚ​ና​ገ​ራት ሕል​ማ​ቸው ሕዝ​ቤን ስሜን ለማ​ስ​ረ​ሳት ያስ​ባሉ።</verse>
				<verse number="28">የሚ​ያ​ልም ነቢይ ሕል​ምን ይና​ገር፤ ቃሌም ያለ​በት ቃሌን በእ​ው​ነት ይና​ገር። ገለባ ከስ​ንዴ ጋር ምን አለው? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="29">በውኑ ቃሌ እንደ እሳት፥ ድን​ጋ​ዩ​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ቅቅ መዶሻ አይ​ደ​ለ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="30">ስለ​ዚህ እነሆ እያ​ን​ዳ​ንዱ ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ዘንድ ቃሌን በሚ​ሰ​ርቁ ነቢ​ያት ላይ ነኝ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="31">እነሆ ከም​ላ​ሳ​ቸው ትን​ቢ​ትን አው​ጥ​ተው፦ እርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሸክም ነው በሚሉ ነቢ​ያት ላይ ነኝ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤</verse>
				<verse number="32">እነሆ ሐሰ​ትን በሚ​ያ​ልሙ፥ በሚ​ና​ገ​ሩም፥ በሐ​ሰ​ታ​ቸ​ውና በድ​ፍ​ረ​ታ​ቸ​ውም ሕዝ​ቤን በሚ​ያ​ስቱ በነ​ቢ​ያት ላይ ነኝ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እኔም አል​ላ​ክ​ኋ​ቸ​ውም፤ አላ​ዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ው​ምም፤ ለእ​ነ​ዚህ ሕዝብ በማ​ና​ቸ​ውም አይ​ረ​ቡ​አ​ቸ​ውም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="33">ይህ ሕዝብ ወይም ነቢይ ወይም ካህን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሸክም ምን​ድር ነው?” ብሎ ቢጠ​ይ​ቅህ፥ አንተ፥ “ሸክሙ እና​ንተ ናችሁ፤ እጥ​ላ​ች​ሁ​ማ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="34">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሸክም የሚ​ለ​ውን ነቢ​ይ​ንና ካህ​ንን፥ ሕዝ​ብ​ንም ያን ሰውና ቤቱን እቀ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="35">አን​ዱም አንዱ ለባ​ል​ን​ጀ​ራው፥ አን​ዱም አንዱ ለወ​ን​ድሙ እን​ዲህ ይበል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ለ​ሰው ምን​ድን ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ምን ነገር ተና​ገረ?”</verse>
				<verse number="36">ለሰው ሁሉ ቃሉ ሸክም ይሆ​ን​በ​ታ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሸክም ብላ​ችሁ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አት​ጥሩ፤ የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሕ​ያ​ውን አም​ላክ ቃል ለው​ጣ​ች​ኋ​ልና።</verse>
				<verse number="37">ለነ​ቢዩ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን መለ​ሰ​ልህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ የተ​ና​ገ​ረው ምን​ድን ነው?” በሉ ምን ተና​ገረ?</verse>
				<verse number="38">ነገር ግን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሸክም” ብትሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሸክም አት​በሉ ብዬ ልኬ​ባ​ች​ኋ​ለ​ሁና፥ እና​ን​ተም ይህን ቃል፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሸክም ብላ​ች​ኋ​ልና፥</verse>
				<verse number="39">ስለ​ዚህ፥ እነሆ- ፈጽሜ እረ​ሳ​ች​ኋ​ለሁ እና​ን​ተ​ንም፥ ለእ​ና​ን​ተና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም የሰ​ጠ​ኋ​ትን ከተማ ከፊቴ አን​ሥቼ እጥ​ላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="40">የዘ​ለ​ዓ​ለ​ም​ንም ስድ​ብና ከቶ ተረ​ስቶ የማ​ይ​ጠ​ፋ​ውን የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምን ውር​ደት አመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="24">
				<verse number="1">የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የኢ​ዮ​አ​ቄ​ምን ልጅ ኢኮ​ን​ያ​ንን፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም አለ​ቆች፥ ብል​ሃ​ተ​ኞ​ች​ንና እስ​ረ​ኞ​ችን፥ ጓደ​ኞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ማርኮ ወደ ባቢ​ሎን ከአ​ፈ​ለ​ሳ​ቸው በኋላ፥ እነሆ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ ፊት የተ​ቀ​መጡ ሁለት የበ​ለስ ቅር​ጫ​ቶ​ችን አሳ​የኝ።</verse>
				<verse number="2">በአ​ን​ደ​ኛ​ዪቱ ቅር​ጫት አስ​ቀ​ድሞ እንደ ደረሰ በለስ የሚ​መ​ስል እጅግ መል​ካም በለስ ነበ​ረ​ባት፤ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ቅር​ጫት ከክ​ፋቱ የተ​ነሣ ይበላ ዘንድ የማ​ይ​ቻል እጅግ ክፉ በለስ ነበ​ረ​ባት።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ኤር​ም​ያስ ሆይ! የም​ታ​የው ምን​ድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “በለ​ስን አያ​ለሁ፤ እጅግ መል​ካም የሆነ መል​ካም በለስ፥ ከክ​ፋ​ቱም የተ​ነሣ ይበላ ዘንድ የማ​ይ​ቻል እጅግ ክፉ የሆነ ክፉ በለስ ነው” አልሁ።</verse>
				<verse number="4">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="5">“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እን​ደ​ዚህ እንደ መል​ካሙ በለስ፥ እን​ዲሁ ከዚህ ስፍራ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን ምድር የሰ​ደ​ድ​ሁ​ትን የይ​ሁ​ዳን ምርኮ ለበ​ጎ​ነት እመ​ለ​ከ​ተ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="6">ዐይ​ኔ​ንም ለበ​ጎ​ነት በእ​ነ​ርሱ ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ወደ​ዚ​ህ​ችም ምድር ለመ​ል​ካም እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እሠ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ አላ​ፈ​ር​ሳ​ቸ​ውም፤ እተ​ክ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ አል​ነ​ቅ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="7">እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ የሚ​ያ​ውቅ ልብ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በፍ​ጹ​ምም ልባ​ቸው ወደ እኔ ይመ​ለ​ሳ​ሉና ሕዝቤ ይሆ​ኑ​ኛል፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላል፥ “ከክ​ፋቱ የተ​ነሣ ይበላ ዘንድ እን​ደ​ማ​ይ​ቻል እንደ ክፉው በለስ፥ እን​ዲሁ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስን፤ አለ​ቆ​ቹ​ንም፥ በዚች ሀገር የሚ​ቀ​ሩ​ት​ንም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ቅሬታ፥ በግ​ብ​ጽም ሀገር የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን እን​ዲሁ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">በማ​ሳ​ድ​ዳ​ቸ​ውም ስፍራ ሁሉ ለስ​ድ​ብና ለም​ሳሌ፥ ለጥ​ላ​ቻና ለር​ግ​ማን ይሆኑ ዘንድ በም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ እን​ዲ​በ​ተኑ አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">ለእ​ነ​ርሱ፥ ለዘ​ራ​ቸ​ውና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከሰ​ጠ​ኋ​ቸው ምድር እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ሰይ​ፍ​ንና ራብን ቸነ​ፈ​ር​ንም እሰ​ድ​ዳ​ለሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="25">
				<verse number="1">በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት፥ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዓመት፥ ስለ ይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው ቃል ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">ይህ​ንም ቃል ነቢዩ ኤር​ም​ያስ ለይ​ሁዳ ሕዝብ ሁሉና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለተ​ቀ​መጡ ሁሉ እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፦</verse>
				<verse number="3">“ከይ​ሁዳ ንጉሥ ከአ​ሞጽ ልጅ ከኢ​ዮ​ስ​ያስ ከዐ​ሥራ ሦስ​ተ​ኛው ዓመት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባሉት በእ​ነ​ዚህ በሃያ ሦስቱ ዓመ​ታት፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ መጣ፤ እኔም ማልጄ ተነ​ሥቼ ተና​ገ​ር​ኋ​ችሁ፤ ነገር ግን አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም።”</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባሪ​ያ​ዎ​ቹን ነቢ​ያ​ትን ወደ እና​ንተ ላከ፤ እነ​ር​ሱም ማል​ደው ገሠ​ገሡ፤ እና​ን​ተም አል​ሰ​ማ​ች​ኋ​ቸ​ውም፤ ለመ​ስ​ማ​ትም ጆሮ​አ​ች​ሁን አላ​ዘ​ነ​በ​ላ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="5">እር​ሱም፥ “ሁላ​ችሁ እና​ንተ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ች​ሁና ከሥ​ራ​ችሁ ክፋት ተመ​ለሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ለእ​ና​ን​ተና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ በሰ​ጣ​ችሁ ምድር ትቀ​መ​ጣ​ላ​ችሁ አለ።</verse>
				<verse number="6">ትገ​ዙ​ላ​ቸ​ውና ትሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም ዘንድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አት​ከ​ተሉ፤ ክፉም እን​ዳ​ላ​ደ​ር​ግ​ባ​ችሁ በእ​ጃ​ችሁ ሥራ አታ​ስ​ቈ​ጡኝ።</verse>
				<verse number="7">ለእ​ና​ንተ ጕዳት እን​ዲ​ሆን በእ​ጃ​ችሁ ሥራ ታስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="8">ስለ​ዚህ ኀያል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ቃሌን አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምና፤</verse>
				<verse number="9">እነሆ ልኬ የሰ​ሜ​ንን ወገ​ኖች ሁሉ፤ ባሪ​ያ​ዬ​ንም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ በዚ​ችም ምድ​ርና በሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትም ሰዎች ላይ፥ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ባሉ በእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ሁሉ ላይ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ፈጽ​ሜም አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ለጥ​ፋ​ትና ለፉ​ጨት ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ዕፍ​ረት ባድማ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">ከእ​ነ​ር​ሱም የሐ​ሤ​ትን ድም​ፅና የደ​ስ​ታን ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽ​ራን ድም​ጽና የሴት ሙሽ​ራን ድምፅ፥ የወ​ፍ​ጮ​ንም ድምፅ የመ​ብ​ራ​ት​ንም ብር​ሃን አስ​ቀ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">ይህ​ችም ምድር ሁሉ ትጠ​ፋ​ለች፤ ለእ​ነ​ዚ​ህም አሕ​ዛ​ብና ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሰባ ዓመት ይገ​ዛሉ።</verse>
				<verse number="12">“ሰባው ዓመ​ትም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉ​ሥና ያን ሕዝብ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው እቀ​ጣ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ን​ንም ምድር ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">በእ​ር​ስ​ዋም ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ቃሌን ሁሉ፥ ኤር​ም​ያስ በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ላይ በት​ን​ቢት የተ​ና​ገ​ረ​ውን በዚች መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ፥ በዚ​ያች ምድር ላይ አመ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">ብዙ አሕ​ዛ​ብና ታላ​ላ​ቆች ነገ​ሥ​ታት እነ​ር​ሱን ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ እኔም እንደ አደ​ራ​ረ​ጋ​ቸ​ውና እንደ እጃ​ቸው ሥራ እከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="15">የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይለ​ኛል፥ “ያል​ተ​በ​ረዘ የዚ​ህን ቍጣ የወ​ይን ጠጅ ጽዋ ከእጄ ውሰድ፤ አን​ተን የም​ሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ አጠ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">ከም​ሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ውም ሰይፍ የተ​ነሣ ይጠ​ጣሉ፤ ይወ​ላ​ገ​ዳሉ፤ ያብ​ዳ​ሉም።”</verse>
				<verse number="17">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ ጽዋ​ውን ወሰ​ድሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እኔን የላ​ከ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛብ ሁሉ አጠ​ጣ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ፈጽሞ ምድረ በዳ ይሆኑ ዘንድ፥ ለር​ግ​ማ​ንም አደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንና የይ​ሁ​ዳን ከተ​ሞች፥ ነገ​ሥ​ታ​ቷ​ንም፥ አለ​ቆ​ች​ዋ​ንም አጠ​ጣ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">የግ​ብ​ፅ​ንም ንጉሥ ፈር​ዖ​ንን፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም፥ መሳ​ፍ​ን​ቱ​ንና መኳ​ን​ን​ቱን፤ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ፥</verse>
				<verse number="20">የተ​ደ​ባ​ለ​ቀ​ው​ንም ሕዝብ ሁሉ፥ የዖፅ ምድር ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፥ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ምድር ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፤ አስ​ቀ​ሎ​ና​ንም፥ ጋዛ​ንም፥ አቃ​ሮ​ን​ንም፥ የአ​ዛ​ጦ​ን​ንም ቅሬታ፤</verse>
				<verse number="21">ኤዶ​ም​ያ​ስ​ንም፥ ሞዓ​ብ​ንም፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች፤</verse>
				<verse number="22">የጢ​ሮ​ስ​ንም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ፥ የሲ​ዶ​ና​ንም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ፥ በባ​ሕር ማዶ ያሉ የደ​ሴት ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም፤</verse>
				<verse number="23">ድዳ​ን​ንም፥ ቴማ​ን​ንም፥ ሮስ​ንም፥ ፊታ​ቸ​ውን የሚ​ከ​ተ​ቡ​ትን ሁሉ፤</verse>
				<verse number="24">የዓ​ረብ ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፥ በም​ድረ በዳ የሚ​ቀ​መጡ የድ​ብ​ልቅ ሕዝብ ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፤</verse>
				<verse number="25">የዘ​ምሪ ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፥ የኤ​ላም ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፥ የሜ​ዶን ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፤</verse>
				<verse number="26">የቀ​ረ​ቡና የራቁ፥ አንዱ ከሌ​ላው ጋር ያሉ የሰ​ሜን ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፥ በም​ድር ፊት ላይ ያሉ የዓ​ለም መን​ግ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ አጠ​ጣ​ኋ​ቸው፤ የሲ​ሳ​ርም ንጉሥ ከእ​ነ​ርሱ በኋላ ይጠ​ጣል።</verse>
				<verse number="27">አን​ተም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ከም​ሰ​ድ​ደው ሰይፍ የተ​ነሣ ጠጡ፤ ስከ​ሩም፤ ተፍ​ገ​ም​ገሙ፤ ውደ​ቁም፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አት​ነ​ሡም በላ​ቸው።</verse>
				<verse number="28">ይጠ​ጡም ዘንድ ጽዋ​ውን ከእ​ጅህ ለመ​ቀ​በል እንቢ ቢሉ፦ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ፈጽ​ማ​ችሁ ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ” በላ​ቸው።</verse>
				<verse number="29">እነሆ ስሜ የተ​ጠ​ራ​ባ​ትን ከተማ አስ​ጨ​ን​ቃት ዘንድ እጀ​ም​ራ​ለሁ፤ በውኑ እና​ንተ መን​ጻ​ትን ትነ​ጻ​ላ​ች​ሁን? በም​ድር በሚ​ኖሩ ሁሉ ላይ ሰይ​ፍን እጠ​ራ​ለ​ሁና አት​ነ​ጹም፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="30">“ስለ​ዚ​ህም ይህን ቃል ሁሉ ትን​ቢት ትና​ገ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ እን​ዲ​ህም ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላይ ሆኖ እንደ አን​በሳ ያገ​ሣል፤ በቅ​ዱስ ማደ​ሪ​ያ​ውም ሆኖ ድም​ፁን ያሰ​ማል፤ በበ​ረቱ ላይ እጅግ ያገ​ሣል፤ ወይ​ንም እን​ደ​ሚ​ጠ​ምቁ በም​ድር በሚ​ኖሩ ሁሉ ላይ ይጮ​ኻል።</verse>
				<verse number="31">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ሕ​ዛብ ጋር ክር​ክር አለ​ውና ጥፋት እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደ​ር​ሳል፤ ከሥጋ ለባሽ ሁሉም ጋር ይፋ​ረ​ዳል፤ ኀጢ​አ​ተ​ኞ​ች​ንም ለሰ​ይፍ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”</verse>
				<verse number="32">የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ ክፉ ነገር ከሕ​ዝብ ወደ ሕዝብ ይወ​ጣል፤ ጽኑም ዐውሎ ነፋስ ከም​ድር ዳርቻ ይነ​ሣል።</verse>
				<verse number="33">በዚ​ያም ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግዳ​ዮች ከም​ድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆ​ናሉ፤ አይ​ለ​ቀ​ስ​ላ​ቸ​ውም፤ በም​ድር ላይ እንደ ጕድፍ ይሆ​ናሉ እንጂ አይ​ሰ​በ​ሰ​ቡም፤ አይ​ቀ​በ​ሩ​ምም።</verse>
				<verse number="34">ትታ​ረ​ዱና ትበ​ተኑ ዘንድ ቀና​ችሁ ደር​ሶ​አ​ልና፥ እንደ ተወ​ደደ የሸ​ክላ ዕቃ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ች​ሁና እና​ንተ እረ​ኞች! አል​ቅሱ፤ እና​ን​ተም የበ​ጎች አው​ራ​ዎች! ጩኹ።</verse>
				<verse number="35">ከእ​ረ​ኞች የማ​ይ​ጠፋ የለም፤ የበ​ጎች አው​ራ​ዎ​ችም አይ​ድ​ኑም።</verse>
				<verse number="36">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማሰ​ማ​ር​ያ​ቸ​ውን አጥ​ፍ​ቶ​አ​ልና የእ​ረ​ኞች ጩኸት ድምፅ፥ የበ​ጎች አው​ራ​ዎ​ችም ልቅሶ ሆኖ​አል።</verse>
				<verse number="37">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽኑ ቍጣ የተ​ነሣ የሰ​ላም ውበት ፈር​ሶ​አል።</verse>
				<verse number="38">እንደ አን​በሳ መደ​ቡን ለቅ​ቆ​አል፤ ከአ​ረ​ማ​ው​ያን ሰል​ፍና ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽኑ ቍጣ የተ​ነሣ ምድ​ራ​ቸው ምድረ በዳ ሆና​ለ​ችና።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="26">
				<verse number="1">በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም መን​ግ​ሥት መጀ​መ​ሪያ ይህ ቃል ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መጣ፤ አለም፦</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ ቁም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ውስጥ ይሰ​ግዱ ዘንድ ለሚ​መ​ጡት ለይ​ሁዳ ከተ​ሞች ሁሉ ትነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ቃል ሁሉ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ አን​ዲ​ትም ቃል አታ​ጕ​ድል።</verse>
				<verse number="3">ምና​ል​ባት እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ይሰሙ፥ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም ይመ​ለሱ ይሆ​ናል፤ እኔም ስለ ሥራ​ቸው ክፋት ያሰ​ብ​ሁ​ባ​ቸ​ውን ክፉ ነገር እተ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="4">እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በፊ​ታ​ችሁ በሰ​ጠ​ኋት ሕጌ ትሄዱ ዘንድ ባት​ሰ​ሙኝ፥</verse>
				<verse number="5">የባ​ሪ​ያ​ዎ​ችን የነ​ቢ​ያ​ትን ቃል ትሰሙ ዘንድ በማ​ለዳ ወደ እና​ንተ ብል​ካ​ቸው አል​ሰ​ማ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="6">ይህን ቤት እንደ ሴሎ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ይች​ንም ከተማ ለም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ ርግ​ማን አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="7">ካህ​ና​ቱም፥ ነቢ​ያተ ሐሰ​ትም፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ ኤር​ም​ያስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ይህን ቃል ሲና​ገር ሰሙ።</verse>
				<verse number="8">ኤር​ም​ያ​ስም ለሕ​ዝቡ ሁሉ ይና​ገር ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ነገር ሁሉ በፈ​ጸመ ጊዜ ካህ​ና​ትና ነቢ​ያተ ሐሰት፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “ሞትን ትሞ​ታ​ለህ” ብለው ያዙት።</verse>
				<verse number="9">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም፥ “ይህ ቤት እንደ ሴሎ ይሆ​ናል፤ ይችም ከተማ ባድማ ትሆ​ና​ለች፤ የሚ​ኖ​ር​ባ​ትም የለም ብለህ ስለ ምን ትን​ቢት ተና​ገ​ርህ?” ሕዝ​ቡም ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በኤ​ር​ም​ያስ ላይ ተሰ​ብ​ስ​በው ነበር።</verse>
				<verse number="10">የይ​ሁ​ዳም አለ​ቆች ይህን በሰሙ ጊዜ ከን​ጉሡ ቤት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወጡ፤ በአ​ዲ​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ደጅ መግ​ቢያ ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="11">ካህ​ና​ቱና ነቢ​ያተ ሐሰ​ትም ለአ​ለ​ቆ​ቹና ለሕ​ዝቡ ሁሉ፥ “በጆ​ሮ​አ​ችሁ እንደ ሰማ​ችሁ በዚች ከተማ ላይ ትን​ቢት ተና​ግ​ሮ​አ​ልና ይህ ሰው ሞት የሚ​ገ​ባው ነው” ብለው ተና​ገሩ።</verse>
				<verse number="12">ኤር​ም​ያ​ስም ለአ​ለ​ቆ​ችና ለሕ​ዝቡ ሁሉ እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፥ “በሰ​ማ​ች​ሁት ቃል ሁሉ፥ በዚች ቤትና በዚ​ህች ከተማ ላይ ትን​ቢት እና​ገር ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልኮ​ኛል።</verse>
				<verse number="13">አሁ​ንም መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና ሥራ​ች​ሁን አሳ​ምሩ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ና​ገ​ረ​ባ​ች​ሁን ክፉ ነገር ይተ​ዋል።</verse>
				<verse number="14">እኔ ግን፥ እነሆ በእ​ጃ​ችሁ ነኝ፤ በዐ​ይ​ና​ችሁ መል​ካ​ምና ቅን የመ​ሰ​ለ​ውን አድ​ር​ጉ​ብኝ።</verse>
				<verse number="15">ነገር ግን ይህን ቃል ሁሉ በጆ​ሮ​አ​ችሁ እና​ገር ዘንድ በእ​ው​ነቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ እና​ንተ ልኮ​ኛ​ልና ብት​ገ​ድ​ሉኝ ንጹሕ ደምን በራ​ሳ​ች​ሁና በዚች ከተማ፥ በሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም ላይ እን​ድ​ታ​መጡ በር​ግጥ ዕወቁ።”</verse>
				<verse number="16">አለ​ቆ​ቹና ሕዝ​ቡም ሁሉ ለካ​ህ​ና​ትና ለነ​ቢ​ያተ ሐሰት፥ “ይህ ሰው በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ተና​ግ​ሮ​ና​ልና ሞት አይ​ገ​ባ​ውም” አሉ።</verse>
				<verse number="17">ከሀ​ገሩ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ሰዎች ተነ​ሥ​ተው ለሕ​ዝቡ ጉባኤ ሁሉ እን​ዲህ አሏ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">“ሞሬ​ታ​ዊው ሚክ​ያስ በይ​ሁዳ ንጉሥ በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ዘመን ትን​ቢት ይና​ገር ነበር፤ ለይ​ሁ​ዳም ሕዝብ ሁሉ፦ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጽዮን እንደ እርሻ ትታ​ረ​ሳ​ለች፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ምድረ በዳ ትሆ​ና​ለች፤ የቤ​ቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆ​ናል ብሎ ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="19">በውኑ የይ​ሁዳ ንጉሥ ሕዝ​ቅ​ያ​ስና ሕዝቡ ሁሉ ገደ​ሉ​ትን? በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ፈ​ሩ​ምን? ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ አል​ተ​ማ​ለ​ሉ​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ የተ​ና​ገ​ረ​ባ​ቸ​ውን ክፉ ነገር አይ​ተ​ዉ​ምን? እኛም በነ​ፍ​ሳ​ችን ላይ ታላቅ ክፋት እና​ደ​ር​ጋ​ለን።”</verse>
				<verse number="20">ደግ​ሞም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ትን​ቢት የተ​ና​ገረ አንድ ሰው ነበር፤ እር​ሱም የቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ሰው የሸ​ማያ ልጅ ኡርያ ይባል ነበር፤ በዚ​ችም ከተማ፥ በዚ​ችም ምድር ላይ እንደ ኤር​ም​ያስ ቃል ሁሉ ትን​ቢት ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="21">ንጉ​ሡም ኢዮ​አ​ቄም፥ ሠራ​ዊቱ ሁሉ፥ አለ​ቆ​ቹም ሁሉ ቃሉን በሰሙ ጊዜ ንጉሡ ሊገ​ድ​ለው ፈለገ፤ ኡር​ያም ይህን በሰማ ጊዜ ፈርቶ ሸሸ፤ ወደ ግብ​ፅም ገባ።</verse>
				<verse number="22">ንጉ​ሡም ኢዮ​አ​ቄም ሰዎ​ችን ወደ ግብፅ ላከ፤ የአ​ክ​ቦ​ርን ልጅ ኤል​ና​ታ​ንን፥ ሌሎ​ች​ንም ሰዎች ከርሱ ጋራ ወደ ግብፅ ላካ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">ከግ​ብ​ፅም ኡር​ያን አው​ጥ​ተው ወደ ንጉሡ ወደ ኢዮ​አ​ቄም ይዘ​ውት መጡ፤ እር​ሱም በሰ​ይፍ ገደ​ለው፤ ሬሳ​ው​ንም በሕ​ዝብ መቃ​ብር ጣለው።</verse>
				<verse number="24">ነገር ግን በሕ​ዝቡ እጅ እን​ዳ​ይ​ሰ​ጥና እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ሉት የሳ​ፋን ልጅ የአ​ኪ​ቃም እጅ ከኤ​ር​ም​ያስ ጋር ነበ​ረች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="27">
				<verse number="1">በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም መን​ግ​ሥት መጀ​መ​ሪያ ይህ ቃል ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ መጣ።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰን​ሰ​ለ​ትና ቀን​በር ሥራ፤ በአ​ን​ገ​ት​ህም ላይ አድ​ርግ፤</verse>
				<verse number="3">ወደ ይሁዳ ንጉ​ሥም ወደ ሴዴ​ቅ​ያስ፥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በመ​ጡት መል​እ​ክ​ተ​ኞች እጅ ወደ ኤዶ​ም​ያስ ንጉሥ፥ ወደ ሞዓ​ብም ንጉሥ፥ ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ፥ ወደ ጢሮ​ስም ንጉሥ፥ ወደ ሲዶ​ናም ንጉሥ ላክ።”</verse>
				<verse number="4">ለጌ​ቶ​ቻ​ቸው እን​ዲ​ነ​ግሩ እን​ዲህ ብለህ እዘ​ዛ​ቸው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ለጌ​ቶ​ቻ​ችሁ እን​ዲህ በሉ፦</verse>
				<verse number="5">ምድ​ሪ​ቱን፥ በም​ድር ፊት ላይ ያሉ​ትን ሰዎ​ች​ንና እን​ስ​ሶ​ችን በታ​ላቅ ኀይ​ሌና በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችው ክንዴ ፈጥ​ሬ​አ​ለሁ፤ ለዐ​ይ​ኔም መል​ካም ለሆ​ነው እሰ​ጣ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="6">አሁ​ንም ምድ​ርን ሁሉ ለባ​ሪ​ያዬ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቻ​ለሁ፤ ያገ​ለ​ግ​ሉ​ትም ዘንድ የም​ድረ በዳ አራ​ዊ​ትን ደግሞ ሰጥ​ቼ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">የገዛ ራሱም ምድር ጊዜ እስ​ኪ​መጣ ድረስ አሕ​ዛብ ሁሉ ለእ​ር​ሱና ለልጁ ለልጅ ልጁም ይገ​ዛሉ፤ በዚ​ያን ጊዜም ብዙ አሕ​ዛ​ብና ታላ​ላ​ቆች ነገ​ሥ​ታት ለእ​ርሱ ይገ​ዙ​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="8">“ለባ​ቢ​ሎን ንጉ​ሥም ለና​ቡ​ከ​ን​ደ​ነ​ፆር የማ​ይ​ገ​ዛ​ውን፥ ከባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ቀን​በር በታች አን​ገ​ቱን ዝቅ የማ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ሕዝ​ብና መን​ግ​ሥት፥ ያን ሕዝብ በእጁ እስ​ካ​ጠ​ፋው ድረስ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም እቀ​ጣ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="9">እና​ንተ ግን፦ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ አት​ገ​ዙም የሚ​ሉ​አ​ች​ሁን የሐ​ሰት ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንና ምዋ​ር​ተ​ኞ​ቻ​ች​ሁን፥ ሕልም ዐላ​ሚ​ዎ​ቻ​ች​ሁ​ንና ባለ ራእ​ዮ​ቻ​ች​ሁን፥ መተ​ተ​ኞ​ቻ​ች​ሁ​ንም አት​ስሙ፤</verse>
				<verse number="10">ከም​ድ​ራ​ችሁ እን​ዲ​ያ​ር​ቁ​አ​ችሁ፥ እኔም እን​ዳ​ሳ​ድ​ዳ​ችሁ፥ እና​ን​ተም እን​ድ​ት​ጠፉ ሐሰ​ተኛ ትን​ቢ​ትን ይና​ገ​ሩ​ላ​ች​ኋ​ልና።</verse>
				<verse number="11">ነገር ግን ከባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ቀን​በር በታች አን​ገ​ቱን ዝቅ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ው​ንና የሚ​ገ​ዛ​ለ​ትን ሕዝብ በሀ​ገሩ ላይ እተ​ወ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ያር​ሳ​ታል፤ ይቀ​መ​ጥ​ባ​ት​ማል።”</verse>
				<verse number="12">ለይ​ሁዳ ንጉሥ ለሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስም ይህን ቃል ሁሉ ተና​ገ​ርሁ፥ “ከባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ቀን​በር በታች አን​ገ​ታ​ች​ሁን ዝቅ አድ​ርጉ፤ ለእ​ር​ሱና ለሕ​ዝ​ቡም ተገ​ዙ​ላ​ቸው በሕ​ይ​ወ​ትም ኑሩ።</verse>
				<verse number="13">ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ይገዛ ዘንድ እንቢ ስላለ ሕዝብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ፥ አን​ተና ሕዝ​ብህ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ለምን ትሞ​ታ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="14">ሐሰ​ተ​ኛን ትን​ቢት ይና​ገ​ሩ​ላ​ች​ኋ​ልና፦ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ አት​ገ​ዙም የሚ​ሉ​አ​ች​ሁን የነ​ቢ​ያ​ትን ቃል አት​ስሙ።</verse>
				<verse number="15">እኔ አል​ላ​ክ​ኋ​ቸ​ው​ምና፤ ነገር ግን እኔ እን​ዳ​ሳ​ድ​ዳ​ችሁ፥ እና​ን​ተና ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ላ​ችሁ ነቢ​ያ​ትም እን​ድ​ት​ጠፉ በስሜ ሐሰ​ተኛ ትን​ቢ​ትን ይና​ገ​ራሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”</verse>
				<verse number="16">ለካ​ህ​ና​ትም ለዚ​ህም ሕዝብ እን​ዲህ ብዬ ተና​ገ​ርሁ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሐሰ​ተ​ኛ​ውን ትን​ቢት ይና​ገ​ሩ​ላ​ች​ኋ​ልና፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ዕቃ በቅ​ርብ ጊዜ ከባ​ቢ​ሎን ይመ​ለ​ሳል የሚ​ሉ​አ​ች​ሁን የነ​ቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ቃል አት​ስሙ።</verse>
				<verse number="17">እነ​ር​ሱን አት​ስሙ፤ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ተገዙ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ኑሩ፤ ይህ​ችስ ከተማ ስለ ምን ባድማ ትሆ​ና​ለች?</verse>
				<verse number="18">እነ​ርሱ ግን ነቢ​ያት ቢሆኑ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ቢገኝ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና በይ​ሁዳ ንጉሥ ቤት፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የቀ​ሩት ዕቃ​ዎች ወደ ባቢ​ሎን እን​ዳ​ይ​ሄዱ ወደ ሠራ​ዊት ጌታ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይማ​ለሉ።”</verse>
				<verse number="19">ስላ​ል​ወ​ሰ​ዳ​ቸው ዓም​ዶች፥ ስለ ባሕ​ሩም፥ ስለ መቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹም፥ በዚች ከተማ ስለ ቀሩት ዕቃ​ዎች ሁሉ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦</verse>
				<verse number="20">“የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የኢ​ዮ​አ​ቄ​ምን ልጅ ኢኮ​ን​ያ​ን​ንና የይ​ሁ​ዳ​ንና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን አለ​ቆች ሁሉ ማርኮ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ባቢ​ሎን ባፈ​ለ​ሳ​ቸው ጊዜ፥</verse>
				<verse number="21">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና በይ​ሁዳ ንጉሥ ቤት፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ስለ ቀሩት ዕቃ​ዎች የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="22">ወደ ባቢ​ሎን ይወ​ሰ​ዳሉ፤ እስ​ከ​ም​ጐ​በ​ኛ​ቸው ቀን ድረስ በዚያ ይኖ​ራሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በዚ​ያን ጊዜም ትወ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ወደ​ዚ​ህም ስፍራ ትመ​ለ​ሳ​ላ​ችሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="28">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ በዚያ ዓመት፥ በይ​ሁዳ ንጉሥ በሴ​ዴ​ቅ​ያስ መን​ግ​ሥት መጀ​መ​ሪያ፥ በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ሐሰ​ተ​ኛው ነቢይ የገ​ባ​ዖን ሰው የዓ​ዙር ልጅ ሐና​ንያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በካ​ህ​ና​ትና በሕ​ዝብ ሁሉ ፊት እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረኝ፦</verse>
				<verse number="2">“የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አለ፦ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ቀን​በር ሰብ​ሬ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከዚች ስፍራ ወደ ባቢ​ሎን የወ​ሰ​ዳ​ቸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ዕቃ​ዎች ሁሉ በሁ​ለት ዓመት ውስጥ ወደ​ዚ​ህች ስፍራ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="4">ወደ ባቢ​ሎ​ንም የሄ​ዱ​ትን የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የኢ​ዮ​አ​ቄ​ምን ልጅ ኢኮ​ን​ያ​ን​ንና የይ​ሁ​ዳን ምርኮ ሁሉ ወደ​ዚች ስፍራ እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ቀን​በር እሰ​ብ​ራ​ለ​ሁና።”</verse>
				<verse number="5">ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም በካ​ህ​ና​ቱና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በቆ​ሙት ሕዝብ ሁሉ ፊት ለሐ​ሰ​ተ​ኛው ነቢይ ለሐ​ና​ንያ ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="6">ነቢ​ዩም ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ አለ፥ “አሜን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ያድ​ርግ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ዕቃ፥ ምር​ኮ​ው​ንም ሁሉ ከባ​ቢ​ሎን ወደ​ዚህ ስፍራ በመ​መ​ለስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ትን​ቢት ይፈ​ጽም።</verse>
				<verse number="7">ነገር ግን በጆ​ሮ​ህና በሕ​ዝቡ ሁሉ ጆሮ የም​ና​ገ​ረ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤</verse>
				<verse number="8">ከጥ​ንት ከእ​ኔና ከአ​ንተ በፊት የነ​በሩ ነቢ​ያት በብዙ ሀገ​ርና በታ​ላ​ላቅ መን​ግ​ሥ​ታት ላይ ስለ ሰል​ፍና ስለ ክፉ ነገር ስለ ቸነ​ፈ​ርም ትን​ቢት ተና​ገሩ።</verse>
				<verse number="9">ስለ ሰላም ትን​ቢት የተ​ና​ገረ ነቢይ ትን​ቢቱ በደ​ረሰ ጊዜ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ው​ነት የላ​ከው ነቢይ እንደ ሆነ ይታ​ወ​ቃል።”</verse>
				<verse number="10">ሐሰ​ተ​ኛው ነቢይ ሐና​ን​ያም በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት ቀን​በ​ሩን ከነ​ቢዩ ከኤ​ር​ም​ያስ አን​ገት ወስዶ ሰበ​ረው።</verse>
				<verse number="11">ሐና​ን​ያም በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እን​ግ​ዲህ በሁ​ለት ዓመት ውስጥ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ የና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን ቀን​በር ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ አን​ገት እሰ​ብ​ራ​ለሁ” አለ። ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም መን​ገ​ዱን ሄደ።</verse>
				<verse number="12">ሐና​ን​ያም ቀን​በ​ሩን ከነ​ቢዩ ኤር​ም​ያስ አን​ገት ከሰ​በረ በኋላ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="13">“ሂድ፥ ለሐ​ና​ንያ እን​ዲህ ብለህ ንገ​ረው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አንተ የእ​ን​ጨ​ትን ቀን​በር ሰብ​ረ​ሃል፤ እኔ ግን በእ​ርሱ ፋንታ የብ​ረ​ትን ቀን​በር እሠ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ይገ​ዙ​ለት ዘንድ የብ​ረ​ትን ቀን​በር በእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ሁሉ አን​ገት ላይ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይገ​ዙ​ለ​ታል፤ የም​ድረ በዳ አራ​ዊ​ትን ደግሞ ሰጥ​ቼ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="15">ነቢ​ዩም ኤር​ም​ያስ ሐሰ​ተ​ኛ​ውን ሐና​ን​ያን፥ “ሐና​ንያ ሆይ ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ላ​ከ​ህም፤ ነገር ግን ይህ ሕዝብ በሐ​ሰት እን​ዲ​ታ​መን አድ​ር​ገ​ሃል።</verse>
				<verse number="16">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ከገጸ ምድር አስ​ወ​ግ​ድ​ሃ​ለሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐመ​ፅን ተና​ግ​ረ​ሃ​ልና በዚህ ዓመት ትሞ​ታ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="17">ሐሰ​ተ​ኛው ነቢይ ሐና​ን​ያም በዚ​ያው ዓመት በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ሞተ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="29">
				<verse number="1">ነቢዩ ኤር​ም​ያስ ወደ ተረ​ፉት የም​ርኮ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ ወደ ካህ​ና​ቱም፥ ወደ ሐሰ​ተ​ኞች ነቢ​ያ​ቱም፥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ባቢ​ሎን ማርኮ ወዳ​ፈ​ለ​ሰ​ውም ሕዝብ ሁሉ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የላ​ከው የደ​ብ​ዳ​ቤው ቃል ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">ይህም የሆ​ነው ንጉሡ ኢኮ​ን​ያ​ንና እቴ​ጌ​ዪቱ፥ ጃን​ደ​ረ​ቦ​ቹም፥ የይ​ሁ​ዳና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አለ​ቆች ነጻ​ዎ​ችና እሥ​ረ​ኞች፥ ብል​ሃ​ተ​ኞ​ችና ብረት ሠራ​ተ​ኞ​ችም ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከወጡ በኋላ ነው።</verse>
				<verse number="3">ኤር​ም​ያ​ስም የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ ወደ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወደ ባቢ​ሎን በላ​ካ​ቸው በሳ​ፋን ልጅ በኤ​ል​ዓ​ሣና በኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ በገ​ማ​ርያ እጅ ደብ​ዳ​ቤ​ውን እን​ዲህ ሲል ላከው፦</verse>
				<verse number="4">የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ባቢ​ሎን ላስ​ማ​ረ​ክ​ኋ​ቸው ምር​ኮ​ኞች ሁሉ እን​ዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="5">“ቤት ሠር​ታ​ችሁ ተቀ​መጡ፤ አታ​ክ​ል​ትም ተክ​ላ​ችሁ ፍሬ​ዋን ብሉ፤ ተጋቡ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ንም ውለዱ፤</verse>
				<verse number="6">ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም አጋቡ፤ እነ​ር​ሱም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ችን ይው​ለዱ፤ ከዚ​ያም ተባዙ፤ ጥቂ​ቶ​ችም አት​ሁኑ።</verse>
				<verse number="7">በእ​ር​ስዋ ሰላም፥ ሰላም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋ​ልና ወደ እር​ስዋ ላስ​ማ​ረ​ክ​ኋ​ችሁ ሀገር ሰላ​ምን ፈልጉ፥ ስለ እር​ስ​ዋም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸልዩ።”</verse>
				<verse number="8">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ያሉት የሐ​ሰት ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁና ምዋ​ር​ተ​ኞ​ቻ​ችሁ አያ​ታ​ል​ሉ​አ​ችሁ፤ ሕልም አላ​ሚ​ዎች አለ​ም​ን​ላ​ችሁ የሚ​ሉ​አ​ች​ሁን አት​ስሙ፥</verse>
				<verse number="9">በስሜ ሐሰ​ተኛ ትን​ቢ​ትን ይና​ገ​ሩ​ላ​ች​ኋ​ልና፤ እኔም አል​ላ​ክ​ኋ​ቸ​ውም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ሰባው ዓመት በባ​ቢ​ሎን በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ እጐ​በ​ኛ​ች​ኋ​ለሁ፥ ወደ​ዚ​ህም ስፍራ እመ​ል​ሳ​ችሁ ዘንድ መል​ካ​ሚ​ቱን ቃሌን እፈ​ጽ​ም​ላ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">ለእ​ና​ንተ የማ​ስ​ባ​ትን አሳብ እኔ አው​ቃ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ፍጻ​ሜና ተስፋ እሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ የሰ​ላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="12">እና​ን​ተም ትጠ​ሩ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ሄዳ​ች​ሁም ወደ እኔ ትጸ​ል​ያ​ላ​ችሁ፤ እኔም እሰ​ማ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">እና​ንተ ትሹ​ኛ​ላ​ችሁ፤ በፍ​ጹም ልባ​ች​ሁም ከሻ​ች​ሁኝ ታገ​ኙ​ኛ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="14">እገ​ለ​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ምር​ኮ​አ​ች​ሁ​ንም እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ዘንድ እና​ን​ተ​ንም ከበ​ተ​ን​ሁ​በት ስፍራ ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እና​ን​ተ​ንም ለም​ርኮ ወዳ​ፈ​ለ​ስ​ሁ​በት ስፍራ እመ​ል​ሳ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">“እና​ን​ተም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በባ​ቢ​ሎን ነቢ​ያ​ትን አስ​ነ​ሥ​ቶ​ል​ናል ብላ​ች​ኋ​ልና፤</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዳ​ዊት ዙፋን ስለ ተቀ​መጠ ንጉሥ፥ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ስላ​ል​ተ​ማ​ረ​ኩት ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ፥ በዚ​ህች ከተማ ስለ​ሚ​ኖሩ ሕዝብ ሁሉ እን​ዲህ ይላ​ልና፦</verse>
				<verse number="17">የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ሰይ​ፍ​ንና ራብን፥ ቸነ​ፈ​ር​ንም እሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከመ​ጐ​ም​ዘ​ዙም የተ​ነሣ ይበላ ዘንድ እን​ደ​ማ​ይ​ቻል እንደ ክፉ በለስ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="18">በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም አሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ባሳ​ደ​ድ​ሁ​ባ​ቸ​ውም አሕ​ዛብ ሁሉ ዘንድ ለር​ግ​ማ​ንና ለጥ​ፋት፥ ለማ​ፍ​ዋ​ጫም፥ ለመ​ሰ​ደ​ቢ​ያም እን​ዲ​ሆኑ በም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ዘንድ ለመ​በ​ተን አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">ይህም የሆ​ነው ቃሌን ስላ​ል​ሰሙ ነው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በማ​ለዳ ባሪ​ያ​ዎ​ችን ነቢ​ያ​ትን ወደ እነ​ርሱ ሰድ​ጃ​ለ​ሁና፤ እና​ንተ ግን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="20">ስለ​ዚህ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ባቢ​ሎን የሰ​ደ​ድ​ኋ​ችሁ ምር​ኮ​ኞች ሁሉ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።”</verse>
				<verse number="21">የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በስሜ ሐሰ​ተኛ ትን​ቢ​ትን ስለ​ሚ​ና​ገ​ሩ​ላ​ችሁ ስለ ቆልያ ልጅ፥ ስለ አክ​ዓ​ብና ሰለ ማሴው ልጅ ስለ ሴዴ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በዐ​ይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም ፊት ይገ​ድ​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="22">ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ነሣ በባ​ቢ​ሎን ያሉ የይ​ሁዳ ምር​ኮ​ኞች ሁሉ፦ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በእ​ሳት እንደ ጠበ​ሳ​ቸው እንደ ሴዴ​ቅ​ያ​ስና እንደ አክ​ዓብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ር​ግህ የም​ት​ባል ርግ​ማ​ንን ያነ​ሣሉ፤</verse>
				<verse number="23">በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ክፉ አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፥ ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ሚስ​ቶች ጋር አመ​ን​ዝ​ረ​ዋ​ልና፥ ያላ​ዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ው​ንም ቃል በስሜ በሐ​ሰት ተና​ግ​ረ​ዋ​ልና። እኔም አው​ቃ​ለሁ፤ ምስ​ክ​ርም ነኝ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”</verse>
				<verse number="24">ለአ​ሔ​ል​ማ​ዊው ለሸ​ማያ እን​ዲህ በል፦</verse>
				<verse number="25">“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አለው ሕዝብ ሁሉ፥ ወደ ካህ​ኑም ወደ ማሴው ልጅ ወደ ሶፎ​ን​ያስ፥ ወደ ካህ​ና​ቱም ሁሉ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ችን በስሜ እን​ዲህ ስትል ልከ​ሃል፦</verse>
				<verse number="26">ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ረ​ውን ሰው ሁሉ፥ የሚ​ለ​ፈ​ል​ፈ​ው​ንም ሰው ሁሉ በግ​ዞት ታኖ​ረ​ውና በፈ​ሳ​ሽም ታሰ​ጥ​መው ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አለቃ እን​ድ​ት​ሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በካ​ህኑ በዮ​ዳሄ ፋንታ ካህን አድ​ር​ጎ​ሃል።</verse>
				<verse number="27">አሁ​ንስ ትን​ቢት ተና​ጋ​ሪ​ውን የአ​ና​ቶ​ቱን ሰው ኤር​ም​ያ​ስን ስለ ምን አት​ዘ​ል​ፈ​ውም?</verse>
				<verse number="28">እርሱ፦ ምር​ኮው የረ​ዘመ ነውና ቤት ሠር​ታ​ችሁ ተቀ​መጡ፤ አታ​ክ​ል​ትም ተክ​ላ​ችሁ ፍሬ​ዋን ብሉ ብሎ ወደ እኛ ወደ ባቢ​ሎን ልኮ​አ​ልና።”</verse>
				<verse number="29">ካህ​ኑም ሶፎ​ን​ያስ ይህን ደብ​ዳቤ በነ​ቢዩ በኤ​ር​ም​ያስ ጆሮ አነ​በ​በው።</verse>
				<verse number="30">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="31">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አሔ​ል​ማ​ዊው ስለ ሸማያ እን​ዲህ ይላል ብለህ ወደ ምር​ኮ​ኞች ሁሉ ላክ፦ እኔ ሳል​ል​ከው ሸማያ ትን​ቢት ተና​ግ​ሮ​ላ​ች​ኋ​ልና፥ በሐ​ሰ​ትም እን​ድ​ት​ታ​መኑ አድ​ር​ጓ​ች​ኋ​ልና።</verse>
				<verse number="32">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አሔ​ል​ማ​ዊ​ውን ሸማ​ያ​ንና ዘሩን እቀ​ጣ​ለሁ፤ እኔም ለሕ​ዝቤ የማ​ደ​ር​ገ​ውን መል​ካ​ሙን ነገር የሚ​ያይ ሰው በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አይ​ኖ​ር​ላ​ቸ​ውም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐመ​ፃን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="30">
				<verse number="1">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው ቃል ይህ ነው። እን​ዲ​ህም አለው፤</verse>
				<verse number="2">“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የነ​ገ​ር​ሁ​ህን ቃል ሁሉ በመ​ጽ​ሐፍ ጻፍ።</verse>
				<verse number="3">እነሆ! የሕ​ዝ​ቤን የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንና የይ​ሁ​ዳን ምርኮ የም​መ​ል​ስ​በት ዘመን ይመ​ጣ​ልና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ሰጠ​ኋት ምድር እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይገ​ዙ​አ​ታል።”</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ላይ የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “የሚ​ያ​ስ​ፈራ ድምፅ ትሰ​ማ​ላ​ችሁ፤ ፍር​ሀት ነው እንጂ ሰላም አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="6">ጠይቁ፤ ወንድ ይወ​ልድ እንደ ሆነ ተመ​ል​ከቱ፤ ስለ ምን ሰው ሁሉ እንደ ወላድ እጁን በወ​ገቡ ላይ አድ​ርጎ፥ ፊቱም ሁሉ ወደ ጥቍ​ረት ተለ​ውጦ አየሁ?</verse>
				<verse number="7">ወዮ! ያ ቀን ታላቅ ነውና፥ እር​ሱ​ንም የሚ​መ​ስል የለ​ምና፤ ያ የያ​ዕ​ቆብ መከራ ዘመን ነው፤ ነገር ግን ከእ​ርሱ ይድ​ናል።</verse>
				<verse number="8">በዚያ ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ቀን​በ​ርን ከአ​ን​ገ​ትህ እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ እስ​ራ​ት​ህ​ንም እበ​ጥ​ሳ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ለሌላ አት​ገ​ዛም።</verse>
				<verse number="9">ለአ​ም​ላ​ካ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ ለማ​ስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው ለን​ጉ​ሣ​ቸው ለዳ​ዊ​ትም ይገ​ዛሉ።</verse>
				<verse number="10">“እነሆ አን​ተን ከሩቅ፥ ዘር​ህ​ንም ከም​ርኮ ሀገር አድ​ና​ለ​ሁና ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ ሆይ! አት​ፍራ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ተም እስ​ራ​ኤል ሆይ! አት​ደ​ን​ግጥ፤ ያዕ​ቆ​ብም ይመ​ለ​ሳል፤ ያር​ፍ​ማል፤ ተዘ​ል​ሎም ይቀ​መ​ጣል፤ ማንም አያ​ስ​ፈ​ራ​ውም።</verse>
				<verse number="11">አድ​ንህ ዘንድ ከአ​ንተ ጋር ነኝና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ተ​ንም የበ​ተ​ን​ሁ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ፈጽሜ አጠ​ፋ​ለሁ፤ አን​ተን ግን ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋ​ህም፤ በመ​ጠን እቀ​ጣ​ሃ​ለሁ፥” ያለ ቅጣ​ትም ከቶ አል​ተ​ው​ህም።”</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ስብ​ራ​ትህ የማ​ይ​ፈ​ወስ፥ ቍስ​ል​ህም ክፉ ነው።</verse>
				<verse number="13">ትጠ​ገን ዘንድ ክር​ክ​ር​ህን የሚ​ፈ​ር​ድ​ልህ ሰው የለም፤ ቍስ​ል​ህ​ንም የሚ​ፈ​ውስ መድ​ኀ​ኒት የለ​ህም።</verse>
				<verse number="14">ወዳ​ጆ​ችህ ሁሉ ረስ​ተ​ው​ሃል፤ አይ​ፈ​ል​ጉ​ህ​ምም፤ በደ​ልህ ታላቅ ስለ ሆነ፥ ኀጢ​አ​ት​ህም ስለ በዛ፥ በጠ​ላት ማቍ​ሰ​ልና በጨ​ካኝ ቅጣት አቍ​ስ​ዬ​ሃ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="15">ቍስ​ልህ የማ​ይ​ፈ​ወስ ሆኖ​አ​ልና ስለ ስብ​ራ​ትህ ለምን ትጮ​ኻ​ለህ? በደ​ልህ ታላቅ ስለ ሆነ፥ ኀጢ​አ​ት​ህም ስለ በዛ፥ ይህን አድ​ር​ጌ​ብ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">ስለ​ዚህ የሚ​በ​ሉህ ሁሉ ይበ​ላሉ፤ የሚ​ማ​ር​ኩ​ህም ሁላ​ቸው ይማ​ረ​ካሉ፤ የዘ​ረ​ፉ​ህም ይዘ​ረ​ፋሉ፤ የሚ​ማ​ር​ኩ​ህ​ንም ሁሉ ለመ​ማ​ረክ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="17">እኔ ከክፉ ቍስ​ልሽ እፈ​ው​ስ​ሻ​ለሁ፤ ጤና​ሽን እመ​ል​ስ​ል​ሻ​ለሁ፤ ቍስ​ል​ሽ​ንም እፈ​ው​ሳ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ማንም የማ​ይ​ሻት፥ የተ​ጣ​ለች ጽዮን ብለው ጠር​ተ​ው​ሻ​ልና።”</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ የያ​ዕ​ቆ​ብን ድን​ኳን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ለማ​ደ​ሪ​ያ​ውም እራ​ራ​ለሁ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱም በጕ​ብ​ታዋ ላይ ትሠ​ራ​ለች፤ አዳ​ራ​ሹም እንደ ዱሮው የሰው መኖ​ሪያ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="19">ከእ​ር​ሱም ዘንድ የም​ስ​ጋ​ናና የዘ​ፈን ድምፅ ይወ​ጣል፤ እኔም አበ​ዛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አያ​ን​ሱ​ምም።</verse>
				<verse number="20">ልጆ​ቻ​ቸ​ውም እንደ ቀድ​ሞው ይሆ​ናሉ፤ ምስ​ክ​ር​ነ​ታ​ቸ​ውም በፊቴ ጸንቶ ይኖ​ራል፤ የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ቸ​ው​ንም ሁሉ እቀ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="21">አለ​ቃ​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ ውስጥ ይሾ​ማል፤ ገዢ​አ​ቸ​ውም ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ይወ​ጣል፤ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ እኔም እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ እኔ ይመ​ለስ ዘንድ ልብ የሰ​ጠው ማን ነው? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="22">እና​ን​ተም ሕዝብ ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="23">እነሆ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ለመ​ቅ​ሠ​ፍት ወጥ​ቶ​አል፤ የመ​ዓ​ቱ​ንም ጥፋት በኃ​ጥ​ኣን ራስ ላይ አም​ጥ​ቶ​አል፤</verse>
				<verse number="24">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽኑ ቍጣ የል​ቡን አሳብ ሠርቶ እስ​ኪ​ፈ​ጽም ድረስ አይ​መ​ለ​ስም፤ በኋ​ለ​ኛ​ውም ዘመን ታው​ቁ​ታ​ላ​ችሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="31">
				<verse number="1">በዚያ ዘመን ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሁሉ አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ከሰ​ይፍ የተ​ረ​ፈው ሕዝብ በም​ድረ በዳ ሞገስ አገኘ። ሂዱ፦ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም አታ​ጥፉ።”</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሩቅ ተገ​ለ​ጠ​ልኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “በዘ​ለ​ዓ​ለም ፍቅር ወድ​ጄ​ሃ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ በቸ​ር​ነት ሳብ​ሁህ።</verse>
				<verse number="4">የእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ሆይ እንደ ገና እሠ​ራ​ሻ​ለሁ፤ አን​ቺም ትሠ​ሪ​ያ​ለሽ፤ እንደ ገናም ከበ​ሮ​ሽን አን​ሥ​ተሽ ከዘ​ፋ​ኞች ጋር ትወ​ጫ​ለሽ።</verse>
				<verse number="5">እንደ ገናም በሰ​ማ​ርያ ተራ​ሮች ላይ የወ​ይን ተክ​ሎ​ችን ትተ​ክ​ሊ​አ​ለሽ፤ የም​ት​ተ​ክሉ ትከሉ፤ አመ​ስ​ግ​ኑም፤</verse>
				<verse number="6">በኤ​ፍ​ሬም ተራ​ሮች ላይ የሚ​ከ​ራ​ከሩ፦ ተነሡ፤ ወደ ጽዮን ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ውጣ ብለው የሚ​ጠ​ሩ​ባት ቀን ትመ​ጣ​ለ​ችና።”</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “የያ​ዕ​ቆብ ቤት ሆይ! ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም አለ​ቆች ላይ እልል በሉ፤ አውሩ፤ አመ​ስ​ግ​ኑም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕዝ​ቡን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቅሬታ አድ​ኖ​አል በሉ።</verse>
				<verse number="8">እነሆ፥ ከሰ​ሜን ሀገር አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከም​ድ​ርም ዳርቻ ለበ​ዓለ ፋሲካ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ብዙ አሕ​ዛ​ብም ይወ​ለ​ዳሉ፤ ወደ​ዚ​ህም ይመ​ለ​ሳሉ።</verse>
				<verse number="9">እያ​ለ​ቀሱ ሄዱ፤ እኔም በማ​ጽ​ና​ናት አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በወ​ንዝ ዳር በቅን መን​ገድ አስ​ሄ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ር​ሱም አይ​ሰ​ና​ከ​ሉም፤ እኔ ለእ​ስ​ራ​ኤል አባት ነኝና፥ ኤፍ​ሬ​ምም በኵሬ ነውና።”</verse>
				<verse number="10">አሕ​ዛብ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ በሩ​ቅም ላሉ ደሴ​ቶች አው​ሩና፥ “እስ​ራ​ኤ​ልን የበ​ተነ እርሱ ይሰ​በ​ስ​በ​ዋል፤ እረ​ኛም መን​ጋ​ውን እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቅ ይጠ​ብ​ቀ​ዋል በሉ።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዕ​ቆ​ብን ተቤ​ዥ​ቶ​ታል፤ ከበ​ረ​ቱ​በ​ትም እጅ አድ​ኖ​ታል።</verse>
				<verse number="12">ይመ​ጣሉ፤ በጽ​ዮ​ንም ተራራ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ​ነት፥ ወደ እህ​ልና ወደ ወይን ጠጅ፥ ወደ ዘይ​ትም፥ ወደ በጎ​ችና ወደ ላሞች ሀገ​ርም ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም እንደ ረካች ገነት ትሆ​ና​ለች፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አይ​ራ​ቡም።</verse>
				<verse number="13">በዚ​ያን ጊዜም ደና​ግሉ በዘ​ፈን ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ጐበ​ዛ​ዝ​ቱና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹም በአ​ንድ ላይ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ እኔም ልቅ​ሶ​አ​ቸ​ውን ወደ ደስታ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ከኀ​ዘ​ና​ቸ​ውም ደስ አሰ​ኛ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">የካ​ህ​ና​ቱ​ንም የሌ​ዊን ልጆች ሰው​ነት ከፍ ከፍ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ አረ​ካ​ታ​ለሁ፤ ሕዝ​ቤም ከበ​ረ​ከቴ ይጠ​ግ​ባል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="15">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የኀ​ዘን፥ የል​ቅ​ሶና የጩ​ኸት ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆ​ችዋ አለ​ቀ​ሰች፤ የሉ​ምና ስለ ልጆ​ችዋ መጽ​ና​ና​ትን እንቢ አለች።</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ድም​ፅ​ሽን ከል​ቅሶ፥ ዐይ​ኖ​ች​ሽ​ንም ከእ​ንባ ከል​ክዪ፤ ለሥ​ራሽ ዋጋ ይሆ​ና​ልና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከጠ​ላ​ትም ምድር ይመ​ለ​ሳሉ።</verse>
				<verse number="17">ለፍ​ጻ​ሜ​ሽም ተስፋ አለ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ልጆ​ች​ሽም ወደ ሀገ​ራ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ።</verse>
				<verse number="18">“ኤፍ​ሬም ሲጨ​ነቅ መስ​ማ​ትን ሰማሁ፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ ቀጣ​ኸኝ እኔም እን​ዳ​ል​ቀና ወይ​ፈን ተቀ​ጣሁ፤ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኬ ነህና መል​ሰኝ፤ እኔም እመ​ለ​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">ከተ​መ​ለ​ስሁ በኋላ ተጸ​ጸ​ትሁ፤ ከተ​ገ​ሠ​ጽ​ሁም በኋላ ጭኔን ጸፋሁ፤ የብ​ላ​ቴ​ን​ነ​ቴ​ንም ስድብ ተሸ​ክ​ሜ​አ​ለ​ሁና አፈ​ርሁ፥ ተዋ​ረ​ድ​ሁም።</verse>
				<verse number="20">በእ​ው​ነት ኤፍ​ሬም ለእኔ የተ​ወ​ደደ ልጅ ነው፤ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝም ሕፃን ነው፤ በእ​ርሱ ላይ በተ​ና​ገ​ርሁ ቍጥር አስ​በ​ዋ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ አን​ጀቴ ታወ​ከ​ች​ለት፤ ርኅ​ራ​ኄም እራ​ራ​ለ​ታ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="21">“ለራ​ስሽ የመ​ን​ገድ ምል​ክት አድ​ርጊ፥ መን​ገ​ድ​ንም የሚ​መሩ ዐም​ዶ​ችን ትከዪ፤ ልብ​ሽ​ንም ወደ ሄድ​ሽ​በት መን​ገድ ወደ ጥር​ጊ​ያው አቅኚ፤ አንቺ የእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ሆይ! ተመ​ለሺ፤ ወደ እነ​ዚ​ህም ወደ ከተ​ሞ​ችሽ እያ​ለ​ቀ​ስሽ ተመ​ለሺ።</verse>
				<verse number="22">አንቺ ከዳ​ተኛ ልጅ ሆይ! እስከ መቼ ትቅ​በ​ዘ​በ​ዣ​ለሽ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ላይ አዲስ ነገር ፈጥ​ሮ​አ​ልና ሰው ወደ ድኅ​ነት ይመ​ጣል።”</verse>
				<verse number="23">የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ምር​ኮ​አ​ቸ​ውን በመ​ለ​ስሁ ጊዜ በይ​ሁዳ ሀገር በከ​ተ​ሞ​ችዋ፦ የጽ​ድቅ ማደ​ሪያ ሆይ! የቅ​ድ​ስና ተራራ ሆይ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ር​ክህ የሚል ነገ​ርን እንደ ገና ይና​ገ​ራሉ።</verse>
				<verse number="24">በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና በሀ​ገሩ ሁሉ ከገ​በ​ሬ​ዎ​ችና መን​ጋን ይዘው ከሚ​ዞሩ ጋር የሚ​ኖሩ ሰዎች ይገ​ኛሉ።</verse>
				<verse number="25">የተ​ጠ​ማ​ች​ውን ነፍስ ሁሉ አር​ክ​ቻ​ለ​ሁና፥ የተ​ራ​በ​ች​ው​ንም ነፍስ ሁሉ አጥ​ግ​ቤ​አ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="26">ስለ​ዚህ ነቃሁ፤ ተመ​ለ​ከ​ት​ሁም፤ እን​ቅ​ል​ፌም ጣፈ​ጠኝ።</verse>
				<verse number="27">“በእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና በይ​ሁዳ ቤት የሰው ዘርና የእ​ን​ስሳ ዘር የም​ዘ​ራ​በት ዘመን እነሆ ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="28">እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ አፈ​ር​ሳ​ቸ​ውና ክፉ አደ​ር​ግ​ባ​ቸው ዘንድ እንደ ተጋ​ሁ​ባ​ቸው፥ እን​ዲሁ እሠ​ራ​ቸ​ውና እተ​ክ​ላ​ቸው ዘንድ እተ​ጋ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="29">በዚያ ዘመን ሰው ዳግ​መኛ እን​ዲህ አይ​ልም፦ አባ​ቶች ጮርቃ የወ​ይን ፍሬ በሉ፤ የል​ጆ​ችም ጥር​ሶች ጠረሱ፤</verse>
				<verse number="30">ነገር ግን ሰው ሁሉ በገዛ በደሉ ይሞ​ታል፤ ጮር​ቃ​ውን የወ​ይን ፍሬ የሚ​በ​ላም ሁሉ ጥር​ሶቹ ይጠ​ር​ሳሉ።</verse>
				<verse number="31">“እነሆ ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና ከይ​ሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የም​ገ​ባ​በት ወራት ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤</verse>
				<verse number="32">ከግ​ብፅ ሀገር አወ​ጣ​ቸው ዘንድ እጃ​ቸ​ውን በያ​ዝ​ሁ​በት ቀን ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር እንደ ገባ​ሁት ያለ ቃል ኪዳን አይ​ደ​ለም፤ እነ​ርሱ በኪ​ዳኔ አል​ጸ​ኑ​ምና፥ እኔም ቸል አል​ኋ​ቸው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="33">ከእ​ነ​ዚያ ወራት በኋላ ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ጋር የም​ገ​ባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ሕጌን በል​ቡ​ና​ቸው አኖ​ራ​ለሁ፤ በል​ባ​ቸ​ውም እጽ​ፈ​ዋ​ለሁ፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል።</verse>
				<verse number="34">እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ባል​ን​ጀ​ራ​ውን፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወን​ድ​ሙን፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዕወቅ ብሎ አያ​ስ​ተ​ም​ርም፤ ከታ​ናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያው​ቁ​ኛ​ልና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። በደ​ላ​ቸ​ውን እም​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አላ​ስ​ብ​ምና።”</verse>
				<verse number="35">ስሙ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የሚ​ባል፥ ፀሐ​ይን በቀን፥ ጨረ​ቃ​ንና ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም በሌ​ሊት ብር​ሃን አድ​ርጎ የሚ​ሰጥ፥ እን​ዲ​ተ​ም​ሙም የባ​ሕ​ርን ሞገ​ዶች የሚ​ያ​ና​ውጥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="36">“ይህ ሕግ ከፊቴ ቢወ​ገድ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ በዚያ ጊዜ ደግሞ የእ​ስ​ራ​ኤል ዘር በፊቴ ሕዝብ እን​ዳ​ይ​ሆን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይቀ​ራል።”</verse>
				<verse number="37">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰማይ እጅግ ከፍ ቢል፥ የም​ድ​ርም መሠ​ረት ፈጽሞ ዝቅ ቢል በዚያ ጊዜ ስላ​ደ​ረ​ጉት ነገር ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ዘር ሁሉ እን​ቃ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="38">“ከአ​ና​ም​ሄል ግንብ ጀምሮ እስከ ማዕ​ዘኑ በር ድረስ ከተማ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሠ​ራ​በት ዘመን እነሆ ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="39">መጠ​ንዋ ወደ ጋሬብ ኮረ​ብታ በቀ​ጥታ ወደ ፊት ይሄ​ዳል፤ ወደ ጎዓ​ትም ይዞ​ራል።</verse>
				<verse number="40">የአ​ስ​ሬ​ሞ​ትም ሸለቆ ሁሉ እስከ ቄድ​ሮን ወንዝ ድረስ በም​ሥ​ራቅ በኩል እስ​ካ​ለው እስከ ፈረስ በር ማዕ​ዘን ድረስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ይሆ​ናል፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ነ​ቀ​ልም፤ አይ​ፈ​ር​ስ​ምም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="32">
				<verse number="1">በይ​ሁዳ ንጉሥ በሴ​ዴ​ቅ​ያስ በዐ​ሥ​ረ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት፥ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው ቃል ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">በዚያ ጊዜም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሠራ​ዊት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ከብቦ ነበር፤ ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም በይ​ሁዳ ንጉሥ ቤት በነ​በ​ረው በግ​ዞት ቤት አደ​ባ​ባይ ታስሮ ነበር።</verse>
				<verse number="3">የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ብሎ አስ​ጠ​ብ​ቆት ነበ​ርና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ይቺን ከተማ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እር​ሱም ይይ​ዛ​ታል ብለህ ስለ​ምን ትን​ቢት ትና​ገ​ራ​ለህ?</verse>
				<verse number="4">የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ በእ​ው​ነት በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ አልፎ ይሰ​ጣል፤ አፍ ለአ​ፍም ይና​ገ​ረ​ዋል፤ ዐይን ለዐ​ይ​ንም ይተ​ያ​ያሉ እንጂ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን እጅ አያ​መ​ል​ጥም፤</verse>
				<verse number="5">ሴዴ​ቅ​ያ​ስም ወደ ባቢ​ሎን ይገ​ባል፤ እኔም እስ​ክ​ጐ​በ​ኘው ድረስ በዚያ ይኖ​ራል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ጋር ብቷጉ ምንም አይ​ቀ​ና​ች​ሁም።”</verse>
				<verse number="6">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="7">“እነሆ የአ​ጎ​ትህ የሰ​ሎም ልጅ አና​ም​ኤል ወደ አንተ መጥቶ፦ ትገ​ዛው ዘንድ የመ​ቤ​ዠቱ መብት የአ​ንተ ነውና በዓ​ና​ቶት ያለ​ውን እር​ሻ​ዬን ግዛ” ይል​ሃል።</verse>
				<verse number="8">እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል የአ​ጎቴ ልጅ አና​ም​ኤል እኔ ወደ አለ​ሁ​በት ወደ ግዞቱ ቤት አደ​ባ​ባይ መጥቶ፥ “በብ​ን​ያም ሀገር በዓ​ና​ቶት ያለ​ውን እር​ሻ​ዬን ግዛ፤ የመ​ግ​ዛ​ትና የመ​ው​ረስ መብቱ የአ​ንተ ነውና፥ አንተ ታላ​ቃ​ችን ነህና፤ ለአ​ንተ ግዛው” አለኝ። ይህም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ሆነ ዐወ​ቅሁ።</verse>
				<verse number="9">በዐ​ና​ቶ​ትም ያለ​ውን እርሻ ከአ​ጎቴ ልጅ ከአ​ና​ም​ኤል ገዛሁ፤ ዐሥራ ሰባት ሰቅል ብርም መዘ​ን​ሁ​ለት።</verse>
				<verse number="10">የው​ሉ​ንም ወረ​ቀት ጻፍሁ፤ አተ​ም​ሁ​ትም፤ ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም ጠርቼ ብሩን በሚ​ዛን መዘ​ን​ሁ​ለት።</verse>
				<verse number="11">የታ​ተ​መ​ው​ንም የውል ወረ​ቀት ወሰ​ድሁ፤</verse>
				<verse number="12">የአ​ጎ​ቴም ልጅ አና​ም​ኤል፥ የው​ሉ​ንም ወረ​ቀት የፈ​ረሙ ምስ​ክ​ሮች፥ በግ​ዞት ቤት አደ​ባ​ባይ የተ​ቀ​መጡ አይ​ሁ​ድም ሁሉ እያዩ የው​ሉን ወረ​ቀት ለማ​ሴው ልጅ ለኔ​ርያ ልጅ ለባ​ሮክ ሰጠ​ሁት።</verse>
				<verse number="13">በፊ​ታ​ቸ​ውም እን​ዲህ ብዬ ባሮ​ክን አዘ​ዝ​ሁት፦</verse>
				<verse number="14">“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ብዙ ቀን ይጠ​በቅ ዘንድ የታ​ተ​መ​ውን ይህን የውል ወረ​ቀት ወስ​ደህ በሸ​ክላ ዕቃ ውስጥ አኑ​ረው።</verse>
				<verse number="15">የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ሰዎች በዚህ ምድር ቤት​ንና እር​ሻን የወ​ይን ቦታ​ንም እንደ ገና ይገ​ዛሉ።”</verse>
				<verse number="16">ለኔ​ርያ ልጅ ለባ​ሮ​ክም የው​ሉን ወረ​ቀት ከሰ​ጠ​ሁት በኋላ፥ እን​ዲህ ብዬ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለ​ይሁ፦</verse>
				<verse number="17">“ወዮ! አቤቱ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! እነሆ አንተ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በታ​ላቅ ኀይ​ል​ህና በተ​ዘ​ረ​ጋች ክን​ድህ ፈጥ​ረ​ሃል፤ ከአ​ን​ተም የሚ​ሳን ምንም ነገር የለም።</verse>
				<verse number="18">ታላ​ቅና ኀያል አም​ላክ ሆይ! ለብዙ ሺህ ምሕ​ረ​ትን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ የአ​ባ​ቶ​ች​ንም በደል ከእ​ነ​ርሱ በኋላ በል​ጆ​ቻ​ቸው ብብት ትመ​ል​ሳ​ለህ።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ክር ታላቅ በሥ​ራም ብርቱ ነህ፤ ስምህ ታላቅ የሆነ፥ ኀያል፥ ሁሉን ቻይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሁ​ሉም እንደ መን​ገ​ዱና እንደ ሥራው ፍሬ ትሰጥ ዘንድ ዐይ​ኖ​ችህ በሰው ልጆች መን​ገድ ሁሉ ተገ​ል​ጠ​ዋል።</verse>
				<verse number="20">እስከ ዛሬም ድረስ ምል​ክ​ት​ንና ድን​ቅን ነገር በግ​ብፅ ምድር፥ ደግ​ሞም በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በሌ​ሎች ሰዎች መካ​ከል አድ​ር​ገ​ሃል፤ እንደ ዛሬም ለአ​ንተ ስም አድ​ር​ገ​ሃል።</verse>
				<verse number="21">በም​ል​ክ​ትና በድ​ንቅ ነገር፥ በብ​ርቱ እጅና በተ​ዘ​ረ​ጋች ክንድ፥ በታ​ላ​ቅም ግርማ ሕዝ​ብ​ህን እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣህ።</verse>
				<verse number="22">ትሰ​ጣ​ቸ​ውም ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው የማ​ል​ህ​ላ​ቸ​ውን ምድር፥ ወተ​ትና ማርም የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ሰጠ​ሃ​ቸው፤</verse>
				<verse number="23">እነ​ር​ሱም ገብ​ተው ወረ​ሱ​አት፤ ነገር ግን ቃል​ህን አል​ሰ​ሙም፤ በሕ​ግ​ህም አል​ሄ​ዱም፤ ያደ​ር​ጉም ዘንድ ካዘ​ዝ​ሃ​ቸው ሁሉ ምንም አላ​ደ​ረ​ጉም፤ ስለ​ዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመ​ጣ​ህ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">አሕ​ዛ​ብም መጥ​ተው ይህ​ችን ሀገር ያዟት፤ ይህ​ችም ከተማ ከረ​ኃ​ቡና ከጦሩ የተ​ነሣ በወ​ጓት በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሰዎች እጅ ወደ​ቀች፤ እንደ ተና​ገ​ር​ኸ​ውም ሆነ።</verse>
				<verse number="25">አን​ተም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! እር​ሻ​ውን በብር ግዛ፤ ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም ጥራ አል​ኸኝ፤ እኔም ውሉን ጽፌ አተ​ምሁ፤ ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም አቆ​ምሁ፤ ከተ​ማ​ዪቱ ግን ለከ​ለ​ዳ​ው​ያን እጅ ተሰ​ጥ​ታ​ለች።”</verse>
				<verse number="26">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="27">“እነሆ እኔ የሥጋ ለባሽ ሁሉ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ በውኑ ከእኔ የሚ​ሰ​ወር ነገር አለን?</verse>
				<verse number="28">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ይችን ከተማ ለከ​ለ​ዳ​ው​ያን እጅና ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እር​ሱም ይይ​ዛ​ታል።</verse>
				<verse number="29">ይችን ከተማ የሚ​ወጉ ከለ​ዳ​ው​ያን ይመ​ጣሉ፤ ከተ​ማ​ዋ​ንም በእ​ሳት ያነ​ድ​ዱ​አ​ታል፤ ያስ​ቈ​ጡ​ኝም ዘንድ በሰ​ገ​ነ​ታ​ቸው ላይ ለበ​ዓል ያጠ​ኑ​ባ​ቸ​ውን፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት የመ​ጠ​ጥን ቍር​ባን ያፈ​ሰ​ሱ​ባ​ቸ​ውን ቤቶች ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="30">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና የይ​ሁዳ ልጆች ከታ​ና​ሽ​ነ​ታ​ቸው ጀምሮ በፊቴ ክፉ ነገ​ርን ብቻ አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እኔን በእ​ጃ​ቸው ሥራ ከማ​ስ​ቈ​ጣት በቀር ሌላ ሥራ አላ​ደ​ረ​ጉ​ምና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="31">ከፊቴ አስ​ወ​ግ​ዳት ዘንድ ይህች ከተማ ከሠ​ሩ​አት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በቁ​ጣ​ዬና በመ​ዓቴ ውስጥ ናትና፤</verse>
				<verse number="32">ይህም እኔን ያስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ፥ እነ​ር​ሱና ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸው፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፥ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፥ የይ​ሁ​ዳም ሰዎች፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ኖሩ ስለ አደ​ረ​ጉት ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና ስለ ይሁዳ ልጆች ክፋት ሁሉ ነው።</verse>
				<verse number="33">ፊታ​ቸ​ው​ንም ሳይ​ሆን ጀር​ባ​ቸ​ውን ወደ እኔ መለሱ፤ እኔም በማ​ለዳ ተነ​ሥቼ ሳስ​ተ​ም​ራ​ቸው ተግ​ሣ​ጽን ይቀ​በሉ ዘንድ አል​ሰ​ሙም።</verse>
				<verse number="34">ያረ​ክ​ሱ​ትም ዘንድ ስሜ በተ​ጠ​ራ​በት ቤት ውስጥ ርኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውን አኖሩ።</verse>
				<verse number="35">ይሁ​ዳን ወደ ኀጢ​አት እን​ዲ​ያ​ገ​ቡት፥ ይህን ርኵ​ሰት ያደ​ርጉ ዘንድ፥ እኔ ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ት​ንና በልቤ ያላ​ሰ​ብ​ሁ​ትን ነገር፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለሞ​ሎክ በእ​ሳት ያሳ​ልፉ ዘንድ በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ዎች ለበ​ዓል ሠሩ።”</verse>
				<verse number="36">አሁን እን​ግ​ዲህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ ስለ እር​ስዋ፥ “በሰ​ይ​ፍና በራብ በቸ​ነ​ፈ​ርም ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ ትሰ​ጣ​ለች ስለ​ም​ት​ላት ከተማ እን​ዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="37">እነሆ በቍ​ጣ​ዬና በመ​ዓቴ፥ በታ​ላ​ቅም መቅ​ሠ​ፍቴ እነ​ር​ሱን ካሳ​ደ​ድ​ሁ​ባት ሀገር ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ​ዚ​ህም ስፍራ እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ተዘ​ል​ለ​ውም እን​ዲ​ኖሩ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="38">እነ​ር​ሱም ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="39">ለእ​ነ​ር​ሱም፥ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ለል​ጆ​ቻ​ቸው መል​ካም ይሆ​ን​ላ​ቸው ዘንድ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዲ​ፈ​ሩኝ ሌላ መን​ገ​ድና ሌላ ልብ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="40">ከእ​ነ​ር​ሱም እን​ዳ​ል​መ​ለስ፥ ከእ​ነ​ርሱ ጋር የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምን ቃል ኪዳን እገ​ባ​ለሁ፤ ከእ​ኔም ዘንድ ፈቀቅ እን​ዳ​ይሉ መፈ​ራ​ቴን በል​ባ​ቸው ውስጥ አኖ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="41">ለእ​ነ​ር​ሱም መል​ካ​ምን በማ​ድ​ረግ ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ው​ነ​ትም በፍ​ጹም ልቤና በፍ​ጹም ነፍሴ በዚ​ህች ምድር እተ​ክ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="42">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ሁሉ በዚህ ሕዝብ ላይ እን​ዳ​መ​ጣሁ፥ እን​ዲሁ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ላ​ቸ​ውን በጎ​ነት ሁሉ አመ​ጣ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="43">እና​ን​ተም፦ ያለ ሰውና ያለ እን​ስሳ ያለች ባድማ ናት፤ ለከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም እጅ ተሰ​ጥ​ታ​ለች በም​ት​ሉ​አት ምድር እር​ሻን እንደ ገና ይገ​ዛሉ።</verse>
				<verse number="44">ምር​ኮ​ኞ​ቻ​ቸ​ው​ንም እመ​ል​ሳ​ለ​ሁና በብ​ን​ያም ሀገር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዙሪያ ባሉ ስፍ​ራ​ዎች፥ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች በደ​ጋ​ውም ባሉ ከተ​ሞች፥ በቆ​ላ​ውም ባሉ ከተ​ሞች፥ በደ​ቡ​ብም ባሉ ከተ​ሞች፥ ሰዎች እር​ሻ​ውን በብር ይገ​ዛሉ፤ በው​ሉም ወረ​ቀት ፈር​መው ያት​ማሉ፤ ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም ያቆ​ማሉ፤” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="33">
				<verse number="1">ኤር​ም​ያስ ገና በግ​ዞት ቤት አደ​ባ​ባይ ታስሮ ሳለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሁለ​ተኛ ጊዜ እን​ዲህ ሲል መጣ​ለት፦</verse>
				<verse number="2">“ስሙ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆነ፥ ምድ​ርን የፈ​ጠ​ራት፥ የሠ​ራ​ትና ያጸ​ናት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="3">ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመ​ል​ስ​ል​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም የማ​ታ​ው​ቀ​ውን ታላ​ቅና ኀይ​ለኛ ነገ​ርን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለም​ሽ​ግና ለመ​ከ​ላ​ከያ ስለ ፈረ​ሱት ስለ​ዚ​ህች ከተማ ቤቶች፥ ስለ ይሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት ቤቶች እን​ዲህ ይላ​ልና፦</verse>
				<verse number="5">የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ተዋ​ጊ​ዎች ለመ​ዋ​ጋት መጥ​ተ​ዋል፤ ነገር ግን በቍ​ጣ​ዬና በመ​ዓቴ በገ​ደ​ል​ኋ​ቸው ሰዎች ሬሳ​ዎች እሞ​ላ​ታ​ለሁ፥ ስለ ክፋ​ታ​ቸው ሁሉ ፊቴን ከዚ​ህች ከተማ እመ​ል​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="6">እነሆ ፈው​ስ​ንና መድ​ኀ​ኒ​ትን እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ እፈ​ው​ሳ​ታ​ለ​ሁም፤ የሰ​ላ​ም​ንና የእ​ው​ነ​ት​ንም መን​ገድ እገ​ል​ጥ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">የይ​ሁ​ዳን ምር​ኮ​ኞች፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ምር​ኮ​ኞች እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ቀድ​ሞም እንደ ነበሩ አድ​ርጌ እሠ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">እኔ​ንም ከበ​ደ​ሉ​በት ኀጢ​አት ሁሉ አነ​ጻ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔም የበ​ደ​ሉ​ኝ​ንና ያመ​ፁ​ብ​ኝን ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ይቅር እላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">ይህ​ችም ከተማ እኔ የም​ሠ​ራ​ላ​ቸ​ውን በጎ​ነት ሁሉ በሚ​ሰሙ፥ እኔም ስላ​መ​ጣ​ሁ​ላ​ቸው በጎ​ነ​ትና ሰላም ሁሉ በሚ​ፈ​ሩና በሚ​ደ​ነ​ግጡ አሕ​ዛብ ሁሉ ፊት ለደ​ስታ፥ ለክ​ብ​ርና ለገ​ና​ን​ነት ትሆ​ና​ለች።”</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እና​ንተ፦ ያለ ሰውና ያለ እን​ስሳ ያለች ባድማ ናት በም​ት​ሉ​አት በዚች ስፍራ፥ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው በሌለ፥ ያለ ሰውና ያለ እን​ስሳ ባድማ በሆኑ በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ፥</verse>
				<verse number="11">የሐ​ሤት ድም​ፅና የደ​ስታ ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽራ ድም​ፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ የሚሉ ሰዎች ድምፅ፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የም​ስ​ጋ​ናን መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​መጡ ሰዎች ድምፅ እንደ ገና ይሰ​ማል። የዚ​ያ​ችን ምድር ምር​ኮ​ኞች ቀድሞ እንደ ነበረ አድ​ርጌ እመ​ል​ሳ​ለ​ሁና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="12">የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ባድማ ሆኖ፥ ያለ ሰውና ያለ እን​ስሳ ባለው በዚህ ስፍራ በከ​ተ​ሞ​ችም ሁሉ መን​ጎ​ቻ​ቸ​ውን የሚ​ያ​ሳ​ር​ፉ​በት የእ​ረ​ኞች መኖ​ሪያ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="13">በደ​ጋው ላይ ባሉ ከተ​ሞች፥ በቆ​ላ​ውም ባሉ ከተ​ሞች፥ በደ​ቡ​ብም ባሉ ከተ​ሞች፥ በብ​ን​ያ​ምም ሀገር፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዙሪያ ባሉ ስፍ​ራ​ዎች፥ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች በጎቹ በተ​ቈ​ጣ​ጣ​ሪ​ያ​ቸው እጅ እንደ ገና ያል​ፋሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”</verse>
				<verse number="14">“እነሆ ስለ እስ​ራ​ኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የሰ​ጠ​ሁ​ትን መል​ካም የተ​ስፋ ቃል የም​ፈ​ጽ​ም​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="15">በዚ​ያም ዘመን በዚ​ያም ጊዜ ለዳ​ዊት የጽ​ድ​ቅን ቍጥ​ቋጥ አበ​ቅ​ል​ለ​ታ​ለሁ፤ እር​ሱም ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን በም​ድር ያደ​ር​ጋል።</verse>
				<verse number="16">በዚ​ያም ዘመን ይሁዳ ይድ​ናል፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተዘ​ልላ ትቀ​መ​ጣ​ለች፤ የም​ት​ጠ​ራ​በ​ትም ስም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቃ​ችን ተብሎ ነው።</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ዙፋን ላይ የሚ​ቀ​መጥ ሰው ከዳ​ዊት ዘንድ አይ​ታ​ጣም።</verse>
				<verse number="18">የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ርብ፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን የሚ​ያ​ቃ​ጥል፥ ሁል​ጊ​ዜም የሚ​ሠዋ ሰው ከሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ዘንድ በእኔ ፊት አይ​ታ​ጣም።”</verse>
				<verse number="19">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="20">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ቀንና ሌሊት በወ​ራ​ታ​ቸው እን​ዳ​ይ​ሆኑ የቀን ቃል ኪዳ​ኔ​ንና የሌ​ሊት ቃል ኪዳ​ኔን ማፍ​ረስ ብት​ችሉ፥</verse>
				<verse number="21">በዙ​ፋኑ ላይ የሚ​ነ​ግሥ ልጅ እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ለት ከባ​ሪ​ያዬ ከዳ​ዊት ጋር፥ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ከሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ደግሞ ይፈ​ር​ሳል።</verse>
				<verse number="22">የሰ​ማ​ይን ሠራ​ዊት መቍ​ጠር፥ የባ​ሕ​ር​ንም አሸዋ መስ​ፈር እን​ደ​ማ​ይ​ቻል፥ እን​ዲሁ የባ​ሪ​ያ​ዬን የዳ​ዊ​ትን ዘርና የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​ኝን ሌዋ​ው​ያ​ንን አበ​ዛ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="23">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="24">“ይህ ሕዝብ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ረ​ጣ​ቸ​ውን ሁለ​ቱን ወገን ጥሎ​አ​ቸ​ዋል፥ እን​ዲሁ በፊ​ታ​ቸው ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ሕዝብ እን​ዳ​ይ​ሆን ሕዝ​ቤን አቃ​ል​ለ​ዋል ያለ​ውን ነገር አት​መ​ለ​ከ​ት​ምን?</verse>
				<verse number="25">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የቀ​ንና የሌ​ሊት ቃል ኪዳ​ኔን የሰ​ማ​ይ​ንና የም​ድ​ር​ንም ሥር​ዐት ያላ​ጸ​ናሁ እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="26">እኔም ደግሞ በአ​ብ​ር​ሃ​ምና በይ​ስ​ሐቅ በያ​ዕ​ቆ​ብም ዘር ላይ ገዢ​ዎች ይሆኑ ዘንድ ከዘሩ እን​ዳ​ላ​ስ​ነሣ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንና የባ​ሪ​ያ​ዬን የዳ​ዊ​ትን ዘር እጥ​ላ​ለሁ፤ ምር​ኮ​አ​ቸ​ውን እመ​ል​ሳ​ለ​ሁና፥ እም​ራ​ቸ​ው​ማ​ለ​ሁና።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="34">
				<verse number="1">የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርና ሠራ​ዊቱ ሁሉ፥ ከእ​ጁም ግዛት በታች ያሉ የም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ፥ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንና የይ​ሁ​ዳን ከተ​ሞች ሁሉ ይወጉ በነ​በረ ጊዜ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦</verse>
				<verse number="2">“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሂድ፤ ለይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ለሴ​ዴ​ቅ​ያስ ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በለው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ይች ከተማ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ ተላ​ልፋ ትሰ​ጣ​ለች፤ ይይ​ዛ​ታል፤ በእ​ሳ​ትም ያቃ​ጥ​ላ​ታል።</verse>
				<verse number="3">አን​ተም በር​ግጥ ትያ​ዛ​ለህ፤ በእ​ጁም አል​ፈህ ትሰ​ጣ​ለህ እንጂ ከእጁ አታ​መ​ል​ጥም፤ ዐይ​ን​ህም የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ዐይን ታያ​ለች፤ እር​ሱም ከአ​ንተ ጋር አፍ ለአፍ ይና​ገ​ራል፤ ወደ ባቢ​ሎ​ንም ትገ​ባ​ለህ።</verse>
				<verse number="4">“ነገር ግን የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አንተ እን​ዲህ ይላል፦ በሰ​ይፍ አት​ሞ​ትም፤</verse>
				<verse number="5">ነገር ግን በሰ​ላም ትሞ​ታ​ለህ፥ ከአ​ንተ በፊት እንደ ነበሩ እንደ ዱሮ ነገ​ሥ​ታት አባ​ቶ​ችህ እሳት ይቃ​ጠ​ል​ላ​ቸው እንደ ነበር እን​ዲሁ ያቃ​ጥ​ሉ​ል​ሃ​ልና፦ ወየው! ጌታ ሆይ! እያሉ ያለ​ቅ​ሱ​ል​ሃል፤ እኔ ቃልን ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="6">ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም ይህን ቃል ሁሉ ለይ​ሁዳ ንጉሥ ለሴ​ዴ​ቅ​ያስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="7">የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ሠራ​ዊት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንና የቀ​ሩ​ትን የይ​ሁ​ዳን ከተ​ሞች ሁሉ፥ ለኪ​ሶ​ንና አዚ​ቃ​ንም ይወጋ ነበር። እነ​ዚህ የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞች በይ​ሁዳ ከተ​ሞች መካ​ከል ቀር​ተው ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="8">ስለ አር​ነ​ታ​ቸው ዐዋጅ እን​ዲ​ነ​ግር ንጉሡ ሴዴ​ቅ​ያስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከነ​በሩ ሕዝብ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን ከአ​ደ​ረገ በኋላ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው ቃል ይህ ነው።</verse>
				<verse number="9">ሰው ሁሉ ዕብ​ራዊ የሆነ ወንድ ባሪ​ያ​ው​ንና ዕብ​ራ​ዊት የሆ​ነች ሴት ባሪ​ያ​ውን አር​ነት እን​ዲ​ያ​ወጣ፥ አይ​ሁ​ዳዊ ወን​ድ​ሙ​ንም ማንም እን​ዳ​ይ​ገዛ፤</verse>
				<verse number="10">ሰው ሁሉ ወንድ ባሪ​ያ​ው​ንና ሴት ባሪ​ያ​ውን አር​ነት እን​ዲ​ያ​ወጣ፥ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ማንም እን​ዳ​ይ​ገ​ዛ​ቸው ወደ ቃል ኪዳኑ የገቡ አለ​ቆች ሁሉና ሕዝቡ ሁሉ ሰሙ፤ አር​ነ​ትም አወ​ጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ነገር ግን ከዚያ በኋላ ተመ​ል​ሰው አር​ነት ያወ​ጡ​አ​ቸ​ውን ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውን አስ​መ​ለሱ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎ​ችም አድ​ር​ገው ገዙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">ስለ​ዚህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="13">“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ከባ​ር​ነት ቤት ከግ​ብፅ ሀገር በአ​ወ​ጣ​ኋ​ቸው ቀን ከእ​ነ​ርሱ ጋር እን​ዲህ ስል ቃል ኪዳን አደ​ረ​ግሁ፦</verse>
				<verse number="14">ስድ​ስት ዓመት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥ የተ​ሸ​ጠ​ላ​ች​ሁን፥ ስድ​ስ​ትም ዓመት የተ​ገ​ዛ​ላ​ች​ሁን ዕብ​ራዊ ወን​ድ​ማ​ች​ሁን እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ አር​ነት ታወ​ጡ​ታ​ላ​ችሁ፤ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ግን አል​ሰ​ሙ​ኝም፤ ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም አላ​ዘ​ነ​በ​ሉም።</verse>
				<verse number="15">እና​ን​ተም ዛሬ ተመ​ል​ሳ​ችሁ ሰው ሁሉ ባል​ን​ጀ​ራ​ውን አር​ነት ለማ​ው​ጣት ዓመተ ኅድ​ገ​ትን በማ​ድ​ረግ በዐ​ይኔ ፊት ቅን የሆ​ነ​ውን ነገር አድ​ር​ጋ​ችሁ ነበር፤ ስሜም በሚ​ጠ​ራ​በት ቤት ውስጥ በፊቴ ቃል ኪዳን አድ​ር​ጋ​ችሁ ነበር።</verse>
				<verse number="16">ነገር ግን ተመ​ል​ሳ​ችሁ ስሜን አስ​ነ​ቀ​ፋ​ችሁ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም በፈ​ቃ​ዳ​ቸው እን​ዲ​ሄዱ አር​ነት ያወ​ጣ​ች​ኋ​ቸ​ውን ወን​ድና ሴት ባሪ​ያ​ዎ​ቻ​ች​ሁን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎች እን​ዲ​ሆ​ኑ​ላ​ችሁ መለ​ሳ​ች​ኋ​ቸው።”</verse>
				<verse number="17">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰው ሁሉ ለወ​ን​ድ​ሙና ለባ​ል​ን​ጀ​ራው ዓመተ ኅድ​ገ​ትን ለማ​ድ​ረግ እኔን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ እነሆ እኔ ለሰ​ይ​ፍና ለቸ​ነ​ፈር፥ ለራ​ብም ዓመተ ኅድ​ገ​ትን አው​ጅ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በም​ድ​ርም መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ መካ​ከል እበ​ት​ና​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="18">ቃል ኪዳ​ኔን የተ​ላ​ለ​ፉ​ትን ሰዎች፥ በፊቴ ያደ​ረ​ጉ​ትን ቃል ኪዳን ያል​ፈ​ጸ​ሙ​ትን፥ እን​ቦ​ሳ​ው​ንም ቈር​ጠው በቍ​ራጩ መካ​ከል ያለ​ፉ​ትን አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">የይ​ሁ​ዳን አለ​ቆ​ችና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን አለ​ቆች፥ ጃን​ደ​ረ​ቦ​ች​ንና ካህ​ና​ት​ንም፥ በእ​ን​ቦ​ሳም ቍራጭ መካ​ከል ያለ​ፉ​ትን የሀ​ገ​ሩን ሕዝብ ሁሉ፥</verse>
				<verse number="20">ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ፥ ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም ለሚ​ሹ​አት እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ሬሳ​ቸ​ውም ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት መብል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="21">የይ​ሁ​ዳ​ንም ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስ​ንና መኳ​ን​ን​ቱን ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም ለሚ​ሹ​አት እጅ ከእ​ና​ን​ተም ለተ​መ​ለ​ሱት ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሠራ​ዊት እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="22">እነሆ እኔ አዝ​ዛ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ወደ​ዚ​ህ​ችም ሀገር እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ይወ​ጋሉ፤ ይይ​ዙ​አ​ት​ማል፤ በእ​ሳ​ትም ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ታል፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም ከተ​ሞች ሰው የሌ​ለ​በት ባድማ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="35">
				<verse number="1">በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም ዘመን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፤ እን​ዲህ ሲል፦</verse>
				<verse number="2">“ወደ ሬካ​ባ​ው​ያን ቤት ሄደህ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አም​ጥ​ተህ ከክ​ፍ​ሎቹ ወደ አን​ዲቱ አግ​ባ​ቸው፤ የወ​ይን ጠጅም አጠ​ጣ​ቸው።”</verse>
				<verse number="3">የከ​ባ​ስ​ንን ልጅ የኤ​ር​ም​ያ​ስን ልጅ ያእ​ዛ​ን​ያ​ንና ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንም፥ ልጆ​ቹ​ንም ሁሉ የሬ​ካ​ባ​ው​ያ​ንን ቤተ ሰብእ ሁሉ ወሰ​ድ​ኋ​ቸው፤</verse>
				<verse number="4">ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በበ​ረ​ኛው በሰ​ሎም ልጅ በማ​ሴው ጓዳ በላይ ባለው በአ​ለ​ቆቹ ጓዳ አጠ​ገብ ወደ አለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ ጎዶ​ልያ ልጅ ወደ ሐና​ንያ ልጆች ጓዳ አገ​ባ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">በሬ​ካ​ባ​ው​ያ​ንም ልጆች ፊት የወ​ይን ጠጅ የሞ​ላ​ባ​ቸ​ውን ማድ​ጋ​ዎ​ች​ንና ጽዋ​ዎ​ችን አኑሬ፥ “የወ​ይ​ኑን ጠጅ ጠጡ” አል​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">እነ​ርሱ ግን እን​ዲህ አሉ፥ “የወ​ይ​ኑን ጠጅ አን​ጠ​ጣም፤ አባ​ታ​ችን የሬ​ካብ ልጅ ኢዮ​ና​ዳብ እና​ን​ተና ልጆ​ቻ​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የወ​ይን ጠጅ አት​ጠጡ ብሎ አዝ​ዞ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="7">በም​ት​ኖ​ሩ​ባት ምድር ላይ ብዙ ዘመን እን​ድ​ት​ኖሩ፥ በዕ​ድ​ሜ​አ​ችሁ ሙሉ በድ​ን​ኳን ውስጥ ተቀ​መጡ እንጂ ቤትን አት​ሥሩ፤ ዘር​ንም አት​ዝሩ፤ ወይ​ንም አት​ት​ከሉ፤ አን​ዳ​ችም አይ​ሁ​ን​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="8">እኛም የአ​ባ​ታ​ች​ንን የሬ​ካብ ልጅ የኢ​ዮ​ና​ዳ​ብን ቃል ባዘ​ዘን ነገር ሁሉ ታዝ​ዘ​ናል፤ እኛም ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ንም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ንም ዕድ​ሜ​አ​ች​ንን ሙሉ የወ​ይን ጠጅ አል​ጠ​ጣ​ንም፤</verse>
				<verse number="9">የም​ን​ቀ​መ​ጥ​በ​ት​ንም ቤት አል​ሠ​ራ​ንም፤ የወ​ይን ቦታና እርሻ፥ ዘርም የለ​ንም።</verse>
				<verse number="10">በድ​ን​ኳን ውስጥ ተቀ​ም​ጠ​ናል፤ አባ​ታ​ች​ንም ኢዮ​ና​ዳብ ያዘ​ዘ​ንን ሁሉ ሰም​ተ​ናል፤ አድ​ር​ገ​ና​ልም።</verse>
				<verse number="11">ነገር ግን የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በዚች ምድር ላይ በዘ​መተ ጊዜ፦ ኑ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሠራ​ዊ​ትና ከሶ​ርያ ሠራ​ዊት ፊት የተ​ነሣ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ሂድ፤ አልን፤ እን​ዲ​ሁም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መ​ጥን።”</verse>
				<verse number="12">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="13">“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሂድና ለይ​ሁዳ ሰዎ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለሚ​ቀ​መጡ ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ቃሌን ትሰሙ ዘንድ ተግ​ሣ​ጽን አት​ቀ​በ​ሉ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="14">የሬ​ካብ ልጅ ኢዮ​ና​ዳብ ልጆቹ የወ​ይን ጠጅ እን​ዳ​ይ​ጠጡ ያዘ​ዛ​ቸው ቃል ተፈ​ጸመ፤ ለአ​ባ​ታ​ቸ​ውም ትእ​ዛዝ ታዝ​ዘ​ዋ​ልና እስከ ዛሬ ድረስ ወይን አይ​ጠ​ጡም፤ እኔም በማ​ለዳ ስለ እና​ንተ ተና​ገ​ርሁ፤ ሆኖም አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም።</verse>
				<verse number="15">ደግ​ሞም፦ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ ሥራ​ች​ሁ​ንም አሳ​ምሩ፤ ታገ​ለ​ግ​ሉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አት​ከ​ተሉ፤ ለእ​ና​ን​ተና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በሰ​ጠ​ሁት ምድር ትቀ​መ​ጣ​ላ​ችሁ እያ​ልሁ ባሪ​ያ​ዎ​ችን ነቢ​ያ​ትን ሁሉ ልኬ​ባ​ችሁ ነበር፤ እና​ንተ ግን ጆሮ​አ​ች​ሁን አላ​ዘ​ነ​በ​ላ​ች​ሁም፤ እኔ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም።</verse>
				<verse number="16">የሬ​ካብ ልጅ የኢ​ዮ​ና​ዳብ ልጆች አባ​ታ​ቸው ያዘ​ዛ​ቸ​ውን ትእ​ዛዝ ፈጽ​መ​ዋል፤ ይህ ሕዝብ ግን አል​ሰ​ማ​ኝም፤</verse>
				<verse number="17">ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በተ​ና​ገ​ር​ኋ​ቸው ጊዜ አል​ሰ​ሙ​ምና፥ በጠ​ራ​ኋ​ቸ​ውም ጊዜ አል​መ​ለ​ሱ​ል​ኝ​ምና የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ባ​ቸ​ውን ክፉ ነገር ሁሉ በይ​ሁዳ ላይ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በሚ​ቀ​መጡ ሁሉ ላይ አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="18">ኤር​ም​ያ​ስም ሬካ​ባ​ው​ያ​ንን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ባ​ታ​ች​ሁን የኢ​ዮ​ና​ዳ​ብን ትእ​ዛዝ ሰም​ታ​ች​ኋ​ልና፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ሁሉ ጠብ​ቃ​ች​ኋ​ልና፥ ያዘ​ዛ​ች​ሁ​ንም ሁሉ አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና፥</verse>
				<verse number="19">ስለ​ዚህ በፊቴ የሚ​ቆም ሰው ከሬ​ካብ ልጅ ከኢ​ዮ​ና​ዳብ ወገን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ታ​ጣም፥” ይላል የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="36">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት ይህ ቃል ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ።</verse>
				<verse number="2">“አንድ የመ​ጽ​ሐፍ ክር​ታስ ውሰድ፥ ለአ​ን​ተም ከተ​ና​ገ​ር​ሁ​በት ቀን ከይ​ሁዳ ንጉሥ ከኢ​ዮ​ስ​ያስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ላይ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ህን ቃል ሁሉ ጻፍ​በት።</verse>
				<verse number="3">ምና​ል​ባት የይ​ሁዳ ቤት ከክፉ መን​ገ​ዳ​ቸው ይመ​ለሱ ዘንድ፥ እኔም በደ​ላ​ቸ​ው​ንና ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይቅር እል ዘንድ፥ እኔ አደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ ያል​ሁ​ት​ንና ያሰ​ብ​ሁ​ትን ክፉ ነገር ሁሉ ይሰሙ ይሆ​ናል።”</verse>
				<verse number="4">ኤር​ም​ያ​ስም የኔ​ር​ዩን ልጅ ባሮ​ክን ጠራ፤ ባሮ​ክም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ርሱ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ሁሉ ከኤ​ር​ም​ያስ አፍ በመ​ጽ​ሐፉ ክር​ታስ ጻፈ።</verse>
				<verse number="5">ኤር​ም​ያ​ስም ባሮ​ክን እን​ዲህ ሲል አዘ​ዘው፥ “እኔ እስ​ረኛ ነኝ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትም እገባ ዘንድ አል​ች​ልም።</verse>
				<verse number="6">አንተ ግን ገብ​ተህ ከአፌ የጻ​ፍ​ኸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በጾም ቀን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሕ​ዝቡ ጆሮ በክ​ር​ታሱ አን​ብብ፤ ደግ​ሞም ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው በሚ​ወጡ በይ​ሁዳ ሰዎች ሁሉ ጆሮ አን​ብ​በው።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ሕዝብ ላይ የተ​ና​ገ​ረው ቍጣ​ውና መዓቱ ታላቅ ነውና ምና​ል​ባት ልመ​ና​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትደ​ርስ ይሆ​ናል፤ ሁሉም ከክፉ መን​ገ​ዳ​ቸው ይመ​ለሱ ይሆ​ናል።”</verse>
				<verse number="8">የኔ​ር​ዩም ልጅ ባሮክ ነቢዩ ኤር​ም​ያስ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረገ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በመ​ጽ​ሐፉ አነ​በበ።</verse>
				<verse number="9">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ ኢዮ​አ​ቄም በነ​ገሠ በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ዓመት በዘ​ጠ​ነ​ኛው ወር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ቀ​መጡ ሕዝብ ሁሉ፥ ከይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የመጡ ሕዝብ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለመ​ጾም ዐዋጅ ነገሩ።</verse>
				<verse number="10">ባሮ​ክም የኤ​ር​ም​ያ​ስን ቃል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በላ​ይ​ኛው አደ​ባ​ባይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በአ​ዲሱ በር መግ​ቢያ ባለው በጸ​ሓ​ፊው በሳ​ፋን ልጅ በገ​ማ​ርያ ክፍል በሕ​ዝቡ ሁሉ ጆሮ በመ​ጽ​ሐፉ አን​በበ።</verse>
				<verse number="11">የሳ​ፋ​ንም ልጅ የገ​ማ​ርያ ልጅ ሚክ​ያስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሁሉ ከመ​ጽ​ሐፉ ሰማ።</verse>
				<verse number="12">ወደ ንጉ​ሡም ቤት ወደ ጸሓ​ፊው ክፍል ወረደ፤ እነ​ሆም አለ​ቆቹ ሁሉ፥ ጸሓ​ፊው ኤሊ​ሳማ፥ የሸ​ማያ ልጅ ድላያ፥ የዓ​ክ​ቦር ልጅ ኤል​ና​ታን፥ የሳ​ፋን ልጅ ገማ​ርያ፥ የሐ​ና​ንያ ልጅ ሴዴ​ቅ​ያስ፥ አለ​ቆ​ቹም ሁሉ በዚያ ተቀ​ም​ጠው ነበር።</verse>
				<verse number="13">ሚክ​ያ​ስም ባሮክ በሕ​ዝቡ ጆሮ በመ​ጽ​ሐፉ በአ​ነ​በበ ጊዜ የሰ​ማ​ውን ቃል ሁሉ ነገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">አለ​ቆ​ቹም ሁሉ፥ “በሕ​ዝቡ ጆሮ ያነ​በ​ብ​ኸ​ውን ክር​ታስ በእ​ጅህ ይዘህ ና” ብለው የኩሲ ልጅ የሰ​ሌ​ምያ ልጅ የና​ታ​ንያ ልጅ ይሁ​ዳን ወደ ኔርዩ ልጅ ወደ ባሮክ ላኩ። የኔ​ር​ዩም ልጅ ባሮክ ክር​ታ​ሱን በእጁ ይዞ ወደ እነ​ርሱ ወረደ።</verse>
				<verse number="15">እነ​ር​ሱም፥ “እስኪ ተቀ​መጥ፤ በጆ​ሮ​አ​ች​ንም አን​ብብ” አሉት። ባሮ​ክም በጆ​ሮ​አ​ቸው አነ​በ​በው።</verse>
				<verse number="16">እን​ዲ​ህም ሆነ፦ ቃሉን ሁሉ በሰሙ ጊዜ ፈር​ተው እርስ በር​ሳ​ቸው ተመ​ካ​ከሩ፤ ባሮ​ክ​ንም፥ “ይህን ቃል ሁሉ በር​ግጥ ለን​ጉሡ እን​ና​ገ​ራ​ለን” አሉት።</verse>
				<verse number="17">ባሮ​ክ​ንም፥ “ይህን ቃል ሁሉ እን​ዴት እንደ ጻፍ​ኸው ንገ​ረን” ብለው ጠየ​ቁት።</verse>
				<verse number="18">ባሮ​ክም፥ “ኤር​ም​ያስ ይህን ቃል ከአፉ ይነ​ግ​ረኝ ነበር፤ እኔም በመ​ጽ​ሐፉ ላይ እጽፍ ነበር” ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">አለ​ቆ​ቹም ባሮ​ክን፥ “አን​ተና ኤር​ም​ያስ ሂዱ፤ ተሸ​ሸጉ፤ ወዴ​ትም እንደ ሆና​ችሁ ማንም አይ​ወቅ” አሉት።</verse>
				<verse number="20">ወደ ንጉ​ሡም ወደ አደ​ባ​ባይ ገቡ፥ ክር​ታ​ሱ​ንም በጸ​ሓ​ፊው በኤ​ሊ​ሳማ ክፍል አኑ​ረ​ውት ነበር፤ ቃሉ​ንም ሁሉ ለን​ጉሡ ተና​ገሩ።</verse>
				<verse number="21">ንጉ​ሡም ክር​ታ​ሱን ያመጣ ዘንድ ይሁ​ዳን ላከ፤ እር​ሱም ከጸ​ሓ​ፊው ከኤ​ሊ​ሳማ ክፍል ወሰ​ደው፤ ይሁ​ዳም በን​ጉ​ሡና በን​ጉሡ አጠ​ገብ በቆ​ሙት አለ​ቆች ሁሉ ጆሮ አነ​በ​በው።</verse>
				<verse number="22">ንጉ​ሡም በዘ​ጠ​ነ​ኛው ወር በክ​ረ​ምት በሚ​ቀ​መ​ጥ​በት ቤት ተቀ​ምጦ ነበር፤ በፊ​ቱም እሳት ይነ​ድድ ነበር።</verse>
				<verse number="23">ይሁ​ዳም ሦስ​ትና አራት ዐምድ ያህል በአ​ነ​በበ ቍጥር፥ ንጉሡ በብ​ርዕ መቍ​ረጫ ቀደ​ደው፤ ክር​ታ​ሱ​ንም በም​ድጃ ውስጥ በአ​ለው እሳት ፈጽሞ እስ​ኪ​ቃ​ጠል ድረስ በም​ድጃ ውስጥ ወደ አለው እሳት ጣለው።</verse>
				<verse number="24">ንጉ​ሡም፥ ይህ​ንም ቃል ሁሉ የሰሙ አገ​ል​ጋ​ዮቹ ሁሉ አል​ደ​ነ​ገ​ጡም፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አል​ቀ​ደ​ዱም።</verse>
				<verse number="25">ነገር ግን ኤል​ና​ታ​ንና ጎዶ​ልያ፥ ገማ​ር​ያም ክር​ታ​ሱን እን​ዳ​ያ​ቃ​ጥል ንጉ​ሡን ለመ​ኑት፤ እርሱ ግን አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="26">ንጉ​ሡም ጸሓ​ፊ​ውን ባሮ​ክ​ንና ነቢ​ዩን ኤር​ም​ያ​ስን ይይዙ ዘንድ የን​ጉ​ሡን ልጅ ይረ​ሕ​ም​ኤ​ል​ንና የዓ​ዝ​ር​ኤ​ልን ልጅ ሠራ​ያን የዓ​ብ​ድ​ኤ​ል​ንም ልጅ ሰሌ​ም​ያን አዘዘ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሰወ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="27">ንጉ​ሡም፥ ባሮክ ከኤ​ር​ም​ያስ አፍ የጻ​ፈው ቃል ያለ​በ​ትን ክር​ታስ ካቃ​ጠለ በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="28">“ዳግ​መ​ኛም ሌላ ክር​ታስ ውሰድ፤ የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ኢዮ​አ​ቄም በአ​ቃ​ጠ​ለው ክር​ታስ ላይ የነ​በ​ረ​ውን የቀ​ድ​ሞ​ውን ቃል ሁሉ ጻፍ​በት።</verse>
				<verse number="29">የይ​ሁ​ዳ​ንም ንጉሥ ኢዮ​አ​ቄ​ምን እን​ዲህ በለው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አንተ፦ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በር​ግጥ ይመ​ጣል፤ ይች​ንም ሀገር ያፈ​ር​ሳ​ታል፤ ሰውና እን​ስ​ሳም ያል​ቃሉ ብለህ ለምን ጻፍ​ህ​በት? ብለህ ይህን ክር​ታስ አቃ​ጥ​ለ​ሃል።</verse>
				<verse number="30">ስለ​ዚ​ህም ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮ​አ​ቄም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዳ​ዊት ዙፋን ላይ የሚ​ቀ​መጥ ልጅ አይ​ኖ​ር​ለ​ትም፥ ሬሳ​ውም በቀን ለት​ኩ​ሳት፥ በሌ​ሊ​ትም ለው​ርጭ ይጣ​ላል።</verse>
				<verse number="31">ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም እር​ሱ​ንና ዘሩን አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም በመ​ዓት እጐ​በ​ኛ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም አል​ሰ​ሙ​ምና የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ባ​ቸ​ውን ክፉ ነገር ሁሉ በእ​ነ​ርሱ ላይና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሚ​ቀ​መጡ በይ​ሁ​ዳም ሰዎች ላይ አመ​ጣ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="32">ኤር​ም​ያ​ስም ሌላ ክር​ታስ ወሰደ፤ ለኔ​ር​ዩም ልጅ ለጸ​ሓ​ፊው ለባ​ሮክ ሰጠው፤ እር​ሱም የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​አ​ቄም በእ​ሳት ያቃ​ጠ​ለ​ውን የመ​ጽ​ሐ​ፉን ቃል ሁሉ ከኤ​ር​ም​ያስ አፍ ጻፈ​በት፤ ደግ​ሞም እንደ ቀድ​ሞው ያለ ቃል ብዙ ቃል ተጨ​መ​ረ​በት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="37">
				<verse number="1">የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በይ​ሁዳ ያነ​ገ​ሠው የኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ ሴዴ​ቅ​ያስ በኢ​ዮ​አ​ቄም ልጅ በኢ​ኮ​ን​ያን ፋንታ ነገሠ።</verse>
				<verse number="2">እር​ሱም ሆነ፥ አገ​ል​ጋ​ዮቹ፥ የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ በነ​ቢዩ በኤ​ር​ም​ያስ እጅ የተ​ና​ገ​ረ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ሙም።</verse>
				<verse number="3">ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ፥ “ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እኛ ጸልይ” ብሎ የሰ​ሌ​ም​ያን ልጅ ዮካ​ል​ንና ካህ​ኑን የማ​ሴ​ውን ልጅ ሶፎ​ን​ያ​ስን ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ ላከ።</verse>
				<verse number="4">እር​ሱ​ንም በግ​ዞት ቤት ገና አላ​ገ​ቡ​ትም ነበ​ርና ኤር​ም​ያስ በሕ​ዝቡ መካ​ከል ይወ​ጣና ይገባ ነበር።</verse>
				<verse number="5">የፈ​ር​ዖ​ንም ሠራ​ዊት ከግ​ብፅ ወጣ፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ከብ​በ​ዋት የነ​በሩ ከለ​ዳ​ው​ያን ይህን ወሬ​አ​ቸ​ውን በሰሙ ጊዜ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="6">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="7">የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ከእኔ ትጠ​ይቁ ዘንድ የላ​ካ​ች​ሁን የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ እን​ዲህ በሉት፦ እነሆ ሊረ​ዳ​ችሁ የወ​ጣው የፈ​ር​ዖን ሠራ​ዊት ወደ ሀገሩ ወደ ግብፅ ይመ​ለ​ሳል።</verse>
				<verse number="8">ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም ተመ​ል​ሰው ይህ​ችን ከተማ ይዋ​ጉ​አ​ታል፤ ይይ​ዙ​አ​ት​ማል፤ በእ​ሳ​ትም ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ታል።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አይ​ሄ​ዱ​ምና፦ ከለ​ዳ​ው​ያን በር​ግጥ ከእኛ ዘንድ ይሄ​ዳሉ ብላ​ችሁ ራሳ​ች​ሁን አታ​ታ​ልሉ።</verse>
				<verse number="10">ነገር ግን እና​ን​ተን የሚ​ወ​ጉ​ትን የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ጭፍራ ሁሉ ብት​መቱ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጥቂት ተወ​ግ​ተው ያል​ሞቱ ቢቀሩ ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ በስ​ፍ​ራው ይነ​ሣሉ፤ ይህ​ቺ​ንም ሀገር በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላሉ።”</verse>
				<verse number="11">የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ሠራ​ዊት ከፈ​ር​ዖን ሠራ​ዊት ፊት የተ​ነሣ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በተ​መ​ለሰ ጊዜ እን​ዲህ ሆነ፤</verse>
				<verse number="12">ኤር​ም​ያስ በሕ​ዝቡ መካ​ከል ይኖር ዘንድ ወደ ብን​ያም ሀገር ሊሄድ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣ።</verse>
				<verse number="13">በብ​ን​ያ​ምም በር በነ​በረ ጊዜ የሐ​ና​ንያ ልጅ የሰ​ሌ​ምያ ልጅ ሳሩያ የተ​ባለ በር ጠባቂ በዚያ ነበረ፤ እር​ሱም፥ “ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን መኰ​ብ​ለ​ልህ ነው” ብሎ ነቢ​ዩን ኤር​ም​ያ​ስን ያዘው።</verse>
				<verse number="14">ኤር​ም​ያ​ስም፥ “ሐሰት ነው፤ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን መኰ​ብ​ለሌ አይ​ደ​ለም” አለ፤ እርሱ ግን አል​ሰ​ማ​ውም፤ ሳሩ​ያም ኤር​ም​ያ​ስን ይዞ ወደ አለ​ቆች አመ​ጣው።</verse>
				<verse number="15">አለ​ቆ​ችም በኤ​ር​ም​ያስ ላይ ተቈ​ጥ​ተው መቱት፤ የግ​ዞት ቤት አድ​ር​ገ​ውት ነበ​ርና ወደ ጸሓ​ፊው ወደ ዮና​ታን ቤት ላኩት።</verse>
				<verse number="16">ኤር​ም​ያ​ስም ወደ ጕድ​ጓድ ቤት ወደ ጓዳ​ዎቹ ገባ፤ ኤር​ም​ያ​ስም በዚያ ብዙ ቀን ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="17">ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ ልኮ አስ​መ​ጣው፥ ንጉ​ሡም በቤቱ፥ “በውኑ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሆነ ቃል አለን?” ብሎ በቈ​ይታ ጠየ​ቀው። ኤር​ም​ያ​ስም፥ “አዎን አለ፤ ደግ​ሞም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ አል​ፈህ ትሰ​ጣ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="18">ኤር​ም​ያ​ስም ደግሞ ንጉ​ሡን ሴዴ​ቅ​ያ​ስን እን​ዲህ አለው፥ “በግ​ዞት ቤት የጣ​ላ​ች​ሁኝ አን​ተን፥ ወይስ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን፥ ወይስ ሕዝ​ብ​ህን ምን በድ​ያ​ችሁ ነው?</verse>
				<verse number="19">የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በእ​ና​ን​ተና በዚ​ህች ሀገር አይ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁም ብለው ትን​ቢት ይና​ገ​ሩ​ላ​ችሁ የነ​በሩ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ችሁ ወዴት አሉ?</verse>
				<verse number="20">አሁ​ንም አቤቱ ንጉሥ ሆይ! ልመ​ናዬ ወደ አንተ ይድ​ረስ፤ በዚያ እን​ዳ​ል​ሞት ወደ ጸሓ​ፊው ወደ ዮና​ታን ቤት አት​መ​ል​ሰኝ።”</verse>
				<verse number="21">ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ አዘዘ፤ ኤር​ም​ያ​ስ​ንም በግ​ዞት ቤቱ ቅጥር ግቢ አኖ​ሩት፤ እን​ጀ​ራም ሁሉ ከከ​ተማ እስ​ኪ​ጠፋ ድረስ ዕለት ዕለት አንድ አንድ እን​ጀራ ከውጪ ጋጋ​ሪ​ዎች እያ​መጡ ይሰ​ጡት ነበር። እን​ዲ​ሁም ኤር​ም​ያስ በግ​ዞት ቤት ቅጥር ግቢ ተቀ​ምጦ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="38">
				<verse number="1">ኤር​ም​ያስ ለሕ​ዝቡ ሁሉ እን​ዲህ ሲል የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል የና​ታን ልጅ ሰፋ​ን​ያስ፥ የጳ​ስ​ኮ​ርም ልጅ ጎዶ​ል​ያስ፥ የሰ​ሌ​ም​ያም ልጅ ዮካል፥ የመ​ል​ክ​ያም ልጅ ጳስ​ኮር ሰሙ።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በዚች ከተማ የሚ​ቀ​መጥ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ይሞ​ታል፤ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን የሚ​ወጣ ግን በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፤ ነፍ​ሱም እንደ ምርኮ ትሆ​ን​ለ​ታ​ለች፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ይኖ​ራል።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ይች ከተማ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሠራ​ዊት እጅ በር​ግጥ ትሰ​ጣ​ለች፤ እር​ሱም ይይ​ዛ​ታል።”</verse>
				<verse number="4">አለ​ቆ​ቹም ንጉ​ሡን፥ “ይህን የመ​ሰ​ለ​ውን ቃል ሲነ​ግ​ራ​ቸው በዚ​ያች ከተማ የቀ​ሩ​ትን የሰ​ል​ፈ​ኞ​ቹን እጅ፥ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ሁሉ እጅ ያደ​ክ​ማ​ልና ይህ ሰው ይገ​ደል፤ ለዚህ ሕዝብ ክፋ​ትን እንጂ ሰላ​ምን አይ​መ​ኝ​ለ​ት​ምና” አሉት።</verse>
				<verse number="5">ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ፥ “ንጉሡ በእ​ና​ንተ ላይ ምንም ሊያ​ደ​ርግ አይ​ች​ል​ምና እነሆ በእ​ጃ​ችሁ ነው” አለ።</verse>
				<verse number="6">ኤር​ም​ያ​ስ​ንም ወሰ​ዱት፤ በግ​ዞት ቤትም አደ​ባ​ባይ ወደ ነበ​ረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መል​ክያ ጕድ​ጓድ ውስጥ ጣሉት፤ ኤር​ም​ያ​ስ​ንም በገ​መድ አወ​ረ​ዱት። በጕ​ድ​ጓ​ዱም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አል​ነ​በ​ረ​በ​ትም፤ ኤር​ም​ያ​ስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።</verse>
				<verse number="7">በን​ጉ​ሡም ቤት የነ​በ​ረው ጃን​ደ​ረባ ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ዊው አቤ​ሜ​ሌክ ኤር​ም​ያ​ስን በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ እንደ ጣሉት ሰማ።</verse>
				<verse number="8">ንጉ​ሡም በብ​ን​ያም በር ተቀ​ምጦ ነበር። አቤ​ሜ​ሌ​ክም ከን​ጉሡ ቤት ወጥቶ ለን​ጉሡ እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥</verse>
				<verse number="9">“ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! እነ​ዚህ ሰዎች ነቢ​ዩን ኤር​ም​ያ​ስን በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ በመ​ጣ​ላ​ቸው በእ​ርሱ ላይ በአ​ደ​ረ​ጉት ሁሉ ክፉ አድ​ር​ገ​ዋል፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ውስጥ እን​ጀራ ስለ​ሌለ በዚያ በራብ ይሞ​ታል።”</verse>
				<verse number="10">ንጉ​ሡም ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ዊ​ዉን አቤ​ሜ​ሌ​ክን፥ “ከአ​ንተ ጋር ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ውሰድ፤ ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም ሳይ​ሞት ከጕ​ድ​ጓድ አው​ጣው” ብሎ አዘ​ዘው።</verse>
				<verse number="11">አቤ​ሜ​ሌ​ክም ከእ​ርሱ ጋር ሰዎ​ችን ይዞ ሄደ፤ ከቤተ መዛ​ግ​ብ​ቱም በታች ወደ ነበ​ረው ወደ ንጉሥ ቤት ገባ፤ ከዚ​ያም ዕላቂ ጨር​ቅና አሮጌ ገመድ ወሰደ፥ ወደ ኤር​ም​ያ​ስም ወደ ጕድ​ጓዱ ውስጥ በገ​መድ አወ​ረ​ደው።</verse>
				<verse number="12">ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ዊ​ውም አቤ​ሜ​ሌክ ኤር​ም​ያ​ስን፥ “እነ​ዚ​ህን ጨር​ቆች በብ​ብ​ትህ ከገ​መዱ በታች አድ​ርግ” አለው፤ ኤር​ም​ያ​ስም እን​ዲሁ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="13">ኤር​ም​ያ​ስ​ንም በገ​መዱ ጐተ​ቱት፤ ከጕ​ድ​ጓ​ድም አወ​ጡት፤ ኤር​ም​ያ​ስም በግ​ዞት ቤት አደ​ባ​ባይ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="14">ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ ልኮ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ነበ​ረው ወደ ሦስ​ተ​ኛው መግ​ቢያ ወደ እርሱ ነቢ​ዩን ኤር​ም​ያ​ስን አስ​መ​ጣው፤ ንጉ​ሡም ኤር​ም​ያ​ስን፥ “አን​ዲት ነገር እጠ​ይ​ቅ​ሃ​ለሁ፤ ምንም አት​ሸ​ሽ​ገኝ” አለው።</verse>
				<verse number="15">ኤር​ም​ያ​ስም ንጉ​ሡን ሴዴ​ቅ​ያ​ስን፥ “ብነ​ግ​ርህ በውኑ አት​ገ​ድ​ለ​ኝ​ምን? ብመ​ክ​ር​ህም አት​ሰ​ማ​ኝም” አለው።</verse>
				<verse number="16">ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ፥ “ይህ​ችን ነፍስ የፈ​ጠ​ረ​ልን ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! አል​ገ​ድ​ል​ህም፤ ነፍ​ስ​ህ​ንም ለሚሹ ለእ​ነ​ዚህ ሰዎች እጅ አሳ​ልፌ አል​ሰ​ጥ​ህም” ብሎ በቈ​ይታ ለኤ​ር​ም​ያስ ማለ።</verse>
				<verse number="17">ኤር​ም​ያ​ስም ሴዴ​ቅ​ያ​ስን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ አለ​ቆች ብት​ወጣ፥ ነፍ​ስህ በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ለች፤ ይህ​ችም ከተማ በእ​ሳት አት​ቃ​ጠ​ልም፤ አን​ተም፥ ቤት​ህም በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="18">ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ አለ​ቆች ባት​ወጣ ግን፥ ይች ከተማ በከ​ለ​ዳ​ው​ያን እጅ ትሰ​ጣ​ለች፤ በእ​ሳ​ትም ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ታል፤ አን​ተም ከእ​ጃ​ቸው አታ​መ​ል​ጥም” አለው።</verse>
				<verse number="19">ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ ኤር​ም​ያ​ስን፥ “ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን በኰ​በ​ለሉ በአ​ይ​ሁድ እጅ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ኛል፤ እነ​ር​ሱም ያፌ​ዙ​ብ​ኛል ብዬ እፈ​ራ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="20">ኤር​ም​ያ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “አሳ​ል​ፈው አይ​ሰ​ጡ​ህም። እኔ የም​ነ​ግ​ር​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ ለአ​ን​ተም ይሻ​ል​ሃል፤ ነፍ​ስ​ህም በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="21">ትወጣ ዘንድ እንቢ ብትል ግን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሳ​የኝ ቃል ይህ ነው።</verse>
				<verse number="22">እነሆ በይ​ሁዳ ቤት የቀ​ሩ​ትን ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ አለ​ቆች ያወ​ጣሉ፤ እነ​ዚ​ያም ሴቶች፦ ባለ​ሟ​ሎ​ችህ አታ​ል​ለ​ው​ሃል፤ አሸ​ን​ፈ​ው​ህ​ማል፤ እግ​ሮ​ችህ ግን አሁን በጭቃ ውስጥ ከገቡ እነ​ርሱ ከአ​ንተ ወደ ኋላ ተመ​ል​ሰ​ዋል ይላሉ።</verse>
				<verse number="23">ሚስ​ቶ​ች​ህ​ንና ልጆ​ች​ህ​ንም ሁሉ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን ያወ​ጣሉ፤ አን​ተም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ ትያ​ዛ​ለህ እንጂ ከእ​ጃ​ቸው አታ​መ​ል​ጥም፤ ይህ​ችም ከተማ በእ​ሳት ትቃ​ጠ​ላ​ለች።”</verse>
				<verse number="24">ሴዴ​ቅ​ያ​ስም ኤር​ም​ያ​ስን እን​ዲህ አለው፥ “ይህን ቃል ማንም አይ​ወቅ፥ አን​ተም አት​ሞ​ትም።</verse>
				<verse number="25">አለ​ቆቹ ግን እኔ ከአ​ንተ ጋር እንደ ተነ​ጋ​ገ​ርሁ ቢሰሙ፥ ወደ አን​ተም መጥ​ተው፦ ለን​ጉሡ ያል​ኸ​ውን ንገ​ረን፤ አት​ሸ​ሽ​ገ​ንም፤ እኛም አን​ገ​ድ​ል​ህም፤ ደግሞ ንጉሡ ያለ​ህን ንገ​ረን ቢሉህ፥</verse>
				<verse number="26">አንተ በዚያ እሞት ዘንድ ወደ ዮና​ታን ቤት አት​መ​ል​ሰኝ ብዬ በን​ጉሡ ፊት ለመ​ንሁ” በላ​ቸው።</verse>
				<verse number="27">አለ​ቆ​ቹም ሁሉ ወደ ኤር​ም​ያስ መጥ​ተው ጠየ​ቁት፤ ንጉ​ሡም እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ደ​ዚህ ቃል ሁሉ ነገ​ራ​ቸው። ነገ​ሩም አል​ተ​ሰ​ማ​ምና ከእ​ርሱ ጋር መነ​ጋ​ገ​ርን ተዉ።</verse>
				<verse number="28">ኤር​ም​ያ​ስም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እስከ ተያ​ዘ​ች​በት ቀን ድረስ በግ​ዞት ቤቱ አደ​ባ​ባይ ተቀ​መጠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="39">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በይ​ሁዳ ንጉሥ በሴ​ዴ​ቅ​ያስ በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርና ሠራ​ዊቱ ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጥ​ተው ከበ​ቡ​አት።</verse>
				<verse number="2">በሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስም በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በአ​ራ​ተ​ኛው ወር፥ ከወ​ሩም በዘ​ጠ​ነ​ኛው ቀን ከተ​ማ​ዪቱ ተለ​ያ​የች።</verse>
				<verse number="3">የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ አለ​ቆች ሁሉ፥ ማር​ጋ​ና​ሳር፥ ሳማ​ጎት፥ ናቡ​ሳ​ኮር፥ ናቡ​ሰ​ሪስ፥ ናግ​ራ​ጎ​ስ​ና​ሴር፥ ረብ​ማግ፥ ኔር​ጋል ሴሪ​አ​ጼር፥ ከቀ​ሩት ከባ​ቢ​ሎን ንጉሥ አለ​ቆች ሁሉ ጋር ገብ​ተው በመ​ካ​ከ​ለ​ኛው በር ውስጥ ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="4">የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስና ሰል​ፈ​ኞ​ቹም ሁሉ በአ​ዩ​አ​ቸው ጊዜ፥ በሌ​ሊት ሸሹ፤ በን​ጉ​ሡም አት​ክ​ልት መን​ገድ በሁ​ለቱ ቅጥር መካ​ከል በነ​በ​ረው ደጅ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ወጡ፤ በዓ​ረ​ባም መን​ገድ ወጡ።</verse>
				<verse number="5">የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ሠራ​ዊት ተከ​ታ​ተ​ላ​ቸው፤ ሴዴ​ቅ​ያ​ስ​ንም በኢ​ያ​ሪኮ ሜዳ አገ​ኙት፤ ይዘ​ውም በሐ​ማት ምድር ወዳ​ለ​ችው ወደ ዴብ​ላታ ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ ወደ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር አመ​ጡት፤ እር​ሱም ፍር​ድን በእ​ርሱ ላይ ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="6">የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ የሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስን ልጆች በዐ​ይኑ ፊት በዴ​ብ​ላታ ገደ​ላ​ቸው፤ የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ የይ​ሁ​ዳን ታላ​ላ​ቆች ሁሉ ገደለ።</verse>
				<verse number="7">የሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስ​ንም ዐይን አወጣ፤ በሰ​ን​ሰ​ለ​ትም አስሮ ወደ ባቢ​ሎን ወሰ​ደው።</verse>
				<verse number="8">ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም የን​ጉ​ሡ​ንና የሕ​ዝ​ቡን ቤቶች በእ​ሳት አቃ​ጠሉ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቅጥር አፈ​ረሱ።</verse>
				<verse number="9">የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ የቀ​ሩ​ትን ሕዝብ፥ ኰብ​ል​ለ​ውም ወደ እርሱ የገ​ቡ​ትን ሰዎ​ችና የቀ​ረ​ው​ንም የሕ​ዝ​ቡን ቅሬታ ወደ ባቢ​ሎን ማረ​ካ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ግን አን​ዳች ከሌ​ላ​ቸው ከሕ​ዝቡ ድሆች ከፊ​ሎ​ቹን በይ​ሁዳ ሀገር ተዋ​ቸው፤ የወ​ይ​ኑን ቦታና እር​ሻ​ው​ንም በዚያ ጊዜ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንን ስለ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል አዘ​ዘው፦</verse>
				<verse number="12">“ውሰ​ደ​ውና በመ​ል​ካም ተመ​ል​ከ​ተው፤ የሚ​ል​ህ​ንም ነገር አድ​ር​ግ​ለት እንጂ ክፉን ነገር አታ​ድ​ር​ግ​በት።”</verse>
				<verse number="13">የአ​ዛ​ዞች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንም ላከ፤ ናቡ​ሻ​ዝ​ባ​ንም፥ ራፋ​ስ​ቂ​ስም፥ ኔር​ጋል ሴራ​አ​ጼ​ርም፥ ራብ​ማ​ግም፥ የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ አለ​ቆች ሁሉ ላኩ።</verse>
				<verse number="14">ኤር​ም​ያ​ስ​ንም ከግ​ዞት ቤቱ አደ​ባ​ባይ አወ​ጡት፤ ወደ ቤቱም ይወ​ስ​ደው ዘንድ ለሳ​ፋን ልጅ ለአ​ኪ​ቃም ልጅ ለጎ​ዶ​ል​ያስ ሰጡት፤ እን​ዲ​ህም በሕ​ዝብ መካ​ከል ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="15">በግ​ዞት ቤቱ አደ​ባ​ባ​ይም ታስሮ ሳለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እን​ዲህ ሲል ወደ ኤር​ም​ያስ መጣ፦</verse>
				<verse number="16">“ሂድ ለኢ​ት​ዮ​ጵ​ያ​ዊው ለአ​ቤ​ሜ​ሌክ እን​ዲህ በለው፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ለበ​ጎ​ነት ሳይ​ሆን ለክ​ፋት ቃሌን በዚች ከተማ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ በዚ​ያም ቀን በፊ​ትህ ይፈ​ጸ​ማል።</verse>
				<verse number="17">በዚ​ያም ቀን አድ​ን​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ በም​ት​ፈ​ራ​ቸው ሰዎች እጅ አል​ሰ​ጥ​ህም።</verse>
				<verse number="18">ፈጽሜ አድ​ን​ሃ​ለሁ፤ ሰው​ነ​ት​ህም እንደ ምርኮ ትሆ​ን​ል​ሃ​ለች እንጂ በሰ​ይፍ አት​ወ​ድ​ቅም፤ በእኔ ታም​ነ​ሃ​ልና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="40">
				<verse number="1">ወደ ባቢ​ሎን በተ​ማ​ረ​ኩት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ምር​ኮ​ኞች መካ​ከል የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን በሰ​ን​ሰ​ለት አስሮ በወ​ሰ​ደው ጊዜ ከራማ ከለ​ቀ​ቀው በኋላ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">የአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ኤር​ም​ያ​ስን ወሰ​ደው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ክፉ ነገር በዚህ ስፍራ ላይ ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው አደ​ረገ፤ እር​ሱን በድ​ላ​ች​ኋ​ልና፥ ቃሉ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምና ይህ ነገር ሆነ​ባ​ችሁ።</verse>
				<verse number="4">አሁ​ንም እነሆ በእ​ጅህ ካለ​ችው ሰን​ሰ​ለት ዛሬ ፈታ​ሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢ​ሎን መም​ጣት መል​ካም መስሎ ቢታ​ይህ፥ ና፤ እኔም በመ​ል​ካም አይ​ሃ​ለሁ፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢ​ሎን መም​ጣት መል​ካም መስሎ ባይ​ታ​ይህ ግን፥ ተቀ​መጥ፤ ተመ​ል​ከት፥ እነሆ፥ ሀገ​ሪቱ ሁሉ በፊ​ትህ ናት፤ ትሄድ ዘንድ መል​ካም መስሎ በሚ​ታ​ይ​ህና ደስ በሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህም ስፍራ ተቀ​መጥ።”</verse>
				<verse number="5">እር​ሱም ገና ሳይ​መ​ለስ፥ “የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ላይ ወደ ሾመው ወደ ሳፋን ልጅ ወደ አኪ​ቃም ልጅ ወደ ጎዶ​ል​ያስ ተመ​ለስ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር በሕ​ዝቡ መካ​ከል በይ​ሁዳ ምድር ተቀ​መጥ፤ ወይም ትሄድ ዘንድ ለዐ​ይ​ንህ ደስ ወደ​ሚ​ያ​ሰ​ኝህ ስፍራ ሂድ” አለው። የአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ስን​ቅና ስጦታ ሰጥቶ አሰ​ና​በ​ተው።</verse>
				<verse number="6">ኤር​ም​ያ​ስም የአ​ኪ​ቃም ልጅ ጎዶ​ል​ያስ ወደ አለ​በት ወደ መሴፋ ሄደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር በሀ​ገሩ ውስጥ በቀ​ሩት ሕዝብ መካ​ከል ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="7">በየ​ሜ​ዳው የነ​በ​ሩት የጭ​ፍራ አለ​ቆ​ችና ሰዎ​ቻ​ቸው ሁሉ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያ​ስን በሀ​ገሩ ላይ እንደ ሾመ፥ ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ችን ልጆ​ች​ንም፥ ወደ ባቢ​ሎን ያል​ተ​ማ​ረ​ኩ​ት​ንም የም​ድ​ርን ድሆች እን​ዳ​ስ​ጠ​በቀ በሰሙ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="8">የና​ታ​ንያ ልጅ እስ​ማ​ኤል፥ የቃ​ር​ሔም ልጆች ዮሐ​ና​ንና ዮና​ታን፥ የተ​ን​ሁ​ሜ​ትም ልጅ ሠራያ፥ የነ​ጦ​ፋ​ዊ​ውም የዮፌ ልጆች፥ የመ​ከጢ ልጅ አዛ​ን​ያም ከሰ​ዎ​ቻ​ቸው ጋር ወደ ጎዶ​ል​ያስ ወደ መሴፋ መጡ።</verse>
				<verse number="9">የሳ​ፋ​ንም ልጅ የአ​ኪ​ቃም ልጅ ጎዶ​ል​ያስ ለእ​ነ​ር​ሱና ለሰ​ዎ​ቻ​ቸው እን​ዲህ ብሎ ማለ፥ “ለከ​ለ​ዳ​ው​ያን ትገዙ ዘንድ አት​ፍሩ፤ በም​ድር ተቀ​መጡ፤ ለባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ተገዙ፤ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="10">እነሆ እኔም ወደ እኛ በሚ​መ​ጡት ከለ​ዳ​ው​ያን ፊት እቆም ዘንድ በመ​ሴፋ እኖ​ራ​ለሁ፤ እና​ንተ ግን ወይ​ኑ​ንና ፍሬ​ውን፥ ዘይ​ቱ​ንም አከ​ማቹ፤ በየ​ዕ​ቃ​ች​ሁም ውስጥ ክተቱ፤ በያ​ዛ​ች​ኋ​ቸ​ውም ከተ​ሞ​ቻ​ችሁ ተቀ​መጡ።”</verse>
				<verse number="11">በሞ​ዓ​ብና በአ​ሞ​ንም ልጆች መካ​ከል፥ በኤ​ዶ​ም​ያ​ስም፥ በም​ድ​ርም ሁሉ ላይ የነ​በሩ አይ​ሁድ ሁሉ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ የይ​ሁ​ዳን ቅሬታ እን​ዳ​ስ​ቀረ፥ የሳ​ፋ​ን​ንም ልጅ የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያ​ስን በላ​ያ​ቸው እንደ ሾመው ሰሙ።</verse>
				<verse number="12">አይ​ሁ​ድም ሁሉ ከተ​ሰ​ደ​ዱ​በት ስፍራ ሁሉ ተመ​ለሱ፤ ወደ ይሁ​ዳም ሀገር ጎዶ​ል​ያስ ወዳ​ለ​በት ወደ መሴፋ መጡ፤ ወይ​ን​ንና የበ​ጋን ፍሬ፥ ዘይ​ት​ንም እጅግ ብዙ አከ​ማቹ።</verse>
				<verse number="13">የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ በየ​ሜ​ዳ​ውም የነ​በሩ የጭ​ፍራ አለ​ቆች ሁሉ ወደ ጎዶ​ል​ያስ ወደ መሴፋ መጥ​ተው፦</verse>
				<verse number="14">“የአ​ሞን ልጆች ንጉሥ በኣ​ሊስ ይገ​ድ​ልህ ዘንድ የና​ታ​ን​ያን ልጅ እስ​ማ​ኤ​ልን እንደ ላከ ታው​ቃ​ለ​ህን?” አሉት። የአ​ኪ​ቃም ልጅ ጎዶ​ል​ያስ ግን አላ​መ​ና​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="15">የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ “እባ​ክህ፥ ልሂድ፤ ማንም ሳያ​ውቅ የና​ታ​ን​ያን ልጅ እስ​ማ​ኤ​ልን ልግ​ደ​ለው፤ ወደ አንተ የተ​ሰ​በ​ሰቡ አይ​ሁድ ሁሉ እን​ዲ​በ​ተኑ፥ የይ​ሁ​ዳም ቅሬታ እን​ዲ​ጠፋ ነፍ​ስ​ህን ስለ ምን ይገ​ድ​ላል?” ብሎ በመ​ሴፋ በቈ​ይታ ለጎ​ዶ​ል​ያስ ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="16">የአ​ኪ​ቃም ልጅ ጎዶ​ል​ያስ ግን የቃ​ር​ሔን ልጅ ዮሐ​ና​ንን፥ “በእ​ስ​ማ​ኤል ላይ ሐሰት ተና​ግ​ረ​ሃ​ልና ይህን ነገር አታ​ድ​ርግ” አለው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="41">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ከመ​ን​ግ​ሥት ወገ​ንና ከን​ጉሡ ዋና ዋና አለ​ቆች አንዱ የኤ​ሊ​ሳማ ልጅ የና​ታ​ንያ ልጅ እስ​ማ​ኤል ከዐ​ሥር ሰዎች ጋር ወደ መሴፋ ወደ አኪ​ቃም ልጅ ወደ ጎዶ​ል​ያስ መጣ፤ በዚ​ያም በመ​ሴፋ በአ​ንድ ላይ እን​ጀራ በሉ።</verse>
				<verse number="2">የና​ታ​ን​ያም ልጅ እስ​ማ​ኤል ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ዐሥሩ ሰዎች ተነ​ሥ​ተው የሳ​ፋ​ንን ልጅ የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያ​ስን በሰ​ይፍ መቱ፤ የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በሀ​ገሩ ላይ የሾ​መ​ውን ገደሉ።</verse>
				<verse number="3">እስ​ማ​ኤ​ልም ከጎ​ዶ​ል​ያስ ጋር በመ​ሴፋ የነ​በ​ሩ​ትን አይ​ሁድ ሁሉ፥ በዚ​ያም የተ​ገ​ኙ​ትን ከለ​ዳ​ው​ያ​ንን ሁሉ፤ ሰል​ፈ​ኞች ሰዎ​ች​ንም ሁሉ ገደ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">እስ​ማ​ኤል ማንም ሳያ​ውቅ ጎዶ​ል​ያ​ስን ከገ​ደለ በኋላ በሁ​ለ​ተ​ኛው ቀን እን​ዲህ ሆነ፤</verse>
				<verse number="5">ጢማ​ቸ​ውን ላጭ​ተው፥ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ቀድ​ደው እያ​ለ​ቀሱ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ያቀ​ርቡ ዘንድ የእ​ህል ቍር​ባ​ንና ዕጣን በእ​ጃ​ቸው የያዙ፥ ሰማ​ንያ ሰዎች ከሴ​ኬ​ምና ከሴሎ፥ ከሰ​ማ​ር​ያም መጡ።</verse>
				<verse number="6">የና​ታ​ን​ያም ልጅ እስ​ማ​ኤል ከመ​ሴፋ ወጥቶ እያ​ለ​ቀሰ ሊገ​ና​ኛ​ቸው ሄደ፤ በተ​ገ​ና​ኛ​ቸ​ውም ጊዜ፥ “ወደ አኪ​ቃም ልጅ ወደ ጎዶ​ል​ያስ ኑ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">ወደ ከተ​ማም መካ​ከል በመጡ ጊዜ የና​ታ​ንያ ልጅ እስ​ማ​ኤል፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሰዎች ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ በጕ​ድ​ጓ​ድም መካ​ከል ጣሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">በዚ​ያም የተ​ገኙ ዐሥር ሰዎች ቀር​በው እስ​ማ​ኤ​ልን እን​ዲህ አሉት፥ “በሜ​ዳው ድልብ አለ​ንና፥ ገብ​ስና ስንዴ፥ ዘይ​ትና ማርም አለ​ንና አት​ግ​ደ​ለን፤” እር​ሱም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው መካ​ከል እነ​ር​ሱን መግ​ደል ተወ።</verse>
				<verse number="9">እስ​ማ​ኤ​ልም ከጎ​ዶ​ል​ያስ ጋር የገ​ደ​ላ​ቸ​ውን ሰዎች ሬሳ ሁሉ የጣ​ለ​በት ጕድ​ጓድ ንጉሡ አሳ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ ባኦ​ስን ስለ ፈራ የሠ​ራው ጕድ​ጓድ ነበረ፤ የና​ታ​ን​ያም ልጅ እስ​ማ​ኤል የገ​ደ​ላ​ቸ​ውን ሞላ​በት።</verse>
				<verse number="10">እስ​ማ​ኤ​ልም በመ​ሴፋ የነ​በ​ረ​ውን የሕ​ዝ​ቡን ቅሬታ ሁሉ፥ የን​ጉ​ሡን ሴቶች ልጆች፥ የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ለአ​ኪ​ቃም ልጅ ለጎ​ዶ​ል​ያስ የሰ​ጠ​ውን በመ​ሴፋ የቀ​ሩ​ትን ሕዝብ ሁሉ መለሰ፤ የና​ታ​ን​ያም ልጅ እስ​ማ​ኤል ወደ አሞን ልጆች ይሄድ ዘንድ ተነሣ።</verse>
				<verse number="11">የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ የጭ​ፍራ አለ​ቆች ሁሉ የና​ታ​ንያ ልጅ እስ​ማ​ኤል ያደ​ረ​ገ​ውን ክፋት ሁሉ ሰሙ።</verse>
				<verse number="12">ሠራ​ዊ​ቱ​ንም ሁሉ ይዘው ከና​ታ​ንያ ልጅ ከእ​ስ​ማ​ኤል ጋር ሊዋጉ ሄዱ። በገ​ባ​ዖ​ንም ባለው በብዙ ውኃ አጠ​ገብ አገ​ኙት።</verse>
				<verse number="13">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከእ​ስ​ማ​ኤል ጋር የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ የቃ​ር​ሔን ልጅ ዮሐ​ና​ንን ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩ​ትን የጭ​ፍራ አለ​ቆ​ችን ሁሉ ባዩ ጊዜ ደስ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">እስ​ማ​ኤ​ልም ከመ​ሴፋ የማ​ረ​ካ​ቸው ሕዝብ ሁሉ ተመ​ል​ሰው ወደ ቃር​ሔም ልጅ ወደ ዮሐ​ናን ሔዱ።</verse>
				<verse number="15">የና​ታ​ንያ ልጅ እስ​ማ​ኤል ግን ከስ​ም​ንት ሰዎች ጋር ከዮ​ሐ​ናን አመ​ለጠ፥ ወደ አሞ​ንም ልጆች ሄደ።</verse>
				<verse number="16">የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት የጭ​ፍራ አለ​ቆች ሁሉ የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያ​ስን በመ​ሴፋ ከገ​ደ​ለው በኋላ ከና​ታ​ንያ ልጅ ከእ​ስ​ማ​ኤል ያስ​መ​ለ​ሱ​አ​ቸ​ውን የሕ​ዝ​ቡን ቅሬታ ሁሉ፥ ከገ​ባ​ዖን ያስ​መ​ለ​ሱ​አ​ቸ​ውን ኀያ​ላን ሰል​ፈ​ኞ​ችን፥ ሴቶ​ች​ንም፥ ልጆ​ች​ንም፥ ጃን​ደ​ረ​ቦ​ች​ንም ወሰዱ፤</verse>
				<verse number="17">ተነ​ሥ​ተ​ውም ወደ ግብፅ ይሄዱ ዘንድ በቤ​ተ​ል​ሔም አጠ​ገብ በአ​ለው በጌ​ሮት-ከመ​ዓም ተቀ​መጡ፤</verse>
				<verse number="18">እስ​ማ​ኤል የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በሀ​ገሩ ላይ የሾ​መ​ውን የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያ​ስን ስለ ገደ​ለው ከለ​ዳ​ው​ያ​ንን ፈር​ተ​ዋ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="42">
				<verse number="1">የጭ​ፍራ አለ​ቆ​ችም ሁሉ፥ የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ የሐ​ና​ንያ ልጅ ኢዛ​ን​ያስ ሕዝ​ቡም ሁሉ ከታ​ናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ መጡ።</verse>
				<verse number="2">እን​ዲ​ህም አሉት፥ “እባ​ክህ ልመ​ና​ችን በፊ​ትህ ትድ​ረስ፤ ስለ እኛ፥ ስለ እነ​ዚ​ህም ቅሬ​ታ​ዎች ሁሉ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ይ​ልን፤ ዐይ​ኖ​ችህ እንደ አዩን ከብዙ ጥቂት ቀር​ተ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="3">አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የም​ን​ሄ​ድ​በ​ትን መን​ገ​ድና የም​ና​ደ​ር​ገ​ውን ነገር ይን​ገ​ረን።”</verse>
				<verse number="4">ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም አላ​ቸው፥ “ሰም​ታ​ች​ኋል፤ እነሆ እንደ ቃላ​ችሁ ወደ አም​ላ​ካ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጸ​ል​ያ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​መ​ል​ስ​ል​ኝን ሁሉ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ና​ን​ተም አን​ድም ቃል አል​ሸ​ሽ​ግም።”</verse>
				<verse number="5">ኤር​ም​ያ​ስ​ንም፥ “አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ እኛ የላ​ከ​ህን ነገር ሁሉ ባና​ደ​ርግ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችን እው​ነ​ተ​ኛና ታማኝ ምስ​ክር ይሁን።</verse>
				<verse number="6">የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስለ​ም​ን​ሰማ መል​ካም እን​ዲ​ሆ​ን​ልን፥ መል​ካም ወይም ክፉ ቢሆን፥ አን​ተን ወደ እርሱ የም​ን​ል​ክህ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እን​ሰ​ማ​ለን” አሉት።</verse>
				<verse number="7">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከዐ​ሥር ቀን በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ መጣ።</verse>
				<verse number="8">የቃ​ር​ሔ​ም​ንም ልጅ ዮሐ​ና​ንን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩ​ትን የጭ​ፍራ አለ​ቆች ሁሉ፥ ከታ​ናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ ጠራ፤</verse>
				<verse number="9">እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ልመ​ና​ች​ሁን በፊቱ አቀ​ርብ ዘንድ ወደ እርሱ የላ​ካ​ች​ሁኝ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="10">አደ​ር​ግ​ባ​ችሁ ዘንድ ከአ​ሰ​ብ​ሁት ክፉ ነገር ተመ​ል​ሻ​ለ​ሁና በዚች ምድር ብት​ቀ​መጡ እሠ​ራ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ አላ​ፈ​ር​ሳ​ች​ሁም፥ እተ​ክ​ላ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ አል​ነ​ቅ​ላ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="11">ከም​ት​ፈ​ሩት ከባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ፊት አት​ፍሩ፤ አድ​ና​ችሁ ዘንድ፥ ከእ​ጁም አስ​ጥ​ላ​ችሁ ዘንድ እኔ ከእ​ና​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍሩ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="12">ይቅ​ር​ታን እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ይቅ​ርም እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወደ ሀገ​ራ​ች​ሁም እመ​ል​ሳ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">“እና​ንተ ግን በዚች ምድር አን​ቀ​መ​ጥም ብትሉ፥ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ባት​ሰሙ፥</verse>
				<verse number="14">እና​ን​ተም፦ አይ​ደ​ለም፤ ሰልፍ ወደ​ማ​ና​ይ​ባት፥ የመ​ለ​ከ​ትም ድምፅ ወደ​ማ​ን​ሰ​ማ​ባት፥ እን​ጀ​ራ​ንም ወደ​ማ​ን​ራ​ብ​ባት ወደ ግብፅ ምድር እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በዚ​ያም እን​ቀ​መ​ጣ​ለን ብትሉ፥</verse>
				<verse number="15">ስለ​ዚህ እና​ንተ የይ​ሁዳ ቅሬታ ሆይ! አሁን እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ ግብ​ፅም ትገቡ ዘንድ በዚ​ያም ትቀ​መጡ ዘንድ ፊታ​ች​ሁን ብታ​ቀኑ፤</verse>
				<verse number="16">እና​ንተ የም​ት​ፈ​ሩት ሰይፍ በዚያ በግ​ብፅ ምድር ያገ​ኛ​ች​ኋል፤ ስለ እር​ሱም የም​ት​ደ​ነ​ግ​ጡ​በት ራብ በዚያ በግ​ብፅ ይደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋል፤ በዚ​ያም ትሞ​ታ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="17">ወደ ግብ​ፅም ይገቡ ዘንድ፥ በዚ​ያም ይቀ​መጡ ዘንድ ፊታ​ቸ​ውን በሚ​ያ​ቀኑ ሰዎች ሁሉ እን​ዲህ ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ያል​ቃሉ፤ እኔም ከማ​መ​ጣ​ባ​ቸው ክፉ ነገር ማንም አይ​ቀ​ርም፤ ማንም አያ​መ​ል​ጥም።</verse>
				<verse number="18">“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ቍጣ​ዬና መቅ​ሠ​ፍቴ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሚ​ኖሩ ላይ እንደ ፈሰሰ፥ እን​ዲሁ ወደ ግብፅ በገ​ባ​ችሁ ጊዜ መዓቴ ይፈ​ስ​ስ​ባ​ች​ኋል፤ እና​ን​ተም ለጥ​ላ​ቻና ለጥ​ፋት ለስ​ድ​ብና ለር​ግ​ማን ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ ይች​ንም ስፍራ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አታ​ዩ​አ​ትም።</verse>
				<verse number="19">እና​ንተ የይ​ሁዳ ቅሬታ ሆይ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ ግብፅ አት​ግቡ ብሎ ተና​ግ​ሮ​ባ​ች​ኋ​ልና ዛሬ እን​ዳ​ስ​ጠ​ነ​ቀ​ቅ​ኋ​ችሁ በእ​ር​ግጥ ዕወቁ።</verse>
				<verse number="20">እና​ንተ፦ ሰለ እኛ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸልይ፤ አም​ላ​ካ​ች​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ና​ገ​ር​ህን ሁሉ ንገ​ረን፤ እኛም እና​ደ​ር​ገ​ዋ​ለን ብላ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ አም​ላ​ካ​ችሁ ልካ​ች​ሁኝ ነበ​ርና ራሳ​ች​ሁን አታ​ል​ላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="21">እኔም ዛሬ ነግ​ሬ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወደ እና​ን​ተም በላ​ከኝ ነገር ሁሉ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="22">አሁ​ንም ሄዳ​ችሁ እን​ድ​ት​ቀ​መጡ በወ​ደ​ዳ​ች​ሁ​በት ስፍራ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም እን​ድ​ት​ሞቱ በእ​ር​ግጥ ዕወቁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="43">
				<verse number="1">የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሁሉ፥ ለእ​ነ​ርሱ አም​ላ​ካ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የላ​ከ​ውን ይህን ቃል ሁሉ፥ ኤር​ም​ያስ ለሕ​ዝቡ ሁሉ መና​ገ​ርን በፈ​ጸመ ጊዜ እን​ዲህ ሆነ፤</verse>
				<verse number="2">የኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ ኣዛ​ር​ያስ፥ የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ ትዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችም ሰዎች ሁሉ ኤር​ም​ያ​ስን፥ “ሐሰት ተና​ግ​ረ​ሃል፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በዚያ ትቀ​መጡ ዘንድ ወደ ግብፅ አት​ግቡ ብሎ አል​ላ​ከ​ህም፤</verse>
				<verse number="3">ነገር ግን ከለ​ዳ​ው​ያን እን​ዲ​ገ​ድ​ሉን ወደ ባቢ​ሎ​ንም እን​ዲ​ያ​ፈ​ል​ሱን በእ​ጃ​ቸው አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጠን ዘንድ የኔ​ርዩ ልጅ ባሮክ በላ​ያ​ችን ላይ አነ​ሣ​ሥ​ቶ​ሃል” አሉት።</verse>
				<verse number="4">የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ የጭ​ፍራ አለ​ቆ​ችም ሁሉ፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ በይ​ሁዳ ምድር ይቀ​መጡ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ሙም።</verse>
				<verse number="5">የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ የጭ​ፍራ አለ​ቆ​ችም ሁሉ በይ​ሁዳ ምድር ለመ​ቀ​መጥ ከተ​ሰ​ደ​ዱ​ባ​ቸው ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ የተ​መ​ለ​ሱ​ትን የይ​ሁ​ዳን ቅሬታ ሁሉ ወሰዱ።</verse>
				<verse number="6">ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ችን፥ ሕፃ​ና​ቱ​ንም፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ሴቶች ልጆች፥ የአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ከሳ​ፋን ልጅ ከአ​ኪ​ቃም ልጅ ከጎ​ዶ​ል​ያስ ጋር የተ​ዋ​ቸ​ውን ሰዎች ሁሉ፥ ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስ​ንና የኔ​ር​ዩን ልጅ ባሮ​ክ​ንም ወሰዱ።</verse>
				<verse number="7">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል አል​ሰ​ሙ​ምና ወደ ግብፅ ምድር ገቡ፤ እስከ ጣፍ​ናስ ድረ​ስም መጡ።</verse>
				<verse number="8">በጣ​ፍ​ና​ስም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="9">“ታላ​ላ​ቆ​ችን ድን​ጋ​ዮች በእ​ጅህ ውሰድ፥ የይ​ሁ​ዳም ሰዎች እያዩ በጣ​ፍ​ናስ ባለው በፈ​ር​ዖን ቤት ደጅ መግ​ቢያ ሸሽ​ጋ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ልኬ ባሪ​ያ​ዬን የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን አመ​ጣ​ለሁ፤ ዙፋ​ኑ​ንም እኔ በሸ​ሸ​ግ​ኋ​ቸው በእ​ነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮች ላይ አኖ​ራ​ለሁ፤ ጋሻ​ዎ​ቹ​ንም በእ​ነ​ርሱ ላይ ያነ​ሣል።</verse>
				<verse number="11">መጥ​ቶም የግ​ብ​ፅን ምድር ይመ​ታል፤ ለሞ​ትም የሚ​ሆ​ነ​ውን ለሞት፥ ለም​ር​ኮም የሚ​ሆ​ነ​ውን ለም​ርኮ፥ ለሰ​ይ​ፍም የሚ​ሆ​ነ​ውን ለሰ​ይፍ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል።</verse>
				<verse number="12">በግ​ብ​ፅም አማ​ል​ክት ቤቶች እሳ​ትን ያነ​ድ​ዳል፤ ያቃ​ጥ​ላ​ቸ​ው​ማል፤ ይማ​ር​ካ​ቸ​ው​ማል፤ እረ​ኛም ልብ​ሱን እን​ደ​ሚ​ቀ​ምል እን​ዲሁ የግ​ብ​ፅን ሀገር ይቀ​ም​ላ​ታል፤ ከዚ​ያም በሰ​ላም ይወ​ጣል።</verse>
				<verse number="13">በግ​ብፅ ምድ​ርም ያለ​ውን የፀ​ሐይ ከተማ ምሰ​ሶ​ዎ​ችን ይሰ​ብ​ራል፥ የግ​ብ​ፅ​ንም አማ​ል​ክት ቤቶች በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="44">
				<verse number="1">በግ​ብፅ ምድር በሚ​ግ​ዶ​ልና በጣ​ፍ​ናስ፥ በሜ​ም​ፎ​ስም፥ በፋ​ቱ​ራም ሀገር ስለ ተቀ​መጡ አይ​ሁድ ሁሉ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦</verse>
				<verse number="2">“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ሁሉ ያመ​ጣ​ሁ​ትን ክፉ ነገር ሁሉ አይ​ታ​ች​ኋል፤ ከክ​ፋ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ እነሆ ዛሬ ባድማ ሆነ​ዋል፤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸ​ውም የለም።</verse>
				<verse number="3">ይህም የሆ​ነው ያስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ስላ​ደ​ረ​ጉት ክፋት፥ እነ​ር​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ቸው ለማ​ያ​ው​ቁ​አ​ቸው ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት ያጥኑ ዘንድ፥ ያመ​ል​ኳ​ቸ​ውም ዘንድ ስለ​ሄዱ ነው።</verse>
				<verse number="4">በማ​ለ​ዳም ባሪ​ያ​ዎ​ችን ነቢ​ያ​ትን ሁሉ ላክ​ሁ​ባ​ቸው፤ የጠ​ላ​ሁ​ት​ንም ርኩስ ነገር አታ​ድ​ርጉ ብዬ ላክ​ሁ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">ነገር ግን አል​ሰ​ሙ​ኝም፤ ከክ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ተመ​ል​ሰው ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት እን​ዳ​ያ​ጥኑ ጆሮ​አ​ቸ​ውን አል​መ​ለ​ሱም።</verse>
				<verse number="6">ስለ​ዚህ መዓ​ቴና መቅ​ሠ​ፍቴ ወረደ፤ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ ነደደ፤ ዛሬም እንደ ሆነው ጠፍና ባድማ ሆኑ።</verse>
				<verse number="7">“አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከይ​ሁዳ ወገን መካ​ከል ቅሬታ እን​ዳ​ይ​ቀ​ር​ላ​ችሁ፥ ወን​ድ​ንና ሴትን፥ ብላ​ቴ​ና​ንና የሚ​ጠባ ሕፃ​ንን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ታጠፉ ዘንድ ይህን ታላቅ ክፋት በራ​ሳ​ችሁ ላይ ለምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="8">ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም ታጠፉ ዘንድ፥ በም​ድ​ርም አሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል መረ​ገ​ሚ​ያና መሰ​ደ​ቢያ ትሆኑ ዘንድ፥ ለመ​ቀ​መጥ በገ​ባ​ች​ሁ​ባት በግ​ብፅ ምድር ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት በማ​ጠ​ና​ችሁ በእ​ጃ​ችሁ ሥራ ለምን ታስ​ቈ​ጡ​ኛ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="9">በውኑ በይ​ሁዳ ምድ​ርና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ ያደ​ረ​ጉ​ትን የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ክፋት፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ነገ​ሥ​ታት ክፋት፥ የአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ክፋት የሚ​ስ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ክፋት ረስ​ታ​ች​ሁ​ታ​ልን?።</verse>
				<verse number="10">እስከ ዛሬም ድረስ አላ​ረ​ፉም፤ አል​ፈ​ሩ​ምም፤ በእ​ና​ን​ተና በአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ፊት ባኖ​ር​ሁት ሕጌና ሥር​ዐቴ አል​ሄ​ዱም።</verse>
				<verse number="11">“ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይሁ​ዳን ሁሉ አጠፋ ዘንድ፥ ፊቴን ለክ​ፋት በላ​ያ​ችሁ አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">ወደ ግብ​ፅም ይገቡ ዘንድ፥ በዚ​ያም ይቀ​መጡ ዘንድ ፊታ​ቸ​ውን ያቀ​ኑ​ትን የይ​ሁ​ዳን ቅሬታ እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ሁሉም ይጠ​ፋሉ፤ በግ​ብ​ፅም ምድር ይወ​ድ​ቃሉ፤ በሰ​ይ​ፍና በራብ ይጠ​ፋሉ፤ ከታ​ና​ሹም ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ በሰ​ይ​ፍና በራብ ይሞ​ታሉ፤ ለጥ​ላ​ቻና ለጥ​ፋት፥ ለመ​ረ​ገ​ሚ​ያና ለመ​ሰ​ደ​ቢያ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="13">ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም በመ​ዐት እንደ ጐበ​ኘሁ፥ እን​ዲሁ በግ​ብፅ ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን በሰ​ይ​ፍና በራብ በቸ​ነ​ፈ​ርም እጐ​በ​ኛ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">በዚያ ለመ​ቀ​መጥ በል​ባ​ቸው ተስፋ ወደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጓት ወደ ይሁዳ ምድር ይመ​ለሱ ዘንድ በግ​ብፅ ለመ​ኖር ከመጡ ከይ​ሁዳ ቅሬታ ወገን የሚ​ያ​መ​ል​ጥና የሚ​ቀር፥ ወደ​ዚ​ያም የሚ​መ​ለስ አይ​ኖ​ርም፤ ከሚ​ያ​መ​ል​ጥም በቀር ማንም አይ​መ​ለ​ስም።”</verse>
				<verse number="15">ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት ማጠ​ና​ቸ​ውን ያወቁ ሰዎች ሁሉ፥ በዚ​ያም የቆሙ ሴቶች ሁሉ፥ በግ​ብ​ፅም ምድር በጳ​ት​ሮስ የተ​ቀ​መጡ ሕዝብ ሁሉ፥ ታላቅ ጉባኤ ሆነው ለኤ​ር​ም​ያስ መለ​ሱ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አሉ፦</verse>
				<verse number="16">“አንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የነ​ገ​ር​ኸ​ንን ቃል አን​ሰ​ማም።</verse>
				<verse number="17">ነገር ግን እኛና አባ​ቶ​ቻ​ችን፥ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ እና​ደ​ር​ገው እንደ ነበረ፥ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት እና​ጥን ዘንድ፥ የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን እና​ፈ​ስ​ስ​ላት ዘንድ ከአ​ፋ​ችን የወ​ጣ​ውን ቃል ሁሉ በር​ግጥ እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ በዚያ ጊዜም እን​ጀ​ራን እን​ጠ​ግብ ነበር፥ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ልን ነበር፤ ክፉም አና​ይም ነበር።</verse>
				<verse number="18">ለሰ​ማይ ንግ​ሥት ማጠ​ንን፥ ለእ​ር​ስ​ዋም የመ​ጠ​ጥን ቍር​ባን ማፍ​ሰ​ስን ከተ​ውን ወዲህ ግን፥ እኛ ሁላ​ችን አን​ሰ​ናል፤ በሰ​ይ​ፍና በራ​ብም አል​ቀ​ናል።</verse>
				<verse number="19">እኛስ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት ባጠ​ን​ን​ላት፥ የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን ባፈ​ሰ​ስ​ን​ላት ጊዜ፥ በውኑ ያለ ባሎ​ቻ​ችን ምስ​ል​ዋን ለማ​በ​ጀት እን​ጎቻ አድ​ር​ገ​ን​ላት ኖሮ​አ​ልን? የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን አፍ​ስ​ሰ​ን​ላት ኖሮ​አ​ልን?”</verse>
				<verse number="20">ኤር​ም​ያ​ስም ይህን ቃል ለመ​ለ​ሱ​ለት ሕዝብ ሁሉ፦ ለወ​ን​ዶ​ቹና ለሴ​ቶቹ፥ ለሕ​ዝ​ቡም ሁሉ መለ​ሰ​ላ​ቸው እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="21">“እና​ን​ተና አባ​ቶ​ቻ​ችሁ፥ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ች​ሁም፥ አለ​ቆ​ቻ​ች​ሁም የም​ድ​ርም ሕዝብ በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ ያጠ​ና​ች​ሁ​ትን ዕጣን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሰ​በው፥ በል​ቡም ያኖ​ረው አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የሥ​ራ​ች​ሁን ክፋ​ትና ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ትን ርኵ​ሰት ይታ​ገሥ ዘንድ አል​ቻ​ለም፤ ስለ​ዚህ ምድ​ራ​ችሁ ባድማ፥ በረ​ሃና መረ​ገ​ሚያ ሆና​ለች፤ እስከ ዛሬም የሚ​ኖ​ር​ባት የለም።</verse>
				<verse number="23">ስላ​ጠ​ና​ች​ሁት ዕጣን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ላይ ስለ በደ​ላ​ችሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ስላ​ል​ሰ​ማ​ችሁ፥ በሕ​ጉና በሥ​ር​ዐ​ቱም፥ በም​ስ​ክ​ሩም ስላ​ል​ሄ​ዳ​ችሁ፥ ስለ​ዚህ ዛሬ እንደ ሆነ ይች ክፉ ነገር አግ​ኝ​ታ​ች​ኋ​ለች።”</verse>
				<verse number="24">ኤር​ም​ያ​ስም ለሕ​ዝቡ ሁሉ፥ ለሴ​ቶ​ቹም ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “በግ​ብፅ ምድር የም​ት​ኖሩ አይ​ሁድ ሁሉ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።</verse>
				<verse number="25">የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እና​ን​ተና ሚስ​ቶ​ቻ​ችሁ በአ​ፋ​ችሁ፦ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት እና​ጥን ዘንድ፥ የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን እና​ፈ​ስ​ስ​ላት ዘንድ የተ​ሳ​ል​ነ​ውን ስእ​ለ​ታ​ች​ንን በር​ግጥ እን​ፈ​ጽ​ማ​ለን አላ​ችሁ፤ በእ​ጃ​ች​ሁም አደ​ረ​ጋ​ች​ሁት፤ እን​ግ​ዲህ ስእ​ለ​ታ​ች​ሁን አጽኑ፤ ስእ​ለ​ታ​ች​ሁ​ንም ፈጽሙ።</verse>
				<verse number="26">ስለ​ዚህ እና​ንተ በግ​ብፅ ምድር የም​ት​ኖሩ አይ​ሁድ ሁሉ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ በሚ​ኖር በይ​ሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ፦ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ተብሎ እን​ዳ​ይ​ጠራ፥ እነሆ በታ​ላቁ ስሜ ምያ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​እ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="27">እነሆ ለመ​ል​ካም ሳይ​ሆን ለክ​ፋት እተ​ጋ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በግ​ብ​ፅም ምድር ያሉት የይ​ሁዳ ሰዎች ሁሉ እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በሰ​ይ​ፍና በራብ ያል​ቃሉ።</verse>
				<verse number="28">ከሰ​ይ​ፍም የሚ​ያ​መ​ልጡ በቍ​ጥር ጥቂ​ቶች ሰዎች ከግ​ብፅ ምድር ወደ ይሁዳ ምድር ይመ​ለ​ሳሉ፤ ሊቀ​መ​ጡም ወደ ግብፅ ምድር የገ​ቡት የይ​ሁዳ ቅሬታ ሁሉ ከእኔ ወይም ከእ​ነ​ርሱ የማ​ና​ችን ቃል እን​ዲ​ጸና ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="29">“ቃሌም በላ​ያ​ችሁ ለክ​ፋት እን​ዲ​ጸና ታውቁ ዘንድ በዚች ስፍራ በክፉ እን​ደ​ም​ጐ​በ​ኛ​ችሁ ምል​ክ​ታ​ችሁ ይህ ነው፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="30">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስን ጠላቱ ለሆ​ነው፥ ነፍ​ሱ​ንም ለፈ​ለ​ገው ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ አሳ​ልፌ እንደ ሰጠ​ሁት፥ እን​ዲሁ እነሆ የግ​ብ​ፅን ንጉሥ ፈር​ዖን ሖፍ​ራን ለጠ​ላ​ቶቹ፥ ነፍ​ሱ​ንም ለሚ​ፈ​ልጉ እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="45">
				<verse number="1">በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት እነ​ዚ​ህን ቃላት ከኤ​ር​ም​ያስ አፍ በመ​ጽ​ሐፍ በጻ​ፋ​ቸው ጊዜ፥ ነቢዩ ኤር​ም​ያስ ለኔ​ርዩ ልጅ ለባ​ሮክ የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">“ባሮክ ሆይ! የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​እ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይል​ሃል፦</verse>
				<verse number="3">አንተ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ማሜ ላይ ኀዘ​ንን ጨም​ሮ​ብ​ኛ​ልና ወዮ​ልኝ! በል​ቅ​ሶዬ ጩኸት ደክ​ሜ​አ​ለሁ፤ ዕረ​ፍ​ት​ንም አላ​ገ​ኘ​ሁም ብለ​ሃል።</verse>
				<verse number="4">እን​ዲህ በለው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የሠ​ራ​ሁ​ትን አፈ​ር​ሳ​ለሁ፥ የተ​ከ​ል​ሁ​ት​ንም እነ​ቅ​ላ​ለሁ፤ ይኸ​ውም በም​ድር ሁሉ ነው።</verse>
				<verse number="5">ለራ​ስህ ታላ​ላቅ ነገ​ሮ​ችን ትፈ​ል​ጋ​ለ​ህን? በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ እነሆ ክፉ ነገ​ርን አመ​ጣ​ለ​ሁና አት​ፈ​ል​ጋ​ቸው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን በሄ​ድ​ህ​በት ስፍራ ሁሉ ነፍ​ስ​ህን እንደ ምርኮ አድ​ርጌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="46">
				<verse number="1">በአ​ሕ​ዛብ ላይ ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">በግ​ብፅ ላይ፤ በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ በከ​ር​ኬ​ማስ በነ​በ​ረው፥ በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በመ​ታው በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ኒካዑ ሠራ​ዊት፥</verse>
				<verse number="3">“ጋሻና ጦር ያዙ፤ ወደ ሰል​ፍም ቅረቡ።</verse>
				<verse number="4">ፈረ​ሰ​ኞች ሆይ፥ ፈረ​ሶ​ችን ጫኑና ውጡ፤ ራስ ቍር​ንም ደፍ​ታ​ችሁ ቁሙ፤ ጦር​ንም ሰን​ግሉ፤ ጥሩ​ር​ንም ልበሱ።</verse>
				<verse number="5">ፈር​ተው ወደ ኋላ ሲመ​ለሱ፥ ኀያ​ላ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ሲደ​ክሙ፥ ወደ ኋላ​ቸ​ውም ሳይ​መ​ለ​ከቱ ፈጥ​ነው ሲሸሹ ለምን አየሁ? በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ይከ​ቡ​አ​ቸ​ዋል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="6">ፈጣ​ኑም አያ​መ​ል​ጥም፤ ኀያ​ሉም አይ​ድ​ንም፤ በሰ​ሜን በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ በኩል ደክ​መው ወደቁ።</verse>
				<verse number="7">ይህ እንደ ወንዝ የሚ​ነሣ ውኃ​ውም እንደ ወንዝ የሚ​ና​ወጥ ማን ነው?</verse>
				<verse number="8">ግብፅ እንደ ወንዝ ይነ​ሣል፤ ከባ​ሕ​ሩም እን​ደ​ሚ​ታ​ወክ ማዕ​በል ይሆ​ናል፤ እር​ሱም እን​ዲህ ብሏል፥ “እነ​ሣ​ለሁ፤ ምድ​ር​ንም ሁሉ እከ​ድ​ና​ለሁ፤ ከተ​ሞ​ች​ንና የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸ​ውን አጠ​ፋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">በፈ​ረ​ሶች ተቀ​መጡ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንም አዘ​ጋ​ጁና ውጡ፤ ጋሻም የሚ​ያ​ነ​ግቡ የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያና የሊ​ብያ ኀያ​ላን፥ ቀስ​ት​ንም ይዘው የሚ​ስቡ የሉድ ኀያ​ላን ይውጡ።</verse>
				<verse number="10">ያ ቀን ጠላ​ቶ​ቹን የሚ​በ​ቀ​ል​በት የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የበ​ቀል ቀን ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ በልቶ ይጠ​ግ​ባል፤ በደ​ማ​ቸ​ውም ይሰ​ክ​ራል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት በሰ​ሜን ምድር በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ ነውና።</verse>
				<verse number="11">ድን​ግ​ሊቱ የግ​ብፅ ልጅ ሆይ! ወደ ገለ​ዓድ ውጪ፤ የሚ​ቀባ መድ​ኀ​ኒ​ት​ንም ውሰጂ፤ ለም​ንም የማ​ይ​ጠ​ቅ​ም​ሽን መድ​ኀ​ኒት በከ​ንቱ አብ​ዝ​ተ​ሻል።</verse>
				<verse number="12">ጦረ​ኞች በጦ​ረ​ኞች ላይ ተሰ​ና​ክ​ለው ሁለቱ በአ​ን​ድ​ነት ወድ​ቀ​ዋ​ልና አሕ​ዛብ ቃል​ሽን ሰም​ተ​ዋል፤ ልቅ​ሶ​ሽም ምድ​ርን ሞል​ቶ​አ​ታል።”</verse>
				<verse number="13">የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እን​ደ​ሚ​መ​ጣና የግ​ብ​ፅን ምድር እን​ደ​ሚ​መታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለነ​ቢዩ ለኤ​ር​ም​ያስ የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው።</verse>
				<verse number="14">“በግ​ብፅ ተና​ገሩ፤ በሚ​ግ​ዶ​ልም አውሩ፤ በሜ​ም​ፎ​ስና በጣ​ፍ​ናስ አሰሙ፤ ሰይፍ በዙ​ሪ​ያህ ያለ​ውን በል​ቶ​አ​ልና፦ ተነሥ ተዘ​ጋ​ጅም በሉ።</verse>
				<verse number="15">ኀይ​ለ​ኞ​ችህ ስለ ምን ታጡ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስላ​ደ​ከ​ማ​ቸው የሉም።</verse>
				<verse number="16">ብዛ​ታ​ቸ​ውም ደከመ፤ ወደ​ቀም፤ አን​ዱም አንዱ ለጓ​ደ​ኛው፦ ተነሥ፤ ከአ​ረ​ማ​ው​ያን ሰይፍ ፊት ወደ ወገ​ና​ችን ወደ ተወ​ለ​ድ​ን​ባት ምድር እን​መ​ለስ አለው።</verse>
				<verse number="17">በዚ​ያም የግ​ብፅ ንጉሥ የፈ​ር​ዖ​ንን ስም ጊዜ​ውን የሚ​ያ​ሳ​ልፍ ብለው ጠሩት።</verse>
				<verse number="18">እኔ ሕያው ነኝና በተ​ራ​ሮች መካ​ከል እን​ዳለ እንደ አጤ​ቤ​ር​ዮን፥ በባ​ሕ​ርም አጠ​ገብ እን​ዳለ እንደ ቀር​ሜ​ሎስ፥ እን​ዲሁ በእ​ው​ነት ይመ​ጣል፥ ይላል ስሙ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የሆነ ንጉሥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="19">አንቺ በግ​ብፅ የም​ት​ቀ​መጪ ልጅ ሆይ! ሜም​ፎስ ባድማ ትሆ​ና​ለ​ችና፥ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም አይ​ገ​ኝ​ምና ለፍ​ል​ሰት የሚ​ሆን ዕቃ አዘ​ጋጂ።</verse>
				<verse number="20">“ግብፅ የተ​ዋ​በች ጊደር ናት፤ ጥፋት ግን ከሰ​ሜን በኩል ይመ​ጣ​ባ​ታል።</verse>
				<verse number="21">በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ የተ​ቀ​ጠሩ ሠራ​ተ​ኞች በእ​ር​ስዋ ተቀ​ል​በው እንደ ሰቡ ወይ​ፈ​ኖች ናቸው፤ የጥ​ፋ​ታ​ቸው ቀንና የቅ​ጣ​ታ​ቸው ጊዜ መጥ​ቶ​ባ​ቸ​ዋ​ልና ተመ​ለሱ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ሸሹ፤ አል​ቆ​ሙ​ምም።</verse>
				<verse number="22">ሠራ​ዊ​ትም በኀ​ይል ይዘ​ም​ቱ​ባ​ታ​ልና፥ እንደ እን​ጨት ቈራ​ጮ​ችም በም​ሳር ይመ​ጡ​ባ​ታ​ልና ድም​ፅዋ እን​ደ​ም​ት​ሸሽ እባብ ይተ​ማል።</verse>
				<verse number="23">ሊቈ​ጠሩ የማ​ይ​ችሉ የዱ​ር​ዋን ዛፎች ይቈ​ር​ጣሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከአ​ን​በጣ ይልቅ በዝ​ተ​ዋ​ልና፥ ቍጥ​ርም የላ​ቸ​ው​ምና።</verse>
				<verse number="24">የግ​ብፅ ልጅ ታፍ​ራ​ለች፤ በሰ​ሜን ሕዝብ እጅም አልፋ ትሰ​ጣ​ለች።”</verse>
				<verse number="25">የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ የኖእ አሞ​ንን፥ ፈር​ዖ​ን​ንም፥ ግብ​ጽ​ንም፥ አማ​ል​ክ​ቶ​ች​ዋ​ንና ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ች​ዋ​ንም፥ ፈር​ዖ​ን​ንና በእ​ር​ሱም የሚ​ታ​መ​ኑ​ትን እቀ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="26">ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም በሚ​ፈ​ልጉ ሰዎች እጅ፥ በባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ፥ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ እንደ ቀድ​ሞው ዘመን የሰው መኖ​ሪያ ትሆ​ና​ለች፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”</verse>
				<verse number="27">“ነገር ግን አንተ ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ ሆይ! አት​ፍራ፥ አን​ተም እስ​ራ​ኤል ሆይ! አት​ደ​ን​ግጥ፤ እነሆ አን​ተን ከሩቅ፥ ዘር​ህ​ንም ከተ​ማ​ረ​ኩ​ባት ምድር አድ​ና​ለሁ፤ ያዕ​ቆ​ብም ተመ​ልሶ ያር​ፋል፤ ተዘ​ል​ሎም ይተ​ኛል፤ ማንም አያ​ስ​ፈ​ራ​ውም።</verse>
				<verse number="28">አንተ ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ ሆይ! እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ተ​ንም ያሳ​ደ​ድ​ሁ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ፈጽሜ አጠ​ፋ​ለ​ሁና፥ አን​ተን ግን ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋ​ህም፤ በመ​ጠን እቀ​ጣ​ሃ​ለሁ፥ ያለ ቅጣ​ትም አል​ተ​ው​ህም።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="47">
				<verse number="1">ፈር​ዖ​ንም ጋዛን ሳይ​መታ ስለ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ ውኃ ከሰ​ሜን ይነ​ሣል፥ የሚ​ያ​ጥ​ለ​ቀ​ል​ቅም ፈሳሽ ይሆ​ናል፤ በሀ​ገ​ሪ​ቱና በመ​ላዋ ሁሉ፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱና በሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም ላይ ይጐ​ር​ፋል፤ ሰዎ​ቹም ይጮ​ኻሉ፤ በም​ድ​ርም የሚ​ኖሩ ሁሉ ያለ​ቅ​ሳሉ።</verse>
				<verse number="3">ከኀ​ይ​ለ​ኞች ፈረ​ሶች ከኮ​ቴ​ያ​ቸው መጠ​ብ​ጠብ ድምፅ፥ ከሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹም መሽ​ከ​ር​ከር፥ ከመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ቹም መት​መም የተ​ነሣ አባ​ቶች በእ​ጃ​ቸው ድካም ምክ​ን​ያት ወደ ልጆ​ቻ​ቸው አይ​መ​ለ​ሱም።</verse>
				<verse number="4">ይህም የሚ​ሆ​ነው ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ሁሉ ታጠፋ ዘንድ፥ ጢሮ​ስ​ንና ሲዶ​ናን የቀ​ሩ​ት​ንም ረዳ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ታጠፋ ዘንድ ስለ​ም​ት​መ​ጣው ቀን ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንና በከ​ፍ​ቶር ደሴት የቀ​ሩ​ትን ያጠ​ፋ​ልና።</verse>
				<verse number="5">ቡሀ​ነት በጋዛ ላይ መጥ​ቶ​አል፤ አስ​ቀ​ሎና ጠፋች፤ የዔ​ናቅ ቅሬ​ታ​ዎች ሆይ! እስከ መቼ ድረስ ገላ​ች​ሁን ትነ​ጫ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="6">አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ ሆይ! ዝም የማ​ት​ለው እስከ መቼ ነው? ወደ ሰገ​ባህ ግባ፤ ጸጥ ብለ​ህም ዕረፍ።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ስ​ቀ​ሎ​ናና በባ​ሕር ዳር በቀ​ሩ​ትም ቦታ​ዎች ላይ ትእ​ዛዝ ሰጥ​ቶ​አ​ልና፥ በዚ​ያም አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ታ​ልና እን​ዴት ዝም ትላ​ለህ? በዚያ ትነ​ሣ​ለህ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="48">
				<verse number="1">ስለ ሞአብ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ናባው ጠፍ​ታ​ለ​ችና ወዮ​ላት! ቂር​ያ​ታ​ይም አፍ​ራ​ለች፤ ተይ​ዛ​ማ​ለች፤ መጠ​ጊ​ያ​ዋም አፍ​ራ​ለች፤ ደን​ግ​ጣ​ማ​ለች።</verse>
				<verse number="2">ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የሞ​አብ ፈውስ የለም፤ በሐ​ሴ​ቦን ላይ፥ “ኑ ሕዝብ እን​ዳ​ት​ሆን እና​ጥ​ፋት” ብለው ክፉ ነገ​ርን አስ​በ​ው​ባ​ታል። ፈጽሞ ትተ​ዋ​ለች፤ ከኋ​ላዋ ሰይፍ ይመ​ጣ​ልና።</verse>
				<verse number="3">መፍ​ረ​ስና ታላቅ ጥፋት የሚል የጩ​ኸት ቃል ከሖ​ሮ​ና​ይም ተሰማ።</verse>
				<verse number="4">ሞአብ ጠፍ​ታ​ለች፤ ይህ​ንም በሴ​ጎር ተና​ገሩ።</verse>
				<verse number="5">በሎ​ዊት ዓቀ​በት ልቅሶ እያ​ለ​ቀሱ ይወ​ጣ​ሉና፥ በሖ​ሮ​ና​ይ​ምም መን​ገድ የመ​ባ​ባ​ትን ጩኸት ሰም​ተ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">“ሸሽ​ታ​ችሁ ራሳ​ች​ሁን አድኑ፤ እንደ ሜዳ አህያ በም​ድረ በዳ ተቀ​መጡ፤</verse>
				<verse number="7">በሥ​ራ​ሽና በመ​ዝ​ገ​ብሽ ታም​ነ​ሻ​ልና አንቺ ደግሞ ትያ​ዢ​ያ​ለሽ፤ ካሞ​ሽም ከካ​ህ​ና​ቱና ከአ​ለ​ቆቹ ጋር በአ​ን​ድ​ነት ይማ​ረ​ካል።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ፥ ጥፋት ወደ ከተማ ሁሉ ይመ​ጣል፤ አን​ዲ​ትም ከተማ አት​ድ​ንም፤ ሸለ​ቆ​ውም ይጠ​ፋል፤ ሜዳ​ውም ይበ​ላ​ሻል።</verse>
				<verse number="9">በርራ እን​ድ​ት​ወጣ ለሞ​አብ ክንፍ ስጡ​አት፤ ከተ​ሞ​ች​ዋም ባድማ ይሆ​ናሉ፤ የሚ​ኖ​ር​ባ​ቸ​ውም የለም።</verse>
				<verse number="10">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ በቸ​ልታ የሚ​ያ​ደ​ርግ ርጉም ይሁን፤ ሰይ​ፉ​ንም ከደም የሚ​ከ​ለ​ክል ርጉም ይሁን።</verse>
				<verse number="11">“ሞአብ ከል​ጅ​ነቷ ጀምራ ዐረ​ፈች፤ በክ​ብ​ር​ዋም ቅም​ጥል ነበ​ረች፤ ወይ​ን​ዋም ከዕቃ ወደ ዕቃ አል​ተ​ገ​ላ​በ​ጠም፤ ወደ ምር​ኮም አል​ሄ​ደ​ችም፤ ስለ​ዚህ ቃናው በእ​ር​ስዋ ውስጥ ቀር​ቶ​አል፤ መዓ​ዛ​ዋም አል​ተ​ለ​ወ​ጠም።</verse>
				<verse number="12">ስለ​ዚህ እነሆ ጠማ​ሞ​ችን የም​ል​ክ​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ር​ሱም ይጠ​ሙ​በ​ታል፤ ጋኖ​ቹ​ንም ይቀ​ጠ​ቅ​ጣሉ፤ ፊቀ​ኖ​ቹ​ንም ይሰ​ብ​ራሉ።</verse>
				<verse number="13">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ይታ​መ​ን​ባት ከነ​በ​ረው ከቤ​ቴል እን​ዳ​ፈረ፥ እን​ዲሁ ሞአብ ከካ​ሞሽ ታፍ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="14">እና​ንተ፦ እኛ ኀያ​ላን በሰ​ል​ፍም ጽኑ​ዓን ነን እን​ዴት ትላ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="15">ሞዓብ ፈር​ሳ​ለች፤ ከተ​ሞ​ቹ​ዋም ጠፍ​ተ​ዋል፤ የተ​መ​ረ​ጡ​ትም ጐል​ማ​ሶ​ችዋ ወደ መታ​ረድ ወር​ደ​ዋል፥ ይላል ስሙ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="16">የሞ​አብ ጥፋት ሊመጣ ቀር​ቦ​አል፤ መከ​ራ​ውም እጅግ ይፈ​ጥ​ናል።</verse>
				<verse number="17">በዙ​ሪ​ያው ያላ​ችሁ ሁሉ ስሙ​ንም የም​ታ​ውቁ ሁሉ፦ ታላቁ በትር፥ ጠን​ካ​ራ​ውም ሽመል፥ እን​ዴት ተሰ​በረ! ብላ​ችሁ አል​ቅ​ሱ​ለት።</verse>
				<verse number="18">በዲ​ቦን የም​ት​ኖሪ ሆይ! ሞአ​ብን የሚ​ያ​ጠፋ ወጥ​ቶ​ብ​ሻ​ልና፥ አም​ባ​ሽ​ንም ሰብ​ሮ​አ​ልና ከክ​ብ​ርሽ ውረጂ፤ በጭ​ቃም ላይ ተቀ​መጪ።</verse>
				<verse number="19">በአ​ሮ​ዔር የም​ት​ኖሪ ሆይ! በመ​ን​ገድ አጠ​ገብ ቆመሽ ተመ​ል​ከቺ፤ የሸ​ሸ​ው​ንና ያመ​ለ​ጠ​ውን፦ ምን ሆኖ​አል? ብለሽ ጠይ​ቂው።</verse>
				<verse number="20">“ሞአብ ፈር​ሳ​ለ​ችና አፈ​ረች፤ አል​ቅሱ፥ ጩኹም፤ ሞአብ እንደ ጠፋች በአ​ር​ኖን አውሩ።</verse>
				<verse number="21">ፍርድ ይመ​ጣል፤ በሜ​ሶር ምድር፥ በኬ​ሎን፥ በያ​ሳና፥ በሜ​ፍ​ዓት ላይ፤</verse>
				<verse number="22">በዲ​ቦን፥ በና​ባው፥ በቤ​ት​ዲ​ብ​ላ​ታ​ይም ላይ፥</verse>
				<verse number="23">በቂ​ር​ያ​ታ​ይም፥ በቤ​ት​ጋ​ሙል፥ በቤ​ት​ም​ዖን ላይ፥</verse>
				<verse number="24">በቂ​ር​ዮት፥ በቦ​ሶራ፥ በሞ​አ​ብም ምድር ከተ​ሞች ሁሉ ቅር​ብና ሩቅ በሆኑ ላይ ፍርድ መጥ​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="25">የሞ​አብ ቀንድ ተሰ​በረ፤ እጁም ተቀ​ጠ​ቀጠ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="26">“በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኰር​ቶ​አ​ልና፥ አስ​ክ​ሩት፤ ሞአ​ብም በት​ፋቱ ላይ ይን​ከ​ባ​ለ​ላል፤ በእ​ጁም ያጨ​በ​ጭ​ባል፤ ደግሞ መሳ​ቂያ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="27">እስ​ራ​ኤል ለአ​ንተ መሳ​ቂያ አል​ሆ​ነ​ምን? ወይስ በሌ​ቦች መካ​ከል ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልን? ስለ እርሱ በተ​ና​ገ​ርህ ጊዜ ራስ​ህን ትነ​ቀ​ን​ቃ​ለህ።</verse>
				<verse number="28">በሞ​አብ የሚ​ኖሩ ከተ​ሞ​ችን ትተው በዓ​ለት ውስጥ ተቀ​መጡ፤ በገ​ደል አፋ​ፍም ቤቷን እን​ደ​ም​ት​ሠራ እንደ ርግብ ሆኑ።</verse>
				<verse number="29">የሞ​አ​ብን ስድብ፥ የተ​ዋ​ረ​ደ​ው​ንም ብዙ ውር​ደ​ቱን፥ ልቡ​ና​ው​ንም ያስ​ታ​በ​የ​በ​ትን ትዕ​ቢ​ቱን ሰም​ተ​ናል።</verse>
				<verse number="30">እኔ ሥራ​ውን አው​ቃ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እንደ ኀይ​ሉም መጠን እን​ዲሁ ያደ​ረገ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="31">ሰለ​ዚህ ለሞ​አብ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ፤ ለሞ​አ​ብም ሁሉ እጮ​ኻ​ለሁ፤ ለቂ​ር​ሔ​ሬስ ሰዎች አለ​ቅ​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="32">አንቺ የሴ​ባማ ወይን ሆይ! የኢ​ያ​ዜ​ርን ልቅሶ ለአ​ንቺ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ችሽ ባሕ​ርን ተሻ​ግ​ረ​ዋል፤ ወደ ኢያ​ዜ​ርም ባሕር ደር​ሰ​ዋል፤ ሳይ​በ​ስል በሰ​ብ​ል​ሽና በወ​ይ​ንሽ ላይ ጥፋት መጥ​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="33">ሐሤ​ትና ደስታ ከፍ​ሬ​ያ​ማው እር​ሻና ከሞ​አብ ምድር ጠፍ​ተ​ዋል፤ ወይን ከመ​ጥ​መ​ቂ​ያው ጠፍ​ቶ​አል፤ በነ​ግህ የሚ​ጠ​ም​ቁት የለም፤ በሠ​ር​ክም የሚ​ያ​ደ​ር​ጉት የእ​ል​ልታ ድምፅ የለም።</verse>
				<verse number="34">ከሐ​ሴ​ቦን ጩኸት እስከ ኤሊ​ያ​ሊና እስከ ኢያሳ ድረስ ድም​ፃ​ቸ​ውን ሰጥ​ተ​ዋል፤ ከሴ​ጎር እስከ ሖሮ​ና​ይ​ምና እስከ ዔግ​ላት ሺሊ​ሺያ ድረስ ይደ​ር​ሳል፤ የኔ​ም​ሬም ውኃ ደር​ቋ​ልና።</verse>
				<verse number="35">ሞአ​ብ​ንና በኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ ላይ የሚ​ሠ​ዋ​ውን፥ ለአ​ማ​ል​ክ​ቱም የሚ​ያ​ጥ​ነ​ውን አጠ​ፋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="36">“ያተ​ረ​ፈው ትርፉ ጠፍ​ቶ​በ​ታ​ልና ስለ​ዚህ ልቤ ለሞ​አብ እንደ እን​ቢ​ልታ ይጮ​ኻል፤ ልቤም ለቂ​ር​ሔ​ሬስ ሰዎች እንደ እን​ቢ​ልታ ይጮ​ኻል፤</verse>
				<verse number="37">በሰው ሁሉ ራስ ላይ ቡሃ​ነት አለ፤ ጽሕ​ማ​ቸ​ውን ሁሉ ይላ​ጫሉ፤ እጆች ሁሉ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ሁሉም በወ​ገ​ባ​ቸው ማቅን ይታ​ጠ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="38">ሞአ​ብ​ንም ለም​ንም እን​ደ​ማ​ይ​ጠ​ቅም ዕቃ ሰብ​ሬ​አ​ለ​ሁና በሞ​አብ ሰገ​ነት ሁሉ ላይ፥ በአ​ደ​ባ​ባ​ዩም ላይ ልቅሶ አለ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="39">እን​ዴት ተለ​ወ​ጠች! ከእ​ፍ​ረ​ትም የተ​ነሣ ሞአብ ጀር​ባ​ዋን እን​ዴት መለ​ሰች! ሞአ​ብም በዙ​ሪ​ያዋ ላሉት ሁሉ መሳ​ቂ​ያና መሳ​ለ​ቂያ ትሆ​ና​ለች።</verse>
				<verse number="40">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “እነሆ እንደ ንስር ይበ​ር​ራል፤ ክን​ፉ​ንም በሞ​አብ ላይ ይዘ​ረ​ጋል።</verse>
				<verse number="41">ሐቄ​ር​ዮት ተያ​ዘች፤ አን​ባ​ዎ​ች​ዋም ተወ​ስ​ደ​ዋል፤ በዚ​ያም ቀን የሞ​አብ ኀያ​ላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="42">ሞአ​ብም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኰር​ታ​ለ​ችና ሕዝብ ከመ​ሆን ትጠ​ፋ​ለች።</verse>
				<verse number="43">በሞ​አብ የም​ት​ኖር ሆይ! ፍር​ሀ​ትና ጕድ​ጓድ፥ ወጥ​መ​ድም በአ​ንተ ላይ አሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤</verse>
				<verse number="44">እር​ስ​ዋን በም​ጐ​በ​ኝ​በት ዓመት በሞ​አብ ላይ ይህን አመ​ጣ​ለሁ፤ በፍ​ር​ሀት የሸሸ በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ ይወ​ድ​ቃል፤ ከጕ​ድ​ጓ​ድም የወጣ በወ​ጥ​መድ ይያ​ዛል፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="45">ከሰ​ልፍ የሸሹ ከሐ​ሴ​ቦን ጥላ በታች ቆመ​ዋል፤ እሳት ከሐ​ሴ​ቦን፥ ነበ​ል​ባ​ልም ከሴ​ዎን ወጥ​ቶ​አል፤ የሞ​አ​ብ​ንም ማዕ​ዘን፥ የሚ​ጮኹ ልጆ​ች​ንም ራስ በል​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="46">ሞአብ ሆይ! ወዮ​ልሽ! የካ​ሞሸ ወገን ጠፍ​ቶ​አል፤ ወን​ዶች ልጆ​ችሽ ተማ​ር​ከው ተወ​ስ​ደ​ዋ​ልና፥ ሴቶች ልጆ​ች​ሽም ወደ ምርኮ ሄደ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="47">ነገር ግን በኋ​ለ​ኛው ዘመን የሞ​አ​ብን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። የሞ​ዓብ ፍርድ እስ​ከ​ዚህ ድረስ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="49">
				<verse number="1">ስለ አሞን ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሚል​ኮም ጋድን ይወ​ርስ ዘንድ ሕዝ​ቡም በከ​ተ​ሞቹ ላይ ይቀ​መጥ ዘንድ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የሉ​ት​ምን? ወይስ ወራሽ የለ​ው​ምን?</verse>
				<verse number="2">ስለ​ዚህ እነሆ በአ​ሞን ልጆች ከተማ በራ​ባት ላይ የሰ​ልፍ ውካ​ታን የማ​ሰ​ማ​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለጥ​ፋ​ትም ትሆ​ና​ለች፥ መን​ደ​ሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላሉ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም የወ​ረ​ሱ​ትን ይወ​ር​ሳል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="3">ሐሴ​ቦን ሆይ! ጋይ ፈር​ሳ​ለ​ችና አል​ቅ​ሽ​ላት፤ እና​ን​ተም የራ​ባት ሴቶች ልጆች ሆይ! ሚል​ኮም፥ ካህ​ና​ቱና አለ​ቆ​ቹም በአ​ን​ድ​ነት ይማ​ረ​ካ​ሉና ጩኹ፤ ማቅም ታጠቁ፤ አል​ቅ​ሱም።</verse>
				<verse number="4">ማን ይመ​ጣ​ብ​ኛል ብለሽ በሀ​ብ​ትሽ የታ​መ​ንሽ አንቺ ከዳ​ተኛ ልጅ ሆይ! በጠፉ ሸለ​ቆ​ዎ​ችሽ ስለ ምን ትመ​ኪ​ያ​ለሽ?</verse>
				<verse number="5">እነሆ በዙ​ሪ​ያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ ፍር​ሀ​ትን አመ​ጣ​ብ​ሻ​ለሁ፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም በፊ​ታ​ችሁ ወዳ​ለው ስፍራ ትሰ​ደ​ዳ​ላ​ችሁ፤ የሚ​ሸ​ሹ​ት​ንም የሚ​ሰ​በ​ስብ የለም።</verse>
				<verse number="6">ነገር ግን ከዚያ በኋላ የአ​ሞ​ንን ልጆች ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”</verse>
				<verse number="7">ስለ ኤዶ​ም​ያስ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በውኑ በቴ​ማን ጥበብ የለ​ምን? ከብ​ል​ሃ​ተ​ኞ​ችስ ምክር ጠፍ​ቶ​አ​ልን? ጥበ​ባ​ቸ​ውስ አል​ቆ​አ​ልን?</verse>
				<verse number="8">እና​ንተ በድ​ዳን የም​ት​ኖሩ ሆይ! የዔ​ሳ​ውን ጥፋት፥ የም​ጐ​በ​ኝ​በ​ትን ጊዜ አመ​ጣ​በ​ታ​ለ​ሁና ሽሹ፤ ወደ ኋላም ተመ​ለሱ፤ በጥ​ል​ቅም ጕድ​ጓድ ውስጥ ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="9">ወይን ለቃ​ሚ​ዎች ቢመ​ጡ​ብህ፥ ቃር​ሚ​ያ​ውን አይ​ተ​ዉ​ል​ህ​ምን? ሌቦ​ችስ በሌ​ሊት ቢመጡ፥ የሚ​ያ​ጠ​ፉት እስ​ኪ​በ​ቃ​ቸው ድረስ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="10">እኔ ግን ዔሳ​ውን አራ​ቆ​ት​ሁት፤ የተ​ሸ​ሸ​ጉ​ት​ንም ስፍ​ራ​ዎች ገለ​ጥሁ፤ ይሸ​ሸ​ግም ዘንድ አይ​ች​ልም፤ ዘሩም፤ ወን​ድ​ሞ​ቹም፤ ጎረ​ቤ​ቶ​ቹም ጠፍ​ተ​ዋል፥ እር​ሱም የለም።</verse>
				<verse number="11">ድሃ​አ​ደ​ጎ​ች​ህን ተው፤ እኔም በሕ​ይ​ወት አኖ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ መበ​ለ​ቶ​ች​ህም በእኔ ይታ​መ​ናሉ።</verse>
				<verse number="12">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ እነሆ ጽዋ​ውን ያል​ተ​ገ​ባ​ቸው ሰዎች ጠጥ​ተ​ው​ታል፤ አን​ተም መን​ጻ​ትን ትነ​ጻ​ለ​ህን? እን​ግ​ዲህ አት​ነ​ጻም መጠ​ጣ​ትን ትጠ​ጣ​ለ​ህና።</verse>
				<verse number="13">ባሶራ ምድረ በዳ፥ መሰ​ደ​ቢ​ያና መረ​ገ​ሚ​ያም እን​ድ​ት​ሆን በራሴ ምያ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከተ​ሞ​ች​ዋም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባድማ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="14">“ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መስ​ማ​ትን ሰም​ቻ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛብ ሀገ​ሮች ተሰ​ብ​ሰቡ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ላይ ኑ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ውጓት፥ የሚል መል​እ​ክ​ተኛ ተል​ኳል።</verse>
				<verse number="15">እነሆ በሕ​ዝብ ዘንድ የተ​ጠ​ቃህ፥ በሰ​ዎ​ችም ዘንድ የተ​ና​ቅህ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">በዓ​ለት ንቃ​ቃት ውስጥ የም​ት​ቀ​መጥ፥ የተ​ራ​ራ​ውን ከፍታ የም​ት​ይዝ ሆይ! ድፍ​ረ​ት​ህና የል​ብህ ኵራት አነ​ሣ​ሥ​ተ​ው​ሃል። ቤት​ህ​ንም ምንም እንደ ንስር ከፍ ብታ​ደ​ርግ፥ ከዚያ አወ​ር​ድ​ሃ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="17">“ኤዶ​ም​ያ​ስም ምድረ በዳ ትሆ​ና​ለች፤ የሚ​ያ​ል​ፍ​ባ​ትም ሁሉ ይደ​ነ​ቃል፤ ስለ መጣ​ባ​ትም መቅ​ሠ​ፍት ሁሉ ያፍ​ዋ​ጭ​ባ​ታል።</verse>
				<verse number="18">ሰዶ​ምና ገሞራ፥ በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የነ​በ​ሩት ከተ​ሞች እንደ ተገ​ለ​በጡ፥ ይላል ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እን​ዲሁ በዚያ ሰው አይ​ቀ​መ​ጥም፤ የሰው ልጅም አይ​ኖ​ር​ባ​ትም።</verse>
				<verse number="19">እነሆ ከእ​ር​ስዋ ዘንድ በቶሎ አባ​ር​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ዳር ወደ ኤታም እንደ አን​በሳ ይወ​ጣል፤ ጐል​ማ​ሶ​ች​ንም በእ​ር​ስዋ ላይ እሾ​ማ​ለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜን የሚ​ወ​ስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚ​ቃ​ወም እረኛ ማን ነው?”</verse>
				<verse number="20">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኤ​ዶ​ም​ያስ ላይ የመ​ከ​ረ​ባ​ትን ምክር፥ በቴ​ማ​ንም በሚ​ኖሩ ስዎች ላይ ያሰ​ባ​ትን ዐሳብ ስሙ፤ ትን​ን​ሾች በጎ​ችን ዘር​ፈው ይወ​ስ​ዷ​ቸ​ዋል፤ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ት​ንም ማደ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ባድማ ያደ​ር​ጉ​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="21">ከመ​ው​ደ​ቃ​ቸው ድምፅ የተ​ነሣ ምድር ደነ​ገ​ጠች፤ ድም​ፅ​ዋም እንደ ባሕር ድምፅ እነሆ ተሰማ።</verse>
				<verse number="22">እነሆ እንደ ንስር ወጥቶ ይመ​ለ​ከ​ታል፤ ክን​ፉ​ንም በባ​ሶራ ላይ ይዘ​ረ​ጋል፤ በዚ​ያም ቀን የኤ​ዶ​ም​ያስ ኀያ​ላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="23">“ስለ ደማ​ስቆ፤ ክፉ ወሬ ሰም​ተ​ዋ​ልና ሐማ​ትና አር​ፋድ አፈሩ፤ ቀለ​ጡም፤ እንደ ባሕ​ርም ተነ​ዋ​ወጡ፤ ያር​ፉም ዘንድ አይ​ች​ሉም።</verse>
				<verse number="24">ደማ​ስቆ ደከ​መች፤ ተሸ​ብ​ራም ሸሸች፤ እን​ቅ​ጥ​ቅ​ጥም ያዛት፤ እንደ ወላ​ድም ሴት ጣርና ምጥ ያዛት።</verse>
				<verse number="25">የወ​ደ​ዱ​ትን ቦታና ከተማ እን​ዴት አል​ተ​ዉ​ላ​ትም?</verse>
				<verse number="26">ስለ​ዚህ ጐበ​ዛ​ዝቷ በአ​ደ​ባ​ባ​ይዋ ላይ ይወ​ድ​ቃሉ፤ በዚ​ያም ቀን ሰል​ፈ​ኞች ሁሉ ይወ​ድ​ቃሉ፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="27">በደ​ማ​ስ​ቆም ቅጥር ላይ እሳት አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የወ​ልደ አዴ​ር​ንም አዳ​ራ​ሾች ትበ​ላ​ለች።”</verse>
				<verse number="28">የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ስለ መታ​ቸው ስለ ቄዳ​ርና ስለ አሦር መን​ግ​ሥ​ታት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ተነሡ ወደ ቄዳ​ርም ውጡ፤ የም​ሥ​ራ​ቅ​ንም ልጆች አጥፉ።</verse>
				<verse number="29">ድን​ኳ​ና​ቸ​ው​ንና በጎ​ቻ​ቸ​ውን ይወ​ስ​ዳሉ፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንና ዕቃ​ቸ​ውን ሁሉ፥ ግመ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለራ​ሳ​ቸው ይወ​ስ​ዳሉ፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ሁሉ ጥፋ​ትን ጥሩ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="30">እና​ንተ በአ​ሦር የም​ት​ኖሩ ሆይ! የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ተማ​ክ​ሮ​ባ​ች​ኋ​ልና፥ ክፉ አሳ​ብ​ንም አስ​ቦ​ባ​ች​ኋ​ልና ሽሹ፤ ወደ ሩቅም ሂዱ፤ በጥ​ልቅ ጕድ​ጓ​ድም ውስጥ ተቀ​መጡ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="31">“ተነሡ፤ ዕረ​ፍት ወዳ​ለ​በት፥ ተዘ​ል​ሎም ወደ ተቀ​መ​ጠው፥ ደጅና መዝ​ጊያ፥ መወ​ር​ወ​ሪ​ያም ወደ​ሌ​ለው፥ ብቻ​ው​ንም ወደ ተቀ​መ​ጠው ሕዝብ ዝመቱ።</verse>
				<verse number="32">ግመ​ሎ​ቻ​ቸው ለም​ርኮ ይሆ​ናሉ፤ የእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ብዛት ለጥ​ፋት ይሆ​ናል፤ ጠጕ​ራ​ቸ​ው​ንም በዙ​ሪያ የሚ​ላ​ጩ​ትን ሰዎች ወደ ነፋ​ሳት ሁሉ እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከዳ​ር​ቻ​ቸው ሁሉ ጥፋት አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥</verse>
				<verse number="33">አሦ​ርም የወ​ፎች መኖ​ሪ​ያና የዘ​ለ​ዓ​ለም ባድማ ትሆ​ና​ለች፤ በዚ​ያም ሰው አይ​ኖ​ርም፤ የሰው ልጅም አይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም።</verse>
				<verse number="34">በይ​ሁዳ ንጉሥ በሴ​ዴ​ቅ​ያስ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዓመተ መን​ግ​ሥት ስለ ኤላም ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው።</verse>
				<verse number="35">“የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ዋና የኀ​ይ​ላ​ቸው መሣ​ሪያ የሆ​ነ​ውን የኤ​ላ​ምን ቀስት እሰ​ብ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="36">ከአ​ራ​ቱም ከሰ​ማይ ማዕ​ዘ​ናት አራ​ቱን ነፋ​ሳት በኤ​ላም ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ ወደ እነ​ዚ​ያም ነፋ​ሳት ሁሉ እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከኤ​ላም የተ​ሰ​ደዱ ሰዎች የማ​ይ​ደ​ር​ሱ​በት ሕዝብ አይ​ገ​ኝም።</verse>
				<verse number="37">በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ነፍ​ሳ​ቸ​ውን በሚ​ሹ​አት ፊት ኤላ​ምን አስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ለሁ። ክፉ ነገ​ርን እር​ሱም ጽኑ ቍጣ​ዬን አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እስ​ካ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም ድረስ በኋ​ላ​ቸው ሰይ​ፍን እሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="38">ዙፋ​ኔ​ንም በኤ​ላም አኖ​ራ​ለሁ፤ ከዚ​ያም ንጉ​ሡ​ንና መሳ​ፍ​ን​ቱን አጠ​ፋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="39">ነገር ግን በኋ​ለ​ኛው ዘመን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ የኤ​ላ​ምን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="50">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር በባ​ቢ​ሎን ላይ በነ​ቢዩ በኤ​ር​ም​ያስ የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">“ለአ​ሕ​ዛብ ተና​ገሩ፤ አው​ሩም፤ ዓላ​ማ​ው​ንም አንሡ፥ አት​ደ​ብቁ፦ ባቢ​ሎን ተያ​ዘች፤ ቤል አፈረ፤ ሜሮ​ዳክ ፈራች፤ ምስ​ሎ​ች​ዋም አፈሩ፤ ጣዖ​ታ​ቷም ደነ​ገጡ፤ በሉ።</verse>
				<verse number="3">ሕዝቤ ከሰ​ሜን በእ​ር​ስዋ ላይ ወጥ​ት​ዋል፤ ምድ​ር​ዋ​ንም ባድማ ያደ​ር​ጋል፤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም አይ​ገ​ኝም፤ ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ ድረስ ሸሽ​ተው ሄደ​ዋል።</verse>
				<verse number="4">“በዚ​ያም ወራት በዚ​ያም ጊዜ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና የይ​ሁዳ ልጆች በአ​ን​ድ​ነት ሆነው ይመ​ጣሉ፤ እያ​ለ​ቀ​ሱም መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ይሄ​ዳሉ፥ አም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ል​ጋሉ።</verse>
				<verse number="5">ወደ ጽዮን የሚ​ሄ​ዱ​በ​ትን ጎዳና ይመ​ረ​ም​ራሉ፤ ፊታ​ቸ​ው​ንም ወደ ሀገ​ራ​ቸው ይመ​ል​ሳሉ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል​ኪ​ዳን አይ​ረ​ሳ​ምና መጥ​ተው ወደ ፈጣ​ሪ​ያ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይማ​ጠ​ናሉ።</verse>
				<verse number="6">“ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነ​ዋል፤ እረ​ኞ​ቻ​ቸው አሳ​ቱ​አ​ቸው፤ በተ​ራ​ሮ​ችም ላይ የተ​ቅ​በ​ዘ​በዙ አደ​ረ​ጉ​አ​ቸው፤ ከተ​ራራ ወደ ኮረ​ብታ ዐለፉ፤ በረ​ታ​ቸ​ው​ንም ረሱ።</verse>
				<verse number="7">ያገ​ኙ​አ​ቸው ሁሉ በሉ​አ​ቸው፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፦ በጽ​ድቅ ማደ​ሪያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ፥ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ተስፋ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኀጢ​አት ስለ ሠሩ እኛ አና​ሳ​ር​ፋ​ቸ​ውም አሉ።</verse>
				<verse number="8">ከባ​ቢ​ሎን መካ​ከል ሽሹ፤ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ምድር ውጡ፤ በበ​ጎ​ችም ፊት እንደ እባ​ቦች ሁኑ።</verse>
				<verse number="9">እነሆ ከሰ​ሜን ምድር የታ​ላ​ላቅ አሕ​ዛ​ብን ጉባኤ አነ​ሣ​ለሁ፤ በባ​ቢ​ሎ​ንም ላይ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ላይ ይሰ​ለ​ፋሉ፤ ከዚ​ያም ትወ​ሰ​ዳ​ለች፤ ፍላ​ጾ​ቻ​ቸ​ውም ባዶ​ውን እን​ደ​ማ​ይ​መ​ለስ እንደ ብልህ ተዋጊ ፍላጻ ናቸው።</verse>
				<verse number="10">የከ​ላ​ው​ዴ​ዎን ምድር ትዘ​ረ​ፋ​ለች፤ የማ​ረ​ኳ​ትም ሁሉ ይጠ​ግ​ባሉ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="11">“ርስ​ቴን የም​ት​በ​ዘ​ብዙ እና​ንተ ሆይ! ደስ ብሎ​አ​ች​ኋ​ልና፥ ሐሤ​ት​ንም አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና፥ በመ​ስክ ላይም እን​ዳ​ለች ጊደር ሆና​ችሁ ተቀ​ና​ጥ​ታ​ች​ኋ​ልና፥ እንደ ብር​ቱ​ዎ​ችም በሬ​ዎች ቷጋ​ላ​ች​ሁና፤</verse>
				<verse number="12">እና​ታ​ችሁ እጅግ ታፍ​ራ​ለች፤ የወ​ለ​ደ​ቻ​ች​ሁም ትጐ​ሰ​ቍ​ላ​ለች፤ እነሆ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ኋለ​ኛ​ዪቱ ትሆ​ና​ለች፤ ምድረ በዳና ደረቅ ምድር፥ በረ​ሀም ትሆ​ና​ለች።</verse>
				<verse number="13">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ የተ​ነሣ ባድማ ትሆ​ና​ለች እንጂ ሰው አይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም፤ በባ​ቢ​ሎ​ንም በኩል የሚ​ያ​ልፍ ሁሉ ይደ​ነ​ቃል፤ በመ​ጣ​ባ​ትም መቅ​ሠ​ፍት ሁሉ ያፍ​ዋ​ጫል።</verse>
				<verse number="14">“እና​ንተ ቀስ​ትን የም​ት​ገ​ትሩ ሰዎች ሁሉ፥ በባ​ቢ​ሎን ላይ በዙ​ሪ​ያዋ ተሰ​ለፉ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኀጢ​አት ሠር​ታ​ለ​ችና ወር​ው​ሩ​ባት፤ እር​ስ​ዋ​ንም ከመ​ው​ጋት ቸል አት​በሉ፤</verse>
				<verse number="15">እጆ​ችዋ ደክ​መ​ዋ​ልና ክበ​ቡ​አት፤ ግንቧ ወድ​ቋል፤ ቅጥ​ር​ዋም ፈር​ሶ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀል ነውና ተበ​ቀ​ሏት፤ እንደ ሠራ​ች​ውም ሥሩ​ባት።</verse>
				<verse number="16">ዘሪ​ው​ንና በመ​ከር ጊዜ ማጭድ የሚ​ይ​ዘ​ውን ከባ​ቢ​ሎን አጥፉ፤ ከአ​ረ​ማ​ዊው ሰይፍ ፊት የተ​ነሣ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ወገኑ ይመ​ለ​ሳል፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ ሀገሩ ይሸ​ሻል።</verse>
				<verse number="17">“እስ​ራ​ኤል የባ​ዘነ በግ ነው፤ አን​በ​ሶች አሳ​ደ​ዱት፤ መጀ​መ​ሪያ የአ​ሦር ንጉሥ በላው፥ በመ​ጨ​ረ​ሻም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር አጥ​ን​ቱን ቈረ​ጠ​መው።”</verse>
				<verse number="18">ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የአ​ሦ​ርን ንጉሥ እንደ ተበ​ቀ​ልሁ እን​ዲሁ እነሆ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉ​ሥና ምድ​ሩን እበ​ቀ​ላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ወደ ማሰ​ማ​ር​ያው እመ​ል​ሳ​ለሁ፥ በቀ​ር​ሜ​ሎ​ስና በባ​ሳን፥ በኤ​ፍ​ሬም ተራ​ራና በገ​ለ​ዓ​ድም ይሰ​ማ​ራል፤ ነፍ​ሱም ትጠ​ግ​ባ​ለች።</verse>
				<verse number="20">በዚያ ወራት በዚ​ያም ዘመን፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ዚ​ህን በም​ድር የተ​ረ​ፉ​ትን ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና የእ​ስ​ራ​ኤል በደል ይፈ​ለ​ጋል፤ አይ​ኖ​ር​ምም፤ የይ​ሁ​ዳም ኀጢ​አት ይፈ​ለ​ጋል፥ ምንም አይ​ገ​ኝም።</verse>
				<verse number="21">“በላ​ይ​ዋና በሚ​ኖ​ሩ​ባት ላይ በም​ሬት ውጡ፤ ሰይፍ ሆይ! ተበ​ቀዪ፥ ፍጻ​ሜ​ያ​ቸ​ው​ንም አጥፊ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ያዘ​ዝ​ሁ​ሽ​ንም ሁሉ አድ​ርጊ።</verse>
				<verse number="22">የሰ​ል​ፍና የታ​ላቅ ጥፋት ውካታ በም​ድር ላይ አለ።</verse>
				<verse number="23">ምድ​ርን ሁሉ የም​ት​ፈ​ጫት መዶሻ እን​ዴት ደቀ​ቀች! እን​ዴ​ትስ ተሰ​በ​ረች! ባቢ​ሎ​ንስ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እን​ዴት ባድማ ሆነች!</verse>
				<verse number="24">ባቢ​ሎን ሆይ! በመ​ከ​ራው ተይ​ዘሽ ጠፋሽ፤ አን​ቺም ይህ እን​ደ​መ​ጣ​ብሽ አላ​ወ​ቅ​ሽም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተቃ​ው​መ​ሽ​ዋ​ልና ተገ​ኝ​ተ​ሻል፤ ተይ​ዘ​ሽ​ማል።</verse>
				<verse number="25">የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር ይሠራ ዘንድ ሥራ አለ​ውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዕቃ ቤቱን ከፍቶ የቍ​ጣ​ውን ዕቃ ጦር አው​ጥ​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="26">ጊዜዋ ደር​ሶ​አ​ልና ሣጥ​ኖ​ች​ዋን ከፍ​ታ​ችሁ እንደ ዋሻ በር​ብ​ሯት፤ ጨር​ሳ​ች​ሁም አጥ​ፏት፥ ምንም አታ​ስ​ቀ​ሩ​ላት።</verse>
				<verse number="27">ፍሬ​ዋን ሁሉ አድ​ር​ቁ​ባት፤ ወደ መታ​ረ​ድም ይው​ረዱ፤ ቀና​ቸው ደር​ሳ​ለ​ችና፥ እነ​ሱን የሚ​በ​ቀ​ሉ​በት ጊዜ ደር​ሷ​ልና ወዮ​ላ​ቸው!</verse>
				<verse number="28">የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በቀል፥ የመ​ቅ​ደ​ሱ​ንም በቀል፥ በጽ​ዮን ይነ​ግሩ ዘንድ ሸሽ​ተው ከባ​ቢ​ሎን ሀገር ያመ​ለ​ጡት ሰዎች ድምፅ ተሰ​ም​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="29">“ቀስ​ትን የሚ​ገ​ትሩ ቀስ​ተ​ኞ​ችን ሁሉ በባ​ቢ​ሎን ላይ ጥሩ​አ​ቸው፤ በዙ​ሪ​ያዋ ስፈ​ሩ​ባት፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ሰዎች አንድ አያ​ም​ልጥ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተቃ​ው​ማ​ለ​ችና እንደ ሥራዋ መጠን መል​ሱ​ላት፤ እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ችም ሁሉ አድ​ር​ጉ​ባት።</verse>
				<verse number="30">ስለ​ዚህ ጐበ​ዛ​ዝቷ በአ​ደ​ባ​ባ​ይዋ ላይ ይወ​ድ​ቃሉ፤ በዚ​ያም ቀን ሰል​ፈ​ኞ​ችዋ ሁሉ ይጠ​ፋሉ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="31">ትዕ​ቢ​ተኛ ሆይ! አን​ቺን የሚ​በ​ቀ​ሉ​በት ጊዜ፥ ቀንሽ ደር​ሶ​አ​ልና እነሆ በአ​ንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="32">አንቺ ትዕ​ቢ​ተኛ ሆይ!፥ ትደ​ክ​ሚ​ያ​ለሽ፤ ትወ​ድ​ቂ​ያ​ለ​ሽም፤ የሚ​ያ​ነ​ሳ​ሽም የለም፤ በዛ​ፎ​ችሽ ውስጥ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በዙ​ሪ​ያሽ ያለ​ው​ንም ሁሉ ትበ​ላ​ለች።”</verse>
				<verse number="33">የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና የይ​ሁዳ ልጆች በአ​ን​ድ​ነት ተገ​ፍ​ተ​ዋል፤ የማ​ረ​ኩ​አ​ቸ​ውም ሁሉ በኀ​ይል ይይ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ ይለ​ቅ​ቁ​አ​ቸ​ውም ዘንድ እንቢ ብለ​ዋል።</verse>
				<verse number="34">የሚ​ቤ​ዢ​አ​ቸው ብርቱ ነው፤ ስሙም ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ምድ​ርን ያሳ​ርፍ ዘንድ፥ በባ​ቢ​ሎ​ንም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ያውክ ዘንድ ጠላ​ቶ​ቹን ወቀሳ ይወ​ቅ​ሳ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="35">ሰይፍ በከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንና በባ​ቢ​ሎን በሚ​ኖሩ ላይ፥ በመ​ሳ​ፍ​ን​ቶ​ች​ዋና በጥ​በ​በ​ኞ​ችዋ ላይ አለ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="36">ሰይፍ በተ​ዋ​ጊ​ዎ​ችዋ ላይ አለ፤ እነ​ር​ሱም ይደ​ክ​ማሉ። ሰይ​ፍም በኀ​ያ​ላ​ኖ​ችዋ ላይ አለ፤ እነ​ር​ሱም ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="37">ሰይፍ በፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውና በሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸው ላይ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ዋም በተ​ቀ​ላ​ቀሉ ሕዝብ ላይ አለ፤ እነ​ር​ሱም እንደ ሴቶች ይሆ​ናሉ፤ ሰይፍ በመ​ዝ​ገ​ቦ​ችዋ ላይ አለ፤ ይበ​ተ​ና​ሉም።</verse>
				<verse number="38">እር​ስዋ የተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎች ምድር ናትና፥ እነ​ር​ሱም በደ​ሴ​ቶ​ችዋ ይመ​ካ​ሉና ሰይፍ በው​ኆ​ችዋ ላይ አለ፤ እነ​ር​ሱም ይደ​ር​ቃሉ።</verse>
				<verse number="39">ስለ​ዚህ የዱር አራ​ዊት ከተ​ኵ​ላ​ዎች ጋር ይቀ​መ​ጡ​ባ​ታል፤ ሰጎ​ኖ​ችም ይቀ​መ​ጡ​ባ​ታል፤ ሰውም ከዚያ ወዲያ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም፤ እስከ ልጅ ልጅም ድረስ የሚ​ኖ​ር​ባት የለም።</verse>
				<verse number="40">ሰዶ​ም​ንና ገሞ​ራን፥ በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የነ​በ​ሩ​ትን ከተ​ሞች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገለ​በ​ጣ​ቸው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እን​ዲሁ ሰው በዚያ አይ​ቀ​መ​ጥም፤ የሰ​ውም ልጅ አይ​ኖ​ር​ባ​ትም።</verse>
				<verse number="41">“እነሆ ሕዝብ ከሰ​ሜን ይመ​ጣል፤ ታላቅ ሕዝ​ብና ብዙ ነገ​ሥ​ታ​ትም ከም​ድር ዳርቻ ይነ​ሣሉ።</verse>
				<verse number="42">ቀስ​ትና ጦርን ይይ​ዛሉ፤ ጨካ​ኞች ናቸው፤ ምሕ​ረ​ትም አያ​ደ​ር​ጉም፤ ድም​ፃ​ቸው እንደ ባሕር ይተ​ም​ማል፤ በፈ​ረ​ሶ​ችም ላይ ይቀ​መ​ጣሉ፤ የባ​ቢ​ሎን ሴት ልጅ ሆይ እንደ እሳት በአ​ንቺ ላይ ይሰ​ለ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="43">የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ውካ​ታ​ቸ​ውን ሰም​ቶ​አል፤ እጁም ደክ​ማ​ለች፤ ምጥ ወላድ ሴትን እን​ደ​ሚ​ይ​ዛ​ትም ጭን​ቀት ይዞ​ታል፤</verse>
				<verse number="44">እነሆ ከእ​ር​ስዋ ዘንድ በቶሎ አባ​ር​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና እንደ አን​በሳ ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ዳር ወደ ኤታም ምድር ይወ​ጣል፤ ጐል​ማ​ሶ​ቹ​ንም ሁሉ በእ​ር​ስዋ ላይ እሾ​ማ​ለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜን የሚ​ወ​ስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚ​ቋ​ቋም እረኛ ማን ነው?</verse>
				<verse number="45">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በባ​ቢ​ሎን ላይ የመ​ከ​ረ​ባ​ትን ምክር፥ በከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ምድር ላይ ያሰ​ባ​ትን ዐሳብ ስሙ፤ በእ​ው​ነት የበ​ጎ​ቻ​ቸ​ቸው ጠቦ​ቶች ይጠ​ፋሉ፤ በእ​ው​ነት ማደ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ባድማ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="46">ባቢ​ሎ​ንን ከያ​ዝ​ዋት ሰዎች ድምፅ የተ​ነሣ ምድር ተና​ወ​ጠች፤ ጩኸ​ትም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ተሰማ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="51">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ በባ​ቢ​ሎን ላይና በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር በሚ​ኖ​ሩት ላይ የሚ​ያ​ቃ​ጥ​ልና የሚ​ያ​ጠፋ ነፋ​ስን አስ​ነ​ሣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">በባ​ቢ​ሎ​ንም ላይ ተሳ​ዳቢ ሰዎ​ችን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይሰ​ድ​ቧ​ታል፤ ምድ​ር​ዋ​ንም ባዶ ያደ​ር​ጋሉ፤ በመ​ከ​ራም ቀን በዙ​ሪ​ያዋ ይከ​ብ​ቡ​አ​ታል።</verse>
				<verse number="3">በቀ​ስት ወር​ዋ​ሪው ላይ፥ በጥ​ሩ​ርም በሚ​ነ​ሣው ላይ ቀስ​ተ​ኛው ቀስ​ቱን ይገ​ትር፤ ለጐ​በ​ዛ​ዝቷ አት​ዘኑ፤ ሠራ​ዊ​ቷ​ንም ሁሉ አጥፉ።</verse>
				<verse number="4">የተ​ገ​ደ​ሉት በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር ይወ​ድ​ቃሉ፤ የቈ​ሰ​ሉ​ትም በውጭ ይወ​ድ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="5">“ምድ​ራ​ቸው በእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ላይ በተ​ሠ​ራው በደል የተ​ሞ​ላች ብት​ሆ​ንም፥ እስ​ራ​ኤል መበ​ለት አል​ሆ​ነ​ችም፤ ይሁ​ዳም ከአ​ም​ላኩ ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ አል​ራ​ቀም።</verse>
				<verse number="6">ከባ​ቢ​ሎን መካ​ከል ሽሹ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም ነፍ​ሳ​ች​ሁን አድኑ፤ በበ​ደ​ልዋ አት​ጥፉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀል ጊዜ ነውና፥ እር​ሱም ብድ​ራ​ቷን ይከ​ፍ​ላ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="7">ባቢ​ሎን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ውስጥ ምድ​ርን ሁሉ ያሰ​ከ​ረች የወ​ርቅ ጽዋ ነበ​ረች፤ አሕ​ዛ​ብም ከጠ​ጅዋ ጠጥ​ተ​ዋል፤ ስለ​ዚህ አሕ​ዛብ ተን​ገ​ዳ​ግ​ደ​ዋል።</verse>
				<verse number="8">ባቢ​ሎን በድ​ን​ገት ወድቃ ተሰ​ባ​ብ​ራ​ለች፤ አል​ቅ​ሱ​ላት፤ ትፈ​ወ​ስም እንደ ሆነ ለቍ​ስ​ልዋ መድ​ኀ​ኒት ውሰ​ዱ​ላት።</verse>
				<verse number="9">ባቢ​ሎ​ንን ፈወ​ስ​ናት፥ እር​ስዋ ግን አል​ተ​ፈ​ወ​ሰ​ችም፤ ፍር​ድዋ እስከ ሰማይ ደር​ሶ​አ​ልና፥ እስከ ከዋ​ክ​ብ​ትም ድረስ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፥ እን​ተ​ዋት፤ ሁላ​ች​ንም ወደ ሀገ​ራ​ችን እን​ሂድ።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍር​ዳ​ች​ንን አው​ጥ​ቶ​አል፤ ኑ በጽ​ዮን የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ እን​ና​ገር።</verse>
				<verse number="11">“ፍላ​ጾ​ችን አዘ​ጋጁ፤ ጕራ​ን​ጕ​ሬ​ዎ​ች​ንም ሙሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጠ​ፋት ዘንድ ቍጣው በባ​ቢ​ሎን ላይ ነውና የሜ​ዶ​ንን ንጉሥ መን​ፈስ አስ​ነ​ሥ​ቶ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀል የመ​ቅ​ደሱ በቀል ነውና።</verse>
				<verse number="12">በባ​ቢ​ሎን ቅጥ​ሮች ላይ ዓላ​ማ​ውን አንሡ፤ ከጕ​ራ​ን​ጕ​ሬ​አ​ችሁ ጋር ጽኑ፤ ተመ​ል​ካ​ቾ​ችን አቁሙ፤ መሣ​ሪ​ያ​ች​ሁን አዘ​ጋጁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በባ​ቢ​ሎን በሚ​ኖ​ሩት ላይ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ያደ​ርግ ዘንድ ጀም​ሮ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="13">አንቺ በብዙ ውኃ አጠ​ገብ የተ​ቀ​መ​ጥሽ፥ በመ​ዝ​ገ​ብም የበ​ለ​ጠ​ግሽ ሆይ! እንደ ስስ​ትሽ መጠን ፍጻ​ሜሽ ደር​ሶ​አል።</verse>
				<verse number="14">የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል በራሱ ምሎ​አል፦ በእ​ው​ነት ሰዎ​ችን እንደ አን​በጣ እሞ​ላ​ብ​ሻ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም እየ​ሮጡ ይወ​ር​ዱ​ብ​ሻል።”</verse>
				<verse number="15">ምድ​ርን በኀ​ይሉ የፈ​ጠረ፥ ዓለ​ሙን በጥ​በቡ የመ​ሠ​ረተ፥ ሰማ​ያ​ት​ንም በማ​ስ​ተ​ዋሉ የዘ​ረጋ እርሱ ነው።</verse>
				<verse number="16">ድም​ፁን ባሰማ ጊዜ ውኆች በሰ​ማይ ይታ​ወ​ካሉ፤ ከም​ድ​ርም ዳር ደመ​ና​ትን ያወ​ጣል፤ ለዝ​ና​ብም ጊዜ መብ​ረ​ቅን ያደ​ር​ጋል፤ ነፋ​ስ​ንም ከቤተ መዛ​ግ​ብቱ ያወ​ጣል።</verse>
				<verse number="17">ሰው ሁሉ ዕው​ቀ​ትን አጥ​ቶ​አል፥ አን​ጥ​ረ​ኛም ሁሉ ከቀ​ረ​ጸው ምስል የተ​ነሣ አፍ​ሮ​አል፤ ሐሰ​ተ​ኞች ጣዖ​ታ​ትን ሠር​ተ​ዋ​ልና፥ እስ​ት​ን​ፋ​ስም የላ​ቸ​ው​ምና።</verse>
				<verse number="18">ሥራ​ቸው ከንቱ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጐ​በ​ኛ​ቸው ጊዜ ይጠ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="19">የያ​ዕ​ቆብ ዕድል ፋንታ እንደ እነ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ እርሱ የሁሉ ፈጣሪ ነውና። እስ​ራ​ኤ​ልም የር​ስቱ ነገድ ነው። ስሙም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።</verse>
				<verse number="20">“አንቺ የጦር መሣ​ሪ​ያን በተ​ን​ሽ​ብኝ፤ እኔም ሕዝ​ቡን እበ​ት​ን​ብ​ሻ​ለሁ፤ ከአ​ን​ቺም ነገ​ሥ​ታ​ትን አስ​ወ​ግ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="21">በአ​ንቺ ፈረ​ሱ​ንና ፈረ​ሰ​ኛ​ውን እበ​ት​ና​ለሁ፤ በአ​ን​ቺም ሰረ​ገ​ላ​ው​ንና በላዩ የሚ​ቀ​መ​ጠ​ውን እበ​ት​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="22">በአ​ን​ቺም ወን​ድና ሴትን እበ​ት​ና​ለሁ፤ በአ​ን​ቺም ሽማ​ግ​ሌ​ው​ንና ብላ​ቴ​ና​ውን እበ​ት​ና​ለሁ፤ በአ​ን​ቺም ጐል​ማ​ሳ​ው​ንና ቆን​ጆ​ዪ​ቱን እበ​ት​ና​ለሁ፤</verse>
				<verse number="23">በአ​ን​ቺም እረ​ኛ​ው​ንና መን​ጋ​ውን እበ​ት​ና​ለሁ፤ በአ​ን​ቺም አራ​ሹ​ንና ጥማ​ዱን እበ​ት​ና​ለሁ፤ በአ​ን​ቺም አለ​ቆ​ች​ንና መሳ​ፍ​ን​ትን እበ​ት​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="24">በጽ​ዮን በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት ስለ ሠሩት ክፋ​ታ​ቸው ሁሉ በባ​ቢ​ሎ​ንና በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="25">“አንተ ምድ​ርን ሁሉ የም​ታ​ጠፋ አጥፊ ተራራ ሆይ! እነሆ፥ እኔ በአ​ንተ ላይ ነኝ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እጄ​ንም እዘ​ረ​ጋ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ከድ​ን​ጋ​ዮ​ቹም ላይ አን​ከ​ባ​ል​ል​ሃ​ለሁ፤ የተ​ቃ​ጠ​ለም ተራራ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="26">ከአ​ን​ተም ለማ​ዕ​ዘን የሚ​ሆን ድን​ጋ​ይ​ንና ለመ​ሠ​ረት የሚ​ሆን ድን​ጋ​ይን አይ​ወ​ስ​ዱም፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አጠ​ፋ​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="27">“በም​ድር ላይ ዓላ​ማን አንሡ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል መለ​ከ​ትን ንፉ፤ አሕ​ዛ​ብ​ንም ለዩ​ባት፤ የአ​ራ​ራ​ት​ንና የሚ​ኒን የአ​ስ​ከ​ና​ዝ​ንም መን​ግ​ሥ​ታት እዘ​ዙ​ባት፤ ጦረ​ኞ​ች​ንም በላ​ይዋ አቁሙ፤ ብዛ​ታ​ቸው እንደ አን​በጣ የሆኑ ፈረ​ሶ​ችን በላ​ይዋ አውጡ።</verse>
				<verse number="28">አሕ​ዛ​ብ​ንም፥ የሜ​ዶ​ን​ንም ነገ​ሥ​ታት፥ አለ​ቆ​ች​ንም፥ መሳ​ፍ​ን​ት​ንም ሁሉ፥ የግ​ዛ​ታ​ቸ​ው​ንም ምድር ሁሉ ለዩ​ባት።</verse>
				<verse number="29">ማንም እን​ዳ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባት የባ​ቢ​ሎ​ንን ምድር ባድማ ያደ​ር​ጋት ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐሳብ በባ​ቢ​ሎን ላይ ጸን​ቶ​አ​ልና ምድር ተና​ወ​ጠች፤ ታመ​መ​ችም።</verse>
				<verse number="30">የባ​ቢ​ሎን ተዋ​ጊ​ዎች መዋ​ጋ​ትን ትተ​ዋል፤ በአ​ም​ባ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ውስጥ ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ኀይ​ላ​ቸ​ውም ጠፍ​ቶ​አል፤ እንደ ሴቶ​ችም ሆነ​ዋል፤ ማደ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ነድ​ደ​ዋል፤ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ተሰ​ብ​ረ​ዋል።</verse>
				<verse number="31">ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ይነ​ግር ዘንድ ሯጩ ሯጩን ለመ​ገ​ና​ኘት፤ መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውም መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውን ለመ​ገ​ና​ኘት ይሮ​ጣል፤ ከተ​ማዋ ከዳር እስከ ዳር ተይ​ዛ​ለ​ችና፤</verse>
				<verse number="32">መሻ​ገ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ተይ​ዘ​ዋ​ልና፥ ቅጥ​ር​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ሎ​አ​ልና፥ ሰል​ፈ​ኞ​ችም ተማ​ር​ከ​ዋ​ልና።”</verse>
				<verse number="33">የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ቤት እንደ ተረ​ገጠ አው​ድማ ናት፤ ጥቂት ቈይታ የመ​ከር ጊዜ ይደ​ር​ስ​ባ​ታል።</verse>
				<verse number="34">የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በላኝ፤ ከፋ​ፈ​ለ​ኝም፤ እንደ ባዶ ዕቃም አደ​ረ​ገኝ፤ እንደ ዘን​ዶም ዋጠኝ፤ ከሚ​ጣ​ፍ​ጠ​ውም ሥጋዬ ሆዱን ሞላ።</verse>
				<verse number="35">በጽ​ዮን የም​ት​ኖር በእኔ ላይ የተ​ደ​ረገ ግፍና ሥቃይ በባ​ቢ​ሎን ላይ ይሁን ትላ​ለች፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ደሜ በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር በሚ​ኖ​ሩት ላይ ይሁን ትላ​ለች።”</verse>
				<verse number="36">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ የሚ​ገ​ፋ​ሽን እፈ​ር​ድ​በ​ታ​ለሁ፤ በቀ​ል​ሽ​ንም እበ​ቀ​ል​ል​ሻ​ለሁ፤ ባሕ​ር​ዋ​ንም ድርቅ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ምን​ጭ​ዋ​ንም አደ​ር​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="37">ባቢ​ሎ​ንም ባድ​ማና የቀ​በሮ ማደ​ሪያ፥ ማፍ​ዋ​ጫም ትሆ​ና​ለች፤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም ሰው አይ​ገ​ኝም።</verse>
				<verse number="38">በአ​ን​ድ​ነ​ትም እንደ አን​በ​ሶች ያገ​ሣሉ፤ እንደ አን​በ​ሳም ደቦ​ሎች ያጕ​ረ​መ​ር​ማሉ።</verse>
				<verse number="39">በሞ​ቃ​ቸው ጊዜ እን​ዲ​ዝሉ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም እን​ቅ​ልፍ እን​ዲ​ተኙ መጠ​ጥን አጠ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አሰ​ክ​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም፤ ከዚ​ያም በኋላ አይ​ነ​ቁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="40">እንደ ጠቦ​ቶ​ችና እንደ አውራ በጎች፥ እንደ አውራ ፍየ​ሎ​ችም ወደ መታ​ረድ አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="41">“የም​ድ​ርም ሁሉ ክብር እን​ዴት ተያ​ዘች! እን​ዴ​ትስ ተወ​ሰ​ደች! ባቢ​ሎን በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እን​ዴት ለጥ​ፋት ሆነች!</verse>
				<verse number="42">ባሕር በባ​ቢ​ሎን ላይ ወጣ፤ በሞ​ገ​ዱም ብዛት ተከ​ደ​ነች።</verse>
				<verse number="43">ከተ​ሞ​ችዋ ባድ​ማና ደረቅ ምድር፥ ሰውም የማ​ይ​ቀ​መ​ጥ​በት፥ የሰ​ውም ልጅ የማ​ያ​ል​ፍ​በት ምድር ሆኑ።</verse>
				<verse number="44">በባ​ቢ​ሎ​ንም ላይ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤ የዋ​ጠ​ች​ው​ንም ከአ​ፍዋ አስ​ተ​ፋ​ታ​ለሁ፤ አሕ​ዛ​ብም ከዚያ ወዲያ ወደ እር​ስዋ አይ​ሰ​በ​ሰ​ቡም፤ የባ​ቢ​ሎ​ንም ቅጥ​ሮች ይወ​ድ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="45">“ሕዝቤ ሆይ! ከመ​ካ​ከ​ልዋ ውጡ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽኑ ቍጣ ራሳ​ች​ሁን አድኑ።</verse>
				<verse number="46">በም​ድ​ርም ከሚ​ሰማ ወሬ የተ​ነሣ አት​ፍሩ፤ ልባ​ች​ሁም የዛለ አይ​ሁን፤ በአ​ንድ ዓመት ወሬ ይመ​ጣል፤ ከዚ​ያም በኋላ በሌ​ላው ዓመት ወሬ ይመ​ጣል፤ በም​ድ​ርም ላይ ግፍ ይነ​ግ​ሣል፤ አለ​ቃም በአ​ለቃ ላይ ይነ​ሣል።</verse>
				<verse number="47">ስለ​ዚህ እነሆ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ትን የባ​ቢ​ሎ​ንን ምስ​ሎች የም​በ​ቀ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፤ ምድ​ር​ዋም ሁሉ ትደ​ር​ቃ​ለች፤ ተዋ​ግ​ተ​ውም የሞ​ቱት ሁሉ በመ​ካ​ከ​ልዋ ይወ​ድ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="48">አጥ​ፊ​ዎች ከሰ​ሜን ይመ​ጡ​ባ​ታ​ልና ሰማ​ይና ምድር፥ በእ​ነ​ር​ሱም ያለው ሁሉ ስለ ባቢ​ሎን ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="49">ባቢ​ሎ​ንም በእ​ስ​ራ​ኤል ስለ ተገ​ደ​ሉት ትወ​ድ​ቃ​ለች፤ ስለ ባቢ​ሎ​ንም በም​ድር ሁሉ የተ​ገ​ደ​ሉት ይወ​ድ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="50">“ከሰ​ይፍ ያመ​ለ​ጣ​ችሁ ሆይ! ሂዱ፤ አት​ቁሙ፤ በሩቅ ያላ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አስቡ፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም በል​ባ​ችሁ አስቡ።</verse>
				<verse number="51">ስድ​ባ​ች​ንን ስለ ሰማን አፍ​ረ​ናል፤ ባዕ​ዳን ሰዎ​ችም ወደ ቤተ መቅ​ደ​ሳ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ገብ​ተ​ዋ​ልና ውር​ደት ፊታ​ች​ንን ከድ​ኖ​ታል።</verse>
				<verse number="52">ስለ​ዚህ እነሆ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ትን ምስ​ሎ​ች​ዋን የም​በ​ቀ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በም​ድ​ር​ዋም ሁሉ የተ​ገ​ደ​ሉት ይወ​ድ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="53">ባቢ​ሎ​ንም ወደ ሰማይ ብት​ወጣ፥ ቅፅ​ሮ​ች​ዋ​ንም በኀ​ይ​ልዋ ብታ​ጸና፥ ከእኔ ዘንድ አጥ​ፊ​ዎች ይመ​ጡ​ባ​ታል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="54">“ከባ​ቢ​ሎን የጩ​ኸት ድምፅ፥ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ምድር የታ​ላቅ ጥፋት ድምፅ ተሰ​ም​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="55">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባቢ​ሎ​ንን አጥ​ፍ​ቶ​አ​ታ​ልና፥ ከእ​ር​ስ​ዋም ሞገዱ እንደ ብዙ ውኃ​ዎች የሚ​ተ​መ​ውን ታላ​ቁን ድምፅ ዝም አሰ​ኝ​ቶ​አ​ልና፤ የድ​ም​ፃ​ቸው ጩኸት ተሰ​ም​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="56">ጥፋት በባ​ቢ​ሎን ላይ መጥ​ቶ​ባ​ታ​ልና፥ ተዋ​ጊ​ዎ​ችዋ ተያዙ፤ ቀስ​ታ​ቸ​ውም ተሰ​ባ​በረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተበ​ቅ​ሎ​አ​ቸ​ዋ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍዳን ከፍ​ሎ​አ​ቸ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="57">መሳ​ፍ​ን​ቶ​ች​ዋ​ንና ጥበ​በ​ኞ​ች​ዋ​ንም፥ አለ​ቆ​ች​ዋ​ንና ሹሞ​ች​ዋን፥ ኀያ​ላ​ኖ​ች​ዋ​ንም አሰ​ክ​ራ​ለሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አን​ቀ​ላ​ፍ​ተው አይ​ነ​ቁም ይላል ስሙ ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ለው ንጉሥ።</verse>
				<verse number="58">የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሰፊው የባ​ቢ​ሎን ቅጥር ፈጽሞ ይፈ​ር​ሳል፤ ረጃ​ጅ​ሞች በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላሉ፤ ሕዝቡ ለከ​ንቱ ይደ​ክ​ማሉ፤ አሕ​ዛ​ብም በመ​ጀ​መ​ሪያ በእ​ሳት ያል​ቃሉ።”</verse>
				<verse number="59">የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ በነ​ገሠ በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት ከእ​ርሱ ዘንድ ወደ ባቢ​ሎን በሄደ ጊዜ ለማ​ሴው ልጅ ለኔ​ርዩ ልጅ ለሠ​ራያ ነቢዩ ኤር​ም​ያስ ያዘ​ዘው ቃል ይህ ነው።</verse>
				<verse number="60">ሠራ​ያም የቤቱ አዛዥ ነበረ፤ በባ​ቢ​ሎ​ንም ላይ የሚ​መ​ጣ​ውን ክፉ ነገር ሁሉ፥ ስለ ባቢ​ሎን የተ​ጻ​ፈ​ውን ይህን ቃል ሁሉ ኤር​ም​ያስ በአ​ንድ መጽ​ሐፍ ላይ ጻፈው።</verse>
				<verse number="61">ኤር​ም​ያ​ስም ሠራ​ያን እን​ዲህ አለው፥ “ወደ ባቢ​ሎን በገ​ባህ ጊዜ እይ፤ ይህ​ንም ቃል ሁሉ አን​ብ​ብና፦</verse>
				<verse number="62">አቤቱ! ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ ድረስ ማንም እን​ዳ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባት፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ባድማ እን​ድ​ት​ሆን ታጠ​ፋት ዘንድ በዚች ስፍራ ላይ ተና​ግ​ረ​ሃል በል።</verse>
				<verse number="63">ይህ​ንም መጽ​ሐፍ ማን​በብ ከፈ​ጸ​ምህ በኋላ፥ ድን​ጋ​ይን እሰ​ር​በት፤ በኤ​ፍ​ራ​ጥ​ስም ወንዝ ውስጥ ጣለው።</verse>
				<verse number="64">አን​ተም፦ እኔ ከማ​መ​ጣ​ባት ክፉ ነገር የተ​ነሣ እን​ዲሁ ባቢ​ሎን ትሰ​ጥ​ማ​ለች፤ አት​ነ​ሣ​ምም በል።” የኤ​ር​ም​ያስ ቃል እስ​ከ​ዚህ ድረስ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="52">
				<verse number="1">ሴዴ​ቅ​ያስ መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አንድ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም አሚ​ጣል የተ​ባ​ለች የል​ብና ሰው የኤ​ር​ም​ያስ ልጅ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="2">ኢዮ​አ​ቄ​ምም እን​ዳ​ደ​ረገ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="3">ከፊ​ቱም አው​ጥቶ እስ​ኪ​ጥ​ላ​ቸው ድረስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ላይ ሆኖ​አ​ልና፤ ሴዴ​ቅ​ያ​ስም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።</verse>
				<verse number="4">ሴዴ​ቅ​ያ​ስም በነ​ገሠ በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርና ሠራ​ዊቱ ሁሉ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ መጥ​ተው ከበ​ቡ​አት፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም አራት ክንድ ግንብ ሠራ።</verse>
				<verse number="5">ከተ​ማ​ዪ​ቱም እስከ ንጉሡ እስከ ሴዴ​ቅ​ያስ እስከ ዐሥራ አን​ደ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት ድረስ ተከ​ብባ ነበር።</verse>
				<verse number="6">በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ወር በዘ​ጠ​ነ​ኛው ቀን በከ​ተ​ማ​ዪቱ ራብ ጸንቶ ነበር፤ ለሀ​ገ​ሩም ሰዎች እን​ጀራ ታጣ።</verse>
				<verse number="7">ከተ​ማ​ዪ​ቱም ተሰ​በ​ረች፤ ሰል​ፈ​ኞ​ችም ሁሉ ሸሹ፤ በሁ​ለ​ቱም ቅጥር መካ​ከል ባለው በር ወደ ንጉሥ አት​ክ​ልት በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ በሌ​ሊት ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ወጡ። ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዙሪያ ነበሩ፤ በዓ​ረ​ባም መን​ገድ ሄዱ።</verse>
				<verse number="8">የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ሠራ​ዊት ንጉ​ሡን ተከ​ታ​ተ​ሉት፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም ሜዳ ሴዴ​ቅ​ያ​ስን ያዙ፤ ሠራ​ዊ​ቱም ሁሉ ከእ​ርሱ ዘንድ ተበ​ት​ነው ነበር።</verse>
				<verse number="9">ንጉ​ሡ​ንም ይዘው የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ወዳ​ለ​ባት በኤ​ማት ምድር ወዳ​ለ​ችው ወደ ዴብ​ላታ አመ​ጡት፤ እር​ሱም ፍር​ድን በእ​ርሱ ላይ ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="10">የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ የሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስን ልጆች በፊቱ ገደ​ላ​ቸው፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም አለ​ቆች ሁሉ ደግሞ በዴ​ብ​ላታ ገደ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">የሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስ​ንም ዐይ​ኖች አወጣ፤ የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በሰ​ን​ሰ​ለት አሰ​ረው፤ ወደ ባቢ​ሎ​ንም ወሰ​ደው፤ እስ​ኪ​ሞ​ትም ድረስ በግ​ዞት ቤት አኖ​ረው።</verse>
				<verse number="12">በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በዐ​ሥራ ዘጠ​ነ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ፊት የሚ​ቆ​መው የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ።</verse>
				<verse number="13">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የን​ጉ​ሡን ቤት አቃ​ጠለ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቤቶች ሁሉ ፥ ታላ​ላ​ቆ​ችን ቤቶች ሁሉ፥ በእ​ሳት አቃ​ጠለ።</verse>
				<verse number="14">ከአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ጋር የነ​በ​ረው የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሠራ​ዊት ሁሉ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ቅጥር ሁሉ ዙሪ​ያ​ዋን አፈ​ረሱ።</verse>
				<verse number="15">የአ​ዛ​ዦ​ቹም አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን የሕ​ዝ​ቡን ድኆች፥ በከ​ተ​ማም ውስጥ የቀ​ረ​ውን ሕዝብ፥ ሸሽ​ተ​ውም ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ የተ​ጠ​ጉ​ትን፥ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ቅሬታ አመጣ።</verse>
				<verse number="16">የአ​ዛ​ዦ​ቹም አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ከሀ​ገሩ ድኆች ወይን ተካ​ዮ​ችና አራ​ሾች እን​ዲ​ሆኑ አስ​ቀረ።</verse>
				<verse number="17">ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የነ​በ​ሩ​ትን የናስ ዐም​ዶች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የነ​በ​ሩ​ትን መቀ​መ​ጫ​ዎ​ችና የና​ሱን ኩሬ ሰባ​በሩ፤ ናሱ​ንም ወደ ባቢ​ሎን ወሰዱ።</verse>
				<verse number="18">ምን​ቸ​ቶ​ቹ​ንና መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ችን፥ መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ንና ድስ​ቶ​ችን፥ ጭል​ፋ​ዎ​ች​ንም፥ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ት​ንም የናስ ዕቃ ሁሉ ወሰዱ።</verse>
				<verse number="19">የአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ጽዋ​ዎ​ቹን፥ ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹን፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንና ምን​ቸ​ቶ​ቹን፥ መቅ​ረ​ዞ​ቹ​ንና ጭል​ፋ​ዎ​ቹን፥ መን​ቀ​ሎ​ች​ንም፥ የወ​ር​ቁን ዕቃ በወ​ርቅ፥ የብ​ሩ​ንም ዕቃ በብር አድ​ርጎ፥ ወሰደ።</verse>
				<verse number="20">ንጉሡ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ያሠ​ራ​ቸ​ውን ሁለ​ቱን ዐም​ዶች፥ አን​ዱ​ንም ኵሬ፥ ከመ​ቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹም በታች የነ​በ​ሩ​ትን ዐሥራ ሁለ​ቱን የናስ በሬ​ዎች ወሰደ፤ ለእ​ነ​ዚህ የናስ ዕቃ​ዎች ሁሉ ሚዛን አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="21">ዐም​ዶ​ቹም፥ የአ​ንዱ ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስም​ንት ክንድ ነበረ፥ የዙ​ሪ​ያ​ውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ ውፍ​ረ​ቱም ጋት ያህል ነበረ፤ ባዶም ነበረ።</verse>
				<verse number="22">የና​ሱም ጕል​ላት በላዩ ነበረ፤ የአ​ን​ዱም ጕል​ላት ቁመት አም​ስት ክንድ ነበረ፤ በጕ​ል​ላ​ቱም ላይ በዙ​ሪ​ያው ሁሉ ከናስ የተ​ሠሩ መር​በ​ብና ሮማ​ኖች ነበ​ሩ​በት፤ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ዐምድ ደግሞ እን​ደ​ዚህ ያለ ነገ​ርና ሮማ​ኖች ነበ​ሩ​በት።</verse>
				<verse number="23">በስተ ውጭም ዘጠና ስድ​ስት ሮማ​ኖች ነበሩ፤ በመ​ር​በ​ቡም ዙሪያ የነ​በሩ ሮማ​ኖች ሁሉ አንድ መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="24">የአ​ዛ​ዦ​ቹም አለቃ ታላ​ቅን ካህን ሠራ​ያን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ካህን ሶፎ​ን​ያ​ስን፥ ሦስ​ቱ​ንም በረ​ኞች ወሰደ፤</verse>
				<verse number="25">ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በሰ​ል​ፈ​ኞች ላይ ተሾ​መው ከነ​በ​ሩት አን​ዱን ጃን​ደ​ረባ፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ከሚ​ገ​ኙት በን​ጉሡ ፊት ከሚ​ቆ​ሙት ሰባ​ቱን ሰዎች፥ የሀ​ገ​ሩን ሕዝብ የሚ​ያ​ሰ​ል​ፈ​ውን የሠ​ራ​ዊ​ቱን አለቃ ጸሐፊ፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ከተ​ገ​ኙት የሀ​ገሩ ሕዝብ ስድሳ ሰዎ​ችን ወሰደ።</verse>
				<verse number="26">የአ​ዛ​ዦ​ቹም አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ወስዶ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ወዳ​ለ​በት ወደ ዴብ​ላታ ወሰ​ዳ​ቸው።</verse>
				<verse number="27">የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ መታ​ቸው፤ በኤ​ማ​ትም ምድር ባለ​ችው በዴ​ብ​ላታ ገደ​ላ​ቸው፤ እን​ዲሁ ይሁዳ ከሀ​ገሩ ተማ​ረከ።</verse>
				<verse number="28">ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር የማ​ረ​ከው ሕዝብ ይህ ነው፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ሦስት ሺህ ሃያ ሦስት አይ​ሁድ፤</verse>
				<verse number="29">ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት ስም​ንት መቶ ሠላሳ ሁለት ነፍስ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ማር​ኮ​አል፤</verse>
				<verse number="30">በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በሃያ ሦስ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የአ​ዛ​ዦቹ አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ከአ​ይ​ሁድ ሰባት መቶ አርባ አም​ስት ነፍስ ማር​ኮ​አል፤ ሰዎ​ችም ሁሉ አራት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበሩ።</verse>
				<verse number="31">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢኮ​ን​ያን በተ​ማ​ረከ በሠ​ላሳ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት፥ በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሃያ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን፥ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ዮር​ማ​ሮ​ዴቅ በነ​ገሠ በአ​ን​ደ​ኛው ዓመት የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የኢ​ኮ​ን​ያ​ንን ራስ ከፍ ከፍ አደ​ረገ፤ ከወ​ህ​ኒም አወ​ጣው፤</verse>
				<verse number="32">በመ​ል​ካ​ምም ተና​ገ​ረው፤ ዙፋ​ኑ​ንም ከእ​ርሱ ጋር በባ​ቢ​ሎን ከነ​በ​ሩት ነገ​ሥ​ታት ዙፋን በላይ አደ​ረ​ገ​ለት።</verse>
				<verse number="33">በወ​ህ​ኒም ውስጥ ለብ​ሶት የነ​በ​ረ​ውን ልብስ ለወ​ጠ​ለት፥ ኢኮ​ን​ያ​ንም በሕ​ይ​ወቱ ዘመን ሁሉ በፊቱ ሁል​ጊዜ እን​ጀራ ይበላ ነበር።</verse>
				<verse number="34">የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በሕ​ይ​ወቱ ዘመን ሁሉ እስ​ኪ​ሞት ድረስ የዘ​ወ​ትር ድርጎ ዕለት ዕለት ይሰ​ጠው ነበር።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="25">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">አሌፍ። ሕዝብ ሞል​ቶ​ባት የነ​በ​ረች ከተማ ብቻ​ዋን እን​ዴት ተቀ​መ​ጠች! በአ​ሕ​ዛብ ተመ​ልታ የነ​በ​ረች እንደ መበ​ለት ሆና​ለች፤ አሕ​ዛ​ብን ትገዛ የነ​በ​ረች፥ አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ንም ትገዛ የነ​በ​ረች ገባር ሆና​ለች።</verse>
				<verse number="2">ቤት። በሌ​ሊት እጅግ ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ እን​ባ​ዋም በጉ​ን​ጭዋ ላይ አለ፤ ከሚ​ያ​ፈ​ቅ​ሩ​አት ሁሉ የሚ​ያ​ጽ​ና​ናት የለም፤ ወዳ​ጆ​ች​ዋም ሁሉ ወነ​ጀ​ሉ​አት፤ ጠላ​ቶ​ችም ሆኑ​አት።</verse>
				<verse number="3">ጋሜል። ይሁዳ ስለ ውር​ደ​ቷና ስለ ባር​ነቷ ብዛት ተሰ​ደ​ደች፤ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ተቀ​መ​ጠች፤ ዕረ​ፍ​ትም አላ​ገ​ኘ​ችም፤ የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አት ሁሉ በሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አት መካ​ከል ያዙ​ዋት።</verse>
				<verse number="4">ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓል የሚ​መጣ የለ​ምና የጽ​ዮን መን​ገ​ዶች አለ​ቀሱ፤ በሮ​ችዋ ሁሉ ፈር​ሰ​ዋል፤ ካህ​ና​ቷም ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ደና​ግ​ሎ​ች​ዋም ተማ​ረኩ፤ እር​ስ​ዋም በም​ሬት አለች።</verse>
				<verse number="5">ሄ። ስለ ኀጢ​አቷ ብዛት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዋ​ር​ዶ​አ​ታ​ልና የሚ​ዘ​ባ​በ​ቱ​ባት በራ​ስዋ ላይ ሆኑ፤ ጠላ​ቶ​ች​ዋም ተደ​ሰቱ፤ ሕፃ​ና​ቶ​ች​ዋም በአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች ፊት ተማ​ር​ከ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">ዋው። ከጽ​ዮን ሴት ልጅ ውበት ሁሉ ተወ​ስ​ዶ​አል፤ አለ​ቆ​ችዋ መሰ​ማ​ሪያ እን​ደ​ማ​ያ​ገኙ አውራ በጎች ሆኑ፤ ከሚ​ያ​ባ​ር​ሩ​አ​ቸው ፊት ተዳ​ክ​መው ሄዱ።</verse>
				<verse number="7">ዛይ። ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ቀድሞ ወድዳ በሠ​ራ​ችው ሥራ ሁሉ የመ​ከ​ራ​ዋን ወራት አሰ​በች፤ ሕዝ​ብዋ በአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች እጅ በወ​ደቀ ጊዜ፥ የሚ​ረ​ዳ​ትም በሌ​ላት ጊዜ፥ አስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች አዩ​አት፤ በመ​ፍ​ረ​ስ​ዋም ሳቁ።</verse>
				<verse number="8">ሔት። ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እጅግ ኀጢ​አት ሠር​ታ​ለች፤ ስለ​ዚህ ረክ​ሳ​ለች፤ በተ​ጨ​ነ​ቀ​ች​በት ቦታ ያከ​ብ​ሩ​አት የነ​በሩ ሁሉ ውር​ደ​ቷን አይ​ተ​ዋ​ልና አቃ​ለ​ሉ​አት፤ እር​ስ​ዋም እየ​ጮ​ኸች ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ ወደ ኋላ​ዋም ዘወር አለች።</verse>
				<verse number="9">ጤት። ግዳ​ጅዋ ከእ​ግ​ርዋ በታች ነበረ፤ ፍጻ​ሜ​ዋን አላ​ሰ​በ​ችም፤ ከባድ ሸክ​ምን ተሸ​ከ​መች፤ የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ትም የለም፤ አቤቱ! ጠላት ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና መከ​ራ​ዬን ተመ​ል​ከት።</verse>
				<verse number="10">ዮድ። አስ​ጨ​ና​ቂው በም​ኞቷ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ፤ ወደ ጉባ​ኤህ እን​ዳ​ይ​ገቡ ያዘ​ዝ​ሃ​ቸው አሕ​ዛብ ወደ መቅ​ደ​ስዋ ሲገቡ አይ​ታ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="11">ካፍ። ሕዝ​ብዋ ሁሉ እን​ጀራ አጥ​ተው ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ለማ​በ​ር​ታት ፍላ​ጎ​ታ​ቸ​ውን ስለ መብል ሰጥ​ተ​ዋል፤ አቤቱ! ተጐ​ሳ​ቍ​ያ​ለ​ሁና እይ፤ ተመ​ል​ከ​ትም።</verse>
				<verse number="12">ላሜድ። እና​ንተ መን​ገድ ዐላ​ፊ​ዎች ሁሉ! በእ​ና​ንተ ዘንድ ምንም የለ​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽኑ ቍጣው ቀን እኔን እን​ዳ​ስ​ጨ​ነ​ቀ​በት በእኔ ላይ እንደ ተደ​ረ​ገው እንደ እኔ ቍስል የሚ​መ​ስል ቍስል እን​ዳለ ተመ​ል​ከቱ፤ እዩም።</verse>
				<verse number="13">ሜም። ከላይ እሳ​ትን ሰደደ፤ አጥ​ን​ቶ​ች​ንም አቃ​ጠለ፤ ለእ​ግሬ ወጥ​መድ ዘረጋ፤ ወደ ኋላም መለ​ሰኝ፥ አጠ​ፋ​ኝም፤ ቀኑ​ንም ሁሉ መከራ አጸ​ና​ብኝ።</verse>
				<verse number="14">ኖን። በእጄ ስለ​ተ​ታቱ ኀጢ​አ​ቶች ተጋ፤ በአ​ን​ገቴ ላይ ወጥ​ተ​ዋል፤ ጕል​በቴ ደከመ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቋ​ቋ​መው በማ​ል​ች​ለው መከራ እጅ ሰጥ​ቶ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="15">ሳም​ኬት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀያ​ላ​ኖ​ችን ሁሉ ከመ​ካ​ከሌ አስ​ወ​ገ​ዳ​ቸው፤ ምር​ጦ​ችን ያደ​ቅቅ ዘንድ ጊዜን ጠራ​ብኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድን​ግ​ሊ​ቱን የይ​ሁ​ዳን ልጅ በመ​ጭ​መ​ቂያ እን​ደ​ሚ​ጨ​መቅ ወይን ረገ​ጣት። ስለ​ዚ​ህም አለ​ቅ​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">ዔ። የሚ​ያ​ጽ​ና​ናኝ፥ ነፍ​ሴ​ንም የሚ​መ​ል​ሳት ከእኔ ርቆ​አ​ልና ዐይኔ ውኃ ያፈ​ስ​ሳል። ጠላት በር​ት​ቶ​አ​ልና ልጆች ጠፍ​ተ​ዋል።</verse>
				<verse number="17">ፌ። ጽዮን እጅ​ዋን ዘረ​ጋች፤ የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ትም የለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በያ​ዕ​ቆብ ዙሪያ ያሉ​ትን እን​ዲ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁት አዘዘ፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው እንደ ረከ​ሰች ሆና​ለች።</verse>
				<verse number="18">ጻዴ። ቃሉን አማ​ር​ሬ​አ​ለ​ሁና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድቅ ነው። እና​ንተ አሕ​ዛብ ሁሉ እባ​ካ​ችሁ ስሙ፤ መከ​ራ​ዬ​ንም ተመ​ል​ከቱ፤ ደና​ግ​ሎ​ችና ጐል​ማ​ሶች ተማ​ር​ከው ሄደ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="19">ቆፍ። ወዳ​ጆ​ችን ጠራሁ፤ እነ​ር​ሱም ቸል አሉኝ፤ ካህ​ና​ቶ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ያበ​ረቱ ዘንድ መብል ሲፈ​ልጉ በከ​ተማ ውስጥ ሳያ​ገኙ አለቁ።</verse>
				<verse number="20">ሬስ። አቤቱ! ተጨ​ን​ቄ​አ​ለ​ሁና፥ አን​ጀ​ቴም ታው​ኮ​ብ​ኛ​ልና ተመ​ል​ከት፤ መራራ ኀዘን አዝ​ኛ​ለ​ሁና ልቤ በው​ስጤ ተገ​ላ​በ​ጠ​ብኝ፤ በሜዳ ሰይፍ አመ​ከ​ነ​ችኝ፤ በቤ​ትም ሞት አለ።</verse>
				<verse number="21">ሣን። እኔ እን​ደ​ማ​ለ​ቅስ ሰም​ተ​ዋል፤ የሚ​ያ​ጽ​ና​ናኝ የለም፤ ጠላ​ቶች ሁሉ መከ​ራ​ዬን ሰም​ተ​ዋል፤ አንተ አድ​ር​ገ​ኸ​ዋ​ልና ደስ አላ​ቸው፤ ስለ እርሱ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ቃል ታመ​ጣ​ለህ፤ እነ​ር​ሱም እንደ እኔ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="22">ታው። ልቅ​ሶዬ እጅግ ነውና፥ ልቤም ደክ​ሞ​አ​ልና፥ ክፋ​ታ​ቸው ሁሉ ወደ ፊትህ ይድ​ረስ፥ ስለ ኀጢ​አቴ ሁሉ እኔን እንደ ቃረ​ም​ኸኝ እነ​ር​ሱን ቃር​ማ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">አሌፍ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት የጽ​ዮ​ንን ሴት ልጅ ምንኛ አጠ​ቈ​ራት! የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ክብር ከሰ​ማይ ወደ ምድር ጣለ፤ በቍ​ጣ​ውም ቀን የእ​ግ​ሩን መረ​ገጫ አላ​ሰ​በም።</verse>
				<verse number="2">ቤት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የያ​ዕ​ቆ​ብን መል​ካም ነገር ሁሉ አሰ​ጠመ፤ አል​ራ​ራ​ምም፤ በመ​ዓቱ የይ​ሁ​ዳን ሴት ልጅ አን​ባ​ዎች አፈ​ረሰ፤ ወደ ምድ​ርም አወ​ረ​ዳ​ቸው፤ መን​ግ​ሥ​ቷ​ንና ግዛ​ቷ​ንም አረ​ከሰ።</verse>
				<verse number="3">ጋሜል። በጽኑ ቍጣው የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቀንድ ሁሉ ቀጠ​ቀጠ፤ ቀኝ እጁ​ንም ከጠ​ላት ፊት ወደ ኋላ መለሰ፤ እንደ እሳት ነበ​ል​ባል ያዕ​ቆ​ብን አቃ​ጠለ፤ በዙ​ሪ​ያው ያለ​ው​ንም ሁሉ በላ።</verse>
				<verse number="4">ዳሌጥ። ቀስ​ቱን እንደ ተቃ​ዋሚ ጠላት ገተረ፤ እንደ ባላ​ጋ​ራም ቀኝ እጁን አጸና፤ በጽ​ዮን ሴት ልጅ ድን​ኳን ለዐ​ይኑ የሚ​ያ​ም​ረ​ውን ሁሉ ገደለ፤ መዓ​ቱ​ንም እንደ እሳት አፈ​ሰሰ።</verse>
				<verse number="5">ሄ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ጠላት ሆነ​ብኝ፤ እስ​ራ​ኤ​ልን አሰ​ጠመ። አዳ​ራ​ሾ​ች​ዋን ሁሉ ዋጠ፤ አን​ባ​ዎ​ች​ዋ​ንም አጠፋ። በይ​ሁ​ዳም ሴት ልጅ ውር​ደ​ት​ንና ጕስ​ቍ​ል​ናን አበዛ።</verse>
				<verse number="6">ዋው። ማደ​ሪ​ያ​ውን እንደ ወይን ጋረደ፤ በዓ​ሉን ሁሉ አጠፋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ያደ​ረ​ገ​ውን በዓ​ሉ​ንና ሰን​በ​ቱን አስ​ረሳ፤ በቍ​ጣ​ውም መዓት ነገ​ሥ​ታ​ቱን፥ አለ​ቆ​ቹ​ንና ካህ​ና​ቱን አጠፋ።</verse>
				<verse number="7">ዛይ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊ​ያ​ውን ጣለ፤ መቅ​ደ​ሱ​ንም ጠላው፤ የአ​ዳ​ራ​ሾ​ች​ዋ​ንም ቅጥር በጠ​ላት እጅ ሰበረ። እንደ ዓመት በዓል ቀን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ድም​ፃ​ቸ​ውን በዕ​ል​ልታ አሰሙ።</verse>
				<verse number="8">ሔት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ዮ​ንን ሴት ልጅ ቅጥር ያፈ​ርስ ዘንድ ዐሰበ፤ የመ​ለ​ኪ​ያ​ው​ንም ገመድ ዘረጋ፤ እር​ስ​ዋን ከማ​ጥ​ፋት እጁን አል​መ​ለ​ሰም፤ ምሽ​ጉና ቅጥሩ አለ​ቀሱ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ደከሙ።</verse>
				<verse number="9">ጤት። በሮ​ችዋ በመ​ሬት ውስጥ ሰጠሙ፤ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ተሰ​በሩ፤ ንጉ​ሥ​ዋና አለ​ቃዋ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል አሉ፤ ሕግም የለም። ነቢ​ያ​ቷም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ራእይ አላ​ዩም።</verse>
				<verse number="10">ዮድ። የጽ​ዮን ሴት ልጅ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ዝም ብለው በመ​ሬት ላይ ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ትቢ​ያን በራ​ሳ​ቸው ላይ ነሰ​ነሱ፤ ማቅም ታጠቁ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መሳ​ፍ​ን​ቱ​ንና ደና​ግ​ሉን ወደ ምድር አወ​ረ​ዷ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ካፍ። ሕፃ​ኑና ጡት የሚ​ጠ​ባው በከ​ተ​ማ​ዪቱ ጎዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዐይኔ በእ​ንባ ደከ​መች፤ ልቤም ታወከ፤ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ መከራ ክብሬ በም​ድር ላይ ተዋ​ረደ።</verse>
				<verse number="12">ላሜድ። በከ​ተማ ጎዳና እንደ ተወጋ ሰው በዛሉ ጊዜ፥ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም በእ​ና​ቶ​ቻ​ቸው ብብት እለይ-እለይ ባለች ጊዜ፥ እና​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ “እህ​ልና ወይን ወዴት አለ?” ይሉ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="13">ሜም። የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመ​ሰ​ክ​ር​ል​ሻ​ለሁ? በም​ንስ እመ​ስ​ል​ሻ​ለሁ? ድን​ግ​ሊቱ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ ማን ያድ​ን​ሻል? ማንስ ያጽ​ና​ና​ሻል? ስብ​ራ​ትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፤ የሚ​ፈ​ው​ስሽ ማን ነው?</verse>
				<verse number="14">ኖን። ነቢ​ያ​ትሽ ከን​ቱና ዕብ​ደ​ትን አይ​ተ​ው​ል​ሻል፤ ምር​ኮ​ሽን ይመ​ልሱ ዘንድ በደ​ል​ሽን አል​ገ​ለ​ጡም፤ ከን​ቱና የማ​ይ​ረባ ነገ​ር​ንም አይ​ተ​ው​ል​ሻል።</verse>
				<verse number="15">ሳም​ኬት። መን​ገድ ዐላ​ፊ​ዎች ሁሉ እጃ​ቸ​ውን ያጨ​በ​ጭ​ቡ​ብ​ሻል፦ “በውኑ የም​ድር ሁሉ ደስታ፥ አክ​ሊ​ልና ክብር የሚ​ሉ​አት ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ልጅ ላይ ያፍ​ዋ​ጫሉ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ይነ​ቀ​ን​ቃሉ።</verse>
				<verse number="16">ዔ። ጠላ​ቶ​ችሽ ሁሉ አፋ​ቸ​ውን አላ​ቀ​ቁ​ብሽ፤ እያ​ፍ​ዋ​ጩና ጥር​ሳ​ቸ​ውን እያ​ፋጩ፥ “ውጠ​ና​ታል፤ ነገር ግን ተስፋ ያደ​ረ​ግ​ናት ቀን ይህች ናት፤ አግ​ኝ​ተ​ና​ታል አይ​ተ​ና​ት​ማል” ይላሉ።</verse>
				<verse number="17">ፌ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሰ​በ​ውን አደ​ረገ፤ በቀ​ድሞ ዘመን ያዘ​ዘ​ው​ንም ቃል ፈጸመ፤ አፈ​ረ​ሳት፤ አል​ራ​ራ​ላ​ት​ምም፤ ጠላ​ት​ንም ደስ አሰ​ኘ​ብሽ፤ የጠ​ላ​ቶ​ች​ሽ​ንም ቀንድ ከፍ ከፍ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="18">ጻዴ። ልባ​ቸው ወደ ጌታ ጮኸ፤ የጽ​ዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፥ እን​ባ​ሽን እንደ ፈሳሽ ቀንና ሌሊት አፍ​ስሺ፤ ለሰ​ው​ነ​ትሽ ዕረ​ፍት አት​ስጪ፤ የዐ​ይ​ን​ሽ​ንም ብሌን አታ​ቋ​ርጪ።</verse>
				<verse number="19">ቆፍ። ተነሺ፤ በሌ​ሊት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ሰዓት ጩኺ፥ በጌ​ታም ፊት ልብ​ሽን እንደ ውኃ አፍ​ስሺ፤ በጎ​ዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃ​ና​ትሽ ነፍስ እጆ​ች​ሽን ወደ እርሱ አንሺ።</verse>
				<verse number="20">ሬስ። አቤቱ፥ እይ፤ ተመ​ል​ከት ማንን እን​ዲህ ቃረ​ምህ? በውኑ ሴቶች የማ​ኅ​ፀ​ና​ቸ​ውን ፍሬ፥ ያሳ​ደ​ጓ​ቸ​ውን ሕፃ​ናት ይበ​ላ​ሉን? በውኑ ካህ​ኑና ነቢዩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደስ ውስጥ ይገ​ደ​ላ​ሉን?</verse>
				<verse number="21">ሣን። ብላ​ቴ​ና​ውና ሽማ​ግ​ሌው በመ​ን​ገ​ዶች ላይ ተጋ​ደሙ፤ ደና​ግ​ሎ​ችና ጐል​ማ​ሶች ተማ​ር​ከ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፍም ወድ​ቀ​ዋል፤ በረ​ኃብ ገደ​ል​ሃ​ቸው፤ በቍ​ጣ​ህም ቀን ሳት​ራራ አረ​ድ​ሃ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">ታው። የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​ኝን እንደ በዓል ቀን ከዙ​ሪ​ያዬ ጠራ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ቀንም ያመ​ለጠ ወይም የቀረ አል​ተ​ገ​ኘም፤ ያቀ​ማ​ጠ​ል​ኋ​ቸ​ው​ንና ያሳ​ደ​ግ​ኋ​ቸ​ውን ጠላቴ በላ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">አሌፍ። በቍ​ጣው በትር ችግር ያየ ሰው እኔ ነኝ።</verse>
				<verse number="2">ብር​ሃን ወደ​ሌ​ለ​በት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰ​ደኝ።</verse>
				<verse number="3">ዘወ​ትር ቀኑን ሁሉ እጁን በላዬ መለሰ።</verse>
				<verse number="4">ቤት። ሥጋ​ዬ​ንና ቁር​በ​ቴን አስ​ረጀ፥ አጥ​ን​ቴን ሰበረ።</verse>
				<verse number="5">በዙ​ሪ​ያዬ ቅጥር ሠራ​ብኝ፤ የመ​ከ​ራ​ው​ንም ጎዳና በእኔ ላይ አቀና።</verse>
				<verse number="6">እንደ ቀድሞ ሙታን በጨ​ለማ አኖ​ረኝ።</verse>
				<verse number="7">ጋሜል። እን​ዳ​ል​ወጣ በዙ​ሪ​ያዬ ቅጥር ሠራ​ብኝ፤ ሰን​ሰ​ለ​ቴ​ንም አከ​በደ።</verse>
				<verse number="8">በጠ​ራ​ሁና በጮ​ኽሁ ጊዜ ጸሎቴ ተከ​ለ​ከለ።</verse>
				<verse number="9">መን​ገ​ዴን በዓ​ለት ላይ ሠራ፤ ጎዳ​ና​ዬ​ንም አጠረ።</verse>
				<verse number="10">ዳሌጥ። እን​ደ​ም​ት​ሸ​ምቅ ድብ እንደ ተሸ​ሸ​ገም አን​በሳ ሆነ​ብኝ።</verse>
				<verse number="11">ተከ​ተ​ለኝ፤ ጨረ​ሰኝ፤ ባድ​ማም አደ​ረ​ገኝ።</verse>
				<verse number="12">ቀስ​ቱን ገተረ፤ ለፍ​ላ​ጻ​ውም እንደ ዒላማ አደ​ረ​ገኝ።</verse>
				<verse number="13">ሄ። የሰ​ገ​ባ​ውን ፍላ​ጻ​ዎች በኵ​ላ​ሊቴ ውስጥ ተከለ።</verse>
				<verse number="14">ለወ​ገኔ ሁሉ መሳ​ቂያ ሆንሁ፤ ቀኑ​ንም ሁሉ ዘፈ​ኑ​ብኝ።</verse>
				<verse number="15">ምሬ​ትን አጠ​ገ​በኝ፤ በሐ​ሞ​ትም አሰ​ከ​ረኝ።</verse>
				<verse number="16">ዋው። ጥር​ሴን በጭ​ንጫ ሰበረ፤ አመ​ድም አቃ​መኝ።</verse>
				<verse number="17">ነፍ​ሴን ከሰ​ላም አራቀ፤ በጎ ነገ​ርን ረሳሁ።</verse>
				<verse number="18">እኔም፦ ኀይ​ሌን፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ ያለ​ውን ተስ​ፋ​ዬን አጣሁ።</verse>
				<verse number="19">ዛይ። ስደ​ቴ​ንና ችግ​ሬን፥ እሬ​ት​ንና ሐሞ​ትን አስብ።</verse>
				<verse number="20">ነፍሴ እያ​ሰ​በ​ችው በው​ስጤ ፈዘ​ዘች።</verse>
				<verse number="21">ይህ​ችን በልቤ አኖ​ራ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ እታ​ገ​ሣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="22">ሔት። ያል​ጠ​ፋ​ነው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሕ​ረት የተ​ነሣ ነው፤ ርኅ​ራ​ኄው አያ​ል​ቅ​ምና።</verse>
				<verse number="23">ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማ​ኝ​ነ​ትህ ብዙ ነው።</verse>
				<verse number="24">ነፍሴ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እድል ፋን​ታዬ ነው፤ ስለ​ዚህ ጠበ​ቅ​ሁት” አለች።</verse>
				<verse number="25">ጤት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ታ​ገ​ሡት ቸር ነው፤</verse>
				<verse number="26">ለም​ት​ሻ​ውና ለም​ት​ታ​ገሥ፥ ዝም ብላም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማዳን ተስፋ ለም​ታ​ደ​ርግ ነፍስ መል​ካም ነው።</verse>
				<verse number="27">ሰው በታ​ና​ሽ​ነቱ ቀን​በር ቢሸ​ከም መል​ካም ነው።</verse>
				<verse number="28">ዮድ። እርሱ አሸ​ክ​ሞ​ታ​ልና ዝም ብሎ ለብ​ቻው ይቀ​መጥ።</verse>
				<verse number="29">ተስፋ ይሆ​ነው እንደ ሆነ አፉን በአ​ፈር ውስጥ ያኑር።</verse>
				<verse number="30">ጕን​ጩን ለሚ​መ​ታው ይሰ​ጣል፤ ስድ​ብ​ንም ይጠ​ግ​ባል።</verse>
				<verse number="31">ካፍ። ጌታ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ጥ​ል​ምና፤</verse>
				<verse number="32">ያሳ​ዘ​ነ​ውን ሰው እንደ ይቅ​ር​ታው ብዛት ይም​ረ​ዋ​ልና፤</verse>
				<verse number="33">ከልቡ አል​ተ​ቈ​ጣ​ምና፥ የሰ​ው​ንም ልጆች አላ​ሳ​ዘ​ነ​ምና፥</verse>
				<verse number="34">ላሜድ። በም​ድር የተ​ጋ​ዙ​ትን ሁሉ ከእ​ግሩ በታች ይረ​ግ​ጣ​ቸው ዘንድ፥</verse>
				<verse number="35">የሰ​ውን ፍርድ በል​ዑል ፊት ይመ​ልስ ዘንድ፥</verse>
				<verse number="36">በሚ​ፈ​ር​ድ​በት ጊዜ የሰ​ውን ፍርድ ያጣ​ምም ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አላ​ዘ​ዘም።</verse>
				<verse number="37">ሜም። “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያላ​ዘ​ዘው ይመ​ጣል፥</verse>
				<verse number="38">ከል​ዑል አፍም ያል​ወጣ መል​ካም ወይም ክፉ ይሆ​ናል” የሚል ማን ነው?</verse>
				<verse number="39">ሰው ሕያው ሲሆን ስለ ኀጢ​አቱ ለምን ያጕ​ረ​መ​ር​ማል?</verse>
				<verse number="40">ኖን። መን​ገ​ዳ​ች​ንን እን​መ​ር​ም​ርና እን​ፈ​ትን፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​መ​ለስ።</verse>
				<verse number="41">ልባ​ች​ንን ከእ​ጃ​ችን ጋር ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ሰማይ እና​ንሣ።</verse>
				<verse number="42">በድ​ለ​ናል፤ ዐም​ፀ​ና​ልም፤ አን​ተም አል​ራ​ራ​ህ​ል​ንም።</verse>
				<verse number="43">ሳም​ኬት። በቍ​ጣህ ከደ​ን​ኸን፤ አሳ​ደ​ድ​ኸ​ንም፤ ገደ​ል​ኸን፤ አል​ራ​ራ​ህ​ል​ንም።</verse>
				<verse number="44">ጸሎ​ታ​ችን እን​ዳ​ያ​ርግ ራስ​ህን በደ​መና ከደ​ንህ።</verse>
				<verse number="45">እን​ድ​ና​ዝ​ንና እን​ዳ​ና​ይም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል አስ​ቀ​መ​ጥ​ኸን።</verse>
				<verse number="46">ዔ። ጠላ​ቶ​ቻ​ችን ሁሉ በእኛ ላይ አፋ​ቸ​ውን ከፈቱ።</verse>
				<verse number="47">ፍር​ሀ​ትና ቍጣ፥ ጥፋ​ትና ቅጥ​ቃጤ ያዘን።</verse>
				<verse number="48">ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥ​ቃጤ ከዐ​ይኔ የውኃ ጐርፍ ፈሰሰ።</verse>
				<verse number="49">ፌ። ዐይኔ ተደ​ፈ​ነች፤ እን​ግ​ዲህ ከማ​ን​ጋ​ጠጥ ዝም አል​ልም።</verse>
				<verse number="50">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ሆኖ እስ​ኪ​መ​ለ​ከት ድረስ።</verse>
				<verse number="51">ስለ ከተ​ማዬ ቈነ​ጃ​ጅት ሁሉ ዐይኔ ነፍ​ሴን አሳ​ዘ​ነች።</verse>
				<verse number="52">ጻዴ። በከ​ንቱ ነገር ጠላ​ቶች ሁሉ እንደ ወፍ ማደ​ንን አደ​ኑኝ።</verse>
				<verse number="53">ጠላ​ቶች ሕይ​ወ​ቴን በጕ​ድ​ጓድ አጠፉ፤ በላ​ዬም ድን​ጋይ ገጠሙ።</verse>
				<verse number="54">በራሴ ላይ ውኃ ተከ​ነ​በለ፤ እኔም፥ “ጠፋሁ” ብዬ ነበር።</verse>
				<verse number="55">ቆፍ። አቤቱ፥ በጥ​ልቅ ጕድ​ጓድ ውስጥ ሆኜ ስም​ህን ጠራሁ።</verse>
				<verse number="56">አንተ ድም​ፄን ሰማህ፤ ጆሮ​ህ​ንም ከል​መ​ናዬ አት​መ​ልስ።</verse>
				<verse number="57">በጠ​ራ​ሁህ ቀን ወደ እኔ ቅረብ፤ “አት​ፍ​ራም” በለኝ።</verse>
				<verse number="58">ሬስ። አቤቱ፥ የነ​ፍ​ሴን ፍርድ ፈረ​ድህ፤ ሕይ​ወ​ቴ​ንም ተቤ​ዥህ።</verse>
				<verse number="59">አቤቱ፥ ጭን​ቀ​ቴን አይ​ተ​ሃል፤ ፍር​ዴን ፍረ​ድ​ልኝ።</verse>
				<verse number="60">በቀ​ላ​ቸ​ውን ሁሉና በእኔ ላይ ያለ​ውን ዐሳ​ባ​ቸ​ውን ሁሉ አየህ።</verse>
				<verse number="61">ሣን። አቤቱ፥ ስድ​ባ​ቸ​ው​ንና በእኔ ላይ ያለ​ውን ዐሳ​ባ​ቸ​ውን ሁሉ ሰማህ።</verse>
				<verse number="62">የተ​ነ​ሡ​ብ​ኝን ሰዎች ከን​ፈ​ሮች ቀኑ​ንም ሁሉ ያሰ​ቡ​ብ​ኝን ዐሳ​ባ​ቸ​ውን ሰማህ።</verse>
				<verse number="63">መቀ​መ​ጣ​ቸ​ው​ንና መነ​ሣ​ታ​ቸ​ውን ተመ​ል​ከት፤ እኔ መዝ​ፈ​ኛ​ቸው ነኝ።</verse>
				<verse number="64">ታው። አቤቱ፥ እንደ እጃ​ቸው ሥራ ፍዳ​ቸ​ውን ክፈ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="65">የልብ ሕማ​ም​ንና ርግ​ማ​ን​ህን ስጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="66">አቤቱ፥ እንደ ልባ​ቸው ክፋት በቍ​ጣህ ታሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ከሰ​ማ​ይም በታች ታጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">አሌፍ። ወርቁ እን​ዴት ደበሰ! ጥሩው ብር እን​ዴት ተለ​ወጠ! የከ​በ​ረው ዕንቍ በጎ​ዳ​ናው ሁሉ እን​ዴት ተበ​ተነ!</verse>
				<verse number="2">ቤት። ጥሩ ወርቅ የሚ​መ​ስሉ የከ​በሩ የጽ​ዮን ልጆች፥ የሸ​ክላ ሠሪ እጅ እንደ ሠራው እንደ ሸክላ ዕቃ እን​ዴት ተቈ​ጠሩ!</verse>
				<verse number="3">ጋሜል። አራ​ዊት እንኳ ጡታ​ቸ​ውን ገል​ጠው ግል​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን አጠቡ፤ የወ​ገኔ ሴት ልጆች ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጐን ጨካ​ኞች ሆኑ።</verse>
				<verse number="4">ዳሌጥ። ጡት የሚ​ጠ​ባው የሕ​ፃን ምላስ ከጥም የተ​ነሣ ወደ ትና​ጋው ተጣ​በቀ፤ ሕፃ​ናት እን​ጀራ ለመኑ፤ የሚ​ቈ​ር​ስ​ላ​ቸ​ውም የለም።</verse>
				<verse number="5">ሄ። የጣ​ፈጠ ነገር ይበሉ የነ​በሩ በመ​ን​ገድ ጠፉ፤ በቀይ ግምጃ ያድጉ የነ​በሩ የፍግ ክምር አቀፉ።</verse>
				<verse number="6">ዋው። የማ​ንም እጅ ሳይ​ወ​ድ​ቅ​ባት ድን​ገት ከተ​ገ​ለ​በ​ጠች፥ ከሰ​ዶም ኀጢ​አት ይልቅ የወ​ገኔ ሴት ልጅ ኀጢ​አት በዛች።</verse>
				<verse number="7">ዛይ። ቅዱ​ሳ​ኖ​ችዋ ከበ​ረድ ይልቅ ነጡ፤ ከወ​ተ​ትም ይልቅ ነጡ፤ በመ​ው​ጣ​ታ​ቸ​ውም ሰን​ፔር ከሚ​ባል ዕንቍ ይልቅ ፈጽ​መው ቀሉ።</verse>
				<verse number="8">ሔት። ፊታ​ቸው ከጥ​ቀ​ርሻ ይልቅ ጠቍ​ሮ​አል፤ በመ​ን​ገ​ድም አል​ታ​ወ​ቁም፤ ቍር​በ​ታ​ቸው ወደ አጥ​ን​ታ​ቸው ተጣ​ብ​ቆ​አል፤ ደር​ቆ​አል፤ እንደ እን​ጨ​ትም ሆኖ​አል።</verse>
				<verse number="9">ጤት። በሰ​ይፍ የሞ​ቱት በራብ ከሞ​ቱት ይሻ​ላሉ፤ እነ​ዚህ የም​ድ​ርን ፍሬ አጥ​ተው ተወ​ግ​ተ​ውም ዐል​ፈ​ዋል።</verse>
				<verse number="10">ዮድ። የር​ኅ​ሩ​ኆች ሴቶች እጆች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ቀቅ​ለ​ዋል፤ የወ​ገኔ ሴት ልጅ በመ​ቀ​ጥ​ቀ​ጥዋ መብል ሆኖ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ካፍ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓ​ቱን ፈጽ​ሞ​አል፤ ጽኑ ቍጣ​ው​ንም አፍ​ስ​ሶ​አል፤ እሳ​ትን በጽ​ዮን ውስጥ አቃ​ጠለ፤ መሠ​ረ​ቷ​ንም በላች።</verse>
				<verse number="12">ላሜድ። የም​ድር ነገ​ሥ​ታት፥ በዓ​ለ​ምም የሚ​ኖሩ ሁሉ፥ አስ​ጨ​ና​ቂና ጠላት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በር እን​ደ​ሚ​ገባ አላ​መ​ኑም።</verse>
				<verse number="13">ሜም። የጻ​ድ​ቃ​ንን ደም በው​ስ​ጥዋ ስላ​ፈ​ሰሱ፥ ስለ ነቢ​ያቷ ኀጢ​አ​ትና ስለ ካህ​ናቷ በደል ነው።</verse>
				<verse number="14">ኖን። እነ​ርሱ ታው​ረው በመ​ን​ገድ ላይ ተቅ​በ​ዘ​በዙ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ውም እን​ዳ​ይ​ዳ​ሰስ በደም ረክ​ሰ​ዋል።</verse>
				<verse number="15">ሳም​ኬት። እና​ንተ ከር​ኩ​ሳን ራቁ፥ አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው፤ ራቁ፥ ራቁ በሉ​አ​ቸው፤ አት​ን​ኩ​አ​ቸ​ውም። ታው​ከ​ዋ​ልና ዳግ​መኛ እን​ዳ​ይ​ኖ​ሩ​ባት ለአ​ሕ​ዛብ ንገ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">ዔ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፍ​ላ​ቸው ነበረ። ነገር ግን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​መ​ለ​ከ​ታ​ቸ​ውም፤ የካ​ህ​ና​ቱን ፊት አላ​ፈ​ሩም፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹ​ንም አላ​ከ​በ​ሩም።</verse>
				<verse number="17">ፌ። በማ​ያ​ድን ወገን እያ​መ​ንን ረዳ​ታ​ችን ከንቱ ስለ ሆነ፥ እኛ ገና በሕ​ይ​ወት ሳለን ዐይ​ኖ​ቻ​ችን ጠፉ።</verse>
				<verse number="18">ጻዴ። ልጆ​ቻ​ች​ንን ወደ አደ​ባ​ባ​ያ​ችን እን​ዳ​ይ​ወጡ ከለ​ከ​ልን፤ የም​ን​ጠ​ፋ​በት ጊዜ ደር​ሷ​ልና ዘመ​ና​ችን አለቀ፤ የም​ን​ጠ​ፋ​በ​ትም ጊዜ ቀረበ።</verse>
				<verse number="19">ቆፍ። አሳ​ዳ​ጆ​ቻ​ችን ከሰ​ማይ ንስር ይልቅ ፈጣ​ኖች ሆኑ፤ በተ​ራ​ሮች ላይ አሳ​ደ​ዱን፤ በም​ድረ በዳም ሸመ​ቁ​ብን።</verse>
				<verse number="20">ሬስ። ስለ እርሱ፥ “በአ​ሕ​ዛብ ውስጥ በጥ​ላው በሕ​ይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን” ያል​ነው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀባ፥ የሕ​ይ​ወ​ታ​ችን እስ​ት​ን​ፋስ፥ በወ​ጥ​መ​ዳ​ቸው ተያዘ።</verse>
				<verse number="21">ሣን። በዖፅ ምድር የም​ት​ኖሪ የኤ​ዶ​ም​ያስ ሴት ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፥ ሐሤ​ትም አድ​ርጊ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዋ ደግሞ ወደ አንቺ ያል​ፋ​ልና፥ አን​ቺም ትሰ​ክ​ሪ​አ​ለሽ፥ ትራ​ቆ​ቻ​ለ​ሽም።</verse>
				<verse number="22">ታው። የጽ​ዮን ሴት ልጅ ሆይ፥ በደ​ልሽ ተፈ​ጸመ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አያ​ስ​ማ​ር​ክ​ሽም። የኤ​ዶ​ም​ያስ ሴት ልጅ ሆይ፥ በደ​ል​ሽን ይጐ​በ​ኘ​ዋል፤ ኀጢ​አ​ት​ሽ​ንም ይገ​ል​ጣል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">አቤቱ፥ የሆ​ነ​ብ​ንን ዐስብ፤ ተመ​ል​ከት ስድ​ባ​ች​ን​ንም እይ።</verse>
				<verse number="2">ርስ​ታ​ችን ለሌላ፥ ቤቶ​ቻ​ች​ንም ለእ​ን​ግ​ዶች ሆኑ።</verse>
				<verse number="3">ድሀ-አደ​ጎች ሆነ​ናል፤ አባ​ትም የለ​ንም። እና​ቶ​ቻ​ችን እንደ መበ​ለ​ቶች ሆነ​ዋል።</verse>
				<verse number="4">ውኃ​ች​ንን በገ​ን​ዘብ ጠጣን፤ እን​ጨ​ታ​ችን በዋጋ በት​ከ​ሻ​ችን ይመ​ጣል።</verse>
				<verse number="5">ጠላ​ቶ​ቻ​ችን አሳ​ደ​ዱን፤ እኛም ደክ​መ​ናል፤ ዕረ​ፍ​ትም የለ​ንም።</verse>
				<verse number="6">ግብ​ፃ​ው​ያ​ንና አሦ​ራ​ው​ያን፥ እን​ጀ​ራን ያጠ​ግ​ቡን ዘንድ እጃ​ቸ​ውን ሰጡን።</verse>
				<verse number="7">አባ​ቶ​ቻ​ችን ኀጢ​አ​ትን ሠሩ፤ ዛሬም የሉም፤ እኛም በደ​ላ​ቸ​ውን ተሸ​ከ​ምን።</verse>
				<verse number="8">ባሪ​ያ​ዎች ሠል​ጥ​ነ​ው​ብ​ናል፤ ከእ​ጃ​ቸ​ውም የሚ​ታ​ደ​ገን የለም።</verse>
				<verse number="9">ከም​ድረ በዳ ሰይፍ የተ​ነሣ፥ በሕ​ይ​ወ​ታ​ችን እን​ጀ​ራ​ች​ንን እና​መ​ጣ​ለን።</verse>
				<verse number="10">ከራብ የተ​ነሣ ሰው​ነ​ታ​ችን ጠወ​ለገ፤ ቍር​በ​ታ​ች​ንም እንደ ምድጃ ጠቈረ።</verse>
				<verse number="11">በጽ​ዮን ሴቶች፥ በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችም ደና​ግል ተዋ​ረዱ።</verse>
				<verse number="12">አለ​ቆች በእ​ጃ​ቸው ተሰ​ቀሉ፤ የሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ች​ንም ፊት አላ​ከ​በ​ሩም።</verse>
				<verse number="13">ጐል​ማ​ሶች ወፍ​ጮን ተሸ​ከሙ፤ ልጆ​ችም በእ​ን​ጨት ደከሙ።</verse>
				<verse number="14">ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ከአ​ደ​ባ​ባይ ጠፉ፤ ጐል​ማ​ሶ​ችም ከበ​ገ​ና​ቸው ተሻሩ።</verse>
				<verse number="15">የል​ባ​ችን ደስታ ተሽ​ሮ​አል፤ ዘፈ​ና​ችን ወደ ልቅሶ ተለ​ው​ጦ​አል።</verse>
				<verse number="16">የራ​ሳ​ችን አክ​ሊል ወድ​ቆ​አል፤ ኀጢ​አ​ትን ሠር​ተ​ና​ልና ወዮ​ልን!</verse>
				<verse number="17">ስለ​ዚህ ልባ​ችን ታም​ሞ​አል፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር ዐይ​ና​ችን ፈዝ​ዞ​አል፤</verse>
				<verse number="18">የጽ​ዮን ተራራ ባድማ ሆና​ለ​ችና፥ ቀበ​ሮ​ዎ​ችም ተመ​ላ​ል​ሰ​ው​ባ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="19">አቤቱ፥ አንተ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ትኖ​ራ​ለህ፤ ዙፋ​ን​ህም ከት​ው​ልድ እስከ ትው​ልድ ነው።</verse>
				<verse number="20">ስለ ምን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ትረ​ሳ​ና​ለህ? ስለ ምንስ ለረ​ዥም ዘመን ትተ​ወ​ና​ለህ?</verse>
				<verse number="21">አቤቱ፥ ወደ አንተ መል​ሰን፤ እኛም እን​መ​ለ​ሳ​ለን፤ ዘመ​ና​ች​ንን እንደ ቀድሞ አድስ።</verse>
				<verse number="22">ፈጽ​መህ ጥለ​ኸ​ና​ልና፤ እጅ​ግም ተቈ​ጥ​ተ​ኸ​ናል።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="26">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በሠ​ላ​ሳ​ኛው ዓመት በአ​ራ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ቀን በኮ​ቦር ወንዝ በም​ር​ኮ​ኞች መካ​ከል ሳለሁ ሰማ​ያት ተከ​ፈቱ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ራእይ አየሁ።</verse>
				<verse number="2">ንጉሡ ዮአ​ኪን በተ​ማ​ረከ በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ዓመት፥ ከወ​ሩም በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ቀን፥</verse>
				<verse number="3">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሀገር በኮ​ቦር ወንዝ ላይ ወደ ቡዝ ልጅ ወደ ካህኑ ወደ ሕዝ​ቅ​ኤል መጣ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በዚያ በእኔ ላይ ሆነች፤</verse>
				<verse number="4">እኔም አየሁ፤ እነ​ሆም ከሰ​ሜን በኩል ዐውሎ ነፋ​ስና ታላቅ ደመና፥ የሚ​በ​ር​ቅም እሳት መጣ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ፀዳል ነበረ፤ በመ​ካ​ከ​ልም በእ​ሳቱ ውስጥ የሚ​ብ​ለ​ጨ​ለጭ ነገር ነበረ።</verse>
				<verse number="5">ከመ​ካ​ከ​ልም የአ​ራት እን​ስ​ሶች አም​ሳያ ወጣ። መል​ካ​ቸ​ውም እን​ደ​ዚህ ነበረ፤ ሰውም ይመ​ስሉ ነበረ።</verse>
				<verse number="6">ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም አራት አራት ፊት፥ ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም አራት አራት ክንፍ ነበ​ሩት።</verse>
				<verse number="7">እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ቀጥ ያሉ ነበሩ፤ የእ​ግ​ራ​ቸው ሰኰና እንደ ላም እግር ሰኰና ነበረ፤ እንደ ተወ​ለ​ወለ ናስም ይብ​ለ​ጨ​ለጭ ነበር።</verse>
				<verse number="8">በክ​ን​ፎ​ቻ​ቸ​ውም በታች በእ​የ​አ​ራቱ ጐድ​ና​ቸው የሰው እጅ ነበረ፤ ለአ​ራ​ቱም እን​ደ​ዚህ ያሉ ፊትና ክንፍ ነበ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">የሁ​ሉም ክን​ፎ​ቻ​ቸው አንዱ ከአ​ንዱ ጋር የተ​ያ​ያዘ ነው፤ ሲሄ​ዱም ወዲ​ያና ወዲህ ሳይሉ አቅ​ን​ተው ይሄ​ዳሉ፤ አን​ዱም አን​ዱም ወደ​ፊቱ ይሄ​ዳል።</verse>
				<verse number="10">የፊ​ታ​ቸው አም​ሳያ እን​ደ​ዚህ ነው፦ ለአ​ራቱ ሁሉ በቀ​ኛ​ቸው የሰው ፊትና የአ​ን​በሳ ፊት አላ​ቸው፤ ለአ​ራ​ቱም ሁሉ በግ​ራ​ቸው የእ​ን​ስሳ ፊትና የን​ስር ፊት አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ክን​ፋ​ቸ​ውም በላይ ተዘ​ር​ግቶ ነበር፤ የእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሁለት ሁለት ክን​ፋ​ቸው የተ​ያ​ያዙ ነበሩ፤ ሁለት ሁለ​ቱም ገላ​ቸ​ውን ይከ​ድኑ ነበር።</verse>
				<verse number="12">እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ ፊት ቀጥ ብሎ ይሄድ ነበር፤ መን​ፈ​ስም ወደ​ሚ​ሄ​ድ​በት ሁሉ ይሄዱ ነበር፤ ሲሄ​ዱም ወዲ​ያና ወዲህ አይ​ሉም ነበር።</verse>
				<verse number="13">በእ​ን​ስ​ሶ​ቹም መካ​ከል እን​ደ​ሚ​ነ​ድድ የእ​ሳት ፍም ያለ አም​ሳያ ነበረ፤ በእ​ን​ስ​ሶቹ መካ​ከል ወዲ​ህና ወዲያ የሚ​ሄድ እንደ ፋና ያለ አም​ሳያ ነበረ፤ ለእ​ሳ​ቱም ፀዳል ነበ​ረው፤ ከእ​ሳ​ቱም መብ​ረቅ ይወጣ ነበር።</verse>
				<verse number="14">እን​ስ​ሶ​ቹም እንደ መብ​ረቅ አም​ሳያ ይሮ​ጡና ይመ​ለሱ ነበር።</verse>
				<verse number="15">ስመ​ለ​ከ​ትም፥ እነሆ በአ​ራቱ እን​ስ​ሶች አጠ​ገብ በም​ድር ላይ አንድ መን​ኰ​ራ​ኵር አየሁ።</verse>
				<verse number="16">የመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሩም መልክ እንደ ቢረሌ ነበረ፤ አራ​ቱም አንድ አም​ሳያ ነበሩ፤ ሥራ​ቸ​ውም በመ​ን​ኰ​ራ​ኵር ውስጥ እን​ዳለ መን​ኰ​ራ​ኵር ነበረ።</verse>
				<verse number="17">በእ​የ​አ​ራ​ቱም ጐድ​ና​ቸው ይሄዱ ነበር፤ ሲሄ​ዱም ጀር​ባ​ቸ​ውን አይ​መ​ል​ሱም ነበር። ከፍ ከፍ ያሉም ነበሩ።</verse>
				<verse number="18">በአ​ራቱ ዙሪያ ሁሉ ዐይ​ኖ​ችን የተ​መላ ጀር​ባ​ቸ​ውን አየሁ፤</verse>
				<verse number="19">በሄ​ዱም ጊዜ ሠረ​ገ​ላ​ዎች ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይሄ​ዳሉ። እን​ስ​ሶ​ቹም ከም​ድር ሲነሡ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ቹም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይነ​ሣሉ።</verse>
				<verse number="20">ደመና ባለ​በት በዚያ መን​ፈስ አለ፤ እን​ስ​ሶቹ ይሄ​ዳሉ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮቹ ይነ​ሣሉ፤ የሕ​ይ​ወት መን​ፈስ በመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮች አለና።</verse>
				<verse number="21">በሄ​ዱም ጊዜ ይሄ​ዳሉ፤ በቆ​ሙም ጊዜ ይቆ​ማሉ፤ በእ​ነ​ዚያ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮች ውስጥ የሕ​ይ​ወት መን​ፈስ አለና ከም​ድር በተ​ነሡ ጊዜ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮቹ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይነ​ሣሉ።</verse>
				<verse number="22">በእ​ነ​ዚያ እን​ስ​ሶች ራስ ላይ ያለው መልክ ከላይ በክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው ላይ የተ​ዘ​ረጋ የበ​ረድ መልክ እን​ዳ​ለ​በት ጠፈር ነው፤</verse>
				<verse number="23">ከጠ​ፈ​ሩም በታች ክን​ፎ​ቻ​ቸው እርስ በር​ሳ​ቸው ተቃ​ን​ተው ነበር፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ገላ​ውን የሚ​ከ​ድኑ ሁለት ሁለት ክን​ፎች ነበ​ሩት።</verse>
				<verse number="24">ሲሄ​ዱም የክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው ድምፅ እንደ ብዙ ውኃ ድምፅ፥ ሁሉን እን​ደ​ሚ​ችል የአ​ም​ላ​ክም ድምፅ፥ እንደ ታላቅ ሠራ​ዊ​ትም ድምፅ ሆኖ ሰማሁ፤ ሲቆ​ሙም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ይሰ​በ​ስቡ ነበር።</verse>
				<verse number="25">በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ ካለው ጠፈር በላይ ድምፅ ተሰማ፤ ሲቆ​ሙም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ይሰ​በ​ስቡ ነበር።</verse>
				<verse number="26">በራ​ሳ​ቸ​ውም በላይ ከአ​ለው ጠፈር በላይ የሰ​ን​ፔር ድን​ጋይ የሚ​መ​ስል የዙ​ፋን አም​ሳያ ነበረ፤ በዙ​ፋ​ኑም አም​ሳያ ላይ እንደ ሰው መልክ አም​ሳያ ነበረ።</verse>
				<verse number="27">ከወ​ገ​ቡም አም​ሳያ ወደ ላይ የሚ​ብ​ለ​ጨ​ለጭ የወ​ርቅ አም​ሳያ አየሁ፤ ከወ​ገ​ቡም አም​ሳያ ወደ ታች እንደ እሳት አም​ሳያ አየሁ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ፀዳል ነበረ።</verse>
				<verse number="28">በዝ​ናብ ቀን በደ​መና ውስጥ እንደ አለ ቀስተ ደመና አም​ሳያ፥ እን​ዲሁ በዙ​ሪ​ያው ያለ ፀዳል አም​ሳያ ነበረ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ምሳሌ መልክ ይህ ነበረ። በአ​የ​ሁም ጊዜ በግ​ን​ባሬ ተደ​ፋሁ። የሚ​ና​ገ​ር​ንም ድምፅ ሰማሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! በእ​ግ​ርህ ቁም፤ እኔም እና​ገ​ር​ሃ​ለሁ” አለኝ።</verse>
				<verse number="2">በተ​ና​ገ​ረ​ኝም ጊዜ መን​ፈስ በእኔ ላይ መጣ፤ አነ​ሣ​ኝም፤ በእ​ግ​ሬም አቆ​መኝ፤ የሚ​ና​ገ​ረ​ኝ​ንም ሰማሁ።</verse>
				<verse number="3">እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እኔን ወደ አስ​መ​ረ​ሩኝ ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት እል​ክ​ሃ​ለሁ። እነ​ር​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ቸው እስከ ዛሬ ድረስ ዐመ​ፁ​ብኝ።</verse>
				<verse number="4">እነ​ርሱ ፊታ​ቸው የከፋ፥ ልባ​ቸው የደ​ነ​ደነ ልጆች ናቸው። እኔ ወደ እነ​ርሱ እል​ክ​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል በላ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">“እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና ቢሰሙ ወይም ቢፈሩ አንተ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ነቢይ እንደ ሆንህ ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="6">አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ኩር​ን​ች​ትና እሾህ ከአ​ንተ ጋር ቢኖ​ሩም፥ አን​ተም በጊ​ን​ጦች መካ​ከል ብት​ቀ​መጥ፥ አት​ፍ​ራ​ቸው፤ ቃላ​ቸ​ው​ንም አት​ፍራ፤ አንተ ቃላ​ቸ​ውን አት​ፍራ፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ አት​ደ​ን​ግጥ፤ እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና።</verse>
				<verse number="7">እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ስለ​ሆኑ ቢሰሙ ወይም ቢደ​ነ​ግጡ ቃሌን ትነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="8">“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! የም​ነ​ግ​ር​ህን ስማ፤ እን​ደ​እ​ዚያ ዐመ​ፀኛ ቤት ዐመ​ፀኛ አት​ሁን፤ አፍ​ህን ክፈት፤ የም​ሰ​ጥ​ህ​ንም ብላ።”</verse>
				<verse number="9">በአ​የ​ሁም ጊዜ፥ እነሆ እጅ ወደ እኔ ተዘ​ር​ግታ ነበር፤ እነ​ሆም የመ​ጽ​ሐፍ ጥቅ​ልል ነበ​ረ​ባት።</verse>
				<verse number="10">በፊ​ቴም ዘረ​ጋው፤ በው​ስ​ጥና በው​ጭም ተጽ​ፎ​በት ነበረ፤ ጽሑ​ፉም “ልቅ​ሶና ኀዘን፥ ዋይ​ታም” ይል ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ያገ​ኘ​ኸ​ውን ብላ፤ ይህን መጽ​ሐፍ ብላ፤ ሄደ​ህም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተና​ገር” አለኝ።</verse>
				<verse number="2">አፌ​ንም ከፈ​ትሁ፤ መጽ​ሐ​ፉ​ንም አበ​ላኝ።</verse>
				<verse number="3">እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! አፍህ ይብላ፤ በም​ሰ​ጥ​ህም በዚህ መጽ​ሐፍ ሆድ​ህን ሙላ” አለኝ። እኔም በላ​ሁት፤ በአ​ፌም ውስጥ እንደ ማር ጣፈጠ።</verse>
				<verse number="4">እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ተነ​ሥ​ተህ ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት ሂድና ግባ፥ ቃሌ​ንም ንገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት እንጂ ንግ​ግ​ራ​ቸው ልዩ ወደ ሆነ፥ ቋን​ቋ​ቸ​ውም ወደ​ማ​ይ​ታ​ወቅ ሕዝብ አል​ተ​ላ​ክ​ህ​ምና፤</verse>
				<verse number="6">ንግ​ግ​ራ​ቸው ልዩ ወደ ሆነ፥ ቋን​ቋ​ቸ​ውም ሌላ ወደ ሆነ፥ ቃላ​ቸ​ው​ንም ታውቅ ዘንድ ወደ​ማ​ይ​ቻ​ልህ ሕዝብ አል​ላ​ክ​ሁ​ህም። ወደ እነ​ዚ​ያስ ልኬህ ቢሆን ኖሮ በሰ​ሙህ ነበር።</verse>
				<verse number="7">ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ክፉ​ዎ​ችና ልበ ደን​ዳ​ኖች ናቸ​ውና፥ እኔ​ንም መስ​ማት እንቢ ብለ​ዋ​ልና የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት አን​ተን አይ​ሰ​ሙ​ህም።</verse>
				<verse number="8">እነሆ ፊት​ህን በፊ​ታ​ቸው አጸ​ና​ሁት፤ ኀይ​ል​ህ​ንም ከኀ​ይ​ላ​ቸው ይልቅ አጸ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">ሁል​ጊዜ ከዓ​ለት ይልቅ ትጸ​ና​ለህ፤ አት​ፍ​ራ​ቸው፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም አት​ደ​ን​ግጥ፤ ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና።”</verse>
				<verse number="10">እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የነ​ገ​ር​ሁ​ህን ቃሌን ሁሉ በል​ብህ ጠብ​ቀው፤ በጆ​ሮ​ህም ስማው።</verse>
				<verse number="11">ተነ​ሥ​ተ​ህም ወደ ተማ​ረኩ ወደ ወገ​ንህ ልጆች ሂድ፤ እነ​ር​ሱም ቢሰሙ ወይም ቢፈሩ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል ብለህ ንገ​ራ​ቸው” አለኝ።</verse>
				<verse number="12">መን​ፈ​ስም ወደ ላይ ወሰ​ደኝ፤ በኋ​ላ​ዬም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ከቦ​ታው ይባ​ረክ” የሚል የታ​ላቅ ንው​ጽ​ው​ጽታ ድምፅ ሰማሁ።</verse>
				<verse number="13">የእ​ነ​ዚ​ያም እን​ስሳ ክን​ፎች እርስ በር​ሳ​ቸው ሲማቱ፥ በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ችን ድምፅ፥ የታ​ላ​ቁ​ንም ንው​ጽ​ው​ጽታ ድምፅ ሰማሁ።</verse>
				<verse number="14">መን​ፈ​ስም አን​ሥቶ ወሰ​ደኝ፤ እኔም በም​ሬ​ትና በመ​ን​ፈሴ ሙቀት ሄድሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በላዬ በር​ትታ ነበር።</verse>
				<verse number="15">በቴ​ል​አ​ቢ​ብም ወደ አሉ፥ በኮ​ቦ​ርም ወንዝ አጠ​ገብ ወደ ተቀ​መጡ ምር​ኮ​ኞች መጣሁ፤ በተ​ቀ​መ​ጡ​በ​ትም ቦታ ተቀ​መ​ጥሁ፤ በዚ​ያም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው እየ​ተ​መ​ላ​ለ​ስሁ ሰባት ቀን ተቀ​መ​ጥሁ።</verse>
				<verse number="16">ከሰ​ባ​ቱም ቀን በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="17">“የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ጕበኛ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ የአ​ፌን ቃል ስማ፤ በቃ​ሌም ገሥ​ጻ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">እኔ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን፥ “በእ​ር​ግጥ ትሞ​ታ​ለህ ባል​ሁት ጊዜ አን​ተም ባት​ነ​ግ​ረው፥ ነፍ​ሱም እን​ድ​ት​ድን ከክፉ መን​ገዱ ይመ​ለስ ዘንድ ለኀ​ጢ​አ​ተ​ኛው ባት​ነ​ግ​ረው፥ ያ ኀጢ​አ​ተኛ በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ ደሙን ግን ከእ​ጅህ እፈ​ል​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">ነገር ግን አንተ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ብት​ገ​ሥ​ጸው እር​ሱም ከኀ​ጢ​አ​ቱና ከክፉ መን​ገዱ ባይ​መ​ለስ፥ በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ አንተ ግን ነፍ​ስ​ህን ታድ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="20">ደግሞ ጻድቁ ከጽ​ድቁ ተመ​ልሶ ኀጢ​አት በሠራ ጊዜ እኔ በፊቱ ዕን​ቅ​ፋት ባደ​ርግ፥ እርሱ ይሞ​ታል፤ አን​ተም አል​ነ​ገ​ር​ኸ​ው​ምና በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ ያደ​ረ​ጋ​ትም የጽ​ድቅ ነገር አት​ታ​ሰ​ብ​ለ​ትም፤ ደሙን ግን ከእ​ጅህ እፈ​ል​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="21">ነገር ግን ኀጢ​አት እን​ዳ​ይ​ሠራ ጻድ​ቁን ብት​ገ​ሥ​ጸው፥ እር​ሱም ኀጢ​አት ባይ​ሠራ፥ ጻድቅ ነውና በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፤ አን​ተም ነፍ​ስ​ህን አድ​ነ​ሃል።”</verse>
				<verse number="22">በዚ​ያም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእኔ ላይ ነበ​ረች፤ እር​ሱም፥ “ተነ​ሥ​ተህ ወደ ሜዳ ሂድ፤ በዚ​ያም እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ” አለኝ።</verse>
				<verse number="23">እኔም ተነ​ሥቼ ወደ ሜዳው ሄድሁ፤ እነ​ሆም በኮ​ቦር ወንዝ እን​ዳ​የ​ሁት ክብር ያለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር በዚያ ቆሞ ነበር፤ በግ​ም​ባ​ሬም ተደ​ፋሁ።</verse>
				<verse number="24">መን​ፈ​ስም ወደ እኔ መጣ፤ በእ​ግ​ሬም አቆ​መኝ፤ ተና​ገ​ረ​ኝም እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “ሂድ ገብ​ተህ ቤት​ህን ዝጋ።</verse>
				<verse number="25">አን​ተም፥ የሰው ልጅ ሆይ! እነሆ ገመድ ያደ​ር​ጉ​ብ​ሃል፤ ያስ​ሩ​ህ​ማል፤ አን​ተም ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አት​ወ​ጣም፤</verse>
				<verse number="26">እኔም ምላ​ስ​ህን ከት​ና​ጋህ ጋር አጣ​ብ​ቃ​ታ​ለሁ፤ አን​ተም ዲዳ ትሆ​ና​ለህ፤ እነ​ር​ሱም ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና የሚ​ዘ​ልፍ ሰው አት​ሆ​ን​ባ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="27">ነገር ግን በተ​ና​ገ​ር​ሁህ ጊዜ አፍ​ህን እከ​ፍ​ታ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና አንተ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሚ​ሰማ ይስማ፤ እንቢ የሚ​ልም እንቢ ይበል” ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ጡብን ወስ​ደህ በፊ​ትህ አኑ​ራት፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ከተማ ሥዕል ሣል​ባት፤</verse>
				<verse number="2">በው​ስ​ጧም የሚ​ዋ​ጉ​በት ግን​ብን ሥራ፤ በሠ​ራ​ዊ​ትም ክበ​ባት፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ጦር አስ​ፍር፤ የሚ​ዋጋ ጦር​ንም ወደ አደ​ባ​ባ​ይዋ ላክ።</verse>
				<verse number="3">የብ​ረት ምጣ​ድም ወስ​ደህ በአ​ን​ተና በከ​ተ​ማ​ዪቱ መካ​ከል ለብ​ረት ቅጥር አድ​ር​ገው፤ ፊት​ህ​ንም ወደ እር​ስዋ አቅና፤ የተ​ከ​በ​በ​ችም ትሆ​ና​ለች፤ አን​ተም ትከ​ብ​ባ​ታ​ለህ። ይህም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ምል​ክት ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="4">“አን​ተም በግራ ጎንህ ተኛ፤ በም​ት​ተ​ኛ​በ​ትም ቀን ቍጥር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ኀጢ​አት አኑ​ር​ባት፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ትሸ​ከ​ማ​ለህ።</verse>
				<verse number="5">እኔም የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ዓመ​ታት ለአ​ንተ የቀን ቍጥር እን​ዲ​ሆ​ን​ልህ ሦስት መቶ ዘጠና ቀን ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቤት ኃጢ​አት ትሸ​ከ​ማ​ለህ፤</verse>
				<verse number="6">እነ​ዚ​ህ​ንም በፈ​ጸ​ምህ ጊዜ በቀኝ ጎንህ ትተ​ኛ​ለህ፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም ቤት ኀጢ​አት አርባ ቀን ትሸ​ከ​ማ​ለህ፤ አን​ዱን ቀን አንድ ዓመት አደ​ረ​ግ​ሁ​ልህ።</verse>
				<verse number="7">ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ከበባ ፊት​ህን ታቀ​ና​ለህ፤ ክን​ድ​ህ​ንም ታጸ​ና​ለህ፤ በእ​ር​ሷም ትን​ቢ​ትን ትና​ገ​ራ​ለህ።</verse>
				<verse number="8">እነ​ሆም ገመድ አደ​ር​ግ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የም​ት​ከ​በ​ብ​በ​ት​ንም ወራት እስ​ክ​ት​ፈ​ጽም ድረስ ከጎን ወደ ጎንህ አት​ገ​ላ​በ​ጥም።</verse>
				<verse number="9">“አን​ተም ስን​ዴ​ንና ገብ​ስን፥ አተ​ር​ንና ባቄ​ላን፥ ምስ​ር​ንና አጃን ወደ አንተ ውሰድ፤ በአ​ንድ ዕቃም ውስጥ አድ​ር​ገህ እን​ጀራ ጋግር፤ በጎ​ንህ እንደ ተኛ​ህ​ባት ቀን ቍጥር ሦስት መቶ ዘጠና ቀን ትበ​ላ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="10">የም​ት​በ​ላ​ውም በሚ​ዛን በየ​ቀኑ ሃያ ሃያ ሰቅል ይሁን፤ በየ​ጊ​ዜው ትበ​ላ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="11">ውኃ​ው​ንም በልክ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ከስ​ድ​ስት እጅ አንድ እጅ ትጠ​ጣ​ለህ፤ በየ​ጊ​ዜው ትጠ​ጣ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="12">የገ​ብስ እን​ጎ​ቻ​ንም ትበ​ላ​ለህ፤ በሰው ኵስም ታበ​ስ​ለ​ዋ​ለህ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ታዳ​ፍ​ነ​ዋ​ለህ።”</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እነ​ር​ሱን በም​በ​ት​ን​ባ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ንጹሕ ያል​ሆነ እን​ጀ​ራ​ቸ​ውን ይበ​ላሉ” አለ።</verse>
				<verse number="14">እኔም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! ይህ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም፤ እነሆ ሰው​ነቴ አል​ረ​ከ​ሰ​ችም፤ ከታ​ና​ሽ​ነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ጥን​ብና አውሬ የሰ​በ​ረ​ውን ከቶ አል​በ​ላ​ሁም፤ ርኵ​ስም ሥጋ በአፌ ውስጥ አል​ገ​ባም” አልሁ።</verse>
				<verse number="15">እር​ሱም፥ “እነሆ በሰው ኵስ ፋንታ የከ​ብት ኩበት ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ በእ​ር​ሱም እን​ጀ​ራ​ህን ትጋ​ግ​ራ​ለህ” አለኝ።</verse>
				<verse number="16">ደግ​ሞም እን​ዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እን​ጀራ በትር እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ በች​ግር እያሉ እን​ጀ​ራን በሚ​ዛን ይበ​ላሉ፥ እየ​ደ​ነ​ገ​ጡም ውኃን በልክ ይጠ​ጣሉ፤</verse>
				<verse number="17">ይህም እን​ጀ​ራ​ንና ውኃን እን​ዲ​ያጡ፥ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም እን​ዲ​ገ​ዳ​ደሉ፥ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም እን​ዲ​ጠፉ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ራስን ከሚ​ላጭ ምላጭ ይልቅ የተ​ሳለ ጐራ​ዴን ውሰድ፤ ወስ​ደ​ህም በእ​ር​ስዋ ራስ​ህ​ንና ጢም​ህን ተላጭ፤ ሚዛ​ን​ንም ውሰድ፤ ጠጕ​ሩ​ንም ትከ​ፋ​ፍ​ለ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="2">የእ​ስ​ራ​ት​ህም ወራት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ በከ​ተ​ማ​ዪቱ መካ​ከል ሢሶ​ውን በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ሢሶ​ው​ንም ወስ​ደህ ዙሪ​ያ​ውን በጎ​ራዴ ትመ​ታ​ለህ፤ ሢሶ​ው​ንም ወደ ነፋስ ትበ​ት​ና​ለህ፤ እኔም በኋ​ላ​ቸው ጎራዴ እመ​ዝ​ዛ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">ከዚ​ያም በቍ​ጥር ጥቂ​ቶ​ቹን ውሰድ፤ በመ​ጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ህም ቋጥ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ከእ​ነ​ር​ሱም ደግሞ ወስ​ደህ በእ​ሳት ውስጥ ትጥ​ላ​ለህ፤ በእ​ሳ​ትም ታቃ​ጥ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም እሳት ይወ​ጣል፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቤት ሁሉ እን​ዲህ ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።”</verse>
				<verse number="5">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህች ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ናት፤ እር​ስ​ዋ​ንና አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ዋ​ንም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፥</verse>
				<verse number="6">እር​ስ​ዋም ከአ​ሕ​ዛብ ይልቅ ፍር​ዴን በኀ​ጢ​አት ለወ​ጠች፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ከአሉ ሀገ​ሮች ሁሉ ይልቅ ትእ​ዛ​ዜን ተላ​ለ​ፈች፤ ፍር​ዴን ጥለ​ዋ​ልና፥ በት​እ​ዛ​ዜም አል​ሄ​ዱ​ምና።</verse>
				<verse number="7">ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በዙ​ሪ​ያ​ችሁ ላሉት አሕ​ዛብ ሰበብ ሆና​ች​ኋ​ልና፥ በት​እ​ዛ​ዜም አል​ሄ​ዳ​ች​ሁ​ምና፥ ፍር​ዴ​ንም አል​ጠ​በ​ቃ​ች​ሁ​ምና፥ በዙ​ሪ​ያ​ች​ሁም እንደ አሉ እንደ አሕ​ዛብ ፍርድ እንኳ አላ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ምና፥</verse>
				<verse number="8">ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ራሴ በአ​ንቺ ላይ ነኝ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ፊት ፍር​ድን በመ​ካ​ከ​ልሽ አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">ስለ ርኵ​ሰ​ት​ሽም ሁሉ ያል​ሠ​ራ​ሁ​ትን፥ እር​ሱ​ንም የሚ​መ​ስል ደግሞ የማ​ል​ሠ​ራ​ውን ነገር እሠ​ራ​ብ​ሻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">ስለ​ዚህ በመ​ካ​ከ​ልሽ አባ​ቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ይበ​ላሉ፤ ልጆ​ችም አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ይበ​ላሉ፤ ፍር​ድ​ንም አደ​ር​ግ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ከአ​ን​ቺም የቀ​ረ​ውን ሁሉ ወደ ነፋ​ሳት ሁሉ እበ​ት​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">ስለ​ዚህ እኔ ሕያው ነኝና በእ​ድ​ፍ​ሽና በር​ኵ​ሰ​ትሽ መቅ​ደ​ሴን ስላ​ረ​ከ​ስሽ፥ ስለ​ዚህ በእ​ው​ነት እኔ አሳ​ን​ስ​ሻ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ዐይ​ኔም አይ​ራ​ራም፤ እኔም ይቅር አል​ልም።</verse>
				<verse number="12">ከአ​ን​ቺም ሢሶው በቸ​ነ​ፈር ይሞ​ታል፤ በመ​ካ​ከ​ል​ሽም በራብ ያል​ቃል፤ ሢሶ​ውም በዙ​ሪ​ያሽ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃል፤ ሢሶ​ው​ንም ወደ ነፋ​ሳት ሁሉ እበ​ት​ና​ለሁ፤ በኋ​ላ​ቸ​ውም ሰይ​ፍን እመ​ዝ​ዛ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">“ቍጣ​ዬ​ንና መዓ​ቴ​ንም በእ​ነ​ርሱ ላይ እጨ​ር​ሳ​ለሁ፤ መዓ​ቴ​ንም በፈ​ጸ​ም​ሁ​ባ​ቸው ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቅ​ን​ዓቴ እንደ ተና​ገ​ርሁ ታው​ቂ​ያ​ለሽ።</verse>
				<verse number="14">በዙ​ሪ​ያ​ሽም በአሉ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል በሚ​ያ​ል​ፉም ሁሉ ፊት ከል​ጆ​ችሽ ጋር አጠ​ፋ​ሻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">በቍ​ጣ​ዬና በመ​ቅ​ሠ​ፍቴ በተ​በ​ቀ​ል​ሁሽ ጊዜ በዙ​ሪ​ያሽ በአሉ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ትጨ​ነ​ቂ​ያ​ለሽ፤ ትደ​ነ​ግ​ጫ​ለ​ሽም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">ለማ​ጥ​ፋ​ትም የሆ​ነ​ውን፥ አጠ​ፋ​ች​ሁም ዘንድ የም​ሰ​ድ​ደ​ውን የራብ ፍላጻ በላ​ያ​ችሁ በሰ​ደ​ድሁ ጊዜ፥ ራብን እጨ​ም​ር​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ የእ​ን​ጀ​ራ​ች​ሁ​ንም በትር እሰ​ብ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="17">ራብ​ንና ክፉ​ዎ​ችን አራ​ዊት እሰ​ድ​ድ​ብ​ሻ​ለሁ፤ እቀ​ሥ​ፍ​ሻ​ለሁ፤ ልጆ​ች​ሽ​ንም ያጠ​ፋሉ ቸነ​ፈ​ርና ደምም በአ​ንቺ ላይ ይመ​ጡ​ብ​ሻል፤ ሰይ​ፍ​ንም አመ​ጣ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ይከ​ቡ​ሻ​ልም። እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊት​ህን ወደ እስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች አቅና፤ ትን​ቢ​ትም ተና​ገ​ር​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ለእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች የጌ​ታን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ በላ​ቸው፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለተ​ራ​ሮ​ችና ለኮ​ረ​ብ​ቶች፥ ለም​ን​ጮ​ችና ለሸ​ለ​ቆ​ዎች እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ሰይ​ፍን አመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቻ​ች​ሁ​ንም አጠ​ፋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ይፈ​ር​ሳሉ፤ የፀ​ሐይ ምስ​ሎ​ቻ​ች​ሁም ይሰ​በ​ራሉ፤ የተ​ገ​ደሉ ሰዎ​ቻ​ች​ሁ​ንም በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ችሁ ፊት እጥ​ላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ሬሳ​ዎች በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸው ፊት አኖ​ራ​ለሁ፤ አጥ​ን​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቻ​ችሁ ዙሪያ እበ​ት​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="6">በም​ት​ኖ​ሩ​ባ​ትም ስፍራ ሁሉ ከተ​ሞች ይፈ​ር​ሳሉ፥ የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችም ሁሉ ውድማ ይሆ​ናሉ፤ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ይፈ​ር​ሳሉ፤ ባድ​ማም ይሆ​ናሉ፤ ጣዖ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ይሰ​በ​ራሉ፤ ያል​ቃ​ሉም፤ የፀ​ሐይ ምስ​ሎ​ቻ​ች​ሁም ይጠ​ፋሉ፤ ሥራ​ች​ሁም ይሻ​ራል።</verse>
				<verse number="7">ሙታ​ኖ​ቻ​ች​ሁም በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ይወ​ድ​ቃሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="8">“ነገር ግን በሀ​ገ​ሮች በተ​በ​ተ​ና​ችሁ ጊዜ ከእ​ና​ንተ ከአ​ሕ​ዛብ ጦር የዳ​ኑ​ትን አስ​ቀ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">በዚያ በተ​ማ​ረ​ኩ​በት በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ከእ​ና​ንተ የዳ​ኑት ያስ​ቡ​ኛል፤ ለሰ​ሰ​ኑ​በት፥ ከእ​ኔም ለራ​ቁ​በት ለል​ቡ​ና​ቸው፥ ለሰ​ሰኑ፥ ጣዖ​ት​ንም ለተ​ከ​ተሉ ለዓ​ይ​ኖ​ቻ​ቸው ማልሁ፤ ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ እን​ዳ​መ​ለኩ መጠን ስለ ሥራ​ቸው ክፋት ፊታ​ቸ​ውን ይነ​ጫሉ።</verse>
				<verse number="10">እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ፤ ይህን ክፉ ነገር አደ​ር​ግ​ባ​ቸው ዘንድ መና​ገሬ ለከ​ንቱ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ጅህ አጨ​ብ​ጭብ፤ በእ​ግ​ር​ህም አሸ​ብ​ሽብ፤ ስለ እስ​ራ​ኤል ቤት ርኵ​ሰት ሁሉ ወዮ ወዮ በል፤ በረ​ኀ​ብና በጦር፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ይጠ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="12">በሩቅ ያለው በቸ​ነ​ፈር ይሞ​ታል፤ በቅ​ር​ብም ያለው በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃል፤ በሀ​ገር የቀ​ረ​ውና የተ​ከ​በ​በ​ውም በራብ ይሞ​ታል፤ እን​ዲሁ መዓ​ቴን እፈ​ጽ​ም​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">ሬሳ​ዎ​ቻ​ቸው በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸው መካ​ከ​ልና በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ዙሪያ በወ​ደቁ ጊዜ በረ​ዣ​ዥም ኮረ​ብታ ሁሉ፥ በተ​ራ​ሮ​ችም ራሶች ሁሉ፥ በዕ​ን​ጨ​ቱም ጥላ ሥር ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ፥ መል​ካም መዓ​ዛን ባጠ​ኑ​በት ከቅ​ጠሉ ሁሉ በታች ሬሳ​ዎ​ቻ​ቸው በወ​ደቁ ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="14">እጄ​ንም እዘ​ረ​ጋ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በሚ​ኖ​ሩ​በ​ትም ስፍራ ሁሉ ምድ​ሪ​ቱን ከዴ​ብ​ላታ ምድረ በዳ ይልቅ ውድ​ማና በረሃ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ምድር እን​ዲህ ይላል፦ ፍጻሜ በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር ላይ መጣ፤ በም​ድ​ሪቱ በአ​ራ​ቱም ማዕ​ዘን ፍጻሜ መጣ።</verse>
				<verse number="3">አሁ​ንም ፍጻሜ በአ​ንቺ ላይ ደር​ሶ​አል። ቍጣ​ዬ​ንም እሰ​ድ​ድ​ብ​ሻ​ለሁ፤ እንደ መን​ገ​ድ​ሽም መጠን እፈ​ር​ድ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ጕስ​ቍ​ል​ና​ሽ​ንም ሁሉ አመ​ጣ​ብ​ሻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">ዐይ​ኔም አይ​ራ​ራ​ል​ሽም፤ እኔም ይቅር አል​ል​ሽም፤ መን​ገ​ድ​ሽ​ንም አመ​ጣ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ርኵ​ሰ​ት​ሽም በመ​ካ​ከ​ልሽ ነው፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="5">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ክፋት በክ​ፋት ላይ፤ እነሆ ይመ​ጣል።</verse>
				<verse number="6">ፍጻሜ መጥ​ቶ​አል፤ ፍጻሜ መጥ​ቶ​አል፤ ነቅ​ቶ​ብ​ሻል፤ እነሆ ደር​ሶ​አል።</verse>
				<verse number="7">በሀ​ገር የም​ት​ኖር ሆይ! ስብ​ራ​ትህ ጊዜው ደረሰ፤ ቀኑም ቀረበ፤ የሽ​ብር ቀን ነው እንጂ የተ​ራራ ላይ ዕል​ልታ አይ​ደ​ለም፤</verse>
				<verse number="8">አሁን በቅ​ርብ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ስ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ቍጣ​ዬ​ንም እፈ​ጽ​ም​ብ​ሻ​ለሁ፤ እን​ደ​መ​ን​ገ​ድ​ሽም መጠን እፈ​ር​ድ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ጕስ​ቍ​ል​ና​ሽ​ንም ሁሉ አመ​ጣ​ብ​ሻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">ዐይ​ኔም አይ​ራ​ራም፤ እኔም ይቅር አል​ልም፤ መን​ገ​ድ​ሽ​ንም አመ​ጣ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ርኵ​ሰ​ት​ሽም በመ​ካ​ከ​ልሽ ነው፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ቀ​ሥፍ እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="10">“እነሆ ቀኑ ደር​ሶ​አል፤ እነሆ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ወጥ​ታ​ለች፤ ስብ​ራ​ትህ ደር​ሶ​አል፤ ብት​ርም አብ​ባ​ለች፤ ስድ​ብም በዝ​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="11">የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛው ምር​ኩዝ ተሰ​በረ፤ በደል በዛች፤ ይኸ​ውም በሁ​ከት አይ​ደ​ለም፤ በች​ኮ​ላም አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="12">ጊዜው መጥ​ቶ​አል፤ ቀኑ እነሆ ቀር​ቦ​አል፤ መቅ​ሠ​ፍቷ በሁ​ለ​ን​ተ​ናዋ መል​ቶ​አ​ልና የሚ​ገዛ ደስ አይ​በ​ለው፤ የሚ​ሸ​ጥም አይ​ዘን።</verse>
				<verse number="13">የገ​ዛው ወደ ሻጩ አይ​መ​ለ​ስም፤ ዳግ​መ​ኛም በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፤ ሁለ​ን​ተ​ና​ዋን አይ​ቶ​አ​ልና አል​ተ​መ​ለ​ሰም፤ የሰው ሕይ​ወቱ በዐ​ይኑ ፊት ነው።</verse>
				<verse number="14">“መለ​ከ​ቱን ንፉ፤ ሁሉ​ንም አዘ​ጋጁ፤ ነገር ግን መዓቴ በብ​ዙ​ዎች ሁሉ ላይ ነውና ወደ ሰልፍ የሚ​ሄድ የለም።</verse>
				<verse number="15">ሰይፍ በውጭ፥ ቸነ​ፈ​ርና ራብ በው​ስጥ አለ፤ በሜዳ ያለው በሰ​ይፍ ይሞ​ታል፤ በከ​ተ​ማም ያለ​ውን ቸነ​ፈ​ርና ራብ ይፈ​ጁ​ታል።</verse>
				<verse number="16">ከእ​ነ​ር​ሱም የሚ​ሸሹ ይድ​ናሉ፤ መብ​ረ​ርን እን​ደ​ሚ​ማር ርግ​ብም በተ​ራራ ላይ ይሆ​ናሉ፤ እኔም በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ሁሉ እገ​ድ​ላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="17">እጅ ሁሉ ትደ​ክ​ማ​ለች፤ ጕል​በ​ትም ሁሉ እንደ ውኃ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="18">ማቅም ትታ​ጠ​ቃ​ላ​ችሁ፤ ድን​ጋ​ጤም ይሸ​ፍ​ና​ች​ኋል፤ በፊ​ትም ሁሉ ላይ ሐፍ​ረት ይሆ​ናል፤ በራ​ሳ​ች​ሁም ሁሉ ላይ ቡሃ​ነት ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="19">ብራ​ቸ​ውን በጎ​ዳ​ና​ዎቹ ላይ ይጥ​ላሉ፤ ወር​ቃ​ቸ​ውም ይረ​ክ​ሳል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓት ቀን ብራ​ቸ​ውና ወር​ቃ​ቸው አያ​ድ​ና​ቸ​ውም። እርሱ የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው እን​ቅ​ፋት ሆኖ​አ​ልና ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን አያ​ጠ​ግ​ቡም፤ ሆዳ​ቸ​ው​ንም አይ​ሞ​ሉም።</verse>
				<verse number="20">የክ​ብ​ሩ​ንም ጌጥ ወደ ትዕ​ቢት ለወጡ፤ የር​ኵ​ስ​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ምስ​ሎች አደ​ረ​ጉ​ባት፤ ስለ​ዚህ እኔ በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ርኩስ አድ​ር​ጌ​አ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="21">በባ​ዕ​ድም እጅ ለን​ጥ​ቂያ፥ በም​ድር ኀጢ​አ​ተ​ኞ​ችም እጅ ለብ​ዝ​በዛ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ያረ​ክ​ሱ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="22">ፊቴን ከእ​ነ​ርሱ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ሥር​ዐ​ቴ​ንም ያረ​ክ​ሳሉ፤ ኀይ​ለ​ኞች ይገ​ቡ​ባ​ታል፤ ያረ​ክ​ሱ​አ​ት​ማል።</verse>
				<verse number="23">“ምድር በአ​ሕ​ዛብ እንደ ተመ​ላች፥ ከተ​ማም በኀ​ጢ​አት ተመ​ል​ታ​ለ​ችና ሰን​ሰ​ለት ሥራ።</verse>
				<verse number="24">ከአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ከሁሉ የሚ​ከ​ፉ​ትን አመ​ጣ​ለሁ፤ ቤታ​ቸ​ው​ንም ይወ​ር​ሳሉ፥ የኀ​ያ​ላ​ን​ንም ትዕ​ቢት አጠ​ፋ​ለሁ፤ መቅ​ደ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ይረ​ክ​ሳሉ።</verse>
				<verse number="25">ጥፋት መጥ​ቶ​አል፤ ሰላ​ምም ይሻሉ፤ እር​ሱም አይ​ገ​ኝም።</verse>
				<verse number="26">ድን​ጋጤ በድ​ን​ጋጤ ላይ ይመ​ጣል፤ ወዮታ በወ​ዮታ ላይ ይከ​ተ​ላል፤ ከነ​ቢ​ዩም ዘንድ ራእ​ይን ይሻሉ፤ ከካ​ህ​ኑም ዘንድ ሕግ፥ ከሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ዘንድ ምክር ይጠ​ፋል።</verse>
				<verse number="27">ንጉ​ሡም ያለ​ቅ​ሳል፥ አለ​ቃም ውር​ደ​ትን ይለ​ብ​ሳል፤ የም​ድ​ርም ሕዝብ እጅ ትሰ​ላ​ለች፤ እንደ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም መጠን አደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በፍ​ር​ዳ​ቸ​ውም መጠን እፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ዓመት በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ቀን በቤቴ ተቀ​ምጬ ሳለሁ፥ የይ​ሁ​ዳም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች በፊቴ ተቀ​ም​ጠው ሳሉ፥ በዚያ የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በላዬ መጣ።</verse>
				<verse number="2">እኔም አየሁ፤ እነ​ሆም ከወ​ገቡ በታች እንደ እሳት የሚ​መ​ስል የሰው አም​ሳያ ነበረ፤ ከወ​ገ​ቡም ወደ ላይ እንደ ፀዳል ምሳሌ፥ እን​ደ​ሚ​ያ​ን​ጸ​ባ​ርቅ አይ​ነት ነበረ።</verse>
				<verse number="3">እጅ መሳ​ይ​ንም ዘረጋ፤ በራስ ጠጕ​ሬም ያዘኝ፤ መን​ፈ​ስም በም​ድ​ርና በሰ​ማይ መካ​ከል አነ​ሣኝ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ራእይ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ሰሜን ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ በር መግ​ቢያ ቅን​አት የተ​ባ​ለው ምስል ወደ አለ​በት አመ​ጣኝ፤</verse>
				<verse number="4">እነ​ሆም ቀድሞ በሜዳ እንደ አየ​ሁት ራእይ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ክብር በዚያ ነበረ።</verse>
				<verse number="5">እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ዐይ​ን​ህን ወደ ሰሜን መን​ገድ አንሣ” አለኝ። ዐይ​ኔ​ንም ወደ ሰሜን መን​ገድ አነ​ሣሁ፤ እነ​ሆም በመ​ሠ​ዊ​ያው በር በሰ​ሜን በኩል በመ​ግ​ቢ​ያው ይህ የቅ​ን​ዓት ምስል ነበረ። ከዚ​ያም ወደ ምሥ​ራቅ ያስ​ገ​ባል።</verse>
				<verse number="6">እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ከመ​ቅ​ደሴ ያር​ቁኝ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት በዚህ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን፥ ታላ​ቁን ርኵ​ሰት ታያ​ለ​ህን? ደግ​ሞም ተመ​ል​ሰህ ከዚህ የበ​ለጠ ታላቅ ርኵ​ሰት ታያ​ለህ” አለኝ።</verse>
				<verse number="7">ወደ አደ​ባ​ባ​ዩም መግ​ቢያ አስ​ገ​ባኝ፤ በአ​የ​ሁም ጊዜ፥ እነሆ በግ​ንቡ ውስጥ ፉካ ነበረ።</verse>
				<verse number="8">እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ግን​ቡን ንደ​ለው” አለኝ፤ ግን​ቡ​ንም በነ​ደ​ል​ሁት ጊዜ ደጃፍ አገ​ኘሁ።</verse>
				<verse number="9">እር​ሱም፥ “ግባ፤ በዚህ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ክፉ​ውን ርኵ​ሰት እይ” አለኝ።</verse>
				<verse number="10">እኔም ገባ​ሁና፥ እነሆ በግ​ንቡ ዙሪያ ላይ የተ​ን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች አዕ​ዋ​ፍና እን​ስ​ሳ​ትን ምሳሌ ከን​ቱና ርኩስ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቤት ጣዖ​ታት ሁሉ ተሥ​ለው አየሁ።</verse>
				<verse number="11">በፊ​ታ​ቸ​ውም ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሰባ ሰዎ​ችና የሳ​ፋን ልጅ ያእ​ዛ​ንያ ቆመው ነበር፤ ሰውም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ በእጁ ጥና​ውን ይዞ ነበር፥ የዕ​ጣ​ኑም ጢስ ሽታ ይወጣ ነበር።</verse>
				<verse number="12">እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሽማ​ግ​ሌ​ዎች በስ​ውር እያ​ን​ዳ​ንዱ በሥ​ዕሉ ቤት የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን አይ​ተ​ሃ​ልን? እነ​ርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አያ​የ​ንም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ሪ​ቱን ትቶ​አ​ታል ይላ​ሉና” አለኝ።</verse>
				<verse number="13">እር​ሱም፥ “ከዚያ የበ​ለ​ጠ​ውን የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ታላቅ ኀጢ​አት ታይ ዘንድ ና” አለኝ።</verse>
				<verse number="14">ወደ ሰሜ​ንም ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በር አመ​ጣኝ፤ እነ​ሆም፥ ሴቶች ለተ​ሙዝ እያ​ለ​ቀሱ በዚያ ተቀ​ም​ጠው ነበር።</verse>
				<verse number="15">እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን አይ​ተ​ሃ​ልን? ደግሞ ከዚህ የበ​ለጠ ርኵ​ሰት ታያ​ለህ” አለኝ።</verse>
				<verse number="16">ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ አመ​ጣኝ፤ እነ​ሆም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ መግ​ቢያ ፊት በወ​ለ​ሉና በመ​ሠ​ዊ​ያው መካ​ከል ሃያ አም​ስት የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ፤ ጀር​ባ​ቸ​ውም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ፥ ፊታ​ቸ​ውም ወደ ምሥ​ራቅ ነበረ፤ እነ​ር​ሱም ወደ ምሥ​ራቅ ለፀ​ሐይ ይሰ​ግዱ ነበር።</verse>
				<verse number="17">እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን አይ​ተ​ሃ​ልን? በዚህ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ይህን ኀጢ​አት ያደ​ርጉ ዘንድ ለይ​ሁዳ ቤት ጥቂት ነገር ነውን? ምድ​ሪ​ቱን በኀ​ጢ​አት ሞል​ተ​ዋ​ታል፤ ያስ​ቈ​ጡ​ኝም ዘንድ ተመ​ል​ሰ​ዋል፤ እነ​ሆም ቅር​ን​ጫ​ፉን አስ​ረ​ዝ​መ​ዋል። ይዘ​ባ​በ​ታ​ሉም።</verse>
				<verse number="18">ስለ​ዚህ እኔ ደግሞ በመ​ዓት እሠ​ራ​ለሁ፤ ዐይኔ አይ​ራ​ራም፤ እኔም ይቅ​ርታ አላ​ደ​ር​ግም፤ ወደ ጆሮ​ዬም በታ​ላቅ ድምፅ ቢጮኹ አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም” አለኝ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">እር​ሱም፥ “እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው የሚ​ያ​ጠ​ፉ​ባት መሣ​ሪ​ያን በእ​ጃ​ቸው ይዘው ከተ​ማ​ዪ​ቱን የሚ​ቀ​ሥፉ ይቅ​ረቡ” ብሎ በታ​ላቅ ድምፅ በጆ​ሮዬ ጮኸ።</verse>
				<verse number="2">እነ​ሆም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ገጀሞ መሣ​ሪያ በእ​ጃ​ቸው ይዘው ስድ​ስት ሰዎች ወደ ሰሜን ከሚ​መ​ለ​ከ​ተው ከላ​ይ​ኛው በር መን​ገድ መጡ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም የበ​ፍታ ልብስ የለ​በ​ሰና የሰ​ን​ፔር መታ​ጠ​ቂያ በወ​ገቡ የታ​ጠቀ አንድ ሰው ነበረ። እነ​ር​ሱም ገብ​ተው በናሱ መሠ​ዊያ አጠ​ገብ ቆሙ።</verse>
				<verse number="3">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ክብር በበ​ላዩ ከነ​በ​ረ​በት ኪሩብ ተነ​ሥቶ ወደ ቤቱ መድ​ረክ ሄዶ ነበር፤ በፍ​ታም የለ​በ​ሰ​ውን፥ የሰ​ን​ፔር መታ​ጠ​ቂ​ያም በወ​ገቡ የታ​ጠ​ቀ​ውን ሰው ጠራ።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በከ​ተ​ማ​ዪቱ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መካ​ከል እለፍ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ዋም ስለ ተሠ​ራው ኀጢ​አት ሁሉ በሚ​ያ​ለ​ቅ​ሱና በሚ​ተ​ክዙ ሰዎች ግን​ባር ላይ ምል​ክት ጻፍ አለው።</verse>
				<verse number="5">እኔም እየ​ሰ​ማሁ ለሌ​ሎቹ፦ በስ​ተ​ኋ​ላው ወደ ከተ​ማው ግቡ፤ ግደ​ሉም፤ ዐይ​ና​ችሁ አይ​ራራ፤ ይቅ​ርም አት​በሉ፤</verse>
				<verse number="6">ሽማ​ግ​ሌ​ው​ንና ጎበ​ዙን፥ ድን​ግ​ሊ​ቱ​ንም፥ ሕፃ​ና​ቱ​ንና ሴቶ​ቹን፥ ፈጽ​ማ​ችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምል​ክቱ ወደ አለ​በት ሰው ሁሉ አት​ቅ​ረቡ፤ በመ​ቅ​ደ​ሴም ጀምሩ” አላ​ቸው። በቤ​ቱም አን​ጻር ባሉ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጀመሩ።</verse>
				<verse number="7">እር​ሱም፥ “ቤቱን አር​ክሱ፤ ወጥ​ታ​ችሁ ግደሉ፤ በሙ​ታ​ንም መን​ገ​ዶ​ችን ሙሉ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">ሲገ​ድ​ሉም እኔ ብቻ​ዬን ቀርቼ ሳለሁ በግ​ን​ባሬ ተደ​ፍቼ፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! ወዮ! መዓ​ት​ህን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ስታ​ፈ​ስስ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቅሬታ ሁሉ ታጠ​ፋ​ለ​ህን?” ብዬ ጮኽሁ።</verse>
				<verse number="9">እር​ሱም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልና የይ​ሁዳ ቤት ኀጢ​አት እጅግ በዝ​ቶ​አል፤ ምድ​ሪ​ቱም በብዙ አሕ​ዛብ እንደ ተመ​ላች ከተ​ማ​ዪ​ቱም እን​ዲሁ ዓመ​ፅ​ንና ርኵ​ሰ​ትን ተሞ​ል​ታ​ለች፤ እነ​ር​ሱም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ሪ​ቱን ትቶ​አ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አያ​ይም” ብለ​ዋል።</verse>
				<verse number="10">“እኔም ደግሞ በዐ​ይኔ አል​ራ​ራም፤ ይቅ​ር​ታም አላ​ደ​ር​ግም፤ መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንም በራ​ሳ​ቸው ላይ እመ​ል​ሳ​ለሁ” አለኝ።</verse>
				<verse number="11">እነ​ሆም በፍታ የለ​በ​ሰው፥ የሰ​ን​ፔር መታ​ጠ​ቂ​ያም በወ​ገቡ የታ​ጠ​ቀው ሰው መጣ፥ “ያዘ​ዝ​ኸ​ኝ​ንም አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ” ብሎ በቃሉ መለሰ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">እኔም አየሁ፤ እነ​ሆም በኪ​ሩ​ቤል ራስ ላይ ባለው ጠፈር በላ​ያ​ቸው እንደ ሰን​ፔር ድን​ጋይ ያለ ዙፋን የሚ​መ​ስል መልክ ተገ​ለጠ።</verse>
				<verse number="2">በፍ​ታም የለ​በ​ሰ​ውን ሰው፥ “በመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮች መካ​ከል በኪ​ሩብ በታች ግባ፤ ከኪ​ሩ​ቤ​ልም መካ​ከል ከአ​ለው እሳት ፍም እጆ​ች​ህን ሙላ፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ላይ በት​ነው” ብሎ ተና​ገ​ረው። እኔም እያ​የሁ ገባ።</verse>
				<verse number="3">ሰው​የ​ውም ሲገባ ኪሩ​ቤል በቤቱ ቀኝ በኩል ቆመው ነበር፤ ደመ​ና​ውም ውስ​ጠ​ኛ​ውን አደ​ባ​ባይ ሞላ።</verse>
				<verse number="4">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ርም ከኪ​ሩ​ቤል ወጥቶ በቤቱ መድ​ረክ ላይ ቆመ፤ ቤቱም በደ​መ​ናው ተሞላ፤ አደ​ባ​ባ​ዩም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ፀዳል ተሞላ።</verse>
				<verse number="5">የኪ​ሩ​ቤ​ልም የክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው ድምፅ ሁሉን የሚ​ችል አም​ላክ እን​ደ​ሚ​ና​ገ​ረው ያለ ድምፅ እስከ ውጭው አደ​ባ​ባይ ድረስ በሩቅ ይሰማ ነበር።</verse>
				<verse number="6">የተ​ቀ​ደሰ በፍ​ታም የለ​በ​ሰ​ውን ሰው፥ “ከመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮቹ ከኪ​ሩ​ቤል መካ​ከል እሳት ውሰድ” ብሎ በአ​ዘ​ዘው ጊዜ እርሱ ገብቶ በመ​ን​ኰ​ራ​ኵር አጠ​ገብ ቆመ።</verse>
				<verse number="7">ከኪ​ሩ​ቤል መካ​ከ​ልም አንዱ ኪሩብ እጁን በኪ​ሩ​ቤል መካ​ከል ወደ አለው እሳት ዘር​ግቶ ከዚያ እሳት ወሰደ፤ የተ​ቀ​ደሰ በፍ​ታም በለ​በ​ሰው ሰው እጅ አኖ​ረው፤ እር​ሱም ይዞ ወጣ።</verse>
				<verse number="8">ኪሩ​ቤ​ል​ንም አየሁ፤ ከክ​ን​ፎ​ቻ​ቸ​ውም በታች የሰው እጅ መሳይ አለ።</verse>
				<verse number="9">እኔም አየሁ፤ እነ​ሆም በኪ​ሩ​ቤል አጠ​ገብ አራት መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮች ነበሩ፤ አንዱ መን​ኰ​ራ​ኵር በአ​ንዱ ኪሩብ፥ አንዱ መን​ኰ​ራ​ኵር በአ​ንዱ ኪሩብ አጠ​ገብ ነበረ። የመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ቹም መልክ እንደ ቢረሌ ድን​ጋይ ነበረ።</verse>
				<verse number="10">የአ​ራ​ቱም መልክ አንድ ይመ​ስል ነበር፤ መል​ካ​ቸ​ውም በመ​ን​ኰ​ራ​ኵር ውስጥ እንደ አለ መን​ኰ​ራ​ኵር ነበረ።</verse>
				<verse number="11">ሲሔ​ዱም በአ​ራቱ ጎድ​ና​ቸው ይሄዱ ነበር። ሲሄ​ዱም ወዲ​ያና ወዲህ አይ​ሉም ነበር፤ መጀ​መ​ሪ​ያው ወደ​ሚ​ያ​መ​ለ​ክ​ት​በት ስፍራ ይሄዱ ነበር፤ ሲሄ​ዱም ወዲ​ያና ወዲህ አይ​ሉም ነበር።</verse>
				<verse number="12">ገላ​ቸ​ውም ሁሉ፥ ጀር​ባ​ቸ​ውም፥ እጆ​ቻ​ቸ​ውም፤ ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውም፥ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ቹም፤ ለአ​ራቱ የነ​በሩ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮች በዙ​ሪ​ያ​ቸው ዐይ​ኖች ተሞ​ል​ተው ነበር።</verse>
				<verse number="13">አራ​ቱም መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮች እኔ እየ​ሰ​ማሁ ጌል​ጌል ተብ​ለው ተጠሩ።</verse>
				<verse number="14">ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም አራት አራት ፊት ነበ​ሩት፤ አን​ደ​ኛው ፊት የኪ​ሩብ ፊት፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም የሰው ፊት፥ ሦስ​ተ​ኛው የአ​ን​በሳ ፊት፥ አራ​ተ​ኛ​ውም የን​ስር ፊት ነበረ።</verse>
				<verse number="15">እነ​ዚ​ህም በኮ​ቦር ወንዝ በእ​ን​ስ​ሶች አም​ሳል ያየ​ኋ​ቸው ኪሩ​ቤል በረሩ።</verse>
				<verse number="16">ኪሩ​ቤ​ልም ሲሄዱ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮቹ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ተያ​ይ​ዘው ይሄዱ ነበር፤ ኪሩ​ቤ​ልም ይበሩ ዘንድ ክን​ፋ​ቸ​ውን ከም​ድር በሚ​ያ​ነሡ ጊዜ ከእ​ነ​ርሱ ጋር የተ​ያ​ያዘ መን​ኰ​ራ​ኵ​ራ​ቸው አይ​መ​ለ​ስም ነበር።</verse>
				<verse number="17">የሕ​ይ​ወት መን​ፈስ በው​ስ​ጣ​ቸው ነበ​ርና እነ​ዚህ ሲቆሙ እነ​ዚ​ያም ይቆሙ ነበር፤ እነ​ዚ​ህም ሲበ​ርሩ፥ እነ​ዚያ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይበ​ርሩ ነበር።</verse>
				<verse number="18">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ከቤቱ መድ​ረክ ላይ ወጥቶ በኪ​ሩ​ቤል ላይ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="19">ኪሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ዘረጉ፤ እኔም እያ​የሁ ከም​ድር በረሩ፤ በወ​ጡም ጊዜ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮቹ በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸው ነበሩ፤ፊት ለፊት በአ​ለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መግ​ቢያ በር ዳርቻ ቆሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ክብር ከእ​ነ​ርሱ ጋራ በላ​ያ​ቸው ነበረ።</verse>
				<verse number="20">ይህ በኮ​ቦር ወንዝ ከእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በታች ያየ​ሁት እን​ስሳ ነው፤ ኪሩ​ቤ​ልም እንደ ነበሩ ዐወ​ቅሁ።</verse>
				<verse number="21">ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አራት አራት ፊት፥ ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም አራት አራት ክንፍ ነበ​ሩት፤ የሰ​ውም እጅ አም​ሳያ ከክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው በታች ነበረ።</verse>
				<verse number="22">ፊቶ​ቻ​ቸ​ውም በኮ​ቦር ወንዝ ከእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ክብር በታች ያየ​ኋ​ቸ​ውን ፊቶች ይመ​ስሉ ነበር፤ እነ​ር​ሱና መል​ካ​ቸ​ውም እን​ዲሁ ነበረ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም አቅ​ንቶ ወደ ፊት ይሄድ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">መን​ፈ​ስም አነ​ሣኝ፤ ወደ ምሥ​ራ​ቅም አን​ጻር ወደ​ሚ​ያ​ሳ​የው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በር ወሰ​ደኝ። እነ​ሆም በበሩ መግ​ቢያ ሃያ አም​ስት ሰዎች ነበሩ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም የሕ​ዝ​ቡን አለ​ቆች የዓ​ዙ​ርን ልጅ ያእ​ዛ​ን​ያ​ንና የበ​ና​ያስ ልጅ ፈላ​ጥ​ያን አየሁ።</verse>
				<verse number="2">እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነ​ዚህ ከን​ቱን የሚ​ያ​ስቡ፥ በዚ​ችም ከተማ ክፉን ምክር የሚ​መ​ክሩ ሰዎች ናቸው።</verse>
				<verse number="3">እነ​ር​ሱም፦ በውኑ ቤቶች በድ​ን​ገት የሚ​ሠሩ አይ​ደ​ለ​ምን? ይህች ከተማ ድስት እኛም ሥጋ ነን ብለ​ዋል።</verse>
				<verse number="4">ስለ​ዚህ የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት ተና​ገ​ር​ባ​ቸው፤ ትን​ቢት ተና​ገር።”</verse>
				<verse number="5">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በላዬ መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል ብለህ ተና​ገር፦ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ይህን ነገር ተና​ግ​ራ​ች​ኋል፤ እኔም የሰ​ው​ነ​ታ​ች​ሁን በደል አው​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="6">በዚ​ህች ከተማ ውስጥ ግዳ​ዮ​ቻ​ች​ሁን አብ​ዝ​ታ​ች​ኋል፤ በጎ​ዳ​ና​ዎ​ች​ዋም ሙታ​ና​ች​ሁን ሞል​ታ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="7">ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በመ​ካ​ከ​ልዋ ያኖ​ራ​ች​ኋ​ቸው ግዳ​ዮ​ቻ​ችሁ እነ​ርሱ ሥጋ ናቸው፤ ይህ​ችም ከተማ ድስት ናት፤ እና​ን​ተን ግን ከመ​ካ​ከ​ልዋ አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">ሰይ​ፍን ትፈ​ራ​ላ​ችሁ፤ እኔም ሰይ​ፍን አመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="9">ከመ​ካ​ከ​ል​ዋም አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ በባ​ዕ​ዳ​ንም እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ በላ​ያ​ች​ሁም ፍር​ድን አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">በሰ​ይፍ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተራ​ሮች እፈ​ር​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="11">ይህች ከተማ ድስት አት​ሆ​ን​ላ​ች​ሁም፤ እና​ን​ተም በመ​ካ​ከ​ልዋ ሥጋ አት​ሆ​ኑም፤ እኔም በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች እፈ​ር​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="12">በት​እ​ዛዜ አል​ሄ​ዳ​ች​ሁ​ምና፥ ፍር​ዴ​ንም አላ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ምና፥ በዙ​ሪ​ያ​ች​ሁም እን​ደ​ሚ​ኖ​ሩት እንደ አሕ​ዛብ ሕግ አድ​ር​ጋ​ች​ኋል።”</verse>
				<verse number="13">ትን​ቢ​ትም በተ​ና​ገ​ርሁ ጊዜ የበ​ና​ያስ ልጅ ፈላ​ጥያ ሞተ፤ እኔም በግ​ን​ባሬ ተደ​ፍቼ፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! ወዮ! ወዮ​ልኝ! በውኑ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቅሬታ ፈጽ​መህ ታጠ​ፋ​ለ​ህን?” ብዬ በታ​ላቅ ድምፅ ጮኽሁ።</verse>
				<verse number="14">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="15">“የሰው ልጅ ሆይ! በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖሩ፦ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ራቁ፤ ይህች ምድር ርስት ሆና ለእኛ ተሰ​ጥ​ታ​ለች የሚ​ሉ​አ​ቸው ወን​ድ​ሞ​ች​ህና ዘመ​ዶ​ችህ፥ የም​ርኮ ሰዎ​ች​ህም ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ ያል​ቃሉ።</verse>
				<verse number="16">ስለ​ዚህ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ ወደ አሕ​ዛብ አር​ቄ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ ሀገ​ሮ​ችም እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ይሁን እንጂ በመ​ጡ​ባ​ቸው ሀገ​ሮች በእ​ነ​ዚያ ትንሽ መቅ​ደስ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ በል።</verse>
				<verse number="17">ስለ​ዚ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከአ​ሕ​ዛብ ዘንድ እቀ​በ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከበ​ተ​ን​ሁ​ባ​ቸ​ውም ሀገ​ሮች እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ምድር እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="18">ወደ​ዚ​ያም ይመ​ጣሉ፤ በደ​ል​ንና ርኵ​ሰ​ት​ንም ሁሉ ከእ​ር​ስዋ ያስ​ወ​ግ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="19">ሌላ ልብ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም አዲስ መን​ፈስ አሳ​ድ​ራ​ለሁ፤ ከሥ​ጋ​ቸ​ውም ውስጥ የድ​ን​ጋ​ዩን ልብ አወ​ጣ​ለሁ፤ የሥ​ጋ​ንም ልብ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="20">በት​እ​ዛ​ዜም ይሄዱ ዘንድ፥ ፍር​ዴ​ንም ይጠ​ብ​ቁና ያደ​ርጉ ዘንድ እነ​ርሱ ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል፥ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="21">ጣዖት በሚ​ያ​መ​ል​ኩ​በት ልባ​ቸ​ውና በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው እንደ ልባ​ቸው ቢሄዱ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን በራ​ሳ​ቸው ላይ እመ​ል​ሳ​ለሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="22">ኪሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ዘረጉ፥ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ችም በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸው ነበሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ክብር በላ​ያ​ቸው ነበረ።</verse>
				<verse number="23">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ከከ​ተ​ማ​ዪቱ መካ​ከል ተነ​ሥቶ በከ​ተ​ማ​ዪቱ ምሥ​ራቅ በኩል በአ​ለው ተራራ ላይ ቆመ።</verse>
				<verse number="24">መን​ፈ​ስም አነ​ሣኝ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በራ​እይ ወደ ከላ​ው​ዴ​ዎን ምድር ወደ ምር​ኮ​ኞቹ አመ​ጣኝ።</verse>
				<verse number="25">ያየ​ሁ​ትም ራእይ ከእኔ ወጣ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያሳ​የ​ኝን ነገር ሁሉ ለም​ር​ኮ​ኞች ተና​ገ​ርሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“የሰው ልጅ ሆይ! በዐ​መ​ፀኛ ቤት መካ​ከል ተቀ​ም​ጠ​ሃል፤ እነ​ርሱ ያዩ ዘንድ ዐይን አላ​ቸው ነገር ግን አያ​ዩም፤ ይሰ​ሙም ዘንድ ጆሮ አላ​ቸው፤ ነገር ግን አይ​ሰ​ሙም፤ እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና።</verse>
				<verse number="3">አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! የስ​ደ​ተኛ እክት አዘ​ጋጅ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ቀን ለቀን ተማ​ረክ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ከስ​ፍራ ወደ ሌላ ስፍራ ተማ​ር​ከህ ሂድ፤ እነ​ር​ሱም ዐመ​ፀኛ ቤት እንደ ሆኑ ምን​አ​ል​ባት ያስ​ተ​ውሉ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="4">ቀን ለቀ​ንም በፊ​ታ​ቸው እክ​ት​ህን እንደ ስደ​ተኛ እክት አው​ጣው፤ በማ​ታም ጊዜ በዐ​ይ​ና​ቸው እያ​ዩህ ስደ​ተ​ኞች እን​ደ​ሚ​ወጡ እን​ዲሁ ውጣ።</verse>
				<verse number="5">በፊ​ታ​ቸ​ውም ግን​ቡን ነድ​ለህ በዚያ ውጣ።</verse>
				<verse number="6">ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ምል​ክት አድ​ር​ጌ​ሃ​ለ​ሁና በፊ​ታ​ቸው ዕቃ​ህን በት​ከ​ሻህ ላይ አን​ግ​ተው፤ በጨ​ለ​ማም ተሸ​ክ​መህ ውጣ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም እን​ዳ​ታይ ፊት​ህን ሸፍን።”</verse>
				<verse number="7">እን​ዳ​ዘ​ዘ​ኝም አደ​ረ​ግሁ፤ ቀን ለቀ​ንም እክ​ቴን እንደ ስደ​ተኛ እክት አወ​ጣሁ፤ በማ​ታም ጊዜ ግን​ቡን በእጄ ነደ​ልሁ፤ በጨ​ለ​ማም አወ​ጣ​ሁት፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም በት​ከ​ሻዬ ላይ አን​ግቼ ተሸ​ከ​ም​ሁት።</verse>
				<verse number="8">በነ​ጋ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="9">“የሰው ልጅ ሆይ! ዐመ​ፀኛ ቤት የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት፦ የም​ታ​ደ​ር​ገው ምን​ድር ነው? አላ​ሉ​ህ​ምን?</verse>
				<verse number="10">አን​ተም፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህ ሸክም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሚ​ኖ​ረው አለቃ ላይ፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም በሚ​ኖ​ሩት በእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ላይ ነው በላ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ደግ​ሞም፦ እኔ ምል​ክ​ታ​ችሁ ነኝ፤ እኔ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እን​ዲሁ ይደ​ረ​ግ​ባ​ቸ​ዋል፥ እነ​ር​ሱ​ንም ማር​ከው ይወ​ስ​ዷ​ቸ​ዋል በል።</verse>
				<verse number="12">በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም የሚ​ኖ​ረው አለቃ በት​ከ​ሻው ላይ አን​ግቶ በጨ​ለማ ይወ​ጣል፤ በዚያ ያወጡ ዘንድ ግን​ቡን ይነ​ድ​ላሉ፤ በዐ​ይ​ኑም ምድ​ርን እን​ዳ​ያይ ፊቱን ይሸ​ፍ​ናል።</verse>
				<verse number="13">መረ​ቤ​ንም በእ​ርሱ ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ በወ​ጥ​መ​ዴም ይያ​ዛል፤ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም ምድር ወደ ባቢ​ሎን አመ​ጣ​ዋ​ለሁ፤ ሆኖም አያ​ያ​ትም፤ በዚ​ያም ይሞ​ታል።</verse>
				<verse number="14">የሚ​ረ​ዱ​ት​ንም፥ በዙ​ሪ​ያው ያሉ​ትን ሁሉ፥ ጭፍ​ሮ​ቹ​ንም ሁሉ ወደ ነፋ​ሳት ሁሉ እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በኋ​ላ​ቸ​ውም ሰይ​ፍን እመ​ዝ​ዛ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል በም​በ​ት​ና​ቸው ጊዜ፥ በሀ​ገ​ሮ​ችም በም​ዘ​ራ​ቸው ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="16">በሚ​ሄ​ዱ​ባ​ቸ​ውም አሕ​ዛብ መካ​ከል ርኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ይና​ገሩ ዘንድ ከሰ​ይ​ፍና ከራብ፥ ከቸ​ነ​ፈ​ርም ጥቂ​ቶች ሰዎ​ችን ከእ​ነ​ርሱ አስ​ቀ​ራ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”</verse>
				<verse number="17">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="18">“የሰው ልጅ ሆይ! እን​ጀ​ራ​ህን በመ​ታ​ወክ ብላ፤ ውኃ​ህ​ንም በፍ​ር​ሃ​ትና በድ​ን​ጋጤ ጠጣ፤</verse>
				<verse number="19">ለም​ድ​ሪ​ቱም ሕዝብ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስለ​ሚ​ኖሩ ስለ እስ​ራ​ኤል ምድ​ርም እን​ዲህ ይላል፦ የሚ​ኖ​ሩ​ባት ሁሉ በዐ​መፅ ይኖ​ራ​ሉና ምድ​ሪቱ በመ​ላዋ ትጠፋ ዘንድ እን​ጀ​ራ​ቸ​ውን በች​ግር ይበ​ላሉ፤ ውኃ​ቸ​ው​ንም በድ​ን​ጋጤ ይጠ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="20">ሰዎች የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸው ከተ​ሞች ይጠ​ፋሉ፤ ምድ​ሪ​ቱም ውድማ ትሆ​ና​ለች፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ በላ​ቸው።”</verse>
				<verse number="21">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="22">“የሰው ልጅ ሆይ! በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር፦ ዘመኑ ረዝ​ሞ​አል፤ ራእ​ዩም ሁሉ ጠፍ​ቶ​አል የም​ት​ሉት ምሳ​ሌው ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="23">ስለ​ዚህ እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህን ምሳሌ አስ​ቀ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ደግሞ ምሳሌ አድ​ር​ገው አይ​ና​ገ​ሩ​ትም፤ አንተ ግን፦ ዘመ​ኑና የራ​እዩ ሁሉ ነገር ቀር​ቦ​አል በላ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">ከዚ​ህም በኋላ በእ​ስ​ራ​ኤል ቤት መካ​ከል ከንቱ ራእ​ይና ውሸ​ተኛ ምዋ​ርት አይ​ሆ​ንም።</verse>
				<verse number="25">እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ የም​ና​ገ​ረ​ውም ቃል ይፈ​ጸ​ማል፤ ደግ​ሞም አይ​ዘ​ገ​ይም፤ እና​ንተ ዐመ​ፀኛ ቤት ሆይ! በዘ​መ​ና​ችሁ ቃሌን እና​ገ​ራ​ለሁ፤ እፈ​ጽ​መ​ው​ማ​ለሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="26">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="27">“የሰው ልጅ ሆይ! ዐመ​ፀ​ኛው የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት፦ ይህቺ የሚ​ያ​ያት ራእይ ለብዙ ዘመን ናት፤ እር​ሱም ለሩቅ ወራት ትን​ቢ​ትን ይና​ገ​ራል” ይላሉ።</verse>
				<verse number="28">ስለ​ዚህ በላ​ቸው፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የም​ና​ገ​ረው ቃል ይፈ​ጸ​ማል እንጂ ከቃሌ ሁሉ ደግሞ የሚ​ዘ​ገይ የለም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት በሚ​ና​ገሩ በእ​ስ​ራ​ኤል ነቢ​ያት ላይ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ከገዛ ልባ​ቸ​ውም ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ በላ​ቸው፤</verse>
				<verse number="3">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ፈጽሞ ሳያዩ ከገዛ ልባ​ቸው አን​ቅ​ተው ትን​ቢት ለሚ​ና​ገሩ ወዮ​ላ​ቸው!</verse>
				<verse number="4">እስ​ራ​ኤል ሆይ! ነቢ​ያ​ትህ በም​ድረ በዳ እን​ደ​ሚ​ኖሩ ቀበ​ሮ​ዎች ናቸው።</verse>
				<verse number="5">ወደ ተሰ​በ​ረው ቅጥር አል​ወ​ጣ​ች​ሁም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀን በሰ​ልፍ ትቆሙ ዘንድ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ቅጥ​ርን አል​ሠ​ራ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሳይ​ል​ካ​ቸው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይላል የሚሉ ሰዎች ሐሰ​ትን ያያሉ፤ ከን​ቱን ያም​ዋ​ር​ታሉ፤ ቃሉ​ንም ማጽ​ናት ይጀ​ም​ራሉ።</verse>
				<verse number="7">እኔም ሳል​ና​ገር፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ​አል ስትሉ፥ ከንቱ ምዋ​ር​ትን የተ​ና​ገ​ራ​ችሁ፥ የሐ​ሰት ራእ​ይ​ንም ያያ​ችሁ አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን?”</verse>
				<verse number="8">ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ከንቱ ነገ​ርን ስለ ተና​ገ​ራ​ችሁ፥ ሐሰ​ተኛ ራእ​ይ​ንም ስለ አያ​ችሁ፥ ስለ​ዚህ እነሆ እኔ በእ​ና​ንተ ላይ ነኝ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="9">እጄም ሐሰ​ተኛ ራእ​ይን በሚ​ያዩ፥ ሕዝ​ቤ​ንም ለማ​ታ​ለል በከ​ንቱ በሚ​ያ​ም​ዋ​ርቱ ነቢ​ያት ላይ ትሆ​ና​ለች። እነ​ር​ሱም በሕ​ዝቤ ማኅ​በር ውስጥ አይ​ኖ​ሩም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት መጽ​ሐፍ አይ​ጻ​ፉም፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ምድር አይ​ገ​ቡም፤ እኔም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="10">ሰላም ሳይ​ኖር፦ ሰላም እያሉ ሕዝ​ቤን አታ​ል​ለ​ዋ​ልና፤ አን​ዱም ሰው ቅጥር ሲሠራ እነ​ርሱ ያለ​ገ​ለባ ይመ​ር​ጉ​ታል፤ ይወ​ድ​ቃ​ልም፤</verse>
				<verse number="11">ያለ ገለ​ባም ለሚ​መ​ር​ጉት ሰዎች፦ ይወ​ድ​ቃል በላ​ቸው። የሚ​ያ​ሰ​ጥም ዝናብ ይዘ​ን​ባል፤ ታላ​ቅም የበ​ረዶ ድን​ጋይ በራ​ሳ​ቸው ላይ አወ​ር​ዳ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይወ​ድ​ቃሉ፤ ኀይ​ለኛ ዐውሎ ነፋ​ስም ይሰ​ነ​ጣ​ጥ​ቀ​ዋል።</verse>
				<verse number="12">እነሆ ግንቡ በወ​ደቀ ጊዜ፦ የመ​ረ​ጋ​ች​ሁት ምርግ ወዴት አለ? አይ​ሉ​አ​ች​ሁ​ምን?</verse>
				<verse number="13">ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በመ​ዓቴ በዐ​ውሎ ነፋስ እሰ​ነ​ጣ​ጥ​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ያጠ​ፋ​ውም ዘንድ በቍ​ጣዬ የሚ​ያ​ሰ​ጥም ዝናብ፥ በመ​ዓ​ቴም ታላቅ የበ​ረዶ ድን​ጋይ አወ​ር​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">ያለ ገለባ የመ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ት​ንም ቅጥር አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ ይወ​ድ​ቃል፤ ወደ ምድ​ርም እጥ​ለ​ዋ​ለሁ፤ መሠ​ረ​ቱም ይታ​ያል፤ እር​ሱም ይና​ዳል፤ በመ​ካ​ከ​ሉም ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="15">መዓ​ቴ​ንም በግ​ንቡ ላይና ያለ​ገ​ለባ በመ​ረ​ጉት ላይ እፈ​ጽ​ማ​ለሁ፤ ግን​ቡም ይወ​ድ​ቃል፤ እኔም፦ ግን​ቡና መራ​ጊ​ዎቹ የሉም እላ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">እነ​ር​ሱም ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ትን​ቢት የሚ​ና​ገሩ፥ የሰ​ላ​ም​ንም ራእይ የሚ​ያ​ዩ​ላት የእ​ስ​ራ​ኤል ነቢ​ያት ናቸው፤ ሰላ​ምም የለም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="17">“አን​ተም፥ የሰው ልጅ ሆይ! ከል​ባ​ቸው አን​ቅ​ተው ትን​ቢት በሚ​ና​ገሩ በሕ​ዝ​ብህ ሴቶች ልጆች ላይ ፊት​ህን አድ​ርግ፤ ትን​ቢ​ትም ተና​ገ​ር​ባ​ቸው፤</verse>
				<verse number="18">እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ነፍ​ስን ለማ​ጥ​መድ ለእጅ ድጋፍ ሁሉ መከዳ ለሚ​ሰፉ፥ ለሰ​ውም ሁሉ ራስ እንደ እየ​ቁ​መቱ ሽፋን ለሚ​ሠሩ ሴቶች ወዮ​ላ​ቸው! የሕ​ዝ​ቤን ነፍስ ታጠ​ም​ዳ​ላ​ችሁ፤ በውኑ እና​ንተ ነፍ​ሳ​ች​ሁን ታድ​ና​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="19">ከንቱ ነገ​ርን ለሚ​ሰ​ሙት ሕዝቤ እየ​ዋ​ሻ​ችሁ ሞት የማ​ይ​ገ​ባ​ቸ​ውን ነፍ​ሳት ትገ​ድሉ ዘንድ፥ በሕ​ይ​ወ​ትም መኖር የማ​ይ​ገ​ባ​ቸ​ውን በሕ​ይ​ወት ታኖሩ ዘንድ ስለ ጭብጥ ገብ​ስና ስለ ቍራሽ እን​ጀራ ሕዝ​ቤን አር​ክ​ሳ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="20">“ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ነፍ​ሳ​ትን እንደ ወፍ በም​ታ​ጠ​ም​ዱ​ባት በመ​ከ​ዳ​ችሁ ላይ ነኝ፤ ከክ​ን​ዳ​ች​ሁም ወስጄ እቀ​ድ​ዳ​ታ​ለሁ፤ እንደ ወፍም የም​ታ​ጠ​ም​ዱ​አ​ቸ​ውን ነፍ​ሳት እለ​ቅ​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="21">ሽፋ​ኖ​ቻ​ች​ሁን ደግሞ እቀ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ሕዝ​ቤ​ንም ከእ​ጃ​ችሁ አድ​ና​ለሁ፤ ከዚ​ያም ወዲያ በእ​ጃ​ችሁ ለመ​ታ​ደን አይ​ሆ​ኑም፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="22">እኔም ያል​መ​ለ​ስ​ሁ​ትን የጻ​ድ​ቁን ልብ ወደ ዐመፃ መል​ሳ​ች​ኋ​ልና፥ በሕ​ይ​ወ​ትም ይኖር ዘንድ ከክፉ መን​ገድ እን​ዳ​ይ​መ​ለስ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛ​ውን እጅ አበ​ር​ት​ታ​ች​ኋ​ልና፤</verse>
				<verse number="23">ስለ​ዚህ፥ ሐሰ​ትን አታ​ዩም፤ እን​ግ​ዲ​ህም ከንቱ ምዋ​ር​ትን አታ​ም​ዋ​ር​ቱም፤ ሕዝ​ቤ​ንም ከእ​ጃ​ችሁ አድ​ና​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች አያሌ ሰዎች ወደ እኔ መጥ​ተው በፊቴ ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="2">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="3">“የሰው ልጅ ሆይ! እነ​ዚህ ሰዎች በል​ባ​ቸው ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አኑ​ረ​ዋል፤ የበ​ደ​ላ​ቸ​ው​ንም መቅ​ሠ​ፍት በፊ​ታ​ቸው አቁ​መ​ዋል፤ እኔስ ለእ​ነ​ርሱ መልስ ልመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ውን?</verse>
				<verse number="4">ስለ​ዚህ ንገ​ራ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፥ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ጣዖ​ቶ​ቹን በልቡ የሚ​ያ​ኖር፥ የበ​ደ​ሉ​ንም መቅ​ሠ​ፍት በፊቱ የሚ​ያ​ቆም ሰው ሁሉ ወደ ነቢዩ ቢመጣ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ጣዖ​ታቱ ብዛት እመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">ይህም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ወገ​ኖች በዐ​ሳ​ባ​ቸው ከእኔ እንደ ተለ​ዩ​በት እንደ ልባ​ቸ​ውና እንደ ርኵ​ሰ​ታ​ቸው ያስ​ታ​ቸው ዘንድ ነው።”</verse>
				<verse number="6">ስለ​ዚህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እን​ዲህ በል፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ንስሓ ግቡ፤ ከበ​ደ​ላ​ች​ሁም ተመ​ለሱ፤ ፊታ​ች​ሁ​ንም ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ሁሉ መልሱ።</verse>
				<verse number="7">ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ከሚ​ቀ​መጡ መጻ​ተ​ኞች የሚ​ሆን፥ ከእኔ ተለ​ይቶ ጣዖ​ቶ​ቹን በልቡ የሚ​ያ​ኖር፥ የበ​ደ​ሉ​ንም መቅ​ሠ​ፍት በፊቱ የሚ​ያ​ቆም ሰው ሁሉ ስለ እኔ ይጠ​ይቅ ዘንድ ወደ ነቢዩ በመጣ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በራሴ እመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">ፊቴ​ንም በዚያ ሰው ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እን​ዲ​ጠ​ፋም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ከሕ​ዝ​ቤም መካ​ከል አስ​ወ​ግ​ደ​ዋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="9">ነቢ​ዩም ቢታ​ለል፥ ቃል​ንም ቢና​ገር፥ ያን ነቢይ ያታ​ለ​ልሁ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፥ እጄ​ንም በእ​ርሱ ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ከሕ​ዝ​ቤም ከእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይሸ​ከ​ማሉ፤ እን​ደ​ሚ​ጠ​ይ​ቀ​ውም ሰው ኀጢ​አት እን​ዲሁ የነ​ቢዩ ኀጢ​አት ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="11">ይኸ​ውም የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ደግሞ ከእኔ ርቀው እን​ዳ​ይ​ስቱ፥ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ እን​ዳ​ይ​ረ​ክሱ ነው፤ እነ​ርሱ ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="12">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="13">“የሰው ልጅ ሆይ! ምድር ብት​በ​ድ​ለኝ፥ ብት​ስት፥ ኀጢ​አ​ትም ብት​ሠራ እጄን በእ​ር​ስዋ አነ​ሣ​ለሁ፤ የእ​ህ​ሉ​ንም ኀይል አጠ​ፋ​ለሁ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ረሀ​ብን እል​ካ​ለሁ፤ ከብ​ቱ​ንና ሰዉ​ንም ከእ​ር​ስዋ አጠ​ፋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">እነ​ዚህ ሦስቱ ሰዎች ኖኅና ዳን​ኤል ኢዮ​ብም በመ​ካ​ከ​ልዋ ቢኖሩ በጽ​ድ​ቃ​ቸው የገዛ ነፍ​ሳ​ቸ​ውን ያድ​ናሉ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="15">በዚ​ያች ሀገር ላይ ክፉ አው​ሬን ባመጣ፥ ፈጽ​ሜም ባጠ​ፋት በዚ​ያም አውሬ ፊት የሚ​ያ​ልፍ ባይ​ገኝ፥</verse>
				<verse number="16">እነ​ዚህ ሦስት ሰዎች በመ​ካ​ከ​ልዋ ቢኖሩ፥ እኔ ሕያው ነኝ! እነ​ርሱ ብቻ​ቸ​ውን ይድ​ናሉ እንጂ ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን አያ​ድ​ኑም፤ ምድ​ሪ​ቱም ባድማ ትሆ​ና​ለች፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="17">ወይም በዚ​ያች ምድር ላይ ሰይፍ አም​ጥቼ፦ ሰይፍ ሆይ! በም​ድ​ሪቱ ላይ እለፊ ብል፥ ሰው​ንና እን​ስ​ሳ​ው​ንም ከእ​ር​ስዋ ባጠፋ፥</verse>
				<verse number="18">እነ​ዚህ ሦስት ሰዎች በመ​ካ​ከ​ልዋ ቢኖሩ፥ እኔ ሕያው ነኝ! እነ​ርሱ ብቻ​ቸ​ውን ይድ​ናሉ እንጂ ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን አያ​ድ​ኑም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="19">ወይም በዚ​ያች ምድር ላይ ቸነ​ፈ​ርን ብሰ​ድድ፥ ሰው​ንና እን​ስ​ሳ​ው​ንም ከእ​ር​ስዋ አጠፋ ዘንድ መዓ​ቴን በደም ባፈ​ስ​ስ​ባት፥</verse>
				<verse number="20">ኖኅና ዳን​ኤል ኢዮ​ብም በመ​ካ​ከ​ልዋ ቢኖሩ፤ እኔ ሕያው ነኝ! በጽ​ድ​ቃ​ቸው ነፍ​ሳ​ቸ​ውን ብቻ ያድ​ናሉ እንጂ ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን አያ​ድ​ኑም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="21">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላል፥ “ይል​ቁ​ንስ ሰው​ንና እን​ስ​ሳን ከእ​ር​ስዋ አጠፋ ዘንድ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ አራ​ቱን ክፉ መቅ​ሠ​ፍ​ቶ​ችን፥ ሰይ​ፍ​ንና ራብን፥ ክፉ​ዎ​ች​ንም አው​ሬ​ዎች፥ ቸነ​ፈ​ር​ንም ስሰ​ድ​ድ​ባት፥</verse>
				<verse number="22">ነገር ግን እነሆ የሚ​ያ​መ​ል​ጡና ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ችን ከእ​ር​ስዋ የሚ​ያ​ወጡ ይቀ​ሩ​ላ​ታል፤ እነሆ ወደ እና​ንተ ይወ​ጣሉ፤ እና​ን​ተም መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንና ሥራ​ቸ​ውን ታያ​ላ​ችሁ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ላይ ስላ​መ​ጣ​ሁት ክፉ ነገር ሁሉ፥ ስላ​መ​ጣ​ሁ​ባ​ትም ነገር ሁሉ ትጽ​ና​ና​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="23">መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንና ሥራ​ቸ​ውን በአ​ያ​ችሁ ጊዜ ያጽ​ና​ኗ​ች​ኋል፤ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ባ​ት​ንም ሁሉ በከ​ንቱ እን​ዳ​ላ​ደ​ረ​ግ​ሁ​ባት ታው​ቃ​ላ​ችሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“የሰው ልጅ ሆይ! የወ​ይን ግንድ ከዱር ዛፎች ሁሉና ከዱር ዛፎች ቅር​ን​ጫ​ፎች ሁሉ ይልቅ ብል​ጫው ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="3">በውኑ ሥራ የሚ​ሠ​ራ​በ​ትን እን​ጨት ከእ​ርሱ ይወ​ስ​ዳ​ሉን? ወይስ ሰዎች ዕቃ የሚ​ን​ጠ​ለ​ጠ​ል​በ​ትን ኩላብ ከእ​ርሱ ይወ​ስ​ዳ​ሉን?</verse>
				<verse number="4">እነሆ ለመ​ቃ​ጠል በእ​ሳት ላይ ተጥ​ሎ​አል፤ እሳ​ቱም ሁለ​ቱን ጫፎ​ቹን በል​ቶ​አል፤ መካ​ከ​ሉም ተቃ​ጥ​ሎ​አል፤ በውኑ ለሥራ ይጠ​ቅ​ማ​ልን?</verse>
				<verse number="5">ከው​ፍ​ረ​ቱም የተ​ነሣ ለሥራ አይ​ሆ​ንም፤ ለም​ት​በ​ላና ለም​ታ​ጠፋ እሳት ይሆ​ናል እንጂ ከዚያ በኋላ በውኑ ለሥራ ይሆ​ና​ልን?</verse>
				<verse number="6">ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዱር ዛፎች መካ​ከል ያለ​ውን የወ​ይን ግንድ እሳት ይበ​ላው ዘንድ እንደ ሰጠ​ሁት፥ እን​ዲሁ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትን አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">ፊቴ​ንም በእ​ነ​ርሱ ላይ አጸ​ና​ለሁ፤ ከእ​ሳ​ትም አይ​ወ​ጡም፤ እሳ​ትም ይበ​ላ​ቸ​ዋል፤ ፊቴ​ንም በእ​ነ​ርሱ ላይ በአ​ጸ​ናሁ ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="8">ዐመ​ፅን አድ​ር​ገ​ዋ​ልና ምድ​ሪ​ቱን ባድማ አደ​ር​ጋ​ለሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“የሰው ልጅ ሆይ! ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ኀጢ​አ​ት​ዋን አስ​ታ​ው​ቃት፤ እን​ዲ​ህም በላት፦</verse>
				<verse number="3">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዲህ ይላል፦ ዘር​ሽና ትው​ል​ድሽ ከከ​ነ​ዓን ምድር ነው፤ አባ​ትሽ አሞ​ራዊ ነበረ፤ እና​ት​ሽም ኬጢ​ያ​ዊት ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="4">በተ​ወ​ለ​ድሽ ጊዜ በዚ​ያው ቀን እት​ብ​ትሽ አል​ታ​ተ​በም፤ ንጹ​ሕም ትሆኚ ዘንድ በውኃ አል​ታ​ጠ​ብ​ሽም፤ በጨ​ውም አል​ተ​ወ​ለ​ወ​ል​ሽም፤ በጨ​ር​ቅም አል​ተ​ጠ​ቀ​ለ​ል​ሽም፤ በጭ​ንም አል​ታ​ቀ​ፍ​ሽም።</verse>
				<verse number="5">በተ​ወ​ለ​ድ​ሽ​በት ቀን ከሰ​ው​ነ​ትሽ ጕስ​ቍ​ልና የተ​ነሣ በሜዳ ላይ ተጣ​ልሽ እንጂ፥ ከዚህ አን​ዳች ይደ​ረ​ግ​ልሽ ዘንድ ዐይኔ አል​ራ​ራ​ል​ሽም፤ ማንም አላ​ዘ​ነ​ል​ሽም።</verse>
				<verse number="6">“በአ​ን​ቺም ዘንድ ባለ​ፍሁ ጊዜ፤ በደ​ም​ሽም ተለ​ው​ሰሽ በአ​የ​ሁሽ ጊዜ፦ ከደ​ምሽ ዳኝ አል​ሁሽ፤</verse>
				<verse number="7">በእ​ርሻ ላይ እንደ አለ ቡቃያ አበ​ዛ​ሁሽ፤ አን​ቺም አደ​ግሽ፤ ታላ​ቅም ሆንሽ፤ በእ​ጅ​ጉም አጌ​ጥሽ፤ ከከ​ተማ ወደ ከተማ ገባሽ፤ ጡቶ​ች​ሽም አጐ​ጠ​ጐጡ፤ ጠጕ​ር​ሽም አደገ፤ ነገር ግን ዕር​ቃ​ን​ሽን ሆንሽ፤ ተራ​ቍ​ተ​ሽም ነበ​ርሽ።</verse>
				<verse number="8">በአ​ንቺ ዘንድ በአ​ለ​ፍ​ሁና በአ​የ​ሁሽ ጊዜ፥ እነሆ ጊዜሽ እንደ ደረሰ፥ በአ​ን​ቺም የሚ​ያ​ድሩ ሰዎች ጊዜ እንደ ደረሰ አየሁ። እጆ​ችን በላ​ይሽ ዘረ​ጋሁ፤ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ሽ​ንም ከደ​ንሁ፤ ማል​ሁ​ል​ሽም፤ ከአ​ን​ቺም ጋራ ቃል ኪዳን ገባሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ቺም ለእኔ ሆንሽ።</verse>
				<verse number="9">በው​ኃም አጠ​ብ​ሁሽ፤ ከደ​ም​ሽም አጠ​ራ​ሁሽ፤ በዘ​ይ​ትም ቀባ​ሁሽ።</verse>
				<verse number="10">ወርቀ ዘቦም አለ​በ​ስ​ሁሽ፤ ጥቁር ጫማም አደ​ረ​ግ​ሁ​ልሽ፤ በጥሩ በፍታ አስ​ታ​ጠ​ቅ​ሁሽ፤ በሐ​ርም ከደ​ን​ሁሽ።</verse>
				<verse number="11">በጌ​ጥም አስ​ጌ​ጥ​ሁሽ፤ በእ​ጅ​ሽም ላይ አን​ባር፥ በአ​ን​ገ​ት​ሽም ላይ ድሪ አደ​ረ​ግ​ሁ​ልሽ።</verse>
				<verse number="12">በአ​ፍ​ን​ጫ​ሽም ቀለ​በት፥ በጆ​ሮ​ሽም ጉትቻ፥ በራ​ስ​ሽም ላይ የክ​ብር አክ​ሊል አደ​ረ​ግሁ።</verse>
				<verse number="13">በወ​ር​ቅና በብር አጌ​ጥሽ፤ ልብ​ስ​ሽም ጥሩ በፍ​ታና ሐር፥ ወርቀ ዘቦም ነበረ፤ አን​ቺም መል​ካ​ምን ዱቄ​ትና ማርን፥ ዘይ​ት​ንም በላሽ፤ ወፈ​ርሽ፤ እጅ​ግም ውብ ሆንሽ፤ ለመ​ን​ግ​ሥ​ትም የተ​ዘ​ጋ​ጀሽ አደ​ረ​ግ​ሁሽ።</verse>
				<verse number="14">ባንቺ ላይ ከአ​ኖ​ር​ኋት ከክ​ብሬ የተ​ነሣ ውበ​ትሽ ፍጹም ነበ​ረና ስምሽ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ተሰማ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="15">“ነገር ግን በው​በ​ትሽ ታም​ነ​ሻል፤ በስ​ም​ሽም አመ​ን​ዝ​ረ​ሻል፤ ምን​ዝ​ር​ና​ሽ​ንም ከመ​ን​ገድ አላፊ ሁሉ ጋር አበ​ዛሽ።</verse>
				<verse number="16">ከል​ብ​ስ​ሽም ወስ​ደሽ በመ​ርፌ የተ​ጠ​ለፉ ጣዖ​ታ​ትን ሠራሽ፤ አመ​ነ​ዘ​ር​ሽ​ባ​ቸ​ውም፤ ስለ​ዚህ ፈጽ​መሽ አል​ገ​ባ​ሽም፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ እን​ዲህ ያለ ነገር አይ​ሆ​ንም።</verse>
				<verse number="17">ከሰ​ጠ​ሁ​ሽም ከወ​ር​ቄና ከብሬ የተ​ሠ​ራ​ውን የክ​ብ​ር​ሽን ዕቃ ወስ​ደሽ የወ​ንድ ምስ​ሎ​ችን ለራ​ስሽ አድ​ር​ገ​ሻል፤ አመ​ን​ዝ​ረ​ሽ​ባ​ቸ​ው​ማል።</verse>
				<verse number="18">ወርቀ ዘቦ​ውን ልብ​ስ​ሽ​ንም ወስ​ደሽ ደረ​ብ​ሽ​ላ​ቸው፤ ዘይ​ቴ​ንና ዕጣ​ኔ​ንም በፊ​ታ​ቸው አኖ​ርሽ።</verse>
				<verse number="19">የሰ​ጠ​ሁ​ሽ​ንም እን​ጀ​ራ​ዬን፥ ያበ​ላ​ሁ​ሽ​ንም ዱቄ​ትና ዘይ​ቱን፥ ማሩ​ንም ጣፋጭ ሽታ አድ​ር​ገሽ በፊ​ታ​ቸው አኖ​ርሽ፤ እን​ዲ​ህም ሆኖ​አል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="20">ለእ​ኔም የወ​ለ​ድ​ሻ​ቸ​ውን ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ሽን ወስ​ደሽ መብል ይሆኑ ዘንድ ሠዋ​ሽ​ላ​ቸው፤ ገደ​ል​ሻ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="21">ልጆ​ችን አረ​ድሽ፤ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትም አሳ​ል​ፈሽ ሰጠሽ፤ በውኑ ግል​ሙ​ት​ናሽ ጥቂት ነውን?</verse>
				<verse number="22">ከኀ​ጢ​አ​ት​ሽና ከዝ​ሙ​ትሽ ሁሉ ይህ ይከ​ፋል፤ አንቺ ዕራ​ቁ​ት​ሽን ሳለሽ፥ ኀፍ​ረ​ትም ሞል​ቶ​ብሽ ሳለሽ፥ በደ​ም​ሽም ተለ​ው​ሰሽ ሳለሽ፥ የሕ​ፃ​ን​ነ​ት​ሽን ወራት አላ​ሰ​ብ​ሽም።</verse>
				<verse number="23">“ከዚ​ህም ከክ​ፋ​ትሽ ሁሉ በኋላ ወዮ​ልሽ! ወዮ​ልሽ! ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="24">የም​ት​ሰ​ስ​ኝ​በ​ትን ቤት ለራ​ስሽ ሠራሽ፤ በአ​ደ​ባ​ባዩ ሁሉ ከፍ ያለ ቦታን አደ​ረ​ግሽ።</verse>
				<verse number="25">በየ​መ​ን​ገዱ ራስ ከፍ ያለ​ውን ቦታ​ሽን ሠራሽ፤ ውበ​ት​ሽ​ንም አረ​ከ​ስሽ፤ ለመ​ን​ገድ አላ​ፊም ሁሉ እግ​ር​ሽን ገለ​ጥሽ፤ ዝሙ​ት​ሽ​ንም አበ​ዛሽ።</verse>
				<verse number="26">አካ​ላ​ቸ​ውም ከወ​ፈረ ከጐ​ረ​ቤ​ቶ​ችሽ ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን ልጆች ጋር አመ​ነ​ዘ​ርሽ፤ እኔ​ንም ታስ​ቆጭ ዘንድ ዝሙ​ት​ሽን አበ​ዛሽ።</verse>
				<verse number="27">ስለ​ዚህ እነሆ እጄን በአ​ንቺ ላይ ዘር​ግ​ቻ​ለሁ፤ ድር​ሻ​ሽ​ንም አጕ​ድ​ያ​ለሁ፤ ለሚ​ጠ​ሉ​ሽም፥ ከመ​ን​ገ​ድሽ ለመ​ለ​ሱ​ሽና ለአ​ሳ​ቱሽ ለፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሴቶች ልጆች ፈቃድ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​ሻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="28">ከአ​ሦ​ራ​ው​ያን ልጆች ጋር ፈጽ​መሽ አመ​ነ​ዘ​ርሽ፤ ከዚ​ህም ጋር ገና አል​ጠ​ገ​ብ​ሽም፤ ዝሙ​ት​ሽም አል​በ​ቃ​ሽም።</verse>
				<verse number="29">እስከ ከነ​ዓን ምድር እስከ ከላ​ው​ዴ​ዎ​ንም ድረስ ዝሙ​ት​ሽን አበ​ዛሽ። ከዚ​ህም ጋር ገና አል​ጠ​ገ​ብ​ሽም።</verse>
				<verse number="30">“ይህን ሁሉ የሴ​ሰኛ ሴት ሥራን ሠር​ተ​ሻ​ልና፥ ከሴ​ቶች ልጆ​ች​ሽም ጋር ሦስት ጊዜ አመ​ን​ዝ​ረ​ሻ​ልና ሴቶች ልጆ​ች​ሽን ምን አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ? ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="31">በየ​መ​ን​ገዱ ራስ የም​ን​ዝ​ር​ና​ሽን ስፍራ ሠር​ተ​ሻል፤ በየ​አ​ደ​ባ​ባ​ዩም ከፍ ያለ​ውን ቦታ​ሽን አድ​ር​ገ​ሻል። ዋጋ​ዋን እን​ደ​ም​ት​ሰ​በ​ስብ እንደ ጋለ​ሞ​ታም አል​ሆ​ን​ሽም።</verse>
				<verse number="32">ከባ​ልዋ ገን​ዘብ ተቀ​ብላ የም​ታ​መ​ነ​ዝር ሴትን ትመ​ስ​ያ​ለሽ።</verse>
				<verse number="33">ለአ​መ​ን​ዝ​ራ​ዎች ሁሉ ዋጋ ይሰ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ አንቺ ግን ለወ​ዳ​ጆ​ችሽ ሁሉ ዋጋ ትሰ​ጫ​ለሽ፤ ከአ​ን​ቺም ጋር ለማ​መ​ን​ዘር በዙ​ሪ​ያሽ ይገ​ቡ​ብሽ ዘንድ መማ​ለ​ጃን ትሰ​ጫ​ቸ​ዋ​ለሽ።</verse>
				<verse number="34">ዝሙ​ትሽ ከሌ​ሎች ሴቶች ዝሙት ልዩ ነው፤ ማንም ለዝ​ሙት የሚ​ከ​ተ​ልሽ የለም፤ ዋጋ ሳይ​ሰ​ጥሽ አንቺ ዋጋ በመ​ስ​ጠ​ትሽ በዚህ ነገር ልዩ ሆነ​ሻል።</verse>
				<verse number="35">“ስለ​ዚህ ዘማ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሚ።</verse>
				<verse number="36">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወር​ቄን በት​ነ​ሻ​ልና ከኀ​ጢ​አት ምኞት በሠ​ራ​ሽው ዝሙት ኀፍ​ረተ ሥጋ​ሽን ገል​ጠ​ሻ​ልና በሰ​ጠ​ሻ​ቸ​ውም በል​ጆ​ችሽ ደም፥</verse>
				<verse number="37">ስለ​ዚህ እነሆ እኔ ከአ​ንቺ ጋር አንድ የሆኑ ውሽ​ሞ​ች​ሽን በአ​ንቺ ላይ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የም​ት​ወ​ጃ​ቸ​ው​ንም ከም​ት​ጠ​ያ​ቸው ጋር በአ​ንቺ ላይ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ይከ​ቡ​ሻል፤ በእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ ጕስ​ቍ​ል​ና​ሽን እገ​ል​ጥ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ሁሉም ኀፍ​ረ​ት​ሽን ያዩ​ብ​ሻል።</verse>
				<verse number="38">በአ​መ​ን​ዝ​ሮ​ችና በደም አፍ​ሳ​ሾች በቀል እበ​ቀ​ል​ሻ​ለሁ፤ በመ​ዓ​ትና በቅ​ን​አት ደምም አስ​ቀ​ም​ጥ​ሻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="39">በእ​ጃ​ቸ​ውም አሳ​ልፌ እሰ​ጥ​ሻ​ለሁ፤ የም​ን​ዝ​ር​ና​ሽ​ንም ስፍራ ያፈ​ር​ሳሉ፤ ከፍ ያለ​ው​ንም ቦታ​ሽን ይገ​ለ​ብ​ጣሉ፤ ልብ​ስ​ሽ​ንም ይገ​ፉ​ሻል፤ የክ​ብ​ር​ሽ​ንም ጌጥ ይወ​ስ​ዳሉ፤ ዕራ​ቁ​ት​ሽ​ንም ይተ​ዉ​ሻል፤ ቷረ​ጃ​ለ​ሽም።</verse>
				<verse number="40">ብዙ ሕዝ​ብን ይሰ​በ​ሰ​ቡ​ብ​ሻል፤ በድ​ን​ጋ​ይም ይወ​ግ​ሩ​ሻል፤ በሰ​ይ​ፋ​ቸ​ውም ይወ​ጉ​ሻል።</verse>
				<verse number="41">ቤቶ​ች​ሽ​ንም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላሉ፤ በብ​ዙም ሴቶች ፊት ይበ​ቀ​ሉ​ሻል፤ ግል​ሙ​ት​ና​ሽ​ንም አስ​ተ​ው​ሻ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ዋጋ አት​ሰ​ጪም።</verse>
				<verse number="42">መዓ​ቴ​ንም በአ​ንቺ ላይ እጨ​ር​ሳ​ለሁ፤ ቅን​ዓ​ቴም ከአ​ንቺ ይር​ቃል፤ እኔም ዝም እላ​ለሁ፤ ደግ​ሞም አል​ቈ​ጣም።</verse>
				<verse number="43">የሕ​ፃ​ን​ነ​ት​ሽን ወራት አላ​ሰ​ብ​ሽ​ምና፥ በዚ​ህም ነገር ሁሉ አስ​ቈ​ጥ​ተ​ሽ​ኛ​ልና፤ ስለ​ዚህ እነሆ እኔ ደግሞ መን​ገ​ድ​ሽን በራ​ስሽ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እን​ደ​ዚ​ህም በበ​ደ​ልሽ ሁሉ ላይ ኀጢ​አ​ትን ሠራሽ።</verse>
				<verse number="44">“እነሆ በም​ሳሌ የሚ​ና​ገር ሁሉ፥ እንደ እና​ቲቱ እን​ዲሁ ልጅቱ ናት፤ እያለ ምሳሌ ይመ​ስ​ል​ብ​ሻል።</verse>
				<verse number="45">አንቺ ባል​ዋ​ንና ልጆ​ች​ዋን የጠ​ላች የእ​ና​ትሽ ልጅ ነሽ፤ አን​ቺም ባሎ​ቻ​ቸ​ው​ንና ልጆ​ቻ​ቸ​ውን የጠሉ የእ​ኅ​ቶ​ችሽ እኅት ነሽ፤ እና​ታ​ችሁ ኬጢ​ያ​ዊት ነበ​ረች፤ አባ​ታ​ች​ሁም አሞ​ራዊ ነበረ።</verse>
				<verse number="46">ታላ​ቂ​ቱም እኅ​ትሽ ከሴ​ቶች ልጆ​ችዋ ጋር በስተ ግራሽ የም​ት​ቀ​መጥ ሰማ​ርያ ናት፤ ታና​ሽ​ቱም እኅ​ትሽ ከሴ​ቶች ልጆ​ችዋ ጋር በሰተ ቀኝሽ የም​ት​ቀ​መጥ ሰዶም ናት።</verse>
				<verse number="47">አንቺ ግን በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው አል​ሄ​ድ​ሽም፤ እንደ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም አላ​ደ​ረ​ግ​ሽም፤ ያው ለአ​ንቺ ጥቂት ነበ​ረና በመ​ን​ገ​ድሽ ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ የሚ​ከፋ ኀጢ​አት አደ​ረ​ግሽ።</verse>
				<verse number="48">እኔ ሕያው ነኝ! አን​ቺና ሴቶች ልጆ​ችሽ እን​ዳ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁት እን​ዲሁ ሰዶ​ምና ሴቶች ልጆ​ችዋ አላ​ደ​ረ​ጉም፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="49">እነሆ የእ​ኅ​ትሽ የሰ​ዶም ኀጢ​አት ይህ ነበረ፤ ትዕ​ቢት፥ እን​ጀ​ራን መጥ​ገብ፥ መዝ​ለ​ልና ሥራን መፍ​ታት፥ ይህ ሁሉ በእ​ር​ስ​ዋና በል​ጆ​ችዋ ነበር፤ የች​ግ​ረ​ኛ​ው​ንና የድ​ሀ​ው​ንም እጅ አላ​ጸ​ና​ችም።</verse>
				<verse number="50">ኰር​ተው ነበር፤ በፊ​ቴም ርኵስ ነገር አደ​ረጉ፤ ስለ​ዚህ እንደ አየሁ አስ​ወ​ገ​ድ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="51">ሰማ​ር​ያም የኀ​ጢ​አ​ት​ሽን እኩ​ሌታ አል​ሠ​ራ​ችም፤ አንቺ ግን ከእ​ኅ​ቶ​ችሽ ይልቅ ኀጢ​አ​ትን አበ​ዛሽ፤ በሠ​ራ​ሽ​ውም ኀጢ​አት ሁሉ አጸ​ደ​ቅ​ሻ​ቸው።</verse>
				<verse number="52">አሁ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ይልቅ አብ​ዝ​ተሽ በሠ​ራ​ሽው ኀጢ​አ​ትሽ እኅ​ቶ​ች​ሽን ስላ​ረ​ከ​ስ​ሻ​ቸው ቅጣ​ት​ሽን ተሸ​ከሚ። ከአ​ን​ቺም ይልቅ አጸ​ደ​ቅ​ሻ​ቸው፤ አን​ችም እፈሪ፤ እፍ​ረ​ት​ሽ​ንም ተሸ​ከሚ፤ እኅ​ቶ​ች​ሽን አጽ​ድ​ቀ​ሻ​ቸ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="53">ምር​ኮ​አ​ቸ​ው​ንም እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ የሰ​ዶ​ምና የሴ​ቶች ልጆ​ች​ዋን ምርኮ፥ የሰ​ማ​ር​ያ​ንና የሴ​ቶች ልጆ​ች​ዋን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ያሉ​ትን የም​ር​ኮ​ኞ​ች​ሽን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="54">ፍዳ​ሽ​ንም ትቀ​በዪ ዘንድ በአ​ስ​ቈ​ጣ​ሽኝ ሥራሽ ሁሉ ታፍ​ሪ​ያ​ለሽ።</verse>
				<verse number="55">እኅ​ቶ​ች​ሽም ሰዶ​ምና ሴቶች ልጆ​ችዋ ወደ ቀድሞ ሁኔ​ታ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ፤ ሰማ​ር​ያና ሴቶች ልጆ​ች​ዋም ወደ ቀድሞ ሁኔ​ታ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ፤ አን​ቺና ሴቶች ልጆ​ች​ሽም ወደ ቀድሞ ሁኔ​ታ​ችሁ ትመ​ለ​ሳ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="56">እኅ​ትሽ ሰዶ​ምም በት​ዕ​ቢ​ትሽ ቀን በአ​ፍሽ አል​ተ​ወ​ሳ​ችም።</verse>
				<verse number="57">ክፋ​ትሽ እንደ ዛሬው ሳይ​ገ​ለጥ ለሶ​ርያ ሴቶች ልጆ​ችና ለጐ​ረ​ቤ​ቶ​ችዋ ሁሉ በዙ​ሪ​ያ​ሽም ለሚ​ከ​ቡሽ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያት ሴቶች ልጆች መሰ​ደ​ቢያ ሆነ​ሻል።</verse>
				<verse number="58">ኀጢ​አ​ት​ሽ​ንና በደ​ል​ሽን ተሽ​ክ​መ​ሻል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="59">“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላል፦ አንቺ ቃል ኪዳ​ንን በማ​ፍ​ረስ መሐ​ላን የና​ቅሽ ሆይ! አንቺ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሽ እኔ ደግሞ አደ​ር​ግ​ብ​ሻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="60">ነገር ግን በሕ​ፃ​ን​ነ​ትሽ ወራት ከአ​ንቺ ጋር ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን ዐስ​ባ​ለሁ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ም​ንም ቃል ኪዳን አጸ​ና​ል​ሻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="61">ታላ​ቆ​ቹ​ንና ታና​ሾ​ቹን እኅ​ቶ​ች​ሽ​ንም በተ​ቀ​በ​ልሽ ጊዜ መን​ገ​ድ​ሽን ታስ​ቢ​ያ​ለሽ፤ ታፍ​ሪ​ማ​ለሽ፤ ለአ​ን​ቺም ልጆች ይሆኑ ዘንድ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ስለ ቃል ኪዳ​ንሽ ግን አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="62">እኔም ቃል ኪዳ​ኔን ከአ​ንቺ ጋር አጸ​ና​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቂ​ያ​ለሽ።</verse>
				<verse number="63">ታስቢ ዘንድ፥ ታፍ​ሪም ዘንድ፥ ደግ​ሞም ስላ​ደ​ረ​ግ​ሽው ነገር ሁሉ ይቅር ባል​ሁሽ ጊዜ፥ስለ ኀፍ​ረ​ትሽ አፍ​ሽን ትከ​ፍቺ ዘንድ አይ​ቻ​ል​ሽም፤” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ምሳሌ መስ​ለህ ንገር፤ እን​ዲ​ህም በል፦</verse>
				<verse number="3">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ታላቅ ክንፍ፥ ረጅ​ምም ጽፍር ያለው፥ ላባ​ንም የተ​ሞላ፥ መልከ ዝን​ጉ​ር​ጉር የሆነ ታላቅ ንስር ወደ ሊባ​ኖስ መጣ፤ የዝ​ግ​ባ​ንም ጫፍ ወሰደ።</verse>
				<verse number="4">ቀን​በ​ጡ​ንም ቀነ​ጠበ፤ ወደ ከነ​ዓ​ንም ምድር ወሰ​ደው፤ ቅጥር ባለው ከተ​ማም አኖ​ረው።</verse>
				<verse number="5">ከም​ድ​ርም ዘር ወሰደ፤ በፍ​ሬ​ያማ እር​ሻም ዘራው፤ በብ​ዙም ውኃ አጠ​ገብ እንደ አኻያ ዛፍ አኖ​ረው።</verse>
				<verse number="6">በበ​ቀ​ለም ጊዜ ቁመቱ ያጠረ፥ ሐረ​ጉም ወደ እርሱ የሚ​መ​ለስ፥ ሥሩም በበ​ታቹ የነ​በረ ሰፊ ወይን ሆነ፤ እን​ዲሁ ወይን ሆነ፤ ሐረ​ግም ሰደደ፤ ቀን​በ​ጥም አወጣ።</verse>
				<verse number="7">“ታላቅ ክን​ፍና ብዙ ጽፍ​ርም ያለው ሌላ ታላቅ ንስር ነበረ፤ እነ​ሆም ያጠ​ጣው ዘንድ ይህ ወይን ሥሩን ወደ እርሱ ሰደደ፤ ሐረ​ጉ​ንም ከተ​ተ​ከ​ለ​በት ከመ​ደቡ ወደ እርሱ አዘ​ነ​በለ።</verse>
				<verse number="8">ሐረ​ግም ያወጣ፥ ፍሬም ያፈራ፥ የከ​በረ ወይ​ንም ይሆን ዘንድ በመ​ል​ካም መሬት ውስጥ፥ በብ​ዙም ውኃ አጠ​ገብ ተተ​ክሎ ነበር።</verse>
				<verse number="9">እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በውኑ ይከ​ና​ወ​ን​ለት ይሆን? ይደ​ር​ቅስ ዘንድ፥ አዲስ የበ​ቀ​ለ​ውስ ቅጠሉ ይጠ​ወ​ልግ ዘንድ ሥሩን አይ​ነ​ቅ​ለ​ው​ምን? ፍሬ​ው​ንስ አይ​ለ​ቅ​መ​ው​ምን? ሥሩም የተ​ነ​ቀ​ለው በብ​ርቱ ክን​ድና በብዙ ሕዝብ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="10">ተተ​ክ​ሎስ፥ እነሆ ይከ​ና​ወ​ን​ለት ይሆን? የም​ሥ​ራቅ ነፋስ ባገ​ኘው ጊዜ ፈጽሞ አይ​ደ​ር​ቅ​ምን? በተ​ተ​ከ​ለ​በት መደብ ላይ ይደ​ር​ቃል።”</verse>
				<verse number="11">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="12">“የሰው ልጅ ሆይ፥ ለአ​ስ​ቈ​ጡኝ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ይህ ትር​ጓሜ ምን እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? በላ​ቸው። እን​ዲ​ህም ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ እነሆ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ፤ ንጉ​ሥ​ዋ​ንና መኳ​ን​ን​ቶ​ች​ዋ​ንም ማረከ፤ ወደ ሀገ​ሩም ወደ ባቢ​ሎን ወሰ​ዳ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">ከመ​ን​ግ​ሥ​ትም ዘር ወስዶ ከእ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ አማ​ለ​ውም፤ የም​ድ​ሪ​ቱ​ንም ኀያ​ላን ወሰደ፤</verse>
				<verse number="14">ይኸ​ውም መን​ግ​ሥቱ እን​ድ​ቷ​ረ​ድና ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ከፍ እን​ዳ​ትል፥ ቃል ኪዳ​ኑን በመ​ጠ​በቅ ጸንታ እን​ድ​ት​ኖር ነው።</verse>
				<verse number="15">እርሱ ግን በእ​ርሱ ላይ ሸፈተ፤ ፈረ​ሶ​ች​ንና ብዙ​ንም ሕዝብ ይሰ​ጡት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ወደ ግብፅ ላከ። በውኑ ይከ​ና​ወ​ን​ለት ይሆን? ይህ​ንስ ያደ​ረገ ያመ​ል​ጣ​ልን? ቃል ኪዳ​ን​ንስ ያፈ​ረሰ ያመ​ል​ጣ​ልን?</verse>
				<verse number="16">“እኔ ሕያው ነኝ! ያነ​ገ​ሠ​ውና መሐ​ላ​ውን የና​ቀ​በት፥ ቃል ኪዳ​ኑ​ንም ያፈ​ረ​ሰ​በት ንጉሥ በሚ​ኖ​ር​በት ስፍራ ከእ​ርሱ ጋር በባ​ቢ​ሎን መካ​ከል በር​ግጥ ይሞ​ታል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="17">ብዙ​ዎ​ችን ነፍ​ሳት ለማ​ስ​ወ​ገድ ምሽ​ግን በመ​ሸጉ፥ ቅጥ​ር​ንም በሠሩ ጊዜ፥ ፈር​ዖን በታ​ላቅ ኀይ​ልና በብዙ ሕዝብ በጦ​ር​ነት አይ​ረ​ዳ​ውም።</verse>
				<verse number="18">ቃል ኪዳ​ኑ​ንም በማ​ፍ​ረስ መሐ​ላ​ውን ንቆ​አል፤ እነ​ሆም እጁን አሳ​ልፌ ሰጠሁ፤ ይህ​ንም ሁሉ አድ​ር​ጎ​አል፤ ስለ​ዚ​ህም አያ​መ​ል​ጥም።</verse>
				<verse number="19">ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝ! የና​ቀ​ውን መሐ​ላ​ዬ​ንና ያፈ​ረ​ሰ​ውን ቃል ኪዳ​ኔን በራሱ ላይ አመ​ጣ​ለሁ በላ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">መረ​ቤ​ንም በእ​ርሱ ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ በወ​ጥ​መ​ድም ይያ​ዛል፤ ወደ ባቢ​ሎ​ንም አመ​ጣ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ኔም ላይ ስላ​ደ​ረ​ገው ዐመፅ በዚያ ከእ​ርሱ ጋር እፋ​ረ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="21">ያመ​ለ​ጡ​ትም ሁሉ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ የቀ​ሩ​ትም ሁሉ ወደ እየ​ነ​ፋ​ሳቱ ይበ​ተ​ናሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ርሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="22">“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከረ​ዥሙ ዝግባ ጫፍ ላይ ቀን​በ​ጥን ወስጄ አኖ​ረ​ዋ​ለሁ፤ ከጫ​ፎ​ቹም አን​ዱን ቀን​በጥ እቀ​ነ​ጥ​በ​ዋ​ለሁ፤ በረ​ዥ​ምና በታ​ላቅ ተራ​ራም ላይ እተ​ክ​ለ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="23">ከፍ ባለው በእ​ስ​ራ​ኤል ተራራ ላይ እተ​ክ​ለ​ዋ​ለሁ፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ች​ንም ያወ​ጣል፤ ፍሬም ያፈ​ራል፤ ታላ​ቅም ዝግባ ይሆ​ናል፤ በበ​ታ​ቹም ወፎች ሁሉ ያር​ፋሉ፤ በቅ​ር​ን​ጫ​ፎ​ቹም ጥላ በክ​ንፍ የሚ​በ​ርር ሁሉ ይጠ​ጋል፤ ቅር​ን​ጫ​ፉም ይሰ​ፋል።</verse>
				<verse number="24">የዱር ዛፎች ሁሉ፥ ረዥ​ሙን ዛፍ ዝቅ ያደ​ረ​ግሁ፥ አጭ​ሩ​ንም ዛፍ ከፍ ያደ​ረ​ግሁ፥ የለ​መ​ለ​መ​ው​ንም ዛፍ ያደ​ረ​ቅሁ፥ የደ​ረ​ቀ​ው​ንም ዛፍ ያለ​መ​ለ​ምሁ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገ​ርሁ፤ እኔም አደ​ረ​ግሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፦ ‘አባ​ቶች ጨርቋ የወ​ይን ፍሬ በሉ፥ የል​ጆ​ችም ጥር​ሶች ጠረሱ’ ብላ​ችሁ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ የም​ት​መ​ስ​ሉት ምሳሌ ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="3">እኔ ሕያው ነኝ! እን​ግ​ዲህ ወዲህ ይህን ምሳሌ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አት​መ​ስ​ሉ​ትም፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="4">እነሆ ነፍ​ሳት ሁሉ የእኔ ናቸው፤ የአ​ባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች እን​ዲሁ የልጅ ነፍስ የእኔ ናት፤ ኀጢ​አት የም​ት​ሠራ ነፍስ እር​ስዋ ትሞ​ታ​ለች።</verse>
				<verse number="5">“ሰውም ጻድቅ ቢሆን ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ር​ንም ቢያ​ደ​ርግ፤</verse>
				<verse number="6">በተ​ራ​ራም ላይ ባይ​በላ፥ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት ጣዖ​ታት ባያ​ነሣ፥ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም ሚስት ባያ​ረ​ክስ፥ አደ​ፍም ወዳ​ለ​ባት ሴት ባይ​ቀ​ርብ፤</verse>
				<verse number="7">ሰው​ንም ባያ​ስ​ጨ​ንቅ፥ ለባለ ዕዳም መያ​ዣ​ውን ቢመ​ልስ፥ ፈጽ​ሞም ባይ​ቀማ፥ ከእ​ን​ጀ​ራ​ውም ለተ​ራበ ቢሰጥ፥ የተ​ራ​ቈ​ተ​ው​ንም ከል​ብሱ ቢያ​ለ​ብስ፤</verse>
				<verse number="8">በአ​ራጣ ባያ​በ​ድር፥ አት​ር​ፎም ባይ​ወ​ስድ፥ እጁ​ንም ከኀ​ጢ​አት ቢመ​ልስ፥ በሰ​ውና በሰው መካ​ከ​ልም የእ​ው​ነ​ትን ፍርድ ቢፈ​ርድ፥</verse>
				<verse number="9">በት​እ​ዛ​ዜም ቢሄድ፥ እው​ነ​ት​ንም ለማ​ድ​ረግ ፍር​ዴን ቢጠ​ብቅ፥ እርሱ ጻድቅ ነው፤ ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="10">“እር​ሱም ቀማ​ኛና ደም አፍ​ሳሽ ልጅን፥ ከዚ​ህም ሁሉ አን​ዳ​ቸ​ውን የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ቢወ​ልድ፥</verse>
				<verse number="11">እር​ሱም በጻ​ድቅ አባቱ መን​ገድ ባይ​ሄድ፥ በተ​ራ​ራም ላይ ቢበላ፥ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም ሚስት ቢያ​ረ​ክስ፥</verse>
				<verse number="12">ድሀ​ው​ንና ችግ​ረ​ኛ​ውን ቢያ​ስ​ጨ​ንቅ፥ ቢቀ​ማም፥ መያ​ዣ​ው​ንም ባይ​መ​ልስ፥ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ወደ ጣዖ​ታት ቢያ​ነሣ፥ ርኩ​ስ​ንም ነገር ቢያ​ደ​ርግ፥</verse>
				<verse number="13">በአ​ራጣ ቢያ​በ​ድር፥ አት​ር​ፎም ቢወ​ስድ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ ሰው በሕ​ይ​ወት አይ​ኖ​ርም፤ ይህን ርኵ​ሰት ሁሉ አድ​ር​ጎ​አ​ልና ፈጽሞ ይሞ​ታል፤ ደሙም በላዩ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="14">“እነ​ሆም ልጅ ቢወ​ልድ፥ እር​ሱም አባቱ የሠ​ራ​ውን ኀጢ​አት አይቶ ቢፈራ፥ እን​ደ​ር​ሱም ባይ​ሠራ፥</verse>
				<verse number="15">በተ​ራራ ላይ ባይ​በላ፥ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት ጣዖ​ታት ባያ​ነሣ፥ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም ሚስት ባያ​ረ​ክስ፤</verse>
				<verse number="16">ሰው​ንም ባያ​ስ​ጨ​ንቅ፥ መያ​ዣ​ው​ንም ባይ​ወ​ስድ፥ ባይ​ቀ​ማም፥ ከእ​ን​ጀ​ራ​ውም ለተ​ራበ ቢሰጥ፥ ለተ​ራ​ቈ​ተ​ውም ልብ​ስን ቢያ​ለ​ብስ፥</verse>
				<verse number="17">እጁ​ንም ከዐ​መፅ ቢመ​ልስ፥ አራ​ጣ​ንም አት​ርፎ ባይ​ወ​ስድ፥ ፍር​ዴ​ንም ቢያ​ደ​ርግ፥ በት​እ​ዛ​ዜም ቢሄድ፥ እርሱ ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል እንጂ በአ​ባቱ ኀጢ​አት አይ​ሞ​ትም።</verse>
				<verse number="18">አባቱ ግን ፈጽሞ በድ​ሎ​አ​ልና፥ ወን​ድ​ሙ​ንም ቀም​ቶ​አ​ልና፥ በሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ክፉን ነገር አድ​ር​ጎ​አ​ልና እነሆ እርሱ በበ​ደሉ ይሞ​ታል።</verse>
				<verse number="19">“እና​ንተ ግን፦ ልጅ የአ​ባ​ቱን ኀጢ​አት ስለ ምን አይ​ሸ​ከ​ምም? ትላ​ላ​ችሁ። ልጅ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ርን በአ​ደ​ረገ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ሁሉ በጠ​በ​ቀና በአ​ደ​ረገ ጊዜ ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል።</verse>
				<verse number="20">ኀጢ​አ​ትን የም​ት​ሠራ ነፍስ እር​ስዋ ትሞ​ታ​ለች፤ ልጅ የአ​ባ​ቱን ኀጢ​አት አይ​ሸ​ከ​ምም፤ አባ​ትም የል​ጁን ኀጢ​አት አይ​ሸ​ከ​ምም፤ የጻ​ድቁ ጽድቅ በራሱ ላይ ይሆ​ናል፤ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ኀጢ​አት በራሱ ላይ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="21">“ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ከአ​ደ​ረ​ጋት ኀጢ​አት ሁሉ ቢመ​ለስ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ሁሉ ቢጠ​ብቅ፥ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ር​ንም ቢያ​ደ​ርግ ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል እንጂ አይ​ሞ​ትም።</verse>
				<verse number="22">የበ​ደ​ለው በደል ሁሉ አይ​ታ​ሰ​ብ​በ​ትም፤ በሠ​ራው ጽድቅ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል።</verse>
				<verse number="23">በውኑ ኀጢ​አ​ተኛ ይሞት ዘንድ መፍ​ቀ​ድን እፈ​ቅ​ዳ​ለ​ሁን? ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከክፉ መን​ገዱ ይመ​ለ​ስና በሕ​ይ​ወት ይኖር ዘንድ ነው እንጂ።</verse>
				<verse number="24">ጻድቁ ግን ከጽ​ድቁ ቢመ​ለስ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም ቢሠራ፥ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ገው ርኵ​ሰት ሁሉ ቢያ​ደ​ርግ፥ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራ​ልን? የሠ​ራው ጽድቅ ሁሉ አይ​ታ​ሰ​ብ​ለ​ትም፤ በአ​ደ​ረ​ገው ዐመ​ፅና በሠ​ራት ኀጢ​አት በዚ​ያች ይሞ​ታል።</verse>
				<verse number="25">“እና​ንተ ግን፦ የጌታ መን​ገድ የቀ​ናች አይ​ደ​ለ​ችም ትላ​ላ​ችሁ። የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እን​ግ​ዲህ ስሙ፤ በውኑ መን​ገዴ የቀ​ናች አይ​ደ​ለ​ች​ምን? ይል​ቅስ የእ​ና​ንተ መን​ገድ ያል​ቀ​ናች አይ​ደ​ለ​ች​ምን?</verse>
				<verse number="26">ጻድቁ ከጽ​ድቁ ቢመ​ለስ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም በሠራ ጊዜ፥ በዚያ ቢሞት፥ እርሱ በአ​ደ​ረ​ገው በደል ይሞ​ታል።</verse>
				<verse number="27">ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ከሠ​ራው ኀጢ​አት ቢመ​ለስ፥ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ር​ንም ቢያ​ደ​ርግ ነፍ​ሱን ይጠ​ብ​ቃል።</verse>
				<verse number="28">ከሠ​ራው ሁሉ በደል አይቶ ተመ​ል​ሶ​አ​ልና ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል እንጂ አይ​ሞ​ትም።</verse>
				<verse number="29">ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት፦ የጌታ መን​ገድ የቀ​ናች አይ​ደ​ለ​ችም ይላሉ። የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በውኑ መን​ገዴ የቀ​ናች አይ​ደ​ለ​ች​ምን? ይል​ቅስ የእ​ና​ንተ መን​ገድ ያል​ቀ​ናች አይ​ደ​ለ​ች​ምን?</verse>
				<verse number="30">የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ስለ​ዚህ እንደ መን​ገዱ በየ​ሰዉ ሁሉ እፈ​ር​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ንስሓ ግቡ፤ ኀጢ​አ​ትም ዕን​ቅ​ፋት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ችሁ ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ሁሉ ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="31">የበ​ደ​ላ​ች​ሁ​ትን በደል ሁሉ ከእ​ና​ንተ ጣሉ፤ አዲስ ልብና አዲስ መን​ፈ​ስ​ንም ለእ​ና​ንተ አድ​ርጉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ስለ ምን ትሞ​ታ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="32">የም​ዋ​ቹን ሞት አል​ፈ​ቅ​ድ​ምና፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ስለ​ዚህ በን​ስሓ ተመ​ለ​ሱና በሕ​ይ​ወት ኑሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">“አን​ተም ለእ​ስ​ራ​ኤል አለቃ ይህን ሙሾ አሙ​ሽ​ለት፤</verse>
				<verse number="2">እን​ዲ​ህም በል፦ እና​ትህ ምን ነበ​ረች? እን​ስት አን​በሳ ነበ​ረች፤ በአ​ን​በ​ሶች መካ​ከል ተጋ​ደ​መች፤ በደ​ቦል አን​በ​ሶ​ችም መካ​ከል ግል​ገ​ሎ​ች​ዋን አሳ​ደ​ገች።</verse>
				<verse number="3">ከግ​ል​ገ​ሎ​ች​ዋም አን​ዱን አወ​ጣች፤ እር​ሱም ደቦል አን​በሳ ሆነ፤ ንጥ​ቂ​ያ​ንም ተማረ፤ ሰዎ​ች​ንም ነጥቆ በላ።</verse>
				<verse number="4">አሕ​ዛ​ብም ስለ እርሱ ሰሙ፤ እር​ሱም በጕ​ድ​ጓ​ዳ​ቸው ተያዘ፤ በሰ​ን​ሰ​ለ​ትም አስ​ረው ወደ ግብፅ ምድር ወሰ​ዱት።</verse>
				<verse number="5">እር​ስ​ዋም ከእ​ር​ስዋ እንደ ወሰ​ዱት ባየች ጊዜ ኀይ​ልዋ ጠፋ፤ ከግ​ል​ገ​ሎ​ች​ዋም ሌላን ወስዳ ደቦል አን​በሳ አደ​ረ​ገ​ችው።</verse>
				<verse number="6">እር​ሱም በአ​ን​በ​ሶች መካ​ከል አደገ፤ ደቦል አን​በ​ሳም ሆነ፤ ንጥ​ቂ​ያም ተማረ፤ ሰዎ​ች​ንም ነጥቆ በላ።</verse>
				<verse number="7">ተዘ​ል​ሎም ይኖ​ራል፤ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም አጠፋ፤ ሀገ​ራ​ቸ​ው​ንም አፈ​ረሰ፤ ከግ​ሣ​ቱም ድምፅ የተ​ነሣ ምድ​ርና ሞላዋ ጠፋች።</verse>
				<verse number="8">አሕ​ዛ​ብም በዙ​ሪ​ያው ከየ​ሀ​ገሩ ሁሉ ተሰ​በ​ሰ​ቡ​በት፤ መረ​ባ​ቸ​ው​ንም በእ​ርሱ ላይ ዘረጉ፤ በወ​ጥ​መ​ዳ​ቸ​ውም ተያዘ።</verse>
				<verse number="9">በሰ​ን​ሰ​ለ​ትም አስ​ረው በቀፎ ውስጥ አኖ​ሩት፤ ወደ ባቢ​ሎ​ንም ንጉሥ አመ​ጡት፤ ድም​ፁም በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ ከዚያ ወዲያ እን​ዳ​ይ​ሰማ ወደ ግዞት ቤት አገ​ቡት።</verse>
				<verse number="10">“እና​ትህ በውኃ አጠ​ገብ እንደ ተተ​ከ​ለች እንደ ወይን ግን​ድና እንደ ጽጌ​ረዳ ነበ​ረች፤ ከው​ኃም ብዛት የተ​ነሣ የም​ታ​ፈ​ራና የም​ት​ሰፋ ሆነች።</verse>
				<verse number="11">ከእ​ር​ስ​ዋም የጸ​ናች በትር ወጣች፤ ለገ​ዥ​ዎ​ችም በትር ሆነች፤ በዛ​ፎ​ችም መካ​ከል ቁመቷ ረዘመ፤ በቅ​ር​ን​ጫ​ፎ​ች​ዋም ርዝ​መቷ ታየ።</verse>
				<verse number="12">ነገር ግን በመ​ዓት ተነ​ቀ​ለች፤ ወደ መሬ​ትም ተጣ​ለች፤ የሚ​ያ​ቃ​ጥ​ልም ነፋስ ፍሬ​ዋን አደ​ረቀ፤ ብር​ቱ​ዎች በት​ሮ​ች​ዋም ተሰ​በ​ሩና ደረቁ፤ እሳ​ትም በላ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">አሁ​ንም በም​ድረ በዳ፥ በደ​ረ​ቅና በተ​ጠ​ማች መሬት ተተ​ከ​ለች።</verse>
				<verse number="14">ከተ​መ​ረ​ጡት ጫፎ​ች​ዋም በትር እሳት ወጣች፤ ፍሬ​ዋ​ንም በላች፤ የነ​ገ​ሥ​ታ​ትም በትር ይሆን ዘንድ የበ​ረታ በትር የለ​ባ​ትም።” ይህ ሙሾ ነው፤ ለል​ቅ​ሶም ይሆ​ናል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፥ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይጠ​ይቁ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሰዎች መጡ፤ በፊ​ቴም ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="2">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="3">“የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔን ትጠ​ይቁ ዘንድ መጥ​ታ​ች​ኋ​ልን? እኔ ሕያው ነኝ! አል​መ​ል​ስ​ላ​ች​ሁም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን በቀ​ልን እበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የሰው ልጅ ሆይ! የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ኀጢ​አት አስ​ታ​ው​ቃ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት በመ​ረ​ጥ​ሁ​በት፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ቤት ዘር በታ​ወ​ቅ​ሁ​በት ቀን፥ በግ​ብ​ፅም ምድር በተ​ገ​ለ​ጥ​ሁ​ላ​ቸው ጊዜ እጄን አን​ሥቼ፦ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ አል​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">በዚያ ቀን ከግ​ብፅ ምድር ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ላ​ቸው፥ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው፥ ከም​ድር ሁሉ ወደ​ም​ት​በ​ልጥ ምድር አወ​ጣ​ቸው ዘንድ እጄን አነ​ሣሁ።</verse>
				<verse number="7">እኔም፦ ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ ርኵ​ሰ​ቱን ከፊቱ ያስ​ወ​ግድ፤ በግ​ብ​ፅም ጣዖ​ታት አት​ር​ከሱ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ አል​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">እነ​ርሱ ግን ዐመ​ፁ​ብኝ፤ ይሰ​ሙ​ኝም ዘንድ አል​ወ​ደ​ዱም፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ ርኵ​ሰ​ቱን ከፊቱ አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ የግ​ብ​ጽ​ንም ጣዖ​ታት አል​ተ​ወም፤ በዚ​ህም ጊዜ በግ​ብፅ ምድር መካ​ከል ቍጣ​ዬን እፈ​ጽ​ም​ባ​ቸው ዘንድ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።</verse>
				<verse number="9">ነገር ግን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው በአሉ፥ ከግ​ብ​ጽም ምድር አወ​ጣ​ቸው ዘንድ በፊ​ታ​ቸው በተ​ገ​ለ​ጥ​ሁ​ላ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ ፊት ስሜ እን​ዳ​ይ​ረ​ክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።</verse>
				<verse number="10">“ከግ​ብ​ፅም ምድር አወ​ጣ​ኋ​ቸው ወደ ምድረ በዳም አመ​ጣ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ሥር​ዐ​ቴ​ንም ሰጠ​ኋ​ቸው፤ ፍር​ዴ​ንም አስ​ታ​ወ​ቅ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">የም​ቀ​ድ​ሳ​ቸ​ውም እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያውቁ ዘንድ፥ በእ​ኔና በእ​ነ​ርሱ መካ​ከል ምል​ክት ይሆኑ ዘንድ ሰን​በ​ታ​ቴን ሰጠ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት በም​ድረ በዳ በት​እ​ዛዜ ሂዱ አል​ኋ​ቸው፤ አል​ሄ​ዱ​ምም፤ ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው ኖሮ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ት​ንም ሕጌን አፈ​ረሱ፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ፈጽ​መው አረ​ከሱ። በዚ​ህም ጊዜ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ቍጣ​ዬን በም​ድረ በዳ አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን በፊ​ታ​ቸው ባወ​ጣ​ኋ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ ፊት ከሁሉ በላይ የሚ​ሆን ስሜን እን​ዳ​ያ​ረ​ክሱ አደ​ረ​ግሁ።</verse>
				<verse number="15">ወተ​ትና ማርም ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ከም​ድር ሁሉ ወደ​ም​ታ​ምር ወደ ሰጠ​ኋ​ቸው ምድር እን​ዳ​ላ​ገ​ባ​ቸው በም​ድረ በዳ በእ​ነ​ርሱ ላይ ፈጽሜ እጄን አነ​ሣሁ።</verse>
				<verse number="16">ፍር​ዴ​ንም ጥሰ​ዋ​ልና፥ በሥ​ር​ዐ​ቴም አል​ሄ​ዱ​ምና፥ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አር​ክ​ሰ​ዋ​ልና በል​ባ​ቸው ዐሳብ ሄዱ።</verse>
				<verse number="17">ነገር ግን እኔ እንደ አላ​ጠ​ፋ​ቸው፥ በም​ድረ በዳም ፈጽሜ እንደ አል​ጨ​ር​ሳ​ቸው ዐይኔ ራራ​ች​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">“ለል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም በም​ድረ በዳ እን​ዲህ አል​ኋ​ቸው፦ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ልማድ አት​ሂዱ፤ ሥር​ዐ​ታ​ቸ​ው​ንም አት​ጠ​ብቁ፤ በበ​ደ​ላ​ቸ​ውም አንድ አት​ሁኑ፤ አት​ር​ከ​ሱም።</verse>
				<verse number="19">እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ፤ በት​እ​ዛዜ ሂዱ፤ ፍር​ዴ​ንም ጠብቁ፤ አድ​ር​ጓ​ትም።</verse>
				<verse number="20">ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ቀድሱ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ምል​ክት ይሁኑ።</verse>
				<verse number="21">ልጆ​ቻ​ቸው ግን አማ​ረ​ሩኝ፤ ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው ኖሮ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ፍር​ዴን ጠብ​ቀው አላ​ደ​ረ​ጉ​ትም፤ በሥ​ር​ዐ​ቴም አል​ሄ​ዱም፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አረ​ከሱ፤ በዚ​ህም ጊዜ፦ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቍጣ​ዬ​ንም በም​ድረ በዳ እፈ​ጽ​ም​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።</verse>
				<verse number="22">ነገር ግን በፊ​ታ​ቸው ባወ​ጣ​ኋ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ ፊት ከሁሉ የሚ​በ​ል​ጠው ስሜ እን​ዳ​ይ​ረ​ክስ አደ​ረ​ግሁ።</verse>
				<verse number="23">ደግ​ሞም ወደ አሕ​ዛብ እበ​ት​ና​ቸው ዘንድ፥ በሀ​ገ​ሮ​ችም እበ​ት​ና​ቸው ዘንድ በም​ድረ በዳ በእ​ነ​ርሱ ላይ እጄን አነ​ሣሁ።</verse>
				<verse number="24">ፍር​ዴን አላ​ደ​ረ​ጉ​ምና፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንም ጥሰ​ዋ​ልና፥ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አር​ክ​ሰ​ዋ​ልና፥ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ዐሳብ ተከ​ት​ለ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="25">ደግ​ሞም መል​ካም ያል​ሆ​ነ​ውን ሥር​ዐት፥ በሕ​ይ​ወት የማ​ይ​ኖ​ሩ​በ​ት​ንም ፍርድ ሰጠ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ እን​ዲ​ያ​ውቁ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ማኅ​ፀን የሚ​ከ​ፍ​ተ​ውን ሁሉ በአ​መ​ጡ​ልኝ ጊዜ፥ በመ​ባ​ቸው አረ​ከ​ስ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="27">“ስለ​ዚህ የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዚ​ህም ደግሞ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ በአ​ደ​ረ​ጉት ዐመፅ አስ​ቈ​ጡኝ።</verse>
				<verse number="28">እሰ​ጣ​ቸ​ውም ዘንድ እጄን ወደ አነ​ሣ​ሁ​ላ​ቸው ምድር አገ​ባ​ኋ​ቸው፤ ከፍ ያለ​ውን ኮረ​ብታ ሁሉ፥ ቅጠ​ላ​ማ​ው​ንም ዛፍ ሁሉ አዩ፤ በዚ​ያም ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸው መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ሠዉ፤ በዚ​ያም የሚ​ያ​ስ​ቈ​ጣ​ኝን፤ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን አቀ​ረቡ፤ በዚ​ያም ደግሞ ጣፋ​ጩን ሽታ​ቸ​ውን አደ​ረጉ፤ በዚ​ያም የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን አፈ​ሰሱ።</verse>
				<verse number="29">እኔም፦ እና​ንተ ወደ እርሱ የም​ት​ሄ​ዱ​በት ከፍታ ምን​ድን ነው? አል​ኋ​ቸው። እስከ ዛሬም ድረስ ስሙ ባማ ተብሎ ተጠ​ር​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="30">ስለ​ዚህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እና​ንተ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ኀጢ​አት ረከ​ሳ​ችሁ፤ አመ​ነ​ዘ​ራ​ችሁ፤ ርኵ​ሰ​ታ​ቸ​ው​ንም ተከ​ተ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="31">ቍር​ባ​ና​ች​ሁን በአ​ቀ​ረ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም በእ​ሳት ባሳ​ለ​ፋ​ችሁ ጊዜ፥ እስከ ዛሬ ድረስ በዐ​ሳ​ባ​ችሁ ሁሉ ረከ​ሳ​ችሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እኔስ እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለ​ሁን? እኔ ሕያው ነኝ! አል​መ​ል​ስ​ላ​ች​ሁም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="32">ለእ​ና​ን​ተም፦ እንደ አሕ​ዛ​ብና እንደ ምድር ወገ​ኖች እን​ሆ​ና​ለን፤ እን​ጨ​ትና ድን​ጋ​ይም እና​መ​ል​ካ​ለን የሚል ከል​ባ​ችሁ የወጣ ዐሳብ አይ​ፈ​ጸ​ም​ላ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="33">“እኔ ሕያው ነኝ! በበ​ረ​ታች እጅና በተ​ዘ​ረ​ጋች ክንድ፥ በፈ​ሰ​ሰ​ችም መዓት እነ​ግ​ሥ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="34">ከአ​ሕ​ዛ​ብም ዘንድ አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከተ​በ​ተ​ና​ች​ሁ​ባ​ትም ሀገር ሁሉ በበ​ረ​ታች እጅና በተ​ዘ​ረ​ጋች ክንድ፥ በፈ​ሰ​ሰ​ችም መዓት እሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="35">ወደ አሕ​ዛ​ብም ምድረ በዳ አመ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ፊት ለፊት ከእ​ና​ንተ ጋር እፋ​ረ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="36">በግ​ብፅ ምድረ በዳ ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ጋር እንደ ተፋ​ረ​ድሁ እን​ዲሁ ከእ​ና​ንተ ጋር እፋ​ረ​ዳ​ለሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="37">ከበ​ት​ሬም በታች አሳ​ል​ፋ​ች​ኋ​ለሁ፤ በቍ​ጥ​ርም እወ​ስ​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="38">ከእ​ና​ን​ተም ዘንድ ዐመ​ፀ​ኞ​ች​ንና የበ​ደ​ሉ​ኝን እለ​ያ​ለሁ፤ ከኖ​ሩ​ባ​ትም ምድር አወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ እስ​ራ​ኤል ምድር ግን አይ​ገ​ቡም፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="39">እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ፥ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሁላ​ችሁ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁን ተዉ፤ ከዚህ በኋላ ስሙኝ፤ ቅዱ​ሱን ስሜ​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በኀ​ጢ​አ​ታ​ች​ሁና በመ​ባ​ችሁ አታ​ር​ክሱ።</verse>
				<verse number="40">“በቅ​ዱሱ ተራ​ራዬ፥ ከፍ ባለው በእ​ስ​ራ​ኤል ተራራ ላይ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በዚያ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ሁላ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይገ​ዙ​ል​ኛል፤ በዚ​ያም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ቀዳ​ም​ያ​ታ​ች​ሁን፥ በኵ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ የቀ​ደ​ሳ​ች​ሁ​ት​ንም ነገር ሁሉ እጐ​በ​ኛ​ለሁ።</verse>
				<verse number="41">ከአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ባወ​ጣ​ኋ​ችሁ ጊዜ፥ ከተ​በ​ተ​ና​ች​ሁ​ባ​ትም ሀገር ሁሉ በሰ​በ​ሰ​ብ​ኋ​ችሁ ጊዜ እንደ ጣፋጭ ሽታ እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ፊት እቀ​ደ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="42">ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም እሰ​ጣት ዘንድ እጄን ወደ አነ​ሣ​ሁ​ላ​ቸው ምድር ወደ እስ​ራ​ኤል ሀገር ባገ​ባ​ኋ​ችሁ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="43">በዚ​ያም የረ​ከ​ሳ​ች​ሁ​ባ​ትን መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና ሥራ​ች​ሁን ሁሉ ታስ​ባ​ላ​ችሁ፤ በፊ​ታ​ች​ሁም አይ​ታ​ችሁ ስለ ሠራ​ች​ሁት ክፋ​ታ​ችሁ ሁሉ ታፍ​ራ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="44">የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እንደ ክፉ መን​ገ​ዳ​ች​ሁና እንደ ርኩስ ሥራ​ችሁ ሳይ​ሆን ስለ ስሜ ስል በሠ​ራ​ሁ​ላ​ችሁ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="45">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፤</verse>
				<verse number="46">“የሰው ልጅ ሆይ! ፊት​ህን ወደ ቴማን አቅና፤ ወደ ዳሮ​ምም ተመ​ል​ከት፤ በና​ጌ​ብም ምድረ በዳ ዱር ንጉሥ ላይ ትን​ቢት ተና​ገር።</verse>
				<verse number="47">ለና​ጌ​ብም ዱር እን​ዲህ በለው፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በአ​ንተ ውስጥ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በው​ስ​ጥ​ህም ያለ​ውን የለ​መ​ለ​መ​ው​ንና የደ​ረ​ቀ​ውን ዛፍ ሁሉ ይበ​ላል፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም ነበ​ል​ባል አይ​ጠ​ፋም፤ ከደ​ቡ​ብም ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ ፊት ሁሉ ይቃ​ጠ​ል​በ​ታል።</verse>
				<verse number="48">እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ነ​ደ​ድ​ሁት ሥጋ ለባሽ ሁሉ ያያል፥ እር​ሱም አይ​ጠ​ፋም።</verse>
				<verse number="49">እኔም፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ይህ አይ​ሁን አልሁ፤ እነ​ርሱ ግን፦ ይህ የነ​ገ​ረን ምሳሌ አይ​ደ​ለ​ምን? ይሉ​ኛል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ​ዚህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ፊት​ህን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አቅና፤ ወደ መቅ​ደ​ሶ​ችም ተመ​ል​ከት፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ምድር ላይ ትን​ቢት ተና​ገር።</verse>
				<verse number="3">ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ምድር እን​ዲህ በል፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በአ​ንቺ ላይ ነኝ፤ ሰይ​ፌ​ንም ከሰ​ገ​ባው እመ​ዝ​ዘ​ዋ​ለሁ፤ ጻድ​ቁ​ንና ኃጥ​ኡን ከአ​ንቺ ዘንድ አጠ​ፋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">እኔም ጻድ​ቁ​ንና ኃጥ​ኡን ከአ​ንቺ ዘንድ ስለ​ማ​ጠፋ፥ ስለ​ዚህ ሰይፌ ከደ​ቡብ ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ በአለ በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ከሰ​ገ​ባው ይመ​ዘ​ዛል።</verse>
				<verse number="5">ሥጋ ለባ​ሹም ሁሉ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይ​ፌን ከሰ​ገ​ባው እንደ መዘ​ዝሁ ያው​ቃል፤ እር​ሱም ደግሞ አይ​መ​ለ​ስም።</verse>
				<verse number="6">ስለ​ዚህ አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ወገ​ብ​ህን በማ​ጕ​በጥ አል​ቅስ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ምርር ብለህ አል​ቅስ።</verse>
				<verse number="7">እነ​ር​ሱም፦ ስለ ምን ታለ​ቅ​ሳ​ለህ? ቢሉህ አንተ እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ስለ​ሚ​መ​ጣው ወሬ ነው፤ ልብም ሁሉ ይቀ​ል​ጣል፤ እጆ​ችም ሁሉ ይዝ​ላሉ፤ ሥጋና መን​ፈስ ሁሉ ይደ​ክ​ማል፤ ከጕ​ል​በ​ትም እዥ ይፈ​ስ​ሳል፤ እነሆ ይመ​ጣል፤ ይፈ​ጸ​ማ​ልም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="8">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="9">“የሰው ልጅ ሆይ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል ብለህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ሰይፍ ሰይፍ የተ​ሳ​ለች፥ የተ​ሰ​ነ​ገ​ለ​ችም ሁኚ።</verse>
				<verse number="10">ወግ​ተሽ ትገ​ድሊ ዘንድ፥ ታብ​ረ​ቀ​ር​ቂም ዘንድ ተሳዪ፤ ትገ​ድ​ሊም ዘንድ፥ ዕን​ጨ​ቱ​ንም ሁሉ ትጥዪ ዘንድ ጨክኚ፤</verse>
				<verse number="11">በእ​ጁም ይይ​ዛት ዘንድ ለአ​ር​በኛ ተሰ​ጠች፤ ሰይፍ በገ​ዳይ እጅ እን​ድ​ት​ሰጥ ተሳ​ለ​ችና ተዘ​ጋ​ጀች።</verse>
				<verse number="12">የሰው ልጅ ሆይ! በሕ​ዝቤ ላይ ነውና፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አለ​ቆች ሁሉ ላይ ነውና ጩኽ፤ ዋይም በል፤ እነ​ርሱ ከሕ​ዝቤ ጋር ለሰ​ይፍ ተሰ​ጥ​ተ​ዋል፤ ስለ​ዚህ እጅ​ህን ጽፋ።</verse>
				<verse number="13">እው​ነት ሆኖ​አ​ልና፤ የራቁ ሕዝቤ ምን ሆኑ? የሉ​ምና፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="14">ስለ​ዚህ አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት ተና​ገር፤ እጅ​ህን በእ​ጅህ ላይ አጨ​ብ​ጭብ፤ የተ​ገ​ደሉ ሰዎች ሰይፍ ሦስት ጊዜ ይደ​ጋ​ግም፤ ይኸ​ውም የታ​ላቅ ግድያ ሰይፍ ነው፤ ያስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ቸ​ዋ​ልም።</verse>
				<verse number="15">ልባ​ቸው እን​ዲ​ቀ​ልጥ፥ መሰ​ና​ክ​ላ​ቸ​ውም እን​ዲ​በዛ የሚ​ገ​ድ​ለ​ውን ሰይፍ በበ​ሮ​ቻ​ቸው ሁሉ ላይ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ ወዮ! ያብ​ረ​ቀ​ርቅ ዘንድ ተሰ​ን​ግ​ሏል፤ ይገ​ድ​ልም ዘንድ ተስ​ሏል።</verse>
				<verse number="16">ፊትህ ወደ አቀ​ናው ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ሂድ።</verse>
				<verse number="17">እኔ ደግሞ እጄን በእጄ ላይ አጨ​በ​ጭ​ባ​ለሁ፤ መዓ​ቴ​ንም እል​ካ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="18">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="19">“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሰይፍ የም​ት​ገ​ባ​ባ​ቸው ሁለት መን​ገ​ዶ​ችን አድ​ርግ፤ ሁለ​ቱም ከአ​ን​ዲት ምድር ይውጡ፤ ምል​ክ​ት​ንም አድ​ርግ፤ በከ​ተ​ማ​ዪቱ መን​ገድ ራስ ላይም አድ​ር​ገው።</verse>
				<verse number="20">ሰይፍ ወደ አሞን ልጆች ሀገር፥ ወደ ራባት፥ ወደ ይሁ​ዳም፥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም፥ በመ​ካ​ከ​ልዋ ይገባ ዘንድ መን​ገ​ድን አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="21">የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ምዋ​ር​ቱን ያም​ዋ​ርት ዘንድ፥ በት​ሩን ያነሣ ዘንድ፥ ጣዖ​ቱ​ንም ይጠ​ይቅ ዘንድ በሁ​ለት መን​ገ​ዶች ራስ ላይ ይቆ​ማል።</verse>
				<verse number="22">የቅ​ጥ​ሩን ማፍ​ረሻ ያደ​ርግ ዘንድ፥ አፍ​ንም በጩ​ኸት ይከ​ፍት ዘንድ፥ በው​ካ​ታም ድም​ፅን ከፍ ያደ​ርግ ዘንድ፥ የቅ​ጥ​ሩን ማፍ​ረሻ በበ​ሮች ላይ ያደ​ርግ ዘንድ፥ አፈ​ርን ይደ​ለ​ድል ዘንድ፥ ምሽ​ግም ይሠራ ዘንድ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ምዋ​ርት በቀኝ እጁ ውስጥ ነበረ።</verse>
				<verse number="23">እርሱ በፊ​ታ​ቸው ምዋ​ር​ትን ያም​ዋ​ር​ታል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ዐስቦ ሰባት ሱባዔ ይቈ​ጥ​ር​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="24">“ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁን ስለ ዐሰ​ባ​ችሁ፥ መተ​ላ​ለ​ፋ​ች​ሁም ስለ ተገ​ለጠ፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም በሥ​ራ​ችሁ ሁሉ ስለ ታየ፥ እና​ን​ተም ስለ ታሰ​ባ​ችሁ፥ በእ​ርሱ ትያ​ዛ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="25">አን​ተም ቀን​ህና የኀ​ጢ​አ​ትህ ቀጠሮ ጊዜ የደ​ረ​ሰ​ብህ፥ ርኩስ ኀጢ​አ​ተኛ የእ​ስ​ራ​ኤል አለቃ ሆይ!</verse>
				<verse number="26">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያ​ውን አው​ልቅ፤ ዘው​ዱ​ንም አርቅ፤ ይህ እን​ዲህ አይ​ሆ​ንም፤ የተ​ዋ​ረ​ደ​ውን ከፍ አድ​ርግ፤ ከፍ ያለ​ው​ንም አዋ​ርድ።</verse>
				<verse number="27">ባድማ፥ ባድማ፥ ባድማ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ ፍርድ ያለው እስ​ኪ​መጣ ድረስ ይህች ደግሞ አት​ሆ​ንም፤ ለእ​ር​ሱም እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="28">“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አሞን ልጆ​ችና ስለ ስድ​ባ​ቸው እን​ዲህ ይላል ብለህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ሰይፍ ሰይፍ ለመ​ግ​ደል ተመ​ዝ​ዞ​አል፤ ጨር​ሶም ያርድ ዘንድ ተሰ​ን​ግ​ሎ​አል በል።</verse>
				<verse number="29">በተ​ገ​ደ​ሉት ኀጢ​አ​ተ​ኞች አን​ገት ላይ ያኖ​ሩህ ዘንድ ከንቱ ራእ​ይን ሲያ​ዩ​ልህ፥ በሐ​ሰት ምዋ​ር​ትም ሲና​ገ​ሩ​ልህ፥ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ቀጠሮ ጊዜ ቀና​ቸው ደረሰ።</verse>
				<verse number="30">ወደ ሰገ​ባ​ውም መል​ሰው፤ በተ​ፈ​ጠ​ር​ህ​ባት ስፍራ አት​ደር፤ በተ​ወ​ለ​ድ​ህ​ባ​ትም ምድር እፈ​ር​ድ​ብ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="31">ቍጣ​ዬ​ንም አፈ​ስ​ስ​ብ​ሃ​ለሁ፤ በመ​ዓ​ቴም እሳት አና​ፋ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ማጥ​ፋ​ት​ንም ለሚ​ያ​ውቁ ለጨ​ካ​ኞች ሰዎች እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="32">ለእ​ሳት ማገዶ ትሆ​ና​ለህ፤ ደም​ህም በም​ድር መካ​ከል ይፈ​ስ​ሳል፤ ደግ​ሞም አት​ታ​ሰ​ብም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ደም በም​ታ​ፈ​ስስ ከተማ ላይ ትፈ​ር​ዳ​ለ​ህን? ርኵ​ሰ​ቷን ሁሉ አስ​ታ​ው​ቃት።</verse>
				<verse number="3">እን​ዲ​ህም በላት፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጊዜሽ እን​ዲ​ደ​ርስ በመ​ካ​ከ​ልሽ ደምን የም​ታ​ፈ​ስሺ፥ እን​ድ​ት​ረ​ክ​ሺም በራ​ስሽ ላይ ጣዖ​ታ​ትን የም​ታ​ደ​ርጊ ከተማ ሆይ!</verse>
				<verse number="4">ባፈ​ሰ​ስ​ሽው ደም በድ​ለ​ሻል፤ ባደ​ረ​ግ​ሻ​ቸ​ውም ጣዖ​ታት ረክ​ሰ​ሻል፤ ቀን​ሽ​ንም አቀ​ረ​ብሽ፤ ዘመ​ን​ሽ​ንም አሳ​ጠ​ርሽ፤ ስለ​ዚህ ለአ​ሕ​ዛብ መሰ​ደ​ቢያ፥ ለሀ​ገ​ሮ​ችም ሁሉ መሳ​ለ​ቂያ አደ​ረ​ግ​ሁሽ።</verse>
				<verse number="5">አንቺ ስምሽ የረ​ከሰ፥ ኀጢ​አ​ትም የሞ​ላ​ብሽ ሆይ! ወደ አንቺ የቀ​ረ​ቡና ከአ​ንቺ የራቁ ይሳ​ለ​ቁ​ብ​ሻል።</verse>
				<verse number="6">“እነሆ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት አለ​ቆች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከዘ​መ​ዶ​ቻ​ቸው ጋር ደም ያፈ​ስሱ ዘንድ በአ​ንቺ ውስጥ ተባ​በሩ።</verse>
				<verse number="7">በአ​ንቺ ውስጥ አባ​ት​ንና እና​ትን አቃ​ለሉ፤ በመ​ካ​ከ​ልሽ በመ​ጻ​ተ​ኛው ላይ በደ​ልን አደ​ረጉ፤ በአ​ንቺ ውስጥ ድሀ አደ​ጉ​ንና መበ​ለ​ቲ​ቱን አስ​ጨ​ነቁ።</verse>
				<verse number="8">ቅድ​ሳ​ቴ​ንም ናቁ፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አረ​ከሱ።</verse>
				<verse number="9">በው​ስ​ጥሽ ደምን ያፈ​ስሱ ዘንድ ሌቦች ሰዎች በአ​ንቺ ውስጥ ነበሩ፤ በአ​ንቺ ውስጥ በተ​ራ​ሮች ላይ በሉ፤ በመ​ካ​ከ​ል​ሽም የማ​ይ​ገባ ነገ​ርን አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="10">በአ​ንቺ ውስጥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ኀፍ​ረተ ሥጋ ገለጡ፤ በአ​ን​ቺም ውስጥ አደፍ ያለ​ባ​ትን አዋ​ረዱ።</verse>
				<verse number="11">ሰውም ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ሚስት ጋር ሰሰነ፤ አባ​ትም የል​ጁን ሚስት በኀ​ጢ​አት አረ​ከሰ፤ በአ​ን​ቺም ዘንድ ወን​ድም የአ​ባ​ቱን ልጅ እኅ​ቱን አስ​ነ​ወረ።</verse>
				<verse number="12">በአ​ንቺ ውስጥ ደምን ያፈ​ስሱ ዘንድ መማ​ለ​ጃን ተቀ​በሉ፤ በአ​ን​ቺም አራ​ጣና ትርፍ ወስ​ደ​ዋል፤ ቀማ​ኛ​ነ​ት​ሽ​ንና ኀጢ​አ​ት​ሽን ፈጸ​ምሽ፤ እኔ​ንም ረሳ​ሽኝ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="13">“ስለ​ዚህ እነሆ አንቺ ባደ​ረ​ግ​ሽው ሥራ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ሽም በነ​በ​ረው ደም ላይ በእጄ አጨ​በ​ጨ​ብሁ።</verse>
				<verse number="14">እኔ በማ​ደ​ር​ግ​ብሽ ወራት ልብሽ ይታ​ገ​ሣ​ልን? ወይስ እጆ​ችሽ ይጸ​ና​ሉን? እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አደ​ር​ገ​ው​ማ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">ወደ አሕ​ዛ​ብም እበ​ት​ን​ሻ​ለሁ፤ በሀ​ገ​ሮ​ችም እዘ​ራ​ሻ​ለሁ፤ ከአ​ን​ቺም ርኵ​ሰ​ትሽ ይጠ​ፋል።</verse>
				<verse number="16">በአ​ሕ​ዛ​ብም ፊት ከአ​ንቺ እወ​ር​ሳ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”</verse>
				<verse number="17">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="18">“የሰው ልጅ ሆይ! የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ የተ​ቀ​ላ​ቀሉ ናስና ቆር​ቆሮ፥ ብረ​ትና እር​ሳስ ሆኑ​ብኝ፤ በማ​ጣ​ሪ​ያም መካ​ከል የተ​ቀ​ላ​ቀለ ብር ሆኑ።</verse>
				<verse number="19">ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሁላ​ችሁ አተላ ሆና​ች​ኋ​ልና ስለ​ዚህ እነሆ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ እሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">እን​ዲ​ያ​ቀ​ል​ጡት እሳት ያና​ፉ​በት ዘንድ ብር​ንና መዳ​ብን፥ ብረ​ት​ንና እር​ሳ​ስን፥ ቆር​ቆ​ሮ​ንም በከ​ውር እን​ደ​ሚ​ሰ​በ​ስቡ፥ እን​ዲሁ በቍ​ጣ​ዬና በመ​ዓቴ እሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ውስጥ እጨ​ም​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ አቀ​ል​ጣ​ች​ሁ​ማ​ለሁ።</verse>
				<verse number="21">በላ​ያ​ችሁ የመ​ዓ​ቴን እሳት አነ​ድ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በመ​ካ​ከ​ሉም ትቀ​ል​ጣ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="22">ብርም በከ​ውር ውስጥ እን​ደ​ሚ​ቀ​ልጥ፥ እን​ዲሁ በው​ስ​ጥዋ ትቀ​ል​ጣ​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓ​ቴን እን​ዳ​ፈ​ሰ​ስ​ሁ​ባ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="23">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="24">“የሰው ልጅ ሆይ! አንቺ ዝናም የማ​ይ​ዘ​ን​ብ​ብሽ፥ በቍጣ ቀን ጠል የማ​ይ​ወ​ር​ድ​ብሽ ምድር ነሽ በላት።</verse>
				<verse number="25">በመ​ካ​ከሏ ያሉ ነቢ​ያት እንደ አን​በሳ ያገ​ሳሉ፤ ይነ​ጥ​ቃሉ፤ ፈጽ​መ​ውም ይቀ​ማሉ፤ ሰው​ነ​ት​ንም ያጠ​ፋሉ፤ መማ​ለ​ጃ​ንም ይቀ​በ​ላሉ፤ በመ​ካ​ከ​ል​ዋም መበ​ለ​ቶ​ችዋ ይበ​ዛሉ።</verse>
				<verse number="26">ካህ​ና​ቷም ሕጌን ጣሱ፤ በመ​ቅ​ደ​ሴም መካ​ከል ቅድ​ሳ​ቴን አረ​ከሱ፤ ከር​ኵ​ሰ​ትም አል​ራ​ቁም፤ በን​ጹ​ሕና በር​ኩስ መካ​ከል ያለ​ው​ንም ልዩ​ነት አላ​ወ​ቁም፤ ዐይ​ና​ቸ​ው​ንም ከሰ​ን​በ​ታቴ ሸፈኑ፤ እኔም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ረከ​ስሁ።</verse>
				<verse number="27">በው​ስ​ጥዋ ያሉ አለ​ቆ​ችዋ የስ​ስ​ትን ትርፍ ለማ​ግ​ኘት ሲሉ ደምን ያፈ​ስሱ ዘንድ፥ ነፍ​ሶ​ች​ንም ያጠፉ ዘንድ እን​ደ​ሚ​ና​ጠቁ ተኵ​ላ​ዎች ናቸው።</verse>
				<verse number="28">ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ይቀ​ቡ​አ​ቸ​ዋል፤ ከንቱ ነገ​ር​ንም ያዩ​ላ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አለ እያ​ሉም በሐ​ሰት ያም​ዋ​ር​ቱ​ላ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን አል​ነ​ገ​ራ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="29">የም​ድር ሕዝብ ግፍን አደ​ረጉ፤ ቅሚ​ያ​ንም ሠሩ፤ ድሆ​ች​ንና ችግ​ረ​ኞ​ችን አስ​ጨ​ነቁ፤ ለመ​ጻ​ተ​ኛ​ውም አል​ፈ​ረ​ዱ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="30">ቅጥ​ርን የሚ​ጠ​ግ​ንን፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋት በፈ​ረ​ሰ​በት በኩል በፊቴ የሚ​ቆ​ም​ላ​ትን ሰው ከእ​ነ​ርሱ መካ​ከል ፈለ​ግሁ፤ ነገር ግን አላ​ገ​ኘ​ሁም።</verse>
				<verse number="31">ስለ​ዚህ ቍጣ​ዬን አፈ​ሰ​ስ​ሁ​ባ​ቸው፤ በመ​ዓ​ቴም እሳት አጠ​ፋ​ኋ​ቸው፤ መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንም በራ​ሳ​ቸው ላይ መለ​ስሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="23">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“የሰው ልጅ ሆይ፥ የአ​ን​ዲት እናት ልጆች የሆኑ ሁለት ሴቶች ነበሩ።</verse>
				<verse number="3">በግ​ብፅ ሀገር አመ​ነ​ዘሩ፤ በኮ​ረ​ዳ​ነ​ታ​ቸው ሳሉ አመ​ነ​ዘሩ፤ በዚ​ያም ጡቶ​ቻ​ቸው ወደቁ፤ በዚ​ያም ድን​ግ​ል​ና​ቸ​ውን አጡ።</verse>
				<verse number="4">ስማ​ቸ​ውም የታ​ላ​ቂቱ ሐላ የታ​ናሽ እኅ​ቷም ሐሊባ ነበረ፤ እኔም አገ​ባ​ኋ​ቸው፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ንም ወለዱ። ስማ​ቸ​ውም ሐላ ሰማ​ርያ ናት፤ ሐሊባ ደግሞ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ናት።</verse>
				<verse number="5">“ሐላም አመ​ነ​ዘ​ረ​ች​ብኝ፤ ወዳ​ጆ​ች​ዋ​ንም የሚ​ቀ​ር​ቡ​አ​ትን አሦ​ራ​ው​ያ​ንን በፍ​ቅር ተከ​ተ​ለ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">እነ​ር​ሱም ሰማ​ያዊ ሐር የለ​በሱ መሳ​ፍ​ን​ትና መኳ​ን​ንት፥ መልከ መል​ካ​ሞች ጐበ​ዛ​ዝት፥ በፈ​ረስ ላይ የሚ​ቀ​መጡ የተ​መ​ረጡ ፈረ​ሰ​ኞች ነበሩ።</verse>
				<verse number="7">ዝሙ​ቷ​ንም ከተ​መ​ረጡ ከአ​ሦር ሰዎች ሁሉ ጋር አደ​ረ​ገች፤ በፍ​ቅር በተ​ከ​ተ​ለ​ቻ​ቸ​ውም ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ ረከ​ሰች።</verse>
				<verse number="8">በግ​ብ​ፅም የነ​በ​ረ​ውን ዝሙ​ቷን አል​ተ​ወ​ችም፤ በዚ​ያም በኮ​ረ​ዳ​ነቷ ጊዜ ከእ​ር​ስዋ ጋር ተኝ​ተው ነበር፤ የድ​ን​ግ​ል​ና​ዋ​ንም ጡቶች ዳብ​ሰው ነበር፤ ዝን​የ​ታ​ቸ​ው​ንም አፍ​ስ​ሰ​ው​ባት ነበር።</verse>
				<verse number="9">ስለ​ዚህ በፍ​ቅር በተ​ከ​ተ​ለ​ቻ​ቸው በወ​ዳ​ጆ​ችዋ በአ​ሦ​ራ​ው​ያን እጆች አሳ​ልፌ ሰጠ​ኋት።</verse>
				<verse number="10">እነ​ር​ሱም ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን ገለጡ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ዋ​ንም ማር​ከው ወሰዱ፤ እር​ስ​ዋ​ንም በሰ​ይፍ ገደሉ፤ በእ​ር​ስ​ዋና በሴ​ቶች ልጆ​ችዋ ላይ በቀ​ልን ስላ​ደ​ረ​ጉ​ባ​ቸው በሴ​ቶች መካ​ከል መተ​ረቻ ሆነች።</verse>
				<verse number="11">“እኅ​ቷም ሐሊባ ይህን አየች፤ ሆኖም ከእ​ር​ስዋ ይልቅ በፍ​ቅር በመ​ከ​ተ​ልዋ ረከ​ሰች፤ ዝሙ​ቷ​ንም ከእ​ኅቷ ዝሙት ይልቅ አበ​ዛች።</verse>
				<verse number="12">የሚ​ቀ​ር​ቡ​አ​ትን መሳ​ፍ​ን​ቱ​ንና መኳ​ን​ን​ቱን ጌጠኛ ልብስ የለ​በ​ሱ​ትን፥ በፈ​ረ​ሶች ላይ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን ፈረ​ሰ​ኞች፥ ሁሉ​ንም መልከ መል​ካ​ሞ​ችን ጐበ​ዛ​ዝት አሦ​ራ​ው​ያ​ንን በፍ​ቅር ተከ​ተ​ለ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">እንደ ረከ​ሱም አየሁ፤ ሁለ​ቱም አንድ መን​ገድ ሄደ​ዋል።</verse>
				<verse number="14">ዳግ​መ​ኛም ዝሙ​ቷን አበ​ዛች፤ በግ​ንብ ላይ የተ​ሣሉ የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሰዎች ሥዕ​ል​ንም አየሁ።</verse>
				<verse number="15">በጥ​ቍር ቀለም የተ​ሣሉ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን መልክ አየሁ፤ በወ​ገ​ባ​ቸው ዝናር የታ​ጠቁ ናቸው፤ በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ ጥልፍ ሰበን የጠ​መ​ጠሙ ናቸው፤ ፊታ​ቸ​ውም ሦስት ወገን ነው፤ ሁሉም በት​ው​ልድ ሀገ​ራ​ቸው የሚ​ኖሩ የባ​ቢ​ሎን ሰዎ​ችን ከለ​ዳ​ው​ያ​ንን ይመ​ስ​ላሉ።</verse>
				<verse number="16">ዐይ​ን​ዋ​ንም ወደ እነ​ርሱ አቅ​ንታ አየ​ቻ​ቸው፤ ወደ ከላ​ው​ዴ​ዎ​ንም ምድር ወደ እነ​ርሱ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከች።</verse>
				<verse number="17">የባ​ቢ​ሎ​ንም ልጆች ወደ እር​ስዋ መጥ​ተው በመ​ኝ​ታዋ ከእ​ር​ስዋ ጋር ተኙ፤ በዝ​ሙ​ታ​ቸ​ውም አረ​ከ​ሱ​አት፤ እር​ስ​ዋም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ረከ​ሰች፤ ነፍ​ስ​ዋም ከእ​ነ​ርሱ ተለ​የች።</verse>
				<verse number="18">ዝሙ​ቷ​ንም ገለ​ጠች፤ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋ​ንም ገለ​ጠች፤ ነፍ​ሴም ከእ​ኅቷ እንደ ተለ​የች እን​ዲሁ ነፍሴ ከእ​ር​ስዋ ተለ​የች።</verse>
				<verse number="19">ነገር ግን በግ​ብፅ ምድር ያመ​ነ​ዘ​ረ​ሽ​በ​ትን የወ​ጣ​ት​ነ​ት​ሽን ዘመን አስ​በሽ ዝሙ​ት​ሽን አበ​ዛሽ።</verse>
				<verse number="20">አካ​ላ​ቸ​ውም እንደ አህ​ዮች አካል፤ ዘራ​ቸ​ውም እንደ ፈረ​ሶች ዘር የሆ​ነ​ውን እነ​ዚ​ያን የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ልጆች በፍ​ቅር ተከ​ተ​ል​ሻ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">ጡትሽ በአ​ጐ​ጠ​ጐጠ ጊዜ በማ​ደ​ሪ​ያሽ በግ​ብፅ ሀገር የሠ​ራ​ሽ​ውን የወ​ጣ​ት​ነ​ት​ሽን ኀጢ​አት አሰ​ብሽ።”</verse>
				<verse number="22">ስለ​ዚህ ሐሊባ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ነፍ​ስሽ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ለ​የች ወዳ​ጆ​ች​ሽን አስ​ነ​ሣ​ብ​ሻ​ለሁ፤ በዙ​ሪ​ያ​ሽም በአ​ንቺ ላይ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="23">እነ​ር​ሱም የባ​ቢ​ሎን ልጆች፥ ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም ሁሉ፥ ፋቁድ፥ ሱሔ፥ ቆዓ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር አሦ​ራ​ው​ያን ሁሉ፥ መልከ መል​ካ​ሞች ጐበ​ዛ​ዝት፥ መሳ​ፍ​ን​ትና መኳ​ን​ንት ሁሉ፥ መሳ​ፍ​ን​ትና አማ​ካ​ሪ​ዎች ሁሉ፥ በሦ​ስት ወገን በፈ​ረስ ላይ የተ​ቀ​መጡ ናቸው።</verse>
				<verse number="24">ስማ​ቸ​ውን ያስ​ጠሩ ሰዎች ሁሉ በመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ርና በሠ​ረ​ገላ፥ በአ​ሕ​ዛ​ብም ጉባኤ ይመ​ጡ​ብ​ሻል፤ ጋሻና አላ​ባሽ ጋሻ፥ ራስ ቍርም ይዘው በዙ​ሪ​ያሽ ጥበቃ ያደ​ር​ጋሉ፤ ፍር​ድ​ንም እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ፍር​ዳ​ቸ​ውም ይፈ​ር​ዱ​ብ​ሻል።</verse>
				<verse number="25">ቅን​አ​ቴ​ንም በአ​ንቺ ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በመ​ዓ​ትም ያደ​ር​ጉ​ብ​ሻል፤ አፍ​ን​ጫ​ሽ​ንና ጆሮ​ሽ​ንም ከአ​ንቺ ይቈ​ር​ጣሉ፤ ከአ​ን​ቺም የቀረ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃል፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ሽ​ንም ማር​ከው ይወ​ስ​ዳሉ፤ ከአ​ን​ቺም የቀ​ሩ​ትን እሳት ትበ​ላ​ቸ​ዋ​ለች።</verse>
				<verse number="26">ልብ​ስ​ሽ​ንም ይገ​ፍ​ፉ​ሻል፤ የክ​ብ​ር​ሽ​ንም ጌጥ ይወ​ስ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="27">ሴሰ​ኝ​ነ​ት​ሽ​ንም፥ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ሽ​ውን ዝሙ​ት​ሽ​ንም ከአ​ንቺ አስ​ቀ​ራ​ለሁ፤ ዐይ​ን​ሽ​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ወደ እነ​ርሱ አታ​ነ​ሺም፤ ግብ​ፅ​ንም ከዚያ ወዲያ አታ​ስ​ቢም።</verse>
				<verse number="28">ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በጠ​ላ​ሻ​ቸው እጅ፥ ነፍ​ስ​ሽም በተ​ለ​የ​ቻ​ቸው እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጥ​ሻ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="29">እነ​ር​ሱም በጥል ያደ​ር​ጉ​ብ​ሻል፤ የደ​ከ​ም​ሽ​በ​ት​ንም ሁሉ ይወ​ስ​ዳሉ፤ ዕራ​ቁ​ት​ሽ​ንና ዕር​ቃ​ን​ሽን አድ​ር​ገ​ውም ይተ​ዉ​ሻል፤ የግ​ል​ሙ​ት​ና​ሽ​ንም ነውር፥ ሴሰ​ኝ​ነ​ት​ሽ​ንና ግል​ሙ​ት​ና​ሽ​ንም ሁሉ ይገ​ል​ጣሉ።</verse>
				<verse number="30">ከአ​ሕ​ዝብ ጋር ስላ​መ​ነ​ዘ​ርሽ፤ በበ​ደ​ላ​ቸ​ውም ስለ ረከ​ስሽ ይህን ያደ​ር​ጉ​ብ​ሻል።</verse>
				<verse number="31">በእ​ኅ​ትሽ መን​ገድ ሄደ​ሻል፤ ስለ​ዚህ ጽዋ​ዋን በእ​ጅሽ እሰ​ጥ​ሻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="32">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የጠ​ለ​ቀ​ው​ንና የሰ​ፋ​ውን፥ ብዙም የሚ​ይ​ዘ​ውን የእ​ኅ​ት​ሽን ጽዋ ትጠ​ጪ​አ​ለሽ፤ ብዙ መጠ​ጥን በሚ​ጠጡ ሰዎ​ችም ዘንድ መሳ​ቂ​ያና መሳ​ለ​ቂያ ትሆ​ኛ​ለሽ።</verse>
				<verse number="33">በእ​ኅ​ትሽ በሰ​ማ​ርያ ጽዋ፥ በድ​ን​ጋ​ጤና በጥ​ፋት ጽዋ፥ በስ​ካ​ርና በው​ር​ደት ትሞ​ሊ​ያ​ለሽ።</verse>
				<verse number="34">ትጠ​ጪ​ዋ​ለሽ፥ ትጨ​ል​ጪ​ው​ማ​ለሽ፤ በዓ​ላ​ት​ሽ​ንና መባ​ቻ​ዎ​ች​ሽን እሽ​ራ​ለሁ፤ እኔ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="35">ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ዘን​ግ​ተ​ሽ​ኛ​ልና፥ ወደ ኋላ​ሽም ጥለ​ሽ​ኛ​ልና አንቺ ደግሞ ሴሰ​ኝ​ነ​ት​ሽ​ንና ኀጢ​አ​ት​ሽን ተሸ​ከሚ።”</verse>
				<verse number="36">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ሐላ​ንና ሐሊ​ባን ተፋ​ረ​ዳ​ቸው፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም አስ​ታ​ው​ቃ​ቸው፤</verse>
				<verse number="37">አመ​ን​ዝ​ረ​ዋ​ልና፥ ደምም በእ​ጃ​ቸው አለና፥ ዝሙ​ታ​ቸ​ው​ንም ወድ​ደ​ዋ​ልና፥ ለእ​ኔም የወ​ለ​ዱ​አ​ቸ​ውን ልጆ​ቻ​ቸ​ውን መብል እን​ዲ​ሆ​ኑ​ላ​ቸው በእ​ሳት አሳ​ል​ፈ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="38">ይህን ደግሞ አድ​ር​ገ​ው​ብ​ኛል፤ በዚያ ቀን መቅ​ደ​ሴን አር​ክ​ሰ​ዋል፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ሽረ​ዋል።</verse>
				<verse number="39">ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸው በሠዉ ጊዜ ፥ በዚ​ያው ቀን ያረ​ክ​ሱት ዘንድ ወደ መቅ​ደሴ ገቡ፤ እነ​ሆም በቤቴ ውስጥ እን​ደ​ዚህ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="40">ከሩቅ ሀገ​ርም ወደ​መጡ ሰዎች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላኩ፤ እነ​ር​ሱም በደ​ረሱ ጊዜ ይታ​ጠ​ባሉ፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይኳ​ላሉ፤ ያጌ​ጣ​ሉም።</verse>
				<verse number="41">በክ​ብር አልጋ ላይ ይቀ​መ​ጣሉ፤ በፊት ለፊ​ታ​ቸ​ውም ማዕድ ተዘ​ጋ​ጅታ ነበር፤ በዕ​ጣ​ኔና በዘ​ይ​ቴም ደስ ይላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="42">የበ​ገ​ና​ውን አው​ታር ድምፅ ይቃ​ኛሉ፤ ከብዙ ሰዎ​ችም ጉባኤ ጋር ሰካ​ራ​ሞቹ ከም​ድረ በዳ መጡ፤ በእ​ጃ​ቸው አን​ባር፥ በራ​ሳ​ቸ​ውም የተ​ዋበ አክ​ሊል አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="43">እኔም፦ ‘አሁን ከእ​ር​ስዋ ጋር ያመ​ነ​ዝ​ራሉ፤ እር​ስ​ዋም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ታመ​ነ​ዝ​ራ​ለች፤’ አልሁ።</verse>
				<verse number="44">ወደ ጋለ​ሞታ እን​ደ​ሚ​ገ​ቡም ወደ እር​ስዋ ገቡ፤ እን​ዲሁ ይሰ​ስኑ ዘንድ ወደ ሐላና ወደ ሐሊባ ገቡ።</verse>
				<verse number="45">ሴቶቹ አመ​ን​ዝ​ሮች ናቸ​ውና፥ በእ​ጃ​ቸ​ውም ደም አለና ጻድ​ቃን ሰዎች በአ​መ​ን​ዝ​ሮ​ቹና በደም አፍ​ሳ​ሾቹ ሴቶች ላይ በሚ​ፈ​ረ​ደው ፍርድ ይፈ​ር​ዱ​ባ​ቸ​ዋል።”</verse>
				<verse number="46">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ጉባ​ኤን አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ለመ​በ​ተ​ንና ለመ​በ​ዝ​በ​ዝም አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="47">ጉባ​ኤ​ውም በድ​ን​ጋይ ይወ​ግ​ሩ​አ​ቸ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፋ​ቸ​ውም ይቈ​ር​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይገ​ድ​ላሉ፤ ቤቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላሉ።</verse>
				<verse number="48">ሴቶ​ችም ሁሉ እንደ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ሠሩ ይማሩ ዘንድ ሴሰ​ኝ​ነ​ትን ከም​ድር ላይ አጠ​ፋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="49">እን​ግ​ዲህ በደ​ላ​ችሁ በላ​ያ​ችሁ ላይ ይመ​ለ​ሳል፤ እና​ን​ተም የጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ኀጢ​አት ትሸ​ከ​ማ​ላ​ችሁ፤ እኔም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="24">
				<verse number="1">በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“የሰው ልጅ ሆይ! የዚ​ህን ቀን፥ የዛ​ሬን ቀን ስም ጻፍ፤ በዚህ ቀን የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይመ​ጣ​ልና።</verse>
				<verse number="3">ለዐ​መ​ፀ​ኛ​ውም ቤት ምሳ​ሌን ተና​ገር እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጣድ፥ ድስ​ቲ​ቱን ጣድ፥ ውኃም ጨም​ር​ባት።</verse>
				<verse number="4">ቍራ​ጭ​ዋ​ንም፥ መል​ካ​ሙን ቍራጭ ሁሉ፥ ጭኑ​ንና ወር​ቹን በእ​ር​ስዋ ውስጥ ጨምር፤ የተ​መ​ረ​ጡ​ት​ንም አጥ​ን​ቶች ሙላ​ባት።</verse>
				<verse number="5">ከመ​ን​ጋው የተ​መ​ረ​ጠ​ውን ውሰድ፤ አጥ​ን​ቶ​ቹም እን​ዲ​በ​ስሉ በበ​ታ​ችዋ እሳት አን​ድድ፤ አፍ​ላው፤ በእ​ጅጉ ይፍላ፤ አጥ​ን​ቶ​ቹም በው​ስ​ጥዋ ይቀ​ቀሉ።</verse>
				<verse number="6">“ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ዝገቷ ላለ​ባት፥ ዝገ​ቷም ከእ​ር​ስዋ ላል​ወጣ ድስት፥ ለደም ከተማ ወዮ​ላት! ቍራጭ ቍራ​ጩን አውጣ፤ ዕጣ አል​ወ​ደ​ቀ​ባ​ትም።</verse>
				<verse number="7">ደም​ዋም በመ​ካ​ከ​ልዋ አለ። በተ​ራ​ቈተ ድን​ጋይ ላይ አደ​ረ​ገ​ችው እንጂ በአ​ፈር ይከ​ደን ዘንድ በመ​ሬት ላይ አላ​ፈ​ሰ​ሰ​ች​ውም።</verse>
				<verse number="8">መዓ​ቴን አወጣ ዘንድ፥ በቀ​ሌ​ንም እበ​ቀል ዘንድ፥ ደምዋ እን​ዳ​ይ​ከ​ደን በተ​ራ​ቈተ ድን​ጋይ ላይ አደ​ረ​ግሁ።</verse>
				<verse number="9">ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ለደም ከተማ ወዮ​ላት! እኔ ደግሞ ማገ​ዶ​ዋን ታላቅ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">ደሟ እስ​ኪ​ያ​ልቅ ድረስ ሥጋዋ ያርር ዘንድ፥ አጥ​ን​ቶ​ች​ዋም ይቀ​ጠ​ቀጡ ዘንድ፤ እን​ጨ​ቱን አበ​ዛ​ለሁ፤ እሳ​ቱ​ንም አነ​ድ​ዳ​ለሁ፥</verse>
				<verse number="11">ድስ​ቷም እስ​ክ​ት​ፈ​ላና እስ​ክ​ት​ሰ​በር ድረስ በፍሙ ላይ አኖ​ራ​ታ​ለሁ፤ ርኵ​ሰ​ት​ዋም በመ​ካ​ከሏ እንደ ሰም ይቀ​ል​ጣል፤ ዝገ​ት​ዋም ይጠ​ፋል፤</verse>
				<verse number="12">በከ​ንቱ ደከ​መች፤ ሆኖም ብዙ ዝገቷ ከእ​ር​ስዋ አል​ለ​ቀ​ቀም።</verse>
				<verse number="13">በር​ኵ​ሰ​ትሽ ሴሰ​ኝ​ነት አለ፤ አነ​ጻ​ሁሽ፤ አል​ነ​ጻ​ሽ​ምና መዓ​ቴን በላ​ይሽ እስ​ክ​ጨ​ርስ ድረስ እን​ግ​ዲህ ከር​ኵ​ሰ​ትሽ አት​ነ​ጺም።</verse>
				<verse number="14">እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ እመ​ጣ​ለሁ፤ እኔም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ አል​ተ​ውም፤ አል​ራ​ራም፤ አል​ጸ​ጸ​ትም፤ እንደ መን​ገ​ድ​ሽና እንደ ሥራ​ሽም እፈ​ር​ድ​ብ​ሻ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ስለ​ዚህ የሰ​ውን ደም እንደ አፈ​ሰ​ስሽ እኔ እፈ​ር​ድ​ብ​ሻ​ለሁ፤ እንደ ኀጢ​አ​ት​ሽም ተበ​ቅዬ አጠ​ፋ​ሻ​ለሁ፤ ስም​ሽም ጐሰ​ቈለ፥ ብዙ ኀዘ​ን​ንም ታዝ​ኛ​ለሽ።”</verse>
				<verse number="15">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="16">“የሰው ልጅ ሆይ! እነሆ የዐ​ይ​ን​ህን አም​ሮት በመ​ቅ​ሠ​ፍት እወ​ስ​ድ​ብ​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም ዋይ አት​በል፤ አታ​ል​ቅ​ስም፤ እን​ባ​ህ​ንም አታ​ፍ​ስስ።</verse>
				<verse number="17">በቀ​ስታ ተክዝ፤ ነገር ግን የሙ​ታ​ንን ልቅሶ አታ​ል​ቅስ፤ መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያ​ህን በራ​ስህ ላይ አድ​ርግ፤ ጫማ​ህ​ንም በእ​ግ​ርህ አጥ​ልቅ፤ ከን​ፈ​ሮ​ች​ህ​ንም አት​ሸ​ፍን፤ የዕ​ዝን እን​ጀ​ራ​ንም አት​ብላ።”</verse>
				<verse number="18">እኔም በማ​ለዳ ለሕ​ዝቡ ተና​ገ​ርሁ፤ ወደ ማታም ሚስቴ ሞተች፤ በነ​ጋ​ውም እንደ ታዘ​ዝሁ አደ​ረ​ግሁ።</verse>
				<verse number="19">ሕዝ​ቡም፥ “ይህ የም​ታ​ደ​ር​ገው ነገር ለእኛ ምን እንደ ሆነ አት​ነ​ግ​ረ​ን​ምን?” አሉኝ።</verse>
				<verse number="20">እኔም እን​ዲህ አል​ኋ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="21">ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የኀ​ይ​ላ​ች​ሁን ትም​ክ​ሕት፥ የዐ​ይ​ና​ች​ሁን አም​ሮት፥ የነ​ፍ​ሳ​ች​ሁ​ንም ምኞት፥ መቅ​ደ​ሴን አረ​ክ​ሳ​ለሁ፤ ያስ​ቀ​ራ​ች​ኋ​ቸ​ውም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችሁ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="22">እኔም እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እና​ንተ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ፤ በአ​ን​ደ​በ​ታ​ቸው አት​ጽ​ና​ኑም፤ የዕ​ዝን እን​ጀ​ራ​ንም አት​በ​ሉም።</verse>
				<verse number="23">መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያ​ች​ሁም በራ​ሳ​ችሁ፥ ጫማ​ች​ሁም በእ​ግ​ራ​ችሁ ይሆ​ናል፤ ዋይ አት​ሉም፤ አታ​ለ​ቅ​ሱ​ምም፤ በኀ​ጢ​አ​ታ​ች​ሁም ትሰ​ለ​ስ​ላ​ላ​ችሁ፤ ሁላ​ች​ሁም ጓደ​ኞ​ቻ​ች​ሁን ታጽ​ና​ና​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="24">ሕዝ​ቅ​ኤ​ልም ምል​ክት ይሆ​ና​ች​ኋል፤ እርሱ እንደ አደ​ረገ ሁሉ እና​ንተ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ፤ ይህም በመጣ ጊዜ እኔ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="25">“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ኀይ​ላ​ቸ​ውን፥ የተ​መ​ኩ​በ​ት​ንም ደስታ፥ የዐ​ይ​ና​ቸ​ው​ንም አም​ሮት፥ የነ​ፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም ምኞት፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በወ​ሰ​ድ​ሁ​ባ​ቸው ቀን፥</verse>
				<verse number="26">በዚያ ቀን ያመ​ለ​ጠው ይህን ነገር በጆ​ሮህ ያሰማ ዘንድ ወደ አንተ ይመ​ጣል።</verse>
				<verse number="27">በዚያ ቀን አፍህ ላመ​ለ​ጠው ይከ​ፈ​ታል፤ አን​ተም ትና​ገ​ራ​ለህ፤ ከዚ​ያም ወዲያ ዲዳ አት​ሆ​ንም፤ ምል​ክ​ትም ትሆ​ና​ቸ​ዋ​ለህ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="25">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“የሰው ልጅ ሆይ! ፊት​ህን ወደ አሞን ልጆች አቅ​ን​ተህ ትን​ቢት ተና​ገ​ር​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ለአ​ሞ​ንም ልጆች እን​ዲህ በል፦ የጌ​ታን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ መቅ​ደሴ በረ​ከሰ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ምድር ባድማ በሆ​ነች ጊዜ፥ የይ​ሁ​ዳም ቤት በተ​ማ​ረኩ ጊዜ ስለ እነ​ርሱ ደስ ብሎ​ሃ​ልና፤</verse>
				<verse number="4">ስለ​ዚህ እነሆ ርስት አድ​ርጌ ለም​ሥ​ራቅ ልጆች አሳ​ልፌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ማደ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውን በአ​ንተ ዘንድ ይሠ​ራሉ፤ ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም በአ​ንተ ውስጥ ይተ​ክ​ላሉ፤ ፍሬ​ህን ይበ​ላሉ፤ ወተ​ት​ህ​ንም ይጠ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="5">የአ​ሞ​ንን ከተማ ለግ​መ​ሎች ማሰ​ማ​ሪያ፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች ለመ​ንጋ መመ​ሰ​ጊያ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="6">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ በእ​ጆ​ችህ አጨ​ብ​ጭ​በ​ሃ​ልና፥ በእ​ግ​ሮ​ች​ህም አሸ​ብ​ሽ​በ​ሃ​ልና፥ ሰው​ነ​ት​ህም በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር ላይ ደስ ብሎ​አ​ታ​ልና፤</verse>
				<verse number="7">ስለ​ዚህ እነሆ እጄን ዘር​ግ​ቼ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም አስ​በ​ዘ​ብ​ዝ​ሃ​ለሁ፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብም ለይች እቈ​ር​ጥ​ሃ​ለሁ፤ ከሀ​ገ​ሮ​ችም እደ​መ​ስ​ስ​ሃ​ለሁ፤ አጠ​ፋ​ሃ​ለ​ሁም፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ።”</verse>
				<verse number="8">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሞአ​ብና ሴይር፦ እነሆ የይ​ሁዳ ቤት እንደ አሕ​ዛብ ሁሉ ነው ብለ​ዋ​ልና፤</verse>
				<verse number="9">ስለ​ዚህ እነሆ የሞ​አ​ብን ጫንቃ ከከ​ተ​ሞቹ፥ በዳ​ር​ቻው ካሉት የም​ድሩ ትም​ክ​ሕት ከሆ​ኑት ከተ​ሞቹ፥ ከቤ​ት​የ​ሺ​ሞት፥ ከባ​ኣ​ል​ሜ​ዎን፥ ከቂ​ር​ያ​ታ​ይም አደ​ክ​ማ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">የአ​ሞን ልጆች በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ እን​ዳ​ይ​ታ​ሰቡ የአ​ሞ​ንን ልጆች ለም​ሥ​ራቅ ልጆች ርስት አድ​ርጌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">በሞ​አ​ብም ላይ በቀ​ልን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”</verse>
				<verse number="12">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ኤዶ​ም​ያስ በይ​ሁዳ ቤት ላይ በቀል አድ​ር​ጎ​አ​ልና፥ ቂምም ይዞ​አ​ልና፥ በቀ​ል​ንም ተበ​ቅ​ሎ​አ​ልና፤</verse>
				<verse number="13">ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እጄን በኤ​ዶ​ም​ያስ ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ዘንድ ሰው​ንና እን​ስ​ሳን አጠ​ፋ​ለሁ፤ ባድ​ማም አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ ከቴ​ማ​ንና ከድ​ዳ​ንም ያመ​ለጡ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="14">በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ ኤዶ​ም​ያ​ስን እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤ እንደ ቍጣ​ዬና እንደ መዓ​ቴም መጠን በኤ​ዶ​ም​ያስ ያደ​ር​ጋሉ፤ በቀ​ሌ​ንም ያው​ቃሉ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="15">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን በቀ​ልን አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፥ በቀ​ላ​ቸ​ው​ንም አጽ​ን​ተ​ዋ​ልና፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጠፉ ዘንድ ነፍ​ሳ​ቸው ደስ ይላ​ታ​ልና፤</verse>
				<verse number="16">ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ እጄን በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ መኳ​ን​ን​ቱ​ንም እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤ የባ​ሕ​ሩ​ንም ዳር ቅሬታ አጠ​ፋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="17">በመ​ዓት መቅ​ሠ​ፍ​ትም ታላቅ በቀል አደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በቀ​ሌ​ንም በላ​ያ​ቸው በአ​ደ​ረ​ግሁ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="26">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ዓመት ከወሩ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“የሰው ልጅ ሆይ፥ ጢሮስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ፦ እሰይ፥ ተሰ​በ​ረች፥ ጠፋ​ችም፥ ሕዝ​ቧም ወደ እር​ስዋ ተመ​ለሱ፤ ሞልታ የነ​በ​ረች አለ​ቀች ብላ​ለ​ችና፤</verse>
				<verse number="3">ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ! እነሆ በአ​ንቺ ላይ ነኝ፤ ባሕ​ርም ሞገ​ድ​ዋን እን​ደ​ም​ታ​ወጣ እን​ዲሁ ብዙ አሕ​ዛ​ብን አወ​ጣ​ብ​ሻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">የጢ​ሮ​ስ​ንም ቅጥ​ሮች ያፈ​ር​ሳሉ፤ ግን​ቦ​ች​ዋ​ንም ያፈ​ር​ሳሉ፤ ትቢ​ያ​ዋ​ንም ከእ​ር​ስዋ እፍ​ቃ​ለሁ፤ እንደ ተራ​ቈተ ድን​ጋ​ይም አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">በባ​ሕር ውስጥ የመ​ረብ ማስጫ ትሆ​ና​ለች፤ እኔ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ብዝ​በዛ ትሆ​ና​ለች።</verse>
				<verse number="6">በሜዳ ያሉ​ትም ሴቶች ልጆ​ችዋ በሰ​ይፍ ይገ​ደ​ላሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="7">“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ጢሮስ ሆይ! እነሆ ከሰ​ሜን የነ​ገ​ሥ​ታት ንጉሥ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን ከፈ​ረ​ሶ​ችና ከሰ​ረ​ገ​ሎች፥ ከፈ​ረ​ሰ​ኞ​ችም፥ ከጉ​ባ​ኤና ከብዙ ሕዝ​ብም ጋር በአ​ንቺ ላይ አመ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">እርሱ በም​ድረ በዳ ያሉ ሴቶች ልጆ​ች​ሽን በሰ​ይፍ ይገ​ድ​ላ​ቸ​ዋል፤ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ንም በአ​ንቺ ላይ ያስ​ቀ​ም​ጣል፤ በዙ​ሪ​ያ​ሽም ግንብ ይሠ​ራል፤ የጦር መሣ​ሪ​ያም ይዘው ይከ​ቡ​ሻል፤ በጦ​ራ​ቸ​ውም ይወ​ጉ​ሻል፤</verse>
				<verse number="9">ግን​ቦ​ች​ሽ​ንና ቅጥ​ር​ሽን በም​ሳር ያፈ​ር​ሳል።</verse>
				<verse number="10">ከፈ​ረ​ሶ​ቹም ብዛት የተ​ነሣ በት​ቢያ ይሸ​ፍ​ን​ሻል፤ ከሠ​ረ​ገላ መን​ኰ​ራ​ኵ​ርና ከፈ​ረ​ሶቹ ድምፅ የተ​ነ​ሣም ቅጥ​ሮ​ች​ሽን ያፈ​ር​ሳል፤ ወን​በዴ መሣ​ሪ​ያ​ውን ይዞ ወደ ምድረ በዳ ቦታ እን​ዲ​ገባ በሮ​ች​ሽን ይገ​ቡ​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="11">ፈረ​ሶቹ አደ​ባ​ባ​ይ​ሽን ይረ​ግ​ጣሉ፤ ሠራ​ዊ​ቶ​ች​ሽ​ንም በሾ​ተል ይገ​ድ​ሏ​ቸ​ዋል፤ የጸና አር​በ​ኛ​ሽ​ንም በም​ድር ላይ ይጥ​ለ​ዋል።</verse>
				<verse number="12">ገን​ዘ​ብ​ሽን ይበ​ረ​ብ​ራሉ፤ መን​ጋ​ሽ​ንም ይዘ​ር​ፋሉ፤ አም​ባ​ሽ​ንም ይን​ዳሉ፤ የተ​ወ​ደዱ ቤቶ​ች​ሽ​ንም ያፈ​ር​ሳሉ፤ እን​ጨ​ቶ​ች​ሽ​ንና ድን​ጋ​ይ​ሽን፥ መሬ​ት​ሽ​ንም በባ​ሕሩ ጥልቅ ውስጥ ይጥ​ሉ​ታል።</verse>
				<verse number="13">የዘ​ፋ​ኞ​ች​ሽ​ንም ብዛት ዝም አሰ​ኛ​ለሁ፤ የመ​ሰ​ን​ቆ​ሽም ድምፅ ከዚያ ወዲያ አይ​ሰ​ማም።</verse>
				<verse number="14">እንደ ተራ​ቈተ ድን​ጋይ አደ​ር​ግ​ሻ​ለሁ፤ የመ​ረ​ብም ማስጫ ትሆ​ኛ​ለሽ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አት​ሠ​ሪም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="15">“ስለ ጢሮስ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሾተ​ላ​ቸ​ውን በመ​ካ​ከ​ልሽ በመ​ዘዙ ጊዜ ከው​ድ​ቀ​ትሽ፥ ከቈ​ሰ​ሉ​ትም ጩኸት የተ​ነሣ፤ ደሴ​ቶች የሚ​ነ​ዋ​ወጡ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="16">የባ​ሕ​ርም አለ​ቆች ሁሉ ከዙ​ፋ​ኖ​ቻ​ቸው ይወ​ር​ዳሉ፤ ዘው​ዳ​ቸ​ውን ከራ​ሳ​ቸው ያወ​ር​ዳሉ፤ ወርቀ ዘቦ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ያወ​ል​ቃሉ፤ በመ​ሬ​ትም ላይ ተቀ​ም​ጠው ይደ​ነ​ግ​ጣሉ፤ ሞታ​ቸ​ው​ንም ይፈ​ራሉ፤ ስለ አን​ቺም ያለ​ቅ​ሳሉ።</verse>
				<verse number="17">በአ​ን​ቺም ላይ ሙሾ ያሞ​ሻሉ፤ እን​ዲ​ህም ይሉ​ሻል፦ በባ​ሕር የተ​ቀ​መ​ጥሽ፥ በባ​ሕ​ርም ውስጥ የጸ​ናሽ፥ ከሚ​ቀ​መ​ጡ​ብ​ሽም ጋር በዙ​ሪ​ያሽ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ያስ​ፈ​ራሽ፥ የከ​በ​ርሽ ከተማ ሆይ! እን​ዴት ጠፋሽ!</verse>
				<verse number="18">አሁን በው​ድ​ቅ​ትሽ ቀን ደሴ​ቶች ይፈ​ራሉ፥ በባ​ሕ​ርም ውስጥ ያሉ ደሴ​ቶች ከመ​ው​ጣ​ትሽ የተ​ነሣ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="19">“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ሰው እን​ደ​ሌ​ለ​ባ​ቸው ከተ​ሞች ባድማ ከተማ ባደ​ረ​ግ​ሁሽ ጊዜ፥ ቀላ​ዩ​ንም ባወ​ጣ​ሁ​ብሽ ጊዜ፥ ብዙ ውኆ​ችም በከ​ደ​ኑሽ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="20">ወደ ጥልቁ ከሚ​ወ​ር​ዱት ጋር ወደ ቀደ​ሙት ሕዝብ አወ​ር​ድ​ሻ​ለሁ። በም​ድ​ርም ላይ በሕ​ይ​ወ​ትሽ ጸን​ተሽ እን​ዳ​ት​ኖ​ሪም ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ሰዎች ጋር ቀድሞ በፈ​ረ​ሰው ቤት ከም​ድር በታች አኖ​ር​ሻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="21">ለሞት እሰ​ጥ​ሻ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም አት​ኖ​ሪም፤ ይፈ​ል​ጉ​ሻል፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አያ​ገ​ኙ​ሽም፤ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="27">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ጢሮስ ሙሾ አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="3">በባ​ሕር መግ​ቢያ የም​ት​ኖር፥ በብ​ዙም ደሴ​ቶች ላይ ከሚ​ኖሩ አሕ​ዛብ ጋር ንግ​ድን የም​ታ​ደ​ርግ ጢሮ​ስን እን​ዲህ በላት፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ! አንቺ፦ በው​በት ፍጹም ነኝ ብለ​ሻል።</verse>
				<verse number="4">ዳር​ቻሽ በባ​ሕር ውስጥ ነው፤ ልጆ​ች​ሽም ውበ​ት​ሽን ፈጽ​መ​ዋል።</verse>
				<verse number="5">ሳን​ቃ​ዎ​ች​ሽን ሁሉ ከሳ​ኔር ጥድ ሠር​ተ​ዋል፤ ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ሽ​ንም ይሠ​ሩ​ልሽ ዘንድ ከሊ​ባ​ኖስ ዝግ​ባን ወስ​ደ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">ከባ​ሳን ኮም​ቦል መቅ​ዘ​ፊ​ያ​ሽን ሠር​ተ​ዋል፤ መቅ​ደ​ስ​ሽ​ንም በዝ​ኆን ጥርስ ሠሩ፤ ከኪ​ቲም ደሴ​ቶች ዛፍም ቤቶ​ች​ሽን ሠር​ተ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">ዓላማ እን​ዲ​ሆ​ን​ልሽ ሸራሽ ከግ​ብፅ በፍ​ታና ከወ​ርቀ ዘቦ ተሠ​ር​ቶ​አል፤ መደ​ረ​ቢ​ያ​ሽም ከኤ​ሊሳ ደሴ​ቶች ሰማ​ያ​ዊና ቀይ ሐር ተሠ​ር​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="8">አለ​ቆ​ችሽ በሲ​ዶና ይኖሩ ነበር፤ የአ​ራድ ሰዎ​ችም ቀዛ​ፊ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ ጢሮስ ሆይ! ጥበ​በ​ኞ​ችሽ በአ​ንቺ ዘንድ ነበሩ፤ የመ​ር​ከ​ቦ​ች​ሽም መሪ​ዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="9">በአ​ንቺ ውስጥ የነ​በሩ የጌ​ባል ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ጥበ​በ​ኞ​ችዋ ስብ​ራ​ት​ሽን ይጠ​ግኑ ነበር፤ ከአ​ን​ቺም ጋር ይነ​ግዱ ዘንድ የባ​ሕር መር​ከ​ቦች ሁሉና መር​ከ​በ​ኞ​ቻ​ቸው በመ​ካ​ከ​ልሽ ነበሩ።</verse>
				<verse number="10">ፋር​ስና ሉድ፥ ሊብ​ያም በሠ​ራ​ዊ​ትሽ ውስጥ ሰል​ፈ​ኞ​ችሽ ነበሩ፤ ጋሻና ራስ ቍርም በአ​ንቺ ውስጥ ያን​ጠ​ለ​ጥሉ ነበር፤ እነ​ር​ሱም ክብ​ር​ሽን ሰጡ።</verse>
				<verse number="11">የአ​ራድ ልጆ​ችና ሠራ​ዊ​ቶ​ችሽ በቅ​ጥ​ሮ​ችሽ ላይ በዙ​ሪያ ነበሩ፤ ገማ​ዳ​ው​ያ​ንም በግ​ን​ቦ​ችሽ ውስጥ ነበሩ፤ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ው​ንም በዙ​ሪያ በቅ​ጥ​ርሽ ላይ አን​ጠ​ለ​ጠሉ፤ ውበ​ት​ሽ​ንም ፈጽ​መ​ዋል።</verse>
				<verse number="12">“ከኀ​ይ​ልሽ ሁሉ ብዛት የተ​ነሣ የተ​ር​ሴስ ሰዎች ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ ገበ​ያ​ሽን ብር፥ ወር​ቅና ብረት፥ ቆር​ቆ​ሮና እር​ሳ​ስም አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="13">ያዋ​ንና ቶቤል፥ ሞሳ​ሕም ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ ንግ​ድ​ሽ​ንም በሰ​ዎች ነፍ​ሳ​ትና በናስ ዕቃ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="14">ከቴ​ር​ጋማ ቤትም የነ​በ​ሩት ሰዎች ፈረ​ሶ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን፥ በቅ​ሎ​ዎ​ች​ንም ወደ ገበ​ያሽ አመ​ጡ​ልሽ።</verse>
				<verse number="15">የሮ​ድ​ያን ልጆ​ችም ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፥ ብዙ የሆኑ የደ​ስ​ያት ሰዎ​ችም የዝ​ኆን ጥርስ ይነ​ግ​ዱ​ልሽ ነበር፤ ከዚ​ያም የመጡ ሰዎች ዋጋ​ሽን ይሰ​ጡሽ ነበር።</verse>
				<verse number="16">የሶ​ር​ያም ሰዎች ከገ​ን​ዘ​ብሽ ብዛት የተ​ነሣ ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፥ ከአ​ን​ቺም ጋር አንድ ከሆኑ ከብዙ ሰዎች ጋር ትነ​ግጂ ነበር፤ ነጭ ሐር​ንና ዕን​ቍን፥ ቀይ ሐር​ንና ወርቀ ዘቦን ከር​ከ​ዴን የሚ​ባል ዕን​ቍ​ንና ልባ​ን​ጃም የሚ​ባል ሽቱን ከተ​ር​ሴስ ያመ​ጡ​ልሽ ነበር፤ ገበ​ያ​ሽ​ንም ረዓ​ሙ​ትና ቆር​ኮር መሉት።</verse>
				<verse number="17">ይሁ​ዳና እስ​ራ​ኤል ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ ስን​ዴ​ንም ይሸ​ም​ቱ​ልሽ ነበር፤ ሰሊ​ሆ​ት​ንና በለ​ሶ​ንን፥ ዘይ​ት​ንና የተ​ወ​ደደ ማርን፥ ርጢ​ን​ንም ከአ​ንቺ ጋር አንድ ይሆኑ ዘንድ ሰጡሽ።</verse>
				<verse number="18">ከሥ​ራሽ ብዛ​ትና ከብ​ል​ጽ​ግ​ናሽ ሁሉ ብዛት የተ​ነሣ የደ​ማ​ስቆ ሰዎች ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ በኬ​ል​ቦን የወ​ይን ጠጅ፥ በነ​ጭም የበግ ጠጕር ይነ​ግዱ ነበር።</verse>
				<verse number="19">ዳንና ያዋን፤ ከኦ​ሴል የተ​ሠራ ብረ​ት​ንና ብር​ጕ​ድን፥ ቀረ​ፋ​ንም ያመ​ጡ​ልሽ ነበር።</verse>
				<verse number="20">ድዳን በተ​መ​ረጡ እን​ስ​ሳ​ትና በሠ​ረ​ገ​ላ​ቸው፥ በክ​ብር ልብ​ስም ነጋ​ዴሽ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="21">ዓረ​ብና የቄ​ዳር አለ​ቆች ሁሉ የእ​ጅሽ ነጋ​ዴ​ዎች ነበሩ፤ በግ​መ​ሎ​ችና በአ​ውራ በጎች፥ በፍ​የ​ሎ​ችም በእ​ነ​ዚህ ከአ​ንቺ ጋር ይነ​ግዱ ነበር።</verse>
				<verse number="22">የሳ​ባና የራ​ዕማ ነጋ​ዴ​ዎች እነ​ዚህ ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ ንግ​ድ​ሽን በጥሩ ሽቱና በከ​በረ ድን​ጋይ ሁሉ፥ በወ​ር​ቅም አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="23">የካ​ራ​ንና የካኔ፥ የኤ​ደ​ንም ሰዎች ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ አሦ​ርና ኪል​ማ​ድም ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ።</verse>
				<verse number="24">እነ​ዚህ በአ​ማረ ልብስ፥ በሰ​ማ​ያዊ ካባ፥ በወ​ርቀ ዘቦም፥ በዝ​ግባ በተ​ሠ​ራች፥ በገ​መ​ድም በታ​ሰ​ረች፥ በግ​ም​ጃም በተ​ሞ​ላች ሣጥን በገ​በ​ያሽ ይነ​ግዱ ነበር።</verse>
				<verse number="25">የተ​ር​ሴስ መር​ከ​ቦች ሸቀ​ጥ​ሽን የሚ​ሸ​ከሙ ነበሩ፤ አን​ቺም ተሞ​ል​ተሽ ነበር፤ በባ​ሕ​ርም ውስጥ እጅግ ከበ​ርሽ።</verse>
				<verse number="26">“ቀዛ​ፊ​ዎ​ችሽ ወደ ትልቁ ውኃ አመ​ጡሽ፤ የም​ሥ​ራቅ ነፋስ በባ​ሕር ውስጥ ሰበ​ረሽ።</verse>
				<verse number="27">ኀይ​ል​ሽና ዋጋሽ፥ ንግ​ድ​ሽም፥ መር​ከ​በ​ኞ​ች​ሽም፥ መር​ከብ መሪ​ዎ​ች​ሽም፥ ሰባ​ራ​ሽን የሚ​ጠ​ግኑ ነጋ​ዴ​ዎ​ች​ሽም፥ በአ​ን​ቺም ዘንድ ያሉ ሰል​ፈ​ኞ​ችሽ ሁሉ በው​ስ​ጥሽ ከአ​ሉት ጉባኤ ሁሉ ጋር በወ​ደ​ቅ​ሽ​በት ቀን በባ​ሕር ውስጥ ይጠ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="28">ከጩ​ኸ​ትሽ የተ​ነሣ የመ​ር​ከ​ብሽ መሪ​ዎች ፍር​ሀ​ትን ፈሩ።</verse>
				<verse number="29">ቀዛ​ፊ​ዎ​ችም ሁሉ፥ በመ​ር​ከብ የተ​ጫ​ኑ​ትም መር​ከብ መሪ​ዎ​ችም ሁሉ ከመ​ር​ከ​ቦ​ቻ​ቸው ይወ​ር​ዳሉ፤ በየ​ብ​ስም ላይ ይቆ​ማሉ፤</verse>
				<verse number="30">ድም​ፃ​ቸ​ው​ንም በአ​ንቺ ላይ ያሰ​ማሉ፤ ምርር ብለ​ውም ይጮ​ኻሉ፤ በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ ትቢያ ይነ​ሰ​ን​ሳሉ፤ አመ​ድም ያነ​ጥ​ፋሉ።</verse>
				<verse number="31">ስለ አን​ቺም የራ​ሳ​ቸ​ውን ጠጕር ይላ​ጫሉ፤ ማቅም ያሸ​ር​ጣሉ፤ በነ​ፍ​ስም ምሬት ስለ አንቺ መራራ ልቅ​ሶን ያለ​ቅ​ሳሉ።</verse>
				<verse number="32">ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ሙሾን ያሞ​ሹ​ል​ሻል፤ በባ​ሕር መካ​ከል እንደ ታወ​ከች እንደ ጢሮስ ያለ ማን ነበር? ይላሉ።</verse>
				<verse number="33">በባ​ሕር ውስጥ ምን ያህል ዋጋ ታገኚ ነበር? በብ​ል​ጥ​ግ​ናሽ ብዛት ብዙ አሕ​ዛ​ብን አጠ​ገ​ብሽ፤ ከአ​ን​ቺም ጋር አንድ ከሆ​ኑት ለይ​ተሽ የም​ድ​ርን ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ባለ​ጸ​ጎች አደ​ረ​ግ​ሻ​ቸው።</verse>
				<verse number="34">አሁን ግን በጥ​ልቅ ውኃ ውስጥ በባ​ሕር ተሰ​ብ​ረ​ሻል፤ ከአ​ንቺ ጋር አንድ የሆኑ ሁሉ በመ​ካ​ከ​ልሽ ወድ​ቀ​ዋል። ቀዛ​ፊ​ዎ​ች​ሽም ሁሉ ይወ​ድ​ቃሉ፤</verse>
				<verse number="35">በደ​ሴ​ቶች የሚ​ኖሩ ሁሉ አለ​ቀ​ሱ​ልሽ፤ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅግ ፈር​ተ​ዋል ፊታ​ቸ​ው​ንም ነጭ​ተው አለ​ቀሱ።</verse>
				<verse number="36">የአ​ሕ​ዛብ ነጋ​ዴ​ዎ​ችም አፍ​ዋ​ጩ​ብሽ፤ አን​ቺም ፈጽ​መሽ ትጠ​ፊ​ያ​ለሽ፤ ከእ​ግ​ዲ​ህም ወዲያ እስከ ዘለ​ዓ​ለም አት​ኖ​ሪም።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="28">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! የጢ​ሮ​ስን አለቃ እን​ዲህ በለው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ልብህ ኰር​ት​ዋል፥ አንተ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሕር መካ​ከል እን​ዲ​ቀ​መጥ እኔም ተቀ​ም​ጫ​ለሁ ብለ​ሃ​ልና፤ አንተ ሰው ስት​ሆን ልብ​ህን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብ ብታ​ደ​ር​ግም አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ህም።</verse>
				<verse number="3">ከዳ​ን​ኤል ይልቅ አንተ ጥበ​በኛ ነህን? ብል​ሃ​ተ​ኞ​ችም በጥ​በ​ባ​ቸው አላ​ስ​ተ​ማ​ሩ​ህም።</verse>
				<verse number="4">በጥ​በ​ብ​ህና በማ​ስ​ተ​ዋ​ልህ ብል​ጽ​ግ​ናን ለራ​ስህ አግ​ኝ​ተ​ሃ​ልን? ወር​ቅ​ንና ብር​ንም በግ​ምጃ ቤትህ ውስጥ ሰብ​ስ​በ​ሃ​ልን?</verse>
				<verse number="5">በታ​ላቅ ጥበ​ብ​ህና በን​ግ​ድህ ብል​ጽ​ግ​ና​ህን አብ​ዝ​ተ​ሃል፤ በብ​ል​ጽ​ግ​ና​ህም ልብህ ኰር​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="6">ሰለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ልብ​ህን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፤</verse>
				<verse number="7">ስለ​ዚህ እነሆ የሌላ ሀገር ሰዎ​ችን፥ የአ​ሕ​ዛብ ጨካ​ኞ​ችን አመ​ጣ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ሰይ​ፋ​ቸ​ው​ንም በጥ​በ​ብህ ውበት ላይ ይመ​ዝ​ዛሉ፤ ክብ​ር​ህ​ንም ያረ​ክ​ሳሉ።</verse>
				<verse number="8">ወደ ጕድ​ጓድ ያወ​ር​ዱ​ሃል፤ በሰ​ይ​ፍም ትሞ​ታ​ለህ፤ ሬሳ​ህ​ንም ወደ ባሕር ይጥ​ሉ​ታል።</verse>
				<verse number="9">አንተ ሰው ስት​ሆን ለሚ​ገ​ድ​ሉህ ሰዎች፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ ትላ​ቸ​ዋ​ለ​ህን? ሰው ነህ እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ህም።</verse>
				<verse number="10">የሚ​ወ​ጉ​ህም ሰዎች ብዙ​ዎች ናቸው፤ ያል​ተ​ገ​ረ​ዙ​ትን ሰዎች ሞት ትሞ​ታ​ለህ፤ የሚ​ገ​ድ​ሉ​ህም ሰዎች ያል​ተ​ገ​ረ​ዙት ናቸው፤ በእ​ጃ​ቸ​ውም ትሞ​ታ​ለህ። እኔ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”</verse>
				<verse number="11">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="12">“የሰው ልጅ ሆይ! በጢ​ሮስ ንጉሥ ላይ ሙሾ አሙ​ሽ​በት፤ እን​ዲ​ህም በለው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጥበ​ብን የተ​ሞ​ላህ፥ ውበ​ት​ህም የተ​ፈ​ጸመ መደ​ም​ደ​ሚያ አንተ ነህ።</verse>
				<verse number="13">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነት በዔ​ድን ነበ​ርህ፤ የከ​በረ ዕን​ቍስ ሁሉ፥ ሰር​ድ​ዮን፥ ቶጳ​ዝ​ዮን፥ አል​ማዝ፥ ቢረሌ፥ መረ​ግድ፥ ኢያ​ሰ​ጲድ፥ ሰን​ፔር፥ በሉር፥ የሚ​ያ​ብ​ረ​ቀ​ርቅ ዕንቍ፥ ወር​ቅም ልብ​ስህ ነበረ፤ የከ​በ​ሮ​ህና የእ​ን​ቢ​ል​ታህ ሥራ በአ​ንተ ዘንድ ነበረ፤ በተ​ፈ​ጠ​ር​ህ​በ​ትም ቀን ተዘ​ጋ​ጅ​ተው ነበር።</verse>
				<verse number="14">አንተ ልት​ጋ​ርድ የተ​ቀ​ባህ ኪሩብ ነበ​ርህ፤ በተ​ቀ​ደ​ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ ላይ አኖ​ር​ሁህ፤ በእ​ሳት ድን​ጋ​ዮች መካ​ከል ተመ​ላ​ለ​ስህ።</verse>
				<verse number="15">ከተ​ፈ​ጠ​ር​ህ​በት ቀን ጀም​ረህ በደል እስ​ከ​ሚ​ገ​ኝ​ብህ ድረስ በመ​ን​ገ​ድህ ፍጹም ነበ​ርህ።</verse>
				<verse number="16">በን​ግ​ድ​ህም ብዛት ግፍ በው​ስ​ጥህ ተሞላ፤ ኀጢ​አ​ት​ንም ሠራህ፤ ስለ​ዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ ጣል​ሁህ፤ የም​ት​ጋ​ርድ ኪሩብ ሆይ! ከእ​ሳት ድን​ጋ​ዮች መካ​ከል አጠ​ፋ​ሁህ።</verse>
				<verse number="17">በው​በ​ትህ ምክ​ን​ያት ልብህ ኰር​ቶ​አል፤ ከክ​ብ​ርህ የተ​ነሣ ጥበ​ብ​ህን አረ​ከ​ስህ፤ በም​ድር ላይ ጣል​ሁህ፤ ያዩ​ህም፥ ይዘ​ብ​ቱ​ብ​ህም ዘንድ በነ​ገ​ሥ​ታት ፊት አሳ​ልፌ ሰጠ​ሁህ።</verse>
				<verse number="18">በበ​ደ​ልህ ብዛት፥ በን​ግ​ድ​ህም ኀጢ​አት መቅ​ደ​ስ​ህን አረ​ከ​ስህ፤ ስለ​ዚህ እሳ​ትን ከው​ስ​ጥህ አው​ጥ​ቻ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋም በል​ታ​ሃ​ለች፤ በሚ​ያ​ዩ​ህም ሁሉ ፊት በም​ድር ላይ አመድ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">በአ​ሕ​ዛ​ብም ውስጥ የሚ​ያ​ው​ቁህ ሁሉ ያለ​ቅ​ሱ​ል​ሃል፤ አን​ተም ለድ​ን​ጋጤ ሆነ​ሃል፤ እስከ ዘለ​ዓ​ለ​ምም አት​ኖ​ርም።”</verse>
				<verse number="20">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="21">የሰው ልጅ ሆይ! ፊት​ህን ወደ ሲዶና አቅ​ን​ተህ ትን​ቢት ተና​ገ​ር​ባት፤ እን​ዲ​ህም በል፦</verse>
				<verse number="22">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሲዶና ሆይ! እነሆ በአ​ንቺ ላይ ነኝ፤ በው​ስ​ጥ​ሽም እከ​ብ​ራ​ለሁ፤ ፍር​ድ​ንም በአ​ደ​ረ​ግ​ሁ​ብሽ ጊዜ፥ በተ​ቀ​ደ​ስ​ሁ​ብ​ሽም ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቂ​ያ​ለሽ።</verse>
				<verse number="23">ቸነ​ፈ​ር​ንም በአ​ንቺ ላይ፥ ደም​ንም በጎ​ዳ​ናሽ ላይ እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ከዙ​ሪ​ያ​ሽም በላ​ይሽ ባለ ሰይፍ የተ​ወጉ በመ​ካ​ከ​ልሽ ይወ​ድ​ቃሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="24">ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት የሚ​ወጋ እሾህ፥ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ከአሉ ከና​ቋ​ቸው ሁሉ የሚ​ያ​ቈ​ስል ኩር​ን​ችት አይ​ሆ​ንም፤ እኔም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="25">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ከተ​በ​ተ​ኑ​ባ​ቸው አሕ​ዛብ ዘንድ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብና በሕ​ዝብ ፊትም እቀ​ደ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ለባ​ሪ​ያዬ ለያ​ዕ​ቆ​ብም በሰ​ጠ​ኋት ምድ​ራ​ቸው ይቀ​መ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="26">ተዘ​ል​ለ​ውም ይቀ​መ​ጡ​ባ​ታል፤ ቤቶ​ች​ንም ይሠ​ራሉ፤ ወይ​ኑ​ንም ይተ​ክ​ላሉ፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም በአሉ በሚ​ን​ቋ​ቸው ሁሉ ላይ ፍር​ድን በአ​ደ​ረ​ግሁ ጊዜ ተዘ​ል​ለው ይቀ​መ​ጣሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አም​ላክ እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="29">
				<verse number="1">በዐ​ሥ​ረ​ኛው ዓመት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“የሰው ልጅ ሆይ! ፊት​ህን በግ​ብጽ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ላይ አድ​ርግ፤ በእ​ር​ሱና በግ​ብፅ ሁሉ ላይም ትን​ቢት ተና​ገር፤</verse>
				<verse number="3">እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በወ​ን​ዞች መካ​ከል የሚ​ተኛ፥ ወንዙ የእኔ ነው፤ ለራ​ሴም ሠር​ቼ​ዋ​ለሁ የሚል ታላቅ ዘንዶ የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን ሆይ! እነሆ በአ​ንተ ላይ ነኝ።</verse>
				<verse number="4">በመ​ን​ጋ​ጋ​ዎ​ችህ መቃ​ጥን አገ​ባ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የወ​ን​ዞ​ች​ህ​ንም ዓሦች ሁሉ ወደ ቅር​ፊ​ትህ አጣ​ብ​ቃ​ለሁ፤ ከወ​ን​ዞ​ች​ህም መካ​ከል አወ​ጣ​ሃ​ለሁ፤ የወ​ን​ዞ​ች​ህም ዓሦች ሁሉ ወደ ቅር​ፊ​ትህ ይጣ​በ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="5">አን​ተ​ንና የወ​ን​ዞ​ች​ህን ዓሦች ሁሉ ወደ ምድረ በዳ እጥ​ላ​ለሁ፤ በም​ድ​ርም ፊት ላይ ትወ​ድ​ቃ​ለህ እንጂ አት​ከ​ማ​ችም፤ አት​ሰ​በ​ሰ​ብ​ምም፤ መብ​ልም አድ​ርጌ ለም​ድር አራ​ዊ​ትና ለሰ​ማይ ወፎች ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="6">ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት የሸ​ን​በቆ በትር ሁነ​ሃ​ቸ​ዋ​ልና በግ​ብፅ የሚ​ኖሩ ሁሉ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="7">በእጅ በያ​ዙህ ጊዜ ተሰ​በ​ርህ፤ ጫን​ቃ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አቈ​ሰ​ልህ፤ በተ​ደ​ገ​ፉ​ብ​ህም ጊዜ ተሰ​በ​ርህ፤ ወገ​ባ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አን​ቀ​ጠ​ቀ​ጥህ።</verse>
				<verse number="8">“ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ሰይ​ፍን አመ​ጣ​ብ​ሃ​ለሁ፦ ሰው​ንና እን​ስ​ሳ​ንም ከአ​ንተ ዘንድ አጠ​ፋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">የግ​ብ​ፅም ምድር ባድ​ማና ውድማ ትሆ​ና​ለች፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ፤ አንተ፦ ወንዙ የእኔ ነው፤ የሠ​ራ​ሁ​ትም እኔ ነኝ ብለ​ሃ​ልና።</verse>
				<verse number="10">ስለ​ዚህ፥ እነሆ በአ​ን​ተና በወ​ን​ዞ​ችህ ላይ ነኝ፤ የግ​ብ​ፅ​ንም ምድር ከሚ​ግ​ዶል ጀምሮ እስከ ሰዌ​ኔና እስከ ኢት​ዮ​ጵያ ዳርቻ ድረስ በጦ​ርና በቸ​ነ​ፈር ውድ​ማና ባድማ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">የሰው እግር አያ​ል​ፍ​ባ​ትም፤ የእ​ን​ስ​ሳም ኮቴ አይ​ረ​ግ​ጣ​ትም፥ እስከ አርባ ዓመ​ትም ድረስ ማንም አይ​ኖ​ር​ባ​ትም።</verse>
				<verse number="12">ባድ​ማም በሆኑ ምድ​ሮች መካ​ከል የግ​ብ​ፅን ምድር ባድማ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ በፈ​ረ​ሱ​ትም ከተ​ሞች መካ​ከል ከተ​ሞ​ችዋ አርባ ዓመት ፈር​ሰው ይቀ​መ​ጣሉ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም ወደ አሕ​ዛብ እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በሀ​ገ​ሮ​ችም እዘ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="13">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ከአ​ርባ ዓመት በኋላ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን ከተ​በ​ተ​ኑ​ባ​ቸው አሕ​ዛብ ዘንድ እሰ​በ​ስ​ባ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="14">የግ​ብ​ፅ​ንም ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ወደ ተወ​ለ​ዱ​ባ​ትም ምድር ወደ ጳት​ሮስ እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በዚ​ያም የተ​ዋ​ረ​ደች መን​ግ​ሥት ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="15">እንደ ገና በአ​ሕ​ዛብ ላይ ከፍ ከፍ እን​ዳ​ይሉ ትንሽ መን​ግ​ሥት ይሆ​ናሉ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ላይ እን​ዳ​ይ​በዙ አሳ​ን​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እነ​ር​ሱን በተ​ከ​ተሉ ጊዜ እር​ስዋ በደ​ልን ታሳ​ስ​ባ​ለች፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ መታ​መኛ አት​ሆ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ እኔም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”</verse>
				<verse number="17">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="18">“የሰው ልጅ ሆይ! የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ሠራ​ዊ​ቱን በጢ​ሮስ ላይ ጽኑ ሥራን አሠ​ራ​ቸው፤ ራስ ሁሉ የተ​ላጨ፥ ጫን​ቃም ሁሉ የተ​ላጠ ሆኖ​አል፤ ነገር ግን በላ​ይዋ ስለ አሠ​ራው ሥራ እር​ሱና ሠራ​ዊቱ ከጢ​ሮስ ደመ​ወዝ አል​ተ​ቀ​በ​ሉም።</verse>
				<verse number="19">ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የግ​ብ​ፅን ምድር ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ ብዛ​ቷ​ንም ይወ​ስ​ዳል፤ ምር​ኮ​ዋ​ንም ይማ​ር​ካል፤ ብዝ​በ​ዛ​ዋ​ንም ይበ​ዘ​ብ​ዛል፤ ይህም ለሠ​ራ​ዊቱ ደመ​ወዝ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="20">ስለ እኔ ሠር​ተ​ዋ​ልና በጢ​ሮስ ላይ ስለ አገ​ለ​ገ​ለው አገ​ል​ግ​ሎት የግ​ብ​ፅን ምድር ደመ​ወዝ አድ​ርጌ ሰጥ​ቼ​ዋ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="21">“በዚያ ቀን ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ቀን​ድን አበ​ቅ​ላ​ለሁ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ለአ​ንተ የተ​ከ​ፈተ አፍን እሰ​ጥ​ሀ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="30">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ዋይ! በሉ፥ ለቀኑ ወዮ!</verse>
				<verse number="3">ቀኑ ቅርብ ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ቅርብ ነው፤ የደ​መና ቀን፥ የአ​ሕ​ዛብ ማለ​ቂያ ጊዜ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="4">ሰይፍ በግ​ብፅ ላይ ይመ​ጣል፤ ሁከ​ትም በኢ​ት​ዮ​ጵያ ይሆ​ናል፤ የተ​ገ​ደ​ሉ​ትም በግ​ብፅ ውስጥ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ብዛ​ቷ​ንም ይወ​ስ​ዳሉ፤ መሠ​ረ​ቷም ይፈ​ር​ሳል።</verse>
				<verse number="5">ኢት​ዮ​ጵ​ያና ፉጥ፥ ሉድም፥ ዓረ​ብም ሁሉ፥ ኩብም፤ ሊብ​ያም፤ ቀር​ጤ​ስም የተ​ደ​ባ​ለቀ ሕዝ​ብም ሁሉ፥ ቃል ኪዳ​ን​ንም የገ​ባ​ችው ምድር ልጆች ከእ​ነ​ርሱ ጋር በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="6">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላል፦ ግብ​ፅን የሚ​ደ​ግፉ ይወ​ድ​ቃሉ፤ የኀ​ይ​ል​ዋም ትዕ​ቢት ይወ​ር​ዳል፤ ከሚ​ግ​ዶል ጀምሮ እስከ ሰዌኔ ድረስ በእ​ር​ስዋ ውስጥ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="7">ባድ​ማም በሆኑ ሀገ​ሮች መካ​ከል ባድማ ይሆ​ናሉ፤ ከተ​ሞ​ች​ዋም በፈ​ረሱ ከተ​ሞች መካ​ከል ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="8">እሳ​ት​ንም በግ​ብፅ ላይ በአ​ነ​ደ​ድሁ ጊዜ፥ ረዳ​ቶ​ች​ዋም ሁሉ በተ​ሰ​በሩ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="9">በዚያ ቀን መል​እ​ክ​ተ​ኞች ተዘ​ል​ለው የሚ​ኖ​ሩ​ትን ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያ​ንን ለማ​ጥ​ፋት ከፊቴ በመ​ር​ከብ ይወ​ጣሉ፤ በግ​ብ​ፅም ቀን ሁከት ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል፤ እነሆ፥ ይመ​ጣ​ልና።</verse>
				<verse number="10">“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የግ​ብ​ፅን ብዛት በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ አጠ​ፋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">እር​ሱና ሕዝቡ የአ​ሕ​ዛ​ብም ኀያ​ላን ምድ​ሪ​ቱን ለማ​ጥ​ፋት ይላ​ካሉ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም በሰ​ይፍ ይወ​ጉ​አ​ቸ​ዋል፤ ምድ​ሪ​ቱም በሙ​ታን ትሞ​ላ​ለች።</verse>
				<verse number="12">ወን​ዞ​ች​ንም ምድረ በዳ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም በክፉ ሰዎች እጅ እሰ​ጣ​ለሁ፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንና ሞላ​ዋ​ንም በባ​ዕ​ዳን እጅ ባድማ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጣዖ​ቶ​ቹን አጠ​ፋ​ለሁ፤ ምስ​ሎ​ቹ​ንም ከሜ​ም​ፎስ እሽ​ራ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ያም በግ​ብፅ ምድር አለቃ አይ​ሆ​ንም፤ በግ​ብፅ ምድር ላይም ፍር​ሀ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">ጳት​ሮ​ስ​ንም አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ በጣ​ኔ​ዎ​ስም ላይ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በዲ​ዮ​ስ​ጶ​ሊን ላይም ፍር​ድን አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">በግ​ብ​ፅም ኀይል በሲን ላይ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ሳ​ለሁ፤ የሜ​ም​ፎ​ስ​ንም ብዛት አጠ​ፋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">በግ​ብ​ፅም ላይ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ሲንም ትታ​ወ​ካ​ለች፤ ኖእም ትሰ​በ​ራ​ለች፤ ሜም​ፎ​ስም ምድረ በዳ ትሆ​ና​ለች።</verse>
				<verse number="17">የሄ​ል​ዮቱ ከተ​ማና የቡ​ባ​ስ​ቱም ጐል​ማ​ሶች በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ሴቶ​ችም ይማ​ረ​ካሉ።</verse>
				<verse number="18">የግ​ብ​ፅን ቀን​በር በዚያ በሰ​በ​ርሁ ጊዜ በጣ​ፍ​ናስ ቀኑ ይጨ​ል​ማል፤ የኀ​ይ​ል​ዋም ትዕ​ቢት ይጠ​ፋ​ባ​ታል፤ ደመ​ናም ይጋ​ር​ዳ​ታል፤ ሴቶች ልጆ​ች​ዋም ይማ​ረ​ካሉ።</verse>
				<verse number="19">እን​ዲሁ በግ​ብፅ ላይ ፍር​ድን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”</verse>
				<verse number="20">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ዓመት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="21">“የሰው ልጅ ሆይ! የግ​ብ​ፅን ንጉሥ የፈ​ር​ዖ​ንን ክንድ ሰብ​ሬ​አ​ለሁ፥ እነ​ሆም ይድን ዘንድ መድ​ኃ​ኒት ቀብ​ተው አያ​ደ​ር​ቁ​ትም፤ ሰይ​ፉ​ንም ለመ​ያዝ ኀይ​ልን ያገኝ ዘንድ አል​ታ​ሰ​ረም።</verse>
				<verse number="22">ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ላይ ነኝ የጸ​ና​ች​ው​ንና የተ​ሰ​በ​ረ​ች​ው​ንም ክን​ዱን እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ ሰይ​ፉ​ንም ከእጁ አስ​ጥ​ለ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="23">ግብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እበ​ት​ና​ለሁ፤ በሀ​ገ​ሮ​ችም መካ​ከል እዘ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="24">የባ​ቢ​ሎ​ን​ንም ንጉሥ ክንድ አበ​ረ​ታ​ለሁ፤ ሰይ​ፌ​ንም በእጁ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ግብ​ፅ​ንም ይወ​ጋ​በ​ታል፥ ምር​ኮ​ዋ​ንም ይማ​ር​ካል፤ ሰለ​ባ​ዋ​ንም ይሰ​ል​ባል።</verse>
				<verse number="25">የባ​ቢ​ሎ​ን​ንም ንጉሥ ክንድ አጸ​ና​ለሁ፤ የፈ​ር​ዖ​ንም ክንድ ይወ​ድ​ቃል፤ ሰይ​ፌ​ንም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ በሰ​ጠሁ ጊዜ፥ እር​ሱም በግ​ብፅ ምድር ላይ በዘ​ረ​ጋው ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="26">ግብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እበ​ት​ና​ለሁ፤ በሀ​ገ​ሮ​ችም መካ​ከል እዘ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ሁሉም እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="31">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ዓመት በሦ​ስ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“የሰው ልጅ ሆይ! የግ​ብ​ፅን ንጉሥ ፈር​ዖ​ን​ንና ሕዝ​ቡን እን​ዲህ በላ​ቸው፦ በታ​ላ​ቅ​ነ​ትህ ማንን ትመ​ስ​ላ​ለህ?</verse>
				<verse number="3">እነሆ አሦር ጫፉ እንደ ተዋበ፥ ችፍ​ግ​ነቱ ጥላ እንደ ሰጠ፥ ቁመ​ቱም እንደ ረዘመ፥ ራሱም ወደ ደመ​ና​ዎች እንደ ደረሰ እንደ ሊባ​ኖስ ዝግባ ነበረ።</verse>
				<verse number="4">ውኃም አበ​ቀ​ለው፥ ቀላ​ይም አሳ​ደ​ገው፥ ወን​ዞ​ችም በተ​ተ​ከ​ለ​በት ዙሪያ ይጎ​ርፉ ነበር፤ ፈሳ​ሾ​ቹ​ንም ወደ ምድረ በዳ ዛፍ ሁሉ ላከ።</verse>
				<verse number="5">ስለ​ዚህ ቁመቱ ከም​ድረ በዳ ዛፍ ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ አለ፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹም በዙ፤ ጫፎ​ቹም ከብዙ ውኆች የተ​ነሣ ረዘሙ።</verse>
				<verse number="6">የሰ​ማ​ይም ወፎች ሁሉ በቅ​ር​ን​ጫ​ፎቹ ላይ ተዋ​ለዱ፤ የም​ድ​ርም አራ​ዊት ሁሉ ከጫ​ፎቹ በታች ተዋ​ለዱ፤ ከጥ​ላ​ውም በታች ታላ​ላ​ቆች አሕ​ዛብ ሁሉ ይቀ​መጡ ነበር።</verse>
				<verse number="7">ሥሩም በብዙ ውኃ አጠ​ገብ ነበ​ረና በታ​ላ​ቅ​ነ​ቱና በጫ​ፎቹ ርዝ​መት የተ​ዋበ ነበረ።</verse>
				<verse number="8">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነት የነ​በሩ ዝግ​ባ​ዎች አይ​ተ​ካ​ከ​ሉ​ትም፥ ጥዶ​ችም ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹን፥ አስታ የሚ​ባ​ለ​ውም ዛፍ ጫፎ​ቹን አይ​መ​ሳ​ሰ​ሉ​ትም ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ገነት ዛፍ ሁሉ በው​በቱ አይ​መ​ስ​ለ​ውም ነበር።</verse>
				<verse number="9">በጫ​ፎቹ ብዛት ውብ አደ​ረ​ግ​ሁት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ገነት በዔ​ድን የነ​በሩ ዛፎች ሁሉ ቀኑ​በት።</verse>
				<verse number="10">“ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ቁመ​ትህ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፥ ራስ​ህም በደ​መ​ናት መካ​ከል ደር​ሶ​አ​ልና፤ ትዕ​ቢ​ቱ​ንም አየሁ፤</verse>
				<verse number="11">በአ​ሕ​ዛ​ብም አለ​ቆች እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም እንደ ክፋቱ መጠን ያደ​ር​ግ​በ​ታል፤ እኔም አሳ​ድ​ደ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">የሌላ ሀገር ሰዎች፥ የአ​ሕ​ዛብ ጨካ​ኞች የሆኑ፥ ቈር​ጠው ጣሉት፤ በተ​ራ​ሮ​ችና በሸ​ለ​ቆ​ዎች ሁሉ ውስጥ ጫፎቹ ወደቁ፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹም በም​ድር ፈሳ​ሾች ሁሉ ላይ ተሰ​ባ​በሩ፤ የም​ድ​ርም አሕ​ዛብ ሁሉ ከጥ​ላው ተመ​ል​ሰው ተዉት።</verse>
				<verse number="13">በወ​ደ​ቀው ግንድ ላይ የሰ​ማይ ወፎች ሁሉ ይቀ​መ​ጣሉ፤ የም​ድ​ርም አራ​ዊት ሁሉ በቅ​ር​ን​ጫ​ፎቹ ላይ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="14">በው​ኃው አጠ​ገብ ያሉ የዕ​ን​ጨ​ቶች ሁሉ ቁመት እን​ዳ​ይ​ረ​ዝም ራሱም ወደ ደመና እን​ዳ​ይ​ደ​ርስ ያንም ውኃ የሚ​ጠ​ጡት እን​ጨ​ቶች ሁሉ በር​ዝ​መ​ታ​ቸው ከእ​ርሱ ጋራ እን​ዳ​ይ​ተ​ካ​ከሉ ሁሉም ወደ መቃ​ብር በሚ​ወ​ርዱ ሰዎች መካ​ከል በጥ​ልቅ ምድር ሞቱ።</verse>
				<verse number="15">“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ ሲኦል በወ​ረ​ደ​በት ቀን ልቅ​ሶን አስ​ለ​ቀ​ስሁ፤ ቀላ​ዩ​ንም ስለ እርሱ ሸፈ​ን​ሁት፤ ፈሳ​ሾ​ች​ንም ከለ​ከ​ልሁ፤ ታላ​ላ​ቆ​ችም ውኆች ተከ​ለ​ከሉ፤ ሊባ​ኖ​ስ​ንም ስለ እርሱ አሳ​ዘ​ን​ሁት። የዱ​ርም ዛፎች ሁሉ ስለ እርሱ ዛሉ።</verse>
				<verse number="16">ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ወደ ሲኦል በጣ​ል​ሁት ጊዜ ከመ​ው​ደቁ ድምፅ የተ​ነሣ አሕ​ዛ​ብን አን​ቀ​ጠ​ቀ​ጥሁ፤ ውኃም የሚ​ጠጡ ሁሉ፥ ምር​ጦ​ችና መል​ካ​ሞች የሊ​ባ​ኖስ ዛፎች፥ የዔ​ድን ዛፎች ሁሉ በታ​ች​ኛው ምድር ውስጥ ተጽ​ና​ን​ተ​ዋል።</verse>
				<verse number="17">እነ​ር​ሱም በሰ​ይፍ ወደ ተገ​ደ​ሉት ወደ ሲኦል ከእ​ርሱ ጋር ወረዱ፤ በጥ​ላው ሥር ይኖሩ የነ​በሩ ዘሮ​ቹም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ጠፉ።</verse>
				<verse number="18">“በክ​ብ​ርና በታ​ላ​ቅ​ነት በዔ​ድን ዛፎች መካ​ከል ማንን ትመ​ስ​ላ​ለህ? ነገር ግን ከዔ​ድን ዛፎች ጋር ወደ ታች​ኛው ምድር ያወ​ር​ዱ​ሃል፤ በሰ​ይ​ፍም በተ​ገ​ደ​ሉት ባል​ተ​ገ​ረ​ዙት መካ​ከል ትተ​ኛ​ለህ። ይህም ፈር​ዖ​ንና የሕ​ዝቡ ብዛት ሁሉ ነው፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="32">
				<verse number="1">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈር​ዖን ሙሾ አሙሽ፤ እን​ዲ​ህም በለው፦ የአ​ሕ​ዛ​ብን አን​በሳ መስ​ለህ ነበር፤ ነገር ግን እንደ ባሕር ዘንዶ ሆነ​ሃል፤ ወን​ዞ​ች​ህ​ንም ወግ​ተ​ሃል፤ ውኃ​ው​ንም በእ​ግ​ርህ አደ​ፍ​ር​ሰ​ሃል፥ ወን​ዞ​ች​ህ​ንም በተ​ረ​ከ​ዝህ ረግ​ጠ​ሃል።</verse>
				<verse number="3">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በብዙ አሕ​ዛብ ጉባኤ መረ​ቤን እዘ​ረ​ጋ​ብ​ሃ​ለሁ፤ በመ​ረ​ቤም አወ​ጣ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">በሰፊ ምድረ በዳም እጥ​ል​ሃ​ለሁ፤ የሰ​ማ​ይ​ንም ወፎች ሁሉ አሳ​ር​ፍ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የም​ድ​ር​ንም አራ​ዊት ሁሉ ከአ​ንተ አጠ​ግ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">ሥጋ​ህን በተ​ራ​ሮች ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በደ​ም​ህም አረ​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="6">የም​ቷ​ኝ​ባ​ት​ንም ምድር እስከ ተረ​ራ​ሮች ድረስ በደ​ምህ አጠ​ጣ​ለሁ፤ መስ​ኖ​ዎ​ችም ከአ​ንተ ይሞ​ላሉ።</verse>
				<verse number="7">በጠ​ፋ​ህም ጊዜ ሰማ​ዮ​ችን እሸ​ፍ​ና​ለሁ፤ ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም አጨ​ል​ማ​ለሁ፤ ፀሐ​ዩ​ንም በደ​መና እሸ​ፍ​ና​ለሁ፤ ጨረ​ቃም ብር​ሃ​ኑን አይ​ሰ​ጥም።</verse>
				<verse number="8">የሰ​ማ​ይን ብር​ሃ​ኖች ሁሉ በላ​ይህ አጨ​ል​ማ​ለሁ፤ በም​ድ​ር​ህም ላይ ጨለ​ማን አደ​ር​ጋ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="9">በማ​ታ​ው​ቃ​ቸ​ውም ሀገ​ሮች በአሉ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ድል መሆ​ን​ህን በአ​ሰ​ማሁ ጊዜ የብዙ ሕዝ​ብን ልብ አስ​ጨ​ን​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">ብዙ አሕ​ዛ​ብን አስ​ደ​ን​ቅ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ሰይ​ፌም በፊ​ታ​ቸው በተ​ወ​ረ​ወ​ረች ጊዜ ንጉ​ሦ​ቻ​ቸው እጅግ አድ​ር​ገው ይፈ​ራሉ፤ በወ​ደ​ቅ​ህ​ባ​ትም ቀን እያ​ን​ዳ​ንዱ ስለ ነፍሱ በየ​ጊ​ዜው ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣል።”</verse>
				<verse number="11">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሰይፍ ይመ​ጣ​ብ​ሃል።</verse>
				<verse number="12">በኀ​ያ​ላን ሰይፍ ኀይ​ል​ህን እጥ​ላ​ለሁ፤ ሁሉ የአ​ሕ​ዛብ ጨካ​ኞች ናቸው፤ የግ​ብ​ፅ​ንም ትዕ​ቢት ያጠ​ፋሉ፤ ኀይ​ል​ዋም ሁሉ ይደ​መ​ሰ​ሳል።</verse>
				<verse number="13">በብ​ዙም ውኃ አጠ​ገብ ያሉ​ትን እን​ስ​ሶች ሁሉ አጠ​ፋ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ የሰው እግር አያ​ደ​ፈ​ር​ሳ​ትም፤ የእ​ን​ስ​ሳም ኮቴ አይ​ረ​ግ​ጣ​ትም።</verse>
				<verse number="14">በዚ​ያን ጊዜ ውኆ​ቻ​ቸ​ውን አጠ​ራ​ለሁ፤ ወን​ዞ​ቻ​ቸ​ውም እንደ ዘይት ይፈ​ስ​ሳሉ፤ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="15">የግ​ብ​ፅ​ንም ምድር ባድ​ማና ውድማ በአ​ደ​ረ​ግሁ ጊዜ፥ ምድ​ርም በመ​ላዋ በጠ​ፋች ጊዜ፥ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ት​ንም ሁሉ በቀ​ሠ​ፍሁ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="16">ይኸ​ውም ሙሾ ነው፤ ሙሾን ያሞ​ሹ​ለ​ታል፤ የአ​ሕ​ዛብ ሴቶች ልጆች ያሞ​ሹ​ለ​ታል፤ ስለ ግብ​ፅና ስለ ኀይ​ልዋ ሁሉ ያሞ​ሹ​ለ​ታል፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="17">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="18">“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ኀይል ዋይ በል፤ እር​ስ​ዋ​ንና የብ​ር​ቱ​ዎ​ቹን አሕ​ዛብ ሴቶች ልጆች ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ወደ ታች​ኛው ምድር ጣላ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">በው​በት የም​ት​በ​ል​ጪው ማን ነው? ውረጂ ካል​ተ​ገ​ረ​ዙ​ትም ጋር ተኚ።</verse>
				<verse number="20">በሰ​ይፍ በተ​ገ​ደ​ሉት መካ​ከል ከእ​ርሱ ጋር በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ኀይ​ሉም ሁሉ ይጠ​ፋል፤ እር​ስ​ዋ​ንና ብዛ​ቷን ሁሉ ጐትቱ።</verse>
				<verse number="21">የኀ​ያ​ላን አለ​ቆች በሲ​ኦል ውስጥ ሆነው ከረ​ዳ​ቶቹ ጋር ይና​ገ​ሩ​ታል፤ በሰ​ይ​ፍም የተ​ገ​ደ​ሉት ያል​ተ​ገ​ረዙ ወር​ደው ተኝ​ተ​ዋል።</verse>
				<verse number="22">“አሦ​ርና ሠራ​ዊቱ ሁሉ በዚያ ተገ​ደሉ፤ ሁሉም ድል ተነሡ፤ ወደ ጥልቅ ዐዘ​ቅ​ትም ጣሉ​አ​ቸው ሠራ​ዊ​ቱም በመ​ቃ​ብር ዙሪያ ናቸው፤ ሁሉም በሰ​ይፍ ወድ​ቀው ተገ​ደሉ።</verse>
				<verse number="23">መቃ​ብ​ራ​ቸው በጕ​ድ​ጓዱ በው​ስ​ጠ​ኛው ክፍል ነው፤ ጉባ​ኤ​ዋም በመ​ቃ​ብ​ርዋ ዙሪያ ነው፤ በሕ​ያ​ዋን ምድር ያስ​ፈሩ ሁሉ በሰ​ይፍ ወድ​ቀው ተገ​ድ​ለ​ዋል።</verse>
				<verse number="24">“ኤላ​ምም በዚያ አለች፤ ኀይ​ል​ዋም ሁሉ በመ​ቃ​ብ​ርዋ ዙሪያ ነው፤ በሕ​ያ​ዋን ምድር ያስ​ፈሩ ሁሉ በሰ​ይፍ ወድ​ቀው ተገ​ድ​ለ​ዋል፤ ሳይ​ገ​ረ​ዙም ወደ ታች​ኛው ምድር ወር​ደ​ዋል፤ ወደ ጕድ​ጓ​ድም ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ቅጣ​ታ​ቸ​ውን አግ​ኝ​ተ​ዋል።</verse>
				<verse number="25">በተ​ገ​ደ​ሉት መካ​ከል ከብ​ዛቷ ሁሉ ጋር መኝ​ታን አድ​ር​ገ​ው​ላ​ታል፤ መቃ​ብ​ርዋ በዙ​ሪ​ያዋ ነው፤ ሁሉም ያል​ተ​ገ​ረ​ዙና በሰ​ይፍ የተ​ገ​ደሉ ናቸው፤ በሕ​ያ​ዋ​ንም ምድር ያስ​ፈሩ ነበር፤ ወደ ጕድ​ጓ​ድም ከሚ​ወ​ርዱ ጋር እፍ​ረ​ታ​ቸ​ውን ተሸ​ክ​መ​ዋል፤ በተ​ገ​ደ​ሉ​ትም መካ​ከል ተሰ​ጥ​ተ​ዋል።</verse>
				<verse number="26">“ሞሳ​ሕና ቶቤል፥ ሠራ​ዊ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ በዚያ አሉ፤ መቃ​ብ​ራ​ቸ​ውም በዙ​ሪ​ያ​ቸው ነው፤ ሁሉም ሳይ​ገ​ረዙ በሰ​ይፍ ተገ​ድ​ለ​ዋል፤ በሕ​ያ​ዋን ምድር ያስ​ፈሩ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="27">በሕ​ያ​ዋ​ንም ምድር ኀያ​ላ​ኑን ያስ​ፈሩ ነበ​ርና፤ መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይዘው ወደ ሲኦል ከወ​ረዱ፥ ሰይ​ፋ​ቸ​ው​ንም ከራ​ሳ​ቸው በታች ከአ​ደ​ረጉ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም በአ​ጥ​ን​ታ​ቸው ላይ ከሆነ ጋር ከወ​ደቁ ካል​ተ​ገ​ረዙ ኀያ​ላን ጋር ይተ​ኛሉ።</verse>
				<verse number="28">አን​ተም ደግሞ ባል​ተ​ገ​ረ​ዙት መካ​ከል ትሰ​በ​ራ​ለህ፤ በሰ​ይ​ፍም ከተ​ገ​ደ​ሉት ጋር ትተ​ኛ​ለህ።</verse>
				<verse number="29">“ኤዶ​ም​ያ​ስና ነገ​ሥ​ታቷ፥ አለ​ቆ​ች​ዋም ሁሉ በዚያ አሉ፤ በሰ​ይፍ ከተ​ገ​ደ​ሉት ጋር</verse>
				<verse number="30">ከአ​ል​ተ​ገ​ረ​ዙና ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ተኝ​ተ​ዋል፤ የሰ​ሜን አለ​ቆች ሁሉ፥ ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም ሁሉ ከተ​ገ​ደ​ሉት ጋር ወር​ደው በዚያ አሉ፤ በኀ​ይ​ላ​ቸ​ውም ያስ​ፈሩ በነ​በ​ረው ፍር​ሀት አፍ​ረ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፍም ከተ​ገ​ደ​ሉት ጋር ያል​ተ​ገ​ረ​ዙት ተኝ​ተ​ዋል፤ ወደ ጕድ​ጓ​ድም ከሚ​ወ​ር​ዱት ጋር ቅጣ​ታ​ቸ​ውን ተሸ​ክ​መ​ዋል።</verse>
				<verse number="31">“በሰ​ይፍ የተ​ገ​ደሉ ፈር​ዖ​ንና ሠራ​ዊቱ ሁሉ ያዩ​አ​ቸ​ዋል፤ ፈር​ዖ​ንም ስለ ኀይ​ላ​ቸው ሁሉ ይጽ​ና​ናል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="32">መፈ​ራ​ቴን በሕ​ያ​ዋን ምድር አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ ፈር​ዖ​ንና ሠራ​ዊቱ ሁሉ በሰ​ይፍ በተ​ገ​ደ​ሉት፥ ባል​ተ​ገ​ረ​ዙት መካ​ከል ይተ​ኛሉ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="33">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“የሰው ልጅ ሆይ! ለሕ​ዝ​ብህ ልጆች ተና​ገር እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጦርን በም​ድር ላይ በአ​መ​ጣሁ ጊዜ፥ የም​ድር ሕዝብ ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አንድ ሰውን ወስ​ደው ለራ​ሳ​ቸው ጕበኛ ቢያ​ደ​ርጉ፥</verse>
				<verse number="3">እር​ሱም በም​ድር ላይ የመ​ጣ​ውን ጦር በአየ ጊዜ መለ​ከ​ትን ቢነፋ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ቢያ​ስ​ጠ​ነ​ቅቅ፤</verse>
				<verse number="4">የመ​ለ​ከ​ቱን ድምፅ የሚ​ሰማ ሰው ባይ​ጠ​ነ​ቀቅ፥ ጦር መጥቶ ቢወ​ስ​ደው፥ ደሙ በራሱ ላይ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="5">የመ​ለ​ከ​ቱን ድምፅ ሰምቶ ስላ​ል​ተ​ጠ​ነ​ቀቀ ደሙ በራሱ ላይ ይሆ​ናል፤ ቢጠ​ነ​ቀ​ቅስ ኖሮ ነፍ​ሱን በአ​ዳነ ነበር።</verse>
				<verse number="6">ጕበ​ኛው ግን ጦር ሲመጣ ቢያይ፥ መለ​ከ​ቱ​ንም ባይ​ነፋ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ባያ​ስ​ጠ​ነ​ቅቅ፥ ጦርም መጥቶ አንድ ሰው ከእ​ነ​ርሱ ቢወ​ስድ፥ እርሱ በኀ​ጢ​አቱ ተወ​ስ​ዶ​አል፤ ደሙን ግን ከጕ​በ​ኛው እጅ እፈ​ል​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ጕበኛ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ ከአፌ ቃሌን ስማ፤ ከእ​ኔም ዘንድ አስ​ጠ​ን​ቅ​ቃ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን፦ ኀጢ​አ​ተኛ ሆይ! በር​ግጥ ትሞ​ታ​ለህ ባልሁ ጊዜ፥ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ከክፉ መን​ገዱ ታስ​ጠ​ነ​ቅቅ ዘንድ ባት​ና​ገር፥ ያ ኀጢ​አ​ተኛ በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ ደሙን ግን ከእ​ጅህ እፈ​ል​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">ነገር ግን ከመ​ን​ገዱ ይመ​ለስ ዘንድ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ብታ​ስ​ጠ​ነ​ቅ​ቀው፥ እር​ሱም ከመ​ን​ገዱ ባይ​መ​ለስ፥ በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ አንተ ግን ነፍ​ስ​ህን ታድ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="10">“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት፦ እና​ንተ፦ በደ​ላ​ች​ንና ኀጢ​አ​ታ​ችን በላ​ያ​ችን አሉ፤ እኛም ሰል​ስ​ለ​ን​ባ​ቸ​ዋል፤ እን​ዴ​ትስ በሕ​ይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን? ብላ​ችሁ ተና​ግ​ራ​ች​ኋል በላ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">እኔ ሕያው ነኝና ኀጢ​አ​ተ​ኛው ከመ​ን​ገዱ ተመ​ልሶ በሕ​ይ​ወት ይኖር ዘንድ እንጂ ኀጢ​አ​ተ​ኛው ይሞት ዘንድ አል​ፈ​ቅ​ድም፤ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ተመ​ለሱ፤ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ ስለ ምንስ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ? በላ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! የሕ​ዝ​ብ​ህን ልጆች እን​ዲህ በላ​ቸው፦ በበ​ደ​ለ​በት ቀን የጻ​ድቅ ጽድቁ አያ​ድ​ነ​ውም፤ ኀጢ​አ​ተ​ኛም ከኀ​ጢ​አቱ በተ​መ​ለ​ሰ​በት ቀን በኀ​ጢ​አቱ አይ​ሰ​ና​ከ​ልም፤ ጻድ​ቁም ኀጢ​አት በሠ​ራ​በት ቀን በጽ​ድቁ በሕ​ይ​ወት አይ​ኖ​ርም።</verse>
				<verse number="13">እኔ ጻድ​ቁን፦ በር​ግጥ በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ለህ ባልሁ ጊዜ፥ እርሱ በጽ​ድቁ ታምኖ ኀጢ​አት ቢሠራ በሠ​ራው ኀጢ​አት ይሞ​ታል እንጂ ጽድቁ አይ​ታ​ሰ​ብ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="14">እኔም ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን፦ በር​ግጥ ትሞ​ታ​ለህ ባልሁ ጊዜ፥ እርሱ ከኀ​ጢ​አቱ ተመ​ልሶ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ርን ቢያ​ደ​ርግ፤</verse>
				<verse number="15">ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም መያ​ዣን ቢመ​ልስ፥ የነ​ጠ​ቀ​ው​ንም ቢከ​ፍል፥ በሕ​ይ​ወ​ትም ትእ​ዛዝ ቢሄድ፥ ኀጢ​አ​ትም ባይ​ሠራ፥ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል እንጂ አይ​ሞ​ትም።</verse>
				<verse number="16">የሠ​ራ​ውም ኀጢ​አት ሁሉ አይ​ታ​ሰ​ብ​በ​ትም፤ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ርን አድ​ር​ጎ​አ​ልና፤ በእ​ር​ግጥ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል።</verse>
				<verse number="17">“የሕ​ዝ​ብህ ልጆች፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገድ የቀና አይ​ደ​ለም ይላሉ፤ ነገር ግን የእ​ነ​ርሱ መን​ገድ የቀና አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="18">ጻድቅ ከጽ​ድቁ ተመ​ልሶ ኀጢ​አ​ትን ቢሠራ ይሞ​ት​በ​ታል።</verse>
				<verse number="19">ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ከኀ​ጢ​አቱ ተመ​ልሶ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን ቢያ​ደ​ርግ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ር​በ​ታል።</verse>
				<verse number="20">እና​ንተ ግን፦ የጌታ መን​ገድ የቀና አይ​ደ​ለም ትላ​ላ​ችሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ላይ እንደ መን​ገ​ዳ​ችሁ እፈ​ር​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="21">እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በተ​ማ​ረ​ክን በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር ከወ​ሩም በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ቀን ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ለጠ አንድ ሰው ወደ እኔ መጥቶ፦ ከተ​ማ​ዪቱ ተያ​ዘች አለኝ።</verse>
				<verse number="22">ያመ​ለ​ጠ​ውም ሳይ​መጣ በመሸ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእኔ ላይ ነበ​ረች፤ በነ​ጋ​ውም ወደ እኔ እስ​ኪ​መጣ ድረስ አፌን ከፈተ፤ አፌም ተከ​ፈ​ተች፤ ከዚ​ያም በኋላ እኔ ዲዳ አል​ሆ​ን​ሁም።</verse>
				<verse number="23">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፥</verse>
				<verse number="24">“የሰው ልጅ ሆይ! በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር በአሉ በባ​ድማ ስፍ​ራ​ዎች የተ​ቀ​መጡ፦ አብ​ር​ሃም ብቻ​ውን ሳለ ምድ​ሪ​ቱን ወረሰ፤ እኛም ብዙ​ዎች ነን፤ ምድ​ሪ​ቱም ርስት ሆና ለእኛ ተሰ​ጥ​ታ​ለች ይላሉ። ስለ​ዚህ እን​ዲህ በላ​ቸው፦</verse>
				<verse number="25">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከደም ጋር ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ዐይ​ና​ች​ሁ​ንም ወደ ጣዖ​ቶ​ቻ​ችሁ ታነ​ሣ​ላ​ችሁ፤ ደም​ንም ታፈ​ስ​ሳ​ላ​ችሁ፤ በውኑ ምድ​ሪ​ቱን ትወ​ር​ሳ​ላ​ች​ሁን?</verse>
				<verse number="26">ሰይ​ፋ​ች​ሁን ይዛ​ችሁ ቆማ​ች​ኋል፤ ርኩስ ነገ​ርን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ፤ የባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ች​ሁ​ንም ሚስ​ቶች ታስ​ነ​ው​ራ​ላ​ችሁ፤ በውኑ ምድ​ሪ​ቱን ትወ​ር​ሳ​ላ​ች​ሁን? ስለ​ዚ​ህም እን​ዲህ በላ​ቸው፦</verse>
				<verse number="27">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና በባ​ድማ ስፍ​ራ​ዎች ያሉ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ በም​ድረ በዳ ያለ​ውን ለአ​ራ​ዊት መብል አድ​ርጌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ በአ​ም​ባ​ዎ​ችና በዋ​ሻ​ዎች ያሉ በቸ​ነ​ፈር ይሞ​ታሉ።</verse>
				<verse number="28">ምድ​ሪ​ቱ​ንም ባድ​ማና ውድማ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ የኀ​ይ​ል​ዋም ስድብ ይቀ​ራል፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተራ​ሮች ባድማ ይሆ​ናሉ፤ ማንም አያ​ል​ፍ​ባ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="29">ስላ​ደ​ረ​ጉ​ትም ርኵ​ሰት ሁሉ ምድ​ሪ​ቱን ባድ​ማና ውድማ ባደ​ረ​ግሁ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="30">“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! የሕ​ዝ​ብህ ልጆች በቅ​ጥር አጠ​ገ​ብና በቤት ደጆች ውስጥ ስለ አንተ ይና​ገ​ራሉ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም አንዱ ከአ​ንዱ ጋር፦ እን​ሂ​ድና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ለ​ውን ቃል እን​ስማ ይላሉ።</verse>
				<verse number="31">ሕዝብ እን​ደ​ሚ​መጣ ወደ አንተ ይመ​ጣሉ፤ እንደ ሕዝ​ቤም በፊ​ትህ ይቀ​መ​ጣሉ፤ ቃል​ህ​ንም ይሰ​ማሉ፤ ነገር ግን አያ​ደ​ር​ጉ​ትም፤ በአ​ፋ​ቸው ሐሰት ነገር አለና፥ ልባ​ቸ​ውም ጣዖ​ታ​ትን ይከ​ተ​ላ​ልና።</verse>
				<verse number="32">እነሆ አንተ መል​ካም ድምፅ እን​ዳ​ለው እን​ደ​ሚ​ወ​ደድ መዝ​ሙር ማለ​ፊ​ያም አድ​ርጎ በገና እን​ደ​ሚ​ጫ​ወት ሰው ሁነ​ህ​ላ​ቸ​ዋል፤ ቃል​ህ​ንም ይሰ​ማሉ ነገር ግን አያ​ደ​ር​ጉ​ትም።</verse>
				<verse number="33">እነ​ር​ሱም እን​ዲህ ይላሉ፦ እነሆ ይህ ይመ​ጣል፤ በመ​ጣም ጊዜ እነ​ርሱ ነቢይ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው እንደ ነበረ ያው​ቃሉ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="34">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት ተና​ገር፤ በእ​ስ​ራ​ኤል እረ​ኞች ላይ ትን​ቢት ተና​ገር፤ እረ​ኞ​ች​ንም እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ራሳ​ቸ​ውን ለሚ​ያ​ሰ​ማሩ ለእ​ስ​ራ​ኤል እረ​ኞች ወዮ​ላ​ቸው! እረ​ኞች ራሳ​ቸ​ውን ያሰ​ማ​ራ​ሉን? እረ​ኞች በጎ​ችን ያሰ​ማሩ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ቸ​ው​ምን?</verse>
				<verse number="3">ወተ​ቱን ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ጠጕ​ሩ​ንም ትለ​ብ​ሳ​ላ​ችሁ፤ የወ​ፈ​ሩ​ትን ታር​ዳ​ላ​ችሁ፤ በጎ​ቹን ግን አታ​ሰ​ማ​ሩም።</verse>
				<verse number="4">የደ​ከ​መ​ውን አላ​ጸ​ና​ች​ሁ​ትም፤ የታ​መ​መ​ው​ንም አል​ፈ​ወ​ሳ​ች​ሁ​ትም፤ የተ​ሰ​በ​ረ​ው​ንም አል​ጠ​ገ​ና​ች​ሁ​ትም፤ የባ​ዘ​ነ​ው​ንም አል​መ​ለ​ሳ​ች​ሁ​ትም፤ የጠ​ፋ​ው​ንም አል​ፈ​ለ​ጋ​ች​ሁ​ትም፤ በኀ​ይ​ልና በጭ​ቈ​ናም ገዛ​ች​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">በጎ​ችም እረ​ኛን በማ​ጣት ተበ​ተኑ፤ ለዱ​ርም አራ​ዊት ሁሉ መብል ሆኑ።</verse>
				<verse number="6">በጎች በተ​ራ​ሮች ሁሉና በረ​ዘሙ ኮረ​ብ​ቶች ሁሉ ላይ ተበ​ት​ነ​ዋል፤ በጎ​ችም በም​ድር ፊት ሁሉ ላይ ተበ​ት​ነ​ዋል፤ የሚ​ፈ​ል​ግም አል​ነ​በ​ረም፤ የሚ​መ​ል​ስም አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="7">“ስለ​ዚህ እረ​ኞች ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤</verse>
				<verse number="8">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና እረ​ኞች ስለ​ሌሉ፥ እረ​ኞ​ችም በጎ​ችን ስላ​ል​ፈ​ለጉ፥ እረ​ኞ​ችም ራሳ​ቸ​ውን እንጂ በጎ​ችን ስላ​ላ​ሰ​ማሩ፥ በጎች ንጥ​ቂያ ሆነ​ዋ​ልና፥ በጎ​ችም ለዱር አራ​ዊት ሁሉ መብል ሆነ​ዋ​ልና፤</verse>
				<verse number="9">ስለ​ዚህ እረ​ኞች ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።</verse>
				<verse number="10">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በእ​ረ​ኞች ላይ ነኝ፤ በጎ​ች​ንም ከእ​ጃ​ቸው እፈ​ል​ጋ​ለሁ፤ በጎ​ች​ንም ከማ​ሰ​ማ​ራት አስ​ተ​ዋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም ወዲያ እረ​ኞች በጎ​ችን አያ​ሰ​ማ​ሩም፤ በጎ​ች​ንም ከአ​ፋ​ቸው አድ​ና​ለሁ፤ መብ​ልም አይ​ሆ​ኑ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="11">“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ራሴ በጎ​ችን እሻ​ለሁ፤ እጐ​በ​ኛ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም።</verse>
				<verse number="12">በደ​መ​ናና በጭ​ጋግ ቀን እረኛ ከበ​ጎቹ መካ​ከል የተ​ለ​የ​ውን እን​ደ​ሚ​ፈ​ልግ፥ እን​ደ​ዚሁ በጎ​ችን እፈ​ል​ጋ​ለሁ፤ በደ​መ​ናና በጭ​ጋግ ቀን ከተ​በ​ተ​ኑ​ባ​ቸው ሀገ​ሮች ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">ከአ​ሕ​ዛ​ብም ዘንድ አወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከሀ​ገ​ሮ​ችም ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ ገዛ ሀገ​ራ​ቸ​ውም አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተራ​ሮች ላይ፥ በፈ​ሳ​ሾ​ችም አጠ​ገብ፥ በም​ድ​ርም ላይ ሰዎች በሚ​ኖ​ሩ​ባት ስፍራ ሁሉ አሰ​ማ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">በመ​ል​ካም ማሰ​ማ​ርያ አስ​ማ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ጕረ​ኖ​አ​ቸ​ውም በረ​ዥ​ሞቹ በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ ይሆ​ናል፤ በዚያ በመ​ል​ካም ጕረኖ ውስጥ ይመ​ሰ​ጋሉ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተራ​ሮች ላይ በለ​መ​ለመ ማሰ​ማ​ርያ ይሰ​ማ​ራሉ።</verse>
				<verse number="15">እኔ ራሴ በጎ​ችን አሰ​ማ​ራ​ለሁ፤ አስ​መ​ስ​ጋ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="16">የጠ​ፋ​ው​ንም እፈ​ል​ጋ​ለሁ፤ የባ​ዘ​ነ​ው​ንም እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ የተ​ሰ​በ​ረ​ው​ንም እጠ​ግ​ና​ለሁ፤ የደ​ከ​መ​ው​ንም አጸ​ና​ለሁ፤ የወ​ፈ​ረ​ው​ንና የበ​ረ​ታ​ው​ንም እጠ​ብ​ቃ​ለሁ፤ በፍ​ር​ድም እጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="17">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እና​ን​ተም መን​ጋዬ ሆይ! እነሆ በበ​ግና በበግ መካ​ከል፥ በአ​ውራ በግና በአ​ውራ ፍየ​ልም መካ​ከል እፈ​ር​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="18">የቀ​ረ​ውን ማሰ​ማ​ር​ያ​ች​ሁን በእ​ግ​ራ​ችሁ የረ​ገ​ጣ​ች​ሁት፥ የተ​ሰ​ማ​ራ​ች​ሁ​በት መል​ካሙ መሰ​ማ​ርያ ባይ​በ​ቃ​ችሁ ነውን? የቀ​ረ​ው​ንስ ውኃ በእ​ግ​ራ​ችሁ ያደ​ፈ​ረ​ሳ​ች​ሁት፥ ጥሩ​ውን ውኃ መጠ​ጣ​ታ​ችሁ ባይ​በ​ቃ​ችሁ ነውን?</verse>
				<verse number="19">በጎ​ችም በእ​ግ​ራ​ችሁ በረ​ገ​ጣ​ች​ሁት ይሰ​ማ​ራሉ፤ በእ​ግ​ራ​ች​ሁም ያደ​ፈ​ረ​ሳ​ች​ሁ​ትን ይጠ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="20">“ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ቸ​ዋል፦ እነሆ እኔ በወ​ፈ​ሩት በጎ​ችና በከ​ሱት በጎች መካ​ከል እፈ​ር​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="21">እስ​ክ​ት​በ​ት​ኑ​አ​ቸው ድረስ በእ​ን​ቢ​ያና በት​ከሻ ስለ​ም​ት​ገ​ፉ​አ​ቸው፥ የደ​ከ​ሙ​ት​ንም ሁሉ በቀ​ን​ዳ​ችሁ ስለ​ም​ት​ወ​ጉ​አ​ቸው፥</verse>
				<verse number="22">ስለ​ዚህ መን​ጋ​ዬን አድ​ና​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ንጥ​ቂያ አይ​ሆ​ኑም፤ በበ​ግና በበግ መካ​ከ​ልም እፈ​ር​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="23">በላ​ያ​ቸ​ውም አንድ እረኛ አቆ​ማ​ለሁ፤ እር​ሱም ያሰ​ማ​ራ​ቸ​ዋል፤ እር​ሱም ባሪ​ያዬ ዳዊት ነው፤ እረ​ኛም ይሆ​ና​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="24">እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ባሪ​ያዬ ዳዊ​ትም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አለቃ ይሆ​ናል፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="25">“የሰ​ላ​ም​ንም ቃል ኪዳን ከዳ​ዊት ቤት ጋር አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ክፉ​ዎ​ች​ንም አራ​ዊት ከም​ድር አጠ​ፋ​ለሁ፤ ተዘ​ል​ለ​ውም በም​ድረ በዳ ይኖ​ራሉ፤ በዱ​ርም ውስጥ ይተ​ኛሉ።</verse>
				<verse number="26">እነ​ር​ሱ​ንና በኮ​ረ​ብ​ታዬ ዙሪያ ያሉ​ትን ስፍ​ራ​ዎች እባ​ር​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ዝና​ቡ​ንም በጊ​ዜው አወ​ር​ዳ​ለሁ፤ የበ​ረ​ከ​ትም ዝናብ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="27">የም​ድረ በዳ ዛፍም ፍሬ​ውን ይሰ​ጣል፤ ምድ​ርም ቡቃ​ያ​ዋን ትሰ​ጣ​ለች፤ በም​ድ​ራ​ቸ​ውም በሰ​ላም ታም​ነው ይኖ​ራሉ፤ የቀ​ን​በ​ራ​ቸ​ው​ንም ማነቆ በሰ​በ​ርሁ ጊዜ፥ ከሚ​ገ​ዙ​አ​ቸ​ውም እጅ ባዳ​ን​ኋ​ቸው ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="28">እን​ግ​ዲህ ለአ​ሕ​ዛብ ንጥ​ቂያ አይ​ሆ​ኑም፤ የም​ድ​ርም አራ​ዊት አይ​በ​ሉ​አ​ቸ​ዋም፤ ተዘ​ል​ለ​ውም ይቀ​መ​ጣሉ፤ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ቸ​ውም የለም።</verse>
				<verse number="29">የሰ​ላ​ምን ተክል አቆ​ም​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲ​ህም ከራብ የተ​ነሣ በም​ድር አያ​ል​ቁም፤ የአ​ሕ​ዛ​ብ​ንም ስድብ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​ሸ​ከ​ሙም።</verse>
				<verse number="30">እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው ከእ​ነ​ርሱ ጋር እን​ዳ​ለሁ፥ እነ​ር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሕዝቤ እንደ ሆኑ ያው​ቃሉ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="31">እና​ን​ተም በጎች፥ የማ​ሰ​ማ​ሪ​ያዬ በጎች፥ ሰዎች ናችሁ፤ እኔም አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="35">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“የሰው ልጅ ሆይ! ፊት​ህን ወደ ሴይር ተራራ መልስ፤ ትን​ቢ​ትም ተና​ገ​ር​በት፤</verse>
				<verse number="3">እን​ዲ​ህም በለው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሴ​ይር ተራራ ሆይ! እነሆ በአ​ንተ ላይ ነኝ፤ እጄን እዘ​ረ​ጋ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ባድ​ማና ውድ​ማም አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">ከተ​ሞ​ች​ህ​ንም አፈ​ራ​ር​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አን​ተም ባድማ ትሆ​ና​ለህ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ።</verse>
				<verse number="5">የዘ​ለ​ዓ​ለም ጠላት ሁነ​ሃ​ልና፥ በመ​ከ​ራ​ቸ​ውም ጊዜ በኀ​ይ​ለ​ኛ​ይቱ የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ቀጠሮ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በሰ​ይፍ እጅ ጥለ​ሃ​ቸ​ዋ​ልና፤</verse>
				<verse number="6">ስለ​ዚህ እኔ ሕያው ነኝ! በደም እንደ በደ​ልህ ደም ያሳ​ድ​ድ​ሃል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="7">የሴ​ይ​ር​ንም ተራራ ውድማ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ሰው​ንና እን​ስ​ሳ​ው​ንም አጠ​ፋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">ተራ​ሮ​ች​ህ​ንም በተ​ገ​ደ​ሉት ሰዎች እሞ​ላ​ለሁ፤ በኮ​ረ​ብ​ቶ​ች​ህና በሸ​ለ​ቆ​ዎ​ችህ፥ በፈ​ሳ​ሾ​ች​ህም ሁሉ ላይ በሰ​ይፍ የተ​ገ​ደ​ሉት ሁሉ ይወ​ድ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="9">ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ባድማ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ ከተ​ሞ​ች​ህም ሰው የማ​ይ​ኖ​ር​ባ​ቸው ይሆ​ናሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ።</verse>
				<verse number="10">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚያ ሳለ፥ አንተ፥ እነ​ዚህ ሁለቱ ሕዝ​ቦች፥ እነ​ዚ​ህም ሁለቱ ሀገ​ሮች ለእኔ ይሆ​ናሉ፤ እኔም እወ​ር​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ ብለ​ሃ​ልና፤</verse>
				<verse number="11">ስለ​ዚህ እኔ ሕያው ነኝ! እንደ ቍጣህ መጠን፥ እነ​ር​ሱ​ንም ጠል​ተህ እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ኸው እንደ ቅን​አ​ትህ መጠን እኔ እፈ​ር​ድ​ብ​ሃ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በፈ​ረ​ድ​ሁ​ብ​ህም ጊዜ በእ​ነ​ርሱ ዘንድ የታ​ወ​ቅሁ እሆ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">አን​ተም፦ ፈር​ሰ​ዋል፤ መብ​ልም ሆነው ለእኛ ተሰ​ጥ​ተ​ዋል ብለህ በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ስድብ ሁሉ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰማ​ሁት ታው​ቃ​ለህ።</verse>
				<verse number="13">አንተ አፍ​ህን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ እንደ አደ​ረ​ግህ እኔ ሰም​ቼ​አ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="14">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላል፥ “ምድር ሁሉ ደስ ሲላት አን​ተን ባድማ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ርስት ባድማ ስለ ሆነ በላዩ ደስ እን​ዳ​ለህ፥ እን​ዲሁ አደ​ር​ግ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የሴ​ይር ተራራ ሆይ! አን​ተና መላው ኤዶ​ም​ያስ ባድማ ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="36">
				<verse number="1">“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ትን​ቢት ተና​ገር፦ የእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ በላ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጠላት በእ​ና​ንተ ላይ፦ እሰይ! ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጥፋት፥ ለእኛ ርስት ሆነ​ዋል ብሎ​አ​ልና፤</verse>
				<verse number="3">ስለ​ዚህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ለቀ​ሩት አሕ​ዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙ​ሪ​ያ​ችሁ ያሉ አሕ​ዛብ አዋ​ር​ደ​ዋ​ች​ኋ​ልና፤ ውጠ​ዋ​ች​ሁ​ማ​ልና፥ እና​ን​ተም የተ​ና​ጋ​ሪ​ዎች ከን​ፈር መተ​ረ​ቻና የአ​ሕ​ዛብ ማላ​ገጫ ሆና​ች​ኋ​ልና፤</verse>
				<verse number="4">ስለ​ዚህ፥ እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ሆይ! የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ። ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለተ​ራ​ሮ​ችና ለኮ​ረ​ብ​ቶች፥ ለፈ​ሳ​ሾ​ችና ለሸ​ለ​ቆ​ዎች፥ ለም​ድረ በዳ​ዎች፥ ባዶ ለሆ​ኑ​ትና ለፈ​ረ​ሱት፥ በዙ​ሪያ ላሉት ለቀ​ሩት አሕ​ዛብ ምር​ኮና መሣ​ለ​ቂያ ለሆ​ኑት ከተ​ሞች እን​ዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="5">ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያሳ​ድ​ዱ​አ​ትና ይበ​ዘ​ብ​ዙ​አት ዘንድ በል​ባ​ቸው ሁሉ ደስ​ታና በነ​ፍ​ሳ​ቸው ንቀት ምድ​ሬን ርስት አድ​ር​ገው ለራ​ሳ​ቸው በሰጡ በቀ​ሩት አሕ​ዛ​ብና በኤ​ዶ​ም​ያስ ሁሉ ላይ በቅ​ን​አቴ እሳት ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="6">ስለ​ዚህ ስለ እስ​ራ​ኤል ምድር ትን​ቢት ተና​ገር፤ ለተ​ራ​ሮ​ችና ለኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም፥ ለፈ​ሳ​ሾ​ችና ለሸ​ለ​ቆ​ዎ​ችም እን​ዲህ በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የአ​ሕ​ዛ​ብን ስድብ ስለ ተሸ​ከ​ማ​ችሁ በቅ​ን​አ​ቴና በመ​ዓቴ ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዙ​ሪ​ያ​ችሁ በአሉ አሕ​ዛብ ላይ እኔ እጄን አነ​ሣ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ኀፍ​ረ​ታ​ቸ​ውን ይሸ​ከ​ማሉ።</verse>
				<verse number="8">“የእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ሆይ! ሕዝቤ ይመጡ ዘንድ ተስፋ ያደ​ር​ጋ​ሉና ወይ​ና​ች​ሁ​ንና ፍሬ​ያ​ች​ሁን ይበ​ላሉ።</verse>
				<verse number="9">እነሆ እኔ ለእ​ና​ንተ ነኝና፤ ወደ እና​ን​ተም እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ትታ​ረ​ሳ​ላ​ችሁ፤ ትዘ​ራ​ላ​ች​ሁም፤</verse>
				<verse number="10">እኔም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ሰዎች ሁሉ ሁሉ​ንም አበ​ዛ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በከ​ተ​ሞ​ችም ሰዎች ይኖ​ሩ​ባ​ቸ​ዋል፤ ባድ​ማ​ዎ​ቹም ስፍ​ራ​ዎች ይሠ​ራሉ።</verse>
				<verse number="11">ሰው​ንና እን​ስ​ሳ​ው​ንም አበ​ዛ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይበ​ዛሉ፤ ያፈ​ሩ​ማል፤ እንደ ጥን​ታ​ች​ሁም ሰዎ​ችን አኖ​ር​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ቀድ​ሞም እንደ አደ​ረ​ግ​ሁ​ላ​ችሁ መል​ካም አደ​ር​ግ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="12">ሰዎ​ች​ንም፥ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን በእ​ና​ንተ ላይ አበ​ዛ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይወ​ር​ሱ​አ​ች​ኋል፤ ርስ​ትም ትሆ​ኑ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ ልጅ አልባ አታ​ደ​ር​ጓ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="13">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነ​ርሱ፦ ሰው በላ​ተኛ ነሽ፤ በሕ​ዝ​ብ​ሽም መካ​ከል ልጆ​ች​ሽን አጥ​ፍ​ተ​ሻል ብለ​ዋ​ች​ኋ​ልና፤</verse>
				<verse number="14">ስለ​ዚህ ዳግ​መኛ ሰው በላ​ተኛ አት​ሆ​ኝም፤ ዳግ​መ​ኛም ሕዝ​ብ​ሽን ልጅ አልባ አታ​ደ​ር​ጊም፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="15">ዳግ​መ​ኛም የአ​ሕ​ዛ​ብን ስድብ አላ​ሰ​ማ​ብ​ሽም፤ ዳግ​መ​ኛም የአ​ሕ​ዛ​ብን ውር​ደት አት​ሸ​ከ​ሚም፤ ዳግ​መ​ኛም ሕዝ​ብ​ሽን አታ​ሰ​ና​ክ​ዪም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”</verse>
				<verse number="16">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="17">“የሰው ልጅ ሆይ! የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት በም​ድ​ራ​ቸው በተ​ቀ​መጡ ጊዜ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸ​ውና በጣ​ዖ​ታ​ቸው አረ​ከ​ሱ​አት፤ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም በፊቴ እንደ አደፍ ርኵ​ሰት ነበረ።</verse>
				<verse number="18">በም​ድር ላይ ስለ አፈ​ሰ​ሱት ደም፥ በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ስለ አረ​ከ​ሱ​አት መዓ​ቴን አፈ​ሰ​ስ​ሁ​ባ​ቸው፤</verse>
				<verse number="19">ወደ አሕ​ዛ​ብም በተ​ን​ኋ​ቸው፤ ወደ ሀገ​ሮ​ችም ዘራ​ኋ​ቸው፤ እንደ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውና እንደ በደ​ላ​ቸ​ውም መጠን ፈረ​ድ​ሁ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">ወደ ገቡ​ባ​ቸ​ውም ወደ አሕ​ዛብ በመጡ ጊዜ፥ ሰዎች እነ​ር​ሱን፦ ከም​ድ​ራ​ቸው የወጡ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ እነ​ዚህ ናቸው ሲሉ​አ​ቸው ቅዱስ ስሜን አረ​ከሱ።</verse>
				<verse number="21">እኔ ግን የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት በመ​ጡ​ባ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ስለ አረ​ከ​ሱት ስለ ቅዱስ ስሜ ስል ራራ​ሁ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">“ስለ​ዚህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በገ​ባ​ች​ሁ​ባ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ስላ​ረ​ከ​ሳ​ች​ሁት ስለ ቅዱስ ስሜ ነው እንጂ ስለ እና​ንተ የም​ሠራ አይ​ደ​ለ​ሁም።</verse>
				<verse number="23">በአ​ሕ​ዛ​ብም ዘንድ የረ​ከ​ሰ​ውን፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ያረ​ከ​ሳ​ች​ሁ​ትን ገናና ስሜን እቀ​ድ​ሰ​ዋ​ለሁ፤ በዐ​ይ​ና​ቸ​ውም ዘንድ በተ​ቀ​ደ​ስ​ሁ​ባ​ችሁ ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ አሕ​ዛብ ያው​ቃሉ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="24">ከአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከየ​ሀ​ገ​ሩም ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወደ ገዛ ምድ​ራ​ች​ሁም እመ​ል​ሳ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="25">ጥሩ ውኃ​ንም እረ​ጭ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ከር​ኵ​ሰ​ታ​ችሁ ሁሉ ትነ​ጻ​ላ​ችሁ፤ ከጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ አነ​ጻ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="26">አዲስ ልብ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ አዲስ መን​ፈ​ስ​ንም በው​ስ​ጣ​ችሁ አኖ​ራ​ለሁ፤ የድ​ን​ጋ​ዩ​ንም ልብ ከሥ​ጋ​ችሁ አወ​ጣ​ለሁ፤ የሥ​ጋ​ንም ልብ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="27">መን​ፈ​ሴ​ንም በው​ስ​ጣ​ችሁ አኖ​ራ​ለሁ፤ በት​እ​ዛ​ዜም እን​ድ​ት​ሄዱ አደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤ ፍር​ዴ​ንም ትጠ​ብ​ቃ​ላ​ችሁ ታደ​ር​ጉ​ት​ማ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="28">ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በሰ​ጠ​ኋት ምድር ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤ ሕዝ​ብም ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="29">ከር​ኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ሁሉ አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እህ​ል​ንም እጠ​ራ​ዋ​ለሁ፤ አበ​ዛ​ው​ማ​ለሁ፤ ራብ​ንም አላ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="30">ደግ​ሞም የራ​ብን ስድብ ከአ​ሕ​ዛብ ዘንድ እን​ዳ​ት​ሸ​ከሙ የዛ​ፍን ፍሬና የእ​ር​ሻ​ውን መከር አበ​ዛ​ለሁ።</verse>
				<verse number="31">ክፉ​ውን መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና መል​ካም ያይ​ደ​ለ​ውን ሥራ​ች​ሁ​ንም ታስ​ባ​ላ​ችሁ፤ ስለ በደ​ላ​ች​ሁና ስለ ርኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ራሳ​ች​ሁን ትጸ​የ​ፋ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="32">ይህን የሠ​ራሁ ስለ እና​ንተ እን​ዳ​ይ​ደለ በእ​ና​ንተ ዘንድ የታ​ወቀ ይሁን፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ስለ መን​ገ​ዳ​ችሁ እፈ​ሩና ተዋ​ረዱ።</verse>
				<verse number="33">“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ሁሉ በአ​ነ​ጻ​ኋ​ችሁ ጊዜ በከ​ተ​ሞች ሰዎ​ችን አኖ​ራ​ለሁ፤ ባድ​ማ​ዎ​ቹም ስፍ​ራ​ዎች ይሠ​ራሉ።</verse>
				<verse number="34">ባድማ የነ​በ​ረች፥ በመ​ን​ገ​ደ​ኛም ሁሉ ዐይን ዘንድ ባድማ የነ​በ​ረች ምድር ትታ​ረ​ሳ​ለች።</verse>
				<verse number="35">ሰዎ​ችም ባድማ የነ​በ​ረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆና​ለች፤ የፈ​ረ​ሱት፥ ባድማ የሆ​ኑት፥ የጠ​ፉ​ትም ከተ​ሞች ተመ​ሽ​ገ​ዋል፤ ሰውም የሚ​ኖ​ር​ባ​ቸው ሆነ​ዋል ይላሉ።</verse>
				<verse number="36">በዙ​ሪ​ያ​ች​ሁም የቀ​ሩት አሕ​ዛብ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፈ​ረ​ሱ​ትን ስፍ​ራ​ዎች እንደ ሠራሁ፥ ውድማ የሆ​ነ​ው​ንም እንደ ተከ​ልሁ ያው​ቃሉ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፥ እኔም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="37">“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ስለ​ዚህ ደግሞ አደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ይሹ​ኛል፤ ሰው​ንም እንደ መንጋ አበ​ዛ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="38">እንደ ተቀ​ደሱ በጎች፥ በበ​ዓ​ላ​ቶ​ችዋ ቀን እን​ደ​ሚ​ሆኑ እንደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በጎች እን​ዲሁ የፈ​ረ​ሱት ከተ​ሞች በሰ​ዎች መንጋ ይሞ​ላሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="37">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በላዬ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በመ​ን​ፈሱ አወ​ጣኝ፤ አጥ​ን​ቶ​ችም በሞ​ሉ​በት ሸለቆ መካ​ከል አኖ​ረኝ።</verse>
				<verse number="2">በእ​ነ​ር​ሱም አን​ጻር በዙ​ሪ​ያ​ቸው አዞ​ረኝ፤ እነ​ሆም በሜ​ዳው እጅግ ነበሩ፤ እነ​ሆም እጅግ ደር​ቀው ነበር።</verse>
				<verse number="3">እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነ​ዚህ አጥ​ን​ቶች በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራ​ሉን?” አለኝ። እኔም፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! አንተ ታው​ቃ​ለህ” አልሁ።</verse>
				<verse number="4">እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “በእ​ነ​ዚህ አጥ​ን​ቶች ላይ ትን​ቢት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ እና​ንተ የደ​ረ​ቃ​ችሁ አጥ​ን​ቶች ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።</verse>
				<verse number="5">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ነ​ዚህ አጥ​ን​ቶች እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በእ​ና​ንተ ላይ የሕ​ይ​ወ​ትን መን​ፈስ አመ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="6">ጅማ​ት​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሥጋ​ንም አወ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ ቍር​በ​ትን እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ትን​ፋ​ሽ​ንም አገ​ባ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="7">እን​ዳ​ዘ​ዘ​ኝም ትን​ቢት ተና​ገ​ርሁ፤ ስና​ገ​ርም ድምፅ ሆነ፤ እነ​ሆም መና​ወጥ ሆነ፤ አጥ​ን​ቶ​ች​ንም እየ​ራሱ በሆነ በሰ​ው​ነቱ ከአ​ጥ​ን​ቶች ጋር አንድ አደ​ረ​ጋ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">እኔም አየሁ፤ እነ​ሆም ጅማት ነበ​ረ​ባ​ቸው፤ ሥጋም ወጣ፤ ቍር​በ​ትም በላ​ያ​ቸው ተዘ​ረጋ፤ ትን​ፋሽ ግን አል​ነ​በ​ረ​ባ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="9">እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት ተና​ገር፤ ለነ​ፋስ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ለነ​ፋ​ስም፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ነፋስ ሆይ! ከአ​ራቱ ነፋ​ሳት ዘንድ ና፤ እነ​ዚህ ሙታን በሕ​ይ​ወት ይኖሩ ዘንድ እፍ በል​ባ​ቸው በል” አለኝ።</verse>
				<verse number="10">እን​ዳ​ዘ​ዘ​ኝም ትን​ቢት ተና​ገ​ርሁ፤ ትን​ፋ​ሽም ገባ​ባ​ቸው፤ ሕያ​ዋ​ንም ሆኑ፤ እጅ​ግም ታላቅ ሠራ​ዊት ሆነው በእ​ግ​ራ​ቸው ቆሙ።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተና​ገ​ረኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነ​ዚህ አጥ​ን​ቶች የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ናቸው፤ እነሆ! አጥ​ን​ቶ​ቻ​ችን ደር​ቀ​ዋል፤ ተስ​ፋ​ች​ንም ጠፍ​ቶ​አል፤ ፈጽ​መ​ንም ተቈ​ር​ጠ​ናል ብለ​ዋል።</verse>
				<verse number="12">ስለ​ዚህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሕዝቤ ሆይ! እነሆ መቃ​ብ​ራ​ች​ሁን እከ​ፍ​ታ​ለሁ፤ ከመ​ቃ​ብ​ራ​ች​ሁም አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ምድር አገ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">ሕዝቤ ሆይ! መቃ​ብ​ራ​ች​ሁን በከ​ፈ​ትሁ ጊዜ፥ ከመ​ቃ​ብ​ራ​ች​ሁም በአ​ወ​ጣ​ኋ​ችሁ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="14">መን​ፈ​ሴ​ንም በው​ስ​ጣ​ችሁ አሳ​ድ​ራ​ለሁ፤ እና​ን​ተም በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤ በገዛ ምድ​ራ​ች​ሁም አኖ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ርሁ፥ እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ሁም ታው​ቃ​ላ​ችሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”</verse>
				<verse number="15">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="16">“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! አንድ በትር ውሰ​ድና፦ ይሁ​ዳ​ንና ባል​ን​ጀ​ሮ​ቹን፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች በላዩ ጻፍ፤ ሌላም በትር ውሰ​ድና፦ የኤ​ፍ​ሬም በትር ለዮ​ሴ​ፍና ለባ​ል​ን​ጀ​ሮቹ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ብለህ በላዩ ጻፍ።</verse>
				<verse number="17">አንድ በት​ርም እን​ዲ​ሆኑ አን​ዱን ከሁ​ለ​ተ​ኛው ጋር ለአ​ንተ አጋ​ጥም፤ በእ​ጅ​ህም ውስጥ አንድ ይሁኑ።</verse>
				<verse number="18">የሕ​ዝ​ብ​ህም ልጆች፦ ይህ የም​ታ​ደ​ር​ገው ነገር ምን ማለት እንደ ሆነ አት​ነ​ግ​ረ​ን​ምን? ብለው በተ​ና​ገ​ሩህ ጊዜ፥ አንተ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="19">እነሆ በኤ​ፍ​ሬም እጅ ያለ​ውን የዮ​ሴ​ፍን በትር ባል​ን​ጀ​ሮ​ቹ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ነገ​ዶች እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ከይ​ሁዳ በትር ጋር አጋ​ጥ​ማ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አንድ በት​ርም አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ጄም ውስጥ አንድ ይሆ​ናሉ በላ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">የም​ት​ጽ​ፍ​ባ​ቸ​ውም በት​ሮች በፊ​ታ​ቸው በእ​ጅህ ውስጥ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="21">አን​ተም እን​ዲህ ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከገ​ቡ​ባ​ቸው ከአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ከስ​ፍ​ራም ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ምድር አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="22">በም​ድ​ርም ላይ በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ አንድ ሕዝብ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ አንድ ንጉ​ሥም በሁ​ላ​ቸው ላይ ይነ​ግ​ሣል፤ ከዚያ ወዲያ ሁለት ሕዝብ አይ​ሆ​ኑም፤ ከዚያ ወዲ​ያም ሁለት መን​ግ​ሥት ሆነው አይ​ለ​ያ​ዩም።</verse>
				<verse number="23">ከዚያ ወዲ​ያም በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸው፥ በመ​ተ​ላ​ለ​ፋ​ቸ​ውም ሁሉ አይ​ረ​ክ​ሱም፤ ኀጢ​አ​ትም ከሠ​ሩ​ባት ዐመፅ ሁሉ አድ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አነ​ጻ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ ሕዝ​ብም ይሆ​ኑ​ኛል፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="24">“ባሪ​ያ​ዬም ዳዊት በላ​ያ​ቸው ንጉሥ ይሆ​ናል፤ ለሁ​ሉም አንድ እረኛ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ በፍ​ር​ዴም ይሄ​ዳሉ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ይጠ​ብ​ቃሉ፤ ያደ​ር​ጓ​ት​ማል።</verse>
				<verse number="25">አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በኖ​ሩ​ባት፤ ለባ​ሪ​ያዬ ለያ​ዕ​ቆብ በሰ​ጠ​ኋት ምድር ይኖ​ራሉ፤ እነ​ር​ሱና ልጆ​ቻ​ቸው፥ የልጅ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ሩ​ባ​ታል፤ ባሪ​ያ​ዬም ዳዊት ለዘ​ለ​ዓ​ለም አለቃ ይሆ​ና​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="26">የሰ​ላ​ምም ቃል ኪዳን ከእ​ነ​ርሱ ጋር አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ቃል ኪዳን ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ እኔም እባ​ር​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አበ​ዛ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ መቅ​ደ​ሴ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አኖ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="27">ማደ​ሪ​ያ​ዬም በላ​ያ​ቸው ላይ ይሆ​ናል፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል።</verse>
				<verse number="28">መቅ​ደ​ሴም ለዘ​ለ​ዓ​ለም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው በሆነ ጊዜ፥ እኔ እስ​ራ​ኤ​ልን የም​ቀ​ድ​ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ አሕ​ዛብ ያው​ቃሉ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="38">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“የሰው ልጅ ሆይ! ፊት​ህን በጎግ ላይና በማ​ጎግ ምድር ላይ፥ በሮስ በሞ​ሳ​ሕና በቶ​ቤል አለቃ ላይ አቅ​ና​በት፤ ትን​ቢ​ትም ተና​ገ​ር​በት፤</verse>
				<verse number="3">እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሮስ፥ የሞ​ሣ​ሕና የቶ​ቤል አለቃ ጎግ ሆይ! እነሆ! እኔ በአ​ንተ ላይ ነኝ።</verse>
				<verse number="4">እመ​ል​ስ​ህ​ማ​ለሁ፤ በመ​ን​ጋ​ጋ​ህም ልጓም አገ​ባ​ብ​ሃ​ለሁ፤ አን​ተ​ንና ሠራ​ዊ​ት​ህን ሁሉ፥ ፈረ​ሶ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን፥ የጦር ልብስ የለ​በ​ሱ​ትን ሁሉ፥ ጋሻና ራስ ቍርን፥ ሰይ​ፍ​ንም የያ​ዙ​ትን ሁሉ አወ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">ፋር​ስ​ንና ኢት​ዮ​ጵ​ያን፥ ሊብ​ያ​ንም፥ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ጋሻና የራስ ቍርን የለ​በ​ሱ​ትን ሁሉ፥</verse>
				<verse number="6">ጎሜ​ር​ንና ከእ​ርሱ ጋር ያሉ​ትን ሁሉ፥ በሰ​ሜን ዳር​ቻም ያለ​ውን የቴ​ር​ጋ​ማን ቤትና ጭፍ​ሮ​ቹን ሁሉ፥ ብዙ​ዎ​ች​ንም ሕዝ​ቦች ከአ​ንተ ጋር አወ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">“አን​ተና ወደ አንተ የተ​ሰ​በ​ሰቡ ወገ​ኖ​ችህ ሁሉ ተዘ​ጋጁ፤ አን​ተም ራስ​ህን አዘ​ጋ​ጅ​ተህ ጠባቂ ሁና​ቸው።</verse>
				<verse number="8">ከብዙ ዘመ​ንም በኋላ ትፈ​ለ​ጋ​ለህ፤ በኋ​ለ​ኛ​ውም ዘመን፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም ባድማ በነ​በሩ በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ ከብዙ ሕዝብ ውስጥ ወደ ተሰ​በ​ሰ​በች፥ ከሰ​ይፍ ወደ ተመ​ለ​ሰች ምድር ትገ​ባ​ለህ፤ እር​ስ​ዋም ከሕ​ዝብ ውስጥ ወጥ​ታ​ለች፤ ሁሉም በሰ​ላም ይቀ​መ​ጡ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="9">እንደ ዝናም ትወ​ጣ​ለህ፤ እንደ ደመ​ናም ምድ​ርን ትሸ​ፍን ዘንድ ትደ​ር​ሳ​ለህ፤ አን​ተም ከብዙ ሕዝ​ብና ሠራ​ዊት ጋር ትወ​ድ​ቃ​ለህ።”</verse>
				<verse number="10">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በዚያ ቀን ነገር ወደ ልብህ ይገ​ባል፥ ክፉ አሳ​ብ​ንም ታስ​ባ​ለህ፤ እን​ዲ​ህም ትላ​ለህ፦</verse>
				<verse number="11">ወደ ጠፋች ሀገር እወ​ጣ​ለሁ፤ ተዘ​ል​ለው በሰ​ላም ወደ​ሚ​ኖሩ፥ ሁላ​ቸው ሳይ​ፈሩ ያለ ቅጥ​ርና ያለ መወ​ር​ወ​ሪያ፥ ያለ መዝ​ጊ​ያም ወደ​ሚ​ቀ​መ​ጡ​ባት ምድር እገ​ባ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="12">ምር​ኮን ትማ​ርክ ዘንድ፥ ብዝ​በ​ዛ​ንም ትበ​ዘ​ብዝ ዘንድ፥ ባድ​ማም በነ​በሩ፥ አሁ​ንም ሰዎች በሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸው ስፍ​ራ​ዎች ላይ፥ ከአ​ሕ​ዛ​ብም በተ​ሰ​በ​ሰበ፥ ከብ​ትና ዕቃ​ንም በአ​ገኘ፥ በም​ድ​ርም መካ​ከል በተ​ቀ​መጠ ሕዝብ ላይ እጅ​ህን ትመ​ል​ሳ​ለህ።</verse>
				<verse number="13">ሳባና ድዳን፥ የተ​ር​ሴ​ስም ነጋ​ዴ​ዎች፥ መን​ደ​ሮ​ች​ዋም ሁሉ፦ ምር​ኮን ትማ​ርክ ዘንድ መጥ​ተ​ሃ​ልን? ብዝ​በ​ዛ​ንስ ትበ​ዘ​ብዝ ዘንድ፥ ብር​ንና ወር​ቅ​ንስ ትወ​ስድ ዘንድ፥ ከብ​ት​ንና ዕቃ​ንስ ትወ​ስድ ዘንድ፥ እጅ​ግስ ብዙ ምርኮ ትማ​ርክ ዘንድ ወገ​ን​ህን ሰብ​ስ​በ​ሃ​ልን? ይሉ​ሃል።”</verse>
				<verse number="14">አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ስለ​ዚህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ጎግ​ንም እን​ዲህ በለው፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዚያ ቀን ሕዝቤ እስ​ራ​ኤል በሰ​ላም በተ​ቀ​መጠ ጊዜ አንተ የም​ት​ነሣ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="15">አን​ተም፥ ከአ​ን​ተም ጋር ብዙ ሕዝብ ሁላ​ቸው በፈ​ረ​ሶች ላይ የተ​ቀ​መጡ፥ ታላቅ ወገ​ንና ብርቱ ሠራ​ዊት፥ ከሰ​ሜን ዳርቻ ከስ​ፍ​ራ​ችሁ ትመ​ጣ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="16">ምድ​ር​ንም ትሸ​ፍን ዘንድ እንደ ደመና በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ትወ​ጣ​ለህ። በኋ​ለ​ኛው ዘመን ይሆ​ናል፤ ጎግ ሆይ! በፊ​ታ​ቸው በተ​ቀ​ደ​ስ​ሁ​ብህ ጊዜ፥ አሕ​ዛብ ያው​ቁኝ ዘንድ በም​ድሬ ላይ አወ​ጣ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="17">“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጎግ እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ነ​ርሱ ላይ እን​ደ​ማ​መ​ጣህ፥ በዚ​ያች ዘመን ብዙ ዓመት ትን​ቢት በተ​ና​ገሩ በባ​ሪ​ያ​ዎች በእ​ስ​ራ​ኤል ነቢ​ያት እጅ በቀ​ደ​መው ዘመን ስለ እርሱ የተ​ና​ገ​ርሁ አንተ ነህን?</verse>
				<verse number="18">በዚ​ያም ቀን ጎግ በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር ላይ በመጣ ጊዜ መቅ​ሠ​ፍቴ በመ​ዓቴ ይመ​ጣል ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="19">በቅ​ን​አ​ቴና በመ​ዓቴ እሳት ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፦ በእ​ር​ግጥ በዚያ ቀን በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር ጽኑ መና​ወጥ ይሆ​ናል፤</verse>
				<verse number="20">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት የተ​ነሣ የባ​ሕር ዓሣ​ዎ​ችና የሰ​ማይ ወፎች፥ የም​ድረ በዳም አራ​ዊት፥ በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀሱ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ሁሉ፥ በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ኖሩ ሰዎች ሁሉ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ተራ​ሮ​ችም ይገ​ለ​ባ​በ​ጣሉ፤ ገዳ​ላ​ገ​ደ​ሎ​ችም ይወ​ድ​ቃሉ፤ ቅጥ​ርም ሁሉ ወደ ምድር ይወ​ድ​ቃል።</verse>
				<verse number="21">በተ​ራ​ሮ​ችም ሁሉ በእ​ርሱ ላይ ፍር​ሀ​ትን እጠ​ራ​ለሁ፤ የሰ​ውም ሁሉ ሰይፍ በወ​ን​ድሙ ላይ ይሆ​ናል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="22">በቸ​ነ​ፈ​ርና በደም እፈ​ር​ድ​በ​ታ​ለሁ፤ ዶፍም፥ የበ​ረ​ዶም ድን​ጋይ፥ እሳ​ትና ድኝም በእ​ር​ሱና በጭ​ፍ​ሮቹ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር በአሉ በብዙ ሕዝብ ላይ አዘ​ን​ባ​ለሁ።</verse>
				<verse number="23">ታላቅ እሆ​ና​ለሁ፤ እቀ​ደ​ስ​ማ​ለሁ፤ እመ​ሰ​ገ​ና​ለ​ሁም፤ በብዙ አሕ​ዛ​ብም ዐይን የታ​ወ​ቅሁ እሆ​ና​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="39">
				<verse number="1">“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! በጎግ ላይ ትን​ቢ​ትን ተና​ገር እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሮስ የሞ​ሣ​ሕና የቶ​ቤል አለቃ ጎግ ሆይ! እነሆ እኔ በአ​ንተ ላይ ነኝ፤</verse>
				<verse number="2">እሰ​በ​ስ​ብ​ሃ​ለሁ፤ እመ​ራ​ሃ​ለሁ፤ ከሰ​ሜ​ንም ዳርቻ አወ​ጣ​ሃ​ለሁ፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ተራ​ሮች እወ​ስ​ድ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">ከግራ እጅ​ህም ቀስ​ት​ህን አስ​ጥ​ል​ሃ​ለሁ፤ ከቀኝ እጅ​ህም ፍላ​ጾ​ች​ህን አስ​ረ​ግ​ፍ​ሃ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተራ​ሮች ላይ እጥ​ል​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">አን​ተና ጭፍ​ሮ​ችህ ሁሉ፥ ከአ​ን​ተም ጋር ያሉ ሕዝብ በም​ድረ በዳ ፊት ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ ለሚ​ና​ጠቁ ወፎች ሁሉና ለም​ድር አራ​ዊ​ትም መብል አድ​ርጌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">አንተ በሜዳ ፊት ላይ ትወ​ድ​ቃ​ለህ፤ እኔ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="6">በማ​ጎ​ግም ላይ፥ በሰ​ላ​ምም በደ​ሴ​ቶች በሚ​ቀ​መጡ ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="7">ቅዱ​ሱም ስሜ በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ይታ​ወ​ቃል፤ ቅዱ​ሱ​ንም ስሜን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አላ​ረ​ክ​ስም፤ አሕ​ዛ​ብም የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እኔ እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="8">እነሆ ይመ​ጣል፤ እን​ደ​ሚ​ሆ​ንም ታው​ቃ​ላ​ችሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ያል​ሁት ቀን ይህ ነው።</verse>
				<verse number="9">በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ከተ​ሞች የሚ​ኖሩ ይወ​ጣሉ፤ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ንም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላሉ፤ አላ​ባሽ አግሬ ጋሻ​ንና ጋሻን፥ ቀስ​ት​ንና ፍላ​ጻ​ዎ​ችን፥ የእጅ በት​ሮ​ች​ንና ጦር​ንም ያቃ​ጥ​ላሉ፤ ሰባት ዓመት በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="10">እን​ጨ​ትን ከሜዳ አይ​ወ​ስ​ዱም፤ ከዱ​ርም አይ​ቈ​ር​ጡም፤ ነገር ግን የጦር መሣ​ሪ​ያን በእ​ሳት ያነ​ድ​ዳሉ፤ የገ​ፈ​ፉ​አ​ቸ​ው​ንም ይገ​ፍ​ፋሉ፤ የበ​ዘ​በ​ዙ​አ​ቸ​ው​ንም ይበ​ዘ​ብ​ዛሉ፤ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="11">“በዚ​ያም ቀን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ በባ​ሕር ምሥ​ራቅ የሚ​ያ​ል​ፉ​በ​ትን ሸለቆ፥ የመ​ቃ​ብ​ርን ስፍራ ለጎግ እሰ​ጣ​ለሁ፤ የሚ​ያ​ል​ፉ​ት​ንም ይከ​ለ​ክ​ላል፤ በዚ​ያም ጎግ​ንና ሠራ​ዊ​ቱን ሁሉ ይቀ​ብ​ራሉ፤ የሸ​ለ​ቆ​ው​ንም ስም የጎግ መቃ​ብር ብለው ይጠ​ሩ​ታል።</verse>
				<verse number="12">ምድ​ር​ንም ያነ​ደዱ የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሰባት ወር መቃ​ብር እየ​ቈ​ፈሩ ይቀ​ብ​ሯ​ቸ​ዋል፤</verse>
				<verse number="13">የም​ድ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ይቀ​ብ​ሯ​ቸ​ዋል፤ እኔም በም​መ​ሰ​ገ​ን​በት ቀን ለክ​ብር ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="14">ምድ​ር​ንም ለማ​ጽ​ዳት በም​ድሩ ላይ ወድ​ቀው የቀ​ሩ​ትን የሚ​ቀ​ብሩ፥ ዘወ​ትር በም​ድሩ ላይ የሚ​ዞ​ሩ​ትን ሰዎች ይቀ​ጥ​ራሉ፤ ከሰ​ባት ወርም በኋላ ይመ​ረ​ም​ራሉ።</verse>
				<verse number="15">በም​ድ​ርም የሚ​ዞ​ሩት ያል​ፋሉ፤ የሰ​ው​ንም አጥ​ንት ቢያዩ፥ ቀባ​ሪ​ዎች በጎግ መቃ​ብር ሸለቆ እስ​ኪ​ቀ​ብ​ሩት ድረስ ምል​ክት ያኖ​ሩ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="16">ደግ​ሞም የከ​ተ​ማ​ዪቱ ስም የመ​ቃ​ብር ቦታ ይባ​ላል። እን​ዲሁ ምድ​ሪ​ቱን ያጸ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="17">“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ለሚ​በ​ርሩ ወፎች ሁሉና ለም​ድር አራ​ዊት ሁሉ እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ኑ፤ ተከ​ማቹ፤ ሥጋ​ንም ትበሉ ዘንድ፥ ደም​ንም ትጠጡ ዘንድ በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ ወደ​ማ​ር​ድ​ላ​ችሁ መሥ​ዋ​ዕት፥ እር​ሱም ታላቅ መሥ​ዋ​ዕት፥ ከየ​ሰ​ፍ​ራው ሁሉ ተሰ​ብ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="18">የኀ​ያ​ላ​ኑን ሥጋ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ የም​ድ​ር​ንም አለ​ቆች፥ የአ​ውራ ፍየ​ሎ​ች​ንና የአ​ውራ በጎ​ችን፥ የወ​ይ​ፈ​ኖ​ች​ንና፥ የባ​ሳ​ንን ፍሪ​ዳ​ዎች ሁሉ፥ ደም ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="19">እኔም ከማ​ር​ድ​ላ​ችሁ መሥ​ዋ​ዕት እስ​ክ​ት​ጠ​ግቡ ድረስ ጮማን ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ እስ​ክ​ት​ሰ​ክ​ሩም ድረስ ደምን ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="20">ከማ​ዕ​ዴም ከፈ​ረ​ሶ​ችና ከፈ​ረ​ሰ​ኞች፥ ከኀ​ያ​ላ​ንና ከሰ​ል​ፈ​ኞች ሁሉ ሥጋን ትጠ​ግ​ባ​ላ​ችሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="21">“ክብ​ሬ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ፍር​ዴን፥ በላ​ያ​ቸ​ውም ያኖ​ር​ኋ​ትን እጄን ያያሉ።</verse>
				<verse number="22">ከዚች ቀን ጀምሮ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="23">አሕ​ዛ​ብም የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ምክ​ን​ያት እንደ ተማ​ረኩ ያው​ቃሉ፤ ስለ ከዱኝ እኔም ፊቴን ከእ​ነ​ርሱ ስለ መለ​ስሁ፥ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ አሳ​ልፌ ሰጠ​ኋ​ቸው፥ እነ​ር​ሱም ሁሉ በሰ​ይፍ ወደቁ።</verse>
				<verse number="24">እንደ ርኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውም እንደ መተ​ላ​ለ​ፋ​ቸ​ውም መጠን አደ​ረ​ግ​ሁ​ባ​ቸው፤ ፊቴ​ንም ከእ​ነ​ርሱ መለ​ስሁ።</verse>
				<verse number="25">“ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አሁን የያ​ዕ​ቆ​ብን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ እራ​ራ​ለሁ፤ ስለ ቅዱስ ስሜም እቀ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="26">በም​ድ​ራ​ቸው ተዘ​ል​ለው በተ​ቀ​መጡ ጊዜ እፍ​ረ​ታ​ቸ​ው​ንና የበ​ደ​ሉ​ኝን በደ​ላ​ቸ​ውን ሁሉ ይሸ​ከ​ማሉ፤ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ቸ​ውም የለም።</verse>
				<verse number="27">ከአ​ሕ​ዛ​ብም ዘንድ በመ​ለ​ስ​ኋ​ቸው ጊዜ፥ ከአ​ሕ​ዛ​ብም ሀገ​ሮች በሰ​በ​ሰ​ብ​ኋ​ቸው ጊዜ፥ በብዙ አሕ​ዛ​ብም ፊት በተ​ቀ​ደ​ስ​ሁ​ባ​ቸው ጊዜ፥</verse>
				<verse number="28">እኔም ወደ አሕ​ዛብ አስ​ማ​ር​ኬ​አ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፥ ወደ ገዛ ምድ​ራ​ቸ​ውም ሰብ​ስ​ቤ​አ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ፤ በዚ​ያም ከእ​ነ​ርሱ አንድ ሰው ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ አላ​ስ​ቀ​ርም፤</verse>
				<verse number="29">ፊቴ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አል​መ​ል​ስም፤ መዓ​ቴን በእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ላይ አፍ​ስ​ሻ​ለ​ሁና፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="40">
				<verse number="1">በተ​ማ​ረ​ክን በሃያ አም​ስ​ተ​ኛው ዓመት በዓ​መቱ መጀ​መ​ሪያ ከወሩ በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን፥ ከተ​ማ​ዪቱ ከተ​መ​ታች በኋላ በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ዓመት፥ በዚ​ያው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረ፤ እር​ሱም ወደ​ዚያ ወሰ​ደኝ።</verse>
				<verse number="2">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራእይ ወደ እስ​ራ​ኤል ምድር አመ​ጣኝ፤ እጅ​ግም በረ​ዘመ ተራራ ላይ አኖ​ረኝ፤ በዚ​ያም ላይ እንደ ከተማ ሆኖ የተ​ሠራ ነገር በፊቴ ነበረ።</verse>
				<verse number="3">ወደ​ዚ​ያም አመ​ጣኝ፤ እነ​ሆም መልኩ እን​ደ​ሚ​ያ​ን​ፀ​ባ​ርቅ ናስ መልክ የመ​ሰለ አንድ ሰው በዚያ ነበረ፤ በእ​ጁም የተ​ልባ እግር ገመ​ድና የመ​ለ​ኪያ ዘንግ ነበረ፤ እር​ሱም በበሩ አጠ​ገብ ቆሞ ነበር።</verse>
				<verse number="4">ያም ሰው፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን አሳ​ይህ ዘንድ አንተ ወደ​ዚህ መጥ​ተ​ሃ​ልና በዐ​ይ​ንህ እይ፤ በጆ​ሮ​ህም ስማ፤ የማ​ሳ​ይ​ህ​ንም ሁሉ በል​ብህ ጠብቅ፤ የም​ታ​የ​ው​ንም ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ንገር” አለኝ።</verse>
				<verse number="5">እነ​ሆም በቤቱ ውጭ በዙ​ሪ​ያው ቅጥር ነበረ፤ በሰ​ው​የ​ውም እጅ የክ​ንዱ ልክ አንድ ክንድ ከጋት የሆነ ስድ​ስት ክንድ ያለ​በት የመ​ለ​ኪያ ዘንግ ነበረ፤ የቅ​ጥ​ሩ​ንም ስፋት አንድ ዘንግ ቁመ​ቱ​ንም አንድ ዘንግ አድ​ርጎ ለካ።</verse>
				<verse number="6">ወደ ምሥ​ራቅ ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተ​ውም በር መጣ፤ በሰ​ባ​ቱም ደረ​ጃ​ዎች ላይ ወጣ፤ በበሩ በኩል ያለ​ው​ንም የመ​ድ​ረ​ኩን ወለል ወር​ዱን አንድ ዘንግ አድ​ርጎ ለካ፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወለል ወርድ አንድ ዘንግ ነበረ።</verse>
				<verse number="7">የዕቃ ቤቱ ሁሉ ርዝ​መት አንድ ዘንግ፤ ወር​ዱም አንድ ዘንግ ነበረ፤ በዕቃ ቤቶ​ቹም መካ​ከል አም​ስት ክንድ ነበረ፤ በበ​ሩም ደጀ ሰላም፤ በስ​ተ​ው​ስጥ በኩል የሚ​ገኝ የበሩ የመ​ድ​ረክ ወለል አንድ ዘንግ ነበረ።</verse>
				<verse number="8">በስ​ተ​ው​ስ​ጥም ያለ​ውን የበ​ሩን ደጀ​ሰ​ላም አንድ ዘንግ አድ​ርጎ ለካ።</verse>
				<verse number="9">የበ​ሩ​ንም ደጀ ሰላም ስም​ንት ክንድ፤ የግ​ን​ቡ​ንም አዕ​ማድ ወርድ ሁለት ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ የበ​ሩም ደጀ ሰላም በስ​ተ​ው​ስጥ ነበረ።</verse>
				<verse number="10">የም​ሥ​ራ​ቁም ዕቃ ቤቶች በዚህ በኩል ሦስት፥ በዚ​ያም በኩል ሦስት፥ ነበሩ፤ ለሦ​ስ​ቱም አንድ ልክ ነበረ፤ የግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ወርድ በዚህ በኩ​ልና በዚያ በኩል አንድ ልክ ነበረ።</verse>
				<verse number="11">የበ​ሩ​ንም መግ​ቢያ ወርድ ዐሥር ክንድ፥ የበ​ሩ​ንም ርዝ​መት ዐሥራ ሦስት ክንድ አድ​ርጎ ለካ።</verse>
				<verse number="12">በዕቃ ቤቱም ፊት በዚህ በኩል አንድ ክንድ፥ በዚ​ያም በኩል አንድ ክንድ የሆነ ዳርቻ ነበረ፤ የዕቃ ቤቱም በዚህ በኩል ስድ​ስት ክንድ በዚ​ያም በኩል ስድ​ስት ክንድ ነበሩ።</verse>
				<verse number="13">ከአ​ን​ዱም የዕቃ ቤት ደርብ ጀምሮ እስከ ሌላው ደርብ ድረስ የበ​ሩን ወርድ ሃያ አም​ስት ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ በሩና በሩም ትይዩ ነበረ።</verse>
				<verse number="14">ደጀ ሰላ​ሙ​ንም ሃያ ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ በበ​ሩም ደጀ ሰላም ዙሪያ አደ​ባ​ባይ ነበረ።</verse>
				<verse number="15">ከበ​ሩም መግ​ቢያ ፊት ጀምሮ እስከ ውስ​ጠ​ኛው የበሩ ደጀ ሰላም መጨ​ረሻ ድረስ አምሳ ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="16">በዕቃ ቤቶ​ቹም በበሩ ውስጥ በዙ​ሪ​ያው በነ​በ​ሩ​ትም በግ​ንቡ አዕ​ማድ የዐ​ይነ ርግብ መስ​ኮ​ቶች ነበ​ሩ​ባ​ቸው፤ ደግ​ሞም በደጀ ሰላሙ ውስጥ በዙ​ሪ​ያው መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ሁሉ ላይ የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ር​ጾ​ባ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="17">ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባ​ይም አገ​ባኝ፤ እነ​ሆም በአ​ደ​ባ​ባዩ ዙሪያ የተ​ሠሩ ዕቃ ቤቶ​ችና ወለል ነበሩ፤ በወ​ለ​ሉም ላይ ሠላሳ ዕቃ ቤቶች ነበሩ።</verse>
				<verse number="18">ወለ​ሉም በበ​ሮች አጠ​ገብ ነበረ፤ ይህም ታች​ኛው ወለል እንደ በሮቹ ርዝ​መት መጠን ነበረ።</verse>
				<verse number="19">ከታ​ች​ኛ​ውም በር ፊት ጀምሮ እስከ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ ፊት ድረስ ወር​ዱን አንድ መቶ ክንድ አድ​ርጎ ወደ ምሥ​ራ​ቅና ወደ ሰሜን ለካ።</verse>
				<verse number="20">ወደ ሰሜ​ንም መራኝ፤ እነ​ሆም በው​ጭው አደ​ባ​ባይ ያለ ወደ ሰሜን የሚ​መ​ለ​ከት በር ነበረ፤ ርዝ​መ​ቱ​ንና ወር​ዱ​ንም ለካ።</verse>
				<verse number="21">የዕቃ ቤቶ​ቹም በዚህ በኩል ሦስት፥ በዚ​ያም በኩል ሦስት ነበሩ፤ የግ​ንቡ አዕ​ማ​ድና መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም፥ ወደ ምሥ​ራቅ የሚ​ያ​ሳዩ ዘን​ባ​ባ​ዎ​ቹም አምሳ ክንድ ነበሩ፤ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="22">መስ​ኮ​ቶ​ቹም፥ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም፥ የዘ​ን​ባባ ዛፎ​ቹም ወደ ምሥ​ራቅ እን​ደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር ልክ ነበሩ፤ ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ደ​ርሱ ሰባት ደረ​ጃ​ዎች ነበሩ፤ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም በፊቱ ነበሩ።</verse>
				<verse number="23">በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በሰ​ሜ​ኑና በም​ሥ​ራቁ በኩል በሌ​ላው በር አን​ጻር በር ነበረ፤ ከበ​ርም እስከ በር አንድ መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ።</verse>
				<verse number="24">ወደ ደቡ​ብም መራኝ፤ እነ​ሆም ወደ ደቡብ የሚ​መ​ለ​ከት በር ነበረ፤ የግ​ን​ቡን አዕ​ማ​ድና መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹ​ንም እን​ደ​ዚ​ያው መጠን አድ​ርጎ ለካ።</verse>
				<verse number="25">በእ​ር​ሱና በመ​ዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ዙሪያ እንደ እነ​ዚያ መስ​ኮ​ቶች የሚ​መ​ስሉ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ ርዝ​መቱ አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="26">ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ደ​ርሱ ሰባት ደረ​ጃ​ዎች ነበሩ፤ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም በፊቱ ነበሩ፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ላይ አንዱ በዚህ አን​ዱም በዚያ ወገን ሆኖ የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ር​ጾ​ባ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="27">በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በደ​ቡብ በኩል በር ነበረ፤ ከበር እስከ በር ድረስ በደ​ቡብ በኩል መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ።</verse>
				<verse number="28">በደ​ቡ​ብም በር በኩል ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ አገ​ባኝ፤ እን​ደ​ዚ​ያ​ውም መጠን አድ​ርጎ የደ​ቡ​ብን በር ለካ፤</verse>
				<verse number="29">እን​ደ​ዚ​ያ​ውም መጠን አድ​ርጎ የዕቃ ቤቶ​ቹ​ንና የግ​ን​ቡን አዕ​ማድ፥ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለካ፤ በእ​ር​ሱና በመ​ዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ዙሪያ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ ርዝ​መቱ አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="30">በዙ​ሪ​ያ​ውም ደጀ ሰላ​ሞች ነበሩ፤ ርዝ​መ​ታ​ቸ​ውም ሃያ አም​ስት ክንድ፥ ወር​ዳ​ቸ​ውም አም​ስት ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="31">መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ወደ ውጭው አደ​ባ​ባይ ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ላይ የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ርጾ ነበር፤ ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ደ​ርሱ ስም​ንት ደረ​ጃ​ዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="32">በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በም​ሥ​ራቅ በኩል አገ​ባኝ፤ በሩ​ንም ለካ፤ መጠ​ኑም እንደ እነ​ዚያ ነበረ።</verse>
				<verse number="33">እን​ደ​ዚ​ያም መጠን የዕቃ ቤቶ​ቹ​ንና የግ​ን​ቡን አዕ​ማድ፥ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ለካ፤ በእ​ር​ሱና በመ​ዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ዙሪያ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ ርዝ​መ​ቱም አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="34">መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም በስተ ውጭ ወደ አለው አደ​ባ​ባይ ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ላይ በዚ​ህና በዚያ ወገን የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ርጾ ነበር፤ ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ደ​ርሱ ስም​ንት ደረ​ጃ​ዎች ነበ​ሩት።</verse>
				<verse number="35">በሰ​ሜ​ንም ወደ አለው በር አመ​ጣኝ፤ እን​ደ​ዚ​ያ​ውም መጠን ለካው፤</verse>
				<verse number="36">የዕቃ ቤቶ​ቹ​ንና የግ​ን​ቡን አዕ​ማድ፥ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ለካ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም መስ​ኮ​ቶች ነበ​ሩ​በት፤ ርዝ​መ​ቱም አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="37">የግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ወደ ውጭው አደ​ባ​ባይ ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ላይ በዚ​ህና በዚያ ወገን የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ርጾ ነበር፤ ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ወጡ ስም​ንት ደረ​ጃ​ዎች ነበ​ሩት።</verse>
				<verse number="38">በበ​ሮ​ቹም በግ​ንቡ አዕ​ማድ አጠ​ገብ ዕቃ ቤቱና መዝ​ጊ​ያው ነበሩ፤ በዚ​ያም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያጥቡ ነበር።</verse>
				<verse number="39">የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት፥ የኀ​ጢ​አ​ቱ​ንና የበ​ደ​ሉ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ያር​ዱ​ባ​ቸው ዘንድ፥ በበሩ ደጀ ሰላም በዚህ ወገን ሁለት ገበ​ታ​ዎች፥ በዚ​ያም ወገን ሁለት ገበ​ታ​ዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="40">በሰ​ሜን በኩል በአ​ለው በር በስ​ተ​ው​ጭው፥ በመ​ወ​ጣ​ጫው ደረ​ጃ​ዎች አጠ​ገብ፥ በአ​ንዱ ወገን ሁለት ገበ​ታ​ዎች ነበሩ፤ በሌ​ላ​ውም ወገን በበሩ ደጀ ሰላም በኩል ሁለት ገበ​ታ​ዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="41">በበሩ አጠ​ገብ በዚህ ወገን አራት ገበ​ታ​ዎች፥ በዚ​ያም ወገን አራት ገበ​ታ​ዎች ነበሩ፤ መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ር​ዱ​ባ​ቸው ገበ​ታ​ዎች ስም​ንት ነበሩ።</verse>
				<verse number="42">ስለ​ሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም መሥ​ዋ​ዕት ርዝ​መ​ታ​ቸው አንድ ክንድ ተኩል ወር​ዳ​ቸ​ውም አንድ ክንድ ተኩል ቁመ​ታ​ቸ​ውም አንድ ክንድ የሆኑ፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ሌላ​ውን መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ር​ዱ​በ​ትን ዕቃ ያኖ​ሩ​ባ​ቸው ዘንድ፥ ከተ​ጠ​ረበ ድን​ጋይ የተ​ሠሩ አራት ገበ​ታ​ዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="43">በዙ​ሪ​ያ​ውም በስ​ተ​ው​ስጥ የነ​በ​ረው የለ​ዘበ ከን​ፈ​ራ​ቸው አንድ ጋት ነበረ፤ በገ​በ​ታ​ውም ላይ መክ​ደኛ ነበረ፤ ከፀ​ሐ​ይና ከዝ​ና​ምም የተ​ሰ​ወረ ነበረ።</verse>
				<verse number="44">ወደ ውስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ አገ​ባኝ፤ እነ​ሆም ሁለት ቤቶች ነበሩ፤ አንዱ ወደ ሰሜን በሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር አጠ​ገብ ነበረ፤ መግ​ቢ​ያ​ውም ወደ ደቡብ ይመ​ለ​ከት ነበረ፤ ሌላ​ውም ወደ ደቡብ በሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር አጠ​ገብ ነበረ፤ መግ​ቢ​ያ​ውም ወደ ሰሜን ይመ​ለ​ከት ነበር።</verse>
				<verse number="45">ሰው​ዬ​ውም፥ “ይህ ወደ ደቡብ የሚ​መ​ለ​ከት ቤት ለማ​ገ​ል​ገል ለሚ​ተጉ ካህ​ናት ነው።</verse>
				<verse number="46">ወደ ሰሜ​ንም የሚ​መ​ለ​ከ​ተው ቤት መሠ​ዊ​ያ​ዉን ለማ​ገ​ል​ገል ለሚ​ተጉ ካህ​ናት ነው፤ እነ​ዚህ ከሌዊ ልጆች መካ​ከል ያገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ርቡ የሳ​ዶቅ ልጆች ናቸው” አለኝ።</verse>
				<verse number="47">አደ​ባ​ባ​ዩ​ንም በአ​ራት ማዕ​ዘኑ ርዝ​መ​ቱን መቶ ክንድ፥ ወር​ዱ​ንም መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ መሠ​ዊ​ያ​ውም በቤቱ ፊት ነበረ።</verse>
				<verse number="48">ወደ ቤቱም ደጀ ሰላም አመ​ጣኝ፤ የደጀ ሰላ​ሙ​ንም የግ​ንብ አዕ​ማድ ወርድ በዚህ ወገን አም​ስት ክንድ፤ በዚ​ያም ወገን አም​ስት ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ የበ​ሩም ወርድ ዐሥራ አራት ክንድ ነበረ፤ በበ​ሩም በዚህ ወገ​ንና በዚያ ወገን የነ​በ​ሩት ግን​ቦች ሦስት ሦስት ክንድ ነበሩ።</verse>
				<verse number="49">የደጀ ሰላ​ሙም ርዝ​መት ሃያ ክንድ፥ ወር​ዱም ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፥ ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ደ​ርሱ ዐሥር ደረ​ጃ​ዎች ነበሩ፤ አንድ በዚህ ወገን፥ አን​ድም በዚያ ወገን ሆነው በመ​ቃ​ኖቹ አጠ​ገብ የግ​ንብ አዕ​ማድ ነበሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="41">
				<verse number="1">ወደ መቅ​ደ​ሱም አገ​ባኝ፤ የግ​ን​ቡ​ንም አዕ​ማድ ወርድ በዚህ ወገን ስድ​ስት ክንድ፥ በዚ​ያም ወገን ስድ​ስት ክንድ አድ​ርጎ ለካ።</verse>
				<verse number="2">የመ​ግ​ቢ​ያ​ውም ወርድ ዐሥር ክንድ ነበረ፤ የመ​ግ​ቢ​ያ​ውም መቃ​ኖች በዚህ ወገን አም​ስት ክንድ፥ በዚ​ያም ወገን አም​ስት ክንድ ነበሩ፤ ርዝ​መ​ቱ​ንም አርባ ክንድ፥ ወር​ዱ​ንም ሃያ ክንድ አድ​ርጎ ለካ።</verse>
				<verse number="3">ወደ ውስ​ጥም ገባ፤ የመ​ግ​ቢ​ያ​ው​ንም የግ​ንብ አዕ​ማድ ወርድ ሁለት ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ የመ​ግ​ቢ​ያ​ውም ወርድ ስድ​ስት ክንድ ነበረ፤ የመ​ግ​ቢ​ያ​ውም ግንብ ወርድ በዚህ ወገን ሰባት ክንድ፥ በዚ​ያም ወገን ሰባት ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="4">በመ​ቅ​ደ​ሱም ፊት ርዝ​መ​ቱን አርባ ክንድ፥ ወር​ዱ​ንም ሃያ ክንድ አድ​ርጎ ለካና፥ “ይህ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳን ነው” አለኝ።</verse>
				<verse number="5">የመ​ቅ​ደ​ሱ​ንም ግንብ ስድ​ስት ክንድ፥ በመ​ቅ​ደ​ሱም ዙሪያ ሁሉ ያሉ​ትን የጓ​ዳ​ዎ​ቹን ሁሉ ወርድ አራት ክንድ አድ​ርጎ ለካ።</verse>
				<verse number="6">ጓዳ​ዎ​ቹም አንዱ ከአ​ንዱ በላይ በሦ​ስት ደርብ ነበሩ፤ በእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ደርብ ሠላሳ ጓዳ​ዎች ነበሩ። በመ​ቅ​ደ​ሱም ግንብ ዙሪያ ደገ​ፋ​ዎች ይሆኑ ዘንድ አረ​ፍ​ቶች ነበሩ፤ ከመ​ቅ​ደሱ ግንብ ጋር ግን​አ​ል​ተ​ያ​ያ​ዙም ነበር።</verse>
				<verse number="7">በቤ​ቱም ዙሪያ ባለ ግንብ ውስጥ በነ​በ​ሩት አረ​ፍ​ቶች ምክ​ን​ያት ላይ​ኞቹ ጓዳ​ዎች ከታ​ች​ኞቹ ጓዳ​ዎች ይበ​ልጡ ነበር፤ ከታ​ች​ኛ​ውም ደርብ ወደ መካ​ከ​ለ​ኛው፥ ከመ​ካ​ከ​ለ​ኛ​ውም ደርብ ወደ ሦስ​ተ​ኛው የሚ​ወ​ጣ​በት ደረጃ ነበረ።</verse>
				<verse number="8">ለመ​ቅ​ደ​ሱም ከፍ ያለ ወለል በዙ​ሪ​ያው እን​ዳ​ለው አየሁ፤ የጓ​ዳ​ዎ​ቹም መሠ​ረት ቁመቱ ሙሉ ዘንግ የሚ​ያ​ህል ስድ​ስት ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="9">የጓ​ዳ​ዎ​ቹም የው​ጭው ግንብ ወርድ አም​ስት ክንድ ነበረ፤ በመ​ቅ​ደ​ሱም ጓዳ​ዎች አጠ​ገብ የቀረ አንድ ባዶ ስፍራ ነበረ።</verse>
				<verse number="10">በዕቃ ቤቶ​ቹም መካ​ከል ወርዱ በቤቱ ዙሪያ ሁሉ ሃያ ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="11">የጓ​ዳ​ዎ​ቹም መግ​ቢያ ብቻ​ውን ወደ​ሚ​ኖ​ረው ስፍራ ነበረ፤ አንዱ ደጅ ወደ ሰሜን መን​ገድ፤ አን​ዱም ደጅ ወደ ደቡብ መን​ገድ፥ ብቻ​ውን የሚ​ኖ​ረው ስፍራ ወርዱ አም​ስት ክንድ በዙ​ሪ​ያው ነበር።</verse>
				<verse number="12">በም​ዕ​ራ​ብም በኩል በልዩ ስፍራ አን​ጻር የነ​በረ ግቢ ስፋቱ ሰባ ክንድ ነበረ። በግ​ቢ​ውም ዙሪያ የነ​በረ ግንብ ወርዱ አም​ስት ክንድ፥ ርዝ​መ​ቱም ዘጠና ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="13">የቤተ መቅ​ደ​ሱ​ንም ርዝ​መት መቶ ክንድ፥ የል​ዩ​ውን ስፍ​ራና ግቢ​ውን ከግ​ንቡ ጋር አንድ መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ።</verse>
				<verse number="14">ደግ​ሞም በም​ሥ​ራቅ በኩል የነ​በ​ረ​ውን የቤተ መቅ​ደ​ሱ​ንና የል​ዩ​ውን ስፍራ ወር​ድና ቁመት አንድ መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ።</verse>
				<verse number="15">ወደ​ኋ​ላ​ውም በአ​ለው በልዩ ስፍራ አን​ጻር የነ​በ​ረ​ውን የግ​ቢ​ውን ርዝ​መት፥ በዚ​ህና በዚያ ከነ​በ​ሩት ከግ​ን​ቦቹ ጋር አንድ መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ የው​ስ​ጡ​ንም መቅ​ደስ፥ የአ​ዳ​ራ​ሹ​ንም መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎች ለካ።</verse>
				<verse number="16">መድ​ረ​ኮቹ፥ መስ​ኮ​ቶ​ቹና አዕ​ማዱ፥ በስ​ተ​ው​ስጥ ያለው ክፍል ደጀ ሰላ​ሙም በእ​ን​ጨት ተለ​ብ​ጠው ነበር፤ በሦ​ስ​ቱም ዙሪያ የዐ​ይነ ርግብ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ። መቅ​ደ​ሱም በመ​ድ​ረኩ አን​ጻር ከመ​ሬት ጀምሮ እስከ መስ​ኮ​ቶቹ ድረስ በእ​ን​ጨት ተለ​ብጦ ነበር፤ መስ​ኮ​ቶ​ቹም የዐ​ይነ ርግብ ነበሩ፤</verse>
				<verse number="17">በደ​ጁም ላይ እስከ ውስ​ጠ​ኛው ክፍል ድረስ፥ በው​ጭም ግንቡ ሁሉ ውስ​ጡም፥ ውጭ​ውም ዙሪ​ያ​ውን ተለ​ብጦ ነበር።</verse>
				<verse number="18">ኪሩ​ቤ​ልና የዘ​ን​ባ​ባው ዛፎች ተቀ​ር​ጸ​ው​በት ነበር፤ የዘ​ን​ባ​ባ​ውም ዛፍ ከኪ​ሩ​ብና ከኪ​ሩብ መካ​ከል ነበረ፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ዱም ኪሩብ ሁለት ፊት ነበ​ረው።</verse>
				<verse number="19">በአ​ንድ ወገን ወደ አለው የዘ​ን​ባባ ዛፍ የሰው ፊት ይመ​ለ​ከት ነበር፤ በሌ​ላ​ውም ወገን ወደ አለው ዘን​ባባ የአ​ን​በሳ ፊት ይመ​ለ​ከት ነበር፤ በቤቱ ሁሉ ዙሪያ እን​ደ​ዚህ ተቀ​ርጾ ነበር።</verse>
				<verse number="20">ከመ​ሬት አን​ሥቶ እስከ ደጁ ራስ ድረስ ኪሩ​ቤ​ልና የዘ​ን​ባባ ዛፎች ተቀ​ር​ጸው ነበር፤ የመ​ቅ​ደሱ ግንብ እን​ደ​ዚህ ነበረ።</verse>
				<verse number="21">የመ​ቅ​ደሱ መቃ​ኖ​ችም አራት ማዕ​ዘን ነበሩ፤ የመ​ቅ​ደሱ ፊትም መልኩ እን​ደ​ሌ​ላው መልክ ነበረ።</verse>
				<verse number="22">መሠ​ዊ​ያ​ውም ቁመቱ ሦስት ክንድ፥ ርዝ​መቱ ሁለት ክንድ፥ ወር​ዱም ሁለት ክንድ ሆኖ ከእ​ን​ጨት ተሠ​ርቶ ነበር፤ ማዕ​ዘ​ኖ​ቹም፥ እግ​ሩም፥ አገ​ዳ​ዎ​ቹም ከእ​ን​ጨት ተሠ​ር​ተው ነበር፤ እር​ሱም፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያለ​ችው ገበታ ይህች ናት” አለኝ።</verse>
				<verse number="23">ለመ​ቅ​ደ​ሱና ለተ​ቀ​ደ​ሰው ስፍራ ሁለት መዝ​ጊ​ያ​ዎች ነበ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ መዝ​ጊ​ያም ሁለት ተዘ​ዋ​ዋሪ ሳን​ቃ​ዎች ነበ​ሩት፤ ለአ​ንዱ መዝ​ጊያ ሁለት፥ ለሌ​ላ​ውም መዝ​ጊያ ሁለት ሳን​ቃ​ዎች ነበ​ሩት።</verse>
				<verse number="25">በግ​ን​ቡም ላይ በተ​ቀ​ረ​ጹት ዓይ​ነት በእ​ነ​ዚህ በመ​ቅ​ደሱ መዝ​ጊ​ያ​ዎች ላይ ኪሩ​ቤ​ልና የዘ​ን​ባባ ዛፎች ተቀ​ር​ጸው ነበር፤ በስ​ተ​ው​ጭም በአ​ለው በደጀ ሰላሙ ፊት የእ​ን​ጨት መድ​ረክ ነበረ።</verse>
				<verse number="26">በደጀ ሰላ​ሙም በሁ​ለቱ ወገን በዚ​ህና በዚያ የዐ​ይነ ርግብ መስ​ኮ​ቶ​ችና የተ​ቀ​ረጹ የዘ​ን​ባባ ዛፎች ነበ​ሩ​በት፤ የመ​ቅ​ደ​ሱም ጓዳ​ዎ​ችና የእ​ን​ጨቱ መድ​ረክ እን​ዲሁ ነበሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="42">
				<verse number="1">በው​ጭም አደ​ባ​ባይ በሰ​ሜኑ መን​ገድ በም​ሥ​ራቅ በኩል አወ​ጣኝ፤ በል​ዩ​ውም ስፍራ አን​ጻ​ርና በሰ​ሜን በኩል በአ​ለው ግቢ ፊት ለፊት ወዳ​ሉት አም​ስት ዕቃ ቤቶች አገ​ባኝ።</verse>
				<verse number="2">መቶ ክንድ በሆ​ነው ርዝ​መት ፊት በሰ​ሜን በኩል መዝ​ጊያ ነበረ፤ ወር​ዱም አምሳ ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="3">በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በሃ​ያው ክንድ አን​ጻር፥ በው​ጭ​ውም አደ​ባ​ባይ በወ​ለሉ አን​ጻር በሦ​ስት ደርብ በት​ይዩ የተ​ሠራ መተ​ላ​ለ​ፊያ ነበረ።</verse>
				<verse number="4">በዕቃ ቤቶ​ቹም ፊት በስ​ተ​ው​ስጥ ወርዱ ዐሥር ክንድ፥ ርዝ​መቱ መቶ ክንድ የሆነ መን​ገድ ነበረ፤ መግ​ቢ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ሰሜን ይመ​ለ​ከቱ ነበር።</verse>
				<verse number="5">መተ​ላ​ለ​ፊ​ያ​ውም አሳ​ጥ​ሮ​አ​ቸ​ዋ​ልና ላይ​ኞቹ ዕቃ ቤቶች ከመ​ካ​ከ​ለ​ኞ​ቹና ከታ​ች​ኞቹ ይልቅ አጫ​ጭር ነበሩ።</verse>
				<verse number="6">በሦ​ስ​ትም ደርብ ተሠ​ር​ተው ነበ​ርና፥ በአ​ደ​ባ​ባ​ዩም እን​ዳ​ሉት አዕ​ማድ፥ አዕ​ማድ አል​ነ​በ​ሩ​ላ​ቸ​ው​ምና ስለ​ዚህ ከመ​ካ​ከ​ለ​ኞ​ቹና ከታ​ች​ኞቹ ይልቅ ጠባብ ነበሩ።</verse>
				<verse number="7">በውጭ በዕቃ ቤቶቹ አጠ​ገብ ያለው፥ ወደ ውጭው አደ​ባ​ባይ የሚ​ያ​መ​ለ​ክ​ተው ቅጥር፥ በዕቃ ቤቶች ትይዩ የሆነ ርዝ​መቱ አምሳ ክንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="8">በመ​ቅ​ደሱ ፊት የነ​በ​ሩት ዕቃ ቤቶች ርዝ​መ​ታ​ቸው መቶ ክንድ ሲሆን፥ በው​ጭው አደ​ባ​ባይ በኩል የነ​በ​ሩት ዕቃ ቤቶች ርዝ​መ​ታ​ቸው አምሳ ክንድ ነበ​ረና።</verse>
				<verse number="9">ከእ​ነ​ዚ​ህም ዕቃ ቤቶች በታች በስ​ተ​ም​ሥ​ራቅ በኩል፥ ሰው ከው​ጭው አደ​ባ​ባይ የሚ​ገ​ባ​በት መግ​ቢያ ነበረ፤ ይህም በቅ​ጥሩ ራስ አጠ​ገብ ነበረ።</verse>
				<verse number="10">በደ​ቡ​ብም በኩል በል​ዩው ስፍ​ራና በግ​ቢው አን​ጻር ዕቃ ቤቶች ነበሩ።</verse>
				<verse number="11">በስ​ተ​ፊ​ታ​ቸ​ውም የነ​በረ መን​ገድ በሰ​ሜን በኩል እንደ ነበ​ረው እንደ ዕቃ ቤቶቹ መን​ገድ አም​ሳል ነበር። ርዝ​መ​ታ​ቸ​ውም፥ ወር​ዳ​ቸ​ውም፥ መው​ጫ​ቸ​ውም፥ ሥር​ዐ​ታ​ቸ​ውም፥ መዝ​ጊ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም በዚ​ያው ልክ ነበሩ።</verse>
				<verse number="12">በደ​ቡ​ብም በኩል ከአ​ሉት ዕቃ ቤቶች በታች በም​ሥ​ራቅ በኩል በቅ​ጥሩ ራስ አጠ​ገብ መግ​ቢያ በር ነበር።</verse>
				<verse number="13">እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “በልዩ ስፍራ አን​ጻር በሰ​ሜ​ንና በደ​ቡብ በኩል ያሉ ዕቃ ቤቶች፥ እነ​ርሱ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ርቡ የሳ​ዶቅ ልጆች ካህ​ናቱ ከሁሉ ይልቅ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ምግብ የሚ​በ​ሉ​ባ​ቸው ቤቶች ናቸው። ስፍ​ራው ቅዱስ ነውና በዚያ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ነገር፥ የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የኀ​ጢ​አ​ቱ​ንና የበ​ደ​ሉን መሥ​ዋ​ዕት ያኖ​ራሉ።</verse>
				<verse number="14">ካህ​ና​ቱም በገቡ ጊዜ ከመ​ቅ​ደሱ በው​ጭው አደ​ባ​ባይ አይ​ወ​ጡም፤ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ትን ልብ​ሳ​ቸ​ውን ግን ቅዱስ ነውና በዚያ ያኖ​ሩ​ታል፤ ሌላም ልብስ ለብ​ሰው ወደ ሕዝብ ይወ​ጣሉ።”</verse>
				<verse number="15">ውስ​ጠ​ኛ​ው​ንም ቤት ለክቶ በፈ​ጸመ ጊዜ ወደ ምሥ​ራቅ በሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር መን​ገድ አወ​ጣኝ፤ እር​ሱ​ንም ዙሪ​ያ​ውን ለካው።</verse>
				<verse number="16">ወደ ምሥ​ራቅ በሚ​መ​ለ​ከ​ተ​ውም በር ኋላ ቆመ፤ የም​ሥ​ራ​ቁን ወገን በመ​ለ​ኪያ ዘንግ አም​ስት መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ።</verse>
				<verse number="17">ወደ ሰሜ​ንም ዞረ፤ የሰ​ሜ​ኑ​ንም ወገን በመ​ለ​ኪያ ዘንግ አም​ስት መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ።</verse>
				<verse number="18">ወደ ደቡ​ብም ዞረ፤ የደ​ቡ​ቡ​ንም ወገን በመ​ለ​ኪያ ዘንግ አም​ስት መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ።</verse>
				<verse number="19">ወደ ምዕ​ራ​ብም ዞረ፤ የም​ዕ​ራ​ቡ​ንም ወገን በመ​ለ​ኪያ ዘንግ አም​ስት መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ።</verse>
				<verse number="20">በአ​ራ​ቱም ወገን ለካ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንና ያል​ተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ይለይ ዘንድ ርዝ​መቱ አም​ስት መቶ ክንድ፥ ወር​ዱም አም​ስት መቶ ክንድ የሆነ ቅጥር በዙ​ሪ​ያው ነበረ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="43">
				<verse number="1">ወደ ምሥ​ራ​ቅም ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር አመ​ጣኝ።</verse>
				<verse number="2">እነ​ሆም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ክብር ከም​ሥ​ራቅ መን​ገድ መጣ፤ ድም​ፁም እንደ ብዙ ውኆች ይተ​ምም ነበር፤ ከክ​ብ​ሩም የተ​ነሣ ምድር ታበራ ነበር።</verse>
				<verse number="3">ያየ​ሁ​ትም ራእይ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ለማ​ጥ​ፋት በመ​ጣሁ ጊዜ እንደ አየ​ሁት ራእይ ነበረ፤ ራእ​ዩም በኮ​ቦር ወንዝ እን​ደ​አ​የ​ሁት ራእይ ነበረ፤ እኔም በግ​ም​ባሬ ተደ​ፋሁ።</verse>
				<verse number="4">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ወደ ምሥ​ራቅ በሚ​መ​ለ​ከት በር ወደ መቅ​ደሱ ገባ።</verse>
				<verse number="5">መን​ፈ​ስም አነ​ሣኝ፤ ወደ ውስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ አገ​ባኝ፤ እነ​ሆም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር መቅ​ደ​ሱን መል​ቶት ነበር።</verse>
				<verse number="6">በመ​ቅ​ደ​ሱም ሆኖ የሚ​ና​ገ​ረ​ኝን ሰማሁ፤ በአ​ጠ​ገ​ቤም ሰው ቆሞ ነበር።</verse>
				<verse number="7">እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለዘ​ለ​ዓ​ለም የም​ቀ​መ​ጥ​በት የዙ​ፋኔ ስፍ​ራና የእ​ግሬ ጫማ መረ​ገጫ ይህ ነው። ዳግ​መ​ኛም የእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸው በዝ​ሙ​ታ​ቸ​ውና በከ​ፍ​ታ​ዎ​ቻ​ቸው በአ​ለው በነ​ገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸው ሬሳ ቅዱስ ስሜን አያ​ረ​ክ​ሱም።</verse>
				<verse number="8">መድ​ረ​ካ​ቸ​ውን በመ​ድ​ረኬ አጠ​ገብ፥ መቃ​ና​ቸ​ው​ንም በመ​ቃኔ አጠ​ገብ አድ​ር​ገ​ዋ​ልና። በእ​ኔና በእ​ነ​ርሱ መካ​ከል ግንብ ብቻ ነበረ፤ በሠ​ሩ​ትም ርኵ​ሰት ቅዱስ ስሜን አረ​ከሱ፤ ስለ​ዚህ በቍ​ጣዬ አጠ​ፋ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">አሁ​ንም ዝሙ​ታ​ቸ​ው​ንና የነ​ገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሬሳ ከእኔ ዘንድ ያርቁ፤ እኔም ለዘ​ለ​ዓ​ለም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አድ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ሥራ​ቸ​ው​ንና ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይተዉ ዘንድ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ይህን ቤት አሳ​ያ​ቸው፤ አም​ሳ​ያ​ው​ንም ይለኩ።</verse>
				<verse number="11">እነ​ር​ሱም ስለ ሠሩት ሥራ ሁሉ መቅ​ሠ​ፍ​ታ​ቸ​ውን ያገ​ኛሉ፤ አን​ተም የቤ​ቱን መል​ክና ምሳ​ሌ​ውን፥ መው​ጫ​ው​ንም፥ መግ​ቢ​ያ​ው​ንም፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም፥ ሕጉ​ንም ሁሉ አስ​ታ​ው​ቃ​ቸው፤ ሥር​ዐ​ቱ​ንና ሕጉን ሁሉ ይጠ​ብቁ ዘንድ፥ ያደ​ር​ጉ​ትም ዘንድ በፊ​ታ​ቸው ጻፈው።</verse>
				<verse number="12">በተ​ራ​ራው ራስ ላይ ያለ​ውን ቤቱ​ንና የቤ​ቱን ሥር​ዐት ሣል፤ የዙ​ሪ​ያ​ውም ዳርቻ ሁሉ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው። እነሆ የቤቱ ሕግ ይህ ነው።”</verse>
				<verse number="13">የመ​ሠ​ዊ​ያው ልክ በክ​ንድ ይህ ነው፤ ክን​ዱም ክንድ ተጋት ነው። የመ​ሠ​ረ​ቱም ቁመቱ አንድ ክንድ፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ ነው፤ አንድ ስን​ዝ​ርም ክፈፍ ዳር ዳሩን በዙ​ሪ​ያው አለ፤ የመ​ሠ​ዊ​ያው ቁመት እን​ዲሁ ነው።</verse>
				<verse number="14">በመ​ሬ​ቱም ላይ ከአ​ለው መሠ​ረት ጀምሮ እስከ ታች​ኛው እር​ከን ድረስ ሁለት ክንድ፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ ነው፤ ከት​ን​ሹም እር​ከን ጀምሮ እስከ ትልቁ እር​ከን ድረስ አራት ክንድ፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ ነው።</verse>
				<verse number="15">ምድ​ጃ​ውም አራት ክንድ ነው፤ በም​ድ​ጃ​ውም ላይ አንድ ክንድ ወደ ላይ ከፍ የሚሉ አራት ቀን​ዶች አሉ​በት።</verse>
				<verse number="16">የም​ድ​ጃ​ውም ርዝ​መት ዐሥራ ሁለት ክንድ፥ ወር​ዱም ዐሥራ ሁለት ክንድ ነው፥ አራ​ቱም ማዕ​ዘን ትክ​ክል ነው።</verse>
				<verse number="17">የእ​ር​ከ​ኑም ርዝ​መት ዐሥራ አራት ክንድ፥ ወር​ዱም ዐሥራ አራት ክንድ ነው፤ አራ​ቱም መዐ​ዝን ትክ​ክል ነው፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ያለው ክፈፍ የክ​ንድ እኩ​ሌታ ነው፤ መሠ​ረ​ቱም በዙ​ሪ​ያው አንድ ክንድ ነው፤ ደረ​ጃ​ዎ​ቹም ወደ ምሥ​ራቅ ይመ​ለ​ከ​ታሉ።”</verse>
				<verse number="18">እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡ​በት ዘንድ፥ ደሙ​ንም ይረ​ጩ​በት ዘንድ በሚ​ሠ​ሩ​በት ቀን የመ​ሠ​ዊ​ያው ሕግ ይህ ነው።</verse>
				<verse number="19">ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ለሚ​ቀ​ርቡ ከሳ​ዶቅ ዘር ለሚ​ሆኑ ለሌ​ዋ​ው​ያኑ ካህ​ናት ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን ከመ​ን​ጋው አንድ ወይ​ፈን ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="20">ከደ​ሙም ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ በአ​ራቱ የመ​ሠ​ዊያ ቀን​ዶ​ቹም፥ በእ​ር​ከ​ኑም በአ​ራቱ ማዕ​ዘን ላይ፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም በአ​ለው ክፈፍ ላይ ትረ​ጨ​ዋ​ለህ፤ እን​ዲሁ ታነ​ጻ​ዋ​ለህ፤ ታስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ት​ማ​ለህ።</verse>
				<verse number="21">ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን ወይ​ፈን ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ በመ​ቅ​ደ​ሱም ውጭ በቤቱ በተ​ለ​የው ስፍራ ይቃ​ጠ​ላል።</verse>
				<verse number="22">በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን ነውር የሌ​ለ​በ​ትን አውራ ፍየል ታቀ​ር​ባ​ለህ፤ በወ​ይ​ፈ​ኑም እን​ዳ​ነ​ጹት እን​ዲሁ መሠ​ዊ​ያ​ውን ያነ​ጹ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="23">ማን​ጻ​ቱ​ንም ከፈ​ጸ​ምህ በኋላ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ወይ​ፈን፥ ከበ​ጎ​ችም ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ጠቦት በግ ታቀ​ር​ባ​ለህ፤</verse>
				<verse number="24">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ታቀ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ካህ​ና​ቱም ጨው ይጨ​ም​ሩ​ባ​ቸ​ዋል፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ር​ቡ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="25">ሰባት ቀንም በየ​ዕ​ለቱ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን አውራ ፍየል ታቀ​ር​ባ​ለህ፤ ነው​ርም የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን አንድ ወይ​ፈ​ንና ከበ​ጎ​ችም አንድ ጠቦት በግ ያቀ​ር​ባሉ።</verse>
				<verse number="26">ሰባት ቀን ለመ​ሠ​ዊ​ያው ያስ​ተ​ሠ​ር​ያሉ፤ ያነ​ጹ​ታል፤ ይቀ​ድ​ሱ​ት​ማል።</verse>
				<verse number="27">ቀኖ​ቹ​ንም በፈ​ጸሙ ጊዜ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ከዚ​ያም በኋላ ካህ​ናቱ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያደ​ር​ጋሉ፤ እኔም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="44">
				<verse number="1">ወደ ምሥ​ራ​ቅም ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው በስተ ውጭ ወደ አለው ወደ መቅ​ደሱ በር መለ​ሰኝ፤ ተዘ​ግ​ቶም ነበር።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ይህች በር ተዘ​ግታ ትኖ​ራ​ለች እንጂ አት​ከ​ፈ​ትም፤ ሰውም አይ​ገ​ባ​ባ​ትም፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገብ​ቶ​ባ​ታ​ልና ተዘ​ግታ ትኖ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="3">አለ​ቃው ግን እርሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ጀራ ይበላ ዘንድ ይቀ​መ​ጥ​ባ​ታል፤ በበሩ ይገ​ባል፤ በዚ​ያም መን​ገድ ይወ​ጣል።”</verse>
				<verse number="4">በሰ​ሜ​ኑም በር መን​ገድ በቤቱ ፊት አገ​ባኝ፤ እኔም አየሁ እነ​ሆም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መል​ቶት ነበር፤ እኔም በግ​ም​ባሬ ተደ​ፋሁ።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ልብ አድ​ርግ፤ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ሥር​ዐ​ትና ሕግ ሁሉ የም​ነ​ግ​ር​ህን ሁሉ በዐ​ይ​ንህ ተመ​ል​ከት፤ በጆ​ሮ​ህም ስማ፤ የቤ​ቱ​ንም መግ​ቢያ፥ የመ​ቅ​ደ​ሱ​ንም መውጫ ሁሉ ልብ አድ​ርግ።</verse>
				<verse number="6">ለዐ​መ​ፀ​ኛው ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እን​ዲህ በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ርኵ​ሰ​ታ​ችሁ ሁሉ ይብ​ቃ​ችሁ።</verse>
				<verse number="7">እን​ጀ​ራ​ዬን፥ ስብ​ንና ደምን በም​ታ​ቀ​ር​ቡ​በት ጊዜ በመ​ቅ​ደሴ ውስጥ ይሆኑ ዘንድ ቤቴ​ንም ያረ​ክሱ ዘንድ፥ በል​ባ​ቸ​ውና በሥ​ጋ​ቸው ያል​ተ​ገ​ረ​ዙ​ትን እን​ግ​ዶ​ችን ሰዎች አግ​ብ​ታ​ች​ኋ​ልና፥ በር​ኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ሁሉ ቃል ኪዳ​ኔን አፍ​ር​ሳ​ች​ኋ​ልና።</verse>
				<verse number="8">የመ​ቅ​ደ​ሴን ሥር​ዐት አል​ጠ​በ​ቃ​ች​ሁም፤ ነገር ግን የመ​ቅ​ደ​ሴን ሥር​ዐት የሚ​ጠ​ብቁ ሌሎ​ችን ለራ​ሳ​ችሁ ሾማ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="9">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ከአ​ሉት ሁሉ በል​ቡና በሥ​ጋው ያል​ተ​ገ​ረዘ የባ​ዕድ ልጅ እን​ግዳ ሁሉ ወደ መቅ​ደሴ አይ​ግባ።</verse>
				<verse number="10">ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም በሳቱ ጊዜ ጣዖ​ታ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለው ከእኔ ዘንድ የሳቱ ሌዋ​ው​ያን ሳይ​ቀር ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይሸ​ከ​ማሉ።</verse>
				<verse number="11">ነገር ግን በመ​ቅ​ደሴ ውስጥ አገ​ል​ጋ​ዮች ይሆ​ናሉ፤ በቤ​ቱም በሮች በረ​ኞች ይሆ​ናሉ፤ በቤ​ቱም ውስጥ ያገ​ለ​ግ​ላሉ፤ ለሕ​ዝ​ቡም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ሌላ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ይሠ​ዋሉ፤ ያገ​ለ​ግ​ሉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ በፊ​ታ​ቸው ይቆ​ማሉ።</verse>
				<verse number="12">በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ፊት አገ​ል​ግ​ለ​ዋ​ቸው ነበ​ሩና፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት የኀ​ጢ​አት እን​ቅ​ፋት ሆነ​ዋ​ልና ስለ​ዚህ እጄን በላ​ያ​ቸው አን​ሥ​ቻ​ለሁ፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይሸ​ከ​ማሉ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="13">እኔ​ንም በክ​ህ​ነት ለማ​ገ​ል​ገል ወደ እኔ አይ​ቀ​ር​ቡም፤ ወደ ተቀ​ደ​ሰ​ውም ነገ​ሬና ወደ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳን ነገር አይ​ቀ​ር​ቡም፤ እፍ​ረ​ታ​ቸ​ው​ንና የሠ​ሩ​ት​ንም ርኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውን ይሸ​ከ​ማሉ።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን ለአ​ገ​ል​ግ​ሎቱ ሁሉና በእ​ርሱ ውስጥ ለሚ​ደ​ረ​ገው ሁሉ የቤ​ቱን ሥር​ዐት ጠባ​ቂ​ዎች አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">“ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከእኔ ዘንድ በሳቱ ጊዜ የመ​ቅ​ደ​ሴን ሥር​ዐት የጠ​በቁ የሳ​ዶቅ ልጆች ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ይቀ​ር​ባሉ፤ ስቡ​ንና ደሙ​ንም ወደ እኔ ያቀ​ርቡ ዘንድ በፊቴ ይቆ​ማሉ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="16">ወደ መቅ​ደ​ሴም ይገ​ባሉ፤ ያገ​ለ​ግ​ሉ​ኝም ዘንድ ወደ ገበ​ታዬ ይቀ​ር​ባሉ፤ ሥር​ዐ​ቴ​ንም ይጠ​ብ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="17">ወደ ውስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በር በገቡ ጊዜ የተ​ልባ እግር ልብስ ይል​በሱ፤ በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በርና በቤቱ ውስጥ በአ​ገ​ለ​ገሉ ጊዜ ከበግ ጠጕር አን​ዳች ነገር በላ​ያ​ቸው አይ​ሁን።</verse>
				<verse number="18">በራ​ሳ​ቸው ላይ የተ​ልባ እግር መጠ​ም​ጠ​ሚያ ይሁን፤ በወ​ገ​ባ​ቸ​ውም ላይ የተ​ልባ እግር ሱሪ ይሁን፤ የሚ​ያ​ልብ ነገር አይ​ታ​ጠቁ።</verse>
				<verse number="19">ወደ ውጭ​ውም አደ​ባ​ባይ ወደ ሕዝብ በወጡ ጊዜ ያገ​ለ​ገ​ሉ​በ​ትን ልብ​ሳ​ቸ​ውን ያው​ልቁ፤ በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ዕቃ ቤት ውስጥ ያኑ​ሩት፤ ሕዝ​ቡ​ንም በል​ብ​ሳ​ቸው እን​ዳ​ይ​ቀ​ድሱ ሌላ​ውን ልብስ ይል​በሱ።</verse>
				<verse number="20">ራሳ​ቸ​ው​ንም አይ​ላጩ፥ የራ​ሳ​ቸ​ው​ንም ጠጕር ይከ​ር​ከሙ እንጂ ጠጕ​ራ​ቸ​ውን አያ​ሳ​ድጉ።</verse>
				<verse number="21">ካህ​ና​ቱም ሁሉ በው​ስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ ሲገቡ የወ​ይን ጠጅ አይ​ጠጡ።</verse>
				<verse number="22">መበ​ለ​ቲ​ቱ​ንና የተ​ፈ​ታ​ች​ይ​ቱን አያ​ግቡ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ዘር ግን ድን​ግ​ሊ​ቱን ወይም የካ​ህን ሚስት የነ​በ​ረ​ች​ይ​ቱን መበ​ለት ያግቡ።</verse>
				<verse number="23">በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውና ባል​ተ​ቀ​ደ​ሰው መካ​ከል ይለዩ ዘንድ ሕዝ​ቤን ያስ​ተ​ምሩ፤ ንጹ​ሕና ንጹሕ ባል​ሆ​ነው መካ​ከል ይለዩ ዘንድ ያሳ​ዩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">ክር​ክ​ርም በሆነ ጊዜ ለመ​ፍ​ረድ ይቁሙ፤ እንደ ፍርዴ ይፍ​ረዱ፤ በበ​ዓ​ላቴ ሁሉ ሕጌ​ንና ሥር​ዐ​ቴን ይጠ​ብቁ፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ይቀ​ድሱ።</verse>
				<verse number="25">እን​ዳ​ይ​ረ​ክ​ሱም ወደ ሞተ ሰው አይ​ግቡ፤ ነገር ግን ለአ​ባት፥ ወይም ለእ​ናት፥ ወይም ለወ​ንድ ልጅ፥ ወይም ለሴት ልጅ፥ ወይም ለወ​ን​ድም፥ ወይም ላል​ተ​ዳ​ረች እኅት ይር​ከሱ።</verse>
				<verse number="26">ከነ​ጻም በኋላ ሰባት ቀን ይቍ​ጠ​ሩ​ለት።</verse>
				<verse number="27">በመ​ቅ​ደ​ስም ውስጥ ያገ​ለ​ግል ዘንድ ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ ወደ መቅ​ደሱ በሚ​ገ​ባ​በት ቀን የኀ​ጢ​አ​ትን መሥ​ዋ​ዕት ያቅ​ርብ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="28">“ርስት አይ​ሆ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ እኔ ርስ​ታ​ቸው ነኝ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዘንድ ርስት አት​ስ​ጡ​አ​ቸው፤ እኔ ርስ​ታ​ቸው ነኝ፤</verse>
				<verse number="29">የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ንና የኀ​ጢ​አ​ትን መሥ​ዋ​ዕት የን​ስ​ሓ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ይበ​ላሉ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ እርም የሆ​ነው ነገር ሁሉ ለእ​ነ​ርሱ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="30">የበ​ኵ​ራቱ ሁሉ መጀ​መ​ሪያ ከየ​ዓ​ይ​ነቱ፥ ከቍ​ር​ባ​ና​ች​ሁም ሁሉ የማ​ን​ሣት ቍር​ባን ሁሉ ለካ​ህ​ናት ይሆ​ናል፤ በቤ​ታ​ች​ሁም ውስጥ በረ​ከት ያድር ዘንድ የአ​ዝ​መ​ራ​ች​ሁን ቀዳ​ም​ያት ለካ​ህ​ናቱ ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="31">ከዎ​ፍም ሆነ ከእ​ን​ስሳ የበ​ከ​ተ​ው​ንና አውሬ የሰ​በ​ረ​ውን ካህ​ናት አይ​ብ​ሉት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="45">
				<verse number="1">“ርስ​ትም አድ​ር​ጋ​ችሁ ምድ​ርን በዕጣ በም​ታ​ካ​ፍ​ሉ​በት ጊዜ ከም​ድር የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን የዕጣ ክፍል መባ አድ​ር​ጋ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ። ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ሺህ ክንድ ይሆ​ናል፤ በዳ​ር​ቻው ሁሉ ዙሪ​ያው የተ​ቀ​ደሰ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="2">ከእ​ር​ሱም ርዝ​መቱ አም​ስት መቶ፥ ወር​ዱም አም​ስት መቶ ክንድ አራት ማዕ​ዘን የሆነ ቦታ ለመ​ቅ​ደሱ ይሆ​ናል፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ባዶ ስፍራ የሚ​ሆን አምሳ ክንድ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="3">ከዚ​ያው ልክ ደግሞ ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ ክንድ፥ ወር​ዱም ዐሥር ሺህ ክንድ የሆነ ስፍራ ትለ​ካ​ለህ፤ በእ​ር​ሱም ውስጥ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳን የሆነ መቅ​ደስ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="4">ከም​ድ​ርም የተ​ቀ​ደሰ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ለሚ​ቀ​ርቡ ለመ​ቅ​ደሱ አገ​ል​ጋ​ዮች ለካ​ህ​ናቱ ይሆ​ናል፤ ለቤ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የሚ​ሆን ስፍራ፥ ለመ​ቅ​ደ​ስም የሚ​ሆን የተ​ቀ​ደሰ ስፍራ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="5">ርዝ​መ​ቱም ሃያ አም​ስት ሺህ፥ ወር​ዱም ዐሥር ሺህ የሆነ ስፍራ ለቤቱ አገ​ል​ጋ​ዮች ለሌ​ዋ​ው​ያን መኖ​ሪያ ርስት ከሃያ ዕቃ ቤቶች ጋር ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="6">“ለከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ይዞታ በተ​ቀ​ደ​ሰው የዕጣ ክፍል መባ አጠ​ገብ ወርዱ አም​ስት ሺህ፥ ርዝ​መ​ቱም ሃያ አም​ስት ሺህ የሆ​ነ​ውን ስፍራ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ። እር​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="7">ለአ​ለ​ቃ​ውም የሆነ የዕጣ ክፍል በተ​ቀ​ደ​ሰው መባና በከ​ተ​ማ​ዪቱ ይዞታ አጠ​ገብ በዚ​ህና በዚያ ይሆ​ናል፤ በተ​ቀ​ደ​ሰው መባና በከ​ተ​ማ​ዪቱ ይዞታ ፊት በም​ዕ​ራብ በኩል ወደ ምዕ​ራብ፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ወደ ምሥ​ራቅ ይሆ​ናል፤ ርዝ​መ​ቱም እንደ አንድ ነገድ ዕጣ ክፍል ሆኖ ከም​ድሩ ከም​ዕ​ራቡ ዳርቻ ጀምሮ እስከ ምሥ​ራቁ ዳርቻ ድረስ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="8">ይህም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ይዞታ ይሆ​ን​ለ​ታል፤ የሕ​ዝቤ አለ​ቆ​ችም ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ምድ​ሪ​ቱን እንደ ነገ​ዳ​ቸው መጠን ይሰ​ጡ​አ​ቸ​ዋል እንጂ ሕዝ​ቤን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አያ​ስ​ጨ​ን​ቋ​ቸ​ውም።”</verse>
				<verse number="9">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አለ​ቆች ሆይ! ይብ​ቃ​ችሁ፤ ግፍ​ንና ዐመ​ፅን አስ​ወ​ግዱ፤ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅ​ንም አድ​ርጉ፤ ቅሚ​ያ​ች​ሁን ከሕ​ዝቤ ላይ አርቁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="10">እው​ነ​ተኛ ሚዛን፥ እው​ነ​ተ​ኛም የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ እው​ነ​ተ​ኛም የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ ይሁ​ን​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="11">እን​ዲ​ሁም የኢ​ፍና የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ አንድ ይሁን፤ የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ፥ የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ ክፍል፥ የኢፍ መስ​ፈ​ሪ​ያ​ውም የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ ክፍል ይሁን። መስ​ፈ​ሪ​ያው እንደ ቆሮስ መስ​ፈ​ሪያ ይሁን።</verse>
				<verse number="12">ሰቅ​ሉም ሃያ አቦሊ ይሁን፤ ሃያ ሰቅል፥ ሃያ አም​ስት ሰቅል፥ ዐሥራ አም​ስት ሰቅል፥ ምናን ይሁ​ን​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="13">“የም​ታ​ቀ​ር​ቡት መባ ይህ ነው፤ ከአ​ንድ ቆሮስ መስ​ፈ​ሪያ ስንዴ አንድ ስድ​ስ​ተኛ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ከአ​ን​ድም ቆሮስ መስ​ፈ​ሪያ ገብስ አንድ ስድ​ስ​ተኛ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="14">የዘ​ይ​ቱም ደንብ፥ ከእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ የባ​ዶ​ስን ዐሥ​ረኛ ክፍል ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ዐሥር የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ አንድ የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ነውና።</verse>
				<verse number="15">ከእ​ስ​ራ​ኤል ማሰ​ማ​ርያ ከመ​ን​ጋው ከሁ​ለት መቶው አን​ዱን የበግ ጠቦት ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ይህ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁን ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ችሁ ዘንድ ለእ​ህል ቍር​ባ​ንና ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ይሆ​ናል” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="16">የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ይህን መባ ለእ​ስ​ራ​ኤል አለቃ ይሰ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="17">በየ​በ​ዓ​ላ​ቱም፥ በየ​መ​ባ​ቻ​ውም፥ በየ​ሰ​ን​በ​ታ​ቱም በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ዓመት በዓል ሁሉ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የመ​ጠ​ጡ​ንም ቍር​ባን መስ​ጠት በአ​ለ​ቃው ላይ ይሆ​ናል፤ እርሱ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል።”</verse>
				<verse number="18">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ከመ​ን​ጋው ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ወይ​ፈን ውሰድ፤ መቅ​ደ​ሱ​ንም አንጻ።</verse>
				<verse number="19">ካህ​ኑም ከኀ​ጢ​አቱ መሥ​ዋ​ዕት ደም ወስዶ በመ​ቅ​ደሱ መቃ​ኖ​ችና በመ​ሠ​ዊ​ያው እር​ከን በአ​ራቱ ማዕ​ዘን፥ በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በበሩ መቃ​ኖች ላይ ይር​ጨው።</verse>
				<verse number="20">ከወ​ሩም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን እን​ዲሁ አድ​ርግ፤ ይኸ​ውም ስለ ሳተ​ውና ስለ በደ​ለው ሁሉ ነው። እን​ዲሁ ስለ ቤቱ አስ​ተ​ስ​ርዩ።</verse>
				<verse number="21">“በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን የፋ​ሲ​ካን በዓል ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ። እስከ ሰባት ቀንም ድረስ ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="22">በዚ​ያም ቀን አለ​ቃው ለራ​ሱና ለሀ​ገሩ ሕዝብ ሁሉ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን ወይ​ፈን ያቅ​ርብ።</verse>
				<verse number="23">በበ​ዓ​ሉም በሰ​ባቱ ቀኖች የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቅ​ርብ፤ ሰባ​ቱን ቀኖች በየ​ዕ​ለቱ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሰባት ወይ​ፈ​ንና ሰባት አውራ በጎች ያቅ​ርብ፤ ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት በየ​ዕ​ለቱ ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል ያቅ​ርብ።</verse>
				<verse number="24">ለአ​ን​ድም ወይ​ፈን አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለአ​ን​ድም አውራ በግ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለአ​ን​ድም የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ አንድ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ዘይት ለእ​ህል ቍር​ባን ያቅ​ርብ።</verse>
				<verse number="25">በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን በበ​ዓሉ ሰባት ቀኖች፥ የኃ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን ከዘ​ይቱ ጋር እን​ዲሁ ያቅ​ርብ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="46">
				<verse number="1">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በው​ስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ ወደ ምሥ​ራቅ የሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር ሥራ በሚ​ሠ​ራ​በት በስ​ድ​ስቱ ቀን ተዘ​ግቶ ይቈይ፤ ነገር ግን በሰ​ን​በት ቀን ይከ​ፈት፤ በመ​ባቻ ቀንም ይከ​ፈት።</verse>
				<verse number="2">አለ​ቃው በስተ ውጭ ባለው በር በደጀ ሰላሙ መን​ገድ ገብቶ በበሩ መቃን አጠ​ገብ ይቁም፤ ካህ​ና​ቱም የእ​ር​ሱን የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቅ​ርቡ፥ እር​ሱም በበሩ መድ​ረክ ላይ ይስ​ገድ፤ ከዚ​ያም በኋላ ይውጣ፤ በሩ ግን እስከ ማታ ድረስ አይ​ዘጋ።</verse>
				<verse number="3">የሀ​ገ​ርም ሕዝብ በዚያ በር መግ​ቢያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሰ​ን​በ​ታ​ትና በመ​ባቻ ይስ​ገዱ።</verse>
				<verse number="4">አለ​ቃ​ውም በሰ​ን​በት ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​በው የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸው ስድ​ስት የበግ ጠቦ​ቶች፥ ነው​ርም የሌ​ለ​በት አንድ አውራ በግ ይሁን፤</verse>
				<verse number="5">የእ​ህ​ሉም ቍር​ባን ለአ​ውራ በጉ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ይሁን፤ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም የእ​ህል ቍር​ባን እጁ እንደ ቻለ ያህል ይሁን፥ ለአ​ን​ዱም የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ አንድ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ዘይት ያቅ​ርብ።</verse>
				<verse number="6">በመ​ባ​ቻም ቀን ነውር የሌ​ለ​በ​ትን አንድ ወይ​ፈን፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ው​ንም ስድ​ስት ጠቦ​ቶ​ችና አንድ አውራ በግ ያቅ​ርብ፤</verse>
				<verse number="7">ለወ​ይ​ፈ​ኑም አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለአ​ው​ራ​ውም በግ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም እጁ እንደ ቻለው ያህል፥ ለአ​ን​ዱም የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ አንድ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ዘይት ለእ​ህሉ ቍር​ባን ያቅ​ርብ።</verse>
				<verse number="8">አለ​ቃ​ውም በሚ​ገ​ባ​በት ጊዜ በበሩ ደጀ ሰላም መን​ገድ ይግባ፤ በዚ​ያ​ውም ይውጣ።</verse>
				<verse number="9">“የሀ​ገሩ ሕዝብ ግን በየ​ክ​ብረ በዓሉ ቀን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመጡ ጊዜ በሰ​ሜን በር በኩል ሊሰ​ግድ የሚ​ገ​ባው በደ​ቡብ በር በኩል ይውጣ፤ በደ​ቡ​ብም በር የሚ​ገ​ባው በሰ​ሜን በር በኩል ይውጣ፤ በፊት ለፊት ይውጣ እንጂ በገ​ባ​በት በር አይ​መ​ለስ።</verse>
				<verse number="10">ሕዝቡ በሚ​ገ​ቡ​በት ጊዜ አለ​ቃው በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ይግባ፤ በሚ​ወ​ጡ​በ​ትም ጊዜ ይውጣ።</verse>
				<verse number="11">በበ​ዓ​ላ​ትና በክ​ብረ በዓል ቀኖች የእ​ህሉ ቍር​ባን ለወ​ይ​ፈኑ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለአ​ውራ በጉ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም እጁ እን​ደ​ሚ​ች​ለው ያህል፥ ለአ​ንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዱቄት አንድ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ዘይት ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="12">አለ​ቃ​ውም በፈ​ቃዱ የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም በፈ​ቃዱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት በአ​ቀ​ረበ ጊዜ፥ ወደ ምሥ​ራቅ የሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር ይከ​ፈ​ት​ለት፤ በሰ​ን​በ​ትም ቀን እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርግ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቅ​ርብ፤ ከዚ​ያም በኋላ ይውጣ፤ ከወ​ጣም በኋላ በሩ ይዘጋ።</verse>
				<verse number="13">“በየ​ዕ​ለ​ቱም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​በ​ትን የአ​ንድ ዓመት የበግ ጠቦት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቀ​ር​ባ​ለህ፤ በየ​ማ​ለ​ዳው ታቀ​ር​በ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="14">ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ህ​ልን ቍር​ባን፥ በኢን መስ​ፈ​ሪያ ሢሶ ዘይት የተ​ለ​ወሰ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ስድ​ስ​ተኛ እጅ የስ​ንዴ ዱቄ​ትን፤ በየ​ማ​ለ​ዳው ታቀ​ር​ባ​ለህ፤ ይህ የሚ​ደ​ረግ ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ሥር​ዐት ነው።</verse>
				<verse number="15">እን​ዲሁ ዘወ​ትር ለሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ጠቦ​ቱ​ንና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን ዘይ​ቱ​ንም በየ​ማ​ለ​ዳው ያቀ​ር​ባሉ።”</verse>
				<verse number="16">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “አለ​ቃው ከል​ጆቹ ለአ​ንዱ ከር​ስቱ ስጦታ ቢሰጥ ለል​ጆቹ ይሁን፤ የር​ስት ይዞታ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="17">ነገር ግን ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ለአ​ንዱ ከር​ስቱ ስጦታ ቢሰጥ እስከ ነፃ​ነት ዓመት ድረስ ለእ​ርሱ ይሁን፥ ከዚ​ያም በኋላ ለአ​ለ​ቃው ይመ​ለስ፤ ርስቱ ግን ለል​ጆቹ ይሁን።</verse>
				<verse number="18">አለ​ቃ​ውም ሕዝ​ቡን ከይ​ዞ​ታ​ቸው ያወ​ጣ​ቸው ዘንድ ከር​ስ​ታ​ቸው በግድ አይ​ወ​ሰድ፤ ሕዝቤ ሁሉ ከየ​ይ​ዞ​ታ​ቸው እን​ዳ​ይ​ነ​ቀሉ ከገዛ ይዞ​ታው ለል​ጆቹ ርስ​ትን ይስጥ።”</verse>
				<verse number="19">በበ​ሩም አጠ​ገብ በአ​ለው መግ​ቢያ ወደ ሰሜን ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው ለካ​ህ​ናት ወደ​ሚ​ሆን ወደ ተቀ​ደ​ሰው ዕቃ ቤት አገ​ባኝ፤ እነ​ሆም በኋ​ላው በባ​ሕር በኩል አንድ ስፍራ ነበረ።</verse>
				<verse number="20">እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “ካህ​ናቱ ሕዝ​ቡን ለመ​ቀ​ደስ ወደ ውጭው አደ​ባ​ባይ እን​ዳ​ይ​ወጡ የበ​ደ​ሉን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​በ​ስ​ሉ​በት፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን የሚ​ጋ​ግ​ሩ​በት ስፍራ ይህ ነው።”</verse>
				<verse number="21">በው​ጭው አደ​ባ​ባይ አወ​ጣኝ፤ በአ​ደ​ባ​ባ​ይም ወዳ​ለው ወደ አራቱ ማዕ​ዘን አዞ​ረኝ፤ እነ​ሆም፥ በአ​ደ​ባ​ባዩ ማዕ​ዘን ሁሉ አደ​ባ​ባይ ነበረ።</verse>
				<verse number="22">በአ​ደ​ባ​ባዩ በአ​ራቱ ማዕ​ዘን ርዝ​መቱ አርባ ክንድ፥ ወር​ዱም ሠላሳ ክንድ የሆነ የታ​ጠረ አደ​ባ​ባይ ነበረ፤ በማ​ዕ​ዘኑ ላሉ ለእ​ነ​ዚህ ለአ​ራቱ ስፍ​ራ​ዎች አንድ ልክ ነበ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">በአ​ራ​ቱም ዙሪያ ሁሉ ግንብ ነበረ፥ በግ​ን​ቡም ሥር በዙ​ሪ​ያው የመ​ቀ​ቀያ ቦታ ነበረ።</verse>
				<verse number="24">እር​ሱም፥ “እነ​ዚህ የቤቱ አገ​ል​ጋ​ዮች የሕ​ዝ​ቡን መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​በ​ስ​ሉ​ባ​ቸው ስፍ​ራ​ዎች ናቸው” አለኝ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="47">
				<verse number="1">ወደ መቅ​ደ​ሱም መዝ​ጊያ መለ​ሰኝ፤ እነ​ሆም ውኃ ከቤቱ መድ​ረክ በታች ወደ ምሥ​ራቅ ይወጣ ነበር፤ የቤቱ ፊት ወደ ምሥ​ራቅ ይመ​ለ​ከት ነበ​ርና፤ ውኃ​ውም ከቤቱ ከቀኝ ወገን በታች በመ​ሠ​ዊ​ያው በደ​ቡብ በኩል ይወ​ርድ ነበር።</verse>
				<verse number="2">በሰ​ሜ​ኑም በር በኩል አወ​ጣኝ፤ በስተ ውጭ በአ​ለው መን​ገድ፥ ወደ ምሥ​ራቅ ወደ​ሚ​መ​ለ​ከት በስተ ውጭ ወዳ​ለው በር አዞ​ረኝ፤ እነ​ሆም ውኃው በቀኝ በኩል ይፈ​ስስ ነበር።</verse>
				<verse number="3">ሰው​ዮ​ውም የመ​ለ​ኪያ ገመድ በእጁ ይዞ ወደ ምሥ​ራቅ ወጣ፤ አንድ ሺህም ክንድ ለካ፤ በው​ኃ​ውም ውስጥ አሻ​ገ​ረኝ፤ ውኃ​ውም እስከ ቍር​ጭ​ም​ጭ​ሚት ደረሰ።</verse>
				<verse number="4">ደግሞ አንድ ሺህ ለካ፤ በው​ኃ​ውም ውስጥ አሻ​ገ​ረኝ፤ ውኃ​ውም እስከ ጉል​በት ደረሰ፤ ደግ​ሞም አንድ ሺህ ለካ፤ በው​ኃ​ውም ውስጥ አሻ​ገ​ረኝ፤ ውኃ​ውም እስከ ወገብ ደረሰ።</verse>
				<verse number="5">ደግሞ አንድ ሺህ ለካ ልሻ​ገ​ረ​ውም የማ​ል​ች​ለው ወንዝ ሆነ፤ ውኃ​ውም ጥልቅ ነበረ፤ የሚ​ዋ​ኝ​በ​ትም ውኃ ነበረ፤ ሰው ሊሻ​ገ​ረው የማ​ይ​ች​ለው ወንዝ ነበረ።</verse>
				<verse number="6">እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! አይ​ተ​ሃ​ልን?” አለኝ። አመ​ጣ​ኝም፤ ወደ ወን​ዙም ዳር መለ​ሰኝ።</verse>
				<verse number="7">በተ​መ​ለ​ስ​ሁም ጊዜ፥ እነሆ በወ​ንዙ ዳር በዚ​ህና በዚያ እጅግ ብዙ ዛፎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="8">እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “ይህ ውኃ ወደ ምሥ​ራቅ ወደ ገሊላ ይወ​ጣል፤ ወደ ዓረ​ባም ይወ​ር​ዳል፤ ወደ ባሕ​ሩም ይገ​ባል፤ ወደ ባሕ​ሩም ወደ ረከ​ሰው ውኃ በገባ ጊዜ ውኃ​ውን ይፈ​ው​ሰ​ዋል።</verse>
				<verse number="9">ሕያው ነፍስ ያለው ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ ሁሉ ወንዙ በሚ​ገ​ባ​በት ስፍራ ሁሉ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፤ ይህም ውኃ በዚያ ስለ ደረሰ ዓሣ​ዎች እጅግ ይበ​ዛሉ፤ የባ​ሕ​ሩም ውኃ ይፈ​ወ​ሳል፤ ወን​ዙም በሚ​መ​ጣ​በት ያለው ሁሉ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል።</verse>
				<verse number="10">ዓሣ አጥ​ማ​ጆ​ችም ከዓ​ይ​ን​ጋዲ ጀምሮ እስከ ዓይ​ን​ኤ​ግ​ላ​ይም ድረስ በዚያ ይቆ​ማሉ። ያም መረብ መዘ​ር​ጊያ ይሆ​ናል፤ ዓሣ​ዎ​ችም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣ​ዎች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው እጅግ ይበ​ዛሉ።</verse>
				<verse number="11">ረግ​ረ​ጉና ዕቋ​ሪው ውኃ ግን ጨው እንደ ሆነ ይኖ​ራል እንጂ አይ​ፈ​ወ​ስም።</verse>
				<verse number="12">በወ​ን​ዙም አጠ​ገብ በዳሩ ላይ በዚ​ህና በዚያ ፍሬው የሚ​በላ ዛፍ ሁሉ ይበ​ቅ​ላል፤ ቅጠ​ሉም አይ​ረ​ግ​ፍም፤ ፍሬ​ውም አይ​ጐ​ድ​ልም፤ ውኃ​ውም ከመ​ቅ​ደስ ይወ​ጣ​ልና በየ​ወሩ ሁሉ የፍሬ በኵር ያገ​ኛል፤ ፍሬ​ውም ለመ​ብል፥ ቅጠ​ሉም ለመ​ድ​ኀ​ኒት ይሆ​ናል።”</verse>
				<verse number="13">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ርስት አድ​ር​ጋ​ችሁ ለዐ​ሥራ ሁለቱ የእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ምድ​ሪ​ቱን የም​ት​ከ​ፍ​ሉ​በት ድን​በር ይህ ነው። ለዮ​ሴፍ ሁለት ዕጣ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="14">ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ እጄን አን​ሥቼ ነበ​ርና እና​ንተ እኩል አድ​ር​ጋ​ችሁ ተካ​ፈ​ሉት፤ ይህ​ችም ምድር ርስት ትሆ​ና​ች​ኋ​ለች።</verse>
				<verse number="15">“የም​ድ​ሪ​ቱም ድን​በር ይህ ነው። በሰ​ሜኑ ወገን ከታ​ላቁ ባሕር ጀምሮ በሔ​ት​ሎን መን​ገድ ወደ ጽዳድ መግ​ቢያ፤</verse>
				<verse number="16">ሐማት፥ ቤሮታ፥ በደ​ማ​ስቆ ድን​በ​ርና በሐ​ማት ድን​በር መካ​ከል ያለው ሲብ​ራ​ይም፥ በሐ​ው​ራን ድን​በር አጠ​ገብ ያለው ሐጸ​ር​ሃ​ቲ​ኮን።</verse>
				<verse number="17">ድን​በሩ ከባ​ሕሩ በደ​ማ​ስቆ ድን​በር ላይ ያለው ሐጽ​ር​ዔ​ናን ይሆ​ናል፥ በሰ​ሜን በኩል የሐ​ማት ድን​በር አለ። የሰ​ሜኑ ድን​በር ይህ ነው።</verse>
				<verse number="18">የም​ሥ​ራ​ቁም ድን​በር በሐ​ው​ራን በደ​ማ​ስ​ቆና በገ​ለ​ዓድ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ምድር መካ​ከል ዮር​ዳ​ኖስ ይሆ​ናል። ከሰ​ሜኑ ድን​በር ጀምሮ እስከ ምሥ​ራቁ ባሕር እስከ ታማር ድረስ የም​ሥ​ራቁ ድን​በር ይህ ነው።</verse>
				<verse number="19">የደ​ቡ​ቡም ድን​በር ከታ​ማር ጀምሮ እስከ ሜሪባ ቃዴስ ውኃ እስከ ግብፅ ወንዝ እስከ ታላቁ ባሕር ይሆ​ናል። የደ​ቡ​ቡም ድን​በር ይህ ነው።</verse>
				<verse number="20">የም​ዕ​ራ​ቡም ድን​በር ከደ​ቡቡ ድን​በር ጀምሮ እስከ ሐማት መግ​ቢያ አን​ጻር ድረስ ታላቁ ባሕር ይሆ​ናል። የም​ዕ​ራቡ ድን​በር ይህ ነው።</verse>
				<verse number="21">“ይህ​ችን ምድር እና​ንተ ዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስ​ራ​ኤል ትከ​ፋ​ፈ​ላ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="22">ለእ​ና​ን​ተና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ለሚ​ቀ​መጡ፥ በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል ልጆ​ችን ለሚ​ወ​ልዱ መጻ​ተ​ኞች ርስት አድ​ር​ጋ​ችሁ በዕጣ ትካ​ፈ​ሉ​አ​ታ​ላ​ችሁ፤ እነ​ር​ሱም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል እንደ አሉ የሀ​ገር ልጆች ይሆ​ኑ​ላ​ች​ኋል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ዶች መካ​ከል ከእ​ና​ንተ ጋር ርስ​ትን ይወ​ር​ሳሉ።</verse>
				<verse number="23">መጻ​ተ​ኛ​ውም በማ​ና​ቸ​ውም ነገድ መካ​ከል ቢቀ​መጥ በዚያ ርስ​ትን ትሰ​ጡ​ታ​ላ​ችሁ፤ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="48">
				<verse number="1">“የነ​ገ​ዶ​ችም ስም ይህ ነው። በሔ​ት​ሎን መን​ገድ አጠ​ገብ ወደ ሐማት መግ​ቢያ፥ በደ​ማ​ስ​ቆም ድን​በር በአ​ለው በሐ​ጸ​ር​ዔ​ናን በሐ​ማ​ትም አጠ​ገብ በሰ​ሜን በኩል ይጀ​ም​ራል። ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ይሆ​ናል። ለዳን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="2">ከዳ​ንም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለአ​ሴር አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="3">ከአ​ሴ​ርም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለን​ፍ​ታ​ሌም አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="4">ከን​ፍ​ታ​ሌም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለም​ናሴ አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="5">ከም​ና​ሴም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለኤ​ፍ​ሬም አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="6">ከኤ​ፍ​ሬ​ምም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለሮ​ቤል አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="7">ከሮ​ቤ​ልም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለይ​ሁዳ አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="8">“ከይ​ሁ​ዳም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለመባ የተ​ለየ ክፍል ይሆ​ናል፤ ወርዱ ሃያ አም​ስት ሺህ ክንድ ይሆ​ናል፤ ርዝ​መ​ቱም ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ከዕጣ ክፍ​ሎች እንደ አንዱ ይሆ​ናል፤ ቤተ መቅ​ደ​ሱም በመ​ካ​ከሉ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="9">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ት​ለ​ዩት መባ ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ ወር​ዱም ዐሥር ሺህ ክንድ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="10">የመ​ቅ​ደ​ሱም ቀዳ​ም​ያት ለካ​ህ​ናቱ ይሆ​ናል፤ በሰ​ሜን በኩል ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ፥ በም​ዕ​ራ​ብም በኩል ወርዱ ዐሥር ሺህ፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ወርዱ ዐሥር ሺህ፥ በደ​ቡ​ብም በኩል ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ ክንድ ይሆ​ናል። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤተ መቅ​ደስ በመ​ካ​ከሉ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="11">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በሳቱ ጊዜ፥ ሌዋ​ው​ያን እንደ ሳቱ ላል​ሳ​ቱት፥ ሥር​ዐ​ቴን ለጠ​በ​ቁት፥ ከሳ​ዶቅ ልጆች ወገን ለተ​ቀ​ደ​ሱት ካህ​ናት ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="12">ከም​ድ​ርም መባ የተ​ለየ ሌላ መባ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ ከተ​ቀ​ደ​ሱ​ትም ይልቅ የተ​ቀ​ደሰ ይሆ​ናል፤ በሌ​ዋ​ው​ያን ድን​በር አጠ​ገብ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="13">በካ​ህ​ና​ቱም ድን​በር አቅ​ራ​ቢያ ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ፥ ወር​ዱም ዐሥር ሺህ የሆነ ዕጣ ለሌ​ዋ​ው​ያን ይሆ​ናል፤ ርዝ​መቱ ሁሉ ሃያ አም​ስት ሺህ፥ ወር​ዱም ሃያ ሺህ ክንድ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="14">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቀ​ደሰ ነውና ከእ​ርሱ ምንም አይ​ሸ​ጡም፤ አይ​ለ​ው​ጡ​ምም፤ የም​ድ​ሩም ቀዳ​ም​ያት አይ​ፋ​ለ​ስም።</verse>
				<verse number="15">በሃያ አም​ስቱ ሺህ አን​ጻር አም​ስት ሺህ ወርድ ያለው የቀረ ቅዱስ ያይ​ደለ ስፍራ ለከ​ተ​ማ​ዪቱ ለጋራ ጉዳ​ይዋ፥ ለመ​ኖ​ሪያ፥ ለማ​ሰ​ማ​ር​ያም ይሆ​ናል፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱም በመ​ካ​ከሉ ትሆ​ና​ለች።</verse>
				<verse number="16">ልክ​ዋም ይህ ነው፤ በሰ​ሜን በኩል አራት ሺህ አም​ስት መቶ፥ በደ​ቡ​ብም በኩል አራት ሺህ አም​ስት መቶ፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል አራት ሺህ አም​ስት መቶ፥ በም​ዕ​ራ​ብም በኩል አራት ሺህ አም​ስት መቶ ክንድ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="17">ለከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ማሰ​ማ​ርያ ይኖ​ራ​ታል፤ በሰ​ሜን በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በደ​ቡ​ብም በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በም​ዕ​ራ​ብም በኩል ሁለት መቶ አምሳ ክንድ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="18">“በተ​ቀ​ደ​ሰው መባ አን​ጻር የተ​ረ​ፈው ርዝ​መቱ ወደ ምሥ​ራቅ ዐሥር ሺህ፥ ወደ ምዕ​ራ​ብም ዐሥር ሺህ ክንድ ይሆ​ናል። በተ​ቀ​ደ​ሰው መባ አን​ጻር ይሆ​ናል። ፍሬ​ውም ከተ​ማ​ዪ​ቱን ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ መብል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="19">ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ከተ​ማ​ዪ​ቱን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ያር​ሱ​ታል።</verse>
				<verse number="20">መባው ሁሉ ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ሺህ ክንድ ይሆ​ናል፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን መባ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ይዞታ ጋር አራት ማዕ​ዘን አድ​ር​ጋ​ችሁ ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="21">“በተ​ቀ​ደ​ሰው መባና በከ​ተ​ማ​ዪቱ ይዞታ፥ በዚ​ህና በዚያ ወገን የቀ​ረው ለአ​ለ​ቃው ይሆ​ናል፤ በመ​ባው በሃያ አም​ስት ሺህ ፊት እስከ ምሥ​ራቁ ድን​በር፥ በም​ዕ​ራ​ብም በኩል በሃያ አም​ስት ሺህ ፊት እስከ ምዕ​ራቡ ድን​በር፥ እንደ ዕጣ ክፍል ሁሉ መጠን፥ ለአ​ለ​ቃው ይሆ​ናል፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም መባና ቤተ መቅ​ደሱ በመ​ካ​ከሉ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="22">የሌ​ዋ​ው​ያን ርስት፥ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ይዞታ ለአ​ለ​ቃው በሆ​ነው መካ​ከል ይሆ​ናል፤ በይ​ሁዳ ድን​በ​ርና በብ​ን​ያም ድን​በር መካ​ከል የአ​ለ​ቃው ዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="23">“ለቀ​ሩ​ትም ነገ​ዶች እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለብ​ን​ያም አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="24">ከብ​ን​ያ​ምም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለስ​ም​ዖን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="25">ከስ​ም​ዖ​ንም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለይ​ሳ​ኮር አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="26">ከይ​ሳ​ኮ​ርም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለዛ​ብ​ሎን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="27">ከዛ​ብ​ሎ​ንም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለጋድ አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="28">ከጋ​ድም ድን​በር ቀጥሎ በደ​ቡብ በኩል ድን​በሩ ከታ​ማር ጀምሮ እስከ ሜሪባ ቃዴስ ውኃ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="29">ርስት አድ​ር​ጋ​ችሁ ለእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች በዕጣ የም​ታ​ካ​ፍ​ሉ​አት ምድር ይህች ናት፤ የእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ዕጣ እን​ደ​ዚህ ነው፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="30">“የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም መው​ጫ​ዎች እነ​ዚህ ናቸው። በሰ​ሜን ወገን ልኩ አራት ሺህ አም​ስት መቶ ክንድ ነው።</verse>
				<verse number="31">የከ​ተ​ማ​ዪቱ በሮች እንደ እስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ስም ይሆ​ናሉ፤ በሰ​ሜን በኩል አንዱ የሮ​ቤል በር፤ አን​ዱም የይ​ሁዳ በር፥ አን​ዱም የሌዊ በር ሦስት በሮች ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="32">በም​ሥ​ራ​ቁም ወገን አራት ሺህ አም​ስት መቶ ክንድ፥ ሦስ​ትም በሮች አሉ፤ አንዱ የዮ​ሴፍ በር፥ አን​ዱም የብ​ን​ያም በር፥ አን​ዱም የዳን በር ነው።</verse>
				<verse number="33">በደ​ቡ​ቡም ወገን ልኩ አራት ሺህ አም​ስት መቶ ክንድ፥ ሦስ​ትም በሮች አሉ፤ አንዱ የስ​ም​ዖን በር፥ አን​ዱም የይ​ሳ​ኮር በር፥ አን​ዱም የዛ​ብ​ሎን በር ነው።</verse>
				<verse number="34">በም​ዕ​ራ​ቡም ወገን ልኩ አራት ሺህ አም​ስት መቶ ክንድ፥ ሦስ​ትም በሮች አሉ፤ አንዱ የጋድ በር፥ አን​ዱም የአ​ሴር በር፥ አን​ዱም የን​ፍ​ታ​ሌም በር ነው።</verse>
				<verse number="35">ዙሪ​ያ​ዋም ዐሥራ ስም​ንት ሺህ ክንድ ይሆ​ናል፥ ከዚ​ያም ቀን ጀምሮ የከ​ተ​ማ​ዪቱ ስም፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ አለ’ ተብሎ ይጠ​ራል።”</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="27">
			<chapter number="1">
			</chapter>
			<chapter number="2">
			</chapter>
			<chapter number="3">
			</chapter>
			<chapter number="4">
			</chapter>
			<chapter number="5">
			</chapter>
			<chapter number="6">
			</chapter>
			<chapter number="7">
			</chapter>
			<chapter number="8">
			</chapter>
			<chapter number="9">
			</chapter>
			<chapter number="10">
			</chapter>
			<chapter number="11">
			</chapter>
			<chapter number="12">
			</chapter>
		</book>
		<book number="28">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት በዖ​ዝ​ያ​ንና በኢ​ዮ​አ​ታም በአ​ካ​ዝና በሕ​ዝ​ቅ​ያ​ስም ዘመን በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በኢ​ዮ​አስ ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ዘመን ወደ ብኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">ወደ ሆሴዕ የመጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃሉ መጀ​መ​ሪያ ይህ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆሴ​ዕን፥ “ምድ​ሪቱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርቃ ታመ​ነ​ዝ​ራ​ለ​ችና ሂድ፤ ዘማ​ዊ​ቱን ሴትና የዘ​ማ​ዊ​ቱን ልጆች ለአ​ንተ ውሰድ” አለው።</verse>
				<verse number="3">እር​ሱም ሄዶ የዴ​ብ​ላ​ይ​ምን ልጅ ጎሜ​ርን አገባ፤ እር​ስ​ዋም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደ​ች​ለት።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ከጥ​ቂት ዘመን በኋላ የኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ልን ደም በይ​ሁዳ ቤት ላይ እበ​ቀ​ላ​ለ​ሁና፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት መን​ግ​ሥ​ትን እሽ​ራ​ለ​ሁና ስሙን ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ብለህ ጥራው፤</verse>
				<verse number="5">በዚ​ያም ጊዜ እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ሸለቆ ውስጥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቀስት እሰ​ብ​ራ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="6">ደግሞ ፀነ​ሰች፤ ሴት ልጅ​ንም ወለ​ደች። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “መለ​የ​ትን እለ​ያ​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ ይቅር እላ​ቸው ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አል​ም​ራ​ቸ​ው​ምና ስም​ዋን ኢሥ​ህ​ልት ብለህ ጥራት፤</verse>
				<verse number="7">ነገር ግን የይ​ሁ​ዳን ልጆች ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አድ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ በቀ​ስት ወይም በሰ​ይፍ፥ ወይም በጦር፥ ወይም በሠ​ረ​ገላ፥ ወይም በፈ​ረ​ሶች፥ ወይም በፈ​ረ​ሰ​ኞች የማ​ድ​ና​ቸው አይ​ደ​ለም” አለው።</verse>
				<verse number="8">ኢሥ​ህ​ል​ት​ንም ጡት ባስ​ጣ​ሏት ጊዜ፥ ደግሞ ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሕዝቤ አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምና፥ እኔም አም​ላክ አል​ሆ​ና​ች​ሁ​ምና ስሙን ኢሕ​ዝ​ብየ ብለህ ጥራው” አለው።</verse>
				<verse number="10">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ቍጥር እን​ደ​ማ​ይ​ሰ​ፈ​ርና እን​ደ​ማ​ይ​ቈ​ጠር እንደ ባሕር አሸዋ ይሆ​ናል፤ እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ “እና​ንተ ሕዝቤ አይ​ደ​ላ​ች​ሁም” ተብሎ በተ​ነ​ገ​ረ​በት በዚያ ስፍራ የሕ​ያው አም​ላክ ልጆች ይባ​ላሉ።</verse>
				<verse number="11">የይ​ሁዳ ልጆ​ችና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በአ​ን​ድ​ነት ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም አንድ አለቃ ይሾ​ማሉ፤ ከም​ድ​ሪ​ቱም ይወ​ጣሉ፤ የኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ቀን ታላቅ ይሆ​ና​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ሕዝቤ፥ እኅ​ታ​ች​ሁ​ንም፦ ሥህ​ልት በሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">እና​ታ​ችሁ ሚስቴ አይ​ደ​ለ​ች​ምና፥ እኔም ባልዋ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና እና​ታ​ች​ሁን ተዋ​ቀ​ሱ​አት። ዝሙ​ቷን ከፊቷ፥ ምን​ዝ​ር​ና​ዋ​ንም ከጡ​ቶ​ችዋ መካ​ከል አስ​ወ​ግ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">ዕራ​ቁ​ት​ዋ​ንም እን​ድ​ት​ቆም አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ እንደ ሕፃ​ን​ነ​ትዋ ወራት፥ እንደ ተወ​ለ​ደ​ች​ባት እንደ መጀ​መ​ሪ​ያ​ዪ​ቱም ቀን አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ። እንደ ምድረ በዳም አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ ውኃም እን​ደ​ሌ​ላት ምድር አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ በው​ኃም ጥም እገ​ድ​ላ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">የዝ​ሙት ልጆች ናቸ​ውና ልጆ​ች​ዋን ይቅር አል​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="5">እና​ታ​ቸው አመ​ን​ዝ​ራ​ለ​ችና፤ የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸ​ውም፥ “እን​ጀ​ራ​ዬ​ንና ውኃ​ዬን፥ ቀሚ​ሴ​ንና መደ​ረ​ቢ​ያ​ዬን፥ ዘይ​ቴ​ንና የሚ​ገ​ባ​ኝን ሁሉ የሚ​ሰ​ጡኝ ወዳ​ጆ​ችን እከ​ተ​ላ​ቸው ዘንድ እሄ​ዳ​ለሁ” ብላ​ለ​ችና አሳ​ፈ​ረ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">ስለ​ዚህ እነሆ ጎዳ​ና​ዋን በእ​ሾህ አጥ​ረ​ዋ​ለሁ፤ መን​ገ​ድ​ዋ​ንም እዘ​ጋ​ዋ​ለሁ፤ ማለ​ፊ​ያም ታጣ​ለች።</verse>
				<verse number="7">ወዳ​ጆ​ች​ዋ​ንም ትከ​ተ​ላ​ለች፤ ነገር ግን አት​ደ​ር​ስ​ባ​ቸ​ውም፤ ትፈ​ል​ጋ​ቸ​ው​ማ​ለች፤ ነገር ግን አታ​ገ​ኛ​ቸ​ውም፤ እር​ስ​ዋም፥ “ከዛሬ ይልቅ የዚ​ያን ጊዜ ይሻ​ለኝ ነበ​ርና ተመ​ልሼ ወደ ቀደ​መው ባሌ እሄ​ዳ​ለሁ” ትላ​ለች።</verse>
				<verse number="8">እር​ስ​ዋም እህ​ል​ንና ወይ​ንን ዘይ​ት​ንም የሰ​ጠ​ኋት፥ ብር​ንና ወር​ቅን ያበ​ዛ​ሁ​ላት እኔ እንደ ሆንሁ አላ​ወ​ቀ​ችም። እር​ስዋ ግን ወር​ቁ​ንና ብሩን ለጣ​ዖት አደ​ረ​ገች።</verse>
				<verse number="9">ስለ​ዚህ እህ​ሌን በጊ​ዜው፥ ወይ​ኔ​ንም በወ​ራቱ እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ኀፍ​ረ​ቷ​ንም እን​ዳ​ት​ሸ​ፍን ልብ​ሴ​ንና መጎ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ዬን እገ​ፍ​ፋ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">አሁ​ንም በወ​ዳ​ጆ​ችዋ ፊት ነው​ር​ዋን እገ​ል​ጣ​ለሁ፤ ከእ​ጄም ማንም አያ​ድ​ና​ትም።</verse>
				<verse number="11">ደስ​ታ​ዋ​ንም ሁሉ፥ በዓ​ላ​ቶ​ች​ዋ​ንም፥ መባ​ቻ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ ሰን​በ​ቶ​ች​ዋ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቶ​ች​ዋ​ንም ሁሉ አስ​ቀ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">እር​ስ​ዋም፥ “ወዳ​ጆች የሰ​ጡኝ ዋጋዬ ይህ ነው” ያለ​ች​ውን ሁሉ ወይ​ን​ዋ​ንና በለ​ስ​ዋን አጠ​ፋ​ለሁ፤ ምስ​ክ​ርም ይሆኑ ዘንድ አኖ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የም​ድረ በዳም አራ​ዊ​ትና የሰ​ማይ ወፎች፥ የም​ድር ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችም ይበ​ሉ​ታል።</verse>
				<verse number="13">እኔን ረስታ ወዳ​ጆ​ች​ዋን እየ​ተ​ከ​ተ​ለች፥ በጕ​ት​ቾ​ች​ዋና በጌ​ጥ​ዋም እያ​ጌ​ጠች ለበ​ኣ​ሊም የሠ​ዋ​ች​በ​ትን ወራት እበ​ቀ​ል​ባ​ታ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="14">ስለ​ዚህ እነሆ አቅ​በ​ዘ​ብ​ዛ​ታ​ለሁ፤ ወደ ምድረ በዳም አመ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ለል​ብ​ዋም እና​ገ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">ከዚ​ያም የተ​ገ​ኘ​ውን ገን​ዘ​ብ​ዋን እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ምክ​ር​ዋ​ንም በአ​ኮር ሸለቆ እገ​ል​ጣ​ለሁ፤ እንደ ሕፃ​ን​ነ​ትዋ ወራት፥ ከግ​ብ​ፅም እንደ ወጣ​ች​በት ቀን ትዘ​ም​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="16">በዚያ ቀን ባሌ ብለሽ ትጠ​ሪ​ኛ​ለሽ እንጂ ዳግ​መኛ በዓ​ሊም ብለሽ አት​ጠ​ሪ​ኝም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤</verse>
				<verse number="17">የበ​ዓ​ሊ​ምን ስሞች ከአ​ፍዋ አሰ​ወ​ግ​ዳ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፥ ስማ​ቸ​ውም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​ታ​ሰ​ብም።</verse>
				<verse number="18">በዚ​ያም ቀን ከም​ድር አራ​ዊ​ትና ከሰ​ማይ ወፎች፥ ከመ​ሬ​ትም ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ጋር ቃል ኪዳን አደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ። ቀስ​ት​ንና ሰይ​ፍን፥ ጦር​ንም ከም​ድሩ እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ ተዘ​ል​ለ​ሽም ትቀ​መ​ጫ​ለሽ።</verse>
				<verse number="19">ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ለእኔ እን​ድ​ት​ሆኚ አጭ​ሻ​ለሁ፤ በጽ​ድ​ቅና በፍ​ርድ በም​ሕ​ረ​ትና በይ​ቅ​ርታ አጭ​ሻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">ለእ​ኔም እን​ድ​ት​ሆኚ በመ​ታ​መን አጭ​ሻ​ለሁ፤ አን​ቺም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታው​ቂ​አ​ለሽ።</verse>
				<verse number="21">በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለሰ​ማይ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ሰማ​ይም ለም​ድር ይመ​ል​ሳል፤</verse>
				<verse number="22">ምድ​ርም ለእ​ህል፥ ለወ​ይ​ንና ለዘ​ይት ትመ​ል​ሳ​ለች፤ እነ​ር​ሱም ለኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ይመ​ል​ሳሉ።</verse>
				<verse number="23">በም​ድ​ርም ላይ ለእኔ እዘ​ራ​ታ​ለሁ፤ ይቅ​ርታ የሌ​ላ​ትን ይቅር እላ​ታ​ለሁ፤ ያል​ተ​ወ​ደ​ደች የነ​በ​ረ​ች​ውን እወ​ድ​ዳ​ታ​ለሁ፤ ሕዝ​ቤም ያል​ሆ​ነ​ውን፥ “አንተ ሕዝቤ ነህ” እለ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም፥ “አንተ ጌታ​ዬና አም​ላኬ ነህ” ይለ​ኛል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ ሌሎች አማ​ል​ክት ቢመ​ለ​ሱና የዘ​ቢብ ጥፍ​ጥ​ፍን ቢወ​ድዱ እን​ኳን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ደ​ሚ​ወ​ድ​ዳ​ቸው አን​ተም ክፋ​ትና ዝሙት ያለ​ባ​ትን ሴት ውደድ” አለኝ።</verse>
				<verse number="2">እኔም በዐ​ሥራ አም​ስት ብርና በአ​ንድ ቆሮስ መስ​ፈ​ሪያ ተኩል ገብ​ስና በአ​ንድ ፊቀን ወይን ተወ​ዳ​ጀ​ኋት።</verse>
				<verse number="3">“ከእኔ ጋር ብዙ ወራት ተቀ​መጪ፤ አታ​መ​ን​ዝ​ሪም፤ ሌላ ሰው​ንም አታ​ግቢ፤ እኔም ከአ​ንቺ ጋር እኖ​ራ​ለሁ” አል​ኋት።</verse>
				<verse number="4">የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ያለ ንጉ​ሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥ​ዋ​ዕ​ትና ያለ ምሥ​ዋዕ፤ ያለ ካህ​ንና ያለ ራእይ፤ ያለ ኤፉ​ድና ያለ ተራ​ፊም ብዙ ወራት ይቀ​መ​ጣ​ሉና፤</verse>
				<verse number="5">ከዚ​ያም በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተመ​ል​ሰው አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ንጉ​ሣ​ቸ​ውን ዳዊ​ትን ይፈ​ል​ጋሉ፤ በኋ​ለ​ኛ​ውም ዘመን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ቸር​ነ​ቱን ያስ​ቡ​ታል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ! እው​ነ​ትና ምሕ​ረት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ማወቅ በም​ድር ስለ​ሌለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ላይ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ይወ​ቅ​ሳ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።</verse>
				<verse number="2">ነገር ግን ሐሰት፥ ግዳ​ይና ስር​ቆት፥ ምን​ዝ​ር​ናም ምድ​ርን ሞል​ተ​ዋል፤ ደም​ንም ከደም ጋር ይቀ​ላ​ቅ​ላሉ።</verse>
				<verse number="3">ስለ​ዚህ ምድ​ሪቱ ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ በእ​ር​ስ​ዋም ከሚ​ቀ​መጡ ሁሉ ከም​ድር አራ​ዊ​ትና ከሰ​ማይ ወፎች፤ ከም​ድ​ርም ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ጋር ትጠ​ፋ​ለች፤ የባ​ሕ​ሩም ዓሦች ያል​ቃሉ።</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን ሕዝቤ እን​ደ​ሚ​ከ​ራ​ከር ካህን ነውና እን​ግ​ዲህ የሚ​ከ​ራ​ከር፥ ማንም አይ​ኑር፥ የሚ​ዘ​ል​ፍም ማንም አይ​ኑር።</verse>
				<verse number="5">በቀ​ንም ትደ​ክ​ማ​ለህ፤ ነቢ​ዩም ከአ​ንተ ጋር ይደ​ክ​ማል፤ እና​ታ​ች​ሁም ሌሊ​ትን ትመ​ስ​ላ​ለች።</verse>
				<verse number="6">ሕዝቤ አእ​ምሮ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው ይመ​ስ​ላሉ፤ አን​ተም አእ​ም​ሮህ ተለ​ይ​ቶ​ሃ​ልና እኔ ካህን እን​ዳ​ት​ሆ​ነኝ እተ​ው​ሃ​ለሁ፤ የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም ሕግ ረስ​ተ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ልጆ​ች​ህን እረ​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">እንደ ብዛ​ታ​ቸው መጠን ኀጢ​አት ሠሩ​ብኝ፤ እኔም ክብ​ራ​ቸ​ውን ወደ ውር​ደት እለ​ው​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">ሕዝ​ቤ​ንም ኀጢ​አ​ታ​ቸው ትበ​ላ​ቸ​ዋ​ለች፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም በበ​ደ​ላ​ቸው ይወ​ስ​ዷ​ታል።</verse>
				<verse number="9">እንደ ሕዝ​ቡም እን​ዲሁ ካህኑ ይሆ​ናል፤ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸ​ውም እበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ሥራ​ቸ​ውም እከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መጠ​በቅ ትተ​ዋ​ልና ሲበሉ አይ​ጠ​ግ​ቡም፤ ሲያ​መ​ነ​ዝ​ሩም አይ​በ​ዙም።</verse>
				<verse number="11">የሕ​ዝቤ ልቡ​ና​ቸው ዝሙ​ትን፥ መጠ​ጥ​ንና ስካ​ርን ወደደ።</verse>
				<verse number="12">ሕዝቤ በዝ​ሙት መን​ፈስ ስተ​ዋ​ልና ከአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውም ርቀው አመ​ን​ዝ​ረ​ዋ​ልና በት​ርን ይጠ​ይ​ቃሉ፤ በት​ሩም ይመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="13">በተ​ራ​ሮ​ችም ራስና በኮ​ረ​ብ​ታ​ዎች ላይ ይሠ​ዋሉ፤ ጥላ​ውም መል​ካም ነውና ከኮ​ም​በ​ልና ከል​ብን፥ ከአ​ሆ​ማም ዛፍ በታች ያር​ዳሉ፤ ስለ​ዚህ ሴቶች ልጆ​ቻ​ችሁ ይሰ​ስ​ናሉ፤ ሙሽ​ሮ​ቻ​ች​ሁም ያመ​ነ​ዝ​ራሉ።</verse>
				<verse number="14">ወን​ዶ​ችም ደግሞ ከአ​መ​ን​ዝ​ሮች ጋር ይጫ​ወ​ታ​ሉና፥ ከጋ​ለ​ሞ​ቶ​ችም ጋር ይሠ​ዋ​ሉና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችሁ በሰ​ሰኑ ጊዜ፥ ሙሽ​ሮ​ቻ​ች​ሁም በአ​መ​ነ​ዘሩ ጊዜ አል​ቀ​ጣ​ኋ​ቸ​ውም፤ የማ​ያ​ስ​ተ​ው​ልም ሕዝብ ከአ​መ​ን​ዝራ ጋር ይቀ​ላ​ቀ​ላል።</verse>
				<verse number="15">እስ​ራ​ኤል ሆይ! አንተ አላ​ዋቂ አት​ሁን፤ አን​ተም ይሁዳ! ወደ ጌል​ጌላ አት​ሂድ፤ ወደ ቤት​አ​ዊ​ንም አት​ውጡ፤ በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አት​ማሉ።</verse>
				<verse number="16">እስ​ራ​ኤል እን​ደ​ም​ት​ደ​ነ​ብር ጊደር ደን​ብ​ሮ​አል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ፊው ቦታ እንደ ጠቦት ያሰ​ማ​ራ​ዋል።</verse>
				<verse number="17">እን​ዲ​ሁም ኤፍ​ሬም ከጣ​ዖ​ታት ጋር ተጋ​ጠመ፤ ለራ​ሱም ዕን​ቅ​ፋ​ትን አኖረ።</verse>
				<verse number="18">ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም መረ​ጣ​ቸው፤ ፈጽ​መ​ውም አመ​ነ​ዘሩ፤ በክ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ውር​ደ​ትን መረጡ።</verse>
				<verse number="19">አንተ በክ​ን​ፎ​ችዋ ውስጥ የነ​ፋስ መና​ወጥ ነህ፤ ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ያፍ​ራሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">ካህ​ናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! አድ​ምጡ፤ የን​ጉሥ ቤት ሆይ! ልብ አድ​ርጉ፤ ለሚ​መ​ለ​ከት ወጥ​መድ፥ በታ​ቦ​ርም ላይ የተ​ዘ​ረጋ አሽ​ክላ ሆና​ች​ኋ​ልና ፍርድ በእ​ና​ንተ ላይ ነው።</verse>
				<verse number="2">የሚ​ያ​ድኑ አዳ​ኞች ያጠ​ም​ዱ​ባት ዘንድ ተከ​ሏት፤ እኔ ግን መካ​ሪ​ያ​ችሁ ነኝ።</verse>
				<verse number="3">እኔ ኤፍ​ሬ​ምን አው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ከእኔ አል​ራ​ቀም፤ ኤፍ​ሬም ዛሬ አመ​ን​ዝ​ሮ​አ​ልና፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ረክ​ሶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="4">ወደ አም​ላ​ካ​ቸው ይመ​ለሱ ዘንድ ልባ​ቸ​ውን አላ​ቀ​ኑም፤ የዝ​ሙት መን​ፈስ በው​ስ​ጣ​ቸው አለና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አላ​ወ​ቁ​ት​ምና።</verse>
				<verse number="5">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ትዕ​ቢት በፊቱ ይመ​ሰ​ክ​ራል፤ ስለ​ዚህ እስ​ራ​ኤ​ልና ኤፍ​ሬም በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ይደ​ክ​ማሉ፤ ይሁ​ዳም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይደ​ክ​ማል።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ለመ​ሻት ከበ​ጎ​ቻ​ቸ​ውና ከላ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር ይሄ​ዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከእ​ነ​ርሱ ተለ​ይ​ቶ​አ​ልና አያ​ገ​ኙ​ትም።</verse>
				<verse number="7">ዲቃ​ሎ​ችን ልጆች ወል​ደ​ዋ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከድ​ተ​ዋል፤ አሁ​ንም ኵብ​ኵባ እነ​ር​ሱ​ንና ርስ​ታ​ቸ​ውን ይበ​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="8">በኮ​ረ​ብታ ላይ መለ​ከ​ትን ንፉ፤ በተ​ራ​ሮ​ችም ላይ ጩኹ፤ ብን​ያም በተ​ዋ​ረ​ደ​በት በቤ​ት​አ​ዌን ዐዋጅ ንገሩ።</verse>
				<verse number="9">ኤፍ​ሬም በዘ​ለፋ ቀን ለጥ​ፋት ይሆ​ናል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ዶች የታ​መ​ነ​ውን ነገር አሳ​የሁ።</verse>
				<verse number="10">የይ​ሁዳ አለ​ቆች ድም​በ​ርን እን​ደ​ሚ​ያ​ፈ​ርሱ ሆነ​ዋል፤ እኔም መዓ​ቴን እንደ ውኃ አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">ኤፍ​ሬም የተ​ገፋ ሆነ፤ በፍ​ር​ድም ተረ​ገጠ፤ ከን​ቱን ይከ​ተል ዘንድ ጀም​ሮ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="12">እኔም ለኤ​ፍ​ሬም እንደ ብል፥ ለይ​ሁ​ዳም ቤት እንደ ነቀዝ እሆ​ን​በ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">ኤፍ​ሬ​ምም ደዌ​ውን አያት፤ ይሁ​ዳም ሥቃ​ዩን አያት፤ ኤፍ​ሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ወደ ንጉ​ሡም ወደ ኢያ​ሪም መል​እ​ክ​ተ​ኛን ላከ፤ እርሱ ግን ፈጽሞ ይፈ​ው​ሳ​ችሁ ዘንድ አል​ቻ​ለም፤ ከእ​ና​ን​ተም ሕማም አል​ተ​ወ​ገ​ደም።</verse>
				<verse number="14">እኔም ለኤ​ፍ​ሬም እንደ ነብር፥ ለይ​ሁ​ዳም ቤት እንደ አን​በሳ ደቦል እሆ​ና​ለ​ሁና፤ እኔም ነጥቄ እሄ​ዳ​ለሁ፤ እወ​ስ​ድ​ማ​ለሁ፤ የሚ​ያ​ድ​ና​ቸ​ውም የለም።</verse>
				<verse number="15">እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ፥ ፊቴ​ንም እስ​ኪሹ ድረስ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ወደ ስፍ​ራ​ዬም እመ​ለ​ሳ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">በመ​ከ​ራ​ቸው ጊዜ በማ​ለዳ ወደ እኔ ይገ​ሰ​ግ​ሳሉ፤ እን​ዲ​ህም ይላሉ፥ “ኑ፤ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​መ​ለስ፤ እርሱ ሰብ​ሮ​ና​ልና፥ እር​ሱም ይፈ​ው​ሰ​ናል፤ እርሱ መት​ቶ​ና​ልና፥ እር​ሱም ይጠ​ግ​ነ​ናል።</verse>
				<verse number="2">ከሁ​ለት ቀን በኋላ ያድ​ነ​ናል፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ያስ​ነ​ሣ​ናል፤ በፊ​ቱም በሕ​ይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን።</verse>
				<verse number="3">እን​ወ​ቀው፤ እና​ው​ቀ​ውም ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ከ​ተል፤ እንደ ወገ​ግ​ታም ተዘ​ጋ​ጅቶ እና​ገ​ኘ​ዋ​ለን፤ በም​ድ​ርም ላይ እንደ መጀ​መ​ሪ​ያ​ውና እንደ ኋለ​ኛው ዝናብ ወደ እኛ ይመ​ጣል።</verse>
				<verse number="4">“ምሕ​ረ​ታ​ችሁ እንደ ማለዳ ደመና፥ በማ​ለ​ዳም እን​ደ​ሚ​ያ​ልፍ ጠል ነውና ኤፍ​ሬም ሆይ! ምን ላድ​ር​ግ​ልህ? ይሁዳ ሆይ! ምን ላድ​ር​ግ​ልህ?</verse>
				<verse number="5">ስለ​ዚህ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁን አጨ​ድ​ኋ​ቸው፤ በአ​ፌም ቃል ገደ​ል​ኋ​ቸው፤ ፍር​ዴም እንደ ብር​ሃን ይወ​ጣል።</verse>
				<verse number="6">ከመ​ሥ​ዋ​ዕት ይልቅ ምሕ​ረ​ትን፥ ከሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት ይልቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማወቅ እወ​ድ​ዳ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="7">እነ​ርሱ ግን ቃል ኪዳ​ንን እን​ደ​ሚ​ያ​ፈ​ርስ ሰው ሆኑ፤ በዚ​ያም ላይ ከዱኝ።</verse>
				<verse number="8">ገለ​ዓድ ከን​ቱን የም​ት​ሠ​ራና በደም የተ​ቀ​ባች ከተማ ናት፥</verse>
				<verse number="9">ሰውን እን​ደ​ሚ​ያ​ደቡ ወን​በ​ዴ​ዎች፥ እን​ዲሁ ካህ​ናት በሴ​ኬም መን​ገድ ላይ አድ​ብ​ተው ይገ​ድ​ላሉ፤ ዐመ​ፅ​ንም ያደ​ር​ጋሉ።</verse>
				<verse number="10">በእ​ስ​ራ​ኤል ቤት የሚ​ያ​ሰ​ፈ​ራን ነገር አይ​ቻ​ለሁ፤ በዚያ የኤ​ፍ​ሬ​ም​ንም ዝሙት አየሁ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ረክ​ሶ​አል።</verse>
				<verse number="11">ይሁዳ ሆይ! የሕ​ዝ​ቤን ምርኮ በም​መ​ል​ስ​በት ጊዜ ለአ​ንተ ደግሞ መከር ተወ​ስ​ኖ​ል​ሃል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">በሐ​ሰት አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፥ ሌባም ገብ​ቶ​አ​ልና፥ በው​ጭም ወን​በ​ዴ​ዎች ቀም​ተ​ዋ​ልና እስ​ራ​ኤ​ልን እፈ​ውስ ዘንድ በወ​ደ​ድሁ ጊዜ የኤ​ፍ​ሬም ኀጢ​አ​ትና የሰ​ማ​ርያ ክፋት ተገ​ለጠ።</verse>
				<verse number="2">ወን​ጀ​ላ​ቸ​ውን አንድ ያደ​ርጉ ዘንድ በል​ባ​ቸው እንደ አሰቡ ክፋ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ዐሰ​ብሁ፤ አሁ​ንም ክፋ​ታ​ቸው ከብ​ባ​ቸ​ዋ​ለች፤ በደ​ላ​ቸ​ውም በፊቴ አለች።</verse>
				<verse number="3">ነገ​ሥ​ታቱ በክ​ፋ​ታ​ቸው፥ አለ​ቆ​ቹም በሐ​ሰ​ታ​ቸው ደስ ተሰኙ።</verse>
				<verse number="4">ሁሉም አመ​ን​ዝ​ራ​ዎች ናቸው፤ ጋጋሪ እን​ደ​ሚ​ያ​ነ​ድ​ድ​በት እንደ ምድጃ ናቸው፤ ሁሉም እስ​ኪ​ቦካ ድረስ እሳ​ትን መቈ​ስ​ቈ​ስና እር​ሾን መለ​ወስ ይቈ​ያል።</verse>
				<verse number="5">በን​ጉ​ሦ​ቻ​ችን ቀን አለ​ቆች ከወ​ይን ጠጅ ሙቀት የተ​ነሣ ታመሙ፤ እነ​ር​ሱም ከዋ​ዘ​ኞች ጋር እጆ​ቻ​ቸ​ውን ዘረጉ።</verse>
				<verse number="6">እያ​ደቡ ልባ​ቸ​ውን እንደ ምድጃ አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ዋል፤ ጋጋ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ሌሊ​ቱን ሁሉ አን​ቀ​ላፋ፤ በጠ​ባም ጊዜ እንደ እሳት ነበ​ል​ባል ይነ​ድ​ዳል።</verse>
				<verse number="7">ሁሉም እንደ ምድጃ ግለ​ዋል፤ ፈራ​ጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ወደቁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም መካ​ከል የሚ​ጠ​ራኝ የለም።</verse>
				<verse number="8">ኤፍ​ሬም ከሕ​ዝቡ ጋር ተደ​ባ​ለቀ፤ ኤፍ​ሬም እን​ዳ​ል​ተ​ገ​ላ​በጠ ቂጣ ነው።</verse>
				<verse number="9">ጠላት ጕል​በ​ቱን በላው፤ እርሱ ግን አላ​ወ​ቀም፤ ሽበ​ትም ወጣ​በት፤ እር​ሱም ገና አላ​ስ​ተ​ዋ​ለም።</verse>
				<verse number="10">የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ውር​ደ​ቱና ስድቡ በፊቱ ነው፤ ወደ አም​ላ​ካ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን አል​ተ​መ​ለ​ሱም፤ በዚ​ህም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ፈ​ለ​ጉ​ትም።</verse>
				<verse number="11">ኤፍ​ሬ​ምም ልብ እን​ደ​ሌ​ላት እንደ ሰነፍ ርግብ ነው፤ ግብ​ፅን ጠሩ፤ ወደ አሦ​ርም ሄዱ።</verse>
				<verse number="12">ሲሄ​ዱም አሽ​ክ​ላ​ዬን እዘ​ረ​ጋ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ሰማይ ወፎ​ችም አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ መከ​ራ​ቸ​ውን ሲሰሙ እገ​ሥ​ጻ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">ከእኔ ፈቀቅ ብለ​ዋ​ልና ወዮ​ላ​ቸው! እኔ​ንም ስለ በደሉ ደን​ግ​ጠ​ዋል! እኔ ታደ​ግ​ኋ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን በሐ​ሰት ተና​ገ​ሩ​ብኝ።</verse>
				<verse number="14">በመ​ኝ​ታ​ቸው ላይ ሆነው ያለ​ቅሱ ነበር እንጂ በል​ባ​ቸው ወደ እኔ አል​ጮ​ኹም፤ ስለ እህ​ልና ስለ ወይን ይገ​ዳ​ደሉ ነበር፤</verse>
				<verse number="15">በእ​ኔም ዘንድ ተገ​ሠጹ፤ እኔም ክን​ዳ​ቸ​ውን አጸ​ናሁ፤ እነ​ርሱ ግን ክፉ ነገ​ርን መከ​ሩ​ብኝ።</verse>
				<verse number="16">ወደ ከንቱ ነገር ተመ​ለሱ፤ እንደ ጠማማ ቀስ​ትም ሆኑ፤ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም ከም​ላ​ሳ​ቸው ስን​ፍና የተ​ነሣ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ይህም በግ​ብፅ ምድር ውስጥ መሳ​ለ​ቂያ ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">በብ​ብ​ታ​ቸው እንደ መሬት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት እንደ ንስር ይመ​ጣል። ቃል ኪዳ​ኔን ተላ​ል​ፈ​ዋ​ልና፥ በሕ​ጌም ላይ ዐም​ፀ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="2">አም​ላክ ሆይ! እኛ እስ​ራ​ኤል ዐወ​ቅ​ንህ ብለው ወደ እኔ ይጮ​ኻሉ።</verse>
				<verse number="3">እስ​ራ​ኤል ደግ​ነ​ቱን ጥሎ​አ​ልና፤ ጠላ​ትም ያሳ​ድ​ደ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="4">ራሳ​ቸ​ውን አነ​ገሡ፤ ከእ​ኔም ዘንድ አይ​ደ​ለም፤ አለ​ቆ​ች​ንም አደ​ረጉ፤ እኔም አላ​ወ​ቅ​ሁም፤ ለጥ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ከብ​ራ​ቸ​ውና ከወ​ር​ቃ​ቸው ጣዖ​ታ​ትን ለራ​ሳ​ቸው አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="5">ሰማ​ርያ ሆይ! እም​ቦ​ሳ​ሽን መልሺ፤ ቍጣ​ዬም በላ​ያ​ቸው ነድ​ዶ​አል፤ እስከ መቼም ድረስ ንጹሕ ሊሆኑ አይ​ች​ሉም።</verse>
				<verse number="6">ይህ ደግሞ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ነው፤ ሠራ​ተኛ ሠራው፤ እር​ሱም አም​ላክ አይ​ደ​ለም፤ ሰማ​ርያ ሆይ! እን​ቦ​ሳሽ ተቅ​በ​ዝ​ብ​ዞ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="7">ነፋ​ስን ዘር​ተ​ዋ​ልና ዐውሎ ነፋ​ስን አጨዱ፤ ለነ​ዶ​አ​ቸ​ውም ኀይል የለ​ውም፤ ከፍ​ሬ​ውም ዱቄት አይ​ገ​ኝም፤ ቢገ​ኝም ጠላት ይበ​ላ​ዋል።</verse>
				<verse number="8">እስ​ራ​ኤል ተው​ጦ​አል፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ዛሬ እንደ ግትቻ ዕቃ ሆኖ​አል።</verse>
				<verse number="9">ለብ​ቻ​ውም እን​ደ​ሚ​ቀ​መጥ እንደ ምድረ በዳ አህያ ወደ አሦር ወጥ​ተ​ዋል፤ ኤፍ​ሬ​ምም እንደ ገና ለመ​ለመ፤ እጅ መን​ሻ​ንም ወደደ።</verse>
				<verse number="10">ስለ​ዚህ ለአ​ሕ​ዛብ አል​ፈው ይሰ​ጣሉ፤ እኔም አሁን እቀ​በ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ንጉ​ሥ​ንና አለ​ቆ​ች​ንም ይቀቡ ዘንድ ፈጽ​መው ያን​ሣሉ።</verse>
				<verse number="11">ኤፍ​ሬም መሠ​ዊ​ያን አብ​ዝ​ቶ​አ​ልና የወ​ደ​ደው መሠ​ዊያ ለኀ​ጢ​አት ሆነ​በት።</verse>
				<verse number="12">ብዙ ሕጎ​ችን እጽ​ፍ​ለ​ታ​ለሁ፤ ነገር ግን ሥር​ዐ​ቱና የተ​ወ​ደ​ደው መሠ​ዊ​ያው እንደ እን​ግዳ ነገር ተቈ​ጠሩ።</verse>
				<verse number="13">መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም ቢሠዉ፥ ሥጋ​ንም ቢበሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ቀ​በ​ላ​ቸ​ውም፤ አሁ​ንም በደ​ላ​ቸ​ውን ያስ​ባል፤ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ይበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋል፤ እነ​ር​ሱም ወደ ግብፅ ይመ​ለ​ሳሉ፤ በአ​ሦ​ርም ርኩስ ነገ​ርን ይበ​ላሉ።</verse>
				<verse number="14">እስ​ራ​ኤል ፈጣ​ሪ​ውን ረስ​ቶ​አል፤ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ች​ንም ሠር​ቶ​አል፤ ይሁ​ዳም የተ​መ​ሸ​ጉ​ትን ከተ​ሞች አብ​ዝ​ቶ​አል፤ እኔ ግን በከ​ተ​ሞች ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ መሠ​ረ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትበ​ላ​ለች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">እስ​ራ​ኤል ሆይ! ከአ​ም​ላ​ክህ ርቀህ አመ​ን​ዝ​ረ​ሃ​ልና እንደ አሕ​ዛብ ደስ አይ​በ​ልህ፤ ሐሴ​ት​ንም አታ​ድ​ርግ፤ ከእ​ህ​ሉና ከወ​ይኑ አው​ድማ ሁሉ ይልቅ የግ​ል​ሙ​ትና ዋጋን ወድ​ደ​ሃል።</verse>
				<verse number="2">የእ​ህሉ አው​ድ​ማና የወ​ይኑ መጭ​መ​ቂያ አላ​ወ​ቃ​ቸ​ውም፤ ወይ​ኑም ጐደ​ለ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድር ላይ አይ​ቀ​መ​ጡም፤ ኤፍ​ሬ​ምም በግ​ብፅ ይቀ​መ​ጣል፤ በአ​ሦ​ርም ርኩስ ነገ​ርን ይበ​ላሉ።</verse>
				<verse number="4">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የወ​ይን ጠጅን ቍር​ባን አያ​ቀ​ር​ቡም፤ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውም ደስ አያ​ሰ​ኘ​ውም፤ እንደ ኀዘ​ንም እን​ጀራ ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል፤ የሚ​በ​ላ​ውም ሁሉ ይረ​ክ​ሳል፤ እን​ጀ​ራ​ቸ​ውም ለሰ​ው​ነ​ታ​ቸው ይሆ​ናል እንጂ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ገ​ባም።</verse>
				<verse number="5">በዓ​መት በዓል ቀንና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል ቀን ምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="6">ስለ​ዚህ እነሆ ከግ​ብፅ ጕስ​ቍ​ልና የተ​ነሣ ሸሽ​ተው ይሄ​ዳሉ፤ ሜም​ፎ​ስም ትቀ​በ​ላ​ቸ​ዋ​ለች፤ በማ​ከ​ማ​ስም ይቀ​ብ​ሩ​አ​ቸ​ዋል፤ ጥፋ​ትም ወር​ቃ​ቸ​ውን ይወ​ር​ሳል፥ እሾ​ህም በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸው ውስጥ ይበ​ቅ​ላል።</verse>
				<verse number="7">የበ​ቀል ወራት መጥ​ቶ​አል፤ የፍ​ዳም ወራት ደር​ሶ​አል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም እንደ አበደ ነቢ​ይና ርኩስ መን​ፈስ እንደ አለ​በት ሰው ይታ​መ​ማል፤ ከኀ​ጢ​አ​ት​ህና ከጠ​ላ​ት​ነ​ትህ ብዛት የተ​ነ​ሣም ቍጣ​ህን አበ​ዛህ።</verse>
				<verse number="8">ኤፍ​ሬም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ጉበኛ ነበረ፤ አሁን ግን ነቢዩ በመ​ን​ገዱ ሁሉ ላይ ክፉ ወጥ​መድ ሆነ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ርኵ​ሰ​ትን አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="9">በጊ​ብዓ ዘመን እንደ ነበረ እጅግ ረከሱ፤ እር​ሱም በደ​ላ​ቸ​ውን ያስ​ባል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይበ​ቀ​ላል።</verse>
				<verse number="10">እስ​ራ​ኤ​ልን በም​ድረ በዳ እንደ አለ ወይን ሆኖ አገ​ኘ​ሁት፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያዋ ዓመት እንደ በለስ በኵ​ራት ሆነው አየ​ኋ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን ወደ ብዔ​ል​ፌ​ጎር መጡ፤ ለነ​ው​ርም ተለዩ፤ እንደ ወደ​ዱ​ትም ርኩስ ሆኑ።</verse>
				<verse number="11">ኤፍ​ሬ​ምም እንደ ወፍ በረረ፤ ክብ​ራ​ቸው ከመ​ፅ​ነ​ስና ከመ​ው​ለድ፥ ከማ​ማ​ጥም ነበር።</verse>
				<verse number="12">ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቢያ​ሳ​ድጉ ከሰው ለይች ልጅ አልባ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ሥጋዬ ከእ​ነ​ርሱ ነውና ወዮ​ላ​ቸው!</verse>
				<verse number="13">እኔ እንደ አየሁ የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ለወ​ጥ​መድ ተሰ​ጥ​ተ​ዋል፤ ኤፍ​ሬ​ምም ልጆ​ቹን ወደ ገዳ​ዮች አወጣ።</verse>
				<verse number="14">አቤቱ! ስጣ​ቸው፤ ምን ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ? መካን ማኅ​ፀ​ንን፥ የደ​ረ​ቁ​ት​ንም ጡቶች ስጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">ክፋ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ በጌ​ል​ገላ አለ፤ በዚያ ጠል​ቻ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ስለ ሠሩት ክፋት ከቤቴ አሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ አል​ወ​ድ​ዳ​ቸ​ውም፤ አለ​ቆ​ቻ​ቸው ሁሉ ዐመ​ፀ​ኞች ናቸ​ውና።</verse>
				<verse number="16">ኤፍ​ሬም ታመመ፤ ሥሩም ደረቀ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ፍሬ አያ​ፈ​ራም፤ ደግ​ሞም ቢወ​ልዱ የተ​ወ​ደ​ደ​ውን የማ​ኅ​ፀ​ና​ቸ​ውን ፍሬ እገ​ድ​ላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="17">አል​ሰ​ሙ​ት​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጥ​ላ​ቸ​ዋል፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ተቅ​በ​ዝ​ባ​ዦች ይሆ​ናሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">እስ​ራ​ኤል ፍሬው የበ​ዛ​ለት የለ​መ​ለመ ወይን ነው፤ እንደ ፍሬው ብዛት መሠ​ዊ​ያ​ዉን አብ​ዝ​ቶ​አል፤ እንደ ምድ​ሩም ማማር መጠን ሐው​ል​ቶ​ችን ሠር​ተ​ዋል።</verse>
				<verse number="2">ልባ​ቸው ተከ​ፈለ፤ አሁ​ንም ይጠ​ፋሉ፤ እርሱ መሠ​ዊ​ያ​ቸ​ውን ያፈ​ር​ሳል፤ ሐው​ል​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ያጠ​ፋል።</verse>
				<verse number="3">አሁ​ንም፥ “ንጉሥ የለ​ንም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ፈ​ራ​ን​ምና፤ ንጉ​ሥስ ምን ያደ​ር​ግ​ል​ናል?” ይላሉ።</verse>
				<verse number="4">የማ​ይ​ረ​ባ​ውን የሐ​ሰት ቃል ይና​ገ​ራሉ፤ ቃል ኪዳ​ንም ያደ​ር​ጋሉ፤ ስለ​ዚህ መር​ዛም ሣር በእ​ርሻ ትልም ላይ እን​ደ​ሚ​በ​ቅል ፍርድ ይበ​ቅ​ል​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="5">የሰ​ማ​ርያ ሰዎች በቤ​ት​አ​ዌን እን​ቦሳ አጠ​ገብ ይኖ​ራሉ፤ ሕዝቡ ያለ​ቅ​ሱ​ለ​ታል፤ ክብ​ሩም ከእ​ርሱ ዘንድ ወጥ​ቶ​አ​ልና እን​ዳ​ዘ​ኑ​በት እን​ዲሁ በክ​ብሩ ደስ ይላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">ለን​ጉሡ ለኢ​ያ​ሪም እጅ መንሻ ይሆን ዘንድ አስ​ረው ወደ አሦር ይወ​ስ​ዱ​ታል፤ ኤፍ​ሬ​ምን እፍ​ረት ይይ​ዘ​ዋል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በም​ክሩ ያፍ​ራል።</verse>
				<verse number="7">ሰማ​ርያ ንጉ​ሥ​ዋን እንደ ጥራጊ በውኃ ላይ ጣለ​ችው።</verse>
				<verse number="8">የእ​ስ​ራ​ኤል ኀጢ​አት የሆ​ኑት የአ​ዎን የኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች ይፈ​ር​ሳሉ፤ እሾ​ህና አሜ​ከ​ላም በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ላይ ይበ​ቅ​ላሉ፤ ተራ​ሮ​ች​ንም፥ “ክደ​ኑን፤ ኮረ​ብ​ቶ​ች​ንም፦ ውደ​ቁ​ብን” ይሉ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="9">እስ​ራ​ኤል ከጊ​ብዓ ዘመን ጀምሮ ኀጢ​አ​ትን ሠር​ቶ​አል፤ በዚ​ያም ጸን​ተ​ዋል፤ በጊ​ብዓ ላይ ጦር አይ​ደ​ር​ስ​ባ​ቸ​ው​ምን? መጥ​ቶም የዐ​መፅ ልጆ​ችን ገሠ​ጻ​ቸው፤</verse>
				<verse number="10">ስለ ሁለ​ቱም ኀጢ​አ​ቶ​ቻ​ቸው በገ​ሠ​ጻ​ቸው ጊዜ አሕ​ዛብ በላ​ያ​ቸው ይሰ​በ​ሰ​ቡ​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="11">ኤፍ​ሬ​ምም ቀን​በ​ርን እንደ ለመ​ደች ጊደር ነው፤ እኔ ግን በአ​ን​ገቱ ውበት እጫ​ን​በ​ታ​ለሁ፤ በኤ​ፍ​ሬም ላይ እጠ​ም​ድ​በ​ታ​ለሁ፤ ይሁ​ዳ​ንም እለ​ጕ​መ​ዋ​ለሁ፤ ያዕ​ቆ​ብም ለራሱ መን​ግ​ሥ​ትን ያስ​ተ​ካ​ክ​ላል።</verse>
				<verse number="12">ለእ​ና​ንተ ጽድ​ቅን ዝሩ፤ የሕ​ይ​ወት ፍሬን ሰብ​ስቡ፤ የጥ​በ​ብ​ንም ብር​ሃን ለራ​ሳ​ችሁ አብሩ፤ የጽ​ድ​ቃ​ችሁ መከር እስ​ኪ​ደ​ርስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈል​ጉት።</verse>
				<verse number="13">ዐመ​ፅን ለምን ተከ​ላ​ችሁ? ኀጢ​አ​ት​ንስ ለምን አጨ​ዳ​ችሁ፤ የሐ​ሰ​ት​ንም ፍሬ በል​ታ​ች​ኋል፤ በሠ​ረ​ገ​ሎ​ች​ህና በሠ​ራ​ዊ​ትህ ብዛት ታም​ነ​ሃል።</verse>
				<verse number="14">በሕ​ዝ​ብ​ህም መካ​ከል ጥፋት ይነ​ሣል፤ እና​ትም በል​ጆ​ችዋ ላይ በተ​ጣ​ለች ጊዜ የሰ​ል​ማን አለቃ ቤት​አ​ር​ብ​ኤ​ልን በጦ​ር​ነት ቀን እን​ዳ​ፈ​ረሰ፥ አም​ባ​ዎ​ችህ ሁሉ ይፈ​ር​ሳሉ።</verse>
				<verse number="15">የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ክፋት የተ​ነሣ እን​ዲሁ አደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በነ​ጋም ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ ይጥ​ሉ​ታል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">እስ​ራ​ኤል ሕፃን በነ​በረ ጊዜ ወደ​ድ​ሁት፤ ልጄ​ንም ከግ​ብፅ ጠራ​ሁት፤</verse>
				<verse number="2">አብ​ዝች ብጠ​ራ​ቸው አጥ​ብ​ቀው ከፊቴ ራቁ፤ ለበ​ዓ​ሊ​ምም ይሠዉ ነበር፤ ለተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎ​ችም ያጥኑ ነበር።</verse>
				<verse number="3">እኔም ኤፍ​ሬ​ምን ወደ​ድ​ሁት፤ በክ​ን​ዴም ተቀ​በ​ል​ሁት፤ እኔም እፈ​ው​ሳ​ቸው እንደ ነበ​ርሁ አላ​ወ​ቁም።</verse>
				<verse number="4">በሰው ገመድ በፍ​ቅ​ርም እስ​ራት ሳብ​ኋ​ቸው፤ ለእ​ነ​ር​ሱም ፊቱን በጥፊ እን​ደ​ሚ​መ​ቱት ሰው ሆን​ሁ​ላ​ቸው፤ ወደ እር​ሱም እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ፤ እች​ለ​ው​ማ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">ኤፍ​ሬም በግ​ብፅ ተቀ​መጠ፤ አሦ​ርም ንጉሡ ነው፤ መመ​ለ​ስን እንቢ ብሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="6">ጦር በከ​ተ​ማው ደከ​መች፤ ከእ​ጁም ይለ​ያ​ታል፤ ከሥ​ራ​ቸ​ውም ፍሬ ይበ​ላሉ።</verse>
				<verse number="7">ሕዝ​ቤም ከመ​ኖ​ሪ​ያው ተነ​ሥ​ቶ​አል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በክ​ብሩ ላይ ተቈጣ፤ ከፍ ከፍም አያ​ደ​ር​ገ​ውም።</verse>
				<verse number="8">እኔም “አም​ል​ኮ​ቴን ትተ​ሃል አልሁ፤ ኤፍ​ሬም ሆይ! እን​ዴት አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ? እስ​ራ​ኤል ሆይ! እን​ዴ​ትስ እደ​ግ​ፍ​ሃ​ለሁ? እን​ዴ​ትስ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ? እንደ አዳማ ነውን? ወይስ እንደ ሲባዮ? ልቤ በው​ስጤ ተና​ው​ጣ​ለች፤ ምሕ​ረ​ቴም ተገ​ል​ጣ​ለች።</verse>
				<verse number="9">እኔ አም​ላክ ነኝ እንጂ ሰው አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና፥ በመ​ካ​ካ​ል​ህም ቅዱሱ ነኝና እን​ግ​ዲህ የቍ​ጣ​ዬን መቅ​ሠ​ፍት አላ​ደ​ር​ግም፤ ኤፍ​ሬ​ም​ንም ያጠ​ፉት ዘንድ አል​ተ​ውም፤ ወደ ከተ​ማም አል​ገ​ባም አልሁ።</verse>
				<verse number="10">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እከ​ተ​ለው ዘንድ እሄ​ዳ​ለሁ፤ እርሱ ያድ​ነ​ና​ልና፤ እር​ሱም እንደ አን​በሳ ያገ​ሣል፤ የውኃ ልጆ​ችም ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="11">እንደ ወፍ ከግ​ብፅ፥ እንደ ርግ​ብም ከአ​ሶር ምድር እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ ይወ​ጣሉ፤ ወደ ቤታ​ቸ​ውም እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">ኤፍ​ሬም በሐ​ሰት፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና ይሁ​ዳም በተ​ን​ኰል ከበ​ቡኝ፤ አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐወ​ቃ​ቸው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቅዱስ ሕዝብ ተባሉ።</verse>
				<verse number="2">ኤፍ​ሬም ግን ክብ​ር​ንና ከንቱ ነገ​ርን የሚ​ያ​ሳ​ድድ ክፉ ጋኔን ነው። ሁል​ጊ​ዜም ሐሰ​ት​ንና ተን​ኰ​ልን ያበ​ዛል፤ ከአ​ሦ​ርም ጋር ቃል ኪዳን ያደ​ር​ጋል፤ ምሕ​ረ​ትም ያደ​ር​ጉ​ለት ዘንድ ወደ ግብፅ ዘይ​ትን ይል​ካል።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ ከይ​ሁዳ ጋር ይዋ​ቀ​ሳል፤ ያዕ​ቆ​ብ​ንም እንደ መን​ገዱ ይበ​ቀ​ለ​ዋል፤ እንደ ሥራ​ውም ይከ​ፍ​ለ​ዋል።</verse>
				<verse number="4">በማ​ኅ​ፀን ውስጥ ወን​ድ​ሙን በተ​ረ​ከዙ ያዘው፤ በደ​ካ​ማ​ነ​ቱም ጊዜ ከአ​ም​ላክ ጋር ታገለ።</verse>
				<verse number="5">ከመ​ል​አ​ኩም ጋር ታግሎ አሸ​ነፈ፤ አል​ቅ​ሶም ለመ​ነኝ። በቤ​ት​አ​ዎ​ንም አገ​ኘኝ፤ በዚ​ያም ከእኔ ጋር ተነ​ጋ​ገረ።</verse>
				<verse number="6">ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​ሰ​ቢ​ያው ነው።</verse>
				<verse number="7">ስለ​ዚህ ወደ አም​ላ​ክህ ተመ​ለስ፤ ምሕ​ረ​ት​ንና ፍር​ድን ጠብቅ፤ ዘወ​ት​ርም ወደ አም​ላ​ክህ ቅረብ።</verse>
				<verse number="8">በከ​ነ​ዓን እጅ የዐ​መፅ ሚዛን አለ፤ ቅሚ​ያ​ንም ይወ​ድ​ዳል።</verse>
				<verse number="9">ኤፍ​ሬ​ምም፥ “ባለ​ጸጋ ሆኜ​አ​ለሁ፤ ሀብ​ት​ንም አግ​ኝ​ቻ​ለሁ፤ በድ​ካ​ሜም ሁሉ ኀጢ​አት የሚ​ሆን በደል አይ​ገ​ኝ​ብ​ኝም” አለ።</verse>
				<verse number="10">እኔም ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ሁህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ እንደ ዓመት በዓል ቀንም እንደ ገና በድ​ን​ኳን አስ​ቀ​ም​ጥ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">ለነ​ቢ​ያ​ትም ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ ራእ​ይ​ንም አብ​ዝ​ቻ​ለሁ፤ በነ​ቢ​ያ​ትም እጅ ተመ​ስ​ያ​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">በገ​ለ​ዓድ ባይ​ሆ​ንም እንኳ በጌ​ል​ጌላ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን የሚ​ሠዉ አለ​ቆች ስተ​ዋል፤ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም በእ​ርሻ ትልም ላይ እንደ አለ የድ​ን​ጋይ ክምር ነው።</verse>
				<verse number="13">ያዕ​ቆብ ወደ ሶርያ ሀገር ሸሸ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ስለ ሚስት አገ​ለ​ገለ፤ ስለ ሚስ​ትም ጠበቀ።</verse>
				<verse number="14">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በነ​ቢይ እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣው፤ በነ​ቢ​ይም ጠበ​ቀው።</verse>
				<verse number="15">ኤፍ​ሬም ተመ​ረረ፤ ተቈ​ጣም፤ ደሙም በላዩ ላይ ይፈ​ስ​ሳል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስድ​ቡን በራሱ ላይ ይመ​ል​ሳል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">ኤፍ​ሬም እንደ ተና​ገረ በእ​ስ​ራ​ኤል ሥር​ዐ​ቱን ወሰደ፤ ለበ​ዓ​ልም አደ​ረ​ገው፤ ሞተም።</verse>
				<verse number="2">ዳግ​መ​ኛም በደሉ፤ ጠራቢ በሚ​ሠ​ራው አም​ሳል ከወ​ር​ቃ​ቸ​ውና ከብ​ራ​ቸው ጣዖ​ትን ሠሩ፤ እን​ዲ​ህም አሉ “ሰውን ሠዉ፤ ላሙ ግን አል​ቋል።”</verse>
				<verse number="3">ስለ​ዚ​ህም እንደ ማለዳ ደመና፥ በጥ​ዋት እን​ደ​ሚ​ያ​ልፍ ጠል፥ በዐ​ውሎ ነፋ​ስም ከዐ​ው​ድማ እን​ደ​ሚ​በ​ተን እብቅ፥ ከም​ድ​ጃም እን​ደ​ሚ​ወጣ ጢስ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="4">ሰማ​ይን ያጸ​ናሁ፥ ምድ​ር​ንም የፈ​ጠ​ርሁ፥ እጆ​ችም የሰ​ማይ ሠራ​ዊ​ትን ያቆሙ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ። እን​ዳ​ት​ከ​ተ​ላ​ቸ​ውም እነ​ር​ሱን አላ​ሳ​የ​ሁ​ህም። ከግ​ብፅ ምድ​ርም ያወ​ጣ​ሁህ እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር ሌላ አም​ላክ አት​ወቅ፤ ከእኔ በቀር የሚ​ያ​ድ​ንህ የለ​ምና።</verse>
				<verse number="5">በም​ድረ በዳና በዞ​ር​ህ​በት ምድር ሁሉ ጠበ​ቅ​ሁህ።</verse>
				<verse number="6">ከተ​ሰ​ማ​ራ​ችሁ በኋላ ጠገ​ባ​ችሁ፤ በጠ​ገ​ባ​ች​ሁም ጊዜ ልባ​ችሁ ታበየ፤ ስለ​ዚ​ህም ረሳ​ች​ሁኝ።</verse>
				<verse number="7">ስለ​ዚ​ህም ለይ​ሁዳ ቤት እንደ አን​በሳ፥ ለኤ​ፍ​ሬ​ምም እንደ ነብር ሆን​ሁ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">በአ​ሦ​ራ​ው​ያ​ንም መን​ገድ አጠ​ገብ እንደ ተራበ ድብ እገ​ጥ​ማ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የል​ባ​ቸ​ው​ንም ሥር እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤ በዚ​ያም የዱር አን​በ​ሶች ይበ​ሏ​ቸ​ዋል፤ የም​ድረ በዳም አራ​ዊት ይነ​ጣ​ጠ​ቋ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="9">እስ​ራ​ኤል ሆይ! በመ​ከ​ራህ ጊዜ ማን ይረ​ዳ​ሃል?</verse>
				<verse number="10">ንጉ​ሥህ ወዴት አለ? በየ​ከ​ተ​ማህ ሁሉ እስኪ ያድ​ንህ! ንጉ​ሥና አለቃ ስጠኝ የም​ት​ለኝ እስኪ እነ​ርሱ ይበ​ቀ​ሉ​ልህ?</verse>
				<verse number="11">በቍ​ጣዬ ንጉ​ሥን ሰጠ​ሁህ፤ በመ​ዓ​ቴም ሻር​ሁት።</verse>
				<verse number="12">የዐ​መ​ፅ​ህን ወን​ጀል ታገ​ሥ​ሁት፤ የኤ​ፍ​ሬም ኀጢ​አ​ቱም ተከ​ማ​ች​ት​ዋል ።</verse>
				<verse number="13">ምጥ እንደ ያዛት ሴት ጭንቅ ይይ​ዘ​ዋል፤ ይህ ልጅ ሰነፍ ነው፤ አዋ​ቂም አይ​ደ​ለም፤ በል​ጆ​ችም ተግ​ሣጽ አይ​ጸ​ናም።</verse>
				<verse number="14">ከሲ​ኦል እጅ እታ​ደ​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከሞ​ትም እቤ​ዣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ሞት ሆይ! መው​ጊ​ያህ ወዴት አለ? ሲኦል ሆይ! ድል መን​ሣ​ትህ ወዴት አለ? ደስ​ታህ ከዐ​ይ​ኖ​ችህ ተሰ​ወ​ረች።</verse>
				<verse number="15">ከወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል ይለ​ያል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከም​ድረ በዳ የሚ​ያ​ቃ​ጥል ነፋ​ስን ያመ​ጣል፤ ሥሩን ያደ​ር​ቃል፤ ምን​ጩ​ንም ያነ​ጥ​ፋል፤ ምድ​ርን ያደ​ር​ቃል፤ የተ​ወ​ደዱ ዕቃ​ዎ​ች​ንም ሁሉ ያጠ​ፋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">ሰማ​ርያ በአ​ም​ላ​ክዋ ላይ ዐም​ፃ​ለ​ችና ፈጽማ ትጠ​ፋ​ለች፤ በሰ​ይ​ፍም ይወ​ድ​ቃሉ፤ ሕፃ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል፤ እር​ጉ​ዞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይሰ​ነ​ጥ​ቋ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="2">እስ​ራ​ኤል ሆይ! በኀ​ጢ​አ​ትህ ወድ​ቀ​ሃ​ልና ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ለስ።</verse>
				<verse number="3">ከእ​ና​ንተ ጋር ቃልን ውሰዱ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተመ​ለሱ። እን​ዲ​ህም በሉት፥ “ኀጢ​አ​ትን ሁሉ አስ​ወ​ግድ፤ በቸ​ር​ነ​ትም ተቀ​በ​ለን፤ በወ​ይ​ፈ​ንም ፈንታ የከ​ን​ፈ​ራ​ች​ንን ፍሬ ለአ​ንተ እን​ሰ​ጣ​ለን።</verse>
				<verse number="4">አሦር አያ​ድ​ነ​ንም፤ በፈ​ረ​ስም ላይ አን​ቀ​መ​ጥም፤ ድሃ​አ​ደ​ጉም በአ​ንተ ዘንድ ይቅ​ር​ታን ያገ​ኛ​ልና ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የእ​ጆ​ቻ​ች​ንን ሥራ አም​ላ​ኮ​ቻ​ችን ናችሁ አን​ላ​ቸ​ውም።”</verse>
				<verse number="5">ቍጣዬ ከእ​ርሱ ዘንድ ተመ​ል​ሶ​አ​ልና ሀገ​ራ​ቸ​ውን አድ​ና​ለሁ፤ በእ​ው​ነ​ትም እወ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="6">ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም እንደ ጠል እሆ​ነ​ዋ​ለሁ፤ እንደ አበ​ባም ያብ​ባል፥ እንደ ሊባ​ኖ​ስም ሥሩን ይሰ​ድ​ዳል።</verse>
				<verse number="7">ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹም ይዘ​ረ​ጋሉ፤ ውበ​ቱም እንደ ወይራ፥ ሽታ​ውም እንደ ሊባ​ኖስ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="8">ተመ​ል​ሰ​ውም ከጥ​ላው ሥር ይቀ​መ​ጣሉ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ይኖ​ራሉ፤ ከእ​ህ​ሉም የተ​ነሣ ይጠ​ግ​ባሉ፤ እንደ ወይ​ንም አረግ ያብ​ባሉ ፤ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ውም እንደ ሊባ​ኖስ ወይን ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="9">ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ጣዖት ለኤ​ፍ​ሬም ምን​ድን ነው? እኔ አደ​ከ​ም​ሁት፤ አጸ​ና​ሁ​ትም፤ እኔ እንደ ተወ​ደደ አበባ አፈ​ራ​ዋ​ለሁ፤ ፍሬ​ህም በእኔ ዘንድ ይገ​ኛል።</verse>
				<verse number="10">ይህን ነገር የሚ​ያ​ስ​ተ​ውል ጠቢብ፤ የሚ​ያ​ው​ቃ​ትም አስ​ተ​ዋይ ማን ነው? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገ​ዶች ቀና​ዎች ናቸው፥ ጻድ​ቃ​ንም ይሄ​ዱ​ባ​ቸ​ዋል፤ ኃጥ​አን ግን ይወ​ድ​ቁ​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="29">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">ወደ ባቱ​ኤል ልጅ ወደ ኢዮ​ኤል የመ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">እና​ንተ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች! ይህን ስሙ፤ በም​ድ​ርም የም​ት​ኖሩ ሁሉ አድ​ምጡ። ይህ በዘ​መ​ና​ችሁ ወይስ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ዘመን ሆኖ ነበ​ርን?</verse>
				<verse number="3">ይህን ለል​ጆ​ቻ​ችሁ ንገሩ፤ ልጆ​ቻ​ች​ሁም ለል​ጆ​ቻ​ቸው፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ለኋ​ለ​ኛው ትው​ልድ ይን​ገሩ።</verse>
				<verse number="4">ከተ​ምች የቀ​ረ​ውን አን​በጣ በላው፤ ከአ​ን​በ​ጣም የቀ​ረ​ውን ደጎ​ብያ በላው፤ ከደ​ጎ​ብ​ያም የቀ​ረ​ውን ኩብ​ኩባ በላው።</verse>
				<verse number="5">እና​ንተ ሰካ​ራ​ሞች፥ ንቁ፤ ለመ​ስ​ከ​ርም ወይ​ንን የም​ት​ጠጡ እና​ንተ ሁላ​ችሁ! ተድ​ላና ደስታ ከአ​ፋ​ችሁ ጠፍ​ት​ዋ​ልና አል​ቅሱ፤ እዘ​ኑም።</verse>
				<verse number="6">ቍጥ​ርም የሌ​ለው ብርቱ ሕዝብ በም​ድሬ ላይ ወጥ​ቶ​አ​ልና፤ ጥር​ሳ​ቸው እንደ አን​በሳ ጥርስ፥ ክን​ዳ​ቸ​ውም እንደ አን​በሳ ደቦል ክንድ ነው።</verse>
				<verse number="7">ወይ​ኔን ባዶ ምድር አደ​ረ​ገው፤ በለ​ሴ​ንም ሰበ​ረው፤ ተመ​ለ​ከ​ተ​ውም፥ ጣለ​ውም፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹም ነጡ።</verse>
				<verse number="8">ስለ ልጅ​ነት ባልዋ ማቅ ለብሳ እን​ደ​ም​ታ​ለ​ቅስ ድን​ግል አል​ቅሺ።</verse>
				<verse number="9">መሥ​ዋ​ዕ​ቱና የመ​ጠጡ ቍር​ባን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ተወ​ግ​ዶ​አል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሠ​ውያ የም​ታ​ገ​ለ​ግሉ ካህ​ናቱ፥ አል​ቅሱ።</verse>
				<verse number="10">እር​ሻው ምድረ በዳ ሆኖ​አል፤ ምድ​ሪ​ቱም ታል​ቅስ፤ እህሉ ጠፍ​ቶ​አ​ልና፥ ወይ​ኑም ደር​ቆ​አ​ልና፥ ዘይ​ቱም ጐድ​ሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="11">መከሩ ከእ​ር​ሻ​ቸው ጠፍ​ቶ​አ​ልና ገበ​ሬ​ዎች ስለ ስን​ዴ​ውና ስለ ገብሱ ዐፈሩ፤ የወ​ይን አት​ክ​ል​ተ​ኞ​ችም ስለ ወይኑ አለ​ቀሱ።</verse>
				<verse number="12">ወይኑ ደር​ቆ​አል፤ በለ​ሱም ጠፍ​ቶ​አል፤ ሮማ​ኑና ተምሩ፥ እን​ኮ​ዩም፥ የም​ድ​ርም ዛፎች ሁሉ ደር​ቀ​ዋል፤ ደስ​ታም ከሰው ልጆች ዘንድ ርቆ​አል።</verse>
				<verse number="13">መሥ​ዋ​ዕ​ቱና የመ​ጠጡ ቍር​ባን ከአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ቤት ቀር​ቶ​አ​ልና እና​ንተ ካህ​ናት! ማቅ ታጥ​ቃ​ችሁ አል​ቅሱ፤ እና​ን​ተም የመ​ሠ​ውያ አገ​ል​ጋ​ዮች! ዋይ በሉ፤ እና​ን​ተም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች ኑና በማቅ ላይ ተኙ።</verse>
				<verse number="14">ጾምን ቀድሱ፤ ምህ​ላ​ንም ዐውጁ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹ​ንና በም​ድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሰብ​ስቡ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ን​ድ​ነት ጩኹ።</verse>
				<verse number="15">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ቀር​ቦ​አ​ልና ለቀኑ ወዮ! ወዮ! እር​ሱም በጥ​ፋት ላይ እንደ ጥፋት ይመ​ጣል።</verse>
				<verse number="16">ከዐ​ይ​ኖ​ቻ​ችሁ ፊት ምግብ፥ ከአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም ቤት ደስ​ታና ሐሤት ጠፍ​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="17">ጊደ​ሮች ከም​ሳ​ጋ​ቸው ጠፉ፤ ጎተ​ራ​ዎች ባዶ ሆኑ፤ ዐው​ድ​ማ​ዎ​ቹም ፈራ​ረሱ፤ እህሉ ደር​ቆ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="18">እን​ግ​ዲህ ለራ​ሳ​ችን ምን እን​ሰ​ብ​ስብ? የእ​ን​ስ​ሳት ጠባ​ቂ​ዎች አለ​ቀሱ፤ ማሰ​ማ​ሪያ የላ​ቸ​ው​ምና፥ የበ​ጎች መን​ጋ​ዎ​ችም ጠፍ​ተ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="19">አቤቱ! እሳት የም​ድረ በዳ​ውን ውበት አጥ​ፍ​ቶ​አ​ልና፥ ነበ​ል​ባ​ሉም የዱ​ሩን ዛፍ ሁሉ አቃ​ጥ​ሎ​አ​ልና ወደ አንተ እጮ​ኻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">ፈሳሹ ውኃ ደር​ቆ​አ​ልና፥ እሳ​ቱም የም​ድረ በዳ​ውን ውበት በል​ቶ​አ​ልና የም​ድር አራ​ዊት ወደ አንተ አን​ጋ​ጠጡ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">በጽ​ዮን መለ​ከ​ትን ንፉ፤ በቅ​ዱ​ሱም ተራ​ራዬ ላይ ዐዋጅ ንገሩ፤ በም​ድ​ርም የሚ​ኖሩ ሁሉ ይደ​ን​ግጡ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን መጥ​ቶ​አ​ልና፥ እር​ሱም ቀር​ቦ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="2">የጨ​ለ​ማና የነ​ፋስ ቀን፥ የደ​መ​ናና የጉም ቀን ነው፤ ታላ​ቅና ብርቱ ሕዝብ በተ​ራ​ሮች ላይ እንደ ወገ​ግታ ተዘ​ር​ግ​ቶ​አል፤ ከዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ጀምሮ እንደ እርሱ ያለ አል​ነ​በ​ረም፤ ከእ​ር​ሱም በኋላ እስከ ልጅ ልጅ ድረስ እንደ እርሱ ያለ አይ​ሆ​ንም።</verse>
				<verse number="3">እሳት በፊ​ታ​ቸው ትበ​ላ​ለች፥ በኋ​ላ​ቸ​ውም ነበ​ል​ባል ታቃ​ጥ​ላ​ለች፤ ምድ​ሪቱ በፊ​ታ​ቸው እንደ ደስታ ገነት፥ በኋ​ላ​ቸ​ውም እንደ ምድረ በዳ በረሃ ናት፤ ከእ​ር​ሱም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም።</verse>
				<verse number="4">መል​ካ​ቸው እንደ ፈረስ መልክ ነው፤ እንደ ፈረ​ሶ​ችም ይሮ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="5">ድም​ፃ​ቸ​ውም በተ​ራራ ላይ እንደ አሉ ሠረ​ገ​ሎች ድምፅ፥ ገለ​ባ​ው​ንም እን​ደ​ሚ​በላ እንደ እሳት ነበ​ል​ባል ድምፅ ነው፤ ለሰ​ል​ፍም እንደ ተዘ​ጋጀ እንደ ብዙና ብርቱ ሠራ​ዊት ያኰ​በ​ኵ​ባሉ።</verse>
				<verse number="6">ከፊ​ታ​ቸው አሕ​ዛብ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ የሰ​ውም ፊት ሁሉ እንደ ድስት ጥላ​ሸት ይጠ​ቍ​ራል።</verse>
				<verse number="7">እንደ ተዋ​ጊ​ዎች ይሮ​ጣሉ፤ እንደ ጦረ​ኞ​ችም በቅ​ጥሩ ላይ ይወ​ጣሉ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም በመ​ን​ገዱ ላይ ይራ​መ​ዳል፤ ከእ​ር​ም​ጃ​ቸ​ውም አያ​ፈ​ገ​ፍ​ጉም።</verse>
				<verse number="8">አንዱ ከሌ​ላው ርቆ አይ​ቆ​ምም፤ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይዘው ይሮ​ጣሉ፤ በመ​ሣ​ሪ​ያ​ቸው ላይ ይወ​ድ​ቃሉ፤ እነ​ር​ሱም አይ​ጠ​ፉም።</verse>
				<verse number="9">ከተ​ሞ​ችን ይይ​ዛሉ፤ በቅ​ጥ​ሩም ላይ ይሮ​ጣሉ፤ ወደ ቤቶ​ችም ይወ​ጣሉ፤ እንደ ሌባም በመ​ስ​ኮ​ቶች ይገ​ባሉ።</verse>
				<verse number="10">ምድ​ሪ​ቱም ከፊ​ታ​ቸው ትደ​ነ​ግ​ጣ​ለች፤ ሰማ​ይም ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣል፤ ፀሐ​ይና ጨረ​ቃም ይጨ​ል​ማሉ፤ ከዋ​ክ​ብ​ትም ብር​ሃ​ና​ቸ​ውን ይሰ​ው​ራሉ።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሠ​ራ​ዊቱ ፊት ድም​ፁን ይሰ​ጣል፤ ሰፈሩ እጅግ ብዙ ነውና፥ የቃ​ሉም ሥራ ጽኑዕ ነውና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀን ታላ​ቅና እጅግ የም​ታ​ስ​ፈራ ናትና፥ ፈጽማ ትገ​ለ​ጣ​ለች፥ መጠኗ ምን​ድን ነው? ማንስ ይች​ላ​ታል?</verse>
				<verse number="12">አሁ​ንስ ይላል አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “በፍ​ጹም ልባ​ችሁ በጾም፥ በል​ቅ​ሶና በዋ​ይታ ወደ እኔ ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="13">ልባ​ች​ሁን እንጂ ልብ​ሳ​ች​ሁን አት​ቅ​ደዱ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓ​ሪና ይቅር ባይ፥ ቍጣው የዘ​ገየ ምሕ​ረ​ቱም የበዛ፥ ለክ​ፋ​ትም የተ​ጸ​ጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመ​ለሱ።”</verse>
				<verse number="14">የሚ​መ​ለ​ስና የሚ​ጸ​ጸት እንደ ሆነ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ህ​ልና የመ​ጠጥ ቍር​ባን የሚ​ሆን በረ​ከ​ትን በኋላ የሚ​ያ​ተ​ርፍ እንደ ሆነ ማን ያው​ቃል?</verse>
				<verse number="15">በጽ​ዮን መለ​ከ​ትን ንፉ፤ ጾም​ንም ቀድሱ፤ ምህ​ላ​ንም ዐውጁ፤</verse>
				<verse number="16">ሕዝ​ቡ​ንም ሰብ​ስቡ፤ ማኅ​በ​ሩ​ንም ቀድሱ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹ​ንም ጥሩ፤ ጡት የሚ​ጠ​ቡ​ት​ንና ሕፃ​ና​ትን ሰብ​ስቡ፤ ሙሽ​ራው ከእ​ል​ፍኙ፥ ሙሽ​ራ​ዪ​ቱም ከጫ​ጕ​ላዋ ይውጡ።</verse>
				<verse number="17">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋ​ዮች ካህ​ናት በወ​ለ​ሉና በም​ሥ​ዋዑ መካ​ከል እያ​ለ​ቀሱ፥ “አቤቱ! ለሕ​ዝ​ብህ ራራ፤ አሕ​ዛ​ብም ይገ​ዙ​አ​ቸው ዘንድ ርስ​ት​ህን ለማ​ላ​ገጫ አሳ​ል​ፈህ አት​ስጥ፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል፦ አም​ላ​ካ​ቸው ወዴት ነው? ስለ ምን ይላሉ?” ይበሉ።</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ምድሩ ቀና፤ ለሕ​ዝ​ቡም ራራ​ለት።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መልሶ ሕዝ​ቡን፥ “እነሆ እህ​ል​ንና ወይ​ንን፥ ዘይ​ት​ንም እሰ​ድ​ድ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም በእ​ርሱ ትጠ​ግ​ባ​ላ​ችሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል መሰ​ደ​ቢያ አላ​ደ​ር​ጋ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="20">የሰ​ሜ​ን​ንም ሠራ​ዊት ከእ​ና​ንተ ዘንድ አር​ቃ​ለሁ፤ ወደ በረ​ሃና ወደ ምድረ በዳ እሰ​ደ​ዋ​ለሁ፤ ፊቱን ወደ መጀ​መ​ሪ​ያው ባሕር፥ ጀር​ባ​ው​ንም ወደ ኋለ​ኛው ባሕር አድ​ርጌ አሳ​ድ​ደ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ትዕ​ቢ​ትን አድ​ር​ጎ​አ​ልና ግማቱ ይወ​ጣል፤ ክር​ፋ​ቱም ይነ​ሣል።”</verse>
				<verse number="21">“ምድር ሆይ! አት​ፍሪ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነገር አድ​ር​ጎ​አ​ልና ፈጽሞ ደስ ይበ​ልሽ፤ ሐሤ​ትም አድ​ርጊ።</verse>
				<verse number="22">እና​ንተ የም​ድር እን​ስ​ሶች ሆይ! የም​ድረ በዳው ማሰ​ማ​ርያ ለም​ል​ሞ​አ​ልና፥ ዛፉም ፍሬ​ውን አፍ​ር​ቶ​አ​ልና፥ በለ​ሱና ወይ​ኑም ኀይ​ላ​ቸ​ውን ሰጥ​ተ​ዋ​ልና አት​ፍሩ።</verse>
				<verse number="23">እና​ንተ የጽ​ዮን ልጆች ሆይ! በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ሐሤ​ትም አድ​ርጉ፤ ምግ​ብን በጽ​ድቅ ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና፥ እንደ ቀድ​ሞ​ውም የበ​ል​ጉ​ንና የመ​ከ​ሩን ዝናብ ያዘ​ን​ብ​ላ​ች​ኋ​ልና።</verse>
				<verse number="24">ዐው​ድ​ማ​ዎ​ችም እህ​ልን ይሞ​ላሉ፤ መጭ​መ​ቂ​ያ​ዎ​ችም የወ​ይን ጠጅ​ንና ዘይ​ትን አት​ረ​ፍ​ር​ፈው ያፈ​ስ​ሳሉ።</verse>
				<verse number="25">የሰ​ደ​ድ​ሁ​ባ​ችሁ ታላቁ ሠራ​ዊቴ አን​በ​ጣና ደጎ​ብያ፥ ኩብ​ኩ​ባና ተምች ስለ በላ​ቸው ዓመ​ታት እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="26">ብዙ መብል ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ትጠ​ግ​ቡ​ማ​ላ​ችሁ፤ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ተአ​ም​ራ​ትን የሠ​ራ​ውን የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ታመ​ሰ​ግ​ና​ላ​ችሁ፤ ሕዝ​ቤም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አያ​ፍ​ርም።</verse>
				<verse number="27">እኔም በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል እን​ዳ​ለሁ፥ እኔም አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእ​ኔም በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ሕዝ​ቤም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አያ​ፍ​ርም።</verse>
				<verse number="28">“ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ መን​ፈ​ሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈ​ስ​ሳ​ለሁ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም ትን​ቢ​ትን ይና​ገ​ራሉ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ሕል​ምን ያል​ማሉ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ች​ሁም ራእ​ይን ያያሉ፤</verse>
				<verse number="29">ደግ​ሞም በዚያ ወራት በወ​ን​ዶ​ችና በሴ​ቶች ባሪ​ያ​ዎች ላይ መን​ፈ​ሴን አፈ​ስ​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="30">በላይ በሰ​ማይ ድን​ቆ​ችን አሳ​ያ​ለሁ፤ በታች በም​ድ​ርም ደምና እሳት የጢ​ስም ጭጋግ።</verse>
				<verse number="31">ታላ​ቋና ግልጥ የሆ​ነ​ችው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ሳት​መጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረ​ቃም ወደ ደም ይለ​ወ​ጣል።</verse>
				<verse number="32">እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም የሚ​ጠራ ሁሉ ይድ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ፥ በጽ​ዮን ተራ​ራና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይድ​ናሉ። ደግ​ሞም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጠ​ራ​ቸው፥ የም​ሥ​ራች የሚ​ሰ​በ​ክ​ላ​ቸው ይገ​ኛሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">“እነ​ሆም በዚያ ወራ​ትና በዚያ ዘመን፥ የይ​ሁ​ዳ​ንና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">አሕ​ዛ​ብን ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም ሸለቆ አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል በተ​በ​ተ​ኑ​በ​ትና ምድ​ሬን በተ​ካ​ፈ​ሉ​በት በዚያ ስለ ወገ​ኖች ስለ ርስቴ ስለ እስ​ራ​ኤል እወ​ቅ​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">በሕ​ዝ​ቤም ላይ ዕጣ ተጣ​ጣሉ፤ ወንድ ልጅን ለአ​መ​ን​ዝ​ሮች ዋጋ ሰጡ፤ ሴት ልጅ​ንም ለወ​ይን ጠጅ ሸጡ፤ ጠጡም።</verse>
				<verse number="4">“ጢሮ​ስና ሲዶና የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም አው​ራጃ ገሊ​ላም ሁሉ ሆይ! ከእ​ና​ንተ ጋራ ምን አለኝ? እና​ንተ በቀ​ልን ትበ​ቀ​ሉ​ኛ​ላ​ች​ሁን? ቂም​ንስ ትቀ​የ​ሙ​ኛ​ላ​ች​ሁን? ፈጥኜ በች​ኰላ ፍዳን በራ​ሳ​ችሁ ላይ እመ​ል​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">ብሬ​ንና ወር​ቄን ወስ​ዳ​ች​ኋ​ልና፥ የተ​ወ​ደ​ደ​ው​ንም መል​ካ​ሙን ዕቃ​ዬን ወደ ቤተ መቅ​ደ​ሳ​ችሁ አግ​ብ​ታ​ች​ኋ​ልና፥</verse>
				<verse number="6">ከዳ​ር​ቻ​ቸ​ውም ታር​ቁ​አ​ቸው ዘንድ የይ​ሁ​ዳን ልጆ​ችና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ልጆች ለግ​ሪክ ልጆች ሸጣ​ች​ኋ​ልና፥</verse>
				<verse number="7">እነሆ እነ​ር​ሱን ከሸ​ጣ​ች​ሁ​በት ስፍራ አስ​ነ​ሣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ብድ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም በራ​ሳ​ችሁ ላይ እመ​ል​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን በይ​ሁዳ ልጆች እጅ እሸ​ጣ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ለሩ​ቆቹ ሕዝብ በም​ርኮ ይሸ​ጡ​አ​ች​ኋል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="9">“ይህን በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ዐውጁ፤ ለሰ​ልፍ ተዘ​ጋጁ፤ ኀያ​ላ​ንን አስ​ነሡ፤ ሰል​ፈ​ኞች ሁሉ ይቅ​ረቡ፤ ይው​ጡም።</verse>
				<verse number="10">ማረ​ሻ​ች​ሁን ሰይፍ፥ ማጭ​ዳ​ች​ሁ​ንም ጦር ለማ​ድ​ረግ ቀጥ​ቅጡ፤ ደካ​ማ​ውም፦ እኔ ብርቱ ነኝ ይበል።</verse>
				<verse number="11">እና​ንተ በዙ​ሪያ ያላ​ችሁ አሕ​ዛብ ሁሉ፥ ፈጥ​ና​ችሁ ኑ፥ ተሰ​ብ​ሰቡ፤ የዋ​ሃ​ንም ሰል​ፈ​ኞች ይሁኑ።</verse>
				<verse number="12">“አሕ​ዛብ ሁሉ ይነሡ፤ ወደ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ሸለ​ቆም ይውጡ፤ በዙ​ሪያ ባሉ አሕ​ዛብ ሁሉ ላይ እፈ​ርድ ዘንድ በዚያ እቀ​መ​ጣ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="13">መከሩ ደር​ሶ​አ​ልና ማጭድ ስደዱ፤ መጭ​መ​ቂ​ያ​ውም ሞል​ቶ​አ​ልና ኑ ርገጡ፤ ክፋ​ታ​ቸ​ውም በዝ​ቶ​አ​ልና መጭ​መ​ቂያ ሁሉ ፈስ​ሶ​አል።”</verse>
				<verse number="14">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን በፍ​ርድ ሸለቆ ቀር​ቦ​አ​ልና ውካ​ታ​ዎች በፍ​ርድ ሸለቆ ተሰሙ።</verse>
				<verse number="15">ፀሐ​ይና ጨረቃ ይጨ​ል​ማሉ፤ ከዋ​ክ​ብ​ትም ብር​ሃ​ና​ቸ​ውን ይሰ​ው​ራሉ።</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጽ​ዮን ሆኖ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ ይጮ​ኻል፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሆኖ ቃሉን ይሰ​ጣል፤ ሰማ​ይና ምድ​ርም ይና​ወ​ጣሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ለሕ​ዝቡ ይራ​ራል፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ያጸ​ናል።</verse>
				<verse number="17">“እኔም በተ​ቀ​ደሰ ተራ​ራዬ በጽ​ዮን የም​ቀ​መጥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ያን ጊዜም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ቀ​ደ​ሰች ከተማ ትሆ​ና​ለች፥ እን​ግ​ዶ​ችም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አያ​ል​ፉ​ባ​ትም።</verse>
				<verse number="18">“በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ተራ​ሮች ማርን ያን​ጠ​ባ​ጥ​ባሉ፤ ኮረ​ብ​ቶ​ችም ወተ​ትን ያፈ​ስ​ሳሉ፤ በይ​ሁ​ዳም ያሉት ፈፋ​ዎች ሁሉ ውኃን ያጐ​ር​ፋሉ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ምንጭ ትፈ​ል​ቃ​ለች፤ የሰ​ኪ​ኖ​ን​ንም ሸለቆ ታጠ​ጣ​ለች።</verse>
				<verse number="19">በሀ​ገ​ራ​ቸው ንጹ​ሑን ደም አፍ​ስ​ሰ​ዋ​ልና በይ​ሁዳ ልጆች ላይ ስለ አደ​ረ​ጉት ግፍ ግብፅ ምድረ በዳ፥ ኤዶ​ም​ያ​ስም በረሃ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="20">ነገር ግን ይሁዳ ለዘ​ለ​ዓ​ለም፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ለልጅ ልጅ መኖ​ሪያ ትሆ​ና​ለች።</verse>
				<verse number="21">እኔም ደማ​ቸ​ውን እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤ አላ​ነ​ጻ​ቸ​ው​ምም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጽ​ዮን ያድ​ራል።”</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="30">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በቴ​ቁሔ በላም ጠባ​ቂ​ዎች መካ​ከል የነ​በረ አሞጽ በይ​ሁዳ ንጉሥ በዖ​ዝ​ያን ዘመን፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በዮ​አስ ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ዘመን፥ የም​ድር መና​ወጥ ከሆ​ነ​በት ከሁ​ለት ዓመት በፊት ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያየው ቃል ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">እን​ዲ​ህም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጽ​ዮን ሆኖ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ ይና​ገ​ራል፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሆኖ ቃሉን ይሰ​ጣል፤ የእ​ረ​ኞ​ችም ማሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎች ያለ​ቅ​ሳሉ፤ የቀ​ር​ሜ​ሎ​ስም ራስ ይደ​ር​ቃል።”</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የገ​ለ​ዓ​ድን ነፍሰ ጡሮች በብ​ረት መጋዝ ሰን​ጥ​ቀ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የደ​ማ​ስቆ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="4">በአ​ዛ​ሄል ቤት ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የወ​ልደ አዴ​ር​ንም መሠ​ረ​ቶች ትበ​ላ​ለች።</verse>
				<verse number="5">የደ​ማ​ስ​ቆ​ንም ቍል​ፎች እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ በአ​ዎን ሸለቆ የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም ሰዎች አጠ​ፋ​ለሁ፤ የካ​ራን ሰዎች ወገ​ኖ​ች​ንም እቈ​ራ​ር​ጣ​ለሁ፤ የሶ​ርያ ሕዝ​ብም ወደ ቂር ይማ​ረ​ካሉ፤” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በኤ​ዶ​ም​ያስ ይዘ​ጉ​ባ​ቸው ዘንድ የሰ​ሎ​ሞ​ንን ምርኮ ማር​ከ​ዋ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጋዛ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="7">በጋዛ ቅጥር ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ መሠ​ረ​ቶ​ች​ዋ​ንም ትበ​ላ​ለች።</verse>
				<verse number="8">የአ​ዛ​ጦን ነዋ​ሪ​ዎ​ችን አጠ​ፋ​ለሁ፤ የአ​ስ​ቀ​ሎ​ናም ሕዝብ ይጠ​ፋ​ለሁ፤ እጄ​ንም በአ​ቃ​ሮን ላይ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን የቀ​ሩ​ትም ይጠ​ፋሉ” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የሰ​ሎ​ሞን ምር​ኮ​ኞ​ችን በኤ​ዶ​ም​ያስ ዘግ​ተ​ዋ​ልና፥ የወ​ን​ድ​ሞ​ች​ንም ቃል ኪዳን አላ​ሰ​ቡ​ምና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጢ​ሮስ ኀጢ​አት አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="10">በጢ​ሮስ ቅጥር ላይ እሳ​ትን አሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ መሠ​ረ​ቶ​ች​ዋ​ንም ትበ​ላ​ለች።”</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦“ወን​ድ​ሙን በሰ​ይፍ አሳ​ድ​ዶ​ታ​ልና፥ በም​ድር ላይም ማኅ​ፀ​ንን አር​ክ​ሶ​አ​ልና፥ የሚ​ዘ​ል​ፈ​ው​ንና የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ውን በር​ብ​ሮ​አ​ልና፥ መዓ​ቱ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጠብ​ቆ​አ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የኤ​ዶ​ም​ያስ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="12">በቴ​ማን ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የቅ​ጥ​ር​ዋ​ንም መሠ​ረ​ቶች ትበ​ላ​ለች።”</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ዳር​ቻ​ቸ​ውን ያሰፉ ዘንድ የገ​ለ​ዓ​ድን ነፍሰ ጡሮች ቀድ​ደ​ዋ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የአ​ሞን ልጆች ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስም።</verse>
				<verse number="14">በራባ ቅጥር ላይ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በጦ​ር​ነት ቀን በጩ​ኸት መሠ​ረ​ቶ​ች​ዋን ትበ​ላ​ለች፤ በፍ​ጻ​ሜ​ዋም ቀን ትና​ወ​ጣ​ለች።</verse>
				<verse number="15">ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ውን፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንና ካህ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን በአ​ን​ድ​ነት ይማ​ር​ኳ​ቸ​ዋል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የኤ​ዶ​ም​ያ​ስን ንጉሥ አጥ​ንት አመድ እስ​ኪ​ሆን ድረስ አቃ​ጥ​ሎ​ታ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የሞ​ዓብ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="2">በሞ​ዓብ ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የከ​ተ​ሞ​ች​ዋ​ንም መሠ​ረ​ቶች ትበ​ላ​ለች፤ ሞዓ​ብም በድ​ካ​ምና በው​ካታ፥ በመ​ለ​ከ​ትም ድምፅ ይሞ​ታል፤</verse>
				<verse number="3">ፈራ​ጅ​ንም ከመ​ካ​ከ​ልዋ አጠ​ፋ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አለ​ቆ​ች​ዋን ሁሉ እገ​ድ​ላ​ለሁ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም አል​ጠ​በ​ቁ​ምና፥ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የተ​ከ​ተ​ሉት ከንቱ ነገር አስ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የይ​ሁዳ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="5">በይ​ሁዳ ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም መሠ​ረ​ቶች ትበ​ላ​ለች።”</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ጻድ​ቁን በብር፥ ችጋ​ረ​ኛ​ው​ንም ምድ​ርን በሚ​ረ​ግ​ጡ​በት አንድ ጥንድ ጫማ ሸጠ​ው​ታ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የእ​ስ​ራ​ኤል ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="7">የድ​ሆ​ችን ራስ ይቀ​ጠ​ቅ​ጣሉ፤ የት​ሑ​ታ​ን​ንም ፍርድ ያጣ​ም​ማሉ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም ስም ያረ​ክሱ ዘንድ አባ​ትና ልጁ ወደ አን​ዲት ሴት ይገ​ባሉ፤</verse>
				<verse number="8">ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አስ​ረው ለመ​ሥ​ዊ​ያው መጋ​ረጃ ያደ​ር​ጋሉ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውም ቤት የቅ​ሚያ ወይን ጠጅ ይጠ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="9">እኔ ግን ቁመቱ እንደ ዝግባ ቁመት፥ ብር​ታ​ቱም እንደ ወይራ ዛፍ የነ​በ​ረ​ውን አሞ​ራ​ዊ​ውን ከፊ​ታ​ቸው አጠ​ፋሁ፤ ፍሬ​ው​ንም ከላዩ፥ ሥሩ​ንም ከታቹ አጠ​ፋሁ።</verse>
				<verse number="10">የአ​ሞ​ራ​ዊ​ው​ንም ምድር ትወ​ርሱ ዘንድ ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣ​ኋ​ችሁ፤ በም​ድረ በዳም አርባ ዓመት መራ​ኋ​ችሁ።</verse>
				<verse number="11">ከወ​ንድ ልጆ​ቻ​ች​ሁም ነቢ​ያ​ትን፥ ከጐ​በ​ዛ​ዝ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ለእኔ የተ​ለ​ዩ​ትን አስ​ነ​ሣሁ፤ እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ! ይህ እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለ​ምን?” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="12">“እና​ንተ ግን ለእኔ የተ​ለ​ዩ​ትን የወ​ይን ጠጅ አጠ​ጣ​ች​ኋ​ቸው፤ ነቢ​ያ​ቱ​ንም፥ “ትን​ቢ​ትን አት​ና​ገሩ ብላ​ችሁ ከለ​ከ​ላ​ች​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">“ስለ​ዚህ ሠረ​ገላ ብር​ዑን እን​ዲ​ያ​ደቅ፥ በበ​ታ​ቻ​ችሁ ባለ መሬት እኔ አደ​ቅ​ቃ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">የሚ​ሮጥ ሰው ማም​ለጥ አይ​ች​ልም፤ ኀይ​ለ​ኛ​ውም በብ​ር​ታቱ አይ​ዝም፤ አር​በ​ኛ​ውም ነፍ​ሱን አያ​ድ​ንም።</verse>
				<verse number="15">ቀስ​ተ​ኛ​ውም አይ​ቆ​ምም፤ ፈጣ​ኑም አያ​መ​ል​ጥም፤ ፈረ​ሰ​ኛ​ውም ነፍ​ሱን አያ​ድ​ንም፤</verse>
				<verse number="16">ልበ ሙሉው ኀይ​ለ​ኛም በኀ​ይሉ አይ​ተ​ማ​መ​ንም፤ ነገር ግን በዚያ ቀን ዕራ​ቁ​ቱን ሆኖ ይሸ​ሻል” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ና​ን​ተና ከግ​ብፅ ምድር በአ​ወ​ጣ​ሁት ወገን ሁሉ ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ይህን ቃል ስሙ፤ እን​ዲ​ህም አልሁ፦</verse>
				<verse number="2">“እኔ ከም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ እና​ን​ተን ብቻ​ች​ሁን አው​ቄ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ ሁሉ እበ​ቀ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="3">በውኑ ሁለት ሰዎች ሳይ​ተ​ያዩ በአ​ን​ድ​ነት ይሄ​ዳ​ሉን?</verse>
				<verse number="4">ወይስ አን​በሳ የሚ​ነ​ጥ​ቀው ነገር ሳያ​ገኝ በጫ​ካው ውስጥ በከ​ንቱ ያገ​ሣ​ልን? ወይስ የአ​ን​በሳ ደቦል አን​ዳች ሳይዝ በመ​ደቡ ሆኖ በከ​ንቱ ይጮ​ኻ​ልን?</verse>
				<verse number="5">ወይስ ወፍ፥ አጥ​ማጅ ከሌ​ለው፥ በም​ድር ላይ በወ​ጥ​መድ ይያ​ዛ​ልን? ወይስ ወስ​ፈ​ን​ጠር አን​ዳች ሳይዝ ከም​ድር በከ​ንቱ ይፈ​ና​ጠ​ራ​ልን?</verse>
				<verse number="6">ወይስ በከ​ተማ ውስጥ መለ​ከት ሲነፋ ሕዝቡ አይ​ደ​ነ​ግ​ጡ​ምን? ወይስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያላ​ዘ​ዘው ክፉ ነገር በከ​ተማ ላይ ይመ​ጣ​ልን?</verse>
				<verse number="7">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለባ​ሪ​ያ​ዎቹ ለነ​ቢ​ያት ያል​ገ​ለ​ጠ​ው​ንና ያል​ነ​ገ​ረ​ውን ምንም አያ​ደ​ር​ግ​ምና።</verse>
				<verse number="8">አን​በ​ሳው አገሣ፤ የማ​ይ​ፈራ ማን ነው? ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገረ፤ ትን​ቢት የማ​ይ​ና​ገር ማን ነው?</verse>
				<verse number="9">በፋ​ርስ ሀገ​ሮ​ችና በግ​ብፅ ሀገ​ሮች ዐው​ጁና፥ “በሰ​ማ​ርያ ተራ​ሮች ላይ ተሰ​ብ​ሰቡ፤ በው​ስ​ጥ​ዋም የሆ​ነ​ውን ታላ​ቁን ተአ​ምር፥ በመ​ካ​ካ​ል​ዋም ያለ​ውን ግፍ ተመ​ል​ከቱ” በሉ።</verse>
				<verse number="10">“በፊቷ የሚ​መ​ጣ​ባ​ትን አላ​ወ​ቀ​ችም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በሀ​ገ​ራ​ቸው ቅሚ​ያ​ንና ግፍን የሚ​ያ​ከ​ማቹ ናቸው።”</verse>
				<verse number="11">ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እስከ ጢሮስ በአ​ለው ዙሪ​ያሽ ድረስ ምድ​ርሽ ይጠ​ፋል፥ ብር​ታ​ት​ሽ​ንም ከአ​ንቺ ያወ​ር​ዳል፤ ሀገ​ሮ​ች​ሽም ይበ​ዘ​በ​ዛሉ።”</verse>
				<verse number="12">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እረኛ ከአ​ን​በሳ አፍ ሁለት እግ​ርን ወይም የጆ​ሮን ጫፍ እን​ደ​ሚ​ያ​ድን፥ እን​ዲሁ በሰ​ማ​ርያ በአ​ሕ​ዛብ ፊትና በደ​ማ​ስቆ የተ​ቀ​መ​ጡት የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይድ​ናሉ።</verse>
				<verse number="13">“ካህ​ናት ሆይ! ስሙ፤ በያ​ዕ​ቆ​ብም ቤት ላይ መስ​ክሩ፥ ይላል ሁሉን የሚ​ችል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="14">እስ​ራ​ኤ​ልን ስለ ኀጢ​አቱ በም​በ​ቀ​ል​በት ቀን የቤ​ቴ​ልን መሠ​ዊ​ያ​ዎች ደግሞ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤ የመ​ሠ​ዊ​ያው ቀን​ዶች ይሰ​በ​ራሉ፤ ወደ ምድ​ርም ይወ​ድ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="15">የክ​ረ​ም​ቱ​ንና የበ​ጋ​ዉን ቤት እመ​ታ​ለሁ፤ በዝ​ሆ​ንም ጥርስ የተ​ለ​በ​ጡት ቤቶች ይጠ​ፋሉ፤ ሌሎ​ችም ታላ​ላ​ቆች ቤቶች ይፈ​ር​ሳሉ” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">በሰ​ማ​ርያ ተራራ የም​ት​ኖሩ፥ ድሆ​ች​ንም የም​ት​በ​ድሉ፥ ችግ​ረ​ኞ​ች​ንም የም​ታ​ስ​ጨ​ንቁ፥ ጌቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም፦ አምጡ እን​ጠጣ የም​ትሉ እና​ንተ የባ​ሳን ላሞች ሆይ! ይህን ቃል ስሙ።</verse>
				<verse number="2">ጌታ አግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “እና​ን​ተን በሰ​ልፍ ዕቃ፥ ቅሬ​ታ​ች​ሁ​ንም በመ​ቃ​ጥን የሚ​ወ​ስ​ዱ​በት ቀን እነሆ በላ​ያ​ችሁ ይመ​ጣል” ብሎ በቅ​ዱ​ስ​ነቱ ምሎ​አል።</verse>
				<verse number="3">“ዕራ​ቁ​ታ​ች​ሁን ያወ​ጡ​አ​ች​ኋል፤ እርስ በር​ሳ​ች​ሁም ትተ​ያ​ያ​ላ​ችሁ፤ በሬ​ማ​ንም ተራራ ትጣ​ላ​ላ​ችሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="4">“ወደ ቤቴል ገብ​ታ​ችሁ ኀጢ​አ​ትን ሠራ​ችሁ፤ በጌ​ል​ገ​ላም ኀጢ​አ​ትን አበ​ዛ​ችሁ፤ በየ​ማ​ለ​ዳ​ውም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ በየ​ሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁን አቀ​ረ​ባ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="5">ሕጉን በውጭ አነ​በ​ባ​ችሁ፤ የታ​መ​ነም አላ​ች​ሁት፤ በፈ​ቃ​ዳ​ች​ሁም የም​ታ​ቀ​ር​ቡ​ትን አው​ጁና አውሩ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="6">“በከ​ተ​ማ​ችሁ ሁሉ ጥር​ስን ማጥ​ረ​ስን፥ በስ​ፍ​ራ​ች​ሁም ሁሉ እን​ጀ​ራን ማጣ​ትን ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ እና​ንተ ግን ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="7">መከር ሳይ​ደ​ርስ ገና ከሦ​ስት ወር በፊት ዝና​ብን ከለ​ከ​ል​ኋ​ችሁ፤ በአ​ን​ድም ከተማ ላይ አዘ​ነ​ብሁ፤ በሌ​ላ​ውም ከተማ ላይ እን​ዳ​ይ​ዘ​ንብ አደ​ረ​ግሁ፤ በአ​ንድ ወገን ዘነበ፤ ያል​ዘ​ነ​በ​በ​ትም ወገን ደረቀ።</verse>
				<verse number="8">የሁ​ለት ወይም የሦ​ስት ከተ​ሞች ሰዎች ወደ አን​ዲት ከተማ ውኃ ይጠጡ ዘንድ ሄዱ፤ ነገር ግን አል​ረ​ኩም፤ እና​ንተ ግን ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="9">በአ​ባ​ርና በቸ​ነ​ፈር መታ​ኋ​ችሁ፤ አት​ክ​ል​ታ​ችሁ፥ ወይ​ና​ች​ሁና በለ​ሳ​ችሁ፥ ወይ​ራ​ች​ሁም ከበጀ በኋላ ተምች በላው፤ ይህም ሆኖ እና​ንተ ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="10">“በግ​ብፅ እንደ ሆነው ሞትን ሰደ​ድ​ሁ​ባ​ችሁ፤ ጐበ​ዛ​ዝ​ቶ​ቻ​ች​ሁን በሰ​ይፍ ገደ​ልሁ፤ ፈረ​ሶ​ቻ​ች​ሁ​ንም አስ​ማ​ረ​ክሁ፤ በሰ​ፈ​ራ​ች​ሁም እሳ​ትን ሰድጄ አጠ​ፋ​ኋ​ችሁ፤ በዚ​ህም ሁሉ እና​ንተ ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="11">ሰዶ​ም​ንና ገሞ​ራን አስ​ቀ​ድሜ እንደ ገለ​በ​ጥ​ኋ​ቸው፥ እን​ዲሁ ገለ​በ​ጥ​ኋ​ችሁ፤ እና​ን​ተም ከእ​ሳት ውስጥ እንደ ተነ​ጠቀ ትን​ታግ ሆና​ችሁ፤ በዚ​ህም ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="12">“ስለ​ዚህ እስ​ራ​ኤል ሆይ! እን​ደ​ዚህ አደ​ር​ግ​ብ​ሃ​ለሁ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሆይ! እን​ደ​ዚህ ስለ​ማ​ደ​ር​ግ​ብህ የአ​ም​ላ​ክ​ህን ስም ለመ​ጥ​ራት ተዘ​ጋጅ።</verse>
				<verse number="13">እነሆ ነጐ​ድ​ጓ​ድን የሚ​ያ​ጸና፥ ነፋ​ስ​ንም የፈ​ጠረ፥ የመ​ሢ​ሕን ነገር ለሰው የሚ​ነ​ግር፥ ንጋ​ትን ጭጋግ የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በም​ድ​ርም ከፍ​ታ​ዎች ላይ የሚ​ረ​ግጥ፥ ስሙ ሁሉን የሚ​ችል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በእ​ና​ንተ ላይ ለሙሾ የማ​ነ​ሣ​ውን ይህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።</verse>
				<verse number="2">የእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ወደ​ቀች፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አት​ነ​ሣም፤ በም​ድ​ርዋ ላይ ተጣ​ለች፤ የሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ትም የለም።</verse>
				<verse number="3">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “ሺህ ከሚ​ወ​ጡ​ባት ከተማ መቶ ይቀ​ራሉ፤ መቶም ከሚ​ወ​ጡ​ባት ከተማ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ዐሥር ይቀ​ራሉ።”</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “እኔን ፈልጉ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="5">ነገር ግን ጌል​ገላ ፈጽሞ ትማ​ረ​ካ​ለ​ችና፥ ቤቴ​ልም እን​ዳ​ል​ነ​በ​ረች ትሆ​ና​ለ​ችና ቤቴ​ልን አት​ፈ​ልጉ፤ ወደ ጌል​ገ​ላም አት​ሂዱ፤ ወደ ቤር​ሳ​ቤ​ህም አት​ለፉ።”</verse>
				<verse number="6">በዮ​ሴፍ ቤት እሳት እን​ዳ​ት​ቃ​ጠል፥ እን​ዳ​ት​በ​ላ​ቸ​ውም የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቤት እሳት የሚ​ያ​ጠ​ፋ​ላ​ቸው እን​ዳ​ያጡ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈልጉ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍር​ድን በሰ​ማይ ያደ​ር​ጋል፤ ጽድ​ቅ​ንም በም​ድር ላይ ይመ​ሠ​ር​ታል።</verse>
				<verse number="8">ሁሉን የሚ​ሠ​ራና የሚ​ያ​ቅ​ናና፥ ብር​ሃ​ኑን ወደ መስዕ የሚ​መ​ል​ሰው፥ ቀኑን እንደ ሌሊት የሚ​ያ​ጨ​ል​መው፥ የባ​ሕ​ሩ​ንም ውኃ ጠርቶ በም​ድር ፊት የሚ​ያ​ፈ​ስ​ሰው ስሙ ሁሉን የሚ​ችል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።</verse>
				<verse number="9">በኀ​ያ​ላን ላይ ቅጥ​ቃ​ጤን፥ በአ​ን​ባ​ዎ​ችም ላይ ጕስ​ቍ​ል​ናን ያመ​ጣል።</verse>
				<verse number="10">በበሩ የሚ​ገ​ሥ​ጸ​ውን ጠሉ፤ እው​ነ​ት​ንም የሚ​ና​ገ​ረ​ውን ተጸ​የፉ።</verse>
				<verse number="11">ድሃ​ው​ንም ደብ​ድ​ባ​ች​ኋ​ልና፤ መማ​ለ​ጃ​ንም ከእ​ርሱ ወስ​ዳ​ች​ኋ​ልና፤ ያማሩ ቤቶ​ች​ንም መር​ጣ​ችሁ ሠር​ታ​ች​ኋ​ልና፥ ነገር ግን አት​ኖ​ሩ​ባ​ቸ​ውም፤ ያማሩ የወ​ይን ቦታ​ዎ​ችም ተክ​ላ​ች​ኋል፤ ነገር ግን ወይ​ንን አት​ጠ​ጡም።</verse>
				<verse number="12">ጻድ​ቁን የም​ታ​ስ​ጨ​ንቁ፥ ጉቦ​ንም የም​ት​ቀ​በሉ፥ በበ​ሩም የች​ግ​ረ​ኛ​ውን ፍርድ የም​ታ​ጣ​ምሙ እና​ንተ ሆይ! በደ​ላ​ችሁ እን​ዴት እንደ በዛ፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም እን​ዴት እንደ ጸና እኔ ዐው​ቃ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="13">ስለ​ዚህ ዘመኑ ክፉ ነውና በዚያ ዘመን አስ​ተ​ዋይ ዝም ይላል።</verse>
				<verse number="14">በሕ​ይ​ወት ትኖሩ ዘንድ መል​ካ​ሙን ፈልጉ፤ ክፉ​ው​ንም አይ​ደ​ለም፤ እን​ዲሁ እና​ንተ እንደ ተና​ገ​ራ​ችሁ ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="15">ክፉ​ውን ጥሉ፤ መል​ካ​ሙ​ንም ውደዱ፤ በበ​ሩም አደ​ባ​ባይ ፍር​ድን አጽኑ፤ ምና​ል​ባት ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዮ​ሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="16">ስለ​ዚህ ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በየ​አ​ደ​ባ​ባዩ ሁሉ ላይ ዋይታ ይሆ​ናል፤ በየ​መ​ን​ገ​ዱም ሁሉ ላይ ወዮ ወዮ ይባ​ላል፤ ገበ​ሬ​ዎ​ቹም ወደ ልቅሶ፥ አል​ቃ​ሾ​ቹም ወደ ዋይታ ይጠ​ራሉ።</verse>
				<verse number="17">በመ​ካ​ከ​ልህ አል​ፋ​ለ​ሁና በጎ​ዳ​ናው ሁሉ ልቅሶ ይሆ​ናል” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="18">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቀን ለም​ት​ፈ​ልጉ ወዮ​ላ​ችሁ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቀን ለምን ትፈ​ል​ጋ​ላ​ችሁ? ጨለማ ነው እንጂ ብር​ሃን አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="19">ከአ​ን​በሳ ፊት እንደ ሸሸ፥ ድብም እን​ዳ​ገ​ኘው ሰው፥ ወደ ቤትም ገብቶ እጁን በግ​ድ​ግዳ ላይ እን​ዳ​ስ​ደ​ገ​ፈና እባብ እንደ ነደ​ፈው ሰው ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="20">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ብር​ሃን ሳይ​ሆን ጨለማ አይ​ደ​ለ​ምን? ፀዳል የሌ​ለ​ውም ድቅ​ድቅ ጨለማ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="21">ዓመት በዓ​ላ​ች​ሁን ጠል​ች​ዋ​ለሁ፤ አር​ቄ​ው​ማ​ለሁ፤ መዓዛ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን አላ​ሸ​ትም።</verse>
				<verse number="22">የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁ​ንና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ና​ች​ሁን ብታ​ቀ​ር​ቡ​ል​ኝም እንኳ አል​ቀ​በ​ለ​ውም፤ የድ​ኅ​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁ​ንም አል​መ​ለ​ከ​ትም።</verse>
				<verse number="23">የዝ​ማ​ሬ​ህ​ንም ጩኸት ከእኔ ዘንድ አርቅ፤ የመ​ሰ​ን​ቆ​ህ​ንም ዜማ አላ​ዳ​ም​ጥም።</verse>
				<verse number="24">ነገር ግን ፍርድ እንደ ውኃ፥ ጽድ​ቅም እን​ደ​ማ​ይ​ደ​ርቅ ፈሳሽ ይፍ​ሰስ።</verse>
				<verse number="25">“የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በውኑ በም​ድረ በዳ አርባ ዓመት ሙሉ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና ቍር​ባ​ንን አቅ​ር​ባ​ች​ሁ​ል​ኛ​ልን?</verse>
				<verse number="26">ለራ​ሳ​ች​ሁም የሠ​ራ​ች​ኋ​ቸ​ውን ምስ​ሎች፥ የሞ​ሎ​ክን ድን​ኳ​ንና የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የሬ​ፋ​ንን ኮከብ አነ​ሣ​ችሁ።</verse>
				<verse number="27">ስለ​ዚህ ከደ​ማ​ስቆ ወደ​ዚያ አስ​ማ​ር​ካ​ች​ኋ​ለሁ” ይላል ስሙ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የተ​ባለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">ጽዮ​ንን ለሚ​ንቁ፥ በሰ​ማ​ር​ያም ተራራ ለሚ​ታ​መኑ ሰዎች ወዮ​ላ​ቸው፤ የአ​ሕ​ዛ​ብን አለ​ቆች ለቀ​ሙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ፥ ወደ ካልኔ ተሻ​ግ​ራ​ችሁ ተመ​ል​ከቱ፤ ከዚ​ያም ወደ ኤማ​ት​ራባ እለፉ፤ ከዚ​ያም ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ጌት ውረዱ፤ እነ​ርሱ ከእ​ነ​ዚህ መን​ግ​ሥ​ታት ይበ​ረ​ታሉ፤ ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ከድ​ን​በ​ራ​ቸው ይሰ​ፋ​ልና።</verse>
				<verse number="3">ክፉ ቀንን ለሚ​ፈ​ል​ጓት፥ የሐ​ሰት ሰን​በ​ታ​ትን ለሚ​ያ​ቀ​ራ​ር​ቡና አንድ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ፥</verse>
				<verse number="4">ከዝ​ሆን ጥርስ በተ​ሠራ አልጋ ላይ ለሚ​ተኙ፥ በም​ን​ጣ​ፋ​ቸው ደስ ለሚ​ሰኙ፥ ከበ​ጎ​ችም መንጋ ጠቦ​ትን፥ ከጋ​ጥም ውስጥ ጥጃን ለሚ​መ​ገቡ፥</verse>
				<verse number="5">ከበ​ገ​ናው ድምፅ ጋር አስ​ተ​ባ​ብ​ረው ለሚ​ያ​ጨ​በ​ጭቡ ሰዎች፤ ይኸ​ውም የማ​ያ​ልፍ ለሚ​መ​ስ​ላ​ቸ​ውና እን​ደ​ሚ​ያ​መ​ል​ጣ​ቸው ለማ​ያ​ውቁ፤</verse>
				<verse number="6">በጽዋ የቀላ ወይን ለሚ​ጠጡ፥ እጅግ በአ​ማረ ሽቱም ለሚ​ቀቡ፥ በዮ​ሴፍ ስብ​ራት ለማ​ያ​ስቡ ወዮ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">ስለ​ዚህ ከአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸው አስ​ቀ​ድ​መው ይማ​ረ​ካሉ፤ ሯጮች የሚ​ሆኑ የኤ​ፍ​ሬም ፈረ​ሶ​ችም ያል​ቃሉ።</verse>
				<verse number="8">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “የያ​ዕ​ቆ​ብን ትዕ​ቢት አረ​ክ​ሳ​ለሁ፤ ሀገ​ሮ​ቹ​ንም ጠላሁ፤ ከተ​ሞ​ቹ​ንም ከሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸው ሰዎች ጋር አጠ​ፋ​ለሁ” ብሎ በራሱ ምሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="9">እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ዐሥር ሰዎች በአ​ንድ ቤት ውስጥ ቢቀሩ እነ​ርሱ ይሞ​ታሉ፤ የቀ​ሩት ግን ይተ​ር​ፋሉ።</verse>
				<verse number="10">አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ከቤት ያወጡ ዘንድ ቤተ​ሰ​ቦ​ቻ​ቸው በወ​ሰ​ዱ​አ​ቸው ጊዜ፥ ቤት ጠባ​ቂ​ውን በአ​ንተ ዘንድ የቀረ አለን? በአ​ለው ጊዜ እርሱ የለም ይላል። ያም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም እን​ዳ​ት​ጠራ ዝም በል ይለ​ዋል።</verse>
				<verse number="11">እነ​ሆም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዝ​ዛል፤ ታላ​ቁ​ንም ቤት በማ​ፍ​ረስ፥ ታና​ሹ​ንም ቤት በመ​ሰ​ባ​በር ይመ​ታል።</verse>
				<verse number="12">ፍር​ድን ወደ ቍጣ፥ የእ​ው​ነ​ት​ንም ፍሬ ወደ እሬት ለው​ጣ​ች​ኋ​ልና፥ በውኑ ፈረ​ሶች በጭ​ንጫ ላይ ይሮ​ጣ​ሉን? ወይስ በሬ​ዎች በዚያ ላይ ያር​ሳ​ሉን?</verse>
				<verse number="13">በከ​ንቱ ነገር ደስ የሚ​ላ​ችሁ በኀ​ይ​ላ​ችን ቀን​ዶ​ችን አበ​ቀ​ልን የም​ትሉ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="14">“የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ እነሆ እኔ የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቋ​ች​ሁን ሕዝብ አስ​ነ​ሣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥” ይላል የሠ​ራ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ር​ሱም ከሐ​ማት መግ​ቢያ ጀም​ረው እስከ ዐረባ ወንዝ ድረስ ትገቡ ዘንድ አይ​ፈ​ቅ​ዱ​ላ​ች​ሁም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አሳ​የኝ፤ እነ​ሆም ከም​ሥ​ራቅ አን​በጣ ይመ​ጣል፤ አን​ዱም ኵብ​ኵባ ንጉሡ ጎግ ነበረ።</verse>
				<verse number="2">የም​ድ​ሩ​ንም ሣር በልቶ ይጨ​ር​ሳል፤ እኔም፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! ይቅር እን​ድ​ትል እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ ያዕ​ቆ​ብን ማን ያነ​ሣ​ዋል? ጥቂት ነውና” አልሁ።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ​ዚህ ነገር ራራ፤ “ይህ አይ​ሆ​ንም፤” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="4">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አሳ​የኝ፤ እነ​ሆም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ፍ​ረድ በቃሉ እሳ​ትን ጠራ፤ እር​ስ​ዋም ታላ​ቁን ቀላ​ይና ምድ​ርን በላች።</verse>
				<verse number="5">እኔም፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! እን​ድ​ት​ተው እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ ያዕ​ቆ​ብን ማን ያነ​ሣ​ዋል? ጥቂት ነውና” አልሁ።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ​ዚህ ነገር ራራ፤ “ይህ ደግሞ አይ​ሆ​ንም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="7">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አሳ​የኝ፤ እነ​ሆም አንድ ሰው በቱ​ንቢ በተ​ሠራ ቅጥር ላይ ቆሞ ነበር፤ በእ​ጁም ቱንቢ ነበር።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አሞጽ ሆይ! የም​ታ​የው ምን​ድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “ቱንቢ ነው” አልሁ። ጌታም፥ “እነሆ! በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ቱንቢ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ደግሞ ይቅር አል​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="9">መሳ​ቂያ የሆኑ የኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች ይፈ​ር​ሳሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መቅ​ደ​ሶች ባድማ ይሆ​ናሉ፤ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ቤት ላይ በሰ​ይፍ እነ​ሣ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="10">የቤ​ቴ​ልም ካህን አሜ​ስ​ያስ ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ወደ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ልኮ፥ “አሞጽ በእ​ስ​ራ​ኤል ቤት መካ​ከል ዐም​ፆ​ብ​ሃል፤ ምድ​ሪ​ቱም ቃሉን ሁሉ ልት​ሸ​ከም አት​ች​ልም” አለ።</verse>
				<verse number="11">አሞጽ፥ “ኢዮ​ር​ብ​ዓም በሰ​ይፍ ይሞ​ታል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ከሀ​ገሩ ተማ​ርኮ ይሄ​ዳል” ብሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="12">አሜ​ስ​ያ​ስም አሞ​ጽን፥ “ባለ ራእዩ ሆይ! ሂድ፤ ወደ ይሁዳ ምድር ሽሽ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጥ፥ በዚ​ያም ትን​ቢ​ትን ተና​ገር፤</verse>
				<verse number="13">ነገር ግን ቤቴል የን​ጉሥ መቅ​ደ​ስና የመ​ን​ግ​ሥት ቤት ናትና ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በዚህ ደግሞ ትን​ቢት አት​ና​ገር” አለው።</verse>
				<verse number="14">አሞ​ጽም መልሶ አሜ​ስ​ያ​ስን አለው፥ “እኔ ላም ጠባ​ቂና በለስ ለቃሚ ነኝ እንጂ ነቢይ ወይም የነ​ቢይ ልጅ አይ​ደ​ለ​ሁም፤</verse>
				<verse number="15">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ​ቹን ከመ​ከ​ተል ወሰ​ደኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ሂድ፥ ለሕ​ዝቤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ትን​ቢት ተና​ገር አለኝ።</verse>
				<verse number="16">አሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ አንተ፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ትን​ቢት አት​ና​ገር፥ የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንም ቤት አት​ዘ​ብ​ዝ​ባ​ቸው ብለ​ሃል።</verse>
				<verse number="17">ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሚስ​ትህ በከ​ተ​ማ​ይቱ ውስጥ አመ​ን​ዝራ ትሆ​ና​ለች፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ህም በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ምድ​ር​ህም በገ​መድ ትከ​ፈ​ላ​ለች፤ አን​ተም በረ​ከ​ሰች ምድር ትሞ​ታ​ለህ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ከም​ድሩ ተማ​ርኮ ይሄ​ዳል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አሳ​የኝ፤ እነ​ሆም የቃ​ር​ሚያ ፍሬ የሞ​ላ​በት ዕን​ቅብ ነበረ።</verse>
				<verse number="2">እር​ሱም፥ “አሞጽ ሆይ! የም​ታ​የው ምን​ድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “የቃ​ር​ሚያ ፍሬ የሞ​ላ​በት ዕን​ቅብ ነው” አል​ሁት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “ፍጻሜ በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ መጥ​ቶ​አል፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ደግሞ ይቅር አል​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="3">ያን​ጊ​ዜም በመ​ቅ​ደ​ሶ​ቻ​ቸው ዋይ ዋይ ይላሉ” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በየ​ስ​ፍ​ራው የሚ​ወ​ድ​ቀው ሬሳ ይበ​ዛ​ልና፤ እነ​ር​ሱም ይጠ​ፋ​ሉና።</verse>
				<verse number="4">ችግ​ረ​ኛ​ውን በጥ​ዋት የም​ታ​ስ​ጨ​ንቁ፥ የሀ​ገ​ሩ​ንም ድሃ የም​ት​ቀሙ እና​ንተ ሆይ!</verse>
				<verse number="5">“እህ​ልን እን​ሸጥ ዘንድ መባ​ቻው መቼ ያል​ፋል? የኢፍ መስ​ፈ​ሪ​ያ​ው​ንም እያ​ሳ​ነ​ስን፥ ሰቅ​ሉ​ንም እያ​በ​ዛን፥ በሐ​ሰ​ተ​ኛም ሚዛን እያ​ታ​ለ​ልን፥</verse>
				<verse number="6">ድሃ​ውን በብር፥ ችግ​ረ​ኛ​ው​ንም በአ​ንድ ጥንድ ጫማ እን​ገዛ ዘንድ፥ በእ​ህ​ላ​ች​ንም ንግድ እን​ድ​ን​ጠ​ቀም ሰን​በት መቼ ያል​ፋል? የም​ትሉ እና​ንተ ሆይ! ይህን ስሙ።”</verse>
				<verse number="7">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በያ​ዕ​ቆብ ትዕ​ቢት እን​ዲህ ብሎ ምሎ​አል፥ “ሥራ​ች​ሁን ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ምንም አል​ረ​ሳም።</verse>
				<verse number="8">በውኑ ምድ​ሪቱ ስለ​ዚህ ነገር አት​ና​ወ​ጥ​ምን? በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖር ሁሉ አያ​ለ​ቅ​ስ​ምን? ጦር​ነት እንደ ወንዝ ይፈ​ስ​ሳል፤ እንደ ግብ​ፅም ወንዝ ይሞ​ላል፤ ደግ​ሞም ይወ​ር​ዳል።</verse>
				<verse number="9">በዚ​ያም ቀን ፀሐይ በቀ​ትር ይገ​ባል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ብር​ሃ​ንም በም​ድር ላይ በቀን ይጨ​ል​ማል።</verse>
				<verse number="10">ዓመት በዓ​ላ​ች​ሁ​ንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማ​ሬ​ያ​ች​ሁ​ንም ወደ ዋይታ እለ​ው​ጣ​ለሁ፤ ማቅ​ንም በወ​ገብ ሁሉ ላይ፥ ቡሃ​ነ​ት​ንም በራስ ሁሉ ላይ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ እንደ ወዳጅ ልቅሶ አደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉት እንደ መከራ ቀን ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="11">“እነሆ በም​ድር ላይ ራብን የም​ሰ​ድ​ድ​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ከመ​ስ​ማት እንጂ እን​ጀ​ራን ከመ​ራ​ብና ውኃን ከመ​ጠ​ማት አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="12">ከባ​ሕ​ርም እስከ ባሕር ድረስ፥ ከሰ​ሜ​ንም እስከ ምሥ​ራቅ ድረስ ይቅ​በ​ዘ​በ​ዛሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ለመ​ሻት ይር​ዋ​ር​ዋ​ጣሉ፤ አያ​ገ​ኙ​ት​ምም።</verse>
				<verse number="13">በዚያ ቀን መልከ መል​ካ​ሞቹ ደና​ግ​ልና ጐበ​ዛ​ዝቱ በጥም ይዝ​ላሉ።</verse>
				<verse number="14">ዳን ሆይ፥ ሕያው አም​ላ​ክ​ህን! ደግ​ሞም፦ ሕያው የቤ​ር​ሳ​ቤ​ህን አም​ላክ ብለው በሰ​ማ​ርያ መማ​ፀኛ የሚ​ምሉ፥ እነ​ርሱ ይወ​ድ​ቃሉ፥ ደግ​ሞም አይ​ነ​ሡም።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ሠ​ው​ያው ላይ ቆሞ አየ​ሁት፤ እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “አበ​ቦች የተ​ሳ​ሉ​ባ​ቸ​ውን ምሰ​ሶ​ዎ​ችን ምታ፤ መድ​ረ​ኮ​ቹም ይና​ወ​ጣሉ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ቍረጥ፤ እኔም ከእ​ነ​ርሱ የቀ​ሩ​ትን በሰ​ይፍ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ ከሚ​ሸ​ሹ​ትም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም፤ ከሚ​ያ​መ​ል​ጡ​ትም የሚ​ድን የለም።</verse>
				<verse number="2">ወደ ሲኦል ቢወ​ርዱ እጄ ከዚያ ታወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለች፤ ወደ ሰማ​ይም ቢወጡ ከዚያ አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="3">በቀ​ር​ሜ​ሎስ ራስ ውስጥ ቢሸ​ሸጉ ፈልጌ ከዚያ አወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በባ​ሕ​ሩም ጥልቅ ውስጥ ከዐ​ይኔ ቢደ​በቁ በዚያ እባ​ቡን አዝ​ዛ​ለሁ፤ እር​ሱም ይነ​ድ​ፋ​ቸ​ዋል፤</verse>
				<verse number="4">በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ፊት ተማ​ር​ከው ቢሄዱ በዚያ ሰይ​ፍን አዝ​ዛ​ታ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋም ትገ​ድ​ላ​ቸ​ዋ​ለች፤ ዐይ​ኔ​ንም ለመ​ል​ካም ሳይ​ሆን ለክ​ፋት በእ​ነ​ርሱ ላይ እጥ​ላ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="5">ሁሉን የሚ​ችል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ርን ሁሉ ይዳ​ስ​ሳል፤ ያነ​ዋ​ው​ጣ​ታ​ልም፤ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም ሁሉ ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ግድያ እንደ ወንዝ ይፈ​ስ​ሳል፤ ደግ​ሞም እንደ ግብፅ ወንዝ ይወ​ር​ዳል።</verse>
				<verse number="6">አዳ​ራ​ሹን በሰ​ማይ የሠራ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም በም​ድር ላይ የመ​ሠ​ረተ፥ የባ​ሕ​ር​ንም ውኃ ጠርቶ በም​ድር ፊት የሚ​ያ​ፈ​ስ​ሰው እርሱ ነው፤ ስሙም ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።</verse>
				<verse number="7">“የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ! እና​ንተ ለእኔ እንደ ኢት​ዮ​ጵያ ልጆች አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ ምድር፥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ከቀ​ጰ​ዶ​ቅያ፥ ሶር​ያ​ው​ያ​ን​ንም ከጕ​ድ​ጓድ ያወ​ጣሁ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="8">እነሆ የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖች በኀ​ጢ​አ​ተኛ መን​ግ​ሥት ላይ ናቸው፤ ከም​ድ​ርም ፊት አጠ​ፋ​ታ​ለሁ፤ ነገር ግን የያ​ዕ​ቆ​ብን ቤት ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="9">እነሆ አዝ​ዛ​ለሁ፤ እህ​ልም በመ​ንሽ እን​ደ​ሚ​ዘራ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል እዘ​ራ​ለሁ፤ ነገር ግን አን​ዲት ቅን​ጣት በም​ድር ላይ አት​ወ​ድ​ቅም።</verse>
				<verse number="10">ክፉው ነገር አይ​ደ​ር​ስ​ብ​ንም፤ አያ​ገ​ኘ​ን​ምም የሚሉ የሕ​ዝቤ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ሁሉ በሰ​ይፍ ይሞ​ታሉ።</verse>
				<verse number="11">“በዚያ ቀን የወ​ደ​ቀ​ች​ውን የዳ​ዊ​ትን ቤት አነ​ሣ​ለሁ፤ የተ​ና​ደ​ው​ንም ቅጥ​ር​ዋን እጠ​ግ​ና​ለሁ፤ የፈ​ረ​ሰ​ው​ንም አድ​ሳ​ለሁ፤ እንደ ቀደ​መ​ውም ዘመን እሠ​ራ​ታ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="12">ይኸ​ውም የቀሩ ሰዎ​ች​ንና ስሜም የተ​ጠ​ራ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ይፈ​ልጉ ዘንድ ነው” ይላል ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="13">“እነሆ፥ እን​ዲህ ያለ ወራት ይመ​ጣ​ልን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እርሻ ከአ​ጨዳ ጋር፥ ዘርም ከእ​ሸት ጋር አንድ ይሆ​ናል፤ ከተ​ራ​ሮ​ችም ማር ይፈ​ስ​ሳል፤ ኮረ​ብ​ታ​ውም ይለ​መ​ል​ማል።</verse>
				<verse number="14">የሕ​ዝ​ቤን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ የፈ​ረ​ሱ​ት​ንም ከተ​ሞች ሠር​ተው ይቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ዋል፤ ወይ​ን​ንም ይተ​ክ​ላሉ፤ የወ​ይን ጠጃ​ቸ​ው​ንም ይጠ​ጣሉ፤ ተክ​ልን ይተ​ክ​ላሉ፤ ፍሬ​ው​ንም ይበ​ላሉ።</verse>
				<verse number="15">በም​ድ​ራ​ቸ​ውም እተ​ክ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ከሰ​ጠ​ኋ​ቸው ከም​ድ​ራ​ቸው አይ​ነ​ቀ​ሉም” ይላል ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="31">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">የአ​ብ​ድዩ ራእይ። ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ኤዶ​ም​ያስ እን​ዲህ ይላል፦ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መስ​ማ​ትን ሰማሁ፤ ከባ​ቢን ወደ አሕ​ዛብ ልኮ፥ “ተነሡ፤ በላ​ይ​ዋም እን​ነ​ሣና እን​ው​ጋት።</verse>
				<verse number="2">እነሆ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ታናሽ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ አንተ እጅግ ተን​ቀ​ሃል።</verse>
				<verse number="3">በተ​ሰ​ነ​ጠ​ቀም ዓለት ውስጥ እን​ደ​ሚ​ኖር- ማደ​ሪ​ያ​ው​ንም ከፍ ከፍ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በል​ቡም፦ ወደ ምድር የሚ​ያ​ወ​ር​ደኝ ማን ነው? እን​ደ​ሚል፥ የል​ብህ ትዕ​ቢት እጅግ አኵ​ር​ቶ​ሃል።</verse>
				<verse number="4">እንደ ንስር መጥ​ቀህ ብት​ወጣ፥ ቤት​ህም በከ​ዋ​ክ​ብት መካ​ከል ቢሆን፥ ከዚያ አወ​ር​ድ​ሃ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="5">“ሌቦች ቢመ​ጡ​ብህ፥ ወይም ወን​በ​ዴ​ዎች በሌ​ሊት ቢመጡ፥ የሚ​በ​ቃ​ቸ​ውን የሚ​ሰ​ርቁ አይ​ደ​ሉ​ምን? ወይ​ንም የሚ​ቈ​ርጡ ወደ አንተ ቢመጡ ቃር​ሚያ አያ​ስ​ቀ​ሩ​ምን?</verse>
				<verse number="6">ዔሳ​ውን እን​ዴት መረ​መ​ሩት! የሸ​ሸ​ገ​ው​ንም እን​ዴት ወሰ​ዱ​በት!</verse>
				<verse number="7">የተ​ማ​ማ​ል​ሃ​ቸው ሰዎች ሁሉ ወደ ዳር​ቻህ ሰደ​ዱህ፤ የተ​ስ​ማ​ሙ​ህም ሰዎች ተነ​ሡ​ብህ፤ አሸ​ነ​ፉ​ህም፤ በበ​ታ​ች​ህም አሽ​ክላ ዘረ​ጉ​ብህ፤ እነ​ር​ሱም ማስ​ተ​ዋል የላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="8">በዚያ ቀን ከኤ​ዶ​ም​ያስ ጥበ​በ​ኞ​ችን፥ ከዔ​ሳው ተራ​ራም ማስ​ተ​ዋ​ልን አጠ​ፋ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="9">ከዔ​ሳው ተራራ ሰዎች ሁሉ ይጠፉ ዘንድ የቴ​ማን ሰል​ፈ​ኞ​ችህ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="10">“በወ​ን​ድ​ምህ በያ​ዕ​ቆብ ላይ ስለ ተደ​ረገ ኀጢ​አ​ትና ግድያ ኀፍ​ረት ይከ​ድ​ን​ሃል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ትጠ​ፋ​ለህ።</verse>
				<verse number="11">በፊቱ አን​ጻር በቆ​ምህ ቀን፥ አሕ​ዛብ ጭፍ​ራ​ውን በማ​ረ​ኩ​በት፥ እን​ግ​ዶ​ችም በበሩ በገ​ቡ​በት፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዕጣ በተ​ጣ​ጣ​ሉ​በት ቀን አንተ ደግሞ ከእ​ነ​ርሱ እንደ አንዱ ነበ​ርህ።</verse>
				<verse number="12">በጠ​ላት ቀን ወን​ድ​ም​ህን ዝቅ አድ​ር​ገህ ትመ​ለ​ከ​ተው ዘንድ፥ በጥ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ቀን በይ​ሁዳ ልጆች ላይ ደስ ይልህ ዘንድ፥ በጭ​ን​ቀ​ታ​ቸ​ውም ቀን በት​ዕ​ቢት ትና​ገር ዘንድ ባል​ተ​ገ​ባህ ነበር።</verse>
				<verse number="13">በች​ግ​ራ​ቸ​ውም ቀን በሕ​ዝቤ በር ትገባ ዘንድ፥ በጥ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ቀን ጉባ​ኤ​ያ​ቸ​ውን ትመ​ለ​ከት ዘንድ፥ በእ​ል​ቂ​ታ​ቸ​ውም ቀን በሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ላይ አደጋ ትጥል ዘንድ አይ​ገ​ባ​ህም ነበር።</verse>
				<verse number="14">የሸ​ሹ​ት​ንም ለማ​ጥ​ፋት በመ​ተ​ላ​ለ​ፊያ መን​ገ​ዳ​ቸው ትቆም ዘንድ፥ ድል በተ​ነ​ሡ​በ​ትም ቀን ከእ​ርሱ ያመ​ለ​ጡ​ትን ለማ​ስ​ጨ​ነቅ ትከ​ብ​ባ​ቸው ዘንድ ባል​ተ​ገ​ባህ ነበር።</verse>
				<verse number="15">“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ቀር​ቦ​አ​ልና፥ አንተ እንደ አደ​ረ​ግ​ኸው እን​ዲሁ ይደ​ረ​ግ​ብ​ሃል፤ ፍዳ​ህም በራ​ስህ ላይ ይመ​ለ​ሳል።</verse>
				<verse number="16">በቅ​ዱሱ ተራ​ራዬ ላይ እንደ ጠጣህ እን​ዲሁ አሕ​ዛብ ሁሉ ወይ​ንን ይጠ​ጣሉ፤ አዎን፥ ይጠ​ጣሉ፥ ይጨ​ል​ጡ​ማል፤ እን​ዳ​ል​ነ​በ​ሩም ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="17">“ነገር ግን በጽ​ዮን ተራራ ላይ መድ​ኀ​ኒት ይሆ​ናል፤ እር​ሱም ቅዱስ ይሆ​ናል፤ የያ​ዕ​ቆ​ብም ቤት ሰዎች የወ​ረ​ሱ​አ​ቸ​ውን ይወ​ር​ሳሉ።</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተና​ግ​ሮ​አ​ልና የያ​ዕ​ቆብ ቤት እሳት፥ የዮ​ሴ​ፍም ቤት ነበ​ል​ባል፥ የዔ​ሳ​ውም ቤት ገለባ ይሆ​ናሉ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል፤ ይበ​ሉ​አ​ቸ​ው​ማል፤ ከዔ​ሳ​ውም ቤት ቅሬታ አይ​ኖ​ርም።</verse>
				<verse number="19">የደ​ቡ​ብም ሰዎች የዔ​ሳ​ውን ተራራ፥ የቆ​ላ​ውም ሰዎች ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ይወ​ር​ሳሉ፤ የኤ​ፍ​ሬ​ም​ንም ተራራ፥ የሰ​ማ​ር​ያን፥ የብ​ን​ያ​ም​ንና የገ​ለ​ዓ​ድን ሀገር ይወ​ር​ሳሉ።</verse>
				<verse number="20">ይህም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የጭ​ፍ​ራ​ቸው ምርኮ የከ​ነ​ዓ​ንን ስፍራ ሁሉ እስከ ሰራ​ጵታ ድረስ ይወ​ር​ሳል፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ምር​ኮ​ኞች እስከ ኤፍ​ራታ ድረስ የደ​ቡ​ብን ከተ​ሞች ይወ​ር​ሳሉ።</verse>
				<verse number="21">የዳ​ኑ​ትም የዔ​ሳ​ውን ተራራ ይበ​ቀ​ሉት ዘንድ ከጽ​ዮን ተራራ ይዘ​ም​ታሉ፤ መን​ግ​ሥ​ትም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሆ​ናል።”</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="32">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“ተነ​ሥ​ተህ ወደ ታላ​ቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ የክ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ጩኸት ወደ ፊቴ ወጥ​ቶ​አ​ልና ለእ​ነ​ርሱ ስበክ።”</verse>
				<verse number="3">ዮናስ ግን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ ተር​ሴስ ይሸሽ ዘንድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮ​ጴም ወረደ፤ ወደ ተር​ሴ​ስም የም​ታ​ልፍ መር​ከብ አገኘ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ኰብ​ልሎ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ወደ ተር​ሴስ ይሄድ ዘንድ ዋጋ ሰጥቶ ወደ እር​ስዋ ገባ።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሕሩ ላይ ታላቅ ነፋ​ስን አመጣ፤ በባ​ሕ​ሩም ላይ ታላቅ ማዕ​በል ሆነ፤ መር​ከ​ቢ​ቱም ልት​ሰ​በር ቀረ​በች።</verse>
				<verse number="5">መር​ከ​በ​ኞ​ቹም ፈሩ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ አም​ላኩ ጮኸ፤ መር​ከ​ቢ​ቱም እን​ድ​ት​ቀ​ል​ል​ላ​ቸው በው​ስ​ጥዋ የነ​በ​ረ​ውን ዕቃ ወደ ባሕር ጣሉት፤ ዮናስ ግን ወደ መር​ከቡ ውስ​ጠ​ኛው ክፍል ወርዶ ነበር፥ ተኝ​ቶም ያን​ኳ​ርፍ ነበር።</verse>
				<verse number="6">የመ​ር​ከ​ቡም አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “ምነው ተኝ​ተ​ሃል? እን​ዳ​ን​ጠፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ነን ዘንድ ተነ​ሥ​ተህ አም​ላ​ክ​ህን ጥራ” አለው።</verse>
				<verse number="7">እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክ​ን​ያት እንደ አገ​ኘን እና​ውቅ ዘንድ ኑ፤ ዕጣ እን​ጣ​ጣል” ተባ​ባሉ። ዕጣም ተጣ​ጣሉ፤ ዕጣ​ውም በዮ​ናስ ላይ ወደቀ።</verse>
				<verse number="8">የዚ​ያን ጊዜም፥ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክ​ን​ያት እን​ዳ​ገ​ኘን እባ​ክህ ንገ​ረን፤ ሥራህ ምን​ድን ነው? ከወ​ዴ​ትስ መጣህ? ወዴ​ትስ ትሄ​ዳ​ለህ? ሀገ​ርህ የት ነው? ወገ​ን​ህስ ምን​ድን ነው?” አሉት።</verse>
				<verse number="9">እር​ሱም፥ “እኔ ዕብ​ራዊ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪያ ነኝ፤ ባሕ​ሩ​ንና የብ​ሱን የፈ​ጠ​ረ​ውን የሰ​ማ​ይን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ል​ካ​ለሁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">እነ​ዚ​ያም ሰዎች ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ኰበ​ለለ እርሱ ስለ ነገ​ራ​ቸው ዐው​ቀ​ዋ​ልና እጅግ ፈር​ተው፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ኸው ምን​ድን ነው?” አሉት።</verse>
				<verse number="11">ባሕሩ ይታ​ወክ ነበ​ርና፥ ታላቅ ማዕ​በ​ልም ተነ​ሥቶ ነበ​ርና፥ “ባሕሩ ጸጥ ይል​ልን ዘንድ እን​ግ​ዲህ ምን እና​ድ​ር​ግህ?” አሉት።</verse>
				<verse number="12">እር​ሱም፥ “ይህ ታላቅ ማዕ​በል በእኔ ምክ​ን​ያት እንደ አገ​ኛ​ችሁ ዐው​ቃ​ለ​ሁና አን​ሥ​ታ​ችሁ ወደ ባሕሩ ጣሉኝ፤ ባሕ​ሩም ጽጥ ይል​ላ​ች​ኋል” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">ሰዎቹ ግን ወደ ምድሩ ሊመ​ለሱ አጥ​ብ​ቀው ቀዘፉ፤ ዳሩ ግን ባሕሩ እጅግ አብ​ዝቶ ይና​ወ​ጥ​ባ​ቸው ነበ​ርና አል​ቻ​ሉም።</verse>
				<verse number="14">ሁሉም አንድ ሆነው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ “አቤቱ! አንተ እንደ ወደ​ድህ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ስለ​ዚህ ሰው ነፍስ አታ​ጥ​ፋን፤ ንጹሕ ደም​ንም አታ​ድ​ር​ግ​ብን።” አሉ።</verse>
				<verse number="15">ዮና​ስ​ንም ወስ​ደው ወደ ባሕሩ ጣሉት፤ ባሕ​ሩም ከመ​ና​ወጡ ጸጥ አለ።</verse>
				<verse number="16">ሰዎ​ቹም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጅግ ፈሩ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ፤ ስእ​ለ​ት​ንም ተሳሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዮና​ስን ይው​ጠው ዘንድ ታላቅ ዓሣ አን​በ​ሪን አዘዘ፤ ዮና​ስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣ አን​በ​ሪው ሆድ ውስጥ ነበረ።</verse>
				<verse number="2">ዮና​ስም በዓሣ አን​በ​ሪው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አም​ላኩ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለየ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="3">“በመ​ከ​ራዬ ሳለሁ ወደ አም​ላኬ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኽሁ፤ በሲ​ኦ​ልም ሆድ ውስጥ የጩ​ኸ​ቴን ድምፅ ሰማኝ፤ ቃሌ​ንም አዳ​መ​ጥህ።</verse>
				<verse number="4">ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ውስጥ ጣል​ኸኝ፥ ፈሳ​ሾ​ችም ከበ​ቡኝ፤ ማዕ​በ​ል​ህና ሞገ​ድህ ሁሉ በላዬ ዐለፉ።</verse>
				<verse number="5">እኔም፦ ከዐ​ይ​ንህ ፊት ተጣ​ልሁ፤ ነገር ግን ወደ ቅዱስ መቅ​ደ​ስህ ደግሞ እመ​ለ​ከ​ታ​ለ​ሁን? አልሁ።</verse>
				<verse number="6">ውኃ እስከ ነፍሴ ድረስ ፈሰሰ፤ ጥልቁ ባሕር በዙ​ሪ​ያዬ ከበ​በኝ፤</verse>
				<verse number="7">እነሆ ራሴ ወደ ታች ወደ ተራ​ሮች መሠ​ረት ወረደ፤ ከጥ​ንት ጀምሮ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችዋ ወደ ተዘጉ ምድር ወረ​ድሁ፤ አቤቱ ፈጣ​ሪዬ! ሕይ​ወቴ ጥፋት ሳያ​ገ​ኛት ወዳ​ንተ ትውጣ።</verse>
				<verse number="8">ነፍሴ በዛ​ለ​ች​ብኝ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አሰ​ብ​ሁት፤ ጸሎ​ቴም ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅ​ደ​ስህ ትግባ።</verse>
				<verse number="9">ከን​ቱ​ነ​ት​ንና ሐሰ​ትን የሚ​ጠ​ብቁ፤ ይቅ​ር​ታ​ቸ​ውን ትተ​ዋል።</verse>
				<verse number="10">እኔ ግን ከም​ስ​ጋ​ናና ከኑ​ዛዜ ቃል ጋር እሠ​ዋ​ል​ሃ​ለሁ፤ የድ​ኅ​ነቴ አም​ላክ ሆይ! የተ​ሳ​ል​ሁ​ትን ለአ​ንተ እከ​ፍ​ላ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዓሣ አን​በ​ሪ​ውን አዘ​ዘው፤ እር​ሱም ዮና​ስን በየ​ብስ ላይ ተፋው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ሁለ​ተኛ ወደ ዮናስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">“ተነ​ሥ​ተህ ወደ​ዚ​ያች ወደ ታላ​ቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ የነ​ገ​ር​ሁ​ህ​ንም የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውን ስብ​ከት ስበ​ክ​ላት” አለው።</verse>
				<verse number="3">ዮና​ስም ተነ​ሥቶ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነ​ዌም ታላቅ ከተማ ነበ​ረች፤ የቅ​ጥ​ር​ዋም ዙሪያ በእ​ግር የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ያህል ነበረ።</verse>
				<verse number="4">ዮና​ስም የአ​ንድ ቀን መን​ገድ ያህል ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም፥ “በሦ​ስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገ​ለ​በ​ጣ​ለች አለ።”</verse>
				<verse number="5">የነ​ነዌ ሰዎ​ችም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመኑ፤ ለጾም ዐዋጅ ነገሩ፤ ከታ​ላ​ቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።</verse>
				<verse number="6">ወሬ​ውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እር​ሱም ከዙ​ፋኑ ተነ​ሥቶ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ውን አወ​ለቀ፤ ማቅም ለበሰ፤ በአ​መ​ድም ላይ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="7">ዐዋ​ጅም አስ​ነ​ገረ፤ በነ​ነ​ዌም ውስጥ የን​ጉ​ሡ​ንና የመ​ኳ​ን​ን​ቱን ትእ​ዛዝ አሳ​ወጀ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ሰዎ​ችና እን​ስ​ሶች፥ ላሞ​ችና በጎች አን​ዳች አይ​ቅ​መሱ፤ አይ​ሰ​ማ​ሩም፤ ውኃ​ንም አይ​ጠጡ፤</verse>
				<verse number="8">ሰዎ​ችና እን​ስ​ሶ​ችም ማቅ ይል​በሱ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ን​ድ​ነት ይጩኹ፤ ሰዎ​ችም ሁሉ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውና በእ​ጃ​ቸው ከአ​ለው ግፍ ይመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="9">እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ይምራን፥ ከጽኑ ቁጣውም ይመለስ እንደሆነ ማን ያውቃል?”</verse>
				<verse number="10">እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ ከተናገረው ክፉ ነገር ተመለሰ፤ አላደረገውምም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ዮና​ስም ፈጽሞ አዘነ፤ ተከ​ዘም።</verse>
				<verse number="2">ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸለየ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ፥ በሀ​ገሬ ሳለሁ የተ​ና​ገ​ር​ሁት ይህ አል​ነ​በ​ረ​ምን? አንተ ቸርና ይቅር ባይ፥ ታጋ​ሽም፥ ምሕ​ረ​ት​ህም የበዛ፥ ከክ​ፉው ነገ​ርም የም​ት​መ​ለስ አም​ላክ እንደ ሆንህ ዐውቄ ነበ​ርና ስለ​ዚህ ወደ ተር​ሴስ ለመ​ኰ​ብ​ለል ፈጥኜ ነበር።</verse>
				<verse number="3">አሁ​ንም አቤቱ! ከሕ​ይ​ወት ሞት ይሻ​ለ​ኛ​ልና እባ​ክህ! ነፍ​ሴን ከእኔ ውሰድ።”</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዮና​ስን፥ “ፈጽ​መህ ታዝ​ና​ለ​ህን?” አለው።</verse>
				<verse number="5">ዮና​ስም ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ወጣ፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ፊት ለፊት ተቀ​መጠ፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም የሚ​ሆ​ነ​ውን እስ​ኪ​ያይ ድረስ በዚያ ለራሱ ዳስ ሠርቶ ከጥ​ላው በታች ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ቅልን አዘዘ፤ ከጭ​ን​ቀ​ቱም ታድ​ነው ዘንድ በራሱ ላይ ጥላ እን​ድ​ት​ሆን በዮ​ናስ ራስ ላይ ከፍ ከፍ አደ​ረ​ጋት፤ ዮና​ስም ስለ ቅሊቱ እጅግ ደስ አለው።</verse>
				<verse number="7">በነ​ጋው ግን ወገግ ባለ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትልን አዘዘ፤ እር​ስ​ዋም ቅሊ​ቱን መታ​ቻት፤ ደረ​ቀ​ችም።</verse>
				<verse number="8">ፀሐ​ይም በወ​ጣች ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትኩስ የም​ሥ​ራቅ ነፋ​ስን አዘዘ፤ ዮና​ስ​ንም እስ​ኪ​ዝል ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለራ​ሱም ተስፋ ቈርጦ፥ “ከሕ​ይ​ወት ሞት ይሻ​ለ​ኛል” አለ።</verse>
				<verse number="9">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዮና​ስን፥ “በውኑ ስለ​ዚች ቅል ታዝ​ና​ለ​ህን?” አለው። እር​ሱም፥ “እስ​ክ​ሞት ድረስ እጅግ አዝ​ኛ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አንተ ትበ​ቅል ዘንድ ላል​ደ​ከ​ም​ህ​ባት፥ ላላ​ሳ​ደ​ግ​ሃ​ትም፥ በአ​ንድ ሌሊት ለበ​ቀ​ለች፥ በአ​ንድ ሌሊ​ትም ለደ​ረ​ቀ​ችው ቅል አዝ​ነ​ሃል።</verse>
				<verse number="11">እኔስ ቀኛ​ቸ​ው​ንና ግራ​ቸ​ውን የማ​ይ​ለዩ ከመቶ ሃያ ሺህ የሚ​በ​ልጡ ሰዎ​ችና ብዙ እን​ስ​ሶች ላሉ​ባት ለታ​ላ​ቂቱ ከተማ ለነ​ነዌ አላ​ዝ​ን​ምን?” አለው።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="33">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታምና በአካዝ በሕዝቅያስም ዘመን ወደ ሞሬታዊው ወደ ሚክያስ የመጣው፥ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው፥ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">እናንተ አሕዛብ ሁሉ፥ ስሙ፥ ምድርም ሙላዋም ታድምጥ፥ ጌታ እግዚአብሔርም፥ እርሱም በቅዱስ መቅደሱ የሆነ ጌታ፥ ይመስክርባችሁ።</verse>
				<verse number="3">እነሆ፥ እግዚአብሔር ከስፍራው ይወጣል፥ ወርዶም በምድር ከፍታዎች ላይ ይረግጣል።</verse>
				<verse number="4">ተራሮችም በእሳት ፊት እንዳለ ሰም፥ በገደልም ወርዶ እንደሚፈስስ ውኃ፥ በበታቹ ይቀልጣሉ፥ ሸለቆችም ይሰነጠቃሉ።</verse>
				<verse number="5">ይህ ሁሉ ስለ ያዕቆብ በደልና ስለ እስራኤል ቤት ኃጢአት ነው። የያዕቆብም በደል ምንድር ነው? ሰማርያ አይደለችምን? የይሁዳስ የኮረብታው መስገጃ ምንድር ነው? ኢየሩሳሌም አይደለችምን?</verse>
				<verse number="6">ስለዚህ ሰማርያን በሜዳ እንደሚገኝ የድንጋይ ክምር፥ ወይን እንደሚተከልበትም ስፍራ አደርጋታለሁ፥ ድንጋዮችዋንም ወደ ሸለቆ እወረውራለሁ፥ መሠረቶችዋንም እገልጣለሁ።</verse>
				<verse number="7">የተቀረጹትም ምስሎችዋ ይደቅቃሉ፥ በግልሙትና ያገኘችው ዋጋ ሁሉ በእሳት ይቃጠላል፥ ጣዖታትዋንም ሁሉ አጠፋለሁ፥ በግልሙትና ዋጋ ሰበሰባቻቸው፥ ወደ ግልሙትናም ዋጋ ይመለሳሉና።</verse>
				<verse number="8">ስለዚህ ነገር ዋይ ብላ ታለቅሳለች፥ ባዶ እግርዋንና ዕራቁትዋን ሆና ትሄዳለች፥ እንደ ቀበሮ ታለቅሳለች፥ እንደ ሰጐንም ዋይ ትላለች፥</verse>
				<verse number="9">ቁስልዋ የማይፈወስ ነውና፥ እስከ ይሁዳም ደርሶአልና፥ ወደ ሕዝቤም በር ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቦአልና።</verse>
				<verse number="10">በጌት ላይ አታውሩ፥ በአኮ ላይ እንባን አታድርጉ፥ በቤትዓፍራ በትቢያ ላይ ተንከባለሉ።</verse>
				<verse number="11">በሻፊር የምትቀመጪ ሆይ፥ በዕራቁትነትሽና በእፍረት እለፊ፥ በጸዓናን የምትቀመጠው አልወጣችም፥ የቤትኤጼል ልቅሶ ከእናንተ ዘንድ መኖሪያውን ይወስዳል።</verse>
				<verse number="12">ክፉ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ እስከ ኢየሩሳሌም በር ድረስ ወርዶአልና በማሮት የምትቀመጠው በጎነትን ትጠባበቃለች።</verse>
				<verse number="13">በለኪሶ የምትቀመጪ ሆይ፥ ሰረገላውን ለፈረስ እሰሪ፥ እርስዋ ለጽዮን ሴት ልጆች የኃጢአት መጀመሪያ ነበረች፥ የእስራኤል በደል በአንቺ ዘንድ ተገኝቶአልና።</verse>
				<verse number="14">ስለዚህ ትሎት ለሞሬሼትጌት ትሰጪአለሽ፥ የአክዚብ ቤቶች ለእስራኤል ነገሥታት አታላይ ይሆናሉ።</verse>
				<verse number="15">በመሪሳ የምትቀመጪ ሆይ፥ ወራሽ አመጣብሻለሁ፥ የእስራኤል ክብር ወደ ዓዶላም ይመጣል።</verse>
				<verse number="16">ተማርከው ከአንቺ ዘንድ ወጥተዋልና ስለ ተድላሽ ልጆች ራስሽን ንጪ፥ ጠጕርሽንም ተቈረጪ፥ ቡሃነትሽንም እንደ ንስር አስፊ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">በመኝታቸው ላይ በደልን ለሚያስቡ ክፋትንም ለሚያደርጉ ወዮላቸው! ኃይል በእጃቸው ነውና ሲነጋ ይፈጽሙታል።</verse>
				<verse number="2">በእርሻው ላይ ይመኛሉ፥ በግዴታም ይይዙታል፥ በቤቶችም ላይ ይመኛሉ፥ ይወስዱአቸውማል፥ ሰውንና ቤቱን፥ ሰውንና ርስቱንም ይነጥቃሉ።</verse>
				<verse number="3">ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህ ወገን ላይ በክፉ አስባለሁ፥ ከዚያም አንገታችሁን አታነሡም፥ ዘመኑም ክፉ ነውና ቀጥ ብላችሁ አትሄዱም።</verse>
				<verse number="4">በዚያ ቀን በምሳሌ ይመስሉባችኋል፥ በጽኑ ልቅሶም ያለቅሱላችኋል፥ እነርሱም፦ ፈጽመን ጠፍተናል፥ የሕዝቤን እድል ፈንታ ይሰፍራል፥ እርሱንም የሚከለክል የለም፥ እርሻችንን ለዓመፀኞች ይከፍላል ይላሉ።</verse>
				<verse number="5">ስለዚህ በእግዚአብሔር ጉባኤ መካከል በዕጣ ገመድ የሚጥል አይኖርህም።</verse>
				<verse number="6">ትንቢት አትናገሩ ብለው ይናገራሉ፥ በእነዚህ ላይ ትንቢት አይናገሩም፥ ስድብም አይርቅም።</verse>
				<verse number="7">የያዕቆብ ቤት የተባልህ ሆይ፥ በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ የማይታገሥ ነውን? ወይስ ሥራው እንደዚያች ናትን? ቃሌስ በቅን ለሚሄድ በጎነት አያደርግምን?</verse>
				<verse number="8">ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ሕዝቤ እንደ ጠላት ሆኖ ተነሥቶአል፥ ቀሚስንና መጐናጸፊያን ገፈፋችሁ፥ ሳይፈሩም፥ የሚያልፉትን ከሰልፍ እንደሚመለሱ አደረጋችኋቸው።</verse>
				<verse number="9">የሕዝቤንም ሴቶች ከተሸለሙ ቤቶቻቸው አሳደዳችኋቸው፥ ከሕፃናቶቻቸውም ክብሬን ለዘላለም ወሰዳችሁ።</verse>
				<verse number="10">በዚህ ዕረፍት የላችሁምና ተነሥታችሁ ሂዱ፥ በርኵሰት ምክንያት ክፉ ጥፋት ታጠፋችኋለች።</verse>
				<verse number="11">ነፋስንም ተከትሎ፦ ስለ ወይን ጠጅና ስለ ስካር ትንቢት እናገርልሃለሁ ብሎ ሐሰትን የሚናገር ሰው ቢኖር እርሱ ለዚህ ሕዝብ ነቢይ ይሆናል።</verse>
				<verse number="12">ያዕቆብ ሆይ፥ ሁልንተናህን ፈጽሞ እሰበስባለሁ፥ የእስራኤልንም ቅሬታ ፈጽሞ አከማቻለሁ፥ እንደ ባሶራ በጎችና እንደ መንጋ በማሰማርያቸው ውስጥ በአንድነት አኖራቸዋለሁ፥ ከሰው ብዛት የተነሣ ድምፃቸውን ያሰማሉ።</verse>
				<verse number="13">ሰባሪው በፊታቸው ወጥቶአል፥ እነርሱም ሰብረው ወደ በሩ አልፈዋል፥ በእርሱም በኩል ወጥተዋል፥ ንጉሣቸውም በፊታቸው አልፎአል፥ እግዚአብሔርም በራሳቸው ላይ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">እንዲህም አልሁ፦ የያዕቆብ አለቆችና የእስራኤል ቤት ገዦች ሆይ፥ እባካችሁ ስሙኝ፥ ፍርድን ታውቁ ዘንድ አይገባችሁምን?</verse>
				<verse number="2">መልካሙን ጠልታችኋል፥ ክፉውንም ወድዳችኋል፥ ቁርበታቸውን ገፍፋችኋቸዋል፥ ሥጋቸውንም ከአጥንታቸው ለያይታችኋል፥</verse>
				<verse number="3">የሕዝቤን ሥጋ በልታችኋል፥ ቁርበታቸውንም ገፍፋችኋቸዋል፥ አጥንታቸውንም ሰብራችኋል፥ ለአፍላል እንደሚሆን ሥጋ ለድስትም እንደሚሆን ሙዳ ቈራረጣችኋቸው።</verse>
				<verse number="4">የዚያን ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉ፥ እርሱም አይሰማቸውም፥ ሥራቸውንም ክፉ አድርገዋልና በዚያን ጊዜ ፊቱን ከእነርሱ ይሰውራል።</verse>
				<verse number="5">እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚያስቱ ነቢያት እንዲህ ይላል፥ በጥርሳቸው ሲነክሱ በሰላም ይሰብካሉ፥ በአፋቸው ግን አንዳች በማይሰጥ ሰው ላይ ሰልፍን ያስቡበታል።</verse>
				<verse number="6">ስለዚህ ሌሊት ይሆንባችኋል እንጂ ራእይ አይሆንላችሁም፥ ጨለማም ይሆንባችኋል እንጂ አታምዋርቱም፥ ፀሐይም በነቢያት ላይ ትገባለች፥ ቀኑም ይጠቁርባቸዋል።</verse>
				<verse number="7">ከእግዚአብሔርም ዘንድ መልስ የለምና ባለ ራእዩቹ ያፍራሉ፥ ምዋርተኞችም ይዋረዳሉ፥ ሁሉም ከንፈራቸውን ይሸፍናሉ።</verse>
				<verse number="8">እኔ ግን በደሉን ለያዕቆብ፥ ኃጢአቱንም ለእስራኤል እነግር ዘንድ በእግዚአብሔር መንፈስ ኃይልንና ፍርድን ብርታትንም ተሞልቻለሁ።</verse>
				<verse number="9">ፍርድን የምትጠሉ ቅን ነገርንም ሁሉ የምታጣምሙ እናንተ የያዕቆብ ቤት አለቆችና የእስራኤል ቤት ገዦች ሆይ፥ እባካችሁ ይህን ስሙ።</verse>
				<verse number="10">ጽዮንን በደም፥ ኢየሩሳሌምንም በኃጢአት ይሠራሉ።</verse>
				<verse number="11">አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፥ ከዚህም ጋር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።</verse>
				<verse number="12">ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌም የድንጋይ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">በመጨረሻውም ዘመን የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፥ አሕዛብም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ።</verse>
				<verse number="2">ከጽዮን ሕግ፥ ከኢየሩሳሌምም የእግዚአብሔር ቃል ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው፦ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፥ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በፍለጋውም እንሄዳለን ይላሉ።</verse>
				<verse number="3">በብዙዎችም አሕዛብ መካከል ይፈርዳል፥ በሩቅም ባሉ በብርቱዎች አሕዛብ ላይ ይበይናል፥ ሰይፋቸውንም ማረሻ፥ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፥ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም ከእንግዲህም ወዲህ ሰልፍ አይማሩም።</verse>
				<verse number="4">የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር አፍም ተናግሮአልና ሰው እያንዳንዱ ከወይኑና ከበለሱ በታች ይቀመጣል፥ የሚያስፈራውም የለም።</verse>
				<verse number="5">ሕዝብም ሁሉ እያንዳንዱ በየአምላኩ ስም ይሄዳል፥ እኛም በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ለዘላለም እንሄዳለን።</verse>
				<verse number="6">በዚያ ቀን አንካሳይቱን እሰበስባለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የባከነችውንና ያስጨነቅኋትንም አከማቻለሁ፥</verse>
				<verse number="7">አንካሳይቱንም ለቅሬታ፥ ወደ ሩቅም የተጣለችውን ለብርቱ ሕዝብ አደርጋታለሁ፥ ከዚያም ወዲያ እስከ ዘላለም ድረስ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ በእነርሱ ላይ ይነግሣል።</verse>
				<verse number="8">አንተም የመንጋ ግንብ ሆይ፥ የጽዮን ሴት ልጅ አምባ፥ ወደ አንተ ትመጣለች፥ የቀደመችው ግዛት፥ የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ መንግሥት ትደርሳለች።</verse>
				<verse number="9">አሁንስ ለምን ትጮኺአለሽ? እንደምትወልድ ሴት ምጥ የደረሰብሽ፥ ንጉሥ ስለሌለሽ ነውን? ወይስ መካሪ ስለ ጠፋብሽ ነውን?</verse>
				<verse number="10">የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እንደምትወልድ ሴት አምጠሽ ውለጂ፥ አሁን ከከተማ ትወጫለሽና፥ በሜዳም ትቀመጫለሽ፥ ወደ ባቢሎንም ትደርሻለሽ፥ በዚያም ያድንሻል፥ በዚያም እግዚአብሔር ከጠላቶችሽ እጅ ይቤዥሻል።</verse>
				<verse number="11">አሁንም፦ ርኩስ ትሁን፥ ዓይናችንም በጽዮን ላይ ይይ የሚሉ ብዙ አሕዛብ በአንቺ ላይ ተሰብስበዋል።</verse>
				<verse number="12">ነገር ግን የእግዚአብሔርን አሳብ አያውቁም፥ ምክሩንም አያስተውሉም፥ እንደ ነዶ ወደ አውድማ አከማችቶአቸዋልና።</verse>
				<verse number="13">የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ቀንድሽን ብረት፥ ጥፍርሽንም ናስ አደርጋለሁና ተነሺ አሂጂ፥ ብዙ አሕዛብንም ታደቅቂአለሽ፥ ትርፋቸውንም ለእግዚአብሔር፥ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ ትቀድሻለሽ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">የጭፍሮች ሴት ልጅ ሆይ፥ ጭፍሮችሽን አሁን ሰብስቢ፥ ከብቦ አስጨንቆናል፥ የእስራኤልን ፈራጅ ጕንጩን በበትር ይመታሉ።</verse>
				<verse number="2">አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።</verse>
				<verse number="3">ስለዚህ ወላጂቱ እስከምትወልድበት ጊዜ ድረስ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፥ የቀሩትም ወንድሞቹ ወደ እስራኤል ልጆች ይመለሳሉ።</verse>
				<verse number="4">እርሱም ይቆማል፥ በእግዚአብሔርም ኃይል በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ግርማ መንጋውን ይጠብቃል፥ እነርሱም ይኖራሉ፥ እርሱ አሁን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ይሆናልና።</verse>
				<verse number="5">ይህም ለሰላም ይሆናል፥ አሦራዊውም ወደ አገራችን በገባ ጊዜ፥ ምድራችንንም በረገጠ ጊዜ ሰባት እረኞችና ስምንት አለቆች እናስነሣበታለን።</verse>
				<verse number="6">የአሦርንም አገር በሰይፍ፥ የናምሩድንም አገር በመግቢያው ውስጥ ያፈርሳሉ፥ አሦራዊውም ወደ አገራችን በገባ ጊዜ፥ ዳርቾቻችንንም በረገጠ ጊዜ እርሱ ይታደገናል።</verse>
				<verse number="7">የያዕቆብም ቅሬታ በብዙ አሕዛብ መካከል ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፥ በሣር ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥ ሰውንም እንደማይጠብቅ፥ የሰውንም ልጆች ተስፋ እንደማያደርግ ይሆናል።</verse>
				<verse number="8">በዱር አራዊትም መካከል እንዳለ አንበሳ፥ በበጎች መንጋም መካከል አልፎ እንደሚረግጥ፥ የሚታደግም ሳይኖር እንደሚነጥቅ እንደ አንበሳ ደቦል፥ እንዲሁ የያዕቆብ ቅሬታ በአሕዛብና በብዙ ወገኖች መካከል ይሆናል።</verse>
				<verse number="9">እጅህ በጠላቶችህ ላይ ከፍ ከፍ ትበል፥ ጠላቶችህም ሁሉ ይጥፉ።</verse>
				<verse number="10">በዚያም ቀን ፈረሶችህን ከመካከልህ አጠፋለሁ፥ ሰረገሎችህንም እሰብራለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥</verse>
				<verse number="11">የምድርህንም ከተሞች አጠፋለሁ፥ ምሽጎችህንም ሁሉ አፈርሳለሁ፥</verse>
				<verse number="12">መተትንም ከእጅህ አጠፋለሁ፥ ምዋርተኞችም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆኑልህም፥</verse>
				<verse number="13">የተቀረጹትን ምስሎችህንና ሐውልቶችህን ከመካከልህ አጠፋለሁ፥ ለእጅህም ሥራ ከእንግዲህ ወዲህ አትሰግድም፥</verse>
				<verse number="14">የማምለኪያ ዐፀዶችህንም ከመካከልህ እነቅላለሁ፥ ከተሞችህንም አፈርሳለሁ።</verse>
				<verse number="15">ባልሰሙም አሕዛብ ላይ በቍጣና በመዓት እበቀላለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">አሁን፦ ተነሣ፥ በተራሮችም ፊት ተፋረድ፥ ኮረብቶችም ቃልህን ይስሙ ብሎ እግዚአብሔር የሚለውን ስሙ።</verse>
				<verse number="2">ተራሮች ሆይ፥ ጠንካሮች የምድር መሠረቶችም ሆይ፥ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ክርክር አለውና፥ ከእስራኤልም ጋር ይፋረዳልና የእግዚአብሔርን ክርክር ስሙ።</verse>
				<verse number="3">ሕዝቤ ሆይ፥ ምን አድርጌለሁ? በምንስ አድክሜሃለሁ? መስክርብኝ።</verse>
				<verse number="4">ከግብጽ ምድር አውጥቼሃለሁ፥ ከባርነት ቤትም ተቤዥቼሃለሁ፥ በፊትህም ሙሴንና አሮንን ማርያምንም ልኬልህ ነበር።</verse>
				<verse number="5">ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፥ የቢዖርም ልጅ በለዓም የመለሰለትን አሁን አስብ፥ የእግዚአብሔርንም የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድ ከሰጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ አስብ።</verse>
				<verse number="6">ምን ይዤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ልምጣና በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ? የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንዱን ዓመት ጥጃ ይዤ በፊቱ ልምጣን?</verse>
				<verse number="7">እግዚአብሔርስ በሺህ አውራ በጎች ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋልን? ወይስ የበኵር ልጄን ስለ በደሌ፥ የሆዴንም ፍሬ ስለ ነፍሴ ኃጢአት እሰጣለሁን?</verse>
				<verse number="8">ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?</verse>
				<verse number="9">የእግዚአብሔር ድምፅ ከተማይቱን ይጠራታል፥ ስምህን መፍራት ጥበብ ነው፥ የመቅሠፍትን በትር፥ እርሱንም ያዘጋጀ ማን እንደ ሆነ ስሙ።</verse>
				<verse number="10">በውኑ በኃጢአተኛ ቤት የኃጢአት መዝገብ፥ የተጸየፈውም ውሸተኛ መስፈሪያ ገና አለ ይሆን?</verse>
				<verse number="11">በአባይ ሚዛንና በከረጢት ባለ በተንኰል መመዘኛ ንጹሕ እሆናለሁን?</verse>
				<verse number="12">ባለ ጠጎችዋን ግፍ ሞልቶባቸዋል፥ በእርስዋም የሚኖሩ በሐሰት ተናግረዋል፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ተንኰለኛ ነው።</verse>
				<verse number="13">ስለዚህ እኔ ደግሞ በክፉ ቍስል መታሁህ፥ ስለ ኃጢአትህም አፈረስሁህ።</verse>
				<verse number="14">ትበላለህ፥ ነገር ግን አትጠግብም፥ ችጋርህም በመካከልህ ይሆናል፥ ትወስዳለህ፥ ነገር ግን አታድንም፥ የምታድነውንም ለሰይፍ እሰጣለሁ።</verse>
				<verse number="15">ትዘራለህ፥ ነገር ግን አታጭድም፥ ወይራውንም ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን ዘይቱን አትቀባም፥ ወይኑንም ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን የወይን ጠጁን አትጠጣም።</verse>
				<verse number="16">አንተን ለጥፋት፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ለማፍዋጫ እሰጥ ዘንድ የዘንበሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቃችኋል፥ በምክራቸውም ሄዳችኋል፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">የዛፍ ፍሬና የወይን ፍሬ ከተለቀሙ በኋላ እንደ ቀረው ቃርሚያ ሆኛለሁና ወዮልኝ! መብል የሚሆን ዘለላ፥ ነፍሴም የተመኘችው በመጀመሪያ የበሰለው በለስ የለም።</verse>
				<verse number="2">ደግ ሰው ከምድር ጠፍቶአል፥ በሰውም መካከል ቅን የለም፥ ሁሉ ደምን ለማፍሰስ ያደባሉ፥ ሰውም ሁሉ ወንድሙን በመረብ ለመያዝ ይከታተለዋል።</verse>
				<verse number="3">እጆቻቸውን ለክፋት ያነሣሉ፥ አለቃውና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፥ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጕናሉ።</verse>
				<verse number="4">ከእነርሱም ሁሉ የተሻለው እርሱ እንደ አሜከላ ነው፥ ከሁሉም ቅን የሆነው እንደ ኵርንችት ነው፥ ጠባቆችህ የሚጐበኙበት ቀን መጥቶአል፥ አሁን ይሸበራሉ።</verse>
				<verse number="5">ባልንጀራን አትመኑ፥ በወዳጅም አትታመኑ፥ የአፍህን ደጅ በብብትህ ከምትተኛው ጠብቅ።</verse>
				<verse number="6">ወንድ ልጅ አባቱን ይንቃልና፥ ሴት ልጅ በእናትዋ ላይ፥ ምራቲቱም በአማትዋ ላይ ትነሣለችና፥ የሰው ጠላቶች የቤቱ ሰዎች ናቸውና።</verse>
				<verse number="7">እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር እመለከታለሁ፥ የመድኃኒቴንም አምላክ ተስፋ አደርጋለሁ፥ አምላኬም ይሰማኛል።</verse>
				<verse number="8">ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልሽ።</verse>
				<verse number="9">በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና እስኪምዋገትልኝ ድረስ፥ ፍርድን ለእኔ እስኪያደርግ ድረስ ቍጣውን እታገሣለሁ። ወደ ብርሃን ያወጣኛል፥ ጽድቅንም አያለሁ።</verse>
				<verse number="10">ጠላቴም ታያለች፥ እኔንም፦ አምላክህ እግዚአብሔር ወዴት ነው? ያለች በእፍረት ትከደናለች።</verse>
				<verse number="11">ዓይኖቼ ይመለከቱአታል፥ አሁን እንደ መንገድ ጭቃ ትረገጣለች። ቅጥርሽ በሚሠራበት በዚያ ቀን ድንበርሽ ትስፋፋለች።</verse>
				<verse number="12">በዚያ ቀን ከአሦርና ከግብጽ ከተሞች፥ ከግብጽ እስከ ወንዙ፥ ከባሕርም እስከ ባሕር፥ ከተራራም እስከ ተራራ ድረስ ወደ አንቺ ይመጣሉ።</verse>
				<verse number="13">ምድሪቱ ግን በሚኖሩባት በሥራቸው ፍሬ ምክንያት ባድማ ትሆናለች።</verse>
				<verse number="14">በቀርሜሎስ መካከል ባለው ዱር ብቻቸውን የተቀመጡት ሰዎችህ፥ የርስትህን በጎች፥ በበትርህ አግድ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።</verse>
				<verse number="15">ከግብጽ ምድር እንደ ወጣህበት ዘመን ተአምራትን አሳያቸዋለሁ።</verse>
				<verse number="16">አሕዛብ አይተው በጕልበታቸው ሁሉ ያፍራሉ፥ እጃቸውን በአፋቸው ላይ ያኖራሉ፥ ጆሮአቸውም ትደነቍራለች፥ እንደ እባብም መሬት ይልሳሉ፥</verse>
				<verse number="17">እንደ ምድርም ተንቀሳቃሾች እየተንቀጠቀጡ ከግንባቸው ይመጣሉ፥ ፈርተውም ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመጣሉ፥ ስለ አንተም ይፈራሉ።</verse>
				<verse number="18">በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱንም ቅሬታ ዓመፅ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረትን ይወድዳልና ቍጣውን ለዘላለም አይጠብቅም።</verse>
				<verse number="19">ተመልሶ ይምረናል፥ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል፥ ኃጢአታችንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል።</verse>
				<verse number="20">ከቀድሞ ዘመን ጀምረህ ለአባቶቻችን የማልህላቸውን እውነት ለያዕቆብ፥ ምሕረትንም ለአብርሃም ታደርጋለህ።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="34">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">ስለ ነነዌ የተነገረ ሸክም፣ የኤልቆሻዊው የናሆም የራእዩ መጽሐፍ ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው፣ እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው፣ እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል።</verse>
				<verse number="3">እግዚአብሔር ትዕግሥተኛ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ በደለኛውንም፦ ንጹሕ ነህ አይልም፣ እግዚአብሔር በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ አለው፥ ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው።</verse>
				<verse number="4">ባሕሩንም ይገሥጻታል፥ ያደርቃትማል፥ ወንዞችንም ሁሉ ያደርቃል፣ ባሳንና ቀርሜሎስም ላልተዋል፥ የሊባኖስም አበባ ጠውልጎአል።</verse>
				<verse number="5">ተራሮችም ከእርሱ የተነሣ ታወኩ፥ ኮረብቶችም ቀለጡ፣ ምድርና ዓለም የሚኖሩበትም ሁሉ ከፊቱ ተናወጡ።</verse>
				<verse number="6">በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው? የቍጣውንም ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቆች ተሰነጠቁ።</verse>
				<verse number="7">እግዚአብሔር መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፣ በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃል።</verse>
				<verse number="8">ስፍራዋን ግን በሚያጥለቀልቅ ጎርፍ ፈጽሞ ያጠፋታል፥ ጠላቶቹንም ወደ ጨለማ ያሳድዳቸዋል።</verse>
				<verse number="9">በእግዚአብሔር ላይ የምታስቡት ምንድር ነው? እርሱ ፈጽሞ ያጠፋል፥ መከራም ሁለተኛ አይነሣም።</verse>
				<verse number="10">እርስ በእርሳቸው እንደ ተመሰቃቀለ እሾህ ቢሆኑ፥ በመጠጣቸውም ቢሰክሩ እንደ ደረቅ ገለባ ፈጽመው ይጠፋሉ።</verse>
				<verse number="11">በእግዚአብሔር ላይ በክፉ የሚያስብ፥ ክፋትን የሚመክር፥ ከአንተ ዘንድ ወጥቶአል።</verse>
				<verse number="12">እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ኃይለኞችና ብዙዎች ቢሆኑ እንዲሁ ይቈረጣሉ፥ እርሱም ያልቃል። እኔም አስጨንቄሃለሁ፥ ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ አላስጨንቅህም።</verse>
				<verse number="13">አሁንም ቀንበሩን ከአንተ እሰብራለሁ፥ እስራትህንም እበጥሳለሁ።</verse>
				<verse number="14">እግዚአብሔርም ከስምህ ማንም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይዘራ ስለ አንተ አዝዞአል፣ ከአምላኮችህ ቤት የተቀረጸውንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል አጠፋለሁ። አንተም የተጠቃህ ነህና መቃብርህን እምሳለሁ።</verse>
				<verse number="15">እነሆ፥ የምስራችን የሚያመጣ ሰላምንም የሚያወራ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው! ይሁዳ ሆይ፥ አጥፊው ፈጽሞ ጠፍቶአልና፥ ከእንግዲህም ወዲህ በአንተ ዘንድ አያልፍምና ዓመት በዓሎችህን አድርግ፥ ስእለቶችህን ክፈል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">የሚቀጠቅጥ በአንተ ላይ ወጥቶአል፣ ምሽግን ጠብቅ፥ መንገድንም ሰልል፣ ወገብህን አጽና፥ ኃይልህንም እጅግ አበርታ።</verse>
				<verse number="2">ዘራፊዎች ዘርፈዋቸዋልና፥ የወይናቸውንም አረግ አጥፍተዋልና እግዚአብሔር የያዕቆብን ክብር እንደ እስራኤል ክብር ይመልሳል።</verse>
				<verse number="3">የኃያላኑ ጋሻ ቀልቶአል፥ ጽኑዓንም ቀይ ልብስ ለብሰዋል። እርሱም በሚያዘጋጅበት ቀን ሰረገሎች እንደ እሳት ይንቦገቦጋሉ፣ የጦሩም ሶመያ ይወዛወዛል።</verse>
				<verse number="4">ሰረገሎች በመንገድ ላይ ይነጕዳሉ፥ አደባባይም ይጋጫሉ፣ መልካቸው እንደ ፋና ነው፥ እንደ መብረቅም ይከንፋሉ።</verse>
				<verse number="5">መሳፍንቱን ያስባል፣ በአረማመዳቸው ይሰናከላሉ፣ ፈጥነው በቅጥርዋ ላይ ይወጣሉ፥ መጠጊያም ተዘጋጀለት።</verse>
				<verse number="6">የወንዞቹም መዝጊያዎች ተከፈቱ፥ የንጉሡ ቤትም ቀለጠች።</verse>
				<verse number="7">ንግሥት ተገለጠች፥ ተማረከችም፥ ሴቶች ባሪያዎችዋም እንደ ርግብ እየጮኹና ደረታቸውን እየመቱ ዋይ ዋይ ይላሉ።</verse>
				<verse number="8">ነነዌ ግን ከዱሮ ዘመን ጀምራ እንደ ተከማቸ ውኃ ነበረች፣ አሁን ግን ይሸሻሉ፣ እነርሱም፦ ቁሙ፥ ቁሙ ይላሉ፥ ነገር ግን የሚመለስ የለም።</verse>
				<verse number="9">መዝገብዋ መጨረሻ የለውምና፥ የከበረውም የዕቃዋ ሁሉ ብዛት አይቈጠርምና ብሩን በዝብዙ፥ ወርቁንም በዝብዙ።</verse>
				<verse number="10">ባዶና ባድማ ምድረ በዳም ሆናለች፣ ልብ ቀልጦአል፥ ጕልበቶችም ተብረክርከዋል፣ በወገብም ሁሉ ሕማም አለ፥ የሰዎችም ሁሉ ፊት ጠቍሮአል።</verse>
				<verse number="11">የአንበሾችም መደብ፥ የአንበሾችም ደቦል የሚሰማራበት፥ አንበሳውና አንበሳይቱ ግልገሉም ሳይፈሩ የሚሄዱት ስፍራ ወዴት ነው?</verse>
				<verse number="12">አንበሳው ለልጆቹ የሚበቃውን ነጠቀ፥ ለእንስቶቹም ሰበረላቸው ዋሻውን በንጥቂያ፥ መደቡንም በቅሚያ ሞልቶታል።</verse>
				<verse number="13">እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ሰረገሎችዋንም አቃጥዬ አጤሳለሁ፥ ሰይፍም የአንበሳ ደቦሎችሽን ይበላቸዋል፣ ንጥቂያሽንም ከምድር አጠፋለሁ፥ የመልክተኞችሽን ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ አይሰማም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ለደም ከተማ ወዮላት! በሁለንተናዋ ሐሰትና ቅሚያ ሞልቶባታል፣ ንጥቂያ ከእርስዋ አያልቅም።</verse>
				<verse number="2">የአለንጋ ድምፅ፥ የመንኰራኵርም ድምፅ፥ የፈረሶችም ኮቴ፥ የፈጣን ሰረገላም ጩኸት ተሰምቶአል፣</verse>
				<verse number="3">ፈረሰኛው ይጋልባል፥ ሰይፍም ይንቦገቦጋል፥ ጦርም ይብለጨለጫል፣ የተገደሉትም ይበዛሉ፥ በድኖችም በክምር ይከመራሉ፥ ሬሳቸውም አይቈጠርም፣ በሬሳቸውም ይሰናከላሉ።</verse>
				<verse number="4">ስለ ተዋበችው ጋለሞታ ግልሙትና ብዛት ይህ ሆኖአል፣ እርስዋም በመተትዋ እጅግ በለጠች፥ አሕዛብንም በግልሙትናዋ፥ ወገኖችንም በመተትዋ ሸጠች።</verse>
				<verse number="5">እነሆ፥ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ልብስሽን በፊትሽ እገልጣለሁ፣ ኅፍረተ ሥጋሽንም ለአሕዛብ፥ ነውርሽንም ለመንግሥታት አሳያለሁ።</verse>
				<verse number="6">ርኵሰትንም በላይሽ እጥላለሁ፥ እንቅሽማለሁ፥ ማላገጫም አደርግሻለሁ።</verse>
				<verse number="7">የሚያይሽም ሁሉ ከአንቺ ሸሽቶ፦ ነነዌ ባድማ ሆናለች፣ የሚያለቅስላትስ ማን ነው? የሚያጽናናትንስ ከወዴት እፈልጋለሁ? ይላል።</verse>
				<verse number="8">አንቺ በመስኖች መካከል ከተቀመጠችው፥ ውኃም በዙሪያዋ ከነበራት፥ ምሽግዋም ባሕር ከነበረ፥ ቅጥርዋም በባሕር ውስጥ ከነበረ ከኖእ አሞን ትበልጫለሽን?</verse>
				<verse number="9">ኢትዮጵያና ግብጽ የማይቈጠር ኃይልዋ ነበሩ፣ ፉጥና ልብያ ረዳቶችዋ ነበሩ።</verse>
				<verse number="10">እርስዋ ግን ተማርካ ፈለሰች፣ ሕፃናቶችዋ በመንገድ ሁሉ ራስ ላይ ተፈጠፈጡ፣ በከበርቴዎችዋም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፥ ታላላቆችዋም ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ።</verse>
				<verse number="11">አንቺም ትሰክሪአለሽ ወራዳም ትሆኛለሽ፣ አንቺ ደግሞ ከጠላት የተነሣ መጠጊያን ትፈልጊአለሽ።</verse>
				<verse number="12">አምባሽ ሁሉ የመጀመሪያውን የበሰለ ፍሬ እንደ ያዙ እንደ በለስ ዛፎች ነው፣ ቢወዛወዝ በሚበላው አፍ ውስጥ ይወድቃል።</verse>
				<verse number="13">እነሆ፥ በመካከልሽ ያሉ ሕዝብሽ ሴቶች ናቸው፣ የአገርሽ በሮች ለጠላቶችሽ ፈጽሞ ተከፍተዋል፥ እሳትም መወርወሪያዎችህን በልቶአል።</verse>
				<verse number="14">ከብበው ያስጨንቁሻልና ውኃን ቅጂ፣ አምባሽን አጠንክሪ፣ ወደ ጭቃ ገብተሽ እርገጪ፣ የጡብን መሠሪያ ያዢ።</verse>
				<verse number="15">በዚያ እሳት ይበላሻል፥ ሰይፍ ያጠፋሻል፥ እንደ ደጎብያ ይበላሻል፣ እንደ ደጎብያ ብዢ፥ እንደ አንበጣም ተባዢ።</verse>
				<verse number="16">ነጋዴዎችሽን ከሰማይ ከዋክብት ይልቅ አበዛሽ፣ ደጎብያ ተዘረጋ፥ በረረም።</verse>
				<verse number="17">በአንቺ ዘንድ ዘውድ የጫኑት እንደ አንበጣ፥ አለቆችሽም እንደሚንቀሳቀሱ ኩብኩባዎች ናቸው፣ በብርድ ቀን በቅጥር ውስጥ ይቀመጣሉ፥ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ያኰበኵባሉ፣ ስፍራቸው በየት እንደ ሆነ አይታወቅም።</verse>
				<verse number="18">የአሦር ንጉሥ ሆይ፥ እረኞችህ አንቀላፍተዋል፣ መኳንንቶችህም ዐርፈዋል፣ ሕዝብህም በተራሮች ላይ ተበትኖአል፥ የሚሰበስበውም የለም።</verse>
				<verse number="19">ስብራትህ አይፈወስም፥ ቁስልህም ክፉ ነው፣ ወሬህንም የሚሰሙ ሁሉ እጃቸውን በአንተ ላይ ያጨበጭባሉ፣ ክፋትህ ሁልጊዜ ያላለፈችበት ሰው ማን ነውና?</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="35">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">ነቢዩ ዕንባቆም ያየው ሸክም ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">አቤቱ፥ እኔ ስጮኽ የማትሰማው እስከ መቼ ነው? ስለ ግፍ ወደ አንተ እጮኻለሁ፥ አንተም አታድንም።</verse>
				<verse number="3">በደልንስ ስለ ምን አሳየኸኝ? ጠማምነትንስ ስለ ምን ትመለከታለህ? ጥፋትና ግፍ በፊቴ ነው፣ ጠብና ክርክር ይነሣሉ።</verse>
				<verse number="4">ስለዚህ ሕግ ላልቶአል፥ ፍርድም ድል ነሥቶ አይወጣም፣ ኃጢአተኛ ጻድቅን ይከብባልና፣ ስለዚህ ፍርድ ጠማማ ሆኖ ይወጣል።</verse>
				<verse number="5">እናንተ የምትንቁ ሆይ፥ አንድ ቢተርክላችሁ ስንኳ የማታምኑትን ሥራ በዘመናችሁ እሠራለሁና እዩ፥ ተመልከቱ፥ ተደነቁ።</verse>
				<verse number="6">እነሆ፥ የእነርሱ ያልሆነውን መኖሪያ ይወርሱ ዘንድ በምድር ስፋት ላይ የሚሄዱትን መራሮችንና ፈጣኖችን ሕዝብ ከለዳውያንን አስነሣለሁ።</verse>
				<verse number="7">እነርሱ የሚያስፈሩና የሚያስደነግጡ ናቸው፣ ፍርዳቸውና ክብራቸው ከራሳቸው ይወጣል።</verse>
				<verse number="8">ፈረሶቻቸውም ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፥ ከማታም ተኵላ ይልቅ ጨካኞች ናቸው፣ ፈረሰኞቻቸውም ይንሳፈፋሉ፥ ከሩቅም ይመጣሉ፥ ለመብልም እንደሚቸኵል ንስር ይበርራሉ።</verse>
				<verse number="9">ሁሉም ለግፍ ሥራ ይመጣሉ፥ ፊታቸውንም እንደ ምሥራቅ ነፋስ ያቀናሉ፣ ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ይሰበስባሉ።</verse>
				<verse number="10">በነገሥታት ላይ ያላግጣሉ፥ መሳፍንትም ዋዛ ሆነውላቸዋል፣ በምሽጉ ሁሉ ይስቃሉ፥ አፈሩንም ከምረው ይወስዱታል።</verse>
				<verse number="11">የዚያን ጊዜም እንደ ነፋስ አልፎ ይሄዳል፥ ይበድልማል፣ ኃይሉንም አምላክ ያደርገዋል።</verse>
				<verse number="12">አቤቱ፥ የተቀደስህ አምላኬ ሆይ፥ አንተ ከዘላለም ጀምሮ አልነበርህምን? እኛ አንሞትም፣ አቤቱ፥ ለፍርድ ሠርተኸዋል፥ ለተግሣጽም አድርገኸዋል።</verse>
				<verse number="13">ዓይኖችህ ክፉ እንዳያዩ ንጹሐን ናቸው፥ ጠማምነትንም ትመለከት ዘንድ አትችልም፣ አታላዮችንስ ለምን ትመለከታለህ? ኃጢአተኛውስ ከእርሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጠው ስለምን ዝም ትላለህ?</verse>
				<verse number="14">ሰዎችንም እንደ ባሕር ዓሣዎች፥ አለቃም እንደሌላቸው ተንቀሳቃሾች ለምን ታደርጋቸዋለህ?</verse>
				<verse number="15">ሁሉን በመቃጥን ያወጣል፥ በመረቡም ይይዛቸዋል፥ በአሽክላውም ውስጥ ያከማቻቸዋል፣ ስለዚህ ደስ እያለው እልል ይላል።</verse>
				<verse number="16">እድል ፈንታው በእነርሱ ሰብታለችና፥ መብሉም በዝቶአልና ስለዚህ ለመረቡ ይሠዋል፥ ለአሽክላውም ያጥናል።</verse>
				<verse number="17">ስለዚህ መረቡን ይጥላልን? አሕዛብንም ዘወትር ይገድል ዘንድ አይራራምን?</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፥ በአምባ ላይም እወጣለሁ፣ የሚናገረኝንም፥ ስለ ክርክሬም የምመልሰውን አውቅ ዘንድ እመለከታለሁ።</verse>
				<verse number="2">እግዚአብሔርም መለሰልኝ እንዲህም አለ፦ አንባቢው ይፈጥን ዘንድ ራእዩን ጻፍ፥ በጽላትም ላይ ግለጠው።</verse>
				<verse number="3">ራእዩ ገና እስከ ተወሰነው ጊዜ ነው፥ ወደ ፍጻሜውም ይቸኵላል፥ እርሱም አይዋሽም፣ ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ታገሠው፣ እርሱ አይዘገይም።</verse>
				<verse number="4">እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፣ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል።</verse>
				<verse number="5">እርሱ አታላይና ኵሩ ሰው ነው፣ በስፍራው ዐርፎ አይቀመጥም፣ ስስቱን እንደ ሲኦል ያሰፋል፥ እርሱም እንደ ሞት አይጠግብም፣ አሕዛብንም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበስባል፥ ወገኖቹንም ሁሉ ወደ እርሱ ያከማቻል።</verse>
				<verse number="6">እነዚህ ሁሉ፦ ለእርሱ ያልሆነውን ወደ እርሱ ለሚሰበስብ መያዣውንም ለራሱ የሚያበዛ ወዮለት! እስከ መቼ ነው? እያሉ ምሳሌ አይመስሉበትምን?</verse>
				<verse number="7">ተረትም አይተርቱበትምን? የሚነክሱህ ድንገት አይነሡብህምን? የሚያስጨንቁህም ይነቃሉ፣ ለእነርሱም ብዝበዛ ትሆናለህ።</verse>
				<verse number="8">የሰውን ደም ስላፈሰስህ፥ በምድሪቱና በከተማይቱም በእርስዋም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፥ አንተ ብዙዎችን አሕዛብን በዝብዘሃልና ከአሕዛብ የቀሩት ሁሉ ይበዘብዙሃል።</verse>
				<verse number="9">ከክፉ እንዲድን ጐጆውን በከፍታ ላይ ያደርግ ዘንድ ለቤቱ ክፉ ትርፍን ለሚሰበስብ ወዮለት!</verse>
				<verse number="10">ብዙ አሕዛብን አጥፍተሃልና ለቤትህ እፍረትን መክረሃል፥ በነፍስህም ላይ ኃጢአትን አድርገሃል።</verse>
				<verse number="11">ድንጋይም ከግንብ ውስጥ ይጮኻል፥ እንጨትም ከውቅር ውስጥ ይመልስለታል።</verse>
				<verse number="12">ከተማን በደም ለሚሠራ፥ ከተማንም በኃጢአት ለሚመሠርት ወዮለት!</verse>
				<verse number="13">እነሆ፥ አሕዛብ ስለ እሳት እንዲሠሩ፥ ወገኖችም ስለ ከንቱነት እንዲደክሙ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ አይደለምን?</verse>
				<verse number="14">ውኃ ባሕርን እንደሚከድን ምድር የእግዚአብሔርን ክብር በማወቅ ትሞላለችና።</verse>
				<verse number="15">ኅፍረተ ሥጋውን ለማየት ባልንጀራውን ለሚያጠጣ፥ ክፉንም ለሚጨምርበት፥ ለሚያሰክረውም ወዮለት!</verse>
				<verse number="16">በክብር ፋንታ እፍረት ሞልቶብሃል፣ አንተ ደግሞ ጠጥተህ ተንገድገድ፣ የእግዚአብሔር የቀኙ ጽዋ ይመለስብሃል፥ እፍረትም በክብርህ ላይ ይሆናል።</verse>
				<verse number="17">የሰውንም ደም ስላፈሰስህ፥ በምድሪቱና በከተማይቱም በእርስዋም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፥ በሊባኖስ ላይ የሠራኸው ግፍ ይከድንሃል፣ የአራዊትም አደጋ ያስፈራራሃል።</verse>
				<verse number="18">የተቀረጸውን ምስል ሠሪው የቀረጸው ለምን ጥቅም ነው? ዲዳንም ጣዖት ይሠራ ዘንድ ሠሪው የታመነበቱ፥ ሐሰትን የሚያስተምር ቀልጦ የተሠራ ምን ይጠቅማል?</verse>
				<verse number="19">እንጨቱን፦ ንቃ፥ ዲዳውንም ድንጋይ፦ ተነሣ ለሚለው ወዮለት! በውኑ ይህ ያስተምራልን? እነሆ፥ በወርቅና በብር ተለብጦአል፥ ምንም እስትንፋስ የለበትም።</verse>
				<verse number="20">እግዚአብሔር ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፣ ምድርም ሁሉ በፊቱ ዝም ትበል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">የነቢዩ የዕንባቆም ጸሎት በመዝሙር።</verse>
				<verse number="2">አቤቱ፥ ዝናህን ሰምቼ ፈራሁ፣ አቤቱ፥ በዓመታት መካከል ሥራህን ፈጽም፣ በዓመታት መካከል ትታወቅ፣ በመዓት ጊዜ ምሕረትን አስብ።</verse>
				<verse number="3">እግዚአብሔር ከቴማን፥ ቅዱሱም ከፋራን ተራራ ይመጣል። ክብሩ ሰማያትን ከድኖአል፥ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል።</verse>
				<verse number="4">ፀዳሉም እንደ ብርሃን ነው፣ ጨረር ከእጁ ወጥቶአል፣ ኃይሉም በዚያ ተሰውሮአል።</verse>
				<verse number="5">ቸነፈር በፊቱ ይሄዳል፥ የእሳትም ነበልባል ከእግሩ ይወጣል።</verse>
				<verse number="6">ቆመ፥ ምድርንም አወካት፣ ተመለከተ፥ አሕዛብንም አናወጠ፣ የዘላለምም ተራሮች ተቀጠቀጡ፥ የዘላለምም ኮረብቶች ቀለጡ፣ መንገዱ ከዘላለም ነው።</verse>
				<verse number="7">የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፣ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።</verse>
				<verse number="8">በውኑ እግዚአብሔር በወንዞች ላይ ተቈጥቶአልን? ቍጣህ በወንዞች ላይ፥ መዓትህም በባሕር ላይ ነውን? በፈረሶችህና በማዳንህ ሰረገሎች ላይ ተቀምጠሃልና።</verse>
				<verse number="9">በቃልህ እንደ ማልህ መቅሠፍትህን አወጣህ፣ ቀስትህንም ገተርህ፣ ምድርን ሰንጥቀህ ፈሳሾችን አወጣህ።</verse>
				<verse number="10">ተራሮች አንተን አይተው ተጨነቁ፣ የውኃ ሞገድ አልፎአል፣ ቀላዩም ድምፁን ሰጥቶአል፥ እጁንም ወደ ላይ አንሥቶአል።</verse>
				<verse number="11">ፍላጾችህ ከወጡበት ብርሃን የተነሣ፥ ከሚንቦገቦገውም ከጦርህ ፀዳል የተነሣ፥ ፀሐይና ጨረቃ በመኖሪያቸው ቆሙ።</verse>
				<verse number="12">በምድር ላይ በመዓት ተራመድህ፣ አሕዛብን በቍጣ አሄድሃቸው።</verse>
				<verse number="13">ሕዝብህን ለመታደግ፥ የቀባኸውንም ለማዳን ወጣህ፣ የኃጢአተኛውን ቤት ራስ ቀጠቀጥህ፣ መሠረቱን እስከ አንገቱ ድረስ ገለጥህ።</verse>
				<verse number="14">የአለቆችን ራስ በገዛ በትራቸው ወጋህ፣ እኔን ይበትኑ ዘንድ እንደ ዐውሎ ነፋስ መጡ፣ ችግረኛውን በስውር ለመዋጥ ደስታቸው ነው።</verse>
				<verse number="15">ፈረሶችህን በባሕር፥ በብዙ ውኆችም ላይ አስረገጥህ።</verse>
				<verse number="16">እኔ ሰምቻለሁ፥ ልቤም ደነገጠብኝ፣ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፣ መንቀጥቀጥ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፣ በስፍራዬ ሆኜ ተናወጥሁ፣ በሚያስጨንቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።</verse>
				<verse number="17">ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥</verse>
				<verse number="18">እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፣ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።</verse>
				<verse number="19">ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፣ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፣ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="36">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በይሁዳ ንጉሥ በአሞጽ ልጅ በኢዮስያስ ዘመን ወደ ሕዝቅያስ ልጅ ወደ አማርያ ልጅ ወደ ጎዶልያስ ልጅ ወደ ኵሲ ልጅ ወደ ሶፎንያስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">ነገርን ሁሉ ከምድር ፊት ፈጽሜ አጠፋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="3">ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፣ የሰማይን ወፎችና የባሕርን ዓሣዎች ማሰናከያንም ከኃጢአተኞች ጋር አጠፋለሁ፣ ሰውንም ከምድር ፊት እቈርጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="4">እጄንም በይሁዳ ላይ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ላይ እዘረጋለሁ፣ ከዚህም ስፍራ የበኣልን ቅሬታና የጣዖታቱን ካህናት ስም አጠፋለሁ፣</verse>
				<verse number="5">በሰገነትም ላይ ለሰማይ ሠራዊት የሚሰግዱትን፥ በእግዚአብሔርና በንጉሣቸው በሚልኮም ምለው የሚሰግዱትን፥</verse>
				<verse number="6">እግዚአብሔርንም ከመከተል የተመለሱትን፥ እግዚአብሔርንም ያልፈለጉትንና ያልጠየቁትን አጠፋለሁ።</verse>
				<verse number="7">የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፥ እግዚአብሔር መሥዋዕትን አዘጋጅቶአልና፥ የጠራቸውንም ቀድሶአልና በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ።</verse>
				<verse number="8">በእግዚአብሔርም መሥዋዕት ቀን አለቆችንና የንጉሥን ልጆች እንግዳ ልብስ የሚለብሱትንም ሁሉ እቀጣለሁ።</verse>
				<verse number="9">በዚያም ቀን በመድረኩ ላይ የሚዘልሉትን፥ የጌታቸውን ቤት ዓመፃንና ሽንገላን የሚሞሉትን እቀጣለሁ።</verse>
				<verse number="10">በዚያ ቀን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ከዓሣው በር የጩኸት ድምፅ፥ ከከተማውም በሁለተኛው ክፍል ውካታ፥ ከኮረብቶቹም ታላቅ ሽብር ይሆናል።</verse>
				<verse number="11">እናንተ በመክቴሽ የምትኖሩ ሆይ፥ የከነዓን ሕዝብ ሁሉ ጠፍተዋልና፥ ብርም የተሸከሙ ሁሉ ተቈርጠዋልና አልቅሱ።</verse>
				<verse number="12">በዚያም ዘመን ኢየሩሳሌምን በመብራት እመረምራለሁ፣ በአተላቸውም ላይ የሚቀመጡትን፥ በልባቸውም፦ እግዚአብሔር መልካምን አያደርግም፥ ክፉም አያደርግም የሚሉትን ሰዎች እቀጣለሁ።</verse>
				<verse number="13">ብልጥግናቸውም ለምርኮ ይሆናል፥ ቤቶቻቸውም ይፈርሳሉ፣ ቤቶችንም ይሠራሉ፥ ነገር ግን አይቀመጡባቸውም፣ ወይንንም ይተክላሉ፥ የወይን ጠጁን ግን አይጠጡም።</verse>
				<verse number="14">ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአል፣ የእግዚአብሔር ቀን ድምፅ ቀርቦአል እጅግም ፈጥኖአል፣ ኃያሉም በዚያ በመራራ ልቅሶ ይጮኻል።</verse>
				<verse number="15">ያ ቀን የመዓት ቀን የመከራና የጭንቀት ቀን፥ የመፍረስና የመጥፋት ቀን፥ የጨለማና የጭጋግ ቀን፥ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን፥</verse>
				<verse number="16">በተመሸጉ ከተሞችና በረዘሙ ግንቦች ላይ የመለከትና የሰልፍ ጩኸት ቀን ነው።</verse>
				<verse number="17">በእግዚአብሔርም ላይ ኃጢአት ሠርተዋልና እንደ ዕውር እስኪሄዱ ድረስ ሰዎችን አስጨንቃለሁ፣ ደማቸውም እንደ ትቢያ፥ ሥጋቸውም እንደ ጕድፍ ይፈስሳል።</verse>
				<verse number="18">በእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፣ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ፈጥኖ ይጨርሳቸዋልና ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">እናንተ እፍረት የሌላችሁ ሕዝብ ሆይ፥ ትእዛዝ ሳይወጣ፥ ቀኑም እንደ ገለባ ሳያልፍ፥ የእግዚአብሔርም ቍጣ ትኵሳት ሳይመጣባችሁ፥ የእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ሳይደርስባችሁ ተሰብሰቡ፥ ተከማቹም።</verse>
				<verse number="2"></verse>
				<verse number="3">እናንተ ፍርዱን የጠበቃችሁ የምድር ትሑታን ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፈልጉ፣ ጽድቅንም ፈልጉ፥ ትሕትናንም ፈልጉ፣ ምናልባት በእግዚአብሔር ቍጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል።</verse>
				<verse number="4">ጋዛ ትበረበራለች፥ አስቀሎናም ባድማ ትሆናለች፣ አዛጦንንም በቀትር ወደ ውጭ ያሳድዱአታል፥ አቃሮንም ትነቀላለች።</verse>
				<verse number="5">በባሕር ዳር ለሚኖሩ ለከሊታውያን ሕዝብ ወዮላቸው! የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፥ የእግዚአብሔር ቃል በአንተ ላይ ነው፥ የሚቀመጥብህም ሰው እንዳይኖር አጠፋሃለሁ።</verse>
				<verse number="6">ቀርጤስም የእረኞች መኖሪያና የመንጎች በረት ይሆናል።</verse>
				<verse number="7">የባሕሩም ዳር ለይሁዳ ቤት ቅሬታ ይሆናል፥ በዚያም ይሰማራሉ፣ አምላካቸው እግዚአብሔር ይጐበኛቸዋልና፥ ምርኮአቸውንም ይመልሳልና በአስቀሎና ቤቶች ውስጥ ማታ ይተኛሉ።</verse>
				<verse number="8">በሕዝቤም ላይ ያላገጡባትን፥ በድንበራቸውም ላይ እየታበዩ የተናገሩባትን የሞዓብን ማላገጥና የአሞንን ልጆች ስድብ ሰምቻለሁ።</verse>
				<verse number="9">ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና በእርግጥ ሞዓብ እንደ ሰዶም፥ የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ፥ የሳማ ስፍራና የጨው ጕድጓድ ለዘላለምም ምድረ በዳ ሆነው ይኖራሉ፣ የሕዝቤም ቅሬታ ይበዘብዛቸዋል፥ ከወገኔም የተረፉት ይወርሱአቸዋል።</verse>
				<verse number="10">በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ አላግጠዋልና፥ እየታበዩም ተናግረዋልና ይህ ስለ ትዕቢታቸው ያገኛቸዋል።</verse>
				<verse number="11">እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርንም አማልክት ሁሉ ያከሳቸዋል፣ በአሕዛብም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በስፍራቸው ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።</verse>
				<verse number="12">እናንተም ኢትዮጵያውያን ደግሞ፥ በሰይፌ ትገደላላችሁ።</verse>
				<verse number="13">እርሱም በሰሜን ላይ እጁን ይዘረጋል፥ አሦርንም ያጠፋል፣ ነነዌንም ባድማ፥ እንደ በረሃም ደረቅ ያደርጋታል።</verse>
				<verse number="14">መንጎችም የምድርም አራዊት ሁሉ በውስጥዋ ይመሰጋሉ፣ ይብራና ጃርት በዓምዶችዋ መካከል ያድራሉ፣ ድምፃቸው በመስኮቶችዋ ይጮኻል፣ የዝግባም እንጨት ሥራ ይገለጣልና በመድረኮችዋ ላይ ጥፋት ይሆናል።</verse>
				<verse number="15">ተዘልላ የተቀመጠች፥ በልብዋም፦ እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም ያለች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፣ አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ እንዴት ሆነች! በእርስዋ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፍዋጫል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ለዓመፀኛይቱና ለረከሰች ለአስጨናቂይቱም ከተማ ወዮላት!</verse>
				<verse number="2">ድምፅን አልሰማችም፥ ተግሣጽንም አልተቀበለችም፣ በእግዚአብሔርም አልታመነችም፥ ወደ አምላክዋም አልቀረበችም።</verse>
				<verse number="3">በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ እንደሚያገሡ አንበሶች ናቸው፣ ፈራጆችዋም እስከ ነገ ድረስ ምንም እንደማያስቀሩ እንደ ማታ ተኵላዎች ናቸው።</verse>
				<verse number="4">ነቢያቶችዋ ቅሌታሞችና ተንኰለኞች ሰዎች ናቸው፣ ካህናቶችዋም መቅደሱን አርክሰዋል፥ በሕግም ላይ ግፍ ሠርተዋል።</verse>
				<verse number="5">እግዚአብሔር በውስጥዋ ጻድቅ ነው፣ ክፋትን አያደርግም፣ ፍርዱን በየማለዳው ወደ ብርሃን ያወጣል፥ ሳያወጣውም አይቀርም፣ ዓመፀኛው ግን እፍረትን አያውቅም።</verse>
				<verse number="6">አሕዛብን አጥፍቻለሁ፣ ግንቦቻቸው ሁሉ ፈርሰዋል፣ መንገዳቸውን ማንም እንዳያልፍባት ምድረ በዳ አድርጌአለሁ፥ ከተሞቻቸውም ማንም እንዳይኖርባቸው፥ አንድስ እንኳ እንዳይቀመጥባቸው ፈርሰዋል።</verse>
				<verse number="7">እኔም- ይፈሩኛል፥ ተግሣጽንም ይቀበላሉ፣ ካዘዝኋትም ሁሉ ከዓይንዋ ምንም አይጠፋም ብዬ ነበር፣ እነርሱ ግን በማለዳ ተነሥተው ድርጊታቸውን ሁሉ አረከሱ።</verse>
				<verse number="8">መዓቴንና የቍጣዬን ትኵሳት ሁሉ አፈስስባቸው ዘንድ ፍርዴ አሕዛብን ለመሰብሰብ፥ መንግሥታትንም ለማከማቸት ነውና፥ ምድርም ሁሉ በቅንዓቴ እሳት ትበላለችና ስለዚህ ለመበዝበዝ እስከምነሣበት ቀን ድረስ ጠብቁኝ፥ ይላል እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="9">በዚያን ጊዜም አሕዛብ ሁሉ አንድ ሆነው እግዚአብሔርን ያገለግሉት ዘንድ ስሙን እንዲጠሩ ንጹሕን ልሳን እመልስላቸዋለሁ።</verse>
				<verse number="10">ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የሚማልዱኝ፥ የተበተኑትን ሴቶች ልጆቼ፥ ቍርባኔን ያመጡልኛል።</verse>
				<verse number="11">በዚያን ጊዜ እየታበዩ የሚፎክሩትን ከመካከልሽ አወጣለሁና፥ አንቺም በቅዱስ ተራራዬ ዳግመኛ አትኰሪምና በዚያ ቀን በእኔ ላይ ተላልፈሽ በሠራሽው ሥራ ሁሉ አታፍሪም።</verse>
				<verse number="12">በመካከልሽም የዋህና ትሑት ሕዝብን አስቀራለሁ፣ በእግዚአብሔርም ስም ይታመናሉ።</verse>
				<verse number="13">የእስራኤል ቅሬታ ኃጢአትን አይሠሩም፥ ሐሰትንም አይናገሩም፥ በአፋቸውም ውስጥ ተንኰለኛ ምላስ አይገኝም፣ እነርሱም ይሰማራሉ፥ ይመሰጉማል፥ የሚያስፈራቸውም የለም።</verse>
				<verse number="14">የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ዘምሪ፣ እስራኤል ሆይ፥ እልል በል፣ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ በፍጹም ልብሽ ሐሴት አድርጊ ደስም ይበልሽ።</verse>
				<verse number="15">እግዚአብሔር ፍርድሽን አስወግዶአል፥ ጠላትሽንም ጥሎአል፣ የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር በመካከልሽ አለ፥ ከእንግዲህም ወዲህ ክፉ ነገርን አታዪም።</verse>
				<verse number="16">በዚያን ቀን ለኢየሩሳሌም፦ ጽዮን ሆይ፥ አትፍሪ፥ እጆችሽም አይዛሉ።</verse>
				<verse number="17">አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፣ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል ይባላል።</verse>
				<verse number="18">ከጉባኤው ርቀው የሚያዝኑትን፥ ከአንቺም የሆኑትን እሰበስባለሁ፣ ስድብ እንደ ሸክም ከብዶባቸው ነበር።</verse>
				<verse number="19">በዚያ ዘመን እነሆ፥ ባስጨነቁሽ ሁሉ ላይ አደርግባቸዋለሁ፣ አንካሳይቱንም አድናለሁ፥ የተጣለችውንም እሰበስባታለሁ፣ ባፈሩባትም ምድር ሁሉ ላይ ለምስጋናና ለከበረ ስም አደርጋቸዋለሁ።</verse>
				<verse number="20">በዚያ ዘመን አስገባችኋለሁ፥ በዚያም ዘመን እሰበስባችኋለሁ፣ ምርኮአችሁንም በዓይናችሁ ፊት በመለስሁ ጊዜ በምድር አሕዛብ ሁሉ መካከል ለከበረ ስምና ለምስጋና አደርጋችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="37">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በንጉሡ በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ ወደ ይሁዳ አለቃ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤል፥ ወደ ታላቁም ካህን ወደ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦ ይህ ሕዝብ፦ ዘመኑ አልደረሰም፥ የእግዚአብሔር ቤት የሚሠራበት ዘመን አልደረሰም ይላል ብሎ ተናገረ።</verse>
				<verse number="3">የእግዚአብሔርም ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ እንዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="4">በውኑ ይህ ቤት ፈርሶ ሳለ እናንተ ራሳችሁ በተሸለሙ ቤቶቻችሁ ለመኖር ጊዜው ነውን?</verse>
				<verse number="5">አሁንም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ።</verse>
				<verse number="6">ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ፣ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም፣ ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልረካችሁም፣ ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም፣ ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ያደርገው ዘንድ ደመወዙን ተቀበለ።</verse>
				<verse number="7">የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ።</verse>
				<verse number="8">ወደ ተራራው ውጡ፥ እንጨትንም አምጡ፥ ቤቱንም ሥሩ፣ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል፥ እኔም እመሰገናለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="9">እናንተ ብዙ ነገርን ተስፋ አደረጋችሁ፥ እነሆም፥ ጥቂት ሆነ፣ ወደ ቤትም ባገባችሁት ጊዜ እፍ አልሁበት። ይህ ስለ ምንድር ነው? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተ ሁሉ ወደ እየቤታችሁ እየሮጣችሁ የእኔ ቤት ፈርሶ ስለ ተቀመጠ ነው።</verse>
				<verse number="10">ስለዚህ ሰማያት በላያችሁ ጠልን ከልክለዋል፥ ምድሪቱም ፍሬዋን ከልክላለች።</verse>
				<verse number="11">እኔም በምድርና በተራሮች፥ በእህልና በወይንም፥ በዘይትና ምድርም በምታበቅለው ላይ፥ በሰዎችና በእንስሶችም ላይ፥ እጅም በሚደክምበት ሁሉ ላይ ድርቅን ጠርቻለሁ።</verse>
				<verse number="12">የሰላትያልም ልጅ ዘሩባቤል፥ ታላቁም ካህን የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ፥ የቀሩትም ሕዝብ ሁሉ የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ድምፅ የነቢዩንም የሐጌን ቃል፥ አምላካቸው እግዚአብሔር እንደ ላከው ሁሉ ሰሙ፣ ሕዝቡም በእግዚአብሔር ፊት ፈሩ።</verse>
				<verse number="13">የእግዚአብሔርም መልእክተኛ ሐጌ በእግዚአብሔር መልእክት ሕዝቡን፦ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር ብሎ ተናገረ።</verse>
				<verse number="14">እግዚአብሔርም የይሁዳን አለቃ የሰላትያልን ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስ፥ የታላቁንም ካህን የኢዮሴዴቅን ልጅ የኢያሱን መንፈስ፥ የቀሩትንም ሕዝብ ሁሉ መንፈስ አስነሣ፣ በንጉሡም በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በሀያ አራተኛው ቀን መጡ፥ የአምላካቸውንም የሠራዊትን ጌታ የእግዚአብሔርን ቤት ሠሩ።</verse>
				<verse number="15"></verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">በሰባተኛው ወር ከወሩም በሀያ አንደኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ እንዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">ለይሁዳ አለቃ ለሰላትያል ልጅ ለዘሩባቤል፥ ለታላቁም ካህን ለኢዮሴዴቅ ልጅ ለኢያሱ፥ ለቀሩትም ሕዝብ እንዲህ ስትል ተናገር፦</verse>
				<verse number="3">በቀድሞ ክብሩ ሳለ ይህን ቤት ያየ በእናንተ መካከል የቀረ ማን ነው? ዛሬስ እንዴት ሆኖ አያችሁት? በዓይናችሁ እንደ ምናምን አይደለምን?</verse>
				<verse number="4">አሁን ግን፥ ዘሩባቤል ሆይ፥ በርታ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ ታላቁም ካህን የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ሆይ፥ በርታ፥ እናንተም የአገሩ ሕዝብ ሆይ፥ በርቱና ሥሩ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="5">መንፈሴም በመካከላችሁ ይኖራልና አትፍሩ።</verse>
				<verse number="6">የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ገና አንድ ጊዜ በቅርብ ዘመን እኔ ሰማያትንና ምድርን ባሕርንና የብስንም አናውጣለሁ፣</verse>
				<verse number="7">አሕዛብን ሁሉ አናውጣለሁ፥ በአሕዛብ ሁሉ የተመረጠውም ዕቃ ይመጣል፣ ይህንም ቤት በክብር እሞላዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="8">ብሩ የእኔ ነው፥ ወርቁም የእኔ ነው፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="9">ከፊተኛው ይልቅ የዚህ የሁለተኛው ቤት ክብር ይበልጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በዚህም ስፍራ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="10">በዳርዮስም በሁለተኛው ዓመት በዘጠነኛው ወር በሀያ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ እንዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="11">የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ካህናቱን ስለ ሕጉ ጠይቅ፣</verse>
				<verse number="12">አንድ ሰው የተቀደሰ ሥጋ በልብሱ ዘርፍ ቢይዝ፥ በዘርፉም እንጀራ ወይም ወጥ፥ ወይም የወይን ጠጅ፥ ወይም ዘይት፥ ወይም ማናቸውም መብል ቢነካ ያ የተነካው በውኑ ይቀደሳልን? ብለህ ካህናቱን ጠይቃቸው፣ ካህናቱም፦ አይሆንም ብለው መለሱ።</verse>
				<verse number="13">ሐጌም፦ በሬሳ የረከሰ ሰው ከእነዚህ አንዱን ቢነካ ያ የተነካው በውኑ ይረክሳልን? አለ። ካህናቱም፦ አዎን ይረክሳል ብለው መለሱ።</verse>
				<verse number="14">ሐጌም መልሶ እንዲህ አለ፦ ይህ ሕዝብና ይህ ወገን በፊቴ እንዲሁ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፣ የእጃቸውም ሥራ ሁሉ እንዲሁ ነው፣ በዚያም ያቀረቡት ነገር ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="15">አሁንም ድንጋይ በድንጋይ ላይ በእግዚአብሔር መቅደስ ሳይነባበር፥ ከዛሬ ጀምራችሁ ወዳለፈው ዘመን ልብ አድርጉ።</verse>
				<verse number="16">በዚያን ዘመን ሁሉ ሰው ሀያ መስፈሪያ ወዳለበት ምርት በመጣ ጊዜ፥ የተገኘው አሥር መስፈሪያ ብቻ ነው፣ አምሳ ማድጋም ይቀዳ ዘንድ ወደ መጥመቂያው በመጣ ጊዜ፥ የተገኘው ሀያ ብቻ ነው።</verse>
				<verse number="17">በእጃችሁ ሥራ ሁሉ ላይ በዋግና በአረማሞ በበረዶም መታኋችሁ፣ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="18">ከዛሬው ከዘጠነኛው ወር ከሀያ አራተኛው ቀን ጀምራችሁ የሚመጣውን ዘመን ልብ አድርጉ፣ የእግዚአብሔር መቅደስ መሠረት ከተተከለበት ቀን ጀምሮ ልብ አድርጉ።</verse>
				<verse number="19">ዘር በጎተራ ገና ይኖራልን? ወይንና በለስ ሮማንና ወይራ አላፈሩም፣ ከዚህች ቀን ጀምሬ እባርካችኋለሁ።</verse>
				<verse number="20">በወሩ በሀያ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ሁለተኛ ወደ ሐጌ እንዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="21">ለይሁዳ አለቃ ለዘሩባቤል ተናገር እንዲህም በል፦ ሰማያትንና ምድርን አናውጣለሁ፣</verse>
				<verse number="22">የመንግሥታትንም ዙፋን እገለብጣለሁ፥ የአሕዛብንም መንግሥታት ኃይል አጠፋለሁ፣ ሰረገሎችንና የሚቀመጡባቸውንም እገለብጣለሁ፣ ፈረሶችና ፈረሰኞቻቸውም እያንዳንዳቸው በወንድማቸው ሰይፍ ይወድቃሉ።</verse>
				<verse number="23">ባሪያዬ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል ሆይ፥ በዚያ ቀን እወስድሃለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እኔ መርጬሃለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እንደ ቀለበት ማተሚያ አደርግሃለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="38">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስምንተኛው ወር የእግዚአብሔር ቃል ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">እግዚአብሔር በአባቶቻችሁ ላይ እጅግ ተቈጥቶ ነበር።</verse>
				<verse number="3">ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ እኔ ተመለሱ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="4">የቀደሙት ነቢያት ለአባቶቻችሁ እንዲህ ብለው ሰብከዋል፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፣ እነርሱ ግን አልሰሙም፥ እኔንም አላደመጡም፣ እንደ እነርሱ አትሁኑ፥ ይላል እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="5">አባቶቻችሁ ወዴት ናቸው? ነቢያትስ ለዘላለም በሕይወት ይኖራሉን?</verse>
				<verse number="6">ለባሪያዎቼስ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? እነርሱም ተመልሰው፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ያደርግብን ዘንድ እንዳሰበ እንዲሁ አድርጎብናል አሉ።</verse>
				<verse number="7">በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት ሳባጥ በሚባል በአሥራ አንደኛው ወር በሀያ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="8">እነሆም፥ አንድ ሰው በመጋላ ፈረስ ተቀምጦ በሌሊት አየሁ፥ እርሱም በሸለቆው ውስጥ ባሉ በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆሞ ነበር፣ በስተ ኋላውም መጋላና ሐመር አንባላይም ፈረሶች ነበሩ።</verse>
				<verse number="9">እኔም፦ ጌታዬ ሆይ፥ እነዚህ ምንድር ናቸው? አልሁ። ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ፦ እነዚህ ምን እንደ ሆኑ አሳይሃለሁ አለኝ።</verse>
				<verse number="10">በባርሰነት ዛፎች መካከልም ቆሞ የነበረው ሰው፦ እነዚህ በምድር ላይ ይመላለሱ ዘንድ እግዚአብሔር የላካቸው ናቸው ብሎ መለሰ።</verse>
				<verse number="11">በባርሰነት ዛፎች መካከልም ቆሞ የነበረውን የእግዚአብሔርን መልአክ፦ በምድር ላይ ተመላለስን፥ እነሆም፥ ምድር ሁሉ ዝም ብላ ዐርፋ ተቀምጣለች ብለው መለሱለት።</verse>
				<verse number="12">የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ፦ አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ።</verse>
				<verse number="13">እግዚአብሔርም መልሶ ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው።</verse>
				<verse number="14">ስለዚህም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ፦ ስበክ እንዲህም በል፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ በታላቅ ቅንዓት በኢየሩሳሌምና በጽዮን ቀንቻለሁ።</verse>
				<verse number="15">እኔ ጥቂት ብቻ ተቈጥቼ ሳለሁ እነርሱ ክፋትን ስላገዙት፥ ባልተቸገሩት አሕዛብ ላይ እጅግ ተቈጥቻለሁ።</verse>
				<verse number="16">ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ኢየሩሳሌም በምሕረት ተመልሻለሁ፣ ቤቴ ይሠራባታል፣ በኢየሩሳሌምም ላይ ገመድ ይዘረጋበታል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="17">ደግሞም እንዲህ ስትል ስበክ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከተሞቼ ደግሞ በበጎ ነገር ይረካሉ፣ እግዚአብሔርም ደግሞ ጽዮንን ያጽናናል፥ ኢየሩሳሌምንም ደግሞ ይመርጣል።</verse>
				<verse number="18">ዓይኖቼንም አንሥቼ እነሆ፥ አራት ቀንዶች አየሁ።</verse>
				<verse number="19">ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረውን መልአክ፦ እነዚህ ምንድር ናቸው? አልሁት። እርሱም፦ እነዚህ ይሁዳንና እስራኤልን ኢየሩሳሌምንም የበተኑ ቀንዶች ናቸው ብሎ መለሰልኝ።</verse>
				<verse number="20">እግዚአብሔርም አራት ጠራቢዎች አሳየኝ።</verse>
				<verse number="21">እኔም፦ እነዚህ የመጡት ምን ሊሠሩ ነው? አልሁ። እርሱም፦ አንድ ሰው ራሱን እስከማያነሣ ድረስ እነዚህ ቀንዶች ይሁዳን የበተኑ ናቸው፣ እነዚህ ግን ሊያስፈራሩአቸው፥ የይሁዳንም አገር ይበትኑ ዘንድ ቀንዳቸውን ያነሡትን የአሕዛብን ቀንዶች ሊጥሉ መጥተዋል ብሎ ተናገረ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ዓይኖቼንም አነሣሁ፣ እነሆም፥ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ አንድ ሰውን አየሁ።</verse>
				<verse number="2">እኔም፦ አንተ ወዴት ትሄዳለህ? አልሁ። እርሱም፦ የኢየሩሳሌምን ወርድና ርዝመት ስንት መሆኑን ሰፍሬ አይ ዘንድ እሄዳለሁ አለኝ።</verse>
				<verse number="3">እነሆም፥ ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ወጣ፥ ሌላም መልአክ ሊገናኘው ወጣ፥ እንዲህም አለው፦</verse>
				<verse number="4">ሩጥ፥ ይህንም ጕልማሳ እንዲህ በለው፦ ኢየሩሳሌም በውስጥዋ ካሉት ሰዎችና እንስሶች ብዛት የተነሣ ቅጥር እንደሌላቸው መንደሮች ሆና ትኖራለች።</verse>
				<verse number="5">እኔ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ፥ በውስጥዋም ክብርን እሆናለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="6">እናንተ ሆይ፥ ከሰሜን ምድር ሽሹ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ እንደ አራቱ የሰማይ ነፋሳት በትኛችኋለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="7">አንቺ ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሪ ጽዮን ሆይ፥ ኰብልዪ።</verse>
				<verse number="8">የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ከክብሩ በኋላ ወደ በዘበዙአችሁ አሕዛብ ልኮኛል፣ የሚነካችሁ የዓይኑን ብሌን የሚነካ ነውና።</verse>
				<verse number="9">እነሆ፥ እጄን በላያቸው አወዛውዛለሁ፥ ተገዝተው ለነበሩት ብዝበዛ ይሆናሉ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።</verse>
				<verse number="10">የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እነሆ፥ መጥቼ በመካከልሽ እኖራለሁና ዘምሪ ደስም ይበልሽ፥ ይላል እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="11">በዚያም ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፥ ሕዝብም ይሆኑኛል፣ በመካከልሽም እኖራለሁ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ አንቺ እንደ ላከኝ ታውቂአለሽ።</verse>
				<verse number="12">እግዚአብሔርም ይሁዳን እድል ፈንታው አድርጎ በተቀደሰችው ምድር ይወርሰዋል፥ ኢየሩሳሌምንም ዳግመኛ ይመርጣል።</verse>
				<verse number="13">እግዚአብሔር ከተቀደሰ ማደሪያው ነቅቶአልና ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሆይ፥ በፊቱ ዝም በል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">እርሱም ታላቁን ካህን ኢያሱን በእግዚአብሔር መልአክ ፊት ቆሞ አሳየኝ፥ ሰይጣንም ይከስሰው ዘንድ በስተ ቀኙ ቆሞ ነበር።</verse>
				<verse number="2">እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦ ሰይጣን ሆይ፥ እግዚአብሔር ይገሥጽህ፣ ኢየሩሳሌምን የመረጠ እግዚአብሔር ይገሥጽህ፣ በውኑ ይህ ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ አይደለምን? አለው።</verse>
				<verse number="3">ኢያሱም እድፋም ልብስ ለብሶ በመልአኩ ፊት ቆሞ ነበር።</verse>
				<verse number="4">እርሱም መልሶ በፊቱ የቆሙትን፦ እድፋሙን ልብስ ከእርሱ ላይ አውልቁ አላቸው። እርሱንም፦ እነሆ፥ አበሳህን ከአንተ አርቄአለሁ፥ ጥሩ ልብስም አለብስሃለሁ አለው።</verse>
				<verse number="5">ደግሞ፦ ንጹሕ ጥምጥም በራስ ላይ አድርጉ አለ። እነርሱም በራሱ ላይ ንጹሕ ጥምጥም አደረጉ፥ ልብስንም አለበሱት፣ የእግዚአብሔርም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር።</verse>
				<verse number="6">የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያሱ እንዲህ ሲል አዳኘበት፦</verse>
				<verse number="7">የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገዴ ብትሄድ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፥ በቤቴ ላይ ትፈርዳለህ፥ አደባባዮቼንም ትጠብቃለህ፥ በዚህም ከቆሙት ከእነዚህ ጋር መግባትን እሰጣለሁ።</verse>
				<verse number="8">ታላቁ ካህን ኢያሱ ሆይ፥ ስማ፣ በፊትህም የሚቀመጡት ባልንጀሮች ለምልክት የሚሆኑ ሰዎች ናቸውና ይስሙ፣ እነሆ፥ እኔ ባሪያዬን ቍጥቋጥ አወጣለሁ።</verse>
				<verse number="9">በኢያሱ ፊት ያኖርሁት ድንጋይ እነሆ አለ፣ በአንዱ ድንጋይ ላይ ሰባት ዓይኖች አሉ፣ እነሆ፥ ቅርጹን እቀርጻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ የዚያችንም ምድር በደል በአንድ ቀን አስወግዳለሁ።</verse>
				<verse number="10">በዚያ ቀን፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እያንዳንዱ ከወይኑና ከበለሱ በታች ሆኖ ባልንጀራውን ይጠራል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ተመልሶ ከእንቅልፋ እንደሚነቃ ሰው አነቃኝ።</verse>
				<verse number="2">እርሱም፦ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦እነሆ፥ ሁለንተናው ወርቅ የሆነውን መቅረዝ አየሁ፣ የዘይትም ማሰሮ በራሱ ላይ ነበረ፥ ሰባትም መብራቶች ነበሩበት፣ በራሱም ላይ ለነበሩት መብራቶች ሰባት ቧንቧዎች ነበሩአቸው።</verse>
				<verse number="3">ሁለት የወይራ ዛፎች፥ አንዱ በማሰሮው በስተ ቀኝ አንዱም በስተ ግራው ሆነው፥ በአጠገቡ ነበሩ አልሁ።</verse>
				<verse number="4">ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረውም መልአክ መልሼ፦ ጌታዬ ሆይ፥ እነዚህ ምንድር ናቸው? አልሁት።</verse>
				<verse number="5">ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረውም መልአክ መልሶ፦ እነዚህ ምን እንደ ሆኑ አታውቅምን? አለኝ። እኔም፦ ጌታዬ ሆይ፥ አላውቅም አልሁ።</verse>
				<verse number="6">መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፦ በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="7">ታላቅ ተራራ ሆይ፥ አንተ ምንድር ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፣ ሰዎችም፦ ሞገስ፥ ሞገስ ይሁንለት ብለው እየጮኹ እርሱ መደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል ብሎ ተናገረኝ።</verse>
				<verse number="8">የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="9">የዘሩባቤል እጆች ይህን ቤት መሠረቱ፥ የእርሱም እጆች ይፈጽሙታል፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።</verse>
				<verse number="10">የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? እነዚህ ሰባቱ ደስ ብሎአቸው በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ያያሉ፣ እነዚህም በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የእግዚአብሔር ዓይኖች ናቸው።</verse>
				<verse number="11">እኔም መልሼ፦ በመቅረዙ በስተ ቀኝና በስተ ግራ ያሉ እነዚህ ሁለት የወይራ ዛፎች ምንድር ናቸው? አልሁት።</verse>
				<verse number="12">ሁለተኛም መልሼ፦ በሁለቱ የወርቅ ቧንቧዎች አጠገብ ሆነው የወርቁን ዘይት የሚያፈስሱ እነዚህ ሁለት የወይራ ቅርንጫፎች ምንድር ናቸው? አልሁት።</verse>
				<verse number="13">እርሱም መልሶ፦ እነዚህ ምን እንደ ሆኑ አታውቅምን? አለኝ። እኔም ፦ ጌታ ሆይ፥ አላውቅም አልሁት።</verse>
				<verse number="14">እርሱም፦ በምድር ሁሉ ጌታ አጠገብ የቆሙት ሁለቱ የተቀቡት እነዚህ ናቸው አለኝ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">ተመልሼም ዓይኖቼን አነሣሁ፥ እነሆም፥ አንድ በራሪ የመጽሐፍ ጥቅልል አየሁ።</verse>
				<verse number="2">እርሱም፦ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦ በራሪ የመጽሐፍ ጥቅልል አያለሁ፣ ርዝመቱ ሀያ ክንድ ወርዱም አሥር ክንድ ነው አልሁ።</verse>
				<verse number="3">እንዲህም አለኝ፦ ይህ በምድር ፊት ሁሉ ላይ የሚወጣው እርግማን ነው፣ የሚሰርቅ ሁሉ በእርሱ ላይ በዚህ በኩል እንደ ተጻፈው ሁሉ ይጠፋል፥ በሐሰት የሚምልም ሁሉ በእርሱ ላይ በዚያ በኩል እንደ ተጻፈው ሁሉ ይጠፋል።</verse>
				<verse number="4">እኔ አስወጣዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ወደ ሚሰርቀውም ቤት፥ በሐሰትም በስሜ ወደሚምለው ቤት ይገባል፣ በቤቱም ውስጥ ይኖራል፥ እርሱንም፥ እንጨቱንና ድንጋዩን፥ ይበላል።</verse>
				<verse number="5">ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ወጥቶ፦ ዓይኖችህን አንሣ፥ ይህችንም የምትወጣው ምን እንደ ሆነች እይ አለኝ።</verse>
				<verse number="6">እኔም፦ ምንድር ናት? አልሁ። እርሱም፦ ይህች የምትወጣው የኢፍ መስፈሪያ ናት አለኝ። ደግሞም፦ በምድር ሁሉ ላይ ያለ በደላቸው ይህ ነው አለ።</verse>
				<verse number="7">እነሆም፥ የእርሳሱን መክሊት አነሡት፣ እነሆም፥ በኢፍ መስፈሪያው ውስጥ አንዲት ሴት ተቀምጣ ነበር።</verse>
				<verse number="8">እርሱም፦ ይህች ክፋት ናት አለኝ፣ በኢፍ መስፈሪያው ውስጥ ጣላት፥ የእርሳሱንም ጠገራ በመስፈሪያ አፍ ላይ ጣለ።</verse>
				<verse number="9">ዓይኖቼንም አንሥቼ አየሁ፥ እነሆም፥ ሁለት ሴቶች ወጡ፥ ነፋስም በክንፎቻቸው ነበረ፣ ክንፎቻቸውም እንደ ሽመላ ክንፎች ነበሩ፣ የኢፍ መስፈሪያውንም በምድርና በሰማይ መካከል አነሡት።</verse>
				<verse number="10">ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረውን መልአክ፦ እነዚህ የኢፍ መስፈሪያውን ወዴት ይወስዱታል? አልሁት።</verse>
				<verse number="11">እርሱም፦ በሰናዖር ምድር ቤት ይሠሩለት ዘንድ ይወስዱታል፣ በተዘጋጀም ጊዜ በዚያ በስፍራው ይኖራል አለኝ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">ተመልሼም ዓይኖቼን አነሣሁ፥ እነሆም፥ አራት ሰረገሎች ከሁለት ተራራ መካከል ሲወጡ አየሁ፣ ተራሮቹም የናስ ተራሮች ነበሩ።</verse>
				<verse number="2">በፊተኛው ሰረገላ መጋላ ፈረሶች፥ በሁለተኛውም ሰረገላ ዱሪ ፈረሶች ነበሩ፥</verse>
				<verse number="3">በሦስተኛውም ሰረገላ አምባላይ ፈረሶች፥ በአራተኛውም ሰረገላ ቅጥልጣል ፈረሶች ነበሩ።</verse>
				<verse number="4">ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረውም መልአክ መልሼ፦ ጌታዬ ሆይ፥ እነዚህ ምንድር ናቸው? አልሁት።</verse>
				<verse number="5">መልአኩም መልሶ፦ እነዚህ በምድር ሁሉ ጌታ ፊት ከቆሙበት ስፍራ የሚወጡ አራቱ የሰማይ ነፋስት ናቸው።</verse>
				<verse number="6">ዱሪ ፈረሶች ያሉበት ወደ ሰሜን ይወጣል፣ አምባላዮቹም ከእነርሱ በኋላ ይወጣሉ፥ ቅጥልጣሎቹም ወደ ደቡብ ይወጣሉ አለኝ።</verse>
				<verse number="7">መጋላዎቹም ደግሞ ወጡ በምድርም ይመላለሱ ዘንድ ለመሄድ ይፈልጉ ነበር፣ እርሱም፦ ሂዱ፥ በምድር ላይ ተመላለሱ አለ። እነርሱም በምድር ላይ ተመላለሱ።</verse>
				<verse number="8">ጮኾም፦ እነሆ፥ ወደ ሰሜን ምድር የሚወጡት እነርሱ መንፈሴን በሰሜን ምድር ላይ አሳርፈዋል ብሎ ተናገረኝ።</verse>
				<verse number="9">የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="10">ከባቢሎን ከመጡት ምርኮኞች ከሔልዳይና ከጦብያ ከዮዳኤም ውሰድ፣ በዚያም ቀን መጥተህ ወደ ሶፎንያስ ልጅ ወደ ኢዮስያስ ቤት ግባ።</verse>
				<verse number="11">ብርንና ወርቅን ከእነርሱ ውሰድ፥ አክሊሎችንም ሥራ፣ በታላቁም ካህን በኢዮሴዴቅ ልጅ በኢያሱ ራስ ላይ ድፋቸው፥ እንዲህም በለው፦</verse>
				<verse number="12">የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ስሙ ቍጥቋጥ የሚባል ሰው በስፍራው ይበቅላል፥ የእግዚአብሔርንም መቅደስ ይሠራል።</verse>
				<verse number="13">እርሱ የእግዚአብሔርን መቅደስ ይሠራል፥ ክብርንም ይሸከማል፥ በዙፋኑም ላይ ተቀምጦ ይነግሣል፣ በዙፋኑም ላይ ካህን ይሆናል፥ የሰላምም ምክር በሁለቱ መካከል ይሆናል።</verse>
				<verse number="14">አክሊሎችም ለሔሌምና ለጦብያ ለዮዳኤም ለሶፎንያስም ልጅ ለሔን በእግዚአብሔር መቅደስ ውስጥ ለመታሰቢያ ይሆናሉ።</verse>
				<verse number="15">በሩቅም ያሉት መጥተው የእግዚአብሔርን መቅደስ ይሠራሉ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። የአምላካችሁንም የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቃችሁ ብትሰሙ ይህ ይሆናል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">በንጉሡም በዳርዮስ በአራተኛው ዓመት ካሴሉ በሚባል በዘጠነኛው ወር በአራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዘካርያስ መጣ።</verse>
				<verse number="2">የቤቴልም ሰዎች ሳራሳርንና ሬጌሜሌክን ሰዎቻቸውንም በእግዚአብሔር ፊት ይለምኑ ዘንድ፥</verse>
				<verse number="3">ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ቤት ካህናት ለነቢያትም፦ ባለፉት ዓመታት እንዳደረግሁት በአምስተኛው ወር መለየትና ማልቀስ ይገባኛልን? ብለው ይናገሩ ዘንድ ልኮአቸው ነበር።</verse>
				<verse number="4">የሠራዊትም ጌታ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="5">ለምድሩ ሕዝብ ሁሉ ለካህናትም እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ በዚህ በሰባው ዓመት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር በጾማችሁና ባለቀሳችሁ ጊዜ፥ በውኑ ለእኔ ጾም ጾማችሁልኝ?</verse>
				<verse number="6">በምትበሉበትና በምትጠጡበትስ ጊዜ፥ ለራሳችሁ የምትበሉና የምትጠጡ አይደላችሁምን?</verse>
				<verse number="7">ኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ያሉ ከተሞች ገና ሰዎች ባሉባቸው ጊዜ፥ በምቾትም ተቀምጠው ሳሉ፥ ደቡቡና ቈላውም ሰዎች ባሉባቸው ጊዜ፥ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት እጅ የተናገረውን ቃል መስማት አይገባችሁምን?</verse>
				<verse number="8">የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="9">የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ እውነተኛውን ፍርድ ፍረዱ፣ ቸርነትንና ምሕረትን ሁላችሁ ለወንድሞቻችሁ አድርጉ፣ መበለቲቱንና ደሀ አደጉን፥</verse>
				<verse number="10">መጻተኛውንና ችግረኛውን አትበድሉ፣ ከእናንተም ማንም በወንድሙ ላይ ክፉውን ነገር በልቡ አያስብ።</verse>
				<verse number="11">እነርሱ ግን ደንደሳቸውን አዞሩ እንጂ መስማትን እምቢ አሉ፣ እንዳይሰሙም ጆሮአቸውን አደነቈሩ።</verse>
				<verse number="12">የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት እጅ በመንፈሱ የላከውን ሕጉንና ቃሉን እንዳይሰሙ ልባቸውን እንደ አልማዝ አጠነከሩ፣ ስለዚህ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ቍጣ መጣ።</verse>
				<verse number="13">እኔ በጠራሁ ጊዜ እነርሱ እንዳልሰሙኝ፥ እንዲሁ እነርሱ በሚጠሩበት ጊዜ እኔ አልሰማም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣</verse>
				<verse number="14">ወደ ማያውቁአቸውም አሕዛብ ሁሉ በዐውሎ ነፋስ በተንኋቸው። እንዲሁ ከእነርሱ በኋላ ምድሪቱ ባድማ ሆናለች፥ የሚተላለፍባትና የሚመላለስባትም አልነበረም፣ ያማረችውንም ምድር ባድማ አደረጉአት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">የሠራዊትም ጌታ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="2">የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለ ጽዮን ታላቅ ቅንዓት ቀንቻለሁ፥ በታላቅም ቍጣ ስለ እርስዋ ቀንቻለሁ።</verse>
				<verse number="3">እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ጽዮን ተመልሻለሁ፥ በኢየሩሳሌምም መካከል እኖራለሁ፣ ኢየሩሳሌምም የእውነት ከተማ ትባላለች፣ የሠራዊትም ጌታ የእግዚአብሔር ተራራ የተቀደሰ ተራራ ይባላል።</verse>
				<verse number="4">የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዳግመኛ ሽማግሌዎችና ባልቴቶች በኢየሩሳሌም አደባባይ ይቀመጣሉ፣ ሰውም ሁሉ ከዕድሜው ብዛት የተነሣ ምርኩዝ በእጁ ይይዛል።</verse>
				<verse number="5">የከተማይቱም አደባባዮች በእነዚያ በሚጫወቱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ይሞላሉ።</verse>
				<verse number="6">የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህ ወራት በዚህ ሕዝብ ቅሬታ ዓይን ዘንድ ድንቅ ቢሆን፥ በውኑ በእኔ ዓይን ዘንድ ደግሞ ድንቅ ይሆናልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="7">የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሕዝቤን ከምሥራቅ ምድርና ከምዕራብ ምድር አድነዋለሁ፣</verse>
				<verse number="8">አመጣቸዋለሁም፥ በኢየሩሳሌምም ውስጥ ይኖራሉ፣ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል፥ እኔም በእውነትና በጽድቅ አምላክ እሆናቸዋለሁ።</verse>
				<verse number="9">የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መቅደሱ ይሠራ ዘንድ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቤት ከተመሠረተበት ቀን ጀምሮ ከነቢያት አፍ ይህን ቃል በዚህ ዘመን የሰማችሁ እናንተ ሆይ፥ እጃችሁን አበርቱ።</verse>
				<verse number="10">ከዚያ ወራት አስቀድሞ ለሰውና ለእንስሳ ዋጋ አልነበረምና፣ እኔም ሰውን ሁሉ በወንድሙ ላይ አስነሥቼ ነበርና ከአስጨናቂው የተነሣ ለሚገባውና ለሚወጣው ሰላም አልነበረም።</verse>
				<verse number="11">አሁን ግን እንደ ቀደመው ዘመን በዚህ ሕዝብ ቅሬታ ላይ አልሆንም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="12">ነገር ግን ሰላምን እዘራለሁ፣ ወይኑ ፍሬውን ይሰጣል፥ ምድርም አዝመራዋን ታወጣለች፥ ሰማያትም ጠላቸውን ይሰጣሉ፣ ለዚህም ሕዝብ ቅሬታ ይህን ነገር ሁሉ አወርሳለሁ።</verse>
				<verse number="13">የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በአሕዛብ ዘንድ እርግማን እንደ ነበራችሁ፥ እንዲሁ አድናችኋለሁ፥ በረከትም ትሆናላችሁ፣ አትፍሩ፥ እጃችሁንም አበርቱ።</verse>
				<verse number="14">የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ አባቶቻችሁ እጅግ ባስቈጡኝ ጊዜ ክፉ ለማድረግ እንዳሰብሁ፥ እንዳልተጸጸትሁም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥</verse>
				<verse number="15">እንዲሁ ዳግመኛ ለኢየሩሳሌምና ለይሁዳ ቤት በዚህ ወራት በጎነትን አደርግ ዘንድ አስቤአለሁ፣ አትፍሩ።</verse>
				<verse number="16">የምትሠሩት ነገር ይህ ነው፣ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ፣ በበር አደባባያችሁም የእውነትንና የሰላምን ፍርድ ፍረዱ፣</verse>
				<verse number="17">ሁላችሁም በባልንጀራችሁ ላይ ክፉን ነገር በልባችሁ አታስቡ፣ የሐሰትንም መሐላ አትውደዱ፣ ይህን ነገር ሁሉ እጠላለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="18">የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦</verse>
				<verse number="19">የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሐሤትም በዓላት ይሆናል፣ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ።</verse>
				<verse number="20">የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በብዙ ከተሞች የሚቀመጡ አሕዛብ ገና ይመጣሉ፣</verse>
				<verse number="21">በአንዲትም ከተማ የሚኖሩ ሰዎች፦ እግዚአብሔርን እንለምን ዘንድ፥ የሠራዊትንም ጌታ እግዚአብሔርን እንፈልግ ዘንድ ኑ እንሂድ፣ እኔም እሄዳለሁ እያሉ ወደ ሌላ ከተማ ይሄዳሉ።</verse>
				<verse number="22">ብዙ ወገኖችና ኃይለኞች አሕዛብ በኢየሩሳሌም የሠራዊትን ጌታ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ፥ እግዚአብሔርንም ይለምኑ ዘንድ ይመጣሉ።</verse>
				<verse number="23">የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ዘመን ከአሕዛብ ቋንቋ ሁሉ አሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው፦ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና ከእናንተ ጋር እንሂድ ይላሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">የእግዚአብሔር ቃል ሸክም በሴድራክ ምድር ላይ ነው፥ በደማስቆም ላይ ያርፋል፣ የእግዚአብሔር ዓይን ወደ ሰውና ወደ እስራኤል ነገድ ሁሉ ዘንድ ነው፣</verse>
				<verse number="2">ደግሞም በዳርቻዋ ባለችው በሐማት ላይ፥ እጅግ ጠቢበኞች በሆኑ በጢሮስና በሲዶና ላይ ነው።</verse>
				<verse number="3">ጢሮስም ምሽግን ለራስዋ ሠርታለች፥ ብሩንም እንደ አፈር ጥሩውንም ወርቅ እንደ መንገድ ጭቃ አከማችታለች።</verse>
				<verse number="4">እነሆ፥ ጌታ ይገፍፋታል፥ በባሕርም ላይ ያለውን ብርታትዋን ይመታል፣ እርስዋም በእሳት ትበላለች።</verse>
				<verse number="5">አስቀሎና አይታ ትፈራለች፣ ጋዛ ደግሞ አይታ እጅግ ትታመማለች፣ አቃሮንም እንዲሁ፥ ተስፋዋ ይቈረጣልና፣ ንጉሡም ከጋዛ ይጠፋል፥ በአስቀሎናም የሚቀመጥ አይገኝም።</verse>
				<verse number="6">የተደባለቀ ወገን በአዛጦን ይቀመጣል፥ የፍልስጥኤማውያንንም ትዕቢት አጠፋለሁ።</verse>
				<verse number="7">ደሙንም ከአፉ ውስጥ ርኩሱንም ነገር ከጥርሱ መካከል አስወግዳለሁ፣ እርሱም ደግሞ ለአምላካችን ቅሬታ ይሆናል፣ በይሁዳም እንደ አለቃ ይሆናል፥ አቃሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል።</verse>
				<verse number="8">እኔም ማንም እንዳይሄድና እንዳይመለስ እንደ ጠባቂ ጦር ሆኖ በቤቴ ዙሪያ ሰፈር አደርጋለሁ፣ አሁንም በዓይኔ አይቻለሁና ከዚህ በኋላ አስጨናቂ አያልፍባቸውም።</verse>
				<verse number="9">አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፣ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፣ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፣ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫንይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።</verse>
				<verse number="10">ሰረገላውንም ከኤፍሬም ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም አጠፋለሁ የሰልፉም ቀስት ይሰበራል፥ ለአሕዛብም ሰላምን ይናገራል፣ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕር፥ ከወንዙም እስከ ምድር ዳርቻ ድርስ ይሆናል።</verse>
				<verse number="11">ለአንቺም ደግሞ ስለ ቃል ኪዳንሽ ደም፥ እስሮችሽን ውኃ ከሌለበት ጕድጓድ አውጥቻለሁ።</verse>
				<verse number="12">እናንተ በተስፋ የምትኖሩ እስሮች ሆይ፥ ወደ ጽኑ አምባ ተመለሱ፣ ሁለት እጥፍ አድርጌ እንድመልስልሽ ዛሬ እነግርሻለሁ።</verse>
				<verse number="13">ይሁዳን ለእኔ ገትሬአለሁ፣ ቀስቱን በኤፍሬም ሞልቼአለሁ፣ ጽዮን ሆይ፥ ልጆችሽን በግሪክ ልጆች ላይ አስነሣለሁ፥ አንቺንም እንደ ኃያል ሰው ሰይፍ አደርግሻለሁ።</verse>
				<verse number="14">እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ይገለጣል፥ ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይወጣል፣ ጌታ እግዚአብሔርም መለከትን ይነፋል፥ በደቡብም ዐውሎ ነፋስ ይሄዳል።</verse>
				<verse number="15">የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይጠብቃቸዋል፣ እነርሱም ይበሉአቸዋል፥ የወንጭፉንም ድንጋዮች ይረግጣሉ፣ እንደ ወይን ጠጅም ይጠጡአቸዋል፥ እንደ ጥዋዎችም እንደ መሠዊያም ማዕዘኖች የተሞሉ ይሆናሉ።</verse>
				<verse number="16">በዚያም ቀን አምላካቸው እግዚአብሔር እንደ ሕዝቡ መንጋ ያድናቸዋል፣ እነርሱም ለአክሊል እንደሚሆኑ እንደ ከበሩ ድንጋዮች ይሆናሉ፥ በምድሩም ላይ ይብለጨለጫሉ።</verse>
				<verse number="17">በጎነቱ እንዴት ታላቅ ነው! ውበቱስ እንዴት ታላቅ ነው! እህል ጐበዛዝቱን፥ ጉሽ ጠጅም ቈነጃጅቱን ያለመልማል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">በኋለኛው ዝናብ ጊዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ ዝናቡን ለምኑ፣ እግዚአብሔር መብረቅ ያደርጋል፣ እርሱም የበልግ ዝናብን ለእያንዳንዱም በሜዳ ውስጥ ሣርን ይሰጣል።</verse>
				<verse number="2">ተራፊም ከንቱነትን ተናግረዋልና፥ ምዋርተኞችም ውሸትን አይተዋልና፣ ሕልምንም የሚያዩ በሐሰት ተናግረዋል፥ በከንቱም ያጽናናሉ፣ እረኛም የላቸውምና እንደ በጎች ተቅበዝብዘዋል ተጨንቀውማል።</verse>
				<verse number="3">ቍጣዬ በእረኞች ላይ ነድዶአል፥ አውራ ፍየሎችንም እቀጣለሁ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም የይሁዳን ቤት መንጋውን ጐብኝቶአል፥ በሰልፍም ውስጥ እንዳለ እንደ ክብሩ ፈረስ ያደርጋቸዋል።</verse>
				<verse number="4">ከእርሱ ዘንድ የማዕዘኑ ድንጋይ፥ ከእርሱም ዘንድ ችንካሩ፥ ከእርሱም ዘንድ የሰልፍ ቀስት፥ ከእርሱም ዘንድ አስገባሪው ሁሉ በአንድ ላይ ይመጣሉ።</verse>
				<verse number="5">በሰልፍም ጊዜ ጠላቶቻቸውን በመንገድ ጭቃ ውስጥ እንደሚረግጡ ኃያላን ይሆናሉ፣ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ነውና ይዋጋሉ፥ ፈረሰኞችም ያፍራሉ።</verse>
				<verse number="6">ወድጃቸዋለሁና የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፥ የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ፣ አደላድላቸዋለሁም፣ እመልሳቸዋለሁ፣ እኔም አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝና፥ እኔም እሰማቸዋለሁና እንዳልጣልኋቸው ይሆናሉ።</verse>
				<verse number="7">የኤፍሬምም ሰዎች እንደ ኃያላን ይሆናሉ፥ ልባቸውም የወይን ጠጅ እንደ ጠጣ ሰው ደስ ይለዋል፣ ልጆቻቸውም አይተው ደስ ይላቸዋል፥ ልባቸውም በእግዚአብሔር ሐሤት ያደርጋል።</verse>
				<verse number="8">ተቤዥቼአቸዋለሁና በፉጨት ጠርቼ እሰበስባቸዋለሁ፣ ቀድሞም በዝተው እንደ ነበሩ ይበዛሉ።</verse>
				<verse number="9">በአሕዛብም መካከል ብዘራቸው እንኳ በሩቅ አገር ሳሉ ያስቡኛል፥ ከልጆቻቸውም ጋር በሕይወት ይኖራሉ፥ ይመለሱማል።</verse>
				<verse number="10">ከግብጽም ምድር እመልሳቸዋለሁ፥ ከአሦርም እሰበስባቸዋለሁ፣ ወደ ገለዓድና ወደ ሊባኖስ ምድር አመጣቸዋለሁ፥ የሚበቃም ቦታ አይገኝላቸውም።</verse>
				<verse number="11">እርሱም በጭንቅ ባሕር ያልፋል፥ የባሕርንም ሞገድ ይመታል፥ የወንዙም ጥልቅ ሁሉ ይደርቃል፣ የአሦርም ትዕቢት ይዋረዳል፥ የግብጽም በትረ መንግሥት ይርቃል።</verse>
				<verse number="12">በአምላካቸው በእግዚአብሔር አበረታቸዋለሁ፥ በስሙም ይመካሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">ሊባኖስ ሆይ፥ ደጆችህን ክፈት፥ እሳትም ዝግባዎችህን ትብላ።</verse>
				<verse number="2">የጥድ ዛፍ ሆይ፥ ዝግባ ወድቆአልና፥ ከበርቴዎችም ጠፍተዋልና ዋይ በል፣ እናንተም የባሳን ዛፎች ሆይ፥ ጽኑው ጫካ ተቈርጦአልና ዋይ በሉ።</verse>
				<verse number="3">የእረኞች ክብር ተዋርዶአልና የዋይታቸው ድምፅ ተሰምቶአል፣ የዮርዳኖስ ትዕቢት ተዋርዶአልና የአንበሶች ግሣት ድምፅ ተሰምቶአል።</verse>
				<verse number="4">አምላኬ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎአል፦ ለእርድ የሚሆኑትን በጎች ጠብቅ።</verse>
				<verse number="5">የገዙአቸው ያርዱአቸዋል፥ ራሳቸውንም እንደ በደለኞች አድርገው አይቈጥሩም፣ የሸጡአቸውም፦ ባለ ጠጋ ሆነዋልና እግዚአብሔር ይመስገን ይላሉ፣ እረኞቻቸውም አይራሩላቸውም።</verse>
				<verse number="6">ከእንግዲህ ወዲህ በምድር ላይ ለሚኖሩ አልራራም፥ ይላል እግዚአብሔር፣ እነሆም፥ ሰውን ሁሉ በባልንጀራውና በንጉሡ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፣ ምድሪቱም ይመታሉ፥ ከእጃቸውም አላድናቸውም።</verse>
				<verse number="7">እኔም ለእርድ የሚሆኑትን በጎች፥ የመንጋውን ችግረኞች ጠበቅሁ። ሁለት በትሮችንም ወሰድሁ፣ የአንዲቱን ስም ውበት የሁለተኛይቱንም ስም ማሰሪያ ብዬ ጠራሁ፣ መንጋውንም ጠበቅሁ።</verse>
				<verse number="8">በአንድ ወርም ሦስቱን እረኞች አጠፋሁ፣ ነፍሴም ተሰቀቀቻቸው፥ ነፍሳቸውም ደግሞ እኔን ጠላች።</verse>
				<verse number="9">እኔም፦ እናንተን አልጠብቅም፣ የሚሞተው ይሙት፥ የሚጠፋውም ይጥፋ፣ የቀረውም እያንዳንዱ የባልንጀራውን ሥጋ ይብላ አልሁ።</verse>
				<verse number="10">እኔም ከሕዝቦች ሁሉ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን አፈርስ ዘንድ ውበት የተባለችውን በትሬን ወስጄ ቈረጥሁ።</verse>
				<verse number="11">በዚያም ቀን ተሰበረች፣ እንዲሁም እኔን የተመለከቱ የመንጋው ችግረኞች የእግዚአብሔር ቃል እንደ ነበረ አወቁ።</verse>
				<verse number="12">እኔም፦ ደስ ብሎአችሁ እንደ ሆነ ዋጋዬን ስጡኝ፣ ያለዚያ ግን ተውት አልሁ። እነርሱም ለዋጋዬ ሠላሳ ብር መዘኑ።</verse>
				<verse number="13">እግዚአብሔርም፦ የተስማሙበትን የከበረውን ዋጋዬን በግምጃ ቤቱ ውስጥ አኑረው አለኝ። እኔም ሠላሳውን ብር ወስጄ በእግዚአብሔር ቤት ባለው በግምጃ ቤቱ ውስጥ አኖርሁት።</verse>
				<verse number="14">በይሁዳና በእስራኤል መካከል ያለውንም ወንድማማችነት እሰብር ዘንድ ማሰሪያ የተባለቸውን ሁለተኛይቱን በትሬን ቈረጥሁ።</verse>
				<verse number="15">እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ዳግመኛም የሰነፍን እረኛ ዕቃ ውሰድ።</verse>
				<verse number="16">እነሆ፥ በአገሩ ውስጥ እረኛ አስነሣለሁ፣ እርሱም የጠፋውን አያስብም፥ የባዘነውን አይፈልግም፥ የተሰበረውን አይጠግንም፣ የዳነውንም አይቀልብም፥ ነገር ግን የሰባውን ሥጋ ይበላል፥ ሰኰናውንም ይቀለጣጥማል።</verse>
				<verse number="17">መንጋውን ለሚተው ለምናምንቴ እረኛ ወዮለት! ሰይፍ በክንዱና በቀኝ ዓይኑ ላይ ይሆናል፣ ክንዱም አጥብቃ ትደርቃለች፥ ቀኝ ዓይኑም ፈጽማ ትጨልማለች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">ስለ እስራኤል የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው። ሰማያትን የዘረጋ፥ ምድርንም የመሠረተ፥ የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="2">እነሆ፥ ኢየሩሳሌምን በዙሪያዋ ላሉት ለአሕዛብ ሁሉ የመንገድገድ ዋንጫ አደርጋታለሁ፣ ደግሞም ኢየሩሳሌም ስትከበብ በይሁዳ ላይ እንዲሁ ይሆናል።</verse>
				<verse number="3">በዚያም ቀን ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ፣ የሚሸከሙአት ሁሉ እጅግ ይቈስላሉ፣ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በላይዋ ላይ ይከማቻሉ።</verse>
				<verse number="4">በዚያ ቀን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ፈረስን ሁሉ በድንጋጤ፥ ተቀማጭንም በእብድነት እመታለሁ፣ ዓይኖቼንም በይሁዳ ላይ እከፍታለሁ፥ የአሕዛብንም ፈረሶች ሁሉ በዕውርነት እመታለሁ።</verse>
				<verse number="5">የይሁዳም አለቆች በልባቸው፦ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ በአምላካቸው በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ብርታት አለ ይላሉ።</verse>
				<verse number="6">በዚያ ቀን የይሁዳን አለቆች በእንጨት መካከል እንዳለ ትንታግ፥ በነዶችም መካከል እንዳለ እንደ ፋና ነበልባል አደርጋቸዋለሁ፣ በቀኝና በግራ በዙሪያ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይበላሉ፣ ከዚያም ወዲያ ኢየሩሳሌም በስፍራዋ በኢየሩሳሌም ትኖራለች።</verse>
				<verse number="7">እግዚአብሔርም የዳዊት ቤት ክብርና የኢየሩሳሌም ሰዎች ክብር በይሁዳ ክብር ላይ እንዳይታበይ የይሁዳን ድንኳኖች አስቀድሞ ያድናል።</verse>
				<verse number="8">በዚያ ቀን እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት ይመክትላቸዋል፣ በዚያም ቀን ከእነርሱ መካከል ደካማው እንደ ዳዊት ይሆናል፣ የዳዊትም ቤት በፊታቸው እንደ እግዚአብሔር መልአክ እንደ አምላክ ይሆናል።</verse>
				<verse number="9">በዚያም ቀን በኢየሩሳሌም ላይ የሚመጡትን አሕዛብ ሁሉ ለማጥፋት እጋደላለሁ።</verse>
				<verse number="10">በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፣ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።</verse>
				<verse number="11">በዚያ ቀን በመጊዶን ሜዳ እንደ ነበረው እንደ ሐዳድሪሞን ልቅሶ ታላቅ ልቅሶ በኢየሩሳሌም ይሆናል።</verse>
				<verse number="12">ምድሪቱም ታለቅሳለች፣ እያንዳንዱ ወገን ለብቻው፥ የዳዊት ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ የናታን ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣</verse>
				<verse number="13">የሌዊ ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ የሰሜኢ ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣</verse>
				<verse number="14">የቀሩት ወገኖች ሁሉ እያንዳንዱ ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው ያለቅሳሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">በዚያ ቀን ለዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ከኃጢአትና ከርኵሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።</verse>
				<verse number="2">በዚያ ቀን፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ የጣዖታትን ስም ከምድር አጠፋለሁ፥ ከዚያም በኋላ አይታሰቡም፣ ደግሞም ሐሰተኞችን ነቢያትና ርኩስ መንፈስን ከምድር ላይ አስወግዳለሁ።</verse>
				<verse number="3">ማንም ደግሞ ትንቢት ቢናገር የወለዱት አባቱና እናቱ፦ አንተ በእግዚአብሔር ስም ሐሰትን ተናግረሃልና በሕይወት አትኖርም ይሉታል፣ ትንቢትንም ሲናገር የወለዱት አባቱና እናቱ ይወጉታል።</verse>
				<verse number="4">በዚያም ቀን ነቢያቱ ሁሉ ትንቢትን ሲናገሩ እያንዳንዱ ስለ ራእዩ ያፍራል፣ ያታልሉም ዘንድ የማቅ ልብስ አይለብሱም።</verse>
				<verse number="5">እርሱ ግን፦ ከታናሽነቴ ጀምሮ ባሪያ ሆኜ ነበርሁና ገበሬ ሰው ነኝ እንጂ ነቢይ አይደለሁም ይላል።</verse>
				<verse number="6">ሰውም፦ ይህ በእጅህ መካከል ያለ ቁስል ምንድር ነው? ይለዋል። እርሱም፦ በወዳጆቼ ቤት የቈሰልሁት ቍስል ነው ይላል።</verse>
				<verse number="7">ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እረኛውን ምታ፥ በጎቹም ይበተናሉ፣ እጄንም በታናናሾች ላይ እመልሳለሁ።</verse>
				<verse number="8">በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ክፍል ተቈርጠው ይሞታሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ ሦስተኛውም ክፍል በእርስዋ ውስጥ ይቀራል።</verse>
				<verse number="9">ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል፥ ብዝበዛሽንም በውስጥሽ ይካፈላሉ።</verse>
				<verse number="2">አሕዛብንም ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ ለሰልፍ እሰበስባለሁ፣ ከተማይቱም ትያዛለች፥ ቤቶችም ይበዘበዛሉ፥ ሴቶችም ይነወራሉ፣ የከተማይቱም እኵሌታ ለምርኮ ይወጣል፥ የቀረው ሕዝብ ግን ከከተማ አይጠፋም።</verse>
				<verse number="3">እግዚአብሔርም ይወጣል፥ በሰልፍም ቀን እንደ ተዋጋ ከእነዚያ አሕዛብ ጋር ይዋጋል።</verse>
				<verse number="4">በዚያም ቀን እግሮቹ በኢየሩሳሌም ትይዩ በምሥራቅ በኩል ባለው በደብረ ዘይት ላይ ይቆማሉ፣ ደብረ ዘይትም በመካከል ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ይሰነጠቃል፥ እጅግም ታላቅ ሸለቆ ይሆናል፣ የተራራውም እኵሌታ ወደ ሰሜን፥ እኵሌታውም ወደ ደቡብ ይርቃል።</verse>
				<verse number="5">የተራሮችም ሸለቆ እስከ አጸል ይደርሳልና በተራሮች ሸለቆ ትሸሻላችሁ፣ በይሁዳም ንጉሥ በዖዝያን ዘመን ከሆነው ከምድር መናወጥ ፊት እንደ ሸሻችሁ ትሸሻላችሁ፣ አምላኬ እግዚአብሔርም ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ይመጣል።</verse>
				<verse number="6">በዚያም ቀን በረዶና ውርጭ እንጂ ብርሃን አይሆንም።</verse>
				<verse number="7">አንድ ቀንም ይሆናል፥ እርሱም በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ይሆናል፣ ቀንም አይሆንም፥ ሌሊትም አይሆንም፣ ሲመሽም ብርሃን ይሆናል።</verse>
				<verse number="8">በዚያም ቀን የሕይወት ውኃ ከኢየሩሳሌም ይወጣል፣ እኵሌታው ወደ ምሥራቁ ባሕር፥ እኵሌታውም ወደ ምዕራቡ ባሕር ይሄዳል፣ ይህ በበጋና በክረምት ይሆናል።</verse>
				<verse number="9">እግዚአብሔርም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፣ በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል።</verse>
				<verse number="10">ምድር ሁሉ ከጌባ ጀምሮ በኢየሩሳሌምም ደቡብ በኩል እስካለችው እስከ ሬሞን ድረስ ተለውጣ እንደ ዓረባ ትሆናለች፣ እርስዋም ከፍ ከፍ ትላለች፥ ከብንያምም በር ጀምሮ እስከ ፊተኛው በር ስፍራ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ፥ ከሐናንኤልም ግንብ ጀምሮ እስከ ንጉሡ መጥመቂያ ድረስ በስፍራዋ ትኖራለች።</verse>
				<verse number="11">ሰዎችም ይኖሩባታል፥ ከዚያም ወዲያ እርግማን አይሆንም፣ ኢየሩሳሌምም ተዘልላ ትኖራለች።</verse>
				<verse number="12">እግዚአብሔርም ከኢየሩሳሌም ጋር የተዋጉትን አሕዛብ ሁሉ የሚቀሥፍበት ቸነፈር ይህ ነው፣ በእግራቸው ሲቆሙ ሥጋቸው ይበሰብሳል፥ ዓይኖቻቸውም በዓይነስባቸው ውስጥ ይበሰብሳሉ፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል።</verse>
				<verse number="13">በዚያም ቀን ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ሽብር በእነርሱ ላይ ይሆናል፣ እያንዳንዱም የባልንጀራውን እጅ ይይዛል፥ እጁም በባልንጀራው እጅ ላይ ይነሣል።</verse>
				<verse number="14">ይሁዳም ደግሞ በኢየሩሳሌም ውስጥ ሆኖ ይዋጋል፣ በዙሪያም ያሉት የአሕዛብ ሁሉ ሀብት እጅግ ብዙ ወርቅና ብር ልብስም ይሰበሰባል።</verse>
				<verse number="15">በፈረስና በበቅሎ፥ በግመልና በአህያ፥ በዚያም ሰፈር ባለ እንስሳ ሁሉ ላይ የሆነ ቸነፈር እንደዚያ ያለ ቸነፈር ይሆናል።</verse>
				<verse number="16">በኢየሩሳሌም ላይ ከመጡት ከአሕዛብ ሁሉ የቀሩት ሁሉ ለንጉሡ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ዘንድ፥ የዳስ በዓልንም ያከብሩ ዘንድ በየዓመቱ ይወጣሉ።</verse>
				<verse number="17">ከምድርም ወገኖች ሁሉ ለንጉሡ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ለማይወጡ ለእነርሱ ዝናብ አይዘንብላቸውም።</verse>
				<verse number="18">የግብጽም ወገን ባይወጣ ወደዚያም ባይመጣ፥ እግዚአብሔር የዳስ በዓልን ያከብሩ ዘንድ የማይወጡትን አሕዛብ የሚቀሥፍበት ቸነፈር በእርሱ ላይ ይሆናል።</verse>
				<verse number="19">የግብጽ ቅጣት፥ የዳስ በዓልንም ያከብሩ ዘንድ የማይወጡት የአሕዛብ ሁሉ ቅጣት እንደዚህ ይሆናል።</verse>
				<verse number="20">በዚያ ቀን በፈረሶች ሻኵራ ላይ፦ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ተብሎ ይጻፋል፣ በእግዚአብሔርም ቤት ያሉ ምንቸቶች በመሠዊያው ፊት እንዳሉ ዳካዎች ይሆናሉ።</verse>
				<verse number="21">በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ምንቸቶችም ሁሉ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ይሆናሉ፣ የሚሠውትም ሰዎች ሁሉ ይመጣሉ ከእነዚያም ወስደው ይቀቅሉባቸዋል፣ በዚያም ቀን በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቤት ከነዓናዊው ከእንግዲህ ወዲያ አይገኝም።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="39">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በሚልክያስ እጅ ለእስራኤል የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው።</verse>
				<verse number="2">ወድጃችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ እናንተ ግን፦ በምን ወደድኸን? ብላችኋል። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል እግዚአብሔር ያዕቆብንም ወደድሁ፥ ዔሳውንም ጠላሁ።</verse>
				<verse number="3">ተራሮቹንም በረሃ አደረግኋቸው፥ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮች አሳልፌ ሰጠኋቸው።</verse>
				<verse number="4">ኤዶምያስ፦ እኛ ፈርሰናል፥ ነገር ግን የፈረሰውን መልሰን እንሠራለን ቢል፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነርሱ ይሠራሉ፥ እኔ ግን አፈርሳለሁ፣ በሰዎችም ዘንድ፦ የበደል ዳርቻና እግዚአብሔር ለዘላለም የተቈጣው ሕዝብ ይባላል።</verse>
				<verse number="5">ዓይኖቻችሁም ያያሉ፥ እናንተም፦ እግዚአብሔር ከእስራኤል ዳርቻ ወዲያ ታላቅ ይሁን ትላላችሁ።</verse>
				<verse number="6">እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፣ እኔስ አባት ከሆንሁ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተም፦ ስምህን ያቃለልን በምንድር ነው? ብላችኋል።</verse>
				<verse number="7">በመሠዊያዬ ላይ ርኩስ እንጀራ ታቀርባላችሁ። እናንተም፦ ያረከስንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። የእግዚአብሔር ገበታ የተነቀፈ ነው በማለታችሁ ነው።</verse>
				<verse number="8">ዕውር መሥዋዕትንም ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? አንካሳውንና የታመመውን ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? ያንን ለአለቃህ አቅርብ፣ በውኑ በአንተ ደስ ይለዋልን? ወይስ ፊትህን ይቀበላልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="9">አሁንም ጸጋን ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔርን ለምኑ፣ ይህ ከእጃችሁ የተሰጠ ሲሆን ከቶ ፊታችሁን ይቀበላልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="10">በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ ዘንድ ደጅ የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥ ቍርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="11">ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፣ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፣ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="12">እናንተ ግን፦ የእግዚአብሔር ገበታ ርኩስ ነው፣ ፍሬውና መብሉም የተናቀ ነው በማለታችሁ አስነቀፋችሁት።</verse>
				<verse number="13">እናንተ፦ እነሆ፥ ይህ ድካም ነው ብላችሁ ጢቅ አላችሁበት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በቅሚያ የያዛችሁትንም አንካሳውንም የታመመውንም አቅርባችኋል፣ እንዲሁ ቍርባንን ታመጣላችሁ፣ በውኑ ከእጃችሁ ይህን ልቀበለውን? ይላል እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="14">እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ስሜም በአሕዛብ ዘንድ የተፈራ ነውና በመንጋው ውስጥ ተባት እያለው ለጌታ ተስሎ ነውረኛውን የሚሠዋ ሸንጋይ ሰው ርጉም ይሁን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">አሁንም እናንተ ካህናት ሆይ፥ ይህ ትእዛዝ ለእናንተ ነው።</verse>
				<verse number="2">ለስሜ ክብር ትሰጡ ዘንድ ባትሰሙ፥ በልባችሁም ባታደርጉት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እርግማን እሰድዳባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማታለሁ፣ አሁንም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና እኔ ረግሜአታለሁ።</verse>
				<verse number="3">እነሆ፥ ክንዳችሁን እገሥጻለሁ፥ የመሥዋዕታችሁንም ፋንድያ በፊታችሁ ላይ እበትናለሁ፣ ከእርሱም ጋር በአንድነት ትወሰዳላችሁ።</verse>
				<verse number="4">ቃል ኪዳኔ ከሌዊ ጋር ይሆን ዘንድ ይህን ትእዛዝ እንደ ሰደድሁላችሁ ታውቃላችሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="5">ቃል ኪዳኔ ከእርሱ ጋር የሕይወትና የሰላም ቃል ኪዳን ነበረ፣ ይፈራ ዘንድም እነርሱን ሰጠሁት፣ እርሱም ፈራኝ፥ ከስሜም የተነሣ ደነገጠ።</verse>
				<verse number="6">የእውነት ሕግ በአፉ ውስጥ ነበረች፥ በከንፈሩም ውስጥ በደል አልተገኘበትም፣ ከእኔም ጋር በሰላምና በቅንነት ሄደ፥ ብዙ ሰዎችንም ከኃጢአት መለሰ።</verse>
				<verse number="7">ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል፥ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል።</verse>
				<verse number="8">እናንተ ግን ከመንገዱ ፈቀቅ ብላችኋል፣ በሕግም ብዙ ሰዎችን አሰናክላችኋል፣ የሌዊንም ቃል ኪዳን አስነውራችኋል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="9">ስለዚህ መንገዴን እንዳልጠበቃችሁ፥ በሕግም ለሰው ፊት እንዳዳላችሁ መጠን፥ እኔ ደግሞ በሕዝብ ሁሉ ፊት የተናቃችሁና የተዋረዳችሁ አድርጌአችኋለሁ።</verse>
				<verse number="10">ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን? የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማስነቀፍ እኛ እያንዳዳችን ወንድማችንን ስለ ምን አታለልን?</verse>
				<verse number="11">እግዚአብሔር የወደደውን መቅደስ ይሁዳ አርክሶአልና፥ የእንግዳውንም አምላክ ልጅ ሚስት አድርጎ አግብቶአልና ይሁዳ አታልሎአል፥ በእስራኤልና በኢየሩሳሌም ውስጥ ርኵሰት ተሠርቶአል።</verse>
				<verse number="12">ይህን ከሚያደርግ ሰው፥ እግዚአብሔር የሚጠራውንና የሚመልሰውን ለሠራዊትም ጌታ ለእግዚአብሔር ቍርባን የሚያቀርበውን ከያዕቆብ ድንኳን ያጠፋል።</verse>
				<verse number="13">ይህንም ደግሞ አድርጋችኋል፣ እግዚአብሔር ቍርባኑን ዳግመኛ እንዳይመለከት፥ ከእጃችሁም በደስታ እንዳይቀበለው መሠዊያውን በእንባና በልቅሶ በኅዘንም ትከድናላችሁ።</verse>
				<verse number="14">እናንተም፦ ስለ ምንድር ነው? ብላችኋል። ሚስትህ ባልንጀራህና የቃል ኪዳንህ ሚስት ሆና ሳለች እርስዋን አታልለሃታልና እግዚአብሔር በአንተና በልጅነት ሚስትህ መካከል ምስክር ስለ ሆነ ነው።</verse>
				<verse number="15">እግዚአብሔር የሕይወትን መንፈስ አንድ አድርጎ ጠብቆልን የለምን? እርሱም የሚፈልገው ምንድር ነው? ዘር አይደለምን? ስለዚህ መንፈሳችሁን ጠብቁ፥ ማንም የልጅነት ሚስቱን አያታልል።</verse>
				<verse number="16">መፋታትን እጠላለሁ፥ ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፥ ልብሱንም በግፍ ሥራ የሚከድነውን ሰው እጠላለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ስለዚህ እንዳታታልሉ መንፈሳችሁን ጠብቁ።</verse>
				<verse number="17">እግዚአብሔርን በቃላችሁ አታክታችኋል። እናንተም፦ ያታከትነው በምንድር ነው? ብላችኋል። ክፉን የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ መልካም ነው፥ እርሱም በእነርሱ ደስ ይለዋል፣ ወይስ፦ የፍርድ አምላክ ወዴት አለ? በማለታችሁ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፣ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፣ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="2">ነገር ግን እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን ቀን መታገሥ የሚችል ማን ነው? እርሱስ በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማን ነው?</verse>
				<verse number="3">እርሱም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ የሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል፣ እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ።</verse>
				<verse number="4">እግዚአብሔርም እንደ ዱሮው ዘመንና እንደ ቀደሙት ዓመታት በይሁዳና በኢየሩሳሌም ቍርባን ደስ ይለዋል።</verse>
				<verse number="5">ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="6">እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም፣ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ ስለዚህ የጠፋችሁ አይደላችሁም።</verse>
				<verse number="7">ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል፥ እርስዋንም አልጠበቃችሁም። ወደ እኔ ተመለሱ፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተ ግን፦ የምንመለሰው በምንድር ነው? ብላችኋል።</verse>
				<verse number="8">ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም፦ የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው።</verse>
				<verse number="9">እናንተ፥ ይህ ሕዝብ ሁሉ፥ እኔን ሰርቃችኋልና በእርግማን ርጉሞች ናችሁ።</verse>
				<verse number="10">በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፣ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="11">ስለ እናንተ ነቀዙን እገሥጻለሁ፥ የምድራችሁንም ፍሬ አያጠፋም፣ በእርሻችሁም ያለው ወይን ፍሬውን አያረግፍም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="12">የተድላ ምድር ትሆናላችሁና አሕዛብ ሁሉ ብፁዓን ብለው ይጠሩአችኋል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="13">ቃላችሁ በእኔ ላይ ድፍረት ሆኖአል፥ ይላል እግዚአብሔር። እናንተ ግን፦ በአንተ ላይ ደፍረን የተናገርነው በምንድር ነው? ብላችኋል።</verse>
				<verse number="14">እናንተም፦ እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፣ ትእዛዙንስ በመጠበቅ፥ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ፊት ኀዘንተኞች ሆነን በመሄድ ምን ይረባናል?</verse>
				<verse number="15">አሁንም የሚታበዩትን ሰዎች ብፁዓን ብለን እንጠራቸዋለን፣ ክፉንም የሚሠሩ ጸንተዋል እግዚአብሔርንም ይፈታተናሉ፥ ያመልጣሉም ብላችኋል።</verse>
				<verse number="16">የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈሩ እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩ፣ እግዚአብሔርም አደመጠ፥ ሰማም፥ እግዚአብሔርንም ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ መጽሐፍ በፊቱ ተጻፈ።</verse>
				<verse number="17">እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ።</verse>
				<verse number="18">ተመልሳችሁም በጻድቁና በኃጢአተኛው መካከል፥ ለእግዚአብሔር በሚገዛውና በማይገዛው መካከል ትለያላችሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፣ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፣ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="2">ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፣ እናንተም ትወጣላችሁ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ትፈነጫላችሁ።</verse>
				<verse number="3">በምሠራበት ቀን በደለኞች ከእግራችሁ ጫማ በታች አመድ ይሆናሉና እናንተ ትረግጡአቸዋላችሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።</verse>
				<verse number="4">ለእስራኤል ሁሉ ሥርዓትንና ፍርድን አድርጌ በኮሬብ ያዘዝሁትን የባሪያዬን የሙሴን ሕግ አስቡ።</verse>
				<verse number="5">እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።</verse>
				<verse number="6">መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።</verse>
			</chapter>
		</book>
	</testament>
	<testament name="New">
		<book number="40">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።</verse>
				<verse number="2">አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤</verse>
				<verse number="3">ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ፤</verse>
				<verse number="4">ኤስሮምም አራምን ወለደ፤ አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤</verse>
				<verse number="5">ሰልሞንም ከራኬብ ቦኤዝን ወለደ፤ ቦኤዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤</verse>
				<verse number="6">እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ፤ ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ።</verse>
				<verse number="7">ሰሎሞንም ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓምም አብያን ወለደ፤ አብያም አሣፍን ወለደ፤</verse>
				<verse number="8">አሣፍም ኢዮሣፍጥን ወለደ፤ ኢዮሣፍጥም ኢዮራምን ወለደ፤ ኢዮራምም ዖዝያንን ወለደ፤</verse>
				<verse number="9">ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ፤ ኢዮአታምም አካዝን ወለደ፤</verse>
				<verse number="10">አካዝም ሕዝቅያስን ወለደ፤ ሕዝቅያስም ምናሴን ወለደ፤ ምናሴም አሞፅን ወለደ፤</verse>
				<verse number="11">አሞፅም ኢዮስያስን ወለደ፤ ኢዮስያስም በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ።</verse>
				<verse number="12">ከባቢሎንም ምርኮ በኋላ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ፤</verse>
				<verse number="13">ዘሩባቤልም አብዩድን ወለደ፤ አብዩድም ኤልያቄምን ወለደ፤ ኤልያቄምም አዛርን ወለደ፤</verse>
				<verse number="14">አዛርም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪምን ወለደ፤ አኪምም ኤልዩድን ወለደ፤</verse>
				<verse number="15">ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም ማታንን ወለደ፤ ማታንም ያዕቆብን ወለደ፤</verse>
				<verse number="16">ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ።</verse>
				<verse number="17">እንግዲህ ትውልድ ሁሉ ከአብርሃም እስከ ዳዊት አሥራ አራት ትውልድ፥ ከዳዊትም እስከ ባቢሎን ምርኮ አሥራ አራት ትውልድ፥ ከባቢሎንም ምርኮ እስከ ክርስቶስ አሥራ አራት ትውልድ ነው።</verse>
				<verse number="18">የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።</verse>
				<verse number="19">እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ።</verse>
				<verse number="20">እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፤ እንዲህም አለ “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ! ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።</verse>
				<verse number="21">ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኀጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።”</verse>
				<verse number="22">በነቢይ ከጌታ ዘንድ፥</verse>
				<verse number="23">“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፤ ትርጓሜውም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” የሚል ነው።</verse>
				<verse number="24">ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቅቶ የጌታ መልአክ እንዳዘዘው አደረገ፤ እጮኛውንም ወሰደ፤</verse>
				<verse number="25">የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና” እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።</verse>
				<verse number="2"></verse>
				<verse number="3">ንጉሡ ሄሮድስም ሰምቶ ደነገጠ፤ ኢየሩሳሌምም ሁሉ ከእርሱ ጋር፤</verse>
				<verse number="4">የካህናትንም አለቆች የሕዝቡንም ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ ክርስቶስ ወዴት እንዲወለድ ጠየቃቸው።</verse>
				<verse number="5">እነርሱም “ ‘አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና’ ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው” አሉት።</verse>
				<verse number="6"></verse>
				<verse number="7">ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገልን በስውር ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከእነርሱ በጥንቃቄ ተረዳ።</verse>
				<verse number="8">ወደ ቤተ ልሔምም እነርሱን ሰድዶ “ሂዱ፤ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ” አላቸው።</verse>
				<verse number="9">እነርሱም ንጉሡን ሰምተው ሄዱ፤ እነሆም፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር።</verse>
				<verse number="10">ኮከቡንም ባዩ ጊዜ በታላቅ ደስታ እጅግ ደስ አላቸው።</verse>
				<verse number="11">ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ወድቀውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።</verse>
				<verse number="12">ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ተረድተው በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ።</verse>
				<verse number="13">እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ “ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፤ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ” አለው።</verse>
				<verse number="14">እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ “ልጄን ከግብጽ ጠራሁት” የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብጽ ሄደ፤ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ።</verse>
				<verse number="15"></verse>
				<verse number="16">ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።</verse>
				<verse number="17">ያን ጊዜ እንዲህ ሲል በነቢዩ በኤርምያስ የተነገረው ተፈጸመ፤</verse>
				<verse number="18">“ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ልቅሶና ብዙ ዋይታ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ መጽናናትም አልወደደችም፤ የሉምና።”</verse>
				<verse number="19">ሄሮድስም ከሞተ በኋላ፥ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በግብጽ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ</verse>
				<verse number="20">“የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፤ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ” አለ።</verse>
				<verse number="21">እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ያዘና ወደ እስራኤል አገር ገባ።</verse>
				<verse number="22">በአባቱም በሄሮድስ ፈንታ አርኬላዎስ በይሁዳ እንደ ነገሠ በሰማ ጊዜ፥ ወደዚያ መሄድን ፈራ፤ በሕልምም ተረድቶ ወደ ገሊላ አገር ሄደ፤</verse>
				<verse number="23">በነቢያት “ናዝራዊ ይባላል” የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ።</verse>
				<verse number="2"></verse>
				<verse number="3">በነቢዩ በኢሳይያስ “ ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ ጥርጊያውንም አቅኑ’ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ” የተባለለት ይህ ነውና።</verse>
				<verse number="4">ራሱም ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፤ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሓ ማር ነበረ።</verse>
				<verse number="5">ያን ጊዜ ኢየሩሳሌም ይሁዳም ሁሉ በዮርዳኖስም ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፤</verse>
				<verse number="6">ኀጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።</verse>
				<verse number="7">ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው “እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ?</verse>
				<verse number="8">እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤</verse>
				<verse number="9">በልባችሁም ‘አብርሃም አባት አለን’ እንደምትሉ አይምሰላችሁ፤ እላችኋለሁና ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል።</verse>
				<verse number="10">አሁንስ ምሳር በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቍኦረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።</verse>
				<verse number="11">እኔስ “ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤</verse>
				<verse number="12">መንሹም በእጁ ነው፤ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፤ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”</verse>
				<verse number="13">ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።</verse>
				<verse number="14">ዮሐንስ ግን “እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል፤ አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?” ብሎ ይከለክለው ነበር።</verse>
				<verse number="15">ኢየሱስም መልሶ “አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና” አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።</verse>
				<verse number="16">ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኀ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤</verse>
				<verse number="17">እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” አለ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው።</verse>
				<verse number="2">አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ።</verse>
				<verse number="3">ፈታኝም ቀርቦ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል!” አለው።</verse>
				<verse number="4">እርሱም መልሶ “ ‘ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም’ ተብሎ ተጽፎአል” አለው።</verse>
				<verse number="5">ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ</verse>
				<verse number="6">“ ‘መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል፤ እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል’ ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር” አለው።</verse>
				<verse number="7">ኢየሱስም “ ‘ጌታን አምላክህን አትፈታተነው’ ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል” አለው።</verse>
				<verse number="8">ደግሞ ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፤ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ</verse>
				<verse number="9">“ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="10">ያን ጊዜ ኢየሱስ “ሂድ፤ አንተ ሰይጣን ‘ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ’ ተብሎ ተጽፎአልና” አለው።</verse>
				<verse number="11">ያን ጊዜ ዲያቢሎስ ተወው፤ እነሆም፥ መላእክት ቀርበው ያገለግሉት ነበር።</verse>
				<verse number="12">ኢየሱስም ዮሐንስ አልፎ እንደ ተሰጠ በሰማ ጊዜ ወደ ገሊላ ፈቀቅ ብሎ ሄደ።</verse>
				<verse number="13">ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎንና በንፍታሌም አገር በባሕር አጠገብ ወደ አለችው ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ።</verse>
				<verse number="14">በነቢዩም በኢሳይያስ እንዲህ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ፤</verse>
				<verse number="15">ምድርና የንፍታሌም ምድር፥ የባሕር መንገድ፥ በዮርዳኖስ ማዶ፥ የአሕዛብ ገሊላ፤</verse>
				<verse number="16">ቀመጠው ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤ በሞት አገርና ጥላ ለተቀመጡትም ብርሃን ወጣላቸው።”</verse>
				<verse number="17">ከዚያ ዘመን ጀምሮኢየሱስ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” እያለ ይሰብክ ጀመር።</verse>
				<verse number="18">በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስም ሁለት ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፤ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።</verse>
				<verse number="19">እርሱም “በኋላዬ ኑ፤ ሰዎችንም አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ” አላቸው።</verse>
				<verse number="20">ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት።</verse>
				<verse number="21">ከዚያም እልፍ ብሎ ሌሎችን ሁለት ወንድማማች የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በታንኳ መረባቸውን ሲያበጁ አየ፤ ጠራቸውም።</verse>
				<verse number="22">እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት።</verse>
				<verse number="23">ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር።</verse>
				<verse number="24">ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።</verse>
				<verse number="25">ከገሊላም ከዐሥሩ ከተማም ከኢየሩሳሌምም ከይሁዳም ከዮርዳኖስም ማዶ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ፤ በተቀመጠም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረቡ፤</verse>
				<verse number="2">አፉንም ከፍቶ አስተማራቸው እንዲህም አለ፦</verse>
				<verse number="3">“ንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፤መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።</verse>
				<verse number="4">የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፤መፅናናትን ያገኛሉና።</verse>
				<verse number="5">የዋሆች ብፁዓን ናቸው፤ምድርን ይወርሳሉና።</verse>
				<verse number="6">ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፤ይጠግባሉና።</verse>
				<verse number="7">የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፤ይማራሉና።</verse>
				<verse number="8">ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፤እግዚአብሔርን ያዩታልና።</verse>
				<verse number="9">የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፤የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።</verse>
				<verse number="10">ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፤መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።</verse>
				<verse number="11">“ቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።</verse>
				<verse number="12">ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፤ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።”</verse>
				<verse number="13">እናንተ “ድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።</verse>
				<verse number="14">“ንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።</verse>
				<verse number="15">መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል፤በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።</verse>
				<verse number="16">መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።</verse>
				<verse number="17">“ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም።</verse>
				<verse number="18">እውነት እላችኋለሁ፤ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፤ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ።</verse>
				<verse number="19">እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤ የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል።</verse>
				<verse number="20">እላችኋለሁና ጽድቃችሁ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ካልበለጠ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።</verse>
				<verse number="21">“ለቀደሙት ‘አትግደል’ እንደተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል።</verse>
				<verse number="22">እኔ ግን እላችኋለሁ፤በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።</verse>
				<verse number="23">እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ፥ በዚያም ወንድምህ አንዳች በአንተ ላይ እንዳለው ብታስብ፥</verse>
				<verse number="24">በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፤አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፤በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ።</verse>
				<verse number="25">አብረኸው በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ፈጥነህ ተስማማ፤ ባላጋራ ለዳኛ እንዳይሰጥህ ዳኛም ለሎሌው፤ወደ ወህኒም ትጣላለህ፤</verse>
				<verse number="26">እውነት እልሃለሁ፥ የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከቶ ከዚያ አትወጣም።</verse>
				<verse number="27">“ ‘አታመንዝር’ ዝንደተባለ ሰምታችኋል።</verse>
				<verse number="28">እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል።</verse>
				<verse number="29">ቀኝ ዐይንህም ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻልሃልና።</verse>
				<verse number="30">ቀኝ እጅህም ብታሰናክልህ ቆርጠህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻላልና።</verse>
				<verse number="31">“ ‘ሚስቱን የሚፈታት ሁሉ የፍችዋን ጽሕፈት ይስጣት’ ተባለ።</verse>
				<verse number="32">እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል፤ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።</verse>
				<verse number="33">“ደግሞ ለቀደሙት ‘በውሸት አትማል ነገር ግን መሐላዎችህን ለጌታ ስጥ’ እንደተባለ ሰምታችኋል።</verse>
				<verse number="34">እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ከቶ አትማሉ፤ በሰማይ አይሆንም የእግዚአብሔር ዙፋን ነውና፤</verse>
				<verse number="35">በምድርም አይሆንም የእግሩ መረገጫ ናትና፤ በኢየሩሳሌምም አይሆንም የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናትና፤</verse>
				<verse number="36">በራስህም አትማል፤ አንዲቱን ጠጉር ነጭ ወይም ጥቁር ልታደርግ አትችልምና።</verse>
				<verse number="37">ነገር ግን ቃላችሁ አዎን አዎን ወይም አይደለም አይደለም ይሁን፤ ከነዚህም የወጣ ከክፉው ነው።</verse>
				<verse number="38">“ ‘ዐይን ስለ ዐይን ጥርስም ስለ ጥርስ’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል።</verse>
				<verse number="39">እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤</verse>
				<verse number="40">እንዲከስህም እጀ ጠባብህንም እንዲወስድ ለሚወድ መጎናጸፊያህን ደግሞ ተውለት፤</verse>
				<verse number="41">ማንም ሰው አንድ ምዕራፍ ትሄድ ዘንድ ቢያስገድድህ ሁለተኛውን ከእርሱ ጋር ሂድ።</verse>
				<verse number="42">ለሚለምንህ ስጥ፤ ከአንተም ይበደር ዘንድ ከሚወደው ፈቀቅ አትበል።</verse>
				<verse number="43">“ ‘ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል።</verse>
				<verse number="44">እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።</verse>
				<verse number="45"></verse>
				<verse number="46">የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?</verse>
				<verse number="47">ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?</verse>
				<verse number="48">እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">“ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም።</verse>
				<verse number="2">“እንግዲህ ምጽዋት ስታደርግ፥ ግብዞች በሰው ዘንድ ሊከበሩ በምኩራብ በመንገድም እንደሚያደርጉ በፊትህ መለከት አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።</verse>
				<verse number="3">አንተ ግን ምጽዋት ስታደርግ ምጽዋትህ በስውር እንዲሆን ቀኝህ የምትሠራውን ግራህ አትወቅ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።</verse>
				<verse number="4"></verse>
				<verse number="5">“ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።</verse>
				<verse number="6">አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ፤ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።</verse>
				<verse number="7">“አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ።</verse>
				<verse number="8">ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና።</verse>
				<verse number="9">እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ!</verse>
				<verse number="10">ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤</verse>
				<verse number="11">የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤</verse>
				<verse number="12">እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤</verse>
				<verse number="13">ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።’</verse>
				<verse number="14">ለሰዎች ኀጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤</verse>
				<verse number="15">ለሰዎች ግን ኀጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኀጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።</verse>
				<verse number="16">“ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።</verse>
				<verse number="17">አንተ ግን ስትጦም፥ በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ፤ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።</verse>
				<verse number="18"></verse>
				<verse number="19">“ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤</verse>
				<verse number="20">ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤</verse>
				<verse number="21">መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና።</verse>
				<verse number="22">“የሰውነት መብራት ዐይን ናት። ዐይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፤</verse>
				<verse number="23">ዐይንህ ግን ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማውስ እንዴት ይበረታ!</verse>
				<verse number="24">“ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።</verse>
				<verse number="25">“ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?</verse>
				<verse number="26">ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፤ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?</verse>
				<verse number="27">ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው?</verse>
				<verse number="28">ስለ ልብስስ ስለ ምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፤</verse>
				<verse number="29">አይደክሙም አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፤ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም።</verse>
				<verse number="30">እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት?</verse>
				<verse number="31">እንግዲህ ‘ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን?’ ብላችሁ አትጨነቁ፤</verse>
				<verse number="32">ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና።</verse>
				<verse number="33">ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።</verse>
				<verse number="34">“ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">“እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፤ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።</verse>
				<verse number="2"></verse>
				<verse number="3">በወንድምህም ዐይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፤ በዐይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም?</verse>
				<verse number="4">ወይም ወንድምህን ‘ከዐይንህ ጕድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ’ እንዴትስ ትለዋለህ? እነሆም፥ በዐይንህ ምሰሶ አለ።</verse>
				<verse number="5">አንተ ግብዝ፤ አስቀድመህ ከዐይንህ ምሰሶውን አውጣ፤ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዐይን ጕድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።</verse>
				<verse number="6">በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ።</verse>
				<verse number="7">“ለምኑ፤ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፤ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፤ ይከፈትላችሁማል።</verse>
				<verse number="8">የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፤ የሚፈልገውም ያገኛል፤ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።</verse>
				<verse number="9">ወይስ ልጁ እንጀራ ቢለምነው ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው?</verse>
				<verse number="10">ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን?</verse>
				<verse number="11">እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው!</verse>
				<verse number="12">እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና።</verse>
				<verse number="13">“በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ መንገዱም ትልቅ ነውና፤ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤</verse>
				<verse number="14">ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፤ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።</verse>
				<verse number="15">“የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውስጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።</verse>
				<verse number="16">ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?</verse>
				<verse number="17">እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፤ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል።</verse>
				<verse number="18">መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም።</verse>
				<verse number="19">መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል።</verse>
				<verse number="20">ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።</verse>
				<verse number="21">በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ!’ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።</verse>
				<verse number="22">በዚያ ቀን ብዙዎች ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን?’ ይሉኛል።</verse>
				<verse number="23">የዚያን ጊዜም ‘ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ አመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ’ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።</verse>
				<verse number="24">“ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል።</verse>
				<verse number="25">ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት ገፋው፤ በዐለት ላይም ስለ ተመሠረተ አልወደቀም።</verse>
				<verse number="26">ይህንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል።</verse>
				<verse number="27">ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት መታው፤ ወደቀም፤ አወዳደቁም ታላቅ ሆነ።”</verse>
				<verse number="28">ኢየሱስም ይህን ነገር በጨረሰ ጊዜ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ፤ እንደ ጻፎቻቸው ሳይሆን፥</verse>
				<verse number="29">እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበርና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">ከተራራም በወረደ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት።</verse>
				<verse number="2">እነሆም፥ ለምጻም ቀርቦ “ጌታ ሆይ! ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ” እያለ ሰገደለት።</verse>
				<verse number="3">እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና “እወዳለሁ፤ ንጻ” አለው። ወዲያውም ለምጹ ነጻ።</verse>
				<verse number="4">ኢየሱስም “ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ሙሴ ያዘዘውን መባ አቅርብ” አለው።</verse>
				<verse number="5">ወደ ቅፍርናሆምም በገባ ጊዜ የመቶ አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ</verse>
				<verse number="6">“ጌታ ሆይ!ብላቴናዬ ሽባ ሆኖ እጅግ እየተሣቀየ በቤት ተኝቶአል” ብሎ ለመነው።</verse>
				<verse number="7">ኢየሱስም “እኔ መጥቼ እፈውሰዋለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="8">የመቶ አለቃውም መልሶ “ጌታ ሆይ! በቤቴ ጣራ በታች ልትገባ አይገባኝም፤ ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር፤ ብላቴናዬም ይፈወሳል።</verse>
				<verse number="9">እኔ ደግሞ ለሌሎች ተገዥ ነኝና፤ ከእኔም በታች ጭፍራ አለኝ፤ አንዱንም ‘ሂድ’ ብለው ይሄዳል፤ ሌላውንም ‘ና’ ብለው ይመጣል፤ ባሪያዬንም ‘ይህን አድርግ’ ብለው ያደርጋል” አለው።</verse>
				<verse number="10">ኢየሱስም ሰምቶ ተደነቀና ለተከተሉት እንዲህ አለ “እውነት እላችኋለሁ፤ በእስራኤል እንኳ እንዲህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም።</verse>
				<verse number="11">እላችኋለሁም፥ ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ፤ ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር በመንግሥተ ሰማያት ይቀመጣሉ፤</verse>
				<verse number="12">የመንግሥት ልጆች ግን በውጭ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”</verse>
				<verse number="13">ኢየሱስም ለመቶ አለቃ “ሂድና እንዳመንህ ይሁንልህ፤” አለው። ብላቴናውም በዚያች ሰዓት ተፈወሰ።</verse>
				<verse number="14">ኢየሱስም ወደ ጴጥሮስ ቤት ገብቶ አማቱን በንዳድ ታማ ተኝታ አያት፤</verse>
				<verse number="15">እጅዋንም ዳሰሰ፤ ንዳዱም ለቀቃት፤ ተነሥታም አገለገለቻቸው።</verse>
				<verse number="16">በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደረባቸውን ብዙዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ በነቢዩ በኢሳይያስ “እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ መናፍስትን በቃኣሉ አወጣ፤ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ።</verse>
				<verse number="17"></verse>
				<verse number="18">ኢየሱስም ብዙ ሰዎች ሲከቡት አይቶ ወደ ማዶ እንዲሻገሩ አዘዘ።</verse>
				<verse number="19">አንድ ጸሐፊም ቀርቦ “መምህር ሆይ! ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ፤” አለው።</verse>
				<verse number="20">ኢየሱስም “ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፤ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም፤” አለው።</verse>
				<verse number="21">ከደቀ መዛሙርቱም ሌላው “ጌታ ሆይ! አስቀድሜ እንድሄድ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ፤” አለው።</verse>
				<verse number="22">ኢየሱስ “ተከተለኝ፤ ሙታናቸውንም እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤” አለው።</verse>
				<verse number="23">ወደ ታንኳም ሲገባ ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት።</verse>
				<verse number="24">እነሆም ማዕበሉ ታንኳይቱን እስኪደፍናት ድረስ በባሕር ታላቅ መናወጥ ሆነ፤ እርሱ ግን ተኝቶ ነበር።</verse>
				<verse number="25">ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው “ጌታ ሆይ! አድነን፤ ጠፋን፤” እያሉ አስነሡት።</verse>
				<verse number="26">እርሱም “እናንተ እምነት የጎደላችሁ! ስለ ምን ትፈራላችሁ?” አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።</verse>
				<verse number="27">ሰዎቹም “ነፋሳትና ባሕርስ ስንኳ የሚታዘዙለት፥ ይህ እንዴት ያለ ሰው ነው?” እያሉ ተደነቁ።</verse>
				<verse number="28">ወደ ማዶም ወደ ጌርጋሴኖን አገር በመጣ ጊዜ፥ አጋንንት ያደሩባቸው ሁለት ሰዎች ከመቃብር ወጥተው ተገናኙት፤ እነርሱም ሰው በዚያ መንገድ ማለፍ እስኪሳነው ድረስ እጅግ ክፉዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="29">እነሆም “ኢየሱስ ሆይ! የእግዚአብሔር ልጅ! ከአንተ ጋር ምን አለን? ጊዜው ሳይደርስ ልታሠቃየን ወደዚህ መጣህን?” እያሉ ጮኹ።</verse>
				<verse number="30">ከእነርሱም ርቆ የብዙ እሪያ መንጋ ይሰማራ ነበር።</verse>
				<verse number="31">አጋንንቱም “ታወጣንስ እንደሆንህ፥ ወደ እሪያው መንጋ ስደደን፤” ብለው ለመኑት። “ሂዱ፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="32">እነርሱም ወጥተው ወደ እሪያዎቹ ሄዱና ገቡ፤ እነሆም የእሪያዎቹ መንጋ ሁሉ ከአፋፉ ወደ ባሕር እየተጣደፉ ሮጡ፤ በውሃም ውስጥ ሞቱ።</verse>
				<verse number="33">እረኞችም ሸሹ፤ ወደ ከተማይቱም ሄደው ነገሩን ሁሉ አጋንንትም በአደሩባቸው የሆነውን አወሩ።</verse>
				<verse number="34">እነሆም ከተማው ሁሉ ኢየሱስን ሊገናኝ ወጣ፤ ባዩትም ጊዜ ከአገራቸው እንዲሄድላቸው ለመኑት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">በታንኳም ገብቶ ተሻገረና ወደ ገዛ ከተማው መጣ።</verse>
				<verse number="2">እነሆም፥ በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን “አንተ ልጅ! አይዞህ፤ ኀጢአትህ ተሰረየችልህ፤” አለው።</verse>
				<verse number="3">እነሆም ከጻፎቹ አንዳንዶቹ በልባቸው “ይህስ ይሳደባል፤” አሉ።</verse>
				<verse number="4">ኢየሱስም አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ “ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ?</verse>
				<verse number="5">‘ኀጢአትህ ተሰረየችልህ’ ከማለት ወይስ ‘ተነሣና ሂድ’ ከማለት ማናቸው ይቀላል?</verse>
				<verse number="6">ነገር ግን በምድር ላይ ኀጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ለሰው ልጅ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፤” በዚያን ጊዜ ሽባውን “ተነሣ፤ አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ፤” አለው።</verse>
				<verse number="7">ተነሥቶም ወደ ቤቱ ሄደ።</verse>
				<verse number="8">ሕዝቡም አይተው ተደነቁ፤ ለሰውም እንዲህ ያለ ሥልጣን የሰጠ እግዚአብሔርን አከበሩ።</verse>
				<verse number="9">ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና “ተከተለኝ” አለው። ተነሥቶም ተከተለው።</verse>
				<verse number="10">በቤቱም በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ እነሆ፥ ብዙ ቀራጮችና ኀጢአተኞች መጥተው ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር አብረው ተቀመጡ።</verse>
				<verse number="11">ፈሪሳውያንም አይተው ደቀ መዛሙርቱን “መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር አብሮ ስለ ምን ይበላል?” አሉአቸው።</verse>
				<verse number="12">ኢየሱስም ሰምቶ “ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤነኞች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤</verse>
				<verse number="13">ነገር ግን ሄዳችሁ ‘ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም፤’ ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ፤ ኀጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="14">በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው “እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው፥ ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው?” አሉት።</verse>
				<verse number="15">ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።</verse>
				<verse number="16">በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፤ መቀደዱም የባሰ ይሆናል።</verse>
				<verse number="17">በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን አቁማዳው ይፈነዳል፤ የወይን ጠጁም ይፈሳል፤ አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፤ ሁለቱም ይጠባበቃሉ።”</verse>
				<verse number="18">ይህንም ሲነግራቸው አንድ መኰንን መጥቶ “ልጄ አሁን ሞተች፤ ነገር ግን መጥተህ እጅህን ጫንባት፥ በሕይወትም ትኖራለች፤” እያለ ሰገደለት።</verse>
				<verse number="19">ኢየሱስም ተነሥቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተከተለው።</verse>
				<verse number="20">እነሆም ከዐሥራ ሁለት ዓመት ጀምሮ ደም የሚፈስሳት ሴት በኋላው ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤</verse>
				<verse number="21">በልብዋ “ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ እድናለሁ፤” ትል ነበረችና።</verse>
				<verse number="22">ኢየሱስም ዘወር ብሎ አያትና “ልጄ ሆይ! አይዞሽ፤ እምነትሽ አድኖሻል፤” አላት። ሴቲቱም ከዚያች ሰዓት ጀምራ ዳነች።</verse>
				<verse number="23">ኢየሱስም ወደ መኰንኑ ቤት በደረሰ ጊዜ፥ እምቢልተኞችንና የሚንጫጫውን ሕዝብ አይቶ</verse>
				<verse number="24">“ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችምና ፈቀቅ በሉ፤” አላቸው። በጣምም ሳቁበት።</verse>
				<verse number="25">ሕዝቡን ግን ከአስወጡ በኋላ ገብቶ እጅዋን ያዛት፤ ብላቴናይቱም ተነሣች።</verse>
				<verse number="26">ያም ዝና ወደዚያ አገር ሁሉ ወጣ።</verse>
				<verse number="27">ኢየሱስም ከዚያ ሲያልፍ ሁለት ዕውሮች “የዳዊት ልጅ ሆይ! ማረን፤” ብለው እየጮሁ ተከተሉት።</verse>
				<verse number="28">ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ዕውሮቹ ወደ እርሱ ቀረቡ፤ ኢየሱስም “ይህን ማድረግ እንድችል ታምናላችሁን?” አላቸው። “አዎን፥ ጌታ ሆይ!” አሉት።</verse>
				<verse number="29">በዚያን ጊዜ “እንደ እምነታችሁ ይሁንላችሁ፤” ብሎ ዐይኖቻቸውን ዳሰሰ።</verse>
				<verse number="30">ዐይኖቻቸውም ተከፈቱ። ኢየሱስም “ማንም እንዳያውቅ ተጠንቀቁ፤” ብሎ በብርቱ አዘዛቸው።</verse>
				<verse number="31">እነርሱ ግን ወጥተው በዚያ አገር ሁሉ ስለ እርሱ አወሩ።</verse>
				<verse number="32">እነርሱም ሲወጡ እነሆ ጋኔን ያደረበትን ድዳ ሰው ወደ እርሱ አመጡ።</verse>
				<verse number="33">ጋኔኑንም ካወጣው በኋላ ድዳው ተናገረ። ሕዝቡም “እንዲህ ያለ በእስራኤል ዘንድ ከቶ አልታየም፤” እያሉ ተደነቁ።</verse>
				<verse number="34">ፈሪሳውያን ግን “በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል፤” አሉ።</verse>
				<verse number="35">ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ፥ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር።</verse>
				<verse number="36">ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው።</verse>
				<verse number="37">በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን “መከሩስ ብዙ ነው፤ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤</verse>
				<verse number="38">እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት፤” አላቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ እርሱ ጠርቶ፥ እንዲያወጡአቸው በርኩሳን መናፍስት ላይ ደዌንና ሕማምንም ሁሉ እንዲፈውሱ ሥልጣን ሰጣቸው።</verse>
				<verse number="2">የዐሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ይህ ነው፤ መጀመሪያው ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን ወንድሙ እንድርያስም፥ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብም ወንድሙ ዮሐንስም፥</verse>
				<verse number="3">ፊልጶስም በርተሎሜዎስም፥ ቶማስም ቀራጩ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም ታዴዎስም የተባለው ልብድዮስ፥</verse>
				<verse number="4">ቀነናዊውም ስምዖን ደግሞም አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ።</verse>
				<verse number="5">እነዚህን ዐሥራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸው፤ አዘዛቸውም፤ እንዲህም አለ “በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፤ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ፤</verse>
				<verse number="6">ይልቅስ የእስራኤል ቤት ወደሚሆኑ ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ እንጂ።</verse>
				<verse number="7">ሄዳችሁም ‘መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች፤’ ብላችሁ ስበኩ።</verse>
				<verse number="8">ድውዮችን ፈውሱ፤ ሙታንን አስነሡ፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ አጋንንትን አውጡ፤ በከንቱ ተቀበላችሁ፤ በከንቱ ስጡ።</verse>
				<verse number="9">ወርቅ ወይም ብር ወይም ናስ በመቀነታችሁ፥</verse>
				<verse number="10">ወይም ለመንገድ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አትያዙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና።</verse>
				<verse number="11">በምትገቡባትም በማናቸይቱም ከተማ ወይም መንደር፥ በዚያ የሚገባው ማን እንደ ሆነ በጥንቃቄ መርምሩ፤ እስክትወጡም ድረስ በዚያ ተቀመጡ።</verse>
				<verse number="12">ወደ ቤትም ስትገቡ ሰላምታ ስጡ፤</verse>
				<verse number="13">ቤቱም የሚገባው ቢሆን ሰላማችሁ ይድረስለት፤ ባይገባው ግን ሰላማችሁ ይመለስላችሁ።</verse>
				<verse number="14">ከማይቀበላችሁም ቃላችሁንም ከማይሰሙ ሁሉ፥ ከዚያ ቤት ወይም ከዚያች ከተማ ስትወጡ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ።</verse>
				<verse number="15">እውነት እላችኋለሁ፤ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ አገር ይቀልላቸዋል።</verse>
				<verse number="16">“እነሆ እኔ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።</verse>
				<verse number="17">ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤</verse>
				<verse number="18">ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን፥ ስለ እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ።</verse>
				<verse number="19">አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤</verse>
				<verse number="20">በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና።</verse>
				<verse number="21">ወንድምም ወንድሙን፥ አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ፤ ይገድሉአቸውማል።</verse>
				<verse number="22">በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።</verse>
				<verse number="23">በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፤ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።</verse>
				<verse number="24">“ደቀ መዝሙር ከመምህሩ፥ ባሪያም ከጌታው አይበልጥም።</verse>
				<verse number="25">ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!</verse>
				<verse number="26">“እንግዲህ አትፍሩአቸው፤ የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና።</verse>
				<verse number="27">በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ።</verse>
				<verse number="28">ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።</verse>
				<verse number="29">ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም።</verse>
				<verse number="30">የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቍኦጥሮአል።</verse>
				<verse number="31">እንግዲህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ።</verse>
				<verse number="32">ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤</verse>
				<verse number="33">በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።</verse>
				<verse number="34">“በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም።</verse>
				<verse number="35">ሰውን ከአባቱ፥ ሴት ልጅንም ከእናትዋ፥ ምራትንም ከአማትዋ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና፤</verse>
				<verse number="36">ለሰውም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል።</verse>
				<verse number="37">ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።</verse>
				<verse number="38">መስቀሉንም የማይዝ በኋላዬም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።</verse>
				<verse number="39">ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል፤ ነፍሱንም ስለ እኔ የሚያጠፋ ያገኛታል።</verse>
				<verse number="40">“እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።</verse>
				<verse number="41">ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፤ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።</verse>
				<verse number="42">ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">ኢየሱስም ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ማዘዝ በፈጸመ ጊዜ በከተሞቻቸው ሊያስተምርና ሊሰብክ ከዚያ አለፈ።</verse>
				<verse number="2">ዮሐንስም በወህኒ ሳለ የክርስቶስን ሥራ ሰምቶ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከና</verse>
				<verse number="3">“የሚመጣው አንተ ነህን? ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” አለው።</verse>
				<verse number="4">ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው “ሄዳችሁ ያያችሁትን የሰማችሁትንም ለዮሐንስ ንገሩት፤</verse>
				<verse number="5">ዕውሮች ያያሉ፤ አንካሶችም ይሄዳሉ፤ ለምጻሞችም ይነጻሉ፤ ደንቆሮችም ይሰማሉ፤ ሙታንም ይነሣሉ፤</verse>
				<verse number="6">ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤ በእኔም የማይሰናከለው ሁሉ ብፁዕ ነው።”</verse>
				<verse number="7">እነዚያም ሲሄዱ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ እንዲህም አለ “ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣችሁ?</verse>
				<verse number="8">ነፋስ የሚወዘውዘውን ሸምበቆን? ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀጭን ልብስ የለበሰ ሰውን? እነሆ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታት ቤት አሉ።</verse>
				<verse number="9">ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ፥ ከነቢይም የሚበልጠውን።</verse>
				<verse number="10">‘እነሆ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልእክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፤’</verse>
				<verse number="11">ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና። እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤ በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።</verse>
				<verse number="12">ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፤ ግፈኞችም ይናጠቋታል።</verse>
				<verse number="13">ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ፤</verse>
				<verse number="14">ልትቀበሉትስ ብትወዱ፥ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይህ ነው።</verse>
				<verse number="15">የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።</verse>
				<verse number="16">ነገር ግን “ይህን ትውልድ በምን እመስለዋለሁ? በገበያ የሚቀመጡትን ልጆች ይመስላሉ፤ እነርሱም ባልንጀሮቻቸውን እየጠሩ</verse>
				<verse number="17">‘እንቢልታ ነፋንላችሁ ዘፈንም አልዘፈናችሁም ሙሾ አወጣንላችሁ፤ ዋይ ዋይም አላላችሁም’ ይሉአቸዋል።</verse>
				<verse number="18">ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፤ እነርሱም ‘ጋኔን አለበት’ አሉት።</verse>
				<verse number="19">የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፤ እነርሱም ‘እነሆ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኀጢአተኞች ወዳጅ’ ይሉታል። ጥበብም በልጆችዋ ጸደቀች።”</verse>
				<verse number="20">በዚያን ጊዜ የሚበዙ ተአምራት የተደረገባቸውን ከተማዎች ንስሐ ስላልገቡ ሊነቅፋቸው ጀመረ እንዲህም አለ</verse>
				<verse number="21">“ወዮልሽ ኮራዚ! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን፥ ማቅ ለብሰው አመድም ነስንሰው ከብዙ ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበርና።</verse>
				<verse number="22">ነገር ግን እላችኋለሁ፤ በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል።</verse>
				<verse number="23">አንቺም ቅፍርናሆም፥ እስከ ሰማይ ከፍ አልሽን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ፤ በአንቺ የተደረገው ተአምራት በሰዶም ተደርጎ ቢሆን፥ እስከ ዛሬ በኖረች ነበርና።</verse>
				<verse number="24">ነገር ግን እላችኋለሁ፤ በፍርድ ቀን ከአንቺ ይልቅ ለሰዶም አገር ይቀልላታል።”</verse>
				<verse number="25">በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “አባት ሆይ! የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።</verse>
				<verse number="26">አዎን አባት ሆይ! ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።</verse>
				<verse number="27">ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።</verse>
				<verse number="28">እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ።</verse>
				<verse number="29">ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤</verse>
				<verse number="30">ቀንበሬ ልዝብ፤ ሸክሜም ቀሊል ነውና።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በሰንበት ቀን በእርሻ መካከል አለፈ፤ ደቀ መዛሙርቱም ተራቡና እሸት ይቀጥፉ ይበሉም ጀመር።</verse>
				<verse number="2">ፈሪሳውያንም አይተው “እነሆ ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት ማድረግ ያልተፈቀደውን ያደርጋሉ፤” አሉት።</verse>
				<verse number="3">እርሱ ግን እንዲህ አላቸው “ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት በተራቡ ጊዜ፥ እርሱ ያደረገውን፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ገባ ካህናትም ብቻ እንጂ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሊበሉት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕቱን ኅብስት እንደ በላ አላነበባችሁምን?</verse>
				<verse number="4"></verse>
				<verse number="5">ካህናትም በሰንበት በመቅደስ ሰንበትን እንዲያረክሱ ኀጢአትም እንዳይሆንባቸው በሕጉ አላነበባችሁምን?</verse>
				<verse number="6">ነገር ግን እላችኋለሁ፤ ከመቅደስ የሚበልጥ ከዚህ አለ።</verse>
				<verse number="7">‘ምሕረትን እወዳለሁ፤ መሥዋዕትንም አይደለም፤’ ያለው ምን እንደሆነ ብታውቁስ ኀጢአት የሌለባቸውን ባልኵኦነናችሁም ነበር።</verse>
				<verse number="8">የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነውና።”</verse>
				<verse number="9">ከዚያም አልፎ ወደ ምኩራባቸው ገባ።</verse>
				<verse number="10">እነሆም እጁ የሰለለች ሰው ነበረ፤ ይከሱትም ዘንድ “በሰንበት መፈወስ ተፈቅዶአልን?” ብለው ጠየቁት።</verse>
				<verse number="11">እርሱ ግን “ከእናንተ አንድ በግ ያለው በሰንበት በጉድጓድ ቢወድቅበት፥ ይዞ የማያወጣው ሰው ማን ነው?</verse>
				<verse number="12">እንግዲህ ሰው ከበግ ይልቅ እንደምን አይበልጥም! ስለዚህ በሰንበት መልካም መሥራት ተፈቅዶአል፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="13">ከዚያም በኋላ ሰውየውን “እጅህን ዘርጋ፤” አለው። ዘረጋትም፤ እንደ ሁለተኛይቱም ደህና ሆነች።</verse>
				<verse number="14">ፈሪሳውያን ግን ወጥተው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ተማከሩበት።</verse>
				<verse number="15">ኢየሱስም አውቆ ከዚያ ፈቀቅ አለ። ብዙ ሰዎችም ተከተሉት፤ ሁሉንም ፈወሳቸው፤ እንዳይገልጡትም አዘዛቸው፤</verse>
				<verse number="16">በነቢዩ በኢሳይያስ የተባለው ይፈጸም ዘንድ እንዲህ ሲል</verse>
				<verse number="17"></verse>
				<verse number="18">“እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፤ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል።</verse>
				<verse number="19">አይከራከርም፤ አይጮህምም፤ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም።</verse>
				<verse number="20">ፍርድን ድል ለመንሣት እስኪያወጣ፥ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፤ የሚጤስን የጥዋፍ ክርም አያጠፋም።</verse>
				<verse number="21">አሕዛብም በስሙ ተስፋ ያደርጋሉ።”</verse>
				<verse number="22">ከዚህም በኋላ ጋኔን ያደረበትን ዕውር ድዳም ወደ እርሱ አመጡ፤ ዕውሩም ዲዳውም እስኪያይና እስኪናገር ድረስ ፈወሰው።</verse>
				<verse number="23">ሕዝቡም ሁሉ ተገረሙና “እንጃ ይህ ሰው የዳዊት ልጅ ይሆንን?” አሉ።</verse>
				<verse number="24">ፈሪሳውያን ግን ሰምተው “ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም፤” አሉ።</verse>
				<verse number="25">ኢየሱስ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው “እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁላ ትጠፋለች፤” እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማም ሁሉ ወይም ቤት አይቆምም።</verse>
				<verse number="26">ሰይጣንም ሰይጣንን የሚያወጣ ከሆነ፥ እርስ በርሱ ተለያየ፤ እንግዲህ መንግሥቱ እንዴት ትቆማለች?</verse>
				<verse number="27">እኔስ በብዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ ልጆቻችሁ በማን ያወጡአቸዋል? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል።</verse>
				<verse number="28">እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች።</verse>
				<verse number="29">ወይስ ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ እቃውን ሊነጥቀው እንዴት ይችላል? ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል።</verse>
				<verse number="30">ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፤ ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል።</verse>
				<verse number="31">ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ኀጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም።</verse>
				<verse number="32">በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም።</verse>
				<verse number="33">“ዛፍ ከፍሬዋ ትታወቃለችና ዛፍዋን መልካም፥ ፍሬዋንም መልካም አድርጉ፤ ወይም ዛፍዋን ክፉ ፍሬዋንም ክፉ አድርጉ።</verse>
				<verse number="34">እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ለመናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና።</verse>
				<verse number="35">መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል።</verse>
				<verse number="36">እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤</verse>
				<verse number="37">ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ።”</verse>
				<verse number="38">በዚያን ጊዜ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ መለሱና “መምህር ሆይ! ከአንተ ምልክት እንድናይ እንወዳለን፤” አሉ።</verse>
				<verse number="39">እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው “ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፤ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።</verse>
				<verse number="40">ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።</verse>
				<verse number="41">የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፤ እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ።</verse>
				<verse number="42">ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፤ እነሆም ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።</verse>
				<verse number="43">“ርኩስ መንፈስ ግን ከሰው በወጣ ጊዜ፥ ዕረፍት እየፈለገ ውሃ በሌለበት ቦታ ያልፋል፤ አያገኝምም።</verse>
				<verse number="44">በዚያን ጊዜም ‘ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ፤’ ይላል፤ ቢመጣም ባዶ ሆኖ ተጠርጎና አጊጦ ያገኘዋል።</verse>
				<verse number="45">ከዚያ ወዲያ ይሄድና ከእርሱ የከፉትን ሰባት ሌሎችን አጋንንት ከእርሱ ጋር ይወስዳል፤ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያም ሰው ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ይብስበታል። ለዚህ ክፉ ትውልድ ደግሞ እንዲሁ ይሆንበታል።”</verse>
				<verse number="46">ገናም ለሕዝቡ ሲናገር፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር።</verse>
				<verse number="47">አንዱም “እነሆ እናትህና ወንድሞችህ ሊነጋገሩህ ፈልገው በውጭ ቆመዋል፤” አለው።</verse>
				<verse number="48">እርሱ ግን ለነገረው መልሶ “እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው?” አለው።</verse>
				<verse number="49">እጁንም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ “እነሆ እናቴና ወንድሞቼ፤</verse>
				<verse number="50">በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነውና፤” አለ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">በዚያን ቀን ኢየሱስ ከቤት ወጥቶ በባሕር አጠገብ ተቀመጠ፤</verse>
				<verse number="2">እርሱም በታንኳ ገብቶ እስኪቀመጥ ድረስ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ሕዝቡም ሁሉ በወደቡ ቆመው ነበር።</verse>
				<verse number="3">በምሳሌም ብዙ ነገራቸው እንዲህም አላቸው “እነሆ ዘሪ ሊዘራ ወጣ።</verse>
				<verse number="4">እርሱም ሲዘራ አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀ፤ ወፎችም መጥተው በሉት።</verse>
				<verse number="5">ሌላውም ብዙ መሬት በሌለበት በጭንጫ ላይ ወደቀ፤ ጥልቅ መሬትም ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፤</verse>
				<verse number="6">ፀሐይ በወጣ ጊዜ ግን ጠወለገ፥ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ።</verse>
				<verse number="7">ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፤ እሾህም ወጣና አነቀው።</verse>
				<verse number="8">ሌላውም በመልካም መሬት ወደቀ፤ አንዱም መቶ፥ አንዱም ስድሳ፥ አንዱም ሠላሳ ፍሬ ሰጠ።</verse>
				<verse number="9">የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”</verse>
				<verse number="10">ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው “ስለ ምን በምሳሌ ትነግራቸዋለህ?” አሉት።</verse>
				<verse number="11">እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸ “ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።</verse>
				<verse number="12">ላለው ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።</verse>
				<verse number="13">ስለዚህ እያዩ ስለማያዩ እየሰሙም ስለማይሰሙ ስለማያስተውሉም በምሳሌ እነግራቸዋለሁ።</verse>
				<verse number="14">‘መስማት ትሰማላችሁና አታስተውሉም፤ ማየትም ታያላችሁና አትመለከቱም።</verse>
				<verse number="15">በዐይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዐይናቸውንም ጨፍነዋል፤’ የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል።</verse>
				<verse number="16">የእናንተ ግን ዐይኖቻችሁ ስለሚያዩ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ ብፁዓን ናቸው።</verse>
				<verse number="17">እውነት እላችኋለሁ፥ ብዙዎች ነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን ሊያዩ ተመኝተው አላዩም፤ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙም።</verse>
				<verse number="18">“እንግዲህ እናንተ የዘሪውን ምሳሌ ስሙ።</verse>
				<verse number="19">የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ፥ ክፉው ይመጣል፤ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው።</verse>
				<verse number="20">በጭንጫ ላይ የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ ወዲያው በደስታ የሚቀበለው ነው፤</verse>
				<verse number="21">ነገር ግን ለጊዜው ነው እንጂ በእርሱ ሥር የለውም፤ በቃሉ ምክንያትም መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላል።</verse>
				<verse number="22">በእሾህ መካከል የተዘራውም ይህ ቃሉን የሚሰማ ነው፤ የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት መታለል ቃሉን ያንቃል፤ የማያፈራም ይሆናል።</verse>
				<verse number="23">በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው፤ እርሱም ፍሬ ያፈራል፤ አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ያደርጋል።”</verse>
				<verse number="24">ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው፤ እንዲህም አለ “መንግሥተ ሰማያት በእርሻው መልካም ዘርን የዘራን ሰው ትመስላለች።</verse>
				<verse number="25">ሰዎቹ ሲተኙ ግን ጠላቱ መጣና በስንዴው መካከል እንክርዳድን ዘርቶ ሄደ።</verse>
				<verse number="26">ስንዴውም በበቀለና በአፈራ ጊዜ እንክርዳዱ ደግሞ ያን ጊዜ ታየ።</verse>
				<verse number="27">የባለቤቱም ባሮች ቀርበው ‘ጌታ ሆይ! መልካምን ዘር በእርሻህ ዘርተህ አልነበርህምን? እንክርዳዱንስ ከወዴት አገኘ?’ አሉት።</verse>
				<verse number="28">እርሱም ‘ጠላት ይህን አደረገ፤’ አላቸው። ባሮቹም ‘እንግዲህ ሄደን ብንለቅመው ትወዳለህን?’ አሉት።</verse>
				<verse number="29">እርሱ ግን ‘እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከእርሱ ጋር እንዳትነቅሉት አይሆንም።</verse>
				<verse number="30">ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን “እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፤ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ፤” እላለሁ’ አለ።”</verse>
				<verse number="31">ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው፤ እንዲህም አለ “መንግሥተ ሰማያት ሰው ወስዶ በእርሻው የዘራትን የሰናፍጭ ቅንጣት ትመስላለች፤</verse>
				<verse number="32">እርስዋም ከዘር ሁሉ ታንሳለች፤ በአደገች ጊዜ ግን፥ ከአታክልቶች ትበልጣለች የሰማይም ወፎች መጥተው በቅርንጫፎችዋ እስኪሰፍሩ ድረስ ዛፍ ትሆናለች።”</verse>
				<verse number="33">ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፤ እንዲህም አለ “መንግሥተ ሰማያት ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ሴት ወስዳ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።”</verse>
				<verse number="34">ኢየሱስም ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፤ በነቢዩም “በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም።</verse>
				<verse number="35"></verse>
				<verse number="36">በዚያን ጊዜ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው “የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጕምልን፤” አሉት።</verse>
				<verse number="37">እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው “መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ እርሻውም ዓለም ነው፤</verse>
				<verse number="38">መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤</verse>
				<verse number="39">እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፤ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፤ አጫጆችም መላእክት ናቸው።</verse>
				<verse number="40">እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል።</verse>
				<verse number="41">የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፤ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፤</verse>
				<verse number="42">ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።</verse>
				<verse number="43">በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።</verse>
				<verse number="44">“ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፤ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ።</verse>
				<verse number="45">“ደግሞ መንግሥተ ሰማያት መልካምን ዕንቁ የሚሻ ነጋዴን ትመስላለች፤</verse>
				<verse number="46">ዋጋዋም እጅግ የበዛ አንዲት ዕንቁ በአገኘ ጊዜ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ገዛት።</verse>
				<verse number="47">“ደግሞ መንግሥተ ሰማያት ወደ ባሕር የተጣለች ከሁሉም ዐይነት የሰበሰበች መረብን ትመስላለች፤</verse>
				<verse number="48">በሞላችም ጊዜ ወደ ወደቡ አወጡአት፤ ተቀምጠውም መልካሙን ለቅመው በዕቃዎች ውስጥ አከማቹ፤ ክፉውን ግን ወደ ውጭ ጣሉት።</verse>
				<verse number="49">በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል፤ መላእክት መጥተው ኀጢአተኞችን ከጻድቃን መካከል ይለዩአቸዋል፤ ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤</verse>
				<verse number="50">በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”</verse>
				<verse number="51">ኢየሱስም “ይህን ሁሉ አስተዋላችሁን?” አላቸው፤ “አዎን” አሉት።</verse>
				<verse number="52">እርሱም “ስለዚህ የመንግሥተ ሰማያት ደቀ መዝሙር የሆነ ጻፊ ሁሉ ከመዝገቡ አዲሱንና አሮጌውን የሚያወጣ ባለቤትን ይመስላል፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="53">ኢየሱስም እነዚህም ምሳሌዎች ከጨረሰ በኋላ ከዚያ ሄደ።</verse>
				<verse number="54">ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በምኩራባቸው ያስተምራቸው ነበር፤ እንዲህም አሉ “ይህን ጥበብና ተአምራት ይህ ከወዴት አገኘው?</verse>
				<verse number="55">ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ፥ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን?</verse>
				<verse number="56">እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው?” ተሰናከሉበትም።</verse>
				<verse number="57">ኢየሱስ ግን “ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤቱ በቀር ሳይከበር አይቀርም፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="58">በአለማመናቸውም ምክንያት በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">በዚያ ዘመን የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስ የኢየሱስን ዝና ሰማ፤</verse>
				<verse number="2">ለሎሌዎቹም “ይህ መጥምቁ ዮሐንስ ነው፤ እርሱ ከሙታን ተነሥቶአል፤ ስለዚህም ኃይል በእርሱ ይደረጋል፤” አለ።</verse>
				<verse number="3">ሄሮድስ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን አስይዞ አሳስሮት በወህኒ አኑሮት ነበርና፤</verse>
				<verse number="4">ዮሐንስ “እርስዋ ለአንተ ትሆን ዘንድ አልተፈቀደም፤” ይለው ነበርና።</verse>
				<verse number="5">ሊገድለውም ወዶ ሳለ፥ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስለ አዩት ፈራቸው።</verse>
				<verse number="6">ነገር ግን ሄሮድስ የተወለደበት ቀን በሆነ ጊዜ፥ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከላቸው ዘፈነች፤ ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው፤</verse>
				<verse number="7">ስለዚህም የምትለምነውን ሁሉ እንዲሰጣት በመሐላ ተስፋ አደረገላት።</verse>
				<verse number="8">እርስዋም በእናትዋ ተመክራ “የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ በዚህ በወጭት ስጠኝ፤” አለችው።</verse>
				<verse number="9">ንጉሡም አዘነ፤ ነገር ግን ስለ መሐላው ከእርሱም ጋር ተቀምጠው ስላሉት ሰዎች እንዲሰጡአት፤ አዘዘ፤</verse>
				<verse number="10">ልኮም የዮሐንስን ራስ በወህኒ አስቆረጠው።</verse>
				<verse number="11">ራሱንም በወጭት አምጥተው ለብላቴናይቱ ሰጡአት፤ ወደ እናትዋም ወሰደችው።</verse>
				<verse number="12">ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው በድኑን ወሰዱና ቀበሩት፤ መጥተውም ለኢየሱስ አወሩለት።</verse>
				<verse number="13">ኢየሱስም በሰማ ጊዜ ከዚያ ብቻውን ወደ ምድረ በዳ በታንኳ ፈቀቅ አለ፤ ሕዝቡም ሰምተው ከከተማዎቹ በእግር ተከተሉት።</verse>
				<verse number="14">ወጥቶም ብዙ ሕዝብ አየና አዘነላቸው፤ ድውዮቻቸውንም ፈወሰ።</verse>
				<verse number="15">በመሸም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው “ቦታው ምድረ በዳ ነው፤ አሁንም ሰዓቱ አልፎአል፤ ወደ መንደሮች ሄደው ለራሳቸው ምግብ እንዲገዙ ሕዝቡን አሰናብት፤” አሉት።</verse>
				<verse number="16">ኢየሱስም “እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው እንጂ ሊሄዱ አያስፈልግም፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="17">እነርሱም “ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ በቀር በዚህ የለንም፤” አሉት።</verse>
				<verse number="18">እርሱም “እነዚያን ወደዚህ አምጡልኝ፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="19">ሕዝቡም በሣር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፤ አምስቱንም እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና ባረከ፤ እንጀራውንም ቆርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ።</verse>
				<verse number="20">ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ የተረፈውንም ቁርስራሽ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ አነሡ።</verse>
				<verse number="21">ከሴቶችና ከልጆችም በቀር የበሉት አምስት ሺህ ወንዶች ያህሉ ነበር።</verse>
				<verse number="22">ወዲያውም ሕዝቡን ሲያሰናብት ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ በታንኳይቱ ገብተው ወደ ማዶ እንዲቀድሙት ግድ አላቸው።</verse>
				<verse number="23">ሕዝቡንም አሰናብቶ ይጸልይ ዘንድ ብቻውን ወደ ተራራ ወጣ። በመሸም ጊዜ ብቻውን በዚያ ነበረ።</verse>
				<verse number="24">ታንኳይቱም አሁን በባሕር መካከል ሳለች፥ ነፋስ ከወደ ፊት ነበርና በማዕበል ትጨነቅ ነበር።</verse>
				<verse number="25">ከሌሊቱም በአራተኛው ክፍል ኢየሱስ በባሕር ላይ እየሄደ ወደ እነርሱ መጣ።</verse>
				<verse number="26">ደቀ መዛሙርቱም በባሕር ላይ ሲሄድ ባዩት ጊዜ “ምትሐት ነው” ብለው ታወኩ፤ በፍርሃትም ጮኹ።</verse>
				<verse number="27">ወዲያውም ኢየሱስ ተናገራቸውና “አይዞአችሁ፤ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="28">ጴጥሮስም መልሶ “ጌታ ሆይ! አንተስ ከሆንህ በውሃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ፤” አለው።</verse>
				<verse number="29">እርሱም፦ ና አለው። ጴጥሮስም ከታንኳይቱ ወርዶ ወደ ኢየሱስ ሊደርስ በውሃው ላይ ሄደ።</verse>
				<verse number="30">ነገር ግን የነፋሱን ኃይል አይቶ ፈራ፤ ሊሰጥምም በጀመረ ጊዜ “ጌታ ሆይ! አድነኝ፤” ብሎ ጮኸ።</verse>
				<verse number="31">ወዲያውም ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘውና “አንተ እምነት የጎደለህ፤ ስለምን ተጠራጠርህ?” አለው።</verse>
				<verse number="32">ወደ ታንኳይቱም በወጡ ጊዜ ነፋሱ ተወ።</verse>
				<verse number="33">በታንኳይቱም የነበሩት “በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤” ብለው ሰገዱለት።</verse>
				<verse number="34">ተሻግረውም ወደ ጌንሴሬጥ ምድር መጡ።</verse>
				<verse number="35">የዚያ ቦታ ሰዎችም ባወቁት ጊዜ በዙርያው ወዳለ አገር ሁሉ ላኩ፤ ሕመምተኞችንም ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤</verse>
				<verse number="36">የልብሱንም ጫፍ ብቻ ሊዳስሱ ይለምኑት ነበር፤ የዳሰሱትም ሁሉ ዳኑ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">በዚያን ጊዜ ጻፎችና ፈሪሳውያን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢየሱስ ቀረቡና</verse>
				<verse number="2">“ደቀ መዛሙርትህ ስለ ምን የሽማግሎችን ወግ ይተላለፋሉ? እንጀራ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡምና፤” አሉት።</verse>
				<verse number="3">እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው “እናንተስ ስለ ወጋችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለ ምን ትተላለፋላችሁ?</verse>
				<verse number="4">እግዚአብሔር ‘አባትህንና እናትህን አክብር፤’ ደግሞ ‘አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት፤’ ብሎአልና፤</verse>
				<verse number="5">እናንተ ግን ‘አባቱን ወይም እናቱን “ከእኔ የምትጠቀምበት መባ ነው የሚል ሁሉ፥</verse>
				<verse number="6">አባቱን ወይም እናቱን አያከብርም፤” ትላላችሁ፤’ ስለ ወጋችሁም የእግዚአብሔርን ቃል ሻራችሁ።</verse>
				<verse number="7">እናንተ ግብዞች፥ ኢሳይያስ ስለ እናንተ</verse>
				<verse number="8">‘ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤</verse>
				<verse number="9">የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል፤’ ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።”</verse>
				<verse number="10">ሕዝቡንም ጠርቶ “ስሙ አስተውሉም፤</verse>
				<verse number="11">ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም፤ ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="12">በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው “ፈሪሳውያን ይህን ቃል ሰምተው እንደ ተሰናከሉ አወቅህን?” አሉት።</verse>
				<verse number="13">እርሱ ግን መልሶ “የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል።</verse>
				<verse number="14">ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ፤” አለ።</verse>
				<verse number="15">ጴጥሮስም መልሶ “ምሳሌውን ተርጕምልን፤” አለው።</verse>
				<verse number="16">ኢየሱስም እንዲህ አለ “እናንተ ደግሞ እስካሁን የማታስተውሉ ናችሁን?</verse>
				<verse number="17">ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ እንዲጣል አትመለከቱምን?</verse>
				<verse number="18">ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል፤ ሰውንም የሚያረክሰው ያ ነው።</verse>
				<verse number="19">ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና።</verse>
				<verse number="20">ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው እንጂ፥ ባልታጠበ እጅ መብላትስ ሰውን አያረክሰውም።”</verse>
				<verse number="21">ኢየሱስም ከዚያ ወጥቶ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና አገር ሄደ።</verse>
				<verse number="22">እነሆም ከነናዊት ሴት ከዚያ አገር ወጥታ “ጌታ ሆይ! የዳዊት ልጅ ማረኝ፤ ልጄን ጋኔን ክፉኛ ይዞአታል፤” ብላ ጮኸች።</verse>
				<verse number="23">እርሱ ግን አንዳች አልመለሰላትም። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው “በኋላችን ትጮኻለችና አሰናብታት፤” እያሉ ለመኑት።</verse>
				<verse number="24">እርሱም መልሶ “ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም፤” አለ።</verse>
				<verse number="25">እርስዋ ግን መጥታ “ጌታ ሆይ! እርዳኝ፤” እያለች ሰገደችለት።</verse>
				<verse number="26">እርሱ ግን መልሶ “የልጆችን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባም፤” አለ።</verse>
				<verse number="27">እርስዋም “አዎን ጌታ ሆይ! ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ፤” አለች።</verse>
				<verse number="28">በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ “አንቺ ሴት፥ እምነትሽ ታላቅ ነው፤ እንደወደድሽ ይሁንልሽ፤” አላት። ልጅዋም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ዳነች።</verse>
				<verse number="29">ኢየሱስም ከዚያ አልፎ ወደ ገሊላ ባሕር አጠገብ መጣ፤ ወደ ተራራም ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ።</verse>
				<verse number="30">ብዙ ሕዝብም አንካሶችን፥ ዕውሮችንም፥ ድዳዎችንም፥ ጉንድሾችንም፥ ሌሎችንም ብዙ ይዘው ወደ እርሱ ቀረቡ በኢየሱስም እግር አጠገብ አስቀመጡአቸው፤ ፈወሳቸውም፤</verse>
				<verse number="31">ስለዚህም ሕዝቡ ድዳዎች ሲናገሩ፥ ጉንድሾችም ሲድኑ፥ አንካሶችም ሲሄዱ፥ ዕውሮችም ሲያዩ አይተው ተደነቁ፤ የእስራኤልንም አምላክ አከበሩ።</verse>
				<verse number="32">ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ “ሕዝቡ ከእኔ ጋር እስካሁን ሦስት ቀን ውለዋልና የሚበሉት ስለሌላቸው አዝንላቸዋለሁ፤ በመንገድም እንዳይዝሉ ጦማቸውን ላሰናብታቸው አልወድም፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="33">ደቀ መዛሙርቱም “ይህን ያህል ሕዝብ የሚያጠግብ ይህን ያህል እንጀራ በምድረ በዳ ከወዴት እናገኛለን?” አሉት።</verse>
				<verse number="34">ኢየሱስም “ስንት እንጀራ አላችሁ?” አላቸው። እነርሱም “ሰባት፥ ጥቂትም ትንሽ ዓሣ” አሉት።</verse>
				<verse number="35">ሕዝቡም በምድር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፤</verse>
				<verse number="36">ሰባቱንም እንጀራ ዓሣውንም ይዞ አመሰገነ፤ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ።</verse>
				<verse number="37">ሁሉም በሉና ጠገቡ፤ የተረፈውንም ቁርስራሽ ሰባት ቅርጫት ሙሉ አነሡ።</verse>
				<verse number="38">የበሉትም ከሴቶችና ከልጆች በቀር አራት ሺህ ወንዶች ነበሩ።</verse>
				<verse number="39">ሕዝቡንም ካሰናበተ በኋላ ወደ ታንኳይቱ ገብቶ ወደ መጌዶል አገር መጣ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያንም ቀርበው ሲፈትኑት ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ለመኑት።</verse>
				<verse number="2">እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው “በመሸ ጊዜ ‘ሰማዩ ቀልቶአልና ብራ ይሆናል’ ትላላችሁ።</verse>
				<verse number="3">ማለዳም ‘ሰማዩ ደምኖ ቀልቶአልና ዛሬ ይዘንባል’ ትላላችሁ። የሰማዩን ፊትማ መለየት ታውቃላችሁ፤ የዘመኑንስ ምልክት መለየት አትችሉምን?</verse>
				<verse number="4">ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፤ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።” ትቶአቸውም ሄደ።</verse>
				<verse number="5">ደቀ መዛሙርቱም ወደ ማዶ በመጡ ጊዜ እንጀራ መያዝን ረሱ።</verse>
				<verse number="6">ኢየሱስም “ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁና ተጠበቁ፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="7">እነርሱም “እንጀራ ባንይዝ ነው፤” ብለው እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ።</verse>
				<verse number="8">ኢየሱስም አውቆ እንዲህ አላቸው “እናንተ እምነት የጐደላችሁ፥ እንጀራ ስለ ሌላችሁ ስለ ምን እርስ በርሳችሁ ትነጋገራላችሁ? ገና አታስተውሉምን?</verse>
				<verse number="9">ለአምስቱ ሺህ አምስቱ እንጀራ፥ ስንት መሶብም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን?</verse>
				<verse number="10">ወይስ ለአራቱ ሺህ ሰባቱ እንጀራ፥ ስንት ቅርጫትም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን?</verse>
				<verse number="11">ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ እንድትጠበቁ ብዬ ስለ እንጀራ እንዳልተናገርኋችሁ እንዴት አታስተውሉም?”</verse>
				<verse number="12">እነርሱም ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ትምህርት እንጂ ከእንጀራ እርሾ እንዲጠበቁ እንዳላላቸው ያን ጊዜ አስተዋሉ።</verse>
				<verse number="13">ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን “ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል?” ብሎ ጠየቀ።</verse>
				<verse number="14">እነርሱም “አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው፤” ይላሉ አሉት።</verse>
				<verse number="15">እርሱም “እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ?” አላቸው።</verse>
				<verse number="16">ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ፤” አለ።</verse>
				<verse number="17">ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።</verse>
				<verse number="18">እኔም እልሃለሁ፤ አንተ ጴጥሮስ ነህ፤ በዚችም ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።</verse>
				<verse number="19">የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፤ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።”</verse>
				<verse number="20">ያን ጊዜም እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ለማንም እንዳይነግሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው።</verse>
				<verse number="21">ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር።</verse>
				<verse number="22">ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ “አይሁንብህ ጌታ ሆይ! ይህ ከቶ አይደርስብህም፤” ብሎ ሊገሥጸው ጀመረ።</verse>
				<verse number="23">እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን “ወደ ኋላዬ ሂድ፤ አንተ ሰይጣን! የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና፥ ዕንቅፋት ሆነህብኛል፤” አለው።</verse>
				<verse number="24">በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ “እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።</verse>
				<verse number="25">ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል።</verse>
				<verse number="26">ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?</verse>
				<verse number="27">የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል።</verse>
				<verse number="28">እውነት እላችኋለሁ፥ የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ እዚህ ከሚቆሙት ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።</verse>
				<verse number="2">በፊታቸውም ተለወጠ፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፤ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።</verse>
				<verse number="3">እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው።</verse>
				<verse number="4">ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን፦ “ጌታ ሆይ! በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ፤” አለ።</verse>
				<verse number="5">እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆም፥ ከደመናው “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ።</verse>
				<verse number="6">ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ፤ እጅግም ፈርተው ነበር።</verse>
				<verse number="7">ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና “ተነሡ፤ አትፍሩም፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="8">ዐይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም።</verse>
				<verse number="9">ከተራራውም በወረዱ ጊዜ ኢየሱስ “የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ፤” ብሎ አዘዛቸው።</verse>
				<verse number="10">ደቀ መዛሙርቱም “እንግዲህ ጻፎች ‘ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ ይገባዋል፤’ ስለ ምን ይላሉ?” ብለው ጠየቁት።</verse>
				<verse number="11">ኢየሱስም መልሶ “ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል፤ ሁሉንም ያቀናል፤</verse>
				<verse number="12">ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ኤልያስ ከዚህ በፊት መጣ፤ የወደዱትንም ሁሉ አደረጉበት እንጂ አላወቁትም፤ እንዲሁም ደግሞ የሰው ልጅ ከእነርሱ መከራ ይቀበል ዘንድ አለው፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="13">በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለ መጥምቁ ስለ ዮሐንስ እንደ ነገራቸው አስተዋሉ።</verse>
				<verse number="14">ወደ ሕዝቡም ሲደርሱ አንድ ሰው ወደ እርሱ ቀረበና ተንበርክኮ</verse>
				<verse number="15">“ጌታ ሆይ! ልጄን ማርልኝ፥ በጨረቃ እየተነሣበትክፉኛ ይሣቀያልና፤ ብዙ ጊዜ በእሳት ብዙ ጊዜም በውሃ ይወድቃልና።</verse>
				<verse number="16">ወደ ደቀ መዛሙርትህም አመጣሁት ሊፈውሱትም አቃታቸው፤” አለው።</verse>
				<verse number="17">ኢየሱስም መልሶ “የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደዚህ ወደ እኔ አምጡት፤” አለ።</verse>
				<verse number="18">ኢየሱስም ገሠጸው፤ ጋኔኑም ከእርሱ ወጣ፤ ብላቴናውም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ተፈወሰ።</verse>
				<verse number="19">ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ብቻቸውን ወደ ኢየሱስ ቀረቡና “እኛ ልናወጣው ያልቻልን ስለ ምን ነው?” አሉት።</verse>
				<verse number="20">ኢየሱስም “ስለ እምነታችሁ ማነስ ነው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ ‘ከዚህ ወደዚያ እለፍ፤’ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም።</verse>
				<verse number="21">ይህ ዐይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="22">በገሊላም ሲመላለሱ ኢየሱስ “የሰው ልጅ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጥ ዘንድ አለው፤ ይገድሉትማል፤</verse>
				<verse number="23">በሦስተኛውም ቀን ይነሣል፤” አላቸው። እጅግም አዘኑ።</verse>
				<verse number="24">ወደ ቅፍርናሆምም በመጡ ጊዜ ግብር የሚቀበሉ ሰዎች ወደ ጴጥሮስ ቀረቡና “መምህራችሁ ሁለቱን ዲናር አይገብርምን?” አሉት።</verse>
				<verse number="25">“አዎን ይገብራል” አለ። ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ኢየሱስ አስቀድሞ “ስምዖን ሆይ! ምን ይመስልሃል? የምድር ነገሥታት ቀረጥና ግብር ከማን ይቀበላሉ? ከልጆቻቸው? ወይስ ከእንግዶች?” አለው።</verse>
				<verse number="26">ጴጥሮስም “ከእንግዶች” ባለው ጊዜ ኢየሱስ “እንኪያስ ልጆቻቸው ነጻ ናቸው።</verse>
				<verse number="27">ነገር ግን እንዳናሰናክላቸው፥ ወደ ባሕር ሂድና መቃጥን ጣል፤ መጀመሪያም የሚወጣውን ዓሣ ውሰድና አፉን ስትከፍት እስታቴር ታገኛለህ፤ ያን ወስደህ ስለ እኔና ስለ አንተ ስጣቸው፤” አለው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">በዚያች ሰዓት ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው “በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን?” አሉት።</verse>
				<verse number="2">ሕፃንም ጠርቶ በመካከላቸው አቆመ፤</verse>
				<verse number="3">እንዲህም አለ “እውነት እላችኋለሁ፥ ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።</verse>
				<verse number="4">እንግዲህ እንደዚህ ሕፃን ራሱን የሚያዋርድ ሁሉ፥ በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጥ እርሱ ነው።</verse>
				<verse number="5">“እንደዚህም ያለውን አንድ ሕፃን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤</verse>
				<verse number="6">በእኔም ከሚያምኑ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ፥ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ይሻለው ነበር።</verse>
				<verse number="7">“ወዮ ለዓለም ስለ ማሰናከያ፤ ማሰናከያ ሳይመጣ አይቀርምና፤ ነገር ግን በእርሱ ጠንቅ ማሰናከያ ለሚመጣበት ለዚያ ሰው ወዮለት!</verse>
				<verse number="8">እጅህ ወይም እግርህ ብታሰናክልህ፥ ቈርጠህ ከአንተ ጣላት፤ ሁለት እጅ ወይም ሁለት እግር ኖሮህ ወደ ዘላለም እሳት ከምትጣል ይልቅ አንካሳ ወይም ጕንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሀል።</verse>
				<verse number="9">ዐይንህ ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነመ እሳት ከምትጣል ይልቅ አንዲት ዐይን ኖራህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል።</verse>
				<verse number="10">“ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና።</verse>
				<verse number="11">የሰው ልጅ የጠፋውን ለማዳን መጥቶአልና።</verse>
				<verse number="12">“ምን ይመስላችኋል? ለአንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩት ከእነርሱም አንዱ ቢባዝን፥ ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ትቶ ሄዶም የባዘነውን አይፈልግምን?</verse>
				<verse number="13">ቢያገኘውም፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ካልባዘኑቱ ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእርሱ ደስ ይለዋል።</verse>
				<verse number="14">እንደዚሁ ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱ እንዲጠፋ በሰማያት ያለው አባታችሁ ፈቃድ አይደለም።</verse>
				<verse number="15">“ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤</verse>
				<verse number="16">ባይሰማህ ግን፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፥ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ፤</verse>
				<verse number="17">እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ።</verse>
				<verse number="18">እውነት እላችኋለሁ፥ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል።</verse>
				<verse number="19">ደግሞ እላችኋለሁ፥ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ፥ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል።</verse>
				<verse number="20">ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።”</verse>
				<verse number="21">በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ወደ እርሱ ቀርቦ “ጌታ ሆይ! ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት? እስከ ሰባት ጊዜን?” አለው።</verse>
				<verse number="22">ኢየሱስ እንዲህ አለው “እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ አልልህም።</verse>
				<verse number="23">“ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ባሮቹን ሊቈጣጠር የወደደን ንጉሥ ትመስላለች።</verse>
				<verse number="24">መቈጣጠርም በጀመረ ጊዜ፥ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ።</verse>
				<verse number="25">የሚከፍለውም ቢያጣ፥ እርሱና ሚስቱ ልጆቹም ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ።</verse>
				<verse number="26">ስለዚህ ባሪያው ወድቆ ሰገደለትና ‘ጌታ ሆይ! ታገሠኝ፤ ሁሉንም እከፍልሃለሁ፤’ አለው።</verse>
				<verse number="27">የዚያም ባሪያ ጌታ አዘነለትና ለቀቀው፤ ዕዳውንም ተወለት።</verse>
				<verse number="28">ነገር ግን ያ ባሪያ ወጥቶ ከባልንጀሮቹ ከባሮቹ መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን አንዱን አገኘና ‘ዕዳህን ክፈለኝ’ ብሎ ያዘና አነቀው።</verse>
				<verse number="29">ስለዚህ ባልንጀራው ባሪያ ወድቆ ‘ታገሠኝ፤ ሁሉንም እከፍልሃለሁ፤’ ብሎ ለመነው።</verse>
				<verse number="30">እርሱም አልወደደም፤ ግን ሄዶ ዕዳውን እስኪከፍል ድረስ በወኅኒ አኖረው።</verse>
				<verse number="31">ባልንጀሮቹ የሆኑ ባሮችም ያደረገውን አይተው እጅግ አዘኑ፤ መጥተውም የሆነውን ሁሉ ለጌታቸው ገለጡ።</verse>
				<verse number="32">ከዚያ ወዲያ ጌታው ጠርቶ ‘አንተ ክፉ ባሪያ፥ ስለ ለመንኸኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤</verse>
				<verse number="33">እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን?’ አለው።</verse>
				<verse number="34">ጌታውም ተቈጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው ድረስ ለሚሣቅዩት አሳልፎ ሰጠው።</verse>
				<verse number="35">ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ፥ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርግባችኋል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">ኢየሱስም ይህን ነገር ከፈጸመ በኋላ፥ ከገሊላ ሄዶ ወደ ይሁዳ አውራጃ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ መጣ።</verse>
				<verse number="2">ብዙ ሕዝብም ተከተሉት፤ በዚያም ፈወሳቸው።</verse>
				<verse number="3">ፈሪሳውያንም ወደ እርሱ ቀረቡና ሲፈትኑት “ሰው በሆነው ምክንያት ሁሉ ሚስቱን ሊፈታ ተፈቅዶለታልን?” አሉት።</verse>
				<verse number="4">እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አለ “ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው፤</verse>
				<verse number="5">አለም ‘ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ፤’ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን?</verse>
				<verse number="6">ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው።”</verse>
				<verse number="7">እነርሱም “እንኪያስ ሙሴ የፍችዋን ጽሕፈት ሰጥተው እንዲፈቱአት ስለ ምን አዘዘ?” አሉት።</verse>
				<verse number="8">እርሱም “ሙሴስ ስለ ልባችሁ ጥንካሬ ሚስቶቻችሁን ትፈቱ ዘንድ ፈቀደላችሁ፤ ከጥንት ግን እንዲህ አልነበረም።</verse>
				<verse number="9">እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን ፈትቶ ሌላዪቱን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፤ የተፈታችውንም የሚያገባ ያመነዝራል፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="10">ደቀ መዛሙርቱም “የባልና የሚስት ሥርዐት እንዲህ ከሆነ መጋባት አይጠቅምም፤” አሉት።</verse>
				<verse number="11">እርሱ ግን “ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም፤</verse>
				<verse number="12">በእናት ማኅፀን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ፤ ሰውም የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ፤ ስለ መንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ። ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው አላቸው።”</verse>
				<verse number="13">በዚያን ጊዜ እጁን እንዲጭንባቸውና እንዲጸልይ ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ገሠጹአቸው።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን ኢየሱስ “ሕፃናትን ተዉአቸው፤ ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉ ናትና” አለ፤</verse>
				<verse number="15">እጁንም ጫነባቸውና ከዚያ ሄደ።</verse>
				<verse number="16">እነሆም፥ አንድ ሰው ቀርቦ “መምህር ሆይ! የዘላለምን ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ላድርግ” አለው።</verse>
				<verse number="17">እርሱም “ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ፤” አለው።</verse>
				<verse number="18">እርሱም “የትኞችን?” አለው። ኢየሱስም “አትግደል፥ አታመንዝር፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥</verse>
				<verse number="19">አባትህንና እናትህንአክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው።”</verse>
				<verse number="20">ጐበዙም “ይህንማ ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ፤ ደግሞስ የሚጐድለኝ ምንድር ነው?” አለው።</verse>
				<verse number="21">ኢየሱስም “ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፤ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፤ መጥተህም ተከተለኝ፤” አለው።</verse>
				<verse number="22">ጐበዙም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነ ሄደ።</verse>
				<verse number="23">ኢየሱስም ለደቀ መዛሙርቱ “እውነት እላችኋለሁ፥ ለባለጠጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ጭንቅ ነው።</verse>
				<verse number="24">ዳግመኛም እላችኋለሁ፤ ባለጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል፤” አለ።</verse>
				<verse number="25">ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው እጅግ ተገረሙና “እንኪያስ ማን ሊድን ይችላል?” አሉ።</verse>
				<verse number="26">ኢየሱስም እነርሱን ተመልክቶ “ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="27">በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ “እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤ እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን?” አለው።</verse>
				<verse number="28">ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በዐሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ።</verse>
				<verse number="29">ስለ ስሜም ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል፤ የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል።</verse>
				<verse number="30">ነገር ግን ብዙዎቹ ፊተኞች ኋለኞች፥ ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">“መንግሥተ ሰማያት ለወይኑ አትክልት ሠራተኞችን ሊቀጥር ማልዶ የወጣ ባለቤት ሰውን ትመስላለችና።</verse>
				<verse number="2">ሠራተኞችንም በቀን አንድ ዲናር ተስማምቶ ወደ ወይኑ አትክልት ሰደዳቸው።</verse>
				<verse number="3">በሦስት ሰዓትም ወጥቶ ሥራ የፈቱ ሌሎችን በአደባባይ ቆመው አየ፤</verse>
				<verse number="4">እነዚያንም ‘እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ፤ የሚገባውንም እሰጣችኋለሁ፤’ አላቸው። እነርሱም ሄዱ።</verse>
				<verse number="5">ደግሞም በስድስትና በዘጠኝ ሰዓት ወጥቶ እንዲሁ አደረገ።</verse>
				<verse number="6">በአሥራ አንደኛውም ሰዓት ወጥቶ ሌሎችን ቆመው አገኘና ‘ሥራ ፈትታችሁ ቀኑን ሁሉ በዚህ ስለ ምን ትቆማላችሁ?’ አላቸው።</verse>
				<verse number="7">‘የሚቀጥረን ስለ አጣን ነው፤’ አሉት። እርሱም ‘እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ የሚገባውንም ትቀበላላችሁ፤’ አላቸው።</verse>
				<verse number="8">በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ጌታ አዛዡን ‘ሠራተኞችን ጥራና ከኋለኞች ጀምረህ እስከ ፊተኞች ድረስ ደመወዝ ስጣቸው፤’ አለው።</verse>
				<verse number="9">በአሥራ አንደኛው ሰዓትም የገቡ መጥተው እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ።</verse>
				<verse number="10">ፊተኞችም በመጡ ጊዜ አብዝተው የሚቀበሉ መስሎአቸው ነበር፤ እነርሱም ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ።</verse>
				<verse number="11">ተቀብለውም ‘እነዚህ ኋለኞች አንድ ሰዓት ሠሩ፤ የቀኑንም ድካምና ትኩሳት ከተሸከምን ከእኛ ጋር አስተካከልሃቸው፤’ ብለው በባለቤቱ ላይ አንጕኦራጕኦሩ።</verse>
				<verse number="12"></verse>
				<verse number="13">እርሱ ግን መልሶ ከእነርሱ ለአንዱ እንዲህ አለው ‘ወዳጄ ሆይ! አልበደልሁህም በአንድ ዲናር አልተስማማኸኝምን?</verse>
				<verse number="14">ድርሻህን ውሰድና ሂድ፤ እኔ ለዚህ ለኋለኛው እንደ አንተ ልሰጠው እወዳለሁ፤ በገንዘቤ የወደድሁትን አደርግ ዘንድ መብት የለኝምን?</verse>
				<verse number="15">ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንሁ ዐይንህ ምቀኛ ናትን?</verse>
				<verse number="16">እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።’ ”</verse>
				<verse number="17">ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ሊወጣ ሳለ፥ በመንገድ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ብቻቸውን ወደ እርሱ አቅርቦ</verse>
				<verse number="18">“እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች ይሰጣል፤ የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል፤</verse>
				<verse number="19">ሊዘባበቱበትም ሊገርፉትም ሊሰቅሉትም ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="20">በዚያን ጊዜ የዘብዴዎስ ልጆች እናት ከልጆችዋ ጋር እየሰገደችና አንድ ነገር እየለመነች ወደ እርሱ ቀረበች።</verse>
				<verse number="21">እርሱም “ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት። እርስዋም “እነዚህ ሁለቱ ልጆቼ አንዱ በቀኝህ አንዱም በግራህ በመንግሥትህ እንዲቀመጡ እዘዝ፤” አለችው።</verse>
				<verse number="22">ኢየሱስ ግን መልሶ “የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ ልጠጣው ያለውን ጽዋ ልትጠጡ እኔም የምጠመቀውን ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን?” አለ። “እንችላለን” አሉት።</verse>
				<verse number="23">እርሱም “ጽዋዬንስ ትጠጣላችሁ፤ በቀኝና በግራ መቀመጥ ግን ከአባቴ ዘንድ ለተዘጋጀላቸው ነው እንጂ እኔ የምሰጥ አይደለሁም፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="24">ዐሥሩም ሰምተው በሁለቱ ወንድማማች ተቍኦጡ።</verse>
				<verse number="25">ኢየሱስ ግን ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው “የአሕዛብ አለቆች እንዲገዙአቸው ታላላቆቹም በላያቸው እንዲሠለጥኑ ታውቃላችሁ።</verse>
				<verse number="26">በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፤</verse>
				<verse number="27">ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የእናንተ ባሪያ ይሁን፤</verse>
				<verse number="28">እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”</verse>
				<verse number="29">ከኢያሪኮም ሲወጡ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት።</verse>
				<verse number="30">እነሆም፥ ሁለት ዕውሮች በመንገድ ዳር ተቀምጠው፥ ኢየሱስ እንዲያልፍ በሰሙ ጊዜ “ጌታ ሆይ! የዳዊት ልጅ፥ ማረን” ብለው ጮኹ።</verse>
				<verse number="31">ሕዝቡም ዝም እንዲሉ ገሠጹአቸው፤ እነርሱ ግን “ጌታ ሆይ! የዳዊት ልጅ፥ ማረን” እያሉ አብዝተው ጮኹ።</verse>
				<verse number="32">ኢየሱስም ቆሞ ጠራቸውና “ምን ላደርግላችሁ ትወዳላችሁ?” አለ።</verse>
				<verse number="33">“ጌታ ሆይ! ዐይኖቻችን ይከፈቱ ዘንድ” አሉት።</verse>
				<verse number="34">ኢየሱስም አዘነላቸውና ዐይኖቻቸውን ዳሰሰ፤ ወዲያውም አዩና ተከተሉት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">ወደ ኢየሩሳሌምም ቀርበው ወደ ደብረዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ፥ ያን ጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከ፤</verse>
				<verse number="2">እንዲህም አላቸው “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፤ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርስዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ።</verse>
				<verse number="3">ማንም አንዳች ቢላችሁ ‘ለጌታ ያስፈልጉታል፤’ በሉ፤ ወዲያውም ይሰዳቸዋል።”</verse>
				<verse number="4">“ለጽዮን ልጅ ‘እነሆ፥ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፤’ በሉአት።” ተብሎ በነቢይ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ።</verse>
				<verse number="5"></verse>
				<verse number="6">ደቀ መዛሙርቱም ሄደው ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤</verse>
				<verse number="7">አህያይቱንና ውርንጫዋንም አመጡለት፤ ልብሳቸውንም በእነርሱ ላይ ጫኑ፤ ተቀመጠባቸውም።</verse>
				<verse number="8">ከሕዝቡም እጅግ ብዙዎች ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፤ ሌሎችም ከዛፍ ጫፍ ጫፉን እየቍኦረጡ በመንገድ ላይ ያነጥፉ ነበር።</verse>
				<verse number="9">የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሣዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር።</verse>
				<verse number="10">ወደ ኢየሩሳሌምም በገባ ጊዜ መላው ከተማ “ይህ ማን ነው?” ብሎ ተናወጠ።</verse>
				<verse number="11">ሕዝቡም “ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ነው፤” አሉ።</verse>
				<verse number="12">ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አስወጣ፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና</verse>
				<verse number="13">“ ‘ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤’ ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="14">በመቅደስም ዕውሮችና አንካሶች ወደ እርሱ ቀረቡና ፈወሳቸው።</verse>
				<verse number="15">ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ!” እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው</verse>
				<verse number="16">“እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን?” አሉት። ኢየሱስም “እሰማለሁ፤ ‘ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ፤’ የሚለውን ቃል ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው።</verse>
				<verse number="17">ትቶአቸውም ከከተማ ወደ ቢታንያ ወጣ፤ በዚያም አደረ።</verse>
				<verse number="18">በማለዳም ወደ ከተማ ሲመለስ ተራበ።</verse>
				<verse number="19">በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና “ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ፤” አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች።</verse>
				<verse number="20">ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው “በለሲቱ ያንጊዜውን እንዴት ደረቀች?” ብለው ተደነቁ።</verse>
				<verse number="21">ኢየሱስም መልሶ “እውነት እላችኋለሁ፤ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩም፥ በበለሲቱ እንደ ሆነባት ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ እንኳ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር፤’ ብትሉት ይሆናል፤</verse>
				<verse number="22">አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="23">ወደ መቅደስም ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሎች ወደ እርሱ ቀረቡና “በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?” አሉት።</verse>
				<verse number="24">ኢየሱስም መልሶ “እኔ ደግሞ አንዲት ነገር እጠይቃችኋለሁ፤ እናንተም ያችን ብትነግሩኝ እኔ ደግሞ እነዚህን በምን ሥልጣን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ፤</verse>
				<verse number="25">የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይ ወይስ ከሰው?” አላቸው። እነርሱም እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ “ ‘ከሰማይ’ ብንል ‘እንኪያስ ስለ ምን አላመናችሁበትም?’ ይለናል፤</verse>
				<verse number="26">‘ከሰው’ ግን ብንል፥ ዮሐንስን ሁሉም እንደ ነቢይ ያዩታልና ሕዝቡን እንፈራለን” አሉ።</verse>
				<verse number="27">ለኢየሱስም መልሰው “አናውቅም” አሉት። እርሱም ደግሞ “እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ አልነግራችሁም፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="28">“ነገር ግን ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት፤ ወደ አንደኛው ቀርቦ ‘ልጄ ሆይ! ዛሬ ሂድና በወይኔ አትክልት ሥራ፤’ አለው።</verse>
				<verse number="29">እርሱም መልሶ ‘አልወድም፤’ አለ፤ ኋላ ግን ተጸጸተና ሄደ።</verse>
				<verse number="30">ወደ ሁለተኛውም ቀርቦ እንዲሁ አለው እርሱም መልሶ ‘እሺ ጌታዬ፤’ አለ፤ ነገር ግን አልሄደም።</verse>
				<verse number="31">ከሁለቱ የአባቱን ፈቃድ ያደረገ ማን ነው?” “ፊተኛው” አሉት። ኢየሱስ እንዲህ አላቸው “እውነት እላችኋለሁ፥ ቀራጮችና ጋለሞቶች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሙአችኋል።</verse>
				<verse number="32">ዮሐንስ በጽድቅ መንገድ መጥቶላችሁ ነበርና፤ አላመናችሁበትም፤ ቀራጮችና ጋለሞቶች ግን አመኑበት፤ እናንተም ይህን አይታችሁ ታምኑበት ዘንድ በኋላ ንስሐ አልገባችሁም።</verse>
				<verse number="33">“ሌላ ምሳሌ ስሙ። የወይን አትክልት የተከለ ባለቤት ሰው ነበረ፤ ቅጥርም ቀጠረለት፤ መጥመቂያም ማሰለት፤ ግንብም ሠራና ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።</verse>
				<verse number="34">የሚያፈራበትም ጊዜ ሲቀርብ፥ ፍሬውን ሊቀበሉ ባሮቹን ወደ ገበሬዎች ላከ።</verse>
				<verse number="35">ገበሬዎቹም ባሮቹን ይዘው አንዱን ደበደቡት፤ አንዱንም ገደሉት፤ ሌላውንም ወገሩት።</verse>
				<verse number="36">ደግሞ ከፊተኞች የሚበዙ ሌሎች ባሮችን ላከ፤ እንዲሁም አደረጉባቸው።</verse>
				<verse number="37">በኋላ ግን ‘ልጄንስ ያፍሩታል፤’ ብሎ ልጁን ላከባቸው።</verse>
				<verse number="38">ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፤ እንግደለውና ርስቱን እናግኝ፤’ ተባባሉ።</verse>
				<verse number="39">ይዘውም ከወይኑ አትክልት አወጡና ገደሉት።</verse>
				<verse number="40">እንግዲህ የወይኑ አትክልት ጌታ በሚመጣ ጊዜ በእነዚህ ገበሬዎች ምን ያደርግባቸዋል?”</verse>
				<verse number="41">እነርሱም “ክፉዎችን በክፉ ያጠፋቸዋል፤ የወይኑንም አትክልት ፍሬውን በየጊዜው ለሚያስረክቡ ለሌሎች ገበሬዎች ይሰጠዋል፤” አሉት።</verse>
				<verse number="42">ኢየሱስ እንዲህ አላቸው “ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው፤’ የሚለውን ከቶ በመጽሐፍ አላነበባችሁምን?</verse>
				<verse number="43">ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ትወሰዳለች፤ ፍሬዋንም ለሚያደርግ ሕዝብ ትሰጣለች።</verse>
				<verse number="44">በዚህም ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይቀጠቀጣል፤ ድንጋዩ ግን የሚወድቅበትን ሁሉ ይፈጨዋል።”</verse>
				<verse number="45">የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ምሳሌዎቹን ሰምተው ስለ እነርሱ እንደ ተናገረ አስተዋሉ፤</verse>
				<verse number="46">ሊይዙትም ሲፈልጉት ሳሉ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስላዩት ፈሩአቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">ኢየሱስም መለሰ ደግሞም በምሳሌ ነገራቸው እንዲህም አለ</verse>
				<verse number="2">“መንግሥተ ሰማያት ለልጁ ሰርግ ያደረገ ንጉሥን ትመስላለች።</verse>
				<verse number="3">የታደሙትንም ወደ ሰርጉ ይጠሩ ዘንድ ባሮቹን ላከ፤ ሊመጡም አልወደዱም።</verse>
				<verse number="4">ደግሞ ሌሎችን ባሮች ልኮ ‘የታደሙትን እነሆ፥ ድግሴን አዘጋጀሁ፤ ኮርማዎቼና የሰቡት ከብቶቼ ታርደዋል፤ ሁሉም ተዘጋጅቶአል፤ ወደ ሰርጉ ኑ፤ በሉአቸው፤’ አለ።</verse>
				<verse number="5">እነርሱ ግን ቸል ብለው አንዱ ወደ እርሻው፥ ሌላውም ወደ ንግዱ ሄደ፤</verse>
				<verse number="6">የቀሩትም ባሮቹን ይዘው አንገላቱአቸው፤ ገደሉአቸውም።</verse>
				<verse number="7">ንጉሡም ተቈጣ፤ ጭፍሮቹንም ልኮ እነዚያን ገዳዮች አጠፋ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ።</verse>
				<verse number="8">በዚያን ጊዜ ባሮቹን ‘ሰርጉ ተዘጋጅቶአል፤ ነገር ግን የታደሙት የማይገባቸው ሆኑ፤</verse>
				<verse number="9">እንግዲህ ወደ መንገድ መተላለፊያ ሄዳችሁ ያገኛችሁትን ሁሉ ወደ ሰርጉ ጥሩ፤’ አለ።</verse>
				<verse number="10">እነዚያም ባሮች ወደ መንገድ ወጥተው ያገኙትን ሁሉ ክፉዎችንም በጎዎችንም ሰበሰቡ፤ የሰርጉንም ቤት ተቀማጮች ሞሉት።</verse>
				<verse number="11">“ንጉሡም የተቀመጡትን ለማየት በገባ ጊዜ በዚያ የሰርግ ልብስ ያለበሰ አንድ ሰው አየና ‘ወዳጄ ሆይ!</verse>
				<verse number="12">የሰርግ ልብስ ሳትለብስ እንዴት ወደዚህ ገባህ?’ አለው እርሱም ዝም አለ።</verse>
				<verse number="13">በዚያን ጊዜ ንጉሡ አገልጋዮቹን ‘እጁንና እግሩን አስራችሁ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፤’ አለ።</verse>
				<verse number="14">የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።”</verse>
				<verse number="15">ስለዚህ ፈሪሳውያን ሄዱና እንዴት አድርገው በነገር እንዲያጠምዱት ተማከሩ።</verse>
				<verse number="16">ደቀ ዛሙርታቸውንም ከሄሮድስ ወገን ጋር ላኩበት፤ እነርሱም “መምህር ሆይ! እውነተኛ እንደ ሆንህ በእውነትም የእግዚአብሔርን መንገድ እንድታስተምር እናውቃለን፤ ለማንምም አታደላም፤ የሰውን ፊት አትመለከትምና፤</verse>
				<verse number="17">እንግዲህ ምን ይመስልሃል? ንገረን ለቄሳር ግብር መስጠት ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም?” አሉት።</verse>
				<verse number="18">ኢየሱስም ክፋታቸውን አውቆ “እናንተ ግብዞች፥ ስለ ምን ትፈትኑኛላችሁ?</verse>
				<verse number="19">የግብሩን ብር አሳዩኝ፤” አለ። እነርሱም ዲናር አመጡለት።</verse>
				<verse number="20">እርሱም “ይህች መልክ ጽሕፈቲቱስ የማን ናት?” አላቸው።</verse>
				<verse number="21">“የቄሳር ነው፤” አሉት። በዚያን ጊዜ “እንኪያስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="22">ይህንም ሰምተው ተደነቁ፤ ትተውትም ሄዱ።</verse>
				<verse number="23">በዚያን ቀን “ትንሣኤ ሙታን የለም፤” የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ ቀረቡ፤</verse>
				<verse number="24">እንዲህም ብለው ጠየቁት “መምህር ሆይ! ሙሴ ‘አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ሲሞት ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ፤’ አለ።</verse>
				<verse number="25">ሰባት ወንድማማች በእኛ ዘንድ ነበሩ፤ ፊተኛውም ሚስት አግብቶ ሞተ፤ ዘርም ስለሌለው ሚስቱን ለወንድሙ ተወለት፤</verse>
				<verse number="26">እንዲሁ ደግሞ ሁለተኛው ሦስተኛውም፥ እስከ ሰባተኛው ድረስ።</verse>
				<verse number="27">ከሁሉም በኋላ ሴቲቱ ሞተች።</verse>
				<verse number="28">ሁሉ አግብተዋታልና በትንሣኤ ቀን ከሰባቱ ለማናቸው ሚስት ትሆናለች?”</verse>
				<verse number="29">ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ።</verse>
				<verse number="30">በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም።</verse>
				<verse number="31">ስለ ትንሣኤ ሙታን ግን ‘እኔ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ፤’ የሚል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ እናንተ የተባለውን አላነበባችሁምን? የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም።”</verse>
				<verse number="32"></verse>
				<verse number="33">ሕዝቡም ይህን ሰምተው በትምህርቱ ተገረሙ።</verse>
				<verse number="34">ፈሪሳውያንም ሰዱቃውያንን ዝም እንዳሰኛቸው በሰሙ ጊዜ አብረው ተሰበሰቡ።</verse>
				<verse number="35">ከእነርሱም አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው</verse>
				<verse number="36">“መምህር ሆይ! ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት?” ብሎ ጠየቀው።</verse>
				<verse number="37">ኢየሱስም እንዲህ አለው “ ‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።’</verse>
				<verse number="38">ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።</verse>
				<verse number="39">ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም ‘ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ፤’ የምትለው ናት።</verse>
				<verse number="40">በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል።”</verse>
				<verse number="41">ፈሪሳውያንም ተሰብስበው ሳሉ፥ ኢየሱስ “ስለ ክርስቶስ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ልጅ ነው?” ብሎ ጠየቃቸው። “የዳዊት ልጅ ነው፤” አሉት።</verse>
				<verse number="42"></verse>
				<verse number="43">እርሱም “እንኪያስ ዳዊት ‘ጌታ ጌታዬን “ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ፤” አለው፤’ ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል?</verse>
				<verse number="44"></verse>
				<verse number="45">ዳዊትስ ጌታ ብሎ ከጠራው፥ እንዴት ልጁ ይሆናል?” አላቸው።</verse>
				<verse number="46">አንድም ቃል ስንኳ ይመልስለት ዘንድ የተቻለው የለም፤ ከዚያ ቀንም ጀምሮ ወደ ፊት ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="23">
				<verse number="1">በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለሕዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሎ ነገራቸው</verse>
				<verse number="2">“ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል።</verse>
				<verse number="3">ስለዚህ ያዘዙአችሁን ሁሉ አድርጉ፤ ጠብቁትም፤ ነገር ግን እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ።</verse>
				<verse number="4">ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ፤ እነርሱ ግን በጣታቸው ስንኳ ሊነኩት አይወዱም።</verse>
				<verse number="5">ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ፤ ዘርፉንም ያስረዝማሉ፤</verse>
				<verse number="6">በግብዣም የከበሬታ ስፍራ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥</verse>
				<verse number="7">በገበያም ሰላምታና ‘መምህር ሆይ! መምህር ሆይ!’ ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ።</verse>
				<verse number="8">እናንተ ግን ‘መምህር’ ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ።</verse>
				<verse number="9">አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም ‘አባት’ ብላችሁ አትጥሩ።</verse>
				<verse number="10">ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና ‘ሊቃውንት’ ተብላችሁ አትጠሩ።</verse>
				<verse number="11">ከእናንተም የሚበልጠው አገልጋያችሁ ይሆናል።</verse>
				<verse number="12">ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፤ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል።</verse>
				<verse number="13">“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።</verse>
				<verse number="14">እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! በጸሎት ርዝመት እያመካኛችሁ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ፥ ወዮላችሁ፤ ስለዚህ የባሰ ፍርድ ትቀበላላችሁ።</verse>
				<verse number="15">እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! አንድ ሰው ልታሳምኑ በባሕርና በደረቅ ስለምትዞሩ፥ በሆነም ጊዜ ከእናንተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የባሰ የገሃነም ልጅ ስለምታደርጉት፥ ወዮላችሁ።</verse>
				<verse number="16">“እናንተ ‘ማንም በቤተ መቅደስ የሚምል ምንም የለበትም፤ ማንም በቤተ መቅደስ ወርቅ የሚምል ግን በመሐላው ይያዛል፤’ የምትሉ፥ ዕውሮች መሪዎች፥ ወዮላችሁ።</verse>
				<verse number="17">እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች! ማናቸው ይበልጣል? ወርቁ ነውን? ወይስ ወርቁን የቀደሰው ቤተ መቅደስ?</verse>
				<verse number="18">ደግማችሁም ‘ማንም በመሠዊያው የሚምል ምንም የለበትም፤ ማንም በላዩ ባለው መባ የሚምል ግን በመሐላው ይያዛል፤’ ትላላችሁ።</verse>
				<verse number="19">እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች! ማናቸው ይበልጣል? መባው ነውን? ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው?</verse>
				<verse number="20">እንግዲህ በመሠዊያው የሚምለው በእርሱና በእርሱ ላይ ባለው ሁሉ ይምላል፤</verse>
				<verse number="21">በቤተ መቅደስም የሚምለው በእርሱና በእርሱ በሚኖረው ይምላል፤</verse>
				<verse number="22">በሰማይም የሚምለው በእግዚአብሔር ዙፋንና በእርሱ ላይ በተቀመጠው ይምላል።</verse>
				<verse number="23">“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር።</verse>
				<verse number="24">እናንተ ዕውሮች መሪዎች! ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ።</verse>
				<verse number="25">“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ፥ ወዮላችሁ።</verse>
				<verse number="26">አንተ ዕውር ፈሪሳዊ! ውጭው ደግሞ ጥሩ እንዲሆን አስቀድመህ የጽዋውንና የወጭቱን ውስጡን አጥራ።</verse>
				<verse number="27">“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጡ ግን የሙታን አጥንት ርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ፥ ወዮላችሁ።</verse>
				<verse number="28">እንዲሁ እናንተ ደግሞ በውጭ ለሰው እንደ ጻድቃን ትታያላችሁ፤ በውስጣችሁ ግን ግብዝነትና ዐመፀኝነት ሞልቶባችኋል።</verse>
				<verse number="29">“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ የጻድቃንንም መቃብር ስለምታስጌጡና</verse>
				<verse number="30">‘በአባቶቻችን ዘመን ኖረን በሆነስ በነቢያት ደም ባልተባበርናቸውም ነበር፤’ ስለምትሉ፥ ወዮላችሁ።</verse>
				<verse number="31">እንግዲያስ የነቢያት ገዳዮች ልጆች እንደሆናችሁ በራሳችሁ ላይ ትመሰክራላችሁ።</verse>
				<verse number="32">እናንተ ደግሞ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ሙሉ።</verse>
				<verse number="33">እናንተ እባቦች! የእፉኝት ልጆች! ከገሃነም ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ?</verse>
				<verse number="34">ስለዚህ፥ እነሆ፥ ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ ትሰቅሉማላችሁ፥ ከእነርሱም በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤</verse>
				<verse number="35">ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችኋል።</verse>
				<verse number="36">እውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይደርሳል።</verse>
				<verse number="37">“ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ! ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም።</verse>
				<verse number="38">እነሆ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል።</verse>
				<verse number="39">እላችኋለሁና፥ ‘በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤’ እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="24">
				<verse number="1">ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ቀረቡ።</verse>
				<verse number="2">እርሱ ግን መልሶ “ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="3">እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው “ንገረን፤ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው?” አሉት።</verse>
				<verse number="4">ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።</verse>
				<verse number="5">ብዙዎች ‘እኔ ክርስቶስ ነኝ፤’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።</verse>
				<verse number="6">ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።</verse>
				<verse number="7">ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፤ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤</verse>
				<verse number="8">እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።</verse>
				<verse number="9">“በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ይገድሉአችሁማል፤ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።</verse>
				<verse number="10">በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ፤ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤</verse>
				<verse number="11">ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ፤</verse>
				<verse number="12">ከዐመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች።</verse>
				<verse number="13">እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።</verse>
				<verse number="14">ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፤ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።</verse>
				<verse number="15">“እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፤</verse>
				<verse number="16">በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉት ወደ ተራራዎች ይሽሹ፥</verse>
				<verse number="17">በሰገነትም ያለ በቤቱ ያለውን ሊወስድ አይውረድ፤</verse>
				<verse number="18">በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ።</verse>
				<verse number="19">በዚያችም ወራት ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው።</verse>
				<verse number="20">ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፤</verse>
				<verse number="21">በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና።</verse>
				<verse number="22">እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ።</verse>
				<verse number="23">በዚያን ጊዜ ማንም ‘እነሆ፥ ክርስቶስ እዚህ አለ፤’ ወይም ‘እዚያ አለ፤’ ቢላችሁ አትመኑ፤</verse>
				<verse number="24">ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፤ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።</verse>
				<verse number="25">እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ።</verse>
				<verse number="26">እንግዲህ ‘እነሆ፥ በበረሀ ነው፤’ ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ ‘እነሆ፥ በእልፍኝ ነው፤’ ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤</verse>
				<verse number="27">መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ፥ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና፤</verse>
				<verse number="28">በድን ወዳለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ።</verse>
				<verse number="29">“ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤</verse>
				<verse number="30">የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፤ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፤ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤</verse>
				<verse number="31">መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፤ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ።</verse>
				<verse number="32">“ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቍኦጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤</verse>
				<verse number="33">እንዲሁ እናንተ ደግሞ ይህን ሁሉ ስታዩ በደጅ እንደ ቀረበ እወቁ።</verse>
				<verse number="34">እውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም።</verse>
				<verse number="35">ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።</verse>
				<verse number="36">“ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም።</verse>
				<verse number="37">የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና።</verse>
				<verse number="38">በዚያች ወራት ከጥፋት ውሃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥</verse>
				<verse number="39">የጥፋት ውሃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።</verse>
				<verse number="40">በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በእርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል አንዱም ይቀራል፤</verse>
				<verse number="41">ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱ ትወሰዳለች አንዲቱም ትቀራለች።</verse>
				<verse number="42">ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።</verse>
				<verse number="43">“ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ፤ ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር።</verse>
				<verse number="44">ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፤ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።</verse>
				<verse number="45">“እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎች ላይ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው?</verse>
				<verse number="46">ጌታው መጥቶ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባሪያ ብፁዕ ነው፤</verse>
				<verse number="47">እውነት እላችኋለሁ፤ ባለው ሁሉ ላይ ይሾመዋል።</verse>
				<verse number="48">ያ ክፉ ባሪያ ግን ‘ጌታዬ እስኪመጣ ይዘገያል፤’ ብሎ በልቡ ቢያስብ፥</verse>
				<verse number="49">ባልንጀሮቹን ባሮች ሊመታ ቢጀምር፥ ከሰካሮችም ጋር ቢበላና ቢጠጣ፥</verse>
				<verse number="50">የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቃት ቀን ባላወቃትም ሰዓት ይመጣል፤</verse>
				<verse number="51">ከሁለትም ይሰነጥቀዋል፤ እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="25">
				<verse number="1">“በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ ዐሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።</verse>
				<verse number="2">ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ።</verse>
				<verse number="3">ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና፤</verse>
				<verse number="4">ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ።</verse>
				<verse number="5">ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ፥ ሁሉም እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።</verse>
				<verse number="6">እኩል ሌሊትም ሲሆን ‘እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፤ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ፤’ የሚል ውካታ ሆነ።</verse>
				<verse number="7">በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሡና መብራታቸውን አዘጋጁ።</verse>
				<verse number="8">ሰነፎቹም ልባሞቹን ‘መብራታችን ሊጠፋብን ነው፤ ከዘይታችሁ ስጡን፤’ አሉአቸው።</verse>
				<verse number="9">ልባሞቹ ግን መልሰው ‘ምናልባት ለእኛና ለእናንተ ባይበቃስ፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ፤’ አሉአቸው።</verse>
				<verse number="10">ሊገዙም በሄዱ ጊዜ ሙሽራው መጣ፤ ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሰርግ ገቡ፤ ደጁም ተዘጋ።</verse>
				<verse number="11">በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! ክፈትልን፤’ አሉ።</verse>
				<verse number="12">እርሱ ግን መልሶ ‘እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም፤’ አለ።</verse>
				<verse number="13">ቀኒቱንና ስዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።</verse>
				<verse number="14">“ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደ ሰጣቸው እንዲሁ ይሆናልና፤</verse>
				<verse number="15">ለእያንዳንዱ እንደ ዐቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ።</verse>
				<verse number="16">አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት፤ ሌላም አምስት አተረፈ፤</verse>
				<verse number="17">እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ።</verse>
				<verse number="18">አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቈፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ።</verse>
				<verse number="19">ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው።</verse>
				<verse number="20">አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ ‘ጌታ ሆይ! አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት፤’ አለ።</verse>
				<verse number="21">ጌታውም ‘መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፥ በጥቂቱ ታምነሃል፤ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ፤’ አለው።</verse>
				<verse number="22">ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ ‘ጌታ ሆይ! ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት፤’ አለ።</verse>
				<verse number="23">ጌታውም ‘መልካም፥ አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፤ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ፤’ አለው።</verse>
				<verse number="24">አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ ‘ጌታ ሆይ! ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤</verse>
				<verse number="25">ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ፤’ አለ።</verse>
				<verse number="26">ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው ‘አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባሪያ፥ ካልዘራሁባት እንዳጭድ ካልበተንሁባትም እንድሰበስብ ታውቃለህን?</verse>
				<verse number="27">ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፤ እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር።</verse>
				<verse number="28">ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት ዐሥር መክሊትም ላለው ስጡት፤</verse>
				<verse number="29">ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና፤ ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።</verse>
				<verse number="30">የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።’</verse>
				<verse number="31">“የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤</verse>
				<verse number="32">አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፤</verse>
				<verse number="33">በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል።</verse>
				<verse number="34">ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል ‘እናንተ የአባቴ ቡሩካን! ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።</verse>
				<verse number="35">ተርቤ አብልታችሁኛልና፤ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፤ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፤ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፤</verse>
				<verse number="36">ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፤ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።’</verse>
				<verse number="37">ጻድቃንም መልሰው ይሉታል ‘ጌታ ሆይ! ተርበህ አይተን መቼ አበላንህ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?</verse>
				<verse number="38">እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ?</verse>
				<verse number="39">ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን?’</verse>
				<verse number="40">ንጉሡም መልሶ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት፤’ ይላቸዋል።</verse>
				<verse number="41">በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል ‘እናንተ ርጉማን! ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።</verse>
				<verse number="42">ተርቤ አላበላችሁኝምና፤ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፤</verse>
				<verse number="43">እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፤ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፤ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።’</verse>
				<verse number="44">እነርሱ ደግሞ ይመልሱና ‘ጌታ ሆይ! ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም?’ ይሉታል።</verse>
				<verse number="45">ያን ጊዜ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም፤’ ብሎ ይመልስላቸዋል።</verse>
				<verse number="46">እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="26">
				<verse number="1">ኢየሱስም እነዚህን ቃሎች ሁሉ በፈጸመ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="2">ለደቀ መዛሙርቱ “ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካ እንዲሆን ታውቃላችሁ፤ የሰው ልጅም ሊሰቀል አልፎ ይሰጣል፤” አለ።</verse>
				<verse number="3">በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝብም ሽማግሎች ቀያፋ በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ፤</verse>
				<verse number="4">ኢየሱስንም በተንኰል ሊያስይዙት ሊገድሉትም ተማከሩ፤</verse>
				<verse number="5">ነገር ግን “በሕዝቡ ዘንድ ሁከት እንዳይነሣ በበዓል አይሁን፤” አሉ።</verse>
				<verse number="6">ኢየሱስም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ፥</verse>
				<verse number="7">አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቱ የሞላው የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች፤ በማዕድም ተቀምጦ ሳለ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።</verse>
				<verse number="8">ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው ተቈጡና “ይህ ጥፋት ለምንድር ነው?</verse>
				<verse number="9">ይህ በብዙ ዋጋ ተሽጦ ለድሆች ሊሰጥ ይቻል ነበርና፤” አሉ።</verse>
				<verse number="10">ኢየሱስም ይህን አውቆ እንዲህ አላቸው “መልካም ሥራ ሠርታልኛለችና ሴቲቱንስ ስለ ምን ታደክሙአታላችሁ?</verse>
				<verse number="11">ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፤ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም፤</verse>
				<verse number="12">እርስዋ ይህን ሽቱ በሰውነቴ ላይ አፍስሳ ለመቃብሬ አደረገች።</verse>
				<verse number="13">እውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ወንጌል በዓለም ሁሉ በማናቸውም ስፍራ በሚሰበክበት እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል።”</verse>
				<verse number="14">በዚያን ጊዜ የአስቆሮቱ ይሁዳ የሚባለው ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ወደ ካህናት አለቆች ሄዶ</verse>
				<verse number="15">“ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ?” እነርሱም ሠላሳ ብር መዘኑለት።</verse>
				<verse number="16">ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ አሳልፎ ሊሰጠው ምቹ ጊዜ ይሻ ነበር።</verse>
				<verse number="17">በቂጣው በዓል በመጀመሪያ ቀን ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው “ፋሲካን ትበላ ዘንድ ወዴት ልናሰናዳልህ ትወዳለህ?” አሉት።</verse>
				<verse number="18">እርሱም “ወደ ከተማ ከእገሌ ዘንድ ሄዳችሁ ‘መምህር ጊዜዬ ቀርቦአል፤ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ከአንተ ዘንድ ፋሲካን አደርጋለሁ ይላል’ በሉት፤” አለ።</verse>
				<verse number="19">ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ ፋሲካንም አሰናዱ።</verse>
				<verse number="20">በመሸም ጊዜ ከዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጠ።</verse>
				<verse number="21">ሲበሉም “እውነት እላችኋለሁ፤ ከእናንተ አንዱ እኔን አሳልፎ ይሰጣል፤” አለ።</verse>
				<verse number="22">እጅግም አዝነው እያንዳንዱ “ጌታ ሆይ! እኔ እሆንን?” ይሉት ጀመር።</verse>
				<verse number="23">እርሱም መልሶ “ከእኔ ጋር እጁን በወጭቱ ያጠለቀ፥ እኔን አሳልፎ የሚሰጥ እርሱ ነው።</verse>
				<verse number="24">የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት፤ ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር፤” አለ።</verse>
				<verse number="25">አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳም መልሶ “መምህር ሆይ! እኔ እሆንን?” አለ፤ “አንተ አልህ፤” አለው።</verse>
				<verse number="26">ሲበሉም ኢየሱስ ኅብስትን አንሥቶ ባረከ፤ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና “እንካችሁ፥ ብሉ፤ ይህ ሥጋዬ ነው፤” አለ።</verse>
				<verse number="27">ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው፤ እንዲህም አለ፤ “ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤</verse>
				<verse number="28">ስለ ብዙዎች ለኀጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።</verse>
				<verse number="29">ነገር ግን እላችኋለሁ፤ በአባቴ መንግሥት ከእናንተ ጋር ከዚህ ከወይን ፍሬ አዲሱን እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ ከዛሬ ጀምሬ አልጠጣም።”</verse>
				<verse number="30">መዝሙርም ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ወጡ።</verse>
				<verse number="31">በዚያን ጊዜ ኢየሱስ “በዚች ሌሊት ሁላችሁ በእኔ ትሰናከላላችሁ፤ ‘እረኛውን እመታለሁ፤ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ፤’ የሚል ተጽፎአልና፤</verse>
				<verse number="32">ከተነሣሁ በኋላ ግን ወደ ገሊላ እቀድማችኋለሁ፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="33">ጴጥሮስም መልሶ “ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እኔ ከቶ አልሰናከልም፤” አለው።</verse>
				<verse number="34">ኢየሱስም “እውነት እልሃለሁ፤ በዚች ሌሊት ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” አለው።</verse>
				<verse number="35">ጴጥሮስም “ከአንተ ጋር መሞት እንኳ የሚያስፈልገኝ ቢሆን፥ ከቶ አልክድህም፤” አለው። ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ደግሞ እንደዚሁ አሉ።</verse>
				<verse number="36">በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ጌቴሴማኒ ወደምትባል ስፍራ መጣ፤ ደቀ መዛሙርቱንም “ወዲያ ሄጄ ስጸልይ ሳለ በዚህ ተቀመጡ፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="37">ጴጥሮስንም ሁለቱንም የዘብዴዎስን ልጆች ወስዶ ሊያዝን ሊተክዝም ጀመር።</verse>
				<verse number="38">“ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ቆዩ፤ ከእኔም ጋር ትጉ፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="39">ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ “አባቴ! ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን፤” አለ።</verse>
				<verse number="40">ወደ ደቀ መዛሙርቱም መጣ፤ ተኝተውም አገኛቸውና ጴጥሮስን “እንዲሁም ከእኔ ጋር አንዲት ሰዓት እንኳ ልትተጉ አልቻላችሁምን?</verse>
				<verse number="41">ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች፤ ሥጋ ግን ደካማ ነው፤” አለው።</verse>
				<verse number="42">ደግሞ ሁለተኛ ሄዶ ጸለየና “አባቴ! ይህች ጽዋ ሳልጠጣት ታልፍ ዘንድ የማይቻል እንደ ሆነ፥ ፈቃድህ ትሁን፤” አለ።</verse>
				<verse number="43">ደግሞም መጥቶ ዐይኖቻቸው በእንቅልፍ ከብደው ነበርና ተኝተው አገኛቸው።</verse>
				<verse number="44">ደግሞም ትቶአቸው ሄደ፤ ሦስተኛም ያንኑ ቃል ደግሞ ጸለየ።</verse>
				<verse number="45">ከዚያ ወዲያ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥቶ “እንግዲህስ ተኙ፤ ዕረፉም፤ እነሆ፥ ሰዓቲቱ ቀርባለች፤ የሰው ልጅም በኀጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል።</verse>
				<verse number="46">ተነሡ፤ እንሂድ፤ እነሆ፥ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቦአል፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="47">ይህንም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፤ ከእርሱም ጋር ብዙ ሕዝብ ሰይፍና ጐመድ ይዘው ከካህናት አለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሎች ዘንድ መጡ።</verse>
				<verse number="48">አሳልፎ የሚሰጠውም “የምስመው እርሱ ነው፤ ያዙት፤” ብሎ ምልክት ሰጥቶአቸው ነበር።</verse>
				<verse number="49">ወዲያውም ወደ ኢየሱስ ቀረበና “መምህር ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን፤” ብሎ ሳመው።</verse>
				<verse number="50">ኢየሱስም “ወዳጄ ሆይ! ለምን ነገር መጣህ?” አለው። በዚያን ጊዜ ቀረቡ፤ እጃቸውንም በኢየሱስ ላይ ጭነው ያዙት።</verse>
				<verse number="51">እነሆም፥ ከኢየሱስ ጋር ከነበሩት አንዱ እጁን ዘርግቶ ሰይፉን መዘዘና የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ጆሮውን ቈረጠው።</verse>
				<verse number="52">በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለው “ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ።</verse>
				<verse number="53">ወይስ አባቴን እንድለምን እርሱም አሁን ከዐሥራ ሁለት ጭፍሮች የሚበዙ መላእክት እንዲሰድልኝ የማይችል ይመስልሃልን?</verse>
				<verse number="54">እንዲህ ከሆነስ ‘እንደዚህ ሊሆን ይገባል፤’ የሚሉ መጻሕፍት እንዴት ይፈጸማሉ?”</verse>
				<verse number="55">በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ለሕዝቡ “ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ ወጣችሁን? በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስቀመጥ ሳለሁ አልያዛችሁኝም።</verse>
				<verse number="56">ነገር ግን ይህ ሁሉ የሆነ የነቢያት መጻሕፍት ይፈጸሙ ዘንድ ነው፤” አለ። በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ትተውት ሸሹ።</verse>
				<verse number="57">ኢየሱስን የያዙትም ጻፎችና ሽማግሎች ወደ ተከማቹበት ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ወሰዱት።</verse>
				<verse number="58">ጴጥሮስ ግን እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ ሩቅ ሆኖ ተከተለው፤ የነገሩንም ፍጻሜ ያይ ዘንድ ወደ ውስጥ ገብቶ ከሎሌዎቹ ጋር ተቀመጠ።</verse>
				<verse number="59">የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ሸንጎውም ሁሉ እንዲገድሉት በኢየሱስ ላይ የሐሰት ምስክር ይፈልጉ ነበር፤ አላገኙም፤</verse>
				<verse number="60">ብዙም የሐሰት ምስክሮች ምንም ቢቀርቡ አላገኙም።</verse>
				<verse number="61">በኋላም ሁለት ቀርበው “ይህ ሰው ‘የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ አፍርሼ በሦስት ቀን ልሠራው እችላለሁ፤’ ብሎአል፤” አሉ።</verse>
				<verse number="62">ሊቀ ካህናቱም ተነሥቶ “እነዚህ ለሚመሰክሩብህ አንድ ስንኳ አትመልስምን?” አለው።</verse>
				<verse number="63">ኢየሱስ ግን ዝም አለ። ሊቀ ካህናቱም “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ፤” አለው።</verse>
				<verse number="64">ኢየሱስም “አንተ አልህ፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኀይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ፤” አለው።</verse>
				<verse number="65">በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ “ተሳድቦአል፤ እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን ይመስላችኋል?” አለ።</verse>
				<verse number="66">እነርሱም “ሞት ይገባዋል!” ብለው መለሱ።</verse>
				<verse number="67">በዚያን ጊዜ በፊቱ ተፉበት፤ ጐሰሙትም፤ ሌሎችም በጥፊ መትተው “ክርስቶስ ሆይ! በጥፊ የመታህ ማን ነው?</verse>
				<verse number="68">ትንቢት ተናገርልን፤” አሉ።</verse>
				<verse number="69">ጴጥሮስም ከቤት ውጭ በአጥሩ ግቢ ተቀምጦ ነበር፤ አንዲት ገረድም ወደ እርሱ ቀርባ “አንተ ደግሞ ከገሊላው ከኢየሱስ ጋር ነበርህ፤” አለችው።</verse>
				<verse number="70">እርሱ ግን “የምትዪውን አላውቀውም፤” ብሎ በሁሉ ፊት ካደ።</verse>
				<verse number="71">ወደ በሩም ሲወጣ ሌላይቱ አየችውና በዚያ ላሉት “ይህ ደግሞ ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበረ፤” አለች።</verse>
				<verse number="72">ዳግመኛም ሲምል “ሰውየውን አላውቀውም፤” ብሎ ካደ።</verse>
				<verse number="73">ጥቂትም ቈይተው በዚያ ቆመው የነበሩ ቀርበው ጴጥሮስን “አነጋገርህ ይገልጥሃልና፥ በእውነት አንተ ደግሞ ከእነርሱ ወገን ነህ፤” አሉት።</verse>
				<verse number="74">በዚያን ጊዜ “ሰውየውን አላውቀውም፤” ብሎ ራሱን ሊረግምና ሊምል ጀመረ። ወዲያውም ዶሮ ጮኸ።</verse>
				<verse number="75">ጴጥሮስም “ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” ያለው የኢየሱስ ቃል ትዝ አለው፤ ወደ ውጭም ወጥቶ መራራ ልቅሶ አለቀሰ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="27">
				<verse number="1">ሲነጋም የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ፤</verse>
				<verse number="2">አስረውም ወሰዱት፤ ለገዢው ለጴንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።</verse>
				<verse number="3">በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፤ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ</verse>
				<verse number="4">“ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ፤” አለ። እነርሱ ግን “እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ፤” አሉ።</verse>
				<verse number="5">ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ።</verse>
				<verse number="6">የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው “የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም፤” አሉ።</verse>
				<verse number="7">ተማክረውም የሸክላ ሠሪውን መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙበት።</verse>
				<verse number="8">ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ “የደም መሬት” ተባለ።</verse>
				<verse number="9">በዚያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ የተባለው “ከእስራኤል ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን፥ የተገመተውን ዋጋ ሠላሳ ብር ያዙ፤</verse>
				<verse number="10">ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሠሪ መሬት ሰጡት።” የሚል ተፈጸመ።</verse>
				<verse number="11">ኢየሱስም በገዢው ፊት ቆመ፤ ገዢውም “የአይሁድ ንጉሥ አንተ ነህን?” ብሎ ጠየቀው፤ ኢየሱስም “አንተ አልህ፤” አለው።</verse>
				<verse number="12">የካህናት አለቆችም ሽማግሎችም ሲከሱት ምንም አልመለሰም።</verse>
				<verse number="13">በዚያን ጊዜ ጲላጦስ “ስንት ያህል እንዲመሰክሩብህ አትሰማምን?” አለው።</verse>
				<verse number="14">ገዢውም እጅግ እስኪደነቅ ድረስ አንዲት ቃል ስንኳ አልመለሰለትም።</verse>
				<verse number="15">በዚያም በዓል ሕዝቡ የወደዱትን አንድ እስረኛ ሊፈታላቸው ለገዢው ልማድ ነበረው።</verse>
				<verse number="16">በዚያን ጊዜም በርባን የሚባል በጣም የታወቀ እስረኛ ነበራቸው።</verse>
				<verse number="17">እንግዲህ እነርሱ ተሰብስበው ሳሉ ጲላጦስ “በርባንን ወይስ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ?” አላቸው፤</verse>
				<verse number="18">በቅንዓት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና።</verse>
				<verse number="19">እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ “ስለ እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ፤” ብላ ላከችበት።</verse>
				<verse number="20">የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ግን በርባንን እንዲለምኑ ኢየሱስን ግን እንዲያጠፉ ሕዝቡን አባበሉ።</verse>
				<verse number="21">ገዢውም መልሶ “ከሁለቱ ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ?” አላቸው፤ እነርሱም “በርባንን” አሉ።</verse>
				<verse number="22">ጲላጦስ “ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው?” አላቸው፤ ሁሉም “ይሰቀል!” አሉ።</verse>
				<verse number="23">ገዢውም “ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው?” አለ፤ እነርሱ ግን “ይሰቀል!” እያሉ ጩኸት አበዙ።</verse>
				<verse number="24">ጲላጦስም ሁከት እንዲጀመር እንጂ አንዳች እንዳይረባ ባየ ጊዜ፥ ውሃ አንሥቶ “እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ እናንተ ተጠንቀቁ፤” ሲል በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ።</verse>
				<verse number="25">ሕዝቡም ሁሉ መልሰው “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን፤” አሉ።</verse>
				<verse number="26">በዚያን ጊዜ በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ገርፎ ሊሰቀል አሳልፎ ሰጠ።</verse>
				<verse number="27">በዚያን ጊዜ የገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ውስጥ ወሰዱት፤ ጭፍራውንም ሁሉ ወደ እርሱ አከማቹ።</verse>
				<verse number="28">ልብሱንም ገፈው ቀይ ልብስ አለበሱት፤</verse>
				<verse number="29">ከእሾህም አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፤ በፊቱም ተንበርክከው “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን፤” እያሉ ዘበቱበት፤</verse>
				<verse number="30">ተፉበትም፤ መቃውንም ይዘው ራሱን መቱት።</verse>
				<verse number="31">ከዘበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፤ ልብሱንም አለበሱት፤ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።</verse>
				<verse number="32">ሲወጡም ስምዖን የተባለው የቀሬናን ሰው አገኙ፤ እርሱንም መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት።</verse>
				<verse number="33">ትርጓሜው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሆን ጎልጎታ ወደሚባለው ስፍራ በደረሱ ጊዜም፥</verse>
				<verse number="34">በሐሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፤ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም።</verse>
				<verse number="35">ከሰቀሉትም በኋላ ልብሱን ዕጣ ጥለው ተካፈሉ፤</verse>
				<verse number="36">በዚያም ተቀምጠው ይጠብቁት ነበር።</verse>
				<verse number="37">“ይህ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ ነው፤” የሚል የክሱን ጽሕፈት ከራሱ በላይ አኖሩ።</verse>
				<verse number="38">በዚያን ጊዜ ሁለት ወንበዴዎች አንዱ በቀኝ አንዱም በግራ ከእርሱ ጋር ተሰቀሉ።</verse>
				<verse number="39">የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበር፤</verse>
				<verse number="40">“ቤተ መቅደስን የምታፈርስ በሦስት ቀንም የምትሠራው፥ ራስህን አድን፤ የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ ከመስቀል ውረድ፤” አሉት።</verse>
				<verse number="41">እንዲሁም ደግሞ የካህናት አለቆች ከጻፎችና ከሽማግሎች ጋር እየዘበቱበት እንዲህ አሉ</verse>
				<verse number="42">“ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ሊያድን አይችልም፤ የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ፥ አሁን ከመስቀል ይውረድ፤ እኛም እናምንበታለን።</verse>
				<verse number="43">በእግዚአብሔር ታምኖአል፤ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፤’ ብሎአልና ከወደደውስ አሁን ያድነው።”</verse>
				<verse number="44">ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዴዎች ደግሞ ያንኑ እያሉ ይነቅፉት ነበር።</verse>
				<verse number="45">ከስድስት ሰዓትም ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።</verse>
				<verse number="46">በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ?” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም “አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ?” ማለት ነው።</verse>
				<verse number="47">በዚያም ከቆሙት ሰዎች ሰምተው “ይህስ ኤልያስን ይጠራል፤” አሉ።</verse>
				<verse number="48">ወዲያውም ከእነርሱ አንዱ ሮጠ፤ ሰፍነግም ይዞ ሆምጣጤ ሞላበት፤ በመቃም አድርጎ አጠጣው።</verse>
				<verse number="49">ሌሎቹ ግን “ተው፤ ኤልያስ መጥቶ ያድነው እንደ ሆነ እንይ፤” አሉ።</verse>
				<verse number="50">ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።</verse>
				<verse number="51">እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፤ ምድርም ተናወጠች፤ ዐለቶችም ተሰነጠቁ፤</verse>
				<verse number="52">መቃብሮችም ተከፈቱ፤ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤</verse>
				<verse number="53">ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።</verse>
				<verse number="54">የመቶ አለቃም ከእርሱም ጋር ኢየሱስን የሚጠብቁ መናወጡንና የሆነውን ነገር አይተው “ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ፤” ብለው እጅግ ፈሩ።</verse>
				<verse number="55">ኢየሱስን እያገለገሉ ከገሊላ የተከተሉት ብዙ ሴቶች በሩቅ ሆነው ሲመለከቱ በዚያ ነበሩ፤</verse>
				<verse number="56">ከእነርሱም መግደላዊት ማርያምና የያዕቆብና የዮሳ እናት ማርያም የዘብዴዎስም የልጆቹ እናት ነበሩ።</verse>
				<verse number="57">በመሸም ጊዜ ዮሴፍ የተባለው ባለ ጠጋ ሰው ከአርማትያስ መጣ፤ እርሱም ደግሞ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበረ፤</verse>
				<verse number="58">ይኸውም ወደ ጲላጦስ ቀርቦ የኢየሱስን ሥጋ ለመነው።</verse>
				<verse number="59">ጲላጦስም እንዲሰጡት አዘዘ። ዮሴፍም ሥጋውን ይዞ በንጹሕ በፍታ ከፈነው፤</verse>
				<verse number="60">ከዐለት በወቀረው በአዲሱ መቃብርም አኖረው፤ በመቃብሩም ደጃፍ ታላቅ ድንጋይ አንከባሎ ሄደ።</verse>
				<verse number="61">መግደላዊት ማርያምም ሁለተኛይቱም ማርያም በመቃብሩ አንጻር ተቀምጠው በዚያ ነበሩ።</verse>
				<verse number="62">በማግሥቱም ከመዘጋጀት በኋላ በሚሆነው ቀን፥ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ወደ ጲላጦስ ተሰበሰቡና</verse>
				<verse number="63">“ጌታ ሆይ! ያ አሳች በሕይወቱ ገና ሳለ ‘ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ፤’ እንዳለ ትዝ አለን።</verse>
				<verse number="64">እንግዲህ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው በሌሊት እንዳይሰርቁት ለሕዝቡም ‘ከሙታን ተነሣ፤’ እንዳይሉ፥ የኋለኛይቱ ስሕተት ከፊተኛይቱ ይልቅ የከፋች ትሆናለችና መቃብሩ እስከ ሦስተኛ ቀን ድረስ እንዲጠበቅ እዘዝ፤” አሉት።</verse>
				<verse number="65">ጲላጦስም “ጠባቆች አሉአችሁ፤ ሄዳችሁ እንዳወቃችሁ አስጠብቁ፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="66">እነርሱም ሄደው ከጠባቆች ጋር ድንጋዩን አትመው መቃብሩን አስጠበቁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="28">
				<verse number="1">በሰንበትም መጨረሻ መጀመሪያው ቀን ሲነጋ መግደላዊት ማርያምና ሁለተኛይቱ ማርያም መቃብሩን ሊያዩ መጡ።</verse>
				<verse number="2">እነሆም፥ የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ።</verse>
				<verse number="3">መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ።</verse>
				<verse number="4">ጠባቆቹም እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ፤ እንደ ሞቱም ሆኑ።</verse>
				<verse number="5">መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው “እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና፤</verse>
				<verse number="6">እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና፤ በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።</verse>
				<verse number="7">ፈጥናችሁም ሂዱና ‘ከሙታን ተነሣ፤ እነሆም፥ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል በዚያም ታዩታላችሁ፤’ ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሩአቸው።</verse>
				<verse number="8">እነሆም ነገርኋችሁ።” በፍርሃትና በታላቅ ደስታም ፈጥነው ከመቃብር ሄዱ፤ ለደቀ መዛሙርቱም ሊያወሩ ሮጡ።</verse>
				<verse number="9">እነሆም፥ ኢየሱስ አገኛቸውና “ደስ ይበላችሁ፤” አላቸው። እነርሱም ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት።</verse>
				<verse number="10">በዚያን ጊዜ ኢየሱስ “አትፍሩ፤ ሄዳችሁ ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ለወንድሞቼ ተናገሩ፤ በዚያም ያዩኛል፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="11">ሲሄዱም ሳሉ እነሆ፥ ከጠባቆቹ አንዳንድ ወደ ከተማ መጥተው የሆነውን ሁሉ ለካህናት አለቆች አወሩ።</verse>
				<verse number="12">ከሽማግሎች ጋርም ተሰብስበው ተማከሩና ለጭፍሮች ብዙ ገንዘብ ሰጥተዋቸው</verse>
				<verse number="13">“እኛ ተኝተን ሳለን ደቀ መዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰረቁት” በሉ።</verse>
				<verse number="14">ይህም በገዢው ዘንድ የተሰማ እንደ ሆነ፥ እኛ እናስረዳዋለን፤ እናንተም ያለ ሥጋት እንድትሆኑ እናደርጋለን፤” አሉአቸው።</verse>
				<verse number="15">እነርሱም ገንዘቡን ተቀብለው እንደ አስተማሩአቸው አደረጉ። ይህም ነገር በአይሁድ ዘንድ እስከ ዛሬ ድረስ ሲወራ ይኖራል።</verse>
				<verse number="16">ዐሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት ግን ኢየሱስ ወዳዘዛቸው ተራራ ወደ ገሊላ ሄዱ፤</verse>
				<verse number="17">ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት፤ የተጠራጠሩ ግን ነበሩ።</verse>
				<verse number="18">ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።</verse>
				<verse number="19">እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም፥ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”</verse>
				<verse number="20"></verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="41">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ።</verse>
				<verse number="2">“እነሆ፥ መንገድህን የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፤ ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ ጥርጊያውንም አቅኑ፤’ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ” ተብሎ በነቢዩ በኢሳይያስ እንደ ተጻፈ፥</verse>
				<verse number="3"></verse>
				<verse number="4">ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀ የንስሐንም ጥምቀት ለኀጢአት ስርየት እየሰበከ መጣ።</verse>
				<verse number="5">የይሁዳም አገር ሁሉ የኢየሩሳሌምም ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፤ ኀጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።</verse>
				<verse number="6">ዮሐንስም የግመል ጠጉር ለብሶ በወገቡ ጠፍር ይታጠቅ አንበጣና የበረሓ ማርም ይበላ ነበር።</verse>
				<verse number="7">“ተጎንብሼ የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ በኋላዬ ይመጣል።</verse>
				<verse number="8">እኔ በውሃ አጠመቅኋችሁ፤ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል፤” እያለ ይሰብክ ነበር።</verse>
				<verse number="9">በዚያ ወራትም ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት መጥቶ ከዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ።</verse>
				<verse number="10">ወዲያውም ከውሃው በወጣ ጊዜ ሰማያት ሲቀደዱ መንፈስም እንደ ርግብ ሲወርድበት አየና “የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፤</verse>
				<verse number="11">በአንተ ደስ ይለኛል፤” የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ።</verse>
				<verse number="12">ወዲያውም መንፈስ ወደ ምድረ በዳ አወጣው።</verse>
				<verse number="13">በምድረ በዳም ከሰይጣን እየተፈተነ አርባ ቀን ሰነበተ፤ ከአራዊትም ጋር ነበረ፤ መላእክቱም አገለገሉት።</verse>
				<verse number="14">ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና</verse>
				<verse number="15">“ዘመኑ ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች፤ ንስሐ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ፤” እያለ ወደ ገሊላ መጣ።</verse>
				<verse number="16">በገሊላ ባሕርም አጠገብ ሲያልፍ ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፤ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።</verse>
				<verse number="17">ኢየሱስም “በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="18">ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት።</verse>
				<verse number="19">ከዚያም ጥቂት እልፍ ብሎ የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ደግሞ በታንኳ ላይ መረባቸውን ሲያበጁ አየ።</verse>
				<verse number="20">ወዲያውም ጠራቸው፤ አባታቸውንም ዘብዴዎስን ከሞያተኞቹ ጋር በታንኳ ላይ ትተው ተከትለውት ሄዱ።</verse>
				<verse number="21">ወደ ቅፍርናሆምም ገቡ፤ ወዲያውም በሰንበት ወደ ምኵራብ ገብቶ አስተማረ።</verse>
				<verse number="22">እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበር እንጂ እንደ ጻፎች አይደለምና በትምህርቱ ተገረሙ።</verse>
				<verse number="23">በዚያን ጊዜም በምኩራባቸው ርኵስ መንፈስ ያለው ሰው ነበረ፤</verse>
				<verse number="24">እርሱም “የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄአለሁ! የእግዚአብሔር ቅዱሱ!” ብሎ ጮኸ።</verse>
				<verse number="25">ኢየሱስም “ዝም በል፤ ከእርሱም ውጣ፤” ብሎ ገሠጸው።</verse>
				<verse number="26">ርኵሱም መንፈስ አንፈራገጠውና በታላቅ ድምፅ ጮኾ ከእርሱ ወጣ።</verse>
				<verse number="27">ሁሉም “ይህ ምንድር ነው? በሥልጣን ርኵሳን መናፍስትን ያዝዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታልና ይህ አዲስ ትምህርት ምንድር ነው?” ብለው እስኪጠያየቁ ድረስ አደነቁ።</verse>
				<verse number="28">ዝናውም ወዲያው በየስፍራው ወደ ገሊላ ዙሪያ ሁሉ ወጣ።</verse>
				<verse number="29">ወዲያውም ከምኵራብ ወጥቶ ከያዕቆብና ከዮሐንስ ጋር ወደ ስምዖንና ወደ እንድርያስ ቤት ገባ።</verse>
				<verse number="30">የስምዖንም አማት በንዳድ ታማ ተኝታ ነበር፤ ስለ እርስዋም ወዲያው ነገሩት።</verse>
				<verse number="31">ቀርቦም እጅዋን ይዞ አስነሣት፤ ንዳዱም ወዲያው ለቀቃትና አገለገለቻቸው።</verse>
				<verse number="32">ፀሐይም ገብቶ በመሸ ጊዜ፥ የታመሙትንና አጋንንት ያደረባቸውን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤</verse>
				<verse number="33">ከተማይቱም ሁላ በደጅ ተሰብስባ ነበር።</verse>
				<verse number="34">በልዩ ልዩ ደዌም የታመሙትን ብዙዎችን ፈወሰ፤ ብዙዎችንም አጋንንት አወጣ፤ አጋንንትም ክርስቶስ መሆኑን አውቀው ነበርና ሊናገሩ አልፈቀደላቸውም።</verse>
				<verse number="35">ማለዳም ተነሥቶ ገና ሌሊት ሳለ ወጣ፤ ወደ ምድረ በዳም ሄዶ በዚያ ጸለየ።</verse>
				<verse number="36">ስምዖንና ከእርሱ ጋር የነበሩትም ገሥግሠው ተከተሉት፤</verse>
				<verse number="37">ባገኙትም ጊዜ “ሁሉ ይፈልጉሃል፤” አሉት።</verse>
				<verse number="38">እርሱም “በዚያ ደግሞ ልሰብክ ወደ ሌላ ስፍራ በቅርብ ወዳሉ መንደሮች እንሂድ፤ ስለዚህ መጥቻለሁና፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="39">በምኵራባቸውም እየሰበከ አጋንንትንም እያወጣ ወደ ገሊላ ሁሉ መጣ።</verse>
				<verse number="40">ለምጻምም ወደ እርሱ መጥቶ ተንበረከከና “ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ፤” ብሎ ለመነው።</verse>
				<verse number="41">ኢየሱስም አዘነለት እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና “እወድዳለሁ፤ ንጻ፤” አለው።</verse>
				<verse number="42">በተናገረም ጊዜ ለምጹ ወዲያው ለቀቀውና ነጻ።</verse>
				<verse number="43">በብርቱም ተናግሮ ወዲያው አሰናበተው፤</verse>
				<verse number="44">“ለማንም አንዳች እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ ያዘዘውን አቅርብ፤” አለው።</verse>
				<verse number="45">እርሱ ግን ሲወጣ ብዙ ሊሰብክና ነገሩን ሊያወራ ጀመረ፤ ስለዚህም ኢየሱስ ተገልጦ ወደ ከተማ መግባት ወደ ፊት ተሳነው፤ ነገር ግን በውጭ በምድረ በዳ ይኖር ነበር፤ ከየስፍራውም ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ደግሞ ገብቶ በቤት እንደ ሆነ ተሰማ።</verse>
				<verse number="2">በደጅ ያለው ስፍራም እስኪጠባቸው ድረስ ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ፤ ቃሉንም ይነግራቸው ነበር።</verse>
				<verse number="3">አራት ሰዎችም የተሸከሙትን ሽባ አመጡለት።</verse>
				<verse number="4">ስለ ሕዝቡም ብዛት ወደ እርሱ ማቅረብ ቢያቅታቸው እርሱ ያለበትን የቤቱን ጣራ አነሡ፤ ነድለውም ሽባው የተኛበትን አልጋ አወረዱ።</verse>
				<verse number="5">ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን “አንተ ልጅ! ኀጢአትህ ተሰረየችልህ፤” አለው።</verse>
				<verse number="6">ከጻፎችም አንዳንዶቹ በዚያ ተቀምጠው ነበር በልባቸውም “ይህ ሰው ስለ ምን እንደዚህ ያለ ስድብ ይናገራል?</verse>
				<verse number="7">ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኀጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል፤” ብለው አሰቡ።</verse>
				<verse number="8">ወዲያውም ኢየሱስ በልባቸው እንዲህ እንዳሰቡ በመንፈስ አውቆ እንዲህ አላቸው “በልባችሁ ይህን ስለ ምን ታስባላችሁ?</verse>
				<verse number="9">ሽባውን ‘ኀጢአትህ ተሰረየችልህ፤’ ከማለት ወይስ ‘ተነሣ አልጋህንም ተሸከምና ሂድ፤’ ከማለት ማናቸው ይቀላል?</verse>
				<verse number="10">ነገር ግን ለሰው ልጅ በምድር ላይ ኀጢአትን ሊያስተሰርይ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፤”</verse>
				<verse number="11">ሽባውን “አንተን እልሃለሁ፥ ተነሣ፤ አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ፤” አለው።</verse>
				<verse number="12">ተነሥቶም ወዲያው አልጋውን ተሸክሞ በሁሉ ፊት ወጣ፤ ስለዚህም ሰዎች ሁሉ ተገረሙና “እንዲህ ያለ ከቶ አላየንም፤” ብለው እግዚአብሔርን አከበሩ።</verse>
				<verse number="13">ደግሞም በባሕር አጠገብ ወጣ፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡና አስተማራቸው።</verse>
				<verse number="14">ሲያልፍም በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረውን የእልፍዮስን ልጅ ሌዊን አየና “ተከተለኝ፤” አለው። ተነሥቶም ተከተለው።</verse>
				<verse number="15">በቤቱም በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ ብዙ ቀራጮችና ኀጢአተኞች ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጡ፤ ብዙ ነበሩ፤ ይከተሉትም ነበር።</verse>
				<verse number="16">ጻፎችና ፈሪሳውያንም ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው ለደቀ መዛሙርቱ “ከቀራ ጮችና ከኀጢአተኞች ጋር የሚበላና የሚጠጣ ስለ ምንድር ነው?” አሉ።</verse>
				<verse number="17">ኢየሱስም ሰምቶ “ሕመምተኞች እንጂ ብርቱዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤ ኀጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="18">የዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና ፈሪሳውያን ይጾሙ ነበር። መጥተውም “የዮሐንስና የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት የሚጾሙት የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን የማይጾሙት ስለ ምንድር ነው?” አሉት።</verse>
				<verse number="19">ኢየሱስም አላቸው “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎች ሊጾሙ ይችላሉን? ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊጾሙ አይችሉም።</verse>
				<verse number="20">ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ በዚያ ወራትም ይጾማሉ።</verse>
				<verse number="21">በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚጥፍ የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አዲሱ መጣፊያ አሮጌውን ይቦጭቀዋል፤ መቀደዱም የባሰ ይሆናል።</verse>
				<verse number="22">በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል፤ የወይኑም ጠጅ ይፈሳል፤ አቁማዳውም ይጠፋል፤ አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ።”</verse>
				<verse number="23">በሰንበትም በእርሻ መካከል ሲያልፍ ደቀ መዛሙርቱ እየሄዱ እሸት ይቀጥፉ ጀመር።</verse>
				<verse number="24">ፈሪሳውያንም “እነሆ፥ በሰንበት ያልተፈቀደውን ስለ ምን ያደርጋሉ?” አሉት።</verse>
				<verse number="25">እርሱም “ዳዊት ባስፈለገውና በተራበ ጊዜ፥ እርሱ አብረውት ከነበሩት ጋር ያደረገውን፥</verse>
				<verse number="26">አብያተር ሊቀ ካህናት በነበረ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ገባ፥ ከካህናት በቀር መብላት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕትን እንጀራ እንደ በላ፥ ከእርሱም ጋር ለነበሩት እንደ ሰጣቸው ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው።</verse>
				<verse number="27">ደግሞ “ሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሮአል እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም፤</verse>
				<verse number="28">እንዲሁም የሰው ልጅ ለሰንበት እንኳ ጌታዋ ነው፤” አላቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ደግሞም ወደ ምኵራብ ገባ፤ በዚያም እጁ የሰለለች ሰው ነበር፤</verse>
				<verse number="2">ሊከሱትም በሰንበት ይፈውሰው እንደ ሆነ ይጠባበቁት ነበር።</verse>
				<verse number="3">እጁ የሰለለችውንም ሰው “ተነሥተህ ወደ መካከል ና፤” አለው።</verse>
				<verse number="4">“በሰንበት በጎ ማድረግ ተፈቅዶአልን? ወይስ ክፉ? ነፍስ ማዳን ወይስ መግደል?” አላቸው፤ እነርሱም ዝም አሉ።</verse>
				<verse number="5">ስለ ልባቸውም ድንዛዜ አዝኖ ዙሪያውን እየተመለከተ በቍጣ አያቸው፤ ሰውየውንም “እጅህን ዘርጋ፤” አለው። ዘረጋትም፤ እጁም ዳነች።</verse>
				<verse number="6">ፈሪሳውያንም ወጥተው ወዲያው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ከሄሮድስ ወገን ጋር ተማከሩበት።</verse>
				<verse number="7">ኢየሱስም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ባህር ፈቀቅ አለ፤ ከገሊላ የመጡም ብዙ ሰዎች ተከተሉት፤</verse>
				<verse number="8">እንዴት ትልቅ ነገርም እንዳደረገ ሰምተው ብዙ ሰዎች ከይሁዳ ከኢየሩሳሌምም ከኤዶምያስም ከዮርዳኖስ ማዶም ከጢሮስና ከሲዶና ምድርም ወደ እርሱ መጡ።</verse>
				<verse number="9">ሰዎቹም እንዳያጋፉት ታንኳን ያቆዩለት ዘንድ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው፤</verse>
				<verse number="10">ብዙ ሰዎችን አድኖ ነበርና፥ ስለዚህም ሥቃይ ያለባቸው ሁሉ እንዲዳስሱት ይወድቁበት ነበር።</verse>
				<verse number="11">ርኵሳን መናፍስትም ባዩት ጊዜ በፊቱ ተደፍተው “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤” እያሉ ጮኹ።</verse>
				<verse number="12">እንዳይገልጡትም በጣም አዘዛቸው።</verse>
				<verse number="13">ወደ ተራራም ወጣ፤ ራሱም የወደዳቸውን ወደ እርሱ ጠራ፤ ወደ እርሱም ሄዱ።</verse>
				<verse number="14">ከእርሱም ጋር እንዲኖሩና ለመስበክ እንዲልካቸው፥</verse>
				<verse number="15">ድውዮችንም ሊፈውሱ አጋንንትንም ሊያወጡ ሥልጣን ይሆንላቸው ዘንድ ዐሥራ ሁለት አደረገ፤</verse>
				<verse number="16">ስምዖንንም ጴጥሮስ ብሎ ሰየመው፤</verse>
				<verse number="17">የዘብዴዎስንም ልጅ ያዕቆብን የያዕቆብንም ወንድም ዮሐንስን ቦአኔርጌስ ብሎ ሰየማቸው፤ የነጎድጓድ ልጆች ማለት ነው፤</verse>
				<verse number="18">እንድርያስንም ፊልጶስንም በርተሎሜውስንም ማቴዎስንም ቶማስንም የእልፍዮስን ልጅ ያዕቆብንም ታዴዎስንም ቀነናዊውንም ስምዖንን፥</verse>
				<verse number="19">አሳልፎ የሰጠውንም የአስቆሮቱን ይሁዳን።</verse>
				<verse number="20">ወደ ቤትም መጡ፤ እንጀራም መብላት ስንኳ እስኪሳናቸው ድረስ እንደ ገና ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ።</verse>
				<verse number="21">ዘመዶቹም ሰምተው “አበደ” ብለዋልና ሊይዙት ወጡ።</verse>
				<verse number="22">ከኢየሩሳሌም የወረዱ ጻፎችም “ብዔል ዜቡል አለበት፤” ደግሞ “በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል፤” ብለው ተናገሩ።</verse>
				<verse number="23">እነርሱንም ወደ እርሱ ጠርቶ በምሳሌ አላቸው “ሰይጣን ሰይጣንን ሊያወጣው እንዴት ይችላል?</verse>
				<verse number="24">መንግሥትም እርስ በርስዋ ከተለያየች ያች መንግሥት ልትቆም አትችልም፤</verse>
				<verse number="25">ቤትም እርስ በርሱ ከተለያየ ያ ቤት ሊቆም አይችልም።</verse>
				<verse number="26">ሰይጣንም ራሱን ተቃውሞ ከተለያየ፥ መጨረሻ ይሆንበታል እንጂ ሊቆም አይችልም።</verse>
				<verse number="27">ነገር ግን አስቀድሞ ኀይለኛውን ሳያስር ወደ ኀይለኛው ቤት ገብቶ ዕቃውን ሊበዘብዝ የሚችል የለም፤ ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል።</verse>
				<verse number="28">“እውነት እላችኋለሁ፤ ለሰው ልጆች ኀጢአት ሁሉ የሚሳደቡትም ስድብ ሁሉ ይሰረይላቸዋል፤</verse>
				<verse number="29">በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚሳደብ ሁሉ ግን የዘላለም ኀጢአት ዕዳ ይሆንበታል እንጂ ለዘላለም አይሰረይለትም።”</verse>
				<verse number="30">“ርኵስ መንፈስ አለበት፤” ይሉ ነበርና።</verse>
				<verse number="31">እናቱና ወንድሞቹም መጡ፤ በውጭም ቆመው ወደ እርሱ ልከው አስጠሩት።</verse>
				<verse number="32">ብዙ ሰዎችም በዙሪያው ተቀምጠው ነበሩና “እነሆ፥ እናትህ ወንድሞችህም በውጭ ቆመው ይፈልጉሃል፤” አሉት።</verse>
				<verse number="33">መልሶም “እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነ ማን ናቸው?” አላቸው።</verse>
				<verse number="34">በዙሪያው ተቀምጠው ወደ ነበሩትም ተመለከተና “እነሆ እናቴ ወንድሞቼም።</verse>
				<verse number="35">የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ ነው፤ እኅቴም፤ እናቴም፤” አለ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ደግሞም በባሕር ዳር ሊያስተምር ጀመረ። እጅግ ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ ስለ ተሰበሰቡ እርሱ በታንኳ ገብቶ በባሕር ላይ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ በባሕር ዳር በምድር ላይ ነበሩ።</verse>
				<verse number="2">በምሳሌም ብዙ ያስተምራቸው ነበር፤ በትምህርቱም አላቸው።</verse>
				<verse number="3">“ስሙ! እነሆ፥ ዘሪ ሊዘራ ወጣ።</verse>
				<verse number="4">ሲዘራም አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀና ወፎች መጥተው በሉት።</verse>
				<verse number="5">ሌላውም ብዙ መሬት በሌለበት በጭንጫ ላይ ወደቀና ጥልቅ መሬት ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፤</verse>
				<verse number="6">ፀሐይም ሲወጣ ጠወለገ፤ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ።</verse>
				<verse number="7">ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፤ እሾህም ወጣና አነቀው፤ ፍሬም አልሰጠም።</verse>
				<verse number="8">ሌላውም በመልካም መሬት ላይ ወደቀና ወጥቶ አድጎ ፍሬ ሰጠ፤ አንዱም ሠላሳ አንዱም ስድሳ አንዱም መቶ አፈራ።</verse>
				<verse number="9">የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ፤” አለ።</verse>
				<verse number="10">ብቻውንም በሆነ ጊዜ በዙሪያው የነበሩት ከዐሥራ ሁለቱ ጋር ስለ ምሳሌው ጠየቁት።</verse>
				<verse number="11">እንዲህም አላቸው “ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ በውጭ ላሉት ግን፥ ‘አይተው እንዲያዩ እንዳይመለከቱም፤ ሰምተውም እንዲሰሙ እንዳያስተውሉም፤ እንዳይመለሱ ኀጢአታቸውም እንዳይሰረይላቸው’ ነገር ሁሉ በምሳሌ ይሆንባቸዋል።”</verse>
				<verse number="12"></verse>
				<verse number="13">አላቸውም “ይህን ምሳሌ አታውቁምን? እንዴትስ ምሳሌዎቹን ሁሉ ታውቃላችሁ?</verse>
				<verse number="14">ዘሪው ቃሉን ይዘራል። ቃልም በተዘራበት በመንገድ ዳር የሆኑት እነዚህ ናቸው፤</verse>
				<verse number="15">በሰሙት ጊዜም ሰይጣን ወዲያው መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ቃል ይወስዳል።</verse>
				<verse number="16">እንዲሁም በጭንጫ ላይ የተዘሩት እነዚህ ናቸው፤ ቃሉንም ሰምተው ወዲያው በደስታ ይቀበሉታል፤</verse>
				<verse number="17">ለጊዜው ነው እንጂ በእነርሱ ሥር የላቸውም፤ ኋላም በቃሉ ምክንያት መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላሉ።</verse>
				<verse number="18">በእሾህም የተዘሩት ሌሎች ናቸው፤ ቃሉን የሰሙት እነዚህ ናቸው፤</verse>
				<verse number="19">የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌላውም ነገር ምኞት ገብተው ቃሉን ያንቃሉ፤ የማያፈራም ይሆናል።</verse>
				<verse number="20">በመልካምም መሬት የተዘሩት ቃሉን ሰምተው የሚቀበሉት አንዱም ሠላሳ አንዱም ስድሳ አንዱም መቶ ፍሬ የሚያፈሩት እነዚህ ናቸው።”</verse>
				<verse number="21">እንዲህም አላቸው “መብራትን ከዕንቅብ ወይስ ከአልጋ በታች ሊያኖሩት ያመጡታልን? በመቅረዝ ላይ ሊያኖሩት አይደለምን?</verse>
				<verse number="22">እንዲገለጥ ባይሆን የተሰወረ የለምና፤ ወደ ግልጥ እንዲመጣ እንጂ የተሸሸገ የለም።</verse>
				<verse number="23">የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ።”</verse>
				<verse number="24">አላቸውም “ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ። በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል፤ ለእናንተም ይጨመርላችኋል።</verse>
				<verse number="25">ላለው ይሰጠዋልና፤ ከሌለውም ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።”</verse>
				<verse number="26">እርሱም አለ፤ “በምድር ዘርን እንደሚዘራ ሰው የእግዚአብሔር መንግሥት እንደዚህ ናት፤</verse>
				<verse number="27">ሌሊትና ቀን ይተኛልም፤ ይነሣልም፤ እርሱም እንዴት እንደሚሆን ሳያውቅ ዘሩ ይበቅላል፤ ያድግማል።</verse>
				<verse number="28">ምድሪቱም አውቃ በመጀመሪያ ቡቃያ ኋላም ዛላ ኋላም በዛላው ፍጹም ሰብል ታፈራለች።</verse>
				<verse number="29">ፍሬ ግን ሲበስል መከር ደርሶአልና ወዲያው ማጭድ ይልካል።”</verse>
				<verse number="30">እርሱም አለ “የእግዚአብሔርን መንግሥት በምን እናስመስላታለን? ወይስ በምን ምሳሌ እንመስላታለን?</verse>
				<verse number="31">እንደ ሰናፍጭ ቅንጣት ናት፤ እርስዋም በምድር በተዘራች ጊዜ በምድር ካለ ዘር ሁሉ ታንሳለች፤</verse>
				<verse number="32">በተዘራችም ጊዜ ትወጣለች፤ ከአትክልትም ሁሉ የምትበልጥ ትሆናለች፤ የሰማይ ወፎችም በጥላዋ ሊሰፍሩ እስኪችሉ ታላላቅ ቅርንጫፎች ታደርጋለች።”</verse>
				<verse number="33">መስማትም በሚችሉበት መጠን እነዚህን በሚመስል በብዙ ምሳሌ ቃሉን ይነግራቸው ነበር፤ ያለ ምሳሌ ግን አልነገራቸውም፤</verse>
				<verse number="34">ለብቻቸውም ሲሆኑ ነገሩን ሁሉ ለገዛ ደቀ መዛሙርቱ ይፈታላቸው ነበር።</verse>
				<verse number="35">በዚያም ቀን በመሸ ጊዜ “ወደ ማዶ እንሻገር፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="36">ሕዝቡንም ትተው በታንኳዪቱ ውስጥ እንዳለ ወሰዱት፤ ሌሎች ታንኳዎችም ከእርሱ ጋር ነበሩ።</verse>
				<verse number="37">ብርቱ ዐውሎ ነፋስም ተነሣና ውሃ በታንኳይቱ እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ በታንኳይቱ ይገባ ነበር።</verse>
				<verse number="38">እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ አንቅተውም “መምህር ሆይ! ስንጠፋ አይገድህምን?” አሉት።</verse>
				<verse number="39">ነቅቶም ነፋሱን ገሠጸው፤ ባሕሩንም “ዝም በል፤ ፀጥ በል፤” አለው። ነፋሱም ተወ ታላቅ ፀጥታም ሆነ።</verse>
				<verse number="40">“እንዲህ የምትፈሩ ስለ ምን ነው? እንዴትስ እምነት የላችሁም?” አላቸው።</verse>
				<verse number="41">እጅግም ፈሩና “እንግዲህ ነፋስም ባሕርም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው?” ተባባሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">ወደ ባሕር ማዶም ወደ ጌርጌሴኖን አገር መጡ።</verse>
				<verse number="2">ከታንኳይቱም በወጣ ጊዜ፥ ርኵስ መንፈስ የያዘው ሰው ከመቃብር ወጥቶ ወዲያው ተገናኘው፤</verse>
				<verse number="3">እርሱም በመቃብር ይኖር ነበር፤ በሰንሰለትም ስንኳ ማንም ሊያስረው በዚያን ጊዜ አይችልም ነበር፤</verse>
				<verse number="4">ብዙ ጊዜ በእግር ብረትና በሰንሰለት ይታሰር ነበርና፤ ዳሩ ግን ሰንሰለቱን ይበጣጥስ እግር ብረቱንም ይሰባብር ነበር፤ ሊያሸንፈውም የሚችል አልነበረም፤</verse>
				<verse number="5">ሁልጊዜም ሌሊትና ቀን በመቃብርና በተራራ ሆኖ ይጮኽ ነበር፤ ሰውነቱንም በድንጋይ ይቧጭር ነበር።</verse>
				<verse number="6">ኢየሱስንም ከሩቅ ባየ ጊዜ ሮጦ ሰገደለት፤</verse>
				<verse number="7">በታላቅ ድምፅም እየጮኸ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለኝ? እንዳታሠቃየኝ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤” አለ፤</verse>
				<verse number="8">“አንተ ርኵስ መንፈስ፥ ከዚህ ሰው ውጣ፤” ብሎት ነበርና።</verse>
				<verse number="9">“ስምህ ማን ነው?” ብሎ ጠየቀው። “ብዙዎች ነንና ስሜ ሌጌዎን ነው፤” አለው፤</verse>
				<verse number="10">ከአገርም ውጭ እንዳይሰዳቸው አጥብቆ ለመነው።</verse>
				<verse number="11">በዚያም በተራራ ጥግ ብዙ የእሪያ መንጋ ይሰማራ ነበርና</verse>
				<verse number="12">“ወደ እሪያዎቹ እንድንገባ ስደደን፤” ብለው ለመኑት።</verse>
				<verse number="13">ኢየሱስም ፈቀደላቸው። ርኵሳን መናፍስቱም ወጥተው ወደ እሪያዎቹ ገቡ፤ ሁለት ሺህም የሚያህል መንጋ ከአፋፉ ወደ ባሕር ተጣደፉና በባሕር ሰጠሙ።</verse>
				<verse number="14">እረኞቹም ሸሽተው በከተማውና በአገሩ አወሩ፤ ነገሩም ምን እንደ ሆነ ለማየት መጡ።</verse>
				<verse number="15">ወደ ኢየሱስም መጡ፤ አጋንንትም ያደሩበትን ሌጌዎንም የነበረበትን ሰው ተቀምጦ ለብሶም ልቡም ተመልሶ አዩና ፈሩ።</verse>
				<verse number="16">ያዩት ሰዎችም አጋንንት ላደሩበት ሰው የሆነውንና ስለ እሪያዎቹ ተረኩላቸው።</verse>
				<verse number="17">ከአገራቸውም እንዲሄድላቸው ይለምኑት ጀመር።</verse>
				<verse number="18">ወደ ታንኳይቱም በገባ ጊዜ አጋንንት አድረውበት የነበረው ሰው ከእርሱ ጋር እንዲኖር ለመነው።</verse>
				<verse number="19">ኢየሱስም አልፈቀደለትም፤ ነገር ግን “ወደ ቤትህ ወደ ቤተ ሰዎችህ ዘንድ ሄደህ ጌታ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገልህ እንዴትስ እንደ ማረህ አውራላቸው፤” አለው።</verse>
				<verse number="20">ሄዶም ኢየሱስ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገለት ዐሥር ከተማ በሚባል አገር ይሰብክ ጀመር፤ ሁሉም ተደነቁ።</verse>
				<verse number="21">ኢየሱስም ደግሞ በታንኳይቱ ወደ ማዶ ከተሻገረ በኋላ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ በባሕርም አጠገብ ነበረ።</verse>
				<verse number="22">ኢያኢሮስ የተባለ ከምኵራብ አለቆች አንዱ መጣ፤ ባየውም ጊዜ በእግሩ ላይ ወደቀና</verse>
				<verse number="23">“ታናሽቱ ልጄ ልትሞት ቀርባለችና እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት፤” ብሎ አጥብቆ ለመነው።</verse>
				<verse number="24">ከእርሱም ጋር ሄደ። ብዙ ሕዝብም ተከተሉት አጋፉትም።</verse>
				<verse number="25">ከዐሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፤</verse>
				<verse number="26">ከብዙ ባለ መድኃኒቶችም ብዙ ተሠቃየች፤ ገንዘብዋንም ሁሉ ከስራ ባሰባት እንጂ ምንም አልተጠቀመችም፤</verse>
				<verse number="27">የኢየሱስንም ወሬ ሰምታ በስተኋላው በሰዎች መካከል መጥታ ልብሱን ዳሰሰች</verse>
				<verse number="28">“ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ እድናለሁ፤” ብላለችና።</verse>
				<verse number="29">ወዲያውም የደምዋ ምንጭ ደረቀ፤ ከሥቃይዋም እንደዳነች በሰውነትዋ አወቀች።</verse>
				<verse number="30">ወዲያውም ኢየሱስ ከእርሱ ኃይል እንደ ወጣ በገዛ ራሱ አውቆ በሕዝቡ መካከል ዘወር ብሎ “ልብሴን የዳሰሰ ማን ነው?” አለ።</verse>
				<verse number="31">ደቀ መዛሙርቱም “ሕዝቡ ሲያጋፉህ እያየህ ‘ማን ዳሰሰኝ?” ትላለህን?” አሉት።</verse>
				<verse number="32">ይህንም ያደረገችውን ለማየት ዘወር ብሎ ይመለከት ነበር።</verse>
				<verse number="33">ሴቲቱ ግን የተደረገላትን ስላወቀች፥ እየፈራች እየተንቀጠቀጠችም፥ መጥታ በፊቱ ተደፋች፤ እውነቱንም ሁሉ ነገረችው።</verse>
				<verse number="34">እርሱም “ልጄ ሆይ! እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፤ ከሥቃይሽም ተፈወሽ፤” አላት።</verse>
				<verse number="35">እርሱም ገና ሲናገር ከምኵራብ አለቃው ቤት ዘንድ የመጡት “ልጅህ ሞታለች፤ ስለ ምን መምህሩን አሁን ታደክመዋለህ?” አሉት።</verse>
				<verse number="36">ኢየሱስ ግን የተናገሩትን ቃል አድምጦ ለምኵራቡ አለቃ “እመን ብቻ እንጂ አትፍራ፤” አለው።</verse>
				<verse number="37">ከጴጥሮስም ከያዕቆብም ከያዕቆብም ወንድም ከዮሐንስ በቀር ማንም እንዲከተለው አልፈቀደም።</verse>
				<verse number="38">ወደ ምኵራቡ አለቃ ቤትም መጥቶ ሰዎች ሲንጫጩና ሲያለቅሱ ዋይታም ሲያበዙ አየ፤</verse>
				<verse number="39">ገብቶም “ስለ ምን ትንጫጫላችሁ? ታለቅሳላችሁም? ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="40">በጣምም ሳቁበት። እርሱ ግን ሁሉን አስወጥቶ የብላቴናይቱን አባትና እናት ከእርሱ ጋር የነበሩትንም ይዞ ብላቴናይቱ ወዳለችበት ገባ።</verse>
				<verse number="41">የብላቴናይቱንም እጅ ይዞ “ጣሊታ ቁሚ!” አላት፤ ፍችውም “አንቺ ብላቴና ተነሽ እልሻለሁ!” ነው።</verse>
				<verse number="42">ብላቴናይቱም የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረችና ወዲያው ቆማ ተመላለሰች። ወዲያውም ታላቅ መገረም ተገረሙ።</verse>
				<verse number="43">ይህንም ማንም እንዳያውቅ አጥብቆ አዞአቸው “የምትበላውን ስጡአት፤” አላቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">ከዚያም ወጥቶ ወደ ገዛ አገሩ መጣ፤ ደቀ መዛሙርቱም ተከተሉት።</verse>
				<verse number="2">ሰንበትም በሆነ ጊዜ በምኵራብ ያስተምር ጀመር፤ ብዙዎችም ሰምተው ተገረሙና “እነዚህን ነገሮች ይህ ከወዴት አገኛቸው? ለዚህ የተሰጠችው ጥበብ ምንድር ናት? በእጁም የሚደረጉ እንደነዚህ ያሉ ተአምራት ምንድር ናቸው?</verse>
				<verse number="3">ይህስ ጸራቢው የማርያም ልጅ የያቆብም የዮሳም የይሁዳም የስምዖንም ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ በዚህ በእኛ ዘንድ አይደሉምን?” አሉ፤ ይሰናከሉበትም ነበር።</verse>
				<verse number="4">ኢየሱስም “ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ዘመዶቹ ከገዛ ቤቱም በቀር ሳይከበር አይቀርም፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="5">በዚያም በጥቂቶች ድውዮች ላይ እጁን ጭኖ ከመፈወስ በቀር፥ ተአምር ሊያደርግ ምንም አልቻለም።</verse>
				<verse number="6">ስለ አለማመናቸውም ተደነቀ። በመንደሮችም እያስተማረ ይዞር ነበር።</verse>
				<verse number="7">ዐሥራ ሁለቱንም ወደ እርሱ ጠራ፤ ሁለት ሁለቱንም ይልካቸው ጀመር፤ በርኵሳን መናፍስትም ላይ ሥልጣን ሰጣቸው፤</verse>
				<verse number="8">ለመንገድም ከበትር በቀር እንጀራም ቢሆን ከረጢትም ቢሆን መሐለቅም በመቀነታቸው ቢሆን እንዳይዙ አዘዛቸው።</verse>
				<verse number="9">“በእግራችሁ ጫማ አድርጉ እንጂ ሁለት እጀ ጠባብ አትልበሱ፤” አለ።</verse>
				<verse number="10">“በማናቸውም ስፍራ ወደ ቤት ብትገቡ ከዚያ እስክትወጡ ድረስ በዚያው ተቀመጡ።</verse>
				<verse number="11">ከማይቀበሉአችሁና ከማይሰሙአችሁ ስፍራ ሁሉ፥ ከዚያ ወጥታችሁ ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ ከእግራችሁ በታች ያለውን ትቢያ አራግፉ። እውነት እላችኋለሁ፤ ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ በፍርድ ቀን ይቀልላቸዋል፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="12">ወጥተውም ንስሐ እንዲገቡ ሰበኩ፤</verse>
				<verse number="13">ብዙ አጋንንትንም አወጡ፤ ብዙ ድውዮችንም ዘይት እየቀቡ ፈወሱአቸው።</verse>
				<verse number="14">ስሙም ተገልጦአልና ንጉሡ ሄሮድስ በሰማ ጊዜ “መጥምቁ ዮሐንስ ከሙታን ተነሥቶአል፤ ስለዚህም ኀይል በእርሱ ይደረጋል፤” አለ።</verse>
				<verse number="15">ሌሎችም “ኤልያስ ነው፤” አሉ፤ ሌሎችም “ከነቢያት እንደ አንዱ ነቢይ ነው፤” አሉ።</verse>
				<verse number="16">ሄሮድስ ግን ሰምቶ “እኔ ራሱን ያስቈረጥሁት ዮሐንስ ይህ ነው፤ እርሱ ከሙታን ተነሥቶአል፤” አለ።</verse>
				<verse number="17">ሄሮድስ የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን አግብቶ ነበርና በእርስዋ ምክንያት ራሱ ልኮ ዮሐንስን አስይዞ በወኅኒ አሳስሮት ነበር፤</verse>
				<verse number="18">ዮሐንስ ሄሮድስን “የወንድምህ ሚስት ለአንተ ልትሆን አልተፈቀደም፤” ይለው ነበርና።</verse>
				<verse number="19">ሄሮድያዳ ግን ተቃውማው ልትገድለው ትፈልግ ነበር፤ አልቻለችም፤</verse>
				<verse number="20">ሄሮድስ ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ ሰው እንደ ሆነ አውቆ ይፈራውና ይጠባበቀው ነበር፤ እርሱንም ሰምቶ በብዙ ነገር ያመነታ ነበር፤ በደስታም ይሰማው ነበር።</verse>
				<verse number="21">ሄሮድስም በተወለደበት ቀን ለመኳንንቱና ለሻለቆቹ ለገሊላም ሹማምንት ግብር ባደረገ ጊዜ ምቹ ቀን ሆነላትና</verse>
				<verse number="22">የሄሮድያዳ ልጅ ገብታ ስትዘፍን ሄሮድስንና ከእርሱ ጋር የተቀመጡትን ደስ አሰኘቻቸው። ንጉሡም ብላቴናይቱን “የምትወጂውን ሁሉ ለምኚኝ፤ እሰጥሽማለሁ፤” አላት፤</verse>
				<verse number="23">“የመንግሥቴ እኩሌታ ስንኳ ቢሆን የምትለምኚውን ሁሉ እሰጥሻለሁ፤” ብሎ ማለላት።</verse>
				<verse number="24">ወጥታም ለእናትዋ “ምን ልለምነው?” አለች። እርስዋም “የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ” አለች።</verse>
				<verse number="25">ወዲያውም ፈጥና ወደ ንጉሡ ገብታ “የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ በወጭት አሁን ልትሰጠኝ እወዳለሁ፤” ብላ ለመነችው።</verse>
				<verse number="26">ንጉሡም እጅግ አዝኖ ስለ መሐላው ከእርሱም ጋር ስለ ተቀመጡት ሊነሣት አልወደደም።</verse>
				<verse number="27">ወዲያውም ንጉሡ ባለ ወግ ልኮ ራሱን እንዲያመጣ አዘዘው። ሄዶም በወኅኒ ራሱን ቈረጠ፤</verse>
				<verse number="28">ራሱንም በወጭት አምጥቶ ለብላቴናይቱ ሰጣት፤ ብላቴናይቱም ለእናትዋ ሰጠች።</verse>
				<verse number="29">ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው መጡ፤ በድኑንም ወስደው ቀበሩት።</verse>
				<verse number="30">ሐዋርያትም ወደ ኢየሱስ ተሰብስበው ያደረጉትንና ያስተማሩትን ሁሉ ነገሩት።</verse>
				<verse number="31">“እናንተ ራሳችሁ ብቻችሁን ወደ ምድረ በዳ ኑና ጥቂት ዕረፉ፤” አላቸው፤ የሚመጡና የሚሄዱ ብዙዎች ነበሩና፥ ለመብላት እንኳ ጊዜ አጡ።</verse>
				<verse number="32">በታንኳውም ብቻቸውን ወደ ምድረ በዳ ሄዱ።</verse>
				<verse number="33">ሰዎችም ሲሄዱ አዩአቸው፤ ብዙዎችም አወቁአቸውና ከከተሞች ሁሉ በእግር እየሮጡ ወዲያ ቀደሙአቸው፤ ወደ እርሱም ተሰበሰቡ።</verse>
				<verse number="34">ኢየሱስም ወጥቶ ብዙ ሕዝብ አየና እረኛ እንደሌላቸው በጎች ስለ ነበሩ አዘነላቸው፤ ብዙም ነገር ያስተምራቸው ጀመር።</verse>
				<verse number="35">በዚያን ጊዜም ብዙ ሰዓት ካለፈ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው “ቦታው ምድረ በዳ ነው፤ አሁንም መሽቶአል፤</verse>
				<verse number="36">የሚበሉት የላቸውምና በዙሪያ ወዳሉ ገጠሮችና መንደሮች ሄደው እንጀራ ለራሳቸው እንዲገዙ አሰናብታቸው፤” አሉት።</verse>
				<verse number="37">እርሱ ግን መልሶ “እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው፤” አላቸው። “ሄደን እንጀራ በሁለት መቶ ዲናር እንግዛላቸውን? እንዲበሉም እንስጣቸውን?” አሉት።</verse>
				<verse number="38">እርሱም “ስንት እንጀራ አላችሁ? ሂዱና እዩ፤” አላቸው። ባወቁም ጊዜ “አምስት፥ ሁለትም ዓሣ፤” አሉት።</verse>
				<verse number="39">ሁሉንም በየክፍሉ በለመለመ ሣር ላይ እንዲያስቀምጡአቸው አዘዛቸው።</verse>
				<verse number="40">መቶ መቶውና አምሳ አምሳው እየሆኑ በተራ በተራ ተቀመጡ።</verse>
				<verse number="41">አምስቱንም እንጀራ ሁለቱንም ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና ባረከ፤ እንጀራውንም ቈርሶ እንዲያቀርቡላቸው ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤</verse>
				<verse number="42">ሁለቱን ዓሣ ደግሞ ለሁሉ ከፈለ። ሁሉም በልተው ጠገቡ፤</verse>
				<verse number="43">ከቍርስራሹም ዐሥራ ሁለት መሶብ የሞላ አነሡ፤ ከዓሣውም ደግሞ።</verse>
				<verse number="44">እንጀራውንም የበሉት ወንዶቹ አምስት ሺህ ነበሩ።</verse>
				<verse number="45">ወዲያውም ሕዝቡን ሲያሰናብት ሳለ ደቀ መዛሙርቱ በታንኳ ገብተው ወደ ማዶ ወደ ቤተ ሳይዳ እንዲቀድሙት ግድ አላቸው።</verse>
				<verse number="46">ካሰናበታቸውም በኋላ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ።</verse>
				<verse number="47">በመሸም ጊዜ ታንኳይቱ በባሕር መካከል ሳለች እርሱ ብቻውን በምድር ላይ ነበረ።</verse>
				<verse number="48">ነፋስ ከወደ ፊታቸው ነበረና እየቀዘፉ ሲጨነቁ አይቶ፥ ከሌሊቱ በአራተኛው ክፍል በባሕር ላይ እየሄደ ወደ እነርሱ መጣ፤ ሊያልፋቸውም ይወድ ነበር።</verse>
				<verse number="49">እነርሱ ግን በባሕር ላይ ሲሄድ ባዩት ጊዜ ምትሀት መሰላቸውና ጮኹ፤</verse>
				<verse number="50">ሁሉ አይተውታልና ታወኩም። ወዲያውም ተናገራቸውና “አይዞአችሁ፤ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="51">ወደ እነርሱም ወደ ታንኳይቱ ገባ፤ ነፋሱም ተወ፤ እነርሱ ራሳቸው ያለ መጠን እጅግ ተገረሙ፤</verse>
				<verse number="52">ስለ እንጀራው አላስተዋሉምና፤ ነገር ግን ልባቸው ደንዝዞ ነበር።</verse>
				<verse number="53">ተሻግረውም ወደ ምድር ወደ ጌንሴሬጥ ደረሱ፤ ታንኳይቱንም አስጠጉ።</verse>
				<verse number="54">ከታንኳይቱም ሲወጡ ወዲያው አውቀውት</verse>
				<verse number="55">በዚያች አገር ሁሉ ዙሪያ ሮጡና እርሱ እንዳለ ወደ ሰሙበት ስፍራ ሕመምተኞችን በአልጋ ላይ ያመጡ ጀመር።</verse>
				<verse number="56">በገባበትም ስፍራ ሁሉ፥ መንደርም ከተማም ገጠርም ቢሆን፥ በገበያ ድውዮችን ያኖሩ ነበር፤ የልብሱንም ጫፍ እንኳ ሊዳስሱ ይለምኑት ነበር፤ የዳሰሱትም ሁሉ ዳኑ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">ፈሪሳውያንና ከጻፎች ወገን ከኢየሩሳሌም የመጡትም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ።</verse>
				<verse number="2">ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንድ በርኵስ ማለት ባልታጠበ እጅ እንጀራ ሲበሉ አዩ።</verse>
				<verse number="3">ፈሪሳውያንና አይሁድም ሁሉ የሽማግሎችን ወግ ሲጠብቁ እጃቸውን ደኅና አድርገው ሳይታጠቡ አይበሉምና፤</verse>
				<verse number="4">ከገበያም ተመልሰው ካልታጠቡ አይበሉም፤ ጽዋንም ማድጋንም የናስ ዕቃንም አልጋንም እንደ ማጠብ ሌላ ነገር ሊጠብቁት የተቀበሉት ብዙ አለ።</verse>
				<verse number="5">ፈሪሳውያንና ጻፎችም “ደቀ መዛሙርትህ እንደ ሽማግሌዎች ወግ ስለ ምን አይሄዱም? ነገር ግን እጃቸውን ሳይታጠቡ እንጀራ ይበላሉ፤” ብለው ጠየቁት።</verse>
				<verse number="6">እርሱ ግን እንዲህ አላቸው “ኢሳይያስ ስለ እናንተ ስለ ግብዞች ‘ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤</verse>
				<verse number="7">የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል፤’ ተብሎ እንደ ተጻፈ በእውነት ትንቢት ተናገረ።</verse>
				<verse number="8">የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ ጽዋን ማድጋንም እንደ ማጠብ የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ፤ ይህንም የመሰለ ብዙ ሌላ ነገር ታደርጋላችሁ።”</verse>
				<verse number="9">እንዲህም አላቸው “ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እጅግ ንቃችኋል።</verse>
				<verse number="10">ሙሴ ‘አባትህንና እናትህን አክብር፤’ ደግሞም ‘አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት፤’ ብሎአልና።</verse>
				<verse number="11">እናንተ ግን ትላላችሁ ‘ሰው አባቱን ወይም እናቱን ከእኔ የምትጠቀምበት ነገር ሁሉ ቍርባን ማለት መባ ነው፤’ ቢል፥</verse>
				<verse number="12">ለአባቱና ለእናቱ ምንም እንኳ ሊያደርግ ወደ ፊት አትፈቅዱለትም፤</verse>
				<verse number="13">ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤ እንደዚሁም ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ።”</verse>
				<verse number="14">ደግሞም ሕዝቡን ጠርቶ “ሁላችሁ እኔን ስሙ፤ አስተውሉም።</verse>
				<verse number="15">ከሰው የሚወጡት ሰውን የሚያረክሱ ናቸው እንጂ ከሰው ውጭ የሚገባውስ ሊያረክሰው የሚችል ምንም የለም።</verse>
				<verse number="16">የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="17">ከሕዝቡ ዘንድ ወደ ቤት ከገባ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ምሳሌውን ጠየቁት።</verse>
				<verse number="18">እርሱም “እናንተ ደግሞ እንደዚህ የማታስተውሉ ናችሁን? ከውጭ ወደ ሰው የሚገባ ሊያረክሰው ምንም እንዳይችል አትመለከቱምን?</verse>
				<verse number="19">ወደ ሆድ ገብቶ ወደ እዳሪ ይወጣል እንጂ ወደ ልብ አይገባምና፤ መብልን ሁሉ እያጠራ፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="20">እርሱም አለ “ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ያ ነው።</verse>
				<verse number="21">ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፥</verse>
				<verse number="22">ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና፤</verse>
				<verse number="23">ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል፤ ሰውን ያረክሰዋል።”</verse>
				<verse number="24">ከዚያም ተነሥቶ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና አገር ሄደ። ወደ ቤትም ገብቶ ማንም እንዳያውቅበት ወደደ፤ ሊሰወርም አልተቻለውም፤</verse>
				<verse number="25">ወዲያው ግን ታናሺቱ ልጅዋ ርኵስ መንፈስ ያደረባት አንዲት ሴት ስለ እርሱ ሰምታ መጣችና በእግሩ ላይ ተደፋች፤</verse>
				<verse number="26">ሴቲቱም ግሪክ፥ ትውልድዋም ሲሮፊኒቃዊት ነበረች፤ ከልጅዋ ጋኔን ያወጣላት ዘንድ ለመነችው።</verse>
				<verse number="27">ኢየሱስ ግን “ልጆቹ በፊት ይጠግቡ ዘንድ ተዪ፤ የልጆቹን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባምና” አላት።</verse>
				<verse number="28">እርስዋም መልሳ “አዎን፥ ጌታ ሆይ! ቡችሎች እንኳ ከማዕድ በታች ሆነው የልጆችን ፍርፋሪ ይበላሉ፤” አለችው።</verse>
				<verse number="29">እርሱም “ስለዚህ ቃልሽ ሂጂ፤ ጋኔኑ ከልጅሽ ወጥቶአል፤” አላት።</verse>
				<verse number="30">ወደ ቤትዋም ሄዳ ጋኔኑ ወጥቶ ልጅዋም በአልጋ ላይ ተኝታ አገኘች።</verse>
				<verse number="31">ደግሞም ከጢሮስ አገር ወጥቶ በሲዶና አልፎ ዐሥር ከተማ በሚባል አገር መካከል ወደ ገሊላ ባሕር መጣ።</verse>
				<verse number="32">ደንቆሮና ኰልታፋም የሆነ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፤</verse>
				<verse number="33">እጁንም ይጭንበት ዘንድ ለመኑት። ከሕዝቡም ለይቶ ለብቻው ወሰደው፤ ጣቶቹንም በጆሮቹ አገባ፤ እንትፍም ብሎ መላሱን ዳሰሰ፤</verse>
				<verse number="34">ወደ ሰማይም አሻቅቦ አይቶ ቃተተና “ኤፍታህ” አለው፤ እርሱም “ተከፈት” ማለት ነው።</verse>
				<verse number="35">ወዲያውም ጆሮቹ ተከፈቱ የምላሱም እስራት ተፈታ፤ አጥርቶም ተናገረ።</verse>
				<verse number="36">“ለማንም አትንገሩ፤” ብሎ አዘዛቸው፤ እነርሱ ግን ባዘዛቸውም መጠን ይልቅ እጅግ አወሩት።</verse>
				<verse number="37">ያለ መጠንም ተገረሙና “ሁሉን ደኅና አድርጎአል፤ ደንቆሮችም እንዲሰሙ ዲዳዎችም እንዲናገሩ ያደርጋል፤” አሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">በዚያ ወራት ደግሞ ብዙ ሕዝብ ነበረ፤ የሚበሉትም ስለሌላቸው ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ</verse>
				<verse number="2">“ሕዝቡ ከእኔ ጋር እስካሁን ሦስት ቀን ውለዋልና የሚበሉት ስለሌላቸው አዝንላቸዋለሁ፤</verse>
				<verse number="3">ከእነርሱም አንዳንዶቹ ከሩቅ መጥተዋልና፥ ጦማቸውን ወደ ቤታቸው ባሰናብታቸው በመንገድ ይዝላሉ፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="4">ደቀ መዛሙርቱም “በዚህ በምድረ በዳ እንጀራ ከየት አግኝቶ ሰው እነዚህን ማጥገብ ይችላል?” ብለው መለሱለት።</verse>
				<verse number="5">እርሱም “ስንት እንጀራ አላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው፤ እነርሱም “ሰባት” አሉት።</verse>
				<verse number="6">ሕዝቡም በምድር እንዲቀመጡ አዘዘ። ሰባቱንም እንጀራ ይዞ አመሰገነ፤ ቈርሶም እንዲያቀርቡላቸው ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ ለሕዝቡም አቀረቡ።</verse>
				<verse number="7">ጥቂትም ትንሽ ዓሣ ነበራቸው፤ ባረከውም፤ ይህንም ደግሞ እንዲያቀርቡላቸው አዘዘ።</verse>
				<verse number="8">በሉም፤ ጠገቡም፤ የተረፈውንም ቍርስራሽ ሰባት ቅርጫት አነሡ።</verse>
				<verse number="9">የበሉትም አራት ሺህ ያህል ነበሩ፤ አሰናበታቸውም።</verse>
				<verse number="10">ወዲያውም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳይቱ ገብቶ ወደ ዳልማኑታ አገር መጣ።</verse>
				<verse number="11">ፈሪሳውያንም ወጡና ሊፈትኑት ከሰማይ ምልክት ከእርሱ ፈልገው ከእርሱ ጋር ይከራከሩ ጀመር።</verse>
				<verse number="12">በመንፈሱም እጅግ ቃተተና “ይህ ትውልድ ስለ ምን ምልክት ይፈልጋል? እውነት እላችኋለሁ፤ ለዚህ ትውልድ ምልክት አይሰጠውም፤” አለ።</verse>
				<verse number="13">ትቶአቸውም እንደ ገና ወደ ታንኳይቱ ገብቶ ወደ ማዶ ሄደ።</verse>
				<verse number="14">እንጀራ መያዝም ረሱ፤ ለእነርሱም ከአንድ እንጀራ በቀር በታንኳይቱ አልነበራቸውም።</verse>
				<verse number="15">እርሱም “ተጠንቀቁ፤ ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ እርሾ ተጠበቁ፤” ብሎ አዘዛቸው።</verse>
				<verse number="16">እርስ በርሳቸውም “እንጀራ ስለሌለን ይሆናል፤” ብለው ተነጋገሩ።</verse>
				<verse number="17">ኢየሱስም አውቆ እንዲህ አላቸው “እንጀራ ስለሌላችሁ ስለ ምን ትነጋገራላችሁ? ገና አልተመለከታችሁምን? አላስተዋላችሁምን?</verse>
				<verse number="18">ልባችሁስ ደንዝዞአልን? ዐይን ሳላችሁ አታዩምን? ጆሮስ ሳላችሁ አትሰሙምን? ትዝስ አይላችሁምን?</verse>
				<verse number="19">አምስቱን እንጀራ ለአምስት ሺህ በቈረስሁ ጊዜ፥ ቍርስራሹ የሞላ ስንት መሶብ አነሣችሁ” እነርሱም “ዐሥራ ሁለት፤” አሉት።</verse>
				<verse number="20">ሰባቱን እንጀራስ ለአራት ሺህ በቈረስሁ ጊዜ፥ ቍርስራሹ የሞላ ስንት ቅርጫት አነሣችሁ? እነርሱም “ሰባት” አሉት።</verse>
				<verse number="21">“ገና አላስተዋላችሁምን?” አላቸው።</verse>
				<verse number="22">ወደ ቤተ ሳይዳም መጡ። ዕውርም አመጡለት፤ እንዲዳስሰውም ለመኑት።</verse>
				<verse number="23">ዕውሩንም እጁን ይዞ ከመንደር ውጭ አወጣው፤ በዐይኑም ተፍቶበት እጁንም ጭኖበት “አንዳች ታያለህን?” ብሎ ጠየቀው።</verse>
				<verse number="24">አሻቅቦም “ሰዎች እንደ ዛፍ ሲመላለሱ አያለሁ፤” አለ።</verse>
				<verse number="25">ከዚህም በኋላ ደግሞ እጁን በዐይኑ ላይ ጫነበት፤ አጥርቶም አየ፤ ዳነም፤ ከሩቅም ሳይቀር ሁሉን ተመለከተ።</verse>
				<verse number="26">ወደ ቤቱም ሰደደውና “ወደ መንደሩ አትግባ፤ በመንደሩም ለማንም አንዳች አትናገር፤” አለው።</verse>
				<verse number="27">ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም በፊልጶስ ቂሣርያ ወዳሉ መንደሮች ወጡ፤ በመንገድም “ሰዎች እኔ ማን እንደ ሆንሁ ይላሉ?” ብሎ ደቀ መዛሙርቱን ጠየቃቸው።</verse>
				<verse number="28">እነርሱም “መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ከነቢያት አንዱ” ብለው ነገሩት።</verse>
				<verse number="29">“እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። ጴጥሮስም “አንተ ክርስቶስ ነህ፤” ብሎ መለሰለት።</verse>
				<verse number="30">ስለ እርሱም ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው።</verse>
				<verse number="31">የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ በሽማግሌዎችም በካህናት አለቆችም በጻፎችም ሊናቅ፥ ሊገደልም ከሦስት ቀንም በኋላ ሊነሣ እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር።</verse>
				<verse number="32">ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ ይገሥጸው ጀመር።</verse>
				<verse number="33">እርሱ ግን ዘወር አለ፤ ደቀ መዛሙርቱንም አይቶ ጴጥሮስን ገሠጸውና “ወደ ኋላዬ ሂድ! አንተ ሰይጣን! የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን ነገር አታስብምና፤” አለ።</verse>
				<verse number="34">ሕዝቡንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጠርቶ እንዲህ አላቸው “በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።</verse>
				<verse number="35">ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና፤ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን ያድናታል።</verse>
				<verse number="36">ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?</verse>
				<verse number="37">ሰውስ ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?</verse>
				<verse number="38">በዚህም በዘማዊና በኀጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር በመጣ ጊዜ በእርሱ ያፍርበታል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">እውነት እላችኋለሁ፥ በዚህ ከቆሙት ሰዎች የእግዚአብሔር መንግሥት በኀይል ስትመጣ እስኪያዩ ድረስ፥ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች አሉ፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="2">ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፤ ልብሱም አንጸባረቀ፤</verse>
				<verse number="3">አጣቢም በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ።</verse>
				<verse number="4">ኤልያስና ሙሴም ታዩአቸው፤ ከኢየሱስም ጋር ይነጋገሩ ነበር።</verse>
				<verse number="5">ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን “መምህር ሆይ! በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ፤” አለው።</verse>
				<verse number="6">እጅግ ስለ ፈሩ የሚለውን አያውቅም ነበር።</verse>
				<verse number="7">ደመናም መጥቶ ጋረዳቸው፤ ከደመናውም “የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ።</verse>
				<verse number="8">ድንገትም ዞረው ሲመለከቱ ከእነርሱ ጋር ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም።</verse>
				<verse number="9">ከተራራውም ሲወርዱ የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያዩትን ለማንም እንዳይነግሩ አዘዛቸው።</verse>
				<verse number="10">ቃሉንም ይዘው “ከሙታን መነሣት ምንድር ነው?” እያሉ እርስ በርሳቸው ተጠያየቁ።</verse>
				<verse number="11">እነርሱም “ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ እንዲገባው ጻፎች ስለ ምን ይላሉ?” ብለው ጠየቁት።</verse>
				<verse number="12">እርሱም መልሶ “ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል፤ ሁሉንም ያቀናል፤ ስለ ሰው ልጅም እንዴት ተብሎ ተጽፎአል? ብዙ መከራ እንዲቀበል እንዲናቅም።</verse>
				<verse number="13">ነገር ግን እላችኋለሁ፤ ኤልያስ ደግሞ መጥቶአል፤ ስለ እርሱም እንደ ተጸፈ የወደዱትን ሁሉ አደረጉበት፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="14">ወደ ደቀ መዛሙርቱም በመጣ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ሲከብቡአቸው ጻፎችም ከእነርሱ ጋር ሲከራከሩ አየ።</verse>
				<verse number="15">ወዲያውም ሕዝቡ ሁሉ ባዩት ጊዜ ደነገጡ፤ ወደ እርሱም ሮጠው እጅ ነሡት።</verse>
				<verse number="16">ጻፎችንም “ስለ ምን ከእነርሱ ጋር ትከራከራላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው።</verse>
				<verse number="17">ከሕዝቡ አንዱ መልሶ “መምህር ሆይ! ድዳ መንፈስ ያደረበትን ልጄን ወደ አንተ አምጥቼአለሁ፤</verse>
				<verse number="18">በያዘውም ስፍራ ሁሉ ይጥለዋል፤ አረፋም ይደፍቃል፤ ጥርሱንም ያፋጫል፤ ይደርቃልም፤ እንዲያወጡለትም ለደቀ መዛሙርትህ ነገርኋቸው፤ አልቻሉምም” አለው።</verse>
				<verse number="19">እርሱም መልሶ “የማታምን ትውልድ ሆይ! እስከመቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደ እኔ አምጡት፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="20">ወደ እርሱም አመጡት። እርሱንም ባየ ጊዜ ያ መንፈስ ወዲያው አንፈራገጠው፤ ወደ ምድርም ወድቆ አረፋ እየደፈቀ ተንፈራፈረ።</verse>
				<verse number="21">አባቱንም “ይህ ከያዘው ስንት ዘመን ነው?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም “ከሕፃንነቱ ጀምሮ ነው፤</verse>
				<verse number="22">ብዙ ጊዜም ሊያጠፋው ወደ እሳትም ወደ ውኀም ጣለው፤ ቢቻልህ ግን እዘንልን፤ እርዳንም፤” አለው።</verse>
				<verse number="23">ኢየሱስም “ቢቻልህ ትላለህ? ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፤” አለው።</verse>
				<verse number="24">ወዲያውም የብላቴናው አባት ጮኾ “አምናለሁ፤ አለማመኔን እርዳው፤” አለ።</verse>
				<verse number="25">ኢየሱስም ሕዝቡ እንደ ገና ሲራወጥ አይቶ ርኵሱን መንፈስ ገሠጸና “አንተ ድዳ ደንቆሮም መንፈስ፥ እኔ አዝሃለሁ፤ ከእርሱ ውጣ! ከእንግዲህም አትግባበት፤” አለው።</verse>
				<verse number="26">ጮኾም እጅግም አንፈራግጦት ወጣ፤ ብዙዎችም “ሞተ” እስኪሉ ድረስ እንደ ሙት ሆነ።</verse>
				<verse number="27">ኢየሱስ ግን እጁን ይዞ አስነሣው፤ ቆመም።</verse>
				<verse number="28">ወደ ቤትም ከገባ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ “እኛ ልናወጣው ያልቻልን ስለ ምንድር ነው?” ብለው ብቻውን ጠየቁት።</verse>
				<verse number="29">“ይህ ወገን በጸሎትና በጦም ካልሆነ በምንም ሊወጣ አይችልም፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="30">ከዚያም ወጥተው በገሊላ በኩል አለፉ፤ ደቀ መዛሙርቱንም ያስተምር ስለ ነበር ማንም ያውቅ ዘንድ አልወደደም፤ ለእነርሱም “የሰው ልጅ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጣል፤ ይገድሉትማል፤ ተገድሎም በሦስተኛው ቀን ይነሣል፤” ይላቸው ነበር።</verse>
				<verse number="31"></verse>
				<verse number="32">እነርሱም ነገሩን አላስተዋሉም፤ እንዳይጠይቁትም ፈሩ።</verse>
				<verse number="33">ወደ ቅፍርናሆምም መጣ። በቤትም ሆኖ “በመንገድ እርስ በርሳችሁ ምን ተነጋገራችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው።</verse>
				<verse number="34">እነርሱ ግን በመንገድ “ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን?” ተባብለው ነበርና ዝም አሉ።</verse>
				<verse number="35">ተቀምጦም ዐሥራ ሁለቱን ጠርቶ “ሰው ፊተኛ ሊሆን ቢወድ ከሁሉ በኋላ የሁሉም አገልጋይ ይሁን፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="36">ሕፃንም ይዞ በመካከላቸው አቆመው፤ አቅፎም</verse>
				<verse number="37">“እንደዚህ ካሉ ሕፃናት አንዱን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤ የሚቀበለኝም ሁሉ የላከኝን እንጂ እኔን አይቀበልም አላቸው።”</verse>
				<verse number="38">ዮሐንስ መልሶ “መምህር ሆይ! አንድ ሰው በስምህ አጋንንትን ሲያወጣ አየነው፤</verse>
				<verse number="39">ስለማይከተለንም ከለከልነው፤” አለው። ኢየሱስ ግን አለ “በስሜ ተአምር ሠርቶ በቶሎ በእኔ ላይ ክፉ መናገር የሚችል ማንም የለምና አትከልክሉት፤</verse>
				<verse number="40">የማይቃወመን እርሱ ከእኛ ጋር ነውና።</verse>
				<verse number="41">የክርስቶስ ስለ ሆናችሁ በስሜ ጽዋ ውኀ የሚያጠጣችሁ ሁሉ፥ ዋጋው እንዳይጠፋበት እውነት እላችኋለሁ።</verse>
				<verse number="42">“በእኔም ከሚያምኑት ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለው ነበር።</verse>
				<verse number="43">እጅህ ብታሰናክልህ ቍረጣት፤ ሁለት እጅ ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ወደማይጠፋ እሳት ከመሄድ ጕንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻላል።</verse>
				<verse number="44"></verse>
				<verse number="45">እግርህ ብታሰናክልህ ቍረጣት፤ ሁለት እግር ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ወደማይጠፋ እሳት ከመጣል አንካሳ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል።</verse>
				<verse number="46"></verse>
				<verse number="47">ዐይንህ ብታሰናክልህ አውጣት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነመ እሳት ከመጣል አንዲት ዐይን ኖራህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል።</verse>
				<verse number="48"></verse>
				<verse number="49">ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና፤ መሥዋዕትም ሁሉ በጨው ይቀመማል።</verse>
				<verse number="50">ጨው መልካም ነው፤ ጨው ግን አልጫ ቢሆን በምን ታጣፍጡታላችሁ? በነፍሳችሁ ጨው ይኑርባችሁ፤ እርስ በርሳችሁም ተስማሙ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">ከዚያም ተነሥቶ በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ይሁዳ አገር መጣ፤ ደግሞም ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ እንደ ልማዱም ደግሞ ያስተምራቸው ነበር።</verse>
				<verse number="2">ፈሪሳውያንም ቀርበው “ሰው ሚስቱን ሊፈታ ተፈቅዶለታልን?” ብለው ሊፈትኑት ጠየቁት።</verse>
				<verse number="3">እርሱ ግን መልሶ “ሙሴ ምን አዘዛችሁ?” አላቸው።</verse>
				<verse number="4">እነርሱም “ሙሴስ የፍችዋን ጽሕፈት ጽፎ እንዲፈታት ፈቀደ፤” አሉ።</verse>
				<verse number="5">ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው “ስለ ልባችሁ ጥንካሬ ይህችን ትእዛዝ ጻፈላችሁ።</verse>
				<verse number="6">ከፍጥረት መጀመሪያ ግን እግዚአብሔር ወንድና ሴት አደረጋቸው፤</verse>
				<verse number="7">ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፤</verse>
				<verse number="8">ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ፤ ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም።</verse>
				<verse number="9">እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው።”</verse>
				<verse number="10">በቤትም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ ነገር ጠየቁት።</verse>
				<verse number="11">እርሱም “ሚስቱን ፈትቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ በእርስዋ ላይ ያመነዝራል፤</verse>
				<verse number="12">እርስዋም ባልዋን ፈትታ ሌላ ብታገባ ታመነዝራለች፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="13">እንዲዳስሳቸውም ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ያመጡአቸውን ገሠጹአቸው።</verse>
				<verse number="14">ኢየሱስ ግን አይቶ ተቈጣና “ሕፃናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉ፤ አትከልክሉአቸው፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ናትና።</verse>
				<verse number="15">እውነት እላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበላት ሁሉ ከቶ አይገባባትም፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="16">አቀፋቸውም እጁንም ጭኖ ባረካቸው።</verse>
				<verse number="17">እርሱም በመንገድ ሲወጣ አንድ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ተንበረከከለትና “ቸር መምህር ሆይ! የዘላለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ?” ብሎ ጠየቀው።</verse>
				<verse number="18">ኢየሱስም “ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም።</verse>
				<verse number="19">ትእዛዛትን ታውቃለህ፤ አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ አታታልል፥ አባትህንና እናትህን አክብር፤” አለው።</verse>
				<verse number="20">እርሱም መልሶ “መምህር ሆይ! ይህን ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ፤” አለው።</verse>
				<verse number="21">ኢየሱስም ወደ እርሱ ተመልክቶ ወደደውና “አንድ ነገር ጐደለህ፤ ሂድ፤ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ለድሆች ስጥ፤ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ፤ መስቀሉንም ተሸክመህ ና፤ ተከተለኝ፤” አለው።</verse>
				<verse number="22">ነገር ግን ስለዚህ ነገር ፊቱ ጠቈረ፤ ብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነም ሄደ።</verse>
				<verse number="23">ኢየሱስም ዘወር ብሎ አይቶ ደቀ መዛሙርቱን “ገንዘብ ላላቸው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ይሆናል፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="24">ደቀ መዛሙርቱም እነዚህን ቃሎች አደነቁ። ኢየሱስም ደግሞ መልሶ “ልጆች ሆይ! በገንዘብ ለሚታመኑ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው።</verse>
				<verse number="25">ባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="26">እነርሱም ያለ መጠን ተገረሙና እርስ በርሳቸው “እንግዲያ ማን ሊድን ይችላል?” ተባባሉ።</verse>
				<verse number="27">ኢየሱስም ተመለከታቸውና “ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ እንጂ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉ ይቻላልና፤” አለ።</verse>
				<verse number="28">ጴጥሮስም “እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤” ይለው ጀመር።</verse>
				<verse number="29">ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ “እውነት እላችኋለሁ፤ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ቤትን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ፥</verse>
				<verse number="30">አሁን በዚህ ዘመን ከስደት ጋር ቤቶችን ወንድሞችንና እኅቶችንም እናቶችንም ልጆችንም እርሻንም መቶ እጥፍ፥ በሚመጣውም ዓለም የዘላለም ሕይወት የማይቀበል ማንም የለም።</verse>
				<verse number="31">ግን ብዙ ፊተኞች ኋለኞች ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ።”</verse>
				<verse number="32">ወደ ኢየሩሳሌምም ሊወጡ በመንገድ ነበሩ፤ ኢየሱስም ይቀድማቸው ነበርና ተደነቁ፤ የተከተሉትም ይፈሩ ነበር። ደግሞም ዐሥራ ሁለቱን ወደ እርሱ አቅርቦ ይደርስበት ዘንድ ያለውን ይነግራቸው ጀመር</verse>
				<verse number="33">“እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች አልፎ ይሰጣል፤ የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል፤ ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል፤</verse>
				<verse number="34">ይዘብቱበትማል፤ ይተፉበትማል፤ ይገርፉትማል፤ ይገድሉትማል፤ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="35">የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስም ወደ እርሱ ቀርበው “መምህር ሆይ! የምንለምንህን ሁሉ እንድታደርግልን እንወዳለን፤” አሉት።</verse>
				<verse number="36">እርሱም “ምን ላደርግላችሁ ትወዳላችሁ?” አላቸው።</verse>
				<verse number="37">እነርሱም “በክብርህ ጊዜ አንዳችን በቀኝ አንዳችንም በግራህ መቀመጥን፤” ስጠን አሉት።</verse>
				<verse number="38">ኢየሱስ ግን “የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ፥ እኔ የምጠመቀውንስ ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን?” አላቸው።</verse>
				<verse number="39">እነርሱም “እንችላለን፤” አሉት። ኢየሱስም “እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ፤ እኔ የምጠመቀውንም ጥምቀት ትጠመቃላችሁ፤</verse>
				<verse number="40">በቀኛና በግራ መቀመጥ ግን ለተዘጋጀላቸው ነው እንጂ የምሰጥ እኔ አይደለሁም፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="41">ዐሥሩም ሰምተው በያዕቆብና በዮሐንስ ይቈጡ ጀመር።</verse>
				<verse number="42">ኢየሱስም ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው “የአሕዛብ አለቆች ተብሎ የምታስቡት እንዲገዙአቸው ታላላቆቻቸውም በላያቸው እንዲሠለጥኑ ታውቃላችሁ።</verse>
				<verse number="43">በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፤</verse>
				<verse number="44">ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የሁሉ ባሪያ ይሁን፤</verse>
				<verse number="45">እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”</verse>
				<verse number="46">ወደ ኢያሪኮም መጡ። ከደቀ መዛሙርቱና ከብዙ ሕዝብ ጋር ከኢያሪኮ ሲወጣ የጤሜዎስ ልጅ ዕውሩ በርጤሜዎስ እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ነበር።</verse>
				<verse number="47">የናዝሬቱ ኢየሱስም እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ “የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ!” ማረኝ እያለ ይጮኽ ጀመር።</verse>
				<verse number="48">ብዙዎችም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን “የዳዊት ልጅ ሆይ! ማረኝ” እያለ አብዝቶ ጮኸ።</verse>
				<verse number="49">ኢየሱስም ቆመና “ጥሩት” አለ። ዕውሩንም “አይዞህ፤ ተነሣ፤ ይጠራሃል፤” ብለው ጠሩት።</verse>
				<verse number="50">እርሱም እየዘለለ ተነሣና ልብሱን ጥሎ ወደ ኢየሱስ መጣ።</verse>
				<verse number="51">ኢየሱስም መልሶ “ምን ላደርግልህ ትወዳለህ?” አለው። ዕውሩም “መምህር ሆይ! አይ ዘንድ፤” አለው።</verse>
				<verse number="52">ኢየሱስም “ሂድ፤ እምነትህ አድኖሃል፤” አለው። ወዲያውም አየ በመንገድም ተከተለው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">ወደ ኢየሩሳሌምም ከደብረ ዘይት አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረቡ ጊዜ፥ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ልኮ</verse>
				<verse number="2">“በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፤ ወዲያውም ወደ እርስዋ ገብታችሁ ከሰው ማንም ገና ያልተቀመጠበት ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ።</verse>
				<verse number="3">ማንም ‘ስለ ምን እንዲህ ታደርጋላችሁ?’ ቢላችሁ ‘ለጌታ ያስፈልገዋል፤’ በሉት፤ ወዲያውም ደግሞ ወደዚህ ይሰደዋል፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="4">ሄዱም፤ ውርንጫውንም በመንገድ መተላለፊያ በደጅ ውጭ ታስሮ አገኙት፤ ፈቱትም።</verse>
				<verse number="5">በዚያም ከቆሙት አንዳንዶቹ “ውርንጫውን የምትፈቱት ምን ልታደርጉት ነው?” አሉአቸው።</verse>
				<verse number="6">እነርሱም ኢየሱስ እንዳዘዘ አሉአቸው፤ ተዉአቸውም።</verse>
				<verse number="7">ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አመጡት፤ ልብሳቸውንም በላዩ ጣሉ፤ ተቀመጠበትም።</verse>
				<verse number="8">ብዙ ሰዎችም ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፤ ሌሎችም ከዛፍ ቅጠሎችን እየቈረጡ ያነጥፉ ነበር።</verse>
				<verse number="9">የሚቀድሙትም የሚከተሉትም “ሆሣዕና! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤</verse>
				<verse number="10">በጌታ ስም የምትመጣ የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት፤ ሆሣዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር።</verse>
				<verse number="11">ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ መቅደስ ገባ፤ ዘወር ብሎም ሁሉን ከተመለከተ በኋላ፥ ጊዜው መሽቶ ስለ ነበረ ከዐሥራ ሁለቱ ጋር ወደ ቢታንያ ወጣ።</verse>
				<verse number="12">በማግሥቱም ከቢታንያ ሲወጡ ተራበ።</verse>
				<verse number="13">ቅጠልም ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ምናልባት አንዳች ይገኝባት እንደ ሆነ ብሎ መጣ፤ ነገር ግን የበለስ ወራት አልነበረምና መጥቶ ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም።</verse>
				<verse number="14">መልሶም “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ፤” አላት። ደቀ መዛሙርቱም ሰሙ።</verse>
				<verse number="15">ወደ ኢየሩሳሌምም መጡ። ወደ መቅደስም ገብቶ በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ያወጣ ጀመር፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጭዎችንም ወንበሮች ገለበጠ፤</verse>
				<verse number="16">ዕቃም ተሸክሞ ማንም በመቅደስ ሊያልፍ አልፈቀደም።</verse>
				<verse number="17">አስተማራቸውም “‘ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ትባላለች፤’ ተብሎ የተጻፈ አይደለምን? እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="18">የካህናት አለቆችም ጻፎችም ሰምተው፥ ሕዝቡ ሁሉ በትምህርቱ ይገረሙ ስለ ነበር ይፈሩት ነበርና እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ፈለጉ።</verse>
				<verse number="19">ማታ ማታም ከከተማ ወደ ውጭ ይወጣ ነበር።</verse>
				<verse number="20">ማለዳም ሲያልፉ በለሲቱን ከሥርዋ ደርቃ አዩአት።</verse>
				<verse number="21">ጴጥሮስም ትዝ ብሎት “መምህር ሆይ! እነሆ፥ የረገምሃት በለስ ደርቃለች፤” አለው።</verse>
				<verse number="22">ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው “በእግዚአብሔር እመኑ።</verse>
				<verse number="23">እውነት እላችኋለሁ፤ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር፤’ ቢል ይሆንለታል።</verse>
				<verse number="24">ስለዚህ እላችኋለሁ፤ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፤ ይሆንላችሁማል።</verse>
				<verse number="25">ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኀጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት።</verse>
				<verse number="26">እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም ኀጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።”</verse>
				<verse number="27">ደግሞም ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። እርሱም በመቅደስ ሲመላለስ፥ የካህናት አለቆችና ጻፎች ሽማግሌዎችም ወደ እርሱ መጥተው</verse>
				<verse number="28">“እነዚህን በምን ሥልጣን ታደርጋለህ? ወይስ እነዚህን ለማድረግ ይህን ሥልጣን ማን ሰጠህ?” አሉት።</verse>
				<verse number="29">ኢየሱስም “እኔም አንዲት ነገር እጠይቃችኋለሁ፤ እናንተም መልሱልኝ፤ እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ።</verse>
				<verse number="30">የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ነበረችን ወይስ ከሰው? መልሱልኝ፡” አላቸው።</verse>
				<verse number="31">እርስ በርሳቸውም ሲነጋገሩ “‘ከሰማይ ነው፤’ ብንል ‘እንግዲያውስ ስለ ምን አላመናችሁበትም?’ ይለናል፤</verse>
				<verse number="32">ነገር ግን ‘ከሰው ነው’ እንበልን?” አሉ፤ ሁሉ ዮሐንስን በእውነት እንደ ነቢይ ያዩት ነበርና ሕዝቡን ፈሩ።</verse>
				<verse number="33">ለኢየሱስም መልሰው “አናውቅም፤” አሉት ኢየሱስም “እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ አልነግራችሁም፤” አላቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">በምሳሌም ይነግራቸው ጀመር። “አንድ ሰው የወይን አትክልት ተከለ፤ ቅጥርም ቀጠረለት፤ መጥመቂያም ማሰለት፥ ግንብም ሠራና ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።</verse>
				<verse number="2">በጊዜውም ከወይን አትክልት ፍሬ ከገበሬዎቹ እንዲቀበል አንድ ባሪያ ወደ ገበሬዎቹ ላከ፤</verse>
				<verse number="3">ይዘውም ደበደቡት፤ ባዶውንም ሰደዱት።</verse>
				<verse number="4">ዳግመኛም ሌላውን ባሪያ ወደ እነርሱ ላከ፤ እርሱንም ወግረው ራሱን አቈሰሉት፤ አዋርደውም ሰደዱት።</verse>
				<verse number="5">ሌላውንም ላከ፤ እርሱንም ገደሉት፤ ከሌሎችም ከብዙዎች አንዳንዱን ደበደቡ፤ አንዳንዱንም ገደሉ።</verse>
				<verse number="6">የሚወደው አንድ ልጅ ገና ነበረው፤ ‘ልጄንስ ያፍሩታል፤’ ብሎ እርሱን ከሁሉ በኋላ ወደ እነርሱ ላከ።</verse>
				<verse number="7">እነዚያ ገበሬዎች ግን እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፤ እንግደለው፤ ርስቱም ለኛ ይሆናል፤’ ተባባሉ።</verse>
				<verse number="8">ይዘውም ገደሉት፤ ከወይኑም አትክልት ወደ ውጭ ጣሉት።</verse>
				<verse number="9">እንግዲህ የወይኑ አትክልት ጌታ ምን ያደርጋል? ይመጣል፤ ገበሬዎቹንም ያጠፋል፤ የወይኑንም አትክልት ለሌሎች ይሰጣል።</verse>
				<verse number="10">‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው።’ የሚለውን ይህን መጽሐፍ አላነበባችሁምን?”</verse>
				<verse number="11"></verse>
				<verse number="12">ምሳሌውንም ስለ እነርሱ እንደ ተናገረ አውቀዋልና ሊይዙት ፈለጉ፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ። ትተውትም ሄዱ።</verse>
				<verse number="13">በንግግርም ሊያጠምዱት ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ ወገን የሆኑትን ወደ እርሱ ላኩ።</verse>
				<verse number="14">መጥተውም “መምህር ሆይ! የሰውን ፊት ሳትመለከት በእውነት የእግዚአብሔር መንገድ ታስተምራለህና እውነተኛ እንደ ሆንህ ለማንምም እንዳታደላ እናውቃለን፤ ለቄሳር ግብር መስጠት ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም? እንስጥን ወይስ አንስጥ?” አሉት።</verse>
				<verse number="15">እርሱ ግን ግብዝነታቸውን አውቆ “ለምን ትፈትኑኛላችሁ? አየው ዘንድ አንድ ዲናር አምጡልኝ፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="16">እነርሱም አመጡለት። “ይህች መልክ ጽሕፈቲቱስ የማን ናት?” አላቸው፤ እነርሱም “የቄሳር ናት፤” አሉት።</verse>
				<verse number="17">ኢየሱስም መልሶ “የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ፤” አላቸው። በእርሱም ተደነቁ።</verse>
				<verse number="18">ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ መጥተው ጠየቁት እንዲህም አሉት</verse>
				<verse number="19">“መምህር ሆይ! ሙሴ “የአንድ ሰው ወንድም ሚስቱን ትቶ ልጅ ሳያስቀር ቢሞት፥ ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ፤’ ብሎ ጻፈልን።</verse>
				<verse number="20">ሰባት ወንድማማቾች ነበሩ፤ ፊተኛውም ሚስት አግብቶ ዘር ሳያስቀር ሞተ፤</verse>
				<verse number="21">ሁለተኛውም አገባት፤ ዘርም ሳይተው ሞተ፤ ሦስተኛውም እንዲሁ፤</verse>
				<verse number="22">ሰባቱም አገቡአት፤ ዘርም አላስቀሩም። ከሁሉም በኋላ ሴቲቱ ደግሞ ሞተች።</verse>
				<verse number="23">ሰባቱ አግብተዋታልና በትንሣኤ ቀን ሲነሡ ከእነርሱ ለማናቸው ሚስት ትሆናለች?”</verse>
				<verse number="24">ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው “መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኀይል አታውቁምና ስለዚህ የምትስቱ አይደለምን?</verse>
				<verse number="25">ከሙታንስ ሲነሡ በሰማያት እንዳሉ መላእክት ይሆናሉ እንጂ አያገቡም፤ አይጋቡምም።</verse>
				<verse number="26">ስለ ሙታን ግን እንዲነሡ እግዚአብሔር ‘እኔ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ፤’ እንዳለው በሙሴ መጽሐፍ በቍጥቋጦው ዘንድ የተጻፈውን አላነበባችሁምን?</verse>
				<verse number="27">የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም። እንግዲህ እጅግ ትስታላችሁ።”</verse>
				<verse number="28">ከጻፎችም አንዱ ቀርቦ ሲከራከሩ ሰማና መልካም አድርጎ እንደ መለሰላቸው አስተውሎ “ከሁሉ ፊተኛይቱ ትእዛዝ ማናቸይቱ ናት?” ብሎ ጠየቀው።</verse>
				<verse number="29">ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው “ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ ‘እስራኤል ሆይ! ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፤</verse>
				<verse number="30">አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኀይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ፤’ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።</verse>
				<verse number="31">ሁለተኛይቱም ‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤’ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም።”</verse>
				<verse number="32">ጻፊውም “መልካም ነው፤ መምህር ሆይ! ‘አንድ ነው፤ ከእርሱም በቀር ሌላ የለም፤’ ብለህ በእውነት ተናገርህ፤</verse>
				<verse number="33">በፍጹም ልብ በፍጹም አእምሮም በፍጹም ነፍስም በፍጹም ኀይልም እርሱን መውደድ፥ ባልንጀራንም እንደ ራስ መውደድ በሙሉ ከሚቃጠል መሥዋዕትና ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ የሚበልጥ ነው፡” አለው።</verse>
				<verse number="34">ኢየሱስም በማስተዋል እንደ መለሰ አይቶ “አንተ ከእግዚአብሔር መንግሥት የራቅህ አይደለህም፤” አለው። ከዚህም በኋላ ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።</verse>
				<verse number="35">ኢየሱስም በመቅደስ ሲያስተምር መልሶ እንዲህ አለ “ጻፎች ‘ክርስቶስ የዳዊት ልጅ ነው፤’ እንዴት ይላሉ?</verse>
				<verse number="36">ዳዊት ራሱ በመንፈስ ቅዱስ ‘ጌታ ጌታዬን ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው አለ።’</verse>
				<verse number="37">ዳዊትም ራሱ ጌታ አለው፤ እንዴትስ ልጁ ይሆናል?” ብዙ ሕዝብም በደስታ ይሰሙት ነበር።</verse>
				<verse number="38">ሲያስተምርም እንዲህ አለ “ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞርን፥ በገበያም ሰላምታን፥ በምኵራብም የከበሬታን ወንበር፥ በግብዣም የከበሬታን ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ፤</verse>
				<verse number="39"></verse>
				<verse number="40">የመበለቶችን ቤት የሚበሉ፤ ጸሎታቸውንም በማስረዘም የሚያመካኙ፤ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ።”</verse>
				<verse number="41">ኢየሱስም በመዝገብ አንጻር ተቀምጦ ሕዝቡ በመዝገብ ውስጥ ገንዘብ እንዴት እንዲጥሉ ያይ ነበር፤ ብዙ ባለ ጠጎችም ብዙ ይጥሉ ነበር፤</verse>
				<verse number="42">አንዲትም ድሀ መበለት መጥታ አንድ ሳንቲም የሚያህሉ ሁለት ናስ ጣለች።</verse>
				<verse number="43">ደቀ መዛሙርቱንም ጠርቶ “እውነት እላችኋለሁ፤ በመዝገብ ውስጥ ከሚጥሉት ሁሉ ይልቅ ይህች ድሀ መበለት አብልጣ ጣለች፤</verse>
				<verse number="44">ሁሉ ከትርፋቸው ጥለዋልና፤ ይህች ግን ከጕድለትዋ የነበራትን ሁሉ ትዳርዋን ሁሉ ጣለች፤” አላቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">እርሱም ከመቅደስ ሲወጣ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ “መምህር ሆይ! እንዴት ያሉ ድንጋይዎችና እንዴት ያሉ ሕንጻዎች እንደ ሆኑ እይ፤” አለው።</verse>
				<verse number="2">ኢየሱስም መልሶ “እነዚህን ታላላቅ ሕንጻዎች ታያለህን? ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም፤” አለው።</verse>
				<verse number="3">በመቅደስም ትይዩ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ጴጥሮስና ያዕቆብ ዮሐንስም እንድርያስም</verse>
				<verse number="4">“ንገረን፤ ይህ መቼ ይሆናል? ይህስ ሁሉ ይፈጸም ዘንድ እንዳለው ምልክቱ ምንድር ነው?” ብለው ለብቻቸው ጠየቁት።</verse>
				<verse number="5">ኢየሱስም መልሶ እንዲህ ይላቸው ጀመር “ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።</verse>
				<verse number="6">ብዙዎች ‘እኔ ነኝ፤’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።</verse>
				<verse number="7">ጦርንም የጦርንም ወሬ በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና፤ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው።</verse>
				<verse number="8">ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፤ በልዩ ልዩ ስፍራ የምድር መናወጥ ይሆናል፤ ራብ ይሆናል፤ እነዚህ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።</verse>
				<verse number="9">“እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በምኵራብም ትገረፋላችሁ፤ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ እኔ በገዥዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ።</verse>
				<verse number="10">አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበክ ዘንድ ይገባል።</verse>
				<verse number="11">ሲጐትቱአችሁና አሳልፈው ሲሰጡአችሁም ምን እንድትናገሩ አስቀድማችሁ አትጨነቁ፤ ዳሩ ግን በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ፤ የሚነግረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና።</verse>
				<verse number="12">ወንድምም ወንድሙን አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ፤ ይገድሉአቸውማል።</verse>
				<verse number="13">በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።</verse>
				<verse number="14">“ነገር ግን በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋት ርኵሰት በማይገባው ስፍራ ቆሞ ብታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፤ በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፤</verse>
				<verse number="15">በሰገነትም ያለ ወደ ቤት አይውረድ፤ ከቤቱም አንዳች ይወስድ ዘንድ አይግባ፤</verse>
				<verse number="16">በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ።</verse>
				<verse number="17">በዚያን ወራትም ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው።</verse>
				<verse number="18">ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ፤</verse>
				<verse number="19">በዚያን ወራት እግዚአብሔር ከፈጠረው ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያልሆነ ደግሞም የማይሆን የመከራ ዐይነት ይሆናልና።</verse>
				<verse number="20">ጌታስ ወራቶቹን ባያሳጥር፥ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም፤ ነገር ግን ስለ መረጣቸው ምርጦች ወራቶቹን አሳጠረ።</verse>
				<verse number="21">በዚያን ጊዜም ማንም ‘እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ፤’ ወይም ‘እነሆ፥ ከዚያ አለ፤’ ቢላችሁ አትመኑ፤</verse>
				<verse number="22">ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፤ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ያስቱ ዘንድ ምልክትና ድንቅ ያደርጋሉ።</verse>
				<verse number="23">እናንተ ግን ተጠንቀቁ፤ እነሆ፥ አስቀድሜ ሁሉን ነገርኋችሁ።</verse>
				<verse number="24">“በነዚያ ቀኖች ግን ከዚያ መከራ በኋላ ፀሐይ ይጨልማል፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤</verse>
				<verse number="25">ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያትም ኀይላት ይናወጣሉ።</verse>
				<verse number="26">በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በብዙ ኀይልና ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።</verse>
				<verse number="27">በዚያን ጊዜም መላእክትን ይልካል፤ ከአራቱ ነፋሳትም ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ የተመረጡትን ይሰበስባቸዋል።</verse>
				<verse number="28">“ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ።</verse>
				<verse number="29">እንዲሁ ደግሞ እናንተ ይህን ሁሉ መሆኑን ስታዩ ቀርቦ በደጅ እንደ ሆነ እወቁ።</verse>
				<verse number="30">እውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም።</verse>
				<verse number="31">ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።</verse>
				<verse number="32">“ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም።</verse>
				<verse number="33">ጊዜው መቼ እንዲሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ፤ ጸልዩም።</verse>
				<verse number="34">ቤቱን ትቶ ወደ ሌላ አገር እንደ ሄደ ሰው ነው፤ ለባሮቹም ሥልጣን ለእያንዳንዱም ሥራውን ሰጥቶ በረኛውን እንዲተጋ አዘዘ።</verse>
				<verse number="35">እንግዲህ በማታ ቢሆን ወይም በእኩለ ሌሊት ወይም ዶሮ ሲጮኽ ወይም በማለዳ ቢሆን ባለቤቱ መቼ እንዲመጣ አታውቁምና</verse>
				<verse number="36">ድንገት መጥቶ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ስለዚህ ትጉ።</verse>
				<verse number="37">ለእናንተም የምነግራችሁ ለሁሉ እላለሁ፤ ትጉ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካና የቂጣ በዓል ነበረ። የካህናት አለቆችም ጻፎችም እንዴት አድርገው በተንኰል እንደሚይዙትና እንደሚገድሉት ይፈልጉ ነበር።</verse>
				<verse number="2">“የሕዝብ ሁከት እንዳይሆን በበዓል አይሁን፤” ይሉ ነበርና።</verse>
				<verse number="3">እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በነበረ ጊዜ፥ በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ጥሩ የናርዶስ ሽቶ የሞላበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች፤ ብልቃጡንም ሰብራ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።</verse>
				<verse number="4">አንዳንዶችም “ይህ የሽቶ ጥፋት ለምንድር ነው?</verse>
				<verse number="5">ይህ ሽቶ ከሦስት መቶ ዲናር በሚበልጥ ዋጋ ተሽጦ ለድሆች ሊሰጥ ይቻል ነበርና፤” ብለው በራሳቸው ይቈጡ ነበር፤ እርስዋንም ነቀፉአት።</verse>
				<verse number="6">ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ “ተዉአት፤ ስለ ምን ታደክሙአታላችሁ? መልካም ሥራ ሠርታልኛለች።</verse>
				<verse number="7">ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፤ በማናቸውም በወደዳችሁት ጊዜ መልካም ልታደርጉላቸው ትችላላችሁ፤ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም።</verse>
				<verse number="8">የተቻላትን አደረገች፤ አስቀድማ ለመቃብሬ ሥጋዬን ቀባችው።</verse>
				<verse number="9">እውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ወንጌል በዓለሙ ሁሉ በሚሰበክበት በማናቸውም ስፍራ፥ እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ ሊሆን ይነገራል።”</verse>
				<verse number="10">ከዐሥራ ሁለቱም አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ ሊሰጠው ወደ ካህናት አለቆች ሄደ።</verse>
				<verse number="11">ሲሰሙም ደስ አላቸው፤ ብርም ይሰጡት ዘንድ ተስፋ ሰጡት። በሚመች ጊዜም እንዴት አድርጎ አሳልፎ እንዲሰጠው ይፈልግ ነበር።</verse>
				<verse number="12">የፋሲካን በግ በሚያርዱበት በቂጣ በዓል መጀመሪያ ቀን ደቀ መዛሙርቱ “ፋሲካን ትበላ ዘንድ ወዴት ሄደን ልናሰናዳ ትወዳለህ?” አሉት።</verse>
				<verse number="13">ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት ላከ፤ እንዲህም አላቸው “ወደ ከተማ ሂዱ፤ ማድጋ ውኀ የተሸከመ ሰውም ይገናኛችኋል፤ተከተሉት።</verse>
				<verse number="14">የሚገባበትንም የቤቱን ጌታ ‘መምህሩ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ቤት ወዴት ነው? ይላል፤’ በሉት።</verse>
				<verse number="15">እርሱም በደርብ ላይ ያለውን የተሰናዳና የተነጠፈ ታላቅ አዳራሽ ያሳያችኋል፤በዚያም አሰናዱልን።”</verse>
				<verse number="16">ደቀ መዛሙርቱም ወጡ፤ ወደከተማም ሄደው እንዳላቸው አገኙ፤ ፋሲካንም አሰናዱ።</verse>
				<verse number="17">በመሸም ጊዜ ከዐሥራ ሁለቱ ጋር መጣ።</verse>
				<verse number="18">ተቀምጠውም ሲበሉ ኢየሱስ “እውነት እላችኋለሁ፥ ከእናንተ አንዱ፥ እርሱም ከእኔ ጋር የሚበላው አሳልፎ ይሰጠኛል፤” አለ።</verse>
				<verse number="19">እነርሱም ያዝኑ፥ እያንዳንዳቸውም “እኔ እሆንን?” ይሉት ጀመር።</verse>
				<verse number="20">እርሱም መልሶ “ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ከእኔ ጋር ወደ ወጭቱ እጁን የሚያጠልቀው ነው።</verse>
				<verse number="21">የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት! ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="22">ሲበሉም ኢየሱስ ኅብስትን አንሥቶ ባረከ፤ ቈርሶም ሰጣቸውና “እንካችሁ፤ ይህ ሥጋዬ ነው፤” አለ።</verse>
				<verse number="23">ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው፤ ሁሉም ከእርሱ ጠጡ።</verse>
				<verse number="24">እርሱም “ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው።</verse>
				<verse number="25">እውነት እላችኋለሁ በእግዚአብሔር መንግሥት ከወይኑ ፍሬ አዲሱን እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ ደግሞ አልጠጣውም፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="26">መዝሙርም ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ወጡ።</verse>
				<verse number="27">ኢየሱስም “በዚች ሌሊት ሁላችሁ በእኔ ትሰናከላላችሁ፤ ‘እረኛዉን እመታለሁ፤ በጎችም ይበተናሉ፤’ የሚል ተጽፎአልና።</verse>
				<verse number="28">ነገር ግን ከተነሣሁ በኋላ ወደ ገሊላ እቀድማችኋለሁ፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="29">ጴጥሮስም “ሁሉም ቢሰናከሉ እኔ ግን ከቶ አልሰናከልም፤” አለው።</verse>
				<verse number="30">ኢየሱስም “እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ በዚች ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” አለው።</verse>
				<verse number="31">እርሱም ቃሉን አበርትቶ “ከአንተ ጋር የምሞት እንኳ ቢሆን ከቶ አልክድህም፤” አለ። ሁሉም ደግሞ እንደዚሁ አሉ።</verse>
				<verse number="32">ጌቴሴማኒ ወደምትባልም ስፍራ መጡ፤ ደቀ መዛሙርቱንም “ስጸልይ ሳለሁ፥ በዚህ ተቀመጡ፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="33">ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ከእርሱ ጋር ወሰደ፤ ሊደነግጥም ሊተክዝም ጀመረና</verse>
				<verse number="34">“ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ቈዩ፤ ትጉም፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="35">ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በምድርም ወድቆ፥ ይቻልስ ቢሆን ሰዓቲቱ ከእርሱ እንድታልፍ ጸለየና</verse>
				<verse number="36">“አባ አባት ሆይ! ሁሉ ይቻልሃል፤ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን አንተ የምትወደው እንጂ እኔ የምወደው አይሁን፤” አለ።</verse>
				<verse number="37">መጣም፤ ተኝተውም አገኛቸው፤ ጴጥሮስንም “ስምዖን ሆይ! ተኝተሃልን? አንዲት ሰዓት ስንኳ ልትተጋ አልቻልህምን?</verse>
				<verse number="38">ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉ፤ ጸልዩም፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች፤ ሥጋ ግን ደካማ ነው፤” አለው።</verse>
				<verse number="39">ደግሞም ሄዶ ያንኑ ቃል ጸለየ።</verse>
				<verse number="40">ደግሞም መጥቶ ዐይኖቻቸው በእንቅልፍ ከብደው ነበርና ተኝተው አገኛቸው፤ የሚመልሱለትንም አላወቁም።</verse>
				<verse number="41">ሦስተኛም መጥቶ “እንግዲህስ ተኙ፤ ዕረፉም፤ ይበቃል፤ ሰዓቲቱ ደረሰች፤ እነሆ፥ የሰው ልጅ በኀጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል።</verse>
				<verse number="42">ተነሡ፤ እንሂድ፤ እነሆ፥ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቦአል፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="43">ወዲያውም ገና ሲናገር ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፤ ከእርሱም ጋር ብዙ ሰዎች ሰይፍና ጐመድ ይዘው ከካህናት አለቆችና ከጻፎች ከሽማግሌዎችም ዘንድ መጡ።</verse>
				<verse number="44">አሳልፎ የሚሰጠውም “የምስመው እርሱ ነው፤ ያዙት፤ ተጠንቅቃችሁም ውሰዱት፤” ብሎ ምልክት ሰጥቶአቸው ነበር።</verse>
				<verse number="45">መጥቶም ወዲያው ወደ እርሱ ቀረበና “መምህር ሆይ! መምህር ሆይ!” ብሎ ሳመው፤</verse>
				<verse number="46">እነርሱም እጃቸውን በእርሱ ላይ ጭነው ያዙት።</verse>
				<verse number="47">በአጠገብ ከቆሙት ግን አንዱ ሰይፉን መዞ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መታ፤ ጆሮውንም ቈረጠ።</verse>
				<verse number="48">ኢየሱስም መልሶ “ወንበዴ እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ መጣችሁን?</verse>
				<verse number="49">በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስኖር አልያዛችሁኝም፤ ነገር ግን መጻሕፍት ይፈጸሙ ዘንድ ይህ ሆነ፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="50">ሁሉም ትተውት ሸሹ።</verse>
				<verse number="51">ዕርቃኑን በነጠላ የሸፈነ አንድ ጎበዝ ይከተለው ነበር፤</verse>
				<verse number="52">ጎበዛዝቱም ያዙት፤ እርሱ ግን ነጠላውን ትቶ ዕራቁቱን ሸሸ።</verse>
				<verse number="53">ኢየሱስንም ወደ ሊቀ ካህናቱ ወሰዱት፤ የካህናት አለቆችም ሁሉ ሽማግሌዎችም ጻፎችም ተሰበሰቡ።</verse>
				<verse number="54">ጴጥሮስም እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ በሩቁ ተከተለው፤ ከሎሌዎችም ጋር ተቀምጦ እሳት ይሞቅ ነበር።</verse>
				<verse number="55">የካህናት አለቆችም ሸንጎውን ሁሉ እንዲገድሉት በኢየሱስ ላይ ምስክር ይፈልጉ ነበር፤ አላገኙምም፤</verse>
				<verse number="56">ብዙዎች በሐሰት ይመሰክሩበት ነበርና፤ ምስክርነታቸው ግን አልተስማማም።</verse>
				<verse number="57">ሰዎችም ተነሥተው “እኔ ይህን በእጅ የተሠራውን ቤተ መቅደስ አፈርሰዋለሁ፤ በሦስት ቀንም ሌላውን በእጅ ያልተሠራውን እሠራለሁ፤” ሲል ሰማነው፤ ብለው በሐሰት መሰከሩበት።</verse>
				<verse number="58"></verse>
				<verse number="59">ምስክርነታቸውም እንዲሁ እንኳ አልተስማማም።</verse>
				<verse number="60">ሊቀ ካህናቱም በመካከላቸው ተነሥቶ “አንዳች አትመልስምን? እነዚህስ በአንተ ላይ የሚመሰክሩብህ ምንድር ነው?” ብሎ ኢየሱስን ጠየቀው።</verse>
				<verse number="61">እርሱ ግን ዝም አለ፤ አንዳችም አልመለሰም። ደግሞ ሊቀ ካህናቱ ጠየቀውና “የቡሩክ ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህን?” አለው።</verse>
				<verse number="62">ኢየሱስም “እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም በኀይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ፤” አለ።</verse>
				<verse number="63">ሊቀ ካህናቱም ልብሱን ቀደደና “ከእንግዲህ ወዲህ ምስክሮችን ምን ያስፈልገናል?</verse>
				<verse number="64">ስድቡን ሰማችሁ፤ ምን ይመስላችኋል?” አለ። እነርሱም ሁሉ “ሞት ይገባዋል!” ብለው ፈረዱበት።</verse>
				<verse number="65">አንዳንዶችም ይተፉበት ፊቱንም ሸፍነው ይጐስሙትና “ትንቢት ተናገር፤” ይሉት ጀመር፤ ሎሌዎችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።</verse>
				<verse number="66">ጴጥሮስም በግቢ ውስጥ ወደ ታች ሳለ ከሊቀ ካህናቱ ገረዶች አንዲቱ መጣች፤</verse>
				<verse number="67">ጴጥሮስም እሳት ሲሞቅ አይታ ተመለከተችውና “አንተ ደግሞ ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበርህ፤” አለችው።</verse>
				<verse number="68">እርሱ ግን “የምትዪውን አላውቅም፤ አላስተውልምም፤” ብሎ ካደ። ወደ ውጭም ወደ ደጅ ወጣ፤ ዶሮም ጮኸ።</verse>
				<verse number="69">ገረዲቱም አይታው በዚያ ለቆሙት “ይህም ከእነርሱ ወገን ነው፤” ስትል ሁለተኛ ትነግራቸው ጀመር።</verse>
				<verse number="70">እርሱም ደግሞ ካደ። ጥቂት ቈይተውም በዚያ የቆሙት ዳግመኛ ጴጥሮስን “የገሊላ ሰው ነህና ከእነርሱ ወገን በእውነት ነህ፤” አሉት።</verse>
				<verse number="71">እርሱ ግን “ይህን የምትሉትን ሰው አላውቀውም፤” ብሎ እራሱን ይረግምና ይምል ጀመር። ወዲያውም ዶሮ ሁለተኛ ጮኸ።</verse>
				<verse number="72">ጴጥሮስንም ኢየሱስ “ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” ያለው ቃል ትዝ አለው፤ ነገሩንም አስቦ አለቀሰ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">ወዲያውም ማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎችና ከጻፎች ከሸንጎውም ሁሉ ጋር ከተማከሩ በኋላ፥ ኢየሱስን አሳስረው ወሰዱትና ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት።</verse>
				<verse number="2">ጲላጦስም “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም “አንተ አልህ፤” ብሎ መለሰለት።</verse>
				<verse number="3">የካህናት አለቆችም ብዙ ያሳጡት ነበር፤ እርሱ ግን ምንም አልመለሰም።</verse>
				<verse number="4">ጲላጦስም ደግሞ “አንዳች አትመልስምን? እነሆ፥ በስንት ነገር ያሳጡሃል” ብሎ ጠየቀው።</verse>
				<verse number="5">ኢየሱስም ከዚያ በኋላ ጲላጦስ እስኪደነቅ ድረስ ምንም አልመለሰም።</verse>
				<verse number="6">በዚያም በዓል የለመኑትን አንድ እስረኛ ይፈታላቸው ነበር።</verse>
				<verse number="7">በዐመፅም ነፍስ ከገደሉት ከዐመፀኞች ጋር የታሰረ በርባን የተባለ ነበረ።</verse>
				<verse number="8">ሕዝቡም ወጥተው እንደ ልማዱ ያደርግላቸው ዘንድ እየጮኹ ይለምኑት ጀመር።</verse>
				<verse number="9">ጲላጦስም “የአይሁድን ንጉሥ እፈታላችሁ ዘንድ ትወዳላችሁን?” ብሎ መለሰላቸው፤</verse>
				<verse number="10">የካህናት አለቆች በቅንዓት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና።</verse>
				<verse number="11">የካህናት አለቆች ግን በርባንን በእርሱ ፈንታ ይፈታላቸው ዘንድ ሕዝቡን አወኩአቸው።</verse>
				<verse number="12">ጲላጦስም ዳግመኛ መልሶ “እንግዲህ የአይሁድ ንጉሥ የምትሉትን ምን ላደርገው ትወዳላችሁ?” አላቸው።</verse>
				<verse number="13">እነርሱም ዳግመኛ “ስቀለው!” እያሉ ጮኹ።</verse>
				<verse number="14">ጲላጦስም “ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው?” አላቸው። እነርሱ ግን “ስቀለው!” እያሉ ጩኸት አበዙ።</verse>
				<verse number="15">ጲላጦስም የሕዝቡን ፈቃድ ሊያደርግ ወዶ በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስንም ገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠ።</verse>
				<verse number="16">ወታደሮችም ፕራይቶሪዮን ወደሚባል ግቢ ውስጥ ወሰዱት፤ ጭፍራውንም ሁሉ በአንድነት ጠሩ።</verse>
				<verse number="17">ቀይ ልብስም አለበሱት፤ የእሾህ አክሊልም ጐንጕነው ደፉበት፤</verse>
				<verse number="18">“የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን፤” እያሉ እጅ ይነሱት ጀመር፤</verse>
				<verse number="19">ራሱንም በመቃ መቱት፤ ተፉበትም፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት።</verse>
				<verse number="20">ከተዘባበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፤ ልብሱንም አለበሱት፤ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።</verse>
				<verse number="21">አንድ መንገድ አላፊም የአሌክስንድሮስና የሩፎስ አባት ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰው ከገጠር ሲመጣ መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት።</verse>
				<verse number="22">ትርጓሜውም የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሆን ጎልጎታ ወደተባለ ስፍራ ወሰዱት።</verse>
				<verse number="23">ከርቤም የተቀላቀለበትን የወይን ጠጅ እንዲጠጣ ሰጡት፤ እርሱ ግን አልተቀበለም።</verse>
				<verse number="24">ሰቀሉትም፤ ልብሱንም ማን ማን እንዲወስድ ዕጣ ተጣጥለው ተካፈሉ።</verse>
				<verse number="25">በሰቀሉትም ጊዜ ሦስት ሰዓት ነበረ።</verse>
				<verse number="26">የክሱ ጽሕፈትም “የአይሁድ ንጉሥ” የሚል ተጽፎ ነበር።</verse>
				<verse number="27">ከእርሱም ጋር ሁለት ወንበዴዎች አንዱን በቀኙ አንዱንም በግራው ሰቀሉ።</verse>
				<verse number="28">መጽሐፍም “ከዐመፀኞች ጋር ተቆጠረ፤” ያለው ተፈጸመ።</verse>
				<verse number="29">የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበርና “ዋ! ቤተ መቅደስን የምታፈርስ በሦስት ቀንም የምትሠራ፥</verse>
				<verse number="30">ከመስቀል ወርደህ ራስህን አድን፡” አሉ።</verse>
				<verse number="31">እንዲሁም የካህናት አለቆች ደግሞ ከጻፎች ጋር እርስ በርሳቸው እየተዘባበቱ “ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ሊያድን አይችልም፤</verse>
				<verse number="32">አይተን እናምን ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስ አሁን ከመስቀል ይውረድ፤” አሉ። ከእርሱም ጋር የተሰቀሉት ይነቅፉት ነበር።</verse>
				<verse number="33">ስድስት ሰዓትም በሆነ ጊዜ፥ እስከ ዘጠኝ ሰዓት በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።</verse>
				<verse number="34">በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ “ኤሎሄ! ኤሎሄ! ላማ ሰበቅታኒ?” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ትርጓሜውም “አምላኬ! አምላኬ! ለምን ተውኸኝ?” ማለት ነው።</verse>
				<verse number="35">በዚያም ከቆሙት ሰዎች ሰምተው “እነሆ፥ ኤልያስን ይጠራል፤” አሉ።</verse>
				<verse number="36">አንዱም ሮጦ ሆምጣጤ በሰፍነግ ሞላ በመቃም አድርጎ “ተዉ፤ ኤልያስ ሊያወርደው ይመጣ እንደ ሆነ እንይ፤” እያለ አጠጣው።</verse>
				<verse number="37">ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ነፍሱንም ሰጠ።</verse>
				<verse number="38">የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ።</verse>
				<verse number="39">በዚያም በአንጻሩ የቆመ የመቶ አለቃ እንደዚህ ጮኾ ነፍሱን እንደ ሰጠ ባየ ጊዜ “ይህ ሰው በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ፤” አለ።</verse>
				<verse number="40">ሴቶችም ደግሞ በሩቅ ሆነው ይመለከቱ ነበር፤ ከእነርሱም በገሊላ ሳለ ይከተሉትና ያገለግሉት የነበሩ መግደላዊት ማርያም የታናሹ ያዕቆብና የዮሳም እናት ማርያም ሰሎሜም ነበሩ፤</verse>
				<verse number="41">ከእርሱም ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የወጡ ሌሎች ብዙዎች ሴቶች ነበሩ።</verse>
				<verse number="42">አሁንም በመሸ ጊዜ የሰንበት ዋዜማ የሆነ የማዘጋጀት ቀን ስለ ነበረ፥</verse>
				<verse number="43">የከበረ አማካሪ የሆነ የአርማትያስ ዮሴፍ መጣ፤ እርሱም ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር፤ ደፍሮም ወደ ጲላጦስ ገባና የኢየሱስን ሥጋ ለመነው።</verse>
				<verse number="44">ጲላጦስም “አሁኑን እንዴት ሞተ?” ብሎ ተደነቀ፤ የመቶ አለቃውንም ጠርቶ “ከሞተ ቆይቶአልን?” ብሎ ጠየቀው፤</verse>
				<verse number="45">ከመቶ አለቃውም ተረድቶ በድኑን ለዮሴፍ ሰጠው።</verse>
				<verse number="46">በፍታም ገዝቶ አውርዶም በበፍታ ከፈነው፤ ከዐለትም በተወቀረ መቃብር አኖረው፤ በመቃብሩ ደጃፍም ድንጋይ አንከባለለ።</verse>
				<verse number="47">መግደላዊትም ማርያም የዮሳም እናት ማርያም ወዴት እንዳኖሩት ይመለከቱ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">ሰንበትም ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም የያዕቆብም እናት ማርያም ሰሎሜም መጥተው ሊቀቡት ሽቶ ገዙ።</verse>
				<verse number="2">ከሳምንቱም በፊተኛው ቀን እጅግ በማለዳ ፀሐይ ከወጣ በኋላ ወደ መቃብር መጡ።</verse>
				<verse number="3">እርስ በርሳቸውም “ድንጋዩን ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል?” ይባባሉ ነበር፤</verse>
				<verse number="4">ድንጋዩ እጅግ ትልቅ ነበርና፤ አሻቅበውም አይተው ድንጋዩ ተንከባሎ እንደ ነበር ተመለከቱ።</verse>
				<verse number="5">ወደ መቃብሩም ገብተው ነጭ ልብስ የተጐናጸፈ ጐልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ።</verse>
				<verse number="6">እርሱ ግን “አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል፤ በዚህ የለም፤ እነሆ፥ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ።</verse>
				<verse number="7">ነገር ግን ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ለጴጥሮስም ‘ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፤ እንደ ነገራችሁ በዚያ ታዩታላችሁ፤’ ብላችሁ ንገሩአቸው፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="8">መንቀጥቀጥና መደንገጥ ይዞአቸው ነበርና ወጥተው ከመቃብር ሸሹ፤ ይፈሩ ነበርና ለማንም አንዳች አልነገሩም። እነርሱም ያዘዛቸውን ሁሉ ለጴጥሮስና ከእርሱ ጋር ላሉት በአጭሩ ተናገሩ። ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ራሱ ለዘላለም ድኅነት የሆነውን የማይለወጠውን ቅዱስ ወንጌል ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያው ድረስ በእጃቸው ላከው።</verse>
				<verse number="9">ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን ማልዶ በተነሣ ጊዜ፥ አስቀድሞ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለመግደላዊት ማርያም ታየ።</verse>
				<verse number="10">እርስዋ ሄዳ ከእርሱ ጋር ሆነው ለነበሩት ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ሳሉ አወራችላቸው፤</verse>
				<verse number="11">እነርሱም ሕያው እንደ ሆነ ለእርስዋም እንደ ታያት ሲሰሙ አላመኑም።</verse>
				<verse number="12">ከዚህም በኋላ ከእነርሱ ለሁለቱ ወደ ባላገር ሲሄዱ በመንገድ በሌላ መልክ ተገለጠ፤</verse>
				<verse number="13">እነርሱም ሄደው ለሌሎቹ አወሩ፤ እነዚያንም ደግሞ አላመኑአቸውም።</verse>
				<verse number="14">ኋላም በማዕድ ተቀምጠው ሳሉ ለዐሥራ አንዱ ተገለጠ፤ ተነሥቶም ያዩትን ስላላመኑአቸው አለማመናቸውንና የልባቸውን ጥንካሬ ነቀፈ።</verse>
				<verse number="15">እንዲህም አላቸው “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።</verse>
				<verse number="16">ያመነ የተጠመቀም ይድናል፤ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።</verse>
				<verse number="17">ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤</verse>
				<verse number="18">እባቦችን ይይዛሉ፤የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጐዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ፤ እነርሱም ይድናሉ።</verse>
				<verse number="19">ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።</verse>
				<verse number="20">እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፤ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፤ በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="42">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በእኛ ዘንድ የተ​ፈ​ጸ​መ​ው​ንና የታ​መ​ነ​ውን የሥ​ራ​ውን ዜና በሥ​ር​ዐት ሊጽፉ የጀ​መሩ ብዙ​ዎች ናቸው።</verse>
				<verse number="2">ከእኛ አስ​ቀ​ድሞ በዐ​ይን ያዩ​ትና የቃሉ አገ​ል​ጋ​ዮች የነ​በሩ እንደ አስ​ተ​ላ​ለ​ፉ​ልን፤</verse>
				<verse number="3">የከ​በ​ርህ ቴዎ​ፍ​ሎስ ሆይ፥ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ተከ​ትዬ፥ ሁሉ​ንም በየ​ተ​ራው እው​ነ​ተ​ኛ​ውን እጽ​ፍ​ልህ ዘንድ መል​ካም ሁኖ ታየኝ።</verse>
				<verse number="4">የተ​ማ​ር​ኸ​ውን የነ​ገ​ሩን እው​ነት ጠን​ቅ​ቀህ ታውቅ ዘንድ።</verse>
				<verse number="5">በይ​ሁዳ ንጉሥ በሄ​ሮ​ድስ ዘመን ከአ​ብያ ክፍል የሆነ ዘካ​ር​ያስ የሚ​ባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስ​ቱም ከአ​ሮን ልጆች ወገን ነበ​ረች፤ ስም​ዋም ኤል​ሳ​ቤጥ ነበረ።</verse>
				<verse number="6">ሁለ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጻድ​ቃን ነበሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥር​ዐ​ትና በት​እ​ዛ​ዙም ሁሉ ያለ ነውር የሚ​ሄዱ ነበሩ።</verse>
				<verse number="7">ልጅም አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም፤ ኤል​ሳ​ቤጥ መካን ነበ​ረ​ችና፤ ሁለ​ቱም አር​ጅ​ተው ነበር፤ ዘመ​ና​ቸ​ውም አልፎ ነበር።</verse>
				<verse number="8">እር​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በተ​ራው የክ​ህ​ነ​ትን ሥራ በሚ​ሠ​ራ​በት ጊዜ፥</verse>
				<verse number="9">ካህ​ናት እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጉት የሚ​ያ​ጥ​ን​በት ጊዜ ደረሰ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደ​ስም ገባ።</verse>
				<verse number="10">ዕጣን በሚ​ያ​ጥ​ን​በት ጊዜም ሕዝቡ በሙሉ በውጭ ይጸ​ልዩ ነበር።</verse>
				<verse number="11">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም በዕ​ጣን መሠ​ው​ያው በስ​ተ​ቀኝ ቆሞ ታየው።</verse>
				<verse number="12">ዘካ​ር​ያ​ስም ባየው ጊዜ ደነ​ገጠ፤ ፍር​ሀ​ትም ረዓ​ድም ወረ​ደ​በት።</verse>
				<verse number="13">መል​አ​ኩም እን​ዲህ አለው፥ “ዘካ​ር​ያስ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ ጸሎ​ትህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተሰ​ም​ቶ​አ​ልና፤ ሚስ​ትህ ኤል​ሣ​ቤ​ጥም ትፀ​ን​ሳ​ለች፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ድ​ል​ሃ​ለች፤ ስሙ​ንም ዮሐ​ንስ ትለ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="14">ደስ​ታና ሐሤ​ትም ይሆ​ን​ል​ሃል፤ በመ​ወ​ለ​ዱም ብዙ​ዎች ደስ ይላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="15">እርሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ታላቅ ይሆ​ና​ልና የወ​ይን ጠጅና የሚ​ያ​ሰ​ክ​ርም መጠጥ ሁሉ አይ​ጠ​ጣም፤ ከእ​ናቱ ማሕ​ፀን ጀም​ሮም መን​ፈስ ቅዱስ ይመ​ላ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="16">ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ብዙ​ዎ​ችን ወደ አም​ላ​ካ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ል​ሳ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="17">እር​ሱም የአ​ባ​ቶ​ችን ልብ ወደ ልጆች፥ የከ​ሓ​ድ​ያ​ን​ንም ዐሳብ ወደ ጻድ​ቃን ዕው​ቀት ይመ​ልስ ዘንድ፥ ሕዝ​ብ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ዘ​ጋጀ ያደ​ርግ ዘንድ በኤ​ል​ያስ መን​ፈ​ስና ኀይል በፊቱ ይሄ​ዳል።”</verse>
				<verse number="18">ዘካ​ር​ያ​ስም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ እን​ዲህ አለው፥ “ይህ እን​ደ​ሚ​ሆን በምን አው​ቃ​ለሁ? እነሆ፥ እኔ አር​ጅ​ች​አ​ለሁ፤ የሚ​ስ​ቴም ዘመ​ንዋ አል​ፏል።”</verse>
				<verse number="19">መል​አ​ኩም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እኔ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የም​ቆ​መው ገብ​ር​ኤል ነኝ፤ ይህ​ንም እነ​ግ​ር​ህና አበ​ሥ​ርህ ዘንድ ወደ አንተ ተል​ኬ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">አሁ​ንም በጊ​ዜው የሚ​ሆ​ነ​ው​ንና የሚ​ፈ​ጸ​መ​ውን ነገ​ሬን አላ​መ​ን​ኽ​ኝ​ምና ይህ እስ​ኪ​ሆን ድረስ ዲዳ ትሆ​ና​ለህ፤ መና​ገ​ርም ይሳ​ን​ሃል።”</verse>
				<verse number="21">ሕዝቡ ግን ዘካ​ር​ያ​ስን ይጠ​ብ​ቁት ነበር፤ በቤተ መቅ​ደስ ውስጥ ዘግ​ይቶ ነበ​ርና እጅግ ተደ​ነቁ።</verse>
				<verse number="22">ወደ እነ​ርሱ ወደ ውጭ በወጣ ጊዜም እነ​ር​ሱን ማነ​ጋ​ገር ተሳ​ነው፤ በቤተ መቅ​ደ​ስም የተ​ገ​ለ​ጠ​ለት እን​ዳለ ዐወቁ፤ እን​ዲ​ሁም ዲዳ ሆኖ በእጁ እያ​መ​ለ​ከ​ታ​ቸው ኖረ።</verse>
				<verse number="23">ከዚ​ህም በኋላ የማ​ገ​ል​ገሉ ወራት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ ወደ ቤቱ ገባ።</verse>
				<verse number="24">ከእ​ነ​ዚ​ያም ቀኖች በኋላ ሚስቱ ኤል​ሳ​ቤጥ ፀነ​ሰች፤ ፅን​ስ​ዋ​ንም ለአ​ም​ስት ወር ሸሸ​ገች፤ እን​ዲህ ስትል፦</verse>
				<verse number="25">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ወራት ከሰው ስድ​ቤን ያርቅ ዘንድ በጐ​በ​ኘኝ ጊዜ እን​ዲህ አደ​ረ​ገ​ልኝ።”</verse>
				<verse number="26">በስ​ድ​ስ​ተ​ኛ​ውም ወር መል​አኩ ገብ​ር​ኤል ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ስሟ ናዝ​ሬት ወደ​ም​ት​ባ​ለው ወደ አን​ዲት የገ​ሊላ ከተማ ከዳ​ዊት ወገን ለሚ​ሆን ዮሴፍ ለሚ​ባል ሰው ወደ ታጨ​ችው ወደ አን​ዲት ድን​ግል ተላከ፤</verse>
				<verse number="27">የዚ​ያ​ችም ድን​ግል ስምዋ ማር​ያም ይባል ነበረ።</verse>
				<verse number="28">መል​አ​ኩም ወደ እር​ስዋ ገብቶ፥ “ደስ ያለሽ፥ ጸጋ​ንም የተ​መ​ላሽ ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካንቺ ጋር ነው፤ ከሴ​ቶች ተለ​ይ​ተሽ አንቺ የተ​ባ​ረ​ክሽ ነሽ” አላት።</verse>
				<verse number="29">እር​ስ​ዋም በአ​የ​ችው ጊዜ ከአ​ነ​ጋ​ገሩ የተ​ነሣ ደነ​ገ​ጠ​ችና “ይህ እን​ዴት ያለ ሰላ​ምታ ነው?” ብላ ዐሰ​በች።</verse>
				<verse number="30">መል​አ​ኩም እን​ዲህ አላት፥ “ማር​ያም ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን አግ​ኝ​ተ​ሻ​ልና አት​ፍሪ።</verse>
				<verse number="31">እነሆ፥ ትፀ​ን​ሻ​ለሽ፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ ስሙ​ንም ኢየ​ሱስ ትይ​ዋ​ለሽ።</verse>
				<verse number="32">እር​ሱም ታላቅ ነው፤ የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅም ይባ​ላል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም የአ​ባ​ቱን የዳ​ዊ​ትን ዙፋን ይሰ​ጠ​ዋል።</verse>
				<verse number="33">ለያ​ዕ​ቆብ ወገ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ ይነ​ግ​ሣል፤ ለመ​ን​ግ​ሥ​ቱም ፍጻሜ የለ​ውም።”</verse>
				<verse number="34">ማር​ያ​ምም መል​አ​ኩን፥ “ወንድ ስለ​ማ​ላ​ውቅ ይህ እን​ዴት ይሆ​ን​ል​ኛል?” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="35">መል​አ​ኩም መልሶ እን​ዲህ አላት፥ “መን​ፈስ ቅዱስ ያድ​ር​ብ​ሻል፤ የል​ዑል ኀይ​ልም ይጋ​ር​ድ​ሻል፤ ከአ​ንቺ የሚ​ወ​ለ​ደ​ውም ቅዱስ ነው፤ የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅም ይባ​ላል።</verse>
				<verse number="36">እነሆ፥ ከዘ​መ​ዶ​ችሽ ወገን የም​ት​ሆን ኤል​ሣ​ቤ​ጥም እር​ስዋ እንኳ በእ​ር​ጅ​ናዋ ወንድ ልጅን ፀን​ሳ​ለች፤ መካን ትባል የነ​በ​ረ​ችው ከፀ​ነ​ሰች እነሆ፥ ይህ ስድ​ስ​ተኛ ወር ነው።</verse>
				<verse number="37">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሳ​ነው ነገር የለ​ምና”።</verse>
				<verse number="38">ማር​ያ​ምም መል​አ​ኩን፥ “እነ​ሆኝ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪ​ያው አለሁ፤ እንደ ቃልህ ይሁ​ን​ልኝ” አለ​ችው፤ ከዚህ በኋ​ላም መል​አኩ ከእ​ር​ስዋ ዘንድ ሄደ።</verse>
				<verse number="39">በዚ​ያም ወራት ማር​ያም ፈጥና ተነ​ሣች፤ ወደ ተራ​ራ​ማው ሀገር ወደ ይሁዳ ከተ​ማም ደረ​ሰች።</verse>
				<verse number="40">ወደ ዘካ​ር​ያስ ቤትም ገብታ ለኤ​ል​ሣ​ቤጥ ሰላ​ምታ ሰጠ​ቻት።</verse>
				<verse number="41">ኤል​ሳ​ቤ​ጥም የማ​ር​ያ​ምን ሰላ​ምታ በሰ​ማች ጊዜ ፅንሱ በማ​ኅ​ፀ​ንዋ ዘለለ፤ በኤ​ል​ሣ​ቤ​ጥም መን​ፈስ ቅዱስ መላ​ባት።</verse>
				<verse number="42">በታ​ላቅ ቃልም ጮሃ እን​ዲህ አለች፥ “ከሴ​ቶች ተለ​ይ​ተሽ አንቺ የተ​ባ​ረ​ክሽ ነሽ፤ የማ​ኅ​ፀ​ን​ሽም ፍሬ ቡሩክ ነው።</verse>
				<verse number="43">የጌ​ታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እኔ ምን​ድን ነኝ?</verse>
				<verse number="44">እነሆ፥ ሰላ​ምታ ስት​ሰ​ጭኝ ቃል​ሽን በሰ​ማሁ ጊዜ፥ ፅንሱ በማ​ኅ​ፀኔ በደ​ስታ ዘሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="45">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የነ​ገ​ሩሽ ቃል እን​ደ​ሚ​ሆን የም​ታ​ምኚ አንቺ ብፅ​ዕት ነሽ።”</verse>
				<verse number="46">ማር​ያ​ምም እን​ዲህ አለች፥ “ሰው​ነቴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታከ​ብ​ረ​ዋ​ለች።</verse>
				<verse number="47">ልቡ​ና​ዬም በአ​ም​ላኬ በመ​ድ​ኀ​ኒቴ ሐሤት ታደ​ር​ጋ​ለች።</verse>
				<verse number="48">የባ​ር​ያ​ውን ትሕ​ትና ተመ​ል​ክ​ቶ​አ​ልና። እነሆ፥ ከዛሬ ጀምሮ ትው​ልድ ሁሉ ብፅ​ዕት ይሉ​ኛል።</verse>
				<verse number="49">ታላቅ ሥራን ሠር​ቶ​ል​ኛ​ልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።</verse>
				<verse number="50">ይቅ​ር​ታ​ውም ለሚ​ፈ​ሩት ለልጅ ልጅ ነው።</verse>
				<verse number="51">በክ​ንዱ ኀይ​ልን አደ​ረገ፤ በል​ባ​ቸው ዐሳብ የሚ​ታ​በ​ዩ​ት​ንም በተ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="52">ኀያ​ላ​ኑን ከዙ​ፋ​ና​ቸው አዋ​ረ​ዳ​ቸው፤ ትሑ​ታ​ኑ​ንም ከፍ ከፍ አደ​ረ​ጋ​ቸው።</verse>
				<verse number="53">የተ​ራ​ቡ​ትን ከበ​ረ​ከቱ አጠ​ገ​ባ​ቸው፤ ባለ​ጠ​ጎ​ች​ንም ባዶ እጃ​ቸ​ውን ሰደ​ዳ​ቸው።</verse>
				<verse number="54">ብላ​ቴ​ና​ውን እስ​ራ​ኤ​ልን ተቀ​በ​ለው፤ ይቅ​ር​ታ​ው​ንም ዐሰበ።</verse>
				<verse number="55">ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለዘሩ እስከ ዘለ​ዓ​ለም እንደ ተና​ገ​ረው።”</verse>
				<verse number="56">ማር​ያ​ምም ሦስት ወር ያህል በእ​ር​ስዋ ዘንድ ተቀ​መ​ጠች፤ ከዚህ በኋ​ላም ወደ ቤቷ ተመ​ለ​ሰች።</verse>
				<verse number="57">የኤ​ል​ሣ​ቤ​ጥም የመ​ው​ለ​ጃዋ ጊዜ ደረሰ፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች።</verse>
				<verse number="58">ዘመ​ዶ​ች​ዋና ጎረ​ቤ​ቶ​ች​ዋም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር​ነ​ቱን እን​ዳ​በ​ዛ​ላት በሰሙ ጊዜ ከእ​ር​ስዋ ጋር ደስ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="59">ከዚ​ህም በኋላ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ሕፃ​ኑን ሊገ​ዝ​ሩት መጡ፤ በአ​ባ​ቱም ስም ዘካ​ር​ያስ ብለው ጠሩት።</verse>
				<verse number="60">እናቱ ግን መልሳ፥ “አይ​ሆ​ንም፥ ዮሐ​ንስ ይባል እንጂ” አለች።</verse>
				<verse number="61">እነ​ር​ሱም፥ “ከዘ​መ​ዶ​ችሽ ስሙ እን​ደ​ዚህ የሚ​ባል የለም” አሉ​አት።</verse>
				<verse number="62">አባ​ቱ​ንም ጠቅ​ሰው፥ “ማን ሊሉት ትወ​ዳ​ለህ?” አሉት።</verse>
				<verse number="63">ብራ​ናም ለመ​ነና “ስሙ ዮሐ​ንስ ይባል” ብሎ ጻፈ፤ ሁሉም አደ​ነቁ።</verse>
				<verse number="64">ያን​ጊ​ዜም አፉ ተከ​ፈተ፤ አን​ደ​በ​ቱም ተና​ገረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገነ።</verse>
				<verse number="65">በዚ​ያም ሀገር ሰው ሁሉ ላይ ፍር​ሀት ሆነ፤ ይህም ነገር ሁሉ በይ​ሁዳ በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ሁሉ ተወራ።</verse>
				<verse number="66">የሰ​ሙ​ትም ሁሉ፥ “እን​ግ​ዲህ ይህ ሕፃን ምን ይሆን?” እያሉ በል​ባ​ቸው አኖ​ሩት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረ​ችና።</verse>
				<verse number="67">በአ​ባቱ በዘ​ካ​ር​ያ​ስም መን​ፈስ ቅዱስ መላ​በት፤ እን​ዲ​ህም ብሎ ትን​ቢት ተና​ገረ፦</verse>
				<verse number="68">“ይቅር ያለን፥ ለወ​ገ​ኖ​ቹም ድኅ​ነ​ትን ያደ​ረገ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤</verse>
				<verse number="69">ከባ​ር​ያው ከዳ​ዊት ቤት የም​ን​ድ​ን​በ​ትን ቀንድ አስ​ነ​ሣ​ልን፤</verse>
				<verse number="70">ከጥ​ንት ጀምሮ በነ​በሩ በቅ​ዱ​ሳን በነ​ቢ​ያት አፍ እንደ ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="71">ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን እጅ፥ ከሚ​ጠ​ሉ​ንም ሁሉ እጅ ያድ​ነን ዘንድ።</verse>
				<verse number="72">ቸር​ነ​ቱን ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ጋር ያደ​ርግ ዘንድ፥ ቅዱስ ኪዳ​ኑ​ንም ያስብ ዘንድ።</verse>
				<verse number="73">ለአ​ባ​ታ​ችን ለአ​ብ​ር​ሃም የማ​ለ​ውን መሐላ ያስብ ዘንድ።</verse>
				<verse number="74">ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን እጅ ድነን ያለ ፍር​ሀት፥</verse>
				<verse number="75">በቅ​ድ​ስ​ናና በጽ​ድቅ በፊቱ በዘ​መ​ና​ችን ሁሉ እን​ድ​ና​መ​ል​ከው ይሰ​ጠን ዘንድ።</verse>
				<verse number="76">አን​ተም ሕፃን፥ የል​ዑል ነቢይ ትባ​ላ​ለህ፤ መን​ገ​ዱን ትጠ​ርግ ዘንድ በፊቱ ትሄ​ዳ​ለ​ህና።</verse>
				<verse number="77">ኀጢ​አ​ታ​ቸው ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸው ዘንድ መድ​ኀ​ኒ​ታ​ቸ​ውን እን​ዲ​ያ​ውቁ ለአ​ሕ​ዛብ ትሰ​ጣ​ቸው ዘንድ።</verse>
				<verse number="78">ከአ​ር​ያም በጐ​በ​ኘን በአ​ም​ላ​ካ​ችን በይ​ቅ​ር​ታ​ውና በቸ​ር​ነቱ።</verse>
				<verse number="79">በጨ​ለ​ማና በሞት ጥላ ለነ​በ​ሩት ብር​ሃ​ኑን ያሳ​ያ​ቸው ዘንድ፥ እግ​ሮ​ቻ​ች​ን​ንም ወደ ሰላም ጎዳና ያቀና ዘንድ ወጣ።”</verse>
				<verse number="80">ሕፃ​ኑም አደገ፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ጸና፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም እስ​ከ​ታ​የ​በት ቀን ድረስ በም​ድረ በዳ ኖረ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">በዚ​ያም ወራት እን​ዲህ ሆነ፤ ሰው ሁሉ ይቈ​ጠር ዘንድ ከአ​ው​ግ​ስ​ጦስ ቄሣር ትእ​ዛዝ ወጣ።</verse>
				<verse number="2">ቄሬ​ኔ​ዎስ ለሶ​ርያ መስ​ፍን በነ​በረ ጊዜ ይህ የመ​ጀ​መ​ርያ ቈጠራ ሆነ።</verse>
				<verse number="3">ሰው ሁሉ ሊቈ​ጠር ወደ​የ​ከ​ተ​ማው ሄደ።</verse>
				<verse number="4">ዮሴ​ፍም ከገ​ሊላ አው​ራጃ ከና​ዝ​ሬት ከተማ ወደ ይሁዳ፥ ቤተ ልሔም ወደ​ም​ት​ባ​ለው ወደ ዳዊት ከተማ ወጣ፤ እርሱ ከዳ​ዊት ሀገ​ርና ከዘ​መ​ዶ​ቹም ወገን ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="5">ፀንሳ ሳለች ከእ​ጮ​ኛው ከማ​ር​ያም ጋር ይጻፍ ዘንድ ሄደ።</verse>
				<verse number="6">በዚያ ሳሉም የም​ት​ወ​ል​ድ​በት ቀን ደረሰ።</verse>
				<verse number="7">የበ​ኵር ልጅ​ዋ​ንም ወለ​ደች፤ አውራ ጣቱ​ንም አሰ​ረ​ችው፤ በጨ​ር​ቅም ጠቀ​ለ​ለ​ችው፤ በበ​ረ​ትም አስ​ተ​ኛ​ችው፤ በማ​ደ​ር​ያ​ቸው ቦታ አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ው​ምና።</verse>
				<verse number="8">በዚያ ሀገር እረ​ኞች ነበሩ፤ ሌሊ​ቱ​ንም ተግ​ተው መን​ጋ​ቸ​ውን ይጠ​ብቁ ነበር።</verse>
				<verse number="9">እነ​ሆም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸው ቆመ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብር​ሃን በዙ​ሪ​ያ​ቸው አበራ፤ ታላቅ ፍር​ሀ​ት​ንም ፈሩ።</verse>
				<verse number="10">መል​አ​ኩም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እነሆ፥ ለእ​ና​ን​ተና ለሕ​ዝቡ ሁሉ ደስታ የሚ​ሆን ታላቅ የም​ሥ​ራች እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለ​ሁና አት​ፍሩ።</verse>
				<verse number="11">እነሆ፥ ዛሬ በዳ​ዊት ከተማ መድ​ኅን ተወ​ል​ዶ​ላ​ች​ኋል፤ ይኸ​ውም ቡሩክ ጌታ ክር​ስ​ቶስ ነው።</verse>
				<verse number="12">ለእ​ና​ን​ተም ምል​ክቱ እን​ዲህ ነው፦ ሕፃን አውራ ጣቱን ታስሮ፥ በጨ​ር​ቅም ተጠ​ቅ​ልሎ በበ​ረት ውስጥ ተኝቶ ታገ​ኛ​ላ​ቸሁ።”</verse>
				<verse number="13">ድን​ገ​ትም ከዚያ መል​አክ ጋር ብዙ የሰ​ማይ ሠራ​ዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገኑ መጡ።</verse>
				<verse number="14">“ክብር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማ​ያት፥ ሰላ​ምም በም​ድር፥ ለሰው ልጅም በጎ ፈቃድ ሆነ” ይሉ ነበር።</verse>
				<verse number="15">ከዚ​ህም በኋላ መላ​እ​ክት ከእ​ነ​ርሱ ዘንድ ወደ ሰማይ በዐ​ረጉ ጊዜ እነ​ዚያ እረ​ኞች ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “እስከ ቤተ ልሔም እን​ሂድ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የገ​ለ​ጠ​ል​ንን ይህን ነገር እን​ወቅ” አሉ።</verse>
				<verse number="16">ፈጥ​ነ​ውም ሄዱ፤ ማር​ያ​ም​ንና ዮሴ​ፍን አገ​ኙ​አ​ቸው፤ ሕፃ​ኑ​ንም በበ​ረት ውስጥ ተኝቶ አገ​ኙት።</verse>
				<verse number="17">በአ​ዩም ጊዜ የነ​ገ​ሩ​አ​ቸው ስለ​ዚህ ሕፃን እንደ ሆነ ዐው​ቀው አወሩ።</verse>
				<verse number="18">የሰ​ሙ​ትም ሁሉ እረ​ኞቹ የነ​ገ​ሩ​አ​ቸ​ውን አደ​ነቁ።</verse>
				<verse number="19">ማር​ያም ግን ይህን ሁሉ ትጠ​ብ​ቀው፥ በል​ብ​ዋም ታኖ​ረው ነበር።</verse>
				<verse number="20">እረ​ኞ​ችም እንደ ነገ​ሩ​አ​ቸው ባዩ​ትና በሰ​ሙት ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​ከ​በ​ሩና እያ​መ​ሰ​ገኑ ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="21">ስም​ንት ቀን በተ​ፈ​ጸመ ጊዜም ሕፃ​ኑን ሊገ​ዝ​ሩት ወሰ​ዱት፤ በማ​ኅ​ፀ​ንዋ ሳት​ፀ​ን​ሰው መል​አኩ እን​ዳ​ወ​ጣ​ለ​ትም ስሙን ኢየ​ሱስ አሉት።</verse>
				<verse number="22">የመ​ን​ጻ​ታ​ቸ​ውም ወራት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ እንደ ሙሴ ሕግ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቆ​ሙት ዘንድ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወሰ​ዱት።</verse>
				<verse number="23">“በኵር ሆኖ የሚ​ወ​ለድ ወንድ ልጅ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ይባ​ላል” ተብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ እንደ ተጻፈ፥</verse>
				<verse number="24">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ እንደ ታዘዘ ሁለት ዋኖስ ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ስለ እርሱ መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገው ያቀ​ር​ቡ​ለት ዘንድ።</verse>
				<verse number="25">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ስሙ ስም​ዖን የሚ​ባል አንድ ሰው ነበር፤ እር​ሱም ጻድ​ቅና ደግ ሰው ነበር፤ እር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ደስ​ታ​ቸ​ውን ያይ ዘንድ ተስፋ ያደ​ርግ ነበር፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስም ያደ​ረ​በት ነበር።</verse>
				<verse number="26">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መሲሕ ሳያይ እን​ደ​ማ​ይ​ሞት መን​ፈስ ቅዱስ ገል​ጦ​ለት ነበር።</verse>
				<verse number="27">መን​ፈ​ስም ወደ ቤተ መቅ​ደስ ወሰ​ደው፤ ዘመ​ዶ​ቹም በሕግ የተ​ጻ​ፈ​ውን ያደ​ር​ጉ​ለት ዘንድ ሕፃ​ኑን ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ወደ ቤተ መቅ​ደስ በአ​ገ​ቡት ጊዜ፥</verse>
				<verse number="28">እርሱ ደግሞ ተቀ​ብሎ በክ​ንዱ ታቀ​ፈው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገ​ነው።</verse>
				<verse number="29">እን​ዲ​ህም አለ፤ “አቤቱ፥ እንደ አዘ​ዝህ ዛሬ ባር​ያ​ህን በሰ​ላም ታሰ​ና​ብ​ተ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="30">ዐይ​ኖች ትድ​ግ​ና​ህን አይ​ተ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="31">በወ​ገ​ንህ ሁሉ ፊት ያዘ​ጋ​ጀ​ኸ​ውን፥</verse>
				<verse number="32">ለአ​ሕ​ዛብ ብር​ሃ​ንን፥ ለወ​ገ​ንህ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ክብ​ርን ትገ​ልጥ ዘንድ።”</verse>
				<verse number="33">ዮሴ​ፍና እናቱ ግን በእ​ርሱ ላይ ስለ​ሚ​ና​ገ​ረው ያደ​ንቁ ነበር።</verse>
				<verse number="34">ስም​ዖ​ንም ባረ​ካ​ቸው፤ እና​ቱን ማር​ያ​ም​ንም እን​ዲህ አላት፤ “እነሆ፥ ይህ ሕፃን ከእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ለብ​ዙ​ዎች ለመ​ው​ደ​ቃ​ቸ​ውና ለመ​ነ​ሣ​ታ​ቸው፥ ለሚ​ቃ​ወ​ሙ​ትም ምል​ክት ይሆን ዘንድ የተ​ሠ​የመ ነው፤</verse>
				<verse number="35">ባንቺ ግን በል​ብሽ ፍላጻ ይገ​ባል፤ የብ​ዙ​ዎ​ቹን ዐሳብ ይገ​ልጥ ዘንድ።”</verse>
				<verse number="36">ከአ​ሴር ወገን የም​ት​ሆን የፋ​ኑ​ኤል ልጅ ሐና የም​ት​ባል ነቢ​ይት ነበ​ረች፤ አር​ጅ​ታም ነበር፤ ከድ​ን​ግ​ል​ና​ዋም በኋላ ከባል ጋር ሰባት ዓመት ኖረች።</verse>
				<verse number="37">ሰማ​ንያ አራት ዓመ​ትም መበ​ለት ሆና ኖረች፤ በጾ​ምና በጸ​ሎ​ትም እያ​ገ​ለ​ገ​ለች፥ ቀንም ሆነ ሌሊት ከቤተ መቅ​ደስ አት​ወ​ጣም ነበር።</verse>
				<verse number="38">ያን​ጊ​ዜም ተነ​ሥታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ነች፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ድኅ​ነት ተስፋ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ስለ እርሱ ተና​ገ​ረች።</verse>
				<verse number="39">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ ከፈ​ጸሙ በኋላ ወደ ገሊላ ወደ ከተ​ማ​ቸው ወደ ናዝ​ሬት ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="40">ሕፃ​ኑም አደገ፤ በመ​ን​ፈ​ስም ጠነ​ከረ፤ ጥበ​ብ​ንም የተ​መላ ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸጋ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="41">ዘመ​ዶ​ቹም በየ​ዓ​መቱ ለፋ​ሲካ በዓል ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይሄዱ ነበር።</verse>
				<verse number="42">ዐሥራ ሁለት ዓመ​ትም በሞ​ላው ጊዜ እንደ አስ​ለ​መዱ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለበ​ዓል ወጡ።</verse>
				<verse number="43">ሥራ​ቸ​ው​ንም ጨር​ሰው ተመ​ለሱ፤ ሕፃኑ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቀርቶ ነበር፤ ዮሴ​ፍና እና​ቱም አላ​ወ​ቁም ነበር።</verse>
				<verse number="44">በመ​ን​ገ​ድም ከሰ​ዎች ጋር ያለ መስ​ሎ​አ​ቸው ነበር፤ ያንድ ቀን መን​ገ​ድ​ንም ከሄዱ በኋላ ዕለ​ቱን ከዘ​መ​ዶቹ፥ ከሚ​ያ​ው​ቁ​ትም ዘንድ ፈለ​ጉት።</verse>
				<verse number="45">ባላ​ገ​ኙ​ትም ጊዜ እየ​ፈ​ለ​ጉት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="46">ከዚ​ህም በኋላ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን በቤተ መቅ​ደስ በሊ​ቃ​ው​ንት መካ​ከል ተቀ​ምጦ ሲሰ​ማ​ቸ​ውና ሲጠ​ይ​ቃ​ቸው አገ​ኙት።</verse>
				<verse number="47">የሰ​ሙ​ትም ሁሉ አስ​ተ​ዋ​ይ​ነ​ቱ​ንና አመ​ላ​ለ​ሱን ያደ​ንቁ ነበር።</verse>
				<verse number="48">በአ​ዩ​ትም ጊዜ ደነ​ገጡ፤ እና​ቱም፥ “ልጄ፥ ለምን እን​ዲህ አደ​ረ​ግ​ኸን? እነሆ አባ​ት​ህም፥ እኔም ስን​ፈ​ል​ግህ ደከ​ምን” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="49">እር​ሱም፥ “ለምን ትፈ​ል​ጉ​ኛ​ላ​ችሁ? በአ​ባቴ ቤት ልኖር እን​ደ​ሚ​ገ​ባኝ አላ​ወ​ቃ​ች​ሁ​ምን?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="50">እነ​ርሱ ግን የነ​ገ​ራ​ቸ​ውን ቃል አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም።</verse>
				<verse number="51">ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሂዶ ወደ ናዝ​ሬት ወረደ፤ ይታ​ዘ​ዝ​ላ​ቸ​ውም ነበር፤ እናቱ ግን ይህን ሁሉ ነገር ትጠ​ብ​ቀው፥ በል​ብ​ዋም ታኖ​ረው ነበር።</verse>
				<verse number="52">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ፥ በሰ​ውም ዘንድ፥ በጥ​በ​ብና በአ​ካል በሞ​ገ​ስም አደገ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ጢባ​ር​ዮስ ቄሣር በነ​ገሠ በዐ​ሥራ አም​ስት ዓመት ጴን​ጤ​ና​ዊው ጲላ​ጦስ የይ​ሁዳ ገዢ ሆኖ ሳለ፥ ሄሮ​ድ​ስም በገ​ሊላ የአ​ራ​ተ​ኛው ክፍል ገዢ ሳለ፥ ወን​ድሙ ፊል​ጶ​ስም የኢ​ጡ​ር​ያ​ስና የጥ​ራ​ኮ​ኒ​ዶስ አራ​ተኛ ክፍል ገዢ፥ ሊሳ​ን​ዮ​ስም የሳ​ብ​ላ​ኒስ አራ​ተኛ ክፍል ገዢ ሆነው ሳሉ፥</verse>
				<verse number="2">ሐናና ቀያ​ፋም ሊቃነ ካህ​ናት በነ​በ​ሩ​በት ወራት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በም​ድረ በዳ ወደ ዘካ​ር​ያስ ልጅ ወደ ዮሐ​ንስ መጣ።</verse>
				<verse number="3">ስለ ኀጢ​አት ስር​የት ለን​ስሓ የሚ​ያ​በቃ ጥም​ቀ​ትን እየ​ሰ​በከ በዮ​ር​ዳ​ኖስ አው​ራጃ ዞረ።</verse>
				<verse number="4">በም​ድረ በዳ የሚ​ጮኽ የአ​ዋጅ ነጋሪ ድምፅ በነ​ቢዩ በኢ​ሳ​ይ​ያስ መጽ​ሐፍ ቃል እንደ ተጻፈ፥ እን​ዲህ ሲል፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ጥረጉ፤ ጥር​ጊ​ያ​ው​ንም አስ​ተ​ካ​ክሉ።</verse>
				<verse number="5">ጐድ​ጓ​ዳው ሁሉ ይምላ፤ ተራ​ራ​ውም፥ ኮረ​ብ​ታ​ውም ሁሉ ዝቅ ይበል፤ ሰን​ከ​ል​ካ​ላ​ውም የቀና ጥር​ጊያ ይሁን፤ ወጣ ገባው መን​ገ​ድም ይስ​ተ​ካ​ከል።</verse>
				<verse number="6">ሰውም ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትድ​ግና ይይ።”</verse>
				<verse number="7">ዮሐ​ን​ስም ሊያ​ጠ​ም​ቃ​ቸው የመ​ጡ​ትን ሰዎች እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንት የእ​ፉ​ኝት ልጆች፥ ከሚ​መ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ታመ​ልጡ ዘንድ ማን ነገ​ራ​ችሁ?</verse>
				<verse number="8">እን​ግ​ዲህ ለን​ስሓ የሚ​ያ​በ​ቃ​ች​ሁን ሥራ ሥሩ፤ አብ​ር​ሃም አባ​ታ​ችን አለን በማ​ለት የም​ታ​መ​ልጡ አይ​ም​ሰ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮች ለአ​ብ​ር​ሃም ልጆ​ችን ማስ​ነ​ሣት እን​ደ​ሚ​ችል እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">እነሆ፥ ምሳር በዛ​ፎች ላይ ተቃ​ጥ​ቶ​አል፤ መል​ካም ፍሬ የማ​ያ​ፈ​ራ​ው​ንም ዛፍ ሁሉ ይቈ​ር​ጡ​ታል፤ ወደ እሳ​ትም ይጥ​ሉ​ታል።”</verse>
				<verse number="10">ሕዝ​ቡም፥ “እን​ግ​ዲህ ምን እና​ድ​ርግ?” ብለው ጠየ​ቁት።</verse>
				<verse number="11">እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሁለት ልብስ ያለው አን​ዱን ለሌ​ለው ይስጥ፤ ምግብ ያለ​ውም እን​ዲሁ ያድ​ርግ።”</verse>
				<verse number="12">ቀራ​ጮ​ችም ሊያ​ጠ​ም​ቃ​ቸው መጡና፥ “መም​ህር፥ ምን እና​ድ​ርግ?” ብለው ጠየ​ቁት።</verse>
				<verse number="13">እር​ሱም፥ “ከታ​ዘ​ዛ​ች​ሁት አት​ር​ፋ​ችሁ አት​ው​ሰዱ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">ጭፍ​ሮ​ችም መጥ​ተው፥ “እኛሳ ምን እና​ድ​ርግ?” አሉት፤ “በደ​መ​ወ​ዛ​ችሁ ኑሩ እንጂ በማ​ንም ግፍ አት​ሥሩ፤ ማን​ንም አት​ቀሙ፤ አት​በ​ድ​ሉም” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">ሕዝ​ቡም ሁሉ በል​ባ​ቸው ዐሰቡ፤ ዮሐ​ን​ስም ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ መሰ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">ዮሐ​ን​ስም መልሶ ሁሉ​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ በውኃ አጠ​ም​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ግን የሚ​በ​ል​ጠኝ የጫ​ማ​ውን ማሰ​ሪያ እንኳ ልፈ​ታ​ለት የማ​ይ​ገ​ባኝ ይመ​ጣል፤ እርሱ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ፥ በእ​ሳ​ትም ያጠ​ም​ቃ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="17">መንሹ በእጁ ነው፤ የዐ​ው​ድ​ማ​ው​ንም እህል ያጠ​ራል፤ ስን​ዴ​ው​ንም በጎ​ተ​ራው ይሰ​በ​ስ​ባል፤ ገለ​ባ​ውን ግን በማ​ይ​ጠፋ እሳት ያቃ​ጥ​ላል።”</verse>
				<verse number="18">ሕዝ​ቡ​ንም ይገ​ስ​ጻ​ቸ​ውና በሌ​ላም በብዙ ነገር የም​ሥ​ራች ይነ​ግ​ራ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="19">ዮሐ​ን​ስም የአ​ራ​ተ​ኛው ክፍል ገዢ ሄሮ​ድ​ስን የወ​ን​ድ​ሙን የፊ​ል​ጶ​ስን ሚስት ሄሮ​ድ​ያ​ዳን ስለ​ማ​ግ​ባ​ቱና ሄሮ​ድስ ያደ​ር​ገው ስለ​ነ​በ​ረው ክፉ ነገር ሁሉ ይገ​ሥ​ጸው ነበር።</verse>
				<verse number="20">ደግ​ሞም ከዚህ ሁሉ በላይ ጨምሮ ዮሐ​ን​ስን ተቀ​የ​መ​ውና በግ​ዞት ቤት አስ​ገ​ባው።</verse>
				<verse number="21">ሕዝ​ቡም ሁሉ ከተ​ጠ​መቁ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ተጠ​መቀ፤ ሲጸ​ል​ይም ሰማይ ተከ​ፈተ።</verse>
				<verse number="22">መን​ፈስ ቅዱ​ስም የር​ግብ መልክ ባለው አካል አም​ሳል በእ​ርሱ ላይ ወረደ፤ ከሰ​ማ​ይም፥ “የም​ወ​ድህ፥ በአ​ን​ተም ደስ የሚ​ለኝ ልጄ አንተ ነህ” የሚል ቃል መጣ። ሉቃ. 9፥35።</verse>
				<verse number="23">የጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዕድ​ሜዉ ሠላሳ ዓመት ያህል ነበር፤ የዮ​ሴፍ ልጅም ይመ​ስ​ላ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="24">የኤሊ ልጅ፥ የማቲ ልጅ፥ የሌዊ ልጅ፥ የሜ​ልኪ ልጅ፥ የዮና ልጅ፥ የዮ​ሴፍ ልጅ፥</verse>
				<verse number="25">የማ​ታ​ትዩ ልጅ፥ የአ​ሞጽ ልጅ፥ የና​ሆም ልጅ፥ የኤ​ስ​ሎም ልጅ፥ የናጌ ልጅ፥</verse>
				<verse number="26">የማ​አት ልጅ፥ የማ​ታ​ትዩ ልጅ፥ የሴ​ሜይ ልጅ፥ የዮ​ሴፍ ልጅ፥ የዮዳ ልጅ፥</verse>
				<verse number="27">የዮ​ናን ልጅ፥ የሬስ ልጅ፥ የዘ​ሩ​ባ​ቤል ልጅ፥ የሰ​ላ​ት​ያል ልጅ፥ የኔሪ ልጅ፥</verse>
				<verse number="28">የሜ​ልኪ ልጅ፥ የሐዲ ልጅ፥ የዮሳ ልጅ፥ የቆ​ሳም ልጅ፥ የኤ​ል​ሞ​ዳም ልጅ፥ የኤር ልጅ፥</verse>
				<verse number="29">የዮ​ሴዕ ልጅ፥ የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ፥ የዮ​ራም ልጅ፥ የማ​ጣት ልጅ፥ የሌዊ ልጅ፥</verse>
				<verse number="30">የስ​ም​ዖን ልጅ፥ የይ​ሁዳ ልጅ፥ የዮ​ሴፍ ልጅ፥ የዮ​ናን ልጅ፥ የኤ​ል​ያ​ቄም ልጅ፥</verse>
				<verse number="31">የሜ​ልያ ልጅ፥ የማ​ይ​ናን ልጅ፥ የማ​ጣት ልጅ፥ የና​ታን ልጅ፥ የዳ​ዊት ልጅ፥</verse>
				<verse number="32">የዕ​ሤይ ልጅ፥ የኢ​ዮ​ቤድ ልጅ፥ የቦ​ዔዝ ልጅ፥ የሰ​ል​ሞን ልጅ፥ የነ​ዓ​ሶን ልጅ፥</verse>
				<verse number="33">የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ፥ የአ​ራም ልጅ፥ የኦ​ርኒ ልጅ፥ የኤ​ስ​ሮም ልጅ፥ የፋ​ሬስ ልጅ፤ የይ​ሁዳ ልጅ፥</verse>
				<verse number="34">የያ​ዕ​ቆብ ልጅ፥ የይ​ስ​ሐቅ ልጅ፥ የአ​ብ​ር​ሃም ልጅ፥ የታራ ልጅ፥ የና​ኮር ልጅ፥</verse>
				<verse number="35">የሴ​ሩኅ ልጅ፥ የራ​ግው ልጅ፥ የፋ​ሌቅ ልጅ፥ የኤ​ቦር ልጅ፥ የሳላ ልጅ፥</verse>
				<verse number="36">የቃ​ይ​ናን ልጅ፥ የአ​ር​ፋ​ክ​ስድ ልጅ፥ የሴም ልጅ፥ የኖኅ ልጅ፥ የላ​ሜሕ ልጅ፥</verse>
				<verse number="37">የማ​ቱ​ሳላ ልጅ፥ የሄ​ኖክ ልጅ፥ የያ​ሬድ ልጅ፥ የመ​ላ​ል​ኤል ልጅ፥ የቃ​ይ​ናን ልጅ፥</verse>
				<verse number="38">የሄ​ኖስ ልጅ፥ የሴት ልጅ፥ የአ​ዳም ልጅ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተመ​ልቶ ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ተመ​ለሰ፤ መን​ፈ​ስም ወደ ምድረ በዳ ወሰ​ደው።</verse>
				<verse number="2">አርባ መዓ​ል​ትና አርባ ሌሊት ከዲ​ያ​ብ​ሎስ ተፈ​ተነ፥ በእ​ነ​ዚ​ያም ቀኖች ምንም አል​በ​ላም፤ እነ​ዚ​ያም ቀኖች ከተ​ፈ​ጸሙ በኋላ ተራበ።</verse>
				<verse number="3">ዲያ​ብ​ሎ​ስም፥ “አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ከሆ​ን​ህስ ይህ ድን​ጋይ እን​ጀራ ይሁን በል” አለው።</verse>
				<verse number="4">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ሰው የሚ​ኖ​ረው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ በሚ​ወ​ጣው ቃል ነው እንጂ በእ​ን​ጀራ ብቻ አይ​ደ​ለም የሚል ተጽ​ፎ​አል” አለው።</verse>
				<verse number="5">ዲያ​ብ​ሎ​ስም ወደ ረዥም ተራራ አወ​ጣው፤ የዓ​ለ​ምን መን​ግ​ሥ​ታ​ትም ሁሉ በቅ​ፅ​በት አሳ​የው።</verse>
				<verse number="6">ዲያ​ብ​ሎ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “ይህን ሁሉ ግዛት፥ ይህ​ንም ክብር ለአ​ንተ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ ለእኔ ተሰ​ጥ​ቶ​አ​ልና፤ ለወ​ደ​ድ​ሁ​ትም እሰ​ጠ​ዋ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="7">ስለ​ዚህ አንተ በፊቴ ብት​ሰ​ግ​ድ​ልኝ ይህ ሁሉ ለአ​ንተ ይሁ​ን​ልህ።”</verse>
				<verse number="8">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ሰይ​ጣን ከኋ​ላዬ ሂድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላ​ክህ ልት​ሰ​ግድ፥ እር​ሱ​ንም ብቻ ልታ​መ​ልክ ተጽ​ፎ​አል” አለው።</verse>
				<verse number="9">ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወስዶ በቤተ መቅ​ደሱ የማ​ዕ​ዘን ጫፍ ላይ አቆ​መው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ከሆ​ን​ህስ አንተ ራስህ ወደ ታች መር ብለህ ውረድ።</verse>
				<verse number="10">በመ​ን​ገ​ድህ ይጠ​ብ​ቁህ ዘንድ መላ​እ​ክ​ትን ስለ አንተ ያዝ​ዛ​ቸ​ዋል፤</verse>
				<verse number="11">እግ​ር​ህም በድ​ን​ጋይ እን​ዳ​ት​ሰ​ነ​ካ​ከል በእ​ጃ​ቸው ያነ​ሡ​ሃል” ተብሎ ተጽ​ፎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="12">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ፈጣ​ሪህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አት​ፈ​ታ​ተ​ነው” ተብ​ሎ​አል አለው።</verse>
				<verse number="13">ዲያ​ብ​ሎ​ስም በዚህ ሁሉ እር​ሱን መፈ​ታ​ተ​ኑን ከፈ​ጸመ በኋላ እስከ ጊዜው ከእ​ርሱ ተለየ።</verse>
				<verse number="14">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ኀይል ተመ​ልሶ ወደ ገሊላ ሄደ፤ ዝና​ውም በሀ​ገሩ ሁሉ ተሰማ።</verse>
				<verse number="15">በየ​ም​ኵ​ራ​ባ​ቸ​ውም ሁሉ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ነበር፤ ትም​ህ​ር​ቱ​ንም ያደ​ንቁ ነበር፤ ሁሉም ያመ​ሰ​ግ​ኑት ነበር።</verse>
				<verse number="16">ወደ አደ​ገ​በት ወደ ናዝ​ሬ​ትም ሄደ፤ በሰ​ን​በት ቀንም እን​ዳ​ስ​ለ​መደ ወደ ምኵ​ራብ ገባ፤ ሊያ​ነ​ብም ተነሣ።</verse>
				<verse number="17">የነ​ቢ​ዩን የኢ​ሳ​ይ​ያ​ስ​ንም መጽ​ሐፍ ሰጡት፤ መጽ​ሐ​ፉ​ንም በገ​ለጠ ጊዜ እን​ዲህ የሚል የተ​ጻ​ፈ​በ​ትን ስፍራ አገኘ።</verse>
				<verse number="18">“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በላዬ ነው፤ ስለ​ዚህ ቀብቶ ለድ​ሆች የም​ሥ​ራ​ችን እነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ፥ ለተ​ማ​ረ​ኩ​ትም ነጻ​ነ​ትን እሰ​ብ​ክ​ላ​ቸው ዘንድ፥ ያዘ​ኑ​ት​ንም ደስ አሰ​ኛ​ቸው ዘንድ፥ ዕው​ሮ​ችም ያዩ ዘንድ፥ የተ​ገ​ፉ​ት​ንም አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ የታ​ሰ​ሩ​ት​ንም እፈ​ታ​ቸው ዘንድ፥ የቈ​ሰ​ሉ​ት​ንም አድ​ና​ቸው ዘንድ፥</verse>
				<verse number="19">የተ​መ​ረ​ጠ​ች​ው​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዓመት እሰ​ብክ ዘንድ ላከኝ።”</verse>
				<verse number="20">መጽ​ሐ​ፉ​ንም አጥፎ ለተ​ላ​ላ​ኪው ሰጠ​ውና ተቀ​መጠ፤ በም​ኲ​ራ​ብም የነ​በ​ሩት ሁሉ ዐይ​ና​ቸ​ውን አት​ኲ​ረው ተመ​ለ​ከ​ቱት።</verse>
				<verse number="21">እር​ሱም፥ “የዚህ የመ​ጽ​ሐፍ ነገር ዛሬ በጆ​ሮ​አ​ችሁ ደረሰ፤ ተፈ​ጸ​መም” ይላ​ቸው ጀመር።</verse>
				<verse number="22">ሁሉም የን​ግ​ግ​ሩን መከ​ና​ወን መሰ​ከ​ሩ​ለት፤ የአ​ን​ደ​በ​ቱ​ንም ቅል​ጥ​ፍና እያ​ደ​ነቁ፥ “ይህ የዮ​ሴፍ ልጅ አይ​ደ​ለ​ምን?” ይሉ ነበር።</verse>
				<verse number="23">እር​ሱም፥ “በውኑ ባለ መድ​ኀ​ኒት ራስ​ህን አድን፤ በቅ​ፍ​ር​ና​ሆም ያደ​ረ​ግ​ኸ​ው​ንና የሰ​ማ​ነ​ውን ሁሉ በዚ​ህም በሀ​ገ​ርህ ደግሞ አድ​ርግ ብላ​ችሁ ይህ​ችን ምሳሌ ትመ​ስ​ሉ​ብ​ኛ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ነቢይ በሀ​ገሩ አይ​ከ​ብ​ርም።</verse>
				<verse number="25">እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በነ​ቢዩ በኤ​ል​ያስ ዘመን በም​ድር ሁሉ ብርቱ ረኃብ እስ​ኪ​ሆን ድረስ ሰማይ ሦስት ዓመት ከስ​ድ​ስት ወር በተ​ዘ​ጋ​በት ጊዜ ብዙ መበ​ለ​ቶች በእ​ስ​ራ​ኤል ውስጥ ነበሩ።</verse>
				<verse number="26">ኤል​ያስ የሲ​ዶና ክፍል በም​ት​ሆን በስ​ራ​ጵታ ወደ​ም​ት​ኖር ወደ አን​ዲት መበ​ለት ሴት እንጂ ከእ​ነ​ዚህ ወደ አን​ዲቱ እን​ኳን አል​ተ​ላ​ከም።</verse>
				<verse number="27">በነ​ቢዩ በኤ​ል​ሳዕ ዘመ​ንም ብዙ ለም​ጻ​ሞች በእ​ስ​ራ​ኤል ውስጥ ነበሩ፤ ነገር ግን ከሶ​ር​ያ​ዊው ከን​ዕ​ማን በቀር ከእ​ነ​ዚያ አንድ እን​ኳን አል​ነ​ጻም።”</verse>
				<verse number="28">በም​ኵ​ራ​ብም የነ​በ​ሩት ሁሉ ይህን ሰም​ተው ተቈጡ።</verse>
				<verse number="29">ያን​ጊ​ዜም ተነ​ሥ​ተው ከከ​ተማ ወደ ውጭ አወ​ጡት፤ ገፍ​ተ​ውም ይጥ​ሉት ዘንድ ከተ​ማ​ቸው ተሠ​ር​ታ​ባት ወደ ነበ​ረች ተራራ ጫፍ ወሰ​ዱት።</verse>
				<verse number="30">እርሱ ግን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አልፎ ሄደ።</verse>
				<verse number="31">ወደ ገሊላ ከተ​ማም ወደ ቅፍ​ር​ና​ሆም ወረደ፤ በሰ​ን​በ​ትም ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="32">አነ​ጋ​ገ​ሩም በት​እ​ዛዝ ነበ​ርና ትም​ህ​ር​ቱን ያደ​ንቁ ነበር።</verse>
				<verse number="33">በም​ኵ​ራ​ብም ርኩስ መን​ፈስ የያ​ዘው አንድ ሰው ነበር፤ በታ​ላቅ ቃልም ጮኾ፦</verse>
				<verse number="34">“የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ ሆይ፥ ከአ​ንተ ጋር ምን አለን? ያለ​ጊ​ዜ​አ​ችን ልታ​ጠ​ፋን መጣ​ህን? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ሆይ፥ አንተ ማን እን​ደ​ሆ​ንህ ዐው​ቅ​ሃ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="35">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ዝም በልና ከእ​ርሱ ውጣ” ብሎ ገሠ​ጸው፤ ጋኔ​ኑም በም​ኵ​ራቡ መካ​ከል ጣለ​ውና ከእ​ርሱ ወጣ፤ ነገር ግን ምንም አል​ጐ​ዳ​ውም።</verse>
				<verse number="36">ሁሉም ደነ​ገጡ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተነ​ጋ​ገሩ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ይህ ነገር ምን​ድን ነው? ክፉ​ዎ​ችን አጋ​ን​ንት በሥ​ል​ጣ​ንና በኀ​ይል ያዝ​ዛ​ቸ​ዋ​ልና፥ እነ​ር​ሱም ይወ​ጣ​ሉና።”</verse>
				<verse number="37">ዝና​ውም በዙ​ሪ​ያዉ ባሉ መን​ደ​ሮች ሁሉ ወጣ፤ ተሰ​ማም።</verse>
				<verse number="38">ከም​ኵ​ራ​ቡም ወጥቶ ወደ ስም​ዖን ቤት ገባ፤ የስ​ም​ዖን አማ​ትም በብ​ርቱ ንዳድ ታማ ነበ​ርና ስለ እር​ስዋ ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="39">በአ​ጠ​ገ​ብ​ዋም ቁሞ ንዳ​ድ​ዋን ገሠ​ጸ​ውና ተዋት፤ ወዲ​ያ​ውም ተነ​ሥታ አገ​ለ​ገ​ለ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="40">ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ ልዩ ልዩ ደዌ ያለ​ባ​ቸ​ውን ድው​ያን ሁሉ አመ​ጡ​ለት፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ላይ እጁን ጭኖ ፈወ​ሳ​ቸው።</verse>
				<verse number="41">ብዙ አጋ​ን​ን​ትም፥ “አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ክር​ስ​ቶስ ነህ” እያ​ሉና እየ​ጮሁ ይወጡ ነበር፤ እር​ሱም ይገ​ሥ​ጻ​ቸው ነበር፤ ክር​ስ​ቶ​ስም እንደ ሆነ ያውቁ ነበ​ርና እን​ዲ​ና​ገሩ አይ​ፈ​ቅ​ድ​ላ​ቸ​ውም ነበር።</verse>
				<verse number="42">በነጋ ጊዜም ወጥቶ ወደ ምድረ በዳ ሄደ፤ ሕዝ​ቡም እየ​ፈ​ለ​ጉት ወደ እርሱ ሄዱ፤ አል​ፎ​አ​ቸው እን​ዳ​ይ​ሄ​ድም አቆ​ሙት።</verse>
				<verse number="43">እርሱ ግን፥ “ስለ​ዚህ ተል​ኬ​አ​ለ​ሁና ለሌ​ሎች ከተ​ሞች ደግሞ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ወን​ጌል እነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ ይገ​ባ​ኛል” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="44">በገ​ሊላ ምኲ​ራ​ቦ​ችም ይሰ​ብክ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">ብዙ ሰዎ​ችም በእ​ርሱ ዘንድ ነበሩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ይሰሙ ነበር፤ እርሱ ግን በጌ​ን​ሴ​ሬጥ ባሕር ወደብ ቁሞ ነበር።</verse>
				<verse number="2">በባ​ሕ​ሩም ዳር ሁለት ታን​ኳ​ዎች ቁመው አየ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ውስጥ ዓሣ አጥ​ማ​ጆች መረ​ባ​ቸ​ውን ሊያ​ጥቡ ወረዱ።</verse>
				<verse number="3">ከሁ​ለቱ ታን​ኳ​ዎች ወደ አን​ዲቱ ታንኳ ወጣ፤ ይቺ​ውም ታንኳ የስ​ም​ዖን ነበ​ረች፤ “ከም​ድር ጥቂት እልፍ አድ​ር​ጋት” አለው፤ በታ​ን​ኳ​ዪ​ቱም ውስጥ ተቀ​ምጦ ሕዝ​ቡን አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ትም​ህ​ር​ቱ​ንም ከፈ​ጸመ በኋላ ስም​ዖ​ንን፥ “ወደ ጥልቁ ባሕር ፈቀቅ በል፤ መረ​ቦ​ቻ​ች​ሁ​ንም ለማ​ጥ​መድ ጣሉ” አለው።</verse>
				<verse number="5">ስም​ዖ​ንም መልሶ፥ “መም​ህር፥ ሌሊ​ቱን ሁሉ ደክ​መ​ናል፤ የያ​ዝ​ነ​ውም የለም፤ ነገር ግን ስለ አዘ​ዝ​ኸን መረ​ቦ​ቻ​ች​ንን እን​ጥ​ላ​ለን” አለው።</verse>
				<verse number="6">እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸ​ውም ባደ​ረጉ ጊዜ፥ መረቡ እስ​ኪ​ቀ​ደድ ድረስ ብዙ ዓሣ ተያዘ።</verse>
				<verse number="7">መጥ​ተ​ውም ይረ​ዱ​አ​ቸው ዘንድ በሌላ ታንኳ የነ​በ​ሩ​ትን ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ጠሩ፤ መጥ​ተ​ውም እስ​ኪ​ጠ​ልቁ ድረስ ሁለ​ቱን ታን​ኳ​ዎች ሞሉ።</verse>
				<verse number="8">ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ይህን አይቶ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እግር በታች ሰገ​ደና፥ “እኔ ኀጢ​አ​ተኛ ሰው ነኝና አቤቱ ከእኔ ፈቀቅ በል፤” አለው።</verse>
				<verse number="9">እር​ሱና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ሁሉ ስለ ተያ​ዘው ዓሣ ተደ​ን​ቀው ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="10">እን​ዲ​ሁም የስ​ም​ዖን ባል​ን​ጀ​ራ​ዎች የነ​በሩ የዘ​ብ​ዴ​ዎስ ልጆች ያዕ​ቆ​ብና ዮሐ​ንስ ተደ​ነቁ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ስም​ዖ​ንን፥ “አት​ፍራ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ህስ ሰውን ታጠ​ም​ዳ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="11">ታን​ኳ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ወደ ምድር አወ​ጡና ሁሉን ትተው ተከ​ተ​ሉት።</verse>
				<verse number="12">በአ​ን​ዲት ከተማ ሳለም ሁለ​መ​ናው ለም​ጻም የሆነ ሰው መጣ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ባየው ጊዜ በፊቱ ወድቆ ሰገ​ደ​ለ​ትና፥ “አቤቱ ብት​ወ​ድስ ልታ​ነ​ጻኝ ትች​ላ​ለህ” እያለ ማለ​ደው።</verse>
				<verse number="13">እጁ​ንም ዘር​ግቶ ዳሰ​ሰ​ውና፥ “እወ​ዳ​ለሁ ንጻ” አለው፤ ያን​ጊ​ዜም ለምጹ ለቀ​ቀው።</verse>
				<verse number="14">ለማ​ንም እን​ዳ​ይ​ና​ገር ከለ​ከ​ለው፤ “ነገር ግን ሄደህ ራስ​ህን ለካ​ህን አስ​መ​ር​ምር፤ ምስ​ክ​ርም ይሆ​ን​ባ​ቸው ዘንድ ስለ ነጻህ ሙሴ እንደ አዘዘ መባ​ህን አቅ​ርብ” ብሎ አዘ​ዘው።</verse>
				<verse number="15">ዜና​ውም በሁሉ ተሰማ፤ ብዙ ሰዎ​ችም ትም​ህ​ር​ቱን ሊሰሙ፥ ከደ​ዌ​አ​ቸ​ውም ሊፈ​ወሱ ይመጡ ነበር።</verse>
				<verse number="16">እርሱ ግን ወደ ምድረ በዳ እየ​ወጣ ይጸ​ልይ ነበር።</verse>
				<verse number="17">ከዚ​ህም በኋላ፥ ከዕ​ለ​ታት በአ​ንድ ቀን ሲያ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው እን​ዲህ ሆነ፤ ከገ​ሊ​ላና ከይ​ሁዳ መን​ደ​ሮች፥ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የመጡ ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንና የኦ​ሪት መም​ህ​ራን ነበሩ፤ እር​ሱም ይፈ​ውስ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ነበረ።</verse>
				<verse number="18">እነሆ፥ ሰዎች በአ​ልጋ ተሸ​ክ​መው ሽባ የሆነ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፤ እን​ዲ​ፈ​ው​ሰ​ውም ወደ እርሱ ሊያ​ስ​ገ​ቡት ወደዱ።</verse>
				<verse number="19">ሰውም ተጨ​ና​ንቆ ነበ​ርና የሚ​ያ​ስ​ገ​ቡ​በት አጡ፤ ወደ ሰገ​ነ​ትም ወጡ፤ ጣራ​ው​ንም አፍ​ር​ሰው ወደ ቤቱ ውስጥ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ፊት ከነ​አ​ል​ጋው አወ​ረ​ዱት።</verse>
				<verse number="20">እም​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም አይቶ ያን ሰው፥ “ኀጢ​አ​ትህ ተሰ​ረ​የ​ልህ” አለው።</verse>
				<verse number="21">ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “የሚ​ሳ​ደብ ይህ ማን ነው? ከአ​ንዱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀር ኀጢ​አ​ትን ማስ​ተ​ስ​ረይ ማን ይች​ላል?” ብለው ያስቡ ጀመር።</verse>
				<verse number="22">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም የሚ​ያ​ስ​ቡ​ትን ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በል​ባ​ችሁ ምን ታስ​ባ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="23">ኀጢ​አ​ትህ ተሰ​ረ​የ​ልህ ከማ​ለ​ትና ተነ​ሥ​ተህ ሂድ ከማ​ለት ማና​ቸው ይቀ​ላል?</verse>
				<verse number="24">ለሰው ልጅ በም​ድር ላይ ኀጢ​አ​ትን ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ ሥል​ጣን እን​ዳ​ለው እን​ድ​ታ​ውቁ፤ ያን ሽባ፦ ተነ​ሣና አል​ጋ​ህን ተሸ​ክ​መህ ወደ ቤትህ ሂድ ብዬ​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="25">ያን​ጊ​ዜም ተነ​ሥቶ ተኝ​ቶ​በት የነ​በ​ረ​ውን አልጋ በፊ​ታ​ቸው ተሸ​ክሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገነ ወደ ቤቱ ሄደ።</verse>
				<verse number="26">ሁሉም ተደ​ነቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገ​ኑት፤ እጅ​ግም እየ​ፈሩ፥ “ዛሬ ድንቅ ነገር አየን” አሉ።</verse>
				<verse number="27">ከዚ​ህም በኋላ ከዚያ ወጥቶ ሌዊ የሚ​ባል ቀራጭ ሰው በቀ​ረጥ መቀ​በ​ያው ቦታ ተቀ​ምጦ አየና፥ “ተከ​ተ​ለኝ” አለው።</verse>
				<verse number="28">ሁሉ​ንም ተወና ተነ​ሥቶ ተከ​ተ​ለው።</verse>
				<verse number="29">ሌዊም በቤቱ ታላቅ ግብዣ አደ​ረ​ገ​ለት፤ ብዙ ሰዎ​ችም ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ለምሳ ተቀ​ም​ጠው የነ​በሩ ቀራ​ጮ​ችና ኀጢ​አ​ተ​ኞች፥ ሌሎ​ችም ብዙ​ዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="30">ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “ከቀ​ራ​ጮ​ችና ከኃ​ጥ​ኣን ጋር ለምን ትበ​ላ​ላ​ችሁ? ትጠ​ጡ​ማ​ላ​ችሁ?” ብለው በደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ላይ አን​ጐ​ራ​ጐሩ።</verse>
				<verse number="31">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ባለ መድ​ኀ​ኒ​ትን በሽ​ተ​ኞች እንጂ ጤነ​ኞች አይ​ሹ​ትም።</verse>
				<verse number="32">ኃጥ​ኣ​ንን ወደ ንስሓ እንጂ ጻድ​ቃ​ንን ልጠራ አል​መ​ጣ​ሁም።”</verse>
				<verse number="33">እነ​ር​ሱም፥ “የዮ​ሐ​ንስ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ስለ​ምን በብዙ ይጾ​ማሉ? ጸሎ​ትስ ስለ​ምን ያደ​ር​ጋሉ? የፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወገ​ኖች የሆ​ኑ​ትም ስለ​ምን እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋሉ? ያንተ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ግን ለምን ይበ​ላሉ? ይጠ​ጣ​ሉም?” አሉት።</verse>
				<verse number="34">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የሙ​ሽ​ራው ሚዜ​ዎች ሙሽ​ራው ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሳለ መጾም አይ​ች​ሉም።</verse>
				<verse number="35">ነገር ግን ሙሽ​ራ​ውን ከእ​ነ​ርሱ የሚ​ወ​ስ​ዱ​በት ቀን ይመ​ጣል፤ ያን​ጊ​ዜም ይጾ​ማሉ።”</verse>
				<verse number="36">በም​ሳ​ሌም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በአ​ሮጌ ልብስ ቀዳዳ ላይ የአ​ዲስ ልብስ እራፊ የሚ​ጥፍ የለም፤ ያለ​ዚያ ግን አዲሱ አሮ​ጌ​ውን ይቀ​ድ​ደ​ዋል፤ አዲሱ እራ​ፊም ከአ​ሮ​ጌው ጋር አይ​ስ​ማ​ማም።</verse>
				<verse number="37">አዲስ ጠጅ​ንም በአ​ሮጌ ረዋት የሚ​ያ​ደ​ርግ የለም፤ ያለ​ዚያ ግን ይቀ​ድ​ደ​ዋል፤ ወይ​ኑም ይፈ​ስ​ሳል፤ ረዋ​ቱም ይቀ​ደ​ዳል።</verse>
				<verse number="38">ነገር ግን አዲ​ሱን ጠጅ በአ​ዲስ ረዋት ያደ​ር​ጉ​ታል፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ይጠ​ባ​በ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="39">የከ​ረ​መ​ውን የወ​ይን ጠጅ ሊጠጣ ወድዶ አዲ​ሱን የሚሻ የለም፤ የከ​ረ​መው ይሻ​ላል ይላ​ልና።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ ደግሞ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በሰ​ን​በት ቀን በእ​ርሻ መካ​ከል ሄደ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እሸት ቈር​ጠው በእ​ጃ​ቸው እያሹ በሉ።</verse>
				<verse number="2">ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “በሰ​ን​በት ሊደ​ረግ የማ​ይ​ገ​ባ​ውን ለምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?” አሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እር​ሱና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትም በተ​ራቡ ጊዜ ዳዊት ያደ​ረ​ገ​ውን አላ​ነ​በ​ባ​ች​ሁ​ምን?</verse>
				<verse number="4">ወደ ቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገባ፥ ከካ​ህ​ና​ቱም ብቻ በቀር ሊበ​ሉት የማ​ይ​ገ​ባ​ውን የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን ኅብ​ስት ወስዶ እንደ በላ፥ አብ​ረ​ውት ለነ​በ​ሩ​ትም እንደ ሰጣ​ቸው አላ​ነ​በ​ባ​ች​ሁ​ምን?</verse>
				<verse number="5">የሰው ልጅ ለሰ​ን​በት ጌታዋ ነው” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">ከዚ​ህም በኋላ በሌ​ላ​ይቱ ሰን​በት ወደ ምኵ​ራቡ ገባና አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፤ በዚ​ያም ቀኝ እጁ የሰ​ለ​ለች ሰው ነበረ።</verse>
				<verse number="7">ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም የሚ​ከ​ሱ​በት ምክ​ን​ያት ያገኙ ዘንድ፥ በሰ​ን​በት ይፈ​ው​ሰው እንደ ሆነ ብለው ይጠ​ባ​በ​ቁት ነበር።</verse>
				<verse number="8">እርሱ ግን ዐሳ​ባ​ቸ​ውን ያው​ቅ​ባ​ቸው ነበ​ርና እጁ የሰ​ለ​ለ​ች​ውን ሰው፥ “ተነ​ሥ​ተህ በመ​ካ​ከል ቁም” አለው፤ ተነ​ሥ​ቶም ቆመ።</verse>
				<verse number="9">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እጠ​ይ​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ በሰ​ን​በት ሊደ​ረግ የሚ​ገ​ባው ምን​ድ​ነው? መል​ካም መሥ​ራት ነውን? ወይስ ክፉ መሥ​ራት? ነፍ​ስን ማዳን ነውን? ወይስ መግ​ደል?”</verse>
				<verse number="10">እነ​ር​ሱም ዝም አሉ፤ ወደ እነ​ር​ሱም ዙሮ ከተ​መ​ለ​ከተ በኋላ፦ ያን ሰው፥ “እጅ​ህን ዘርጋ” አለው፤ ሰው​ዬ​ውም ዘረ​ጋት፤ እጁም ዳነ​ችና እንደ ሁለ​ተ​ኛ​ይቱ ሆነች።</verse>
				<verse number="11">እነ​ርሱ ግን፥ እጅግ ተቈጡ፤ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱ​ስም ምን እን​ድ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​በት እርስ በር​ሳ​ቸው ተማ​ከሩ።</verse>
				<verse number="12">በዚ​ያም ወራት ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ሊጸ​ልይ ወደ ተራራ ወጣ፤ ሌሊ​ቱን ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ልይ ነበር፤</verse>
				<verse number="13">ሲነ​ጋም ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን ወደ እርሱ ጠራ​ቸው፤ ከው​ስ​ጣ​ቸ​ውም ዐሥራ ሁለ​ቱን መረጠ፤ ሐዋ​ር​ያት ብሎም ሰየ​ማ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">እነ​ር​ሱም እነ​ዚህ ናቸው፦ ጴጥ​ሮስ የተ​ባ​ለው ስም​ዖን፥ ወን​ድ​ሙም እን​ድ​ር​ያስ፥ ያዕ​ቆ​ብና ዮሐ​ንስ፥ ፊል​ጶ​ስና በር​ተ​ሎ​ሜ​ዎስ።</verse>
				<verse number="15">ማቴ​ዎ​ስና ቶማስ፥ የእ​ል​ፍ​ዮስ ልጅ ያዕ​ቆ​ብና ቀናዒ የሚ​ባ​ለው ስም​ዖን።</verse>
				<verse number="16">የያ​ዕ​ቆብ ወን​ድም ይሁዳ፥ የከ​ዳ​ውና አሳ​ልፎ የሰ​ጠው ያስ​ቆ​ሮቱ ሰው ይሁ​ዳም ናቸው።</verse>
				<verse number="17">ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ወርዶ በሰፊ ቦታ ቆመ፤ ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ወገን ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከመ​ላው ይሁ​ዳና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ከጢ​ሮ​ስና ከሲ​ዶና ባሕር ዳርቻ ትም​ህ​ር​ቱን ሊሰሙ፥ ከደ​ዌ​አ​ቸ​ውም ሊፈ​ወሱ የመ​ጡት ከሕ​ዝቡ ወገን እጅግ ብዙ​ዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="18">ክፉ​ዎች አጋ​ን​ንት ያደ​ሩ​ባ​ቸ​ውም ይፈ​ወሱ ነበር።</verse>
				<verse number="19">ሕዝቡ ሁሉ ሊዳ​ስ​ሱት ይሹ ነበር፤ ኀይል ከእ​ርሱ ይወጣ ነበ​ርና፥ ሁሉ​ንም ይፈ​ው​ሳ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="20">እር​ሱም ወደ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ዐይ​ኖ​ቹን አን​ሥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ድሆች፥ ብፁ​ዓን ናችሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት የእ​ና​ንተ ናትና።</verse>
				<verse number="21">ዛሬ የም​ት​ራቡ፥ ብፁ​ዓን ናችሁ፤ ትጠ​ግ​ባ​ላ​ች​ሁና፤ ዛሬ የም​ታ​ለ​ቅሱ፥ ብፁ​ዓን ናችሁ፤ ትስ​ቃ​ላ​ች​ሁና።</verse>
				<verse number="22">ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ቢጠ​ሉ​አ​ችሁ፥ ከሰው ለይ​ተው ቢአ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ችሁ፥ ቢሰ​ድ​ቡ​አ​ችሁ፥ ክፉ ስምም ቢአ​ወ​ጡ​ላ​ችሁ ብፁ​ዓን ናችሁ።</verse>
				<verse number="23">ያን​ጊዜ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ በደ​ስ​ታም ዝለሉ፤ ዋጋ​ችሁ በሰ​ማይ ብዙ ነውና፤ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ነቢ​ያ​ትን እን​ዲሁ አድ​ር​ገ​ዋ​ቸው ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="24">ነገር ግን እና​ንተ ባለ​ጠ​ጎች፥ ወዮ​ላ​ችሁ፥ ደስ​ታ​ች​ሁን ጨር​ሳ​ች​ኋ​ልና።</verse>
				<verse number="25">ዛሬ ለም​ት​ጠ​ግቡ፥ ወዮ​ላ​ችሁ፥ ትራ​ባ​ላ​ች​ሁና፤ ዛሬ ለም​ት​ስ​ቁም ወዮ​ላ​ችሁ፥ ታዝ​ና​ላ​ች​ሁና፤ ታለ​ቅ​ሳ​ላ​ች​ሁ​ምና።</verse>
				<verse number="26">ሰዎች ሁሉ ስለ እና​ንተ መል​ካ​ሙን ነገር ቢና​ገ​ሩ​ላ​ችሁ ወዮ​ላ​ችሁ፥ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ለሐ​ሰ​ተ​ኞች ነቢ​ያት እን​ዲህ ያደ​ርጉ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="27">“ለም​ት​ሰ​ሙኝ ለእ​ና​ንተ ግን እን​ዲህ እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ውደዱ፤ ለሚ​ጠ​ሉ​አ​ች​ሁም መል​ካም አድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="28">የሚ​ረ​ግ​ሙ​አ​ች​ሁን መር​ቁ​አ​ቸው፤ ለሚ​በ​ድ​ሉ​አ​ች​ሁም ጸል​ዩ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="29">ጕን​ጭ​ህን ለሚ​መ​ታ​ህም ሁለ​ተ​ኛ​ይ​ቱን ስጠው፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ህን ለሚ​ወ​ስ​ድም ቀሚ​ስ​ህን ደግሞ አት​ከ​ል​ክ​ለው።</verse>
				<verse number="30">ለሚ​ለ​ም​ን​ህም ሁሉ ስጥ፤ ገን​ዘ​ብ​ህን የሚ​ወ​ስ​ደ​ው​ንም እን​ዲ​መ​ልስ አት​ጠ​ይ​ቀው።</verse>
				<verse number="31">ሰዎች ሊያ​ደ​ር​ጉ​ላ​ችሁ እን​ደ​ም​ት​ወ​ዱ​ትም እን​ዲሁ እና​ንተ አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="32">የሚ​ወ​ድ​ዱ​አ​ች​ሁን ብቻ ብት​ወ​ዱማ እን​ግ​ዲህ ዋጋ​ችሁ ምን​ድን ነው? ይህ​ንስ ኃጥ​ኣ​ንም ያደ​ር​ጋሉ፤ የሚ​ወ​ድ​ዳ​ቸ​ው​ንም ይወ​ድ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="33">በጎ ለሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ላ​ችሁ በጎ ብታ​ደ​ርጉ እን​ግ​ዲህ ዋጋ​ችሁ ምን​ድን ነው? እን​ዲ​ህስ ኃጥ​ኣ​ንም ያደ​ር​ጋሉ።</verse>
				<verse number="34">እን​ዲ​ከ​ፍ​ላ​ችሁ ተስፋ ለም​ታ​ደ​ር​ጉት ብታ​በ​ድሩ እን​ግ​ዲህ ዋጋ​ችሁ ምን​ድን ነው? ኃጥ​ኣ​ንም በአ​በ​ደ​ሩት ልክ ይከ​ፍ​ሉ​አ​ቸው ዘንድ ለኃ​ጥ​ኣን ያበ​ድ​ራ​ሉና።</verse>
				<verse number="35">አሁ​ንም ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ውደዱ፤ መል​ካ​ምም አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ እን​ዲ​መ​ል​ሱ​ላ​ችሁ ተስፋ ሳታ​ደ​ርጉ አበ​ድሩ፤ ዋጋ​ች​ሁም ብዙ ይሆ​ናል፤ የል​ዑ​ልም ልጆች ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ እርሱ ለበ​ጎ​ዎ​ችና ለክ​ፉ​ዎች ቸር ነውና።</verse>
				<verse number="36">ሰማ​ያዊ አባ​ታ​ችሁ የሚ​ራራ እንደ ሆነ እና​ን​ተም የም​ት​ራሩ ሁኑ።</verse>
				<verse number="37">አት​ፍ​ረዱ፥ አይ​ፈ​ረ​ድ​ባ​ች​ሁ​ምም፤ አት​በ​ድሉ፥ አይ​በ​ድ​ሉ​አ​ች​ሁ​ምም፤ ይቅር በሉ፥ ይቅ​ርም ይሉ​አ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="38">ስጡ፥ ይሰ​ጣ​ች​ኋ​ልም፤ የሞ​ላና የበዛ፥ የተ​ት​ረ​ፈ​ረ​ፈም መል​ካም መስ​ፈ​ሪያ በዕ​ቅ​ፋ​ችሁ ይሰ​ጡ​አ​ች​ኋል፤ በሰ​ፈ​ራ​ች​ሁ​በ​ትም መስ​ፈ​ሪያ ይሰ​ፍ​ሩ​ላ​ች​ኋል።”</verse>
				<verse number="39">ምሳ​ሌም መሰ​ለ​ላ​ቸ​ውና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ዕውር ዕው​ርን ሊመራ ይች​ላ​ልን? ሁለ​ቱስ በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ ይወ​ድቁ የለ​ምን?</verse>
				<verse number="40">ከመ​ም​ህሩ የሚ​በ​ልጥ ደቀ መዝ​ሙር የለም፤ ለሁ​ሉም መጠኑ እንደ መም​ህሩ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="41">በወ​ን​ድ​ምህ ዐይን ውስጥ ያለ​ውን ጕድፍ ለምን ታያ​ለህ? በዐ​ይ​ንህ ውስጥ ያለ​ውን ምሰሶ አታ​ይ​ምን?</verse>
				<verse number="42">ወን​ድ​ም​ህ​ንም፦ ወን​ድሜ ሆይ፥ ታገሥ፤ በዐ​ይ​ንህ ያለ​ውን ጕድፍ ላው​ጣ​ልህ ልት​ለው እን​ደ​ምን ትች​ላ​ለህ? አንተ ግን በዐ​ይ​ንህ ውስጥ ያለ​ውን ምሰሶ አታ​ይም፤ አንተ ግብዝ፥ አስ​ቀ​ድሞ ከዐ​ይ​ንህ ምሰ​ሶ​ውን አውጣ፤ ከዚህ በኋላ በባ​ል​ን​ጀ​ራህ ዐይን ውስጥ ያለ​ውን ጕድፍ ታወጣ ዘንድ አጥ​ር​ተህ ታያ​ለህ።</verse>
				<verse number="43">ክፉ ፍሬን የሚ​ያ​ፈራ መል​ካም ዛፍ የለም፤ መል​ካም ፍሬ የሚ​ያ​ፈራ ክፉ ዛፍም የለም።</verse>
				<verse number="44">ዛፍ ሁሉ ከፍ​ሬው ይታ​ወ​ቃል፤ ከእ​ሾህ በለ​ስን አይ​ለ​ቅ​ሙም፤ ከደ​ን​ደ​ርም ወይ​ንን አይ​ለ​ቅ​ሙም።</verse>
				<verse number="45">መል​ካም ሰው ከልቡ መል​ካም መዝ​ገብ መል​ካ​ምን ያወ​ጣል፤ ክፉ ሰውም ከልቡ ክፉ መዝ​ገብ ክፉ ነገ​ርን ያወ​ጣል፤ ከልብ የተ​ረ​ፈ​ውን አፍ ይና​ገ​ራ​ልና።</verse>
				<verse number="46">“ለምን አቤቱ፥ አቤቱ፥ ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ? የም​ላ​ች​ሁ​ንም አታ​ደ​ር​ጉም።</verse>
				<verse number="47">ወደ እኔ የሚ​መ​ጣና ቃሌን ሰምቶ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውም ሁሉ የሚ​መ​ስ​ለ​ውን አሳ​ያ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="48">መሠ​ረ​ቱን አጥ​ልቆ ቈፍሮ የመ​ሠ​ረ​ተና ቤቱን በዐ​ለት ላይ የሠራ ሰውን ይመ​ስ​ላል፤ ብዙ ፈሳ​ሾች በመጡ ጊዜ ጎር​ፎች ያን ቤት ገፉት፤ ሊያ​ነ​ዋ​ው​ጡ​ትም አል​ቻ​ሉም፤ በዐ​ለት ተሠ​ር​ቶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="49">ቃሌን ሰምቶ የማ​ያ​ደ​ር​ገው ሰው ግን ቤቱን ያለ መሠ​ረት በአ​ፈር ላይ የሠራ ሰውን ይመ​ስ​ላል፤ ጎር​ፎች ገፉት፤ ወዲ​ያ​ው​ኑም ወደቀ፤ የዚ​ያም ቤት አወ​ዳ​ደቁ ታላቅ ሆነ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">ለሕ​ዝ​ቡም ቃሉን ነግሮ ከፈ​ጸመ በኋላ ወደ ቅፍ​ር​ና​ሆም ገባ።</verse>
				<verse number="2">አንድ የመቶ አለ​ቃም ነበረ፤ አገ​ል​ጋ​ዩም ታሞ ሊሞት ቀርቦ ነበር፤ እር​ሱም በእ​ርሱ ዘንድ የተ​ወ​ደደ ነበር።</verse>
				<verse number="3">የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስ​ንም ነገር በሰማ ጊዜ፥ መጥቶ አገ​ል​ጋ​ዩን እን​ዲ​ያ​ድ​ን​ለት ይማ​ል​ዱት ዘንድ የአ​ይ​ሁ​ድን ሽማ​ግ​ሎች ወደ እርሱ ላከ።</verse>
				<verse number="4">ወደ ጌታ​ችን ወደ ኢየ​ሱ​ስም መጥ​ተው ማለ​ዱት፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “ፈጥ​ነህ ውረድ፤ ይህን ልታ​ደ​ር​ግ​ለት ይገ​ባ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="5">እርሱ ወገ​ና​ች​ንን ይወ​ዳ​ልና፤ ምኵ​ራ​ባ​ች​ን​ንም ሠር​ቶ​ል​ና​ልና።”</verse>
				<verse number="6">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሄደ፤ ወደ ቤቱም በቀ​ረበ ጊዜ፥ የመቶ አለ​ቃዉ ወዳ​ጆ​ቹን እን​ዲህ ብሎ ላከ፥ “አቤቱ፥ አት​ድ​ከም፤ ከቤቴ ጣራ በታች ልት​ገባ አይ​ገ​ባ​ኝ​ምና።</verse>
				<verse number="7">እኔም ወደ አንተ ልመጣ አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ነገር ግን በቃ​ልህ እዘዝ፤ ብላ​ቴ​ና​ዬም ይድ​ናል።</verse>
				<verse number="8">እኔም እኮ ገዢ ሰው ነኝ፤ ወታ​ደ​ሮ​ችም አሉኝ፤ አን​ዱን ሂድ ብለው ይሄ​ዳል፤ ሌላ​ው​ንም ና ብለው ይመ​ጣል፤ አገ​ል​ጋ​ዬ​ንም እን​ዲህ አድ​ርግ ብለው ያደ​ር​ጋል።”</verse>
				<verse number="9">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ከእ​ርሱ በሰማ ጊዜ አደ​ነ​ቀው፤ ዘወር ብሎም ይከ​ተ​ሉት ለነ​በ​ሩት ሕዝብ፥ “እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልስ እንኳ እን​ዲህ ያለ እም​ነት ያለው ሰው አላ​ገ​ኘ​ሁም” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">የተ​ላ​ኩ​ትም በተ​መ​ለሱ ጊዜ ብላ​ቴ​ና​ውን ድኖ አገ​ኙት።</verse>
				<verse number="11">በማ​ግ​ሥ​ቱም ናይን ወደ​ም​ት​ባል ወደ አን​ዲት ከተማ ሄደ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ብዙ ሕዝ​ብም አብ​ረ​ውት ሄዱ።</verse>
				<verse number="12">ወደ ከተ​ማው በር በደ​ረሰ ጊዜም እነሆ፥ ያን​ዲት መበ​ለት ሴት ልጅ ሙቶ ሬሳ​ውን ተሸ​ክ​መው ሲሄዱ አገኘ፤ ይኸ​ውም ለእ​ናቱ አንድ ነበረ፤ ብዙ​ዎ​ችም የከ​ተማ ሰዎች አብ​ረ​ዋት ነበሩ።</verse>
				<verse number="13">ጌታ​ች​ንም በአ​ያት ጊዜ አዘ​ነ​ላ​ትና፥ “አታ​ል​ቅሺ” አላት።</verse>
				<verse number="14">ቀር​ቦም ቃሬ​ዛ​ውን ያዘ፤ የተ​ሸ​ከ​ሙ​ትም ቆሙ፤ እር​ሱም፥ “አንተ ጐበዝ ተነሥ እል​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="15">የሞ​ተ​ውም ተነ​ሥቶ ተቀ​መጠ፤ መና​ገ​ርም ጀመረ፤ ለእ​ና​ቱም ሰጣት።</verse>
				<verse number="16">ሁሉም ፈሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገኑ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ታላቅ ነቢይ ተነ​ሣ​ልን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ጐብ​ኝ​ቶ​አ​ልና።”</verse>
				<verse number="17">ይህም የእ​ርሱ ዜና በይ​ሁዳ ሀገ​ሮች ሁሉና በአ​ው​ራ​ጃዋ ሁሉ ተሰማ።</verse>
				<verse number="18">ይህ​ንም ሁሉ ደቀ መዝ​ሙ​ርቱ ለዮ​ሐ​ንስ ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="19">ዮሐ​ን​ስም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሁለ​ቱን ጠርቶ፥ “የሚ​መ​ጣው አንተ ነህን? ወይስ ተስፋ የም​ና​ደ​ር​ገው ሌላ አለ?” ብሎ ወደ ጌታ​ችን ወደ ኢየ​ሱስ ላካ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ወደ እርሱ ደር​ሰው፥ “የሚ​መ​ጣው አንተ ነህን? ወይስ ተስፋ የም​ና​ደ​ር​ገው ሌላ አለ? ብሎ መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ ወደ አንተ ልኮ​ናል” አሉት።</verse>
				<verse number="21">ያን​ጊ​ዜም ብዙ​ዎ​ችን ከደ​ዌ​አ​ቸ​ውና ከሕ​መ​ማ​ቸው ከክ​ፉ​ዎች አጋ​ን​ን​ትም ፈወ​ሳ​ቸው፤ ለብ​ዙ​ዎች ዕው​ራ​ንም እን​ዲ​ያዩ ብር​ሃ​ንን ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሄዳ​ችሁ ያያ​ች​ሁ​ት​ንና የሰ​ማ​ች​ሁ​ትን ለዮ​ሐ​ንስ ንገ​ሩት፤ ዕው​ሮች ያያሉ፤ አን​ካ​ሶ​ችም ይሄ​ዳሉ፤ ለም​ጻ​ሞ​ችም ይነ​ጻሉ፤ ደን​ቆ​ሮ​ችም ይሰ​ማሉ፤ ሙታ​ንም ይነ​ሣሉ፤ ለድ​ሆ​ችም ወን​ጌል ይሰ​በ​ካል።</verse>
				<verse number="23">በእ​ኔም የማ​ይ​ሰ​ና​ከል ብፁዕ ነው።”</verse>
				<verse number="24">የዮ​ሐ​ንስ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም ከሄዱ በኋላ ለሕ​ዝቡ ስለ መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ እን​ዲህ ይላ​ቸው ጀመር፥ “ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣ​ችሁ? ከነ​ፋስ የተ​ነሣ የሚ​ወ​ዛ​ወዝ ሸን​በ​ቆን ነውን?</verse>
				<verse number="25">ወይስ ምን ልታዩ ወጥ​ታ​ች​ኋል? ቀጭን ልብስ የለ​በ​ሰ​ውን ሰው ነውን? እነሆ፥ በክ​ብር ልብስ ያጌ​ጡስ በነ​ገ​ሥ​ታት ቤት አሉ።</verse>
				<verse number="26">ወይስ ምን ልታዩ ወጥ​ታ​ች​ኋል? ነቢ​ይን ነውን? አዎን፥ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከነ​ቢ​ይም ይበ​ል​ጣል።</verse>
				<verse number="27">እነሆ፥ መን​ገ​ድ​ህን በፊ​ትህ የሚ​ጠ​ርግ መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ዬን በፊ​ትህ እል​ካ​ለሁ፥ ተብሎ ስለ እርሱ የተ​ጻ​ፈ​ለት ይህ ነው።</verse>
				<verse number="28">እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሴቶች ከወ​ለ​ዱ​አ​ቸው መካ​ከል ከመ​ጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ የሚ​በ​ልጥ ማንም አል​ተ​ነ​ሣም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ግን የሚ​ያ​ን​ሰው ይበ​ል​ጠ​ዋል።”</verse>
				<verse number="29">ሕዝ​ቡም ሁሉ ቀራ​ጮ​ችም በሰሙ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጻድቅ ነው አሉት፤ የዮ​ሐ​ን​ስን ጥም​ቀት ተጠ​ም​ቀው ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="30">ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንና የሕግ ጻፎች ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ተቃ​ወሙ፤ በእ​ርሱ አል​ተ​ጠ​መ​ቁ​ምና።</verse>
				<verse number="31">“እን​ግ​ዲህ የዚ​ችን ትው​ልድ ሰዎች በምን እመ​ስ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ? ማን​ንስ ይመ​ስ​ላሉ?</verse>
				<verse number="32">በገ​በያ ተቀ​ም​ጠው ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ጠር​ተው፥ “አቀ​ነ​ቀ​ን​ላ​ችሁ፥ አል​ዘ​ፈ​ና​ች​ሁ​ምም፤ ሙሾም አወ​ጣ​ን​ላ​ችሁ፥ አላ​ለ​ቀ​ሳ​ች​ሁ​ምም የሚ​ሉ​አ​ቸው ልጆ​ችን ይመ​ስ​ላሉ።</verse>
				<verse number="33">መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ እህል ሳይ​በላ ወይ​ንም ሳይ​ጠጣ መጥቶ ነበ​ርና ጋኔን አለ​በት አላ​ች​ሁት።</verse>
				<verse number="34">የሰው ልጅም እየ​በ​ላና እየ​ጠጣ መጣ፤ እና​ንተ ግን እነሆ፥ በላ​ተ​ኛና ወይን ጠጪ ሰው፥ የኃ​ጥ​ኣ​ንና የቀ​ራ​ጮች ወዳጅ አላ​ች​ሁት።</verse>
				<verse number="35">ጥበ​ብም ከል​ጆ​ችዋ ሁሉ ጸደ​ቀች።”</verse>
				<verse number="36">ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም አንዱ በእ​ርሱ ዘንድ ምሳ እን​ዲ​በላ ለመ​ነው፤ ወደ ፈሪ​ሳ​ዊ​ውም ቤት ገብቶ በማ​ዕድ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="37">እነሆ፥ ከዚ​ያች ከተማ ሰዎ​ችም አን​ዲት ኀጢ​አ​ተኛ ሴት በፈ​ሪ​ሳ​ዊው ቤት በማ​ዕድ እን​ደ​ተ​ቀ​መጠ ዐውቃ ሽቱ የሞ​ላ​በት የአ​ል​ባ​ስ​ጥ​ሮስ ቢል​ቃጥ ገዝታ መጣች።</verse>
				<verse number="38">በስ​ተ​ኋ​ላ​ውም በእ​ግ​ሮቹ አጠ​ገብ ቆማ አለ​ቀ​ሰች፤ እግ​ሮ​ቹ​ንም በእ​ን​ባዋ ታርስ ነበር፥ በራስ ጠጕ​ር​ዋም እግ​ሮ​ቹን ታብ​ሰ​ውና ትስ​መው፥ ሽቱም ትቀ​ባው ነበር።</verse>
				<verse number="39">የጠ​ራው ፈሪ​ሳ​ዊም ባየ ጊዜ በልቡ ዐሰበ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህስ ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህቺ የም​ት​ዳ​ስ​ሰው ሴት ማን እንደ ሆነች፥ እን​ዴ​ትስ እንደ ነበ​ረች ባላ​ወ​ቀም ነበ​ርን? ኀጢ​አ​ተኛ ናትና።”</verse>
				<verse number="40">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ስም​ዖን ሆይ፥ የም​ነ​ግ​ርህ ነገር አለኝ” አለው፤ እር​ሱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ተና​ገር” አለው።</verse>
				<verse number="41">እር​ሱም እን​ዲህ አለው፥ “ለአ​ንድ አበ​ዳሪ ሁለት ባለ ዕዳ​ዎች ነበ​ሩት፤ በአ​ንዱ አም​ስት መቶ ዲናር ነበ​ረ​በት፤ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም አምሳ።</verse>
				<verse number="42">የሚ​ከ​ፍ​ሉ​ትም ባጡ ጊዜ ለሁ​ለ​ቱም ተወ​ላ​ቸው፤ እን​ግ​ዲህ ከሁ​ለቱ አብ​ልጦ ሊወ​ደው የሚ​ገ​ባው ማን​ኛው ነው?”</verse>
				<verse number="43">ስም​ዖ​ንም መልሶ፥ “ብዙ​ውን የተ​ወ​ለት ነው እላ​ለሁ” አለው፤ እር​ሱም፥ “መል​ካም ፈረ​ድህ” አለው።</verse>
				<verse number="44">ወደ ሴቲ​ቱም ዘወር ብሎ ስም​ዖ​ንን እን​ዲህ አለው፥ “ይህ​ቺን ሴት ታያ​ታ​ለ​ህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ ለእ​ግ​ሮች ውኃ ስንኳ አል​ሰ​ጠ​ኸ​ኝም፤ እር​ስዋ ግን አል​ቅሳ በእ​ን​ባዋ እግ​ሬን አራ​ሰች፤ በጠ​ጕ​ር​ዋም አበ​ሰች።</verse>
				<verse number="45">አን​ተስ ሰላ​ምታ አል​ሰ​ጠ​ኸ​ኝም፤ እር​ስዋ ግን ከገ​ባሁ ጀምሮ እግ​ሬን ከመ​ሳም አላ​ቋ​ረ​ጠ​ችም።</verse>
				<verse number="46">አንተ ራሴን እንኳ ዘይት አል​ቀ​ባ​ኸ​ኝም፤ እር​ስዋ ግን እግ​ሬን ሽቱ ቀባ​ችኝ።</verse>
				<verse number="47">ስለ​ዚ​ህም እል​ሃ​ለሁ፤ ብዙ ኀጢ​ኣቷ ተሰ​ር​ዮ​ላ​ታል፤ በብዙ ወድ​ዳ​ለ​ችና፤ ጥቂት የሚ​ወ​ድድ ጥቂት ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል፤ ብዙ የሚ​ወ​ድ​ድም ብዙ ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።”</verse>
				<verse number="48">ሴቲ​ቱ​ንም፥ “ኀጢ​ኣ​ትሽ ተሰ​ረ​የ​ልሽ” አላት።</verse>
				<verse number="49">በማ​ዕዱ የተ​ቀ​መ​ጡ​ትም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ኀጢ​አ​ትን የሚ​ያ​ስ​ተ​ሰ​ርይ ይህ ማነው?” ይሉ ጀመር።</verse>
				<verse number="50">ሴቲ​ቱ​ንም አላት፥ “እም​ነ​ትሽ አድ​ኖ​ሻል፤ በሰ​ላም ሂጂ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በየ​ከ​ተ​ማ​ዉና በየ​መ​ን​ደሩ ተመ​ላ​ለሰ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መን​ግ​ሥት ሰበ​ከ​ላ​ቸው፤ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸ​ውም፤ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ።</verse>
				<verse number="2">ከክ​ፉ​ዎች አጋ​ን​ን​ትና ከደ​ዌ​ያ​ቸው ያዳ​ና​ቸው ሴቶ​ችም አብ​ረ​ውት ነበሩ። እነ​ር​ሱም፦ መግ​ደ​ላ​ዊት የም​ት​ባ​ለው ሰባት አጋ​ን​ንት የወ​ጡ​ላት ማር​ያም፥</verse>
				<verse number="3">የሄ​ሮ​ድስ አዛዥ የነ​በ​ረው የኩዛ ሚስት ዮሐና፥ ሶስ​ናም፥ በገ​ን​ዘ​ባ​ቸው ያገ​ለ​ግ​ሉት የነ​በሩ ብዙ​ዎች ሌሎ​ችም ነበሩ።</verse>
				<verse number="4">ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ ከየ​ከ​ተ​ማ​ዉም ሁሉ ወደ እርሱ የመ​ጡት ሲያ​ዳ​ም​ጡት እን​ዲህ ያለ ምሳሌ ነገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">“ዘሪ ዘሩን ሊዘራ ወጣ፤ ሲዘ​ራም አን​ዳ​ንዱ በመ​ን​ገድ ወደ​ቀና ተረ​ገጠ፤ የሰ​ማይ ወፎ​ችም በሉት።</verse>
				<verse number="6">ሌላ​ውም በጭ​ንጫ መሬት ላይ ወደቀ፤ በበ​ቀ​ለም ጊዜ ወዲ​ያው ደረቀ፤ ሥር አል​ነ​በ​ረ​ው​ምና።</verse>
				<verse number="7">ሌላ​ዉም በእ​ሾህ መካ​ከል ወደቀ፤ እሾ​ሁም አብሮ አደ​ገና አነ​ቀው።</verse>
				<verse number="8">በመ​ል​ካም መሬት ላይ የወ​ደቀ ዘርም ነበረ፤ በበ​ቀ​ለም ጊዜ መቶ እጥፍ አፈራ።” ይህ​ንም ብሎ፥ “የሚ​ሰማ ጆሮ ያለው ይስማ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም፥ “ይህቺ ምሳሌ ምን​ድን ናት?” ብለው ጠየ​ቁት።</verse>
				<verse number="10">እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ምሥ​ጢር ማወቅ ለእ​ና​ንተ ተሰ​ጥ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ ለእ​ነ​ዚያ ግን አይ​ተው እን​ዳ​ያዩ፥ ሰም​ተ​ውም እን​ዳ​ይ​ሰሙ፥ እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉም በም​ሳሌ ነው።</verse>
				<verse number="11">ምሳ​ሌ​ዉም ይህ ነው፤ ዘሩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ነው፤</verse>
				<verse number="12">በመ​ን​ገድ የወ​ደ​ቀው ቃሉን የሚ​ሰሙ ናቸው፤ አም​ነ​ውም እን​ዳ​ይ​ድኑ ሰይ​ጣን መጥቶ ቃሉን ከል​ባ​ቸው ይወ​ስ​ድ​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="13">በጭ​ን​ጫም ላይ የወ​ደ​ቀው ሰም​ተው ነገ​ሩን በደ​ስታ የሚ​ቀ​በ​ሉት ናቸው፤ ነገር ግን ለጊ​ዜው ያም​ናሉ እንጂ ሥር የላ​ቸ​ውም፤ መከ​ራም በአ​ገ​ኛ​ቸው ጊዜ ይክ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="14">በእ​ሾ​ህም መካ​ከል የወ​ደ​ቀው ቃሉን ሰም​ተው የባ​ለ​ጠ​ግ​ነት ዐሳብ፥ የኑ​ሮም መቈ​ር​ቈር የተ​ድ​ላና የደ​ስታ መጣ​ፈ​ጥም የሚ​አ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ቸ​ውና ፍሬ የማ​ያ​ፈሩ ናቸው።</verse>
				<verse number="15">በመ​ል​ካም ምድር የወ​ደ​ቀው ግን ቃሉን በበ​ጎና በን​ጹሕ ልብ የሚ​ሰ​ሙና የሚ​ጠ​ብ​ቁት፥ ታግ​ሠ​ውና ጨክ​ነ​ውም የሚ​ያ​ፈሩ ናቸው።</verse>
				<verse number="16">“መብ​ራ​ትን አብ​ርቶ፥ ዕቃም ከድኖ ከአ​ልጋ በታች የሚ​ያ​ኖ​ራት የለም፤ ነገር ግን የሚ​መ​ላ​ለ​ሱት ብር​ሃ​ንን ያዩ ዘንድ በመ​ቅ​ረዝ ላይ ያኖ​ራ​ታል።</verse>
				<verse number="17">የማ​ይ​ገ​ለጥ የተ​ሰ​ወረ የለ​ምና፤ የማ​ይ​ታ​ይም ወደ ግል​ጥም የማ​ይ​መጣ የተ​ከ​ደነ የለም፤</verse>
				<verse number="18">እን​ግ​ዲህ እን​ዴት እን​ደ​ም​ት​ሰሙ አስ​ተ​ውሉ፤ ላለው ይሰ​ጠ​ዋል፤ ከሌ​ለው ግን ያው ያለው የሚ​መ​ስ​ለው እንኳ ይወ​ሰ​ድ​በ​ታል።”</verse>
				<verse number="19">እና​ቱና ወን​ድ​ሞ​ቹም ወደ እርሱ መጡ፤ ነገር ግን ሕዝቡ ብዙ ነበ​ርና ሊያ​ገ​ኙት አል​ቻ​ሉም።</verse>
				<verse number="20">“እና​ት​ህና ወን​ድ​ሞ​ችህ ከውጭ ቆመ​ዋል፤ ሊያ​ዩ​ህም ይሻሉ” አሉት።</verse>
				<verse number="21">እር​ሱም መልሶ፥ “እና​ቴና ወን​ድ​ሞች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰም​ተው የሚ​ያ​ደ​ርጉ እነ​ዚህ ናቸው” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">ከዕ​ለ​ታት በአ​ን​ዲት ቀንም እን​ዲህ ሆነ፤ እርሱ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ወደ ታንኳ ወጣና፥ “ኑ ወደ ባሕሩ ማዶ እን​ሻ​ገር” አላ​ቸው እነ​ር​ሱም ሄዱ።</verse>
				<verse number="23">ሲሄ​ዱም አን​ቀ​ላፋ፤ በባ​ሕ​ሩም ላይ ዐውሎ ነፋስ መጣ፤ ውኃ​ዉም ታን​ኳ​ቸ​ውን ሞላው፤ እነ​ር​ሱም ተጨ​ነቁ።</verse>
				<verse number="24">ቀር​በ​ውም፥ “መም​ህር ሆይ፥ መም​ህር ሆይ፥ ልን​ጠፋ ነው” ብለው ቀሰ​ቀ​ሱት፤ ተነ​ሥ​ቶም ነፋ​ሱ​ንና የው​ኃ​ዉን ማዕ​በል ገሠ​ጻ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ዝም አሉ፤ ታላቅ ፀጥ​ታም ሆነ።</verse>
				<verse number="25">እር​ሱም “እም​ነ​ታ​ችሁ ወዴት አለ?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ፈር​ተው ተደ​ነቁ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ውኃም ነፋ​ስም የሚ​ታ​ዘ​ዙ​ለት ይህ ማነው?” አሉ።</verse>
				<verse number="26">ከዚህ በኋላ በገ​ሊላ ወደብ አቅ​ጣጫ ወዳ​ለ​ችው ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ኖን ሀገር በታ​ንኳ ሄዱ።</verse>
				<verse number="27">ወደ ምድ​ርም በወ​ረዱ ጊዜ ጋኔን ያደ​ረ​በት ሰው ከከ​ተማ ወጥቶ ተገ​ና​ኘው፤ ልብ​ሱ​ንም ከጣለ ብዙ ዘመን ሆኖት ነበር፤ በመ​ቃ​ብር ብቻ ይኖር ነበር እንጂ ወደ ቤት አይ​ገ​ባም ነበር፤</verse>
				<verse number="28">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ባየው ጊዜ ጮኸ፤ ሮጦም ሰገ​ደ​ለት፤ “የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ኢየ​ሱስ ሆይ፥ ካንተ ጋር ምን አለኝ?” እያ​ለም በታ​ላቅ ቃል ጮኸ፤ እን​ዳ​ያ​ሠ​ቃ​የ​ውም ማለ​ደው።</verse>
				<verse number="29">ክፉ​ውን ጋኔን ከዚያ ሰው ላይ እን​ዲ​ወጣ ያዝ​ዘው ነበ​ርና፤ ዘወ​ት​ርም አእ​ም​ሮ​ዉን ያሳ​ጣው ነበ​ርና፤ ብላ​ቴ​ኖ​ችም በእ​ግር ብረት አስ​ረው ይጠ​ብ​ቁት ነበር፤ እግር ብረ​ቱ​ንም ይሰ​ብር ነበር፤ ጋኔ​ኑም በም​ድረ በዳ ያዞ​ረው ነበር።</verse>
				<verse number="30">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ስምህ ማነው?” ብሎ ጠየ​ቀው፤ እር​ሱም፥ “ስሜ ሌጌ​ዎን ነው” አለው፤ ብዙ አጋ​ን​ንት ይዘ​ውት ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="31">ወደ ጥል​ቁም ይገቡ ዘንድ እን​ዳ​ይ​ሰ​ድ​ዳ​ቸው ማለ​ዱት።</verse>
				<verse number="32">በዚ​ያም ብዙ የእ​ሪያ መንጋ በተ​ራራ ላይ ተሰ​ማ​ርቶ ነበር፤ ወደ እሪ​ያ​ዎ​ችም እን​ዲ​ገ​ቡ​ባ​ቸው ይፈ​ቅ​ድ​ላ​ቸው ዘንድ ማለ​ዱት፤ እር​ሱም ፈቀ​ደ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="33">እነ​ዚያ አጋ​ን​ን​ትም ከዚያ ሰው ላይ ወጥ​ተው ወደ እሪ​ያ​ዎች ገቡ፤ የእ​ሪ​ያ​ዎ​ችም መንጋ አብ​ደው ከገ​ደሉ ወደ ባሕር ጠል​ቀው ሞቱ።</verse>
				<verse number="34">እረ​ኞ​ችም የሆ​ነ​ውን ባዩ ጊዜ ሸሽ​ተው ሄዱና ገብ​ተው በከ​ተ​ማ​ዉና በመ​ን​ደሩ አወሩ።</verse>
				<verse number="35">ሰዎ​ችም የሆ​ነ​ውን ያዩ ዘንድ ወጡ፤ ሄደ​ውም ወደ ጌታ​ችን ወደ ኢየ​ሱስ በደ​ረሱ ጊዜ አጋ​ን​ንት የወ​ጡ​ለ​ትን ያን ሰው አእ​ም​ሮዉ ተመ​ል​ሶ​ለት ልብ​ሱን ለብሶ፥ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እግር አጠ​ገብ ተቀ​ምጦ አገ​ኙ​ትና ፈሩ።</verse>
				<verse number="36">ያዩ​ትም ሰዎች ጋኔን አድ​ሮ​በት የነ​በ​ረው ሰው እን​ዴት እንደ ዳነ ነገ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="37">በጌ​ር​ጌ​ሴ​ኖ​ንም ዙሪያ ያሉ ሰዎች ከእ​ነ​ርሱ ዘንድ እን​ዲ​ሄ​ድ​ላ​ቸው ማለ​ዱት፤ ጽኑ ፍር​ሀት ይዞ​አ​ቸ​ዋ​ልና፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በታ​ንኳ ሆኖ ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="38">ያም አጋ​ን​ንት የወ​ጡ​ለት ሰው ከእ​ርሱ ጋር ይሄድ ዘንድ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ማለ​ደው፤</verse>
				<verse number="39">እርሱ ግን፥ “ወደ ቤትህ ተመ​ል​ሰህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ረ​ገ​ል​ህን ታላቅ ነገር ሁሉ ተና​ገር” ብሎ አሰ​ና​በ​ተው። እር​ሱም ሄዶ በከ​ተ​ማዉ ሁሉ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያደ​ረ​ገ​ለ​ትን ሁሉ ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="40">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በተ​መ​ለሰ ጊዜ ሕዝቡ በአ​ን​ድ​ነት ተቀ​በ​ሉት፤ ሁሉ ይጠ​ባ​በ​ቁት ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="41">እነ​ሆም ኢያ​ኢ​ሮስ የሚ​ባል ሰው መጣ፤ እር​ሱም የም​ኵ​ራብ ሹም ነበር፤ ከጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ እግር በታ​ችም ሰገደ። ወደ ቤቱም ይገባ ዘንድ ለመ​ነው።</verse>
				<verse number="42">ዕድ​ሜዋ ዐሥራ ሁለት ዓመት የሚ​ሆ​ናት አን​ዲት ልጅ ነበ​ረ​ችው፤ እር​ስ​ዋም ልት​ሞት ቀርባ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="43">ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከእ​ርሱ ጋር ሲሄድ ሰዎች ያጨ​ና​ን​ቁት ነበር፤ ከዐ​ሥራ ሁለት ዓመ​ትም ጀምሮ ደም ይፈ​ስ​ሳት የነ​በ​ረች ሴት መጣች፤ ገን​ዘ​ብ​ዋ​ንም ሁሉ ለባ​ለ​መ​ድ​ኀ​ኒ​ቶች ሰጥታ ጨርሳ ነበር፤ ነገር ግን ሊያ​ድ​ናት የቻለ ማንም አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="44">ቀር​ባም በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ በስ​ተ​ኋ​ላው ቆመ​ችና የል​ብ​ሱን ጫፍ ዳሰ​ሰች፤ ያን​ጊ​ዜም የደ​ምዋ መፍ​ሰስ ቆመ።</verse>
				<verse number="45">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ማን ዳሰ​ሰኝ?” አለ፤ ሁሉም ካዱ፤ ጴጥ​ሮ​ስና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ሰው ይጋ​ፋ​ህና ያጨ​ና​ን​ቅህ የለ​ምን? አንተ ግን ማን ዳሰ​ሰኝ? ትላ​ለህ” አሉት።</verse>
				<verse number="46">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የዳ​ሰ​ሰኝ አለ፤ ከእኔ ኀይል እንደ ወጣ ዐው​ቃ​ለ​ሁና” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="47">ሴቲ​ቱም እን​ዳ​ል​ተ​ሰ​ወ​ረ​ላት ባየች ጊዜ እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠች ሄዳ ሰገ​ደ​ች​ለት፤ በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት በምን ምክ​ን​ያት ወደ እርሱ እንደ ቀረ​በ​ችና የል​ብ​ሱን ጫፍ እንደ ዳሰ​ሰች ወዲ​ያ​ውም እንደ ዳነች ተና​ገ​ረች።</verse>
				<verse number="48">እር​ሱም፥ “ልጄ ሆይ፥ እም​ነ​ትሽ አዳ​ነ​ችሽ፤ በሰ​ላም ሂጂ” አላት።</verse>
				<verse number="49">ይህ​ንም ሲና​ገር አንድ ሰው ከም​ኵ​ራቡ ሹም ቤት መጥቶ፥ “ልጅ​ህስ ሞታ​ለች እን​ግ​ዲህ መም​ህ​ሩን አታ​ድ​ክ​መው” አለው።</verse>
				<verse number="50">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በሰማ ጊዜ የም​ኵ​ራ​ቡን ሹም፥ “አት​ፍራ፥ ብቻ እመን፤ ልጅ​ህስ ትድ​ና​ለች” አለው።</verse>
				<verse number="51">ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ከጴ​ጥ​ሮስ፥ ከያ​ዕ​ቆ​ብና ከዮ​ሐ​ንስ፥ ከብ​ላ​ቴ​ና​ይ​ቱም አባ​ትና እናት በቀር ማንም ከእ​ርሱ ጋር ሌላ ሰው ይገባ ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደም።</verse>
				<verse number="52">ሁሉም እያ​ለ​ቀሱ ዋይ ዋይ ይሉ​ላት ነበር፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ግን፥ “አታ​ል​ቅሱ፤ ብላ​ቴ​ና​ይቱ ተኝ​ታ​ለች እንጂ አል​ሞ​ተ​ችም” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="53">እንደ ሞተ​ችም ዐው​ቀ​ዋ​ልና ሳቁ​በት።</verse>
				<verse number="54">እርሱ ግን ሁሉን ወደ ውጭ አስ​ወ​ጣና እጅ​ዋን ይዞ ጠራት፤ እን​ዲ​ህም አላት፥ “ አንቺ ብላ​ቴና ተነሺ።”</verse>
				<verse number="55">ወዲ​ያ​ውም ነፍ​ስዋ ተመ​ል​ሶ​ላት ፈጥና ቆመች፥ የም​ት​በ​ላ​ው​ንም ይሰ​ጡ​አት ዘንድ አዘዘ።</verse>
				<verse number="56">አባ​ቷና እና​ቷም አደ​ነቁ፤ እርሱ ግን የሆ​ነ​ውን ለማ​ንም እን​ዳ​ይ​ነ​ግሩ ከለ​ከ​ላ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">ዐሥራ ሁለ​ቱ​ንም ሐዋ​ር​ያት ጠራና፦ በአ​ጋ​ን​ንት ሁሉ ላይ፥ ድው​ያ​ን​ንም ይፈ​ውሱ ዘንድ ኀይ​ል​ንና ሥል​ጣ​ንን ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት እን​ዲ​ሰ​ብኩ፥ ድው​ያ​ን​ንና ሕሙ​ማ​ን​ንም ሁሉ እን​ዲ​ፈ​ውሱ ላካ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “በት​ርም ቢሆን፥ ከረ​ጢ​ትም ቢሆን፥ እን​ጀ​ራም ቢሆን፥ ወር​ቅም ቢሆን፥ ሁለት ልብ​ስም ቢሆን ለመ​ን​ገድ ምንም አት​ያዙ።</verse>
				<verse number="4">በም​ት​ገ​ቡ​በት ቤት በዚያ ተቀ​መጡ፤ እስ​ክ​ት​ሄ​ዱም ድረስ ከዚያ አት​ውጡ።</verse>
				<verse number="5">የማ​ይ​ቀ​በ​ሉ​አ​ችሁ ቢሆን ግን ከዚ​ያች ከተማ ወጥ​ታ​ችሁ ምስ​ክር ሊሆ​ን​ባ​ቸው የእ​ግ​ራ​ች​ሁን ትቢያ አራ​ግፉ።”</verse>
				<verse number="6">ወጥ​ተ​ውም በየ​አ​ው​ራ​ጃዉ መን​ደ​ሮች ዞሩ፤ በስ​ፍ​ራ​ውም ሁሉ ወን​ጌ​ልን ሰበኩ፤ ድው​ያ​ን​ንም ፈወሱ።</verse>
				<verse number="7">የአ​ራ​ተ​ኛው ክፍል ገዥ ሄሮ​ድ​ስም የተ​ደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ሰምቶ የሚ​ና​ገ​ረ​ውን ያጣ ነበር፤ መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ ተነሣ የሚሉ ነበ​ሩና።</verse>
				<verse number="8">ኤል​ያስ ተገ​ለጠ የሚ​ሉም ነበሩ፤ ከቀ​ደ​ሙት ነቢ​ያት አንዱ ተነ​ሥ​ቶ​አል የሚ​ሉም ነበ​ሩና።</verse>
				<verse number="9">ሄሮ​ድ​ስም፥ “እኔ የዮ​ሐ​ን​ስን ራስ አስ​ቈ​ረ​ጥሁ፤ እን​ግ​ዲህ ስለ እርሱ ሲወራ የም​ሰ​ማው ይህ ማነው?” አለ፤ ሊያ​የ​ውም ይሻ ነበር።</verse>
				<verse number="10">ሐዋ​ር​ያ​ትም በተ​መ​ለሱ ጊዜ ያደ​ረ​ጉ​ትን ሁሉ ነገ​ሩት፤ እር​ሱም ለብ​ቻ​ቸው ይዞ​አ​ቸው ቤተ ሳይዳ ከም​ት​ባል ከተማ አጠ​ገብ ወደ አለ ምድረ በዳ ወጡ።</verse>
				<verse number="11">ሕዝ​ቡም ዐው​ቀው ተከ​ተ​ሉት፤ እር​ሱም ተቀ​በ​ላ​ቸው፤ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥ​ትም አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፤ ሊፈ​ወሱ የሚ​ሹ​ት​ንም አዳ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="12">ቀኑም በመሸ ጊዜ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ርት መጥ​ተው፥ “ያለ​ን​በት ምድረ በዳ ነውና በዙ​ሪ​ያ​ችን ወዳሉ መን​ደ​ሮ​ችና ገጠ​ሮች ሄደው እን​ዲ​ያ​ድሩ የሚ​በ​ሉ​ት​ንም እን​ዲ​ያ​ገኙ ሕዝ​ቡን አሰ​ና​ብት” አሉት።</verse>
				<verse number="13">እርሱ ግን፥ “እና​ንተ የሚ​በ​ሉ​ትን ስጡ​አ​ቸው” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚ​በቃ ምግብ ልን​ገዛ ካል​ሄ​ድን ከአ​ም​ስት እን​ጀ​ራና ከሁ​ለት ዓሣ በቀር ሌላ በዚህ የለ​ንም” አሉት።</verse>
				<verse number="14">ሰዎ​ቹም አም​ስት ሺህ ያህሉ ነበር፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱ​ንም፥ “አምሳ አም​ሳ​ውን በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸው አስ​ቀ​ም​ጡ​አ​ቸው” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">እን​ዲ​ሁም አደ​ረጉ፤ ሁሉም ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="16">አም​ስ​ቱን እን​ጀ​ራና ሁለ​ቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ ተመ​ለ​ከተ፤ ባረከ፤ ቈር​ሶም ለሕ​ዝቡ እን​ዲ​ያ​ቀ​ርቡ ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">ሁሉም በል​ተው ጠገቡ፤ ያነ​ሡ​ትም የተ​ረ​ፈው ቍር​ስ​ራሽ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሞላ።</verse>
				<verse number="18">ከዚ​ህም በኋላ ብቻ​ውን ሲጸ​ልይ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ከእ​ርሱ ጋር ሳሉ፥ “ሰዎች ማን ይሉ​ኛል?” ብሎ ጠየ​ቃ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ ነው የሚ​ሉህ አሉ፤ ኤል​ያስ ነው የሚ​ሉ​ህም አሉ፤ ከቀ​ደ​ሙት ነቢ​ያት አንዱ ተነ​ሥ​ቶ​አል የሚ​ሉ​ህም አሉ” አሉት።</verse>
				<verse number="20">እር​ሱም፥ “እና​ን​ተስ ማን ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው፤ ጴጥ​ሮ​ስም መልሶ፥ “አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሲሕ ነህ” አለው።</verse>
				<verse number="21">ይህ​ንም ለማ​ንም እን​ዳ​ይ​ና​ገሩ ገሠ​ጻ​ቸ​ውና ከለ​ከ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">“ለሰው ልጅ ብዙ መከራ ያጸ​ኑ​በት ዘንድ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና የካ​ህ​ናት አለ​ቆች፥ ጻፎ​ችም ይፈ​ት​ኑት ዘንድ፥ ይገ​ድ​ሉ​ትም ዘንድ፥ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ይነሣ ዘንድ አለው” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">ሁሉ​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሊከ​ተ​ለኝ የሚ​ወድ ሰው ራሱን ይካድ፤ ጨክ​ኖም የሞ​ቱን መስ​ቀል ይሸ​ከም፤ ዕለት ዕለ​ትም ይከ​ተ​ለኝ።</verse>
				<verse number="24">ሰው​ነ​ቱን ሊያ​ድን የሚ​ወድ ሁሉ ይጥ​ላ​ታል፤ ስለ እኔ ሰው​ነ​ቱን የጣለ ግን ያድ​ና​ታል።</verse>
				<verse number="25">ሰው ዓለ​ሙን ሁሉ ቢገዛ ነፍ​ሱ​ንም ካጣ ምን ይረ​ባ​ዋል?</verse>
				<verse number="26">በእ​ኔና በቃሌ የሚ​ያ​ፍር ሁሉ የሰው ልጅ በክ​ብሩ፥ በአ​ባ​ቱም ክብር፥ ቅዱ​ሳ​ን​መ​ላ​እ​ክ​ትን አስ​ከ​ትሎ ሲመጣ ያፍ​ር​በ​ታል።</verse>
				<verse number="27">እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚህ ከቆ​ሙት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት እስ​ኪ​ያ​ዩ​አት ድረስ ሞትን የማ​ይ​ቀ​ምሱ አሉ።”</verse>
				<verse number="28">ከዚ​ህም ነገር በኋላ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ጴጥ​ሮ​ስን፥ ያዕ​ቆ​ብ​ንና ዮሐ​ን​ስን ይዞ​አ​ቸው ሊጸ​ልይ ወደ ተራራ ወጣ።</verse>
				<verse number="29">ሲጸ​ል​ይም የፊቱ መልክ ተለ​ወጠ፤ ልብ​ሱም ነጭ ሆነ፤ እንደ መብ​ረ​ቅም አብ​ለ​ጨ​ለጨ።</verse>
				<verse number="30">እነ​ሆም፥ ሁለት ሰዎች መጥ​ተው ከእ​ርሱ ጋር ይነ​ጋ​ገሩ ነበር። እነ​ር​ሱም ሙሴና ኤል​ያስ ነበሩ።</verse>
				<verse number="31">በክ​ብ​ርም ተገ​ል​ጠው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይደ​ረግ ዘንድ ያለ​ውን ክብ​ሩ​ንና መው​ጣ​ቱን ተና​ገሩ፤</verse>
				<verse number="32">ጴጥ​ሮ​ስ​ንና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ት​ንም ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው በእ​ን​ቅ​ልፍ ፈዝ​ዘው አገኘ፤ በነ​ቁም ጊዜ ክብ​ሩ​ንና ከእ​ርሱ ጋር ቆመው የነ​በ​ሩ​ትን ሁለት ሰዎች አዩ።</verse>
				<verse number="33">ከዚ​ህም በኋላ ከእ​ርሱ ሲለዩ ጴጥ​ሮስ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን፥ “መም​ህር፥ ሆይ፥ እዚህ ብን​ኖር ለእኛ መል​ካም ነው፤ ሦስት ሰቀ​ላ​ዎ​ች​ንም እን​ሥራ፤ አን​ዱን ለአ​ንተ፥ አን​ዱ​ንም ለሙሴ፥ አን​ዱ​ንም ለኤ​ል​ያስ” አለው፤ የሚ​ና​ገ​ረ​ው​ንም አያ​ው​ቅም ነበር።</verse>
				<verse number="34">ይህ​ንም ሲና​ገር ደመና መጣና ጋረ​ዳ​ቸው፤ ወደ ደመ​ና​ውም በገቡ ጊዜ ፈሩ።</verse>
				<verse number="35">ከደ​መ​ና​ውም ውስጥ፥ “የመ​ረ​ጥ​ሁት ልጄ ይህ ነው፤ እር​ሱን ስሙት” የሚል ቃል መጣ።</verse>
				<verse number="36">ቃሉም ከመጣ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ብቻ​ውን ተገኘ፤ እነ​ርሱ ግን ዝም አሉ፤ ያዩ​ት​ንና የሰ​ሙ​ት​ንም በዚያ ጊዜ ለማ​ንም አል​ተ​ና​ገ​ሩም።</verse>
				<verse number="37">በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከተ​ራ​ራው ወረዱ፤ ብዙ ሕዝ​ብም ተቀ​በ​ሉት።</verse>
				<verse number="38">አንድ ሰውም በሕ​ዝቡ መካ​ከል ጮኾ እን​ዲህ አለው፥ “መም​ህር ሆይ፥ እርሱ ለእኔ አንድ ነውና ልጄን ታይ​ልኝ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="39">እነሆ፥ ጋኔን ሊነ​ጥ​ቀኝ ነው፤ ድን​ገ​ትም ያስ​ጮ​ኸ​ዋል፤ ጥሎም ያፈ​ራ​ግ​ጠ​ዋል፤ አረ​ፋም ያስ​ደ​ፍ​ቀ​ዋል፤ ቀጥ​ቅጦ በጭ​ንቅ ይተ​ወ​ዋል።</verse>
				<verse number="40">እን​ዲ​ያ​ወ​ጡ​ትም ደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ህን ለመ​ን​ሁ​አ​ቸው፤ ነገር ግን ማው​ጣት ተሳ​ና​ቸው።”</verse>
				<verse number="41">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “የማ​ታ​ምን ከዳ​ተኛ ትው​ልድ፥ እስከ መቼ ከእ​ና​ንተ ጋር እኖ​ራ​ለሁ? እስከ መቼስ እታ​ገ​ሣ​ች​ኋ​ለሁ? ልጅ​ህን ወደ​ዚህ አም​ጣው” አለው።</verse>
				<verse number="42">ሲያ​መ​ጣ​ውም ጋኔኑ ጣለ​ውና አፈ​ራ​ገ​ጠው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያን ክፉ ጋኔን ገሠ​ጸው፤ ልጁ​ንም አዳ​ነው፤ ለአ​ባ​ቱም ሰጠው። ሁሉም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላ​ቅ​ነት የተ​ነሣ አደ​ነቁ።</verse>
				<verse number="43">እነ​ር​ሱም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ባደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት ሁሉ ሲደ​ነቁ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን እን​ዲህ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="44">“እና​ን​ተስ ይህን ነገር በል​ባ​ችሁ አኑ​ሩት፤ የሰው ልጅ በሰ​ዎች እጅ ተላ​ልፎ ይሰጥ ዘንድ አለ​ውና።”</verse>
				<verse number="45">እነ​ርሱ ግን ይህን ነገር አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉ​ትም፤ እን​ዳ​ይ​መ​ረ​ም​ሩት ከእ​ነ​ርሱ የተ​ሰ​ወረ ነውና፤ ስለ​ዚህ ነገ​ርም እን​ዳ​ይ​ጠ​ይ​ቁት ይፈ​ሩት ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="46">እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ ማን እን​ደ​ሚ​በ​ልጥ ዐሰቡ።</verse>
				<verse number="47">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በል​ቡ​ና​ቸው የሚ​ያ​ስ​ቡ​ትን ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና አንድ ሕፃን ወስዶ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አቆ​መው።</verse>
				<verse number="48">እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “በስሜ እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ሕፃን የሚ​ቀ​በል እኔን ይቀ​በ​ላል፥ እኔ​ንም የሚ​ቀ​በል የላ​ከ​ኝን ይቀ​በ​ላል፤ ራሱን ከሁሉ ዝቅ የሚ​ያ​ደ​ርግ እርሱ ታላቅ ይሆ​ናል።”</verse>
				<verse number="49">ዮሐ​ን​ስም መልሶ፥ “መም​ህር ሆይ፥ በስ​ምህ ጋኔን ሲያ​ወጣ ያየ​ነው አንድ ሰው አለ፤ ከእ​ኛም ጋር አል​ተ​ከ​ተ​ለ​ህ​ምና ከለ​ከ​ል​ነው፤” አለው።</verse>
				<verse number="50">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አት​ከ​ል​ክ​ሉት፤ ባለ​ጋ​ራ​ችሁ ካል​ሆነ ባል​ን​ጀ​ራ​ችሁ ነውና” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="51">የመ​ው​ጣቱ ወራ​ትም በቀ​ረበ ጊዜ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ሄድ ፊቱን አቀና።</verse>
				<verse number="52">በፊ​ቱም መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ ሄደ​ውም ያዘ​ጋ​ጁ​ለት ዘንድ ወደ ሰማ​ርያ ከተማ ገቡ።</verse>
				<verse number="53">ነገር ግን አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​ትም፤ ፊቱን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አቅ​ንቶ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="54">ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ያዕ​ቆ​ብና ዮሐ​ን​ስም ይህን ባዩ ጊዜ፥ “አቤቱ፥ ኤል​ያስ እንደ አደ​ረገ እሳት ከሰ​ማይ ወርዶ ያጥ​ፋ​ቸው እን​ድ​ንል ትፈ​ቅ​ዳ​ለ​ህን?” አሉት።</verse>
				<verse number="55">እርሱ ግን ዘወር ብሎ፥ “ከምን መን​ፈስ እንደ ሆና​ችሁ አታ​ው​ቁም” ብሎ ገሠ​ጻ​ቸው።</verse>
				<verse number="56">የሰው ልጅ የሰ​ውን ነፍስ ሊያ​ድን እንጂ ሊያ​ጠፋ አል​መ​ጣም። ወደ ሌላም መን​ደር ሄዱ።</verse>
				<verse number="57">ከዚህ በኋላ በመ​ን​ገድ ሲሄዱ አንድ ሰው፥ “መም​ህር፥ ወደ​ም​ት​ሄ​ድ​በት ልከ​ተ​ል​ህን?” አለው።</verse>
				<verse number="58">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም “ለቀ​በ​ሮ​ዎች ጕድ​ጓድ አላ​ቸው፤ ለሰ​ማይ ወፎ​ችም ጎጆ አላ​ቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን የሚ​ያ​ስ​ጠ​ጋ​በት የለ​ውም” አለው።</verse>
				<verse number="59">ሌላ​ው​ንም፥ “ተከ​ተ​ለኝ” አለው፤ እርሱ ግን፥ “አቤቱ፥ በፊት ሄጄ አባ​ቴን እን​ድ​ቀ​ብ​ረው ፍቀ​ድ​ልኝ” አለው።</verse>
				<verse number="60">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ሙታ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ይቀ​ብሩ ዘንድ ሙታ​ንን ተዉ​አ​ቸው፤ አንተ ግን ሂድና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ስበክ” አለው።</verse>
				<verse number="61">ሦስ​ተ​ኛ​ውም፥ “አቤቱ፥ ልከ​ተ​ል​ህን? ነገር ግን ሄጄ ቤተ ሰቦ​ችን ሁሉ እን​ድ​ሰ​ና​በት ፍቀ​ድ​ልኝ” አለው።</verse>
				<verse number="62">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ማንም ዕርፍ ይዞ እያ​ረሰ ወደ ኋላው የሚ​መ​ለ​ከት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት የተ​ገባ አይ​ሆ​ንም” አለው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ሌሎች ሰባ ሰዎ​ችን መረጠ፤ ሁለት ሁለት አድ​ር​ጎም ሊሄ​ድ​በት ወደ አለው ከተ​ማና መን​ደር በፊቱ ላካ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም አላ​ቸው፥ “መከሩ ብዙ ነው፤ ሠራ​ተ​ኛው ግን ጥቂት ነው፤ እን​ግ​ዲህ ለመ​ከሩ ሠራ​ተኛ ጨምሮ ይልክ ዘንድ ባለ መከ​ሩን ለም​ኑት።</verse>
				<verse number="3">ሂዱ፤ እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተ​ኵ​ላ​ዎች መካ​ከል እል​ካ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">ከረ​ጢ​ትም፥ ስል​ቻም፥ ጫማም፥ ምንም ምን አት​ያዙ፤ በመ​ን​ገ​ድም ማን​ንም ሰላም አት​በሉ።</verse>
				<verse number="5">ወደ ገባ​ች​ሁ​በት ቤትም አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ ‘ለዚህ ቤት ሰዎች ሰላም ይሁን’ በሉ።</verse>
				<verse number="6">በዚ​ያም የሰ​ላም ልጅ ቢኖር ሰላ​ማ​ችሁ ያድ​ር​በ​ታል፤ ያለ​ዚያ ግን ሰላ​ማ​ችሁ ይመ​ለ​ስ​ላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="7">በዚ​ያም ቤት ተቀ​መጡ፤ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ገ​ኘ​ው​ንም ብሉ፥ ጠጡም፤ ለሠ​ራ​ተኛ ዋጋው ይገ​ባ​ዋ​ልና፤ ከቤ​ትም ወደ ቤት አት​ሂዱ።</verse>
				<verse number="8">ወደ ማና​ቸ​ውም ከተማ ብት​ገቡ፥ የዚያ ከተማ ሰዎ​ችም ቢቀ​በ​ሉ​አ​ችሁ ያቀ​ረ​ቡ​ላ​ች​ሁን ብሉ።</verse>
				<verse number="9">በው​ስ​ጥዋ የሚ​ገ​ኙ​ትን ድው​ያ​ን​ንም ፈውሱ፤ ‘የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥት ወደ እና​ንተ ቀር​ባ​ለች’ በሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">ነገር ግን ወደ ማና​ቸ​ውም ከተማ ብት​ገቡ፥ የዚ​ያች ከተማ ሰዎ​ችም ባይ​ቀ​በ​ሉ​አ​ችሁ ወደ አደ​ባ​ባ​ይዋ ወጥ​ታ​ችሁ የእ​ግ​ራ​ች​ሁን ትቢያ አራ​ግፉ። እን​ዲ​ህም በሉ፦</verse>
				<verse number="11">ከከ​ተ​ማ​ችሁ የተ​ጣ​በ​ቀ​ብ​ንን ትቢያ እን​ኳን እና​ራ​ግ​ፍ​ላ​ች​ኋ​ለን፤ ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ወደ እና​ንተ እንደ ቀረ​በች ይህን ዕወቁ።</verse>
				<verse number="12">በፍ​ርድ ቀን ሰዶም ከዚ​ያች ከተማ ይልቅ እን​ደ​ም​ት​ሻል ይቅ​ር​ታ​ንም እን​ደ​ም​ታ​ገኝ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">“ኮራዚ ወዮ​ልሽ! ቤተ ሳይዳ ወዮ​ልሽ! በእ​ና​ንተ የተ​ደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት በጢ​ሮ​ስና በሲ​ዶና ተደ​ርጎ ቢሆን ቀድሞ ማቅ ለብ​ሰው አመ​ድም ነስ​ን​ሰው በተ​ቀ​መጡ ንስ​ሓም በገቡ ነበር።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን ጢሮ​ስና ሲዶና ከእ​ና​ንተ ይልቅ በፍ​ርድ ቀን ይቅ​ር​ታን ያገ​ኛሉ።</verse>
				<verse number="15">አን​ቺም ቅፍ​ር​ና​ሆም እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ከፍ ብትዪ እስከ ሲኦል ትወ​ር​ጃ​ለሽ።</verse>
				<verse number="16">“እና​ን​ተን የሚ​ሰማ እኔን ይሰ​ማል፤ እና​ን​ተ​ንም እንቢ የሚል እኔን እንቢ ይላል፤ እኔ​ንም እንቢ የሚል የላ​ከ​ኝን እንቢ ይላል፤ እኔ​ንም የሚ​ሰማ የላ​ከ​ኝን ይሰ​ማል።”</verse>
				<verse number="17">እነ​ዚ​ያም ሰባው ደስ ብሎ​አ​ቸው ተመ​ለ​ሱና፥ “አቤቱ፥ አጋ​ን​ንት ስንኳ በስ​ምህ ተገ​ዙ​ልን” አሉት።</verse>
				<verse number="18">እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሰይ​ጣ​ንን ከሰ​ማይ እንደ መብ​ረቅ ሲወ​ድቅ አየ​ሁት።</verse>
				<verse number="19">እነሆ፥ ጊን​ጦ​ች​ንና እባ​ቦ​ችን፥ የጠ​ላ​ት​ንም ኀይል ሁሉ ትረ​ግጡ ዘንድ ሥል​ጣ​ንን ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ የሚ​ጐ​ዳ​ች​ሁም ነገር የለም።</verse>
				<verse number="20">ነገር ግን አጋ​ን​ንት ስለ ተገ​ዙ​ላ​ችሁ በዚህ ደስ አይ​በ​ላ​ችሁ፤ ግን ስማ​ችሁ በሰ​ማ​ያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="21">በዚ​ያች ሰዓ​ትም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ደስ አለው፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “የሰ​ማ​ይና የም​ድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከዐ​ዋ​ቂ​ዎ​ችና ከአ​ስ​ተ​ዋ​ዮች ሰው​ረህ ለሕ​ፃ​ናት ስለ​ገ​ለ​ጥ​ኸው አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፤ አዎን፥ አባት ሆይ፥ ፈቃ​ድህ በፊ​ትህ እን​ዲሁ ሆኖ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="22">ሁሉ ከአ​ባቴ ዘንድ ተሰ​ጠኝ፤ ወልድ ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚ​ያ​ውቅ የለም፤ አብም ማን እንደ ሆነ ከወ​ልድ በቀር የሚ​ያ​ውቅ የለም። ወልድ ግን ለወ​ደ​ደው ይገ​ል​ጥ​ለ​ታል።”</verse>
				<verse number="23">ተመ​ል​ሶም ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን ለብ​ቻ​ቸው አድ​ርጎ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የም​ታ​ዩ​ትን የሚ​ያዩ ዐይ​ኖች ብፁ​ዓን ናቸው።</verse>
				<verse number="24">ብዙ ነቢ​ያ​ትና ነገ​ሥ​ታት እና​ንተ የም​ታ​ዩ​ትን ሊያዩ ተመኙ፤ አላ​ዩ​ምም፤ እና​ንተ የም​ት​ሰ​ሙ​ት​ንም ሊሰሙ ተመኙ፥ አል​ሰ​ሙም።”</verse>
				<verse number="25">ከዚህ በኋላ አንድ ሕግ ዐዋቂ ሊፈ​ት​ነው ተነ​ሣና፥ “መም​ህር ሆይ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እወ​ርስ ዘንድ ምን ላድ​ርግ?” አለው።</verse>
				<verse number="26">እር​ሱም፥ “በኦ​ሪት ምን ተጽ​ፎ​አል? እን​ዴ​ትስ ታነ​ብ​ባ​ለህ?” አለው።</verse>
				<verse number="27">እር​ሱም መልሶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክ​ህን በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹም ሰው​ነ​ትህ፥ በፍ​ጹም ኀይ​ልህ፥ በፍ​ጹም ዐሳ​ብህ ውደ​ደው፤ ባል​ን​ጀ​ራ​ህ​ንም እንደ ራስህ ውደድ ይላል” አለው።</verse>
				<verse number="28">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “መል​ካም መል​ሰ​ሃል፤ እን​ዲሁ አድ​ርግ፤ ትድ​ና​ለ​ህም” አለው።</verse>
				<verse number="29">ራሱን ሊያ​ከ​ብር ባል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም ሊንቅ ወድዶ፥ “ባል​ን​ጀ​ራዬ ማነው?” አለው።</verse>
				<verse number="30">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “አንድ ሰው ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ኢያ​ሪኮ ይወ​ርድ ነበር፤ ሽፍ​ቶ​ችም አገ​ኙት፤ ደበ​ደ​ቡት፥ አቈ​ሰ​ሉት፥ ልብ​ሱ​ንም ገፍ​ፈው፤ በሕ​ይ​ወ​ትና በሞት መካ​ከል ጥለ​ውት ሄዱ።</verse>
				<verse number="31">አንድ ካህ​ንም በዚ​ያች መን​ገድ ሲወ​ርድ ድን​ገት አገ​ኘው፤ አይ​ቶም አል​ፎት ሄደ።</verse>
				<verse number="32">እን​ዲ​ሁም አንድ ሌዋዊ በዚያ ቦታ አገ​ኘ​ውና፥ አይቶ እንደ ፊተ​ኛው አል​ፎት ሄደ።</verse>
				<verse number="33">አንድ ሳም​ራዊ ግን በዚ​ያች መን​ገድ ሲሄድ አገ​ኘው፤ አይ​ቶም አዘ​ነ​ለት።</verse>
				<verse number="34">ወደ እር​ሱም ቀረበ፤ ቍስ​ሉ​ንም አጋ​ጥሞ አሰ​ረ​ለት፤ በቍ​ስሉ ላይም ወይ​ንና ዘይት ጨመ​ረ​ለት፤ በአ​ህ​ያ​ውም ላይ አስ​ቀ​ምጦ እን​ዲ​ፈ​ው​ሰው የእ​ን​ግ​ዶ​ችን ቤት ወደ​ሚ​ጠ​ብ​ቀው ወሰ​ደው፤ የሚ​ድ​ን​በ​ት​ንም ዐሰበ።</verse>
				<verse number="35">በማ​ግ​ሥ​ቱም ሁለት ዲናር አው​ጥቶ ለእ​ን​ግዳ ቤት ጠባ​ቂው ሰጠ​ውና፦ ‘በዚህ አስ​ታ​ም​ልኝ፤ ከዚህ የሚ​በ​ልጥ ለእ​ርሱ የም​ታ​ወ​ጣው ቢኖር እኔ በተ​መ​ለ​ስሁ ጊዜ እከ​ፍ​ል​ሃ​ለሁ’ አለው።</verse>
				<verse number="36">እን​ግ​ዲህ ሽፍ​ቶች ለደ​በ​ደ​ቡት ሰው ከእ​ነ​ዚህ ከሦ​ስቱ ባል​ን​ጀራ የሚ​ሆ​ነው ማን​ኛው ይመ​ስ​ል​ሃል?”</verse>
				<verse number="37">እር​ሱም“ምሕ​ረት ያደ​ረ​ገ​ለት ነዋ” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እን​ኪ​ያስ አን​ተም ሂድና እን​ዲሁ አድ​ርግ” አለው።</verse>
				<verse number="38">ከዚ​ህም በኋላ ሄደው ወደ አን​ዲት መን​ደር ገቡ፤ ማርታ የም​ት​ባል አን​ዲት ሴትም በቤቷ ተቀ​በ​ለ​ችው።</verse>
				<verse number="39">ማር​ያም የም​ት​ባል እኅ​ትም ነበ​ረ​ቻት፤ እር​ስ​ዋም ከጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ እግር አጠ​ገብ ተቀ​ምጣ ትም​ህ​ር​ቱን ትሰማ ነበር።</verse>
				<verse number="40">ማርታ ግን ብዙ በማ​ዘ​ጋ​ጀት ትደ​ክም ነበር፤ ቆማም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኅቴ ትታኝ ብቻ​ዬን ስሠራ አያ​ሳ​ዝ​ን​ህ​ምን? ርጃት በላት” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="41">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላት፥ “ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትደ​ክ​ሚ​ያ​ለሽ፥ ትቸ​ገ​ሪ​ያ​ለ​ሽም፤ ታዘ​ጋ​ጂ​ያ​ለ​ሽም።</verse>
				<verse number="42">ጥቂት ይበ​ቃል፤ ያም ባይ​ሆን አንድ ይበ​ቃል፤ ማር​ያ​ምስ የማ​ይ​ቀ​ሙ​አ​ትን መል​ካም ዕድል መረ​ጠች።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ በአ​ን​ዲት ቦታ ጸለየ፤ ጸሎ​ቱን በጨ​ረሰ ጊዜም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ አንዱ፥ “ጌታ ሆይ፥ ዮሐ​ንስ ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ እንደ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው ጸሎት አስ​ተ​ም​ረን” አለው።</verse>
				<verse number="2">እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በም​ት​ጸ​ል​ዩ​በት ጊዜ እን​ዲህ በሉ፦ በሰ​ማ​ያት የም​ት​ኖር አባ​ታ​ችን ሆይ፥ ስምህ ይቀ​ደስ፤ መን​ግ​ሥ​ትህ ትምጣ፤ ፈቃ​ድህ በሰ​ማይ እንደ ሆነ እን​ዲ​ሁም በም​ድር ይሁን።</verse>
				<verse number="3">የዕ​ለት ምግ​ባ​ች​ንን በየ​ዕ​ለቱ ስጠን።</verse>
				<verse number="4">እኛም የበ​ደ​ለ​ንን ሁሉ ይቅር እን​ድ​ንል በደ​ላ​ች​ንን ይቅር በለን፤ አቤቱ፥ ወደ ፈተና አታ​ግ​ባን፤ ከክፉ ሁሉ አድ​ነን እንጂ።”</verse>
				<verse number="5">እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ወዳጅ ያለው ሰው ቢኖር በመ​ን​ፈቀ ሌሊ​ትም ወደ እርሱ ሄዶ እን​ዲህ ቢለው፦ ‘ወዳጄ ሆይ ሦስት እን​ጀራ አበ​ድ​ረኝ።</verse>
				<verse number="6">ወዳጄ ከመ​ን​ገድ መጥ​ቶ​ብ​ኛ​ልና የማ​ቀ​ር​ብ​ለት የለ​ኝም።’</verse>
				<verse number="7">ያ ወዳ​ጁም ከው​ስጥ ሆኖ፦ ‘አት​ዘ​ብ​ዝ​በኝ፤ ደጁን አጥ​ብ​ቀን ዘግ​ተ​ናል፤ ልጆ​ችም ከእኔ ጋር በአ​ልጋ ላይ ተኝ​ተ​ዋል፤ እሰ​ጥህ ዘንድ መነ​ሣት አል​ች​ልም’ ይለ​ዋ​ልን?</verse>
				<verse number="8">ወዳጁ ስለ​ሆነ ሊሰ​ጠው ባይ​ነሣ እንኳ እን​ዳ​ይ​ዘ​በ​ዝ​በው ተነ​ሥቶ የወ​ደ​ደ​ውን ያህል ይሰ​ጠ​ዋል።</verse>
				<verse number="9">እኔም እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ለምኑ፥ ይሰ​ጣ​ች​ኋ​ልም፤ ፈልጉ፥ ታገ​ኛ​ላ​ች​ሁም፤ ደጅ ምቱ፥ ይከ​ፈ​ት​ላ​ች​ኋ​ልም።</verse>
				<verse number="10">የሚ​ለ​ምን ሁሉ ይሰ​ጠ​ዋ​ልና፤ የሚ​ፈ​ል​ግም ያገ​ኛ​ልና፤ ደጅ ለሚ​መ​ታም ይከ​ፈ​ት​ለ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="11">ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ልጁ ዳቦ የሚ​ለ​ም​ነው አባት ቢኖር ድን​ጋይ ይሰ​ጠ​ዋ​ልን? ዓሣ ቢለ​ም​ነ​ውስ በዓሣ ፋንታ እባ​ብን ይሰ​ጠ​ዋ​ልን?</verse>
				<verse number="12">ወይስ ዕን​ቍ​ላል ቢለ​ም​ነው በዕ​ን​ቍ​ላል ፋንታ ጊንጥ ይሰ​ጠ​ዋ​ልን?</verse>
				<verse number="13">እና​ንተ ክፉ​ዎች ስት​ሆኑ ለል​ጆ​ቻ​ችሁ መል​ካም ስጦ​ታን መስ​ጠ​ትን የም​ታ​ውቁ ከሆነ፥ የሰ​ማይ አባ​ታ​ች​ሁማ ለሚ​ለ​ም​ኑት መል​ካ​ሙን ሀብተ መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዴት አብ​ዝቶ ይሰ​ጣ​ቸው ይሆን?”</verse>
				<verse number="14">ዲዳና ደን​ቆሮ ጋኔ​ን​ንም ያወጣ ነበር፤ ጋኔ​ኑም በወጣ ጊዜ ዲዳና ደን​ቆሮ የነ​በ​ረው ተና​ገረ፤ ሰዎ​ችም አደ​ነቁ።</verse>
				<verse number="15">ነገር ግን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው፥ “በአ​ጋ​ን​ንት አለቃ በብ​ዔል ዜቡል አጋ​ን​ን​ትን ያወ​ጣ​ቸ​ዋል” ያሉ ነበሩ፤ እር​ሱም መልሶ፥ “ሰይ​ጣን ሰይ​ጣ​ንን ማው​ጣት እን​ደ​ምን ይቻ​ለ​ዋል?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">ሌሎ​ችም ሊፈ​ት​ኑት ከእ​ርሱ ዘንድ ከሰ​ማይ ምል​ክ​ትን ይፈ​ልጉ ነበር።</verse>
				<verse number="17">እርሱ ግን የሚ​ያ​ስ​ቡ​ትን ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እርስ በር​ስዋ የም​ት​ለ​ያይ መን​ግ​ሥት ሁሉ ትጠ​ፋ​ለች፤ ቤትም እርስ በርሱ ቢለ​ያይ ያ ቤት ይወ​ድ​ቃል።</verse>
				<verse number="18">ሰይ​ጣ​ንስ እርስ በርሱ ከተ​ለ​ያየ መን​ግ​ሥቱ እን​ዴት ይጸ​ናል? በአ​ጋ​ን​ንት አለቃ በብ​ዔል ዜቡል አጋ​ን​ን​ትን ያወ​ጣል ትላ​ላ​ች​ሁና።</verse>
				<verse number="19">እኔ በብ​ዔል ዜቡል አጋ​ን​ን​ትን የማ​ወጣ ከሆነ፥ ልጆ​ቻ​ችሁ በምን ያወ​ጡ​አ​ቸ​ዋል? ስለ​ዚህ እነ​ርሱ ይፋ​ረ​ዱ​አ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="20">እኔ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት አጋ​ን​ን​ትን የማ​ወጣ ከሆነ እን​ግ​ዲህ አሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ወደ እና​ንተ ደር​ሳ​ለች።</verse>
				<verse number="21">ኀይ​ለኛ ሰው በጦር መሣ​ሪያ ቤቱን የጠ​በቀ እንደ ሆነ ገን​ዘቡ ሁሉ ደኅና ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="22">ከእ​ርሱ የሚ​በ​ረ​ታው ቢመ​ጣና ቢያ​ሸ​ን​ፈው ግን፥ ይታ​መ​ን​በት የነ​በ​ረ​ውን የጦር መሣ​ሪ​ያ​ውን ይገ​ፈ​ዋል፤ የማ​ረ​ከ​ው​ንና የዘ​ረ​ፈ​ውን ገን​ዘ​ቡ​ንም ይወ​ስ​ዳል።</verse>
				<verse number="23">ከእኔ ጋር ያል​ሆነ ባለ​ጋ​ራዬ ነው፤ ከእኔ ጋር የማ​ይ​ሰ​በ​ስ​ብም ይበ​ት​ን​ብ​ኛል።</verse>
				<verse number="24">“ክፉ ጋኔ​ንም ከሰው በወጣ ጊዜ ውኃ ወደ​ሌ​ለ​በት ምድረ በዳ ይሄ​ዳል፤ የሚ​ያ​ር​ፍ​በ​ት​ንም መኖ​ሪያ ይሻል፤ ያላ​ገኘ እንደ ሆነም ወደ ወጣ​ሁ​በት ቤቴ እመ​ለ​ሳ​ለሁ ይላል።</verse>
				<verse number="25">በመ​ጣም ጊዜ ተጠ​ርጎ አጊ​ጦም ያገ​ኘ​ዋል።</verse>
				<verse number="26">ከዚ​ህም በኋላ ይሄ​ድና ከእ​ርሱ የሚ​ከፉ ሌሎች ባል​ን​ጀ​ሮ​ቹን ሰባት አጋ​ን​ንት ያመ​ጣል፤ ገብ​ተ​ውም በዚያ ሰው ያድ​ሩ​በ​ታል፤ ለዚያ ሰውም ከፊ​ተ​ኛው ይልቅ የኋ​ለ​ኛው የከፋ ይሆ​ን​በ​ታል።”</verse>
				<verse number="27">ከዚ​ህም በኋላ ይህን ሲና​ገር ከሕ​ዝቡ መካ​ከል አን​ዲት ሴት ድም​ፅ​ዋን አሰ​ምታ፥ “የተ​ሸ​ከ​መ​ችህ ማኅ​ፀን ብፅ​ዕት ናት፤ የጠ​ባ​ሃ​ቸው ጡቶ​ችም ብፁ​ዓት ናቸው” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="28">እር​ሱም፥ “ብፁ​ዓ​ንስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰም​ተው የሚ​ጠ​ብቁ ናቸው” አላት።</verse>
				<verse number="29">ብዙ ሰዎ​ችም ተሰ​ብ​ስ​በው ሳሉ እን​ዲህ ይላ​ቸው ጀመረ ፥ “ይቺ ትው​ልድ ክፉ ናት፤ ምል​ክ​ትም ትሻ​ለች፤ ነገር ግን ከነ​ቢዩ ከዮ​ናስ ምል​ክት በቀር ምል​ክት አይ​ሰ​ጣ​ትም።</verse>
				<verse number="30">ዮናስ ለነ​ነዌ ሰዎች ምል​ክት እንደ ሆና​ቸው የሰው ልጅም ለዚች ትው​ልድ እን​ዲሁ ምል​ክት ይሆ​ና​ታል።</verse>
				<verse number="31">የአ​ዜብ ንግ​ሥት በፍ​ርድ ቀን ከዚች ትው​ልድ ጋር ተነ​ሥታ ትፋ​ረ​ዳ​ቸ​ዋ​ለች፤ የሰ​ሎ​ሞ​ንን ጥበብ ልት​ሰማ ከም​ድር ዳርቻ መጥ​ታ​ለ​ችና፤ እነሆ፥ ከሰ​ሎ​ሞን የሚ​በ​ልጥ በዚህ አለ።</verse>
				<verse number="32">የነ​ነዌ ሰዎች በፍ​ርድ ቀን ከዚች ትው​ልድ ጋር ተነ​ሥ​ተው ይፋ​ረ​ዱ​አ​ታል፤ ያሳ​ፍ​ሩ​አ​ታ​ልም፤ ዮናስ በሰ​በ​ከ​ላ​ቸው ጊዜ ንስሓ ገብ​ተ​ዋ​ልና፤ እነሆ፥ ከዮ​ናስ የሚ​በ​ልጥ በዚህ አለ።</verse>
				<verse number="33">“በስ​ውር ቦታ ወይም ከዕ​ን​ቅብ በታች ሊያ​ኖ​ራት መብ​ራ​ትን የሚ​ያ​በራ የለም፤ የሚ​መ​ላ​ለሱ ሁሉ ብር​ሃ​ንን ያዩ ዘንድ በመ​ቅ​ረ​ዝዋ ላይ ያኖ​ራ​ታል እንጂ።</verse>
				<verse number="34">የሰ​ው​ነ​ትህ መብ​ራት ዐይ​ንህ ነው፤ ዐይ​ንህ ብሩህ ከሆነ ሰው​ነ​ትህ ሁሉ ብሩህ ነው፤ ዐይ​ንህ ታማሚ ቢሆን ግን፤ ሰው​ነ​ትህ ሁሉ ጨለማ ነው።</verse>
				<verse number="35">እን​ግ​ዲህ ብር​ሃ​ንህ ጨለማ እን​ዳ​ይ​ሆን ተጠ​ን​ቀቅ።</verse>
				<verse number="36">ሰው​ነ​ትህ ሁሉ ብሩህ ከሆነ በአ​ን​ተም ላይ ምንም ጨለማ ባይ​ኖ​ር​ብህ የመ​ብ​ረቅ ብር​ሃን እን​ደ​ሚ​ያ​በ​ራ​ልህ ሁለ​ን​ተ​ናህ ብሩህ ይሆ​ናል።”</verse>
				<verse number="37">ይህ​ንም ሲነ​ግ​ራ​ቸው አንድ ፈሪ​ሳዊ በእ​ርሱ ዘንድ ምሳ እን​ዲ​በላ ለመ​ነው፤ ገብ​ቶም ለምሳ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="38">ፈሪ​ሳ​ዊ​ዉም አይቶ አደ​ነቀ፤ ምሳ ለመ​ብ​ላት እጁን አል​ታ​ጠ​በም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="39">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “እና​ንተ ፈሪ​ሳ​ው​ያን፥ ዛሬ የጽ​ዋ​ው​ንና የወ​ጭ​ቱን ውጭ​ውን ታጥ​ቡ​ታ​ላ​ችሁ፤ ታጠ​ሩ​ታ​ላ​ች​ሁም፤ ውስጡ ግን ቅሚ​ያ​ንና ክፋ​ትን የተ​መላ ነው።</verse>
				<verse number="40">እና​ንተ ሰነ​ፎች፥ የው​ጭ​ውን የፈ​ጠረ የው​ስ​ጡ​ንስ የፈ​ጠረ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="41">ነገር ግን የሚ​ወ​ደ​ደ​ውን ምጽ​ዋት አድ​ር​ጋ​ችሁ ስጡ፤ ሁሉም ንጹሕ ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="42">የእ​ን​ስ​ላ​ልና የጤና አዳም፥ ከአ​ት​ክ​ል​ትም ሁሉ ዐስ​ራት የም​ታ​ገቡ ፍር​ድ​ንና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍቅር ቸል የም​ትሉ እና​ንተ ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን፥ ወዮ​ላ​ችሁ! ይህ​ንም ልታ​ደ​ርጉ ይገ​ባ​ች​ኋል፥ ያንም አት​ተዉ።</verse>
				<verse number="43">እና​ንተ ግብ​ዞች ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን፥ ወዮ​ላ​ችሁ! በም​ኵ​ራብ ፊት ለፊት መቀ​መ​ጥን፥ በገ​በ​ያም እጅ መነ​ሣ​ትን ትወ​ዳ​ላ​ች​ሁና።</verse>
				<verse number="44">እና​ንተ ግብ​ዞች ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን፥ ወዮ​ላ​ችሁ! ሰዎች ሳያ​ውቁ በላዩ እን​ደ​ሚ​መ​ላ​ለ​ሱ​በት እንደ ተሰ​ወረ መቃ​ብር ናች​ሁና።”</verse>
				<verse number="45">ከሕግ ዐዋ​ቂ​ዎ​ችም አንዱ መልሶ፥ “መም​ህር ሆይ፥ ይህን ስትል እኛን እኮ መስ​ደ​ብህ ነው” አለው።</verse>
				<verse number="46">እር​ሱም እን​ዲህ አለው፤ “ለእ​ና​ንተ ለሕግ ዐዋ​ቂ​ዎች ወዮ​ላ​ችሁ! ሰውን ከባድ ሸክም ታሸ​ክ​ሙ​ታ​ላ​ችሁ፤ እና​ንተ ግን ያን ሸክም በአ​ን​ዲት ጣታ​ችሁ እን​ኳን አት​ነ​ኩ​ትም።</verse>
				<verse number="47">እና​ንተ ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን፥ ወዮ​ላ​ችሁ! አባ​ቶ​ቻ​ችሁ የገ​ደ​ሉ​አ​ቸ​ውን የነ​ቢ​ያ​ትን መቃ​ብር ትሠ​ራ​ላ​ች​ሁና።</verse>
				<verse number="48">የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሥራ ደስ አሰ​ኝ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ የም​ት​መ​ሰ​ክ​ሩ​ባ​ቸ​ውም እና​ንተ ራሳ​ችሁ ናችሁ፤ እነ​ርሱ የገ​ደ​ሉ​አ​ቸ​ውን መቃ​ብ​ራ​ቸ​ውን እና​ንተ ትሠ​ራ​ላ​ች​ሁና።</verse>
				<verse number="49">ስለ​ዚህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበቡ እን​ዲህ አለች፦ እነሆ፥ እኔ ነቢ​ያ​ት​ንና ሐዋ​ር​ያ​ትን ወደ እነ​ርሱ እል​ካ​ለሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ይገ​ድ​ላሉ፤ ያሳ​ድ​ዳ​ሉም።</verse>
				<verse number="50">ዓለም ከተ​ፈ​ጠረ ጀምሮ እስ​ከ​ዚ​ህች ትው​ልድ ድረስ ስለ ፈሰ​ሰው ስለ ነቢ​ያት ሁሉ ደም ይበ​ቀ​ላ​ቸው ዘንድ፥</verse>
				<verse number="51">ከአ​ቤል ደም ጀምሮ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውና በቤተ መቅ​ደሱ መካ​ከል እስከ ገደ​ሉት እስከ ዘካ​ር​ያስ ደም ድረስ እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ ከዚች ትው​ልድ ይፈ​ለ​ጋል።</verse>
				<verse number="52">እና​ንተ ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን፥ ወዮ​ላ​ችሁ! የጽ​ድ​ቅ​ንና የዕ​ው​ቀ​ትን መክ​ፈቻ ወስ​ዳ​ችሁ ትሰ​ው​ራ​ላ​ች​ሁና፤ እና​ን​ተም አት​ገ​ቡ​ምና፤ የሚ​ገ​ቡ​ት​ንም መግ​ባ​ትን ትከ​ለ​ክ​ሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="53">በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት ይህን ሲነ​ግ​ራ​ቸው ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን አጽ​ን​ተው ይጣ​ሉት፥ ይቀ​የ​ሙ​ትም ጀመር።</verse>
				<verse number="54">በአ​ነ​ጋ​ገ​ሩም ሊያ​ስ​ቱ​ትና ሊያ​ጣ​ሉት ያደ​ቡ​በት ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">በዚ​ያን ጊዜም እጅግ ብዙ ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው እስ​ኪ​ረ​ጋ​ገጡ ድረስ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱ​ንም እን​ዲህ ይላ​ቸው ጀመረ፥ “አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን እርሾ ተጠ​በቁ፤ ይኸ​ውም ግብ​ዝ​ነት ነው።</verse>
				<verse number="2">የማ​ይ​ገ​ለጥ የተ​ሰ​ወረ፥ የማ​ይ​ታ​ይም የተ​ሸ​ሸገ የለ​ምና።</verse>
				<verse number="3">በጨ​ለማ የም​ት​ና​ገ​ሩት በብ​ር​ሃን ይሰ​ማል፤ በእ​ል​ፍ​ኝም ውስጥ በጆሮ የም​ት​ን​ሾ​ካ​ሾ​ኩት በሰ​ገ​ነት ይሰ​በ​ካል።</verse>
				<verse number="4">ለእ​ና​ንተ ለወ​ዳ​ጆች እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ሥጋ​ች​ሁን የሚ​ገ​ድ​ሉ​ትን አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው፤ ከዚ​ህም የበ​ለጠ ማድ​ረግ የሚ​ች​ሉት የላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="5">ነገር ግን፤ የም​ት​ፈ​ሩ​ትን አሳ​ያ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተስ ከገ​ደለ በኋላ ወደ ገሃ​ነም ሊጥል ሥል​ጣን ያለ​ውን ፍሩት፤ አዎ፥ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እር​ሱን ፍሩ።</verse>
				<verse number="6">አም​ስት ወፎች በሁ​ለት ሻሚ መሐ​ለቅ ይሸጡ የለ​ምን? ከእ​ነ​ርሱ አን​ዲቱ ስን​ኳን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አት​ረ​ሳም።</verse>
				<verse number="7">የእ​ና​ን​ተስ የራስ ጠጕ​ራ​ችሁ ሁሉ የተ​ቈ​ጠረ ነው፤ እን​ግ​ዲህ አት​ፍሩ፤ ከብዙ ወፎች እና​ንተ ትበ​ል​ጣ​ላ​ች​ሁና።</verse>
				<verse number="8">“እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ በሰው ፊት የሚ​ያ​ም​ን​ብ​ኝን ሁሉ እኔም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ፊት አም​ነ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">በሰው ፊት የሚ​ክ​ደ​ኝን ግን እኔም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ፊት እክ​ደ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">በሰው ልጅ ላይ የስ​ድብ ቃል የሚ​ና​ገር ሁሉ ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ላይ የስ​ድብ ቃል የሚ​ና​ገር ግን በዚህ ዓለ​ምም ሆነ በሚ​መ​ጣው ዓለም አይ​ሰ​ረ​ይ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="11">ወደ አደ​ባ​ባይ ወደ ሹሞ​ቹና ወደ ነገ​ሥ​ታቱ፥ ወደ መኳ​ን​ን​ቱም በሚ​ወ​ስ​ዱ​አ​ችሁ ጊዜ የም​ት​ሉ​ት​ንና የም​ት​ና​ገ​ሩ​ትን አታ​ስቡ።</verse>
				<verse number="12">ያን​ጊዜ በእ​ና​ንተ ላይ የሚ​ና​ገ​ረው መን​ፈስ ቅዱስ ነውና።”</verse>
				<verse number="13">ከሕ​ዝ​ቡም አንዱ፥ “መም​ህር ሆይ፥ ርስ​ቴን እን​ዲ​ያ​ካ​ፍ​ለኝ ለወ​ን​ድሜ ንገ​ረው” አለው።</verse>
				<verse number="14">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አንተ ሰው፥ በእ​ና​ንተ ላይ አካ​ፋ​ይና ዳኛ አድ​ርጎ ማን ሾመኝ?” አለው።</verse>
				<verse number="15">“ዕወቁ፤ ከቅ​ሚ​ያም ሁሉ ተጠ​በቁ፤ ሰው የሚ​ድን ገን​ዘብ በማ​ብ​ዛት አይ​ደ​ለ​ምና” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">ምሳ​ሌም መሰ​ለ​ላ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፤ “እር​ሻው የበ​ጀ​ለ​ትና ሀገር የተ​መ​ቸው አንድ ባለ​ጸጋ ሰው ነበረ።</verse>
				<verse number="17">እህ​ሌን የማ​ኖ​ር​በት የለ​ኝ​ምና ምን ላድ​ርግ ብሎ በልቡ ዐሰበ።</verse>
				<verse number="18">እር​ሱም አለ፦ እን​ዲህ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የቀ​ድ​ሞ​ውን ጎተ​ራ​ዬን አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ ከእ​ርሱ የሚ​በ​ልጥ ሌላ ጎተ​ራም እሠ​ራ​ለሁ፤ እህ​ሌ​ንና በረ​ከ​ቴ​ንም በዚያ እሰ​በ​ስ​ባ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">ሰው​ነ​ቴ​ንም እን​ዲህ እላ​ታ​ለሁ፦ ሰው​ነቴ ሆይ፥ የሰ​በ​ሰ​ብ​ሁ​ልሽ ለብዙ ዓመ​ታት የሚ​በ​ቃሽ የደ​ለበ ብዙ ሀብት አለሽ፤ እን​ግ​ዲህ ወዲህ ዕረፊ፥ ብዪ፤ ጠጪም፤ ደስም ይበ​ልሽ።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አንተ ሰነፍ! በዚች ሌሊት ነፍ​ስ​ህን ከሥ​ጋህ ለይ​ተው ይወ​ስ​ዷ​ታል፤ እን​ግ​ዲህ ያጠ​ራ​ቀ​ም​ኸው ለማን ይሆ​ናል? አለው።</verse>
				<verse number="21">ሀብ​ትን ለራሱ የሚ​ሰ​በ​ስብ፤ ሀብ​ቱም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያል​ሆነ እን​ዲሁ ነው።”</verse>
				<verse number="22">ለደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ስለ​ዚህ እላ​ች​ህ​ዋ​ለሁ፤ ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ስለ​ም​ት​በ​ሉ​ትና ስለ​ም​ት​ጠ​ጡት፥ ለሰ​ው​ነ​ታ​ች​ሁም ስለ​ም​ት​ለ​ብ​ሱት አት​ጨ​ነቁ።</verse>
				<verse number="23">ነፍስ ከም​ግብ ትበ​ል​ጣ​ለ​ችና፤ ሰው​ነ​ትም ከል​ብስ ይበ​ል​ጣ​ልና።</verse>
				<verse number="24">የማ​ይ​ዘ​ሩ​ት​ንና የማ​ያ​ጭ​ዱ​ትን፥ ጎተ​ራና ጕድ​ጓድ የሌ​ላ​ቸ​ውን የቍ​ራ​ዎ​ችን ጫጭ​ቶች ተመ​ል​ከቱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ይመ​ግ​ባ​ቸ​ዋል፤ እን​ግ​ዲህ እና​ንተ ከወ​ፎች እን​ዴት እጅግ አት​በ​ል​ጡም?</verse>
				<verse number="25">ከእ​ና​ን​ተስ ዐስቦ በቁ​መቱ ላይ አንድ ክንድ መጨ​መር የሚ​ቻ​ለው ማነው?</verse>
				<verse number="26">ይህን ቀላ​ሉን የማ​ት​ችሉ ከሆነ በሌ​ላው ለምን ትጨ​ነ​ቃ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="27">እነሆ፥ አበ​ባ​ዎ​ችን እን​ደ​ሚ​ያ​ድጉ ተመ​ል​ከቱ፤ አይ​ፈ​ት​ሉም፤ አይ​ደ​ክ​ሙም፤ ነገር ግን እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሰሎ​ሞን እንኳ በክ​ብሩ ዘመን ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ እንደ አንዱ አል​ለ​በ​ሰም።</verse>
				<verse number="28">እነሆ፥ ዛሬ ያለ​ውን፥ ነገም ወደ እሳት የሚ​ጣ​ለ​ውን የአ​በባ አገዳ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ የሚ​ያ​ደ​ር​ገው ከሆነ፥ እና​ንተ እም​ነት የጐ​ደ​ላ​ችሁ፥ ለእ​ና​ን​ተማ እን​ዴት አብ​ልጦ አያ​ደ​ር​ግ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="29">እና​ን​ተም የም​ት​በ​ሉ​ት​ንና የም​ት​ጠ​ጡ​ትን አት​ፈ​ልጉ፤ ወዲ​ያና ወዲ​ህም አት​በሉ፤ አት​ጨ​ነ​ቁ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="30">ይህን ሁሉ በውጭ ያሉ የዓ​ለም አሕ​ዛብ ይሹ​ታ​ልና፤ ለእ​ና​ን​ተስ አባ​ታ​ችሁ ይህን ሁሉ እን​ደ​ም​ት​ሹት ያው​ቃል።</verse>
				<verse number="31">ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥ​ትና ጽድቅ ሹ፤ ይህም ሁሉ ይጨ​መ​ር​ላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="32">“አንተ ታናሽ መንጋ፥ አት​ፍራ፤ አባ​ታ​ችሁ መን​ግ​ሥ​ቱን ሊሰ​ጣ​ችሁ ወዶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="33">ሀብ​ታ​ች​ሁን ሸጣ​ችሁ ምጽ​ዋት ስጡ፤ ሌባ በማ​ያ​ገ​ኝ​በት ነቀ​ዝም በማ​ያ​በ​ላ​ሽ​በት፥ የማ​ያ​ረጅ ከረ​ጢት፥ የማ​ያ​ል​ቅም መዝ​ገብ በሰ​ማ​ያት ለእ​ና​ንተ አድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="34">መዝ​ገ​ባ​ችሁ ካለ​በት ልባ​ችሁ በዚያ ይኖ​ራ​ልና።</verse>
				<verse number="35">“ወገ​ባ​ችሁ የታ​ጠቀ መብ​ራ​ታ​ች​ሁም የበራ ይሁን።</verse>
				<verse number="36">እና​ን​ተም፥ በመ​ጣና በር በመታ ጊዜ ወዲ​ያው ይከ​ፍ​ቱ​ለት ዘንድ ከሰ​ርግ እስ​ኪ​መ​ለስ ጌታ​ቸ​ውን እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቁ ሰዎች ሁኑ።</verse>
				<verse number="37">ጌታ​ቸው በመጣ ጊዜ እን​ዲህ ሲያ​ደ​ር​ጉና ሲተጉ የሚ​ያ​ገ​ኛ​ቸው አገ​ል​ጋ​ዮች ብፁ​ዓን ናቸው፤ እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወገ​ቡን ታጥቆ በማ​ዕድ ያስ​ቀ​ም​ጣ​ቸ​ዋል፤ እየ​ተ​መ​ላ​ለ​ሰም ያገ​ለ​ግ​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="38">ከሌ​ሊቱ በሁ​ለ​ተ​ኛው ወይም በሦ​ስ​ተ​ኛው ክፍል ቢመ​ጣና እን​ዲሁ ቢያ​ገ​ኛ​ቸው እነ​ዚያ አገ​ል​ጋ​ዮች ብፁ​ዓን ናቸው።</verse>
				<verse number="39">ነገር ግን ይህን ዕወቁ፤ ባለ​ቤት ሌባ የሚ​መ​ጣ​በ​ትን ጊዜ ቢያ​ውቅ ተግቶ በጠ​በቀ፥ ቤቱ​ንም እን​ዲ​ቈ​ፍ​ሩት ባል​ፈ​ቀ​ደም ነበር።</verse>
				<verse number="40">እና​ን​ተም ተዘ​ጋ​ጅ​ታ​ችሁ ኑሩ፤ የሰው ልጅ ባል​ጠ​ረ​ጠ​ራ​ች​ሁ​በት ሰዓት ይመ​ጣ​ልና።”</verse>
				<verse number="41">ጴጥ​ሮ​ስም፥ “አቤቱ፥ ይህን ምሳሌ የም​ት​ና​ገ​ረው ለእኛ ነውን? ወይስ ለሁሉ ነው?” አለው።</verse>
				<verse number="42">ጌታ​ች​ንም እን​ዲህ አለው፥ “ምግ​ባ​ቸ​ውን በየ​ጊ​ዜው ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ጌታው በቤ​ተ​ሰቡ ላይ የሚ​ሾ​መው ደግ ታማ​ኝና ብልህ መጋቢ ማን ይሆን?</verse>
				<verse number="43">ጌታው በመጣ ጊዜ እን​ዲህ ሲያ​ደ​ርግ የሚ​ያ​ገ​ኘው አገ​ል​ጋይ ብፁዕ ነው።</verse>
				<verse number="44">እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ በሀ​ብቱ ሁሉ ላይ ይሾ​መ​ዋል፤</verse>
				<verse number="45">ነገር ግን ያ ክፉ አገ​ል​ጋይ በልቡ፦ ጌታዬ ቶሎ አይ​መ​ጣም ቢል፥ በጌ​ታው ቤት ያሉ​ት​ንም ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ችን አገ​ል​ጋ​ዮች ሊደ​በ​ድ​ብና ሊያ​ጕ​ላላ ቢጀ​ምር፥ ከሰ​ካ​ራ​ሞ​ችም ጋር ቢበ​ላና ቢጠጣ፥ ቢሰ​ክ​ርም፥</verse>
				<verse number="46">የዚያ አገ​ል​ጋይ ጌታ ባል​ጠ​ረ​ጠ​ረው ዕለት፥ ባላ​ወ​ቀ​ውም ሰዓት መጥቶ ከሁ​ለት ይሰ​ነ​ጥ​ቀ​ዋል፤ ዕድ​ሉ​ንም ከማ​ይ​ታ​መኑ ጋር ያደ​ር​ገ​ዋል።</verse>
				<verse number="47">የጌ​ታ​ውን ፈቃድ ዐውቆ እንደ ፈቃዱ የማ​ይ​ሠ​ራና የማ​ያ​ዘ​ጋጅ የዚያ አገ​ል​ጋይ ቅጣቱ ብዙ ነው።</verse>
				<verse number="48">ያላ​ወቀ ግን ባይ​ሠ​ራም ቅጣቱ ጥቂት ነው፤ ብዙ ከሰ​ጡት ብዙ ይፈ​ል​ጉ​በ​ታ​ልና። ጥቂት ከሰ​ጡ​ትም ጥቂት ይፈ​ል​ጉ​በ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="49">“በም​ድር ላይ እሳ​ትን አም​ጥ​ቼ​አ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋን ከማ​ን​ደድ በቀር ምን እሻ​ለሁ?</verse>
				<verse number="50">ነገር ግን፤ የም​ጠ​መ​ቃት ጥም​ቀት አለ​ችኝ፤ እስ​ክ​ፈ​ጽ​ማ​ትም ድረስ እጅግ እታ​ገ​ሣ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="51">ሕዝ​ቡ​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ለም​ድር ሰላ​ምን ያመ​ጣሁ ይመ​ስ​ላ​ች​ኋ​ልን? እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ አይ​ደ​ለም፤ ሰይ​ፍ​ንና መለ​ያ​የ​ትን ነው እንጂ።</verse>
				<verse number="52">ከእ​ን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ አም​ስት ሰዎች በአ​ንድ ቤት ቢኖሩ ሦስቱ ከሁ​ለቱ፥ ሁለ​ቱም ከሦ​ስቱ ይለ​ያሉ፤</verse>
				<verse number="53">አባት ከልጁ፥ ልጅም ከአ​ባቱ ይለ​ያል፤ እናት ከል​ጅዋ፥ ልጅም ከእ​ናቷ ትለ​ያ​ለች፤ አማት ከም​ራቷ፥ ምራ​ትም ከአ​ማቷ ትለ​ያ​ለች።”</verse>
				<verse number="54">ከዚ​ህም በኋላ ሕዝ​ቡን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ደመና በም​ዕ​ራብ በኩል ደምኖ ባያ​ችሁ ጊዜ ‘ዝናም ይመ​ጣል’ ትላ​ላ​ችሁ፤ እን​ዲ​ሁም ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="55">የአ​ዜብ ነፋስ በነ​ፈሰ ጊዜም ‘ድርቅ ይሆ​ናል፤’ ትላ​ላ​ችሁ እን​ዲ​ሁም ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="56">እና​ንት ግብ​ዞች! የሰ​ማ​ዩ​ንና የም​ድ​ሩን ፊት መመ​ር​መር ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን እነ​ዚ​ህን ዘመ​ናት መመ​ር​መ​ርን እን​ዴት አታ​ው​ቁም?</verse>
				<verse number="57">እና​ንተ ራሳ​ችሁ እው​ነ​ቱን ለምን አት​ፈ​ር​ዱም?</verse>
				<verse number="58">ከባ​ለ​ጋ​ራህ ጋር ወደ ሹም በም​ት​ሄ​ድ​በት ጊዜ ወደ ዳኛ እን​ዳ​ይ​ወ​ስ​ድህ በመ​ን​ገድ ሳለህ ታረቅ፤ ዕዳ​ህ​ንም ክፈል፤ ዳኛው ለሎ​ሌው አሳ​ልፎ ይሰ​ጥ​ሃ​ልና። ሎሌ​ውም በወ​ኅኒ ቤት ያስ​ር​ሃል።</verse>
				<verse number="59">ያለ​ብ​ህን የመ​ጨ​ረ​ሻ​ዋን ግማሽ ሣን​ቲም ቢሆን እስ​ክ​ት​ጨ​ርስ ድረስ አት​ወ​ጣም እል​ሃ​ለሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">በዚያ ወራ​ትም ሰዎች ወደ እርሱ መጥ​ተው ጲላ​ጦስ ደማ​ቸ​ውን ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸው ጋር ስለ ቀላ​ቀ​ለው ስለ ገሊላ ሰዎች ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="2">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ይህች መከራ ስለ አገ​ኘ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ገሊ​ላ​ው​ያን ከገ​ሊላ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ተለ​ይ​ተው ኀጢ​ኣ​ተ​ኞች የሆኑ ይመ​ስ​ሉ​አ​ች​ኋ​ልን?</verse>
				<verse number="3">አይ​ደ​ለም፤ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ንስሓ ካል​ገ​ባ​ችሁ ሁላ​ችሁ እንደ እነ​ርሱ ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="4">ወይስ እነ​ዚያ በሰ​ሊ​ሆም ግንብ ተጭኖ የገ​ደ​ላ​ቸው ዐሥራ ስም​ንቱ ሰዎች ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሰዎች ይልቅ ተለ​ይ​ተው ኀጢ​እ​ታ​ኞች ይመ​ስ​ሉ​አ​ች​ኋ​ልን?</verse>
				<verse number="5">አይ​ደ​ለም፤ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ንስሓ ካል​ገ​ባ​ችሁ ሁላ​ችሁ እንደ እነ​ርሱ ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="6">እን​ዲ​ህም ብሎ መሰ​ለ​ላ​ቸው፥ “አንድ ሰው በታ​ወ​ቀች በወ​ይኑ ቦታ ውስጥ በለስ ነበ​ረ​ችው፤ ፍሬ​ዋን ሊወ​ስድ ወደ እር​ስዋ ሄዶ አላ​ገ​ኘም።</verse>
				<verse number="7">የወ​ይ​ኑን ጠባ​ቂም፦ “የዚ​ችን በለስ ፍሬ ልወ​ስድ ስመ​ላ​ለስ እነሆ፥ ሦስት ዓመት ነው፤ አላ​ገ​ኘ​ሁም፤ እን​ግ​ዲ​ህስ ምድ​ራ​ች​ንን እን​ዳ​ታ​ቦ​ዝን ቍረ​ጣት” አለው።</verse>
				<verse number="8">እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “አቤቱ አፈር ቈፍሬ በሥሯ እስከ አስ​ታ​ቅ​ፋት፥ ፍግም እስከ አፈ​ስ​ባት ድረስ የዘ​ን​ድ​ሮን እንኳ ተዋት።</verse>
				<verse number="9">ምና​ል​ባት ለከ​ርሞ ታፈራ እንደ ሆነ፥ ያለ​ዚያ ግን እን​ቈ​ር​ጣ​ታ​ለን።”</verse>
				<verse number="10">በሰ​ን​በ​ትም በአ​ንድ ምኵ​ራብ ውስጥ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ዐሥራ ስም​ንት ዓመት ሙሉ ጋኔን ያጐ​በ​ጣት አን​ዲት ሴት ነበ​ረች፤ ጐባ​ጣም ነበ​ረች፤ ከቶ ቀጥ ብላ መቆም አት​ች​ልም ነበር።</verse>
				<verse number="12">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም አይቶ ራራ​ላት፥ ጠር​ቶም፥ “ሴትዮ፥ ከደ​ዌሽ ተፈ​ት​ተ​ሻል” አላት።</verse>
				<verse number="13">እጁ​ንም በላ​ይዋ ጫነ፤ ያን​ጊ​ዜም ፈጥና ቀጥ አለች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገ​ነ​ችው።</verse>
				<verse number="14">የም​ኵ​ራቡ ሹምም ጌታ ኢየ​ሱስ በሰ​ን​በት ፈው​ሶ​አ​ልና፤ እየ​ተ​ቈጣ መልሶ ሕዝ​ቡን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሥራ​ች​ሁን የም​ት​ሠ​ሩ​ባ​ቸው ስድ​ስት ቀኖች ያሉ አይ​ደ​ለ​ምን? ያን​ጊዜ ኑና ተፈ​ወሱ፤ በሰ​ን​በት ቀን ግን አይ​ሆ​ንም።”</verse>
				<verse number="15">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ አላ​ቸው፥ “እና​ንት ግብ​ዞች፥ እና​ን​ተሳ አህ​ያ​ች​ሁን ወይም በሬ​አ​ች​ሁን በሰ​ን​በት ቀን ገለባ ከሚ​በ​ላ​በት አት​ፈ​ቱ​ት​ምን? ውኃ ልታ​ጠ​ጡ​ትስ አት​ወ​ስ​ዱ​ት​ምን?</verse>
				<verse number="16">ይህቺ የአ​ብ​ር​ሃም ልጅ እነሆ፥ ሰይ​ጣን ከአ​ሰ​ራት ዐሥራ ስም​ንት ዓመት ነው፤ እር​ስ​ዋስ በሰ​ን​በት ቀን ከእ​ስ​ራቷ ልት​ፈታ አይ​ገ​ባ​ምን?”</verse>
				<verse number="17">ይህ​ንም ባለ ጊዜ በእ​ርሱ ላይ በጠ​ላ​ት​ነት የተ​ነ​ሡ​በት ሁሉ አፈሩ፤ ነገር ግን ሕዝቡ ሁሉ ከእ​ርሱ ስለ​ሚ​ደ​ረ​ገው ድንቅ ነገር ሁሉ ደስ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">በዚያ ቀንም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “መን​ግ​ሥተ ሰማ​ያት ምን ትመ​ስ​ላ​ለች? በም​ንስ እመ​ስ​ላ​ታ​ለሁ?</verse>
				<verse number="19">ሰው ወስዶ በእ​ርሻ ውስጥ የዘ​ራት የሰ​ና​ፍጭ ቅን​ጣ​ትን ትመ​ስ​ላ​ለች፤ አደ​ገች፤ ታላቅ ዛፍም ሆነች፤ የሰ​ማይ ወፎ​ችም በቅ​ር​ን​ጫ​ፎ​ችዋ ውስጥ ተጠ​ለሉ።”</verse>
				<verse number="20">ዳግ​መ​ኛም እን​ዲህ አለ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት በምን እመ​ስ​ላ​ታ​ለሁ?</verse>
				<verse number="21">ሴት ወስዳ ሦስት መስ​ፈ​ሪያ ዱቄት የለ​ወ​ሰ​ች​በ​ትን፥ ሁሉ​ንም እን​ዲ​ቦካ ያደ​ረ​ገ​ውን እርሾ ትመ​ስ​ላ​ለች”።</verse>
				<verse number="22">በየ​ከ​ተ​ማ​ውና በየ​መ​ን​ደሩ እየ​ሄደ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እየ​ተ​መ​ላ​ለሰ ያስ​ተ​ምር ነበር።</verse>
				<verse number="23">አንድ ሰውም፥ “አቤቱ የሚ​ድኑ ጥቂ​ቶች ናቸ​ውን?” አለው። እርሱ ግን እን​ዲህ አላ​ቸው፦</verse>
				<verse number="24">“ወደ ጠባቡ በር ትገቡ ዘንድ በርቱ፤ እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ሊገቡ የሚሹ ብዙ​ዎች ናቸው፤ ግን አይ​ች​ሉም።</verse>
				<verse number="25">ባለ​ቤቱ ተነ​ሥቶ ደጁን ይዘ​ጋ​ልና፤ ያን​ጊዜ ከደጅ ቆመው፦ ‘አቤቱ፥ አቤቱ፥ ክፈ​ት​ልን’ እያሉ በር ሊመቱ ይጀ​ም​ራሉ፤ መል​ሶም፦ ከወ​ዴት እንደ ሆና​ችሁ አላ​ው​ቃ​ች​ሁም ይላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="26">ከዚ​ህም በኋላ፦ በፊ​ትህ በላን፥ ጠጣን፥ በአ​ደ​ባ​ባ​ያ​ች​ንም አስ​ተ​ማ​ርህ ልትሉ ትጀ​ም​ራ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="27">እር​ሱም እን​ዲህ ይላ​ቸ​ዋል፦ እና​ንተ ከወ​ዴት እንደ ሆና​ችሁ አላ​ው​ቃ​ች​ሁም፤ ዐመ​ፅን የም​ታ​ደ​ርጉ ሁላ​ችሁ፥ ከእኔ ራቁ፤</verse>
				<verse number="28">አብ​ር​ሃ​ምን፥ ይስ​ሐ​ቅ​ንና ያዕ​ቆ​ብን፥ ነቢ​ያ​ት​ንም ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት በአ​ያ​ች​ኋ​ቸው ጊዜ እና​ን​ተን ወደ ውጭ ያወ​ጡ​አ​ች​ኋል፤ በዚ​ያም ልቅ​ሶና ጥርስ ማፋ​ጨት ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="29">ከም​ሥ​ራ​ቅና ከም​ዕ​ራብ፥ ከሰ​ሜ​ንና ከደ​ቡብ ይመ​ጣሉ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥት በማ​ዕድ ይቀ​መ​ጣሉ፤</verse>
				<verse number="30">ኋለ​ኞች ፊተ​ኞች ይሆ​ናሉ፤ ፊተ​ኞ​ችም ኋለ​ኞች ይሆ​ናሉ።”</verse>
				<verse number="31">በዚ​ያ​ችም ቀን ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወገን ሰዎች መጥ​ተው፥ “ከዚህ ውጣና ሂድ፤ ሄሮ​ድስ ሊገ​ድ​ልህ ይሻ​ልና” አሉት።</verse>
				<verse number="32">እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሂዱና ያችን ቀበሮ እን​ዲህ በሉ​አት፤ እነሆ፥ ዛሬና ነገ አጋ​ን​ን​ትን አወ​ጣ​ለሁ፤ ሕይ​ወ​ት​ንም አድ​ላ​ለሁ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን እፈ​ጽ​ማ​ለሁ።</verse>
				<verse number="33">ዛሬና ነገስ አለሁ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ግን እሄ​ዳ​ለሁ፤ ነቢይ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እንጂ በውጭ ሊሞት አይ​ገ​ባ​ው​ምና።</verse>
				<verse number="34">“ነቢ​ያ​ትን የም​ት​ገ​ድ​ሊ​ያ​ቸው፥ ወደ አንቺ የተ​ላ​ኩ​ትን ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም የም​ት​ደ​በ​ድ​ቢ​ያ​ቸው ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ዶሮ ጫጩ​ቶ​ች​ዋን ከክ​ን​ፍዋ በታች እን​ደ​ም​ት​ሰ​በ​ስብ ልጆ​ች​ሽን ልሰ​በ​ስ​ባ​ቸው ምን ያህል ወደ​ድሁ? ነገር ግን እንቢ አላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="35">እነሆ፥ ቤታ​ችሁ ምድረ በዳ ሆኖ ይቀ​ር​ላ​ች​ኋል፤ ከዛሬ ወዲያ ‘በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የሚ​መጣ ቡሩክ ነው’ እስ​ክ​ትሉ ድረስ እን​ደ​ማ​ታ​ዩኝ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ ሄዶ ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን አለ​ቆች ወደ አንዱ ቤት በሰ​ን​በት ቀን እህል ሊበላ ገባ፤ እነ​ርሱ ግን ይጠ​ባ​በ​ቁት ነበር።</verse>
				<verse number="2">እነ​ሆም፥ ሆዱ የተ​ነፋ አንድ ሰው በፊቱ ነበር።</verse>
				<verse number="3">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ ሕግ ዐዋ​ቂ​ዎ​ች​ንና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንን፥ “በሰ​ን​በት ድውይ መፈ​ወስ ይገ​ባ​ልን? ወይስ አይ​ገ​ባም?” ብሎ ጠየ​ቃ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">እነ​ር​ሱም ዝም አሉ፤ ይዞም ፈወ​ሰ​ውና ሰደ​ደው።</verse>
				<verse number="5">“ከእ​ና​ንተ በሬው ወይም አህ​ያው በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ የወ​ደ​ቀ​በት አንድ ሰው ቢኖር ዕለ​ቱን በሰ​ን​በት ቀን ያነ​ሣው የለ​ምን?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">ስለ​ዚ​ህም ነገር ሊመ​ል​ሱ​ለት አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="7">በምሳ ላይ ለነ​በ​ሩ​ትም ወደ ላይ​ኛው ወን​በር ሲሽ​ቀ​ዳ​ደሙ ባያ​ቸው ጊዜ ምሳሌ መስሎ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">እን​ዲ​ህም አለ፥ “ለምሳ የጠ​ራህ ሰው ቢኖ​ርና ብት​ሄድ በላ​ይ​ኛው መቀ​መጫ አት​ቀ​መጥ፤ ምና​ል​ባት ከአ​ንተ የሚ​በ​ልጥ ይመጣ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="9">በኋላ ያ አን​ተ​ንም እር​ሱ​ንም የጠራ መጥቶ፦ ይህን ቦታ ለእ​ርሱ ተው​ለት ይል​ሃ​ልና፤ ያን​ጊ​ዜም አፍ​ረህ ትመ​ለ​ሳ​ለህ፤ ወደ ዝቅ​ተኛ ቦታም ትወ​ር​ዳ​ለህ።</verse>
				<verse number="10">የጠ​ራህ ሰው ቢኖ​ርና ብት​ሄድ ግን የጠ​ራህ በመጣ ጊዜ ወዳጄ ወደ ላይ​ኛው መቀ​መጫ ውጣ ይልህ ዘንድ በታ​ች​ኛው መቀ​መጫ ተቀ​መጥ፤ ያን​ጊ​ዜም ከአ​ንተ ጋር ለማ​ዕድ በተ​ቀ​መ​ጡት ሰዎች ፊት ክብር ይሆ​ን​ል​ሃል።</verse>
				<verse number="11">ራሱን ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ይዋ​ረ​ዳ​ልና፤ ራሱ​ንም ያሚ​ያ​ዋ​ርድ ከፍ ይላ​ልና።”</verse>
				<verse number="12">የጠ​ራ​ው​ንም እን​ዲህ አለው፥ “በበ​ዓል ምሳ ወይም ራት በም​ታ​ደ​ር​ግ​በት ጊዜ ወዳ​ጆ​ች​ህ​ንና ወን​ድ​ሞ​ች​ህን፥ ዘመ​ዶ​ች​ህ​ንና ጎረ​ቤ​ቶ​ች​ህን፥ ባለ​ጸ​ጎች ባል​ን​ጀ​ሮ​ች​ህ​ንም አት​ጥራ፤ እነ​ር​ሱም ይጠ​ሩ​ሃ​ልና፤ ብድ​ርም ይሆ​ን​ብ​ሃ​ልና።</verse>
				<verse number="13">ነገር ግን በበ​ዓል ምሳ በም​ታ​ደ​ር​ግ​በት ጊዜ ድሆ​ች​ንና ጦም አዳ​ሪ​ዎ​ችን፥ ዕው​ሮ​ችን፥ እጅና እግ​ርም የሌ​ላ​ቸ​ውን ጥራ።</verse>
				<verse number="14">አን​ተም ብፁዕ ትሆ​ና​ለህ፤ የሚ​ከ​ፍ​ሉህ የላ​ቸ​ው​ምና፤ ነገር ግን ጻድ​ቃን በሚ​ነ​ሡ​በት ጊዜ ዋጋ​ህን ታገ​ኛ​ለህ።”</verse>
				<verse number="15">ለምሳ ከተ​ቀ​መ​ጡ​ትም አንዱ ይህን ሰምቶ፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እህል የሚ​በላ ብፁዕ ነው” አለው።</verse>
				<verse number="16">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አንድ ሰው ታላቅ ምሳ አደ​ረ​ገና ብዙ ሰዎ​ችን ጠራ።</verse>
				<verse number="17">ለምሳ የተ​ጠ​ሩ​በ​ትም ቀን በደ​ረሰ ጊዜ የታ​ደ​ሙ​ትን ይጠ​ራ​ቸው ዘንድ አገ​ል​ጋ​ዩን ላከ፤ እር​ሱም ሄዶ የታ​ደ​ሙ​ትን፦ አሁን ምሳ​ውን ፈጽ​መን አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ና​ልና ኑ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">ሁሉም በአ​ንድ ቃል ተባ​ብ​ረው እንቢ አሉ፤ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው፦ እርሻ ገዝ​ች​አ​ለሁ፤ ሄጄም ላያት እሻ​ለሁ፤ እንቢ እንደ አላ​ልሁ ቍጠ​ር​ልኝ በለው አለው።</verse>
				<verse number="19">ሁለ​ተ​ኛ​ውም፦ አም​ስት ጥማድ በሬ ገዝ​ቻ​ለሁ፤ ላያ​ቸ​ውና ልፈ​ት​ና​ቸው እሄ​ዳ​ለሁ፤ እንደ መጣሁ፥ እንቢ እንደ አላ​ል​ሁም ቍጠ​ር​ልኝ በለው አለው።</verse>
				<verse number="20">ሦስ​ተ​ኛ​ውም፦ ሚስት አግ​ብ​ች​አ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ ልመጣ አል​ች​ልም በለው አለው።</verse>
				<verse number="21">አገ​ል​ጋ​ዩም ተመ​ልሶ ለጌ​ታው ይህ​ንኑ ነገ​ረው፤ ያን​ጊ​ዜም ባለ​ቤቱ ተቈጣ፤ አገ​ል​ጋ​ዩ​ንም፦ ፈጥ​ነህ ወደ አደ​ባ​ባ​ይና ወደ ከተ​ማው ጐዳና ሂድ፤ ድሆ​ች​ንና ጦም አዳ​ሪ​ዎ​ችን፥ ዕው​ሮ​ች​ንና አን​ካ​ሶ​ችን ወደ​ዚህ አም​ጣ​ልኝ አለው።</verse>
				<verse number="22">ከዚ​ህም በኋላ አገ​ል​ጋዩ፦ አቤቱ እንደ አዘ​ዝ​ኸኝ አደ​ረ​ግሁ፤ ገናም ቦታ አለ አለው።</verse>
				<verse number="23">ጌታ​ውም አገ​ል​ጋ​ዩን፦ ወደ መን​ገ​ዶ​ችና ወደ ከተ​ማው ቅጥር ፈጥ​ነህ ሂድና ቤቴ እን​ዲ​መላ ይገቡ ዘንድ ግድ በላ​ቸው አለው።</verse>
				<verse number="24">ከእ​ነ​ዚህ ከታ​ደ​ሙት ሰዎች አንዱ ስን​ኳን ማዕ​ዴን እን​ደ​ማ​ይ​ቀ​ም​ሳት እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="25">ከዚ​ህም በኋላ ብዙ ሰዎች አብ​ረ​ውት ሲሄዱ መለስ ብሎ እን​ዲህ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">“ወደ እኔ የሚ​መጣ፥ ሊከ​ተ​ለ​ኝም የሚ​ወድ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን፥ ሚስ​ቱ​ንና ልጆ​ቹን፥ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንና እኅ​ቶ​ቹን፥ የራ​ሱ​ንም ሰው​ነት እንኳ ቢሆን የማ​ይ​ጠላ ደቀ መዝ​ሙሬ ሊሆን አይ​ች​ልም።</verse>
				<verse number="27">መስ​ቀ​ሉን ተሸ​ክሞ ሊከ​ተ​ለኝ የማ​ይ​መጣ ደቀ መዝ​ሙሬ ሊሆን አይ​ች​ልም።”</verse>
				<verse number="28">“ከእ​ና​ን​ተም ወገን የግ​ንብ ቤት መሥ​ራት የሚ​ወድ ቢኖር ይጨ​ር​ሰው ዘንድ የሚ​ችል እንደ ሆነ አስ​ቀ​ድሞ ተቀ​ምጦ የሚ​ፈ​ጅ​በ​ትን የማ​ያ​ስብ ማን ነው?</verse>
				<verse number="29">መሠ​ረ​ቱን ጥሎ መጨ​ረስ ያቃ​ተ​ውም እንደ ሆነ ያዩት ሁሉ፥</verse>
				<verse number="30">‘ይህ ሰው ሊሠራ ጀመረ፤ ግን መጨ​ረስ ተሳ​ነው’ እያሉ ሊዘ​ብ​ቱ​በት ይጀ​ም​ራሉ።</verse>
				<verse number="31">ንጉ​ሥም ሌላ​ውን ንጉሥ ይወጋ ዘንድ ሊሄድ ቢወድ ሁለት እልፍ ይዞ ወደ እርሱ የሚ​መ​ጣ​ውን በአ​ንድ እልፍ ሊዋ​ጋው ይችል እንደ ሆነ አስ​ቀ​ድሞ ተቀ​ምጦ ይመ​ክር የለ​ምን?</verse>
				<verse number="32">ያለ​ዚያ ግን፥ ገና በሩቁ ሳለ አማ​ላ​ጆች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ልኮ ዕርቅ ይለ​ም​ናል።</verse>
				<verse number="33">እን​ግ​ዲህ እን​ደ​ዚሁ ከእ​ና​ንተ ወገን ከሁሉ ያል​ወጣ፥ የእ​ርሱ ገን​ዘብ ከሆ​ነ​ውም ሁሉ ያል​ተ​ለየ ደቀ መዝ​ሙሬ ሊሆን አይ​ች​ልም።</verse>
				<verse number="34">“ጨው መል​ካም ነው፤ ጨው አልጫ ከሆነ እን​ግ​ዲህ በምን ያጣ​ፍ​ጡ​ታል?</verse>
				<verse number="35">ለም​ድ​ርም ቢሆን፥ ለፍግ መቆ​ለ​ያም ቢሆን አይ​ረ​ባም፤ ነገር ግን ወደ ውጭ ይጥ​ሉ​ታል፤ የሚ​ሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">ቀራ​ጮ​ችና ኀጢ​ኣ​ተ​ኞ​ችም ሊሰ​ሙት ወደ እርሱ ይቀ​ርቡ ነበር።</verse>
				<verse number="2">ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “ይህስ ኀጢ​ኣ​ተ​ኞ​ችን ይቀ​በ​ላል፤ አብ​ሮ​አ​ቸ​ውም ይበ​ላል” ብለው አን​ጐ​ራ​ጐሩ።</verse>
				<verse number="3">እን​ዲ​ህም ብሎ መሰ​ለ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">“ከእ​ና​ንተ መካ​ከል መቶ በጎች ያሉት ሰው ቢኖር፥ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዲቱ ብት​ጠ​ፋው ዘጠና ዘጠ​ኙን በም​ድረ በዳ ትቶ እስ​ኪ​ያ​ገ​ኛት ድረስ ይፈ​ል​ጋት ዘንድ ወደ ጠፋ​ችው ይሄድ የለ​ምን?</verse>
				<verse number="5">በአ​ገ​ኛ​ትም ጊዜ ደስ ብሎት በት​ከ​ሻው ላይ ይሸ​ከ​ማ​ታል።</verse>
				<verse number="6">ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ፥ ወዳ​ጆ​ቹ​ንና ጎረ​ቤ​ቶ​ቹን ጠርቶ፦ የጠ​ፋ​ች​ኝን በጌን አግ​ኝ​ቼ​አ​ታ​ለ​ሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበ​ላ​ችሁ ይላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ እን​ዲሁ ንስሓ ከማ​ያ​ስ​ፈ​ል​ጋ​ቸው ከዘ​ጠና ዘጠኙ ጻድ​ቃን ይልቅ ንስሓ ስለ​ሚ​ገባ ስለ አንድ ኀጢ​ኣ​ተኛ በሰ​ማ​ያት ፍጹም ደስታ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="8">“ዐሥር ድሪም ያላት ሴት ብት​ኖር፥ አን​ዲቱ ብት​ጠ​ፋ​ባት መብ​ራት አብ​ርታ በቤቷ ያለ​ውን ሁሉ እየ​ፈ​ነ​ቀ​ለች እስ​ክ​ታ​ገ​ኛት ድረስ ተግታ ትፈ​ልግ የለ​ምን?</verse>
				<verse number="9">ያገ​ኘ​ቻት እንደ ሆነም ወዳ​ጆ​ች​ዋ​ንና ጎረ​ቤ​ቶ​ች​ዋን ጠርታ፦ ‘የጠ​ፋ​ች​ኝን ድሪ​ሜን አግ​ኝ​ቼ​አ​ታ​ለ​ሁና፥ ከእኔ ጋር ደስ ይበ​ላ​ችሁ’ ትላ​ቸ​ዋ​ለች።</verse>
				<verse number="10">እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ እን​ዲሁ ንስሓ ስለ​ሚ​ገባ ስለ አንድ ኀጢ​ኣ​ተኛ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ፊት በሰ​ማ​ያት ደስታ ይሆ​ናል።”</verse>
				<verse number="11">ዳግ​መ​ኛም እን​ዲህ አለ፥ “አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበ​ሩት።</verse>
				<verse number="12">ታናሹ ልጁም አባ​ቱን፦ ‘አባቴ ሆይ፥ ከገ​ን​ዘ​ብህ የሚ​ደ​ር​ሰ​ኝን ከፍ​ለህ ስጠኝ’ አለው፤ ገን​ዘ​ቡ​ንም ከፍሎ ሰጠው።</verse>
				<verse number="13">ከጥ​ቂት ቀን በኋ​ላም ያ ትንሹ ልጁ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ ሰብ​ስቦ ወደ ሩቅ ሀገር ሄደ፤ በዚ​ያም በመ​ዳ​ራት እየ​ኖረ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ በተነ፤ አጠ​ፋም።</verse>
				<verse number="14">ገን​ዘ​ቡ​ንም ሁሉ በጨ​ረሰ ጊዜ፥ በዚያ ሀገር ጽኑ ራብ መጣ፤ እር​ሱም ተቸ​ገረ።</verse>
				<verse number="15">ሄዶም ከዚያ ሀገር ሰዎች ለአ​ንዱ ተቀ​ጠረ፤ እሪ​ያ​ዎ​ች​ንም ይጠ​ብቅ ዘንድ ወደ እር​ሻው ቦታ ሰደ​ደው።</verse>
				<verse number="16">እሪ​ያ​ዎች ከሚ​መ​ገ​ቡት ተረ​ን​ቃ​ሞም ይጠ​ግብ ዘንድ ተመኘ፤ ግን የሚ​ሰ​ጠው አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="17">በል​ቡም እን​ዲህ ብሎ ዐሰበ፦ እህል የሚ​ተ​ር​ፋ​ቸው የአ​ባቴ ሠራ​ተ​ኞች ምን ያህል ናቸው? እኔ ግን በዚህ በረ​ኃብ ልሞት ነው።</verse>
				<verse number="18">ተነ​ሥቼ ወደ አባቴ ልሂ​ድና እን​ዲህ ልበ​ለው፦ ‘አባቴ ሆይ፥ በሰ​ማ​ይም፥ በፊ​ት​ህም በደ​ልሁ።</verse>
				<verse number="19">እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህስ ልጅህ ልባል አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እንደ አንዱ አድ​ር​ገኝ።’</verse>
				<verse number="20">ተነ​ሥ​ቶም ወደ አባቱ ሄደ፤ አባ​ቱም ከሩቅ አየ​ውና ራራ​ለት፤ ሮጦም አን​ገ​ቱን አቅፎ ሳመው።</verse>
				<verse number="21">ልጁም፦ ‘አባቴ ሆይ፥ በሰ​ማ​ይም፥ በፊ​ት​ህም በደ​ልሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ልጅህ ልባል አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ነገር ግን ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እንደ አንዱ አድ​ር​ገኝ’ አለው።</verse>
				<verse number="22">አባ​ቱም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን እን​ዲህ አላ​ቸው፦ ‘ያማሩ ልብ​ሶ​ችን ቶሎ አም​ጡና አል​ብ​ሱት፤ ለጣ​ቱም ቀለ​በት፥ ለእ​ግ​ሩም ጫማ አድ​ር​ጉ​ለት፤’</verse>
				<verse number="23">የሰ​ባ​ውን ፍሪ​ዳም አም​ጡና እረዱ፤ እን​ብላ፤ ደስም ይበ​ለን።</verse>
				<verse number="24">ይህ ልጄ ሞቶ ነበር፤ አሁን ግን ሕያው ሆኖ​አ​ልና፥ ጠፍ​ቶም ነበር፤ ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልና ደስ ይላ​ቸ​ውም ጀመር።</verse>
				<verse number="25">“ታላቁ ልጁም በእ​ርሻ ነበ​ርና ተመ​ልሶ ወደ ቤቱ አጠ​ገብ በደ​ረሰ ጊዜ የዘ​ፈ​ኑ​ንና የመ​ሰ​ን​ቆ​ውን ድምፅ ሰማ።</verse>
				<verse number="26">ከአ​ባቱ ብላ​ቴ​ኖ​ችም አን​ዱን ጠርቶ፦ ‘ይህ የም​ሰ​ማው ምን​ድን ነው?’ አለው።</verse>
				<verse number="27">እር​ሱም፦ ‘ወን​ድ​ምህ ከሄ​ደ​በት መጣ፤ አባ​ት​ህም የሰ​ባ​ውን ፍሪዳ አረደ፤ በሕ​ይ​ወት አግ​ኝ​ቶ​ታ​ልና’ አለው።</verse>
				<verse number="28">ተቈ​ጥ​ቶም ‘አል​ገ​ባም’ አለ፤ አባ​ቱም ወጥቶ ማለ​ደው።</verse>
				<verse number="29">መል​ሶም አባ​ቱን እን​ዲህ አለው፦ ‘እነሆ፥ ይህን ያህል ዓመት ተገ​ዛ​ሁ​ልህ፤ ፈጽሞ ከት​እ​ዛ​ዝህ አል​ወ​ጣ​ሁም፤ ለእኔ ግን ከባ​ል​ን​ጀ​ሮች ጋር ደስ እን​ዲ​ለኝ አንድ የፍ​የል ጠቦት እንኳ አል​ሰ​ጠ​ኸ​ኝም።</verse>
				<verse number="30">ከአ​መ​ን​ዝ​ሮች ጋር ገን​ዘ​ብ​ህን ሁሉ የጨ​ረሰ ይህ ልጅህ በተ​መ​ለሰ ጊዜ ግን የሰ​ባ​ውን ፍሪዳ አረ​ድ​ህ​ለት።’</verse>
				<verse number="31">አባ​ቱም እን​ዲህ አለው፦ ‘ልጄ አን​ተማ እኮ ዘወ​ትር ከእኔ ጋር ነህ፤ የእኔ የሆ​ነው ሁሉ የአ​ንተ ነው።</verse>
				<verse number="32">ነገር ግን ይህ ወን​ድ​ምህ ሞቶ ነበረ፤ ሕያው ሆኖ​አ​ልና፥ ጠፍ​ቶም ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልና፥ ደስ ሊለን፥ ሐሤ​ትም ልና​ደ​ርግ ይገ​ባል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “መጋቢ የነ​በ​ረው አንድ ባለ​ጸጋ ሰው ነበረ፤ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ እን​ደ​ሚ​በ​ትን አድ​ር​ገው በእ​ርሱ ዘንድ ከሰ​ሱት።</verse>
				<verse number="2">ጌታ​ውም ጠርቶ፦ ‘በአ​ንተ ላይ የም​ሰ​ማው ይህ ነገር ምን​ድን ነው? እን​ግ​ዲህ ወዲህ ለእኔ መጋቢ ልት​ሆን አት​ች​ል​ምና የመ​ጋ​ቢ​ነ​ት​ህን ሂሳብ አስ​ረ​ክ​በኝ’ አለው።</verse>
				<verse number="3">ያም መጋቢ ዐስቦ እን​ዲህ አለ፦ ‘ምን ላድ​ርግ? አሁን ጌታዬ ከመ​ጋ​ቢ​ነቴ ይሽ​ረ​ኛል፤ ማረስ አል​ች​ልም፤ ለመ​ለ​መ​ንም አፍ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">እን​ግ​ዲህ ጌታዬ ከም​ግ​ብ​ናዬ የሻ​ረኝ እንደ ሆነ በቤ​ታ​ቸው ይቀ​በ​ሉኝ ዘንድ የማ​ደ​ር​ገ​ውን እኔ ዐው​ቃ​ለሁ።’</verse>
				<verse number="5">ለጌ​ታ​ውም ዕዳ የሚ​ከ​ፍ​ሉ​ትን ጠራ​ቸው፤ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ው​ንም፦ ‘ለጌ​ታዬ የም​ት​ከ​ፍ​ለው ዕዳ ምን ያህል ነው?’ አለው፤ እር​ሱም፦ ‘መቶ ማድጋ ዘይት ነው’ አለው።</verse>
				<verse number="6">‘እነሆ፥ ደብ​ዳ​ቤህ፤ ተቀ​ም​ጠህ አምሳ ማድጋ አለ​ብኝ ብለህ ፈጥ​ነህ ጻፍ’ አለው።</verse>
				<verse number="7">ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም፦ ‘አን​ተሳ ለጌ​ታዬ የም​ት​ከ​ፍ​ለው ዕዳ ምን ያህል ነው?’ አለው፤ እር​ሱም፦ ‘መቶ ማድጋ ስንዴ ነው’ አለው፤ ‘እነሆ፥ ደብ​ዳ​ቤህ፤ ተቀ​ም​ጠህ ሰማ​ንያ አለ​ብኝ ብለህ ፈጥ​ነህ ጻፍ’ አለው።</verse>
				<verse number="8">ጌታ​ውም ዐመ​ፀ​ኛ​ውን መጋቢ እንደ ብልህ ሰው ስለ ሠራ አመ​ሰ​ገ​ነው፤ ከብ​ር​ሃን ልጆች ይልቅ የዚህ ዓለም ልጆች በዓ​ለ​ማ​ቸው ይራ​ቀ​ቃ​ሉና።</verse>
				<verse number="9">እኔም እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ባለ​ቀ​ባ​ችሁ ጊዜ እነ​ርሱ በዘ​ለ​ዓ​ለም ቤታ​ቸው ይቀ​በ​ሉ​አ​ችሁ ዘንድ በዐ​መፃ ገን​ዘብ ለእ​ና​ንተ ወዳ​ጆች አድ​ር​ጉ​በት።</verse>
				<verse number="10">“በጥ​ቂት የሚ​ታ​መን በብዙ ይታ​መ​ናል፤ በጥ​ቂት የሚ​ያ​ም​ፅም በብ​ዙም ቢሆን ያም​ፃል።</verse>
				<verse number="11">በዐ​መፃ ገን​ዘብ ካል​ታ​መ​ና​ችሁ በእ​ው​ነ​ተ​ኛው ገን​ዘብ ማን ያም​ና​ች​ኋል?</verse>
				<verse number="12">በሌ​ላ​ውስ ገን​ዘብ ካል​ታ​መ​ና​ችሁ የራ​ሱን ማን ይሰ​ጣ​ች​ኋል?</verse>
				<verse number="13">ለሁ​ለት ጌቶች መገ​ዛት የሚ​ችል አገ​ል​ጋይ የለም፤ ካል​ሆ​ነም አን​ዱን ይወ​ድ​ዳል፤ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ይጠ​ላል፤ ወይም ለአ​ንዱ ይታ​ዘ​ዛል፤ ለሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም እንቢ ይላል፤ እን​ዲ​ሁም እና​ንተ ገን​ዘብ እየ​ወ​ደ​ዳ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መገ​ዛት አት​ች​ሉም።”</verse>
				<verse number="14">ገን​ዘ​ብን የሚ​ወዱ ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ይህን ሁሉ ነገር ሰም​ተው ተጠ​ቃ​ቀ​ሱ​በት።</verse>
				<verse number="15">እር​ሱም፥ “እና​ን​ተስ ለሰው ይም​ሰል ትመ​ጻ​ደ​ቃ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልቡ​ና​ች​ሁን ያው​ቃል፤ በሰው ዘንድ የከ​በረ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ናቀ ይሆ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="16">“ኦሪ​ትም ነቢ​ያ​ትም ከጥ​ንት ጀምሮ እስከ ዮሐ​ንስ ድረስ ነበሩ፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ይሰ​በ​ካል፤ ሁሉም ወደ እር​ስዋ ይጋ​ፋል።</verse>
				<verse number="17">ነገር ግን ከኦ​ሪት አን​ዲት ቃል ከም​ት​ወ​ድቅ ሰማ​ይና ምድር ቢያ​ልፍ ይቀ​ላል።</verse>
				<verse number="18">“ሚስ​ቱን ፈትቶ ሌላ​ዪ​ቱን የሚ​ያ​ገባ ሁሉ ያመ​ነ​ዝ​ራል፤ ባልዋ የፈ​ታ​ት​ንም የሚ​ያ​ገባ ያመ​ነ​ዝ​ራል።</verse>
				<verse number="19">“አንድ ባለ​ጸጋ ሰው ነበረ፤ ቀይ ሐርና ነጭ ሐር፥ እጅ​ግም ቀጭን ልብስ ይለ​ብስ ነበር፤ ዘወ​ት​ርም ተድ​ላና ደስታ ያደ​ርግ ነበር።</verse>
				<verse number="20">በቍ​ስል ሕመም ተይዞ በባ​ለ​ጸ​ጋው ደጅ የወ​ደቀ አል​ዓ​ዛር የሚ​ባል አንድ ድሃም ነበረ።</verse>
				<verse number="21">ከባ​ለ​ጸ​ጋው ማዕድ የሚ​ወ​ድ​ቀ​ው​ንም ፍር​ፋሪ ሊመ​ገብ ይመኝ ነበር፤ ውሾ​ችም እየ​መጡ ቍስ​ሉን ይል​ሱት ነበር።</verse>
				<verse number="22">ከዚ​ህም በኋላ ድሃው ሞተ፤ መላ​እ​ክ​ትም ወደ አብ​ር​ሃም አጠ​ገብ ወሰ​ዱት፤ ባለ​ጸ​ጋ​ውም ደግሞ ሞተ፤ ተቀ​በ​ረም፤</verse>
				<verse number="23">በሲ​ኦ​ልም በሥ​ቃይ ሳለ ዐይ​ኖ​ቹን አን​ሥቶ አብ​ር​ሃ​ምን ከሩቅ አየው፤ አል​ዓ​ዛ​ር​ንም በአ​ጠ​ገቡ ተቀ​ምጦ አየው።</verse>
				<verse number="24">‘አባት አብ​ር​ሃም ሆይ፥ እዘ​ን​ልኝ፤ በዚች እሳት እጅግ ተሠ​ቃ​ይ​ቻ​ለ​ሁና፥ ጣቱን ከውኃ ነክሮ ምላ​ሴን ያቀ​ዘ​ቅ​ዝ​ልኝ ዘንድ አል​ዓ​ዛ​ርን ላከው’ ብሎ ተጣራ።</verse>
				<verse number="25">አብ​ር​ሃም ግን እን​ዲህ አለው፦ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ በሕ​ይ​ወ​ትህ ተድ​ላና ደስታ እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ፥ አል​ዓ​ዛ​ርም እን​ዲሁ ሁል​ጊዜ በች​ጋር እንደ ነበረ ዐስብ፤ አሁን ግን እን​ዲሁ እርሱ በዚህ ፈጽሞ ተድ​ላና ደስታ ያደ​ር​ጋል፤ አንተ ግን መከራ ትቀ​በ​ላ​ለህ።</verse>
				<verse number="26">ከዚ​ህም ሁሉ ጋር ከዚህ ወደ እና​ንተ ማለፍ የሚሹ እን​ዳ​ይ​ችሉ፥ ከእ​ና​ንተ ወገን የሆ​ኑ​ትም ወደ እኛ እን​ዳ​ይ​ሻ​ገሩ በእ​ኛና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ታላቅ ገደል አለ’</verse>
				<verse number="27">እር​ሱም እን​ዲህ አለው፦ ‘አባት አብ​ር​ሃም ሆይ፥ አል​ዓ​ዛ​ርን ወደ አባቴ ቤት እን​ድ​ት​ል​ከው እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="28">አም​ስት ወን​ድ​ሞች ስለ አሉኝ ይን​ገ​ራ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ደግሞ ወደ​ዚች የሥ​ቃይ ቦታ እን​ዳ​ይ​መጡ ይስሙ።’</verse>
				<verse number="29">አብ​ር​ሃ​ምም፦ ‘ሙሴና ነቢ​ያት አሉ​አ​ቸው፤ እነ​ር​ሱን ይስሙ’ አለው።</verse>
				<verse number="30">እር​ሱም፦ ‘የለም፤ አባት አብ​ር​ሃም ሆይ፥ ከሙ​ታን አንዱ ወደ እነ​ርሱ ካል​ሄ​ደና ካል​ነ​ገ​ራ​ቸው ንስሓ አይ​ገ​ቡም’ አለው።</verse>
				<verse number="31">አብ​ር​ሃ​ምም፦ ‘ሙሴ​ንና ነቢ​ያ​ትን ካል​ሰ​ሙማ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ የተ​ነሣ ቢኖ​ርም እንኳ አይ​ሰ​ሙ​ትም፤ አያ​ም​ኑ​ት​ምም’ አለው።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “መሰ​ና​ክል ግድ ይመ​ጣል፤ ነገር ግን መሰ​ና​ክ​ልን ለሚ​ያ​መ​ጣት ሰው ወዮ​ለት።</verse>
				<verse number="2">ከእ​ነ​ዚህ ከታ​ና​ና​ሾቹ አን​ዱን ከሚ​ያ​ሰ​ና​ክል ይልቅ አህያ የሚ​ፈ​ጭ​በት የወ​ፍጮ ድን​ጋይ በአ​ን​ገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር ቢሰ​ጥም በተ​ሻ​ለው ነበር።</verse>
				<verse number="3">ለራ​ሳ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ፤ ወን​ድ​ምህ አን​ተን ቢበ​ድል ብቻ​ህን ምከ​ረው፤ ቢጸ​ጸት ግን ይቅር በለው።</verse>
				<verse number="4">በየ​ቀኑ ሰባት ጊዜ ቢበ​ድ​ልም ሰባት ጊዜ ከተ​ጸ​ጸተ ይቅር በለው።”</verse>
				<verse number="5">ሐዋ​ር​ያ​ትም ጌታን፥ “እም​ነ​ትን ጨም​ር​ልን” አሉት።</verse>
				<verse number="6">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የሰ​ና​ፍጭ ቅን​ጣት ታህል እም​ነት ብት​ኖ​ራ​ችሁ ይህ​ችን ሾላ ከሥ​ርሽ ተነ​ቅ​ለሽ በባ​ሕር ውስጥ ተተ​ከዪ ብት​ሉ​አት ትታ​ዘ​ዝ​ላ​ች​ኋ​ለች።”</verse>
				<verse number="7">“አራሽ ወይም ከብት ጠባቂ አገ​ል​ጋይ ያለው ከእ​ና​ንተ ማን ነው? ከእ​ር​ሻው በተ​መ​ለሰ ጊዜ ጌታው ና፥ ፈጥ​ነህ ወደ​ዚህ ውጣና ከእኔ ጋር በማ​ዕድ ተቀ​መጥ ይለ​ዋ​ልን?</verse>
				<verse number="8">እራ​ቴን አዘ​ጋ​ጅ​ልኝ፥ እስ​ክ​በ​ላና እስ​ክ​ጠጣ ድረ​ስም ታጥ​ቀህ አሳ​ል​ፍ​ልኝ፤ ከዚ​ህም በኋላ አንተ ብላ፥ ጠጣም ይለው የለ​ምን?</verse>
				<verse number="9">እን​ግ​ዲህ ጌታው ያዘ​ዘ​ውን ሥራ​ውን ቢሠራ ለዚያ አገ​ል​ጋይ ምስ​ጋና አለ​ውን?</verse>
				<verse number="10">እን​ዲሁ እና​ን​ተም ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁን ሁሉ አድ​ር​ጋ​ችሁ ‘እኛ ሥራ ፈቶች አገ​ል​ጋ​ዮች ነን፤ ለመ​ሥ​ራ​ትም የሚ​ገ​ባ​ንን ሠራን’ በሉ።”</verse>
				<verse number="11">ከዚህ በኋላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሲሄድ በሰ​ማ​ር​ያና በገ​ሊላ መካ​ከል ዐለፈ።</verse>
				<verse number="12">ወደ አን​ዲት መን​ደ​ርም ሲገባ ለምጽ የያ​ዛ​ቸው ዐሥር ሰዎች ተቀ​በ​ሉ​ትና ራቅ ብለው ቆሙ።</verse>
				<verse number="13">ድም​ጻ​ቸ​ው​ንም ከፍ አድ​ር​ገው፥ “ጌታ ኢየ​ሱስ ሆይ፥ እዘ​ን​ልን” አሉ።</verse>
				<verse number="14">ባያ​ቸ​ውም ጊዜ፥ “ወደ ካህን ሂዱና ራሳ​ች​ሁን አስ​መ​ር​ምሩ” አላ​ቸው፤ ሲሄ​ዱም ነጹ።</verse>
				<verse number="15">ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ እንደ ነጻ ባየ ጊዜ፥ በታ​ላቅ ቃል እያ​መ​ሰ​ገነ ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="16">በግ​ን​ባ​ሩም ወድቆ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እግር በታች ሰገ​ደና አመ​ሰ​ገ​ነው፤ ሰው​የ​ውም ሳም​ራዊ ነበር።</verse>
				<verse number="17">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለ፤ “የነጹ ዐሥር አል​ነ​በ​ሩ​ምን? እን​ግ​ዲህ ዘጠኙ የት አሉ?</verse>
				<verse number="18">ወገኑ ሌላ ከሆነ ከዚህ ሰው በቀር ለእ​ነ​ዚያ ተመ​ልሶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማመ​ስ​ገን ተሳ​ና​ቸ​ውን?”</verse>
				<verse number="19">እር​ሱ​ንም፥ “ተነ​ሥና ሂድ፤ እም​ነ​ትህ አዳ​ነ​ችህ” አለው።</verse>
				<verse number="20">ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት መቼ ትመ​ጣ​ለች?” ብለው ጠየ​ቁት፤ እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት በመ​ጠ​ባ​በቅ አት​መ​ጣም።</verse>
				<verse number="21">እን​ኋት፥ በዚህ ናት፤ ወይም እነ​ኋት፥ በዚያ ናት አይ​ሉ​አ​ትም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥ​ትስ እነ​ኋት፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ናት።”</verse>
				<verse number="22">ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱ​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ከሰው ልጆች ቀኖች አን​ዲ​ቱን ታዩ ዘንድ የም​ት​መ​ኙ​በት ወራት ይመ​ጣል፤ ነገር ግን አታ​ዩ​አ​ትም።</verse>
				<verse number="23">እነሆ፥ በዚህ ነው፥ ወይም እነሆ፥ በዚያ ነው ቢሉ​አ​ችሁ አት​ውጡ፤ አት​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="24">መብ​ረቅ ብልጭ ብሎ ከሰ​ማይ ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ እን​ደ​ሚ​ያ​በራ የሰው ልጅ አመ​ጣጡ እን​ዲሁ ነውና።</verse>
				<verse number="25">ነገር ግን ከዚህ ሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ብዙ መከ​ራን ይቀ​በ​ላል፤ ይህች ትው​ል​ድም ትን​ቀ​ዋ​ለች፤ ትፈ​ታ​ተ​ነ​ዋ​ለ​ችም።</verse>
				<verse number="26">በኖኅ ዘመን እንደ ሆነው የሰው ልጅ በሚ​መ​ጣ​በት ጊዜ እን​ዲሁ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="27">ኖኅ ወደ መር​ከብ እስከ ገባ​በት ቀን ድረስ ሲበ​ሉና ሲጠጡ፥ ሲያ​ገ​ቡና ሲጋቡ ነበረ፤ የጥ​ፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን አንድ አድ​ርጎ አጠፋ።</verse>
				<verse number="28">በሎጥ ዘመ​ንም ሲበ​ሉና ሲጠጡ፥ ቤት ሲሠ​ሩና ተክል ሲተ​ክሉ፥ ሲሸ​ጡና ሲገዙ ነበረ።</verse>
				<verse number="29">ሎጥ ከሰ​ዶም በወ​ጣ​በት ቀን ግን ከሰ​ማይ እሳ​ትና ዲን ዘነመ፤ ሁሉ​ንም አጠፋ።</verse>
				<verse number="30">የሰው ልጅም በሚ​መ​ጣ​በት ቀን እን​ዲሁ ይሆ​ናል፤ አይ​ታ​ወ​ቅ​ምም።</verse>
				<verse number="31">ያን​ጊ​ዜም በሰ​ገ​ነት ላይ ያለ፥ ገን​ዘ​ቡም በም​ድር ቤት የሆ​ነ​በት ሰው ለመ​ው​ሰድ አይ​ው​ረድ፤ በዱር ያለም ወደ ኋላው አይ​መ​ለስ።</verse>
				<verse number="32">የሎ​ጥን ሚስት ዐስ​ቡ​አት።</verse>
				<verse number="33">ነፍ​ሱን ሊያ​ድ​ናት የሚ​ወድ ይጣ​ላት፤ ስለ እኔ ነፍ​ሱን የሚ​ጥ​ላ​ትም ያድ​ና​ታል።</verse>
				<verse number="34">እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ሁለት ሰዎች በአ​ንድ አልጋ ይተ​ኛሉ፤ አን​ዱን ይወ​ስ​ዳሉ፤ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ይተ​ዋሉ።</verse>
				<verse number="35">ሁለት ሴቶ​ችም በአ​ንድ ወፍጮ ይፈ​ጫሉ፤ አን​ዲ​ቱን ይወ​ስ​ዳሉ፤ ሁለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱ​ንም ይተ​ዋሉ።</verse>
				<verse number="36">ሁለት ሰዎች በአ​ንድ እርሻ ላይ ይኖ​ራሉ፤ አን​ዱን ይወ​ስ​ዳሉ፤ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ይተ​ዋሉ።”</verse>
				<verse number="37">እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “አቤቱ፥ ወዴት ነው?” አሉት፤ እር​ሱም፥ “ገደላ በአ​ለ​በት አሞ​ሮች በዚያ ይሰ​በ​ሰ​ባሉ” አላ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">ዘወ​ትር እን​ዲ​ጸ​ልዩ፥ እን​ዳ​ይ​ሰ​ለ​ቹም በም​ሳሌ ነገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “በአ​ን​ዲት ከተማ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የማ​ይ​ፈራ፥ ሰው​ንም የማ​ያ​ፍር አንድ ዳኛ ነበር።</verse>
				<verse number="3">በዚ​ያ​ችም ከተማ አን​ዲት መበ​ለት ነበ​ረች፤ ዕለት ዕለ​ትም ወደ እርሱ እየ​መ​ጣች ከባ​ለ​ጋ​ራዬ ፍረ​ድ​ልኝ ትለው ነበር።</verse>
				<verse number="4">እንቢ ብሎም አዘ​ገ​ያት። ከዚ​ህም በኋላ በልቡ ዐስቦ እን​ዲህ አለ፦ ‘ምንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ባል​ፈራ፥ ሰው​ንም ባላ​ፍር</verse>
				<verse number="5">ይህቺ ሴት እን​ዳ​ት​ዘ​በ​ዝ​በኝ፥ ዘወ​ት​ርም እየ​መ​ጣች እን​ዳ​ታ​ታ​ክ​ተኝ እፈ​ር​ድ​ላ​ታ​ለሁ’።”</verse>
				<verse number="6">ጌታ​ች​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ዐመ​ፀ​ኛው ዳኛ ያለ​ውን ስሙ።</verse>
				<verse number="7">እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ዓ​ል​ትና በሌ​ሊት ወደ እርሱ ለሚ​ጮኹ ለወ​ዳ​ጆቹ አይ​ፈ​ር​ድ​ምን? ወይስ ቸል ይላ​ቸ​ዋ​ልን?</verse>
				<verse number="8">እላ​ች​ኋ​ለሁ ፈጥኖ ይፈ​ር​ድ​ላ​ቸ​ዋል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በም​ድር ላይ እም​ነ​ትን ያገኝ ይሆን?”</verse>
				<verse number="9">ራሳ​ቸ​ውን ለሚ​ያ​መ​ጻ​ድ​ቁና ባል​ን​ጀ​ራ​ቸ​ውን ለሚ​ንቁ እን​ዲህ ብሎ መሰ​ለ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">“ሁለት ሰዎች ሊጸ​ልዩ ወደ ቤተ መቅ​ደስ ወጡ፤ አንዱ ፈሪ​ሳዊ፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ቀራጭ ነበር።</verse>
				<verse number="11">ፈሪ​ሳ​ዊ​ውም ቆመና እን​ዲህ ብሎ ጸለየ፦ ‘አቤቱ እንደ ሌሎች ሰዎች፥ እንደ ቀማ​ኞ​ችና እንደ ዐመ​ፀ​ኞች፥ እንደ አመ​ን​ዝ​ሮ​ችም፥ ወይም እን​ደ​ዚህ ቀራጭ ያላ​ደ​ረ​ግ​ኸኝ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">እኔ በየ​ሳ​ም​ንቱ ሁለት ቀን እጾ​ማ​ለሁ፤ ከማ​ገ​ኘ​ውም ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ እሰ​ጣ​ለሁ።’</verse>
				<verse number="13">ቀራጩ ግን ራቅ ብሎ ቆመ፤ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ወደ ላይ ወደ ሰማይ ሊያ​ነሣ አል​ወ​ደ​ደም፤ ደረ​ቱ​ንም እየ​መታ፦ ‘አቤቱ፥ እኔን ኀጢ​ኣ​ተ​ኛ​ውን ይቅር በለኝ’ አለ።</verse>
				<verse number="14">እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመ​ለሰ፤ ራሱን ከፍ ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ይዋ​ረ​ዳ​ልና፤ ራሱ​ንም የሚ​ያ​ዋ​ርድ ይከ​ብ​ራ​ልና።”</verse>
				<verse number="15">ይባ​ር​ካ​ቸ​ውም ዘንድ ሕፃ​ና​ትን ወደ እርሱ አመ​ጡ​አ​ቸው፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አይ​ተው ገሠ​ጹ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ጠራ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ሕፃ​ና​ትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉ​አ​ቸው፥ አት​ከ​ል​ክ​ሉ​አ​ቸ​ውም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እንደ እነ​ዚህ ላሉት ናትና።</verse>
				<verse number="17">እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት እንደ ሕፃ​ናት ያል​ተ​ቀ​በ​ላት አይ​ገ​ባ​ባ​ትም።”</verse>
				<verse number="18">አንድ አለ​ቃም፥ “ቸር መም​ህር፥ ምን ሥራ ሠርቼ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እወ​ር​ሳ​ለሁ?” አለው።</verse>
				<verse number="19">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “ለምን ቸር ትለ​ኛ​ለህ? ከአ​ንዱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀር ቸር የለም።</verse>
				<verse number="20">ትእ​ዛ​ዛ​ቱን አንተ ራስህ ታው​ቃ​ለህ፤ ‘አት​ግ​ደል፤ አታ​መ​ን​ዝር፤ አት​ስ​ረቅ፤ በሐ​ሰት አት​መ​ስ​ክር፤ አባ​ት​ህ​ንና እና​ት​ህ​ንም አክ​ብር።’</verse>
				<verse number="21">እር​ሱም፦ ‘ይህ​ንስ ሁሉ ከል​ጅ​ነቴ ጀምሬ እስከ ዛሬ ጠብ​ቄ​አ​ለሁ’።” አለው።</verse>
				<verse number="22">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ሰምቶ እን​ዲህ አለው፥ “አን​ዲት ቀር​ታ​ሃ​ለች፤ ሂድና ያለ​ህን ሁሉ ሸጠህ ለነ​ዳ​ያን ስጥ፤ በሰ​ማ​ይም መዝ​ገብ ታገ​ኛ​ለህ፤ መጥ​ተ​ህም ተከ​ተ​ለኝ።”</verse>
				<verse number="23">እርሱ ግን ይህን ሰምቶ በጣም አዘነ፤ እርሱ እጅግ ባለ​ጸጋ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="24">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እጅግ ሲያ​ዝን አይቶ እን​ዲህ አለ፥ “ገን​ዘብ ላላ​ቸው ሰዎች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት መግ​ባት እን​ዴት ጭንቅ ነው!</verse>
				<verse number="25">ባለ​ጸጋ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ከሚ​ገባ ይልቅ ግመል በመ​ርፌ ቀዳዳ ሊያ​ልፍ ይቀ​ላል።”</verse>
				<verse number="26">የሰ​ሙ​ትም፥ “እን​ግ​ዲህ ማን ሊድን ይች​ላል?” አሉ።</verse>
				<verse number="27">እርሱ ግን “በሰው ዘንድ የማ​ይ​ቻ​ለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይቻ​ላል” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="28">ጴጥ​ሮ​ስም፥ “እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከ​ት​ለ​ን​ሃል፤ እን​ግ​ዲህ ምን እና​ገ​ኛ​ለን?” አለው።</verse>
				<verse number="29">እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ቤቱ​ንና ዘመ​ዶ​ቹን፥ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንና ሚስ​ቱን፥ ልጆ​ቹ​ንም ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት የሚ​ተው፥</verse>
				<verse number="30">በዚህ ዓለም መቶ እጥፍ ዋጋ፥ በሚ​መ​ጣ​ውም ዓለም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን የማ​ይ​ቀ​በል ማንም የለም።”</verse>
				<verse number="31">ዐሥራ ሁለ​ቱ​ንም ወሰ​ዳ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እነሆ፥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ወ​ጣ​ለን፤ በነ​ቢ​ያ​ትም የተ​ጻ​ፈው ሁሉ በሰው ልጅ ላይ ይፈ​ጸ​ማል።</verse>
				<verse number="32">ለአ​ሕ​ዛብ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ታል፤ ይዘ​ብ​ቱ​በ​ታ​ልም፤ ይሰ​ድ​ቡ​ታ​ልም፤ ይተ​ፉ​በ​ታ​ልም።</verse>
				<verse number="33">ይገ​ር​ፉ​ታል፤ ይገ​ድ​ሉ​ታ​ልም፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ቀን ይነ​ሣል።”</verse>
				<verse number="34">እነ​ርሱ ግን፤ ከተ​ና​ገ​ራ​ቸው ያስ​ተ​ዋ​ሉት የለም፤ ይህ ነገር ከእ​ነ​ርሱ የተ​ሰ​ወረ ነበ​ርና፤ የተ​ና​ገ​ረ​ው​ንም አያ​ው​ቁም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="35">ከዚ​ህም በኋላ ኢያ​ሪኮ በደ​ረሱ ጊዜ አንድ ዕውር በጎ​ዳና ተቀ​ምጦ ይለ​ምን ነበር።</verse>
				<verse number="36">የሚ​ያ​ል​ፈ​ው​ንም ሰው ድምፅ ሰምቶ፥ “ይህ የም​ሰ​ማው ምን​ድን ነው?” አለ።</verse>
				<verse number="37">እነ​ር​ሱም፥ “የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ ያል​ፋል” ብለው ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="38">ድም​ፁ​ንም ከፍ አድ​ርጎ፥ “የዳ​ዊት ልጅ ኢየ​ሱስ ሆይ፥ ማረኝ” አለ።</verse>
				<verse number="39">የሚ​መ​ሩ​ትም ዝም እን​ዲል ገሠ​ጹት፤ እርሱ ግን በጣም ጮኾ፥ “የዳ​ዊት ልጅ ሆይ፥ ማረኝ” አለ።</verse>
				<verse number="40">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ቆመና ወደ እርሱ እን​ዲ​ያ​መ​ጡት አዘዘ።</verse>
				<verse number="41">ወደ እር​ሱም በደ​ረሰ ጊዜ፥ “ምን ላደ​ር​ግ​ልህ ትወ​ዳ​ለህ?” ብሎ ጠየ​ቀው፤ እር​ሱም፥ “ጌታ ሆይ፥ ዐይ​ኖች እን​ዲ​ያዩ ነው” አለው።</verse>
				<verse number="42">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እይ፤ እም​ነ​ትህ አዳ​ነ​ችህ” አለው።</verse>
				<verse number="43">በዚ​ያን ጊዜም አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገነ፤ ተከ​ተ​ለ​ውም፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አይ​ተው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ኑት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ ኢያ​ሪኮ ገብቶ በዚያ ያልፍ ነበር።</verse>
				<verse number="2">እነሆ፥ የቀ​ራ​ጮች አለቃ ስሙ ዘኬ​ዎስ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበር፤ እር​ሱም ባለ​ጸጋ ነበር።</verse>
				<verse number="3">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ያየው ዘንድ፥ ማን እንደ ሆነም ያውቅ ዘንድ ይሻ ነበር፤ የሰው ብዛ​ትም ይከ​ለ​ክ​ለው ነበር፤ ቁመቱ አጭር ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="4">ወደ ፊቱም ሮጠ፤ ያየው ዘን​ድም በሾላ ላይ ወጣ፤ በዚ​ያች መን​ገድ ያልፍ ዘንድ አለ​ውና።</verse>
				<verse number="5">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ​ዚያ በደ​ረሰ ጊዜ አሻ​ቅቦ አየ​ውና፥ “ዘኬ​ዎስ ሆይ፥ ፈጥ​ነህ ውረድ፤ ዛሬ በቤ​ትህ እውል ዘንድ አለ​ኝና” አለው።</verse>
				<verse number="6">ፈጥ​ኖም ወረደ፤ ደስ እያ​ለ​ውም ወደ ቤቱ ይዞት ገባ።</verse>
				<verse number="7">ሁሉም አይ​ተው “ወደ ኀጢ​ኣ​ተኛ ሰው ቤት ሊውል ገባ” ብለው አን​ጐ​ራ​ጐሩ።</verse>
				<verse number="8">ዘኬ​ዎ​ስም ቆመና ጌታ​ች​ንን እን​ዲህ አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አሁን የገ​ን​ዘ​ቤን እኩ​ሌታ ለነ​ዳ​ያን እሰ​ጣ​ለሁ፤ የበ​ደ​ል​ሁ​ትም ቢኖር ስለ አንድ ፋንታ አራት እጥፍ እከ​ፍ​ለ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="9">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “ዛሬ ለዚህ ቤት ሕይ​ወት ሆነ፤ እርሱ የአ​ብ​ር​ሃም ልጅ ነውና።</verse>
				<verse number="10">የሰው ልጅ የጠ​ፋ​ውን ሊፈ​ል​ግና ሊያ​ድን መጥ​ቶ​አ​ልና።”</verse>
				<verse number="11">ይህ​ንም ሲሰሙ፤ ምሳሌ መስሎ ነገ​ራ​ቸው፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ቀርቦ ነበ​ርና፤ እነ​ር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ወዲ​ያ​ውኑ የም​ት​ገ​ለጥ መስ​ሎ​አ​ቸው ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="12">እን​ዲ​ህም አለ፥ “አንድ የከ​በረ ሰው መን​ግ​ሥት ይዞ ሊመ​ለስ ወደ ሩቅ ሀገር ሄደ።</verse>
				<verse number="13">ዐሥ​ሩን አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ጠርቶ ዐሥር ምናን ሰጣ​ቸ​ውና፦ እን​ግ​ዲህ እስ​ክ​መ​ለስ ድረስ ነግዱ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">የሀ​ገሩ ሰዎች ግን ይጠ​ሉት ነበ​ርና፥ ይህ በእኛ ላይ ሊነ​ግሥ አን​ሻም ብለው አከ​ታ​ት​ለው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላኩ።</verse>
				<verse number="15">ከዚ​ህም በኋላ፤ መን​ግ​ሥ​ትን ይዞ በተ​መ​ለሰ ጊዜ እንደ አተ​ረፉ ያውቅ ዘንድ ምናን የሰ​ጣ​ቸ​ውን ብላ​ቴ​ኖ​ቹን እን​ዲ​ያ​መ​ጡ​አ​ቸው አዘዘ።</verse>
				<verse number="16">አን​ደ​ኛ​ውም መጥቶ፦ አቤቱ፥ ምና​ንህ ዐሥር ነበር፤ እነሆ ዐሥር ምናን አት​ር​ፌ​አ​ለሁ አለው።</verse>
				<verse number="17">ጌታ​ውም፦ መል​ካም፥ አንተ በጎ አገ​ል​ጋይ በጥ​ቂት የታ​መ​ንህ ስለ​ሆ​ንህ በብዙ ላይ እሾ​ም​ሃ​ለሁ፤ በዐ​ሥሩ ከተ​ሞች ላይ ተሾም አለው።</verse>
				<verse number="18">ሁለ​ተ​ኛ​ውም መጥቶ፦ አቤቱ፥ ምና​ንህ አም​ስት ነበር፤ አም​ስት አት​ር​ፌ​አ​ለሁ አለው።</verse>
				<verse number="19">እር​ሱ​ንም፦ አን​ተም በአ​ም​ስት ከተ​ሞች ተሾም አለው።</verse>
				<verse number="20">ሦስ​ተ​ኛ​ውም መጥቶ እን​ዲህ አለው፦ አቤቱ፥ በእኔ ዘንድ የነ​በ​ረ​ቺው ምና​ንህ እነ​ኋት፤ በጨ​ርቅ ጠቅ​ልዬ አኑ​ሬ​አት ነበር።</verse>
				<verse number="21">አንተ ያላ​ኖ​ር​ኸ​ውን የም​ት​ወ​ስድ፥ ያል​ዘ​ራ​ኸ​ውን የም​ታ​ጭድ፥ ያል​በ​ተ​ን​ኸ​ው​ንም የም​ት​ሰ​በ​ስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንህ ስለ​ማ​ው​ቅህ ፈር​ቼ​ሃ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="22">ጌታ​ውም እን​ዲህ አለው፦ አንተ ክፉ ሰነፍ አገ​ል​ጋይ፥ እኔ ያላ​ስ​ቀ​መ​ጥ​ሁ​ትን የም​ወ​ስድ፥ ያል​ዘ​ራ​ሁ​ትን የማ​ጭድ፥ ያል​በ​ተ​ን​ሁ​ት​ንም የም​ሰ​በ​ስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለ​ህን? እንደ ቃልህ እፈ​ር​ድ​ብ​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="23">ለምን ገን​ዘ​ቤን ወደ ለዋ​ጮች አላ​ስ​ገ​ባ​ህም? እኔም መጥቼ ከት​ርፉ ጋር በወ​ሰ​ድ​ሁት ነበር።</verse>
				<verse number="24">ከዚያ የቆ​ሙ​ት​ንም፦ ይህን ምናን ከእ​ርሱ ተቀ​ብ​ላ​ችሁ ዐሥር ምናን ላለው ስጡት አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">እነ​ር​ሱም አቤቱ፥ ዐሥር ምናን ያለው አይ​ደ​ለ​ምን? አሉት።</verse>
				<verse number="26">እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፦ ላለው ሁሉ ይሰ​ጡ​ታል፤ ይጨ​ም​ሩ​ለ​ታ​ልም፤ የሌ​ለ​ውን ግን ያን ያለ​ው​ንም ቢሆን ይወ​ስ​ዱ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="27">ነገር ግን እነ​ዚ​ያን ልነ​ግ​ሥ​ባ​ቸው ያል​ወ​ደ​ዱ​ትን ጠላ​ቶ​ችን ወደ​ዚህ አም​ጡና በፊቴ ውጉ​አ​ቸው።”</verse>
				<verse number="28">ይህ​ንም ተና​ግሮ ወደ ፊት ሄደ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወጣ።</verse>
				<verse number="29">ደብረ ዘይት ወደ​ሚ​ባል ተራራ አጠ​ገብ ወዳ​ሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታ​ንያ በቀ​ረበ ጊዜ፥ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሁለ​ቱን ላከ።</verse>
				<verse number="30">እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “በፊ​ታ​ችሁ ወደ አለ​ችው መን​ደር ሂዱ፤ ገብ​ታ​ች​ሁም ሰው ያል​ተ​ቀ​መ​ጠ​በት የታ​ሰረ ውር​ንጫ ታገ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ፈት​ታ​ች​ሁም አም​ጡ​ልኝ።</verse>
				<verse number="31">ለምን ትፈ​ቱ​ታ​ላ​ችሁ? የሚ​ላ​ችሁ ቢኖር ጌታው ይሻ​ዋል በሉ።”</verse>
				<verse number="32">የተ​ላ​ኩ​ትም ሄደው እንደ አላ​ቸው አገኙ።</verse>
				<verse number="33">ውር​ን​ጫ​ው​ንም ሲፈቱ ባለ​ቤ​ቶቹ “ውር​ን​ጫ​ውን ለምን ትፈ​ቱ​ታ​ላ​ችሁ?” አሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="34">እነ​ር​ሱም “ጌታው ይሻ​ዋል” አሉ።</verse>
				<verse number="35">ይዘ​ውም ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወሰ​ዱት፤ በው​ር​ን​ጫው ላይም ልብ​ሳ​ቸ​ውን ጭነው ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን በዚያ ላይ አስ​ቀ​መ​ጡት።</verse>
				<verse number="36">ሲሄ​ዱም በመ​ን​ገድ ልብ​ሳ​ቸ​ውን አነ​ጠፉ።</verse>
				<verse number="37">ወደ ደብረ ዘይት ዐቀ​በት መው​ረ​ጃም በደ​ረሱ ጊዜ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ በሙሉ ስለ አዩት ኀይል ሁሉ ደስ ይላ​ቸ​ውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በታ​ላቅ ቃል ያመ​ሰ​ግ​ኑት ዘንድ ጀመሩ።</verse>
				<verse number="38">እን​ዲህ እያሉ፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የሚ​መጣ ቡሩክ ነው፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ቡሩክ ነው፤ ሰላም በም​ድር፥ በአ​ር​ያ​ምም ክብር ይሁን።”</verse>
				<verse number="39">ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም በሕ​ዝቡ መካ​ከል፥ “መም​ህር ሆይ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ህን ገሥ​ጻ​ቸው” ያሉት ነበሩ።</verse>
				<verse number="40">እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እነ​ዚህ ዝም ቢሉ እኒህ ድን​ጋ​ዮች ይጮ​ሀሉ።”</verse>
				<verse number="41">በደ​ረሰ ጊዜም ከተ​ማ​ዪ​ቱን አይቶ አለ​ቀ​ሰ​ላት።</verse>
				<verse number="42">እን​ዲ​ህም አላት፥ “አን​ቺስ ብታ​ውቂ ሰላ​ምሽ ዛሬ ነበረ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ግን ከዐ​ይ​ኖ​ችሽ ተሰ​ወረ።</verse>
				<verse number="43">ጠላ​ቶ​ችሽ አን​ቺን የሚ​ከ​ቡ​በት ቀን ይመ​ጣል፤ ይከ​ት​ሙ​ብ​ሻል፤ ያስ​ጨ​ን​ቁ​ሻ​ልም፤ በአ​ራቱ ማዕ​ዘ​ንም ከብ​በው ይይ​ዙ​ሻል።</verse>
				<verse number="44">አን​ቺን ይጥ​ሉ​ሻል፤ ልጆ​ች​ሽ​ንም ከአ​ንቺ ጋር ይጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል፤ ድን​ጋ​ይ​ንም በደ​ን​ጋይ ላይ አይ​ተ​ዉ​ል​ሽም፤ የይ​ቅ​ር​ታ​ሽን ዘመን አላ​ወ​ቅ​ሽ​ምና።”</verse>
				<verse number="45">ወደ ቤተ መቅ​ደ​ስም ገብቶ በዚያ የሚ​ሸ​ጡ​ት​ንና የሚ​ገ​ዙ​ትን ሁሉ አስ​ወጣ፤ የለ​ዋ​ጮ​ች​ንም መደ​ር​ደ​ሪያ፥ የር​ግብ ሻጮ​ች​ንም ወን​በር ገለ​በጠ።</verse>
				<verse number="46">“ቤቴ የጸ​ሎት ቤት ይባ​ላል የሚል ጽሑፍ አለ፤ እና​ንተ ግን የሌ​ቦ​ችና የቀ​ማ​ኞች ዋሻ አደ​ረ​ጋ​ች​ሁት” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="47">ዘወ​ት​ርም በመ​ቅ​ደስ ያስ​ተ​ምር ነበር፤ የካ​ህ​ናት አለ​ቆች፥ ጻፎ​ችና የሕ​ዝብ ታላ​ላ​ቆ​ችም ሊገ​ድ​ሉት ይሹ ነበር።</verse>
				<verse number="48">ነገር ግን የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን አጡ፤ ሕዝቡ ሁሉ ትም​ህ​ር​ቱን በመ​ስ​ማት ይመ​ሰጡ ነበ​ርና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ በአ​ንድ ቀን ሕዝ​ቡን በመ​ቅ​ደስ ሲያ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው፥ ወን​ጌ​ል​ንም ሲነ​ግ​ራ​ቸው፥ የካ​ህ​ናት አለ​ቆች፥ ጻፎ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ተነ​ሡ​በት።</verse>
				<verse number="2">“ይህን በማን ሥል​ጣን ታደ​ር​ጋ​ለህ? ይህ​ንስ እን​ድ​ታ​ደ​ርግ ማን ፈቀ​ደ​ልህ? እስኪ ንገ​ረን” አሉት።</verse>
				<verse number="3">እር​ሱም መልሶ፥ “እኔም አን​ዲት ነገ​ርን እጠ​ይ​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ንገ​ሩኝ፤</verse>
				<verse number="4">የዮ​ሐ​ንስ ጥም​ቀት ከወ​ዴት ናት? ከሰ​ማይ ናትን? ወይስ ከሰው?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም እን​ዲህ ተባ​ባሉ፤ “ከሰ​ማይ ነው ብን​ለው ለምን አላ​መ​ና​ች​ሁ​ትም? ይለ​ናል።</verse>
				<verse number="6">ከሰው ነው ብን​ለ​ውም ሕዝቡ ሁሉ በድ​ን​ጋይ ይወ​ግ​ሩ​ናል፤ ሁሉም ዮሐ​ንስ ነቢይ እንደ ሆነ አም​ነ​ው​በ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="7">ከወ​ዴት እንደ ሆነች አና​ው​ቅም” ብለው መለ​ሱ​ለት።</verse>
				<verse number="8">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔም ይህን በማን ሥል​ጣን እን​ደ​ማ​ደ​ርግ አል​ነ​ግ​ራ​ች​ሁም” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ለሕ​ዝ​ቡም ይህን ምሳሌ ይመ​ስ​ል​ላ​ቸው ጀመረ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “አንድ ሰው ወይን ተከለ፤ መጭ​መ​ቂ​ያም አስ​ቈ​ፈረ፤ ግን​ብም ሠራ​ለት፤ ለገ​ባ​ሮ​ችም ሰጥቶ ወደ ሩቅ ሀገር ሄደ፤ ሳይ​መ​ለ​ስም ዘገየ።</verse>
				<verse number="10">የመ​ከሩ ወራት በሆነ ጊዜም ወደ ገባ​ሮቹ፥ ከወ​ይኑ ፍሬ ይል​ኩ​ለት ዘንድ አገ​ል​ጋ​ዩን ላከ፤ ገባ​ሮቹ ግን አገ​ል​ጋ​ዩን ደብ​ድ​በው ባዶ እጁን ሰደ​ዱት።</verse>
				<verse number="11">ዳግ​መ​ኛም ሌላ​ውን አገ​ል​ጋ​ዩን ላከ፤ እር​ሱ​ንም ደብ​ድ​በ​ውና አዋ​ር​ደው ባዶ እጁን ሰደ​ዱት።</verse>
				<verse number="12">ደግሞ ሦስ​ተ​ኛ​ውን አገ​ል​ጋ​ዩን ላከ፤ እር​ሱ​ንም አቍ​ስ​ለው ሰደ​ዱት።</verse>
				<verse number="13">የወ​ይኑ ባለ​ቤ​ትም፦ እን​ግ​ዲህ ምን ላድ​ርግ? ምና​ል​ባት እር​ሱን እንኳ አይ​ተው ያፍሩ እንደ ሆነ የም​ወ​ደ​ውን ልጄን ልላክ ብሎ ላከው።</verse>
				<verse number="14">ገባ​ሮ​ቹም ባዩት ጊዜ ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፥ እን​ግ​ደ​ለ​ውና ርስ​ቱን እን​ው​ሰድ ብለው ተማ​ከሩ።</verse>
				<verse number="15">ከወ​ይኑ ቦታም ወደ ውጭ አው​ጥ​ተው ገደ​ሉት።</verse>
				<verse number="16">የወ​ይኑ ባለ​ቤት በመጣ ጊዜ እን​ግ​ዲህ ምን ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል? ይመ​ጣል፤ እነ​ዚ​ያ​ንም ገባ​ሮች ይገ​ድ​ላ​ቸ​ዋል፤ ወይ​ኑ​ንም ለሌ​ሎች ገባ​ሮች ይሰ​ጣል፤” ቃሉ​ንም ሰም​ተው፥ “አይ​ሆ​ንም፤ እን​ዲህ አይ​ደ​ረ​ግም” አሉ።</verse>
				<verse number="17">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ተመ​ለ​ከ​ተና እን​ዲህ አላ​ቸው፤ “ግን​በ​ኞች የና​ቁ​አት ድን​ጋይ እር​ስዋ የማ​ዕ​ዘን ራስ ሆነች፥ የሚ​ለው ጽሑፍ ምን​ድ​ነው?</verse>
				<verse number="18">በዚ​ያች ድን​ጋይ ላይ የወ​ደቀ ሁሉ ይቀ​ጠ​ቀ​ጣል፤ እር​ስ​ዋም የወ​ደ​ቀ​ች​በ​ትን ታደ​ቅ​ቀ​ዋ​ለች።”</verse>
				<verse number="19">ያን ጊዜም የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ጻፎች ሊይ​ዙት ወደዱ፤ ይህን ስለ እነ​ርሱ እንደ መሰለ ዐው​ቀ​ዋ​ልና፤ ነገር ግን ሕዝ​ቡን ፈሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">ከእ​ነ​ር​ሱም ተለ​ይ​ተው ከሄዱ በኋላ፥ የሚ​ጠ​ባ​በ​ቁ​ትን አዘ​ጋ​ጁ​ለት፤ በአ​ነ​ጋ​ገ​ሩም ያስ​ቱት ዘንድ ወደ መኳ​ን​ን​ትና ወደ መሳ​ፍ​ንት አሳ​ል​ፈው ሊሰ​ጡት ራሳ​ቸ​ውን የሚ​ያ​መ​ጻ​ድቁ ሰላ​ዮ​ችን ወደ እርሱ ላኩ።</verse>
				<verse number="21">እነ​ር​ሱም እን​ዲህ ብለው ጠየ​ቁት፥ “መም​ህር ሆይ፥ አንተ እው​ነት እን​ደ​ም​ት​ና​ገ​ርና እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ምር፥ ፊት አይ​ተ​ህም እን​ደ​ማ​ታ​ዳላ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መን​ገድ በቀ​ጥታ እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ምር እና​ው​ቃ​ለን።</verse>
				<verse number="22">ለቄ​ሣር ግብር መስ​ጠት ይገ​ባል? ወይስ አይ​ገ​ባም?”</verse>
				<verse number="23">ተን​ኰ​ላ​ቸ​ው​ንም ዐውቆ፥ “ለምን ትፈ​ት​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ? ገን​ዘ​ቡን አሳ​ዩኝ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">አም​ጥ​ተ​ውም አሳ​ዩት፤ “መልኩ፥ ጽሕ​ፈ​ቱስ የማ​ነው?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “የቄ​ሣር ነው” ብለው መለ​ሱ​ለት።</verse>
				<verse number="25">እር​ሱም፥ “እን​ኪ​ያስ የቄ​ሣ​ርን ለቄ​ሣር፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጡ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት በአ​ነ​ጋ​ገሩ ማሳ​ሳት ተሳ​ና​ቸው፤ መል​ሱ​ንም አድ​ን​ቀው ዝም አሉ።</verse>
				<verse number="27">“ሙታን አይ​ነ​ሡም” ከሚሉ ከሰ​ዱ​ቃ​ው​ያ​ንም አን​ዳ​ንድ ሰዎች ወደ እርሱ መጡ።</verse>
				<verse number="28">እነ​ር​ሱም እን​ዲህ ብለው ጠየ​ቁት፥ “መም​ህር ሆይ፥ ሙሴ፦ ‘ወን​ድሙ ልጅ ሳይ​ወ​ልድ ሚስ​ቱን ትቶ የሞ​ተ​በት ሰው ቢኖር ወን​ድሙ ሚስ​ቱን አግ​ብቶ ለወ​ን​ድሙ ዘር ይተካ’ ሲል ጽፎ​ል​ናል።</verse>
				<verse number="29">እን​ግ​ዲህ ከእኛ ዘንድ ሰባት ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች ነበሩ፤ ታላቁ ሚስት አግ​ብቶ ልጅ ሳይ​ወ​ልድ ሞተ።</verse>
				<verse number="30">እን​ደ​ዚ​ሁም ሁለ​ተ​ኛው አገ​ባት፤ እር​ሱም ልጅ ሳይ​ወ​ልድ ሞተ፤</verse>
				<verse number="31">ሦስ​ተ​ኛ​ውም አገ​ባት፤ እን​ዲ​ሁም ሰባቱ ሁሉ አገ​ቡ​አት፤ ልጅ ሳይ​ወ​ል​ዱም ሞቱ።</verse>
				<verse number="32">ከሁ​ሉም በኋላ ያቺ ሴት ሞተች።</verse>
				<verse number="33">እን​ግ​ዲህ ሙታን በሚ​ነ​ሡ​በት ጊዜ ከእ​ነ​ርሱ ለማ​ን​ኛው ሚስት ትሆ​ና​ለች? ሰባ​ቱም ሁሉ አግ​ብ​ተ​ዋት ነበ​ርና።”</verse>
				<verse number="34">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የዚህ ዓለም ልጆች ያገ​ባሉ፥ ይጋ​ባ​ሉም፤ ይወ​ል​ዳሉ፥ ይዋ​ለ​ዳ​ሉም።</verse>
				<verse number="35">ያን ዓለ​ምና የሙ​ታ​ንን ትን​ሣኤ ሊወ​ርሱ የሚ​ገ​ባ​ቸው እነ​ዚያ ግን አያ​ገ​ቡም፤ አይ​ጋ​ቡም።</verse>
				<verse number="36">እን​ግ​ዲህ ወዲህ ሞት የለ​ባ​ቸ​ውም፤ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ናቸው እንጂ፤ የት​ን​ሣኤ ልጆ​ችም ስለ​ሆኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="37">ሙታን እን​ደ​ሚ​ነ​ሡስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ‘እኔ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ ነኝ’ ብሎ በቍ​ጥ​ቋ​ጦው ዘንድ እንደ አነ​ጋ​ገ​ረው ሙሴ ተና​ግ​ሮ​አል።</verse>
				<verse number="38">እን​ኪ​ያስ የሕ​ያ​ዋን አም​ላክ እንጂ የሙ​ታን አም​ላክ አይ​ደ​ለም፤ ሁሉም በእ​ርሱ ዘንድ ሕያ​ዋን ናቸ​ውና።”</verse>
				<verse number="39">ከጻ​ፎ​ችም ወገን የሆኑ ሰዎች፥ “መም​ህር ሆይ፥ መል​ካም ብለ​ሃል” ብለው መለሱ።</verse>
				<verse number="40">ከዚያ ወዲህ ግን ሊጠ​ይ​ቀው የደ​ፈረ ማንም የለም።</verse>
				<verse number="41">እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ክር​ስ​ቶ​ስን እን​ዴት የዳ​ዊት ልጅ ይሉ​ታል?</verse>
				<verse number="42">እርሱ ራሱ ዳዊት በመ​ዝ​ሙር መጽ​ሐፍ ‘ጌታ ጌታ​ዬን በቀኜ ተቀ​መጥ፥</verse>
				<verse number="43">ጠላ​ቶ​ች​ህን ከእ​ግ​ርህ ጫማ በታች እስከ አደ​ር​ጋ​ቸው ድረስ’ ብሏል።</verse>
				<verse number="44">እን​ግ​ዲህ እርሱ ራሱ ዳዊት ‘ጌታዬ’ ያለው እን​ዴት ልጁ ይሆ​ናል?”</verse>
				<verse number="45">ሕዝ​ቡም ሲሰሙ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን እን​ዲህ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="46">“ልብ​ሳ​ቸ​ውን አን​ዘ​ር​ፍ​ፈው ወዲያ ወዲህ ማለ​ትን ከሚሹ፥ በገ​በያ እጅ መነ​ሣ​ት​ንና በአ​ደ​ባ​ባይ ፊት ለፊት፥ በማ​ዕ​ድም ጊዜ በከ​በ​ሬታ መቀ​መጫ መቀ​መ​ጥን ከሚ​ወዱ ጻፎች ተጠ​በቁ።</verse>
				<verse number="47">የመ​በ​ለ​ቶ​ችን ገን​ዘብ የሚ​በሉ፥ ለም​ክ​ን​ያት ጸሎ​ት​ንም የሚ​ያ​ስ​ረ​ዝሙ እነ​ዚህ ታላቅ ፍር​ድን ይቀ​በ​ላሉ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">በሙ​ዳየ ምጽ​ዋቱ መባ​ቸ​ውን የሚ​ያ​ገቡ ባለ​ጠ​ጎ​ችን አየ።</verse>
				<verse number="2">አን​ዲት ድሃ መበ​ለ​ትም ሁለት መሐ​ለቅ ስታ​ስ​ገባ አየ።</verse>
				<verse number="3">እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይህቺ ድሃ መበ​ለት ከሁሉ ይልቅ አብ​ዝታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አገ​ባች።</verse>
				<verse number="4">እነ​ዚህ ሁሉ ከተ​ረ​ፋ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አግ​ብ​ተ​ዋ​ልና፤ ይህቺ ግን ከድ​ህ​ነቷ ያላ​ትን ጥሪ​ቷን ሁሉ አገ​ባች።”</verse>
				<verse number="5">ስለ ቤተ መቅ​ደ​ስም ድን​ጋዩ ያማረ ነው፥ አሠ​ራ​ሩም ያጌጠ ነው የሚ​ሉት ነበሩ።</verse>
				<verse number="6">እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ይህን ታያ​ላ​ች​ሁን? በእ​ዚህ ቦታ ድን​ጋይ በድ​ን​ጋይ ላይ የማ​ይ​ተ​ው​በ​ትና ሳይ​ፈ​ርስ የማ​ይ​ቀ​ር​በት ዘመን ይመ​ጣል።”</verse>
				<verse number="7">እነ​ር​ሱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ይህ መቼ ይደ​ረ​ጋል? ይህስ የሚ​ሆ​ን​በት ጊዜው፥ ምል​ክ​ቱስ ምን​ድን ነው?” ብለው ጠየ​ቁት።</verse>
				<verse number="8">እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ብዙ​ዎች እኔ ክር​ስ​ቶስ ነኝ፤ ጊዜ​ውም ደር​ሶ​አል እያሉ በስሜ ይመ​ጣ​ሉና እን​ዳ​ያ​ስ​ቱ​አ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ተከ​ት​ላ​ችሁ አት​ሂዱ።</verse>
				<verse number="9">ጦር​ነ​ት​ንና ጠብን፥ ክር​ክ​ር​ንም በሰ​ማ​ችሁ ጊዜ አት​ደ​ን​ግጡ፤ አስ​ቀ​ድሞ ይህ ይሆን ዘንድ ግድ ነውና፤ ነገር ግን ወዲ​ያው የሚ​ፈ​ጸም አይ​ደ​ለም።”</verse>
				<verse number="10">እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ሕዝብ በሕ​ዝብ ላይ፥ ነገ​ሥ​ታ​ትም በነ​ገ​ሥ​ታት ላይ ይነ​ሣሉ።</verse>
				<verse number="11">በየ​ሀ​ገሩ ታላቅ የም​ድር መነ​ዋ​ወ​ጥና ራብ፥ በሰ​ውም ላይ በሽ​ታና ፍር​ሀት ይመ​ጣል፤ በሰ​ማ​ይም ታላቅ ምል​ክት ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="12">ከዚ​ህም ሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ይይ​ዙ​አ​ች​ኋል፤ ወደ አደ​ባ​ባ​ዮ​ችም ይወ​ስ​ዱ​አ​ች​ኋል፤ ያሳ​ድ​ዱ​አ​ች​ኋል፤ ያስ​ሩ​አ​ች​ኋል፤ ስለ ስሜም ወደ ነገ​ሥ​ታ​ትና ወደ መሳ​ፍ​ንት ይወ​ስ​ዱ​አ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="13">ይህም በእ​ነ​ርሱ ላይ ምስ​ክር ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="14">ዕወቁ፤ የም​ት​ና​ገ​ሩ​ት​ንም በል​ባ​ችሁ አታ​ስቡ።</verse>
				<verse number="15">በእ​ና​ንተ ላይ የሚ​ነሡ ሊመ​ል​ሱ​ላ​ች​ሁና ሊከ​ራ​ከ​ሯ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ችሉ እኔ አፍ​ንና ጥበ​ብን እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">ወላ​ጆ​ቻ​ች​ሁና ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ፥ ወዳ​ጆ​ቻ​ች​ሁና ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ችሁ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​አ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="17">ሁሉም ስለ ስሜ ይጠ​ሉ​አ​ች​ኋል፤ ይገ​ድ​ሉ​አ​ች​ኋ​ልም።</verse>
				<verse number="18">ነገር ግን ከራስ ጠጕ​ራ​ችሁ አን​ዲቱ እንኳ አት​ጠ​ፋም።</verse>
				<verse number="19">በት​ዕ​ግ​ሥ​ታ​ች​ሁም ነፍ​ሳ​ች​ሁን ገን​ዘብ ታደ​ር​ጓ​ታ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="20">“ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ጭፍ​ሮች ከብ​በ​ዋት ባያ​ችሁ ጊዜ ጥፋቷ እንደ ደረሰ ዕወቁ።</verse>
				<verse number="21">ያን​ጊዜ በይ​ሁዳ ያሉ ወደ ተራራ ይሽሹ፤ በመ​ካ​ከ​ልዋ ያሉም ከእ​ር​ስዋ ይውጡ፤ በአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ችዋ ያሉም ወደ እር​ስዋ አይ​ግቡ።</verse>
				<verse number="22">በእ​ር​ስዋ ላይ የተ​ጻ​ፈው ሁሉ ይፈ​ጸም ዘንድ እር​ስ​ዋን የሚ​በ​ቀ​ሉ​በት ጊዜዋ ነውና።</verse>
				<verse number="23">ነገር ግን በዚያ ወራት ለፀ​ነ​ሱና ለሚ​ያ​ጠቡ ወዮ​ላ​ቸው፤ በም​ድር ላይ ጽኑ መከራ፥ በዚ​ህም ሕዝብ ላይ መቅ​ሠ​ፍት ይሆ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="24">በሰ​ይፍ ስለት ይወ​ድ​ቃሉ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ይማ​ረ​ካሉ፤ የአ​ሕ​ዛብ ጊዜ​ያ​ቸው እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ አሕ​ዛብ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ይረ​ግ​ጡ​አ​ታል።</verse>
				<verse number="25">“በፀ​ሐ​ይና በጨ​ረቃ፥ በከ​ዋ​ክ​ብ​ትም ላይ ምል​ክት ይሆ​ናል፤ በም​ድር ላይም አሕ​ዛብ ይጨ​ነ​ቃሉ፤ ከባ​ሕ​ሩና ከሞ​ገዱ ድምፅ የተ​ነ​ሣም ይሸ​በ​ራሉ።</verse>
				<verse number="26">በዓ​ለም ላይ ከሚ​መ​ጣው ፍር​ሀ​ትና ሽብር የተ​ነ​ሣም የሰ​ዎች ነፍስ ትዝ​ላ​ለች፤ ያን​ጊዜ የሰ​ማ​ያት ኀይል ይና​ወ​ጣ​ልና።</verse>
				<verse number="27">ያን​ጊ​ዜም በሰ​ማይ ደመና፥ በፍ​ጹም ኀይ​ልና ክብር ሲመጣ የሰ​ውን ልጅ ያዩ​ታል።</verse>
				<verse number="28">ይህም ሁሉ በሆነ ጊዜ ወደ ላይ አቅ​ን​ታ​ችሁ ተመ​ል​ከቱ፤ ራሳ​ች​ሁ​ንም አንሡ፤ የሚ​ያ​ድ​ና​ችሁ መጥ​ቶ​አ​ልና።”</verse>
				<verse number="29">ምሳ​ሌም መስሎ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በለ​ስ​ንና ዛፎ​ችን ሁሉ እዩ።</verse>
				<verse number="30">ለም​ል​መ​ውም ያያ​ች​ኋ​ቸው እንደ ሆነ መከር እንደ ደረሰ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="31">እን​ዲሁ እና​ን​ተም ይህ እንደ ሆነ ስታዩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እንደ ደረ​ሰች ዕወቁ።</verse>
				<verse number="32">እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይህ ሁሉ እስ​ኪ​ደ​ረግ ድረስ ይህቺ ትው​ልድ አታ​ል​ፍም።</verse>
				<verse number="33">ሰማ​ይና ምድር ያል​ፋል፤ ቃሌ ግን አያ​ል​ፍም።</verse>
				<verse number="34">“ራሳ​ች​ሁን ጠብቁ፤ በመ​ብ​ልና በመ​ጠጥ፥ በመ​ቀ​ማ​ጠ​ልና የዓ​ለ​ምን ኑሮ በማ​ሰብ ልባ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ፤ ያቺ ቀንም በድ​ን​ገት ትደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋ​ለች።</verse>
				<verse number="35">በም​ድር በሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ላይ እንደ ተዘ​ረ​ጋች ወጥ​መድ ትደ​ር​ሳ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="36">እን​ግ​ዲህ ከዚህ ከሚ​መ​ጣው ሁሉ በጸ​ሎ​ታ​ችሁ ማም​ለጥ እን​ድ​ት​ችሉ፥ በሰው ልጅ ፊትም እን​ድ​ት​ቆሙ ሁል​ጊዜ ትጉ።”</verse>
				<verse number="37">ቀን ቀን በመ​ቅ​ደስ ያስ​ተ​ምር ነበር፤ ሌሊት ግን ወጥቶ ደብረ ዘይት በሚ​ባ​ለው ተራራ ያድር ነበር።</verse>
				<verse number="38">ሕዝ​ቡም ሁሉ ቃሉን ሊሰሙ እርሱ ወዳ​ለ​በት ወደ መቅ​ደስ ማል​ደው ይሄዱ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">ፋሲ​ካም የሚ​ባ​ለው የቂጣ በዓል ቀረበ።</verse>
				<verse number="2">የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ጻፎ​ችም ሊገ​ድ​ሉት ይሹ ነበር፤ ነገር ግን ሕዝ​ቡን ይፈ​ሩ​አ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="3">ቍጥሩ ከዐ​ሥራ ሁለቱ በነ​በ​ረው በአ​ስ​ቆ​ሮቱ ይሁዳ ልብ ሰይ​ጣን አደረ።</verse>
				<verse number="4">ሄዶም ከካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ከታ​ላ​ላ​ቆች ጋር እር​ሱን አሳ​ልፎ እን​ዲ​ሰ​ጣ​ቸው ተነ​ጋ​ገረ።</verse>
				<verse number="5">ደስ ብሏ​ቸ​ውም ሠላሳ ብር ሊሰ​ጡት ተስ​ማሙ።</verse>
				<verse number="6">እር​ሱም እሺ አለ፤ ሰው ሳይ​ኖ​ርም እር​ሱን አሳ​ልፎ ሊሰ​ጣ​ቸው ምቹ ጊዜ ይሻ ነበር።</verse>
				<verse number="7">የፋ​ሲ​ካን በግ የሚ​ያ​ር​ዱ​ባት የቂጣ በዓ​ልም ደረ​ሰች።</verse>
				<verse number="8">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ጴጥ​ሮ​ስ​ንና ዮሐ​ን​ስን፥ “ሂዱና የም​ን​በ​ላ​ውን የፋ​ሲካ በግ አዘ​ጋ​ጁ​ልን” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">እነ​ር​ሱም፥ “ወዴት ልና​ዘ​ጋ​ጅ​ልህ ትወ​ዳ​ለህ?” አሉት።</verse>
				<verse number="10">እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ወደ ከተማ በገ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ የውኃ ማድጋ የተ​ሸ​ከመ ሰው ታገ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ወደ​ሚ​ገ​ባ​በ​ትም ቤት እር​ሱን ተከ​ተ​ሉት።</verse>
				<verse number="11">የዚ​ያን ቤት ጌታ፦ መም​ህር ከደቀ መዛ​ሙ​ርቴ ጋር የፋ​ሲ​ካን በግ የም​በ​ላ​በት ቤት ወዴት ነው? ብሎ​ሃል በሉት።</verse>
				<verse number="12">እር​ሱም በሰ​ገ​ነት ላይ የተ​ነ​ጠፈ ታላቅ አዳ​ራሽ ያሳ​ያ​ች​ኋል፤ በዚያ አዘ​ጋ​ጁ​ልን።”</verse>
				<verse number="13">በሄ​ዱም ጊዜ እን​ዳ​ላ​ቸው አገኙ፤ የፋ​ሲ​ካ​ው​ንም በግ አዘ​ጋጁ።</verse>
				<verse number="14">ሰዓ​ቱም በደ​ረሰ ጊዜ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በማ​ዕድ ተቀ​መጠ፤ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ከእ​ርሱ ጋር ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="15">እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ከመ​ከ​ራዬ አስ​ቀ​ድሞ ይህን ፋሲካ ከእ​ና​ንተ ጋር ልበላ እጅግ ወደ​ድሁ።</verse>
				<verse number="16">ነገር ግን፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ እን​ግ​ዲህ ከእ​ርሱ እን​ደ​ማ​ል​በላ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">ጽዋ​ው​ንም ተቀ​ብሎ አመ​ሰ​ገነ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህን እንኩ ሁላ​ች​ሁም ተካ​ፈ​ሉት።</verse>
				<verse number="18">እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እስ​ክ​ት​መጣ ድረስ፤ እን​ግ​ዲህ ወዲህ ከዚህ የወ​ይን ፍሬ አል​ጠ​ጣም።”</verse>
				<verse number="19">ኅብ​ስ​ቱ​ንም አነሣ፤ አመ​ስ​ገነ፤ ፈት​ቶም ሰጣ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ስለ እና​ንተ ቤዛ ሆኖ የሚ​ሰጥ ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህ​ንም ለመ​ታ​ሰ​ቢ​ያዬ አድ​ር​ጉት፤”</verse>
				<verse number="20">እን​ዲ​ሁም ከእ​ራት በኋላ ጽዋ​ዉን አን​ሥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ይህ ጽዋ ስለ እና​ንተ በሚ​ፈ​ስ​ሰው ደሜ የሚ​ሆን አዲስ ኪዳን ነው።</verse>
				<verse number="21">“ነገር ግን አሳ​ልፎ የሚ​ሰ​ጠኝ ሰው እጅ እነሆ፥ በማ​ዕድ ከእኔ ጋር ነው።</verse>
				<verse number="22">የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄ​ዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ በእጁ ለሚ​ሰ​ጥ​በት ለዚያ ሰው ወዮ​ለት።”</verse>
				<verse number="23">ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ከእ​ነ​ርሱ ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ ማን እንደ ሆነ እርስ በር​ሳ​ቸው ተነ​ጋ​ገሩ።</verse>
				<verse number="24">ከዚ​ህም በኋላ ከእ​ነ​ርሱ ማን እን​ደ​ሚ​በ​ልጥ እርስ በር​ሳ​ቸው ተከ​ራ​ከሩ።</verse>
				<verse number="25">እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አሕ​ዛ​ብን ንጉ​ሦ​ቻ​ቸው ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ በላ​ያ​ቸ​ውም ሥል​ጣን ያላ​ቸው ቸር​ነት አድ​ራ​ጊ​ዎች ይባ​ላሉ።</verse>
				<verse number="26">ለእ​ና​ንተ ግን እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ታላቁ እንደ ታናሽ ይሁ​ና​ችሁ፤ አለ​ቃ​ውም እንደ አገ​ል​ጋይ ይሁን።</verse>
				<verse number="27">የሚ​በ​ልጥ ማን​ኛው ነው? በማ​ዕድ ላይ የተ​ቀ​መ​ጠው ነው? ወይስ የሚ​ላ​ላ​ከው? በማ​ዕድ ላይ የተ​ቀ​መ​ጠው አይ​ደ​ለ​ምን? እነሆ፥ እኔ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እንደ አገ​ል​ጋይ ነኝ።</verse>
				<verse number="28">ነገር ግን ስለ እኔ የታ​ገ​ሣ​ችሁ እና​ንተ በመ​ከ​ራዬ ከእኔ ጋር ናችሁ።</verse>
				<verse number="29">አባቴ ለእኔ እንደ ሰጠኝ፥ እኔም ለእ​ና​ንተ መን​ግ​ሥ​ትን አዘ​ጋ​ጅ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="30">በመ​ን​ግ​ሥቴ በማ​ዕዴ ትበ​ሉና ትጠጡ ዘንድ፥ በወ​ን​በ​ሮ​ችም ተቀ​ም​ጣ​ችሁ በዐ​ሥራ ሁለቱ ነገደ እስ​ራ​ኤል ትፈ​ርዱ ዘንድ።”</verse>
				<verse number="31">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ስም​ዖን፥ ስም​ዖን ሆይ፥ ሰይ​ጣን እንደ አጃ ሊያ​በ​ጥ​ራ​ችሁ አሁን ልመ​ናን ለመነ።</verse>
				<verse number="32">እኔ ግን ሃይ​ማ​ኖ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ደ​ክም ስለ እና​ንተ ጸለ​ይሁ፤ አን​ተም ተመ​ል​ሰህ ወን​ድ​ሞ​ች​ህን አጽ​ና​ቸው።”</verse>
				<verse number="33">እር​ሱም፥ “አቤቱ፥ እኔ ለመ​ታ​ሰ​ርም ቢሆን፥ ለሞ​ትም ቢሆን እንኳ ከአ​ንተ ጋራ ለመ​ሄድ የተ​ዘ​ጋ​ጀሁ ነኝ” አለው።</verse>
				<verse number="34">እርሱ ግን፥ “ጴጥ​ሮስ ሆይ፥ እል​ሃ​ለሁ፥ ዛሬ ዶሮ ሳይ​ጮኽ እን​ደ​ማ​ታ​ው​ቀኝ ሦስት ጊዜ ትክ​ደ​ኛ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="35">ደግ​ሞም፥ “ያለ ስልቻ፥ ያለ ከረ​ጢ​ትና ያለ ጫማ በላ​ክ​ኋ​ችሁ ጊዜ በውኑ የተ​ቸ​ገ​ራ​ች​ሁት ነገር ነበ​ርን?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “የለም” አሉት።</verse>
				<verse number="36">እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አሁን ግን ኮሮጆ ያለው ኮሮ​ጆ​ውን ይያዝ፤ ከረ​ጢ​ትም ያለው እን​ዲሁ ያድ​ርግ፤ ሰይፍ የሌ​ለ​ውም ልብ​ሱን ሸጦ ሰይፍ ይግዛ።</verse>
				<verse number="37">እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ከኃ​ጥ​ኣን ጋር ተቈ​ጠረ ተብሎ የተ​ጻ​ፈው በእኔ ይደ​ር​ሳል፤ ስለ እኔ የተ​ጻ​ፈ​ውም ሁሉ ይፈ​ጸ​ማል።”</verse>
				<verse number="38">እነ​ር​ሱም፥ “አቤቱ፥ እነሆ፥ እዚህ በእኛ ዘንድ ሁለት ሰይ​ፎች አሉ” አሉት፤ እር​ሱም፥ “እን​ግ​ዲ​ያስ ይበ​ቃ​ች​ኋል” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="39">ወጥ​ቶም እን​ዳ​ስ​ለ​መ​ደው ይጸ​ልይ ዘንድ ወደ ደብረ ዘይት ሄደ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ተከ​ተ​ሉት።</verse>
				<verse number="40">ከዚ​ያም ደርሶ፥ “ወደ መከራ እን​ዳ​ት​ገቡ ጸልዩ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="41">የድ​ን​ጋይ ውር​ወራ ያህ​ልም ከእ​ነ​ርሱ ፈቀቅ ብሎ እየ​ሰ​ገደ ጸለየ።</verse>
				<verse number="42">እን​ዲ​ህም አለ፥ “አባት ሆይ፥ ብት​ፈ​ቅ​ድስ ይህን ጽዋ ከእኔ አሳ​ል​ፈው፤ ነገር ግን የአ​ንተ ፈቃድ ይሁን እንጂ የእኔ ፈቃድ አይ​ሁን።”</verse>
				<verse number="43">የሚ​ያ​በ​ረ​ታ​ታው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም ከሰ​ማይ ታየው።</verse>
				<verse number="44">ፈራ፤ መላ​ል​ሶም ጸለየ፤ ላቡም በም​ድር ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ እንደ ደም ነጠ​ብ​ጣብ ሆነ።</verse>
				<verse number="45">ከሚ​ጸ​ል​ይ​በ​ትም ተነ​ሥቶ ወደ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሄደ፤ ከኀ​ዘ​ንም የተ​ነሣ ተኝ​ተው አገ​ኛ​ቸው።</verse>
				<verse number="46">“ስለ ምን ትተ​ኛ​ላ​ችሁ? ወደ ፈተና እን​ዳ​ት​ገቡ ተነ​ሡና ጸልዩ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="47">ይህ​ንም ሲነ​ግ​ራ​ቸው ሕዝቡ ደረሱ፤ ከዐ​ሥራ ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ አንዱ ይሁ​ዳም ይመ​ራ​ቸው ነበር፤ ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ቀርቦ ሳመው፤ የሰ​ጣ​ቸ​ውም ምል​ክት ይህ ነበር፤ “የም​ስ​መው እርሱ ነውና እር​ሱን አጽ​ን​ታ​ችሁ ያዙት” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="48">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይሁ​ዳን፥ “በመ​ሳም የሰ​ውን ልጅ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጠ​ዋ​ለ​ህን?” አለው።</verse>
				<verse number="49">አብ​ረ​ውት የነ​በ​ሩ​ትም የሆ​ነ​ውን ባዩ ጊዜ፥ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን፥ “አቤቱ፥ በሰ​ይፍ ልን​መ​ታ​ቸው ትፈ​ቅ​ዳ​ለ​ህን?” አሉት።</verse>
				<verse number="50">ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ የሊቀ ካህ​ና​ቱን አገ​ል​ጋይ መታው፤ ቀኝ ጆሮ​ው​ንም ቈረ​ጠው።</verse>
				<verse number="51">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ይህ​ንስ ተው” አለ፤ ወዲ​ያ​ውም ጆሮ​ውን ዳስሶ አዳ​ነው።</verse>
				<verse number="52">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሊይ​ዙት ወደ እርሱ የመ​ጡ​ትን የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችን፥ የቤተ መቅ​ደስ ሹሞ​ች​ንና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሌባን እን​ደ​ም​ት​ይዙ በሰ​ይ​ፍና በጎ​መድ ልት​ይ​ዙኝ መጣ​ች​ሁን?</verse>
				<verse number="53">ዘወ​ት​ርም ከእ​ና​ንተ ጋር በቤተ መቅ​ደስ ስኖር እጃ​ች​ሁን እንኳ አል​ዘ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ብ​ኝም፤ ነገር ግን ጊዜ​ያ​ችሁ ይህ ነው፤ የጨ​ለ​ማው አበ​ጋ​ዝም ሥል​ጣኑ ይህ ነው።”</verse>
				<verse number="54">ይዘ​ውም ወደ ሊቀ ካህ​ናቱ ቤት ወሰ​ዱት፤ ጴጥ​ሮ​ስም ከሩቅ ይከ​ተ​ለው ነበር።</verse>
				<verse number="55">በግ​ቢ​ውም ውስጥ እሳት አን​ድ​ደው ተቀ​መጡ፤ ጴጥ​ሮ​ስም አብ​ሮ​አ​ቸው በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="56">በእ​ሳ​ቱም ብር​ሃን በኩል ተቀ​ምጦ ሳለ አን​ዲት ብላ​ቴና አየ​ችው፤ እርሱ መሆ​ኑ​ንም ለየ​ች​ውና፥ “ይህም ከእ​ርሱ ጋር ነበር” አለች።</verse>
				<verse number="57">እርሱ ግን፥ “ሴትዮ! የም​ት​ዪ​ውን አላ​ው​ቅም” ብሎ ካደ።</verse>
				<verse number="58">ከጥ​ቂት ጊዜም በኋላ ሌላ ሰው አየ​ውና፥ “አን​ተም ከእ​ነ​ርሱ ወገን ነህ” አለው፤ ጴጥ​ሮስ ግን፥ “አንተ ሰው! እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም” አለው።</verse>
				<verse number="59">አን​ዲት ሰዓት ያህ​ልም ቈይቶ አንድ ሌላ ሰው፥ “ይህም በእ​ው​ነት ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ሰው​የ​ውም የገ​ሊላ ሰው ነው” ብሎ አስ​ጨ​ነ​ቀው።</verse>
				<verse number="60">ጴጥ​ሮስ ግን፥ “አንተ ሰው! የም​ት​ለ​ውን አላ​ው​ቅም” አለው፤ እር​ሱም ይህን ሲና​ገር ያን​ጊዜ ዶሮ ጮኸ።</verse>
				<verse number="61">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዘወር ብሎ ጴጥ​ሮ​ስን አየው፤ ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ዛሬ ዶሮ ሳይ​ጮኽ ሦስት ጊዜ ትክ​ደ​ኛ​ለህ” ያለ​ውን የጌ​ታ​ች​ንን ቃል ዐሰበ።</verse>
				<verse number="62">ጴጥ​ሮ​ስም ወደ ውጭ ወጥቶ መራራ ልቅ​ሶን አለ​ቀሰ።</verse>
				<verse number="63">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ይዘ​ውት የነ​በ​ሩት ሰዎ​ችም ይዘ​ባ​በ​ቱ​በ​ትና ይደ​በ​ድ​ቡት ነበር።</verse>
				<verse number="64">ሸፍ​ነ​ውም ፊቱን በጥፊ ይመ​ቱት ነበር፤ “ፊት​ህን በጥፊ የመ​ታህ ማነው? ንገ​ረን” እያ​ሉም ይጠ​ይ​ቁት ነበር።</verse>
				<verse number="65">ሌላም ብዙ ነገር እየ​ተ​ሳ​ደቡ በእ​ርሱ ላይ ይና​ገሩ ነበር።</verse>
				<verse number="66">በነ​ጋም ጊዜ፥ የካ​ህ​ናት አለ​ቆች፥ ጻፎ​ችና የሕ​ዝቡ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ተሰ​ብ​ስ​በው ወደ ሸን​ጎ​አ​ቸው ወሰ​ዱት።</verse>
				<verse number="67">“አንተ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆንህ በግ​ልጥ ንገ​ረን” አሉት፤ እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ብነ​ግ​ራ​ች​ሁም አታ​ም​ኑ​ኝም።</verse>
				<verse number="68">ብጠ​ይ​ቃ​ች​ሁም አት​መ​ል​ሱ​ል​ኝም፤ ወይም አት​ተ​ዉ​ኝም።</verse>
				<verse number="69">ነገር ግን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ቀኝ ይቀ​መ​ጣል።”</verse>
				<verse number="70">ሁሉም፥ “እን​ግ​ዲ​ያስ አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ነህን?” አሉት፤ እር​ሱም፥ “እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆንሁ እና​ንተ ትላ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="71">እነ​ር​ሱም፥ “ስለ እርሱ ምን ምስ​ክር እን​ሻ​ለን? እኛ ራሳ​ችን ሲና​ገር ሰም​ተ​ናል” አሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="23">
				<verse number="1">ሁሉም በሙሉ ተነ​ሥ​ተው ወደ ጲላ​ጦስ ወሰ​ዱት።</verse>
				<verse number="2">እን​ዲ​ህም እያሉ ይከ​ስ​ሱት ጀመር፥ “ይህ ሰው ለቄ​ሣር ግብር እን​ዳ​ይ​ሰጡ ሲከ​ለ​ክ​ልና ሕዝ​ቡን ሲያ​ሳ​ምፅ፥ ራሱ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ክር​ስ​ቶ​ስን ሲያ​ደ​ርግ አገ​ኘ​ነው።”</verse>
				<verse number="3">ጲላ​ጦ​ስም፥ “አንተ የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ ነህን?” ብሎ ጠየ​ቀው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ እንደ ሆንሁ አንተ አልህ” አለው።</verse>
				<verse number="4">ጲላ​ጦ​ስም ለካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ለሕ​ዝቡ፥ “በዚህ ሰው ላይ ያገ​ኘ​ሁት አን​ድስ እንኳ በደል የለም” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">ሕዝ​ቡም፥ “ከገ​ሊላ ጀምሮ እስ​ከ​ዚህ ድረስ በመ​ላው ይሁዳ እያ​ስ​ተ​ማረ ሕዝ​ቡን ያው​ካል” እያሉ አጽ​ን​ተው ጮኹ።</verse>
				<verse number="6">ጲላ​ጦ​ስም “ገሊላ” ሲሉ ሰምቶ፤ ሰው​የዉ ገሊ​ላዊ እንደ ሆነ የገ​ሊ​ላን ሰዎች ጠየቀ።</verse>
				<verse number="7">ከሄ​ሮ​ድስ ግዛ​ትም ውስጥ መሆ​ኑን ዐውቆ ወደ ሄሮ​ድስ ላከው፤ ሄሮ​ድስ በዚያ ወራት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="8">ሄሮ​ድ​ስም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ባየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ዜና​ውን ስለ​ሚ​ሰማ ከረ​ጅም ጊዜ ጀምሮ ሊያ​የው ይሻ ነበ​ርና፤ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ው​ንም ተአ​ም​ራት ሊያይ ይመኝ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="9">በብዙ ነገ​ርም መረ​መ​ረው፤ እርሱ ግን አን​ድስ እንኳ አል​መ​ለ​ሰ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="10">የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ጻፎ​ችም ቆመው በብዙ ያሳ​ጡት ነበር።</verse>
				<verse number="11">ሄሮ​ድ​ስም ከሠ​ራ​ዊቱ ጋር አቃ​ለ​ለው፤ አፌ​ዘ​በ​ትም፤ የሚ​ያ​ን​ፀ​ባ​ርቅ ልብ​ስም አል​ብሶ ወደ ጲላ​ጦስ መልሶ ሰደ​ደው።</verse>
				<verse number="12">በዚ​ያም ቀን ሄሮ​ድ​ስና ጲላ​ጦስ ተስ​ማሙ፤ ቀድሞ ጥል ነበ​ራ​ቸ​ውና።</verse>
				<verse number="13">ጲላ​ጦ​ስም የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ች​ንና መኳ​ን​ን​ቱን፥ ሕዝ​ቡ​ንም ጠራ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ይህን ሰው ሕዝ​ብን ያሳ​ም​ፃል ብላ​ችሁ ወደ እኔ አመ​ጣ​ች​ሁት፤ በፊ​ታ​ች​ሁም እነሆ፥ መረ​መ​ር​ሁት፤ ግን እና​ንተ ካቀ​ረ​ባ​ች​ሁት ክስ በዚህ ሰው ላይ ያገ​ኘ​ሁት አን​ዳች በደል የለም።</verse>
				<verse number="15">ወደ ሄሮ​ድ​ስም ሰድ​ጃ​ችሁ ነበር፤ እር​ሱም ምንም ስላ​ላ​ገ​ኘ​በት ወደ እኛ መል​ሶ​ታል፤ ለሞ​ትም የሚ​ያ​በቃ ያደ​ረ​ገው ነገር የለም።</verse>
				<verse number="16">እነሆ፥ እኔም እን​ግ​ዲህ ገርፌ ልተ​ወው” አለ።</verse>
				<verse number="17">በየ​በ​ዓ​ሉም ከእ​ስ​ረ​ኞች አንድ ሊፈ​ታ​ላ​ቸው ልማድ ነበር።</verse>
				<verse number="18">ሁሉም በሙሉ፥ “ይህን አስ​ወ​ግ​ደው፥ ስቀ​ለ​ውም፥ በር​ባ​ንን ግን ፍታ​ልን” ብለው ጮሁ።</verse>
				<verse number="19">ያ በር​ባን ግን በከ​ተማ ሁከት ያደ​ረ​ገና ነፍስ በመ​ግ​ደል የታ​ሰረ ነበር።</verse>
				<verse number="20">ጲላ​ጦ​ስም ኢየ​ሱ​ስን ሊፈ​ታው ወድዶ፥ “ ኢየ​ሱ​ስን ልፈ​ታ​ላ​ችሁ ትወ​ዳ​ላ​ች​ሁን?” ብሎ እንደ ገና ተና​ገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">እነ​ርሱ ግን፥ “ስቀ​ለው! ስቀ​ለው!” እያሉ ይጮሁ ነበር።</verse>
				<verse number="22">ጲላ​ጦ​ስም ለሦ​ስ​ተኛ ጊዜ፥ “ምን ክፉ ነገር አደ​ረገ? እነሆ፥ ለሞት የሚ​ያ​በቃ ምክ​ን​ያት አላ​ገ​ኘ​ሁ​በ​ትም፤ እን​ኪ​ያስ ልግ​ረ​ፈ​ውና ልተ​ወው” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">እን​ዲ​ሰ​ቅ​ሉ​ትም ቃላ​ቸ​ውን ከፍ አድ​ር​ገው እየ​ጮሁ ለመኑ፤ ጩኸ​ታ​ቸ​ውና የካ​ህ​ናት አለ​ቆች ድም​ፅም በረታ።</verse>
				<verse number="24">ጲላ​ጦ​ስም የለ​መ​ኑት ይሆ​ን​ላ​ቸው ዘንድ ፈረ​ደ​በት።</verse>
				<verse number="25">ያን የለ​መ​ኑ​ትን፥ ነፍስ በመ​ግ​ደ​ልና ሁከት በማ​ድ​ረግ የታ​ሰ​ረ​ው​ንም ሰው ፈታ​ላ​ቸው፤ ኢየ​ሱ​ስን ግን ለፈ​ቃ​ዳ​ቸው አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">በወ​ሰ​ዱ​ትም ጊዜ የቀ​ሬና ሰው ስም​ዖ​ንን ከዱር ሲመ​ለስ ያዙት፤ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱ​ስም በስ​ተ​ኋላ መስ​ቀ​ሉን አሸ​ከ​ሙት።</verse>
				<verse number="27">ብዙ ሰዎ​ችም ተከ​ተ​ሉት፤ ሴቶ​ችም “ዋይ ዋይ” እያሉ ያዝ​ኑ​ለ​ትና ያለ​ቅ​ሱ​ለት ነበሩ።</verse>
				<verse number="28">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መለስ ብሎ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ልጆች ሆይ፥ ለራ​ሳ​ች​ሁና ለል​ጆ​ቻ​ችሁ አል​ቅሱ እንጂ ለእ​ኔስ አታ​ል​ቅ​ሱ​ልኝ።</verse>
				<verse number="29">መካ​ኖች፥ ያል​ወ​ለዱ ማኅ​ፀ​ኖ​ችና ያላ​ጠቡ ጡቶ​ችም የተ​መ​ሰ​ገኑ ናቸው የሚ​ሉ​በት ወራት ይመ​ጣ​ልና።</verse>
				<verse number="30">ያን​ጊ​ዜም ተራ​ሮ​ችን ‘በላ​ያ​ችን ውደቁ፤ ኮረ​ብ​ቶ​ች​ንም ሰው​ሩን’ ይሉ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="31">በዚህ ርጥብ ዕን​ጨት እን​ዲህ ያደ​ረጉ በደ​ረ​ቁማ እን​ዴት ይሆን?”</verse>
				<verse number="32">ሌሎች ሁለት ወን​በ​ዴ​ዎ​ች​ንም ከእ​ርሱ ጋር ሊሰ​ቅሉ ወሰዱ።</verse>
				<verse number="33">ቀራ​ንዮ ወደ​ሚ​ባ​ለው ቦታ በደ​ረሱ ጊዜም፥ በዚያ ሰቀ​ሉት፤ እነ​ዚ​ያ​ንም ሁለት ወን​በ​ዴ​ዎች አን​ዱን በቀኙ አን​ዱ​ንም በግ​ራው ሰቀሉ።</verse>
				<verse number="34">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አባት ሆይ፥ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ኣያ​ው​ቁ​ምና ይቅር በላ​ቸው” አለ፤ በል​ብ​ሱም ላይ ዕጣ ተጣ​ጣ​ሉና ተካ​ፈሉ።</verse>
				<verse number="35">ሕዝ​ቡም ቆመው ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ አለ​ቆ​ችም፥ “ሌሎ​ችን አዳነ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ረጠ ክር​ስ​ቶስ ከሆነ ራሱን ያድን” እያሉ ያፌ​ዙ​በት ነበር።</verse>
				<verse number="36">ጭፍ​ሮ​ችም ይዘ​ብ​ቱ​በት ነበር፤ ወደ እር​ሱም ቀር​በው ሆም​ጣጤ አመ​ጡ​ለት።</verse>
				<verse number="37">እን​ዲ​ህም ይሉት ነበር፥ “አንተ የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ ከሆ​ን​ህስ ራስ​ህን አድን።”</verse>
				<verse number="38">በራ​ስ​ጌ​ውም ደብ​ዳቤ ጻፉ፤ ጽሕ​ፈ​ቱም በሮ​ማ​ይ​ስጥ፥ በጽ​ር​ዕና በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ሆኖ “የአ​ይ​ሁድ ንጉ​ሣ​ቸው ይህ ነው” የሚል ነበር።</verse>
				<verse number="39">አብ​ረው ተሰ​ቅ​ለው ከነ​በ​ሩት አንዱ ወን​በዴ፥ “አን​ተስ ክር​ስ​ቶስ ከሆ​ንህ ራስ​ህን አድን፤ እኛ​ንም አድ​ነን” ብሎ ተሳ​ደበ።</verse>
				<verse number="40">ጓደ​ኛ​ውም መልሶ ገሠ​ጸው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “አንተ በዚህ ፍርድ ውስጥ ሳለህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክ​ህን አት​ፈ​ራ​ው​ምን?</verse>
				<verse number="41">በእ​ኛስ በሚ​ገባ ተፈ​ር​ዶ​ብ​ናል፤ እንደ ሥራ​ች​ንም ፍዳ​ች​ንን ተቀ​በ​ልን፤ ይህ ግን ምንም የሠ​ራው ክፉ ሥራ የለም።”</verse>
				<verse number="42">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም፥ “አቤቱ፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ትህ በመ​ጣህ ጊዜ ዐስ​በኝ” አለው።</verse>
				<verse number="43">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እው​ነት እል​ሃ​ለሁ፥ ዛሬ በገ​ነት ከእኔ ጋር ትሆ​ና​ለህ።”</verse>
				<verse number="44">ቀትር በሆነ ጊዜም በስ​ድ​ስት ሰዓት ፀሐይ ጨለመ፤ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረ​ስም ዓለም ሁሉ ጨለማ ሆነ።</verse>
				<verse number="45">ፀሐ​ዩም በጨ​ለመ ጊዜ የቤተ መቅ​ደሱ መጋ​ረጃ ከላይ እስከ ታች ከመ​ካ​ከሉ ተቀ​ደደ።</verse>
				<verse number="46">ያን​ጊ​ዜም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ፥ “አባት ሆይ፥ ነፍ​ሴን በአ​ንተ እጅ አደራ እሰ​ጣ​ለሁ” ብሎ ጮኸ፤ ይህ​ንም ብሎ ነፍ​ሱን ሰጠ።</verse>
				<verse number="47">የመቶ አለ​ቃ​ውም የሆ​ነ​ውን ነገር አይቶ፥ “ይህ ሰው በእ​ው​ነት ጻድቅ ነበረ”ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ነው።</verse>
				<verse number="48">ይህ​ንም ለማ​የት ተሰ​ብ​ስ​በው የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ የሆ​ነ​ውን ባዩ ጊዜ፥ ደረ​ታ​ቸ​ውን እየ​መቱ ወደ ቤታ​ቸው ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="49">የሚ​ያ​ው​ቁት ሁሉና ከገ​ሊላ ጀምሮ የተ​ከ​ተ​ሉ​ትም ሴቶች በሩቁ ቆመው ይህን ያዩ ነበር።</verse>
				<verse number="50">እነሆ፥ በጎና ጻድቅ ሰው፥ የሸ​ንጎ አማ​ካ​ሪም የሆነ ዮሴፍ የሚ​ባል ሰው መጣ።</verse>
				<verse number="51">እር​ሱም በአ​ይ​ሁድ በም​ክ​ራ​ቸ​ውና በሥ​ራ​ቸው አል​ተ​ባ​በ​ረም ነበር፤ ሀገ​ሩም የይ​ሁዳ ዕጣ የሚ​ሆን አር​ማ​ት​ያስ ነበር፤ እር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ተስፋ ያደ​ርግ ነበር።</verse>
				<verse number="52">ወደ ጲላ​ጦ​ስም ሄዶ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ሥጋ ለመነ።</verse>
				<verse number="53">ሥጋ​ው​ንም አው​ርዶ በበ​ፍታ ገነ​ዘው፤ ማንም ባል​ተ​ቀ​በ​ረ​በት፥ ከድ​ን​ጋ​ይም በተ​ፈ​ለ​ፈለ መቃ​ብር ቀበ​ረው፤ ታላቅ ድን​ጋ​ይም አን​ከ​ባ​ልሎ መቃ​ብ​ሩን ገጥሞ ሄደ።</verse>
				<verse number="54">ያም ቀን የሰ​ን​በት መግ​ቢያ ዐርብ ነበር።</verse>
				<verse number="55">ከገ​ሊ​ላም ከእ​ርሱ ጋር የመጡ ሁለት ሴቶች ተከ​ት​ለው፥ መቃ​ብ​ሩን፥ ሥጋ​ው​ንም እን​ዴት እን​ዳ​ኖ​ሩት አዩ። ተመ​ል​ሰ​ውም ሽቱና ዘይት አዘ​ጋጁ፤ ነገር ግን በሰ​ን​በት አል​ሄ​ዱም፤ ሕጋ​ቸው እን​ዲህ ነበ​ርና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="24">
				<verse number="1">ከሳ​ም​ን​ቱም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዪቱ ቀን ያዘ​ጋ​ጁ​ትን ሽቶ ይዘው እጅግ ማል​ደው ወደ መቃ​ብሩ ሄዱ፤ ሌሎች ሴቶ​ችም አብ​ረ​ዋ​ቸው ነበሩ።</verse>
				<verse number="2">ያቺ​ንም ድን​ጋይ ከመ​ቃ​ብሩ ላይ ተን​ከ​ባ​ልላ አገ​ኙ​አት።</verse>
				<verse number="3">ገብ​ተ​ውም የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ሥጋ አላ​ገ​ኙም።</verse>
				<verse number="4">ስለ​ዚ​ህም ነገር የሚ​ሉ​ትን አጥ​ተው ሲያ​ደ​ንቁ ሁለት ሰዎች ከፊ​ታ​ቸው ቆመው ታዩ​አ​ቸው፤ ልብ​ሳ​ቸ​ውም ያብ​ረ​ቀ​ርቅ ነበር።</verse>
				<verse number="5">ፈር​ተ​ውም ፊታ​ቸ​ውን ወደ ምድር አቀ​ረ​ቀሩ። እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “ሕያ​ዉን ከሙ​ታን ጋር ለምን ትሹ​ታ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="6">በዚህ የለም፤ ተነ​ሥ​ቶ​አል። በገ​ሊላ ሳለ ለእ​ና​ንተ እን​ዲህ ሲል የተ​ና​ገ​ረ​ውን ዐስቡ፦</verse>
				<verse number="7">የሰው ልጅ በኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞች ሰዎች እጅ ተላ​ልፎ ይሰጥ ዘንድ አለው፤ ይሰ​ቅ​ሉ​ታል፤ ይገ​ድ​ሉ​ታል፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ይነ​ሣል።” 10፥33-34፤ ሉቃ. 9፥22፤ 18፥31-33።</verse>
				<verse number="8">ቃሉ​ንም ዐሰቡ።</verse>
				<verse number="9">ከመ​ቃ​ብ​ርም ተመ​ል​ሰው ለዐ​ሥራ አን​ዱና ለቀ​ሩት ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸው ሁሉ ይህን ነገር ነገ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">እነ​ዚ​ያም መግ​ደ​ላ​ዊት ማር​ያም፥ ዮሐና፥ የያ​ዕ​ቆብ እናት ማር​ያም፥ አብ​ረ​ዋ​ቸው የነ​በ​ሩት ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ይህን ለሐ​ዋ​ር​ያት ነገ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ይህም ነገር በፊ​ታ​ቸው እንደ ተረት መሰ​ላ​ቸ​ውና አላ​መ​ኑ​አ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="12">ጴጥ​ሮ​ስም ተነሣ፤ ወደ መቃ​ብ​ርም ፈጥኖ ሄደ፤ ዝቅ ብሎም በተ​መ​ለ​ከተ ጊዜ በፍ​ታ​ውን ለብ​ቻው ተቀ​ምጦ አየ፤ የሆ​ነ​ው​ንም እያ​ደ​ነቀ ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="13">በዚ​ያም ቀን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ሁለት ሰዎች ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስድሳ ምዕ​ራፍ ያህል ወደ​ም​ት​ር​ቀው ኤማ​ሁስ ወደ​ም​ት​ባ​ለው መን​ደር ሄዱ።</verse>
				<verse number="14">እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ስለ ሆነው ነገር ሁሉ ይነ​ጋ​ገሩ ነበር።</verse>
				<verse number="15">እነ​ር​ሱም ይህን ሲነ​ጋ​ገ​ሩና ሲመ​ራ​መሩ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ እነ​ርሱ ቀረበ፤ አብ​ሮ​አ​ቸ​ውም ሄደ።</verse>
				<verse number="16">እን​ዳ​ያ​ው​ቁ​ትም ዐይ​ና​ቸው ተይዞ ነበር።</verse>
				<verse number="17">ጌታ​ች​ንም፥ “በት​ካዜ እየ​ሄ​ዳ​ችሁ እርስ በር​ሳ​ችሁ የም​ት​ነ​ጋ​ገ​ሩት ይህ ነገር ምን​ድን ነው?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">ከእ​ነ​ር​ሱም ቀለ​ዮጳ የሚ​ባ​ለው አንዱ መልሶ፥ “አንተ ብቻ ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ግዳ ነህን? በእ​ነ​ዚህ ቀኖ​ችስ በው​ስ​ጥዋ የተ​ደ​ረ​ገ​ውን አታ​ው​ቅ​ምን?” አለው።</verse>
				<verse number="19">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ይህ ምን​ድ​ነው?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉት፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊትና በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት በቃ​ሉና በሥ​ራው ብርቱ ነቢ​ይና እው​ነ​ተኛ ሰው ስለ​ነ​በ​ረው ስለ ናዝ​ሬቱ ስለ ኢየ​ሱስ፥</verse>
				<verse number="20">የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና መኳ​ን​ን​ቶ​ቻ​ችን አሳ​ል​ፈው እንደ ሰጡት፥ ሞትም እንደ ፈረ​ዱ​በ​ትና እንደ ሰቀ​ሉት ነው።</verse>
				<verse number="21">እኛ ግን እስ​ራ​ኤ​ልን ያድ​ና​ቸው ዘንድ ያለው እርሱ እንደ ሆነ ተስፋ እና​ደ​ርግ ነበር፤ ከዚ​ህም ሁሉ ጋር ይህ ነገር ከሆነ ዛሬ ሦስ​ተኛ ቀን ነው።</verse>
				<verse number="22">ደግ​ሞም ሴቶች ከእኛ ዘንድ ወደ መቃ​ብር ገስ​ግ​ሠው ሄደው ነበ​ርና አስ​ደ​ን​ቀው ነገ​ሩን።</verse>
				<verse number="23">ሥጋ​ው​ንም በአ​ላ​ገኙ ጊዜ ተመ​ል​ሰው፦ ተነ​ሥ​ቶ​አል ያሉ​አ​ቸ​ውን የመ​ላ​እ​ክ​ትን መልክ እንደ አዩ ነገ​ሩን።</verse>
				<verse number="24">ከእ​ኛም ዘንድ ወደ መቃ​ብር ሄደው እን​ዲሁ ሴቶች እንደ ተና​ገ​ሩት ሆኖ ያገ​ኙት አሉ፤ እር​ሱን ግን አላ​ዩ​ትም።”</verse>
				<verse number="25">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰነ​ፎች፥ ነቢ​ያ​ትም የተ​ና​ገ​ሩ​ትን ነገር ሁሉ ከማ​መን ልባ​ችሁ የዘ​ገየ፥</verse>
				<verse number="26">ክር​ስ​ቶስ እን​ዲህ ይሞት ዘንድ ወደ ክብ​ሩም ይመ​ለስ ዘንድ ያለው አይ​ደ​ለ​ምን?”</verse>
				<verse number="27">እር​ሱም ከሙ​ሴና ከነ​ቢ​ያት፥ ከመ​ጻ​ሕ​ፍ​ትም ሁሉ ስለ እርሱ የተ​ነ​ገ​ረ​ውን ይተ​ረ​ጕ​ም​ላ​ቸው ጀመር።</verse>
				<verse number="28">ሊሄ​ዱ​ባት ወደ ነበ​ረ​ችው መን​ደ​ርም ተቃ​ረቡ፤ እርሱ ግን ይር​ቃ​ቸው ጀመር።</verse>
				<verse number="29">እነ​ር​ሱም፥ “መሽ​ቶ​አ​ልና፥ ፀሐ​ይም ተዘ​ቅ​ዝ​ቆ​አ​ልና፥ ከእኛ ጋር እደር” ብለው ግድ አሉት፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሊያ​ድር ገባ።</verse>
				<verse number="30">ከዚ​ህም በኋላ አብ​ሮ​አ​ቸው ለማ​ዕድ ተቀ​ምጦ ሳለ እን​ጀ​ራ​ውን አን​ሥቶ ባረከ፤ ቈር​ሶም ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="31">ዐይ​ና​ቸ​ውም ተገ​ለ​ጠና ዐወ​ቁት፤ ወዲ​ያ​ው​ኑም ከእ​ነ​ርሱ ተሰ​ወረ።</verse>
				<verse number="32">እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም እን​ዲህ አሉ፥ “በመ​ን​ገድ ሲነ​ግ​ረን፥ መጻ​ሕ​ፍ​ት​ንም ሲተ​ረ​ጕ​ም​ልን ልባ​ችን ይቃ​ጠ​ል​ብን አል​ነ​በ​ረ​ምን?”</verse>
				<verse number="33">በዚ​ያ​ችም ሰዓት ተነ​ሥ​ተው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ፤ ዐሥራ አን​ዱን ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትና አብ​ረ​ዋ​ቸው የነ​በ​ሩ​ት​ንም ተሰ​ብ​ስ​በው አገ​ኙ​አ​ቸው፤</verse>
				<verse number="34">እን​ዲህ እያሉ፥ “ጌታ​ችን በእ​ው​ነት ተነ​ሥ​ቶ​አል፤ ለስ​ም​ዖ​ንም ታይ​ቶ​ታል።”</verse>
				<verse number="35">እነ​ር​ሱም በመ​ን​ገድ የሆ​ነ​ው​ንና እን​ጀ​ራ​ውን ሲቈ​ርስ ጌታ​ች​ንን እን​ዴት እን​ዳ​ወ​ቁት ነገ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="36">ይህ​ንም ሲነ​ጋ​ገሩ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቆመና፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን፤ አት​ፍሩ፤ እኔ ነኝ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="37">እነ​ርሱ ግን ፈሩ፤ ደነ​ገ​ጡም፤ ምት​ሐ​ት​ንም የሚ​ያዩ መሰ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="38">እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ምን ያስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ች​ኋል? በል​ባ​ች​ሁስ እን​ዲህ ያለ ዐሳብ ለምን ይነ​ሣ​ሣል?</verse>
				<verse number="39">እጄ​ንና እግ​ሬን እዩ፤ ዳስ​ሱ​ኝም፤ እኔ እንደ ሆን​ሁም ዕወቁ፤ በእኔ እን​ደ​ም​ታ​ዩት ለም​ት​ሐት አጥ​ን​ትና ሥጋ የለ​ው​ምና።”</verse>
				<verse number="40">ይህ​ንም ብሎ እጆ​ቹ​ንና እግ​ሮ​ቹን አሳ​ያ​ቸው።</verse>
				<verse number="41">ከድ​ን​ጋጤ የተ​ነ​ሣም ገና ሳያ​ምኑ ደስ ብሎ​አ​ቸ​ውም ሲያ​ደ​ንቁ ሳሉ፥ “በዚህ አን​ዳች የሚ​በላ አላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="42">እነ​ር​ሱም ከተ​ጠ​በሰ ዓሣ አንድ ቁራጭ፤ ከማር ወለ​ላም ጥቂት ሰጡት።</verse>
				<verse number="43">ተቀ​ብ​ሎም በፊ​ታ​ቸው በላ፤ የተ​ረ​ፈ​ው​ንም አን​ሥቶ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="44">እር​ሱም፥ “በሙሴ ኦሪት፥ በነ​ቢ​ያ​ትና በመ​ዝ​ሙ​ርም ስለ እኔ የተ​ነ​ገ​ረው ይፈ​ጸም ዘንድ እን​ዳ​ለው፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ሳለሁ የነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ ነገሬ ይህ ነው” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="45">ከዚ​ህም በኋላ መጻ​ሕ​ፍ​ትን እን​ዲ​ያ​ስ​ተ​ውሉ አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን ከፈ​ተ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="46">እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ክር​ስ​ቶስ እን​ዲ​ሞት በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከሙ​ታን ተለ​ይቶ እን​ዲ​ነሣ፥</verse>
				<verse number="47">ንስ​ሓና የኀ​ጢ​ኣት ስር​የት ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጀምሮ በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ እን​ዲ​ሰ​በክ እን​ዲሁ ተጽ​ፎ​አል።</verse>
				<verse number="48">እና​ን​ተም ለዚህ ነገር ምስ​ክ​ሮች ናችሁ።</verse>
				<verse number="49">እነሆ፥ እኔ የአ​ባ​ቴን ተስፋ ለእ​ና​ንተ እል​ካ​ለሁ፤ እና​ንተ ግን ከአ​ር​ያም ኀይ​ልን እስ​ክ​ት​ለ​ብሱ ድረስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከተማ ተቀ​መጡ።”</verse>
				<verse number="50">እስከ ቢታ​ን​ያም ወደ ውጭ አወ​ጣ​ቸው፤ እጁ​ንም አን​ሥቶ በላ​ያ​ቸ​ውም ጭኖ ባረ​ካ​ቸው።</verse>
				<verse number="51">እየ​ባ​ረ​ካ​ቸ​ውም ራቃ​ቸው፤ ወደ ሰማ​ይም ዐረገ።</verse>
				<verse number="52">እነ​ር​ሱም ሰገ​ዱ​ለ​ትና በታ​ላቅ ደስታ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="53">በቤተ መቅ​ደ​ስም ዘወ​ትር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገ​ኑና እያ​ገ​ለ​ገሉ ኖሩ። ከሰባ ሁለቱ አር​ድ​እት አንዱ ወን​ጌ​ላዊ ሉቃስ የጻ​ፈው ወን​ጌል ተፈ​ጸመ። የጻ​ፈ​ውም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ወደ ሰማይ በዐ​ረገ በሃያ አንድ ዓመት ቀላ​ው​ዴ​ዎስ ቄሣር በነ​ገሠ በዐ​ሥራ አራት ዓመት በጽ​ርዕ ቋንቋ ለመ​ቄ​ዶ​ንያ ሰዎች ነው። ምስ​ጋና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁን። አሜን።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="43">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በመ​ጀ​መ​ሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበረ፤ ቃልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነበረ።</verse>
				<verse number="2">ይህም በመ​ጀ​መ​ሪያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበረ።</verse>
				<verse number="3">ሁሉም በእ​ርሱ ሆነ፤ ከሆ​ነ​ውም ሁሉ ያለ እርሱ ምንም የሆነ የለም።</verse>
				<verse number="4">ሕይ​ወት በእ​ርሱ ነበረ፥ ሕይ​ወ​ትም የሰው ብር​ሃን ነበረ፤</verse>
				<verse number="5">ብር​ሃ​ንም በጨ​ለማ ያበ​ራል፤ ጨለ​ማም አላ​ገ​ኘ​ውም።</verse>
				<verse number="6">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ላከ ስሙ ዮሐ​ንስ የሚ​ባል አንድ ሰው ነበር።</verse>
				<verse number="7">እር​ሱም ሁሉ በእ​ርሱ በኩል እን​ዲ​ያ​ምን ስለ ብር​ሃን ይመ​ሰ​ክር ዘንድ ለም​ስ​ክ​ር​ነት መጣ።</verse>
				<verse number="8">ስለ ብር​ሃን ምስ​ክር ሊሆን መጣ እንጂ እርሱ ራሱ ብር​ሃን አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="9">ለሰው ሁሉ የሚ​ያ​በ​ራው እው​ነ​ተ​ኛው ብር​ሃ​ንስ ወደ ዓለም የመ​ጣው ነው።</verse>
				<verse number="10">በዓ​ለም ነበረ፤ ዓለ​ሙም በእ​ርሱ ሆነ፤ ዓለሙ ግን አላ​ወ​ቀ​ውም።</verse>
				<verse number="11">ወደ ወገ​ኖቹ መጣ፤ ወገ​ኖቹ ግን አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​ትም።</verse>
				<verse number="12">ለተ​ቀ​በ​ሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚ​ያ​ምኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች እን​ዲ​ሆኑ ሥል​ጣ​ንን ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">እነ​ር​ሱም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተወ​ለዱ እንጂ ከሥ​ጋ​ዊና ከደ​ማዊ ግብር ወይም ከወ​ን​ድና ከሴት ፈቃድ አል​ተ​ወ​ለ​ዱም።</verse>
				<verse number="14">ያም ቃል ሥጋ ሆነ፤ በእ​ኛም አደረ፤ ለአ​ባቱ አንድ እንደ ሆነ ልጅ ክብር ያለ ክብ​ሩን አየን፤ ጸጋ​ንና እው​ነ​ትን የተ​መላ ነው።</verse>
				<verse number="15">ምስ​ክሩ ዮሐ​ንስ ስለ እርሱ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ ተና​ገረ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እኔ ስለ እርሱ ከእኔ በፊት የነ​በረ ከእኔ በኋላ ይመ​ጣል ያል​ኋ​ችሁ ሰው ይህ ነው፥ እርሱ ከእኔ አስ​ቀ​ድሞ ነበ​ረና።”</verse>
				<verse number="16">እኛም ሁላ​ችን ከሙ​ላቱ በጸጋ ላይ ጸጋን ተቀ​በ​ልን።</verse>
				<verse number="17">ኦሪት በሙሴ ተሰ​ጥ​ታን ነበ​ርና፤ ጸጋና እው​ነት ግን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሆነ​ልን።</verse>
				<verse number="18">በአ​ባቱ ዕቅፍ ያለ አንድ ልጅ እርሱ ገለ​ጠ​ልን እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንስ ከቶ ያየው የለም።</verse>
				<verse number="19">አይ​ሁድ፥ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ይጠ​ይ​ቁት ዘንድ ካህ​ና​ት​ንና ሌዋ​ው​ያ​ንን ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በላኩ ጊዜ የዮ​ሐ​ንስ ምስ​ክ​ር​ነት ይህ ነው።</verse>
				<verse number="20">እር​ሱም፥ “እኔ ክር​ስ​ቶስ አይ​ደ​ለ​ሁም” ብሎ አመነ እንጂ አል​ካ​ደም።</verse>
				<verse number="21">“እን​ኪያ አንተ ማነህ? አንተ ኤል​ያስ ነህን?” ብለው ጠየ​ቁት፤ “አይ​ደ​ለ​ሁም” አለ፤ “እን​ኪያ አንተ ነቢዩ ነህን?” አሉት፤ “አይ​ደ​ለ​ሁም” አለ።</verse>
				<verse number="22">“እን​ኪ​ያስ አንተ ማነህ? ለላ​ኩ​ንም መልስ እን​ድ​ን​ሰጥ ስለ ራስህ ማን ትላ​ለህ?” አሉት።</verse>
				<verse number="23">እር​ሱም፥ “ነቢዩ ኢሳ​ይ​ያስ እንደ ተና​ገረ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ጥረጉ እያለ በም​ድረ በዳ የሚ​ሰ​ብክ የዐ​ዋጅ ነጋሪ ድምፅ እኔ ነኝ” አለ።</verse>
				<verse number="24">የተ​ላ​ኩ​ትም ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ነበሩ።</verse>
				<verse number="25">“እን​ኪ​ያስ ክር​ስ​ቶ​ስን ካል​ሆ​ንህ፥ ኤል​ያ​ስ​ንም ካል​ሆ​ንህ፥ ነቢ​ይ​ንም ካል​ሆ​ንህ ለምን ታጠ​ም​ቃ​ለህ?” ብለው ጠየ​ቁት።</verse>
				<verse number="26">ዮሐ​ን​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ በውኃ አጠ​ም​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ነገር ግን እና​ንተ የማ​ታ​ው​ቁት በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ቆሞ​አል።</verse>
				<verse number="27">ከእኔ በኋላ የሚ​መ​ጣው፥ ከእኔ በፊት የነ​በ​ረው፥ የጫ​ማ​ውን ጠፍር ልፈታ እንኳ የማ​ይ​ገ​ባኝ ነው።”</verse>
				<verse number="28">ዮሐ​ንስ ያጠ​ም​ቅ​በት በነ​በ​ረው በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በቢ​ታ​ንያ በቤተ ራባ እን​ዲህ ሆነ።</verse>
				<verse number="29">በማ​ግ​ሥ​ቱም ዮሐ​ንስ ወደ እርሱ ሲመጣ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን አይቶ እን​ዲህ አለ፤ “እነሆ፥ የዓ​ለ​ሙን ኀጢ​ኣት የሚ​ያ​ስ​ወ​ግድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ።</verse>
				<verse number="30">ከእኔ በፊት የነ​በረ ሰው ከእኔ በኋላ ይመ​ጣል ብዬ ስለ እርሱ የነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ ይህ ነው፤ እርሱ ከእኔ አስ​ቀ​ድሞ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="31">እኔ አላ​ው​ቀ​ውም ነበር፤ ነገር ግን እስ​ራ​ኤል እን​ዲ​ያ​ው​ቁት ስለ​ዚህ እኔ በውኃ ላጠ​ምቅ መጣሁ።”</verse>
				<verse number="32">ዮሐ​ን​ስም ምስ​ክ​ር​ነ​ቱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ፥ “መን​ፈስ ቅዱስ ከሰ​ማይ እንደ ርግብ ወርዶ በራሱ ላይ ሲቀ​መጥ አየሁ።</verse>
				<verse number="33">እኔም አላ​ው​ቀ​ውም ነበር፤ ነገር ግን በውኃ እን​ዳ​ጠ​ምቅ የላ​ከኝ እርሱ መን​ፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀ​መ​ጥ​በት የም​ታ​የው በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የሚ​ያ​ጠ​ምቅ እርሱ ነው አለኝ።</verse>
				<verse number="34">እኔም ራሴ አይ​ቻ​ለሁ፤ እር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ እኔ ምስ​ክሩ ነኝ።”</verse>
				<verse number="35">በማ​ግ​ሥ​ቱም ደግሞ ዮሐ​ንስ ከሁ​ለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ቆሞ ሳለ፥</verse>
				<verse number="36">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ሲሄድ አይቶ “እነሆ፥ የዓ​ለ​ሙን ኀጢ​ኣት የሚ​ያ​ስ​ወ​ግድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ” አለ።</verse>
				<verse number="37">ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እን​ዲህ ሲል ሰም​ተው ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ተከ​ተ​ሉት።</verse>
				<verse number="38">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዘወር ብሎ ሲከ​ተ​ሉት አየና፥ “ምን ትሻ​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="39">እነ​ር​ሱም፥ “ረቢ፥ ትር​ጓ​ሜ​ውም መም​ህር ሆይ፥ ማለት ነው፤ ወዴት ትኖ​ራ​ለህ?” አሉት።</verse>
				<verse number="40">እር​ሱም “መጥ​ታ​ችሁ እዩ” አላ​ቸው፤ ሄደ​ውም የሚ​ኖ​ር​በ​ትን አዩ፤ ያን ዕለ​ትም እስከ ዐሥር ሰዓት ድረስ በእ​ርሱ ዘንድ ዋሉ።</verse>
				<verse number="41">ከዮ​ሐ​ንስ ዘንድ ሰም​ተው ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከተ​ከ​ተ​ሉት ከሁ​ለ​ቱም አንዱ የስ​ም​ዖን ጴጥ​ሮስ ወን​ድም እን​ድ​ር​ያስ ነበር።</verse>
				<verse number="42">እር​ሱም መጀ​መ​ሪያ ወን​ድሙ ስም​ዖ​ንን አግ​ኝቶ “በት​ር​ጓ​ሜው ክር​ስ​ቶስ የሚ​ሉት መሲ​ሕን አገ​ኘ​ነው” አለው።</verse>
				<verse number="43">እር​ሱም ወደ ጌታ​ችን ወደ ኢየ​ሱስ ወሰ​ደው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ባየው ጊዜ፥ “ አንተ የዮና ልጅ ስም​ዖን ነህን? አንተ ኬፋ ትባ​ላ​ለህ፤” አለው፤ ትር​ጓ​ሜ​ውም ጴጥ​ሮስ ማለት ነው።</verse>
				<verse number="44">በማ​ግ​ሥ​ቱም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ ገሊላ ሊሄድ ወደደ፤ ፊል​ጶ​ስ​ንም አገ​ኘ​ውና “ተከ​ተ​ለኝ” አለው።</verse>
				<verse number="45">ፊል​ጶስ ግን ከእ​ን​ድ​ር​ያ​ስና ከጴ​ጥ​ሮስ ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበር።</verse>
				<verse number="46">ፊል​ጶ​ስም ናት​ና​ኤ​ልን አገ​ኘ​ውና፥ “ሙሴ በኦ​ሪት፥ ነቢ​ያ​ትም ስለ እርሱ የጻ​ፉ​ለ​ትን የዮ​ሴ​ፍን ልጅ የና​ዝ​ሬ​ቱን ኢየ​ሱ​ስን አገ​ኘ​ነው” አለው።</verse>
				<verse number="47">ናት​ና​ኤ​ልም፥ “በውኑ ከና​ዝ​ሬት ደግ ሰው ሊወጣ ይቻ​ላ​ልን?” አለው፤ ፊል​ጶ​ስም፥ “መጥ​ተህ እይ” አለው።</verse>
				<verse number="48">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ናት​ና​ኤ​ልን ወደ እርሱ ሲመጣ ባየው ጊዜ ስለ እርሱ “እነሆ፥ በልቡ ተን​ኰል የሌ​ለ​በት እው​ነ​ተኛ እስ​ራ​ኤ​ላዊ ይህ ነው” አለ።</verse>
				<verse number="49">ናት​ና​ኤ​ልም፥ “በየት ታው​ቀ​ኛ​ለህ?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ገና ፊል​ጶስ ሳይ​ጠ​ራህ በበ​ለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አይ​ች​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="50">ናት​ና​ኤ​ልም መልሶ፥ “መም​ህር ሆይ፥ በእ​ው​ነት አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ነህ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አንተ ነህ” አለው።</verse>
				<verse number="51">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “በበ​ለስ ዛፍ ሥር አየ​ሁህ ስለ አል​ሁህ አመ​ን​ህን? ከዚህ የሚ​በ​ልጥ ታያ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="52">“እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ሰማ​ያት ሲከ​ፈቱ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መላ​እ​ክት ወደ ሰው ልጅ ሲወ​ር​ዱና ሲወጡ ታያ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን የገ​ሊላ ክፍል በም​ት​ሆን በቃና ሰርግ ሆነ፤ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ እና​ትም በዚያ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="2">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስና ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።</verse>
				<verse number="3">የወ​ይን ጠጃ​ቸ​ውም ባለቀ ጊዜ እናቱ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን፥ “የወ​ይን ጠጅ እኮ የላ​ቸ​ውም” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="4">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አንቺ ሆይ ካንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አል​ደ​ረ​ሰም” አላት።</verse>
				<verse number="5">እና​ቱም ለአ​ሳ​ላ​ፊ​ዎቹ፥ “የሚ​ላ​ች​ሁን ሁሉ አድ​ርጉ” አለ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">በዚ​ያም እንደ አይ​ሁድ ልማድ የሚ​ያ​ነ​ጹ​ባ​ቸው ስድ​ስት የድ​ን​ጋይ ጋኖች ነበሩ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም እያ​ን​ዳ​ንዱ ሁለት ወይም ሦስት እን​ስራ ይይዙ ነበር።</verse>
				<verse number="7">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ጋኖ​ቹን ውኃ ሙሉ​አ​ቸው” አላ​ቸው፤ እስከ አፋ​ቸ​ውም እስከ ላይ ሞሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">“አሁ​ንም ቅዱና ወስ​ዳ​ችሁ ለአ​ሳ​ዳ​ሪው ስጡት” አላ​ቸው፤ ወስ​ደ​ውም ሰጡት።</verse>
				<verse number="9">አሳ​ዳ​ሪ​ውም ያን የወ​ይን ጠጅ የሆ​ነ​ውን ውኃ ቀምሶ አደ​ነቀ፤ ከወ​ዴት እንደ መጣም አላ​ወ​ቀም፤ የቀ​ዱት አሳ​ላ​ፊ​ዎች ግን የወ​ይን ጠጅ የሆ​ነ​ውን ያን ውኃ ያውቁ ነበር። ውኃ​ዉን የሞሉ እነ​ርሱ ነበ​ሩና።</verse>
				<verse number="10">አሳ​ዳ​ሪ​ውም ሙሽ​ራ​ውን ጠርቶ፥ “ሰው ሁሉ መል​ካ​ሙን የወ​ይን ጠጅ አስ​ቀ​ድሞ ያጠ​ጣል፤ ከጠ​ገቡ በኋ​ላም ተር​ታ​ውን ያመ​ጣል፤ አንተ ግን መል​ካ​ሙን የወ​ይን ጠጅ እስ​ካ​ሁን አቈ​የህ” አለው።</verse>
				<verse number="11">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቃና ዘገ​ሊላ ያደ​ረ​ገው የተ​አ​ም​ራት መጀ​መ​ሪያ ይህ ነው፤ ክብ​ሩ​ንም ገለጠ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አመ​ኑ​በት።</verse>
				<verse number="12">ከዚ​ህም በኋላ እር​ሱና እናቱ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹና ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ወደ ቅፍ​ር​ና​ሆም ወረዱ፤ በዚ​ያም ብዙ ያይ​ደለ ጥቂት ቀን ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="13">የአ​ይ​ሁ​ድም የፋ​ሲ​ካ​ቸው በዓል ቀርቦ ነበር፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣ።</verse>
				<verse number="14">በቤተ መቅ​ደ​ስም በሬ​ዎ​ች​ንና በጎ​ችን፥ ርግ​ቦ​ች​ንም የሚ​ሸ​ጡ​ትን፥ ገን​ዘብ ለዋ​ጮ​ች​ንም ተቀ​ም​ጠው አገኘ።</verse>
				<verse number="15">የገ​መ​ድም ጅራፍ አበጀ፤ በጎ​ች​ንና በሬ​ዎ​ችን፥ ሁሉ​ንም ከቤተ መቅ​ደስ አስ​ወጣ፤ የለ​ዋ​ጮ​ች​ንም ገን​ዘብ በተነ፤ ገበ​ታ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ገለ​በጠ።</verse>
				<verse number="16">ርግብ ሻጮ​ች​ንም፥ “ይህን ከዚህ አውጡ፤ የአ​ባ​ቴን ቤት የን​ግድ ቤት አታ​ድ​ርጉ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም፥ “የቤ​ትህ ቅናት በላኝ” የሚል ቃል ተጽፎ እን​ዳለ ዐሰቡ።</verse>
				<verse number="18">አይ​ሁ​ድም መል​ሰው፥ “ይህን የም​ታ​ደ​ርግ ምን ምል​ክት ታሳ​ያ​ለህ?” አሉት።</verse>
				<verse number="19">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ይህን ቤተ መቅ​ደስ አፍ​ር​ሱት፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን አነ​ሣ​ዋ​ለሁ” ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">አይ​ሁ​ድም፥ “ይህ ቤተ መቅ​ደስ በአ​ርባ ስድ​ስት ዓመት ተሠራ፤ አን​ተስ በሦ​ስት ቀኖች ውስጥ ታነ​ሣ​ዋ​ለ​ህን?” አሉት።</verse>
				<verse number="21">እርሱ ግን ይህን የተ​ና​ገ​ረው ቤተ መቅ​ደስ ስለ ተባለ ሰው​ነቱ ነበር።</verse>
				<verse number="22">ከሙ​ታን በተ​ነሣ ጊዜም ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ስለ​ዚህ እንደ ነገ​ራ​ቸው ዐሰቡ፤ በመ​ጻ​ሕ​ፍት ቃልና ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በነ​ገ​ራ​ቸ​ውም ነገር አመኑ።</verse>
				<verse number="23">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በፋ​ሲካ በዓል በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሳለ ብዙ ሰዎች ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ራት ባዩ ጊዜ በስሙ አመኑ።</verse>
				<verse number="24">እርሱ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ግን አያ​ም​ና​ቸ​ውም ነበር፤ ሁሉን እያ​ን​ዳ​ን​ዱን ያው​ቀ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="25">የሰ​ው​ንም ግብ​ሩን ሊነ​ግ​ሩት አይ​ሻም፤ እርሱ በሰው ያለ​ውን ያውቅ ነበ​ርና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወገን የአ​ይ​ሁድ አለቃ የሆነ ኒቆ​ዲ​ሞስ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ።</verse>
				<verse number="2">እር​ሱም በሌ​ሊት ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መጥቶ እን​ዲህ አለው፥ “መም​ህር ሆይ፥ ልታ​ስ​ተ​ምር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እንደ መጣህ እና​ው​ቃ​ለን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ይህን ተአ​ምር ሊያ​ደ​ርግ የሚ​ችል የለ​ምና።”</verse>
				<verse number="3">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “እው​ነት እው​ነት እል​ሀ​ለሁ፤ ዳግ​መኛ ያል​ተ​ወ​ለደ ሰው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ለማ​የት አይ​ች​ልም” አለው።</verse>
				<verse number="4">ኒቆ​ዲ​ሞ​ስም፥ “ሰው ከሸ​መ​ገለ በኋላ ዳግ​መኛ መወ​ለድ እን​ደ​ምን ይች​ላል? ዳግ​መኛ ይወ​ለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማኅ​ፀን ተመ​ልሶ መግ​ባት ይች​ላ​ልን?” አለው።</verse>
				<verse number="5">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እው​ነት እው​ነት እል​ሀ​ለሁ፤ ዳግ​መኛ ከው​ኃና ከመ​ን​ፈስ ቅዱስ ያል​ተ​ወ​ለደ ሰው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ሊገባ አይ​ች​ልም።</verse>
				<verse number="6">ከሥጋ የተ​ወ​ለደ ሥጋ ነውና፤ ከመ​ን​ፈ​ስም የተ​ወ​ለደ መን​ፈስ ነውና።</verse>
				<verse number="7">ስለ​ዚ​ህም ዳግ​መኛ ልት​ወ​ለዱ ይገ​ባ​ች​ኋል ስለ አል​ሁህ አታ​ድ​ንቅ።</verse>
				<verse number="8">ነፋስ ወደ ወደ​ደው ይነ​ፍ​ሳ​ልና፤ ድም​ፁ​ንም ትሰ​ማ​ለህ፤ ነገር ግን ከየት እን​ደ​ሚ​መጣ ወዴ​ትም እን​ደ​ሚ​ሄድ አታ​ው​ቅም፤ ከመ​ን​ፈስ የሚ​ወ​ለድ ሁሉ እን​ዲሁ ነው።”</verse>
				<verse number="9">ኒቆ​ዲ​ሞ​ስም መልሶ፥ “ይህ ሊሆን እን​ዴት ይቻ​ላል?” አለው።</verse>
				<verse number="10">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “አንተ የእ​ስ​ራ​ኤል መም​ህ​ራ​ቸው ነህ፤ ነገር ግን እን​ዴት ይህን አታ​ው​ቅም?” አለው።</verse>
				<verse number="11">እው​ነት እው​ነት እል​ሃ​ለሁ፤ የም​ና​ው​ቀ​ውን እን​ና​ገ​ራ​ለን፤ ያየ​ነ​ው​ንም እን​መ​ሰ​ክ​ራ​ለን፤ ነገር ግን ምስ​ክ​ር​ነ​ታ​ች​ንን አት​ቀ​በ​ሉ​ንም።</verse>
				<verse number="12">በም​ድር ያለ​ውን ስነ​ግ​ራ​ችሁ ካላ​መ​ና​ች​ሁኝ በሰ​ማይ ያለ​ውን ብነ​ግ​ራ​ችሁ እን​ዴት ታም​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="13">ከሰ​ማይ ከወ​ረ​ደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፤ እር​ሱም በሰ​ማይ የሚ​ኖ​ረው ነው።</verse>
				<verse number="14">ሙሴ በም​ድረ በዳ እባ​ቡን እንደ ሰቀ​ለው የሰው ልጅ እን​ዲሁ ይሰ​ቀል ዘንድ አለው።</verse>
				<verse number="15">ያመ​ነ​በት ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕያው ሆኖ እን​ዲ​ኖር እንጂ እን​ዳ​ይ​ጠፋ።</verse>
				<verse number="16">በእ​ርሱ የሚ​ያ​ምን ሁሉ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እን​ዲ​ያ​ገኝ እንጂ እን​ዳ​ይ​ጠፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አን​ድያ ልጁን ቤዛ አድ​ርጎ እስ​ኪ​ሰጥ ድረስ ዓለ​ሙን እን​ዲህ ወዶ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="17">ዓለም በእ​ርሱ ይድን ዘንድ ነው እንጂ በዓ​ለም እን​ዲ​ፈ​ርድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን ወደ​ዚህ ዓለም አል​ላ​ከ​ው​ምና።</verse>
				<verse number="18">በእ​ርሱ ያመነ አይ​ፈ​ረ​ድ​በ​ትም፤ በእ​ርሱ ያላ​መነ ግን ፈጽሞ ተፈ​ር​ዶ​በ​ታል፤ በአ​ንዱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ስም አላ​መ​ነ​ምና።</verse>
				<verse number="19">ፍር​ዱም ይህ ነው፤ ብር​ሃን ወደ ዓለም መጥ​ቶ​አ​ልና፤ ሰውም ሥራው ክፉ ስለ​ሆነ ከብ​ር​ሃን ይልቅ ጨለ​ማን መር​ጦ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="20">ሥራው ክፉ የሆነ ሁሉ ብር​ሃ​ንን ይጠ​ላ​ልና፤ ክፉም ስለ​ሆነ ሥራው እን​ዳ​ይ​ገ​ለ​ጥ​በት ወደ ብር​ሃን አይ​መ​ጣም።</verse>
				<verse number="21">እው​ነ​ትን የሚ​ሠራ ግን ሥራው ይገ​ለጥ ዘንድ ወደ ብር​ሃን ይመ​ጣል፤ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብሎ ይሠ​ራ​ልና።</verse>
				<verse number="22">ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ወደ ይሁዳ ምድር ሄደ፤ በዚ​ያም እያ​ጠ​መቀ አብ​ሮ​አ​ቸው ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="23">ዮሐ​ን​ስም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሳ​ሌም አቅ​ራ​ቢያ በሄ​ኖን ያጠ​ምቅ ነበር፤ በዚያ ብዙ ውኃ ነበ​ርና፤ ብዙ ሰዎ​ችም ወደ እርሱ እየ​መጡ ያጠ​ም​ቃ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="24">ዮሐ​ንስ ገና ወደ ወኅኒ ቤት አል​ገ​ባም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="25">ከዚ​ህም በኋላ በዮ​ሐ​ንስ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትና በአ​ይ​ሁድ መካ​ከል ስለ ማን​ጻት ክር​ክር ሆነ፤</verse>
				<verse number="26">ወደ ዮሐ​ን​ስም ሄደው፥ “መም​ህር ሆይ፥ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ካንተ ጋር የነ​በ​ረው፥ አን​ተም የመ​ሰ​ከ​ር​ህ​ለት እርሱ እነሆ፥ ያጠ​ም​ቃል፤ ሁሉም ወደ እርሱ ይሄ​ዳል” አሉት።</verse>
				<verse number="27">ዮሐ​ን​ስም መልሶ እን​ዲህ አለ፥ “ሰው ከሰ​ማይ ካል​ተ​ሰ​ጠው በስ​ተ​ቀር እርሱ ራሱ ጸጋን ገን​ዘብ ሊያ​ደ​ርግ ምንም አይ​ች​ልም።</verse>
				<verse number="28">እኔ ክር​ስ​ቶስ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ነገር ግን እን​ድ​ሰ​ብ​ክ​ለት ከእ​ርሱ በፊት ተል​ኬ​አ​ለሁ እን​ዳ​ል​ኋ​ችሁ እና​ንተ ራሳ​ችሁ ምስ​ክ​ሮች ናችሁ።</verse>
				<verse number="29">ሙሽራ ያለ​ችው ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚ​ሰ​ማው የሙ​ሽ​ራው ሚዜ ግን በሙ​ሽ​ራው ቃል እጅግ ደስ ይለ​ዋል፤ የእኔ ደስታ አሁን ተፈ​ጸ​መች።</verse>
				<verse number="30">የእ​ርሱ ትበ​ዛ​ለች፤ የእኔ ግን ታንስ ዘንድ ይገ​ባል።”</verse>
				<verse number="31">ከላይ የመ​ጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከም​ድር የተ​ገ​ኘ​ውም ምድ​ራዊ ነው፤ የም​ድ​ሩ​ንም ይና​ገ​ራል፤ ከሰ​ማይ የመ​ጣው ግን ከሁሉ በላይ ነው።</verse>
				<verse number="32">ባየ​ውና በሰ​ማው ይመ​ሰ​ክ​ራል፤ ነገር ግን ምስ​ክ​ር​ነ​ቱን የሚ​ቀ​በ​ለው የለም።</verse>
				<verse number="33">ምስ​ክ​ር​ነ​ቱን የተ​ቀ​በለ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተኛ እንደ ሆነ አተመ።</verse>
				<verse number="34">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የላ​ከው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ይና​ገ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ሱን ሰፍሮ አይ​ሰ​ጥ​ምና።</verse>
				<verse number="35">አብ ልጁን ይወ​ዳ​ልና፥ ሁሉን በእጁ ሰጠው።</verse>
				<verse number="36">በወ​ልድ የሚ​ያ​ምን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት አለው፤ በወ​ልድ የማ​ያ​ምን ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቍጣ መቅ​ሠ​ፍት በላዩ ይኖ​ራል እንጂ ሕይ​ወ​ትን አያ​ይም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከዮ​ሐ​ንስ ይልቅ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትን እንደ አበ​ዛና እን​ደ​ሚ​ያ​ጠ​ምቅ ፈሪ​ሳ​ው​ያን መስ​ማ​ታ​ቸ​ውን ዐወቀ።</verse>
				<verse number="2">ነገር ግን ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ እንጂ እርሱ ራሱ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ አላ​ጠ​መ​ቀም።</verse>
				<verse number="3">የይ​ሁ​ዳ​ንም ምድር ትቶ ዳግ​መኛ ወደ ገሊላ ሄደ።</verse>
				<verse number="4">በሰ​ማ​ርያ በኩ​ልም ሲያ​ልፍ ሳለ፥</verse>
				<verse number="5">ያዕ​ቆብ ለልጁ ለዮ​ሴፍ በሰ​ጠው በወ​ይን ቦታ አቅ​ራ​ቢያ ወደ አለ​ችው ሲካር ወደ​ም​ት​ባ​ለው የሰ​ማ​ርያ ከተማ ደረሰ።</verse>
				<verse number="6">በዚ​ያም የያ​ዕ​ቆብ የውኃ ጕድ​ጓድ ነበረ። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መን​ገድ በመ​ሄድ ደክሞ በዚያ ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ተቀ​መጠ፤ ጊዜ​ውም ስድ​ስት ሰዓት ያህል ነበር።</verse>
				<verse number="7">እነሆ፥ ከሰ​ማ​ርያ አን​ዲት ሴት ውኃ ልት​ቀዳ መጣች፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ውኃ አጠ​ጪኝ” አላት።</verse>
				<verse number="8">ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማ ሄደው ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="9">ያቺ የሰ​ማ​ርያ ሴትም፥ “አንተ አይ​ሁ​ዳዊ ስት​ሆን፥ እኔም ሳም​ራ​ዊት ስሆን እን​ዴት ከእኔ ዘንድ ውኃ ልት​ጠጣ ትለ​ም​ና​ለህ?” አለ​ችው፤ አይ​ሁድ ከሳ​ም​ራ​ው​ያን ጋር በሥ​ር​ዐት አይ​ተ​ባ​በ​ሩም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="10">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስጦ​ታና ውኃ አጠ​ጪኝ ብሎ የሚ​ለ​ም​ንሽ ማን እንደ ሆነ ብታ​ው​ቂስ አንቺ ደግሞ በለ​መ​ን​ሺው ነበር፤ እር​ሱም የሕ​ይ​ወ​ትን ውኃ በሰ​ጠሽ ነበር” ብሎ መለ​ሰ​ላት።</verse>
				<verse number="11">ያቺ ሴትም እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ መቅጃ እንኳ የለ​ህም፤ ጕድ​ጓ​ዱም ጥልቅ ነው፤ እን​ግ​ዲህ የሕ​ይ​ወት ውኃ ከወ​ዴት ታገ​ኛ​ለህ?</verse>
				<verse number="12">ይህን ጕድ​ጓድ ከሰ​ጠን ከአ​ባ​ታ​ችን ከያ​ዕ​ቆብ አንተ ትበ​ል​ጣ​ለ​ህን? እር​ሱም ልጆ​ቹም፥ ከብ​ቶ​ቹም ከእ​ርሱ ጠጥ​ተ​ዋል።”</verse>
				<verse number="13">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላት፥ “ከዚህ ውኃ የሚ​ጠጣ ሁሉ ዳግ​መኛ ይጠ​ማል።</verse>
				<verse number="14">እኔ ከም​ሰ​ጠው ውኃ የሚ​ጠጣ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ጠ​ማም፤ እኔ የም​ሰ​ጠው ውኃ በው​ስጡ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የሚ​ፈ​ልቅ የውኃ ምንጭ ይሆ​ን​ለ​ታል እንጂ።”</verse>
				<verse number="15">ሴቲ​ቱም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እን​ዳ​ል​ጠማ፥ ዳግ​መ​ኛም ውኃ ልቀዳ ወደ​ዚህ እን​ዳ​ል​መጣ እባ​ክህ ከዚህ ውኃ ስጠኝ፤” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="16">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ሂደሽ ባል​ሽን ጥሪና ወደ​ዚህ ነይ” አላት።</verse>
				<verse number="17">ሴቲ​ቱም፥ “ባል የለ​ኝም” ብላ መለ​ሰ​ች​ለት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላት፥ “ባል የለ​ኝም በማ​ለ​ትሽ መል​ካም ተና​ገ​ርሽ።</verse>
				<verse number="18">ቀድሞ አም​ስት ባሎች ነበ​ሩሽ፤ ዛሬ አብ​ሮሽ ያለው ግን ባልሽ አይ​ደ​ለም፤ ይህ​ንስ እው​ነት አልሽ።”</verse>
				<verse number="19">ሴቲ​ቱም እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ፥ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">አባ​ቶ​ቻ​ችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እና​ንተ ግን ይሰ​ግ​ዱ​በት ዘንድ የሚ​ገ​ባው ስፍራ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነው ትላ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="21">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላት፥ “አንቺ ሴት በዚህ ተራራ ወይም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ብቻ ለአብ የማ​ይ​ሰ​ግ​ዱ​በት ሰዓት እን​ደ​ም​ት​መጣ እመ​ኝኝ።</verse>
				<verse number="22">እና​ንተ ለማ​ታ​ው​ቁት ትሰ​ግ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እኛ ግን ለም​ና​ው​ቀው እን​ሰ​ግ​ዳ​ለን፤ መድ​ኀ​ኒት ከአ​ይ​ሁድ ወገን ነውና።</verse>
				<verse number="23">ነገር ግን በእ​ው​ነት የሚ​ሰ​ግዱ በመ​ን​ፈ​ስና በእ​ው​ነት ለአብ የሚ​ሰ​ግ​ዱ​ባት ጊዜ ትመ​ጣ​ለች፤ እር​ስ​ዋም አሁን ናት። አብ እን​ዲህ የሚ​ሰ​ግ​ዱ​ለ​ትን ይሻ​ልና።</verse>
				<verse number="24">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነውና፤ የሚ​ሰ​ግ​ዱ​ለ​ትም በመ​ን​ፈ​ስና በእ​ው​ነት ይሰ​ግ​ዱ​ለት ዘንድ ይገ​ባል።”</verse>
				<verse number="25">ሴቲ​ቱም፥ “ክር​ስ​ቶስ የሚ​ሉት መሲሕ እን​ደ​ሚ​መጣ እና​ው​ቃ​ለን፤ እር​ሱም በሚ​መጣ ጊዜ ሁሉን ይነ​ግ​ረ​ናል” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="26">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የማ​ነ​ጋ​ግ​ርሽ እኔ እርሱ ነኝ” አላት።</verse>
				<verse number="27">በዚ​ያም ጊዜ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ መጡ፤ ከሴት ጋርም ይነ​ጋ​ገር ነበ​ርና ተደ​ነቁ፤ ነገር ግን፥ “ምን ትሻ​ለህ? ወይስ ከእ​ር​ስዋ ጋር ለምን ትነ​ጋ​ገ​ራ​ለህ?” ያለው የለም።</verse>
				<verse number="28">ሴቲ​ቱም እን​ስ​ራ​ዋን ትታ ወደ ከተማ ገባች፤ ለሰ​ዎ​ችም ነገ​ረች።</verse>
				<verse number="29">“የሠ​ራ​ሁ​ትን ሁሉ የነ​ገ​ረ​ኝን ሰው ታዩ ዘንድ ኑ፤ እንጃ፥ እርሱ ክር​ስ​ቶስ ይሆን?”</verse>
				<verse number="30">ከከ​ተ​ማም ወጥ​ተው ወደ እርሱ ሄዱ።</verse>
				<verse number="31">በዚ​ህም ጊዜ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ፥ “መም​ህር ሆይ፥ እህል ብላ” ብለው ለመ​ኑት።</verse>
				<verse number="32">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ የም​በ​ላው እና​ንተ የማ​ታ​ው​ቁት ምግብ አለኝ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="33">ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “አን​ዳች የሚ​በ​ላው ምግብ ያመ​ጣ​ለት ሰው ይኖር ይሆን?” ተባ​ባሉ።</verse>
				<verse number="34">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ኔስ መብል የላ​ከ​ኝን የአ​ባ​ቴን ፈቃድ አደ​ርግ ዘንድ፥ ሥራ​ው​ንም እፈ​ጽም ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="35">እና​ንተ እስከ አራት ወር ድረስ መከር ይሆ​ናል የም​ትሉ አይ​ደ​ለ​ምን? እነሆ፥ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ዐይ​ና​ች​ሁን አንሡ፤ መከ​ሩም ሊደ​ርስ እንደ ገረጣ ምድ​ሩን ተመ​ል​ከቱ።</verse>
				<verse number="36">አጫ​ጅም ዋጋ​ውን ያገ​ኛል፤ የሚ​ዘ​ራና የሚ​ያ​ጭ​ድም በአ​ን​ድ​ነት ደስ እን​ዲ​ላ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ፍሬን ይሰ​በ​ስ​ባል።</verse>
				<verse number="37">አንዱ ይዘ​ራል፥ ሌላ​ውም ያጭ​ዳል የሚ​ለው ቃል በዚህ እው​ነት ሆኖ​አል።</verse>
				<verse number="38">እኔም ያል​ደ​ከ​ማ​ች​ሁ​በ​ትን እን​ድ​ታ​ጭዱ ላክ​ኋ​ችሁ፤ ሌሎች ደከሙ፤ እና​ን​ተም በድ​ካ​ማ​ቸው ገባ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="39">“የሠ​ራ​ሁ​ትን ሁሉ ነገ​ረኝ” ብላ የመ​ሰ​ከ​ረ​ችው ሴት ስለ ነገ​ረ​ቻ​ቸ​ውም ከዚ​ያች ከሰ​ማ​ርያ ከተማ ብዙ​ዎች አመ​ኑ​በት።</verse>
				<verse number="40">ሳም​ራ​ው​ያ​ንም ሁሉ ወደ እርሱ መጥ​ተው በእ​ነ​ርሱ ዘንድ እን​ዲ​ኖር ማለ​ዱት፤ ሁለት ቀንም ያህል በዚያ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="41">ስለ ቃሉም እጅግ ብዙ​ዎች አመ​ኑ​በት።</verse>
				<verse number="42">ሴቲ​ቱ​ንም፥ “እኛ ራሳ​ችን ይህ በእ​ው​ነት የዓ​ለም መድ​ኀ​ኒት ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ ሰም​ተ​ንና ተረ​ድ​ተን ነው እንጂ በአ​ንቺ ቃል ያመ​ን​በት አይ​ደ​ለም” አሏት።</verse>
				<verse number="43">ከሁ​ለት ቀንም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከዚያ ወጥቶ ወደ ገሊላ ሄደ።</verse>
				<verse number="44">ነቢይ በገዛ ሀገሩ እን​ደ​ማ​ይ​ከ​ብር እርሱ ራሱ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መሰ​ከረ።</verse>
				<verse number="45">ወደ ገሊ​ላም ደግሞ በገባ ጊዜ ገሊ​ላ​ው​ያን ሁሉ ተቀ​በ​ሉት፤ እነ​ርሱ ለበ​ዓል ሄደው ስለ ነበር በበ​ዓሉ ቀን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ምር አይ​ተው ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="46">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ውኃ​ውን የወ​ይን ጠጅ ወደ አደ​ረ​ገ​በት የገ​ሊላ ክፍል ወደ​ም​ት​ሆን ወደ ቃና ዳግ​መኛ ሄደ። በቅ​ፍ​ር​ና​ሆም ልጁ የታ​መ​መ​በት የን​ጉሥ ወገን የሆነ አንድ ሰው ነበረ፤</verse>
				<verse number="47">እር​ሱም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከይ​ሁዳ ወደ ገሊላ እንደ መጣ በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ ሄደ፤ ሊሞት ቀርቦ ነበ​ርና ወርዶ ልጁን ያድ​ን​ለት ዘንድ ለመ​ነው፤</verse>
				<verse number="48">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ምል​ክ​ት​ንና ድንቅ ሥራን ካላ​ያ​ችሁ አታ​ም​ኑም” አለው።</verse>
				<verse number="49">ያም የን​ጉሥ ወገን የሆነ ሰው፥ “አቤቱ፥ ልጄ ሳይ​ሞት ፈጥ​ነህ ውረድ” አለው።</verse>
				<verse number="50">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ሂድ፤ ልጅ​ህስ ድኖ​አል” አለው፤ ያም ሰው፦ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በነ​ገ​ረው ቃል አምኖ ሄደ።</verse>
				<verse number="51">ሲወ​ር​ድም አገ​ል​ጋ​ዮቹ ተቀ​በ​ሉ​ትና፥ “ልጅ​ህስ ድኖ​አል” ብለው ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="52">የዳ​ነ​ባ​ትን ሰዓ​ቷ​ንም ጠየ​ቃ​ቸው፤ “ትና​ን​ትና በሰ​ባት ሰዓት ንዳዱ ተወው” አሉት።</verse>
				<verse number="53">አባ​ቱም፥ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፥ “ልጅህ ድኖ​አል” ባለ​በት ሰዓት እንደ ሆነች ዐወቀ፤ እር​ሱም፥ ቤተ ሰቦ​ቹም ሁሉ አመኑ።</verse>
				<verse number="54">ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከይ​ሁዳ ወደ ገሊላ መጥቶ ያደ​ረ​ገው ሁለ​ተ​ኛው ተአ​ምር ይህ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ በአ​ይ​ሁድ በዓል እን​ዲህ ሆነ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣ።</verse>
				<verse number="2">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በበ​ጎች በር አጠ​ገብ መጠ​መ​ቂያ ነበ​ረች፤ ስም​ዋ​ንም በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቤተ ሳይዳ ይሉ​አ​ታል፤ አም​ስት እር​ከ​ኖ​ችም ነበ​ሩ​አት።</verse>
				<verse number="3">በዚ​ያም ዕው​ሮ​ችና አን​ካ​ሶች፥ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውም የሰ​ለለ ብዙ ድው​ያን ተኝ​ተው የው​ኃ​ዉን መና​ወጥ ይጠ​ባ​በቁ ነበር።</verse>
				<verse number="4">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ወደ መጠ​መ​ቂ​ያዉ ወርዶ ውኃ​ዉን በሚ​ያ​ና​ው​ጠው ጊዜ፥ ከው​ኃዉ መና​ወጥ በኋላ በመ​ጀ​መ​ሪያ ወርዶ የሚ​ጠ​መቅ ካለ​በት ደዌ ሁሉ ይፈ​ወስ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="5">በዚ​ያም ከታ​መመ ሠላሳ ስም​ንት ዓመት የሆ​ነው አንድ ሰው ነበር።</verse>
				<verse number="6">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያን ሰው በአ​ል​ጋዉ ተኝቶ ባየ ጊዜ በደዌ ብዙ ዘመን እንደ ቈየ ዐውቆ፥ “ልት​ድን ትወ​ዳ​ለ​ህን?” አለው።</verse>
				<verse number="7">ድው​ዩም መልሶ፥ “አዎን ጌታዬ ሆይ፥ ነገር ግን ውኃዉ በተ​ና​ወጠ ጊዜ ወደ መጠ​መ​ቂ​ያዉ የሚ​ያ​ወ​ር​ደኝ ሰው የለ​ኝም፤ እኔ በም​መ​ጣ​በት ጊዜ ሌላው ቀድ​ሞኝ ይወ​ር​ዳል” አለው።</verse>
				<verse number="8">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ተነ​ሥና አል​ጋ​ህን ተሸ​ክ​መህ ሂድ” አለው።</verse>
				<verse number="9">ወዲ​ያ​ው​ኑም ያ ሰው ድኖ አል​ጋ​ውን ተሸ​ክሞ ሄደ፤ ያች ቀንም ሰን​በት ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="10">አይ​ሁ​ድም የዳ​ነ​ውን ሰው፥ “ዛሬ ሰን​በት ነው፤ አል​ጋ​ህን ልት​ሸ​ከም አይ​ገ​ባ​ህም” አሉት።</verse>
				<verse number="11">እር​ሱም መልሶ፥ “ያዳ​ነኝ እርሱ፦ አል​ጋ​ህን ተሸ​ክ​መህ ሂድ አለኝ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">አይ​ሁ​ድም፥ “አል​ጋ​ህን ተሸ​ክ​መህ ሂድ ያለህ ሰው​ዬው ማነው?” ብለው ጠየ​ቁት።</verse>
				<verse number="13">ያ የተ​ፈ​ወ​ሰው ግን ያዳ​ነው ማን እንደ ሆነ አላ​ወ​ቀም፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በዚያ ቦታ በነ​በ​ሩት ብዙ ሰዎች መካ​ከል ተሰ​ውሮ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="14">ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያን የዳ​ነ​ውን ሰው በቤተ መቅ​ደስ አገ​ኘ​ውና፥ “እነሆ፥ ድነ​ሃል፤ ግን ከዚህ የባሰ እን​ዳ​ያ​ገ​ኝህ ዳግ​መኛ እን​ዳ​ት​በ​ድል ተጠ​ን​ቀቅ” አለው።</verse>
				<verse number="15">ያም ሰው ሄዶ ያዳ​ነው ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ እንደ ሆነ ለአ​ይ​ሁድ ነገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">ስለ​ዚ​ህም አይ​ሁድ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ያሳ​ድ​ዱ​ትና ሊገ​ድ​ሉ​ትም ይሹ ነበር፤ በሰ​ን​በት እን​ዲህ ያደ​ርግ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="17">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “አባቴ እስከ ዛሬ ይሠ​ራል፤ እኔም እሠ​ራ​ለሁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">ስለ​ዚ​ህም አይ​ሁድ ሊገ​ድ​ሉት በጣም ይፈ​ልጉ ነበር፤ “ሰን​በ​ትን የሚ​ሽር ነው” በማ​ለት ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ደግ​ሞም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን “አባቴ ነው ይላል፤ ራሱ​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ያስ​ተ​ካ​ክ​ላል” በማ​ለት ነው እንጂ።</verse>
				<verse number="19">ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወልድ ከራሱ ብቻ ምንም ሊያ​ደ​ርግ አይ​ች​ልም፤ አብ ሲያ​ደ​ርግ ያየ​ውን ነው እንጂ፤ ወል​ድም አብ የሚ​ሠ​ራ​ውን ያንኑ እን​ዲሁ ይሠ​ራል።</verse>
				<verse number="20">አብ ልጁን ይወ​ዳ​ልና የሚ​ሠ​ራ​ው​ንም ሥራ ሁሉ ያሳ​የ​ዋል፤ እና​ን​ተም ታደ​ንቁ ዘንድ ከዚህ የሚ​በ​ልጥ ሥራን ያሳ​የ​ዋል።</verse>
				<verse number="21">አብ ሙታ​ንን እን​ደ​ሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ቸው፥ ሕይ​ወ​ት​ንም እን​ደ​ሚ​ሰ​ጣ​ቸው እን​ዲሁ ወል​ድም ለሚ​ወ​ድ​ዳ​ቸው ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣል።</verse>
				<verse number="22">አብ ከቶ በማ​ንም አይ​ፈ​ር​ድም፤ ፍር​ዱን ሁሉ ለወ​ልድ ሰጠው እንጂ።</verse>
				<verse number="23">ሰዎች ሁሉ አብን እን​ደ​ሚ​ያ​ከ​ብሩ ወል​ድን ያከ​ብሩ ዘንድ፤ ወል​ድን የማ​ያ​ከ​ብር ግን የላ​ከ​ውን አብን አያ​ከ​ብ​ርም።</verse>
				<verse number="24">እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ቃሌን የሚ​ሰማ በላ​ከ​ኝም የሚ​ያ​ምን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ያገ​ኛል፤ ከሞ​ትም ወደ ሕይ​ወት ተሻ​ገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይ​ሄ​ድም።</verse>
				<verse number="25">“እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሙታን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ ቃል የሚ​ሰ​ሙ​በት ሰዓት ይመ​ጣል፤ እር​ሱም አሁን ነው፤ የሚ​ሰ​ሙ​ትም ይድ​ናሉ።</verse>
				<verse number="26">ለአብ በራሱ ሕይ​ወት እን​ዳ​ለው፥ እን​ዲ​ሁም ደግሞ ለወ​ልድ በራሱ ሕይ​ወት እን​ዲ​ኖ​ረው ሰጠው።</verse>
				<verse number="27">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ የሰው ልጅ ነውና ይፈ​ርድ ዘንድ ሥል​ጣ​ንን ሰጠው።</verse>
				<verse number="28">“በመ​ቃ​ብር ያሉ ሁሉ ቃሉን የሚ​ሰ​ሙ​ባት ጊዜ ትመ​ጣ​ለ​ችና ስለ​ዚህ አታ​ድ​ንቁ።</verse>
				<verse number="29">መል​ካም የሠሩ ለሕ​ይ​ወት ትን​ሣኤ፥ ክፉ የሠ​ሩም ለፍ​ርድ ትን​ሣኤ ይነ​ሣሉ።</verse>
				<verse number="30">እኔ ከራሴ አን​ዳች አደ​ርግ ዘንድ አል​ች​ልም፤ እንደ ሰማሁ እፈ​ር​ዳ​ለሁ እንጂ፤ ፍር​ዴም እው​ነት ነው፤ የላ​ከ​ኝን ፈቃድ እንጂ የእ​ኔን ፈቃድ አል​ሻ​ምና።</verse>
				<verse number="31">“እኔ ለራሴ ብመ​ሰ​ክር ምስ​ክ​ር​ነቴ እው​ነት አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="32">ነገር ግን ለእኔ የሚ​መ​ሰ​ክር ሌላ ነው፤ ስለ እኔ የመ​ሰ​ከ​ረው ምስ​ክ​ር​ነ​ቱም እው​ነት እን​ደ​ሆነ አው​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="33">እና​ንተ ወደ ዮሐ​ንስ ልካ​ችሁ አል​ነ​በ​ረ​ምን? እር​ሱም ምስ​ክ​ር​ነ​ቱን በእ​ው​ነት ነገ​ራ​ችሁ።</verse>
				<verse number="34">እኔ ግን የሰ​ውን ምስ​ክ​ር​ነት የምሻ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ነገር ግን እና​ንተ ትድኑ ዘንድ ይህን እላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="35">እርሱ የሚ​ነ​ድና የሚ​ያ​በራ መብ​ራት ነበረ፤ እና​ን​ተም አን​ዲት ሰዓት በብ​ር​ሃኑ ደስ ሊላ​ችሁ ወደ​ዳ​ችሁ።</verse>
				<verse number="36">እኔ ግን ከዮ​ሐ​ንስ ምስ​ክ​ር​ነት የሚ​በ​ልጥ ምስ​ክር አለኝ፤ ልሠ​ራ​ውና ልፈ​ጽ​መው አባቴ የሰ​ጠኝ ሥራ፥ አብ እንደ ላከኝ ያ የም​ሠ​ራው ሥራ ምስ​ክሬ ነውና።</verse>
				<verse number="37">የላ​ከኝ አብም ስለ እኔ መስ​ክ​ሮ​አል፤ ከሆ​ነም ጀምሮ ቃሉን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ መል​ኩ​ንም አላ​ያ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="38">ቃሉም የላ​ች​ሁም፤ በእ​ና​ንተ ዘን​ድም አይ​ኖ​ርም፤ እርሱ የላ​ከ​ውን አላ​መ​ና​ች​ሁ​ምና።</verse>
				<verse number="39">መጻ​ሕ​ፍ​ትን መር​ምሩ፤ በእ​ነ​ርሱ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን የም​ታ​ገኙ ይመ​ስ​ላ​ች​ኋ​ልና፤ እነ​ር​ሱም የእኔ ምስ​ክ​ሮች ናቸው።</verse>
				<verse number="40">ሕይ​ወ​ትን ታገኙ ዘንድ ወደ እኔ ልት​መጡ አት​ወ​ዱም።</verse>
				<verse number="41">እኔ ከሰው ክብ​ርን ልቀ​በል አል​ሻም።</verse>
				<verse number="42">ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍቅር በእ​ና​ንተ እን​ደ​ሌ​ለ​ባ​ችሁ ዐወ​ቅሁ።</verse>
				<verse number="43">እኔ በአ​ባቴ ስም መጣሁ፥ አል​ተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁ​ኝ​ምም፤ ሌላው ግን በራሱ ስም ቢመጣ እር​ሱን ትቀ​በ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="44">ከባ​ል​ን​ጀ​ራ​ችሁ ክብ​ርን የም​ት​መ​ርጡ፥ ከአ​ንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብ​ርን የማ​ትሹ እና​ንተ እን​ዴት ልታ​ምኑ ትች​ላ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="45">እኔ በአብ ዘንድ የም​ከ​ስ​ሳ​ችሁ አይ​ም​ሰ​ላ​ችሁ፤ የሚ​ከ​ስ​ሳ​ች​ሁስ አለ፤ እር​ሱም እና​ንተ ተስፋ የም​ታ​ደ​ር​ጉት ሙሴ ነው።</verse>
				<verse number="46">ሙሴ​ንስ አም​ና​ች​ሁት ቢሆን እኔ​ንም ባመ​ና​ች​ሁኝ ነበር፤ እርሱ ስለ እኔ ጽፎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="47">ሙሴ የጻ​ፈ​ውን ካላ​መ​ና​ችሁ ግን የእ​ኔን ቃል እን​ዴት ታም​ና​ላ​ችሁ?”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">ከዚህ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ወደ ጥብ​ር​ያ​ዶስ ሄደ።</verse>
				<verse number="2">በበ​ሽ​ተ​ኞ​ችም ላይ ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ራት ስለ አዩ ብዙ ሰዎች ተከ​ተ​ሉት፤</verse>
				<verse number="3">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ ተራራ ወጣ፤ ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ጋር በዚያ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="4">የአ​ይ​ሁድ የፋ​ሲካ በዓ​ልም ቀርቦ ነበር።</verse>
				<verse number="5">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዐይ​ኖ​ቹን አን​ሥቶ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ሲመጡ አየና ፊል​ጶ​ስን፥ “ለእ​ነ​ዚህ ሰዎች የም​ና​በ​ላ​ቸው እን​ጀራ ከወ​ዴት እን​ግዛ?” አለው።</verse>
				<verse number="6">ሲፈ​ት​ነው ይህን አለ እንጂ፥ እር​ሱስ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ያውቅ ነበር።</verse>
				<verse number="7">ፊል​ጶ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “ከእ​ነ​ርሱ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ጥቂት ጥቂት ይወ​ስዱ ዘንድ የሁ​ለት መቶ ዲናር እን​ጀራ አይ​በ​ቃ​ቸ​ውም።”</verse>
				<verse number="8">ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አንዱ የስ​ም​ዖን ጴጥ​ሮስ ወን​ድም እን​ድ​ር​ያስ እን​ዲህ አለው፥</verse>
				<verse number="9">“አም​ስት የገ​ብስ እን​ጀ​ራና ሁለት ዓሣ የያዘ ብላ​ቴና በዚህ አለ፤ ነገር ግን እነ​ዚህ ይህን ለሚ​ያ​ህል ሰው ምን ይበ​ቃሉ?”</verse>
				<verse number="10">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ሰዎ​ቹን እን​ዲ​ቀ​መጡ አድ​ርጉ” አለ፤ የዚያ ቦታም ሣሩ ብዙ ነበር፤ ወን​ዶ​ቹም በመ​ስኩ ላይ ተቀ​መጡ፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም አም​ስት ሺህ ያህል ነበር።</verse>
				<verse number="11">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያን እን​ጀራ ይዞ አመ​ሰ​ገነ፤ ቈር​ሶም ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሰጣ​ቸው፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ለተ​ቀ​መ​ጡት ሰዎች ሰጡ​አ​ቸው፤ ከዓ​ሣ​ውም እን​ዲሁ የፈ​ለ​ጉ​ትን ያህል ሰጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">ከጠ​ገ​ቡም በኋላ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን፥ “ከቍ​ር​ስ​ራሹ ምንም የሚ​ወ​ድቅ እን​ዳ​ይ​ኖር የተ​ረ​ፈ​ውን ቍር​ስ​ራሽ አንሡ፤” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">እነ​ር​ሱም ሰበ​ሰቡ፥ በል​ተው ከጠ​ገቡ በኋ​ላም ከአ​ም​ስቱ የገ​ብስ እን​ጀራ የተ​ረ​ፈው ቍር​ስ​ራሽ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሞላ።</verse>
				<verse number="14">ሕዝ​ቡም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ራት አይ​ተው፥ “ይህ በእ​ው​ነት ወደ ዓለም የሚ​መ​ጣው ነቢይ ነው” አሉ።</verse>
				<verse number="15">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መጥ​ተው ነጥ​ቀው ሊያ​ነ​ግ​ሡት እን​ደ​ሚሹ ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና ብቻ​ውን ወደ ተራራ ሄደ።</verse>
				<verse number="16">በመ​ሸም ጊዜ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ወደ ባሕር ወረዱ።</verse>
				<verse number="17">ወደ ታን​ኳም ወጡ፤ ወደ ባሕር ማዶ ወደ ቅፍ​ር​ና​ሆ​ምም ሄዱ፤ እነ​ሆም፥ ፈጽሞ ጨለማ ሆነ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ እነ​ርሱ ገና አል​መ​ጣም ነበር።</verse>
				<verse number="18">ባሕሩ ግን ይታ​ወክ ነበር፤ ጽኑ ነፋስ ይነ​ፍስ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="19">ሃያ አም​ስት ወይም ሠላሳ ምዕ​ራፍ ያህል ከሄዱ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን በባ​ሕር ላይ ሲሄድ አዩት፤ ወደ ታን​ኳዉ በቀ​ረበ ጊዜም ፈሩ።</verse>
				<verse number="20">እር​ሱም፥ “እኔ ነኝ፤ አት​ፍሩ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">ወደ ታን​ኳ​ው​ዪቱ ሊያ​ወ​ጡት ሲሹም ታን​ኳ​ዪቱ ወዲ​ያ​ውኑ ሊሄዱ ወደ ወደ​ዱ​በት ወደብ ደረ​ሰች።</verse>
				<verse number="22">በማ​ግ​ሥ​ቱም ከባ​ሕሩ ዳር ቆመው የነ​በሩ ሰዎች ከአ​ን​ዲት ታንኳ በቀር ከዚያ ሌላ ታንኳ እን​ዳ​ል​ነ​በረ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ለብ​ቻ​ቸው ሄዱ እንጂ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ወደ ታንኳ እን​ዳ​ል​ወጣ አዩ።</verse>
				<verse number="23">ደግ​ሞም ጌታ​ችን የባ​ረ​ከ​ውን እን​ጀራ ከበ​ሉ​በት ቦታ አቅ​ራ​ቢያ ከጥ​ብ​ር​ያ​ዶስ ሌሎች ታን​ኳ​ዎች መጥ​ተው ነበር።</verse>
				<verse number="24">እነ​ዚያ ሰዎ​ችም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም በዚያ እን​ዳ​ል​ነ​በሩ ባዩ ጊዜ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ይፈ​ል​ጉት ዘንድ በእ​ነ​ዚያ ታን​ኳ​ዎች ገብ​ተው ወደ ቅፍ​ር​ና​ሆም መጡ።</verse>
				<verse number="25">በባ​ሕሩ ዳርም ባገ​ኙት ጊዜ፥ “መም​ህር ሆይ፥ ወደ​ዚህ መቼ መጣህ?” አሉት።</verse>
				<verse number="26">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ንተ የም​ት​ፈ​ል​ጉኝ እን​ጀራ ስለ በላ​ች​ሁና ስለ ጠገ​ባ​ችሁ ነው እንጂ ተአ​ም​ራት ስለ አያ​ችሁ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="27">የሰው ልጅ ለሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ለሚ​ኖር መብል ሥሩ እንጂ ለሚ​ጠ​ፋው መብል አይ​ደ​ለም፤ ይህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ አት​ሞ​ታ​ልና።”</verse>
				<verse number="28">“እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ እን​ሠራ ዘንድ ምን እና​ድ​ርግ?” አሉት።</verse>
				<verse number="29">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ይህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ እርሱ በላ​ከው ታምኑ ዘንድ ነው፤” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="30">እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉት፥ “የም​ት​ሠ​ራ​ውን አይ​ተን በአ​ንተ እና​ምን ዘንድ ምን ተአ​ም​ራት ታደ​ር​ጋ​ለህ?</verse>
				<verse number="31">አባ​ቶ​ቻ​ች​ንስ ‘ሊበሉ እን​ጀራ ከሰ​ማይ ሰጣ​ቸው’ ተብሎ እንደ ተጻፈ በም​ድረ በዳ መና በሉ።</verse>
				<verse number="32">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ያን እን​ጀራ ከሰ​ማይ የሰ​ጣ​ችሁ ሙሴ አይ​ደ​ለም፤ አባቴ ከሰ​ማይ የእ​ው​ነት እን​ጀ​ራን ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋል እንጂ።</verse>
				<verse number="33">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ጀራ ከሰ​ማይ የሚ​ወ​ርድ፤ ለዓ​ለ​ምም ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ ነውና።”</verse>
				<verse number="34">እነ​ር​ሱም፥ “አቤቱ ከዚያ እን​ጀራ ሁል​ጊዜ ስጠን” አሉት።</verse>
				<verse number="35">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የሕ​ይ​ወት እን​ጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚ​መጣ ከቶ አይ​ራ​ብም፤ በእኔ የሚ​ያ​ም​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ጠ​ማም።</verse>
				<verse number="36">ነገር ግን እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ አያ​ች​ሁኝ፤ አላ​መ​ና​ች​ሁ​ብ​ኝ​ምም።</verse>
				<verse number="37">አብ የሚ​ሰ​ጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመ​ጣል፤ ወደ እኔ የሚ​መ​ጣ​ው​ንም ከቶ ወደ ውጭ አላ​ወ​ጣ​ውም።</verse>
				<verse number="38">ከሰ​ማይ የወ​ረ​ድሁ የላ​ከ​ኝን ፈቃድ እንጂ፥ ፈቃ​ዴን ላደ​ርግ አይ​ደ​ለ​ምና።</verse>
				<verse number="39">የላ​ከኝ የአብ ፈቃ​ድም ይህ ነው፤ ከሰ​ጠኝ ሁሉ አን​ድስ እንኳ ቢሆን እን​ዳ​ይ​ጠፋ ነው፤ ነገር ግን እኔ በኋ​ለ​ኛ​ዪቱ ቀን አስ​ነ​ሣ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="40">የአ​ባቴ ፈቃዱ ይህ ነው፤ ወል​ድን አይቶ የሚ​ያ​ም​ን​በት ሁሉ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እን​ዲ​ያ​ገኝ ነው፤ እኔም በመ​ጨ​ረ​ሻ​ዪቱ ቀን አስ​ነ​ሣ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="41">አይ​ሁ​ድም ስለ እርሱ አን​ጐ​ራ​ጐሩ፤ “ከሰ​ማይ የወ​ረደ የሕ​ይ​ወት እን​ጀራ እኔ ነኝ” ብሎ​አ​ቸ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="42">“እኛ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን የም​ና​ው​ቃ​ቸው ይህ የዮ​ሴፍ ልጅ ኢየ​ሱስ አይ​ደ​ለ​ምን? እን​ግ​ዲህ እን​ዴት ከሰ​ማይ ወረ​ድሁ ይለ​ናል?” አሉ።</verse>
				<verse number="43">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እርስ በር​ሳ​ችሁ አታ​ን​ጐ​ራ​ጕሩ።</verse>
				<verse number="44">የላ​ከኝ አብ ካል​ሳ​በው በቀር ወደ እኔ መም​ጣ​ትን የሚ​ችል የለም፤ እኔም በመ​ጨ​ረ​ሻ​ዪቱ ቀን አስ​ነ​ሣ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="45">‘ሁሉም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ማሩ ይሆ​ናሉ’ ተብሎ በነ​ቢ​ያት መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል፤ እን​ግ​ዲህ ከአ​ባቴ የሰማ ሁሉ ተምሮ ወደ እኔ ይመ​ጣል።</verse>
				<verse number="46">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆ​ነው በቀር አብን ያየው ማንም የለም፤ እር​ሱም አብን አየው።</verse>
				<verse number="47">እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በእኔ የሚ​ያ​ምን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት አለው።</verse>
				<verse number="48">የሕ​ይ​ወት እን​ጀራ እኔ ነኝ።</verse>
				<verse number="49">አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁስ በም​ድረ በዳ መና በሉ፥ ሞቱም።</verse>
				<verse number="50">ከእ​ርሱ የበላ ሁሉ እን​ዳ​ይ​ሞት ከሰ​ማይ የወ​ረደ እን​ጀራ ይህ ነው።”</verse>
				<verse number="51">“ከሰ​ማይ የወ​ረደ የሕ​ይ​ወት እን​ጀራ እኔ ነኝ፤ ከዚህ እን​ጀራ የሚ​በላ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል፤ ስለ ዓለም ሕይ​ወት የም​ሰ​ጠው ይህ እን​ጀራ ሥጋዬ ነው።”</verse>
				<verse number="52">አይ​ሁ​ድም፥ “ይህ እን​በላ ዘንድ ሥጋ​ውን ሊሰ​ጠን እን​ዴት ይች​ላል?” ብለው እርስ በር​ሳ​ቸው ተከ​ራ​ከሩ።</verse>
				<verse number="53">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ የሰ​ውን ልጅ ሥጋ ካል​በ​ላ​ችሁ፥ ደሙ​ንም ካል​ጠ​ጣ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የላ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="54">ሥጋ​ዬን የሚ​በላ፥ ደሜ​ንም የሚ​ጠጣ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት አለው፤ እኔም በኋ​ለ​ኛ​ዪቱ ቀን አነ​ሣ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="55">ሥጋዬ እው​ነ​ተኛ መብል ነውና፤ ደሜም እው​ነ​ተኛ መጠጥ ነውና።</verse>
				<verse number="56">ሥጋ​ዬን የሚ​በላ፥ ደሜ​ንም የሚ​ጠጣ በእኔ ይኖ​ራል፤ እኔም በእ​ርሱ እኖ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="57">የላ​ከኝ አብ ሕያው እንደ ሆነ፥ እኔም ስለ አብ ሕያው ነኝ፤ ሥጋ​ዬ​ንም የሚ​በላ እርሱ ደግሞ ስለ እኔ ሕያው ሆኖ ይኖ​ራል።</verse>
				<verse number="58">ከሰ​ማይ የወ​ረደ እን​ጀራ ይህ ነው፤ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ በል​ተ​ውት እን​ደ​ሞ​ቱ​በት ያለ መና አይ​ደ​ለም፤ ይህን እን​ጀራ የሚ​በላ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕያው ሆኖ ይኖ​ራል።”</verse>
				<verse number="59">በቅ​ፍ​ር​ና​ሆ​ምም በም​ኵ​ራብ ሲያ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው ይህን ተና​ገረ፤</verse>
				<verse number="60">ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ብዙ​ዎቹ ይህን ሰም​ተው፥ “ይህ ነገር የሚ​ያ​ስ​ጨ​ንቅ ነው፤ ማንስ ሊሰ​ማው ይች​ላል?” አሉ።</verse>
				<verse number="61">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ስለ​ዚህ ነገር እንደ አን​ጐ​ራ​ጐሩ በልቡ ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ይህ ያሰ​ና​ክ​ላ​ች​ኋ​ልን?</verse>
				<verse number="62">እን​ግ​ዲህ የሰው ልጅ ቀድሞ ወደ ነበ​ረ​በት ሲያ​ርግ ብታ​ዩት እን​ዴት ይሆን?</verse>
				<verse number="63">ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ መን​ፈስ ነው፤ ሥጋ ግን አን​ዳች አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ ይህም እኔ የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ ቃል መን​ፈስ ነው፤ ሕይ​ወ​ትም ነው።</verse>
				<verse number="64">ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ውስጥ የማ​ያ​ምኑ አሉ፤” ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከጥ​ንት ጀምሮ የማ​ያ​ም​ኑ​በት እነ​ማን እንደ ሆኑ፥ የሚ​ያ​ሲ​ዘ​ውም ማን እንደ ሆነ ያውቅ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="65">እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ስለ​ዚህ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከአብ ካል​ተ​ሰ​ጠው በቀር ወደ እኔ መም​ጣት የሚ​ቻ​ለው የለም።”</verse>
				<verse number="66">ስለ​ዚ​ህም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ወደ ኋላ​ቸው የተ​መ​ለሱ ብዙ​ዎች ናቸው፤ ከዚ​ያም ወዲህ አብ​ረ​ውት አል​ሄ​ዱም።</verse>
				<verse number="67">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዐሥራ ሁለ​ቱን፥ “እና​ንተ ደግሞ ልት​ሄዱ ትሻ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="68">ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “አቤቱ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም የሕ​ይ​ወት ቃል እያ​ለህ ወደ ማን እን​ሄ​ዳ​ለን?</verse>
				<verse number="69">እኛስ የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ክር​ስ​ቶስ አንተ እንደ ሆንህ አም​ነ​ናል፤ አው​ቀ​ና​ልም።”</verse>
				<verse number="70">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ እና​ን​ተን ዐሥራ ሁለ​ታ​ች​ሁን መር​ጫ​ችሁ የለ​ምን? ነገር ግን ከእ​ና​ንተ አንዱ ሰይ​ጣን ነው።”</verse>
				<verse number="71">ይህ​ንም ስለ ስም​ዖን ልጅ ስለ አስ​ቆ​ሮ​ታ​ዊው ይሁዳ ተና​ገረ፤ እርሱ ያሲ​ዘው ዘንድ አለ​ውና፤ እር​ሱም ከዐ​ሥራ ሁለቱ አንዱ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">ከዚህ በኋ​ላም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በገ​ሊላ ይመ​ላ​ለስ ነበረ፤ ወደ ይሁዳ ምድ​ርም ሊሄድ አል​ወ​ደ​ደም፤ አይ​ሁድ ሊገ​ድ​ሉት ይሹ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="2">የአ​ይ​ሁ​ድም የዳስ በዓ​ላ​ቸው ደርሶ ነበር።</verse>
				<verse number="3">ወን​ድ​ሞ​ቹም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እን​ዲህ አሉት- “ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትህ የም​ት​ሠ​ራ​ውን ሥራ​ህን እን​ዲ​ያዩ ከዚህ ወጥ​ተህ ወደ ይሁዳ ሀገር ሂድ።</verse>
				<verse number="4">ሊገ​ለጥ ወድዶ ሳለ በስ​ውር አን​ዳች ነገር የሚ​ያ​ደ​ርግ ማንም የለ​ምና፤ አንተ ግን ይህን የም​ታ​ደ​ርግ ከሆነ ራስ​ህን ለዓ​ለም ግለጥ።</verse>
				<verse number="5">ወን​ድ​ሞቹ ገና አላ​መ​ኑ​በ​ትም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="6">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ጊዜዬ ገና አል​ደ​ረ​ሰም፤ የእ​ና​ንተ ጊዜ ግን ዘወ​ትር የተ​ዘ​ጋጀ ነው።</verse>
				<verse number="7">ዓለም እና​ን​ተን ሊጠ​ላ​ችሁ አይ​ች​ልም፤ እኔን ግን ይጠ​ላ​ኛል፤ ሥራዉ ክፉ እንደ ሆነ እኔ እመ​ሰ​ክ​ር​በ​ታ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="8">እና​ን​ተም ወደ​ዚህ በዓል ውጡ፤ እኔ አሁን ወደ​ዚህ በዓል አል​ወ​ጣም፤ ጊዜዬ ገና አል​ደ​ረ​ሰ​ምና።”</verse>
				<verse number="9">እር​ሱም እን​ዲህ ብሎ​አ​ቸው በገ​ሊላ ቀረ።</verse>
				<verse number="10">ወን​ድ​ሞቹ ለበ​ዓል ከወጡ በኋላ፥ እር​ሱም ያን​ጊዜ በግ​ልጥ ሳይ​ሆን ተሰ​ውሮ ወጣ።</verse>
				<verse number="11">አይ​ሁ​ድም፥ “ያ ወዴት ነው?” እያሉ በበ​ዓሉ ይፈ​ል​ጉት ጀመር።</verse>
				<verse number="12">ሕዝ​ቡም ስለ እርሱ ብዙ አን​ጐ​ራ​ጐሩ፥ “ደግ ሰው ነው” ያሉ ነበሩ፤ ሌሎች ግን፥ “አይ​ደ​ለም፤ ሕዝ​ቡን ያስ​ታል እንጂ” አሉ።</verse>
				<verse number="13">ነገር ግን፥ አይ​ሁ​ድን በመ​ፍ​ራት የእ​ር​ሱን ነገር ገልጦ የተ​ና​ገረ አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="14">በበ​ዓሉ ቀኖች እኩ​ሌ​ታም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ መቅ​ደስ ወጥቶ ያስ​ተ​ምር ጀመረ።</verse>
				<verse number="15">አይ​ሁ​ድም፥ “ይህ ሳይ​ማር መጽ​ሐ​ፍን እን​ዴት ያው​ቃል?” እያሉ ትም​ህ​ር​ቱን አደ​ነቁ።</verse>
				<verse number="16">ስለ​ዚ​ህም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ትም​ህ​ርቴ የላ​ከኝ ናት እንጂ የእኔ አይ​ደ​ለ​ችም።</verse>
				<verse number="17">ፈቃ​ዱን ሊያ​ደ​ርግ የሚ​ወ​ድድ ግን ትም​ህ​ርቴ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እንደ ሆነች፥ የም​ና​ገ​ረ​ውም ከራሴ እን​ዳ​ይ​ደለ እርሱ ያው​ቃል።</verse>
				<verse number="18">ከራሱ የሚ​ና​ገር የራ​ሱን ክብር ይሻል፤ የላ​ከ​ውን ያከ​ብር ዘንድ የሚ​ፈ​ልግ ግን እው​ነ​ተኛ ነው፤ ሐሰ​ትም የለ​በ​ትም።</verse>
				<verse number="19">ሙሴ ኦሪ​ትን ሰጥ​ቶ​አ​ችሁ የለ​ምን? ከእ​ና​ንተ አንዱ ስንኳ ኦሪ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ የለም፤ እን​ግ​ዲህ ልት​ገ​ድ​ሉኝ ለምን ትሻ​ላ​ችሁ?”</verse>
				<verse number="20">ሕዝ​ቡም፥ “ጋኔን አለ​ብ​ህን? ማን ሊገ​ድ​ልህ ይሻል?” ብለው መለ​ሱ​ለት።</verse>
				<verse number="21">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ አላ​ቸው፥ “አንድ ሥራ ሠራሁ፤ ሁላ​ች​ሁም አደ​ነ​ቃ​ችሁ።</verse>
				<verse number="22">ስለ​ዚህ ሙሴ ግዝ​ረ​ትን ሰጥ​ቶ​አ​ችሁ ነበር፤ ነገር ግን ከአ​ባ​ቶች ናት እንጂ ከሙሴ አይ​ደ​ለ​ችም፤ በሰ​ን​በ​ትም ሰውን ትገ​ዝ​ሩ​ታ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="23">የሙሴ ሕግ እን​ዳ​ይ​ሻር ሰው በሰ​ን​በት የሚ​ገ​ዘር ከሆነ እን​ግ​ዲያ ሰውን ሁለ​ን​ተ​ና​ውን በሰ​ን​በት ባድ​ነው ለምን ትነ​ቅ​ፉ​ኛ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="24">የእ​ው​ነት ፍርድ ፍረዱ እንጂ ለሰው ፊት በማ​ድ​ላት አት​ፍ​ረዱ።”</verse>
				<verse number="25">ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሰዎ​ችም እን​ዲህ የሚሉ ነበሩ፥ “ይህ አይ​ሁድ ሊገ​ድ​ሉት የሚ​ሹት አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="26">እነሆ፥ እርሱ በገ​ሀድ ይና​ገ​ራል፤ እነ​ርሱ ግን ምንም የሚ​ሉት የለም፤ ይህ በእ​ው​ነት ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ ምና​ል​ባት አለ​ቆች ዐው​ቀው ይሆን?</verse>
				<verse number="27">ነገር ግን ይህን ከየት እንደ ሆነ እና​ው​ቃ​ለን፤ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ጊዜስ ከወ​ዴት እንደ ሆነ ማንም አያ​ው​ቅም”።</verse>
				<verse number="28">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በመ​ቅ​ደስ ሲያ​ስ​ተ​ምር ቃሉን ከፍ አድ​ርጎ እን​ዲህ አለ፥ “እኔን ታው​ቁ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ከወ​ዴ​ትም እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ እኔ ራሴ የመ​ጣሁ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ነገር ግን እና​ንተ የማ​ታ​ው​ቁት የላ​ከኝ እው​ነ​ተኛ አለ።</verse>
				<verse number="29">እኔ ግን አው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ እኔ ከእ​ርሱ ነኝና፥ እር​ሱም ልኮ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="30">ስለ​ዚ​ህም ሊይ​ዙት ወደው ነበር፤ ነገር ግን እጁን በእ​ርሱ ላይ ያነሣ የለም፤ ጊዜዉ ገና አል​ደ​ረ​ሰም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="31">ከሕ​ዝ​ቡም ብዙ​ዎች አመ​ኑ​በ​ትና፥ “በውኑ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ጊዜ ይህ ሰው ካደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት የሚ​በ​ልጥ ያደ​ር​ጋ​ልን?” አሉ።</verse>
				<verse number="32">ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ሕዝቡ በእ​ርሱ ምክ​ን​ያት እንደ አጕ​ረ​መ​ረሙ ሰሙ፤ የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ይይ​ዙት ዘንድ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውን ላኩ።</verse>
				<verse number="33">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ጥቂት ቀን አብ​ሬ​አ​ችሁ እኖ​ራ​ለሁ፤ ከዚ​ህም በኋላ ወደ ላከኝ እሄ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="34">ትሹ​ኛ​ላ​ችሁ፤ አታ​ገ​ኙ​ኝ​ምም፤ እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በ​ትም እና​ንተ መም​ጣት አት​ች​ሉም።”</verse>
				<verse number="35">አይ​ሁ​ድም እርስ በር​ሳ​ቸው እን​ዲህ አሉ፥ “እኛ ልና​ገ​ኘው የማ​ን​ችል ይህ ወዴት ይሄ​ዳል? ወይስ የግ​ሪ​ክን ሰዎች ለማ​ስ​ተ​ማር በግ​ሪክ ሀገር ወደ ተበ​ተ​ኑት ይሄ​ዳ​ልን?</verse>
				<verse number="36">‘ትሹ​ኛ​ላ​ችሁ፤ አታ​ገ​ኙ​ኝ​ምም፤ እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በት እና​ንተ መም​ጣት አት​ች​ሉም’ የሚ​ለን ይህ ነገር ምን​ድን ነው?”</verse>
				<verse number="37">በኋ​ለ​ኛ​ዪቱ በታ​ላ​ቅዋ የበ​ዓል ቀንም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ቆመና ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ እን​ዲህ አለ፥ “የተ​ጠማ ወደ እኔ ይም​ጣና ይጠጣ።</verse>
				<verse number="38">በእ​ኔም የሚ​ያ​ምን መጽ​ሐፍ እንደ ተና​ገረ የሕ​ይ​ወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈ​ስ​ሳል።”</verse>
				<verse number="39">ይህ​ንም የሚ​ያ​ም​ኑ​በት ሰዎች ይቀ​በ​ሉት ዘንድ ስለ አላ​ቸው ስለ መን​ፈስ ቅዱስ ተና​ገረ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ገና ስላ​ል​ከ​በረ መን​ፈስ ቅዱስ ገና አል​ወ​ረ​ደም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="40">ከሕ​ዝ​ቡም ብዙ ሰዎች ይህን ነገር ሰም​ተው “በእ​ው​ነት ይህ ነቢይ ነው” አሉ።</verse>
				<verse number="41">“ክር​ስ​ቶስ ነው” ያሉም አሉ፤ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም እን​ዲህ አሉ፥ “በውኑ ክር​ስ​ቶስ ከገ​ሊላ ይወ​ጣ​ልን?</verse>
				<verse number="42">መጽ​ሐፍ ‘ክር​ስ​ቶስ ከዳ​ዊት ዘርና ከዳ​ዊት ከተማ ከቤተ ልሔም ይመ​ጣል’ ይል የለ​ምን?”</verse>
				<verse number="43">ስለ እር​ሱም ሕዝቡ እርስ በር​ሳ​ቸው ተለ​ያዩ።</verse>
				<verse number="44">ከእ​ነ​ር​ሱም ሊይ​ዙት የወ​ደዱ ነበሩ፤ ነገር ግን በእ​ርሱ ላይ እጁን ያነሣ የለም።</verse>
				<verse number="45">ሎሌ​ዎ​ቹም ወደ ካህ​ናት አለ​ቆ​ችና ወደ ፈሪ​ሳ​ው​ያን ተመ​ለሱ፤ እነ​ር​ሱም፥ “ያላ​መ​ጣ​ች​ሁት ለም​ን​ድን ነው?” አሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="46">ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም መል​ሰው፥ “ያ ሰው እንደ ተና​ገ​ረው ያለ ከቶ ሰው አል​ተ​ና​ገ​ረም” አሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="47">ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም መል​ሰው እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “እና​ን​ተም ደግሞ ተሳ​ሳ​ታ​ች​ሁን?</verse>
				<verse number="48">ከአ​ለ​ቆች ወይም ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ያመ​ነ​በት አለን?</verse>
				<verse number="49">ኦሪ​ትን ከማ​ያ​ውቁ ከእ​ነ​ዚህ ስሑ​ታን ሕዝብ በቀር፤ እነ​ር​ሱም የተ​ረ​ገሙ ናቸው።”</verse>
				<verse number="50">ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ ቀድሞ በሌ​ሊት ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ የሄ​ደው ኒቆ​ዲ​ሞስ እን​ዲህ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="51">“ሕጋ​ችን አስ​ቀ​ድሞ ሳይ​ሰማ፤ የሠ​ራ​ው​ንም ሳያ​ውቅ በሰው ይፈ​ር​ዳ​ልን?”</verse>
				<verse number="52">እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “አን​ተም ደግሞ ከገ​ሊላ ነህን? ከገ​ሊላ ነቢይ እን​ደ​ማ​ይ​ነሣ መር​ም​ርና እይ” አሉት።</verse>
				<verse number="53">ሁሉም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ወደ ቤታ​ቸው ሄዱ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ ደብረ ዘይት ሄደ።</verse>
				<verse number="2">በጥ​ዋ​ትም ገስ​ግሦ ዳግ​መኛ ወደ ቤተ መቅ​ደስ ገባ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ እር​ሱም ተቀ​ምጦ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ጀመር።</verse>
				<verse number="3">ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም በዝ​ሙት የተ​ያ​ዘች ሴት ወደ እርሱ አም​ጥ​ተው በመ​ካ​ከል አቆ​ሙ​አት።</verse>
				<verse number="4">እን​ዲ​ህም አሉት፥ “መም​ህር ሆይ፥ ይቺን ሴት ስታ​መ​ነ​ዝር አግ​ኝ​ተን ያዝ​ናት።</verse>
				<verse number="5">እን​ደ​ዚ​ችም ያለ​ችው በድ​ን​ጋይ እን​ድ​ት​ደ​በ​ደብ ሙሴ በኦ​ሪት አዘ​ዘን፤ እን​ግ​ዲህ አንተ ስለ እር​ስዋ ምን ትላ​ለህ?”</verse>
				<verse number="6">በእ​ር​ሱም ላይ ምክ​ን​ያት ሊያ​ገኙ ሲፈ​ት​ኑት ይህን አሉ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ጐን​በስ ብሎ በጣቱ በም​ድር ላይ ጻፈ።</verse>
				<verse number="7">ብዙ ጊዜ መላ​ል​ሰው በጠ​የ​ቁት ጊዜም ዐይ​ኖ​ቹን አን​ሥቶ፥ “ከእ​ና​ንተ ኀጢ​ኣት የሌ​ለ​በት አስ​ቀ​ድሞ ድን​ጋይ ይጣ​ል​ባት” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">ዳግ​መ​ኛም ጐን​በስ ብሎ በጣቱ በም​ድር ላይ ጻፈ።</verse>
				<verse number="9">እነ​ርሱ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ኅሊ​ና​ቸው ወቅ​ሶ​አ​ቸው ከሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች ጀምሮ እስከ ኋለ​ኞቹ ድረስ፥ አን​ዳ​ንድ እያሉ ወጡ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ብቻ​ውን ቀረ፤ ሴት​ዮ​ዪ​ቱም በመ​ካ​ከል ቆማ ነበር።</verse>
				<verse number="10">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ቀና ብሎ ወደ እር​ስዋ ተመ​ለ​ከ​ተና እን​ዲህ አላት፥ “አንቺ ሴት፥ የሚ​ከ​ሱሽ ወዴት አሉ?”</verse>
				<verse number="11">እር​ስ​ዋም፥ “ጌታ ሆይ፥ የማ​የው የለም” ብላ መለ​ሰ​ች​ለት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔም አል​ፈ​ር​ድ​ብ​ሽም፤ ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ዳግ​መኛ ኀጢ​ኣት አት​ሥሪ” አላት።</verse>
				<verse number="12">ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፥ “የዓ​ለም ብር​ሃን እኔ ነኝ፤ የሚ​ከ​ተ​ለኝ የሕ​ይ​ወት ብር​ሃ​ንን ያገ​ኛል እንጂ በጨ​ለማ ውስጥ አይ​መ​ላ​ለ​ስም” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “አንተ ስለ ራስህ ትመ​ሰ​ክ​ራ​ለህ፤ እን​ግ​ዲ​ያስ ምስ​ክ​ር​ነ​ትህ እው​ነት አይ​ደ​ለም” አሉት።</verse>
				<verse number="14">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ ስለ​ራሴ ብመ​ሰ​ክ​ርም ምስ​ክ​ር​ነቴ እው​ነት ነው፤ ከየት እን​ደ​መ​ጣሁ፥ ወዴት እን​ደ​ም​ሄ​ድም አው​ቃ​ለ​ሁና፤ እና​ንተ ግን ከየት እንደ መጣሁ ወዴት እን​ደ​ም​ሄ​ድም አታ​ው​ቁም።</verse>
				<verse number="15">እና​ንተ ሥጋዊ ፍር​ድን ትፈ​ር​ዳ​ላ​ችሁ፤ እኔ ግን በማ​ንም አል​ፈ​ር​ድም።</verse>
				<verse number="16">እኔ ብፈ​ር​ድም እው​ነ​ትን እፈ​ር​ዳ​ለሁ፤ እኔና የላ​ከኝ አብ ነን እንጂ አንድ ብቻ​ዬን አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና።</verse>
				<verse number="17">የሁ​ለት ሰዎች ምስ​ክ​ር​ነት የታ​መነ እንደ ሆነ በሕ​ጋ​ችሁ ተጽ​ፎ​አል።</verse>
				<verse number="18">እኔ ስለ ራሴ ምስ​ክር ነኝ፤ የላ​ከኝ አብም ይመ​ሰ​ክ​ር​ል​ኛል።”</verse>
				<verse number="19">እነ​ር​ሱም፥ “አባ​ትህ የት ነው?” አሉት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔን አታ​ው​ቁም፤ አባ​ቴ​ንም አታ​ው​ቁም፤ እኔ​ንስ ብታ​ውቁ አባ​ቴ​ንም ባወ​ቃ​ች​ሁት ነበር” ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቤተ መቅ​ደስ ሲያ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው በሙ​ዳየ ምጽ​ዋት አጠ​ገብ ይህን ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ነገር ግን አል​ያ​ዙ​ትም፤ ጊዜው ገና አል​ደ​ረ​ሰም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="21">ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፥ “እኔ እሄ​ዳ​ለሁ ትሹ​ኛ​ላ​ች​ሁም፤ ነገር ግን አታ​ገ​ኙ​ኝም፤ በኀ​ጢ​ኣ​ታ​ች​ሁም ትሞ​ታ​ላ​ችሁ፤ እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በ​ትም እና​ንተ መም​ጣት አይ​ቻ​ላ​ች​ሁም” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">አይ​ሁ​ድም፥ “እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በት እና​ንተ መም​ጣት አት​ች​ሉም የሚ​ለን እርሱ ራሱን ይገ​ድል ይሆን? እንጃ!” አሉ።</verse>
				<verse number="23">እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ን​ተስ ከታች ናችሁ፤ እኔ ግን ከላይ ነኝ፤ እና​ንተ ከዚህ ዓለም ናችሁ፤ እኔ ግን ከዚህ ዓለም አይ​ደ​ለ​ሁም።</verse>
				<verse number="24">እነሆ፥ በኀ​ጢ​ኣ​ታ​ችሁ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ እን​ዳ​ል​ኋ​ችሁ፥ እኔ እንደ ሆንሁ ባታ​ምኑ በኀ​ጢ​ኣ​ት​ችሁ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="25">እነ​ር​ሱም፥ “አንተ ማነህ?” አሉት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በመ​ጀ​መ​ሪያ ነግ​ሬ​አ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="26">ስለ እና​ንተ የም​ና​ገ​ረ​ውና የም​ፈ​ር​ደው ብዙ አለኝ፤ የላ​ከ​ኝም እው​ነ​ተኛ ነው፤ እኔ በእ​ርሱ ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን ለዓ​ለም እና​ገ​ራ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="27">ነገር ግን ስለ አብ እንደ ነገ​ራ​ቸው አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም።</verse>
				<verse number="28">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የሰ​ውን ልጅ ከፍ ከፍ በአ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ጊዜ እኔ እንደ ሆንሁ ያን​ጊዜ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ አባቴ እንደ አስ​ተ​ማ​ረ​ኝም እን​ዲሁ እና​ገ​ራ​ለሁ እንጂ የም​ና​ገ​ረው ከእኔ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="29">የላ​ከ​ኝም ከእኔ ጋር አለ፤ አብ ብቻ​ዬን አይ​ተ​ወ​ኝም፤ እኔም ዘወ​ትር ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን አደ​ር​ጋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="30">ይህ​ንም በተ​ና​ገረ ጊዜ ብዙ​ዎች በእ​ርሱ አመኑ።</verse>
				<verse number="31">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያመ​ኑ​በ​ትን አይ​ሁድ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ን​ተም በቃሌ ጸን​ታ​ችሁ ብት​ኖሩ በእ​ው​ነት ደቀ መዛ​ሙ​ርቴ ናችሁ።</verse>
				<verse number="32">እው​ነ​ት​ንም ታው​ቋ​ታ​ላ​ችሁ፤ እው​ነ​ትም አር​ነት ታወ​ጣ​ች​ኋ​ለች።”</verse>
				<verse number="33">እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “እኛ የአ​ብ​ር​ሃም ዘር ነን፤ ከሆነ ጀምሮ ለማ​ንም ከቶ ባሮች አል​ሆ​ንም፤ እን​ግ​ዲህ እን​ዴት አር​ነት ትወ​ጣ​ላ​ችሁ ትለ​ና​ለህ?” አሉት።</verse>
				<verse number="34">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ኀጢ​ኣ​ትን የሚ​ሠራ ሁሉ የኀ​ጢ​ኣት ባርያ ነው።</verse>
				<verse number="35">ባርያ ዘወ​ትር በቤት አይ​ኖ​ርም፤ ልጅ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።</verse>
				<verse number="36">ወልድ አር​ነት ካወ​ጣ​ችሁ በእ​ው​ነት አር​ነት የወ​ጣ​ችሁ ናችሁ።</verse>
				<verse number="37">የአ​ብ​ር​ሃም ዘር እንደ ሆና​ች​ሁስ አው​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን ቃሌ በእ​ና​ንተ ዘንድ አይ​ኖ​ር​ምና ልት​ገ​ድ​ሉኝ ትሻ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="38">እኔ በአ​ባቴ ዘንድ ያየ​ሁ​ትን እና​ገ​ራ​ለሁ፤ እና​ን​ተም በአ​ባ​ታ​ችሁ ያያ​ች​ሁ​ትን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="39">እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “የእ​ኛስ አባ​ታ​ችን አብ​ር​ሃም ነው” አሉት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የአ​ብ​ር​ሃም ልጆች ብት​ሆ​ኑስ የአ​ብ​ር​ሃ​ምን ሥራ በሠ​ራ​ችሁ ነበር።</verse>
				<verse number="40">አሁ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን እው​ነት የም​ነ​ግ​ራ​ች​ሁን ሰው ልት​ገ​ድ​ሉኝ ትሻ​ላ​ችሁ፤ አብ​ር​ሃ​ምስ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ገም።</verse>
				<verse number="41">እና​ንተ ግን የአ​ባ​ታ​ች​ሁን ሥራ ትሠ​ራ​ላ​ችሁ።” እነ​ር​ሱም፥ “እኛ ከዝ​ሙት አል​ተ​ወ​ለ​ድ​ንም፤ ነገር ግን አንድ አባት አለን፤ እር​ሱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው” አሉት።</verse>
				<verse number="42">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አባ​ታ​ችሁ ቢሆ​ንስ እኔን በወ​ደ​ዳ​ች​ሁኝ ነበር፤ እኔ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጥቼ መጥ​ቻ​ለ​ሁና፤ እኔ በገዛ እጄ የመ​ጣሁ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ እርሱ ላከኝ እንጂ።</verse>
				<verse number="43">እን​ግ​ዲህ ቃሌን ለምን አታ​ስ​ተ​ው​ሉም? ቃሌን መስ​ማት ስለ​ማ​ት​ችሉ ነው።</verse>
				<verse number="44">እና​ን​ተስ ከአ​ባ​ታ​ችሁ ከሰ​ይ​ጣን ናችሁ፤ የአ​ባ​ታ​ች​ሁ​ንም ፈቃድ ልታ​ደ​ርጉ ትወ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እርሱ ከጥ​ንት ጀምሮ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ በእ​ው​ነ​ትም አይ​ቆ​ምም፤ በእ​ርሱ ዘንድ እው​ነት የለ​ምና፤ ሐሰ​ት​ንም በሚ​ና​ገ​ር​በት ጊዜ ከራሱ አን​ቅቶ ይና​ገ​ራል፤ ሐሰ​ተኛ ነውና፤ የሐ​ሰ​ትም አባት ነውና።</verse>
				<verse number="45">እኔ ግን እው​ነ​ትን እና​ገ​ራ​ለ​ሁና አታ​ም​ኑ​ኝም።</verse>
				<verse number="46">ስለ ኀጢ​ኣት ከእ​ና​ንተ የሚ​ወ​ቅ​ሰኝ ማን ነው? እኔ እው​ነት የም​ና​ገር ከሆ​ንሁ ለምን አታ​ም​ኑ​ኝም?</verse>
				<verse number="47">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ይሰ​ማል፤ ስለ​ዚህ እና​ንተ አት​ሰ​ሙ​ኝም፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምና።”</verse>
				<verse number="48">አይ​ሁ​ድም፥ “አንተ ሳም​ራዊ እንደ ሆንህ፥ ጋኔ​ንም እንደ አለ​ብህ መና​ገ​ራ​ችን በሚ​ገባ አይ​ደ​ለ​ምን?” ብለው ጠየ​ቁት።</verse>
				<verse number="49">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ አባ​ቴን አከ​ብ​ራ​ለሁ እንጂ ጋኔን የለ​ብ​ኝም፤ እና​ንተ ግን ትን​ቁ​ኛ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="50">እኔ ለራሴ ክብ​ርን አል​ሻም፤ የሚሻ፥ የሚ​ፈ​ር​ድም አለ።</verse>
				<verse number="51">እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ቃሌን የሚ​ጠ​ብቅ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሞትን አይ​ቀ​ም​ስም።”</verse>
				<verse number="52">አይ​ሁ​ድም እን​ዲህ አሉት፥ “አሁን ጋኔን እን​ዳ​ለ​ብህ ዐወ​ቅን፤ አብ​ር​ሃም ስንኳ ሞቶ​አል፤ ነቢ​ያ​ትም ሞተ​ዋል፤ አንተ ግን ቃሌን የሚ​ጠ​ብቅ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሞትን አይ​ቀ​ም​ስም ትላ​ለህ።</verse>
				<verse number="53">በውኑ ከሞ​ተው ከአ​ባ​ታ​ችን ከአ​ብ​ር​ሃም፥ አንተ ትበ​ል​ጣ​ለ​ህን? ነቢ​ያ​ትም ሞቱ፤ ራስ​ህን ማን ታደ​ር​ጋ​ለህ?”</verse>
				<verse number="54">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ ራሴን ባከ​ብር ክብሬ ምንም አይ​ጠ​ቅ​መ​ኝም፤ የሚ​ያ​ከ​ብ​ረ​ኝስ እና​ንተ አም​ላ​ካ​ችን የም​ት​ሉት አባቴ አለ።</verse>
				<verse number="55">እና​ን​ተም አታ​ው​ቁ​ትም፤ እኔ ግን ኣው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ አላ​ው​ቀ​ውም ብልም እንደ እና​ንተ ሐሰ​ተኛ እሆ​ና​ለሁ፤ እኔ አው​ቀ​ዋ​ለሁ ቃሉ​ንም እጠ​ብ​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="56">አባ​ታ​ችሁ አብ​ር​ሃም የእ​ኔን ቀን ያይ ዘንድ ተመኘ፤ አይ​ቶም ደስ አለው።”</verse>
				<verse number="57">አይ​ሁ​ድም፥ “ገና አምሳ ዓመት ያል​ሞ​ላህ እን​ዴት አብ​ር​ሃ​ምን አየህ?” አሉት።</verse>
				<verse number="58">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ አብ​ር​ሃም ሳይ​ወ​ለድ እኔ አለሁ።” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="59">ሊደ​በ​ድ​ቡ​ትም ድን​ጋይ አነሡ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ግን ተሰ​ወ​ራ​ቸው፤ ከቤተ መቅ​ደ​ስም ወጣ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም አልፎ ሄደ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">ከዚ​ያም ሲያ​ልፍ ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ሰው አየ።</verse>
				<verse number="2">ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደው በማን ኀጢ​ኣት ነው? በራሱ ነውን? ወይስ በወ​ላ​ጆቹ?” ብለው ጠየ​ቁት።</verse>
				<verse number="3">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ሊገ​ለ​ጥ​በት ነው እንጂ እርሱ አል​በ​ደ​ለም፤ ወላ​ጆ​ቹም አል​በ​ደ​ሉም።</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን ቀን ሳለ የላ​ከ​ኝን ሥራ ልሠራ ይገ​ባ​ኛል፤ ማንም ሥራ ሊሠራ የማ​ይ​ች​ል​ባት ሌሊት ትመ​ጣ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="5">በዓ​ለም ሳለሁ፤ የዓ​ለም ብር​ሃን እኔ ነኝ።”</verse>
				<verse number="6">ይህ​ንም ብሎ በም​ድር ላይ ምራ​ቁን እን​ትፍ አለ፤ በም​ራ​ቁም ጭቃ አድ​ርጎ የዕ​ዉ​ሩን ዐይ​ኖች ቀባው።</verse>
				<verse number="7">እን​ዲ​ህም አለው፥ “ሂድና በሰ​ሊ​ሆም መጠ​መ​ቂያ ታጠብ” ትር​ጓ​ሜ​ውም የተ​ላከ ማለት ነው፤ ሄዶም ታጠ​በና እያየ ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="8">ጎረ​ቤ​ቶ​ቹና ቀድሞ የሚ​ያ​ው​ቁት፥ ሲለ​ም​ንም ያዩት የነ​በ​ሩት ግን፥ “ይህ በመ​ን​ገድ ተቀ​ምጦ ይለ​ምን የነ​በ​ረው አይ​ደ​ለም?” አሉ።</verse>
				<verse number="9">“ይህ እርሱ ነው” ያሉ አሉ፤ ሌሎ​ችም፥ “አይ​ደ​ለም፤ ይመ​ስ​ለ​ዋል እንጂ” አሉ፤ እርሱ ራሱ ግን፥ “እኔ ነኝ” አለ።</verse>
				<verse number="10">እነ​ር​ሱም፥ “ዐይ​ኖ​ችህ እን​ዴት ተገ​ለጡ?” አሉት።</verse>
				<verse number="11">እር​ሱም መልሶ፥ “ኢየ​ሱስ የሚ​ባ​ለው ሰው በም​ራቁ ጭቃ አድ​ርጎ ዐይ​ኖ​ችን ቀባ​ኝና ሂደህ በሰ​ሊ​ሆም ውኃ ታጠብ አለኝ፤ ሄጄም ታጠ​ብ​ሁና አየሁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">አይ​ሁ​ድም፥ “ሰው​የው የት አለ?” አሉት፤ እር​ሱም፥ “አላ​ው​ቅም” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">ያን ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደ​ው​ንም ሰው ወደ ፈሪ​ሳ​ው​ያን ወሰ​ዱት።</verse>
				<verse number="14">ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በም​ራቁ ጭቃ አድ​ርጎ ዐይ​ኖ​ቹን ያበ​ራ​በት ቀኑ ሰን​በት ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="15">ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም እን​ዴት እን​ዳየ ዳግ​መኛ ጠየ​ቁት፤ እር​ሱም፥ “በም​ራቁ ጭቃ አድ​ርጎ በዐ​ይ​ኖች አኖ​ረው፥ ታጥ​ቤም አየሁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም አን​ዳ​ን​ዶች፥ “ይህ ሰው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለም፤ ሰን​በ​ትን አያ​ከ​ብ​ር​ምና” አሉ፤ ሌሎች ግን “ኀጢ​ኣ​ተኛ ሰው እን​ዲህ ያለ ተአ​ም​ራት ማድ​ረግ እን​ዴት ይች​ላል?” አሉ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተለ​ያዩ።</verse>
				<verse number="17">ዳግ​መ​ኛም ዕዉ​ሩን፥ “አንተ ስለ እርሱ ምን ትላ​ለህ? ዐይ​ኖ​ች​ህን ከፍ​ቶ​ል​ሃ​ልና” አሉት፤ እር​ሱም፥ “ነቢይ ነው” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">አይ​ሁ​ድም የዚ​ያን ያየ​ውን ሰው ወላ​ጆች እስ​ኪ​ጠሩ ድረስ ዕዉር ሆኖ እንደ ተወ​ለደ፥ እን​ዳ​የም አላ​መ​ኑም።</verse>
				<verse number="19">“ዕዉር ሆኖ ተወ​ለደ የም​ት​ሉት ልጃ​ችሁ ይህ ነውን? እን​ግ​ዲያ አሁን እን​ዴት ያያል?” ብለው ጠየ​ቁ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">ወላ​ጆ​ቹም መል​ሰው እን​ዲህ አሉ፥ “ይህ ልጃ​ችን እንደ ሆነ፥ ዕዉር ሆኖም እንደ ተወ​ለደ እና​ው​ቃ​ለን።</verse>
				<verse number="21">አሁን ግን እን​ዴት እን​ደ​ሚ​ያይ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ማን እንደ አበ​ራ​ለት አና​ው​ቅም፤ እር​ሱን ጠይ​ቁት፤ ዐዋቂ ነውና፤ ስለ ራሱም መና​ገር ይች​ላ​ልና።”</verse>
				<verse number="22">ወላ​ጆቹ አይ​ሁ​ድን ስለ ፈሩ ይህን አሉ፥ “እርሱ ክር​ስ​ቶስ ነው ብሎ በእ​ርሱ የሚ​ያ​ምን ቢኖር ከም​ኵ​ራብ ይውጣ” ብለው አይ​ሁድ ተስ​ማ​ም​ተው ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="23">ስለ​ዚ​ህም ወላ​ጆቹ፥ “ዐዋቂ ነውና እር​ሱን ጠይ​ቁት” አሉ።</verse>
				<verse number="24">ዕውር የነ​በ​ረ​ው​ንም ሰው ዳግ​መኛ ጠር​ተው፥ “ሂድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና አቅ​ርብ፤ ይህ ሰው ኀጢ​ኣ​ተኛ እንደ ሆነ እኛ እና​ው​ቃ​ለን” አሉት።</verse>
				<verse number="25">ያም ሰው መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እርሱ ኀጢ​ኣ​ተኛ እንደ ሆነ እኔ አላ​ው​ቅም፤ እኔ ዕዉር እንደ ነበ​ርሁ፤ አሁን ግን እን​ደ​ማይ ይህን አንድ ነገር ብቻ አው​ቃ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="26">ዳግ​መ​ኛም፥ “ምን አደ​ረ​ገ​ልህ? ዐይ​ኖ​ች​ህ​ንስ እን​ደ​ምን አበ​ራ​ልህ?” አሉት።</verse>
				<verse number="27">እር​ሱም መልሶ፥ “አት​ሰ​ሙ​ኝም እንጂ ነገ​ር​ኋ​ችሁ፤ እን​ግ​ዲህ ደግሞ ምን ልት​ሰሙ ትሻ​ላ​ችሁ? እና​ን​ተም ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ልት​ሆኑ ትሻ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="28">እነ​ር​ሱም ሰደ​ቡት፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “አንተ የእ​ርሱ ደቀ መዝ​ሙር ሁን፤ እኛስ የሙሴ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ነን።</verse>
				<verse number="29">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እንደ ተነ​ጋ​ገ​ረው እና​ው​ቃ​ለን፤ ይህን ግን ከወ​ዴት እንደ ሆነ አና​ው​ቅም።”</verse>
				<verse number="30">ያም ሰው መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ከወ​ዴት እንደ ሆነ፥ አታ​ው​ቁ​ት​ምና ይህ እጅግ ድንቅ ነው፤ ነገር ግን ዐይ​ኖ​ችን አበ​ራ​ልኝ።</verse>
				<verse number="31">እኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ራ​ው​ንና ፈቃ​ዱን የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን እር​ሱን ይሰ​ማ​ዋል እንጂ ኃጥ​ኣ​ንን እን​ደ​ማ​ይ​ሰ​ማ​ቸው እና​ው​ቃ​ለን።</verse>
				<verse number="32">ዓለም ከተ​ፈ​ጠረ ጀምሮ ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ዐይ​ኖች ያበራ አል​ተ​ሰ​ማም።</verse>
				<verse number="33">ይህ ሰው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባይ​ሆን ኖሮ ምንም ማድ​ረግ ባል​ቻ​ለም ነበር።”</verse>
				<verse number="34">እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “ራስህ በኀ​ጢ​ኣት የተ​ወ​ለ​ድህ አንተ እኛን ታስ​ተ​ም​ረ​ና​ለ​ህን?” አሉት፤ ወደ ውጭም አወ​ጡት።</verse>
				<verse number="35">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ ውጭ እን​ዳ​ወ​ጡት ሰማ፤ አገ​ኘ​ው​ምና፥ “አንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ታም​ና​ለ​ህን?” አለው።</verse>
				<verse number="36">ያ ሰውም፥ “አቤቱ፥ አም​ን​በት ዘንድ እርሱ ማነው?” ብሎ መለ​ሰ​ለት።</verse>
				<verse number="37">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የም​ታ​የው፥ ከአ​ንተ ጋርም የሚ​ነ​ጋ​ገ​ረው እርሱ ነው” አለው።</verse>
				<verse number="38">እር​ሱም፥ “አቤቱ፥ አም​ና​ለሁ” ብሎ ሰገ​ደ​ለት።</verse>
				<verse number="39">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ የማ​ያ​ዩት እን​ዲ​ያዩ፥ የሚ​ያ​ዩ​ትም እን​ዲ​ታ​ወሩ ወደ​ዚህ ዓለም ለፍ​ርድ መጥ​ቻ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="40">ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ይህን ሲና​ገር ሰም​ተው፥ “እኛ ደግሞ ዕዉ​ሮች ነን?” አሉት።</verse>
				<verse number="41">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ዕዉ​ሮ​ችስ ብት​ሆኑ ኀጢ​ኣት ባል​ሆ​ነ​ባ​ች​ሁም ነበር፤ አሁን ግን እና​ያ​ለን ትላ​ላ​ችሁ፤ አታ​ዩ​ምም፤ ስለ​ዚ​ህም ኀጢ​ኣ​ታ​ችሁ ጸንቶ ይኖ​ራል” አላ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">“እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወደ በጎች ስፍራ በበሩ የማ​ይ​ገባ፥ በሌ​ላም በኩል የሚ​ገባ ሌባ፥ ወን​በ​ዴም ነው።</verse>
				<verse number="2">በበሩ የሚ​ገባ ግን የበ​ጎች ጠባቂ ነው።</verse>
				<verse number="3">ለእ​ርሱ በረ​ኛው ይከ​ፍ​ት​ለ​ታል፤ በጎ​ቹም ቃሉን ይሰ​ሙ​ታል፤ እር​ሱም በጎ​ቹን በየ​ስ​ማ​ቸው ይጠ​ራ​ቸ​ዋል፤ አው​ጥ​ቶም ያሰ​ማ​ራ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="4">ሁሉ​ንም አው​ጥቶ ባሰ​ማ​ራ​ቸው ጊዜ በፊት በፊ​ታ​ቸው ይሄ​ዳል፤ በጎ​ቹም ይከ​ተ​ሉ​ታል፤ ቃሉን ያው​ቃ​ሉና።</verse>
				<verse number="5">ሌላ​ውን ግን ይሸ​ሹ​ታል እንጂ አይ​ከ​ተ​ሉ​ትም፤ የሌ​ላ​ውን ቃሉን አያ​ው​ቁ​ምና።”</verse>
				<verse number="6">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ምሳሌ ነገ​ራ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን የነ​ገ​ራ​ቸ​ውን አላ​ወ​ቁም።</verse>
				<verse number="7">ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ የበ​ጎች በር እኔ ነኝ።</verse>
				<verse number="8">ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦ​ችና ወን​በ​ዴ​ዎች ናቸው፤ ነገር ግን፤ በጎች አል​ሰ​ሙ​አ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="9">እው​ነ​ተ​ኛዉ የበ​ጎች በር እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩ​ልም የሚ​ገባ ይድ​ናል፤ ይገ​ባ​ልም ይወ​ጣ​ልም፤ መሰ​ማ​ር​ያም ያገ​ኛል።</verse>
				<verse number="10">ሌባ ግን ሊሰ​ር​ቅና ሊያ​ርድ፥ ሊያ​ጠ​ፋም ካል​ሆነ በቀር አይ​መ​ጣም፤ እኔ ግን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እን​ዲ​ያ​ገኙ፥ እጅ​ግም እን​ዲ​በ​ዛ​ላ​ቸው መጣሁ።</verse>
				<verse number="11">“ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፤ ቸር ጠባቂ ስለ በጎቹ ነፍ​ሱን ይሰ​ጣል።</verse>
				<verse number="12">ጠባቂ ያይ​ደለ፥ በጎ​ቹም ገን​ዘቡ ያይ​ደሉ ምን​ደኛ ግን፥ ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎ​ቹን ትቶ ይሸ​ሻል፤ ተኵ​ላም መጥቶ በጎ​ችን ይነ​ጥ​ቃ​ቸ​ዋል፥ ይበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ልም።</verse>
				<verse number="13">ምን​ደ​ኛስ ይሸ​ሻል፤ ስለ በጎ​ችም አያ​ዝ​ንም፤ ምን​ደኛ ነውና።</verse>
				<verse number="14">ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፤ የእኔ የሆ​ኑ​ትን መን​ጋ​ዎ​ችን አው​ቃ​ለሁ፤ የእኔ የሆ​ኑ​ትም ያው​ቁ​ኛል።</verse>
				<verse number="15">አብ እኔን እን​ደ​ሚ​ያ​ው​ቀኝ እኔም አብን አው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ለበ​ጎ​ችም ቤዛ አድ​ርጌ ሰው​ነ​ቴን አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">ከዚህ ቦታ ያይ​ደሉ ሌሎች በጎ​ችም አሉኝ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ወደ​ዚህ አመ​ጣ​ቸው ዘንድ ይገ​ባ​ኛል፤ ቃሌ​ንም ይሰ​ሙ​ኛል፤ ለአ​ንድ እረ​ኛም አንድ መንጋ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="17">ስለ​ዚ​ህም፤ አብ ይወ​ድ​ደ​ኛል፥ እንደ ገና አስ​ነ​ሣት ዘንድ እኔ ነፍ​ሴን እሰ​ጣ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="18">ከእኔ ማንም አይ​ወ​ስ​ዳ​ትም፤ ነገር ግን እኔ በፈ​ቃዴ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ እኔ ላኖ​ራት ሥል​ጣን አለኝ፤ መልሼ እወ​ስ​ዳት ዘንድ ሥል​ጣን አለ​ኝና፤ ይህ​ንም ትእ​ዛዝ ከአ​ባቴ ተቀ​በ​ልሁ።”</verse>
				<verse number="19">ስለ​ዚ​ህም ነገር አይ​ሁድ እን​ደ​ገና እርስ በር​ሳ​ቸው ተለ​ያዩ።</verse>
				<verse number="20">ከእ​ነ​ር​ሱም ብዙ​ዎች፥ “ጋኔን ይዞት ያብ​ዳል፤ ለም​ንስ ታዳ​ም​ጡ​ታ​ላ​ችሁ?” አሉ።</verse>
				<verse number="21">ሌሎ​ችም ይህ ነገር ጋኔን ከያ​ዘው ሰው የሚ​ገኝ አይ​ደ​ለም፤ ጋኔን የዕ​ዉ​ሮ​ችን ዐይን ማብ​ራት ይች​ላ​ልን?” አሉ።</verse>
				<verse number="22">በዚ​ያም ወራት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የመ​ቅ​ደስ መታ​ደስ በዓል ሆነ፤ ክረ​ም​ትም ነበር።</verse>
				<verse number="23">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቤተ መቅ​ደስ በሰ​ሎ​ሞን ደጅ መመ​ላ​ለሻ ይመ​ላ​ለስ ነበር።</verse>
				<verse number="24">አይ​ሁ​ድም እር​ሱን ከብ​በው፥ “እስከ መቼ ድረስ ሰው​ነ​ታ​ች​ንን ታስ​ጨ​ን​ቀ​ና​ለህ? አንተ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆንህ ገል​ጠህ ንገ​ረን” አሉት።</verse>
				<verse number="25">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አታ​ም​ኑ​ኝም እንጂ ነገ​ር​ኋ​ችሁ፤ እኔ በአ​ባቴ ስም የም​ሠ​ራው ሥራ እርሱ ምስ​ክሬ ነው።</verse>
				<verse number="26">እና​ንተ ግን አታ​ም​ኑ​ኝም፤ እንደ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ከበ​ጎች ውስጥ አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምና።</verse>
				<verse number="27">የእኔ የሆኑ በጎች ግን ቃሌን ይሰ​ሙ​ኛል፤ እኔም አው​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይከ​ተ​ሉ​ኛል።</verse>
				<verse number="28">እኔም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም አይ​ጠ​ፉም፤ ከእ​ጄም የሚ​ነ​ጥ​ቃ​ቸው የለም።</verse>
				<verse number="29">እነ​ር​ሱን የሰ​ጠኝ አባቴ እርሱ ከሁሉ ይበ​ል​ጣ​ልና፤ ከአ​ባ​ቴም እጅ መን​ጠቅ የሚ​ችል የለም።</verse>
				<verse number="30">እኔና አብ አንድ ነን።”</verse>
				<verse number="31">ዳግ​መ​ኛም አይ​ሁድ ሊወ​ግ​ሩት ድን​ጋይ አነሡ።</verse>
				<verse number="32">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ከአ​ባቴ ብዙ መል​ካም ሥራ አሳ​የ​ኋ​ችሁ፤ ከእ​ነ​ርሱ በየ​ት​ኛው ሥራ ምክ​ን​ያት ትወ​ግ​ሩ​ኛ​ላ​ችሁ?”</verse>
				<verse number="33">አይ​ሁ​ድም፥ “አንተ፥ ሰው ስት​ሆን ራስ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታደ​ር​ጋ​ለ​ህና፤ ስለ መሳ​ደ​ብህ ነው እንጂ ስለ መል​ካም ሥራ​ህስ አን​ወ​ግ​ር​ህም” አሉት።</verse>
				<verse number="34">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ አማ​ል​ክት ናችሁ አልሁ ተብሎ በኦ​ሪ​ታ​ችሁ ተጽፎ የለ​ምን?</verse>
				<verse number="35">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል የመ​ጣ​ላ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ያን አማ​ል​ክት ካላ​ቸው፥ የመ​ጽ​ሐፉ ቃል ይታ​በል ዘንድ አይ​ቻ​ልም።</verse>
				<verse number="36">እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ነኝ ብላ​ችሁ፥ አብ የቀ​ደ​ሰ​ው​ንና ወደ ዓለ​ምም የላ​ከ​ውን እን​ዴት ትሳ​ደ​ባ​ለህ? ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="37">የአ​ባ​ቴን ሥራ ባል​ሠራ በእኔ አት​መኑ።</verse>
				<verse number="38">ከሠ​ራሁ ግን፥ እኔን እን​ኳን ባታ​ምኑ እኔ በአብ እን​ዳ​ለሁ አብም በእኔ እን​ዳለ ታው​ቁና ትረዱ ዘንድ ሥራ​ዬን እመኑ።”</verse>
				<verse number="39">ዳግ​መ​ኛም ሊይ​ዙት ፈለጉ፤ ከእ​ጃ​ቸ​ውም አመ​ለጠ።</verse>
				<verse number="40">ዳግ​መ​ኛም ቀድሞ ዮሐ​ንስ ያጠ​ም​ቅ​በት ወደ ነበ​ረው ስፍራ ወደ ዮር​ዳ​ኖስ ማዶ ሄደ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="41">ብዙ​ዎ​ችም ወደ እርሱ ሄደው፥ “ዮሐ​ንስ ምንም ያደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት የለም፤ ነገር ግን ዮሐ​ንስ ስለ​ዚህ ሰው የተ​ና​ገ​ረው ሁሉ እው​ነት ሆነ” አሉ።</verse>
				<verse number="42">በዚ​ያም ብዙ ሰዎች አመ​ኑ​በት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">የማ​ር​ያ​ምና የእ​ኅቷ የማ​ርታ መን​ደር በሚ​ሆን በቢ​ታ​ንያ ስሙ አል​ዓ​ዛር የሚ​ባል የታ​መመ አንድ ሰው ነበር።</verse>
				<verse number="2">ማር​ያም ግን ጌታ​ች​ንን ሽቱ የቀ​ባ​ችው፥ እግ​ሩ​ንም በጠ​ጕ​ርዋ ያሸ​ችው ናት፤ ወን​ድ​ምዋ አል​ዓ​ዛ​ርም ታሞ ነበር።</verse>
				<verse number="3">እኅ​ቶ​ቹም፥ “ጌታ​ችን ሆይ፥ እነሆ፥ የም​ት​ወ​ደው ታሞ​አል” ብለው ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ላኩ።</verse>
				<verse number="4">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሰምቶ እን​ዲህ አለ፥ “ይህ ደዌ በእ​ርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ይከ​ብር ዘንድ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይ​ደ​ለም።”</verse>
				<verse number="5">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ማር​ታ​ንና እኅ​ቷን ማር​ያ​ምን፥ አል​ዓ​ዛ​ር​ንም ይወ​ዳ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="6">እንደ ታመመ በሰማ ጊዜM በነ​በ​ረ​በት ቦታ ሁለት ቀን ቈየ።</verse>
				<verse number="7">ከዚ​ህም በኋላ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን፥ “ኑ፥ ወደ ይሁዳ ሀገር ደግሞ እን​ሂድ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ አይ​ሁድ ሊወ​ግ​ሩህ ይሹ አል​ነ​በ​ረ​ምን? ዛሬ ደግሞ አንተ ወደ​ዚያ ልት​ሄድ ትሻ​ለ​ህን?” አሉት።</verse>
				<verse number="9">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ቀኑ ዐሥራ ሁለት ሰዓት አይ​ደ​ለ​ምን? በቀን የሚ​ሄድ አይ​ሰ​ና​ከ​ልም፤ የዚ​ህን ዓለም ብር​ሃን ያያ​ልና።</verse>
				<verse number="10">በሌ​ሊት የሚ​ሄድ ግን ይሰ​ነ​ካ​ከ​ላል፤ በው​ስጡ የሚ​ያ​የው ብር​ሃን የለ​ምና።”</verse>
				<verse number="11">ይህ​ንም ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ነገ​ራ​ቸው፤ ከዚ​ህም በኋላ፥ “ወዳ​ጃ​ችን አል​ዓ​ዛር ተኝ​ቶ​አል፤ ነገር ግን ላነ​ቃው እሄ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም፥ “አቤቱ፥ ከተ​ኛስ ይነ​ቃል፤ ይድ​ና​ልም” አሉት።</verse>
				<verse number="13">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ስለ ሞቱ ተና​ገረ፤ እነ​ርሱ ግን ስለ እን​ቅ​ልፍ መተ​ኛት መስ​ሎ​አ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="14">ከዚህ በኋ​ላም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ገልጦ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አል​ዓ​ዛር ሞተ።</verse>
				<verse number="15">ታም​ኑም ዘንድ እኔ በዚያ ባለ​መ​ኖሬ ስለ እና​ንተ ደስ ይለ​ኛል፤ ነገር ግን ኑ፥ ወደ እርሱ እን​ሂድ።”</verse>
				<verse number="16">ዲዲ​ሞስ የሚ​ሉት ቶማ​ስም፥ ባል​ን​ጀ​ሮ​ቹን ደቀ መዛ​ሙ​ርት፥ “እኛም ከእ​ርሱ ጋር እን​ሞት ዘንድ እን​ሂድ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ ቢታ​ንያ ሄደ፤ ከዚ​ያም በደ​ረሰ ጊዜ ከተ​ቀ​በረ አራት ቀን ሆኖት አገ​ኘው።</verse>
				<verse number="18">ቢታ​ን​ያም ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዐሥራ አም​ስት ምዕ​ራፍ ያህል ቅርብ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="19">ከአ​ይ​ሁ​ድም ስለ ወን​ድ​ማ​ቸው ሊያ​ጽ​ና​ኑ​አ​ቸው ወደ ማር​ያ​ምና ወደ ማርታ የሄዱ ብዙ​ዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="20">ማር​ታም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ እንደ መጣ በሰ​ማች ጊዜ ወጥታ ተቀ​በ​ለ​ችው፤ ማር​ያም ግን በቤት ተቀ​ምጣ ነበር።</verse>
				<verse number="21">ማር​ታም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በዚህ ኖረህ ቢሆን ወን​ድሜ ባል​ሞ​ተም ነበር።</verse>
				<verse number="22">አሁ​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ት​ለ​ም​ነ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲ​ሰ​ጥህ አው​ቃ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="23">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ወን​ድ​ም​ሽስ ይነ​ሣል” አላት።</verse>
				<verse number="24">ማር​ታም፥ “ሙታን በሚ​ነ​ሡ​ባት በኋ​ለ​ኛ​ዪቱ ቀን እን​ደ​ሚ​ነሣ አው​ቃ​ለሁ” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="25">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም አላት፥ “ትን​ሣ​ኤና ሕይ​ወት እኔ ነኝ፤ የሚ​ያ​ም​ን​ብኝ ቢሞ​ትም ይነ​ሣል።</verse>
				<verse number="26">ሕያው የሆነ የሚ​ያ​ም​ን​ብ​ኝም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ሞ​ትም፤ ይህ​ንስ ታም​ኛ​ለ​ሽን?”</verse>
				<verse number="27">እር​ስ​ዋም፥ “አዎን፥ ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ወደ ዓለም የሚ​መ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆንህ እኔ አም​ና​ለሁ” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="28">ይህ​ንም ብላ ሄደች፤ እኅ​ቷን ማር​ያ​ም​ንም ቀስ ብላ ጠራ​ችና፥ “እነሆ፥ መም​ህ​ራ​ችን መጥቶ ይጠ​ራ​ሻል” አለ​ቻት።</verse>
				<verse number="29">እር​ስ​ዋም ይህን በሰ​ማች ጊዜ ፈጥና ተነ​ሣች፤ ወደ እር​ሱም ሄደች።</verse>
				<verse number="30">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ማርታ በተ​ቀ​በ​ለ​ች​በት ስፍራ ነበረ እንጂ ገና ወደ መን​ደር አል​ገ​ባም ነበር።</verse>
				<verse number="31">ሊያ​ጽ​ና​ኑ​አት መጥ​ተው በቤት ከእ​ር​ስዋ ጋር የነ​በሩ አይ​ሁ​ድም ፈጥና ተነ​ሥታ እንደ ወጣች ባዩ ጊዜ በዚያ ለወ​ን​ድ​ምዋ ልታ​ለ​ቅስ ወደ መቃ​ብሩ የም​ት​ሄድ መስ​ሎ​አ​ቸው ተከ​ተ​ሉ​አት።</verse>
				<verse number="32">ማር​ያ​ምም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ አለ​በት ስፍራ ደረ​ሰ​ችና በአ​የ​ችው ጊዜ ከእ​ግሩ በታች ሰግዳ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በዚህ ኑረህ ቢሆን ወን​ድሜ ባል​ሞ​ተም ነበር” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="33">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እር​ስዋ ስታ​ለ​ቅስ፥ ከእ​ር​ስዋ ጋር የመጡ አይ​ሁ​ድም ሲያ​ለ​ቅሱ ባየ ጊዜ በልቡ አዘነ፤ በራ​ሱም ታወከ።</verse>
				<verse number="34">እር​ሱም፥ “የት ቀበ​ራ​ች​ሁት?” አለ፤ እነ​ር​ሱም፥ “አቤቱ፥ መጥ​ተህ እይ” አሉት።</verse>
				<verse number="35">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ባ​ውን አፈ​ሰሰ።</verse>
				<verse number="36">አይ​ሁ​ድም፥ “ምን ያህል ይወ​ደው እንደ ነበር እዩ” አሉ።</verse>
				<verse number="37">ከእ​ነ​ር​ሱም መካ​ከል፥ “ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ዐይን ያበ​ራው ይህ ሰው ይህስ እን​ዳ​ይ​ሞት ሊያ​ደ​ርግ ባል​ቻ​ለም ነበ​ርን?” ያሉ ነበሩ።</verse>
				<verse number="38">ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በልቡ አዘነ፤ ወደ መቃ​ብ​ሩም ሄደ፤ መቃ​ብ​ሩም ዋሻ ነበር፤ በላ​ዩም ታላቅ ድን​ጋይ ተገ​ጥ​ሞ​በት ነበር።</verse>
				<verse number="39">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ድን​ጋ​ዩን አንሡ” አላ​ቸው፤ የሟቹ እኅት ማር​ታም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አራት ቀን ሆኖ​ታ​ልና ፈጽሞ ሸትቶ ይሆ​ናል” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="40">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ብታ​ም​ናስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ታያ​ለሽ አላ​ል​ሁ​ሽም ነበ​ርን?” አላት።</verse>
				<verse number="41">ድን​ጋ​ዩ​ንም አነሡ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዐይ​ኖ​ቹን አቅ​ንቶ እን​ዲህ አለ፥ “አባት ሆይ፥ ሰም​ተ​ኸ​ኛ​ልና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="42">እኔም ዘወ​ትር እን​ደ​ም​ት​ሰ​ማኝ አው​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን አንተ እንደ ላክ​ኸኝ ያምኑ ዘንድ በዚህ ቆመው ስላ​ሉት ሰዎች ይህን እና​ገ​ራ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="43">ይህ​ንም ብሎ በታ​ላቅ ቃል ጮኸና፥ “አል​ዓ​ዛር፥ ና፤ ወደ ውጭ ውጣ” አለ።</verse>
				<verse number="44">ሞቶ የነ​በ​ረ​ውም እንደ ተገ​ነዘ፥ እጁ​ንና እግ​ሩ​ንም እንደ ታሰረ፥ ፊቱም በሰ​በን እንደ ተጠ​ቀ​ለለ ወጣ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እን​ግ​ዲ​ህስ ፍቱ​ትና ተዉት ይሂድ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="45">ስለ​ዚህ ከአ​ይ​ሁ​ድም ወደ ማር​ታና ወደ ማር​ያም መጥ​ተው የነ​በሩ ብዙ ሰዎች ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያደ​ረ​ገ​ውን አይ​ተው በእ​ርሱ አመኑ።</verse>
				<verse number="46">ከእ​ነ​ር​ሱም መካ​ከል ወደ ፈሪ​ሳ​ው​ያን ሄደው የከ​ሰ​ሱት ነበሩ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያደ​ረ​ገ​ው​ንም ሁሉ ነገ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="47">የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ጉባ​ኤ​ውን ሰብ​ስ​በው እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “እነሆ፥ ይህ ሰው ብዙ ተአ​ም​ራት ያደ​ር​ጋል፤ ምን እና​ድ​ርግ?</verse>
				<verse number="48">እን​ዲሁ ብን​ተ​ወ​ውም ሁሉ ያም​ኑ​በ​ታል፤ የሮም ሰዎ​ችም መጥ​ተው ሀገ​ራ​ች​ን​ንና ወገ​ና​ች​ንን ይወ​ስ​ዱ​ብ​ናል።”</verse>
				<verse number="49">በዚ​ያ​ችም ዓመት የካ​ህ​ናት አለቃ የነ​በ​ረው ስሙ ቀያፋ የተ​ባ​ለው ከእ​ነ​ርሱ አንዱ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ን​ተስ ምንም አታ​ው​ቁም።</verse>
				<verse number="50">ምንም አት​መ​ክ​ሩም፤ ሕዝቡ ሁሉ ከሚ​ጠፋ ስለ ሕዝቡ አንድ ሰው ቢሞት ይሻ​ለ​ናል።”</verse>
				<verse number="51">ይህ​ንም ከልቡ የተ​ና​ገ​ረው አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን በዚ​ያች ዓመት የካ​ህ​ናት አለቃ ነበ​ርና ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ስለ ሕዝብ ሁሉ ቤዛ ሆኖ ይሞት ዘንድ ስላ​ለው ይህን ትን​ቢት ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="52">ስለ ሕዝብ ብቻ አል​ነ​በ​ረም፤ የተ​በ​ተ​ኑ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ልጆች በአ​ን​ድ​ነት ይሰ​በ​ስ​ባ​ቸው ዘንድ ነው እንጂ።</verse>
				<verse number="53">ከዚ​ያ​ችም ቀን ጀምሮ የካ​ህ​ናት አለ​ቆች ሊገ​ድ​ሉት ተማ​ከሩ።</verse>
				<verse number="54">ከዚ​ያም ወዲያ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በአ​ይ​ሁድ መካ​ከል በግ​ልጥ አል​ተ​መ​ላ​ለ​ሰም፤ ነገር ግን ለም​ድረ በዳ አቅ​ራ​ቢያ ወደ ሆነች ምድር፥ ኤፍ​ሬም ወደ​ም​ት​ባል ከተማ ሄደ፤ በዚ​ያም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="55">የአ​ይ​ሁ​ድም የፋ​ሲካ በዓል ቀርቦ ነበር፤ ብዙ ሰዎ​ችም ከበ​ዓሉ አስ​ቀ​ድሞ ራሳ​ቸ​ውን ያነጹ ዘንድ ከየ​ሀ​ገሩ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጥ​ተው ነበር።</verse>
				<verse number="56">አይ​ሁ​ድም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ይፈ​ል​ጉት ጀመር፤ በቤተ መቅ​ደ​ስም ቆመው እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ምን ይመ​ስ​ላ​ች​ኋል? ለበ​ዓል አይ​መጣ ይሆን?” ተባ​ባሉ።</verse>
				<verse number="57">የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ያለ​በ​ትን የሚ​ያ​ውቅ ቢኖር ይይ​ዙት ዘንድ እን​ዲ​ያ​መ​ለ​ክ​ታ​ቸው አዘዙ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">ፋሲካ ከሚ​ው​ል​በት ከስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ቀን አስ​ቀ​ድሞ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከሙ​ታን ያስ​ነ​ሣው አል​ዓ​ዛር ወደ ነበ​ረ​በት ወደ ቢታ​ንያ መጣ።</verse>
				<verse number="2">በዚ​ያም ምሳ አደ​ረ​ጉ​ለት፤ ማር​ታም ታሳ​ል​ፍ​ላ​ቸው ነበር፤ አብ​ረ​ውት ምሳ ከበ​ሉ​ትም አንዱ አል​ዓ​ዛር ነበር።</verse>
				<verse number="3">ማር​ያም ግን ዋጋዉ የከ​በ​ረና የበዛ አንድ ነጥር የጥሩ ናር​ዶስ ሽቱ ወሰ​ደ​ችና የጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እግር ቀባ​ችው፤ በፀ​ጕ​ሯም አሸ​ችው፤ የዚያ ሽቱ መዓ​ዛም ቤቱን መላው።</verse>
				<verse number="4">ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ አንዱ የነ​በረ ያሲ​ዘው ዘንድ ያለው የስ​ም​ዖን ልጅ አስ​ቆ​ሮ​ታ​ዊው ይሁዳ ግን እን​ዲህ አለ።</verse>
				<verse number="5">“ለነ​ዳ​ያን ይሰጥ ዘንድ ይህን ሽቱ ለሦ​ስት መቶ ዲናር ለምን አል​ሸ​ጡ​ትም?”</verse>
				<verse number="6">ይህ​ንም ያለ፥ ድሆች አሳ​ዝ​ነ​ውት አይ​ደ​ለም፤ ሌባ ነበ​ርና፥ ሙዳየ ምጽ​ዋ​ቱ​ንም ሲጠ​ብቅ በው​ስጡ ከሚ​ገ​ባው ይወ​ስድ ነበ​ርና ስለ​ዚህ ነው እንጂ።</verse>
				<verse number="7">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ለም​ቀ​በ​ር​በት ቀን ትጠ​ብ​ቀው ዘንድ ተዉ​አት።</verse>
				<verse number="8">ድሆች ግን ዘወ​ትር አብ​ረ​ዋ​ችሁ አሉ፤ ዘወ​ት​ርም ታገ​ኙ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ በወ​ደ​ዳ​ች​ሁም ጊዜ መል​ካም ታደ​ር​ጉ​ላ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ እኔን ግን ዘወ​ትር የም​ታ​ገ​ኙኝ አይ​ደ​ለም።”</verse>
				<verse number="9">ከአ​ይ​ሁ​ድም ብዙ ሰዎች ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በዚያ እን​ዳለ በዐ​ወቁ ጊዜ ወደ እርሱ መጡ፤ የመ​ጡ​ትም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ለማ​የት ብቻ አል​ነ​በ​ረም፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣ​ዉን አል​ዓ​ዛ​ር​ንም ያዩ ዘንድ ነበር እንጂ።</verse>
				<verse number="10">የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችም አል​ዓ​ዛ​ርን ሊገ​ድ​ሉት ተማ​ከሩ።</verse>
				<verse number="11">ከአ​ይ​ሁድ ብዙ​ዎች ስለ እርሱ እየ​ሄዱ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ያምኑ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="12">በማ​ግ​ሥ​ቱም ለበ​ዓል መጥ​ተው የነ​በሩ ብዙ ሰዎች ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ደ​ሚ​መጣ በሰሙ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="13">የዘ​ን​ባባ ዛፍ ዝን​ጣፊ ይዘው “ሆሣ​ዕና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የሚ​መጣ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ቡሩክ ነው” እያሉ ወጥ​ተው ተቀ​በ​ሉት።</verse>
				<verse number="14">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም የአ​ህያ ውር​ንጫ አግ​ኝቶ በእ​ር​ስዋ ላይ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="15">“የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ አት​ፍሪ፤ እነሆ፥ ንጉ​ሥሽ በአ​ህያ ውር​ንጫ ተቀ​ምጦ ይመ​ጣል” ተብሎ እንደ ተጻፈ፤</verse>
				<verse number="16">ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አስ​ቀ​ድ​መው ይህን ነገር አላ​ወ​ቁም፤ ነገር ግን ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከከ​በረ በኋላ በዚያ ጊዜ ይህ ነገር ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ፥ ይህ​ንም እንደ አደ​ረ​ጉ​ለት ትዝ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">ከዚ​ያም አብ​ረ​ውት የነ​በ​ሩት ሕዝብ አል​ዓ​ዛ​ርን ከመ​ቃ​ብር እንደ ጠራው፥ ከሙ​ታ​ንም እንደ አስ​ነ​ሣው መሰ​ከ​ሩ​ለት።</verse>
				<verse number="18">ስለ​ዚ​ህም ነገር ሕዝቡ ሁሉ ሊቀ​በ​ሉት ወጡ፤ ይህን ተአ​ም​ራት እንደ አደ​ረገ ሰም​ተ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="19">ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “የም​ታ​ገ​ኙት ምንም ጥቅም እን​ደ​ሌለ ታያ​ላ​ች​ሁን? እነሆ፥ ዓለም ሁሉ ተከ​ት​ሎ​ታል” ተባ​ባሉ።</verse>
				<verse number="20">ከጽ​ርዕ ሰዎ​ችም ይሰ​ግዱ ዘንድ ለበ​ዓል የወጡ ነበሩ።</verse>
				<verse number="21">እነ​ር​ሱም ከገ​ሊላ፥ የቤተ ሳይዳ ሰው ወደ ሆነው ወደ ፊል​ጶስ ሄደው፥ “አቤቱ፥ ጌታ ኢየ​ሱ​ስን ልና​የው እን​ወ​ድ​ዳ​ለን” ብለው ለመ​ኑት።</verse>
				<verse number="22">ፊል​ጶ​ስም ሄዶ ለእ​ን​ድ​ር​ያስ ነገ​ረው፤ እን​ድ​ር​ያ​ስና ፊል​ጶ​ስም ሄደው ለጌ​ታ​ችን ለኢ​የ​ሱስ ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="23">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፤ “አሁን የሰው ልጅ ይከ​ብር ዘንድ ጊዜው ደረሰ።</verse>
				<verse number="24">እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ የስ​ንዴ ቅን​ጣት በም​ድር ላይ ካል​ወ​ደ​ቀ​ችና ካል​ሞ​ተች ብቻ​ዋን ትኖ​ራ​ለች፤ ከሞ​ተች ግን ብዙ ፍሬን ታፈ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="25">ነፍ​ሱን የሚ​ወ​ዳት ይጥ​ላ​ታል፤ በዚህ ዓለም ነፍ​ሱን የሚ​ጥ​ላ​ትም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ይጠ​ብ​ቃ​ታል።</verse>
				<verse number="26">እኔን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለኝ ካለ ይከ​ተ​ለኝ፤ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለኝ እኔ ባለ​ሁ​በት በዚያ ይኖ​ራ​ልና፤ እኔን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለ​ኝ​ንም አብ ያከ​ብ​ረ​ዋል።</verse>
				<verse number="27">“አሁ​ንስ ነፍሴ ታወ​ከች፤ ግን ምን እላ​ለሁ? አባት ሆይ፥ ከዚች ሰዓት ነፍ​ሴን አድ​ናት፤ ነገር ግን ስለ​ዚህ ነገር ለዚች ሰዓት ደር​ሻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="28">አባት ሆይ፥ ልጅ​ህን አክ​ብ​ረው።” ከሰ​ማ​ይም፥ “አከ​በ​ር​ሁህ፤ ደግ​ሞም እን​ደ​ገና አከ​ብ​ር​ሃ​ለሁ፤” የሚል ቃል መጣ።</verse>
				<verse number="29">በዚያ ቆመው ይሰሙ የነ​በሩ ሕዝብ ግን “ነጐ​ድ​ጓድ ነው” አሉ፤ “መል​አክ ተና​ገ​ረው” ያሉም አሉ።</verse>
				<verse number="30">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ይህ ቃል የመጣ ስለ እና​ንተ ነው እንጂ ስለ እኔ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="31">አሁን የዚህ ዓለም ፍርድ ደረሰ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ የዚ​ህን ዓለም ገዥ ወደ ውጭ አስ​ወ​ጥ​ተው ይሰ​ዱ​ታል።</verse>
				<verse number="32">እኔም ከም​ድር ከፍ ከፍ ካልሁ ሁሉን ወደ እኔ እስ​ባ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="33">ይህ​ንም ያለ በምን ዐይ​ነት ሞት ይሞት ዘንድ እን​ዳ​ለው ሲያ​መ​ለ​ክ​ታ​ቸው ነው።</verse>
				<verse number="34">ሕዝ​ቡም፥ “እኛስ ክር​ስ​ቶስ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዲ​ኖር በኦ​ሪት ሰም​ተን ነበር፤ እን​ግ​ዲህ እን​ዴት አንተ ‘የሰው ልጅ ከፍ ከፍ ይል ዘንድ አለው’ ትለ​ና​ለህ? እን​ግ​ዲህ ይህ የሰው ልጅ ማን ነው?” ብለው መለ​ሱ​ለት።</verse>
				<verse number="35">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ ገና ለጥ​ቂት ጊዜ ብር​ሃን ከእ​ና​ንተ ጋር ነው፤ በጨ​ለማ የሚ​መ​ላ​ለስ የሚ​ሄ​ድ​በ​ትን አያ​ው​ቅ​ምና ጨለማ እን​ዳ​ያ​ገ​ኛ​ችሁ ብር​ሃን ሳለ​ላ​ችሁ ተመ​ላ​ለሱ፤</verse>
				<verse number="36">የብ​ር​ሃን ልጆች ትሆኑ ዘንድ ብር​ሃን ሳለ​ላ​ችሁ በብ​ር​ሃን እመኑ” ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ተና​ግሮ ሄደ፤ ተሰ​ወ​ራ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="37">ይህ​ንም ያህል ተአ​ም​ራት በፊ​ታ​ቸው ሲያ​ደ​ርግ አላ​መ​ኑ​በ​ትም።</verse>
				<verse number="38">“አቤቱ፥ ምስ​ክ​ር​ነ​ታ​ች​ንን ማን ያም​ነ​ናል? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ክንድ ለማን ተገ​ለጠ?” ያለው የነ​ቢዩ የኢ​ሳ​ይ​ያስ ቃል ይደ​ርስ ዘንድ።</verse>
				<verse number="39">ስለ​ዚ​ህም ማመን ተሳ​ና​ቸው፤ ኢሳ​ይ​ያስ ዳግ​መኛ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="40">“በዐ​ይ​ና​ቸው አይ​ተው፥ በል​ባ​ቸ​ውም አስ​ተ​ው​ለው እን​ዳ​ይ​መ​ለ​ሱና እን​ዳ​ል​ፈ​ው​ሳ​ቸው ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው ታወሩ፤ ልባ​ቸ​ውም ደነ​ደነ።”</verse>
				<verse number="41">ኢሳ​ይ​ያስ ጌት​ነ​ቱን አይ​ቶ​አ​ልና፥ ይህን ተና​ገረ፤ ስለ እር​ሱም መሰ​ከረ።</verse>
				<verse number="42">ከሕ​ዝቡ አለ​ቆ​ችም ያመ​ኑ​በት ብዙ​ዎች ነበሩ፤ ነገር ግን ከም​ኵ​ራብ አስ​ወ​ጥ​ተው እን​ዳ​ይ​ሰ​ዱ​አ​ቸው በፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ምክ​ን​ያት አል​መ​ሰ​ከ​ሩ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="43">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ይልቅ የሰ​ውን ክብር ወደ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="44">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ እን​ዲህ አለ፥ “በእኔ የሚ​ያ​ምን በላ​ከ​ኝም ነው እንጂ በእኔ ብቻ የሚ​ያ​ምን አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="45">እኔን ያየ የላ​ከ​ኝን አየ።</verse>
				<verse number="46">በእኔ የሚ​ያ​ምን ሁሉ በጨ​ለማ እን​ዳ​ይ​ኖር ብር​ሃን እኔ ወደ ዓለም መጣሁ።</verse>
				<verse number="47">ቃሌን ሰምቶ የማ​ይ​ጠ​ብ​ቀ​ውን እኔ የም​ፈ​ር​ድ​በት አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ዓለ​ምን ላድን እንጂ በዓ​ለም ልፈ​ር​ድ​በት አል​መ​ጣ​ሁ​ምና።</verse>
				<verse number="48">የሚ​ክ​ደ​ኝን፥ ቃሌ​ንም የማ​ይ​ቀ​በ​ለ​ውን ግን የሚ​ፈ​ር​ድ​በት አለ፤ እኔ የተ​ና​ገ​ር​ሁት ቃል እርሱ በመ​ጨ​ረ​ሻ​ዪቱ ቀን ይፈ​ር​ድ​በ​ታል።</verse>
				<verse number="49">የተ​ና​ገ​ር​ሁት ከእኔ የሆነ አይ​ደ​ለ​ምና፤ ነገር ግን የላ​ከኝ አብ እን​ድ​ና​ገር፥ እን​ዲ​ህም እን​ድል እርሱ ትእ​ዛ​ዝን ሰጠኝ።</verse>
				<verse number="50">ትእ​ዛ​ዙም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት እንደ ሆነ አው​ቃ​ለሁ፤ እኔም የም​ና​ገ​ረ​ውን አብ እን​ዳ​ለኝ እን​ዲሁ እና​ገ​ራ​ለሁ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">ከፋ​ሲካ በዓል አስ​ቀ​ድሞ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከዚህ ዓለም ወደ ላከው ወደ አብ ይሄድ ዘንድ ጊዜው እንደ ደረሰ ባወቀ ጊዜ በዓ​ለም ያሉ​ትን የወ​ደ​ዳ​ቸ​ውን ወገ​ኖ​ቹን ፈጽሞ ወደ​ዳ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">ራት ሲበ​ሉም አሳ​ልፎ ይሰ​ጠው ዘንድ በስ​ም​ዖን ልጅ በአ​ስ​ቆ​ሮቱ ሰው በይ​ሁዳ ልብ ሰይ​ጣን አደረ።</verse>
				<verse number="3">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ወጣ፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ደ​ሚ​ሄድ ባወቀ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="4">ራት ከሚ​በ​ሉ​በት ተነ​ሥቶ ልብ​ሱን አኖ​ረና ማበሻ ጨርቅ አን​ሥቶ ወገ​ቡን ታጠቀ።</verse>
				<verse number="5">በኵ​ስ​ኵ​ስ​ቱም ውኃ ቀድቶ የደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን እግር ያጥብ ጀመር፤ በዚያ በታ​ጠ​ቀው ማበሻ ጨር​ቅም አበሰ።</verse>
				<verse number="6">ወደ ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ደረሰ፤ እር​ሱም፥ “አቤቱ፥ አንተ እግ​ሬን ታጥ​በ​ኛ​ለ​ህን?” አለው።</verse>
				<verse number="7">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ የም​ሠ​ራ​ውን አንተ ዛሬ አታ​ው​ቅም፤ ኋላ ግን ታስ​ተ​ው​ለ​ዋ​ለህ” ብሎ መለ​ሰ​ለት።</verse>
				<verse number="8">ጴጥ​ሮ​ስም፥ “መቼም ቢሆን አንተ እግ​ሬን አታ​ጥ​በ​ኝም” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እው​ነት እው​ነት እል​ሃ​ለሁ፤ እኔ እግ​ር​ህን ካላ​ጠ​ብ​ሁህ ከእኔ ጋር ዕድል ፋንታ የለ​ህም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።</verse>
				<verse number="9">ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም፥ “አቤቱ፥ እን​ኪ​ያስ የም​ታ​ጥ​በኝ እጆ​ች​ንና ራሴ​ንም እንጂ እግ​ሮ​ችን ብቻ አይ​ደ​ለም፤” አለው።</verse>
				<verse number="10">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ፈጽሞ የታ​ጠበ ከእ​ግሩ በቀር ሊታ​ጠብ አያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ውም፤ ሁለ​ን​ተ​ናው ንጹሕ ነውና፤ እና​ን​ተማ ንጹ​ሓን ናችሁ፤ ነገር ግን ሁላ​ችሁ አይ​ደ​ላ​ች​ሁም” አለው።</verse>
				<verse number="11">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም አሳ​ልፎ የሚ​ሰ​ጠ​ውን ያውቅ ነበ​ርና ስለ​ዚህ “ሁላ​ችሁ ንጹ​ሓን አይ​ደ​ላ​ች​ሁም” አለ።</verse>
				<verse number="12">እግ​ራ​ቸ​ው​ንም ካጠ​ባ​ቸው በኋላ ልብ​ሱን አን​ሥቶ ለበ​ሰና እንደ ገና ከእ​ነ​ርሱ ጋር ተቀ​መጠ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ያደ​ረ​ግ​ሁ​ላ​ች​ሁን ዐወ​ቃ​ች​ሁን?</verse>
				<verse number="13">እና​ንተ ‘መም​ህ​ራ​ችን፥ ጌታ​ች​ንም’ ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ፤ መል​ካም ትላ​ላ​ችሁ፤ እኔ እን​ዲሁ ነኝና።</verse>
				<verse number="14">እን​ግ​ዲህ እኔ መም​ህ​ራ​ች​ሁና ጌታ​ችሁ ስሆን እግ​ራ​ች​ሁን ካጠ​ብ​ኋ​ችሁ እና​ን​ተም እን​ዲሁ የባ​ል​ጀ​ሮ​ቻ​ች​ሁን እግር ልታ​ጥቡ ይገ​ባ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="15">እኔ እንደ አደ​ረ​ግ​ሁ​ላ​ችሁ እና​ን​ተም ልታ​ደ​ርጉ ምሳሌ ሰጥ​ቻ​ች​ኋ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="16">እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከጌ​ታው የሚ​በ​ልጥ አገ​ል​ጋይ የለም፤ ከላ​ከው የሚ​በ​ልጥ መል​እ​ክ​ተ​ኛም የለም።</verse>
				<verse number="17">ይህ​ንም ዐው​ቃ​ችሁ ብት​ሠሩ ብፁ​ዓን ናችሁ።</verse>
				<verse number="18">ነገር ግን ይህን የም​ና​ገር ስለ ሁላ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ የመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው እነ​ማን እንደ ሆኑ እኔ አው​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን መጽ​ሐፍ ‘እን​ጀ​ራ​ዬን የሚ​መ​ገብ ተረ​ከ​ዙን በእኔ ላይ አነሣ’ ያለው ይፈ​ጸም ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="19">በሆ​ነም ጊዜ እኔ እንደ ሆንሁ ታምኑ ዘንድ ከዛሬ ጀምሮ ከመ​ሆኑ አስ​ቀ​ድሞ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ የም​ል​ከ​ውን የሚ​ቀ​በል እኔን ይቀ​በ​ላል፤ እኔ​ንም የሚ​ቀ​በል የላ​ከ​ኝን ይቀ​በ​ላል።”</verse>
				<verse number="21">ይህ​ንም ተና​ግሮ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በልቡ አዘነ፤ መሰ​ከረ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ና​ንተ አንዱ አሳ​ልፎ ይሰ​ጠ​ኛል።”</verse>
				<verse number="22">ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ይህን ስለ ማን እንደ ተና​ገረ ተጠ​ራ​ጥ​ረው እርስ በር​ሳ​ቸው ተያዩ፤</verse>
				<verse number="23">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይወ​ደው የነ​በረ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ አንዱ በጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ አጠ​ገብ ተቀ​ምጦ ነበር።</verse>
				<verse number="24">ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም እር​ሱን ጠቀ​ሰና፥ “ይህን ስለ ማን እንደ ተና​ገረ ጠይ​ቀህ ንገ​ረን” አለው።</verse>
				<verse number="25">ያም ደቀ መዝ​ሙር በጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ አጠ​ገብ ቀረብ ብሎ፥ “ጌታ ሆይ፥ እርሱ ማነው?” አለው።</verse>
				<verse number="26">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ይህ እኔ እን​ጀራ በወጥ አጥ​ቅሼ የም​ሰ​ጠው ነው” አለው፤ ያን ጊዜም እን​ጀራ በወጥ አጥ​ቅሶ ለስ​ም​ዖን ልጅ ለአ​ስ​ቆ​ሮ​ታ​ዊው ይሁዳ ሰጠው።</verse>
				<verse number="27">እን​ጀ​ራ​ው​ንም ከተ​ቀ​በለ በኋላ ወዲ​ያ​ውኑ በይ​ሁዳ ልብ ሰይ​ጣን አደ​ረ​በት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እን​ግ​ዲህ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ፈጥ​ነህ አድ​ርግ” አለው።</verse>
				<verse number="28">አብ​ረ​ው​ትም በማ​ዕድ የተ​ቀ​መ​ጡት ስለ ምን ይህን እን​ዳ​ለው አላ​ወ​ቁም።</verse>
				<verse number="29">ሙዳየ ምጽ​ዋቱ በይ​ሁዳ ዘንድ ነበ​ረና፥ ለበ​ዓል የም​ን​ሻ​ውን ወይም ለነ​ዳ​ያን የም​ን​ሰ​ጠ​ውን ግዛ ያለው የመ​ሰ​ላ​ቸው ነበሩ።</verse>
				<verse number="30">ይሁ​ዳም ያን እን​ጀራ ተቀ​ብሎ ወዲ​ያ​ውኑ ወጣ፥ ሌሊ​ትም ነበር።።</verse>
				<verse number="31">ይሁ​ዳም ከወጣ በኋላ ያን​ጊዜ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አሁን የሰው ልጅ ከበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ርሱ ከበረ።</verse>
				<verse number="32">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ርሱ ከከ​በረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እር​ሱን ያከ​ብ​ረ​ዋል፥ ያን​ጊ​ዜም ያከ​ብ​ረ​ዋል።</verse>
				<verse number="33">ልጆች ሆይ፥ ገና ጥቂት ጊዜ ከእ​ና​ንተ ጋር አለሁ፤ ትሹ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ለአ​ይ​ሁ​ድም እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በት እና​ንተ መም​ጣት አይ​ቻ​ላ​ች​ሁም እን​ዳ​ል​ኋ​ቸው፥ አሁ​ንም ለእ​ና​ንተ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="34">“እርስ በር​ሳ​ችሁ ቷደዱ ዘንድ፥ አዲስ ትእ​ዛዝ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ እንደ ወደ​ድ​ኋ​ችሁ እና​ን​ተም እን​ዲሁ እርስ በር​ሳ​ችሁ ተዋ​ደዱ።</verse>
				<verse number="35">እርስ በር​ሳ​ች​ሁም ብቷ​ደዱ፥ የእኔ ደቀ መዛ​ሙ​ርት እንደ ሆና​ችሁ በዚህ ሁሉ ያው​ቋ​ች​ኋል።”</verse>
				<verse number="36">ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ጌታ ሆይ፥ ወዴት ትሄ​ዳ​ለህ?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ወደ​ም​ሄ​ድ​በት አሁን ልት​ከ​ተ​ለኝ አት​ች​ልም፤ ኋላ ግን ትከ​ተ​ለ​ኛ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="37">ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ጌታ ሆይ፥ ስለ ምን አሁን ልከ​ተ​ልህ አል​ች​ልም? እኔ ነፍ​ሴ​ንም እንኳ ቢሆን ስለ አንተ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="38">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፤ “ነፍ​ስ​ህን ስለ እኔ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጣ​ለ​ህን? እው​ነት እው​ነት እል​ሃ​ለሁ፤ ሦስት ጊዜ እስ​ክ​ት​ክ​ደኝ ዶሮ አይ​ጮ​ህም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">“ልባ​ችሁ አይ​ደ​ን​ግጥ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እመኑ፤ በእ​ኔም እመኑ።</verse>
				<verse number="2">በአ​ባቴ ቤት ብዙ ማደ​ሪ​ያና ማረ​ፊያ አለ፤ እን​ዲ​ህስ ባይ​ሆን ኖሮ ቦታ ላዘ​ጋ​ጅ​ላ​ችሁ እሄ​ዳ​ለሁ እላ​ችሁ ነበር።</verse>
				<verse number="3">ከሄ​ድ​ሁና ቦታ ካዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ላ​ች​ሁም ዳግ​መኛ እመ​ጣ​ለሁ፤ እና​ን​ተም እኔ በአ​ለ​ሁ​በት ትኖሩ ዘንድ ወደ እኔ እወ​ስ​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">ወዴ​ትም እን​ደ​ም​ሄድ ራሳ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ መን​ገ​ዱ​ንም ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="5">ቶማ​ስም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ የም​ት​ሄ​ድ​በ​ትን የማ​ና​ውቅ እን​ግ​ዲህ መን​ገ​ዱን እን​ዴት እና​ው​ቃ​ለን?” አለው።</verse>
				<verse number="6">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “የእ​ው​ነ​ትና የሕ​ይ​ወት መን​ገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካል​ሆነ በቀር ወደ አብ የሚ​መጣ የለም።</verse>
				<verse number="7">እኔ​ንስ ብታ​ው​ቁኝ አባ​ቴ​ንም ባወ​ቃ​ች​ሁት ነበር፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ግን አው​ቃ​ች​ሁ​ታል፤ አይ​ታ​ች​ሁ​ት​ማል።”</verse>
				<verse number="8">ፊል​ጶ​ስም፥ “ጌታ ሆይ፥ አብን አሳ​የ​ንና ይበ​ቃ​ናል” አለው።</verse>
				<verse number="9">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “ፊል​ጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን አብ​ሬ​አ​ችሁ ስኖር አታ​ወ​ቀ​ኝ​ምን? እኔን ያየ አብን አየ፤ እን​ግ​ዲህ እን​ዴት አብን አሳ​የን ትላ​ለህ?</verse>
				<verse number="10">እኔ በአብ እን​ዳ​ለሁ አብም በእኔ እን​ዳለ አታ​ም​ን​ምን? እኔ የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ ይህ ቃልም ከራሴ የተ​ና​ገ​ር​ሁት አይ​ደ​ለም፤ በእኔ ያለ አብ እርሱ ይህን ሥራ ይሠ​ራ​ዋል እንጂ።</verse>
				<verse number="11">እኔ በአብ እን​ዳ​ለሁ፥ አብም በእኔ እን​ዳለ እመኑ፤ ያለ​ዚ​ያም ስለ ሥራዬ እመ​ኑኝ።</verse>
				<verse number="12">“እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በእኔ የሚ​ያ​ምን እኔ የም​ሠ​ራ​ውን ሥራ እር​ሱም ይሠ​ራል፤ ከዚ​ያም የሚ​በ​ልጥ ይሠ​ራል፤ እኔ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="13">አብ በወ​ልድ ይከ​ብር ዘንድ በስሜ የም​ት​ለ​ም​ኑ​ትን ሁሉ አደ​ር​ግ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">በስሜ የም​ት​ለ​ም​ኑት ነገር ቢኖር ያን አደ​ር​ግ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">“ከወ​ደ​ዳ​ች​ሁ​ኝስ ትእ​ዛ​ዜን ጠብቁ።</verse>
				<verse number="16">እኔም አብን እለ​ም​ነ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ከእ​ና​ንተ ጋር ይኖር ዘንድ ሌላ አጽ​ናኝ ይል​ክ​ላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="17">እር​ሱም ዓለም ስለ​ማ​ያ​የ​ውና ስለ​ማ​ያ​ው​ቀው ሊቀ​በ​ለው የማ​ይ​ቻ​ለው የእ​ው​ነት መን​ፈስ ነው፤ እና​ንተ ግን ታው​ቁ​ታ​ላ​ችሁ፤ በእ​ና​ንተ ዘንድ ይኖ​ራ​ልና፤ ያድ​ር​ባ​ች​ሁ​ማ​ልና።</verse>
				<verse number="18">“የሙት ልጆች ትሆኑ ዘንድ አል​ተ​ዋ​ች​ሁም፤ ወደ እና​ንተ እመ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">ገና ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ዓለም አያ​የ​ኝም፤ እና​ንተ ግን ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና፤ እና​ን​ተም ሕያ​ዋን ትሆ​ና​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="20">እኔ በአብ እን​ዳ​ለሁ፥ አብም በእኔ እን​ዳለ፥ እና​ን​ተም በእኔ፥ እኔም በእ​ና​ንተ እን​ዳ​ለሁ ያን​ጊዜ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="21">ትእ​ዛዜ በእ​ርሱ ዘንድ ያለ የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውም የሚ​ወ​ደኝ እርሱ ነው፤ የሚ​ወ​ደ​ኝ​ንም አባቴ ይወ​ደ​ዋል፤ እኔም እወ​ደ​ዋ​ለሁ፤ ራሴ​ንም እገ​ል​ጥ​ለ​ታ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="22">የአ​ስ​ቆ​ሮቱ ሰው ያይ​ደለ ይሁ​ዳም፥ “ጌታ ሆይ፥ ለዓ​ለም ያይ​ደለ ለእኛ ራስ​ህን ትገ​ልጥ ዘንድ እን​ዳ​ለህ የተ​ና​ገ​ር​ኸው ምን​ድን ነው?” አለው።</verse>
				<verse number="23">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ አለው፥ “የሚ​ወ​ደኝ ቃሌን ይጠ​ብ​ቃል፤ አባ​ቴም ይወ​ደ​ዋል፤ ወደ እር​ሱም መጥ​ተን በእ​ርሱ ዘንድ ማደ​ሪያ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።</verse>
				<verse number="24">የማ​ይ​ወ​ደኝ ግን ቃሌን አይ​ጠ​ብ​ቅም፤ ይህም የም​ት​ሰ​ሙት ቃል የላ​ከኝ የአብ ቃል ነው እንጂ የእኔ ቃል አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="25">“ከእ​ና​ን​ተም ጋር ሳለሁ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ።</verse>
				<verse number="26">ነገር ግን አብ በስሜ የሚ​ል​ከው የእ​ው​ነት መን​ፈስ ጰራ​ቅ​ሊ​ጦስ እርሱ ሁሉን ያስ​ተ​ም​ራ​ች​ኋል፤ እኔ የነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁ​ንም ሁሉ ያሳ​ስ​ባ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="27">“ሰላ​ምን እተ​ው​ላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ሰላ​ሜ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ የም​ሰ​ጣ​ችሁ ዓለም እን​ደ​ሚ​ሰ​ጠው አይ​ደ​ለም፤ ልባ​ችሁ አይ​ደ​ን​ግጥ፤ አት​ፍ​ሩም።</verse>
				<verse number="28">እኔ እን​ደ​ም​ሄድ ወደ እና​ን​ተም እን​ደ​ም​መ​ለስ የነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁን ሰም​ታ​ች​ኋል፤ ብት​ወ​ዱ​ኝስ ወደ አብ በመ​ሄዴ ደስ ባላ​ችሁ ነበር፤ እርሱ አብ ይበ​ል​ጠ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="29">አሁ​ንም ይህ በሆነ ጊዜ ታምኑ ዘንድ አስ​ቀ​ድሜ ሳይ​ሆን ነገ​ር​ኋ​ችሁ።</verse>
				<verse number="30">እን​ግ​ዲህ ወዲህ ከእ​ና​ንተ ጋር ብዙ አል​ና​ገ​ርም፤ የዚህ ዓለም ገዢ ይመ​ጣ​ልና፤ በእ​ኔም ላይ ምንም አያ​ገ​ኝም።</verse>
				<verse number="31">ነገር ግን አብን እን​ደ​ም​ወ​ደው ዓለም ያውቅ ዘንድ አብ ትእ​ዛ​ዙን እንደ ሰጠኝ እን​ዲሁ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ተነሡ ከዚህ፤ እን​ሂድ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">“እው​ነ​ተኛ የወ​ይን ሐረግ እኔ ነኝ፤ ተካ​ዩም አባቴ ነው።</verse>
				<verse number="2">በእኔ ያለ​ውን፥ ፍሬ የማ​ያ​ፈ​ራ​ውን ቅር​ን​ጫ​ፍም ሁሉ ያስ​ወ​ግ​ደ​ዋል፤ የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን ቅር​ን​ጫፍ ሁሉ ግን በብዙ እን​ዲ​ያ​ፈራ ያጠ​ራ​ዋል።</verse>
				<verse number="3">እና​ንተ ግን ስለ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ቃል ፈጽ​ማ​ችሁ ንጹ​ሓን ናችሁ።</verse>
				<verse number="4">በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእ​ና​ንተ፤ ቅር​ን​ጫፍ በወ​ይኑ ግንድ ከአ​ል​ኖረ ብቻ​ውን ሊያ​ፈራ እን​ደ​ማ​ይ​ችል እና​ን​ተም እን​ዲሁ በእኔ ካል​ኖ​ራ​ችሁ ፍሬ ማፍ​ራት አት​ች​ሉም።</verse>
				<verse number="5">እኔ የወ​ይን ግንድ ነኝ፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹም እና​ንተ ናችሁ፤ በእኔ የሚ​ኖር እኔም በእ​ርሱ፥ ብዙ ፍሬ የሚ​ያ​ፈራ እርሱ ነው፤ ያለ እኔ ምንም ማድ​ረግ አት​ች​ሉ​ምና።</verse>
				<verse number="6">በእኔ የማ​ይ​ኖር ቢኖር እንደ ደረቅ ቅር​ን​ጫፍ ወደ ውጭ ይጥ​ሉ​ታል፤ ሰብ​ስ​በ​ውም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​ታል።</verse>
				<verse number="7">በእ​ኔም ብት​ኖሩ ቃሌም በእ​ና​ንተ ቢኖር የም​ት​ሹ​ትን ሁሉ ትለ​ም​ና​ላ​ችሁ፤ ይደ​ረ​ግ​ላ​ች​ሁ​ማል።</verse>
				<verse number="8">ብዙ ፍሬ ብታ​ፈሩ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቴም ብት​ሆኑ በዚህ አባቴ ይከ​በ​ራል።</verse>
				<verse number="9">አብ እንደ ወደ​ደኝ እን​ዲሁ ወደ​ድ​ኋ​ችሁ፤ በፍ​ቅ​ሬም ኑሩ።</verse>
				<verse number="10">የም​ት​ወ​ዱኝ ብት​ሆኑ ትእ​ዛ​ዜን ጠብቁ፤ እኔ የአ​ባ​ቴን ትእ​ዛዝ እንደ ጠበ​ቅሁ፥ በፍ​ቅ​ሩም እን​ደ​ም​ኖር እና​ን​ተም ትእ​ዛ​ዜን ብት​ጠ​ብቁ በፍ​ቅሬ ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="11">ደስ​ታዬ በእ​ና​ንተ ይኖር ዘንድ፥ ደስ​ታ​ች​ሁም ፍጹም ይሆን ዘንድ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ።</verse>
				<verse number="12">“እኔ እንደ ወደ​ድ​ኋ​ችሁ እርስ በር​ሳ​ችሁ እን​ድ​ቷ​ደዱ የእኔ ትእ​ዛዝ ይህች ናት።</verse>
				<verse number="13">ስለ ወዳ​ጆቹ ሕይ​ወ​ቱን አሳ​ልፎ የሚ​ሰጥ ሰው ያለ እንደ ሆነ ከዚህ የሚ​በ​ልጥ ፍቅር የለም።</verse>
				<verse number="14">እና​ን​ተስ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁን ሁሉ ካደ​ረ​ጋ​ችሁ ወዳ​ጆች ናችሁ።</verse>
				<verse number="15">እን​ግ​ዲህ ወዲህ ባሮች አል​ላ​ች​ሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን አያ​ው​ቅ​ምና፤ እና​ን​ተን ግን ወዳ​ጆች እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በአ​ባቴ ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን ሁሉ ነግ​ሬ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="16">እኔ መረ​ጥ​ኋ​ችሁ እንጂ እና​ንተ የመ​ረ​ጣ​ች​ሁኝ አይ​ደ​ለም፤ እን​ድ​ት​ሄዱ፥ ፍሬም እን​ድ​ታ​ፈሩ፥ ፍሬ​አ​ች​ሁም እን​ዲ​ኖር፤ አብ​ንም በስሜ የም​ት​ለ​ም​ኑት ነገር ቢኖር ሁሉን እን​ዲ​ሰ​ጣ​ችሁ ሾም​ኋ​ችሁ።</verse>
				<verse number="17">እርስ በር​ሳ​ች​ሁም እን​ድ​ቷ​ደዱ ይህን አዝ​ዣ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="18">“ዓለም ቢጠ​ላ​ችሁ አስ​ቀ​ድሞ እኔን እንደ ጠላ ዕወቁ።</verse>
				<verse number="19">እና​ን​ተስ ከዓ​ለም ብት​ሆኑ ዓለም በወ​ደ​ዳ​ችሁ ነበር፤ ዓለም ወገ​ኖ​ቹን ይወ​ዳ​ልና፤ ነገር ግን እኔ ከዓ​ለም መረ​ጥ​ኋ​ችሁ እንጂ እና​ንተ ከዓ​ለም አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምና ስለ​ዚህ ዓለም ይጠ​ላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="20">እኔ፦ ከጌ​ታው የሚ​በ​ልጥ አገ​ል​ጋይ የለም ያል​ኋ​ች​ሁን ቃሌን ዐስቡ፤ እኔን ካሳ​ደዱ እና​ን​ተ​ንም ያሳ​ድ​ዱ​አ​ች​ኋል፤ ቃሌን ጠብ​ቀው ቢሆ​ንስ ቃላ​ች​ሁ​ንም በጠ​በቁ ነበር።</verse>
				<verse number="21">ነገር ግን ስለ ስሜ ይህን ሁሉ ያደ​ር​ጉ​ባ​ች​ኋል፤ የላ​ከ​ኝን አያ​ው​ቁ​ት​ምና።</verse>
				<verse number="22">ባል​መ​ጣ​ሁና ባል​ነ​ገ​ር​ኋ​ቸ​ውስ ኖሮ ኀጢ​አት ባል​ሆ​ነ​ባ​ቸ​ውም ነበር፤ አሁን ግን ለኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ምክ​ን​ያት የላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="23">እኔን የሚ​ጠላ አባ​ቴን ይጠ​ላል።</verse>
				<verse number="24">ሌላ ያል​ሠ​ራ​ውን ሥራ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ባል​ሠራ ኖሮ ኀጢ​አት ባል​ሆ​ነ​ባ​ቸ​ውም ነበር፤ አሁን ግን እኔ​ንም አባ​ቴ​ንም አይ​ተ​ዋል፤ ጠል​ተ​ው​ማል።</verse>
				<verse number="25">ነገር ግን በኦ​ሪ​ታ​ቸው፦ በከ​ንቱ ጠሉኝ ተብሎ የተ​ጻ​ፈው ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="26">“እኔ ከአብ ዘንድ የም​ል​ክ​ላ​ችሁ ጰራ​ቅ​ሊ​ጦስ እር​ሱም ከአብ የሚ​ወጣ የእ​ው​ነት መን​ፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመ​ሰ​ክ​ራል።</verse>
				<verse number="27">እና​ን​ተም ትመ​ሰ​ክ​ራ​ላ​ችሁ፤ ከጥ​ንት ጀምሮ ከእኔ ጋር ኑራ​ች​ኋ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">“እን​ዳ​ት​ሰ​ና​ከሉ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ።</verse>
				<verse number="2">ከም​ኵ​ራ​ባ​ቸው ያስ​ወ​ጡ​አ​ች​ኋል፤ ደግ​ሞም እና​ን​ተን የሚ​ገ​ድ​ላ​ችሁ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ያ​ቀ​ርብ የሚ​መ​ስ​ል​በት ጊዜ ይመ​ጣል።</verse>
				<verse number="3">ይህ​ንም የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ባ​ችሁ አብ​ንም፥ እኔ​ንም ስላ​ላ​ወቁ ነው።</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን ጊዜው ሲደ​ርስ እኔ እንደ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ታስቡ ዘንድ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ። አስ​ቀ​ድሜ ግን ይህን አል​ነ​ገ​ር​ክ​ኋ​ች​ሁም ነበር፤ ከእ​ና​ንተ ጋር ነበ​ር​ሁና።</verse>
				<verse number="5">አሁን ግን ወደ ላከኝ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ከእ​ና​ንተ አንዱ እንኳ፦ ‘ወዴት ትሄ​ዳ​ለህ?’ ብሎ አይ​ጠ​ይ​ቀ​ኝም።</verse>
				<verse number="6">ነገር ግን ይህን ስለ ነገ​ር​ኋ​ችሁ በል​ባ​ችሁ ኀዘን ሞላ።</verse>
				<verse number="7">“እኔ በእ​ው​ነት የሚ​ሆ​ነ​ውን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ ብሄድ ይሻ​ላ​ች​ኋል፤ እኔ ካል​ሄ​ድሁ ጰራ​ቅ​ሊ​ጦስ ወደ እና​ንተ አይ​መ​ጣ​ምና፤ እኔ ከሄ​ድሁ ግን እር​ሱን እል​ክ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">እር​ሱም በመጣ ጊዜ ዓለ​ምን ስለ ኀጢ​አ​ትና ስለ ጽድቅ፥ ስለ ፍር​ድም ይዘ​ል​ፈ​ዋል።</verse>
				<verse number="9">ስለ ኀጢ​ኣት፥ በእኔ አላ​መ​ኑ​ምና ነው፤</verse>
				<verse number="10">ስለ ጽድቅ፥ እኔ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለ​ሁና፥ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም አታ​ዩ​ኝ​ምና ነው።</verse>
				<verse number="11">ስለ ፍር​ድም፥ የዚህ ዓለም ገዢ ይፈ​ረ​ድ​በ​ታ​ልና ነው።</verse>
				<verse number="12">“የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ ብዙ ነገር ነበ​ረኝ፤ ነገር ግን አሁን ልት​ሸ​ከ​ሙት አት​ች​ሉም።</verse>
				<verse number="13">ያ የእ​ው​ነት መን​ፈስ በመጣ ጊዜ ግን ወደ እው​ነት ሁሉ ይመ​ራ​ች​ኋል፤ የሚ​ሰ​ማ​ውን ሁሉ ይና​ገ​ራል እንጂ እርሱ ከራሱ አይ​ና​ገ​ር​ምና፤ የሚ​መ​ጣ​ው​ንም ይነ​ግ​ራ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="14">እር​ሱም እኔን ያከ​ብ​ረ​ኛል፤ ከእኔ ወስዶ ይነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ልና።</verse>
				<verse number="15">ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው፤ ስለ​ዚ​ህም ከእኔ ወስዶ ይነ​ግ​ራ​ች​ኋል አል​ኋ​ችሁ።</verse>
				<verse number="16">“ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታ​ዩ​ኝ​ምም፤ ደግ​ሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ደ​ገ​ናም ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለ​ሁና።”</verse>
				<verse number="17">ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታ​ዩ​ኝ​ምም፤ ደግ​ሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ደ​ገ​ናም ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ፥ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለ​ሁና የሚ​ለን ይህ ነገር ምን​ድ​ነው?” ተባ​ባሉ።</verse>
				<verse number="18">“ይህ ጥቂት የሚ​ለን ምን​ድ​ነው? የሚ​ና​ገ​ረ​ውን አና​ው​ቅም” አሉ።</verse>
				<verse number="19">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሊጠ​ይ​ቁት እን​ደ​ሚሹ ዐውቆ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታ​ዩ​ኝ​ምም፤ ደግ​ሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ደ​ገ​ናም ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ” ስለ አል​ኋ​ችሁ፥ ስለ​ዚህ ነገር እርስ በር​ሳ​ችሁ ትመ​ራ​መ​ራ​ላ​ች​ሁን?</verse>
				<verse number="20">“እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ንተ ታለ​ቅ​ሳ​ላ​ችሁ፤ ታዝ​ኑ​ማ​ላ​ችሁ፤ ዓለ​ምም ደስ ይለ​ዋል፤ እና​ንተ ግን ታዝ​ና​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን ኀዘ​ና​ችሁ ወደ ደስታ ይለ​ወ​ጣል።</verse>
				<verse number="21">ሴት በም​ት​ወ​ል​ድ​በት ጊዜ ወራቷ ስለ ደረሰ ታዝ​ና​ለች፤ ነገር ግን ልጅ​ዋን ከወ​ለ​ደች በኋላ ስለ ደስ​ታዋ ከዚያ ወዲያ ምጥ​ዋን አታ​ስ​በ​ውም፤ በዓ​ለም ወንድ ልጅን ወል​ዳ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="22">እና​ን​ተም ዛሬ ታዝ​ና​ላ​ችሁ፤ እን​ደ​ገ​ናም አያ​ች​ኋ​ለሁ፤ ልባ​ች​ሁም ደስ ይለ​ዋል፤ ደስ​ታ​ች​ሁ​ንም የሚ​ወ​ስ​ድ​ባ​ችሁ የለም።</verse>
				<verse number="23">ያን​ጊ​ዜም እኔን የም​ት​ለ​ም​ኑኝ አን​ዳች የለም፤ እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በስሜ አብን ብት​ለ​ም​ኑት ሁሉን ይሰ​ጣ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="24">እስ​ካ​ሁን ምንም በስሜ አል​ለ​መ​ና​ች​ሁም፤ ደስ​ታ​ችሁ ፍጹም ይሆን ዘንድ ለምኑ፤ ታገ​ኙ​ማ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="25">“ዛሬስ በም​ሳሌ ነገ​ር​ኋ​ችሁ፤ ነገር ግን የአ​ብን ነገር ገልጬ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ ለእ​ና​ንተ በም​ሳሌ የማ​ል​ና​ገ​ር​በት ጊዜ ይመ​ጣል።</verse>
				<verse number="26">ያን​ጊዜ በስሜ ትለ​ም​ና​ላ​ችሁ፤ እኔም ስለ እና​ንተ አብን እለ​ም​ነ​ዋ​ለህ አል​ላ​ች​ሁም፤</verse>
				<verse number="27">እና​ንተ ስለ ወደ​ዳ​ች​ሁኝ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ወጣሁ ስለ አመ​ና​ች​ሁ​ብኝ እርሱ ራሱ አብ ወድ​ዷ​ች​ኋ​ልና።</verse>
				<verse number="28">ከአብ ወጣሁ፤ ወደ ዓለ​ምም መጣሁ፤ ዳግ​መ​ኛም ዓለ​ምን እተ​ወ​ዋ​ለሁ፤ ወደ አብም እሄ​ዳ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="29">ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እን​ዲህ አሉት፥ “እነሆ፥ ዛሬ ገል​ጠህ ትና​ገ​ራ​ለህ፤ ምንም በም​ሳሌ የተ​ና​ገ​ር​ኸው የለም።</verse>
				<verse number="30">አሁን አንተ ሁሉን እን​ደ​ም​ታ​ውቅ፥ ማንም ሊነ​ግ​ርህ እን​ደ​ማ​ትሻ ዐወ​ቅን፤ በዚ​ህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ወጣህ እና​ም​ና​ለን።”</verse>
				<verse number="31">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አሁን ታም​ና​ላ​ች​ሁን?</verse>
				<verse number="32">እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ በየ​ቦ​ታዉ የም​ት​በ​ታ​ተ​ኑ​በት፥ እኔ​ንም ብቻ​ዬን የም​ት​ተ​ዉ​በት ጊዜ ይደ​ር​ሳል፤ ደር​ሶ​አ​ልም፤ እኔ ግን ብቻ​ዬን አይ​ደ​ለ​ሁም፤ አብ ከእኔ ጋር ነውና።</verse>
				<verse number="33">በእ​ኔም ሰላ​ምን እን​ድ​ታ​ገኙ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ፤ በዓ​ለም ግን መከ​ራን ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን ጽኑ፤ እኔ ዓለ​ሙን ድል ነሥ​ቼ​ዋ​ለ​ሁና።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ነገር ተና​ግሮ ዐይ​ኖ​ቹን ወደ ሰማይ አነ​ሣና እን​ዲህ አለ፥ “አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደር​ሶ​አ​ልና ልጅህ ያከ​ብ​ርህ ዘንድ ልጅ​ህን አክ​ብ​ረው፤</verse>
				<verse number="2">ሥጋ በለ​በ​ሰው ሁሉ ላይ ሥል​ጣ​ንን እንደ ሰጠ​ኸው መጠን ለሰ​ጠ​ኸው ሁሉ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ።</verse>
				<verse number="3">ብቻ​ህን እው​ነ​ተኛ አም​ላክ የሆ​ንህ አን​ተን፥ የላ​ክ​ኸ​ው​ንም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ናት።</verse>
				<verse number="4">እኔ ልሠ​ራው የሰ​ጠ​ኸ​ኝን ሥራ ፈጽሜ በም​ድር ላይ አከ​በ​ር​ሁህ።</verse>
				<verse number="5">አሁ​ንም አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር ከአ​ንተ ጋር በነ​በ​ረኝ ክብር በአ​ንተ ዘንድ አክ​ብ​ረኝ።</verse>
				<verse number="6">“ከዓ​ለም ለይ​ተህ ለሰ​ጠ​ኸኝ ሰዎች ስም​ህን ገለ​ጥሁ፤ ያንተ ነበሩ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ለእኔ ሰጥ​ተ​ኸ​ኛል፤ ቃል​ህ​ንም ጠበቁ።</verse>
				<verse number="7">የሰ​ጠ​ኸ​ኝም ሁሉ ከአ​ንተ እንደ ሆነ ዛሬ ዐወቁ።</verse>
				<verse number="8">የሰ​ጠ​ኽ​ኝን ቃል ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፤ እነ​ር​ሱም ተቀ​ብ​ለው ከአ​ንተ እንደ ወጣሁ በእ​ው​ነት ዐወቁ፤ አን​ተም እንደ ላክ​ኸኝ አመኑ።</verse>
				<verse number="9">እኔ ስለ እነ​ርሱ እለ​ም​ና​ለሁ፤ የም​ለ​ም​ንህ ስለ ዓለም አይ​ደ​ለም፤ ስለ ሰጠ​ኸኝ ነው እንጂ፤ ያንተ ናቸ​ውና።</verse>
				<verse number="10">የእ​ኔም የሆነ ሁሉ የአ​ንተ ነው፤ የአ​ን​ተም የሆነ የእኔ ነው፤ እኔም በእ​ነ​ርሱ ከብ​ሬ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">እን​ግ​ዲህ በዓ​ለም አል​ኖ​ርም፤ እነ​ርሱ ግን በዓ​ለም ይኖ​ራሉ፤ እኔም ወደ አንተ እመ​ጣ​ለሁ፤ ቅዱስ አባት ሆይ፥ እነ​ዚ​ህን የሰ​ጠ​ኸ​ኝን እንደ እኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ በስ​ምህ ጠብ​ቃ​ቸው፤</verse>
				<verse number="12">እኔ በዓ​ለም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሳለሁ ግን የሰ​ጠ​ኸ​ኝን በስ​ምህ እጠ​ብ​ቃ​ቸው ነበር፤ ጠበ​ቅ​ኋ​ቸ​ውም፤ የመ​ጽ​ሐ​ፉም ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ከጥ​ፋት ልጅ በቀር ከእ​ነ​ርሱ አንድ ስን​ኳን አል​ጠ​ፋም።</verse>
				<verse number="13">አሁን ግን ወደ አንተ እመ​ጣ​ለሁ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ደስ​ታዬ ፍጹም ይሆን ዘንድ ይህን በዓ​ለም እና​ገ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">እኔ ቃል​ህን ሰጠ​ኋ​ቸው፤ ዓለም ግን ጠላ​ቸው፤ እኔ ከዓ​ለም እን​ዳ​ይ​ደ​ለሁ እነ​ርሱ ከዓ​ለም አይ​ደ​ሉ​ምና።</verse>
				<verse number="15">ከክፉ ነገር እን​ድ​ት​ጠ​ብ​ቃ​ቸው ነው እንጂ ከዓ​ለም እን​ድ​ት​ለ​ያ​ቸው አል​ለ​ም​ንም።</verse>
				<verse number="16">እኔ ከዓ​ለም እን​ዳ​ይ​ደ​ለሁ ከዓ​ለም አይ​ደ​ሉ​ምና።</verse>
				<verse number="17">በእ​ው​ነ​ትህ ቀድ​ሳ​ቸው፤ ቃልህ እው​ነት ነውና።</verse>
				<verse number="18">አንተ እኔን ወደ ዓለም እንደ ላክ​ኸኝ እኔም እነ​ር​ሱን ወደ ዓለም ላክ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">እነ​ር​ሱም በእ​ው​ነት ቅዱ​ሳን ይሆኑ ዘንድ ስለ እነ​ርሱ እኔ ራሴን እቀ​ድ​ሳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">“የም​ለ​ም​ን​ህም ስለ እነ​ዚህ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በቃ​ላ​ቸው ስለ​ሚ​ያ​ም​ኑ​ብ​ኝም ነው እንጂ፤</verse>
				<verse number="21">ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ አንተ አብ በእኔ እን​ዳ​ለህ፥ እኔም በአ​ንተ እን​ዳ​ለሁ፥ እነ​ር​ሱም እንደ እኛ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ አን​ተም እንደ ላክ​ኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ።</verse>
				<verse number="22">እኔም የሰ​ጠ​ኸ​ኝን ክብር ሰጠ​ኋ​ቸው፤ እኛ አንድ እን​ደ​ሆን እነ​ር​ሱም እንደ እኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ።</verse>
				<verse number="23">እኔ በእ​ነ​ርሱ እኖ​ራ​ለሁ፤ አን​ተም በእኔ፤ በአ​ንድ ፍጹ​ማን ይሆኑ ዘንድ፤ አን​ተም እንደ ላክ​ኸ​ኝና እንደ ወደ​ድ​ኸኝ እኔም እነ​ር​ሱን እንደ ወደ​ድ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">አባት ሆይ፥ የሰ​ጠ​ኸኝ እነ​ዚህ እኔ ባለ​ሁ​በት አብ​ረ​ውኝ ይኖሩ ዘን​ድና የሰ​ጠ​ኸ​ኝን ክብ​ሬን ያዩ ዘንድ እወ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር ወድ​ደ​ኸ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="25">ጻድቅ አባት ሆይ፥ ዓለም አላ​ወ​ቀ​ህም፤ እኔ ግን ዐወ​ቅ​ሁህ፤ እነ​ዚ​ህም አንተ እንደ ላክ​ኸኝ ዐወቁ።</verse>
				<verse number="26">እኔን የወ​ደ​ድ​ህ​በት ፍቅር በእ​ነ​ርሱ ይኖር ዘንድ፥ እኔም በእ​ነ​ርሱ እኖር ዘንድ ስም​ህን ነገ​ር​ኋ​ቸው፤ ደግ​ሞም እነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ተና​ግሮ አት​ክ​ልት ወደ አለ​በት ስፍራ ወደ ቄድ​ሮስ ወንዝ ማዶ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ወጣ፤ ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ጋር ወደ​ዚያ ገባ።</verse>
				<verse number="2">አሳ​ልፎ የሚ​ሰ​ጠው ይሁ​ዳም ያን ስፍራ ያው​ቀው ነበር፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ወደ​ዚያ ብዙ ጊዜ ይሄድ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="3">ይሁ​ዳም ከካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወታ​ደ​ሮ​ችን ተቀ​በለ፤ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም በረ​ዳ​ት​ነት ወሰደ፤ ፋኖ​ስና የችቦ መብ​ራት፥ የጦር መሣ​ሪ​ያም ይዞ ወደ​ዚያ ሄደ።</verse>
				<verse number="4">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም የሚ​ደ​ር​ስ​በ​ትን ሁሉ ዐውቆ ወደ እነ​ርሱ ወደ ውጭ ወጣና፥ “ማንን ትሻ​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">“የና​ዝ​ሬ​ቱን ኢየ​ሱ​ስን” ብለው መለ​ሱ​ለት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ ነኝ” አላ​ቸው፤ አሳ​ልፎ የሰ​ጠው ይሁ​ዳም በዚ​ያው አብ​ሮ​አ​ቸው ቆሞ ነበር።</verse>
				<verse number="6">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ ነኝ” ባላ​ቸው ጊዜ፤ ወደ ኋላ​ቸው ተመ​ል​ሰው በም​ድር ላይ ወደቁ።</verse>
				<verse number="7">ከዚ​ህም በኋላ እን​ደ​ገና፥ “ማንን ትሻ​ላ​ችሁ?” ብሎ ጠየ​ቃ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “የና​ዝ​ሬ​ቱን ኢየ​ሱ​ስን” አሉት።</verse>
				<verse number="8">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ ነኝ አል​ኋ​ችሁ፤ እኔን የም​ትሹ ከሆነ እነ​ዚ​ህን ተዉ​አ​ቸው፤ ይሂዱ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ይህም፥ “ከእ​ነ​ዚህ ከሰ​ጠ​ኸኝ አንድ ስንኳ አል​ጠ​ፋም” ያለው ቃሉ ይፈ​ጸም ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="10">ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ሾተል ነበ​ረው፤ ሾተ​ሉ​ንም መዝዞ የሊቀ ካህ​ና​ቱን አገ​ል​ጋይ መትቶ ቀኝ ጆሮ​ውን ቈረ​ጠው፤ የዚ​ህም አገ​ል​ጋይ ስም ማል​ኮስ ይባል ነበር።</verse>
				<verse number="11">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ጴጥ​ሮ​ስን፥ “ሾተ​ል​ህን ወደ አፎቷ መልስ፤ አብ የሰ​ጠ​ኝን ጽዋ ሳል​ጠጣ እተ​ወ​ዋ​ለ​ሁን?” አለው።</verse>
				<verse number="12">ጭፍ​ሮ​ችና የሺ አለ​ቃው፥ የአ​ይ​ሁ​ድም ሎሌ​ዎች ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ይዘው አሰ​ሩት።</verse>
				<verse number="13">አስ​ቀ​ድ​ሞም ወደ ሐና ወሰ​ዱት፤ በዚ​ያች ዓመት የካ​ህ​ናት አለቃ ለነ​በ​ረው ለቀ​ያፋ አማቱ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="14">ቀያ​ፋም “ስለ ሕዝቡ ሁሉ አንድ ሰው ቢሞት ይሻ​ላል” ብሎ አይ​ሁ​ድን የመ​ከ​ራ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="15">ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስና ሌላው ደቀ መዝ​ሙ​ርም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከሩቅ ተከ​ተ​ሉት፤ ያ ደቀ መዝ​ሙር ግን በሊቀ ካህ​ናቱ ዘንድ የታ​ወቀ ነበር፤ ከጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ ጋርም ወደ ሊቀ ካህ​ናቱ ግቢ ገባ።</verse>
				<verse number="16">ጴጥ​ሮስ ግን በስ​ተ​ውጭ በበሩ ቆሞ ነበር፤ ያም በሊቀ ካህ​ናቱ ዘንድ ይታ​ወቅ የነ​በ​ረው ሌላው ደቀ መዝ​ሙር ወጣና ለበ​ረ​ኛ​ዪቱ ነግሮ ጴጥ​ሮ​ስን አስ​ገ​ባው።</verse>
				<verse number="17">በረ​ኛ​ዪቱ አገ​ል​ጋ​ይም፥ “አን​ተም ከዚያ ሰው ደቀ መዛ​ሙ​ርት ወገን አይ​ደ​ለ​ህ​ምን?” አለ​ችው፤ እር​ሱም፥ “አይ​ደ​ለ​ሁም” አላት።</verse>
				<verse number="18">አገ​ል​ጋ​ዮ​ችና ሎሌ​ዎ​ችም በዚያ ቆመው እሳት አን​ድ​ደው ይሞቁ ነበር፤ የዚ​ያች ሌሊት ብርድ ጽኑ ነበ​ርና፤ ጴጥ​ሮ​ስም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቆሞ ይሞቅ ነበረ።</verse>
				<verse number="19">ሊቀ ካህ​ና​ቱም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን፦ ስለ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱና ስለ ትም​ህ​ርቱ ጠየ​ቀው።</verse>
				<verse number="20">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እኔ ለዓ​ለም በግ​ልጥ ተና​ገ​ርሁ፤ አይ​ሁድ ሁሉ በሚ​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት በም​ኵ​ራ​ብም፥ በቤተ መቅ​ደ​ስም ሁል​ጊዜ አስ​ተ​ማ​ርሁ፤ በስ​ው​ርም የተ​ና​ገ​ር​ሁት አን​ዳች ነገር የለም።</verse>
				<verse number="21">እን​ግ​ዲህ እኔን ለምን ትጠ​ይ​ቀ​ኛ​ለህ? የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን የሰ​ሙ​ኝን ጠይ​ቃ​ቸው፤ እኔም የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን እነሆ፥ እነ​ርሱ ያው​ቃሉ።”</verse>
				<verse number="22">ይህ​ንም ባለ​ጊዜ ከቆ​ሙት ሎሌ​ዎች አንዱ፥ “ለሊቀ ካህ​ናቱ እን​ዲህ ትመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለ​ህን?” ብሎ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን በጥፊ መታው።</verse>
				<verse number="23">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ክፉ ተና​ግሬ እንደ ሆንሁ ስለ ክፉ መስ​ክ​ር​ብኝ፤ መል​ካም ተና​ግሬ እንደ ሆንሁ ግን ለምን ትመ​ታ​ኛ​ለህ?” አለው።</verse>
				<verse number="24">ሐናም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እንደ ታሰረ ወደ ሊቀ ካህ​ናቱ ወደ ቀያፋ ላከው።</verse>
				<verse number="25">ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር፤ “አን​ተስ ከእ​ርሱ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ወገን አይ​ደ​ለ​ህ​ምን?” አሉት፤ እር​ሱም፥ “አይ​ደ​ለ​ሁም” ብሎ ካደ።</verse>
				<verse number="26">ጴጥ​ሮስ ጆሮ​ውን ከቈ​ረ​ጠው ሰው ዘመ​ዶች ወገን የሆነ ከሊቀ ካህ​ናቱ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም አንድ ሰው፥ “እኔ በአ​ት​ክ​ልት ቦታ ውስጥ ከእ​ርሱ ጋር አይ​ችህ አል​ነ​በ​ረ​ምን?” አለው።</verse>
				<verse number="27">ጴጥ​ሮ​ስም ደግሞ ካደ፤ ያን​ጊ​ዜም ዶሮ ጮኸ።</verse>
				<verse number="28">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ከቀ​ያፋ ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ ወሰ​ዱት፤ አይ​ሁድ ግን ፈጽሞ ስለ ነጋ የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ ሳይ​በሉ እን​ዳ​ይ​ረ​ክሱ ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ አል​ገ​ቡም።</verse>
				<verse number="29">ጲላ​ጦ​ስም ወደ እነ​ርሱ ወደ ውጭ ወጥቶ፥ “ይህን ሰው ወደ እኔ ያመ​ጣ​ች​ሁ​በት በደሉ ምን​ድ​ነው?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="30">እነ​ር​ሱም፥ “ክፉ የሠራ ባይ​ሆ​ንስ ወደ አንተ አሳ​ል​ፈን ባል​ሰ​ጠ​ነው ነበር” ብለው መለ​ሱ​ለት።</verse>
				<verse number="31">ጲላ​ጦ​ስም፥ “እና​ንተ ወስ​ዳ​ችሁ እንደ ሕጋ​ችሁ ፍረ​ዱ​በት” አላ​ቸው፤ አይ​ሁ​ድም፥ “እኛስ ማን​ንም ልን​ገ​ድል አል​ተ​ፈ​ቀ​ደ​ል​ንም” አሉት።</verse>
				<verse number="32">ይህም በምን ዐይ​ነት ሞት ይሞት ዘንድ እን​ዳ​ለው ሲያ​መ​ለ​ክት የተ​ና​ገ​ረው የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="33">ጲላ​ጦ​ስም እን​ደ​ገና ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ ገብቶ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ጠራና፥ “የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ አንተ ነህን?” አለው።</verse>
				<verse number="34">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ይህን የም​ት​ና​ገር ከራ​ስህ ነውን? ወይስ ስለ እኔ የነ​ገ​ረህ ሌላ አለን?” ብሎ መለ​ሰ​ለት።</verse>
				<verse number="35">ጲላ​ጦ​ስም መልሶ፥ “እኔ አይ​ሁ​ዳዊ ነኝን? ለእኔ አሳ​ል​ፈው የሰ​ጡህ ወገ​ኖ​ች​ህና ሊቃነ ካህ​ናት አይ​ደ​ሉ​ምን? Aረ ምን አድ​ር​ገ​ሃል?” አለው።</verse>
				<verse number="36">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የእኔ መን​ግ​ሥት ከዚህ ዓለም አይ​ደ​ለ​ችም፤ መን​ግ​ሥ​ቴስ በዚህ ዓለም ብት​ሆን ኖሮ ለአ​ይ​ሁድ እን​ዳ​ል​ሰጥ አሽ​ከ​ሮች በተ​ዋ​ጉ​ልኝ ነበር፤ አሁ​ንም መን​ግ​ሥቴ ከዚህ አይ​ደ​ለ​ችም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።</verse>
				<verse number="37">ጲላ​ጦ​ስም፥ “እን​ግ​ዲያ አንተ ንጉሥ ነህን?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ራስህ ትላ​ለህ፤ እኔ ስለ​ዚህ ተወ​ለ​ድሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ለእ​ው​ነት ልመ​ሰ​ክር ወደ ዓለም መጣሁ፤ ከእ​ው​ነት የሆነ ሁሉ ቃሌን ይሰ​ማ​ኛል” አለው።</verse>
				<verse number="38">ጲላ​ጦ​ስም፥ “እው​ነት ምን​ድ​ነው?” አለው፤ ይህ​ንም ተና​ግሮ ዳግ​መኛ ወደ አይ​ሁድ ወጣና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ አን​ዲት ስን​ኳን በደል አላ​ገ​ኘ​ሁ​በ​ትም።</verse>
				<verse number="39">ነገር ግን በየ​ዓ​መቱ በፋ​ሲካ በዓል ከእ​ስ​ረ​ኞች አንድ እን​ድ​ፈ​ታ​ላ​ችሁ ልማድ አላ​ችሁ፤ እን​ግ​ዲህ የአ​ይ​ሁ​ድን ንጉሥ ልፈ​ታ​ላ​ችሁ ትወ​ዳ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="40">ዳግ​መ​ኛም ድም​ፃ​ቸ​ውን ከፍ አድ​ር​ገው፥ “በር​ባ​ንን እንጂ ይህን አይ​ደ​ለም፤” አሉ፤ በር​ባን ግን ወን​በዴ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ ጲላ​ጦስ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ይዞ ገረ​ፈው።</verse>
				<verse number="2">ጭፍ​ሮ​ችም የእ​ሾህ አክ​ሊል ጐን​ጕ​ነው በራሱ ላይ ደፉ​በት፤ የቀይ ሐር መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያም አለ​በ​ሱት።</verse>
				<verse number="3">ወደ እር​ሱም እየ​መጡ፥ “የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአ​ንተ ይሁን” ይሉት ነበር፤ በጥ​ፊም ይመ​ቱት ነበር።</verse>
				<verse number="4">ጲላ​ጦ​ስም እን​ደ​ገና ወደ ውጭ ወጣና፥ “እነሆ፥ በእ​ርሱ ላይ አን​ዲት በደል ስን​ኳን ያገ​ኘ​ሁ​በት እን​ደ​ሌለ ታውቁ ዘንድ ወደ ውጭ አወ​ጣ​ላ​ች​ኋ​ለሁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም የእ​ሾህ አክ​ሊል ደፍቶ፥ የቀይ ሐር መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያም ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ፤ ጲላ​ጦ​ስም፥ “እነሆ፥ ሰው​ዬው” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">ሊቃነ ካህ​ና​ትና ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ባዩት ጊዜ፥ “ስቀ​ለው! ስቀ​ለው!” እያሉ ጮሁ፤ ጲላ​ጦ​ስም፥ “እና​ንተ ራሳ​ችሁ ውሰ​ዱና ስቀ​ሉት፤ እኔስ በእ​ርሱ ላይ በደል አላ​ገ​ኘ​ሁ​በ​ትም” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">አይ​ሁ​ድም መል​ሰው፥ “እኛ ሕግ አለን፤ እንደ ሕጋ​ች​ንም ሊሞት ይገ​ባል፤ ራሱን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ አድ​ር​ጎ​አ​ልና” አሉት።</verse>
				<verse number="8">ጲላ​ጦ​ስም ይህን ነገር ሰምቶ እጅግ ፈራ።</verse>
				<verse number="9">ደግ​ሞም ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ ገባና ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን፥ “አንተ ከወ​ዴት ነህ?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ግን ምንም አል​መ​ለ​ሰ​ለ​ትም።</verse>
				<verse number="10">ጲላ​ጦ​ስም፥ “ለእ​ኔም አት​ነ​ግ​ረ​ኝ​ምን? ልሰ​ቅ​ልህ ሥል​ጣን እንደ አለኝ፥ ወይም ልፈ​ታህ ሥል​ጣን እን​ዳ​ለኝ፥ አታ​ው​ቅ​ምን?” አለው።</verse>
				<verse number="11">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ከሰ​ማይ ካል​ተ​ሰ​ጠህ በቀር በእኔ ላይ አን​ዳች ሥል​ጣን የለ​ህም፤ ስለ​ዚህ ለአ​ንተ አሳ​ልፎ የሰ​ጠኝ ሰው ታላቅ ኀጢ​ኣት አለ​በት” አለው።</verse>
				<verse number="12">ስለ​ዚ​ህም ጲላ​ጦስ ሊፈ​ታው ወድዶ ነበር፤ አይ​ሁድ ግን፥ “ይህን ከፈ​ታ​ኸው የቄ​ሣር ወዳጅ አይ​ደ​ለ​ህም፤ ራሱን ንጉሥ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው ሁሉ በቄ​ሣር ላይ የሚ​ያ​ምፅ ነውና” ብለው ጮሁ።</verse>
				<verse number="13">ጲላ​ጦ​ስም ይህን ሰምቶ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ወደ ውጭ አወ​ጣው፤ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስ​ጥም ገበታ ተብሎ በሚ​ጠ​ራው “ጸፍ​ጸፍ” በሚ​ሉት ቦታ ላይ በወ​ን​በር ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="14">የፋ​ሲ​ካም የመ​ዘ​ጋ​ጀት ቀን ነበር፤ ጊዜ​ዉም ስድ​ስት ሰዓት ያህል ነበር፤ ጲላ​ጦ​ስም አይ​ሁ​ድን፥ “እነሆ፥ ንጉ​ሣ​ችሁ” አላ​ቸው፤</verse>
				<verse number="15">እነ​ርሱ ግን፥ “አስ​ወ​ግ​ደው! ስቀ​ለው!” እያሉ ጮሁ። ጲላ​ጦ​ስም፥ “ንጉ​ሣ​ች​ሁን ልስ​ቀ​ለ​ውን?” አላ​ቸው፤ ሊቃነ ካህ​ና​ቱም፥ “ከቄ​ሣር በቀር ሌላ ንጉሥ የለ​ንም” ብለው መለሱ።</verse>
				<verse number="16">ከዚህ በኋላ ሊሰ​ቅ​ሉት አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ተቀ​ብ​ለው ወሰ​ዱት።</verse>
				<verse number="17">መስ​ቀ​ሉ​ንም ተሸ​ክሞ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ጎል​ጎታ ወደ ተባ​ለው ቀራ​ንዮ ወደ​ሚ​ባል ቦታ ወጣ።</verse>
				<verse number="18">በዚ​ያም ሰቀ​ሉት፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አን​ዱን በቀኝ፥ አን​ዱ​ንም በግራ አድ​ር​ገው ሌሎች ሁለት ወን​በ​ዴ​ዎ​ችን ሰቀሉ፤ ኢየ​ሱ​ስ​ንም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ሰቀሉ።</verse>
				<verse number="19">ጲላ​ጦ​ስም ጽሕ​ፈት ጽፎ በመ​ስ​ቀሉ ላይ አኖረ፤ ጽሕ​ፈ​ቱም፥ “የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ” የሚል ነበር።</verse>
				<verse number="20">ከአ​ይ​ሁ​ድም ይህ​ቺን ጽሕ​ፈት ያነ​በ​ብ​ዋት ብዙ​ዎች ነበሩ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን የሰ​ቀ​ሉ​በት ቦታ ለከ​ተማ ቅርብ ነበ​ርና፤ ጽሕ​ፈ​ቱም የተ​ጻ​ፈው በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ፥ በሮ​ማ​ይ​ስ​ጥና በግ​ሪክ ነበር።</verse>
				<verse number="21">ሊቃነ ካህ​ና​ትም ጲላ​ጦ​ስን አሉት፥ “እርሱ ራሱ ‘እኔ የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ ነኝ’ እን​ዳለ እንጂ የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ ብለህ አት​ጻፍ።”</verse>
				<verse number="22">ጲላ​ጦ​ስም፥ “የጻ​ፍ​ሁ​ትን ጻፍሁ” ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">ጭፍ​ሮ​ችም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን በሰ​ቀ​ሉት ጊዜ ልብ​ሶ​ቹን ወስ​ደው ከጭ​ፍ​ሮቹ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አራት ክፍል አድ​ር​ገው መደ​ቡት፤ ቀሚ​ሱ​ንም ወሰዱ፤ ቀሚ​ሱም ከላይ ጀምሮ የተ​ሠራ ሥረ​ወጥ እንጂ የተ​ሰፋ አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="24">እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ዕጣ እን​ጣ​ጣ​ልና ለደ​ረሰ ይድ​ረ​ሰው እንጂ አን​ቅ​ደ​ደው ተባ​ባሉ፤” ይህም “ልብ​ሶ​ችን ለራ​ሳ​ቸው ተካ​ፈሉ፤ በቀ​ሚ​ሴም ላይ ዕጣ ተጣ​ጣሉ” ያለው የመ​ጽ​ሐፍ ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ነው፤ ጭፍ​ሮ​ችም እን​ዲሁ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="25">በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ መስ​ቀል አጠ​ገ​ብም እናቱ፥ የእ​ና​ቱም እኅት፥ የቀ​ለ​ዮ​ጳም ሚስት ማር​ያም፥ መግ​ደ​ላ​ዊት ማር​ያ​ምም ቆመው ነበር።</verse>
				<verse number="26">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እና​ቱ​ንና የሚ​ወ​ደ​ውን ደቀ መዝ​ሙ​ሩን ቆመው ባያ​ቸው ጊዜ እና​ቱን፥ “አንች ሆይ፥ እነሆ፥ ልጅሽ” አላት።</verse>
				<verse number="27">ከዚ​ህም በኋላ ደቀ መዝ​ሙ​ሩን፥ “እና​ትህ እነ​ኋት” አለው፤ ከዚ​ያ​ችም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝ​ሙሩ ተቀ​ብሎ ወደ ቤቱ ወሰ​ዳት።</verse>
				<verse number="28">ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ሁሉ እንደ ተፈ​ጸመ ባየ ጊዜ የመ​ጽ​ሐፉ ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ “ተጠ​ማሁ” አለ።</verse>
				<verse number="29">በዚ​ያም ሆም​ጣጤ የመ​ላ​በት ማሰሮ ነበር፤ እነ​ር​ሱም ሆም​ጣ​ጤ​ውን በሰ​ፍ​ነግ ሞል​ተው በስ​ምዛ ዘንግ ከአፉ አገ​ና​ኝ​ተው ጨመ​ቁት።</verse>
				<verse number="30">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሆም​ጣ​ጤ​ውን ቀምሶ፥ “ሁሉ ተፈ​ጸመ” አለ፤ ራሱ​ንም አዘ​ን​ብሎ ነፍ​ሱን ሰጠ።</verse>
				<verse number="31">አይ​ሁድ ግን የመ​ዘ​ጋ​ጀት ቀን ነበ​ርና፥ የዚ​ያች ሰን​በ​ትም ቀን ታላቅ ናትና “ሥጋ​ቸው በሰ​ን​በት በመ​ስ​ቀል ላይ አይ​ደር” አሉ፤ ጭን ጭና​ቸ​ው​ንም ሰብ​ረው ያወ​ር​ዷ​ቸው ዘንድ ጲላ​ጦ​ስን ለመ​ኑት።</verse>
				<verse number="32">ጭፍ​ሮ​ችም መጥ​ተው ከእ​ርሱ ጋር የተ​ሰ​ቀ​ሉ​ትን የአ​ን​ደ​ኛ​ው​ንና የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውን ጭኖች ሰበሩ።</verse>
				<verse number="33">ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሄደው ፈጽሞ እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ጭኑን አል​ሰ​በ​ሩም።</verse>
				<verse number="34">ነገር ግን ከጭ​ፍ​ሮቹ አንዱ የቀኝ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ያን​ጊ​ዜም ከእ​ርሱ ደምና ውኃ ወጣ።</verse>
				<verse number="35">ያየ​ውም መሰ​ከረ፤ ምስ​ክ​ር​ነ​ቱም እው​ነት ነው፤ እር​ሱም እና​ንተ ልታ​ምኑ እው​ነት እን​ደ​ሚ​ና​ገር ያው​ቃል።</verse>
				<verse number="36">ይህ ሁሉ የሆ​ነው “ከእ​ርሱ ዐፅ​ሙን አት​ስ​በሩ” ያለው የመ​ጽ​ሐፍ ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="37">ሌላ​ዉም መጽ​ሐፍ ደግሞ“ የወ​ጉ​ትን ያዩ​ታል” ይላል።</verse>
				<verse number="38">ከዚ​ህም በኋላ አይ​ሁ​ድን ስለ​ፈራ በስ​ውር የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ደቀ መዝ​ሙር የነ​በ​ረው የአ​ር​ማ​ት​ያስ ሰው ዮሴፍ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ሥጋ ይወ​ስድ ዘንድ ጲላ​ጦ​ስን ለመ​ነው፤ ጲላ​ጦ​ስም ፈቀ​ደ​ለት። እር​ሱም ሄዶ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ሥጋ ወሰደ።</verse>
				<verse number="39">ቀድሞ በሌ​ሊት ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ሄዶ የነ​በ​ረው ኒቆ​ዲ​ሞ​ስም መጣ፤ ቀብ​ተ​ውም የሚ​ቀ​ብ​ሩ​በ​ትን መቶ ወቄት የከ​ር​ቤና የሬት ቅል​ቅል ሽቶ አመጣ።</verse>
				<verse number="40">እንደ አይ​ሁድ አገ​ና​ነዝ ሥር​ዐ​ትም የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ሥጋ ወስ​ደው ከሽቱ ጋር በበ​ፍታ ገነ​ዙት።</verse>
				<verse number="41">በዚ​ያም በተ​ሰ​ቀ​ለ​በት ቦታ የአ​ት​ክ​ልት ስፍራ ነበር፤ በዚያ የአ​ት​ክ​ልት ስፍራ ውስ​ጥም በው​ስጡ ሰው ያል​ተ​ቀ​በ​ረ​በት አዲስ መቃ​ብር ነበር።</verse>
				<verse number="42">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም በዚያ ቀበ​ሩት፤ ለአ​ይ​ሁድ የመ​ሰ​ና​ዳት ቀን ነበ​ርና፤ መቃ​ብ​ሩም ለሰ​ቀ​ሉ​በት ቦታ ቅርብ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">ከሳ​ም​ን​ቱም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያዉ ቀን ማር​ያም መግ​ደ​ላ​ዊት በማ​ለዳ ገና ጨለማ ሳለ ወደ መቃ​ብር መጣች፤ ድን​ጋ​ዩ​ንም ከመ​ቃ​ብሩ አፍ ተነ​ሥቶ አገ​ኘ​ችው።</verse>
				<verse number="2">ፈጥ​ናም ወደ ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስና ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ይወ​ደው ወደ ነበ​ረው ወደ​ዚያ ወደ ሌላዉ ደቀ መዝ​ሙር መጥታ፥ “ጌታ​ዬን ከመ​ቃ​ብር ወስ​ደ​ው​ታል፤ ወዴ​ትም እንደ ወሰ​ዱት አላ​ው​ቅም” አለ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ጴጥ​ሮ​ስና ያ ሌላዉ ደቀ መዝ​ሙ​ርም ወጥ​ተው ወደ መቃ​ብሩ ሄዱ።</verse>
				<verse number="4">ሁለ​ቱም በአ​ን​ድ​ነት ሲሮጡ ያ ሌላዉ ደቀ መዝ​ሙር ጴጥ​ሮ​ስን ቀድ​ሞት ወደ መቃ​ብሩ ደረሰ።</verse>
				<verse number="5">ጐን​በስ ብሎም ሲመ​ለ​ከት በፍ​ታ​ዉን ተቀ​ምጦ አየ፤ ነገር ግን ወደ ውስጥ አል​ገ​ባም።</verse>
				<verse number="6">ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ተከ​ት​ሎት ደረ​ሰና ወደ መቃ​ብሩ ገባ፤</verse>
				<verse number="7">በፍ​ታ​ዉ​ንም በአ​ንድ ወገን ተቀ​ምጦ አየ፤ በራሱ ላይ የነ​በ​ረው መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያም ሳይ​ቃ​ወስ ለብ​ቻው ተጠ​ቅ​ልሎ አየ፤ ከበ​ፍ​ታዉ ጋርም አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="8">ከዚ​ህም በኋላ አስ​ቀ​ድሞ ወደ መቃ​ብሩ የደ​ረ​ሰው ሌላዉ ደቀ መዝ​ሙር ገባ፤ አይ​ቶም አመነ፤</verse>
				<verse number="9">ከሙ​ታን ተለ​ይቶ ይነሣ ዘንድ እንደ አለው በመ​ጻ​ሕ​ፍት የተ​ጻ​ፈ​ውን ገና አላ​ወ​ቁም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="10">ከዚ​ህም በኋላ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ተመ​ል​ሰው ወደ ቤታ​ቸው ገቡ።</verse>
				<verse number="11">ማር​ያም ግን ከመ​ቃ​ብሩ በስ​ተ​ውጭ እያ​ለ​ቀ​ሰች ቆማ ነበረ፤ እያ​ለ​ቀ​ሰ​ችም ወደ መቃ​ብሩ ጐን​በስ ብላ ተመ​ለ​ከ​ተች።</verse>
				<verse number="12">ሁለት መላ​እ​ክ​ት​ንም ነጭ ልብስ ለብ​ሰው የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ሥጋ በነ​በ​ረ​በት ቦታ አንዱ በራ​ስጌ፥ አን​ዱም በግ​ርጌ ተቀ​ም​ጠው አየች።</verse>
				<verse number="13">እነ​ዚያ መላ​እ​ክ​ትም፥ “አንቺ ሴት፥ ምን ያስ​ለ​ቅ​ስ​ሻል?” አሉ​አት፤ እር​ስ​ዋም፥ “ጌታ​ዬን ከመ​ቃ​ብር ውስጥ ወስ​ደ​ው​ታል፤ ወዴ​ትም እንደ ወሰ​ዱት አላ​ው​ቅም” አለ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">ይህ​ንም ተና​ግራ ወደ ኋላዋ መለስ ስትል ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ቆሞ አየ​ችው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እንደ ሆነ አላ​ወ​ቀ​ችም።</verse>
				<verse number="15">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አንቺ ሴት፥ ምን ያስ​ለ​ቅ​ስ​ሻል? ማን​ንስ ትሺ​ያ​ለሽ?” አላት፤ እር​ስዋ ግን የአ​ት​ክ​ልት ቦታ ጠባቂ መስ​ሎ​አት፥ “ጌታዬ፥ አንተ ወስ​ደ​ኸው እንደ ሆነ ሄጄ ወደ እኔ እን​ዳ​መ​ጣ​ውና ሽቱ እን​ድ​ቀ​ባው ወዴት እንደ አኖ​ር​ኸው ንገ​ረኝ” አለ​ችው።</verse>
				<verse number="16">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ማር​ያም!” አላት፤ እር​ስ​ዋም መለስ ብላ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ፥ “ረቡኒ!” አለ​ችው፤ ትር​ጓ​ሜ​ዉም “መም​ህር” ማለት ነው።</verse>
				<verse number="17">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አት​ን​ኪኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላ​ረ​ግ​ሁ​ምና፤ ነገር ግን ወደ ወን​ድ​ሞች ሂጂና፦ ወደ አባቴ፥ ወደ አባ​ታ​ችሁ ወደ አም​ላኬ፥ ወደ አም​ላ​ካ​ች​ሁም አር​ጋ​ለሁ አለ ብለሽ ንገ​ሪ​አ​ቸው” አላት።</verse>
				<verse number="18">ማር​ያም መግ​ደ​ላ​ዊ​ትም ሄደች፤ ጌታን እንደ አየች፥ ይህ​ንም እን​ዳ​ላት ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ነገ​ረ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">ያም ከሳ​ም​ንቱ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን በመሸ ጊዜ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ አይ​ሁ​ድን ስለ ፈሩ ተሰ​ብ​ስ​በው የነ​በ​ሩ​በት ቤት ደጁ ተቈ​ልፎ ሳለ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መጥቶ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቆመና፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">ይህ​ንም ብሎ እጆ​ቹ​ንና ጎኑን አሳ​ያ​ቸው፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ጌታ​ች​ንን ባዩት ጊዜ ደስ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዳግ​መኛ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን፤ አብ እኔን እንደ ላከኝ እን​ዲሁ እኔ እና​ን​ተን እል​ካ​ች​ኋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="22">ይህ​ንም ብሎ እፍ አለ​ባ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተቀ​በሉ።</verse>
				<verse number="23">ኀጢ​ኣ​ታ​ቸ​ውን ይቅር ያላ​ች​ሁ​ላ​ቸው ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ዋል፤ ይቅር ያላ​ላ​ች​ኋ​ቸው ግን አይ​ሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ውም።”</verse>
				<verse number="24">ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በመጣ ጊዜ ዲዲ​ሞስ የሚ​ሉት ከዐ​ሥራ ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ርት አንዱ ቶማስ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="25">ሌሎች ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም፥ “ጌታ​ች​ንን አየ​ነው” አሉት፤ እርሱ ግን፥ “የች​ን​ካ​ሩን ምል​ክት በእጁ ካላ​የሁ፥ ጣቴ​ንም ወደ ተቸ​ነ​ከ​ረ​በት ካል​ጨ​መ​ርሁ፥ እጄ​ንም ወደ ጎኑ ካላ​ገ​ባሁ አላ​ም​ንም” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">ከስ​ም​ንት ቀን በኋ​ላም ዳግ​መኛ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ በው​ስጡ ሳሉ፥ ቶማ​ስም አብ​ሮ​አ​ቸው ሳለ በሩ እንደ ተዘጋ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መጣ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ቆመና፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="27">ከዚ​ህም በኋላ ቶማ​ስን፥ “ጣት​ህን ወዲህ አም​ጣና እጆ​ችን እይ፤ እጅ​ህ​ንም አም​ጣና ወደ ጎኔ አግባ፤ እመን እንጂ ተጠ​ራ​ጣሪ አት​ሁን” አለው።</verse>
				<verse number="28">ቶማ​ስም፥ “ጌታዬ አም​ላ​ኬም” ብሎ መለሰ።</verse>
				<verse number="29">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ስለ አየ​ኸኝ አመ​ን​ህን? ብፁ​ዓ​ንስ ሳያዩ የሚ​ያ​ምኑ ናቸው” አለው።</verse>
				<verse number="30">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በዚህ መጽ​ሐፍ ያል​ተ​ጻፈ ብዙ ሌላ ተአ​ም​ራት በደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ፊት አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="31">ነገር ግን ይህ የተ​ጻፈ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ እና​ንተ ታምኑ ዘንድ፥ አም​ና​ች​ሁም በስሙ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ታገኙ ዘንድ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በጥ​ብ​ር​ያ​ዶስ ባሕር አጠ​ገብ ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ እን​ደ​ገና ተገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም ተገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">ስም​ዖን ጴጥ​ሮስ፥ ዲዲ​ሞስ የሚ​ሉት ቶማስ፥ ከገ​ሊላ ቃና የሆ​ነው ናት​ና​ኤል፥ የዘ​ብ​ዴ​ዎስ ልጆ​ችና ሌሎ​ችም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሁለት አብ​ረው ነበሩ።</verse>
				<verse number="3">ስም​ዖን ጴጥ​ሮስ፥ “እኔ ዓሣ ላጠ​ምድ እሄ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “እኛም አብ​ረ​ንህ እን​መ​ጣ​ለን” አሉት፤ ሄደ​ውም ወደ ታንኳ ገቡ፤ ግን በዚ​ያች ሌሊት የያ​ዙት ምንም የለም።</verse>
				<verse number="4">በነጋ ጊዜም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በባ​ሕሩ ዳር ቆሞ ነበር፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አዩት፤ ግን ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ እንደ ሆነ አላ​ወ​ቁም።</verse>
				<verse number="5">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ልጆች ሆይ አን​ዳች የሚ​በላ ነገር አላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “የለም” አሉት።</verse>
				<verse number="6">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “መረ​ባ​ች​ሁን በታ​ን​ኳ​ዪቱ በስ​ተ​ቀኝ በኩል ጣሉ፤ ታገ​ኛ​ላ​ች​ሁም” አላ​ቸው፤ መረ​ባ​ቸ​ው​ንም በጣሉ ጊዜ ከተ​ያ​ዘው ዓሣ ብዛት የተ​ነሣ ስቦ ማው​ጣት ተሳ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="7">ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ይወ​ደው የነ​በረ ያ ደቀ መዝ​ሙ​ርም ለጴ​ጥ​ሮስ፥ “ጌታ​ችን ነው እኮ” አለው፤ ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ጌታ​ችን እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ የሚ​ለ​ብ​ሰ​ውን ልብስ አን​ሥቶ በወ​ገቡ ታጠቀ፤ ራቁ​ቱን ነበ​ርና ወደ ባሕር ተወ​ረ​ወረ።</verse>
				<verse number="8">ሌሎች ደቀ መዛ​ሙ​ርት ግን በታ​ንኳ መጡ፤ ከሁ​ለት መቶ ክንድ ያህል በቀር ከም​ድር አል​ራ​ቁም ነበ​ርና፤ ዓሣ የመ​ላ​ባ​ቸ​ውን መረ​ቦ​ቻ​ቸ​ው​ንም እየ​ሳቡ ሄዱ።</verse>
				<verse number="9">ወደ ምድ​ርም በወ​ረዱ ጊዜ ፍሙ መርቶ፥ ዓሣም በላዩ ሆኖ፥ እን​ጀ​ራም ተሠ​ርቶ አገኙ።</verse>
				<verse number="10">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አሁን ከያ​ዛ​ች​ኋ​ቸው ዓሣ​ዎች አምጡ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ወደ ታንኳ ገብቶ መቶ አምሳ ሦስት ታላ​ላቅ ዓሣ​ዎ​ችን መልቶ የነ​በ​ረ​ውን መረብ ወደ ምድር ሳበ፤ ብዛ​ቱም ይህን ያህል ሲሆን መረቡ አል​ተ​ቀ​ደ​ደም።</verse>
				<verse number="12">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ኑ፥ ምሳ ብሉ” አላ​ቸው፤ ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አንተ ማነህ? ብሎ ሊጠ​ይ​ቀው የደ​ፈረ የለም፤ ጌታ​ችን እንደ ሆነ ዐው​ቀ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="13">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መጣና ኅብ​ስ​ቱን አን​ሥቶ ሰጣ​ቸው፤ ከዓ​ሣ​ውም እን​ዲሁ።</verse>
				<verse number="14">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ከሙ​ታን ተለ​ይቶ ከተ​ነሣ በኋላ ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሲገ​ለ​ጥ​ላ​ቸው ይህ ሦስ​ተኛ ጊዜዉ ነበር።</verse>
				<verse number="15">ምሳም ከበሉ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፦ ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስን፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ከእ​ነ​ዚህ ይልቅ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ እር​ሱም፥ “አዎን፥ ጌታዬ ሆይ፥ እኔ እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “በጎ​ችን ጠብቅ” አለው።</verse>
				<verse number="16">ዳግ​መ​ኛም፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ እር​ሱም፥ “አዎን፥ ጌታዬ ሆይ፥ እኔ እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ “ጠቦ​ቶ​ችን አሰ​ማራ” አለው።</verse>
				<verse number="17">ሦስ​ተኛ ጊዜም፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ ጴጥ​ሮ​ስም ሦስት ጊዜ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን? ስላ​ለው ተከዘ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታው​ቃ​ለህ፤ እኔም እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ “እን​ኪ​ያስ ግል​ገ​ሎ​ችን ጠብቅ” አለው።</verse>
				<verse number="18">“እው​ነት እው​ነት እል​ሃ​ለሁ፤ አንተ ጐል​ማሳ ሳለህ በገዛ እጅህ ወገ​ብ​ህን ታጥ​ቀህ ወደ ወደ​ድ​ኸው ትሄድ ነበር፤ በሸ​መ​ገ​ልህ ጊዜ ግን እጆ​ች​ህን ትዘ​ረ​ጋ​ለህ፤ ወገ​ብ​ህ​ንም ሌላ ያስ​ታ​ጥ​ቅ​ሃል፤ ወደ​ማ​ት​ወ​ደ​ውም ይወ​ስ​ድ​ሃል።”</verse>
				<verse number="19">በምን ሞት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያከ​ብር ዘንድ እን​ዳ​ለው ሲያ​መ​ለ​ክት ይህን ተና​ገረ፤ ይህ​ንም ብሎ ተከ​ተ​ለኝ አለው።</verse>
				<verse number="20">ጴጥ​ሮ​ስም መለስ ብሎ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ይወ​ደው የነ​በ​ረ​ውን ያን ደቀ መዝ​ሙር ሲከ​ተ​ለው አየ፤ እር​ሱም ራት ሲበሉ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ አጠ​ገብ የነ​በ​ረ​ውና “ጌታ ሆይ፥ አሳ​ልፎ የሚ​ሰ​ጥህ ማነው?” ያለው ነው።</verse>
				<verse number="21">ጴጥ​ሮ​ስም እር​ሱን አይቶ፥ “ጌታ ሆይ፥ ይህስ እን​ዴት ይሆ​ናል?” አለው።</verse>
				<verse number="22">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እስ​ክ​መጣ ይኖር ዘንድ ብወ​ድ​ድስ አን​ተን ምን አግ​ዶህ፤ አንተ ግን ተከ​ተ​ለኝ” አለው።</verse>
				<verse number="23">ያም ደቀ መዝ​ሙር እን​ደ​ማ​ይ​ሞት ይህ ነገር በወ​ን​ድ​ሞች ዘንድ ተነ​ገረ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ግን፥ “እስ​ክ​መጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ብወ​ድ​ድስ አን​ተን ምን አግ​ዶህ” አለ እንጂ አይ​ሞ​ትም አላ​ለ​ውም።</verse>
				<verse number="24">ስለ​ዚህ ነገር ምስ​ክር የሆነ፥ ስለ እር​ሱም ይህን የጻፈ ይህ ደቀ መዝ​ሙር ነው፤ ምስ​ክ​ር​ነ​ቱም እው​ነት እንደ ሆነ እኛ እና​ው​ቃ​ለን።</verse>
				<verse number="25">ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ የሠ​ራ​ቸው ሌሎች ብዙ ሥራ​ዎች አሉ፤ ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ቢጻፍ ግን የተ​ጻ​ፉ​ትን መጻ​ሕ​ፍት ዓለም ስን​ኳን ባል​ቻ​ላ​ቸ​ውም ነበር። ከዐ​ሥራ ሁለቱ ሐዋ​ር​ያት አንዱ የዘ​ብ​ዴ​ዎስ ልጅ ሐዋ​ር​ያው ዮሐ​ንስ ጌታ​ችን በሥጋ ወደ ሰማይ ባረገ በሠ​ላሳ ዓመት፥ ቄሳር ኔሮን በነ​ገሠ በሰ​ባት ዓመት በዮ​ና​ና​ው​ያን ቋንቋ ለኤ​ፌ​ሶን ሰዎች የጻ​ፈ​ፍው ወን​ጌል ተፈ​ጸመ። ምስ​ጋና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁን። አሜን።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="44">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">ቴዎ​ፍ​ሎስ ሆይ፥ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሊያ​ደ​ር​ገ​ውና ሊያ​ስ​ተ​ም​ረው የጀ​መ​ረ​ውን ሥራ ሁሉ አስ​ቀ​ድሜ በመ​ጽ​ሐፍ ጽፌ​ል​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የመ​ረ​ጣ​ቸው ሐዋ​ር​ያ​ትን አዝዞ እስከ ዐረ​ገ​ባት ቀን ድረስ ያለ​ውን ጽፌ​ል​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">ሕማ​ማ​ትን ከተ​ቀ​በለ በኋላ ብዙ ተአ​ም​ራት በማ​ሳ​የት አርባ ቀን ሙሉ እየ​ተ​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው፥ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥ​ትም እየ​ነ​ገ​ራ​ቸ​ውና እያ​ስ​ተ​ማ​ራ​ቸው ሕያው ሆኖ ራሱ​ን​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር አብሮ ሳለ፥ “ከእኔ የሰ​ማ​ች​ሁ​ትን የአ​ብን ተስፋ ጠብቁ” ብሎ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዳ​ይ​ወጡ አዘ​ዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">“ዮሐ​ንስ በውኃ አጠ​መቀ፤ እና​ንተ ግን እስከ ቅርብ ቀን ድረስ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ትጠ​መ​ቃ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">እነ​ር​ሱም ተሰ​ብ​ስ​በው ሳሉ፥ “ጌታ ሆይ፥ በዚህ ወራት ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መን​ግ​ሥ​ትን ትመ​ል​ሳ​ለ​ህን?” ብለው ጠየ​ቁት።</verse>
				<verse number="7">እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አብ በገዛ ሥል​ጣኑ የወ​ሰ​ነ​ውን ቀኑ​ንና ዘመ​ኑን ልታ​ውቁ አል​ተ​ፈ​ቀ​ደ​ላ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="8">ነገር ግን መን​ፈስ ቅዱስ በእ​ና​ንተ ላይ በወ​ረደ ጊዜ ኀይ​ልን ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ሁሉ፥ በሰ​ማ​ር​ያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረ​ስም ምስ​ክ​ሮች ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="9">ይህ​ንም እየ​ነ​ገ​ራ​ቸው ከፍ ከፍ አለ፤ ደመ​ናም ተቀ​በ​ለ​ችው፤ እነ​ር​ሱም ወደ እርሱ እያዩ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ከዐ​ይ​ና​ቸ​ውም ተሰ​ወረ።</verse>
				<verse number="10">እነ​ር​ሱም ወደ ሰማይ አተ​ኵ​ረው ሲመ​ለ​ከቱ እነሆ፥ ሁለት ሰዎች ነጫጭ ልብስ ለብ​ሰው በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸው ቆመው ታዩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">እነ​ር​ሱም፥ “እና​ንተ የገ​ሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እየ​አ​ያ​ችሁ ለምን ቆማ​ች​ኋል? ይህ ከእ​ና​ንተ ወደ ሰማይ ያረ​ገው ኢየ​ሱስ፥ ከእ​ና​ንተ ወደ ሰማይ ሲያ​ርግ እን​ዳ​ያ​ች​ሁት እን​ዲሁ ዳግ​መኛ ይመ​ጣል” አሏ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">ከዚ​ህም በኋላ ደብረ ዘይት ከሚ​ባ​ለው ተራራ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ፤ እር​ሱም ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሰ​ን​በት መን​ገድ ያህል የራቀ ነው።</verse>
				<verse number="13">ወደ ማደ​ሪ​ያ​ቸ​ውም በደ​ረሱ ጊዜ ጴጥ​ሮስ፥ ዮሐ​ንስ፥ ያዕ​ቆብ፥ እን​ድ​ር​ያስ፥ ፊል​ጶስ፥ ቶማስ፥ ማቴ​ዎስ፥ በር​ተ​ሎ​ሜ​ዎስ፥ የእ​ል​ፍ​ዮስ ልጅ ያዕ​ቆብ፥ ቀና​ተ​ኛው ስም​ዖን፥ የያ​ዕ​ቆብ ልጅ ይሁ​ዳም ወደ​ሚ​ኖ​ሩ​በት ሰገ​ነት ወጡ።</verse>
				<verse number="14">እነ​ዚህ ሁሉ ከሴ​ቶ​ችና ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እናት ከማ​ር​ያም፥ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹም ጋር በአ​ን​ድ​ነት ለጸ​ሎት ይተጉ ነበር።</verse>
				<verse number="15">ያን​ጊ​ዜም ጴጥ​ሮስ ተነ​ሣና በወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል ቆመ፤ መቶ ሃያ ያህል ሰዎ​ችም በዚያ ሳሉ እን​ዲህ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">“እና​ንተ ሰዎች ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ስሙ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ለያ​ዙት መሪ ስለ ሆና​ቸው ስለ ይሁዳ መን​ፈስ ቅዱስ አስ​ቀ​ድሞ በዳ​ዊት አፍ የተ​ና​ገ​ረው የመ​ጽ​ሐፍ ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ይገ​ባል።</verse>
				<verse number="17">እር​ሱም ከእኛ ጋር ተቈ​ጥሮ ነበር፤ ለዚ​ህም አገ​ል​ግ​ሎት ታድሎ ነበር።</verse>
				<verse number="18">ከዚ​ህም በኋላ ይህ ሰው በዐ​መፅ ዋጋዉ መሬት ገዛ፤ በም​ድር ላይም በግ​ን​ባሩ ወደ​ቀና ከመ​ካ​ከሉ ተሰ​ነ​ጠቀ፤ አን​ጀ​ቱም ሁሉ ተዘ​ረ​ገፈ።</verse>
				<verse number="19">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ዜናዉ ተሰማ፤ ያም መሬት በቋ​ን​ቋ​ቸው አኬ​ል​ዳማ ተብሎ ተጠራ፤ ይኸ​ውም የደም መሬት ማለት ነው።</verse>
				<verse number="20">በመ​ዝ​ሙር መጽ​ሐፍ ‘መኖ​ሪ​ያዉ ምድረ በዳ ትሁን፤ በው​ስ​ጧም የሚ​ኖር አይ​ኑር፤ ሹመ​ቱ​ንም ሌላ ይው​ሰድ’ ተብሎ ተጽ​ፎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="21">እን​ግ​ዲህ ከዮ​ሐ​ንስ ጥም​ቀት ጀምሮ ከእኛ ዘንድ እስ​ካ​ረ​ገ​በት ቀን ድረስ፥</verse>
				<verse number="22">ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በእኛ መካ​ከል በገ​ባ​በ​ትና በወ​ጣ​በት ዘመን ሁሉ ከእኛ ጋር አብ​ረው ከነ​በ​ሩት ከእ​ነ​ዚህ ሰዎች አንዱ ከእኛ ጋር የት​ን​ሣ​ኤዉ ምስ​ክር ይሆን ዘንድ ይገ​ባል።”</verse>
				<verse number="23">ኢዮ​ስ​ጦስ የሚ​ሉ​ትን በር​ና​ባስ የተ​ባ​ለ​ውን ዮሴ​ፍ​ንና ማት​ያ​ስን ሁለ​ቱን ሰዎች አቆሙ።</verse>
				<verse number="24">እን​ዲ​ህም ብለው ጸለዩ፥ “አቤቱ፥ ልብን ሁሉ የም​ታ​ውቅ አንተ፥ ከእ​ነ​ዚህ ከሁ​ለቱ የመ​ረ​ጥ​ኸ​ውን አን​ዱን ግለጥ።</verse>
				<verse number="25">ይሁዳ ወደ ሀገሩ ይሄድ ዘንድ የተ​ዋ​ትን ይህ​ቺን የአ​ገ​ል​ግ​ሎ​ትና የሐ​ዋ​ር​ያ​ነ​ትን ቦታ የሚ​ቀ​በ​ላ​ትን ግለጥ።”</verse>
				<verse number="26">ዕጣም አጣ​ጣ​ሏ​ቸው፤ ዕጣ​ዉም በማ​ት​ያስ ላይ ወጣ፤ ከዐ​ሥራ አንዱ ሐዋ​ር​ያት ጋራም ተቈ​ጠረ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ኀም​ሳው ቀንም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥ ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት በአ​ንድ ቦታ ተሰ​ብ​ስ​በው ነበር።</verse>
				<verse number="2">ድን​ገ​ትም እንደ ዐውሎ ነፋስ ድምፅ ያለ ከሰ​ማይ ድምፅ መጣ፤ የነ​በ​ሩ​በ​ት​ንም ቤት ሞላው።</verse>
				<verse number="3">እንደ እሳት የተ​ከ​ፋ​ፈሉ የእ​ሳት ላን​ቃ​ዎ​ችም ታዩ​አ​ቸው፤ በሁ​ሉም ላይ ተቀ​መ​ጡ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ሁሉም መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተሞሉ፤ ይና​ገሩ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ እንደ አደ​ላ​ቸው መጠ​ንም እየ​ራ​ሳ​ቸው በሀ​ገሩ ሁሉ ቋንቋ ይና​ገሩ ጀመሩ።</verse>
				<verse number="5">ከሰ​ማይ በታች ካሉ አሕ​ዛብ ሁሉ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖሩ ደጋግ የአ​ይ​ሁድ ሰዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="6">ይህ​ንም ቃል ሲና​ገሩ ሰም​ተው ሁሉም ደን​ግ​ጠው ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሁሉም በየ​ሀ​ገ​ራ​ቸው ቋንቋ ሲና​ገሩ ሰም​ተ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና የሚ​ሉ​ትን አጡ።</verse>
				<verse number="7">ተገ​ረሙ፤ አደ​ነ​ቁም፥ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “እነ​ዚህ የሚ​ና​ገ​ሩት ሁሉ የገ​ሊላ ሰዎች አይ​ደ​ሉ​ምን?</verse>
				<verse number="8">እን​ግ​ዲህ በየ​ሀ​ገ​ራ​ችን ቋንቋ ሲና​ገሩ እን​ዴት እን​ሰ​ማ​ቸ​ዋ​ለን?</verse>
				<verse number="9">እኛ በተ​ወ​ለ​ድ​ን​በት በጳ​ርቴ፥ በሜድ፥ በኢ​ላ​ሜጤ፥ በሁ​ለቱ ወን​ዞች መካ​ከል፥ በይ​ሁዳ፥ በቀ​ጰ​ዶ​ቅያ፥ በጳ​ን​ጦ​ስና በእ​ስያ፥</verse>
				<verse number="10">በፍ​ር​ግያ፥ በጵ​ን​ፍ​ልያ፥ በግ​ብፅ፥ በሊ​ብያ አው​ራጃ፥ በቀ​ር​ኔን የም​ን​ኖር፥ ከሮ​ሜም የመ​ጣን አይ​ሁድ፥ መጻ​ተ​ኞ​ችም፥</verse>
				<verse number="11">ከቀ​ር​ጤ​ስና ከዐ​ረ​ብም የመ​ጣን፥ እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጌት​ነት በየ​ሀ​ገ​ራ​ችን ቋንቋ ሲና​ገሩ እን​ሰ​ማ​ቸ​ዋ​ለን።”</verse>
				<verse number="12">ሁሉም ተገ​ረሙ፤ የሚ​ሉ​ት​ንም አጡ፥ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “እንጃ! ይህ ነገር ምን ይሆን?” ተባ​ባሉ።</verse>
				<verse number="13">እኩ​ሌ​ቶቹ ግን “እነ​ዚ​ህስ ጉሽ ጠጅ ጠግ​በው ሰክ​ረ​ዋል” ብለው ሳቁ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">ጴጥ​ሮ​ስም ከዐ​ሥራ አንዱ ጋር ቆሞ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ እን​ዲህ አለ፥ “እና​ንተ የአ​ይ​ሁድ ሰዎች፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የም​ት​ኖሩ ሁሉ፥ ይህን ዕወቁ፤ ቃሌ​ንም ስሙ።</verse>
				<verse number="15">ለእ​ና​ንተ እንደ መሰ​ላ​ችሁ እነ​ዚህ የሰ​ከሩ አይ​ደ​ሉም፤ ከቀኑ ገና ሦስ​ተኛ ሰዓት ነውና።</verse>
				<verse number="16">ነገር ግን ይህ በነ​ቢዩ በኢ​ዩ​ኤል የተ​ባ​ለው ነው።</verse>
				<verse number="17">በኋ​ለ​ኛ​ዪቱ ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ሥጋን በለ​በሰ ሁሉ ላይ ከመ​ን​ፈሴ አፈ​ስ​ሳ​ለሁ፤ ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ች​ሁና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችሁ ትን​ቢት ይና​ገ​ራሉ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ችሁ ራእ​ይን ያያሉ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ሕል​ምን ያል​ማሉ።</verse>
				<verse number="18">በወ​ን​ዶ​ችና በሴ​ቶች ባሮች ላይም ያን​ጊዜ መን​ፈ​ሴን አፈ​ስ​ሳ​ለሁ፤ ትን​ቢ​ትም ይና​ገ​ራሉ።</verse>
				<verse number="19">በላይ በሰ​ማይ ተአ​ም​ራ​ትን፥ በታች በም​ድ​ርም ምል​ክ​ቶ​ችን፥ ደምን እሳ​ት​ንና ጢስ​ንም እሰ​ጣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">የም​ት​ገ​ለ​ጠው ታላ​ቅዋ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ሳት​መጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረ​ቃም ወደ ደም ይለ​ወ​ጣል።</verse>
				<verse number="21">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም የሚ​ጠራ ሁሉ ይድ​ናል።</verse>
				<verse number="22">“እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ነገር ስሙ፤ እን​ደ​ም​ታ​ው​ቁት በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ ባደ​ረ​ገው በከ​ሃ​ሊ​ነቱ በተ​አ​ም​ራ​ቱና በድ​ንቅ ሥራ​ዎቹ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የገ​ለ​ጠ​ላ​ች​ሁን ሰው የና​ዝ​ሬ​ቱን ኢየ​ሱ​ስን ስሙ።</verse>
				<verse number="23">እር​ሱ​ንም በተ​ወ​ሰ​ነው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክ​ርና በቀ​ደ​መው ዕው​ቀቱ እና​ንተ አሳ​ል​ፋ​ችሁ በኃ​ጥ​ኣን እጅ ሰጣ​ች​ሁት፤ ሰቅ​ላ​ች​ሁም ገደ​ላ​ች​ሁት።</verse>
				<verse number="24">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን የሞ​ትን ማሰ​ሪያ ፈቶ ከሙ​ታን ለይቶ አስ​ነ​ሣው፤ ሞት እር​ሱን ሊይ​ዘው አይ​ች​ል​ምና።</verse>
				<verse number="25">ዳዊ​ትም ስለ እርሱ እን​ዲህ አለ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሁል​ጊዜ በፊቴ አየ​ዋ​ለሁ፤ እን​ዳ​ል​ታ​ወክ በቀኜ ነውና።</verse>
				<verse number="26">ስለ​ዚህ ልቤን ደስ አለው፤ አን​ደ​በ​ቴም ሐሤት አደ​ረገ፤ ሥጋ​ዬም ደግሞ በተ​ስ​ፋው አደረ።</verse>
				<verse number="27">ነፍ​ሴን በሲ​ኦል አት​ተ​ዋ​ት​ምና፥ ጻድ​ቅ​ህ​ንም ጥፋ​ትን ያይ ዘንድ አት​ሰ​ጠ​ው​ምና።</verse>
				<verse number="28">የሕ​ይ​ወ​ትን መን​ገድ አሳ​የ​ኸኝ፤ ከፊ​ትህ ጋራ ደስ​ታን አጠ​ገ​ብ​ኸኝ።</verse>
				<verse number="29">“እና​ንተ ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ስለ አባ​ቶች አለቃ ስለ ዳዊት ነገር እንደ ሞተ እንደ ተቀ​በ​ረም፥ መቃ​ብ​ሩም እስከ ዛሬ ድረስ በእኛ ዘንድ እንደ አለ ገልጬ እን​ድ​ነ​ግ​ራ​ችሁ ትፈ​ቅ​ዱ​ል​ኛ​ላ​ች​ሁን?</verse>
				<verse number="30">ነቢይ ስለ ነበረ፥ ከአ​ብ​ራ​ኩም የተ​ገ​ኘ​ውን በዙ​ፋኑ እን​ዲ​ያ​ነ​ግ​ሥ​ለት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሐ​ላን እንደ ማለ​ለት ስለ ዐወቀ፥</verse>
				<verse number="31">ክር​ስ​ቶስ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ እን​ደ​ሚ​ነሣ፥ ሥጋ​ዉም በመ​ቃ​ብር እን​ደ​ማ​ይ​ቀር፥ ጥፋ​ት​ንም እን​ደ​ማ​ያይ አስ​ቀ​ድሞ ዐውቆ ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="32">እር​ሱን ኢየ​ሱ​ስን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ነ​ሣው፤ ለዚ​ህም እኛ ሁላ​ችን ምስ​ክ​ሮቹ ነን።</verse>
				<verse number="33">አሁን ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ብሎና የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ተስፋ ከአብ ገን​ዘብ አድ​ርጎ ይህን ዛሬ የም​ታ​ዩ​ት​ንና የም​ት​ሰ​ሙ​ትን አፈ​ሰ​ሰው።</verse>
				<verse number="34">ዳዊት ወደ ሰማይ አል​ወ​ጣም፥ ነገር ግን እርሱ አለ፦ ጌታ ጌታ​ዬን አለው፦ በቀኜ ተቀ​መጥ።</verse>
				<verse number="35">ጠላ​ቶ​ች​ህን ከእ​ግ​ርህ ጫማ በታች እስ​ክ​ጥ​ላ​ቸው ድረስ።</verse>
				<verse number="36">እን​ግ​ዲህ የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሁሉ እና​ንተ የሰ​ቀ​ላ​ች​ሁ​ትን ኢየ​ሱ​ስን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጌታም መሢ​ሕም እን​ዳ​ደ​ረ​ገው በር​ግጥ ይወቁ።”</verse>
				<verse number="37">ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ ልባ​ቸው ተከ​ፈተ፤ ጴጥ​ሮ​ስ​ንና ወን​ድ​ሞቹ ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ምን እና​ድ​ርግ?” አሏ​ቸው።</verse>
				<verse number="38">ጴጥ​ሮ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ንስሓ ግቡ፤ ሁላ​ች​ሁም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ተጠ​መቁ፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም ይሰ​ረ​ይ​ላ​ች​ኋል፤ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስ​ንም ጸጋ ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="39">ተስ​ፋዉ ለእ​ና​ን​ተና ለል​ጆ​ቻ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ች​ንም ለሚ​ጠ​ራ​ቸው ርቀው ለነ​በሩ ሁሉ ነውና።”</verse>
				<verse number="40">ሌላም ብዙ ነገር ነገ​ራ​ቸው፤ “ከዚህ ከክፉ ዓለ​ምም ነፍ​ሳ​ች​ሁን አድኑ” ብሎ መከ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="41">ቃሉ​ንም ተቀ​ብ​ለው ተጠ​መቁ፤ በዚ​ችም ዕለት ሦስት ሺህ ያህል ሰዎች ተጨ​መሩ።</verse>
				<verse number="42">በሐ​ዋ​ር​ያት ትም​ህ​ር​ትና በአ​ን​ድ​ነት ማዕ​ድን በመ​ባ​ረክ፥ በጸ​ሎ​ትም ጸን​ተው ይኖሩ ነበር።</verse>
				<verse number="43">ሰው ሁሉ ፈራ​ቸው፤ በሐ​ዋ​ር​ያ​ትም እጅ ብዙ ተአ​ም​ራ​ትና ድንቅ ሥራ ይደ​ረግ ነበር።</verse>
				<verse number="44">ያመ​ኑ​ትም ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ይኖሩ ነበር፤ ገን​ዘ​ባ​ቸ​ውም ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ነበር።</verse>
				<verse number="45">መሬ​ታ​ቸ​ው​ንና ጥሪ​ታ​ቸ​ው​ንም እየ​ሸጡ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ እን​ደ​ሚ​ያ​ሻው ይሰጡ ነበር።</verse>
				<verse number="46">ሁል​ጊ​ዜም አንድ ልብ ሆነው በቤተ መቅ​ደስ ያገ​ለ​ግሉ ነበር፤ በቤ​ትም ኅብ​ስ​ትን ይቈ​ርሱ ነበር፤ በደ​ስ​ታና በልብ ቅን​ን​ነ​ትም ምግ​ባ​ቸ​ውን ይመ​ገቡ ነበር።</verse>
				<verse number="47">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያመ​ሰ​ግኑ ነበር፤ በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ዘንድ መወ​ደድ ነበ​ራ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ድ​ኑ​ትን ዕለት ዕለት በእ​ነ​ርሱ ላይ ይጨ​ምር ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም በዘ​ጠኝ ሰዓት ለጸ​ሎት በአ​ን​ድ​ነት ወደ ቤተ መቅ​ደስ ወጡ።</verse>
				<verse number="2">ከእ​ናቱ ማኅ​ፀ​ንም ጀምሮ እግሩ ሽባ ሆኖ የተ​ወ​ለደ አንድ ሰው ነበር፤ ወደ መቅ​ደ​ስም ከሚ​ገ​ቡት ምጽ​ዋት ይለ​ምን ዘንድ ሁል​ጊዜ እየ​ተ​ሸ​ከሙ መል​ካም በሚ​ል​ዋት በመ​ቅ​ደስ ደጃፍ ያስ​ቀ​ም​ጡት ነበር።</verse>
				<verse number="3">ጴጥ​ሮ​ስ​ንና ዮሐ​ን​ስ​ንም ወደ መቅ​ደስ ሲገቡ አይቶ ምጽ​ዋት ይሰ​ጡት ዘንድ ለመ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ጴጥ​ሮ​ስም ከዮ​ሐ​ንስ ጋር ትኩር ብሎ ተመ​ለ​ከ​ተው፥ “ወደ እኛ ተመ​ል​ከት” አለው፤</verse>
				<verse number="5">ወደ እነ​ር​ሱም ተመ​ለ​ከተ፤ ምጽ​ዋት እን​ደ​ሚ​ሰ​ጡ​ትም ተስፋ አድ​ርጎ ነበር።</verse>
				<verse number="6">ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ወር​ቅና ብር የለ​ኝም፤ ያለ​ኝን ግን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ እነሆ፥ በና​ዝ​ሬቱ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ተነ​ሥ​ተህ ሂድ” አለው።</verse>
				<verse number="7">በቀኝ እጁም ይዞ አስ​ነ​ሣው፤ ያን​ጊ​ዜም እግ​ሩና ቍር​ጭ​ም​ጭ​ምቱ ጸና።</verse>
				<verse number="8">ዘሎም ቆመ፤ እየ​ሮ​ጠና እየ​ተ​ራ​መ​ደም ሄደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም እያ​መ​ሰ​ገነ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ወደ ቤተ መቅ​ደስ ገባ።</verse>
				<verse number="9">ሕዝ​ቡም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገነ ሲመ​ላ​ለስ አዩት።</verse>
				<verse number="10">እር​ሱም መል​ካም በም​ት​ባ​ለው በመ​ቅ​ደስ ደጃፍ ተቀ​ምጦ ምጽ​ዋት ይለ​ምን የነ​በ​ረው እንደ ሆነ ዐወ​ቁት፤ በእ​ር​ሱም ከሆ​ነው የተ​ነሣ መገ​ረ​ምና መደ​ነቅ ሞላ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም ይዘ​ውት ወደ መቅ​ደስ ሲገቡ ሕዝቡ ሁሉ ደን​ግ​ጠው ወደ ሰሎ​ሞን መመ​ላ​ለሻ ወደ እነ​ርሱ ሮጡ።</verse>
				<verse number="12">ጴጥ​ሮ​ስም ሕዝ​ቡን ባያ​ቸው ጊዜ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንት የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ለምን ታደ​ን​ቃ​ላ​ችሁ? እኛ​ንስ በኀ​ይ​ላ​ች​ንና በጽ​ድ​ቃ​ችን ይህን ሰው በእ​ግሩ እን​ዲ​ሄድ እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ነው አስ​መ​ስ​ላ​ችሁ ለምን ታዩ​ና​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="13">የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ የይ​ስ​ሐቅ አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም አም​ላክ፥ እና​ንተ አሳ​ል​ፋ​ችሁ የሰ​ጣ​ች​ሁ​ትን፥ እር​ሱም ሊተ​ወው ወዶ ሳለ በጲ​ላ​ጦስ ፊት የካ​ዳ​ች​ሁ​ትን ልጁን ኢየ​ሱ​ስን ገለ​ጠው።</verse>
				<verse number="14">እና​ንተ ግን ቅዱ​ሱ​ንና ጻድ​ቁን ካዳ​ች​ሁት፤ ነፍሰ ገዳ​ዩን ሰውም እን​ዲ​ያ​ድ​ን​ላ​ችሁ ለመ​ና​ችሁ።</verse>
				<verse number="15">የሕ​ይ​ወ​ትን ባለ​ቤት ግን ገደ​ላ​ች​ሁት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሙ​ታን ለይቶ አስ​ነ​ሣው፤ ለዚ​ህም እኛ ምስ​ክ​ሮቹ ነን።</verse>
				<verse number="16">ስሙን በማ​መን ይህን የም​ታ​ዩ​ት​ንና የም​ታ​ው​ቁ​ትን የእ​ርሱ ስም አጸ​ናው፤ እር​ሱ​ንም በማ​መን በፊ​ታ​ችሁ ይህን ሕይ​ወት ሰጠው።</verse>
				<verse number="17">“አሁ​ንም ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ አለ​ቆ​ቻ​ችሁ እን​ዳ​ደ​ረጉ ይህን ባለ​ማ​ወቅ እን​ዳ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁት አው​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ክር​ስ​ቶስ መከ​ራን እን​ዲ​ቀ​በል በነ​ቢ​ያት ሁሉ አፍ አስ​ቀ​ድሞ እንደ ተና​ገረ እን​ዲሁ ፈጸመ።</verse>
				<verse number="19">እን​ግ​ዲህ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ ይሰ​ረ​ይ​ላ​ችሁ ዘንድ ንስሓ ግቡ፥ ተመ​ለ​ሱም።</verse>
				<verse number="20">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘን​ድም የይ​ቅ​ርታ ዘመን ይመ​ጣል። አስ​ቀ​ድሞ የመ​ረ​ጠ​ው​ንም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ይል​ክ​ላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከጥ​ንት ጀምሮ በቅ​ዱ​ሳን ነቢ​ያቱ አፍ እስከ ተና​ገ​ረው የመ​ደ​ራ​ጀት ዘመን ድረስ ሰማይ ይቀ​በ​ለው ዘንድ ይገ​ባል።</verse>
				<verse number="22">ሙሴም አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን እን​ዲህ ብሎ​አ​ቸ​ዋል፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችን ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስ​ነ​ሣ​ላ​ች​ኋል፤ የሚ​ነ​ግ​ራ​ች​ሁን ሁሉ ስሙት።</verse>
				<verse number="23">ያን ነቢይ የማ​ት​ሰ​ማው ነፍ​ስም ሁሉ ከወ​ገ​ኖ​ችዋ ተለ​ይታ ትጥፋ።</verse>
				<verse number="24">ከሳ​ሙ​ኤል ጀምሮ ከእ​ር​ሱም በኋላ የተ​ነሡ ነቢ​ያት ሁሉ ስለ እነ​ዚህ ቀኖች ተና​ግ​ረ​ዋል፤ አስ​ተ​ም​ረ​ዋ​ልም።</verse>
				<verse number="25">እና​ን​ተም የነ​ቢ​ያት ልጆች ናችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን በሠ​ራው ሥር​ዐ​ትም የተ​ወ​ለ​ዳ​ችሁ ናችሁ፤ ለአ​ብ​ር​ሃም፦ ‘በዘ​ርህ የም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ ይባ​ረ​ካሉ’ ብሎ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="26">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አስ​ቀ​ድሞ ልጁን አስ​ነ​ሣ​ላ​ችሁ፤ ሁላ​ች​ሁም ከክ​ፋ​ታ​ችሁ እን​ድ​ት​መ​ለሱ ይባ​ር​ካ​ችሁ ዘንድ ላከው።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ሕዝ​ቡ​ንም ሲያ​ስ​ተ​ምሩ ሊቃነ ካህ​ና​ትና የቤተ መቅ​ደስ ሹም፥ ሰዱ​ቃ​ው​ያ​ንም መጡ።</verse>
				<verse number="2">ሕዝ​ቡን ስለ አስ​ተ​ማ​ሩና በኢ​የ​ሱ​ስም የሙ​ታ​ንን ትን​ሣኤ ስለ ሰበኩ በእ​ነ​ርሱ ተና​ደዱ።</verse>
				<verse number="3">እጃ​ቸ​ው​ንም ዘር​ግ​ተው ያዙ​አ​ቸው፤ ጊዜ​ዉም ፈጽሞ መሽቶ ነበ​ርና እስከ ማግ​ሥቱ ድረስ በወ​ኅኒ ቤት አገ​ቡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ቃሉ​ንም ሰም​ተው ያመኑ ብዙ ሰዎች ናቸው፤ ያመ​ኑት ወን​ዶች ቍጥ​ርም አም​ስት ሺህ ያህል ሆነ።</verse>
				<verse number="5">በማ​ግ​ሥ​ቱም አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውና ሽማ​ግ​ሎች፥ ጻፎ​ችም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="6">ሊቀ ካህ​ናቱ ሐና፥ ቀያ​ፋም፥ ዮሐ​ን​ስና እለ​እ​ስ​ክ​ን​ድ​ሮ​ስም፥ የሊቀ ካህ​ና​ቱም ወገን ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበሩ።</verse>
				<verse number="7">በአ​ደ​ባ​ባ​ይም አቆ​ሙና፥ “እና​ንተ ይህን በማን ስምና በማን ኀይል አደ​ረ​ጋ​ች​ሁት?” ብለው መረ​መ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">ያን​ጊ​ዜም በጴ​ጥ​ሮስ መን​ፈስ ቅዱስ ሞላ​በ​ትና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የሕ​ዝብ አለ​ቆ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሆይ፥ ስሙ፤</verse>
				<verse number="9">ዛሬ ለበ​ሽ​ተ​ኛው በተ​ደ​ረ​ገው ረድ​ኤት ምክ​ን​ያት በእ​ና​ንተ ዘንድ እኛ የሚ​ፈ​ረ​ድ​ብን ከሆነ እን​ግ​ዲያ ይህ ሰው በምን ዳነ?</verse>
				<verse number="10">እን​ግ​ዲህ እና​ንተ ሁላ​ችሁ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወገን ሁሉ፥ እና​ንተ በሰ​ቀ​ላ​ች​ሁት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሙ​ታን ለይቶ በአ​ስ​ነ​ሣው በና​ዝ​ሬቱ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ይህ ሰው እንደ ዳነና በፊ​ታ​ች​ሁም እንደ ቆመ በር​ግጥ ዕወቁ።</verse>
				<verse number="11">ይህ እና​ንተ ግን​በ​ኞች የና​ቃ​ች​ሁት ድን​ጋይ ነውና፤ እር​ሱም የማ​ዕ​ዘን ራስ ሆነ።</verse>
				<verse number="12">መዳ​ንም በሌላ በማ​ንም የለም፤ ከሰ​ማይ በታች እን​ድ​ን​በት ዘንድ የሚ​ገ​ባን ለሰው የተ​ሰጠ ሌላ ስም ከቶ የለ​ምና።”</verse>
				<verse number="13">ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም ግልጥ አድ​ር​ገው ሲና​ገሩ ባዩ​አ​ቸው ጊዜ፥ ያል​ተ​ማ​ሩና መጽ​ሐ​ፍን የማ​ያ​ውቁ ሰዎች እንደ ሆኑ ዐው​ቀው አደ​ነቁ፤ ሁል​ጊ​ዜም ከኢ​የ​ሱስ ጋር እንደ ነበሩ ዐወቁ።</verse>
				<verse number="14">ያን የዳ​ነ​ውን ሰውም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቆሞ በአ​ዩት ጊዜ የሚ​ሉ​ትን አጡ።</verse>
				<verse number="15">ከሸ​ን​ጎ​ውም ጥቂት ፈቀቅ አደ​ረ​ጉ​አ​ቸ​ውና እርስ በር​ሳ​ቸው ተነ​ጋ​ገሩ።</verse>
				<verse number="16">እን​ዲ​ህም አሉ፥ “እነ​ዚ​ህን ሰዎች ምን እና​ድ​ር​ጋ​ቸው? እነሆ፥ በእ​ነ​ርሱ የሚ​ደ​ረ​ገው ተአ​ምር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ዘንድ ታወቀ፤ ግል​ጥም ሆነ፤ ልን​ሰ​ው​ረ​ውም አን​ች​ልም።</verse>
				<verse number="17">ነገር ግን በሕ​ዝቡ ዘንድ እጅግ እን​ዳ​ይ​ስ​ፋፋ ዳግ​መኛ በኢ​የ​ሱስ ስም ሰውን እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ምሩ አጠ​ን​ክ​ረን እን​ገ​ሥ​ጻ​ቸው።”</verse>
				<verse number="18">ጠር​ተ​ውም፦“ በኢ​የ​ሱስ ስም ፈጽሞ አት​ና​ገሩ አታ​ስ​ተ​ም​ሩም” ብለው አዘ​ዙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም እን​ዲህ ብለው መለ​ሱ​ላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያይ​ደለ እና​ን​ተን ልን​ሰማ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይገ​ባ​ልን? እስኪ እና​ንተ ራሳ​ችሁ ፍረዱ።</verse>
				<verse number="20">እኛስ ያየ​ነ​ው​ንና የሰ​ማ​ነ​ውን ከመ​ና​ገር ዝም እንል ዘንድ አን​ች​ልም።”</verse>
				<verse number="21">እነ​ር​ሱ​ንም የሚ​ቀ​ጡ​በት ምክ​ን​ያት ስለ አጡ​ባ​ቸው ገሥ​ጸው ለቀ​ቁ​አ​ቸው፤ ስለ ተደ​ረ​ገው ተአ​ምር ሕዝቡ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="22">ይህ የድ​ኅ​ነት ምል​ክት ለተ​ደ​ረ​ገ​ለት ለዚያ ሰው ከአ​ርባ ዓመት ይበ​ል​ጠው ነበ​ረና።</verse>
				<verse number="23">ተፈ​ት​ተ​ውም ወደ ሰዎ​ቻ​ቸው ሄዱ፤ ሊቃነ ካህ​ና​ትና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ያሉ​አ​ቸ​ውን ሁሉ ነገ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ በአ​ን​ድ​ነት ቃላ​ቸ​ውን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ አድ​ር​ገው እን​ዲህ አሉ፥ “ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን፥ ባሕ​ር​ንም፥ በው​ስ​ጣ​ቸው ያለ​ው​ንም ሁሉ የፈ​ጠ​ርህ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥</verse>
				<verse number="25">አንተ ራስህ በአ​ባ​ታ​ችን በባ​ሪ​ያህ በዳ​ዊት አፍ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ እን​ዲህ ብለህ የተ​ና​ገ​ርህ፦ አሕ​ዛብ ለምን ተሰ​በ​ሰቡ? ሕዝ​ቡስ ለምን ከንቱ ነገ​ርን ተና​ገሩ?</verse>
				<verse number="26">የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ለምን ተነሡ? አለ​ቆ​ችስ ከእ​ነ​ርሱ ጋር አብ​ረው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በመ​ሲሑ ላይ ለምን ዶለቱ?</verse>
				<verse number="27">በቀ​ባ​ኸው በቅ​ዱስ ልጅህ ላይ ሄሮ​ድ​ስና ጰን​ጤ​ና​ዊው ጲላ​ጦስ ከወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸ​ውና ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ጋር በእ​ው​ነት በዚች ሀገር ላይ ዶለቱ።</verse>
				<verse number="28">እጅ​ህና ምክ​ርህ እን​ዲ​ደ​ረግ የወ​ሰ​ኑ​ትን ይፈ​ጽሙ ዘንድ።</verse>
				<verse number="29">አሁ​ንም አቤቱ፥ ትም​ክ​ህ​ታ​ቸ​ውን ተመ​ል​ከት፤ ቃል​ህ​ንም በግ​ልጥ ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ ለባ​ሮ​ችህ ስጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="30">በቅ​ዱሱ ልጅ​ህም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ሕሙ​ማ​ንን ትፈ​ውስ ዘንድ ተአ​ም​ራ​ት​ንና ድንቅ ሥራ​ንም ታደ​ርግ ዘንድ እጅ​ህን ዘርጋ።”</verse>
				<verse number="31">ሲጸ​ል​ዩም በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​ብ​ስ​በው የነ​በ​ሩ​በት ቦታ ተና​ወጠ፤ በሁ​ሉም ላይ መን​ፈስ ቅዱስ መላ​ባ​ቸ​ውና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በግ​ልጥ አስ​ተ​ማሩ።</verse>
				<verse number="32">ያመ​ኑ​ትም ሁሉ አንድ ልብና አን​ዲት ነፍስ ሆነው ይኖሩ ነበር፤ በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም የሁሉ ገን​ዘብ በአ​ን​ድ​ነት ነበር እንጂ “ይህ የእኔ ገን​ዘብ ነው” የሚል አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="33">ሐዋ​ር​ያ​ትም የጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ትን​ሣኤ በታ​ላቅ ኀይል ይመ​ሰ​ክሩ ነበር፤ በሕ​ዝ​ቡም ዘንድ ታላቅ ጸጋ ነበ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="34">ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ስንኳ ችግ​ረኛ አል​ነ​በ​ረም፤ ቤትና መሬት ያላ​ቸ​ውም ሁሉ እየ​ሸጡ ገን​ዘ​ቡን ያመጡ ነበር።</verse>
				<verse number="35">አም​ጥ​ተ​ውም በሐ​ዋ​ር​ያት እግር አጠ​ገብ ያኖ​ሩት ነበር፤ እነ​ር​ሱም ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ እንደ ፍላ​ጎቱ ይከ​ፍ​ሉት ነበር።</verse>
				<verse number="36">በሐ​ዋ​ር​ያ​ትም ዘንድ ትር​ጓ​ሜዉ የመ​ጽ​ና​ናት ልጅ የሚ​ሆን በር​ና​ባስ የተ​ባለ የሌዊ ወገን ስሙን ዮሴፍ የሚ​ሉት አንድ የቆ​ጵ​ሮስ ሰው ነበር።</verse>
				<verse number="37">እር​ሻም ነበ​ረ​ውና ሽጦ ገን​ዘ​ቡን አም​ጥቶ በሐ​ዋ​ር​ያት እግር አጠ​ገብ አኖ​ረው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">ሐና​ንያ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ሚስ​ቱም ሰጲራ ትባል ነበር፤ መሬ​ቱ​ንም ሸጠ።</verse>
				<verse number="2">ከሚ​ስ​ቱም ጋራ ተማ​ክሮ የዋ​ጋ​ዉን እኩ​ሌታ አስ​ቀረ፤ የዋ​ጋ​ው​ንም እኩ​ሌታ አም​ጥቶ በሐ​ዋ​ር​ያት እግር አጠ​ገብ አስ​ቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="3">ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ሐና​ንያ ሆይ፥ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ታታ​ል​ለው ዘንድ፥ የመ​ሬ​ት​ህ​ንም ዋጋ ከፍ​ለህ ታስ​ቀር ዘንድ ሰይ​ጣን በል​ብህ እን​ዴት አደረ?</verse>
				<verse number="4">ጥን​ቱን ሳት​ሸ​ጠው ያንተ አል​ነ​በ​ረ​ምን? ከሸ​ጥ​ኸ​ውስ በኋላ በፈ​ቃ​ድህ አል​ነ​በ​ረ​ምን? ይህን ነገር በል​ብህ ለምን ዐሰ​ብህ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንጂ ሰውን አላ​ታ​ለ​ል​ህም” አለው።</verse>
				<verse number="5">ሐና​ን​ያም ይህን በሰማ ጊዜ ወድቆ ሞተ፤ ጽኑ ፍር​ሀ​ትም ሆነ፤ የሰ​ሙ​ትም ሁሉ ፈሩ።</verse>
				<verse number="6">ከእ​ነ​ር​ሱም ጐል​ማ​ሶች ተነ​ሥ​ተው ገነ​ዙት፤ ተሸ​ክ​መ​ውም ወስ​ደው ቀበ​ሩት።</verse>
				<verse number="7">ይህም ከሆነ ከሦ​ስት ሰዓት በኋላ ሚስቱ መጣች፤ ባል​ዋም የሆ​ነ​ውን ሳታ​ውቅ ገባች።</verse>
				<verse number="8">ጴጥ​ሮ​ስም፥ “እስኪ ንገ​ሪኝ፥ መሬ​ታ​ች​ሁን የሸ​ጣ​ች​ሁት ይህን ለሚ​ያ​ህል ነውን?” አላት፤ እር​ስ​ዋም፥ “አዎን፥ እን​ዲሁ ነው” አለች።</verse>
				<verse number="9">ጴጥ​ሮ​ስም፥ “እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ፈስ ትፈ​ታ​ተ​ኑት ዘንድ እን​ዴት ተባ​በ​ራ​ችሁ? እነሆ፥ ባል​ሽን የቀ​በ​ሩት ሰዎች እግ​ሮች በበር ናቸው፤ አን​ቺ​ንም ይወ​ስ​ዱ​ሻል” አላት።</verse>
				<verse number="10">ያን​ጊ​ዜም ከእ​ግሩ በታች ወድቃ ሞተች፤ ጐል​ማ​ሶ​ችም በገቡ ጊዜ በድ​ን​ዋን አገኙ፤ ወስ​ደ​ውም በባ​ልዋ አጠ​ገብ ቀበ​ሩ​አት።</verse>
				<verse number="11">በአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ና​ትና ይህ​ንም ነገር በሰ​ሙት ሁሉ ላይ ታላቅ ፍር​ሀት ሆነ።</verse>
				<verse number="12">በሐ​ዋ​ር​ያት እጅም በሕ​ዝቡ ዘንድ ተአ​ም​ራ​ትና ድንቅ ሥራ​ዎች ይሠሩ ነበር፤ በቤተ መቅ​ደ​ስም በሰ​ሎ​ሞን መመ​ላ​ለሻ በአ​ን​ድ​ነት ነበሩ።</verse>
				<verse number="13">ሕዝ​ቡም እጅግ ያከ​ብ​ሩ​አ​ቸው ነበረ። ከሌ​ሎ​ችም ይቀ​ር​ባ​ቸው ዘንድ አንድ ስን​ኳን የሚ​ደ​ፍር አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="14">በጌ​ታ​ች​ንም የሚ​ያ​ምኑ ብዙ​ዎች ይጨ​መሩ ነበር፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶ​ችም ብዙ​ዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="15">ጴጥ​ሮ​ስም አልፎ ሲሄድ ጥላው ያር​ፍ​ባ​ቸው ዘንድ ድው​ዮ​ችን በአ​ል​ጋና በቃ​ሬዛ እያ​መጡ በአ​ደ​ባ​ባይ ያስ​ቀ​ም​ጡ​አ​ቸው ነበር፤</verse>
				<verse number="16">ደግ​ሞም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዙሪያ ከአሉ ከተ​ሞች ብዙ​ዎች ይመጡ ነበር፤ የታ​መ​ሙ​ት​ንና ክፉ​ዎች አጋ​ን​ንት የያ​ዙ​አ​ቸ​ው​ንም ያመጡ ነበር፥ ሁሉም ይፈ​ወሱ ነበር።</verse>
				<verse number="17">ሊቀ ካህ​ና​ቱና አብ​ረ​ውት የነ​በ​ሩት የሰ​ዱ​ቃ​ው​ያን ወገ​ኖ​ችም ቀን​ተው በእ​ነ​ርሱ ላይ ተነሡ።</verse>
				<verse number="18">እጃ​ቸ​ው​ንም በሐ​ዋ​ር​ያት ላይ አነሡ፤ ያዙ​አ​ቸ​ውም፤ በሕ​ዝቡ ወኅኒ ቤትም አስ​ገ​ቧ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ግን በሌ​ሊት የወ​ኅኒ ቤቱን ደጃፍ ከፍቶ አወ​ጣ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">“ሂዱ፤ ወደ ቤተ መቅ​ደ​ስም ግቡና ለሕ​ዝብ ይህን የሕ​ይ​ወት ቃል አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው።”</verse>
				<verse number="21">ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ ጥዋት ገስ​ግ​ሠው ወደ ቤተ መቅ​ደስ ገቡና አስ​ተ​ማሩ፤ ሊቀ ካህ​ና​ቱና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ግን ጉባ​ኤ​ው​ንና ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችን ሁሉ ሰበ​ሰቡ፤ ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም ያመ​ጡ​አ​ቸው ዘንድ ወደ ወኅኒ ቤት ላኩ።</verse>
				<verse number="22">አሽ​ከ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም መጥ​ተው በወ​ኅኒ ቤት አጡ​አ​ቸ​ውና ተመ​ል​ሰው ነገ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">“ወኅኒ ቤቱ​ንም ዙሪ​ያ​ውን ተዘ​ግቶ በቍ​ል​ፍም ተቈ​ልፎ አገ​ኘ​ነው፤ ወታ​ደ​ሮ​ቹም በሩን ይጠ​ብቁ ነበር፤ ነገር ግን ከፍ​ተን በገ​ባን ጊዜ በው​ስጥ ያገ​ኘ​ነው የለም” አሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">ሊቃነ ካህ​ና​ትና የቤተ መቅ​ደሱ ሹምም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ፥ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን አጥ​ተው፥ “እንጃ ይህ ምን ይሆን?” አሉ።</verse>
				<verse number="25">አንድ ሰውም መጥቶ፥ “ያሰ​ራ​ች​ኋ​ቸው እነ​ዚያ ሰዎች እነሆ፥ በቤተ መቅ​ደስ ውስጥ ናቸው፤ ቆመ​ውም ሕዝ​ቡን ያስ​ተ​ም​ራሉ” ብሎ ነገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">ከዚ​ህም በኋላ የቤተ መቅ​ደሱ ሹም ከሎ​ሌ​ዎቹ ጋር ሔዶ አባ​ብሎ አመ​ጣ​ቸው፤ በግ​ድም አይ​ደ​ለም፤ በድ​ን​ጋይ እን​ዳ​ይ​ደ​በ​ድ​ቧ​ቸው ሕዝ​ቡን ይፈሩ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="27">አም​ጥ​ተ​ውም በሸ​ንጎ መካ​ከል አቆ​ሙ​አ​ቸው፤ ሊቀ ካህ​ና​ቱም መረ​መ​ራ​ቸው፤</verse>
				<verse number="28">“በኢ​የ​ሱስ ስም ለማ​ንም እን​ዳ​ታ​ስ​ተ​ምሩ ከል​ክ​ለ​ና​ችሁ አል​ነ​በ​ረ​ምን? እነሆ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን በት​ም​ህ​ር​ታ​ችሁ ሞላ​ች​ኋት፤ የዚ​ያ​ንም ሰው ደም በእኛ ላይ ታመ​ጡ​ብን ዘንድ ትሻ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="29">ጴጥ​ሮ​ስና ሐዋ​ር​ያ​ትም መል​ሰው እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “ለሰው ከመ​ታ​ዘዝ ይልቅ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​ዘዝ ይገ​ባል።</verse>
				<verse number="30">የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ፥ እና​ንተ ክዳ​ችሁ በዕ​ን​ጨት ላይ ሰቅ​ላ​ችሁ የገ​ደ​ላ​ች​ሁ​ትን ኢየ​ሱ​ስን አስ​ነ​ሣው።</verse>
				<verse number="31">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እር​ሱን ለእ​ስ​ራ​ኤል ንስ​ሓን፥ የኀ​ጢ​አ​ት​ንም ስር​የት ይሰጥ ዘንድ ራስም አዳ​ኝም አደ​ረ​ገው፤ በቀ​ኙም አስ​ቀ​መ​ጠው።</verse>
				<verse number="32">እኛም ለዚህ ነገር ምስ​ክ​ሮቹ ነን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ታ​ዘ​ዙት የሰ​ጣ​ቸው መን​ፈስ ቅዱ​ስም ምስ​ክር ነው።”</verse>
				<verse number="33">ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ ተበ​ሳጩ፤ ጥር​ሳ​ቸ​ው​ንም አፋጩ፤ ሊገ​ድ​ሉ​አ​ቸ​ውም ወደዱ።</verse>
				<verse number="34">በሸ​ን​ጎ​ዉም በሕ​ዝቡ ሁሉ ዘንድ የከ​በረ የኦ​ሪት መም​ህር ስሙን ገማ​ል​ያል የሚ​ሉት አንድ ፈሪ​ሳዊ ተነሣ፤ ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም ከጉ​ባ​ኤዉ ጥቂት ፈቀቅ እን​ዲ​ያ​ደ​ር​ጉ​አ​ቸው አዘዘ።</verse>
				<verse number="35">እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሆይ፥ በእ​ነ​ዚህ ሰዎች በም​ታ​ደ​ር​ጉት ነገር ለራ​ሳ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ።</verse>
				<verse number="36">ቀድ​ሞም ከዚህ ዘመን በፊት ቴዎ​ዳስ ተነ​ሥቶ ራሱን ከፍ ከፍ አደ​ረገ፤ አራት መቶ ሰዎ​ችም ተከ​ተ​ሉት፤ ነገር ግን እር​ሱም ጠፋ፤ የተ​ከ​ተ​ሉ​ትም ሁሉ ተበ​ታ​ተኑ፤ እንደ ኢም​ን​ትም ሆኑ።</verse>
				<verse number="37">ከእ​ር​ሱም በኋላ ሰዎች ለግ​ብር በተ​ቈ​ጠ​ሩ​በት ወራት ገሊ​ላ​ዊው ይሁዳ ተነሣ፤ ብዙ ሕዝ​ብም ተከ​ተ​ሉት፤ እር​ሱም ሞተ፤ የተ​ከ​ተ​ሉ​ትም ሁሉ ተበ​ታ​ተኑ።</verse>
				<verse number="38">አሁ​ንም እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ከእ​ነ​ዚህ ሰዎች ራቁ፤ ተዉ​አ​ቸ​ውም፤ ይህ ምክ​ራ​ቸው፥ ይህም ሥራ​ቸው ከሰው የተ​ገኘ ከሆነ ያል​ፋል ይጠ​ፋ​ልም።</verse>
				<verse number="39">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመጣ ከሆነ ግን ልታ​ፈ​ር​ሱት አት​ች​ሉም፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጋር እን​ደ​ሚ​ጣላ አት​ሁኑ።”</verse>
				<verse number="40">እሺም አሰ​ኛ​ቸው፤ ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም ጠር​ተው ገረ​ፉ​አ​ቸው፤ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም በኢ​የ​ሱስ ስም እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ገሥ​ጸው ተዉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="41">እነ​ር​ሱም ከሸ​ን​ጎው ፊት ደስ እያ​ላ​ቸው ወጡ፤ ስለ ስሙ መከራ ይቀ​በሉ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ አድ​ሎ​አ​ቸ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="42">ሁል​ጊ​ዜም በቤተ መቅ​ደ​ስና በቤት ስለ ጌታ​ችን ስለ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ ማስ​ተ​ማ​ር​ንና መስ​በ​ክን አል​ተ​ዉም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">በዚ​ያም ወራት ደቀ መዛ​ሙ​ርት በበዙ ጊዜ ከግ​ሪክ የመጡ ደቀ መዛ​ሙ​ርት በአ​ይ​ሁድ ምእ​መ​ናን ላይ አን​ጐ​ራ​ጐ​ሩ​ባ​ቸው፤ የዕ​ለት የዕ​ለ​ቱን ምግብ ሲያ​ካ​ፍሉ ባል​ቴ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ቸል ይሉ​ባ​ቸው ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="2">ዐሥራ ሁለ​ቱም ሐዋ​ር​ያት ሕዝ​ቡን ሁሉ ጠር​ተው እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ትተን ማዕ​ድን እና​ገ​ለ​ግል ዘንድ የሚ​ገባ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="3">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ከእ​ና​ንተ ወገን በመ​ል​ካም የተ​መ​ሰ​ከ​ረ​ላ​ቸ​ውን መን​ፈስ ቅዱ​ስና ጥበብ የሞ​ላ​ባ​ቸ​ውን ሰባት ሰዎ​ችን ምረጡ፤ ለዚህ ሥራም እን​ሾ​ማ​ቸ​ዋ​ለን።</verse>
				<verse number="4">እኛ ግን ለጸ​ሎ​ትና ቃሉን ለማ​ስ​ተ​ማር እን​ተ​ጋ​ለን።”</verse>
				<verse number="5">ይህም ነገር በእ​ነ​ርሱ ዘንድ የተ​ወ​ደደ ሆነ፤ ሃይ​ማ​ኖቱ የቀ​ናና መን​ፈስ ቅዱስ ያደ​ረ​በ​ትን ሰው እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስን፥ ፊል​ጶ​ስን፥ ጵሮ​ኮ​ሮ​ስን፥ ኒቃ​ሮ​ናን፥ ጢሞ​ናን፥ ጰር​ሜ​ናን፥ ወደ ይሁ​ዲ​ነት የተ​መ​ለ​ሰ​ውን የአ​ን​ጾ​ኪ​ያ​ውን ኒቆ​ላ​ዎ​ስ​ንም መረጡ።</verse>
				<verse number="6">በሐ​ዋ​ር​ያ​ትም ፊት አቆ​ሙ​አ​ቸው፤ ጸል​የ​ውም እጃ​ቸ​ውን በራ​ሳ​ቸው ላይ ጫኑ።</verse>
				<verse number="7">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ከፍ ከፍ አለ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ምእ​መ​ናን እጅግ በዙ፤ ከካ​ህ​ና​ትም መካ​ከል ያመኑ ብዙ​ዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="8">እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋና ኀይል የመ​ላ​በት ሰው ነበር፤ በሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ታላ​ላቅ ተአ​ም​ራ​ት​ንና ድንቅ ሥራን ይሠራ ነበር።</verse>
				<verse number="9">የነጻ ወጭ​ዎች ከም​ት​ባ​ለው ምኵ​ራ​ብም ከቀ​ሬ​ናና ከእ​ስ​ክ​ን​ድ​ርያ፥ ከቂ​ል​ቅ​ያና ከእ​ስያ የሆኑ ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስን ይከ​ራ​ከ​ሩት ነበር።</verse>
				<verse number="10">ነገር ግን ይቃ​ወ​ሙት ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ በጥ​በ​ብና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="11">ከዚ​ህም በኋላ “ይህን ሰው በሙ​ሴና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ የስ​ድ​ብን ቃል ሲና​ገር ሰም​ተ​ነ​ዋል” የሚሉ የሐ​ሰት ምስ​ክ​ሮ​ችን አስ​ነ​ሡ​በት፤</verse>
				<verse number="12">ሕዝ​ቡን፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ች​ንና ጸሓ​ፊ​ዎ​ች​ንም አነ​ሳ​ሡ​አ​ቸው፤ ከበ​ውም እየ​ጐ​ተቱ ወደ ሸንጎ አቀ​ረ​ቡት።</verse>
				<verse number="13">የሐ​ሰት ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም አቆ​ሙ​በት፤ እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉ፥ “ይህ ሰው በዚህ ቤተ መቅ​ደስ ላይና በኦ​ሪት ላይ የስ​ድብ ቃል እየ​ተ​ና​ገረ ዝም በል ቢሉት እንቢ አለ፤</verse>
				<verse number="14">የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ ይህን ቤተ መቅ​ደስ ያፈ​ር​ሰ​ዋል፤ ሙሴም የሰ​ጠ​ንን ኦሪ​ታ​ች​ንን ይሽ​ራል ሲል ሰም​ተ​ነ​ዋል።”</verse>
				<verse number="15">በሸ​ን​ጎም ተቀ​ም​ጠው የነ​በ​ሩት ሁሉ ትኩር ብለው ተመ​ለ​ከ​ቱት፤ ፊቱ​ንም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ፊት ሆኖ አዩት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">ሊቀ ካህ​ና​ቱም፥ “በእ​ው​ነት እን​ዲህ ብለ​ሃ​ልን?” አለው።</verse>
				<verse number="2">እር​ሱም እን​ዲህ አለ፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንና አባ​ቶ​ቻ​ችን ሆይ፥ ስሙ፤ የክ​ብር አም​ላክ ለአ​ባ​ታ​ችን ለአ​ብ​ር​ሃም በሁ​ለት ወን​ዞች መካ​ከል ሳለ ወደ ካራ​ንም ሳይ​መጣ ተገ​ለ​ጠ​ለት።</verse>
				<verse number="3">‘ካገ​ርህ ውጣ፤ ከዘ​መ​ዶ​ች​ህም ተለይ፤ እኔም ወደ​ማ​ሳ​ይህ ሀገር ና’ አለው።</verse>
				<verse number="4">ከዚ​ህም በኋላ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሀገር ወጥቶ በካ​ራን ተቀ​መጠ፤ ከዚ​ያም አባቱ ከሞተ በኋላ፥ ዛሬ እና​ንተ ወደ አላ​ች​ሁ​ባት ወደ​ዚች ሀገር አመ​ጣው።</verse>
				<verse number="5">በው​ስ​ጥ​ዋም አንድ ጫማ ታህል ስን​ኳን ርስት አል​ሰ​ጠ​ውም፤ ነገር ግን እርሱ ከእ​ር​ሱም በኋላ ዘሩ ሊገ​ዛት ልጅ ሳይ​ኖ​ረው ያን​ጊዜ እር​ስ​ዋን ያወ​ር​ሰው ዘንድ ተስፋ ሰጠው።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለው፦ ‘ዘርህ በባ​ዕድ ሀገር መጻ​ተ​ኞች ሆነው ይኖ​ራሉ፤ አራት መቶ ዓመ​ትም ባሮች አድ​ር​ገው ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ መከ​ራም ያጸ​ኑ​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">ደግ​ሞም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አለ፤ ባሮች አድ​ር​ገው በሚ​ገ​ዙ​አ​ቸው ወገ​ኖች እኔ እፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ህም በኋላ ይወ​ጣሉ፤ በዚ​ህም ሀገር ያመ​ል​ኩ​ኛል።’</verse>
				<verse number="8">የግ​ዝ​ረ​ት​ንም ኪዳን ሰጠው፤ ከዚ​ህም በኋላ ይስ​ሐ​ቅን ወለደ፤ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀንም ገረ​ዘው፤ እን​ዲሁ ይስ​ሐ​ቅም ያዕ​ቆ​ብን፥ ያዕ​ቆ​ብም ዐሥራ ሁለ​ቱን የቀ​ደሙ አባ​ቶ​ችን ገረዙ።</verse>
				<verse number="9">“የቀ​ደሙ አባ​ቶ​ችም በዮ​ሴፍ ላይ ቀን​ተው ወደ ግብፅ ሀገር ሸጡት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ከእ​ርሱ ጋር ነበረ።</verse>
				<verse number="10">ከመ​ከ​ራ​ውም ሁሉ አዳ​ነው፤ በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ፊትም ሞገ​ስ​ንና ጥበ​ብን ሰጠው፤ በግ​ብ​ፅና በቤቱ ሁሉ ላይ ቢት​ወ​ደድ አድ​ርጎ ሾመው።</verse>
				<verse number="11">በግ​ብ​ፅና በከ​ነ​ዓን ሀገር ሁሉ ረኃ​ብና ታላቅ ጭንቅ መጣ፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም የሚ​በ​ሉት አጡ።</verse>
				<verse number="12">ያዕ​ቆ​ብም በግ​ብፅ ሀገር እህል እን​ዳለ ሰማ፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ን​ንም አስ​ቀ​ድሞ ላካ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">ወደ ግብ​ፅም እንደ ገና በተ​መ​ለሱ ጊዜ ወን​ድ​ሞቹ ዮሴ​ፍን ዐወ​ቁት፤ ፈር​ዖ​ንም የዮ​ሴ​ፍን ዘመ​ዶች ዐወ​ቃ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">ዮሴ​ፍም አባ​ቱን ያዕ​ቆ​ብ​ንና ዘመ​ዶ​ቹን ሁሉ እን​ዲ​ጠ​ሩ​አ​ቸው ላከ፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም ሰባ አም​ስት ነፍስ ነበር።</verse>
				<verse number="15">“ያዕ​ቆ​ብም ወደ ግብፅ ወረደ፥ እር​ሱም አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሞቱ።</verse>
				<verse number="16">ወደ ሴኬ​ምም አፍ​ል​ሰው አብ​ር​ሃም ከሴ​ኬም አባት ከኤ​ሞር ልጆች በገ​ን​ዘቡ በገ​ዛው መቃ​ብር ቀበ​ሩ​ዋ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ብ​ር​ሃም የማ​ለ​ለት የተ​ስ​ፋው ዘመን በደ​ረሰ ጊዜ እስ​ራ​ኤል በዙ፤ የግ​ብ​ፅ​ንም ሀገር መሉ።</verse>
				<verse number="18">ይህም ዮሴ​ፍን የማ​ያ​ው​ቀው ሌላ ንጉሥ በግ​ብፅ እስከ ነገሠ ድረስ ነበር።</verse>
				<verse number="19">እር​ሱም ወገ​ኖ​ቻ​ች​ንን ተተ​ን​ኵሎ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን መከራ አጸ​ና​ባ​ቸው፤ ወንድ ልጅ​ንም ሁሉ እን​ዲ​ገ​ድሉ አዘዘ።</verse>
				<verse number="20">“ያን​ጊ​ዜም ሙሴ ተወ​ለደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊትም የተ​ወ​ደደ ሆነ፤ ለሦ​ስት ወርም በአ​ባቱ ቤት አሳ​ደ​ጉት።</verse>
				<verse number="21">በተ​ጣ​ለም ጊዜ የፈ​ር​ዖን ልጅ አነ​ሣ​ችው፤ ልጅም ይሆ​ናት ዘንድ አሳ​ደ​ገ​ችው።</verse>
				<verse number="22">ሙሴም የግ​ብ​ፅን ጥበብ ሁሉ ተማረ፤ በሚ​ና​ገ​ረ​ውና በሚ​ሠ​ራ​ውም ሁሉ ብርቱ ሆነ።</verse>
				<verse number="23">“አርባ ዓመት ሲሞ​ላ​ውም ወን​ድ​ሞ​ቹን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሊጐ​በ​ኛ​ቸው በልቡ ዐሰበ።</verse>
				<verse number="24">አንድ ግብ​ፃ​ዊም ዕብ​ራ​ዊ​ውን ሲበ​ድ​ለው አገ​ኘና ለዚያ ለተ​በ​ደ​ለው ረድቶ ግብ​ፃ​ዊ​ውን ገደ​ለው በአ​ሸ​ዋም ቀበ​ረው።</verse>
				<verse number="25">እር​ሱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ ድኅ​ነ​ትን እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ላ​ቸው የሚ​ያ​ስ​ተ​ውሉ መስ​ሎት ነበር፤ እነ​ርሱ ግን አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም።</verse>
				<verse number="26">በማ​ግ​ሥ​ቱም ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ሁለት ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው ሲጣሉ አገኘ፤ ሊያ​ስ​ታ​ር​ቃ​ቸ​ውም ወድዶ፦ ‘እና​ን​ተማ ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች ናችሁ፤ እርስ በር​ሳ​ችሁ ለምን ትጣ​ላ​ላ​ችሁ?’ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="27">ያም ባል​ን​ጀ​ራ​ውን የሚ​በ​ድ​ለው ገፋው፤ እን​ዲ​ህም አለው፦ ‘አን​ተን በእኛ ላይ ዳኛና ፈራጅ አድ​ርጎ ማን ሾመህ?</verse>
				<verse number="28">ወይስ ትና​ን​ትና ግብ​ፃ​ዊ​ውን እንደ ገደ​ል​ኸው እኔ​ንም ልት​ገ​ድ​ለኝ ትሻ​ለ​ህን?’</verse>
				<verse number="29">ስለ​ዚ​ህም ነገር ሙሴ ኮብ​ልሎ በም​ድ​ያም ሀገር ስደ​ተኛ ሆኖ ኖረ፤ በዚ​ያም ሁለት ልጆ​ችን ወለደ።</verse>
				<verse number="30">“አርባ ዓመ​ትም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ በበ​ረሃ በደ​ብረ ሲና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ በቍ​ጥ​ቋጦ መካ​ከል በእ​ሳት ነበ​ል​ባል ታየው።</verse>
				<verse number="31">ሙሴም አይቶ በአ​የው ተደ​ነቀ፤ ሊያ​ስ​ተ​ው​ለ​ውም ቀረበ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው።</verse>
				<verse number="32">‘እኔ የአ​ባ​ቶ​ችህ አም​ላክ፥ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐቅ አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ ነኝ፤’ ሙሴም ተን​ቀ​ጠ​ቀጠ፤ መረ​ዳ​ትም አል​ቻ​ለም።</verse>
				<verse number="33">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለው፦ ‘ጫማ​ህን ከእ​ግ​ርህ አው​ልቅ፤ የቆ​ም​ህ​ባት ምድር የተ​ቀ​ደ​ሰች ናትና።</verse>
				<verse number="34">በግ​ብፅ ያሉ​ትን የወ​ገ​ኖ​ችን መከራ ማየ​ትን አይ​ቻ​ለሁ፤ ጩኸ​ታ​ቸ​ው​ንም ሰም​ቻ​ለሁ፤ ላድ​ና​ቸ​ውም ወር​ጃ​ለሁ፤ አሁ​ንም ና ወደ ግብፅ ሀገር ልላ​ክህ።’</verse>
				<verse number="35">“በእኛ ላይ አለ​ቃና ፈራጅ ማን አድ​ር​ጎ​ሃል? ብለው የካ​ዱ​ትን ያን ሙሴን በቍ​ጥ​ቋ​ጦው መካ​ከል በታ​የው በመ​ል​አኩ እጅ እር​ሱን መል​እ​ክ​ተ​ኛና አዳኝ አድ​ርጎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላከው።</verse>
				<verse number="36">እር​ሱም አርባ ዘመን በግ​ብፅ ሀገ​ርና በኤ​ር​ትራ ባሕር፥ በበ​ረ​ሃም ተአ​ም​ራ​ት​ንና ድንቅ ሥራን እየ​ሠራ አወ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="37">ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ መካ​ከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስ​ነ​ሣ​ላ​ች​ኋ​ልና እር​ሱን ስሙት’ ያላ​ቸው ይህ ሙሴ ነው።</verse>
				<verse number="38">በም​ድረ በዳ በማ​ኅ​በሩ መካ​ከል የነ​በረ እርሱ ነው፤ በደ​ብረ ሲና ከአ​ነ​ጋ​ገ​ረው መል​አ​ክና፤ ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ጋር ለእኛ ሊሰ​ጠን የሕ​ይ​ወ​ትን ቃል የተ​ቀ​በለ እርሱ ነው።</verse>
				<verse number="39">አባ​ቶ​ቻ​ችን ለእ​ርሱ መታ​ዘ​ዝን እንቢ አሉ፤ ከዱ​ትም፤ ልባ​ቸ​ው​ንም ወደ ግብፅ ሀገር መለሱ።</verse>
				<verse number="40">አሮ​ን​ንም፦ ‘በፊት በፊ​ታ​ችን የሚ​ሄዱ አማ​ል​ክ​ትን ሥራ​ልን፤ ያ ከም​ድረ ግብፅ ያወ​ጣን ሙሴ የሆ​ነ​ውን አና​ው​ቅ​ምና’ አሉት።</verse>
				<verse number="41">ያን​ጊ​ዜም የጥጃ ምስል ሠሩ፤ ለጣ​ዖ​ቱም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ፤ በእ​ጃ​ቸው ሥራም ደስ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="42">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተለ​ያ​ቸው፤ የሰ​ማይ ጭፍ​ራን ያመ​ል​ኩም ዘንድ ተዋ​ቸው፤ የነ​ቢ​ያት መጽ​ሐፍ እን​ዲህ እን​ዳለ፤ ‘እና​ንት የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሆይ፥ በውኑ በም​ድረ በዳ ሳላ​ችሁ አርባ ዐመት ያቀ​ረ​ባ​ች​ሁ​ልኝ ቍር​ባ​ንና መሥ​ዋ​ዕት አለን?</verse>
				<verse number="43">ነገር ግን የሞ​ሎ​ህን ድን​ኳን አነ​ሣ​ችሁ፤ ሬፋን የሚ​ባ​ለ​ው​ንም ኮከብ አመ​ለ​ካ​ችሁ፤ ትሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም ዘንድ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን አበ​ጃ​ችሁ፤ እኔም ወደ ባቢ​ሎን እን​ድ​ት​ማ​ረኩ አደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ለሁ።’</verse>
				<verse number="44">“ሙሴን ተና​ግሮ እንደ አዘ​ዘው በአ​ሳ​የው ምሳሌ የሠ​ራት የም​ስ​ክር ድን​ኳን በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ዘንድ በም​ድረ በዳ ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="45">ኢያ​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም በተራ ተቀ​ብ​ለው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ፊት አስ​ወ​ጥቶ ወደ ሰደ​ዳ​ቸው ወደ አሕ​ዛብ ሀገር ከእ​ነ​ርሱ ጋር አገ​ቡ​አት፤ እስከ ዳዊት ዘመ​ንም ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="46">ዳዊ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ባለ​መ​ዋ​ል​ነ​ትን አግ​ኝቶ ለያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ ማደ​ሪያ ያገኝ ዘንድ ለመነ።</verse>
				<verse number="47">ሰሎ​ሞን ግን ቤትን ሠራ​ለት።</verse>
				<verse number="48">ነገር ግን ልዑል የሰው እጅ በሠ​ራው ቤት የሚ​ኖር አይ​ደ​ለም፤ ነቢይ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="49">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድ​ርም የእ​ግሬ መረ​ገጫ ናት፤ ምን ዐይ​ነት ቤት ትሠ​ሩ​ል​ኛ​ላ​ችሁ? የማ​ር​ፍ​በት ቦታስ ምን ዐይ​ነት ቦታ ነው?</verse>
				<verse number="50">ይህን ሁሉ እጆች የሠ​ሩት አይ​ደ​ለ​ምን?’</verse>
				<verse number="51">“እና​ንተ አን​ገ​ታ​ችሁ የደ​ነ​ደነ፥ ልባ​ች​ሁም የተ​ደ​ፈነ፥ ጆሮ​አ​ች​ሁም የደ​ነ​ቈረ፥ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ዘወ​ትር ትቃ​ወ​ማ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="52">አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ከነ​ቢ​ያት ያላ​ሳ​ደ​ዱት ማን አለ? ዛሬም እና​ንተ አሳ​ል​ፋ​ችሁ የሰ​ጣ​ች​ሁ​ት​ንና የገ​ደ​ላ​ች​ሁ​ትን የጻ​ድ​ቁን መም​ጣት አስ​ቀ​ድ​መው የተ​ና​ገ​ሩ​ትን ገደ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="53">በመ​ላ​እ​ክ​ትም ሥር​ዐት ኦሪ​ትን ተቀ​ብ​ላ​ችሁ አል​ጠ​በ​ቃ​ች​ሁ​ትም።”</verse>
				<verse number="54">ይህ​ንም ሰም​ተው ተበ​ሳጩ፤ ልባ​ቸ​ውም ተና​ደደ፤ ጥር​ሳ​ቸ​ው​ንም አፋ​ጩ​በት።</verse>
				<verse number="55">በእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስም ላይ መን​ፈስ ቅዱስ መላ፤ ወደ ሰማ​ይም ተመ​ለ​ከተ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር፥ ኢየ​ሱ​ስም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀኝ ቆሞ አየ።</verse>
				<verse number="56">“እነሆ ሰማይ ተከ​ፍቶ፤ የሰው ልጅም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀኝ ቆሞ አያ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="57">እነ​ር​ሱም በታ​ላቅ ቃል ጮኹ፤ ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም ደፈኑ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ተነ​ሥ​ተው ከበ​ቡት።</verse>
				<verse number="58">ከከ​ተ​ማም ወደ ውጭ ጐት​ተው አው​ጥ​ተው ወገ​ሩት፤ የሚ​ወ​ግ​ሩት ሰዎ​ችም ልብ​ሳ​ቸ​ውን ሳውል በሚ​ባል ጐል​ማሳ እግር አጠ​ገብ አስ​ቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="59">እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስም፥ “ጌታዬ ኢየ​ሱስ ሆይ፥ ነፍ​ሴን ተቀ​በል” እያለ ሲጸ​ልይ ይወ​ግ​ሩት ነበር።</verse>
				<verse number="60">በጕ​ል​በ​ቱም ተን​በ​ር​ክኮ፥ “አቤቱ፥ ይህን ኀጢ​አት አት​ቍ​ጠ​ር​ባ​ቸው” ብሎ በታ​ላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህ​ንም ብሎ ሞተ፤ ሳው​ልም በእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖስ ሞት ተባ​ባሪ ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">በዚያ ወራ​ትም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለ​ችው ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ላይ ታላቅ ስደት ሆነ፤ ከሐ​ዋ​ር​ያ​ትም በቀር ሁሉም በይ​ሁ​ዳና በሰ​ማ​ርያ ባሉ አው​ራ​ጃ​ዎች ሁሉ ተበ​ተኑ።</verse>
				<verse number="2">እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስ​ንም ደጋግ ሰዎች አን​ሥ​ተው ቀበ​ሩት፤ ታላቅ ልቅ​ሶም አለ​ቀ​ሱ​ለት።</verse>
				<verse number="3">ሳውል ግን ገና አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ና​ትን ይቃ​ወም ነበር፤ የሰ​ው​ንም ቤት ሁሉ ይበ​ረ​ብር ነበር፤ ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም እየ​ጐ​ተተ ወደ ወኅኒ ቤት ያስ​ገ​ባ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="4">የተ​በ​ተ​ኑት ግን እየ​ተ​ዘ​ዋ​ወሩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰበኩ፥ አስ​ተ​ማ​ሩም።</verse>
				<verse number="5">ፊል​ጶ​ስም ወደ ሰማ​ርያ ከተማ ወረደ፤ ስለ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰበ​ከ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">ሕዝ​ቡም የነ​ገ​ራ​ቸ​ውን በሰ​ሙና ያደ​ር​ገው የነ​በ​ረ​ውን ተአ​ም​ራት በአዩ ጊዜ በአ​ንድ ልብ የፊ​ል​ጶ​ስን ነገር ተቀ​በሉ።</verse>
				<verse number="7">ርኩ​ሳን መና​ፍ​ስት ያደ​ሩ​ባ​ቸ​ውም ብዙ​ዎች ነበ​ሩና፥ በታ​ላቅ ቃል እየ​ጮኹ ይወጡ ነበር፤ ብዙ​ዎች ልም​ሾ​ዎ​ችና አን​ካ​ሶ​ችም ይፈ​ወሱ ነበር።</verse>
				<verse number="8">በዚ​ያ​ችም ከተማ ታላቅ ደስታ ሆነ።</verse>
				<verse number="9">በዚ​ያ​ችም ከተማ ሲሞን የሚ​ባል አንድ ሰው ነበር፤ የሰ​ማ​ርያ ሰዎ​ች​ንም ያስት ነበር፤ ሰው​የዉ ሥራ​የኛ ነበር፤ ራሱ​ንም ታላቅ ያደ​ርግ ነበር።</verse>
				<verse number="10">ከታ​ና​ና​ሾ​ቹም ጀምሮ እስከ ታላ​ላ​ቆቹ ድረስ “ታላቁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ይህ ነው” እያሉ ሁሉም ያደ​ም​ጡት ነበር።</verse>
				<verse number="11">ከብዙ ዘመ​ንም ጀምሮ በጥ​ን​ቈ​ላው ያታ​ል​ላ​ቸው ስለ ነበር ያዳ​ም​ጡት ነበር።</verse>
				<verse number="12">ነገር ግን ፊል​ጶስ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥ​ትና ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሰብ​ኮ​ላ​ቸው በአ​መኑ ጊዜ ሴቶ​ችም ወን​ዶ​ችም ተጠ​መቁ።</verse>
				<verse number="13">ሲሞ​ንም ወዲ​ያ​ውኑ አምኖ ተጠ​መቀ፤ ፊል​ጶ​ስ​ንም ይከ​ተል ጀመር፤ በፊ​ል​ጶ​ስም እጅ የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ርና ታላቅ ኀይል ባየ ጊዜ ይደ​ነቅ ነበር።</verse>
				<verse number="14">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የነ​በሩ ሐዋ​ር​ያ​ትም የሰ​ማ​ርያ ሰዎች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እንደ ተቀ​በሉ በሰሙ ጊዜ ጴጥ​ሮ​ስ​ንና ዮሐ​ን​ስን ወደ እነ​ርሱ ላኩ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">ወር​ደ​ውም መን​ፈስ ቅዱ​ስን እን​ዲ​ቀ​በሉ ጸለ​ዩ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ተጠ​መቁ እንጂ ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው በአ​ንዱ ላይ ስንኳ መን​ፈስ ቅዱስ ገና አል​ወ​ረ​ደም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="17">በዚያ ጊዜም እጃ​ቸ​ውን ጫኑ​ባ​ቸው፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስ​ንም ተቀ​በሉ።</verse>
				<verse number="18">ሲሞ​ንም ሐዋ​ር​ያት እጃ​ቸ​ውን በጫ​ኑ​በት ሰው ላይ መን​ፈስ ቅዱስ እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ ባየ ጊዜ ገን​ዘብ አመ​ጣ​ላ​ቸ​ውና፥</verse>
				<verse number="19">“እጄን በም​ጭ​ን​በት ሰው ላይ መን​ፈስ ቅዱስ ይወ​ርድ ዘንድ ለእ​ኔም ይህን ሥል​ጣን ስጡኝ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">ጴጥ​ሮስ ግን እን​ዲህ አለው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጸጋ በገ​ን​ዘብ ልት​ገዛ ዐስ​በ​ሃ​ልና ገን​ዘ​ብህ ከአ​ንተ ጋር ይጥፋ።</verse>
				<verse number="21">በዚህ ነገር ዕድ​ልና ርስት የለ​ህም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ልብህ የቀና አይ​ደ​ለ​ምና።</verse>
				<verse number="22">አሁ​ንም ከክ​ፋ​ትህ ተመ​ለ​ስና ንስሓ ግባ። የል​ቡ​ና​ህ​ንም ዐሳብ ይተ​ው​ልህ እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለምን።</verse>
				<verse number="23">በመ​ራራ መርዝ ተመ​ር​ዘህ፥ በዐ​መፃ ማሰ​ሪያ ተተ​ብ​ት​በህ የም​ት​ኖር ሆነህ አይ​ሃ​ለ​ሁና።”</verse>
				<verse number="24">ሲሞ​ንም መልሶ፥ “ካላ​ች​ሁት ሁሉ ምንም እን​ዳ​ይ​ደ​ር​ስ​ብኝ እና​ንተ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለም​ኑ​ልኝ” አለ።</verse>
				<verse number="25">እነ​ር​ሱም ከመ​ሰ​ከ​ሩና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ከተ​ና​ገሩ በኋላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ፤ በብ​ዙ​ዎች የሰ​ማ​ርያ መን​ደ​ሮ​ችም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አስ​ተ​ማሩ።</verse>
				<verse number="26">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም ፊል​ጶ​ስን ተና​ገ​ረው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “በቀ​ትር ጊዜ ተነ​ሣና በደ​ቡብ በኩል ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ጋዛ በሚ​ያ​ወ​ር​ደው በም​ድረ በዳው መን​ገድ ሂድ።”</verse>
				<verse number="27">ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ እነ​ሆም፥ የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንግ​ሥት የሕ​ን​ደኬ ጃን​ደ​ረባ ከሹ​ሞ​ችዋ የበ​ለጠ፥ በሀ​ብ​ቷም ሁሉ ላይ በጅ​ሮ​ንድ የነ​በረ፥ አንድ የኢ​ት​ዮ​ጵያ ሰው ነበር፤ እር​ሱም ሊሰ​ግድ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ።</verse>
				<verse number="28">ሲመ​ለ​ስም በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ተቀ​ምጦ የነ​ቢዩ የኢ​ሳ​ይ​ያ​ስን መጽ​ሐፍ ያነብ ነበር።</verse>
				<verse number="29">መን​ፈስ ቅዱ​ስም ፊል​ጶ​ስን፥ “ሂድ፤ ይህን ሰረ​ገላ ተከ​ተ​ለው” አለው።</verse>
				<verse number="30">ፊል​ጶ​ስም ፈጥኖ ደርሶ የነ​ቢ​ዩን የኢ​ሳ​ይ​ያ​ስን መጽ​ሐፍ ሲያ​ነብ ሰማው፤ ፊል​ጶ​ስም፥ “በውኑ የም​ታ​ነ​በ​ውን ታው​ቀ​ዋ​ለ​ህን?” አለው።</verse>
				<verse number="31">ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም፥ “ያስ​ተ​ማ​ረኝ ሳይ​ኖር በምን አው​ቀ​ዋ​ለሁ?” አለው፤ ወደ ሰረ​ገ​ላ​ውም ወጥቶ አብ​ሮት ይቀ​መጥ ዘንድ ፊል​ጶ​ስን ለመ​ነው።</verse>
				<verse number="32">ያነ​በው የነ​በረ የመ​ጽ​ሐፉ ቃልም እን​ዲህ የሚል ነበር፤ “እንደ በግ ወደ መታ​ረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦ​ትም በሚ​ሸ​ል​ተው ፊት እን​ደ​ማ​ይ​ና​ገር እን​ዲሁ አፉን አል​ከ​ፈ​ተም።</verse>
				<verse number="33">በው​ር​ደቱ ፍርዱ ተወ​ገደ፤ ሕይ​ወቱ ከም​ድር ተወ​ግ​ዶ​አ​ልና ትው​ል​ዱን ማን ይና​ገ​ራል?”</verse>
				<verse number="34">ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም ለፊ​ል​ጶስ መልሶ፥ “ነቢዩ ስለ ማን እን​ዲህ ይላል? ስለ ራሱ ነውን? ወይስ ስለ ሌላ? እባ​ክህ ንገ​ረኝ” አለው።</verse>
				<verse number="35">ፊል​ጶ​ስም አፉን ከፈተ፤ ስለ ኢየ​ሱ​ስም ከዚ​ያው መጽ​ሐፍ ጀምሮ አስ​ተ​ማ​ረው።</verse>
				<verse number="36">በመ​ን​ገድ ሲሄ​ዱም ወደ ውኃ ደረሱ፤ ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም፥ “እነሆ፥ ውኃ፥ መጠ​መ​ቅን ምን ይከ​ለ​ክ​ለ​ኛል?” አለው።</verse>
				<verse number="37">ፊል​ጶ​ስም፥ “በፍ​ጹም ልብህ ብታ​ምን ይገ​ባ​ሃል” አለው፤ ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም መልሶ፥ “ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ እኔ አም​ና​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="38">ሰረ​ገ​ላ​ው​ንም እን​ዲ​ያ​ቆሙ አዘዘ፤ አቁ​መ​ውም ፊል​ጶ​ስና ጃን​ደ​ረ​ባው በአ​ን​ድ​ነት ወደ ውኃው ወረዱ፤ አጠ​መ​ቀ​ውም።</verse>
				<verse number="39">ከው​ኃ​ዉም ከወጡ በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ፊል​ጶ​ስን ነጥቆ ወሰ​ደው፤ ጃን​ደ​ረ​ባ​ዉም ከዚያ ወዲያ አላ​የ​ውም፤ ደስ እያ​ለ​ውም መን​ገ​ዱን ሄደ።</verse>
				<verse number="40">ፊል​ጶ​ስም አዛ​ጦን ወደ​ም​ት​ባል ሀገር ደረሰ፤ በከ​ተ​ማ​ዎ​ችም ሁሉ እየ​ተ​ዘ​ዋ​ወረ ወደ ቂሳ​ርያ እስ​ኪ​ደ​ርስ ድረስ ያስ​ተ​ምር ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">ሳውል ግን የጌ​ታን ደቀ መዛ​ሙ​ርት ለመ​ግ​ደል ገና እየ​ዛተ ወደ ሊቀ ካህ​ናቱ ሄደ።</verse>
				<verse number="2">ምን​አ​ል​ባት በመ​ን​ገድ የሚ​ያ​ገ​ኘው ሰው ቢኖር ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም እያ​ሰረ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ጣ​ቸው ዘንድ በደ​ማ​ስቆ ላሉት ምኵ​ራ​ቦች የሥ​ል​ጣን ደብ​ዳቤ ከሊቀ ካህ​ናቱ ለመነ።</verse>
				<verse number="3">ሲሄ​ድም ወደ ደማ​ስቆ ከተማ አቅ​ራ​ቢያ በደ​ረሰ ጊዜ መብ​ረቅ ድን​ገት ከሰ​ማይ ብልጭ አለ​በት።</verse>
				<verse number="4">በም​ድር ላይም ወደቀ፤ ወዲ​ያ​ውም፥ “ሳውል፥ ሳውል፥ ለምን ታሳ​ድ​ደ​ኛ​ለህ?” የሚ​ለ​ውን ቃል ሰማ።</verse>
				<verse number="5">ሳው​ልም፥ “አቤቱ፥ አንተ ማነህ?” አለው፤ እር​ሱም፥ “አንተ የም​ታ​ሳ​ድ​ደኝ የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ ነኝ፤ በሾለ ብረት ላይ ብት​ቆም ለአ​ንተ ይብ​ስ​ሃል” አለው።</verse>
				<verse number="6">እር​ሱም እየ​ፈ​ራና እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጠ፥ “አቤቱ፥ ምን እን​ዳ​ደ​ርግ ትሻ​ለህ?” አለው፤ ጌታም፥ “ተነ​ሣና ወደ ከተማ ግባ፤ በዚ​ያም ልታ​ደ​ር​ገው የሚ​ገ​ባ​ህን ይነ​ግ​ሩ​ሃል” አለው።</verse>
				<verse number="7">ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ሰዎች ድምፅ እየ​ሰሙ ማን​ንም ሳያዩ ተደ​ን​ቀው ቆሙ።</verse>
				<verse number="8">ሳው​ልም ከም​ድር ተነሣ፤ ነገር ግን ዐይ​ኖቹ ተገ​ል​ጠው ሳሉ የሚ​ያ​የው ነገር አል​ነ​በ​ረም፤ እየ​መ​ሩም ወደ ደማ​ስቆ አገ​ቡት።</verse>
				<verse number="9">በዚ​ያም ሳያይ ሳይ​በ​ላና ሳይ​ጠጣ ሦስት ቀን ቈየ።</verse>
				<verse number="10">በደ​ማ​ስ​ቆም ስሙን ሐና​ንያ የሚ​ሉት አንድ ደቀ መዝ​ሙር ነበር፤ ጌታም በራ​እይ ተገ​ልጦ፥ “ሐና​ንያ” ብሎ ጠራው፤ እር​ሱም፥ “አቤቱ፥ እነ​ሆኝ” አለ።</verse>
				<verse number="11">ጌታም፥ “ተነ​ሣና ቅን በም​ት​ባ​ለው መን​ገድ ሂድ፤ በይ​ሁዳ ቤትም ከጠ​ር​ሴስ ሀገር የመጣ ሳውል የሚ​ባል ሰው ፈልግ፤ እርሱ አሁን ይጸ​ል​ያ​ልና” አለው።</verse>
				<verse number="12">ሳው​ልም በራ​እይ ሐና​ንያ የሚ​ባል ሰው ወደ እርሱ ገብቶ ያይ ዘንድ እጁን ሲጭ​ን​በት አየ።</verse>
				<verse number="13">ሐና​ንያ ግን መልሶ እን​ዲህ አለ፥ “አቤቱ፥ ስለ​ዚህ ሰው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በቅ​ዱ​ሳ​ኖ​ችህ ላይ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ክፉ ነገር ሁሉ ከብዙ ሰዎች ሰም​ቻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">ወደ​ዚ​ህም ከካ​ህ​ናቱ አለቃ አስ​ፈ​ቅዶ የመጣ ስም​ህን የሚ​ጠ​ሩ​ትን ሁሉ ሊያ​ስር ነው።”</verse>
				<verse number="15">ጌታ​ች​ንም እን​ዲህ አለው፥ “ተነ​ሥና ሂድ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብና በነ​ገ​ሥ​ታት፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ፊት ስሜን ይሸ​ከም ዘንድ ለእኔ የተ​መ​ረጠ ዕቃ አድ​ር​ጌ​ዋ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="16">እኔም ስለ ስሜ መከ​ራን ይቀ​በል ዘንድ እን​ዳ​ለው አሳ​የ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="17">ያን​ጊ​ዜም ሐና​ንያ ሄደ፤ ወደ ቤትም ገባ፤ እጁ​ንም ጫነ​በ​ትና፥ “ወን​ድሜ ሳውል፥ በመ​ን​ገድ ስት​መጣ የታ​የህ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ታይና መን​ፈስ ቅዱስ ይመ​ላ​ብህ ዘንድ ወደ አንተ ልኮ​ኛል” አለው።</verse>
				<verse number="18">ያን​ጊ​ዜም ፈጥኖ እንደ ቅር​ፊት ያለ ነገር ከዐ​ይ​ኖቹ ላይ ተገፎ ወደቀ፤ ዐይ​ኖ​ቹም ተገ​ለጡ፤ ወዲ​ያ​ውም አየ፤ ተነ​ሥ​ቶም ተጠ​መቀ።</verse>
				<verse number="19">እህ​ልም በላ፤ በረ​ታም፤ ጥቂት ቀንም ከደቀ መዛ​ሙ​ርት ጋር በደ​ማ​ስቆ ሰነ​በተ።</verse>
				<verse number="20">ወዲ​ያ​ው​ኑም “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ነው” ብሎ ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በየ​ም​ኵ​ራ​ቦቹ ሰበከ፥ አስ​ተ​ማ​ረም።</verse>
				<verse number="21">የሰ​ሙ​ትም ሁሉ አደ​ነቁ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይህን ስም የሚ​ጠ​ሩ​ትን ሁሉ ይጠ​ላ​ቸው የነ​በ​ረው ይህ አይ​ደ​ለ​ምን? ስለ​ዚህ ወደ​ዚህ የመ​ጣው እያ​ሰረ ወደ ሊቀ ካህ​ናቱ ሊወ​ስ​ዳ​ቸው አይ​ደ​ለ​ምን?”</verse>
				<verse number="22">ሳውል ግን እየ​በ​ረታ ሔደ፤ በደ​ማ​ስ​ቆም ለነ​በ​ሩት አይ​ሁድ ይህ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ እያ​ስ​ረዳ መልስ አሳ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">ከብዙ ቀንም በኋላ አይ​ሁድ ሳው​ልን ይገ​ድ​ሉት ዘንድ ተማ​ከሩ።</verse>
				<verse number="24">ሳውል ግን በእ​ርሱ ላይ ሊያ​ደ​ር​ጉት የሚ​ሹ​ትን ዐወ​ቀ​ባ​ቸው፤ ሊገ​ድ​ሉ​ትም በቀ​ንና በሌ​ሊት የከ​ተ​ማ​ውን በር ይጠ​ብቁ ነበር።</verse>
				<verse number="25">ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም በሌ​ሊት ወሰ​ዱት፤ በቅ​ር​ጫ​ትም አድ​ር​ገው በቅ​ጽሩ ድም​ድ​ማት ላይ አወ​ረ​ዱት።</verse>
				<verse number="26">ሳው​ልም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በደ​ረሰ ጊዜ ሊገ​ና​ኛ​ቸው ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትን ፈለ​ጋ​ቸው። ሁሉም ፈሩት፤ የጌ​ታ​ችን ደቀ መዝ​ሙር እንደ ሆነ አላ​መ​ኑ​ትም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="27">በር​ና​ባ​ስም አግ​ኝቶ ወደ ሐዋ​ር​ያት ወሰ​ደው፤ ጌታ​ች​ንም በመ​ን​ገድ እንደ ተገ​ለ​ጠ​ለ​ትና እንደ አነ​ጋ​ገ​ረው፥ በደ​ማ​ስ​ቆም በኢ​የ​ሱስ ስም እንደ አስ​ተ​ማረ ነገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="28">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አብ​ሮ​አ​ቸው ይገ​ባና ይወጣ ነበረ፤ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ስምም በግ​ልጥ ያስ​ተ​ምር ነበር።</verse>
				<verse number="29">ከግ​ሪክ ሀገር መጥ​ተው የነ​በ​ሩ​ት​ንም አይ​ሁድ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበር፤ እነ​ር​ሱም ደግሞ ሊገ​ድ​ሉት ፈለጉ።</verse>
				<verse number="30">ወን​ድ​ሞ​ችም ይህን ባወቁ ጊዜ ወደ ቂሳ​ርያ አወ​ረ​ዱት፤ ከዚ​ያም ወደ ጠር​ሴስ ላኩት።</verse>
				<verse number="31">በይ​ሁዳ፥ በሰ​ማ​ር​ያና በገ​ሊላ ያሉ አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ በሰ​ላም ኖሩ፤ ታነ​ጹም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በመ​ፍ​ራት ጸን​ተው ኖሩ፤ ሕዝ​ቡም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ አጽ​ና​ኝ​ነት በዙ።</verse>
				<verse number="32">ከዚ​ህም በኋላ ጴጥ​ሮስ በየ​ቦ​ታዉ ሲዘ​ዋ​ወር በልዳ ወደ​ሚ​ኖ​ሩት ቅዱ​ሳን ዘንድ ደረሰ።</verse>
				<verse number="33">በዚ​ያም ኤንያ የተ​ሰኘ ሰውን አገኘ፤ እር​ሱም ታሞ በአ​ልጋ ከተኛ ስም​ንት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ ሽባ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="34">ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ኤንያ ሆይ፥ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ይፈ​ው​ስህ፤ ተነ​ሥና አል​ጋ​ህን አን​ጥፍ” አለው፤ ያን​ጊ​ዜም ተነሣ።</verse>
				<verse number="35">በል​ዳና በሳ​ሮና የሚ​ኖ​ሩም ሁሉ እር​ሱን አይ​ተው ወደ ጌታ​ችን ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="36">በኢ​ዮጴ ሀገ​ርም ጣቢታ የም​ት​ባል አን​ዲት ደቀ መዝ​ሙር ነበ​ረች፤ በት​ር​ጓ​ሜ​ውም ዶር​ቃስ ይሉ​አ​ታል፤ ፌቆ ማለት ነው፤ እር​ስ​ዋም ብዙ ደጋግ ሥራ ትሠራ ነበር፤ ምጽ​ዋ​ትም ትሰጥ ነበር።</verse>
				<verse number="37">ያን​ጊ​ዜም ታማ ሞተ​ችና በድ​ን​ዋን አጥ​በው በሰ​ገ​ነት አስ​ተ​ኙ​አት።</verse>
				<verse number="38">ልዳም ለኢ​ዮጴ ቅርብ ነበ​ርና ደቀ መዛ​ሙ​ርት ጴጥ​ሮስ በዚያ እን​ዳለ ሰም​ተው ወደ እነ​ርሱ መም​ጣት እን​ዳ​ይ​ዘ​ገይ ይማ​ል​ዱት ዘንድ ሁለት ሰዎ​ችን ወደ እርሱ ላኩ።</verse>
				<verse number="39">ጴጥ​ሮ​ስም ተነ​ሥቶ አብ​ሮ​አ​ቸው ሄደ፤ በደ​ረ​ሰም ጊዜ ወደ ሰገ​ነት አወ​ጡት፤ ባል​ቴ​ቶ​ችም ሁሉ ወደ እርሱ መጥ​ተው በፊቱ ቆሙ፤ ያለ​ቅ​ሱ​ላ​ትም ነበር፤ ዶር​ቃ​ስም በሕ​ይ​ወት ሳለች የሠ​ራ​ች​ውን ቀሚ​ሱ​ንና መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ውን አሳ​ዩት።</verse>
				<verse number="40">ጴጥ​ሮ​ስም ሁሉን ካስ​ወጣ በኋላ ተን​በ​ር​ክኮ ጸለየ፤ ወደ በድ​ን​ዋም መለስ ብሎ፥ “ጣቢታ ሆይ፥ ተነሽ” አላት፤ እር​ስ​ዋም ዐይ​ኖ​ች​ዋን ገለ​ጠች፤ ያን​ጊ​ዜም ጴጥ​ሮ​ስን አየ​ችው፤ ቀና ብላም ተቀ​መ​ጠች።</verse>
				<verse number="41">እጁ​ንም ለእ​ር​ስዋ ሰጥቶ አስ​ነ​ሣት፤ ቅዱ​ሳ​ን​ንና ባል​ቴ​ቶ​ች​ንም ጠርቶ እር​ስ​ዋን አድኖ ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="42">በኢ​ዮ​ጴም ያሉ ሁሉ ይህን ሰሙ፤ ብዙ​ዎ​ችም በጌ​ታ​ችን አመኑ።</verse>
				<verse number="43">ጴጥ​ሮ​ስም በኢ​ዮጴ በቍ​ር​በት ፋቂው በስ​ም​ዖን ቤት ብዙ ቀን ተቀ​መጠ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">በቂ​ሳ​ር​ያም ቆር​ኔ​ሌ​ዎስ የሚ​ባል አንድ ሰው ነበረ፤ ኢጣ​ሊቄ ለሚ​ሉት ጭፍ​ራም የመቶ አለቃ ነበር።</verse>
				<verse number="2">እር​ሱም ጻድ​ቅና ከነ​ቤተ ሰቡ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ነበር፤ ለሕ​ዝ​ቡም ብዙ ምጽ​ዋት ይሰጥ ነበር፤ ዘወ​ት​ርም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ልይ ነበር።</verse>
				<verse number="3">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም በራ​እይ ከቀኑ በዘ​ጠኝ ሰዓት በግ​ልጥ ታየው፤ ወደ እር​ሱም ገብቶ፥ “ቆር​ኔ​ሌ​ዎስ ሆይ፥” አለው።</verse>
				<verse number="4">ወደ​እ​ር​ሱም ተመ​ል​ክቶ ፈራና፥ “አቤቱ፥ ምን​ድን ነው?” አለ፤ መል​አ​ኩም እን​ዲህ አለው፥ “ጸሎ​ት​ህም ምጽ​ዋ​ት​ህም መል​ካም መታ​ሰ​ቢያ ሆኖ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐር​ጎ​አል።</verse>
				<verse number="5">አሁ​ንም ጴጥ​ሮስ የሚ​ባ​ለ​ውን ስም​ዖ​ንን ይጠ​ሩ​ልህ ዘንድ ወደ ኢዮጴ ከተማ ሰዎ​ችን ላክ።</verse>
				<verse number="6">እር​ሱም ቤቱ በባ​ሕር አጠ​ገብ ባለው በቍ​ር​በት ፋቂው በስ​ም​ዖን ቤት እን​ግ​ድ​ነት ተቀ​ም​ጦ​አል። ልታ​ደ​ር​ገው የሚ​ገ​ባ​ህን እርሱ ይነ​ግ​ር​ሃል።”</verse>
				<verse number="7">ያነ​ጋ​ገ​ረ​ውም መል​አክ ከሄደ በኋላ ከሎ​ሌ​ዎቹ ሁለት፥ ከማ​ይ​ለ​ዩት ጭፍ​ሮ​ቹም አንድ ደግ ወታ​ደር ጠራ።</verse>
				<verse number="8">ነገ​ሩ​ንም ሁሉ ነግሮ ወደ ኢዮጴ ከተማ ላካ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">በማ​ግ​ሥ​ቱም ሄደው ወደ ከተ​ማ​ዪቱ በር ደረሱ፤ ጴጥ​ሮ​ስም በቀ​ትር ጊዜ ሊጸ​ልይ ወደ ሰገ​ነት ወጥቶ ነበር።</verse>
				<verse number="10">በተ​ራበ ጊዜም ምሳ ሊበላ ወደደ፤ እነ​ር​ሱም እያ​ዘ​ጋጁ ሳሉ ተመ​ስጦ መጣ​በት።</verse>
				<verse number="11">ሰማ​ይም ተከ​ፍቶ በአ​ራቱ ማዕ​ዘን የተ​ያዘ እንደ ታላቅ መጋ​ረጃ ያለ ዕቃ ወደ ምድር ሲወ​ርድ አየ።</verse>
				<verse number="12">በው​ስ​ጡም አራት እግር ያለው እን​ስሳ ሁሉ፥ አራ​ዊ​ትም፥ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ስም፥ የሰ​ማ​ይም ወፎች ነበ​ሩ​በት።</verse>
				<verse number="13">“ጴጥ​ሮስ ሆይ፥ ተነ​ሥና አር​ደህ ብላ” የሚል ቃል ወደ እርሱ መጣ።</verse>
				<verse number="14">ጴጥ​ሮስ ግን፥ “አቤቱ፥ ከቶ አይ​ሆ​ንም፤ ርኩስ፥ የሚ​ያ​ጸ​ይ​ፍም ከቶ በልች አላ​ው​ቅም” አለው።</verse>
				<verse number="15">ዳግ​መ​ኛም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጹሕ ያደ​ረ​ገ​ውን አንተ አታ​ር​ክስ” የሚል ቃል ወደ እርሱ መጣ።</verse>
				<verse number="16">ይህ​ንም ሦስት ጊዜ አለው፤ ወዲ​ያ​ው​ኑም ዕቃዉ ወደ ሰማይ ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="17">ጴጥ​ሮ​ስም ስለ አየው ራእይ ምን እንደ ሆነ ሲያ​ወ​ጣና ሲያ​ወ​ርድ ከቆ​ር​ኔ​ሌ​ዎስ ተል​ከው የመጡ ሰዎች የስ​ም​ዖ​ንን ቤት እየ​ጠ​የቁ በደጅ ቁመው ነበር።</verse>
				<verse number="18">ተጣ​ር​ተ​ውም፦ ጴጥ​ሮስ የተ​ባለ ስም​ዖን በእ​ን​ግ​ድ​ነት በዚያ ይኖር እንደ ሆነ ጠየቁ።</verse>
				<verse number="19">ጴጥ​ሮ​ስም ስለ ታየው ራእይ ሲያ​ወጣ ሲያ​ወ​ርድ መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዲህ አለው፥ “እነሆ፥ ሦስት ሰዎች ይፈ​ል​ጉ​ሃል።</verse>
				<verse number="20">ተነ​ሥና ውረድ፤ ምንም ሳት​ጠ​ራ​ጠር ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሂድ፤ እኔ ልኬ​አ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና።”</verse>
				<verse number="21">ጴጥ​ሮ​ስም ወደ እነ​ዚያ ሰዎች ወረ​ደና፥ “እነሆ፥ የም​ት​ፈ​ል​ጉኝ እኔ ነኝ፤ ለምን መጥ​ታ​ች​ኋል?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">እነ​ር​ሱም፥ “የመቶ አለቃ ቆር​ኔ​ሌ​ዎስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ጻድቅ ሰው ነው፤ በአ​ይ​ሁ​ድም ወገ​ኖች ሁሉ የተ​መ​ሰ​ከ​ረ​ለት ነው፤ ቅዱስ መል​አክ ተገ​ልጦ አን​ተን ወደ ቤቱ እን​ዲ​ጠ​ራህ የም​ታ​ስ​ተ​ም​ረ​ው​ንም እን​ዲ​ሰማ አዝ​ዞ​ታል፤” አሉት።</verse>
				<verse number="23">እር​ሱም ተቀ​ብሎ አሳ​ደ​ራ​ቸው፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም ተነ​ሥቶ አብ​ሮ​አ​ቸው ሄደ፤ በኢ​ዮጴ ከተማ ከሚ​ኖ​ሩት ወን​ድ​ሞ​ችም አብ​ረ​ውት የሄዱ ነበሩ።</verse>
				<verse number="24">በማ​ግ​ሥ​ቱም ወደ ቂሳ​ርያ ከተማ ገባ፤ ቆር​ኔ​ሌ​ዎ​ስም ዘመ​ዶ​ቹ​ንና የቅ​ርብ ወዳ​ጆ​ቹን ጠርቶ ይጠ​ብ​ቃ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="25">ጴጥ​ሮ​ስም በገባ ጊዜ ቆር​ኔ​ሌ​ዎስ ተቀ​በ​ለው፤ ከእ​ግሩ በታ​ችም ወድቆ ሰገ​ደ​ለት።</verse>
				<verse number="26">ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ተነሥ እኔም እንደ አን​ተው ሰው ነኝ” ብሎ አነ​ሣው።</verse>
				<verse number="27">ከእ​ር​ሱም ጋር እየ​ተ​ነ​ጋ​ገረ ገባ፤ ወደ እር​ሱም የመጡ ብዙ ሰዎ​ችን አገኘ።</verse>
				<verse number="28">ጴጥ​ሮ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ለአ​ይ​ሁ​ዳዊ ሰው ሄዶ ከባ​ዕድ ወገን ጋር መቀ​ላ​ቀል እን​ደ​ማ​ይ​ገ​ባው ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ለእኔ ግን ከሰው ማን​ንም ቢሆን እን​ዳ​ል​ጸ​የ​ፍና ርኩስ ነው እን​ዳ​ልል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​የኝ።</verse>
				<verse number="29">አሁ​ንም ስለ ላካ​ች​ሁ​ብኝ ሳል​ጠ​ራ​ጠር ወደ እና​ንተ መጣሁ፤ በምን ምክ​ን​ያት እንደ ጠራ​ች​ሁኝ እጠ​ይ​ቃ​ች​ኋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="30">ቆር​ኔ​ሌ​ዎ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “የዛሬ አራት ቀን በዘ​ጠኝ ሰዓት በዚች ሰዓት በቤቴ ስጸ​ልይ የሚ​ያ​ን​ፀ​ባ​ርቅ ልብስ የለ​በሰ አንድ ሰው በፊቴ ቆሞ ታየኝ።</verse>
				<verse number="31">እን​ዲ​ህም አለኝ፦ ቆር​ኔ​ሌ​ዎስ ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጸሎ​ትህ ተሰማ፤ ምጽ​ዋ​ት​ህም ታሰ​በ​ልህ።</verse>
				<verse number="32">አሁ​ንም ወደ ኢዮጴ ከተማ ላክና በባ​ሕር አቅ​ራ​ቢያ ባለ​ችው በቍ​ር​በት ፋቂው በስ​ም​ዖን ቤት የሚ​ኖ​ረ​ውን ጴጥ​ሮስ የተ​ባ​ለ​ውን ስም​ዖ​ንን ይጥ​ሩ​ልህ፤ እርሱ መጥቶ የም​ት​ድ​ን​በ​ትን ይነ​ግ​ር​ሃል።</verse>
				<verse number="33">ስለ​ዚ​ህም ወዲ​ያ​ውኑ ወደ አንተ ላክሁ፤ ወደ እኛ በመ​ም​ጣ​ት​ህም መል​ካም አደ​ረ​ግህ፤ አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ህን ሁሉ ልን​ሰማ እነሆ፥ እኛ ሁላ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዚህ አለን።”</verse>
				<verse number="34">ጴጥ​ሮ​ስም አፉን ከፈ​ተና እን​ዲህ አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ፊት እን​ደ​ማ​ያ​ዳላ በእ​ው​ነት አየሁ።</verse>
				<verse number="35">ነገር ግን በሕ​ዝብ ሁሉ ዘንድ እር​ሱን የሚ​ፈ​ራና እው​ነ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ በእ​ርሱ ዘንድ የተ​ወ​ደደ ነው።</verse>
				<verse number="36">ቃሉን ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላከ፤ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰላ​ምን ነገ​ራ​ቸው፤ እር​ሱም የሁሉ ገዢ ነው።</verse>
				<verse number="37">ዮሐ​ንስ ከሰ​በ​ከው ጥም​ቀት በኋላ ከገ​ሊላ ጀምሮ በይ​ሁዳ የሆ​ነ​ውን ነገር ሁሉ እና​ንተ ራሳ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="38">ስለ ናዝ​ሬቱ ስለ ኢየ​ሱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ን​ፈስ ቅዱስ በኀ​ይ​ልም እንደ ቀባው፥ እየ​ዞ​ረም መል​ካም እንደ አደ​ረገ፥ ሰይ​ጣን ያሸ​ነ​ፋ​ቸ​ው​ንም እንደ ፈወሰ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="39">በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ እኛ ምስ​ክ​ሮች ነን፤ እር​ሱ​ንም በዕ​ን​ጨት ላይ ሰቅ​ለው ገደ​ሉት።</verse>
				<verse number="40">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ከሙ​ታን ለይቶ አስ​ነ​ሣው፤ በግ​ልጥ እን​ዲ​ታ​ይም አደ​ረ​ገው።</verse>
				<verse number="41">ይኸ​ውም ለሕ​ዝቡ ሁሉ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን አስ​ቀ​ድሞ ለመ​ረ​ጣ​ቸ​ውና ምስ​ክ​ሮች ለሚ​ሆ​ኑት ብቻ ነው እንጂ፤ የመ​ረ​ጣ​ቸው የተ​ባ​ል​ንም እኛ ነን፤ ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይቶ ከተ​ነሣ በኋላ ከእ​ርሱ ጋር የበ​ላን የጠ​ጣ​ንም እኛ ነን።</verse>
				<verse number="42">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በሕ​ያ​ዋ​ንና በሙ​ታን ላይ ፈራጅ ሆኖ የተ​ሾመ እርሱ እንደ ሆነ ለሕ​ዝብ እና​ስ​ተ​ምር ዘንድ አዘ​ዘን።</verse>
				<verse number="43">ለሚ​ያ​ም​ኑ​በ​ትም ሁሉ ኀጢ​አ​ታ​ቸው በስሙ እን​ደ​ሚ​ሰ​ረ​ይ​ላ​ቸው ነቢ​ያት ሁሉ ምስ​ክ​ሮቹ ናቸው።”</verse>
				<verse number="44">ጴጥ​ሮ​ስም ይህን ነገር ሲነ​ግ​ራ​ቸው ይህን ትም​ህ​ርት በሰ​ሙት ሰዎች ሁሉ ላይ መን​ፈስ ቅዱስ ወረደ።</verse>
				<verse number="45">ከጴ​ጥ​ሮስ ጋር የመጡ ከአ​ይ​ሁድ ወገን የሆኑ ምእ​መ​ናን ሁሉ ደነ​ገጡ፤ የመ​ን​ፈስ ቅዱስ ጸጋ በአ​ሕ​ዝብ ላይ ወር​ዶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="46">በልዩ ልዩ ሀገር ቋንቋ ሲና​ገሩ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሲያ​መ​ሰ​ግኑ ሰም​ተ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="47">ጴጥ​ሮ​ስም፥ “እንደ እኛ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ከተ​ቀ​በሉ በኋላ እን​ግ​ዲህ በውኃ እን​ዳ​ይ​ጠ​መቁ ውኃን ሊከ​ለ​ክ​ላ​ቸው የሚ​ችል ማነው?” አለ።</verse>
				<verse number="48">በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ስም እን​ዲ​ጠ​መቁ አዘ​ዛ​ቸው። ከዚ​ህም በኋላ ጥቂት ቀን አብ​ሮ​አ​ቸው እን​ዲ​ቀ​መጥ ጴጥ​ሮ​ስን ማለ​ዱት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">ሐዋ​ር​ያ​ትና በይ​ሁዳ የነ​በሩ ወን​ድ​ሞ​ችም አሕ​ዛብ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እንደ ተቀ​በሉ ሰሙ።</verse>
				<verse number="2">ጴጥ​ሮ​ስም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በወጣ ጊዜ ከአ​ይ​ሁድ ወገን የሆ​ኑት ወን​ድ​ሞች ተቃ​ወ​ሙት።</verse>
				<verse number="3">“ወደ አል​ተ​ገ​ረ​ዙት ሰዎች ቤት ገብ​ተህ አብ​ረ​ሃ​ቸው በል​ተ​ሃል” አሉት።</verse>
				<verse number="4">ጴጥ​ሮ​ስም ከመ​ጀ​መ​ሪያ ጀምሮ ይነ​ግ​ራ​ቸው ጀመረ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">“በኢ​ዮጴ ከተማ ሳለሁ ስጸ​ልይ ተመ​ስጦ መጣ​ብ​ኝና ራእይ አየሁ፤ ታላቅ መጋ​ረጃ የመ​ሰለ ዕቃ በአ​ራቱ ማዕ​ዘን ተይዞ ከሰ​ማይ ወረደ፤ ወደ እኔም መጣ።</verse>
				<verse number="6">በው​ስ​ጡም አራት እግር ያላ​ቸው እን​ስ​ሳ​ንና አራ​ዊ​ትን፥ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ች​ንም፥ የሰ​ማይ ወፎ​ች​ንም አየሁ።</verse>
				<verse number="7">‘ጴጥ​ሮስ ሆይ፥ ተነ​ሥና አር​ደህ ብላ’ የሚ​ለ​ኝ​ንም ቃል ሰማሁ።</verse>
				<verse number="8">‘አቤቱ፥ ከቶ አይ​ሆ​ንም፤ ንጹሕ ያል​ሆነ ርኩስ ነገር ወደ አፌ ገብቶ አያ​ው​ቅም’ አልሁ።</verse>
				<verse number="9">ደግ​ሞም፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጹሕ ያደ​ረ​ገ​ውን አንተ አታ​ር​ክ​ሰው’ የሚል ቃል ከሰ​ማይ መለ​ሰ​ልኝ።</verse>
				<verse number="10">እን​ዲ​ህም መላ​ልሶ ሦስት ጊዜ ነገ​ረኝ፤ ዳግ​መ​ኛም ሁሉ ተጠ​ቅ​ልሎ ወደ ሰማይ ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="11">በዚ​ያ​ችም ሰዓት ከቂ​ሳ​ርያ ወደ እኔ የተ​ላኩ ሦስት ሰዎች መጡ፤ እኔ ባለ​ሁ​በት ግቢ በርም ቆሙ።</verse>
				<verse number="12">መን​ፈስ ቅዱ​ስም፦ ‘ሳት​ጠ​ራ​ጠር አብ​ረ​ሃ​ቸው ሂድ’ አለኝ፤ እነ​ዚህ ስድ​ስቱ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ተከ​ት​ለ​ውኝ መጡና ወደ​ዚያ ሰው ቤት ገባን።</verse>
				<verse number="13">እር​ሱም በቤቱ ቆሞ ሳለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ እን​ዳየ ‘ወደ ኢዮጴ ከተማ ልከህ ጴጥ​ሮስ የተ​ባ​ለ​ውን ስም​ዖ​ንን ይጥ​ሩ​ልህ።</verse>
				<verse number="14">አን​ተና ቤተ ሰቦ​ችህ ሁሉ የም​ት​ድ​ኑ​በ​ትን ነገር እርሱ ይነ​ግ​ር​ሃል’ እንደ አለው ነገ​ረን።</verse>
				<verse number="15">ላስ​ተ​ም​ራ​ቸው በጀ​መ​ርሁ ጊዜም ቀድሞ በእኛ ላይ እንደ ወረደ ሁሉ መን​ፈስ ቅዱስ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ ወረደ።</verse>
				<verse number="16">‘ዮሐ​ንስ በውኃ አጠ​መቀ፤ እና​ንተ ግን፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ትጠ​መ​ቃ​ላ​ችሁ’ ያለ​ውን የጌ​ታ​ች​ንን ቃል ዐሰ​ብሁ።</verse>
				<verse number="17">እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ለአ​መ​ን​ነው ለእኛ እንደ ሰጠን፥ ያን ጸጋ​ውን እንደ እኛ አስ​ተ​ካ​ክሎ ከሰ​ጣ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልከ​ለ​ክል የም​ችል እኔ ማነኝ?”</verse>
				<verse number="18">ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ ዝም አሉ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ሕ​ዛብ ደግሞ ለሕ​ይ​ወት የሚ​ሆን ንስ​ሓን ሰጣ​ቸው እንጃ” እያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ።</verse>
				<verse number="19">በእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖስ ሞት ምክ​ን​ያት የተ​በ​ተ​ኑት ግን፤ ወደ ፊንቄ ወደ ቆጵ​ሮ​ስና ወደ አን​ጾ​ኪያ ደረሱ፤ ቃሉ​ንም ለአ​ይ​ሁድ ብቻ እንጂ ለአ​ን​ድስ እንኳ አይ​ና​ገ​ሩም ነበር።</verse>
				<verse number="20">ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ወደ አን​ጾ​ኪያ ሄደው ለአ​ረ​ማ​ው​ያን የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ነገር ያስ​ተ​ማሩ የቆ​ጵ​ሮ​ስና የቄ​ሬና ሰዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="21">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ወደ ጌታም ተመ​ል​ሰው ያመኑ ሰዎች ቍጥ​ራ​ቸው በዛ።</verse>
				<verse number="22">ስለ እነ​ርሱ የተ​ነ​ገ​ረ​ውም ይህ ነገር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለ​ችው ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ዘንድ ተሰማ፤ በር​ና​ባ​ስ​ንም ወደ አን​ጾ​ኪያ ላኩት።</verse>
				<verse number="23">በደ​ረሰ ጊዜም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጸጋ አየና ደስ አለው፤ በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸን​ተው ይኖሩ ዘንድ መከ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">ደግ ሰው፥ መን​ፈስ ቅዱስ ያደ​ረ​በት፥ ሃይ​ማ​ኖ​ተ​ኛም ነበ​ርና፤ በጌ​ታ​ች​ንም አም​ነው ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ ተጨ​መሩ።</verse>
				<verse number="25">ከዚ​ህም በኋላ በር​ና​ባስ ሳው​ልን ሊፈ​ልግ ወደ ጠር​ሴስ ሄደ፤ በአ​ገ​ኘ​ውም ጊዜ ወደ አን​ጾ​ኪያ ወሰ​ደው።</verse>
				<verse number="26">በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም አንድ ዓመት አብ​ረው ተቀ​መጡ፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንም አስ​ተ​ማሩ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም መጀ​መ​ሪያ በአ​ን​ጾ​ኪያ ክር​ስ​ቲ​ያን ተብ​ለው ተጠሩ።</verse>
				<verse number="27">ያን​ጊ​ዜም ነቢ​ያት ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አን​ጾ​ኪያ ወረዱ።</verse>
				<verse number="28">ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም አጋ​ቦስ የተ​ባለ አንድ ሰው ተነ​ሥቶ በዓ​ለም ሁሉ ጽኑ ረኃብ እን​ደ​ሚ​መጣ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ተገ​ል​ጦ​ለት ተና​ገረ፤ ይህም በቄ​ሣር ቀላ​ው​ዴ​ዎስ ዘመን ሆነ።</verse>
				<verse number="29">ከዚ​ህም በኋላ ደቀ መዛ​ሙ​ርት እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው የሚ​ች​ሉ​ትን ያህል አወ​ጣ​ጥ​ተው በይ​ሁዳ ሀገር ለሚ​ኖ​ሩት ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ርዳ​ታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ።</verse>
				<verse number="30">እን​ደ​ዚ​ህም አድ​ር​ገው በበ​ር​ና​ባ​ስና በሳ​ውል እጅ ወደ ቀሳ​ው​ስት ላኩት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">በዚ​ያም ወራት ሄሮ​ድስ የቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንን ሹሞች ያዛ​ቸው፤ መከ​ራም አጸ​ና​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">የዮ​ሐ​ን​ስ​ንም ወን​ድም ያዕ​ቆ​ብን በሰ​ይፍ ገደ​ለው።</verse>
				<verse number="3">አይ​ሁ​ድ​ንም ደስ እን​ዳ​ላ​ቸው አይቶ ጴጥ​ሮ​ስን ደግሞ ያዘው፤ ያን​ጊ​ዜም የፋ​ሲካ በዓል ነበር።</verse>
				<verse number="4">ይዞም ወኅኒ ቤት አስ​ገ​ባው፤ ለሚ​ጠ​ብ​ቁት ለዐ​ሥራ ስድ​ስቱ ወታ​ደ​ሮ​ችም አሳ​ልፎ ሰጠው፤ ከፋ​ሲ​ካም በኋላ ወደ ሕዝብ ሊያ​ቀ​ር​በው ወድዶ ነበር።</verse>
				<verse number="5">ጴጥ​ሮ​ስ​ንም በወ​ኅኒ ቤት ይጠ​ብ​ቁት ነበር፤ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ዘወ​ትር ስለ እርሱ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ልዩ ነበር።</verse>
				<verse number="6">ሄሮ​ድ​ስም ማለዳ ያቀ​ር​በው ዘንድ በወ​ደ​ደ​ባት በዚ​ያች ሌሊት ጴጥ​ሮስ ሁለ​ቱን እጆ​ቹን በሰ​ን​ሰ​ለት ታስሮ በሁ​ለት ወታ​ደ​ሮች መካ​ከል ተኝቶ ነበር፤ ጠባ​ቂ​ዎ​ችም የወ​ኅኒ ቤቱን በር ይጠ​ብቁ ነበር።</verse>
				<verse number="7">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ወርዶ በአ​ጠ​ገቡ ቆመ፤ በቤ​ትም ውስጥ ብር​ሃን ሆነ፤ ጴጥ​ሮ​ስ​ንም ጎኑን ነክቶ ቀሰ​ቀ​ሰ​ውና፥ “ፈጥ​ነህ ተነሥ” አለው፥ ሰን​ሰ​ለ​ቶ​ቹም ከእ​ጆቹ ወል​ቀው ወደቁ።</verse>
				<verse number="8">መል​አ​ኩም፥ “ወገ​ብ​ህን ታጠቅ፥ ጫማ​ህ​ንም ተጫማ” አለው፤ እንደ አዘ​ዘ​ውም አደ​ረገ፤ “ልብ​ስ​ህ​ንም ልበ​ስና ተከ​ተ​ለኝ” አለው።</verse>
				<verse number="9">ተከ​ት​ሎ​ትም ወጣ፤ ጴጥ​ሮስ ግን ራእይ የሚ​ያይ ይመ​ስ​ለው ነበረ እንጂ በመ​ል​አኩ የሚ​ደ​ረ​ገው ነገር እው​ነት እንደ ሆነ አላ​ወ​ቀም ነበር።</verse>
				<verse number="10">መጀ​መ​ሪ​ያ​ው​ንና ሁለ​ተ​ኛ​ውን ዘብ አል​ፈው ወደ ከተማ ወደ​ም​ት​ወ​ስ​ደው ወደ ብረቱ መዝ​ጊያ ደረሱ፤ ያን​ጊ​ዜም መዝ​ጊ​ያው ራሱ ተከ​ፈ​ተ​ላ​ቸው፤ ወጥ​ተ​ውም በአ​ንድ ስላች መን​ገድ ሄዱ፤ መል​አ​ኩም ጴጥ​ሮ​ስን ትቶት ሄደ።</verse>
				<verse number="11">ያን​ጊ​ዜም የጴ​ጥ​ሮስ ልቡና ተመ​ለ​ሰ​ለ​ትና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ኩን ልኮ ከሄ​ሮ​ድስ እጅና የአ​ይ​ሁድ ሕዝብ ይጠ​ብ​ቁት ከነ​በ​ረው ሁሉ እንደ አዳ​ነኝ በእ​ው​ነት አሁን ዐወ​ቅሁ” አለ።</verse>
				<verse number="12">ከዚ​ህም በኋላ በአ​ስ​ተ​ዋለ ጊዜ ብዙ​ዎች ወን​ድ​ሞች ተሰ​ብ​ስ​በው ይጸ​ል​ዩ​በት ወደ ነበ​ረው ማር​ቆስ ወደ​ተ​ባ​ለው ወደ ዮሐ​ንስ እናት ወደ ማር​ያም ቤት ሄደ።</verse>
				<verse number="13">ጴጥ​ሮ​ስም በሩን አን​ኳኳ፤ ሮዴ የም​ት​ባል ብላ​ቴ​ናም ልት​ከ​ፍ​ት​ለት መጣች።</verse>
				<verse number="14">የጴ​ጥ​ሮ​ስም ድምፅ መሆ​ኑን ዐውቃ ከደ​ስታ የተ​ነሣ አል​ከ​ፈ​ተ​ች​ለ​ትም፤ ነገር ግን ጴጥ​ሮስ በበር ቆሞ ሳለ ሮጣ ነገ​ረ​ቻ​ቸው።</verse>
				<verse number="15">እነ​ር​ሱም “አብ​ደ​ሻ​ልን? አንድ ጊዜ ታገሺ” አሉ​አት፤ እር​ስዋ ግን እርሱ እንደ ሆነ ታረ​ጋ​ግጥ ነበር። እነ​ር​ሱም፥ “ምና​ል​ባት መል​አኩ ይሆ​ናል” አሉ።</verse>
				<verse number="16">ጴጥ​ሮስ ግን በሩን ማን​ኳ​ኳ​ቱን ቀጠለ፤ ከፍ​ተ​ውም ባዩት ጊዜ ተደ​ነቁ።</verse>
				<verse number="17">እርሱ ግን ዝም እን​ዲሉ በእጁ አመ​ለ​ከ​ታ​ቸው፤ ከወ​ኅኒ ቤትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አወ​ጣው ነገ​ራ​ቸው፤ “ይህ​ንም ለያ​ዕ​ቆ​ብና ለወ​ን​ድ​ሞች ሁሉ ንገሩ” አላ​ቸው፤ ከዚ​ያም ወጥቶ ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።</verse>
				<verse number="18">በነጋ ጊዜም ወታ​ደ​ሮች፥ “ጴጥ​ሮስ ምን ሆነ?” ብለው ታወኩ።</verse>
				<verse number="19">ሄሮ​ድስ ግን አስ​ፈ​ልጎ ባጣው ጊዜ ጠባ​ቂ​ዎ​ችን መረ​መረ፤ ይገ​ድ​ሉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ አዘዘ፤ ከዚ​ህም በኋላ ከይ​ሁዳ ወደ ቂሳ​ርያ ወርዶ በዚያ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="20">ሄሮ​ድ​ስም በጢ​ሮ​ስና በሲ​ዶና ሰዎች ተቈ​ጥቶ ነበር፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ወደ እርሱ መጥ​ተው የን​ጉ​ሡን ቢት​ወ​ደድ በላ​ስ​ጦ​ስን እን​ዲ​ያ​ስ​ታ​ር​ቃ​ቸው ማለ​ዱት፤ የሀ​ገ​ራ​ቸው ምግብ ከን​ጉሥ ሄር​ድስ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="21">ከዚ​ህም በኋላ አንድ ቀን ሄሮ​ድስ ልብሰ መን​ግ​ሥ​ቱን ለብሶ፥ በአ​ደ​ባ​ባይ ተገ​ኝቶ ይፈ​ርድ ጀመረ።</verse>
				<verse number="22">ሕዝ​ቡም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ነው፤ የሰው ቃልም አይ​ደ​ለም” እያሉ ጮኹ።</verse>
				<verse number="23">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ስለ አል​ሰጠ ያን​ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ቀሠ​ፈው፤ ተል​ቶም ሞተ።</verse>
				<verse number="24">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ከፍ አለ፤ በዛም።</verse>
				<verse number="25">በር​ና​ባ​ስና ሳው​ልም አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውን ፈጽ​መው ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ፤ ማር​ቆስ የተ​ባ​ለ​ውን ዮሐ​ን​ስ​ንም አስ​ከ​ት​ለ​ውት መጡ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">በአ​ን​ጾ​ኪያ በነ​በ​ረ​ችው ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ነቢ​ያ​ትና መም​ህ​ራን ነበሩ፤ እነ​ር​ሱም በር​ና​ባስ፥ ኔጌር የተ​ባ​ለው ስም​ዖን፥ የቀ​ሬ​ናው ሉቅ​ዮስ፥ ከአ​ራ​ተ​ኛው ክፍል ገዢ ከሄ​ሮ​ድስ ጋር ያደ​ገው ምናሔ፥ ሳው​ልም ነበሩ።</verse>
				<verse number="2">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ሲሠሩ፥ ሲጾ​ሙም መን​ፈስ ቅዱስ፥ “በር​ና​ባ​ስ​ንና ሳው​ልን እኔ ለፈ​ለ​ግ​ኋ​ቸው ሥራ ለዩ​ልኝ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ያን​ጊ​ዜም ከጾ​ሙና ከጸ​ለዩ፥ እጃ​ቸ​ው​ንም በራ​ሳ​ቸው ላይ ከጫ​ኑ​ባ​ቸው በኋላ ላኩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ከመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ተል​ከው ወደ ሴሌ​ው​ቅያ ወረዱ፤ ከዚ​ያም በመ​ር​ከብ ወደ ቆጵ​ሮስ ሄዱ።</verse>
				<verse number="5">ወደ ሰል​ሚና ሀገ​ርም ገብ​ተው በአ​ይ​ሁድ ምኵ​ራ​ቦች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አስ​ተ​ማሩ፤ ዮሐ​ን​ስም እየ​አ​ገ​ለ​ገ​ላ​ቸው ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበር።</verse>
				<verse number="6">በደ​ሴ​ቲ​ቱም ሁሉ ሲዘ​ዋ​ወሩ ጳፉ ወደ​ም​ት​ባል ሀገር ደረሱ፤ በዚ​ያም አንድ አይ​ሁ​ዳዊ የሆነ ሐሰ​ተኛ ነቢ​ይና አስ​ማ​ተኛ ሰው አገኙ፤ ስሙም በር​ያ​ሱስ ይባ​ላል።</verse>
				<verse number="7">እር​ሱም ብልህ ሰው በሆነ ሰር​ግ​ዮስ ጳው​ሎስ በሚ​ባል አገረ ገዢ ዘንድ ይኖር ነበረ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ሊሰማ ወድዶ በር​ና​ባ​ስ​ንና ሳው​ልን ወደ እርሱ ጠራ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">አስ​ማ​ተ​ኛው ኤል​ማ​ስም የስሙ ትር​ጓሜ እን​ዲህ ነበ​ረና፥ ገዥ​ውን ከማ​መን ሊከ​ለ​ክ​ለው ፈልጎ ተቃ​ወ​ማ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ጳው​ሎስ በተ​ባ​ለው በሳ​ውል ላይም ቅዱስ መን​ፈስ ሞላ​በት፤ አተ​ኵ​ሮም ተመ​ለ​ከ​ተው።</verse>
				<verse number="10">እን​ዲ​ህም አለው፥ “ሽን​ገ​ላ​ንና ክፋ​ትን ሁሉ የተ​መ​ላህ፥ የሰ​ይ​ጣን ልጅ፥ የጽ​ድቅ ሁሉ ጠላት ሆይ፥ የቀ​ና​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ማጣ​መ​ም​ህን ትተው ዘንድ እንቢ አል​ህን?</verse>
				<verse number="11">እነሆ፥ አሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በአ​ንተ ላይ ነው፤ ዕው​ርም ትሆ​ና​ለህ፤ እስከ ጊዜ​ውም ፀሐ​ይን አታ​ይም፤” ወዲ​ያ​ው​ኑም ታወረ፤ ጨለ​ማም ዋጠው፤ የሚ​መ​ራ​ውም ፈለገ።</verse>
				<verse number="12">አገረ ገዢ​ውም የሆ​ነ​ውን በአየ ጊዜ ተገ​ረመ፤ በጌ​ታ​ችን ትም​ህ​ር​ትም አመነ።</verse>
				<verse number="13">ከዚ​ህም በኋላ እነ ጳው​ሎስ ከጳፉ ከተማ ወጥ​ተው ሄዱና የጵ​ን​ፍ​ልያ አው​ራጃ ወደ​ም​ት​ሆን ወደ ጰር​ጌን ገቡ፤ ዮሐ​ንስ ግን ትቶ​አ​ቸው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሰ።</verse>
				<verse number="14">እነ​ር​ሱም ከጰ​ር​ጌን አል​ፈው የጲ​ስ​ድያ አው​ራጃ ወደ​ም​ት​ሆን ወደ አን​ጾ​ኪያ ደረሱ፤ በሰ​ን​በት ቀንም ወደ ምኵ​ራብ ገብ​ተው ተቀ​መጡ።</verse>
				<verse number="15">ኦሪ​ት​ንና ነቢ​ያ​ትን ካነ​በቡ በኋ​ላም የም​ኵ​ራቡ አለ​ቆች፥ “እና​ንተ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ለሕ​ዝብ ሊነ​ገር የሚ​ገ​ባው የም​ክር ቃል እንደ አላ​ችሁ ተና​ገሩ” ብለው ላኩ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">ጳው​ሎ​ስም ተነ​ሥቶ ዝም እን​ዲሉ አዘ​ዘና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንት የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎ​ችና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የም​ት​ፈሩ ሁሉ፥ ስሙ።</verse>
				<verse number="17">የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ አም​ላክ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን መረ​ጣ​ቸው፤ ወገ​ኖ​ቹ​ንም በተ​ሰ​ደ​ዱ​በት በም​ድረ ግብፅ ከፍ ከፍ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ ከዚ​ያም ከፍ ባለ ክንዱ አወ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">አርባ ዘመ​ንም በም​ድረ በዳ መገ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">ሰባ​ቱን የከ​ነ​ዓ​ንን አሕ​ዛብ አጥ​ፍቶ ምድ​ራ​ቸ​ውን አወ​ረ​ሳ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">ከዚ​ህም በኋላ አራት መቶ አምሳ ዓመት እስከ ነቢዩ እስከ ሳሙ​ኤል ዘመን ድረስ መሳ​ፍ​ን​ትን ሾመ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">ከዚ​ያም ወዲያ ንጉሥ ያነ​ግ​ሥ​ላ​ቸው ዘንድ ለመኑ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከብ​ን​ያም ነገድ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ሰው የቂ​ስን ልጅ ሳኦ​ልን አርባ ዓመት አነ​ገ​ሠ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">እር​ሱ​ንም ሻረው፤ ከእ​ር​ሱም በኋላ ዳዊ​ትን አነ​ገ​ሠ​ላ​ቸው፤ ‘የእ​ሴ​ይን ልጅ ዳዊ​ትን ፈቃ​ዴን ሁሉ የሚ​ፈ​ጽም እንደ ልቤም የታ​መነ ሰው ሆኖ አገ​ኘ​ሁት’ ብሎ መሰ​ከ​ረ​ለት።</verse>
				<verse number="23">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተስፋ እንደ ሰጣ​ቸው ከዳ​ዊት ዘር ለእ​ስ​ራ​ኤል መድ​ኀ​ኒት አድ​ርጎ ኢየ​ሱ​ስን አመ​ጣ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">እርሱ ከመ​ም​ጣቱ አስ​ቀ​ድሞ ዮሐ​ንስ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ሁሉ የን​ስሓ ጥም​ቀ​ትን ሰበ​ከ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">ዮሐ​ን​ስም መል​እ​ክ​ቱን ሲፈ​ጽም እን​ዲህ አላ​ቸው፦ ‘እኔን ለምን ትጠ​ራ​ጠ​ሩ​ኛ​ላ​ችሁ? እር​ሱን አይ​ደ​ለ​ሁም፤ የጫ​ማ​ውን ማዘ​ቢያ ከእ​ግሩ ልፈታ የማ​ይ​ገ​ባኝ ከእኔ በኋላ እነሆ፥ ይመ​ጣል።’</verse>
				<verse number="26">“እና​ንተ ከአ​ብ​ር​ሃም ወገን የተ​ወ​ለ​ዳ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የም​ት​ፈሩ፥ ይህ የሕ​ይ​ወት ቃል ለእ​ና​ንተ ተል​ኮ​አል።</verse>
				<verse number="27">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩና አለ​ቆ​ቻ​ቸው ግን እር​ሱን አላ​ወ​ቁም፤ የነ​ቢ​ያት መጻ​ሕ​ፍ​ት​ንም በየ​ሰ​ን​በቱ ሁሉ ሲያ​ነቡ አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉ​ትም፤ ነገር ግን ይሙት በቃ ፈረ​ዱ​በት፥ ስለ እርሱ የተ​ጻ​ፈ​ው​ንም ሁሉ ፈጸ​ሙ​በት።</verse>
				<verse number="28">ለሞ​ትም የሚ​ያ​በቃ ምንም በደል ባላ​ገ​ኙ​በት ጊዜ እን​ዲ​ገ​ድ​ለው ጲላ​ጦ​ስን ለመ​ኑት።</verse>
				<verse number="29">ስለ እር​ሱም የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ ከፈ​ጸሙ በኋላ ከመ​ስ​ቀል አው​ር​ደው በመ​ቃ​ብር ቀበ​ሩት።</verse>
				<verse number="30">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ከሙ​ታን ለይቶ አስ​ነ​ሣው።</verse>
				<verse number="31">ከተ​ነ​ሣም በኋላ ከገ​ሊላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አብ​ረ​ውት ለወ​ጡት ብዙ ቀን ተገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው። እነ​ር​ሱም በሕ​ዝብ ዘንድ ምስ​ክ​ሮች ሆኑት።</verse>
				<verse number="32">“እኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ያና​ገ​ረ​ላ​ቸ​ውን ተስፋ እን​ነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለን።</verse>
				<verse number="33">በሁ​ለ​ተ​ኛው መዝ​ሙር፦ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለ​ድ​ሁህ’ እን​ዳለ ኢየ​ሱ​ስን አስ​ነ​ሥቶ ተስ​ፋ​ውን ለእኛ ለል​ጆ​ቻ​ቸው ፈጽ​ሞ​አል።</verse>
				<verse number="34">መፍ​ረስ መበ​ስ​በ​ስ​ንም እን​ዳ​ያይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሙ​ታን ለይቶ እን​ዳ​ስ​ነ​ሣው እን​ዲህ አለ፦ ‘የታ​መ​ነ​ውን የዳ​ዊ​ትን ቅዱስ ተስፋ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="35">በሌላ ስፍ​ራም እን​ዲህ ይላል፦ ‘ጻድ​ቅ​ህን መፍ​ረስ መበ​ስ​በ​ስን ያይ ዘንድ አት​ሰ​ጠ​ውም።’</verse>
				<verse number="36">ዳዊት ግን በዘ​መኑ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ አገ​ል​ግ​ሎ​አል፤ እንደ አባ​ቶቹ ሞተ፥ ተቀ​በ​ረም፤ መፍ​ረስ መበ​ስ​በ​ስ​ንም አይ​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="37">ይህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያስ​ነ​ሣው ግን መፍ​ረስ መበ​ስ​በ​ስን አላ​የም።</verse>
				<verse number="38">እን​ግ​ዲህ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ በእ​ርሱ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ እን​ደ​ሚ​ሰ​ረ​ይ​ላ​ችሁ ተስፋ የሰ​ጣ​ች​ሁን ዕወቁ።</verse>
				<verse number="39">ከሁ​ሉም ይልቅ በሙሴ ሕግ መጽ​ደቅ የተ​ሳ​ና​ችሁ ናችሁ። በእ​ርሱ ግን ያመነ ሁሉ ይጸ​ድ​ቃል።</verse>
				<verse number="40">እን​ግ​ዲህ እን​ዲህ የሚ​ለው የነ​ቢ​ያት ቃል እን​ዳ​ይ​ደ​ር​ስ​ባ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ።</verse>
				<verse number="41">‘እነሆ፥ እና​ንተ የም​ታ​ቃ​ልሉ፥ እዩ፤ ተደ​ነ​ቁም፤ ያለ​ዚያ ግን ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ፤ ማንም ቢነ​ግ​ራ​ችሁ የማ​ታ​ም​ኑ​ትን ሥራ እኔ በዘ​መ​ና​ችሁ እሠ​ራ​ለ​ሁና።’ ”</verse>
				<verse number="42">ከም​ኵ​ራ​ብም ከወጡ በኋላ ይህን ነገር በሁ​ለ​ተ​ኛው ሰን​በት እን​ዲ​ነ​ግ​ሩ​አ​ቸው ማለ​ዱ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="43">ጉባ​ኤ​ውም በተ​ፈታ ጊዜ ከአ​ይ​ሁ​ድና ወደ ይሁ​ዲ​ነት ከተ​መ​ለ​ሱት ከደ​ጋጉ ሰዎች ብዙ​ዎች ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስን ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ይድኑ ዘንድ እያ​ስ​ረዱ ነገ​ሯ​ቸው።</verse>
				<verse number="44">በሁ​ለ​ተ​ኛው ሰን​በ​ትም የከ​ተ​ማው ሰዎች ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ይሰሙ ዘንድ ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="45">አይ​ሁ​ድም የተ​ሰ​በ​ሰ​በ​ውን ብዙ ሕዝብ ባዩ ጊዜ ቀኑ​ባ​ቸው፤ እየ​ተ​ሳ​ደ​ቡም ጳው​ሎስ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ተቃ​ወሙ።</verse>
				<verse number="46">ጳው​ሎ​ስና በር​ና​ባ​ስም ደፍ​ረው እን​ዲህ ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ለእ​ና​ንተ አስ​ቀ​ድሞ ልን​ነ​ግ​ራ​ችሁ ይገ​ባል፤ እንቢ ብት​ሉና ራሳ​ች​ሁን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የተ​ዘ​ጋጀ ባታ​ደ​ርጉ ግን እነሆ፥ ወደ አሕ​ዛብ እን​መ​ለ​ሳ​ለን።</verse>
				<verse number="47">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ እስከ ምድር ዳርቻ ላሉት ሁሉ መድ​ኀ​ኒት ትሆን ዘንድ ለአ​ሕ​ዛብ ብር​ሃን አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ” ብሎ አዝ​ዞ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="48">አሕ​ዛ​ብም ይህን ሰም​ተው ደስ አላ​ቸው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል አከ​በሩ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትም የተ​ዘ​ጋጁ ሁሉ አመኑ።</verse>
				<verse number="49">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል በሀ​ገሩ ሁሉ ተዳ​ረሰ።</verse>
				<verse number="50">አይ​ሁድ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈሩ የከ​በሩ ሴቶ​ች​ንና የከ​ተ​ማ​ውን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች አነ​ሳ​ሡ​አ​ቸው፤ በጳ​ው​ሎ​ስና በበ​ር​ና​ባስ ላይም ስደ​ትን አስ​ነሡ፤ ከሀ​ገ​ራ​ቸ​ውም አባ​ረ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="51">እነ​ርሱ ግን የእ​ግ​ራ​ቸ​ውን ትቢያ አራ​ግ​ፈ​ው​ባ​ቸው ወደ ኢቆ​ን​ዮን ሄዱ።</verse>
				<verse number="52">መን​ፈስ ቅዱ​ስም በደቀ መዛ​ሙ​ርት ላይ ሞላ፤ ደስም አላ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">ኢቆ​ን​ዮን በም​ት​ባል ከተ​ማም እንደ ሁል​ጊ​ዜው ወደ አይ​ሁድ ምኵ​ራብ ገቡ፤ ከአ​ይ​ሁ​ድና ከአ​ረ​ማ​ው​ያ​ንም ብዙ ሰዎች እስ​ኪ​ያ​ምኑ ድረስ አስ​ተ​ማሩ።</verse>
				<verse number="2">ማመ​ንን እንቢ ያሉት የአ​ይ​ሁድ ወገ​ኖች ግን የአ​ሕ​ዝ​ብን ልብ በወ​ን​ድ​ሞች ላይ አነ​ሣሡ፤ አስ​ከ​ፉም።</verse>
				<verse number="3">በጌ​ታም ፊት ደፍ​ረው እያ​ስ​ተ​ማሩ፥ እር​ሱም የጸ​ጋ​ውን ቃል ምስ​ክር እያ​ሳ​የ​ላ​ቸው፥ በእ​ጃ​ቸ​ውም ድንቅ ሥራና ተአ​ም​ራ​ትን እያ​ደ​ረ​ገ​ላ​ቸው ብዙ ወራት ኖሩ።</verse>
				<verse number="4">የከ​ተ​ማ​ውም ሕዝብ ሁሉ ተለ​ያዩ፤ እኩ​ሌ​ቶቹ ወደ አይ​ሁድ፥ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም ወደ ሐዋ​ር​ያት ሆኑ።</verse>
				<verse number="5">አሕ​ዛ​ብና አይ​ሁድ ግን ከአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸው ጋር ሊያ​ን​ገ​ላ​ት​ዋ​ቸ​ውና በድ​ን​ጋይ ሊደ​በ​ድ​ቧ​ቸው ተነሡ።</verse>
				<verse number="6">ሐዋ​ር​ያ​ትም ይህን ዐው​ቀው ወደ ሊቃ​ኦ​ንያ ከተ​ሞች ወደ ልስ​ጥ​ራ​ንና ወደ ደር​ቤን፥ ወደ​የ​አ​ው​ራ​ጃ​ውም ሸሹ።</verse>
				<verse number="7">በዚ​ያም ወን​ጌ​ልን ሰበኩ።</verse>
				<verse number="8">በል​ስ​ጥ​ራ​ንም እግሩ የሰ​ለለ፥ ከእ​ና​ቱም ማኅ​ፀን ጀምሮ ሽባ የሆነ፥ ከቶም ሂዶ የማ​ያ​ውቅ አንድ ሰው ተቀ​ምጦ ነበር።</verse>
				<verse number="9">እር​ሱም ጳው​ሎ​ስን ሲያ​ስ​ተ​ምር ሰማው፤ ጳው​ሎ​ስም ትኩር ብሎ ተመ​ለ​ከ​ተው፤ እም​ነት እን​ዳ​ለ​ውና እን​ደ​ሚ​ድ​ንም ተረዳ።</verse>
				<verse number="10">ድም​ፁ​ንም ከፍ አድ​ርጎ፥ “ተነ​ሥና ቀጥ ብለህ በእ​ግ​ርህ ቁም እል​ሃ​ለሁ” አለው፤ ወዲ​ያ​ው​ኑም ተነ​ሥቶ ተመ​ላ​ለሰ።</verse>
				<verse number="11">ሕዝ​ቡም ጳው​ሎስ ያደ​ረ​ገ​ውን ባዩ ጊዜ፥ “አማ​ል​ክት ሰዎ​ችን መስ​ለው ወደ እኛ ወረዱ” እያሉ በሊ​ቃ​ኦ​ንያ ቋንቋ ጮኹ።</verse>
				<verse number="12">በር​ና​ባ​ስን ድያ አሉት፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም የት​ም​ህ​ርቱ መሪ እርሱ ነበ​ርና ሄር​ሜን ብለው ጠሩት።</verse>
				<verse number="13">በከ​ተ​ማ​ውም ፊት ለፊት ቤተ መቅ​ደስ ያለው የድያ ካህን ኮር​ማ​ዎ​ች​ንና የአ​በባ አክ​ሊ​ሎ​ችን ወደ ደጃፍ አመጣ፤ ከሕ​ዝ​ቡም ጋር ሆኖ ሊሠ​ዋ​ላ​ቸው ወደደ።</verse>
				<verse number="14">ሐዋ​ር​ያት በር​ና​ባ​ስና ጳው​ሎ​ስም በሰሙ ጊዜ፥ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀደዱ፤ ፈጥ​ነ​ውም እየ​ጮኹ ወደ ሕዝቡ ሄዱ።</verse>
				<verse number="15">እን​ዲ​ህም አሉ​አ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰዎች፥ ይህን ነገር ለምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ? እኛስ እንደ እና​ንተ የም​ን​ሞት ሰዎች አይ​ደ​ለ​ን​ምን? ነገር ግን ይህን ከንቱ ነገር ትታ​ችሁ ሰማ​ይና ምድ​ርን፥ ባሕ​ር​ንም በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም ያለ​ውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትመ​ለሱ ዘንድ ወን​ጌ​ልን እና​ስ​ተ​ም​ራ​ች​ኋ​ለን።</verse>
				<verse number="16">አሕ​ዛ​ብን ሁሉ በቀ​ድሞ ዘመን እንደ ነበ​ሩ​በት እንደ ጠባ​ያ​ቸው ሊኖሩ ተዋ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">ከዚ​ህም ሁሉ ጋር መል​ካም ሥራን እየ​ሠራ ከሰ​ማይ ዝና​ምን፥ ፍሬ የሚ​ሆ​ን​በ​ት​ንም ወራት ሲሰ​ጠን፥ ልባ​ች​ን​ንም በመ​ብ​ልና በደ​ስታ ሲሞ​ላው ራሱን ያለ ምስ​ክር አል​ተ​ወም።”</verse>
				<verse number="18">ይህ​ንም ብለው እን​ዳ​ይ​ሠ​ዉ​ላ​ቸው ሕዝ​ቡን በግድ አስ​ተ​ዉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">አይ​ሁ​ድም ከአ​ን​ጾ​ኪ​ያና ከኢ​ቆ​ንያ መጡ፤ ልባ​ቸ​ው​ንም እን​ዲ​ያ​ጠ​ኑ​ባ​ቸው አሕ​ዛ​ብን አባ​በ​ሉ​አ​ቸው፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም እየ​ጐ​ተቱ ከከ​ተማ ውጭ አው​ጥ​ተው በድ​ን​ጋይ ደበ​ደ​ቡት፤ የሞ​ተም መሰ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ከበ​ቡት፤ ነገር ግን ተነ​ሥቶ አብ​ሮ​አ​ቸው ወደ ከተማ ገባ፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም ከበ​ር​ና​ባስ ጋር ወደ ደር​ቤን ሄደ።</verse>
				<verse number="21">በዚ​ያ​ችም ከተማ ወን​ጌ​ልን ሰበኩ፤ ብዙ ሰዎ​ች​ንም ደቀ መዛ​ሙ​ርት አድ​ር​ገው ወደ ልስ​ጥ​ራን፥ ወደ ኢቆ​ን​ዮ​ንና ወደ አን​ጾ​ኪያ ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="22">የደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ንም ልቡና አጽ​ናኑ፤ በሃ​ይ​ማ​ኖ​ትም እን​ዲ​ጸኑ፦“ በብዙ ድካ​ምና መከራ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እን​ገባ ዘንድ ይገ​ባ​ናል” እያሉ መከ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">ለቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ቀሳ​ው​ስ​ትን ሾሙ፤ ጾሙ፤ ጸለ​ዩም፤ ለሚ​ታ​መ​ኑ​በት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አደራ ሰጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">ከጲ​ስ​ድ​ያም ዐል​ፈው ጵን​ፍ​ልያ ደረሱ።</verse>
				<verse number="25">ጴር​ጌን በተ​ባ​ለ​ችው ከተ​ማም ቃሉን ከተ​ና​ገሩ በኋላ ወደ ኢጣ​ሊያ ወረዱ።</verse>
				<verse number="26">ከዚ​ያም ስለ​ሚ​ሠ​ሩት ሥራ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አደራ ወደ ተሰ​ጡ​በት ወደ አን​ጾ​ኪያ በመ​ር​ከብ ሄዱ።</verse>
				<verse number="27">አን​ጾ​ኪ​ያም በደ​ረሱ ጊዜ ምእ​መ​ና​ኑን ሁሉ ሰብ​ስ​በው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ረ​ገ​ላ​ቸ​ውን ሁሉ፥ ለአ​ሕ​ዛ​ብም የሃ​ይ​ማ​ኖ​ትን በር እንደ ከፈ​ተ​ላ​ቸው ነገ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="28">ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም ጋር አያሌ ቀን ተቀ​መጡ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">ከይ​ሁዳ ሀገ​ርም የወ​ረዱ ሰዎች፥ “እንደ ሙሴ ሕግ ካል​ተ​ገ​ዘ​ራ​ችሁ ልት​ድኑ አት​ች​ሉም” እያሉ ወን​ድ​ሞ​ችን ያስ​ተ​ምሩ ነበር።</verse>
				<verse number="2">ሕዝ​ቡም እጅግ ታወኩ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስ​ንም ተከ​ራ​ከ​ሩ​አ​ቸው፤ ስለ​ዚህ ነገ​ርም ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስን፥ ጓደ​ኞ​ቻ​ቸ​ው​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አሉት ወደ ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስት ሊል​ኳ​ቸው ተማ​ከሩ።</verse>
				<verse number="3">ከቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም በተ​ላኩ ጊዜ ወደ ሰማ​ር​ያና ወደ ፊንቄ ደር​ሰው አሕ​ዛብ ወደ ሃይ​ማ​ኖት እንደ ተመ​ለሱ ነገ​ሩ​ቸ​አ​ቸው፤ ወን​ድ​ሞ​ች​ንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰ​ኙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በደ​ረሱ ጊዜም ምእ​መ​ና​ንና ሐዋ​ር​ያት፥ ቀሳ​ው​ስ​ትም ተቀ​በ​ሉ​አ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ያደ​ረ​ገ​ላ​ቸ​ውን ነገ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">ነገር ግን ካመ​ኑት ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወገን አን​ዳ​ን​ዶች ተነ​ሥ​ተው፥ “ትገ​ዝ​ሩ​አ​ቸው ዘን​ድና የሙ​ሴን ሕግ እን​ዲ​ጠ​ብቁ ታዝ​ዙ​አ​ቸው ዘንድ ይገ​ባል” አሉ።</verse>
				<verse number="6">ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስ​ትም ስለ​ዚህ ነገር የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ያዩ ዘንድ ተሰ​በ​ሰቡ።</verse>
				<verse number="7">ብዙ ክር​ክ​ርም ከተ​ከ​ራ​ከሩ በኋላ ጴጥ​ሮስ ተነ​ሥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ስሙ፤ ለአ​ሕ​ዛብ ከአፌ የወ​ን​ጌ​ሉን ቃል እን​ዳ​ሰ​ማ​ቸ​ውና እን​ዲ​ያ​ምኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ እንደ መረ​ጠኝ እና​ንተ ራሳ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="8">ልብን የሚ​ያ​ውቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእኛ እንደ ሰጠን መን​ፈስ ቅዱ​ስን በመ​ስ​ጠት መሰ​ከ​ረ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="9">ልባ​ቸ​ው​ንም በእ​ም​ነት አን​ጽቶ ከእኛ አል​ለ​ያ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="10">አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አት​ፈ​ታ​ተ​ኑት፤ እኛም አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ልን​ሸ​ከ​መው ያል​ቻ​ል​ነ​ውን ቀን​በር በደቀ መዛ​ሙ​ርት ጫንቃ ላይ ለምን ትጭ​ና​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="11">ነገር ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጸጋ እን​ድን ዘንድ እን​ታ​መ​ና​ለን፤ እነ​ር​ሱም እንደ እኛ ይድ​ናሉ።”</verse>
				<verse number="12">ያን​ጊ​ዜም ሕዝቡ ሁሉ ጸጥ ብለው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ያደ​ረ​ገ​ላ​ቸ​ውን ተአ​ም​ራ​ትና ድንቅ ሥራ ሁሉ ሲና​ገሩ ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስን አዳ​መ​ጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">እነ​ር​ሱም ጸጥ ባሉ ጊዜ ያዕ​ቆብ መልሶ እን​ዲህ አለ፥ “ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ስሙኝ።</verse>
				<verse number="14">ስም​ዖ​ንም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ አሕ​ዛ​ብን ይቅር እን​ዳ​ላ​ቸ​ውና ከው​ስ​ጣ​ቸ​ውም ለስሙ ሕዝ​ብን እንደ መረጠ ተና​ግ​ሮ​አል።</verse>
				<verse number="15">በዚ​ህም መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ እንደ ተና​ገረ የነ​ቢ​ያት ቃል ይስ​ማ​ማል።</verse>
				<verse number="16">ከዚ​ህም በኋላ የወ​ደ​ቀ​ች​ውን የዳ​ዊ​ትን ቤት መልሼ እሠ​ራ​ታ​ለሁ፤ ፍራ​ሽ​ዋ​ንም አድ​ሳ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="17">የቀ​ሩት ሰዎ​ችና ስሜም የተ​ጠ​ራ​ባ​ቸው አሕ​ዛብ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ልጉ ዘንድ፥ ይላል ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤</verse>
				<verse number="18">ከጥ​ንት ጀምሮ ሥራው ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የታ​ወቀ ነው።</verse>
				<verse number="19">“አሁ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​መ​ለሱ አሕ​ዛብ ላይ ሥር​ዐት አታ​ክ​ብዱ እላ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">ነገር ግን ለጣ​ዖት ከሚ​ሠ​ዋው፥ ከዝ​ሙት፥ ሞቶ የተ​ገ​ኘ​ው​ንና ደም ከመ​ብ​ላት እን​ዲ​ርቁ፥ ለራ​ሳ​ቸው የሚ​ጠ​ሉ​ት​ንም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ላይ እን​ዳ​ያ​ደ​ርጉ እዘ​ዙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">ሙሴም ከጥ​ንት ጀምሮ በየ​ከ​ተ​ማዉ የሚ​ሰ​ብ​ክ​ላ​ቸው ትም​ህ​ርት ነበር፤ በየ​ም​ኵ​ራ​ቡም በየ​ሰ​ን​በቱ ያነ​ብ​ቡት ነበር።”</verse>
				<verse number="22">ከዚ​ህም በኋላ ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስት ሕዝ​ቡም ሁሉ ከጳ​ው​ሎ​ስና ከበ​ር​ና​ባስ ጋር ወደ አን​ጾ​ኪያ የሚ​ል​ኳ​ቸ​ውን ሰዎች ይመ​ርጡ ዘንድ ተስ​ማሙ፤ ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸው መካ​ከ​ልም የተ​ማ​ሩ​ትን ሰዎች በር​ና​ባስ የተ​ባለ ይሁ​ዳ​ንና ሲላ​ስን መረጡ።</verse>
				<verse number="23">እን​ዲህ የም​ትል መል​እ​ክ​ትም በእ​ጃ​ቸው ጻፉ፤ “ከሐ​ዋ​ር​ያ​ትና ከቀ​ሳ​ው​ስት ከወ​ን​ድ​ሞ​ችም በአ​ን​ጾ​ኪያ፥ በሶ​ር​ያና በኪ​ል​ቅያ ለሚ​ኖሩ፥ ከአ​ሕ​ዛብ ላመኑ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ትድ​ረስ፤ ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን፥ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="24">ያላ​ዘ​ዝ​ና​ቸው ሰዎች ከእኛ ወጥ​ተው፦ ‘ትገ​ዘሩ ዘን​ድና የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ ትጠ​ብቁ ዘንድ ይገ​ባ​ች​ኋል’ ብለው በነ​ገር እንደ አወ​ኩ​አ​ች​ሁና ልባ​ች​ሁን እንደ አና​ወ​ጡት ሰም​ተ​ናል።</verse>
				<verse number="25">ሁላ​ችን ከተ​ሰ​በ​ሰ​ብን በኋላ በአ​ንድ ቃል በየን፤ አንድ ሆነ​ንም ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከጳ​ው​ሎ​ስና ከበ​ር​ና​ባስ ጋር ወደ እና​ንተ የም​ን​ል​ካ​ቸ​ውን ሰዎች መረ​ጥን።</verse>
				<verse number="26">እነ​ር​ሱም ስለ ጌታ​ችን ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን አሳ​ል​ፈው የሰጡ ሰዎች ናቸው።</verse>
				<verse number="27">ይሁ​ዳ​ንና ሲላ​ስን ልከ​ና​ቸ​ዋ​ልና እነ​ርሱ በቃ​ላ​ቸው ይህን ያስ​ረ​ዱ​አ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="28">ሥር​ዐት እን​ዳ​ና​ከ​ብድ ሌላም ሸክም እን​ዳ​ን​ጨ​ምር መን​ፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር ነውና፤ ነገር ግን ይህን በግድ ትተዉ ዘንድ እና​ዝ​ዛ​ች​ኋ​ለን።</verse>
				<verse number="29">ለአ​ማ​ል​ክት የተ​ሠ​ዋ​ውን፥ ሞቶ የተ​ገ​ኘ​ውን፥ ደም​ንም አት​ብሉ፤ ከዝ​ሙ​ትም ራቁ፤ በራ​ሳ​ችሁ የም​ት​ጠ​ሉ​ት​ንም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ላይ አታ​ድ​ርጉ፥ ከእ​ነ​ዚህ ሥራ​ዎ​ችም ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ብት​ጠ​ብቁ በሰ​ላም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤ ደኅና ሁኑ።”</verse>
				<verse number="30">እነ​ር​ሱም ተል​ከው ወደ አን​ጾ​ኪያ ወረዱ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ሰብ​ስ​በው የተ​ላ​ከ​ውን ደብ​ዳቤ ሰጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="31">እነ​ር​ሱም አን​ብ​በው እጅግ ደስ አላ​ቸው፥ ተጽ​ና​ኑም።</verse>
				<verse number="32">ይሁ​ዳና ሲላ​ስም መም​ህ​ራን ነበ​ሩና አስ​ተ​ማ​ሩ​አ​ቸው፤ ወን​ድ​ሞ​ች​ንም በብዙ ቃል አጽ​ና​ኑ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="33">በእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ አያሌ ቀን ከተ​ቀ​መጡ በኋላ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ተሰ​ና​ብ​ተው በሰ​ላም ወደ ሐዋ​ር​ያት ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="34">ሲላስ ግን በዚያ ሊቈይ ወደደ።</verse>
				<verse number="35">ጳው​ሎ​ስና በር​ና​ባ​ስም በአ​ን​ጾ​ኪያ ቈዩ፤ ከሌ​ሎች ብዙ ሰዎች ጋርም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰበኩ፤ አስ​ተ​ማ​ሩም።</verse>
				<verse number="36">ከጥ​ቂት ቀን በኋ​ላም ጳው​ሎስ በር​ና​ባ​ስን፦“እን​ግ​ዲ​ህስ እን​መ​ለ​ስና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ባስ​ተ​ማ​ር​ን​ባ​ቸው ሀገ​ሮች ያሉ​ትን ወን​ድ​ሞች እን​ጐ​ብ​ኛ​ቸው፤ እን​ዴት እን​ዳ​ሉም እን​ወቅ” አለው።</verse>
				<verse number="37">በር​ና​ባ​ስም ማር​ቆስ የተ​ባ​ለ​ውን ዮሐ​ን​ስን ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይዞት ሊሄድ ወደደ።</verse>
				<verse number="38">ጳው​ሎስ ግን ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሊወ​ስ​ደው አል​ፈ​ቀ​ደም፤ እነ​ርሱ በጵ​ን​ፍ​ልያ ሳሉ ትቶ​አ​ቸው ሄዶ​አ​ልና፤ አብ​ሮ​አ​ቸ​ውም ለሥራ አል​መ​ጣም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="39">ስለ​ዚ​ህም ተኰ​ራ​ር​ፈው እርስ በር​ሳ​ቸው ተለ​ያዩ፤ በር​ና​ባ​ስም ማር​ቆ​ስን ይዞ በመ​ር​ከብ ወደ ቆጵ​ሮስ ሄደ።</verse>
				<verse number="40">ጳው​ሎስ ግን ሲላ​ስን መረጠ፤ ወን​ድ​ሞ​ችም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አደራ ከሰ​ጡት በኋላ ሄደ።</verse>
				<verse number="41">በሶ​ር​ያና በኪ​ል​ቅ​ያም እየ​ዞረ አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ና​ትን አጽ​ናና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">ወደ ደር​ቤ​ንና ወደ ልስ​ጥ​ራን ከተ​ማም ደረሰ፤ እነ​ሆም፥ በዚያ የአ​ን​ዲት ያመ​ነች አይ​ሁ​ዳ​ዊት ልጅ ጢሞ​ቴ​ዎስ የሚ​ባል አንድ ደቀ መዝ​ሙር ነበር፤ አባቱ ግን አረ​ማዊ ነበረ።</verse>
				<verse number="2">በደ​ር​ቤ​ንና በል​ስ​ጥ​ራን በኢ​ቆ​ን​ዮ​ንም ያሉ ወን​ድ​ሞች ሁሉ ይመ​ሰ​ክ​ሩ​ለት ነበር።</verse>
				<verse number="3">ጳው​ሎ​ስም ከእ​ርሱ ጋር ይዞት ሊሄድ ወደደ፤ በዚ​ያም ሀገር ስለ አሉት አይ​ሁድ ወስዶ ገረ​ዘው፤ አባቱ አረ​ማዊ እንደ ነበረ ሁሉም ያውቁ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="4">በየ​ከ​ተ​ማ​ውም ሲሔዱ፥ ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያዘ​ዙ​ትን ሥር​ዐት አስ​ተ​ማ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ና​ትም በሃ​ይ​ማ​ኖት ጸኑ፤ ዕለት ዕለ​ትም ቍጥ​ራ​ቸው ይበዛ ነበር።</verse>
				<verse number="6">ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በእ​ስያ እን​ዳ​ይ​ና​ገሩ መን​ፈስ ቅዱስ ስለ​ከ​ለ​ከ​ላ​ቸው ወደ ፍር​ግ​ያና ወደ ገላ​ትያ አው​ራጃ ሄዱ፤</verse>
				<verse number="7">ሚስያ በደ​ረሱ ጊዜም ወደ ቢታ​ንያ ሊሄዱ ወደዱ፤ የጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ መን​ፈስ ግን አል​ፈ​ቀ​ደ​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="8">ከሚ​ስ​ያም ዐል​ፈው ወደ ጢሮ​አዳ ወረዱ።</verse>
				<verse number="9">ለጳ​ው​ሎ​ስም በሌ​ሊት አንድ መቄ​ዶ​ናዊ ሰው ቁሞ፥ “ወደ እኛ ወደ መቄ​ዶ​ንያ ዕለ​ፍና ርዳን” እያለ ሲማ​ል​ደው በራ​እይ ተገ​ለ​ጸ​ለት።</verse>
				<verse number="10">ራእ​ዩ​ንም ባየ ጊዜ ወዲ​ያ​ውኑ ወደ መቄ​ዶ​ንያ ልን​ሄድ ወደ​ድን፤ ወን​ጌ​ልን እን​ሰ​ብ​ክ​ላ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ጠ​ራን መስ​ሎ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="11">ከጢ​ሮ​አ​ዳም ወጥ​ተን ወደ ሰሞ​ት​ራቄ ገባን፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም ናጶሊ ወደ​ም​ት​ባ​ለው ሀገር በመ​ር​ከብ መጣን።</verse>
				<verse number="12">ከዚ​ያም ወደ ፊል​ጵ​ስ​ዩስ ሄድን፤ ይህ​ች​ውም የመ​ቄ​ዶ​ንያ ዋና ከተ​ማና የሮም ቅኝ ግዛት ነበ​ረች፤ በዚ​ያ​ችም ሀገር ጥቂት ቀን ሰነ​በ​ትን።</verse>
				<verse number="13">በሰ​ን​በት ቀንም ከከ​ተ​ማዉ በር ወደ ባሕሩ ዳር ወጣን፤ በዚያ የጸ​ሎት ቤት ያለ መስ​ሎን ነበ​ርና፤ በዚ​ያም ተቀ​ም​ጠን፥ በዚያ ለተ​ሰ​በ​ሰቡ ሴቶች እና​ስ​ተ​ምር ጀመ​ርን።</verse>
				<verse number="14">በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ቀይ ሐር የም​ት​ሸጥ ከት​ያ​ጥ​ሮን ሀገር የመ​ጣች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈራ አን​ዲት ሴት ነበ​ረች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልቡ​ና​ዋን ከፍ​ቶ​ላት ነበ​ርና ጳው​ሎስ የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ረ​ውን ታዳ​ምጥ ነበር፤ ስም​ዋም ልድያ ይባል ነበር።</verse>
				<verse number="15">እር​ስ​ዋም ከቤተ ሰቦ​ችዋ ጋር ተጠ​መ​ቀች፤ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አማኝ ካደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ኝስ ወደ ቤቴ ገብ​ታ​ችሁ እደሩ” ብላ ማለ​ደ​ችን፤ የግ​ድም አለ​ችን።</verse>
				<verse number="16">ለጸ​ሎት ስን​ሄ​ድም የም​ዋ​ር​ተ​ኛ​ነት መን​ፈስ ያደ​ረ​ባት አን​ዲት ልጅ አገ​ኘ​ችን፤ በጥ​ን​ቈ​ላም የም​ታ​ገ​ኘ​ውን ብዙ እጅ መንሻ ለጌ​ቶ​ችዋ ታገባ ነበር።</verse>
				<verse number="17">ከዚ​ህም በኋላ ጳው​ሎ​ስ​ንና እኛን እየ​ተ​ከ​ተ​ለች፥ “እነ​ዚህ ሰዎች የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች ናቸው፤ የሕ​ይ​ወ​ት​ንም መን​ገድ ያስ​ተ​ም​ሩ​አ​ች​ኋል” እያ​ለች ትጮኽ ነበር።</verse>
				<verse number="18">ብዙ ቀንም እን​ዲሁ ታደ​ርግ ነበር፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም አሳ​ዘ​ነ​ችው፤ መለስ ብሎም፥ “መን​ፈስ ርኩስ፥ ከእ​ር​ስዋ እን​ድ​ት​ወጣ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም አዝ​ዤ​ሃ​ለሁ” አለው፤ ወዲ​ያ​ው​ኑም ተዋት።</verse>
				<verse number="19">ጌቶ​ች​ዋም የም​ታ​ገ​ባ​ላ​ቸው የጥ​ቅ​ማ​ቸው ተስፋ እንደ ቀረ ባዩ ጊዜ ጳው​ሎ​ስ​ንና ሲላ​ስን ይዘው በገ​በያ እየ​ጐ​ተቱ ወደ ገዢ​ዎች ወሰ​ዱ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">ወደ ገዢ​ዎ​ችም አቅ​ር​በው፥ “እነ​ዚህ ሰዎች ከተ​ማ​ች​ንን ያሸ​ብ​ሩ​ብ​ናል፤ እነ​ር​ሱም አይ​ሁድ ናቸው።</verse>
				<verse number="21">እኛ የሮሜ ሰዎች ስን​ሆ​ንም ልና​ደ​ር​ገው የማ​ይ​ገ​ባ​ንን ሕግ ይና​ገ​ራሉ” አሉ።</verse>
				<verse number="22">ሕዝ​ቡም ተነ​ሡ​ባ​ቸው፤ ገዢ​ዎ​ቹም ልብ​ሳ​ቸ​ውን ገፍ​ፈው በበ​ትር ይመ​ቱ​አ​ቸው ዘንድ አዘዙ።</verse>
				<verse number="23">በብ​ዙም ደብ​ድ​በው አሰ​ሩ​አ​ቸው፤ የወ​ህኒ ቤቱን ዘበ​ኛም አጽ​ንቶ እን​ዲ​ጠ​ብ​ቃ​ቸው አዘ​ዙት።</verse>
				<verse number="24">እር​ሱም ትእ​ዛ​ዙን ተቀ​ብሎ ወደ ውስ​ጠ​ኛው ወኅኒ ቤት አስ​ገ​ባ​ቸው፤ እግ​ራ​ቸ​ው​ንም በግ​ንድ አጣ​ብቆ ጠረ​ቃ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">በመ​ን​ፈቀ ሌሊ​ትም ጳው​ሎ​ስና ሲላስ ጸለዩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በዜማ አመ​ሰ​ገ​ኑት፤ እስ​ረ​ኞ​ቹም ይሰ​ሙ​አ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="26">ድን​ገ​ትም ታላቅ ንው​ጽ​ው​ጽታ ሆነ፤ የወ​ህኒ ቤቱ መሠ​ረ​ትም ተና​ወጠ፤ በሮ​ችም ሁሉ ያን​ጊዜ ተከ​ፈቱ፤ የሁ​ሉም እግር ብረ​ቶ​ቻ​ቸው እየ​ወ​ለቁ ወደቁ።</verse>
				<verse number="27">የወ​ህኒ ቤቱ ጠባ​ቂም ከእ​ን​ቅ​ልፉ በነቃ ጊዜ በሮች ሁሉ ተከ​ፍ​ተው አየ፤ ሰይ​ፉ​ንም መዝዞ ራሱን ሊገ​ድል ወደደ፤ እስ​ረ​ኞቹ ያመ​ለ​ጡት መስ​ሎት ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="28">ጳው​ሎ​ስም፥ “በራ​ስህ ክፉ ነገር አታ​ድ​ርግ፤ ሁላ​ች​ንም ከዚህ አለን” ብሎ በታ​ላቅ ቃል ጮኸ።</verse>
				<verse number="29">መብ​ራት አም​ጥ​ቶም እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጠ ወደ ውስጥ ሄደና ለጳ​ው​ሎ​ስና ለሲ​ላስ ወድቆ ሰገደ።</verse>
				<verse number="30">ወደ ውጭም አው​ጥቶ “ጌቶች፥ እድን ዘንድ ምን ላድ​ርግ?” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="31">እነ​ር​ሱም፥ “በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እመን፤ አን​ተና ቤተ ሰብ​ህም ሁሉ ትድ​ና​ላ​ችሁ” አሉት።</verse>
				<verse number="32">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ለእ​ር​ሱና በቤቱ ላሉት ሁሉ ነገ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="33">ወዲ​ያ​ው​ኑም በሌ​ሊት ወስዶ ቍስ​ላ​ቸ​ውን አጠ​በ​ላ​ቸው፤ እር​ሱም በዚ​ያው ጊዜ ከቤተ ሰቡ ሁሉ ጋር ተጠ​መቀ።</verse>
				<verse number="34">ወደ ቤቱም አግ​ብቶ ማዕድ አቀ​ረ​በ​ላ​ቸው፤ በጌ​ታ​ችን ስለ አመ​ነም እርሱ ከቤተ ሰቡ ጋር ደስ አለው።</verse>
				<verse number="35">በነጋ ጊዜም፥ ገዢ​ዎቹ፥ “እነ​ዚ​ያን ሰዎች ፈት​ታ​ችሁ ልቀ​ቋ​ቸው” ብለው ብላ​ቴ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ላኩ።</verse>
				<verse number="36">የወ​ህኒ ቤቱ ጠባ​ቂም በሰማ ጊዜ ሄዶ ገዢ​ዎቹ “ይፈቱ” ብለው እንደ ላኩ ይህን ነገር ለጳ​ው​ሎ​ስና ለሲ​ላስ ነገ​ራ​ቸው፤ “አሁ​ንም ውጡና በሰ​ላም ሂዱ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="37">ጳው​ሎስ ግን፥ “እኛ የሮም ሰዎች ስን​ሆን፥ ያለ ፍርድ በአ​ደ​ባ​ባይ ገረ​ፉን፤ አሰ​ሩ​ንም፤ አሁ​ንም በስ​ውር ሊያ​ወ​ጡን ይሻሉ፤ አይ​ሆ​ንም፥ ራሳ​ቸው መጥ​ተው ያው​ጡን” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="38">ብላ​ቴ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ሄደው ይህ​ንን ነገር ለገ​ዢ​ዎቹ ነገ​ሩ​አ​ቸው፤ የሮም ሰዎች መሆ​ና​ቸ​ው​ንም ሰም​ተው ደነ​ገጡ።</verse>
				<verse number="39">መጥ​ተ​ውም ከከ​ተ​ማ​ቸው እን​ዲ​ወጡ ማለ​ዱ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="40">ከወ​ኅኒ ቤቱም ከወጡ በኋላ ወደ ልድያ ቤት ገብ​ተው ወን​ድ​ሞ​ችን አገኙ፤ አጽ​ና​ን​ተ​ዋ​ቸ​ውም ሔዱ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">አን​ፊ​ጶ​ልና አጶ​ሎ​ንያ ወደ​ሚ​ባሉ ሀገ​ሮ​ችም ሄዱ፤ የአ​ይ​ሁድ ምኵ​ራብ ወደ አለ​በት ወደ ተሰ​ሎ​ን​ቄም ደረሱ።</verse>
				<verse number="2">ጳው​ሎ​ስም እንደ አስ​ለ​መ​ደው ወደ እነ​ርሱ ገብቶ ሦስት ሳም​ንት ከመ​ጻ​ሕ​ፍት እየ​ጠ​ቀሰ ሲከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ሰነ​በተ።</verse>
				<verse number="3">ክር​ስ​ቶስ እን​ዲ​ሞት ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይቶ እን​ዲ​ነሣ፥ እየ​ተ​ረ​ጐ​መና እየ​አ​ስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፥ “ይህ እኔ የነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ ነው” ይል ነበር።</verse>
				<verse number="4">ከእ​ነ​ር​ሱና ከደ​ጋ​ጎች አረ​ማ​ው​ያ​ንም ብዙ ሰዎች፥ ከታ​ላ​ላ​ቆች ሴቶ​ችም ጥቂ​ቶች ያይ​ደሉ አም​ነው ከጳ​ው​ሎ​ስና ከሲ​ላስ ጋር ሆኑ።</verse>
				<verse number="5">የማ​ያ​ምኑ አይ​ሁድ ግን ቀኑ​ባ​ቸው፤ ከገ​በ​ያም ክፉ​ዎች ሰዎ​ችን አም​ጥ​ተው፥ ሰዎ​ች​ንም ሰብ​ስ​በው ሀገ​ሪ​ቱን አወ​ኳት፤ ፈለ​ጓ​ቸ​ውም፤ የኢ​ያ​ሶ​ንን ቤትም በረ​በሩ፤ ወደ ሕዝ​ቡም ሊያ​ወ​ጧ​ቸው ሽተው ነበር።</verse>
				<verse number="6">በአ​ጧ​ቸ​ውም ጊዜ ኢያ​ሶ​ንን ጐተ​ቱት፤ በዚ​ያም የነ​በ​ሩ​ትን ጓደ​ኞች ጭምር ወደ ሹሞቹ ወሰ​ዱ​አ​ቸው፤ እየ​ጮ​ኹም እን​ዲህ ይሉ ነበር፥ “ዓለ​ምን የሚ​ያ​ው​ኳት እነ​ዚህ ናቸው፤ ወደ​ዚ​ህም መጥ​ተ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">ይህ ኢያ​ሶ​ንም ተቀ​በ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም በቄ​ሣር ላይ የወ​ን​ጀል ሥራ ይሠ​ራሉ፤ ሌላ ሕግ​ንም ያስ​ተ​ም​ራሉ፤ ኢየ​ሱ​ስም ሌላ ንጉሥ ነው” ይላሉ።</verse>
				<verse number="8">ሕዝ​ቡና የከ​ተ​ማው ሹሞ​ችም ይህን በሰሙ ጊዜ ታወኩ።</verse>
				<verse number="9">ከኢ​ያ​ሶ​ንና ከጓ​ደ​ኞ​ቹም ዋስ ተቀ​ብ​ለው ለቀ​ቁ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">ወን​ድ​ሞች ግን ጳው​ሎ​ስ​ንና ሲላ​ስን በሌ​ሊት ወደ ቤርያ ሸኙ​አ​ቸው፤ ወደ​ዚ​ያም በደ​ረሱ ጊዜ ወደ አይ​ሁድ ምኵ​ራብ ገቡ።</verse>
				<verse number="11">በተ​ሰ​ሎ​ንቄ ካሉ​ትም እነ​ርሱ ይሻ​ላሉ፤ በፍ​ጹም ደስታ ቃላ​ቸ​ውን ተቀ​ብ​ለ​ዋ​ልና፤ ነገ​ሩም እንደ አስ​ተ​ማ​ሩ​አ​ቸው እንደ ሆነ ለመ​ረ​ዳት ዘወ​ትር መጻ​ሕ​ፍ​ትን ይመ​ረ​ምሩ ነበር።</verse>
				<verse number="12">ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ያመኑ ብዙ​ዎች ነበሩ፤ ከአ​ረ​ማ​ው​ያን ወገን የሆኑ ብዙ ደጋግ ሴቶ​ችም ነበሩ፤ ወን​ዶ​ችም ብዙ​ዎች ነበሩ።</verse>
				<verse number="13">በተ​ሰ​ሎ​ንቄ የነ​በሩ አይ​ሁድ ግን ጳው​ሎስ በቤ​ርያ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እንደ አስ​ተ​ማረ ባወቁ ጊዜ፥ ወደ​ዚያ መጥ​ተው ሕዝ​ቡን አወ​ኩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="14">ያን​ጊ​ዜም ወን​ድ​ሞች ጳው​ሎ​ስን ሸኝ​ተው ወደ ባሕር አደ​ረ​ሱት፤ ሲላ​ስና ጢሞ​ቴ​ዎስ ግን በዚ​ያው ቀሩ።</verse>
				<verse number="15">ጳው​ሎ​ስን የሸ​ኙት ሰዎ​ችም እስከ አቴና ከተማ ድረስ አብ​ረ​ውት መጥ​ተው ነበ​ርና ፈጥ​ነው ይከ​ተ​ሉት ዘንድ ወደ ሲላ​ስና ወደ ጢሞ​ቴ​ዎስ ላካ​ቸው፤ ተመ​ል​ሰ​ውም ሄዱ።</verse>
				<verse number="16">ጳው​ሎ​ስም በአ​ቴና ሆኖ ሲጠ​ብ​ቃ​ቸው ከተ​ማው ሁሉ ጣዖት ሲያ​መ​ልኩ ባየ ጊዜ ልቡ​ናው ተበ​ሳጨ።</verse>
				<verse number="17">ስለ​ዚ​ህም በም​ኵ​ራብ አይ​ሁ​ድ​ንና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ሩ​ትን፥ ሁል​ጊ​ዜም በገ​በያ የሚ​ያ​ገ​ኛ​ቸ​ውን ሁሉ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="18">የኤ​ፌ​ቆ​ሮ​ስን ትም​ህ​ርት ከተ​ማሩ ፈላ​ስ​ፋ​ዎች መካ​ከ​ልና ረዋ​ቅ​ያ​ው​ያን ከሚ​ባ​ሉት ወገን የሆኑ ሌሎች ፈላ​ስ​ፎ​ችም የተ​ከ​ራ​ከ​ሩት ነበሩ፤ እኩ​ሌ​ቶ​ችም፥ “ይህ ለፍ​ላፊ ምን ሊና​ገር ይፈ​ል​ጋል?” ይሉ ነበር፤ ሌሎ​ችም፥ “ስለ ኢየ​ሱስ ከሙ​ታን ስለ መነ​ሣ​ቱም ሰብ​ኮ​ላ​ቸ​ዋ​ልና የአ​ዲስ አም​ላክ ትም​ህ​ር​ትን ያስ​ተ​ም​ራል” አሉ።</verse>
				<verse number="19">ይዘ​ውም አር​ዮ​ስ​ፋ​ጎስ ወደ​ሚ​ባል ሸንጎ ወሰ​ዱት፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “ይህን የም​ታ​ስ​ተ​ም​ረ​ውን አዲስ ትም​ህ​ርት እና​ውቅ ዘንድ ይቻ​ለ​ና​ልን? እስቲ ንገ​ረን?</verse>
				<verse number="20">በጆ​ሮ​አ​ችን እን​ግዳ ነገር ታሰ​ማ​ና​ለ​ህና እኛም ይህ ነገር ምን እንደ ሆነ ልን​ረዳ እን​ወ​ዳ​ለን።”</verse>
				<verse number="21">የአ​ቴና ሰዎ​ችና በዚ​ያም የነ​በሩ እን​ግ​ዶች ሁሉ አዲስ ነገ​ርን ከመ​ና​ገ​ርና ከመ​ስ​ማት በቀር ሌላ ዐሳብ አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="22">ጳው​ሎ​ስም በአ​ር​ዮ​ስ​ፋ​ጎስ ውስጥ ቆሞ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የአ​ቴና ሰዎች! በሥ​ራ​ችሁ ሁሉ አማ​ል​ክ​ትን ማም​ለክ እን​ደ​ም​ታ​በዙ አያ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="23">በዚ​ህም ሳልፍ ‘ለማ​ይ​ታ​ወቅ አም​ላክ’ የሚል ጽሕ​ፈት ያለ​በ​ትን የም​ታ​መ​ል​ኩ​በ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ች​ሁን አየሁ፤ እነሆ፥ እኔ ይህን ሳታ​ውቁ የም​ታ​መ​ል​ኩ​ትን እገ​ል​ጽ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="24">ዓለ​ሙ​ንና በእ​ር​ሱም ያለ​ውን ሁሉ የፈ​ጠረ አም​ላክ እርሱ የሰ​ማ​ይና የም​ድር ጌታ ነውና እጅ በሠ​ራው መቅ​ደስ አይ​ኖ​ርም።</verse>
				<verse number="25">እር​ሱም ሕይ​ወ​ት​ንና እስ​ት​ን​ፋ​ስን፥ ሌላ​ው​ንም ነገር ሁሉ ለሁሉ ይሰ​ጣ​ልና እንደ ችግ​ረኛ የሰው እጅ አያ​ገ​ለ​ግ​ለ​ውም።</verse>
				<verse number="26">እር​ሱም በም​ድር ሁሉ ላይ ይኖሩ ዘንድ ሰዎ​ችን ሁሉ ከአ​ንድ ሰው ፈጠረ፤ ይኖ​ሩ​ባ​ትም ዘንድ ዘመ​ን​ንና ቦታን ወስኖ ሠራ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="27">ምና​ል​ባት ያገ​ኙት እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ል​ጉት ዘንድ፤ ነገር ግን ከሁ​ላ​ችን የራቀ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="28">እኛ በእ​ርሱ ሕይ​ወ​ትን እና​ገ​ኛ​ለን፤ በእ​ር​ሱም እን​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሳ​ለን፤ በእ​ር​ሱም ጸን​ተን እን​ኖ​ራ​ለን፤ ከመ​ካ​ከ​ላ​ች​ሁም፦ ‘እኛ ዘመ​ዶቹ ነን’ የሚሉ ፈላ​ስ​ፎች አሉ።</verse>
				<verse number="29">እን​ግ​ዲህ እኛ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘመ​ዶች ከሆን በሰው ዕው​ቀ​ትና ብል​ሀት በተ​ቀ​ረጸ በድ​ን​ጋ​ይና በብር፥ በወ​ር​ቅም አም​ላ​ክ​ነ​ቱን ልን​መ​ስ​ለው አይ​ገ​ባም።</verse>
				<verse number="30">የቀ​ድ​ሞ​ው​ንስ ያለ ማወቅ ዘመን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​ል​ፎ​ታል፤ ዛሬ ግን በመ​ላው ዓለም ንስሓ እን​ዲ​ገቡ ሰውን ሁሉ አዝ​ዞ​አል።</verse>
				<verse number="31">በመ​ረ​ጠው ሰው እጅ በዓ​ለም በእ​ው​ነት የሚ​ፈ​ር​ድ​ባ​ትን ቀን ወስ​ኖ​አ​ልና፤ እር​ሱን ከሙ​ታን ለይቶ በማ​ስ​ነ​ሣ​ቱም ብዙ​ዎ​ችን ወደ ሃይ​ማ​ኖት መል​ሶ​አ​ልና።”</verse>
				<verse number="32">የሙ​ታ​ን​ንም ትን​ሣኤ በሰሙ ጊዜ እኩ​ሌ​ቶቹ አፌ​ዙ​በት፤ ሌሎ​ችም፥ “ስለ​ዚህ ነገር በሌላ ቀን እና​ዳ​ም​ጥ​ሃ​ለን” አሉት።</verse>
				<verse number="33">ጳው​ሎ​ስም ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ወጥቶ ሄደ።</verse>
				<verse number="34">አም​ነው የተ​ከ​ተ​ሉት ሰዎ​ችም ነበሩ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ ከአ​ር​ዮ​ስ​ፋ​ጎስ ባለ​ሥ​ል​ጣ​ኖች ወገን የሚ​ሆን ዲዮ​ና​ስ​ዮስ ነበር፤ ደማ​ሪስ የም​ት​ባል ሴትም ነበ​ረች፤ ሌሎ​ችም አብ​ረ​ዋ​ቸው ነበሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">ከዚህ በኋላ ጳው​ሎስ ከአ​ቴና ወጥቶ ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሄደ።</verse>
				<verse number="2">አቂላ የሚ​ባል አንድ አይ​ሁ​ዳ​ዊም አገኘ፤ የት​ው​ልድ ሀገ​ሩም ጳን​ጦስ ነው፤ እር​ሱም ከጥ​ቂት ወራት በፊት ከኢ​ጣ​ልያ ተሰዶ መጣ፤ ሚስቱ ጵር​ስ​ቅ​ላም አብ​ራው ነበ​ረች፤ ቀላ​ው​ዴ​ዎስ አይ​ሁድ ከሮም እን​ዲ​ሰ​ደዱ አዝዞ ነበ​ርና ወደ እነ​ርሱ መጣ።</verse>
				<verse number="3">ሥራ​ቸው አንድ ስለ ነበረ ድን​ኳን ሰፊ​ዎ​ችም ስለ ነበሩ ከእ​ነ​ርሱ ጋር አብሮ ኖረ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ይሠሩ ነበር።</verse>
				<verse number="4">ጳው​ሎ​ስም በየ​ሰ​ን​በቱ በም​ኵ​ራብ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበር፤ አይ​ሁ​ድ​ንና አረ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ያሳ​ም​ና​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="5">ሲላ​ስና ጢሞ​ቴ​ዎ​ስም ከመ​ቄ​ዶ​ንያ በወ​ረዱ ጊዜ ጳው​ሎስ፥ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ ለአ​ይ​ሁድ እየ​መ​ሰ​ከረ ቃሉን በማ​ስ​ተ​ማር ይተጋ ነበር።</verse>
				<verse number="6">እነ​ር​ሱም በተ​ቃ​ወ​ሙ​ትና በሰ​ደ​ቡት ጊዜ ልብ​ሱን አራ​ግፎ፥ “እን​ግ​ዲህ እኔ ንጹሕ ነኝ፤ ደማ​ችሁ በራ​ሳ​ችሁ ላይ ነው፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ ወደ አሕ​ዛብ እሄ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="7">ከዚ​ያም አልፎ ስሙ ኢዮ​ስ​ጦስ ወደ​ሚ​ባል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ወደ​ሚ​ፈራ ሰው ቤት ገባ፤ ቤቱም በም​ኵ​ራብ አጠ​ገብ ነበር።</verse>
				<verse number="8">የም​ኵ​ራብ አለቃ ቀር​ስ​ጶ​ስም ከነ​ቤተ ሰቡ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አመነ፤ ከቆ​ሮ​ን​ቶስ ሰዎ​ችም ብዙ​ዎች ሰም​ተው አም​ነው ተጠ​መቁ።</verse>
				<verse number="9">ጌታ​ች​ንም ጳው​ሎ​ስን በሌ​ሊት ራእይ እን​ዲህ አለው፥ “አት​ፍራ፥ ነገር ግን ተና​ገር፥ ዝምም አት​በል፤</verse>
				<verse number="10">እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና ማንም ሊጐ​ዳህ የሚ​ነ​ሣ​ብህ የለም፤ በዚች ከተማ ብዙ ሕዝብ አሉ​ኝና።”</verse>
				<verse number="11">ጳው​ሎ​ስም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እየ​አ​ስ​ተ​ማ​ራ​ቸው ዓመት ከስ​ድ​ስት ወር በቆ​ሮ​ን​ቶስ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="12">ጋል​ዮ​ስም የአ​ካ​ይያ አገረ ገዢ በሆነ ጊዜ አይ​ሁድ ተባ​ብ​ረው በጳ​ው​ሎስ ላይ ተነሡ፤ ወደ ሸን​ጎም አመ​ጡት።</verse>
				<verse number="13">እን​ዲ​ህም አሉት፥ “ይህ ሰው ኦሪ​ትን በመ​ቃ​ወም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ልኩ ዘንድ ሰዎ​ችን ያባ​ብ​ላል።”</verse>
				<verse number="14">ጳው​ሎ​ስም ይመ​ል​ስ​ላ​ቸው ዘንድ አፉን ሊከ​ፍት ወድዶ ሳለ አገረ ገዢው ጋል​ዮስ መልሶ አይ​ሁ​ድን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ አይ​ሁድ ሆይ፥ የበ​ደ​ላ​ችሁ በደል ቢኖር፥ ወይም ሌላ በደል ቢኖ​ር​በት አቤ​ቱ​ታ​ች​ሁን በሰ​ማ​ሁና ባከ​ራ​ከ​ር​ኋ​ችሁ ነበር።</verse>
				<verse number="15">ስለ ትም​ህ​ር​ትና ስለ ስሞች፥ ስለ ሕጋ​ች​ሁም የም​ት​ከ​ራ​ከሩ ከሆነ ግን ለራ​ሳ​ችሁ ዕወቁ፤ እኔ እን​ዲህ ያለ ነገር ልሰማ አል​ፈ​ቅ​ድም።”</verse>
				<verse number="16">ከሸ​ን​ጎ​ውም አባ​ረ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">አረ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ የም​ኵ​ራ​ቡን አለቃ ሶስ​ቴ​ን​ስን ይዘው በሸ​ንጎ ፊት ደበ​ደ​ቡት፤ የእ​ር​ሱም ነገር ጋል​ዮ​ስን ምንም አላ​ሳ​ዘ​ነ​ውም።</verse>
				<verse number="18">ጳው​ሎ​ስም እንደ ገና በወ​ን​ድ​ሞቹ ዘንድ ጥቂት ቀን ተቀ​መጠ፤ በሰ​ላ​ምም ሸኙ​ትና ወደ ሶርያ በባ​ሕር ተጓዘ፤ ጵር​ስ​ቅ​ላና አቂ​ላም አብ​ረ​ውት ነበሩ፤ ስእ​ለ​ትም ነበ​ረ​በ​ትና በክ​ን​ክ​ራ​ኦስ ራሱን ተላጨ።</verse>
				<verse number="19">ወደ ኤፌ​ሶ​ንም ደረሱ፤ በዚ​ያም ተዋ​ቸ​ውና እርሱ ብቻ​ውን ወደ ምኵ​ራብ ገብቶ አይ​ሁ​ድን ተከ​ራ​ከ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">እነ​ር​ሱም ብዙ ጊዜ እን​ዲ​ሰ​ነ​ብት ማለ​ዱት፤ ነገር ግን አል​ወ​ደ​ደም።</verse>
				<verse number="21">ከዚ​ህም በኋላ በሚ​ሸ​ኙት ጊዜ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢፈ​ቅድ እን​ደ​ገና እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ አሁን ግን የሚ​መ​ጣ​ውን በዓል በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላደ​ርግ እወ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው፤ ከኤ​ፌ​ሶ​ንም በመ​ር​ከብ ሄደ።</verse>
				<verse number="22">ወደ ቂሳ​ር​ያም ደረሰ፤ ከዚ​ያም ወጥቶ ለቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ሰላ​ምታ ከሰጠ በኋላ ወደ አን​ጾ​ኪያ ሄደ።</verse>
				<verse number="23">ጥቂት ቀንም ተቀ​መጠ፤ ከዚ​ያም ወጥቶ በገ​ላ​ት​ያና በፍ​ር​ግያ በኩል በተራ እየ​ዞረ ሄደ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ንም አጸ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="24">በእ​ስ​ክ​ን​ድ​ር​ያም የሚ​ኖር፥ ንግ​ግር የሚ​ች​ልና መጽ​ሐ​ፍን የሚ​ያ​ውቅ አጵ​ሎስ የሚ​ባል አንድ አይ​ሁ​ዳዊ ሰው ወደ ኤፌ​ሶን መጣ።</verse>
				<verse number="25">እር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ የተ​ማረ ነበር፤ ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሊያ​ስ​ተ​ም​ርና ሊመ​ሰ​ክር ከልቡ የሚ​ተጋ ነበር፤ ነገር ግን የዮ​ሐ​ን​ስን ጥም​ቀት ብቻ ተጠ​ምቆ ነበር።</verse>
				<verse number="26">እር​ሱም በም​ኵ​ራብ በግ​ልጥ ይና​ገር ጀመር፤ ጵር​ስ​ቅ​ላና አቂ​ላም በሰ​ሙት ጊዜ ወደ ማደ​ሪ​ያ​ቸው ወስ​ደው ፍጹም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ አስ​ረ​ዱት።</verse>
				<verse number="27">ወደ አካ​ይ​ያም ሊሄድ በወ​ደደ ጊዜ ወን​ድ​ሞች አጽ​ና​ኑት፤ እን​ዲ​ቀ​በ​ሉ​ትም ወደ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ጻፉ​ለት፤ ወደ እነ​ር​ሱም በደ​ረሰ ጊዜ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ላመ​ኑት ብዙ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፤ ትልቅ ርዳ​ታም ረዳ​ቸው።</verse>
				<verse number="28">ተሰ​ብ​ስ​በው ሳሉም በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት አይ​ሁ​ድን በግ​ልጥ እጅግ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበር፤ ስለ ኢየ​ሱ​ስም እርሱ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ ከመ​ጻ​ሕ​ፍት ማስ​ረጃ ያመ​ጣ​ላ​ቸው ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ አጵ​ሎስ በቆ​ሮ​ን​ቶስ ሳለ፥ ጳው​ሎስ ላይ ላዩን ሄዶ ወደ ኤፌ​ሶን መጣ፤ በዚ​ያም ጥቂት ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትን አገኘ።</verse>
				<verse number="2">“ካመ​ና​ችሁ ጀምሮ በውኑ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተቀ​ብ​ላ​ች​ኋ​ልን?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “አል​ተ​ቀ​በ​ል​ንም መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዳለ ስንኳ አል​ሰ​ማ​ንም” አሉት።</verse>
				<verse number="3">እር​ሱም፥ “እን​ኪያ በምን ተጠ​መ​ቃ​ችሁ?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “በዮ​ሐ​ንስ ጥም​ቀት” አሉት።</verse>
				<verse number="4">ጳው​ሎ​ስም፥ “ዮሐ​ንስ ከእ​ርሱ በኋላ በሚ​መ​ጣው በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እን​ዲ​ያ​ምኑ እየ​ሰ​በከ የን​ስሓ ጥም​ቀ​ትን አጠ​መቀ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">እነ​ር​ሱም ይህን በሰሙ ጊዜ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ተጠ​መቁ።</verse>
				<verse number="6">ጳው​ሎ​ስም እጁን በጫ​ነ​ባ​ቸው ጊዜ መን​ፈስ ቅዱስ በእ​ነ​ርሱ ላይ ወረደ፤ ያን​ጊ​ዜም በሀ​ገሩ ሁሉ ቋንቋ ተና​ገሩ፤ ትን​ቢ​ትም ተና​ገሩ።</verse>
				<verse number="7">ሰዎ​ቹም ሁሉ ዐሥራ ሁለት ያህሉ ነበር።</verse>
				<verse number="8">ጳው​ሎ​ስም ወደ ምኵ​ራብ ገብቶ በግ​ልጥ አስ​ተ​ማረ፤ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥት እያ​ስ​ተ​ማ​ራ​ቸ​ውና እያ​ሳ​መ​ና​ቸው ሦስት ወር ቈየ።</verse>
				<verse number="9">በተ​ሰ​በ​ሰ​በ​ውም ሕዝብ ፊት አን​ዳ​ን​ዶች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትም​ህ​ርት ላይ ክፉ እየ​ተ​ና​ገሩ ባላ​መኑ ጊዜ፥ ጳው​ሎስ ከእ​ነ​ርሱ ተለየ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱ​ንም ይዞ ጢራ​ኖስ በሚ​ባል መም​ህር ቤት ሁል​ጊዜ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="10">በእ​ስ​ያም ያሉ አይ​ሁ​ድና አረ​ማ​ው​ያን ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እስ​ኪ​ሰሙ ድረስ እን​ደ​ዚሁ ሁለት ዓመት ኖረ።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጳ​ው​ሎስ እጅ ታላ​ላቅ ሥራን ይሠራ ነበር።</verse>
				<verse number="12">ከል​ብሱ ዘር​ፍና ከመ​ጠ​ም​ጠ​ሚ​ያዉ ጫፍ ቈር​ጠው እየ​ወ​ሰዱ በድ​ው​ያኑ ላይ ያኖ​ሩት ነበር፤ እነ​ር​ሱም ይፈ​ወሱ ነበር፤ ክፉ​ዎች መና​ፍ​ስ​ትም ይወጡ ነበር።</verse>
				<verse number="13">ከአ​ይ​ሁ​ድም አስ​ማት እያ​ደ​ረጉ የሚ​ዞሩ ሰዎች ክፉ​ዎች መና​ፍ​ስት ባሉ​ባ​ቸው ላይ “ጳው​ሎስ በሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ር​በት በኢ​የ​ሱስ ስም እና​ም​ላ​ች​ኋ​ለን” እያሉ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ስም ይጠ​ሩ​ባ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="14">እኒህ እን​ዲህ ያደ​ርጉ የነ​በ​ሩ​ትም የካ​ህ​ናቱ አለቃ የአ​ይ​ሁ​ዳ​ዊው የአ​ስ​ቂዋ ልጆች ናቸው፤ እነ​ር​ሱም ሰባት ነበሩ።</verse>
				<verse number="15">ያም ክፉ መን​ፈስ፥ “በኢ​የ​ሱስ አም​ና​ለሁ፥ ጳው​ሎ​ስ​ንም አው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲህ እና​ንተ እነ​ማን ናችሁ?” ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">ያም ክፉ መን​ፈስ የያ​ዘው ሰው ተነ​ሣ​ባ​ቸው፤ አየ​ለ​ባ​ቸ​ውም፤ አሸ​ነ​ፋ​ቸ​ውም፤ አቍ​ስ​ሎም ከዚያ ቤት አስ​ወ​ጥቶ አባ​ረ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">ይህም ነገር በኤ​ፌ​ሶን በሚ​ኖሩ በአ​ይ​ሁ​ድና በአ​ረ​ማ​ው​ያን ሁሉ ዘንድ ተሰማ፤ ሁሉም ፈሩ፤ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስ​ንም ስም ከፍ ከፍ አደ​ረጉ።</verse>
				<verse number="18">ያመ​ኑ​ትም ሁሉ እየ​መጡ ስለ ሠሩት ንስሓ ይገቡ ነበር።</verse>
				<verse number="19">ብዙ​ዎች አስ​ማ​ተ​ኞ​ችም መጽ​ሐ​ፎ​ቻ​ቸ​ውን እየ​ሰ​በ​ሰቡ እያ​መጡ በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት በእ​ሳት ያቃ​ጥሉ ነበር፤ ያቃ​ጠ​ሏ​ቸው የመ​ጽ​ሐ​ፎች ዋጋም አምሳ ሺህ ብር ነበር።</verse>
				<verse number="20">እን​ዲ​ህም እያለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በኀ​ይል ያድ​ግና ይበ​ረታ ነበር።</verse>
				<verse number="21">ይህም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ ጳው​ሎስ በመ​ቄ​ዶ​ን​ያና በአ​ካ​ይያ በኩል አልፎ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሊሄድ በልቡ ዐሰበ፥ “እዚ​ያም ከደ​ረ​ስሁ በኋላ ሮሜን ላያት ይገ​ባ​ኛል” አለ።</verse>
				<verse number="22">ከሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​ትም ሁለ​ቱን ጢሞ​ቴ​ዎ​ስ​ንና አር​ስ​ጦ​ስን ወደ መቄ​ዶ​ንያ ላከ፤ እርሱ ራሱ ጳው​ሎስ ግን ብዙ ቀን በእ​ስያ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="23">በዚ​ያም ወራት ስለ​ዚህ ትም​ህ​ርት ብዙ ሁከት ሆነ።</verse>
				<verse number="24">በዚ​ያም ብር ሠሪ የሆነ ድሜ​ጥ​ሮስ የሚ​ባል አንድ ሰው ነበር፤ ለአ​ር​ጤ​ም​ስም ከብር የቤተ መቅ​ደስ ምስል ይሠራ ነበር፤ አን​ጥ​ረ​ኞ​ች​ንም እያ​ሠራ ብዙ ገን​ዘብ ይሰ​ጣ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="25">አን​ጥ​ረ​ኞ​ች​ንና ይህን የመ​ሰ​ለ​ውን ሥራ የሚ​ሠ​ሩ​ት​ንም ሁሉ ሰብ​ስቦ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰዎች ሆይ፥ ጥቅም የም​ና​ገ​ኘው በዚህ ሥራ​ችን እንደ ሆነ እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="26">አሁን ግን እን​ደ​ም​ታ​ዩ​ትና እን​ደ​ም​ት​ሰ​ሙት ይህ ጳው​ሎስ ኤፌ​ሶ​ንን ብቻ ሳይ​ሆን መላ​ውን እስ​ያን አሳተ፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንም መለሰ፤ በሰው እጅ የሚ​ሠ​ሩ​ት​ንም ሁሉ አማ​ል​ክት አይ​ደ​ሉም አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="27">አሁን የም​ን​ቸ​ገር በዚህ ነገር ብቻ አይ​ደ​ለም፤ እስ​ያና መላው ዓለም የሚ​ያ​መ​ል​ካት የታ​ላቋ የአ​ር​ጤ​ም​ስም መቅ​ደስ ክብር ይቀ​ራል፤ ገና​ና​ነ​ቷም ይሻ​ራል።”</verse>
				<verse number="28">ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ ተቈ​ጡና ድም​ፃ​ቸ​ውን ከፍ አድ​ር​ገው፥ “የኤ​ፌ​ሶን አር​ጤ​ምስ ክብ​ርዋ ታላቅ ነው” አሉ።</verse>
				<verse number="29">ከተ​ማ​ውም ሁሉ ታወከ፤ የመ​ቄ​ዶ​ን​ያን ሰዎች የጳ​ው​ሎ​ስን ወዳ​ጆች ጋይ​ዮ​ስ​ንና አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮ​ስ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ጋር እየ​ጐ​ተ​ቱ​በ​አ​ን​ድ​ነት ወደ ጨዋ​ታው ቦታ ሮጡ።</verse>
				<verse number="30">ጳው​ሎ​ስም ወደ አሕ​ዛብ መካ​ከል ሊገባ ወድዶ ነበር፤ ነገር ግን ደቀ መዛ​ሙ​ርት ከለ​ከ​ሉት።</verse>
				<verse number="31">ከእ​ስ​ያም የሆኑ ታላ​ላ​ቆች ወዳ​ጆቹ ወደ ጨዋ​ታው ቦታ እን​ዳ​ይ​ገባ ልከው ማለ​ዱት።</verse>
				<verse number="32">በዚ​ያም በጨ​ዋ​ታው ቦታ የነ​በሩ ሰዎች እየ​ጮኹ ቈዩ፤ በሌ​ላም ቋንቋ የሚ​ጮሁ ነበሩ፤ በጉ​ባ​ኤው ታላቅ ድብ​ል​ቅ​ልቅ ሆኖ ነበ​ርና፤ ከእ​ነ​ርሱ የሚ​በ​ዙት ግን በምን ምክ​ን​ያት እንደ ተሰ​በ​ሰቡ አያ​ው​ቁም ነበር።</verse>
				<verse number="33">በዚያ የነ​በሩ አይ​ሁ​ድም እስ​ክ​ን​ድ​ሮስ የሚ​ባል አይ​ሁ​ዳዊ ሰውን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አስ​ነሡ፤ እር​ሱም ተነ​ሥቶ በእጁ ምል​ክት ሰጠና ለሕ​ዝቡ ሊከ​ራ​ከ​ር​ላ​ቸው ወደደ።</verse>
				<verse number="34">አይ​ሁ​ዳዊ እን​ደ​ሆ​ነም ባወቁ ጊዜ “የኤ​ፌ​ሶን አር​ጤ​ምስ ክብ​ርዋ ታላቅ ነው” እያሉ ሁለት ሰዓት ያህል ሁሉም በአ​ንድ ድምፅ ጮሁ።</verse>
				<verse number="35">ከዚ​ህም በኋላ የከ​ተ​ማው ጸሓፊ ተነ​ሥቶ ሕዝ​ቡን ጸጥ አሰ​ኝቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የኤ​ፌ​ሶን ሰዎች ሆይ፥ ስሙ፤ የኤ​ፌ​ሶን ከተማ ታላ​ቂ​ቱን አር​ጤ​ም​ስ​ንና ከሰ​ማይ የወ​ረ​ደ​ውን ጣዖ​ት​ዋን እን​ደ​ም​ት​ጠ​ብቅ የማ​ያ​ውቅ ማነው?</verse>
				<verse number="36">ስለ​ዚ​ህም እር​ስ​ዋን መቃ​ወም የሚ​ቻ​ለው ያለ አይ​መ​ስ​ለ​ኝም፤ አሁ​ንም ይህን በጠ​ብና በክ​ር​ክር ሳይ​ሆን በቀ​ስታ ልና​ደ​ር​ገው ይገ​ባ​ናል።</verse>
				<verse number="37">የአ​ማ​ል​ክ​ትን ቤት ያል​ዘ​ረ​ፉ​ት​ንና በአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ችን ላይ ክፉ ቃልን ያል​ተ​ና​ገ​ሩ​ትን እነ​ዚ​ህን ሰዎች እነሆ ወደ እዚህ አም​ጥ​ታ​ች​ኋ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="38">ድሜ​ጥ​ሮ​ስና ከእ​ርሱ ጋር ያሉ አን​ጥ​ረ​ኞች ግን በማ​ንም ላይ ጠብ እን​ዳ​ላ​ቸው እርስ በር​ሳ​ቸው ይከ​ራ​ከሩ፤ እነ​ሆም በከ​ተ​ማው ውስጥ ፍርድ ቤት አለ፤ ዳኞ​ችም አሉ።</verse>
				<verse number="39">ነገር ግን ይህ የም​ት​ከ​ራ​ከ​ሩ​በት ነገር ሌላ ከሆነ በሕግ ሸንጎ ይፈ​ታል።</verse>
				<verse number="40">ዛሬም በደል ሳይ​ኖር በአ​መ​ጣ​ች​ሁ​ብን ክር​ክር እኛ እን​ቸ​ገ​ራ​ለ​ንና ስለ​ዚህ ክር​ክር የም​ን​ወ​ቃ​ቀ​ሰው ነገር የለም፥” ይህ​ንም ብሎ ሸን​ጎ​ውን ፈታ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">ክር​ክ​ሩም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ ጳው​ሎስ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን ጠራና አጽ​ና​ና​ቸው፤ ተሰ​ና​በ​ታ​ቸ​ውም፤ ወጥ​ቶም ወደ መቄ​ዶ​ንያ ሄደ።</verse>
				<verse number="2">በዚያ አው​ራ​ጃም አልፎ ሄደ፤ በቃ​ሉም ብዙ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ግሪክ ሀገር ሄደ።</verse>
				<verse number="3">በዚ​ያም ሦስት ወር ተቀ​መጠ፤ ወደ ሶር​ያም በመ​ር​ከብ ለመ​ሄድ ዐስቦ ሳለ አይ​ሁድ ስለ ተማ​ከ​ሩ​በት ወደ መቄ​ዶ​ንያ ሊመ​ለስ ቈረጠ።</verse>
				<verse number="4">ከእ​ር​ሱም ጋር የቤ​ርያ ሀገር ሰው የሚ​ሆን ሱሲ​ጳ​ጥ​ሮስ፥ የተ​ሰ​ሎ​ን​ቄም ሰዎች አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮ​ስና ሲኮ​ን​ዱስ፥ የደ​ር​ቤኑ ሰው ጋይ​ዮ​ስና ጢሞ​ቴ​ዎ​ስም፥ የእ​ስያ ሰዎች የሚ​ሆኑ ቲኪ​ቆ​ስና ጥሮ​ፊ​ሞ​ስም አብ​ረ​ውት ሄዱ።</verse>
				<verse number="5">እነ​ር​ሱም ቀድ​መ​ውን ሄደው በጢ​ሮ​አስ ቆዩን።</verse>
				<verse number="6">እኛ ግን ከፋ​ሲካ በኋላ ከፊ​ል​ጵ​ስ​ዩስ ተነ​ሥ​ተን በባ​ሕር ላይ ተጕ​ዘን በአ​ም​ስት ቀን ወደ ጢሮ​አስ ደረ​ስን፤ በዚ​ያም ሰባት ቀን ተቀ​መ​ጥን።</verse>
				<verse number="7">ከሳ​ም​ን​ቱም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን እሑድ ማዕድ ለመ​ባ​ረክ ተሰ​ብ​ስ​በን ሳለን ጳው​ሎስ በማ​ግ​ሥቱ የሚ​ሄድ ነውና ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ጀመረ፤ እስከ መን​ፈቀ ሌሊ​ትም ድረስ ትም​ህ​ር​ቱን አስ​ረ​ዘመ።</verse>
				<verse number="8">ተሰ​ብ​ስ​በን በነ​በ​ር​ን​በት ሰገ​ነ​ትም ብዙ መብ​ራት ነበር።</verse>
				<verse number="9">ስሙ አው​ጤ​ክስ የሚ​ባል አንድ ጐል​ማሳ ልጅም በመ​ስ​ኮት በኩል ተቀ​ምጦ ሳለ ከባድ እን​ቅ​ልፍ አን​ቀ​ላ​ፍቶ ነበር፤ ጳው​ሎ​ስም ትም​ህ​ር​ቱን ባስ​ረ​ዘመ ጊዜ ያ ጐል​ማሳ ከእ​ን​ቅ​ልፉ ብዛት የተ​ነሣ ከተ​ኛ​በት ከሦ​ስ​ተ​ኛው ፎቅ ወደ ታች ወደቀ፤ ሬሳ​ው​ንም አነ​ሡት።</verse>
				<verse number="10">ጳው​ሎ​ስም ወርዶ በላዩ ወደቀ፤ አቅ​ፎም ያዘው፤ እነ​ር​ሱ​ንም፥ “ነፍሱ አለ​ችና አት​ደ​ን​ግጡ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="11">ከዚ​ህም በኋላ ወደ ሰገ​ነት ወጣ፤ ማዕ​ዱ​ንም ባርኮ በላ፤ እስ​ኪ​ነ​ጋም ድረስ ብዙ ትም​ህ​ርት አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፤ ከዚያ በኋ​ላም ተነ​ሥቶ ሄደ።</verse>
				<verse number="12">ብላ​ቴ​ና​ው​ንም ደኅና ሆኖ ወሰ​ዱት፤ እጅ​ግም ደስ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">እኛ ግን በመ​ር​ከብ ሆነን ወደ አሶስ ሄድን፤ ከዚያ ጳው​ሎ​ስን ልን​ቀ​በ​ለው እንሻ ነበ​ርና፤ እን​ደ​ዚሁ በእ​ግር እን​ደ​ሚ​መጣ ነግ​ሮን ነበ​ርና ተቀ​በ​ል​ነው።</verse>
				<verse number="14">አሶ​ስም ደረ​ስን፤ በመ​ር​ከ​ብም ይዘ​ነው ወደ ሚጢ​ሊኒ ሄድን።</verse>
				<verse number="15">በማ​ግ​ሥ​ቱም ከዚያ ወጥ​ተን በኪ​ዮስ ፊት ለፊት ደረ​ስን፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም ወደ ሳሞስ አለ​ፍን፤ በት​ሮ​ጊ​ሊ​ዮም ተቀ​መ​ጥን፤ ከዚህ ቀን በኋ​ላም ወደ መሊጡ ደረ​ስን።</verse>
				<verse number="16">ጳው​ሎ​ስም በእ​ስያ እን​ዳ​ይ​ዘ​ገይ በኤ​ፌ​ሶን በኩል ሊሄድ ቈርጦ ነበር፤ የሚ​ቻ​ለ​ውም ቢሆን ለበ​ዓለ ኀምሳ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ድ​ረስ ቸኵሎ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="17">ከመ​ሊ​ጡም የቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንን ቀሳ​ው​ስት ይጠ​ሩ​አ​ቸው ዘንድ ወደ ኤፌ​ሶን ላከ።</verse>
				<verse number="18">ወደ እር​ሱም በመጡ ጊዜ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ወደ እስያ ከገ​ባ​ሁ​በት ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ጀምሮ በዘ​መኑ ሁሉ ከእ​ና​ንተ ዘንድ እንደ ተቀ​መ​ጥሁ እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​ገ​ለ​ገ​ልሁ በፍ​ጹም መከ​ራና በል​ቅሶ ከአ​ይ​ሁ​ድም ሴራ የተ​ነሣ በደ​ረ​ሰ​ብኝ ፈተና እየ​ተ​ጋ​ደ​ልሁ፥</verse>
				<verse number="20">በጉ​ባ​ኤም ሆነ በቤት ስነ​ግ​ራ​ች​ሁና ሳስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ከሚ​ጠ​ቅ​ማ​ችሁ ነገር አን​ዳች ስን​ኳን አላ​ስ​ቀ​ረ​ሁ​ባ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="21">ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መመ​ለ​ስ​ንና በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ማመ​ንን ለአ​ይ​ሁ​ድና ለአ​ረ​ማ​ው​ያን እየ​መ​ሰ​ከ​ርሁ፤</verse>
				<verse number="22">አሁ​ንም እነሆ በመ​ን​ፈስ ታሥሬ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እሄ​ዳ​ለሁ፤ ነገር ግን በዚያ የሚ​ያ​ገ​ኘ​ኝን አላ​ው​ቅም።</verse>
				<verse number="23">ነገር ግን መን​ፈስ ቅዱስ፦ በየ​ከ​ተ​ማው መከ​ራና እስ​ራት ይጠ​ብ​ቅ​ሃል ብሎ ይመ​ሰ​ክ​ር​ል​ኛል።</verse>
				<verse number="24">ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የጸ​ጋ​ውን ወን​ጌል እን​ዳ​ስ​ተ​ምር ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የተ​ቀ​በ​ል​ሁ​ትን ሩጫ​ዬን እን​ድ​ጨ​ር​ስና መል​እ​ክ​ቴ​ንም እን​ድ​ፈ​ጽም ነው እንጂ ለሰ​ው​ነቴ ምንም አላ​ስ​ብ​ላ​ትም።</verse>
				<verse number="25">አሁ​ንም እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት የሰ​በ​ክ​ሁ​ላ​ችሁ እና​ንተ ሁላ​ችሁ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ፊቴን እን​ደ​ማ​ታ​ዩኝ እኔ ዐው​ቄ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="26">እኔ ከሁ​ላ​ች​ሁም ደም ንጹሕ እንደ ሆንሁ እነሆ ዛሬ በዚች ሌሊት እመ​ሰ​ክ​ር​ላ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="27">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክር ሁሉ የሰ​ወ​ር​ኋ​ች​ሁና ያል​ነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ የለም።</verse>
				<verse number="28">አሁ​ንም በገዛ ደሙ የዋ​ጃ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ትጠ​ብቁ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ እና​ን​ተን ጳጳ​ሳት አድ​ርጎ ለሾ​መ​ባት ለመ​ን​ጋው ሁሉና ለራ​ሳ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ።</verse>
				<verse number="29">ከእኔ በኋላ ለመ​ን​ጋ​ዪቱ የማ​ይ​ራሩ ነጣ​ቂ​ዎች ተኵ​ላ​ዎች እን​ደ​ሚ​መጡ እኔ አው​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="30">ደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ንም ወደ እነ​ርሱ ይመ​ልሱ ዘንድ ጠማማ ትም​ህ​ር​ትን የሚ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ሰዎች ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ይነ​ሣሉ።</verse>
				<verse number="31">ስለ​ዚ​ህም ትጉ፤ እኔ ሁላ​ች​ሁ​ንም ሳስ​ተ​ምር ሦስት ዓመት ሙሉ ሌትም ቀንም እን​ባዬ እን​ዳ​ል​ተ​ገታ ዐስቡ።</verse>
				<verse number="32">አሁ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ሊያ​ን​ጻ​ችሁ፥ በቅ​ዱ​ሳ​ንም ሁሉ መካ​ከል ርስ​ትን ሊሰ​ጣ​ችሁ ለሚ​ች​ለው ለጸ​ጋው ቃል አደራ ሰጥ​ቻ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="33">ወር​ቅም ቢሆን፥ ብርም ቢሆን፥ ልብ​ስም ቢሆን ከእ​ና​ንተ ከአ​ንዱ ስንኳ አል​ተ​መ​ኘ​ሁም።</verse>
				<verse number="34">እነ​ዚ​ህም እጆች ለም​ሻው ነገ​ርና ከእ​ኔም ጋር ላሉት እን​ዳ​ገ​ለ​ገሉ እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="35">በድ​ካ​ማ​ች​ንና በሥ​ራ​ችን ነዳ​ያ​ንን እን​ቀ​በ​ላ​ቸው ዘንድ እን​ደ​ሚ​ገ​ባን ይህን አስ​ተ​ም​ሬ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ ‘ከሚ​ቀ​በል ይልቅ የሚ​ሰጥ ብፁዕ ነው’ ያለ​ው​ንም የጌ​ታ​ች​ንን የኢ​የ​ሱ​ስን ቃል ዐስቡ።”</verse>
				<verse number="36">ይህ​ንም ከአለ በኋላ ተን​በ​ር​ክኮ አብ​ረ​ውት ካሉት ሁሉ ጋር ጸለየ።</verse>
				<verse number="37">ሁሉም እጅግ አለ​ቀሱ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም አን​ገ​ቱን አቅ​ፈው ሳሙት።</verse>
				<verse number="38">ይል​ቁ​ንም “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ፊቴን አታ​ዩ​ትም” ስለ አላ​ቸው እጅግ አዘኑ። እስከ መር​ከ​ብም ድረስ ሸኙት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">ከእ​ነ​ር​ሱም ከተ​ለ​የን በኋላ እኛ በመ​ር​ከብ ተሳ​ፍ​ረን፥ መን​ገ​ዳ​ች​ን​ንም አቅ​ን​ተን ወደ ቆስ መጣን፤ በበ​ነ​ጋ​ውም ወደ ሮዶስ፥ ከዚ​ያም ወደ ጳጥራ ገባን።</verse>
				<verse number="2">ወደ ፊን​ቄም የሚ​ያ​ልፍ መር​ከብ አግ​ኝ​ተን በዚያ ላይ ተሳ​ፍ​ረን ሄድን።</verse>
				<verse number="3">ቆጵ​ሮ​ስ​ንም አየ​ናት፤ በስተ ግራ​ች​ንም ትተ​ናት ወደ ሶርያ ሄድን፤ ወደ ጢሮ​ስም ወረ​ድን፤ በመ​ር​ከብ ያለ​ውን ጭነት ሁሉ በዚያ ያራ​ግፉ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="4">በዚ​ያም ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትን አገ​ኘ​ንና በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ሰባት ቀን ተቀ​መ​ጥን፤ እነ​ር​ሱም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ተገ​ል​ጾ​ላ​ቸው ጳው​ሎ​ስን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዳ​ይ​ወጣ ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="5">ከዚ​ህም በኋላ ለመ​ሄድ ወጣን፤ ሁሉም ከሚ​ስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ከል​ጆ​ቻ​ቸው ጋር እስከ ከተ​ማው ውጭ ሸኙን፤ በባ​ሕ​ሩም ዳር ተን​በ​ር​ክ​ከን ጸለ​ይን።</verse>
				<verse number="6">እርስ በር​ሳ​ች​ንም ተሳ​ስ​መን ተሰ​ነ​ባ​በ​ትን፤ ከዚ​ህም በኋላ ወደ መር​ከብ ወጣን፤ እነ​ር​ሱም ወደ ቤታ​ቸው ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="7">እኛም ከጢ​ሮስ ወጥ​ተን አካ ወደ​ም​ት​ባል ሀገር መጣን፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ን​ንም አግ​ኝ​ተን ሰላም አል​ና​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ አንድ ቀን አደ​ርን።</verse>
				<verse number="8">በማ​ግ​ሥ​ቱም ወጥ​ተን ወደ ቂሳ​ርያ ሄድን፤ ወደ ወን​ጌ​ላ​ዊው ወደ ፊል​ጶስ ቤትም ገባን፤ እር​ሱም ከሰ​ባቱ ወን​ድ​ሞች ዲያ​ቆ​ናት አንዱ ነው።</verse>
				<verse number="9">ለእ​ር​ሱም ትን​ቢት የሚ​ና​ገሩ አራት ደና​ግል ሴቶች ልጆች ነበ​ሩት።</verse>
				<verse number="10">በእ​ር​ሱም ዘንድ ብዙ ቀን ኖርን፤ ከይ​ሁ​ዳም አጋ​ቦስ የሚ​ባል አንድ ነቢይ ወረደ።</verse>
				<verse number="11">ወደ እኛም መጣና የጳ​ው​ሎ​ስን መታ​ጠ​ቂያ አን​ሥቶ እጁ​ንና እግ​ሩን በገዛ እጁ አስሮ እን​ዲህ አለ፥ “መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዲህ ይላል፤ የዚ​ህን መታ​ጠ​ቂያ ጌታ አይ​ሁድ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዲህ ያስ​ሩ​ታል፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ታል።”</verse>
				<verse number="12">ይህ​ንም ሰም​ተን የሀ​ገ​ሪ​ቱን ሰዎች ይዘን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዳ​ይ​ወጣ ጳው​ሎ​ስን ማለ​ድ​ነው።</verse>
				<verse number="13">ጳው​ሎስ ግን መልሶ፥ “ለምን እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ? እያ​ለ​ቀ​ሳ​ችሁ ልቤን ትሰ​ብ​ሩ​ታ​ላ​ችሁ፤ እኔ እኮ ተስፋ የማ​ደ​ር​ገው መከ​ራ​ንና እግር ብረ​ትን ብቻ አይ​ደ​ለም፤ እኔ ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ሞ​ትም ቢሆን የቈ​ረ​ጥሁ ነኝ” አለ።</verse>
				<verse number="14">እንቢ ባለ ጊዜም ዝም አልን፤ እኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፈ​ቀ​ደው ይሁን ብለን ተው​ነው።</verse>
				<verse number="15">ከእ​ነ​ዚ​ያም ቀኖች በኋላ ተዘ​ጋ​ጅ​ተን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣን።</verse>
				<verse number="16">ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም ከቂ​ሳ​ርያ አብ​ረ​ውን የመጡ ነበሩ፤ ሄደ​ንም ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዎቹ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ወገን ከሆ​ነው በቆ​ጵ​ሮስ በሚ​ኖ​ረው በም​ና​ሶን ቤት አደ​ርን።</verse>
				<verse number="17">ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በደ​ረ​ስን ጊዜም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን በደ​ስታ ተቀ​በ​ሉን።</verse>
				<verse number="18">በማ​ግ​ሥ​ቱም ጳው​ሎስ ከእኛ ጋር ወደ ያዕ​ቆብ ገባ፤ ቀሳ​ው​ስ​ትም ሁሉ በዚያ ነበሩ።</verse>
				<verse number="19">ጳው​ሎ​ስም ሰላ​ምታ ካቀ​ረ​በ​ላ​ቸው በኋላ በእ​ርሱ ሐዋ​ር​ያ​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ሕ​ዛብ ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ነገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="20">እነ​ር​ሱም ሰም​ተው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ወን​ድ​ማ​ችን ሆይ፥ ከአ​ይ​ሁድ መካ​ከል ያመ​ኑት ስንት አእ​ላ​ፋት እንደ ሆኑ ታያ​ለ​ህን? ሁሉም ለኦ​ሪት የሚ​ቀኑ ናቸው።</verse>
				<verse number="21">ነገር ግን የማ​ይ​ሆ​ነ​ውን እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ምር፥ የሙ​ሴ​ንም ሕግ እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ዋ​ቸው፥ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ያሉ ያመኑ አይ​ሁ​ድ​ንም ልጆ​ቻ​ቸ​ውን እን​ዳ​ይ​ገ​ርዙ፥ የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ እን​ዳ​ይ​ፈ​ጽሙ እን​ደ​ም​ት​ከ​ለ​ክ​ላ​ቸው ስለ አንተ ነግ​ረ​ዋ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="22">አሁ​ንሳ ምን ይሁን? ሕዝቡ ወደ​ዚህ እንደ መጣህ ይሰ​ሙና ይሰ​በ​ሰቡ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="23">ስለ​ዚ​ህም ይህን የም​ል​ህን አድ​ርግ፦ ብፅ​ዐት ያላ​ቸው አራት ሰዎች በእኛ ዘንድ አሉ።</verse>
				<verse number="24">ይዘ​ሃ​ቸው ሂድ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ራስ​ህን አንጻ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም እን​ዲ​ላጩ ስለ እነ​ርሱ ገን​ዘብ ክፈ​ል​ላ​ቸው፤ የሚ​ያ​ሙ​ህም በሐ​ሰት እንደ ሆነ፥ አን​ተም የኦ​ሪ​ትን ሕግ እን​ደ​ም​ት​ጠ​ብቅ ሁሉም ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="25">ስለ​ሚ​አ​ም​ኑት አሕ​ዛብ ግን እርም ከሆ​ነ​ውና ለጣ​ዖ​ታት ከሚ​ሠ​ዉት፥ ከዝ​ሙት፥ ሞቶ የተ​ገ​ኘ​ው​ንና ደምን ከመ​ብ​ላት እን​ዲ​ከ​ለ​ከሉ እኛ አዝ​ዘ​ናል።”</verse>
				<verse number="26">ያን​ጊ​ዜም ጳው​ሎስ ሰዎ​ችን ይዞ በማ​ግ​ሥቱ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነጻ። የመ​ን​ጻ​ታ​ቸ​ው​ንም ወራት መድ​ረ​ሱን ከነ​ገ​ራ​ቸው በኋላ ሁሉም እየ​አ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርቡ ዘንድ ወደ ቤተ መቅ​ደስ ይዞ​አ​ቸው ገባ።</verse>
				<verse number="27">በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከእ​ስያ የመጡ አይ​ሁድ ጳው​ሎ​ስን በመ​ቅ​ደስ አዩት፤ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ በእ​ርሱ ላይ አነ​ሳ​ሥ​ተው ያዙት።</verse>
				<verse number="28">እየ​ጮ​ሁም እን​ዲህ አሉ፥ “እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሆይ፥ ርዱን፤ በየ​ስ​ፍ​ራው ሕዝ​ባ​ች​ንን፥ ኦሪ​ት​ንም፥ ይህ​ንም ስፍራ የሚ​ቃ​ወም ትም​ህ​ርት ለሰው ሁሉ የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር እነሆ፥ ይህ ሰው ነው፤ አሁ​ንም አረ​ማ​ው​ያ​ንን ወደ መቅ​ደስ አስ​ገባ፤ ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም አረ​ከሰ።</verse>
				<verse number="29">የኤ​ፌ​ሶን ሀገር ሰው የሆነ ጥሮ​ፊ​ሞ​ስን ከጳ​ው​ሎስ ጋር በከ​ተማ አይ​ተ​ውት ነበ​ርና፤ ጳው​ሎ​ስም ወደ ቤተ መቅ​ደስ ያስ​ገ​ባው መስ​ሎ​አ​ቸው ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="30">ከተ​ማ​ውም ሁሉ ታወከ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ እየ​ሮጡ ሄደው ጳው​ሎ​ስን ጐት​ተው ከቤተ መቅ​ደስ አወ​ጡት፤ በሩ​ንም ሁሉ ዘጉ።</verse>
				<verse number="31">ሊገ​ድ​ሉ​ትም ፈል​ገው ብዙ ደበ​ደ​ቡት፤ ወዲ​ያ​ውም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በመ​ላዋ እንደ ታወ​ከች የሚ​ገ​ልጥ መል​እ​ክት ወደ ሻለ​ቃው ደረ​ሰ​ለት።</verse>
				<verse number="32">በዚያ ጊዜም ጭፍ​ሮ​ቹን ከአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸው ጋር ይዞ ወደ እነ​ርሱ ሄደ፤ እነ​ር​ሱም የሻ​ለ​ቃ​ውን ጭፍ​ሮች ባዩ ጊዜ ጳው​ሎ​ስን መም​ታ​ታ​ቸ​ውን ተዉ።</verse>
				<verse number="33">የሻ​ለ​ቃ​ውም ቀረብ ብሎ ያዘው፤ በሁ​ለት ሰን​ሰ​ለ​ትም እን​ዲ​ታ​ሰር አዘዘ፤ “ምን​ድ​ነው? ምንስ አደ​ረገ?” ብሎም ጠየቀ።</verse>
				<verse number="34">ሕዝ​ቡም እኩ​ሌ​ቶቹ እን​ዲህ ነው፤ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም እን​ዲህ አይ​ደ​ለም እያሉ ይጮሁ ነበር፤ ሻለ​ቃ​ውም ሕዝቡ የሚ​ታ​ወ​ክ​በ​ትን ርግ​ጡን ማወቅ ተሣ​ነው፤ ወደ ወታ​ደ​ሮ​ቹም ሰፈር እን​ዲ​ወ​ስ​ዱት አዘዘ።</verse>
				<verse number="35">ደረ​ጃ​ው​ንም በሚ​ወ​ጣ​በት ጊዜ ወታ​ደ​ሮች ተሸ​ክ​መው አወ​ጡት፤ ሰው ይጋፋ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="36">ብዙ​ዎ​ችም ይከ​ተ​ሉት ነበር፤ ሕዝ​ቡም፥ “አስ​ወ​ግ​ዱት” እያሉ ይጮሁ ነበር።</verse>
				<verse number="37">ወደ ሰፈ​ርም በደ​ረሰ ጊዜ ጳው​ሎስ ሻለ​ቃ​ውን፥ “ላነ​ጋ​ግ​ርህ ትፈ​ቅ​ድ​ል​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ ሻለ​ቃ​ውም፥ “የጽ​ርዕ ቋንቋ ታው​ቃ​ለ​ህን?” አለው።</verse>
				<verse number="38">“ምና​ል​ባት ከዚህ በፊት ወን​ጀል የሠ​ራ​ህና ከነ​ፍሰ ገዳ​ዮች አራት ሺህ ሰዎ​ችን ይዘህ ወደ ምድረ በዳ የወ​ጣህ ያ ግብ​ፃዊ አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን?” አለው።</verse>
				<verse number="39">ጳው​ሎ​ስም፥ “እኔስ አይ​ሁ​ዳዊ ሰው ነኝ፤ የተ​ወ​ለ​ድ​ሁ​ባ​ትም ሀገር ጠር​ሴስ የታ​ወ​ቀች የቂ​ል​ቅያ ከተማ ናት፤ ለሕ​ዝ​ቡም እን​ድ​ነ​ግ​ራ​ቸው ትፈ​ቅ​ድ​ልኝ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="40">በፈ​ቀ​ደ​ለ​ትም ጊዜ ጳው​ሎስ በደ​ረ​ጃው ላይ ቆሞ እጁን ወደ ሕዝቡ ዘረጋ፤ እጅ​ግም ጸጥታ በሆነ ጊዜ ጳው​ሎስ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ ተና​ገረ፤ እን​ዲ​ህም አለ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">“እና​ንተ ወን​ድ​ሞ​ችና አባ​ቶች፥ አሁን በፊ​ታ​ችሁ የም​ና​ገ​ረ​ውን ስሙኝ።”</verse>
				<verse number="2">በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ እን​ደ​ሚ​ነ​ግ​ራ​ቸው በሰ​ሙም ጊዜ ጸጥ ብለው አዳ​መ​ጡት።</verse>
				<verse number="3">ጳው​ሎ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ አይ​ሁ​ዳዊ ሰው ነኝ፤ የቂ​ል​ቅያ ክፍል በም​ት​ሆን በጠ​ር​ሴስ ከተማ ተወ​ለ​ድሁ፤ በዚ​ችም ከተማ ከገ​ማ​ል​ያል እግር ሥር ሆኜ አደ​ግሁ፤ የአ​ባ​ቶ​ች​ንም ሕግ ተማ​ርሁ፤ እና​ንተ ሁላ​ችሁ ዛሬ እን​ደ​ም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀና​ተኛ ነበ​ርሁ።</verse>
				<verse number="4">ይህን ትም​ህ​ርት የሚ​ከ​ተሉ ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም እያ​ሰ​ርሁ ወደ ወህኒ ቤት አሳ​ልፌ በመ​ስ​ጠት እስከ ሞት ድረስ አሳ​ደ​ድ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">እን​ዲ​ቀ​ጡም ከዚያ ያሉ​ትን አስሬ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመ​ጣ​ቸው ዘንድ በደ​ማ​ስቆ ወደ አሉ ወን​ድ​ሞች እን​ድ​ሄድ ከእ​ነ​ርሱ ዘንድ የሥ​ል​ጣን ደብ​ዳቤ የተ​ቀ​በ​ል​ኋ​ቸው ሊቀ ካህ​ና​ቱና መም​ህ​ራን ሁሉ ይመ​ሰ​ክ​ራሉ።</verse>
				<verse number="6">“ከዚህ በኋላ ወደ ደማ​ስቆ ስሄድ ቀትር በሆነ ጊዜ ወደ ከተ​ማው አቅ​ራ​ቢያ ደርሼ ሳለሁ ድን​ገት ታላቅ መብ​ረቅ ከሰ​ማይ በእኔ ላይ አን​ፀ​ባ​ረቀ።</verse>
				<verse number="7">በም​ድር ላይም ወደ​ቅሁ ‘ሳውል ሳውል ለምን ታሳ​ድ​ደ​ኛ​ለህ?’ የሚል ቃል​ንም ሰማሁ።</verse>
				<verse number="8">እኔም መልሼ፦ ‘አቤቱ፥ አንተ ማነህ?’ አል​ሁት፤ እር​ሱም፦ ‘አንተ የም​ታ​ሳ​ድ​ደኝ የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ ነኝ’ አለኝ።</verse>
				<verse number="9">አብ​ረ​ውኝ የነ​በ​ሩ​ትም መብ​ረ​ቁን አይ​ተው ደነ​ገጡ፤ ነገር ግን ይና​ገ​ረኝ የነ​በ​ረ​ውን ቃል አል​ሰ​ሙም።</verse>
				<verse number="10">‘አቤቱ፥ ጌታዬ ምን ላድ​ርግ?’ አልሁ፤ ጌታም፦ ‘ተነ​ሥና ወደ ደማ​ስቆ ሂድ፤ ልታ​ደ​ር​ገው የሚ​ገ​ባ​ህ​ንም ሁሉ በዚያ ይነ​ግ​ሩ​ሃል’ አለኝ።</verse>
				<verse number="11">ከዚ​ያም በኋላ ከመ​ብ​ረቁ ነፀ​ብ​ራቅ የተ​ነሣ ዐይ​ኔን ታወ​ርሁ፤ አብ​ረ​ውኝ የነ​በ​ሩ​ትም እየ​መ​ሩኝ ወደ ደማ​ስቆ ደረ​ስሁ።</verse>
				<verse number="12">“እንደ ሕጉም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሐና​ንያ የሚ​ባል አንድ ሰው ነበረ፤ በደ​ማ​ስ​ቆም የሚ​ኖሩ አይ​ሁድ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑት ነበር።</verse>
				<verse number="13">ወደ እኔም መጥቶ በፊቴ ቆመና፦ ‘ወን​ድሜ ሳውል ሆይ፥ እይ’ አለ፤ ያን​ጊ​ዜም ወደ እርሱ አየሁ።</verse>
				<verse number="14">እን​ዲ​ህም አለኝ፤ ‘የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ ፈቃ​ዱን ታው​ቅና ጽድ​ቁ​ንም ታይ ዘንድ፥ ቃሉ​ንም ከአ​ን​ደ​በቱ ትሰማ ዘንድ መረ​ጠህ።</verse>
				<verse number="15">በሕ​ዝ​ብም ሁሉ ዘንድ ባየ​ኸ​ውና በሰ​ማ​ኸው ምስ​ክር ትሆ​ነ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="16">አሁ​ንም የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ልን​ገ​ርህ፦ ተነሥ ስሙን እየ​ጠ​ራህ ተጠ​መቅ፤ ከኀ​ጢ​አ​ት​ህም ታጠብ።’</verse>
				<verse number="17">“ከዚ​ህም በኋላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ልሼ በቤተ መቅ​ደስ ስጸ​ልይ ተመ​ስጦ መጣ​ብኝ።</verse>
				<verse number="18">‘ስለ እኔ የም​ት​መ​ሰ​ክ​ረ​ውን ምስ​ክ​ር​ነት አይ​ቀ​በ​ሉ​ህ​ምና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ፈጥ​ነህ ውጣ’ ሲለኝ አየ​ሁት።</verse>
				<verse number="19">እኔም እን​ዲህ አል​ሁት፦ ‘ጌታዬ ሆይ፥ በአ​ንተ የሚ​ያ​ም​ኑ​ትን በየ​ም​ኵ​ራ​ቦ​ቻ​ቸው ሳስ​ራ​ቸ​ውና ስደ​በ​ድ​ባ​ቸው የነ​በ​ርሁ እኔ እንደ ሆንሁ እነ​ርሱ ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="20">ሰማ​ዕ​ት​ህን እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስን በገ​ደ​ሉ​ትም ጊዜ እኔ እዚያ አብ​ሬ​አ​ቸው ነበ​ርሁ፤ የገ​ዳ​ዮ​ች​ንም ልብስ እጠ​ብቅ ነበር።’</verse>
				<verse number="21">እር​ሱም፦ ‘ሂድ ርቀው ወደ አሉ አሕ​ዛብ እል​ክ​ሃ​ለ​ሁና’ ” አለኝ።</verse>
				<verse number="22">ከጳ​ው​ሎ​ስም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ “ይህ በሕ​ይ​ወት ሊኖር አይ​ገ​ባ​ው​ምና እን​ዲህ ያለ​ውን ሰው ከም​ድር አስ​ወ​ግ​ደው” እያሉ ጮሁ።</verse>
				<verse number="23">እነ​ር​ሱም እየ​ጮ​ሁና ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም እየ​ወ​ረ​ወሩ ትቢ​ያ​ውን ወደ ላይ ሲበ​ትኑ፥</verse>
				<verse number="24">የሻ​ለ​ቃው የሚ​ጮ​ሁ​በት ስለ ምን እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ ወደ ወታ​ደ​ሮች ሰፈር እን​ዲ​ያ​ገ​ቡ​ትና እየ​ገ​ረፉ የሠ​ራ​ውን እን​ዲ​መ​ረ​ም​ሩት አዘዘ።</verse>
				<verse number="25">ሊገ​ር​ፉ​ትም በአ​ጋ​ደ​ሙት ጊዜ ጳው​ሎስ በአ​ጠ​ገቡ የነ​በ​ረ​ውን የመቶ አለቃ፥ “የሮ​ማን ሰው ያለ ፍርድ ልት​ገ​ርፉ ይገ​ባ​ች​ኋ​ልን?” አለው።</verse>
				<verse number="26">የመቶ አለ​ቃ​ውም ይህን በሰማ ጊዜ፥ ወደ ሻለ​ቃው ሄደና፥ “ይህ ሰው ሮማዊ ነው፥ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ዕወቅ” ብሎ ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="27">የሻ​ለ​ቃ​ውም ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “አንተ ሮማዊ ነህን? እስኪ ንገ​ረኝ” አለው፤ ጳው​ሎ​ስም፥ “አዎን” አለው።</verse>
				<verse number="28">የሻ​ለ​ቃ​ውም መልሶ፥ “እኔ ይህ​ችን ዜግ​ነት ያገ​ኘ​ኋት ብዙ ገን​ዘብ ሰጥቼ ነው” አለው፤ ጳው​ሎ​ስም፥ “እኔማ የተ​ወ​ለ​ድሁ በዚ​ያው ነው” አለው።</verse>
				<verse number="29">ከዚ​ህም በኋላ ይመ​ረ​ም​ሩት ዘንድ የሚ​ሹት ተዉት፤ የሻ​ለ​ቃ​ውም ሮማዊ መሆ​ኑን በዐ​ወቀ ጊዜ“ ለምን አሰ​ር​ሁት?” ብሎ ፈራ።</verse>
				<verse number="30">በማ​ግ​ሥ​ቱም የሻ​ለ​ቃው አይ​ሁድ የሚ​ከ​ሱት ስለ ምን እን​ደ​ሆነ ያውቅ ዘንድ ወደ​ደና ከእ​ስ​ራቱ ፈታው፤ ሊቃነ ካህ​ና​ቱና ሸን​ጎ​ውም ሁሉ እን​ዲ​መጡ አዘዘ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም አም​ጥቶ በፊ​ታ​ቸው አቆ​መው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="23">
				<verse number="1">ጳው​ሎ​ስም በአ​ደ​ባ​ባዩ ወደ​አ​ሉት ሰዎች አተ​ኵሮ ተመ​ለ​ከ​ተና፥ “እና​ንተ ሰዎች ወን​ድ​ሞች፥ እኔስ እስ​ከ​ዚች ቀን ድረስ በመ​ል​ካም ሕሊና ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሳገ​ለ​ግል ኑሬ​አ​ለሁ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="2">ሊቀ ካህ​ናቱ ሐና​ንያ ግን ጳው​ሎ​ስን አፉን እን​ዲ​መ​ቱት በአ​ጠ​ገቡ ቆመው የነ​በ​ሩ​ትን አዘዘ።</verse>
				<verse number="3">ጳው​ሎ​ስም መልሶ፥ “አንተ የተ​ለ​ሰነ ግድ​ግዳ በሕግ ልት​ፈ​ር​ድ​ብኝ ተቀ​ም​ጠህ ሳለ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዝ​ዛ​ለ​ህን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ታ​ሃል” አለው።</verse>
				<verse number="4">በአ​ጠ​ገቡ ቆመው የነ​በ​ሩ​ትም ጳው​ሎ​ስን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሾ​መ​ውን ሊቀ ካህ​ናት እን​ዴት ትሳ​ደ​ባ​ለህ?” አሉት።</verse>
				<verse number="5">ጳው​ሎ​ስም፥ “ወን​ድ​ሞች፥ ሊቀ ካህ​ናት መሆ​ኑን አላ​ው​ቅም መጽ​ሐፍ ‘በሕ​ዝ​ብህ አለቃ ላይ ክፉ አት​ና​ገር’ ይላ​ልና” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">ጳው​ሎ​ስም እኩ​ሌ​ቶቹ ሰዱ​ቃ​ው​ያን እኩ​ሌ​ቶ​ቹም ፈሪ​ሳ​ው​ያን እንደ ሆኑ ዐውቆ፥ “እኔ ፈሪ​ሳዊ የፈ​ሪ​ሳዊ ልጅ ነኝ፤ ስለ ተስ​ፋና ስለ ሙታን መነ​ሣ​ትም ይፈ​ረ​ድ​ብ​ኛል” ብሎ በአ​ደ​ባ​ባይ ጮኸ።</verse>
				<verse number="7">እን​ዲ​ህም ባለ ጊዜ ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንና ሰዱ​ቃ​ው​ያን ተጣሉ፤ ሸን​ጎ​ውም ተከ​ፋ​ፈለ።</verse>
				<verse number="8">ሰዱ​ቃ​ው​ያን፥ “ሙታን አይ​ነ​ሡም፤ መል​አ​ክም የለም፤ መን​ፈ​ስም የለም” ይላ​ሉና፤ ፈሪ​ሳ​ው​ያን ግን ይህ ሁሉ እን​ዳለ ያም​ናሉ።</verse>
				<verse number="9">ታላቅ ውካ​ታም ሆነ፤ ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ወገን የሆኑ ጸሐ​ፍት ተነ​ሥ​ተው ይጣ​ሉና ይከ​ራ​ከሩ ጀመሩ፤ “በዚህ ሰው ላይ ያገ​ኘ​ነው ክፉ ነገር የለም፤ መን​ፈስ ወይም መል​አክ ተና​ግ​ሮት እንደ ሆነ እንጃ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አን​ጣላ” አሉ።</verse>
				<verse number="10">እጅ​ግም በታ​ወኩ ጊዜ ጳው​ሎ​ስን እን​ዳ​ይ​ነ​ጥ​ቁት የሻ​ለ​ቃው ፈራና መጥ​ተው ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አው​ጥ​ተው ወደ ወታ​ደ​ሮች ሰፈር ይወ​ስ​ዱት ዘንድ ወታ​ደ​ሮ​ቹን አዘዘ።</verse>
				<verse number="11">በሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ሌሊት ጌታ​ችን ለጳ​ው​ሎስ ተገ​ልጦ፥ “ጽና፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ምስ​ክር እንደ ሆን​ኸኝ እን​ዲሁ በሮም ምስ​ክር ትሆ​ነ​ኛ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="12">በነ​ጋም ጊዜ አይ​ሁድ ተሰ​ብ​ስ​በው፥ ጳው​ሎ​ስን እስ​ኪ​ገ​ድ​ሉት ድረስ እን​ዳ​ይ​በ​ሉና እን​ዳ​ይ​ጠጡ ተስ​ማ​ም​ተው ተማ​ማሉ።</verse>
				<verse number="13">ይህ​ንም ለማ​ድ​ረግ የተ​ማ​ማ​ሉት ሰዎች ከአ​ርባ ይበዙ ነበር።</verse>
				<verse number="14">እነ​ር​ሱም ወደ ሊቃነ ካህ​ና​ትና ወደ መም​ህ​ራን ሄደው እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “ጳው​ሎ​ስን እስ​ክ​ን​ገ​ድ​ለው ድረስ እነሆ፥ እን​ዳ​ን​በ​ላና እን​ዳ​ን​ጠጣ ፈጽ​መን ተማ​ም​ለ​ናል።</verse>
				<verse number="15">አሁ​ንም እና​ንተ ከሸ​ን​ጎው ጋር ወደ ሻለ​ቃው ሂዱና የም​ት​መ​ረ​ም​ሩ​ትና የም​ት​ጠ​ይ​ቁት አስ​መ​ስ​ላ​ችሁ ጳው​ሎ​ስን እን​ዲ​ያ​መ​ጣው ንገ​ሩት፤ እኛ ግን ወደ እና​ንተ ከመ​ድ​ረሱ አስ​ቀ​ድሞ ልን​ገ​ድ​ለው ቈር​ጠ​ናል።”</verse>
				<verse number="16">የጳ​ው​ሎ​ስም የእ​ኅቱ ልጅ ምክ​ራ​ቸ​ውን በሰማ ጊዜ ሄዶ ወደ ወታ​ደ​ሮች ሰፈር ገባና ለጳ​ው​ሎስ ነገ​ረው።</verse>
				<verse number="17">ጳው​ሎ​ስም ከመቶ አለ​ቆች አን​ዱን ጠርቶ፥ “የሚ​ነ​ግ​ረው ነገር አለና ይህን ልጅ ወደ የሻ​ለ​ቃው አድ​ር​ስ​ልኝ” አለው።</verse>
				<verse number="18">የመቶ አለ​ቃ​ውም ልጁን ይዞ ወደ የሻ​ለ​ቃው ወሰ​ደ​ውና፥ “የሚ​ነ​ግ​ርህ ስለ አለው እስ​ረ​ኛው ጳው​ሎስ ይህን ልጅ ወደ አንተ እን​ዳ​ደ​ር​ሰው ለመ​ነኝ” አለው።</verse>
				<verse number="19">የሻ​ለ​ቃ​ውም ልጁን በእጁ ይዞ ለብ​ቻው ገለል አድ​ርጎ፥ “የም​ት​ነ​ግ​ረኝ ነገሩ ምን​ድ​ነው?” አለው።</verse>
				<verse number="20">ልጁም እን​ዲህ አለው፥ “አይ​ሁድ አጥ​ብ​ቀህ የም​ት​መ​ረ​ም​ረው መስ​ለህ ጳው​ሎ​ስን ነገ ወደ ሸንጎ ታወ​ር​ድ​ላ​ቸው ዘንድ ሊማ​ል​ዱህ እን​ዲህ መክ​ረ​ዋል።</verse>
				<verse number="21">አንተ ግን እሽ አት​በ​ላ​ቸው፤ ሊገ​ድ​ሉት ሽም​ቀ​ዋ​ልና፤ እስ​ኪ​ገ​ድ​ሉ​ትም ድረስ እን​ዳ​ይ​በ​ሉና እን​ዳ​ይ​ጠጡ እን​ዲህ የተ​ማ​ማሉ ሰዎች ከአ​ርባ ይበ​ዛሉ፤ አሁ​ንም እስ​ክ​ት​ል​ክ​ላ​ቸው ይጠ​ብ​ቃሉ እንጂ እነ​ርሱ ቈር​ጠ​ዋል።”</verse>
				<verse number="22">ከዚ​ህም በኋላ፤ የሻ​ለ​ቃው፥ “ይህን ነገር ለእኔ መን​ገ​ር​ህን ለማ​ንም እን​ዳ​ት​ገ​ልጽ” ብሎ አሰ​ና​በ​ተው።</verse>
				<verse number="23">ከመቶ አለ​ቆ​ችም ሁለ​ቱን ጠርቶ፥ “ከወ​ታ​ደ​ሮች ሁለት መቶ ሰውና ሰባ ፈረ​ሰ​ኞች፥ ሁለት መቶ ቀስ​ተ​ኞ​ችም ምረጡ፤ ከሌ​ሊ​ቱም በሦ​ስት ሰዓት ወደ ቂሣ​ርያ ይሂዱ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">አህ​ያም አም​ጥ​ተው ጳው​ሎ​ስን በዚያ አስ​ቀ​ም​ጠው ወደ ቂሣ​ርያ አገረ ገዢ ወደ ፊል​ክስ እን​ዲ​ወ​ስ​ዱት አዘ​ዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">እን​ዲህ የም​ትል ደብ​ዳ​ቤም ጻፈ​ለት።</verse>
				<verse number="26">“ከሉ​ስ​ዮስ ቀላ​ው​ዴ​ዎስ፥ ለክ​ቡር አገረ ገዢ ፊል​ክስ፥ ሰላም ለአ​ንተ ይሁን።</verse>
				<verse number="27">ይህን ሰው አይ​ሁድ ያዙት፤ ሊገ​ድ​ሉ​ትም ፈለጉ፤ ከወ​ታ​ደ​ሮ​ችም ጋር ተከ​ላ​ከ​ል​ሁ​ለት፥ የሮም ሰው መሆ​ኑ​ንም ዐውቄ አዳ​ን​ሁት።</verse>
				<verse number="28">በምን ምክ​ን​ያ​ትም እን​ደ​ሚ​ከ​ሱት በደ​ሉን አውቅ ዘንድ ወደ ሸንጎ አቅ​ርቤ መረ​መ​ር​ሁት።</verse>
				<verse number="29">ስለ ሕጋ​ቸ​ውም ብቻ እንደ ከሰ​ሱት ተረ​ዳሁ፤ ለሞ​ትና ለመ​ታ​ሰር የሚ​ያ​በቃ ሌላ በደል ግን የለ​በ​ትም።</verse>
				<verse number="30">አይ​ሁ​ድም በዚህ ሰው ላይ በመ​ሸ​መቅ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን በዐ​ወ​ቅሁ ጊዜ ወደ አንተ ላክ​ሁት፤ ከሳ​ሾ​ቹ​ንም ወደ አንተ እን​ዲ​መ​ጡና በፊ​ትህ እን​ዲ​ፋ​ረ​ዱት አዝ​ዣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ደኅና ሁን።”</verse>
				<verse number="31">ጭፍ​ሮ​ችም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው አደ​ረጉ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም በሌ​ሊት ወሰ​ዱት፤ ወደ አን​ቲ​ጳ​ጥ​ሪ​ስም አደ​ረ​ሱት።</verse>
				<verse number="32">በማ​ግ​ሥ​ቱም ከእ​ርሱ ጋር ይሄዱ ዘንድ ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ትተው እነ​ርሱ ወደ ሰፈር ተመ​ለሱ።</verse>
				<verse number="33">ከዚ​ህም በኋላ ወደ ቂሣ​ርያ ገቡ፤ ወደ አገረ ገዢ​ውም ደረሱ፤ የተ​ላ​ከ​ው​ንም ደብ​ዳቤ ለአ​ገረ ገዢው ሰጡት፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም ወደ እርሱ አቀ​ረ​ቡት።</verse>
				<verse number="34">ደብ​ዳ​ቤ​ው​ንም ካነ​በበ በኋላ ከማን ግዛት እንደ ሆነ ጠየ​ቀው። ከኪ​ል​ቅያ የመጣ መሆ​ኑ​ንም ባወቀ ጊዜ፦</verse>
				<verse number="35">“እን​ኪ​ያስ ከሳ​ሾ​ችህ ሲመጡ እን​ሰ​ማ​ሃ​ለን” አለው፤ በሄ​ሮ​ድ​ስም ግቢ እን​ዲ​ጠ​ብ​ቁት አዘዘ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="24">
				<verse number="1">በአ​ም​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሊቀ ካህ​ናቱ ሐና​ንያ ከመ​ም​ህ​ራ​ኑና ጠር​ጠ​ሉስ ከሚ​ባል አንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም በአ​ገረ ገዢው ዘንድ ከሰ​ሱት።</verse>
				<verse number="2">ጳው​ሎ​ስም በቀ​ረበ ጊዜ ጠር​ጠ​ሉስ እን​ዲህ እያለ ይከ​ስ​ሰው ጀመረ፤</verse>
				<verse number="3">“ክቡር ፊል​ክስ ሆይ፥ በዘ​መ​ንህ ብዙ ሰላ​ምን አግ​ኝ​ተ​ናል፤ በጥ​በ​ብ​ህም በየ​ጊ​ዜው በየ​ሀ​ገሩ የሕ​ዝቡ ኑሮ የተ​ሻ​ሻለ ሆኖ​አል፤ ሥር​ዐ​ት​ህ​ንም በሁሉ ዘንድ ስት​መ​ሰ​ገን አግ​ኝ​ተ​ና​ታል።</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን ነገር እን​ዳ​ላ​በ​ዛ​ብህ በአ​ጭሩ ትሰ​ማኝ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">ይህን ሰው ሲሳ​ደ​ብና ወን​ጀል ሲሠራ፥ አይ​ሁ​ድ​ንም ሁሉ በየ​ሀ​ገሩ ሲያ​ውክ፥ ናዝ​ራ​ው​ያን የተ​ባ​ሉት ወገ​ኖች የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩ​ት​ንም ክህ​ደት ሲያ​ስ​ተ​ምር አግ​ኝ​ተ​ነ​ዋል።</verse>
				<verse number="6">ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም ሊያ​ረ​ክስ ሲሞ​ክር ያዝ​ነው፤ እንደ ሕጋ​ች​ንም ልን​ፈ​ር​ድ​በት ፈል​ገን ነበር።</verse>
				<verse number="7">ነገር ግን የሻ​ለ​ቃው ሉስ​ዮስ መጥቶ በብዙ ጭንቅ ከእ​ጃ​ችን ነጥቆ ወደ አንተ ላከው።</verse>
				<verse number="8">ከሳ​ሾ​ቹ​ንም ወደ አንተ እን​ዲ​መጡ አዘ​ዛ​ቸው፤ የከ​ሰ​ስ​ን​በ​ት​ንም ነገር ሁሉ መር​ም​ረህ ከእ​ርሱ ልት​ረዳ ትች​ላ​ለህ።”</verse>
				<verse number="9">አይ​ሁ​ድም፥ “እው​ነት ነው፤ እን​ዲሁ ነው” ብለው መለሱ።</verse>
				<verse number="10">ሀገረ ገዢ​ውም እን​ዲ​ና​ገር ጳው​ሎ​ስን ጠቀ​ሰው፤ ጳው​ሎ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ከብዙ ዘመን ጀምሮ የዚህ ሕዝብ አስ​ተ​ዳ​ዳሪ እንደ ሆንህ አው​ቃ​ለሁ፤ ጠባ​ያ​ቸ​ው​ንም ታው​ቃ​ለህ። አሁ​ንም ደስ እያ​ለኝ ክር​ክ​ሬን አቀ​ር​ባ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">እሰ​ግድ ዘንድ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ከወ​ጣሁ ዐሥራ ሁለት ቀን እን​ደ​ማ​ይ​ሆን ልታ​ው​ቀው ትች​ላ​ለህ፤</verse>
				<verse number="12">በም​ኵ​ራብ ቢሆን፥ በቤተ መቅ​ደ​ስም ቢሆን፥ በከ​ተ​ማም ቢሆን ሕዝ​ብን ሳውክ፥ ከማ​ንም ጋር ስከ​ራ​ከር አላ​ገ​ኙ​ኝም።</verse>
				<verse number="13">በሚ​ከ​ስ​ሱኝ ሁሉ በፊ​ትህ ማስ​ረጃ ማቅ​ረብ አይ​ች​ሉም።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን ይህን አረ​ጋ​ግ​ጥ​ል​ሃ​ለሁ፤ እኔ በሕግ ያለ​ውን፥ በነ​ቢ​ያ​ትም የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ አምኜ እነ​ርሱ ክህ​ደት ብለው በሚ​ጠ​ሩት ትም​ህ​ርት የአ​ባ​ቶ​ችን አም​ላክ አመ​ል​ከ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">እነ​ር​ሱም ለጻ​ድ​ቃ​ንና ለኃ​ጥ​ኣን የሙ​ታን ትን​ሣኤ ይሆን ዘንድ እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቁ ለእ​ኔም እን​ዲሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ተስፋ አለኝ።</verse>
				<verse number="16">እን​ዲሁ እኔም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በሰው ፊት ሁል​ጊዜ የማ​ታ​ወ​ላ​ውል ሕሊና ትኖ​ረኝ ዘንድ እጋ​ደ​ላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="17">ከብዙ ዓመ​ታ​ትም በኋላ ለወ​ገ​ኖች ምጽ​ዋ​ት​ንና መሥ​ዋ​ዕ​ትን ላደ​ርግ መጣሁ።</verse>
				<verse number="18">በዚ​ያም ጊዜ ከእ​ስያ የመጡ አይ​ሁድ ከሕ​ዝብ ጋር በመ​ከ​ራ​ከር፥ ወይም በፍ​ጅት ሳይ​ሆን በመ​ቅ​ደስ ስነጻ አገ​ኙኝ።</verse>
				<verse number="19">አሁ​ንም በእኔ ላይ ነገር ከአ​ላ​ቸው ወደ አንተ ይም​ጡና ይክ​ሰ​ሱኝ።</verse>
				<verse number="20">ወይም እኔ በሸ​ንጎ ቆሜ ሳለሁ ያገ​ኙ​ብኝ በደል እንደ አለ እነ​ዚህ ራሳ​ቸው ይመ​ስ​ክሩ።</verse>
				<verse number="21">በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቆሜ ከአ​ስ​ተ​ማ​ር​ኋት አን​ዲት ትም​ህ​ርት በቀር ያደ​ረ​ግ​ሁት ክፉ ነገር የለም። ‘ሙታን ይነ​ሣሉ’ በማ​ለ​ቴም ዛሬ በአ​ንተ ዘንድ በእኔ ይፈ​ረ​ድ​ብ​ኛል።”</verse>
				<verse number="22">ፊል​ክስ ግን አይ​ሁድ ከጥ​ንት ጀምሮ የክ​ር​ስ​ቲ​ያ​ንን ወገ​ኖች ሕግና ትም​ህ​ርት እን​ደ​ሚ​ቃ​ወሙ ያውቅ ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም “እን​ኪ​ያስ የሺ አለ​ቃው ሉስ​ዮስ በመጣ ጊዜ ነገ​ራ​ች​ሁን እና​ውቅ ዘንድ እን​መ​ረ​ም​ራ​ለን” ብሎ ቀጠ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="23">የመቶ አለ​ቃ​ው​ንም ጳው​ሎ​ስን እን​ዲ​ጠ​ብ​ቀው፥ በሰፊ ቦታም እን​ዲ​ያ​ኖ​ረው፥ እን​ዳ​ያ​ጠ​ብ​በ​ትም፥ ሊያ​ገ​ለ​ግ​ሉት በመጡ ጊዜም ከወ​ዳ​ጆቹ አን​ዱን ስንኳ እን​ዳ​ይ​ከ​ለ​ክ​ል​በት አዘዘ።</verse>
				<verse number="24">ከጥ​ቂት ቀንም በኋላ ፊል​ክስ ከአ​ይ​ሁ​ዳ​ዊት ሚስቱ ከድ​ሩ​ሲላ ጋር መጣ። ልኮም ጳው​ሎ​ስን አስ​ጠ​ራው፤ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስለ ማመ​ንም የሚ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር ሰማው።</verse>
				<verse number="25">እር​ሱም ስለ ጽድ​ቅና ስለ ንጽ​ሕና፥ ስለ​ሚ​መ​ጣ​ውም ኵነኔ በነ​ገ​ራ​ቸው ጊዜ በዚህ የተ​ነሣ ፊል​ክስ ፈራና ጳው​ሎ​ስን፥ “አሁ​ንስ ሂድ፤ በተ​መ​ቸ​ኝም ጊዜ ልኬ አስ​ጠ​ራ​ሃ​ለሁ” አለው።</verse>
				<verse number="26">ፊል​ክ​ስም እን​ዲ​ፈ​ታው ጳው​ሎስ ገን​ዘብ የሚ​ሰ​ጠው መስ​ሎት ነበር፤ ስለ​ዚህ ዘወ​ትር ይጠ​ራ​ውና ያነ​ጋ​ግ​ረው ነበር።</verse>
				<verse number="27">ሁለት ዓመ​ትም ካለፈ በኋላ፥ ፊል​ክስ ተሻ​ረና ጶር​ቅ​ዮስ ፊስ​ጦስ የሚ​ባል ሌላ ሀገረ ገዢ በእ​ርሱ ቦታ መጣ፤ ፊል​ክ​ስም በግ​ልጥ ለአ​ይ​ሁድ ሊያ​ዳላ ወደደ፤ ስለ​ዚ​ህም ጳው​ሎ​ስን እንደ ታሰረ ተወው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="25">
				<verse number="1">ፊስ​ጦ​ስም ወደ ቂሣ​ርያ ደርሶ ሦስት ቀን ሰነ​በተ፤ ከዚ​ህም በኋላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣ።</verse>
				<verse number="2">ሊቃነ ካህ​ና​ትና የአ​ይ​ሁድ ሽማ​ግ​ሎ​ችም ከበ​ቡት፤ የጳ​ው​ሎ​ስ​ንም ነገር ነገ​ሩት።</verse>
				<verse number="3">ልኮም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ እን​ዲ​ያ​ስ​መ​ጣ​ውና እን​ዲ​ሰ​ጣ​ቸው ለመ​ኑት፤ እነ​ርሱ ግን ወደ​ዚያ ሄደው በመ​ን​ገድ ሸም​ቀው ሊገ​ድ​ሉት ፈል​ገው ነበር።</verse>
				<verse number="4">ፊስ​ጦ​ስም ጳው​ሎ​ስን በቂ​ሣ​ርያ እን​ደ​ሚ​ጠ​ብ​ቁት፥ እር​ሱም ራሱ ወደ​ዚ​ያው በቶሎ እን​ደ​ሚ​ሄድ መለ​ሰ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">አይ​ሁ​ድ​ንም፥ “ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ የሚ​ችሉ ካሉ ከከ​ሰ​ሳ​ች​ሁት ከዚያ ሰው ጋር እን​ዲ​ከ​ራ​ከሩ ከእኔ ጋር ይው​ረዱ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">ስም​ንት ወይም ዐሥር ቀን በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ከሰ​ነ​በተ በኋላ ወደ ቂሣ​ርያ ሄደ፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም በፍ​ርድ ወን​በር ተቀ​ምጦ ጳው​ሎ​ስን እን​ዲ​ያ​መ​ጡት አዘዘ።</verse>
				<verse number="7">ጳው​ሎ​ስም በቀ​ረበ ጊዜ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የወ​ረዱ አይ​ሁድ ከብ​በ​ውት ቆሙ፤ ሊረቱ በማ​ይ​ች​ሉ​በ​ትም ብዙና ከባድ ክስ ከሰ​ሱት።</verse>
				<verse number="8">ጳው​ሎ​ስም ሲመ​ልስ፥ “በአ​ይ​ሁድ ሕግ ላይ ቢሆን፥ በቤተ መቅ​ደ​ስም ላይ ቢሆን፥ በቄ​ሣር ላይም ቢሆን አን​ዳች የበ​ደ​ል​ሁት የለም” አለ።</verse>
				<verse number="9">ፊስ​ጦስ ግን አይ​ሁድ እን​ዲ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑት ወዶ ጳው​ሎ​ስን፥ “ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጥ​ተህ ስለ​ዚህ ነገር በዚያ ከእኔ ዘንድ ልት​ከ​ራ​ከር ትሻ​ለ​ህን?” አለው።</verse>
				<verse number="10">ጳው​ሎ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፤ “እኔ ወደ ቄሣር ዙፋን ችሎት እቀ​ር​ባ​ለሁ፤ ፍር​ዴም በዚያ ሊታ​ይ​ልኝ ይገ​ባል፤ በአ​ይ​ሁ​ድም ላይ የበ​ደ​ል​ሁት በደል እን​ደ​ሌ​ለኝ ከሰው ሁሉ ይልቅ አንተ ራስህ ታው​ቃ​ለህ።</verse>
				<verse number="11">ከበ​ደ​ልሁ ወይም ለሞት የሚ​ያ​በ​ቃኝ የሠ​ራ​ሁት ክፉ ሥራ ካለ ሞት አይ​ፈ​ረ​ድ​ብኝ አል​ልም፤ ነገር ግን እነ​ዚህ በደል የሌ​ለ​ብ​ኝን በከ​ንቱ የሚ​ከ​ስ​ሱኝ ከሆነ፥ ለእ​ነ​ርሱ አሳ​ልፎ ሊሰ​ጠኝ ለማን ይቻ​ለ​ዋል? እኔ ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ ብያ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="12">ከዚ​ህም በኋላ ፊስ​ጦስ ከአ​ማ​ካ​ሪ​ዎቹ ጋር ተማ​ክሮ፥ “ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ ካልህ ወደ ቄሣር ትሄ​ዳ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="13">ከጥ​ቂት ቀን በኋ​ላም ንጉሥ አግ​ሪ​ጳና በር​ኒቄ ወደ ቂሣ​ርያ ወር​ደው ፊስ​ጦ​ስን ተገ​ና​ኙት።</verse>
				<verse number="14">በእ​ርሱ ዘንድ ብዙ ቀን ከቈዩ በኋላ ፊስ​ጦስ የጳ​ው​ሎ​ስን ነገር ለን​ጉሡ ነገ​ረው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ፊል​ክስ በእ​ስር ቤት ትቶት የሄደ አንድ እስ​ረኛ ሰው በእ​ዚህ አለ።</verse>
				<verse number="15">በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሳለ​ሁም ሊቃነ ካህ​ና​ትና የአ​ይ​ሁድ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወደ እኔ መጥ​ተው እን​ድ​ፈ​ር​ድ​በት ማለ​ዱኝ።</verse>
				<verse number="16">እኔም፦ ተከ​ሳሹ በከ​ሳ​ሾቹ ፊት ሳይ​ቆም፥ ለተ​ከ​ሰ​ሰ​በ​ትም ምላሽ ይሰጥ ዘንድ ፋንታ ሳያ​ገኝ ማንም ቢሆን አሳ​ልፎ መስ​ጠት የሮ​ማ​ው​ያን ሕግ አይ​ደ​ለም ብየ መለ​ስ​ሁ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="17">ከዚ​ህም በኋላ፤ በዚሁ በተ​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ ሳል​ዘ​ገይ በማ​ለዳ በፍ​ርድ ወን​በር ተቀ​ምጬ፥ ያን ሰው እን​ዲ​ያ​መ​ጡት አዘ​ዝሁ።</verse>
				<verse number="18">የከ​ሰ​ሱ​ትም በቆሙ ጊዜ፥ እኔ እንደ አሰ​ብ​ሁት በከ​ሰ​ሱት ክስ የሠ​ራው ምንም ነገር የለም።</verse>
				<verse number="19">ስለ ሃይ​ማ​ኖ​ታ​ቸው ከሆ​ነው ክር​ክ​ርና ስለ ሞተው፥ ጳው​ሎስ ግን ሕያው ነው ስለ​ሚ​ለው ሰው ስለ ኢየ​ሱስ ከሆ​ነው ክር​ክር በቀር፤</verse>
				<verse number="20">ስለ ክር​ክ​ራ​ቸ​ውም የማ​ደ​ር​ገ​ውን አጥቼ ጳው​ሎ​ስን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሄደህ በዚያ ልት​ከ​ራ​ከር ትወ​ዳ​ለ​ህን? አል​ሁት።</verse>
				<verse number="21">ጳው​ሎስ ግን እንቢ ብሎ፥ እን​ዲ​ድን ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ አለ፤ ከዚ​ህም በኋላ ወደ ቄሣር እስ​ክ​ል​ከው ድረስ እን​ዲ​ጠ​ብ​ቁት አዘ​ዝሁ።”</verse>
				<verse number="22">አግ​ሪ​ጳም ፊስ​ጦ​ስን፥ “እኔም ያን ሰው ልሰ​ማው እወ​ዳ​ለሁ” አለው፤ ፊስ​ጦ​ስም፥ “እን​ግ​ዲ​ያስ ነገ ትሰ​ማ​ዋ​ለህ” አለው።</verse>
				<verse number="23">በማ​ግ​ሥ​ቱም አግ​ሪ​ጳና በር​ኒቄ በብዙ ግርማ መጡ፤ ከመ​ሳ​ፍ​ን​ቱና ከከ​ተ​ማው ታላ​ላቅ ሰዎች ጋርም ወደ ፍርድ ቤት ገቡ፤ ፊስ​ጦ​ስም ጳው​ሎ​ስን እን​ዲ​ያ​መ​ጡት አዘዘ።</verse>
				<verse number="24">ፊስ​ጦ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ንጉሥ አግ​ሪጳ ሆይ፥ እና​ን​ተም ከእኛ ጋር ያላ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሁላ​ችሁ፥ ስሙ፤ አይ​ሁድ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በሕ​ይ​ወት ይኖር ዘንድ እን​ዳ​ይ​ገ​ባው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሆነ በዚህ እየ​ጮሁ የለ​መ​ኑኝ ይህ የም​ታ​ዩት ሰው እነሆ።</verse>
				<verse number="25">እኔ ግን ለሞት የሚ​ያ​ደ​ር​ሰው በደል እን​ዳ​ል​ሠራ እጅግ መር​ምሬ፥ እር​ሱም ራሱ ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ ማለ​ትን ስለ​ወ​ደደ እን​ግ​ዲህ ልል​ከው ቈር​ጫ​ለሁ።</verse>
				<verse number="26">ነገር ግን ስለ እርሱ ወደ ጌታዬ የም​ጽ​ፈው የታ​ወቀ ነገር የለ​ኝም። ስለ​ዚህ ከተ​መ​ረ​መረ በኋላ የም​ጽ​ፈ​ውን አገኝ ዘንድ ወደ እና​ንተ ይል​ቁ​ንም ንጉሥ አግ​ሪጳ ሆይ ወደ አንተ አመ​ጣ​ሁት።</verse>
				<verse number="27">የበ​ደሉ ደብ​ዳቤ ሳይ​ኖር እስ​ረ​ኛን ወደ ንጉሥ መላክ አይ​ገ​ባ​ምና፤ ለእ​ኔም ነገ​ሩም ሆነ አስሮ መላኩ አስ​ቸ​ግ​ሮ​ኛል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="26">
				<verse number="1">አግ​ሪ​ጳም ጳው​ሎ​ስን፥ “ስለ ራስህ ትና​ገር ዘንድ ፈቅ​ደ​ን​ል​ሃል” አለው፤ ከዚ​ህም በኋላ ጳው​ሎስ እጁን አነ​ሣና ይነ​ግ​ራ​ቸው ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦</verse>
				<verse number="2">“ንጉሥ አግ​ሪጳ ሆይ፥ አይ​ሁድ እኔን ስለ ከሰ​ሱ​በት ነገር ሁሉ ዛሬ በአ​ንተ ዳኝ​ነት እከ​ራ​ከር ዘንድ ስለ ተገ​ባኝ ራሴን እንደ ተመ​ሰ​ገነ አድ​ርጌ እቈ​ጥ​ረ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">የአ​ይ​ሁ​ድን ጠባ​ያ​ቸ​ው​ንና ክር​ክ​ራ​ቸ​ውን አጥ​ብ​ቀህ ታው​ቃ​ለ​ህና ታግ​ሠህ ታደ​ም​ጠኝ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">“ከል​ጅ​ነቴ ጀምሮ በወ​ገ​ኖች መካ​ከል በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የኖ​ር​ሁ​ትን ኑሮ አይ​ሁድ ሁሉ ያው​ቃሉ።</verse>
				<verse number="5">ሊመ​ሰ​ክ​ሩም ከወ​ደዱ እኔ ፈሪ​ሳዊ ሆኜ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ሕግ እን​ደ​ም​ኖር ከጥ​ንት ጀምሮ እነ​ርሱ ያው​ቁ​ል​ኛል።</verse>
				<verse number="6">አሁ​ንም ከጥ​ንት ጀምሮ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን የተ​ሰ​ጠ​ውን ተስፋ በመ​ታ​መን ከፍ​ርድ በታች ቆሜ​አ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">ንጉሥ አግ​ሪጳ ሆይ፥ ዐሥራ ሁለቱ ነገ​ዶ​ቻ​ችን በመ​ዓ​ል​ትም በሌ​ሊ​ትም እር​ሱን እያ​ገ​ለ​ገሉ ወደ እር​ስዋ ይደ​ርሱ ዘንድ ተስፋ ያደ​ር​ጋሉ፤ አይ​ሁ​ድም የሚ​ከ​ስ​ሱኝ ስለ​ዚህ ተስፋ ነው።</verse>
				<verse number="8">እን​ዴ​ትስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙታ​ንን እን​ደ​ሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ቸው በእ​ና​ንተ ዘንድ የማ​ይ​ታ​መን ሆኖ ይቈ​ጠ​ራል?</verse>
				<verse number="9">“እኔም ብዙ ጊዜ በና​ዝ​ሬቱ በኢ​የ​ሱስ ስም ላይ ክፉ ነገር ላደ​ርግ ቈርጬ ነበር።</verse>
				<verse number="10">ይህ​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ረ​ግ​ሁት፤ ከሊ​ቃነ ካህ​ና​ትም ሥል​ጣን ተቀ​ብዬ ከቅ​ዱ​ሳን ብዙ​ዎ​ችን ወደ ወኅኒ ቤት አስ​ገ​ባ​ኋ​ቸው፤ ሲገ​ድ​ሏ​ቸ​ውም አብሬ እመ​ክር ነበ​ርሁ።</verse>
				<verse number="11">በየ​ም​ኵ​ራቡ ሁሉ የማ​ስ​ገ​ደጃ ማዘዣ አም​ጥቼ፥ በግድ የኢ​የ​ሱ​ስን ስም እን​ዲ​ሰ​ድቡ ዘወ​ትር መከራ አጸ​ና​ባ​ቸው ነበር፤ ይል​ቁ​ንም ወደ ሌሎች ከተ​ማ​ዎች እያ​ሳ​ደ​ድሁ ከፋ​ሁ​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="12">“ይህ​ንም ለመ​ፈ​ጸም ከሊ​ቃነ ካህ​ናት ሥል​ጣን ተቀ​ብዬ ወደ ደማ​ስቆ ከተማ ሄድሁ።</verse>
				<verse number="13">ንጉሥ ሆይ፥ እኩል ቀን በሆነ ጊዜ በመ​ን​ገድ ስሄድ ከፀ​ሐይ ይልቅ የሚ​በራ መብ​ረቅ በእ​ኔና ከእኔ ጋር ይሄዱ በነ​በ​ሩት ላይ ከሰ​ማይ ሲያ​ን​ፀ​ባ​ርቅ አየሁ።</verse>
				<verse number="14">ሁላ​ች​ንም በም​ድር ላይ በወ​ደ​ቅን ጊዜ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ፦ ‘ሳውል ሳውል ለምን ታሳ​ድ​ደ​ኛ​ለህ? በሾለ ብረት ላይ መር​ገጥ ለአ​ንተ ይብ​ስ​ሃል’ የሚ​ለ​ኝን ቃል ሰማሁ።</verse>
				<verse number="15">እኔም፦ ‘አቤቱ አንተ ማነህ?’ አልሁ፤ ጌታም አለኝ፦ ‘እኔ አንተ የም​ታ​ሳ​ድ​ደኝ ኢየ​ሱስ ነኝ።</verse>
				<verse number="16">ነገር ግን ተነ​ሣና በእ​ግ​ርህ ቁም፤ እኔን ባየ​ህ​በ​ትና ወደ​ፊ​ትም በም​ታ​ይ​በት ነገር አገ​ል​ጋ​ይና ምስ​ክር አድ​ርጌ ልሾ​ምህ ስለ​ዚህ ተገ​ል​ጬ​ል​ሃ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="17">እኔም ከሕ​ዝ​ቡና ወደ እነ​ርሱ ከም​ል​ክህ ከአ​ሕ​ዛብ አድ​ን​ሃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="18">ይኸ​ውም ዐይ​ና​ቸ​ውን ትከ​ፍ​ት​ላ​ቸው ዘንድ፥ ከጨ​ለ​ማም ወደ ብር​ሃን፥ ሰይ​ጣ​ንን ከማ​ም​ለ​ክም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትመ​ል​ሳ​ቸው ዘንድ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸው ዘንድ፥ በስ​ሜም በማ​መን ከቅ​ዱ​ሳን ጋር አን​ድ​ነ​ትን ያገኙ ዘንድ ነው።’</verse>
				<verse number="19">“አሁ​ንም ንጉሥ አግ​ሪጳ ሆይ፥ ከሰ​ማይ የተ​ገ​ለ​ጠ​ል​ኝን ራእይ አል​ካ​ድ​ሁም።</verse>
				<verse number="20">አስ​ቀ​ድሜ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በደ​ማ​ስቆ ላሉት፥ ለይ​ሁዳ አው​ራ​ጃ​ዎ​ችም ሁሉ ነገ​ር​ኋ​ቸው፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ንስሓ ገብ​ተው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ለሱ ዘንድ፥ ለን​ስ​ሓ​ቸ​ውም የሚ​ገባ ሥራን ይሠሩ ዘንድ አስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">ሰለ​ዚ​ህም ብቻ አይ​ሁድ በመ​ቅ​ደስ ያዙኝ፤ ሊገ​ድ​ሉ​ኝም ወደዱ።</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አዳ​ነ​ኝና ለታ​ላ​ቁም፥ ለታ​ና​ሹም እየ​መ​ሰ​ከ​ርሁ እስከ ዛሬ ደረ​ስሁ፤ ይደ​ረግ ዘንድ ካለው፥ ነቢ​ያት ከተ​ና​ገ​ሩት፥ ሙሴም ከተ​ና​ገ​ረው ሌላ ያስ​ተ​ማ​ር​ሁት የለም።</verse>
				<verse number="23">ክር​ስ​ቶስ እን​ደ​ሚ​ሞት፥ ከሙ​ታን ተለ​ይ​ቶም አስ​ቀ​ድሞ እን​ደ​ሚ​ነሣ፥ ለሕ​ዝ​ብና ለአ​ሕ​ዛብ ሁሉ፥ ለመ​ላ​ውም ዓለም እን​ደ​ሚ​ያ​በራ።”</verse>
				<verse number="24">ይህ​ንም ስለ ራሱ ሲና​ገር ሀገረ ገዢው ፊስ​ጦስ መለሰ፤ ድም​ፁ​ንም ከፍ አድ​ርጎ፥ “ጳው​ሎስ ሆይ፥ ልታ​ብድ ነውን? ብዙ ትም​ህ​ርት እኮ ልብን ይነ​ሣል” አለው።</verse>
				<verse number="25">ጳው​ሎ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “ክቡር ፊስ​ጦስ ሆይ፥ እው​ነ​ትና የተ​ጣራ ነገ​ርን እና​ገ​ራ​ለሁ እንጂ ዕብ​ደ​ትስ የለ​ብ​ኝም።</verse>
				<verse number="26">በፊቱ ገልጬ የም​ና​ገ​ር​ለት እርሱ ራሱ ንጉሥ አግ​ሪጳ ያው​ቅ​ል​ኛል፤ ከዚ​ህም የሚ​ሳ​ተው ነገር ያለ አይ​መ​ስ​ለ​ኝም፤ ወደ ጎን የተ​ሰ​ወረ አይ​ደ​ለ​ምና።</verse>
				<verse number="27">ንጉሥ አግ​ሪጳ ሆይ፥ እነሆ፥ በነ​ቢ​ያት ቃል ታም​ና​ለ​ህን? እን​ደ​ም​ታ​ም​ንም አው​ቃ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="28">አግ​ሪ​ጳም ጳው​ሎ​ስን፥ “አሁ​ንስ ወደ ክር​ስ​ቲ​ያ​ን​ነት ልታ​ገ​ባኝ ጥቂት ብቻ ቀር​ቶ​ሃል” አለው።</verse>
				<verse number="29">ጳው​ሎ​ስም፥ “በጥ​ቂ​ትም ቢሆን፥ በብ​ዙም ቢሆን አንተ ብቻ ሳት​ሆን ዛሬ የሚ​ሰ​ሙኝ ሁሉ ደግሞ ከዚህ ከእ​ስ​ራቴ በቀር እንደ እኔ እን​ዲ​ሆኑ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጸ​ል​ያ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="30">ከዚ​ህም በኋላ ንጉሡ፥ ሀገረ ገዥ​ውም፥ በር​ኒ​ቄም፥ ሹሞ​ቻ​ቸ​ውም ተነሡ።</verse>
				<verse number="31">ለብ​ቻ​ቸ​ውም ገለል ብለው እርስ በር​ሳ​ቸው እን​ዲህ ብለው ተነ​ጋ​ገሩ፥ “ይህ ሰው እን​ዲ​ሞት ወይም እን​ዲ​ታ​ሰር የሚ​ያ​በቃ የሠ​ራው በደል የለም።”</verse>
				<verse number="32">አግ​ሪ​ጳም ፊስ​ጦ​ስን፥ “ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ ባይል ኖሮ ይህ ሰው ይፈታ ዘንድ በተ​ገባ ነበር” አለው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="27">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ ፊስ​ጦስ ወደ ቄሣር ወደ ኢጣ​ልያ በመ​ር​ከብ እን​ሄድ ዘንድ ባዘዘ ጊዜ ጳው​ሎስ ከሌ​ሎች እስ​ረ​ኞች ጋር አብሮ የአ​ው​ግ​ስ​ጦስ ጭፍራ ለነ​በረ ዩል​ዮስ ለሚ​ባል የመቶ አለቃ ተሰጠ።</verse>
				<verse number="2">በተ​ነ​ሣ​ንም ጊዜ ወደ እስያ በም​ት​ሄድ በአ​ድ​ራ​ማ​ጢስ መር​ከብ ተሳ​ፈ​ርን፤ የተ​ሰ​ሎ​ንቄ ሀገር ሰው የሚ​ሆን መቄ​ዶ​ን​ያ​ዊው አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮ​ስም አብ​ሮን ሄደ።</verse>
				<verse number="3">በማ​ግ​ሥ​ቱም ወደ ሲዶና ደረ​ስን፤ ዩል​ዮ​ስም ለጳ​ው​ሎስ አዘ​ነ​ለት፤ ወደ ወዳ​ጆቹ እን​ዲ​ሄ​ድና በእ​ነ​ርሱ ዘንድ እን​ዲ​ያ​ር​ፍም ፈቀ​ደ​ለት።</verse>
				<verse number="4">ከዚ​ያም ወጥ​ተን ነፋስ ፊት ለፊት ነበ​ርና በቆ​ጵ​ሮስ በኩል ዐለ​ፍን።</verse>
				<verse number="5">ወደ ኪል​ቅ​ያና ወደ ጵን​ፍ​ልያ ባሕ​ርም ገብ​ተን የሉ​ቅያ ክፍል ወደ​ም​ት​ሆ​ነው ወደ ሙራ ሄድን።</verse>
				<verse number="6">በዚ​ያም የመቶ አለ​ቃው ወደ ኢጣ​ልያ የም​ት​ሄድ የእ​ስ​ክ​ን​ድ​ር​ያን መር​ከብ አገኘ፤ ወደ እር​ስ​ዋም አስ​ገ​ባን።</verse>
				<verse number="7">ብዙ ቀንም እያ​ዘ​ገ​ምን ሄድን፤ በጭ​ን​ቅም ወደ ቀኒ​ዶስ አን​ጻር ደረ​ስን፤ ወደ​ዚ​ያም በቀ​ጥታ ለመ​ድ​ረስ ነፋስ ቢከ​ለ​ክ​ለን በቀ​ር​ጤስ በኩል በሰ​ል​ሙና ፊት ለፊት ዐለ​ፍን።</verse>
				<verse number="8">ባጠ​ገ​ብ​ዋም በጭ​ንቅ ስና​ልፍ ላሲያ ለም​ት​ባ​ለው ከተማ አቅ​ራ​ቢያ ወደ ሆነ​ችው መል​ካም ወደብ ወደ​ም​ት​ባ​ለው ቦታ ደረ​ስን።</verse>
				<verse number="9">በዚ​ያም ብዙ ቀን ቈየን፤ የአ​ይ​ሁ​ድም የጾም ወራት አልፎ ስለ ነበረ በመ​ር​ከብ ለመ​ሄድ የሚ​ያ​ስ​ፈራ ነበ​ርና ጳው​ሎስ እን​ዲህ ብሎ መከ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">“እና​ንተ ሰዎች ሆይ፥ ስሙኝ፤ ጕዞ​አ​ችን በብዙ ጭን​ቀ​ትና በከ​ባድ ጥፋት ላይ ሆኖ አያ​ለሁ፤ ይህ​ንም የም​ለው ጥፋቱ በራ​ሳ​ች​ንም ሕይ​ወት እንጂ በጭ​ነ​ቱና በመ​ር​ከቡ ብቻ ስላ​ል​ሆነ ነው።”</verse>
				<verse number="11">የመቶ አለ​ቃው ግን ለመ​ር​ከቡ ባለ​ቤ​ትና ለመ​ሪው ይታ​ዘዝ ነበር፤ የጳ​ው​ሎ​ስን ቃል ግን አይ​ቀ​በ​ልም ነበር።</verse>
				<verse number="12">ያም ወደብ ክረ​ም​ቱን ሊከ​ር​ሙ​በት የማ​ይ​መች ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም ብዙ​ዎች ከዚያ ይወጡ ዘንድ ይቻ​ላ​ቸው እንደ ሆነ በቀኝ በኩል ወደ አለው ፊንቄ ወደ​ሚ​ባ​ለው ወደ ሁለ​ተ​ኛው የቀ​ር​ጤስ ወደብ ይደ​ርሱ ዘንድ ወደዱ።</verse>
				<verse number="13">ልከኛ የአ​ዜብ ነፋ​ስም ነፈሰ፤ እነ​ር​ሱም እንደ ወደዱ የሚ​ደ​ርሱ መስ​ሎ​አ​ቸው ነበር፤ መል​ሕ​ቁ​ንም አነሡ፤ በቀ​ር​ጤ​ስም አጠ​ገብ ሄዱ።</verse>
				<verse number="14">ከጥ​ቂት ጊዜ በኋ​ላም አው​ራ​ቂስ የሚ​ሉት ጽኑዕ ዓውሎ ነፋስ መጣ።</verse>
				<verse number="15">መር​ከ​ባ​ች​ንም ተመ​ትታ ተነ​ጠ​ቀች፤ ቀዛ​ፊ​ዎ​ችም በነ​ፋሱ ፊት ለፊት መቆም አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና ተዉ​አት፤ ብቻ​ዋ​ንም ሄደች።</verse>
				<verse number="16">ከዚ​ህም በኋላ ቄዳ ወደ​ም​ት​ባል ደሴት እስ​ክ​ን​ገባ ድረስ ነፋሱ ነፈሰ፤ በጭ​ን​ቅም ታን​ኳ​ች​ንን ለመ​ግ​ታት ቻልን።</verse>
				<verse number="17">ከዚህ በኋላ ተጋ​ግ​ዘን በገ​መድ አጠ​ና​ከ​ር​ናት፤ ከዚ​ህም ቀጥሎ ቀዛ​ፊ​ዎች ወደ ጥልቁ ባሕር እን​ዳ​ይ​ወ​ድቁ በፈሩ ጊዜ ሸራ​ውን አወ​ረዱ፤እን​ዲ​ሁም እን​ድ​ን​ሄድ አደ​ረ​ግን።</verse>
				<verse number="18">በማ​ግ​ሥ​ቱም ማዕ​በል ጸና​ብን፤ ከጭ​ነ​ቱም ወደ ባሕር ጣልን።</verse>
				<verse number="19">በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን በመ​ር​ከብ ያለ​ውን ሁሉ በእ​ጃ​ችን እያ​ነ​ሣን በባ​ሕር ላይ ጣልን።</verse>
				<verse number="20">ብዙ ቀንም ፀሐ​ይ​ንና ጨረ​ቃን ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም ሳናይ ማዕ​በሉ ጸና​ብን፤ ለመ​ዳ​ንም ተስፋ ቈር​ጠን ነበር።</verse>
				<verse number="21">ከእ​ኛም መብል የበላ አል​ነ​በ​ረም። ጳው​ሎ​ስም ተነ​ሥቶ በመ​ካ​ከል ቆመና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰዎች ሆይ፥ ቀድሞ ቃሌን ሰም​ታ​ች​ሁኝ ቢሆን ከቀ​ር​ጤ​ስም ባት​ወጡ ኖሮ ከዚህ ጕዳ​ትና መከራ በዳ​ና​ችሁ ነበር።</verse>
				<verse number="22">አሁ​ንም እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ መር​ከ​ባ​ችን እንጂ ከመ​ካ​ከ​ላ​ችን አንድ ሰው ስንኳ አይ​ጠ​ፋ​ምና አት​ፍሩ።</verse>
				<verse number="23">እኔ ለእ​ርሱ የም​ሆ​ንና የማ​መ​ል​ከው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የላ​ከው መል​አክ በዚች ሌሊት በአ​ጠ​ገቤ ቆሞ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="24">እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፦ ‘ጳው​ሎስ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ በቄ​ሣር ፊት ልት​ቆም ይገ​ባ​ሃል፤ ከአ​ን​ተም ጋር የሚ​ሄ​ዱ​ትን ሁሉ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ንተ ሰጥ​ቶ​ሃል።’</verse>
				<verse number="25">አሁ​ንም ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ እንደ ነገ​ረኝ እን​ደ​ሚ​ሆን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ና​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="26">ነገር ግን ወደ አን​ዲት ደሴት እን​ደ​ር​ሳ​ለን።”</verse>
				<verse number="27">በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛ​ውም ቀን በመ​ን​ፈቀ ሌሊት በአ​ድ​ርያ ባሕር ስን​ጓዝ ቀዛ​ፊ​ዎች ወደ የብሱ የደ​ረሱ መሰ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="28">መለ​ኪያ ገመድ ጣሉ፤ በሰው ቁመ​ትም ሃያ አገኙ፤ ከዚ​ያም ጥቂት ፈቀቅ ብለው ዳግ​መኛ ጣሉ፤ በሰው ቁመ​ትም ዐሥራ አም​ስት አገኙ።</verse>
				<verse number="29">ድን​ጋ​ያማ በሆነ ቦታም እን​ዳ​ይ​ወ​ድቁ ፈሩ፤ ስለ​ዚ​ህም ከመ​ር​ከቡ በስ​ተ​ኋላ አራት መል​ሕቅ በባ​ሕሩ ላይ ጣሉ፤ ፈጥኖ እን​ዲ​ነ​ጋም ጸለዩ።</verse>
				<verse number="30">ከዚህ በኋ​ላም ቀዛ​ፊ​ዎቹ ከመ​ር​ከብ ሊኮ​በ​ልሉ በወ​ደዱ ጊዜ ወደ ኋላ ሊመ​ለሱ ከም​ድር ላይ ሆነው መር​ከ​ባ​ቸ​ውን የሚ​ያ​ጠ​ና​ክሩ መስ​ለው ጀል​ባ​ቸ​ውን ወደ ባሕር አወ​ረዱ።</verse>
				<verse number="31">ጳው​ሎ​ስም ይህን ባየ ጊዜ ለመቶ አለ​ቃ​ውና ለወ​ታ​ደ​ሮቹ፥ “እነ​ዚህ ቀዛ​ፊ​ዎች በመ​ር​ከብ ውስጥ ከሌሉ መዳን አት​ች​ሉም” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="32">ወታ​ደ​ሮ​ችም ወዲ​ያ​ውኑ ተነ​ሥ​ተው የታ​ን​ኳ​ዪ​ቱን ገመድ ቈር​ጠው ትወ​ድቅ ዘንድ ተዉ​አት።</verse>
				<verse number="33">ሊነ​ጋም በጀ​መረ ጊዜ ጳው​ሎስ እህል እን​ዲ​በሉ ሁሉ​ንም ማለ​ዳ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እህል ከተ​ዋ​ችሁ ዛሬ ዐሥራ አራት ቀን ነው።</verse>
				<verse number="34">አሁ​ንም እሺ በሉ​ኝና ምግብ ብሉ፤ ራሳ​ች​ሁ​ንም አድኑ፥ ከእ​ና​ንተ ከአ​ንዱ የራስ ጠጕር እንኳ አት​ጠ​ፋ​ምና።”</verse>
				<verse number="35">ይህ​ንም ተና​ግሮ ኅብ​ስ​ቱን አን​ሥቶ በሁ​ሉም ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገነ፤ ቈር​ሶም ይበላ ዘንድ ጀመረ።</verse>
				<verse number="36">ሁሉም ተጽ​ናኑ፤ እህ​ልም ቀመሱ።</verse>
				<verse number="37">በመ​ር​ከቡ ውስጥ የነ​በ​ሩ​ትም ቍጥ​ራ​ቸው ሁለት መቶ ሰባ ስድ​ስት ነፍስ ነበር።</verse>
				<verse number="38">በል​ተ​ውም በጠ​ገቡ ጊዜ በመ​ር​ከቡ ውስጥ የነ​በ​ረ​ውን ስንዴ ወደ ባሕር ጣሉት፤ መር​ከ​ቡ​ንም አቃ​ለሉ።</verse>
				<verse number="39">በነጋ ጊዜም ቀዛ​ፊ​ዎች ቦታ​ውን አል​ለ​ዩም፤ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም አላ​ወ​ቁም፤ ነገር ግን ለባ​ሕሩ አቅ​ራ​ቢያ የሆ​ነ​ውን የደ​ሴት ተራ​ሮች አዩ፤ መር​ከ​ባ​ቸ​ው​ንም ወደ እዚያ ሊያ​ስ​ጠጉ ፈለጉ።</verse>
				<verse number="40">መል​ሕ​ቁ​ንም ፈት​ተው በባ​ሕር ላይ ጣሉት፤ የሚ​ያ​ቆ​ሙ​በ​ት​ንም አመ​ቻ​ች​ተው እንደ ነፋሱ አነ​ፋ​ፈስ መጠን ትን​ሹን ሸራ ሰቀሉ፤ ወደ ባሕሩ ዳር​ቻም ሄድን።</verse>
				<verse number="41">መር​ከ​ቢ​ቱም በሁ​ለት ታላ​ላቅ ድን​ጋ​ዮች መካ​ከል ተቀ​ረ​ቀ​ረች፤ ባሕ​ሩም ጥልቅ ነበረ። ከወ​ደ​ፊ​ቷም ተያ​ዘች፤ አል​ተ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰ​ች​ምም፤ ከሞ​ገ​ዱም የተ​ነሣ በስ​ተ​ኋላ በኩል ጎን​ዋን ተሰ​ብራ ተጐ​ረ​ደች፤ ቀዛ​ፊ​ዎ​ችም ወደ​ፊት ሊገ​ፉ​አት አል​ቻ​ሉም።</verse>
				<verse number="42">ወታ​ደ​ሮ​ቹም ዋኝ​ተው እን​ዳ​ያ​መ​ልጡ እስ​ረ​ኞ​ችን ለመ​ግ​ደል ተማ​ከሩ።</verse>
				<verse number="43">የመቶ አለ​ቃው ግን ጳው​ሎ​ስን ሊያ​ድ​ነው ወድ​ዶ​አ​ልና ምክ​ራ​ቸ​ውን እንቢ አለ፤ ዋና የሚ​ያ​ው​ቁ​ት​ንም ዋኝ​ተው ወደ ምድር እን​ዲ​ወጡ አዘ​ዛ​ቸው።</verse>
				<verse number="44">የቀ​ሩ​ትም በመ​ር​ከቡ ስብ​ር​ባሪ ዕን​ጨ​ትና በሳ​ን​ቃው ላይ ተሻ​ገሩ፤ ሌሎ​ችም በመ​ር​ከቡ ገመድ ላይ እየ​ተ​ን​ጠ​ላ​ጠሉ ተሻ​ገሩ፤ ሁሉም እን​ዲህ ባለ ሁኔታ በደ​ኅና ወደ ምድር ደረሱ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="28">
				<verse number="1">ከዚ​ህም በኋላ በደ​ኅና በደ​ረ​ስን ጊዜ ደሴ​ቲቱ መላ​ጥያ እን​ደ​ም​ት​ባል ዐወ​ቅን።</verse>
				<verse number="2">በዚያ የሚ​ኖ​ሩት አረ​ማ​ው​ያ​ንም አዘ​ኑ​ልን፤ መል​ካም ነገ​ር​ንም አደ​ረ​ጉ​ልን፤ ከቍ​ሩም ጽና​ትና ከዝ​ናሙ ብዛት የተ​ነሣ እሳት አን​ድ​ደው እን​ድ​ን​ሞቅ ሁላ​ች​ን​ንም ሰበ​ሰ​ቡን።</verse>
				<verse number="3">ጳው​ሎ​ስም ብዙ ጭራሮ ሰብ​ስቦ በእ​ሳቱ ላይ ጨመ​ረው፤ እፉ​ኝ​ትም ከእ​ሳቱ ወላ​ፈን የተ​ነሣ ወጥታ ጳው​ሎ​ስን እጁን ነደ​ፈ​ችው።</verse>
				<verse number="4">አረ​ማ​ው​ያ​ንም እፉ​ኝቱ በጳ​ው​ሎስ እጅ ላይ ተን​ጠ​ል​ጥላ ባዩ ጊዜ እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ይመ​ስ​ላል፤ ከባ​ሕር እንኳ በደ​ኅና ቢወ​ጣም በሕ​ይ​ወት ይኖር ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ አል​ተ​ወ​ውም” አሉ።</verse>
				<verse number="5">ጳው​ሎስ ግን እጁን አራ​ግፎ እፉ​ኝ​ቱን በእ​ሳት ውስጥ ጣላት፤ ጕዳ​ትም አላ​ገ​ኘ​ውም።</verse>
				<verse number="6">እነ​ርሱ ግን ወዲ​ያ​ውኑ የሚ​ያ​ብጥ ወይም ሞቶ የሚ​ወ​ድቅ መስ​ሎ​አ​ቸው ነበር። እያ​ዩ​ትም ብዙ ሰዓት ቆሙ፤ አን​ዳ​ችም እንደ አል​ጐ​ዳው በአዩ ጊዜም፥ “ይህስ አም​ላክ ነው” ብለው ቃላ​ቸ​ውን ለወጡ።</verse>
				<verse number="7">በዚያ ቦታም አጠ​ገብ ስሙን ፑፕ​ል​ዮስ የሚ​ሉት የደ​ሴ​ቲቱ አለቃ መሬት ነበር፤ እር​ሱም ሦስት ቀን ሙሉ በደ​ስታ በቤቱ ተቀ​ብሎ አስ​ተ​ና​ገ​ደን።</verse>
				<verse number="8">የፑ​ፕ​ል​ዮ​ስም አባት በን​ዳ​ድና በተ​ቅ​ማጥ ታሞ ተኝቶ ይኖር ነበር፤ ጳው​ሎ​ስም እርሱ ወዳ​ለ​በት ገብቶ ጸለ​የ​ለት፤ እጁ​ንም በላዩ ጭኖ ፈወ​ሰው።</verse>
				<verse number="9">ያደ​ረ​ገ​ው​ንም ይህን ተአ​ምር ባዩ ጊዜ በዚ​ያች ደሴት ያሉ​ትን ድው​ያን ሁሉ አመ​ጡ​ለት፤ ፈወ​ሳ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="10">እጅግ ታላቅ ክብ​ርም አከ​በ​ሩን፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ ለመ​ሄድ በተ​ነ​ሣን ጊዜ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ንን ስንቅ ሰጡን።</verse>
				<verse number="11">ከሦ​ስት ወር በኋ​ላም በዚ​ያች ደሴት ወደ ከረ​መ​ችው ወደ እስ​ክ​ን​ድ​ርያ መር​ከብ ወጣን፤ በዚ​ያች መር​ከብ ላይም የዲ​ዮ​ስ​ቆ​ሮስ ምል​ክት ነበ​ረ​ባት፤ ይኸ​ውም “የመ​ር​ከ​በ​ኞች አም​ላክ” የሚ​ሉት ነው።</verse>
				<verse number="12">ከዚ​ያም ሄደን ወደ ሰራ​ኩስ ደረ​ስን፤ በዚ​ያም ሦስት ቀን ተቀ​መ​ጥን።</verse>
				<verse number="13">ከዚ​ያም ሄደን ሬቅ​ዩን ወደ​ም​ት​ባል ሀገር ደረ​ስን፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም ወጣን፤ ከአ​ንድ ቀንም በኋላ ከጐ​ንዋ ነፋስ በነ​ፈሰ ጊዜ በሁ​ለ​ተ​ኛው ቀን ወደ ፑቲ​ዮ​ሉስ ደረ​ስን።</verse>
				<verse number="14">በዚ​ያም ወን​ድ​ሞ​ችን አግ​ኝ​ተን ተቀ​በ​ሉን፤ በእ​ነ​ርሱ ዘን​ድም ሰባት ቀን እን​ድ​ን​ቀ​መጥ ለመ​ኑን፤ ከዚ​ያም በኋላ ሄደን ወደ ሮሜ ደረ​ስን።</verse>
				<verse number="15">በዚ​ያም ያሉት ወን​ድ​ሞች ስለ እኛ በሰሙ ጊዜ፤ አፍ​ዩስ ፋሩስ እስ​ከ​ሚ​ባ​ለው ገበ​ያና እስከ ሦስ​ተ​ኛው ማረ​ፊያ ድረስ ወጥ​ተው ተቀ​በ​ሉን፤ ጳው​ሎ​ስም ባያ​ቸው ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገነ፤ ልቡም ተጽ​ናና።</verse>
				<verse number="16">ወደ ሮሜም በገ​ባን ጊዜ የመቶ አለ​ቃው እስ​ረ​ኞ​ችን ለሠ​ራ​ዊቱ አለቃ አስ​ረ​ከበ፤ ጳው​ሎስ ግን ከሚ​ጠ​ብ​ቀው አንድ ወታ​ደር ጋር ለብ​ቻው ይቀ​መጥ ዘንድ ፈቀ​ደ​ለት።</verse>
				<verse number="17">ከሦ​ስት ቀንም በኋላ ጳው​ሎስ የአ​ይ​ሁ​ድን ታላ​ላቅ ሰዎች ሰበ​ሰ​ባ​ቸው፤ በተ​ሰ​በ​ሰ​ቡም ጊዜ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኔ በሕ​ዝ​ቡም ላይ ቢሆን፥ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሕግ ላይ ቢሆን ያደ​ረ​ግ​ሁት ክፉ ነገር የለም፤ ነገር ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ ታሰ​ርሁ ለሮም ሰዎች አሳ​ል​ፈው ሰጡኝ።</verse>
				<verse number="18">እነ​ር​ሱም መር​ም​ረው ለሞት የሚ​ያ​በቃ በደል ስለ​አ​ላ​ገ​ኙ​ብኝ ሊፈ​ቱኝ ወደዱ።</verse>
				<verse number="19">አይ​ሁድ ግን ሊቃ​ወ​ሙኝ በተ​ነሡ ጊዜ ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ ለማ​ለት ግድ ሆነ​ብኝ፤ ነገር ግን ወገ​ኖ​ችን የም​ከ​ስ​በት ነገር ኖሮኝ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="20">ስለ​ዚ​ህም ላያ​ችሁ፥ ልነ​ግ​ራ​ች​ሁና ላስ​ረ​ዳ​ችሁ ወደ እኔ እን​ድ​ት​መጡ ማለ​ድ​ኋ​ችሁ፤ ስለ እስ​ራ​ኤል ተስፋ በዚህ ሰን​ሰ​ለት ታስ​ሬ​አ​ለ​ሁና።”</verse>
				<verse number="21">የአ​ይ​ሁድ ታላ​ላቅ ሰዎ​ችም እን​ዲህ አሉት፥ “ለእ​ኛስ ከይ​ሁዳ ሀገር ስለ አንተ መል​እ​ክት አል​ደ​ረ​ሰ​ንም፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከመ​ጡት ወን​ድ​ሞ​ችም ቢሆን አንድ ስንኳ ከዚህ አስ​ቀ​ድሞ ስለ አንተ ክፉ ነገር ያወ​ራን፥ የነ​ገ​ረ​ንም የለም።</verse>
				<verse number="22">ነገር ግን በዚህ ነገር በየ​ስ​ፍ​ራው ሁሉ እን​ዲ​ጣሉ በእኛ ዘንድ ታው​ቋ​ልና የአ​ን​ተን ዐሳብ ደግሞ ከአ​ንተ እን​ሰማ ዘንድ እን​ወ​ድ​ዳ​ለን።”</verse>
				<verse number="23">ከዚ​ህም በኋላ ወደ እርሱ የሚ​መ​ጡ​በ​ትን ቀን ቀጠ​ሩ​ትና ብዙ​ዎች ወዳ​ረ​ፈ​በት ወደ እርሱ መጡ፤ ከጥ​ዋ​ትም ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እየ​መ​ሰ​ከረ ስለ ጌታ​ችን ስለ ኢየ​ሱ​ስም ከሙሴ ኦሪ​ትና ከነ​ቢ​ያት እየ​ጠ​ቀሰ ነገ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="24">ከእ​ነ​ር​ሱም እኩ​ሌ​ቶቹ የተ​ና​ገ​ረ​ውን አመኑ፤ እኩ​ሌ​ቶቹ ግን አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​ትም።</verse>
				<verse number="25">እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ባል​ተ​ስ​ማሙ ጊዜ ጳው​ሎስ አን​ዲት ቃል ከተ​ና​ገረ በኋላ ከእ​ርሱ ተመ​ለሱ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “መን​ፈስ ቅዱስ በነ​ቢዩ በኢ​ሳ​ይ​ያስ አን​ደ​በት ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን በእ​ው​ነት እን​ዲህ ብሎ መል​ካም ነገር ተና​ግ​ሮ​አል።</verse>
				<verse number="26">‘ወደ​ዚህ ሕዝብ ሂድና እን​ዲህ በላ​ቸው፦ መስ​ማ​ትን ትሰ​ማ​ላ​ችሁ፤ ግን አታ​ስ​ተ​ው​ሉም፤ ማየ​ት​ንም ታያ​ላ​ችሁ፤ ግን አት​መ​ለ​ከ​ቱም።</verse>
				<verse number="27">በዐ​ይ​ና​ቸው እን​ዳ​ያዩ፥ በጆ​ሮ​አ​ቸ​ውም እን​ዳ​ይ​ሰሙ፥ በል​ባ​ቸ​ውም እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ውሉ፥ ወደ እኔም እን​ዳ​ይ​መ​ለ​ሱና ይቅር እን​ዳ​ል​ላ​ቸው የዚህ ሕዝብ ልባ​ቸው ደን​ድ​ኖ​አ​ልና፥ ጆሮ​አ​ቸ​ውም ደን​ቁ​ሮ​አ​ልና፥ ዐይ​ና​ቸ​ው​ንም ጨፍ​ነ​ዋ​ልና’።</verse>
				<verse number="28">እን​ግ​ዲህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ገ​ኘች ይህቺ ድኅ​ነት ለአ​ሕ​ዛብ እን​ደ​ም​ት​ሆን ዕወቁ፤ እነ​ር​ሱም ይሰ​ሙ​ታል።”</verse>
				<verse number="29">ይህ​ንም በተ​ና​ገ​ራ​ቸው ጊዜ አይ​ሁድ እርስ በር​ሳ​ቸው እጅግ እየ​ተ​ከ​ራ​ከሩ ወጥ​ተው ሄዱ።</verse>
				<verse number="30">ጳው​ሎ​ስም በገ​ን​ዘቡ በተ​ከ​ራ​የው ቤት ሁለት ዓመት ተቀ​መጠ፤ ወደ እርሱ የሚ​መ​ጣ​ው​ንም ሁሉ ይቀ​በል ነበር።</verse>
				<verse number="31">ማንም ሳይ​ከ​ለ​ክ​ለው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ይሰ​ብክ ነበር፤ ስለ ጌታ​ችን ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም እጅግ ገልጦ ያስ​ተ​ምር ነበር።</verse>
				<verse number="32">ጳው​ሎ​ስም በመ​ጀ​መ​ሪያ ጊዜ ወደ ኔሮን ቄሣር ገብቶ ነበ​ርና ረትቶ በሰ​ላም ሄደ፤ ከዚ​ህም በኋላ ሁለት ዓመት ኖሮ ከሮም ወጣ።</verse>
				<verse number="33">ከዚ​ህም በኋላ ወደ ሮም ተመ​ልሶ የኔ​ሮን ቄሣር ዘመ​ዶ​ችን አጠ​መቀ፤ በኔ​ሮን ትእ​ዛ​ዝም በሰ​ይፍ ተመ​ትቶ መከ​ራ​ው​ንም ታግሦ ሰማ​ዕት ሆነ። ወን​ጌ​ላ​ዊው ሉቃስ የጻ​ፈው የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ መጽ​ሐፍ ተፈ​ጸመ። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን አሜን።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="45">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ወን​ጌል ለማ​ስ​ተ​ማር ተለ​ይቶ ከተ​ጠራ ሐዋ​ርያ፥ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አገ​ል​ጋይ ከሚ​ሆን ከጳ​ው​ሎስ፥</verse>
				<verse number="2">በነ​ቢ​ያቱ ቃልና በቅ​ዱ​ሳት መጻ​ሕ​ፍት አስ​ቀ​ድሞ በተ​ስፋ ያና​ገ​ረው፥</verse>
				<verse number="3">ከዳ​ዊት ዘር ሰው ሆኖ በሥጋ ስለ ተወ​ለደ ስለ ልጁ፥</verse>
				<verse number="4">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ በኀ​ይ​ሉና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ፥ ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይቶ በመ​ነ​ሣቱ ስለ አሳየ ስለ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ፥</verse>
				<verse number="5">በስሙ እን​ዲ​ያ​ምኑ አሕ​ዛ​ብን ልና​ስ​ተ​ምር ሐዋ​ር​ያት ተብ​ለን የተ​ሾ​ም​ን​በ​ትና ጸጋን ያገ​ኘ​ን​በት፥</verse>
				<verse number="6">እና​ን​ተም ዛሬ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ለማ​መን እንደ ተጠ​ራ​ችሁ።</verse>
				<verse number="7">በሮሜ ላላ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ወ​ዳ​ችሁ፥ ለመ​ረ​ጣ​ች​ሁና ላከ​በ​ራ​ችሁ ሁሉ፥ ከአ​ባ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰላ​ምና ጸጋ ለእ​ና​ንተ ይሁን።</verse>
				<verse number="8">አስ​ቀ​ድሜ ስለ ሁላ​ችሁ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ፤ ማመ​ና​ችሁ በዓ​ለም ሁሉ ተሰ​ም​ታ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="9">ባለ​ማ​ቋ​ረጥ በም​ጸ​ል​የው ጸሎት እን​ደ​ማ​ስ​ባ​ችሁ ልጁ በአ​ስ​ተ​ማ​ረው ወን​ጌል በፍ​ጹም ልቡ​ናዬ የማ​መ​ል​ከው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክሬ ነው።</verse>
				<verse number="10">ወደ እና​ንተ እመጣ ዘን​ድም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃዱ መን​ገ​ዴን ያቃ​ና​ልኝ ዘንድ ዘወ​ትር እጸ​ል​ያ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">ትጸኑ ዘንድ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ስጦታ እን​ድ​ታ​ገኙ ላያ​ችሁ እወ​ዳ​ለ​ሁና፤</verse>
				<verse number="12">ይህ​ንም ማለቴ በመ​ካ​ከ​ላ​ችን ባለች በእ​ና​ን​ተና በእኔ እም​ነት አብ​ረን በእ​ና​ንተ እን​ድ​ን​ጽ​ናና ነው።</verse>
				<verse number="13">ነገር ግን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በሌ​ሎች አሕ​ዛብ እንደ ሆነ በእ​ና​ን​ተም ዋጋ​ዬን አገኝ ዘንድ ሁል​ጊዜ ወደ እና​ንተ ልመጣ እንደ ወደ​ድሁ፥ እስከ ዛሬ ድረ​ስም እንደ ተሳ​ነኝ ልታ​ውቁ እወ​ድ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">ለአ​ረ​ማ​ው​ያ​ንና ላል​ተ​ማሩ፥ ለጥ​በ​በ​ኞ​ችና ለማ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉም ሁሉ አስ​ተ​ምር ዘንድ ዕዳ አለ​ብኝ።</verse>
				<verse number="15">ይል​ቁ​ንም በሮሜ ላላ​ችሁ ለእ​ና​ንተ ወን​ጌ​ልን ላስ​ተ​ም​ራ​ችሁ እተ​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">ወን​ጌ​ልን ለማ​ስ​ተ​ማር አላ​ፍ​ር​ምና፤ አስ​ቀ​ድሞ አይ​ሁ​ዳ​ዊን፥ ደግ​ሞም አረ​ማ​ዊን፥ የሚ​ያ​ም​ኑ​በ​ትን ሁሉ የሚ​ያ​ድ​ና​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይሉ ነውና።</verse>
				<verse number="17">“ጻድቅ በእ​ም​ነት ይኖ​ራል” ብሎ መጽ​ሐፍ እንደ ተና​ገረ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድቅ ከእ​ም​ነት ወደ እም​ነት በእ​ርሱ ይገ​ለ​ጣ​ልና።</verse>
				<verse number="18">እው​ነ​ትን ዐው​ቀው በክ​ፋ​ታ​ቸው በሚ​ለ​ው​ጡ​አት በዐ​መ​ፀ​ና​ውና በኀ​ጢ​አ​ተ​ናው ሰው ሁሉ ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ሠ​ፍት ከሰ​ማይ ይመ​ጣል።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ገለ​ጠ​ላ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማወቅ በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና።</verse>
				<verse number="20">የማ​ይ​ታ​የው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሕ​ርይ እር​ሱም የዘ​ለ​ዓ​ለም ኀይ​ሉና ጌት​ነቱ ከዓ​ለም ፍጥ​ረት ጀምሮ የፈ​ጠ​ረ​ውን ፍጥ​ረት በማ​ሰ​ብና በመ​መ​ር​መር ይታ​ወ​ቃል፤ መልስ የሚ​ሰ​ጡ​በ​ትን ምክ​ን​ያት እን​ዳ​ያ​ገኙ።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሲያ​ው​ቁት እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ነቱ አላ​ከ​በ​ሩ​ትም፤ አላ​መ​ሰ​ገ​ኑ​ት​ምም፤ ነገር ግን ካዱት፤ በአ​ሳ​ባ​ቸ​ውም ረከሱ፤ ልቡ​ና​ቸ​ውም ባለ​ማ​ወቅ ጨለመ።</verse>
				<verse number="22">ጥበ​በ​ኞች ነን ሲሉ አላ​ዋ​ቆች ሆኑ።</verse>
				<verse number="23">የማ​ይ​ሞ​ተ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር በሚ​ሞት ሰውና በዎ​ፎች፥ አራት እግር ባላ​ቸ​ውም፥ በሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ትም መልክ መስ​ለው ለወጡ።</verse>
				<verse number="24">ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርስ በር​ሳ​ቸው ሥጋ​ቸ​ውን ሊያ​ዋ​ርዱ በል​ባ​ቸው ፍት​ወት ወደ ርኵ​ሰት አሳ​ልፎ ተዋ​ቸው።</verse>
				<verse number="25">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እው​ነት ሐሰት አድ​ር​ገ​ዋ​ታ​ልና፤ ተዋ​ር​ደ​ውም ፍጥ​ረ​ቱን አም​ል​ከ​ዋ​ልና፤ ሁሉን የፈ​ጠ​ረ​ውን ግን ተዉት፤ እር​ሱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቡሩክ አም​ላክ ነው፤ አሜን።</verse>
				<verse number="26">ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክፉ መቅ​ሠ​ፍ​ትን አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ ሴቶ​ቻ​ቸ​ውም ለባ​ሕ​ር​ያ​ቸው የሚ​ገ​ባ​ውን ትተው ለባ​ሕ​ር​ያ​ቸው የማ​ይ​ገ​ባ​ውን ሠሩ።</verse>
				<verse number="27">ወን​ዶ​ችም እን​ዲሁ ለባ​ሕ​ር​ያ​ቸው የሚ​ገ​ባ​ውን ሴቶ​ችን ትተው በፍ​ት​ወት ተቃ​ጠሉ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም እየ​ተ​መ​ላ​ለሱ፥ ወን​ዶች በወ​ን​ዶች ላይ የሚ​ያ​ዋ​ር​ዳ​ቸ​ውን ነውር ሠሩ፤ ነገር ግን ፍዳ​ቸ​ውን ያገ​ናሉ፤ ፍዳ​ቸ​ውም በራ​ሳ​ቸው ይመ​ለ​ሳል።</verse>
				<verse number="28">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​ወቅ ባል​ወ​ደዱ መጠን እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን የማ​ይ​ገ​ባ​ውን ይሠሩ ዘንድ ሰነፍ አእ​ም​ሮን ሰጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="29">እነ​ር​ሱም ዐመ​ፅን ሁሉ፥ ክፋ​ት​ንም፥ ምኞ​ት​ንም፥ ቅሚ​ያ​ንም፥ ቅና​ት​ንም የተ​መሉ ናቸው፤ ምቀ​ኞች፥ ነፍሰ ገዳ​ዮች፥ ከዳ​ተ​ኞች፥ ተን​ኰ​ለ​ኞች፥ ኩሩ​ዎች፥ ጠባ​ያ​ቸ​ው​ንና ግብ​ራ​ቸ​ው​ንም ያከፉ ናቸው።</verse>
				<verse number="30">ሐሜ​ተ​ኞች፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ጠሉ፥ ተሳ​ዳ​ቢ​ዎች፥ ትዕ​ቢ​ተ​ኞች፥ ትም​ክ​ሕ​ተ​ኞች፥ ክፋ​ትን የሚ​ፈ​ላ​ለጉ፥ ለወ​ላ​ጆ​ቻ​ቸ​ውም የማ​ይ​ታ​ዘዙ ናቸው።</verse>
				<verse number="31">የማ​ያ​ስ​ተ​ውሉ፥ ዝን​ጉ​ዎች፥ ፍቅ​ርም፥ ምሕ​ረ​ትም የሌ​ላ​ቸው ናቸው።</verse>
				<verse number="32">ይህን እን​ዲህ ላደ​ረገ ሞት እን​ደ​ሚ​ገ​ባው እነ​ርሱ ራሳ​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍርድ እያ​ወቁ፥ እነ​ርሱ ብቻ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉት አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ሌላ​ውን ያነ​ሣ​ሡ​ታል፤ ያሠ​ሩ​ታ​ልም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">አንተ ሰው ሆይ፥ እው​ነት ለሚ​ፈ​ር​ደው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን ትመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለህ? በወ​ን​ድ​ምህ ላይ የም​ት​ጠ​ላ​ውን ያን ሥራ አንተ ራስህ ከሠ​ራ​ኸው በራ​ስህ የም​ት​ፈ​ርድ አይ​ደ​ለ​ምን? አንተ ራስህ ያን ሥራ ትሠ​ራ​ዋ​ለ​ህና።</verse>
				<verse number="2">ይህም እን​ደ​ዚህ በሚ​ያ​ደ​ርጉ ሰዎች ላይ ቅጣት የሚ​ያ​መጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርዱ እው​ነት እንደ ሆነ እና​ው​ቃ​ለን።</verse>
				<verse number="3">አንተ ሰው ሆይ፥ በሌላ ላይ አይ​ተህ የም​ት​ጠ​ላ​ው​ንና የም​ት​ነ​ቅ​ፈ​ውን ያን አንተ ራስህ የም​ት​ሠ​ራው ከሆነ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ እን​ደ​ም​ታ​መ​ልጥ ታስ​ባ​ለ​ህን?</verse>
				<verse number="4">ወይስ በቸ​ር​ነቱ ብዛት በመ​ታ​ገሡ፥ ለአ​ን​ተም እሺ በማ​ለቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ዋቂ ልታ​ደ​ር​ገው ታስ​ባ​ለ​ህን? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ቸር​ነቱ አን​ተን ወደ ንስሓ እን​ዲ​መ​ል​ስህ አታ​ው​ቅ​ምን?</verse>
				<verse number="5">ነገር ግን ልቡ​ና​ህን እንደ ማጽ​ና​ትህ፥ ንስ​ሓም እንደ አለ​መ​ግ​ባ​ትህ መጠን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተና ፍርድ በሚ​ገ​ለ​ጥ​በት ቀን መቅ​ሠ​ፍ​ትን ለራ​ስህ ታከ​ማ​ቻ​ለህ።</verse>
				<verse number="6">እርሱ በእ​ው​ነ​ተና ፍርዱ ለሁሉ እንደ ሥራው ይከ​ፍ​ለ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="7">በበጎ ምግ​ባር ጸን​ተው ለሚ​ታ​ገሡ፥ ምስ​ጋ​ናና ክብ​ርን፥ የማ​ይ​ጠፋ ሕይ​ወ​ት​ንም ለሚሹ እርሱ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="8">ለሚ​ክ​ዱና እው​ነ​ትን ለሚ​ለ​ውጡ፥ ዐመ​ፅ​ንም ለሚ​ወ​ድዱ ሰዎች ዋጋ​ቸው ቍጣና መቅ​ሠ​ፍት ነው።</verse>
				<verse number="9">መከ​ራና ጭን​ቀት አስ​ቀ​ድሞ በአ​ይ​ሁ​ዳዊ፥ ደግ​ሞም በአ​ረ​ማዊ፥ ሥራዉ ክፉ በሆነ ሰው ሁሉ ላይ ነው።</verse>
				<verse number="10">ምስ​ጋ​ናና ክብር፥ ሰላ​ምም አስ​ቀ​ድሞ ለአ​ይ​ሁ​ዳዊ፥ ደግ​ሞም ለአ​ረ​ማዊ፥ ሥራዉ መል​ካም ለሆነ ሁሉ ነው።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ፊት አያ​ዳ​ላ​ምና።</verse>
				<verse number="12">ከሕግ ወጥ​ተው የበ​ደሉ በሕግ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ ያለ ሕግ የበ​ደሉ ሁሉም ያለ ሕግ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="13">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሕግን የሚ​ያ​ደ​ርጉ ይጸ​ድ​ቃሉ እንጂ ሕግን የሚ​ሰሙ አይ​ጸ​ድ​ቁ​ምና።</verse>
				<verse number="14">ሕግ የሌ​ላ​ቸው አሕ​ዛ​ብስ እንኳ ለራ​ሳ​ቸው ሕግ ይሠ​ራሉ፤ ራሳ​ቸው ለራ​ሳ​ቸው ሕግን ይደ​ነ​ግ​ጋሉ፤ በሕ​ጋ​ቸው የታ​ዘ​ዘ​ው​ንም ያደ​ር​ጋሉ።</verse>
				<verse number="15">በል​ባ​ቸው የተ​ጻ​ፈ​ውን የሕግ ሥራ ያሳ​ያሉ፤ ከሥ​ራ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ይታ​ወ​ቃል፤ ሕሊ​ና​ቸ​ውም ይመ​ሰ​ክ​ር​ባ​ቸ​ዋል፤ ይፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ልም።</verse>
				<verse number="16">ይህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እኔ በወ​ን​ጌል እን​ዳ​ስ​ተ​ማ​ርሁ ሰዎ​ችን በል​ቡ​ና​ቸው የሰ​ወ​ሩ​ት​ንና የሸ​ሸ​ጉ​ትን በሚ​መ​ረ​ም​ር​በት ጊዜ የሚ​ና​ገ​ሩ​ትና የሚ​መ​ል​ሱት እን​ደ​ሌለ ስለ​ሚ​ያ​ውቁ ነው።</verse>
				<verse number="17">አንተ አይ​ሁ​ዳዊ፥ በኦ​ሪ​ትህ የም​ታ​ርፍ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የም​ት​መካ ከሆ​ንህ፥</verse>
				<verse number="18">ፈቃ​ዱን የም​ታ​ውቅ፥ መል​ካ​ሙ​ንም የም​ት​ለይ፥ ኦሪ​ት​ንም የተ​ማ​ርህ ከሆ​ንህ፥</verse>
				<verse number="19">አንተ የዕ​ው​ሮች መሪ፥ በጨ​ለ​ማም ላሉት ብር​ሃን እንደ ሆንህ በራ​ስህ የም​ት​ታ​መን ከሆ​ንህ፥</verse>
				<verse number="20">ሰነ​ፎ​ችን ልባ​ሞች የም​ታ​ደ​ርግ፥ ሕፃ​ና​ትን የም​ታ​ስ​ተ​ምር፥ ጻድ​ቅና የም​ት​ከ​ብ​ር​በ​ትን የኦ​ሪ​ትን ሕግ የም​ታ​ውቅ የም​ት​መ​ስል፥</verse>
				<verse number="21">እን​ግ​ዲህ ሌላ​ውን የም​ታ​ስ​ተ​ምር ራስ​ህን እን​ዴት አታ​ስ​ተ​ም​ርም? አት​ስ​ረቁ ትላ​ለህ፤ ነገር ግን አንተ ራስህ ትሰ​ር​ቃ​ለህ።</verse>
				<verse number="22">አታ​መ​ን​ዝሩ ትላ​ለህ፤ ነገር ግን አንተ ራስህ ታመ​ነ​ዝ​ራ​ለህ፤ ወደ ጐል​ማሳ ሚስ​ትም ትሄ​ዳ​ለህ፤ ጣዖ​ትን ትጸ​የ​ፋ​ለህ፤ አንተ ግን ቤተ መቅ​ደ​ስን ትዘ​ር​ፋ​ለህ።</verse>
				<verse number="23">በኦ​ሪት ትመ​ካ​ለህ፤ ነገር ግን አንተ ራስህ ኦሪ​ትን በመ​ሻር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቃ​ል​ለ​ዋ​ለህ።</verse>
				<verse number="24">እንደ ተጻ​ፈም “እነሆ፥ በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት አሕ​ዛብ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ይሰ​ድ​ባሉ።”</verse>
				<verse number="25">ኦሪ​ት​ንም ብት​ፈ​ጽም ግዝ​ረት ትጠ​ቅ​ም​ሃ​ለች፤ ኦሪ​ትን ባት​ፈ​ጽም ግን ግዝ​ረ​ትህ አለ​መ​ገ​ዘር ትሆ​ን​ብ​ሃ​ለች።</verse>
				<verse number="26">አንተ ሳት​ገ​ዘር ብት​ኖር፥ ኦሪ​ት​ንም ብት​ጠ​ብቅ አለ​መ​ገ​ዘ​ርህ መገ​ዘር ትሆ​ን​ል​ሃ​ለች።</verse>
				<verse number="27">ተገ​ዝ​ረህ ኦሪ​ትን ከም​ታ​ፈ​ርስ በተ​ፈ​ጥሮ ያገ​ኘ​ሃት አለ​መ​ገ​ዘ​ርህ አብ​ራህ ብት​ኖር ይሻ​ል​ሃል፤ ኦሪ​ትን ከም​ታ​ፈ​ርስ ከአ​ንተ ከተ​ገ​ዘ​ር​ኸው ያ ያል​ተ​ገ​ዘ​ረው፥ ኦሪ​ትን የሚ​ፈ​ጽ​መው ይሻ​ላል።</verse>
				<verse number="28">በውኑ ለሰው ይም​ሰል አይ​ሁ​ዳዊ መሆን ይገ​ባ​ልን? ለሰው ፊትስ ተብሎ ይገ​ዘ​ሩ​አ​ልን?</verse>
				<verse number="29">ዳሩ ግን አይ​ሁ​ዳ​ዊ​ነት በስ​ውር ነው፤ መገ​ዘ​ርም በመ​ን​ፈስ የልብ መገ​ዘር እንጂ በኦ​ሪት ሥር​ዐት አይ​ደ​ለም፤ ምስ​ጋ​ና​ውም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው እንጂ ከሰው አይ​ደ​ለም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">እን​ግ​ዲህ አይ​ሁ​ዳዊ የመ​ባል ትርፉ ምን​ድን ነው? የግ​ዝ​ረ​ትስ ጥቅ​ምዋ ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="2">በሁሉ ነገር ብዙ ነው፤ ነገር ግን ከዚያ አስ​ቀ​ድሞ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል አደራ ተሰ​ጣ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">የማ​ያ​ምኑ ቢኖ​ሩስ የእ​ነ​ርሱ አለ​ማ​መን ሌላ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ያ​ምን ይከ​ለ​ክ​ላ​ልን? አይ​ከ​ለ​ክ​ልም።</verse>
				<verse number="4">መጽ​ሐፍ፥ “በነ​ገ​ርህ ትጸ​ድቅ ዘንድ፥ በፍ​ር​ድ​ህም ታሸ​ንፍ ዘንድ” ብሎ እንደ ተና​ገረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተና ነውና፥ ሰውም ሁሉ ሐሰ​ተና ነውና።</verse>
				<verse number="5">በእኔ ኀጢ​አት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድቅ ከጸና እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰው ላይ ቅጣ​ትን ቢያ​መጣ ይበ​ድ​ላ​ልን? አይ​በ​ድ​ልም፤ የም​ና​ገ​ረ​ው​ንም በሰው ልማድ እና​ገ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="6">እን​ዲ​ህማ ከሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ለም እን​ደ​ምን ይፈ​ር​ዳል?</verse>
				<verse number="7">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነት በእኔ ሐሰ​ተ​ና​ነት ለክ​ብሩ ከፍ ከአለ እን​ግ​ዲህ እኔን እንደ ኀጢ​አ​ተና ለምን ይፈ​ር​ድ​ብ​ናል?</verse>
				<verse number="8">በውኑ እና መል​ካም ነገር እና​ገኝ ዘንድ ክፉ ነገር እና​ድ​ርግ እን​ደ​ም​ንል አስ​መ​ስ​ለው የሚ​ጠ​ረ​ጥ​ሩ​ንና የሚ​ነ​ቅ​ፉን ሰዎች እን​ደ​ሚ​ሰ​ድ​ቡን ነን? ለእ​ነ​ር​ሱስ ቅጣ​ታ​ቸው ተዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="9">እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? ከእ​ነ​ርሱ እን​በ​ል​ጣ​ለን? አይ​ደ​ለም፤ አይ​ሁ​ዳ​ዊ​ንም፥ አረ​ማ​ዊ​ንም እነሆ፥ አስ​ቀ​ድ​መን ነቅ​ፈ​ና​ቸ​ዋል፤ ሁሉም ስተ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="10">መጽ​ሐፍ እን​ዲህ እን​ዳለ “አንድ ስንኳ ጻድቅ የለም።</verse>
				<verse number="11">አስ​ተ​ዋ​ይም የለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ሻው የለም።</verse>
				<verse number="12">ሁሉም ተባ​ብሮ በደለ፤ በጎ ሥራ​ንም የሚ​ሠራ የለም፤ አንድ ስንኳ ቢሆን የለም።</verse>
				<verse number="13">ጕረ​ሮ​አ​ቸው እንደ ተከ​ፈተ መቃ​ብር ነው፤ በአ​ን​ደ​በ​ታ​ቸ​ውም ሸነ​ገሉ፤ ከከ​ን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም በታች የእ​ባብ መርዝ አለ፤</verse>
				<verse number="14">አፋ​ቸው መራራ ነው፤ መር​ገ​ም​ንም የተ​ሞላ ነው።</verse>
				<verse number="15">እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ደምን ለማ​ፍ​ሰስ ፈጣ​ኖች ናቸው።</verse>
				<verse number="16">በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ጥፋ​ትና ጕስ​ቍ​ልና አለ።</verse>
				<verse number="17">የሰ​ላ​ምን መን​ገድ አያ​ው​ቋ​ትም።</verse>
				<verse number="18">በዐ​ይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት የለም።”</verse>
				<verse number="19">አን​ደ​በት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለ​ምም ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚ​ና​ገ​ረው ሁሉ በኦ​ሪት ላሉት እንደ ተነ​ገረ እና​ው​ቃ​ለን።</verse>
				<verse number="20">ከኦ​ሪት የተ​ነሣ ኀጢ​አት ስለ ታወ​ቀች ሰው ሁሉ የኦ​ሪ​ትን ሥር​ዐት በመ​ፈ​ጸም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አይ​ጸ​ድ​ቅም።</verse>
				<verse number="21">አሁን ግን በኦ​ሪ​ትና በነ​ቢ​ያት የተ​መ​ሰ​ከ​ረ​ላት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድቅ ያለ ኦሪት ተገ​ለ​ጠች።</verse>
				<verse number="22">የሚ​ያ​ም​ኑ​በት ሁሉ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን በማ​መን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይጸ​ድ​ቃሉ።</verse>
				<verse number="23">በዚ​ህም ልዩ​ነት የለም፤ ሁሉም ፈጽ​መው በድ​ለ​ዋ​ልና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማክ​በ​ር​ንም ትተ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="24">ጽድቅ ግን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ቤዛ​ነት ያለ ዋጋ በእ​ርሱ ቸር​ነት ሆነ።</verse>
				<verse number="25">እር​ሱ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ም​ነት የሚ​ገኝ፥ በደ​ሙም የሆነ ማስ​ተ​ስ​ረያ አድ​ርጎ አቆ​መው፤ ይህም ከጥ​ንት ጀምሮ በበ​ደ​ሉት ላይ ጽድ​ቁን ይገ​ልጥ ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="26">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታጋሽ በመ​ሆኑ፥ እሺ በማ​ለ​ቱም እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ፥ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም የሚ​ያ​ም​ኑ​ትን እን​ደ​ሚ​ያ​ጸ​ድ​ቃ​ቸው ዛሬ ያውቁ ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="27">ትም​ክ​ሕት ወዴት አለ? እርሱ ቀር​ቶ​አል፤ በየ​ት​ና​ውስ ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይ​ደ​ለም፤ በእ​ም​ነት ሕግ ነው እንጂ።</verse>
				<verse number="28">ሰው የኦ​ሪ​ትን ሥራ ሳይ​ሠራ በእ​ም​ነት እን​ዲ​ጸ​ድቅ እና​ው​ቃ​ለ​ንና።</verse>
				<verse number="29">በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ይ​ሁድ ለብ​ቻ​ቸው ነውን? ለአ​ሕ​ዛ​ብስ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="30">አዎን፥ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ነው፤ የተ​ገ​ዘ​ረ​ውን በእ​ም​ነት የሚ​ያ​ጸ​ድቅ፥ ያል​ተ​ገ​ዘ​ረ​ው​ንም በእ​ም​ነት የሚ​ያ​ጸ​ድ​ቀው እርሱ አንዱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና።</verse>
				<verse number="31">እን​ግ​ዲህ በእ​ም​ነት ኦሪ​ትን እን​ሽ​ራ​ለን? አን​ሽ​ርም፤ ኦሪ​ትን እና​ጸ​ና​ለን እንጂ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">እን​ግ​ዲህ በሥጋ የቀ​ድሞ አባ​ታ​ችን የሆ​ነው አብ​ር​ሃም ምን አገኘ እን​ላ​ለን? ይህን በሥ​ራው አግ​ኝ​ቶ​አ​ልን?</verse>
				<verse number="2">አብ​ር​ሃም በሥ​ራው ጸድ​ቆስ ቢሆን ትም​ክ​ሕት በሆ​ነው ነበር፤ ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="3">መጽ​ሐ​ፍስ ምን ይላል? አብ​ር​ሃም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አመነ፤ ጽድ​ቅም ሆኖ ተቈ​ጠ​ረ​ለት።</verse>
				<verse number="4">ለሚ​ሠራ ዋጋው እን​ደ​ሚ​ገ​ባው እንጂ በለ​ጋ​ስ​ነት እንደ ሰጡት ሆኖ አይ​ቈ​ጠ​ር​በ​ትም።</verse>
				<verse number="5">ለማ​ይ​ሠራ ግን ኀጢ​አ​ተ​ና​ውን በሚ​ያ​ጸ​ድ​ቀው ካመነ እም​ነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቈ​ጠ​ር​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="6">የኦ​ሪ​ትን ሥራ ሳይ​ፈ​ጽም ማመኑ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ጽድቅ ሆኖ የሚ​ቈ​ጠ​ር​ለ​ትን ሰው ዳዊት “ብፁዕ” በሚ​ል​በት አን​ቀጽ እን​ዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="7">“መተ​ላ​ለ​ፋ​ቸው የቀ​ረ​ላ​ቸው፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም የተ​ሰ​ረ​የ​ላ​ቸው ብፁ​ዓን ናቸው።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በደ​ሉን የማ​ይ​ቈ​ጥ​ር​በት ሰው ብፁዕ ነው።”</verse>
				<verse number="9">እን​ግ​ዲህ ይህ ብፅ​ዕና ስለ መገ​ዘር ተነ​ገ​ረን? ወይስ ስለ አለ​መ​ገ​ዘር? እም​ነቱ ለአ​ብ​ር​ሃም ጽድቅ ሆኖ ተቈ​ጠ​ረ​ለት እን​ላ​ለ​ንና።</verse>
				<verse number="10">ለአ​ብ​ር​ሃም ጽድቅ ሆኖ የተ​ቈ​ጠ​ረ​ለት መቼ ነው? ተገ​ዝሮ ሳለ ነውን? ወይስ ሳይ​ገ​ዘር? ሳይ​ገ​ዘር ነው እንጂ ተገ​ዝሮ ሳለ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="11">ሳይ​ገ​ዘር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ​ር​ሃ​ምን በእ​ም​ነት እንደ አጸ​ደ​ቀው በእ​ርሱ ላይ ይታ​ወቅ ዘንድ ግዝ​ረ​ትን የጽ​ድቅ ማኅ​ተም ትሆ​ነው ዘንድ ምል​ክት አድ​ርጎ ሰጠው። ሳይ​ገ​ዘሩ ለሚ​ያ​ምኑ ሁሉ አባት ሊሆን፥ አብ​ር​ሃም በእ​ም​ነት እንደ ከበረ እነ​ር​ሱም በእ​ም​ነት እን​ደ​ሚ​ከ​ብሩ ያውቁ ዘንድ ሰጠው።</verse>
				<verse number="12">ለተ​ገ​ዘ​ሩ​ትም አባት ይሆን ዘንድ ነው፤ ነገር ግን ለተ​ገ​ዘ​ሩት ብቻ አይ​ደ​ለም፤ እርሱ አባ​ታ​ችን አብ​ር​ሃም ሳይ​ገ​ዘር እንደ አመነ ሳይ​ገ​ዘሩ የአ​ባ​ታ​ችን የአ​ብ​ር​ሃ​ምን የሃ​ይ​ማ​ኖ​ቱን ፍለጋ ለሚ​ከ​ተሉ ደግሞ ነው እንጂ።</verse>
				<verse number="13">አብ​ር​ሃም፥ ዘሩም ዓለ​ምን ይወ​ርስ ዘንድ ተስፋ ያገኘ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት አይ​ደ​ለም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ እር​ሱ​ንም በማ​መን በእ​ው​ነ​ተና ሃይ​ማ​ኖቱ ይህን አገኘ እንጂ።</verse>
				<verse number="14">የኦ​ሪ​ትን ሕግ የፈ​ጸመ ብቻ ተስፋ የሚ​ያ​ገኝ፥ ዓለ​ም​ንም የሚ​ወ​ርስ ቢሆን ኖሮ፥ ለአ​ብ​ር​ሃም እም​ነቱ ባል​ጠ​ቀ​መ​ውም ነበር፤ ተስ​ፋ​ው​ንም ባላ​ገ​ኘም ነበር።</verse>
				<verse number="15">የኦ​ሪት ሕግ በአ​ፍ​ራሹ ላይ ቅጣ​ትን ያመ​ጣ​ልና፤ የኦ​ሪት ሕግም ከሌለ መተ​ላ​ለፍ የለም።</verse>
				<verse number="16">ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለዘሩ የሰ​ጠው ተስፋ የታ​መነ ይሆን ዘንድ፥ የሚ​ጸ​ድቁ በእ​ም​ነት እንጂ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ፈ​ጸም ብቻ እን​ዳ​ይ​ደለ ያውቁ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቅን በእ​ም​ነት አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="17">“ለብ​ዙ​ዎች አሕ​ዛብ አባት አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈ ሙታ​ንን በሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ቸው፥ የሌ​ሉ​ት​ንም እንደ አሉ በሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ቸው በአ​መ​ነ​በት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አብ​ር​ሃም የሁ​ላ​ችን አባት ነው።</verse>
				<verse number="18">አብ​ር​ሃም “ዘርህ እን​ዲሁ ይሆ​ናል” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተስፋ እንደ ሰጠው ተስፋ ባል​ነ​በረ ጊዜ የብ​ዙ​ዎች አሕ​ዛብ አባት እን​ደ​ሚ​ሆን አመነ።</verse>
				<verse number="19">አብ​ር​ሃም የመቶ ዓመት ሽማ​ግሌ ስለ​ሆነ እንደ ምውት የሆ​ነ​ውን የራ​ሱን ሥጋና የሣራ ማኅ​ፀን ምውት መሆ​ኑን እያየ በእ​ም​ነት አል​ተ​ጠ​ራ​ጠ​ረም።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያና​ገ​ረ​ለ​ት​ንም ተስፋ ይቀ​ራል ብሎ አል​ተ​ጠ​ራ​ጠ​ረም፤ በእ​ም​ነት ጸና እንጂ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብ​ርን ሰጠ።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሰ​ጠ​ውን ተስፋ ሊያ​ደ​ር​ግ​ለት እን​ደ​ሚ​ችል በፍ​ጹም ልቡ አመነ።</verse>
				<verse number="22">ስለ​ዚ​ህም ጽድቅ ሆኖ ተቈ​ጠ​ረ​ለት።</verse>
				<verse number="23">ነገር ግን “ጽድቅ ሆኖ ተቈ​ጠ​ረ​ለት” የሚ​ለው ቃል የተ​ጻፈ ስለ እርሱ ብቻ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="24">ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን የተ​ሰ​ቀ​ለ​ውን፥ ሊያ​ስ​ነ​ሣ​ንና ሊያ​ጸ​ድ​ቀን የተ​ነ​ሣ​ውን ጌታ​ች​ንን ኢየ​ሱ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ በአ​ስ​ነ​ሣው ስለ​ም​ና​ምን ስለ እናም ነው እንጂ።</verse>
				<verse number="25"></verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">እን​ግ​ዲህ በእ​ም​ነት ከጸ​ደ​ቅን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሰላ​ምን እና​ገ​ና​ለን።</verse>
				<verse number="2">በእ​ር​ሱም አማ​ካ​ኝ​ነት ወደ​ቆ​ም​ን​በት ወደ ጸጋው በእ​ም​ነት ተመ​ራን፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ተስፋ እን​መ​ካ​ለን።</verse>
				<verse number="3">የም​ን​መካ በእ​ር​ስዋ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በመ​ከ​ራ​ችን ደግሞ እን​መ​ካ​ለን እንጂ፤ መከራ በእና ላይ ትዕ​ግ​ሥ​ትን እን​ደ​ሚ​ያ​መጣ እና​ው​ቃ​ለ​ንና።</verse>
				<verse number="4">ትዕ​ግ​ሥ​ትም መከራ ነው፤ በመ​ከ​ራም ተስፋ ይገ​ናል።</verse>
				<verse number="5">ተስ​ፋም አያ​ሳ​ፍ​ርም፤ በሰ​ጠን በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍቅር በል​ባ​ችን መል​ቶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="6">ክር​ስ​ቶ​ስም እና ኀጢ​አ​ተ​ኞች ስን​ሆን ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ይሞት ዘንድ ዘመኑ ሲደ​ርስ መጣ።</verse>
				<verse number="7">ስለ ክፉ​ዎች በጭ​ንቅ ጊዜ ስንኳ ቢሆን ሊሞት የሚ​ደ​ፍር አይ​ገ​ኝም፤ ስለ ደጋጉ ግን ሊሞት የሚ​ጨ​ክን የሚ​ገኝ እን​ዳለ እንጃ።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን ያህል እንደ ወደ​ደን እነሆ፥ እዩ፤ እና ኀጢ​አ​ተ​ኞች ስን​ሆን ክር​ስ​ቶስ ስለ እና ሞተ።</verse>
				<verse number="9">እን​ግ​ዲህ በደሙ ዛሬ ከጸ​ደ​ቅን ከሚ​መ​ጣው መከራ በእ​ርሱ እን​ድ​ና​ለን።</verse>
				<verse number="10">እና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶቹ ስን​ሆን በልጁ ሞት ይቅር ካለን፥ ከታ​ረ​ቀን በኋ​ላም በልጁ ሕይ​ወት እን​ዴት የበ​ለጠ ያድ​ነን!</verse>
				<verse number="11">በዚህ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በእ​ርሱ ይቅ​ር​ታ​ውን ባገ​ኘ​ን​በት በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እን​መ​ካ​ለን እንጂ።</verse>
				<verse number="12">ስለ​ዚ​ህም በአ​ንድ ሰው በደል ምክ​ን​ያት ኀጢ​አት ወደ ዓለም ገባች፤ ስለ​ዚ​ችም ኀጢ​አት ሞት ገባ፤ እን​ደ​ዚ​ሁም ሁሉ ኀጢ​አ​ትን ስለ አደ​ረጉ በሰው ሁሉ ላይ ሞት መጣ።</verse>
				<verse number="13">ኦሪት እስከ መጣች ድረስ ኀጢ​አት ምን እንደ ሆነች ሳት​ታ​ወቅ በዓ​ለም ውስጥ ነበ​ረች፤ ነገር ግን የኦ​ሪት ሕግ ገና ስላ​ል​መጣ ኀጢ​አት ተብላ አት​ቈ​ጠ​ርም ነበር።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን በአ​ዳም ኀጢ​አት ምክ​ን​ያት ከአ​ዳም እስከ ሙሴ የበ​ደ​ሉ​ት​ንም ያል​በ​ደ​ሉ​ት​ንም ሞት ገዛ​ቸው፤ ሁሉ በአ​ዳም አም​ሳል ተፈ​ጥ​ሮ​አ​ልና፥ አዳ​ምም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእ​ርሱ አም​ሳሉ ነውና።</verse>
				<verse number="15">ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋው በበ​ደ​ላ​ችን መጠን የሆ​ነ​ብን አይ​ደ​ለም፤ በአ​ንድ ሰው በደል ብዙ​ዎች ከሞቱ፥ እን​ግ​ዲህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ፥ በአ​ንዱ ሰው በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ቤዛ​ነት በሰ​ጠን ሀብቱ ሕይ​ወት በብ​ዙ​ዎች ላይ እን​ዴት እጅግ ይበዛ ይሆን?</verse>
				<verse number="16">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋው በአ​ንዱ ሰው ኀጢ​አት መጠን የሆ​ነ​ብን አይ​ደ​ለም፤ የኀ​ጢ​አት ፍርድ ከአ​ንድ ሰው ወጥታ ሁሉ ከተ​ቀ​ጣ​ባት፥ ጸጋው ከበ​ደ​ላ​ችን እንደ ምን ያነ​ጻን ይሆን? የዘ​ለ​ዓ​ለ​ም​ንስ ሕይ​ወት እን​ዴት ይሰ​ጠን ይሆን?</verse>
				<verse number="17">የአ​ንዱ ሰው ኀጢ​አት ሞትን ካነ​ገ​ሠ​ችው በአ​ንድ ሰው በደ​ልም ሞት ከገ​ዛን፥ የአ​ንዱ ሰው የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የጸ​ጋው ብዛ​ትና የጽ​ድቁ ስጦታ እን​ዴት እጅግ ያጸ​ድ​ቀን ይሆን? የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ት​ንስ እን​ዴት ያበ​ዛ​ልን ይሆን?</verse>
				<verse number="18">እን​ግ​ዲህ በአ​ንዱ ሰው በደል ዓለም ሁሉ እንደ ተፈ​ረ​ደ​በት፥ እን​ዲሁ ደግሞ በአ​ንዱ ሰው ጽድቅ ሰው ሁሉ ይጸ​ድ​ቃል።</verse>
				<verse number="19">በአ​ንድ ሰው አለ​መ​ታ​ዘዝ ብዙ​ዎች ኀጢ​አ​ተ​ኞች እንደ ሆኑ፥ እን​ዲሁ ደግሞ በአ​ንድ ሰው መታ​ዘዝ ብዙ​ዎች ጻድ​ቃን ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="20">ኦሪ​ትስ ኀጢ​አ​ትን ታበ​ዛት ዘንድ መጣች፤ ኀጢ​አ​ትም ከበ​ዛች ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ በዛች።</verse>
				<verse number="21">ኀጢ​አ​ትም ሞትን እንደ አነ​ገ​ሠ​ችው እን​ዲሁ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ጽድ​ቅን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ታነ​ግ​ሠ​ዋ​ለች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ እን​ዲ​በዛ ኀጢ​አት እን​ሥ​ራን? አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="2">ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችን የተ​ለ​የን እኛ እን​ግ​ዲህ እን​ዴት ዳግ​መኛ በእ​ር​ስዋ ጸን​ተን መኖር እን​ች​ላ​ለን?</verse>
				<verse number="3">ነገር ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የተ​ጠ​መ​ቅን እኛ ሁላ​ችን በሞቱ እንደ ተጠ​መ​ቅን ሁላ​ችሁ ይህን ዕወቁ።</verse>
				<verse number="4">በሞ​ቱም እን​መ​ስ​ለው ዘንድ ከእ​ርሱ ጋር በጥ​ም​ቀት ተቀ​በ​ርን፤ እርሱ ክር​ስ​ቶስ በአ​ባቱ ጌት​ነት ከሙ​ታን እንደ ተነሣ እኛም እንደ እርሱ በሐ​ዲስ ሕይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን።</verse>
				<verse number="5">በሞቱ ከመ​ሰ​ል​ነ​ውም በት​ን​ሣ​ኤው እን​መ​ስ​ለ​ዋ​ለን።</verse>
				<verse number="6">ነገር ግን የኀ​ጢ​አ​ትን ሥጋ ይሽር ዘንድ ከእ​ርሱ ጋር የተ​ሰ​ቀ​ለው አሮ​ጌው ሰው​ነ​ታ​ችን እንደ ሆነ ይህን እና​ው​ቃ​ለን፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ዳግ​መና ለኀ​ጢ​አት እን​ገዛ ዘንድ አን​መ​ለ​ስም።</verse>
				<verse number="7">የሞ​ተስ ከኀ​ጢ​አት ነጻ ወጥ​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="8">ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋር ከሞ​ት​ንም ከእ​ርሱ ጋር በሕ​ይ​ወት እን​ደ​ም​ን​ኖር እና​ም​ና​ለን።</verse>
				<verse number="9">ክር​ስ​ቶስ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ እንደ ተነሣ፥ ዳግ​መ​ኛም እን​ደ​ማ​ይ​ሞት፥ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ሞት እን​ደ​ማ​ይ​ገ​ዛው እና​ው​ቃ​ለን።</verse>
				<verse number="10">የሞተ አንድ ጊዜ ሞተ፤ በሞ​ቱም ኀጢ​አ​ትን ሻራት፤ የተ​ነ​ሣም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተነሣ።</verse>
				<verse number="11">እን​ዲሁ እና​ን​ተም ራሳ​ች​ሁን ለኀ​ጢ​አት ምው​ታን አድ​ርጉ፤ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕያ​ዋን ሁኑ።</verse>
				<verse number="12">በዚህ በሚ​ሞት ሰው​ነ​ታ​ችሁ ኀጢ​አ​ትን አታ​ን​ግ​ሡ​አት፤ ለም​ኞ​ቱም እሽ አት​በ​ሉት።</verse>
				<verse number="13">ከሙ​ታን ተለ​ይቶ እንደ ተነሣ፥ ራሳ​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት አድ​ርጉ እንጂ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለኀ​ጢ​አት የዐ​መፅ የጦር መሣ​ሪያ አታ​ድ​ር​ጉት፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ድቅ የጦር መሣ​ሪያ አድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="14">እን​ግ​ዲህ ኀጢ​አት አት​ገ​ዛ​ች​ሁም፤ የኦ​ሪ​ትን ሕግ ከመ​ሥ​ራት ወጥ​ታ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ገብ​ታ​ች​ኋ​ልና።</verse>
				<verse number="15">እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? የኦ​ሪ​ትን ሕግ ከመ​ሥ​ራት ወጥ​ተን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ስለ ገባን ኀጢ​አት እን​ሥ​ራን? አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="16">ለም​ት​ታ​ዘ​ዙ​ለት፥ እሺ ለም​ት​ሉ​ትም እና​ንተ አገ​ል​ጋ​ዮች እንደ ሆና​ችሁ አታ​ው​ቁ​ምን? ለተ​ባ​በ​ራ​ች​ሁ​ለ​ትስ ራሳ​ች​ሁን እንደ አስ​ገ​ዛ​ችሁ አታ​ው​ቁ​ምን? ኀጢ​አ​ት​ንም እሺ ብት​ሉ​አት፥ ተባ​ብ​ራ​ች​ሁም ብት​በ​ድሉ እና​ንት ለሞት ተገ​ዢ​ዎች ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ ጽድ​ቅ​ንም እሺ ብት​ሉ​አት ለበጎ ሥራም ብት​ተ​ባ​በሩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች ናችሁ።</verse>
				<verse number="17">የኀ​ጢ​አት ተገ​ዦች ስት​ሆኑ ምሳ​ሌ​ነቱ ለተ​ሰ​ጣ​ችሁ ለም​ት​ማ​ሩት ትም​ህ​ርት ታዝ​ዛ​ች​ኋ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።</verse>
				<verse number="18">አሁን ግን ከኀ​ጢ​አት ነጻ ሁና​ችሁ ለጽ​ድቅ ተገ​ዝ​ታ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="19">ስለ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ድካም በሰው ልማድ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ዕወቁ፤ ቀድሞ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለኀ​ጢ​አ​ትና ለር​ኵ​ሰት፥ ለዐ​መ​ፃም እንደ አስ​ገ​ዛ​ችሁ፥ እን​ዲሁ አሁ​ንም ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለጽ​ድ​ቅና ለቅ​ድ​ስና አስ​ገዙ።</verse>
				<verse number="20">ለኀ​ጢ​አት ትገዙ በነ​በ​ረ​በት ጊዜ ከጽ​ድቅ ነፃ ነበ​ራ​ች​ሁና።</verse>
				<verse number="21">በዚ​ያን ጊዜ ሥራ​ች​ሁም እነሆ፥ ዛሬ ታፍ​ሩ​በ​ታ​ላ​ችሁ፤ መጨ​ረ​ሻው ሞት ነውና።</verse>
				<verse number="22">ዛሬ ግን ከኀ​ጢ​አት ነጻ ወጣ​ችሁ፤ ራሳ​ች​ሁ​ንም ለጽ​ድቅ አስ​ገ​ዛ​ችሁ፤ ለቅ​ድ​ስ​ናም ፍሬን አፈ​ራ​ችሁ፤ ፍጻ​ሜው ግን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ነው።</verse>
				<verse number="23">የኀ​ጢ​አት ትር​ፍዋ ሞት ነውና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን! ሕግን ለሚ​ያ​ስ​ተ​ውሉ እና​ገ​ራ​ለ​ሁና፤ ሰው በሕ​ይ​ወት ባለ​በት ሁሉ ሕግ እን​ዲ​ገ​ዛው አታ​ው​ቁ​ምን?</verse>
				<verse number="2">ባል ያላት ሴት ባልዋ በሕ​ይ​ወት ሳለ ከእ​ርሱ ጋር በሕግ የታ​ሰ​ረች ናት፤ ባልዋ የሞተ እንደ ሆነ ግን በሚ​ስ​ት​ነት ታስ​ራ​በት ከኖ​ረ​ችው ሕግ የተ​ፈ​ታች ናት።</verse>
				<verse number="3">ስለ​ዚህ ባልዋ በሕ​ይ​ወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብት​ሆን አመ​ን​ዝራ ትሆ​ና​ለች፤ ባልዋ ቢሞት ግን ከሕግ ነፃ ወጥ​ታ​ለች፤ ለሌላ ወንድ ብት​ሆ​ንም አመ​ን​ዝራ አት​ባ​ልም።</verse>
				<verse number="4">ወን​ድ​ሞች ሆይ! እና​ንተ እን​ዲሁ የክ​ር​ስ​ቶስ አካል ስለ ሆና​ችሁ ከኦ​ሪት ተለ​ይ​ታ​ች​ኋል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍሬ እን​ድ​ታ​ፈሩ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ ለተ​ነ​ሣው ለዳ​ግ​ማዊ አዳም ሆና​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="5">የሰ​ውን ሕግ በሠ​ራን ጊዜ ግን በኦ​ሪት ሕግ ደካ​ማ​ነት ቅጣቱ ጸና​ብን፤ ሞት​ንም አፈ​ራን።</verse>
				<verse number="6">አሁን ግን ታስ​ረ​ን​በት ከነ​በ​ረው ከኦ​ሪት ሕግ ነፃ ወጥ​ተ​ናል፤ ስለ​ዚህ በብ​ሉይ መጽ​ሐፍ ሳይ​ሆን በአ​ዲሱ መን​ፈ​ሳዊ ሕይ​ወት እን​ገ​ዛ​ለን።</verse>
				<verse number="7">እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? ኦሪት ኀጢ​አት ናትን? አይ​ደ​ለ​ችም፤ ነገር ግን ኦሪት ባት​ሠራ ኀጢ​አ​ትን ባላ​ወ​ቅ​ኋ​ትም ነበር፤ ኦሪት፥ “አት​መኝ” ባትል ኖሮም ምኞ​ትን ፈጽሞ ባላ​ወ​ቅ​ኋ​ትም ነበር።</verse>
				<verse number="8">ያችም ትእ​ዛዝ ለኀ​ጢ​አት ምክ​ን​ያት ሆነ​ቻት፤ ምኞ​ት​ንም ሁሉ አመ​ጣ​ች​ብኝ፤ ቀድሞ ግን ኦሪት ሳት​ሠራ ኀጢ​አት ሙት ነበ​ረች።</verse>
				<verse number="9">እኔም ቀድሞ ኦሪት ሳት​ሠራ ሕያው ነበ​ርሁ፤ የኦ​ሪት ትእ​ዛዝ በመ​ጣች ጊዜ ግን ኀጢ​አት ሕይ​ወ​ትን አገ​ኘች፤ እኔ ግን ሞትሁ።</verse>
				<verse number="10">ለሕ​ይ​ወት የተ​ሠ​ራ​ች​ልኝ ያቺ ሕግ ለሞት ሆና አገ​ኘ​ኋት።</verse>
				<verse number="11">ኀጢ​አት በዚ​ያች ትእ​ዛዝ ምክ​ን​ያት አሳ​ተ​ችኝ፤ በእ​ር​ሷም ገደ​ለ​ችኝ።</verse>
				<verse number="12">አሁ​ንም ቢሆን ኦሪ​ትስ ቅድ​ስት ናት፤ ትእ​ዛ​ዝ​ዋም ቅዱ​ስና እው​ነት ነው፤ መል​ካ​ምም ነው፤ በረ​ከ​ትም ነው።</verse>
				<verse number="13">እን​ግ​ዲህ ያ መል​ካም ነው ብዬ የማ​ስ​በው ነገር በውኑ አጥፊ ሆነኝ እላ​ለ​ሁን? አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ኀጢ​አት ኀጢ​አት እንደ ሆነች በታ​ወ​ቀች ጊዜ ሞትን አበ​ዛ​ች​ብኝ፤ ከዚ​ያም ትእ​ዛዝ የተ​ነሣ ኀጢ​አ​ተ​ናው እን​ዲ​ታ​ወቅ፥ ኀጢ​አ​ትም ተለ​ይታ እን​ድ​ት​ታ​ወቅ ኦሪት መል​ካ​ሙን ከክፉ ልት​ለይ ተሠ​ር​ታ​ለች።</verse>
				<verse number="14">የኦ​ሪት ሕግ መን​ፈ​ሳዊ እንደ ሆነ እና​ው​ቃ​ለን፤ እኔ ግን ለኀ​ጢ​አት የተ​ሸ​ጥሁ ሥጋዊ ነኝ።</verse>
				<verse number="15">የማ​ደ​ር​ገ​ውን አላ​ው​ቅ​ምና፤ የም​ወ​ደ​ው​ንም ያን ምንም አላ​ደ​ር​ገ​ው​ምና፤ ያንኑ የም​ጠ​ላ​ውን ብቻ እሠ​ራ​ለሁ እንጂ።</verse>
				<verse number="16">የማ​ል​ወ​ደ​ውን የም​ሠራ ከሆ​ንሁ ግን ያ የኦ​ሪት ሕግ መሠ​ራት ለበጎ እንደ ሆነ ምስ​ክሩ እኔ ነኝ።</verse>
				<verse number="17">እን​ግ​ዲ​ያስ በእኔ ላይ ያደ​ረች ኀጢ​አት ናት እንጂ፥ ያን የማ​ደ​ር​ገው እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም።</verse>
				<verse number="18">በእኔ ማለት በሥ​ጋዬ መል​ካም ነገር እን​ደ​ማ​ይ​ኖር አው​ቃ​ለሁ፤ መል​ካም ሥራ ለመ​ሥ​ራት መሻ​ቱስ በእኔ ዘንድ አለ፤ በጎ ምግ​ባር መሥ​ራት ግን የለ​ኝም።</verse>
				<verse number="19">ያን የም​ወ​ደ​ው​ንም በጎ ነገር የማ​ደ​ርግ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ያን የም​ጠ​ላ​ውን ክፉ​ውን አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">የማ​ል​ወ​ደ​ው​ንስ የም​ሠራ ከሆነ የም​ሠ​ራው እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ በእኔ ላይ ያደ​ረች ኀጢ​አት ናት እንጂ።</verse>
				<verse number="21">መል​ካም ሥራ እን​ድ​ሠራ የፈ​ቀ​ደ​ል​ኝን ያን ሕግ እርሱ ክፉ ነገር አም​ጥ​ቶ​ብኝ አገ​ኘ​ሁት።</verse>
				<verse number="22">በል​ቡ​ናዬ ውስጥ ያለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ መል​ካም ነው።</verse>
				<verse number="23">ነገር ግን በሰ​ው​ነቴ ውስጥ ያለ​ውን ሌላ የኀ​ጢ​አት ሕግ እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ፤ በል​ቡ​ና​ዬም ውስጥ ካለው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ጋር ተሰ​ል​ፈው ተዋጉ፤ በሰ​ው​ነቴ ውስጥ ያለው ያ የኀ​ጢ​አት ሕግም በረ​ታና ወደ እርሱ ማረ​ከኝ።</verse>
				<verse number="24">እኔ ምንና ወራዳ ሰው ነኝ፤ ከዚህ ሟች ሰው​ነቴ ማን ባዳ​ነኝ?</verse>
				<verse number="25">በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ እኔ በልቤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ እገ​ዛ​ለሁ፤ በሥ​ጋዬ ግን ለኀ​ጢ​አት ሕግ እገ​ዛ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">እን​ግ​ዲህ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ላሉት በመ​ን​ፈስ እንጂ በሥጋ ለማ​ይ​መ​ላ​ለሱ ፍርድ የለ​ባ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="2">በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የተ​ሰ​ጠን ሕይ​ወት የሚ​ገ​ኝ​በት የመ​ን​ፈስ ሕግ እርሱ ከኀ​ጢ​አ​ትና ከሞት ሕግ ነጻ አው​ጥ​ቶ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="3">ስለ ሥጋ ደካ​ማ​ነት የኦ​ሪት ሕግ ከሞት ማዳን በተ​ሳ​ነው ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኀ​ጢ​ኣ​ተና ሥጋ ምሳሌ ልጁን ላከ፤ ያች​ንም ኀጢ​አት በሥ​ጋው ቀጣት።</verse>
				<verse number="4">እናን ያጸ​ድ​ቀን ዘንድ፥ የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ ሠርቶ እንደ ፈጸመ ሰው ያደ​ር​ገን ዘንድ፤ ይህም በመ​ን​ፈ​ሳዊ ሕግ ጸን​ተው ለሚ​ኖሩ ነው እንጂ በሥጋ ሕግ ለሚ​ሠሩ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="5">እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚ​ኖሩ የሥ​ጋን ነገር ያስ​ባ​ሉና፤ እንደ መን​ፈስ ፈቃድ የሚ​ኖሩ ግን የመ​ን​ፈ​ስን ነገር ያስ​ባሉ።</verse>
				<verse number="6">የሥጋ ዐሳብ ሞትን ያመ​ጣ​ብ​ናል፤ የመ​ን​ፈስ ዐሳብ ግን ሰላ​ም​ንና ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጠ​ናል።</verse>
				<verse number="7">የሥጋ ዐሳብ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላቱ ነውና፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ ስለ​ማ​ይ​ገዛ፥ መፈ​ጸም አይ​ቻ​ለ​ውም።</verse>
				<verse number="8">ለሥ​ጋዊ ፈቃ​ዳ​ቸው የሚ​ሠሩ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ ማሰ​ኘት አይ​ች​ሉም።</verse>
				<verse number="9">እና​ንተ ግን ለመ​ን​ፈ​ሳዊ ሕግ እንጂ ለሥ​ጋ​ችሁ ፈቃድ የም​ት​ሠሩ አይ​ደ​ላ​ች​ሁም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በእ​ና​ንተ አድሮ ይኖ​ራ​ልና፤ የክ​ር​ስ​ቶስ መን​ፈስ ያላ​ደ​ረ​በት ግን እርሱ የእ​ርሱ ወገን አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="10">ክር​ስ​ቶስ ካደ​ረ​ባ​ችሁ ግን ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ከኀ​ጢ​አት ሥራ ለዩ፤ መን​ፈ​ሳ​ች​ሁ​ንም ለጽ​ድቅ ሥራ ሕያው አድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="11">ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ካደ​ረ​ባ​ችሁ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣው እርሱ አድ​ሮ​ባ​ችሁ ባለ መን​ፈሱ ለሟች ሰው​ነ​ታ​ችሁ ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ታል።</verse>
				<verse number="12">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ አሁ​ንም በሥ​ጋ​ችን ሳለን በሥጋ ፈቃድ እን​ኖር ዘንድ አይ​ገ​ባም።</verse>
				<verse number="13">እንደ ሥጋ ፈቃድ ብት​ኖሩ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን በመ​ን​ፈ​ሳዊ ሥራ የሥ​ጋ​ች​ሁን ፈቃድ ብት​ገ​ድሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="14">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ የሚ​ሠሩ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ናቸው።</verse>
				<verse number="15">ዳግ​መ​ናም አባ አባት ብለን የም​ን​ጮ​ህ​በ​ትን የል​ጅ​ነት መን​ፈስ ተቀ​በ​ላ​ችሁ እንጂ እንደ ገና ለፍ​ር​ሀት የባ​ር​ነት መን​ፈ​ስን አል​ተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁ​ምና።</verse>
				<verse number="16">እና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች እን​ደ​ሆን ለል​ቡ​ና​ችን ምስ​ክሩ እርሱ መን​ፈስ ቅዱስ ነው።</verse>
				<verse number="17">እና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ከሆን ወራ​ሾቹ ነን፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወራ​ሾች ከሆ​ንም የክ​ር​ስ​ቶስ ወራ​ሾቹ ነን፤ በመ​ከራ ከመ​ሰ​ል​ነ​ውም በክ​ብር እን​መ​ስ​ለ​ዋ​ለን።</verse>
				<verse number="18">ነገር ግን የዚህ ዓለም መከራ ለእና ሊገ​ለጥ ከአ​ለው ክብር ጋር እን​ደ​ማ​ይ​ተ​ካ​ከል ዐስቡ።</verse>
				<verse number="19">የዓ​ለም ተስ​ፋው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ መም​ጣት ይጠ​ባ​በቅ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="20">ዓለም ባለ​ማ​ወቅ ለከ​ንቱ ነገር ተገ​ዝ​ቶ​አ​ልና በተ​ስፋ ስለ አስ​ገ​ዛው ነው እንጂ በፈ​ቃዱ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="21">ነገር ግን አስቶ በባ​ር​ነት ከሚ​ገ​ዛው ከዚህ ወጥቶ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ወደ አገ​ኙ​አት የነ​ጻ​ነት ክብር ይገባ ዘንድ ተስፋ አለው።</verse>
				<verse number="22">እስ​ካ​ሁን ዓለም ሁሉ ያዘ​ነና የተ​ከዘ እንደ ሆነ እና​ው​ቃ​ለን።</verse>
				<verse number="23">ነገር ግን የሚ​ተ​ክዝ ዓለም ብቻ አይ​ደ​ለም፤ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ፈለማ የተ​ቀ​በ​ል​ነው እናም ደግሞ እና​ዝ​ና​ለን እንጂ፤ የነ​ፍ​ሳ​ች​ንን ድኅ​ነት እና​ገኝ ዘንድ የል​ጅ​ነ​ትን ክብር ተስፋ እና​ደ​ር​ጋ​ለ​ንና፤ በእ​ም​ነ​ትም ድነ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="24">የሚ​ታ​የ​ውን ተስፋ ማድ​ረግ ተስፋ አይ​ደ​ለም፤ የሚ​ያ​የ​ው​ንማ እን​ዴት ተስፋ ያደ​ር​ጋል? እን​ዴ​ትስ ይጠ​ብ​ቃል?</verse>
				<verse number="25">የማ​ይ​ታ​የ​ውን ተስፋ ብና​ደ​ርግ ግን እር​ሱን ተስፋ አድ​ር​ገን በእ​ርሱ እንደ ጸናን መጠን ትዕ​ግ​ሥ​ታ​ችን ይታ​ወ​ቃል።</verse>
				<verse number="26">መን​ፈስ ቅዱ​ስም ከድ​ካ​ማ​ችን ይረ​ዳ​ናል፤ እን​ግ​ዲ​ያስ ተስ​ፋ​ች​ንን ካላ​ወ​ቅን ጸሎ​ታ​ችን ምን​ድ​ነው? ነገር ግን እርሱ ራሱ መን​ፈስ ቅዱስ ስለ መከ​ራ​ች​ንና ስለ ችግ​ራ​ችን ይፈ​ር​ድ​ል​ናል።</verse>
				<verse number="27">እር​ሱም ልባ​ች​ንን ይመ​ረ​ም​ራል፤ ልብ የሚ​ያ​ስ​በ​ው​ንም እርሱ ያው​ቃል፤ ስለ ቅዱ​ሳ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይፈ​ር​ዳል።</verse>
				<verse number="28">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ወ​ዱ​ትን ምር​ጦ​ቹን በበጎ ምግ​ባር ሁሉ እን​ደ​ሚ​ረ​ዳ​ቸው እና​ው​ቃ​ለን።</verse>
				<verse number="29">ልጁ በብ​ዙ​ዎች ወን​ድ​ሞች መካ​ከል በኵር ይሆን ዘንድ አስ​ቀ​ድሞ ያወ​ቃ​ቸ​ው​ንና የመ​ረ​ጣ​ቸ​ውን እነ​ር​ሱን ልጁን ይመ​ስሉ ዘንድ አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="30">ያዘ​ጋ​ጃ​ቸ​ውን እነ​ር​ሱን ጠራ፤ የጠ​ራ​ቸ​ው​ንም እነ​ር​ሱን አጸ​ደቀ፤ የአ​ጸ​ደ​ቃ​ቸ​ው​ንም እነ​ር​ሱን አከ​በረ።</verse>
				<verse number="31">እን​ግ​ዲህ ስለ​ዚህ ምን እን​ላ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእና ጋር ከሆነ ማን ይች​ለ​ናል?</verse>
				<verse number="32">ለልጁ ስንኳ አል​ራ​ራም፤ ስለ ሁላ​ችን ቤዛ አድ​ርጎ አሳ​ልፎ ሰጠው እንጂ፥ እን​ግ​ዲህ እርሱ ሁሉን እን​ዴት አይ​ሰ​ጠ​ንም?</verse>
				<verse number="33">እን​ግ​ዲህ እርሱ ራሱ ካጸ​ደቀ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ረ​ጣ​ቸ​ውን ሰዎች የሚ​ቃ​ወ​ማ​ቸው ማነው?</verse>
				<verse number="34">የሚ​ፈ​ር​ድስ ማነው? የሞ​ተው፥ ይል​ቁ​ንም ከሙ​ታን ተለ​ይቶ የተ​ነ​ሣው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀኝ የተ​ቀ​መ​ጠው፥ ደግሞ ስለ እና የሚ​ፈ​ር​ደው ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነው።</verse>
				<verse number="35">ከክ​ር​ስ​ቶስ ፍቅር ማን ይለ​የ​ናል? መከራ ነውን? ኀዘን ነውን? ስደት ነውን? ራብ ነውን? መራ​ቆት ነውን? ጭን​ቀት ነውን? ሾተል ነውን?</verse>
				<verse number="36">መጽ​ሐፍ እን​ዳለ፥ “ስለ አንተ ዘወ​ትር ይገ​ድ​ሉ​ናል፤ እን​ደ​ሚ​ታ​ረዱ በጎ​ችም ሆነ​ናል።”</verse>
				<verse number="37">ነገር ግን በወ​ደ​ደን በእ​ርሱ ሁሉን ድል እን​ነ​ሣ​ለን።</verse>
				<verse number="38">ነገር ግን ሞትም ቢሆን፥ ሕይ​ወ​ትም ቢሆን፥ መላ​እ​ክ​ትም ቢሆኑ፥ አለ​ቆ​ችም ቢሆኑ፥ ያለ​ውም ቢሆን፥ የሚ​መ​ጣ​ውም ቢሆን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ካለ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍቅር ሊለ​የን እን​ደ​ማ​ይ​ችል አም​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="39">ኀይ​ልም ቢሆን፥ ከፍ​ታም ቢሆን፥ ዝቅ​ታም ቢሆን፥ ሌላ ፍጥ​ረ​ትም ቢሆን ከክ​ር​ስ​ቶስ ፍቅር ሊለ​የን የሚ​ችል የለም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">በክ​ር​ስ​ቶስ እው​ነት እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሐሰ​ትም አል​ና​ገ​ርም። ሕሊ​ና​ዬም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ይመ​ሰ​ክ​ር​ል​ናል፤</verse>
				<verse number="2">በጊ​ዜው ሁሉ ብዙ ኀዘን፥ የማ​ያ​ቋ​ር​ጥም ጭን​ቀት በልቤ አለ።</verse>
				<verse number="3">በሥጋ ዘመ​ዶ​ችና ወን​ድ​ሞች ስለ​ሚ​ሆኑ እኔ ከክ​ር​ስ​ቶስ እለይ ዘንድ እጸ​ል​ያ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">እና​ህም ልጅ​ነት፥ ክብር፥ ኪዳን፥ ሕግና አም​ልኮ ያላ​ቸው፥ ተስ​ፋም የተ​ሰ​ጣ​ቸው እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ናቸው።</verse>
				<verse number="5">እነ​ር​ሱም አባ​ቶ​ቻ​ችን ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ክር​ስ​ቶስ በሥጋ ተወ​ለደ፤ እር​ሱም ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቡሩክ አም​ላክ ነው፤ አሜን።</verse>
				<verse number="6">ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል አይ​ታ​በ​ልም፤ እስ​ራ​ኤል ሁሉ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን አይ​ደ​ሉ​ምና።</verse>
				<verse number="7">የአ​ብ​ር​ሃም ዘር ሁሉ ልጆቹ የሆ​ኑት አይ​ደ​ለም፤ ከይ​ስ​ሐቅ ዘር ይጠ​ራ​ል​ሃል አለው እንጂ።</verse>
				<verse number="8">ልጆች እን​ዲ​ሆ​ኑት ተስፋ ያና​ገ​ረ​ለት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ናቸው፤ እነ​ዚህ ከሥጋ የተ​ወ​ለዱ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች አይ​ደ​ሉም።</verse>
				<verse number="9">“ከርሞ እንደ ዛሬ ወደ አንተ እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ ሣራም ወንድ ልጅ ታገ​ና​ለች፤” ብሎ ተስፋ ሰጥ​ቶ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="10">ነገር ግን ለእ​ር​ስዋ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ርብ​ቃም ለአ​ባ​ታ​ችን ለይ​ስ​ሐቅ መንታ በፀ​ነ​ሰች ጊዜ፥</verse>
				<verse number="11">ሳይ​ወ​ለዱ፥ ክፉና መል​ካም ሥራም ሳይ​ሠሩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መም​ረጡ በምን እንደ ሆነ ይታ​ወቅ ዘንድ፥</verse>
				<verse number="12">እርሱ የጠ​ራው ነው እንጂ ሰው በሥ​ራው የሚ​መ​ረጥ አን​ዳ​ይ​ደ​ለም ያውቁ ዘንድ፥ ለር​ብቃ፥ “ታላቁ ለታ​ናሹ ይገ​ዛል” አላት።</verse>
				<verse number="13">“ያዕ​ቆ​ብን ወደ​ድሁ፤ ዔሳ​ውን ግን ጠላሁ” ተብሎ እን​ዲሁ ተጽ​ፎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="14">እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ላ​ልን? አያ​ደ​ላም።</verse>
				<verse number="15">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ አለው፥ “የም​ም​ረ​ውን እም​ረ​ዋ​ለሁ፤ ይቅር የም​ለ​ው​ንም ይቅር እለ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="16">አሁ​ንም ለሮ​ጠና ለቀ​ደመ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ላለው ነው እንጂ።</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለፈ​ር​ዖን በመ​ጽ​ሐፍ እን​ዲህ አለው፥ “ኀይ​ሌን በአ​ንተ ላይ እገ​ልጥ ዘንድ፥ ስሜም በም​ድር ሁሉ ይሰማ ዘንድ ስለ​ዚህ አስ​ነ​ሣ​ሁህ።”</verse>
				<verse number="18">እነሆ፥ የሚ​ወ​ድ​ደ​ውን ይም​ረ​ዋል፤ የሚ​ወ​ድ​ደ​ው​ንም ልቡን ያጸ​ና​ዋል።</verse>
				<verse number="19">እን​ግ​ዲህ ምን ትላ​ለህ? አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትነ​ቅ​ፈ​ዋ​ለ​ህን? ምክ​ሩ​ንስ የሚ​ቃ​ወ​ማት አለን?።</verse>
				<verse number="20">ሰው ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ከ​ራ​ከ​ረው አንተ ምን​ድን ነህ? ሥራ ሠሪ​ውን እን​ዲህ አታ​ድ​ር​ገኝ ሊለው ይች​ላ​ልን?</verse>
				<verse number="21">ሸክላ ሠሪ ከአ​ንድ ጭቃ ግማ​ሹን ለክ​ብር፥ ግማ​ሹ​ንም ለኀ​ሳር አድ​ርጎ ዕቃን ሊሠራ አይ​ች​ል​ምን?</verse>
				<verse number="22">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይ​ሉን የሚ​ገ​ል​ጽ​በ​ትን ቅጣ​ቱን ሊያ​ሳይ ቢወድ፥ ትዕ​ግ​ሥ​ቱን ካሳየ በኋላ ለማ​ጥ​ፋት የተ​ዘ​ጋ​ጁ​ትን ቍጣ​ውን የሚ​ገ​ል​ጽ​ባ​ቸ​ውን መላ​እ​ክት ያመ​ጣል።</verse>
				<verse number="23">ዳግ​መ​ናም የክ​ብ​ሩን ባለ​ጠ​ግ​ነት ሊያ​ሳይ ቢወድ አስ​ቀ​ድሞ ለወ​ደ​ዳ​ቸ​ውና ለጠ​ራ​ቸው ለይ​ቅ​ርታ የተ​ዘ​ጋጁ የም​ሕ​ረት መላ​እ​ክ​ትን ያመ​ጣል።</verse>
				<verse number="24">ወደ ክብሩ የጠ​ራ​ንና የሰ​በ​ሰ​በ​ንም እና ነን፤ ነገር ግን ከአ​ሕ​ዛ​ብም ነው እንጂ ከአ​ይ​ሁድ ብቻ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="25">ነቢዩ ሆሴዕ እን​ዲህ እን​ዳለ “ወገኔ ያል​ነ​በ​ረ​ውን ወገኔ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ወዳጄ ያል​ነ​በ​ረ​ች​ው​ንም ወዳጄ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="26">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወገ​ኖች አይ​ደ​ላ​ች​ሁም ይባሉ በነ​በ​ሩ​በት ሀገ​ርም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ይሆ​ናሉ።”</verse>
				<verse number="27">ኢሳ​ይ​ያ​ስም ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ ስለ እስ​ራ​ኤል እን​ዲህ አለ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ቍጥ​ራ​ቸው እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆ​ንም የተ​ረ​ፉት ይድ​ናሉ።</verse>
				<verse number="28">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ለም ውስጥ ያደ​ር​ገው ዘንድ ያለ​ውን ያለ​ቀና የተ​ቈ​ረጠ ነገ​ርን ይና​ገ​ራ​ልና።”</verse>
				<verse number="29">ኢሳ​ይ​ያ​ስም አስ​ቀ​ድሞ እንደ ተና​ገረ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸባ​ኦት ዘር ያስ​ቀ​ረ​ልን ባይ​ሆን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆን፥ ገሞ​ራ​ንም በመ​ሰ​ልን ነበር።”</verse>
				<verse number="30">እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? ጽድ​ቅን ያል​ፈ​ለ​ጉ​አት አሕ​ዛብ ስንኳ ጽድ​ቅን አገ​ኙ​አት፤ በእ​ም​ነ​ትም ጸደቁ።</verse>
				<verse number="31">እስ​ራ​ኤል ግን ኦሪ​ትን ሲከ​ተሉ መጽ​ደቅ ተሳ​ና​ቸው፤ የኦ​ሪ​ታ​ቸ​ውን ሥራ አል​ፈ​ጸ​ሙ​ምና።</verse>
				<verse number="32">ይህስ ስለ​ምን ነው? ጽድ​ቃ​ቸው የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት እንጂ በእ​ም​ነት ስለ አል​ሆነ ነው፤ የእ​ን​ቅ​ፋት ድን​ጋይ አሰ​ነ​ካ​ከ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="33">መጽ​ሐፍ እን​ዲሁ “በጽ​ዮን የእ​ን​ቅ​ፋት ድን​ጋ​ይ​ንና የማ​ሰ​ና​ከያ ዐለ​ትን አኖ​ራ​ለሁ፤ ያመ​ነ​ባ​ትም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አያ​ፍ​ርም” ብሎ​አ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">ወን​ድ​ሞች፥ የእ​ኔስ የልቤ ምኞት፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የማ​ቀ​ር​በው ጸሎ​ትም እስ​ራ​ኤል እን​ዲ​ድኑ ነው።</verse>
				<verse number="2">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲ​ቀኑ ምስ​ክ​ራ​ቸው እኔ ነኝና፤ ነገር ግን ዐው​ቀው አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="3">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጽድቅ አያ​ው​ቁ​አ​ት​ምና በራ​ሳ​ቸ​ውም ጽድቅ ጸን​ተው ሊኖሩ ወደዱ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድቅ ግን መገ​ዛት ተሳ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="4">የኦ​ሪት ጽድቅ ፍጻ​ሜስ ለሚ​ያ​ም​ኑ​በት ሁሉ በክ​ር​ስ​ቶስ ማመን ነው።</verse>
				<verse number="5">ሙሴም “የኦ​ሪ​ትን ጽድቅ መሥ​ራ​ትን የፈ​ጸመ ሁሉ በእ​ርሱ ይጸ​ድ​ቅ​በ​ታል” አለ።</verse>
				<verse number="6">የእ​ም​ነት ጽድቅ ግን እን​ዲህ ይላል፥ “በል​ብህ ወደ ሰማይ ማን ይወ​ጣል?” አት​በል፤ ከሰ​ማይ የወ​ረ​ደው ክር​ስ​ቶስ ነው።</verse>
				<verse number="7">“ወደ ጥል​ቁም ማን ይወ​ር​ዳል?” አት​በል፤ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ የተ​ነ​ሣው ክር​ስ​ቶስ ነው።</verse>
				<verse number="8">መጽ​ሐፍ እን​ዲሁ፥ “ቃል ለል​ብ​ህም ለአ​ፍ​ህም ቀር​ቦ​ል​ሃል ይል የለ​ምን?” ይህም የም​ን​ሰ​ብ​ከው የእ​ም​ነት ቃል ነው።</verse>
				<verse number="9">ኢየ​ሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአ​ፍህ ብት​መ​ሰ​ክር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሙ​ታን ለይቶ እንደ አስ​ነ​ሣው በል​ብህ ብታ​ምን ትድ​ና​ለህ።</verse>
				<verse number="10">በልቡ የሚ​ያ​ምን ይጸ​ድ​ቃ​ልና፤ በአ​ፉም የሚ​መ​ሰ​ክር ይድ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="11">መጽ​ሐፍ፥ “የሚ​ያ​ም​ን​በት ሁሉ አያ​ፍ​ርም” ብሎ​አል።</verse>
				<verse number="12">አይ​ሁ​ዳ​ዊ​ንና አረ​ማ​ዊን አል​ለ​የም፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባለ​ጸጋ ስለ​ሆነ ለለ​መ​ነው ሁሉ ይበ​ቃ​ልና።</verse>
				<verse number="13">“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም የሚ​ጠራ ሁሉ ይድ​ናል።”</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን ያላ​መ​ኑ​በ​ትን እን​ዴት ይጠ​ሩ​ታል? ባል​ሰ​ሙ​ትስ እን​ዴት ያም​ናሉ? ያለ ሰባ​ኪስ እን​ዴት ይሰ​ማሉ?</verse>
				<verse number="15">“መል​ካ​ሙን የም​ሥ​ራች የሚ​ያ​ወሩ እግ​ሮ​ቻ​ቸው እን​ዴት ያማሩ ናቸው?” ተብሎ እንደ ተጻፈ ካል​ተ​ላኩ እን​ዴት ይሰ​ብ​ካሉ?</verse>
				<verse number="16">ነገር ግን ሁሉም የወ​ን​ጌ​ልን ትም​ህ​ርት የሰሙ አይ​ደ​ለም፤ ኢሳ​ይ​ያ​ስም፥ “አቤቱ፥ ምስ​ክ​ር​ነ​ታ​ች​ን​ንስ ማን አመነ? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ክንዱ ለማን ተገ​ለጠ?” ብሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="17">ማመን ከመ​ስ​ማት ነው፤ መስ​ማ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ነው።</verse>
				<verse number="18">ነገር ግን እን​ዲህ እላ​ለሁ፤ በውኑ እስ​ራ​ኤል ብቻ አል​ሰ​ሙ​ምን? መጽ​ሐፍ “ነገ​ራ​ቸው በም​ድር ሁሉ ተሰማ፤ ቃላ​ቸ​ውም እስከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ” ብሎ የለ​ምን?</verse>
				<verse number="19">እስ​ራ​ኤል ብቻ አል​ሰ​ሙ​ምን? ሙሴስ አስ​ቀ​ድሞ እን​ዲህ ብሎ​አ​ቸው የለ​ምን? “እኔ በማ​ያ​ስ​ተ​ውሉ ወገ​ኖች አስ​ቀ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወገን ባል​ሆ​ነ​ውም አስ​ቈ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="20">ኢሳ​ይ​ያ​ስም ደፍሮ፥ “ለአ​ል​ፈ​ለ​ጉኝ ተገ​ኘሁ፤ ለአ​ል​ጠ​የ​ቁ​ኝም ተገ​ለ​ጥ​ሁ​ላ​ቸው” ብሏል።</verse>
				<verse number="21">ለእ​ስ​ራ​ኤል ግን “ሁል​ጊዜ ከዳ​ተ​ኞ​ችና ወን​ጀ​ለ​ኞች ወደ​ሆ​ኑት ሕዝብ እጄን ዘረ​ጋሁ” ብሎ​አል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">እን​ግ​ዲህ እላ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ጣላ​ቸ​ውን? አይ​ደ​ለም፤ እኔ ደግሞ ከአ​ብ​ር​ሃም ዘር ከብ​ን​ያም ወገን የሆ​ንሁ እስ​ራ​ኤ​ላዊ ነኝ።</verse>
				<verse number="2">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ ያወ​ቃ​ቸ​ውን ሕዝ​ቡን አል​ጣ​ላ​ቸ​ውም፤ ኤል​ያስ እስ​ራ​ኤ​ልን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል በከ​ሰ​ሳ​ቸው ጊዜ መጽ​ሐፍ ያለ​ውን አታ​ው​ቁ​ምን?</verse>
				<verse number="3">“አቤቱ፥ ነቢ​ያ​ት​ህን ገደሉ፤ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ች​ህ​ንም አፈ​ረሱ፤ እኔም ብቻ​ዬን ቀረሁ፤ ነፍ​ሴ​ንም ይሿ​ታል።”</verse>
				<verse number="4">የተ​ገ​ለ​ጠ​ለ​ትስ ምን አለው? “ለጣ​ዖት ያል​ሰ​ገዱ ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስ​ቀ​ር​ቻ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="5">እን​ዲ​ሁም ዛሬ በዚህ ዘመን በጸጋ የተ​መ​ረ​ጡና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያመኑ ቅሬ​ታ​ዎች አሉ።</verse>
				<verse number="6">በጸጋ ከጸ​ደቁ ግን በሥ​ራ​ቸው አይ​ደ​ለማ፤ በሥ​ራም የሚ​ጸ​ድቁ ከሆነ ጸጋ ጸጋ አይ​ባ​ልም።</verse>
				<verse number="7">እን​ግ​ዲህ ምን​ድን ነው? እስ​ራ​ኤል የፈ​ለ​ገ​ውን አላ​ገ​ኘም። የተ​መ​ረ​ጠው ግን አግ​ኝ​ቶ​አል፤ የቀ​ሩ​ትም ታወሩ።</verse>
				<verse number="8">መጽ​ሐፍ እን​ዳለ፥ “እስከ ዛሬ ድረስ በዐ​ይ​ና​ቸው እን​ዳ​ያዩ በጆ​ሮ​አ​ቸ​ውም እን​ዳ​ይ​ሰሙ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደን​ዛዛ አእ​ም​ሮን ሰጣ​ቸው።”</verse>
				<verse number="9">ዳዊ​ትም እን​ዲህ ብሎ​አል፥ “ማዕ​ዳ​ቸው በፊ​ታ​ቸው ወጥ​መ​ድና አሽ​ክላ፥ መሰ​ና​ከ​ያና ፍዳም ትሁ​ን​ባ​ቸው።</verse>
				<verse number="10">እን​ዳ​ያዩ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው ይጨ​ልሙ፤ ዘወ​ት​ርም ጀር​ባ​ቸው ይጕ​በጥ።”</verse>
				<verse number="11">እን​ግ​ዲህ እላ​ለሁ፤ ሊወ​ድቁ ተሰ​ና​ከ​ሉን? አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን እስ​ራ​ኤል ይቀኑ ዘንድ እነ​ርሱ በመ​ሰ​ና​ከ​ላ​ቸው ለአ​ሕ​ዛብ ድኅ​ነት ሆነ።</verse>
				<verse number="12">የእ​ነ​ርሱ መሰ​ና​ከል ለዓ​ለም ባለ​ጸ​ግ​ነት፥ በደ​ላ​ቸ​ውም ለአ​ሕ​ዛብ ባለ​ጸ​ግ​ነት ከሆነ ፍጹ​ም​ነ​ታ​ቸ​ውማ እን​ዴት በሆነ ነበር?</verse>
				<verse number="13">ለእ​ና​ንተ ለአ​ሕ​ዛብ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ እኔ ለአ​ሕ​ዛብ ሐዋ​ር​ያ​ቸው እንደ መሆኔ መጠን መል​እ​ክ​ቴን አከ​ብ​ራ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">ይህም በዚህ ዘመ​ዶ​ችን አስ​ቀ​ና​ቸው እንደ ሆነ፥ ከእ​ነ​ርሱ ወገን የሆ​ኑ​ት​ንም አድን እንደ ሆነ ነው።</verse>
				<verse number="15">የእ​ነ​ርሱ መው​ጣት ለዓ​ለም ዕርቅ ከሆነ ይል​ቁ​ንም መመ​ለ​ሳ​ቸው ምን ይሆን? ከሙ​ታን በመ​ነ​ሣት የሚ​ገኝ ሕይ​ወት ነው።</verse>
				<verse number="16">እር​ሾው ቅዱስ ከሆነ ቡሆ​ውም እን​ዲሁ ቅዱስ ነው፤ ሥርዋ ቅዱስ ከሆ​ነም ቅር​ን​ጫ​ፎ​ችዋ እን​ዲሁ ቅዱ​ሳን ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="17">ከቅ​ር​ን​ጫ​ፎ​ችዋ አን​ዳ​ን​ዶቹ ቢሰ​በሩ የዱር ወይራ የሆ​ንህ አን​ተን በእ​ነ​ርሱ ፋንታ ተከሉ፤ የእ​ነ​ር​ሱ​ንም ሥር​ነት አገ​ኘህ፤ እንደ እነ​ር​ሱም ዘይት ሆንኽ።</verse>
				<verse number="18">በቅ​ር​ን​ጫ​ፎች ላይ አት​ኵራ፤ ብት​ኰራ ግን ሥሩ አን​ተን ይሸ​ከ​ም​ሃል እንጂ አንተ ሥሩን የም​ት​ሸ​ከ​መው አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="19">ቅር​ን​ጫ​ፎ​ችዋ ተሰ​በሩ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ፋንታ “እኔ የዘ​ይት ቅር​ን​ጫፍ ሆንሁ” ትል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="20">አላ​መ​ኑ​ምና ተሰ​በሩ፤ አንተ ግን ስለ አመ​ንህ ቆመ​ሃል፤ እን​ግ​ዲህ ፈር​ተህ ኑር እንጂ ራስ​ህን ከፍ ከፍ አታ​ድ​ርግ።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ፈ​ጥ​ሮ​አ​ቸው ቅር​ን​ጫ​ፎች ለነ​በሩ ለእ​ነ​ዚያ ከአ​ል​ራ​ራ​ላ​ቸው ለአ​ን​ተም አይ​ራ​ራ​ል​ህም፤</verse>
				<verse number="22">እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ርኅ​ራ​ኄ​ው​ንና ጭካ​ኔ​ውን አስ​ተ​ውል፤ የወ​ደ​ቁ​ትን ቀጣ​ቸው፤ አን​ተን ግን ይቅር እን​ዳ​ለህ ብት​ኖር ማረህ፤ ያለ​ዚያ ግን አን​ተም ትቈ​ረ​ጣ​ለህ።</verse>
				<verse number="23">እነ​ር​ሱም ባለ​ማ​መ​ና​ቸው ጸን​ተው ባይ​ኖሩ ይተ​ከ​ላሉ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዳግ​መና ሊተ​ክ​ላ​ቸው ይች​ላ​ልና።</verse>
				<verse number="24">አንተ የዱር ወይራ፥ አን​ተን ስንኳ ከበ​ቀ​ል​ህ​በት ቈርጦ ባል​በ​ቀ​ል​ህ​በት በመ​ል​ካሙ ዘይት ስፍራ ከተ​ከ​ለህ፥ ይል​ቁን ጥን​ቱን ዘይት የነ​በ​ሩ​ትን እነ​ዚ​ያን በበ​ቀ​ሉ​በት ስፍራ እን​ዴት አብ​ልጦ ሊተ​ክ​ላ​ቸው አይ​ች​ልም?</verse>
				<verse number="25">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ እና ዐዋ​ቂ​ዎች ነን እን​ዳ​ትሉ ይህን ምሥ​ጢር ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ፦ አሕ​ዛብ ሁሉ እስ​ኪ​ገቡ ድረስ ከእ​ስ​ራ​ኤል እኩ​ሌ​ቶ​ችን የልብ ድን​ቍ​ርና አግ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="26">ከዚህ በኋ​ላም መላው እስ​ራ​ኤል ይድ​ናሉ፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ እን​ዳለ፥ “አዳኝ ከጽ​ዮን ይወ​ጣል፤ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ኀጢ​አ​ትን ያስ​ወ​ግ​ዳል።</verse>
				<verse number="27">ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ባራ​ቅ​ሁ​ላ​ቸው ጊዜ ከእ​ነ​ርሱ ጋር የም​ገ​ባው ኪዳን ይህ ነው።”</verse>
				<verse number="28">በወ​ን​ጌል በኩል ስለ እና​ንተ ጠላ​ቶ​ቻ​ችን ናቸው፤ በም​ርጫ በኩል ግን ስለ አባ​ቶች ወዳ​ጆች ናቸው።</verse>
				<verse number="29">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋና በመ​ጥ​ራቱ ጸጸት የለ​ምና።</verse>
				<verse number="30">ቀድሞ እና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ አል​ታ​ዘ​ዛ​ች​ሁት፥ ዛሬ ግን በእ​ነ​ርሱ አለ​መ​ታ​ዘዝ ይቅር እን​ዳ​ላ​ችሁ፥</verse>
				<verse number="31">እን​ዲ​ሁም እና​ንተ በተ​ማ​ራ​ች​ሁት ምሕ​ረት እነ​ርሱ ምሕ​ረ​ትን እን​ዲ​ያ​ገኙ እነ​ርሱ ዛሬ አል​ታ​ዘ​ዙ​ትም።</verse>
				<verse number="32">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁሉን ይቅር ይለው ዘንድ ሁሉን በኀ​ጢ​አት ውስጥ ዘግ​ቶ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="33">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባለ​ጠ​ግ​ነት፥ ጥበ​ብና ዕው​ቀት እን​ዴት ጥልቅ ነው! ለመ​ን​ገ​ዱም ፍለጋ የለ​ውም፤ ፍር​ዱ​ንም የሚ​ያ​ው​ቀው የለም።</verse>
				<verse number="34">“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዐሳ​ቡን ማን ያው​ቃል? ወይስ ማን ተማ​ከ​ረው?</verse>
				<verse number="35">ብድ​ሩን ይከ​ፍል ዘንድ ለእ​ርሱ አስ​ቀ​ድሞ ማን አበ​ደ​ረው?”</verse>
				<verse number="36">ሁሉ ከእ​ርሱ፥ በእ​ር​ሱና ለእ​ርሱ ነውና፤ ለእ​ር​ሱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ክብር ምስ​ጋና ይሁን። አሜን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕያ​ውና ቅዱስ፥ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝም መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ጋ​ችሁ ታቀ​ርቡ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርኅ​ራኄ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ። ይህም በዕ​ው​ቀት የሚ​ሆን አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ችሁ ነው።</verse>
				<verse number="2">ይህን ዓለም አት​ም​ሰሉ፤ ልባ​ች​ሁ​ንም አድሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ወ​ደ​ውን መል​ካ​ሙ​ንና እው​ነ​ቱን፥ ፍጹ​ሙ​ንም መር​ምሩ።</verse>
				<verse number="3">በተ​ሰ​ጠኝ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ሁላ​ች​ሁም እን​ዳ​ት​ታ​በዩ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ራሳ​ች​ሁን ከዝ​ሙት የም​ታ​ነ​ጹ​በ​ትን ዐስቡ እንጂ ትዕ​ቢ​ትን አታ​ስቡ፤ ሁሉም እንደ እም​ነቱ መጠን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አደ​ለው ይኑር።</verse>
				<verse number="4">በአ​ንዱ ሰው​ነ​ታ​ችን ብዙ የአ​ካል ክፍ​ሎች እን​ዳሉ፥ ሥራ​ቸ​ውም ልዩ ልዩ እንደ ሆነ፥</verse>
				<verse number="5">እን​ዲሁ ሁላ​ችን ብዙ​ዎች ስን​ሆን በክ​ር​ስ​ቶስ አንድ አካል ነን፤ እርስ በር​ሳ​ች​ንም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችን የሌ​ላው አካ​ሎች ነን፤ ስጦ​ታ​ውም ልዩ ልዩ ነው፤</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ጠን ጸጋ መጠን ልዩ ልዩ ስጦታ አለን። ትን​ቢት የሚ​ና​ገር እንደ እም​ነቱ መጠን ይና​ገር።</verse>
				<verse number="7">የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ልም በማ​ገ​ል​ገሉ ይትጋ፤ የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ርም በማ​ስ​ተ​ማሩ ይትጋ፤</verse>
				<verse number="8">የሚ​መ​ክ​ርም በመ​ም​ከሩ ይትጋ፤ የሚ​ሰ​ጥም በል​ግ​ስና ይስጥ፤ የሚ​ገ​ዛም በት​ጋት ይግዛ፤ የሚ​መ​ጸ​ው​ትም በደ​ስታ ይመ​ጽ​ውት።</verse>
				<verse number="9">ፍቅ​ራ​ችሁ ያለ ግብ​ዝ​ነት ይሁን፤ ከክፉ ራቁ፤ በጎ​ው​ንም ያዙ፤ ለጽ​ድቅ አድሉ፤</verse>
				<verse number="10">እርስ በር​ሳ​ችሁ በወ​ን​ድ​ማ​ማ​ች​ነት መዋ​ደድ ተዋ​ደዱ፤ የም​ት​ራ​ሩም ሁኑ፤ እርስ በር​ሳ​ችሁ ተከ​ባ​በሩ፤ መም​ህ​ሮ​ቻ​ች​ሁ​ንም አክ​ብሩ።</verse>
				<verse number="11">ለሥራ ከመ​ት​ጋት አት​ስ​ነፉ፤ በመ​ን​ፈስ ሕያ​ዋን ሁኑ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዙ፤</verse>
				<verse number="12">በተ​ስፋ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ በመ​ከራ ታገሡ፤ ለጸ​ሎት ትጉ።</verse>
				<verse number="13">በች​ግ​ራ​ቸው ቅዱ​ሳ​ንን ለመ​ር​ዳት ተባ​በሩ፤ እን​ግዳ መቀ​በ​ል​ንም አዘ​ው​ትሩ።</verse>
				<verse number="14">የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ች​ሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አት​ር​ገሙ።</verse>
				<verse number="15">ደስ ከሚ​ለው ጋር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ከሚ​ያ​ለ​ቅ​ሰው ጋርም አል​ቅሱ።</verse>
				<verse number="16">እርስ በር​ሳ​ች​ሁም በአ​ንድ ዐሳብ ተስ​ማሙ፤ ትዕ​ቢ​ትን ግን አታ​ስቡ፤ ራሱን የሚ​ያ​ዋ​ር​ደ​ው​ንም ሰው ምሰሉ፤ እና ዐዋ​ቆች ነን አት​በሉ።</verse>
				<verse number="17">ክፉ ላደ​ረ​ገ​ባ​ች​ሁም ክፉ አት​መ​ል​ሱ​ለት፤ በሰው ሁሉ ፊት በጎ​ውን ተነ​ጋ​ገሩ።</verse>
				<verse number="18">ቢቻ​ላ​ች​ሁስ ከሰው ሁሉ ጋር በሰ​ላም ኑሩ።</verse>
				<verse number="19">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ ራሳ​ችሁ አት​በ​ቀሉ፤ ቍጣን አሳ​ል​ፏት፥ “እኔ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤ እኔ ብድ​ራ​ትን እከ​ፍ​ላ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ተብሎ ተጽ​ፎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="20">ጠላ​ትህ ቢራብ አብ​ላው፤ ቢጠ​ማም አጠ​ጣው፤ ይህን ብታ​ደ​ርግ የእ​ሳት ፍሕም በራሱ ላይ ትከ​ም​ራ​ለህ።</verse>
				<verse number="21">ክፉ​ውን በመ​ል​ካም ሥራ ድል ንሣው እንጂ ክፉ​ውን በክፉ ድል አት​ን​ሣው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">ሰው ሁሉ በበ​ላይ ላሉ ባለ​ሥ​ል​ጣ​ኖች ይገዛ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ል​ተ​ገኘ በቀር ሥል​ጣን የለ​ምና፤ ያሉ​ትም ባለ​ሥ​ል​ጣ​ኖች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሾሙ ናቸው።</verse>
				<verse number="2">ለባ​ለ​ሥ​ል​ጣን አል​ገ​ዛም ያለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ እንቢ ማለቱ ነው፤ መገ​ዛ​ትን እንቢ የሚ​ሉም በራ​ሳ​ቸው ላይ ቅጣ​ትን ያመ​ጣሉ።</verse>
				<verse number="3">ሹሞች ሥራው ክፉ ለሆነ ሰው እንጂ መል​ካም ለሚ​ሠራ የሚ​አ​ስ​ፈሩ አይ​ደ​ሉም፤ ሹሞ​ችን እን​ዳ​ት​ፈራ ብት​ፈ​ልግ መል​ካም አድ​ርግ፤ እነ​ርሱ ደግሞ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፤</verse>
				<verse number="4">አንተ ሥራ​ህን ታሳ​ምር ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​እ​ክ​ተ​ኞች ናቸ​ውና። ክፉ ብታ​ደ​ርግ ግን ፍራ፤ ሰይፍ የታ​ጠ​ቁም ለከ​ንቱ አይ​ደ​ለም፤ ክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎ​ችን ለመ​ቅ​ጣት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች ናቸ​ውና።</verse>
				<verse number="5">ስለ​ዚህ ቍጣን ስለ መፍ​ራት ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ስለ ሕሊና ደግሞ መገ​ዛት ግድ ነው።</verse>
				<verse number="6">ስለ​ዚ​ህም ግብር ታገ​ቡ​ላ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ ለዚህ ሥራ የተ​ሾሙ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች ናቸ​ውና፤</verse>
				<verse number="7">ለሁ​ሉም እን​ደ​ሚ​ገ​ባው አድ​ርጉ፤ ግብር ለሚ​ገ​ባው ግብ​ርን ስጡ፤ ቀረጥ ለሚ​ገ​ባው ቀረ​ጥን ስጡ፤ ዐሥ​ራት ለሚ​ገ​ባው ዐሥ​ራ​ትን ስጡ፤ ሊፈ​ሩት የሚ​ገ​ባ​ውን ፍሩ፤ ክብር የሚ​ገ​ባ​ው​ንም አክ​ብሩ።</verse>
				<verse number="8">እርስ በር​ሳ​ችሁ ከመ​ዋ​ደድ በቀር ለማ​ንም ዕዳ አይ​ኑ​ር​ባ​ችሁ፤ ባል​ን​ጀ​ራ​ውን የወ​ደደ ግን ሕግን ሁሉ ፈጸመ።</verse>
				<verse number="9">በኦ​ሪት እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “አታ​መ​ን​ዝር፤ አት​ግ​ደል፤ አት​ስ​ረቅ፤ በሐ​ሰት አት​መ​ስ​ክር፥ አት​መኝ፤” ደግሞ ሌላ ትእ​ዛዝ አለ፤ ነገር ግን የሁ​ሉም ራስ “ ባል​ን​ጀ​ራ​ህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚ​ለው ነው።</verse>
				<verse number="10">ባል​ን​ጀ​ራ​ዉን የሚ​ወድ በባ​ል​ን​ጀ​ራዉ ላይ ክፉ ሥራ አይ​ሠ​ራም፤ ስለ​ዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው።</verse>
				<verse number="11">ከእ​ን​ቅ​ልፍ የም​ት​ነ​ቁ​በት ጊዜ እንደ ደረሰ ዕወቁ፤ ካመ​ን​በት ጊዜ ይልቅ መዳ​ና​ችን ዛሬ ወደ እና ደር​ሳ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="12">ሌሊቱ አል​ፎ​አል፤ ቀኑም ቀር​ቦ​አል። እን​ግ​ዲህ የጨ​ለ​ማን ሥራ ከእና እና​ርቅ፤ የብ​ር​ሃ​ን​ንም ጋሻ ጦር እን​ል​በስ።</verse>
				<verse number="13">በቀን እን​ደ​ሚ​ሆን በጽ​ድቅ ሥራ እን​መ​ላ​ለስ፤ በዘ​ፈ​ንና በስ​ካር፥ በዝ​ሙ​ትና በመ​ዳ​ራ​ትም አይ​ሁን፤ በክ​ር​ክ​ርና በቅ​ና​ትም አይ​ሁን።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ልበ​ሱት፤ የሥ​ጋ​ች​ሁ​ንም ምኞት አታ​ስቡ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">እም​ነቱ ደካማ የሆ​ነ​ውን ሰው ታገ​ሡት፤ በዐ​ሳ​ቡም አት​ፍ​ረዱ።</verse>
				<verse number="2">ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደ ተፈ​ቀ​ደ​ለት የሚ​ያ​ምን ሁሉን ይብላ፤ የሚ​ጠ​ራ​ጠር ግን አት​ክ​ልት ይብላ።</verse>
				<verse number="3">የሚ​በ​ላ​ውም የማ​ይ​በ​ላ​ውን አይ​ና​ቀው፤ የማ​ይ​በ​ላ​ውም የሚ​በ​ላ​ውን አይ​ን​ቀ​ፈው፤ ሁሉ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አው​ቆ​አ​ቸ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="4">እን​ግ​ዲህ የሌ​ላ​ውን ሎሌ የም​ት​ነ​ቅፍ አንተ ማነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወ​ድቅ ለጌ​ታው ነው። ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ነ​ሣው ይች​ላ​ልና ይቆ​ማል።</verse>
				<verse number="5">ከቀን ቀን የሚ​ከ​ለ​ከል አለና፤ ዘወ​ት​ርም የሚ​ከ​ለ​ከል አለና፤ ነገር ግን ሁሉም ልቡ እንደ ወደደ ያድ​ርግ።</verse>
				<verse number="6">አን​ዳ​ንድ ቀን የተ​ከ​ለ​ከ​ለም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተከ​ለ​ከለ፤ ዘወ​ትር የተ​ከ​ለ​ከ​ለም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተከ​ለ​ከለ፤ የበ​ላም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያመ​ሰ​ግ​ነ​ዋል፤ ያል​በ​ላም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​በ​ላም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያመ​ሰ​ግ​ነ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">ከመ​ካ​ከ​ላ​ች​ንም ለራሱ የሚ​ኖር፥ ለራ​ሱም የሚ​ሞት የለም።</verse>
				<verse number="8">በሕ​ይ​ወት ብን​ኖ​ርም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ኖ​ራ​ለን፤ ብን​ሞ​ትም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ሞ​ታ​ለን፤ እን​ግ​ዲህ በሕ​ይ​ወት ብን​ኖ​ርም ብን​ሞ​ትም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነን።</verse>
				<verse number="9">ስለ​ዚህ ሕያ​ዋ​ን​ንና ሙታ​ንን ይገዛ ዘንድ ክር​ስ​ቶስ ሞተ፥ ተነ​ሣም።</verse>
				<verse number="10">እን​ግ​ዲህ በወ​ን​ድ​ምህ ላይ የም​ት​ፈ​ርድ አንተ ምን​ድን ነህ? ወን​ድ​ም​ህ​ንስ የም​ት​ነ​ቅፍ አንተ ምን​ድን ነህ? ሁላ​ችን በክ​ር​ስ​ቶስ የፍ​ርድ ዙፋን ፊት እን​ቆ​ማ​ለ​ንና።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “እኔ ሕያው ነኝ፤ ጕል​በ​ትም ሁሉ ለእኔ ይሰ​ግ​ዳል፤ አን​ደ​በ​ትም ሁሉ ለእኔ ይገ​ዛል።”</verse>
				<verse number="12">እነሆ፥ ሁላ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እን​ደ​ም​ን​መ​ረ​መር ታወቀ።</verse>
				<verse number="13">እን​ግ​ዲህ ከዛሬ ጀምሮ እርስ በር​ሳ​ችን አን​ነ​ቃ​ቀፍ፤ ይል​ቁ​ንም ለወ​ን​ድም እን​ቅ​ፋ​ትን ወይም ማሰ​ና​ከ​ያን ማንም እን​ዳ​ያ​ኖር ይህን ዐስቡ።</verse>
				<verse number="14">በራሱ ርኩስ የሆነ ነገር እን​ደ​ሌለ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ሆኜ ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤ ተረ​ድ​ቼ​አ​ለ​ሁም፤ ነገር ግን ማና​ቸ​ውም ነገር ርኩስ እን​ደ​ሚ​ሆን ለሚ​ያ​ስብ ያ ለእ​ርሱ ርኩስ ነው።</verse>
				<verse number="15">በመ​ብል ምክ​ን​ያት ባል​ን​ጀ​ራ​ህን የም​ታ​ሳ​ዝን ከሆ​ንህ ፍቅር የለ​ህም፤ በውኑ ክር​ስ​ቶስ ስለ እርሱ የሞ​ተ​ለት ያ ሰው በመ​ብል ምክ​ን​ያት ሊጐዳ ይገ​ባ​ልን?</verse>
				<verse number="16">እን​ግ​ዲህ ጌታ​ችን የሰ​ጠ​ንን መል​ካ​ሙን ነገር አታ​ሰ​ድቡ።</verse>
				<verse number="17">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ጽድ​ቅና ሰላም፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም የሆነ ደስታ ነው እንጂ መብ​ልና መጠጥ አይ​ደ​ለ​ምና።</verse>
				<verse number="18">እን​ዲህ አድ​ርጎ ለክ​ር​ስ​ቶስ የሚ​ገዛ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝና በሰ​ውም ዘንድ የተ​መ​ረጠ ነው።</verse>
				<verse number="19">አሁ​ንም ወን​ድ​ማ​ችን ይታ​ነጽ ዘንድ ሰላ​ምን እን​ከ​ተ​ላት።</verse>
				<verse number="20">በመ​ብል ምክ​ን​ያት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍጥ​ረት አና​ፍ​ርስ፤ ለን​ጹ​ሓን ሁሉ ንጹሕ ነው፤ ለሰ​ውስ ክፉው ነገር በመ​ጠ​ራ​ጠር መብ​ላት ነው።</verse>
				<verse number="21">ለወ​ን​ድም ዕን​ቅ​ፋት ከመ​ሆን ሥጋን አለ​መ​ብ​ላት ወይ​ን​ንም አለ​መ​ጠ​ጣት ይሻ​ላል።</verse>
				<verse number="22">እም​ነት ካለህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ባመ​ን​ኸው እም​ነት ራስ​ህን አጽና፤ ባገ​ኘው አእ​ም​ሮም ራሱን የሚ​ዘ​ልፍ ብፁዕ ነው።</verse>
				<verse number="23">የሚ​ጠ​ራ​ጠር ግን ቢበላ ይፈ​ረ​ድ​በ​ታል፤ በማ​መን አል​ሆ​ነ​ምና፤ ያለ እም​ነ​ትም የሚ​ደ​ረግ ሁሉ ኀጢ​አ​ትና በደል ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">የሚ​ገ​ባስ እና ብር​ቱ​ዎች ደካ​ሞ​ችን በድ​ካ​ማ​ቸው እን​ድ​ን​ረ​ዳ​ቸው ነው፤ ለራ​ሳ​ች​ንም አና​ድላ።</verse>
				<verse number="2">ሁላ​ች​ንም በእ​ው​ነ​ትና በመ​ል​ካም ሥራ ይታ​ነጽ ዘንድ ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ችን እና​ድላ።</verse>
				<verse number="3">ክር​ስ​ቶ​ስም፥ “አን​ተን የነ​ቀ​ፉ​በት ነቀፋ በእኔ ላይ ደረሰ” ብሎ መጽ​ሐፍ እንደ ተና​ገረ ለራሱ ያደላ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="4">የተ​ጻ​ፈው ሁሉ በመ​ታ​ገ​ሣ​ች​ንና መጻ​ሕ​ፍ​ትን በመ​ታ​መ​ና​ችን ተስ​ፋ​ች​ንን እና​ገኝ ዘንድ እና ልን​ማ​ር​በት ተጻፈ።</verse>
				<verse number="5">የት​ዕ​ግ​ሥ​ትና የመ​ጽ​ና​ናት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ፈቃድ እርስ በር​ሳ​ችን አንድ ዐሳብ መሆ​ንን ይስ​ጠን።</verse>
				<verse number="6">ሁላ​ችን አንድ ሆነን በአ​ንድ አፍ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ሰ​ግ​ነው ዘንድ።</verse>
				<verse number="7">አሁ​ንም ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ች​ሁን ተቀ​በሉ፤ ክር​ስ​ቶስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ተቀ​ብ​ሎ​አ​ች​ኋ​ልና።</verse>
				<verse number="8">እን​ግ​ዲህ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እው​ነት ለማ​ድ​ረግ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ን​ንም ተስፋ ያጸና ዘንድ ለግ​ዝ​ረት መል​እ​ክ​ተና ሆነ እላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">አሕ​ዛ​ብም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤ ይቅር ብሎ​አ​ቸ​ዋ​ልና፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “አቤቱ፥ ስለ​ዚህ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እገ​ዛ​ል​ሃ​ለሁ፤ ስም​ህ​ንም አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ።”</verse>
				<verse number="10">ዳግ​መ​ናም መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አል፥ “አሕ​ዛብ ከሕ​ዝቡ ጋር ደስ ይበ​ላ​ችሁ።”</verse>
				<verse number="11">ዳግ​መ​ናም እን​ዲህ አለ፥ “አሕ​ዛብ ሁላ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።”</verse>
				<verse number="12">ኢሳ​ይ​ያ​ስም ደግሞ እን​ዲህ ብሎ​አል፥ “የእ​ሴይ ዘር ይነ​ሣል፤ ከእ​ርሱ የሚ​ነ​ሣ​ውም ለአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ ይሆ​ናል፤ ሕዝ​ቡም ተስፋ ያደ​ር​ጉ​ታል።”</verse>
				<verse number="13">የተ​ስፋ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ኀይል በተ​ስፋ ያበ​ዛ​ችሁ ዘንድ በእ​ም​ነት ደስ​ታ​ንና ሰላ​ምን ሁሉ ይፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="14">ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እኔም በጎ ምግ​ባ​ርን ሁሉ እን​ደ​ም​ት​ፈ​ጽሙ እታ​መ​ን​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ንተ ፍጹም ዕው​ቀ​ትን የተ​መ​ላ​ችሁ ናችሁ፤ ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ች​ሁ​ንም ልታ​ስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው ትች​ላ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="15">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አገ​ኘ​ሁት ጸጋ ላሳ​ስ​ባ​ችሁ በአ​ን​ዳ​ንድ ቦታ በድ​ፍ​ረት ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="16">በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን አገ​ለ​ግል ዘንድ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወን​ጌ​ልም እገዛ ዘንድ፥ በእኔ ትም​ህ​ርት አሕ​ዛብ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የተ​ወ​ደ​ደና የተ​መ​ረጠ መሥ​ዋ​ዕት ይሆኑ ዘንድ።</verse>
				<verse number="17">ለእ​ኔም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መመ​ኪ​ያዬ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነው።</verse>
				<verse number="18">አሕ​ዛ​ብም እን​ዲ​ያ​ምኑ ክር​ስ​ቶስ በቃ​ልም በሥ​ራም ያደ​ረ​ገ​ል​ኝን እና​ገር ዘንድ እደ​ፍ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">በኀ​ይ​ልና በተ​አ​ም​ራት፥ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ኀይ​ልና ድንቅ ሥራን በመ​ሥ​ራ​ትም፥ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አው​ራ​ጃ​ዎች ጀምሬ እስከ እል​ዋ​ሪ​ቆን ድረስ እንደ አስ​ተ​ማ​ርሁ፥ የክ​ር​ስ​ቶ​ስ​ንም ወን​ጌል ፈጽሞ እንደ ሰበ​ክሁ እና​ገር ዘንድ እደ​ፍ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">ወን​ጌ​ልን ለማ​ስ​ተ​ማር ተጋሁ፤ ነገር ግን በሌላ መሠ​ረት ላይ እን​ዳ​ላ​ንጽ የክ​ር​ስ​ቶስ ስም ወደ ተጠ​ራ​በት አል​ሄ​ድ​ሁም።</verse>
				<verse number="21">“ወሬው ያል​ደ​ረ​ሳ​ቸው ያው​ቁ​ታል፤ ያል​ሰ​ሙ​ትም ያስ​ተ​ው​ሉ​ታል” ብሎ መጽ​ሐፍ እንደ ተና​ገረ ነው።</verse>
				<verse number="22">ዘወ​ትር ወደ እና​ንተ ልመጣ እወ​ድድ ነበር፤ ነገር ግን ተሳ​ነኝ።</verse>
				<verse number="23">አሁን ግን በዚህ ሀገር ሥራ​ዬን ስለ ጨረ​ስሁ፥ ከብዙ ጊዜም ጀምሮ ወደ እና​ንተ ልመጣ እተጋ ስለ ነበር፤</verse>
				<verse number="24">ወደ አስ​ባ​ንያ ስሄድ እግረ መን​ገ​ዴን ላያ​ችሁ ተስፋ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ቀደም ብዬ ከእ​ና​ንተ ጋር ደስ ካለኝ በኋ​ላም ከእ​ና​ንተ ወደ​ዚያ እሄ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="25">አሁን ግን ቅዱ​ሳ​ንን ለመ​ር​ዳት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እሄ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="26">መቄ​ዶ​ን​ያና አካ​ይያ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅዱ​ሳን መካ​ከል ላሉ ድሆች አስ​ተ​ዋ​ጽ​ፅኦ ለማ​ድ​ረግ ተባ​ብ​ረ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="27">የሚ​ገ​ባ​ቸ​ውም ሰለ​ሆነ በመ​ን​ፈ​ሳዊ ሥራ አሕ​ዛ​ብን ከተ​ባ​በ​ሩ​አ​ቸው ለሰ​ው​ነ​ታ​ቸው በሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ጋ​ቸው ሊረ​ዱ​አ​ቸው ይገ​ባል።</verse>
				<verse number="28">እን​ግ​ዲህ ይህን ፍሬ ጨር​ሼና አትሜ በእ​ና​ንተ በኩል ወደ አስ​ባ​ንያ እሄ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="29">ነገር ግን በመ​ጨ​ረሻ ጊዜ በክ​ር​ስ​ቶስ ወን​ጌል በረ​ከት ፍጹ​ም​ነት እን​ደ​ም​ት​መጣ አም​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="30">ወን​ድ​ሞች፥ በጸ​ሎ​ታ​ችሁ ስለ እኔ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ጋር ትተጉ ዘንድ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ፍቅር እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="31">ይኸ​ውም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያሉ ቅዱ​ሳ​ንን በአ​ገ​ል​ግ​ሎቴ ደስ አሰ​ና​ቸው ዘንድ በይ​ሁዳ ሀገር ካሉ ዐላ​ው​ያን እን​ዲ​ያ​ድ​ነኝ ነው።</verse>
				<verse number="32">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቢፈ​ቅድ በደ​ስታ ወደ እና​ንተ መጥቼ ከእ​ና​ንተ ጋር ዐርፍ ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="33">የሰ​ላም አም​ላክ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">ለክ​ን​ክ​ራ​ኦስ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን የም​ት​ላ​ላ​ከ​ውን እኅ​ታ​ች​ንን ፌቤ​ንን አደራ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="2">ለቅ​ዱ​ሳ​ንም እን​ደ​ሚ​ገባ በጌ​ታ​ችን ተቀ​በ​ሉ​አት፤ እር​ስዋ ለብ​ዙ​ዎች፥ ለእ​ኔም ረዳት ናትና፤ ለች​ግ​ራ​ች​ሁም በፈ​ቀ​ዳ​ች​ሁት ቦታ መድ​ቡ​አት።</verse>
				<verse number="3">በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሥራ ከእኔ ጋር የተ​ባ​በ​ሩ​ትን ጵር​ስ​ቅ​ላ​ንና አቂ​ላን ሰላም በሉ፤</verse>
				<verse number="4">ስለ እኔ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ለመ​ከራ አሳ​ል​ፈው ሰጥ​ተ​ዋ​ልና፤ የማ​መ​ሰ​ግ​ና​ቸ​ውም እኔ ብቻ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ከአ​ሕ​ዛብ ያመኑ ምእ​መ​ናን ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​አ​ቸ​ዋል እንጂ።</verse>
				<verse number="5">በቤ​ታ​ቸው ያሉ​ትን ማኅ​በረ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ሰላም በሉ፤ ወዳጄ ኤጴ​ኔ​ጦ​ስ​ንም እን​ዴት ነህ? በሉ፤ ይኸ​ውም በእ​ስያ በክ​ር​ስ​ቶስ ላመኑ ሁሉ መጀ​መ​ሪ​ያ​ቸው ነው።</verse>
				<verse number="6">ለእ​ና​ንተ ብዙ የደ​ከ​መ​ች​ላ​ች​ሁን ማር​ያ​ም​ንም ሰላም በሉ።</verse>
				<verse number="7">ከዘ​መ​ዶች ወገን የሚ​ሆ​ኑ​ትን ከእኔ ጋር ያመኑ እን​ድ​ራ​ና​ቆ​ስ​ንና ዩል​ያ​ንን ሰላም በሉ፤ ቀደም ሲል ክር​ስ​ቶ​ስን እንደ አገ​ለ​ገሉ ሐዋ​ር​ያት ያው​ቁ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="8">በክ​ር​ስ​ቶስ ወን​ድሜ የሆ​ነ​ውን አም​ጵ​ል​ያ​ጦ​ስን ሰላም በሉ።</verse>
				<verse number="9">የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ሥራ በመ​ሥ​ራት የም​ን​ተ​ባ​በ​ረ​ውን ኡሩ​ባ​ኖ​ስን፥ ወዳጄ ስን​ጣ​ክ​ን​ንም ሰላም በሉ።</verse>
				<verse number="10">በክ​ር​ስ​ቶስ የተ​መ​ረ​ጠ​ውን ኤጤ​ሌ​ንን ሰላም በሉ፤ እነ አር​ስ​ጠ​ቦ​ሎ​ስ​ንም ሰላም በሉ።</verse>
				<verse number="11">ከዘ​መ​ዶች ወገን የሚ​ሆን ሄሮ​ድ​ዮ​ናን ሰላም በሉ፤ በን​ር​ቃ​ሶስ ቤት ያሉ​ት​ንና በክ​ር​ስ​ቶስ ያመ​ኑ​ትን ምእ​መ​ናን ሰላም በሉ።</verse>
				<verse number="12">በጌ​ታ​ችን ስም መከራ የተ​ቀ​በ​ሉ​ትን የጢ​ሮ​ፊ​ሞ​ና​ንና የጢ​ሮ​ፊ​ሞ​ስን ወገ​ኖች ሰላም በሉ። በጌ​ታ​ችን ስም ብዙ የደ​ከ​መች እኅ​ታ​ች​ንን ጠር​ሴ​ዳን ሰላም በሉ።</verse>
				<verse number="13">ጌታ​ችን የመ​ረ​ጠው ሩፎ​ንን፥ እና​ቱ​ንም፥ ለእ​ኔም እናቴ የሆ​ነ​ች​ውን ሰላም በሉ።</verse>
				<verse number="14">አስ​ቀ​ሪ​ጦ​ስን፥ አል​ሶ​ን​ጳን፥ ሄር​ሜ​ስን፥ ጳጥ​ሮ​ባ​ስን፥ ሄር​ማ​ስን፥ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ያሉ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ን​ንም ሰላም በሉ።</verse>
				<verse number="15">ፊሎ​ሎ​ጎ​ስን፥ ዩል​ያን፥ ኔር​ዮ​ስን፥ እኅ​ቱ​ንም አሊ​ን​ጳ​ስን ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ያሉ ቅዱ​ሳ​ንን ሁሉ ሰላም በሉ።</verse>
				<verse number="16">እርስ በር​ሳ​ችሁ በተ​ቀ​ደሰ ሰላ​ምታ ሰላም ተባ​ባሉ፤ የክ​ር​ስ​ቶስ ማኅ​በረ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ሰላም ይሉ​አ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="17">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እና​ንተ የተ​ማ​ራ​ች​ሁ​ትን ትም​ህ​ርት የሚ​ቃ​ወ​ሙ​ትን፥ መለ​ያ​የ​ት​ንና ማሰ​ና​ከ​ያን የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን እን​ድ​ታ​ው​ቁ​ባ​ቸው እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ተለዩ፤</verse>
				<verse number="18">እነ​ርሱ ለጌ​ታ​ችን ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ያይ​ደለ ለሆ​ዳ​ቸው ይገ​ዛ​ሉና፤ በነ​ገር ማታ​ለ​ልና በማ​ለ​ዛ​ዘ​ብም የብ​ዙ​ዎች የዋ​ሃ​ንን ልብ ያስ​ታሉ፤</verse>
				<verse number="19">መታ​ዘ​ዛ​ች​ሁም በሁሉ ዘንድ ተሰ​ም​ቶ​አል፤ እኔም በእ​ና​ንተ ደስ ይለ​ናል፤ ለመ​ል​ካም ነገር ጠቢ​ባን፥ ለክፉ ነገ​ርም የዋ​ሃን እን​ድ​ት​ሆኑ እፈ​ል​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">የሰ​ላም አም​ላ​ክም ፈጥኖ ሰይ​ጣ​ንን ከእ​ግ​ራ​ችሁ በታች ይቀ​ጥ​ቅ​ጠው፤ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጸጋ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።</verse>
				<verse number="21">ከእኔ ጋር በሥራ የሚ​ተ​ባ​በ​ረው ጢሞ​ቴ​ዎ​ስም፥ ከዘ​መ​ዶች ወገን የሚ​ሆኑ ሉቅ​ዮ​ስም፥ ኢያ​ሶ​ንም፥ ሱሲ ጴጥ​ሮ​ስም ሰላም ይሉ​አ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="22">ይህ​ችን መል​እ​ክት የጻ​ፍ​ኋት እኔ ጤር​ጥ​ዮስ በጌ​ታ​ችን ስም ሰላም እላ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="23">እኔ​ንና አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ና​ትን ሁሉ በእ​ን​ግ​ድ​ነት የተ​ቀ​በለ ጋይ​ዮ​ስም ሰላም ብሎ​አ​ች​ኋል፤ የከ​ተ​ማው መጋቢ አር​ስ​ጦ​ስና ወን​ድ​ማ​ችን ቁአ​ስ​ጥ​ሮ​ስም ሰላም ብለ​ዋ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="24">ከዓ​ለም አስ​ቀ​ድሞ ምሥ​ጢሩ ተሰ​ውሮ ስለ ነበረ ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በማ​ስ​ተ​ም​ራት ትም​ህ​ርት ላይ ሊያ​ጸ​ና​ችሁ የሚ​ች​ለው እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።</verse>
				<verse number="25">ይህም በነ​ቢ​ያት ቃልና የዘ​ለ​ዓ​ለም ገዥ በሚ​ሆን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ በዚህ ወራት ተገ​ለጠ፤ አሕ​ዛብ ሁሉ ይህን ሰም​ተ​ውና ዐው​ቀው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ያምኑ ዘንድ።</verse>
				<verse number="26">ብቻ​ውን ጠቢብ ለሆ​ነው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ይሁን፤ አሜን።</verse>
				<verse number="27">የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጸጋ ከሁ​ላ​ችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን። በቆ​ሮ​ን​ቶስ ተጽፋ ለክ​ን​ክ​ራ​ኦስ ማኅ​በረ ክር​ስ​ቲ​ያን በም​ት​ላ​ላ​ከው በፌ​ቤን እጅ ወደ ሮሜ ሰዎች የተ​ላ​ከ​ችው መል​እ​ክት ተፈ​ጸ​መች። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ አሜን።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="46">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈቃድ የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሐዋ​ርያ ሊሆን ከተ​ጠራ ከጳ​ው​ሎ​ስና ከወ​ን​ድ​ማ​ችን ከሶ​ስ​ቴ​ንስ፥</verse>
				<verse number="2">በቆ​ሮ​ን​ቶስ ሀገር ላለች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ለከ​በ​ሩና ቅዱ​ሳን ለተ​ባሉ የእ​ነ​ር​ሱና የእኛ ጌታ የሆ​ነ​ውን የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ስም በየ​ስ​ፍ​ራው ለሚ​ጠሩ ሁሉ፥</verse>
				<verse number="3">ከአ​ባ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘንድ ሰላ​ምና ጸጋ ለእ​ና​ንተ ይሁን።</verse>
				<verse number="4">ስለ እና​ንተ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ለእ​ና​ንተ ስለ​ተ​ሰ​ጣ​ችሁ ጸጋ ዘወ​ትር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">በአ​ነ​ጋ​ገር ሁሉ፥ በዕ​ው​ቀ​ትም ሁሉ ከብ​ራ​ች​ሁ​በ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="6">ለክ​ር​ስ​ቶስ መመ​ስ​ከሬ በእ​ና​ንተ እንደ ጸና መጠን።</verse>
				<verse number="7">ፍጹ​ማ​ንም እን​ድ​ት​ሆኑ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስ​ንም መም​ጣት ተስፋ አድ​ር​ጋ​ችሁ ፍጹም ጸጋን እን​ዳ​ታጡ፥</verse>
				<verse number="8">እር​ሱም በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ቀን ያለ ነውር ትገኙ ዘንድ እስከ ፍጻሜ ያጸ​ና​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="9">ከልጁ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የጠ​ራ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መነ ነው።</verse>
				<verse number="10">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን! አንድ ቃል እን​ድ​ት​ና​ገሩ፥ እን​ዳ​ታ​ዝኑ፥ ፍጹ​ማ​ንም እን​ድ​ት​ሆኑ፥ ሁላ​ች​ሁ​ንም፦ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፤ እን​ዳ​ት​ለ​ያ​ዩም አንድ ልብና አንድ አሳብ ሆና​ችሁ ኑሩ።</verse>
				<verse number="11">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ! እን​ደ​ም​ት​ጣ​ሉና እን​ደ​ም​ት​ከ​ራ​ከሩ ከቀ​ሎ​ኤስ ወገ​ኖች ስለ እና​ንተ ነገ​ሩኝ።</verse>
				<verse number="12">እነሆ፥ እርስ በር​ሳ​ችሁ፥ “እኔ የጳ​ው​ሎስ ነኝ፤ እኔ የአ​ጵ​ሎስ ነኝ፤ እኔ የኬፋ ነኝ፤ እኔ የክ​ር​ስ​ቶስ ነኝ” የም​ት​ሉ​ትን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">ክር​ስ​ቶስ ተከ​ፍ​ሎ​አ​ልን? ወይስ በውኑ ጳው​ሎስ ስለ እና​ንተ ተሰ​ቅ​ሎ​አ​ልን? ወይስ በጳ​ው​ሎስ ስም ተጠ​ም​ቃ​ች​ኋ​ልን?</verse>
				<verse number="14">ከቀ​ር​ስ​ጶ​ስና ከጋ​ይ​ዮስ በቀር ከእ​ና​ንተ ወገን ሌላ ስላ​ላ​ጠ​መ​ቅሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">በእ​ርሱ ስም ተጠ​መ​ቅን የሚል እን​ዳ​ይ​ኖር።</verse>
				<verse number="16">ነገር ግን የእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስን ቤተ ሰብእ አጥ​ም​ቄ​አ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲህ ሌላም ያጠ​መ​ቅ​ሁት እን​ዳለ አላ​ው​ቅም።</verse>
				<verse number="17">ክር​ስ​ቶስ ወን​ጌ​ልን ለመ​ስ​በክ እንጂ ለማ​ጥ​መቅ አል​ላ​ከ​ኝ​ምና፥ የክ​ር​ስ​ቶ​ስን መስ​ቀ​ሉን ከንቱ እን​ዳ​ና​ደ​ርግ ነገ​ርን በማ​ራ​ቀቅ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="18">የመ​ስ​ቀሉ ነገር በሚ​ጠፉ ሰዎች ዘንድ ስን​ፍና ነውና፥ ለም​ን​ድ​ነው ለእኛ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ነው።</verse>
				<verse number="19">መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “እኔ የጥ​በ​በ​ኞ​ችን ጥበብ አጠ​ፋ​ለሁ፤ የመ​ካ​ሪ​ዎ​ች​ንም ምክር እን​ቃ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="20">እን​ግ​ዲህ ጥበ​በኛ ማን ነው? ጸሓ​ፊስ ማን ነው? ይህን ዓለ​ምስ የሚ​መ​ረ​ም​ረው ማን ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዚ​ህን ዓለም ጥበብ ስን​ፍና አላ​ደ​ረ​ገ​ው​ምን?</verse>
				<verse number="21">ሰዎች በጥ​በ​ባ​ቸው በማ​ያ​ው​ቁት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ ስን​ፍና በሚ​መ​ስ​ላ​ቸው ትም​ህ​ርት ያመ​ኑ​ትን ሊያ​ድ​ና​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወድ​ዶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="22">አይ​ሁድ ምል​ክ​ትን ይጠ​ይ​ቃሉ፤ የጽ​ርዕ ሰዎ​ችም ጥበ​ብን ይሻሉ።</verse>
				<verse number="23">እኛ ግን የተ​ሰ​ቀ​ለ​ውን ክር​ስ​ቶ​ስን እን​ሰ​ብ​ካ​ለን፤ ይህም ለአ​ይ​ሁድ ማሰ​ና​ከያ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ስን​ፍና ነው።</verse>
				<verse number="24">ለእኛ ለዳ​ን​ነው ግን ከአ​ይ​ሁድ፥ ከአ​ረ​ሚም ብን​ሆን ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጥበብ ነው።</verse>
				<verse number="25">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስን​ፍና ከሰው ይልቅ ይጠ​በ​ባ​ልና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ድካም ከሰው ይልቅ ይበ​ረ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="26">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን! እን​ግ​ዲህ እን​ዴት እንደ ተጠ​ራ​ችሁ እዩ፤ በሥጋ እጅግ ብዙ​ዎች ዐዋ​ቂ​ዎች አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምና፥ ብዙ​ዎች ኀያ​ላ​ንም አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምና፥ በዘ​መ​ድም ብዙ​ዎች ደጋ​ጎች አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምና።</verse>
				<verse number="27">ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​በ​ኞ​ችን ሊያ​ሳ​ፍር የዚ​ህን ዓለም ሰነ​ፎች መረጠ፤ ኀይ​ለ​ኞ​ች​ንም ያሳ​ፍር ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዚ​ህን ዓለም ደካ​ሞች መረጠ።</verse>
				<verse number="28">አለን የሚ​ሉ​ት​ንም ያሳ​ፍር ዘንድ ዘመድ የሌ​ላ​ቸ​ው​ንና የተ​ና​ቁ​ትን፥ ከቍ​ጥ​ርም ያል​ገ​ቡ​ትን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መረጠ።</verse>
				<verse number="29">ሰው ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዳ​ይ​መካ።</verse>
				<verse number="30">እና​ን​ተም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከእ​ርሱ ናችሁ፤ በእ​ር​ሱም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብ​ንና ጽድ​ቅን፥ ቅድ​ስ​ና​ንና ቤዛ​ነ​ትን አገ​ኘን።</verse>
				<verse number="31">መጽ​ሐፍ እንደ አለው ይሆን ዘንድ “የሚ​መ​ካስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመካ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኔም ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ በማ​ባ​በ​ልና ነገ​ርን በማ​ራ​ቀቅ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትም​ህ​ርት ላስ​ተ​ም​ራ​ችሁ የመ​ጣሁ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="2">ከተ​ሰ​ቀ​ለው ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በቀር በእ​ና​ንተ ዘንድ ሌላ ነገር እሰ​ማ​ለሁ ብዬ አል​ጠ​ረ​ጠ​ር​ሁም ነበር።</verse>
				<verse number="3">እኔም በድ​ካ​ምና በፍ​ር​ሀት፥ በብዙ መን​ቀ​ጥ​ቀ​ጥም መጣሁ።</verse>
				<verse number="4">ቃሌም፥ ትም​ህ​ር​ቴም መን​ፈ​ስ​ንና ኀይ​ልን በመ​ግ​ለጥ ነበር እንጂ በሚ​ያ​ባ​ብል በጥ​በብ ቃል አል​ነ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="5">ማመ​ና​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል እንጂ በሰው ጥበብ እን​ዳ​ይ​ሆን።</verse>
				<verse number="6">ለዐ​ዋ​ቆች ጥበ​ብን እን​ነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለን፤ ነገር ግን የዚ​ህን ዓለም ጥበብ ወይም ያልፉ ዘንድ ያላ​ቸ​ውን የዚ​ህን ዓለም ሹሞች ጥበብ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="7">ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ ከዘ​መ​ናት በፊት ለክ​ብ​ራ​ችን የወ​ሰ​ነ​ውን ተሰ​ው​ሮም የነ​በ​ረ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ በም​ሥ​ጢር እን​ና​ገ​ራ​ለን።</verse>
				<verse number="8">የዚህ ዓለም ሹሞ​ችም አላ​ወ​ቁ​ትም፤ ይህ​ንስ ቢያ​ውቁ ኑሮ የክ​ብር ባለ​ቤ​ትን ባል​ሰ​ቀ​ሉ​ትም ነበር።</verse>
				<verse number="9">ነገር ግን መጽ​ሐፍ፥ “ዐይን ያላ​የው፥ ጆሮም ያል​ሰ​ማው፥ በሰ​ውም ልቡና ያል​ታ​ሰበ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ወ​ዱት ያዘ​ጋ​ጀው ነው።” ብሎ የለ​ምን?</verse>
				<verse number="10">ለእ​ኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ን​ፈሱ ገለ​ጠ​ልን፤ መን​ፈስ ቅዱስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጥልቅ ምሥ​ጢ​ሩን ያው​ቃ​ልና።</verse>
				<verse number="11">በሰው ልቡና ያለ​ውን የሚ​ያ​ውቅ ሰው ማን ነው? በእ​ርሱ ያለ​ችው ነፍሱ ናት እንጂ፤ እን​ዲ​ሁም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በቀር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አሳብ የሚ​ያ​ውቅ የለም።</verse>
				<verse number="12">እኛ የዚ​ህን ዓለም መን​ፈስ የተ​ቀ​በ​ልን አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠ​ንን ጸጋ እና​ውቅ ዘንድ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሆ​ነ​ውን መን​ፈስ ተቀ​በ​ልን።</verse>
				<verse number="13">ይህም ትም​ህ​ር​ታ​ችን ከሰው የተ​ገኘ ትም​ህ​ርት አይ​ደ​ለም፤ የአ​ነ​ጋ​ገር ጥበ​ብም አይ​ደ​ለም፤ መን​ፈስ ቅዱስ የገ​ለ​ጸው ትም​ህ​ርት ነው እንጂ፤ መን​ፈ​ሳዊ ጥበ​ብም ከመ​ን​ፈስ ቅዱስ የሚ​ሆ​ነ​ውን መር​ም​ረው ለሚ​ያ​ውቁ ለመ​ን​ፈ​ሳ​ው​ያን ነው።</verse>
				<verse number="14">ለሥ​ጋዊ ሰው ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነገር ሞኝ​ነት ይመ​ስ​ለ​ዋ​ልና፥ አይ​ቀ​በ​ለ​ውም፤ በመ​ን​ፈ​ስም የሚ​መ​ረ​መር ስለ​ሆነ ሊያ​ውቅ አይ​ች​ልም።</verse>
				<verse number="15">መን​ፈስ ቅዱስ ያደ​ረ​በት ሰው ግን ሁሉን ይመ​ረ​ም​ራል፤ እር​ሱን ግን የሚ​መ​ረ​ም​ረው የለም።</verse>
				<verse number="16">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አሳብ ማን ያው​ቃል? መካ​ሩስ ማን ነው? እኛ ግን ክር​ስ​ቶስ የሚ​ገ​ል​ጠው ዕው​ቀት አለን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ወድ​ሞች ሆይ፥ እኔስ የሥ​ጋና የደም እንደ መሆ​ና​ችሁ፥ ክር​ስ​ቶ​ስ​ንም በማ​መን ሕፃ​ናት እንደ መሆ​ና​ችሁ እንጂ እንደ መን​ፈ​ሳ​ው​ያን ላስ​ተ​ም​ራ​ችሁ አል​ቻ​ል​ሁም።</verse>
				<verse number="2">ወተ​ትን ጋት​ኋ​ችሁ፤ ጽኑ መብ​ልም ያበ​ላ​ኋ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ ገና አል​ጠ​ነ​ከ​ራ​ች​ሁ​ምና፤</verse>
				<verse number="3">በሥ​ጋዊ ሕግም ትኖ​ራ​ላ​ች​ሁና እርስ በር​ሳ​ችሁ የም​ት​ቃ​ኑና የም​ት​ከ​ራ​ከሩ ከሆነ ግን ሥጋ​ው​ያን መሆ​ና​ችሁ አይ​ደ​ለ​ምን? እንደ ሰው ልማ​ድስ የም​ት​ኖሩ መሆ​ና​ችሁ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="4">ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ፥ “እኔ የጳ​ው​ሎስ ነኝ” የሚል አለና፤ ሌላ​ውም፥ “እኔ የአ​ጵ​ሎስ ነኝ” ቢል እና​ንተ ሥጋ​ው​ያን መሆ​ና​ችሁ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="5">እን​ግ​ዲህ ጳው​ሎስ ምን​ድን ነው? አጵ​ሎ​ስስ ምን​ድን ነው? እነ​ር​ሱስ በቃ​ላ​ቸው የአ​መ​ና​ችሁ አገ​ል​ጋ​ዮች ናቸው፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰጠው ነው።</verse>
				<verse number="6">እኔ ተከ​ልሁ፤ አጵ​ሎ​ስም አጠጣ፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​ደገ።</verse>
				<verse number="7">አሁ​ንም የሚ​ተ​ክ​ልም ቢሆን፥ የሚ​ያ​ጠ​ጣም ቢሆን የሚ​ጠ​ቅ​መው ነገር የለም፤ የሚ​ያ​ሳ​ድግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው እንጂ።</verse>
				<verse number="8">የሚ​ተ​ክ​ልም፥ የሚ​ያ​ጠ​ጣም አንድ ናቸው፤ ሁሉም እንደ ድካ​ማ​ቸው ዋጋ​ቸ​ውን ይቀ​በ​ላሉ።</verse>
				<verse number="9">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ እን​ተ​ባ​በ​ራ​ለ​ንና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋ​ዮች ነንና፤ እና​ን​ተም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕንፃ ናችሁ።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰጠኝ ጸጋ መጠን እንደ ብልህ የጠ​ራ​ቢ​ዎች አለቃ ሆኜ እኔ መሠ​ረት ጣልሁ፤ ሌላ​ውም በእ​ርሱ ላይ ያን​ጻል፤ እያ​ን​ዳ​ንዱ ግን በእ​ርሱ ላይ እን​ዴት እን​ደ​ሚ​ያ​ንጽ ይጠ​ን​ቀቅ።</verse>
				<verse number="11">ነገር ግን ከተ​መ​ሠ​ረ​ተው በቀር ሌላ መሠ​ረት ሊመ​ሠ​ርት የሚ​ችል የለም፤ መሠ​ረ​ቱም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነው።</verse>
				<verse number="12">በዚህ መሠ​ረት ላይ በወ​ር​ቅና በብር፥ በከ​በረ ድን​ጋ​ይና በእ​ን​ጨት፥ በሣ​ርና በአ​ገዳ የሚ​ያ​ንጽ ቢኖ​ርም፥</verse>
				<verse number="13">የእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ሥራ ይገ​ለ​ጻል፤ እሳ​ትም በፈ​ተ​ነው ጊዜ ቀኑ ይገ​ል​ጠ​ዋል፤ የእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱ​ንም ሥራ እሳት ይፈ​ት​ነ​ዋል።</verse>
				<verse number="14">ሥራው ጸንቶ የተ​ገ​ኘ​ለት ሰው ዋጋ​ውን የሚ​ቀ​በል እርሱ ነው።</verse>
				<verse number="15">ሥራው የተ​ቃ​ጠ​ለ​በት ግን ዋጋ​ውን ያጣል፤ እር​ሱም ከእ​ሳት እን​ደ​ሚ​ድን ሰው ይድ​ናል።</verse>
				<verse number="16">እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደስ እንደ ሆና​ችሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ስም በእ​ና​ንተ ላይ አድሮ እን​ደ​ሚ​ኖር አታ​ው​ቁ​ምን?</verse>
				<verse number="17">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ መቅ​ደስ የሚ​ያ​ፈ​ር​ሰ​ውን ግን እር​ሱን ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያፈ​ር​ሰ​ዋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደስ ነውና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደ​ስም እና​ንተ ራሳ​ችሁ ናችሁ፤ እን​ግ​ዲ​ያስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ መቅ​ደስ አታ​ር​ክሱ።</verse>
				<verse number="18">ራሳ​ች​ሁን አታ​ስቱ፤ ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ በዚህ ዓለም ጥበ​በኛ እንደ ሆነ የሚ​ያ​ስብ ሰው ጥበ​በኛ ይሆን ዘንድ ራሱን ዐላ​ዋቂ ያድ​ርግ።</verse>
				<verse number="19">የዚህ ዓለም ጥበብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ድን​ቍ​ርና ነውና፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “ጠቢ​ባ​ንን የሚ​ገ​ታ​ቸው ተን​ኰ​ላ​ቸው ነው።”</verse>
				<verse number="20">ዳግ​መኛ “የጥ​በ​በ​ኞች አሳብ ከንቱ እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያው​ቃል” ብሎ​አል።</verse>
				<verse number="21">ስለ​ዚ​ህም እን​ግ​ዲህ አንዱ ስንኳ በሰው አይ​መካ፤ ሁሉ የእ​ና​ንተ ነውና።</verse>
				<verse number="22">ጳው​ሎ​ስም ቢሆን፥ አጵ​ሎ​ስም ቢሆን፥ ጴጥ​ሮ​ስም ቢሆን፥ ዓለ​ምም ቢሆን፥ ሕይ​ወ​ትም ቢሆን፥ ሞትም ቢሆን፥ ያለ​ውም ቢሆን፥ የሚ​መ​ጣ​ውም ቢሆን ሁሉ የእ​ና​ንተ ነው።</verse>
				<verse number="23">እና​ንተ ግን የክ​ር​ስ​ቶስ ናችሁ፤ ክር​ስ​ቶ​ስም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">እኛ የክ​ር​ስ​ቶስ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ሥ​ጢሩ መጋ​ቢ​ዎች እንደ ሆን ሰው ስለ እኛ እን​ዲህ ያስብ።</verse>
				<verse number="2">እን​ግ​ዲህ በዚህ ከመ​ጋ​ቢ​ዎች እያ​ን​ዳ​ንዱ ቸርና ታማኝ ሆኖ እን​ዲ​ገኝ ይፈ​ለ​ጋል።</verse>
				<verse number="3">ለእ​ኔስ በእ​ና​ንተ ዘንድ መመ​ስ​ገን ውር​ደት ነው፤ ጻድቅ ብት​ሉኝ፥ በመ​ዋቲ ሰው ዘን​ድም ቸር ብላ​ችሁ ብታ​ከ​ብ​ሩኝ እኔ ለራሴ አል​ፈ​ር​ድም።</verse>
				<verse number="4">የሚ​ያ​ጠ​ራ​ጥ​ረ​ኝና ትዝ የሚ​ለኝ ነገር የለም፤ በዚ​ህም ራሴን አላ​መ​ጻ​ድ​ቅም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ረ​ም​ረ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="5">ጊዜው ሳይ​ደ​ርስ ዛሬ ለምን ትመ​ረ​ም​ራ​ላ​ቸሁ? በጨ​ለማ ውስጥ የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም የሚ​ያ​በራ፥ የል​ብን አሳ​ብም የሚ​ገ​ልጥ ጌታ​ችን ይመ​ጣል፤ ያን​ጊዜ ሁሉም ዋጋ​ውን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይቀ​በ​ላል።</verse>
				<verse number="6">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ! እኔም፥ አጵ​ሎ​ስም ብን​ሆን መከራ የተ​ቀ​በ​ል​ነው ስለ እና​ንተ ነው፤ እና​ንተ እን​ድ​ት​ማሩ፥ ከመ​ጻ​ሕ​ፍት ቃልም ወጥ​ታ​ችሁ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ላይ እን​ዳ​ት​ታ​በዩ ነው።</verse>
				<verse number="7">ማን ይመ​ረ​ም​ር​ሃል? የም​ት​ታ​በ​ይስ በም​ን​ድን ነው? ከሌላ ያላ​ገ​ኘ​ኸው አለ​ህን? ያለ​ህ​ንም ከሌላ ካገ​ኘህ እን​ዳ​ላ​ገኘ ለምን ትኮ​ራ​ለህ?</verse>
				<verse number="8">እና​ንተ አሁን ጠግ​ባ​ች​ኋል፤ በል​ጽ​ጋ​ች​ኋ​ልም፤ ያለ​እ​ኛም ፈጽ​ማ​ችሁ ነግ​ሣ​ች​ኋል፤ እኛም ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ድ​ን​ነ​ግሥ ብት​ነ​ግሡ አግ​ባብ በሆነ ነበር።</verse>
				<verse number="9">እኔስ ለሞት ዝግ​ጁ​ዎች እንደ መሆ​ና​ችን እኛን ሐዋ​ር​ያ​ቱን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኋ​ለ​ኞች ያደ​ረ​ገን ይመ​ስ​ለ​ኛል፤ እኛ ለሰ​ዎ​ችም፥ ለአ​ለ​ቆ​ችም፥ ለዓ​ለ​ምም መዘ​ባ​በቻ ሆነ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="10">እኛስ ስለ ክር​ስ​ቶስ ብለን አላ​ዋ​ቂ​ዎች ነን፤ እና​ንተ ግን በክ​ር​ስ​ቶስ ጠቢ​ባን ናችሁ፤ እኛ ደካ​ሞች ነን፤ እና​ንተ ግን ብር​ቱ​ዎች ናችሁ፤ እና​ንተ ክቡ​ራን ናችሁ፤ እኛ ግን የተ​ዋ​ረ​ድን ነን።</verse>
				<verse number="11">እኛ እስ​ከ​ዚች ቀን ድረስ እን​ራ​ባ​ለን፤ እን​ጠ​ማ​ለን፤ እን​ራ​ቈ​ታ​ለን፤ እን​ሰ​ደ​ዳ​ለን፤ ማረ​ፊ​ያም የለ​ንም፤ እን​ደ​በ​ደ​ባ​ለ​ንም።</verse>
				<verse number="12">በእ​ጃ​ችን ሥራ እያ​ገ​ለ​ገ​ልን እን​ደ​ክ​ማ​ለን፤ ይረ​ግ​ሙ​ናል፤ እኛ ግን እን​መ​ር​ቃ​ቸ​ዋ​ለን፤ ያሳ​ድ​ዱ​ናል፤ እኛ ግን እን​ጸ​ል​ይ​ላ​ቸ​ዋ​ለን፤ እን​ታ​ገ​ሣ​ቸ​ዋ​ለ​ንም።</verse>
				<verse number="13">ይሰ​ድ​ቡ​ናል፥ እን​ማ​ል​ዳ​ቸ​ዋ​ለን፤ በዓ​ለም እንደ ጊጤ ሆን፤ በሁ​ሉም ዘንድ የተ​ና​ቅን ሆን።</verse>
				<verse number="14">ይህ​ንም የጻ​ፍ​ሁ​ላ​ችሁ ላሳ​ፍ​ራ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ ልጆ​ችና ወዳ​ጆች እንደ መሆ​ና​ችሁ ልመ​ክ​ራ​ች​ሁና ላስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ነው እንጂ፤ እኔ ለሁ​ላ​ችሁ ቤዛ​ችሁ ነኝ፤ እና​ንተ ግን አላ​ፈ​ራ​ች​ሁ​ኝም።</verse>
				<verse number="15">በክ​ር​ስ​ቶስ ብዙ መም​ህ​ራን ቢኖ​ሩ​አ​ች​ሁም አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ብዙ​ዎች አይ​ደ​ሉም፤ እኔ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በት​ም​ህ​ርት ወል​ጄ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="16">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ! እኔን እን​ድ​ት​መ​ስሉ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="17">ስለ​ዚ​ህም በየ​ስ​ፍ​ራው በአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ እን​ዳ​ስ​ተ​ማ​ርሁ በክ​ር​ስ​ቶስ ኢየ​ሱስ የሄ​ድ​ሁ​በ​ትን መን​ገድ ይገ​ል​ጥ​ላ​ችሁ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መ​ነና ልጄ ወዳጄ የሆነ ጢሞ​ቴ​ዎ​ስን ልኬ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="18">እነሆ፥ ወደ እና​ንተ ስላ​ል​መ​ጣሁ ከእ​ና​ንተ ወገን የታ​በዩ ሰዎች አሉ።</verse>
				<verse number="19">እን​ኪ​ያስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢፈ​ቅድ ፈጥኜ እመ​ጣ​ለሁ፤ ነገር ግን የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችን ነገር አል​ሻም፤ ኀይ​ላ​ቸ​ውን እሻ​ለሁ እንጂ።</verse>
				<verse number="20">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት በኀ​ይል እንጂ በቃል አይ​ደ​ለ​ምና።</verse>
				<verse number="21">እን​ዴት ሆኜ ወደ እና​ንተ ልመጣ ትወ​ዳ​ላ​ችሁ? በበ​ትር ነውን? ወይስ በፍ​ቅ​ርና በቅ​ን​ነት መን​ፈስ?</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">በእ​ና​ንተ ላይ ዝሙት ይሰ​ማል፤ እን​ደ​ዚህ ያለው ዝሙ​ትም አረ​ማ​ው​ያን እንኳ የማ​ያ​ደ​ር​ጉት ነው፤ ያባ​ቱን ሚስት ያገባ አለና።</verse>
				<verse number="2">እና​ን​ተም ከዚህ ጋር ትዕ​ቢ​ተ​ኞች ናችሁ፤ ይል​ቁ​ንም ይህን ያደ​ረ​ገው ከእ​ና​ንተ ይለይ ዘንድ ለምን አላ​ዘ​ና​ች​ሁ​በ​ትም?</verse>
				<verse number="3">እኔ በሥ​ጋዬ ከእ​ና​ንተ ጋር ባል​ኖር፥ በመ​ን​ፈሴ ከእ​ና​ንተ ጋር አለሁ፤ እነሆ፥ ከእ​ና​ንተ ጋር እንደ አለሁ ሆኜ፥ ይህን ሥራ የሠ​ራ​ውን እፈ​ር​ድ​በ​ታ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ፥ በእኔ ሥል​ጣን፥ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱ​ስም ኀይል፥</verse>
				<verse number="5">ሥጋ​ውን ጎድቶ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ቀን ነፍሱ ትድን ዘንድ እን​ዲህ ያለ​ውን ሰው ለሰ​ይ​ጣን አሳ​ል​ፋ​ችሁ ስጡት።</verse>
				<verse number="6">እን​ግ​ዲ​ያስ መታ​በ​ያ​ችሁ መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ ጥቂቱ እርሾ ብዙ​ውን ሊጥ እን​ደ​ሚ​ያ​መጥ አታ​ው​ቁ​ምን?</verse>
				<verse number="7">እን​ግ​ዲህ ለአ​ዲስ ቡሆ ትሆኑ ዘንድ አሮ​ጌ​ውን እርሾ ከእ​ና​ንተ አርቁ፤ ገና ቂጣ ናች​ሁና፤ ፋሲ​ካ​ችን ክር​ስ​ቶስ ተሠ​ውቶ የለ​ምን?</verse>
				<verse number="8">አሁ​ንም በዓ​ላ​ች​ሁን አድ​ርጉ፤ ነገር ግን እው​ነ​ትና ንጽ​ሕና ባለው እርሾ ነው እንጂ በአ​ሮ​ጌው እርሾ፥ በኀ​ጢ​አ​ትና በክ​ፋት እር​ሾም አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="9">ከዘ​ማ​ው​ያን ጋር አንድ እን​ዳ​ት​ሆኑ በዚህ መል​እ​ክት ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="10">የዚህ ዓለም ዝሙት ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ቀማ​ኞ​ችና ዘራ​ፊ​ዎች፥ ጣዖ​ትን የሚ​ያ​መ​ልኩ ደግሞ አሉ፤ ያለ​ዚ​ያስ ከዚህ ዓለም ልት​ለዩ ይገ​ባል።</verse>
				<verse number="11">አሁ​ንም ከወ​ን​ድ​ሞች መካ​ከል ዘማዊ፥ ወይም ገን​ዘ​ብን የሚ​መኝ፥ ወይም ጣዖ​ትን የሚ​ያ​መ​ልክ፥ ወይም ዐመ​ፀኛ፥ ወይም ተራ​ጋሚ፥ ወይም ሰካ​ራም፥ ወይም የሚ​ቀማ ቢኖር እን​ደ​ዚህ ካለ ሰው ጋር አንድ እን​ዳ​ት​ሆኑ ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ፥ እን​ደ​ዚህ ካለው ሰው ጋር መብ​ልም እንኳ አት​ብሉ፤</verse>
				<verse number="12">ምን አግ​ዶኝ፥ በውጭ ባለው ላይ እፈ​ር​ድ​በ​ታ​ለሁ? እና​ን​ተስ በው​ስጥ ከእ​ና​ንተ ጋር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ፈር​ዳ​ችሁ ቅጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">በውጭ ያሉ​ትን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ ይቀ​ጣ​ቸ​ዋ​ልም፤ ክፉ​ውን ከእ​ና​ንተ አርቁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">እን​ግ​ዲህ በሚ​ነ​ቅፉ ሰዎች ዘንድ ልት​ከ​ራ​ከሩ አት​ድ​ፈሩ፤ ከጓ​ደ​ኛው ጋር በዐ​መ​ፀ​ኞች ዘንድ ሊከ​ራ​ከር የሚ​ችል አለን? በደ​ጋ​ጎች ዘንድ አይ​ደ​ለ​ምን? ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ጋር ክር​ክር ያለው ቢኖ​ርም በቅ​ዱ​ሳን ዘንድ ይከ​ራ​ከር፤ በሚ​ነ​ቅ​ፉና በዐ​መ​ፀ​ኞች ዘንድ ግን አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="2">ቅዱ​ሳን ሰውን ሁሉ እን​ደ​ሚ​ዳኙ አታ​ው​ቁ​ምን? እና​ንተ ሰውን ሁሉ የም​ት​ዳኙ ከሆ​ና​ችሁ ይህን ትን​ሹን ነገር ልት​ዳኙ አይ​ገ​ባ​ች​ሁ​ምን?</verse>
				<verse number="3">የዚ​ህ​ንስ ዓለም ዳኝ​ነት ተዉ​ትና በመ​ላ​እ​ክት ስንኳ እን​ድ​ን​ፈ​ርድ አታ​ው​ቁ​ምን?</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን የዚህ ዓለም ክር​ክር ያላ​ቸው ሰዎች ቢኖሩ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን የተ​ሾሙ የበ​ታች ወን​ድ​ሞች ይስ​ሙ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">ይህ​ንም የም​ላ​ችሁ ስዘ​ል​ፋ​ችሁ ነው፤ እን​ግ​ዲህ ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸሁ ወን​ድ​ማ​ማ​ቾ​ችን ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር ማስ​ታ​ረቅ የሚ​ችል ሽማ​ግሌ የለ​ምን?</verse>
				<verse number="6">ነገር ግን ወን​ድም ከወ​ን​ድሙ ጋር ይካ​ሰ​ሳል፤ ይህም በማ​ያ​ምኑ ፊት ይደ​ረ​ጋል።</verse>
				<verse number="7">እን​ግ​ዲህ ፀብና ክር​ክር ካላ​ችሁ፥ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ጀምሮ ውር​ደት እን​ደ​ሚ​ሆ​ን​ባ​ችሁ ዕወቁ፤ እን​ግ​ዲ​ያማ እን​ዴት አት​ነ​ጠ​ቁም? እን​ዴ​ትስ አት​ገ​ፉም?</verse>
				<verse number="8">አሁ​ንም ቢሆን፥ እና​ንተ ዐመ​ፀ​ኞ​ችና ቀማ​ኞች ናችሁ፤ እን​ደ​ዚ​ህም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ትበ​ድ​ላ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="9">ዐመ​ፀ​ኞች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት እን​ደ​ማ​ይ​ወ​ርሱ አታ​ው​ቁ​ምን? አያ​ስ​ቱ​አ​ችሁ፤ ሴሰ​ኞች፥ ወይም ጣዖ​ትን የሚ​ያ​መ​ልኩ፥ ወይም አመ​ን​ዝ​ራ​ዎች፥ ወይም ቀላ​ጮች፥ ወይም በወ​ንድ ላይ ዝሙ​ትን የሚ​ሠሩ፥ የሚ​ሠ​ሩ​ባ​ቸ​ውም ቢሆኑ፤</verse>
				<verse number="10">ሌቦች፥ ወይም ቀማ​ኞች፥ ወይም ሰካ​ሮች፥ ወይም ተሳ​ዳ​ቢ​ዎች፥ ወይም ነጣ​ቂ​ዎች፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት አይ​ወ​ር​ሱ​አ​ትም።</verse>
				<verse number="11">እን​ግ​ዲህ እና​ንተ እን​ዲህ ስት​ሆኑ እነ​ማን ናችሁ? ነገር ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም መን​ፈስ ታጥ​ባ​ች​ኋል፤ ተቀ​ድ​ሳ​ች​ኋል፤ ጸድ​ቃ​ች​ኋ​ልም።</verse>
				<verse number="12">በሆ​ነው ሁሉ ላይ ሥል​ጣን አለኝ፤ ግን ሁሉ የሚ​ጠ​ቅ​መኝ አይ​ደ​ለም፤ ሁሉም ይቻ​ለ​ኛል፤ ነገር ግን በእኔ ላይ እን​ዲ​ሠ​ለ​ጥን የማ​ደ​ር​ገው ምንም የለም።</verse>
				<verse number="13">መብል ለሆድ ነው ፤ ሆድም ለመ​ብል ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሁለ​ቱ​ንም ይሽ​ራ​ቸ​ዋል፤ ሥጋ​ች​ሁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው እንጂ ለዝ​ሙት አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሥ​ጋ​ችሁ ነው።</verse>
				<verse number="14">ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ከሙ​ታን ያስ​ነ​ሣው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኛ​ንም በከ​ሃ​ሊ​ነቱ ያስ​ነ​ሣ​ናል።</verse>
				<verse number="15">ሥጋ​ችሁ የክ​ር​ስ​ቶስ አካል እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? እን​ግ​ዲህ የክ​ር​ስ​ቶ​ስን አካል ወስ​ዳ​ችሁ የአ​መ​ን​ዝራ አካል ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ች​ሁን? አይ​ገ​ባም።</verse>
				<verse number="16">ከአ​መ​ን​ዝራ ጋር የተ​ገ​ናኘ ከእ​ር​ስዋ ጋር አንድ አካል እን​ዲ​ሆን አታ​ው​ቁ​ምን? መጽ​ሐፍ፥ “ሁለቱ አንድ አካል ይሆ​ናሉ” ብሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="17">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር የተ​ዋ​ሐደ ግን ከእ​ርሱ ጋር አንድ መን​ፈስ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="18">ከዝ​ሙት ራቁ፤ ኀጢ​አት የሚ​ሠራ ሰው ሁሉ ከሥ​ጋው ውጭ ይሠ​ራ​ልና፤ ዝሙ​ትን የሚ​ሠራ ግን ራሱ በሥ​ጋው ላይ ኀጢ​አ​ትን ይሠ​ራል።</verse>
				<verse number="19">ሥጋ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁት በእ​ና​ንተ አድሮ ላለ ለመ​ን​ፈስ ቅዱስ ቤተ መቅ​ደስ እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? ለራ​ሳ​ች​ሁም አይ​ደ​ላ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="20">በዋጋ ተገ​ዝ​ታ​ች​ኋ​ልና፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በሥ​ጋ​ችሁ አክ​ብ​ሩት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">ስለ ጻፋ​ች​ሁ​ል​ኝስ ለሰው ወደ ሴት አለ​መ​ቅ​ረብ ይሻ​ለ​ዋል።</verse>
				<verse number="2">ነገር ግን እን​ዳ​ት​ሴ​ስኑ ሰው ሁሉ በሚ​ስቱ ይወ​ሰን፤ ሴትም ሁላ በባ​ልዋ ትወ​ሰን።</verse>
				<verse number="3">ለሚ​ስ​ትም ባልዋ የሚ​ገ​ባ​ትን ያድ​ር​ግ​ላት፤ እን​ዲሁ ሚስ​ትም ለባ​ልዋ የሚ​ገ​ባ​ውን ታድ​ር​ግ​ለት።</verse>
				<verse number="4">ሚስት በራ​ስዋ አካል ሥል​ጣን የላ​ትም፤ ሥል​ጣን ለባ​ልዋ ነው እንጂ፤ እን​ዲ​ሁም ባል በራሱ አካል ሥል​ጣን የለ​ውም፤ ሥል​ጣን ለሚ​ስቱ ነው እንጂ።</verse>
				<verse number="5">ለጸ​ሎት እን​ድ​ት​ተጉ ከም​ት​ስ​ማ​ሙ​በት ጊዜ ብቻ በቀር፥ ባልና ሚስት አት​ለ​ያዩ፤ ዳግ​መኛ ሰይ​ጣን ድል እን​ዳ​ያ​ደ​ር​ጋ​ችሁ በአ​ን​ድ​ነት ኑሩ፤ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ደካማ ነውና ።</verse>
				<verse number="6">ይህ​ንም የም​ላ​ችሁ እንደ ፈቃድ ነው እንጂ፥ ላዝ​ዛ​ችሁ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="7">ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆን እወ​ዳ​ለ​ሁና፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አደ​ለው ጸጋ ይኑር፤ ግብሩ እን​ዲህ የሆነ አለና፤ ግብሩ ሌላ የሆ​ነም አለና።</verse>
				<verse number="8">ነገር ግን ያላ​ገ​ቡ​ት​ንና አግ​ብ​ተው የፈ​ቱ​ትን እንደ እኔ ሆነው ቢኖሩ ይሻ​ላ​ቸ​ዋል እላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">መታ​ገሥ ባይ​ችሉ ግን ያግቡ፤ በፍ​ት​ወት ከመ​ቃ​ጠል ማግ​ባት ይሻ​ላ​ልና።</verse>
				<verse number="10">ያገ​ቡ​ት​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ አዝ​ዛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በራሴ ትእ​ዛ​ዝም አይ​ደ​ለም፤ ሚስ​ትም ከባ​ልዋ አት​ፋታ።</verse>
				<verse number="11">ከተ​ፋ​ታ​ችም ብቻ​ዋን ትኑር፤ ያለ​ዚያ ከባ​ልዋ ጋር ትታ​ረቅ፤ ባልም ሚስ​ቱን አይ​ፍታ።</verse>
				<verse number="12">ሌላ​ውን ግን ከራሴ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ከጌ​ታ​ች​ንም አይ​ደ​ለም፤ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን መካ​ከል የማ​ታ​ምን፥ ባል​ዋ​ንም የም​ታ​ፈ​ቅር ከእ​ር​ሱም ጋር ለመ​ኖር የም​ት​ወድ ሚስት ያለ​ችው ሰው ቢኖር ሚስ​ቱን አይ​ፍታ።</verse>
				<verse number="13">ሴቲ​ቱም የማ​ያ​ም​ንና ሚስ​ቱ​ንም የሚ​ያ​ፈ​ቅር ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ሊኖር የሚ​ወድ ባል ቢኖ​ራት ባል​ዋን አት​ፍታ።</verse>
				<verse number="14">የማ​ያ​ምን ባል በሚ​ስቱ ይቀ​ደ​ሳ​ልና፤ የማ​ታ​ምን ሚስ​ትም በባ​ልዋ ትቀ​ደ​ሳ​ለ​ችና፤ ያለ​ዚ​ያማ ልጆ​ቻ​ቸው ርኩ​ሳን ይሆ​ናሉ፤ አሁን ግን ቅዱ​ሳን ናቸው።</verse>
				<verse number="15">የማ​ያ​ምን ግን ቢፈታ ይፍታ፤ ወን​ድ​ምና እኅት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰ​ላም ስለ ጠራ​ቸው እን​ደ​ዚህ ላለ ግብር አይ​ገ​ዙ​ምና።</verse>
				<verse number="16">ሚስ​ትም ባል​ዋን ታድ​ነው እንደ ሆነ አታ​ው​ቅ​ምና፤ ባልም ሚስ​ቱን ያድ​ናት እንደ ሆነ አያ​ው​ቅ​ምና።</verse>
				<verse number="17">ነገር ግን ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አደ​ለው፥ ሁሉም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ጠራው እን​ዲሁ ይኑር፤ ለአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ና​ትም ሁሉ እን​ዲህ ሥር​ዐት እን​ሠ​ራ​ለን።</verse>
				<verse number="18">ተገ​ዝሮ ሳለ የተ​ጠራ ቢኖር አለ​መ​ገ​ዘ​ርን አይ​መኝ፤ ያል​ተ​ገ​ዘ​ረም ቢጠራ ከዚያ ወዲያ አይ​ገ​ዘር።</verse>
				<verse number="19">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ መጠ​በቅ ነው እንጂ መገ​ዘ​ርም አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም አይ​ጎ​ዳም።</verse>
				<verse number="20">ሁሉ እንደ ተጠራ እን​ዲሁ ይኑር።</verse>
				<verse number="21">አንተ ባርያ ሳለህ ብታ​ምን አያ​ሳ​ዝ​ንህ፤ የሚ​ቻ​ልህ ከሆነ ግን ነጻ​ነ​ት​ህን አግኝ።</verse>
				<verse number="22">የተ​ጠራ ባሪያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነጻ​ነት ያለው ነውና፤ እን​ዲሁ ነጻ​ነት ያለ​ውም ከተ​ጠራ የክ​ር​ስ​ቶስ ባርያ ነው።</verse>
				<verse number="23">በዋጋ ገዝ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና የሰው ተገ​ዦች አት​ሁኑ።</verse>
				<verse number="24">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሁላ​ች​ሁም በተ​ጠ​ራ​ች​ሁ​በት እን​ዲሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኑሩ።</verse>
				<verse number="25">ስለ ደና​ግ​ልም የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ አይ​ደ​ለም፤ ታማኝ እን​ድ​ሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ያለኝ እንደ መሆኔ ምክ​ሬን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ።</verse>
				<verse number="26">ነገር ግን እን​ዲህ ይመ​ስ​ለ​ኛል፤ በግድ ይህ ሊመ​ረጥ ይሻ​ላ​ልና እን​ዲህ ሆኖ ቢኖር ለሰው ይሻ​ለ​ዋል።</verse>
				<verse number="27">ከሚ​ስ​ትህ ጋር ሳለህ ከእ​ር​ስዋ መፋ​ታ​ትን አትሻ፤ ሚስት ከሌ​ለህ ግን ሚስ​ትን አትሻ።</verse>
				<verse number="28">ብታ​ገ​ባም ኀጢ​አት አይ​ሆ​ን​ብ​ህም፤ ድን​ግ​ሊ​ቱም ባል ብታ​ገባ ኀጢ​አት አይ​ሆ​ን​ባ​ትም፤ ያገቡ ግን ለራ​ሳ​ቸው ድካ​ምን ይሻሉ፤ እኔም ይህን የም​ላ​ችሁ ስለ​ማ​ዝ​ን​ላ​ችሁ ነው።</verse>
				<verse number="29">ነገር ግን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን እን​ዲህ ይቀ​ናል፤ የዚህ ዓለም ኑሮ ሁሉ ሊያ​ልፍ ቀር​ቦ​አ​ልና፤ አሁ​ንም ያገቡ እን​ዳ​ላ​ገቡ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="30">ያለ​ቀሱ እን​ዳ​ላ​ለ​ቀሱ ይሆ​ናሉ፤ ደስ ያላ​ቸ​ውም ደስ እን​ዳ​ላ​ላ​ቸው ይሆ​ናሉ፤ የሸ​ጡም እን​ዳ​ል​ሸጡ ይሆ​ናሉ፤ የገ​ዙም እን​ዳ​ል​ገዙ ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="31">የበሉ እን​ዳ​ል​በሉ ይሆ​ናሉ፤ የጠ​ጡም እን​ዳ​ል​ጠጡ ይሆ​ናሉ፤ የዚህ ዓለም ተድላ ሁሉ ያል​ፋ​ልና።</verse>
				<verse number="32">እኔስ ያለ አሳብ ልት​ኖሩ እወ​ዳ​ለሁ፤ ያላ​ገባ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ ሊያ​ሰ​ኘው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ነገር ያስ​ባ​ልና።</verse>
				<verse number="33">ያገባ ግን ሚስ​ቱን ደስ ሊያ​ሰኝ የዚ​ህን ዓለም ኑሮ ያስ​ባል።</verse>
				<verse number="34">እን​ዲህ ከሆነ ግን ተለ​ያየ፤ አግ​ብታ የፈ​ታች ሴትም ያላ​ገ​ባች ድን​ግ​ልም ብት​ሆን ነፍ​ስ​ዋም ሥጋ​ዋም ይቀ​ደስ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታስ​በ​ዋ​ለች፤ ያገ​ባች ግን ባል​ዋን ደስ ልታ​ሰኝ የዚ​ህን ዓለም ኑሮ ታስ​ባ​ለች።</verse>
				<verse number="35">ይህ​ንም የም​ላ​ችሁ እን​ዲ​ጠ​ቅ​ማ​ችሁ ነው፤ ላጠ​ም​ዳ​ችሁ ግን አይ​ደ​ለም፤ ኑሮ​አ​ችሁ አንድ ወገን እን​ዲ​ሆ​ንና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያለ​መ​ጠ​ራ​ጠር እን​ድ​ታ​ገ​ለ​ግ​ሉት ነው እንጂ።</verse>
				<verse number="36">በሸ​መ​ገለ ጊዜ ስለ ድን​ግ​ል​ናው እን​ደ​ሚ​ያ​ፍር የሚ​ያ​ስብ ሰው ቢኖር እን​ዲህ ሊሆን ይገ​ባል፤ የወ​ደ​ደ​ውን ያድ​ርግ፤ ቢያ​ገ​ባም ኀጢ​አት የለ​በ​ትም።</verse>
				<verse number="37">በልቡ የቈ​ረ​ጠና ያላ​ወ​ላ​ወለ ግን የወ​ደ​ደ​ውን ሊያ​ደ​ርግ ይች​ላል፤ ግድም አይ​በ​ሉት፤ ድን​ግ​ል​ና​ው​ንም ይጠ​ብቅ ዘንድ በልቡ ቢጸና መል​ካም አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="38">ድን​ግ​ሊ​ቱን ያገባ መል​ካም አደ​ረገ፤ ያላ​ገባ ግን የም​ት​ሻ​ለ​ውን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="39">ሴት ባልዋ በሕ​ይ​ወት ሳለ የታ​ሠ​ረች ናት፤ ባልዋ የሞተ እንደ ሆነ ግን ነጻ ናት፤ የወ​ደ​ደ​ች​ውን ታግባ፤ ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁን።</verse>
				<verse number="40">በም​ክሬ ጸንታ እን​ዲሁ ብት​ኖር ግን ብፅ​ዕት ናት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእኔ ላይ ያለ ይመ​ስ​ለ​ኛል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">ለጣ​ዖ​ታት ስለ​ሚ​ሠዉ መሥ​ዋ​ዕ​ቶች ሁላ​ች​ንም ዕው​ቀት እን​ዳ​ለን እና​ው​ቃ​ለን፤ ዕው​ቀት ያስ​ታ​ብ​ያል፤ ፍቅር ግን ያን​ጻል።</verse>
				<verse number="2">ዐወ​ቅሁ የሚል ቢኖር፥ ሊያ​ውቅ የሚ​ገ​ባ​ውን ገና አላ​ወ​ቀም።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ወድ ሰው ግን እርሱ በእ​ርሱ ዘንድ በእ​ው​ነት የታ​ወቀ ነው።</verse>
				<verse number="4">ለጣ​ዖ​ታት የተ​ሠ​ዋ​ውን ስለ​መ​ብ​ላት ግን ጣዖት ሁሉ በዓ​ለም ከንቱ እን​ደ​ሆነ፥ ከአ​ንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ እና​ው​ቃ​ለን።</verse>
				<verse number="5">አማ​ል​ክት የሚ​ሉ​አ​ቸው ነገ​ሮች አሉና፤ በሰ​ማ​ይም ቢሆን፥ በም​ድ​ርም ቢሆን፥ ብዙ አማ​ል​ክ​ትና ብዙ ጌቶች ቢኖሩ፥</verse>
				<verse number="6">ለእ​ኛስ ሁሉ ከእ​ርሱ የሆነ፥ እኛም ለእ​ርሱ የሆን አንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ አለን፤ ሁሉ በእ​ርሱ የሆነ፥ እኛም በእ​ርሱ የሆን አንድ ጌታ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም አለን።</verse>
				<verse number="7">ነገር ግን ሁሉ የሚ​ያ​ው​ቀው አይ​ደ​ለም፤ እስከ ዛሬ በጣ​ዖ​ታት ልማድ፥ ለጣ​ዖት የተ​ሠ​ዋ​ውን የሚ​በሉ አሉ፤ ኅሊ​ና​ቸ​ውም ደካማ ስለ​ሆነ ይረ​ክ​ሳል።</verse>
				<verse number="8">መብል ግን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አያ​ደ​ር​ሰ​ንም፤ ብን​በ​ላም አይ​ረ​ባ​ንም፤ ባን​በ​ላም አይ​ጎ​ዳ​ንም።</verse>
				<verse number="9">ነገር ግን እና​ን​ተን በማ​የት ሌላው እን​ዳ​ይ​ሰ​ና​ከል ተጠ​ን​ቀቁ።</verse>
				<verse number="10">አንተ አማኙ በጣ​ዖት ቤት በማ​ዕድ ተቀ​ም​ጠህ ያየህ ቢኖር ያ ልቡ ደካማ የሆነ ሰው ወዲ​ያው ለጣ​ዖት የተ​ሠ​ዋ​ውን ደፍሮ ይበ​ላል።</verse>
				<verse number="11">ክር​ስ​ቶስ ስለ እርሱ የሞ​ተ​ለት ያ ደካማ ወን​ድም አን​ተን በማ​የት ይጎ​ዳል።</verse>
				<verse number="12">በባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ችሁ ላይ እን​ዲህ የም​ት​በ​ድሉ ከሆነ ደካማ ሕሊ​ና​ቸ​ው​ንም የም​ታ​ቈ​ስሉ ከሆነ ክር​ስ​ቶ​ስን ትበ​ድ​ላ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="13">ነገር ግን በመ​ብል ምክ​ን​ያት ወን​ድሜ የሚ​ሰ​ና​ከል ከሆነ ወን​ድ​ሜን እን​ዳ​ላ​ሰ​ና​ክል ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥጋን አል​በ​ላም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">እኔ ነጻ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ሐዋ​ር​ያስ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ያየሁ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? እና​ን​ተስ በጌ​ታ​ችን ሥራዬ አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን?</verse>
				<verse number="2">ለሌ​ሎች ሐዋ​ር​ያ​ቸው ባል​ሆ​ንም ለእ​ና​ን​ተስ ሐዋ​ር​ያ​ችሁ እኔ ነኝ፤ በጌ​ታ​ችን የሐ​ዋ​ር​ያ​ነቴ ማኅ​ተም እና​ንተ ናች​ሁና።</verse>
				<verse number="3">ለሚ​ከ​ራ​ከ​ሩኝ መልሴ እን​ዲህ ነው።</verse>
				<verse number="4">በውኑ ልን​በ​ላና ልን​ጠጣ አይ​ገ​ባ​ን​ምን?</verse>
				<verse number="5">እንደ ሌሎች ሐዋ​ር​ያት ሁሉና፥ እንደ ጌታ​ችን ወን​ድ​ሞች እንደ ኬፋም ከሴ​ቶች እኅ​ታ​ች​ንን ይዘን ልን​ዞር አይ​ገ​ባ​ን​ምን?</verse>
				<verse number="6">ወይስ ሥራን ለመ​ተው መብት የሌ​ለን እኔና በር​ና​ባስ ብቻ ነን?</verse>
				<verse number="7">የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ልም ምግ​ቡን ያገኝ ዘንድ ነው፤ ወይን ተክሎ ፍሬ​ውን የማ​ይ​በላ ማን ነው? መን​ጋ​ው​ንስ ጠብቆ ወተ​ቱን የማ​ይ​ጠጣ ማን ነው?</verse>
				<verse number="8">በውኑ ለሰው ይም​ሰል እና​ገ​ራ​ለ​ሁን? የሙሴ መጽ​ሐፍ ኦሪ​ትስ እን​ዲህ ብሎ የለ​ምን፦</verse>
				<verse number="9">“እህ​ል​ህን በም​ታ​በ​ራ​ይ​በት ጊዜ የበ​ሬ​ውን አፉን አት​ሰ​ረው።” እን​ግ​ዲህ ይህን የጻፈ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሬ አሳ​ዝ​ኖት ነውን?</verse>
				<verse number="10">ይህን የሚ​ለው ፈጽሞ ስለ እኛ አይ​ደ​ለ​ምን? የሚ​ያ​ርስ በተ​ስፋ ሊያ​ርስ፥ የሚ​ያ​በ​ራ​ይም እን​ዲ​ካ​ፈል በተ​ስፋ ሊያ​በ​ራይ ስለ​ሚ​ገ​ባው በእ​ው​ነት ስለ እኛ ተጽ​ፎ​አል።</verse>
				<verse number="11">እኛ መን​ፈ​ሳ​ዊ​ውን ነገር ከዘ​ራ​ን​ላ​ችሁ ሥጋ​ዊ​ውን ነገር ብና​ጭድ ታላቅ ነገር ነውን?</verse>
				<verse number="12">በእኛ ሹመት ሌላ የሚ​ቀ​ድ​መን ከሆነ የሚ​ሻ​ላ​ች​ሁን እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ እኔ ይህን አል​ፈ​ለ​ግ​ሁ​ትም፤ ነገር ግን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ትም​ህ​ርት እን​ዳ​ላ​ሰ​ና​ክል በሁሉ እታ​ገ​ሣ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">የጣ​ዖ​ታቱ ካህ​ናት የጣ​ዖ​ታ​ቱን መባ እን​ደ​ሚ​በሉ አታ​ው​ቁ​ምን? መሠ​ዊ​ያ​ውን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉም መሥ​ዋ​ዕ​ቱን እን​ደ​ሚ​ካ​ፈሉ አታ​ው​ቁ​ምን? ለቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሹሞች መተ​ዳ​ደ​ሪ​ያ​ቸው የቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ ነው።</verse>
				<verse number="14">ጌታ​ች​ንም እን​ዲሁ ወን​ጌ​ልን ለሚ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ሰዎች ለሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው መተ​ዳ​ደ​ሪያ በዚ​ያው ወን​ጌ​ልን በማ​ስ​ተ​ማር ይሆን ዘንድ አዘዘ።</verse>
				<verse number="15">እኔ ግን ይህ​ንም ቢሆን አል​ፈ​ቀ​ድ​ሁ​ትም፤ ይህን የጻ​ፍ​ሁም ይህን እን​ዳ​ገኝ ብዬ አይ​ደ​ለም፤ እኔ ግን ምስ​ጋ​ናዬ ከሚ​ቀ​ር​ብኝ ሞት ይሻ​ለ​ኛል።</verse>
				<verse number="16">ወን​ጌ​ልን ባስ​ተ​ም​ርም መመ​ስ​ገን አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ታዝዤ አድ​ር​ጌ​ዋ​ለ​ሁና፤ ወን​ጌ​ልን ባላ​ስ​ተ​ምር ደግሞ ወዮ​ልኝ።</verse>
				<verse number="17">ይህ​ንስ በፈ​ቃዴ አድ​ር​ጌው ብሆን ዋጋ​ዬን ባገ​ኘሁ ነበር፤ በግድ ከሆነ ግን በተ​ሰ​ጠኝ መጋ​ቢ​ነት አገ​ለ​ገ​ልሁ።</verse>
				<verse number="18">እን​ግ​ዲህ ዋጋዬ ምን​ድን ነው? ወን​ጌ​ልን ባስ​ተ​ም​ርም በሹ​መቴ የማ​ገ​ኘው ሳይ​ኖር ወን​ጌ​ልን ያለ ዋጋ እን​ዳ​ስ​ተ​ምር ባደ​ርግ ነው።</verse>
				<verse number="19">እኔ ከሁሉ ይልቅ ነጻ ስሆን ብዙ​ዎ​ችን ወደ ሃይ​ማ​ኖት እሰ​በ​ስ​ባ​ቸው ዘንድ እንደ ባሪያ ራሴን ለሁሉ አስ​ገ​ዛሁ።</verse>
				<verse number="20">አይ​ሁ​ድን እጠ​ቅ​ማ​ቸው ዘንድ ለአ​ይ​ሁድ እንደ አይ​ሁ​ዳዊ ሆን​ሁ​ላ​ቸው፤ ከኦ​ሪት በታች ያሉ​ትን እጠ​ቅም ዘንድ እኔ ራሴ ከኦ​ሪት በታች ሳል​ሆን ከኦ​ሪት በታች ላሉት ከኦ​ሪት በታች እን​ዳለ ሰው ሆን​ሁ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ የዘ​ነ​ጋሁ ሳል​ሆን፥ በክ​ር​ስ​ቶስ ሕግም ሳለሁ ሕግ የሌ​ላ​ቸ​ውን እጠ​ቅ​ማ​ቸው ዘንድ ሕግ ለሌ​ላ​ቸው ሕግ እን​ደ​ሌ​ለው ሆን​ሁ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="22">ደካ​ሞ​ች​ንም እጠ​ቅ​ማ​ቸው ዘንድ ለደ​ካ​ሞች እንደ ደካማ ሆን​ሁ​ላ​ቸው፤ በሁሉ መን​ገድ አን​ዳ​ን​ዶ​ቹን አድን ዘንድ ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነ​ርሱ ሆንሁ።</verse>
				<verse number="23">በወ​ን​ጌ​ልም ትም​ህ​ርት አን​ድ​ነት ይኖ​ረኝ ዘንድ ስለ ወን​ጌል ትም​ህ​ርት ሁሉን አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="24">በእ​ሽ​ቅ​ድ​ም​ድም ስፍራ የሚ​ሽ​ቀ​ዳ​ደሙ ሁሉ እን​ደ​ሚ​ፋ​ጠኑ አታ​ው​ቁ​ምን? ለቀ​ደ​መው የሚ​ደ​ረ​ግ​ለት ዋጋ አለ፤ እን​ዲሁ እና​ን​ተም እን​ድ​ታ​ገኙ ፈጽ​ማ​ችሁ ሩጡ።</verse>
				<verse number="25">የሚ​ታ​ገል ሁሉ በሁሉ ነገር ይታ​ገ​ሣል፤ እነ​ር​ሱስ የሚ​ጠ​ፋ​ው​ንና የሚ​ያ​ል​ፈ​ውን የም​ስ​ጋ​ና​ቸ​ውን ዋጋ አክ​ሊል ያገኙ ዘንድ ይበ​ረ​ታሉ፤ እኛ ግን የማ​ያ​ል​ፈ​ውን አክ​ሊል ለማ​ግ​ኘት እን​ታ​ገ​ሣ​ለን።</verse>
				<verse number="26">እኔ ያለ አሳብ እን​ደ​ሚ​ሮጥ ሁሉ እን​ዲሁ አል​ሮ​ጥም፤ ነፋ​ስ​ንም እን​ደ​ሚ​ጐ​ስም ሁሉ እን​ዲሁ አል​ጋ​ደ​ልም።</verse>
				<verse number="27">ነገር ግን ለሌላ ሳስ​ተ​ምር፥ እኔ ለራሴ የተ​ና​ቅሁ እን​ዳ​ል​ሆን ሰው​ነ​ቴን አስ​ጨ​ን​ቃ​ታ​ለሁ፥ ሥጋ​ዬ​ንም አስ​ገ​ዛ​ዋ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ አባ​ቶ​ቻ​ችን ሁሉ ደመና እንደ ጋረ​ዳ​ቸው ሁሉም በባ​ሕር መካ​ከል አል​ፈው እንደ ሄዱ ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">ሁሉ​ንም ሙሴ በደ​መ​ናና በባ​ሕር አጠ​መ​ቃ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ሁሉም ያን መን​ፈ​ሳዊ ምግብ ተመ​ገቡ።</verse>
				<verse number="4">ሁሉም ያን መን​ፈ​ሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ ይኸ​ውም በኋ​ላ​ቸው ከሚ​ሄ​ደው ከመ​ን​ፈ​ሳዊ ዐለት የጠ​ጡት ነው፤ ያም ዐለት ክር​ስ​ቶስ ነበረ።</verse>
				<verse number="5">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ከእ​ነ​ርሱ በሁ​ሉም ደስ አላ​ለ​ውም፤ ብዙ​ዎቹ በም​ድረ በዳ ወድ​ቀ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="6">እነ​ርሱ እንደ ተመኙ እኛ ደግሞ ክፉ እን​ዳ​ን​መኝ እነ​ርሱ ለእኛ ምሳሌ ሆኑ​ልን።</verse>
				<verse number="7">“አሕ​ዛብ ተቀ​መጡ፤ ይበ​ሉና ይጠ​ጡም ጀመር፤ ሊዘ​ፍ​ኑም ተነሡ” ብሎ መጽ​ሐፍ እንደ ተና​ገረ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዳ​ን​ዶቹ እንደ አመ​ለኩ ጣዖ​ትን የም​ታ​መ​ልኩ አት​ሁኑ።</verse>
				<verse number="8">ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዳ​ን​ዶቹ እንደ ሴሰኑ፥ በአ​ንድ ቀንም ሃያ ሦስት ሺህ ሰዎች እንደ ወደቁ አን​ሴ​ስን።</verse>
				<verse number="9">ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዳ​ን​ዶቹ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ ተፈ​ታ​ተ​ኑት፥ ነዘር እባ​ብም እንደ አጠ​ፋ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አን​ፈ​ታ​ተን።</verse>
				<verse number="10">ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዳ​ን​ዶቹ እን​ዳ​ን​ጐ​ራ​ጐ​ሩ​በት፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ትም እን​ደ​ጠፉ አና​ን​ጐ​ራ​ጕር።</verse>
				<verse number="11">እነ​ር​ሱን ያገ​ኛ​ቸው ይህ ሁሉ ነገር በኋላ ዘመን ለም​ን​ነ​ሣው ለእኛ ትም​ህ​ር​ትና ምክር ሊሆ​ነን ምሳሌ ሆኖ ተጻፈ።</verse>
				<verse number="12">አሁ​ንም ያ ቆሜ​አ​ለሁ ብሎ በራሱ የሚ​ታ​መን ሰው እርሱ እን​ዳ​ይ​ወ​ድቅ ይጠ​ን​ቀቅ።</verse>
				<verse number="13">በሰው ላይ እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ሰው ያለ ፈተና ነው እንጂ ሌላ ፈተና አያ​ገ​ኛ​ች​ሁም። በም​ት​ች​ሉት መከራ ነው እንጂ በማ​ት​ች​ሉት መከራ ትፈ​ተኑ ዘንድ ያል​ተ​ዋ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ እር​ሱም ከፈ​ተና ትድኑ ዘንድ በመ​ከራ ጊዜ ይረ​ዳ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="14">ወን​ድ​ሞች! አሁ​ንም ጣዖት ከማ​ም​ለክ ሽሹ።</verse>
				<verse number="15">ለዐ​ዋ​ቂ​ዎች እን​ደ​ሚ​ነ​ገር እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ትክ​ክ​ለ​ኛ​ው​ንም እና​ንተ ራሳ​ችሁ ፍረዱ።</verse>
				<verse number="16">ይህ የም​ን​ባ​ር​ከው የበ​ረ​ከት ጽዋ ከክ​ር​ስ​ቶስ ደም ጋር አንድ አይ​ደ​ለ​ምን? የም​ን​ፈ​ት​ተው ይህስ ኅብ​ስት ከክ​ር​ስ​ቶስ ሥጋ ጋር አንድ አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="17">ኅብ​ስቱ አንድ እንደ ሆነ እን​ዲሁ እኛም ብዙ​ዎች ስን​ሆን አንድ አካል ነን፤ ሁላ​ችን ከአ​ንድ ኅብ​ስት እን​ቀ​በ​ላ​ለ​ንና።</verse>
				<verse number="18">እስ​ራ​ኤል ዘሥ​ጋን ተመ​ል​ከቱ፤ መሥ​ዋ​ዕ​ቱን ይበ​ላሉ፤ ከመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ጋር አንድ ይሆኑ አል​ነ​በ​ረ​ምን?</verse>
				<verse number="19">እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? ለጣ​ዖ​ታት የሚ​ሠዋ መሥ​ዋ​ዕት ከንቱ ነው፤ ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከንቱ ናቸው።</verse>
				<verse number="20">አሕ​ዛ​ብም የሚ​ሠዉ ለአ​ጋ​ን​ንት ነው እንጂ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን የአ​ጋ​ን​ንት ተባ​ባ​ሪ​ዎች እን​ድ​ት​ሆኑ አል​ፈ​ቅ​ድ​ላ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="21">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጽዋና የአ​ጋ​ን​ን​ትን ጽዋ አንድ አድ​ር​ጋ​ችሁ መጠ​ጣት አት​ች​ሉም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማዕ​ድና የአ​ጋ​ን​ን​ት​ንም ማዕድ በአ​ን​ድ​ነት ልት​በሉ አት​ች​ሉም።</verse>
				<verse number="22">እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​ስ​ቀ​ና​ውን? በውኑ እኛ ከእ​ርሱ እን​በ​ረ​ታ​ለን?</verse>
				<verse number="23">ሁሉ ተፈ​ቅ​ዶ​ል​ኛል፤ ነገር ግን ሁሉ የሚ​ጠ​ቅም አይ​ደ​ለም፤ ሁሉ ተፈ​ቅ​ዶ​ል​ኛል፤ ነገር ግን ሁሉ የሚ​ያ​ንጽ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="24">ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ችሁ እንጂ ለራ​ሳ​ችሁ አታ​ድሉ።</verse>
				<verse number="25">ደግ​ሞም በሥጋ ገበያ የሚ​ሸ​ጡ​ትን ሁሉ ከሕ​ሊና የተ​ነሣ ሳት​መ​ራ​መሩ ብሉ።</verse>
				<verse number="26">“ምድር በመ​ላዋ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናትና።”</verse>
				<verse number="27">ያላ​መነ ሰው ቢጠ​ራ​ችሁ፥ ልት​ሄ​ዱም ብት​ወዱ ያቀ​ረ​ቡ​ላ​ች​ሁን ሁሉ ከሕ​ሊና የተ​ነሣ ሳት​መ​ራ​መሩ ብሉ።</verse>
				<verse number="28">እን​ግ​ዲህ “ይህ ለጣ​ዖት የተ​ሠዋ ነው” ያላ​ችሁ ቢኖር ግን፥ ስለ ነገ​ራ​ች​ሁና ባል​ን​ጀ​ራ​ች​ሁም የሚ​ጠ​ራ​ጠር ስለ​ሆነ አት​ብሉ።</verse>
				<verse number="29">ነጻ​ነ​ታ​ች​ሁን እን​ዳ​ይ​ነ​ቅ​ፉ​አት አስ​ረ​ድ​ተ​ዋ​ች​ኋ​ልና።</verse>
				<verse number="30">በጸጋ ብበላ ግን በነ​ገሩ ስለ​ማ​መ​ሰ​ግን ለምን ይነ​ቅ​ፉ​ኛል።</verse>
				<verse number="31">ብት​በ​ሉም፥ ብት​ጠ​ጡም የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር አድ​ር​ጉት።</verse>
				<verse number="32">ለአ​ይ​ሁ​ድም፥ ለአ​ረ​ማ​ው​ያ​ንም፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ያለ ማሰ​ና​ከል አር​አያ ሁኑ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="33">እኔም ሁሉን በሁሉ ነገር ደስ እን​ዳ​ሰኝ ይድኑ ዘንድ የብ​ዙ​ዎ​ችን ተድላ እሻ​ለሁ እንጂ የራ​ሴን ተድላ የምሻ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">እኔ ክር​ስ​ቶ​ስን እን​ደ​ም​መ​ስ​ለው እኔን ምሰሉ።</verse>
				<verse number="2">ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ አመ​ሰ​ግ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ ዘወ​ትር ታስ​ቡ​ኛ​ላ​ች​ሁና፤ ያስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ች​ሁ​ንም ትም​ህ​ርት ጠብ​ቃ​ች​ኋ​ልና።</verse>
				<verse number="3">ነገር ግን የወ​ንድ ሁሉ ራሱ ክር​ስ​ቶስ፥ የሴ​ትም ራስዋ ወንድ፤ የክ​ር​ስ​ቶ​ስም ራሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነ ልታ​ውቁ እወ​ድ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">ራሱን ተከ​ና​ንቦ የሚ​ጸ​ልይ ወይም የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር ወንድ ሁሉ ራሱን ያዋ​ር​ዳል።</verse>
				<verse number="5">ራስ​ዋን ሳት​ከ​ና​ነብ የም​ት​ጸ​ልይ ወይም የም​ታ​ስ​ተ​ምር ሴት ሁላ ራስ​ዋን ታዋ​ር​ዳ​ለች፤ ራስ​ዋን እንደ ተላ​ጨች መሆ​ንዋ ነውና።</verse>
				<verse number="6">ሴት ካል​ተ​ከ​ና​ነ​በች ትላጭ ወይም ጠጕ​ር​ዋን ትቈ​ረጥ፤ ለሴት ጠጕ​ር​ዋን መቈ​ረጥ ወይም መላ​ጨት ውር​ደት ከሆነ ትከ​ና​ነብ።</verse>
				<verse number="7">ወንድ በሚ​ጸ​ል​ይ​በት ጊዜ ሊከ​ና​ነብ አይ​ገ​ባ​ውም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አር​አ​ያ​ውና አም​ሳሉ ነውና፤ ሴትም ለባ​ልዋ ክብር ናት።</verse>
				<verse number="8">ሴት ከወ​ንድ ተገ​ኝ​ታ​ለ​ችና፤ ወንድ ግን ከሴት የተ​ገኘ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="9">ወንድ ስለ ሴት አል​ተ​ፈ​ጠ​ረም፤ ሴት ስለ ወንድ ተፈ​ጠ​ረች እንጂ።</verse>
				<verse number="10">ስለ​ዚ​ህም ሴት ስለ መላ​እ​ክት፥ ሥል​ጣን ለራ​ስዋ ሊሆን ይገ​ባል፤</verse>
				<verse number="11">ነገር ግን አሁን ሴት ከባሏ አት​ለይ፤ ወን​ድም ከሚ​ስቱ አይ​ለይ፤ ሁላ​ች​ሁም በጌ​ታ​ችን ኑሩ።</verse>
				<verse number="12">ሴት ከወ​ንድ እንደ ተገ​ኘች እን​ዲሁ ወንድ ከሴት ተገኘ፤ ነገር ግን ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።</verse>
				<verse number="13">እስኪ እና​ንተ ራሳ​ችሁ ፍረዱ፤ ሴት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ት​ጸ​ል​ይ​በት ጊዜ ልት​ከ​ና​ነብ አይ​ገ​ባ​ምን?</verse>
				<verse number="14">ተፈ​ጥ​ሮ​ዋስ አያ​ስ​ረ​ዳ​ች​ሁ​ምን? ወንድ ግን ጠጕ​ሩን ቢያ​ሳ​ድግ ነውር ነው።</verse>
				<verse number="15">ለሴት ግን ጠጕ​ር​ዋን ብታ​ሳ​ድግ ክብ​ርዋ ነው፤ ለሴት ጠጕ​ርዋ እንደ ቀጸላ ሆኖ ተሰ​ጥ​ቶ​አ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="16">ነገር ግን የሚ​ጠ​ራ​ጠር ቢኖር እኛ ወይም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን እን​ዲህ ያለ ልማድ የለ​ንም።</verse>
				<verse number="17">ይህ​ንም የነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ ላመ​ሰ​ግ​ና​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ በም​ት​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት ጊዜ ወደ ዝቅ​ተኛ እንጂ ወደ​ሚ​ሻል ግብር አት​ሄ​ዱ​ምና።</verse>
				<verse number="18">ከሁሉ አስ​ቀ​ድሞ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በም​ት​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ እን​ደ​ም​ት​ጣ​ሉና እን​ደ​ም​ት​ከ​ራ​ከሩ ሰም​ቻ​ለሁ፤ የማ​ም​ነ​ውም አለኝ።</verse>
				<verse number="19">ከእ​ና​ንተ የተ​መ​ረ​ጡት ወን​ድ​ሞች ተለ​ይ​ተው እን​ዲ​ታ​ወቁ ትለ​ያዩ ዘንድ ግድ ነው።</verse>
				<verse number="20">እን​ግ​ዲህ እና​ን​ተም በም​ት​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት ጊዜ የም​ት​በ​ሉና የም​ት​ጠጡ ለጌ​ታ​ችን ቀን እን​ደ​ሚ​ገባ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="21">ወደ ምግብ ትሽ​ቀ​ዳ​ደ​ማ​ላ​ችሁ፤ የተ​ራቡ በአ​ጠ​ገ​ባ​ችሁ እያሉ እና​ንተ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ትጠ​ግ​ባ​ላ​ችሁ፤ ትሰ​ክ​ራ​ላ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="22">በውኑ የም​ት​በ​ሉ​በ​ትና የም​ት​ጠ​ጡ​በት ቤት የላ​ች​ሁ​ምን? ወይስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ታስ​ነ​ቅ​ፋ​ላ​ች​ሁን? ነዳ​ያ​ን​ንስ ታሳ​ፍ​ሩ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ች​ሁን? ምን እላ​ለሁ? በዚህ አመ​ሰ​ግ​ና​ች​ኋ​ለ​ሁን? አላ​መ​ሰ​ግ​ና​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="23">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተማ​ርሁ አስ​ተ​ም​ሬ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እር​ሱን ራሱን በያ​ዙ​ባት በዚ​ያች ሌሊት ኅብ​ስ​ቱን አነሣ።</verse>
				<verse number="24">አመ​ሰ​ገነ፤ ባረከ፤ ፈተተ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እንኩ ብሉ፤ ስለ እና​ንተ የሚ​ሰ​ጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ዬ​ንም እን​ዲሁ አድ​ርጉ።”</verse>
				<verse number="25">እን​ዲ​ሁም ኅብ​ስ​ቱን ከተ​ቀ​በሉ በኋላ ጽዋ​ውን አን​ሥቶ፥ “አዲስ ሥር​ዐት የሚ​ጸ​ና​በት ይህ ጽዋ ደሜ ነው እን​ዲህ አድ​ርጉ፤ በም​ት​ጠ​ጡ​በ​ትም ጊዜ አስ​ቡኝ” አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="26">ይህን ኅብ​ስት በም​ት​በ​ሉ​በት፥ ይህ​ንም ጽዋ በም​ት​ጠ​ጡ​በት ጊዜ ሁሉ ጌታ​ችን እስ​ከ​ሚ​መ​ጣ​በት ቀን ድረስ ሞቱን ትና​ገ​ራ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="27">አሁ​ንም ሳይ​ገ​ባው ይህን ኅብ​ስት የበላ፥ ይህ​ንም ጽዋ የጠጣ የጌ​ታ​ችን ሥጋ​ውና ደሙ ስለ​ሆነ ዕዳ አለ​በት።</verse>
				<verse number="28">አሁ​ንም ሰው ራሱን መር​ም​ሮና አን​ጽቶ ከዚህ ኅብ​ስት ይብላ፤ ከዚ​ህም ጽዋ ይጠጣ።</verse>
				<verse number="29">ሳይ​ገ​ባው፥ የጌ​ታ​ችን ሥጋም እንደ ሆነ ሳያ​ውቅ፥ ሰው​ነ​ቱ​ንም ሳያ​ነጻ፥ የሚ​በ​ላና የሚ​ጠጣ ለራሱ ፍር​ዱ​ንና መቅ​ሠ​ፍ​ቱን ይበ​ላል፤ ይጠ​ጣ​ልም።</verse>
				<verse number="30">ስለ​ዚህ ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ የደ​ከ​ሙና የታ​መሙ ብዙ​ዎች ናቸው፤ ብዙ​ዎ​ችም በድ​ን​ገት አን​ቀ​ላ​ፍ​ተ​ዋል።</verse>
				<verse number="31">እኛ በራ​ሳ​ችን ብን​ፈ​ርድ ኖሮ ባል​ተ​ፈ​ረ​ደ​ብ​ንም ነበር።</verse>
				<verse number="32">ነገር ግን በተ​ፈ​ረ​ደ​ብን ጊዜ ከዓ​ለም ጋር እን​ዳ​ን​ኰ​ነን በጌታ እን​ገ​ሠ​ጻ​ለን።</verse>
				<verse number="33">አሁ​ንም ወን​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ለምሳ በም​ት​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት ጊዜ እርስ በር​ሳ​ችሁ ተጠ​ባ​በቁ፤</verse>
				<verse number="34">መሰ​ብ​ሰ​ባ​ችሁ ለፍዳ እን​ዳ​ይ​ሆን፥ የተ​ራበ ቢኖር በቤቱ ይብላ፤ አት​ነ​ቃ​ቀ​ፉም፤ ሌላ​ውን ሥር​ዐት ግን መጥቼ እሠ​ራ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ስለ መን​ፈስ ቅዱስ ስጦ​ታም ታውቁ ዘንድ እንጂ አላ​ዋ​ቆች ልት​ሆኑ አን​ወ​ድ​ድም።</verse>
				<verse number="2">ቀድ​ሞም እና​ንተ አሕ​ዛብ በነ​በ​ራ​ችሁ ጊዜ ዲዳ​ዎች ጣዖ​ታ​ትን ታመ​ልኩ እንደ ነበር፥ ጣዖ​ትም በማ​ም​ለክ ረክ​ሳ​ችሁ እንደ ነበር፥ ወደ ወሰ​ዱ​አ​ች​ሁም ትሄዱ እንደ ነበር ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="3">ስለ​ዚ​ህም ማንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ሲና​ገር፥ “ኢየ​ሱስ ውጉዝ ነው” የሚል እን​ደ​ሌለ፥ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ካል​ሆነ በቀር “ኢየ​ሱስ ጌታ ነው” ሊል አን​ድስ እን​ኳን እን​ዳ​ይ​ችል አስ​ታ​ው​ቃ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">መን​ፈስ ቅዱስ አንድ ሲሆን ስጦ​ታው ልዩ ልዩ ነው።</verse>
				<verse number="5">ጌታም አንድ ሲሆን ልዩ ልዩ አገ​ል​ግ​ሎ​ቶች አሉ።</verse>
				<verse number="6">ሁሉን በሁሉ የሚ​ያ​ደ​ርግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አንድ ሲሆን ልዩ ልዩ አሠ​ራር አለ።</verse>
				<verse number="7">ለሁ​ሉም ጌታ እየ​ረዳ በየ​ዕ​ድሉ እን​ደ​ሚ​ገ​ባ​ውና እን​ደ​ሚ​ጠ​ቅ​መው ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ በግ​ልጥ ይሰ​ጠ​ዋል፤</verse>
				<verse number="8">በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የጥ​በብ ቃል የሚ​ሰ​ጠው አለ፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም የዕ​ው​ቀት ቃል የሚ​ሰ​ጠው አለ።</verse>
				<verse number="9">ለአ​ን​ዱም በዚ​ያው መን​ፈስ እም​ነት፥ ለአ​ን​ዱም በአ​ንዱ መን​ፈስ የመ​ፈ​ወስ ስጦታ፥</verse>
				<verse number="10">ለአ​ን​ዱም ተአ​ም​ራ​ትን ማድ​ረግ፥ ለአ​ን​ዱም ትን​ቢ​ትን መና​ገር፥ ለአ​ን​ዱም መና​ፍ​ስ​ትን መለ​የት፥ ለአ​ን​ዱም በልዩ ዓይ​ነት ልሳን መና​ገር፥ ለአ​ን​ዱም በል​ሳ​ኖች የተ​ነ​ገ​ረ​ውን መተ​ር​ጐም ይሰ​ጠ​ዋል።</verse>
				<verse number="11">በዚ​ህም ሁሉ ያው አንዱ መን​ፈስ ቅዱስ ሁሉን ይረ​ዳል፤ ለሁ​ሉም እንደ ወደደ ያድ​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="12">አካል አንድ እንደ ሆነ ብዙ የአ​ካል ክፍ​ሎ​ችም እንደ አሉ​በት፥ ነገር ግን የአ​ካል ክፍ​ሎች ሁሉ ብዙ​ዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ ክር​ስ​ቶስ ደግሞ እን​ዲሁ ነው፤</verse>
				<verse number="13">እኛ ሁላ​ች​ንም በአ​ንድ መን​ፈስ አንድ አካል ለመ​ሆን ተጠ​ም​ቀ​ናል፤ አይ​ሁድ ብን​ሆን፥ አረ​ማ​ው​ያ​ንም ብን​ሆን፥ ባሪ​ያ​ዎ​ችም ብን​ሆን፥ ነጻ​ዎ​ችም ብን​ሆን ሁላ​ችን አንድ መን​ፈስ ጠጥ​ተ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="14">የአ​ካ​ላ​ች​ንም ክፍሉ ብዙ ነው እንጂ አንድ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="15">እግ​ርም፥ “እኔ እጅ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና የአ​ካል ክፍል አይ​ደ​ለ​ሁም” ብትል ይህን በማ​ለቷ የአ​ካል ክፍል መሆ​ንዋ ይቀ​ራ​ልን?</verse>
				<verse number="16">ጆሮም፥ “እኔ ዐይን አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና የአ​ካል ክፍል አይ​ደ​ለ​ሁም” ብትል ይህን በማ​ለቷ የአ​ካል ክፍል መሆ​ንዋ ይቀ​ራ​ልን?</verse>
				<verse number="17">አካል ሁሉ ዐይን ቢሆን ኖሮ መስ​ማት ከየት በተ​ገኘ ነበር፤ አካ​ልስ ሁሉ ጆሮ ቢሆን ኖሮ ማሽ​ተት ከየት በተ​ገኘ ነበር?</verse>
				<verse number="18">አሁን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ካ​ላ​ች​ንን ክፍል በሰ​ው​ነ​ታ​ችን ውስጥ እርሱ እንደ ወደደ እየ​ራሱ አከ​ና​ውኖ መደ​በው።</verse>
				<verse number="19">የአ​ካል ክፍሉ አንድ ቢሆን ኖሮ አካል የት በተ​ገኘ ነበር?</verse>
				<verse number="20">አሁ​ንም የአ​ካል ክፍ​ሎች ብዙ​ዎች ናቸው ፤ አካሉ ግን አንድ ነው።</verse>
				<verse number="21">ዐይን እጅን፥ “አል​ፈ​ል​ግ​ሽም” ልት​ላት አት​ች​ልም፤ ራስም፥ “እግ​ሮ​ችን አል​ፈ​ል​ጋ​ች​ሁም” ልት​ላ​ቸው አት​ች​ልም።</verse>
				<verse number="22">ደካ​ሞች የሚ​መ​ስ​ሉህ የአ​ካል ክፍ​ሎች ይል​ቁን የሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ጉህ ናቸው።</verse>
				<verse number="23">ከአ​ካ​ልም ክፍ​ሎች የተ​ናቁ ለሚ​መ​ስ​ሉን ክብ​ርን እን​ጨ​ም​ር​ላ​ቸ​ዋ​ለን፤ ለም​ና​ፍ​ር​ባ​ቸ​ውም የአ​ካል ክፍ​ሎች ክብር ይጨ​መ​ር​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="24">ለከ​በ​ረው የአ​ካ​ላ​ችን ክፍል ክብ​ርን አን​ሻ​ለ​ትም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሰው​ነ​ታ​ች​ንን አስ​ማ​ም​ቶ​ታል፤ ይል​ቁ​ንም ታና​ሹን የአ​ካል ክፍል አክ​ብ​ሮ​ታል።</verse>
				<verse number="25">የአ​ካ​ላ​ችን ክፍ​ሎች እርስ በር​ሳ​ቸው እን​ዳ​ይ​ለ​ያዩ፥ አካ​ላ​ችን ሳይ​ነ​ጣ​ጠል በክ​ብር እን​ዲ​ተ​ካ​ከል አስ​ማ​ማው።</verse>
				<verse number="26">አንዱ የአ​ካል ክፍል ቢታ​መም ከእ​ርሱ ጋር የአ​ካል ክፍ​ሎች ሁሉ ይታ​መ​ማሉ፤ አንዱ የአ​ካል ክፍል ደስ ቢለ​ውም የአ​ካል ክፍ​ሎች ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ደስ ይላ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="27">እን​ግ​ዲህ እና​ንተ የክ​ር​ስ​ቶስ አካሉ ናችሁ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም የአ​ካሉ ክፍ​ሎች ናችሁ።</verse>
				<verse number="28">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን የሾ​ማ​ቸው አስ​ቀ​ድሞ ሐዋ​ር​ያ​ትን፥ ሁለ​ተ​ኛም ነቢ​ያ​ትን፥ ሦስ​ተ​ኛም መም​ህ​ራ​ንን፥ ከዚ​ህም በኋላ ተአ​ም​ራ​ትና ኀይል ማድ​ረግ የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን፥ ቀጥ​ሎም የመ​ፈ​ወስ ሀብት የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን፥ የመ​ር​ዳ​ትም ሀብት የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን፥ የመ​ም​ራ​ትና ቋን​ቋን የመ​ና​ገር ሀብት የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ነው።</verse>
				<verse number="29">በውኑ ሁሉ ሐዋ​ር​ያ​ትን ይሆ​ና​ሉን? ሁሉስ ነቢ​ያ​ትን ይሆ​ና​ሉን? ሁሉስ መም​ህ​ራ​ንን ይሆ​ና​ሉን? ለሁ​ሉስ ተአ​ም​ራ​ትን የማ​ድ​ረግ ኀይል ይሰ​ጣ​ልን?</verse>
				<verse number="30">ለሁ​ሉስ የመ​ፈ​ወስ ሀብት ይሰ​ጣ​ልን? ሁሉስ በቋ​ንቋ ይና​ገ​ራ​ሉን? ሁሉስ ይተ​ረ​ጕ​ማ​ሉን?</verse>
				<verse number="31">ነገር ግን ለም​ት​በ​ል​ጠው ጸጋ ቅኑ፤ ደግ​ሞም የም​ት​ሻ​ለ​ውን መን​ገድ አስ​ተ​ም​ራ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">የሰ​ውን ሁሉ ቋንቋ ባውቅ፥ የመ​ላ​እ​ክ​ት​ንም ሁሉ ቋንቋ ባውቅ፥ ነገር ግን ፍቅር ከሌ​ለኝ እን​ደ​ሚ​ጮህ ነሐስ፥ ወይም እን​ደ​ሚ​መታ ከበሮ መሆኔ ነው።</verse>
				<verse number="2">ትን​ቢት ብና​ገር፥ የተ​ሰ​ው​ረ​ውን ሁሉ፥ ጥበ​ብ​ንም ሁሉ ባውቅ፥ ተራራ እስከ ማፍ​ለስ የሚ​ያ​ደ​ርስ ፍጹም እም​ነ​ትም ቢኖ​ረኝ ፍቅር ከሌ​ለኝ ከንቱ ነኝ።</verse>
				<verse number="3">ገን​ዘ​ቤን ሁሉ ለም​ጽ​ዋት ብሰጥ፥ ሥጋ​ዬ​ንም ለእ​ሳት መቃ​ጠል ብሰጥ፥ ነገር ግን ፍቅር ከሌ​ለኝ ምንም አይ​ጠ​ቅ​መ​ኝም።</verse>
				<verse number="4">ፍቅር ያስ​ታ​ግ​ሣል፤ ፍቅር ያስ​ተ​ዛ​ዝ​ናል፤ ፍቅር አያ​ቀ​ና​ናም፤ ፍቅር አያ​ስ​መ​ካም፤ ፍቅር ልቡ​ናን አያ​ስ​ታ​ብ​ይም።</verse>
				<verse number="5">ብቻ​ዬን ይድ​ላኝ አያ​ሰ​ኝም፤ አያ​በ​ሳ​ጭም፤ ክፉ ነገ​ር​ንም አያ​ሳ​ስ​ብም።</verse>
				<verse number="6">ጽድ​ቅን በመ​ሥ​ራት ደስ ያሰ​ኛል እንጂ፥ ግፍን በመ​ሥ​ራት ደስ አያ​ሰ​ኝም።</verse>
				<verse number="7">በሁሉ ያቻ​ች​ላል፤ በሁ​ሉም ያስ​ተ​ማ​ም​ናል፤ በሁ​ሉም ተስፋ ያስ​ደ​ር​ጋል፥ በሁ​ሉም ያስ​ታ​ግ​ሣል።</verse>
				<verse number="8">ፍቅር ለዘ​ወ​ትር አይ​ጥ​ልም፤ ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ርም ያል​ፋል፤ ይሻ​ራ​ልም፤ በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚ​ና​ገ​ርም ያል​ፋል፤ ይቀ​ራል፤ የሚ​ራ​ቀ​ቅም ያል​ፋል፤ ይጠ​ፋል።</verse>
				<verse number="9">በየ​ገጹ ጥቂት ጥቂት እና​ው​ቃ​ለ​ንና፤ ጥቂት ጥቂት ትን​ቢ​ትም እን​ና​ገ​ራ​ለ​ንና።</verse>
				<verse number="10">ፍጹም የሆነ ሲመጣ ግን ያ ተከ​ፍሎ የነ​በ​ረው ይሻ​ራል።</verse>
				<verse number="11">እኔ ልጅ በነ​በ​ርሁ ጊዜ እንደ ልጅ እና​ገር ነበር፤ እንደ ልጅም አስብ ነበር፤ እንደ ልጅም እመ​ክር ነበር፤ በአ​ደ​ግሁ ጊዜ ግን የል​ጅ​ነ​ትን ጠባይ ሁሉ ሻርሁ።</verse>
				<verse number="12">አሁን ግን ታወ​ቀኝ፤ በግ​ል​ጥም ተረ​ዳኝ፤ በመ​ስ​ታ​ወ​ትም እን​ደ​ሚ​ያይ ሰው ዛሬ በድ​ን​ግ​ዝ​ግ​ዝታ እና​ያ​ለን፤ ያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እና​ያ​ለን፤ አሁን በከ​ፊል፥ ኋላ ግን እንደ ተገ​ለ​ጠ​ልኝ መጠን ሁሉን አው​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">አሁ​ንም እነ​ዚህ ሦስቱ እም​ነት፥ ተስ​ፋና ፍቅር ጸን​ተው ይኖ​ራሉ፤ ከሁሉ ግን ፍቅር ይበ​ል​ጣል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">ፍቅ​ርን ተከ​ተ​ሏት፤ ለመ​ን​ፈ​ሳዊ ስጦታ፥ ይል​ቁ​ንም ትን​ቢት ለመ​ና​ገር ተፎ​ካ​ከሩ።</verse>
				<verse number="2">በቋ​ንቋ የሚ​ና​ገር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንጂ ለሰው የሚ​ና​ገር አይ​ደ​ለም። የሚ​ና​ገ​ረ​ውን የሚ​ሰ​ማው የለ​ምና፥ ነገር ግን በመ​ን​ፈስ ምሥ​ጢ​ርን ይና​ገ​ራል።</verse>
				<verse number="3">ትን​ቢ​ትን የሚ​ና​ገር ግን ለማ​ነ​ጽና ለመ​ም​ከር፥ ለማ​ረ​ጋ​ጋ​ትም ለሰው ይና​ገ​ራል።</verse>
				<verse number="4">በቋ​ንቋ የሚ​ና​ገር ራሱን ያን​ጻል፤ የሚ​ተ​ረ​ጕም ግን የክ​ር​ስ​ቲ​ያን ማኅ​በ​ርን ያን​ጻል።</verse>
				<verse number="5">ሁላ​ች​ሁም በቋ​ንቋ ልት​ና​ገሩ እወ​ዳ​ለሁ፤ ይል​ቁ​ንም ትን​ቢት ልት​ና​ገሩ እወ​ዳ​ለሁ፤ ሳይ​ተ​ረ​ጕም በቋ​ንቋ ከሚ​ና​ገር ይልቅ ትን​ቢት የሚ​ና​ገር እጅግ ይበ​ል​ጣ​ልና፤ ቢተ​ረ​ጕም ግን ማኅ​በ​ሩን ያን​ጻል።</verse>
				<verse number="6">አሁ​ንም ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ወደ እና​ንተ መጥቼ በማ​ታ​ው​ቁት ቋንቋ ባነ​ጋ​ግ​ራ​ችሁ፥ የጥ​በብ ነገ​ር​ንም ቢሆን፥ የት​ን​ቢ​ት​ንም ነገር ቢሆን፥ የማ​ስ​ተ​ማር ሥራ​ንም ቢሆን ገልጬ ካል​ነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ የም​ጠ​ቅ​ማ​ችሁ ጥቅም ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="7">ነፍስ የሌ​ለው ድምፅ የሚ​ሰጥ እንደ መሰ​ንቆ፥ ወይም እንደ ክራር ያለ መሣ​ሪያ በስ​ልት ካል​ተ​መታ መሰ​ን​ቆው ወይም ክራሩ የሚ​ለ​ውን ማን ያው​ቃል?</verse>
				<verse number="8">መለ​ከት የሚ​ነ​ፋም በታ​ወ​ቀው ስልት ካል​ነፋ ለጦ​ር​ነት ማን ይዘ​ጋ​ጃል?</verse>
				<verse number="9">እን​ዲ​ሁም እና​ንተ በማ​ይ​ታ​ወቅ ቋንቋ ብት​ና​ገሩ፥ ይህ​ን​ኑም ገል​ጣ​ችሁ ባት​ተ​ረ​ጕሙ የም​ት​ሉ​ት​ንና የም​ት​ና​ገ​ሩ​ትን ማን ያው​ቃል? ከነ​ፋስ ጋር እን​ደ​ም​ት​ነ​ጋ​ገሩ ትሆ​ና​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="10">በዓ​ለም ልዩ ልዩ ቋን​ቋ​ዎች አሉ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ትር​ጕም የሌ​ለው አን​ድም የለም።</verse>
				<verse number="11">የቋ​ን​ቋ​ውን ትር​ጓሜ ካላ​ወ​ቅሁ እኔ ለሚ​ያ​ነ​ጋ​ግ​ረኝ እንደ እን​ግዳ እሆ​ን​በ​ታ​ለሁ፤ የሚ​ያ​ነ​ጋ​ግ​ረኝ እር​ሱም ለእኔ እንደ እን​ግዳ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="12">እን​ዲሁ እና​ን​ተም ለመ​ን​ፈስ ቅዱስ ስጦታ ተፎ​ካ​ከሩ፤ ትበ​ዙም ዘንድ ማኅ​በሩ የሚ​ታ​ነ​ጽ​በ​ትን ፈልጉ።</verse>
				<verse number="13">በማ​ያ​ው​ቀው ቋንቋ የሚ​ና​ገር ሰውም መተ​ር​ጐም እን​ዲ​ችል ይጸ​ልይ።</verse>
				<verse number="14">በማ​ላ​ው​ቀው ቋንቋ የም​ጸ​ልይ ከሆ​ንሁ ቃሌ ብቻ ይጸ​ል​ያል፤ ልቤ ግን ባዶ ነው።</verse>
				<verse number="15">እን​ግ​ዲህ ምን አደ​ር​ጋ​ለሁ በመ​ን​ፈስ እጸ​ል​ያ​ለሁ፤ በማ​ስ​ተ​ዋ​ልም እማ​ል​ዳ​ለሁ፤ በመ​ን​ፈሴ እዘ​ም​ራ​ለሁ፤ በማ​ስ​ተ​ዋ​ልም እዘ​ም​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">አንተ በመ​ን​ፈስ ብታ​መ​ሰ​ግን፥ ያ የቆ​መው ያል​ተ​ማ​ረው በአ​ንተ ምስ​ጋና ላይ እን​ዴት አሜን ይላል? የም​ት​ና​ገ​ረ​ው​ንና የም​ት​ጸ​ል​የ​ውን አያ​ው​ቅ​ምና።</verse>
				<verse number="17">እነሆ፥ አን​ተስ መል​ካም ታመ​ሰ​ግ​ና​ለህ፤ ነገር ግን ሌላው እን​ዴት ይታ​ነ​ጻል?</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ፤ ከሁ​ላ​ችሁ ይልቅ እኔ በቋ​ን​ቋ​ዎች እና​ገ​ራ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="19">ነገር ግን ሌሎ​ችን አስ​ተ​ምር ዘንድ፥ በቋ​ንቋ ከሚ​ነ​ገር ብዙ ቃል ይልቅ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በአ​እ​ም​ሮዬ አም​ስት ቃላ​ትን ልና​ገር እሻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በአ​እ​ምሮ እንደ ሕፃ​ናት አት​ሁኑ፤ ነገር ግን ለክፉ ነገር እንደ ሕፃ​ናት ሁኑ፤ በዕ​ው​ቀ​ትም ፍጹ​ማን ሁኑ።</verse>
				<verse number="21">በኦ​ሪ​ትም፥ “ይህን ሕዝብ በሌ​ሎች ቋን​ቋ​ዎ​ችና በሌላ አን​ደ​በት እና​ገ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እን​ዲ​ሁም ሆኖ አይ​ሰ​ሙ​ኝም ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ብሎ​አል።</verse>
				<verse number="22">አሁ​ንም ቋንቋ መና​ገር ለማ​ያ​ምኑ ሰዎች ለም​ል​ክት ነው፤ ለሚ​ያ​ምኑ ግን አይ​ደ​ለም፤ ትን​ቢ​ትም ለሚ​ያ​ምኑ ነው እንጂ ለማ​ያ​ምኑ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="23">ሕዝቡ ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ቢሰ​በ​ሰቡ፥ ሁሉም በልዩ ልዩ ቋንቋ ቢና​ገሩ፥ አላ​ዋ​ቂ​ዎች፥ ወይም የማ​ያ​ምኑ ቢመጡ አብ​ደ​ዋል ይሉ​አ​ቸው የለ​ምን?</verse>
				<verse number="24">ሁሉም ትን​ቢት ቢና​ገሩ ግን የማ​ያ​ምኑ ወይም አላ​ዋ​ቂ​ዎች ቢመጡ ሁሉ ይከ​ራ​ከ​ሩ​አ​ቸው የለ​ምን? ሁሉስ ያሳ​ፍ​ሩ​አ​ቸው የለ​ምን?</verse>
				<verse number="25">በል​ባ​ቸው የደ​በ​ቁ​ትም ይገ​ለ​ጣል፤ ከዚህ በኋላ ያ የማ​ያ​ም​ነው ተመ​ልሶ ይጸ​ጸ​ታል፤ በግ​ን​ባ​ሩም ወድቆ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ግ​ዳል፥ በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ዳ​ለም ይና​ገ​ራል።</verse>
				<verse number="26">አሁ​ንም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ሁላ​ችሁ በም​ት​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት ጊዜ መዝ​ሙር አላ​ችሁ፤ ትም​ህ​ርት አላ​ችሁ፤ መግ​ለጥ አላ​ችሁ፤ በቋ​ንቋ መና​ገር አላ​ችሁ፤ መተ​ር​ጐ​ምም አላ​ችሁ፤ ሁሉም ለሚ​ታ​ነ​ጽ​በት ጥቅም አድ​ር​ጉት።</verse>
				<verse number="27">በቋ​ንቋ የሚ​ና​ገር ቢኖር ሁለት ሁለት፥ ወይም ቢበዛ ሦስት ሦስት እየ​ሆኑ በተራ ይና​ገሩ፤ ሌላ​ውም ይተ​ር​ጕ​ም​ለት።</verse>
				<verse number="28">የሚ​ተ​ረ​ጕም ከሌለ ግን በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በቋ​ንቋ የሚ​ና​ገ​ረው ዝም ይበል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መካ​ከ​ልና በእ​ርሱ መካ​ከል ይና​ገር።</verse>
				<verse number="29">ነቢ​ያ​ትም ቃላ​ቸው ለቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ይታ​ወቅ ዘንድ ሁለት ሁለት፥ ወይም ሦስት ሦስት ሆነው ይና​ገሩ።</verse>
				<verse number="30">ተቀ​ምጦ ሳለ ምሥ​ጢር የተ​ገ​ለ​ጠ​ለት ቢኖር ፊተ​ኛው ዝም ይበል።</verse>
				<verse number="31">ሁሉ እን​ዲ​ማር፥ ሁሉም ደስ እን​ዲ​ለው፥ እን​ዲ​ጸ​ናም ሁላ​ችሁ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ትን​ቢት ልት​ና​ገሩ ትች​ላ​ላ​ች​ሁና።</verse>
				<verse number="32">የነ​ቢ​ያት ሀብት ለነ​ቢ​ያት ይሰ​ጣ​ልና።</verse>
				<verse number="33">በቅ​ዱ​ሳን ጉባኤ ሁሉ እን​ደ​ሚ​ደ​ረግ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ላም አም​ላክ እንጂ የሁ​ከት አም​ላክ አይ​ደ​ለ​ምና።</verse>
				<verse number="34">ሴቶ​ችም በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ዝም ይበሉ፤ ሊታ​ዘዙ እንጂ ሊና​ገሩ አል​ተ​ፈ​ቀ​ደ​ምና፤ ኦሪ​ትም እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="35">ለሴት በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን መና​ገር ክል​ክል ነው፤ ሊማሩ ከወ​ደዱ ደግሞ በቤ​ታ​ቸው ባሎ​ቻ​ቸ​ውን ይጠ​ይቁ።</verse>
				<verse number="36">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ከእ​ና​ንተ ብቻ ወጥ​ቶ​አ​ልን? ወይስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እና​ንተ ብቻ ደር​ሶ​አ​ልን?</verse>
				<verse number="37">ራሱን እንደ ነቢይ አድ​ርጎ ወይም መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዳ​ደ​ረ​በት አድ​ርጎ የሚ​ቈ​ጥር ቢኖር፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ነውና ይህን የጻ​ፍ​ሁ​ላ​ች​ሁን ይወቅ።</verse>
				<verse number="38">ነገር ግን ይህን የማ​ያ​ውቅ ቢኖር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አያ​ው​ቀ​ውም።</verse>
				<verse number="39">አሁ​ንም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ትን​ቢ​ትን ለመ​ና​ገር ቅኑ፤ በቋ​ንቋ የሚ​ና​ገ​ረ​ው​ንም አት​ከ​ል​ክ​ሉት።</verse>
				<verse number="40">ነገር ግን ሁሉን በአ​ገ​ባ​ብና በሥ​ር​ዐት አድ​ርጉ፤</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ያስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ች​ሁ​ንና የተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁ​ትን ያላ​ች​ሁ​በ​ትን፥ በእ​ር​ሱም የም​ት​ድ​ኑ​በ​ትን ወን​ጌል አሳ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">ያስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ች​ሁን ታስቡ እንደ ሆነ በቃሌ አስ​ተ​ም​ሬ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ ያለ​ዚያ ግን ማመ​ና​ችሁ ከንቱ ነው።</verse>
				<verse number="3">እኔ የተ​ማ​ር​ሁ​ትን አስ​ቀ​ድሜ መጽ​ሐፍ እን​ደ​ሚል እን​ዲህ ብዬ አስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ችሁ፥ “ክር​ስ​ቶስ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ሞተ።</verse>
				<verse number="4">ተቀ​በረ፤ እንደ ተጻ​ፈም በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ተነሣ።”</verse>
				<verse number="5">ለጴ​ጥ​ሮስ ታየው፤ ከዚ​ህም በኋላ ለዐ​ሥራ አንዱ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ታያ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">ከዚ​ህም በኋላ ከአ​ም​ስት መቶ ለሚ​በዙ ወን​ድ​ሞች በአ​ንድ ጊዜ ታያ​ቸው፤ ከእ​ነ​ርሱ ብዙ​ዎቹ እስከ ዛሬ አሉ፤ አን​ዳ​ን​ዶቹ ግን አን​ቀ​ላ​ፍ​ተ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">ከዚ​ህም በኋላ ለያ​ዕ​ቆብ ታየው፤ ኋላም ለሐ​ዋ​ር​ያት ሁሉ፤</verse>
				<verse number="8">ከሁ​ሉም በኋላ ጭን​ጋፍ ለም​መ​ስል ለእኔ ታየኝ።</verse>
				<verse number="9">ከሐ​ዋ​ር​ያት ሁሉ እኔ አን​ሣ​ለ​ሁና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ስለ አሳ​ደ​ድሁ ሐዋ​ርያ ተብዬ ልጠራ የማ​ይ​ገ​ባኝ፥</verse>
				<verse number="10">ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አሁን እኔ ባለ​ሁ​በት አለሁ፤ ለእ​ኔም የሰ​ጠኝ ጸጋው ለከ​ንቱ የሆ​ነ​ብኝ አይ​ደ​ለም፤ እኔም ከሁሉ ይልቅ ደከ​ምሁ፤ ነገር ግን በእኔ ላይ ያደ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አጸ​ናኝ እንጂ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም።</verse>
				<verse number="11">አሁ​ንም እኔም ብሆን፥ እነ​ር​ሱም ቢሆኑ እን​ዲህ እና​ስ​ተ​ም​ራ​ለን፤ እና​ን​ተም እን​ዲሁ አም​ና​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="12">ክር​ስ​ቶስ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ ተነ​ሥ​ቶ​አል ብለን ለሌ​ላው የም​ና​ስ​ተ​ምር ከሆነ፥ እን​ግ​ዲህ ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ሙታን አይ​ነ​ሡም የሚሉ እን​ዴት ይኖ​ራሉ?</verse>
				<verse number="13">ሙታን የማ​ይ​ነሡ ከሆነ ክር​ስ​ቶ​ስም ከሙ​ታን ተለ​ይቶ አል​ተ​ነ​ሣማ፤</verse>
				<verse number="14">ክር​ስ​ቶ​ስም ከሙ​ታን ካል​ተ​ነሣ እን​ግ​ዲ​ያስ ትም​ህ​ር​ታ​ችን ከንቱ ነው፤ የእ​ና​ን​ተም እም​ነ​ታ​ችሁ ከንቱ ነው።</verse>
				<verse number="15">እኛም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ የሐ​ሰት ምስ​ክ​ሮች ሆነ​ናል፤ ክር​ስ​ቶ​ስን አስ​ነ​ሣው ብለ​ና​ልና፥ እን​ግ​ዲያ ሳያ​ስ​ነ​ሣው ነውን?።</verse>
				<verse number="16">ሙታን የማ​ይ​ነሡ ከሆነ ክር​ስ​ቶ​ስም ከሙ​ታን አል​ተ​ነ​ሣማ።</verse>
				<verse number="17">ክር​ስ​ቶ​ስም ከሙ​ታን ካል​ተ​ነሣ ማመ​ና​ችሁ ከንቱ ነው፤ ገናም በኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ አላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="18">እን​ግ​ዲ​ያስ በክ​ር​ስ​ቶስ አም​ነው የሞቱ ጠፍ​ተ​ዋላ።</verse>
				<verse number="19">በዚህ ዓለም ሕይ​ወት ብቻ ክር​ስ​ቶ​ስን ተስፋ ከአ​ደ​ረ​ግ​ነው ከሰው ሁሉ ይልቅ ጉዳ​ተ​ኞች ነን።</verse>
				<verse number="20">አሁ​ንም ክር​ስ​ቶስ ከሞቱ ሰዎች ሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ተነ​ሥ​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="21">በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ሰው ሞት መጥ​ቶ​አ​ልና፤ በሁ​ለ​ተ​ኛው ሰው ትን​ሣኤ ሙታን ሆነ።</verse>
				<verse number="22">ሁሉ በአ​ዳም እን​ደ​ሚ​ሞት እን​ዲሁ በክ​ር​ስ​ቶስ ሁሉ ሕያ​ዋን ይሆ​ናሉ።</verse>
				<verse number="23">ነገር ግን ሰው ሁሉ በየ​ሥ​ር​ዐቱ ይነ​ሣል፤ በመ​ጀ​መ​ሪያ ከሙ​ታን የተ​ነሣ ክር​ስ​ቶስ ነው፤ ከዚያ በኋላ በክ​ር​ስ​ቶስ ያመኑ እርሱ በሚ​መ​ጣ​በት ጊዜ ይነ​ሣሉ።</verse>
				<verse number="24">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ መን​ግ​ሥ​ቱን እጅ ባደ​ረገ ጊዜ፥ ገዥም ሁሉ፥ ንጉ​ሥም ሁሉ፥ ኀይ​ልም ሁሉ በተ​ሻረ ጊዜ፥ ያን​ጊዜ ፍጻሜ ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="25">ጠላ​ቶቹ ሁሉ ከእ​ግሩ በታች እስ​ኪ​ወ​ድቁ ድረስ ይነ​ግሥ ዘንድ አለ​ውና።</verse>
				<verse number="26">ከዚያ በኋላ የመ​ጨ​ረ​ሻው ጠላት ይሻ​ራል፤ ይኸ​ውም ሞት ነው።</verse>
				<verse number="27">ሁሉን ከእ​ግሩ በታች አስ​ገ​ዝ​ቶ​ለ​ታ​ልና፥ “ሁሉ ይገ​ዛ​ለት” ባለ ጊዜ ግን ሁሉን ከሚ​ያ​ስ​ገ​ዛ​ለት በቀር እንደ ሆነ የታ​ወቀ ነው።</verse>
				<verse number="28">ሁሉም በተ​ገ​ዛ​ለት ጊዜ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሁሉ ቦታ በሁሉ ይሆን ዘንድ፥ ያን ዕለት ወል​ድም ሁሉን ላስ​ገ​ዛ​ለት ይገ​ዛል።</verse>
				<verse number="29">ያለ​ዚ​ያማ ለምን ያጠ​ም​ቃሉ? ሙታን እን​ዲ​ነሡ አይ​ደ​ለ​ምን? ሙታን የማ​ይ​ነሡ ከሆ​ነስ ለምን ያጠ​ም​ቃሉ?</verse>
				<verse number="30">እን​ግ​ዲህ እኛስ ሁል​ጊዜ መከ​ራን ስለ​ምን እን​ቀ​በ​ላ​ለን?</verse>
				<verse number="31">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በሆ​ነ​ውና በእ​ና​ንተ ላይ ባለኝ ትም​ክ​ህት ሁል​ጊዜ እገ​ደ​ላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="32">በውኑ በኤ​ፌ​ሶን ከአ​ውሬ ጋር የታ​ገ​ልሁ ለሰው ብዬ ነውን? ምንስ ይጠ​ቅ​መ​ኛል? ሙታን የማ​ይ​ነሡ ከሆነ እን​ግ​ዲህ እን​ብላ እን​ጠጣ፥ ነገም እን​ሞ​ታ​ለን።</verse>
				<verse number="33">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን አያ​ስ​ቱ​አ​ችሁ፤ ክፉ ነገር መል​ካም ጠባ​ይን ያበ​ላ​ሻ​ልና።</verse>
				<verse number="34">ለጽ​ድቅ ትጉ፤ አት​ሳቱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የማ​ያ​ው​ቁት ሰዎች አሉና፤ ነገር ግን እን​ድ​ታ​ፍሩ ይህን እላ​ች​ኋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="35">ሙታን እን​ዴት ይነ​ሣሉ? የሚ​ነ​ሡስ በምን አካ​ላ​ቸው ነው? የሚል አለ።</verse>
				<verse number="36">አንተ ሰነፍ! አንተ የም​ት​ዘ​ራው እን​ኳን ካል​ፈ​ረሰ አይ​በ​ቅ​ልም።</verse>
				<verse number="37">የም​ት​ዘ​ራ​ውም የስ​ንዴ ቢሆን፥ የሌ​ላም ቢሆን የም​ት​ዘ​ራት ቅን​ጣት ብቻ ናት እንጂ ይህ ኋላ የሚ​ገ​ኘው አገ​ዳው አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="38">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እንደ ወደደ አገ​ዳን ይሰ​ጠ​ዋል፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ዘርም አገ​ዳው እየ​ራሱ ነው።</verse>
				<verse number="39">የፍ​ጥ​ረቱ ሁሉ አካል አንድ አይ​ደ​ለ​ምና፤ የሰው አካል ሌላ ነው፤ የእ​ን​ስ​ሳም አካል ሌላ ነው፤ የወፍ አካ​ልም ሌላ ነው፤ የዓሣ አካ​ልም ሌላ ነው።</verse>
				<verse number="40">ሰማ​ያዊ አካል አለ፤ ምድ​ራዊ አካ​ልም አለ፤ ነገር ግን በሰ​ማይ ያለው አካል ክብሩ ልዩ ነው፤ በም​ድ​ርም ያለው አካል ክብሩ ልዩ ነው።</verse>
				<verse number="41">የፀ​ሐይ ክብሩ ሌላ ነው፤ የጨ​ረ​ቃም ክብሩ ሌላ ነው፤ የከ​ዋ​ክ​ብ​ትም ክብ​ራ​ቸው ሌላ ነው፤ ኮከብ ከኮ​ከብ በክ​ብር ይበ​ል​ጣ​ልና።</verse>
				<verse number="42">የሙ​ታን ትን​ሣ​ኤ​ያ​ቸው እን​ዲሁ ነው፥ በሚ​ፈ​ርስ አካል ይዘ​ራል፤ በማ​ይ​ፈ​ርስ አካል ይነ​ሣል።</verse>
				<verse number="43">በው​ር​ደት ይዘ​ራል፤ በክ​ብር ይነ​ሣል፤ በድ​ካም ይዘ​ራል፤ በኀ​ይል ይነ​ሣል።</verse>
				<verse number="44">ሥጋዊ አካል ይዘ​ራል፤ መን​ፈ​ሳዊ አካል ይነ​ሣል፤ ሥጋዊ አካል አለና መን​ፈ​ሳዊ አካ​ልም ደግሞ አለ።</verse>
				<verse number="45">መጽ​ሐፍ እን​ዲሁ ብሎ​አ​ልና የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ሰው አዳም በነ​ፍስ ሕያው ሆኖ ተፈ​ጠረ፤ ሁለ​ተ​ኛው አዳም ግን ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ መን​ፈስ ነው።</verse>
				<verse number="46">ነገር ግን አስ​ቀ​ድሞ ሥጋ​ዊው፥ ቀጥ​ሎም መን​ፈ​ሳ​ዊው ነው እንጂ፥ መን​ፈ​ሳ​ዊው መጀ​መ​ሪ​ያው አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="47">መጀ​መ​ሪ​ያው ሰው ከመ​ሬት የተ​ገኘ መሬ​ታዊ ነው፤ ሁለ​ተ​ኛው ሰው ከሰ​ማይ የወ​ረደ ሰማ​ያዊ ነው።</verse>
				<verse number="48">መሬ​ታ​ው​ያኑ እን​ደ​ዚያ እንደ መሬ​ታ​ዊው ናቸው፤ ሰማ​ያ​ው​ያ​ኑም እን​ደ​ዚያ እንደ ሰማ​ያ​ዊው ናቸው።</verse>
				<verse number="49">የመ​ሬ​ታ​ዊ​ውን መልክ እንደ ለበ​ስን እን​ዲሁ የሰ​ማ​ያ​ዊ​ውን መልክ ደግሞ እን​ለ​ብ​ሳ​ለን።</verse>
				<verse number="50">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ይህን እን​ነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለን፦ ሥጋ​ዊና ደማዊ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት አይ​ወ​ር​ስም፥ የሚ​ፈ​ር​ሰው የማ​ይ​ፈ​ር​ሰ​ውን አይ​ወ​ር​ስም።</verse>
				<verse number="51">እነሆ፥ አንድ ምሥ​ጢ​ርን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፥ ሁላ​ችን የም​ን​ሞት አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="52">ነገር ግን የኋ​ለ​ኛው መለ​ከት ሲነፋ ሁላ​ችን እንደ ዐይን ጥቅሻ በአ​ንድ ጊዜ እን​ለ​ወ​ጣ​ለን፤ መለ​ከት ይነ​ፋል፤ ሙታ​ንም የማ​ይ​ፈ​ርሱ ሁነው ይነ​ሣሉ፤ እኛም እን​ለ​ወ​ጣ​ለን።</verse>
				<verse number="53">ይህ የሚ​ፈ​ር​ሰው የማ​ይ​ፈ​ር​ሰ​ውን፥ ይህም የሚ​ሞ​ተው የማ​ይ​ሞ​ተ​ውን ይለ​ብስ ዘንድ አለ​ውና።</verse>
				<verse number="54">ይህ የሚ​ፈ​ር​ሰው የማ​ይ​ፈ​ር​ሰ​ውን በለ​በሰ ጊዜ፥ የሚ​ሞ​ተ​ውም የማ​ይ​ሞ​ተ​ውን በለ​በሰ ጊዜ፤ “ሞት በመ​ሸ​ነፍ ተዋጠ” ተብሎ የተ​ጻ​ፈው ያን​ጊዜ ይፈ​ጸ​ማል።</verse>
				<verse number="55">“ሞት ሆይ፥ እን​ግ​ዲህ መው​ጊ​ያህ ወዴት አለ? መቃ​ብር ሆይ፥ አሸ​ና​ፊ​ነ​ትህ ወዴት አለ?”</verse>
				<verse number="56">የሞት መው​ጊያ ኀጢ​አት ናት፥ የኀ​ጢ​አ​ትም ኀይ​ልዋ ኦሪት ናት።</verse>
				<verse number="57">በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ድል መን​ሣ​ትን ለሰ​ጠን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን።</verse>
				<verse number="58">አሁ​ንም የተ​ወ​ደ​ዳ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የጸ​ና​ች​ሁና የማ​ት​ና​ወጡ ሁኑ፤ ዘወ​ትር በጎ ምግ​ባ​ርን አብ​ዝ​ታ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አበ​ር​ክቱ፤ ስለ ጌታ​ችን መድ​ከ​ማ​ችሁ ለከ​ንቱ እን​ዳ​ይ​ደለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">ለቅ​ዱ​ሳን ስለ​ሚ​ደ​ረ​ገው አስ​ተ​ዋ​ፅኦ በገ​ላ​ትያ ላሉት ምእ​መ​ናን እንደ ደነ​ገ​ግ​ሁት እና​ን​ተም እን​ዲሁ አድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="2">እኔ ስመጣ ይህ የገ​ን​ዘብ ማዋ​ጣት ያን​ጊዜ እን​ዳ​ይ​ሆን፥ ከእ​ና​ንተ ሰው ሁሉ በየ​ሳ​ም​ንቱ እሑድ የተ​ቻ​ለ​ውን ያወ​ጣጣ፤ ያገ​ኘ​ው​ንም በቤቱ ይጠ​ብቅ።</verse>
				<verse number="3">በመ​ጣሁ ጊዜም ስጦ​ታ​ች​ሁን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያደ​ርሱ ዘንድ የመ​ረ​ጣ​ች​ኋ​ቸ​ውን ሰዎች መል​እ​ክ​ቴን ጨምሬ እል​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">ለመ​ሄድ ቢቻ​ለኝ ግን እኔ ራሴ እሄ​ዳ​ለ​ሁና፥ እነ​ር​ሱም አብ​ረ​ውኝ ይሄ​ዳሉ።</verse>
				<verse number="5">መቄ​ዶ​ን​ያም ደርሼ ወደ እና​ንተ እመ​ጣ​ለሁ፤ በመ​ቄ​ዶ​ንያ በኩል አል​ፋ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="6">እና​ን​ተም ወደ​ም​ሄ​ድ​በት ትሸ​ኙኝ ዘንድ ምን​አ​ል​ባት የሆ​ነ​ውን ቀን ያህል በእ​ና​ንተ ዘንድ እቈይ፥ ወይም እከ​ርም ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="7">አሁን እግረ መን​ገ​ዴን ላያ​ችሁ አል​ሻም፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፈ​ቀደ እንደ ሆነ የሆ​ነ​ውን ቀን ያህል በእ​ና​ንተ ዘንድ እን​ደ​ም​ቈይ ተስፋ አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="8">እስከ በዓለ ኀምሳ በኤ​ፌ​ሶን እቈ​ያ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">ሥራ የሞ​ላ​በት ታላቅ በር ተከ​ፍ​ቶ​ል​ኛ​ልና፤ ነገር ግን ብዙ​ዎች ተቃ​ዋ​ሚ​ዎች አሉ።</verse>
				<verse number="10">ጢሞ​ቴ​ዎ​ስም በመጣ ጊዜ በእ​ና​ንተ ዘንድ ያለ ፍር​ሀት እን​ዲ​ኖር ተጠ​ን​ቀቁ፤ እንደ እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ይሠ​ራ​ልና።</verse>
				<verse number="11">የሚ​ን​ቀ​ውም አይ​ኑር፤ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ጋር እጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለ​ሁና፥ ወደ እኔ እን​ዲ​መጣ በሰ​ላም ሸኙት።</verse>
				<verse number="12">ስለ ወን​ድ​ማ​ችን ስለ አጵ​ሎ​ስም ከወ​ን​ድ​ሞች ጋር ወደ እና​ንተ እን​ዲ​መጣ መላ​ልሼ ማል​ጄው ነበር፤ አሁን ሊመጣ አል​ወ​ደ​ደም፤ በተ​ቻ​ለው ጊዜ ግን ይመ​ጣል።</verse>
				<verse number="13">ትጉ፤ በሃ​ይ​ማ​ኖ​ትም ቁሙ፤ ታገሡ ጽኑ፤</verse>
				<verse number="14">ሁሉን በፍ​ቅር አድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="15">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስና የፈ​ር​ዶ​ና​ጥስ፥ የአ​ካ​ይ​ቆ​ስም ቤተ​ሰ​ቦች፥ የአ​ካ​ይያ መጀ​መ​ሪ​ያ​ዎች እንደ ሆኑ፥ ቅዱ​ሳ​ን​ንም ለማ​ገ​ል​ገል ራሳ​ቸ​ውን እንደ ሰጡ ታውቁ ዘንድ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="16">እና​ን​ተም እንደ እነ​ዚህ ላሉ​ትና ከእኛ ጋር በሥራ ተባ​ብሮ ለሚ​ደ​ክም ሁሉ ትታ​ዘ​ዙ​ላ​ቸው ዘንድ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="17">እስ​ጢ​ፋ​ኖስ፥ ፈር​ዶ​ና​ጥ​ስና አካ​ይ​ቆስ በመ​ም​ጣ​ታ​ቸ​ውም ደስ ይለ​ኛል፤ እና​ንተ ያጐ​ደ​ላ​ች​ሁ​ትን እነ​ርሱ ፈጽ​መ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="18">እነ​ርሱ መን​ፈ​ሴ​ንና መን​ፈ​ሳ​ች​ሁን ደስ አሰ​ኝ​ተ​ዋል፤ እን​ዲህ ያሉ​ት​ንም ዕወ​ቋ​ቸው።</verse>
				<verse number="19">በእ​ስያ ያሉ ምእ​መ​ናን ሰላ​ምታ ያቀ​ር​ቡ​ላ​ች​ኋል፤ አቂ​ላና ጵር​ስ​ቅላ በቤ​ታ​ቸው ከእ​ነ​ርሱ ጋር ያሉ ምእ​መ​ና​ንም ሁሉ በጌ​ታ​ችን እጅግ ሰላ​ምታ ያቀ​ር​ቡ​ላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="20">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ሁሉ ሰላ​ምታ ያቀ​ር​ቡ​ላ​ች​ኋል፤ በተ​ቀ​ደ​ሰች ሰላ​ምታ እርስ በር​ሳ​ችሁ ሰላም ተባ​ባሉ።</verse>
				<verse number="21">እኔ ጳው​ሎስ ይህን ሰላ​ምታ በእጄ ጻፍሁ።</verse>
				<verse number="22">ጌታ​ች​ንን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን የማ​ይ​ወ​ደው የተ​ለየ ይሁን፤ ጌታ​ችን ይመ​ጣል።</verse>
				<verse number="23">የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጸጋ ከእ​ና​ንተ ጋራ ይሁን።</verse>
				<verse number="24">የእ​ኔም ፍቅር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን። አሜን። በኤ​ፌ​ሶን ተጽፎ በጢ​ሞ​ቴ​ዎ​ስና በእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖስ፥ በፈ​ር​ዶ​ና​ጥ​ስና በአ​ካ​ይ​ቆስ እጅ ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች የተ​ላ​ከው መጀ​መ​ሪ​ያዉ መል​እ​ክት ተፈ​ጸመ። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን። አሜን።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="47">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈቃድ የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሐዋ​ርያ ከሆነ ጳው​ሎ​ስና ከወ​ን​ድ​ማ​ችን ጢሞ​ቴ​ዎስ በቆ​ሮ​ን​ቶስ ሀገር ላለ​ችው የእ​ግ​ዚ​አ​ሔር ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንና በአ​ካ​ይያ ሀገር ላሉ ቅዱ​ሳን ሁሉ፥</verse>
				<verse number="2">ከአ​ባ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሰላ​ምና ጸጋ ለእ​ና​ንተ ይሁን።</verse>
				<verse number="3">የም​ሕ​ረት አባት፥ የመ​ጽ​ና​ና​ትም ሁሉ አም​ላክ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ጽ​ና​ናን በዚያ መጽ​ና​ናት በመ​ከራ ያሉ​ትን ሁሉ ማጽ​ና​ናት እን​ችል ዘንድ ከመ​ከ​ራ​ችን ሁሉ ያጽ​ና​ናን እርሱ ይመ​ስ​ገን።</verse>
				<verse number="5">የክ​ር​ስ​ቶስ መከራ በእኛ ላይ እንደ በዛ መጠን እን​ዲሁ መጽ​ና​ና​ታ​ች​ንም በክ​ር​ስ​ቶስ ይበ​ዛ​ልና።</verse>
				<verse number="6">መከራ ብን​ቀ​በ​ልም እና​ንተ እን​ድ​ት​ድ​ኑና እን​ድ​ት​ጽ​ናኑ ነው፤ ብን​ጽ​ና​ናም እኛ የተ​ቀ​በ​ል​ነ​ውን ያን መከራ በመ​ታ​ገሥ ስለ​ሚ​ደ​ረግ መጽ​ና​ና​ታ​ችሁ ነው።</verse>
				<verse number="7">ስለ እና​ንተ ያለን ተስ​ፋም የጸና ነው፤ መከ​ራ​ች​ንን እንደ ተካ​ፈ​ላ​ችሁ መጠን፥ እን​ዲሁ በመ​ጽ​ና​ና​ታ​ች​ንም እን​ደ​ም​ት​ተ​ባ​በሩ እና​ው​ቃ​ለን።</verse>
				<verse number="8">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በእ​ስያ መከራ እንደ ተቀ​በ​ልን ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ፤ ለሕ​ይ​ወ​ታ​ችን ተስፋ እስ​ክ​ን​ቈ​ርጥ ድረስ ከዐ​ቅ​ማ​ችን በላይ እጅግ መከራ ጸን​ቶ​ብን ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="9">ሙታ​ንን በሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንጂ በራ​ሳ​ችን እን​ዳ​ን​ታ​መን በው​ስ​ጣ​ችን ለመ​ሞት ቈር​ጠን ነበር።</verse>
				<verse number="10">እር​ሱም እን​ዲህ ካለ ሞት አዳ​ነን፤ ያድ​ነ​ን​ማል፤ አሁ​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ድ​ነን እር​ሱን እን​ታ​መ​ና​ለን።</verse>
				<verse number="11">በብ​ዙ​ዎች ጸሎት ጸጋን እና​ገኝ ዘንድ፥ ብዙ​ዎ​ችም በእኛ ፋንታ ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ እና​ንተ በጸ​ሎ​ታ​ችሁ ርዱን።</verse>
				<verse number="12">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር​ነ​ትና ይቅ​ርታ መመ​ኪ​ያ​ች​ንና የነ​ፃ​ነ​ታ​ችን ምስ​ክር ይህቺ ናትና፥ በሥ​ጋዊ ጥበብ ሳይ​ሆን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይል​ቁ​ንም በእ​ና​ንተ ዘንድ ተመ​ላ​ለ​ስን።</verse>
				<verse number="13">የም​ታ​ነ​ቡ​ት​ንና የም​ታ​ው​ቁ​ትን ነው እንጂ፥ ሌላ የም​ን​ጽ​ፍ​ላ​ችሁ የለ​ምና፥ ይህ​ንም እስከ ፍጻሜ እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ው​ሉት ተስፋ አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">እኛ መመ​ኪ​ያ​ችሁ እን​ደ​ሆን፥ እን​ዲሁ እና​ን​ተም በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ቀን መመ​ኪ​ያ​ችን እን​ድ​ት​ሆኑ በከ​ፊል እን​ዳ​ወ​ቃ​ችሁ ተስፋ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።</verse>
				<verse number="15">በዚ​ህም ታምኜ ጸጋን በዕ​ጥፍ እን​ድ​ታ​ገኙ በመ​ጀ​መ​ሪያ ወደ እና​ንተ እመጣ ዘንድ መከ​ርሁ።</verse>
				<verse number="16">በእ​ና​ን​ተም በኩል ወደ መቄ​ዶ​ንያ እን​ዳ​ልፍ፥ ዳግ​መ​ኛም ከመ​ቄ​ዶ​ንያ እን​ድ​መ​ለ​ስና እና​ን​ተም ደግሞ ወደ ይሁዳ ሀገር ትሸ​ኙኝ ዘንድ መከ​ርሁ።</verse>
				<verse number="17">እን​ግ​ዲህ ይህን የመ​ከ​ርሁ በውኑ የሠ​ራ​ሁት እንደ አላ​ዋቂ ሰው ሆኜ ነውን? ወይስ በእኔ በኩል አዎን አዎን፥ አይ​ደ​ለም አይ​ደ​ለም ማለት እን​ዲ​ሆን ያን የም​መ​ክ​ረው ለሰው ይም​ሰል ነውን?</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መነ ነው፤ ለእ​ና​ን​ተም የሚ​ነ​ገ​ረው ቃላ​ችን እው​ነ​ትና ሐሰት አል​ተ​ቀ​ላ​ቀ​ለ​በ​ትም።</verse>
				<verse number="19">እኛ ማለት እኔ ጳው​ሎስ፥ ስል​ዋ​ኖ​ስና ጢሞ​ቴ​ዎስ የሰ​በ​ክ​ን​ላ​ችሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እው​ነ​ትና ሐሰት አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ስለ እርሱ ያስ​ተ​ማ​ር​ነው እው​ነት ነው።</verse>
				<verse number="20">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠው ተስፋ ሁሉ በክ​ር​ስ​ቶስ እው​ነት ሆኖ​አ​ልና፤ ስለ​ዚ​ህም በእ​ርሱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር አሜን እን​ላ​ለን።</verse>
				<verse number="21">ከእ​ና​ንተ ጋር በክ​ር​ስ​ቶስ ስም የሚ​ያ​ጸ​ና​ንና የቀ​ባን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።</verse>
				<verse number="22">ደግ​ሞም ያተ​መ​ንና የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ፈለማ በል​ቡ​ና​ችን የሰ​ጠን እርሱ ነው።</verse>
				<verse number="23">እኔ ለእ​ና​ንተ በመ​ራ​ራት ወደ ቆሮ​ን​ቶስ እን​ዳ​ል​መ​ጣሁ፥ ስለ ራሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ክር አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="24">ደስ የሚ​ላ​ች​ሁን እን​ድ​ታ​ደ​ርጉ እን​ረ​ዳ​ች​ኋ​ለን እንጂ እን​ድ​ታ​ምኑ ግድ የም​ን​ላ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ በእ​ም​ነት ቆማ​ች​ኋ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">እን​ግ​ዲህ እያ​ዘ​ንሁ ወደ እና​ንተ እን​ዳ​ል​መጣ በልቤ ይህን ወሰ​ንሁ።</verse>
				<verse number="2">እኔ ካሳ​ዘ​ን​ኋ​ች​ሁማ እኔ ካሳ​ዘ​ን​ሁት በቀር ማን ደስ ያሰ​ኘ​ኛል?</verse>
				<verse number="3">የእኔ ደስታ የሁ​ላ​ችሁ እንደ ሆነ በሁ​ላ​ችሁ አም​ኛ​ለ​ሁና በመ​ጣሁ ጊዜ ደስ ሊያ​ሰ​ኙኝ ከሚ​ገ​ባ​ቸው ኀዘን እን​ዳ​ያ​ገ​ኘኝ ይህን ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="4">ከብዙ መከ​ራና ከልብ ጭን​ቀት የተ​ነሣ በብዙ እንባ ይህን ጽፌ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ነገር ግን እጅግ እን​ደ​ም​ወ​ዳ​ችሁ እን​ድ​ታ​ውቁ ነው እንጂ እን​ድ​ታ​ዝኑ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="5">ማንም ያሳ​ዘ​ነኝ ቢሆን፥ እኔን ብቻ ያሳ​ዘነ አይ​ደ​ለም። ከእ​ና​ንተ አንድ ሳይ​ቀር ሁላ​ች​ሁ​ንም አሳ​ዘነ እንጂ፤ አሁ​ንም ሥር​ዐት አላ​ጸ​ና​ባ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="6">እን​ደ​ዚህ ላለው ሰው ከእ​ና​ንተ ከብ​ዙ​ዎች ያገ​ኘ​ችው ይህች ተግ​ሣጽ ትበ​ቃ​ዋ​ለች።</verse>
				<verse number="7">ደግ​ሞም እን​ዲህ ያለው ሰው ከኀ​ዘን ብዛት የተ​ነሣ እን​ዳ​ይ​ዋጥ ይቅር ልት​ሉ​ትና ልታ​ጽ​ና​ኑት ይገ​ባል።</verse>
				<verse number="8">ስለ​ዚ​ህም ከእ​ርሱ ጋር ፍቅ​ርን እን​ድ​ታ​ጸኑ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">ስለ​ዚ​ህም በሁሉ ትታ​ዘ​ዙኝ እንደ ሆነ፥ ፈቃ​ዳ​ች​ሁን ዐውቅ ዘንድ ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="10">ይቅር የም​ት​ሉት ቢኖር፥ እኔም ከእ​ና​ንተ ጋር ይቅር እለ​ዋ​ለሁ፤ እኔም ይቅር ያል​ሁ​ትን በክ​ር​ስ​ቶስ ፊት ስለ እና​ንተ ይቅር ብያ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">ሰይ​ጣን እን​ዳ​ያ​ታ​ል​ለን አሳ​ቡን የም​ን​ስ​ተው አይ​ደ​ለ​ምና።</verse>
				<verse number="12">ለክ​ር​ስ​ቶ​ስም ወን​ጌል ጢሮ​አዳ በደ​ረ​ስሁ ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሩ ተከ​ፈ​ተ​ልኝ።</verse>
				<verse number="13">ወን​ድ​ሜን ቲቶን ስላ​ላ​ገ​ኘ​ሁት ለሰ​ው​ነቴ ዕረ​ፍት አላ​ገ​ኘ​ሁም፤ ነገር ግን ከእ​ርሱ ተለ​ይች ወደ መቄ​ዶ​ንያ ሄድሁ።</verse>
				<verse number="14">በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘወ​ትር ድል በመ​ን​ሣቱ የሚ​ጠ​ብ​ቀን፥ በየ​ሀ​ገ​ሩም ሁሉ የዕ​ው​ቀ​ቱን መዓዛ በእኛ የሚ​ገ​ልጥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።</verse>
				<verse number="15">በሚ​ድ​ኑ​ትና በሚ​ጠ​ፉት ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የክ​ር​ስ​ቶስ መዓዛ እኛ ነንና።</verse>
				<verse number="16">የሞት መዓዛ የሚ​ገ​ባ​ቸው ለሞት፥ የሕ​ይ​ወት መዓዛ የሚ​ገ​ባ​ቸ​ውም ለሕ​ይ​ወት ናቸው፤ ነገር ግን ይህ የሚ​ገ​ባው ማነው?</verse>
				<verse number="17">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በሌላ ቀላ​ቅ​ለው እን​ደ​ሚ​ሸ​ቅጡ እንደ ብዙ​ዎች አይ​ደ​ለ​ን​ምና፤ በቅ​ን​ነት ግን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተላከ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በክ​ር​ስ​ቶስ እን​ና​ገ​ራ​ለን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን አሁን ደግሞ ራሳ​ች​ንን እያ​መ​ሰ​ገን ልን​ነ​ግ​ራ​ችሁ እን​ጀ​ም​ራ​ለ​ንን? ወይስ እንደ ሌሎች ስለ እኛ ወደ እና​ንተ ደብ​ዳቤ እን​ዲ​ጽ​ፉ​ላ​ችሁ፥ ወይስ እና​ንተ ትጽ​ፉ​ልን ዘንድ የም​ን​ሻው አለን?</verse>
				<verse number="2">የእ​ኛስ መጽ​ሐ​ፋ​ችን እና​ንተ ናችሁ፤ በል​ባ​ችን ውስ​ጥም ተጽ​ፋ​ች​ኋል፤ ትታ​ወ​ቃ​ላ​ች​ሁም፤ ሰውም ሁሉ ያነ​ብ​ባ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="3">እና​ንተ ራሳ​ች​ሁም በእኛ የተ​ላ​ከች የክ​ር​ስ​ቶስ መል​እ​ክት እንደ ሆና​ችሁ ያው​ቃሉ፤ ይህ​ቺ​ውም የተ​ጻ​ፈች በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነው እንጂ በቀ​ለም አይ​ደ​ለም፤ በሥጋ ልብ ሠሌ​ዳ​ነት ነው እንጂ በድ​ን​ጋይ ሠሌ​ዳም አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን በክ​ር​ስ​ቶስ በኩል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እን​ዲህ ያለ እም​ነት አለን።</verse>
				<verse number="5">ኀይ​ላ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ሆነ ከእኛ ከራ​ሳ​ችን እንደ ሆነ አድ​ር​ገን ምንም ልና​ስብ አይ​ገ​ባ​ንም።</verse>
				<verse number="6">በመ​ን​ፈስ እንጂ በፊ​ደል ለማ​ይ​ሆን ለአ​ዲስ ሕግ አገ​ል​ጋ​ዮች አደ​ረ​ገን፤ ፊደል ይገ​ድ​ላል፥ መን​ፈስ ግን ሕያው ያደ​ር​ጋል።</verse>
				<verse number="7">ስለ​ዚያ ስለ አለ​ፈው የፊቱ ብር​ሃን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የሙ​ሴን ፊት መመ​ል​ከት እስ​ኪ​ሳ​ና​ቸው ድረስ በዚ​ያች በድ​ን​ጋይ ላይ በፊ​ደል ለተ​ቀ​ረ​ጸች ለሞት መል​እ​ክት ክብር ከተ​ደ​ረ​ገ​ላት፥</verse>
				<verse number="8">ለመ​ን​ፈስ ቅዱስ መል​እ​ክ​ትማ ምንኛ እጅግ ክብር ሊደ​ረግ ይገባ ይሆን?</verse>
				<verse number="9">ኵነ​ኔን ለም​ታ​መጣ መል​እ​ክት ብዙ ክብር ከተ​ደ​ረ​ገ​ላት የጽ​ድቅ መል​እ​ክ​ትማ ምን ያህል ትከ​ብ​ርና ትመ​ሰ​ገን ይሆን?</verse>
				<verse number="10">በዚህ ፍጹም ክብር ባነ​ጻ​ጸ​ሯት ጊዜ የከ​በ​ረ​ችው እን​ዳ​ል​ከ​በ​ረች ትሆ​ና​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="11">ያ የሚ​ያ​ል​ፈው ክብር ካገኘ፥ ያ ጸንቶ የሚ​ኖ​ረ​ውማ እን​ዴት እጅግ ክብር ያገኝ ይሆን?</verse>
				<verse number="12">እን​ግ​ዲህ ይህን ያህል ተስፋ ካለን በግ​ልጥ ፊት ለፊት ልን​ቀ​ርብ እን​ች​ላ​ለን።</verse>
				<verse number="13">የዚ​ያን ይሻር የነ​በ​ረ​ውን መጨ​ረሻ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዳ​ያ​ዩት ፊቱን ይሸ​ፍን እንደ ነበ​ረው እንደ ሙሴ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ ልባ​ቸው ተሸ​ፍ​ኖ​አል፤ ያም መጋ​ረጃ ብሉይ ኪዳን በተ​ነ​በ​በት ዘመን ሁሉ ጸንቶ ኖሮ​አል፤ ክር​ስ​ቶስ እስ​ኪ​ያ​ሳ​ል​ፈው ድረስ አል​ተ​ገ​ለ​ጠ​ምና።</verse>
				<verse number="15">እስከ ዛሬም የሙ​ሴን ሕግ ሲያ​ነ​ብቡ ያ መጋ​ረጃ ልባ​ቸ​ውን ይሸ​ፍ​ና​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="16">ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​መ​ለሱ ጊዜ ግን ያ መጋ​ረጃ ከእ​ነ​ርሱ ይር​ቃል።</verse>
				<verse number="17">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነውና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ባለ​በ​ትም በዚያ ነፃ​ነት አለ።</verse>
				<verse number="18">እኛስ ሁላ​ችን ፊታ​ች​ንን ገል​ጠን በመ​ስ​ተ​ዋት እን​ደ​ሚ​ያይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር እና​ያ​ለን፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ እንደ ተሰ​ጠን መጠን የእ​ር​ሱን አር​አያ እን​መ​ስል ዘንድ ከክ​ብር ወደ ክብር እን​ገ​ባ​ለን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ስለ​ዚህ እንደ ቸር​ነቱ የሰ​ጠን ይህ መል​እ​ክት አለ​ንና አን​ሰ​ለ​ችም።</verse>
				<verse number="2">ነገር ግን በስ​ውር የሚ​ሠ​ራ​ውን አሳ​ፋሪ ሥራ እን​ተ​ወው፤ በተ​ን​ኰ​ልም አን​መ​ላ​ለስ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል በው​ሸት አን​ቀ​ላ​ቅል፤ ለሰ​ውም ሁሉ አር​አያ ስለ መሆን እው​ነ​ትን ገል​ጠን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ራሳ​ች​ንን እና​ጽና።</verse>
				<verse number="3">ወን​ጌ​ላ​ችን የተ​ሰ​ወረ ቢሆ​ንም እንኳ፥ የተ​ሰ​ወ​ረ​ባ​ቸው ለሚ​ጠ​ፉት ነው።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​መ​ስ​ለው የክ​ር​ስ​ቶስ የክ​ብሩ ወን​ጌል ብር​ሃን እን​ዳ​ያ​በ​ራ​ላ​ቸው የዚህ ዓለም አም​ላክ ልባ​ቸ​ውን አሳ​ው​ሮ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="5">ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ጌታ እንደ ሆነ እን​ሰ​ብ​ካ​ለን እንጂ ራሳ​ች​ንን የም​ን​ሰ​ብክ አይ​ደ​ለም፤ ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ብለን ራሳ​ች​ንን ለእ​ና​ንተ አስ​ገ​ዛን።</verse>
				<verse number="6">በጨ​ለማ ውስጥ “ብር​ሃን ይብራ” ያለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ፊት የክ​ብ​ሩን ዕው​ቀት ብር​ሃን በል​ባ​ችን አብ​ር​ቶ​ል​ና​ልና።</verse>
				<verse number="7">ነገር ግን ከእኛ ያይ​ደለ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ገኘ ታላቅ ኀይል ይሆን ዘንድ በሸ​ክላ ዕቃ ውስጥ ይህ መዝ​ገብ አለን።</verse>
				<verse number="8">በሁሉ መከ​ራን እን​ቀ​በ​ላ​ለን፤ ነገር ግን አን​ጨ​ነ​ቅም፤ እን​ና​ቃ​ለን፥ ነገር ግን ተስፋ አን​ቈ​ር​ጥም።</verse>
				<verse number="9">እን​ሰ​ደ​ዳ​ለን፤ ነገር ግን አን​ጣ​ልም፤ እን​ወ​ድ​ቃ​ለን፤ ነገር ግን አን​ጠ​ፋም።</verse>
				<verse number="10">የክ​ር​ስ​ቶስ ሕይ​ወቱ በዚህ በሟች ሰው​ነ​ታ​ችን ላይ ይገ​ለጥ ዘንድ፥ ዘወ​ትር የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ሞት በሥ​ጋ​ችን እን​ሸ​ከ​ማ​ለን።</verse>
				<verse number="11">በሕ​ይ​ወት የም​ን​ኖር እኛም በሟች ሰው​ነ​ታ​ችን ላይ የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሕይ​ወቱ ይገ​ለጥ ዘንድ፥ ዘወ​ትር ስለ ኢየ​ሱስ ክስ​ር​ቶስ ብለን ተላ​ል​ፈን ለሞት እን​ሰ​ጣ​ለን።</verse>
				<verse number="12">ስለ​ዚ​ህም ሞት በእኛ ላይ፥ ሕይ​ወ​ትም በእ​ና​ንተ ላይ ይሠ​ራል።</verse>
				<verse number="13">አንድ የእ​ም​ነት መን​ፈስ አለን፤ መጽ​ሐፍ፥ “አመ​ንሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ተና​ገ​ርሁ” እን​ዳለ እኛም አመን፤ ስለ​ዚ​ህም ተና​ገ​ርን።</verse>
				<verse number="14">ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ያስ​ነ​ሣው እርሱ እኛ​ንም እንደ እርሱ እን​ዲ​ያ​ስ​ነ​ሣን፥ ከእ​ና​ን​ተም ጋር በፊቱ እን​ዲ​ያ​ቆ​መን እና​ው​ቃ​ለን።</verse>
				<verse number="15">ጸጋው በብ​ዙ​ዎች ላይ ትት​ረ​ፈ​ረፍ ዘንድ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የክ​ብሩ ምስ​ጋና ይበዛ ዘንድ ሁሉ ስለ እና​ንተ ነውና።</verse>
				<verse number="16">ስለ​ዚህ አን​ሰ​ልች፤ በውጭ ያለው ሰው​ነ​ታ​ችን ያረ​ጃ​ልና፤ በው​ስጥ ያለው ሰው​ነ​ታ​ችን ግን ዘወ​ትር ይታ​ደ​ሳል።</verse>
				<verse number="17">ቀላል የሆ​ነው የጊ​ዜው መከ​ራ​ችን ክብ​ር​ንና ጌት​ነ​ትን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አብ​ዝቶ ያደ​ር​ግ​ል​ና​ልና።</verse>
				<verse number="18">የማ​ይ​ታ​የ​ውን እንጂ የሚ​ታ​የ​ውን ተስፋ አና​ደ​ር​ግም፤ የሚ​ታ​የው ኀላፊ ነውና፥ የማ​ይ​ታ​የው ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ኖር ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">በም​ድር ያለው ማደ​ሪያ ቤታ​ችን ቢፈ​ር​ስም፥ በሰ​ማይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሰው እጅ ያል​ሠ​ራው ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ቤት እን​ዳ​ለን እና​ው​ቃ​ለን።</verse>
				<verse number="2">ስለ እርሱ የም​ን​ደ​ክ​ም​ለ​ትን በሰ​ማይ ያለ​ውን ቤታ​ች​ንን እን​ለ​ብስ ዘንድ እር​ሱን ተስፋ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።</verse>
				<verse number="3">ከለ​በ​ስ​ነ​ውም በኋላ ዕራ​ቍ​ታ​ች​ንን የም​ን​ገኝ አይ​ደ​ለ​ንም።</verse>
				<verse number="4">በዚህ ቤት ውስጥ ሳለ​ንም ከከ​ባ​ድ​ነቱ የተ​ነሣ እጅግ እና​ዝ​ና​ለን፤ ነገር ግን ሟች በሕ​ይ​ወት ይዋጥ ዘንድ ሌላ ልን​ለ​ብስ እንጂ ልን​ገ​ፈፍ አን​ወ​ድም።</verse>
				<verse number="5">ለዚ​ህም ያዘ​ጋ​ጀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ እር​ሱም የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ፈለማ ሰጠን።</verse>
				<verse number="6">እን​ግ​ዲህ ሁል​ጊዜ እመኑ፥ ጨክ​ኑም፤ በዚህ ሥጋ ሳላ​ች​ሁም እና​ንተ እን​ግ​ዶች እንደ ሆና​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ከሥ​ጋ​ች​ሁም ተለ​ይ​ታ​ችሁ ወደ ጌታ​ችን ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="7">በእ​ም​ነት እን​ኖ​ራ​ለን፤ በማ​የ​ትም አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="8">ታም​ነ​ናል፤ ይል​ቁ​ንም ከሥ​ጋ​ችን ተለ​ይ​ተን ወደ ጌታ​ችን እን​ሄ​ዳ​ለ​ንና ደስ ይለ​ናል።</verse>
				<verse number="9">አሁ​ንም ብን​ኖ​ርም፥ ብን​ሞ​ትም እር​ሱን ደስ ለማ​ሰ​ኘት እን​ጥ​ራ​ለን።</verse>
				<verse number="10">መል​ካም ቢሆን፥ ክፉም ቢሆን በሥ​ጋ​ችን እንደ ሠራ​ነው ዋጋ​ች​ንን እን​ቀ​በል ዘንድ፥ ሁላ​ችን በክ​ር​ስ​ቶስ የፍ​ርድ ዙፋን ፊት እን​ቆ​ማ​ለ​ንና።</verse>
				<verse number="11">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ዐው​ቀን ሰዎ​ችን እና​ሳ​ም​ና​ለን፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እኛ የተ​ገ​ለ​ጥን ነን፤ እን​ዲ​ሁም በል​ቡ​ና​ችሁ የተ​ገ​ለ​ጥን እንደ ሆን እን​ታ​መ​ና​ለን።</verse>
				<verse number="12">በዚህ ደግሞ በእ​ና​ንተ ዘንድ ራሳ​ች​ንን የም​ና​መ​ሰ​ግን አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን እኛ እን​ደ​ም​ን​መ​ካ​ባ​ችሁ፥ እና​ን​ተም በእኛ እን​ድ​ት​መኩ፥ ከልብ ሳይ​ሆን ለሰው ይም​ሰል በሚ​መኩ ሰዎች ዘንድ መልስ እን​ዲ​ሆ​ና​ችሁ ምክ​ን​ያ​ትን እን​ሰ​ጣ​ች​ኋ​ለን።</verse>
				<verse number="13">እኛ ሰነ​ፎች ብን​ሆ​ንም፥ ስን​ፍ​ና​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ዐዋ​ቂ​ዎች ብን​ሆ​ንም ዐዋ​ቂ​ነ​ታ​ችን ለእ​ና​ንተ ነው።</verse>
				<verse number="14">የክ​ር​ስ​ቶስ ፍቅር በዚህ አሳብ እን​ድ​ን​ጸና ያስ​ገ​ድ​ደ​ናል፤ ሁሉ ፈጽ​መው ስለ ሞቱ አንዱ ስለ ሁሉ ቤዛ ሆኖ ሞቶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="15">በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ሩ​ትም ስለ እነ​ርሱ ቤዛ ሆኖ ለሞ​ተ​ውና ለተ​ነ​ሣ​ውም እንጂ ወደ​ፊት ለራ​ሳ​ቸው የሚ​ኖሩ እን​ዳ​ይ​ሆኑ እርሱ ስለ ሁሉ ቤዛ ሆኖ ሞተ።</verse>
				<verse number="16">ስለ​ዚህ ከአ​ሁን ጀምሮ በሥጋ የም​ና​ው​ቀው የለም፤ ክር​ስ​ቶ​ስ​ንም በሥጋ ብና​ው​ቀው አሁን ግን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የም​ና​ው​ቀው አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="17">አሁ​ንም በክ​ር​ስ​ቶስ የሆ​ነው ሁሉ አዲስ ፍጥ​ረት ነው፤ የቀ​ደ​መ​ውም አለፈ፤ እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ።</verse>
				<verse number="18">ነገር ግን ሁሉ በክ​ር​ስ​ቶስ ከራሱ ጋር ከአ​ስ​ታ​ረ​ቀን፥ የማ​ስ​ታ​ረቅ መል​እ​ክ​ት​ንም ከሰ​ጠን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="19">ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይቅር ብሎ በደ​ላ​ቸ​ው​ንም ሳያ​ስብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በክ​ር​ስ​ቶስ ዓለ​ሙን ከራሱ ጋር አስ​ታ​ር​ቆ​አ​ልና፤ የዕ​ርቅ ቃሉ​ንም በእኛ ላይ አደ​ረገ፤ የይ​ቅ​ር​ታ​ው​ንም መል​እ​ክት ሰጠን።</verse>
				<verse number="20">እኛስ በክ​ር​ስ​ቶስ አም​ሳል እን​ለ​ም​ና​ለን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእኛ መጽ​ና​ና​ትን ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጋር ትታ​ረቁ ዘንድ በክ​ር​ስ​ቶስ እን​ለ​ም​ና​ች​ኋ​ለን።</verse>
				<verse number="21">ኀጢ​አት የሌ​ለ​በት እርሱ እኛን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጸ​ድ​ቀን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን እንደ ኃጥእ አድ​ር​ጓ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">ከእ​ር​ሱም ጋር አብ​ረን እየ​ሠ​ራን፥ የተ​ቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ለከ​ንቱ እን​ዳ​ታ​ደ​ር​ጓት እን​ማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለን።</verse>
				<verse number="2">እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በተ​መ​ረ​ጠ​ችው ቀን ሰማ​ሁህ፤ በመ​ዳ​ንም ቀን ረዳ​ሁህ” እነሆ፥ የተ​መ​ረ​ጠ​ችው ቀን ዛሬ ናት።</verse>
				<verse number="3">አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ች​ንም እን​ዳ​ይ​ነ​ቀፍ፥ በአ​ን​ዳች ነገር ማሰ​ና​ከያ እን​ዳ​ን​ሰጥ እን​ጠ​ን​ቀቅ።</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን በሁሉ ራሳ​ች​ንን አቅ​ን​ተን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች እን​ሁን፤ በብዙ ትዕ​ግ​ሥ​ትና በመ​ከራ፥ በች​ግ​ርና በጭ​ን​ቀት ሁሉ፥</verse>
				<verse number="5">በመ​ገ​ረ​ፍና በመ​ታ​ሰር፥ በድ​ካ​ምና በመ​ታ​ወክ፥ በመ​ት​ጋ​ትና በመ​ጾም፥</verse>
				<verse number="6">በን​ጽ​ሕ​ናና በዕ​ው​ቀት፥ በም​ክ​ርና በመ​ታ​ገሥ፥ በቸ​ር​ነ​ትና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ፥ አድ​ልዎ በሌ​ለ​በት ፍቅር፥</verse>
				<verse number="7">በእ​ው​ነት ቃል፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ለቀ​ኝና ለግራ በሚ​ሆን የጽ​ድቅ የጦር ዕቃ፥</verse>
				<verse number="8">በክ​ብ​ርና በው​ር​ደት፥ በም​ር​ቃ​ትና በር​ግ​ማን፥ እንደ አሳ​ቾች ስን​ታይ እው​ነ​ተ​ኞች ነን።</verse>
				<verse number="9">እን​ደ​ማ​ይ​ታ​ወቁ ስን​ታይ የታ​ወ​ቅን ነን፤ እንደ ሰነ​ፎች ስን​ታ​ይም ልባ​ሞች ነን፤ እንደ ሙታን ስን​ታይ ሕያ​ዋን ነን፤ የተ​ቀ​ጣን ስን​ሆ​ንም አን​ገ​ደ​ልም።</verse>
				<verse number="10">ኀዘ​ን​ተ​ኞች ስን​ሆን ዘወ​ትር ደስ​ተ​ኞች ነን፤ እንደ ድሆች ስን​ሆን ብዙ​ዎ​ችን እና​በ​ለ​ጽ​ጋ​ለን፤ ምንም የሌ​ለን ስን​ሆን ሁሉ በእ​ጃ​ችን ነው።</verse>
				<verse number="11">የቆ​ሮ​ን​ቶስ ሰዎች ሆይ፥ ለእ​ና​ንተ አፋ​ችን የተ​ከ​ፈተ ነው፤ ልባ​ች​ንም የሰፋ ነው።</verse>
				<verse number="12">ከእ​ና​ንተ የደ​ረሰ ኀዘን በእኛ የለም፤ ከእ​ኛም በእ​ና​ንተ ላይ የደ​ረሰ ኀዘን የለም፤ ነገር ግን በል​ባ​ችሁ አዝ​ና​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="13">ልጆች እንደ መሆ​ና​ችሁ፥ ይህን እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ና​ንተ ላይ ስለ​ሚ​ገ​ባኝ ብድ​ራቴ እና​ንተ ፍቅ​ራ​ች​ሁን አስ​ፉ​ልኝ።</verse>
				<verse number="14">ተጠ​ራ​ጣ​ሪ​ዎች አት​ሁኑ፤ ወደ​ማ​ያ​ምኑ ሰዎች አን​ድ​ነ​ትም አት​ሂዱ፤ ጽድ​ቅን ከኀ​ጢ​አት ጋር አንድ የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት ማን ነው? ብር​ሃ​ን​ንስ ከጨ​ለማ ጋር የሚ​ቀ​ላ​ቅል ማን ነው?</verse>
				<verse number="15">ክር​ስ​ቶ​ስን ከቤ​ል​ሆር ጋር አንድ የሚ​ያ​ደ​ር​ገው ማን ነው? ወይስ ምእ​መ​ና​ንን ከመ​ና​ፍ​ቃን ጋር አንድ ወገን የሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ቸው ማን ነው?</verse>
				<verse number="16">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦ​ትስ በጣ​ዖት ቤት ውስጥ የሚ​ያ​ኖር ማን ነው? የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪ​ያ​ዎች እኛ አይ​ደ​ለ​ን​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፥ “እኔ በእ​ነ​ርሱ አድ​ራ​ለሁ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም እኖ​ራ​ለሁ፤ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝቤ ይሆ​ኑ​ኛል።”</verse>
				<verse number="17">ስለ​ዚ​ህም “ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ተለ​ይ​ታ​ችሁ ውጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩ​ሳ​ንም አት​ቅ​ረቡ፥ እኔም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="18">አባት እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ አለ ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ግ​ዲህ ይህ ተስፋ ያለን ስለ​ሆን ራሳ​ች​ንን እና​ንጻ፤ ሥጋ​ች​ንን አና​ር​ክስ፤ ነፍ​ሳ​ች​ን​ንም አና​ሳ​ድፍ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በመ​ፍ​ራት የም​ን​ቀ​ደ​ስ​በ​ትን እን​ሥራ።</verse>
				<verse number="2">አሁ​ንም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ታገ​ሡን፥ የበ​ደ​ል​ነው የለም፤ የገ​ፋ​ነ​ውም የለም፤ ያጠ​ፋ​ነ​ውም የለም፤ የቀ​ማ​ነ​ውም የለም።</verse>
				<verse number="3">ይህ​ንም የም​ለው በእ​ና​ንተ ለመ​ፍ​ረድ አይ​ደ​ለም፤ ለሞ​ትም፥ ለሕ​ይ​ወ​ትም ቢሆን እና​ንተ በል​ባ​ችን እን​ዳ​ላ​ችሁ ፈጽሜ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="4">በእ​ና​ንተ ዘንድ እን​ዲሁ ብዙ መወ​ደድ አለኝ፤ ስለ እና​ን​ተም የም​መ​ካ​በት ብዙ ነው፤ መጽ​ና​ና​ት​ንም አገ​ኘሁ፤ ከመ​ከ​ራ​ዬም ሁሉ ይልቅ ደስ​ታዬ በዛ​ልኝ።</verse>
				<verse number="5">ወደ መቄ​ዶ​ን​ያም በደ​ረ​ስን ጊዜ ለሰ​ው​ነ​ታ​ችን ጥቂት ስን​ኳን ዕረ​ፍት አላ​ገ​ኘ​ንም፤ በሁ​ሉም መከራ አጸ​ኑ​ብን እንጂ፤ በው​ጭም መጋ​ደል ነበር፤ በው​ስ​ጥም ፍር​ሀት ነበር።</verse>
				<verse number="6">ነገር ግን ያዘ​ኑ​ትን የሚ​ያ​ጽ​ናና እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቲቶ መም​ጣት አጽ​ና​ናን።</verse>
				<verse number="7">በመ​ም​ጣቱ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በአ​ጽ​ና​ና​ች​ሁት ማጽ​ና​ና​ትም ነው እንጂ፤ ለእኛ እን​ደ​ም​ታ​ስ​ቡና እን​ደ​ም​ት​ቀኑ ፍቅ​ራ​ች​ሁን ነግ​ሮ​ናል፤ ይህ​ንም ሰምቼ ደስ​ታዬ በእ​ና​ንተ በዛ።</verse>
				<verse number="8">መጀ​መ​ሪያ በጻ​ፍ​ሁት መል​እ​ክት ባሳ​ዝ​ና​ች​ሁም እንኳ አያ​ጸ​ጽ​ተ​ኝም፤ ብጸ​ጸ​ትም፥ እነሆ ያች መል​እ​ክት ለጥ​ቂት ጊዜ ብቻ እን​ዳ​ሳ​ዘ​ነ​ቻ​ችሁ አያ​ለሁ።</verse>
				<verse number="9">አሁን ግን እኔ ስለ እርሷ በብዙ ደስ ይለ​ኛል፤ ደስ​ታ​ዬም ስለ አዘ​ና​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ ንስሓ ልት​ገቡ ስለ አዘ​ና​ችሁ እንጂ፤ ከእ​ና​ንተ አንዱ ስንኳ እን​ዳ​ይ​ጠፋ፥ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብላ​ችሁ አዝ​ና​ች​ኋ​ልና።</verse>
				<verse number="10">ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተብሎ የሚ​ደ​ረግ ኀዘን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን የሚ​ያ​ሰጥ ንስሓ ነው። ስለ ዓለም የሚ​ደ​ረግ ኀዘን ግን ሞትን ያመ​ጣል።</verse>
				<verse number="11">እነሆ፥ ያ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብላ​ችሁ ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ኀዘን ምንም የማ​ታ​ውቁ እስከ መሆን ደር​ሳ​ችሁ፥ ራሳ​ች​ሁን በበጎ ሥራና በን​ጽ​ሕና እስ​ክ​ታ​ጸኑ ድረስ፥ ትጋ​ት​ንና ክር​ክ​ርን፥ ቍጣ​ንና ፍር​ሀ​ትን፥ ናፍ​ቆ​ት​ንና ቅን​ዐ​ትን፥ በቀ​ል​ንም አደ​ረ​ገ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="12">ይህን የጻ​ፍ​ሁ​ላ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስለ እኛ እንደ ተጋ​ችሁ ይታ​ወቅ ዘንድ ነው እንጂ ስለ በደ​ለና ስለ ተበ​ደለ ሰው አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="13">ስለ​ዚ​ህም ተጽ​ና​ን​ተ​ናል፤ በመ​ጽ​ና​ና​ታ​ች​ንም ስለ ቲቶ ደስታ አብ​ልጦ ደስ አለን፤ በሁ​ላ​ችሁ ዘንድ ሰው​ነ​ቱን አሳ​ር​ፋ​ች​ኋ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="14">ስለ እና​ንተ ለእ​ርሱ በተ​መ​ካ​ሁ​በት ሁሉ አላ​ሳ​ፈ​ራ​ች​ሁ​ኝ​ምና፤ ነገር ግን ሁሉን ለእ​ና​ንተ በእ​ው​ነት እንደ ተና​ገ​ርን፥ እን​ደ​ዚሁ ደግሞ በቲቶ ፊት ትም​ክ​ህ​ታ​ችን እው​ነት ሆነ።</verse>
				<verse number="15">ስለ​ዚ​ህም እጅግ ያመ​ሰ​ግ​ና​ች​ኋል፤ እንደ ታዘ​ዛ​ች​ሁ​ለት፥ በመ​ፍ​ራ​ትና በመ​ደ​ን​ገ​ጥም እንደ ተቀ​በ​ላ​ች​ሁት ያስ​ባ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="16">እኔም በሁሉ ነገር እተ​ማ​መ​ና​ች​ኋ​ለ​ሁና ደስ ይለ​ኛል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ለመ​ቄ​ዶ​ንያ አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት የተ​ሰ​ጠ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጸጋ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">በብዙ መከራ ከመ​ፈ​ተ​ና​ቸው የተ​ነሣ ደስ​ታ​ቸው በዝ​ቶ​አ​ልና፤ በድ​ህ​ነ​ታ​ቸው ጥል​ቅ​ነ​ትም የለ​ጋ​ስ​ነ​ታ​ቸው ባለ​ጠ​ግ​ነት በዝ​ታ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="3">እነ​ርሱ ሲቻ​ላ​ቸው፥ ሳይ​ቻ​ላ​ቸ​ውም እን​ስጥ በማ​ለት ቈራ​ጦች ለመ​ሆ​ና​ቸው ምስ​ክ​ራ​ቸው እኔ ነኝና።</verse>
				<verse number="4">ለቅ​ዱ​ሳን ስለ​ሚ​ሆ​ነው አገ​ል​ግ​ሎት እን​ዲ​ተ​ባ​በሩ ይህን ቸር​ነት መላ​ል​ሰው ማለ​ዱን።</verse>
				<verse number="5">እነ​ርሱ አስ​ቀ​ድ​መው በፈ​ቃ​ዳ​ቸው፥ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈቃድ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ ለእ​ኛም አሳ​ል​ፈው ሰጥ​ተ​ዋ​ልና እኛ እንደ አሰ​ብ​ነው አይ​ደ​ለም፤</verse>
				<verse number="6">ይህ​ንም የቸ​ር​ነት ሥራ እንደ ጀመረ ይፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ ዘንድ ቲቶን ማለ​ድ​ነው።</verse>
				<verse number="7">በሁሉ ነገር በእ​ም​ነ​ትና በቃል፥ በዕ​ው​ቀ​ትም፥ በት​ጋ​ትም በእ​ና​ንተ ዘንድ በሆ​ነው ሁሉ እኛን በመ​ው​ደ​ዳ​ችሁ ፍጹ​ማን እንደ ሆና​ችሁ፥ እን​ዲ​ሁም ደግሞ ይህ​ቺን ስጦታ አብዙ።</verse>
				<verse number="8">በግድ የም​ላ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ለዚህ ሥራ የሚ​ተ​ጉ​ለት አሉና የፍ​ቅ​ራ​ች​ሁን እው​ነ​ተ​ኛ​ነት አሁን መር​ምሬ ተረ​ዳሁ።</verse>
				<verse number="9">የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ቸር​ነ​ቱን ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ በእ​ርሱ ድህ​ነት እና​ንተ ባለ​ጸ​ጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ባለ​ጸጋ ሲሆን፥ ስለ እና​ንተ ራሱን ድሃ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="10">በዚ​ህም የሚ​ጠ​ቅ​ማ​ች​ሁን እመ​ክ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ይህን ከማ​ድ​ረ​ጋ​ችሁ በፊት ፈቅ​ዳ​ች​ኋ​ልና፤ ከአ​ምና ጀም​ሮም ይህን ጀም​ራ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="11">አሁ​ንም አድ​ርጉ፤ ፈጽ​ሙም፤ መፍ​ቀድ ከመ​ሻት ነውና፤ ማድ​ረ​ግም ከማ​ግ​ኘት ነውና።</verse>
				<verse number="12">ፈቃድ ካለም፥ ሰው በሚ​ቻ​ለው መጠን ቢሰጥ ይመ​ሰ​ገ​ናል፤ በማ​ይ​ቻ​ለ​ውም መጠን አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="13">በዚህ ወራት ተካ​ክ​ላ​ችሁ እን​ድ​ት​ኖሩ ነው እንጂ ሌላው እን​ዲ​ያ​ርፍ እና​ን​ተን የም​ና​ስ​ጨ​ንቅ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="14">ኑሮ​አ​ችሁ በሁሉ የተ​ካ​ከለ ይሆን ዘንድ፥ የእ​ና​ንተ ትርፍ የእ​ነ​ር​ሱን ጕድ​ለት ይመ​ላ​ልና፥ የእ​ነ​ር​ሱም ትርፍ የእ​ና​ን​ተን ጕድ​ለት ይመ​ላ​ልና።</verse>
				<verse number="15">መጽ​ሐፍ እን​ዳለ፥ “ብዙ ያለው አላ​ተ​ረ​ፈም፤ ጥቂት ያለ​ውም አላ​ጐ​ደ​ለም።”</verse>
				<verse number="16">በቲቶ ልብ ስለ እና​ንተ ያን መት​ጋት የሰጠ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ነው።</verse>
				<verse number="17">ልመ​ና​ች​ን​ንም ተቀ​ብሎ፥ ጨክኖ ወደ እና​ንተ ይመጣ ዘንድ ቸኵ​ሏል።</verse>
				<verse number="18">ስለ ወን​ጌል ትም​ህ​ርት አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ ያመ​ሰ​ገ​ኑ​ትን ወን​ድ​ማ​ች​ን​ንም ከእ​ርሱ ጋር ልከ​ናል።</verse>
				<verse number="19">ይህም ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብ​ርና የእ​ኛን በጎ ፈቃድ ለማ​ሳ​የት በም​ና​ገ​ለ​ግ​ል​ባት በዚች ጸጋ ከእኛ ጋር አንድ ይሆን ዘንድ በአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ተሾመ።</verse>
				<verse number="20">ስለ​ም​ና​ገ​ለ​ግ​ለው ስለ​ዚህ ለጋስ ስጦታ ማንም እን​ዳ​ይ​ነ​ቅ​ፈን እን​ጠ​ነ​ቀ​ቃ​ለን።</verse>
				<verse number="21">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ብቻ ያይ​ደለ፥ ነገር ግን በሰው ፊትም መል​ካ​ሙን ነገር እና​ስ​ባ​ለ​ንና።</verse>
				<verse number="22">በብዙ የፈ​ተ​ን​ነ​ው​ንና በሁ​ሉም ነገር ትጉህ ሆኖ ያገ​ኘ​ነ​ውን አሁ​ንም በእ​ና​ንተ እጅግ ስለ​ሚ​ታ​መን ከፊት ይልቅ እጅግ ትጉ የሚ​ሆ​ነ​ውን ወን​ድ​ማ​ች​ንን ከእ​ነ​ርሱ ጋር እን​ል​ካ​ለን።</verse>
				<verse number="23">ቲቶም ቢሆን፥ ስለ እና​ንተ አብ​ሮኝ የሚ​ሠራ ጓደ​ኛዬ ነው፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ቢሆኑ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር የአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሐዋ​ር​ያት ናቸው።</verse>
				<verse number="24">አሁ​ንም መዋ​ደ​ዳ​ች​ሁ​ንና እኛም በእ​ና​ንተ የም​ን​መ​ካ​በ​ትን ሥራ በአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ፊት በግ​ልጥ አሳ​ዩ​አ​ቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">ለቅ​ዱ​ሳን ስለ​ሚ​ደ​ረ​ገው አገ​ል​ግ​ሎት የም​ጽ​ፍ​ላ​ችሁ ብዙ አለኝ</verse>
				<verse number="2">እና​ንተ እን​ደ​ም​ት​ተጉ አው​ቃ​ለ​ሁና፤ ስለ​ዚ​ህም “የአ​ካ​ይያ ሰዎች እኮ ከአ​ምና ጀምሮ አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ዋል” ብዬ በመ​ቄ​ዶ​ንያ ሰዎች ዘንድ አመ​ሰ​ገ​ን​ኋ​ችሁ፤ እነ​ሆም የእ​ና​ንተ መፎ​ካ​ከር ብዙ​ዎ​ችን ሰዎች አት​ግ​ቶ​አ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="3">በዚ​ህም ያመ​ሰ​ገ​ን​ና​ችሁ ምስ​ጋና በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ሐሰት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ብን፥ እንደ ነገ​ር​ና​ቸ​ውም ተዘ​ጋ​ጅ​ታ​ችሁ እን​ዲ​ያ​ገ​ኙ​አ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ችን ወደ እና​ንተ ላክ​ና​ቸው።</verse>
				<verse number="4">ምና​ል​ባት የመ​ቄ​ዶ​ንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ቢመ​ጡና ሳታ​ዘ​ጋጁ ቢያ​ገ​ኙ​አ​ችሁ እና​ንተ ታፍ​ራ​ላ​ችሁ ባል​ልም እኛ ስለ እና​ንተ ከነ​ገ​ር​ና​ቸው የተ​ነሣ እና​ፍ​ራ​ለን።</verse>
				<verse number="5">ስለ​ዚ​ህም አስ​ቀ​ድ​መው ወደ እና​ንተ መጥ​ተው በቅ​ድ​ሚያ የተ​ና​ገ​ራ​ች​ኋ​ትን በረ​ከ​ታ​ች​ሁን እን​ዲ​ያ​ዘ​ጋጁ ወን​ድ​ሞ​ችን ማለ​ድሁ፤ እን​ደ​ዚ​ህም የተ​ዘ​ጋጀ ይሁን፤ በረ​ከ​ትን እን​ደ​ም​ታ​ገ​ኙ​በት እንጂ በን​ጥ​ቂያ እንደ ተወ​ሰ​ደ​ባ​ችሁ አይ​ሁን።</verse>
				<verse number="6">አሳ​ንሶ የሚ​ዘራ ለእ​ርሱ እን​ዲሁ መከሩ ያን​ስ​በ​ታል፤ በብዙ የሚ​ዘራ ግን በብዙ ያመ​ር​ታል።</verse>
				<verse number="7">ሁሉ ልቡ እንደ ወደደ ያድ​ርግ፤ በደ​ስታ ይስጡ እንጂ በግድ አይ​ሆ​ንም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በደ​ስታ የሚ​ሰ​ጠ​ውን ይወ​ዳ​ልና።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካ​ሙን ነገር ሁሉ ሊያ​በ​ዛ​ላ​ችሁ ይች​ላል፤ ፍጹም በረ​ከ​ቱ​ንም ለዘ​ወ​ትር ያበ​ዛ​ላ​ችሁ ዘንድ፥ ለሁ​ሉም ታተ​ር​ፉ​ታ​ላ​ችሁ፤ በጎ ሥራ መሥ​ራ​ት​ንም ታበ​ዛ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="9">“በተነ፤ ለድ​ሃም ሰጠ፤ ጽድ​ቁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል” ብሎ መጽ​ሐፍ እንደ ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="10">እርሱ ዘርን ለዘሪ ይሰ​ጣል፤ እህ​ል​ንም ለም​ግብ ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ ዘራ​ች​ሁ​ንም ያበ​ዛ​ላ​ች​ኋል፤ የጽ​ድ​ቃ​ች​ሁ​ንም መከር ያበ​ጃል።</verse>
				<verse number="11">ለብዙ ሰዎች ስለ ሰጣ​ች​ሁም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ጋና በም​ታ​ደ​ር​ግ​ላ​ችሁ ልግ​ስና ሁሉ ባለ​ጸ​ጎች ትሆ​ና​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="12">ይህቺ የዚህ ሥራ አገ​ል​ግ​ሎት ግዳጅ የም​ት​ፈ​ጽ​መው ለዚህ ለቅ​ዱ​ሳን ችግር መሟ​ላት ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በቅ​ዱ​ሳን ዘን​ድም ደግሞ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ጋና ታበ​ዛ​ለች።</verse>
				<verse number="13">ክር​ስ​ቶስ ላስ​ተ​ማ​ራት ትም​ህ​ርት ታዝ​ዛ​ች​ኋ​ልና፥ ሁላ​ች​ሁም ደስ ብሎ​አ​ች​ሁና ተባ​ብ​ራ​ችሁ አወ​ጣ​ጥ​ታ​ች​ኋ​ልና በዚች በሃ​ይ​ማ​ኖ​ታ​ችሁ ፈተና ምክ​ን​ያት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤</verse>
				<verse number="14">እነ​ር​ሱም ስለ እና​ንተ ይጸ​ል​ያሉ፤ ስለ አደ​ረ​ባ​ችሁ ታላቅ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋም ሊያ​ዩ​አ​ችሁ ይመ​ኛሉ።</verse>
				<verse number="15">ስለ​ማ​ት​መ​ረ​መ​ርና ባላ​ሰ​ቡ​አት ጊዜ ስለ​ም​ት​መ​ጣው ጸጋው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኔ ጳው​ሎስ በእ​ና​ንተ ዘንድ ፊት ለፊት ሳለሁ ትሑት የሆ​ንሁ፥ ከእ​ና​ንተ ብርቅ ግን የም​ደ​ፍ​ራ​ችሁ በክ​ር​ስ​ቶስ የዋ​ህ​ነ​ትና ቸር​ነት እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፥ በፍ​ቅ​ራ​ችሁ እታ​መ​ና​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="2">ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ እሠ​ራ​ለሁ፤ በሥ​ጋዊ ሥር​ዐ​ትም እን​ደ​ም​ን​ኖር አድ​ር​ገው በሚ​ጠ​ረ​ጥ​ሩን ሰዎች ላይ በድ​ፍ​ረት ለመ​ና​ገር አስ​ባ​ለሁ፤ እና​ንተ ግን በዚህ ዓይ​ነት ድፍ​ረት እን​ድ​ና​ገር እን​ዳ​ታ​ደ​ር​ጉኝ እለ​ም​ና​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">በሥ​ጋ​ች​ንስ እን​ሄ​ዳ​ለን፤ ነገር ግን በእ​ር​ሱው ሥር​ዐት የም​ን​ሄ​ድና የም​ን​ዋጋ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="4">የጦር ዕቃ​ችን ሥጋዊ አይ​ደ​ለ​ምና፥ ጽኑ ምሽ​ግን በሚ​ያ​ፈ​ርስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ነው እንጂ።</verse>
				<verse number="5">ልብ ሁሉ ይማ​ረክ ዘንድ ኅሊ​ናም ለክ​ር​ስ​ቶስ ይገዛ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ የሚ​ታ​በ​የ​ው​ንና ከፍ ከፍ የሚ​ለ​ውን እና​ፈ​ር​ሳ​ለን።</verse>
				<verse number="6">እና​ንተ ትእ​ዛ​ዝን በፈ​ጸ​ማ​ችሁ ጊዜ የማ​ይ​ገ​ዛ​ውን ሁሉ እኛ ልን​በ​ቀ​ለው ዝግ​ጁ​ዎች ነን።</verse>
				<verse number="7">በፊ​ታ​ችሁ ያለ​ውን ተመ​ል​ከቱ፤ ማንም በክ​ር​ስ​ቶስ ያመነ ቢሆን፥ ይህን እንደ ገና በራሱ ይቍ​ጠ​ረው፤ እርሱ የክ​ር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ እኛም እን​ዲሁ ነንና።</verse>
				<verse number="8">እና​ን​ተን ለማ​ነጽ እንጂ፥ እና​ን​ተን ለማ​ፍ​ረስ ያይ​ደለ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ና​ንተ ላይ በሰ​ጠን ሥል​ጣን እጅግ የተ​መ​ካ​ሁት መመ​ካት ቢኖር አላ​ፍ​ርም።</verse>
				<verse number="9">ነገር ግን በመ​ል​እ​ክ​ቶች የማ​ስ​ፈ​ራ​ራ​ችሁ እን​ዳ​ይ​መ​ስ​ላ​ችሁ፥ ይህን ትም​ክ​ሕ​ቴን እተ​ወ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">ከሰ​ዎች መካ​ከል “መል​እ​ክ​ቶቹ ከባ​ዶ​ችና አስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች ናቸው፤ ሰው​ነቱ ግን ደካማ ነው፤ ነገ​ሩም ተርታ ነው” የሚሉ አሉና።</verse>
				<verse number="11">ነገር ግን ይህን ነገር የሚ​ና​ገር ይህን ይወቅ፤ በሌ​ለ​ን​በት ጊዜ በመ​ል​እ​ክ​ታ​ችን እንደ ተገ​ለ​ጠው እንደ ቃላ​ችን፥ ባለ​ን​በ​ትም ጊዜ በሥ​ራ​ችን እን​ዲሁ ነን።</verse>
				<verse number="12">እነ​ርሱ ራሳ​ቸ​ውን በአ​ሰ​ቡ​ትና በገ​መ​ገ​ሙት መጠን ራሳ​ቸ​ውን ከሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑት ሰዎች ጋር ራሳ​ች​ንን ልን​ቈ​ጥር፥ ወይም ራሳ​ች​ንን ልና​ስ​ተ​ያይ አን​ደ​ፍ​ርም፤ እነ​ርሱ ራሳ​ቸ​ውም የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን ትር​ጕ​ሙን አያ​ው​ቁ​ትም።</verse>
				<verse number="13">እኛስ ወደ እና​ንተ እስ​ክ​ን​ደ​ርስ ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በወ​ሰ​ነ​ልን ሕግና ሥር​ዐት እንጂ፥ ከዐ​ቅ​ማ​ችን አል​ፈን እጅግ አን​መ​ካም።</verse>
				<verse number="14">ወደ እና​ንተ እን​ደ​ማ​ን​ደ​ርስ አድ​ር​ገን፥ ራሳ​ች​ንን የም​ና​መ​ሰ​ግን አይ​ደ​ለ​ምና፤ ነገር ግን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ሕግ በማ​ስ​ተ​ማር ወደ እና​ንተ ደር​ሰ​ናል።</verse>
				<verse number="15">እኛስ በማ​ይ​ገባ ሌላ በደ​ከ​መ​በት አን​መ​ካም፤ ነገር ግን ሃይ​ማ​ኖ​ታ​ችሁ እን​ድ​ት​ሰፋ፥ የተ​ሠ​ራ​ች​ላ​ችሁ ሕግም በእ​ና​ንተ እን​ድ​ት​ጸና ተስፋ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።</verse>
				<verse number="16">አብ​ዝ​ተ​ንም እና​ስ​ተ​ም​ራ​ች​ኋ​ለን፤ ያን​ጊ​ዜም መጠ​ና​ችን ከሥ​ራ​ችን ጋር ከፍ ከፍ ይላል፤ እኛስ ቀና ባል​ሆ​ነ​ውና በማ​ይ​ገ​ባው አን​መ​ካም።</verse>
				<verse number="17">“የሚ​መካ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመካ።”</verse>
				<verse number="18">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያከ​በ​ረው ብቻ ይከ​ብ​ራል እንጂ ራሱን የሚ​ያ​ከ​ብር የተ​መ​ረጠ አይ​ደ​ለም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">በስ​ን​ፍ​ናዬ እና​ገር ዘንድ ጥቂት ልት​ታ​ገ​ሡኝ ይገባ ነበር፤ ቢሆ​ንም በር​ግጥ ታገ​ሡኝ፤</verse>
				<verse number="2">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ገባ ቅን​ዐት እቀ​ና​ላ​ች​ኋ​ለ​ሁና፤ ወደ እርሱ አቀ​ር​ባ​ችሁ ዘንድ ለአ​ንዱ ንጹሕ ድን​ግል ሙሽራ ለክ​ር​ስ​ቶስ አጭ​ቻ​ች​ኋ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="3">ነገር ግን እባብ ሔዋ​ንን በተ​ን​ኰሉ እን​ዳ​ሳ​ታት፥ አሳ​ባ​ችሁ ከክ​ር​ስ​ቶስ የዋ​ህ​ነ​ትና ንጽ​ሕና ምና​ል​ባት እን​ዳ​ይ​ለ​ወጥ ብዬ እፈ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">ወደ እና​ንተ የመ​ጣና እኛ ወደ አላ​ስ​ተ​ማ​ር​ና​ችሁ ወደ ሌላ ኢየ​ሱስ የጠ​ራ​ችሁ ቢኖር፥ ወይም ያል​ተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁት ሌላ መን​ፈስ ቢኖር፥ ወይም ያል​ተ​ማ​ራ​ች​ሁት ሌላ ወን​ጌል ቢኖር ልት​ጠ​ብ​ቁን ይገ​ባል።</verse>
				<verse number="5">እኔ ግን ሌሎች ሐዋ​ር​ያት ከአ​ስ​ተ​ማ​ሩት ያጐ​ደ​ል​ሁ​ባ​ችሁ የለም ይመ​ስ​ለ​ኛል።</verse>
				<verse number="6">እኔ በአ​ነ​ጋ​ገሬ አላ​ዋቂ ብሆ​ንም በዕ​ው​ቀት ግን እን​ዲሁ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ነገር ግን ሁሉን በሁሉ እገ​ል​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">ወይስ ራሴን በሁሉ ያዋ​ረ​ድሁ በደ​ልሁ ይሆን? እና​ንተ ከፍ ከፍ ትሉ ዘንድ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ወን​ጌል ያለ ዋጋ አስ​ተ​ም​ሬ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="8">እና​ን​ተን አገ​ለ​ግል ዘንድ፥ ከሌ​ሎች አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ተቀ​ብዬ፥ ለም​ግቤ ያህል ወሰ​ድሁ፤</verse>
				<verse number="9">ከእ​ና​ንተ ዘንድ በነ​በ​ር​ሁ​በት ጊዜም፥ ስቸ​ገር ገን​ዘ​ባ​ች​ሁን አል​ተ​መ​ኘ​ሁም። ባል​በ​ቃ​ኝም ጊዜ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከመ​ቄ​ዶ​ንያ መጥ​ተው አሙ​አ​ሉ​ልኝ፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ እን​ዳ​ል​ከ​ብ​ድ​ባ​ችሁ በሁሉ ተጠ​ነ​ቀ​ቅሁ፤ ወደ ፊትም እጠ​ነ​ቀ​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="10">የክ​ር​ስ​ቶስ ዕው​ነት አብ​ሮኝ ይኖ​ራ​ልና፥ ይህቺ ደስ​ታዬ በአ​ካ​ይያ አው​ራጃ አል​ተ​ከ​ለ​ከ​ለ​ች​ብ​ኝም።</verse>
				<verse number="11">ስለ​ምን ነው? አል​ወ​ዳ​ች​ሁ​ምና ነውን? እን​ደ​ም​ወ​ድ​ዳ​ች​ሁስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያው​ቃል።</verse>
				<verse number="12">ነገር ግን ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትም ቢሆን፥ የማ​ደ​ር​ገ​ውም ቢሆን፥ እነ​ርሱ እንደ እኛ የሚ​መ​ኩ​በ​ትን ያገኙ ዘንድ፥ ምክ​ን​ያት የሚ​ሹ​ትን ምክ​ን​ያት አሳ​ጣ​ቸው ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="13">የሚ​ተ​ነ​ኰሉ፥ ራሳ​ቸ​ውን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ሐዋ​ር​ያት የሚ​ያ​ስ​መ​ስሉ፥ ዐመ​ፅ​ንም የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሐሰ​ተ​ኞች ሐዋ​ር​ያት አሉና።</verse>
				<verse number="14">ይህም አያ​ስ​ደ​ን​ቅም፤ ሰይ​ጣን ራሱ ተለ​ውጦ እንደ ብር​ሃን መል​አክ ይመ​ስ​ላ​ልና።</verse>
				<verse number="15">መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹም የጽ​ድቅ መላ​እ​ክ​ትን ቢመ​ስሉ፥ ይህ ታላቅ ነገር አይ​ደ​ለም፤ ፍጻ​ሜ​ያ​ቸው ግን እንደ ሥራ​ቸው ነው።</verse>
				<verse number="16">ደግ​ሞም እን​ዲህ እላ​ለሁ፦ ሰነፍ የሚ​ያ​ደ​ር​ገኝ አይ​ኑር፤ ያውም ብሆን እኔ ጥቂት እመካ ዘንድ እንደ ሰነፍ እንኳ ብሆን ተቀ​በ​ሉኝ።</verse>
				<verse number="17">ይህም ቢሆን የም​ና​ገ​ረው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ገባ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ስለ​ዚ​ህች ትም​ክ​ሕቴ እንደ ሰነፍ እና​ገ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="18">በሥ​ጋዊ ሥር​ዐት የሚ​መኩ ብዙ​ዎች ናቸ​ውና እኔ ደግሞ እመ​ካ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">እና​ንተ ልባ​ሞች ስት​ሆኑ ሰነ​ፎ​ችን መስ​ማት ደስ ያሰ​ኛ​ች​ኋ​ልና።</verse>
				<verse number="20">የሚ​ገ​ዙ​አ​ች​ሁ​ንና የሚ​ቀ​ሙ​አ​ች​ሁን፥ መባያ የሚ​ያ​ደ​ር​ጓ​ች​ሁ​ንና የሚ​ታ​በ​ዩ​ባ​ች​ሁን፥ ፊታ​ች​ሁ​ንም በጥፊ የሚ​መ​ት​ዋ​ች​ሁን ትታ​ገ​ሡ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ች​ሁና።</verse>
				<verse number="21">እኛ እንደ ደካ​ሞች መስ​ለን እንደ ነበ​ርን፥ ይህን በው​ር​ደት እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ነገር ግን ማንም በሚ​ደ​ፍ​ር​በት እኔ ደግሞ እደ​ፍ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="22">እነ​ርሱ ዕብ​ራ​ው​ያን ቢሆኑ እኔም እንደ እነ​ርሱ ነኝ፤ እነ​ርሱ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ቢሆኑ እኔም እንደ እነ​ርሱ ነኝ፤ እነ​ርሱ የአ​ብ​ር​ሃም ልጆች ቢሆኑ እኔም እንደ እነ​ርሱ ነኝ።</verse>
				<verse number="23">እነ​ርሱ የክ​ር​ስ​ቶስ አገ​ል​ጋ​ዮች ቢሆ​ኑም እኔም እንደ ሰነፍ ለራሴ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ እኔ እበ​ል​ጣ​ለሁ፤ እጅ​ግም ደከ​ምሁ፤ ብዙ ጊዜ ተገ​ረ​ፍሁ፤ ብዙ ጊዜም ታሰ​ርሁ፤ ብዙ ጊዜም ለሞት ተዘ​ጋ​ጀሁ።</verse>
				<verse number="24">አይ​ሁድ አን​ዲት ስት​ቀር አም​ስት ጊዜ አርባ አርባ ገረ​ፉኝ።</verse>
				<verse number="25">ሦስት ጊዜ በበ​ትር ደበ​ደ​ቡኝ፤ አንድ ጊዜ በድ​ን​ጋይ መቱኝ፤ መር​ከቤ ሦስት ጊዜ ተሰ​በ​ረች፤ በጥ​ልቁ ባሕር ውስጥ ስዋኝ አድሬ፥ ስዋኝ ዋልሁ።</verse>
				<verse number="26">በመ​ን​ገድ ዘወ​ትር መከራ እቀ​በል ነበር፤ በወ​ን​ዝም መከራ ተቀ​በ​ልሁ፤ ወን​በ​ዴ​ዎ​ችም አሠ​ቃ​ዩኝ፤ ዘመ​ዶ​ችም አስ​ጨ​ነ​ቁኝ፤ አሕ​ዛብ መከራ አጸ​ኑ​ብኝ፤ በከ​ተማ መከራ ተቀ​በ​ልሁ፤ በበ​ረ​ሃም መከራ ተቀ​በ​ልሁ፤ በባ​ሕ​ርም መከራ ተቀ​በ​ልሁ፤ ሐሰ​ተ​ኞች መም​ህ​ራን መከራ አጸ​ኑ​ብኝ።</verse>
				<verse number="27">በድ​ካ​ምና በጥ​ረት፥ ብዙ ጊዜም ዕን​ቅ​ልፍ በማ​ጣት፥ በመ​ራ​ብና በመ​ጠ​ማት፥ አብ​ዝ​ቶም በመ​ጾም፥ በብ​ር​ድና በመ​ራ​ቆት ተቸ​ገ​ርሁ።</verse>
				<verse number="28">የቀ​ረ​ው​ንም ነገር ሳል​ቈ​ጥር ዕለት ዕለት የሚ​ከ​ብ​ድ​ብኝ የአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ አሳብ ነው።</verse>
				<verse number="29">ታሞ እኔ የማ​ላ​ዝ​ን​ለት ማን ነው? በድ​ሎስ እኔ የማ​ል​ደ​ነ​ግ​ጥ​ለት ማን ነው?</verse>
				<verse number="30">መመ​ካት የሚ​ገባ ከሆ​ነስ እኔም በመ​ከ​ራዬ እመ​ካ​ለሁ።</verse>
				<verse number="31">ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቡሩክ አም​ላክ የሆነ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሐሰት እን​ደ​ማ​ል​ና​ገር ያው​ቃል።</verse>
				<verse number="32">በደ​ማ​ስቆ ከተማ ከን​ጉሥ አር​ስ​ጣ​ስ​ዮስ በታች የሆነ የአ​ሕ​ዛብ አለቃ ሊይ​ዘኝ ወድዶ የደ​ማ​ስ​ቆን ከተማ ያስ​ጠ​ብቅ ነበር።</verse>
				<verse number="33">በቅ​ር​ጫ​ትም አድ​ር​ገው በመ​ስ​ኮቱ በኩል በአ​ጥሩ ላይ አወ​ረ​ዱኝ፤ ከእ​ጁም አመ​ለ​ጥሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">እነሆ መመ​ካት ይቻ​ለ​ኛል፤ ነገር ግን አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ ደግ​ሞም ወደ ጌታ ራእ​ይና መገ​ለጥ እሄ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">በክ​ር​ስ​ቶስ ያመነ አንድ ሰው አው​ቃ​ለሁ፤ ዘመኑ ከዐ​ሥራ አራት ዓመት በፊት ነው፤ ነገር ግን በሥ​ጋው ይሁን በነ​ፍሱ እንጃ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያው​ቃል፤ ያን ሰው እስከ ሦስ​ተ​ኛው ሰማይ ድረስ ነጥ​ቀው ወሰ​ዱት።</verse>
				<verse number="3">ያን ሰው አው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ በሥ​ጋው ይሁን በነ​ፍሱ እንጃ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያው​ቃል።</verse>
				<verse number="4">ወደ ገነ​ትም ነጥ​ቀው ወሰ​ዱት፤ በዚ​ያም ሰው ሊና​ገ​ረው የማ​ይ​ች​ለ​ውን የማ​ይ​ተ​ረ​ጐም ነገር ሰማ።</verse>
				<verse number="5">ስለ​ዚ​ህም እን​ደ​ዚህ ባለው እመ​ካ​ለሁ፤ በመ​ከ​ራዬ እንጂ በራ​ሴስ አል​መ​ካም።</verse>
				<verse number="6">ልመካ ብሻም አላ​ዋቂ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ እው​ነ​ቱን እና​ገ​ራ​ለ​ሁና፤ ነገር ግን ስላ​ዩ​ኝና ስለ ሰሙኝ እን​ደ​ም​በ​ልጥ አድ​ር​ገው እን​ዳ​ይ​ጠ​ራ​ጠ​ሩኝ ትቸ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">ስለ​ዚ​ህም ቢሆን በብዙ ራእይ እን​ዳ​ል​ታ​በይ ሰው​ነ​ቴን የሚ​ወጋ እር​ሱም የሚ​ጐ​ስ​መኝ የሰ​ይ​ጣን መል​እ​ክ​ተኛ ተሰ​ጠኝ።</verse>
				<verse number="8">ስለ​ዚ​ህም ከእኔ ያር​ቀው ዘንድ ጌታ​ዬን ሦስት ጊዜ ማለ​ድ​ሁት።</verse>
				<verse number="9">እር​ሱም፥ “ጸጋዬ ይበ​ቃ​ሀል፤ ኀይ​ልስ በደዌ ያል​ቃል” አለኝ፤ የክ​ር​ስ​ቶ​ስም ኀይል በእኔ ላይ ያድር ዘንድ በመ​ከ​ራዬ ልመካ ወደ​ድሁ።</verse>
				<verse number="10">ስለ​ዚ​ህም ስለ ክር​ስ​ቶስ መከራ መቀ​በ​ልን፥ መሰ​ደ​ብን፥ መጨ​ነ​ቅን፥ መሰ​ደ​ድን፥ መቸ​ገ​ር​ንም ወደ​ድሁ፤ መከራ በተ​ቀ​በ​ልሁ ጊዜ ወዲ​ያ​ውኑ እበ​ረ​ታ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="11">እነሆ እና​ንተ ስላ​ገ​በ​ራ​ች​ሁኝ በመ​መ​ካቴ ሰነፍ ሆንሁ፤ ለእ​ኔማ በእ​ና​ንተ ዘንድ ልከ​ብ​ርና እና​ን​ተም ምስ​ክ​ሮች ልት​ሆ​ኑኝ ይገ​ባኝ ነበር፤ እኔ እንደ ኢም​ንት ብሆ​ንም ዋና​ዎቹ ሐዋ​ር​ያት ሁሉ ከሠ​ሩት ሥራ ያጐ​ደ​ል​ሁ​ባ​ችሁ የለ​ምና።</verse>
				<verse number="12">የሐ​ዋ​ር​ያት ምል​ክ​ትስ በፍ​ጹም ትዕ​ግ​ሥ​ትና በተ​አ​ም​ራት፥ ድንቅ ሥራ በመ​ሥ​ራ​ትና በኀ​ይ​ላት ተደ​ር​ጎ​ላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="13">እከ​ብ​ድ​ባ​ችሁ ዘንድ ወደ እና​ንተ ካለ​መ​ም​ጣቴ በቀር፥ ከአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ ያሳ​ነ​ስ​ኋ​ችሁ በም​ን​ድን ነው? ይህ​ቺን በደ​ሌን ይቅር በሉኝ።</verse>
				<verse number="14">እነሆ ወደ እና​ንተ ልመጣ ስዘ​ጋጅ ይህ ሦስ​ተ​ኛዬ ነው፤ ነገር ግን አል​ተ​ፋ​ጠ​ን​ሁም ገን​ዘ​ባ​ች​ሁን ያይ​ደለ፥ እና​ን​ተን እሻ​ለ​ሁና፤ ልጆች ለወ​ላ​ጆ​ቻ​ቸው ያይ​ደለ ወላ​ጆች ለል​ጆ​ቻ​ቸው ሊያ​ከ​ማቹ ይገ​ባ​ልና፤</verse>
				<verse number="15">እኔ ግን እጥፍ ድርብ አወ​ጣ​ለሁ፤ ስለ ሕይ​ወ​ታ​ች​ሁም ሰው​ነ​ቴን አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እና​ን​ተ​ንም እጅግ ብወ​ዳ​ችሁ ራሴን ወደ​ድሁ።</verse>
				<verse number="16">እኔ አል​ከ​በ​ድ​ሁ​ባ​ች​ሁም፤ ነገር ግን ምክር ዐዋቂ ሆኜ በመ​ጠ​በብ ወሰ​ድ​ኋ​ችሁ።</verse>
				<verse number="17">በውኑ ይህን አድ​ር​ጉ​ልኝ ብዬ ወደ እና​ንተ የላ​ክ​ሁት መል​እ​ክት አለን? ወይስ የቀ​ማ​ኋ​ችሁ ነገር አለን? እንጃ።</verse>
				<verse number="18">እነሆ ቲቶን ማለ​ድ​ሁት፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ሌላ​ውን ወን​ድ​ማ​ች​ንን ላክ​ሁት፤ በውኑ ቲቶ የበ​ደ​ላ​ችሁ በደል አለን? በእ​ርሱ በአ​ደ​ረው መን​ፈስ የም​ን​መ​ላ​ለስ፥ እር​ሱም የሄ​ደ​በ​ትን ፍለጋ የም​ን​ከ​ተል አይ​ደ​ለ​ን​ምን?</verse>
				<verse number="19">እኛስ ደግሞ ስለ ራሳ​ችን የም​ን​ከ​ራ​ከ​ራ​ችሁ ይመ​ስ​ላ​ች​ኋ​ልን? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በክ​ር​ስ​ቶስ ሆነን እን​ና​ገ​ራ​ለን፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ይህ ሁሉ ግን እና​ንተ ትታ​ነጹ ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="20">ነገር ግን ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ እን​ደ​ም​ወ​ደው ሆና​ችሁ ያላ​ገ​ኘ​ኋ​ችሁ እንደ ሆነ፤ እኔም እን​ደ​ማ​ት​ወ​ዱት እሆ​ን​ባ​ች​ኋ​ለሁ ብዬ እፈ​ራ​ለሁ፤ ወይም እኮ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ክር​ክር፥ ኵራት፥ መቀ​ና​ናት፥ መበ​ሳ​ጨት፥ መዘ​ባ​በት፥ ወይም መተ​ማ​ማት፥ መታ​ወክ፥ ወይም ልብን ማስ​ታ​በይ ይኖር ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="21">ወይም እንደ ገና ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሳ​ዝ​ነኝ ይሆ​ናል፤ በድ​ለው ንስሓ ላል​ገ​ቡም ስለ ርኵ​ስ​ነ​ታ​ቸ​ውና ስለ መዳ​ራ​ታ​ቸው፥ ስለ​ሚ​ሠ​ሩት ዝሙ​ታ​ቸ​ውም ለብ​ዙ​ዎች አዝን ይሆ​ናል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">ወደ እና​ንተ ስመጣ እነሆ ይህ ሦስ​ተ​ኛዬ ነው፤ ነገር ሁሉ፥ በሁ​ለት ወይም በሦ​ስት ምስ​ክር አፍ የሚ​ጸና አይ​ደ​ለ​ምን?</verse>
				<verse number="2">ጥን​ቱን አስ​ቀ​ድሜ ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አሁ​ንም አስ​ቀ​ድሜ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ቀድሞ ከእ​ና​ንተ ጋር ሳለሁ እንደ ነገ​ር​ሁ​አ​ችሁ፥ አስ​ቀ​ድሞ ለበ​ደሉ፥ ለሌ​ሎ​ችም ሁሉ እንደ ገና የመ​ጣሁ እንደ ሆነ ርኅ​ራኄ እን​ዳ​ላ​ደ​ርግ፥ እን​ዲሁ ሳል​ኖር ለሦ​ስ​ተኛ ጊዜ እና​ገ​ራ​ለሁ፥</verse>
				<verse number="3">ክር​ስ​ቶስ በእኔ አድሮ እን​ደ​ሚ​ና​ገር ማስ​ረጃ ትሻ​ላ​ች​ሁና፤ እር​ሱም ሁሉ የሚ​ቻ​ለው ነው እንጂ፥ በእ​ና​ንተ ዘንድ የሚ​ሳ​ነው የለም።</verse>
				<verse number="4">በድ​ካም ተሰ​ቅ​ሎ​አ​ልና፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይል ሕያው ነውና፤ እኛም ከእ​ርሱ ጋር እን​ደ​ክ​ማ​ለ​ንና፤ ነገር ግን ስለ እና​ንተ በሚ​ሆን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ከእ​ርሱ ጋር በሕ​ይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን።</verse>
				<verse number="5">በሃ​ይ​ማ​ኖት ጸን​ታ​ችሁ እንደ ሆነ ራሳ​ች​ሁን መር​ምሩ፤ እና​ንተ ራሳ​ች​ሁን ፈትኑ፤ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ዳለ አታ​ው​ቁ​ምን? እን​ዲህ ካል​ሆነ ግን እና​ንተ የተ​ና​ቃ​ችሁ ናችሁ።</verse>
				<verse number="6">እኛም ብን​ሆን የተ​ና​ቅን እን​ዳ​ይ​ደ​ለን እን​ደ​ም​ታ​ውቁ እኔ አም​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">ምንም ክፉ ሥራ እን​ዳ​ት​ሠሩ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ጸ​ል​ያ​ለን፤ መል​ካም ነገር እን​ድ​ታ​ደ​ርጉ ብቻ ነው እንጂ እኛ ደጎች ልን​ባል አይ​ደ​ለም፤ እኛም እንደ ተናቁ ሰዎች እን​ሆ​ና​ለን።</verse>
				<verse number="8">ለዕ​ው​ነት ጸን​ተን እን​ኖ​ራ​ለን እንጂ፤ ከዕ​ው​ነት መው​ጣት አን​ች​ል​ምና።</verse>
				<verse number="9">እና​ንተ ትበ​ረቱ ዘንድ እኛ ስን​ደ​ክም ደስ ይለ​ናል። ጸሎ​ታ​ች​ንም እና​ንተ ፍጹ​ማን ትሆኑ ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="10">ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለማ​ፍ​ረስ ያይ​ደለ ለማ​ነጽ በሰ​ጠን ሥል​ጣን ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ ቍርጥ ነገር እን​ዳ​ላ​ደ​ር​ግ​ባ​ችሁ፥ ሥል​ጣን እን​ዳ​ለው ሰው ከእ​ና​ንተ ጋር ሳል​ኖር ይህን እጽ​ፋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">ወድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ግ​ዲህ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ጽኑ፤ ታገሡ፤ በአ​ንድ ልብም ሁኑ፤ በሰ​ላም ኑሩ፤ የሰ​ላ​ምና የፍ​ቅር አም​ላ​ክም ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን።</verse>
				<verse number="12">በተ​ቀ​ደሰ ሰላ​ምታ እርስ በር​ሳ​ችሁ ሰላም ተባ​ባሉ፤ ቅዱ​ሳን ሁሉ እን​ዴት ናችሁ? ይሏ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="13">የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጸጋ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍቅር፥ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም አን​ድ​ነት ከሁ​ላ​ችሁ ጋር ይሁን። አሜን። የመ​ቄ​ዶ​ንያ ክፍል በም​ት​ሆን በፊ​ል​ጵ​ስ​ዩስ ተጽፎ በቲ​ቶና በሉ​ቃስ እጅ ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች የተ​ላ​ከው ሁለ​ተ​ኛዉ መል​እ​ክት ተፈ​ጸመ። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን፤ አሜን።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="48">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስና ከሙ​ታን ለይቶ በአ​ስ​ነ​ሣው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ ነው እንጂ ከሰ​ዎች ወይም በሰው ሐዋ​ርያ ካል​ሆነ ከጳ​ው​ሎስ፥</verse>
				<verse number="2">አብ​ረ​ውኝ ካሉ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም፥ በገ​ላ​ትያ ላሉ አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያን፤</verse>
				<verse number="3">ከአ​ባ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰላ​ምና ጸጋ ለእ​ና​ንተ ይሁን።</verse>
				<verse number="4">በክፉ ከሚ​ቃ​ወም ከዚህ ዓለም ያድ​ነን ዘንድ በአ​ባ​ታ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈቃድ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ራሱን አሳ​ልፎ ሰጠ።</verse>
				<verse number="5">ለእ​ርሱ ክብር ይሁን፤ ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም አሜን።</verse>
				<verse number="6">በጸ​ጋዉ የጠ​ራ​ች​ሁን ክር​ስ​ቶ​ስን ከማ​መን ወደ ልዩ ወን​ጌል እን​ዴት ፈጥ​ነው እን​ዳ​ስ​ወ​ጧ​ችሁ አደ​ን​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">እርሱ ግን ሌላ አይ​ደ​ለም፤ የሚ​ያ​ው​ኳ​ችሁ ከክ​ር​ስ​ቶ​ስም ወን​ጌል ሊያ​ጣ​ምሙ የሚ​ወዱ አሉ እንጂ።</verse>
				<verse number="8">እና​ንተ ግን የእ​ኛን ፍለጋ ተከ​ተሉ፤ እና​ን​ተስ እኛም ብን​ሆን ወይም መል​አክ ከሰ​ማይ ወርዶ እኛ ካስ​ተ​ማ​ር​ና​ችሁ ወን​ጌል ሌላ ቢሰ​ብ​ክ​ላ​ችሁ ውጉዝ ይሁን።</verse>
				<verse number="9">አስ​ቀ​ድሜ እንደ አልሁ አሁ​ንም ደግሞ እላ​ለሁ፦ ካስ​ተ​ማ​ር​ና​ችሁ ሌላ ትም​ህ​ርት ያስ​ተ​ማ​ራ​ችሁ ቢኖር ውጉዝ ይሁን።</verse>
				<verse number="10">አሁ​ንስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያይ​ደለ ለሰው ብዬ አስ​ተ​ም​ራ​ለ​ሁን? ወይስ ሰውን ደስ አሰ​ኛ​ለ​ሁን? ሰውን ደስ ላሰኝ ብወ​ድስ የክ​ር​ስ​ቶስ ባሪያ አይ​ደ​ለ​ሁም።</verse>
				<verse number="11">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ያስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ችሁ ወን​ጌል ስለ ሰው እን​ዳ​ይ​ደለ አስ​ታ​ው​ቃ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">ጌታ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ገለ​ጠ​ልኝ እንጂ፥ እኔ ከሰው አል​ተ​ቀ​በ​ል​ሁ​ትም፤ አል​ተ​ማ​ር​ሁ​ት​ምም።</verse>
				<verse number="13">በአ​ይ​ሁድ ሥር​ዐት ውስጥ በነ​በ​ርሁ ጊዜ፥ የነ​በ​ረ​ውን የቀ​ድሞ ሥራ​ዬን ሰም​ታ​ች​ኋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን እጅግ አሳ​ድ​ድና መከራ አጸ​ና​ባ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="14">ለአ​ባ​ቶች ሥር​ዐት እጅግ ቀና​ተኛ ነበ​ር​ሁና በወ​ገ​ኖች ዘንድ ከጓ​ደ​ኞች ሁሉ በአ​ይ​ሁድ ዘንድ እጅግ ከበ​ርሁ።</verse>
				<verse number="15">ከእ​ናቴ ማኅ​ፀን ለይቶ ያወ​ጣኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በወ​ደደ ጊዜ በጸ​ጋው ጠራኝ።</verse>
				<verse number="16">በስ​ሙም ለአ​ሕ​ዛብ ወን​ጌ​ልን አስ​ተ​ምር ዘንድ፥ በእ​ጄም የልጁ ክብር ይታ​ወቅ ዘንድ ልጁን ገለ​ጠ​ልኝ፤ ያን​ጊ​ዜም ከሥ​ጋ​ዊና ከደ​ማዊ ሰው ጋር አል​ተ​ማ​ከ​ር​ሁም።</verse>
				<verse number="17">ከእኔ በፊት ወደ ነበ​ሩት ወደ ሐዋ​ር​ያ​ትም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አል​ወ​ጣ​ሁም፤ ነገር ግን ወደ ዐረብ ሀገር ሄድሁ፤ ዳግ​መ​ኛም ወደ ደማ​ስቆ ተመ​ለ​ስሁ።</verse>
				<verse number="18">ከሦ​ስት ዓመት በኋላ ግን ኬፋን ላየው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣሁ፤ በእ​ርሱ ዘን​ድም ዐሥራ አም​ስት ቀን ሰነ​በ​ትሁ።</verse>
				<verse number="19">ነገር ግን የጌ​ታ​ችን ወን​ድም ያዕ​ቆ​ብን እንጂ ከሐ​ዋ​ር​ያት ሌላ አላ​የ​ሁም።</verse>
				<verse number="20">ስለ​ም​ጽ​ፍ​ላ​ች​ሁም ነገር እነሆ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሐሰት አል​ና​ገ​ርም።</verse>
				<verse number="21">ከዚ​ህም በኋላ ወደ ሶር​ያና ወደ ቂል​ቅያ አው​ራጃ መጣሁ።</verse>
				<verse number="22">በክ​ር​ስ​ቶ​ስም ያሉት የይ​ሁዳ ሀገር ማኅ​በረ ክር​ስ​ቲ​ያን ፊቴን አያ​ው​ቁም ነበር።</verse>
				<verse number="23">ነገር ግን “ቀድሞ ምእ​መ​ና​ንን ያሳ​ድድ የነ​በ​ረው እርሱ በፊት ያጠ​ፋው የነ​በ​ረ​ውን የሃ​ይ​ማ​ኖት ትም​ህ​ርት ዛሬ ይሰ​ብ​ካል” ሲባል ወሬ​ዬን ይሰሙ ነበር።</verse>
				<verse number="24">ስለ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑት ነበር።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ከዐ​ሥራ አራት ዓመ​ትም በኋላ ከበ​ር​ና​ባስ ጋር እንደ ገና ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣሁ፤ ቲቶ​ንም ይዠው ሄድሁ።</verse>
				<verse number="2">እንደ ተገ​ለ​ጠ​ል​ኝም ወጣሁ፤ በከ​ንቱ እን​ዳ​ል​ሮጥ፥ ወይም በከ​ንቱ ሮጬ እን​ዳ​ል​ሆነ፥ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል የም​ሰ​ብ​ከ​ውን ወን​ጌል አለ​ቆች መስ​ለው ለሚ​ታ​ዩት አስ​ታ​ወ​ቅ​ኋ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">አብ​ሮኝ የነ​በ​ረው ቲቶም አረ​ማዊ ሲሆን እን​ዲ​ገ​ዘር ግድ አላ​ል​ሁ​ትም።</verse>
				<verse number="4">ይኸ​ውም ባሪ​ያ​ዎች ያደ​ር​ጉን ዘንድ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ያገ​ኘ​ና​ትን ነጻ​ነት ሊሰ​ልሉ በስ​ውር ወደ እኛ የገቡ ሐሰ​ተ​ኞች መም​ህ​ራ​ንን ደስ አይ​በ​ላ​ቸው ብዬ ነው።</verse>
				<verse number="5">ለም​ንም ይሆ​ናሉ ብለን የማ​ና​ስ​ባ​ቸው ናቸው፤ እው​ነ​ተ​ኛው ትም​ህ​ርት በእ​ና​ንተ ይጸና ዘንድ አን​ዲት ሰዓ​ትም እንኳ አል​ተ​ገ​ዛ​ን​ላ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="6">አለ​ቆች የመ​ሰ​ሉት ግን ቀድሞ እነ​ርሱ እን​ዴት እንደ ነበሩ ልና​ገር አያ​ገ​ደ​ኝም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ፊት አያ​ዳ​ላ​ምና፤ አለ​ቆች የመ​ሰ​ሉ​ትም ከራ​ሳ​ቸው ምንም ነገር የጨ​መ​ሩ​ልኝ የለ​ምና።</verse>
				<verse number="7">የጴ​ጥ​ሮስ ትም​ህ​ርት በተ​ገ​ዘሩ በአ​ይ​ሁድ ዘንድ እንደ ታመ​ነ​ለት፥ የእ​ኔም ትም​ህ​ርት ባል​ተ​ገ​ዘሩ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ እንደ ታመነ ዐው​ቀ​ዋል እንጂ።</verse>
				<verse number="8">ወደ ተገ​ዘሩ አይ​ሁድ በተ​ላከ ጊዜ ጴጥ​ሮ​ስን የረ​ዳው እርሱ እኔ​ንም ባል​ተ​ገ​ዘሩ አሕ​ዛብ ዘንድ ረዳኝ።</verse>
				<verse number="9">የሰ​ጠ​ኝ​ንም ጸጋ ዐው​ቀው አዕ​ማድ የሚ​ሏ​ቸው ያዕ​ቆ​ብና ኬፋ፥ ዮሐ​ን​ስም እኛ ወደ አሕ​ዛብ፥ እነ​ር​ሱም ወደ አይ​ሁድ እን​ድ​ን​ሄድ ለእ​ኔና ለበ​ር​ና​ባስ ቀኝ እጃ​ቸ​ውን ሰጡን።</verse>
				<verse number="10">ይል​ቁ​ንም ነዳ​ያ​ንን እን​ድ​ና​ስ​ባ​ቸው ነው፤ ስለ​ዚ​ህም ይህን ነገር ልፈ​ጽ​መው ተጋሁ።</verse>
				<verse number="11">ነገር ግን ኬፋ ወደ አን​ጾ​ኪያ በመጣ ጊዜ ፊት ለፊት ተቃ​ወ​ም​ሁት፤ ነቅ​ፈ​ውት ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="12">ሰዎች ከያ​ዕ​ቆብ ዘንድ ከመ​ም​ጣ​ታ​ቸው በፊት፥ ከአ​ረ​ማ​ው​ያን ጋር ይበላ ነበ​ርና፥ በመጡ ጊዜ ግን ተለ​ያ​ቸው፤ ከአ​ይ​ሁድ ወገን የሆ​ኑ​ትን ፈር​ቶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="13">ከአ​ይ​ሁድ ወገ​ንም ወደ​ዚህ ግብር የተ​መ​ለሱ ብዙ​ዎች ነበሩ፤ በር​ና​ባ​ስም እንኳ በግ​ብ​ዝ​ነ​ታ​ቸው ተባ​በረ።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን ወደ እው​ነ​ተ​ኛው ወን​ጌል እግ​ራ​ቸ​ውን እን​ዳ​ላ​ቀኑ ባየሁ ጊዜ፥ በሰው ሁሉ ፊት ኬፋን እን​ዲህ አል​ሁት፥ “አንተ አይ​ሁ​ዳዊ ስት​ሆን በአ​ይ​ሁድ ሥር​ዐት ያይ​ደለ፥ በአ​ረ​ማ​ው​ያን ሥር​ዐት የም​ት​ኖር ከሆነ እን​ግ​ዲህ አይ​ሁድ እን​ዲ​ሆኑ አረ​ማ​ው​ያ​ንን ለምን ታስ​ገ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለህ?”</verse>
				<verse number="15">እኛ በት​ው​ል​ዳ​ችን አይ​ሁድ ነን፤ ኀጢ​አ​ተ​ኞች የሆኑ አሕ​ዛ​ብም አይ​ደ​ለ​ንም።</verse>
				<verse number="16">ሰው በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በማ​መን እንጂ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት እን​ደ​ማ​ይ​ጸ​ድቅ እና​ው​ቃ​ለ​ንና፤ እኛም የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት ሳይ​ሆን በእ​ርሱ በማ​መ​ና​ችን እን​ጸ​ድቅ ዘንድ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አም​ነ​ናል፤ ሰው ሁሉ በኦ​ሪት ሥራ አይ​ጸ​ድ​ቅ​ምና።</verse>
				<verse number="17">በክ​ር​ስ​ቶስ ልን​ጸ​ድቅ የም​ንሻ እኛ እንደ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ከሆን እን​ግ​ዲህ ክር​ስ​ቶስ የኀ​ጢ​አት አገ​ል​ጋይ መሆኑ ነውን? አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="18">ያን ያፈ​ረ​ስ​ሁ​ትን መልሼ የማ​ንጽ ከሆነ ራሴን ሕግ አፍ​ራሽ አደ​ረ​ግሁ።</verse>
				<verse number="19">እኔስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕያው ሆኜ በሁ​ለ​ተ​ኛው ሕግ እኖር ዘንድ ከቀ​ደ​መው ሕግ ተለ​የሁ።</verse>
				<verse number="20">ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋርም ተሰ​ቀ​ልሁ፤ ሕይ​ወ​ቴም አለ​ቀች፤ ነገር ግን በክ​ር​ስ​ቶስ ሕይ​ወት አለሁ፤ ዛሬም በሥ​ጋዬ የም​ኖ​ረ​ውን ኑሮ የወ​ደ​ደ​ኝን ስለ እኔም ራሱን አሳ​ልፎ የሰ​ጠ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ በማ​መን እኖ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="21">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ጸጋ አል​ክ​ድም፤ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት የሚ​ጸ​ድቁ ከሆነ እን​ኪ​ያስ ክር​ስ​ቶስ በከ​ንቱ ሞተ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">እና​ንተ ሰነ​ፎች የገ​ላ​ትያ ሰዎች ሆይ፥ ለዐ​ይን በሚ​ታ​የው እው​ነት እን​ዳ​ታ​ምኑ ማን አታ​ለ​ላ​ችሁ? እር​ሱም እን​ዲ​ሰ​ቀል አስ​ቀ​ድሞ የተ​ጻ​ፈ​ለት ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነው።</verse>
				<verse number="2">በእ​ና​ንተ ዘንድ ይህን ብቻ ላውቅ እወ​ድ​ዳ​ለሁ፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስን የተ​ቀ​በ​ላ​ችሁ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት ነውን? ወይስ ሃይ​ማ​ኖ​ትን በመ​ስ​ማት?</verse>
				<verse number="3">እን​ዲ​ህን ሰነ​ፎች ናች​ሁን? የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ሥራ ከጀ​መ​ራ​ችሁ በኋላ የሥ​ጋን ሕግ ልት​ሠሩ ትመ​ለ​ሳ​ላ​ች​ሁን?</verse>
				<verse number="4">ይህን ያህል መከራ ተቀ​ብ​ላ​ችሁ፥ ለከ​ንቱ አደ​ረ​ጋ​ች​ሁት።</verse>
				<verse number="5">እርሱ መን​ፈስ ቅዱ​ስን የሚ​ሰ​ጣ​ችሁ፥ ኀይ​ል​ንም የሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ላ​ችሁ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት ነውን? ወይስ ሃይ​ማ​ኖ​ትን በመ​ስ​ማት ነው?</verse>
				<verse number="6">አብ​ር​ሃም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አመነ፥ ጽድ​ቅም ሆኖ እንደ ተቈ​ጠ​ረ​ለት፥</verse>
				<verse number="7">እን​ግ​ዲህ ያመ​ኑት የአ​ብ​ር​ሃም ልጆች እንደ ሆኑ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="8">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሕ​ዛ​ብን በእ​ም​ነት እን​ደ​ሚ​ያ​ጸ​ድ​ቃ​ቸው መጽ​ሐፍ አስ​ቀ​ድሞ ገል​ጦ​አ​ልና፤ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ በእ​ርሱ እን​ዲ​ባ​ረኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ ለአ​ብ​ር​ሃም ተስፋ ሰጠው።</verse>
				<verse number="9">አሁ​ንም የሚ​ያ​ምኑ ከአ​መ​ነው ከአ​ብ​ር​ሃም ጋር ይባ​ረ​ካሉ።</verse>
				<verse number="10">በኦ​ሪት ሕግ ያሉ ሁሉ በእ​ር​ግ​ማን ውስጥ ይኖ​ራሉ፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በዚህ በኦ​ሪት መጽ​ሐፍ ውስጥ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ የማ​ይ​ፈ​ጽ​ምና የማ​ይ​ጠ​ብቅ ርጉም ይሁን።”</verse>
				<verse number="11">የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራ​ትስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እን​ደ​ማ​ይ​ጸ​ድቁ ይታ​ወ​ቃል፤ “ጻድቅ ግን በእ​ም​ነት ይድ​ናል” ተብሎ ተጽ​ፎ​አል።</verse>
				<verse number="12">ኦሪ​ትስ ሠርቶ የፈ​ጸመ ይኖ​ር​በ​ታል እንጂ በእ​ም​ነት የሚ​ያ​ጸ​ድቅ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="13">እኛ​ንስ ክር​ስ​ቶስ ስለ እኛ የኦ​ሪ​ትን መር​ገም በመ​ሸ​ከሙ ከኦ​ሪት መር​ገም ዋጅ​ቶ​ናል፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በእ​ን​ጨት ላይ የተ​ሰ​ቀለ ሁሉ ርጉም ነው።”</verse>
				<verse number="14">እኛ በክ​ር​ስ​ቶስ አም​ነን የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ተስፋ እን​ድ​ና​ገኝ የአ​ብ​ር​ሃም በረ​ከት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ወደ አሕ​ዛብ ይመ​ለስ ዘንድ።</verse>
				<verse number="15">ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እንደ ሰው ልማድ እን​ና​ገ​ራ​ለን፤ ሰውም እን​ኳን የጸ​ና​ውን ኪዳን አይ​ን​ቅም አይ​ጨ​ም​ር​በ​ት​ምም።</verse>
				<verse number="16">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ብ​ር​ሃም፥ “ለአ​ን​ተና ለዘ​ርህ” ብሎ ተስፋ ሰጠው፤ ለብ​ዙ​ዎች እን​ደ​ሚ​ና​ገር አድ​ርጎ ለአ​ን​ተና ለዘ​ሮ​ችህ አላ​ለ​ውም፤ ለአ​ንድ እን​ደ​ሚ​ና​ገር አድ​ርጎ፥ “ለዘ​ርህ” አለው እንጂ ይኸ​ውም ክር​ስ​ቶስ ነው።</verse>
				<verse number="17">እን​ግ​ዲህ እን​ዲህ እላ​ለሁ፦ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሰጠ ይህ ኪዳን ጽኑዕ ነው፤ ከዚ​ህም በኋላ በአ​ራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኦሪት መጣች፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠ​ውን ተስፋ ልት​ከ​ለ​ክል አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="18">መው​ረስ የኦ​ሪ​ትን ሕግ በመ​ሥ​ራት ከሆነ እን​ግ​ዲህ በሰ​ጠው ተስፋ አይ​ደ​ለማ፤ እነሆ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ ለአ​ብ​ር​ሃም ተስ​ፋ​ውን ሰጠው።</verse>
				<verse number="19">ታዲያ ኦሪት ለምን ተሠ​ራች? ኦሪ​ትስ ኀጢ​አ​ትን ታበ​ዛት ዘንድ፥ ተስፋ ያደ​ረ​ገ​ለት ያ ዘር እስ​ኪ​መጣ ድረስ፥ በመ​ላ​እ​ክት በኩል በመ​ካ​ከ​ለ​ኛው እጅ ወረ​ደች።</verse>
				<verse number="20">መካ​ከ​ለ​ኛው ግን ማንም አይ​ደ​ለም፤ አንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው እንጂ።</verse>
				<verse number="21">እን​ግ​ዲህ ኦሪት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠ​ውን ተስፋ ልት​ከ​ለ​ክል መጣ​ችን? አይ​ደ​ለም፤ ማዳን የሚ​ቻ​ለው ሕግ ተሠ​ርቶ ቢሆ​ንማ፥ በእ​ው​ነት በዚያ ሕግ ጽድቅ በተ​ገኘ ነበር።</verse>
				<verse number="22">ነገር ግን ተስፋ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በማ​መን ይሆን ዘንድ፥ ያመ​ኑ​ትም ያገ​ኙት ዘንድ፥ መጽ​ሐፍ ሁሉን በኀ​ጢ​አት ዘግ​ቶ​ታል።</verse>
				<verse number="23">እም​ነት ሳይ​መጣ ኦሪት ጠበ​ቀ​ችን፤ ወደ​ሚ​መ​ጣ​ውም እም​ነት መራ​ችን።</verse>
				<verse number="24">እን​ግ​ዲህ ኦሪት በእ​ርሱ በማ​መን እን​ጸ​ድቅ ዘንድ ወደ ክር​ስ​ቶስ መሪ ሆነ​ችን።</verse>
				<verse number="25">እን​ግ​ዲህ እም​ነት ከመ​ጣች መሪ አን​ሻም።</verse>
				<verse number="26">በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በማ​መን ሁላ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ሆነ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="27">በክ​ር​ስ​ቶስ የተ​ጠ​መ​ቃ​ችሁ እና​ን​ተማ ክር​ስ​ቶ​ስን ለብ​ሳ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="28">በዚ​ህም አይ​ሁ​ዳዊ፥ ወይም አረ​ማዊ የለም፤ ገዢ፥ ወይም ተገዢ የለም፤ ወንድ፥ ወይም ሴት የለም፤ ሁላ​ችሁ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አንድ ናች​ሁና።</verse>
				<verse number="29">ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከሆ​ና​ች​ሁም እን​ግ​ዲህ ተስ​ፋ​ውን የም​ት​ወ​ርሱ የአ​ብ​ር​ሃም ዘር እና​ንተ ናችሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ነገር ግን እላ​ለሁ፤ ወራሹ ሕፃን ሳለ ለሁሉ ጌታ ሲሆን ከአ​ገ​ል​ጋይ የሚ​ለይ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="2">ነገር ግን አባቱ እስከ ቀጠ​ረ​ለት ዕድሜ ድረስ በአ​ያት ወይም በሞ​ግ​ዚት እጅ ይጠ​በ​ቃል።</verse>
				<verse number="3">እን​ዲሁ እኛም ሕፃ​ናት በነ​በ​ርን ጊዜ፥ ለዚህ ዓለም ስሕ​ተት ተገ​ዝ​ተን ነበር።</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን ቀጠ​ሮው በደ​ረሰ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን ላከ፤ ከሴ​ትም ተወ​ለደ፤ የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ ፈጸመ።</verse>
				<verse number="5">እኛ የል​ጅ​ነ​ትን ክብር እን​ድ​ና​ገኝ በኦ​ሪት የነ​በ​ሩ​ትን ይዋጅ ዘንድ።</verse>
				<verse number="6">ልጆች እንደ መሆ​ና​ችሁ መጠን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አባ አባቴ ብላ​ችሁ የም​ት​ጠ​ሩ​ትን የል​ጁን መን​ፈስ በል​ባ​ችሁ አሳ​ደረ።</verse>
				<verse number="7">እን​ኪ​ያስ እና​ንተ ልጆች ናችሁ እንጂ ባሮች አይ​ደ​ላ​ች​ሁም፤ ልጆች ከሆ​ና​ች​ሁም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወራ​ሾች ናችሁ።</verse>
				<verse number="8">ነገር ግን ቀድሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ባለ​ማ​ወ​ቃ​ችሁ፥ በባ​ሕ​ር​ያ​ቸው አማ​ል​ክት ላል​ሆኑ ተገ​ዝ​ታ​ችሁ ነበር።</verse>
				<verse number="9">ዛሬ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዐወ​ቃ​ች​ሁት፤ ይል​ቁ​ንም እርሱ ዐወ​ቃ​ችሁ፤ እንደ ገና ደግሞ ወደ​ዚያ ወደ ደካ​ማው፥ ወደ ድሀው ወደ​ዚህ ዓለም ጣዖት ተመ​ል​ሳ​ችሁ፥ ትገ​ዙ​ላ​ቸው ዘንድ እን​ዴት ፈጠ​ራን ትሻ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="10">ዕለ​ት​ንና ወርን፥ ጊዜ​ንና ዓመ​ታ​ትን ትጠ​ብ​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="11">ስለ እና​ንተ በከ​ንቱ ደክሜ እንደ ሆነ ብዬ እፈ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="12">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኔ ደግሞ እንደ እና​ንተ ሁኛ​ለሁ፤ እንደ እኔ ሁኑ ብዬ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፤ አን​ዳች አል​በ​ደ​ላ​ች​ሁ​ኝ​ምና።</verse>
				<verse number="13">መጀ​መ​ሪያ ወን​ጌ​ልን በሰ​በ​ክ​ሁ​ላ​ችሁ ጊዜ፥ ከሥጋ ድካም የተ​ነሣ እንደ ነበር ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="14">መከራ እቀ​በል በነ​በ​ረ​በት ጊዜ አል​ሰ​ለ​ቻ​ች​ሁ​ኝም፤ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ፥ እንደ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ተቀ​በ​ላ​ች​ሁኝ እንጂ በሰ​ው​ነቴ አል​ና​ቃ​ች​ሁ​ኝም።</verse>
				<verse number="15">አሁ​ንስ ደስ ማሰ​ኘ​ታ​ችሁ ወዴት አለ? ቢቻ​ላ​ች​ሁስ ዐይ​ና​ች​ሁ​ንም እንኳ ቢሆን አው​ጥ​ታ​ችሁ ትሰ​ጡኝ እንደ ነበረ፥ እኔ ምስ​ክ​ራ​ችሁ ነኝ።</verse>
				<verse number="16">እው​ነ​ቱን ስለ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ባላ​ጋራ ሆን​ኋ​ች​ሁን?</verse>
				<verse number="17">እነ​ዚ​ያማ ይቀ​ኑ​ባ​ች​ኋል፤ ነገር ግን በእ​ነ​ርሱ ላይ እን​ድ​ት​ቀኑ ሊዘ​ጉ​አ​ችሁ ይወ​ዳሉ እንጂ ለመ​ል​ካም አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="18">መቅ​ና​ትስ ዘወ​ትር ለመ​ል​ካም ሥራ ልት​ቀኑ ይገ​ባል፤ ነገር ግን እኔ ከእ​ና​ንተ ዘንድ ባለ​ሁ​በት ጊዜ ብቻ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="19">ልጆች፥ እንደ ገና የም​ጨ​ነ​ቅ​ላ​ችሁ ክር​ስ​ቶስ በል​ባ​ችሁ እስ​ኪ​ሣ​ል​ባ​ችሁ ድረስ ነው።</verse>
				<verse number="20">ቃሌን ለውጬ አሁን በእ​ና​ንተ ዘንድ ልገኝ እሻ​ለሁ፤ ስለ እና​ንተ የም​ና​ገ​ረ​ውን አጣ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="21">በኦ​ሪት ሕግ እን​ኑር ትላ​ላ​ች​ሁን? ኦሪ​ትን አት​ሰ​ሙ​አ​ት​ምን?</verse>
				<verse number="22">አብ​ር​ሃም ሁለት ልጆ​ችን አን​ዱን ከባ​ሪ​ያ​ዪቱ፥ አን​ዱ​ንም ከእ​መ​ቤ​ቲቱ እንደ ወለደ ተጽ​ፎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="23">ነገር ግን ከባ​ሪ​ያ​ዪቱ የተ​ወ​ለ​ደው ልደቱ ልዩ ነው፤ በሰው ልማድ ተወ​ለደ፤ ከእ​መ​ቤ​ቲቱ የተ​ወ​ለ​ደው ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ጠው ተስፋ ተወ​ለደ።</verse>
				<verse number="24">ይህም የሁ​ለቱ ሥር​ዐት ምሳሌ ነው፤ አን​ዲቱ ከደ​ብረ ሲና ለባ​ር​ነት ትወ​ል​ዳ​ለች፤ እር​ስ​ዋም አጋር ናት።</verse>
				<verse number="25">አጋ​ርም በዐ​ረብ ሀገር ያለች ደብረ ሲና ናት፤ ከዛ​ሬ​ዪቱ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ጋር ትነ​ጻ​ጸ​ራ​ለች፤ ከል​ጆ​ችዋ ጋርም ትገ​ዛ​ለች።</verse>
				<verse number="26">የላ​ይ​ኛ​ዪቱ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ግን በነ​ፃ​ነት የም​ት​ኖር ናት፤ እር​ስ​ዋም እና​ታ​ችን ናት።</verse>
				<verse number="27">“የማ​ት​ወ​ልድ መካን ደስ ይላ​ታል፤ ምጥ የማ​ታ​ው​ቀ​ውም ደስ ብሎ​አት እልል ትላ​ለች፤ ባል ካላት ይልቅ የፈ​ቲቱ ልጆች ብዙ​ዎች ናቸ​ውና” ተብሎ ተጽ​ፎ​አል።</verse>
				<verse number="28">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኛስ እንደ ይስ​ሐቅ የተ​ስፋ ልጆች ነን።</verse>
				<verse number="29">ነገር ግን በሥጋ ልማድ የተ​ወ​ለ​ደው በመ​ን​ፈ​ሳዊ ግብር የተ​ወ​ለ​ደ​ውን በዚያ ጊዜ እን​ዳ​ሳ​ደ​ደው ዛሬም እን​ዲሁ ነው።</verse>
				<verse number="30">ነገር ግን መጽ​ሐፍ ምን ይላል? “የባ​ሪ​ያ​ዪቱ ልጅ ከእ​መ​ቤ​ቲቱ ልጅ ጋር አይ​ወ​ር​ስ​ምና ባሪ​ያ​ዪ​ቱን ከል​ጅዋ ጋር አስ​ወ​ጥ​ተህ ስደ​ዳት”</verse>
				<verse number="31">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ አሁ​ንም እኛ የእ​መ​ቤ​ቲቱ ነን እንጂ የባ​ሪ​ያ​ዪቱ ልጆች አይ​ደ​ለ​ንም፤ ክር​ስ​ቶስ ነጻ አው​ጥ​ቶ​ና​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">እን​ግ​ዲህ ጸን​ታ​ችሁ ቁሙ፤ እንደ ገናም በባ​ር​ነት ቀን​በር አት​ኑሩ።</verse>
				<verse number="2">እነሆ፥ እኔ ጳው​ሎስ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ “ብት​ገ​ዘ​ሩም በክ​ር​ስ​ቶስ ዘንድ ምንም አይ​ጠ​ቅ​ማ​ች​ሁም።”</verse>
				<verse number="3">ደግ​ሞም ለተ​ገ​ዘረ ሰው ሁሉ የኦ​ሪ​ትን ሕግ መፈ​ጸም እን​ደ​ሚ​ገ​ባው እመ​ሰ​ክ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">በኦ​ሪት ልት​ጸ​ድቁ የም​ት​ፈ​ልጉ እና​ንተ ከክ​ር​ስ​ቶስ ተለ​ይ​ታ​ችሁ ከጸ​ጋዉ ወድ​ቃ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="5">እኛ ግን በመ​ን​ፈስ ቅዱስ፥ በእ​ም​ነ​ትም ልን​ጸ​ድቅ ተስፋ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።</verse>
				<verse number="6">በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘንድ በፍ​ቅር የም​ት​ሠራ እም​ነት እንጂ መገ​ዘር አይ​ጠ​ቅ​ም​ምና፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም ግዳጅ አይ​ፈ​ጽ​ም​ምና።</verse>
				<verse number="7">ቀድ​ሞስ በመ​ል​ካም ተፋ​ጥ​ና​ችሁ ነበር፤ በእ​ው​ነት እን​ዳ​ታ​ምኑ ማን አሰ​ና​ከ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="8">ይህ መፋ​ጠ​ና​ችሁ ከሚ​ጠ​ራ​ችሁ አይ​ደ​ለ​ምና።</verse>
				<verse number="9">ጥቂት እርሾ ብዙ​ውን ዱቄት መጻጻ ያደ​ር​ገው የለ​ምን?</verse>
				<verse number="10">እኔ ሌላ እን​ዳ​ታ​ስቡ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አም​ኛ​ችሁ ነበር፤ የሚ​ያ​ው​ካ​ችሁ ግን የሆ​ነው ቢሆን ፍዳ​ውን ይሸ​ከ​ማል።</verse>
				<verse number="11">ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እኔ ግዝ​ረ​ትን ገና የም​ሰ​ብክ ከሆነ፥ እን​ግ​ዲህ ለምን ያሳ​ድ​ዱ​ኛል? እን​ግ​ዲህ የክ​ር​ስ​ቶስ የመ​ስ​ቀሉ ተግ​ዳ​ሮት እን​ዲ​ያው ቀር​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="12">የሚ​ያ​ው​ኩ​አ​ች​ሁም ሊለዩ ይገ​ባል።</verse>
				<verse number="13">ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እና​ን​ተስ ለነ​ጻ​ነት ተጠ​ር​ታ​ች​ኋል፤ ነገር ግን በሥ​ጋ​ችሁ ፈቃድ ለነ​ጻ​ነ​ታ​ችሁ ምክ​ን​ያት አታ​ድ​ር​ጉ​ላት፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁም በፍ​ቅር ተገዙ።</verse>
				<verse number="14">“ወን​ድ​ም​ህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚ​ለው አንድ ቃል ሕግን ሁሉ ይፈ​ጽ​ማ​ልና።</verse>
				<verse number="15">እርስ በር​ሳ​ችሁ የም​ት​በ​ላ​ሉና የም​ት​ነ​ካ​ከሱ ከሆነ ግን፥ እርስ በር​ሳ​ችሁ እን​ዳ​ት​ተ​ላ​ለቁ ተጠ​ን​ቀቁ።</verse>
				<verse number="16">እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በመ​ን​ፈስ ኑሩ እንጂ የሥ​ጋ​ች​ሁን ፈቃድ አታ​ድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="17">ሥጋ መን​ፈስ የማ​ይ​ሻ​ውን ይሻ​ልና፥ መን​ፈ​ስም ሥጋ የማ​ይ​ሻ​ውን ይሻ​ልና፥ የም​ት​ሹ​ት​ንም እን​ዳ​ታ​ደ​ርጉ እርስ በር​ሳ​ቸው ይጣ​ላሉ።</verse>
				<verse number="18">የመ​ን​ፈ​ስን ፈቃድ የም​ት​ከ​ተሉ ከሆ​ና​ችሁ፥ ከኦ​ሪት ወጥ​ታ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="19">የሥ​ጋም ሥራው ይታ​ወ​ቃል፤ እር​ሱም ዝሙት፥ ርኵ​ሰት፥ መዳ​ራት፥</verse>
				<verse number="20">ጣዖት ማም​ለክ፥ ሥራይ ማድ​ረግ፥ መጣ​ላት፥ ኵራት፥ የም​ን​ዝር ጌጥ፥ ቅናት፥ ቍጣ፥ ጥር​ጥር፥ ፉክ​ክር፥ ምቀ​ኝ​ነት፥ መጋ​ደል፥ ስካር ይህ​ንም የመ​ሰለ ሁሉ ነው።</verse>
				<verse number="21">አስ​ቀ​ድሜ እንደ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት አያ​ይም።</verse>
				<verse number="22">የመ​ን​ፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕ​ግ​ሥት፥ ምጽ​ዋት፥ ቸር​ነት፥ እም​ነት፥ ገር​ነት፥ ንጽ​ሕና ነው።</verse>
				<verse number="23">ከዚህ ሕግ የሚ​በ​ልጥ የለም።</verse>
				<verse number="24">በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ያመኑ ግን ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ከም​ኞ​ትና ከኀ​ጢ​አት ለዩ።</verse>
				<verse number="25">አሁ​ንም በመ​ን​ፈስ እን​ኑር፤ በመ​ን​ፈ​ስም እን​መ​ላ​ለስ።</verse>
				<verse number="26">ኩሩ​ዎች አን​ሁን፤ እርስ በር​ሳ​ችን አን​ተ​ማማ፤ እርስ በር​ሳ​ች​ንም አን​ቀ​ናና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ከእ​ና​ንተ ወገን የተ​ሳ​ሳተ ሰው ቢኖር በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የጸ​ና​ችሁ እና​ንት እን​ዳ​ት​ሳ​ሳቱ ለራ​ሳ​ችሁ እየ​ተ​ጠ​በ​ቃ​ችሁ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ሰው ቅን​ነት ባለው ልቡና አጽ​ኑት።</verse>
				<verse number="2">ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ውን ሸክም ይሸ​ከም፤ በዚ​ህም የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ሕግ ትፈ​ጽ​ማ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="3">አን​ዱም ምንም ሳይ​ሆን ምንም የሆነ ቢመ​ስ​ለው ራሱን ያታ​ል​ላ​ልና።</verse>
				<verse number="4">ለሌላ ያይ​ደለ ለራሱ መመ​ኪያ እን​ዲ​ሆ​ነው ሁሉም ሥራ​ዉን ይመ​ር​ምር።</verse>
				<verse number="5">ሁሉም ሸክ​ሙን ይሸ​ከ​ማ​ልና።</verse>
				<verse number="6">ይህ​ንም ነገር ንኡሰ ክር​ስ​ቲ​ያን ይስ​ማው፤ መል​ካ​ሙ​ንም ነገር ሁሉ ከሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ረው ይማር።</verse>
				<verse number="7">አያ​ስ​ቱ​አ​ችሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ዘ​ብት አይ​ኑር፤ ሰውም የሚ​ዘ​ራ​ውን ያጭ​ዳል።</verse>
				<verse number="8">በሥ​ጋው የሚ​ዘራ ሞትን ያጭ​ዳል፤ በመ​ን​ፈ​ሱም የሚ​ዘራ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ያጭ​ዳል።</verse>
				<verse number="9">በጎ ሥራ መሥ​ራ​ትን ቸል አን​በል፥ በጊ​ዜው እና​ገ​ኘ​ዋ​ለ​ንና።</verse>
				<verse number="10">እን​ግ​ዲህ ጊዜ ሳለን ለሁሉ መል​ካም ሥራ እና​ድ​ርግ፤ ይል​ቁ​ንም ለሃ​ይ​ማ​ኖት ሰዎች።</verse>
				<verse number="11">በእጄ እንደ ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ እዩ።</verse>
				<verse number="12">ለሰው ፊት ሊያ​ደሉ የሚ​ወዱ እነ​ዚያ እን​ድ​ት​ገ​ዘሩ ያስ​ገ​ድ​ዱ​አ​ች​ኋል፤ ነገር ግን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን መስ​ቀል እን​ዳ​ት​ከ​ተሉ ነው።</verse>
				<verse number="13">የተ​ገ​ዘ​ሩ​ትም ቢሆኑ በሰ​ው​ነ​ታ​ችሁ እን​ደ​ም​ት​መኩ ልት​ገ​ዘሩ ይወ​ዳሉ እንጂ ኦሪ​ትን አል​ጠ​በ​ቁም።</verse>
				<verse number="14">እኔ ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ መስ​ቀል እንጂ በሌላ አል​መ​ካም፤ በእኔ ዘንድ ዓለሙ የሞተ ነው፥ እኔም በዓ​ለሙ ዘንድ የሞ​ትሁ ነኝ።</verse>
				<verse number="15">በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘንድ አዲስ ፍጥ​ረት መሆን ነው እንጂ መገ​ዘር አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም ግዳጅ አይ​ፈ​ጽ​ምም።</verse>
				<verse number="16">ይህን ሕግ ለሚ​ፈ​ጽሙ ሰዎች ሰላ​ምና ይቅ​ርታ ይሁን፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወገ​ኖች በሆኑ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይም ይሁን።</verse>
				<verse number="17">እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህስ የሚ​ያ​ደ​ክ​መኝ አይ​ኑር፤ እኔ የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን መከራ በሥ​ጋዬ እሸ​ከ​ማ​ለሁ።</verse>
				<verse number="18">ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጸጋ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን፤ አሜን። በሮሜ ተጽፋ በቲቶ እጅ ወደ ገላ​ትያ ሰዎች የተ​ላ​ከች መል​እ​ክት ተፈ​ጸ​መች። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን፤ አሜን።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="49">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈቃድ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሐዋ​ርያ ከሆነ ከጳ​ው​ሎስ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ላመኑ በኤ​ፌ​ሶን ላሉ ቅዱ​ሳን፥</verse>
				<verse number="2">ከአ​ባ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰላ​ምና ጸጋ ለእ​ና​ንተ ይሁን።</verse>
				<verse number="3">በክ​ር​ስ​ቶስ ኢየ​ሱስ በሰ​ማ​ያዊ ስፍራ በመ​ን​ፈ​ሳዊ በረ​ከት ሁሉ የባ​ረ​ከን የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።</verse>
				<verse number="4">ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር በፊቱ ቅዱ​ሳን፥ ንጹ​ሓ​ንና ያለ ነውር በፍ​ቅር ያደ​ር​ገን ዘንድ ለእ​ርሱ መረ​ጠን።</verse>
				<verse number="5">በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም እንደ ውድ ፈቃዱ ለእ​ርሱ ልጆች ልን​ሆን አስ​ቀ​ድሞ ወሰ​ነን።</verse>
				<verse number="6">በሚ​ወ​ደው ልጁ የሰ​ጠን የጸ​ጋው ክብር ይመ​ሰ​ገን ዘንድ።</verse>
				<verse number="7">በእ​ር​ሱም እንደ ቸር​ነቱ ብዛት በደሙ ድኅ​ነ​ትን አገ​ኘን፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንም ተሰ​ረ​የ​ልን።</verse>
				<verse number="8">ይኸ​ውም በፍ​ጹም ጥበ​ብና ምክር ለእኛ አብ​ዝቶ ያደ​ረ​ገው ነው።</verse>
				<verse number="9">እንደ ወደ​ደም በእ​ርሱ የወ​ሰ​ነ​ውን፥ የፈ​ቃ​ዱን ምሥ​ጢር ገለ​ጠ​ልን።</verse>
				<verse number="10">የሚ​ደ​ር​ስ​በ​ት​ንም ጊዜ​ውን ወሰነ፤ በሰ​ማ​ይና በም​ድር ያለ​ውም ሁሉ ይታ​ደስ ዘንድ ክር​ስ​ቶ​ስን በሁሉ ላይ አላ​ቀው።</verse>
				<verse number="11">እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚ​ሠራ እንደ እርሱ አሳብ አስ​ቀ​ድ​መን የተ​ወ​ሰን በእ​ርሱ ርስ​ትን ተቀ​በ​ልን።</verse>
				<verse number="12">ይኸ​ውም አስ​ቀ​ድ​መን በክ​ር​ስ​ቶስ ኢየ​ሱስ ተስፋ ያደ​ረ​ግን እኛ ለክ​ብሩ ምስ​ጋና እን​ሆን ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="13">እና​ን​ተም ልት​ድ​ኑ​በት የተ​ማ​ራ​ች​ሁ​ትን የእ​ው​ነት ቃል ሰም​ታ​ች​ሁና አም​ና​ችሁ፤ ተስፋ ባደ​ረ​ገ​ላ​ችሁ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ታተ​ማ​ችሁ።</verse>
				<verse number="14">ይኸ​ውም ለጌ​ት​ነቱ ክብር የር​ስ​ታ​ችን መያዣ፥ የሕ​ይ​ወ​ታ​ች​ንም ቤዛ​ነት ነው።</verse>
				<verse number="15">ስለ​ዚ​ህም እኔ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ማመ​ና​ች​ሁን፥ ቅዱ​ሳ​ን​ንም ሁሉ መው​ደ​ዳ​ች​ሁን ሰምቼ፥</verse>
				<verse number="16">ስለ እና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማመ​ስ​ገ​ን​ንና በጸ​ሎ​ቴም እና​ን​ተን ማሰ​ብን አላ​ቋ​ረ​ጥ​ሁም።</verse>
				<verse number="17">ይኸ​ውም የክ​ብር ባለ​ቤት የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጥ​በ​ብን መን​ፈስ ይሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ፥ ዕው​ቀ​ቱ​ንም ይገ​ል​ጽ​ላ​ችሁ ዘንድ፥</verse>
				<verse number="18">ዐይነ ልቡ​ና​ች​ሁ​ንም ያበ​ራ​ላ​ችሁ ዘንድ፥ የተ​ጠ​ራ​ች​ሁ​በት ተስ​ፋም ምን እንደ ሆነ፥ በቅ​ዱ​ሳ​ንም የር​ስቱ ክብር ባለ​ጸ​ግ​ነት ምን እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ፥</verse>
				<verse number="19">በክ​ር​ስ​ቶስ እንደ አደ​ረ​ገው እንደ ከሃ​ሊ​ነቱ ታላ​ቅ​ነት በም​ና​ምን በእኛ ላይ የሚ​ያ​ደ​ር​ገው የከ​ሃ​ሊ​ነቱ ጽናት ብዛት ምን እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="20">ከሙ​ታን ለይቶ ባስ​ነ​ሣው፥ በሰ​ማ​ይም በቀኙ ባስ​ቀ​መ​ጠው፥</verse>
				<verse number="21">ከመ​ላ​እ​ክት ሁሉ በላይ ከመ​ኳ​ን​ን​ትና ከኀ​ይ​ላት፥ ከአ​ጋ​እ​ዝ​ትና ከሚ​ጠ​ራ​ውም ስም ሁሉ በላይ፥ በዚህ ዓለም ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በሚ​መ​ጣ​ውም ዓለም እንጂ።</verse>
				<verse number="22">ሁሉ​ንም ከእ​ግሩ በታች አድ​ርጎ አስ​ገ​ዛ​ለት፤ ከሁሉ በላይ የሆነ እር​ሱን ለቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ራስ አደ​ረ​ገው።</verse>
				<verse number="23">ይህ​ች​ውም አካሉ ናት፤ የሁ​ሉም ፍጻ​ሜው እርሱ ነው፤ ሁሉ​ንም በሁሉ ይፈ​ጽ​ማል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">እና​ን​ተም በኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ምው​ታን ሆና​ችሁ ነበር።</verse>
				<verse number="2">ይኸ​ውም ቀድሞ በዚህ ዓለም ሥር​ዐት፥ አሁን በከ​ሓ​ድ​ያን ልጆች የሚ​በ​ረ​ታ​ታ​ባ​ቸ​ውና፥ በነ​ፋስ አም​ሳል የሚ​ገ​ዛ​ቸው አለቃ እንደ ነበ​ረው ፈቃድ ጸን​ታ​ችሁ የነ​በ​ራ​ች​ሁ​በት ነው።</verse>
				<verse number="3">እኛ ሁላ​ችን ቀድሞ እንደ ሥጋ​ችን ምኞት ኖርን፤ የሥ​ጋ​ች​ን​ንም ፈቃ​ድና ያሰ​ብ​ነ​ውን አደ​ረ​ግን፤ እንደ ሌሎች ኃጥ​አ​ንም ሁሉ የጥ​ፋት ልጆች ሆንን።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በም​ሕ​ረቱ ባለ​ጸ​ግ​ነ​ትና በወ​ደ​ደን በፍ​ቅሩ ብዛት፥</verse>
				<verse number="5">በኃ​ጢ​አ​ታ​ችን የሞ​ትን ሳለን በክ​ር​ስ​ቶስ ሕይ​ወ​ትን ሰጠን፤ በጸ​ጋ​ውም ዳንን።</verse>
				<verse number="6">በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም አስ​ነ​ሥቶ በሰ​ማ​ያት ከእ​ርሱ ጋር አኖ​ረን።</verse>
				<verse number="7">በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ይቅር ስላ​ለን የጸ​ጋ​ውን ባለ​ጠ​ግ​ነት ብዛት በሚ​መ​ጣው ዓለም ይገ​ልጥ ዘንድ፥</verse>
				<verse number="8">አም​ነን በጸ​ጋው ድነ​ና​ልና፤ ይህም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ነው እንጂ የእ​ና​ንተ ሥራ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="9">የሚ​መ​ካም እን​ዳ​ይ​ኖር በም​ግ​ባ​ራ​ችን አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="10">እን​መ​ላ​ለ​ስ​በት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ ላዘ​ጋ​ጀው በጎ ሥራ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የፈ​ጠ​ረን ፍጥ​ረቱ ነንና።</verse>
				<verse number="11">እና​ንተ አሕ​ዛብ አስቡ፤ ቀድሞ በሥጋ ሥር​ዐት ነበ​ራ​ችሁ፤ ያል​ተ​ገ​ዘ​ሩም ይሉ​አ​ችሁ ነበር፤ እን​ዲህ የሚ​ሉ​አ​ች​ሁም የተ​ገ​ዘሩ ሰዎች ናቸው፤ ግዝ​ረት ግን በሥጋ ላይ የሚ​ደ​ረግ የሰው እጅ ሥራ ነው።</verse>
				<verse number="12">ያን​ጊዜ ክር​ስ​ቶ​ስን አታ​ው​ቁ​ትም ነበር፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕግ የተ​ለ​ያ​ችሁ ነበ​ራ​ችሁ፤ ከተ​ስ​ፋው ሥር​ዐ​ትም እን​ግ​ዶች ነበ​ራ​ችሁ፤ ተስ​ፋም አል​ነ​በ​ራ​ች​ሁም፤ በዚ​ህም ዓለም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አታ​ው​ቁ​ትም ነበር።</verse>
				<verse number="13">አሁን ግን ቀድሞ ርቃ​ችሁ የነ​በ​ራ​ችሁ እና​ንተ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሆና​ችሁ በክ​ር​ስ​ቶስ ደም ቀረ​ባ​ችሁ።</verse>
				<verse number="14">ሁለ​ቱን አንድ ያደ​ረገ ሰላ​ማ​ችን እርሱ ነውና፥ በሥ​ጋ​ውም በመ​ካ​ከል የነ​በ​ረ​ውን የጥል ግድ​ግዳ አፍ​ርሶ ጥልን ሻረ።</verse>
				<verse number="15">ሁለ​ቱ​ንም አድሶ አንድ ያደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ በሥ​ር​ዐቱ የት​እ​ዛ​ዝን ሕግ አጠፋ፤ ዕር​ቅ​ንም አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="16">በመ​ስ​ቀ​ሉም በአ​ንድ ሥጋው ሁለ​ቱን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቀ​ረ​ባ​ቸው፤ በእ​ር​ሱም ጥልን አጠፋ።</verse>
				<verse number="17">መጥ​ቶም፤ ቀር​በን ለነ​በ​ር​ነው ሰላ​ምን፥ ርቃ​ችሁ ለነ​በ​ራ​ች​ሁት ለእ​ና​ን​ተም ሰላ​ምን ሰጠን።</verse>
				<verse number="18">እርሱ መር​ቶ​ና​ልና፤ ሁለ​ታ​ች​ን​ንም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ወደ አባቱ አቅ​ር​ቦ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="19">እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ እና​ንተ ከቅ​ዱ​ሳን ጋር ባላ​ገ​ሮ​ችና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ ሰቦች እንጂ እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች አይ​ደ​ላ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="20">በነ​ቢ​ያ​ትና በሐ​ዋ​ር​ያት መሠ​ረት ላይ ታን​ጻ​ች​ኋ​ልና የሕ​ን​ጻው የማ​ዕ​ዘን ራስ ድን​ጋ​ይም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነው፤</verse>
				<verse number="21">እር​ሱም ሕንጻ ሁሉ የሚ​ያ​ያ​ዝ​በት፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤተ መቅ​ደስ ግንብ የሚ​ያ​ድ​ግ​በት ነው።</verse>
				<verse number="22">እና​ንተ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪያ ልት​ሆኑ በእ​ርሱ ታነ​ጻ​ችሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ስለ​ዚህ አሕ​ዛብ ሆይ ስለ እና​ንተ እኔ ጳው​ሎስ የክ​ር​ስ​ቶስ እስ​ረ​ኛው ነኝ።</verse>
				<verse number="2">ስለ እና​ንተ የሰ​ጠ​ኝን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የጸ​ጋ​ውን ስጦታ ሰም​ታ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="3">አስ​ቀ​ድሞ በጥ​ቂቱ እንደ ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ ይህን ምሥ​ጢር ገልጦ አሳ​ይ​ቶ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="4">ይህ​ንም በም​ታ​ነ​ቡ​በት ጊዜ፥ የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ምሥ​ጢር ማስ​ተ​ዋ​ሌን ለማ​ወቅ ትች​ላ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="5">በሌላ ዘመን ለሰው ልጆች ያል​ተ​ገ​ለጠ ዛሬ ለቅ​ዱ​ሳን ሐዋ​ር​ያ​ቱና ለነ​ቢ​ያቱ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ እንደ ተገ​ለጠ፥</verse>
				<verse number="6">አሕ​ዛ​ብን ወራ​ሾ​ቹና አካሉ ያደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ፥ በወ​ን​ጌ​ልም ትም​ህ​ርት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በሆ​ነው ተስፋ አንድ ይሆኑ ዘንድ።</verse>
				<verse number="7">በኀ​ይሉ አጋ​ዥ​ነት እንደ ሰጠኝ እንደ ጸጋው ስጦታ መጠን እኔ መል​እ​ክ​ተ​ኛና አዋጅ ነጋሪ የሆ​ን​ሁ​ለት፥</verse>
				<verse number="8">ከቅ​ዱ​ሳን ሁሉ ለማ​ንስ ለእኔ የማ​ይ​መ​ረ​መ​ረ​ውን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ባለ​ጸ​ግ​ነት ለአ​ሕ​ዛብ አስ​ተ​ምር ዘንድ ይህን ጸጋ ሰጠኝ።</verse>
				<verse number="9">ሁሉን በፈ​ጠረ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​ሰ​ወረ የዚህ ምሥ​ጢር ሥር​ዐ​ት​ንም ለሁሉ እገ​ልጥ ዘንድ፤</verse>
				<verse number="10">ብዙ ልዩ ልዩ የሆ​ነች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በኩል በሰ​ማ​ያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለ​ቆ​ችና ሥል​ጣ​ናት ትታ​ወቅ ዘንድ፤</verse>
				<verse number="11">ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር የወ​ሰ​ናት፥ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም የፈ​ጸ​ማት፥</verse>
				<verse number="12">እኛ ጸጋ​ንና ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን ያገ​ኘ​ን​በት፥ በሃ​ይ​ማ​ኖት ወደ​ሚ​ገ​ኘው ተስ​ፋም ያደ​ረ​ሰ​በት፤</verse>
				<verse number="13">ስለ​ዚ​ህም ስለ እና​ንተ ለክ​ብ​ራ​ችሁ የም​ታ​ገ​ኘ​ኝን መከ​ራ​ዬን ቸል እን​ዳ​ይ​ላት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እማ​ል​ደ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">ስለ​ዚ​ህም በል​ቡ​ናዬ ተን​በ​ር​ክኬ ለአብ እሰ​ግ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">በሰ​ማ​ይና በም​ድር ያሉ ነገ​ዶች ሁሉ ለሚ​ጠ​ሩት ለእ​ርሱ፤</verse>
				<verse number="16">እንደ ጌት​ነቱ ምላት ይሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ፥ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ኀይል ያጸ​ና​ችሁ ዘንድ።</verse>
				<verse number="17">በል​ባ​ችሁ ውስጥ በፍ​ቅር ሥር መሠ​ረ​ታ​ችሁ የጸና ሲሆን ክር​ስ​ቶስ በሃ​ይ​ማ​ኖት በሰው ውስጥ ያድ​ራ​ልና።</verse>
				<verse number="18">ስፋ​ቱና ርዝ​መቱ፥ ምጥ​ቀ​ቱና ጥል​ቀቱ ምን ያህል እንደ ሆነ ከቅ​ዱ​ሳን ሁሉ ጋር ለማ​ስ​ተ​ዋል ትችሉ ዘንድ፥</verse>
				<verse number="19">የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ፍቅር ለመ​ረ​ዳት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍጹ​ም​ነት በሁሉ ፍጹ​ማን ትሆኑ ዘንድ።</verse>
				<verse number="20">በከ​ሃ​ሊ​ነቱ እንደ ረዳን መጠን፥ የም​ና​ስ​በ​ው​ንና የም​ን​ለ​ም​ነ​ውን ሁሉ ትሠሩ ዘንድ፥ ታበ​ዙም ዘንድ ሊያ​ጸ​ና​ችሁ ለሚ​ችል፥</verse>
				<verse number="21">ለእ​ርሱ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ፥ በት​ው​ልድ ሁሉ ምስ​ጋና ይሁን ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ አሜን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ለተ​ጠ​ራ​ሁ​ላት አጠ​ራር በሚ​ገባ ትኖሩ ዘንድ በክ​ር​ስ​ቶስ እስ​ረኛ የሆ​ንሁ እኔ ጳው​ሎስ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">በፍ​ጹም የዋ​ህ​ነት ራሳ​ች​ሁን ዝቅ አድ​ር​ጋ​ችሁ እየ​ታ​ገ​ሣ​ችሁ፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁም እሺ እያ​ላ​ችሁ፥ በፍ​ቅር እየ​ተ​ጋ​ች​ሁና እየ​ተ​ባ​በ​ራ​ችሁ፥</verse>
				<verse number="3">በአ​ንድ መን​ፈ​ስና በሰ​ላም ማሰ​ሪ​ያ​ነት እየ​ተ​ጠ​በ​ቃ​ችሁ፥</verse>
				<verse number="4">ለአ​ንዱ ተስ​ፋ​ችሁ እንደ መጠ​ራ​ታ​ችሁ መጠን፥ አንድ አካ​ልና አንድ መን​ፈስ ትሆኑ ዘንድ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">ጌታ አንድ ነው፤ ሃይ​ማ​ኖ​ትም አን​ዲት ናት፤ ጥም​ቀ​ትም አን​ዲት ናት።</verse>
				<verse number="6">በሁሉ ሙሉ የሚ​ሆን ሁሉም ከእ​ርሱ የተ​ገኘ ከሁ​ሉም በላይ ያለ የሁሉ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንድ ነው።</verse>
				<verse number="7">ከእኛ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ በክ​ር​ስ​ቶስ ስጦታ መጠን ጸጋው ተሰ​ጥ​ቶ​ናል።</verse>
				<verse number="8">“ምር​ኮን ማር​ከህ ወደ ሰማይ ወጣህ፤ ጸጋ​ህ​ንም ለሰው ልጅ ሰጠህ” ይላ​ልና።</verse>
				<verse number="9">ከም​ድር በታች ካል​ወ​ረደ መው​ጣቱ ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="10">የወ​ረ​ደው እርሱ ነው፤ ሁሉ​ንም ይመላ ዘንድ ከሰ​ማ​ያት ሁሉ በላይ የወ​ጣው ደግሞ እርሱ ነው።</verse>
				<verse number="11">እር​ሱም ጸጋን ሰጠ፤ ከቤተ ሰቦ​ቹም ሐዋ​ር​ያ​ትን፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ነቢ​ያ​ት​ንና የወ​ን​ጌል ሰባ​ኪ​ዎ​ችን፥ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ንና መም​ህ​ራ​ንን ሾመ።</verse>
				<verse number="12">ቅዱ​ሳን ለአ​ገ​ል​ግ​ሎቱ ሥራና ለክ​ር​ስ​ቶስ አካል ሕንጻ እን​ዲ​ጸኑ፤</verse>
				<verse number="13">ሁላ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ በማ​መ​ንና በማ​ወቅ አንድ እስ​ክ​ን​ሆን ድረስ በክ​ር​ስ​ቶስ ምል​ዐት መጠን፥ አካለ መጠን እንደ አደ​ረሰ እንደ አንድ ሙሉ ሰው እስ​ክ​ን​ሆን ድረስ፥</verse>
				<verse number="14">እን​ግ​ዲህ በሽ​ን​ገ​ላ​ቸው ያስቱ ዘንድ በሚ​ተ​ና​ኰሉ ሰዎች ተን​ኰል ምክ​ን​ያት በት​ም​ህ​ርት ነፋስ ሁሉ ወዲ​ያና ወዲህ እየ​ተ​ፍ​ገ​መ​ገ​ም​ንና እየ​ተ​ን​ሳ​ፈ​ፍን ሕፃ​ናት አን​ሁን።</verse>
				<verse number="15">ነገር ግን በፍ​ቅር እው​ነ​ተ​ኞች እን​ሆን ዘንድ ራስ ወደ ሆነው ወደ እርሱ ወደ ክር​ስ​ቶስ እን​ደግ።</verse>
				<verse number="16">ከእ​ርሱ የተ​ነሣ አካል ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ክፍል በልክ እን​ደ​ሚ​ሠራ፥ በተ​ሰ​ጠው በሥር ሁሉ እየ​ተ​ጋ​ጠ​መና እየ​ተ​ያ​ያዘ፥ ራሱን በፍ​ቅር ለማ​ነጽ አካ​ሉን ያሳ​ድ​ጋል።</verse>
				<verse number="17">እን​ግ​ዲህ በል​ባ​ቸው ከንቱ አሳብ እን​ደ​ሚ​ኖሩ እንደ አሕ​ዛብ እን​ዳ​ት​ኖሩ ይህን እላ​ለሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እመ​ሰ​ክ​ራ​ለሁ።</verse>
				<verse number="18">ልቡ​ና​ቸው የተ​ጨ​ፈነ ነው፤ በስ​ን​ፍ​ና​ቸ​ውና በድ​ን​ቍ​ር​ና​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ሰ​ጣ​ቸው ሕይ​ወት የተ​ለዩ ናቸው።</verse>
				<verse number="19">ተስፋ የቈ​ረጡ ናቸው፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ለጕ​ስ​ቍ​ልና፥ ለር​ኵ​ሰ​ትና ለመ​ዳ​ራት አሳ​ል​ፈው ሰጡ።</verse>
				<verse number="20">እና​ንተ ግን ክር​ስ​ቶ​ስን የተ​ማ​ራ​ች​ሁት እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="21">በር​ግጥ ከሰ​ማ​ች​ሁት፥ እው​ነት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነውና እው​ነ​ትን በእ​ርሱ ዘንድ ትማ​ራ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="22">የቀ​ድሞ ጠባ​ያ​ች​ሁን ከእ​ና​ንተ አርቁ፤ ይህ​ንም ስሕ​ተት በሚ​ያ​መ​ጣው ምኞት ስለ​ሚ​ጠ​ፋው ስለ አሮ​ጌው ሰው​ነት እላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="23">የል​ቡ​ና​ች​ሁን ዕው​ቀት አድሱ።</verse>
				<verse number="24">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ው​ነት፥ በቅ​ን​ነ​ትና በን​ጽ​ሕና ያደ​ሰ​ውን አዲ​ሱን ሰው​ነት ልበ​ሱት።</verse>
				<verse number="25">ስለ​ዚ​ህም ሐሰ​ትን ተዉ​አት፤ ሁላ​ች​ሁም ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ጋር እው​ነ​ትን ተነ​ጋ​ገሩ፤ እኛ አንድ አካል ነንና።</verse>
				<verse number="26">ተቈጡ፤ አት​በ​ድ​ሉም፤ ፀሐይ ሳይ​ጠ​ል​ቅም ቍጣ​ች​ሁን አብ​ርዱ።</verse>
				<verse number="27">ለሰ​ይ​ጣ​ንም መን​ገ​ድን አት​ስ​ጡት።</verse>
				<verse number="28">የሚ​ሰ​ር​ቅም እን​ግ​ዲህ አይ​ስ​ረቅ፤ ነገር ግን ድሃ​ውን ይረዳ ዘንድ በእ​ጆቹ መል​ካም እየ​ሠራ ይድ​ከም።</verse>
				<verse number="29">የሚ​ሰ​ሙ​አ​ችሁ ሞገ​ስን ያገኙ ዘንድ፥ ግዳ​ጃ​ችሁ እን​ዲ​ፈ​ጸም መል​ካም ነገር እንጂ ክፉ ነገር ሁሉ ከአ​ፋ​ችሁ አይ​ውጣ።</verse>
				<verse number="30">በዳ​ና​ችሁ ጊዜ የታ​ተ​ማ​ች​ሁ​በ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቅዱስ መን​ፈስ አታ​ሳ​ዝ​ኑት።</verse>
				<verse number="31">መራ​ራ​ነ​ት​ንና ቍጣን፥ ብስ​ጭ​ት​ንና ርግ​ማ​ንን፥ ጥፋ​ት​ንና ስድ​ብን ሁሉ ከክፉ ነገር ሁሉ ጋር ከእ​ና​ንተ አርቁ።</verse>
				<verse number="32">እርስ በር​ሳ​ች​ሁም ቸሮ​ችና ርኅ​ሩ​ኆች ሁኑ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በክ​ር​ስ​ቶስ ይቅር እን​ዳ​ላ​ችሁ ይቅር ተባ​ባሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">እን​ግ​ዲህ እንደ ተወ​ደዱ ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሰሉ።</verse>
				<verse number="2">ክር​ስ​ቶስ እንደ ወደ​ዳ​ችሁ፥ ራሱ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ የሚ​ሆን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ቍር​ባን አድ​ርጎ እንደ ሰጠ​ላ​ችሁ በፍ​ቅር ተመ​ላ​ለሱ።</verse>
				<verse number="3">ነገር ግን ለቅ​ዱ​ሳን እን​ደ​ሚ​ገ​ባ​ቸው፥ ዝሙ​ትና ርኵ​ሰት ሁሉ ወይም ቅሚያ አይ​ሰ​ማ​ባ​ችሁ።</verse>
				<verse number="4">የሚ​ያ​ሳ​ፍር ነገ​ርም፥ የስ​ን​ፍና ነገ​ርም፥ ወይም የማ​ይ​ገባ የዋዛ ነገር በእ​ና​ንተ ዘንድ አይ​ሁን፤ ማመ​ስ​ገን ይሁን እንጂ።</verse>
				<verse number="5">ሴሰኛ፥ ወይም ኀጢ​አ​ተኛ፥ ወይም ቀማኛ፥ ወይም ጣዖ​ትን የሚ​ያ​መ​ልክ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ በክ​ር​ስ​ቶስ መን​ግ​ሥት ዕድል ፋንታ እን​ደ​ሌ​ለው ይህን ዕወቁ።</verse>
				<verse number="6">በከ​ንቱ ነገ​ርም የሚ​ያ​ስ​ታ​ችሁ አይ​ኑር፤ በእ​ርሱ ምክ​ን​ያት በከ​ሓ​ዲ​ዎች ልጆች ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓት ይመ​ጣ​ልና።</verse>
				<verse number="7">እን​ግ​ዲህ አት​ም​ሰ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">ቀድሞ ጨለማ ነበ​ራ​ች​ሁና፥ ዛሬ ግን በጌ​ታ​ችን ብር​ሃን ሆና​ች​ኋል። እን​ግ​ዲ​ህስ እንደ ብር​ሃን ልጆች ተመ​ላ​ለሱ።</verse>
				<verse number="9">የብ​ር​ሃን ፍሬው በጎ ሥራና እው​ነት፥ ቅን​ነ​ትም ሁሉ ነውና።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን መር​ምሩ።</verse>
				<verse number="11">የሥራ ፍሬ ከሌ​ላ​ቸው፥ ሁለ​ን​ተ​ና​ቸ​ውም ጨለማ ከሆነ ሰዎች ጋር አት​ተ​ባ​በሩ፤ ገሥ​ጹ​አ​ቸው እንጂ።</verse>
				<verse number="12">በስ​ውር የሚ​ሠ​ሩት ሥራ ለመ​ና​ገር የሚ​ያ​ሳ​ፍር ነውና።</verse>
				<verse number="13">ነገር ግን በብ​ር​ሃን የተ​ገ​ለጠ ሁሉ ይታ​ወ​ቃል፤ የሚ​ታ​የው ሁሉ ብር​ሃን ነውና።</verse>
				<verse number="14">“የተ​ኛህ ንቃ ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይ​ተህ ተነሥ፤ ክር​ስ​ቶ​ስም ያበ​ራ​ል​ሃል” ብሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="15">እን​ግ​ዲህ እንደ ዐዋ​ቂ​ዎች እንጂ እንደ አላ​ዋ​ቂ​ዎች ሳይ​ሆን እን​ዴት እን​ደ​ም​ት​መ​ላ​ለሱ በጥ​ን​ቃቄ ዕወቁ።</verse>
				<verse number="16">ቀኖች ክፉ​ዎች ናቸ​ውና ዘመ​ኑን ዋጁት።</verse>
				<verse number="17">ስለ​ዚ​ህም ሰነ​ፎች አት​ሁኑ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈቃድ አስ​ተ​ውሉ እንጂ።</verse>
				<verse number="18">መዳ​ራት ነውና ወይን በመ​ጠ​ጣት አት​ስ​ከሩ፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተመሉ እንጂ።</verse>
				<verse number="19">መዝ​ሙ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን፥ የተ​ቀ​ደሰ ማሕ​ሌ​ት​ንም አን​ብቡ፤ በል​ባ​ች​ሁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቀኙ፤ ዘም​ሩም።</verse>
				<verse number="20">ዘወ​ት​ርም ስለ ሁሉ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ ምስ​ጋና አቅ​ርቡ።</verse>
				<verse number="21">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ፍ​ራት ለባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ችሁ ራሳ​ች​ሁን ዝቅ አድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="22">ሴቶ​ችም ለጌ​ታ​ችን እን​ደ​ሚ​ታ​ዘዙ ለባ​ሎ​ቻ​ቸው ይታ​ዘዙ።</verse>
				<verse number="23">ክር​ስ​ቶስ አካሉ ለሆ​ነ​ችው ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ራስዋ አዳ​ኝ​ዋም እንደ ሆነ ወንድ ለሴት ራስዋ ነውና።</verse>
				<verse number="24">ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ለክ​ር​ስ​ቶስ እን​ደ​ም​ት​ታ​ዘዝ፥ እን​ዲ​ሁም ሴቶች ለባ​ሎ​ቻ​ቸው በሁሉ ይታ​ዘዙ።</verse>
				<verse number="25">ወን​ዶ​ችም ክር​ስ​ቶስ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንን እንደ ወደ​ዳት፥ ራሱ​ንም ስለ እር​ስዋ ቤዛ አድ​ርጎ እንደ ሰጠ​ላት ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ይው​ደዱ።</verse>
				<verse number="26">በውኃ ጥም​ቀ​ትና በቃሉ ይቀ​ድ​ሳ​ትና ያነ​ጻት ዘንድ፥</verse>
				<verse number="27">የነ​ጻ​ችና የተ​ቀ​ደ​ሰች ትሆን ዘንድ እንጂ በላ​ይዋ እድ​ፈት ወይም ርኵ​ሰት እን​ዳ​ያ​ገ​ኝ​ባት፥ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ኑን ለእ​ርሱ የከ​በ​ረች ያደ​ር​ጋት ዘንድ፤</verse>
				<verse number="28">እን​ዲ​ሁም ወን​ዶች ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን እንደ ራሳ​ቸው አድ​ር​ገው ይው​ደዱ፤ ሚስ​ቱ​ንም የወ​ደደ ራሱን ወደደ።</verse>
				<verse number="29">ከቶ ሥጋ​ውን መጥ​ላት የሚ​ቻ​ለው የለም፤ ክር​ስ​ቶስ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንን እንደ መገ​ባት መግቡ፤ ጠብ​ቁም።</verse>
				<verse number="30">እኛ የአ​ካሉ ሕዋ​ሳት ነንና።</verse>
				<verse number="31">“ስለ​ዚ​ህም ወንድ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ይተ​ዋል፤ ከሚ​ስ​ቱም ጋር አንድ ይሆ​ናል፤ ሁለ​ቱም አንድ አካል ይሆ​ናሉ።”</verse>
				<verse number="32">ይህም ምሥ​ጢር ታላቅ ነው፤ እኔም ይህ​ንኑ ስለ ክር​ስ​ቶ​ስና ስለ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያኑ እና​ገ​ረ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="33">እን​ግ​ዲ​ያስ እና​ን​ተም ሁላ​ችሁ እን​ዲሁ ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁን እንደ ራሳ​ችሁ ውደዱ፥ ሴትም ባል​ዋን ትፍ​ራው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">ልጆች ሆይ፥ ለወ​ላ​ጆ​ቻ​ችሁ በጌ​ታ​ችን ታዘዙ፤ ይህ የሚ​ገባ ነውና።</verse>
				<verse number="2">በሕ​ግም ተስፋ ያለው የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ትእ​ዛዝ ይህ ነው፥ “አባ​ት​ህ​ንና እና​ት​ህን አክ​ብር፤</verse>
				<verse number="3">መል​ካም ይሆ​ን​ልህ ዘንድ፥ በም​ድር ላይም ዕድ​ሜህ ይረ​ዝም ዘንድ።”</verse>
				<verse number="4">እና​ን​ተም አባ​ቶች ሆይ፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተግ​ሣ​ጽና ምክር አሳ​ድ​ጉ​አ​ቸው እንጂ አታ​ስ​ቈ​ጡ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም በሥ​ጋ​ችሁ ለሚ​ገ​ዙ​አ​ችሁ ጌቶ​ቻ​ችሁ በፍ​ር​ሀ​ትና በመ​ደ​ን​ገጥ፥ በሰፊ ልብም ለክ​ር​ስ​ቶስ እን​ደ​ም​ት​ገዙ ታዘዙ።</verse>
				<verse number="6">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈቃድ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርጉ እንደ ክር​ስ​ቶስ ባሮች እንጂ ለሰው ደስ እን​ደ​ሚ​ያ​ሰኝ ለታ​ይታ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="7">ለሰው ሳይ​ሆን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ደ​ም​ት​ገዙ በፍ​ጹም ሰው​ነ​ታ​ችሁ በፍ​ቅ​ርና በበጎ ፈቃድ ተገ​ዙ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">ጌታም ቢሆን፥ አገ​ል​ጋ​ይም ቢሆን መል​ካም ያደ​ረገ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ዋጋ እን​ደ​ሚ​ያ​ገኝ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።</verse>
				<verse number="9">እና​ን​ተም ጌቶች ሆይ፥ ቍጣ​ች​ሁን እያ​በ​ረ​ዳ​ችሁ፥ በደ​ላ​ቸ​ው​ንም ይቅር እያ​ላ​ችሁ፥ ትክ​ክ​ለ​ኛ​ውን አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ ፊት አይቶ የማ​ያ​ዳላ ጌታ በእ​ነ​ር​ሱና በእ​ና​ንተ ላይ በሰ​ማይ እንደ አለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።</verse>
				<verse number="10">እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በኀ​ይሉ ጽናት በርቱ።</verse>
				<verse number="11">የሰ​ይ​ጣ​ንን ተን​ኰል መቋ​ቋም እን​ድ​ት​ችሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጋሻ ልበሱ።</verse>
				<verse number="12">ሰል​ፋ​ችሁ፦ ከጨ​ለማ ገዦች ጋርና ከሰ​ማይ በታች ካሉ ከክ​ፉ​ዎች አጋ​ን​ንት ጋር ነው እንጂ ከሥ​ጋ​ዊና ከደ​ማዊ ጋር አይ​ደ​ለ​ምና።</verse>
				<verse number="13">ስለ​ዚ​ህም በክፉ ቀን መቃ​ወም እን​ድ​ት​ችሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጋሻ ያዙ፤ እን​ድ​ት​ጸ​ኑም በሁሉ የተ​ዘ​ጋ​ጃ​ችሁ ሁኑ።</verse>
				<verse number="14">እን​ግ​ዲህ ወገ​ባ​ች​ሁን በእ​ው​ነት ታጥ​ቃ​ችሁ ቁሙ፤ የጽ​ድ​ቅ​ንም ጥሩር ልበሱ።</verse>
				<verse number="15">የሰ​ላም ወን​ጌል ኀይ​ል​ንም ተጫ​ም​ታ​ችሁ ቁሙ።</verse>
				<verse number="16">ከዚ​ህም ሁሉ ጋር የሚ​ን​በ​ለ​በሉ የክ​ፉን ፍላ​ፃ​ዎች ሁሉ ማጥ​ፋት እን​ድ​ት​ችሉ የእ​ም​ነ​ትን ጋሻ አንሡ።</verse>
				<verse number="17">የመ​ዳ​ን​ንም የራስ ቍር በራ​ሳ​ችሁ ላይ ጫኑ፤ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስ​ንም ሰይፍ ያዙ፤ ይኸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ነው።</verse>
				<verse number="18">በጸ​ሎ​ትና በም​ልጃ ሁሉ ዘወ​ትር በመ​ን​ፈስ ጸልዩ፤ ከዚ​ህም ጋር ስለ ቅዱ​ሳን ሁሉ ለመ​ጸ​ለይ ሁል​ጊዜ ትጉ፤</verse>
				<verse number="19">ለእ​ኔም፦ ቃልን እን​ዲ​ሰ​ጠኝ፥ አፌ​ንም ከፍቼ የወ​ን​ጌ​ልን ምሥ​ጢር በግ​ልጥ እን​ድ​ና​ገር ጸል​ዩ​ልኝ።</verse>
				<verse number="20">ስለ ወን​ጌ​ልም በእ​ስ​ራት መል​እ​ክ​ተኛ የሆ​ንሁ፦ መና​ገር እን​ደ​ሚ​ገ​ባኝ ስለ እርሱ በግ​ልጥ እና​ገር ዘንድ ጸልዩ።</verse>
				<verse number="21">እና​ን​ተም ዜና​ዬን እን​ድ​ታ​ውቁ የም​ን​ወ​ደው ወን​ድ​ማ​ችን የታ​መነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ቲኪ​ቆስ የም​ሠ​ራ​ውን ሁሉ ያስ​ረ​ዳ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="22">ዜና​ዬን ታውቁ ዘንድ፥ ልባ​ች​ሁም ይጽ​ናና ዘንድ፥ ስለ​ዚህ ወደ እና​ንተ ላክ​ሁት።</verse>
				<verse number="23">ከአ​ባ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ፥ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ከእ​ም​ነት ጋር ሰላ​ምና ፍቅር ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ይሁን።</verse>
				<verse number="24">ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ባለ መጥ​ፋት ከሚ​ወ​ዱት ሁሉ ጋር ጸጋ ይሁን። አሜን። በሮሜ ተጽፋ በቲ​ኪ​ቆስ እጅ ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች የተ​ላ​ከች መል​እ​ክት ተፈ​ጸ​መች። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን። አሜን።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="50">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ባር​ያ​ዎች ከጳ​ው​ሎ​ስና ከጢ​ሞ​ቴ​ዎስ፥ በፊ​ል​ጵ​ስ​ዩስ ለሚ​ኖሩ፤ ከቀ​ሳ​ው​ስ​ትና ከዲ​ያ​ቆ​ናት ጋር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ላሉ ቅዱ​ሳን ሁሉ፤</verse>
				<verse number="2">ከአ​ባ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰላ​ምና ጸጋ ለእ​ና​ንተ ይሁን።</verse>
				<verse number="3">እና​ን​ተን በማ​ስ​ብ​በት ጊዜ ሁሉ ዘወ​ትር አም​ላ​ኬን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="4">ስለ እና​ን​ተም ሁል​ጊዜ እጸ​ል​ያ​ለሁ፤ የደ​ስታ ጸሎ​ትም አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዪቱ ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ በወ​ን​ጌል ትም​ህ​ርት ከእኔ ጋር አንድ በመ​ሆ​ና​ችሁ፥</verse>
				<verse number="6">እርሱ የጀ​መ​ረ​ላ​ች​ሁን በጎ​ውን ሥራ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እስ​ከ​ሚ​መ​ጣ​በት ቀን ድረስ እርሱ እን​ደ​ሚ​ፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ አም​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="7">ስለ እና​ንተ ይህን ላስብ ይገ​ባ​ኛል፤ በም​ታ​ሰ​ር​በ​ትና በም​ከ​ራ​ከ​ር​በት፥ ወን​ጌ​ል​ንም በማ​ስ​ተ​ም​ር​በት ጊዜ ከእኔ ጋራ በጸጋ ስለ ተባ​በ​ራ​ችሁ በልቤ ውስጥ ናች​ሁና።</verse>
				<verse number="8">በክ​ር​ስ​ቶስ ፍቅር ሁላ​ች​ሁን እን​ደ​ም​ወ​ዳ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክሬ ነው።</verse>
				<verse number="9">ስለ​ዚ​ህም በአ​እ​ም​ሮና በልብ ጥበብ ሁሉ ፍቅ​ራ​ችሁ እን​ዲ​በዛ፥ እን​ዲ​ጨ​ም​ርም እጸ​ል​ያ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="10">የሚ​ሻ​ለ​ውን ሥራ እን​ድ​ት​መ​ረ​ም​ሩና እን​ድ​ት​ፈ​ትኑ፥ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ቀን ያለ ዕን​ቅ​ፋት ቅዱ​ሳን ትሆኑ ዘንድ፦</verse>
				<verse number="11">ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋ​ናና ክብ​ርም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የጽ​ድ​ቅን ፍሬ ትሞሉ ዘንድ እጸ​ል​ያ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="12">ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ይህ የደ​ረ​ሰ​ብኝ በእ​ው​ነት ወን​ጌ​ልን ለማ​ስ​ፋ​ፋት እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ እወ​ድ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="13">ስለ ክር​ስ​ቶስ ስም መታ​ሰ​ሬም በአ​ደ​ባ​ባዩ ሁሉና በሰው ሁሉ ዘንድ ታው​ቆ​አል።</verse>
				<verse number="14">ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ብዙ​ዎቹ በእ​ስ​ራቴ ምክ​ን​ያት በጌታ ታመኑ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ያለ ፍር​ሀት ጨክ​ነው ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ እጅግ ተደ​ፋ​ፈሩ።</verse>
				<verse number="15">ከእ​ነ​ርሱ አን​ዳ​ን​ዶች በቅ​ና​ታ​ቸ​ውና በክ​ር​ክ​ራ​ቸው፥ ሌሎ​ችም በበጎ ፈቃድ ስለ ክር​ስ​ቶስ ሊሰ​ብ​ኩና ሊያ​ስ​ተ​ምሩ የወ​ደዱ አሉ።</verse>
				<verse number="16">በፍ​ቅር የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩም አሉ፤ ወን​ጌ​ልን ለማ​ስ​ተ​ማር እንደ ተሾ​ምሁ ያው​ቃ​ሉና።</verse>
				<verse number="17">በኵ​ራት ስለ ክር​ስ​ቶስ የሚ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ግን፥ ይህን አድ​ር​ገው በእ​ስ​ራቴ ላይ መከራ ሊጨ​ም​ሩ​ብኝ መስ​ሎ​አ​ቸው ነው እንጂ በእ​ው​ነት አይ​ደ​ለም፤ በቅ​ን​ነ​ትም አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="18">ነገር ግን ምን አለ? በየ​ም​ክ​ን​ያቱ በእ​ው​ነ​ትም ቢሆን፥ በሐ​ሰ​ትም ቢሆን፥ ስለ ክር​ስ​ቶስ ይና​ገ​ራሉ፤ ሰው​ንም ሁሉ ወደ እርሱ ይጠ​ራሉ፤ በዚ​ህም ደስ ብሎ​ኛል፤ ወደ​ፊ​ትም ደስ ይለ​ኛል።</verse>
				<verse number="19">እኔም ይህቺ ሥራ በጸ​ሎ​ታ​ች​ሁና በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ መን​ፈስ ወደ ሕይ​ወት እን​ደ​ም​ታ​ደ​ር​ሰኝ አው​ቃ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">በም​ንም እን​ደ​ማ​ላ​ፍር ተስፋ እንደ አደ​ረ​ግ​ሁና እን​ደ​ታ​መ​ንሁ እንደ ወት​ሮው በልብ ደስታ በግ​ል​ጥ​ነት፥ አሁ​ንም የክ​ር​ስ​ቶስ ክብር በሕ​ይ​ወ​ቴም ቢሆን፥ በሞ​ቴም ቢሆን በሰ​ው​ነቴ ይገ​ለ​ጣል።</verse>
				<verse number="21">እኔ በሕ​ይ​ወት ብኖ​ርም ክር​ስ​ቶ​ስን ለማ​ገ​ል​ገል ነው፤ ብሞ​ትም ዋጋ አለኝ።</verse>
				<verse number="22">ነገር ግን በሥጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆ​ንም ምን እን​ደ​ም​መ​ርጥ አላ​ው​ቅም።</verse>
				<verse number="23">በእ​ነ​ዚህ በሁ​ለቱ እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ እኔስ ከዚህ ዓለም ልለይ፥ በከ​ክ​ር​ስ​ቶ​ስም ዘንድ ልኖር እወ​ዳ​ለሁ፤ ይል​ቁ​ንም ለእኔ ይህ ይሻ​ለ​ኛል፤ ይበ​ል​ጥ​ብ​ኛ​ልም።</verse>
				<verse number="24">ደግ​ሞም ስለ እና​ንተ በሕ​ይ​ወተ ሥጋ ብኖር ይሻ​ላል።</verse>
				<verse number="25">ይህ​ንም ዐውቄ ለማ​ደ​ጋ​ች​ሁና በሃ​ይ​ማ​ኖ​ትም ለም​ታ​ገ​ኙት ደስታ እን​ደ​ም​ኖር አም​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="26">ዳግ​መኛ ወደ እና​ንተ በመ​ም​ጣቴ በእኔ ምክ​ን​ያት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የም​ታ​ገ​ኙት ክብር ይበ​ዛ​ላ​ችሁ ዘንድ።</verse>
				<verse number="27">ነገር ግን ምና​ል​ባት የመ​ጣሁ እንደ ሆነ፥ ሳል​ኖ​ርም ቢሆን በወ​ን​ጌል ሃይ​ማ​ኖት እየ​ተ​ጋ​ደ​ላ​ችሁ በአ​ንድ መን​ፈ​ስና በአ​ንድ አካል ጸን​ታ​ችሁ እን​ደ​ም​ት​ኖሩ አይና እሰማ ዘንድ ሥራ​ችሁ ለክ​ር​ስ​ቶስ ትም​ህ​ርት እን​ደ​ሚ​ገባ ይሁን።</verse>
				<verse number="28">የእ​ነ​ርሱ ጥፋት፥ የእ​ና​ን​ተም ሕይ​ወት ይታ​ወቅ ዘንድ የሚ​ቃ​ወ​ሙን ሰዎች በማ​ና​ቸ​ውም አያ​ስ​ደ​ን​ግ​ጧ​ችሁ።</verse>
				<verse number="29">ይህ​ንም ጸጋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ ነገር ግን ስለ እርሱ መከራ ልት​ቀ​በ​ሉም ነው እንጂ ልታ​ም​ኑ​በት ብቻ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="30">እን​ዲ​ሁም እኔን እን​ዳ​ያ​ች​ሁኝ፥ የእ​ኔ​ንም ነገር እንደ ሰማ​ችሁ ምን​ጊ​ዜም ተጋ​ደሉ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">አሁ​ንም በክ​ር​ስ​ቶስ ደስታ፥ ወይም በፍ​ቅር የልብ መጽ​ና​ናት፥ ወይም የመ​ን​ፈስ አን​ድ​ነት፥ ወይም ማዘ​ንና መራ​ራ​ትም በእ​ና​ንተ ዘንድ ካለ፦</verse>
				<verse number="2">እር​ሱን ብቻ ታስቡ ዘንድ፥ አንድ ልብና አንድ ምክ​ርም ሆና​ችሁ፥ በፍ​ቅር ትኖሩ ዘንድ ደስ​ታ​ዬን ፈጽ​ሙ​ልኝ።</verse>
				<verse number="3">በክ​ር​ክ​ርና ከንቱ ውዳ​ሴን በመ​ው​ደድ አት​ሥሩ፤ ትሕ​ት​ናን በያዘ ልቡና ከራ​ሳ​ችሁ ይልቅ ባል​ን​ጀ​ራ​ች​ሁን አክ​ብሩ እንጂ አት​ታ​በዩ።</verse>
				<verse number="4">ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ች​ሁም እንጂ ለየ​ራ​ሳ​ችሁ ብቻ አታ​ስቡ።</verse>
				<verse number="5">ፍጹ​ማን የሆ​ና​ችሁ ሁላ​ችሁ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ለእኛ እንደ አደ​ረ​ገ​ልን ይህን አስቡ።</verse>
				<verse number="6">ይኸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መልኩ ነው፤ ቀምቶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆነ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="7">ነገር ግን የባ​ር​ያን መልክ ይዞ፥ በሰ​ውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ዝቅ አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="8">እንደ ሰውም ሆኖ ራሱን አዋ​ረደ፤ ለሞት እስከ መድ​ረ​ስም ታዘዘ፤ ሞቱም በመ​ስ​ቀል የሆ​ነው ነው።</verse>
				<verse number="9">ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅግ ከፍ ከፍ አደ​ረ​ገው፤ ከስም ሁሉ የሚ​በ​ልጥ ስም​ንም ሰጠው።</verse>
				<verse number="10">ይህም በሰ​ማ​ይና በም​ድር በቀ​ላ​ያ​ትና ከም​ድር በታች ያለ ጕል​በት ሁሉ ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ይሰ​ግድ ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="11">አን​ደ​በ​ትም ሁሉ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ ክብር ጌታ እንደ ሆነ ያምን ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="12">አሁ​ንም ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ዘወ​ትር እን​ደ​ም​ት​ሰ​ሙኝ ሳለሁ ብቻ ሳይ​ሆን፥ ሳል​ኖ​ርም በፍ​ር​ሀ​ትና በመ​ን​ቀ​ጥ​ቀጥ ሆና​ችሁ ለድ​ኅ​ነ​ታ​ችሁ ሥሩ።</verse>
				<verse number="13">ለሚ​ወ​ደው ሥራ የሚ​ረ​ዳ​ችሁ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታ​ውን ይፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="14">የም​ት​ሠ​ሩ​ትን ሁሉ ያለ ማን​ጐ​ራ​ጐ​ርና ያለ መጠ​ራ​ጠር በፍ​ቅ​ርና በስ​ም​ም​ነት ሥሩ።</verse>
				<verse number="15">እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ንጹ​ሓ​ንና የዋ​ሃን ትሆኑ ዘንድ፥ በማ​ያ​ም​ኑና በጠ​ማ​ሞች ልጆች መካ​ከል ነውር ሳይ​ኖ​ር​ባ​ችሁ በዓ​ለም እንደ ብር​ሃን ትታ​ያ​ላ​ችሁ፤</verse>
				<verse number="16">የሕ​ይ​ወ​ትን ቃል እያ​ስ​ተ​ማ​ራ​ችሁ፤ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ቀን እኔ እን​ድ​መካ፤ የሮ​ጥሁ በከ​ንቱ አይ​ደ​ለ​ምና፤ የደ​ከ​ም​ሁም በከ​ንቱ አይ​ደ​ለ​ምና።</verse>
				<verse number="17">ስለ ሃይ​ማ​ኖ​ታ​ች​ሁም የአ​ም​ልኮ መሥ​ዋ​ዕ​ትን እሠ​ዋ​ለሁ። እነ​ሆም እኔ በእ​ና​ንተ ደስ ይለ​ኛል፤</verse>
				<verse number="18">እና​ን​ተም በእኔ ደስ ይበ​ላ​ችሁ። ከእ​ኔም ጋር ሐሤት አድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="19">ጢሞ​ቴ​ዎ​ስን እን​ድ​ል​ክ​ላ​ችሁ፥ እኔም ዜና​ች​ሁን ሰምቼ ደስ እን​ዲ​ለኝ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ተስፋ አደ​ር​ጋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">ከእ​ርሱ በቀር፥ እንደ እኔ ሆኖ በማ​ስ​ተ​ዋል ግዳ​ጃ​ች​ሁን የሚ​ፈ​ጽም የለ​ኝ​ምና።</verse>
				<verse number="21">የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ያይ​ደለ፥ ሁሉም የራ​ሱን ጉዳይ ያስ​ባ​ልና።</verse>
				<verse number="22">ልጅ አባ​ቱን እን​ደ​ሚ​ያ​ገ​ለ​ግል፥ በወ​ን​ጌል ትም​ህ​ርት እንደ አገ​ለ​ገ​ለኝ፥ የዚ​ህን ሰው ጠባ​ዩን ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="23">እን​ግ​ዲህ እን​ዴት እንደ አለሁ በዐ​ወ​ቅሁ ጊዜ፥ እር​ሱን በቶሎ እን​ደ​ም​ል​ከው ተስፋ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="24">እኔም ፈጥኜ እን​ደ​ም​መጣ በጌ​ታ​ችን አም​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="25">አሁ​ንም አብ​ሮኝ የሚ​ሠ​ራ​ውን ወን​ድ​ማ​ች​ንን አፍ​ሮ​ዲ​ጡን ወደ እና​ንተ ልል​ከው አስ​ቤ​አ​ለሁ፤ እር​ሱም የክ​ር​ስ​ቶስ ሎሌ ነው፤ ለእ​ና​ን​ተም መም​ህ​ራ​ችሁ ነው፤ ለእ​ኔም ለች​ግሬ ጊዜ መል​እ​ክ​ተ​ኛዬ ነው።</verse>
				<verse number="26">እንደ ታመመ፥ ለሞ​ትም እንደ ደረሰ መስ​ማ​ታ​ች​ሁን ዐውቆ ሊያ​ያ​ችሁ ይሻ​ልና።</verse>
				<verse number="27">ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማረው፤ በኀ​ዘን ላይ ኀዘን እን​ዳ​ይ​ጨ​መ​ር​ብኝ ለእ​ኔም እንጂ ለእሱ ብቻ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="28">እን​ድ​ታ​ዩ​ትና ደስ እን​ዲ​ላ​ችሁ፥ እኔም እን​ዳ​ላ​ዝን በቶሎ እል​ከ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="29">እን​ግ​ዲህ በጌ​ታ​ችን በፍ​ጹም ደስታ ተቀ​በ​ሉት፤ እን​ደ​ዚህ ያሉ​ት​ንም ሁሉ አክ​ብ​ሩ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="30">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ስለ መሥ​ራት እስከ ሞት ደር​ሶ​አ​ልና፥ ከእኔ መል​እ​ክ​ትም እና​ንተ ያጐ​ደ​ላ​ች​ሁ​ትን ይፈ​ጽም ዘንድ ሰው​ነ​ቱን አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">አሁ​ንም ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ በጌ​ታ​ችን ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ እኔም ስጽ​ፍ​ላ​ችሁ ቸል አል​ልም፤ ያበ​ረ​ታ​ች​ኋ​ልና።</verse>
				<verse number="2">ከው​ሾች ተጠ​በቁ፤ ከክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎ​ችም ተጠ​በቁ፤ ሥጋ​ቸ​ውን ብቻ በመ​ቍ​ረጥ ተገ​ዝ​ረ​ናል ከሚ​ሉም ተጠ​በቁ።</verse>
				<verse number="3">ግዙ​ራ​ንስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ን​ፈስ የም​ና​ገ​ለ​ግ​ለ​ውና የም​ና​መ​ል​ከው እኛ ነን፤ እኛም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እን​መ​ካ​ለን እንጂ በሥ​ጋ​ችን የም​ን​መካ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="4">እኔም ግዝ​ረት ሳለኝ በግ​ዝ​ረት አል​መ​ካም፤ በግ​ዝ​ረት መመ​ካ​ትን የሚ​ያ​ስብ ካለም እኔ እር​ሱን እበ​ል​ጠ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="5">በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን የተ​ገ​ዘ​ርሁ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ከብ​ን​ያም ነገድ ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ዕብ​ራዊ ነኝ፤ በኦ​ሪ​ትም ፈሪ​ሳዊ ነበ​ርሁ።</verse>
				<verse number="6">በኦ​ሪት ጽድ​ቅም ያለ ነውር ሆኜ በቅ​ን​ዐት ምእ​መ​ና​ንን አሳ​ድድ ነበር።</verse>
				<verse number="7">ነገር ግን ስለ ክር​ስ​ቶስ ያን ጥቅ​ሜን ላጣው ወደ​ድሁ።</verse>
				<verse number="8">ክር​ስ​ቶ​ስን አገ​ለ​ግ​ለው ዘንድ፥ ሁሉን የተ​ው​ሁ​ለት፥ እንደ ጕድ​ፍም ያደ​ረ​ግ​ሁ​ለት የጌ​ታ​ዬን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ኀይ​ልና ገና​ና​ነት ስለ​ማ​ውቅ ሁሉን እንደ ኢም​ንት ቈጠ​ር​ሁት።</verse>
				<verse number="9">በእ​ር​ሱም እጸና ዘንድ፥ ዛሬ የኦ​ሪት ጽድቅ ሳይ​ኖ​ረኝ ክር​ስ​ቶ​ስን በማ​መን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ገኝ ጽድቅ አለኝ እንጂ።</verse>
				<verse number="10">በእ​ር​ሱም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን አው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ የመ​ነ​ሣ​ቱ​ንም ኀይል በሕ​ማሙ እሳ​ተ​ፈ​ዋ​ለሁ፤ በሞ​ቱም እመ​ስ​ለ​ዋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="11">ይኸ​ውም ሙታን በሚ​ነሡ ጊዜ ምና​ል​ባት በዚህ አገ​ኘው እንደ ሆነ ብዬ ነው።</verse>
				<verse number="12">ነገር ግን ይህን ፈጽሜ የተ​ቀ​በ​ልሁ አይ​ደ​ለም፤ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስለ እርሱ እኔን የመ​ረ​ጠ​በ​ትን አገኝ ዘንድ እሮ​ጣ​ለሁ እንጂ።</verse>
				<verse number="13">ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እኔ ግን ፍጻ​ሜ​ዬን ገና ያገ​ኘሁ አይ​መ​ስ​ለ​ኝም።</verse>
				<verse number="14">የኋ​ላ​ዬን እረ​ሳ​ለ​ሁና፥ ወደ ፊቴም ፈጥኜ እገ​ሠ​ግ​ሣ​ለ​ሁና፤ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ከፍ ከፍ ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የጥሪ ዋጋ ለማ​ግ​ኘት ወደ ግቡ እፈ​ጥ​ና​ለሁ።</verse>
				<verse number="15">ፍጹ​ማን የሆ​ና​ችሁ ሁላ​ችሁ ይህን አስቡ፤ ሌላ የም​ታ​ስ​ቡት ቢኖ​ርም፥ እር​ሱን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገ​ል​ጥ​ላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="16">ነገር ግን በደ​ረ​ስ​ን​በት ሥራ በአ​ን​ድ​ነት እን​በ​ርታ።</verse>
				<verse number="17">ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እኔን ምሰሉ፤ እን​ዲህ ባለ መን​ገድ የሚ​ሄ​ዱ​ት​ንም እኛን ታዩ እንደ ነበ​ረ​በት ጊዜ ተጠ​ባ​በ​ቋ​ቸው።</verse>
				<verse number="18">ዘወ​ትር እን​ደ​ም​ነ​ግ​ራ​ችሁ፥ ልዩ አካ​ሄድ የሚ​ሄዱ ብዙ​ዎች አሉና፤ አሁ​ንም እነ​ርሱ የክ​ር​ስ​ቶስ የመ​ስ​ቀሉ ጠላ​ቶች እንደ ሆኑ በግ​ልጥ እያ​ለ​ቀ​ስሁ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">እነ​ዚ​ህም ፍጻ​ሜ​ያ​ቸው ለጥ​ፋት የሆነ፥ ሆዳ​ቸ​ውን የሚ​ያ​መ​ልኩ፥ ክብ​ራ​ቸ​ውም ውር​ደት የሆ​ነ​ባ​ቸው፥ ምድ​ራ​ዊ​ዉ​ንም የሚ​ያ​ስቡ ናቸው።</verse>
				<verse number="20">እኛስ ሀገ​ራ​ችን በሰ​ማይ ያለ​ችው ናት፤ ከዚ​ያም እር​ሱን ጌታ​ችን መድ​ኀ​ኒ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን እን​ጠ​ባ​በ​ቃ​ለን።</verse>
				<verse number="21">እር​ሱም እንደ ከሃ​ሊ​ነቱ ረዳ​ት​ነት መጠን የተ​ዋ​ረ​ደ​ውን ሥጋ​ች​ንን የሚ​ያ​ድ​ሰው፥ ክቡር ሥጋ​ዉ​ንም እን​ዲ​መ​ስል የሚ​ያ​ደ​ር​ገው፥ የሚ​ያ​ስ​መ​ስ​ለ​ውም፥ ሁሉም የሚ​ገ​ዛ​ለት ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">አሁ​ንም የተ​ወ​ደ​ዳ​ች​ሁና የም​ና​ፍ​ቃ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ደስ​ታ​ች​ንና አክ​ሊ​ላ​ችን ናችሁ፤ ወዳ​ጆ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ዲህ ቁሙ፤ በጌ​ታ​ች​ንም ጽኑ።</verse>
				<verse number="2">ኤዎ​ድ​ያና ስን​ጣ​ክን ሆይ፥ በአ​ንድ ልብ ጌታ​ች​ንን ለማ​ገ​ል​ገል ታስቡ ዘንድ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="3">ወን​ድ​ሜና አጋዤ ስት​ሪካ ሆይ፥ እን​ድ​ት​ረ​ዳ​ቸው አን​ተ​ንም እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ ወን​ጌ​ልን በማ​ስ​ተ​ማር ከቀ​ሌ​ም​ን​ጦ​ስና ሥራ​ቸው ከተ​ባ​በረ፥ ስማ​ቸ​ውም በሕ​ይ​ወት መጽ​ሐፍ ከተ​ጻ​ፈ​ላ​ቸው ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ሁሉ ጋር ከእ​ኔም ጋር ደክ​መ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="4">ዘወ​ትር በጌ​ታ​ችን ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ደግሜ እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="5">ፍጹ​ም​ነ​ታ​ች​ሁም በሰው ሁሉ ዘንድ ይታ​ወቅ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅርብ ነው፤</verse>
				<verse number="6">በም​ንም አት​ጨ​ነቁ፤ ነገር ግን በሁሉ ነገር ጸልዩ ማል​ዱም፤ እያ​መ​ሰ​ገ​ና​ች​ሁም ልመ​ና​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግለጡ።</verse>
				<verse number="7">ሁሉ የሚ​ገ​ኝ​ባት፥ ከል​ቡ​ናና ከአ​ሳብ ሁሉ በላይ የም​ት​ሆን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰላም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ልባ​ች​ሁ​ንና አሳ​ባ​ች​ሁን ታጽ​ናው።</verse>
				<verse number="8">አሁ​ንም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እው​ነ​ትን ሁሉ፥ ቅን​ነ​ት​ንም ሁሉ፥ ጽድ​ቅ​ንም ሁሉ፥ ንጽ​ሕ​ና​ንም ሁሉ፥ ፍቅ​ር​ንና ስም​ም​ነ​ት​ንም ሁሉ፥ በጎ​ነ​ትም ቢሆን፥ ምስ​ጋ​ናም ቢሆን፥ እነ​ዚ​ህን ሁሉ አስቡ።</verse>
				<verse number="9">ከእኔ የተ​ማ​ራ​ች​ሁ​ት​ንና የተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁ​ትን፥ የሰ​ማ​ች​ሁ​ት​ንና ያያ​ች​ሁ​ት​ንም እነ​ዚ​ህን አድ​ርጉ፤ የሰ​ላም አም​ላ​ክም ከሁ​ላ​ችሁ ጋር ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="10">በጌ​ታ​ችን እጅግ ደስ አለኝ፤ ቢሳ​ና​ችሁ እንኳ አሁ​ንም እን​ደ​ም​ታ​ስ​ቡ​ልኝ፥ ከዱሮ ጀምሮ ለእኔ ችግር ታስቡ፥ ትተ​ጉም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="11">ይህ​ንም የምል ስለ አጣሁ አይ​ደ​ለም፤ ያለኝ እን​ደ​ሚ​በ​ቃኝ አው​ቃ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="12">እኔ ችግ​ሩ​ንም፥ ምቾ​ቱ​ንም እች​ላ​ለሁ፤ ራቡ​ንም፥ ጥጋ​ቡ​ንም፥ ማዘ​ኑ​ንም፥ ደስ​ታ​ው​ንም፥ ሁሉን በሁሉ ለም​ጀ​ዋ​ለሁ፤</verse>
				<verse number="13">በሚ​ያ​ስ​ች​ለኝ በክ​ር​ስ​ቶስ ሁሉን እች​ላ​ለሁ።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን በመ​ከ​ራዬ ጊዜ ተባ​ባ​ሪ​ዎች መሆ​ና​ችሁ መል​ካም አደ​ረ​ጋ​ችሁ።</verse>
				<verse number="15">እና​ንተ የፊ​ል​ጵ​ስ​ዩስ ሰዎች፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ትም​ህ​ርት ከመ​ቄ​ዶ​ንያ ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ፥ ከእ​ና​ንተ ብቻ በቀር ሌላ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በመ​ስ​ጠ​ትም ቢሆን፥ በመ​ቀ​በል ከእኔ ጋር እን​ዳ​ል​ተ​ባ​በሩ እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="16">በተ​ሰ​ሎ​ን​ቄም ሳለሁ ደግሞ፥ አንድ ጊዜና ሁለት ጊዜ ለች​ግሬ ላካ​ች​ሁ​ልኝ።</verse>
				<verse number="17">ይህ​ንም የማ​ነ​ሣ​ሣው ስጦ​ታ​ች​ሁን ፈልጌ አይ​ደ​ለም፤ በእ​ና​ንተ ላይ የጽ​ድቅ ፍሬ ይበዛ ዘንድ ፈልጌ ነው እንጂ።</verse>
				<verse number="18">ነገር ግን ሁሉ አለኝ፤ ይበ​ዛ​ል​ኝ​ማል፤ የመ​ዓዛ ሽታና የተ​ወ​ደደ መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን ስጦ​ታ​ች​ሁን ከአ​ፍ​ሮ​ዲጡ ተቀ​ብዬ አሟ​ል​ቻ​ለሁ።</verse>
				<verse number="19">ፈጣ​ሪዬ እንደ ባለ​ጸ​ግ​ነቱ መጠን፥ በክ​ብር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የም​ት​ሹ​ትን ሁሉ ይፈ​ጽ​ም​ላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="20">ለአ​ባ​ታ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ ምስ​ጋና ይሁን አሜን።</verse>
				<verse number="21">በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ቅዱ​ሳ​ንን ሁሉ ሰላም በሉ፤ በእኔ ዘንድ ያሉ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ሰላ​ምታ ያቀ​ር​ቡ​ላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="22">ቅዱ​ሳ​ንም ሁሉ፥ ይል​ቁ​ንም ከቄ​ሣር ቤተ ሰብእ የሆኑ ሰላ​ምታ ያቀ​ር​ቡ​ላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="23">የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጸጋ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን፤ አሜን። በሮሜ ተጽፋ በጢ​ሞ​ቴ​ዎ​ስና በአ​ፍ​ሮ​ዲጡ እጅ ወደ ፊል​ጵ​ስ​ዩስ ሰዎች የተ​ላ​ከች መል​እ​ክት ተፈ​ጸ​መች። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን አሜን።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="51">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈቃድ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሐዋ​ርያ ከጳ​ው​ሎ​ስና ከወ​ን​ድ​ማ​ችን ከጢ​ሞ​ቴ​ዎስ፥</verse>
				<verse number="2">በቈ​ላ​ስ​ይስ ላሉ ቅዱ​ሳ​ንና በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ላመኑ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ ከአ​ባ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰላ​ምና ጸጋ ለእ​ና​ንተ ይሁን።</verse>
				<verse number="3">የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዘወ​ትር ስለ እና​ንተ እና​መ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለን።</verse>
				<verse number="4">በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ማመ​ና​ች​ሁ​ንና ቅዱ​ሳ​ን​ንም ሁሉ መው​ደ​ዳ​ች​ሁን ከሰ​ማ​ን​በት ጊዜ ጀምሮ፥ ስለ እና​ንተ እን​ጸ​ል​ያ​ለን።</verse>
				<verse number="5">የእ​ው​ነት ቃል በሆ​ነው በወ​ን​ጌል ትም​ህ​ርት፥ አስ​ቀ​ድሞ ስለ ሰማ​ች​ሁት፥ በሰ​ማይ ስለ ተዘ​ጋ​ጀ​ላ​ችሁ ተስ​ፋ​ች​ሁም እን​ጸ​ል​ያ​ለን።</verse>
				<verse number="6">ይህም ወደ እና​ንተ የደ​ረ​ሰ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጸጋ በእ​ው​ነት ከሰ​ማ​ች​ሁ​በ​ትና ከአ​ያ​ች​ሁ​በት ቀን ጀምሮ በመ​ላው ዓለም ያድ​ግና ያፈራ ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="7">ስለ እና​ንተ የሚ​ላክ በክ​ር​ስ​ቶስ የታ​መነ፥ የእ​ኛም ወን​ድ​ማ​ች​ንና አገ​ል​ጋ​ያ​ችን ከሚ​ሆን ከኤ​ጳ​ፍ​ራስ ተም​ራ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="8">እር​ሱም በመ​ን​ፈስ መዋ​ደ​ዳ​ች​ሁን ነገ​ረን።</verse>
				<verse number="9">ስለ​ዚ​ህም እኛ ዜና​ች​ሁን ከሰ​ማን ጀምሮ፥ በፍ​ጹም ጥበ​ብና በፍ​ጹም መን​ፈ​ሳዊ ምክር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈቃድ ማወ​ቅን ትፈ​ጽሙ ዘንድ፥ ስለ እና​ንተ መጸ​ለ​ይ​ንና መለ​መ​ንን አል​ተ​ው​ንም።</verse>
				<verse number="10">ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ገ​ባ​ችሁ ትሄዱ ዘንድ፥ በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያ​ፈ​ራ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በማ​ወቅ እያ​ደ​ጋ​ችሁ፥ በሁሉ ደስ ታሰ​ኙት ዘንድ።</verse>
				<verse number="11">በፍ​ጹም ኀይል፥ በክ​ብሩ ጽናት፥ በፍ​ጹም ትዕ​ግ​ሥት፥ በተ​ስ​ፋና በደ​ስ​ታም ጸን​ታ​ችሁ።</verse>
				<verse number="12">በብ​ር​ሃን ቅዱ​ሳን ለሚ​ታ​ደ​ሉት ርስት የበ​ቃን ያደ​ረ​ገ​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብን አመ​ስ​ግ​ኑት።</verse>
				<verse number="13">ከጨ​ለማ አገ​ዛዝ አዳ​ነን፤ ወደ ተወ​ደ​ደው ልጁ መን​ግ​ሥ​ትም መለ​ሰን።</verse>
				<verse number="14">ድኅ​ነ​ትን ያገ​ኘ​ን​በት፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንም የተ​ሠ​ረ​የ​በት ነው።</verse>
				<verse number="15">ይኸ​ውም የማ​ይ​ታይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​መ​ስ​ለው፥ ከፍ​ጥ​ረቱ ሁሉ በላይ የሆነ በኵር ነው።</verse>
				<verse number="16">በእ​ርሱ ቃል​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁሉን ፈጥ​ሮ​አ​ልና በሰ​ማይ ያለ​ውን፥ በም​ድ​ርም ያለ​ውን፥ የሚ​ታ​የ​ው​ንና የማ​ይ​ታ​የ​ውን፥ መና​ብ​ር​ትም ቢሆኑ፥ አጋ​እ​ዝ​ትም ቢሆኑ፥ መኳ​ን​ን​ትም ቢሆኑ፥ ቀደ​ም​ትም ቢሆኑ፥ ሁሉን በእ​ርሱ ቃል​ነት ፈጥ​ሮ​አ​ቸ​ዋ​ልና፤ ሁሉም በእጁ ሆነ፤ ሁሉም በእ​ርሱ ለእ​ርሱ ተፈ​ጠረ፤</verse>
				<verse number="17">እርሱ ከሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ነበረ፤ ሁሉም በእ​ርሱ ጸና።</verse>
				<verse number="18">እርሱ የቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ራስ ነው፤ በኵር እርሱ ለሁሉ ራስ ይሆን ዘንድ ከሙ​ታን ሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ተነ​ሥ​ቶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="19">ሁሉ በእ​ርሱ ፍጹም ሆኖ ይኖር ዘንድ፥ ወዶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="20">ሁሉ​ንም በእ​ርሱ ይቅር ይለው ዘንድ በመ​ስ​ቀሉ ባፈ​ሰ​ሰው ደም በም​ድ​ርና በሰ​ማ​ያት ላሉ ሰላ​ምን አደ​ረገ።</verse>
				<verse number="21">እና​ን​ተም ቀድሞ በአ​ሳ​ባ​ች​ሁና በክፉ ሥራ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለ​ያ​ች​ሁና ጠላ​ቶች ነበ​ራ​ችሁ።</verse>
				<verse number="22">አሁን ግን በፊቱ ለመ​ቆም የተ​መ​ረ​ጣ​ች​ሁና ንጹ​ሓን፥ ቅዱ​ሳ​ንም ያደ​ር​ጋ​ችሁ ዘንድ በሥ​ጋው ሰው​ነት በሞቱ ይቅር አላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="23">እን​ግ​ዲህ ከሰ​ማ​ች​ሁት ከሰ​ማይ በታች በመ​ላው ዓለም ከተ​ሰ​በ​ከው እኔ ጳው​ሎ​ስም አዋጅ ነጋ​ሪና መል​እ​ክ​ተኛ ሆኜ ከተ​ሾ​ም​ሁ​ለት፥ ከወ​ን​ጌል ትም​ህ​ርት ተስፋ የመ​ሠ​ረ​ታ​ችሁ አቅ​ዋም ሳይ​ና​ወጥ ጨክ​ና​ችሁ በሃ​ይ​ማ​ኖት ብት​ጸኑ፥</verse>
				<verse number="24">አሁ​ንም በመ​ከ​ራዬ ደስ ይለ​ኛል፤ አካሉ ስለ ሆነች ስለ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን፥ ከክ​ር​ስ​ቶስ መከራ ጥቂ​ቱን በሥ​ጋዬ እፈ​ጽ​ማ​ለሁ።</verse>
				<verse number="25">ስለ እና​ንተ በሰ​ጠኝ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥር​ዐት እኔ መል​እ​ክ​ተኛ ሆኜ የተ​ሾ​ም​ሁ​ላት።</verse>
				<verse number="26">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን፥ ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር፥ ሰውም ሳይ​ፈ​ጠር ተሰ​ውሮ የነ​በ​ረ​ውን ምክ​ሩን እፈ​ጽም ዘንድ።</verse>
				<verse number="27">ዛሬ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዚ​ህን ምክር የክ​ብር ባለ​ጸ​ግ​ነት በአ​ሕ​ዛብ ላይ እን​ዲ​ገ​ል​ጽ​ላ​ቸው ለፈ​ቀ​ደ​ላ​ቸው ለቅ​ዱ​ሳን ተገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው፤ የም​ን​ከ​ብ​ር​በት አለ​ኝ​ታ​ችን በእ​ና​ንተ አድሮ ያለ ክር​ስ​ቶስ ነውና።</verse>
				<verse number="28">እር​ሱም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን በማ​መን ፍጹም የሚ​ሆ​ነ​ውን ሰው እና​ቀ​ር​በው ዘንድ፥ እኛ የም​ና​ስ​ተ​ም​ር​ለት፥ ሰውን ሁሉ ወደ እርሱ የም​ን​ጠ​ራ​ለ​ትና የም​ን​ገ​ሥ​ጽ​ለት፥ ሥራ​ው​ንም በጥ​በብ ሁሉ የም​ን​ና​ገ​ር​ለት ነው።</verse>
				<verse number="29">በኀ​ይሉ እን​ደ​ሚ​ረ​ዳኝ እንደ ረድ​ኤቱ መጠን ስለ እርሱ እደ​ክ​ማ​ለሁ፤ እጋ​ደ​ላ​ለ​ሁም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ስለ እና​ንተ እና በሎ​ዶ​ቅያ ስላሉ፥ ፊቴ​ንም በሥጋ ስላ​ላ​ዩት ምእ​መ​ናን ሁሉ ምን ያህል እን​ደ​ም​ጋ​ደል ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ።</verse>
				<verse number="2">ይኸ​ውም ልቡ​ና​ቸው ደስ ይለው ዘንድ፥ ትም​ህ​ር​ታ​ቸ​ውም በማ​ወቅ፥ በፍ​ቅ​ርና ፍጹ​ም​ነት ባለው ባለ​ጸ​ግ​ነት፥ በጥ​በ​ብና በሃ​ይ​ማ​ኖት፥ ስለ ክር​ስ​ቶ​ስም የሆ​ነ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምክር በማ​ወቅ ይጸና ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="3">የተ​ሰ​ወረ የጥ​በ​ብና የም​ክር መዝ​ገብ ሁሉ በእ​ርሱ ዘንድ አለ።</verse>
				<verse number="4">ይህ​ንም የም​ላ​ችሁ በሚ​ያ​ባ​ብል ነገር የሚ​ያ​ስ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ኖር ነው።</verse>
				<verse number="5">እኔ በሥጋ ከእ​ና​ንተ ዘንድ ባል​ኖ​ርም እን​ኳን፥ በመ​ን​ፈስ ከእ​ና​ንተ ጋር ነኝ፤ እነሆ ጠባ​ያ​ች​ሁ​ንና ሥር​ዐ​ታ​ች​ሁን፥ በክ​ር​ስ​ቶ​ስም ያለ የእ​ም​ነ​ታ​ች​ሁን ጽናት ስለ አየሁ ደስ ይለ​ኛል።</verse>
				<verse number="6">እን​ግ​ዲህ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን እንደ ተቀ​በ​ላ​ች​ሁት፥ በእ​ርሱ ተመ​ላ​ለሱ።</verse>
				<verse number="7">በእ​ርሱ ተመ​ሥ​ር​ታ​ችሁ ታነጹ፤ በም​ስ​ጋ​ናው ትበዙ ዘንድ፥ በተ​ማ​ራ​ች​ሁት ሃይ​ማ​ኖት ጽኑ።</verse>
				<verse number="8">ለዚህ ዓለም ስሕ​ተት፥ በክ​ር​ስ​ቶስ ሕግ ያይ​ደለ፥ በሰው ሠራሽ ሥር​ዐት ለከ​ንቱ የሚ​ያ​ታ​ልሉ ሰዎች በነ​ገር ማራ​ቀቅ እን​ዳ​ያ​ታ​ል​ሉ​አ​ችሁ፥ ተጠ​ን​ቀቁ።</verse>
				<verse number="9">በእ​ርሱ ፍጹም መለ​ኮቱ በሥጋ ተገ​ልጦ ይኖ​ራ​ልና።</verse>
				<verse number="10">እና​ን​ተም በእ​ርሱ ፍጹ​ማን ሁኑ፤ እርሱ ለአ​ለ​ቅ​ነት ሁሉና ለሥ​ል​ጣን ሁሉ ራስ ነውና።</verse>
				<verse number="11">የኀ​ጢ​አ​ትን ሰው​ነት ሸለ​ፈት በመ​ግ​ፈፍ በክ​ር​ስ​ቶስ መገ​ረዝ በሰው እጅ የአ​ል​ተ​ደ​ረገ መገ​ረ​ዝን በእ​ርሱ ሆና​ችሁ ተገ​ረ​ዛ​ችሁ።</verse>
				<verse number="12">በጥ​ም​ቀ​ትም ከእ​ርሱ ጋር ተቀ​ብ​ራ​ች​ኋል፤ በእ​ር​ስ​ዋም ከሙ​ታን ለይቶ ባስ​ነ​ሣው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳ​ት​ነ​ትና በሃ​ይ​ማ​ኖት ከእ​ርሱ ጋር ተነ​ሥ​ታ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="13">እና​ን​ተም በኀ​ጢ​አ​ታ​ች​ሁና ሥጋ​ች​ሁን ባለ​መ​ገ​ረዝ ሙታን ነበ​ራ​ች​ሁና፥ ከእ​ርሱ ጋር ሕያ​ዋን አደ​ረ​ጋ​ችሁ፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁ​ንም ሁሉ ይቅር አላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="14">ከባ​ላ​ጋ​ራ​ችን የተ​ነሣ በት​እ​ዛዝ የተ​ጻ​ፈ​ውን የዕ​ዳ​ች​ንን ደብ​ዳቤ ደመ​ሰ​ሰ​ልን፤ ከመ​ካ​ከ​ላ​ች​ንም አራ​ቀው፤ በመ​ስ​ቀ​ሉም ቸነ​ከ​ረው።</verse>
				<verse number="15">አለ​ቆ​ች​ንና ገዢ​ዎ​ችን በመ​ግ​ፈፉ በግ​ልጥ አሳ​ያ​ቸው፤ ራቁ​ቱን በመ​ሆ​ኑም አሳ​ፈ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="16">እን​ግ​ዲህ በመ​ብ​ልም ቢሆን፥ በመ​ጠ​ጥም ቢሆን፥ በልዩ ልዩ በዓ​ላ​ትም ቢሆን፥ በመ​ባ​ቻም ቢሆን፥ በሰ​ን​በ​ትም ቢሆን የሚ​ነ​ቅ​ፋ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ኖር ተጠ​ን​ቀቁ።</verse>
				<verse number="17">ይህ ሁሉ ይመጣ ዘንድ ላለው ጥላ ነውና። አካሉ ግን የክ​ር​ስ​ቶስ ነው።</verse>
				<verse number="18">በመ​ታ​ለ​ልና ራስን ዝቅ በማ​ድ​ረግ ለመ​ላ​እ​ክት አም​ልኮ ትታ​ዘዙ ዘንድ ወድዶ፥ በአ​ላ​የ​ውም በከ​ንቱ የሥ​ጋው ምክር እየ​ተ​መካ የሚ​ያ​ሰ​ን​ፋ​ችሁ አይ​ኑር።</verse>
				<verse number="19">ሥጋ ሁሉ ጸንቶ በሚ​ኖ​ር​በት፥ በሥ​ርና በጅ​ማ​ትም በሚ​ስ​ማ​ማ​በት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሚ​ያ​ድ​ግ​በ​ትና በሚ​ጸ​ና​በት፥ በሚ​ሞ​ላ​በ​ትም በራስ አይ​ጸ​ናም።</verse>
				<verse number="20">ከዚህ ዓለም ኑሮ ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋር ከሞ​ታ​ችሁ እን​ደ​ገና በዓ​ለም እን​ደ​ሚ​ኖሩ ሰዎች እን​ዴት ትሠ​ራ​ላ​ችሁ?</verse>
				<verse number="21">እን​ዴ​ትስ ይህን አት​ዳ​ስስ፥ ይህን አት​ንካ፥ ይህ​ንም አት​ቅ​መስ ይሉ​አ​ች​ኋል?</verse>
				<verse number="22">ይህ ሁሉ እንደ ሰው ትእ​ዛ​ዝና ትም​ህ​ርት ለጥ​ፋት ነውና።</verse>
				<verse number="23">ይህም ስለ ልብ ትሕ​ት​ናና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስለ መፍ​ራት፥ ለሥጋ ስለ አለ​ማ​ዘን ጥበ​ብን ይመ​ስ​ላል፤ ነገር ግን ከሥጋ በላይ ነው እንጂ ምንም ክብር የለ​ውም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋር ከተ​ነ​ሣ​ችሁ ክር​ስ​ቶስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀኝ ተቀ​ምጦ በአ​ለ​በት በላይ ያለ​ውን ሹ።</verse>
				<verse number="2">የላ​ይ​ኛ​ውን አስቡ፤ በም​ድር ያለ​ው​ንም አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="3">እና​ንተ ፈጽ​ማ​ችሁ ሞታ​ች​ኋ​ልና፤ ሕይ​ወ​ታ​ች​ሁም ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋራ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ሠ​ወ​ረች ናትና።</verse>
				<verse number="4">ሕይ​ወ​ታ​ችሁ ክር​ስ​ቶስ በሚ​ገ​ለ​ጥ​በት ጊዜ፥ ያን​ጊዜ ከእ​ርሱ ጋር በፍ​ጹም ክብር ትገ​ለ​ጣ​ላ​ችሁ።</verse>
				<verse number="5">ምድ​ራዊ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም ከዝ​ሙ​ትና ከር​ኵ​ሰት፥ ከጥ​ፋ​ትና ከክፉ ምኞት፥ ጣዖት ማም​ለክ ከሆ​ነው ከቅ​ሚ​ያም ግደ​ሉት።</verse>
				<verse number="6">በእ​ነ​ር​ሱም ምክ​ን​ያት በማ​ይ​ታ​ዘዙ ልጆች ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ጣል።</verse>
				<verse number="7">እና​ን​ተም ቀድሞ በዚህ ሥራ በነ​በ​ራ​ችሁ ጊዜ የሄ​ዳ​ች​ሁ​በት ነው።</verse>
				<verse number="8">አሁ​ንም ቍጣ​ንና ብስ​ጭ​ትን፥ ክፋ​ት​ንና ስድ​ብን፥ የሚ​ያ​ሳ​ፍ​ረ​ው​ንም ነገር ተዉ፤ ከንቱ ነገ​ርም ከአ​ፋ​ችሁ አይ​ውጣ።</verse>
				<verse number="9">አሮ​ጌ​ውን ሰው ከሥ​ራው ጋር ተዉት እንጂ፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን አቷሹ።</verse>
				<verse number="10">ፈጣ​ሪ​ውን ለመ​ም​ሰል በዕ​ው​ቀት የሚ​ታ​ደ​ሰ​ውን አዲ​ሱን ሰው ልበ​ሱት።</verse>
				<verse number="11">በእ​ርሱ ዘንድ አይ​ሁ​ዳዊ፥ ግሪ​ካ​ዊም፥ የተ​ገ​ዘረ፥ ያል​ተ​ገ​ዘ​ረም፥ አረ​መ​ኔም፥ ባላ​ገ​ርም፥ ቤተ ሰብ​እና አሳ​ዳሪ ማለት የለም ነገር ግን ክር​ስ​ቶስ ለሁሉ በሁ​ሉም ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="12">እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ መረ​ጣ​ቸው ቅዱ​ሳ​ንና ወዳ​ጆች፥ ምሕ​ረ​ት​ንና ርኅ​ራ​ኄን፥ ቸር​ነ​ት​ንና ትሕ​ት​ናን፥ የው​ሀ​ት​ንና ትዕ​ግ​ሥ​ትን ልበ​ሱት።</verse>
				<verse number="13">ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ች​ሁን ታገ​ሡ​አ​ቸው፤ እርስ በር​ሳ​ችሁ ይቅር ተባ​ባሉ፤ ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ች​ሁን የነ​ቀ​ፋ​ች​ሁ​በ​ትን ሥራ ተዉ፤ ክር​ስ​ቶስ ይቅር እን​ዳ​ላ​ችሁ እና​ን​ተም እን​ዲሁ አድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="14">ከዚ​ህም ሁሉ ጋር ዘወ​ትር ተፋ​ቀሩ፤ የመ​ጨ​ረ​ሻው ማሰ​ሪያ እርሱ ነውና።</verse>
				<verse number="15">በአ​ንድ አካል የተ​ጠ​ራ​ች​ሁ​ለት የክ​ር​ስ​ቶስ ሰላም በል​ባ​ችሁ ጸንቶ ይኑር፤ ክር​ስ​ቶ​ስ​ንም በማ​መ​ስ​ገን ኑሩ።</verse>
				<verse number="16">በጥ​በብ ሁሉ እን​ድ​ት​በ​ለ​ጽጉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በእ​ና​ንተ ዘንድ ይጽና፤ በመ​ን​ፈ​ስም ራሳ​ች​ሁን አስ​ተ​ምሩ፤ ገሥፁ፤ መዝ​ሙ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን፥ የቅ​ድ​ስና ማሕ​ሌ​ት​ንም በል​ባ​ችሁ በጸጋ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ።</verse>
				<verse number="17">በቃ​ልም ቢሆን፥ ወይም በሥራ የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን ሁሉ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም አድ​ርጉ፤ ስለ እር​ሱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብን አመ​ስ​ግ​ኑት።</verse>
				<verse number="18">ሚስ​ቶች ሆይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ደ​ም​ት​ታ​ዘዙ ለባ​ሎ​ቻ​ችሁ ታዘዙ።</verse>
				<verse number="19">ባሎች ሆይ ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ውደዱ፤ አት​ን​ቀ​ፉ​አ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="20">ልጆች ሆይ ለወ​ላ​ጆ​ቻ​ችሁ በሁሉ ታዘዙ፤ እን​ዲህ ማድ​ረግ ይገ​ባ​ልና፤ ይህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ ያሰ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="21">አባ​ቶች ሆይ እን​ዳ​ያ​ዝኑ ልጆ​ቻ​ች​ሁን አታ​በ​ሳጩ።</verse>
				<verse number="22">አገ​ል​ጋ​ዮች ሆይ በቅን ልብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ፍ​ራት እንጂ ለሰው ደስ እን​ደ​ም​ታ​ሰኙ ለታ​ይታ የም​ት​ገዙ ሳት​ሆኑ፥ በሥጋ ጌቶ​ቻ​ችሁ ለሆኑ በሁሉ ታዘዙ።</verse>
				<verse number="23">ለሰው ሳይ​ሆን ለጌታ እን​ደ​ም​ታ​ደ​ርጉ የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን ሁሉ ከልብ አድ​ር​ጉት።</verse>
				<verse number="24">ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዋጋ​ች​ሁን እን​ደ​ም​ት​ቀ​በሉ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ለክ​ር​ስ​ቶስ ትገ​ዛ​ላ​ች​ሁና፤</verse>
				<verse number="25">የሚ​በ​ድል ግን ፍዳ​ውን ያገ​ኛል፤ እር​ሱም አያ​ደ​ላ​ለ​ትም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ጌቶች ሆይ፥ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቻ​ችሁ ትክ​ክ​ለ​ኛ​ውን አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ እው​ነ​ት​ንም ፍረዱ፤ በሰ​ማይ ጌታ እን​ዳ​ላ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።</verse>
				<verse number="2">በም​ስ​ጋና እየ​ተ​ጋ​ችሁ ለጸ​ሎት ፅሙ​ዳን ሁኑ።</verse>
				<verse number="3">ስለ እርሱ የታ​ሰ​ር​ሁ​ለ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሥ​ጢር እን​ድ​ን​ና​ገር፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃ​ሉን በር ይከ​ፍ​ት​ልን ዘንድ ለእ​ኛም ደግሞ ጸል​ዩ​ልን፤ ለም​ኑ​ል​ንም፤</verse>
				<verse number="4">ልና​ገ​ርም እን​ደ​ሚ​ገ​ባኝ እገ​ል​ጠው ዘንድ ጸል​ዩ​ልኝ።</verse>
				<verse number="5">ዘመ​ኑን እየ​ዋ​ጃ​ችሁ ከሃ​ይ​ማ​ኖት ወደ ተለዩ ሰዎች በማ​ስ​ተ​ዋል ሂዱ።</verse>
				<verse number="6">ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ እን​ዴት እን​ደ​ም​ት​መ​ልሱ ታውቁ ዘንድ ንግ​ግ​ራ​ችሁ ሁል​ጊዜ በጨው እንደ ተቀ​መመ በጸጋ ይሁን።</verse>
				<verse number="7">የተ​ወ​ደደ ወን​ድ​ማ​ች​ንና የታ​መነ አገ​ል​ጋይ፥ በጌታ ሥራም ተባ​ባ​ሪ​ያ​ችን የሆነ ቲኪ​ቆስ የእ​ኔን ዜና ይነ​ግ​ራ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="8">ስለ​ዚህ ሥራ ወደ እና​ንተ የላ​ክ​ሁት ዜና​ዬን ታውቁ ዘንድ፥ ልባ​ች​ሁ​ንም ያጽ​ናና ዘንድ ነው።</verse>
				<verse number="9">ወገ​ና​ችሁ ከሆ​ነው ከም​ን​ወ​ደ​ውና ከታ​መ​ነው ወን​ድ​ማ​ችን ከአ​ና​ሲ​ሞስ ጋር፥ እነ​ርሱ ሥራ​ች​ን​ንና ያለ​ን​በ​ትን ያስ​ረ​ዱ​አ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="10">ከእኔ ጋር የተ​ማ​ረ​ከው አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮስ፥ ወደ እና​ንተ በሚ​መጣ ጊዜ ትቀ​በ​ሉት ዘንድ ስለ እርሱ ያዘ​ዝ​ኋ​ችሁ የበ​ር​ና​ባስ የአ​ባቱ ወን​ድም ልጅ ማር​ቆ​ስም፥</verse>
				<verse number="11">ኢዮ​ስ​ጦስ የተ​ባለ ኢያ​ሱም፥ ከግ​ዙ​ራን ሰዎች ወገን የሚ​ሆኑ እነ​ዚህ ሰላም ይሏ​ች​ኋል። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ሥራ ረዳ​ቶች እነ​ዚህ ብቻ ናቸው፤ እነ​ር​ሱም እኔን አጽ​ና​ን​ተ​ው​ኛል።</verse>
				<verse number="12">ከእ​ና​ንተ ወገን የሚ​ሆን ኤጳ​ፍ​ራ​ስም ሰላም ይላ​ች​ኋል፥ እርሱ የክ​ር​ስ​ቶስ አገ​ል​ጋይ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ወ​ደው ነገር ሁሉ ምሉ​ኣ​ንና ፍጹ​ማን እን​ድ​ት​ሆኑ፥ ስለ እና​ንተ ዘወ​ትር ይጸ​ል​ያል፤ ይማ​ል​ዳ​ልም።</verse>
				<verse number="13">እጅግ እን​ደ​ሚ​ወ​ዳ​ች​ሁና ስለ እና​ንተ በሎ​ዶ​ቅ​ያና በኢ​ያራ ከተማ ስላ​ሉ​ትም እን​ደ​ሚ​ቈ​ረ​ቈር እኔ ምስ​ክሩ ነኝ።</verse>
				<verse number="14">ወዳ​ጃ​ችን ባለ መድ​ኃ​ኒቱ ሉቃ​ስም ሰላም ብሎ​አ​ች​ኋል፤ ዴማ​ስም ሰላም ይላ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="15">በሎ​ዶ​ቅያ ላሉት ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንና ለን​ም​ፋን፥ በቤ​ቱም ላለች ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ሰላ​ምታ አቅ​ር​ቡ​ልኝ።</verse>
				<verse number="16">ይህ​ችን መል​እ​ክት እና​ንተ አን​ብ​ባ​ችሁ፥ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ያነ​ብ​ቡ​አት ዘንድ ወደ ሎዶ​ቅያ ላኩ​አት፤ ዳግ​መ​ኛም እና​ንተ ከሎ​ዶ​ቅያ የጻ​ፍ​ኋ​ትን መል​እ​ክት አን​ብ​ቡ​አት።</verse>
				<verse number="17">አክ​ር​ጳ​ንም “ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሾ​ም​ህ​ባ​ትን መል​እ​ክ​ት​ህን እን​ድ​ት​ፈ​ጽ​ማት ተጠ​ን​ቀቅ” በሉት።</verse>
				<verse number="18">እኔ ጳው​ሎስ በእጄ ጽፌ ሰላም አል​ኋ​ችሁ፤ እስ​ራ​ቴን አስቡ፤ ጸጋ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን፤ አሜን። በሮሜ ተጽፋ በቲ​ኪ​ቆስ እጅ ወደ ቈላ​ስ​ይስ ሰዎች የተ​ላ​ከ​ችው መል​እ​ክት ተፈ​ጸ​መች። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን። አሜን።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="52">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">ጳውሎስና ስልዋኖስ ጢሞቴዎስም፥ በእግዚአብሔር አብ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም ወደምትሆን ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስም ጸጋ ሰላምም ለእናንተ ይሁን።</verse>
				<verse number="2">በጸሎታችን ጊዜ ስለ እናንተ ስናሳስብ፥ የእምነታችሁን ሥራ የፍቅራችሁንም ድካም በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን የተስፋችሁን መጽናት በአምላካችንና በአባታችን ፊት ሳናቋርጥ እያሰብን፥ እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በሁላችሁ ምክንያት እናመሰግናለን፤</verse>
				<verse number="3"></verse>
				<verse number="4">በእግዚአብሔር የምትወደዱ ወንድሞች ሆይ! እንደ ተመረጣችሁ አውቀናልና።</verse>
				<verse number="5">ወንጌላችን በኀይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳትም እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ በእናንተ ዘንድ ስለ እናንተ እንዴት እንደ ነበርን ታውቃላችሁ።</verse>
				<verse number="6">ደግሞ እናንተ ቃሉን በብዙ መከራ ከመንፈስ ቅዱስ ደስታ ጋር ተቀብላችሁ፥ እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ፤</verse>
				<verse number="7">ስለዚህም በመቄዶንያና በአካይያ ላሉት ምእመናን ሁሉ ምሳሌ ሆናችሁላቸው።</verse>
				<verse number="8">ከእናንተ ወጥቶ የጌታ ቃል በመቄዶንያና በአካይያ ብቻ አልተሰማምና፤ ነገር ግን ምንም እንድንናገር እስከማያስፈልግ ድረስ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚሆን እምነታችሁ በሁሉ ስፍራ ተወርቶአል።</verse>
				<verse number="9">እነርሱ ራሳቸው ወደ እናንተ መግባታችን እንዴት እንደነበረ ስለ እኛ ይናገራሉና፤ ለሕያውና ለእውነተኛ አምላክም ታገለግሉ ዘንድ፥ ከሙታንም ያስነሣውን ልጁን እርሱንም ኢየሱስን ከሚመጣው ቍጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቁ ዘንድ፥ ከጣዖቶች ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንደተመለሳችሁ ይናገራሉ።</verse>
				<verse number="10"></verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ወንድሞች ሆይ! ራሳችሁ ወደ እናንተ መግባታችን ከንቱ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ።</verse>
				<verse number="2">ነገር ግን እንደምታውቁት በፊልጵስዩስ አስቀድመን መከራ ተቀብለን ተንገላትተንም፥ በብዙ ገድል የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እንናገር ዘንድ በአምላካችን ደፈርን።</verse>
				<verse number="3">ልመናችን ከስሕተት ወይም ከርኵሰት ወይም ከተንኰል አልነበረምና፤</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን ወንጌልን አደራ ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔር የታመንን ሆነን እንዳገኘን መጠን፥ እንዲሁ እንናገራለን፤ ልባችንን የሚመረምር እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን ደስ እንደምናሰኝ አይደለም።</verse>
				<verse number="5">እንደምታውቁ፥ እያቈላመጥን ከቶ አልተናገርንም፤ እግዚአብሔርም እንደሚመሰክር እያመካኘን በመጐምጀት አልሠራንም፤</verse>
				<verse number="6">የክርስቶስም ሐዋርያት እንደ መሆናችን ልንከብድባችሁ ስንችል፥ ከእናንተ ቢሆን ወይም ከሌሎች ክብርን ከሰው አልፈለግንም።</verse>
				<verse number="7">ነገር ግን ሞግዚት የራስዋን ልጆች እንደምትከባከብ፥ በመካከላችሁ የዋሆች ሆንን፤</verse>
				<verse number="8">እንዲሁም እያፈቀርናችሁ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለማካፈል ብቻ ሳይሆን የገዛ ነፍሳችንን ደግሞ እናካፍላችሁ ዘንድ በጎ ፈቃዳችን ነበረ፤ ለእኛ የተወደዳችሁ ሆናችሁ ነበርና።</verse>
				<verse number="9">ወንድሞች ሆይ! ድካማችንና ጥረታችን ትዝ ይላችኋል፤ ከእናንተ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት ሌሊትና ቀን እየሠራን፥ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ ሰበክን።</verse>
				<verse number="10">በእናንተ በምታምኑ ዘንድ እንዴት ባለ ቅድስናና ጽድቅ ነቀፋም በሌለበት ኑሮ እንደ ሄድን፥ እናንተና እግዚአብሔር ምስክሮች ናችሁ፤</verse>
				<verse number="11">ወደ መንግሥቱ ወደ ክብሩም ለጠራችሁ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እየመከርንና እያጸናን እየመሰከርንላችሁም፥ አባት ለልጆቹ እንደሚሆን ለእያንዳንዳችሁ እንደ ሆንን ታውቃላችሁና።</verse>
				<verse number="12"></verse>
				<verse number="13">ስለዚህም የመልእክትን ቃል እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ከእኛ በተቀበላችሁ ጊዜ፥ በእውነት እንዳለ በእናንተ በምታምኑ ደግሞ እንደሚሠራ እንደ እግዚአብሔር ቃል እንጂ እንደ ሰው ቃል አድርጋችሁ ስላልተቀበላችሁት፥ እኛ ደግሞ እግዚአብሔርን ሳናቋርጥ እናመሰግናለን።</verse>
				<verse number="14">እናንተ ወንድሞች ሆይ! በይሁዳ የሚኖሩትን በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉትን የእግዚአብሔርን ማኅበሮች የምትመስሉ ሆናችኋልና፤ እነርሱ ከአይሁድ መከራ እንደ ተቀበሉ፥ እናንተ ደግሞ ያንን መከራ ከአገራችሁ ሰዎች ተቀብላችኋልና።</verse>
				<verse number="15">እነዚያም ጌታን ኢየሱስን ደግሞ ገደሉ፤ ነቢያትንም እኛንም አሳደዱ፤ እግዚአብሔርንም ደስ አያሰኙም፤ ሰዎችንም ሁሉ ይቃወማሉ፤</verse>
				<verse number="16">ሁልጊዜ ኀጢአታቸውን ይፈጽሙ ዘንድ አሕዛብ እንዲድኑ እንዳንናገራቸው ይከለክሉናልና። ነገር ግን ቍጣው ወደ እነርሱ ፈጽሞ ደርሶአል።</verse>
				<verse number="17">እኛ ግን ወንድሞች ሆይ! በልብ ያይደለ ፊት ለፊት ለጥቂት ጊዜ አጥተናችሁ፥ በብዙ ናፍቆት ፊታችሁን ለማየት እጅግ ሞከርን፤</verse>
				<verse number="18">ወደ እናንተ ልንመጣ ወደን ነበርና፤ እኔ ጳውሎስም አንድና ሁለት ጊዜ፥ ሰይጣን ግን አዘገየን።</verse>
				<verse number="19">ተስፋችን ወይስ ደስታችን ወይስ የትምክህታችን አክሊል ማን ነው? በጌታችን በኢየሱስ ፊት በመምጣቱ እናንተ አይደላችሁምን?</verse>
				<verse number="20">እናንተ ክብራችን ደስታችንም ናችሁና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ስለዚህ ወደ ፊት እንታገሥ ዘንድ ባልተቻለን ጊዜ፥ በአቴና ብቻችንን ልንቀር በጎ ፈቃዳችን ሆነ።</verse>
				<verse number="2">ስለ እምነታችሁም እንዲያጸናችሁና እንዲመክራችሁ ወንድማችንን የእግዚአብሔርንም አገልጋይ ከእኛ ጋርም አብሮ በክርስቶስ ወንጌል የሚሠራውን ጢሞቴዎስን ላክነው፤</verse>
				<verse number="3">በዚህ መከራ ማንም እንዳይናወጥ፥ ለዚህ እንደ ተመረጥን ራሳችሁ ታውቃላችሁና።</verse>
				<verse number="4">በእውነት ከእናንተ ጋር ሳለን፥ መከራ እንቀበል ዘንድ እንዳለን አስቀድመን እንነግራችሁ ነበር፤ እንዲሁም ደግሞ ሆነ፤ ይህንም ታውቃላችሁ።</verse>
				<verse number="5">ስለዚህ እኔ ደግሞ ወደ ፊት እታገሥ ዘንድ ባልተቻለኝ ጊዜ “ፈታኝ ምናልባት ፈትኖአቸዋል፤ ድካማችንም ከንቱ ሆኖአል፤” ብዬ እምነታችሁን ለማወቅ ላክሁ።</verse>
				<verse number="6">አሁን ግን ጢሞቴዎስ ከእናንተ ዘንድ ወደ እኛ መጥቶ ስለ እምነታችሁና ስለ ፍቅራችሁ የምሥራች ብሎ በነገረን ጊዜ፥ እኛም እናያችሁ ዘንድ እንደምንናፍቅ ታዩን ዘንድ እየናፈቃችሁ ሁልጊዜ በመልካም እንደምታስቡን በነገረን ጊዜ፥</verse>
				<verse number="7">ስለዚህ ወንድሞች ሆይ! በእምነታችሁ በኩል በችግራችንና በመከራችን ሁሉ ስለ እናንተ ተጽናናን፤</verse>
				<verse number="8">እናንተ በጌታ ጸንታችሁ ብትቆሙ፥ አሁን በሕይወት እንኖራለንና።</verse>
				<verse number="9">ፊታችሁን ልናይ በእምነታችሁም የጎደለውን ልንሞላበት ሌሊትና ቀን ከመጠን ይልቅ እየጸለይን በአምላካችን ፊት ከእናንተ የተነሣ ስለምንደሰተው ደስታ ሁሉ ለእግዚአብሔር በእናንተ ምክንያት ምን ያህል ምስጋና እናስረክብ ዘንድ እንችላለን?</verse>
				<verse number="10"></verse>
				<verse number="11">አምላካችንና አባታችን ራሱ ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እናንተ መንገዳችንን ያቅና፤</verse>
				<verse number="12">ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ሲመጣ፥ በአምላካችንና በአባታችን ፊት በቅድስና ነቀፋ የሌለበት አድርጎ ልባችሁን ያጸና ዘንድ፥ እኛ ደግሞ ለእናንተ እንደምንሆን ጌታ እርስ በእርሳችሁ ያላችሁን ለሁሉም የሚሆን ፍቅራችሁን ያብዛ፤ ይጨምርም።</verse>
				<verse number="13"></verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">እንግዲህ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! ልትመላለሱ እግዚአብሔርንም ደስ ልታሰኙ እንዴት እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ እንደ ተቀበላችሁ፥ እናንተ ደግሞ እንደምትመላለሱ፥ ከፊት ይልቅ ትበዙ ዘንድ በጌታ በኢየሱስ እንለምናችኋለን፤ እንመክራችሁማለን።</verse>
				<verse number="2">በጌታ በኢየሱስ የትኛውን ትእዛዝ እንደ ሰጠናችሁ ታውቃላችሁና።</verse>
				<verse number="3">ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤</verse>
				<verse number="4">ከዝሙት እንድትርቁ፥ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወት ምኞት አይደለም እንጂ፤ ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን ዕቃ በቅድስናና በክብር ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ፤</verse>
				<verse number="5"></verse>
				<verse number="6">አስቀድመን ደግሞ እንዳልናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።</verse>
				<verse number="7">ለርኵሰት ሳይሆን እግዚአብሔር በቅድስና ጠርቶናልና።</verse>
				<verse number="8">እንግዲህ የማይቀበል ሰውን ያልተቀበለ አይደለም፤ መንፈስ ቅዱስን በእናንተ እንዲኖር የሰጠውን እግዚአብሔርን ነው እንጂ።</verse>
				<verse number="9">እናንተ ራሳችሁ እርስ በርሳችሁ ልትዋደዱ በእግዚአብሔር ተምራችኋልና፥ ስለ ወንድማማች መዋደድ ማንም ይጽፍላችሁ ዘንድ አያስፈልጋችሁም፤</verse>
				<verse number="10">እንዲሁ በመቄዶንያ ሁሉ ላሉት ወንድሞች ሁሉ ታደርጋላችሁና። ነገ ግን ወንድሞች ሆይ!ከፊት ይልቅ ልትበዙ፥ በጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ፥ የራሳችሁንም ጉዳይ ልትጠነቅቁ፥ እንዳዘዝናችሁም በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ ልትሠሩ እንለምናችኋለን።</verse>
				<verse number="11"></verse>
				<verse number="12"></verse>
				<verse number="13">ነገር ግን ወንድሞች ሆይ!ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ደግሞ እንዳታዝኑ፥ አንቀላፍተው ስላሉቱ ታውቁ ዘንድ እንወዳለን።</verse>
				<verse number="14">ኢየሱስ እንደ ሞተና እንደ ተነሣ ካመንን፥ እንዲሁም በኢየሱስ ያንቀላፉቱን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋልና።</verse>
				<verse number="15">በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና፤ እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉቱን አንቀድምም፤</verse>
				<verse number="16">ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፤ ክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤</verse>
				<verse number="17">ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው ታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።</verse>
				<verse number="18">ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">ወንድሞች ሆይ! ለ ዘመናትና ስለ ወራት ምንም እንዲጻፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፤</verse>
				<verse number="2">የጌታ ቀን ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ እንዲሁ ይመጣ ዘንድ ራሳችሁ አጥብቃችሁ አውቃችኋልና።</verse>
				<verse number="3">ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ከቶም አያመልጡም።</verse>
				<verse number="4">እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ! ቀኑ እንደ ሌባ ይደርስባችሁ ዘንድ በጨለማ አይደላችሁም፤</verse>
				<verse number="5">ሁላችሁ የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና፤ እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም።</verse>
				<verse number="6">እንግዲያስ እንንቃ በመጠንም እንኑር እንጂ እንደ ሌሎች አናንቀላፋ።</verse>
				<verse number="7">የሚያንቀላፉ በሌሊት ያንቀላፋሉና፤ የሚሰክሩም በሌሊት ይሰክራሉና፤</verse>
				<verse number="8">እኛ ግን ከቀን ስለ ሆንን፥ የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር የመዳንንም ተስፋ እንደ ራስ ቁር እየለበስን በመጠን እንኑር፤</verse>
				<verse number="9">እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንምና፤ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነው እንጂ።</verse>
				<verse number="10">የምንነቃም ብንሆን፥ የምናንቀላፋም ብንሆን፥ ከእርሱ ጋር አብረን በሕይወት እንኖር ዘንድ ስለ እኛ ሞተ።</verse>
				<verse number="11">ስለዚህ እናንተ ደግሞ እንደምታደርጉ፥ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፤ አንዱም አንዱም ሌላውን ያንጸው።</verse>
				<verse number="12">ወንድሞች ሆይ! በመካከላችሁ የሚደክሙትን በጌታም የሚገዙአችሁን የሚገሥጹአችሁንም ታውቁ ዘንድ፥ ስለ ሥራቸውም በፍቅር ከመጠን ይልቅ ታከብሩአቸው ዘንድ እንለምናችኋለን። እርስ በርሳችሁ በሰላም ሁኑ።</verse>
				<verse number="13"></verse>
				<verse number="14">ወንድሞች ሆይ! እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዐት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።</verse>
				<verse number="15">ማንም ለሌላው በክፉ ፈንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ እርስ በርሳችሁ ለሁሉም መልካሙን ለማድረግ ትጉ።</verse>
				<verse number="16">ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤</verse>
				<verse number="17">ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።</verse>
				<verse number="18"></verse>
				<verse number="19">መንፈስን አታጥፉ፤</verse>
				<verse number="20">ትንቢትን አትናቁ፤ ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ፤</verse>
				<verse number="21"></verse>
				<verse number="22">ከማናቸውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ።</verse>
				<verse number="23">የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።</verse>
				<verse number="24">የሚጠራችሁ የታመነ ነው፤ እርሱም ደግሞ ያደርገዋል።</verse>
				<verse number="25">ወንድሞች ሆይ! ስለ እኛ ጸልዩ።</verse>
				<verse number="26">ከወንድሞች ሁሉ ጋር በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተሰጣጡ።</verse>
				<verse number="27">ይህ መልእክት ለቅዱሳን ወንድሞች ሁሉ እንዲነበብ በጌታ አምላችኋለሁ።</verse>
				<verse number="28">የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="53">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">ጳውሎስና ስልዋኖስ ጢሞቴዎስም፥ በእግዚአብሔር በአባታችን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም ወደምትሆን ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን፤</verse>
				<verse number="2">ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስም ጸጋ ሰላምም ለእናንተ ይሁን።</verse>
				<verse number="3">ወንድሞች ሆይ! እምነታችሁ እጅግ ስለሚያድግ፥ የሁላችሁም የእያንዳንዳችሁ ፍቅር እርስ በርሳችሁ ስለሚበዛ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግድ አለብን፤</verse>
				<verse number="4">ስለዚህ በምትታገሱበት በስደታችሁና በመከራችሁ ሁሉ ከመጽናታችሁና ከእምነታችሁ የተነሣ በእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ስለ እናንተ ራሳችን እንመካለን።</verse>
				<verse number="5">ስለ እርሱ ደግሞ መከራ ለምትቀበሉለት ለእግዚአብሔር መንግሥት የምትበቁ ሆናችሁ ትቈጠሩ ዘንድ ይህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ ምልክት ነው።</verse>
				<verse number="6">ጌታ ኢየሱስ ከኀያላን መላእክቱ ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ፥ መከራን ለሚያሳዩአችሁ መከራን፥ መከራንም ለምትቀበሉ ከእኛ ጋር ዕረፍትን ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና።</verse>
				<verse number="7"></verse>
				<verse number="8">እግዚአብሔርን የማያውቁትን፥ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል፤</verse>
				<verse number="9">በዚያም ቀን በቅዱሳኑ ሊከብር ምስክርነታችንንም አምናችኋልና በሚያምኑት ሁሉ ዘንድ ሊደነቅ ሲመጣ፥ ከጌታ ፊት ከኀይሉም ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ።</verse>
				<verse number="10"></verse>
				<verse number="11">ስለዚህም ደግሞ እንደ አምላካችን እንደ ጌታም እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእናንተ ዘንድ ሊከብር እናንተም በእርሱ ዘንድ ልትከብሩ፥ አምላካችን ለመጥራቱ የምትበቁ አድርጎ ይቈጥራችሁ ዘንድ፥ የበጎነትንም ፈቃድ ሁሉ የእምነትንም ሥራ በኀይል ይፈጽም ዘንድ ስለ እናንተ ሁልጊዜ እንጸልያለን።</verse>
				<verse number="12"></verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ነገር ግን ወንድሞች ሆይ! ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣትና ወደ እርሱ ስለ መሰብሰባችን፥ በመንፈስ ወይም በቃል ወይም ከእኛ እንደሚመጣ በመልእክት “የጌታ ቀን ደርሶአል፤” ብላችሁ ከአእምሮአችሁ ቶሎ እንዳትናወጡ እንዳትደነግጡም እንለምናችኋለን።</verse>
				<verse number="2"></verse>
				<verse number="3">ማንም በማናቸውም መንገድ አያስታችሁ፤ ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዐመፅ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ አይደርስምና።</verse>
				<verse number="4">“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤” ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው።</verse>
				<verse number="5">ገና ከእናንተ ጋር ሳለሁ ይህን እንዳልኋችሁ ትዝ አይላችሁምን?</verse>
				<verse number="6">በገዛ ራሱ ጊዜም ይገለጥ ዘንድ የሚከለክለውን አሁን ታውቃላችሁ።</verse>
				<verse number="7">የዐመፅ ምሥጢር አሁን ይሠራልና፤ ብቻ ከመንገድ እስኪወገድ ድረስ አሁን የሚከለክል አለ።</verse>
				<verse number="8">በዚያም ጊዜ ጌታ ኢየሱስ በአፉ መንፈስ የሚያጠፋው፥ ሲመጣም በመገለጡ የሚሽረው ዐመፀኛ ይገለጣል፤</verse>
				<verse number="9">ይድኑ ዘንድ የእውነት ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉ፥ የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኞች ድንቆችም በዐመፅም መታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነው።</verse>
				<verse number="10"></verse>
				<verse number="11">ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዐመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል።</verse>
				<verse number="12"></verse>
				<verse number="13">እኛ ግን በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ልናመሰግን ግድ አለብን፤ እግዚአብሔር በመንፈስ መቀደስ እውነትንም በማመን ለመዳን እንደ በኵራት መርጦአችኋልና፤</verse>
				<verse number="14">ለዚህም የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር ለማግኘት በወንጌላችን ጠራችሁ።</verse>
				<verse number="15">እንግዲያስ ወንድሞች ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ።</verse>
				<verse number="16">ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና የወደደን በጸጋም የዘላለምን መጽናናት በጎንም ተስፋ የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን ልባችሁን ያጽናኑት፤ በበጎም ሥራና በቃል ሁሉ ያጽኑአችሁ።</verse>
				<verse number="17"></verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! የጌታ ቃል እንዲሮጥ፥ በእናንተም ዘንድ ደግሞ እንደሚሆን እንዲከበር፥ እምነትም ለሁሉ ስለማይሆን ከዐመፀኞችና ከክፉዎች ሰዎች እንድንድን ስለ እኛ ጸልዩ።</verse>
				<verse number="2"></verse>
				<verse number="3">ነገር ግን የሚያጸናችሁ ከክፉውም የሚጠብቃችሁ ጌታ የታመነ ነው።</verse>
				<verse number="4">የምናዛችሁንም አሁን እንድታደርጉ ወደ ፊትም ደግሞ እንድታደርጉ ስለ እናንተ በጌታ ታምነናል።</verse>
				<verse number="5">ጌታም ወደ እግዚአብሔር ፍቅር ወደ ክርስቶስም ትዕግሥት ልባችንን ያቅናው።</verse>
				<verse number="6">ወንድሞች ሆይ! ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዐት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።</verse>
				<verse number="7">እኛን ልትመስሉ እንዴት እንደሚገባችሁ ራሳችሁ ታውቃላችሁና፤ በእናንተ ዘንድ ያለ ሥርዐት አልሄድንምና፤</verse>
				<verse number="8">ከእናንተ ዘንድ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት ሌሊትና ቀን በድካምና በጥረት እየሠራን እንኖር ነበር እንጂ፥ ከማንም እንጀራን እንዲያው አልበላንም።</verse>
				<verse number="9">ይህም እኛን ልትመስሉ ራሳችንን እንደ ምሳሌ እንሰጣችሁ ዘንድ ነበር እንጂ፥ ያለ ሥልጣን ስለ ሆንን አይደለም።</verse>
				<verse number="10">ደግሞ ከእናንተ ጋር ሳለን “ሊሠራ የማይወድ አይብላ፤” ብለን አዘናችሁ ነበርና።</verse>
				<verse number="11">ሥራ ከቶ ሳይሠሩ በሰው ነገር እየገቡ ያለ ሥርዐት ከእናንተ ዘንድ ስለሚሄዱ ስለ አንዳንዶች ሰምተናልና።</verse>
				<verse number="12">እንደነዚህ ያሉትንም በጸጥታ እየሠሩ የገዛ እንጀራቸውን ይበሉ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናዛቸዋለን፤ እንመክራቸውማለን።</verse>
				<verse number="13">እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ! መልካም ሥራን ለመሥራት አትታክቱ።</verse>
				<verse number="14">በዚህ መልእክት ለተላከ ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፥ ይህን ተመልከቱት፤ ያፍርም ዘንድ ከእርሱ ጋር አትተባበሩ።</verse>
				<verse number="15">ነገር ግን እንደ ወንድም ገሥጹት እንጂ እንደ ጠላት አትቍጠሩት።</verse>
				<verse number="16">የሰላምም ጌታ ራሱ በሁሉ መንገድ ዘወትር ሰላምን ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።</verse>
				<verse number="17">በገዛ እጄ የተጻፈ የእኔ የጳውሎስ ሰላምታ ይህ ነው፤ የመልእክቴ ሁሉ ማስረጃ ይህ ነው፤ እንዲህ እጽፋለሁ።</verse>
				<verse number="18">የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="54">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">መድኃኒታችን እግዚአብሔር ተስፋችንም ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳዘዘው ትእዛዝ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥</verse>
				<verse number="2">በእምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነ ለጢሞቴዎስ፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከክርስቶስ ኢየሱስም ከጌታችን ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን።</verse>
				<verse number="3">ወደ መቄዶንያ በሄድሁ ጊዜ፥ አንዳንዶች ልዩ ትምህርትን እንዳያስተምሩና ወደ ተረት መጨረሻም ወደሌለው ወደ ትውልዶች ታሪክ እንዳያደምጡ ልታዛቸው በኤፌሶን ትቀመጥ ዘንድ ለመንሁህ፤ እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮች ክርክርን ያመጣሉና፤ በእምነት ግን ላለ ለእግዚአብሔር መጋቢነት አይጠቅሙም።</verse>
				<verse number="4"></verse>
				<verse number="5">የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው፤</verse>
				<verse number="6">ከእነዚህም አንዳንዶች ስተው የሚሉትን ወይም ስለ እነርሱ አስረግጠው የሚናገሩትን ሳያስተውሉ፥ የሕግ አስተማሪዎች ሊሆኑ እየወደዱ ወደ ከንቱ ንግግር ፈቀቅ ብለዋል።</verse>
				<verse number="7"></verse>
				<verse number="8">ነገር ግን ሰው እንደሚገባ ቢሠራበት ሕግ መልካም እንደ ሆነ እናውቃለን፤</verse>
				<verse number="9">ይኸውም ለበደለኞችና ለማይታዘዙ፥ ለዐመጸኞችና ለኀጢአተኞች፥ ቅድስና ለሌላቸውና ለርኵሳን፥ አባትና እናትን ለሚገድሉ፥ ለነፍሰ ገዳዮችና ለሴሰኞች፥ ከወንድ ጋርም ለሚተኙ፥ በሰዎችም ለሚነግዱ፥ ለውሸተኞችም በውሸትም ለሚምሉ፥ የብሩክ እግዚአብሔርንም ክብር እንደሚገልጥ ለእኔ አደራ እንደ ተሰጠኝ፥ ወንጌል የሆነውን ደኅና ትምህርት ለሚቃወም ለሌላ ነገር ሁሉ ሕግ እንደ ተሠራ እንጂ ለጻድቅ እንዳልተሠራ በማወቅ ነው።</verse>
				<verse number="10"></verse>
				<verse number="11"></verse>
				<verse number="12">ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ኀይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ፤</verse>
				<verse number="13">አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረትን አገኘሁ፤</verse>
				<verse number="14">የጌታችንም ጸጋ በክርስቶስ ኢየሱስ ካሉ ከእምነትና ከፍቅር ጋር አብልጦ በዛ።</verse>
				<verse number="15">“ኀጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ፤” የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኀጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤</verse>
				<verse number="16">ስለዚህ ግን የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት በእርሱ ያምኑ ዘንድ ላላቸው ሰዎች ምሳሌ እንድሆን፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና በምሆን በእኔ ላይ ትዕግስቱን ሁሉ ያሳይ ዘንድ ምህረትን አገኘሁ።</verse>
				<verse number="17">ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።</verse>
				<verse number="18">ልጄ ጢሞቴዎስ ሆይ! አስቀድሞ ስለ አንተ እንደ ተነገረው ትንቢት፥ በእርሱ መልካም ጦርነት ትዋጋ ዘንድ ይህችን ትእዛዝ አደራ እሰጥሃለሁ፤</verse>
				<verse number="19">እምነትና በጎ ሕሊና ይኑርህ፤ አንዳንዶች ሕሊናን ጥለው መርከብ አለ መሪ እንደሚጠፋ በእምነት ነገር ጠፍተዋልና፤</verse>
				<verse number="20">ከእነዚያም እንዳይሳደቡ ይማሩ ዘንድ ለሰይጣን አሳልፌ የሰጠኋቸው ሄሜኔዎስና እስክንድሮስ ናቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ።</verse>
				<verse number="2"></verse>
				<verse number="3">ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው።</verse>
				<verse number="4"></verse>
				<verse number="5">አንድ እግዚአብሔር አለና፤ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፤ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤</verse>
				<verse number="6">ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፤ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤</verse>
				<verse number="7">እኔም ለዚህ ነገር አዋጅ ነጋሪና ሐዋርያ በእምነትና በእውነትም የአሕዛብ አስተማሪ ለመሆን ተሾምሁ፤ እውነት እናገራለሁ፤ አልዋሽም።</verse>
				<verse number="8">እንግዲህ ወንዶች በስፍራ ሁሉ አለ ቍጣና አለ ክፉ አሳብ የተቀደሱትን እጆች እያነሡ እንዲጸልዩ እፈቅዳለሁ።</verse>
				<verse number="9">እንዲሁም ደግሞ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ፤ እግዚአብሔርን እንፈራለን ለሚሉት ሴቶች እንደሚገባ መልካም በማድረግ እንጂ በሽሩባና በወርቅ ወይም በዕንቍ ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሸለሙ።</verse>
				<verse number="10"></verse>
				<verse number="11">ሴት በነገር ሁሉ እየተገዛች በዝግታ ትማር፤</verse>
				<verse number="12">ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም።</verse>
				<verse number="13">አዳም ቀድሞ ተፈጥሮአልና፤ በኋላም ሔዋን ተፈጠረች።</verse>
				<verse number="14">የተታለለም አዳም አይደለም፤ ሴቲቱ ግን ተታልላ በመተላለፍ ወደቀች፤</verse>
				<verse number="15">ነገር ግን በእምነትና በፍቅር በቅድስናም ራሳቸውን እየገዙ ቢኖሩ በመውለድ ትድናለች።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">“ማንም ኤጲስ ቆጶስነትን ቢፈልግ መልካምን ሥራ ይመኛል፤” የሚለው ቃል የታመነ ነው።</verse>
				<verse number="2">እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ የማይነቀፍ፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሠራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥</verse>
				<verse number="3">የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ ነገር ግን ገር የሆነ፥ የማይከራከር፥ ገንዘብን የማይወድ፥</verse>
				<verse number="4">ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ እየገዛ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር፤</verse>
				<verse number="5">ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል?</verse>
				<verse number="6">በትዕቢት ተነፍቶ በዲያቢሎስ ፍርድ እንዳይወድቅ፥ አዲስ ክርስቲያን አይሁን።</verse>
				<verse number="7">በዲያቢሎስ ነቀፋና ወጥመድም እንዳይወድቅ፥ በውጭ ካሉት ሰዎች ደግሞ መልካም ምስክር ሊኖረው ይገባዋል።</verse>
				<verse number="8">እንዲሁም ዲያቆናት ጭምቶች፥ በሁለት ቃል የማይናገሩ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጎመጁ፥ ለነውረኛ ረብ የማይስገበገቡ፥</verse>
				<verse number="9">በንጹሕ ሕሊና የሃይማኖትን ምሥጢር የሚይዙ ሊሆኑ ይገባቸዋል።</verse>
				<verse number="10">እነዚህም ደግሞ አስቀድሞ ይፈተኑ፤ ከዚያም በኋላ ያለ ነቀፋ ቢሆኑ በዲቁና ሥራ ያገልግሉ።</verse>
				<verse number="11">እንዲሁም ሴቶች ጭምቶች፥ የማያሙ፥ ልከኞች፥ በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል።</verse>
				<verse number="12">ዲያቆናት ልጆቻቸውንና የራሳቸውን ቤቶች በመልካም እየገዙ እያንዳንዳቸው የአንዲት ሴት ባሎች ይሁኑ።</verse>
				<verse number="13">በዲቁና ሥራ በመልካም ያገለገሉ ለራሳቸው ትልቅ ማዕርግና በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው እምነት ብዙ ድፍረት ያገኛሉ።</verse>
				<verse number="14">ፈጥኜ ወደ አንተ እንድመጣ ተስፋ አድርጌ ይህን እጽፍልሃለሁ።</verse>
				<verse number="15">ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።</verse>
				<verse number="16">እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">መንፈስ ግን በግልጥ “በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ፤” ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው፥</verse>
				<verse number="2"></verse>
				<verse number="3">እነዚህ ውሸተኞች መጋባትን ይከለክላሉ፤ አምነውም እውነትን የሚያውቁ ከምስጋና ጋር ይቀበሉ ዘንድ እግዚአብሔር ከፈጠረው መብል እንዲርቁ ያዝዛሉ።</verse>
				<verse number="4">እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም ነውና፥ ከምስጋናም ጋር ቢቀበሉት የሚጣል ምንም የለም፤</verse>
				<verse number="5">በእግዚአብሔር ቃልና በጸሎት የተቀደሰ ነውና።</verse>
				<verse number="6">ስለዚህ ወንድሞችን ብታሳስብ፥ በእምነትና በተከተልኸው በመልካም ትምህርት ቃል የምትመገብ የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ።</verse>
				<verse number="7">ነገር ግን ለዚህ ዓለም ከሚመችና የአሮጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ። እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ።</verse>
				<verse number="8">ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።</verse>
				<verse number="9">ይህ ቃል የታመነ ሁሉም እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤</verse>
				<verse number="10">ይህን ለማግኘት እንደክማለንና፤ ስለዚህም እንሰደባለን፤ ይህም ሰውን ሁሉ ይልቁንም የሚያምኑትን በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ ስለምናደርግ ነው።</verse>
				<verse number="11">ይህን እዘዝና አስተምር። በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፥ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው።</verse>
				<verse number="12"></verse>
				<verse number="13">እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር ለማስተማርም ተጠንቀቅ።</verse>
				<verse number="14">በትንቢት ከሽማግሌዎች እጅ መጫን ጋር የተሰጠህን በአንተ ያለውን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል።</verse>
				<verse number="15">ማደግህ በነገር ሁሉ እንዲገለጥ ይህን አስብ፤ ይህንም አዘውትር።</verse>
				<verse number="16">ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፤ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">ሽማግሌ የሆነውን አትገሥጸው፤ እርሱን ግን እንደ አባት፥ ጎበዞችን እንደ ወንድሞች፥ የሸመገሉትን ሴቶች እንደ እናቶች፥ ቆነጃጅቱን እንደ እኅቶች በፍጹም ንጽሕና ለምናቸው።</verse>
				<verse number="2"></verse>
				<verse number="3">በእውነት ባልቴቶች የሆኑትን ባልቴቶች አክብር።</verse>
				<verse number="4">ማንም ባልቴት ግን ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ቢኖሩአት፥ እነርሱ አስቀድመው ለገዛ ቤተ ሰዎቻቸው እግዚአብሔርን መምሰል ያሳዩ ዘንድ፥ ለወላጆቻቸውም ብድራትን ይመልሱላቸው ዘንድ ይማሩ፤ ይህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና የተወደደ ነውና።</verse>
				<verse number="5">ብቻዋንም ኖራ በእውነት ባልቴት የምትሆን በእግዚአብሔር ተስፋ ታደርጋለች፤ ሌትና ቀንም በልመና በጸሎትም ጸንታ ትኖራለች፤</verse>
				<verse number="6">ቅምጥሊቱ ግን በሕይወትዋ ሳለች የሞተች ናት።</verse>
				<verse number="7">ያለ ነቀፋ እንዲሆኑ ይህን ደግሞ እዘዝ።</verse>
				<verse number="8">ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።</verse>
				<verse number="9">ባልቴት በመዝገብ ብትጻፍ ዕድሜዋ ከስድሳ ዓመት እንዳያንስ፤ የአንድም ባል ሚስት የነበረች እንድትሆን ያስፈልጋል፤</verse>
				<verse number="10">ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በጎንም ሥራ ሁሉ በመከተል፥ ይህን መልካም ሥራ በማድረግ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።</verse>
				<verse number="11">ባል የሞተባቸውን ቆነጃጅት ግን አትቀበል፤ በክርስቶስ ላይ ተነሥተው ሲቀማጠሉ ሊያገቡ ይወዳሉና፤</verse>
				<verse number="12">የፊተኛውንም እምነታቸውን ስለ ናቁ ይፈረድባቸዋል፤</verse>
				<verse number="13">ከዚህም ጋር ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራን መፍታት ደግሞ ይማራሉ፤ የማይገባውንም እየተናገሩ ለፍላፊዎችና በነገር ገቢዎች ይሆናሉ እንጂ፥ ሥራ ፈቶች ብቻ አይደሉም።</verse>
				<verse number="14">እንግዲህ ቆነጃጅት ሊያገቡ፥ ልጆችንም ሊወልዱ፥ ቤቶቻቸውንም ሊያስተዳድሩ፥ ተቃዋሚውም የሚሳደብበትን አንድን ምክንያት ስንኳ እንዳይሰጡ እፈቅዳለሁ፤</verse>
				<verse number="15">ከአሁን በፊት አንዳንዶች ሰይጣንን እንዲከተሉ ፈቀቅ ብለዋልና።</verse>
				<verse number="16">ባልቴቶች ያሉት የሚያምን ቢሆን ወይም የምታምን ብትሆን፥ ይርዱአቸው፤ ቤተ ክርስቲያንም እውነተኞችን ባልቴቶች እንድትረዳ አይክበዱባት።</verse>
				<verse number="17">በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።</verse>
				<verse number="18">መጽሐፍ “የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር፤” ደግሞ “ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል፤” ይላልና።</verse>
				<verse number="19">ከሁለት ወይም ከሦስት ምስክር በቀር በሽማግሌ ላይ ክስ አትቀበል።</verse>
				<verse number="20">ሌሎቹ ደግሞ እንዲፈሩ፥ ኀጢአት የሚሠሩትን በሁሉ ፊት ገሥጻቸው።</verse>
				<verse number="21">አንድን እንኳ በአድልዎ ሳታደርግ፥ እነዚህን ያለ ማዘንበል እንድትጠብቅ በእግዚአብሔርና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በተመረጡትም መላእክት ፊት እመክርሃለሁ።</verse>
				<verse number="22">በማንም ላይ ፈጥነህ እጆችህን አትጫን፤ በሌሎችም ኀጢአት አትተባበር፤ ራስህን በንጽህና ጠብቅ።</verse>
				<verse number="23">ስለ ሆድህና ስለ በሽታህ ብዛት ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ እንጂ፥ ወደ ፊት ውሃ ብቻ አትጠጣ።</verse>
				<verse number="24">የአንዳንዶች ሰዎች ኀጢአት የተገለጠ ነው፤ ፍርድንም ያመለክታል፤ ሌሎችን ግን ይከተላቸዋል፤</verse>
				<verse number="25">እንዲሁ መልካም ሥራ ደግሞ የተገለጠ ነው፤ ያልተገለጠም ከሆነ ሊሰወር አይችልም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">የእግዚአብሔር ስምና ትምህርቱ አንዳይሰደብ፥ ከቀንበር በታች ያሉቱ ባሪያዎች ሁሉ ለገዙአቸው ጌቶች ክብር ሁሉ እንደ ተገባቸው ይቍጠሩአቸው።</verse>
				<verse number="2">የሚያምኑም ጌቶች ያሉአቸው፥ ወንድሞች ስለ ሆኑ አይናቁአቸው፤ ነገር ግን በመልካም ሥራቸው የሚጠቅሙ የሚያምኑና የተወደዱ ስለ ሆኑ፥ ከፊት ይልቅ ያገልግሉ።</verse>
				<verse number="3">እነዚህን አስተምርና ምከር። ማንም ልዩ ትምህርት የሚያስተምር ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ጤናማ ቃልና እግዚአብሔርን ለመምሰል በሚስማማ ትምህርት የማይጠጋ ቢሆን፥</verse>
				<verse number="4">በትዕቢት ተነፍቶአል፤ አንዳችም አያውቅም፤ ነገር ግን ምርመራን በቃልም መዋጋትን እንደ በሽተኛ ይናፍቃል፤ ከእነዚህም ቅንዓትና ክርክር ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፤ አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ፥ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ። እንደነዚህ ካሉት ራቅ።</verse>
				<verse number="5"></verse>
				<verse number="6">“ኑሮዬ ይበቃኛል፤” ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤</verse>
				<verse number="7">ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፤</verse>
				<verse number="8">አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን እርሱ ይበቃናል።</verse>
				<verse number="9">ዳሩ ግን ባለ ጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ።</verse>
				<verse number="10">ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፤ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።</verse>
				<verse number="11">አንተ ግን የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል።</verse>
				<verse number="12">መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፤ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ።</verse>
				<verse number="13">ሁሉን በሕይወት በሚጠብቅ በእግዚአብሔር ፊት፥ በጴንጤናዊውም በጲላጦስ ዘንድ መልካሙን መታመን በመሰከረ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት አዝሃለሁ፤</verse>
				<verse number="14">ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ ያለ እድፍና ያለ ነቀፋ ሆነህ ትእዛዙን ጠብቅ፤</verse>
				<verse number="15">ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና ብቻውን የሆነ ገዥ፥ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ ያሳያል።</verse>
				<verse number="16">እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም፤ ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኀይል ይሁን፤ አሜን።</verse>
				<verse number="17">በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።</verse>
				<verse number="18">እውነተኛውን ሕይወት ይይዙ ዘንድ፥ ለሚመጣው ዘመን ለራሳቸው መልካም መሠረት የሚሆንላቸውን መዝገብ እየሰበሰቡ መልካምን እንዲያደርጉ፤ በበጎም ሥራ ባለ ጠጎች እንዲሆኑ፤ ሊረዱና ሊያካፍሉም የተዘጋጁ እንዲሆኑ ምከራቸው።</verse>
				<verse number="19"></verse>
				<verse number="20">ጢሞቴዎስ ሆይ! በውሸት እውቀት ከተባለ ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍና መከራከር እየራቅህ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ፤</verse>
				<verse number="21">ይህ እውቀት አለን ብለው አንዳንዶች ስለ እምነት ስተዋልና። ጸጋ ከአንተ ጋር ይሁን።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="55">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በክርስቶስ ኢየሱስ እንደሚሆን የሕይወት ተስፋ፥ በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፤</verse>
				<verse number="2">ለተወደደው ልጄ ለጢሞቴዎስ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከጌታችንም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን።</verse>
				<verse number="3">ሌትና ቀን በልመናዬ ሳላቋርጥ ስለማስብህ እንደ አባቶቼ አድርጌ በንጹሕ ሕሊና የማመልከውን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤</verse>
				<verse number="4">እንባህን እያሰብሁ በደስታ እሞላ ዘንድ ላይህ እናፍቃለሁ።</verse>
				<verse number="5">በአንተ ያለውን ግብዝነት የሌለበትን እምነትህን አስባለሁ፤ ይህም እምነት ቀድሞ በአያትህ በሎይድ በእናትህም በኤውንቄ ነበረባቸው፤ በአንተም ደግሞ እንዳለ ተረድቼአለሁ።</verse>
				<verse number="6">ስለዚህ ምክንያት እሳት እንደሚያቀጣጥል ሰው እጆቼን በመጫኔ በአንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንድታነሣሣ አሳስብሃለሁ።</verse>
				<verse number="7">እግዚአብሔር የኀይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና።</verse>
				<verse number="8">እንግዲህ በጌታችን ምስክርነት ወይም በእስረኛው በእኔ አትፈር፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ኀይል መጠን ስለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል፤</verse>
				<verse number="9">ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፤ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ፥ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፤</verse>
				<verse number="10">አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቶአል። እርሱ ሞትን ሽሮአልና፤ እኔ ሰባኪና ሐዋርያ አሕዛብንም አስተማሪ እንድሆን በተሾምሁበት በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል።</verse>
				<verse number="11"></verse>
				<verse number="12">ስለዚህም ምክንያት ይህን መከራ ደግሞ ተቀብዬአለሁ፤ ነገር ግን አላፍርበትም፤ ያመንሁትን አውቃለሁና፤ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ሊጠብቅ እንዲችል ተረድቼአለሁ።</verse>
				<verse number="13">በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነትና ፍቅር አድርገህ፥ ከእኔ የሰማኸውንም ጤናማ ቃል ምሳሌ ያዝ፤</verse>
				<verse number="14">መልካሙን አደራ በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ጠብቅ።</verse>
				<verse number="15">በእስያ ያሉቱ ሁሉ ከእኔ ፈቀቅ እንዳሉ ታውቃለህ፤ ከእነርሱም ፊሎጎስና ሄርዋጌኔስ ናቸው።</verse>
				<verse number="16">ጌታ ልሄኔሲፎሩ ቤተ ሰዎች ምሕረትን ይስጥ፤ ብዙ ጊዜ አሳርፎኛልና፤</verse>
				<verse number="17">በሰንሰለቴም አላፈረበትም፤ ነገር ግን በሮሜ ባደረ ጊዜ ፈልጎ ፈልጎ አገኘኝ፤</verse>
				<verse number="18">በዚያን ቀን ከጌታ ምሕረትን እንዲያገኝ ጌታ ይስጠው፤ በኤፌሶንም እንዴት እንዳገለገለኝ አንተ በደኅና ታውቃለህ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">እንግዲህ ልጄ ሆይ! አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ።</verse>
				<verse number="2">ብዙ ሰዎች የመሰከሩለትን ከእኔም የሰማኸውን ሌሎችን ደግሞ ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ።</verse>
				<verse number="3">እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል።</verse>
				<verse number="4">የሚዘምተው ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያጠላልፍም።</verse>
				<verse number="5">ደግሞም በጨዋታ የሚታገል ማንም ቢሆን፥ እንደሚገባ አድርጎ ባይታገል፥ የድሉን አክሊል አያገኝም።</verse>
				<verse number="6">የሚደክመው ገበሬ ፍሬውን ከሚበሉት መጀመሪያ እንዲሆን ይገባዋል።</verse>
				<verse number="7">የምለውን ተመልከት፤ ጌታም በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥህ።</verse>
				<verse number="8">በወንጌል እንደምሰብከው፥ ከሙታን የተነሣውን፥ ከዳዊት ዘርም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ።</verse>
				<verse number="9">ይህንም በመስበክ እንደ ክፉ አድራጊ እስክታሰር ድረስ መከራ እቀበላለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም።</verse>
				<verse number="10">ስለዚህ እነርሱ ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለውን መዳን ከዘላለም ክብር ጋር እንዲያገኙ ስለ ተመረጡት በነገር ሁሉ እጸናለሁ።</verse>
				<verse number="11">እንዲህ የሚለው ቃሉ የታመነ ነው “ከእርሱ ጋር ከሞትን፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንኖራለን፤</verse>
				<verse number="12">ብንጸና፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ እንነግሣለን፤ ብንክደው፥ እርሱ ደግሞ ይክደናል፤</verse>
				<verse number="13">ባናምነው፥ እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና።”</verse>
				<verse number="14">ይህን አሳስባቸው፤ በቃልም እንዳይጣሉ በእግዚአብሔር ፊት ምከራቸው፤ ይህ ምንም የማይረባ የሚሰሙትንም የሚያፈርስ ነውና።</verse>
				<verse number="15">የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።</verse>
				<verse number="16">ነገር ግን ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍ ራቅ፤ ኀጢአተኝነታቸውን ከፊት ይልቅ ይጨምራሉና፤</verse>
				<verse number="17">ቃላቸውም እንደ ጭንቁር ይባላል፤ ከእነርሱም ሄሜኔዎስና ፊሊጦስ ናቸው፤</verse>
				<verse number="18">እነዚህም “ትንሣኤ ከአሁን በፊት ሆኖአል፤” እያሉ ስለ እውነት ስተው የአንዳንዶችን እምነት ይገለብጣሉ።</verse>
				<verse number="19">ሆኖም “ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፤” ደግሞም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዐመፅ ይራቅ፤” የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል።</verse>
				<verse number="20">በትልቅም ቤት የእንጨትና የሸክላ ዕቃ ደግሞ አለ እንጂ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ አይደለም፤ እኵሌቶቹም ለክብር፥ እኵሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፤</verse>
				<verse number="21">እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነጻ፥ ለክብር የሚሆን የተቀደሰም ለጌታውም የሚጠቅም ለበጎም ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ዕቃ ይሆናል።</verse>
				<verse number="22">ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ፤ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል።</verse>
				<verse number="23">ነገር ግን ጠብን እንዲያመጣ አውቀህ ከሰነፎችና ካልተማሩ ምርመራ ራቅ፤</verse>
				<verse number="24">የጌታም ባሪያ ለሰው ሁሉ ገር፥ ለማስተማርም የሚበቃ፥ ለትዕግሥትም የሚጸና ሊሆን እንጂ ሊጣላ አይገባውም።</verse>
				<verse number="25">ደግሞም “ምናልባት እግዚአብሔር እውነትን ያውቁ ዘንድ ንስሓን ይሰጣቸዋልና ፈቃዱን ለማድረግ በዲያብሎስ ሕያዋን ሆነው ከተያዙበት ወጥመድ ወጥተው ወደ አእምሮ ይመለሳሉ፤” ብሎ የሚቃወሙትን በየዋህነት ይቅጣ።</verse>
				<verse number="26"></verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።</verse>
				<verse number="2">ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፤ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ቅድስና የሌላቸው፥</verse>
				<verse number="3">ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥</verse>
				<verse number="4">ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤</verse>
				<verse number="5">የአምልኮት መልክ አላቸው፤ ኀይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።</verse>
				<verse number="6">ወደ ቤቶች ሾልከው እየገቡ ኀጢአታቸው የተከመረባቸውን በልዩ ልዩ ምኞትም የሚወሰዱትን ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉትን ሞኞችን ሴቶች የሚማርኩ፥ ከእነዚህ ዘንድ ናቸውና።</verse>
				<verse number="7"></verse>
				<verse number="8">ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደ ተቃወሙት፥ እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው ስለ እምነትም የተጣሉ ሰዎች ሆነው እውነትን ይቃወማሉ።</verse>
				<verse number="9">ዳሩ ግን የእነዚያ ሞኝነት ደግሞ ግልጥ እንደ ሆነ፥ ሞኝነታቸው ለሁሉ ይገለጣልና ከፊት ይልቅ አይቀናላቸውም።</verse>
				<verse number="10">አንተ ግን ትምህርቴንና አካሄዴን አሳቤንም እምነቴንም ትዕግሥቴንም ፍቅሬንም መጽናቴንም</verse>
				<verse number="11">ስደቴንም መከራዬንም ተከተልህ፤ በአንጾኪያና በኢቆንዮን በልስጥራንም የሆነብኝን የታገሥሁትንም ስደት ታውቃለህ፤ ጌታም ከሁሉ አዳነኝ።</verse>
				<verse number="12">በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ።</verse>
				<verse number="13">ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች እያሳቱና እየሳቱ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ።</verse>
				<verse number="14">አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፤ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤</verse>
				<verse number="15">ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳት መጻሕፍትን አውቀሃል።</verse>
				<verse number="16">የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።</verse>
				<verse number="17"></verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">በእግዚአብሔር ፊት፥ በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ባለው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት፥ በመገለጡና በመንግሥቱም እመክርሃለሁ፤</verse>
				<verse number="2">ቃሉን ስበክ፤ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፤ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ ዝለፍና ገሥጽ፤ ምከርም።</verse>
				<verse number="3">ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና፤ ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ፥ እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ።</verse>
				<verse number="4">እውነትንም ከመስማት ጆሮቻቸውን ይመልሳሉ፤ ወደ ተረትም ፈቀቅ ይላሉ።</verse>
				<verse number="5">አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፤ መከራን ተቀበል፤ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፤ አገልግሎትህን ፈጽም።</verse>
				<verse number="6">በመሥዋዕት እንደሚደረግ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና፥ የምሄድበት ጊዜ ደርሶአል።</verse>
				<verse number="7">መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፤ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፤ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤</verse>
				<verse number="8">ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፤ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፤ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።</verse>
				<verse number="9">በቶሎ ወደ እኔ እንድትመጣ ትጋ፤</verse>
				<verse number="10">ዴማስ የአሁኑን ዓለም ወዶ ትቶኛልና፤ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል፤ ቄርቂስም ወደ ገላትያ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል።</verse>
				<verse number="11">ሉቃስ ብቻ ከእኔ ጋር አለ፤ ማርቆስ ለአገልግሎት ብዙ ይጠቅመኛልና ይዘኸው ከአንተ ጋር አምጣው።</verse>
				<verse number="12">ቲኪቆስን ግን ወደ ኤፌሶን ላክሁት።</verse>
				<verse number="13">ስትመጣ በጢሮአዳ ከአክርጳ ዘንድ የተውሁትን በርኖሱንና መጻሕፍቱን ይልቁንም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ።</verse>
				<verse number="14">የናስ አንጥረኛው እስክንድሮስ እጅግ ከፋብኝ፤ ጌታ እንደ ሥራው ይመልስለታል።</verse>
				<verse number="15">አንተም ደግሞ ከእርሱ ተጠበቅ፤ የምንናገረውን እጅግ ተቃውሞአልና።</verse>
				<verse number="16">በፊተኛው ሙግቴ አንድ ስንኳ አልደረሰልኝም፤ ሁሉም ተዉኝ እንጂ፤ ይህንም አይቍጠርባቸው፤</verse>
				<verse number="17">ዳሩ ግን የስብከቱ ሥራ በእኔ እንዲፈጸም አሕዛብም ሁሉ እንዲሰሙት፥ ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ፤ ከአንበሳ አፍም ዳንሁ።</verse>
				<verse number="18">ጌታም ከክፉ ነገር ሁሉ ያድነኛል፤ ለሰማያዊውም መንግሥት ይጠብቀኛል፤ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።</verse>
				<verse number="19">ለጵርስቅላና ለአቂላ ለሄኔሲፎሩም ቤተ ሰዎች ሰላምታ አቅርብልኝ።</verse>
				<verse number="20">ኤርስጦስ በቆሮንቶስ ቀረ፤ ጥሮፊሞስን ግን ታሞ በሚሊጢን ተውሁት።</verse>
				<verse number="21">ከክረምት በፊት እንድትመጣ ትጋ። ኤውግሎስና ጱዴስ ሊኖስም ቅላውዲያም ወንድሞችም ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል።</verse>
				<verse number="22">ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመንፈስህ ጋር ይሁን። ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="56">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">የእግዚአብሔር ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ በእግዚአብሔር ለተመረጡት እምነት እንዲሆንላቸው በዘላለምም ሕይወት ተስፋ እንደ አምልኮት ያለውን እውነት እንዲያውቁ የተላከ፤ ስለዚህም ሕይወት የማይዋሽ እግዚአብሔር ከዘላለም ዘመናት በፊት ተስፋ ሰጠ።</verse>
				<verse number="2"></verse>
				<verse number="3">በዘመኑም ጊዜ መድኃኒታችን እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ ለእኔ አደራ በተሰጠኝ ስብከት ቃሉን ገለጠ፤</verse>
				<verse number="4">በሃይማኖት ኅብረት እውነተኛ ልጄ ለሚሆን ለቲቶ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከመድኃኒታችንም ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን።</verse>
				<verse number="5">ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ፤</verse>
				<verse number="6">የማይነቀፍና የአንዲት ሚስትባል የሚሆን፥ የሚያምኑም ልጆች ያሉት፥ ስለ መዳራትም ወይም ስለ አለመታዘዝ የማይከሰስ ማንም ቢኖር፥ ሹመው።</verse>
				<verse number="7">ኤጲስቆጶስ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባዋልና፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ፥ ነውረኛ ረብ የማይወድ፥</verse>
				<verse number="8">ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚወድ፥ ጠንቃቃ፥ ጻድቅ፥ ቅዱስ፥ ራሱን የሚገዛ ይሁን፤</verse>
				<verse number="9">ሕይወት በሚገኝበት ትምህርት ደግሞ ሊመክር ተቃዋሚዎቹንም ሊወቅስ ይችል ዘንድ፥ እንደተማረው በታመነ ቃል ይጽና።</verse>
				<verse number="10">የማይታዘዙና ከንቱ የሚናገሩ የሚያታልሉ ይልቁንም ከተገረዙት ወገን የሚሆኑ ብዙ ናቸውና፤</verse>
				<verse number="11">እነዚህም ስለ ነውረኛ ረብ የማይገባውን እያስተማሩ ቤቶችን በሞላው ስለ ሚገለብጡ፥ አፋቸውን መዝጋት ይገባል።</verse>
				<verse number="12">የገዛ ራሳቸው ነቢይ የሆነ ከእነርሱ አንዱ “የቀርጤስ ሰዎች ዘወትር ውሸተኞች፥ ክፉዎች አራዊት፥ በላተኞች፥ ሥራ ፈቶች ናቸው፤” ብሎአል።</verse>
				<verse number="13">ይህ ምስክር እውነተኛ ነው። ስለዚህ ምክንያት የአይሁድን ተረትና ከእውነት ፈቀቅ የሚሉትን ሰዎች ትእዛዝ ሳያዳምጡ፥ በሃይማኖት ጤናሞች እንዲሆኑ በብርቱ ውቀሳቸው።</verse>
				<verse number="14"></verse>
				<verse number="15">ሁሉ ለንጹሖች ንጹሕ ነው፤ ለርኵሳንና ለማያምኑ ግን ንጹሕ የሆነ ምንም የለም፤ ነገር ግን አእምሮአቸውም ሕሊናቸውም ረክሶአል።</verse>
				<verse number="16">እግዚአብሔርን እንዲያውቁ በግልጥ ይናገራሉ፤ ዳሩ ግን የሚያስጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ የማይበቁ ስለ ሆኑ፥ በሥራቸው ይክዱታል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">አንተ ግን ሕይወት ለሚገኝበት ትምህርት የሚገባውን ተናገር።</verse>
				<verse number="2">ሽማግሌዎች ልከኞች፥ ጭምቶች፥ ራሳቸውን የሚገዙ፥ በእምነትና በፍቅር በመጽናትም ጤናሞች እንዲሆኑ ምከራቸው፤</verse>
				<verse number="3">እንዲሁም አሮጊቶች ሴቶች አካሄዳቸው ለቅዱስ አገልግሎት የሚገባ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ፤</verse>
				<verse number="4">ቆነጃጅትም የእግዚአብሔር ቃል እንዳይሰደብ፥ ባሎቻቸውን የሚወዱ፥ ልጆቻቸውን የሚወዱ፥ ራሳቸውን የሚገዙ፥ ንጹሖች፥ በቤት የሚሠሩ፥ በጎዎች፥ ለባሎቻቸው የሚታዘዙ እንዲሆኑ ይምከሩአቸው።</verse>
				<verse number="5"></verse>
				<verse number="6">ጎበዞችም እንዲሁ ራሳቸውን እንዲገዙ ምከራቸው።</verse>
				<verse number="7">የሚቃወም ሰው ስለ እኛ የሚናገረውን መጥፎ ነገር ሲያጣ እንዲያፍር፥ በነገር ሁሉ መልካምን በማድረግህ ምሳሌ የሚሆን ራስህን አሳይ፤ በትምህርትህም ደኅንነትን፥ ጭምትነትን፥ ጤናማና የማይነቀፍ ንግግርን ግለጥ።</verse>
				<verse number="8"></verse>
				<verse number="9">ባሪያዎች ስለ መድኃኒታችን ስለ እግዚአብሔር የሚሆነውን ትምህርት በሁሉ ነገር ያስመሰግኑ ዘንድ፥ ለገዛ ጌቶቻቸው እንዲገዙ በሁሉም ደስ እንዲያሰኙ፥ ሳይቃወሙና ሳይሰርቁም በጎ ታማኝነትን ሁሉ እንዲያሳዩ ምከራቸው።</verse>
				<verse number="10"></verse>
				<verse number="11">ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤</verse>
				<verse number="12">ይህም ጸጋ፥ ኀጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤</verse>
				<verse number="13"></verse>
				<verse number="14">መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።</verse>
				<verse number="15">ይህን በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር፤ ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ለገዦችና ለባለ ሥልጣኖች የሚገዙና የሚታዘዙ፥ ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጁ፥ ማንንም የማይሰድቡ፥ የማይከራከሩ፥ ገሮች፥ ለሰው ሁሉ የዋህነትን ሁሉ የሚያሳዩ እንዲሆኑ ኣሳስባቸው።</verse>
				<verse number="2"></verse>
				<verse number="3">እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ፥</verse>
				<verse number="5">እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤</verse>
				<verse number="6">ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው።</verse>
				<verse number="7"></verse>
				<verse number="8">ቃሉ የታመነ ነው። እግዚአብሔርንም የሚያምኑት በመልካም ሥራ በጥንቃቄ እንዲጸኑ፥ እነዚህን አስረግጠህ እንድትናገር እፈቅዳለሁ። ይህ መልካምና ለሰዎች የሚጠቅም ነው፤</verse>
				<verse number="9">ነገር ግን ሞኝነት ካለው ምርመራና ከትውልዶች ታሪክ ከክርክርም ስለ ሕግም ከሚሆን ጠብ ራቅ፤ የማይጠቅሙና ከንቱዎች ናቸውና፤</verse>
				<verse number="10">መለያየትን የሚያነሣ ሰው ጠማማ እንዲሆን በራሱም ላይ ፈርዶ ኀጢአትን እንዲያደርግ አውቀህ፥ አንድ ጊዜ ሁለት ጊዜም ከገሠጽኸው በኋላ እንዲህ ከሚመስል ሰው ራቅ።</verse>
				<verse number="11"></verse>
				<verse number="12">አርጢሞንን ወይም ቲኪቆስን ወደ አንተ ስልክ፥ ወደ ኒቆጵልዮን ወደ እኔ እንድትመጣ ትጋ፤ በዚያ ልከርም ቈርጫለሁና።</verse>
				<verse number="13">ሕግ አዋቂውን ዜማስንና አጵሎስን ምንም እንዳይጎድልባቸው በጉዞአቸው ተግተህ እርዳ።</verse>
				<verse number="14">ከወገናችንም ያሉት ደግሞ ፍሬ ቢሶች ሆነው እንዳይቀሩ፥ የግድ ስለሚያስፈልገው ነገር በመልካም ሥራ እንዲጸኑ ይማሩ።</verse>
				<verse number="15">ከእኔ ጋር ያሉት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል። በእምነት ለሚወዱን ሰላምታ አቅርብልን። ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="57">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">የክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ ጳውሎስ ወንድሙም ጢሞቴዎስ፥ ለተወደደውና አብሮን ለሚሠራ ለፊልሞና፥</verse>
				<verse number="2">ለእኅታችንም ለአፍብያ፥ ከእኛም ጋር አብሮ ወታደር ለሆነ ለአርክጳ፥ በቤትህም ላለች ቤተ ክርስቲያን፤</verse>
				<verse number="3">ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።</verse>
				<verse number="4">በጌታ በኢየሱስ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ ዘንድ ስላለህ ስለ ፍቅርህና ስለ እምነትህ ሰምቼ፥ በጸሎቴ እያሳሰብሁ ሁልጊዜ አምላኬን አመሰግናለሁ፤</verse>
				<verse number="5"></verse>
				<verse number="6">የእምነትህም ኅብረት፥ በእኛ ዘንድ ያለውን በጎ ነገር ሁሉ በማወቅ፥ ለክርስቶስ ኢየሱስ ፍሬ እንዲያፈራ እለምናለሁ፤</verse>
				<verse number="7">የቅዱሳን ልብ በአንተ ሥራ ስለ ዐረፈ፥ ወንድሜ ሆይ! በፍቅርህ ብዙ ደስታንና መጽናናትን አግኝቼአለሁና።</verse>
				<verse number="8">ስለዚህ የሚገባውን አዝህ ዘንድ በክርስቶስ ምንም እንኳ ብዙ ድፍረት ቢኖረኝ፥</verse>
				<verse number="9">ይልቁንም እንደዚህ የሆንሁ እኔ ጳውሎስ ሽማግሌው፥ አሁንም ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ እስረኛ የሆንሁ፥ ስለ ፍቅር እለምናለሁ።</verse>
				<verse number="10">አስቀድሞ ስላልጠቀመህ፥ አሁን ግን ለእኔም ለአንተም ስለሚጠቅም በእስራቴ ስለ ወለድሁት ስለ ልጄ ስለ አናሲሞስ እለምንሃለሁ።</verse>
				<verse number="11"></verse>
				<verse number="12">እርሱን እልከዋለሁ፤ አንተም ልቤ እንደሚሆን ተቀበለው።</verse>
				<verse number="13">እኔስ በወንጌል እስራት ስለ አንተ እንዲያገለግለኝ ለራሴ ላስቀረው እፈቅድ ነበር፤</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን በጎነትህ በፈቃድህ እንጂ በግድ እንዳይሆን፥ ሳልማከርህ ምንም እንኳ ላደርግ አልወደድሁም።</verse>
				<verse number="15">ተቀብለህ ለዘላለም እንድትይዘው ስለዚህ ምናልባት ለጊዜው ተለይቶሃልና፤</verse>
				<verse number="16">ከእንግዲህ ወዲህ እንደ ባሪያ አይሆንም፤ ነገር ግን ለእኔ በተለየ የተወደደ ወንድም ከሆነ፥ ለአንተማ ይልቅ በሥጋውም በጌታም ዘንድ ከባሪያ የሚሻል የተወደደ ወንድም እንዴት አይሆንም?</verse>
				<verse number="17">እንግዲህ እንደ ባልንጀራ ብትቈጥረኝ፥ እንደ እኔ አድርገህ ተቀበለው።</verse>
				<verse number="18">በአንዳች ነገር የበደለህ ቢኖር ግን ወይም ብድር ያለበት እንደሆነ፥ ይህን በእኔ ላይ ቍጠር፤</verse>
				<verse number="19">እኔ ጳውሎስ “እኔ እመልሰዋለሁ፤” ብዬ በእጄ እጽፋለሁ፤ ከዚህም በላይ ለእኔ የራስህ ደግሞ ብድር እንዳለብህ አልልህም።</verse>
				<verse number="20">አዎን፥ ወንድሜ ሆይ! በጌታ እኔ እንድጠቀምብህ ይሁን፤ በክርስቶስ ልቤን አሳርፍልኝ።</verse>
				<verse number="21">ከምልህ ይልቅ አብልጠህ እንድታደርግ አውቄ እንድትታዘዝም ታምኜ እጽፍልሃለሁ።</verse>
				<verse number="22">ደግሞ ከዚህም ጋር የማስተናገጃ ቤት አዘጋጅልኝ፤ በጸሎታችሁ ለእናንተ እንድሰጥ ተስፋ አደርጋለሁና።</verse>
				<verse number="23">በክርስቶስ ኢየሱስ ከእኔ ጋር የታሰረ ኤጳፍራ</verse>
				<verse number="24">አብረውኝም የሚሠሩ ማርቆስና አርስጥሮኮስ ዴማስም ሉቃስም ሰላምታ ያቀርቡልሃል።</verse>
				<verse number="25">የጌታችን የኢሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="58">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">ከጥ​ንት ጀምሮ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በብዙ ዐይ​ነ​ትና በብዙ ጎዳና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን በነ​ቢ​ያት ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="2">በኋላ ዘመን ግን ሁሉን ወራሽ ባደ​ረ​ገው፥ ሁሉ​ንም በፈ​ጠ​ረ​በት በልጁ ነገ​ረን።</verse>
				<verse number="3">እር​ሱም የክ​ብሩ መን​ጸ​ባ​ረ​ቅና የመ​ልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥ​ል​ጣኑ ቃል እየ​ደ​ገፈ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰ​ማ​ያት በግ​ር​ማው ቀኝ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="4">በዚ​ህን ያህል መብ​ለጥ ከመ​ላ​እ​ክት በላይ ሆኖ ከስ​ማ​ቸው የሚ​በ​ል​ጥና የሚ​ከ​ብር ስምን ወረሰ።</verse>
				<verse number="5">ከመ​ላ​እ​ክ​ትስ ከሆነ ጀምሮ፥ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለ​ድ​ሁህ” ዳግ​መ​ኛም፥ “እኔ አባት እሆ​ነ​ዋ​ለሁ እር​ሱም ልጄ ይሆ​ነ​ኛል” ያለው ከቶ ለማን ነው?</verse>
				<verse number="6">ዳግ​መ​ኛም በኵ​ርን ወደ ዓለም በላ​ከው ጊዜ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ሁሉ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል” አለ።</verse>
				<verse number="7">ስለ መላ​እ​ክ​ቱም፥ “መላ​እ​ክ​ቱን ነፋ​ሳት፥ የሚ​ላ​ኩ​ት​ንም የእ​ሳት ነበ​ል​ባል የሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ቸው እርሱ ነው” አለ።</verse>
				<verse number="8">ስለ ልጁ ግን፥ “ጌታ ሆይ፥ ዙፋ​ንህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነው፤ የመ​ን​ግ​ሥ​ትህ በት​ርም የጽ​ድቅ በትር ነው” አለ።</verse>
				<verse number="9">“ጽድ​ቅን ወደ​ድህ፤ ዐመ​ፃ​ንም ጠላህ፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እን​ዳ​ንተ ካሉት ይልቅ የሚ​በ​ልጥ የደ​ስታ ዘይ​ትን ቀባህ።”</verse>
				<verse number="10">ዳግ​መ​ኛም እን​ዲህ አለ፥ “አቤቱ አንተ አስ​ቀ​ድሞ ምድ​ርን መሠ​ረ​ትህ፤ ሰማ​ያ​ትም የእ​ጆ​ችህ ሥራ ናቸው።</verse>
				<verse number="11">እነ​ርሱ ያል​ፋሉ፤ አንተ ግን ትኖ​ራ​ለህ፤ ሁሉ እንደ ልብስ ያረ​ጃል፤</verse>
				<verse number="12">እንደ መጋ​ረ​ጃም ትጠ​ቀ​ል​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ይለ​ወ​ጣ​ሉም፤ አንተ ግን መቼም መች አንተ ነህ፤ ዘመ​ን​ህም የማ​ይ​ፈ​ጸም ነው።”</verse>
				<verse number="13">ከሆነ ጀምሮ ከመ​ላ​እ​ክት፥ “ጠላ​ቶ​ች​ህን ከእ​ግ​ርህ ጫማ በታች እስከ አደ​ር​ግ​ልህ ድረስ በቀኜ ተቀ​መጥ” ማንን አለው?</verse>
				<verse number="14">መላ​እ​ክት ሁሉ መና​ፍ​ስት አይ​ደ​ሉ​ምን? የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይወ​ርሱ ዘንድ ስለ አላ​ቸው ሰዎ​ችስ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት ይላኩ የለ​ምን?</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ስለ​ዚ​ህም ከሰ​ማ​ነው ነገር ምን​አ​ል​ባት እን​ዳ​ን​ወ​ሰድ ለእ​ርሱ አብ​ዝ​ተን ልን​ጠ​ነ​ቀቅ ይገ​ባ​ናል።</verse>
				<verse number="2">በመ​ላ​እ​ክት የተ​ነ​ገ​ረው ቃል ጽኑ ከሆነ፥ መተ​ላ​ለ​ፍና አለ​መ​ታ​ዘ​ዝም ሁሉ የጽ​ድ​ቅን ብድ​ራት ከተ​ቀ​በለ፥</verse>
				<verse number="3">እኛስ እን​ዲህ ያለ​ውን ታላቅ መዳን ቸል ብን​ለው እን​ዴት እና​መ​ል​ጣ​ለን? ይህ በጌታ በመ​ጀ​መ​ሪያ የተ​ነ​ገረ ነበ​ረና የሰ​ሙ​ትም ለእኛ አጸ​ኑት።</verse>
				<verse number="4">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ራሱ ፈቃድ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ጸጋ በመ​ስ​ጠት፥ በም​ል​ክ​ትና በድ​ንቅ ነገር፥ በልዩ ልዩ ተአ​ም​ራ​ትም መሰ​ከ​ረ​ላ​ቸው፤ ነገ​ራ​ቸ​ው​ንም አስ​ረ​ዳ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="5">ስለ እርሱ የም​ን​ና​ገ​ር​ለ​ትን የሚ​መ​ጣ​ውን ዓለም ለመ​ላ​እ​ክት ያስ​ገዛ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="6">ነገር ግን መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ የመ​ሰ​ከ​ረ​በት ስፍራ አለ፤ “ታስ​በው ዘንድ ሰው ምን​ድን ነው? ትጐ​በ​ኘ​ውስ ዘንድ የሰው ልጅ ምን​ድን ነው?</verse>
				<verse number="7">ከመ​ላ​እ​ክ​ትህ ጥቂት አሳ​ነ​ስ​ኸው፤ የክ​ብ​ርና የም​ስ​ጋና ዘው​ድ​ንም ጫን​ህ​ለት፤ በእ​ጆ​ች​ህም ሥራ ሁሉ ላይ ሾም​ኸው።</verse>
				<verse number="8">ሁሉ​ንም ከእ​ግሩ በታች አድ​ር​ገህ አስ​ገ​ዛ​ህ​ለት።” ሁሉን ለእ​ርሱ ባስ​ገ​ዛ​ለት ጊዜም የተ​ወ​ውና ያላ​ስ​ገ​ዛ​ለት የለም፤ አሁን ግን ሁሉን እን​ዳ​ስ​ገ​ዛ​ለት አና​ይም።</verse>
				<verse number="9">ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀ​ምስ ዘንድ ከመ​ላ​እ​ክት ይልቅ በጥ​ቂት አንሶ የነ​በ​ረ​ውን ኢየ​ሱ​ስን ከሞት መከራ የተ​ነሣ የክ​ብ​ርና የም​ስ​ጋ​ናን ዘውድ ጭኖ እና​የ​ዋ​ለን።</verse>
				<verse number="10">ብዙ ልጆ​ችን ወደ ክብር ሲያ​መጣ የመ​ዳ​ና​ቸ​ውን ራስ በመ​ከራ ይፈ​ጽም ዘንድ ከእ​ርሱ የተ​ነሣ ሁሉ በእጁ ለተ​ያዘ፥ በእ​ር​ሱም ሁሉ ለሆነ ለእ​ርሱ ተገ​ብ​ቶ​ታ​ልና።</verse>
				<verse number="11">እነ​ር​ሱን የቀ​ደ​ሳ​ቸው እርሱ፥ የተ​ቀ​ደ​ሱት እነ​ር​ሱም ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት ከአ​ንዱ ናቸ​ውና። ስለ​ዚ​ህም እነ​ር​ሱን፥ “ወን​ድ​ሞች” ማለ​ትን አያ​ፍ​ርም።</verse>
				<verse number="12">“ስም​ህን ለወ​ን​ድ​ሞች እነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በማ​ኅ​በር መካ​ከ​ልም አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="13">ዳግ​መ​ኛም፥ “እኔና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠኝ ልጆች እነሆ፥” አለ፤ ዳግ​መ​ኛም፥ “እኔ እታ​መ​ን​በ​ታ​ለሁ” አለ።</verse>
				<verse number="14">ልጆች በሥ​ጋና በደም አንድ ናቸ​ውና፤ እርሱ ደግሞ በዚህ ከእ​ነ​ርሱ ጋር አንድ ሆነ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም እንደ ወን​ድም ሆነ​ላ​ቸው፤ መል​አከ ሞትን በሞቱ ይሽ​ረው ዘንድ፥ ይኸ​ውም ሰይ​ጣን ነው።</verse>
				<verse number="15">በሕ​ይ​ወት ዘመ​ና​ቸው ሁሉ ሞትን በመ​ፍ​ራት የተ​ቀ​ጡ​ትን፥ ለባ​ር​ነት የተ​ገ​ዙ​ት​ንም ሁሉ ያሳ​ር​ፋ​ቸው ዘንድ።</verse>
				<verse number="16">የነ​ሣ​ውን ከአ​ብ​ር​ሃም ዘር እንጂ ከመ​ላ​እ​ክት የነ​ሣው አይ​ደ​ለ​ምና።</verse>
				<verse number="17">ስለ​ዚ​ህም የሕ​ዝ​ብን ኀጢ​አት ለማ​ስ​ተ​ስ​ረይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሆ​ነው ነገር ሁሉ የሚ​ም​ርና የታ​መነ ሊቀ ካህ​ናት እን​ዲ​ሆን በነ​ገር ሁሉ ወን​ድ​ሞ​ቹን ሊመ​ስል ተገ​ባው።</verse>
				<verse number="18">እርሱ ራሱ ተፈ​ትኖ መከ​ራን ስለ ተቀ​በለ የሚ​ፈ​ተ​ኑ​ትን ሊረ​ዳ​ቸው ይች​ላ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">አሁ​ንም ከሰ​ማ​ያዊ ጥሪ ተካ​ፋ​ዮች የሆ​ና​ችሁ ቅዱ​ሳን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የሃ​ይ​ማ​ኖ​ታ​ች​ንን ሐዋ​ር​ያና ሊቀ ካህ​ናት ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ተመ​ል​ከቱ።</verse>
				<verse number="2">ሙሴ ደግሞ በቤቱ ሁሉ የታ​መነ እንደ ሆነ፥ እርሱ ለላ​ከው የታ​መነ እው​ነ​ተኛ ነው።</verse>
				<verse number="3">ነገር ግን የባ​ለ​ቤት ክብሩ ከቤቱ እን​ደ​ሚ​በ​ልጥ፥ ክብሩ ከሙሴ ክብር ይልቅ እጅግ ይበ​ል​ጣል፤</verse>
				<verse number="4">ቤትን ሁሉ ሰው ይሠ​ራ​ዋ​ልና፤ ለሁሉ ግን ሠሪው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።</verse>
				<verse number="5">ሙሴስ በኋላ ስለ​ሚ​ነ​ገ​ረው ነገር ምስ​ክር ሊሆን በቤቱ ሁሉ እንደ ሎሌ የታ​መነ ነበረ።</verse>
				<verse number="6">ክር​ስ​ቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ ላይ የታ​መነ ነው፤ እኛም የም​ን​ደ​ፍ​ር​በ​ትን፥ የም​ን​መ​ካ​በ​ት​ንም ተስፋ እስከ መጨ​ረ​ሻው አጽ​ን​ተን ብን​ጠ​ብቅ ቤቱ ነን።</verse>
				<verse number="7">መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “ዛሬ ቃሉን ብት​ሰሙ ልባ​ች​ሁን አታ​ጽኑ።</verse>
				<verse number="8">በም​ድረ በዳ በተ​ፈ​ታ​ተ​ኑ​በት ቀን እንደ አሳ​ዘ​ኑት ጊዜ።</verse>
				<verse number="9">የተ​ፈ​ታ​ተ​ኑኝ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ፈተ​ኑኝ፤ አርባ ዘመ​ንም ሥራ​ዬን አዩ።</verse>
				<verse number="10">ስለ​ዚህ ይህ​ቺን ትው​ልድ ተቈ​ጣ​ኋት፤ እን​ዲ​ህም አልሁ፦ ‘ልባ​ቸው ዘወ​ትር ይስ​ታል፤ እነ​ርሱ ግን መን​ገ​ዴን አላ​ወ​ቁም።’</verse>
				<verse number="11">ወደ ዕረ​ፍቴ አይ​ገ​ቡም ብዬ በቍ​ጣዬ ማልሁ።”</verse>
				<verse number="12">ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ግ​ዲህ ዕወቁ፤ ከእ​ና​ንተ ባንዱ ላይ ስንኳ ሃይ​ማ​ኖት የጐ​ደ​ለ​ውና ተጠ​ራ​ጣሪ፥ ከሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ለ​ያ​ችሁ ክፉ ልብ አይ​ኑር።</verse>
				<verse number="13">ዛሬ የሚ​ባ​ለው ቀን ሳለ ከእ​ና​ንተ ማንም ቢሆን ወደ ኀጢ​አት በሚ​ያ​ደ​ርስ ስሕ​ተት እን​ዳ​ይ​ጸና ሁል​ጊዜ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን መር​ምሩ።</verse>
				<verse number="14">በዚች ጽድቅ እስከ መጨ​ረሻ የቀ​ደ​መ​ውን ሥር​ዐ​ታ​ች​ንን አጽ​ን​ተን ከጠ​በ​ቅን ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋር አንድ ሁነ​ና​ልና።</verse>
				<verse number="15">“ዛሬ ቃሉን ብት​ሰሙ እነ​ዚያ እንደ አሳ​ዘ​ኑት ጊዜ ልባ​ች​ሁን አታ​ጽኑ” ብሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="16">ሰም​ተው ያሳ​ዘ​ኑ​ትስ እነ​ማን ናቸው? በሙሴ እጅ ከግ​ብፅ የወ​ጡት ሁሉ አይ​ደ​ሉ​ምን?</verse>
				<verse number="17">አርባ ዘመን የተ​ቈ​ጣ​ቸ​ውስ እነ​ማን ነበሩ? የበ​ደሉ፥ ሬሳ​ቸ​ውም በም​ድረ በዳ የወ​ደ​ቀው አይ​ደ​ሉ​ምን?</verse>
				<verse number="18">ከካ​ዱት በቀር ወደ ዕረ​ፍቱ እን​ዳ​ይ​ገቡ በማን ላይ ማለ?</verse>
				<verse number="19">አላ​መ​ኑ​ምና፥ ለመ​ግ​ባት እን​ዳ​ል​ቻሉ እነሆ፥ እና​ያ​ለን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">እን​ግ​ዲህ አን​ፍራ፤ ወደ ዕረ​ፍ​ቱም እን​ድ​ን​ገባ ትእ​ዛ​ዙን አን​ተው፤ ከእ​ና​ን​ተም ምን​አ​ል​ባት በተ​ለ​መደ ስሕ​ተት የሚ​ገ​ኝና የሚ​ጸና ቢኖር ወደ ዕረ​ፍቱ እን​ዲ​ገባ የሚ​ተ​ዉት አይ​ም​ሰ​ለው።</verse>
				<verse number="2">ለእ​ነ​ዚያ ደግሞ እንደ ተነ​ገረ ለእ​ኛም የም​ሥ​ራች ተሰ​ብ​ኮ​ል​ናል፤ ነገር ግን የሰ​ሙት ቃል ከሰ​ሚ​ዎቹ ጋር በእ​ም​ነት ስላ​ል​ተ​ዋ​ሐደ አል​ጠ​ቀ​ማ​ቸ​ውም።</verse>
				<verse number="3">ሥራዉ ዓለም ከተ​ፈ​ጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈ​ጸም፥ “እን​ግ​ዲህ ወደ ዕረ​ፍቴ አይ​ገ​ቡም ብዬ በቍ​ጣዬ ማልሁ” እን​ዳለ እኛስ ያመ​ንን ወደ ዕረ​ፍቱ እን​ገ​ባ​ለን።</verse>
				<verse number="4">ስለ ሰባ​ተ​ኛ​ውም ቀን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ከሥ​ራው ሁሉ ዐረፈ” ብሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="5">ዳግ​መ​ኛም፥ “ወደ ዕረ​ፍቴ አይ​ገ​ቡም” ብሎ​አል።</verse>
				<verse number="6">እን​ግ​ዲህ አን​ዳ​ን​ዶች በዚያ እን​ዲ​ገቡ መን​ገድ ስለ ነበ​ራ​ቸው ቀድ​ሞም የም​ሥ​ራች የተ​ሰ​በ​ከ​ላ​ቸው ባለ መታ​ዘዝ ጠንቅ ስላ​ል​ገቡ፦</verse>
				<verse number="7">“ዛሬ ቃሉን ብት​ሰ​ሙት ልባ​ች​ሁን እል​ከኛ አታ​ድ​ርጉ፤” በፊት እንደ ተባለ ይህን ከሚ​ያ​ህል ዘመን በኋላ በዳ​ዊት ሲና​ገር፥ “ዛሬ” ብሎ አንድ ቀን እንደ ገና ይቀ​ጥ​ራል።</verse>
				<verse number="8">ኢያሱ አሳ​ር​ፎ​አ​ቸው ቢሆን ኖሮስ፥ ከብዙ ዘመን በኋላ ስለ ሌላ ቀን ባል​ተ​ና​ገ​ረም ነበር።</verse>
				<verse number="9">እን​ኪ​ያስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ የሚ​ገ​ቡ​በት ጸንቶ የሚ​ኖር ዕረ​ፍት እን​ዳለ ታወቀ።</verse>
				<verse number="10">ወደ ዕረ​ፍቱ የገ​ባስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሥ​ራው እንደ ዐረፈ፥ እነሆ፥ እርሱ ከሥ​ራው ሁሉ ዐረፈ።</verse>
				<verse number="11">እን​ግ​ዲህ እንደ እነ​ዚያ እንደ ካዱት እን​ዳ​ን​ወ​ድቅ፥ ወደ ዕረ​ፍቱ እን​ገባ ዘንድ እን​ፋ​ጠን።</verse>
				<verse number="12">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሕያው ነውና፤ የሚ​ሠ​ራም ሁለት ልሳን ካለው ሰይ​ፍም ሁሉ ይልቅ የተ​ሳለ ነው፤ ነፍ​ስ​ንና መን​ፈ​ስ​ንም፥ ጅማ​ት​ንና ቅል​ጥ​ም​ንም እስ​ኪ​ለይ ድረስ ይወ​ጋል፤ የል​ብ​ንም ስሜ​ትና አሳብ ይመ​ረ​ም​ራል።</verse>
				<verse number="13">እኛን በሚ​ቈ​ጣ​ጠር በእ​ርሱ በዐ​ይ​ኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተ​ራ​ቈ​ተና የተ​ገ​ለጠ ነው እንጂ በእ​ርሱ ፊት የተ​ሰ​ወረ ፍጥ​ረት የለም።</verse>
				<verse number="14">እን​ግ​ዲህ ወደ ሰማ​ያት የወጣ ታላቅ ሊቀ ካህ​ናት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አለን፤ በእ​ርሱ በማ​መን ጸን​ተን እን​ኑር።</verse>
				<verse number="15">ሊቀ ካህ​ና​ታ​ችን ለድ​ካ​ማ​ችን መከራ መቀ​በ​ልን የማ​ይ​ችል አይ​ደ​ለ​ምና፤ ነገር ግን ከብ​ቻዋ ከኀ​ጢ​አት በቀር እኛን በመ​ሰ​ለ​በት ሁሉ የተ​ፈ​ተነ ነው።</verse>
				<verse number="16">እን​ግ​ዲህ ምሕ​ረ​ትን እን​ድ​ን​ቀ​በል፥ በሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ንም ጊዜ የሚ​ረ​ዳ​ንን ጸጋ እን​ድ​ና​ገኝ፥ ወደ ጸጋው ዙፋን በእ​ም​ነት እን​ቅ​ረብ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">ሊቀ ካህ​ናት ሁሉ ስለ ኀጢ​አት መባ​ንና መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሊያ​ቀ​ርብ ከሰው ተመ​ርጦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሆ​ነው ነገር ሁሉ ስለ ሰው ይሾ​ማ​ልና።</verse>
				<verse number="2">እርሱ ራሱም ደካማ ነውና ባለ​ማ​ወ​ቃ​ቸው ከሳቱ ሰዎች ጋር መከ​ራን ሊቀ​በል ይች​ላል።</verse>
				<verse number="3">በዚ​ህም ምክ​ን​ያት ስለ ሕዝብ እን​ደ​ሚ​ያ​ቀ​ርብ እን​ዲሁ ስለ ራሱ ደግሞ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ስለ ኀጢ​አት ማቅ​ረብ ይገ​ባ​ዋል።</verse>
				<verse number="4">እንደ አሮ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተ​ጠራ በቀር፥ ማንም ለራሱ ክብ​ርን የሚ​ወ​ስድ የለም።</verse>
				<verse number="5">እን​ዲሁ ክር​ስ​ቶ​ስም ሊቀ ካህ​ናት ይሆን ዘንድ ራሱን ያከ​በረ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን፥ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔም ዛሬ ወለ​ድ​ሁህ” ያለው እርሱ ራሱ ነው።</verse>
				<verse number="6">ዳግ​መ​ኛም፥ “እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት የዘ​ለ​ዓ​ለም ካህን አንተ ነህ” ይላል።</verse>
				<verse number="7">እር​ሱም ሥጋ ለብሶ በዚህ ዓለም በነ​በ​ረ​በት ጊዜ፥ በታ​ላቅ ጩኸ​ትና እንባ ከሞት ሊያ​ድ​ነው ወደ​ሚ​ች​ለው ጸሎ​ት​ንና ምል​ጃን አቀ​ረበ፤ ጽድ​ቁ​ንም ሰማው።</verse>
				<verse number="8">ልጅም ቢሆን መከ​ራን ስለ ተቀ​በለ መታ​ዘ​ዝን ዐወቀ።</verse>
				<verse number="9">ከተ​ፈ​ጸ​መም በኋላ ለሚ​ታ​ዘ​ዝ​ለት ሁሉ ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ የዘ​ለ​ዓ​ለም መድ​ኅን ሆነ።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት የዘ​ለ​ዓ​ለም ሊቀ ካህ​ናት አለው።</verse>
				<verse number="11">ስለ እር​ሱም የም​ን​ና​ገ​ረው ብዙ ነገር አለን፤ ጆሮ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ስለ ፈዘዙ በቃል ልን​ተ​ረ​ጕ​መው ጭንቅ ነው።</verse>
				<verse number="12">መም​ህ​ራን ልት​ሆኑ ሲገ​ባ​ችሁ፥ ካመ​ና​ችሁ ጀምሮ በት​ም​ህ​ርት ላይ የቈ​ያ​ችሁ ስለ ሆነ፥ እስከ ዛሬም ገና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃ​ሉን መጀ​መ​ሪያ ትም​ህ​ርት ሊያ​ስ​ተ​ም​ሩ​አ​ችሁ ትወ​ዳ​ላ​ችሁ፤ ወተ​ት​ንም ሊግ​ቱ​አ​ችሁ ትሻ​ላ​ችሁ፤ ጽኑ ምግ​ብ​ንም አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="13">ወተ​ትን የሚ​ጋት ሁሉ ሕፃን ስለ​ሆነ፥ የጽ​ድ​ቅን ቃል ሊያ​ውቅ አይ​ሻም።</verse>
				<verse number="14">ጠን​ካራ ምግብ ግን መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ዉን ለመ​ለ​የት በሥ​ራ​ቸው የለ​መደ ልቡና ላላ​ቸው ለፍ​ጹ​ማን ሰዎች ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">ስለ​ዚ​ህም የክ​ር​ስ​ቶ​ስን የነ​ገ​ሩን መጀ​መ​ሪያ ትተን ወደ ፍጻ​ሜው እን​ሂድ፤ እን​ግ​ዲህ ደግሞ ሌላ መሠ​ረት እን​ዳ​ትሹ ዕወቁ፤ ይኸ​ውም ከሞት ሥራ ለመ​መ​ለስ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለማ​መን፥</verse>
				<verse number="2">ጥም​ቀ​ትን፥ በአ​ን​ብ​ሮተ እድ መሾ​ምን፥ የሙ​ታ​ንን ትን​ሣ​ኤና የዘ​ለ​ዓ​ለም ፍር​ድን ለመ​ማር ነው።</verse>
				<verse number="3">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቢፈ​ቅድ ይህን ባደ​ረ​ግን ነበር።</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን አንድ ጊዜ ብር​ሃን የበ​ራ​ላ​ቸ​ውን፥ ሰማ​ያ​ዊ​ው​ንም ስጦታ የቀ​መ​ሱ​ትን፥ ከመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ተካ​ፋ​ዮች ሆነው የነ​በ​ሩ​ትን፥</verse>
				<verse number="5">መል​ካ​ሙን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል፥ የሚ​መ​ጣ​ው​ንም የዓ​ለ​ምን ኀይል የቀ​መ​ሱ​ትን፥</verse>
				<verse number="6">በኋ​ላም የካ​ዱ​ትን እንደ ገና ለን​ስሓ እነ​ር​ሱን ማደስ አይ​ቻ​ልም፤ ራሳ​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ ይሰ​ቅ​ሉ​ታ​ልና፥ ያዋ​ር​ዱ​ት​ማ​ልና።</verse>
				<verse number="7">ምድ​ርም በእ​ር​ስዋ የሚ​ወ​ር​ደ​ውን ዝናም ከጠ​ጣች፥ ያን​ጊዜ ስለ እርሱ ያረ​ሱ​ላ​ትን መላ​ካም ቡቃያ ታበ​ቅ​ላ​ለች፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘን​ድም በረ​ከ​ትን ታገ​ኛ​ለች።</verse>
				<verse number="8">እሾ​ህ​ንና ኵር​ን​ች​ትን ብታ​ወጣ ግን የተ​ጣ​ለች ናት፤ ለመ​ር​ገ​ምም የቀ​ረ​በች ናት፤ ፍጻ​ሜ​ዋም ለመ​ቃ​ጠል ይሆ​ናል።</verse>
				<verse number="9">የተ​መ​ረ​ጣ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ምንም እን​ኳን እን​ዲህ ብን​ላ​ችሁ ሕይ​ወት ወዳ​ለ​ባት ትም​ህ​ርት እን​ድ​ት​ቀ​ርቡ እን​ታ​መ​ን​ባ​ች​ኋ​ለን።</verse>
				<verse number="10">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱ​ሳ​ንን ስለ አገ​ለ​ገ​ላ​ችሁ፥ እስከ አሁ​ንም ስለ​ም​ታ​ገ​ለ​ግ​ሉ​አ​ቸው ያደ​ረ​ጋ​ች​ት​ሁን ሥራ፥ በስ​ሙም ያሳ​ያ​ች​ሁ​ትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዐመ​ፀኛ አይ​ደ​ለ​ምና።</verse>
				<verse number="11">ነገር ግን ሁላ​ች​ሁም በዚች ተስ​ፋ​ችሁ እን​ዲሁ ትጋ​ታ​ች​ሁን እስከ መጨ​ረ​ሻው ታሳዩ ዘንድ እን​ወ​ዳ​ለን።</verse>
				<verse number="12">ዳተ​ኞች እን​ዳ​ት​ሆኑ በሃ​ይ​ማ​ኖ​ትና በት​ዕ​ግ​ሥት ተስ​ፋ​ቸ​ውን የወ​ረ​ሱ​ትን ሰዎች ምሰ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="13">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ብ​ር​ሃም ተስ​ፋ​ዉን በሰ​ጠው ጊዜ ይም​ል​በት ዘንድ ከእ​ርሱ የሚ​በ​ልጥ ሌላ ባይ​ኖር፥ በራሱ ማለ።</verse>
				<verse number="14">እን​ዲህ ብሎ፦“ መባ​ረ​ክን እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፥ ማብ​ዛ​ት​ንም አበ​ዛ​ሃ​ለሁ።”</verse>
				<verse number="15">ከዚ​ህም በኋላ ታግሦ ተስ​ፋ​ዉን አገኘ።</verse>
				<verse number="16">ሰው ግን ከእ​ርሱ በሚ​በ​ል​ጠው ይም​ላል፤ የክ​ር​ክ​ርም መነ​ሻው በመ​ሐላ ይፈ​ጸ​ማል።</verse>
				<verse number="17">ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተስ​ፋ​ውን ለሚ​ወ​ርሱ ሰዎች ምክ​ሩን እን​ደ​ማ​ይ​ለ​ውጥ ሊገ​ልጥ ወደደ፤ እን​ደ​ማ​ይ​ለ​ው​ጥም በመ​ሓላ አጸ​ናው።</verse>
				<verse number="18">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይ​ቻ​ልም፤ በእ​ርሱ ለተ​ማ​ፀን ተጠ​ብ​ቆ​ልን ባለ ተስ​ፋ​ች​ንም ማመ​ንን ላጸ​ናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።</verse>
				<verse number="19">ይህ​ችም ተስፋ ነፍ​ሳ​ችን እን​ዳ​ት​ነ​ዋ​ወጥ እንደ መል​ሕቅ የም​ታ​ጸና ናት፤</verse>
				<verse number="20">እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሊቀ ካህ​ናት ሆኖ ሐዋ​ር​ያ​ችን ኢየ​ሱስ ከእኛ በፊት ወደ ገባ​ባት መጋ​ረ​ጃም ውስጥ የም​ታ​ስ​ገባ ናት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">የሳ​ሌም ንጉሥ፥ የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ካህን የሆነ፥ ይህ መልከ ጼዴቅ፥ አብ​ር​ሃም ነገ​ሥ​ታ​ትን ድል ነሥቶ በተ​መ​ለሰ ጊዜ ከእ​ርሱ ጋር ተገ​ና​ኝቶ ባረ​ከው።</verse>
				<verse number="2">አብ​ር​ሃ​ምም ከገ​ን​ዘቡ ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ ሰጠው፤ መጀ​መ​ሪያ የስሙ ትር​ጓሜ የጽ​ድቅ ንጉሥ ነበር፤ በኋ​ላም የሳ​ሌም ንጉሥ ተባለ፤ የሰ​ላም ንጉሥ ማለት ነው።</verse>
				<verse number="3">አባት የለ​ውም፤ እና​ትም የለ​ች​ውም፤ ትው​ል​ዱም አይ​ታ​ወ​ቅም፤ ለዘ​መኑ መጀ​መ​ሪያ፥ ለሕ​ይ​ወ​ቱም መጨ​ረሻ የለ​ውም፤ ክህ​ነቱ የወ​ልደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሳሌ ሆኖ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።</verse>
				<verse number="4">የአ​ባ​ቶች አለቃ አብ​ር​ሃም ከም​ር​ኮው ሁሉ የሚ​ሻ​ለ​ውን ዐሥ​ራት የሰ​ጠ​ውን የዚ​ህን ካህን ክብር ታያ​ላ​ች​ሁን?</verse>
				<verse number="5">ከሌዊ ልጆ​ችም፥ ክህ​ነ​ትን የሚ​ቀ​በ​ሉት ከሕ​ዝቡ ማለት ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው፥ እነ​ርሱ ምንም ከአ​ብ​ር​ሃም ወገብ ቢወጡ ከእ​ነ​ርሱ ዐሥ​ራ​ትን በሕግ እን​ዲ​ያ​ስ​ወጡ ትእ​ዛዝ አላ​ቸው።</verse>
				<verse number="6">ወገ​ና​ቸው ላይ​ደለ ለእ​ርሱ ግን አብ​ር​ሃም ዐሥ​ራ​ትን ሰጠው፤ እር​ሱም ተስፋ ያለው አብ​ር​ሃ​ምን ባረ​ከው።</verse>
				<verse number="7">ነገር ግን ታላቁ ታና​ሹን እን​ደ​ሚ​ባ​ር​ከው ያለ ጥር​ጥር ይታ​ወ​ቃል።</verse>
				<verse number="8">በዚ​ህስ የሚ​ሞት ሰው ዐሥ​ራ​ትን ይቀ​በ​ላል፤ በወ​ዲ​ያው ግን ሕያው እንደ ሆነ መጽ​ሐፍ የሚ​መ​ሰ​ክ​ር​ለት እርሱ ይቀ​በ​ላል።</verse>
				<verse number="9">እንደ ተነ​ገ​ረም ዐሥ​ራ​ትን የሚ​ቀ​በል ሌዊ ስን​ኳን በአ​ብ​ር​ሃም በኩል ዐሥ​ራ​ትን ሰጠ።</verse>
				<verse number="10">መልከ ጼዴቅ በተ​ገ​ና​ኘው ጊዜ ገና በአ​ባቱ በአ​ብ​ር​ሃም ወገብ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="11">እን​ግ​ዲህ ሕዝቡ በሌዊ ክህ​ነት የተ​መ​ሠ​ረ​ተን ሕግ ተቀ​ብ​ለ​ዋ​ልና በዚያ ክህ​ነት ፍጹ​ም​ነት የተ​ገኘ ቢሆን፥ እንደ አሮን ሹመት የማ​ይ​ቈ​ጠር፥ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ግን የሆነ ሌላ ካህን ሊነሣ ወደ ፊት ስለ​ምን ያስ​ፈ​ል​ጋል?</verse>
				<verse number="12">ክህ​ነ​ታ​ቸው ታልፍ ዘንድ አላ​ትና፤ ክህ​ነ​ታ​ቸው ካለ​ፈ​ችም ኦሪ​ታ​ቸው ታል​ፋ​ለች።</verse>
				<verse number="13">ይህ ነገር የተ​ነ​ገ​ረ​ለት እርሱ በሌላ ወገን ተካ​ፍ​ሎ​አ​ልና፥ ከዚ​ያም መሠ​ዊ​ያ​ውን ያገ​ለ​ገለ ማንም የለም።</verse>
				<verse number="14">ጌታ​ችን ከይ​ሁዳ ነገድ እንደ ወጣ የተ​ገ​ለጠ ነውና፤ ስለ​ዚ​ህም ነገድ ሙሴ ምንም እን​ኳን ስለ ክህ​ነት አል​ተ​ና​ገ​ረም።</verse>
				<verse number="15">ይል​ቁ​ንም ይህ እጅግ ያስ​ረ​ዳል፤ በመ​ልከ ጼዴቅ ክህ​ነት አም​ሳል ሌላ ካህን ይነ​ሣል ብሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="16">ይኸ​ውም በማ​ያ​ልፍ ሕይ​ወት ኀይል እንጂ ለሥ​ጋና ለደም በተ​ሠራ ሕግ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="17">“እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት የዘ​ለ​ዓ​ለም ካህን አንተ ነህ” ብሎ ይመ​ሰ​ክ​ራ​ልና።</verse>
				<verse number="18">ስለ​ዚ​ህም የም​ት​ደ​ክም፥ የማ​ት​ጠ​ቅ​ምም ስለ ሆነች የቀ​ደ​መ​ችው ትእ​ዛዝ ተሽ​ራ​ለች።</verse>
				<verse number="19">ኦሪት ምንም ግዳጅ አል​ፈ​ጸ​መ​ች​ምና፤ ነገር ግን በእ​ር​ስዋ ፋንታ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ን​ቀ​ር​ብ​በት ከእ​ር​ስዋ የሚ​ሻል ተስፋ ገብ​ቶ​አል።</verse>
				<verse number="20">እርሱ ያለ መሐላ አል​ሆ​ነም፤ ያለ መሐላ የተ​ሾሙ ካህ​ናት አሉና።</verse>
				<verse number="21">በመ​ሐላ የሾ​መ​ውን ግን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማለ፥ አይ​ጸ​ጸ​ት​ምም፤ አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት የዘ​ለ​ዓ​ለም ካህን ነህ” አለው።</verse>
				<verse number="22">ኢየ​ሱስ ይህን ያህል በም​ት​በ​ል​ጥና ከፍ ባለች ሹመት ተሾመ።</verse>
				<verse number="23">ለእ​ነ​ዚ​ያስ ብዙ​ዎች ካህ​ናት ነበ​ሩ​አ​ቸው፤ ሞት ይሽ​ራ​ቸው፥ እን​ዲ​ኖ​ሩም አያ​ሰ​ና​በ​ታ​ቸ​ውም ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="24">እርሱ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል፤ ክህ​ነቱ አይ​ሻ​ር​ምና።</verse>
				<verse number="25">ዘወ​ትር በእ​ርሱ በኩል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ር​ቡ​ትን ሊያ​ድ​ና​ቸው ይቻ​ለ​ዋል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ሕያው ነውና ያስ​ታ​ር​ቃ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="26">ቅዱ​ስና ያለ ተን​ኰል፥ ነው​ርም የሌ​ለ​በት፥ ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችም የተ​ለየ፥ ከሰ​ማ​ያ​ትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ ሊቀ ካህ​ናት ይገ​ባ​ናል።</verse>
				<verse number="27">እር​ሱም እንደ እነ​ዚያ ሊቃነ ካህ​ናት አስ​ቀ​ድሞ ስለ ራሱ ኀጢ​አት በኋ​ላም ስለ ሕዝቡ ኀጢ​አት ዕለት ዕለት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሊያ​ቀ​ርብ አያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ውም፤ ራሱን ባቀ​ረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድ​ር​ጎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="28">ኦሪ​ትስ የሚ​ሞት ሰውን ሊቀ ካህ​ናት አድ​ርጋ ትሾ​ማ​ለች፤ ከኦ​ሪት በኋላ የመ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ሐላ ቃሉ ግን ዘለ​ዓ​ለም የማ​ይ​ለ​ወጥ ፍጹም ወል​ድን ካህን አድ​ርጎ ሾመ​ልን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">ከተ​ና​ገ​ር​ነ​ውም ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰ​ማ​ያት በግ​ር​ማው ዙፋን ቀኝ የተ​ቀ​መጠ እን​ዲህ ያለ ሊቀ ካህ​ናት አለን።</verse>
				<verse number="2">እር​ሱም የመ​ቅ​ደ​ስና የእ​ው​ነ​ተ​ኛ​ይቱ ድን​ኳን አገ​ል​ጋይ ነው፤ እር​ስ​ዋም በሰው ሳይ​ሆን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ተ​ከ​ለች ናት።</verse>
				<verse number="3">ሊቀ ካህ​ናት ሁሉ መባ​ንና መሥ​ዋ​ዕ​ትን ያቀ​ርብ ዘንድ ይሾ​ማል፤ ለዚ​ህም ደግሞ የሚ​ያ​ቀ​ር​በው አን​ዳች ነገር ይኖ​ረው ዘንድ ይገ​ባል።</verse>
				<verse number="4">በም​ድር ቢሆን ኖሮ፥ ሊቀ ካህ​ናት ባል​ሆ​ነም ነበር፤ በኦ​ሪት ሕግ መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ርቡ ካህ​ናት በእ​ር​ስዋ አሉና።</verse>
				<verse number="5">እነ​ር​ሱም ሙሴ ድን​ኳ​ኒ​ቱን ሲሠራ ሳለ እንደ ተረዳ፥ ለሰ​ማ​ያዊ ነገር ምሳ​ሌና ጥላ የሚ​ሆ​ነ​ውን ያገ​ለ​ግ​ላሉ፤ “በተ​ራ​ራው እንደ ተገ​ለ​ጠ​ልህ ምሳሌ ሁሉን ታደ​ርግ ዘንድ ተጠ​ን​ቀቅ” ብሎት ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="6">ዛሬ ግን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የም​ት​በ​ል​ጠ​ውን አገ​ል​ግ​ሎት ገን​ዘብ አደ​ረገ፤ ለታ​ላ​ቂቱ ሥር​ዐ​ትም መካ​ከ​ለኛ ሆነ፤ የም​ት​በ​ል​ጠ​ው​ንም ተስፋ ሠራ።</verse>
				<verse number="7">ፊተ​ኛ​ይቱ ያለ ነቀፋ ብት​ሆን ኖሮ ሁለ​ተ​ኛ​ይ​ቱን ባል​ፈ​ለ​ገም ነበር።</verse>
				<verse number="8">ነገር ግን እነ​ር​ሱን ነቅፎ እን​ዲህ አለ፥ “እነሆ፥ ለቤተ እስ​ራ​ኤ​ልና ለቤተ ይሁ​ዳም አዲስ ኪዳን የም​ሠ​ራ​በት ዘመን ይመ​ጣል ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="9">እጃ​ቸ​ውን ይዤ ከም​ድረ ግብፅ ባወ​ጣ​ኋ​ቸው ጊዜ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው እንደ ገባ​ሁት እን​ደ​ዚያ ያለ ኪዳን አይ​ደ​ለም፤ እነ​ርሱ በኪ​ዳኔ አል​ኖ​ሩ​ምና፤ እኔም ቸል ብያ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="10">ከእ​ነ​ዚያ ዘመ​ናት በኋላ ለቤተ እስ​ራ​ኤል የም​ገ​ባው ቃል ይህ ነው፦ ሕጌን በል​ባ​ቸው አሳ​ድ​ራ​ለሁ፤ በሕ​ሊ​ና​ቸ​ውም እጽ​ፈ​ዋ​ለሁ፤ አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝቤ ይሆ​ኑ​ኛል ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።</verse>
				<verse number="11">እን​ግ​ዲህ አንዱ ሌላ​ውን አያ​ስ​ተ​ም​ርም፤ ወን​ድ​ምም ወን​ድ​ሙን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዕወቅ ብሎ አያ​ስ​ተ​ም​ርም፤ ከታ​ናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያው​ቁ​ኛ​ልና።</verse>
				<verse number="12">ዐመ​ፃ​ቸ​ውን እም​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ደግሜ አላ​ስ​ብም።”</verse>
				<verse number="13">አዲስ ትእ​ዛዝ በማ​ለቱ የቀ​ደ​መ​ች​ቱን አስ​ረ​ጃት፤ አሮ​ጌና ውራጅ የሆ​ነ​ውስ ለጥ​ፋት የቀ​ረበ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">ፊተ​ኛ​ይ​ቱም ደግሞ የአ​ገ​ል​ግ​ሎት ሥር​ዐ​ትና የዚህ ዓለም የሆ​ነው መቅ​ደስ ነበ​ራት።</verse>
				<verse number="2">የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዪ​ቱም ድን​ኳን ተዘ​ጋ​ጅታ ነበ​ርና፥ በእ​ር​ስ​ዋም ቅድ​ስት በም​ት​ባ​ለው ውስጥ መቅ​ረ​ዙና ጠረ​ጴ​ዛው፥ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱም ኅብ​ስት ነበ​ረ​ባት።</verse>
				<verse number="3">ከሁ​ለ​ተ​ኛው መጋ​ረጃ በስ​ተ​ኋላ የነ​በ​ረ​ች​ውን የው​ስ​ጠ​ኛ​ዪ​ቱን ድን​ኳን ግን ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳን ይሉ​አት ነበር።</verse>
				<verse number="4">በው​ስ​ጥ​ዋም የወ​ርቅ ማዕ​ጠ​ን​ትና ሁለ​ን​ተ​ና​ዋን በወ​ርቅ የለ​በ​ጡ​አት፥ የኪ​ዳን ታቦት፥ መና ያለ​ባት የወ​ርቅ መሶ​ብና የለ​መ​ለ​መ​ችው የአ​ሮን በትር፥ የኪ​ዳ​ኑም ጽላት ነበ​ሩ​ባት።</verse>
				<verse number="5">በላ​ይ​ዋም ማስ​ተ​ስ​ረ​ያ​ውን የሚ​ጋ​ርዱ የክ​ብር ኪሩ​ቤል ነበሩ፤ ነገር ግን በየ​መ​ልኩ እና​ገ​ረው ዘንድ ዛሬ ጊዜው አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="6">ሥር​ዐቱ፥ ዝግ​ጅ​ቱም እን​ዲህ ነበር፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዪ​ቱም ድን​ኳን በየ​ጊ​ዜው አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውን ይፈ​ጽሙ ዘንድ፥ ካህ​ናት ዘወ​ትር ይገቡ ነበር።</verse>
				<verse number="7">ወደ ሁለ​ተ​ኛ​ዪቱ ክፍል ግን ሊቀ ካህ​ናቱ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ለማ​ስ​ተ​ስ​ረይ ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን ደም ይዞ፥ በየ​ዓ​መቱ አንድ ጊዜ ብቻ​ውን ይገባ ነበር።</verse>
				<verse number="8">ፊተ​ኛ​ይ​ቱም ድን​ኳን በዚህ ገና ቆማ ሳለች፥ ወደ ቅድ​ስት የሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ገና እን​ዳ​ል​ተ​ገ​ለጠ መን​ፈስ ቅዱስ ያሳ​ያል።</verse>
				<verse number="9">ነገር ግን ለሚ​ያ​ቀ​ር​በው ሰው ግዳጅ መፈ​ጸም የማ​ይ​ቻ​ለ​ውን መባና መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡ​በት የነ​በ​ረው ለዚህ ዘመን ምሳሌ ሆነ።</verse>
				<verse number="10">እነ​ዚ​ህም እስከ መታ​ደስ ዘመን ድረስ የተ​ደ​ረጉ፥ ስለ ምግ​ብና ስለ መጠ​ጥም፥ ስለ ልዩ ልዩ ጥም​ቀ​ትም የሚ​ሆኑ የሥጋ ሥር​ዐ​ቶች ብቻ ናቸው።</verse>
				<verse number="11">ክር​ስ​ቶስ ግን ለም​ት​መ​ጣ​ይቱ መል​ካም ነገር ሊቀ ካህ​ናት ሆኖ፥ የሰው እጅ ወደ አል​ሠ​ራት፥ በዚህ ዓለም ወደ አል​ሆ​ነ​ችው፥ ከፊ​ተ​ኛ​ዪቱ ወደ​ም​ት​በ​ል​ጠ​ውና ወደ​ም​ት​ሻ​ለው ድን​ኳን፥</verse>
				<verse number="12">የዘ​ለ​ዓ​ለም መድ​ኀ​ኒ​ትን ገን​ዘብ አድ​ርጎ፥ በገዛ ደሙ አንድ ጊዜ ወደ መቅ​ደስ ገባ እንጂ በላ​ምና በፍ​የል ደም አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="13">የላ​ምና የፍ​የል ደም፥ በረ​ከ​ሱ​ትም ላይ የሚ​ረጭ የጊ​ደር አመድ፥ የሚ​ያ​ነ​ጻና የረ​ከ​ሱ​ት​ንም ሥጋ​ቸ​ውን የሚ​ቀ​ድ​ሳ​ቸው ከሆነ፥</verse>
				<verse number="14">ነውር የሌ​ለው ሆኖ፥ በዘ​ለ​ዓ​ለም መን​ፈስ ራሱን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ረበ የክ​ር​ስ​ቶስ ደም ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ከው ዘንድ ሕሊ​ና​ች​ንን ከሞት ሥራ እን​ዴት ይልቅ ያነጻ ይሆን?</verse>
				<verse number="15">ስለ​ዚህ ኢየ​ሱስ ሞትን ተቀ​ብሎ፥ በቀ​ደ​መው ሥር​ዐት ስተው የነ​በ​ሩ​ትን ያድ​ና​ቸው ዘንድ ወደ ዘለ​ዓ​ለም ርስ​ቱም የጠ​ራ​ቸው ተስ​ፋ​ውን ያገኙ ዘንድ፥ ለአ​ዲ​ሲቱ ኪዳን መካ​ከ​ለኛ ሆነ።</verse>
				<verse number="16">ኑዛዜ ያለ እን​ደ​ሆነ የተ​ና​ዛዡ ሰው ሞት ይመጣ ዘንድ ግድ ነው።</verse>
				<verse number="17">የሙ​አች ሰው ኑዛዜ የጸ​ናች ናት፤ ተና​ዛዡ በሕ​ይ​ወት ባለ​በት ጊዜ አት​ጠ​ቅ​ም​ምና።</verse>
				<verse number="18">ስለ​ዚ​ህም ፊተ​ኛው ኪዳን እንኳ ያለ ደም አል​ከ​በ​ረም።</verse>
				<verse number="19">ሙሴ የኦ​ሪ​ትን ትእ​ዛዝ ሁሉ ለመ​ላው ሕዝብ ከነ​ገረ በኋላ፥ የላ​ምና የፍ​የል ደም ከውኃ ጋር ቀላ​ቅሎ፥ ቀይ የበግ ጠጕ​ርና የስ​ሚዛ ቅጠል ነክሮ መጽ​ሐፈ ኦሪ​ቱ​ንና ሕዝ​ቡን ሁሉ ይረጭ ነበር።</verse>
				<verse number="20">“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዛ​ችሁ የኪ​ዳኑ ደም ይህ ነው” ይላ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="21">ድን​ኳ​ኑ​ንና የመ​ገ​ል​ገ​ያ​ውን ዕቃ ሁሉ በደሙ ይረጭ ነበር።</verse>
				<verse number="22">ደግ​ሞም በቀ​ረ​በው ሁሉ እን​ዲህ ያደ​ርግ ነበር፥ በኦ​ሪት ሕግ ሁሉ በደም ይነጻ ነበር፤ ደም ሳይ​ረጭ ግን አይ​ሰ​ረ​ይም ነበር።</verse>
				<verse number="23">በሰ​ማይ ባለው አም​ሳል የተ​ሠ​ራው ይህ ሥራ፥ በዚህ ደም የሚ​ነጻ ከሆነ፥ ይህ ሰማ​ያዊ መሥ​ዋ​ዕ​ትስ ከዚህ ይበ​ል​ጣል።</verse>
				<verse number="24">ክር​ስ​ቶስ በእጅ ወደ ተሠ​ራች የእ​ው​ነ​ተ​ኛ​ይቱ ምሳሌ ወደ​ም​ት​ሆን ቅድ​ስት አል​ገ​ባ​ምና፥ ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ፥ ወደ እር​ስዋ ወደ ሰማይ ገባ።</verse>
				<verse number="25">ሊቀ ካህ​ናቱ ያደ​ር​ገው እንደ ነበረ፥ በያ​መ​ቱም ደም ይዞ ወደ ቅድ​ስት ይገባ እንደ ነበረ ዘወ​ትር ራሱን የሚ​ሠዋ አይ​ደ​ለም።</verse>
				<verse number="26">ይህስ ባይ​ሆን ዓለም ከተ​ፈ​ጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ በሞተ ነበር፤ አሁን ግን በዓ​ለም ፍጻሜ፥ ራሱን በመ​ሠ​ዋት ኀጢ​አ​ትን ይሽ​ራት ዘንድ አንድ ጊዜ ተገ​ለጠ።</verse>
				<verse number="27">ለሰው አንድ ጊዜ ሞት፥ ከዚ​ያም በኋላ ፍርድ እን​ደ​ሚ​ጠ​ብ​ቀው፥</verse>
				<verse number="28">እን​ዲሁ ክር​ስ​ቶ​ስም የብ​ዙ​ዎ​ችን ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ ራሱን አንድ ጊዜ ሠዋ፤ በኋላ ግን ያድ​ና​ቸው ዘንድ ተስፋ ለሚ​ያ​ደ​ር​ጉት ያለ ኀጢ​አት ይገ​ለ​ጥ​ላ​ቸ​ዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እው​ነ​ተኛ አም​ሳል ሳይ​ሆን የነ​ገር ጥላ አለ​ውና፤ ስለ​ዚ​ህም በየ​ዓ​መቱ ዘወ​ትር በሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት በዚያ መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ቀ​ር​ቡ​ትን ሊፈ​ጽም ከቶ አይ​ች​ልም።</verse>
				<verse number="2">ይህስ ባይ​ሆን ከሚ​ሠ​ዉት መሥ​ዋ​ዕት ባረፉ ነበር፥ ለሚ​ሠ​ዉት ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ቸው ነበ​ርና፥ ባአ​ንድ ጊዜም ያነ​ጻ​ቸው ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="3">ነገር ግን በዚ​ያው መሥ​ዋ​ዕት በየ​ዓ​መቱ የኀ​ጢ​አት መታ​ሰ​ቢያ አድ​ር​ገው የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ነበ​ራ​ቸው።</verse>
				<verse number="4">የላ​ምና የፍ​የል ደም ኀጢ​አ​ትን ሊያ​ስ​ተ​ሰ​ርይ አይ​ች​ል​ምና።</verse>
				<verse number="5">ስለ​ዚ​ህም ወደ ዓለም በሚ​መ​ጣ​በት ጊዜ እን​ዲህ አለ፥ “መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና ቍር​ባ​ንን አል​ወ​ደ​ድ​ህም፤ ሥጋን አለ​በ​ስ​ኸኝ እንጂ።</verse>
				<verse number="6">በሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና ስለ ኀጢ​አት በሚ​ቀ​ር​በው መሥ​ዋ​ዕት ደስ አላ​ለ​ህም።</verse>
				<verse number="7">ያን​ጊዜ እነሆ፥ በመ​ጽ​ሐፍ ራስ ስለ እኔ እንደ ተጻፈ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ ፈቃ​ድ​ህን አደ​ርግ ዘንድ መጥ​ቻ​ለሁ አልሁ።”</verse>
				<verse number="8">በዚህ ላይ “መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና መባን፥ በሙሉ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም፥ ስለ ኀጢ​አ​ትም የሚ​ሠዋ መሥ​ዋ​ዕ​ትን አል​ወ​ደ​ድ​ህም፤ በእ​ር​ሱም ደስ አላ​ለ​ህም” ብሎ ተና​ገረ፤ እነ​ዚ​ህም እንደ ሕግ የሚ​ቀ​ርቡ ናቸው።</verse>
				<verse number="9">ከዚህ በኋላ፥ “አም​ላኬ ሆይ፥ ፈቃ​ድ​ህን አደ​ርግ ዘንድ እነሆ፥ መጣሁ” አለ፤ ይህ ቃል የኋ​ለ​ኛ​ውን ያቆም ዘንድ የፊ​ተ​ኛ​ውን ያፈ​ር​ሳል።</verse>
				<verse number="10">በፈ​ቃ​ዱም አንድ ጊዜ በተ​ደ​ረ​ገው በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በሥ​ጋዉ ቍር​ባን ተቀ​ደ​ስን።</verse>
				<verse number="11">ሊቀ ካህ​ና​ትም ሁሉ ዘወ​ትር እያ​ገ​ለ​ገለ ይቆም ነበር፤ ፈጽሞ ኀጢ​አት ማስ​ተ​ስ​ረይ የማ​ይ​ቻ​ላ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ያን መሥ​ዋ​ዕ​ቶች ብቻም ይሠዋ ነበር።</verse>
				<verse number="12">እርሱ ግን ስለ ኀጢ​አት አን​ድን መሥ​ዋ​ዕት ለዘ​ለ​ዓ​ለም አቅ​ርቦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀኝ ተቀ​መጠ።</verse>
				<verse number="13">እን​ግ​ዲህ ጠላ​ቶቹ ከእ​ግሩ በታች እስ​ኪ​ወ​ድቁ ድረስ ይጠ​ብ​ቃል።</verse>
				<verse number="14">ለሚ​ቀ​ደ​ሱ​ትም ለዘ​ለ​ዓ​ለም የም​ት​ሆን አን​ዲት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋ።</verse>
				<verse number="15">መን​ፈስ ቅዱ​ስም ምስ​ክ​ራ​ችን ነው።</verse>
				<verse number="16">“ከእ​ነ​ዚያ ወራ​ቶች በኋላ የም​ገ​ባ​ላ​ቸው ኪዳን ይህቺ ናት ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ሕጌን በል​ባ​ቸው አኖ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በል​ቡ​ና​ቸ​ውም እጽ​ፈ​ዋ​ለሁ ካለ በኋላ።</verse>
				<verse number="17">ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንና በደ​ላ​ቸ​ውን ደግሜ አላ​ስ​ብ​ባ​ቸ​ውም” ብሏል።</verse>
				<verse number="18">እን​ዲ​ህም ኀጢ​አት የሚ​ሰ​ረይ ከሆነ፥ እን​ግ​ዲህ ወዲህ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት አያ​ስ​ፈ​ል​ግም።</verse>
				<verse number="19">እን​ግ​ዲህ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ደም ወደ መቅ​ደስ ለመ​ግ​ባት ባለ​ሙ​አ​ል​ነት አለን።</verse>
				<verse number="20">በሥ​ጋው መጋ​ረጃ በኩል የሕ​ይ​ወ​ት​ንና የጽ​ድ​ቅን መን​ገድ ፈጽሞ አድ​ሶ​ል​ና​ልና።</verse>
				<verse number="21">በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ታላቅ ካህን አለን።</verse>
				<verse number="22">እን​ግ​ዲህ ከክፉ ሕሊና ለመ​ን​ጻት ልባ​ች​ንን ተረ​ጭ​ተን፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ን​ንም በጥሩ ውኃ ታጥ​በን በተ​ረ​ዳ​ን​በት እም​ነት በቅን ልብ እን​ቅ​ረብ።</verse>
				<verse number="23">እን​ግ​ዲህ የማ​ይ​ና​ወ​ጠ​ውን የተ​ስ​ፋ​ች​ንን እም​ነት እና​ጽና፤ ተስፋ የሰጠ እርሱ የታ​መነ ነውና።</verse>
				<verse number="24">በፍ​ቅ​ርና በበጎ ምግ​ባ​ርም ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ችን ጋር እን​ፎ​ካ​ከር።</verse>
				<verse number="25">ሌሎች ልማድ አድ​ር​ገው እንደ ያዙት ማኅ​በ​ራ​ች​ንን አን​ተው፤ እርስ በር​ሳ​ችን እን​መ​ካ​ከር እንጂ፤ ይል​ቁ​ንም ቀኑ ሲቀ​ርብ እያ​ያ​ችሁ አብ​ል​ጣ​ችሁ ይህን አድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="26">እው​ነ​ትን ካወ​ቅ​ናት በኋላ፥ ተጋ​ፍ​ተን ብን​በ​ድል ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት አይ​ኖ​ርም።</verse>
				<verse number="27">ነገር ግን የሚ​ያ​ስ​ፈራ ፍርድ ከሓ​ዲ​ዎ​ች​ንም የሚ​በ​ላ​ቸው የቅ​ናት እሳት ይጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="28">ከሙሴ ሕግ የተ​ላ​ለፈ ቢኖር ሁለት፥ ወይም ሦስት ምስ​ክ​ሮች ከመ​ሰ​ከ​ሩ​በት ያለ ምሕ​ረት ይሞ​ታል።</verse>
				<verse number="29">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ የከዳ፥ ያን​ንም የተ​ቀ​ደ​ሰ​በ​ትን የኪ​ዳ​ኑን ደም እንደ ርኩስ ነገር የቈ​ጠረ፥ የጸ​ጋ​ው​ንም መን​ፈስ ያክ​ፋፋ እን​ዴት ይልቅ የሚ​ብስ ቅጣት የሚ​ገ​ባው ይመ​ስ​ላ​ች​ኋል?</verse>
				<verse number="30">“እኔ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤ እኔም ብድ​ራ​ትን እመ​ል​ሳ​ለሁ፥” ያለ​ውን እና​ው​ቀ​ዋ​ለ​ንና፤ ዳግ​መ​ኛም “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ላይ ይፈ​ር​ዳል።”</verse>
				<verse number="31">በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ መው​ደቅ እጅግ የሚ​ያ​ስ​ፈራ ነው።</verse>
				<verse number="32">እና​ንተ የተ​ጠ​መ​ቃ​ች​ሁ​በ​ት​ንና ብዙ መከራ የታ​ገ​ሣ​ች​ሁ​በ​ትን የቀ​ደ​መ​ውን ዘመን አስቡ፤</verse>
				<verse number="33">እና​ንተ ተሰ​ድ​ባ​ችሁ ነበር፤ መከ​ራም አጽ​ን​ተ​ው​ባ​ችሁ ነበር፤ ተዘ​ባ​ብ​ተ​ው​ባ​ች​ሁም ነበር፤ በዚ​ህም መን​ገድ እን​ዲህ ከሆ​ኑት ጋር ተባ​ብ​ራ​ችሁ ነበር።</verse>
				<verse number="34">በእ​ስ​ራ​ቴም ጊዜ ከእኔ ጋር በመ​ከራ ተባ​ብ​ራ​ች​ኋል፤ የገ​ን​ዘ​ባ​ች​ሁ​ንም መዘ​ረፍ በደ​ስታ ተቀ​ብ​ላ​ች​ኋል፤ በሰ​ማ​ያት ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ኖር ከዚህ የሚ​በ​ል​ጥና የተ​ሻለ ገን​ዘብ እን​ዳ​ላ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።</verse>
				<verse number="35">ትል​ቁን ዋጋ​ች​ሁን የም​ታ​ገ​ኙ​ባ​ትን መታ​መ​ና​ች​ሁን አት​ጣሉ።</verse>
				<verse number="36">ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈቃድ አድ​ር​ጋ​ችሁ የተ​ሰ​ጣ​ች​ሁን ተስፋ ታገኙ ዘንድ መታ​ገሥ ያስ​ፈ​ል​ጋ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="37">“ገና ጥቂት ቀን አለና፤ የሚ​መ​ጣ​ውም ፈጥኖ ይደ​ር​ሳል፥ አይ​ዘ​ገ​ይ​ምም።</verse>
				<verse number="38">ጻድቅ በእ​ም​ነት ይድ​ናል፤ ወደ​ኋላ ቢመ​ለስ ግን ልቡ​ናዬ በእ​ርሱ ደስ አይ​ላ​ትም።”</verse>
				<verse number="39">እኛ ግን ነፍ​ሳ​ቸ​ውን ሊያ​ድኑ ከሚ​ያ​ም​ኑት ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚ​ያ​ፈ​ገ​ፍ​ጉት አይ​ደ​ለ​ንም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">እም​ነ​ትስ ተስፋ ስለ​ም​ና​ደ​ር​ገው ነገር የም​ታ​ረ​ጋ​ግጥ፥ የማ​ና​የ​ው​ንም ነገር የም​ታ​ስ​ረዳ ናት።</verse>
				<verse number="2">በዚ​ህም ለሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች ተመ​ሰ​ከ​ረ​ላ​ቸው።</verse>
				<verse number="3">ዓለም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ተፈ​ጠረ፥ የሚ​ታ​የ​ውም ነገር ከማ​ይ​ታ​የው እንደ ሆነ በእ​ም​ነት እና​ው​ቃ​ለን።</verse>
				<verse number="4">አቤል ከቃ​ኤል ይልቅ የሚ​በ​ልጥ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ም​ነት አቀ​ረበ፤ በዚ​ህም ጻድቅ እንደ ሆነ ተመ​ሰ​ከ​ረ​ለት፤ ምስ​ክ​ሩም መሥ​ዋ​ዕ​ቱን በመ​ቀ​በል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው። በዚ​ህም ከሞተ በኋላ እንኳ ተና​ገረ።</verse>
				<verse number="5">ሄኖክ ሞትን እን​ዳ​ያይ በእ​ም​ነት ተወ​ሰደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ወሰ​ደው አል​ተ​ገ​ኘም፤ ሳይ​ወ​ሰ​ድም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ እንደ አሰ​ኘው ተመ​ስ​ክ​ሮ​ለ​ታል።</verse>
				<verse number="6">ያለ እም​ነ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ ማሰ​ኘት አይ​ቻ​ልም፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ርብ ሰው አስ​ቀ​ድሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳለ፥ ለሚ​ሹ​ትም ዋጋ እን​ደ​ሚ​ሰ​ጣ​ቸው ሊያ​ምን ይገ​ባ​ዋል።</verse>
				<verse number="7">ኖኅም ስለ​ማ​ይ​ታ​የው ነገር የነ​ገ​ሩ​ትን ባመነ ጊዜ ፈራ፤ ቤተ ሰቡ​ንም ያድን ዘንድ ክፍል ያላት መር​ከ​ብን ሠራ፤ በዚ​ህም ዓለ​ምን አስ​ፈ​ረ​ደ​በት፤ በእ​ም​ነ​ትም የሚ​ገ​ኘ​ውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።</verse>
				<verse number="8">አብ​ር​ሃም በተ​ጠራ ጊዜ ርስት አድ​ርጎ ይወ​ር​ሰው ዘንድ ወዳ​ለው ሀገር ለመ​ሄድ በእ​ም​ነት ታዘዘ፤ ወዴት እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ስም ሳያ​ውቅ ሄደ።</verse>
				<verse number="9">በእ​ም​ነ​ትም ከሀ​ገሩ ወጥቶ ተስፋ በሰ​ጠው ሀገር እንደ ስደ​ተኛ በድ​ን​ኳን፥ ተስ​ፋ​ውን ከሚ​ወ​ር​ሱ​አት ከይ​ስ​ሐ​ቅና ከያ​ዕ​ቆብ ጋር ኖረ።</verse>
				<verse number="10">መሠ​ረት ያላ​ትን ሠሪ​ዋና ፈጣ​ሪዋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆ​ነ​ላ​ትን ከተማ ደጅ ይጠኑ ነበ​ርና።</verse>
				<verse number="11">ራስዋ ሳራም መካን ሳለች ባረ​ጀ​ች​በት ወራት ዘር ታስ​ገኝ ዘንድ በእ​ም​ነት ኀይ​ልን አገ​ኘች፤ ተስፋ የሰ​ጣት የታ​መነ እንደ ሆነ አም​ና​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="12">ስለ​ዚ​ህም ደግሞ በብ​ዛ​ታ​ቸው እንደ ሰማይ ኮከብ፥ እን​ደ​ማ​ይ​ቈ​ጠ​ርም በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ የነ​በ​ሩት የሞ​ተን ሰው እንኳ ከመ​ሰ​ለው ከአ​ንዱ ተወ​ለዱ።</verse>
				<verse number="13">እነ​ዚህ ሁሉ አም​ነው ሞቱ፤ ተስ​ፋ​ቸ​ው​ንም አላ​ገ​ኙም፤ ነገር ግን ከሩቅ አይ​ተው እጅ ነሱ​ኣት፤ በም​ድ​ሪ​ቱም ላይ እነ​ርሱ እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች እንደ ሆኑ ዐወቁ።</verse>
				<verse number="14">እን​ዲህ የሚሉ ግን ሀገ​ራ​ቸ​ውን እን​ደ​ሚሹ ያሳ​ያሉ።</verse>
				<verse number="15">ከእ​ር​ስዋ የወ​ጡ​ባ​ትን ሀገር ቢሹ ኖሮስ፥ ወደ እር​ስዋ ሊመ​ለሱ በተ​ቻ​ላ​ቸው ነበር።</verse>
				<verse number="16">አሁን ግን፥ በሰ​ማ​ያት ያለ​ች​ውን የም​ት​በ​ል​ጠ​ውን ሀገር ተስፋ ያደ​ርጉ እንደ ነበር ታወቀ፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው ተብሎ ይጠራ ዘንድ በእ​ነ​ርሱ አያ​ፍ​ርም፤ ተስፋ ያደ​ረ​ጉ​አ​ትን ሀገር አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ላ​ቸ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="17">አብ​ር​ሃ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ተ​ነው ጊዜ ልጁን ይስ​ሐ​ቅን ይሠ​ዋው ዘንድ በእ​ም​ነት ወሰ​ደው።</verse>
				<verse number="18">“በይ​ስ​ሐቅ ዘር ይጠ​ራ​ል​ሃል” ብሎ ተስፋ ያና​ገ​ረ​ለ​ትን አንድ ልጁን አቀ​ረ​በው።</verse>
				<verse number="19">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሙ​ታን ለይቶ ሊያ​ስ​ነ​ሣው እን​ደ​ሚ​ችል አም​ኖ​አ​ልና፤ ስለ​ዚ​ህም ያው የተ​ሰ​ጠው መታ​ሰ​ቢያ ሆነ​ለት።</verse>
				<verse number="20">ያገ​ኙት ዘንድ ስለ አላ​ቸው ነገር ይስ​ሐቅ ያዕ​ቆ​ብ​ንና ኤሳ​ውን በእ​ም​ነት ባረ​ካ​ቸው።</verse>
				<verse number="21">ያዕ​ቆ​ብም በሚ​ሞ​ት​በት ጊዜ የዮ​ሴ​ፍን ልጆች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውን በእ​ም​ነት ባረ​ካ​ቸው፤ በበ​ትሩ ጫፍም ሰገደ።</verse>
				<verse number="22">ዮሴ​ፍም በሚ​ሞ​ት​በት ጊዜ፥ ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ መው​ጣት በእ​ም​ነት ዐሰበ፤ ዐጽ​ሙ​ንም ትተው እን​ዳ​ይ​ወጡ አዘዘ።</verse>
				<verse number="23">ሙሴ በተ​ወ​ለደ ጊዜ በእ​ም​ነት ሦስት ወር በአ​ባቱ ቤት ሸሸ​ጉት፤ ሕፃኑ መል​ካም እንደ ሆነ አይ​ተ​ው​ታ​ልና፤ የን​ጉ​ሥ​ንም ትእ​ዛዝ አል​ፈ​ሩም።</verse>
				<verse number="24">ሙሴም በአ​ደገ ጊዜ የፈ​ር​ዖን የልጅ ልጅ እን​ዳ​ይ​ባል በእ​ም​ነት እንቢ አለ፤</verse>
				<verse number="25">ለጊ​ዜው በኀ​ጢ​አት ከሚ​ገኝ ደስታ ይልቅ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀ​በ​ልን መረጠ።</verse>
				<verse number="26">የክ​ር​ስ​ቶስ የመ​ስ​ቀሉ ተግ​ዳ​ሮት ከግ​ብፅ ሀብት ሁሉ ይልቅ እጅግ የሚ​በ​ልጥ ባለ​ጠ​ግ​ነት እን​ደ​ሚ​ሆን ዐው​ቆ​አ​ልና፥ ዋጋ​ው​ንም ተመ​ል​ክ​ቶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="27">የን​ጉ​ሡ​ንም ቍጣ ሳይ​ፈራ፥ የግ​ብ​ፅን ሀገር በእ​ም​ነት ተወ፤ ከሚ​ያ​የው ይልቅ የማ​ይ​ታ​የ​ውን ሊፈራ ወዶ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="28">ቸነ​ፈር በኵ​ራ​ቸ​ውን እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ባ​ቸው በእ​ም​ነት ፋሲ​ካን አደ​ረገ፤ ደሙ​ንም ረጨ።</verse>
				<verse number="29">በደ​ረቅ ምድር እንደ መሄድ የኤ​ር​ት​ራን ባሕር በእ​ም​ነት ተሻ​ገ​ሩ​አት፤ የግ​ብፅ ሰዎች ግን ሲሞ​ክሩ ሰጠሙ።</verse>
				<verse number="30">ሰባት ቀን ከዞ​ሩ​አት በኋላ የኢ​ያ​ሪኮ ቅጽር በእ​ም​ነት ወደቀ።</verse>
				<verse number="31">ዘማ ረአ​ብም በእ​ም​ነት ከከ​ሓ​ዲ​ዎች ጋር አል​ጠ​ፋ​ችም፤ ጕበ​ኞ​ችን በሰ​ላም ተቀ​ብላ ሰው​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ችና።</verse>
				<verse number="32">እን​ግ​ዲህ ምን እላ​ለሁ? ስለ ጌዴ​ዎን፥ ስለ ባርቅ፥ ስለ ሶም​ሶን፥ ስለ ዮፍ​ታሔ፥ ስለ ዳዊት፥ ስለ ሳሙ​ኤ​ልና ስለ ሌሎች ነቢ​ያት እነ​ግ​ራ​ችሁ ዘንድ ጊዜዬ አጭር ነውና።</verse>
				<verse number="33">እነ​ርሱ በእ​ም​ነት ተጋ​ደሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ትን ድል ነሡ፤ ጽድ​ቅን አደ​ረጉ፤ ተስ​ፋ​ቸ​ውን አገኙ፤ የአ​ና​ብ​ስ​ት​ንም አፍ ዘጉ ።</verse>
				<verse number="34">የእ​ሳት ኀይ​ልን አጠፉ፤ ከሰ​ይፍ ስለት አመ​ለጡ፤ ከድ​ካ​ማ​ቸው በረቱ፤ በጦ​ር​ነት ኀይ​ለ​ኞች ሆኑ፤ የባ​ዕድ ጭፍ​ሮ​ች​ንም አባ​ረሩ።</verse>
				<verse number="35">ሴቶ​ችም እንደ ትን​ሣኤ ቀን ተነ​ሥ​ተ​ው​ላ​ቸው ሙታ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ተቀ​በሉ፤ ተፈ​ር​ዶ​ባ​ቸው የሞ​ቱም አሉ፤ የም​ት​በ​ል​ጠ​ውን ሕይ​ወት ያገኙ ዘንድ ሊድኑ አል​ወ​ደ​ዱ​ምና።</verse>
				<verse number="36">የገ​ረ​ፉ​አ​ቸው፥ የዘ​በ​ቱ​ባ​ቸ​ውና ያሠ​ሩ​አ​ቸው ወደ ወህኒ ያገ​ቡ​አ​ቸ​ውም አሉ።</verse>
				<verse number="37">በመ​ጋዝ የሰ​ነ​ጠ​ቁ​አ​ቸው፥ በድ​ን​ጋይ የወ​ገ​ሩ​አ​ቸው፥ በሰ​ይ​ፍም ስለት የገ​ደ​ሉ​ዋ​ቸው አሉ፤ ማቅ፥ ምን​ጣ​ፍና የፍ​የል ሌጦ ለብ​ሰው ዞሩ፤ ተጨ​ነቁ፤ ተቸ​ገሩ፤ መከራ ተቀ​በሉ፤ ተራቡ፥ ተጠ​ሙም።</verse>
				<verse number="38">ዓለም የማ​ይ​ገ​ባ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው፤ ዱር ለዱ​ርና ተራራ ለተ​ራራ፥ ዋሻ ለዋ​ሻና ፍር​ኩታ ለፍ​ር​ኩ​ታም ዞሩ።</verse>
				<verse number="39">እነ​ዚ​ህም ሁሉ በእ​ም​ነ​ታ​ቸው ተመ​ስ​ክ​ሮ​ላ​ቸው ሳሉ፥ የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን የተ​ስፋ ቃል አላ​ገ​ኙም።</verse>
				<verse number="40">ያለ እኛ ፍጹ​ማን እን​ዳ​ይ​ሆኑ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እኛ የም​ት​በ​ል​ጠ​ውን አስ​ቀ​ድሞ በይ​ኖ​አ​ልና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">እን​ግ​ዲህ እነ​ዚ​ህን የሚ​ያ​ህሉ ምስ​ክ​ሮች እንደ ደመና በዙ​ሪ​ያ​ችን ካሉ​ልን እኛ ደግሞ ሸክ​ምን ሁሉ፥ የኀ​ጢ​አ​ት​ንም ጭን​ቀት ከእኛ አስ​ወ​ግ​ደን፥ በፊ​ታ​ችን ያለ​ውን ሩጫ በት​ዕ​ግ​ሥት እን​ሩጥ።</verse>
				<verse number="2">የእ​ም​ነ​ታ​ች​ን​ንም ራስና ፈጻ​ሚ​ውን ኢየ​ሱ​ስን እን​ከ​ተ​ለው፤ እርሱ ነው​ርን ንቆ፥ በፊ​ቱም ስላ​ለው ደስታ በመ​ስ​ቀል ታግሦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋን ቀኝ ተቀ​ም​ጦ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="3">በነ​ፍ​ሳ​ችሁ ዝላ​ችሁ እን​ዳ​ት​ደ​ክሙ፥ ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች በደ​ረ​ሰ​በት እን​ዲህ ባለ መቃ​ወም የጸ​ና​ውን እስኪ ዐስ​ቡት።</verse>
				<verse number="4">ገና አል​ጸ​ና​ች​ሁ​ምና ደማ​ች​ሁን ለማ​ፍ​ሰስ እስ​ክ​ት​ደ​ርሱ ኀጢ​አ​ትን ተጋ​ደ​ሉ​ኣት፥ አሸ​ን​ፉ​ኣ​ትም፤ ተስ​ፋ​ች​ሁን የም​ታ​ገ​ኙ​ባ​ትን ትም​ህ​ር​ትም ውደ​ዷት።</verse>
				<verse number="5">እንደ ልጆ​ችም ከእ​ና​ንተ ጋር፥ “ልጄ ሆይ፥ የጌ​ታን ቅጣት አታ​ቅ​ልል በሚ​ገ​ሥ​ጽ​ህም ጊዜ አት​ድ​ከም።</verse>
				<verse number="6">እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ወ​ደ​ውን ይገ​ሥ​ጻ​ልና፥ የሚ​ወ​ደ​ደ​ው​ንም ልጅ ሁሉ ይገ​ር​ፈ​ዋል” ብሎ የሚ​ነ​ጋ​ገ​ረ​ውን ምክር ረስ​ታ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="7">ቅጣ​ታ​ች​ሁን ታገሡ፤ ልጆቹ እንደ መሆ​ና​ችሁ ይወ​ዳ​ች​ኋ​ልና፤ አባቱ የማ​ይ​ቈ​ጣው ልጅ ማን ነው?</verse>
				<verse number="8">ነገር ግን ሁሉ የቅ​ጣት ተካ​ፋይ ሆኖ​አ​ልና፥ ያለ ቅጣት ብት​ኖሩ ዲቃ​ሎች እንጂ ልጆች አይ​ደ​ላ​ች​ሁም።</verse>
				<verse number="9">በሥጋ የወ​ለ​ዱን አባ​ቶ​ቻ​ችን የሚ​ቀ​ጡን፥ እኛም የም​ን​ፈ​ራ​ቸው ከሆነ፥ እን​ግ​ዲያ ይል​ቁን ለመ​ን​ፈስ አባ​ታ​ችን ልን​ታ​ዘ​ዝና ልን​ገዛ በሕ​ይ​ወ​ትም ልን​ኖር እን​ዴት ይገ​ባን ይሆን?</verse>
				<verse number="10">እነ​ርሱ መል​ካም ሆኖ እንደ ታያ​ቸው ለጥ​ቂት ቀን ይቀ​ጡ​ናል፤ እርሱ ግን ከቅ​ድ​ስ​ናው እን​ድ​ን​ካ​ፈል ለጥ​ቅ​ማ​ችን ይቀ​ጣ​ናል።</verse>
				<verse number="11">ቅጣት ሁሉ በጊ​ዜው ያሳ​ዝ​ናል እንጂ ደስ አያ​ሰ​ኝም፤ በኋላ ግን ለተ​ቀጡ ሰላ​ምን ያፈ​ራል፤ ጽድ​ቅ​ንም ያሰ​ጣ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="12">ስለ​ዚ​ህም የላ​ሉ​ትን እጆች፥ የሰ​ለ​ሉ​ት​ንም ጕል​በ​ቶች አቅኑ።</verse>
				<verse number="13">አን​ካ​ሳ​ነ​ታ​ችሁ እን​ዲ​ድ​ንና እን​ዳ​ት​ሰ​ነ​ካ​ከሉ ለእ​ግ​ሮ​ቻ​ችሁ የቀና መን​ገ​ድን አድ​ርጉ።</verse>
				<verse number="14">ከሁሉ ጋር ወደ ሰላም ሩጡ፤ ቅድ​ስ​ና​ች​ሁ​ንም አት​ተዉ፤ ያለ እርሱ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​የው የለም።</verse>
				<verse number="15">አስ​ተ​ውሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ጸጋ የሚ​ያ​ቃ​ልል አይ​ኑር፤ ሕማ​ምን የም​ታ​መጣ፥ ብዙ​ዎ​ች​ንም የም​ታ​ስ​ታ​ቸ​ውና የም​ታ​ረ​ክ​ሳ​ቸው መራራ ሥር የም​ት​ገ​ኝ​በ​ትም አይ​ኑር።</verse>
				<verse number="16">ለጥ​ቂት መብል ብኵ​ር​ና​ውን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ሴሰ​ኛና ርኩስ የሚ​ሆን አይ​ኑር።</verse>
				<verse number="17">ከዚያ በኋላ እንኳ በረ​ከ​ትን ሊወ​ርስ በወ​ደደ ጊዜ እንደ ተጣለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና፤ በእ​ን​ባም ተግቶ ምንም ቢፈ​ል​ጋት ለን​ስሓ ስፍራ አላ​ገ​ኘ​ምና።</verse>
				<verse number="18">ሊዳ​ሰስ ወደ​ሚ​ችል ወደ​ሚ​ቃ​ጠ​ልም እሳት ወደ ጭጋ​ግም፥ ወደ ጨለ​ማም ወደ ዐውሎ ነፋ​ስም፥</verse>
				<verse number="19">ወደ መለ​ከት ድም​ፅም፥ ወደ ቃሎ​ችም ነገር አል​ደ​ረ​ሳ​ች​ሁ​ምና፥ ያንም ነገር የሰ​ሙት ሌላ ቃል እን​ዳ​ይ​ጨ​መ​ር​ባ​ቸው ለመኑ።</verse>
				<verse number="20">የተ​ነ​ጋ​ገ​ራ​ቸ​ውን ሊሰ​ሙት አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ውም ነበ​ርና፥ “እን​ስ​ሳም ያን ተራራ ቢቀ​ር​በው በድ​ን​ጋይ ይወ​ግ​ሩት” ነበር።</verse>
				<verse number="21">የታ​ያ​ቸ​ውም እን​ዲህ ግሩም ነበር፤ ሙሴም እን​ኳን፥ “እኔ ፈር​ቻ​ለሁ፥ ደን​ግ​ጫ​ለ​ሁም” አለ።</verse>
				<verse number="22">እና​ንተ ግን፥ የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተማ ወደ​ም​ት​ሆን ወደ ጽዮን ተራራ፥ በሰ​ማ​ያት ወደ አለ​ችው ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ደስ ብሎ​አ​ቸው ወደ​ሚ​ኖሩ አእ​ላፍ መላ​እ​ክ​ትም ደር​ሳ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="23">ስማ​ቸው በሰ​ማይ ወደ ተጻፈ ወደ ማኅ​በረ በኵ​ርም፥ ሁሉን ወደ​ሚ​ገ​ዛም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ወደ ፍጹ​ማን ጻድ​ቃ​ንም ነፍ​ሳት፥</verse>
				<verse number="24">የአ​ዲስ ኪዳ​ንም መካ​ከ​ለኛ ወደ​ሚ​ሆን ወደ ኢየ​ሱስ፥ ከአ​ቤ​ልም ደም ይልቅ የሚ​ሻ​ለ​ውን ወደ​ሚ​ና​ገር ወደ ተረ​ጨው ደሙ ደር​ሳ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="25">ለሚ​ና​ገ​ረው እንቢ እን​ዳ​ትሉ ተጠ​ን​ቀቁ፤ እነ​ርሱ በደ​ብረ ሲና የተ​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸ​ውን እንቢ ስለ አሉት ካል​ዳኑ፥ ከሰ​ማይ ከመ​ጣው ፊታ​ች​ንን ብን​መ​ልስ እኛማ እን​ዴታ?</verse>
				<verse number="26">ያን​ጊዜ ቃል ምድ​ርን አና​ወ​ጣት፤ “አሁ​ንም እኔ ምድ​ርን እንደ ገና አንድ ጊዜ አና​ው​ጣ​ታ​ለሁ” ብሎ ተና​ገረ፤ ምድ​ርን ብቻም አይ​ደ​ለም፤ ሰማ​ይ​ንም ጭምር እንጂ።</verse>
				<verse number="27">አንድ ጊዜ ደግሞ ያለ​ውም ፍጡ​ራን ናቸ​ውና፥ የማ​ይ​ና​ወ​ጠው ይኖር ዘንድ፥ የሚ​ና​ወ​ጠ​ውን እን​ደ​ሚ​ያ​ሳ​ል​ፈው ያሳ​ያል።</verse>
				<verse number="28">ስለ​ዚህ የማ​ይ​ና​ወጥ መን​ግ​ሥ​ትን ስለ​ም​ን​ቀ​በል በማ​ክ​በ​ርና በፍ​ር​ሀት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ እያ​ሰ​ኘን የም​ና​መ​ል​ክ​በ​ትን ጸጋ እን​ያዝ።</verse>
				<verse number="29">አም​ላ​ካ​ችን በእ​ው​ነት የሚ​ያ​ቃ​ጥል እሳት ነውና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ጋር በፍ​ቅር ኑሩ።</verse>
				<verse number="2">እን​ግዳ መቀ​በ​ል​ንም አት​ርሱ፤ በዚህ ምክ​ን​ያት ሳያ​ውቁ መላ​እ​ክ​ትን በእ​ን​ግ​ድ​ነት ለመ​ቀ​በል ያታ​ደሉ አሉና።</verse>
				<verse number="3">ከእ​ነ​ርሱ ጋር አብ​ራ​ች​ኋ​ቸው እንደ ታሰ​ራ​ችሁ ሆና​ችሁ እስ​ረ​ኞ​ችን ዐስቡ፤ መከራ የጸ​ና​ባ​ቸ​ው​ንም በሥ​ጋ​ችሁ ከእ​ነሱ ጋር እን​ዳ​ላ​ችሁ ሆና​ችሁ ዐስቡ።</verse>
				<verse number="4">መጋ​ባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፥ ለመ​ኝ​ታ​ቸ​ውም ርኵ​ሰት የለ​ውም፤ ሴሰ​ኞ​ች​ንና አመ​ን​ዝ​ሮ​ችን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋል።</verse>
				<verse number="5">ገን​ዘብ ሳት​ወዱ ኑሩ፤ ያላ​ች​ሁም ይበ​ቃ​ች​ኋል፤ እርሱ “አል​ጥ​ል​ህም፤ ቸልም አል​ል​ህም” ብሎ​አ​ልና።</verse>
				<verse number="6">አሁ​ንም አም​ነን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይረ​ዳ​ኛል፥ አል​ፈ​ራም፥ ሰው ምን ያደ​ር​ገ​ኛል?” እን​በል።</verse>
				<verse number="7">የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል የነ​ገ​ሩ​አ​ች​ሁን መም​ህ​ሮ​ቻ​ች​ሁን ዐስቡ፤ መል​ካም ጠባ​ያ​ቸ​ውን አይ​ታ​ችሁ በእ​ም​ነት ምሰ​ሉ​አ​ቸው።</verse>
				<verse number="8">ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ትና​ን​ት​ናና ዛሬ እስከ ዘለ​ዓ​ለም የሚ​ኖር እርሱ ነውና።</verse>
				<verse number="9">ሌላ ልዩ ትም​ህ​ርት አታ​ምጡ፤ ልባ​ችሁ በመ​ብል ያይ​ደለ በጸጋ ቢጸና ይበ​ል​ጣ​ልና፤ በዚያ ይሄዱ የነ​በሩ እነ​ዚያ አል​ተ​ጠ​ቀ​ሙ​ምና።</verse>
				<verse number="10">ድን​ኳ​ኒ​ቱን ሲያ​ገ​ለ​ግሉ የነ​በሩ ካህ​ናት ከእ​ርሱ ሊበሉ የማ​ይ​ቻ​ላ​ቸው መሠ​ዊያ አለን፤</verse>
				<verse number="11">ሊቀ ካህ​ናቱ የሚ​ሠ​ዉ​ትን እን​ስሳ ደም ስለ ኀጢ​አት ወደ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳን ያቀ​ርብ ነበ​ርና፤ ሥጋ​ው​ንም ከሰ​ፈር ውጭ ያቃ​ጥ​ሉት ነበር።</verse>
				<verse number="12">ስለ​ዚ​ህም ኢየ​ሱስ ሕዝ​ቡን በደሙ ይቀ​ድ​ሳ​ቸው ዘንድ ከከ​ተማ ውጭ ተሰ​ቀለ።</verse>
				<verse number="13">አሁ​ንም ተግ​ዳ​ሮ​ቱን ተሸ​ክ​መን፥ ወደ እርሱ ወደ ከተ​ማው ውጭ እን​ውጣ።</verse>
				<verse number="14">በዚህ የሚ​ኖር ከተማ ያለን አይ​ደ​ለም፤ የም​ት​መ​ጣ​ውን እን​ሻ​ለን እንጂ።</verse>
				<verse number="15">በውኑ እን​ግ​ዲህ በስሙ እና​ምን ዘንድ የከ​ን​ፈ​ሮ​ቻ​ችን ፍሬ የሚ​ሆን የም​ስ​ጋና መሥ​ዋ​ዕ​ትን በየ​ጊ​ዜው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልና​ቀ​ርብ አይ​ገ​ባ​ን​ምን?</verse>
				<verse number="16">ነገር ግን ለድ​ሆች መራ​ራ​ትን፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር መተ​ባ​በ​ርን አት​ርሱ፤ እን​ዲህ ያለው መሥ​ዋ​ዕት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ ያሰ​ኘ​ዋ​ልና።</verse>
				<verse number="17">ለመ​ም​ህ​ሮ​ቻ​ችሁ ታዘዙ፤ ተገ​ዙ​ላ​ቸ​ውም፤ ስለ እና​ንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ምላሽ የሚ​ሰጡ እንደ መሆ​ና​ቸው፥ ይህን ሳያ​ዝኑ ደስ ብሎ​አ​ቸው ያደ​ር​ጉት ዘንድ ስለ ነፍ​ሳ​ችሁ ይተ​ጋ​ሉና።</verse>
				<verse number="18">ይህም ስለ እኛ ትጸ​ልዩ ዘንድ ይገ​ባ​ች​ኋል፤ ለሁሉ መል​ካም ነገ​ርን እን​ደ​ም​ት​ወ​ዱና እን​ደ​ም​ትሹ እና​ም​ና​ለን።</verse>
				<verse number="19">ይል​ቁ​ንም ፈጥኜ እን​ድ​መ​ለ​ስ​ላ​ችሁ ይህን ታደ​ርጉ ዘንድ አጥ​ብቄ እለ​ም​ና​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="20">በዘ​ለ​ዓ​ለም ኪዳን ደም ለበ​ጎች ትልቅ እረኛ የሆ​ነ​ውን ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከሙ​ታን ያስ​ነ​ሣው፥</verse>
				<verse number="21">የሰ​ላም አም​ላክ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን በእ​ና​ንተ እያ​ደ​ረገ ፈቃ​ዱን ታደ​ርጉ ዘንድ በመ​ል​ካም ሥራ ሁሉ ፍጹ​ማን ያድ​ር​ጋ​ችሁ፤ ለእ​ርሱ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።</verse>
				<verse number="22">ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ የም​ክ​ርን ቃል እን​ድ​ት​ቀ​በሉ እመ​ክ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ በጥ​ቂት ቃል ጽፌ​ላ​ች​ኋ​ለ​ሁና።</verse>
				<verse number="23">ወን​ድ​ማ​ችን ጢሞ​ቴ​ዎስ ከእኛ ወደ እና​ንተ እንደ ተላከ ዕወቁ፤ ፈጥኖ ከመጣ አያ​ች​ኋ​ለሁ።</verse>
				<verse number="24">መም​ህ​ሮ​ቻ​ች​ሁን ሁሉና ቅዱ​ሳ​ን​ንም ሁሉ ሰላም በሉ፥ በኢ​ጣ​ልያ ያሉ ሁሉ ሰላም ብለ​ዋ​ች​ኋል።</verse>
				<verse number="25">የጌ​ታ​ችን ጸጋዉ ከሁ​ላ​ችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን። ወደ ዕብ​ራ​ው​ያን የተ​ላ​ከው መል​እ​ክት ተፈ​ጸመ፤ በኢ​ጣ​ልያ ተጻፈ፤ በጢ​ሞ​ቴ​ዎስ እጅ ተላከ። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን። አሜን።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="59">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑ ለዐሥራ ሁለቱ ወገኖች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን።</verse>
				<verse number="2">ወንድሞቼ ሆይ! የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት፤</verse>
				<verse number="3"></verse>
				<verse number="4">ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም።</verse>
				<verse number="5">ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለእርሱም ይሰጠዋል።</verse>
				<verse number="6">ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና።</verse>
				<verse number="7">ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው።</verse>
				<verse number="8"></verse>
				<verse number="9">የተዋረደው ወንድም ግን በከፍታው፥ ባለ ጠጋም በውርደቱ ይመካ፤ እንደ ሣር አበባ ያልፋልና።</verse>
				<verse number="10"></verse>
				<verse number="11">ፀሐይ ከትኵሳት ጋር ይወጣልና፥ ሣርንም ያጠወልጋልና፥ አበባውም ይረግፋልና፥ የመልኩም ውበት ይጠፋልና፤ እንዲሁ ደግሞ ባለ ጠጋው በመንገዱ ይዝላል።</verse>
				<verse number="12">በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።</verse>
				<verse number="13">ማንም ሲፈተን “በእግዚአብሔር እፈተናለሁ፤” አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል።</verse>
				<verse number="15">ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኀጢአትን ትወልዳለች፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።</verse>
				<verse number="16">የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! አትሳቱ።</verse>
				<verse number="17">በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፤ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።</verse>
				<verse number="18">ለፍጥረቱ የበኵራት ዐይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።</verse>
				<verse number="19">ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤</verse>
				<verse number="20">የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና።</verse>
				<verse number="21">ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ።</verse>
				<verse number="22">ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።</verse>
				<verse number="23">ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤</verse>
				<verse number="24">ራሱን አይቶ ይሄዳልና፤ ወዲያውም እንደ ምን እንደ ሆነ ይረሳል።</verse>
				<verse number="25">ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል።</verse>
				<verse number="26">አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው።</verse>
				<verse number="27">ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ወንድሞቼ ሆይ! በክብር ጌታ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን እምነት ለሰው ፊት በማድላት አትያዙ።</verse>
				<verse number="2">የወርቅ ቀለበት ያደረገና የጌጥ ልብስ የለበሰ ሰው ወደ ጉባኤአችሁ ቢገባ፥ እድፍ ልብስም የለበሰ ድኻ ሰው ደግሞ ቢገባ፥</verse>
				<verse number="3">የጌጥ ልብስም የለበሰውን ተመልክታችሁ “አንተስ በዚህ በመልካም ስፍራ ተቀመጥ፤” ብትሉት፥ ድኻውንም “አንተስ ወደዚያ ቁም” ወይም “ከእግሬ መረገጫ በታች ተቀመጥ፤” ብትሉት፥ ራሳችሁን መለያየታችሁ አይደለምን?</verse>
				<verse number="4">ክፉ አሳብ ያላቸውም ዳኞች መሆናችሁ አይደለምን?</verse>
				<verse number="5">የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለ ጠጎች እንዲሆኑ ለሚወዱትም ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?</verse>
				<verse number="6">እናንተ ግን ድኾችን አዋረዳችሁ። ባለ ጠጎቹ የሚያስጨንቁአችሁ አይደሉምን? ወደ ፍርድ ቤትም የሚጎትቱአችሁ እነርሱ አይደሉምን?</verse>
				<verse number="7">የተጠራችሁበትን መልካሙን ስም የሚሰድቡ እነርሱ አይደሉምን?</verse>
				<verse number="8">ነገር ግን መጽሐፍ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤” እንደሚል የንጉሥን ሕግ ብትፈጽሙ መልካም ታደርጋላችሁ፤</verse>
				<verse number="9">ለሰው ፊት ግን ብታደሉ ኀጢአትን ትሠራላችሁ፤ ሕግም እንደ ተላላፊዎች ይወቅሳችኋል።</verse>
				<verse number="10">ሕግን ሁሉ የሚጠብቅ፥ ነገር ግን በአንዱ የሚሰናከል ማንም ቢኖር በሁሉ በደለኛ ይሆናል፤ “አታመንዝር” ያለው ደግሞ “አትግደል” ብሎአልና፤</verse>
				<verse number="11">ባታመነዝርም፥ ነገር ግን ብትገድል፥ ሕግን ተላላፊ ሆነሃል።</verse>
				<verse number="12">በነጻነት ሕግ ፍርድን ይቀበሉ ዘንድ እንዳላቸው ሰዎች እንዲህ ተናገሩ፤ እንዲህም አድርጉ።</verse>
				<verse number="13">ምሕረትን ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል።</verse>
				<verse number="14">ወንድሞቼ ሆይ! እምነት አለኝ የሚል ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?</verse>
				<verse number="15">ወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ፥</verse>
				<verse number="16">ከእናንተ አንዱም “በደኅና ሂዱ፤ እሳት ሙቁ፤ ጥገቡም፤” ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል?</verse>
				<verse number="17">እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።</verse>
				<verse number="18">ነገር ግን አንድ ሰው “አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፤ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ፤” ይላል።</verse>
				<verse number="19">እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ፤ ይንቀጠቀጡማል።</verse>
				<verse number="20">አንተ ከንቱ ሰው! እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን?</verse>
				<verse number="21">አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?</verse>
				<verse number="22">እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን?</verse>
				<verse number="23">መጽሐፍም “አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት፤” ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ።</verse>
				<verse number="24">ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ።</verse>
				<verse number="25">እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን?</verse>
				<verse number="26">ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ወንድሞቼ ሆይ! ከእናንተ ብዙዎቹ አስተማሪዎች አይሁኑ፤ የባሰውን ፍርድ እንድንቀበል ታውቃላችሁና።</verse>
				<verse number="2">ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።</verse>
				<verse number="3">እነሆ ፈረሶች ይታዘዙልን ዘንድ ልጓም በአፋቸው ውስጥ እናገባለን፤ ሥጋቸውንም ሁሉ እንመራለን።</verse>
				<verse number="4">እነሆ መርከቦች ደግሞ ይህን ያህል ታላቅ ቢሆኑ በዐውሎ ነፋስም ቢነዱ፥ የመሪ ፈቃድ ወደሚወደው ስፍራ እጅግ ታናሽ በሆነ መቅዘፊያ ይመራሉ።</verse>
				<verse number="5">እንዲሁም አንደበት ደግሞ ትንሽ የአካል ክፍል ሆኖ በታላላቅ ነገር ይመካል። እነሆ ትንሽ እሳት እንዴት ያለ ትልቅ ጫካ ያቃጥላል።</verse>
				<verse number="6">አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በሰውነታችን ክፍሎች መካከል ዐመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፤ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፤ በገሃነምም ይቃጠላል።</verse>
				<verse number="7">የአራዊትና የወፎች የተንቀሳቃሾችና በባሕር ያለ የፍጥረት ወገን ሁሉ በሰው ይገራል፤ ደግሞ ተገርቶአል፤</verse>
				<verse number="8">ነገር ግን አንደበትን ሊገራ ማንም ሰው አይችልም፤ የሚገድል መርዝ የሞላበት ወላዋይ ክፋት ነው።</verse>
				<verse number="9">በእርሱ ጌታንና አብን እናመሰግናለን፤ በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን፤</verse>
				<verse number="10">ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ! ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም።</verse>
				<verse number="11">ምንጭስ ከአንድ አፍ የሚጣፍጥንና የሚመርን ውሃ ያመነጫልን?</verse>
				<verse number="12">ወንድሞቼ ሆይ! በለስ ወይራን ወይስ ወይን በለስን ልታፈራ ትችላለችን? ከጨው ውሃም ጣፋጭ ውሃ አይወጣም።</verse>
				<verse number="13">ከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አንዋዋሩ ሥራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ።</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ፤ በእውነትም ላይ አትዋሹ።</verse>
				<verse number="15">ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፤ የሥጋም ነው፤ የአጋንንትም ነው፤</verse>
				<verse number="16">ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ አሉና።</verse>
				<verse number="17">ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ፥ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።</verse>
				<verse number="18">የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉት ሰዎች በሰላም ይዘራል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በአካላችሁ ክፍሎች ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን?</verse>
				<verse number="2">ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤</verse>
				<verse number="3">ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም።</verse>
				<verse number="4">አመንዝሮች ሆይ! ዓለምን መውደድ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።</verse>
				<verse number="5">ወይስ መጽሐፍ “በእኛ ዘንድ ያሳደረው መንፈስ በቅንዓት ይመኛል፤” ያለው በከንቱ እንደ ተናገረ ይመስላችኋልን?</verse>
				<verse number="6">ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል፤” ይላል።</verse>
				<verse number="7">እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤</verse>
				<verse number="8">ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኀጢአተኞች! እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ! ልባችሁን አጥሩ።</verse>
				<verse number="9">ተጨነቁና እዘኑ፤ አልቅሱም፤ ሳቃችሁ ወደ ሐዘን ደስታችሁም ወደ ትካዜ ይለወጥ።</verse>
				<verse number="10">በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ፤ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።</verse>
				<verse number="11">ወንድሞች ሆይ! እርስ በርሳችሁ አትተማሙ። ወንድሙን የሚያማ በወንድሙም የሚፈርድ ሕግን ያማል፤ በሕግም ይፈርዳል፤ በሕግም ብትፈርድ ፈራጅ ነህ እንጂ ሕግን አድራጊ አይደለህም።</verse>
				<verse number="12">ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ ነው፤ እርሱም ሊያድን ሊያጠፋም የሚችል ነው፤ በሌላው ግን የምትፈርድ አንተ ማን ነህ?</verse>
				<verse number="13">አሁንም “ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን፤ በዚያም ዓመት እንኖራለን፤ እንነግድማለን፤ እናተርፍማለን፤” የምትሉ እናንተ! ተመልከቱ፤ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና።</verse>
				<verse number="14">ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና።</verse>
				<verse number="15">በዚህ ፈንታ “ጌታ ቢፈቅድ፥ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን፤” ማለት ይገባችኋል።</verse>
				<verse number="16">አሁን ግን በትዕቢታችሁ ትመካላችሁ፤ እንደዚህ ያለ ትምክህት ሁሉ ክፉ ነው።</verse>
				<verse number="17">እንግዲህ በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኀጢአት ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">አሁንም እናንተ ባለጠጎች! ስለሚደርስባችሁ ጭንቅ ዋይ ዋይ እያላችሁ አልቅሱ።</verse>
				<verse number="2">ሀብታችሁ ተበላሽቶአል፤ ልብሳችሁም በብል ተበልቶአል።</verse>
				<verse number="3">ወርቃችሁም ብራችሁም ዝጎአል፤ ዝገቱም ምስክር ይሆንባችኋል፤ ሥጋችሁንም እንደ እሳት ይበላል። ለኋለኛው ቀን መዝገብን አከማችታችኋል።</verse>
				<verse number="4">እነሆ እርሻችሁን ያጨዱት የሠራተኞች ደመወዝ በእናንተ ተቀምቶ ይጮኻል፤ የአጫጆችም ድምፅ ወደ ጌታ ጸባዖት ጆሮ ገብቶአል።</verse>
				<verse number="5">በምድር ላይ ተቀማጥላችኋል፤ በሴሰኝነትም ኖራችኋል፤ ለእርድ ቀን እንደሚያወፍር ልባችሁን አወፍራችኋል።</verse>
				<verse number="6">ጻድቁን ኰንናችሁታል፤ ገድላችሁትማል፤ እናንተን አይቃወምም።</verse>
				<verse number="7">እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! ጌታ እስኪመጣ ድረስ ታገሡ። እነሆ ገበሬው የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እስኪቀበል ድረስ እርሱን እየታገሠ የከበረውን የመሬት ፍሬ ይጠብቃል።</verse>
				<verse number="8">እናንተ ደግሞ ታገሡ፤ ልባችሁንም አጽኑ፤ የጌታ መምጣት ቀርቦአልና።</verse>
				<verse number="9">ወንድሞች ሆይ! እንዳይፈረድባችሁ እርስ በርሳችሁ አታጉረምርሙ፤ እነሆ ፈራጅ በደጅ ፊት ቆሞአል።</verse>
				<verse number="10">ወንድሞች ሆይ! የመከራና የትዕግሥት ምሳሌ የሆኑትን በጌታ ስም የተናገሩትን ነቢያትን ተመልከቱ።</verse>
				<verse number="11">እነሆ በትዕግሥት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን፤ ኢዮብ እንደ ታገሠ ሰምታችኋል፤ ጌታም እንደ ፈጸመለት አይታችኋል፤ ጌታ እጅግ የሚምር የሚራራም ነውና።</verse>
				<verse number="12">ከሁሉም በፊት ወንድሞቼ ሆይ! በሰማይም ቢሆን በምድርም ቢሆን በሌላ መሐላም ቢሆን በምንም አትማሉ፤ ነገር ግን ከፍርድ በታች እንዳትወድቁ ነገራችሁ አዎን ቢሆን አዎን ይሁን፤ አይደለምም ቢሆን አይደለም ይሁን።</verse>
				<verse number="13">ከእናንተ መከራን የሚቀበል ማንም ቢኖር እርሱ ይጸልይ፤ ደስ የሚለውም ማንም ቢኖር እርሱ ይዘምር።</verse>
				<verse number="14">ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት።</verse>
				<verse number="15">የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል፤ ጌታም ያስነሣዋል፤ ኀጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል።</verse>
				<verse number="16">እርስ በርሳችሁ በኀጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኀይል ታደርጋለች።</verse>
				<verse number="17">ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፤ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፤ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤</verse>
				<verse number="18">ሁለተኛም ጸለየ፤ ሰማዩም ዝናብን ሰጠ፤ ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች።</verse>
				<verse number="19">ወንድሞች ሆይ! ከእናንተ ማንም ከእውነት ቢስት አንዱም ቢመልሰው፥</verse>
				<verse number="20">ኀጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ነፍሱን ከሞት እንዲያድን፥ የኀጢአትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="60">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ጴጥሮስ፥ እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ እንዳወቃቸው በመንፈስም እንደሚቀደሱ፥ ይታዘዙና በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ይረጩ ዘንድ ለተመረጡት በጳንጦስና በገላትያ በቀጰዶቅያም በእስያም በቢታንያም ለተበተኑ መጻተኞች፤ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።</verse>
				<verse number="2"></verse>
				<verse number="3">ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኀይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።</verse>
				<verse number="4"></verse>
				<verse number="5"></verse>
				<verse number="6">በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፤ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል።</verse>
				<verse number="7"></verse>
				<verse number="8">እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።</verse>
				<verse number="9"></verse>
				<verse number="10">ለእናንተም ስለሚሰጠው ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ተግተው እየፈለጉ መረመሩት፤</verse>
				<verse number="11">በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሰከረ፥ በምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር።</verse>
				<verse number="12">ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።</verse>
				<verse number="13">ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።</verse>
				<verse number="14">እንደሚታዘዙ ልጆች ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ።</verse>
				<verse number="15">ዳሩ ግን “እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ፤” ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።</verse>
				<verse number="16"></verse>
				<verse number="17">ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።</verse>
				<verse number="18">ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።</verse>
				<verse number="19"></verse>
				<verse number="20">ዓለም ሳይፈጠር እንኳ አስቀድሞ ታወቀ፤ ነገር ግን እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ፥ ከሙታን ባስነሣው ክብርንም በሰጠው በእግዚአብሔር በእርሱ ስለምታምኑ ስለ እናንተ በዘመኑ መጨረሻ ተገለጠ።</verse>
				<verse number="21"></verse>
				<verse number="22">ለእውነት እየታዘዛችሁ ግብዝነት ለሌለበት ለወንድማማች መዋደድ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።</verse>
				<verse number="23">ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፤ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ።</verse>
				<verse number="24">“ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤</verse>
				<verse number="25">የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል።” በወንጌልም የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">እንግዲህ ክፋትን ሁሉ ተንኰልንም ሁሉ ግብዝነትንም ቅንዓትንም ሐሜትንም ሁሉ አስወግዳችሁ፥</verse>
				<verse number="2">ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።</verse>
				<verse number="3"></verse>
				<verse number="4">በሰውም ወደ ተጣለ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠና ክቡር ወደ ሆነው ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ እየቀረባችሁ፥</verse>
				<verse number="5">እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።</verse>
				<verse number="6">በመጽሐፍ “እነሆ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም፤” ተብሎ ተጽፎአልና።</verse>
				<verse number="7">እንግዲህ ክብሩ ለእናንተ ለምታምኑት ነው፤ ለማያምኑ ግን “አናጢዎች የጣሉት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ የዕንቅፋትም ድንጋይ</verse>
				<verse number="8">የማሰናከያም ዓለት ሆነ፤” የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው።</verse>
				<verse number="9">እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤</verse>
				<verse number="10">እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም፤ አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።</verse>
				<verse number="11">ወዳጆች ሆይ! ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤</verse>
				<verse number="12">ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።</verse>
				<verse number="13">ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥርዐት ሁሉ ተገዙ፤ ለንጉሥም ቢሆን፥ ከሁሉ በላይ ነውና፤</verse>
				<verse number="14">ለመኳንንትም ቢሆን፥ ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት በጎም የሚያደርጉትን ለማመስገን ከእርሱ ተልከዋልና ተገዙ።</verse>
				<verse number="15">በጎ እያደረጋችሁ፥ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና፤</verse>
				<verse number="16">አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ።</verse>
				<verse number="17">ሁሉን አክብሩ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ።</verse>
				<verse number="18">ሎሌዎች ሆይ! ለበጎዎችና ለገሮች ጌቶቻችሁ ብቻ ሳይሆን ለጠማሞች ደግሞ በፍርሃት ሁሉ ተገዙ።</verse>
				<verse number="19">በግፍ መከራን የሚቀበል ሰው እግዚአብሔርን እያሰበ ሐዘንን ቢታገሥ ምስጋና ይገባዋልና።</verse>
				<verse number="20">ኀጢአት አድርጋችሁ ስትጎሰሙ ብትታገሡ፥ ምን ክብር አለበት? ነገር ግን መልካም አድርጋችሁ መከራን ስትቀበሉ ብትታገሡ፥ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋና ይገባዋል።</verse>
				<verse number="21">የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና።</verse>
				<verse number="22">“እርሱም ኀጢአት አላደረገም፤ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤”</verse>
				<verse number="23">ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራንም ሲቀበል አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤</verse>
				<verse number="24">ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።</verse>
				<verse number="25">እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">እንዲሁም እናንተ ሚስቶች ሆይ! ከባሎቻችሁ አንዳንዱ ለትምህርት የማይታዘዙ ቢኖሩ፥ በፍርሃት ያለውን ንጹሑን ኑሮአችሁን እየተመለከቱ ያለ ትምህርት በሚስቶቻቸው ኑሮ እንዲገኙ ተገዙላቸው።</verse>
				<verse number="2"></verse>
				<verse number="3">ለእናንተም ጠጕርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፤</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ።</verse>
				<verse number="5">እንዲህ በቀድሞ ዘመን በእግዚአብሔር ተስፋ ያደረጉት ቅዱሳት ሴቶች ደግሞ ለባሎቻቸው ሲገዙ ተሸልመው ነበርና፤</verse>
				<verse number="6">እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፥ ጌታ ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት፤ እናንተም ከሚያስደነግጥ ነገር አንዳች እንኳ ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ ልጆችዋ ናችሁ።</verse>
				<verse number="7">እንዲሁም እናንተ ባሎች ሆይ! ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድርጋችሁ አክብሩአቸው።</verse>
				<verse number="8">በመጨረሻው ሁላችሁ በአንድ ልብ ሁኑ፤ የሌላው መከራ ለእናንተ እንደሚሆን አድርጉ፤ እንደወንድሞች ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ፤</verse>
				<verse number="9">ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፤ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና።</verse>
				<verse number="10">“ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤</verse>
				<verse number="11">ከክፉ ፈቀቅ ይበል፤ መልካምንም ያድርግ፤ ሰላምን ይሻ፤ ይከተለውም፤</verse>
				<verse number="12">የጌታ ዐይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና፤ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል፤ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው።”</verse>
				<verse number="13">በጎንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው?</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኳ መከራን ብትቀበሉ ብፁዓን ናችሁ። ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ፤ አትናወጡም፤</verse>
				<verse number="15">ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።</verse>
				<verse number="16">በክርስቶስ ያለውን መልካሙን ኑሮአችሁን የሚሳደቡ ሰዎች ክፉን እንደምታደርጉ በሚያሙበት ነገር እንዲያፍሩ በጎ ሕሊና ይኑራችሁ።</verse>
				<verse number="17">የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲህ ቢሆን፥ ክፉ ስለ ማድረግ ሳይሆን በጎ ስለ ማድረግ መከራን ብትቀበሉ ይሻላችኋልና።</verse>
				<verse number="18">ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች አንድ ጊዜ በኀጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤</verse>
				<verse number="19">በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው፤</verse>
				<verse number="20">ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውሃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም።</verse>
				<verse number="21">ይህም ውሃ ደግሞ ማለት ጥምቅት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፤ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፤ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፤ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው፤</verse>
				<verse number="22">እርሱም መላእክትና ሥልጣናት ኀይላትም ከተገዙለት በኋላ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ክርስቶስም በሥጋ ስለ እኛ መከራን ስለተቀበለ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በሥጋ ልትኖሩ በቀረላችሁ ዘመን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሰው ምኞት እንዳትኖሩ፥ እናንተ ደግሞ ያን አሳብ እንደ ዕቃ ጦር አድርጋችሁ ያዙት፤ በሥጋ መከራን የተቀበለ ኀጢአትን ትቶአልና።</verse>
				<verse number="2"></verse>
				<verse number="3">የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።</verse>
				<verse number="4">በዚህም ነገር ወደዚያ መዳራት ብዛት ከእነርሱ ጋር ስለማትሮጡ እየተሳደቡ ይደነቃሉ፤</verse>
				<verse number="5">ግን እነርሱ በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው መልስ ይሰጣሉ።</verse>
				<verse number="6">እንደሰዎች በሥጋ እንዲፈረድባችው በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ ስለዚህ ምክንያት ወንጌል ለሙታን ደግሞ ተሰብኮላቸው ነበርና።</verse>
				<verse number="7">ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቦአል። እንግዲህ እንደ ባለ አእምሮ አስቡ፤</verse>
				<verse number="8">ትጸልዩም ዘንድ በመጠን ኑሩ፤ ፍቅር የኀጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።</verse>
				<verse number="9">ያለ ማንጐራጐር እርስ በርሳችሁ እንግድነትን ተቀባበሉ፤</verse>
				<verse number="10">ልዩ ልዩን የእግዚአብሔርን ጸጋ ደጋግ መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ፥ እያንዳንዳችሁ የጸጋን ስጦታ እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በርሳችሁ አገልግሉ፤</verse>
				<verse number="11">ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ “እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኀይል ነው” ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።</verse>
				<verse number="12">ወዳጆች ሆይ! በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፤</verse>
				<verse number="13">ነገር ግን ክብሩ ሲገለጥ ደግሞ ሐሤት እያደረጋችሁ ደስ እንዲላችሁ፥ በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ ደስ ይበላችሁ።</verse>
				<verse number="14">ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ።</verse>
				<verse number="15">ከእናንተ ማንም ነፍሰ ገዳይ ወይም ሌባ ወይም ክፉ አድራጊ እንደሚሆን ወይም በሌሎች ጉዳይ እንደሚገባ ሆኖ መከራን አይቀበል፤</verse>
				<verse number="16">ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር።</verse>
				<verse number="17">ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?</verse>
				<verse number="18">ጻድቅም በጭንቅ የሚድን ከሆነ ዐመፀኛውና ኀጢአተኛው ወዴት ይታይ ዘንድ አለው?</verse>
				<verse number="19">ስለዚህ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራን የሚቀበሉ፥ መልካምን እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ይስጡ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤</verse>
				<verse number="2">በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤</verse>
				<verse number="3">ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኀይል አትግዙ፤</verse>
				<verse number="4">የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።</verse>
				<verse number="5">እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ልበሱ፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል።</verse>
				<verse number="6">እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኀይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤</verse>
				<verse number="7">እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።</verse>
				<verse number="8">በመጠን ኑሩ፤ ንቁም፤ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤</verse>
				<verse number="9">በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።</verse>
				<verse number="10">በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ፥ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል፤ ያጸናችሁማል፤ ያበረታችሁማል።</verse>
				<verse number="11">ለእርሱ ክብርና ኀይል እስከዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።</verse>
				<verse number="12">እየመከርኋችሁና የምትቆሙባት ጸጋ እውነትኛ የእግዚአብሔር ጸጋ እንድትሆን እየመሰከርሁላችሁ፥ የታመነ ወንድም እንደ ሆነ በቈጠርሁት በስልዋኖስ እጅ በአጭሩ ጽፌላችኋለሁ።</verse>
				<verse number="13">ከእናንተ ጋር ተመርጣ በባቢሎን ያለች ቤተ ክርስቲያን፥ ልጄም ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።</verse>
				<verse number="14">በፍቅር አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። በክርስቶስ ላላችሁ ለሁላችሁ ሰላም ይሁን። አሜን።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="61">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፥ በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ፤</verse>
				<verse number="2">የመለኮቱ ኀይል በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።</verse>
				<verse number="3"></verse>
				<verse number="4">ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ በተስፋው ቃል ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን።</verse>
				<verse number="5">ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥</verse>
				<verse number="6">በበጎነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥</verse>
				<verse number="7">እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ።</verse>
				<verse number="8">እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤</verse>
				<verse number="9">እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፤ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፤ የቀደመውንም ኀጢአቱን መንጻት ረስቶአል።</verse>
				<verse number="10">ስለዚህ ወንድሞች ሆይ! መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና።</verse>
				<verse number="11">እንዲሁ ወደ ዘላለሙ ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋልና።</verse>
				<verse number="12">ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ምንም ብታውቁ፥ በእናንተም ዘንድ ባለ እውነት ምንም ብትጸኑ፥ ስለ እነዚህ ዘወትር እንዳሳስባችሁ ቸል አልልም።</verse>
				<verse number="13">ሁልጊዜም በዚህ አካል ሳለሁ በማሳሰቤ ላነቃችሁ የሚገባኝ ይመስለኛል።</verse>
				<verse number="14">ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመለከተኝ ከዚህ አካሌ መለየቴ ፈጥኖ እንዲሆን አውቃለሁና።</verse>
				<verse number="15">ከመውጣቴም በኋላ እነዚህን ነገሮች እንድታስቡ በየጊዜው ትችሉ ዘንድ እተጋለሁ።</verse>
				<verse number="16">የእርሱን ግርማ አይተን እንጂ በብልሃት የተፈጠረውን ተረት ሳንከተል የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ኀይልና መምጣት አስታወቅናችሁ።</verse>
				<verse number="17">ከገናናው ክብር “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤” የሚል ያ ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ምስጋናን ተቀብሎአልና፤</verse>
				<verse number="18">እኛም በቅዱሱ ተራራ ከእርሱ ጋር ሳለን ይህን ድምፅ ከሰማይ ሲወርድ ሰማን።</verse>
				<verse number="19">ከእርሱም ይልቅ እጅግ የጸና የትንቢት ቃል አለን፤ ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየጠነቀቃችሁ መልካም ታደርጋላችሁ።</verse>
				<verse number="20">ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤</verse>
				<verse number="21">ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፤ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ፤ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤</verse>
				<verse number="2">ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሉአቸዋል፤ በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል።</verse>
				<verse number="3">ገንዘብንም በመመኘት በተፈጠረ ነገር ይረቡባችኋል፤ ፍርዳቸውም ከጥንት ጀምሮ አይዘገይም፤ ጥፋታቸውም አያንቀላፋም።</verse>
				<verse number="4">እግዚአብሔር ኀጢአትን ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው፥</verse>
				<verse number="5">ለቀደመውም ዓለም ሳይራራ ከሌሎች ሰባት ጋር ጽድቅን የሚሰብከውን ኖኅን አድኖ በኀጢአተኞች ዓለም ላይ የጥፋትን ውሃ ካወረደ፥</verse>
				<verse number="6">ኀጢአትንም ያደርጉ ዘንድ ላሉት ምሳሌ አድርጎ ከተማዎችን ሰዶምንና ገሞራን አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎና ገልብጦ ከፈረደባቸው፥</verse>
				<verse number="7">ጻድቅ ሎጥም በመካከላቸው ሲኖር እያየና እየሰማ ዕለት ዕለት በዐመፀኛ ሥራቸው ጻድቅ ነፍሱን አስጨንቆ ነበርና በዐመፀኞች ሴሰኛ ኑሮ የተገፋውን ያን ጻድቅ ካዳነ፥</verse>
				<verse number="8"></verse>
				<verse number="9">ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንዲያድን በደለኞችንም ይልቁንም በርኵስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን ጌትነትንም የሚንቁትን እየቀጣቸው ለፍርድ ቀን እንዴት እንዲጠብቅ ያውቃል። ደፋሮችና ኵሩዎች ሆነው ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይንቀጠቀጡም፤</verse>
				<verse number="10"></verse>
				<verse number="11">ዳሩ ግን መላእክት በኀይልና በብርታት ከእነርሱ ይልቅ ምንም ቢበልጡ፥ በጌታ ፊት በእነርሱ ላይ የስድብን ፍርድ አያመጡም።</verse>
				<verse number="12">እነዚህ ግን ለመጠመድና ለመጥፋት በፍጥረታቸው እንደ ተወለዱ አእምሮ እንደ ሌላቸው እንስሶች ሆነው፥ በማያውቁት ነገር እየተሳደቡ በጥፋታቸው ይጠፋሉ፤</verse>
				<verse number="13">የዐመፃቸውን ደመወዝ ይቀበላሉ። በቀን ሲዘፍኑ እንደ ተድላ ይቆጥሩታል፤ ነውረኞችና ርኵሳን ሆነው ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣ ይዘፍናሉ፤</verse>
				<verse number="14">ምንዝር የሞላባቸው ኀጢአትንም የማይተዉ ዐይኖች አሉአቸው፤ የማይጸኑትን ነፍሳት ያታልላሉ፤ መመኘትን የለመደ ልብ አላቸው፤ የተረገሙ ናቸው።</verse>
				<verse number="15">ቅንን መንገድ ትተው ተሳሳቱ፤ የባሶርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከተሉ፤ እርሱ የዐመፃን ደመወዝ ወደደ፤</verse>
				<verse number="16">ነገር ግን ስለ መተላለፉ ተዘለፈ፤ ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነቢዩን እብድነት አገደ።</verse>
				<verse number="17">ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው እነዚህ ውሃ የሌለባቸው ምንጮች በዐውሎ ነፋስም የተነዱ ደመናዎች ናቸው።</verse>
				<verse number="18">ከንቱና ከመጠን ይልቅ ታላቅ የሆነውን ቃል ይናገራሉና፤ በስሕተትም ከሚኖሩት አሁን የሚያመልጡትን በሥጋ ሴሰኛ ምኞት ያታልላሉ።</verse>
				<verse number="19">ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው “አርነት ትወጣላችሁ፤” እያሉ ተስፋ ይሰጡአቸዋል፤ ሰው ለተሸነፈበት ለእርሱ ተገዝቶ ባሪያ ነውና።</verse>
				<verse number="20">በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዕውቀት ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ ዳግመኛ በእርስዋ ተጠላልፈው የተሸነፉ ቢሆኑ፥ ከፊተኛው ኑሮአቸው ይልቅ የኋለኛው የባሰ ሆኖባቸዋል።</verse>
				<verse number="21">ዕውቀዋት ከተሰጣቸው ከቅድስት ትእዛዝ ከሚመለሱ የጽድቅን መንገድ ባላወቋት በተሻላቸው ነበርና።</verse>
				<verse number="22">“ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፤” ደግሞ “የታጠበች እርያ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች፤” እንደሚባል እውነተኞች ምሳሌዎች ሆኖባቸዋል።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">ወዳጆች ሆይ! አሁን የምጽፍላችሁ መልእክት ይህች ሁለተኛይቱ ናት። በቅዱሳን ነቢያትም ቀድሞ የተባለውን ቃል በሐዋርያቶቻችሁም ያገኛችኋትን የጌታችንንና የመድኃኒታችንን ትእዛዝ እንድታስቡ በሁለቱ እያሳሰብኋችሁ ቅን ልቡናችሁን አነቃቃለሁ።</verse>
				<verse number="2"></verse>
				<verse number="3">በመጨረሻው ዘመን እንደ ራሳቸው ምኞት የሚመላለሱ ዘባቾች በመዘበት እንዲመጡ ይህን በፊት እወቁ፤</verse>
				<verse number="4">እነርሱም “የመምጣቱ የተስፋ ቃል ወዴት ነው? አባቶች ከሞቱባት ጊዜ ከፍጥረት መጀመሪያ ይዞ ሁሉ እንዳለ ይኖራልና፤” ይላሉ።</verse>
				<verse number="5">ሰማያት ከጥንት ጀምረው ምድርም በእግዚአብሔር ቃል ከውሃ ተጋጥማ በውሃ መካከል እንደ ነበሩ ወደው አያስተውሉምና፤</verse>
				<verse number="6">በዚህም ምክንያት ያን ጊዜ የነበረ ዓለም በውሃ ሰጥሞ ጠፋ፤</verse>
				<verse number="7">አሁን ያሉ ሰማያትና ምድር ግን እግዚአብሔርን የማያመልኩት ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ተጠብቀው በዚያ ቃል ለእሳት ቀርተዋል።</verse>
				<verse number="8">እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ! በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።</verse>
				<verse number="9">ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፤ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሓ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።</verse>
				<verse number="10">የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፤ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።</verse>
				<verse number="11">ይህ ሁሉ እንዲህ የሚቀልጥ ከሆነ፥ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት እየጠበቃችሁና እያስቸኰላችሁ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል እንደ ምን ልትሆኑ ይገባችኋል? ስለዚያ ቀን ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይፈታል፤</verse>
				<verse number="12"></verse>
				<verse number="13">ነገር ግን ጽድቅ የሚኖርባትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደ ተስፋ ቃሉ እንጠብቃለን።</verse>
				<verse number="14">ስለዚህ ወዳጆች ሆይ! ይህን እየጠበቃችሁ ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም በእርሱ እንድትገኙ ትጉ፤</verse>
				<verse number="15">የጌታችንም ትዕግሥት መዳናችሁ እንደ ሆነ ቍጠሩ። እንዲህም የተወደደው ወንድማችን ጳውሎስ ደግሞ እንደ ተሰጠው ጥበብ መጠን ጻፈላችሁ፤</verse>
				<verse number="16">በመልእክቱም ሁሉ ደግሞ እንደ ነገረ ስለዚህ ነገር ተናገረ። በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ፤ ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።</verse>
				<verse number="17">እንግዲህ እናንተ ወዳጆች ሆይ! ይህን አስቀድማችሁ ስለምታውቁ፥ በዐመፀኞቹ ስሕተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ፤</verse>
				<verse number="18">ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="62">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤</verse>
				<verse number="2">ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤</verse>
				<verse number="3">እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።</verse>
				<verse number="4">ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን።</verse>
				<verse number="5">ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፦ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።</verse>
				<verse number="6">ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤</verse>
				<verse number="7">ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።</verse>
				<verse number="8">ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።</verse>
				<verse number="9">በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።</verse>
				<verse number="10">ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።</verse>
				<verse number="2">እርሱም የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።</verse>
				<verse number="3">ትእዛዛቱንም ብንጠብቅ በዚህ እንዳወቅነው እናውቃለን።</verse>
				<verse number="4">አውቄዋለሁ የሚል ትእዛዛቱንም የማይጠብቅ ውሸተኛ ነው እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም።</verse>
				<verse number="5">ቃሉን ግን የሚጠብቅ ሁሉ በእርሱ የእግዚአብሔር ፍቅር በእውነት ተፈጽሞአል። በእርሱ እንዳለን በዚህ እናውቃለን፤</verse>
				<verse number="6">በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደ ተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል።</verse>
				<verse number="7">ወንድሞች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረቻችሁ አሮጌ ትእዛዝ እንጂ የምጽፍላችሁ አዲስ ትእዛዝ አይደለችም፤ አሮጌይቱ ትእዛዝ የሰማችኋት ቃል ናት።</verse>
				<verse number="8">ዳግመኛ አዲስ ትእዛዝን እጽፍላችኋለሁ፥ ይህም ነገር በእርሱ በእናንተም እውነተኛ ነው፤ ጨለማው ያልፋልና እውነተኛውም ብርሃን አሁን ይበራል።</verse>
				<verse number="9">በብርሃን አለሁ የሚል ወንድሙንም የሚጠላ እስከ አሁን በጨለማ አለ።</verse>
				<verse number="10">ወንድሙንም የሚወድ በብርሃን ይኖራል ማሰናከያም የለበትም፤</verse>
				<verse number="11">ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ አለ፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ የሚሄድበትንም አያውቅም፥ ጨለማው ዓይኖቹን አሳውሮታልና።</verse>
				<verse number="12">ልጆች ሆይ፥ ኃጢአታችሁ ስለ ስሙ ተሰርዮላችኋልና እጽፍላችኋለሁ።</verse>
				<verse number="13">አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ጎበዞች ሆይ፥ ክፉውን አሸንፋችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ልጆች ሆይ፥ አብን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ።</verse>
				<verse number="14">አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ጐበዞች ሆይ፥ ብርቱዎች ስለ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር ክፉውንም ስለ አሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ።</verse>
				<verse number="15">ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም።</verse>
				<verse number="16"></verse>
				<verse number="17">ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል።</verse>
				<verse number="18">ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን።</verse>
				<verse number="19">ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።</verse>
				<verse number="20">እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ።</verse>
				<verse number="21">እውነትን የምታውቁ ስለ ሆናችሁ፥ ውሸትም ሁሉ ከእውነት እንዳልሆነ ስለምታውቁ እንጂ እውነትን ስለማታውቁ አልጽፍላችሁም።</verse>
				<verse number="22">ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው? አብንና ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።</verse>
				<verse number="23">ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ እንኳ የለውም፤ በወልድ የሚታመን አብ ደግሞ አለው።</verse>
				<verse number="24">እናንተስ ከመጀመሪያ የሰማችሁት በእናንተ ጸንቶ ይኑር። ከመጀመሪያ የሰማችሁት በእናንተ ቢኖር፥ እናንተ ደግሞ በወልድና በአብ ትኖራላችሁ።</verse>
				<verse number="25">እርሱም የሰጠን ተስፋ ይህ የዘላለም ሕይወት ነው።</verse>
				<verse number="26">ስለሚያስቱአችሁ ሰዎች ይህን ጽፌላችኋለሁ።</verse>
				<verse number="27">እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ።</verse>
				<verse number="28">አሁንም፥ ልጆች ሆይ፥ በሚገለጥበት ጊዜ እምነት እንዲሆንልን በመምጣቱም በእርሱ ፊት እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ።</verse>
				<verse number="29">ጻድቅ እንደ ሆነ ካወቃችሁ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከእርሱ እንደ ተወለደ እወቁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም።</verse>
				<verse number="2">ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።</verse>
				<verse number="3">በእርሱም ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ንጹሕ እንደ ሆነ ራሱን ያነጻል።</verse>
				<verse number="4">ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመፅን ደግሞ ያደርጋል፥ ኃጢአትም ዓመፅ ነው።</verse>
				<verse number="5">እርሱም ኃጢአትን ሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፥ በእርሱም ኃጢአት የለም።</verse>
				<verse number="6">በእርሱ የሚኖር ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፤ ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ አላየውም አላወቀውምም።</verse>
				<verse number="7">ልጆች ሆይ፥ ማንም አያስታችሁ፥ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ጽድቅን የሚያደርግ ጻድቅ ነው።</verse>
				<verse number="8">ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፥ ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ኃጢአትን ያደርጋልና።</verse>
				<verse number="9">ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔርም ተወልዶአልና ኃጢአትን ሊያደርግ አይችልም።</verse>
				<verse number="10">የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ የተገለጡ ናቸው፤ ጽድቅን የማያደርግና ወንድሙን የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም።</verse>
				<verse number="11">ከመጀመሪያ የሰማችኋት መልእክት፦ እርስ በርሳችን እንዋደድ የምትል ይህች ናትና፤</verse>
				<verse number="12">ከክፉው እንደ ነበረ ወንድሙንም እንደ ገደለ እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለ ምንስ ገደለው? የገዛ ሥራው ክፉ፥ የወንድሙም ሥራ ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።</verse>
				<verse number="13">ወንድሞች ሆይ፥ ዓለም ቢጠላችሁ አትደነቁ።</verse>
				<verse number="14">እኛ ወንድሞችን የምንወድ ስለ ሆንን ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፤ ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል።</verse>
				<verse number="15">ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ።</verse>
				<verse number="16">እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል።</verse>
				<verse number="17">ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል?</verse>
				<verse number="18">ልጆቼ ሆይ፥ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ።</verse>
				<verse number="19">ልባችንም በእኛ ላይ በሚፈርድበት ሁሉ፥ ከእውነት እንደ ሆንን በዚህ እናውቃለን በፊቱም ልባችንን እናሳርፋለን፥ እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉንም ያውቃል።</verse>
				<verse number="20"></verse>
				<verse number="21">ወዳጆች ሆይ፥ ልባችንስ ባይፈርድብን በእግዚአብሔር ዘንድ ድፍረት አለን፥</verse>
				<verse number="22">ትእዛዙንም የምንጠብቅና በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን የምናደርግ ስለሆንን የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን።</verse>
				<verse number="23">ትእዛዚቱም ይህች ናት፥ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናምን ዘንድ፥ ትእዛዝንም እንደ ሰጠን እርስ በርሳችን እንዋደድ ዘንድ።</verse>
				<verse number="24">ትእዛዙንም የሚጠብቅ በእርሱ ይኖራል እርሱም ይኖርበታል፤ በዚህም በእኛ እንዲኖር ከሰጠን ከመንፈሱ እናውቃለን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።</verse>
				<verse number="2">የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥</verse>
				<verse number="3">ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም እንኳ በዓለም አለ።</verse>
				<verse number="4">ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና።</verse>
				<verse number="5">እነርሱ ከዓለም ናቸው፤ ስለዚህ ከዓለም የሆነውን ይናገራሉ ዓለሙም ይሰማቸዋል።</verse>
				<verse number="6">እኛ ከእግዚአብሔር ነን፤ እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል፤ ከእግዚአብሔር ያልሆነ አይሰማንም። የእውነትን መንፈስና የስሕተትን መንፈስ በዚህ እናውቃለን።</verse>
				<verse number="7">ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ።</verse>
				<verse number="8">ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።</verse>
				<verse number="9">በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።</verse>
				<verse number="10">ፍቅርም እንደዚህ ነው። እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።</verse>
				<verse number="11">ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል።</verse>
				<verse number="12">እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ሆኖአል።</verse>
				<verse number="13">ከመንፈሱ ስለ ሰጠን፥ በእርሱ እንድንኖር እሱም በእኛ እንዲኖር በዚህ እናውቃለን።</verse>
				<verse number="14">እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን።</verse>
				<verse number="15">ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚታመን ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።</verse>
				<verse number="16">እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።</verse>
				<verse number="17">በፍርድ ቀን ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤ እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና።</verse>
				<verse number="18">ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።</verse>
				<verse number="19">እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።</verse>
				<verse number="20">ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?</verse>
				<verse number="21">እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፥ ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል።</verse>
				<verse number="2">እግዚአብሔርን ስንወድ ትእዛዛቱንም ስናደርግ የእግዚአብሔርን ልጆች እንድንወድ በዚህ እናውቃለን።</verse>
				<verse number="3">ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።</verse>
				<verse number="4">ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።</verse>
				<verse number="5">ኢየሱስም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ከሚያምን በቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማን ነው?</verse>
				<verse number="6">በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በውኃውና በደሙ እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም።</verse>
				<verse number="7">መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው።</verse>
				<verse number="8">የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፤ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ።</verse>
				<verse number="9">የሰውን ምስክር ብንቀበል የእግዚአብሔር ምስክር ከእርሱ ይልቅ ይበልጣል፤ ስለ ልጁ የመሰከረው የእግዚአብሔር ምስክር ይህ ነውና።</verse>
				<verse number="10">በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው፤ በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል።</verse>
				<verse number="11">እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው።</verse>
				<verse number="12">ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።</verse>
				<verse number="13">የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።</verse>
				<verse number="14">በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል።</verse>
				<verse number="15">የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን።</verse>
				<verse number="16">ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይለምን፥ ሞትም የማይገባውን ኃጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል። ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ፤ ስለዚያ እንዲጠይቅ አልልም።</verse>
				<verse number="17">ዓመፃ ሁሉ ኃጢአት ነው፥ ሞትም የማይገባው ኃጢአት አለ።</verse>
				<verse number="18">ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን እንዳያደርግ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተወለደው ራሱን እንዲጠብቅ ክፉውም እንዳይነካው እናውቃለን።</verse>
				<verse number="19">ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።</verse>
				<verse number="20">የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።</verse>
				<verse number="21">ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="63">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">በእኛ ስለሚኖርና ከእኛ ጋር ለዘላለም ስለሚሆን እውነት፥ እኔ ሽማግሌው በእውነት ለምወዳቸውና እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ደግሞ ለሚወዱአቸው ለተመረጠች እመቤትና ለልጆችዋ፤</verse>
				<verse number="2"></verse>
				<verse number="3">ከእግዚአብሔር አብና ከአብ ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም በእውነትና በፍቅር ከእኛ ጋር ይሆናሉ።</verse>
				<verse number="4">ትእዛዝን ከአብ እንደ ተቀበልን ከልጆችሽ በእውነት የሚሄዱ አንዳንዶችን ስለ አገኘኋቸው እጅግ ደስ ብሎኛል።</verse>
				<verse number="5">አሁንም እመቤት ሆይ! እርስ በርሳችን እንድንዋደድ እለምንሻለሁ፤ ይህች ከመጀመሪያ በእኛ ዘንድ የነበረች ትእዛዝ ናት እንጂ አዲስ ትእዛዝን እንደምጽፍልሽ አይደለም።</verse>
				<verse number="6">እንደ ትእዛዛቱም እንሄድ ዘንድ ይህ ፍቅር ነው፤ ከመጀመሪያ እንደ ሰማችሁ፥ በእርስዋ ትሄዱ ዘንድ ትእዛዙ ይህች ናት።</verse>
				<verse number="7">ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ገብተዋልና፤ እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ናቸው፤ ይህ አሳቹና የክርስቶስ ተቃዋሚው ነው።</verse>
				<verse number="8">ሙሉ ደመወዝን እንድትቀበሉ እንጂ የሠራችሁትን እንዳታጠፉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።</verse>
				<verse number="9">ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።</verse>
				<verse number="10">ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት፤ ሰላምም አትበሉት፤</verse>
				<verse number="11">ሰላም የሚለው ሰው በክፉ ሥራው ይካፈላልና።</verse>
				<verse number="12">እንድጽፍላችሁ የምፈልገው ብዙ ነገር ሳለኝ በወረቀትና በቀለም ልጽፈው አልወድም፤ ዳሩ ግን ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ወደ እናንተ ልመጣ አፍ ለአፍም ልናገራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።</verse>
				<verse number="13">የተመረጠችው የእኅትሽ ልጆች ሰላምታ ያቀርቡልሻል።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="64">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">ሽማግሌው በእውነት እኔ ለምወደው ለተወደደው ለጋይዮስ።</verse>
				<verse number="2">ወዳጅ ሆይ! ነፍስህ እንደሚከናወን፥ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ።</verse>
				<verse number="3">ወንድሞች መጥተው አንተ በእውነት እንደምትሄድ ስለ እውነትህ ሲመሰክሩ እጅግ ደስ ብሎኛልና።</verse>
				<verse number="4">ልጆቼ በእውነት እንዲሄዱ ከመስማት ይልቅ የሚበልጥ ደስታ የለኝም።</verse>
				<verse number="5">ወዳጅ ሆይ! ምንም እንግዶች ቢሆኑ፥ ለወንድሞች በምታደርገው ሁሉ የታመነ ሥራ ትሠራለህ፤</verse>
				<verse number="6">እነርሱም በማኅበር ፊት ስለ ፍቅርህ መስክረዋል፤ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ አድርገህ በጉዞአቸው ብትረዳ መልካም ታደርጋለህ፤</verse>
				<verse number="7">ከአሕዛብ አንዳች ሳይቀበሉ ስለ ስሙ ወጥተዋልና።</verse>
				<verse number="8">እንግዲህ ከእውነት ጋር አብረን እንድንሠራ እኛ እንዲህ ያሉትን በእንግድነት ልንቀበል ይገባናል።</verse>
				<verse number="9">ወደ ቤተ ክርስቲያን ጻፍሁ፤ ዳሩ ግን ዋናቸው ሊሆን የሚወድ ዲዮጥራፊስ አይቀበለንም።</verse>
				<verse number="10">ስለዚህ እኔ ብመጣ፥ በእኛ ላይ በክፉ ቃል እየለፈለፈ የሚያደርገውን ሥራውን አሳስባለሁ፤ ይህም ሳይበቃው እርሱ ራሱ ወንድሞችን አይቀበልም፤ ሊቀበሉአቸውም የሚወዱትን ከልክሎ ከቤተ ክርስቲያን ያወጣቸዋል።</verse>
				<verse number="11">ወዳጅ ሆይ! በጎ የሆነውን እንጂ ክፉን አትምሰል። በጎ የሚያደርግ ከእግዚአብሔር ነው፤ ክፉን የሚያደርግ ግን እግዚአብሔርን አላየውም።</verse>
				<verse number="12">ለድሜጥሮስ ሁሉ ይመሰክሩለታል፤ እውነት ራስዋም ትመሰክርለታለች፤ እኛም ደግሞ እንመሰክርለታለን፤ ምስክርነታችንም እውነት እንደ ሆነ ታውቃላችሁ።</verse>
				<verse number="13">ልጽፍልህ የምፈልገው ብዙ ነገር ነበረኝ፤ ዳሩ ግን በቀለምና በብርዕ ልጽፍልህ አልወድም፤</verse>
				<verse number="14">ነገር ግን ወዲያው ላይህ ተስፋ አደርጋለሁ፤ አፍ ለአፍም እንነጋገራለን።</verse>
				<verse number="15">ሰላም ለአንተ ይሁን። ወዳጆች ሰላምታ ያቀርቡልሃል። ወዳጆችን በየስማቸው እየጠራህ ሰላምታ አቅርብልኝ።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="65">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ፥ በእግዚአብሔር አብ ተወደው ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ፤</verse>
				<verse number="2">ምሕረትና ሰላም ፍቅርም ይብዛላችሁ።</verse>
				<verse number="3">ወዳጆች ሆይ! ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።</verse>
				<verse number="4">ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኀጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ፤ ብቻውን ንጉሣችንንና ጌታችንንም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።</verse>
				<verse number="5">ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ ከግብጽ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።</verse>
				<verse number="6">መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል።</verse>
				<verse number="7">እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።</verse>
				<verse number="8">እንዲሁም እነዚህ ሰዎች ደግሞ እያለሙ ሥጋቸውን ያረክሳሉ፤ ጌትነትንም ይጥላሉ፤ ሥልጣን ያላቸውንም ይሳደባሉ።</verse>
				<verse number="9">የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር “ጌታ ይገሥጽህ!” አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።</verse>
				<verse number="10">እነዚህ ግን የማያውቁትን ሁሉ ይሳደባሉ፤ አእምሮም እንደሌላቸው እንስሶች በፍጥረታቸው በሚያውቁት ሁሉ በእርሱ ይጠፋሉ።</verse>
				<verse number="11">ወዮላቸው! በቃየል መንገድ ሄደዋልና፤ ስለ ደመወዝም ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል፤ በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል።</verse>
				<verse number="12">እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፤ እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፤ በነፋስ የተወሰዱ ውሃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥</verse>
				<verse number="13">የገዛ ነውራቸውን አረፋ እየደፈቁ ጨካኝ የባሕር ማዕበል፥ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው።</verse>
				<verse number="14">ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ “እነሆ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኀጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኀጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዐመፀኞችም ኀጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኀጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል፤” ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።</verse>
				<verse number="15"></verse>
				<verse number="16">እነዚህ እንደ ምኞታቸው እየሄዱ የሚያንጎራጉሩና ስለ ዕድላቸው የሚያጕረመርሙ ናቸው፤ እንዲረባቸውም ለሰው ፊት እያደሉ አፋቸው ከመጠን ይልቅ ታላቅ ቃል ይናገራል።</verse>
				<verse number="17">እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ! በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤</verse>
				<verse number="18">እነርሱ “በመጨረሻው ዘመን በኀጢአተኝነት እንደ ገዛ ምኞታቸው እየሄዱ ዘባቾች ይሆናሉ፤” ብለዋችኋልና።</verse>
				<verse number="19">እነዚህ የሚያለያዩ ሥጋውያንም የሆኑ መንፈስም የሌላቸው ሰዎች ናቸው።</verse>
				<verse number="20">እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ! ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥</verse>
				<verse number="21">ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።</verse>
				<verse number="22">አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፤ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፤</verse>
				<verse number="23">አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ።</verse>
				<verse number="24">ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው፤</verse>
				<verse number="25">ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኀይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።</verse>
			</chapter>
		</book>
		<book number="66">
			<chapter number="1">
				<verse number="1">ቶሎ ይሆን ዘንድ የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው በእርሱም የተገለጠው ይህ ነው፤ ኢየሱስም በመልአኩ ልኮ ለባሪያው ለዮሐንስ አመለከተ፤</verse>
				<verse number="2">እርሱም ለእግዚአብሔር ቃልና ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ላየውም ሁሉ መሰከረ።</verse>
				<verse number="3">ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው።</verse>
				<verse number="4">ዮሐንስ በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ ካለውና ከነበረው፥ ከሚመጣውም፥ በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት፥ ከታመነውም ምስክር፥ ከሙታንም በኵር፥ የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለወደደን፥ ከኀጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥</verse>
				<verse number="5"></verse>
				<verse number="6">መንግሥትም፥ ለአባቱም ለእግዚአብሔር ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኀይል ይሁን፤ አሜን።</verse>
				<verse number="7">እነሆ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዐይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፤ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፤ አሜን።</verse>
				<verse number="8">ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ “አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ፤” ይላል።</verse>
				<verse number="9">እኔ ወንድማችሁ የሆንሁ ከእናንተም ጋር አብሬ መከራውንና መንግሥቱን የኢየሱስ ክርስቶስንም ትዕግሥት የምካፈል ዮሐንስ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ምስክር ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ።</verse>
				<verse number="10">በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ፤</verse>
				<verse number="11">እንዲሁም “የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊላደልፊያም ወደ ሎዲቅያም በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ፤” አለኝ።</verse>
				<verse number="12">የሚናገረኝንም ድምፅ ለማየት ዘወር አልሁ፤ ዘወርም ብዬ ሰባት የወርቅ መቅረዞች አየሁ፤</verse>
				<verse number="13">በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፤ እርሱም እስከ እግሩ ድረስ ልብስ የለበሰ ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር።</verse>
				<verse number="14">ራሱና የራሱ ጠጕርም እንደ ነጭ የበግ ጠጕር እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፤ ዐይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፤</verse>
				<verse number="15">እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፤ ድምፁም እንደ ብዙ ውሃዎች ድምፅ ነበረ።</verse>
				<verse number="16">በቀኝ እጁም ሰባት ከዋክብት ነበሩት፤ ከአፉም በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ወጣ፤ ፊቱም በኀይል እንደሚበራ እንደ ፀሐይ ነበረ።</verse>
				<verse number="17">ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ፤ እንዲህም አለኝ “አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው እኔ ነኝ፤</verse>
				<verse number="18">ሕያውም እኔ ነኝ፤ ሞቼም ነበርሁ፤ እነሆም ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፤ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።</verse>
				<verse number="19">እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ።</verse>
				<verse number="20">በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="2">
				<verse number="1">“በኤፌሶን ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ በቀኝ እጁ ሰባቱን ከዋክብት የያዘው በሰባቱም የወርቅ መቅረዞች መካከል የሚሄደው እንዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="2">“ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንዳትችል፥ እንዲሁም ሳይሆኑ ‘ሐዋርያት ነን’ የሚሉቱን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ፤</verse>
				<verse number="3">ታግሠህማል፤ ስለ ስሜም ብለህ ጸንተህ አልደከምህም።</verse>
				<verse number="4">ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና።</verse>
				<verse number="5">እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ፤ ንስሓም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሓም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ።</verse>
				<verse number="6">ነገር ግን ይህ አለህ፤ እኔ ደግሞ የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ጠልተሃልና።</verse>
				<verse number="7">መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ።</verse>
				<verse number="8">“በሰምርኔስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ ሞቶ የነበረው ሕያውም የሆነው ፊተኛውና መጨረሻው እንዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="9">“መከራህንና ድህነትህን አውቃለሁ፤ ነገር ግን ባለ ጠጋ ነህ፤ የሰይጣንም ማኅበር ናቸው እንጂ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ የሚሉት የሚሳደቡትን ስድብ አውቃለሁ።</verse>
				<verse number="10">ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ። እነሆ እንድፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፤ ዐሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።</verse>
				<verse number="11">መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል የነሣው በሁለተኛው ሞት አይጐዳም።</verse>
				<verse number="12">“በጴርጋሞንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ያለው እንዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="13">“የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፤ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ ሃይማኖቴን አልካድህም።</verse>
				<verse number="14">ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።</verse>
				<verse number="15">እንዲሁ የኒቆላውያንን ትምህርት እንደ እነዚህ የሚጠብቁ ሰዎች ከአንተ ጋር ደግሞ አሉ።</verse>
				<verse number="16">እንግዲህ ንስሓ ግባ፤ አለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፤ በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ።</verse>
				<verse number="17">መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፤ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፤ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል።</verse>
				<verse number="18">“በትያጥሮንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ እንደ እሳት ነበልባል የሆኑ ዐይኖች ያሉት በእቶንም የነጠረ የጋለ ናስ የሚመስሉ እግሮች ያሉት የእግዚአብሔር ልጅ እንዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="19">“ሥራህንና ፍቅርህን እምነትህንም አገልግሎትህንም ትዕግሥትህንም ከፊተኛውም ሥራህ ይልቅ የኋለኛው እንዲበዛ አውቃለሁ።</verse>
				<verse number="20">ዳሩ ግን ‘ነቢይ ነኝ’ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤</verse>
				<verse number="21">ንስሓም እንድትገባ ጊዜ ሰጠኋት ከዝሙትዋም ንስሓ እንድትገባ አልወደደችም።</verse>
				<verse number="22">እነሆ በአልጋ ላይ እጥላታለሁ፤ ከእርስዋም ጋር የሚያመነዝሩትን ከሥራዋ ንስሓ ባይገቡ በታላቅ መከራ እጥላቸዋለሁ፤</verse>
				<verse number="23">ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።</verse>
				<verse number="24">ዳሩ ግን ይህን ትምህርት ለማትይዙ ሁሉ የሰይጣንንም ጥልቅ ነገር እነርሱ እንደሚሉት ለማታውቁ ለእናንተ በትያጥሮን ለቀራችሁት እላለሁ፤ ሌላ ሸክም አልጭንባችሁም፤</verse>
				<verse number="25">ነገር ግን እስክመጣ ድረስ ያላችሁን ጠብቁ።</verse>
				<verse number="26">ድል ለነሣውና እስከ መጨረሻም ሥራዬን ለጠበቀው እኔ ደግሞ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ በአሕዛብ ላይ ሥልጣንን እሰጠዋለሁ፤ በብረትም በትር ይገዛቸዋል፤ እንደ ሸክላ ዕቃም ይቀጠቀጣሉ፤</verse>
				<verse number="27"></verse>
				<verse number="28">የንጋትንም ኮከብ እሰጠዋለሁ።</verse>
				<verse number="29">መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="3">
				<verse number="1">“በሰርዴስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስትና ሰባቱ ከዋክብት ያሉት እንዲህ ይላል “ሥራህን አውቃለሁ፤ ሕያው እንደ መሆንህ ስም አለህ፤ ሞተህማል።</verse>
				<verse number="2">ሥራህን በአምላኬ ፊት ፍጹም ሆኖ አላገኘሁትምና የነቃህ ሁን፤ ሊሞቱም ያላቸውን የቀሩትን ነገሮች አጽና።</verse>
				<verse number="3">እንግዲህ እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስብ፤ ጠብቀውም፤ ንስሓም ግባ። እንግዲያስ ባትነቃ እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ፤ በማናቸውም ሰዓት እንድመጣብህ ከቶ አታውቅም።</verse>
				<verse number="4">ነገር ግን ልብሳቸውን ያላረከሱ በሰርዴስ ጥቂት ሰዎች ከአንተ ጋር አሉ፤ የተገባቸውም ስለ ሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።</verse>
				<verse number="5">ድል የነሣው እንዲሁ በነጭ ልብስ ይጐናጸፋል፤ ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስስም፤ በአባቴና በመላእክቱም ፊት ለስሙ እመሰክርለታለሁ።</verse>
				<verse number="6">መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።</verse>
				<verse number="7">“በፊላደልፊያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ የዳዊት መክፈቻ ያለው፥ የሚከፍት፥ የሚዘጋም የሌለ፤ የሚዘጋ፥ የሚከፍትም የሌለ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="8">“ሥራህን አውቃለሁ፤ እነሆ በአንተ ፊት የተከፈተ በር ሰጥቼአለሁ፤ ማንም ሊዘጋውም አይችልም፤ ኀይልህ ምንም ትንሽ ቢሆን ቃሌን ጠብቀሃልና፤ ስሜንም አልካድህምና።</verse>
				<verse number="9">እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።</verse>
				<verse number="10">የትዕግሥቴን ቃል ስለ ጠበቅህ እኔ ደግሞ በምድር የሚኖሩትን ይፈትናቸው ዘንድ በዓለም ሁሉ ላይ ሊመጣ ካለው ከፈተናው ሰዓት እጠብቅሃለሁ።</verse>
				<verse number="11">እነሆ ቶሎ ብዬ እመጣለሁ፤ ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን አጽንተህ ያዝ።</verse>
				<verse number="12">ድል የነሣው በአምላኬ መቅደስ ዓምድ እንዲሆን አደርገዋለሁ፤ ወደ ፊትም ከዚያ ከቶ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም፥ ማለት ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደውን አዲሲቱን ኢየሩሳሌምን፥ አዲሱንም ስሜን በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።</verse>
				<verse number="13">መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።</verse>
				<verse number="14">“በሎዲቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል፦</verse>
				<verse number="15">“በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር።</verse>
				<verse number="16">እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።</verse>
				<verse number="17">‘ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ፤ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም፤’ የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥</verse>
				<verse number="18">ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዐይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ።</verse>
				<verse number="19">እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና፤ ንስሓም ግባ።</verse>
				<verse number="20">እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ፤ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ፤ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።</verse>
				<verse number="21">እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፥ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ።</verse>
				<verse number="22">መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="4">
				<verse number="1">ከዚያ በኋላም አየሁ፤ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ “ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ፤” አለ።</verse>
				<verse number="2">ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም ዙፋን በሰማይ ቆሞአል፤ በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤</verse>
				<verse number="3">ተቀምጦም የነበረው በመልኩ የኢያስጲድንና የሰርዲኖን ዕንቍ ይመስል ነበር። በመልኩም መረግድን የመሰለ ቀስተ ደመና በዙፋኑ ዙሪያ ነበረ።</verse>
				<verse number="4">በዙፋኑ ዙሪያም ሃያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፤ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሃያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።</verse>
				<verse number="5">ከዙፋኑም መብረቅና ድምፅ ነጐድጓድም ይወጣል፤ በዙፋኑም ፊት ሰባት የእሳት መብራቶች ይበሩ ነበር፤ እነርሱም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።</verse>
				<verse number="6">በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዐይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።</verse>
				<verse number="7">ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፤ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፤ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፤ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።</verse>
				<verse number="8">አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፤ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዐይኖች ሞልተውባቸዋል፤ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ” እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም።</verse>
				<verse number="9">እንስሶቹም በዙፋን ላይ ለተቀመጠው ከዘላለምም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው ለእርሱ ክብርና ውዳሴ ምስጋናም በሰጡት ጊዜ፥</verse>
				<verse number="10">ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ “ጌታችንና አምላካችን ሆይ! አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኀይልም ልትቀበል ይገባሃል፤” ክብር ውዳሴ ኃይልም እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።</verse>
				<verse number="11"></verse>
			</chapter>
			<chapter number="5">
				<verse number="1">በዙፋኑ ላይም በተቀመጠው በቀኝ እጁ ላይ በውስጥና በኋላ የተጻፈበት በሰባትም ማኅተም የተዘጋ መጽሐፍን አየሁ።</verse>
				<verse number="2">ብርቱም መልአክ “መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ማኅተሞቹንም ይፈታ ዘንድ የሚገባው ማን ነው?” ብሎ በታላቅ ድምፅ ሲያውጅ አየሁ።</verse>
				<verse number="3">በሰማይም ቢሆን በምድርም ላይ ቢሆን ከምድርም በታች ቢሆን መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው ማንም አልተቻለውም።</verse>
				<verse number="4">መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው የሚገባው ማንም ስላልተገኘ እጅግ አለቀስሁ።</verse>
				<verse number="5">ከሽማግሌዎቹም አንዱ “አታልቅስ፤ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፥ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል፤” አለኝ።</verse>
				<verse number="6">በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች መካከልም በሽማግሌዎችም መካከል እንደ ታረደ በግ ቆሞ አየሁ፤ ሰባትም ቀንዶችና ሰባት ዐይኖች ነበሩት፤ እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።</verse>
				<verse number="7">መጥቶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠ ከዚያ ከቀኝ እጁ መጽሐፉን ወሰደው።</verse>
				<verse number="8">መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፤ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።</verse>
				<verse number="9">“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።</verse>
				<verse number="10"></verse>
				<verse number="11">አየሁም፤ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፤</verse>
				<verse number="12">በታላቅም ድምፅ “የታረደው በግ ኀይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል” አሉ።</verse>
				<verse number="13">በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ “በረከትና ክብር ምስጋናም ኀይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን፤” ሲሉ ሰማሁ።</verse>
				<verse number="14">አራቱም እንስሶች ‘አሜን’ አሉ፤ ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="6">
				<verse number="1">በጉም ከሰባቱ ማኅተም አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፤ ከአራቱም እንስሶች አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ “መጥተህ እይ” ሲል ሰማሁ።</verse>
				<verse number="2">አየሁም፤ እነሆም አምባላይ ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፤ አክሊልም ተሰጠው፤ ድልም እየነሣ ወጣ፤ ድል ለመንሣት።</verse>
				<verse number="3">ሁለተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሁለተኛው እንስሳ “መጥተህ እይ” ሲል ሰማሁ።</verse>
				<verse number="4">ሌላም ዳማ ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ ለተቀመጠው ሰላምን ከምድር ይወስድ ዘንድ ሰዎችም እርስ በርሳቸው እንዲተራረዱ ሥልጣን ተሰጠው፤ ታላቅም ሰይፍ ተሰጠው።</verse>
				<verse number="5">ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ “መጥተህ እይ” ሲል ሰማሁ። አየሁም፤ እነሆም ጥቁር ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ያዘ።</verse>
				<verse number="6">በአራቱም እንስሶች መካከል ድምፅ “አንድ እርቦ ስንዴ በዲናር ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፥ ዘይትንና ወይንንም አትጕዳ” ሲል ሰማሁ።</verse>
				<verse number="7">አራተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ የአራተኛው እንስሳ ድምፅ “መጥተህ እይ” ሲል ሰማሁ።</verse>
				<verse number="8">አየሁም፤ እነሆም ሐመር ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።</verse>
				<verse number="9">አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ።</verse>
				<verse number="10">በታላቅ ድምፅም እየጮኹ “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ! እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” አሉ።</verse>
				<verse number="11">ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፤ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው።</verse>
				<verse number="12">ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፤ ታላቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጕር ጥቁር ሆነ፤ ጨረቃም በሞላው እንደ ደም ሆነ፤</verse>
				<verse number="13">በለስም በብርቱ ነፋስ ተናውጣ ቃርያዋን ፍሬ እንደምትጥል የሰማይ ከዋክብት ወደ ምድር ወደቁ፤</verse>
				<verse number="14">ሰማይም እንደ መጽሐፍ ተጠቅልሎ አለፈ፤ ተራራዎችና ደሴቶችም ሁሉ ከስፍራቸው ተወሰዱ።</verse>
				<verse number="15">የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኀይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዐለቶች ተሰወሩ፤</verse>
				<verse number="16">ተራራዎችንና ዐለቶችንም “በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን፤</verse>
				<verse number="17">ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና፤ ማንስ ሊቆም ይችላል?” አሉአቸው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="7">
				<verse number="1">ከዚህም በኋላ በአራቱ የምድር ማዕዘን ቆመው አራት መላእክት አየሁ፤ እነርሱም ነፋስ በምድር ቢሆን ወይም በባሕር ወይም በማንም ዛፍ እንዳይነፍስ አራቱን የምድር ነፋሳት ያዙ።</verse>
				<verse number="2">የሕያው አምላክ ማኅተም ያለውም ሌላ መልአክ ከፀሐይ መውጫ ሲወጣ አየሁ፤ ምድርንና ባሕርንም ሊጐዱ ለተሰጣቸው ለአራቱ መላእክት በታላቅ ድምፅ እየጮኸ</verse>
				<verse number="3">“የአምላካችንን ባሪያዎች ግምባራቸውን እስክናትማቸው ድረስ ምድርን ቢሆን ወይም ባሕርን ወይም ዛፎችን አትጕዱ፤” አላቸው።</verse>
				<verse number="4">የታተሙትንም ቍጥር ሰማሁ፤ ከእስራኤል ልጆች ነገድ ሁሉ የታተሙት መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።</verse>
				<verse number="5">ከይሁዳ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ ታተሙ፤ ከሮቤል ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከጋድ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥</verse>
				<verse number="6">ከአሴር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከንፍታሌም ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከምናሴ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥</verse>
				<verse number="7">ከስምዖን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከሌዊ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከይሳኮር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥</verse>
				<verse number="8">ከዛብሎን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከዮሴፍ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከብንያም ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ ታተሙ።</verse>
				<verse number="9">ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆም አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤</verse>
				<verse number="10">በታላቅም ድምፅ እየጮሁ “ማዳን በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው የአምላካችንና የበጉ ነው!” አሉ።</verse>
				<verse number="11">መላእክቱም ሁሉ በዙፋኑና በሽማግሌዎቹ በአራቱም እንስሶቹ ዙሪያ ቆመው ነበር፤ በዙፋኑም ፊት በግምባራቸው ተደፉ፤ ለእግዚአብሔርም እየሰገዱ</verse>
				<verse number="12">“አሜን በረከትና ገናናነት ጥበብም ምስጋናም ክብርም ኀይልም ብርታትም ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ለአምላካችን ይሁን! አሜን።” አሉ።</verse>
				<verse number="13">ከሽማግሌዎቹም አንዱ ተመልሶ “እነዚህ ነጩን ልብስ የለበሱ እነማን ናቸው? ከወዴትስ መጡ?” አለኝ።</verse>
				<verse number="14">እኔም “ጌታ ሆይ! አንተ ታውቃለህ፤” አልሁት። አለኝም “እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።</verse>
				<verse number="15">ስለዚህ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አሉ፤ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ያመልኩታል፤ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው በእነርሱ ላይ ያድርባቸዋል።</verse>
				<verse number="16">ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም፤ ከእንግዲህም ወዲህ አይጠሙም፤ ፀሐይም ትኵሳትም ሁሉ ከቶ አይወርድባቸውም፤</verse>
				<verse number="17">በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፤ ወደ ሕይወትም ውሃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="8">
				<verse number="1">ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ግማሽ ሰዓት የሚያህል ዝምታ በሰማይ ሆነ።</verse>
				<verse number="2">በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፤ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው።</verse>
				<verse number="3">ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው።</verse>
				<verse number="4">የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ።</verse>
				<verse number="5">መልአኩም ጥናውን ይዞ የመሰዊያውን እሳት ሞላበት፤ ወደ ምድርም ጣለው፤ ነጐድጓድና ድምፅም መብረቅም መናወጥም ሆነ።</verse>
				<verse number="6">ሰባቱንም መለከት የያዙ ሰባቱ መላእክት ሊነፉ ተዘጋጁ።</verse>
				<verse number="7">ፊተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ደምም የተቀላቀለበት በረዶና እሳት ሆነ፤ ወደ ምድርም ተጣለ፤ የምድርም ሲሶው ተቃጠለ፤ የዛፎችም ሲሶው ተቃጠለ፤ የለመለመም ሣር ሁሉ ተቃጠለ።</verse>
				<verse number="8">ሁለተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በእሳት የሚቃጠል ታላቅ ተራራን የሚመስል ነገር በባሕር ተጣለ፤ የባሕርም ሲሶው ደም ሆነ፤</verse>
				<verse number="9">በባሕርም ከሚኖሩ ሕይወት ካላቸው ፍጥረቶች ሲሶው ሞተ፤ የመርከቦችም ሲሶው ጠፋ።</verse>
				<verse number="10">ሦስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እንደ ችቦም የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ፤ በወንዞችና በውሃም ምንጮች ሲሶ ላይ ወደቀ።</verse>
				<verse number="11">የኮከቡም ስም እሬቶ ይባላል፤ የውሃውም ሲሶ መራራ ሆነ፤ መራራም ስለተደረገ በውሃው ጠንቅ ብዙ ሰዎች ሞቱ።</verse>
				<verse number="12">አራተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ የፀሐይ ሲሶና የጨረቃ ሲሶ የከዋክብትም ሲሶ ተመታ፤ የእነዚህ ሲሶ ይጨልም ዘንድ፥ የቀንም ሲሶው እንዳያበራ፥ እንዲሁም የሌሊት።</verse>
				<verse number="13">አየሁም፤ አንድም ንስር በሰማይ መካከል እየበረረ በታላቅ ድምፅ “ሊነፉ ያላቸው የሦስቱ መላእክት መለከት ስለሚቀረው ድምፅ በምድር ላይ ለሚኖሩት ወዮላቸው! ወዮላቸው! ወዮላቸው!” ሲል ሰማሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="9">
				<verse number="1">አምስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ከሰማይም ወደ ምድር ወድቆ የነበረ ኮከብ አየሁ፤ የጥልቁም ጕድጓድ መክፈቻ ተሰጠው።</verse>
				<verse number="2">የጥልቁንም ጕድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ እቶን እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጕድጓዱ ወጣ፤ ፀሐይና አየርም በጕድጓዱ ጢስ ጨለሙ።</verse>
				<verse number="3">ከጢሱም አንበጣዎች ወደ ምድር ወጡ፤ የምድርም ጊንጦች ሥልጣን እንዳላቸው ሥልጣን ተሰጣቸው።</verse>
				<verse number="4">የእግዚአብሔርም ማኅተም በግምባራቸው ከሌለባቸው ሰዎች በቀር በምድር ያለውን ሣር ቢሆንም ወይም ማናቸውንም የለመለመ ነገር ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጐዱ ተባለላቸው።</verse>
				<verse number="5">አምስትም ወር ሊያሰቃዩአቸው ተሰጣቸው እንጂ ሊገድሉአቸው አይደለም፤ እነርሱም የሚያሠቃዩት ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ነድፎ እንደሚያሠቃይ ነው።</verse>
				<verse number="6">በዚያም ወራት ሰዎች ሞትን ይፈልጋሉ፤ አያገኙትምም፤ ሊሞቱም ይመኛሉ፤ ሞትም ከእነርሱ ይሸሻል።</verse>
				<verse number="7">የአንበጣዎቹም መልክ ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ፈረሶች ነው፤ በራሳቸውም ላይ ወርቅ የሚመስሉ አክሊሎች ነበሩአቸው፤ ፊታቸውም እንደ ሰው ፊት ነበረ፤</verse>
				<verse number="8">የሴቶችን ጠጕር የሚመስል ጠጕር ነበራቸው፤ ጥርሳቸውም እንደ አንበሳ ጥርስ ነበረ፤</verse>
				<verse number="9">የብረት ጥሩር የሚመስልም ጥሩር ነበራቸው፤ የክንፋቸውም ድምፅ ወደ ጦርነት እንደሚጋልቡ እንደ ብዙ ፈረሶች ሰረገላዎች ድምፅ ነበረ።</verse>
				<verse number="10">እንደ ጊንጥም ጅራት ያለ ጅራት አላቸው፤ በጅራታቸውም መውጊያ አለ፤ ሰዎችንም አምስት ወር እንዲጐዱ ሥልጣን አላቸው።</verse>
				<verse number="11">በእነርሱም ላይ ንጉሥ አላቸው፤ እርሱም የጥልቅ መልአክ ነው፤ ስሙም በዕብራይስጥ አባዶን በግሪክም አጶልዮን ይባላል።</verse>
				<verse number="12">ፊተኛው ወዮ አልፎአል፤ እነሆ ከዚህ በኋላ ገና ሁለት ወዮ ይመጣል።</verse>
				<verse number="13">ስድስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ካለ በወርቅ ከተሠራ መሠዊያ ቀንዶች አንድ ድምፅ ሰማሁ፤</verse>
				<verse number="14">መለከትም ያለውን ስድስተኛውን መልአክ “በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ የታሰሩትን አራቱን መላእክት ፍታቸው፤” አለው።</verse>
				<verse number="15">የሰዎችንም ሲሶ እንዲገድሉ ለሰዓቱና ለቀኑ ለወሩም ለዓመቱም ተዘጋጅተው የነበሩ አራቱ መላእክት ተፈቱ።</verse>
				<verse number="16">የፈረሰኞችም ጭፍራ ቁጥር ሁለት መቶ ሚሊዮን ነበረ፤ ቁጥራቸውን ሰማሁ።</verse>
				<verse number="17">ፈረሶቹንና በእነርሱም ላይ የተቀመጡትን እንዲሁ በራእይ አየሁ፤ እሳትና ያክንት ዲንም የሚመስል ጥሩር ነበራቸው፤ የፈረሶቹም ራስ እንደ አንበሳ ራስ ነበረ፤ ከአፋቸውም እሳትና ጢስ ዲንም ወጣ።</verse>
				<verse number="18">ከአፋቸውም በወጡት በእሳቱና በጢሱ በዲኑም በእነዚህ ሦስት መቅሰፍቶች የሰዎቹ ሲሶ ተገደለ።</verse>
				<verse number="19">የፈረሶቹ ሥልጣን በአፋቸውና በጅራታቸው ነውና፥ ጅራታቸው እባብን ይመስላልና፥ ራስም አላቸው፤ በእርሱም ይጐዳሉ።</verse>
				<verse number="20">በእነዚህም መቅሠፍቶች ያልተገደሉት የቀሩቱ ሰዎች ለአጋንንትና ያዩ ወይም ይሰሙ ወይም ይሄዱ ዘንድ ለማይችሉ ከወርቅና ከብር ከናስም ከድንጋይም ከእንጨትም ለተሠሩ ለጣዖቶች እንዳይሰግዱ ስለ እጃቸው ሥራ ንስሓ አልገቡም፤</verse>
				<verse number="21">ስለ መግደላቸውም ቢሆን ወይም ስለ አስማታቸው ወይም ስለ ዝሙታቸው ወይም ስለ ስርቆታቸው ንስሓ አልገቡም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="10">
				<verse number="1">ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፤</verse>
				<verse number="2">የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፤ እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።</verse>
				<verse number="3">በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ።</verse>
				<verse number="4">ሰባቱ ነጐድጓድ በተናገሩ ጊዜ ልጽፍ አሰብሁ፤ ከሰማይም “ሰባቱ ነጐድጓዶች የተናገሩትን ነገር በማኅተም ዝጋው፤ አትጻፈውም፤” የሚል ድምፅ ሰማሁ።</verse>
				<verse number="5">በባሕርና በምድርም ላይ ሲቆም ያየሁት መልአክ ቀኝ እጁን ወደ ሰማይ አሻቅቦ ዘረጋ፤</verse>
				<verse number="6">ሰማይንና በእርሱም ያሉትን፥ ምድርንና በእርስዋም ያሉትን፥ ባሕርንና በእርሱም ያሉትን በፈጠረው፥ ከዘላለምም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ሆኖ በሚኖረው ምሎ</verse>
				<verse number="7">“ወደ ፊት አይዘገይም፤ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል፤” አለ።</verse>
				<verse number="8">ከሰማይም የሰማሁት ድምፅ እንደ ገና ሲናገረኝና “ሂድና በባሕርና በምድር ላይ ከሚቆመው መልአክ በእጁ ያለችውን የተከፈተችውን መጽሐፍ ውሰድ፤” ሲል ሰማሁ።</verse>
				<verse number="9">ወደ መልአኩም ሄጄ “ታናሺቱን መጽሐፍ ስጠኝ፤” አልሁት። እርሱም “ውሰድና ብላት፤ ሆድህንም መራራ ታደርገዋለች፤ በአፍህ ግን እንደ ማር ትጣፍጣለች፤” አለኝ።</verse>
				<verse number="10">ከመልአኩም እጅ ታናሺቱን መጽሐፍ ወስጄ በላኋት፤ በአፌም እንደ ማር ጣፋጭ ሆነች፤ ከበላኋት በኋላም ሆዴ መራራ ሆነ።</verse>
				<verse number="11">“በብዙ ወገኖችና በአሕዛብም በቋንቋዎችም በነገሥታትም ላይ እንደ ገና ትንቢት ትናገር ዘንድ ይገባሃል፤” ተባልሁ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="11">
				<verse number="1">በትር የሚመስል መለኪያ ለእኔ ተሰጠኝ፤ እንዲህም ተባልሁ “ተነሥተህ የእግዚአብሔርን መቅደስና መሠዊያውን በዚያም የሚሰግዱትን ለካ።</verse>
				<verse number="2">በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው፤ አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።</verse>
				<verse number="3">ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።”</verse>
				<verse number="4">እነዚህ በምድር ጌታ ፊት የሚቆሙ ሁለቱ ወይራዎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው።</verse>
				<verse number="5">ማንምም ሊጐዳቸው ቢወድ እሳት ከአፋቸው ይወጣል፤ ጠላቶቻቸውንም ይበላል፤ ማንም ሊጐዳቸው ቢወድም እንዲሁ ሊገደል ይገባዋል።</verse>
				<verse number="6">እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ሊዘጉ ሥልጣን አላቸው፤ ውሕሃዎችንም ወደ ደም ሊለውጡ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሠፍት ሁሉ ምድርን ሊመቱ ሥልጣን አላቸው።</verse>
				<verse number="7">ምስክራቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከጥልቁ የሚወጣው አውሬ ይዋጋቸዋል፤ ያሸንፋቸውማል፤ ይገድላቸውማል።</verse>
				<verse number="8">በድናቸውም በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይተኛል፤ እርስዋም በመንፈሳዊ ምሳሌ ሰዶምና ግብጽ የተባለች ደግሞ ጌታቸው የተሰቀለባት ናት።</verse>
				<verse number="9">ከወገኖችና ከነገዶችም ከቋንቋዎችም ከአሕዛብም የሆኑ ሰዎች ሦስት ቀን ተኵል በድናቸውን ይመለከታሉ፤ በድናቸውም ወደ መቃብር ሊገባ አይፈቅዱም።</verse>
				<verse number="10">እነዚህም ሁለት ነቢያት በምድር የሚኖሩትን ስላሠቃዩ በምድር የሚኖሩት በእነርሱ ላይ ደስ ይላቸዋል፤ በደስታም ይኖራሉ፤ እርስ በርሳቸውም ስጦታ ይሰጣጣሉ።</verse>
				<verse number="11">ከሦስቱ ቀን ተኵልም በኋላ ከእግዚአብሔር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው፤ በእግሮቻቸውም ቆሙ፤ ታላቅም ፍርሃት በሚመለከቱት ላይ ወደቀባቸው።</verse>
				<verse number="12">በሰማይም “ወደዚህ ውጡ” የሚላቸውን ታላቅ ድምፅ ሰሙ፤ ጠላቶቻቸውም እየተመለከቱአቸው ወደ ሰማይ በደመና ወጡ።</verse>
				<verse number="13">በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ከከተማይቱም ዐሥረኛው እጅ ወደቀ፤ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፤ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፤ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ።</verse>
				<verse number="14">ሁለተኛው ወዮ አልፎአል፤ እነሆ ሦስተኛው ወዮ በቶሎ ይመጣል።</verse>
				<verse number="15">ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም “የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል፤”</verse>
				<verse number="16">የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ሆኑ። በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው የተቀመጡ ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው</verse>
				<verse number="17">ለእግዚአብሔር እየሰገዱ እንዲህ አሉ “ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ትልቁን ኀይልህን ስለ ያዝህ ስለ ነገሥህም እናመሰግንሃለን፤</verse>
				<verse number="18">አሕዛብም ተቈጡ፤ ቍጣህም መጣ፤ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፤ ለባሪያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ፥ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ።”</verse>
				<verse number="19">በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፤ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፤ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="12">
				<verse number="1">ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ፤ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የዐሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የተቀዳጀች አንዲት ሴት ነበረች።</verse>
				<verse number="2">እርስዋም ፀንሳ ነበር፤ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጭንቃ ጮኸች።</verse>
				<verse number="3">ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ ይኸውም ታላቅ ቀይ ዘንዶነው፤ ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶችም ነበሩት፤ በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ፤</verse>
				<verse number="4">ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።</verse>
				<verse number="5">አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ።</verse>
				<verse number="6">ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቡአት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሓ ሸሸች።</verse>
				<verse number="7">በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፤</verse>
				<verse number="8">አልቻላቸውምም፤ ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም።</verse>
				<verse number="9">ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።</verse>
				<verse number="10">ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ፤ እንዲህ ሲል “አሁን የአምላካችን ማዳንና ኀይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፤ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸውየወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።</verse>
				<verse number="11">እነርሱም በበጉ ደም በምስክራቸውም ቃል ድል ነሡት፤ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም።</verse>
				<verse number="12">ስለዚህ ሰማይና በውስጡ የምታድሩ ሆይ! ደስይበላችሁ፤ ለምድርና ለባሕር ወዮላቸው፤ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና።”</verse>
				<verse number="13">ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት።</verse>
				<verse number="14">ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሓ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።</verse>
				<verse number="15">እባቡም ሴቲቱ በወንዝ እንድትወሰድ ሊያደርግ ወንዝ የሚያህልን ውሃ ከአፉ በስተ ኋላዋ አፈሰሰ።</verse>
				<verse number="16">ምድሪቱም ሴቲቱን ረዳቻት፤ ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው።</verse>
				<verse number="17">ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤</verse>
				<verse number="18">በባሕርም አሸዋ ላይ ቆመ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="13">
				<verse number="1">አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ ዐሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፤ በቀንዶቹም ላይ ዐሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።</verse>
				<verse number="2">ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኀይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው።</verse>
				<verse number="3">ከራሶቹም ለሞት እንደ ታረደ ሆኖ አንዱን አየሁ፤ ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰ። ምድርም ሁሉ አውሬውን እየተከተለ ተደነቀ፤</verse>
				<verse number="4">ለዘንዶውም ሰገዱለት፤ ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና፤ ለአውሬውም “አውሬውን ማን ይመስለዋል? እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል?” እያሉ ሰገዱለት።</verse>
				<verse number="5">ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፤ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።</verse>
				<verse number="6">እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ።</verse>
				<verse number="7">ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፤ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው።</verse>
				<verse number="8">ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ ሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል።</verse>
				<verse number="9">ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ።</verse>
				<verse number="10">ይማረክ ዘንድ ያለው ማንም ቢኖር ወደ ምርኮነት ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል። የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት በዚህ ነው።</verse>
				<verse number="11">ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፤ የበግ ቀንዶችን የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት እንደ ዘንዶም ይናገር ነበር።</verse>
				<verse number="12">በፊተኛውም አውሬ ሥልጣን በእርሱ ፊት ሁሉን ያደርጋል። ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰለት፤ ለፊተኛው አውሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል።</verse>
				<verse number="13">እሳትንም እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር በሰው ፊት እስኪያወርድ ድረስ ታላላቆችን ምልክቶች ያደርጋል።</verse>
				<verse number="14">በአውሬውም ፊት ያደርግ ዘንድ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል፤ የሰይፍም ቍስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬው ምስልን እንዲያደርጉ በምድር የሚኖሩትን ይናገራል።</verse>
				<verse number="15">የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።</verse>
				<verse number="16">ታናናሾችና ታላላቆችም ባለጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፥</verse>
				<verse number="17">የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል።</verse>
				<verse number="18">ጥበብ በዚህ አለ። አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፤ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="14">
				<verse number="1">አየሁም፤ እነሆም በጉ በጽዮን ተራራ ቆሞ ነበር፤ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱ ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።</verse>
				<verse number="2">እንደ ብዙ ውሃም ድምፅና እንደ ታላቅ ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ከሰማይ ድምፅን ሰማሁ፤ ደርዳሪዎችም በገና እንደሚደረድሩ ያለ ድምፅ ሰማሁ።</verse>
				<verse number="3">በዙፋኑም ፊት በአራቱም እንስሶችና በሽማግሌዎቹ ፊት አዲስ ቅኔ ዘመሩ፤ ከምድርም ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራት ሺህ በቀር ያን ቅኔ ሊማር ለማንም አልተቻለውም።</verse>
				<verse number="4">ከሴቶች ጋር ያልረከሱ እነዚህ ናቸው፤ ድንግሎች ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበት የሚከተሉት እነዚህ ናቸው። ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው።</verse>
				<verse number="5">በአፋቸውም ውሸት አልተገኘም፤ ነውር የለባቸውም።</verse>
				<verse number="6">በምድርም ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ይሰብክ ዘንድ የዘላለም ወንጌል ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤</verse>
				<verse number="7">በታላቅ ድምፅም “የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ክብርንም ስጡት፤ ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውሃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት፤” አለ።</verse>
				<verse number="8">ሌላም ሁለተኛ መልአክ “አሕዛብን ሁሉ የዝሙትዋን ቍጣ ወይን ጠጅ ያጠጣች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች!” እያለ ተከተለው።</verse>
				<verse number="9">ሦስተኛም መልአክ በታላቅ ድምፅ እንዲህ እያለ ተከተላቸው፤ “ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግድ በግምባሩም ወይም በእጁ ምልክቱን የሚቀበል ማንም ቢኖር፥</verse>
				<verse number="10">እርሱ ደግሞ በቍጣው ጽዋ ሳይቀላቅል ከተዘጋጀው ከእግዚአብሔር ቍጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል፤ በቅዱሳንም መላእክትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሰቃያል።</verse>
				<verse number="11">የሥቃያቸውም ጢስ ለዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ይወጣል፤ ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት የሚቀበል ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።”</verse>
				<verse number="12">የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁት ኢየሱስንም በማመን የሚጸኑት ቅዱሳን ትዕግሥታቸው በዚህ ነው።</verse>
				<verse number="13">ከሰማይም እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ። “ይህንን ጻፍ፡ ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው።” መንፈስም “አዎን! ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸውም ይከተላቸዋል፤” ይላል።</verse>
				<verse number="14">አየሁም፤ እነሆም ነጭ ደመና በደመናውም ላይ የሰውን ልጅ የሚመስል ተቀምጦአል፤ በራሱም ላይ የወርቅ አክሊል በእጁም ስለታም ማጭድ ነበረው።</verse>
				<verse number="15">ሌላ መልአክም ከመቅደሱ ወጥቶ በደመናው ላይ ለተቀመጠው “የማጨድ ሰዓት ስለ ደረሰ ማጭድህን ስደድና እጨድ፤ የምድሪቱ መከር ጠውልጓልና፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።</verse>
				<verse number="16">በደመናውም ላይ የተቀመጠው ማጭዱን ወደ ምድር ጣለው፤ ምድርም ታጨደች።</verse>
				<verse number="17">ሌላ መልአክም በሰማይ ካለው መቅደስ ወጣ፤ እርሱም ደግሞ ስለታም ማጭድ ነበረው።</verse>
				<verse number="18">በእሳትም ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ ስለታም ማጭድ ያለውን “ዘለላዎቹ ፈጽመው በስለዋልና ስለታሙን ማጭድህን ስደድና በምድር ያለውን የወይን ዛፍ ዘለላዎች ቍረጥ፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጠራ።</verse>
				<verse number="19">መልአኩም ማጭዱን ወደ ምድር ጣለው፤ በምድርም ካለው ከወይን ዛፍ ቈርጦ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር ቍጣ መጥመቂያ ጣለ።</verse>
				<verse number="20">የወይኑም መጥመቂያ ከከተማ ውጭ ተረገጠ፤ እስከ ፈረሶች ልጓምም የሚደርስ ደም ርቀቱ ሺህ ስድስት መቶ ምዕራፍ ሆኖ ከመጥመቂያው ወጣ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="15">
				<verse number="1">ሌላም ታላቅና ድንቅ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ የእግዚአብሔር ቍጣ በእነርሱ ስለሚፈጸም ኋለኛዎቹን ሰባት መቅሠፍቶች የያዙ ሰባት መላእክት ታዩ።</verse>
				<verse number="2">በእሳትም የተቀላቀለውን የብርጭቆ ባሕር የሚመስለውን አየሁ፤ በአውሬውና በምስሉም በስሙም ቍጥር ላይ ድል ነሥተው የነበሩት የእግዚአብሔርን በገና ይዘው በብርጭቆ ባሕር ላይ ሲቆሙ አየሁ።</verse>
				<verse number="3">“ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ! የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፤ የጽድቅም ሥራህ ስለ ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፤ በፊትህም ይሰግዳሉ፤” እያሉ የእግዚአብሔርን ባሪያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ።</verse>
				<verse number="4"></verse>
				<verse number="5">ከዚህም በኋላ አየሁ፤ የምስክርም ድንኳን መቅደስ በሰማይ ተከፈተ፤</verse>
				<verse number="6">ሰባቱንም መቅሠፍት የያዙ ሰባቱ መላእክት ከመቅደሱ ወጡ፤ ከተልባ እግርም የተሠራ ጥሩ የጌጥ ልብስ ለበሱ፤ ደረታቸውንም በወርቅ መታጠቂያ ታጠቁ።</verse>
				<verse number="7">ከአራቱም እንስሶች አንዱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ የሚኖር የእግዚአሔር ቍጣ የሞላባቸውን ሰባት የወርቅ ጽዋዎች ለሰባቱ መላእክት ሰጣቸው።</verse>
				<verse number="8">ከእግዚአብሔርም ክብርና ከኀይሉ ጢስ በመቅደሱ ሞላበት፤ የሰባቱ መላእክት ሰባቱ መቅሰፍት እስኪፈጸሙ ድረስ አንድ እንኳ ወደ መቅደሱ ይገባ ዘንድ አልቻለም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="16">
				<verse number="1">ለሰባቱም መላእክት “ሄዳችሁ የእግዚአብሔርን ቁጣ ጽዋዎች በምድር ውስጥ አፍስሱ፤” የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱ ሰማሁ።</verse>
				<verse number="2">ፊተኛውም ሄዶ ጽዋውን በምድር ውስጥ አፈሰሰ፤ የአውሬውም ምልክት ባለባቸው ለምስሉም በሚሰግዱ ሰዎች ክፉኛ የሚነዘንዝ ቍስል ሆነባቸው።</verse>
				<verse number="3">ሁለተኛውም ጽዋውን በባሕር ውስጥ አፈሰሰ፤ እንደ ሞተም ሰው ደም ሆነ፤ በባሕርም ከሚኖሩት ሕይወት ያለበት ነፍስ ሁሉ ሞተ።</verse>
				<verse number="4">ሦስተኛውም ጽዋውን በወንዞችና በውሃ ምንጮች ውስጥ አፈሰሰ፤ እነርሱም ደም ሆኑ።</verse>
				<verse number="5">የውሃውም መልአክ “ያለህና የነበርህ ጌታ ሆይ! ቅዱስ ሆይ! እንዲህ ስለፈረድህ ጻድቅ ነህ፤</verse>
				<verse number="6">የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ ደምን ደግሞ አጠጥተሃቸዋል፤ የሚገባቸው ነውና፤” ብሎ ሲናገር ሰማሁ።</verse>
				<verse number="7">ከመሰዊያውም “አዎን፤ ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ! ፍርዶችህ እውነትና ጽድቅ ናቸው፤” ብሎ ሲናገር ሰማሁ።</verse>
				<verse number="8">አራተኛውም ጽዋውን በፀሐይ ላይ አፈሰሰ፤ ሰዎችንም በእሳት ልታቃጥል ተሰጣት።</verse>
				<verse number="9">ሰዎችም በታላቅ ትኵሳት ተቃጠሉ፤ በነዚህም መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ፤ ክብርንም እንዲሰጡት ንስሓ አልገቡም።</verse>
				<verse number="10">አምስተኛውም ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ መንግሥቱም ጨለማ ሆነች፤ ከስቃይም የተነሣ መላሶቻቸውን ያኝኩ ነበር፤</verse>
				<verse number="11">ከስቃያቸውና ከቍስላቸውም የተነሣ የሰማይን አምላክ ተሳደቡ፤ ከሥራቸውም ንስሓ አልገቡም።</verse>
				<verse number="12">ስድስተኛውም ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውሃው ደረቀ።</verse>
				<verse number="13">ከዘንዶውም አፍና ከአውሬው አፍ ከሐሰተኛውም ነቢይ አፍ ጓጕንቸሮች የሚመስሉ ሦስት ርኵሳን መናፍስት ሲወጡ አየሁ፤</verse>
				<verse number="14">ምልክት እያደረጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ በታላቁም ሁሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደሚሆነው ጦር እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ።</verse>
				<verse number="15">“እነሆ እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ ኀፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።”</verse>
				<verse number="16">በዕብራይስጥም አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ እስከተቱአቸው።</verse>
				<verse number="17">ሰባተኛውም ጽዋውን በአየር ውስጥ አፈሰሰ፤ ከመቅደሱም ውስጥ “ተፈጽሞአል!” የሚል ታላቅ ድምጽ ከዙፋኑ ወጣ።</verse>
				<verse number="18">መብረቅና ድምጽም ነጎድጓድም ሆኑ፤ ትልቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ሰው በምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ መናውጥ ከቶ አልነበረም፤ ከሁሉ በለጠ።</verse>
				<verse number="19">ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፤ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። ታላቂቱም ባቢሎን የብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የሞላበትን ጽዋ እንዲሰጣት በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች።</verse>
				<verse number="20">ደሴቶችም ሁሉ ሸሹ፤ ተራራዎችም አልተገኙም።</verse>
				<verse number="21">በሚዛንም አንድ ታላንት የሚያህል ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ ሰዎቹም ከበረዶው መቅሰፍት የተነሣ እግዚአብሔርን ተሳደቡ፤ መቅሰፍቱ እጅግ ታላቅ ነውና።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="17">
				<verse number="1">ሰባቱንም ጽዋዎች ከያዙ ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ “ና፤ በብዙም ውሃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን ጋለሞታ ፍርድ አሳይሃለሁ፤</verse>
				<verse number="2">የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ፤ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ፤” ብሎ ተናገረኝ።</verse>
				<verse number="3">በመንፈስም ወደ በረሓ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ።</verse>
				<verse number="4">ሴቲቱም በቀይና በሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፋ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች በዕንቈችም ተሸልማ ነበር፤ በእጅዋም የሚያስጸይፍ ነገር የዝሙትዋም ርኵሰት የሞላባትን የወርቅ ጽዋ ያዘች፤</verse>
				<verse number="5">በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም “ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት” ተብሎ ተጻፈ።</verse>
				<verse number="6">ሴቲቱም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ እጅግ ታላቅ ድንቅ አደነቅሁ።</verse>
				<verse number="7">መልአኩም አለኝ “የምትደነቅ ስለ ምንድር ነው? የሴቲቱን ምስጢርና የሚሸከማትን፥ ሰባት ራሶችና ዐስር ቀንዶች ያሉትን የአውሬውን ምስጢር እኔ እነግርሃለሁ።</verse>
				<verse number="8">ያየኸው አውሬ አስቀድሞ ነበረ፤ አሁንም የለም፤ ከጥልቁም ይወጣ ዘንድ አለው፤ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ ያደንቃሉ።</verse>
				<verse number="9">ጥበብ ያለው አእምሮ በዚህ ነው። ሰባቱ ራሶች ሴቲቱ የተቀመጠችባቸው ሰባት ተራራዎች ናቸው፤</verse>
				<verse number="10">ሰባት ነገሥታት ደግሞ ናቸው፤ አምስቱ ወድቀዋል፤ አንዱም አለ፤ የቀረውም ገና አልመጣም፤ ሲመጣም፥ ጥቂት ጊዜ ሊቆይ ይገባዋል።</verse>
				<verse number="11">የነበረውና የሌለውም አውሬ ራሱ ደግሞ ስምንተኛው ነው፤ ከሰባቱም አንዱ ነው፤ ወደ ጥፋትም ይሄዳል።</verse>
				<verse number="12">ያየሃቸውም ዐሥሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ ዐሥር ነገሥታት ናቸው፤ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።</verse>
				<verse number="13">እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፤ ኀይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ።</verse>
				<verse number="14">እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፤ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።”</verse>
				<verse number="15">አለኝም “ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውሃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም ናቸው።</verse>
				<verse number="16">ያየሃቸውም ዐሥር ቀንዶችና አውሬው ጋለሞታይቱን ይጣላሉ፤ ባዶዋንና ራቁትዋንም ያደርጓታል፤ ሥጋዋንም ይበላሉ፤ በእሳትም ያቃጥሉአታል።</verse>
				<verse number="17">እግዚአብሔር አሳቡን እንዲያደርጉ አንድንም አሳብ እንዲያደርጉ የእግዚአብሔርም ቃል እስኪፈጸም ድረስ መንግሥታቸውን ለአውሬው እንዲሰጡ በልባቸው አገብቶአልና።</verse>
				<verse number="18">ያየሃትም ሴት በምድር ነገሥታት ላይ የምትነግሥ ታላቂቱ ከተማ ናት።”</verse>
			</chapter>
			<chapter number="18">
				<verse number="1">ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች።</verse>
				<verse number="2">በብርቱም ድምፅ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፤ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤</verse>
				<verse number="3">አሕዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቍጣ ወይን ጠጅ የተነሣ ወድቀዋልና፤ የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ፤ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኀይል የተነሣ ባለጠጋዎች ሆኑ፤” ብሎ ጮኸ።</verse>
				<verse number="4">ከሰማይም ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ “ሕዝቤ ሆይ! በኀጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤</verse>
				<verse number="5">ኀጢአትዋ እስከ ሰማይ ድረስ ደርሶአልና፤ እግዚአብሔርም ዐመፃዋን አሰበ።</verse>
				<verse number="6">እርስዋ እንደ ሰጠች መጠን ብድራት መልሱላት፤ እንደ ሥራዋም ሁለት እጥፍ ደርቡባት፤ በቀላቀለችው ጽዋ ሁለት እጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት፤</verse>
				<verse number="7">ራስዋን እንደ አከበረችና እንደ ተቀማጠለች ልክ ሥቃይና ሐዘን ስጡአት። በልብዋ ‘ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ፤ ባልቴትም አልሆንም፤ ሐዘንም ከቶ አላይም፤’ ስላለች፥</verse>
				<verse number="8">ስለዚህ በአንድ ቀን ሞትና ሐዘን ራብም የሆኑ መቅሰፍቶችዋ ይመጣሉ፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።”</verse>
				<verse number="9">ከእርስዋም ጋር የሴሰኑና የተቀማጠሉ የምድር ነገሥታት የመቃጠልዋን ጢስ ሲያዩ ስለ እርስዋ እየጮሁ እያሉ ያለቅሳሉ፤</verse>
				<verse number="10">ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው “አንቺ ታላቂቱ ከተማ! ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን! ወዮልሽ! ወዮልሽ! በአንድ ሰዓት ፍርድሽ ደርሶአልና፤” እያሉ ይናገራሉ።</verse>
				<verse number="11">የመርከባቸውንም ጭነት ከእንግዲህ ወዲህ የሚገዛ የለምና የምድር ነጋዴዎች ያለቅሱላታል፤ ያዝኑላትማል፤</verse>
				<verse number="12">ጭነትም ወርቅና ብር፥ የከበረም ድንጋይ ዕንቁም፥ ቀጭንም ተልባ እግር፥ ቀይም ሐር፥ ሐምራዊም ልብስ፥ የሚሸትም እንጨት ሁሉ፥ ከዝሆን ጥርስም የተሠራ ዕቃ ሁሉ፥ እጅግም ከከበረ እንጨት፥ ከናስም ከብረትም ከዕብነ በረድም የተሠራ ዕቃ ሁሉ፥</verse>
				<verse number="13">ቀረፋም፥ ቅመምም፥ የሚቃጠልም ሽቱ፥ ቅባትም፥ ዕጣንም፥ የወይን ጠጅም፥ ዘይትም፥ የተሰለቀ ዱቄትም፥ ስንዴም፥ ከብትም፥ በግም፥ ፈረስም፥ ሰረገላም፥ ባሪያዎችም፥ የሰዎችም ነፍሳት ነው።</verse>
				<verse number="14">“ነፍስሽም የጎመጀችው ፍሬ ከአንቺ ዘንድ አልፎአል፤ የሚቀማጠልና የሚያጌጥም ነገር ሁሉ ጠፍቶብሻል፤ ሰዎችም ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አያገኙአቸውም።”</verse>
				<verse number="15">እነዚህን የነገዱ በእርስዋም ባለ ጠጋዎች የሆኑት እያለቀሱና እያዘኑ</verse>
				<verse number="16">“በቀጭን ተልባ እግርና በቀይ ሐምራዊም ልብስ ለተጐናጸፈች በወርቅና በከበረ ድንጋይም በዕንቁም ለተሸለመች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት! ይህን የሚያህል ታላቅ ባለ ጠግነት በአንድ ሰዓት ጠፍቶአልና፤” እያሉ ስቃይዋን ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ይቆማሉ። የመርከብም መሪ ሁሉ በመርከብም ወደ ማናቸውም ስፍራ የሚሄድ ሁሉ መርከበኞችም ከባሕርም የሚጠቀሙ ሁሉ በሩቅ ቆሙ፤</verse>
				<verse number="17"></verse>
				<verse number="18">የመቃጠልዋንም ጢስ ባዩ ጊዜ “ታላቂቱን ከተማ የምትመስላት ምን ከተማ ነበረች?” እያሉ ጮኹ።</verse>
				<verse number="19">በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነስንሰው እያለቀሱና እያዘኑ “በባሕር መርከቦች ያሉአቸውን ሁሉ ከባለ ጠግነትዋ የተነሣ ባለ ጠጋዎች ላደረገች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት! በአንድ ሰዓት ጠፍታለችና፤” እያሉ ጮኹ።</verse>
				<verse number="20">“ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን ሐዋርያት ነቢያትም ሆይ! በእርስዋ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።”</verse>
				<verse number="21">አንድም ብርቱ መልአክ ትልቅን ወፍጮ የሚመስልን ድንጋይ አንሥቶ እንዲህ ሲል ወደ ባሕር ወረወረው “ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ ተገፍታ ትወድቃለች፤ ከእንግዲህም ወዲህ ከቶ አትገኝም።</verse>
				<verse number="22">በገና የሚመቱና የሚዘምሩም ድምፅ እንቢልታንና መለከትንም የሚነፉ ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ የእጅ ጥበብም ሁሉ አንድ ብልሃተኛ እንኳ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይገኝም፤ የወፍጮ ድምጽም ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤</verse>
				<verse number="23">የመብራትም ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይበራም፤ የሙሽራና የሙሽራይቱም ድምጽ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና፤ በአስማትሽም አሕዛብ ሁሉ ስተዋልና።”</verse>
				<verse number="24">በእርስዋም ውስጥ የነቢያትና የቅዱሳን ደም በምድርም የታረዱ ሁሉ ደም ተገኘባት።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="19">
				<verse number="1">ከዚህ በኋላ በሰማይ “ሃሌ ሉያ! በዝሙትዋ ምድርን ያጠፋችይቱን ታላቂቱን ጋለሞታ ስለ ፈረደባት፥ የባሪያዎቹንም ደም ከእጅዋ ስለ ተበቀለ፥ ፍርዶቹ እውነትና ጽድቅ ናቸውና ማዳንና ክብር ኀይልም የአምላካችን ነው፤” ብሎ ሲናገር እንደ ብዙ ሕዝብ ታላቅ ድምፅ ያለ ድምፅን ሰማሁ።</verse>
				<verse number="2"></verse>
				<verse number="3">ደግመውም “ሃሌ ሉያ! ጢስዋም ለዘላለም እስከ ዘላለም ይወጣል፤” አሉ።</verse>
				<verse number="4">ሃያ አራቱም ሽማግሌዎችና አራቱ እንስሶች በፊታቸው ተደፍተው በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለእግዚአብሔር “አሜን! ሃሌ ሉያ!” እያሉ ሰገዱለት።</verse>
				<verse number="5">ድምፅም “ባሪያዎቹ ሁሉ እርሱንም የምትፈሩት ታናናሾችና ታላላቆች ሆይ! አምላካችንን አመስግኑ፤” ሲል ከዙፋኑ ወጣ።</verse>
				<verse number="6">እንደ ብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ እንደ ብዙ ውሃዎችም ድምፅ፥ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።</verse>
				<verse number="7">የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን፤ ሐሤትም እናድርግ፤ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ።</verse>
				<verse number="8">ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጐናጸፍ ተሰጥቶአታል።” ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና።</verse>
				<verse number="9">መልአኩም “ወደ በጉ ሰርግ እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸው፤” ብለህ ጻፍ፤ አለኝ። ደግሞም “ይህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል ነው፤” አለኝ።</verse>
				<verse number="10">ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም “እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና፤” አለኝ።</verse>
				<verse number="11">ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም አምባላይ ፈረስ፤ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፤ በጽድቅም ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።</verse>
				<verse number="12">ዐይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፤ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፤ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤</verse>
				<verse number="13">በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፤ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል።</verse>
				<verse number="14">በሰማይም ያሉት ጭፍራዎች ነጭና ጥሩ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ለብሰው በአምባላዮች ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር።</verse>
				<verse number="15">አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።</verse>
				<verse number="16">በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት “የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ” የሚል ስም አለው።</verse>
				<verse number="17">አንድም መልአክ በፀሐይ ውስጥ ቆሞ አየሁ፤ በሰማይም መካከል ለሚበሩ ወፎች ሁሉ “መጥታችሁ የነገሥታትን ሥጋና የሻለቃዎችን ሥጋ የብርቱዎችንም ሥጋ የፈረሶችንም በእነርሱም የተቀመጡትን ሥጋ የጌታዎችንና የባሪያዎችንም የታናናሾችንና የታላላቆችንም ሁሉ ሥጋ እንድትበሉ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር እራት ተከማቹ፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።</verse>
				<verse number="18"></verse>
				<verse number="19">በፈረሱም የተቀመጠውን ጭፍራዎቹንም ይወጉ ዘንድ አውሬውና የምድር ነገሥታት ጭፍራዎቻቸውም ተከማችተው አየሁ።</verse>
				<verse number="20">አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።</verse>
				<verse number="21">የቀሩትም በፈረስ ላይ ከተቀመጠው ከአፉ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ፤ ወፎችም ሁሉ ከሥጋቸው ጠገቡ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="20">
				<verse number="1">የጥልቁንም መክፈቻና ታላቁን ሰንሰለት በእጁ የያዘ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ።</verse>
				<verse number="2">የቀደመውንም እባብ ዘንዶውን እርሱም ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን ያዘው፤</verse>
				<verse number="3">ሺህ ዓመትም አሰረው፤ ወደ ጥልቅም ጣለው፤ አሕዛብንም ወደ ፊት እንዳያስት ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ በእርሱ ላይ ዘግቶ ማኅተም አደረገበት፤ ከዚያም በኋላ ለጥቂት ጊዜ ይፈታ ዘንድ ይገባዋል።</verse>
				<verse number="4">ዙፋኖችንም አየሁ፤ በእነርሱም ላይ ለተቀመጡት ዳኝነት ተሰጣቸው፤ ስለ ኢየሱስም ምስክርና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን ሰዎች ነፍሳት፥ ለአውሬውና ለምስሉም ያልሰገዱትን ምልክቱንም በግምባራቸው በእጆቻቸውም ላይ ያልተቀበሉትን አየሁ፤ ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመት ኖሩና ነገሡ።</verse>
				<verse number="5">የቀሩቱ ሙታን ግን ይህ ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ በሕይወት አልኖሩም። ይህ የፊተኛው ትንሣኤ ነው።</verse>
				<verse number="6">በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው፤ ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፤ ዳሩ ግን የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ፤ ከእርሱም ጋር ይህን ሺህ ዓመት ይነግሣሉ።</verse>
				<verse number="7">ሺሁም ዓመት ሲፈጸም ሰይጣን ከእስራቱ ይፈታል፤</verse>
				<verse number="8">በአራቱም በምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ፥ ጎግንና ማጎግን እንዲያስታቸው ለሰልፍም እንዲያስከትታቸው ይወጣል፤ ቍጥራቸውም እንደ ባሕር አሸዋ የሚያህል ነው።</verse>
				<verse number="9">ወደ ምድርም ስፋት ወጡ፤ የቅዱሳንንም ሰፈርና የተወደደችውን ከተማ ከበቡ፤ እሳትም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወርዳ በላቻቸው።</verse>
				<verse number="10">ያሳታቸውም ዲያብሎስ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣለ፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሰቃያሉ።</verse>
				<verse number="11">ታላቅና ነጭ ዙፋንን በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፤ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም።</verse>
				<verse number="12">ሙታንንም ታናናሾችንና ታላላቆችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ፤ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ።</verse>
				<verse number="13">ባሕርም በእርሱ ውስጥ ያሉትን ሙታን ሰጠ፤ ሞትና ሲኦልም በእነርሱ ዘንድ ያሉትን ሙታን ሰጡ፤ እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን ተከፈለ።</verse>
				<verse number="14">ሞትና ሲኦልም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ። ይህም የእሳት ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው።</verse>
				<verse number="15">በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="21">
				<verse number="1">አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፤ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፤ ባሕርም ወደ ፊት የለም።</verse>
				<verse number="2">ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥ ለባልዋ እንደ ተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ፥ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ።</verse>
				<verse number="3">ታላቅም ድምፅ ከሰማይ “እነሆ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው፤ ከእነርሱም ጋር ያድራል፤ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ፤ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤</verse>
				<verse number="4">እንባዎችንም ሁሉ ከዐይኖቻቸው ያብሳል፤ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፤ ሐዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፤ የቀደመው ሥርዐት አልፎአልና፤” ብሎ ሲናገር ሰማሁ።</verse>
				<verse number="5">በዙፋንም የተቀመጠው “እነሆ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ፤” አለ። ለእኔም “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ፤” አለኝ።</verse>
				<verse number="6">አለኝም “ተፈጽሞአል፤ አልፋና ዖሜጋ፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውሃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ።</verse>
				<verse number="7">ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል፤ አምላክም እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል።</verse>
				<verse number="8">ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”</verse>
				<verse number="9">ሰባቱም ኋለኛዎች መቅሠፍቶች የሞሉባቸውን ሰባቱን ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ “ወደዚህ ና፤ የበጉንም ሚስት ሙሽራይቱን አሳይሃለሁ፤” ብሎ ተናገረኝ።</verse>
				<verse number="10">በመንፈስም ወደ ታላቅና ወደ ረጅም ተራራ ወሰደኝ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ያለባትን ቅድስቲቱን ከተማ ኢየሩሳሌምን ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አሳየኝ፤ ብርሃንዋም እጅግ እንደ ከበረ ድንጋይ እንደ ኢያሰጲድ ድንጋይ ሆኖ እንደ ብርሌ የጠራ ነበረ፤</verse>
				<verse number="11"></verse>
				<verse number="12">ታላቅና ረጅም ቅጥር ነበራት፤ ዐሥራ ሁለትም ደጆች ነበሩአት፤ በደጆቹም ዐሥራ ሁለት መላእክት ቆሙ የዐሥራ ሁለቱም የእስራኤል ልጆች ነገዶች ስሞች ተጽፈውባቸው ነበር።</verse>
				<verse number="13">በምሥራቅ ሦስት ደጆች፥ በሰሜንም ሦስት ደጆች፥ በደቡብም ሦስት ደጆች፥ በምዕራብም ሦስት ደጆች ነበሩ።</verse>
				<verse number="14">ለከተማይቱም ቅጥር ዐሥራ ሁለት መሠረቶች ነበሩአት፤ በእነርሱም ውስጥ የዐሥራ ሁለቱ የበጉ ሐዋርያት ስሞች ተጽፈው ነበር።</verse>
				<verse number="15">የተናገረኝም ከተማይቱንና ደጆችዋን ቅጥርዋንም ይለካ ዘንድ የወርቅ ዘንግ ነበረው።</verse>
				<verse number="16">ከተማይቱም አራት ማዕዘን ነበራት፤ ርዝመትዋም እንደ ስፋትዋ ልክ ነበረ። ከተማይቱንም በዘንግ ለካት፤ ሁለት ሺህ አራት መቶ ኪሎ ሜትር ሆነች፤ ርዝመትዋና ስፋትዋ ከፍታዋም ትክክል ነው።</verse>
				<verse number="17">ቅጥርዋንም ለካ፤ መቶ አርባ አራት ክንድ በሰው ልክ፥ እርሱም በመልአክ ልክ።</verse>
				<verse number="18">ቅጥርዋም ከኢያሰጲድ የተሠራ ነበረ፤ ከተማይቱም ጥሩ ብርጭቆ የሚመስል ጥሩ ወርቅ ነበረች።</verse>
				<verse number="19">የከተማይቱም ቅጥር መሠረት በከበረ ድንጋይ ሁሉ ተጌጦ ነበር፤ ፊተኛው መሠረት ኢያሰጲድ፥ ሁለተኛው ሰንፔር፥ ሦስተኛው ኬልቄዶን፥ አራተኛው መረግድ፥</verse>
				<verse number="20">አምስተኛው ሰርዶንክስ፥ ስድስተኛው ሰርድዮን፥ ሰባተኛው ክርስቲሎቤ፥ ስምንተኛው ቢረሌ፥ ዘጠነኛው ወራውሬ፥ ዐሥረኛው ክርስጵራስስ፥ ዐሥራ አንደኛው ያክንት፥ ዐሥራ ሁለተኛው አሜቴስጢኖስ ነበረ።</verse>
				<verse number="21">ዐሥራ ሁለቱም ደጆች ዐሥራ ሁለት ዕንቆች ነበሩ፤ እየአንዳንዱ ደጅ ከአንድ ዕንቍ የተሠራ ነበረ። የከተማይቱም አደባባይ ጥሩ ብርጭቆ የሚመስል ጥሩ ወርቅ ነበረ።</verse>
				<verse number="22">ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክና በጉ መቅደስዋ ናቸውና መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም።</verse>
				<verse number="23">ለከተማይቱም የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላት መብራትዋም በጉ ስለ ሆነ፥ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጓትም ነበር።</verse>
				<verse number="24">አሕዛብም በብርሃንዋ ይመላለሳሉ፤ የምድርም ነገሥታት ክብራቸውን ወደ እርስዋ ያመጣሉ፤</verse>
				<verse number="25">በዚያም ሌሊት ስለሌለ ደጆችዋ በቀን ከቶ አይዘጉም፤</verse>
				<verse number="26">የአሕዛብንም ግርማና ክብር ወደ እርስዋ ያመጣሉ።</verse>
				<verse number="27">ለበጉም በሆነው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት በቀር፥ ጸያፍ ነገር ሁሉ ርኵሰትና ውሸትም የሚያደርግ ወደ እርስዋ ከቶ አይገባም።</verse>
			</chapter>
			<chapter number="22">
				<verse number="1">በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውሃ ወንዝ አሳየኝ።</verse>
				<verse number="2">በወንዙም ወዲያና ወዲህ በየወሩ እያፈራ ዐሥራ ሁለት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፤ የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝብ መፈወሻ ነበሩ።</verse>
				<verse number="3">ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፤ ባሪያዎቹም ያመልኩታል፤ ፊቱንም ያያሉ፤</verse>
				<verse number="4">ስሙም በግምባሮቻቸው ይሆናል።</verse>
				<verse number="5">ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።</verse>
				<verse number="6">እርሱም “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸው፤ የነቢያትም መናፍስት ጌታ አምላክ በቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ እንዲያሳይ መልአኩን ሰደደ።”</verse>
				<verse number="7">እነሆም “በቶሎ እመጣለሁ። የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብፁዕ ነው፤” አለኝ።</verse>
				<verse number="8">ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ።</verse>
				<verse number="9">እርሱም “እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤” አለኝ።</verse>
				<verse number="10">ለእኔም “ዘመኑ ቀርቦአልና የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው።</verse>
				<verse number="11">ዐመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፤ ርኵሱም ወደ ፊት ይርከስ፤ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፤ ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ፤” አለ።</verse>
				<verse number="12">“እነሆ በቶሎ እመጣለሁ፤ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።</verse>
				<verse number="13">አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።”</verse>
				<verse number="14">ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።</verse>
				<verse number="15">ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።</verse>
				<verse number="16">“እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፤ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”</verse>
				<verse number="17">መንፈሱና ሙሽራይቱም “ና!” ይላሉ። የሚሰማም “ና!” ይበል። የተጠማም ይምጣ፤ የወደደም የሕይወትን ውሃ እንዲያው ይውሰድ።</verse>
				<verse number="18">በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የትንቢት ቃል ለሚሰማ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ፤ ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር፥ እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል፤</verse>
				<verse number="19">ማንምም በዚህ በትንቢት መጽሐፍ ከተጻፉት ቃሎች አንዳች ቢያጎድል፥ በዚህ መጽሐፍ ከተጻፉት ከሕይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር ዕድሉን ያጎድልበታል።</verse>
				<verse number="20">ይህን የሚመሰክር “አዎን በቶሎ እመጣለሁ፤” ይላል። አሜን፤ ጌታ ኢየሱስ ሆይ!ጅ ና።</verse>
				<verse number="21">የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።</verse>
			</chapter>
		</book>
	</testament>
</bible>